Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የግብረሰዶማዊነት አደጋ – (የአቡነ ሳሙኤል ወቅታዊ ጽሑፍ)

$
0
0

(አባ ሳሙኤል)

(አባ ሳሙኤል)

ግብረሰዶማዊነት ማለት በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወይም ተራክቧዊ መማለል ነው። ግብረሰዶማዊነት /Homosexuality/ ተፈጥሯዊ ከሆነው ግንኙነት የተለየ ሲሆን ይህም ወንድ ከወንድ /Gay/፣ ሴት ከሴት /Lesbian/ ጋር የሚፈጸመው ነው። እንዲሁም አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ከተመሳሳይ እና ተቃራኒ ጾታ ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት /Bisexuality/ ይሉታል። ይሁንና በሥነተፈጥሮም ሆነ በሳይንስ እንዲሁም በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮ፣ ጤናማና ተቀባይነት ያለው ወንድ ከሴት፣ ሴት ከወንድ ጋር የሚፈጽሙት ግብረሥጋ ወይም ሩካቤ ብቻ እንደሆነ ነው።

የግብረሰዶማዊነት አደጋ እንዴት ይገለጻል?
ይህን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ለግብረሰዶማዊነት የሚያበቁ ምክንያቶችንና የሚያስከትሉትን አስከፊ ጉዳቶች እናያለን። ምክንያቶቹን ስንጠይቅ የዕጾችና ሱሶች ተገዢ መሆን፣ ተገድዶ መደፈር፣ መጠለፍ፣ ተቃራኒ ጾታዎችን መጥላት፣ ለተመሳሳይ ጾታ መማረክ ወዘተ.. ሲሆን የሚያስከትላቸው አደጋዎችም ድብርት፣ ጭንቀት፣ ራስን መውቀስ፣ የህሊና ጸጸት፣ በከባድ በሽታ መለከፍ፣ ፊስቱላ፣ ራስን ማጥፋት፣ የኢኮኖሚ ውድቀት ወዘተ… ናቸው።ስለግብረሰዶማዊነትና ፀያፍ ልምምዱ በተመለከተ የመጀመሪያውን መረጃ የምናገኘው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው። ከታሪኩ መረዳት እንደምንችለው ከ5000 ዓ.ዓ በፊት የነበሩት የሎጥ ዘመን ሰዎች በዚህ አስከፊና አሳዛኝ ድርጊት ውስጥ በመገኘታቸው፣ ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሣ በወረደው የእሳት ዲን ሰዶምና ጎሞራ የተባሉ ከተሞች መጥፋታቸውን ነው። አሁን ባለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመንም አደጉ ከሚባሉት ምዕራባውያን እስከ ደሀ አገራት ድረስ ርኵስ ተግባሩ ቀጥሎ ይገኛል። በተለይም ምዕራባውያኑ ይህን ርኵስ ተግባር እንደ ሥልጣኔ በመቁጠርና በሰባዊ መብት ስም /በቀጣዩ ጽሑፌ የምናየው ይሆናል/ የሕጋቸው አካል አድርገው በመደንገጋቸው፣ ድርጊቱ ተቀባይነት አግኝቷል። ታዳጊ ሀገራትም ብድርና ዕርዳታ ማግኘት ይችሉ ዘንድ የግብረሰዶማዊነትን ሰነድ እንዲፈርሙ የማባበልና የማስገደድ ዲፕሎማሲያቸውን ተያይዘውታል።

ከሀገራቱ ሁኔታ ለመረዳት እንደሚቻለው የተጽዕኖ ዲፕሎማሲውን በመቀበልና ባለመቀበል የቆሙ እንዳሉ ሁሉ የተንበረከኩም አልጠፉም። ለምሳሌ የዑጋንዳ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ጠንካራ አቋሙን ሲገልጽ ከቆየ በኋላ መጨረሻ ላይ ሊንሸራተት ችሏል። አትዮጵያም በተለያየ ወቅት በዚህ ጫና ውስጥ ያለፈች ስትሆን በዋናነት ግን ግብረሰዶምን በተመለከተ በወንጀል ሕጓ የሚያስቀጣ ድርጊት አድርጋ መደንገጓ ውጫዊዉን ተጽዕኖ በብርቱ እንድትከላከል አስችሏታል። ለዚህ ታላቅ ውሳኔ የሀገሪቱ መሪዎች ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽዖ ምሥጋና ሊቸራቸው ይገባል። የመሪዎቹ ማሳመኛና የመከላከያ ሐሳባቸውም፡-
ሀ/ ሕዝቡ በሚገኝበት የክርስትና እና እስልምና ሃይማኖቶች መጻሕፍት ግብረሰዶማዊነት የተወገዘ መሆኑ፣
ለ/ ለረዥም ዘመናት ከአንዱ ትውልድ ወደ ቀጣዩ ትውልድ በቅብብሎሽ ተጠብቆ የቆየውና አሁንም የሚገኝበት ባህልና ሞራል ግብረሰዶምን ጸያፍና ርኵስ አድርጎ ስለሚያምን ነው። በሌላ በኩል ሕዝብ መንግሥት ነው፤ መንግሥትም ሕዝብ ስለሆነ የሕዝብን ዕሴት ሕዝብ ራሱ ያስከብረዋል።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች የምናየውና የምንሰማው ሁኔታ፣ እኒህ ለዘመናት ተጠብቀው የቆዩት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ሞራላዊ እሴቶቻችን አደጋ ላይ መውደቃቸውን ነው። ጭፈራ ቤቶች፣ የጫትና ደባል ሱስ ማዘውተሪያ ሥፍራዎች፣ ምሽት ክለቦች፣ አንዳንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሳይቀሩ በዚህ የዐመጽ ተግባር መጠለፋቸውን የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ። ከዚህ አኳያ እንደ ሀገር የተደቀነብን ሥጋት ምን ያህል አሰቃቂ እንደሆነ በቃላት መግለጥ ያስቸግራል። ስለሆነም ወላጆች ልጆቻቸውን፣ የሀገር መሪዎች በየተዋረድ ያሉ አመራሮቻቸውን፣ የሃይማኖት
አባቶች ምዕመናኖቻቸውን፣ እንዲሁም በየዘርፉ የሚገኙ ምሑራን ሀገርንና ትውልድን ለማዳን በአንድነት የሚቆሙበት ግዜ አሁን ነው።ከላይ እንደጠቀስኩት ምዕራባውያን ለጸያፍ ድርጊታቸው ዕውቅና ይስጡት እንጂ የተጋፈጡትን ማኅበራዊ ቀውስ ከቶውኑ ሊቋቋሙ አልቻሉም። ቀላል ቁጥር የማይሰጣቸው ዜጎቻቸው ራሳቸውንና ሌላውን በማጥፋት ተግባር ውስጥ መሆናቸውን ከብዙኀን መገናኛዎቻቸው እያየን እየሰማንላቸው ነው። ይህም ሰዶማውያኑ ራሳቸውን በመውቀስና በሚሰማቸው ጸጸት የተነሣ እንደሆነ የሥነልቡና ምሑራን ይናገራሉ።
እንደ CDC /Center for Disease Control/ ያሉ ዓለማቀፍ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል፣ ግብረሰዶማዊነት ከሚያስከትላቸው አያሌ ጉዳቶች ውስጥ ስድስቱን በሳይንሳዊ ጥናታቸው ይፋ ያደረጉ ሲሆን ለግንዛቤ እንዲረዳን በአጭር በአጭሩ እንያቸው፡-

ተላላፊ በሽታ
ሰዶማዊነት በግብረሥጋ ለሚተላለፉ በሽታዎች በተለይም ለባክቴሪያና ቫይረስ ተጋላጭ ያደርጋል። እነዚህ ተላላፊ በሽታ አምጭ ረቂቅ ተዋህሲያን ከአንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው በቀላሉ የሚተላለፉ ሲሆን፣ የበሽታ ተቀባዩ ሰው በተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅም /Immunity system/ ሊቋቋመውና ሊከላከለው የማይችለው ይሆንበታል። እንደ ሲዲሲ መረጃ ከሆነ በአሜሪካ ከጠቅላላው ሕዝብ ሁለት በመቶ ያህሉ ግብረሰዶማዊያን እና ሌዝቢያን ሲሆኑ፣ ከእነዚህም ውስጥ ስልሳ አንድ በመቶዎቹ በደማቸው ውስጥ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ያለባቸውና ከቫይረሱ ጋር መኖራቸውን እንኳ የማያውቁ ናቸው። ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሣ የደም ምርመራ አያደርጉም። ይህ ማለት ለሕይወታቸው ዋጋና ትርጉም አይሰጡም እንደ ማለት ነው።

የኢኮኖሚ ድቀት

በአንድ ሀገር አምራችና የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ የሚባለው ከ15 እስከ 64 ዕድሜ ድረስ ያለው የሰው ኃይል ሲሆን፣ ከ65 ዓመት በላይ የሚገኙ አረጋውያንና ለሥራ ያልደረሱ ሕፃናት ደግሞ ጥገኛ ወይም በኢኮኖሚ መዋቅር ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የሌላቸው እንደሆኑ የሥነ-ምጣኔ ባለሞያዎች ይናገራሉ። ስለዚህ የአንድ ሀገር አምራች ኃይል ሲታመምና በሞት ሲለይ፣ የምርት መጠን የሚቀንስና ተተኪ የሰው ኃይል እስኪዘጋጅ ድረስ ኢኮኖሚው እንደሚናጋ ነው እነዚሁ ባለሙያዎች የሚገልጹት።ከላይ የተጠቀሰው ድርጅት ባካኼደው ጥናት የአሜሪካ መንግሥት፣ ለ40 ሺ ያህል ታማሚዎች ወይም በሥራ ገበታቸው ላይ ላልተገኙ ሠራተኞቹ ማስታመሚያ በዓመት 12 ነጥብ 1 (አሥራ ሁለት ነጥብ አንድ) ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በአመዛኙ የሚሞቱ ናቸው ብሏል። እንግዲህ የበለጸገችዋን አሜሪካን ችግሩ ይህን ያህል ከነቀነቃት ኢትዮጵያንና ሌሎች ደሀ ሀገራትንማ
እንዴታ! እንዴታ!

የአዕምሮ ሕመም

ግብረሰዶማዊነት በርኵሳን መናፍስት ግፊት የሚፈጸም ሰይጣናዊ ተግባር በመሆኑ በመልካምና ቅዱስ መንፈስ ሥራቸውን ከሚያከናውኑ ሰዎች አዕምሮና አስተሳሰብ የተለየ የአዕምሮ ሕመም ያጋጥማቸዋል። ስለዐመፃ ተግባራቸው በቤተሰዎቻቸውና ኅብረተሰቡ ስለሚገለሉ በታናሽነትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ከባድ ለሆነ የአዕምሮ ሕመም ይዳረጋሉ። የጥፋተኝነት መንፈስ፣ ፍርሃት፣ ድብርት፣ ብስጭት፣ ራስን ለማጥፋት መነሣሣት ወዘተ… ዓይነቶቹ ስሜት በግብረሰዶማዊነት የሚመጡ ናቸው። ከጠቅላላው ግብረሰዶማዊ ሃምሣ በመቶ ያህሉ በጭንቀትና ድብርት እንዲሁም ለአደንዛዥ ዕጾች የተጋለጡ ናቸው።
በጥፋተኝነት ስሜት ደግሞ ሁሉም ማለት ይቻላል ራስን በራስ እስከማጥፋት ግዴለሾች ናቸው። የአንድ ግብረሰዶማዊ ዕድሜ ከአንድ ጤነኛ ሰው በ24 ዓመት ያህል ያነሰ እንደሚሆን ጥናቶች ያሳያሉ። በሚያድርባቸው ክፉ መንፈስ የተነሣ ሰዎችን የመጥላት፣ የመተናኮል፣ የመበቀልና ለማናቸውም ግጭቶች በቀላሉ ተጋላጭ ያደርጋቸዋል።

ጠለፋ

ብዙዎቻችን ጠለፋ የሚፈጸምባቸው ለጋብቻ የደረሱ ሴቶች እንደሆኑ እናውቃለን። አሁን ግን ግብረሰዶማዊነት በመስፋፋቱ ምክንያት ጠለፋ የሚፈጸምባቸው ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንድ ሕፃናትም የድርጊቱ ሰለባ ሆነዋል። በንጽጽር ሲታይ በአሜሪካ ከተፈጸሙት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል 24 በመቶው
በግብረሰዶማውያን እና 9 ነጥብ 6 በመቶ ያህሉ በተቃራኒ ጾታዎች ‘Heterosexuals’ እንደሆነ ነው። በእርግጠኝነት ሁሉም ወላጅ በልጁም ሆነ በወገኑ ጠለፋና የአስገድዶ መደፈር ጥቃት እንዲገጥመው አይሻም። ይሁንና በአሁኑ ወቅት ወንጀሉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ሕፃናቱን በተገቢው ሁኔታ ሊቆጣጠር ይገባል። ለሱስ ተጋላጭ በሆኑ ነገሮች እንዳይጠመዱና የርኵሰቱን ዓላማ ከሚያስፋፉ ሰዎች እንዲርቁ መምከርና ማስተማር ያስፈልጋል።

ብዙ የወሲብ ጓደኞችን ማጥመድ
ግብረሰዶማውያን እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ የወሲብ ጓደኞችን ይቀያይራሉ። ይህም እርስ በራሳቸው በሚያድርባቸው አለመተማመንና በጨለምተኝነት ሕይወት መኖራቸውን ያመለክታል። ተመራማሪዎቹ ቤልና ዌንበርግ ስለዚሁ ጉዳይ ባደረጉት ጥናት “83በመቶ ያህሉ ግብረሰዶም አሜሪካውያን 50 ያህል የወሲብ ጓደኛ፣ 43በመቶ ያህሉ 500 የወሲብ ጓደኛ፣ 28በመቶ ያህሉ ደግሞ ከ1000 ወይም ከዚያ በላይ የወሲብ ጓደኞች ይኖራቸዋል” ብለዋል። ሉማን የሚባል ሌላ ተመራማሪ ደግሞ “85በመቶ ያህል ሴቶች፣ 75በመቶ ያህል ወንዶች ለወሲብ ጓደኞቻቸው ታማኝ አይደሉም፤ 4 ነጥብ 5 ያህሉ ግብረሰዶማውያን ለወሲብ ጓደኞቻቸው ይታመናሉ” ይላል። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግብረሰዶማውያን እንደ ዓለማቀፉ ምሥጢራዊ ቡድን /Member of secret society of the world/ ጋር ግንኙነት እንዳላቸውና ይህም ትስስርን በመፍጠር አባላትን ለማብዛት ሚንቀሳቀሱበት ስትራቴጂ መሆኑ ነው።

የኅብረተሰብ እልቂት
ምንም እንኳ በተጠላ ተግባራቸው ቢገለሉም ግብረሰዶማውያን የማኅበረሰብ አባል፣ የሀገር ዜጎችና የዓለም ሕዝብ አካል ናቸው። እናም በሚፈጽሙት ውጉዝ ተግባር የተነሣ ለተለያዩ ሕመሞችና ራስን በራስ ማጥፋት ወዘተ… ተጋልጠው ካለቁ ግለሰብ ሳይሆን ቤተሰብ፣ ቤተሰብ ሳይሆን ኅብረተሰብ ብሎም የሀገር ሞትና ጥፋት ይከተላል። ጋብቻ ተመሥርቶ ዘር ካልተተካ፣ ሥራ ተሠርቶ ምርት ካልጨመረ፣ ሰው ታምሞ ካልዳነ በርግጥም የኅብረተሰብና የሀገር ሞት መሆኑ የማይታበል ነው።እንግዲህ ስለግብረሰዶማዊነት ጠንቅና የሚያስከትለው መዘዝ ይህን ያህል ከተመለከትን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት
እስከ ራዕይ ድረስ ደግሞ ፍጹም የተጠላ እና ሞት የሚገባው ኃጢአት ተደርጎ መጠቀሱን ባለመዘንጋት ነው። ለአብነት ያህል ግን ተከታዮቹን ማየት እንችላለን። ዘፍ ፲፱. ፩- ፴፰ ‹‹ሁለቱ መላእክቶች በመሸ ግዜ ወደ ሰዶም ገቡ። ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ግዜ ሊቀበላቸው ተነሣ። በፊቱንም ተደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፤ አላቸውም ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ፤ ከዚያም እደሩ። እግራችሁንም ታጠቡ። ነገ ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትኼዳላችሁ። ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየሥፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ ቤቱን ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፡-
በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው አሉት። ሎጥም ወንድሞቼ ሆይ! ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ እነርሱን ላውጣላችሁ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ እነርሱ በጣሪያዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና። እነርሱም ወዲያ ሂድ አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ፤ ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል፤ አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን፤ ሎጥንም እጅግ ተጋፉ፤ የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ። ሁለቱም ሰዎች ሎጥን ወደ ቤት አገቡት፤ መዝጊያውንም ዘጉት። በቤቱ ደጃፍ የነበሩትም ሰዎች ከታናሾች ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው። ደጃፉንም ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ። ሮሜ ፩፤፳፮-፳፰ ‹‹ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው።
ሴቶቻቸውም ለባህሪያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕሪያቸውን በማይገባ ለወጡ። እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕሪያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በራሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ። ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስህተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ።››

ማጠቃለያ

ግብረሰዶማዊነት በሃይማኖትም በሳይንስም ጎጂ እና የተጠላ ድርጊት መሆኑን ለማሳየት ሞክሬያለሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲያውም ሰውን ከመግደል በተካከለ ሁኔታ ኃጢአት መሆኑን ተናግሮ ሲያበቃ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ከእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደሌላቸው ገልጿል። አንዳንዶቹ ግን መጽሐፉ አላወገዘንም ሲሉ ይደመጣሉ። ይህ ፍጹም ክህደት ነው። መጽሐፉን ቢክዱ እንኳ ይህች ዓለም በመረጃና በብዙ የተፈጥሮ ምስክርነት የጸናች ናት። ስለዚህ ካላወቁ መማር፣ ከተማሩ የተማሩትን መተግበርና በሥራ ማሳየት ይልቁንም ከዚህ አጸያፊ ተግባር መውጣት አለባቸው። መጽሐፉማ እንኳንስ ግብረሰዶማዊነትን የሚያህል አስከፊ ተግባር ይቅርና ለትንንሽ በደልና ኃጢአት ሥርዓትና ሕግን የሚሠራ መጽሐፍ ነው። ለምሳሌ ከግብረሰዶማዊነት ውጭ ያለው ራስን በራስ የማርካት /Masturbation/ እና መሳሳም ወዘተ… ሁሉ ትክክል እንዳልሆኑ የሚያስተምር መጽሐፍ ነው። ይልቁንም እንደዚህ ሚያደርጉ ሁሉ ሕግን ተላልፈዋልና ንስሐ ካልገቡ፣ ደግመው ወደ ኃጢአት እንዳይመለሱ ቃል ገብተው ለእግዚአብሔር ካልታመኑ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

(አባ ሣሙኤል፤የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ናቸው።)¾ *ይህ ጽሁፍ በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወትቷል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>