Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ስንቴ ልዝለል!!

$
0
0

ከድር አብዱ

Penበአንድ ወቅት አንድ ወዳጄ የነገረኝ ነገር ሁሌም ይታወሰኛል፡፡ የዚህ ወዳጄ ትርክት የሚያጠነጥነው…በራሱ የሀገራት ዕድገት ንፃሬ መሰረት….. ያደጉ፣ እያደጉ ያሉና ኩንድሽ ወይም ፈፅሞ አያድጉም ብሎ ከሰየማቸው ሀገራት መሀከል አንዳንድ ሲበዛ ካስገረሙትና እንደወጉ ከታዘባቸው እልፍ ክስተቶች መካከል ነበር አንዱን ጀባ ያለኝ፡፡

መቼስ ወዳጄ የሀገሩ ጉዳይ አይሆንለትም የመሪዎቿ አጉራ ዘለልነት ባጠቃላይ የሚወዳት ሀገሩ ሁኔታ ውሀ አልቋጥር ቢለው፤ ነገር አለሙ ሁሉ መቅኖ ቢስ እየሆነበት ቢቸገርም ሁሌም ያለመታከት ሀገሬ መቼ ነው ከዚህ የጋሪዮሽ ሽብሻቦ፣ ከዚህ የነተበ አስተዳደር የምትፋታው ብሎ መጠየቅ አይሰለቸውም፡፡ ያደጉት ሀገራት ለዜጎቻቸው ያላቸውን ክብር፣ቀናኢነት ሲያይ ይበልጥ ውስጡ ይደማል፤ እነሱ…በማለት ነበር ወጉን የጀመረው (ያደጉትን ሀገራትን መሆኑ ነው) << እነሱ…ዜጎቻቸው አገሪቷ ከሚኖራት አንጡራ ሀብት ተቋዳሾች ናቸው ይባስ ብሎ 18 አመት ለሞላው አዲስ ጎጆ ወጪ የትዳርን ጣጣ ሁሉ ችለው አይገቡ ገብተው ነው እንደ ወላጅ የሚድሩት፡፡እኛ ጋ ስትመጣ የሀገሬ ሀብት ብሎ ቀልድ የለም አይንህን ላፈር ነው የሚሉህ፡፡ እነሱኮ ሀገሪቱን እንደሻማ አቅልጠው ቢያነዱት ደስታቸው ነው >> አለ በብስጭት፡፡

እኔን የሚገርመኝ አለ ወዳጄ በመቀጠል…<< እኔን የሚገርመኝየምክንያታቸው ተመሳሳይነት ነው ለምሳሌ ሼባው(አጼውን ማለቱ ነው) ከፈጣሪ የተቀባሁ ነኝ ያለኔ ኢትዮጵያ ተረት ነች ሲል ቆይቶ ሌላኛው ባለተራ ወታደር ሲመጣ የመጀመሪያ ስራው የነበረው ሼባውን 8ሜትር ጉድጓድ ውስጥ ወርውሮ አጼውን ራሱን ተረት ማድረግ ነበር፡፡ ይገርማል…የወታደሩ ዳፋ በዚህም አላበቃም ወዲያው ለጠቀና አብዮቱ የዚህች ሀገር ዕጣ ፋንታ ነው ሲል በቀጠናው ደሰኮረ፡፡ እሱም በተራው በሰው ሀገር ስደት የአቢዮቱን ማኒፌስቶ ለብቻው እያነበነበ ተከርችሟል ይህ ሁሉ ሲሆን ኢትዮጵያ ግን እንዳለች አለች፡፡ ይህ ሁሉ ከንቱ ፉከራ የመሪዎቹ የቁም ቅዠት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ከሁሉም ደግሞ የሚገርመው ይህኛው ባለቁምጣ በተራው በትረ መኮንኑን ቢጨብጥም እንደቁራ ያለፉትን መሪዎች ህልም ከመድገም አልቦዘነም ይባስ ብሎ አውራ ፓርቲ ነኝ የሚል የውጦሽ መንገድ አበጅቷል፡፡ሁሉም ሰላም የላቸውም! ጅቦች ናቸው >> አለ በመሰላቸት፡፡

እንዲህም ቀጠለ….<< ያደጉት ሀገራት የምግብም የህሊናም ነፃነት አላቸው እኛ ግን ነፃነቱን እንተወውና ዳቦ….ዳቦ…የዳቦ ያለህ ስንል የአለም ማህበረሰብ ሳይቀር እረ ወገኖቻችሁ በርሀብ ጠኔ አለቁ በማለት ሲጣሩ የኛዎቹ ጉዶች ረሀብ አይደለም የምግብ ዕጥረት ነው በማለት ይሳለቃሉ፡፡>> የሚገርመው አለ ወዳጄ ባለማቋረጥ << የሚገርመው የኛ ህዝብ ራሱ እንኩቶ ነው ለምን መሰለህ ዝለል ሲባል ስንቴ ልዝለል ነው መልሱ……ለምን የለ! ወዴት የለ! ለዚህም ነው እንዲህ እንደ ቡኮ የሚያቦኩን >> በማለት ነበር ወዳጄ ቁጭቱን የገለፀው፡፡ ለዚህ ለወዳጄ አንድ ተጨባጭ ክስተት ላክልለትና ይብቃኝ፡፡

በቅርቡ ከዚህ አለም በሞት የተሰናበቱት የአለም የሰላም ኖቬል ተሸላሚው ኔልሰን ማንዴላ ከ27 አመት የሽብርተኝነት ክስ እስር በኋላ ነፃ ሲወጡ ኢትዮጵያ ለስልጠና በነበሩበት ሰዐት በሀላፊነት ተቀብለው ያስተናግዷቸውና ያሰለጥኗቸው የነበሩትን ግለ-ሰብ ወዴት ደረሱ ብለው ሲጠይቁ የተሰጣቸው መልስ የውሀ ሽታ ሆኑ የሚል ነበር፡፡በዚህን ጊዜ ኔልሰን ማንዴላ በሀዘን ተሰብረው እንዲህ አሉ << ነጭ ጥቁሩን ሲምረው ጥቁር እንዴት ጥቁር ላይ ይህን ያህል ይጨክናል >> ነበር ያሉት የሳቸውን ከነጮች ማርታ ማግኘትና ከእስር በነፃ መለቀቅ አስታውሰው፡፡ የዚህ ፅሁፍ ተጠይቅ እኔም፣ አንተም፣ አንቺም ሁላችንም ጋር ይኖራል፡፡ ዝም ብለን በተቀየሰልን ቦይ መፍሰስ…. ለምን ማለት የለ! ወዴት ማለት የለ!፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>