Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የጨረቃ ፈስ –ክፍል ሁለት። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

የቀልዱ ጎጆ የድቡሽቱን ህልምን ይደረምሳል።

ሥርጉተ ሥላሴ 05.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

 

እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ባለፈው ሳምንት ክፍል አንድን እንዲህ ነበር ያሳርግሁት።

„… ታዲያ ይህንን እያዬን እንዴት ይሳነን በነጠረ አይሁድ ስሙ ወያኔን ብለን ለመጥራት ////// የሴት እሰረኞች መከራ ደግሞ ብዕርም – አንደበትም – ህሊናም – ባህልም – ትውፊትም – ተመክሮም – ደፍሮ ለመናገር አይችሉትም። ተቀብሮ የሚቀር ሚስጥር ነው። ዘመንና ታሪክም አያወጡትም – እኛ ባልነበርንበትና ባልተፈጠርንበት ውስጥ ሃቁን ለህዝብ አደባባይ አውጥቶ መጻፍ አንችልምና! ለመዳህኒተአለም – ለአውደ ምህረቱ – ለመንበሩ ለመንገርም እንኳን አቅም ያንሳል። እንኳንስ ለሚዲያ ፍጆታ ለማዋል። ሃቅ በሆነ አገላለጽ የወያኔ መሰረተ ተፈጥሮው – ሰብዕናውም ከኢትዮጵያዊነት ጠረን ውጪ ነው — እንዲህ ልከውነው። ትግራይ አኮ ለእምነቱና ለባህሉ የበዛ አክራሪ ነው። እነዚህ ከዬት እንደመጡበት፤ ከዬት እንደፈሉ አላውቅም።“

ክፍል ሁለት።

ንጹህ ልብ፣ ቅን ህሊና ያላቸው ወገኖቼ ከልብ ሆነው ይከታተሉኝ ዘንድ በትህትና ዝቅ ብዬ ጠዬቅኩኝ – እኔ ሎሌያቸው ሥርጉተ ሥላሴ ተዚህ ተጭምቷ – ሲዊዝዬ።

  1. መጓጓዣ – እንደ በር። ለመነሻ ትንሽ ነገር ልበል። ዬአንድ የፖለቲካ ድርጅት መሠረቱ ዬሚያምንበት ዓላማው ነው። ዓላማውን ለማስፈጸም የሚችሉ የፈቀዱና የወደዱ ከማህበረሰቡ የተወሰኑት ብቻ አባላትም ይኖሩታል። የአባላቱ ኃላፊነት የአፈጻጸም ድርሻ በግልና በጋራ ይሆናል። አንድ የፓርቲ አባል በአባልነት ብቻ ወይንም አባልነቱንም አመራር አካልነቱንም አክሎ ድርሻ ሊኖረው ይችላል። ጥምር ኃላፊነት እንደ ማለት። እንዴት?

ሀ.        እንደ አንድ አባል ወርሃዊ የፓርቲውን ክፍያ ከመክፈል ጀምሮ የፓርቲውን መሰረታዊ ሰነዶች ማለትም ደንቡን፤ ፕሮግራሙንና የውስጥ መመሪያ የመፈጸም ግዴታ ይኖርበታል። በስብሰባ የመገኘት፤ ድምጽ የመስጠት መብትም፡

ለ.        እንደ አካልነቱ ደግሞ እነዚህን የፓርቲ መሰረታዊ ሰነዶችን ማለትም ፕሮግራሙና ደንቡን ከሁለቱ የሚመነጨውን ዬአፈጻጻም የውስጥ መመሪያውን በተጨማሪም ዓላማውን ወደ ተግባር ለማሸጋገር የሚያስችሉትን የሥራ ንድፎች – ትልሞች  እንደ ተሰጠው ዬእርከኑ ደረጃ ይከታታላል – ይቆጣጠራል። የሥራ ንድፉ ወይንም ትልሙ በሦስት ክፈለ ጊዚያት ይመዳባሉ። ይብራራ –  የረጅምና የአጭር፤ እንዲሁም ሁለቱን የሚያገናኘው በዘመንኛው ቋንቋ link የመከካለኛ ጊዜው ይሆናል። (ረጅም 5- 10 መካከለኛ 1 – 3 አጭር ከሳምንት እስከ አንድ አመት ሊሆን ይችላል)

መነሻዬ ሁለተኛው የወያኔ የቪዲዮ የትነት ድራማ ነው። ቋራርጦ- ለብዶ – ጥፎ – ለጋግቦ በስለላ ተግባር የለመደበት ድውይ ያቀነባባረውን ሁለተኛ የቪዲዮ ምስል ፍላጎት በተመለከተ የተከበሩ ዶር ብርሃኑ ነጋ የግንቦት 7 ሊቀመንበር  ከኢሳትት ጋር በነበራቸው ቆይታ ማብራሪያ ሰጥተውበታል። ማበራሪያው –  የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በድርጅቱ ውስጥ ከነበራቸው የንቅናቄው የግልና የጋራ ሃላፊነት አንጻር ነበር።

1.1      የፓርቲ አካላት እርከን።

አንድ የፓርቲ አካል ትልቁ ዬአመራር አካሉ ጉባኤው ሲሆን ጉባኤው እስኪሰበሰብ ድረስ የጉባኤውን ውሳኔ የሚከውነው ደግሞ ማዕከላዊ ኮሚቴው ሁለተኛውን ደረጃ ይይዛል። ማዕክላዊ ኮሚቴው በተወሰነ ጊዜ ብቻ ስለሚሰበሰብ ማናቸውንም የውሳኔዎቹን ዕለታዊ ተግባራት ኃላፊነቱን የሚሰጠው ለሥራአስፈጻሚ ኮሜቴው ይሆናል። ሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴው እንደ ኮሚቴ በጋራ የሚከውናቸው ተጠያቂ የሚሆንባቸው መስኮች ሲኖሩት ሰፊው የፓርቲው ተልዕኮ የሚከወነው ግን በመምሪያዎች ነው። አንድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የራሱን መምሪያ በግል ሃላፊነቱ የወሉን ድርሻ በሥራ አስፈጻሚ አባልነቱ ይከውናል። የጠቅላላ የፓርቲው መርኃ ህይወት መርሁ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ይሆናል። ስለዚህም ነው የተከበሩ አቶ አንደዳርጋቸው ጽጌን የድርሻ ሰሌዳና የወያኔ ህልም የግንቦትን ጸሐፊ በመያዝ እንደ ጦር የሚፈራውን የግንቦት 7 ሙሉ መረጃ ለማግኘት የማይችል መሆኑን ያብራሩት። በተሰጣቸው የሃላፊነት ማዕቀፍ ውስጥ ብቻ ለዛውም ንቅናቄው በህቡ ስለሚሰራ ሌላም ይፋዊ ነገሮች በአፈጻጻም ሥርዓቶች የተቆለፉ ስለመሆናቸው በአጽህኖት ሊቀመንበሩ የገለጹት። በፓርቲ ህይወት ውስጥ ለቆዬና ለሠራ ሰው ግልጽ ነው።

አሁን እኔ ከዚህ የፓርቲ አደረጃጀትና መርህና ፓርቲውን ከሚመራው ብቸኛ መርሁ ከዴሞክራሲያዊ ማዕክላዊነት ወጣ ያለ እይታ ስላለኝ ነው የግድ ማብራሪያ መስጠት ያስፈለገኝ። ወያኔ ያነጣጠረው ሥምን የማጉደፍ፤ የታማኝትነትን ጥሪት ግድፈትን ቀፍሮ  የፈራውን መጠነ ሰፊ ተቀባይነትን የአረም ፈል ሊያፈላበት ስለፈለገ ይህን በብዕር ቦንብ ድቅቅ ማድረግ እንዲህ አሰኘኝ። አክርክራውንና አተርፍበታለሁ ብሎ ያሰፈሰፈበተን መናኛ ዲስኩሩን አፈር ማስጋጥ ግድ ይላል።

የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እንደ አንድ ኢትዮጵያን የፍትህ ሀገር እንድትሆን ረሃብተኛ ዜጋ ስንመለከታቸው እጅግ ጥልቅ የሆኑ እርስ በእርሳቸው በፋክትና በእውነት ዘለበታማ መስዋዕትነት የከበሩ ሥነ – ምግባር ያላቸው፤ በተግባር የበቁ ዜጋ መሆናቸውን እንመለከትበታለን።

  1.         ምስክርነት

እኔ አጋጣሚ ሰጥቶኝ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን ሁለት ጊዜ መደረክ ላይ አገኘኋቸው። በሙያዬ ሲኔዬር የፖለቲካ ፓርቲ አደራጅ ስለነበርኩኝ ሁለቱንም አጋጣሚዎቼን በግልብ አላለፍኳቸውም ነበር። ውስጣቸውን ጊዜ ወስጄ ነበር ያጠናሁት። መጀመሪያ ያዬኋቸው በጤነኛው ጊዜ ሚያዚያ 29.2006 ሲዊዘርላንድ ጄኔባ ዩነቨርስቲ የሲዊዝ ቅንጅት መሥራች ጉባኤ ላይ እሳቸው „የቅንጅትን መንፈስ ዕያነቡ ሲገልጹ“ እኔ ደግሞ „በጸረ ወንበዴ ትግል የመደራጀት አስፈላጊነትና ድርሻ“ በሚል እርእስ ጊዜ ተሰጥቶኝ አፍ ካለው መቃብር ወጥቼ እንዲህ ካሉትን ታላቅ ሰው ጋር አብሬ ታዳሚ በመሆን ነበር። እንዲሁም በዕለቱ „በጎሳ አስተዳደር የጤና ፖሊሲ ዕጣ ፋንታ የስርጭት ዝበት ያስከተለውን መዘዝ በመረጃ በተደገፈ“ የተከበሩ ዶር አሰፋ ነጋሽ በሰጡበት መድረክ ነበር የተገናኘው። ከስበሰባው በኋላ ስልክም ኢሜልም አላስፈለገኝም። ሀገሬ ኢትዮጵያ ውጭ ሀገር ያላትን ንጡር ሃብት ግን አዬሁበት።

ለሁለተኛ ጊዜ የተገናኘነው ከሦስት ዓመት በኋላ ነበር። በ2009 የካቲት ወር ላይ ነበር። እሳቸው ጄኔባ ዩንቨርስቲ ላይ መድረክ ላይ በገላጭነት አብሬያቸው የነበርኩት መሆኔን ያወቁ አይመስለኝም። ሥሜንም ሆነ ዬኃላፊነት ድርሻዬን አልተናገርኩም። ለግንቦት 7  አውሮፓ አቀፍ መሥራች ናሙናዊ ስብሰባ እሳቸው በገላጭነት ከለንደን እኔ ደግሞ በሰብሳቢነት ከሲዊዘርላንድ ደግመን ፍራንክፍርት አማይን ጀርመን ላይ ተገናኘን። አሁንም አድራሻ ኢሜል አላስፈለገኘም።

ብቻ — በወጣትነቴ ሰፊ እድል አገኝቼ ሊተረጎም የማይችል ብቃት፤ ጥልቅ ተመክሮ፤ ሰፊ እውቀት ካላቸው ወገኖቼ ጋር የሠራሁ ስለነበር ውጭ ሀገር ደግሞ እንዲህ ዓይነት ውስጡ የተደራጀ – መንፈሱ ድርጅት የሆነ የተረጋጋ ሰው በማዬቴ „ተስፋን“ ጸነስኩኝ። በጣም በማስተዋል በልቤ ሙዳይ ወስጥ አስመጠቀኳቸው። ከነዚህ ሁለት ቀናት ውጪ በስልክም በኢሜልም አለተገናኘሁም። ግን መንፈሴን ሸልሜያቸው ኖርኩኝ።

ስለ አቶ አንዳርጋቸውን ጽጌ የመንፈስ ሃብታት 1+1= 2  ወይንም  2×2= 4 ብሎ ሰብዕናቸውንም ሆነ ውስጣቸውን፤ በውስጣቸው ያለውን የማያልቅ ጥሪት፣ ንጹህ ቅን ራዕይ በቀመር መግለጽ የሚቻል አይመስለኝም። ሥራ ነበሩ። በውስጣቸው እራሳቸው ተደላድለው ነበሩ። ራዕያቸው በህዋሳቸው ውስጥ ጽላት ነበር። ኢትዮጵያዊነትን የሚተረጉሙ አመክንዮዎች የሰበለባቸው ነበሩ። የንግግር ሥነ -ጥበብ ሥነ -ምግባርም ከልቡ የተቀበላቸው ልሳነ – ርትዑ ነበሩ። ይልቅ ከ2013 ቃለ ምልልሳቸው feedback ዬቋሰኛው በተቀናቃኝነትን ለመታገል ይመጣል ብለው የሚያስቡትና የሚጠራጠሩት ነገር አለነበረም እኔ ሳያቸው። ስለሆነም እኔ በግሌ ብዙ የሚረብሹኝ ሁኔታዎች ነበሩ። የፖለቲካ ሰው ጠርጣራ መሆን አለበት። ቢሆንስ? ብሎ በህይወቱ ዙሪያ ላሉት ነገሮች አለመመችትን መከብከብ አለበት። አገላለፄ ድፍን ሊሆን ይችላል በሞቴ ፍቀዱለት  —

ካናዳ የሚኖር እጅግ የምወደው ዘመን እንዳይቀማኝ የምሳሳለት ልዩ የሆነ ጓደኛ አለኝ። እኔን በብዙ ነገር ይበልጠኛል። ቀደም ብዬ ስለእሳቸው ስነግረው በአትኩሮት ያዳምጠኛል። ምንም አስተያዬት ግን አይሰጠኝም ነበር። አሁን ይህ ድርጊት ሲፈጸም የሰጡትን የቀደመት ቪዲዮ አይቶ ሥርጉቴ ከምትነግሪኝ በላይ እውነት ሆኖ አገኘሁት አለኝ። የምርም ነው ከልቡ ያዘነው። እንደምታዝኚ አውቄ ነው ዬደወልኩልሽም አለኝ። መተካካት ይኖራል አንዳርጋቸውን መተካት ግን ፈጽሞ አይቻልም። የዘመን ዘለቅ ብቃት እርስተኛ ነውና!

ስለሆነም በምንም ታምር እኛ እያለን የአንዳርጋቸውን ታሪክን ማክሰል ሽፍታው ወያኔ አይችልም። ቁመን እንመሰክራለን። ሥራችን ነው። ትናንት ጠላቶቻችን ታሪካችን ጻፉ እንዳስፈለጋቸው አድርገው። ዘቅዝቀውም አንጠልጥለውም። ዛሬ ግን እልፎች አሏት ልዕልት ኢትዮጵያ። አውሮፓን የመሠረተው የቀደምት ህዋ ድረስ የዘለቀው የቤተክርስትያናት የሊቃናት ገድላት መጸሐፍታት – የትርጓሜ ዕድማታዎች የአመራር ብቃትና ጥበባት ናቸው። የሳይንቲስትነታቸው ምንጭ እናት ኢትዮጵያ ናት።

እኔ እንደማስበው አርበኛ አንዳርጋቸው በጠና ቢታመሙ ስለህመማቸው ሳይሆን በታመሙበት ወቅት ስለሚጓደለው የተሰጣቸው ኃላፊነት መስተጓጎል ይሆናል የበለጠ በሽታቸውን የሚጠነክራባቸው። አብዝቶ በመሥራትና በመልፋት ድካምን ንቆ ትጋትን ማበልጸግ ተፈጥሯቸው ነው ብዬ አምናለሁ። ሌላው በእሳቸው ላይ ዬያሁትና የተገነዘብኩት እንዲሁም ጊዜ ወስጄ ያዳመጥኩት አንድ ነገር አለ። መንፈሳቸውን ለሚሸከመው አካላቸው እረፍት መንሳታቸው ነው። ይህም ብቻ አይደለም አብረዋቸው ለሚሠሩትም ሊደክማቸው ይችል ይሆን ብለውም አያስቡም ነበር ብዬም አስባለሁ። እሳቸው የሚያስቡት የሥራውን ቅልጥፍና ከጥራት ጋር ማዬትን ብቻ ነበር።

ስለዚህ አሁን ጫናን በቀለበት ወዶና ፈቅዶ አግብቶት የኖረው መንፈሳቸው ከጠላት እጅ ሲገባ አካላቸውም ጋር መያያዝ አልቻለም። ተለያይተው ነው የኖሩት ብዬ አስባለሁ። ያን ያህል ጎደሎን ለመሙላት፤ የገቡትን ቃል ዕውን ለማደረግ ሲባትሉ በመንፈሳቸው ላይ ለምሳሌ … 500 ኪሎ ቢጭኑ ቢያንስ ይህን መሸከም እንዲችል አካላቸው ስለሚያሰፈልገው እረፍት፣ አንክብካቤ የተመጠጠነ ጥንቃቄ ሩቡን እንኳን ሊያደርጉ ያልቻሉ ፍጹም የቅንነት ናሙና ሰው ነበሩ። ያስቀመጡት የመንፈስ ጥሪት ቢኖርም ችግር ቢገጥም ሊቋቋም የሚችል ለሥጋቸው፤ መንፈሳቸውን ለሚሸከመው ለአካላቸው ጥሪት አልነበራቸውም። ሥጋቸውን ረስተውት ነው የኖሩት። ሥጋቸው ደግሞ እንደ እኛ የሰው እንጂ ማሽን አልነበረም። ለዚህም ነው በቀጥታ ቪዲዮውን ስታዩት የእኛን ውስጥ ዬሚደበድብ መጎሳቆል የምናዬው። ይህን አምክንዮ ይህን ክስተት የሥነ ልቦና ባለሙያዎች በሚገባ ሊተርጉሙት ይችላሉ ብዬ አስባለሁ። አብሶ የግንቦት ልጆች ይህ ውስጥን በሲባጎ የሚሰረስ ጭብጥ ተክቶ የመገኘትን አቅምን አምጠው መውለድ ያለባቸው ይመስለኛል።

3.      ጸጸት።

ስክነታቸው – እርገታቸው – በተሰጣቸው ጊዜ መንፈስን ይዞ የማቆዬት ብቻ ሳይሆን እንዳይረሱ የማድርግ አቅማቸው ወደር የለሽ ነበር። ስለሆነም እኔ በግሌ ሀዘኔ ጥልቅ ነው። መከፋቴም አጥንቴን ሰንጥቆታል። አመለጡን። እንደ ሰው ልብ ኖሮን እግዚአብሄር ይስጥልን ሳንል። የነፃነት – የርትህ – የፍትህ  – ታጋይነታቸውን ሳናከብረው – አፈሰስነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ከልቡ ሆኖ፤ ከመንፈሱ ሆኖ ዳግም መልሶ በነበሩበት አቅም ለማያገኛቸው ታላቅ የቁርጥ ቀን ልጁ ፍቅሩን ያለውን አክብሮትና አድናቆቱን እንደወርቅ ያፍልቀው ዘንድ በተመስጦበአንክሮ – በትህትና እጠይቃለሁ። ኃላፊነትን ወስዶ ለምልዕት ዕንባ እንዳሉት ሆነ መገኘት መቻል ሥጦታው የአባታችን የመዳህኒዓለም ነው። ይህን ማክበር ደግሞ የአምንያን ግዴታ ነው። መተከያ የለሹን ልጁን የኢትዮጵያ ህዝብ አበክሮ በጸሎት ጥበቃውን ሊያደርግለትም ይገባል ባይ ነኝ።

  1. የተቃጠለ ዬአፈር ጢስ ድራማ።

ከጨረቃ ፈስ ስለ „ኢትዮጵያዊነት“ የምናገኘው አዎንታዊ መረጃ ፈጽሞ የለም። መጠበቅም የለብንም። የከሰለ ያረረ ድራማ። የተኮማተረ – የጠወለገ - የነፈሰበት - የወደቀ- ጊዜው ያለፈበት፤ ተንተርሰውት ያደሩት ኩፍትርትር ያለ አንቀልባ መረጃ ነው ከሰላይ ዞገኛ ምርጦች ዘጋቢዎቻቸው የምናዳምጠው። ለዚህ ስሌት ነው የዘር በሽተኛው የጎጡ መርዝ ያሰከረው ብኩናቸው ወደ ሀገረ ኢትዮጵያ የተመለሰው። የጎረበጠው – ያነገበገበው – ያርመጠመጠው ግንቦት 7 እና ኢሳት ነበሩ። ብዕሩም – ካሜራዉም ለጥፋት እንሆ ይኳትናሉ። ልሳኑን ተዘግቷል። ሳቁን አውጥቶ መሳቅ እንኳን አይችልም። አሜኬላ ተግባሩ ሰብዕዊ ነፃነቱን ደፍኖታል። ቀና ብሎ ከቶም አይሄድም። የአሉላ ዕንባ ፍል ነውና ይገርፈዋል። የዬኋንስም ደም ያቃጥለዋል። ባንዳነት ቅንቅን ነው = ዘነዘና የሚያስቀር። ባንዳነት ነቀዝ ነው – ቀፎ የሚያስቀር። ባንዳነት ዛሬን እያስካደ ነገን ደርምሶ የሚጠብቅ ዕብቅ የራቁትነትነት ጉዞ ነው። ባንዳ ሆኖ ከመኖር ጭንጋፍ ሆኖ አፈር ውስጥ ማደግ በእጅጉ ይበልጣል። ቀን ያልፋል። ክፉ ተግባር ግን ህሊናን አስሮ እንጦርጦስ ይልካል። በምንም መልኩ ቢሆን ሸርና ደባ አንገታቸውን ቀና አድርገው ዋቢ ሊሆኑ አይቸሉም። የጥግ እርብራብም አያዘጋጁም። ይልቅ ናዳና – ንደት – መደርመስን አስከለትለው  ቀንን ይጠብቃሉ።

ወያኔና ግብረ አበሮቹ ዛሬ ያሸነፉን – የቀጡን ሊመስላቸው ይችል ይሆናል። የበደሉ ረመጥ ልቦናችን ውስጥ ኃይልና አቅም ፈጥሮ በዬደቂቃው ከእናት ሃገራችን ፍዳና መከራ ጋር እንድንቆራኝ ያደርጉናል እንጂ የነቃው መንፈሳችን ሊበርደው ከቶውንም አይችልም።

ያ — ዬመከራ ጩኽት የወንበዴው ወጀብ ከሰላማዊ ትግላቸው ያደናቀፋቸው የአርበኞቻችን ዬአብርሃም፤ የሃብታሙ፤ የዳንኤል፣ የሺበሺ  ጩኽት እንደሆን እንረዳለን። የእነሱ ክስ ዬተያያዘው ከማን ጋር እንደሆነ የሚያብራራልን አንበደርም። ቀና ሲሉ ቀንበጦች መንፈሳቸው – ህሊናቸውና ተስፋቸው በግፍ እንዲፈልስ ወያኔ ያደረጋል። ቀደም ባለው ጊዜም የዬካቲቱ የዕህል ዘረፈ ዘመቻው በመጀመሪያ ጥቃቱን የሚሰነዝረው ት/ቤት በማፈረስ ጥቁር ሰሌዳን በማቀጠል ነበር። ስለምን? ወያኔ አዲስ ኢትዮጵያዊ ትውልድን የማዬት ህልም ፈጽሞ ስላልነበረው።

ወመኔው ወያኔ የቀደሙትን ታሪክ ጠገብ አዋቂ ባለግራጫዎችንም ሳይራራ አፍኖ በገደል ለቋል። ቅርሶቻችንም ቢሆኑ ከባንዳው የወያኔ ጥቃት አላመለጡም። የዘረፈውን ዘርፎ፣ የተቀሩትን ነዲድ እሳት ተሸሽጎ በመለቀቅ አቃጥሎ አውድሟቸዋል። ቅዱስ ሥፍራዎችን፣ በፈጣሪ የተመረጡ ቦታዎችን፤ የማህበረ ምዕመኑን መንፈስ ማረፊያ መጽናኛወችን ገዳማት ሆነ መስኪዶችን በትዕቢት ተደፍሯል። ትውልድን መንቀል፤ የቦታዎችን ሥም መደለዝ ወይንም መሰረዝ የተፈጠረበት ባንዳዊ ዶክትሪኑ ነው። ቀጣዩን ትውልድም በዘመቻ አጨዷል። የባድመ ጦርነት ግቡ ያ ነበር። በቀሉ በሁለት የተሳለ አፍ ኢትዮጵያን በላት – ፈጃት።

  1. መቋጫ

ወገኖቼ ውድ ግፉዐን – እኔ እላለሁ ሁሉም ሰው በውስጡ ለመኖር ውስጡን ለእናት ሀገሩ የዕንባ ምጥ መፍቀድ ያስፈልገዋል። ሃብት ቢፈራ፤ ልጅ ቢወለድ፤ ትዳሩ ቢጎመራ፤ ቢማሩት – ቢመራመሩት ሀገር ከሌላ ግንጥል ጌጥ ግማሽ ሹሩባ ነው። ሀገር ማለት ነፍስ ያለው ህይወት ማለት ነው። ባህል ማለት መንፈስ ያለው ኑሮ ማለት ነው። ትውፊት ማለት ትናንት ያለው ነገ ማለት ነው። እምነት ማለት ድግሞ የተስፋ እልፍኝ ማለት ነው። ሁሉም ግን በሽፍታው ወያኔ ተቀጠቀጡ። መጠጊያ ብትን አፈር ለማኝ ሆኑ። የኔዎቹ  የምጥ ጊዜ ነው – የውቂ ደብልቂው አይደለም።

በዘመነ ሂትለር ኦሾትዝ በሚባል የፖላንድ ሀገር ሰው በላ ቦታ የሞት ተረኛ አይሁዶች ተራቸው እስኪደርስ ድረስ ወገኖቻቸውን በመርዝ በናዚ ወታደሮች ተገደው ጨረሱ – እያዩ ለመቀጣጫ። የዛሪዎቹ ኢትዮጵያዊ ናዚዎች ግን ለሆዳቸው ሲሉ ነው የናዚው የወያኔ ግብረ አበር ሆነው ወገኖቻቸውን የሚቀጠቅጡ – የሚያርዱ – የሚደፍሩ – የሚያቃጣሉ – በመርዝ መንፈሳቸውን የሚያቃጥሉት። ዬአርበኛ አንዳርጋቸው ገጽ ተቆርጦ ስንብቶ የተቀቀለ ጎመን ይመስል ነበር። ይህ ግፍ ወዮ! ነው የነነዌን ቁጣ ይልካል። አምላኩን የጠዬቀ የዕንባ ምጥ ዬማዕት ሞገዱን ያዘንባል። ወዮ! ከናዚ ወያኔ ጋር ያበረ – የተባባረ ….. በአንድም በሌላም ቅጣቱ ቀኑን ጠብቆ ይጠጣታል። ሲሆን ከፍልሰታ ግድፍት በፊት አንድ ታምር እናይ —-

ወገኖቼ ጨዋዎቹ፤ ለህሊናችሁ ዬምታድሩት – ጀግኖቻችን ቢሞቱም – አይሞቱም፤ ጀግኖቻችን ታሪካቸውና ገድላቸው ለምለም ነው። መከራቸውን ቆመው ጨርሰዎታልና በቁማቸው የጸደቁ የገነት ፍሬዎች ናቸው። ተጋድሏቸው እጥፍ ትውልድን ይገነባል። ስለሆነም ከሽፍታው ወያኔ ጋር በጀግኖቻችን ፍልቅ የተግባር ማንነት ማናቸውም ዘርፈ ብዙ ፍሬዎች መደራደር የለብንም። ቅራፊ መንፈሳችን ለናዚ መረጃ ማወስ አይኖርብንም። ነገን ያለመው ማንነት አለው። ድንቅ ኢትዮጵያን የናፈቀው የአርበኛው መንፈስ አይሞትም፤ አይድክምም፤ አያንቀላፋም። በእጥፍ ተባዝቶ – በእጥፍ ተራብቶ እሱ በፈቀደ ቀን እሱ ባለለት ምኞትና ተስፋ ዕውን ይሆናሉ። እንበርታ!

የኔዎቹ በዚህ እርእስ ዙሪያ የነበረኝ ቆይታ እንዲህ ተከወነ። የመሰጠርኳት ውበታማ እርእስ ደግሞ አለችኝ።  ከልፋጩ ሁለተኛ የቪዲዮ መረጃ ጋር የቀሩኝ ጥቂት ነገሮችን ስላሉኝ ተመላሽ ነኝ። ማለት ርእሱ ሌላ ጭብጡ ግን ከቀደሙት ሁለት ክፍሎች ጋር የሚወራረስ መሰል ቁምነገሮችን ይዤ እስክመጣ ድረስ ደህና ሁኑልኝ። ውድድድ ….

6. ተግባር – እጣታችሁን እባካችሁ  ከተግባር ጋር አቆራኙት። ፍጥነት …. እሺ

http://ecadforum.com/2014/07/31/urgent-campaign-to-call-fax-white-house/

 

 

  • ማሳሰቢያ ለቤተሰብ – ወያኔ ውሰዱ የፈለግሁት አገኝቻለሁ ቢል። ከርክክቡ በፊት ደማቸው ለማዕከላዊው የለንደን የባይወለጂ ሥነ – ምርምር ማዕከል መላክ አለበት። እዚህ ቦታ ሠራተኛ ሲቀጠር እንኳን ከደህነነት ዋና መ/ቤት መረጃ ያለገኜ አይቀጠረም። የሰው ሥነ – ተፈጥሮና ሳይንስ የሚፋጠጡበት ጥብቅ ቦታ ስለሆነ። ስለዚህ ውስጣቸውን አውልቆ ከሆነ ወያኔ በእጥፍ ድርብ ዕዳውን መክፈል ስላለበት ቅድመ ሁኔታው  በአግባቡ በጥንቃቄ መታደም አለበት።
  • የጨረቃ ፈስ —የጨረቃ ፈስ በልጅኔቴ ነው የመውቀው። መልኩ አፈር ይመስላለ። ቅርጹ ድንቡልቡል ነው። መተንፈሻ የለውም።ስትነከት ትንቡክ ትንቡክ ይላል። የፈር የተቃጠለ አፈር ጢስ ጢስ ብቻ ነው ውስጡ የወያኔ ዘመንም እንደዚሁ  ነው። እራሱ ከመክፈታችሁ በፊት ስትንኩት ትንቡክ ትንብዩክ ነው ሚለው ጠረኑ ደግሞ ስምየለሽ ነው። በቃ ወያኔ ማለት ሁለመናው የተቃጠለ የአፈር ጢስ ነው። ዘር የማያበቀለ የመከነ እሮ!

 

ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር ኢትዮጵያዊነት!

 

እኔው ሥርጉተ ሥላሴ – ለጀግኖቼ ቤተ –  ብቃት ቀናዕይ ነኝ!

 

ፆመ ፍለሰቲትን ለጀግናቻችን ሱባኤ እንያዝበት አደራ -  ህይወቱ ያላችሁ።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

Comment

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>