በወለየሱስ
የኣንድነት እና መኢኣድ ውህደት ፍጹም ጽናት በተሞላበት ኣቓም ጸንተው እዚህ ደርሰዋል። በኢህኣዴግ ስር ሁኖ እዚህ መድረስ ምን ያህል ፈታኝ መሆኑን ተገንዝበን የሚገባውን ድጋፍ ለመስጠት የኛ ፈንታ መሆኑን ላስታውስ እወዳለሁ። ዛሬ 8/1/2014 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰነድ ዝግጅት፣ የጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ፣ የሕዝብ ግንኝነት፣ የመድረክ ዝግጅት እና መስተንግዶ፣ የሕግና ጸጥታ እንዲሁም የፋይናንስ ንዑስ ከሚቴዎችን ማቋቋማቸው ገልጸዋል። ግን ኢህኣዴግ የህዝብ ገንዘብ ኣሰራጭቶ ሳይበታትናቸው ኣለንላችሁ የሚል ከኛ የተጠናከረ ድምጽ ማሰማት ይጠበቃል።
በግለሰቦቹ ለሚወሩት ጆሮ ኣንስጥ። እዚህ የደረሱት ድምጽ ኣግኝተው እንጂ በሩጫ ኣይደለም። ያጠፉት ጥፋት ካለ የድርጅታቸው ኣባላት ይቀይርዋቸው፣ ኣልያም ኢህኣዴግ ካወደቁት በኃላ ድምጽ ሳይሰጥ እንዲሸነፉ ማድረግ። መንግስቱ ሃይለማርያምም ድምጽ ይዞ ከመጣ ይምጣ ኢህኣዴግ ይወገድልን ከዛ በሽግግር ሂደት በድምጽ ማቅረት። ማን ከማን ንጹህ ሁኖ ነው እና እንዲህ ነበር እያልን የራሳችንን ደብቀን በሌሎች እንቅፋት እየሆን የኢህኣዴግን እድሜ የምናራዝም ያለነው።
በውጭ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተመሳሳይ ኣብሮ የመስራት ኣንድነት ማሳየት ኣለብን። ኣንድ ድርጅት ለብቻው የትም እንደማይደርስ ማመን ኣለበት፣ ቢሆን ከኦነግ የበለጠ ማን ነበር እና ግን ኢህኣዴግ እንደማያሳልፍ ተገንዝበን ኣንድነት መፍጠር ግን ኢህኣዴግን ያንበረክከዋል፣ ይበታትነዋል፣ ህዝብ ተስፋ ኣግኝቶ ሆ ይላል፣ ኣወንታዊ ስራ ለመስራት ይመቻል።
ኦነግ፣
ሸንጎ፣
ግንቦት 7፣
ሰማያዊ፣
ኣንድነት (የኣመሪካ)፣
የኣፋር ኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ኣንድነት ግንባር፣
ዴሞክራስያዊ ምንቅስቓስ ህዝቢ ትግራይ፣
የኢትዩጵያ ድርበር ጉዳይ ኮሚቴ፣
የኢትዮጵያ ሕዝብ ኣርበኞች ግንባር፣
ሌሎቻችሁ ተሰባሰቡና ህብረት ፍጠሩ።
በነጻ ኣገር ሕግ የመላይነት ባለበት፣ በጠሬቤዛ ዙርያ መስማማት ያልቻላችሁ እንዴት ነው 90 ሚልዮን ህዝብ ለመምራት የምትችሉ? የግል እውቀትና ልምድ ሊኖራችሁ ይችላል ግን ኣብሮ የመስራትና ኣገር የመምራት ብቃት ልምድ ግን ኣላየንም ወይስ እንደ ኢህኣዴግ ወደ ዘር ትውልዳችሁ ብቻ ነው ግባችሁ። እንዲህ ከሆነ ኢትዮጵያ እያላችሁ ኣታላይ ኣትሁኑ። ኢትዮጵያ ግዙፍ እና ጥልቀት ያለባት ህዝብ መጠርያው ኣታኮላሹት።
ለምን በሃሳብ ተለያይተው የተገዳደሉትን ትምህርት ኣይሆነንም፤ መኢሶንና ኢህኣፓ፣ ኢህኣፓና ወያኔ፣ ሻእቢያና ጀብሃ፣ ኢድዮና ወያኔ፣ ኢህኣፓ በሁለት ሲከፈሉ፣ ቅንጅት ሲበታተኑ፣ ወዘተ ምን ነው ከስህተት ተምረን፣ ይቅር ተባብለን፣ በሕግ የሚጠየቅ ለዳኝነት ትተን፣ ኣወንታዊ ስራ ለመስራት ህዝባችንን ለማበልጸግ ኣናደርግም።
ትምክህቱን ተው እና የሃይማኖት ኣባት ወይም የጭንቅላት ሃኪም ማማከር ያስፈልጋል። ምርጫ 3007 ከመድረሱ በፊት፣ ኢህኣዴግ በኣንድነትና መኢኣድ ገብቶ ሳይበታትናቸው፣ በውጭ ያላቹሁ ተቃዋሚ ማእከላይ ኣመራር ተሎ ምስርታቹሁ የውጪዊን የዲፕሎማሲ ስራ መስራት እና ለሃገር ህዝብ ተስፋ ሆኖ መገኘት የምርጫ 97 ትርኢት ሊደገም ይችላል። ከዘር በሽታ ወጥተን ሃገራዊ ምንነት ኣስቀድመን የጣልያን ሽንፈት በባንዳዎች እንድገመው።