‘ኢጎ’ (Ego) ቃሉ ከግሪክ የተወሰደና ትርጉሙም ‘እኔ’ ወይም ‘እኔነት’ ማለት ነው። ‘እኔ’ና ‘እኔነት’ ራስን ማወቅ፣ መሻትና አሻራ መተውን ደምሮ ህልውናን የሚገልጽ የንቃተ ህሊና አካል ነው። ይህ ስሜት መጠኑን ሲያልፍና ሌላውን አሳንሶ ራስን መሪ፣ አለቃ፣ ቀዳሚ፣ አዛዥ አድርጎ መቁጠር ሲጀመር ወደ (egoist, narcissist) ግለኝነት እኔ ብቻ ወደ ማለት ያድጋል። ነገር ግን ‘ኢጎ’ን በጥቅሉ መጥፎ ቅንፍ ውስጥ መጨመርም ስህተት ይሆናል። ምክንያቱም አኔነትን ማለትም እራስን ማወቅ መሰረታዊና አስፈላጊ ጉዳይ ነውና። ይህ ጽሁፍ የሚያተኩረው ልክ-የለሽ እኔነት ወይም ራስ-ወዳድነት (egoism) ላይ ነው። በርካቶችን “ከእኔ በላይ ለአሳር” በሚያሰኝና እንኳን የሚመኙትን ስልጣን ማጣት የሚኖሩበት አገር መፍርስም ቢሆን እንኳ ከመቻቻል ይልቅ ተያይዞ ገደልን የሚያስመርጥ ውስጣዊ ስሜት ያንጸባርቃሉ። ይህም ጽሁፍ በዚህ ላይ ያተኮረና መፍትሄም አመላካች ይዘት ያለው መልዕክት የማቅረብ መኩራ ያደርጋል። ኢጎ ከልክ ያለፈ ሲሆን ግን ሰው እራስ ወዳድ የሆነና በአህያ እንደተረተው እኔ ካለሁ ሁሉም ለኔ ይኑር አዝማሚያ ያለው “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” አለች እንደሚሉት አይነት ባህሪይን ያላብሳል። ሥዕሉ ይህንን ሀሳብ በመጠኑ ይገልጸዋል የሚል እምነት አለኝ።
↧
ልክየለሽ ራስ-ወዳድነት ሰላምና ነፃነትን የሩቅ ህልም እንዳያደርግብን –ከዳኛቸው ቢያድግልኝ
↧