Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን እንዴት ማፈን ቻለ?

$
0
0

ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን እንዴት ማፈን ቻለ?

ለዚህ ጥያቄ መልስ መስጠት ለግንቦት 7 ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የሞትና የሽረት ጥያቄ ነው:: በቂ ማስረጃ እስክሚሰበሰብ ድረስ አራት አቅጣቻዎችን መመርመር ያስፈልጋል::

1) ለሻቢያ ሁሉ ነገር ከራስ በላይ ነፋስ ነው:: ራሱ ሻቢያ በተዘዋዋሪ ለወያኔ የአቶ አንዳርጋቸውን የበረራ ሰዓታቸውን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል::ይህ እንግዲህ በኤርትራ ውስጥ የሚገኙ የግንቦት 7 መሪዎች ሁኔታውን በደንብ ሰለሚያውቁ ይህ ግምት ሊሆን ወይም ላይሆን እንደሚችል መጠቆም ይችላሉ:: ለምሳሌ ሻቢያም ሆነ በሻቢያ የሚታዘዘው ደሚት ስለ ግንቦት 7 ደስ ያላላቸው ነገር እንዳለ የታዘቡት ነገር አለ ወይ? ሌላም ሌላም የተፈጠሩ ክስተቶች ካሉ መገምገም ይኖርባቸዋል::

2) በሻቢያ የደህንነት መዋቅር ውስጥ ሰርገው የገቡ የወያኔ ሰላዮች አቶ አንዳርጋቸውን ተከታትለው የበረራ ሰዓቱንና ቦታውን አግኝተው ለወያኔ ልከውት እንድሆነም መጣራት አለበት:: የአቶ አንዳርጋቸውን የበረራ ቀንና ሰዓት የሚያውቁት እነማን ነበሩም ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል:: እንደተባለው አቶ አንዳርጋቸው የበረራውን አቅጣጫ በየመን በክል ለማድረግ መወሰኑን በሰዓቱ እነማን ነው ያወቁት? መቼስ ነው ያወቁት?

3) በግንቦት 7 አመራር ውስጥ ያለ ወይም ለአመራሩ በጣም ቅርበት ያለው ግን አንዳርጋቸውን የሚያገኝ ወይም የአንዳርጋቸው የልብ ወዳጅ የሆነ ግለሰብ የበረራ መረጃውን ለወያኔ በክፍተኛ ገንዘብ አሳልፎ ሰጥቶ እንደሆነ መጣራት አለበት::

4) የመጨረሻው አማራጭ ከግንቦት 7ና ከሻቢያ ቁጥጥር ውጭ በየመንና በወያኔ መካከል ለረጅም ጊዜ የተቀነባበረ ሴራ ሊሆን ይችላል:: የየመን መንግሥትና ወያኔ የሰንኣ አየር መንገድ ሃላፊዎች ውስጥ አንድ ለደህነንት እንዲሰራ የተመደበ ሰው የአንዳርጋቸውን ስም ከተሳፋሪዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በየጊዜው እየቃኝ መጨረሻ ላይ አግኝቶ ለየመን ደህነነት ከዛም በኋላ ለወያኔ አሳልፎ አንዳርጋቸው ሊጠለፍ ችሎ ሊሆን ይችላል:: ይህ ሁኔታ ሊሳካ የሚችለው የአንዳርጋቸው ፓስፖርት በእውነተኛ ስሙ የተሰጠው ክሆነ ነው::

ወይም ካልሆነ ከላይ ከተራ ቁጥር አንድ እስክ ሶስት ድረስ እንደተጠቀሰው የአንዳርጋቸውን የፓስፖርት ስም የሚያውቅ የግንቦት 7 አመራር አባል ወይም ለግንቦት 7 በጣም የቀረበ የአንዳርጋቸው የልብ ወዳጅ ወይም ሻቢያ ወይም በሻቢያ ደህነነት ውስጥ ሰርጎ የገባ የወያኔ ሰላይ የአንዳርጋቸውን የበረራ መረጃ ፓስቦርቱ ላይ ካለው ስሙ ጋር ለወያኔ አቀብሎ ከየመን ጋር በመደራደር የተደረገ አፈና ነው::

የአቶ አንዳርጋቸው መታፈን ከአራቱ ምክንያቶች ውጭ ሊሆን አይችልም የሚል ግምት አለ::


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>