ዛሬ የምንገኝበት ዲሞክራሲያዊና ቴክኖሎጂካዊ ዘመን ህዝባዊና መንግስታዊ እውቅና ስለነበረው አንድ ሰው የኦሟሟት ምስጢር ጥያቄ ማቅረብ ወንጀል አይደለም። ግርድፍ ማስረጃን አንተርሶ እውነታው እንዲታወቅ መጻፍም አስተዋይ ህሊና ላለው ሰው መጥፎነቱ አይታየውም። ይልቁንም ተጠየቅነቱ ፋይዳ የሚኖረው ለምን የአንድ ሰው አሟሟት ብቻ የሌሎች ወገኖቻችን አሟሟትም ይታወቅ የሚል መሰረታዊ ጥያቄ ከተነሳ ብቻ ነው። ይህም ቢሆን ይቻላል፡፡ እኔ ግን ጥያቄውን ያቀረብኩት በቅርብ ስለማውቀውና ካገኘሁት ማስረጃም ተነስቼ ነው። ሌሎቹ ደግሞ እንውቃለንና ማስረጃም አለን ብለው ቢነሱ መሰረተ ሀሳባቸውን ደጋፊ እንጅ ተቃዋሚ አይደለሁም ቢሉ አጠቃላይ ትኩረቱ ወደ ዋናው የኣቶ በዓሉ ግርማ አሟሟት ተጠየቅነት ያንደረድረናል።–[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—-