ከሥርጉተ ሥላሴ 13.08.2014 ( ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
በትቢያ – ድሪቶ
በቋሰኛው – ጉቶ
ተመተረ ዘመን – በቅንቅን ተበልቶ፤
በበደል ተቁላልቶ
በግለት ተወግቶ
በቁርሾ ተሰልቶ።
ሲናሳ መራራ – የአስተሳሰብ ንቅዘት
ሲሰነብት እሬት – የባንዳነት ስባት
- ብነት።
ትናትን – ገደለ
ዛሬን – ረሸነ
ነገን – አተነነ
ዬበነነ።
ዞጋማ ቁሌቱ
ቅብረት ነው ስሌቱ
የወያኔ ማቱ
ጥፋቱ።
ዬት ሳውቅህ – በምንህ!?
ቃር=== ማ —- ነው ቃርሚያህ
የደም ሲቃ ግብርህ።
ዘረፋ – ሰርዴታህ
ዕበለትም – አትራፊህ፤
ሲካዳህ – ዕለትህ
የቆዬ ሰው፤ – ይይህ
ትነቱ ዘመድህ – የዘለአለም ስንቅህ
ፍልሰትህ —።
ኤሉሄ! ትላለች እናት ልጇን አጥታ፣
ኤሉሄ! ትላለች ባዕት ዕንባን በልታ፣
ኤሉሄ! ይለዋል ምጣድ የድርቅ ዋልታ
ኤሉሄ ትላለች – እንሥራ ተጠምታ፤
የሲሳዩ ማሳ በዕንባ እዬተፈታ
በጫካ - ገበጣ።
ሸንተረር አነባ – በጉልበት ሲመታ
ወንዙም ሆዱ ባባ – በእርግጫ ሲለጋ
አፈር አለቀሰች – ተግርፋ በአለንጋ ….
… በበቀል ተወራ – ለድርቡሽ ተሰጥታ
ከውስጧ – ተራቁታ።
ጥንት – ከጥዋቱ፤ ልጇ ተቆላምጦ
የሚፈልገውን እንዳዬው መራርጦ …
ታዬ በወያኔ – ቀኑ ተገልብጦ —-
…. ተቀማ ዕህሉን፤ ወገን በወረንጦ
አምጦ።
ወያኔ የሚሉት —- የመከራ ጥሪት
ወያኔ የሚሉት — የአሳሩ ስሌት
ወያኔ የሚሉት —- የመጋኛ ሌሊት
ወያኔ የሚሉት — የአሲድ እፉኝት
ህማማት።
የዋህነት – ቀብሮ
ቅንነትን – ቀብሮ
አብሮነት – ተቀብሮ
ትህትናንም – ቀብሮ
መተዛዘን – ቀብሮ
ነፃነት ተባሮ
መርዛማው ወያኔ – ውሳጣችን – ቆፍሮ
አዬነው እራሱን በጥፋት ተቀብሮ፤
በመንደር ተዋቅሮ
እሮ!
አመዳማ — ጉዞ
ጎርብጥባጣ — አዞ
ሳጥናኤል — ተመዞ
ለጥፋትም — ታዞ፤
ታሪክን – አንቅዞ
ትውፊትን – አፍዝዞ
ባህልን – ጠምዝዞ
መንፈስ – ተገንዞ
ናውዞ።
ሞት ቢሞት ሞቱ ነው
ቢኖርም ሞቱ ነው
ሰኔልና ቹቻ
ስለት ለቋቁቻ።
28.06.2014 ሲዊዘርላንድ ቪንቱርቱር ተጣፈ።
መከራን ሳዳምጠው ደሜን አገኘዋለሁ!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።