Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የጃርት ጉባኤ ርደት (ሥርጉተ ሥላሴ ሲዊዘርላንድ -ዙሪክ)

$
0
0

ባድማ በጃርት ተሰቅዛ

በአረማሞ አራሙቻ ናውዛ

እህህን ሰንቃ ደንዝዛ

ሰቀቀን ታጥቃ አርግዛ።

ሬት ጨጎጎት ተደልዛ

መቀነት በእሾኽ ተገንዛ፣

ቁም ስቅሏን አዬች

ይህው በልዛ።

`ጃርተ ምርት እሾህ

ፍጥረተ ነገሯ ውጋት

በበቀል – ተዋቅራ

በደም – ተቋድሳ

በደጋን ታምሳ – ተደቁሳ፤

እሾህ አዘራች መልሳ፤

የጃርት ገላ መላልሳ።

ህልመ ራዕዩ ምልግልግ

የላንቁሶ ውሃ ዝልግል

ጃርተ – ልብ፤ የእሾህ ልግ

የአሜክላ የቋሳ ድግዳግ።

ጃርትስ አሰኛት የበቀል ብቅል

ቋቱ ’ማያውቅ ግል

የጃርት ህሊና የውጋት ግልል፣

ሰባራ ገል።

እሾህስ አልቦ የለም ጃርት

ከዘረ እሾህ የለም ምርት

የጠቀራ ናስ ሃሞት

ዙሪያ ገባው ማት፤

… ህልፍት የሐገር ቅብረት።

አንተ አለህና በቤትህ

ትሰማለህም ታያለህም

የጃርትን ትዕቢት፤ … የቀን ጥሰት

የበቀል አምላክ አትለፋት፤

የህዝብን ዕንባ ህማማት፤

እ!-እ!-እ!-እ!እ!-እ!-

እም – እም – አም እ——-ም!

 

ውስጥ

 

ይህን ግጥም ለመጀመሪያ ጊዜ መድረክ ላይ ያቀርብኩት የመጀመሪያዋ ሐገራዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ የፓርቲያዋን የአንድነትን ዓላማና ተግባር ለማስተዋወቅ፤ እንዲሁም ደጋፊ አካላትን ለማዋቀር እ.አ.አ በ2008 በታህሳስ ወር አውሮፓ በተዘዋወረችበት ወቅት ሲዊዝ ጄኔባ  መጥታ በነበረችበት ጊዜ ነበር። ከመክፈቻ ንግግሬ በኋላ ግጥሙን አቅርቤ ስጨርስ እንዲህ አለች „አንቺ ምን አለብሽ?! እንዲህ የልብሽን በነፃነት ታቀርቢያለሽ። እኛ የግጥም ምሽት አዘጋጅተን ከቢሮችን ውስጥ በታጣቂዎች ተከበብን“ በማለት ተክዛ ቆዬችና አይኗን ወደ እኔ ላከችው።

eth cryአዬሩ ፈቅዶ ሁለታችንም አገናኘን። በመንፈስ ተቀራረብን – ተዋኽድን። አስተውላም አዬችኝ በውስጧ – እኔም ምላሹን ደረብኳት። ህልሜ ተሳክቶ ሴት አቅሟን ብቃቷን እንዳዛ በወሳኝ የኃላፊነት ቦታ በእርግጠኝነት ስታቀርብ ከማዬት በላይ ሐሴት አልነበረም። ተስፋውንም ቀጠልኩበት። ቃሌን ሳላጥፍ ከተግባር አርበኞቿ፤ ከሲዊዝ የአንድነት ድጋፍ ሰጪ አካሎቿ ጋር ጥሩ የሰመረ የሰላም ጊዜ አሳለፍን። እንዲሁም በአለም ዙሪያ ካሉ ተቆርቋሪዎቿ ጋርም የሚያስመካ የፍቅር አንድነት ገነባንበት። አቅለ ቢሱ ወያኔም ስትመለስ እግር ብረት ለእሷና ለልጇ ለሀልዬ አዘጋጅቶ ቢጠባቅታም ደጋፊዎቿ ግን በያሉበት ታጥቀውና ተግተው ታገሉ። ከአውሮፓ ወደ ቃሊት። እጅግ አስደንጋጭና መራራም ነበር። ዛሬ ደግሞ ለሴት ተቆርቋሪ ሆኖ ሙጃው ወያኔ አለሁኝ ሲል አዳመጥን።

እኔ በግሌ ከጃርት የእሾህ ፈል እንጂ ሌላ እምጠብቀው የለም። ጠንከር ያሉ ትችቶችን ላጥ አድርጎ ማስመሰሉን አቀለጠበት – አይፍር መንፈሱን በአሻቦ ያወራረደ – ግልብ። እንደዚህ ላጥ እያደረገ ቀሰማውን እንደሚያስነካው ስለምን የተባበሩት መንግስታት ድንጋጌዎች አክብሮ በሰቧዕዊ መብት ላይ የሚደልቀውን ጭፈራ አይገታም? ወኔ ካለው በሺህ የሚቆጠሩ ሴት እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፍታ። ከዚህ ከለበጣ ኮሜዲ ተግባሩ በፊት። ሲያንጎላች ይከርምና እንዲህ ይባንናል – የጉም ሽንት። ለቅብ እንዳረገደ እንዳረገረገ 23 ዓመት —– ነጎደ።

የኔዎቹ በሉ ተመራርቅን አንለያይ። የተመቼ ጊዜ እንሆ ተመኘሁላችሁ። ፍቅርና ናፍቆት በገፍም ተላከ ለእናንተ ——– — ለክብረቶቼ።

ማሳሰቢያ — 1.   ግጥሙ – ግንቦት 20 ቀን 2000 ዓ.ም ክላይነአንደልፊንገን – ሲዊዘርላንድ ተጻፈ። ከመጀመሪያው መጸሐፌ „ተስፋ“ ላይ ከገጽ 49 እስከ 50 ይገኛል።

2.  ይህቺ ምልክት ለንባብ እንዲያመች አንድ ፊደል መዋጡን ታመልካታለች – ከትህትና ጋር።

ለቅሶ የሚያበቃበት ቀን ናፈቀኝ!

እግዚአብሄር ህዝባችንና ልዕልት ኢትዮጵያን ይጠበቅ። አሜን!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


ኦሮሞ ነኝ የሚለው ብዙው ሕዝብ በታላቁ ኢትዮጵያዊ ሚንሊክ ላይ ያለው ጥላቻ ከምን የመጣ ነው?

$
0
0

የታላቋ ቀን ልጅ
ሚያዝያ 1 2006 ዓ.ም.

minilik

ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሚንሊክ

እጅግ ክፉና ማንነትን ከሚያዋርዱ ነገሮች አንዱ አእምሮን ከእውነትና ማስተዋል አስርቦ መነሻው ምን እንደሆነ ብዙዎች በማያውቁት ስሜተኝነት መነዳት ነው፡፡ ይን የሰው ልጆችን በስሜተኝነት የመጥለፍ አጋጣሚን ለመፍጠርና በተፈጠረውም አጋጣሚ ራሳቸውን አግዝፈው የሚኖሩ ግን በተፈጥሮ ብስለታቸው የወረዱ ሌሎችንም በእነሱ ደረጃ ከእነሱም ባነሰ ሊያዋርዱ ሌሊት ከቀን እንቅልፉ የሌላቸው ከዚያም በላይ በዕርኩሳን መናፍስት የሚታገዙ ሰብዐዊ ፍጡሮች በዙሪያችን እንደሚያንዣብቡ ብዙዎቻችን አንረዳም፡፡ እንደነዚህ ያሉ ሰዎች አእምሮአቸው በጎ እንዳያስብ የነጠፈና  በምትኩ ክፋትን ከቀን ወደቀን በማሳደግ ራሱን ሰይጣንን የሚተካ ባሕሪን ያዳበሩ ናቸው፡፡  በዚህ አደገኛን በመረቀዘ አእምሮአቸው ሌሎችን የመርዛሉ ያጠፋሉ፡፡ እነዚህ ሰው የሚመስሉ ግን በአካል የሚንቀሳቀሱ ሰይጣኖች ከሚበዙባቸው ቦታዎች ደግሞ ሕዝብ ትላልቅና የተከበሩ ብሎ በሚያስብባቸው ከፍተኛ አመኔታ በሚሰጣቸው ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ የፖለቲካ የሥልጣን መዋቅሮችና የሐይማኖት ተቋሞች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ መዋቅሮች ባሉ መሪዎች ላይ ሰዎች ከፍተኛ አመኔታን ይሰጣሉ፡፡ ግን ብዙ ጊዜ ለአመኔታቸው አጸፋው መልካም ነገር ላይሆን ይችላል፡፡ ብዙም ጊዜ ወድቀትና ወርደት ይሆናል፡፡ ሁለቱም መዋቅሮች እጅግ የበሰለ አእምሮን፣ ቅንነትን፣ የሕዝብ እንደራሴ መሆንን የሚጠይቁ ቢሆም በብዙ የታሪክ ገጠመኞች ግን ተቃራኒው ሲሆን ይስተዋላል፡፡ በአሁን ዘመን ደግሞ ከመቼውም የከፋ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እነዚህ ከላይ የተጣለውን ሰይጣን የሚወክሉ ሰብዓዊ ፍጥረቶች በቅንነትና በበሰለ አእምሮ ለሕዝብና ለአገር ክብር የነበሩ ሰዎች ታሪካቸው እንዳይታወቅ፣ ከታወቀም ራሳቸው በፈጠሩት ሌላ ታሪክ የእነዚህን ባለታሪኮች ታሪክ በማጉደፍና የቀደመ ታሪክን የማያውቅ ሌላ እነሱን የመሰለ ትውልድ ተክቶ የታላላቅ ባለራዕዮችን ታሪክ ጨርሶ እንዲጠፋ በማድረግ የእነሱን ኑሮ ማደላደል አንዱ መገለጫቸው ነው፡፡

እኔ የምናገረው ከስሜተኝነት የተነሳ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ ግን የተረዳሁትን ያህል እናገራለሁ፡፡ ባለማወቅ ግን ልሳሳት እችላለሁ እኔ የተረዳሁት ስህተት ሊሆን ስለሚችል፡፡ የሚያርመኝ ካለም እቀበላለሁ፡፡ ደግሜ እናገራለሁ ከሥሜት የተነሳ አላወራሁም፡፡

በእኔ ግንዛቤና መረዳት በአለፉት አምስተ መቶና ምንአልባትም ከዚያም በላይ እንደ ኢትዮጵያዊው መሪ ሚንሊክ ያለ መሪ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካም ብቻ ሳይየሆን በአለም ላይ ነበረ የሚለኝን የታሪክ ምሁር ትንተና እሻለሁ፡፡ እኔ በአለፉት አምስት መቶ ከዚያም በላይ በሚሆን ዘመን እንደ ኢትዮጵያዊው ሚንሊክ ያለ ታላቅ መሪ እንዳልነበረ አስባለሁ፡፡ በእኛው ዘነድ ስለሚንሊክ ያለን ግንዛቤ ወይም ከላይ በጠቀስኳቸው የወረዱ አእምሮዎች የጎደፈ ወይም በእጅ የያዙት ወርቅ አይነት ብዙም ትኩረት ያልሰጠነው ይመስለኛል፡፡

ዛሬ በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚንሊክ ታሪክ እንኳንስ የማንነታችን መገለጫ አድርገን የምንኮራበት በአንደበታችንም ለመናገር የሚቀፈን ሆኗል፡፡ ብዙዎቻችንም በመርዝ በተለወሰ ሌላ ታሪክ አእምሮአችን የታላቁን ሰው ታሪክ የሚያጎድፍ፡፡ በተለይም  በኢትርዮጵያ ትልቅ ቁጥር አለው ተብሎ በሚታመንለት ኦሮሞ እየተባለ በሚጠራው አብዛኛው ሕዝብ ዘንድ ዛሬ የሚንሊክ ጉዳይ ሲነሳ ያስበረግገዋል፤ እጅግ ያስቆጣዋል፤ ሥሙን አታንሱብኝ ይህን ሥም ከታሪክ ደምስሱት ጩኸት ያሰማል፡፡ ምክነያት ተብሎ ሲጠየቅ በዋነኝነት ብዙ ጊዜ የሚነሱት በሐረር የጨለንቆ ጦርነትና በአርሲ በሚንሊክ ዘመቻ ተፈጸሟል ተብሎ በዘበናውያን ታሪክ አዋቂዎች ነን ባሉ የተሰበከው የጡትና እጅ መቁረጥ (ሀርካ ሙራ ሐርማ ሙራ) ግፍ ነው፡፡

ሚንሊክን ታላቅ ከሚያሰኛቸው ታሪክ አንዱ ዛሬ ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራትን አገር አንድ በማድረጋቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያን አንድ ያደረጉበት ሂደት ደግሞ አልጋ በአልጋ የነበረ ሳይሆን ከብዙ በየስፍራው በነበሩ መሳፍንቶች ጋር ተዋግተው ነው፡፡ በወቅቱ እንደአሁን ዘመን ዲፕሎማሳዊ ሂደት ብዙም የሚያስኬድ አልነበረም፡፡ ሆኖም ሚንሊክ እርግጥም ከዘመኑ በፊት የተፈጠሩ ታላቅ ሰው ስለነበሩ ዲፕሎማሳዊው ሂደት ሁል ጊዜም ቅድሚያ የሰጡት ነበር፡፡ አንድም መስፍን (የአካባቢ መሪ) የሚንሊክን ታላቅ ራዕይ ሳይቃወም ጦርነት የከፈቱበት የለም፡፡ በወቅቱ ግን በነበረው የመሳፍንቶች ኋላ ቀር አስተሳሰብ ከሚንሊክ የቀደመ አስተሳሰብ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ የሚንሊክን አገርን የመገንባት ሂደት የሚተባበር አልነበረም፡፡ የእነዚያ ኋላ ቀር የአካባቢ መሪ ተብዬዎች ሕልም ለራሳቸው ከርስ የሚሞላ ሕዝብን ከመግዛት ያለፈ የዕድገትና ብልፅግና ሕልም ከቶውንም አልነበራቸውም፡፡ ይህ ደግሞ የሕዝብና የአገር ውርደትና ኋላ ቀርነት እንደ እሳት ለአንገበገበው ሚንሊክ እንቅፋት ነበር፡፡ በመሆኑም ሚንሊክ የወደደውን በውድ ያልወደደውን በግድ ማሳመን ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ከብዙ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ካላቸው የአካባባ መሳፍንት ጋር ጦርነት ገጥመዋል፡፡ በጦርነቶቹ ሁሉ የባለራዕዩ የበላይነት የግድ ቢሆንም ጦርነት ጦርነት ነውና ብዙ ጥፋቶች ጠፍተዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የሰዎች ልጆች አልቀዋል፣ ተሰቃይተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ግን የሚንሊክ ፍላጎት ሳይሆን የመሳፍነቶቹ ምርጫ ነበር፡፡

በሀረር ጨለንቆና አርሲ የተከሰቱ ጦርነቶች ሚንሊክ አገርን ለመገንባት ካደረጓቸው ሁለቱ ናቸው፡፡ የጨለንቆው ጦርነት በአስከፊነቱ ብዙ ሕዝብ ያለቀበት ቢሆንም በጦርነት ከሚከሰቱ የተለመዱ ጥፋቶች ሌላ ለየት ያለ የታሪክ ጠባሳ ያቆየ አልመሰለኝም፡፡ የአርሲው ጦርነት ግን እስከዛሬም ድረስ እንዲረሳ አጋጣሚን ለመጠቀም በሚፈልጉ መርዘኞች እንደ መሣሪያነት እያገለገለ ነው፡፡

ሀርካ ሙራ ሐርማ ሙራ! በአማርኛ እጅ መቁረጥ ጡት መቁረጥ ማለት ነው፡፡ ይህ አሳቃቂ ግፍ በአርሲው የሚንሊክ ዘመቻ ተከስቷል እየተባለ ዛሬ ባለው ትውልድ ልዩ ስፍራ የተሰጠው አልፎም ሐውልት የቆመለት ጉዳይ ሆኗል፡፡ እኔ እንዲህ ያሉ ግፎች በዚያ ዘመን በነበሩ ጦርነቶች ሊከሰቱ ከሚችሉ አሳቃቂ ክስተቶች አንዱ ሊሆኑ እንደሚችሉ አምናለሁ፡፡ ሆኖም በአርሲ ተከሰተ የተባለው እንዲህ ያለ ግፍ የታላቁ ሰው ሚንሊክ ትዕዛዝና ይሁንታ አለበት ብዬ አላምንም፡፡ በብዙ ጦርነቶች እንደሚከሰተው፣ ይልቁንም በዚያ የጠበቀ የጦርነት የመምራት አቅምና ቅንጅት በሌለበት ዘመን ከተዋጊዎች አንዱ ወይም ከዚያም በላይ እንዲህ ያለውን ጥፋት ፈፅመውት ይሆናል፡፡ ሚንሊክ ግን እንዲህ ያደረጉትን ወታደሮች ማንነት ቢያውቁ የሚሸልሟቸው እንዳልሆኑ አምናለሁ፡፡ ይልቁንም በሞት ሳይቀር ሊቀጧቸው እንደሚችሉ አምናለሁ፡፡ ይህ የሚንሊክ እውነተኛው ልብ ነው! ሚንሊክ እውነተኛ ጀግና የሚባል ባሕሪ ያላቸው ናቸው፡፡ ጀግና ደግሞ ጨካኝ አይደለም! ጀግና ጠላቶቹ የማይቋቋሙት እንጂ! እነኳንስ በሴቶችና አቅም በሌላቸው ላይ ሊያጠፋቸው የመጣን ጠላት እንኳን ከመግደል ይልቅ ከእነነፍሱ ይዘው ምህረትን ሊያደርጉለት የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ጠላታቸውን እንኳን ገድለው በሬሳው ላይ የሚጨፍሩ አይደሉም፡፡ ይልቁንም አስቸጋሪና የተቋቋማቸው ጠላታቸውን ሲጥሉት ለአስከሬኑ ሳይቀር ክብርን የሚሰጡ ናቸው፡፡ እንዲህ ያለው ተቃራኒ ጠላት የሆነ ግን ጀግና አስከሬን ለውሻና ለአውሬ የሚሰጡ ሳይሆን በክብር የሚቀብሩ ውጊያውን የአላማ እንጂ የተፈጥሮ ጠላትነት እንዳልሆነ የሚያስቡ ናቸው፡፡ ሰውን በሰበዐዊነቱ የሚያከብሩ ልዩ አመለካከት ያላቸው ናቸው፡፡ ይህ የእውነተኞቹ ጀግኖች ልዩ መገለጫ ነው፡፡ ሚንሊክ ይህ ባሕሪ ልዩ መገለጫቸው ከሆኑ አንዱ ነበሩ! በነዚህ መስፈርቶች መሠረት ግን ብዙዎች በኢትዮጵያ ጀግኖች እየተባሉ የተወደሱትን ማንነት ቴዎድሮስን ጨምሮ እጠራጠራለሁ፡፡ ይልቁንስ በቅርብ ታሪክ የምናውቀው ሕወሐት አባል የነበረው ኃያሎም አረአያ እነዚህ የጀግኖች ልዩ መገለጫ ያልኳቸው ባህሪያት እንደነበሩት ብዙ የሰማቸው ገድሎቹ ይናገራሉ፡፡

እንግዲህ በስሜትና በጥላቻ በመረቀዙ አእምሮዎች ሳይሆን እውነትን ለመጋፈጥ በሚደፍሩ አእምሮዎች እኔ የተረዳሁትን የሚንሊክን ማንነት አይደለም የሚል ካለ ለማደመጥ እወዳለሁ፡፡ ሚንሊክ ሩሩህና ይቅር ባይነታቸው ባደረቸው ጦርነቶች ሁሉ በደረሱ እልቂቶችና ጥፋቶች እጅግ ይጸጸቱ ነበር፡፡ ችግሩ አማራጭ ብቻ በማጣታቸው ጦርነቱ ግድ ሆኖማቸው እንጂ፡፡ በደረሰው ጥፋት ካዘኑባቸው ጦርነቶች አንዱ ደግሞ የአርሲው ጦርነት ነው፡፡ በጦርነቱ አሸንፈው አገሩን ከተቆጣጠሩት በኋላም ወታደሮቻቸውን ሕዝቡ ባለማወቁ ምክነያት የደረሰበትን እልቂት አሳዝኗቸው ወታደሮቻቸውን አሸንፌያለሁ በሚል በሕዝቡ ላይ ሌላ በደል እነዳያደርጉበት አዋጅ አውጥተው ሁሉ ነበር፡፡ ለወታደሮቻቸውም የአርሲን ሕዝብ ሲገልጹት ወንድምህ የአርሲ ሕዝብ እያሉ ነበር እንጂ እንደ ጠላት አልነበረም፡፡ ይህን እውነታ የታሪክ አዋቂ ነን የሚሉት ለምን ለሕዝብ ለማሳወቅ አልፈለጉም፡፡ ይልቁንስ የሚንልክ ትዛዛዊ ግፍ ለመሆኑ አጠራጣሪ ስለሆነው ሀርካሙራና ሀርማ ሙራ ማግዘፍን ለምን ፈለጉ፡፡ ሌላው የሚንሊክ ማንነት የተገለጸበት ጦርነት የወላይታው ከንጉስ ጦና ጋር የነበራቸው ጦርነት ነው፡፡ ንጉስ ጦናን አሸንፈው በእጃቸው ካገቡና አላማቸውን ከአሳመኗቸው በኋላ ንግሰናቸውን አጽድቀው እንደሾሟቸው ይነገራል፡፡ ከዚያም በላይ ጦና በጦርነቱ በመቁሰላቸው ምክነያት ሌላውን ሰው ባለማመን ሚንሊክ ራሳቸው እየተከታተሉ እንዲታከሙ ማድረጋቸው ይነገራል፡፡ ሌሎችም አያሌ የሚንሊክን ሕይወት የሚናገሩ መዛግብቶች ሩሩሕና የጅግና ሰው ልዩ መገለጫ የሆኑትን ባሕሪያቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ሚንሊክ ጋር በቀል የለም ጭጋኔም የለም የአላማ ጽኑነትና ታላቅነት እንጂ፡፡ ዘረኝነትም የለም ሰበዐዊነት እንጂ፡፡ በሚንሊክ አስተዳደር ወቅት ኢትዮጵያ ዘመናዊ በሚመስል ፌደራሊዝም ትተዳደር እንደነበር ስነቶቻችን እናውቃለን? አንዳንድ የሚንሊክን አላማ ለመረዳት እመቢ ባሉ መሳፍንት በቀር ከጦርነት በኋላ ሳይቀር ለእነዚያው የተዋጓቸው መሳፍንት ስልጣንን በሰጠት የራሳቸውን አካባቢ እንዲያስተዳድሩ ያደርጉ ነበር፡፡ በወቅቱ የተሸለ ግንዛቤ የነበራቸው እንደነ አባ ጅፋር የጅማው ያሉ የሚንሊክን አላማና ራዕይ ለመረዳት ስላልተቸገሩ በሠላም በአገር አንድ ማድረጉ ሂደት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የሚንሊክ እውነተኛው ታሪክ ዛሬ ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራትን አገር የፈጠሩ፣ አለም ላይ በእሳቸው ዘመን ኡሉ የተባሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ወደ አገር ያስገቡ እነዚህም ስልክ፣ ኤሌክትሪክ፣ መኪና፣ ባቡር፣ ሌሎችም፣ አገርን በዘበናዊ አስተዳደር እንድትመራ የዋቀሩ (ሚኒስቴር መሠረት ያደረገ) ሌሎች ብዙ በአንድ ሰው እድሜ ሊሰሩ የሚችሉ የማይመሰሉ ብዙ ራዕዮችን በተግባር ያስጀመሩ ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ ማድረጋቸው ሳያንስ ሚንሊክን ከቅርብ ወዳጅ እስከ ሩቅ ባላአንጣዎቻቸው እጅግ ፈታኝ መነቆዎች ነበሩባቸው፡፡ በወቅቱ ባለው ኋላቀር አመለካከት ምክነያት ብዙ የቅርብ የተባሉ የቤተመንግስቱና የቤተክህነቱ ሰዎች እንቀፋቶች እንጂ ለሚንሊክ አጋዥ አልነበሩም፡፡ በሚንሊክ የአገር አንድ የማድረግም ሆነ አገርን ወደ ዘመናዊነት መቀየር ሂደት በተሻለ ወሳኝ ሚና የነበራቸው የውጭ አገር ሰዎችና አንዳንድ የቅርብ አባሮቻቸው ናቸው፡፡ ከቅር አባሮቻቸው ደግሞ በተለይም አገርን አንድ በማድረጉ ሂደት የሸዋ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝቦች ከየትኛውም የኢትዮጵ የሕብረተሰብ ክፍል ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ የሸዋ ኦሮምኛ ተናጋሪ በታሪካዊው የአድዋው የሚንሊክ ድልም እንደዛው ከሌሎች በተለየ ነበር፡፡

ዛሬ ላለው አብዛኛው የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ ግን የሚንሊክም ታሪክ እነዛ የሚንሊክ የቀኝ ክንድ የነበሩት ኦሮምኛ ተናጋሪ ሸዌዎችም የሚታየው በበጎ ሳይሆን በጥላቻ ነው፡፡ ምክነያቱ ደግሞ የታላቅ ባለራዕዮች ሕልም የማይገባቸው፣ በተንኮል የነወረ አእምሮ ይዘው ታሪክን በማጉደፍ ትውልድን በእነሱ በተመረዘ አእምሮ ለመበከል ያሰራጩት መርዝ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ለአሁኑ ትውልድ የበለጠ የታሪክ ትውስታና ክፉውም ደጉም ከሞላ ጎደል ከሚታወቀው የደርግና የኃ/ሥላሴ ዘመን ስህተቶች ይልቅ የሚንሊክ ዘመን ስህተትን አቅርቦና አግዝፎ ለማሳየት የተመረዙ አእምሮዎች የሚፈጥሯቸው ሀተታዎች ብዙ ናቸው፡፡ ምክነያቱ ግልጽ ነው አሁን ያለው ትውልድ የሚንሊክን ዘመን እውነተኛ ነገሮች በአካል የሚመሰክርለት የለውም ስለዚህ ምስክር በሌለበት በመሰሪዎቹ አእምሮው ሊመረዝ የሚችለው በቆየው ታሪክ እንጅ በአካል ያሉ መስካሪዎች ባሉበት ታሪክን ለመዋሸት ስለማይመች ነው፡፡ ሌላው ሚንሊክ የሠሩትን ታላላቅ ሥራዎች በበጎነቱ ማንሳቱ ራስን የሚያሶቅስ አደጋ ስላለው ነው፡፡ ዛሬ ላለው ትውልድ የሚንሊክ ዘመን ራዕይ ባለዕዳ አደርጎታልና ነው፡፡ በሚንሊክ ዘመን ራዕይ ይህች አገር ቀጥላ ቢሆን የት በደረሰች ነበር፡፡ ሌላው የሚንሊክ ራዕይ የአገር አንድነትና ብልፅግና ልዩ መሠረት ሥለነበር ይህንን መሠረት ሳያፈርሱ ስለዘረኝነት፣ ቀበሌ ዝቅ ብሎም ስለ ጎጥ እንዲያስብ ሕዝብን ማምከን አይቻልም፡፡

ዛሬ ከየትኛውም ክልል ትልልቅ ከሚባሉ ክልሎች በሚያሳዝን ሁኔታ የኦሮምያ ክልል በልማቱም ሆነ በመልካም አስተዳደሩ ወደ ኋላ መቅረቱ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ መሠረታዊ ምክነያቱ ሕዝቡን ከሌሎች ጋርም ሆነ እርስ በእርስ ትብብር እንዳይኖረው የጥላቻን ዘፈን እየዘፈኑለት የራሳቸውን ኑሮ በተፈጠረላቸው አጋጣሚ እንደ ልባቸው የሚኖሩ ኦሮሞ ነን ባይዮች አደገኛ ዜጎች ናቸው፡፡ ይህንን ከሚያክል ትልቅ ክልልና ሕዝብ አይደለም ኢትዮጵያን ሊመራ የሚችል ክልሉን ሊመራ የሚችል ሰው ታጥቷል፡፡ ኦሮሞ ነኝ የሚለው አብዛኛው የዛሬው ትውልድ ትልቁ እርካታው የሌሎች መውደቅ በተለይም ነፍጠኛ እያሉ የሚጠሩት የአማራውና አሁን በስልጣን ላይ በብዛት እንደተወከለ የሚነገርለት የትግራይ ሕዝብ ውድቀት እንጂ የራሱ ብልጽግና አይደለም፡፡ ለኦምኛ ተናጋሪው ክልል በልማትና በአስተዳደር ወደ ኋላ መቅረት ቁጭት ተሰምቶት ሊሰራ ከሚሞክር መሪና ትውልድ ይልቅ ከብዙ አመታት በፊት የተፈጠሩ የታሪክ ስሕተቶች ደግሞደጋግሞ በማላዘን ሌላ መርዛማና በጥላቻ የተበከለ ትውልድ ለማዘጋጀት ተግቶ የሚሰራው በዝቷል፡፡

ዛሬ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሆኖ ያለው ሕዝብ በዘር (በደም) አንድ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ በደም ግንድ ከሆነ የወለጋና ሐረር ኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ ከሚቀራረበው በላይ የጎጃ አማርኛ ተናጋሪውና የወለጋ ኦሮምኛ ተናጋሪው ይቀራረባሉ፡፡ የባሌና ሸዋ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ከሚቀራረቡት በላይ የሸዋ ኦሮምኛ ተናጋሪና የሸዋ አማርኛ ተናጋሪ የበለጠ የደም ትስስር አላቸው፡፡  በባህልም ቢሆን እንደዚያው ነው፡፡ ዛሬ ዘረኝነትንና የቀበሌ አስተሳሰብን የሚሰብኩ ግን ቋንቋን ተመርኩዘው ግዙፉን ሕዝብ በአንድ ከአጨቁትና ከሌሎች ጋር ሕብረት እንዳይኖረው ከአወሩት በኋላ ወደታች ደግሞ በጎሳና፣ ቀበሌ፣ ዝቅ ብለው በጎጥ ይሸነሽኑታል፡፡ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ከሌሎች በአካባቢው የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ያልተጋጨው የለም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነበር፡፡ ሕዝቡ ለሌሎች ጥላቻ እንዲኖረው ስለሚሰበክ ነው፡፡ አልፎም ይሄው መለያየትን የሚሰብከው መዝሙር እርስ በእርስ ሳይቀር ጥላቻንና ግጭትን አስነስቶ አይተናል፡  እንደወንድማማች የሚተያዩት ጉጂና ቦረናን ሳይቀር ለከፍተኛ ደም መፋሰስ ዳርጓል፡፡

ይሄው ሃያ ምናምን አመት ሙሉ ስለቀድሙት ገዥዎች ጭቆናና በደል ሲነግሩን፡፡ የቀደሙትስ ጨቋኝና ጨካኝ ሆነው የኦሮሞን ሕዝብ ሲበድሉት ኖሩ ተብሎ ይታሰብ ዛሬስ የዚያን ዘመን በደል ሊያስረሳ የሚችል መሪ እንዴት ከዚህ ትልቅ ሕዝብ መካከል ጠፋ፡፡ እውነታው የቀደሙት ጨካኝና በደል አድርሰውም ከሆን ለኦሮምኛ ተናጋሪው የተለየ አልነበረም፡፡ ብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ አማርኛ ተናጋሪ ከነበረው ይልቁንም የነገስታቱ ወገን ነው ተብሎ ከሚታመነው የሸዋ አማርኛ ተናጋሪ ሕዝብ በቀድሞ ነገስታት የተሻለ ተጠቃሚ እንደነበር እናውቃለን፡፡ ሌላው ቀርቶ የነገስታቱ የቅርብ አጋር እየተባለ ዛሬም ድረስ በሌላው የኦሮምኛ ተናጋሪ በጥሩ አይን የማይታየው የሸዋው ኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ በነገስታቱ ዘመን አንዳች ተጠቃሚ እንዳልነበረ አእምሮ ካለን እናስተውላለን፡፡ ለእነዚህ ሕዝቦች ከሌላው በተሻለ የቀረላቸው ሀብት ቢኖር ሌላውን በጥላቻ አለመመልከት ለአገር አንድነትም ልዩ ፍቅር መኖር ነው፡፡

ሌሎች ክልሎች በአቅማቸው ልማታቸውንና የአስተዳደርም ችግራቸውን በፍታት ልዩ መንገድን እየሄዱ ይገኛሉ፡፡ በተለይም የቀድሞው ገዥና ጨቋኝ ተብለው የተፈረደባቸው የአማርኛው ተናጋሪ ሕዝብ ክልል  በቁጭት በሚመስል ሁኔታ እያደገ ለመሆኑ ግልጽ እየሆነና ልዩነቱንም ከሌሎች እያሰፋ መሆኑን እያሳየን ይገኛል፡፡ ትግራይ የገዥውን መንግስት ድጋፍ እያገኝ ስለሆነ ነው እየተባለ ቢታማም እውነታው የእድገት ጥማት ባላቸው መሪዎች ምክነያት እንጂ የማዕከላዊው መንግስት ተፅዕኖ ብቻ እንዳልሆነ እናያየለን፡፡ ደቡብና ሌሎች አናሳ እይተባሉ የሚጠሩ ክልሎች ሳይቀር ከኦሮምያ በተሻለ ዕድገት እያሳዩ ናቸው፡፡ በማዕከላዊውም መንግስት ያላቸው ተሳትፎ ከኦሮምያ ይልቅ የደቡብ የተሻለ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ምክነያቱ ግልጽ ነው ኦሮምያ ኢትዮጵያን በሚወክል አመለካከት ይቅርና ክልሉን እንኳን በሚወክል አመለካከት የተገነባ ሰው ታጥቶበታል፡፡ በደቡብ ብዙ ሕዝቦች ኢትዮጵያዊ መሠረትን በደንብ ያደበሩ ናቸው፡፡ በኦሮምያ  ሌሎችን በመጥላት የተጀመረው ሂደት ዛሬ ወርዶ ቀበሌ ደርሷል፡፡ ወለጋው ወለጋውን፣ አርሲው አርሲውን፣ ታች ወርዶ ደግሞ ሻንቡ ሀረቶ ምናምን እያለ የሚከፋፍል ነው፡፡ ይህ አይነቱ ባሕሪ በሌሎች ክልሎች አይንጸባረቅም ሳይሆን በንጸባረቅም ሌሎች ሌሎችን ጨምረው በሚያማክሉ ከፍተኛ ባለአእምሮዎች ይመክንና ቀበሌ ከሆነ ቀበሌ፣ ከፍ ብሎ በክልልም ከሆን ክልሉን ሳያልፍ ይመክናል፡፡ ኦሮምያ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ የወረደውን የጎጠኝነት ስሜትና አመለካከት የሚያመክን ጠፍቶ ትውልዱ በአብዛኛው በወረደው ጎጠኝነት ስሜት መክኗል፡፡

አሳዛኙ ነገር ተማርን የተሸለ የሕወት ልምድ አልን በሚሉት ይህ የአመለካከት ወርደት በርትቷል፡፡ በተለይም ደግሞ በተለያዩ መንገድ ወደ ውጭ ሄዶ በሚኖረው የኦሮምኛ ተናጋሪው ለሌሎች ያለው ጥላቻ እጅግ የከፋ ነው፡፡ አማራ ወይም ትግሬ የሚባለውን በመጥላት ሌሎችን ይጋብዛል፡፡ ሌሎችንም ወንድም እንደሆነ ሊሰብክ ይሞክራል፡፡ ይህ ጥላቻን ያዘለው ስብከት ከትልቋ ኢትዮጵያ እስከ ታች ተራ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ በቅርቡ በቴዲ አፍሮ ምክነያት የበደሌን ቢራ ላለመጠጣት የተደረገው አድማ አንዱ ሕዝቡ እንዴትና በምን አይነት አመለካከቶች እንደሚመራ በሌላውም ላይ ያለው ጥላቻ ምን ያህል እንደሆነ ያመላከተ ነበር፡፡  ይህን ለሚያሕል አደማ ደግሞ ያደረሰው በሌሎች ከፍተኛ አደናቆትን ያተረፈው የቴዲ አፍሮ  ጥቁር ሰው የሚለው ዘፈኑ እንደነበር ግልፅ ነው፡፡ የቴዲው ጥቁር ሰው ሚንሊክ ግን ለአፍሪካ ሳይቀር ኩራት እንጂ የሚያሳፍር አልነበረም፡፡ በጥላቻ የተመረዘው የእኛው ኦሮምኛ ተናጋሪ ግን ያንን የጥቁር ሕዝብ ሁሉ ክብር የሆነውን ታሪክ ለመስማት አለመፈለግ ብቻም ሳይሆን ያንን ታሪክ የሚያነሱትን በሚያገኘው አጋጣሚ ሊበቀል እንዳለው አየን፡፡ አሁን ያለው እንዲህ የተመረዘው የኦሮምኛ ተናጋሪ ትውልድ ግን ስለሚንሊክም ሆነ በዘመኑ ስለነበሩ ክስተቶች በውል የሚያውቀው ነገር የለም መርዛማና የራሳቸውን ልዩ ፍላጎት በሕዝቡ ሊያሳኩ የሚያሴሩትን ስብከት ተቀበለ እንጂ፡፡

በቅርቡ የሀረካ ሙራ ሐርማ ሙራ መታሰቢያ በሚል አንድ ሐውልት ተመርቋል፡፡ እኔ እውነትም ይህ ክስተት በየትኛውም ስህተት ቢሆን ተከስቶ ከነበረ መታሰቢያ መቆሙ ክፋት አለው ብዬ አላምንም፡፡ ሆኖም ክስተቱ ተፈጠረ ከተባለ ከስንት ዘመን በኋላ ዛሬ ሀውልት ለማቆም የታሰበበት አላማ ያንን ክስተት ለማስታወስ የተደረገ ሳይሆን ይልቁንም ጥላቻን ለማጠናከር እንዲህ ያደረገሕ ሕዝብ ነበር ለማለት የቆመ ሀውልት ሆኖ ነው የተሰማኝ፡፡ አሁን አሁን እንደውም ያ አሳቃዊ ክስትት ሆን ተብሎ የተፈጠረ ታሪክ ነውም ብዬ እየተጠራጠርኩ ነው ከሌሎች ጋር ጥላቻ እንዲፈጠር የሚደረገው ሴራ ብዙ ነውና፡፡  ይህ ሀውልት በተመረቀበት በዚህ ሰሞን የሩዋንዳውም እልቂት ሃያኛ ዓመት የሚታሰበበት ነበር፡፡ ሲታሰብ ግን ልዩ መልዕክት የነበረው የተፈጠረውን ክስተት የሚያስረሳ ሰላምንና የአገር ብልጽግናን በዚያች አገር የማምጣት ራዕን ነው፡፡ ሐውልት እነኳን ለእነዚያ ዜጎች መታሰቢያ ማቆም ቢያስፈልግ ዳግም እንደዚያ ያለ አረመኔነት በዚያች አገር እንዳይከሰት ለትውልድ ማስተማሪያነት እንጂ ቂም በቀለኝነትን ለማቆየት አይሆንም፡፡ የኦሮምያው የሀርካ ሙራ ሐርማ ሙራ ሐውልት ግን ግልጽ መልዕክቱ ሌሎችን በመጥላት የተመረዘውን ብዙ የኦሮምኛ ሕዝብ የበለጠ ጥላቻ እንዲያድርበት ሌሎችም ሌሎችን በመጥላት ተሳትፎ እንዲያደርጉ የታለመ ነው ብዬ አመንኩ፡፡

ብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ በኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ የወደፊት ብሩሕ ራዕይ ደስተኛ አይደለም፡፡ እነዚህ የሕዝቡ አካላት የኢትዮጵያን ውድቀት እጅግ የሚመኙ ናቸው፡፡ ሌላ ቀርቶ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ወይም እነሱ በጣም ከሚጠሉት አማራ ወይም ትግሬ ከሚባለው ሕዝብ ጋር የተያያዘ የራሳቸው ነገር እንኳን እርም ነው፡፡ የአባይ ወንዝን እንደምሳሌ ላንሳው፡፡ የአባይ ወንዝ ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ ብዙ ይነሳል፡፡ መነሻው ደግሞ ጎጃም የጮቄ ተራራ ነው፡፡ ሆኖም አባይን በውል የምታውቁት ካላችሁ አባይን አባይ ያደረገው የጮቄ ተራራ ወይም ከጣና የቀዘፈው ውሀ ሳይሆን ከኦሮምያ የሚነሱ ታላላቅ ወንዞች ናቸው፡፡ በተለይም ደዴሳና ዳቡስ፡፡ ይሄንን ለማስተዋል አሁን ግድብ እየተሰራበት ያለውን ቦታ የሚፈሰውን ውሃና ወደጎጃም ስትሻገሩ የምታዩትን ውሃ አስተውሉ፡፡ ግብጾቹም ይሁኑ ሌሎች እንቅልፍ የሚነሳቸው ጎጃም ያያችሁት አባይ አይደለም ደቡስና ዴዴሳ የደለቡት አባይ እንጂ፡፡ የአባይ ሥም ሲነሳ ግን ብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ ጥሩ ስሜት የለውም፡፡ ግድቡን ጨምሮ ሌሎች ለኢትዮጵያ ብልጽግናም ትልቅ ድርሻ ያላቸው ልማቶችም እንዲሁ በብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ በመልክም አይታዩም፡፡ ግን ለምን? የሚንሊክን ታሪክና ዘመን እንዲህ በጥላቻ የሚያስመለክትስ በእውን የተጨበጠ ይቅር የማያሰኝ ስህተት አለ? ካለስ ይህ ትውልድ እነዴትና በምን ምክነያት እነዚያ ስህተቶች እንደተከሰቱ ምን ያህል ተረድቶ ነው እንዲህ በጥላቻ የተመረዘው?! ነው ወይስ አሁንም እያየን እንዳለንው የኢትዮጵያ ነገር ስለማያደስተው ከኢትዮጵያዊነት ጋር የተቆራኘውን የአገሪቱን መስራች ሚንሊክን በስሜት ብቻ መጥላት ይሆን?

ኦሮምያ ውስጥ ባለፉት ሃያ ምናምን አመት ከተከሰተው ግፍ በላይ በቀደሙ የታሪክ ጊዜያት ለመከሰቱ ጥያቄ እያጫረብኝ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ ጥያቄዎች አሉ! ኦሮምያ የሚባለውም ክልል ይሁን ኦሮምኛ ተናጋሪ የተባለው ሕዝብ ግልጽ በሚታይ ሁኔታ እየተቀደመ እንደሆነ ይረዳ፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ይህ ልዩነት ጎልቶ ሲታይ ይህችን መልዕክቴን ያነበቡ ያስታውሱ ይሆናል፡፡  ግን ለምን???!!

የታላቋ ቀን ልጅ ሚያዝያ 1 2006 ዓ.ም.

 

ሕገመንግስት፤ መብት ተረጋግጧል ወይስ ተረግጧል (ተክለሚካኤል አበበ)

$
0
0

የማርቆስ ብዙነህ ደብዳቤ፤

ተክለሚካኤል አበበ)

ተክለሚካኤል አበበ)

1-      “በርካታ ትምህርት ቤቶች፤ ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ፤ የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን” ይላል፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቅ ክፍል ሀላፊ፤ በአቶ ማርቆስ ብዙነህ ማንደፍሮ፤ መጋቢት 23 ቀን 2006/2014 የተፈረመው ደብዳቤ፡፡ አንድነት፤ ሰልፉን ለማድረግ ያቀረባቸው መስመሮች 3 ሲሆኑ፤ ሶስቱም መስመሮች ከቀበናው የአንድነት ጽ/ቤት ይነሳሉ፡፡ አንደኛው መስመር በአራት ኪሎና በፒያሳ አድርጎ፤ ወደ አዲስ አበባ መስተዳድር ጽ/ቤት ያመራል፡፡ ሁለተኛው አማራጭ በአራት ኪሎ ተጉዞ፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን አልፎ መስቀል አደባባይ ያበቃል፡፡ ሶስተኛው አማራጭ፤ በአራት ኪሎ ፒያሳ፤ ቸርችልን ይዞ ድል ሀውልት ጋር ያበቃል ነበር የሚለው፡፡ ከላይ እንደተመለከታችሁት፤ የአዲስ አበባ መስተዳድር፤ ሶስቱም አማራጮች አልተመቹትም፡፡ የተመረጡት መስመሮች በርካታ ትምህርት ቤቶች የትምህርትና የመንግስት ተቋማት ስለሚገኙበት፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ግንባታ ያለባቸው መንገዶች ስለሆኑ፤ እንዲሁም በእለቱ የህዳሴው ግድብ ግንባታን የተመለከቱ ዝግጅቶች ስላሉ፤ መስተዳድሩ ሰልፉን ሳይፈቀድ ቀረ፡፡

2-     አንድነት ክልከላው ሕገወጥ ነው፤ ሰልፋችንን እንቀጥልበታለን ብሎ አቋሙን ሲያሳውቅ፤ የአዲስ አበባ መስተዳድር ዘግይቶም ቢሆን፤ ተለዋጭ ቀንና መንገድ እንደሚቀበል ጠቆመ፡፡ ወትሮም ቢሆን የአዲስ አበባ መስተዳድር የተከተለው ስልት የማዳከም፤ የማበሳጨት፤ የማሰናከልና ተስፋ የማስቆረጥ እንጂ ጨርሶ የመከልከል አይመስልም፡፡ ስለዚህም ድርጅቱ በተዘጋጀበትና በመረጠው ቀን ባይሆንም፤ በሌላ ቀን እንዲሆን ለመለወጥ አስገደደ፡፡ በርግጥ የአዲስ አበባ መስተዳድር የመጀመሪያውን ሰልፍ ያሰናከለበት ምክንት አግባብ ባይሆንም፤ የአንድነት ልሳን ፍኖተ-ነጻነት፤ የአዲስ አበባ መስተዳርን የዘገየ እሺታ አስጩሆ የዘገበበት መንገድ ብልሀት ይጎድለዋል፡፡ ፍኖት ነጻነት፤ “በመጨረሻ የአዲስ አበባ መስተዳድር እጅ ሰጠ” ነው ያለው፡፡ ይሄ አይነቱ ረታናችሁ፤ አሸነፍናችሁ አካሄድ መንግስት የሚያሸሽ ስለሆነ፤ ፍኖተ ነጻነት ከዚህ አይነቱ አናዳጅ ርእሰ-ዜና መራቅ አለበት፡፡ ኢሳትም ይሄን አይነት ሰራንላችሁ፤ የታባታችሁ የሚል አዋራጅ አዘጋገብ አልፎ አልፎ ይተገብራል፡፡ ፈጣሪ ጊዜና ጉልበት ከሰጠኝ፤ ይሄ አይቱ ጠላትን የማዋረድና የጽንፈንነት አካሄድ ለምን እንደሚጎዳ እጽፋለሁ፡፡ ለጊዜው የፍኖተ ነጻነት ርእስ እንዳልተመቸኝ ሳልጠቅስ አላልፍም፡፡

 

ስለሕገመንግስት፤ መብት ተረጋግጧል ወይስ ተረግጧል

3-     የሆነ ሆኖ፤ ወደሰልፉ ጉዳይ ስንመለስ፤ አሁን በስራ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ሕገመንግስት መሰረት፤ ዜጎች በመሰላቸው ርእስ፤ በጣማቸው ምክንያት፤ በታያቸው ሕልም፤ በተሰማቸው ደስታ፤ ባሳዘናቸው ሰበብ፤ መንግስትን ደግፈውም ይሁን ተቃውመው፤ ሀሳባቸውን በተቃውሞ ወይም በድጋፍ የመግለጽና የመሰብሰብ መብታቸው ተረጋግጧል፡፡ ሕገ-መንግስቱ ራሱን በራሱ ያስፈጽም ይመስል፤ ሕወሀት/ኢህአዴግ ብዙውን ግዜ እንዲህ ያለው መብት በሕገ መንግስቱ ተከብሯል፤ በሕገመንግስቱ ተረጋግጧል እያለ የሚያጭበረብረው ነገር ስላለ፤ ይሄንን የተቃውሞ ሰልፍ በህገመንግስቱ ተከብሯል የሚል አረፍተነገር የተመለከተ ሰው፤ ጥንቃቄ ካላደረገ በስተቀር በሀይለኛው ይሳሳታል፡፡ በሕገ መንግስቱ መሰረት፤ ተረጋግጧል የሚለው ቃል፤ ተከብሯል በሚለው መተርጎም ቢኖርበትም፤ በኢትዮጵያ በተግባር እንደምናየው ግን፤ ተከብሯል በሚለው ሳይሆን፤ በሕገመንግስት ተረግጧል በሚለው ቢተረጎም ይቀላል፡፡ መብቱ በሰበብ አስባቡ ተሸራርፏል፡፡ በአንድነትና በሰማያዊ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ላይ የሚደርሰውን ለተመለከተ ይሄንን መረዳት አያዳግተውም፡፡

4-     ለምሳሌ ሕገመንግስቱ ሰልፍ ከማድረግ በፊት ለሚመለከታቸው አካላት ስለማሳወቅ ብቻ ሲናገር (የአቶ ማርቆስ ብዙነህ ማህተም የሰልፍና ስብሰባ ማሳወቅ ኦፊሰር ነው ይላል)፤ ህግ አውጪዎቹና አስፈጻሚዎቹ ደግሞ፤ የለም ሰልፍ አሳውቅ ሳይሆን አስፈቅድ ነው ብለው ተረጎሙት፡፡ መተርጎም ብቻ ሳይሆን፤ ሕገ መንግስቱ ያረጋገጠውን መብት፤ ሰልፍን የተመለከቱ አዋጆችና ደንቦች አውጥተው ረጋገጡት፡፡ ለምሳሌ የአዲስ አበባ መስተዳድር የስብሰባና ሰልፍ አሰራር ስነ-ስርአት አንቀጽ 5.1 ከላይ በተጠቀሱት የመንግስትና የትምህርት ተቋማት አካባቢ ሰልፍ ማድረግ አይቻልም ይላል፡፡ በካናዳ ቢሆን፤ እነዚህን ሕገመንግስታዊ መብት የሚሸራርፉ አዋጆችና ደንቦች፤ ፍርድቤቶች ዋጋ የለሽ ህጎች ብለው ይወስኑባቸው ወይም ያመክኗቸው ነበር፡፡ እኛ አልታደልንምና፤ እስካሁን እንዳየነው፤ የኢትዮጵያ ፍርድቤቶች እንዲህ ያለውን ሕግ የመሻር ወይም፤ ሕገመንግስቱን ይጥሳል ብለው የመወሰን ስልጣንም ወኔውም አልተመለከትንባቸውም፡፡ ከተመለከትንም፤ ወይ ፍርዱ ወይ ዳኛው አይጸናም፡፡ መንግስት እንዲህ ነው ካለ፤ የኢትዮጵያ ፍርድቤቶችም አብረው እንዲያ ነው ይላሉ፡፡ ከመንግስት ጋር ይስማማሉ፡፡

 

የት ሄደን እንሰለፍ፤ ነው ወይስ እንሰየፍ

5-     ሰልፍ 48 ሰዓት ቀደም ብለህ አሳውቅ የሚለው ድንጋገጌ ሰልፍ አስፈቅድ በሚለው አዋጅ ተሸርፎ ብቻ አላቆመም፡፡ ከአንድነትና መኢአድ እንዲሁም ሰማያዊ ፓርቲ ስኬታማ ሰልፎች በኋላ ደግሞ ሰሞኑን የምንመለከተው፤ ጭራሽኑ ሰልፍ መሰለፊያ ስፍራ የሚያሳጣ ሁኔታ እንዳለ ነው፡፡ ቀደም ሲል ሰልፍ የተከለከለባቸው ስፍራዎች የጦር ሰራዊት ካምፖች፤ ሆስፒታሎችና መሰል ስፍራዎች ነበሩ፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ በትምህርትቤቶች ወይም ዩኒቨርስቲዎች አካባቢም ሰልፍ ማድረግ አይቻልም የሚል ደንብ ወጣ፡፡ ቀጥሎ በእምነት ተቋማት ማለትም በመስጊድና በአብያተክርስቲያናት አካባቢ አይቻልም የሚል አዋጅ/ደንብ ይመጣል፡፡ በአዲስ አበባ በሁሉም ማእዘን ቢኬድ፤ ትምህርትቤት ባይኖር፤ ሆስፒታል አለ፤ ሆስፒታል ባይኖር፤ የጦር ካምፕ አለ፤ የጦር ካምፕ ባይኖር፤ ቤተ-እምነት አለ፤ ቤተ-እምነት ባይኖር፤ ዩኒቨርስቲ አለ፤ ዩኒቨርስቲ ባይኖር መዋእለ-ሕጻናት አለ፤ ያም ባይኖር የሆነ ነገር አለ፡፡ ስለዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ሰለፍ ሊደረግ የሚችልባቸው ስፍራዎች ውሱን በጣም ውሱን ሊሆኑ ነው፡፡ ደግሞስ የተቃውሞ ሰልፍ አንድም መንግስት እንዲሰማው ለማድረግ ሆኖ ሳለ፤ በመንግስት ተቋም በጠገብ መሰልፍ አይቻልም የሚሉት ደንብ እንዴት ያለ ደንብ ነው፡፡ ተቃጠልን እኮ ጎበዝ፡፡

 

የአንድነት የሶስት ወር ዘመቻ

6-    እንግዲህ በዚህ ሁሉ ሕገመንግስቱን የሚሸራርፉ የተጻፉ ደንቦችና አዋጆች፤ ያልተጻፉ አፋናዎችና ትንኮሳዎች ውስጥ ተሸሎክሉከው ነው፤ አንድነቶችና ሰማያዊዎች የተቃውሞ ሰልፎችን የሚያደርጉት፡፡ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ፤ (ከዚህ በኋላ አንድነት እያልኩ ነው የምጠራው)፤ በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ውስጥ ከአዲስ አበባ ተጀምሮ አዲስ አበባ የሚያበቃ፤ በ15-17 ከተሞች የሚደረግ፤ የኑሮ ውድነትን፤ የሰብአዊ መብት ጥሰትና አፈናና፤ የመሬት ባለቤትንትን፤ የሚመለከቱ የተቃውሞ ሰልፎችን አሰናድቷል፡፡ አንድነት በተለያዩ ከተሞች ውስጥ የሚደርጋቸውን ሰልፎች በገንዘብ ለመርዳት በውጭ አገር የሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ኢትዮጵያዊያን ቃል እየገቡ ነው፡፡ መቼም ሲያትል ጎንደሬ ይበዛል፤ ጎንደርን ወስዷል፡፡ አትላንታ አንድ ከተማ ወስዷል፡፡ ላስ ቬጋስም እንደዚያው፡፡ እስካለፈው ወር መጨረሻ ድረስ የቀሩት ከተሞች አምስት ብቻ ናቸው፡፡ የቶሮንቶ አንድነት የድጋፍ ሰጪ ማህበርም የነቀምት ከተማን ሰለፍ ለመርዳት ቃል ገብቷል፡፡ ቀደም ሲል እሁድ ማርች 23 ቀን የአንዱዓለም አራጌን መጽሀፍ ለማከፋፈልና እስረኞችን ለማሰብ በተጠራ ዝግጅት ላይ የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ ታምራት ይገዙ ቶሮንቶ መቀሌንም ስፖንሰር እንደሚያደርግ አስታወቋል፡፡ ስለዚህ፤ ቶሮንቶ ሁለት ከተሞችን ስፖንሰር ያደርጋል ማለት ነው፡፡ ይሄ በረከት ሲያንሰን ነው፡፡

 

እነሆ ቅስቀሳ፤ አጋርነት ለነቀምት፤

7-     አንድነት ቶሮንቶ፤ ለነቀምቱ ሰልፍ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ቅዳሜ ኤፕሪል 26 ቀን፤ ከሰዓት በኋላ፤ ከ3pm ሰኣት ጀምሮ፤ 2050 ዳንፎርዝ ጎዳና ላይ በሚገኘው ሂሩት ካፌ፤ የአብረን እንዋል መርሀግብር አዘጋጅቷል፡፡ ይሄ ጽሁፍ በከፊል የዚያ ዝግጅት ቅስቀሳ አካል ነው፡፡ ልቀስቅሳችሁ ተዘጋጁ፡፡ ቅስቀሳው እንዲህ የሚል ነው፤ አገር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን፤ ከላይ የጠቀስናቸውን መሰናክሎች አልፈው የተቃውሞ ሰልፍ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና ሲሉ፤ ሰልፋቸው በኢህአዴግ ሰራዊት ወይም ፖሊስ ወይም ደህንነቶች እንጂ፤ በገንዘብ እጦት ምክንያት እንዳይሰናከል የማድረግ ግዴታ አለብን የሚል ነው፡፡ በቶሮንቶ አካባቢ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን፤ በዚህ መደበኛ ባልሆነ፤ የአብረን እንዋል ዝግጅት ላይ በመገኘት፤ የበኩላችንን የገንዘብ ልገሳ እንድናደርግ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ፤ ቅዳሜ ኤፕሪል 26 ቀን፤ 2014 ዓ.ም፤ ከሰኣት በኋላ፤ ሂሩት እንገናኝ፡፡

8-     በነገራችን ላይ፤ ቶሮንቶ በቆየሁባቸው ያለፉት 13 ወራት፤ ከገንዘብ ማሰባሰብ ጋር በተያያዘ ቶሮንቶ የሚንቀሳቀሰው ከአቅም በታች ነው ማለት ይቻላል፡፡ ትንሽ ቋጣሪ መስሎብኛል፡፡ በርግጥም በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ ፖለቲካ ነክ ዝግጅቶች ላይ የሚታደሙትንና ያላቸውን የሚወረውሩት ቸሮች፤ ተመሳሳይና የተወሰኑ ሰዎች በመሆናቸው፤ የዚህ ከአቅም በታች የመንቀሳቀስ ተጠያቂዎች እነማን እንደሆኑ እንጃ፡፡ ላለፈው ስርየት ሆኖ፤ ስለሚመጣው ሳስብ ግን፤ እኔ እንዲህ ያለውን አገራዊ ዝግጅት የማየው እንደበረከት ነው፡፡ ይሄ በረከት ለሁላችሁም መድረስ አለበት፡፡ ስለዚህ የመጪው ኤፕሪል 26፤ የአንድነት በረከት እንዳያመልጣችሁ፤ ሂሩት ካፌ እንገናኝ፡፡ በእለቱ በተለያየ ምክንያት መገኘት ያልቻለም፤ የገንዘብ ልገሳውን በሰው መላክ እንደሚችል ወይንም በአንድነት ባንክ ሂሳብ Unity for Human Rights and Democracy: TD Trust; የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ 12682 0041 0883 5209213 መክተት እንደአማራጭ እንደተቀመጠ፤ አንድነት ቶሮንቶ ያወጣው መግለጫ ያሳያል፡፡

 

ከደሴ ወደአዲስ፤ … ወደነቀምት፤ በዚህ 22 አመት እንደነቀምት የተጎዳ ማን አለ፤

9-    በርግጥ የአንድነት የአዲስ አበባ ሰልፍ በተያዘለት ቀን መጋቢት 28 አልቀጠለም፡፡ ይሄ ጽሁፍ ወደህትመት ሲላክ፤ የአዲስ አበባው ሰልፍ ሚያዚያ 5 እንደሚደረግ ቢገመትም፤ አሁን ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ፤ የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰልፉ ቅዳሜ፤ የሰልፉም አቅጣጫ ወደጃንሜዳ ካልሆነ እያለ ነው፡፡ ማደናበር፤ ማናደድ፤ ማዘናጋት ይሉታል ይሄንን ስልት፡፡ እኔ፤ ብልጥ ልጅ የሰጡትን ይዞ ያለቅሳል ነው የምለው፡፡ ፖለቲካና ሕይወት ,ባልመረጥነው መንገድ ውስጥ የመረጥነውን ለማግኘት የምናደርገው ሩጫ ነውና፡፡ መጋቢት 28 ቀን በደሴ የተደረገው ሰልፍ ደማቅና የሚያበረታታ፤ በርግጥም ለሌሎች ከተሞችም መነሳሳትን የሚያመጣ እንደሆነ አስተውያለሁ፡፡ ስለዚህ፤ ነቀምትን ከደሴ የተሻለ ለመቀስቀስና ለማሰለፍ፤ ሁላችንም መረባረብ እንዳለብን ቀስቃሽ አያስፈልገንም፡፡ ደግሞስ በዚህ 22 አመት በኦነግ ስም እንደነቀምት የተጎዳ ማን አለ፡፡ ስለዚህ ነቀምት ተሰልፎ እሪይ ይል ዘንድ ግድ ነው፡፡ ደሴ ነቅሎ ወጥቷል፡፡ ነቀምትም ነቅሎ ይወጣል፡፡ ነቀምት ነቅሎ እንዲወጣም እኛም ከዚህ ከቶሮንቶ ነቅለን እንወጣለን፡፡ ቅዳሜ፤ ሚያዚያ 26 ቀን፤ ከሰዓት በኋላ፤ ከ3 እስከ 6 ሰዓት ሂሩት እንገናኝ፡፡

10-    ለተጨማሪ የአንድነት ዝርዝር አገልግሎቶችና መረጃዎች በአካል በአንድነት በጽህፈት ቤታት፤ ወይም ከታች በተጠቀሱት የመገናኛ መንገዶች ያግኙን፡፡ አንድነትን ለማግኘት፤ ኢሜል፤ unityforhumanrights@gmail.com ፤ ድረገጽ፤ http://andnettoronto.blogspot.ca/. የጽህፈት ቤት አድራሻ፡ B2- 2017 Danforth Avenue, Toronto, ዳንፎርዝ ላይ፤ ከዉድባይን ባቡር ጣቢያ በስተምስራቅ 50 ሜትር ራቅ ብሎ፤ ከዘመን እንጀራ መደብር በተቃራኒ፤ ከትብብር መረዳጃ እድር ጎን፡፡

ተክለሚካኤል አበበ ነኝ፤ ቶሮንቶ፤ ሚያዚያ፤ 2006/2014

“ንብረት የማፍራት መብት መገለፅ ያለበት በብሔረሰብ ደረጃ ሳይሆን በግለሰብ ነው” (አቶ ተክሌ በቀለ)

$
0
0

አቶ ተክሌ በቀለ (የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት)

በዘሪሁን ሙሉጌታ

 

አቶ ተክሌ በቀለ (የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት)

አቶ ተክሌ በቀለ (የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት)

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሁለተኛውን የሕዝብ ንቅናቄ መጀመሩ የሚታወስ ነው። ፓርቲው ከዚህ ቀደመ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል የሕዝባዊ ንቅናቄ መድረኮች አዘጋጅቷል። አሁን ደግሞ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪ ቃል ፕሮግራሙን ይፋ አድርጓል። ባለፈው እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም በደሴ ከተማ ፕሮግራሙን በሰላማዊ ሰልፍ አከናውኗል።

በደሴ ስለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍና “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ የፓርቲውን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተክሌ በቀለ፣ የፓርቲው የውጪ ግንኙነት ኃላፊ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ እና የፖርቲው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ሰልፉን መርተውታል። ከመሬት ባለቤትነትና ከሰልፉ ጋር በተያያዘ የፓርቲውን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተክሌ በቀለን አነጋግረናቸዋል።

ሰንደቅ፡- በደሴ ያካሄዳችሁት ሰላማዊ ሰልፍ ምን ያህል የተሳካ ነበር?

አቶ ተክሌ፡- መጀመሪያ ፕሮግራሙን ያሰብነው በሐዋሳ፣ በአዲስ አበባና በደሴ ከተሞች ነበር። እንደአጋጣሚ ሆኖ የደሴው በመሳካቱ ቅስቀሳ ስናደርግ ቆይተን ሰልፉን ለማካሄድ በቅተናል። የአዲስ አበባውና የሐዋሳው ለሌላ ጊዜ ተዛውሯል። የሐዋሳውን በራሳችን ምክንያት ያራዘምነው ሲሆን፤ የአዲስ አበባው ግን በአስተዳደሩ ችግር ምክንያት ነው።

የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ እንደጠበቅነው በከፍተኛ ሞቅታ ነው ፕሮግራሙ የተጀመረው። በርካታ ሕዝብ ተገኝቶልናል። የሰልፉ አካል ሆኖ በመሐል መንገድ ላይ መፈክር እያሰማ ሲሄድ የነበረው የሕዝብ ብዛት ከ50 እስከ 60 ሺህ ገምተነዋል። ከሰልፉ ጎን ለጎን ዳርና ዳር የሚሄደው ሕዝብ በግምት መቶሺህ ይሆናል። በእኛ እምነት ሕዝቡ በመሬት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የመሬት ጉዳይ የሚያስከፍላቸውን ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመገንዘብ ከፍተኛ የሆነ መነሳሳት አሳይቷል። በተደረገው የሁለት ቀን ቅስቀሳ ያን ያክል ሕዝብ መውጣቱ የሕዝቡም ስሜት ከፍተኛ እንደነበር ያሳያል። በዚህ ወቅት እኔን ያስታወሰኝ በ2002ቱ መርጫ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ “ደሴም ሳይቀር አሸንፈናል” ብለው ነበር። አሁን ሳየው ግን የኢህአዴግ የምርጫ ኮንትራት ሳያበቃ ይሄን ያክል ሕዝብ ወጥቶ “በቃኝ” የማለቱ ሁኔታ ሲታየ ምርጫውን እንዴት ነበር ያሸነፉት ብዬ እንዳስብ አድርጎኛል።

ሰንደቅ፡- መሬት የፖሊሲ ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን ከሰላማዊ ሰልፍ ይልቅ በሕዝባዊ ውይይት ማካሄዱ ይሻላል፤ አለበለዚያ በትንሹም በትልቁም ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት የፓርቲውን ደጋፊዎች ያሰለቻል የሚል ነገር እየተነሳ ነው። ለዚህ ኀሳብ ያለዎት ምላሽ ምንድነው?

አቶ ተክሌ፡-ፕሮግራሙ ሲጀመር የመረጥናቸው ከተሞች ነበሩ። አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ የሀገሪቱ ምሁራን የሚገኙበት የአዳራሽ ውስጥ ስብሰባ አቅደን ነበር። ወደ አደባባይ እየገፋን ያለው ኢህአዴግ ነው። መሬትና ከመሬት ጋር ተያይዞ ለሚፈጠሩ ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊና የፍትህ ችግሮች በተመለከተ በሰላማዊ ሰልፍና በሕዝባዊ የአዳራሽ ስብሰባ ለይተን ነበር። ነገር ግን ገና ከመጀመሪያው አዲስ አበባ ላይ አዳራሽ ማግኘት ተቸግረናል። የመንግስት አዳራሾች ብቻም ሳይሆን በገንዘባችን ከፍለን የሆቴሎችን አዳራሽ ማግኘት አልቻልንም። ወደ ጎዳና እየገፋን ያለው ገዢው መደብ ነው።

ሰንደቅ፡- የመሬት ችግር በከተማና በገጠርም የተለያየ ነው። በሀገሪቱም የችግሩ አይነትና መጠንም የተለያየ ነው። በቀላሉ የሕዝብ ድጋፍ አላችሁ ተብሎ በሚገመተው ደሴ ከተማ ከማካሄድ ይልቅ በደቡብና ኦሮምያ ክልሎች ለምን እንቅስቃሴውን አልጀመራችሁም?

አቶ ተክሌ፡- በአጠቃላይ በመሬት ላይ ያለን እይታ ሦስት አይነት ነው። መሬት በግል፣ በወል ወይም በመንግስት ስር መሆን አለበት የሚል የመሬት ስሪት አቋም አለን። ኢህአዴግ ደግሞ መሬትን በተመለከተ የሚያስቀምጠው ከእኛ ፍፁም የተለየ ነው። በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40 ንዑስ ቁጥር ስድስት ላይ መሬት የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንደሆነ አድርጎ ነው የሚያስቀምጠው። ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በባህል፣ ወዘተ እንጂ ንብረት በማፍራት መብታቸው ሊገለፅ አይችልም። ንብረት የማፍራት መሠረታዊ መብት መገለፅ ያለበት በብሔረሰብ ደረጃ ሳይሆን በግለሰብ ነው። ኢህአዴግ ብሔር ብሔረሰቦች የሚያቋቁሙት መንግስት ነው ብሎ ስለሚያምን በተዘዋዋሪ መሬት የመንግስት እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ይህ ማለት ደግሞ በብሔር ብሔረሰቦች ስም መሬትን ወይም የሕዝብን ንብረት ጠቅልሎ ኢህአዴግ ወስዶታል ማለት እንችላለን። በሌላ አነጋገር ግለሰቦች ከመሬት ባለቤትነት ውጪ ሆነዋል ማለት ነው። በእኛ እምነት የከተማ መሬት የግለሰቦች መሆን አለበት ብለን እናምናለን። የገጠሩ ደግሞ አስቀድሜ እንደነገርኩህ በግል፣ በወል ወይም በጋራ እና በመንግስት መያዝ አለበት።

ወደ ጥያቄህ ስመጣ አጠቃላይ የኢህአዴግ የመሬት ፖሊሲ በብሔር ብሔረሰቦች ሽፋን ከመውሰዱ አንፃር ችግሩ የመላ ሀገሪቱ ነው። ስለዚህ በደሴም ጀመርከው በደቡብ ችግሩ አንድና ተመሳሳይ ነው። በእርግጥ በደሴ የጀመርነው የተሻለ ተቀባይነት አለን በሚል መነሻ ብቻ አይደለም። አንድነት አጠቃላይ ሕዝቡ ከተቃዋሚው ጎራ ጋር እንደወገነ እንረዳለን። ኢህአዴግ የሚዘጋብን ሕዝቡ እንደሚደግፈን ስለሚያውቅ ነው። በእርግጥ አንድነት ያልደረሰባቸው፣ ሌሎች ተቃዋሚዎች ጠንካራ ስራ የሚሰሩባቸው ቦታዎች ይኖራሉ። ያም ሆኖ ስንጀምረው አዲስ አበባና ሐዋሳ ነበር። ደሴ አልነበረም።

ሰንደቅ፡- ገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በመሬትም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የጠራ ፖሊሲ የላቸውም እያለ ነው። በእናንተ እምነት በአሁኑ ወቅት የጠራ ፖሊሲ አለን ብላችሁ ታስባላችሁ?

አቶ ተክሌ፡- በመሬት ላይ ብቻ አይደለም። በአጠቃላይ ከመሬት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች በርካታ ናቸው። የሀገሪቱ አንጡራ ሀብት መሬት እንደሆነ አንረዳለን። ዋነኛ ትኩረታችንም የመሬት ምርታማነት፣ ባለቤትነትና ልማት ነው። ከገዢው ፓርቲ ጋር ካሉን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የአከባበር ልዩነቶች ባሻገርም አንዱና ዋነኛው መሬት ነው። ከሀገሪቱ የችግር ምንጮች ውስጥ አንዱ የመሬት ባለቤትነት ነው። ስለዚህ በዚህ ዙርያ ያሉ ችግሮችን ተረድተናል። ችግሮቹን በመረዳታችንም የጠራ ፖሊሲ ቀርፀናል። ከመሬት ባሻገርም በፋይናንስም በለው፣ በግብርናም ሆነ በውጪ ጉዳይ በማኅበራዊ ጉዳዮች ሀገሪቷዋን ከድህነትና ኋላቀርነት ያወጣል ብለን እናምናለን። ችግራችን የቀረፅናቸውን አማራጭ ፖሊሲዎች ለሕዝብ ማድረስ የምንችልበት የሚዲያ እና ወደ ሕዝቡ የምንቀርብበት መድረክ መዘጋቱ ነው። እና ኢህአዴግ “ተቃዋሚዎች አማራጭ የላቸውም” የሚለው አባባል ድሮ የቀረ ተረት ተረት ነው።

ሰንደቅ፡- በተቃዋሚዎች በኩል ወጥ የሆነ የመሬት ፖሊሲ አይስተዋልም። በተለይ በኦሮሞ ብሔር የተደራጁ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መሬት የመንግስት ይሁን የሚል ዝንባሌ አላቸው። ሌሎቻችሁ ደግሞ “መሬት ይሸጥ ይለወጥ” እስከማለት ትደርሳላችሁ ይህ ደግሞ በምርጫ ወቅት አያስቸግርም?

አቶ ተክሌ፡- ተመሳሳይ ፕሮግራም ያላቸው ፓርቲዎች ውህደት ፈጥረው በአንድ ላይ ቢንቀሳቀሱ ችግሩ ሊፈታ ይችላል። የግል ስልጣንና የቡድናዊ ጥቅምን አስወግደው ወደ ውህደት ቢመጡ መልካም ነው። አሁን ፓርቲዎች ሚዛን በማይደፉ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ቢሆንም፤ ያነገቡት ፕሮግራም የተለያየ አይደለም፤ በመሆኑም ሕዝቡ የተለያዩ ፓርቲዎችን ቢመርጥም የሚመረጠው ፕሮግራም ግን ተቀራራቢና በአመዛኙ አንድ አይነት ነው ለማለት ያስደፍራል። በእርግጥ ከመድረክ ጋር በተያያዘ አንዱ ልዩነት የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ ነው። ሆኖም ግን በመለስተኛ ፕሮግራማችን ላይ መሬትና ያልተፈቱ ሌሎች ጥያቄዎችን ሕዝቡ እንዲፈታቸው ተስማምተናል። ነገር ግን ሕዝቡ ደግሞ ደሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቹን ሙሉ በሙሉ አልተጎናፀፈም። መሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶቹን ያልተጎናፀፈ፣ ሕዝብ ዋነኛ በሆኑ የሕዝብ ችግሮች ላይ መፍትሄ ለማምጣት መጀመሪያ የተነፈገውን መብት ማግኘት አለበት የሚል መረዳት አለ። በመሠረቱ የተጠቀሱት የኦሮሞ ድርጅቶችም መሬት የመንግስት ይሁን ሳይሆን፤ ሕዝቡ ይወስን እያሉ ነው። አረናን ብትወስደው መሬት የግል ቢሆንም፤ መሸጥ መለወጥ የለበትም ይል እና ጉዳዩ የሕገ-መንግስት ማሻሻያን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ሕዝቡን ቀጥተኛ ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው። በድምሩ ስታየው መሬትን በተመለከተ በተቃዋሚዎች ካምፕ ያለው መረዳት የሚያራራቅ ሳይሆን ሊታረቅ የሚችል ጉዳይ ነው።

ሰንደቅ፡- ፓርቲያችሁ በአሁኑ ወቅት የመሬትን ጉዳይ ያነሳው ለምንድን ነው?

አቶ ተክሌ፡- ኢትዮጵያ ውስጥ የስልጣን መባለግን ጨምሮ ከፍተኛ የሙስና ምንጭ የሆነው መሬት ነው። የመሬት ጉዳይ የፍትህ እጦትና የመልካም አስተዳደር ችግር መገለጫዎች አንዱና ዋነኛው ነው። ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አዝጋሚነትና ለማኅበራዊ ችግሮች ምንጩ የመሬት ባለቤትነትና የይዞታ አስተዳደር ችግር ነው። ይህንን እኛ ብቻ ሳንሆን እራሱ ገዢው ፓርቲ የሚያምንበት ጉዳይ ነው። በዚህ ወቅትም ጉዳዩን ልናነሳው የቻልነው ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮች ላይ ግንዛቤ ለመጨበጥ፣ ባለን ፖሊሲም ላይ እንደ ግብአት የሚያስፈልግ ነገር ካለም ለማካተት ነው። በዋናነት ግን የሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውሶች መገለጫ መሆኑን፣ የኢህአዴግ የመሬት ፖሊሲ የተሳሳተና ያስከተለውንም በሙስና የመጨማለቅ ሁኔታን ለማሳየት ነው።

በአሁኑ ወቅት መሬት በኢንቨስትመንት ስም የሙስና መንጭ ሆኗል። ግለሰብ በግለሰብነቱ ከመሬት ባለቤትነት ከራቀ በፖለቲካ ዓይን ስታየው የካድሬዎች መጫወቻ ይሆናል። ይህንን ማረጋገጥ የሚቻለው በተለያዩ ጊዜአት መንግስት የሚያስራቸው ባለስልጣናቱን እያየን ነው።

ሰንደቅ፡- በቀጣይ የምታካሂዱት እንቅስቃሴስ ምን ይመስላል?

አቶ ተክሌ፡- በትላልቅ ከተሞች በተለይም ምሁራንን በቀላሉ በምናገኝበት ቦታ የአዳራሽ ስብሰባዎች እያደረግን፣ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ይደረጋል። በገጠር ደግሞ በወረዳ ደረጃ የሚሰሩ ስራዎች አሉ። ሰላማዊ ሰልፎቹም በተመረጡ ከተሞች ይቀጥላሉ። እንደነገርኩህ መሬትን በተመለከተ ሕዝቡ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኝ ዋነኛ ዓላማችን ነው። በገጠሩም በከተማም ሰፊ እንቅስቃሴ እናደርጋለን ብለን አቅደናል።

ሰንደቅ፡- ይህ መሬትን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ በቀጥታ ከ2007ቱ ምርጫ ጋር የሚያያይዘው ነገር አለ?

አቶ ተክሌ፡- ከምርጫ ጋር አይያያዝም። ምርጫ እንገባለን ወይስ አንገባም የሚለው የብሔራዊ ምክር ቤቱ ውሳኔ ነው የሚሆነው። በአጠቃላይ ያሉትን ሁኔታዎች እያየን የምንወስነው ጉዳይ ነው። አሁን ግን የመሬት ጉዳይ ያለንን ፖሊሲ ከማዳበርና ኅብረተሰቡም በመሬት ላይ የጠራ

የአሩሲና አካባቢው ተወላጅ አማሮች አስቸኯይ መልእክት ለኢትዮጲያዊው!!!

$
0
0

የአሩሲና አካባቢው ተወላጅ አማሮች አስቸኯይ መልእክት ለኢትዮጲያዊው!!! (መጋቢት 30፣ 2006 ዓ.ም.)

454በአማራው አናት ላይ እያንዣበበ ያለውን የጅምላ እልቂት እንዴት ወገኖች ከመጤፍ እንዳልቆጠራችሁት ለኔ ትልቅ እንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ። መቼም ኢትዮጲያዊያኖች ትልቅ የግንዛቤ ችግር ነው ያለብን። ከሰሞኑ በአሩሲ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች በተገኙበት የተመረቀው በተቆረጠ እጅ ላይ የተቀመጠ ጡት የሚያሳይ ሀውልት ከፍተኛና ምናልባትም በኛ ትውልድ ያልተስተዋለ ጎሳን መሠረት ላደረገ ፍጅት ብዙ እርምጃዎችን ያንደረደረን ድርጊት መሆኑን ምን ያህላችን ያስተዋልነው ጉዳይ እንደሆነ ሳሰላስለው ብዙዎቻችን እያስገመገመ ያለውን አርማጌደን አይቀሬነት አምነን የተቀበልን ያህል እንዲሰማኝ ሆኗል። በምረቃው ቦታ የመገኘት እድል የገጠማቸው የአካባቢው ተወላጅ አማሮች በስነስርዓቱ ላይ ስለተገኘው ግዙፍ መጠን የነበረው ታዳሚ እንዲህ ላለ ታላቅ ጥፋት መሳሪያ መሆን ታሪክ የማይረሳው እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊት መሆኑን ገልፀው አሳሳቢም ነው ብለዋል።

ታዳሚው ፊት ላይ ይነበብ የነበረውም የጥላቻ ውፍረትና የበቀልተኝነት ስሜት ስለተከታዩ ነገር አመላካች መሆኑን በሀዘን ገልፀዋል። እስከ አሁን ድረስም በኦነግ እና ኦህዴድ ጭፍን ብሄርተኛ ተከታዮች ዘንድ ሲሰበክ የነበረውን የአማራ ጎሳን ከኦሮሚያ የማፅዳት ውጥን የይለፍ ምልክት የሰጠ ድርጊት አድርገን እንቆጥረዋለን ብለዋል። አክለውም ሁኔታውን ተከትሎ ሀውልቱ በቆመበት አሩሲና አካባቢው እየተስተዋለ ያለው አንዳንድ አፍራሽ እንቅስቃሴ ይህን እምነታቸውን ምክንያታዊ እንደሚያደርገው ገልፀዋል። የዚህ ሴራ አንዱና ብቸኛው አላማ አማራውን ማስፈጀት መሆኑን ገልፀው ሀውልቱም ለዚህ በአማረው ላይ ለሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ህያው ማስጠየቂያ እንደሆነ አብራርተዋል። በህዝቡ መካከል ያለመቻቻልና የጥላቻ መንፈስ ስለሌለ እንዲቀሰቀስ የታሰበው የጎሳ ግጭት የመነሳት እድሉ ጠባብ ነው የሚለው የፖለቲከኞች አስተያየት የግል የፖለቲካ አጀንዳን ለመግፋት ሲባል በዜጎች ህይወት ላይ ቁማር መጫወት መሆኑን ገልፀው የፓለቲከኞቹን በንቃት እንሳተፍበታለን ስለሚሉት የሀገሪቱ ፖለቲካና በህዝቦች ተቻችሎ እና ተሳስቦ የመኖር በሀል ላይ ስላሳረፈው አፍራሽ ተፅዕኖ ያላቸውን ዝቅተኛ መረዳትም የሚያሳጣ ነው ብለዋል። ዛሬ ይህን ከአማራ የፀዳ ኦሮሚያን ስለመመስረት የሚያቀነቅኑ እንደ ኦነግ እና ኦህዴድ ያሉ ብሄርተኛ ድርጅቶች ተከታዮች የሆኑ፣ በዚህ አውዳሚ ፍልስፍና የሰከሩና ህሊናቸው የታወረ ፤ ከዚህ በፊት በአርባጉጉ በበደኖ ወዘተ የተፈፀመውን ዘግናኝ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት አይነት ለመፈፀም ወደሗላ የማይሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አክራሪ ብሄርተኞች መፈልፈላቸውን በማመላከት የዚህን የእልቂት ጥንስስ አውዳሚ መጨረሻ የተቀረው ኢትዮጲያዊ ተረድቶ በሰላማዊ ሰልፍና በመሳሰሉት የእሪታ ድምፁን በአስቸኯይ እንዲያሰማላቸው ጠይቀዋል። ካራ ተስሎብን ወደ ምታችን የምንነዳ በሚሊዮን የምንቆጠር ዜጎች ፖለቲካው ውስጥ በሚርመሠመሡ ጉዶች ጉዳያችን እንዲህ አትኩሮት መነፈጉ የጉዳዩ ብቻ ሳይሆን የመፍትሄውም ብቸኛ ባለቤቶች የመሆናችንን መሪር ሀቅ የጋተን አጋጣሚ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል። አያይዘውም ኢትዮጲያዊው ወገን ለጥያቄያቸው ባፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የማይችል ከሆነ ግን እነሱ የሚቻላቸውን እንደሚያደርጉና አካባቢውን በጅምላ ከመልቀቅ ጀምሮ የተቀረው የአማራ ተወላጅም አካባቢውን በመልቀቅ የራሱንና የልጆቹን ህይወት እንዲታደግ ሰፊ ቅስቀሳ ውስጥ እንደሚሰማሩም አሳስበዋል።

አምደፂዮን ዘተጉለት፤ ከአሩሲ ነገሌ

 

የባልቻ አባነፍሶ ልጆች እንሁን ! (ሚሊዮኖች ድምጽ)

$
0
0

 ነጻነት ዋጋ ያስከፍላል። አገር ቤት ያሉ ወገኖቻችn እጅግ በጣም ከባድና ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ለሰላም፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት ፣ ለነጻነትና ለኢትዮጵያ አንድነት፣ እልህ አስጨራሽ ትግል እያደረጉ ነው። «ሽብርተኞች ናቸው» በሚል በቃሊት ፣ በቂሊንጦ፣ ዝዋይ በመሳሰሉ ዘግናኝ እሥር ቤቶች እየማቀቁ ያሉ ፣ የሰላምና የዴሞክራሲ አርበኞች የሆኑ፣ ብርቅዬ የኢትዮዮጵያ ልጆችን መመልከቱ ይበቃል። አንዱዋለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ ፣ ርዮት አለሙ እያለን ብዙ መዘርዘር እንችላለን።

Balcha ljoch

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአንድ በሩጫ ላይ «ረብሻቹሃል» በሚል ፖሊሲ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ፣  ሰባቱን  የ«ጣይቱ ልጆች» አስሮ ማንገላታቱ በስፋት ተዘግቦ ነበር። በዚህ ሳምንትም፣  የአዲስ አበባ ፖሊሲ፣ ሕዝብን ለመጠበቅና ለማገለገል ሳይሆን፣ ሕዝብን ለማወክና ለማሸበር የተሰማራ እንደሆነ በድጋሚ ያረጋገጠበት ሁኔታ ነዉ የነበረው።

ዘጠኝ  የአንድነት አባላት፣  ሕገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት፣ መጋቢት 28 ቀን ሊደረግ ታስቦ ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ፣ በራሪ ወረቀት በማደል ቅስቀሳ ያደርጋሉ። አልፈሩም። አልደነገጡም። «ሰው ያለ ነጻነቱ ምንድን ነው ?» በሚል፣ ጀግንነታቸውን አሳዩ።  አራቱ ወንድሞቻችን ከፍተኛ ድብደባ ሲደርስባቸው፣ ሁለቱ የረሃብ አድማ አድርገው ከአምሰት ቀናት እሥር በኋላ ይፈታሉ።  ሶስቱ፣ ምንም እንኳን ፍርድ ቤቱ ምንም ወንጀል አልተገኘባቸው የሚል ድምዳሜ ቢደርስም፣ አንድ ሺህ ዶላርና የመንግስት ሰራተኛ ዋስ አቅርቡ በማለቱ፣  እስከአሁን በእሥር ላይ ናቸው።

እነዚህ ዘጠኙ የአንድነት አባላት፣ በድፍረታቸውና በቆራጥነታቸው በርግጥ የባልቻ አባ ነፍሶ ልጆች መሆናቸውን በገሃድ አሳይተዋል። ባደረጉት ሥራ እና በከፈሉት መዋእትነት ትግል ማለት ምን ማለት እንደሆነ አሳይተዉናል።

አዎን ነጻነት ዋጋ ያስከፍላል። አገራችን ኢትዮጵያ ሕግ የበላይ የሆነባት፣. ዜጎቿ በሁሉም የአገሪቷ ክፍል ሳይፈሩ፣ ሳይሸማቀቁ የሚኖሩባት፣ ሰብአዊ መብት ያለ ገደብ የሚከበርባት፣ አንድነቷና ሉአላዊነት የተጠበቀና የበለጸገች ኢትዮጵያ እንድትሆን ከፈለግን፣  ዘጠኝ አይደለም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የጥይቱ ልጆች፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የባልቻ አባ ነፍሶ ልጆች ያስፈልጋሉ።

የሚሊዮኖች ድምጽ እንቅስቃሴ ተጀጀመረ እንጂ አላለቀም። በባህር ዳርና በደሴ፣ የታየው ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ አይደለም። ከአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ሁሉ መነቃነቅ እንዳለብን ለማሳሰብ እንወዳለን። ባለለንበት ቦታ እንደራጅ። እንዴት መሳተፈ፣ እንዴት መርዳት እንዳለብን እንመካከር። ትግሉ የአንድነት ድርጅት ሳይሆን የሚሊዮኖች ነው። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን። የጣይቱ ልጆች፣ የባልቻ አባ ነፍሶ ልጆች እንሁን።

የአዲስ አበባዉ ቅስቀሳ ከተጀመረ ከመጋቢት 25 ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 2 ድረስ የነበረዉን ፣ በባልቻ አባ ነፍሶ ልጆች የደረሰዉን  ለማንበብ ከታች ይመለከቱ። በገንዘብ መርዳት የምንፈልግ  http://www.andinet.org

በመሄድ በፔይፓል  መርዳት አስተዋጾ ማድረግ እንችላለን። ተጨማሪ ማብራሪ ካስፈለገም  millionsforethiopia@gmail.com በሚለው አድራሽ ኢሜል ቢያደርጉልን ሊያገኙን ይችላሉ።

 ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዚያ 2  የባልቻ አባ ነፍሶ ልጆች  ሁኔታ እንደሚከተለው ይከታተሉ

ሐሙስ መጋቢት 25 ቀን 2006 ዓ.

በለገሃር አካባቢ ሲቀሰቅሱ የነበሩ፣  ወጣት አክሊሉ ሰይፉና ሰለሞን ፀሐዬ፣  በለገሃር ፖሊስ ጣቢያ ከፍተኛ ድብደባ ይፈጸምባቸዋል። ሲ.ኤም.ሲ አካባ፣  ኤፍሬም ሰለሞን እና ታሪኬ ኬፋ በተመሳሳይ ሁኔት በፖሊስ ይደበደባሉ። በየካ ክፍል ከተማ፣ እውቁ ደራሲ መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍን፣ ሃብታሙ ታምሩና አሸናፊ ጨመዳም ሕግ መንግስቱ የሚፈቅድላቸውን መብት ተጠቅመው ሰላማዊ የቅስቀሳ በራሪ ወረቀት ሲያሰራጩ በፖሊስ ይታሰራሉ።በቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ በካሳንሺስ አካባቢ፣  ወርቁ እንድሮ እና አክሊሉ ሰይፉ በተመሳሳይ ሁኔታ ታስረዉ ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይወሰዳሉ። በዚችዉ አንድ ቀን ብቻ አራት የአንድነት አባላት ሲደበደቡ አምስት ወደ ወህኒ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ ተወስደዋል።

ዓርብ መጋቢት 26 ቀን 2006 ዓ.

የአንድነት አመራር አባላት ፖሊሶች የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ታሳሪዎቹ ሕግን አክብረዉ በሰላማዊ መንገድ ፓርቲው መመሪያ ሰጧቸው የቀሰቀሱ እንደሆነ ለማስረዳት ቢሞክሩም እስረኞቹ «ከአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ በስማችን ደብዳቤ ካልተፃፈልን አንለቃቸውም» በሚል፣ ፍርድ ቤት ሳይወስዷቸው፣ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ ዜጎች ለሁለተኛ ቀን በወህኒ እንዲቆዩ አድርገዋል።

ቅዳሜ መጋቢት 27 ቀን   2006 ዓ.

አሁንም እስረኞች ክስ ሳይመሰረትባቸው ለሶስተኛ ቀን በእስር እንዲቆዩ ይደረጋል።

እሁድ መጋቢት 28 ቀን    2006 ዓ.

እስረኞቹ ለአራተኛ ቀን ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ ፣ በእስር አሁን ይቆያሉ።

ሰኞ መጋቢት 29 ቀን  2006 ዓ.

አንድነት ፓርቲ ለመጋቢት 28/2006 ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ለህዝብ የተዘጋጀ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ በህገ ወጥ መንገድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከል በስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ የሚገኙት፣ አክሊሉ ሰይፉና ወርቁ እንድሮ መታሰራቸውን በመቃወም የርሃብ አድማ ይመታሉ።

አክሊሉን እና ወርቁ ጨምሮ በየካ ክፍለ ከተማ የታሰሩ ሌሎች ሶስት የአንድነት አባላትም ለአምስተኛ ቀን እንዲታሰሩ ይደረጋል።

ማክሰኞ መጋቢት  30  2006 ዓ.ም  

‹‹የእሪታ ቀን›› ሰላማዊ ሰልፍ ለህዝብ የተዘጋጀ በራሪ ወረቀት ሲያሰራጩ ከተያዙት አምስት የአንድነት አባላት መካከል ስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ የነበሩትና የርሃብ አድማ የመቱት ወርቁ እንድሮና አክሊሉ ሰይፉ ፖሊስ በትናንትናው ዕለት፣ ከአምስት ቀናት እሥር በኋላ ያለምንም ዋስትና ይለቃቸዋል።

በየካ ክፍል ከተማ የታሰሩ መቶ አለቃ አንዳርጌ፣ ሃብታሙ ታምሩና አሸናፊ ጨመዳ ግን ለስድስተኛ ቀን በ እሥር እንዲቆዩ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በ እስር እኒቆዩ ይደረጋል።

ረእቡ  ሚያዚያ 1   2006 ዓ.

የካ ፖሊስ ጣብያ የታሰሩት መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍን፣ ሃብታሙ ታምሩና አሸናፊ ጨመዳ በማለዳዉ የካ ምድብ ችሎት ቀርበው ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጣቸዋል።

የየካ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ክስ ‹‹ተጠርጣሪዎቹ ያለ ፓርቲው ፈቃድ ወረቀት በመበተን አመጽ እንዲነሳ አድርገዋል፣ሌሎች ተባባሪዎቻቸውም ስላልተያዙ እነርሱን በመያዝ ምርመራዬን እንዳጠናክር ተጨማሪ የሰባት ቀን ቀጠሮ ይፈቀድልኝ ››ብሏል፡፡ችሎቱን ለመከታተል በቦታው ተገኝተው የነበሩት የአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ አቶ ነብዩ ባዘዘው፣ ፍርድ ቤቱን በማስፈቀድ‹‹እነዚህን ሰዎች ወረቀት እንዲበትኑ አመራር የሰጠናቸው እኛ ነን፡፡ፖሊስ እነርሱን ፈትቶ እኛን ይሰር ››ከማለታቸውም በላይ‹‹የአዲስ አበባ መስተዳድር ላቀረብንለት የእውቅና ጥያቄ የዘገየ ምላሽ በመስጠቱና ቀኑ እየተቃረበ በመምጣቱ ህዝብ የማስተባበር ስራ እንዲሰራ አድርገናል፡፡መስተዳድሩ የሰልፉን ቀን እንድንቀይር የጠየቀን አርብ ዕለት ነው፡፡አባላቶቻችን ግን የታሰሩት ሐሙስ ዕለት ነው ፡፡ወረቀቱ ከደረሰን በኋላ የቅስቀሳ ስራችን አቁመን ህጉን አክብረናል፡፡ፖሊስ ግን ወገንተኛ ሆኖ አባላቶቻችንን አስሮ እያጉላላ በመሆኑ ያለምንም ዋስትና እንዲፈቱልን እንጠይቃለን››ብለዋል፡፡

ዳኛ ማሞ ሞገስ ፖሊስ ከአዲስ አበባ መስተዳድር የተጻፈውን ደብዳቤ በመመልከት እንዲወስን አመጽ እንዲነሳ ስለመስራታቸው መረጃ አለኝ የሚል ከሆነም ለነገ እንዲያቀርብ ያዛሉ። እስረኞች ለሰባተኛ ቀን በወህኒ እንዲቆዩ ይደረጋል።

 

 ሐሙስ ሚያዚያ 2 ቀን  2006 ዓ.

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሶስት አባላት መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍን፣ሐብታሙ ታምሩና አሸናፊ ጨመዳ በዛሬው ዕለት የካ ምድብ ችሎት ቀርበው አስገራሚ ዋስትና ይጠየቅባቸዋል።

ፓርቲው የ‹‹እሪታ ቀን› በማለት ለሰየመው ሰላማዊ ሰልፍ መገናኛ አካባቢ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ የዛሬ ሳምንት በህገ ወጥ መንገድ የተያዙት የፓርቲው አባላት በዛሬው ዕለት ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡የፓርቲው አመራሮችና አባላት የትግል አጋሮቻቸውን ጉዳይ ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በመምጣታቸው ጉዳያቸው በግልጽ ችሎት መታየት ይገባው የነበረ ቢሆንም በቢሮ በኩል ጉዳያቸው እንዲታይ ተደርጓል፡፡

የአንድነት አባላትን ጉዳይ ይመለከቱ የነበሩት ዳኛ ማሞ ሞገስ ተቀይረው ዳኛ ሬድዋን ጀማል ተሰይመዋል፣ የዛሬው ቀጠሮ ፖሊስ ቀረኝ የሚለውን ምርመራ አጠናክሮ እንዲያቀርብ ካልሆነም በነጻ እንዲሰናበቱ ለመወሰን የነበረ ቢሆንም ‹‹ተጠርጣሪዎቹ አመጽ ለማስነሳት በማቀድ ወረቀት በትነዋል›› የሚለውን ክሱን የሚያስረዳ ማስረጃ ሊያቀርብ አልቻለም፡፡ተጠርጣሪዎቹ ‹ለሰላማዊ ሰልፉ እውቅና መስጠት ይገባው የነበረ አካል በመዘግየቱ እንጂ ወረቀት መበተናችን ህገ ወጥ አያሰኘንም› በማለት ከክሱ በነጻ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡ዳኛው በስተመጨረሻ እያንዳንዳቸው አንድ ሺህ ብርና የመንግስት ሰራተኛ በዋስትና እንዲያቀርቡ በማዘዝ ፋይሉን ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ አድርገዋል፡፡

ገንዘብ በዋስትና እንዲያቀርቡ ከተጠየቁ በኋላ የመንግስት ሰራተኛ በዋስትናው ላይ እንዲጨመር መደረጉም አስገራሚ እንደሆነ በስፍራው የነበሩ አባላት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆነ ሰው ሲታሰር የመንግስት ሰራተኛ ዋስ እሆናለሁ ቢል ከስራው ሊያፈናቅሉት እንደሚችሉ ስለሚገምት፣ ለተቃዋሚዎች የመንግስት ሰራተኛን ዋስ አድርጎ የጠየቀዉን ፍርድ ቤቱ እንዲለውጥ፣ የፓርቲው አመራሮች ለዕለቱ ዳኛ አቤት ብለዋል፡፡

 

ሐሙስ ሚያዚያ 2 ቀን  2006 ዓ.

ዳኛው የአንድነት አመራር አባላትን ጥያቄ አልተቀበለም። እስረኞቹ  አንድ ሺህ ብር ከፍለው፣ የመንግስት ሰራተኛ ዋስ አቅርበው ይፈታሉ። እስረኞቹ የደረሰባቸው ነገር ወደ ኋላ እንደማይጎትታቸው፣ ትግሉን የበለጠ እንደሚያጠናክሩ ይናገራሉ።

አንድ ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? ሲፈቅድ ነው? ወይስ ሲፈቀድለት?

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም
መጋቢት 2006

Pro Mesfinበአለፈው ሳምንት (ፋክት ቁጥር 36) ወይዘሮ መስከረም የተለያዩ መጻሕፍትን በመጥቀስ በሴቶች ላይ ያለውን መጥፎ ጫና በደንብ ያስመሰከረች ይመስለኛል፤ ግን እኮ በሴቶች ላይ ያለው ጫና የቆየ፣ ክፉና ጎጂ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፤ ቁም-ነገሩ ያለው ከዚያ የባህል ጭነት በራስ ጥረት ወጥቶ፣ ነቀፌታንም ሆነ እርማትን ለመቀበል ሳይፈሩና ሳያፍሩ እንደመስከረም በአደባባይ ሀሳብን በመግለጽ በአገርና በወገን ጉዳይ መሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ የተቻለን ሁሉ ማድረጉ ላይ ነው፤ ለዚህ ነው ይህንን መልስ የምጽፈው፤ ወይዘሮ መስከረም በአጋጠሟትና በምታያቸው እንቅፋቶች ላይ ማተኮርዋ እንደርስዋ መንፈሳዊ ወኔው የሌላቸውን ያስፈራራቸዋል እንጂ አያበረታታቸውም፤ የማንንም አፍአዊ ጫና ተቋቁመው በራሳቸው የውስጥ ኃይል እንዲመሩ እናድርግ።

አንድ መጽሐፍን በመጥቀስ ወይዘሮ መስከረም የሚከተለውን ጽፋለች፡–

ፈጣሪ የሠራውን  ውጫዊ  ገጽታን ማሽሞንሞን በቂ እንደሆነ ሲነገራት የኖረች ሴት፣ በምን ተነሳሺነት አእምሮዋን የሚመግብ  እውቀት ልትሻ ትችላለች? … በልጅነት እውቀትን  ወደመሻት ያልተገፋ ማንነት በጉብዝና ወራት አላዋቂ በመሆን ቢወቀስ ትርጉም አይኖረውም፤ …››

ወይዘሮ መስከረም ሔዋን ሲነገራት የማትሰማ የመጀመሪያዋ ሰው (ልብ በሉ ሴት አላልሁም፤) መሆንዋን እንዴት እስከዛሬ ሳታውቅ ቀረች? ባለመጽሐፉም ይሁን መስከረም የሔዋንን ታሪክ ሳያነሡ መቅረታቸው መሠረታዊ ስሕተት ነው፤ በተጠቀሱት ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አንድም እውነትን የሚመስል ነገር የለም፤ መስከረም ‹‹የሔዋን ዘር›› ከማለት በፊት የሔዋንን ሥራ ቆም ብላ ብታስታውስ የጠቀሰችውን መጽሐፍ እኔ እንደምነቅፈው ትነቅፈው ነበር፤ የሔዋን ታሪክ የሚነግረን የሚከተለውን ነው፡ ‹‹ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፣ ለጥበብም  መልካም እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ፤ የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፤›› ዘፍ. 3

የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ ማለት ‹‹እንደእግዚአብሔር መልካምንና ክፉን የሚያውቁ›› ሆኑ ማለት ነው፤ አሁንም ሔዋን መስከረምና ባለመጽሐፉ እንዳቀለሏት አለመሆንዋን መረዳት ይቻል ነበር፤ እንዲያውም ከዚህ በፊት እንደጻፍሁት ሔዋን የመጀመሪያዋ አብዮተኛና የነጻነት እናት ነች ለማለት ይቻላል! በአንጻሩ አዳም የፍርሃት አባት ነው፤ ‹‹ራቁቴን ስለሆንሁ ፈራሁ፤›› ያለው እሱ ነው! ስለዚህ ወይዘሮ መስከረም ‹‹የሔዋን ዘር›› የምትለውን በድላለችና ይቅርታ መጠየቅ ሳያስፈልጋት አይቀርም!

ሔዋን የተጠቀመችው ውጫዊ ገጽታን የሚያሽሞነሙን ሳይሆን የውስጥን የመንፈስ ኃይል ቆፍሮ በማውጣት ነበር፤ በዚህ የውስጥ ኃይል ለሚጠቀም ከውጭ ግፊት አይጠብቅም።

‹‹እውቀትን ወደመሻት ያልተገፋ ማንነት›› አይወቀስም፤ ትላለች ወይዘሮ መስከረም፤ እየተገፉ የሚገኘው ባርነት ነው፤ እውቀት የሚገኘው በነጻነት ነው፤ መገፋት ከእውቀት ያርቃል እንጂ ወደእውቀት አያስቀርብም፤ የመስከረም ዋናው መልእክት ሰላቢውን እንጂ ሰለባውን አትውቀስ የሚል ነው፣ ወይም የኔ ሀሳብ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ዓይነት ሆኖባታል፤ ለመሆኑ ሰለባ የሚሆን ከሌለ ሰላቢ ይኖራል ወይ? ሰለባ ከመሆን በፊት ሰለባ ላለመሆን መጣር አንዱ የኑሮ ዓላማ አይሆንም ወይ? ከዚህ በፊት ስለጨቋኝና ተጨቋኝ ደጋግሜ ጽፌ ነበር፤ ጭቆና የጨቋኙ ባሕርይ የሚሆነውን ያህል የተጨቋኙም ባሕርይ ይሆናል፤ ለጨቋኙ ጭቆና የሚጠቅመውን ያህል ለተጨቋኙም ጭቆና ይጠቅመዋል፤ ለጨቋኙ ጭቆና የኑሮው መሠረት የሆነውን ያህል ለሚርመሰመሱት የጨቋኝ ሎሌዎች ጭቆና የኑሮ መሠረታቸው ነው፤ እንዲህ እያለ ወርዶ ወርዶ የጭቆና ጠቃሚነት ለሎሌው ሎሌ፣ ለሎሌው ሎሌ ሎሌ … በኢትዮጵያ ምናልባትም የመጨረሻዋ የጭቆና ሰለባ ሚስት ትሆናለች፤ ወይም ልጆች ይሆናሉ! ጨቋኝና ተጨቋኝ የባሕርይ ቁርኝት አላቸው፤ አንዱ ያላንዱ አይኖርም፤ ወይዘሮ መስከረም ይህ እውነት ያልሆነበት ሁኔታ ወይም አጋጣሚ የምታውቀው ካለ ብታጋራን ደስ ይለኛል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤›› የሚለው ኢየሱስ ክርስቶስ የሞቱትንና በቁማቸው የሞቱትን ሲያመሳስላቸው ነው! ለእኔ የሚታየኝ እንዲህ ነው።

መስከረም ብዙ ታላላቅ ሴቶችን ጠቅሳለች፤ በእስዋ ግምት ሁሉም በአባታቸው ወይም በባላቸው እየተገፉ ወደትልቅነት መድረኩ የወጡ ናቸው፤ አዙራ ብታየው የጠቀሰቻቸውን ሴቶች ገፉ የምትላቸው ወንዶች መጀመሪያውኑ በሴቶቹ ተገፍተው እንደነበረስ ሊታሰብ አይገባም? ምናልባት ከጠቀሰቻቸው ሴቶች ይልቅ መስከረም የሄለን ኬለርን ታሪክ ብታስታውስ ኖሮ መገፋትን አታነሣም ነበር፤ ሄለን ኬለር በሕጻንነትዋ ዓይኖችዋም ጆሮዎችዋም ሥራቸውን አቆሙ፤ የሄለን ኬለር የመንፈስ ጥንካሬ ከውስጥዋ አዲስና የተሻሉ ዓይኖችንና ጆሮዎችን እንድታበቅልና እንድትማር፣ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲም የመጀመሪያዋ ሴት ምሩቅ ለመሆን እንድትበቃ አድርጓታል፤ ይህች አስደናቂ ሴት ከመቶ ሠላሳ ዓመታት ግድም በፊት ማኅበረሰቡ በሴቶች ላይ የነበረውን አጥር ሰብራ፣ ዓይኖችዋ ባለማየታቸውና ጆሮዎችዋ ባለመስማታቸው የገጠማትን እክል አሸንፋ ራስዋን ከወንዶች በላይ ለማድረግ በቅታለች።

መገፋትን የሚፈልግ ሁሉ፣ ካልገፉት የማይነቃነቅ ሁሉ፣ ሬትን ሲግቱት ይጣፍጣል እያለ የተቀበለ ሁሉ፣ ዶሮ ማታ፣ ዶሮ ማታ፣ እያሉ አታልለው እንኳን ዶሮ የለም ሹሮ ሲሉት የማይናደድ ሁሉ፣ ምኞቱ ልደግ ልመንደግ እያለ ሲነዘንዘው በአፈና ጭጭ የሚል ሁሉ ለወቀሳ ብቻ አይደለም ለውርደትም ክፍት ነው፤ ስለዚህም ተወቅሶ ከውርደት ከዳነ ወቀሳው ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ማለት ነው፤ ዞሮ ዞሮ የሰው ልጆች ሁሉ — ሴት፣ ወንድ፣ ወጣት ሽማግሌ-አሮጊት፣ ባለሥልጣን ተራ፣ ገበሬ ነጋዴ፣ ወታደር ፖሊስ፣ አስተማሪ አስተዳዳሪ፣ ዳኛ ጠበቃ፣ ሀኪም መሀንዲስ፣ … — የፈለገውን ቢሆን ላለበት ሁኔታ ኃላፊነቱ የራሱና የግሉ ነው፤ ራሱን የሚገነባው ወይም ራሱን የሚንደው ራሱ ነው፤ ሰበብ እየፈለጉ ከዚህ ኃላፊነት መውጣት ቀላል ቢመስልም ተመልሶ እምቦጭ ነው፤ ዳገቱን ለመውጣት የሚመረውን እውነት መቀበል ያሻል።

በመጨረሻም በማናቸውም መንገድ፣ በማናቸውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ ወደቁልቁለት የሚገፉትን ወይም የሚነዱትን ‹‹እምቢ!›› ብሎ ድምጹን ያላሰማ ገደል ገብቶ ሲንፈራፈር ከራሱ በቀር የሚወቅሰው የለም፤ አቅመ-ቢስነት ከውጭ አይመጣም።

አባይን ለመንከባከብ የጎሰኛነት አገዛዝ በዲሞክራሳዊ አገዛዝ መተካት አለበት አክሎግ ቢራራ (ዶር)

$
0
0
Dr. Aklog Birara

Dr. Aklog Birara

“ለምንወደው ለዛሬው ሕዝባችንም ሆነ፤ ከዘመን ወደ ዘመን ለሚከተለው ትውልድም ጭምር፤ የዓባይን የውሃ ሃብት ለሕይወቱ  ደህንነትና ለፍላጎቱ ማርኪያ እንዲውል ማድረግ፤ ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ግምት የምትሰጠውና በቅድሚያ የሚያሳስባት ጉዳይ ነው።  አምላካችን ያበረከተላትን ይህን ሃብቷን ለሕዝባቸው ህይወትና ደህንነት በማዋል እንዲጠቀሙበት ከጎረቤት ወዳጅ አገሮች ጋር  በለጋስነት በጋራ ለመካፈል ዝግጁ ብንሆንም፤ ይህን የውሃ ንብረቷን በቁጥር እየጨመረ ለሚሄደው ሕዝቧና በማደግ ላይ ላለው  ኢኮኖሚ ጥቅም እንዲውል ማድረግ የኢትዮጵያ ተቀዳሚና የተቀደሰ ግዴታዋ ነው።”

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


አዎ ማኅበረ ቅዱሳንን ተጠንቀቁ ! ትልቁ ስጋት እሱ ነውና አዲሱ ተስፋዬ

$
0
0

አዲሱ ተስፋዬ

 መነሻ

snaplvrይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ሰንደቅ ጋዜጣ በሚያዝያ 1/2006 ዓ.ም እትሙ ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያወጣው ቃለ መጠይቅና ሀተታ ነው [i] :: ሶስቱም አስተያየት ሰጭዎች “ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ነው:: ስለዚህም መንግስት ሊያፈርሰው ነው ” የሚለው ወቅታዊ ዜና ምንጩ ከየት እንደሆነ ግልጽ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል :: በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበበ ወርቁ ጉዳዩን “በሬ ወለደ ነው” ብለው ሲያጣጥሉት ፣ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ደግሞ ” የዚህ ወሬ ምንጩ ከየት እንደሆነ አናውቅም” ሲሉ ተመሳሳይ ነገር ተናግረዋል።

ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዴ?

በ 1955 እ. ኤ. አ የተመሰረተውና መቀመጫውን በኔዘርላድና በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው  Open Doors : Serving Persecuted Christians Worldwide [ii] የተሰኘው ግዙፍ ድርጅት 2013 እ. ኤ. ኣ ባወጣው World Watch List ላይ ክርስትያኖችን በማሰቃየት በ63 ነጥብ ኢትዮጵያ 15ተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝና ፣ ለዚህም ስቃይ ዋና ተዋናይ ከሆኑት አካላት አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ጽፎ ፣ ሊስቱንም በመላው ዓለም በትኗል [iii] ። ይሄው በመላው ዓለም በድረ ገጽና በተለያዩ ኤለክትሮኒክ ሚድያዎች (hard and soft copy) የተበተነው ሪፖርት ከመስክ የመረጃ ሰራተኞቼ ፣ ከምሁራንና ከሰላዮቼ አገኘሁ ባለው መረጃ መሰረት አቶ መለስ ዜናዊን ሞት ቀደማቸው እንዲ ማኅበረ ቅዱሳንን እንክትክቱን ሊያወጡት አቅደው እንደነበረ ፣ ቀጣዩም ግዜ ማኅበረ ቅዱሳን የሚገንበት ግዜ እንደሚሆንና ይሄም ለተሐድሶዎች አስቸጋሪ ግዜ ስለሚሆን ከማኅበረ ቅዱሳንን እንዲጠበቁ እንዲህ በማለት ያትታል

“The death of Prime Minister Meles Zenawi, who sought to crush Mahibere

Kidusan, the fanatical group inside EOC, is considered a big blow for the renewal movements. Zenawi was not a supporter of those movements, but his actions against Mahibere Kidusan for political survival were considered by the EOC renewal movements as helpful for less squeeze. His replacement, Haile Mariam Desalegn, does not possess the political and religious background required to confront the fanatical group. Mahibere Kidusan is currently riding high and…. In addition to this, the death of the EOC leader is a big shock for the renewal movements as he was reluctant to take action against them. “ [iv]

ይሄው ዓለማቀፋዊ “የክርስትያኖች እንባ ጠባቂ” ነኝ የሚለው ድርጅት ማኅበረ ቅዱሳን በመንግስት የደህንነት መዋቅር ውስጥ ዘልቆ እንደገባና የመንግስትን ስልጣን በመቆጣጠር በተለይ “የተሐድሶን ቡድን ” ለማጥፋት መነሳቱን በዚህ መልኩ ሪፖርቱ ላይ ገልጾታል

(MK) normally monitor the churches. The fanatic group inside the EOC (Mahibere Kidusan) has to be mentioned here. Particularly Open Door Field experts report that the group is now a growing threat for non-traditional protestant churches and renewal movements with in the EOC. The group ( MK) allegedly has an ambition to influence and control the government policies to restrict the activities of other religions. There are reports that Mahibere Kidusan has managed to infiltrate the government security and administrative apparatus. In the absence of a powerful leader and the death of a relatively moderate patriarch (late leader of EOC) the next move of the group is nervously watched.[v]

እስካሁም “ያዋጣናል ፤ ማኅበሩን ለመምታት ጥሩ መላ ነው”  ብለው ያሴሩት “ማኅበሩ አስራት ይወስዳል፣ ግብር አይከፍልም ፣ ሕንጻ ገንብቷል ወዘተ” የሚል ነበር። ማኅበሩ አስራት እንደማይወስድ ፣ ሂሳቡንም በተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኦዲት በማስደረጉና ከግብርና መሰል ክፍተቶች የጸዳ መሆኑን በማረጋገጡና የውንጀላ ክፍተት በመጥፋቱ ሌላ ዜማ ጀምረዋል። አሁን ደሞ ክሱ “ማኅበሩ መንግስት ደህንነት መዋቅር ውስጥ ገብቶ ሊያፈርሰን ነው” የሚል ሆኗል።ይሄም እንደማያዋጣ ያወቁት እኩያን አሁን ደሞ የመጨረሻ ጥይታቸው ተቀይሯል። ማኅበሩ ፖላቲካ ውስጥ ገብቷል እና መንግስት ወዮልህ አይነት ዝባዝንኬ።

 

እናም  ማኅበረ ቅዱሳንን ተጠንቀቁ !

ይሄው ሪፖርት  ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስትያን ውስጥ ገብተው፣ ቤተ ክርስትያንን እየገዘገዙ ላሉ ራሳቸውን ተሐድሶ ብለው ለሰየሙ ውስጠ ተኩላ ወገኖቹ ያስተላለፈው ጥሪ አንድ ነው :: ” አክራሪው ማኅበረ ቅዱሳንን እየበረታና እየጠነከረ ስለሄደ የሚቀጥሉት አመታት ለተሐድሶዎች እጅግ አስቸጋሪ ነውና … ማኅበረ ቅዱሳንን ነቅታችሁ ጠብቁ:: ከዚህም ስጋት የመነጨ ይመስላል ግብረ አበሮቻቸው ማኅበረ ቅዱሳንን ለማወክ ያለ የሌለ ሃይላቸውን አስተባብረው መንጫጫት ከጀመሩ ሰነባተዋል

Now, in his absence and with the government’s reduced leverage, this fanatic group ( Mahibere Kidusan) appears to be taking charge. The coming months may bring difficult times for the renewal movements inside the EOC…the next move of the group is nervously watched.[vi]

ይሄ ድርጅት መንደርተኞች የፈጠሩት የሰፈር እቁብ አይደለም:: በመላው ዓለም ኔት ወርክ ያለው መሰረተ ሰፊ ድርጅት ነው:: የሚያወጣቸውንም ሪፖርቶች ሚሊዮኖች ያነቡታል:: የኢትዮጵያ “ክርስትያኖችን ዋይታ” በተመለከተ ያወጣው ጽሁፍ ግን ይገርማል:: ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ክርትስትያኖች ተገድለዋል:: ተሳደዋል:: አብያተ ክርስትያናትም ተቃጥለዋል:: ገዳማትም ተደፍረዋል:: ክርስትና ለሚገደው አካል እነዚህ ብዙ የሚያስጽፉ ነበሩ:: ይሄ ሪፖርት ግን ያተኮረው ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ነው:: የማኅበሩም ወንጀሎች ብሎ ሊነገረን የሚፈልገው አንድ ነገር ” ማኅበረ ቅዱሳንን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን ትምህርትና ዶግማ አፍርሰው ወደ ሌላ እምነት ድርጅት ለመቀየር የተነሱ ተሐድሶዎችን አላስቀምጥ አለ:: ለተሐድሶ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆነብን “ የሚል ነው:: እንግዲህ የማኅበሩ ወንጀል ይሄ ነው:: ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር የተናገሩትንም አስተያየት ጠምዝዞ ” ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሞት ቀደማቸው እንጂ ሊያፈራርሱት ነበር” በማለት እውነቱን ሳይሆን ምኞቱን ተርኮልናል:: የሚገርመው ” ማኅበረ ቅዱሳንን በማፍስ ሂደት ጉልህ ሚና አልተጫወቱምና ተተኪው ጠቅላይ ሚኒትር አቶ ኃይለማርያምን “አቅም ያነሳቸው” እስከማለት ደፍሯል:: ፓትርያርክ ጳውሎስንም ” ተሐድሶ ላይ እጃቸውን ማንሳት የማይፈልጉ ለዘብተኛ” ሲል አሞግሷቸዋል:: እንደዚህ ድርጅት ዘገባ ቤተ ክርስትያንን ለመሰርሰር ሰርገው የገቡ መናፍቃን ሰማዕታት ሲሆኑ፣ የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም በሚል ለቤተክርስትያን ትውፊትና እምነት መጠበቅ የሚደክመውን ማኅበረ ቅዱሳንን ደግሞ አሸባሪ ፣አክራሪ የሚል የስም ጥላሸት እንዲቀባ ተደርጓል:: እንግዲህ የማህበረ ቅዱሳን ወንጀሉ ይሄ ነው::

 

 

ማኅበረ ቅዱሳን ወሳኝ ሃይል ሆኗል

 

ከቅርብ ግዜ ወዲህ ማኅበረ ቅዱሳንን በአክራሪነትና በነውጠኛነት የመፈረጁ አባዜ በአካዳሚክ ጽሁፎች ላይም እየታየ ነው :: ለምሳሌ የዶክተር ጥበበ እሸቴን የዶክትሬት ማሟያ ጽሁፍ ማንሳት ይቻላል:: ዶክተር ጥበበ በ 1960ዎቹ ውስጥ በነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ተሳትፎ የበራቸው እና በኋላ ደግሞ የፕሮቴስታንቱን ዓለም በመቀላቀል በዛው ድርጅት ውስጥ የአስተዳደር ቦታ እስከመያዝ የደረሱ ሰው ናቸው:: እኚህ ሰው 2009 ላይ The Evangelical Movement in Ethiopia : Resistance and Resilience በሚል ርዕስ የጻፉትን የዶክትሬት ሟሟያ ጽሁፋቸውን አሳትመዋል[vii]:: በዚህ አወዛጋቢ መጽሐፍ ዶክተር ጥበበ ማህበረ ቅዱሳንን militant, aggressive, anti evangelical በማለት ጥላሸት በመቀባት አንባቢን የሚያደናግር አንቀጽ አስፍረዋል:: ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ ነው ነገሩ::

 

The emergence of a highly aggressive and more militant movement that arose with in the Orthodox Church under the name of Mahibere Kidusan in recent years should be seen in multidiscrusive context…     (Mahibere Kidusan) as a nationalistic and strongly anti-evangelical movement enjoying the backing of some orthodox conservative intellectuals and elements of the urban youth , the new religious strain is becoming a significant force [viii]

 

ዶክተር ጥበበ ለምን ዓላማና በምን መረጃ militant ( ነውጠኛ) anti evangelical (ጸረ ወንጌል) እሰከማለት እንደደረሱ ባላውቅም እሳቸውም ግን ገና በ2009 ማኅበረ ቅዱሳን significant force ሆኖዋልና አስቡበት ሲሉ አስገንዝበው ነበር:: ምንም እንኳን ዶክተር ጥበበ እሸቴ በዚህ ጥናታዊ ጽሁፋቸው ላይ በርካታ አመኔታ የሚጎድላቸው ነጥቦችን ቢያስነብቡንም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ፣ ቤተክርትስያኗን ወደ ሌላ እምነት ድርጅት ለመቀየር በስውር የሚሰሩ የተጠናከሩ ህቡዕ ቡድኖች እንዳሉና ተጽኗቸውም በሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ በየማህበራቱ ፣ በየአጥቢያ ቤተክርትያንቱ እንዲሁም ገዳማቱን ሳይቀር መታየት መጀመሩን የውስጥ አዋቂ በሚመስል ሁኔታ እንዲህ በማለት ገልጸውታል::

 

Today, many underground movements are operating with in Ethiopian Orthodox Church, some with evangelical and others with Pentecostal convictions. ..Some of these movements exemplify attempts at religious innovation, though it is hard to plot their trajectories because of their hidden nature and complex character. Such developments are affecting wide ranging areas of the established structure of the Orthodox institutions, such as Sunday Schools, the mahibers, the monastic centers, and even the local churches in major cities. [ix]

 

የፕሮቴስታንቱ ዓለም ፓስተሮችም ከ34,000 የማያንሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርትያናት ውስጥ ገብተው ቤተ ክርስትያኗን ወደ ፕሮቴስታንቱ ዓለም ለመገልበጥ አባላትን እየመለመሉና ስልጠና እየሰጡ እንደሆነ በጀብዱ መልክ በአደባባይ እየተናገሩ ነው::

The evangelist is hopeful that the seeds of revival are being planted and nurtured in the estimated 34,000 Orthodox churches in Ethiopia and abroad. So far more than 600 people have successfully completed the two-week course.[x]

 

አልፎ ተርፎም ማኅበረ ቅዱሳንን ባይኖር የተሐድሶ እንቅስቃሴ ቤተክርትያኗን ሙሉ ለሙሉ ይቆጣጣራት እንደነበር በይፋ እየተጻፉ ነው:: ማኅበረ ቅዱሳንም ላይ ጥርሳቸውን የሚያገጫግጩት ለዚህ እኩይ ዓላማቸው እንቅፋት ስለሆነባቸው ነው ።ለዚህም ዓላማቸው ስኬት ማኅበረ ቅዱሳንን ሊያፈስርና ሊበትን የሚችል ዘርፈ ብዙ ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ:: ቤተ ክህነቱ ውስጥ በገንዘብ የገዟቸው ቅጥረኞቻቸው ማኅበሩን ለማፍረስ የቻሉትን ያህል ሄደዋል::

 

ግን ከኪሳራ ውጭ ማኅበሩ ላይ ምንም ያመጣው ጉዳት አለመኖሩ ያሳሰባቸው አካላት አሁን ደግሞ ቤተ ክህነቱ ውስጥ ሰግስገው ላስገቧቸው ቅጥረኞቻቸውና በገንዘብ ለገዟቸው ይሁዳዎች የመጨረሻ ትንቅንቅ እንዲያደርጉ እንደላኳቸው በየቀኑ የምናየው ሃቅ እየሆነ ነው::

 

ዝነኛው ጋዜጠኛ ተመስገን ዘውዴ የማኅበረ ቅዱሳን የመጨረሻዎቹ ቀናት በሚል ርዕስ በቅርቡ ባስነበበን ግሩም ጽሁፍ ላይም የማኅበሩ ተቃዋሚዎች ቤተ ክህነት ውስጥ አዳራሽ ተፈቅዶላቸው ማድረጋቸውንና የአቋም መግለጫ እስከማውጣት መድረሳቸውን እንዲህ ሲል ነበር ያስነበበን

 

ለመጽሔቱ ዝግጅት ክፍል የደረሰው በድምፅ የተቀረፀ የውይይቱ ሙሉ ክፍል እንደሚያስረዳው፣ ተሰብሳቢዎቹ ማኅበሩን በተመለከተ ያወጡት የአቋም መግለጫ÷ የማኅበሩና የዋነኛ መሥራቾችና አባላት የባንክ አካውንት፣ ቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች ጨምሮ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች፣ ት/ቤቶች፣ የንግድ ተቋማት፣ የአክስዮን ተቋማት፣ የንዋያተ ቅድሳት ማምረቻዎችና ማከፋፈያዎች፣ ከቀረጥ ነጻ የገቡና በመግባት ላይ ያሉ ዕቃዎች በሚመለከታቸው የመንግሥት መሥ/ቤቶች እንዲታገዱ በቅ/ሲኖዶስ አማካይነት ደብዳቤ እንዲጻፍ፤ ከምእመናን በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ የሚቀበለው ዓሥራት እየፈረጠመበት ስለኾነ እንዳይቀበል ይከልከል፤ የግቢ ጉባኤያት(የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) እርሱ በሚቀርፀው ትምህርት እንዳይወሰዱብን በደንብ መሥራት፤ ተጠሪነቱ ከዋና ሥራ አስኪያጅነቱ ሥር ወጥቶ በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ውስጥ አንድ ንኡስ ክፍል ይኹን የሚሉና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡[xi]

 

ይሄን የአቋም መግለጫ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የተሰብሳቢዎቹ አንዱና ዋና እቅድ የግቢ ጉባኤያት(የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) እርሱ በሚቀርፀው ትምህርት እንዳይወሰዱብን በደንብ መሥራት፤የሚል ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ለየግቢ ጉባ ኤያት ቀርጾ ያዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት እና መመርያ መጻሕፍቱ በሙሉ ይታወቃሉ። ቢጋሮቹም ፣ መጻሕፍቱም በሊቃውንቱ ታይተው የተመረመሩና የታረሙ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ናቸው። እርሱ በሚቀርጸው ትምህርት እንዳይወሰዱብን ማለት ትርጉሙ ምንድነው? ይሄ እንግዲህ እየተካሄደ ያለው ቤተ ክህነት አፍንጫ ና ብብት ስር ነው።

 

ማኅበረ ቅዱሳን የኔ ነው ! ያንተ ነው!  ያንቺ ነው! የኛ ነው!

 

ምንም እንኳን ቤተ ክርስትያን ከፈተና ተለይታ ባታውቅም ቅድስት ቤተ ክርስትያናችን አሳሳቢ ፈተና ውስጥ ወድቃለች። ከአውሮፓና አሜሪካ ድረስ ሳይቀር ድርጎ የሚታሰብላቸው ሆድ አምላኪዎች የቤተ ክርስትያንን አባቶችን ክብር በማጉደፍ፣ የቤተ ክርስትያንን ትውፊትና ትምህርት በመገዝገዝ፣ ቤተ ክርስትያንን ወደ መናፍቃኑ ጎራ ለማስረከብ ሌት ተቀን እየሰሩ ይገኛሉ። በተለይም ራሳቸውን ተሐድሶ በሚል የሰየሙ ቡድኖች ቤተ ክርስትያኗን ለማፍረስ ቆርጠው ተነስተዋል። ለዚሁ እኩይ ዓላማቸው መሳካት ማኅበረ ቅዱሳን እንቅፋት ስለሆነባቸው ከምሁር እስከ ተርታው አባል ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዘመቻ ከፍተዋል። የማኅበሩን ስም ለማጥፋት በርካታ ብሎጎች ሥራ ላይ ውለዋል። ብዙ ብር ወጥቶባቸው መጻሕፍት ታትመዋል።ህሊናቸውንና ሃይማኖታቸውን በብር በሸጡ ይሁዳ የቤተ ክህነት ሰዎችም ማኅበሩን ለመምታት ዘርፈ ብዙ ሙከራ ተደርጓል። አንዱም ማኅበሩን ለማፍረስ አቅም ባይኖረውም።አረቦቹ እንደሚተርቱት ውሾቹ ይጮሃሉ።ግመሉ ግን ይጓዛል።

 

እኛስ ለሃይማኖታችን የሚገደን ኦርቶክሳውያንስ ምን እያደረግን ነው? ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስትያን እጅ ነው[xii]። የቤተ ክርስትያን አካል ነው።ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር የሚደረግ ትግል ሁሉ ቤተ ክርስትያንን ለመጣል የሚደረግ ሰይጣናዊ ትግል ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚታወጅ ጦርነት በሙሉ ቤተ ክርትያን ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው ።ማኀበረ ቅዱሳንንም ኢላማ ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ዋነኛ ምክንያት፣ ይሄ ትውልድ ስለ ኦርቶክሳዊ ማንነቱ የላቀ ግንዛቤ እንዲኖረው ማስተማሩና ከቤተ ክርስትያን ጎን መቆሙ ነው ። የማኅበረ ቅዱሳን ጥንካሬ የቤተ ክርስትያን ጥንካሬ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚቀሰሩ ጣቶች በሙሉ ቤተ ክርስትያን ላይ የሚቀሰሩ ጣቶች ናቸው ።ስለዚህ ማኅበሩ ላይ የሚደረጉ ትንኮሳዎች ቤተ ክርስትያን ላይ እይሚደረጉ ትንኮሳዎች ናቸውና እያንዳንዳችን ኦርቶዶክሳውያን ቆመን ማሰብ አለብን አለብን።

 

ማኅበረ ቅዱሳን ይፈርሳል እንዴ ?

 

“ማኅበረ ቅዱሳን ይፈርሳል” ብለው ለሚቃዡ ሰዎችም እውነታውን አውቀውት ከወዲሁ እርማቸውን እንዲያወጡ ትንሽ ልበል። ዛሬ እኮ የትኛውም ዓለም ብትሄድ የማኅበረ ቅዱሳን ሴል (Cell)  የሌለበት ክፍለ ዓለም የለም።ኢትዮጵያ ውስጥ እያንዳንዱ ቀበሌ ድረስ ” እምቢ ለቤተክርስትያኔ” የሚሉ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት አሉልህ።ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ እያንዳንዱ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ ለቤተ ክርስትያን ሁለንተናዊ እድገት ነቅተው የሚሰሩ የማኅበሩ አባላት አሉ ። የማኅበሩ መመርያ እንደሚያዘው እያንዳንዱ የማኅበር አባል የሰንበት ትምህርት ቤት አባል ነው። የትኛውም ቤተ ክርስትያን ሰበካ ጉባኤ ውስጥ ቤ ክርስትያንን ባላቸው አቅም ለማገልገል ቁርጥ አቋም ያላቸው የማኅበሩ አባላት አሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የትኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅት ውስጥ የማኅበሩ አባል የሌለበት የለም ። እያንዳንዱ መስሪያ ቤት ያለ ተቀጣሪ የማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖና አሻራ የሌለበት የለም ። የማኅበሩ ቋሚ አባል ባይሆን እንኳን የማኅበሩ ግን ሙሉ ደጋፊ ነው ።ወይም በዘመኑ ቋንቋ ስትፍቀው ማኅበረ ቅዱሳናዊ ነውማኅበረ ቅዱሳን በየቀኑ ለቤተክርትስያንን ጉዳይ የሚንገበገብ ፣  የሚያስብ ትውልድ ፈጥሯል።ይህ ትውልድ ማኅበረ ቅዱሳናዊ ነው። ቢመረንም ፤ቢዋጠንም።

 

ከኢትዮጵያም ውጭ የማኅበሩ ቅርንጫፍ የሌለበት ቦታ የለም። በተለይ በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ። ዛሬ ዛሬ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ የሚደረጉ የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤያት ከሀገር ውስጡ የማይተናነሱ እየሆኑ ነው። በዓረቡ ዓለምና በዕሥያ ያለው የማኅበሩ እድገትም ቀላል አይደለም። የትኛውም ክፍለ ዓለም ላይ የቤተ ክርስትያን ጉዳይ የሚገደው በቤተ ክርስትያን ጉዳይ ዝም የማይል የማኅበረ ቅዱሳን ሕዋስ አለ። ባጭሩ ማኅበሩ global ሆኗል። ወይ ደግሞ ነፋስ ሆኗል።አትይዘው አትጨብጠው። ነፋስ የማይነፍስበት ቦታ እንደሌለ ሁሉ ማኅበሩ የሌለበት ቦታ የለም።ማን ነበር ማኅበረ ቅዱሳን የሃሳብ መስመር ( Imaginary line) ሆኗል ያለው። ማኅበረ ቅዱሳንን ልዝጋው ብሎ የሚያስብ አላዊ እንኳን ቢመጣ አዲስ አበባና በየዞኑ ያለውን ጽፈት ቤት ሊዘጋ ይችል ይሆናል።ማኅበረ ቅዱሳንን ማጥፋት አይችልም::  ዋናው የማኅበሩ ሥራ የሚሰራው በያንዳንዷ ደብር ፣ በየሰበካ ጉባኤው ፣ በየሰንበት ትቤቱ ፣ በየ አባላቱ ቤት ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚያመጣው ለውጥ insignificant ነው። ሰሜን አሜሪካ ያለው ማዕከል ብቻውን አዲስ አበባ ያለው ማስተባበርያ የሚሰራውን ሥራ የምስራት አቅም አለው። እድሜ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዛሬ አሜሪካ ሆነህ በያንዳንዱ ቀበሌ ፣በያንዳንዱ አጥቢያ ያለውን አባል ለቤተ ክርስትያን ሥራ ማስተባበር ከባድ አይደለም። It is a click or one call away. ማኅበሩ በአንድ የጸሎት ቋንቋ የሚናገሩ ፣ በአንድ የእምነት ልብ የሚመሩ ፤ እንደ አንድ ቃል ተናገሪ እንደ አንድ ልብ መስካሪ የሆኑ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኦርቶክሳውያን ስብስብ ነውና እንዲህ በቀላሉ እንደ አንቧይ ካብ አትንደውም።ብትሰረስረውም መሰረቱ ጠንካራ አለት ነውና አታፈርሰውም። ከሁሉም በላይ የማኅበሩ ጠባቂ እመብርሃን ናትና ገና ይሄ ማኅበር ያድጋል። ይሰፋል።

ማስገንዘቢያ

ይህ ጽሁፍ የኔ የራሴ የግል ምልከታዬ እንጂ ሌላ ማንንም አይወክልም:: አስተያየት ሊሰጡኝ ከወደዱ በዚህ ኢ ሜይል ይላኩልኝ

redawube@gmail.com

 

 

 



[i] http://www.sendeknewspaper.com/images/Sendek-Pics/448/448.pdf

[iii] http://www.opendoors.no/vedlegg/1988472/WWL2013-FullReport-en

[v]  ibid

 

[vi] Ibid

[vii]  Eshete,Tibebe  The Evangelical Movement in Ethiopia : Resistance and Resilience 2009 Bayor University press

[viii]  Ibid ( page 313)

[ix] Ibid ( page 61)

[x] http://www.charismamag.com/blogs/189-j15/features/africa/530-revival-and-persecution-in-ethiopia

[xi] ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፱፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.

የቀደመ ውን ፍቅርህን ትተሃልና የምነቅፍብህ ነገር አለኝ።

$
0
0

ይድረስ በሚኒሶታ ደብረ ሰላም መድሐኒአለም ቤተ ክርስቲያን ለምትገኙ ክርስቲያን ወንድሞቼ እና እህቶቼ፤

እንኳን ለሆሳእና በዓል በሰላም አደረሳችሁ። 

debereselam-medhanialemነበር ለካ እንዲህ ቅርብ ነበር እንዲሉ፤ ባለፉት ዓመታት ደብረ ሰላም መድሐኒአለም በሰሜን አሜሪካ ካሉ አድባራት በታላቅነቱ ከሚጠቀሱት ውስጥ ነበር ብል ማጋነን አይሆንብኝም። እኛን ምእመናኑን ሆነ እንግዶችን እጅጉን ባስደነቀ ግሩም አገልግሎት ኢትዮጵያ  ያለን እስኪመስለን ድረስ በታላቅ ደስታ አምላካችንን በቅዳሴው፣ በማህሌቱ፣ በመዝሙር ስናመሰግን ኖረናል። በእንግድነታችን ሀገር እግዚሃብሄር ፈቃዱ ሆኖ በቤተ መቅደሱ በስርዓተ ተክሊል ጋብቻ ፈጽመን፤ ልጆቻችንን በ40 ቀን በ80 ቀን አስጠምቀን፣ በስጋ ለተለዩን ጸሎተ ፍትሃት አድርሰን ለዓመታት በሰላም በፍቅር እዚህ ደርሰናል። አንዳችን ለሌላው የክፉ ቀን ደራሽ ሆነን፣ ሀዘናችንን ተጋርተን .….ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ…

 

የክልል እና የፌዴራል ምርጫ 2007! (ግርማ ሞገስ)

$
0
0

Girma Moges

ግርማ ሞገስ

ምርጫ 2005 የአካባቢ (የክልል ቀበሌ፣ ወረዳ እና ከተሞች) እንዲሁም የእራስ ገዞቹ የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ  ምክር ቤቶች ምርጫ ነበር። ብዙ የተወራለት የ33ቱ ተቃዋሚዎች ህብረት ቢያንስ ቢያንስ በአዲስ አበባ  ከተለመደው የተቃዋሚዎች ምርጫ ሽሽት የተሻለ ነገር ሊሰራ ነው ብለን በተስፋ ስንጠብቀው ምርጫው ሲቃረብ  ስለ ህውሃት/ኢህአዴግ አምባገነንነት የማናውቅ ይመስል እንደ አዲስ ዜና በህውሃት/ኢህአዴግ ስር ምርጫው ነፃ  አይሆንም አለን። ወዲያው እራሱን ከምርጫ ማግለሉን ገለጸለን። በዚህ አይነት የአዲስ አበባን ምክር ቤት 138  መቀመጫ እና የከንቲባውን ቦታ ካለምንም ፉክክር ተቃዋሚው በነፃ ለህውሃት/ኢህአዴግ በማስረከቡ ዛሬ ሰላማዊ  ሰልፍ ለማድረግ እውቅና ለማግኘት ሳይቀር በዚህ ምክር ቤት ስር በመጉላላት ላይ ይገኛል።  ….….ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ…….

 

 

 

 

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ፪ (ተመስገን ደሳለኝ )

$
0
0

በዚህ ርዕስ ሥር ባለፈው ሳምንት በይደር ካቆየሁት ተከታይ ጽሑፍ በፊት አንድ እርምት የሚያሻው ጉዳይን በአዲስ መስመር ላስቀድም፡፡

ሬዲዮ ፋና እና “አምደኞቹ”

Temesgen-Desalegn4

ተመስገን ደሳለኝ

በ1988 ዓ.ም በኤፈርት ባለቤትነት ስርጭቱን አሀዱ ያለው “ሬዲዮ ፋና”፣ ከምስረታው አንስቶ ዛሬም ድረስ ልክ እንደ በረሃው ዘመን ሁሉ የሥርዓቱ ቀኝ እጅና የርካሽ ፕሮፓጋንዳው ማስተላለፊያ ቱቦ ሆኖ መዝለቁ ለወዳጅም ለጠላትም የማያከራክር ገሀድ የወጣ ሐቅ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተወሰኑ የግል ሚዲያዎች ላይ የርግማን ዘመቻ የታወጀ ይመስል ለተከታታይ ሳምንታት “ስመ-ጥር” ረጋሚዎችን ጣቢያው ድረስ ጋብዞ ማብጠልጠልና ማውገዙን ቀንደኛ ሥራው አድርጎ ይዞታል፡፡ በርግጥ ይህ ዘመቻ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የፕሬስ ድርጅት በኩል በ“ጥናት” ስም የወጣው ውንጀላ ቅጥያ ሲሆን፣ በቅርቡ ኢቲቪ ሰርቶ እንዳጠናቀቀው የሚነገርለት ዶክመንተሪ ፊልም ደግሞ “ሳልሳዊ” ዘመቻ ሆኖ ለጥቆ የሚቀርብ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ሰሞነኛውን የፋና ዘመቻ ከተለመደው አቀራረብ የተለየ የሚያደርገው ከህወሓት ከበሮ መቺነት መሻገር የተሳነው ዛሚ ሬዲዮ ጣቢያን ከወከለው አቶ ዘሪሁን ተሾመ በተጨማሪ፣ የኢዴፓው አቶ ሞሼ ሰሙ እና የ‹‹ፎርቹ››ኑ ጋዜጠኛ ታምራት ወልደጊዮርጊስ በውጋ-ንቀል ስልት የርግማኑ ቡራኬ ሰጪ ሆነው መቅረባቸው ነው፡፡ ‹‹አዲስ አማኝ ከጳጳስ በላይ ልሁን ይላል›› እንዲሉ ሩቅ አላሚው የሕዳሴው ግድብ የሕዝብ ተሳትፎ አስተባባሪ ም/ቤት ምክትል ዳይሬክተር የሆነው ዛዲግ አብረሃም ሆነ ሚኒስትር ዴኤታው ሽመልስ ከማል የረከሰውን የአፈና መንፈስ ‹‹ለማቀደስ›› በቁርጠኝነት መሰለፋቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው፡፡ በርግጥ እነዚህ ሰዎች በቀጥታ ከስርዓቱ ህብስት ተቋዳሽ በመሆናቸው በዚህ ደረጃ ‹‹ማሸብሸባቸው›› ብዙም አያስገርምም፤ አስገራሚው ነገር ታምራት ወልደጊዮርጊስ ‹‹እንቁ›› እና ‹‹ፋክት›› መጽሔቶችን በአንድ ሰው የሚዘጋጁ አስመስሎ ከማቅረብም አልፎ፣ ማሕበረ ቅዱሳን የገጠመውን የመበተን አደጋን በተመለከተ የወጣውን ዘገባ እስከማውገዝ የደረሰበት ጽንፍ ነው፡፡

በወቅቱ ዛዲግ አብረሃ ሚዲያዎቹ እንዲደመሰሱ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ፣ ታምራትም የማሕበረ ቅዱሳን አባላት ተቋማቸውን ከመንግስታዊ አፈና መከላከል እንዳለባቸው የምትመክረውን የ‹‹ፋክት›› ዘገባ ቃል በቃል ጠቅሶ ሲያበቃ ‹‹ቋቅ እያለኝም ቢሆን ከዛዲግ አብረሃ ጋር የምስማማበት ጉዳይ ይህ ነው›› በማለት ከፕሬስ አፈናው ጎን መቆሙን አስረግጦ ተናግሯል፡፡ በአናቱም መጽሔቶቹ ‹‹አብዛኛው ህዝብ የሚፈልገውን መርጠው የሚዘግቡ ናቸው›› ያለበት አውድ ነቀፋ ይሁን ምስጋና ግልፅ ባይሆንም፣ ቢያንስ አምባገነኑን በረከት ስምኦን እና ጋሻ-ጃግሬዎቹን ከማስደሰት፤ ብዙሃኑን ግፉአን ማገልገል የተሻለ ብቻ ሳይሆን የተቀደሰ ተግባር ስለመሆኑ በረከትም በልበ-ሙሉነት እሰጥ-እገባ ሙግት የማይሞክርበት ነጭ እውነት እንደሆነ ታምራት ቢያስተውለው የተሻለ ይመስለኛል፡፡ ግና፣ ሐቁ ይህ ቢሆንም ወንድም ታምራት ራሱ ብቻ ሙያውን አክብሮ የሚሰራ ጋዜጠኛ፤ ሌላውን ደግሞ ኃላፊነት የማይሰማው ከማድረጉም በዘለለ፣ እነዚህን ሚዲያዎች ከአርበኝነት ጋር አዳብሎ ለማውገዝ መሞከሩ የተኮረኮርኩ ያህል ሳልወድ በግድ ያሳቀኝ ጉዳይ ሆኖብኛል፡፡ ምክንያቱም በእኔ እምነት በኢትዮጵያችን ላለፉት ሁለት ዓስርታት ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ለሕግ የማይገዛ እና በሙስና የተጨማለቀ ሥርዓት ከመሆኑ አኳያ በጋዜጠኝነትም ሆነ በየትኛውም ሙያ ለሚንፀባረቅ አርበኝነት የተሻለው ብያኔ፣ ሀገርን ከፍርሰት መታደግ ማለት ነውና፡፡

ደግሞም በዚህች ሀገር ዝግመታዊ-ሞት ፊት ላይ ቆሞ የኮሪደር ሐሜቶችን ከመዘገብ በእጅጉ ለቆና ረቆ በመሻገር የውደቀታችን ምክንያት የሆነውን አገዛዝ በሕዝባዊ እምቢተኝነት ማስወገድ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ብዙ ጊዜ በእንዲህ አይነት ውይይቶች ላይ ሚዛናዊ ለመሆን ይሞክር የነበረው ታምራት (ለዚያኛውም አቋሙ በግሌ አመስግኘው አውቃለሁ)፣ ማሕበረ ቅዱሳንን በተመለከተ የወጡ ዘገባዎችን ባወገዘበት አዛው ሬዲዮ ጣቢያ ስቱዲዮ ውስጥ ተቀምጦ፣ ሽመልስ ከማል አንድ እንኳ የታሰረም የተሰደደም ጋዜጠኛ እንደሌለ ጠቅሶ አይኑን በጨው አጥቦ ሲከራከር ትንፍሽ አለማለቱ የቀራኒዮ መንገድ እና የንግድ ስራ ፍፁም የማይተዋወቁ ሆድና ጀርባ መሆናቸውን የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡

በነገራችን ላይ በዚህ ውይይት የአደባባይ ምሁሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እና የኢትዮ-ምህዳሩ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ መሳተፋቸው ከሞላ ጎደል ከዘመቻው ጀርባ ያለውን ኢህአዴጋዊ ሴራ አጋልጦታል ብዬ አስባለሁና ባርኔጣዬን ከፍ አድርጌ አክብሮቴን ልገልፅላቸው እወዳለሁ፡፡ በተለይ ጉምቱ የፍልስፍና መምህር ዶ/ር ዳኛቸው፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቶችን ብቻ ሳይሆን የሥርዓቱን ሃሳብ አልባነት ለመሞገት ለሚያደርገው አበርክቶ በድጋሚ አመሰግነዋለሁ፡፡…ከዚህ ሁሉ ሰበር ሐተታ በኋላ ወደ ክፍል ሁለቱ ዋናው አጀንዳችን ዘልቀን፣ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ለፍትሕ መበላሸት የዳኝነት ሥርዓቱ ብቻ ሳይሆን ፖሊስ እና ዐቃቤ ሕግም የአንበሳውን ድርሻ ስለመውሰዳቸው ለማመልከት እሞክራለሁ፡፡
ፖሊስ ሲባል…

…የተወሰኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት ዝሆን አድነው እንዲያመጡ በአለቃቸው ይታዘዛሉ፡፡ ከሰዓታት በኋላም ፖሊሶቹ ግዳያቸውን አምጥተው ለአለቃቸው ያስረክባሉ፡፡ ይሁንና አለቅየው ግዳያቸውን ባየ ጊዜ ባለማመን ዓይኖቹ ፈጥጠው ሊወድቁ ደረሱ፤ ለምን ቢሉ፣እሱ ያዘዛቸው ዝሆን፣ እነርሱ ያመጡት ግን ሁለት ጥርሱ የወለቀ፣ አንድ ቀንዱ የተሰበረ፣ አንድ አይኑ የጠፋ፣ ምላሱ የተቆረጠ… ብቻ ምን አለፋችሁ በድብደባ ብዛት ሊሞት የተቃረበ ፍየል ነበርና፡፡ እናም በቁጣ፡-
‹‹ዝሆን አይደል ወይ አምጡ ያልኳችሁ?›› ሲል ያፈጥባቸዋል፤
‹‹ጌታዬ፣ ዝሆን ነኝ ብሎ እኮ አምኗል!›› በማለት ቆፍጣና ፖሊሶቹም በሕብረት መለሱለት፡፡

…ይህችን ቀልድ ለዚህ ንዑስ-ርዕስ መግቢያ ያደረኩት፣ በነባሩ ባሕል እንዲህ ያሉ ጉዳዮች በቀልድ፣ በግጥም፣ በምሳሌዊ አባባል… መገለፃቸው የተለመደ ከመሆኑ አኳያ ስለሀገራችን የፖሊስ አባላት ስንነጋገር ከቀልዷ ጀርባ መራራ እውነት ማድፈጡን አምነን እንድንቀበል ገፊ-ምክንያቶች በመኖራቸው ነው፡፡

እንደሚታወሰው በየትም ሀገር የተፈፀመ ወንጀል ከዐቃቤ ሕግም ሆነ ከፍርድ ቤት በፊት በፖሊስ የምርመራ ሂደት ውስጥ ማለፉ የግድ ነው፡፡ የዘርፉ ምሁራን ‹‹የፖሊስ ምርመራ ሳይንስ ነው›› እንዲሉ ሙያው ክህሎት የሚጠይቅ መሆኑ አይካድም፡፡ ይሁንና ተጨባጩ እውነታ የሚነግረን የ83ቱን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በዘርፉ እንዲሰማሩ የተደረጉት አብዛኞቹ መርማሪዎች ድርጅቱን ለቡሕተ-ሥልጣን ያበቁ ታጋዮች መሆናቸውን ነው፡፡ በርግጥም በረባውም ባልረባውም ወንጀል ተጠርጥሮ እጃቸው የገባውን ሁሉ አፈር-ድሜ በማስጋጥ የ‹‹ሚመረምሩበት›› መንገድ ኩነቱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ ይህ ሁናቴም ይመስለኛል የፖሊስን ሙያ ከሳይንሳዊ ጥበብ ወደ አሳረ-ፍዳ ማሳያ አውርዶ የተጠላ ያደረገው፡፡ ለዚህም ኩነና በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ የሩቁን ትተን የቅርቡን እንኳ ብንመለከት የህዝበ-ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ችሎት ላይ ቀርበው በማዕከላዊ ምርመራ እስር ቤት መርማሪ ፖሊሶቹ ሰብዓዊ መብቶቻቸው ተገርስሶ ሲያበቃ ምን ያህል አካላዊና መንፈሳዊ ስቅየት እንደደረሰባቸው ከተናገሩት መሀል የሚከተሉትን በዋናነት እናገኛለን፡-

‹መርማሪ ፖሊሶቹ እንቅልፍ ከልክለው የተዳከመ አካልን ልብስ አስወልቆ እርቃን በማስቀረት መግረፍ፣ የዘር ፍሬ ብልት ላይ በውሃ የተሞላ ጠርሙስ ማንጠልጠል፣ በኤሌክትሪክ ገመድ የውስጥ እግርን መግረፍ፣ ጢምን በአሰቃቂ ሁኔታ መንጨት፣ እጅና እግርን ሰብዓዊነት በጎደለው መልኩ ለረጅም ሰዓታት ማሰር፣ ጭንቅላትን በቆሸሸ ውሃ ውስጥ መንከር፣ ከ24 ሰዓታት በላይ ቀጥ ብሎ እንዲቆሙ ማስገደድ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ሾክ ማደረግ እና የመሳሰሉት፡፡› በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማትም በተደጋጋሚ ጊዜ በተለይም ከደርግ ስርዓት ጀምሮ ዋነኛ ማሰቃያ በሆነው ማዕከላዊ የምርመራ ጣቢያ የሚፈፀመውን ተግባር በሪፖርት መልክ ማውጣታቸው ይታወሳል፡፡ ከወራት በፊት ሂዩማን ራይትስ ዎች ይህንን የስቃይ ጣቢያ አስመልክቶ ‹‹They want a confession: Torture and Ill-treatment in Ethiopia’s Makelawi Police Station›› በሚል ርዕስ ባሰራጨው ሪፖርት በጣቢያው የሚፈፀመውን ግፍ ከመግለፁም በተጨማሪ፣ ታሳሪዎች እንዴት ባለ ሁኔታ ‹‹የእምነት ቃል››እንደሚሰጡ አመላክቷል፡፡ ለማሳሌም አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ፤ ነገር ግን በጣቢያው ታስሮ የነበረ ሰው ገጠመኝን ከሪፖርቱ እንደሚከተለው ልጥቀሰው፡-

‹‹ወደ ጣቢያው የገባሁ ቀን ኢ-ሜይል አድራሻዬን ከነምስጢር ቁልፉ እንድሰጣቸው ጠየቁኝ፤ ሰጠኋቸው፡፡ በውስጡም ምንም አይነት የፖለቲካ አንድምታ ያለው መልዕክት አልነበረም፡፡ ይሁንና ከሶስት ቀን በኋላ በዛው አድራሻዬ ‹ከኦነግ የተላከ መልዕክት ተግኝቷል› ብለው ጠየቁኝ፡፡ ሆኖም ነገሩን እንደማላውቅ እያወቁ ‹ለእኔ የተላከ መልዕክት ነው› ብለህ ፈርም ሲሉ አዘዙኝ፡፡ እኔም ከታሰርኩ በኋላ የተገኘ በመሆኑ አልፈርምም አልኩ፡፡ በዚህም የተነሳ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመውብኛል፡፡››

በርግጥም የሀገሪቱን የወንጀል ምርመራ ስራን ተነቃፊና ተወጋዥ ያደረገው በእውቀት ማነስ፣ በስቅየት (በቶርቸር) እና በሙስና የተተበተበ መሆኑ ብቻ አይደለም፡፡ በአደረጃጀቱም ነው፤ ለምሳሌ ከፌዴራልና ክልል ፖሊስ በተጨማሪ ግምሩክ የራሱ እስር ቤት፣ የራሱ መርማሪና ዐቃቢ-ሕግያን አሉት፡፡ ፀረ-ሙስናም እንዲሁ የጠረጠረውን ሁሉ አስሮ ይመረምራል፤ ይከስሳልም፡፡ አንዳንድ ምንጮቼ እንዳቀበሉኝ መረጃ ከሆነ ደግሞ በሽብር ጉዳይ የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን (ቡድኖችን) ራሱን ችሎ አስሮ የሚመረምር እና የሚከስ ተቋም በቅርቡ በአዋጅ ሊቋቋም ዝግጅቱ ተጠናቅቋል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁሉ መዋቅራዊ ትስስር በሌለው ሁኔታ በፖሊስ ስራ የመሰማራታቸው ምስጢር፣ አንድም ሳይንስ እንጂ አሳር ዕውቀት ባለመጠየቁ፣ ሁለትም ንፁሀንን ከወንጀለኛ ጋር ደባልቆ ለመውቀጥ ስለሚመች፣ ሶስትም ስርዓቱ ተቀናቃኞቹን ለመደፍጠጥ በ‹‹ሕጋዊ አሠራር›› ሽፋን ተጨማሪ ጡንቻ እንዲኖረው ማስቻሉን በማስላት ይመስለኛል፡፡ በዚህ አይነት ምርመራ የተገኙ መረጃዎችም ፍርድ ቤት ቀርበው እንደሕጋዊ ማስረጃ እየተቆጠሩ እስከ ዕድሜ ልክ የእስር ቅጣት ሲያስበይኑ ደጋግመን ተመልክተናል፡፡

ይህም ሰፊው ሕዝብ በፍርሃት እየተርበደበደ ሰጥ-ለጥ ብሎ እንዲገዛ፤ አሊያም እንደ ጥንቸሊቷ አገር ጥሎ እንዲጠፋ ለማድረግ ያለው ጉልበት በግልፅ ተተግብሮ የታየ የሥርዓቱ የዕለት ተዕለት ምግባር ነውና ከዚህ በላይ ትንታኔ አያሻውም፡፡ ከዚህ ይልቅ የጥንቸሏ አፈ-ታሪክ ተብሎ የሚነገረው ነባራዊ እውነታውን በሚገባ ያንፀባርቃልና እንደወረደ ልጥቀሰው፡-…ከለታት አንድ ቀን አንዲት ጥንቸል ከመጣባት የመዓት ናዳ ማምለጥ የምትችለው ቀዬዋን ጥላ ስትሰደድ እንደሆነ ብቻ በማመኗ ልቧ እስኪፈነዳ ድረስ ጋራ-ሸንተረሩን እያቆራረጠች ስትሮጥ ድንገት ከሀገሪቱ ድንበር አጠገብ ከሚኖር አንድ ግድንግድ ጦጣ ጋር ፊት-ለፊት ተፋጠጠች፣ በድካም ዝላም ቁና ቁና እየተነፈሰች ‹‹ይህ ጦጣ ፖሊስ ይሆን እንዴ?›› ብላ እየተጠራጠረች ማምለጫ ዘዴ ስታውጠነጥን፣አያ ጦጣ፡- ‹‹ወይዘሪት ጥንቸል፣ ለመሆኑ ምን የከበደ ጉዳይ ቢገጥምሽ ነው እንዲህ ልብሽ እስኪፈርስ ድረስ የምትሮጪው?›› ሲል ይጠይቃታል፤‹‹የዝሆን ዘር በሙሉ ከያለበት ተለቅሞ በቁጥጥር ስር እንዲውል አስቸኳይ ትዕዛዝ መውጣቱን እስካሁን አልሰሙም እንዴ?›› ብላ በጥርጣሬ ትክ ብላ እያስተዋለችው ጥያቄውን በጥያቄ ስትመልስለት፣

አያ ጦጣ፣ እጅግ በጣም ከመደነቁም በላይ ግራ ግብት እያለው ‹‹ታዲያ አንቺ ምን አገባሽ፤ ዝሆን አይደለሽ?›› ሲል መልሶ ይጠይቃታል፤ ‹‹ወይ አያ ጦጣ! ዝሆን ባልሆንስ?! አለመሆኔ ተጣርቶ እስክለቀቅ ድረስ ለምን ብዬ ታስሬ ልገረፍ? ደግሞስ በዱላ ብዛት ዝሆን ነኝ ብዬ ያመንኩ እንደሆነ መጨረሻዬ ምን ሊሆን እንደሚችል አስበውታል? ይልቅ እርስዎም አይሞኙ! በጊዜ አብረውኝ ከመዓቱ ዘወር ብለው ቢቆዩ ይሻሎታል፤ ኑ እንሂድ›› ብላ በፍርሃት የተዋጠችው ምስኪኗ ጥንቸል ሩጫዋን ቀጠለች፡፡ …በእኛይቱ የመከራ ምድርም፣ እኛና ኢህአዴግ በዚህ ደረጃ ፍፁም የማንተማመን፣ በጎሪጥ የምንተያይ ሆነን ከቀረን እንደ ዘበት ሃያ ምናምን አመታት ተቆጥረዋል፡፡

ዐቃቢ ሕግ ሲባል….

በዚህ አውድ ሌላው ተጠቃሽ ተቋም፣ ፖሊስ በ‹‹የትም ፍጪው…›› መንገድ ያመጣለትን ‹‹መረጃ›› ሳያላምጥ በመዋጥ ለክስ የሚያበቃው ዐቃቤ ሕግ ሲሆን፣ ለአጠቃላዩ የፍትሕ መዛባትና መጨማለቅም በዕኩል ደረጃ ተጠያቂ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ለአደባባይ ያልበቁ አያሌ የዐቃቢ-ሕግያን ሸፍጦችን ትተን በድህረ ምርጫ 97 የተከሰተውን አለመግባባት ተከትሎ ለእስር ከተዳረጉት የቅንጅት ለአንድነትና ለፍትህ ፓርቲ አመራሮች ጋር የተያያዘውን እንመልከት፡፡ እንደሚታወሰው መጀመሪያ የቀረበባቸው ክስ ‹‹የዘር ማጥፋት›› የሚል የነበረ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ ለረዥም ዓመታት ጥናት ያደረገው አሜሪካዊ ፕ/ር ዶናልድ ሌቨን፣ አቶ መለስን ‹‹ዘር ማጥፋት እኮ ቀልድ አይደለም›› በማለት አጥብቆ ከወቀሰው በኋላ ክሱ ‹‹ሕገ-መንግስቱን በኃይል የመናድ እና ዘር የማጥፋት ሙከራ›› ወደሚል መቀየሩን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ፡፡

የሆነው ሆኖ ጉዳዩ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ዐቃቢ-ሕግያኑ በተከሳሾቹ ላይ በ‹‹ማስረጃ››ነት ካቀረቡት ሰነዶች መካከል የአባላዘር በሽታ የህክምና ምርመራ ወረቀትን ጨምሮ፣ ሀሰተኛ (ፎርጅድ) ደብዳቤዎች እና ከክሱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው የቪዲዮ ፊልሞች እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ‹‹የቃሊቲው መንግስት›› በሚለው መጽሐፉ፣ በጥቅምት 25/1998 ከ‹‹አዲስ አበባ ፖሊ ከፍተኛ ክሊኒክ›› ቢኒያም (የአባቱም ስም ተጠቅሷል) ለተባለ ሰው የአባላዘር ምርመራ አድርጎ የተሰጠው የሕክምና ምስክር ወረቀት ‹‹ሕገ-መንግስቱን በኃይል ለመናድ ሞክረዋል›› በተባሉት የቅንጅት መሪዎች ላይ በ‹‹ማስረጃ››ነት መቅረቡን ከመጥቀሱም በላይ ሰነዱን በገጽ 444 ላይ እንዳለ በማተም ለታሪክ ምስክርነት አብቅቶታል፡፡ መቼም ይህ ሁናቴ አቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያን የወረረው የአሜሪካንን ተልዕኮ ለማስፈፀም ነው? ተብሎ ለቀረበበት ወቀሳ አከል ጥያቄ፣ አሜሪካ የምትሰጠው ዕርዳታ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን መከላከል ላይ ያተኮረ እንደሆነ ከገለፀ በኋላ ‹‹ሶማሊያ ውስጥ ደግሞ በኮንዶም አንዋጋም!›› ብሎ እንደመለሰው አይነት ቧልት አቅልለን እንዳናልፈው የሚያግደን ጉዳዩ ‹‹አንድ ንፁህ በሀሰት ከሚፈረድበት፣ ሺ ወንጀለኞች በነፃ ቢለቀቁ ይመረጣል›› ከሚባልለት ፍትሕ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ነው፡፡

በጥቅሉ ላለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ለእስር የተዳረጉ ንፁሀንም ሆነ በሙስና የተወነጀሉት ላይ እየቀረበ ያለው ክስና ማስረጃዎችን ሥራዬ ብሎ ለመረመረ ሰው፣ የፍትሕ መዛባቱን ደረጃ ፍንትው አድርገው ያሳዩታል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለምሳሌም ከወራት በፊት ‹‹በገቢዎችና ግምሩክ ባለሥልጣን የአ/አ ኤርፖርት ቅ/ጽ/ቤት የመንገደኞች ጓዝ የሥራ ሂደት መሪ›› ባለሥልጣን ላይ የተመሰረተውን ክስ ብናየው እንዲህ የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡-

‹‹ከአሜሪካና ከአውሮፓ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ መንገደኞች ዕቃዎቻቸውን አስፈትሸው ቀረጥና ታክስ ሊከፈልባቸው የሚገቡት ላይ መክፈል እንዳለባቸው ኮንትሮባንድም ከሆነ እንደሚወረሱ እያወቀ ማንነታቸውና ብዛታቸው ያልተለዩ መንገደኞች ዕቃቸው እንዳይፈተሽ ማድረግ፡፡››

መቼም ይህ አይነቱ ክስ በምድራችን የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ማንነታቸውና ብዛታቸው፣ ቀኑና ወሩ ተለይቶ ባልታወቀበት ጊዜ ከመንገደኞች ጋር በመመሳጠር የተሰራ ወንጀል አለ ብሎ ክስ መመስረት ከጥንቆላ በምንም ሊለይ አይችልምና ነው፡፡ ኧረ ለመሆኑስ! የሰዎቹ ቁጥርና ያስገቡት የዕቃ ዓይነት ካልታወቀ ባለሥልጣኑ ‹‹ፈፀመ›› በተባለው ሙስና ሀገሪቱ ከቀረጥ ማግኘት የነበረባትና ያሳጣት ገቢ ምን ያህል ነው? አንድ ብር? አንድ ሺህ? አንድ ሚሊዮን ወይስ አንድ ቢሊዮን? ይሁንና የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ በዚህ መልኩ መቅረቡን በፍርድ ቤት በመቃወማቸው ዐቃቢ ህግ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ይታዘዛል፡፡ ተሻሽሎ የቀረበው ደግሞ ባጭሩ እንዲህ ይጠቀሳል፡-

‹‹ቀኑና ወሩ ተለይቶ ባልታወቀበት በ2002 ዓ.ም ዜግነታቸው አሜሪካዊ የሆነ ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሁለት ሻንጣ የመኪና መለዋወጫ ከተያዘባቸው በኋላ አስለቅቋል፡፡ ግንቦት 24 ቀን 2003 ዓ.ም የሰንሻይን ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ ከዱባይ ሀገር ያስገቡት የመኪና መለዋወጫ ዕቃ እንዲያልፍ ሲያስደርግ በሌላ ባልደረባው ተይዟል፤ ከሐምሌ ወር 2002 ዓ.ም እስከ ነሐሴ ወር 2003 ዓ.ም ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ባለው ጊዜ ከተለያዩ ሀገራት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ መንገደኞች ሠልፍ ይዘው እያለ ከዚህ መለስ ያሉት መንገደኞች ሻንጣቸውን ሳያስፈትሹ፣ ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ እንዲያልፉ ማድረግ፡፡››

እነሆም እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ሀገሪቱ እንዲህ ባሉ የሕግ ባለሙያዎች ስር ወድቃለችና ‹እግዚኦ በሉ›፡፡ እግዚኦታው ግን የሁለቱ እንስቶች ስም እና ያሳለፉት ዕቃ ተመን ባለመታወቁ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም በጽሁፍ በቀረበ ክስ ላይ ከሠልፈኞቹ መካከል ‹‹ከዚህ መለስ ያሉት መንገደኞች…›› ተብሎ ድፍን ያለ ነገር ‹‹መረጃ›› ሆኖ መቅረቡ ነው፡፡ ግና፣ ይህ ምን የሚሉት መረጃ ነው? ያውም ለፍርድ ቤት! እናም ጥያቄያችን እንዲህ እያለ ይቀጥላል፡- የትኛው ሠልፍ ጋ ያሉ መንገደኞች ናቸው በሕገ-ወጥ መንገድ ያለፉት? የቀኙ? የመሀለኛው? የግራው? የሠልፉስ ርዝመት ምን ያህል ነው? የሠልፈኞቹስ ብዛት? አምስት? ሀምሳ ወይስ አምስት መቶ? በርግጥ ክሱ ለአንዱም ጥያቄያችን ምንም አይነት ምላሽ አይሰጥም፡፡ ጉዳዩን ይበልጥ የሚያወሳስበው ደግሞ ይህ ‹ሾላ በድፍን› የሆነ ወንጀል የተፈፀመው ከሐምሌ ወር 2002 ዓ.ም እስከ ነሐሴ ወር 2003 ዓ.ም ድረስ በየቀኑ መሆኑ ነው፡፡ መቼም እነዚህ ሁሉ ጉዶች እውነት ከሆኑ በዚህች ሀገር፣ ማፍያ እንጂ መንግስት አለ ብሎ የሚመሰክር ደፋር ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡

በጥቅሉ የፖሊስም ሆነ የዐቃቢ-ሕግያኑና የዳኞቹ እንዲህ ሙያውን እና ተቋሙን የማራከስ አካሄድ ከአንድ ገፊ-ምክንያት የዘለለ ሌላ መነሾ የምናገኝለት አይመስለኝም፡፡ ይኸውም ሥልጣኑን ለማራዘም ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሰው ኢህአዴግ፣ በዋናነት ዋስትና የሚሆኑትን ፖሊስ፣ ዐቃቢ-ሕግ እና ፍርድ ቤቶችን በታጋዮች እና በካድሬዎች በመሙላት፣ በተለየ የፖለቲካ አቋም ከፊቱ የሚቆሙትን እየጨፈለቀ ለማለፍ አስልቶ የቀመረው በመሆኑ ነው፡፡

ኦርዌላዊ ስርዓት

የዚህን ስርዓት ቅጥ ያጣ አምባገነንነት ማብራራት አድካሚ እየሆነ ነው፡፡ የሚፈርሰው ማህበራዊ ዕሴት፣ የሚናደው ሀገራዊ ማንነት፣ እንደ አምባሻ የሚቆራረሰው መሬት፣ አልፎ ተርፎም እየጠፋ ያለው ትውልድ እና መሰል ጉዳዮችን ጠቃቅሶ፣ የነገይቷ ድህረ-ኢህአዴግ ኢትዮጵያ በገዢው ስብስብ ክፉ መዳፍ ሳቢያ ህልውናዋ ከገደሉ ጠርዝ ላይ ስለመቆሙ ማተት መደጋገም ነውና እንለፈው፡፡ ይህም ሆኖ ግን አገዛዙ በፍትሕ ስርዓቱ በኩል የሚያካሂዳቸው ዘግናኝ ድርጊቶች የመዓቱን ጊዜ ቅርብ የሚያደርጉ መሆናቸውን ማስታወስ (የሚሰማ ባይኖርም) የዜግነት ግዴታ ይመስለኛል፡፡ የአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንትን ጨምሮ፣ ቁጥራቸው የበዛ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት በተደጋጋሚ እንደዘገቡት፣ የዚህች አገር ምስኪን ልጆች በማይታወቁ ድብቅ እስር ቤቶች ጭምር መከራ እየወረደባቸው ነው (እኔ ይህንን ጽሑፍ በማዘጋጅበት፣ እናንተም አሁን በምታነቡበት ሰዓትም ቢሆን ለይተን በማናውቃቸው በርካታ የስቃይ እስር ቤቶች፣ በእልፍ አእላፍ ወገኖቻችን ላይ ግፍ እየተፈፀመ መሆኑን መካድ አይቻልም)፡፡

እነዚህ ማሰቃያ ቦታዎች ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከደቡብ እስከ ሰሜን ባሉት የሀገሪቱ አካባቢዎች ተሰበጣጥረው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ በነዚህ ካምፖችም የሚታጎሩት ዜጐች በዋነኝነት ከገዢው ግንባር የተለየ (የሚቃረን) ፖለቲካዊ አመለካከት ያላቸው ስለመሆኑ የተቋማቱ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡ በተለይም ብረት አንስተው የሚታገሉ ኃይሎች የተነሱባቸው ክልል ተወላጆችን ማሰቃያ ካምፖቹን የሚያደልቡ ‹የተመረጡ› መከረኞች ሆነዋል፡፡ ኢህአዴግ እንጥፍጣፊ ለሕገ-መንግስቱ አክብሮት ቢኖረው፣ የዜጎቹ ወንጀሎች የቱንም ያህል ቢከፉም እንኳ፣ በግልጽ የፍርድ ሂደት ተገቢ የሆነ ተመጣጣኝ ቅጣት ማግኘት በተገባቸው ነበር፡፡

የዚህ አይነቱን የፍትህ ምኩራቡ አስፀያፊ እርክስናን፣ በግላጭ የሚያሳየን ሌላኛው ጭብጥ በኦጋዴናውያኑ ላይ እየወረደ ላለው ግፍ ተጠያቂ ተቋምም ሆነ ባለሥልጣን እስካሁን ድረስ አለመኖሩ ነው፡፡ የስዊድናውያኑን ሁለት ጋዜጠኞች መታሰርና በይቅርታ መፈታት ተከትሎ፤ በክልሉ ያለው ፍርድ ቤት ስለማያውቀው ዝርፊያ፣ እስርና ግድያ በምስልና በድምፅ የተደገፉ ማስረጃዎች ከጥቂት ወራት ወዲህ ተሰምተዋል፡፡ የአካባቢው የቀድሞ ባለስልጣን ወደስዊድን በተሰደደ ማግስት ያቀረባቸውን እነዚህን ማስረጃዎች ኢህአዴግ እንደለመደው የኦብነግ ከንቱ ውግዘት አድርጎ ማለፍ አይቻለውም፡፡ በዚህ ሰው ማስረጃም ሆነ ክልሉን ባጠኑ ምሁራንና ተቋማት ዘገባዎች መሰረት የጠቀስኳቸው ዘግናኝ ክስተቶች ማህበረሰቡን እየናጡት ነው፡፡

በተለይ ልዩ ሚሊሺያ የሚባለው ሕገ-ወጥ ሀይል፣ በሱማሌ ክልል ጎዳና ላይ ያሻውን እያነቀ እንዲያስር፣ ልጃገረዶችን እንዲደፍር፤ ገፋ ካለም በጥይት አረር እንዲረሽን የተተወበት አግባብ የሚመሰክርልን የፍትሕ ስርዓቱ ድምጥማጡ ስለመጥፋቱ ብቻ ነው፡፡ በዚህ መልኩ በሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች ካለዘውግ፣ ሐይማኖት እና ዕድሜ ልዩነት፤ ካለፍርድ ቤት እውቅና እየተፈፀመ ያለው ግፍ፣ የፍትህ ተቋሙ የዜጎችን ህልውና ለመጨፍለቅ ከገዢዎች ጋር በጥብቅ የተጋመደ ስለመሆኑ ያስረግጡልናል፡፡ እንግዲህ ፍትሕና ርትዕ የሰማይ ላይ ሩቅ ተስፋዎች እንዲሆኑብን የፈቀደውን ስርዓት እስከ መቼ መታገስ ይቻለናል? ስለርትዕ በኢትዮጵያ ምድር ላይ መስፈን ሲባልስ፤ የኢህአዴግን ቅፅር በህዝባዊ ሰላማዊ አብዮት ብንንደው፣ መስዋዕትነታችን ሀገርን ከመዓት ለማዳን ሲባል በፈቃደኝነት የሚከፈል ትውልዳዊ ግዴታ አይደለምን?! (በቀጣዩ ከአራጣ ማበደር ወንጀል እስከ መንግስታዊ ሙስና ላሉ ጉዳዮች እና ለፍትሕ ሥርዓቱ ሞቶ መቀበር ማሰሪያ አበጅቼ አጀንዳውን ለጊዜው እደመድመዋለሁ)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

አዲስ አበባ

 

የኢህአዴግ “አሸባሪነት”በ2007 ምርጫ ማንን ያስር ይሆን?

$
0
0

ሳሙኤል ተወልደ በርሔ/ሃርስታድ ኖርዌይ/

2007 electionሰው በላው የኢህአዴግ “አሸባሪነት” ለ2007 ምርጫ ምን እየቆመረ ይሆን?…ኢህአዴግ  ስልጣኑን ከተቃውሞም ሆነ ከነፃው ፕሬስ ወቀሳ የሚያረጋጋበት በርካታ ኢ-ፖለቲካዊ (ኢ-ዴሞክራሲያዊ) አካሔዶች አሉት፡፡ ኢህአዴግ እንደቀደምቶቹ የኢትዮጵያ መንግስታት ሁሉ የተቃውሙትን ፖለቲከኞች አስሯል፤ በዩኒቨርስቲ ውስጥ የአካዳሚ ነፃነታቸውን የጠየቁ ተማሪዎችን በፖሊስ አስደብድቧል፤ ከፍ ሲልም በእስር አሰቃይቷል፡፡ ብዙዎችንም በፖለቲካ አመለካከታቸው (በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ) ከገዛ ሀገራቸው እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡ ንቁ  የፖለቲካ ተሳትፎ በሚያደርግ አባወራ ምክንያት የቤተሰቡ አባላት ከፍተኛ ወከባ እና እንግልት እንዲደርስባቸው አስደርጓል፡፡

የ1997 ዓ.ም ምርጫ ውጤት ፍፁም ወደተቃዋሚዎች ማጋደሉን የተመለከተው እና ስልጣኑ አደጋ ላይ መውደቁን የተገነዘበው ኢህአዴግ ከ97 ዓ.ም በኋላ እስከአሁን ድረስ ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እጅግ አስጨናቂ ማድረጉ የአደባባይ ሐቅ ነው፡፡ ከአስጨናቂ እና ከኢ-ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ርምጃው መካከል በዋነኝነት ሊጠቀስ የሚችለው ደግሞ “አሸባሪነት” የሚለው ታፔላው ነው፡፡

በዚህ ሰው በላ ሐሳዊ ፍረጃውም ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን፣ ሞጋች የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞችን…ባጠቃላይ ስልጣኔን በዓይነ ቁራኛ ይመለከቱብኛል ብሎ ቀይ መስመር ያሰመረባቸውን ሰዎች አስሮ አስቀምጧቸዋል፡፡

በዚህ ስጋቱ የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ በ2007 ዓ.ም በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ንቁ ተሳታፊ ይሆናሉ ብሎ የሚገምታቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም የነፃው ፕሬስ  ሞጋች ጋዜጠኞችን በ“አሸባሪነት” ሰበብ እየቀፈደደ ወህኒ ሊያወርዳቸው እንደሚችል የማይጠረጥር የኢህአዴግን አስከፊ የፖለቲካ ስነ-ባህሪ የማያውቅ ብቻ ነው፡፡

ይህን ያልኩት ያለ በቂ ምክንያት አይደለም፡፡ በ1997 ዓ.ም የምሁራን ስብስብ በነበረው ቅንጅት የደረሰበት ወደር አልባ ሽንፈት ዳግም እንዲደገምበት ስለማይፈልግ ለስልጣኑ የሚያሰጉ ፓርቲዎችን (አመራሮቻቸውን) አነፍንፎ ከመያዝ ወደ ኋላ አይልም፡፡

በዚህም የተነሳ የ2007ቱን ብሔራዊ ምርጫ ተቃዋሚዎች እንደፈለጉ እንዲሆኑበት እና የነፃው  ፕሬስ አባላት በነፃነት እንዲዘግቡት ሁኔታዎችን ያመቻቻል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ እናም በ97  ዓ.ም ምርጫ ለወህኒ ቤት እንደተገበሩት ተቃዋሚዎች እና ጋዜጠኞች ለ2007ቱም ምርጫ እንደ አድባር የሚገበሩ ተቃዋሚዎች እና ጋዜጠኞች አይጠፉም፡፡ ጥያቄው ይገበራሉ ወይስ አይገበሩም? የሚለው ሳይሆን፤ እነማን ይገበራሉ? የሚለው ነው፡፡

ደርግ በዘመነ ስልጣኑ የተቃውሞ ድምፅ ሲያሰሙት የነበሩ ሰዎችን “አድኃሪ፣ አወናባጅ…” ወዘተ እያለ ይፈርጅ ነበር፡፡ ፈርጆ ሲያበቃም “አድኃሪዎች” ምኖች፣ ምናምኖች ያላቸውን ሰዎች  ከማሰርና ከመደብደብ አልፎ እስከ መግደል የደረሰ እርምጃ ይወስድባቸው ነበር፡፡ ደርግ እንዲያ ሲፈርጅ፣ ሲገድል፣ ሲያስር፣ ሲደበድብ የነበረው ለህልውናው ስለሚሰጋ ነበር፡፡

እየፈረጀ ባያስር፣ እያሰረ ባይገድል…የተቃውሞ ድምፅ የሚያሰሙ ወገኖች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ስልጣኑ (ህልውናው) አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ስለሚያምን የስልጣን ትንኮሳ ለሚያደርጉበት ሰዎች እንቅልፍ የለውም ነበር፡፡ ጃንሆይም ተቃውሞ ያሰሙባቸው የነበሩ  የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን “ፀረ ዘውድ፣ ፀረ ንጉስ…” እያሉ በመፈረጅ ለህልውናቸው ማቆያ  ወይም ለስልጣን ማረጋጊያ የሚያግዙ ርምጃዎችን ይተገብሩባቸው ነበር፡፡

እነሆ ኢህአዴግም “ከማን አንሼ” በሚል ስሜት የሰላ ሂስ የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችን፣ ለስልጣኔ  (ለወንበሬ) ያሰጉኛል የሚላቸውን ጠንካራ ተቃዋሚዎችን እያደነ በ“አሸባሪነት” ስም ወህኒ ያወርዳቸው  ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በጋዜጠኞቹ በእነ እስክንድር ነጋ እስር (“የአሸባሪነት ታፔላ”)  ነፃውን ፕሬስ ለማስበርገግ፣ በፖለቲከኞቹ በእነ አንዷለም አራጌ ተመሳሳይ ታፔላ የተቃውሞውን መንደር ለማስደንበር መላ ዘይዶ የተነሳው ገዢው ፓርቲ “አሸባሪ” የሚለውን ሰበብ የህልውናው ማስጠበቂያ “ዘበኛ” ሳያደርገው የቀረ አይመስለኝም፡፡

ጋዜጠኞች በ“አሸባሪነት” ስም ወህኒ በወረዱ ቁጥር መንግስት የሰላ ሂስ ከሚሰነዝሩ የነፃው  ፕሬስ አባላት ሂስ “ነፃ” እየወጣ ይሄዳል፡፡ እንዲሁ ከፍተኛ የህዝብ ቅቡልነት የተቀዳጁ  የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች “አሸባሪ” በሚል ሰረገላ ወህኒ ሲወርዱ ገዥው ፓርቲ የስልጣን ማገሩን ይበልጥ እየተከለው እና እያጠበቀው ይመጣል፡፡ ታዲያ ከ”አሸባሪነት” በላይ  የመንግስትን ህልውና (ስልጣን) እያስጠበቀ ያለ ዘብ ይኖር ይሆን?

ኢህአዴግ “አሸባሪነት”ን ለብቻው የሚረዳበት (የሚተረጉምበት) የተለየ መዝገበ ቃላት እንዳለው የምናውቀው የነ አሜሪካን አቋም በአንክሮ የገመገምን ዕለት ነው፡፡ እንደሚታወቀው አሜሪካና  ኢትዮጵያ “የጸረ ሽብር” አጋር ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት “አሸባሪ” እያለ የሚያስራቸውን ጋዜጠኞች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አሜሪካ “አዎ! አሸባሪ ናቸው” ብላ አታምንም፡፡

ይባስ ብላ “በሽብርተኝነት” ስም የታሰሩ ጋዜጠኞችን እና ፖለቲከኞችን በአስቸኳይ ይፈታ ዘንድ የኢትዮጵያን መንግስት ያሳሰበችበት ጊዜ በርካታ ነው፡፡ የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትም የኢትዮጵያ መንግስት “ሽብርተኛ” እያለ ወህኒ የወረወራቸውን ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች  “ጀግና” እያሉ ሲሸልሟቸው ነው የምናስተውለው፡፡

ከዚህ እውነታ የምንገነዘበው ኢህአዴግ ራሱ በፈለሰፈው እና የተቀረው አለም በማይስማማበት “ሽብርተኝነት” ስም እየነገደ መሆኑን ነው፡፡ አዎ! ሽብርን እና አሸባሪዎችን የማይጠየፍ ጤነኛ  ሰው የለም፡፡ ነገር ግን ኢህአዴግ “አሸባሪ” የሚለውን ቃል የሚተረጉምበት መዝገበ ቃላቱ  ከሌላው አለም የተለየ በመሆኑ ሰርክ እንደተወገዘበት ነው የሚገኘው፡፡

አንድ የማውቃቸው ባለትዳሮች ነበሩ። ምንም እንኳን ዛሬ ተነጣጥለው ለየብቻ መኖር ቢጀምሩም፤ ሚስትየው ባሏ መጠጥ እንዲያቆም ያልተሳለችው ስለት እና ያላንኳኳችው የቤተክርስቲያን በር የለም። ከዚህም ሌላ ጠዋት ከቤት ሊወጣ (ወደ ስራ ሊሄድ ሲል) እግሩን ከመላስ በማይተናነስ መልኩ ማታ ጠጥቶና ሰክሮ እንዳይመጣ ትወተውተዋለች፣ ትለምነዋለች፣ ታስጠነቅቀዋለች።

ውትወታዋም ሆነ ልመናዋ እንዳልሰመረ የምትረዳው ማታ ወደ ቤት ሲመጣ ሰክሮ እየተንገዳገደ  መሆኑን ስትመለከት ነው። ጠዋት ሲወጣ አስጠንቅቃው ማታ ሲገባ የሚሰክረው ለምንና ምን በድላው እንደሆነ ስትጠይቀው `ሰይጣን አሳስቶኝ ነው` ይላታል በመጠጥ የተላወሰው ምላሱ  እየተደናቀፈበት። እሱ እየሰከረ እሷ እየመከረችና እየለመነች ለአንድ አመት ያህል አብረው ቢኖሩም, መፋታታቸው ግን አልቀረም ነበር። አብረው በኖሩባቸው ወቅቶች ጠጥቶ ሲመጣ `ለምን?` ማለቷን አትተውም ነበር። `ሰይጣን አሳስቶኝ ነው` የሚለው ቃል የዘወትር መልሱና ሰበቡ መሆኑን የተገነዘበችው ሚስት `ምን አለበት ለአንድ ቀን እንኳን ሰበብህን ለወጥ ብታደርገው? ሁልጊዜ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው እያልክስ ለምን ታሞኘኛለህ?` ብላ በተናገረች ማግስት እቃዋን ይዛ ላትመለስ ተለየችው።

እውነት ነው! አመቱን ሙሉ ወይም ለአመታት በአንድ በማይለወጥና በማይሻር ሰበብ  አድራጎታችንን (ስህተታችንን) እየሸፋፈንን ለመቀጠል የምናደርገው ሙከራ ሰበባችንን  በሚያደምጠው ሰው ላይ የማይሰረይ መሰላቸት ይፈጥራል። ሁልጊዜ በአንድ ሰበብ ለመጓዝ መሞከር ፋራነታችንን እና አራዳ አለመሆናችንን ያሳብቅብናል።

በማይለወጥ ሰበባቸው (ምክንያታቸው) ልንጠቅሳቸው ከምችላቸው አካላት ደግሞ ገዥያችን ኢህአዴግ አንዱ ነው። ኢህአዴግ መንግስት እንደመሆኑ የአገሪቱን ፀጥታና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ (አንዳንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በርከት ለሚሉ አንዳንድ ጊዜዎች) ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ሙስሊሙን ወክለው የሚንቀሳቀሱ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ሲከስስ ወይም ሲያስር እንደ ምክንያት (ሰበብ) የሚያስቀምጣቸው መልሶች  እጅግ ተመሳሳይ እና ማሻሻያ የማይደረግባቸው ናቸው። ጋዜጠኛን ሲያስር ‹‹ህገ-መንስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በሀይል (በሽብር) ለመናድ ሲቀሳቀስ…›› የምትል የተለመደችውን ምክንያት ያስቀምጣል። ይህ ምክንያት ጋዜጠኛውን ለመክሰሻ አገልግሎት ብቻ የሚውል አይደለም። ተቃዋሚዎችን ሲያስርም ‹‹ሽብርተኛ›› የምትለውን ቃል ለመክሰሻ ፍጆታው ያውላታል። በአሁን ሰአት በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊሙን ተወካዮች ሲያስር እንደ ምክንያት የተጠቀመው ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚዎችን ለመክሰስ የደረደራቸውን ሰበቦቹን ነው።

ከላይ የባለትዳሮቹን የህይወት ተሞክሮ ያነሳሁት ያለ ምክንያት አይደለም። ከኢህአዴግ ምክንያት ድርደራ ጋር ተቀራራቢ (ተመሳሳይ) ባህሪ ስላለው ነው እንጂ። ሚስት ‹‹ሰይጣን አሳስቶኝ ነው›› በሚለው የባሏ ቋሚ ተሰላፊ ሰበብ ትዳሯን እስከመናድ ያደረሰ መሰላቸት  አሳድሮባታል።

የ1997 ዓ.ም የምርጫ ውጤቱ ወደ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካጋደለና ሁኔታዎች ወደአላስፈላጊ አቅጣጫ ከዞሩ በኋላ በርካታ ተቃወሚዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች ወህኒ ወርደዋል። የዛን ጊዜ የታሰሩበት ምክንያት ‹‹ህገ-መንግስቱን እንደ ሾላ በድንጋይ ለማውረድ…›› የሚል ነበር። 1997 ዓ.ም ጥሎን ከነጎደ ዛሬ ወደ ስምንት አመት ሆኖታል። በነዚህ ስምንት አመታቶች ውስጥ ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚው፣ ኑሮው፣ የሰው አስተሳሰብ… በውድቀትና በእድገት ምህዋር ውስጥ ወይ ወደ ላይ ወጥቷል፤ አሊያም ወደታች ወርዷል። በአጠቃላይ ሁኔታው ተለውጧል፤ ተለዋውጧል። “ህገ-መንግስቱንና ህገ-መግስታዊ ስርዓቱን በሀይል (በሽብር) ለመናድ ሲንቀሳቀሱ…›› በመንግስታችን ቋንቋ፤ የቁመት፣ የወርድ፣ የመጠን ለውጥ ሳይደረግባት ይኸው እስከዛሬ እንዳለች አለች። ኢህአዴግ ወደፊት እስከሚኖርበት ጊዜ ድረስም አብራው ትኖራለች፤ ሰንደቁና አርማው ናትና አትጠፋም። ጋዜጠኞች፣ ተቃዋሚዎች፣ ‹‹እምቢየው›› መብቴን የሚሉ ዜጎች ከኢትዮጵያ ምድር  ሲጠፉ ብቻ ነው ያቺ የኢህአዴግ ምክንያት ‹‹በክብር›› ወደ ማህደሯ የምትመለሰው። እስከዚያው ድረስ ግን፤ እንደ ርዕዮተ አለም የተያዘችው ምክንያት ሳትከለስ፣ ሳትበረዝም ሆነ ተሐድሶ ሳይደረግባት በዶግማ (Doctrine) መልክ ትቀጥላለች።

የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ‹‹መንግስት በሽብርተኝነት ሊያስረን እንደሆነ ከታማኝ ምንጮቻችን ሰማን›› ብለው አገር ጥለው ከተሰደዱ በኋላ፤ እንዳሉትም በሌሉበት በሽብርተኝነት ተከስሰውና ‹‹ሽብርተኛ›› ተብለው ተፈርዶባቸዋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ርእዮት አለሙ ተከስሰው የተፈረደባቸው ‹‹ሽብርተኛ›› በምትለዋና ለአዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረቦች በተለጠፈችው ቦሎ ነው። አንድ ጋዜጠኛ ሲታሰር የክሱ ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ የግድ የሚመለከተው አካል መግለጫ እስኪሰጥ መጠበቅ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። አሁን አሁን እከሌ የሚባል ጋዜጠኛ ታሰረ የሚል ወሬ ሲሰማ፤ ያው ‹‹በሽብርተኝነት›› እንደሚከሰስ አስቀድሞ ማረጋገጥ እየተለመደ መጥቷል። ይህ እንዲሆን በር የከፈተው መንግስታችን በተለይም ከ1997 ምርጫ በኋላ እየተከተለው የመጣው ተሐድሶ አልባ ምክንያቱ (ሰበቡ) ነው።

ለአዲስ ነገር ጋዜጠኞች ክስ የተጠቀመውን ምክንያት ለእስክንድር ነጋ፣ ለእስክንድር ነጋ  የተጠቀመውን ለርዕዮት አለሙ… ለውብሸት ታዬ… ነገ  ደግሞ አንድ ጋዜጠኛ ሲታሰር፤ ለእሱም ፍጆታ ያውለዋል።

በአንድ ተመሳሳይ ምክንያት የተለያዩ ጋዜጠኞችን ማሰር አይሰለችም? የሰው ልጅ አንዴ፣ ሁለቴና ሶስቴ በሰይጣን “ሊሳሳት” ይችል ይሆናል። ግን እንዴት ዘለአለአም በሰይጣን እየተሳሳተ ይኖራል?  እያንዳንዱ ጋዜጠኛስ እንዴት ‹‹ሽብርተኛ›› ሊሆን ይችላል?

በደርግ ጊዜ ነው አሉ፤ ‹‹አንድ ሰው አይደለም በጤናው ሰክሮ እንኳን የመንግስቱ ኃይለማርያምን አስተዳደር መውቀስም ሆነ መተቸት አይችልም ነበር ይባላል። “ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል” የሚለው አባባል በደርግ ጊዜ አይሰራም ነበር።” ሲሉ አንድ አባት አጫውተውኛል። ደርግ ከተገረሰሰ ከሃያ ሁለት አመታት በኋላ ማለትም ዛሬ፤ ያውም “ዴሞክራሲና ነፃነት ያለገደብ መስፈኑ” በሚነገርበት በዚህ ጊዜ ሳይሰክሩ መንግስትን መተቸት ከባድ እየሆነ መጥቷል። ከባዱን መከራ እጋፈጠዋለሁ ያለ ጋዜጠኛም ‹‹ያቺ ነገር›› ትመዘዝለታለች።

እንግዲህ በደርግና በኢህአዴግ መካከል ያለውን ልዩነት እንመርምር። በደርግ ጊዜ ተሰክሮም ሆነ ሳይሰከር ትችት እሰነዝራለሁ ማለት ከባድ ነበር። በኢህአዴግ ጊዜ ዲሞክራሲው “ያለ ገደብ”  በመንሰራፋቱ፣ በገደብ ሰክረው ያለገደብ የመንግስትን ስህተት መተቸት ይቻላል። ታዲያ  በመጠጥ ስካር እንጂ በኑሮው ንረት፣ በመልካም አስተዳደር ችግር፣ በመኖሪያ ቤት እጥረት ስካር መንግስትን ማማረር፣ ከማማረርም አልፎ ለተቃውሞ መውጣት “ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች…” ለሚል የክስ ፋይል አሳልፎ ይሰጣል። መቼም አሜሪካና አውሮፓ የሽብርተኞች ደጋፊና አፍቃሪ ስለሆኑ አይደለም-የኢትዮጵያ መንግስት “አሸባሪ” ያላቸውን እነ እስክንድርን እየሸለሙ ያሉት፡፡ እናም ኢህአዴግ ሆይ! የተበላች ዕቁብ የመሰለችውን ምክንያትህን (አሸባሪነትን) ቀየር ብታደርጋትስ?!…

 

 

የበድር አመራሮችን አስመልክቶ የወጣ መግለጫ –ከፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን

$
0
0

ጥቂት የበድር አመራሮች በሰሜን አሜሪካ የሚገኘዉን የሙስሊሙን ማህበረስብ ስም በመጠቀም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉዞ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ

ፈርስት ሒጅራህ ፋዉንዴሽን ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የሚያደርጉትን ሰላማዊ የመብት ትግል መዳረሻዉ ድል እስኪሆን ድረስ በማንኛውም ጉዳይ በጽናት ይደግፋል። በህዝብ የተመረጡት የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ያሳዩት ቁርጠኝነትንና ጽናትን ፈርስት ሒጅራህ በእጅጉ የሚያደንቅም ብቻ ሳይሆን በነዚህ የሰላም አምባሳደሮች ላይ የኢትዮጵያ መንግስት እየፈጸመ ያለዉን ግፍ በማንኛዉም መልኩ የሚፋረደዉ ዘግናኝ እዉነታ ነዉ። እነዚህ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆች የሆኑት ኮሚቴዎች ዛሬም በእስር ቤት ውስጥ ያሳዩት የአመራር ብቃትና ጥንካሬ በአለማችን የታሪክ መዝገብ ላይ የሚሰፍር አኩሪ ታሪክ በመሆኑ ፈርስት ሒጅራህ ኮሚቴዎቹን ከመደገፍም ባሻገር የሚከተል መሆኑን ሲገልጽ በታላቅ በደስታ ነዉ።

የታሰሩት ኮሚቴዎች

የታሰሩት ኮሚቴዎች


የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ላይ እያደረሰ ያለዉን ቀጣይ በደል ለመታደግ የታሰሩትን አሚሮችን (መሪዎችን) በመከተልና ድምጻችን ይሰማ የሚያወጣዉን ትእዛዝ ለመተግበር ፈርስት ሒጅራህ ወደ ሗላ የማይል መሆኑን እያስገነዘበ፤ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የሚያደርጉትን ሰላማዊ ትግል ለማኮላሽት የሚደረግ ማንኛዉንም እንቅስቃሴ ለማጋለጥ ፈርስት ሒጅራህ እምርታዊ በሆነ ትጋት የሚሰራ መሆኑንም ለመግለጽ ይወዳል። እንደ አገር መሪ ሳይሆን እንደ አሸባሪ የሚንቀሳቀሰዉ የኢትዮጵያ መንግስት የፈርስት ሒጅራህ ፋዉንዴሽንን እስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ከግምት ዉስጥ በማስገባት ድርጅቱ የሚያደርገዉን ጠንካራ የመብት ትግል ለማርገብ ያደረጋቸዉ ጥረቶች ሁሉ የመከኑበትን እዉነታ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ማድረጉም ግድ ይላል።

ፈርስት ሒጅራን ጨምሮ ሌሎች በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ማህበራት የመሰረቱት በድር አለምአቀፍ የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ድርጅት የተመሰረተለት አላማን በማፋለስ፤ በድርጅቱ ምስረታ እና አወቃቀር ብሎም አመራር ላይ ወሳኝ ሚና ያለዉንና ለወደፊቱም በድርጅቱ ህልዉና ላይ አይቀሬ ተሳትፎና ድርሻ ያለዉን ፈርስት ሒጅራን በማግለል፤ የኢትዮጵያን መንግስትና የሙስሊሙን ማህበረሰብ እናደራድራለን በማለት አብዛኛዉ ያልወከላቸው ጥቂት የበድር አመራሮች በቅርቡ ስኬት አልባ የሆነን ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ማድረጋቸዉ ይታወቃል። ይህንን ሙሉ ህዝባዊ ይሁንታ ያላገኘዉን ጉዞ ፈርስት ሒጅራህ ፋዉንዴሽን ከዚህ ቀደም እንደተቃወምነዉ አሁንም ሙሉ በሙሉ የሚቃወም መሆኑን እየገልጸ ያለዉንም አቋም ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ማድረግ ይፈልጋል።

ቀደም ሲል በመንግስትና በሙስሊሙ ጉዳይ ላይ ገለልተኛ(ኒውትራል) የሆነ አቋም ነዉ ያለን በማለት በይፋ ይናገሩ የነበሩ ግለሰቦች፤ ዛሬ የኢትዮጵያ መንግስት አትኩሮት ሰጥቶ በልዩ አቀባበል(VIP)አስተናግዶናል፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በከፈትነዉ መስመር መስራቱን እንቀጥላለን፤ ሙስሊሙ ህብረተሠብ አንቅሮ የተፋውን የመንግስት መጅሊስን የሙስሊሙ ጉዳይ ያገባዋል (stakeholder) ነው በማለት እዉቅና በመስጠት አነግረናል፣ኢትዮጵያ ዉስጥ ቢሮ ከፍተናል በማለት ያለ ምንም እፍረት ሙስሊሙን ማህበረሰብ እያወናበዱ ይገኛሉ። እነዚህ ግለሰቦች ባስቸኳይ የያዙትን የህዝብ አደራ አስረክበዉ የድርጅቱ መመሪያ ተተግብሮ ህዝብ ያመነበት ምርጫ እንዲደረግ ፈርስት ሒጅራህ በአጽኖ ይጠይቃል።

የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሙ ማህበረስብ ላይ የሚያደርሰዉን ጭቆና ለማዉገዝ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ወኔ የሌላቸዉ የመንግስትን ጥቅም አስከባሪና መንግሥት በሙስሊሙ ህብረተሰብ መካከል የተፈጠረውን አስጊ አለመግባባትን መፍትሄ ለማስገኘት ነዉ በማላት የተሳሳተ አመለካከታቸዉን ሲያራምዱ የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ አስታራቂ መስለዉ ኢትዮጵያ መሔዳቸዉ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ንቃተ ህሊና እንደናቁ የሚቆጠር እጅግ አሳፋሪ ስራ በመሆኑ ባስቸኳይ ከበድር ድርጅታዊ አሰራር ገለል እንዲሉ ፈርስት ሒጅራህ የጠይቃል።
ፈርስት ሒጅራህ ከጅማሮዉ አንስቶ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በአያሌ መስዋእትነት የገነባዉ በድር፤ ከመስመር በወጡ ጥቂት መሪዎች ግላዊ ፍላጎት የሚፈርስ አይደለም። በመሆኑም ፈርስት ሒጅራህ በመላዉ አለም ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ጋር በመጻጻፍና በመዘዋወር ግንዛቤን የማስጨበጥ ስራ ይሰራል።

ለፊትና (መከፋፈል)የሚለዉን ቃል ብዙ የግል ጥቅም አስጠባቂ አካላት የሚጫወቱበት ካርድ በመሆኑ፤ ፈርስትሒጅራህ በወሰደዉ አቋም ፊትና ፈጣሪዎችን መንቅሮ ለማዉጣት የሚያደርገው ጥረት መላዉ የኢትዮጵያ ሙስሊም ምንም አይነት ግራ መጋባት ሳይስተዋልበት ጥረታችን ከስኬት ይደርስ ዘንድም በዱዓ (በጸሎት) ይበረታ ዘንድም ፈርስት ሒጅራህ ይጣራል። ቀድም ሲል በኢትዮጵያ የሚገኙ ታዋቂ ዳኢዎች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ሰላማዊ ትግሉን ለመቀልበስ ያደረጉት ሙከራ በተባበረዉ የሙስሊሙ ማህበርሰብ ክንድ እንደከሸፈዉ ሁሉ ተመሳሳይ ሴራን ለማክሸፍ ፈርስት ሒጅራህ የሚያደርገዉን ጥረት ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዲረዳዉ ያሳስባል።

ኮሚቴዎቻችንና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች የታሰሩበት፣ የተገረፉበት፣ የተሰቃዩበት፣ የሞቱበትና ብዙዎች የተሰደዱበትን ትግልን ከንቱ ለማድረግ ለሚነሳ ማንኛዉም ሐይል ታጋሾች አንሆንም። በየአደባባዩና በተለያዩ የዲፕሎማሲ መድረኮች በግልጽ ወጥተን ህዝብ ከወከላቸዉ አሚሮቻችን ጎን ቆመን ለመብት ለነጻነት በመታገላችን አንገት ደፊና ይቅርታ ጠያቂዎች አንሆንም። በድር ድርጅታችን ነዉ፦ በድርን ለማዳን ቆርጠን በመነሳታችን መላዉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም በዱዓ (በጸሎት) እንዳይረስን እንማጸናለን።

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በአስቸኯይ ከእስር ይለቀቁ፦

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

አላሁ አክበር

“አዲስ አበባ የኦሮምያ ናት”የሚለውን ቀልድ ተውትና ለእውነተኛ የነጻነት ትግል ተነሱ! (ይድረስ ለጥቂት የኦሮሞ ሊህቃን) –ከፋሲል የኔዓለም

$
0
0

ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም


የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ትግል በሁለት አቅጠጫዎች የሚካሄድ ነው ። አንደኛው ከህወሃትና አጋሮቹ ጋር የሚካሄደው የሽቅብ (vertical) ትግል ሲሆን ሌላው ደግሞ ተቃዋሚዎች እርስ በርስ የሚያካሂዱት የአግድሞሽ (horizontal) ትግል ነው። የአግድሞሹ ትግል ሲዳከም የሽቅብ ትግል ይጠነክራል፣ የአግድሞሹ ትግል ሲጠናከር ደግሞ የሽቅብ ትግል ይዳከማል። ለ23 ዓመታት የተካሄደው የነጻነት ትግል ፍሬ ሊያፈራ ያልቻለው በከፊል የአግድሞሹ ትግል ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ወይም ሊዳፈን ባለመቻሉ ነው። ለወደፊቱም ቢሆን የአግድሞሹ ትግል እየተዳከመ ካልሄደ ሽቅብ የሚካሄደው ትግል ሊጠናከር አይችልም። ህወሃትና አጋሮቹ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተዳክመው የሚገኙበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። ይህን የተዳከመ ሃይል በካልቾ መትቶ ለማባረር የአግድሞሹን ትግል በማዳከም የሽቅብ ትግሉን ማጠናከር ያስፈልጋል፤ የአግድሞሹ ትግል ሊዳከም የሚችለው ደግሞ ዋነኞቹ ተቃዋሚዎች ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ፈርመው የያዙትን ጥይት ወደ ሽቅብ ለመተኮስ መስማማት ሲችሉ ብቻ ነው።

ወደ ሽቅብ የሚደረገውን ትግል ከሚያዳክሙ ሃይሎች መካከል በተቃውሞ ጎራ ተሰልፈናል የሚሉ የተወሰኑ የኦሮሞ “ሊህቃን” በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። እነዚህ ሊህቃን ምን እንደሚፈልጉ አይታወቅም። አቋማቸው በየጊዜው እንደ እስስት የሚለዋወጥ በመሆኑም እንዲህ ናቸው ብሎ አፍን ሞልቶ ለመናገር አይቻልም። እነሱን አምኖ አብሮ ለመታገልም በጣም አስቸጋሪ ነው፤ መቼና የት ቦታ ላይ እንደሚለወጡ አይታወቅም፤ ከእነሱ ጋር አብረው ለመስራት የሞከሩ ድርጅቶች ሁሉ እስከዛሬ አልተሳካላቸውም። እነዚህ ጥቂት ሊህቃን የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎት የሚያውቁ አይመስለኝም። መሽቶ በነጋ ቁጥር አቋማቸውን በብርሃን ፍጥነት ሲለዋዉጡ የምናየውም ለዚህ ይመስለኛል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህ ጥቂት ሊህቃን የመገንጠል አጀንዳቸውን በመተው ለነጻይቷ አገር መወለድ እንደሚሰሩ ሲነግሩን ተስፋ አድርገን ነበር፤ ነገር ግን ሰሞኑን የሚጽፉትና የሚናገሩት አሁንም ካረጁበት የመገንጠል አላማ ፈቅ አለማለታቸውን የሚያሳይ ነው። በተለይ የአዲስ አበባ ከተማን አዲስ ካርታ ለመቃወም የሚያነሱት መከራከሪያ ልብን ዝቅ የሚያደርግና የሰዎቹን እውነተኛ ፍላጎት ገሃድ የሚያወጣ ነው።
Addis-Ababa
ጥቂት የኦሮሞ ሊህቃን የአዲስ አበባን መስፋፋት የሚቃወሙት “መሬቱ የኦሮሞ ነው” ከሚል ጠባብ ስሜት ተነስተው ነው። በአንድ በኩል “አዲስ አበባ የኦሮምያ ናት” ይሉንና በሌላ በኩል ደግሞ “የኦሮምያ ልዩ ዞኖች በአዲስ አበባ ስር መሆን የለባቸውም” ይላሉ። አዲስ አበባ የኦሮሞ መሬት ከሆነ ፣ ልዩ ዞኖቹ በአዲስ አበባ ስር ሆኑ አልሆኑ ምን ልዩነት ያመጣል? ክርክራቸው ስሜት እንዲሰጥ ከፈለጉ “አዲስ አበባ የኦሮሞ አይደለም” ብለው መነሳት አለባቸው። ሳሎን ውስጥ ያለውን ሶፋህን አንዱ ወስዶ መኝታ ቤትህ ውስጥ ቢያደርገው ሶፋ ተሰረቀ ብለህ ልትከስ አትችልም ። መክሰስ የምትችለው ሶፋህን ሌላ ሰው ቤት ካየኸውብቻ ነው። የኦሮምያ መሬት ወደ አዲስ አበባ ዞረ ብሎ ለማልቀስ፣ አዲስ አበባ የኦሮሞ አይደለችም ብሎ ማመንን ይጠይቃል። ይህን የነሳሁት ሊህቃኑ የሚያቀርቡትን የተምታታ ሃሳብ ለማሳየት እንጅ፣ አዲስ አበባም ሆነ ኦሮምያ “የኦሮሞ ብቻ ነው” የሚለውን አስተሳሰብ ለመደገፍ አይደለም።

“ኦሮምያን የኦሮሞ፣ አማራን የአማራ፣ ትግራይን የትግሬ…” ንብረት ብቻ እንደሆኑ አድርጎ ማየቱ የኢትዮጵያን አንድነት የሚያዳክም፣ የአገርን ምንነት ትርጉም የሚያዛባና አደገኛ ነው። ለመሆኑ ማን ነው አዲስ አበባን ለኦሮሞ ብቻ የሰጠው? እንኳንስ አዲስ አበባን ማን ነው ጅማን፣ ቦረናን፣ አዳማን፣ አርሲን ወዘተ የኦሮሞ ብቻ ያደረጋቸው? ማን ነው ባህርዳር ፣ ጎንደር፣ ደሴ ወዘተ የአማራ ብቻ ነው ያለው ? ጋምቤላን ለጋምቤላዎች፣ አፋርን ለአፋሮች ፣ ትግራይን ለትግሬዎች ብቻ የሰጠው ማን ነው? በየትኛው ህግ፣ በየትኛውም አንቀጽ ነው ክልሎች መሬት ተከፋፍለው “ያ ያንተ ይሄ የኔ ነው” የተባባሉት? የይስሙላው ህገመንግስት ( ህገ-አገዛዝ) እንኳ ክልሎች በስራቸው ያለውን መሬት ያስተዳድራሉ አለ እንጅ መሬቱ የእነሱ ብቻ ነው አላላም። የአስተዳደር ባለቤትነት ሰጣቸው እንጅ የውርስ ባለቤትነት አልሰጣቸውም። ክልሎች እስካልተገነጠሉና በአንድ አገር ስር እስካሉ ድረስ “ይሄ የእኔ ያ ያንተ መሬት ነው” ሊሉ አይችሉም፣ የአንዱ መሬት የሌላው፣ የሌላው መሬት የአንዱ ነውና።
የኦሮሞ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባል ትግራይ ሄዶ ሲሞት “ትግራይም የእኔ ናት” ብሎ እንጅ ትግራይ የትግሬዎች ናት ብሎ ስላመነ አይደለም። የአማራ ተወላጅ ኦሮምያ ድንበር ሄዶ የሚሞተውም በተመሳሳይ እምነት ነው። ዛሬ ህወሃት የአገራችንን አንድነት ቢያዳክምም እልፍ አእላፍ ዜጎች ለዚህች አገር መስዋትነት የከፈሉት “ሁሉም የኔ፣ እኔም የሁሉም” በሚል እምነት ነው። እያንዳንዷ ቅንጣት የኦሮምያ አፈር፣ ልክ እንደ ኦሮሞው ሁሉ፣ አማራውንም ታገባዋለች፣ እያንዳንዷ የአማራ ቅንጣት አፈር ፣ ልክ እንደ አማራው ሁሉ፣ ኦሮሞውንም ትመለከተዋለች። በአንድ ጎጆ ስር እስከኖርን ድረስ “ይሄ የእኔ ያ ያንተ” የሚባል ነገር የለም። አዲስ አበባ የሁላችንም ናት፣ ኦሮምያም የሁላችንም ናት፣ ባህርዳርም የሁላችንም ናት፣ መቀሌም የሁላችንም ናት። ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት።

ኦሮምያ የኦሮምያ፣ ትግራይ የትግራይ የሚለው አስተሳሰብም የደባልነት አስተሳሰብ ነው። ደባልነት ከትዳር የሚለየው በማንኛውም ጊዜ የሚፈርስ፣ መተሳሰብ የሌለው፣ ለጊዚያዊ ጥቅም ተብሎ የሚገባበት በመሆኑ ነው። ኢትዮጵያን እንደ ትዳር ትተን እንደ ደባል ህይወት የምንመስላት ከሆነ አደጋ አለው። ጥቂት የኦሮሞ ሊህቃን አዲስ አበባንና ኦሮምያን የእነሱ ብቻ አድርገው ማየት በማቆም፣ የአዲስ አበባን መስፋፋት የሚቃወሙበትን ሌሎች ወንዝ የሚያሻግሩ ምክንያቶችን ማቅረብ አለባቸው። ሊህቃኑ ከኦሮምያና ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ ቦታዎችንም እንደራሳቸው አድርገው መውሰድ መጀመር አለባቸው። እንዲያ ከሆነ ብቻ ነው ስለጋራ ችግር መነጋገር የሚቻለው።
የአዲስ አበባን መስፋፋት የምቃወመው በሁለት ምክንያቶች ነው። አንደኛ፣ አዲስ አበባ ወደ ላይ እንጅ ወደ ጎን መስፋት የለባትም ። አሁን ያለውን ህዝብ ህንጻዎችን ወደ ላይ በማሳደግ ማኖር ይቻላል። ለወደፊቱ ጥሩ የህዝብና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መቅረጽና ማስተዳደር ግድ ይላል።

ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ የአካባቢ ውድመት ስለሚያሳስበኝ ነው። በአዲስ አበባ የሚገነባው ነገር ሁሉ ዘላቂነት ያለው አይመስለኝም። እንበደራለን፣ እንገነባለን፣ እናፈርሳለን። እዳው ደግሞ በውርስ ለልጆቻችን ይተላለፋል። ከተማዋ አረንጓዴነት አይታይባትም፤ ኳስ ሜዳ፣ መናፈሻ ፓርክ ወዘት ቦታ አልተሰጣቸውም። ታሪካዊ ቦታዎች ይወድማሉ። ከተማዋ የቻይና የቴክኖሎጂ ቤተ-ሙከራ ( laboratory) እንጅ ህዝብና አስተዳደር ያለባት ከተማ አትመስልም። ከመንገድና ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ተያይዞ የሚረጩት ኬሚካሎች እንኳ በጤና ላይ ስለሚኖራቸው ጉዳት በቂ ጥናት የሚካሄድባቸው አይመስለኝም። በቃ ሁሉም ነገር ለመታየትና ለፕሮፓጋንዳ ተብሎ ስለሚሰራ ያስጠላል። ደረቅ ህንጻዎችን ማየት የመረረው ሰው አረንጓዴ መስክና አዝመራ ማየት ቢፈልግ ወደ እነዚህ ቦታዎች መሄድ አለበት። ልዩ ዞኖቹ ህንጻ መስሪያ ቦታዎች ከሆኑ የአዲስ አበባ ህዝብ አይኑን የሚያሳርፍበት አረንጓዴ ቦታ አያገኝም። ተፈጥሮን በግዴለሽነት ማውደምም ፍትሃዊ አይደለም።
addis ababa
የኦሮምያ ልዩ ዞኖች በአዲስ አበባ ወይም በኦሮምያ ስር ስለሆኑ ገበሬው ከመፈናቀል አይድንም፣ ልዩነት ቢኖር ፈቃድ ሰጪው ወይ ኦሮምያ ወይ አዲስ አበባ መሆኑ ነው። በለገዳዲና በለገጣፎ አካባቢዎች አንዳንዶች በስማቸው እስከ 30 ቦታዎችን ይዘው ተገኝተዋል፣ የሚያስመዘግቡት የሰው ስም አጥተው በውሾቻቸው ስም ካርታ ያሰሩም አሉ። ይህን የሚያደርጉት ገንዘብ ያላቸው ናቸው። ገንዘብ ያላቸው እነማን ናቸው? ገብረዋህድ ሁሉንም ነገር ይነግረናል። ገብረዋህድ መንግስት እንደነገረን 16 የቤት ካርታዎች አሉት። ስንት ገብረ ዋህዶች እንደሚኖሩ አስቡት። ሰሞኑን አንዱ ወዳጄ በጋምቤላ ስለሚካሄደው የመሬት ዘረፋ ይነግረኝ ነበር። “ህንዶች ሲቀነሱ፣ መሬቱን ተቆጣጥረው የያዙት የህወሃት የቀድሞ መኮንኖች ናቸው” አለኝ። ያሳዝናል!
የኦሮሞንም ሆነ የሌሎችን አካባቢዎች ገበሬዎች ከመፈናቀል ለመታደግ የጎንዮሹን ትግል ለጊዜው ትቶ ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር በማበር ይህን በሙስናና በጎጠኝነት ላይ የተመሰረተ ስርዓት ለማስወገድ መሰባሰብ ግድ ይላል ።


ሰማያዊ ፓርቲ የሚታገለው ማንን ነው ? (ግርማ ካሳ)

$
0
0

ግርማ ካሳ

blue partyሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ አነበብኩ። ገረመኝ። መጋቢት 28 ቀን በአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጉን ባፈረሰ መልኩ በመጋቢት 28 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል ገለጸ። የሰልፉ ቀን ወይንም ቦታ እንዲቀየር የመጠየቅ እንጂ በጥቅሉ ለቀረቡት የሰልፍ ጥያቄዎች እውቅና አንሰጥም የማለት መብት አስተዳደሩ እንደሌለው በመጥቀስ፣ በአስተዳደሩ የተላከዉን ሕገ ወጥ ደብዳቤ አንድነት እንደማይቀበል አሳወቀ። አንድነት ተለዋጭ ቀን እንዲያቀርብ የሚጠይቅ፣ ሕጉን የተከተለ ሁለተኛ ደብዳቤ፣ አስተዳደሩ፣  ላከ። የአንድነት ፓርቲ መጋቢት 28 ቀን ሊደረግ የታሰበውን ሰልፍ ወደ ሚያዚያ 5 ቀን ለማድረግ እንደሚፈልግ አሳወቀ። በሚያዚያ 5 ቀን፣ የሩጫ ዝግጅት ስላለ፣  ቅዳሜ ሚያዚያ 4 ቀን ሰልፉን ማድረግ እንደሚቻል፣ አስተዳደሩ በደብዳቤ  ገለጸ። ግምሽ ቀን የሚሰራበት እንደመሆኑ፣ ቅዳሜ ቀን ሰልፉን ማድረግ እንደማይስማማው የአንድነት ፓርቲ ገልጸ። በሳምንቱ እሁድ ፋሲካ፣ በአስራ አምስት ቀኑ ደግሞ ዳግማይ ትንሳኤ በመሆኑ ፣ ለክርስትና እምነት ተከታዮች አክብሮቱን በመግለጽ፣ ሁለት እሁዶችን (ሚያዚያ  12 እና 19) አልፎ በሚያዚያ 26 ቀን ሰልፉን ለማድረግ ወሰነ።

 

ምንም እንኳን የአዲስ አበባ አስተዳደር መጀመሪያ ላይ የጻፋቸው ሕግ ወጥ ደብዳቤዎች አሳዛኝ የነበሩ ቢሆንም፣ የአንድነት ፓርቲ ሕግ ወጥ ደብዳቤዎችን እንደማይቀበል ካሳወቀበት ጊዜ በኋላ ግን፣ በአንድነት እና በአስተዳደሩ መካከል ሲደረጉ የነበሩት የደብዳቤ ልዉዉጦች ጤናማ መሰሉኝ። ያሉ ልዩነቶችን በሰለጠነ መልኩ ለመፍታት መሞከር ሊበረታታ የሚገባዉ ነው።

 

የአንድነት ፓርቲ ከአስተዳደሩ ጋር በዚህ ሁኔታ እየተነጋገረ ባለበት ሁኔታ፣ ሳይታሰብ የሰማያዊ ፓርቲ ፣ የተለየ ጥያቄዎች ቢኖሩት እሺ፣ ግን አንድነት ባቀረባቸው ጥያቄዎች ዙሪያ፣ ሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ጠራ።  ይሄም ሰማያዊ ፓርቲን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎችን እንድጠይቅ አደረገኝ።

 

የአንድነት ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀንን ያለፈው ዳግማይ ትንሳኤ ስለሆነ ነው። ሰማያዊ ፓርቲ እንደ አብዛኞቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ አካባቢ እየወሰደ ስላለው አቋም ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ፣ የታሰሩ ሙስሊም እስረኞች እንዲፈቱ፣ ጠይቋል። በዚህ ሁኔታ ለሙስሊሙ ማህብረሰብ ከበሬታ መሰጠቱ ተገቢ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ለክርስትና እምነት ተከታዮችም ከበሬታ ማሳየት አልነበረበትምን?  በክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ አመት በዓል በሆነበት፣ በዳግማይ ትንሳኤ ቀን፣  ሰልፍ መጥራት ተገቢ ነዉን ?  ፈረንጆች እንደሚሉት «ሴንሲቲቭ» መሆን አልነበረበትምን ?  ሁሉም እምነቶች መከበር አለባቸው ባይ ነኝ። ሰማያዊ በዚህ ረገድ ትክክል አደረገ አልልም። ይሄ የመጀመሪዉ ነጥቤ ነው።

 

ሰማያዊ ፓርቲ ያነሳቸው ጉዳዮች፣ የአንድነት ፓርቲም ያነሳቸው ጉዳዮች ናቸው። የሕዝቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ሰማያዊና አንድነት ቢዋሃዱ ጥሩ ነበር። ግን ሰማያዊ ለብቻው መጋለብ የሚፈልግ በመሆኑ፣ ተመሳሳይ የፖለቲካ ፕሮግራም ቢኖርምም፣ መዋሃድ አልተቻለም። ነገር ግን የቀረቡ ጥያቄዎች ተመሳሳይ በሆኑበት ሁኔታ፣ ሰማያዊ የራሱን ሰልፍ፣ አንድነት ሊጠራ ባሰበበት ወቅት ለማድረግ ከሚሞክር፣ ከአንድነት ጋር ተነጋግሮ፣  ቢያንስ በጋራ ሰልፍ ቢጠራ መልካም ነበር። ለምን ያ እንዳለሆነ አለገባኝም። ሰልፍ ሲጠራ እኮ አላማ ሊኖረውና ዉጤት ሊያስመዘግብ ይገባል። እንደው ዝም ብሎ ሰልፍ ማድረግ በራሱ የትም አያደርስም። ሰልፍ የሚደረገው ትልቅ መልእክት ለማስተላለፍ ነው። ሰልፉ የተሳካ የሚሆነውም በተቻለ መጠን ብዙ ሕዝብ ሲገኝ ነው።

 

ሰልፉ በጋራ በመጠራቱ፣ እርግጥ ነው ሰማያዊ ለብቻው የተለየ ክሬድት አያስገኝለትም። አንድነትም የተለየ ክሬድት አያገኝም። ክሬድቱን የሚወስዱት በጋራ ነው የሚሆነው። ያ ደግሞ ችግር አለው ብዬ አላስብም። ለሕዝብ የሚያስብ ድርጅት፣  «ድርጅቴ ብቻ ለምን አልተጠቀመም ?» የሚለውን ሳይሆን «ሕዝብን ይጠቅማል ወይ ?» የሚለዉን ጥያቄ ነው የሚያቀርበው። ከድርጅት በላይ የአገርን ጥቅም ያስቀድማል። በዚህ ረገድ ሰማያዊ መጠይቅ አለበት። ይሄ ሁለተኛ ነጥቤ ነው።

 

ሌላው ያስገረምኝ ነገር ቢኖር፣ ሶስተኛ ነጥቤ የማደርገው፣ የአንድነት ፓርቲ በባህር ዳር ሲያደርግ በነበረ ጊዜ፣ ማለት  ሁለት ወራት ገደማ በፊት፣ ለምን ሰማያዊ  በአዲስ አበባ ሰልፍ እንዳልጠራ ነው። ወይንም ደግሞ አንድነት በአዋሳ፣ ድረደዋ በመሳሰሉት ከተሞች ወደፊት ሰልፎች ለማድረግ ባሰበበት ወቅት፣ በአዲስ አበባ ሌላ ሰልፍ ስለማይኖር፣ ያኔ ለምን ሰልፍ እንደማይጠራ ነው።  ለምን ቢያንስ ፣ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተላበሰ፣ ፕሮፌሽናል፣ አክብሮት፣ ለአንድነት ፓርቲ አሳይም ? ለምን አንድነት ሊያደርግ ባሰበበት ወቅት  ሰልፍ ይጠራል ? ባልጠፋ ጊዜ ለምን በዚህ ወቅት ሰማያዊ ጣልቃ ይገባል ? ይህ በአንድነት ፓርቲ ላይ፣ በአገር ዉስጥም ሆነ በአገር ዉጭ ባሉ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ንቀት እንዳላቸው አያሳይምን ? «ሰማያዊዎች የሚታገሉት አገዛዙን ሳይሆን አንድነትን ነው» የሚል ስሜትስ ሰዎች ቢኖራቸው ያስገርማልን ?

 

እንግዲህ ለማጠቃለል ይሄን እላለሁ። ሰማያዊዎች በዚህ ረገድ ትልቅ ስህተት እየሰሩ በመሆናቸው ልብ ይገዙና ቆም ብለው ያስቡ ዘንድ እመክራለሁ። እላለሁ። የአንድነት ፓርቲ ትልቅ መሰረትና ድጋፍ ያለው ድርጅት ነው። አንድነትን ለመደፍጠጥ አስብው ከሆነ፣ የራሳቸው እግር ላይ እንደሚተኩሱ ማወቅ አለባቸው። የአንድነት ፓርቲ የሚያራምደው የሰለጠነ ፖለቲካ የማይመቻቸው፣ «የአገርን ችግር ለመፍታት፣ አንድነት ከኢሕአዴግ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ» ማለቱ ያበሳጫቸው፣  በዉጭ ያሉ ጥቂት ጽኝፈኞችና አክራሪዎች ፣ አንድነት ፓርቲ ተዳክሞ፣  ሰማያዊ ፓርቲ አይሎ እንዲወጣ ከመፈለጋቸው የተነሳ፣ ሆይ ሆይ ፣ እንደሚሏቸው ይገባኛል። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ አገራችን የምትፈልገው እንዲሁ በስሜት የመጋለብ ፖለቲካን ሳይሆን፣ ሕዝቡን በአራቱም ማእዘናት የሚያደራጁ፣ ብስለትና እርጋታ የተሞሉ አመራሮች ያሏቸው፣ በሚስማሙባቸው ጉዳዮች አብሮ ለመስራት የተዘጋጁ፣ የሚከባበሩና የሚቻቻሉ ድርጅቶችን ነው። የጀብደኝነት ፖለቲካን ሕዝቡ አይፈልግም። «እኔ ብቻ ነኝ የማወቀዉ» የሚል ግትር ፖለቲካ ቦታ አይኖረዉም።

 

 

የሁለት መቶ ሁለት ነፍስ የታደገ ማስተዋል –ማህበራዊ ኑሮንም ያዳመጠ ብልህነት። (ከሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 17.04.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
«ማስተዋልን ገንዘቡ የሚያደርግ፣ በወርቅና በብር ከመነገድ ይልቅ በእርሷ መነገድ ይሻላልና። ከቀይ ዕንቁም ትከብራላች፤ የተከበረም ነገር ሁሉ አይተካከላትም። በቀኛዋ ረጅም ዘመን ነው፣ በግራዋም ባለጠጋነትና ክብር። እርስዋን ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት። የተመረኮዘባት ሁሉም ምስጉን ነው። እግዚአብሄር በጥበብ ምድርን መሠረተ በማስተዋልም አጸና። ምሳሌ ም.3 ቁ. 13 እስከ 19 »

PLTበቅድሚያ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አምንያን እንኳን ለ2006 ፀሎተ ሃሙስ አደረሳችሁ – አደረሰን። ልክ የዛሬ ሁለት ወር በዚህች ዕለት የሰማይ ታምር በማስተዋል ተገለጠ። ዓለምም ታደመ – በአጽህኖት በአንክሮ ተደመመ። የወያኔ ገዢ መሬትም ተደፈረ – በጎጥ የጎረና የዘበጠ አስተዳደሩም አፈረ – ተመዘነ።

ማስተዋል የሰማይ ጸጋ ነው። ማስተዋልን እግዚአብሄር አምላክ መርቆ ሲሰጠን እንድናስተውለው ነው። ማስተዋል „ማስተዋልን“ አብክሮ የሚጠይቅ መክሊትና ክህሎት ነው። ክህሎት ነው ያልኩበት ምክንያት ሰው በዕድሜው ተመክሮ ያገኛቸው ትምርቶች ተግባሩን መካሪ እንዲሆኑ መፍቀዱ ብቻ ሳይሆን፤ ከዕድሜ ጋርም በርካታ ባህሪያት እዬሰከኑ ስለሚሄዱ ማስተዋል የበለጠ እያማረበት እዬተዋበ ይሄዳል ለማለት ነው። ማስተዋልን የሰነቀ ግለሰብ፣ ድርጅት ወድቆ አይወድቅም፤ ጉዞው ሁሉ መጪ ነገሮችን አስቀድሞ ዬሚይበት መሳሪያ በመንፈሱ ስላለው የተግባሩ ትልም ሆነ መቋጫው አቅም ያለው እርግጠኝነትን የጠጣ ይሆናል። የፈለገ ዓይነት ያልተጠበቀ ሁኔታ ቢመጣም ይቋቋመዋል። ማስተዋል እኛ እንደምናስበው ለተለዩ ፍጥረቶች አምላካችን የሸለማቸው ሳይሆን ሁላችንም ያለን ሀብት ሆኖ፤ ግን ያላዬነው መሪ ሥነ – ምግባር ነው። ማስተዋልን „የማስተዋል“ የመቻል አቅም ግን ተለይቶ መቀባት ይመሰለኛል።

በማስተዋል የተመራ „ሰላማዊ እንቢተኝነት“ ካዬን ልክ ዛሬ ሁለት ወራችን ነው። „ሰላማዊ እንቢተኝነት“ ከባሩድ በስተቀር በማናቸውም በእጅ በገባ አምክንዮ ሊከወን ይችላል። ክወናው መስዋእትነቱን ሊያቀለው ወይንም ሊያከብደው ይችላል። የጀግናዬ የረ/ አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን ወይንም እንደ ሲዊዞቹ ረ/ አውሮፕላን አብራሪ አበራ ኃይለመድህን የማስተዋል ልክ መለካት ያለበተ እጅግ በዳበረ ማስተዋል የተከወነ መሆኑ ነው። ካለምንም ንብረት ውድመትና ካለምንም ህይወት ጥፋት ብቻ ሳይሆን የመንፈስ ጫና ሳይፈበረክ የተከወነ ጉልበታም ደፋር „የሰላማዊ እንቢተኝነት“ አብነት ነው። የታሪኩ ሂደት ልብ አንጠልጣይ ከመሆኑ ጋር ይህን ተከትሎ በአለማችን በጉልህ የቀጠሉ ተግባራትን ስንመለከት እውነትም እርምጃውና ጥበቃው የአምላካችን የመዳህኒተአለም ስለመሆኑ እንገነዘባለን። 202 ነፍስን በማስተዋል የታደገው ይህ ድንቅ ተግባር ዘመናትን ሊያሻግር የሚችል የብቃት ልቅም – ልቅናም ነው።

ከዬካቲቱ የብልሁ „ሰላማዊ እንቢተኝነት“ በኋላ በአውረፕላን ዙሪያ  ሰማይ ላይ ሆነ የብስ ላይ የተከሰቱ ተግባራት  የእሱን የማስተዋል ብቃት እኛ ካለን የማስተዋል ሃብት ጋር ፍተሻ እንድናደርግበት በሚገባ ያስተምራል። በተጨማሪም ዓለም በሁለት ረዳት አውሮፕላን አብራሪዎች መሃከል ያለውን ብቃትና የብልህነት ደረጃ እንዲገመግም በራሱ ጊዜ በፈቃደ እግዚአብሄር አቅም እዬተለካ ነው። እኔን ስትሞግተኝ የነበረች ባልደረባዬ „ አበራ ሊደነቅ ይገባል“ አለችኝ። ለነገሩ ለእሷም ማስተዋሉ ተገልጦላት።

 

ሀ. የጀግናዬን ማስተዋል የበለጠ የሚያብራራ፤ የሚያበለጽግ አጋዢ ሰሞንተኛ የሰማይና የምድር „እንቢተኝነት“

 

  1. ወርኃ መጋቢት —- እኔ እንደማስበው ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ „ማስተዋሉ“ ያሰቀረውን ዓለም አቀፍ እንግልት፣ ጥፋት፤ የመንፈስ ጭንቀት፤ የማህበራዊ ኑሮ ቀውስ፤ የፖለቲካ ትርምስ ማስተዋልን አለብን ባይ ነኝ። እኛ ብቻ አይደለም እያንዳንዱ ሰው ዓለም ዓቀፍ ድርጅትም። እኔ አስቀድሜ በጻፍኳቸው ጹሑፎች አንድ ነገር ተማጽኜ ነበር። „በአዎንታዊ“ እንድንመለከተው …. ይሄው የማላዥያ አውሮፕላን 26 ሀገሮች ቀንና ሌት  በአውስትራልያ በፐርዝ ውቅያኖስ ማሰኑ … ስንት ገንዘብ? ስንት ነርብ? ስንት ሴል? ስንት ጊዜ? ስንት ዕንባ ፈሰሰበት? ስንት ቤተሰብ ተበተነበት? ሳይንስን ያሸነፈ ጥረት ባተለ። እንዲሁም የቀዝቃዛው ጦርነት አካል ሆኖ ዓለምን እያመሰ ነው። ከሁሉ በላይ „ከሞቱ አሟሟቱ“ ይላል የቀደመው ብሂል፤ ዬሂደቱን ወጥ መረጃ ለመስጠት እንኳን ያላስደፈረ በመሆኑ ተሳፋሪዎች የደረሰባቸው አለመታወቁ ብቻ ሳይሆን፤ ዬታላላቅ ሳይንቲስቶች ጠበብት ሊቃናተ – ሙሁራን የትንበያ ሆነ የጥበብ አቅም ፈተነ – ገመደ።
  2. ወርኃ ሚያዚያ — ከሚዚያ መግቢያ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በጎረቤት ሀገር በጀርመን ታዋቂው የሉፍታንዛ አውሮፕላን ከቱርክ አዬር መንገድ በእጥፍ፤ ከሌሎችም የተሸለ ትርፍን የሚዝቅ ድርጅት፤ ለአብራሪዎቹ የሚከፈለው  ማህያ ጋር ሲነፃፀር አይመጥንም ሲሉ የኖሩ ኖረው በሚዚያ መግቢያ በ2014 ለተከታታይ ቀናት ሞተራቸውን ረ አድርገው ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ሉፍታንዛ ተጓዡን ሲያዘገይ እንኳን ድጎማ የሚያደርግ ሲሆን፤ ያ … ሁሉ በረራ ተጓጉሎ ቀጥ በማለቱ የጀርመን መንግሥት ስንት መዋለ ንዋይ ከሰረ?  ስንት ቀጠሮ ተሰረዘ? የሚችሉ ወደ ፈረንሳይ፣ ወደ ኦስትራሽ ፣ ወደ ሲዊዝ በመሄድ ተጨማሪ ጊዜና ገንዘብ አፈሰሱ። ይህ „የሰላማዊ እንቢተኝነት“ በዚህ መልክ የተካሄደው ጀርመን ተቃውሞን ለማሰማት ዴሞክራሲ ያለበት ሀገር ስለሆነ ነው። የእኛ ግን ሃሳቡን ማሰብ እንኳን አይቻልም፤ እንኳንስ እንዲህ ለተከታታይ ቀናት አውሮፕላን አቁሞ አመጽ ማካሄድ ቀርቶ። አግባብነት ያለው ጥያቄ በግል ለማቅረብ እንኳን ጋዳ ነው። ከዚህ አንጻር ፈቃደ እግዚብሄር በሁሉም አቅጣጫ ሰማይ ላይ ሆነ ምድር ላይ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥ ነገሮችን እዬፈጠረ ወጣቱ ፓይለት የወሰደውን  ውሳኔ፣ የማስተዋልና የብልህነት ብቃት በአዎንታዊነት እያበሰለው ይገኛል። ትርፍ!

 

ለ. የወያኔ መደፈር እልህና ቁጣ ተከታይ እርምጃ።

ይህን በሚመለከት ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ የተበራራ ቀዳሚ የማሳሰቢያ ጭብጥ አቅርቧል። ስለምን በሚስጢር ተያዘ ለሚለው እኔ እንደማስበው ከሆነ —

  1. የሲዊዝ መንግሥት ተጠይቆ አዎንታዊ መልስ እስኪሰጥ ድረስ መጠበቅ ግድ ይል ነበር። ፍርዱን ሊያከብድ የሚችል የወንጀል ክስ አስቀድሞ ወያኔ ቢያሳውቅ፤  የሲዊዝ መንግሥት „አሻም“ ሊል ስለሚችል፤ ምንም ያልተፈጠረ አድርጎ አለሳልሶ ለመስለብ ነበር የጫካው ተመክሮ – የመከረው። ግን ይህ አልተሳካም።
  2. ድርጊቱ ሲከወን በጓዳ ስላልነበር የክሱ መሰረት ተምታቶም ይሁን ቅጥፈት ተሸምቶ መቀነባበር ነበረበት። ለዚህም ወያኔ በቂ ጊዜ ያስፈልገው ነበር። ልክ ሄሮድስ መለስ ሲሞቱ እንደ ተሰራው ድንባስ ትእይንት ቀድሞ መዘጋጀት አለበት ወያኔ ገርድፎ ይሁን ሸርክቶ።
  3. የጀግናው የኃይለመድህን ተግባር ወያኔ ባላለመው፤ ባላሰበው፤ እጅግም ባልገመተው ነበር። ጥቃቱን ያደረሰበትን የመንፈስ ትርትርና ትርምስ መልሶ ለመቋቋም ገዢው ፓርቲ ወያኔ  አቅሙ አልነበረውም። ስለሆነም ወያኔ ትንፋሽ መሰብሰብ ነበረበት። የሚርገበገብ መንፈሱ ተግ ማለት ነበረበት። ደፋር እርምጃ ያስታጠቀውን መንፈሳዊ ቁስለት ለማገገም ጊዜ ማግኘት ለወያኔ በእጅጉ ያስፈልገው ነበር። አዬር ላይ የተወሰደው እርምጃ እንዲህ በግልብ፤ በግብታዊነት የተከወነ አልነበረምና። ሲዊዝ ከገባ በኋላ እንኳን ፎቶውን ለማግኘት አልተቻለም። ስለዚህ ይህን ለመሞገት ልጥፍና ዝግ መሳናዶ አስፈለገው – ወያኔ።

አስተዋዩ አውሮፕላን አብራሪ አበራ ሀይለመድህን መነሻውን፤ መድረሻውን ያወቀ፤ መሬት ላይ የሚጠብቀውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ ጠንቅቆ የተረዳ። ወቅት የሰጠውን ዕድልም ያላሾለከ የማስተዋል ፍሬ ነው። ክንውኖቹ ሁሉ የማስተዋል ማህጸነ – ሚስጢር ናቸው።

 

ሐ. ለቤተሰቦቹ እኔ እምለው።

ውጬ ሀገር የሚኖሩ የፖለቲካ መሪዎች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቾች ሁሉ አስከ 18 ዓመት እስር፤ የእድሜ ልክ እስር፤ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው አሉ። ይህ ወያኔ አቅሙን አለማዋቁን ነው የሚመለከተው እንጂ የሚያመጣው አንዳችም ነገር የለም። ስለዚህ የፈለገውን አይነት ክስ ወያኔ መስርቶ የሚፈልገውን አይነት ውሳኔ ቢሰጥ ወገኖቼ ቅጭጭ አይበላችሁ። ማስተዋልን ወልዳችሁ አሳደጋችሁ። ማስተዋሉ የሸለመው ደህንነት አለና አትስጉ – ለደቂቃ አደራ! ሲዊዝ እንደተፈለገ ተገብቶ የሚዛቅ ምንም ነገር የለም።

ይልቅ አራዊት ስለሆነ ወያኔ ለእናንተ ለራሳችሁ ጥንቃቄ አድርጉ። ጥቃት ሊሰነዝርባቸው የሚችሉ እጅግ በርካታ መስኮች አሉት። ግንኙነትን መወሰን፤ ከተገኘው ቤት አለመመገብ፤ የተገኘውን ሥጦታ አለመቀበል። በፖስታ የሚላኩ ነገሮችን ሁሉ በጥንቃቄ ማዬት ይገባል። በተረፈ „በማስተዋል“ ላይ የወያኔ ማናቸውም ዓይነት ፍርድ ሊያደርስ የሚችለው ምንም ነገር የለም። ከተጀመረ ጀምሮ ያለው የሂደቱ ጠረን ምላሽ ሆነ አዬሩም፤ እንዲሁም አካባቢውም፤ ተያያዥ ነገሮችም እርምጃውን – ውሳኔውን – ማስተዋሉን እንደ ታቦት የሚከበክቡ ናቸው።

አዬር ላይ ሳይቀር የጣሊያንና የፈረንሳይ አውሮፕላኖች እኮ አጀበውታል። ይህ በሰው ሃይል የተከወነ አይደለም። በሳምንቱ እትብቱ በተቀበረበት የተከናወነው ድንቁ የባህርዳሩ የመኢህድና የአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ቀድሞ የተሰናዳ ግን የጄኔቡን ድል ያጀበ ነበር። በጣም ዕንቁ መረጃ ነበር። ከዚህ ሰልፍ በኋላ የሁለቱ ፓርቲዎች ሁኔታስ …? ይህም ሌላ ታምር ይነግረናል። ዙሪያ ገባው በአባታችን በመዳህኒአለም ጥበቃ የሚደረግበት ክንውን ሰለሆነ ጉዳዩን ለፈጣሪ መስጠት ነው። የእውነት ወላጆቹም ቅኖች ናችሁ። እንደገና በማህበራዊ ህይወትን ያቆሰለ ቋሳ አልተከለም። አንድ ነፍስ አልጠፋም። ደም አላጋባም። የማህበራዊ ኑሮን ሥነ -ምግባር በቅጡ ያደመጠ ብልህነት- ልዕለ ምህረት።

 

መ. ባለቤት ስላልነበረው ወቅታዊው ሲዊዛዊ ዘገባው ትንሽ ልበል።

መቼም ጀግናዬ ኃይለመድህነ አበራ በጣም ያስተማረን ነገር ማስተዋልና ትርፉን ነው። ስለዚህ በእሱ ዙሪያ የሚፈሱ መረጃዎች ሁሉ እጅግ በጣም የጥንቃቄን ጥበቃ ይሻሉ። አሁን ሀገር ቤት ያለውን በማስተዋልና በጥንቃቄ መረጃውን ያቀበለን የጋዜጠኛ ተመስገን ዘገባ ዘርጋ አድርጋችሁ ስትመልከቱት „የጉዳዩን ደህንነት“ በሚገባ ጠብቆለታል። ስሜቱን ለመግለጽ እንኳን እራሱን ቀጥቶ በተረጋጋ ቀለማዊ ስክነት ነበር ዕይታውን የገለጸው። ወሸኔ ነው ማለፊያ ወንድምዬ።

ወደ ጉዳዬ ስመጣ አሁን ሲዊዝ ላይ ስላለው ሁኔታ መረጃ ያቀበለን  ዘገባ ባለቤት ቢኖረው መልካም በሆነ ነበር። ተጠያቂነት ሆነ ተመስጋኝነት ጥግ ይኖረዋል። ለማንኛውም ዘጋቢው ማን? መሆኑን ባላውቅም ሊስተካከሉ በሚገባችው ጉዳዮች ላይ ትንሽ ማለት ወደድኩኝ። ስለምን ነገም ሌላ ዘገባ ሊቀርብ ስለሚችል መስተካከል አለበት ብዬ ስለማምን። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/28770 መነሻዬ ይህ ነው።

 

በቅድሚያ ግን የተከበሩ(ችሁ) የመረጃውምንጭዘጋቢ(ዎች) አመሰግናችኋለሁ – የወያኔህልምመክሰሩን፤የወያኔህልም  ውሃበልቶትመቅረቱን፤የወያኔየበቀልቀጣይትልሙአከርካሪውእንኩትኩትማለቱን ስለነጋራችሁን ወይንም ስላበሰራችሁን እግዚአብሄር ይጠብቃችሁ። እግዚአብሄርም ይስጥልን። አሁን ወደ አስተያዬታዊ ማሳሰቪዬ።

 

1       በነገራችን ላይ ሚዲያ ላይ የሚወጣ ማናቸውም ዘገባ ባለቤት እንዲኖሩ የሚዲያ ህግ ያስገድዳል። ነገሩ የኃይልዬ ጉዳይ ሆኖ እንጂ እኔ እራሴ አላነበውም ነበር። የሆነ ሆኖ የእሱን ጉዳይ በባለቤትነት የሚከታተል ሰው ወይንም ቡድን የቆረጠ መሆን አለበት። ምንም ዓይነት ቅንጥብጣቢ ቅሬት ሊኖረው አይገባም። አቋሙ ግልጽና አንድና አንድ መሆን ይኖርበታል። ምክንያቱም በውስጡ ብዙ ነገሮች የተከተቡበት በአጽህኖት የቆረጠ ብልጹግ እርምጃ ነውና። እውነት ለመናገር የዘገባው እርእስ ነርብ ይበጥስ ነበር። „ኢህድግ“ ይህ ቃል ጀግናችን ለወሰደው ለድርጊቱም ክብር የሚመጥን አልነበረም። የተጎመደ ጉድ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ላይ ያለው ህብረ ብሄር ፓርቲ አይደለም። የአንድ ጎሳ ድርጅት ቲፒኤልኤፍ ነው። ይህ ደግሞ አለም ያወቀው ነው። ይህ ወጋ ጠቀም ያለ አገላለጽ እኔ በግሌ ፈጽሞ አይመቸኝም። ጎሰኝነት መርዝ ነው። ወያኔ ስለሆነ ሳይሆን ሌላም ጎሳም እድሉን ቢገኝ የሚያድርገውን ነው ዛሬ ወያኔ እዬፈጸመ ያለው ዕንባን የመርገጥ ተግባር። የህግ ሆነ የተፈጥሮ ጥሰት  መሰረቱ ይሄው ነው። አንድ ጎሳ ሥልጣን ከያዘ ጨቆነ ያለውን ይቀጠቅጣል፤ ተጨቆነ ያለውን ጥበቃ ያደርግለታል። አናሳዎችም ቢሆን ልክ ብዙ ቁጥር እንዳላቸው ይፈለጣሉ – ካለርህራሄ።

ይህ የሚመነጨው ደግሞ የዘር ፖሊሲዎቹ ከተነሱበት ከዞግ ማኒፌስቶው ነው። አንድ የጎሳ ድርጅት ወሳኝ የሆነውን የፖለቲካ ተቋማት በእጁ ካስገባ፤ ዜጎች በዜግነት በሐገራቸው የመኖር መብታቸው ይጠቀጠቃል። ዜግነት ዳር ደንበሩ ይጣሳል። የዜግነት መብት በግፍ ተጥቅልሎ ይጣላል፤ ዜግነት ይደፈራል። ዜግነት ዋጋው ይረክሳል – ይሰረዛል። ከዚህም ባለፈ ለዬጎሳው አጥር ተሰርቶ ግርዶሽ ይበጃል። ቅራኔውም እንዲፋፋም ሁኔታዎች ይመቻቻሉ።

ስለምን? ሥልጣን ላይ ያለው ገዢ ጎሳ ትንፋሹ ጥበቃ የሚያገኘው በዚህ ግጭት ውጤት ነውና። ሌላውን እያተራመሰ እሱ ንጹህ አዬሩን ለሽ ብሎ ይመገባል። አይደለም ሀገር ውስጥ ውጭ ሀገር ያለው የነፃነት ትግሉ ቤተሰብ በጠላታችን ላይ ተስማምተን፤ ነገር ግን ውስጥ ውስጡን ያለው መታመስ መስከን ያልቻለውም ለዚህ ነው። ይህ በግልብ ተሂዶ የሚደረስበት ሳይሆን፤ መሬት ዬያዘ የመንፈሳዊ ጥሪቶች አቅም በተጠና ሁኔታ መገንባትን ይጠይቃል። ድልዳል ያለው ተከታታይነት ያለው ተግባርን መከወን ይፈልጋል። ሳናውቀው እኛም የዚህ ኮስማና የጎሳ ፍቅር ሰለባ ስለሆን፤ እራስንም ታግሎ ማሸነፍ። የወያኔ ትልም ተጠቂ እኛ ብቻ ሳንሆን ዘመኑ እራሱ ሆኗል። አንዱን ዘለን ሌላው ላይ ስንደርስ፤ ቀጥ እንላለን። ምሳሌ በወያኔ አባገነንነት ላይ ተስማምተን ወደ ታሪክ ወይንም ወደ ሃይማኖት አሁን ደግሞ ወደ ፆታዊም እዬዘለቀ ነው ስንደርስ እራሳችን ከዋናው አስኳል ፍላጎታችን መንበር እናወርዳለን። ይህ ደግሞ ለጣሊያን የረጅም ጊዜ ትልም ላደረ ዬጎሳ ድርጅት ህይወቱና የሚፈልገውም ነው።

በጎሳ ማኒፌስቶ  የዘር አድሎ፤ የዘር ግለት፤ የዘር ፍልሰት፤ የዘር መፈናቀል፤ በዘር መጥቃት፤ የዘር የበታችነት፤ የዜግነት ዋጋ ዕጦት መታዬታቸው ግድ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ እዬታመሰችበት ያለው ይህ ነው። ወያኔ ይህን ማራገቢያ ይዞ ያፋፍመዋል። የደጋፊዎችም መደበኛ ተግባር ይኽው ነው። ስለዚህ የመሰረታዊ ችግራችን ምንጩ አናቱ ጉዳይ የጎሳ አስተዳደር ዘረኛ ፋሽስታዊነት ወይንም ሌሎችን በኃይል መጫን ማድቀቅ ነው። (Diskrimnation + rascism = TPLF) ስለዚህ የጀግና ኃይለመድህን ጉዳይ የሚታዬውም ከዚህ አንጸር ነው። «ረዳትፓይለትሃይለመድህንአበራንለማስመለስየኢህአዴግልኡካንበጄኔቫ» ብሎ ርእስ መስጠት አያስኬድም የተዘጋ – የታነቀ መንገድ ነው፣ ለጉዳዩ ፍትህ አሰጣጥ። ለነጻነት ትግሉም ቢሆን ቦንብ የማጉረስ ያህል እጅግ አስጊ አካሄድ ነው። ለብልሁ አውሮፕላን አብራሪም ከጉዳዩ ጋር ያሉ ተያያዥ አንቀፆችን ካል ይግባኝ ይገድላል። አውነት ለመናገር ለዚህ ሥልጡን – ንጡር ድርጊትም እርእሱ ውስጥ ያለው ለወያኔ የህብረ ብሄር ፓርቲነት እውቅና መስጠት የተገባ ፈጽሞ አይደለም። ለቀጣይ ትግላችንም በዚህ መስማማት ካልቻልን የትም አንደርስም።

ለማንኛውም ጉልበት ሊሰጡ የሚችሉ (Siwiss Criminal Cod (STGB) Art. 173, 174, 177, 261)  እነዚህአንቀፆችወያኔንበፍርድአደባባይሲዊዝላይሊሞግቱትየሚችሉናቸው። በእንግሊዘኛ እንዳለያቀርብኩት የህግ ባለሙያዎችለቃልቀርቶ ለአንድ ፊድልእንኳንያላቸውንየከበደየጥንቃቄ ዕይታስለምገነዘብነው “እኔ” ለሚለው አገናዛቢ ቃል „ለእኔ” ከእኔ” ተእኔ” „በእኔ“ አንዲት  ፊደል ከፊት ስትታከል የትርጉሙ መልክ ሆነ አቅጣጫ ይቀዬራል። ስለሆነም ባለቤት ነን ካልን፤ ለምንጽፋቸው ማናቸውም ነገር ሁሉ ጥንቃቄ ማደረግ ግድ ይላል። ሕይወትም ታሪክም ነው። ትርፍ የሚገኘው ከጠንቃቃነት ነው።

2      „ጀግና ሀይለመድህን በቤተሰብ እንደተጠዬቀ“ ዘገባው አመለክቶ ነበር። ይህ በ28.02.2014 የበርኑ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገልፆ ነበር። እኔ የሰላማዊ ሰልፉን ዘገባ ስሠራ መረጃውን ዘልዬ ነበር ሪፖርቱን ያጠናቀርኩት። ፖለቲካ ግርድፍ አይደለም ልም ነው። ደህንነት የሚባል ነገር አለ። ቤቱ ብቻ ሳይሆን ጓሮውና አካባቢው ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል። ለእንሰሳ አስተዳደር ይህን መሰል መረጃ ማቀበል ሆነ መቀለብ አይገባም። ጊዜውን ቢጠብቅ መልካም በሆነ ነበር። መጠበቅ – ማሸነፍ ነው።

3.     ውጭ ስለሚገኙ የህግ ባለሙያዎች በአሉታዊ አስተያዬት ዘገባው ነበረው። ቃሉን በትርጉም ላቃናውና እንዳለ ማቅረብ ስለሚከብደኝ። “ኢትዮጵያዊ የህግ ጠበቆች የሲዊዝ ጠበቆች ለጠዬቋቸው ጥያቄዎች አቅም ያነሰው መልስ እንደሰጡ።” ዘገባው ጠቁሟል። ይህን በሁለት መልክ ማዬት ይገባል።

3.1   መዘርዘር ባልፈልግም ጫና በሁሉም ላይ አለ። ይህን ጥሶ መውጣት መቻል መታደል ነው፤ ባይሆንም መብት ነውና ብዙ መጋፋት አያስፈልግም። የሥራ ክፍፍልም ስለአለ ለሥራው ቅርበት ያላቸው ወገኖች ተግተው በጀመሩት ይቀጥሉ ባይ ነኝ።

3.2  ወቀሳ ላይ ደፈር ብለን ከገባን ሁሉንም አካባቢ መዳሰስ ያስፈልጋል። ጉዳዩ የተፈጸመው ሲዊዝ ሆኖ በተመሳሳይ ቀን በ28.02.2014 ሁለቱም የኢሳት ስቲዲዮዎችና ሪፖርተሮች የተገኙት ኖርዎይ ነበር።

ፀሐፊ ገዛህኝ አበበ ከኖርዎይ እንደዘገበው ቅኒት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላና ጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ መገኘታቸውን ዘግቧል http://ecadforum.com/Amharic/archives/11253/ ሪፖርቱን ለኢሳት ያቀበለውም ጋዜጠኛ ደረጀ ስለመሆኑ አዳምጫለሁ። እኛስ ነው ጥያቄው? ማዳላት ጥሩ አይደለም።

 

ከዚህም ባለፈ “የሲዊዝ ሹሞኞቹ አክቲቢስቶች፤ የነፃነት ትግሉ ኤክስፐርቶች” አልነበሩም። ሁልጊዜም ታች ሆነው ሥራውን የሚጋፈጡትን ብቻ ነው ጉሮሯቸው እስከደርቅ ድረስ መፈክር ሲያስተገቡ ያዬሁት። እርግጥ የሰለጠነ መሳሪያና ታታሪ ቪዲዮ ቀራጭ አይቻለሁ። ሰላማዊ ሰልፉን ዬጠሩት ወገኖች ወንዝ ላይ፤ ዛፍ ጥላ ሥር፤ መንገድ ላይ ብቻ ከሆነ ቦታ በጋራ እንግዳችን እንቀበል ሲሉ መገኘት መልካም ነበር። ከሁሉም የላቀ ፈታኝ ጥሪ ነበር። ግን አልሆነም። ታሪክን ለሚጽፉት ይከብዳል። ስንት ቀንስ በትርጉም ተቃንቶ፤ ተሽፍኖ ሃቅን ከናንቦ ይዘለቃል?! እኔማ ያው ዬቤቴን የከረንትን እንዲሁም  የአንድነትን ናፍቆቶቼን ስለአገኘሁ በመንፈሴ ላይ ምንም ዓይነት ግልምጫም ሆነ ፍጥጫ በሹም ሳይደርስብኝ በሰላም ተግባሬን ከውኜ ነበር የተመለስኩት።

እርግጥ ኖርወዬ ጥሩ እረኛ አባት ስላላቸው እድለኛ ናቸው። ለመታገል የወደዱ ሁሉ ፍቅርና እቅፍ መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ተከታታይነት ያለው ቋሚ  ድርሻንም ለመወጣት ሆነ ለመታገል ይችሉ ዘንድ ተመርቀዋል። እኔም እማደንቀው አመራር ነው ኖሮይ ያለው። አጋጣሚ ሰጥቶኝም በ2009 የታህሳሱ የጂ20 ዓለም ዓቀፍ ስብሰባ ላይ ሄሮድስ መለስ ተገኝተው ስለነበር  ከኮፐን ሀገን የተቃውሞ ስልፍና ስብሰባ ላይ እናቱን ውስጡ ጽላቱ ያደረግ፤ ንቁ አሰባሳቢ እንዳላቸው ዓይኔ አይቷል፤ እንዴትም እንደሚደንከባከባቸው ተመልክቻለሁ። ያን ጊዜ አዎንታዊ ቅናትም ብልት አድርጎኝ ነበር የተመለስኩት። ዶር/ ሙሉአለም አዳሙ ወቅቱ ለሚጠይቀው የትግል መስመር አስቀድሞ የተሰናዳ ወርቅ ወንድም ነው። ለዚህም ነው  የትግል መስመሩ ሁሉ በእኩልነት እንደ ወቅቱ ባህሪና ይዘት በነፃነት ቋሚ አድማጭ ኖሪዎይ ላይ ያለው። አቅማቸውም ጉልበታም የሆነው።

የሆነ ሆኖ ለ28.02.2014 ነገር  ኃይለመድህን አበራ ግን ከዬትኛውም ቦታ የተፈጥሮ ጠረን ለኢሳትና ሆነ “ለኢሳት አክቲቢስቶቹ” ሲዊዝ ይቀርብ ነበር …. አስተካክሉ፣ እረሙ፣ ታዝበናችኋል እንላለን እኔና ብእሬ …. በስንት ወጨፎና ግርፋት ነው እኛ እንኳን ሥራ ያውጣው ብለን ሳንቀመጥ ሁሉንም ታግሰን እኔም ሆንኩ ብዕሬም እንዲሁም እምሳሳለት ጥንቁቅ ሰብዕናዬም እዬተረገጥን የምንታደመው —- እንኳንስ ፍቅርና ክብር፤ እልልታ በገፍ በሩን ቧ አድርጎ ፈክቶ የሚጠብቀው ኢሳት —- የእውነት መገኘት ነበረበት። ኢሳትም በስሚ ስሚ — ቀኑን አሾለከ —– ታሪክ ተከዘ።

4     የዘጋቢ ፊልሙም ጉዳይ የበለጠ ድንቅ ሊሆን የሚችለው ተከድኖ ቢቆይ ነበር። ሲዊዝ መኖር እኮ እጅግ ተዝቆ የማያልቅ ዕውቀት የሚሸመትበት ሀገር ነው። እጅ ስንሰጥ ወደ 8 ወር 300.00 የማይሞላ ወደ ሌላ ካንፕ ስንሸጋገር 400.00 መኖሪያ ፈቃድ ስናገኝ 960.00 ፍራንክ ለወር ይሰጠናል። ያው ከጤና ኢንሹራንሱና ከቤት ኪራዩ ሌላ። ደረጃ በደራጃ ኑሮን እንዴት መኖር እንደሚቻል በረቀቀ ሁኔታ ብልሆቹ ያስተምሩናል። ከካንፑ ውስጥ ልብስም በጣም በርካሽ ይሸጣል። በ1.00 በ5.00 የሲዊዝ ፍራንክ ወዘተ …. መንገድ ላይ ሆነ  ገብያ ላይ ቀለል ያለ እቃ ለያዘ ቅድሚያ ይሰጣሉ። ሐብታቸው – ደስታው – ድሎታቸው ልክና ደንበር አለው። እኛም ያስተማሩንን በመተግበር በራችን እስከ አንቃሩ ሳንከፍት ስሜታቸውን እዬተከተልን መረጃውን ብናቀብል መልካም ነው።

 

5.        ትእግስትን ገርገጭ ያደረገ አስተያዬታዊ ማሳሰቢያ – ለሲዊዝ የሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች።

 

- በሀገረ ሲዊዝ የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ መጠዬቅ ሆነ የማሳወቅ ጉዳይ በደብዳቤ እንጂ በኢሜል የሚታሰብ አይደለም። መልሱም በደብዳቤ መሆን አለበት። አይደለም እኛ ሲዊዞች ከህጋቸው በታች በታች ናቸው። ስለዚህ መጀመሪያ መጨረስ የሚገባነን ሳንጨርስ በተደጋጋሚ ከሥራዓት አስጠባቂዎች ጋር መጋጨት ለሁልጊዜ ለኢትዮጵውያን ሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ሊነሳ የሚችል ይሆናል። ተሳታፊውም ይቀራል። ይህ ትብስብስ ያለ ጉዳይ ፍርጥርጥ አድርጋችሁ ተወያይታችሁ መልክ ልታስይዙት የሚገባ ጉዳይ ነው።

- ጥሪው በኢሜል፤ በሁሉም ሆም ፔጆች፤ በኤስኤምኤስ በተጨማሪነት መጠቀሙ መሰረታዊ ነው።  በኢሳትና በፌስ ቡክ እንደምትጠቀሙት ሁሉ። በአንዱ መረጃውን ማግኘት ይቻላል።

- ጥረው ሲተላለፍ ባለቤት ሊኖረው ይገባል፣ ቋሚ የመገናኛ ቦታ መታወቅ አለበት፤ ተሳታፊ ከዋናው ባቡር ጠቢያ ወርዶ የትኛውን አውቶብስ፣ ትራም፣ እንደሚይዝ መብራራት አለበት፤ የሚወርድበት ስቴሽንም ሆነ በእግር የሚያስኬድ ከሆነም ግልጽ መረጃ ሊሰጥ ይገባል። የአድራሻ ለውጥ ሲኖር ሲቀዬርም በ አስቸኳይ በማናቸውም መንገድ ለተጠሪው በሙሉ መረጃ የማሳወቅ ግዴታ ነው። እኔ በግሌ የስልክ ቁጥር አያሰኜኝም። ደጅ ጥናት ስለማልፈልግ። የምፈልገው ትክለኛ ግልጽ መረጃ ወረቀት ላይ የተጻፈ።

- ተሳታፊውን በሙዑሉ አክብሮትና ፍቅር “እንኳን ደህና መጣችሁ” ሰልፉ ሲያበቃ ደግሞ “እግዚአብሄር ይስጥልን፤ በሰላም ያግባችሁ” መባል አለበት። የመንፈስ ስንቅ አይነት – ለቀጣዩ ጥሪ ምቹ ሁኔታም ማሰናዳት ያስፈልጋል። ለአንድ ሰላማዊ ሰልፍ ጊዜው ገንዘቡ አቅሙ ጤናውም አለ —- በጣሙን አብዝቼ የምጠይቀው – ድካሙን ከብክነት የሚያድን የተደራጀ አቅም፤ ብቃታዊ አመራር።

- ስብሰባም ሲጠራ ማስታወቂያው ይወጣል የሚገኘው የፖለቲካ ሰው ግን አይገለጸም። ለምን? አይገባኝም። ጭራሽም የመረጃ ፍሳት ሳይኖር ይቀራል። ለምሳሌ ኢንጂነር ይልቃል ሲዊዝ መጡ ጄኔባን ብቻ አይተው ተመለሱ። ቢሰማ ቢያንስ እዛው አካበቢ ያሉ ወገኖች መገኘት ይችሉ ነበር።

- በርን ማዕከላዊ ቦታ ከመሆኑም በላይ ፍቅር ናቸው እዛ ያሉ ወገኖች። ሁሉንም ቀዳዳ በተግባር እዬሸፈኑ ያሉትም እነሱ ናቸው። ለማናቸውም ኃላፊነት በቂ ተከታይነት ያለው አቅምም አለ። ስለዚህ የሲዊዝ የነፃነት እንቅስቃሴ በርንን ማዕከል ቢያደረግ መልካም ይመስለኛል። የሲዊዝ ዋና ከተማም ነው።

- ጠሪው በሌለበት ተጠሪው የመገኘት ይህም ያዬሁት ነገር ነው። ከዚህ በላይ የወቅቱን የሰልፈኛውን ሙቀት፤ ፍላጎት፤ ቁጣ ሊያስተናገድ የሚችል አቅም ሊኖር ይገባል። ኤክለፕተስ ዛፍ ፍሬ ሲያፈራ ቅርንጫፉ ፍሬውን የመሸከም አቅም ስለማይኖረው ይዘነጠላል። የሳውዲ ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ግልብጥ ብሎ ተወጥቶ ነበር በግምት ከ300 እስከ 400 ሊሆን የሚችሉ ቅኖች ነበሩ። ተሳትፎው ልባዊ ሀገራዊ – ፍቅራዊ ነበር። እኔ ሲዊዝ ውስጥ አይቼ አላውቅም። ግን ያን ፍል እንባ በሥርዓት መርቶ ለቀጣይ ኃይላፊነት በቋሚነት ለማቆዬት የሚችል የተደራጀ አመራር አልነበረም። በቀጣይ የረዳት አውሮፕላን አብራሪ ጉዳይ ጥሪ ቢኖር ለመሳተፍ እነዚህ ነጥቦች በአግባቡ ሊስተካከሉ ይገባል። በስተቀር ግን ለብክነት ጊዜ የሚሰጥ ሰው አይኖርም።

በመጨረሻ — ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ካሰኛችሁ የቀደምት አንድነቶችን በስተቀር ብሄራዊ ጉዳይን የማስተናገድ አቅም ያላቸው እንደ ሙንሽን፤ ኖርወዬ፤ ሲዊዲንና ፍራንክፈርት የዳበረ ልምድ ስላላቸው በዝግጃታችሁ ቅድሚ ምክር ጠይቁና እናንተ ካላችሁ ተመክሮ ጋር አጋባታችሁ ጥሪያችሁን አክብሮ የሚመጣውን ኃይል በብቃትና በፍቅር ብታስተናግዱ መልካም ነው። አልመለሰብተም ጨረስኩኝ።

 

በመጨረሻ – ለጀመርነው አጠቃላይ አቅጣጫ ጠላትን በስልት ሊረታ የሚችል ሥልጡን – ጥንቁቅ ዘገባዊ አቀራረብ ነበርው የነገረ ኃይለመድህን በወያኔ ጓዳ ያለውን ጭብጥ የጠቆመን የጋዜጠኛ ተመስገን ጥንቅር። እጅግ ለሚዲያ ሰዎች ይረዳልና ደግመን ብናነበው ምርጫዬ ነው ከትህትና ጋር። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/29045

 

እንደ መከወኛ። ናፍቆቶቼ የሀገሬ ልጆች ይሄውላችሁ በገባሁት ቃል መሰረት “የተስፋ ማህጸን” የመጀመሪያ ዝግጅትን በ10.04.2014 ደስ ብሎኝ ድልን እያሰላሁ  ሰራሁት። የተላለፈውን አርኬቡ ላይ አለላችሁ። ቀጣዩ ደግሞ በ27.04.2014 ይሆናል። እያሰባችሁ በዬ15 ቀኑ  በዕለተ ሃሙስ ከ15 እስከ 16 ሰዓት አዬር ላይ ከቻላችሁ፤ ካልቻላችሁ አርኬቡ ላይ አዳምጡ – ጀግና ፍለጋ ጋራ ሸንተረር ከምትጠብቁ ሲዊዝ ላይ የተገኘውን የጀግና ድጋፋዊ መንፈስ አዳምጡ በትህትና። www.lora.ch.tsegaye ወይንም Aktuell Sendung www.tsegaye.ethio.info።ይህንሊንክከአጀንዳችሁብትመዘግቡት አመሰግናለሁ። እኔአልመለሰበተም።የዘርፖለቲካናጦሱለጎረበጠውተቆርቋሪይህችን በመንፈሱ ሰሌዳ ማስቀመጥ ቀላሏ የቤት ሥራ ናትና። በተረፈ የጀግናችን ሁለተኛ ወር ምክንያት በማድረግ ጸልዩለት፤ በፌስ ቡካችሁ በቲተር አካውንታችሁ ላይ እሱን እሰቡት። ቀኑን ለእሱ ስጡት አሁንም ዝቅ ብሎ በሚለምን ትህትና። “ሰላማዊ እንቢተኝነትን በዝምታ የሞሸረ” የእኛ ልዩ ስጦታ ነው ረ/ አውረፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ።

 

መልካም የትንሳኤ በአል ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማንያን ተመኘሁ። እንዲሁም መልካም በጸሎት የመረዳዳት የመተሳሰብ ጊዜ – ይሁንልን። የወንድማችን፤ የልጃችን፤ የጀግናችን፤ የሽልማታችን ቸር ወሬ አምላካችን ያሰማን። አሜን!

 

 

የጀግና ተግባሩ መንበሩ!

የጀግና ውበቱ ተግባሩ!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ!

 

ይድረስ ለሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ቦርድ አባላት –”ለእውነት አብረን እንቁም”

$
0
0

deb

የዛሬ ጽሁፌን በግል ለእናንተ የቦርድ አባላት እንዲደርስ ያደረኩት በምክንያት ስለሆነ ትንሽ ከታገሳችሁኝ አብራራለሁ። አስቀድሜ ግን ይኽን ወንድማዊ ጥሪ ለመላክ ሳስብ ከናነተ አውቃለሁ በሚል በመመጻደቅና በትምክህተኝነት ተነሳስቼ እንዳልሆን እንድትገነዘቡት እፈልጋለሁ። ከሁሉ በፊት ምስጋና መቅደም አለበት ብዬ ስለማምን በሱ ልጀምር።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የከሸፉት የህወሓት የተስፋ ቃላት (ከለምለም ሀይሌ ኖርዌይ)

$
0
0

የደርግ መንግስት ከወደቀ በኋላ በእግሩ የተተካው ህወሓት ይኸው ሥልጣን ላይ ከወጣ 23 ዓመት ሊሆነው ነው። ህወሓት ወደ ሥልጣን ሲመጣ ዲሞክራሲን አሰፍናለው፣ ሰብአዊ መብት አክብሬ አስከብራለው፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብትና እኩልነት ይከበራል፣ ልማት ይመጣል የኢትዮዽያ ሕዝብ ስደት ያበቃል፣ በቀንም ሦስት ጊዜ ይበላል የሚሉት ዋንኞቹ ነበሩ። እስኪ አንድ በአንድ እንያቸው።

lemlem

ለምለም ሀይሌ

1. ሰብአዊና ዲሞክራሲያኢ መብቶችን በተመለከተ ህወሓት ከጫካ ወጥቶ ከተማ እንደገባ ዋንኛ ጩኸቱ ይሄ ነበር። በመጀመሪያ አካባቢ ነፃ ጋዜጦችን ማሳተም፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በፖለቲካ ፓርቲ መደራጀት የመሳሰሉት ነገሮች ጥሩ ጅማሮ ያሳዩ ቢሞስሉም ብዙም ሳይቆይ ግን የህወሓት ትክክለኛ ባሕሪ መገለጥ ጀመረ። ጋዜጠኞችን ማሰርና ማንገላታት፣ ነጻ የሙያ ማኅበራትን ማፍረስ፣ ተቃዋሚዎችን ማሰር ብሎም በስውር ማስገደል፣ የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶች ቀስ በቀስ እየተከለከሉ መጡ። በተለይ ሁላችንም እንደምናውቀው ከምርጫ 97 በኋላ በቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ሰላማዊ ሰልፍና ከቤት ውጪ ስብሰባ ሙሉ ለሙሉ ተከለከለ። ጋዜጠኞች በግፍ ታሰሩ በርካታ ጋዜጦችም ተዘጉ። በምርጫ በኩልም ብናይ ባለፉት 23 አመታት ውስጥ ምንም አይነት ግልጽና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተካሂዶ አያውቅም። በ97 ትንሽ ገርበብ ብሎ የነበረውን በርና የሕዝብ ተስፋ ለማጨለም ህወሓት ከ24 ሰዓት በላይ አልፈጀበትም። ምርጫውን አጭበርብሮ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እስር ቤት አስገብቶ ከ200 የማያንሱ ሰላማዊ ዜጎችን ከገደለና ከ30 ሺህ የማያንሱ ወጣቶችን በተለያዩ እስር ቤቶች አጉሮ ካሰቃየ በኋላ ሀገሪቱ ይባስኑ ሙሉ ለሙሉ ወደ ኋላ ነው የተመለሰቸው።

እንደ ደርግ ጊዜ ዛሬም ዜጎች ፍርድ ቤት ሳይቀረቡ ይታሰራሉ ይገደላሉ። በማዕከላዊና በእስር ቤቶች ውስጥ ዜጎች ይገረፋሉ። ቶርች ይደረጋሉ። በተለይ ሰዎች ከፖለቲካና ከመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከሆነ የታሰሩት የሚደርስባቸው በደል ከፍተኛ ነው። በብርቱካን፣ በበቀለ ገርባ፣ በአንዱ ዓለም አራጌ፣ በእስክንድር በርዮት ዓለሙ፣ በውብሸት ታዬ ላይ የደረሱትና እየደረሱ ያሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ማየቱ በቂ ነው። በአጠቃላይ ለዲሞክራሲ አስፈላጊ የሆኑት ተቋማት ማለትም ነጻ ፍርድ ቤቶች የሉም፣ ነጻና ገለልተኛ የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም የለም ፣ በሕግ አውጪው፣ አስፈጻሚውና ተርጏሚ መካከል ምንም አይነት የሥልጣን ክፍፍል የለም። ሁሉም ነገር በሕግ አስፈጻሚው በዋናነትም በህወሓት ከህወሓትም በጣም ጥቂት በሆኑ ግለሰቦች እጅ ያለው ነው። በአጭሩ ሁሉም ነገር የሚሰራው በባለስልጣናት በጎ ፍቃድ እንጂ በሕግ የበላይነት አይደልም።

2. የብሔር ብሔረሰቦች መብትና እራስን ማስተዳደር ህወሓት ከአጋሮቹ ጋር ሆኖ ያጸደቀው ሕገ መንግስት አንቀጽ 39 ብሔረሰቦች እራሳቸውን እንደሚያስተዳድሩና ከፈለጉም እስከመገንጠል መብት እንዳላቸው ደንግጏል። ክልሎችም ብሔርን መሰረት ባደረገ ሁኔታ ተዋቅረዋል። ልክ ነው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይማራሉ። ነገር ግን በተግባር እንደምናየው ሥልጣኑን በማዕከል ጠቅልሎ የያዘው ህወሓት ነው። ለምሳሌ በእድገት ወደ ኋላ የቀሩ በሚባሉት ክልሎች ውስጥ በሶማሌ፣ ጋምቤላና ቤኒሻንጉል በሙስናና ሌሎች ሰበቦችን በማስቀመጥ የክልሎቹ መሪዎቹ ከቦታቸው ሲነሱ በቀጥታ የሚፈጸመው ከፌደራል መንግስት በሚሄዱት በአባይ ፀሐዬ በዶ/ር ሺፈራውና በመሳሰሉት ባለሥልጣናት ነበር። አሁንም እንደዚያው ነው። ለይስሙላ የክልሎቹ ምክር ቤቶች ተሰብስበው ቢወስኑም ስራው ግን አስቀድሞ ከመጋረጃው ጀርባ ነው የሚጠናቀቀው። ሌሎቹም ክልሎች ቢሆኑ ከዚያ የተለየ ነገር የላቸውም። ለምሳሌ የአቶ አባተ ኪሾ ከደቡብ ክልል ፕሬዚዳንትነት የተነሱትና የታሰሩት በእነ መለስ ዜናዊ ቡድን ነበር። አቶ አባ ዱላ ገመዳ ወደ ፌዴራል መንግስት ሲዛወሩ የኦ.ፒ.ዲ.ዮ. አባላትና ምክር ቤት ተቃውሞ ነበራቸው። በጉዳዩ ላይ መግባባት ስላልነበር በተደጋጋሚ ተሰብስቦ ነበር። በኋላም በእነ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በመተላለፉ እሳቸው ወደ ፌዴራል እንዲመጡ ተደረጎ ሟቹ አቶ አለማየሁ አቶምሳ ነበሩ የተተኩት። በፌዴራል ደረጃ ያለውን አወቃቀርና የሥልጣን ክፍፍል ብናይ ሁሉም ቁልፍ ቦታዎች በህወሓት ቁጥጥር ናቸው።

ባለፉት 21 አመታት ውስጥ የጠ/ሚ ቦታ ከህወሓት እጅ ወጥቶ አያውቅም። አሁንም ለይስሙላ አቶ ሀይለማሪያም ይቀመጡ እንጂ ስልጣኑ ያለው በህወአቶቹ በእነ ደብረጽዮን እጅ ነው። የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርነቱም ቦታ በመሀል ላይ ለ2 አመት ያህል በአቶ ሀ/ማሪያም ከመያዙ ውጪ አሁንም በህወሓት ቁጥጥር ስር ነው። በሠራዊቱ ውስጥ የኤታማዦርነት ቦታ ላለፉት 23 አመታት በህወሓት እጅ ነው። በጄነራል ማዕረግ ያሉት የሥልጣን ቦታዎች ከጥቂቶቹ በቀር በብዛት በህወሓት የተያዙ ናቸው። ከዚያም ወረድ ብሎ ያሉት የማዕረግ ቦታዎች ውስጥ የህወሓት አባላት ቁጥር ብዙ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ የደህንነት መሥሪያ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ በህወሓት ቁጥጥር ሥር ነው። የኦሮሞ፣ አማራና የደቡብ ወይም የሌላ ብሔር አባላት ቁጥር በጣም ጥቂት ነው ወይም ከነጭራሹ የለም በሚባል ደረጃ ነው ያለው። ሁኔታው በዚህ ብቻ አያበቃም ለክልል ፕሬዝዳንቶች አማካሪ እየተደረጉ ይሾሙ የነበሩት ከህወሓት ሲሆን በሁሉም የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ከህወሓት ቢያንስ አንድ ምክትል ሚኒስቴር አለ። የዚህ አላማው ደግሞ ከላይ የተቀመጡትን ከትግራይ ብሔር ውጪ ያሉትን ለመቆጣጠር ነው። በመሆኑም በአጠቃላይ ያለውን ነገር ስናይ ለስሙ በፌዴራል አወቃወር የተመሰረተ መንግስት አለ ቢባልም በተግባር ግን ሁሉ ነገር በማዕከላዊ መንግስት ብሎም በህወሓት ቁጥጥር ስር ነው ያለው። የብሔረሰብ ጥያቄ መልስ ስላላገኘ አሁንም በርካታ ብሔረሰቦች እራሳችንን እናስተዳድር ብለው ብቻ ሳይሆን እንገንጠል ብለው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ ነው። የህወሓትም የብሔሮች እራስን የመስተዳደር ቃልና ተግባር ሳይገናኙ 23 አመታት አለፉ።

3. ልማት ይመጣል፣ በቀን ሦስት ጊዜ ትመገባላችሁ ስደት ይበቃል. . . ይሄ ሌላው ህወሓት-ኢህአዴግ ለሕዝብ ተስፋ ከሰጣቸው ነገሮች አንዱ ፍትሀዊ ልማት ማምጣትና ድህነት መቀነስ ነበር። ነገር ግን የተወሰኑ መሠረተ ልማቶችን ከመገንባት ውጪ ኢኮኖሚው ከግብርና ወጥቶ ወደ ኢንደስትሪው ሽግግር አላደረገም። ዛሬም ከ83% በላይ የሚሆነው የሀገሪቱ ሕዝብ በግብርና ነው የሚተዳደረው የሚኖረውም በገጠር ነው። ከ80% በላይ የሚሆነው የሀገሪቱ ሕዝብ ዛሬም መብራት አያገኝም። ከ65% በላይ የሚሆነው ደግሞ ንጹሕ የመጠጥ ውሀ አያገኝም። ከ35% በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከድህነት ወለል በታች ነው የሚኖረው። አሁንም መንግስት ከ5 ሚሊዮን ለማያንሱ ዜጎች በየአመቱ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይለምናል። ዛሬ አብዛኛው ሕዝብ በቀን ሦስቴ መብላት አይደለም በቀን አንዴ ለመመገብ እየተቸገረ ነው።

በእርግጥ ሥርዓቱ ሀብታም ያረጋቸወና ከገዢው ፓርቲ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በአንድ ሌሊት ከድህነት ወጥተው ሀብታም እየሆኑ ነው። አልፎም ከሙሰኛ ባለሥልጣናት ጋር አብረው እየነገዱና እየዘረፉ በሀገር ውስጥም በውጪም እያጠራቀሙ ነው። ከመልካም አስተዳደር ችግር፣ ከድህነትና ከነጻነት ማጣት የተነሳ በየአመቱ በአማካይ ከ250,000 በላይ ዜጎች በሕጋዊና ሕገ ወጥ መንገድ ይሰደዳሉ። ብዙዎቹም በመንገድ ላይ ይሞታሉ፣ የውስጥ አካላቸው ይሰረቃል፣ ወደ አረብ ሀገራት የሚሄዱት ደግሞ የሚደርስባቸው በደልና ግፍ ብዙ ነው። ዛሬ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያና በሱዳን የስደተኞች ጣቢያ ይገኛሉ። የሀገሪቱ ኢኮኖሚና የንግድ ሥርአት የህወሓት ንብረት በሆነው በኤፈርት ተፅዕኖ ሥር ነው። የሀገሪቱን GDP 40% የሚያክል ካፒታል ይዞ ግዙፍ የንግድ ኢምፓየር መስርቶ እንደፈለገው ኢኮኖሚን እያሽከረከረው ይገኛል። በንግድ ሥርአቱ ውስጥ ፍትሀዊ ውድድር የለም።

በአጠቃላይ ከ23 አምታት በኋላም ሀገሪቱ ከ1983 በፊት እንደነበረችው በአምባገነኖች ስር ነች። የሕግ የበላይነት የለም። ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ የማይታሰብ ነው። የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና የመሳሰሉት መብቶች በገዢው ፓርቲ መልካም ፍቃድ ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው። በተለያዩ ብሔረሰቦች መካከል ዛሬም የሰው ሕይወት እስከማጥፋት የሚያደርሱ ግጭቶች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይከሰታሉ። የብሔረሰቦችም ሆነ የግለሰብ መብት አልተከበረም። ድህነትና ሥራ አጥነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉ ናቸው። ስንደመድመው በሁሉም አቅጣጫ የኢህአዴግ የተስፋ ቃላት ከሽፈዋል።

ለመላውየክርስትና እምነት ተከታዮችመልካም የትንሳኤ በአልይሁንላችሁ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

“በዩኒቨርሲቲው መቆየት ካልቻልኩ የፖለቲካ ፓርቲ እቀላቀላለሁ”–ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

$
0
0

dr dagnachew Assefa
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፤በተለያዩ የፖለቲካ መድረኮች በሚሰነዝሯቸው ጠንካራ ትችቶች ይታወቃሉ፡፡ ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት የነፃውን ፕሬስ ሁኔታ አስመልክቶ በሬድዮ ፋና በተዘጋጀው ውይይት ላይም ተሳትፈዋል፡፡ ጋዜጠኛ ናፍቆት ተስፋዬ ከዶ/ር ዳኛቸው ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ የገባበት ስለጠፋው የዩኒቨርሲቲ የኮንትራት ውል፣ ስለፍርድ ቤት ነፃነት፣“በኢትዮጵያ ውስጥ የመናገር ነፃነት የለም”— ስለማለታቸውና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በስፋት አነጋግራቸዋለች፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለማስተማር የተዋዋሉባቸው ሰነዶች በሙሉ መጥፋታቸውን ሰምቻለሁ፡፡ እውነት ነው?

ከዚህ ቀደም ባልሳሳት—ከአንድ ዓመት ከሁለት ወይም ከሶስት ወር በፊት ይመስለኛል “60 ዓመት ስለሞላህ ኮንትራት ያስፈልግሀል” ተብዬ የሁለት ዓመት ኮንትራት ፈርሜ ነበር፡፡ የዚህ ኮንትራት ግልባጭም ለእኔ የተሰጠኝ ሲሆን በተጨማሪም ለፍልስፍና ዲፓርትመንቱ፣ ለዲኑ ቢሮና ለምክትል ፕሬዚዳንቱ እንዲሁም ለፐርሶኔል ቢሮ በአጠቃላይ አምስት ቦታ ተላከ፡፡ ሆኖም አምስቱም ደብዳቤዎች ሊገኙ አልቻሉም፡፡ ሌላው ቀርቶ እኔም ቢሮ የነበረው ሊገኝ አልቻለም፡፡ እንዲያውም የዲፓርትመንት ኃላፊው፣ የኮሌጁ ዲኑና፣ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ቢሮም “ሲጀመርም ደብዳቤውን ስለማየታችን ትዝ አይለንም” የሚል መልስ ነው የሰጡት፡፡

ከዚያስ?

ከዚያማ ይሄ ሰውዬ ኮንትራት ሳይኖረው ከአንድ ዓመት በላይ አስተማረ እስከ ማለት ደረሱ፡
፡ እኔም በበኩሌ፣“ኮንትራትህ እድሳት ያስፈልገዋል ተብዬ ሂደቱ አራት ወር ስለወሰደ፣ ለአራት ወራት ደሞዜ ታግዶ ነበር፣እድሳቱ ሲያልቅ ደሞዜ መለቀቁ ምልክት አይሆናችሁም ወይ?” ብላቸው ያመነኝ ሰው አልነበረም፡፡ ፐርሶኔል ክፍሎች ግን ፍቃዱ ባይራዘምለት ከአራት ወር በኋላ ደመወዙን አንለቅም ነበር ብለው ተከራከሩ፡፡ ሆኖም የነሱንም ሀሳብ የሚያዳምጣቸው አላገኙም፡፡ አሁን ለጊዜው በዝርዝር ለማስረዳት ባልዘጋጅም፤በጥቅሉ ሰነዱ ባንዳንድ ሰዎች እርዳታ ፐርሶኔል ቢሮ ከሳምንት በላይ ተፈልጎ ተገኝቷል፡፡ይህ ኮንትራት ባይገኝ ኖሮ ምናልባት ከሥራ ለመሰናበት እደርስ ነበር፡፡ አሁን ግን የኮንትራቱ ውል በመገኘቱ ምክንያት እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ ማስተማር እችላለሁ ማለት ነው፡፡ የኮንትራቱ ውል ከመገኘቱ በፊት ግን ደብዳቤ ፅፈውልኝ ነበር፡፡

ምን ዓይነት ደብዳቤ?

“በአንተ እጅ ያለውም ሆነ ሌላው ክፍል የነበረው የኮንትራት ውል ስለጠፋ፣ የተሰጠህን የዓመት ፈቃድ ለጊዜው ይዘነዋል” የሚል፡፡ የእኔ ክርክር ጭብጥ ሁለት መንገድ የተከተለ ነው፡፡ አንዱ የኮንትራት ውሉ ሲሆን ሁለተኛው የዓመት ፈቃዱ ነው፡፡ የኮንትራት ውሉ ተገኘ፡፡ በመጀመሪያ የዓመት ቃዱን የያዙት የኮንትራት ውሉ ስለጠፋ ነበር፡፡ ወረቀቱ ሲገኝ ደግሞ የዓመት ፈቃዱ መለቀቅ ሲገባው አሁን ሌላ ሰበብ አመጡ፡፡ እድሜህ ስልሳ ዓመት ስለሞላና የጡረታ ሂደቱ በደንብ ተካትቶ ፋይልህ ውስጥ ስለሌለ፣ የዓመት ፈቃድህን ሰርዘነዋል አሉኝ፡፡ አሁን “ከሰስፔንሽን” ወደ “ካንስሌሽን” ሄደዋል ማለት ነው፡፡ የዓመት ፈቃዴን ባለፈው ሳምንት ነበር የምጀምረው፣ እሱን ተነጥቄያለሁ እልሻለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በላይ ማለት አልፈልግም፡፡

ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት በሬዲዮ ፋና ላይ በነፃው ፕሬስ ዙሪያ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡ እርስዎም በውይይቱ ላይ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ የውይይቱ ፋይዳ ምንድን ነው ይላሉ?

እንግዲህ አንድ የሬድዮ ጣቢያ ፕሮግራም ሲያዘጋጅ ፋይዳውን የሚያውቀው ሬዲዮ ጣቢያው ራሱ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከሰጡን ርዕስ ተነስቼ አንዳንድ ነገሮችን ለመገመት አያዳግተኝም፡፡ ርዕሱ እንግዲህ በኢትዮጵያ ያሉ የነፃው ፕሬስ ጋዜጦችና መፅሄቶች ምን ይመስላሉ? እንዴትስ ሊሻሻሉ ይችላሉ? የሚል ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ስመለከተው የግሉን (ነፃውን) ፕሬስ በተጠናከረ ሁኔታ መተቸት ይፈልጋሉ፡፡ ሁለተኛ ከመንግስት ጋር ያልተያያዝን ሰዎች በውይይቱ ብንሳተፍ፣ ትችቱ ይሰምራል የሚል አስተሳሰብም ነበራቸው፡፡ ሌላው እኔን በግሌ ብትጠይቂኝ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጆርናሊዝም እና ኮሚዩኒኬሽን ዲፓርትመንት በቅርቡ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ “በኢትዮጵያ ውስጥ የመናገር ነፃነት (Freedom of Speech) የለም” ብዬ ሽንጤን ገትሬ ተከራክሬ ነበር፡፡ ይህም በዩቲዩብ እና በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ስለተሰራጨ፣ ለዚህ ምላሽ በመስጠት ያንን የተሰራጨ ሃሳብ ለማምከን እቅድ የነበራቸው ይመስለኛል፡፡ እኔ በሁለት ፕሮግራሞች ላይ ነው የተሳተፍኩት፣ እነሱ ግን ቀደም ብለው የጀመሩት ይመስለኛል፡፡

ውይይቱ ላይ ተጋብዘው ነው ወይስ በራስዎ ተነሳሽነት?

የሬድዮ ፋናው አቶ ብሩክ ከበደ ጋብዘውኝ ነው የተገኘሁት፡፡

በውይይቱ ላይ“ዶ/ር ዳኛቸው ስሜታዊ ሆነው ነበር”የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ “የድሮ ስርዓት ናፋቂ” የሚል ትችትም ተሰንዝሮቦታል፡፡ የእርስዎ ምላሽ ምንድን ነው?

የስሜታዊነቱን ነገር ያመጡት እንኳን እነሱ ናቸው፡፡ ስድብና ዘለፋውን በመጀመር እነሱ ይቀድማሉ፡፡ “የድሮ ስርዓት ናፋቂ” ለሚለው በእውነቱ በናፍቆት ደረጃ ፍትህ ናፋቂ ነኝ፡፡ዴሞክራሲና የህዝባችንን ነፃነት ናፋቂ ነኝ፡፡ የዱሮ ሥርዓት ናፋቂ የሚሉኝ “አሁን ያለንበት ወርቃማው ጊዜ ነው” የሚሉ ዜጎች ናቸው፡፡ “ያለፈው ስርዓት ናፋቂ” የሚለው አባባል ሆን ብሎ ሰዎችን ለማሸማቀቅ የተፈጠረ ቃል ነው፡፡ በሌላ መልኩ የአሁኑ ስርዓት እኮ በጣም የተሻለ ነው ለማለት ነው፡፡ እኔ የዛሬ 40 ዓመት ወደ ኋላ ሄጄ ለማወዳደር የፈለግሁት አጠቃላይ ሥርኣቱን ሳይሆን የመናገር ነጻነትን በተመለከተ ርዕስ ብቻ ነበር፡፡ ይህንንም ለመናገር የዕድሜ ባለጸጋም ነኝ፡፡ “ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ” በሚባልበት ጊዜ አንድ ዓመት ዩኒቨርሲቲ ተምሬያለሁ፡፡ ያኔ የተሻለ የመናገር ነፃነት ነበር ብያለሁ፡፡ ይህንን አባባሌን አሁንም እደግመዋለሁ፡፡ “በአፄው ጊዜ የፈለግነውን ለመተቸት የዩኒቨርሲቲው ህግ ይፈቅድልናል፡፡ በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ መዲና ነበር፡፡ ዛሬ ግን ተነስተሸ አንድ ፖለቲካዊ የሆነ ጉዳይ ላይ ጠንከር ያለ አስተያየት ብትሰነዝሪ ከጸጥታ ኃይሉ የሚጠብቅሽ ችግር ይኖራል፡፡” ስላልኩኝ ነው “የድሮ ስርዓት ናፋቂ” የተባልኩት፡፡ ይሄ አይነተኛ የሆነ የካድሬዎች ማስፈራሪያና በነፃነት የሚናገሩ ሰዎችን ማሸማቀቂያ መንገድ ነው፡፡ እኔ እኮ የድሮ ትዝታ አለኝ፣ ልናፍቅም እችላለሁ፡፡

ለምሳሌ ከድሮው ስርዓት ምን ምን ይናፍቅዎታል?

ለምሳሌ የእንግሊዝ ፈላስፋ ኤድመን በርክ “Familiarity” የሚል ስለ ትዝታ ያነሳው ሀሳብ አለ፡፡ “ፋሚሊያሪቲ” ምንድነው? መተዋወቅ፣ ያሳለፍነው ትዝታ፣ትውስታ ማለት ሲሆን፤እንደ አርሱ አቀራረብ በአንድ ጉዳይ ላይ ስለተዋወቅን ብቻ መናፈቅ፣ የሰው ልጅ ባህሪና ፀጋ ነው ይላል፡፡ ገባሽ? እኔ የጥንቱን የክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ እናፍቃለሁ፣ የፖሊስ ኦርኬስትራንም እንዲሁ፡፡ ዛሬ አንድ ኪቦርድ አስቀምጠው የሚዘፍኑትን ከምሰማ የእነዚያን ኦርኬስትራዎች ሥራ ብሰማ እናፍቃለሁ፡፡ የፈረሱትን የድሮ ሲኒማ ቤቶች— እነ ሲኒማ አድዋን እናፍቃለሁ፡፡ የድሮውን የመድረክ ተውኔት እናፍቃለሁ፡፡ የድሮው የክብር ዘበኛ አለባበስ ከፈረሳቸውና ከነማዕረግ ልብሳቸው ትዝ ሲለኝ እናፍቃለሁ፡፡ እንዴ ብዙ ብዙ የምናፍቀው ነገር አለኝ— እሱን ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም፡፡ በሰፈሬ ሳልፍ አሁን የደረቀው ቀበና ወንዝ ከነሙላቱ ይናፍቀኛል፣ ድሮ ለምሳሌ ሆቴል ገብተን ክትፎ በ75 ሳንቲም “ቅቤ ይጨመር?” እየተባለ የምንበላው ይናፍቀኛ…..እንዴት ያለ ነገር ነው! ድንች በሥጋ ወጥ 15 ሳንቲም የነበረበት ጊዜ ይናፍቀኛል፡፡ የድሮዎቹ አስተማሪዎቼ ይናፍቁኛል፡፡ ታዲያ የድሮውን መናፈቅ ምን ነውር አለው? ምንስ አድርግ ነው የምባለው?

እርስዎም “የድሮ ስርዓት ናፋቂ” የሚለው አነጋገር የካድሬ ቋንቋ ነው ብለዋል፡፡ ምን ማለት ነው?

ካድሬዎች ሁልጊዜ ያለንበት ስርዓት ነው ወርቃማው ይላሉ፡፡ ያለፈው በጠቅላላው አይረባም ባይ ናቸው፡፡ ሲያስተምሯቸውም እንዲህ እንዲያስቡ ነው፡፡ እኔን “የድሮ ስርዓት ናፋቂ” ያለኝም ወጣት በዚያ ስለወጣ ነው፡፡ በጣም ልጅ ነው፡፡ ከዚህ ቀደምም በሌላ ፕሮግራም ላይ አግኝቼዋለሁ፡፡ ያን ጊዜ አቦይ ስብሀት ባሉበት በጣም ሀሳባዊ የሆነ፣ የአሁኑን ሥርዓት “ፍየልና ነብር የሚሳሳሙበት” ወርቃማ ጊዜ እንደሆነ አድርጎ ሲያወራ፣ “አንተ ልጅ እስኪ አቦይ ስብሀት ጋር ዝም ብለህ አንድ ሁለት ዓመት አሳልፍ፣ ያኔ ፖለቲካህ መሬት የረገጠ ይሆናል” በማለት መክሬው ነበር፡፡

በእርሶ እይታ አሁን ያሉት በጣት የሚቆጠሩ የግሉ ፕሬስ ውጤቶች ምን ይመስላሉ?

እኔ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ማስቀመጥ የፈለግሁት ጉዳይ ምን መሰለሽ? አንደኛ የአንድን አገር የፕሬስ ሁኔታ ለማየት ከፈለግሽ ወደ አወቃቀሩ ነው የምትሄጂው፡፡ አወቃቀሩ አሀዳዊ ነው ወይስ ብዝሀነትን ያስተናገደ ነው የሚለውንም ታያለሽ፡፡ በእኔ እይታ ከአፄ ኃይለሥላሴ እስከ ኮሎኔል መንግስቱና በአሁኑም ስርዓት ስትመጪ አወቃቀሩ አሀዳዊ ነው፣ አንድ ወጥና በአንድ አካል የሚታዘዝ ነው፡፡ዘጠና ሚሊዮን ህዝብ የሚሰማው ዜና ከአንድ ምንጭ የሚቀዳ ነው፡፡ ሁሉንም በሞኖፖል የያዘ ነው፡፡ ይሄ “Univocal” ይባላል፡፡ “Multivocal” የሚባለው ደግሞ ብዙ ውድድር ያለበት፣ በአማራጭ የተሞላ ዜና እና የዜና ምንጭ ያለበት ነው፡፡ አሜሪካ ስትሄጂ CNN አለ፣ ABC አለ፣ ሌሎችም መዓት የዜና አውታሮች አሉ፡፡ እዚህ ይህ አይነት አማራጭ የለም፣ ይመጋገባሉ እንጂ፡፡

ይመጋገባሉ ሲሉ እንዴት ነው?

ለምሳሌ የትግራይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው ወሬ ነው የሚያወራው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት አወቃቀሩ ተመሳሳይና የሚታዘዘው በአንድ አካል ስለሆነ ነው፡፡ ማንም ሰው ቴሌቪዥን ጣቢያ በግሉ የመክፈት መብትም የለውም፡፡ እንዲህም ሆኖ አሁን ትንሽ ለቀቅ ተደርጎ በጥቂቱም ቢሆን ትችትም እየተፃፈ ነው፣ ይህን አልካድኩም፡፡ “Freedom of speech” እና “Freedom of expression” ይለያል ያልኩትም ለዚህ ነው፡፡

እስቲ የሁለቱን ልዩነት ያብራሩልኝ?

ይኸውልሽ “Freedom of speech” ብዙ ነገርን ያካትታል፡፡ ለምሳሌ የመሰብሰብን፣ ማህበራት የማቋቋም፣ ለተለያየ የመረጃ ነፃነት እድል የማግኘትን (“exposure” የሚለው ይገልፀዋል) —– ያካትታል፡፡ በተለያየ አይነት መንገድ መረጃ ክፍት ሆኖና ተፈቅዶለት እንዲያገኝ እድል የሚሰጥ ነው – “Freedom of speech” ማህበራትን ማቋቋምና የመሰብሰብ ነፃነትም በጣም ጠቃሚ ነገሮች ናቸው፡፡ “Freedom of expression” ደግሞ መናገርን (የአንደበትን) ጉዳይ የሚመለከት ነው፡፡ ይሄ ኢትዮጵያ ውስጥ ይፈቀዳል ግን ህዝቡ መረጃ ለማግኘት አማራጮቹ አልሰፉለትም ወይም ህዝቡ ለተለያየ መረጃ “exposed” አይደለም፡፡ ይሄ ነው ልዩነታቸው፡፡ ዋናው ልዩነቱ “Freedom of speech” የሚባለው ነገር ካለ፣ የመረጃ ስብጥሩ ነፃ ነው፡፡ ዜጎች የፈለጉትን መረጃ የማግኘት መብት አላቸው፡፡

እስቲ ለ “Freedom of speech” ማሳያ የሚሆን ምሳሌ ይስጡኝ?

በጣም ጥሩ! ለምሳሌ የአባይ ግድብን ሁኔታ ውሰጂ ፡፡ መንግስት የግድቡ 30 በመቶ ተሰርቷል አለ፡፡ በቃ! እኛ ይህንን ይዘን ነው ቁጭ ያልነው፡፡ አንቺም ስትፅፊ የሚመለከተው አካል የነገረሽን ነው። አማራጭ የመረጃ ምንጭ ቢኖር እኮ 40 በመቶም 45 በመቶም ሊሆን ይችላል የተሰራው፡፡ አሊያም 15 በመቶም 10 በመቶም ሊሆን ይችላል፡፡ ዜጋው የመንግስት አካል የነገረውን እንጂ ሌላ አያውቅም፡፡ አንድ ግብፃዊ ግን እጅግ በርካታ የሬድዮ፣ የጋዜጣና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስላሉት፣ ስለ አባይ ከአንድ ኢትዮጵያዊ በብዙ እጥፍ የበለጠና የተሻለ መረጃ የማግኘት እድል አለው፡፡ ይሄ እንግዲህ ነፃ የመረጃ ምንጭ (Freedom of speech) ምን ማለት እንደሆነ ያሳያል፡፡ የፖለቲካ ፈላስፋዎች እንደሚሉት፣ የዜና አውታሩ የመረጃ ምንጩ በሞኖፖል ከተያዘ፣የህዝቡ አንደበት መናገሩ (Freedom of expression) ጥቅም የለውም፣ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውም ይሄው ነው፡፡

አሁን ያለው ስርዓት (መንግሥት) ራሱ ህግ አውጭ ራሱ ህግ ተርጓሚ ነው፣ ይህ ትክክል አይደለም ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ይሄ ምን ማለት ነው? ህግ አውጭና ተርጓሚው መሆን ያለበትስ ማን ነው?

ዋነው የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ይሄ ነው። “Separation of Power” የሚለው አስተሳሰብ የመጣው ለአንድ መቶ ዓመት ህግንና ነጻነትን በሚመለከት በተነሳው ጥያቄ ዙሪያ ነው፡፡ ይህንንም ለመረዳት መካከለኛው ዘመን ወደ ነበረው የሕግና የሥነ-መለኮት ፍልስፍና እንሂድ፡፡ በዚያን ጊዜ “ህግ የሚገኝ እንጂ የሚረቀቅ አይደለም” የሚለው አስተሳሰብ በሰፊው ተንሰራፍቶ ነበር፡፡

ማነው የሚፅፈው? ማነው የሚያረቅቀው?

በዚያን ወቅት ከላይ በጥቂቱ እንዳልኩት፣ መንግስት ህግ የሚያገኝ አካል እንጂ አርቃቂ አይደለም ብለው ያምኑ ነበር፡፡

እኮ ከየት ነው መንግስት ህግ የሚያገኘው?

ጥሩ ጥያቄ ነው! ከተፈጥሮ ነው ህግ የሚገኘው። ህገ-ተፈጥሮ (Natural Law) ይባላል፡፡ ከዚያ ነው የሚገኘው፡፡ በ15ኛውና በ16ኛው ክፍለ ዘመን ላይ መንግስት ትልቅ እየሆነ እየተስፋፋ ሲመጣ ህግ ማውጣት ግድ ሆነ፡፡ ሆኖም ግን የተወሰነው የአውሮፓ የማኅበረሰብ ክፍል “በፍፁም ህግ ልታወጡ አትችሉም፡፡ ራሳችሁ ህግ አውጥታችሁ ራሳችሁ ልትዳኙን አትችሉም፣ ነጻነታችን አደጋ ላይ ይወድቃል የሚል ክርክር ተነሳ፡፡

ከተፈጥሮ በግልፅ ይገኛሉ የሚባሉት ህጎች ምንድናቸው?

ጥሩ! ሰው መግደል አይፈቀድም – ይሄ ተፈጥሯዊ ህግ ነው፡፡ ሰው የመናገር መብት አለው፡፡ ያጠፋ ሰው ይቀጣል፡፡ የእኛም ፍትሀ-ነገስት ላይ ያሉት እኮ ከተፈጥሮ ህግ የተገኙት ናቸው፡፡ ህገ-ተፈጥሮ ለምሳሌ ወላጅ ልጁን ማሳደግ አለበት፡፡ ልጅ አባቱን አይመታም፡፡ በሰው ልቦና ላይ የተቀረፁ የተፈጥሮ ህጎች እኮ አሉ፡፡ በኋላ የግድ ህግ ማውጣቱ ሲመጣ፣ ህግ አውጭውና ህግ ተርጓሚው ይለያይ ተባለ፡፡ የእነዚህ አካላት መለያየት ግድ የሆነው ከመቶ አመት ጭቅጭቅ በኋላ ነው፡፡ እንግዲህ ከላይ እንዳልኩሽ የሴፓሬሽን ኦፍ ፓወር የመጣው ህግ አውጪውንና ህግ ተርጓሚውን በመለየት ለተቃውሞው ምላሽ ለመስጠት ነው፡፡ወደ ሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ ኢትዮጵያ ውስጥ የህግ የበላይነት ማለት ለምሳሌ አበራሽ በአበራሽ ጉዳይ ላይ ራሷ ወሳኝ ናት አይደለችም? ነው ጥያቄው፡፡ መልሱ መሆን የለበትም ነው፡፡ የህግ የበላይነት ማለት ሌላ ሶስተኛ አካል በተነሳው ጉዳይ ላይ ነፃ ሆኖ ይዳኝ ማለት ነው፡፡ አፄ ኃይለሥላሴ በራሳቸው ጉዳይ ራሳቸው ይዳኙ ነበር። ደርግ በራሱ ጉዳይ ላይ ይዳኝ ነበር፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፣አሁን ኢህአዴግ በራሱ ጉዳይ ላይ ይዳኛል ወይንስ አይዳኝም ብለሽ ብትጠይቂ፤ በእኔ እምነት ይዳኛል፣ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም። ህጉን ተመርኩዞ ነፃ ሆኖ የሚዳኝ ዳኛ የለንም እያልኩሽ ነው፡፡ ኢህአዴግ ጋዜጦችንና ሚዲያውን እንደያዘ ሁሉ፣ፍርድ ቤቶችንም ወጥሮ ይዟል፡፡

ፍርድ ቤቶቹ ነፃ አይደሉም እያሉኝ ነው?

ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ነፃ ሆነው እየሰሩ አይደለም፡፡ ትቀልጃለሽ እንዴ? ከብርቱካን ሚዴቅሳ ወዲህ በዚህች አገር ፍ/ቤት ላይ ማን ነፃ ሆኖ ትክክለኛ ፍትህ ሰጠና ነው፡፡

እስቲ ለዚህ ስጋት እንደ ማሳያ የሚያቀርቡት ካለ ይግለፁልኝ?

ለዚህ ማሳያ ላቅርብልሽ —- የፀረ – ሽብር ህጉን 90 በመቶውን ያመጣነው ከውጭ ቀድተን ነው ይላሉ፡፡

ከውጭ መቀዳቱ ምን ክፋት አለው ይላሉ?

ክፋት አለው ያልኩት እኮ እኔ አይደለሁም! እነሱው የቀዱባቸው አሜሪካኖችና እንግሊዞች ልክ አይደላችሁም በሚል ወጥረው ይዘዋቸዋል፡፡ ለምን ይመስልሻል? ዋናው ነገር ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ የእነሱ ህግ በጣም ስለሚያምር ለጥቁር አይገባውም ብለው ይመስልሻል? አይደለም! “በአገራችሁ ነፃ የሆነ ዳኝነት ስለሌለ ሰው ይጎዳል፣ መጠበቂያ የሌለው ጠብመንጃ ነው” ነው ያሏቸው፡፡ “እኛ እኮ ይህን ህግ ያወጣነው መጠበቂያ ስላለን ነው፡፡ ነፃ ዳኝነት በሌለበት ይህን ህግ እንዴት ሥራ ላይ ታውላላችሁ” ነው ያሏቸው፡፡ ማሳያዬ ይሄ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ማሳያ ትፈልጊያለሽ እንዴ?

ዶ/ር ዳኛቸው “መንግስትና ዩኒቨርሲቲውን ይዘልፋሉ፡፡ ነገር ግን በዩኒቨርሲቲው እያስተማሩ ደሞዝ ያገኛሉ”የሚል ትችት የሚሰነዝሩ አሉ፡፡ የእርስዎ ምላሽ ምንድነው?

ይሄ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው! ይገርምሻል እዚህ አስተሳሰብ ላይም ችግር አለ፡፡ “መንግስትና የህዝብ አስተዳደር” በሚል ርዕስ የዛሬ መቶ ዓመት በገ/ ህይወት ባይከዳኝ የተፃፈ መፅሀፍ አለ፡፡ ፀሐፊው ለአፄ ምኒልክ ምክር ያቀረቡበት አለ፡፡ በመንግስት ላይ አንድ ግድፈት ያየሁት የመንግስት እና የንጉሱ ንብረት ያልተለየ መሆኑ ላይ ነው ብለዋል – ገ/ህይወት ባይከዳኝ፡፡ የደጃዝማቾቹ ንብረትና የአገሬው ህዝብ ንብረት በትክክል መለየት አለበት ነው ያሉት፡፡ እነዚህ ደጃዝማቾችና ሌሎች ሹማምንት በደሞዝ መተዳደር አለባቸው ብለዋል፡፡ የመንግስት ንብረትና የንጉሡ ንብረት መለየት አለበት እኔ አሁንም የምፈራው፣ የፓርቲ ንብረትና የህዝቡ ንብረት አልተለየም ብዬ ነው፡፡ ኢህአዴጎቹ እኛ ቀጥረነው እኛው ስራ ሰጥተነው ይላሉ፡፡

አንድ ነገር ልንገርሽ – አፄ ኃይለ ሥላሴና ራስ ካሳ ከዝምድናቸው ባሻገር የቅርብ ወዳጆች ናቸው፡፡ ቀልድ ይቀላለዳሉ፡፡ ሁለት ታሪክ ነው የማወራሽ። በጅሮንድ ተክለ ሐዋሪያት ተክለማሪያም ከተፈሪ ጋር ተጣልተው ራስ ካሳ ጋር ይሄዱና “ስራ ስጡኝ” ይሏቸዋል፡፡ ራስ ካሳ ግን “አንተ የተፈሪ አሽከር ስለሆንክ ስራ አልሰጥህም” ይሏቸዋል፡፡ ራስ ካሳ “እርሶ ምን ነካዎት? እኔ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰራተኛ እንጂ የተፈሪ አሽከር አይደለሁም” ይላሉ ተ/ሐዋሪያት፡፡ “እኔ አሁን ስራ ለቅቄያለሁ– ለምንስ አሽከር ይሉኛል” ሲሉ ራስ ካሳን ይሞግታሉ፡፡ አየሽ መንግሥትና ንጉሥን ራስ ካሣ መለየት አልቻሉም። ኢህአዴጎችም ከዚህ አስተሳሰብ ስላልተላቀቁ ነው “እኛ ስራ ሰጥተነው፣ እኛ ቤት ሰጥተነው፣ እኛ ደሞዝ እየከፈልነው እኛኑ ይሳደባል ይዘልፋል” የሚሉት፡፡ እኔ ግን ስራ የሰጠችኝ አገሬ ኢትዮጵያ እንጂ እነሱ አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያ “እስከዛሬ በክፉና በደግ ጊዜ ሳናይህ እንዴት መጣህ አላለችም፣ እንኳን ደህና መጣህልኝ ልጄ” ብላ ነው ስራ የሰጠችኝ፤ይህንን አስረግጬ እነግርሻለሁ፡፡ ስለዚህ ስራ የሰጠኝና ደሞዝ የሚከፍለኝ ማን እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡

ከዚህ ቀደም ዶ/ር ዳኛቸው የብአዴን አባል ናቸው የሚል ነገር ተወርቶ በነበረበት ጊዜ ስጠይቅዎት “እንኳን የብአዴን የምወደው የኢህአፓ አባልም አልሆንኩም የየትኛውም ፓርቲ አባል የማልሆነው በአካዳሚክ ስራዬ ላይ ነፃነት እንዳላጣ ነው” ብለውኝ ነበር፡፡ ያስታውሳሉ?

በደንብ አስታውሳለሁ እንጂ!

ታዲያ በአሁኑ ወቅት በየፖለቲካ መድረኮቹ ላይ ፅሁፍ ያቀርባሉ፣ ትችቶችን ይሰነዝራሉ፡፡ ይሄ ነገር በስራዎ ላይስ ተፅዕኖ የለውም?

በጣም ጥሩ! ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ጋር በፍፁም ግንኙነት የለውም፡፡ በአካዳሚክ ስራዬም ላይ ተፅዕኖ አያሳድርም፡፡ እንዴት የሚል ጥያቄ ካነሳሽ ደግሞ፤ እኔ እንደ አንድ ሲቪል ግለሰብ ነው እየተቸሁ ያለሁት፡፡ ሁለት አይነት ምክንያታዊነት አለ- አንደኛው ግለሰባዊ ምክንያታዊነት ይባላል፤ ሁለተኛው ደግሞ ማኅበረሰባዊ ምክንያታዊነት (public reason) ይባላል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ማህበረሰባዊ ምክንያታዊነቴን ተጠቅሜም እየተቸሁ ነው፡፡ ሁለቱ አብረው ይሄዳሉ፡፡ እንደግለሰብ ደግሞ እያስተማርኩ ነው፡፡ በሙያዬም እያገለገልኩ ነው ማለት ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች በፍፁም አይጋጩም፡፡ ምናልባት ሊጋጭ የሚችለው የፓርቲ አባል የሆንኩ እንደሆነ ነው፡፡

የፓርቲ አባል ቢሆኑ የአካዳሚክ ስራውና የፓርቲ አባልነቱ የሚጋጩበትን መንገድ ሊገልፁልኝ ይችላሉ?

ማስተማርም ሆነ የፖለቲካ ስራ የሙሉ ሰዓት ስራ እንጂ የትርፍ ጊዜ ስራ ስላልሆኑ ሁለቱም ራሳቸውን ችለው መሰራት ያለባቸው ነገሮች ናቸው፤ ይጋጫሉ የምልሽ፡፡

ግን እኮ እንደ እርሶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲ የሚስተምሩ ሌሎች ምሁራን በአንድ በኩል እያስተማሩ ወዲህ ደግሞ ፓርቲ እየመሩ ነው፡፡ እንዴት ያዩታል?

እኔ በዚህ በፍፁም አልስማማም! ይሄ የራሴ አቋም ነው፡፡ በእኔ እምነት እነዚህን ስራዎች በአንዴ ስትሰሪ ከሁለቱ አንዱ ይጎዳል ብዬ ነው የምገምተው፡፡ ከበደችና ዘነበችን በአንዴ እወዳለሁ የሚለው ጉዳይ የማያስኬድ ፍልስፍና ነው፡፡ ከከበደችና ከዘነበች በጣም የምወደውን መምረጥ አለብኝ፡፡ አለበለዚያ አንዷን መጉዳቴ ግልፅ ነው፡፡ ይሄ ማለት ወይ ትምህርቱ አሊያም ፖለቲካው ጉዳት ይደርስበታል ማለት ነው፡፡ ይህ የእኔ እምነት ነው። በበኩሌ በዩኒቨርሲቲው ለመቆየት ካልቻልኩ ወደ አንዱ የፖለቲካ ፓርቲ እቀላቀላለሁ፡፡ እያስተማርኩ ግን የየትኛውም ፓርቲ አባል መሆን አልፈልግም፡፡

በአንድ ወቅት ለሰማያዊ ፓርቲ ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ወቅት ከአንድ የጋዜጣ አዘጋጅ ጋር ተጋጭተው ስለነበር የዛ ጋዜጣ መቅረፀ ድምፅ ካልተነሳ ንግግር አላደርግም ማለትዎን ብዙዎች አልወደዱትም፡፡ ዶ/ሩ ምሁር ሆነው ቂምን ለትውልድ ያስተምራሉ በሚል ተተችተዋልና ምን ይላሉ?

አንድና አንድ ነገር ልንገርሽ፡፡ አንድ ሰው ድምፄን አልቀዳም የማለት መብት አለው፡፡ ምሳሌ ልጥቀስልሽ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል በቅርቡ 50ኛ ዓመቱን ሲያከብር፤ ፕሮፌሰር ባህሩ ድምጽ መቅረጽ አትችሉም ብለው መቅረፀ-ድምፅ አስነስተዋል፡፡
እንደዚህ ኣይነት በርካታ ምሳሌዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ የእኔ ምን አዲስ ነገር አለውና ነው? እኔ በጎን እኮ አይደለም ይሄ ጋዜጣ እየሰደበኝ ስለሆነ መቀዳት አልፈልግም ያልኩት፡፡ ማንስ ቢሆን መሰደብ ይፈልጋል እንዴ፡፡ አሁን ያልኩሽ ጋዜጣ ወደፊትም ሊቀዳኝ አይችልም፡፡ በነገራችን ላይ ብዙ ሰዎች በዚህ ነገር ደስተኛ አይደሉም ላልሽው፤ እኔ እንዳንቺ እርግጠኛ ሆኜ ባልናገርም፤ ጓደኞቼ እንደነገሩኝ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አስተያየት ሰጪዎች በማህበረሰብ ሚዲያው በሰጡት አስተያየት፤ በዚህ ጋዜጣ ያለመቀዳት መብት እንዳለኝ ብቻ ሳይሆን ዘለፋቸው ከመስመር የወጣ መሆኑንም መስክረዋል፡፡ ቂም ለምትይው ቂመኛ አይደለሁም፡፡

እኔ እስከምረዳው ድረስ አንድ ሰው፤ በማስታወስና በቂም መካከል ያለውን ልዩነት በቅጡ ሊያውቅ ይገባዋል፡፡ በመሆኑም ማስታወስ ማለት ማቄም ማለት አይደለም፡፡ ስድስት ወርና አንድ ዓመት ያልሞላውን ጉዳይ ማስታወስህ ቂመኛ ያደርግሀል የሚለው አገላለጽ አግባብ አይደለም። አልቀበለውምም፡፡ ከዚህ በፊትም እንዳልኩት ሰዎች እንደዚህ ነህ፤ እንደዚያ ነህ ባሉኝ ቁጥር ራሴን ለመከላከል ምላሽ መስጠቱ ተገቢነቱን አላምንበትም፡፡

አዲስ አድማስ ሚያዚያ 11 ቀን 2006 ዓ.ም

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live