Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የሽብርተኝነት ምንጭ ጭቆና ነው!

$
0
0

Abrham Destaደርጎች ‘ወንበዴዎች’ አሉን፤ ኢህአዴጎች ‘አሸባሪዎች’ አሉን። ያው ነው፤ ገዢዎች ለስልጣናቸው አስጊ የሆነ ሰው (ወይ ቡድን) ሲያጋጥማቸው ስም ሰጥተው የማጥላላት ዘመቻ ያካሂዳሉ።

የማጥላላቱ ዘመቻ ዋና ዓላማ ለስልጣን ስጋት የሆኑ ሰዎች ከህዝብ ለመነጠል ነው፣ ድጋፍ እንዳያገኙ ለማድረግ።

ግን ‘ወንበዴዎች’ ወይ ‘አሸባሪዎች’ እንዴት ይወለዳሉ? እንዴትስ ያድጋሉ? የውንብድና ወይ ሽበራ ምንጭ ጭቆና ነው። የጭቆና ምንጭ አምባገነንነት ነው። አምባገነንነት በሰው ህይወት፣ አስተሳሰብና ሃይማኖት ጣልቃ መግባት ይጨምራል።

ሰው ለመግዛት ጣልቃ መግባት የህዝቦች ነፃነት ማፈን ያመጣል። የሰዎች ነፃነት ማፈን የህዝቦች መብት መጣስ ነው። ህዝቦች መብታቸው ሲጣስ መብታቸውን የሚስያከብሩበት መንገድ ያፈላልጋሉ።

መንግስት በማይፈቅደው መንገድ መብታቸው ለማስከበር ሲንቀሳቀሱ ‘ሕገወጥ’ ተብለው ‘ወንበዴዎች’ ወይ ‘አሸባሪዎች’ ይሰየማሉ። መንግስት ‘ሕግ ለማስከበር’ በሚል ሰበብ የሃይል እርምጃ ይወስዳል። መጀመርያ ሕግ የጣሰ አካል ግን መንግስት ነው፣ የዜጎችን መብት በመጣስ። እናም ችግሩ እየተባባሰ ይሄዳል። ከተባባሰ ደግሞ የሃይል ሚዛን እንጂ የመደገፍና መቃወም ጉዳይ አይሆንም።

ስለዚህ ውንብድና ወይ ሽበራ የሚወለደው ከጭቆና ሲሆን የሚያድገውም በመንግስታዊ ያልተፈለገ የሃይል እርምጃ ነው። መንግስት በያዘው መንገድ ከቀጠለ ሀገራችን ወዳልተፈለገ የብሄርና የሃይማኖት ብጥብጥ ልትገባ ትችላለች።

መንግስት ችግሩ የመፍታት ግዴታ እንጂ የማባብስ መብት የለውም። አሁን እየተወሰደ ባለው የሃይል እርንጃ ምክንያት ብዙ ሙስሊሞች ሳያስቡት ወዳልተፈለገ በሃይል መብትን የማስከበር ተግባር ሊገቡ ይችላሉ። በደርጋዊ እርምጃ ምክንያት ብዙ የትግራይ አርሶአደሮች ሳያስቡት ከህወሓት ጎን ተሰልፈው ለመዋጋት ወስነው ነበርና።

የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ ይሻል። ከሃይማኖት አልፎ የሀገር ጉዳይም ነው።

የሽብርተኝነት ምንጭ ጭቆና ነው። ስለዚህ ሽብተርኝነትን ለመዋጋት ምንጩ ማድረቅ አለብን፤ ጭቆናን መዋጋት አለብን። የሃይል እርምጃ ሽብርተኝነትን የሚያባብስ እንጂ የሚፈታ አይደለም።

It is so!!!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>