የመጀመሪያው የከተሞች ምድብ ተቃውሞው የሚካሄደው በከፍተኛ የድምጽ ተቃውሞ ሲሆን ተቃውሞው የሚደረግባቸው ከተሞችም የሚከተሉት ናቸው፡፡
1) በአዲስ አበባ ከተማ
2) በኦሮሚያ:- መቱ እና ዶዶላ ከተማ
ከላይ በተጠቀሱት ሶስት ከተሞች ተቃውሞው የሚከናወነው በድምጽ ይሆናል፡፡ በአዲስ አበባ ተቃውሞው የሚከናወነው በታላቁ አንዋር መስጂድ ላይ ሲሆን በሌሎቹ ደግሞ የትግሉ ማእከል በሆነ የተመረጠ የከተማው መስጂድ ላይ ይሆናል፡፡
ለተቃውሞው ከሚከተሉት 6 መፈክሮች መሀል የገራልንን መፈክር በወረቀት ላይ አስፍረን ይዘን በመምጣት በተቃውሞው ላይ ከፍ አድርገን እናሳያለን፡፡ መፈክሮቹ የሚከተሉት ናቸው፡-
‹‹ለሀይማኖታዊ መብታችን በፅናት እንቆማለን!!››
‹‹ፍትህ ይስፈን – የታሰሩት ይፈቱ!!›› ‹‹መጅሊስ ለህዝበ ሙስሊሙ ይመለስ!!››
‹‹የእምነት ነፃነታችን ይከበር!!››
‹‹አፈና፣ ግፍ እና ማስገደዱ ይቁም!!››
‹‹የእምነት ቤቶቻችን ክብር ይጠበቅ!››
በእለቱ የምናከናውነው ተቃውሞ ዝርዝር መርሀ ግብር እንደሚከተለው ነው፡-
1. ለ3 ደቂቃ ሰላት እንዳለቀ አንድነታችንን እና ፅኑ መሆናችንን ለማሳየት እጅ ለእጅ በመያያዝ ባለንበት እንቆማለን፤
2. ለ3 ደቂቃ ይዘነው የምንመጣውን መፈክር የሰፈረበት ወረቀት ከፍ በማድረግ የዚያን ጀግና የሀበሻ ልጅ ቢላል (ረ.ዐ) ድንቅ ፅናት በውስጣችን በማሰብ ‹‹አሃዱን አሀድ!! አሃዱን አሀድ!!›› የሚል መፈክር በአንድ ላይ እናሰማለን፤
3. ለ3 ደቂቃ የሃይማኖት እና የሰብአዊ መብቶቻችን በከፍተኛ ሁኔታ እየተጣሱ መሆናቸውን በመቃወምና ሰላማዊ ትግላችን መብት የማስከበር ትልቅ ዓላማ እንዳለው ለማሳየት ‹‹መብታችን ይከበር!›› የሚል መፈክር እናሰማለን፤
4. ለ3 ደቂቃ በዚህ የተከበረው የረመዳን ወር ሀያሉ አላህ ነስሩን እንዲለግሰን ከልባችን ዱዓ እናደርጋለን፤ በመጨረሻም ወደየመጣንበት ሰላማዊነታችንን አንደጠበቅን እንመለሳለን!
ድምፃችን ይሰማ
ድምፃችን ይሰማ