Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ምርጫ በአንድነት ዉስጥ፣ ለአቶ በላይ ፍቃደ ድጋፌን እሰጣለሁ ( ግርማ ካሳ)

$
0
0

ምርጫ በአንድነት ዉስጥ፣ ለአቶ በላይ ፍቃደ ድጋፌን እሰጣለሁ ( ግርማ ካሳ)

 

10537095በኢትዮጵያ አንጋፋ ከሚባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የሚገኙት፣ መኢአድ እና የአንድነት ፓርቲ ዉህደት በቅርቡ ይፈጽማሉ ተብሎ ይገመታል።

በዚህ ዙሪያ፣ ይችን ሰሞን በሶሻልሜዲያዎች፣  አንዳንድ ጤናማ ዉይይቶችን  እያነበብኩኝ ነው። የአንድነት ፓርቲ በቅርቡ ከመኢአድ ጋር ሲዋሃድ ፣ መጀመሪያ የአንድነት እና የመኢአድ ጠቅላላ ጉበኤ፣  የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ባሉበት በተናጥል ይደረጋሉ።  ለዉህዱ ፓርቲ የሚቀርቡ ተወካዮችን እና ዉህዱ ፓርቲን የሚመሩ እጩ  ተወዳዳሪዎች ንያቀርባሉ።በነጋታዉ ከሁለቱም ፓርቲዎች እኩል የተወጣጡ ተወካዮች ያሉበት የዉህዱ ፓርቲ  ጠቅላላ ጉባኤ፣  የዉህዱን ፓርቲ ሊቀመንበር ይመርጣል።

የተከበሩ  ኢንጂነር ግዛቸው ከስድስት ወራት በፊት የአንድነት ፓርቲን እንዲመሩ መመረጣቸው  ይታወቃል።  የመኢአድ እና  የአንድነት  ዉህደት  ሲጠናቀቅ ፣  አንድነትም፣  መኢአድም  እንደ  ድርጅት  ይከስማሉ።  አዲስ  ድርጅት  ነው የሚፈጠረው።  በመሆኑም የኢንጂነር ግዛቸው ምሊቀመንበርነት ከአንድነት  ፓርቲ  ጋር አብሮ  ይከስማል። ኢንጂነር ግዛቸው የዉህዱፓርቲ ሊቀመንበር መሆንከፈለጉ፣  እንደገና ተወዳድረው  መመረጥ ይኖርባቸዋል። ለዚህም ነው ለዉህዱ ፓርቲ ሊቀመንበርነት ለመወዳደር፣  በአንድነት ፓርቲ በኩል እጩ ሆኖ ለመመረጥ፣ ራሳቸዉን ለእጩነት ያቀረቡት።

ከኢንጂነር ግዛቸው በተጨማሪ፣ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በላይ ፍቃዱ እንዲሁም የአንድነት ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የቀድሞ የአንድነት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ትእግስቱ አወል እጩዎች ሆነው ቀርበዋል።

ይህ ፓርቲዉን ለመምራት በአንድነት ዉስጥ እየተደረገ ያለው የምርጫ ፉክክር፣ በጣም የሚያስደስትና የሚያኮራ ነው። «ይሄኛው ይመረጥ፣ ያ ይሻላል» እያሉ አባላትና ደጋፊዎች ሲከራከሩ ማየት፣ በዉጭ አገርም ሆነ ከአገር ዉጭ ባሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ሆነ በገዢዉ ፓርቲ ዘንድ ያልተለመደ ነው።

የአንድነት ፓርቲ አባል ባለመሆኔ፣  በምርጫዉ ለመሳተፍ አልችልም። ነገር ግን የአንድነት ፓርቲ የመሪዎቹና የአባላቱ ብቻ ሳይሆን፣  በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹም ነው ብዬ ስለማምን፣ እኔም እንደ አንድ ፣ በዉጭ አገር የሚኖር ተራ ደጋፊ፣ በቀረቡ እጩዎች ዙሪያ አንዳንድ አስተያየት ለመስጠት እሞክራለሁ።

ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉን  የማያውቅ ሰላማዊ ታጋይ አለ ብዬ አላስብም። የቀድሞ ቅንጅት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ነበሩ። ትዝ ይለኛል፣  በፓልቶክ፣ ቃለ መጠይቅ በመስጠት ላይ እያሉ ነበር፣ ፖሊሶች መጥተው  ወደ እሥር ቤት የወሰዷቸው።  ሁለት አመት ከሌሎች የቅንጅት አመራሮች ጋር በቃሊቲ ተሰቃይተዋል። ሌሎች ስደትን ወይንም የግል ኑሯቸውን መርጠው ፖለቲካዉን ሲተዉ፣  ኢንጂነር ግዛቸው እና እንደ ዶር ሃይሉ አርአያ ያሉ ጥቂቶች ግን፣   ትግሉ ቀጣይነት እንዲኖረው ያደረጉ አንጋፋ መሪዎች ናቸው። ወ/ት ብርቱካን በታሰረች ጊዜ አንድነትን በተጠባባቂ ሊቀመንበርነት የመሩ ሲሆን፣ ከመድረክ መመስረት አንስቶ፣ በርካታ ወጣቶችን ወደ አንድነት እስከ ማምጣት ድረስ፣  ትልቅ ስራ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ሰርተዋል። በአጭሩ የአንድነት ፓርቲ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ካደረጉት ሰዎች መካከል ኢንጂነር ግዛቸው  በዋናነት የሚጠቀሱ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ኢንጂነር ግዛቸው ከዚህ በፊት ላበረከቱት አስተዋጾ አክብሮትና አድናቆቴን ከማቅረብ ዉጭ ሌላ የምለው ነገር አይኖረኝም።

ከዚህ በኋላ ላለው ጉዞ ግን፣ በቅንጅት ጊዜ ከነበረው በተለየ መንፈስ፣ በተለየ ራእይ፣  ሰላማዊ እንቅስቃሴዉን መምራት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ማንዴላ ለነ ኢምቤኪ፣ ሃላፊነቱን እንዳስረከበው፣ ኢንጂነር ገዛቸውም፣ ላፈሯቸው፣  ብቃት ላላቸው አዳዲስ አመራር አባላት፣  ቦታዉን ቢለቁ ጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ከነዚህ አመራር አባላት መካከል፣ እጩ ተወዳዳሪ ሆኖ የቀረበው ፣ አቶ በላይ ፍቃዱ አንዱ ነው።

አቶ በላይ ፍቃደ፣ የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀምነበር ሲሆን፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የፍኖት ኤዲቶሪአል ቦርድ ሰብሳቢ ሆኖ ሰርቷል። ለሹመትና ለስልጣን የማይቸኩል፣  ከበስተጀርባ ሆኖ መስራት የሚወድና በፓርቲዉ ዉስጥ ትልቅ ከበሬታ ያለው አንጋፋ የአንድነት አመራር አባል ነው። ኢንጂነር ግዛቸው እራሳቸው፣  አቶ በላይ፣  ፓርቲዉን ለመምራት ብቃት፣ እውቀትና ብስለት ያለው እንደሆነ ብዙ ጊዜ መስክረዉለታል። የሚሊዮኖች ንቅናቄ ክፍል አንድ ወቅት ከዋና አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ከሌሎች አገር ቤት ካሉ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋርም የቀረበ ግንኙነት ያለው፣ የአንድነት አመራር አባል ነው። በዉጭ አገር ባሉ የአንድነት ደጋፊዎች ዘንድም ትልቅ ድጋፍና ከበሬታ አለው። ወጣቱን ክፍል ፣ የእድሜ ባለጸጎችን፣ በአገር ዉስጥ ያለውን፣ ከአገር ዉጭ ያለውን የአንድነት አባልና ደጋፊ ማሰባሰብ የሚችል ተግባቢ አመራር እንደሆነ ይነገርለታል።

በዚህም ምክንያት፣ እንደ አንድነት ደጋፊ ፣ አቶ በላይ ፍቃደ፣ አንድነትን ወክሎ ለዉህዱ ፓርቲ ሊቀመንበርነት እጩነት ቢቀርብና የዉህዱን ፓርቲ ቢመራ፣ ፍላጎት እንዳለኝ ለመግለጽ እወዳለሁ። አቶ በላይንም  በዚህ አጋጣሚ ኢንዶርስ አደርገዋለሁ።

እኔም ሆንኩኝ ሌሎች መራጭ ያልሆኑ ደጋፊዎች አንዱ ወይንም ሌላዉ እጩ ኢንዶርስ ብናደርግም፣ ወሳኙ ግን አገር ቤት ያሉት የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች ናቸው። አቶ በላይን  ቢመርጡ በጣም ደስተኛ ብሆንም፣   ሌሎች እጩዎች ከተመረጡ ግን ፣ ሙሉ ለሙሉ የጠቅላላ ጉባኤዉን ዉሳኔ እንደማክበር፣ አዲስ ለተመረጠዉ አመራር ድጋፌን እንደምሰጥ ለማሳወቅ እወዳለሁ።

ከሚስጥራዊና ዉስጣዊ አሰራር ወጥቶ፣ ዉድድሮችን ይፋ በማድረግ እንደ እኛ አይነት ደጋፊዎች ሐሳባችንን መግለጽ የምንችልበትን ሁኔታ፣  የአንድነት ፓርቲ በማመቻቸቱም፣ ያለኝ አድናቆትና ምስጋና በማቅረብ አቆማለሁ።

 

በቸር እንሰብት !

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>