Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ለጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ብራቦ ብለናል (ከሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

የወያኔ ማናቸውም የፖሊሲ አይነት ለነፃነት ትግሉ ምኑ ነው?

መልስ —– ምንም!  ከሥርጉተ ሥላሴ 29.03.2014 ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ

1ይድረስ ለማከብርህ ወንድሜ ለጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም። ብራቦ ብለናል። ጥሩ መጠጋጋት ነው እንላለን እኔና ወዷ ብዕሬ። ወያኔን የምትደግፍበት አንድ ነገር መገኘቱ ሸጋ ነው – የሙያዊ ግዴታህ መንፈስ ካላስፈነጠረው። እኔ ደግሞ ይገርምሃል ወንድምዬ የዚህ ተቃራኒ ነኝ። በመጀመሪያ ነገር „ኢህአድግ“ የሚባል ነገር የለም። ኖሮም አያውቅም። ያለው ቲፒኤልፍ የትግራይ ሀዝብ ነፃ አውጪ ነው። ይህ „ኢህአድግ“ የምትለው ማላጋጫ ልባጅ ነው ወይንም ለጠፍ። ወይንም እቃ እቃ መጫወቻ የእንቦይ ካብ።  ለዚህ አቀብት ቁልቁለት የሚያስወርድ ነገር የለውም። በነቂስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚውቀው ጠሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። በአንተ በታላቁ የተግባር አክቲቢስት ይህ ዕውቅና ወያኔ ማግኘቱ እጅግ ዕድለኛ ነው። በተከታታይነት ጭራዋን ይዞ በትጋት አፍኖ በያዘው ሰፊህ ህዝብ እዬሰረሰራ የሚገባ መርዝ አሳምሮና አስማምቶ ይረጭበታል። ለቀፎው የወያኔ ሚዲያና የጎሳ ጥመኞች ጥሩ አልጋ አዘጋጅተኽላቸዋል። በደሉ እራሱ፣ አስከዛሬ የፈሰሰው ደምና ዕንባ ሁሉም አፍ አውጥቶ ቢናገር ፍርዱ ዬት ላይ ሊሆን እንደሚችል ማዬት በተቻለ። …. ለነገሩ ትክለኛው የህሊና ዳኝነት ያለው በህዝብ የህሊና አደባባይ ስለሆነ ልተወው።

 

የማከብርህ ወንድሜ ጋዜጠኛ ፋሲል እንዲህ የቤታችሁ ሥራና ውጥረት መፈናፈኛ ሰጥቷችሁ ነው የወያኔ የመሬት ፖሊሲ አስጨንቆህ ድፍት ብለህ ስትጽፍ ያደረከው? ለዛውም ለማይመለከተን፣ ላልመከርንበት፣ ብስል ከቀሊል ለሚለይበት፣ ላልወሰንበት፣ በባይታወርነት ለምነቀጠቀጠበት የኢትዮጵያን ሙሉ የክብር አካል ለሚፈቀፍቅ ፖሊሲ። አጀብ ነው። ከቶ እኛን ምን አገባን?!

ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል የሚል አንድ ብሂል አለ። አንድ ጊዜ ጠ/ ሚ ሃይለማርያም ደስአለኝ የሟቹን ሄሮድስ መለስ ዜናው ግዛታዊ ግቢ ሊረከቡ በነበረው የመሰናዶ ወቅት ጸሐፊ ተስፋዬ ገብሬ ድምጽ ሆነ ምስል በሚስጥር የሚቀርጽ ነገር በቤተመንግስቱ ወያኔ እንደሚያሰቀምጥ ማጠቀሻ መረጃ ጨምሮ ጽፎ ከረንት ከቤቴ አንብቤ ነበር።

2ታዲያ እኔ እህትህ ያን ጊዜ እኛን ምን አገባን?  ….. ብዬ ከሥር ጠንከር ያለ ትችት መጻፌን አስተዋሳለሁ። አሁን ደግሞ አንተ መሰሉን ነው የምትነግረን። ግልጽነትህ መቼም የሚገዛ ቢሆን ቀዳሚ ተሰላፊዋ እኔ በሆንኩ በነበረ። ለዚህ ከልብ ለጥ ብዬ አስግዳለሁ – አመሰግናለሁ። ውስጥህን ፈቅደህ ማሳዬትህ የማይገኝ ነው። ወደ ዋናው ጉዳዬ ስመጣ ግን  እኛ ስለ አይሁደ የመሬት ስሪት ምን ዶል አደረገን? ስለ በቀለኛው ባንዳ የፖሊሲ አፈጻጸም ሳይጠሩንስ የምን ዝንቁል ነው? ለምንስ መቀላቀል አስፈለገ?


ግን መሬት የኢትዮጵያ የእኛ የምንለው አለን?! አሱን አጥተን መስሎኝ የተሰደድነው። መቼም አንተም እንደምታወቀው 90 ሚሊዮን ህዝብ ልሰደድም ልሸፍትም ቢል አይችልምና አሁንስ መፈናፈኛ አጥቶ ከቀዩ ስለሚፈናቀለው፤ ሞት ለተፈረደበት ሚሊዮን ወገንህስ ታሰረኸለት – ተሰደኸለት – መሰደድህ አልበቃ ብሎ የመጨረሻውን ፍርድ ተቀብለኸበት እንዴት ነው ነገሩ ….. ወንድምዬ? እኔ እህትህ እንድ ሥርጉተ ሥላሴ መንፈስና አቋም ግን የወያኔ ማናቸውም ፖሊሲ በለው፤ ህግ በለው፤ የአፈጻጻም ደንብ በለው፤ ህግ አርቃቂ አካል – አስፈጻሚ ተቋም፣ የዳኝነት ውሎ ድል ምንጥርስ ቅብጥርስ ከነምናምንቴው  ወዘተ ምኔም አይደለም። ቆራጣ ጊዜ አላባክንም። እኔይቱ ላለተርፍበት እማባክናት ብጣቂ ጊዜ የለችኝም። ወያኔ ታጥቆ ስለተናሳበት የጥፋት፤ የንደት፤ የውርስና ቅርስ ፍልሰት ጥብቅናም ልንቆምለት ይገባል ባይም ነኝ። የ40 ዐመቱ ጉዞና ግብዕቱ መሰረቱ አንድ ነው። የቲፒኤልኤፍ የጎጥ ማኒፌስቶ። በቃ! ከዚህ የሚያመልጥ የሰናፍጭ ታክል ነገር የለም። ሁሉም የሚመነጨው ወያኔ ከተነሳበት አላማ ነው። ማናቸውም ህግ በለው ፖሊሲው መርዝ ነው። ከዚህ በተረፈ ማንፌስቶውን የፈጠረውን „ብርቱ ሚስጢር“ እንደ እኔ እንደ ደንቆራዋና ምስኪን ሳይሆን እንደ ታሪክ ሙሁርነትህ፤  እንደ ጋዜጠኝነትህ እንደ ታላቅ የሚዲያ አስተዳዳሪነትህና ኤዲተርነትህ እባክንህን እናትዬ  ብትን አድርገህ መንፈስ ሰሌዳ ላይ አደላድላና ብልቱን አውጣው። መልሱን ታገኘዋለህ። ባለፈም እንደ እኔ ላላ ማህይም ህሊና ዘባ ሲል ጎባጣውን አቃንተህ ትገራበታለህ።

 

4ወንድምአለም ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ ዕውን አለችን ነው ጥያቄው? ለመቶ አመት እኮ እየተቸበቸበች ነው? ከመቶ አመት በኋላም መሬቱ ዘር ስለመሰጠቱ መዳህኒአለም ይወቀው። ዛሬ እንዲህ ቅዱሳኑ ይከላተማሉ። ይሄውልህ ልጁህ ግልገሉን ይዞ መድረሻ አጥቶ እንዲህ ይንከራተትልሃል። ውሎ አድሮም ለትውልዱ ይህን ተከትሎ የሚመጣው ፍልሰትና ቀውስም ዕዳ ነው ልትሸከመው የማትችለው። ረመጥ እያደረ እዬፋመ እያገላበጠ የሚቀጣ ይህ ነው የተዶለተልህ።

ወይ ጉድ! ዘር እንዳይራባም እኮ ወያኔ መላ መቷል።   በታላቋ ትግራይ ህልም ደግሞ ከአፋር የደካ ጎንደርን ወሎም አለፍ ብሎ የአባይን ኣናት ጭምር ለመቆጣጠር እንዲያስችል ሌትና ቀን እዬተሰራበት ነው። መንገዱ ከጁቡቲ ትግራይ፤ ከሱዳን ትግራይ ጦፏል፤ እና …. ከአሲድ ጋር የሚያደራድረን ከቶ ምን ብናኝ  ነገር አለና?! — ቅድሚያ ነጻነት —- ንጹህ አዬር። ከሥጋት የጸዳ ባዕት —–

 

በወያኔ ፖሊሲ ለኢትዮጵውያን ለዛ መሬት ለተደፋበት ብዙኃን ተቆርቋሪ የሆነው የትኛው ተቋም፤ ድርጅት ከቶ የትኛው ነው? የትኛው ይሆን ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ  የሚሸተው? ሰንደቅን የሚያደምጥ ፍላጎትና ዝንባሌ እስረኛ እኮ ነው። – በጠቅላላ የወያኔ ፍትረት የጠላትነት ነው። ለእኛዎቹ እኮ መስቀል አደባባይ የታጠረ ነው። ስለ አፓርታይድ የመሬት ፖሊሲ እንደ ፍጥርጥሩ እሱ ይፈናጠርበት ጎጠኛው ወያኔ … ለምርጫም – ለበጎ ነገርም – ለድርድር የሚያበቃን ነገር ቅንጣት የለም? የውጭ ባዕዳን ፍላጎት አስፈጻሚ የባንዳነት ተልዕኮ እኮ ነው የወያኔ ተግባር።

እርግጥ ነው እንደማንኛውም የጥበብ ሰው ቀድመው የሚያሰጉትን ነገሮች ማመላከት የተገባ ነው። ይህን አከብርልኃለሁ። ነገር ግን ሰለ ነገ የመሬት ድርሻ ወይንም የባለቤትነት ይዞታ አስጨንቆህ ከሆነ የምንፈልገው አይነት የዴሞክራሲ ሥርዓት ሲዘረጋ በህዝብ ድምጽ አዎንታዊ ይሁን አሉንታዊ ምላሽ ያገኛሉ። ድምጽ የሚመራት ሀገር ስትኖርን። የማትቦጫጨቅ የእኩልነት እናት ምድር ስትኖረን። ለዚህ ቢያበቃንም ችግሩ የአዬለ ስለሆነ በቂ ጊዜ፤ የሰከነ ጥናትና ተግባርን ይጠይቃል። እፍ ብላህ ከምድረ ገጽ የምታበነው ችግር አይጠብቅም …. ዳገት ነው -።


እናቴ እመቤቴ ልዕለቴ የሚል እረኛ ሲኖረን፤ ይህ ዝበትና አድሎዊነት ሁሉ ታርቆ በሂደት መልክ ይይዛል። ይስተካከል። ፕሬዚዳንት ክርሰቲና ክሪሸርን የአርጀንቲናዋን፤ ጠቅላይ ሚኒስተር አንጅላ ሜርክልን የጀርመኗን፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ለሥልጣን ያበቀው ሥርዓቱ ስለተዘረጋ ብቻ ነው።

… የድካሙ የትግሉ አቅጣጫም ይህ መሆን አለበት እንጂ ይሄኛው ያኛው እያልን በሳቢያዎች ላይ የምናጠፋውና የምናባክነው ጊዜና ጉልበት ሊኖር አይገባም።  ዘላቂ የመፍትሄ ቁልፍ ሊሆን ከቶውም አይችልም። እንዴት ነው ነገሩ ኢትዮጵያ እራሷ አኮ እስረኛ ናት – የምን ቀልድ ነው!? ከወገብ በላይ ከወገብ በታች ብሎ ትግል የለም። የነፃነት እርቦ ሆነ ሲሶም የለም። ግድ የለህም ወንድምዬ እንስማማ። ምክንያትን እንፈልግ፤ የምክንያትን አቅጣጫ እንመትር በዛ ላይ አቅም የሚመትን ተግባር እንከውን …. ሳቢያን እንዝጋው – ቅርቅር አድርገን።

 

የማከብርህ ጋዜጠኛ ፋሲል እኔ በአቀረብካቸው የመሬት ይዞታ የፖሊሲ ትንታኔና አቅጣጫ ደንቆሮ ስለሆንኩኝ ባለሙያዎቹ እንደ አመጣጡ ይመክቱህ። ግን ጠላቴ ማን እንደሆን አውቃለሁ። የጠላቴ ፍላጎት እንብርት ምን እንደሆን ጠንቅቄ እረዳለሁ። ጠላቴ ለሀገሬ ኢትዮጵያ ያለውን ጠናና አመለካከት አሳምሬ እረዳለሁ። የበሽታው አጠቃላይ አስኳል ዬት ላይ እንዳለ ይገባኛል። በቀዶ ጥገናም ፈውስ እንደማይገኝ አምናለሁ። የመፍትሄው ቁልፍ ሂደት ወሳኙ አካል ምን ስለመሆኑም መንፈሴ በቂ ጥግ አለው።

በተጨማሪም አቅም ምን ላይ ሊፈስ እንደሚገባ ሆነ እንዲሁም ጉልበትና ሃይል ሊፈጥሩ የሚችሉ የመንፈስ ሃብቶች መሰናዶ  ምንና ምን  ሰለመሆናቸው ጠንቅቄ አውቃለሁ። ስለዚህም እላለሁ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ትንሳኤ የወያኔ ማንፌስቶና ፖሊሲ እሰከ ዝክንትል ጓዙ መነቀል አለበት የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ለቅርጥምጣሚ መላሾ የሥርጉተ መንፈስ አያደገድግም …. ኢትዮጵያ የመተንፈሻ ቧንቧዋን አፍኖ በጠላትነት እዬታገላት ያለው መጋኛ ወያኔ ሲወድቅ የቀደሙ ይሁን አሁን ያሉ፤ ወደፊትም ዘምን ሊፈጥራቸው የሚችሉ ችግሮች ሁሉ በመመካካር – በመደጋጋፍ – በመደማማጥ ፈቃዱ ሲሆን የተባረከው ቀን ሲመጣ ሁሉም ያለውን ይዞ እናቱን ከወደቀችበት ማጥ ለማውጣት በቅንነት ወስጥጡን ሰጥቶ የሚሳተፈበት ሥርዓት ሲፈጠር በጣም በእርግጠንነት ከኢትዮጵያውያን አቅምና ቁጥጥር በላይ የሚሆን አንዳችም ችግር አይኖርም።

 

የሚያስደስኝ በወያኔ ቅንጥብጣቢ መንፈሳቸው የማይደለል ጀግኖች ወጣቶች ኢትዮጵያ ላይ መኖራቸው። አይገርምህም ወያኔ ሲገባ ያልተወለዱ ልጆች የፈካ የተስፋ እርምጃ፤ የጎለበት አቅም፤ የራዕይ ጉልበት፤ የጸደቀ መንፈስ፤ የቁርጠኝነት ትንታግነት፤ የጥራት ልዕልና፤ የአስተሳሰብ ሥልጡነት፤ የመንገድ መረጣ ስልታማነት፤ የፈጠራ እርካብን – የአፈጻጻም ሂደቱ ለምነት፤ የሀገር ፍቅርና የአብሮነት ሰማዕትንት፤ እርግጠኝነትና በራስ የመተማማን ሙሉ ብቃት ሙቀቱ ከበቂ በላይ አጥጋቢ ነው። እነዚህ የትናንት እንቡጡች ወያኔ ሲገባ ታቱ ዥግራ ወይንም በእምዬ ትክሻ አንቀልባ የነበረቱ፤ ወይንም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የነበሩት ራህብ ላይ ሆነው፤ አንጀታቸው ጠግቦ ሳያድር  „ሰንድቅአላማ“ በተሳረበት ዘመን አድገው፤ ትምህር ቤት ዜግነታቸውን የሚሸረሽር ሥልጠና እዬተሰጣቸው፤ ነገር ግን ያነን ሁሉ አሸንፈው „አትከፋፍሉን፤ አትለያዩን፤ አንድ ነን፣ አንድ ህዝብ፣ አንድ ሀገር“ ይላሉ ለዚህም ይታሰራሉ – ይገረፋሉ – ይሰደዳሉ፣ ይገለላሉ- ይወቀሳሉ – ተነጥለው ይጠቃሉ። ግን መከራውን እያሸነፉ ወደፊት እዬገሰገሱ ነው —- ከዚህ መርዛማ የወያኔ ዶክትሪን አምልጠው እኛን በተግባር እያስተማሩን ይገኛሉ። የትውልዱ መንፈስ ይህ ነው አድምጡን ይላሉ ጆሮም ህሊናም ከኖረን …..

በዚህ በምታዬው የክልል ሽንሸና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ለመቅበር የተዶለተበት ነበር። ግን ኢትዮጵያዊነት ጠፍቶ የማይጠፋ የነገ ፍቱን መዳህኒት በመሆኑ የተጫነውን ድንጋይ ፈንቅሎ እዬፈካ በቀንበጦቻችን ታዬዋለህ …..

3

እኔ ውጪ ላላውም ወገኔ ቢሆን የተፈጠረበት ሚስጥር ነፃነት በመሆኑ ያገባኛል ባላበት ጉዳይ ሁሉ ተግቶ መሳተፉ፤ ሀገሩ ኢትዮጵያን በዬትኛውም አጋጣሚ ጎላ ብላ እንድትታይ መባተሉ፤ ክብሯ ሲነካ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ በቁጣ ከጥንፍ አስከ ጥንፍ መነሳቱ – ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲነጻጻር ሚዛን ላይ ልታስቀምጠው የማትችል የበቃ – ብቃትን ታያለህ። እርግጥ ስደትና ትግል ሰፊ ፈተና በመሆኑ የሚታገሉን በተርካታ ነገሮች በመኖራቸው፤ በተጨማሪም ከድሉ መዘግዬት ከሚመጡ ጭብጦች ጋር ያሉ ወጣ ገብ ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ማለቴ ግን ብርቱዎች ነን የእውነት።

ለዛውም አንተም እንደምታውቀው የፖለቲካ ትግል በትርፍ ሰዐታት ሰርተህ አይደለም ትርፍ የምታስገኘው። በመደበኛና በቋሚነት ተቀጥረህ የምትሰራው ሆኖ፤ ግን ነገር ግን ተስፋ የሚሰጡ ነገሮች ታያለህ። አንተ የምትደክምለት ሚዲያ ኢሳትም የዚህ ውጤት ነው።  በአጋጣሚ ስለሚዲያው ስለ ኢሳት ካነሳሁ በንጉሦች ንጉሥ ዐፄ ሚኒሊክ የልደት በዐል አስመልክቶ በተነሳው የሃሳብ በለው ድንበር ዘለል ጦርነት በነበራችሁ ውይይት በተጻራሪው ወገን የነበረውን ኮበሌ የሚመጥን ሰው አላቀረባችሁም ነበር። እባካችሁ የሚመክት ብቃትን በሃሳብ ማታገል አድማጭን ወደ በሰለ የሃሳብ መቀራርብ ያመጣልና ጥንቃቄ አድርጉበት። አቅም ማለት እኮ ሃሳብህን የሚሸምት ሰራዊት ማግኘት ማለት ነው።

 

እንድ መቋጫ ወንድሜ ጋዜጠኛ ፋሲል ሙሁራኖቹ ጭብጥን በጭብጥ ማህሏን እያስቀመጡ ይሟገቱህ።  እኔ ማሃይሟ ደግሞ በሀገር ወዳድነት ህልምና ናፍቆቴን ብቻ ስሜቴን አቅርቤ ሃሳቤን ገለጽኩኝ። ለነበረን ጊዜ ምስጋናዬ ከፍቅራዊ እክብሮት ጋር ላኩኝ። በተረፈ ክብረቶቼ ይሄውላችሁ ልጅ ፋሲል የማትመቸኝን ነገር ኮልኩሎ ለዛሬ ያቀድኳትን ጊዜ ተሻማኝ – እናንተንም አደከምኩ ከሳምንት በፊት ብቅ ላል ወስኜ ነበር — ለሰጣችሁኝ ጊዜ ውስጤን ፈቅጄ ሰጠኋችሁ። መልካም ጊዜ።

 

ከ አሲድ የሚገኝ ዘርም ፍሬም የለም!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ!

 

 

 


ስለመሬት መሸጥ መለወጥ -ተጨማሪ ማብራሪያ (ፋሲል የኔዓለም)

$
0
0

 

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ውድ ስርጉትና ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች የጽሁፌን ይዘት በደንብ ባለመረዳት ይመስል “ የምን ጠጋ ጠጋ” ብለውኛል። እኔና ኢህአዴግ ከምንጠጋጋ ጸሃይና መሬት ቢጠጋጉ ይቀላል። ወያኔን የምደግፍበት አንድ ነገር አገኘሁ ማለቴ ስላቅ ነው። ወያኔ መሬት አይሸጥም አይለወጥም ይላል። ይህን ያለው ከ20 በፊት ነው። ዛሬ ግን በሙሉ ልቡ ደፍሮ እንደዛ አይልም። ለምን? ያን ጊዜ የህወሃት ሰዎች ገንዘብ አልነበራቸውም። ዛሬ ግን የአገሪቱን መሬት ጠቅልለው የሚገዙበት ገንዘብ አላቸው። ዛሬ መሬትን በግል አዙር ብንለው መሬቱን እነማን እንደሚገዙት እናውቃለን። በ20 አመት ፖለቲካ ማሰብ የለብንም። ብዙ ህዝብ አገራችን ያለችበትን ሁኔታም የተረዳ አይመስለኝም። ዛሬ ገንዘቡ ኢፈርት በተባለው በህወሃት ድርጅትና በአላሙዲ ስር ነው ያለው። መሬት ወደ ግል ቢዞር እኮ የሚገዙት ሁለቱ ናቸው። እና 90 ሚሊዮኑን ህዝብ ባሪያ እናድርገው። ወያኔን ታግሎ መጣልና አዲስ መንግስት ማቋቋም ተገቢ ነው። አሁን መሬትን ወደ ግል አዙር እያልን ከጨቀጨቅነው ግን በደስታ ያዞርና ሌላው ህዝብ የዝምባብዌ ወይም የደቡብ አፍሪካ እጣ ይገጥመዋል።

 

አንዳንድ ሰው ስለ አዲሱቹ ካፒታሊስቶች የገባው አልመሰለኝም። ኢትዮጵያ እኮ የደቡብ አፍሪካ አይነት የኢኮኖሚ ስርአት እየገነባች ነው። በዘር ላይ የተመሰረተ ስርአት።

ለማንኛውም ለሌሎች አስተያየት ሰጪዎች የሰጠሁትን መልስ እዚህ ላይ እንዳለ አትሜዋለሁ። የአቋም ለውጥ ያደረኩ የሚመስላችሁ ካላችሁ ጽሁፌን እንደገና እንድታነቡት እመክራለሁ።

 

“ዳዊት ሰለሞን የተባለው ሰው በመሬት ዙሪያ ለጻፍኩት መልስ ሰጥቷል። አመሰግናለሁ። እኔ ከ20 አመት የኢህአዴግ የስልጣን ጊዜ በሁዋላ የተገለጠልኝ ሃሳብ እንደሆነ፣ ቀደም ሲል መሬት እንዲሸጥ እንዲለወጥ ስፈልግ እንደነበር የሚያስመሰል ሃሳብ አቅርቧል። ያነሳቸው ሃሳቦች ብዙም ጠናካራ ሆነው ባላገኘኛቸውም፣ ለትምህርት ይሆነን ዘንድ ትንሽ ለማለት ፈለኩ።

 

ቀደም ብየ እንደገለጽኩት መሬት ወደ ግል እንዲዞር ከሚፈልጉት መካከል ነኝ። ነገር ግን በዚህ መንግስት መሪነት የሚደረግን ክፍፍል አልደግፍም። ዶ/ር ታደሰ ብሩ ኢህአዴግ መሬት ወደ ግል መዞሩ ኢህአዴግን ቢጠቅመው ኖሮ እስካሁን ያደርገው ነበር በማለት መሬትን ወደ ግል ማዞር ለፖለቲካው እንደሚጠቅም ገልጿል። የዳዊትም ሃሳብ ተመሳሳይ ይመስላል። የእኔ ሃሳብ ደግሞ መንግስት መሬትን ወደ ግል እንዲያዞር ከመጠየቅ ፣ ስርአቱን ቶሎ አስወግዶ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የሚቋቋመው መንግስት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ያከፋልፍ የሚል ነው።

 

ኢህአዴግ  መሬት ለማከፋፈል ለምን አልፈለገም? ብዙ ሰዎች ህዝቡን ለመቆጣጠር ስለሚመቸው ነው ብለው ምክንያት ይሰጣሉ። ሊሆን ይችላል። ነገር ግን መሬት ወደ ግል ቢዞርም ኢህአዴግ ሌላ የመቆጣጠሪያ ዘዴ መፍጠሩ  እንደማይቀር ማወቅ አለብን።   ለእኔ ዋናው ምክንያት ኢህአዴግ የራሱን ካፒታሊስቶች እስኪፈጥር ጊዜ ለመውሰድ ስለፈለገ ነው። ባለፉት 22 አመታት ወያኔ በአንድ ዘር ላይ የተማከለ ካፒታሊስቶችን ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት አድርጓል። በስልጣን ላይ እስካለ ድረስም ይህንን ስራውን ይቀጥልበታል። ካፒታሊስቶች በቂ ሀብት አጠራቅመው አገሪቱን ሙሉ በሙሉ  የሚቆጣጠሩበት ደረጃ መድረሱን ወያኔ ሲረዳ ፣  ማከፋፈሉ አይቀርም። ምክንያቱም መሬት  ወደ ግል ቢዞር መሬቱን የሚገዙት እነዚህ ካፒታሊስቶች ይሆናሉና። ይህ አካሄድ ደግሞ የአገሪቱ መሬት በጥቂት ካፒታሊስቶች እጅ እንዲወድቅ ያደርጋል። እነዚህ ካፒታሊስቶች ደግሞ በአብዛኛው የአንድ አካባቢ ሰዎች ናቸው። ወደድንም ጠላንም አብዛኛው መሬት በእነሱ እጅ መውደቁ አይቀርም። መሬት በመንግስት ስር ከቆየ ግን አዲሱ መንግስት  ሲመጣ በቀላሉ ይነጥቃቸዋል። አዲስ መንግስት ከመምጣቱ በፊት መሬት ወደ ግል ቢዘር  ፣ የሚመጣው መንግስት ጦርነት የሚገጥመው ከእነዚህ ካፒታሊስቶች ጋር ይሆናል።

 

መለስ በአንድ ወቅት  “መሬትን ወደ ግል ብናዞር መሬቱን የሚገዙት እነማን እንደሆኑ እናውቃለን፣ ሌላው ህዝብ መሬት የሚገዛበት ገንዘብ የለውም ፣ ስለዚህ መሬት ወደ ግል ቢዞር በአንድ ብሄር እጅ ተመልሶ እንዲገባ ማድረግ ነው።” ብሎ ነበር። መለስ አንድ ብሄር የሚለው የፈረደበትን አማራ ነው። መለስ ባለፉት 23 አመታት ሲሰራ የነበረውም ካፒታሊስቶች በአብዛኛው ከራሱ ወገኖች ብቻ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው። በአሁኑ ሰአት መሬትን ወደ ግል ማዞር የአገሪቱ ሰፋፊ መሬቶች በእነዚህ ካፒታሊስቶች እጅ እንዲወድቅ ማድረግ ነው። ወያኔ ዘረኛ መንግስት ባይሆን ኖሮ ችግር አይኖርብኝም ነበር። ዘረኛ መንግስት ደግሞ ፍታሃዊ በሆነ መንገድ መሬት ወደ ግል ያዞራል ብሎ ማለት ራስን ማሞኘት ነው።”

 

ሥጋታችን “አክራሪ” ሃይማኖተኝነት ሳይሆን አክራሪ “አይማኖተኝነት” ነው

$
0
0

አዲስ ጉዳይ መጽሔት
adebabayblog@gmail.com;

ይህንን ጽሑፍ ለመጀመር ትርጓሜ የሚያስፈልጋቸውን ሐሳቦች ብያኔ በመስጠት እነሣለኹ። ሃይማኖት እና አይማኖት። በጥሬ ትርጉሙ ከወሰድነው ሃይማኖት “አሚን፣ ማመን፣ እምነት፣ አምልኮ” ማለት እንደሆነ የግእዝ እና የአማርኛ ቀዳማውያት መዝገበ ቃላት ደራስያን ደስታ ተ/ወልድ እና ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ይነግሩናል። ከዚያም አልፎ በዕለት ተዕለት ቋንቋችንና አነጋገራችን ካየነው ደግሞ እያንዳንዳችን የምንከተለውን እምነት እና ሃይማኖት በየስሙ እየጠራን “እገሌ የተሰኘው ሃይማኖት ተከታይ ነን” እንላለን።

“አይ” ደግሞ “የአሉታና የነቀፌታ ቃል ንኡስ አገባብ ሲኾን በቦታ፣ በኀላፊ፣ በትንቢት፣ ይገባል። ለምሳሌ “አይ ወዲያ፤ አይ በሉ” እንደሚባለው ነቀፌታን የሚያሳይ አገባብ ነው። “አይባልም፣ አይገባም፣ አይደለም፣ አይኾንም” የምንለውን ማስታወስ ነው።

ያዲሳባ ሰው አይጦም አይበላ፤

አያርፍ አይሠራ” እንዲሉ አለቃ ደስታ ተ/ወልድ።

ከ“ሃይማኖት” አሉታን የሚያሳይ “አይማኖት” የሚል ቃል መፍጠሬን ይመለከቷል። ሃይማኖተኛ እንደሚለው እምነት አልባ፣ እግዜር የለሽ (Atheist) መሆን ብቻ ሳይሆን ለሃይማኖት ጥላቻ ያለውን ሰው “አይማኖተኛ” (Antitheist) ብንል ያስኬደናል። ቃሉ ለምን እንዳስፈለገን ወደ ጽሑፉ ገባ ስንል እንገነዘባለን። በፈጣሪ መኖር የማያምኑ (Atheist የሆኑ) ብዙ ሰዎች አሉ። ግን ሃይማኖትና አማኒውን ላይጠሉ ይችላሉ። ሃይማኖትን እና አማኙን ለሚጠሉ ግን አይማኖተኛ (አንቲቴይስት Antitheist) የሚለው ይህ ቅጽል ገላጭ ይሆናል። እናብዛው ካልን “አይማኖተኛ፣ አይማኖተኝነት” ልንለው እንችላለን።

++++

ሃይማኖት ሥር እንደ ሰደደባቸው እንደማንኛቸውም አገሮች ሁሉ ኢትዮጵያም ስለ ሃይማኖት፣ ሃይማኖት በሕብረተሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ስላለውና ሊኖረው ስለሚገባው ድርሻ እና ከፖለቲካ ጋር ስላለው ግንኙነት ሰፊ ውይይት ይደረግበታል። ውይይቱ አዲስ የተጀመረ ባይሆንም በዚህ ዘመን ያለው የጉዳዩ አያያዝ ከሌሎቹ ዘመናት በተለየ ሰፋና ጠለቀ ያለ ትርጉም እየተሰጠው ነው።

አገራችን አዲስ መንግሥት እና አዲስ ሕገ መንግሥት ከተመሠረተባት ካለፈው 20 ዓመት ወዲህ በአገሪቱ ስላሉት እምነቶች፣ ከፖለቲካው ጋር ስላላቸውና ሊኖራቸው ስለሚገባው ግንኙነት ሰፊ መንግሥታዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። ይኸው መንግሥታዊ እንቅስቃሴ በሁሉም ዘንድ ያለው መረዳት አንድ ዓይነት ነው ማለት አይቻልም።

በሕገ መንግሥቱ ላይ መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፤ መንግሥታዊ ሃይማኖት አይኖርም፤ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም” ይላል። (ሕገ መንግሥት አንቀጽ 11)።

አንዱ በአንዱ ተግባር ውስጥ “ጣልቃ አለመግባት” ማለት ምን ማለት ለመሆኑ በራሱ መፍታታት ይኖርበታል። መንግሥት በሃይማኖት ላይ የተመሠረተ፣ አንድን እምነት የመንግሥት እምነት አድርጎ የሚቀበል አይሆንም፤ ሃይማኖትም በራሱ ተነሳሽነት “ሃይማኖታዊ መንግሥት ለመመስረት አይንቀሳቀስም”። በሳዑዲ አረቢያ ወይም በሌሎች የእስልምና አገሮች “የአገሪቱ ብሄራዊ እምነት እስልምና” ሆኖ እንደታወጀው በኢትዮጵያም “ብሔራዊ እምነት የሚባል” አይኖርም ብለን እንውሰድ። በተጨማሪም እምነቶች እንደ ፖለቲካ ፓርቲዎች የራሳቸውን መንግሥት ለማቋቋም አይሞክሩም። በእምነት ስም ለፖለቲካ ማራመጃነት ማንኛውንም ፓርቲ (ሃይማኖታዊ ፓርቲ) ማቋቋም  አይፈቀድም።

ሕገ መንግሥቱ “የሃይማኖት፣ እምነትና አመለካከት ነጻነት” ባለው ክፍል ውስጥ ደግሞ ተጨማሪ እምነት ነክ መብቶች ዘርዝሯል (አንቀጽ 27)። ሲጠቃለል፦ መንግሥት በዜጎች እምነት ነክ ጉዳይ ጥልቃ የማይገባ፣ ከሃይማኖት የራቀ፣ “ሴኩላር” መሆኑን ያስረግጣል።

የመንግሥት ሴኩላርነት፣ ሃይማኖትን እና መንግሥትን የመለየት ፍልስፍና ከራሳችን ያነቃነው ሳይሆን ከሌሎቹ አገራት የቀዳነው እንደመሆኑ ፍልስፍናው እና አስተምህሮው በሌሎቹም ዘንድ ለረዥም ጊዜ ሲሰለቅ የኖረ ነው። አልፍሬድ ስቴፓን የተባሉ ፀሐፊ ዲሞክራሲ በፖለቲካ፣ በመንግሥታትና በሃይማኖቶች መካከል ስላለው ግንኙነት ሲናገሩ በአራት ከፍለው ያስቀምጣሉ።

1ኛ. ሴኩላር የሆነ ይሁን እንጂ ለሃይማኖት ጥላቻ የሌለው መንግሥት አለ፤

2ኛ. ሴኩላር ያልሆነ (እምነት ነክ የሆነ) ይሁን እንጂ ለዲሞክራሲ ጥላቻ የሌለው መንግሥት አለ፤

3ኛ. ሴኩላሪዝም ያቆጠቆጠበት እና ሃይማኖት ምንም ተጽዕኖ የሌለበት ፖለቲካ አለ፤

4ኛ. ሴኩላር የሆነ ነገር ግን ለሃይማኖት ጥላቻ ያለውና በሃይማኖቶች እና በመንግሥት መካከል ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት እንዲመሠረት የሚያደርግ አስተዳደርና ፖለቲካ አለ። (RAY TARAS. “POLAND’S TRANSITION TO A DEMOCRATIC REPUBLIC: The Taming of the Sacred?”. THE SECULAR and THE SACRED NATION, RELIGION AND POLITICS. (2005: p. 143)።

+++

ፈረንሳይ “ሴኩላር” የመንግሥት አስተዳደር የምትከተል ብትሆንምና ባለ ብዙ እምነት አገር ብትሆንም ለብዙ ዘመናት በአገሪቱ የቆየውን የካቶሊክ እምነት እና ባህል ግን ከአገሪቱ ማንነት ላይ ቀርፋ መጣል አትችልም። የሌሎችን እምነቶች ባህል ለማክበር የፈረንሳይ-ካቶሊክ እምነትና ባህል መጥፋት የለበትም። በታሪክ አጋጣሚ ካቶሊካዊነት ያገኘው ሥፍራ አሁን ባለው የእምነት-እኩልነት ምክንያት ሊኮስስ አይችልም።

ብዙ እምነት ካላቸው እና “ሴኩላር” አስተዳደር እንከተላለን ከሚሉት መካከል ሕንድን በተጨማሪ ብናነሣ አገሪቱ የተለያዩ እምነቶች አገር ብትሆንም ሁሉንም አስማምታ በአንድነት ማኖር የቻለችው ግን ገና ከ50 ዓመት ወዲህ ነው። ፓኪስታንን እና ሕንድና ያለያያቸው የርስበርስ ጦርነት የተደረገውና አንዷ ሀገር ሁለት ለመሆን የበቃችው በእምነት ልዩነት መስመር ነው። ፓኪስታን እስልምናን፣ ሕንድ ደግሞ ሒንዱ እምነትን በዋናነት በመያዝ። ሒንዱ ዋነኛው እምነት ቢሆንም አሁን ሕንድ ባላት ለእምነቶች ሁሉ እኩል ዕይታ ምክንያት ባለ ብዙ እምነት አገር ተብላ ትወሰዳለች። ሕገ መንግሥታቸውም ይህንን ያሳያል።

ሕንድ ሌሎች እምነቶችን ትቀበላለች ማለት የሒንዱ እምነት በአገሪቱ ላይ የነበረውን የቆየ አሻራ ታራክሳለች ማለት አይደለም። የአገሪቱ ባህላዊ ማንነት በሒንዱነት ቢበየን የታሪክ አጋጣሚ መሆኑ እሙን ነው። የቆየ እምነት ነውና ታሪካዊ ድርሻው ከፍ ማለቱ የማይጠረጠር ነው። ማንኛውም ሕንዳዊ የፈቀደውን እምነት መከተል ይችላል። ሁሉም እምነት ግን በሕንድ ታሪክ ላይ እኩል ድርሻ የለውም።

ከስፔን እስከ ቱርክ፣ ከፖላንድ እስከ አሜሪካ፣ ሃይማኖት ትልቅ ሥፍራ በሚይዝባቸው ነገር ግን መንግሥታቱ “ሴኩላር” ናቸው በሚባሉባቸው አገሮች በመንግሥታት እና በሃይማኖቶች መካከል እኩያነት፣ መከባበር፣ መተጋገስ እና ሕጋዊነት አለ። መጠናቸው ግን አንዱ ከአንዱ ይለያል።

+++

ባለፉት አርባ ዓመታት በአገራችን ያለው የፖለቲካ እና የሃይማኖት ግንኙነት ብንመለከት “ሴኩላር” መሆኑን ሁለቱም መንግሥ ቢገልጹም “ምን ዓይነት ሴኩላር መንግሥት?” የሚለውን ግን የምንገነዘበው ከድርጊታቸውና ከተግባራቸው ብቻ ነው። አልፍሬድ ስቴፓን  ሐሳቦች መነሻነት ከተመለከትናቸው መንግሥቶቻችን ሴኩላር ብቻ ሳይሆኑ ለሃይማኖት በጎ አመለካከት በሌለው ሴኩላር አስተሳሰብ ላይ የተገነባ ፍልስፍና  የሚከተሉ “አይማኖተኞች” መሆናቸውን መረዳት እንችላለን።

ይህ 40 ዓመት በትክክል ያሳየን አንድ ሐቅ ደግሞ አገራችንን ያጠፋው ይኸው አይማኖታዊ አመለካከት እንጂ ሃይማኖት አለመሆኑን ነው። በቀይ እና ነጭ ሽብር፣ በግራና በቀኝ አስተሳሰብ፣ በቋንቋና በዘር ፖለቲካ ወዘተ ተቆራቁሰን አገራችንን ከማጥፋታችን በስተቀር በሃይማኖት ሰበብ ድሆችና ኋላቀሮች አልሆንም። የእርበርስ ጦርነቶች ሕዝባችንን ያጎሳቆሉት ለአገራችን ችግር ዋነኛ ምክንያት ተደርጋ በምትፈረጀው በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰበብ አይደለም።

መንግሥት ሴኩላር መሆኑ ተገቢ ሊሆን ይችላል። ሃይማኖትን “ሴኩላር” ማድረግ ግን አይማኖተኝነትን በሃይማኖት ላይ መጫን ነው። ሰዎች በምርጫቸው እምነት አልባ መሆን መብታቸው ነው። በግድ እምነታቸውን ማስጣል እና ሃይማኖት ያላቸውን ሰዎች በጎ ባልሆነ አመለካከት መመዘን አይማኖተኝነት ነው። አክራሪነትን እቃወማለሁ። አይማኖታዊ አክራሪነትን ደግሞ የበለጠ እቃወማለሁ። አገራችንን ሲያጠፋ በደንብ አይቼዋለሁና። በተግባር የተገለጸ ሥጋታችን “አክራሪ ኦርቶዶክስ” ሃይማኖተኝነት ሳይሆን አክራሪ “አይማኖተኝነት” ነው።

ይቆየን – ያቆየን

 ህ ጽሑፍ አዲስ አበባ ለሚታተመው የአዲስ ጌዳይ መጽሔት የተጻፈና በዚያም ላይ ለሕትመት የበቃ ነው።

ይድረስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት

$
0
0

 

ኤሎሄ! ቅዱስ! ኤልሻዳይ! አዶናይ! ያህዌ! ጸባዖት! ኢየሱስ! ክርስቶስ! አማኑኤል! በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ሥም! አሜን!

አቤቱ አባት ሆይ ከእኛ ወገን ለአንተ እናት ሆናህ በእሷ በኩል በሥጋ ትዛመደን ዘንድ በመረጥካትና ስለብዙዎች ልቧ (አእምሮዋ) ሐዘንን (ነብዩ እንደተናገራት ፍላጻዎችን) ሁሉ ያስተናግድ ዘንድ ባጸናሀት፣ ቅድስት፣ ንፅህትና ዘላለማዊት ድንግል በሆነች እናትህ ማሪያም ሥም ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እለምንሀለሁ! አሜን!

ብፁዕ አባታችን፡ ከዚህ በፊት የጻፍኩልዎት ደብዳቤ ይደረስዎት አይድረስዎት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ግን እንደደረሰዎት እገምታለሁ እኔ ለአንባብያን በማህበራዊ ድህረገፆች እንዲነበብ ባደርገውም በደብዳቤው መልዕክት የተሳቡ አንዳንድ ሰዎች የእኔን ፍቃድ ጠይቀው በቀጥታ በፋክስ እንላኩልዎት ነግረውኛል፡፡ ጉዳዩ ዛሬ ደግሜ ከማነሳው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ የበፊቱንም ደብዳቤ በድጋሜ አንባብያንም ይሁኑ እርሶም ማመሳከር ትችሉ ዘንድ ከዚሁ መልዕክት ጋር አያየዛለሁ፡፡ ከጉዳዩ መመሳሰል ባሻገር የወራቶቹም መመሳሰል ነገሩን በውል ላስተዋለው አስገራሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ወራት በመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የጾምና ጸሎት እንዲሁም የንስሃ መቀበያ ወቅት እንደሆነ ልብ እንበል፡፡ ልክ የዛሬ ዓመት በዚሁ የጾም ወቅት ተከስቶ የነበረ (እንደውም የዛሬ ዓመት በጌታ ሕማም መታሰቢያ ሳምንት በነበረው የጾሙ ጊዜ ነበር) ጉዳይ ዛሬም ተከስቶ ሳየው ተገረምኩ እናም ተመሳሳይነት ያለው መልዕክት በድጋሜ ለእርሶና ለቤተክርስቲያኒቱ የውጭ ግንኙነጽ ኃላፊ እንዲሁም ለትዝብት ለሕዝብ ማስተላለፍ ፈለግሁ፡፡ ይህ ጉዳይ የመልአከ መንክራት (መምህር)ግርማ ወንድሙን አገልግሎት ይመለከታል፡፡

ሰሞኑን በአቡነ ገሪማ መምህሩን አስመልክቶ እንደተጻፉ የሚያሳዩ ሁለት ተቃራኒ መልዕክት ያለቸው ደብዳቤዎች ለሕዝብ በማሕበራዊ ገጾች በመድረሳቸው የዛሬ ዓመት ተከስቶ የነበረው አይነት ወዥምበር በሕዝብ ዘንድ ፈጥረው ታላቅ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆነው ሰንብተዋል፡፡  የመጀመሪያው ደብዳቤ ከሰባት ወር በፊት እንደተጻፈ የሚያመለክት ሲሆን ደብዳቤው ለመምህሩ ዕውቅና የሰጠና አገልግሎታቸውንም ዓለም ዓቀፍ እንዲሆን የፈቀደ ሲሆን በቅርቡ በተመሳሳይ ፊርማና ማህተብ የወጣው ሌላ ደብዳቤ ደግሞ የበፊቱን በማጭበርበር የወጣ ብሎ የሚከስና የሚያወግዝ ነው፡፡

አሁን ጥያቄው የመምህሩ ችግር ወይንስ የእርሶና የፀሀፊው ሊቀ ጳጳስ ጽ/ቤት ችግር ነው የሚል ነው፡፡  መምህሩ በተጭበረበረ ማህተብና ፊርማ ሌላ ቦታ ያሰሩት ደብዳቤ ከሆነ በእርግጥም መምህሩ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ሆኖም ግን ከእርሶ ጽ/ቤት የወጡ ደብዳቤዎች ከሁኑ መምህሩን የሚያስጠይቃቸው አንዳች ጉዳይ አይታየኝም፡፡  ደብዳቤዎቹ ግን በተጭበረበረ ማህተብ የተጻፉ አይመስሉም፡፡ ፊርማውምና ቲተሩም  ቢሆን የሊቀ ጳጳሱ የራሳቸው እንደሆነ አናያለን፡፡ እነዚህ ተቃራኒ መልዕክት ያላቸው ደብዳቤዎች እንዴት በአንድ ሰው ፊርማ ወጡ ለሚለው የብዞዎች ግምት የጸ/ቤቱ እንደሆነ እንጂ የመምህሩ እንደሆነ አያሳይም፡፡ በተመሳሳይ የዛሬ ዓመት ከዚሁ ከእርሶ ጽ/ቤት የመምህሩን አገልግሎት ያወገዘውና ከእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ያገደው ደብዳቤ ከፍተኛ የሆነ ግድፈትና  የጽ/ቤቱን ደረጃ የማይመጥን በልዩ ሴራ የደብዳቤን ይዘት፣ ሥርዓትና ቅደም ተከተል እንኳን በማያውቁ ግለሰቦች እንደተጻፈ አንበበናል፡፡ የአሁኖቹም ቢሆኑ ከቤተክርስቲያን መሠረታዊ መርሆ ወጣ ባሉ የጎደፉ ሕሊናዎች ሊሆኑ እንሚችሉ አንዳንድ ቃላቶችንና የሁኔታዎችን ሂደት እናያለን፡፡

የመጀመሪያው ደብዳቤ ስሕተት ነው ከተባለና ሁለተኛው እውነተኛ ሆኖ የመምህሩ አገልግሎት እውንም የሚወገዝ አይነት ከሆነ መምህሩ በይፋ የሚሰጡትን አገልግሎት በፖስታ በሚታሸግ ደብዳቤ ብቻ  ሊያውም ለማይመለከተው ሁሉ (አገልግሎትዎ ስህተት ነው ከተባለ የሚመለከተው በመጀመሪያ መምህሩን ነው) የጅምላ ደብዳቤ መጻፍ ስህተት ይመስለኛል፡፡ ይህ ደብዳቤ የተጻፈው በፊት ለተፈው ስህተት ለተባለው ምላሽ ብቻ ከሆነም የበፊቱ ለሚመለከተው ሁሉ ይላልና ይሄም ለሚመለከተው ሁሉ ቢባል ችግር የለውም ካልንና የመምህሩ አገልግሎት ግን ስህተት የለውም ተብሎ ከታመነ ሁለተኛው ደብዳቤ ከመጻፉ በፊት ቢያንስ የበፊቱ በምን አግባብ እንደሆነ ተጠንቶ መምህሩም ተጠይቀው ስህተቱ ይት ጋር እንዳለ ከተረጋገጠ በኋላ ሊሆን ይገባው ነበር፡፡ የመጀመሪያው ደብዳቤ ማንም ይጻፈው ማንም የመምህሩ አገልግሎት ግን እስከታመነበት ድረስ እንደተባለው የበፊቱ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ወይም አግባብ ባልሆነ ሁኔታ የወጣ ከሆነ ደብዳቤውን ማውገዝ ተገቢ ነው በምትኩ ግን የመምህሩን አገልግሎት የሚደግፍ ሌላ ትክክለኛ ደብዳቤ መስጠት የበጎ ሕሊና አሰራር ከመሆኑም ባሻገር አጋጣሚዎችን ለራሳቸው ፍላጎት ሊጠቀሙ የሚያስቡትን በር መዝጋት ነበር፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን የሁለተኛው ደብዳቤ ይዘት የመምህሩን አገልግሎት አንቀበልምና ፍቃድ አለኝ ቢሏችኁ አተቀበሏቸው ጭምር ይመስላል፡፡ በዚህ የይዘት ትርጉም ደግሞ መምህሩ አሁን በይፋ  ተጻፈላቸውም አልተጻፈላቸውም በአለም አቀፍ ደረጃ እየሰጡት ያለው አስተምህሮትና  የፈውስ አገልግሎት በቤተክርስቲያኒቱ ሥምና በእርግጥም በቤተክርስቲያኒቱ አብያት ቅጥር ውስጥ እንደሆነ ስናስብ አገልግሎታቸውን በይፋ መንቀፍ ድፍረት በልታጣ ነበር፡፡ በይዘትና ደረጀ ሚዛን ሲመዘኑ ግን ሁለቱም ደብዳቤዎች የተንገዳገዱና ነገር እንዳለባቸው እንረዳለን፡፡ መምህሩ ግን የሚያውቁት ነገር ያለ አይመስልም፡፡

እኔ የመምህሩን አስተምህሮትም ሆነ የፈውስ አገልግሎት በአትኩሮትና በመገረም በአካልም በጉባዔያቸው በመገኘት  ጭምር የምከታተል ሰው ነኝ፡፡ የመምህሩ አስተምህሮት ዛሬ እንደ አሸን የፈሉት ተራ ሰባክያን አስተምህሮት ከጩኸት የዘለለ ሕይወትን ለመለወጥ አቅም የሌለው ሳይሆን በትኩረት ለአዳመጠው ጥልቅ የሆነ ከልዑል አምላክ ዘንድ በምትፈስ ጥበብ/ፍልስፍና የተዋበ አእምሮና ሕሊና እውነትን እንዲጋፈጧት የሚያስገድድ ነው፡፡ በተግባር የሚያደርጉት የልዑል እግዚአብሔርን ኃይል በገሀድ ማሳየትና የጠላታችንን ሴራ ማጋለጥ የአገልግሎታቸው ምስክሮች ናቸው፡፡  ይህ ነበርና ጥንታዊው የሐዋርያት ክርስትና፡፡ ዛሬ ግን ጰውሎስ እንህ አለ፣ እንዲህ አደረገ፤ ዮሐንስ እንዲህ አለ እንዲህ አደረገ ከሚለን በቀር እነዚያ ታላላቅ ተአምራትን በጌታ ሥም የሚያደርጉትን የሚያደርግ ለመኖሩ ማረጋገጫ እንኳን አጥተናል፡፡ በአንጻሩ ቀሚሳቸውን አስረዝመው እጅጌያቸውን አስፍተው በከተማ በመንገማለል በአለባበሳቸውና በአነጋገራቸው ሊከብዱብን የሚሞክሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ በእንዲህም አይነት ሳይገደቡ በቤተክርስቲያንና በሕዝብ ገንዘብ የራሳቸውን ዓለም የሚቀጩት ይሄ ለቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደርና ሥርዓት አደገኛ ኪሳራ ሆነዋል፡፡   ይህን እውነት ሕሊናችን ሊክደው አይችልም፡፡ በጎ ነገርንና ለልዑለአማላክ መገዛትን በቀጥታ የሚናገሩት ግን መምህሩን ጨምሮ በበጎ አይን አይታዩም፡፡ መምህሩ በልዑል አማላክና በቅዱሳኑ ሥም ከክፉ መናፍስት በመናፍስቱ ከሚመጡ ደዌያትንና የኑሮ ምስቅልቅሎች የተጨነቁትን መታደጋቸው አደገኛ ጠንቋይ አስማተኛ አሰኝቷቸዋል፡፡ እርግጥ አስማተኛ መባላቸውን እኔም ብሆን ቅር የምሰኝበት አይደለም፡፡  የመምህሩ አስማት ግን ሌሎች ክፉዎቹ የሚጠሩት ሳይሆን፣ ኃያሉና ጉልበትን ሁሉ የሚያንበረክከው የክርስቶስና ስሙ በስማቸው የታተመው የቅዱሳኑ ግን ሥም እንደሆነ በአየናችን አይተናል እኛም እንድንሞክረው አድርገው ብዙዎች በሥሙ ክፉውን መንፈስና ጠንቆቹን እተዋጉት ይገኛሉ፡፡ ይህ አስማተ መለኮት መተተኞቹ የሚቋቋሙት አይደለም፡፡ መምህሩ  ጠንቋይና መተተኛ ላለመሆናቸው እኛ ምስክሮች ነን፡፡ ችግሩ ቤተክርስቲያንን የወረሯት መተተኛ ደብተራዎችና ጠንቋዮች ሥራቸው እየከሸፈባቸው ስለሆነ የመምህሩን ከምድረገጽ መጥፋት አጥብቀው ይፈልጉታል፡፡ መጻሕፍ ይጠቅሳሉ፣ ሴራ ይሸርባሉ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ይሞክራሉ፡፡ ግን የልዑል አማላክን ክንድ ሊያጥፍ የሚችል ማን ነው! ሌሎች የተደነባበሩትን ለማደናገር ይሞክራሉ፡፡ አልቀረባቸውም ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክትን ይሻል በማለት የመምህሩን የማዳን ፀጋ ሊያጣጥሉ ይሞክራሉ፡፡ ጌታም ሆነ ሐዋሪያቱ ምልክትን እንድንመረምር አስጠነቀቁን እንጂ አይተን እንዳናምን አልተናገሩም፡፡ ጌታንም ሆነ ሐዋሪያትን የተቀበሏቸው ብዙዎች በአዩት ተዓምር እንጂ በትምህርታቸው እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡ ደግሞ በተግባር የማይገለጥ እምነት የለመድንው ተረት አይነት እንጂ እንዴት እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ በሥሙ ለሚያምኑት ሁሉን ያደርጉ ዘንድ ሥልጣንን እንደሰጣቸው ሲታወስ ምንም ማድረግ የማንችል የመተተኞችታ የክፉ መናፍስት መጫወቻ የሆንን ግን ክርስቲያነ ነን ብለን የሚናምን እስኪ ለክርስትናችን ምልክቱ ምንድነው?

እውነት እንደ መምህር ግረማ ብዙዎችን ከዘመናት ጭንቅ የገላገለ ማን ነው? ብዙዎችንስ እምነታቸውን እንዲያውቁ ያደረገ ማን ነው? ብዙዎቻችን እኮ ክርስትናው ከተረት ያለፈ ትርጉም አልሰጠን ብሎ ነበር! የየትኛው ሰባኪ አስተምሮት ነው ብዙዎችን ከሌላ እምነት ወደክርስትናው የመለሰ? ሰብከት ተብዬዎች ብዙዎች ጦርነትን መለያየትን የሚያውጁ አይደሉም እንዴ! ማነው እንደ እኚህ መምህር ዘር ሳይል ሀይማኖት የተሰጠውን ፀጋ ለሁሉም በእኩል ሊያበረክት የወደደ፡፡ ዘረኝነትና ጎጠኝነትን የሚያስፋፉ አይደሉም እንዴ ዛሬ ቤተክርስቲያኒቱን የወረሯት፡፡ ማን ነው እን እኚህ መምህር ለቤተክርስቲያን ልማት ተሳታፊ የሆነ፡፡ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ለቤተክርስቲያን ዛሬ እያስገባ ያለው በእሳቸው ትምህርት አይደለም እንዴ? ማንው ይህንን ሁሉ ገቢ ለቤተክርስቲያን እያስገባ በነጻ አንዳች ደሞዝ እንኳን ሳይቀበል የሚያገለግል፡፡ በየክብረ በዓል በአሰልቺ ሁኔታ የሚሰበሰብን ገነዘብ  ካላካፈላችሁን፣ አበል ካልከፈላችሁን የሚሉ ሰባክያንና መዘምራን አይደሉም እንዴ ዛሬ የሞሉን፡፡ የጌታን ትዕዛዝ በለመጠበቃቸው ግን መካኖች እንደሆኑ አይረዱም፡፡ በነጻ የተቀበላችሁትን በነጻ ስጡ ይላልና፡፡ እንደመምህሩ ያለ ጸጋ ሊኖረው የሚፈልግ ገዘብን ወዶ ሊሆንለት አይችልም፡፡

አባ በእናንተስ መካከል (በጳጳሳቱ ማለቴ ነው) ስለመምህሩ ለምን ይሄን ያህል መለያየት ተፈጠረ? ጥሩና አስተዋይ መሆናቸውና በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት ብዙዎቹ ጳጳሳት መምህሩን በትክክልም ሲደግፉ በጉባዔያቸውም እየተገኙ ሕዝቡን ሲባርኩ አይተናል፡፡ ደብዳቤዎቹ ማን እንደጻፋቸውም ስለማናውቅ ተጭበረበሩ እንበል፡፡ ግን እኮ አይናችን እያየ ጆሮአችንም እየሰማ ከእናነተ እኮ የመምህሩን አገልግሎት አለም አቀፋዊነት በአንደበታቸው ነው የተናገሩት፡፡ ይሄም ፊልም ነው ሊሉ ይችላሉ፡፡ እኛ ግን በአካል ተገኝተን የያየንና የሰማን ምስክሮች ነን፡፡ ደግሞ እግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት የማንንም ፍቃድና እውቅና ማግኘት ያለባቸው አይመስለኝም፡፡ ጥንታዊው የሐዋሪያትም ጉዞ በካህናትና በነገስታት ፍቃድ ሳይሆን ከአምላካቸው የተሰጠውን ትዕዛዝ ብቻ ከመፈጸም ነበርና፡፡

አባ አሁንም አላለሁ ሕሊና የልዑል አምላክ እንደራሴ ነው፡፡ እውነት ግን ከሕሊናም በላይ ስለሆነች በልዑል አምላክ የምትመሰል ናት፡፡ እግዚአብሔር እውነት ነውና፡፡ በሕሊናችን ካልበደልን እውነትን ብንስታት እንኳን የእውነት ባለቤት እግዚአብሔር እውነትን እንድናውቃት ያደርጋል፡፡ ሁሌም አነሳዋለሁ በሕሊናው ምንም በደል የሌለበት ግን እውነትን ባለማወቁ የክርስቲያኖች አሳዳጅ የነበረውን ሳውል (ቅዱስ ጳውሎስን)፡፡ በተቃራኒው እውነትን አውቆ ግን ሕሊናውን በሰላሳ ብር የሸጠውን ይሁዳንም እናስተውል፡፡ እውነትን ለመቀበል እያወቁ እምቢ ያሉትን የአይሁድ ካህናትንም፡፡ ጳውሎስ ስለሕሊናው ምርጥ የክርስቶስ ምርጥ ሊሆን ተመረጠ እውነት በተገለጠችለት ጊዜ ሕሊናው እውነትን ሊክድ የሚችል አልነበረምና፡፡

አባ አሁንም አላለሁ ሁላችሁም የሕሊናችሁን ንፅሕና እንድትመረምሩ፡፡ በስልጣንና በከፍተኛ ማዕረግ መቀመጥ እንደ አይሁድ ካህናት ክርስቶስን የሚያስክዳችሁ ምቾት አይሁንባችሁ፡፡ ስለ ሕዝብና ስለትውልድ መጨነቅን ልመዱ፡፡ የድህነትን መንገድ ለማሳየት መነገድ የጠፋበትን ታች ወርዳችሁ ምሩት፡፡ ክርስትናው ወግና ልማድ ብቻ ሆኖ ሕዝብ በክፉ ኃይል እንደወደቀ አስተውሉ፡፡ ከልዑል እግዚአብሔር ክብር ሕዝብ ለክፉ መንፈስ እንደተገዛም እዩ፡፡ ጠንቋዮችና ደብተሮች ከፍተኛ ክብር አላቸው፡፡ በቤተክርስቲያኒቱም ከፍተኛ ስልጣን ላይ እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ሲያስፈራሩን ቆይተዋል! ዛሬ ግን ሊቋቋሙት የማችሉትን እኛም ታጥቀናል፡፡ የዛሬ ዓማት በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የነበረው የመምህሩ የማስተማሪያና የፈውስ አገልገሎት መስጫ መድረክ ከነቅዱሳን ሥዕላቶቹ ድምጥማጡ ሲጠፋ ከጠንቋዩች፣ ቃሊቻዎች፣ ሌሎችም ጣዖት አማላኪዎች እየተሰበሰቡ የሚመጡ የጣዖት ማመለኪያ እቃዎች የሚጣሉባት አንዲት ትንሽ ክፍል ግን አንዳች አልተነካችም፡፡ ሰይጣን ነብረቱን ምን ያህል እንደሚጠብቅ ብዙዎቻችን አየን፡፡ ዛሬም ድረስ በዚያው ጊቢ ያቺ ክፍል ብቻዋን አለች፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው  ያለው ፈላስፋው እውነት ነው፡፡ አስደንጋጭም ነው! አንዴ ለማይረባ አእምሮ ከተጣልን በምን ማሰብ እንችላለን፡፡ ጌታን በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል ባሉት ጊዜ የተናገረው አሳዛኝ መልዕክትም በአእምሮዬ መጣ፡፡ “እኔ በአጋንንት አለቃ አጋንንትን የማወጣ ከሆነ ልጆቻችሁ በምን ያወጧቸዋል” አለ፡፡ አዎ በጌታ ሥም ማመን ካልቻልን በምን ክፉውን ልንቋቋመው እንችላለ፡፡

ብዙ ጉዳዩች በአእምሮዬ አሉ እዚሁ ላይ ላቁም ግን ለሁለተኛ ጊዜ እለምንዎታለሁ፡፡ ሥለ ሕሊና ፍርድ ራስዎ በይፋ ይናገሩ፡፡ ስለመምህሩም ስለሌላውም የቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ፡፡ እኛም ስለሕሊናችን አገልጋዮች እንሆናለን፡፡ አምላክም እውነትን እንከተላት ዘንድ እንደ ቅዱስ ጰውሎስ የአይናችንን ቅርፊት ያስወገድልናል! በእውነትም ተጉዘን መንግስቱን እንወርሳለን፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር አእምሮአችንን ይክፈት!

አሜን

የታላቋ ቀን ልጅ መጋቢት 21 2006 ዓ. ም

የማሕበረ ቅዱሳን የመጨረሻዎቹ ቀናት –ከተመስገን ደሳለኝ

$
0
0

“ማሕበረ-ወያኔ” 

mahbere-kidusan-300x168በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የሚመራው መንግስት ከናቅፋ እስከ ጉና ተራራ ያሉ ምሽጎቻቸውን ከሰማይ በጦር አይሮፕላን፣ ከምድር እሳት በሚያዘንቡ ቢ.ኤሞችና መድፎች ሳያቋርጥ ደበድብም፤ በሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን ግዛታቸውን እያሰፉ የተጠናከሩት ‹‹ወንበዴዎች›› ራስ ምታት ሆነውበታል፡፡ የኤርትራ ‹‹ነጻ አውጪ›› ቤዝ-አምባው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለጥቃት የመጋለጥ እድሉ አናሳ በሆነው የሳህል በረሃ በመሆኑ አብዛኛው የአመራር አባል መሸሸጊያው አድርጎታል፡፡

 

በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ አካባቢ የሚንቀሳቀሱት የወያኔ መሪዎች ምሽጋቸው እንደ ሳህል ምቹ ባለመሆኑ፤ በርካታ ክፉ ቀናትን ያሳለፉት በተራራማ አካባቢዎች በሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ገዳማት ውስጥ ተደብቀው እንደሆነና ከቦታ ቦታ መዘዋወር ሲፈልጉም የመነኮሳቱን አልባሳት ይጠቀሙ እንደነበረ በትግሉ ዙሪያ የተዘጋጁ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ በተለይም ታጋይ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሀዬ፣ ግደይ ዘርአፅዮን፣ ስዩም መስፍን፣ ስብሐት ነጋን…. የመሳሰሉ የአመራር አባላት የገዳማቱ ቤተኛ ነበሩ፡፡ ከዚሁ ጋ ተያይዞ የሚነገርም አንድ ታሪክ አለ፤ የመንግስት ፀጥታ ሰራተኞች ሁለት የ‹‹ወንበዴ›› መሪዎች በትግራይ በሚገኝ አንድ ገዳም ውስጥ ከመነኮሳቱ ጋር ተመሳስለው መሸሸጋቸው መረጃ ይደርሳቸውና በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ወታደሮችን በመላክ ዙሪያ ከበባ ያደርጋሉ፡፡ ይሁንና መደበቂያ በመስጠት የረዷቸው መነኮሳት ሁለቱን ታጋዮች ‹‹ወይባ›› በመባል የሚታወቀውን ረጅሙን ቀሚሳቸውን አልብሰው እና ቆብ አስደፍተው ከአካባቢው በማሸሽ ይታደጉዋቸዋል፡፡ የታሪኩ ባለቤት መለስ ዜናዊ እና አባይ ፀሀዬ ነበሩ፡፡ በርግጥ እነዚህ የ‹‹ወንበዴ›› መሪዎች ‹በእንዲህ አይነቱ ከመርፌ አይን እጅግ በጠበበ ዕድል ህይወታችን ከሞት መንጋጋ ተርፎ ኮለኔል መንግሥቱን በጓሮ በር ወደ ዜምባብዌ ሸኝተን በትረ-መንግሥቱን ለመጨበጥና ለሃያ ምናምን ዓመታት ኢትዮጵያን ታህል ታላቅ ሀገር አንቀጥቅጠን ለመግዛት እንበቃለን› የሚል ጠንካራ እምነትና የእርግጠኝነት ስሜት በወቅቱ ነበራቸው ብሎ ማሰብ ለእነርሱም ቢሆን እጅግ አዳጋች ይመስለኛል፤ የሆነው ግን ይህ ነበር፡፡

 

 ‹‹ማሕበረ-ቅዱሳን››

 

መለስ ዜናዊና ጓዶቹ በለስ ቀንቷቸው ባልጠበቁት ፍጥነት የመንግሥት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር እየተቆጣጠሩ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉትን ግስጋሴ ሲያፋጥኑ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥቱ ኃይለማርያም ሰብሳቢበት፣ በደህንነት ሠራተኞች እና የኢሠፓ ካድሬዎች ገፋፊነት ትምህርታቸውን አቋርጠው ለወታደራዊ ስልጠና ደቡብ ኢትዮጵያ ወደሚገኘው ብላቴና የጦር ማሰልጠኛ ከተቱ፤ ዩኒቨርሲቲውም ተዘጋ፡፡

 

…ከመላው ዘማቾቹ አስራ ሁለት የሚሆኑ ተማሪዎች ተሰባስበው ሲያበቁ፣ በየቀኑ ካምፓቸው አቅራቢያ ወደሚገኘው ‹ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን› በመሄድ፣ ከመዓቱ ይታደጋቸው ዘንድ ፈጣሪያቸውን በፀሎት መማፀን የህይወታቸው አካል አደረጉት፤ ከቀናት በኋላም በአንዱ ዕለት አንድም ለመታሰቢያና ለበረከት፣ ሁለትም ስብስቡ ሳይበተን ወደፊት እንዲቀጥል በሚል ዕሳቤ ‹ማህበረ ሚካኤል› ብለው የሰየሙትን የፅዋ ማህበር መሠረቱ፡፡ …ይሁንና ከመካከላቸው አንዳቸውም እንኳ በ1977 ዓ.ም በ‹ፓዊ መተከል› ዞን የተደረገውን ‹የመልሶ ማቋቋም› ፕሮግራም እንዲያመቻቹ በዘመቱ ተማሪዎች ከተመሠረተውና ከተለያዩ የፅዋ ማህበራት ጋር በመዋሀድ የዛሬውን ‹ማህበረ-ቅዱሳን› እንደሚፈጥሩ መገመት የሚችሉበት የነብይነት ፀጋ አልነበራቸውም፤ የሆነው ግን እንዲያ ነበር፡፡

 

 

ኃይማኖትን ጠቅልሎ የመያዝ ዕቅድ

 

በትጥቅ ትግሉ ወቅት የህወሓት አመራር ገዳማትን ለመሸሸጊያነት ብቻ ሳይሆን ለእርካብ መወጣጫነትም ጭምር ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ከድርጅቱ መስራቾች አንዱ የነበረው አረጋዊ በርሄ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ‹‹A Political History of the Tigray People’s Liberation Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilisation in Ethiopi›› በሚል ርዕስ ጽፎት፤ ኋላም ወደ መጽሐፍ በቀየረው የጥናት ጽሁፉ ላይ፣ ‹‹የቤተ-ክርስቲያኗን ሥልጣን (በትግራይ የነበረውን) ለማድቀቅ ሲባል በስብሀት ነጋ የሚመራ የስለላ ቡድን ተቋቋመ፡፡ ይህ ቡድንም ደብረ-ዳሞን ጨምሮ በትግራይ ውስጥ ባሉ ገዳማት አባላቱን መነኮሳት በማስመሰል፣ የገዳማቱን እንቅስቃሴ በህወሓት ፍላጎት ስር የማስገዛት ስራ ሰርቷል›› ሲል በገፅ 317 ላይ ገልጿል፡፡ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ሐይማኖትን ጠቅልሎ ለመያዝ የተነሳበትን ገፊ-ምክንያትም እንዲህ በማለት አብራርቶታል፡-

 

 

‹‹ቤተ-ክርስቲያኗ ተከታዮቿን፣ ለነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እንዲገዙ ከማስተማር በዘለለ የብሔራዊ ንቃት (ማንነት) ማስተማሪያም ነበረች፡፡ …ለህወሓት እንቅስቃሴ እንቅፋት እንደነበረች ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህም ቤተ-ክርስቲያኒቱን በህወሓት ዓላማ ስር ለማሳደር ፍላጎት ነበር፤ በዚህ የተነሳም የእርሷን ተፅእኖ ለማግለል ጥልቅ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡›› (ገፅ 315-316)   ዶ/ር አረጋዊ ‹‹ጥልቅ እርምጃዎች›› ብሎ ከጠቀሳቸው መካከል አንደኛው ‹‹ለአጥቢያ ቀሳውስቱ ኮንፍረንስ በማዘጋጀት፣ በትግራይ ውስጥ ያሉትን ቤተ-ክርስቲያናት ለብቻ ነጥሎ ህወሓት በሚያራምደው የትግራይ ብሔርተኝነት ስር ማካተት›› እንደነበረ በዚሁ መጽሐፍ ጠቅሷል፡፡ ይሁንና አስገምጋሚ መብረቅ የወረደብን ያህል የምንደነግጠው፣ ዶ/ሩ ከዚሁ ጋ አያይዞ ‹‹የተጨቆነው የትግራይ ብሔርተኝነት የተነሳሳውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንን ተፅእኖ ለመገዳደር ነው›› በማለት መመስከሩን ስናነብ ነው፡፡ የአረጋዊ መረጃ የሰሚ-ሰሚ ወይም በቢሆን ሃሳብ የተቀኘ አይደለም፤ ይልቁንም ራሱም በመሪነትና ሃሳብ በማዋጣት ከተሳተፈበት ከድርጅቱ የፖለቲካ ፕሮግራም የተቀዳ እንጂ፡፡

 

የሆነው ሆኖ ህወሓት ከ1970-72 ዓ.ም ድረስ ባሰለጠናቸው ካድሬ ‹‹ካህናት›› አማካኝነት ‹‹ነፃ በወጡ›› መሬቶች ላይ ራሱን የቻለ የቤተ-ክህነት አስተዳደር (ከሲኖዶሱ የተገነጠለ) መመስረቱ ይታወሳል፡፡ ድርጅቱ ለእነዚህ ቤተ-ክርስቲያናት መተዳደሪያ ደንብ ከመቅረፅ አልፎ ዓላማውንም እንደ አስርቱ ትዕዛዛት በፍፁም ልባቸው የተቀበሉ ‹‹መንፈሳዊ ክንፍ›› አድርጓቸው እንደነበረ፣ አረጋዊ በርሄ ተንትኖ አስረድቷል፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰርጎ ገብነት በእስልምናም ላይ መተግበሩ አይዘነጋም፡፡ በተለይም የእምነቱ ተከታዮች በሚበዙበት አካባቢዎች ወላጆቻቸው ሙስሊም የሆኑ ታጋዮችን እየመረጠ እና ከክርስቲያን ቤተሰብ የወጡ ካድሬዎችንም ሀሰተኛ የሙስሊም ስም እየሰጠ ‹የትግሉ ዓላማ እስልምናን ማስፋፋት› እንደሆነ በመግለፅ የፕሮፓጋንዳ ስራ ይሰራ ነበር፡፡ በዚህ ስልቱ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የአንዳንድ ዓረብ ሀገራትን ቀልብ ማግኘት ችሏል፡፡ ይህ ደግሞ ከዓረቦች በገፍ ዕርዳታ ያጎረፈለት ሲሆን፣ ወደ መሀል ሀገር የሚያደርገውን ጉዞም አፋጥኖለታል፡፡

 

ከመንግስት ለውጥ በኋላም ሁለቱን ሐይማኖቶች የተቆጣጠረው በታጋይ ‹‹ካህናት›› እና ‹‹ሼሆች›› ለመሆኑ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ ዛሬም በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት የበላይ በሆነው ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ውስጥ ከሚገኙት አስራ ስምንት መምሪያዎች፣ አስራ ስድስቱ በህወሓት ሰዎች የመያዛቸው ኩነት ስልቱ በተሳካ ሁኔታ መተግበሩን ያስረግጣል፡፡ በተለይ ዋነኛው ሰው አቡነ ማቲያስ ሲኖዶሱን ብቻ በሚመለከት ጉዳይ ላይ ጭምር ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት ‹‹የመንግስት ባለሥልጣናትን ላማክር›› ሲሉ በተደጋጋሚ መደመጣቸው እና አንዳንድ ጳጳሳት ተቃውሞ በሰነዘሩባቸው ቁጥር በአፃፋው ‹‹መንግስት ያግዘኛል ብዬ ነው እዚህ መንበር ላይ የተቀመጥኩት፤ ባያግዘኝ ሥልጣኑን አልቀበልም ነበር›› በማለት በግላጭ ሲመልሱ መስተዋላቸው ለስርዓቱ ጣልቃ-ገብነት እንደማሳያ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ከዚህ ቀደም ለሶስት ወር የቋሚ ሲኖዶሱ አባል ሆነው የሰሩ አንድ ጳጳስም ‹‹ሁልጊዜም ቋሚ ሲኖዶሱ ሲሰበሰብ እርሳቸው (ፓትርያርኩ) ‹መንግስት እንዲህ አለ›፣ ‹መንግስት ሳይፈቅድ›… የሚል ንግግር ይጠቀማሉ›› በማለት ለፋክት አስተያየት ሰጥተዋል (በነገራችን ላይ ፓትርያርኩ የመዘንጋት፣ ለውሳኔ የመቸገር፣ እንቅልፍ የማብዛትና መሰል ችግሮች ስራቸውን እያስተጓጎሉባቸው እንደሆነ ይነገራል፤ ራሳቸውም ‹‹ሲጨንቀኝ እተኛለሁ፤ ስተኛ ደግሞ እረሰዋለሁ›› በማለት ችግሩን አምነው ተቀብለዋል)

 

በእስልምና እምነት ውስጥም የመንግስት ጣልቃ-ገብነት ከቀድሞውም መጅሊስ የባሰ እንደሆነ በርካታ መዕምናን የሚያውቁት እውነታ ነው፡፡ ይህ መጅሊስ የሚዘወረው እንደተለመደው በምክትል ፕሬዚዳንቶች ሲሆን፤ ይች አይነቷ ጨዋታ ደግሞ ህወሓት ጥርሱን የነቀለበት ስለመሆኑ ነጋሪ አያሻም፡፡ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሼህ ከድር ለ17 ዓመታት የትግራይ ክልል መጅሊስና የሸሪአ ፍ/ቤቱን ደርበው በመያዝ መእምናኑን ቀጥቅጠው ሲገዙ ከመቆየታቸውም በላይ ታጋይ እንደነበሩ በኩራት ለመናገር የሚደፍሩ እንደሆነ የቅርብ ሰዎቻቸው ይመሰክራሉ፡፡ በአናቱም ከታማኝ የመረጃ ምንጭ ባይረጋገጥም የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት ሼህ ኪያር መሀመድ ከእኚሁ ‹‹ታጋይ›› ምክትላቸው ጋር በአንዳንድ ጉዳዮች መስማማት ባለመቻላቸው እና ‹‹መንግስት የሚያዘውን ሁሉ ለመስራት ለምን እንገደዳለን?›› የሚል ተቃውሞ እስከማሰማት በመድረሳቸው በቅርቡ ከኃላፊነታቸው ሊነሱ እንደሚችሉ ተወርቷል፡፡

 

 ኢህአዴግ እና ‹‹መንፈሳዊ›› ገበያው

 

ግንባሩ የእምነት ተቋማትን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ጠርንፎ መያዝን እንደ ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የመንቀሳቀሱ መግፍኤን ከሶስት ጉዳዮች አንፃር በአዲስ መስመር ለመተንተን እሞክራለሁ፡-

የመጀመሪያው ቤተ-ክህነት በነገስታቶቹ ዘመን የነበራትን ፖለቲካዊ ተሰሚነት (ምንም እንኳን ራሱ ኢህአዴግም በአፋዊነት ከማውገዝ ቸል ባይልም) ለቅቡልነት መጠቀሚያ የማድረግ ፍላጎቱ ነው፡፡ በገቢር እንደታየውም በኃይል በተቆጣጠራቸውም ሆነ ካድሬዎቹ ሊደርሱባቸው በማይችሉ የገጠር ቀበሌዎች ተቀባይነት ለማግኘት ማህበራዊ አክብሮት ባላቸው ሼሆች፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት… ሲቀሰቅስ ተደጋጋሚ ጊዜ ተስተውሏል፡፡ እንዲሁም የእስልምና እምነት በታሪክ ያሳለፈውን አገዛዛዊ ጭቆናንም ሆነ የደርጉን ሁሉንም ሐይማኖት ማግለልን በማጎን ለፕሮፓጋንዳ ተጠቅሞበታል (በወቅቱ የድርጅቱ አመራር አባል የነበረው አቶ ገብሩ አስራት፣ እንደ ሼሆች በመልበስና በመጠምጠም ከፍተኛ አስተዋፆ ማበርከቱን ብዙሀኑ ታጋዮች አይዘነጉትም) በዚህ ዘመንም በቤተ-እምነቶች ካድሬ-ጳጳሳትንና ካድሬ-n ሼሆችን አሰርጎ የማስገባቱ ምስጢር ይኸው ነው፡፡

 

 

በሁለተኛነት እንደምክንያት ሊጠቀስ የሚችለው የታገለለትን ዘውግ ተኮር ፖለቲካ ያለአንዳች ተግዳሮት ማሳለጥን ታሳቢ ማድረጉ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ሐይማኖቶች ‹‹የሰው ልጅ በሙሉ የአንድ አምላክ ፍጡሮች ናቸው›› በሚል አስተምህሮ የሚመሩ ከመሆናቸው አኳያ፣ በዘውግ ከፋፍሎ ማስተዳደርን ቀላል አያደርገውምና ነው፡፡ ስለዚህም መፍትሔው አክራሪ ብሔርተኛ ‹‹መንፈሳውያን›› በየእምነት ተቋማቱ እንዲፈለፈሉ እና ከፍተኛውን የሥልጣን እርከን መቆጣጠር እንዲችሉ በማብቃት ላይ የተመሰረተ ብቻ መሆኑን የህወሓት መሪዎች ያውቃሉ፡፡ ይህ ‹‹እውቀታቸው››ም ይመስለኛል ሀገራዊ ስሜት የሌላቸው፣ በችሎታ ማነስ እና በስነ-ምግባር ጉድለት የሚታወቁ፤ እንዲሁም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ቅቡል ያልሆኑ ሰዎች ቦታውን እንዲይዙ እስከማድረግ ያደረሳቸው፡፡

 

የራሳቸው የስለላ መዋቅርም በጥቅምት 2 ቀን 1995 ዓ.ም ‹‹ለዋናው መ/ቤት፣ አዲስ አበባ፤ ከ-ል.ዮ፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን ጉዳይ ይመለከታል›› በሚል ርዕስ ለደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት በላከው ጥናታዊ ዘገባ ላይ እውነታውን እንዲህ ሲል ገልፆታል፡- ‹‹…ለፓትርያርኩ ወዳጅነት አላቸው የሚባሉ ሊቃነ ጳጳሳት ከሦስትና አራት ብዙም ያልበለጡ ናቸው፡፡ ፓትርያርኩ ምንም ዓይነት ተቀባይነትና ከበሬታ ያጡ በመሆናቸው ህልውናቸውን የአንዳንድ መሪዎችን ስም በመጥራትና እንደማስፈራሪያ በመጠቀም ላይ የተንጠላጠለ ሆኗል››፡፡ ከዚህ ሪፖርት በኋላም እንኳ ለማስተካከል አለመሞከሩ መከራከሪያውን አምነን እንድንቀበል ያስገድደናል፡፡

 

አገዛዙ መንፈሳዊ ተቋማትን ጠቅልሎ ለመያዝ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ በሶስተኛነት ሊጠቀስ የሚችለው ምክንያት፣ ምንም እንኳ ‹‹ተሳክቷል›› ሊባል ባይቻልም፤ በስነ-ምግባር መታነፅ፣ በሀገር አንድነት ማመን፣ ለሕዝብ ጥቅም መቆም፣ የትኛውንም ህገ-ወጥነት ‹ለምን› ብሎ መጠየቅና መሰል መንፈሳዊ አስተምህሮዎችን መርሁ አድርጎ የሚነሳ ትውልድ እንዳይፈጠር መከላከልን ታሳቢ በማድረግ እየሰራ ያለውን ሴራ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም የስርዓቱ ሰዎች በዚህ መልኩ የሚቀረፅ ትውልድን ዛሬ ባነበሩት አይነት የጭቆና ቀንበር ለተራዘሙ ዓመታት መግዛት ከባድ እንደሆነ ለመረዳት አይሳናቸውምና ነው፡፡ ከዚሁ ጋር አንስተን ማለፍ ያለብን ጭብጥ፤ መቃብር ከሚቆፈርለት የኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ጋር የሚያያዝ ነው፤ የሐይማኖቱና የማዕከላዊ መንግስቱ የቅድመ-አብዮቱ ጋብቻ (በምንም አይነት መከራከሪያ ትክክለኛነቱን ልንሟገትለት ባንችልም)፣ ቤተ-ክርስቲያኗ ለኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነቱ የታሪክ ብያኔ ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጓን አያስክደንም፡፡ ይህም ‹የሐይማኖቱን ተቋም የብሔርተኝነቱ ወካይ ሆኖ እንዲታሰብ ይገፋዋል› ብሎ ለሚያምነው ህወሓት፣ ሐይማኖቱ ተቋማዊ ነፃነት እንዳይኖረው የሚቻለውን ሁሉ ሲያደርግ፤ ሐይማኖቱን በማዳከም የብሔርተኝነት መንፈሱንም ማላላት ይቻላል ከሚል መነሾ ነው ብሎ መደምደም ተምኔታዊ አያስብልም፡፡

 

 ገደል አፋፍ የቆመው ማሕበረ ቅዱሳን…

 

ስርዓቱ የሐይማኖት ተቋማትንና መንፈሳዊ መሪዎቹን ለመቆጣጠር ገፊ-ምክንያቶች ሆነውታል ብዬ ከላይ ለማብራራት የሞከርኳቸውን ሶስት ምክንያቶች ሙሉ ለሙሉ መተግበርን አስቸጋሪ ያደረገበት፣ ቀጥታ በምዕምናኑ የተመሰረቱ ማሕበራት መሆናቸውን መገመት ይቻላል፡፡ ለማስረጃም ያህል ከኦርቶዶክስ ክርስትና-ማሕበረ ቅዱሳን፤ ከእስልምና ያለፉትን ሁለት ዓመታት የእምነቱ ተከታዮች ወካይ ሆኖ የተመረጠው ኮሚቴ አባላት መንግስትንም ሆነ መጅሊሱን በመገዳደር ያደረጉትን አበርክቶ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይሁንና የሙስሊሙን ተወካዮች በገፍ ሰብስቦ እስር ቤት ካጎረ በኋላ፣ ከሲኖዶሱም ሆነ መሰል ማሕበራት ጠንካራ እንደሆነ የሚነገርለትን ማሕበረ ቅዱሳንን ዋነኛ ኢላማው አድርጎ ለመደፍጠጥ የቆረጠ ይመስላል፡፡ የማሕበሩ አባላት በዓለማዊ እውቀት የተራቀቁ፣ በሀገር አንድነት በፍፁም የማይደራደሩ፣ በጥቅመኝነት የማይደለሉ… የመሆናቸው ጉዳይ አገዛዙ ከኃይል አማራጭ የቀለለ መፍትሔ የለም ብሎ እንዲያምን አድርጎታል ብዬ እገምታለሁ፡፡

 

በርግጥ በአቶ መለስ ዜናዊ ይዘጋጅ እንደነበረ ከህልፈቱ በኋላ በተነገረለት የኢህአዴግ የንድፈ ሃሳብ መጽሔት ‹‹አዲስ ራዕይ›› ከተወሰኑ ዓመታት በፊት አብዛኛውን ጊዜ ‹‹የከሰሩ ፖለቲከኞች ‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት፣ አንድ ሐይማኖት አንድ ሀገር› እና ‹ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ቀደም ሲል ሲደርስበት የነበረውን በደል በማራገብና በመቀስቀስ፤ ከዚህም አልፎ ተገቢነት የሌላቸው አዳዲስ ጥያቄዎችን በማቅረብ ለማነሳሳትና ለማተረማመስ ሲሰሩ ማየት የተለመደ ሆኗል›› በማለት ከሚያቀርበው የሾላ-በድፍን ፍረጃ ዘልሎ ብዙም መንፈሳዊ ማሕበራትን በስም ጠቅሶ ሲያወግዝ አይሰማም ነበር፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን ማንኛውንም ሐይማኖታዊ የመብት ጥያቄን ‹‹ወሃቢያም ይሁን ማሕበረ ቅዱሳን…›› በማለት ማውገዙ የተለመደ ሆኗል፡፡ ከውግዘትም ተሻግሮ ጥያቄያቸውን በሕጋዊ መንገድ ወደ አደባባይ ያወጡትን የሙስሊሙን ተወካዮች ሰብስቦ አስሯል፤ በተለያየ ጊዜ የተደረጉ ሰላማዊ ተቃውሞዎችንም በማስታከክ በበርካታ የእምነቱ ተከታዮች ላይ ግድያና ስቀየትን ጨምሮ ብዙ ግፍ በመፈፀም ጉዳዩን በጠብ-መንጃ ብቻ የሚፈታ አድርጎ ካወሳሰበው ሰነባብቷል፡፡

 

‹‹ቀጣዩ የኢህአዴግ ኢላማ ማሕበረ ቅዱሳን ይሆን?›› በሚል ርዕስ ከስድስት ወር በፊት በዚሁ መጽሔት ላይ ለማተት እንደሞከርኩት ሁሉ፤ ከላይ በተዘረዘሩ የፖለቲካ አጀንዳዎች እና በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄደውን አገር አቀፍ ምርጫ በለመደው የማጭበርበር መንገድ አሸንፎ ያለኮሽታ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም ዓለማዊም ሆነ መንፈሳዊ ነፃ ተቋማት እንዳይኖሩ በይፋ ኢ-ሕገ መንግስታዊ ድርጊቶችን እየፈፀመ ያለው የእነ አባይ-በረከት መንግስት፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ትኩረቱን ማሕበረ ቅዱሳን ላይ ማድረጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ይህንን አፈና ለማሳካትም ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ በፍፁም ልባቸው ከመተባበር ለአፍታም እንደማያመነቱ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡

ለምሳሌ ያህልም አንዱን በአዲስ መስመር ላቅርብ፡-

 

ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ሀገረ-ስብከት አስተዳደርን ወደ ዘመናዊነት ለማሻገር ሲኖዶሱ ጥናት ተደርጎ እንዲቀርብለት ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡ እናም ጥናቱ ተጠናቆ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ከአንዳንድ የደብር አስተዳዳሪዎች ብርቱ ተቃውሞ ስለገጠመው፣ በሀገረ-ስብከቱ ሥራ-አስኪያጅ አቡነ እስጢፋኖስ አማካኝነት በጠቅላይ ቤተ-ክህነት አዳራሽ ከሁሉም አድባራትና ገዳማት የተወጣጡ 2700 ሰዎች የሚሳተፉበትና አስራ አራት ቀን የሚፈጅ የውይይት ፕሮግራም ይዘጋጃል፡፡ ይሁንና ውይይቱ በተጀመረ በሁለተኛው ቀን ጠዋት ፓትርያርኩ፣ ከአቡነ እስጢፋኖስ ጋር በስልክ ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው መወዛገባቸውን ሰምቻለሁ፡-

 

‹‹ጥናቱን የሚሰሩት ባለሙያዎች ናቸው ብለውኝ አልነበረም ወይ?››

‹‹አዎ! ታዲያስ ባለሙያዎች ናቸው የሰሩት፡፡››

‹‹አይደለም! የማሕበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው፤ እርስዎ አታለውኛል!››

‹‹የጥናት ኮሚቴው አባላት በቤተ-ክርስቲያን ልጅነታቸውና በየአጥቢያው ባላቸው ተሳትፎ ተጠርተው የመጡ ሙያቸውን ‹አስራት› ያደረጉ ናቸው፡፡››

‹‹በፍፁም! ጥናቱ የማሕበረ ቅዱሳን ነው!››

‹‹ቅዱስ አባታችን ቢሆንስ? ከጠቀመን ችግሩ ምንድን ነው?››

‹‹በቃ! ውይይቱ ከመንግስት ይቋረጥ ተብሏል፡፡››

‹‹ለምን ይቋረጣል?››

‹‹የጥናቱ ተቃዋሚዎች ረብሻ ያስነሳሉና የፀጥታ ስጋት አለ፡፡››

‹‹ለምንድን ነው ረብሻ የሚያስነሱት? ከፈለጉ መጥተው መሳተፍ ይችላሉ፤ እኛ እየተወያየን አይደለም እንዴ! ተቃውሞ ያለው መጥቶ ሃሳቡን ይግለፅ እንጂ ማቋረጥ እንዴት መፍትሄ ይሆናል? ደግሞስ ሲኖዶሱ አይደለም ወይ ‹ሰነዱ ወደታች ወርዶ ይተችበት› ብሎ የወሰነው?››

‹‹የለም! ይቁም ተብሏል፤ ይቁም!››

‹‹እንግዲያውስ የከለከለው አካል ራሱ መጥቶ ይንገረን፡፡››

 

…የስልክ ምልልሱ ከተጠናቀቀ ከሰዓታት በኋላ አንድ ባለሥልጣን አቡነ እስጢፋኖስ ቢሮ ድረስ መጥቶ ትእዛዙን ያስተላለፈው እርሱ እንደሆነ ገልፆ ውይይቱ እንዲቋረጥ አሳሰባቸው፤ እርሳቸውም ‹‹እናቋርጣለን፤ ነገር ግን እናንተ ‹የፀጥታ ስጋት አለ› ብላችሁ በደብዳቤ ኃላፊነቱን ውሰዱ፡፡ እኛም ለካህናቱም ሆነ ለመዕምናኑ ሁኔታውን ዘርዝረን እንገልፃለን›› የሚል ምላሽ ሰጥተው ይሸኙታል፡፡ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ለጊዜው ግልፅ ባልሆነ አንድ ምክንያት መንግስት ‹‹ይቋረጥ›› የሚለውን ማስፈራሪያ ሊያነሳ የቻለው፡፡ ኩነቱ ግን ፓትርያርኩ ማሕበሩን በጥርጣሬ ማየታቸውንና አገዛዙ ለሚወስድበት ማንኛውም አይነት እርምጃ ተባባሪ መሆናቸውን የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡

 

ሌላው መንግስትና ፓትርያርኩ፣ ማሕበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ በሰምና ወርቅነት እየሰሩ መሆናቸውን የሚያመላክተው የዛሬ ሳምንት በጠቅላይ ቤተ-ክህነት የማሕበሩ ተቃዋሚዎች ያደረጉትን ውይይትና የአቋም መግለጫ ስናስተውል ነው፡፡ ለመጽሔቱ ዝግጅት ክፍል የደረሰው በድምፅ የተቀረፀ የውይይቱ ሙሉ ክፍል እንደሚያስረዳው፣ ተሰብሳቢዎቹ ማሕበሩን በተመለከተ ባወጡት የአቋም መግለጫ የሚከተሉትን ነጥቦች ዘርዝረዋል፡- ‹‹የዋነኛ አመራሮቹ የባንክ አካውንት ይመርመር፣ የማሕበሩ ሒሳብ መንግስት በሚመድበው የውጪ ኦዲተር ይመርመር፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቹ (ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸው ቀላልና ከባድ መኪናዎቹ ሳይቀሩ) ወደ ቤተ-ክህነት ይግቡ፣ የንግድ ተቋማቱ (ትምህርት ቤት፣ ሬስቶራንቶቹን፣ ንዋየ ቅድሳት ማምረቻና ማከፋፈያውን) ያስረክብ፣ ከምዕምናን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚቀበለው አስራት እየፈረጠመበት ስለሆነ እንዳይቀበል ይከልከል፣ የግቢ ጉባኤ (በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) እርሱ በሚቀርፀው እንዳይወሰዱ መስራት፣ ተጠሪነቱ ከዋና ሥራ-አስኪያጁ ተነስቶ፣ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ስር አንዱ ንዑስ ክፍል ይሁን…›› የሚሉና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

 

ከዚህ ሴራ ጀርባ ፓትርያርኩና መንግስት በትብብር መቆማቸውን የሚያሳየው በተቀረፀው ድምፅ ላይ፣ የውይይቱ መሪ አዳራሹን መጠቀም የቻሉት በአቡኑ መልካም ፍቃድ እንደሆነና እርሳቸው በዛሬው ውይይት ያልተገኙት የሕዳሴው ግድብ ምክር ቤት አባል በመሆናቸው ግዮን ሆቴል ስብሰባ ስላለባቸው መሆኑን ከመግለፅም በዘለለ፤ ‹‹ቅዱስ አባታችን በዚህ የተቃውሞ ምክንያት ከሥራ የሚባረር የለም አይዟችሁ አትፍሩ ብለውናል›› በማለት ሲናገሩ መደመጣቸው ነው፡፡ በተጨማሪም ‹‹ከዚህ ግቢ አቅም ኖሮት የሚያስወጣን የለም፤ ካስወጡን ግን መንግስታችን ስለሚተባበረን (ቸር ስለሆነ) ከእርሱ ሌላ መሬት ተቀብለን የራሳችንን ቤተ-ክርስቲያን እናቋቁማለን›› እና ‹‹የኦርቶዶክስ እምነት አገልጋዮች የሚል ማሕበር እንመሰርታለን›› እስከማለት መድረሳቸው ከአገዛዙ ጋር ያላቸውን የጠበቀ ቁርኝት ያመላክታል፡፡ በነገራችን ላይ በስብሰባው እንዲሳተፉ ከተጠሩት ከመቶ ስልሳ ዘጠኙ አድባራትና ገዳማት፣ እንዲሁም ከ10 ሺህ በላይ ሠራተኞቻቸው መካከል የተገኙት የስምንት አድባራት አስተዳዳሪዎችና 150 ሠራተኞች ብቻ እንደነበሩ ከመረጃ ምንጮቼ አረጋግጫለሁ፡፡

 

 

በሌላ በኩል ደግሞ በተለይም በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ምኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም አዝማችነት ማሕበሩ ላይ የደቦ ዘመቻ ከተከፈተ ሰነባብቷል፡፡ በተከታታይ በ‹‹ጥናት›› ስም የሚወጡ ወረቀቶች ማሕበሩን ከአክራሪነትም አሻግረው ‹‹የግንቦት ሰባት መንፈሳዊ ክንፍ›› ሲሉ ይወነጅሉታል፡፡ በጥቅሉ የእነዚህ ‹‹ጥናት›› ተብዬዎች መደምደሚያ ‹‹ማሕበሩ የትምክተኞች ምሽግ ነው፣ አክራሪነት አለበት፣ አመራሩና የሕትመት ውጤቶቹ የፖለቲካ አዝማሚያ ይታይባቸዋል፣ በቤተ-ክርስቲያን አስተዳደር ጣልቃ ይገባል፣ ሕዝቡ በመንግስት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው ይሰራል፣ በውጭ ፅንፈኛ የፖለቲካ ኃይሎች ይዘወራል›› የሚሉ ናቸው፡፡ የማሕበሩ የአመራር አባላት እንዲህ አይነቱን ውንጀላ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ከአቶ በረከት ስምኦን እስከ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያም፤ ከአዲስ አበባ የፀጥታ ኃላፊዎች እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ የደህንነት አማካሪ ፀጋዬ በርሄ ድረስ ያሉ ባለሥልጣናትን በቢሮአቸው ተገኝተው ውንጀላው ማስረጃ የማይቀርበበት የሀሰት እንደሆነ ቢያስረዱም መፍትሄ እንዳላገኙ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በግልባጩ በመንግስት ተቋማት ያሉ የፋክት መረጃ አቀባዮች፣ በግንቦት ወር ከሚካሄደው የሲኖዶሱ መደበኛ ጉባኤ በፊት፣ ከሃያ የሚበልጡ የማህበሩ አመራርን ከሽብርተኝነት ጋር በማያያዝ ለመክሰስ እና ማሕበሩንም እንደተለመደው በዶክመንተሪ ፊልም ለመወንጀል ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ከሶስት ሳምንት በፊት በአቡነ ገብርኤል ሰብሳቢነት የሚመራው የሐይማኖቶች ምክር ቤት ስብሰባውን ካጠናቀቀ በኋላ ዶ/ር ሽፈራው አቡኑን ቃል-በቃል የጠየቃቸው ጥያቄም ይህንን መረጃ የሚያጠናክር ነው፡-

 

‹‹በማሕበረ ቅዱሳን አመራር ውስጥ ከሃያ በላይ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት አሉ››

‹‹ለዚህ ምንድን ነው ማስረጃህ? አቅርበውና እስቲ እንየው?››

‹‹ሀገር ውስጥ ካሉ ፅንፈኛ ጋዜጠኞች በተጨማሪ በስደት የሚገኙና በሽብር ተግባር የተሰማሩ ጋዜጠኞች በአመራርነት አሉበት (የሁለት ሰዎችን ስም ጠቅሷል)››

‹‹እኛ እስከምናውቀው ማሕበሩ ከእንዲህ አይነት ተግባር የራቀ ነው፤ እናንተ ማስረጃ አለን ካላችሁ ደግሞ አቅርቡልንና እንየው፤ ከዚህ ውጪ ይህንን አይነት ክስ አንቀበልም፡፡››

 

በአናቱም ከወራት በፊት የስርዓቱ የንድፈ ሃሳብ መጽሔት የማሕበሩን ስም ሳይጠቅስ በደፈናው የወነጀለበትን እና ‹‹ለምን?›› ብለው የሚጠይቁ ጳጳሳትን በሚከተለው አገላለፅ ማሸማቀቁን ስናስታውስ የማሕበሩ ዕጣ-ፈንታ በመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ መቆሙን ያስረግጥልናል፡፡

 

‹‹በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ትርምስና ብጥብጥ ለመፍጠር፤ በኦርቶዶክሶችና ሌሎች ሐይማኖቶች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የሚሞክሩት የደርግና የተለያዩ ትምክህተኛ ኃይሎች ቅሪቶች ናቸው፡፡ እነዚህ የትምክህት ኃይሎችና አንዳንድ የእምነቱ አባቶች በጋራ ሐይማኖትን በፖለቲካ ዓላማ ዙሪያ መጠቀሚያ አድርገው እየሰሩ ለመሆናቸው ከ97 ምርጫ በኋላ እንዳንድ በአሜሪካ የሚገኙ ጳጳሳት ቅንጅት በጠራው ሰልፍ ላይ የሐይማኖት አባትነት ካባቸውን እንደለበሱ ከመሰለፍ አልፈው አስተባባሪ ሆነው መታየታቸው በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡›› (አዲስ ራዕይ ሐምሌ-ነሐሴ 2005)

 

የሆነው ሆኖ ከፍረጃውና ከእስራቱ በተጨማሪ ማሕበሩን ለማዳከም በዋናነት በአገዛዙ የተነደፉት እቅዶች ማሕበሩ መሰረቱን የጣለበት የግቢ ጉባኤን ከመከልከልና ንብረቶቹን ከመውረስ ጋር የሚያያዙ ናቸው (ከላይ የተጠቀሰው የአቋም መግለጫም ለማሕበሩ የደም-ስር የሆኑትን እነዚህን ሁለት ጉዳዮች ትኩረት እንደሰጣቸው ልብ ይሏል)

 

ስቅለትን-ለተቃውሞ

 

ኢህአዴግ ወደ ስልጣነ-መንበሩ ከመጣ ሦስተኛ ዓመት ላይ ‹‹የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ግቦችና ቀጣይ እርምጃዎች›› በሚል ርዕስ ለካድሬዎቹ በበተነው ድርሳን (በሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ የተዘጋጀ ነው ተብሎ ይገመታል)፤ ይህን አሁን የተነጋገርንበትን ሐይማኖታዊ ተቋማትን በሚያቅዳቸው የስልጣን ማራዘሚያ አማራጮች ስለመጠቀም ካወሳ በኋላ ተቋማቱን ለስርዓቱ ፖሊሲዎች እንዲታመኑ ማድረጉ ዋነኛ እንደሆነ ያሰምርበታል፡፡ ይህ የማይቻል ከሆነ ደግሞ፣ እስከ ከፍተኞቹ መንፈሳዊያን መምህራን ድረስ ዘልቆ በመግባት ሐይማኖቶቹን መምራት የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ግብ መሆን እንዳለበት ያው ሰነድ በግልፅ ቋንቋ ይናገራል፡፡ እንግዲህ ከመጅሊሱ እስከ ማሕበረ ቅዱሳን ያየነው መንግስታዊ አፈና የዚህን ሃያ ዓመት የሞላው የተፃፈ ሀሳብ መተግበርን ነው፡፡

 

ግና፣ ከዚህ ቀደም በተፃፈ ነውረኛ ሀሳብ ትግበራ ፊት ከሁለት አስርት በላይ ህልውናውን ለማቆየት የተጋው ማሕበረ ቅዱሳን፣ ከላይ በሚገባ በጠቀስኳቸው አሳማኝ መረጃዎች እና ተጨባጭ ሁነቶች በተከታታይ መከሰት መጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ ተመልክተናል፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ደግሞ፤ መነሳት የሚኖርበት መሰረታዊ ጥያቄ፣ እንዴት ይህን ማሕበር ወደ ቀጣዩ ትውልድ ማሻገር ይቻላል? የሚለው ሲሆን፤ ምላሾቹም ሁለት ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የማሕበሩ አመራሮችና አባላት እስከዚህች ቀን እያደረጉ ያለው የውስጥ ለውስጥ የእርምት እንቅስቃሴን ይመለከታል፡፡ በሐይማኖቱ ተቋማት በኩል ለዓመታት ሲሞከር የቆየው ይኸኛው አማራጭ፣ እንደ አስተዋልነው ማሕበሩን ሞት አፋፍ ላይ ከመድረስ ሊታደገው አልቻለም፡፡ ስለዚህም፣ ወደ ሁለተኛውና ዋነኛ የመፍትሔ አማራጭ መሻገር ግድ የሚል ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ርዕሰ-ጉዳይ ላይ ስፅፍ ለማስረዳት እንደሞከርኩት፤ የማሕበሩ አመራሮች፣  አባላት እና ደጋፊዎች ወደ አደባባይ በመውጣት፤ ማሕበራቸውን ብቻ ሳይሆን ህልውናቸውንና ህያውነታቸውን የመሰረቱበትን ሐይማኖት ለማውደም የሚተጋውን ስርዓት በሰላማዊ አመፅ መናድ ብቸኛው የዚህ አስቸጋሪ ጊዜ መሻገሪያ መንገድ ነው፡፡ በዋናነት የተማሩ ከተሜ ወጣቶችን፣ በአለማዊም ሆነ በትምህርተ-ሐይማኖቱ የማይታሙ ዜጎችን የያዘው ይህ ማሕበር፤ ከህዝበ ሙስሊሙ ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የአደባባይ ተቃውሞ ስኬቶችና ሂደቶች በመማር፤ ፊቱ በተገተረው ኢህአዴግ ላይ በሕጋዊና ሰላማዊ እምቢተኝነት ከማመጽ የተሻለ አማራጭ እንደማይኖረው የሚረዳ ይመስለኛል፡፡

 

‹‹ችግሮች ሁሉ የየራሳቸው በጎ ገፆች አሏቸው›› እንዲሉ፤ ማሕበሩ የደረሰበት ይህ ፈታኝ ጊዜን ተከትለው የሚመጡ ሁለት ወቅቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው፣ በቀጣዩ ወር የሚካሄደው የስቅለት በዓል ነው፡፡ የሐይማኖቱ ተከታዮች በሙሉ በየቤተ-ክርስቲያናቱ የሚውሉበት ይህ በዓል፣ አገዛዙ እጁን ከማህበሩ ላይ እንዲያነሳ ለመጠየቅ የተመቸ ቀን ስለመሆኑ ማስታወስ አባላቱን አሳንሶ መገመት እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሁለተኛውና በእጅጉ የተሻለ ነው ብዬ የማስበው ጊዜ ደግሞ ቀጣዩ የ2007 ምርጫን ነው፡፡ ለየትኞቹም የህገ-መንግስቱ ሀሳቦች አልያም የሞራል ዕሴቶች የማይገዛው ኢህአዴግ፣ በሐይማኖቱ ላይም ሆነ በማሕበሩ ላይ የዘረጋውን የረከሰ እጅ እንዲያነሳ ያለው ብቸኛ አማራጭ ሕዝባዊ አመፅ መሆኑ ላይ እስከተማመንን ድረስ፣ ከዓመታዊ የንግስ በዓላት ጀምሮ ያሉ መድረኮችን በዕቅድ ለመጠቀም የዝግጅቱ ጊዜ ዛሬ ነው፡፡ ይህ አይነቱ የተቃውሞ እንቅስቃሴም፣ ካነሳነው ርዕሰ-ጉዳይ አኳያ የማሕበሩን መኖር የሚሹ ሁሉ ቀጣዩን የምርጫ ወቅት ለማስገደጃነት የመጠቀም ተሞክሮዎቻቸውን ተፈላጊው ብቃት ላይ እንደሚያደርሰው አምናለሁ፡፡ ጥቂት ሊባሉ የማይችሉ አባላቱ፣ የምርጫውን ተጨባጭ ዕድል መንግስታዊ ተቋማት በማሽመድመድ ጭምር እንዴት ስርዓቱን ወደመቃብሩ ማሻገር እንደሚያውቁ ስንገነዘብ፤ ቀሪው ጉዳይ ‹‹ሐይማኖታችሁን ተከላከሉ›› ብለው ላስተማሩት ቅዱሳን መጻሕፍትና ለሰማያዊው መንግስት የመታመን ብቻ እንደሚሆን እንረዳለን፡፡

የኑሮ ውድነት ሽክም የጫነብን ማን ይሆን? –(ግርማ ሠይፉ ማሩ)

$
0
0
Girma-Seifu

ግርማ ሠይፉ ማሩ

በሀገራችን የኑሮ ውድነት ከእለት እለት እየከፋ የድሃውን ህዝብ ጉስቁልና እያበዛ እንደሆነ ነጋሪ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ በቤተ መንግሰትና አካባቢ የሚኖሩት ይህ ጉዳይ አይመለከታቸውም፡፡ ለዚህ የኑሮ ውድነት አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት የዋጋ ንረት መሆኑን ብዙዎች ይረዳሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ ዛሬ ለፅሁፌ ዋና ማጠንጠኛም የማደርገው የዋጋ ንረት ምንስዔው ምን እንደሆነ በተለይ የመንግሰት ሚና ከዚህ አንፃር ምን እንደሆነ ማስረዳት ነው፡፡

በእኔ አረዳድ በአቅርቦት እጥረት ምክንያት የሚከሰት የዋጋ ንረት አቅርቦቱ ሲሻሻል እንደሚቀንስ በሀገራችን እንደ ሲሚንቶ ያለ ጉልዕ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም፡፡ ከወጣበት ጣራ ወርዶ ትክክለኛም ባይሆን ጥሩ የሚባል ደረጃ ደርሶዋል፡፡ ጊዜው መቼ እንደሆነ ባላስታውሰውም በደርግ መንግሰት ማስታወቂያ ሚኒስትር የሚታተም አንድ መፅሄት “ወደ ላይ ተወርውራ የቀረች ኳስ” ብሎ በሀገራችን ዋጋ ከናረ የማይመለስ ነገር እንደሆነ መጣጥፍ ማቅረቡ ትዝ ይለኛል፡፡ እንደምሳሌ የተጠቀመው ግን አንድ ብር የነበረ ውስኪ ሦሰት ብር ገባ የጠርሙስ ውስኪ ዋጋ ቢቀንስም የመለኪያው አልቀንስ አለ የሚል ነበር፡፡ ይህ ግን የኛ ችግር አይመስለኝም፡፡ የእኛ ችግር ስኳር ቢቀንስ፤ ዱቄት ቢቀንስ፤ ወዘተ የሻይና
የኬክ ብሎም የዳቦና ማኪያቶ ዋጋ ይቀንሳል የሚል ተሰፋ የለንም፡፡ ተስፋችን ለምን ጠፋ? ማን አጠፋው? የዚህ ፅሁፍ ማጠንጠኛ ይሆናል፡፡

 

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ወደ መቃብር ካልወረደ ወይም አሁን ያሉተ ሰዎች መቃብር ከመውረዳቸው በፊት የዚህችን ሀገር የመሬት ስሪት የሚለውጥ ነገር ለህዝብ ይዘው በመቅረብ ይህን ጉዳይ ከህገ መንግሰት ድንጋጌነት ማውጣት የሚችሉበትን ዕድል ካልተጠቀሙና ተሰፋ ካልሰጡን ተሰፋችንን ያጠፋው ኢህአዴግ መሆኑ ግልፅ ይሆናል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ገዢው ፓርቲም እንደሚያምነው አብዛኛው ሌባ የተሰባሰበው በመሬት ዙሪያ ነው፡፡ መሬት የመንግሰት ነው፡፡ በፍፁም የህዝብ አይደለም፡፡ በፓርቲ ተመርጠው በመንግሰት የተሾሙት ሌቦች እንደፈለጉ የሚያዙበት የሀብታቸው ምንጭ ነው፡፡ ይህ እንዴት ዋጋ ያንራል ማለት ተገቢ ነው፡፡ ዋጋ ማናር ብቻ አይደለም ህይወትም ያስከፍላል፡፡ አለማየሁ አቶምሳን ልብ ይሏል!!

 

መንግሰት ዜጎችን እያፈናቀለ በሊዝ የሚቸበችበው መሬት አሁን ባለው ሁኔታ እስከ ሰላሳ ሺ ብር በካሬ ሜትር እየተከፈለበት ነው፡፡ በአዲስ አበባችን፡፡ ይህን በሰላሣ ሺ ብር በካሬ ሜትር የሚገዙ ሰዎች የገንዘብ ምንጫቸው ምንድነው? ብለን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ በህጋዊ መንገድ ያገኘውን ገንዘብ በካሬ ለባዶ መሬት (ወርቅ ውስጡ የሌለ ማለት ነው) ይህን ያህል ገንዘብ ከከፈለ፤ ይህን ገንዘብ ለማስመለስ ግልፅ የሆነው ህጋዊ መስመር መሬቱ ላይ ለሚገነባው ቤት ከፍተኛ ዋጋ መጠየቅ ነው፡፡ ይህ ቤት በሽያጭም ይሁን በኪራይ ውድ ይሆናል ስለዚህ እዚህ ቤት ውስጥ የሚሰጥ አገልግሎት ወይም የሚሸጥ ዕቃም ቢያንስ የቤት ኪራዩን መሸፈን ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ ዋጋውን መጨመር የግድ ይላል፡፡ ይህ ትንተና የሚሰራው አዲስ በሚሰሩ በሊዝ ለተገዙ ቤቶች ነው የሚል የዋህ አይጠፋም፡፡ ነገር ግን ቤት አከራዮች አዲሶቹ ዋጋ ሲጨምሩ የድሮዎችም ይህንኑ ተከትለው ነው የኪራይ ዋጋ የሚጨምሩት፡፡ ለምሳሌ በአዲስ አበባ ከተማ ሰርቪስ ቤት በሁለት መቶ ብር ተከራይቶ መኖር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በምንም ዓይነት አንድ ሰርቪስ ቤት ከሺ አምሰት መቶ በታች ማግኘት አይቻልም፡፡ ከገቢያችን አንፃር ማሰተካከያ ቢሰራለት ይህ ዋጋ አሜሪካን አገር እንኳን እንዲህ ዓይነት ዋጋ የለም፡፡

 

በቅርቡ ከአንደ ጓደኛዬ ጋር የመኖሪያ ቤት ገንብተው የሚሸጡ ሪል ኤስቴቶች አካባቢ ጎራ ብለን ነበር፡፡ እነዘህ ቤት ገንቢዎች ዋጋቸው በፍፁም በሀገር ውስጥ የምንኖር ዜጎችን ያማከለ አይደለም፤ ቤታችንን መንግሰት አይሰራልንም የምንል ዜጎችም ብንኖርም እጃችን ተጠምዝዞ መንግሰትን ደጅ እንድንጠና የሚያደርግ ነው፡፡ ለእነዚህ ቤቶች መወደድ አንዱ ምክንያት የመንግሰት የሊዝ ፖሊስ እንደሆነ መረዳት ብዙ እውቀት የሚጠይቅ አይደለም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ ቤት ገንቢዎች ከቤት ገዢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰብሰበው ለመንግሰት ገቢ ያደርጋሉ፡፡ ከቤቱ ዋጋ አስራ አምሰት ከመቶውን የያዘው ለመንግሰት የሚከፈለው ታክስ ነው፡፡ ሌላው የታዘብኩት ነገር ደግሞ ለዋጋ ንረቱ ከሊዝና ታክስ በተጨማሪ ሌላ አቁስል ምክንያት መኖሩ ነው፡፡ ከጋደኛዬ ጋር ቤቱን መግዛት እንዳለብን ከምታግባባን የሽያጭ ሰራተኛ ማዶ ሌላ ሽያጭ ሰራተኛ ሁለት ሴቶችን ከፊት ለፊቷ አሰቀምጣ ቤቱን እንዲገዙ በተመሳሳይ ዝርዝር መረጃ ሰጥታ የማግባባት ሰራዋን ሰታጠናቅቅ፤ በዋጋው ውድነት ብስጭት በማለት የተለያየ ሃሳብ መሰንዘር ይጅምራሉ አንዷ ግን እንደ መፍትሔ ሃሣብ አቅረበች “አንገዛም ማለት አለብን!!” አለች፡፡ ልክ ነበረች ገዢ ሲጠፋ ዋጋ መቀነስ የታወቀ የንግድ ሰርዓት ውስጥ የሚወሰድ እርምጃ ነው፡፡ ትክክለኛ የገበያ ህግ በሚሰራበት ሀገር ማለቴ ነው፡፡ ጓደኛዋ ግን በዚህ መፍትሔ አልተስማማችም እንዲህ አለች “ምን መሰለሽ እዚህ ሀገር ብዙ በህገወጥ መንገድ ገንዘብ የሚያገኙ ሰዎች አሉ፤ እነርሱ ደግሞ በህገወጥ መንገድ ያገኙትን ገንዘብ ህጋዊ ማድረጊያ መንገዳቸው አንዱ ቤት መግዛ ነው” ብላ ተጨማሪውን የዋጋ ንረት ምንጭ ነካችው፡፡

 

ቤት ገንቢዎች ለምን ቤቱን አስወደዱት ብዬ እንደማልከሳቸው ማወቅ አለባቸው ግን በፍፁም ልክ ያልሆነ ነገር በእግረ መንገድ ላስቀምጥ “ይህን ያህል ካሬ ሜትር ቤት በዚይን ያህል ዋጋ” ብለው ማስታወቂያ ሰርተው ለመግዛት የሚሄደው ሰው ግን የሚያገኘው ሰባ ከመቶ ግርማ ሠይፉ ማሩ አይሆንም፡፡ ምን ነው ? ሲባል ለመኪና ማቆሚያ፤ ለመተላለፊያ፤ ለሊፍት፤ ለጋራ አገልግሎት፤ ወዘተ የሚሉ ቦታዎች ተደምረውበታልይባላል፡፡ ይህ ምን ያህል ቤት ፈላጊዎችን እንደሚያሳስት ግን ከሻጮቹም የተሰወረ አይደለም፡፡ ማስታወቂያው ሀቅን መሰረት ያድርግ!! ለቤት ገንቢዎች በእግረ መንገድ ያለኝ ምክር ነው፡፡

 

በዚህች ሀገር የገበያ ህግ እንዳይሰራ እነዚህ ህገወጦች በቀጥታ በጉቦ፣ አገልግሎት በመንፈግ የሚያደርሱብን ጉዳት አልበቃ ብሎዋቸው ሰርቀው ያገኙትን ገንዘብ ህጋዊ ለማድረግ ምስኪን ዜጎች ማረፊያ እንዳይኖረን የሚያደርጉት አስተዋፅኦ እንዲሁም ለዚህም ዋነኛው ተባባሪ በውድ መሬት የሚቸበችበው መንግሰት መሆኑ ታሰቦኝ፤ እንደ አዲሰ እውቅት መብገን ጀመርኩና እናንተም ትበግኑ ዘንድ ነው ይህን ላካፍላችሁ የወደድኩት፡፡ እንግዲ ይህ ገፊ ምክንያት ሆኖን የመሬት ሰሪቱ በዕለት ከዕለት ኑሮዋችን መጥቶ እያሰቃየን ነው ብልን ለለውጥ ካልተነሳን፣ ሌላ ምን በቂ ምክንያት ነው የምንጠብቅው? የሚለው ጥያቄ በእንጥልጥል የሚቆይ ነው፡፡

 

በህጋዊ መንገድ መሬት የሚፈልጉ ሰዎችም ከህገወጦቹ ጋር ነው ግብ ግብ የሚያያዙት፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የቁጥ ቁጥ መሬት አቅርቦት ፖሊስ ነው፡፡ መንግስት የመሬት አቅርቦቱን ሆን ብሎ እያሳጠረ፤ ሌቦቹ እንዲመቻቸው ዕድል እንዲፈጠር እያደረገ ነው፡፡ መሬት በመግቢያዬ እንዳልኳችሁ የመንግሰት ነው እንጂ በፍፁም የህዝብ አይደለም፤ ህዝብማ በመንግሰት እጅ በተያዘ መሬት ሰበብ የሻይና ማኪያቶ ዋጋ ላይ ጭምር ጫና የሚፈጥር ሆኖበታል፡፡ የዚህ መሬትን በመንግስት እጅ የማቆየት ፖሊስ ዋናው ገፊ ምክንያት ፖለቲካም መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ መሬቱን ይዞ የሊዝ ሂሣብ ሳይከፍል፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሳይኖርበት፣ ግብዓቶችን ከቀረጥ ነፃ አሰገብቶ ኮንዶሚኒየም በርካሽ እሰራላሁ እያለ ለዚህም በስልጣን መቆየት አለብን እያለ ይገኛል፡፡ ገዢው ፓርቲ፡፡ ዋናው ፖለቲካዊ ግቡ በስልጣ ገዢውን ፓርቲ ማቆየት ነው፡፡ ይህ ገዢ ፓርቲ በስልጣን ላይ ከቆየ ገዢ መደቦች እየሰረቁ ገንዘብ ያገኛሉ፤ በስርቆት ያገኙትን ገንዘብ ደግሞ በውድም ቢሆን መሬት በመግዛት ዘላቂ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቅላቸው በኢኮኖሚ ደንዳና የሆነ ሰርዓት ይገነባል ብለው ያምናሉ፡፡ ይህች ፍልሰፍና ግን የብዙሃኑን ተጠቃሚነት በጎዳ መልኩ ስለሆነ እየተሰራ ያላው በምንም መልኩ ሊሳካ የሚችል አይደለም፡፡ በአሸዋ ላይ የተሰራ ቤት ዓይነት ነው፡፡ አውሎ ንፋስ አይጠብቅም ትንሽ ንፋስ ጠራርጎ ያፈርሰዋል፡፡ ልብ መግዛት ያለብን ይመስለኛል፡፡

 

ፅሁፌን ከዘጋው በኋላ ዋጋው በአቅርቦት መሻሻል ይቀንሳል ብለን ተሰፋ ያደረግነው ሰኳርም ቢሆን የዋጋ ጭማሪ ያደረገ መሆኑን በሬዲዮ ሰማው፡፡ ይህ ምንም አያስገርምም፡፡ የሚያስገርመው መግለጫ የሰጡት ኃላፊ ማብራሪያ ነው፡፡ የዋጋ ጭማሪ የሚባል ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ለትራንስፖርት ተብሎ ዘጠና አምሰት ሳንቲም በኪሎ ተጨመረ እንጂ፤ የዚህ ምክንያት ደግሞ ቀደም ብሎ ሰኳሩ ከውጭ ስለሚመጣ ከጅቡቲ በቀጥታ ይገባ ስለነበር ነው፡፡ በማለት ቀደም ሲል ስኳር የትራንሰፖርት ወጪ የለበትም የሚል መንፈስ ያለው መግለጫ ሰጡ፡፡ ይህ መግለጫ ህዝቡን እንዴት እንደናቁት ከማሳየት ውጪ አንድም የእውቀትና እውነት መሰረት የለውም፡፡ የዋጋ ጭማሪ አይደለም የትራንሰፖርት ነው!! ምን የሚሉት ፌዝ ነው፡፡ ዋጋ እንዴት ነው የሚተመነው? ፋብሪካው ይህ የመጀመሪያ ምርቱ ነው? እሰከዛሬ ትራንስፖርት ማን ነበር የሚሸፍነው? መግለጫውንም ሁሉንም ትተን አሁንም ቢሆን በተጨመረው ዋጋ ስኳሩ የታለ ነው? ያለው ጭማሪውን ዋጋም ጨምሮ ይገዛል፡፡ የሌለው ድሮ ከሚገዛው መጠን ቀንሶ ይገዛል፡፡ በተለይ የመንግሰት ሰራተኛው በቅርቡ የትራንሰፖርት ዋጋ ተጨመረበት፣ አሁን ደግሞ የስኳር ማጓጓዣ ተጨመረበት፣ ቀጥሎ ስኳርን ተከትሎ ዳቦ ይጨምራል ወዘተ.. ደሞዝ ግን እንዳለች ነው፡፡ መፍትሔው ልጆችን ስኳር ለጤና ጥሩ አይደለም ብሎ ማስተው ነው፡፡ ዳቦ እንዴት ተብሎ ይከለከል ይሆን?

 

ታስታውሱ እንደሆነ የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደረ ዋጋ ይጨምር የነበረው ሙገር ሲምንቶ ፋብሪካ አሁን ዋጋ መቀነሱን ማስታወቂያ ከፍሎ እየነገረን ነው፡፡ ምክንያቱም የመንግሰት ያልሆኑ ተወዳዳሪዎች ስለመጡበት እና እየመጡበት ስለሆነ ነው፡፡ ስኳር ይህን እድል እንዳያገኝ ማዕቀብ ያደረገብን መንግሰት ነው፡፡ ሁሉም ፋብሪካ እኔ እስራለሁ ብሎ፡፡ ቢሰራውም ዋጋ አይቀንስም፡፡ ለምን? የሚታለብ ላም ነው ይለናል፡፡ ስለዚህ ይህን የኑሮ ውድነት የጫነብን እየጫነብንም ያለው፣ በመንግሰት ስም የተቀመጠው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ዘራፊ ቡድን ነው፡፡ ቸር ይግጠመን፡፡

የአቶ ድሪባ ኩማ አስተዳደርና በቅሬታ የምትናጠው አዲስ አበባ

$
0
0

<div>ረፖርተር
መጋቢት 22, 2006 ዓ.ም
በአዲስ ከንቲባና ነባር ካቢኔ ሥራውን የጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰባተኛ ወሩን ይዟል፡፡

አስተዳደሩ የቆየባቸው ሰባት ወራት የሥራ ክንውን የከተማውን ነዋሪዎች ብሶትና ችግር የፈታ ሳይሆን፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ጐልተው የታዩበት ነበር ማለት ይቻላል፡፡

የአቶ ድሪባ ኩማ አስተዳደርና በቅሬታ የምትናጠው አዲስ አበባከ2001 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ለአምስት ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በከንቲባነት ሲመሩ ከነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤትን ቁልፍ የተረከቡት አቶ ድሪባ ኩማ፣ የከተማውን ነዋሪዎች ሲያንገሸግሻቸው የቆየውን የመልካም አስተዳዳር እጦት ችግር በመጠኑም ቢሆን ይፈቱታል የሚል ግምት ተሰጥቶዋቸው እንደነበር ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ቅድሚያ ግምት የሰጡት ዝም ብለው ሳይሆን በፌዴራል መንግሥት ጭምር ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት ያለባቸው በዋናነት፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና የሙስና ጉዳዮች በመሆናቸው ጭምር ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለሚጠይቋቸው የመብትም ሆነ ሌሎች ጥያቄዎች ተገቢ የሆነ ምላሽ ማግኘት ባለመቻላቸው፣ የመልካም አስተዳደር እጦትን በማንሳት ጠዋት ማታ ሲያማርሩ መክረማቸው የአደባባይ ሚስጥር መሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ ይገልጻሉ፡፡

የከተማውን ነዋሪዎች ብሶትና የዕለት ከዕለት ምሬት የተሰማቸው በሚመስል ሁኔታ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ተክተው የተመረጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝም ትኩረት ሰጥተው ከሚንቀሳቀሱባቸው የሥራ ዘርፎች መካከል በዋነኛነት የጠቀሷቸው የመልካም አስጸዳደር እጦትንና ሙስናን መዋጋት እንደነበር ነዋሪዎች ያስታውሳሉ፡፡

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ከንቲባ መሾሙን ተከትሎ፣ በአስተዳደሩ መዋቅር ላይ ለውጥ ተደርጐ የአገልግሎት አሰጣጥ ለውጥ ያመጣል የሚል ግምትም ነበር፡፡ አስተዳደሩም ለውጥ ለማምጣት ቆርጦ የተነሳ በሚመስል ሁኔታ ለሰው ኃይሉ ግምገማዊ ሥልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ በሥልጠናውም 500 ከፍተኛ አመራሮች፣ 3,000 መካከለኛ አመራሮችና 52 ሺሕ ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

<a href=”http://www.zehabesha.com/wp-content/uploads/2014/03/የአቶ-ድሪባ-ኩማ-አስተዳደርና-በቅሬታ-የምትናጠው-አዲስ-አበባ.jpg”><img class=”size-medium wp-image-26797 alignleft” alt=”የአቶ ድሪባ ኩማ አስተዳደርና በቅሬታ የምትናጠው አዲስ አበባ” src=”http://www.zehabesha.com/wp-content/uploads/2014/03/የአቶ-ድሪባ-ኩማ-አስተዳደርና-በቅሬታ-የምትናጠው-አዲስ-አበባ-300×187.jpg” width=”300″ height=”187″ /></a>ነገር ግን መልካም አስተዳዳርን በማስፈንም ሆነ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የኅብረተሰቡ ቅሬታ የሚፈታ አልሆነም፡፡ በዋናነት የመልካም አስተዳደር እጦት ከሚስተዋልባቸው የሥራ ዘርፎች መካከል መሬትና መሬት ነክ ይዞታዎች፣ የትራንስፖርት አቅርቦት፣ ንፁህ የመጠጥ የውኃ አቅርቦት፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትና በአስተዳደሩ ሥልጣን ክልል ውስጥ ባይሆንም የኤሌክትሪክ መቆራረጥና የቴሌኮሙዩኒኬሽን ችግሮች በስፋት የሚስተዋሉ ናቸው፡፡

<em><strong>መሬትና መሬት ነክ ይዞታዎች</strong></em>

የሙስና መፈንጫ ናቸው ተብለው ከተፈረጁ አራት ዘርፎች መካከል አንዱና ዋነኛው መሬትና መሬት ነክ ይዞታዎች ዘርፍ ነው፡፡ በተለይ የቀድሞው ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ የአስተዳደሩን ሥልጣን ከተረከቡበት ከ2001 ዓ.ም. ጀምሮ በዘርፉ ማሻሻያ ለማድረግ ብዙ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡

ከተሠሩት ሥራዎች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ዘርፍን መዋቅር መለወጥ፣ የሰው ኃይሉን ማሟላትና ለሥራው ብቁ ማድረግ ነው፡፡ የሕግ ክፍተቶችን ለመሙላት ደግሞ የፌዴራል መንግሥት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ አዋጅ በኅዳር ወር 2004 ዓ.ም. ወጥቷል፡፡ በዚህ አዋጅ መነሻነት በርካታ ደንቦችና መመርያዎች በአስተዳደሩ ወጥተዋል፡፡

በዚህ መሠረት አስተዳደሩ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከማቋቋሙም በተጨማሪ፣ በሥሩ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ክትትል ባሥልጣን፣ የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ አገልግሎት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት፣ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲና የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ኤጀንሲ መሥሪያ ቤቶች እንዲቋቋሙ ተደርጓል፡፡

እነዚህ መሥሪያ ቤቶች የሚመሩባቸው ሕግጋትና ልዩ ልዩ የሕግ ማዕቀፎች ከመውጣታቸውም በተጨማሪ የሰው ኃይል እንዲሟላላቸው ተደርጓል፡፡

ከአቶ ኩማ ደመቅሳ ሥልጣኑን የተረከቡት አቶ ድሪባ ኩማ የሥልጣን ዘመን፣ የመሬት ዘርፍ በተቀመጠው ዕቅድ መሠረት ቢደራጅም ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ነዋሪዎች ቅሬታ ማንሳታቸው አልቀረም፡፡

በመሬት ተቋማት ላይ እየቀረቡ ከሚገኙ ቅሬታዎች መካከል ከዓመታት በፊት የቀረቡ የመሬት ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸው፣ ለአገር ይበጃሉ የተባሉ ፕሮጀክቶች የሚያቀርቡት የማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎች አለመስተናገዳቸው፣ ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ላይ ዕርምጃ አለመወሰዱ፣ ለጥቃቅን ጉዳዮች ሳይቀር ውሳኔ የሚሰጥ አመራር መጥፋት የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሰነድ አልባ ይዞታዎች ካርታ አሰጣጥ የተጓተተ መሆኑና ለተነሺዎች የሚሰጠው ካሳ ፍትሐዊ አለመሆኑ ከሚነሱ ችግሮች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

አስተዳደሩ እነዚህን ችግሮች በተመለከተ ያለው አቋም በሕግ መሠረት ሊስተናገዱ የማይችሉ ናቸው የሚል ነው፡፡ አለፍ ሲልም ‹‹ችግሩን ተገንዝበናል፣ የኅብረተሰቡን ቅሬታ እንደ ግብዓት ወስደናል…›› የሚል መሆኑን ጥያቄያቸው ያልተመለሰላቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ የሊዝ ሕጉ በዋነኛነት መሬት የሚቀርበው በጨረታ አግባብ ነው ይልና የከተማው ከንቲባ ግን ፋይዳ ያለው ፕሮጀክት ነው ብለው ካመኑ ለካቢኔ ቀርቦ በልዩ ሁኔታ ሊስተናግድ እንደሚችል ይገልጻል፡፡

ነገር ግን ፋይዳ አላቸው ተብለው በልዩ ሁኔታ ይስተናገዳሉ የሚባሉት ፕሮጀክቶች በግልጽና በዝርዝር ባለመቀመጣቸው፣ የመሬት ቢሮ ሠራተኞች የሚቀርቡላቸውን ጥያቄዎች ለማስተናገድ ዝግጁዎች እንዳይሆኑ አድርጓል ሲሉ የሕግ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በዚህ ምክንያት የከተማው የሊዝ ማስፈጸሚያ መመርያና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የሊዝ አዋጅ ብዙም ሥራ ላይ ሳይውሉ እንዲሻሻሉ መመርያ መሰጠቱ እየተነገረ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ባለሀብቶች ቀደም ሲል የቀረቡት የመሬት ጥያቄዎች ሊስተናገዱ ባመቻላቸው ቅሬታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

የከንቲባው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚያስኬዱ አንዳንድ ነገሮች መኖራቸውን፣ የሊዝ አዋጁና የሊዝ አዋጅ ማስፈጸሚያ የትርጉም ችግር ከመጣ እንደሚሻሻል ጠቅሰው፣ የመሬት አቅርቦትን በተመለከተ ግን አስተዳደሩ ትኩረት አድርጎ የነበረው ለኮንዶሚኒየምና ለ40/60 ቤቶች የሚያስፈልጉ ቦታዎችን ማቅረብ ነው፡፡ ለጨረታ የሚቀርቡ መሬቶችን በማዘጋጀት በኩል የተወሰኑ መጓተቶች እንደነበሩና በሚቀጥሉት ወራት ለጨረታ የሚቀርቡ ቦታዎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አቶ አሰግድ ተናግረዋል፡፡ አስተዳደሩ በዓመቱ መጀመርያ ላይ 1,200 ሔክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ እንደሚያቀርብ ገልጾ ነበር፡፡ ነገር ግን በእስካሁኑ ቆይታ የዚህን ዕቅድ ሩብ እንኳ ለገበያ አለማቅረቡን በርካታ ሰዎች ይናገራሉ፡፡

በመሬት ዘርፍ ችግር የነበሩ ጉዳዮችን የቀድሞ አስተዳደር ቅርፅ አስይዞታል የሚሉ በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችና ባለሀብቶች፣ ከከንቲባ ድሪባ ኩማ በርካታ አገልግሎቶች ቢጠብቁም እንዳልተሳካላቸው እየገለጹ ነው፡፡

<em><strong>ውኃ</strong></em>

አስተዳደሩ በግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙ ጥሩ እየተሠራ መሆኑን የገለጸው አንዱ ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በሚመለከት ነው፡፡ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ጥልቅ ጉድጓዶችን በመቆፈርና ግድቦችን በማስፋፋት እንደሚያቀርብ ገልጿል፡፡ አስተዳደሩ ውኃን በሚመለከት በስድስት ወራት ውስጥ የሠራውን ግልጽ ሆኖ በሚታይ ሁኔታ ባያስቀምጥም፣ በጥቅሉ በበጀት ዓመቱ እየሠራቸው ያሉትንና ሊሠራቸው ያቀዳቸውን ተናግሯል፡፡ በበጀት ዓመቱ በአቃቂ 19 ጥልቅ ጉድጓዶችን እየቆፈረ መሆኑንና 80 ሺሕ ሜትር ኩብ ውኃ ማምረቱን በሪፖርቱ ቢገልጽም ወደ ሥርጭት አልገባም፡፡ በለገዳዲ ደግሞ 11 ጥልቅ ጉድጓዶችን መቆፈር መጀመሩንና ሲጠናቀቅ 40 ሺሕ ሜትር ኩብ ውኃ ማምረት እንደሚጀምር ይናገራል፡፡ የድሬ ግድብን በማሻሻልና የለገዳዲ ማጣሪያን በማስፋፋት የውኃን ምርት ወደ 195 ሺሕ ሜትር ኩብ ለማሳደግ እየሠራ መሆኑንም በሪፖርቱ ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ አስተዳደሩ የውኃ ምርትን በማሳደግ በኩል ከፍተኛ የሆነ ሥራ እየሠራና የጀመራቸው የጉድጓድ ቁፈራ፣ ግድብ ማስፋፋትና የክረምት ውኃ ጥበቃን በሚመለከት በኩራት እየተናገረ ቢሆንም፣ በከተማው ውስጥ እየታየ ያለው እውነታ ግን የተገላቢጦሽ መሆኑን ሁሉም ነዋሪዎች ይስማሙበታል፡፡

በከተማው በተለይ ባለፉት አራትና አምስት ወራት ውስጥ የውኃ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ምሬት እየፈጠረ ነው፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት የውኃ እጥረት ያለባቸው የከተማው አካባቢዎች ዳገታማ ቦታዎችና ከማሠራጫ ጣቢያዎች ርቀው የሚገኙ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ግን ከማዕከል አካባቢዎች ጀምሮ የውኃ ችግር ከፍተኛውን ቦታ ይዞ ይገኛል፡፡ የመሠረተ ልማቶች መስፋፋት ለውኃ እጥረት በምክንያትነት ቢጠቀሱም፣ ነዋሪዎች ግን አይስማሙም፡፡ አዲስ አበባ ከተማ እየሰፋች መሆኗን ሁሉም ነዋሪዎች የማይክዱት ሀቅ ነው፡፡ ነገር ግን ከከተማው መስፋፋት ጋር ተያይዞ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራባቸው ከሚገቡ ነገሮች አንዱና ዋነኛው በቂ የውኃ ምርት ማቅረብ ላይ መሆኑን አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የከተማው የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ባልደረባ ይናገራሉ፡፡ ባለሥልጣኑ በንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦትና ፍሳሽ ማስወገጃ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚናገረውና ለመንቀሳቀስ የሚሞክረው በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወራትና በበጀት መዝጊያ ወቅት መሆኑን ሠራተኛው ይናገራሉ፡፡

የበጀት ዓመቱ ሲጀመር በተለይ ውኃ የማይደርስባቸው ቦታዎች ይመረጡና ቅድሚያ ተሰጥቶ እንዲሠሩ በሚል ብዙ ገንዘብ ወጪ እንደሚደረግ የሚናገሩት ሠራተኛው፣ ፕሮጀክቶቹ ከጅምር ቁፋሮ ሳያልፉ በኃላፊዎች የወረቀት ላይና የዓውደ ጥናት ፕሮፓጋንዳ ታጅበው በጀት ዓመቱ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል፡፡ በጀት ዓመቱ ሊዘጋ ወር ሲቀረው፣ በተለይ ፍሳሽ ለማስወገድ በሚል የክረምቱን ጭቃ የሚያባብሱ ቁፋሮዎች በየመኖሪያ ሠፈሮች ይቆፈሩና የተረፈው በጀት እንዲጣጣ እንደሚደረግም አክለዋል፡፡ ይኼ አሠራር የተለመደና አሁንም መልኩን ቀይሮ የተለያዩ ሰበቦች እየተደረደሩ፣ ማለትም የመንገድ ሥራ፣ የባቡር ሀዲድ ዝርጋናታና ሌሎችም ምክንያቶች እየቀረቡ የኅብረተሰቡ ንፁህ የመጠጥ ውኃ የማግኘት ችግር ተባብሶ መቀጠሉን አውስተዋል፡፡

የባለሥልጣኑ ባልደረባ እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ እጦት ከቀናት አልፎ ወራትንም እያስቆጠረ መሆኑን እየገለጹ ናቸው፡፡ በወረቀት ላይ በሚቀርብ ሪፖርት ብቻ የከተማውን የንፁህ መጠጥ ውኃ ችግር ለመፍታት የጉድጓድ ቁፋሮና የግድብ ማስፋፋት ሥራ እያከናወነ ባለበት ሁኔታ፣ ችግሩ ከ25 እስከ 30 ዓመታት የሚወገድበትን ፕሮጀክት ዘርግቶ እየሠራ መሆኑን በስድስት ወራት ያቀረበውን የአፈጻጸም ሪፖርት ነዋሪዎች ውድቅ አድርገውታል፡፡

<em><strong>የቤቶች ልማት ፕሮግራም</strong></em>

አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰበት መሆኑን ከሚናገርባቸው ተቀዳሚ ተግባራት መካከል የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር መቅረፍ ይገኝበታል፡፡ በመሆኑም በከንቲባ ኩማ ዘመን የተጀመሩና ያልተጠናቀቁ 95 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ማጠናቀቅና በበጀት ዓመቱ የ65 ሺሕ ቤቶችን ግንባታ ለማስጀመር መሆኑንም መናገሩ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም በ2003 ዓ.ም. የተጀመሩ 17,171 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታን 92 በመቶ ማጠናቀቁን ጠቁሟል፡፡ በ2004 በጀት ዓመት ደግሞ በማስፋፊያና መልሶ ማልማት በ16 የተመረጡ ቦታዎች 44,709 ነባር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ እያፋጠነ መሆኑንም በስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸሙ ላይ አስታውቋል፡፡ ለሌሎች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች 33,593 ቤቶችን ግንባታ እያፋጠነ መሆኑንና ለ40/60 ቁጠባ ቤቶች ተመዝጋቢዎች በአራት ሳይቶች እየገነባ መሆኑን በሪፖርቱ አካቷል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ በሚመለከት አስተዳደሩ በቅርቡ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠበትን የ50 ሺሕ ቤቶች ግንባታ ጨምሮ በጥሩ ሁኔታ እየሠራ መሆኑንና የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሆነ፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከመናገር አላረፈም፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤትን በሚመለከት የሚናገሩትና አስተዳደሩ ‹‹እየሠራሁ ነው›› የሚለው ግን የሚጣጣምና የሚገናኝ አይደለም፡፡

የመኖሪያ ቤትን ችግር ለመቅረፍ በሚል የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ጽንሰ ሐሳብ የተጀመረው በ1996 ዓ.ም. ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ የከተማው ከንቲባ በነበሩበት ዘመን መሆኑ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ተጋግሎ በነበረው የምርጫ 97 የምረጡኝ ቅስቀሳ ተከትሎ የመጣው የጋራ ቤቶች ግንባታ ምዝገባ፣ በአብዛኛው የከተማ ነዋሪዎች ብዙም ትኩረት አልተሰጠውም ነበር፡፡ ቢሆንም ግን በወቅቱ ከ453 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች መመዝገባቸው ይታወሳል፡፡ ለተከታታይ ዘጠኝ ዓመታት ድጋሚ ምዝገባ ሳይደረግ፣ በ1996 ዓ.ም. ብቻ ለተመዘገቡ ቤት ፈላጊዎች አንድ መቶ ሺሕ ያልሞሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከሰባት ጊዜ በላይ በዕጣዎች፣ ከዕጣ በተጨማሪም በልማት ምክንያት ለሚነሱ ነዋሪዎችና በትዕዛዝ ለተሰጣቸው ሰዎች ተከፋፍለዋል፡፡ በ2005 ዓ.ም. መጨረሻ ወራት ላይ በተደረገው ዳግም ምዝገባ ከ800 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች ሊመዘገቡ ችለዋል፡፡ አስተዳደሩ ምዝገባውን በአራት የተለያዩ ፕሮግራሞች ከፋፍሎ አካሂዷል፡፡ 10/90፣ 20/80፣ 40/60 እና የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት በሚል፡፡

በመኖሪያ ቤት ችግር የሚሰቃዩ ነዋሪዎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ በየወሩ እንዲቆጥቡ በመገደዳቸው ኑሮን የከፋ ቢያደርግባቸውም፣ አማራጭ ስለሌላቸው ከልጆቻቸው የትምህርት ቤት ክፍያ፣ ከቤት ኪራይና ከቀለባቸው አብቃቅተው መቆጠቡን ተያይዘውታል፡፡ ቀደም ብሎ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት የተመዘገቡ ነዋሪዎች አስተዳደሩ በቅርቡ በዕጣ እንደሚያከፋፍል ቃል የገባውን የጋራ መኖሪያ ቤት እየጠበቁ ቢሆንም፣ አስተዳደሩ ግን ቃሉን አልጠበቀም፡፡

በዳግም ምዝገባው (ከሐምሌ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም.) ለነባር ተመዝጋቢዎች ከ17 ሺሕ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ እንደሚከፋፈሉ፣ በድጋሚ በሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም. እንደሚያከፋፍል የተናገረውን ቃል በማጠፍ፣ ዕጣው የሚወጣው በሰኔ ወር ነው በማለቱ ነዋሪዎች ‹‹ድሮም እነሱን ማመን›› በማለት ቅሬታቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ ሌላው አስተዳደሩ በልማት ምክንያት ለሚነሱ ነዋሪዎች የኮንዶሚኒየም ቤት ለመስጠት ቃል የገባ ቢሆንም፣ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ባለመጠናቀቁ በዕቅዱ መሠረት እየሄደ አለመሆኑን የከንቲባው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ አምነዋል፡፡

በመሀል ከተማ በሚገኙ ቦታዎች ላይ ይገነባሉ በሚል በ40/60 ፕሮግራም የበርካታ ቤት ፈላጊዎችን ቀልብ ለመሳብ ፈልጐ የነበረው አስተዳደሩ፣ ያሰበውን ያህል ተመዝጋቢ ባለማግኘቱ በአራት ሳይቶች ላይ እየገነባ ከመሆኑ ባለፈ ብዙም የተሳካ ነገር ሲያደርግ አይስተዋልም፡፡ አዋጭነቱም ጥያቄ ውስጥ የሚገባ በመሆኑ የ40/60 ተመዝጋቢዎች በማኅበር ከተደራጁት ውስጥ  እንዲካተቱ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ግፊት እያደረገ መሆኑም ይሰማል፡፡ በማኅበር ተደራጅቶና መሬት ወስዶ ለመሥራት የተጀመረው ፕሮግራምም የተፈለገውን ያህል እንደልሆነ እየተነገረ ነው፡፡ በአጠቃላይ አስተዳደሩ በቤቶች ልማት ፕሮግራም ላይ እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ባለፉት ስድስት ወራት ከወረቀት ላይ ያለፈ አርኪ ሥራ አለመሥራቱን ያመለክታል፡፡

<em><strong>የቴሌኮምና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ</strong></em>

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ኤሌክትሪክ በተደረጋሚ ከመቆራረጡም በላይ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ለቀናት እየጠፋ መሆኑ የኅብረተሰቡ የዕለት ከዕለት ችግር ሆኗል፡፡

ኤሌክትሪክ በሚቆራረጥበት ወቅት ውኃና የቴሌኮም ኔትወርክ አብረው የሚቋረጡ በመሆናቸው ኅብረተሰቡ ለከፋ ቀውስ እየተጋለጠ ይገኛል፡፡ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በማይኖርበት ወቅት ጭምር ውኃና ቴሌኮም የሚቋረጡ በመሆናቸውም ችግሩን አባብሶታል፡፡

ይህንን ችግር የከተማው ነዋሪዎች በሰፊው የሚያነሱት በመሆኑ፣ አስተዳደሩ ከሁለቱ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር በጋራ ለመሥራት ኮሚቴ አዋቅሯል፡፡

ከንቲባ ድሪባ ኩማ ባቀረቡት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ይህንን ጉዳይ ጠቅሰዋል፡፡ የከንቲባው ሪፖርት እንደሚለው በኤሌክትሪክና በቴሌኮም ላይ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡

የመጀመርያው የከተማው መልሶ ማልማትና ግዙፍ የልማት እንቅስቃሴ በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች የመሠረተ ልማት (ኤሌክትሪክ፣ ውኃና ቴሌኮም) መስመሮች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ከሁለቱ ተቋሞች ጋር የጋራ ሥራ መጀመሩ፣ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ (ቤንች ማርክ) በመነሳት የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

የከንቲባው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ እንደገለጹት በየ15 ቀኑ በጋራ መድረኩ ውይይት ይደረጋል፡፡ እስካሁን ድረስ የቴሌኮም ችግርን ለመፍታት በ400 ቦታዎች ላይ የቴሌኮም አንቴናዎች መትከያ ያስፈልጋል ተብሎ፣ 327 ቦታዎችን አስተዳደሩ መስጠቱንና ቀሪዎቹ በሕንፃዎች አናት ላይ የሚተከሉ በመሆናቸው ኢትዮ ቴሌኮም ከሕንፃ ባለቤቶች ጋር እየተነጋገረበት መሆኑ ተወስቷል፡፡

የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ለማስቀረትም የኤሌክትሪክ መስመሮችና ማስፋፊያ ጣቢያዎችን አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አቶ አሰግድ አክለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኢኮኖሚያዊና በማኅበራዊ ዘርፎች በርካታ ቅሬታዎች እየቀረቡበት ይገኛሉ፡፡ የኅብረተሰቡን ቅሬታ መሠረት በማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት፣ በየወሩ ከኅብረተሰቡ ጋር የሚገናኝበትን አሠራር ከታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ መዘርጋቱን አስታውቆ ነበር፡፡

በዚህ መድረክ በየጊዜው ኅብረተሰቡ በርካታ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን ያለማቋረጥ ከማንሳቱም በላይ፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ችግሩን ከመሠረቱ ለማድረቅ እየሠሩ መሆናቸውን ከመናገር አልተቆጠቡም፡፡

ነገር ግን ከጥቃቅን እስከ ትላልቅ የሚነሱት ችግሮች ከመፍታት ይልቅ ይበልጥ እየተተበተቡ መሄዳቸውን በተለያዩ መድረኮች እየተገለጹ ነው፡፡ በዚህም የከተማው ነዋሪዎች እርካታ እንዲያገኙ ማድረግ አልተቻለም፡፡

ነዋሪዎች እንደሚሉት ለችግሮቹ ሁሉ ቁልፍ የሆነው የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በባለቤትነት ስሜት ሥራዎችን መሥራት አለመቻላቸው፣ ከአቶ ኩማ ጋር የከረመው አሮጌው ካቢኔ እንዳለ ሳይነካ ከአቶ ድሪባ ጋር እንዲቀጥል መደረጉ በምክንያትነት እየተጠቀሰ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበርካታ ችግሮች የተተበተበ በመሆኑ መዋቅራዊ ለውጥና በሙያ የበለፀገ የሰው ኃይል ሥምሪት ወሳኝ መሆኑን ነዋሪዎች በአፅንኦት ይገልጻሉ፡፡
<div></div>
</div>

”የሃይማኖቴን ጠላት ወርውሬ ባልገድል ሞቼ ፈጣሪዬ በደሜ ይበቀልልኝ ” ሰማዕቱ አቡነ አቡነ ጴጥሮስ (ቪድዮ)


ሞቴ ተሰውሮ –ከዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

$
0
0

ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ


ሞቴ ተሰውሮ የሰረስረኛል፣
በያንዳንዱ ዕለት ይሽረረሽረኛል፣
ገንብቶ አሳምሮ ደግሞ ያፈርሰኛል፣
ሾሞ ከፍ አድርጎ ደግሞ ይሽረኛል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የ2007 ዓ. ም አገርአቀፍ ምርጫና የሸንጎ አቋም

$
0
0

መጋቢት 27፣ 2006 (April 5, 2014)

shengoየኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) የሰብዓዊ መብት፣ የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የሕግ የበላይነት፣ የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት…ወዘተ እንዲረጋገጡ፤ የዜጎች እኩልነት እውን
እንዲሆንና በማንኛውም የሃገሪቱ ክፍል በነፃ ተንቀሳቅሰው ሃብትና ጥሪት የማፍራት መብት እንዲኖራቸው ዋስትናም እንዲያገኙ የሚያደርግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ አንድነቷና ሉዓላዊነቷ በተጠበቀ ኢትዮጵያ ውስጥ መመሥረት ያስፈልጋል ብለው የሚያምኑና ለዚህም  የሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪል ማህበራትና ግለሰቦች በኅብረት የፈጠሩት  ድርጅት ነው።  ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ  

እስክንድር –ይናገር!

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 06.04.2014 (ሲወዘርላንድ – ዙሪክ)

Eskinder-Nega

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

ይመስክር – ይናገር
ያ —– አርበኛ ፍቅር
የእናቱን ነገር።
የአቅም – አንደበት፤
የመሆንም – ችሎት።

እስክንድር ይናገር
የአዬር አልቦሽ ኑሮ ——- ይዘርዝር
——————— ይመንዝር።
ትርጉሙ – ለእናቱ
ቅኔውም -  ለአዳራው፣
የማግዶ – ውሎው።
ያስቀደመ – እማን
የድጓውም – ዳን
ዓይነታ – የኪዳን።
ሩ———ቁ፤ ——- አሳቢ
አስቀድሞ – አላሚ
ማግስትን – አቅላሚ
ትንቢትን – ተላሚ።

እስክንድር ይናገር
የእናቱን ነገር።

ተሰራ በእስክንድር
የነፃነት – ቀመር፤
በተግባሩ – ንጥር።
ተበጀ – በእስክንድር
መንፈሳዊ – መስመር
የብራና – ህብር።

የቃና —– አባቱ
ረ ለባቱ።

ዝማሬ ማህሌት
ቀኑ ቀናያለት።

ሚስጥር ተ —— ዚያ፤ ማዶ
ቀራንዮን —— ወዶ፤
እራሱን – ዬሰጠ
ትዳሩን – ዬሰጠ
ናፍቆቱን – ዬሰጠ
ኑሮውን – ዬሰጠ
ምቾቱን – ዬሰጠ
እንግልት – መረጠ
ነገነን ——– ያማጠ።

እስክንድር ይናገር
የእናቱን ነገር።

አለሁልሽ ያለ
ያላወላወለ ————
ብዕር ወለወለ
ለሃቅም አደረ
አብነት —- ሰመረ።
የጽናት አድባሩ
የተቋሙ —-  ድሉ
የወርቅ እሸት ጓሉ
እሱን አሉ አሉ!

ብቃቱ – መካሪ
ኮንፓሱ – መ
ራዕይ – አሳማሪ!

                                  ሥጦታ ለአባ ትርጉም – ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ።

 

 

 

 

ሌሎችም ከደሴ አስተዳዳሪዎች ይማሩ ! ግርማ ካሳ

$
0
0

11ባህር ዳር እንደተደረገው፣  ትላንት መጋቢት 28 ቀን፣  በደሴ ከተማ ፣  ከስድሳ ሺሆች በላይ የተገኙበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል።  የሰልፉን ሁኔታ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ስንመለከት አልፎ አልፎ፣  ሰማያዊ የለበሱ የፖሊስ አባላትን ተመልክተናል። በፖሊስና በሰልፈኞች መካከል ግብግቦች አልተፈጠሩም። የተወረወረ ጠጠር የለም። የተሰበረ ንብረት የለም። የተጎዳ፣ የቆሰለ ወይንም የሞተ ዜጋ የለም። ሰልፉ በሰላም ተጀምሮ ነው በሰላም ያለቀው። እንዲህ አይነት ሰልፍ ደስ ያሰኛል።

 

ለዚህም በዋናናት የደሴን ሕዝብ ላመሰግን እወዳለሁ። ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱን እና ሰላማዊነቱን ነው በድጋሚ ያስመሰከረው። ፈርቶና አንገቱን ደፍቶ መቀመጥ ይችል ነበር። ነገር ግን ፍርሃትን አዉልቆ፣ ከአንገቱ ቀና ብሎ፣ የግፍ ቀንበርን ተቃወመ።  በአደባባይ ድምጹን በማሰማት ጀግንነቱን አሳየ። እኔም፣ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ፣ ሌሎች ኢትዮጵያዉያንን በመቀላቀል፣  በደሴ ሕዝብ መኩራቴን መግለጽ እወዳለሁ።

 

በሁለተኛ ደረጃ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት እና ደጋፊዎችን እንዳመሰግን ይፈቀድልኝ። ሕዝብ የሚያደራጀው ድርጅት ከሌለ ለመንቀሳቀስ፣ አይቻልም ባይባልም፣ ከባድ ነው የሚሆንበት። የአንድነት ፓርቲ በዚህ ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው።

 

የአንድነት ፓርቲ ከአገዛዙ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚ ነን ከሚሉትም በርካታ ቀስቶች ሲወረወሩበት እንደነበረ የሚታወቅ ነው። ዉጭ ተቀምጠው ብዙ የሚያወሩ ፣ ብዙ ብለዋል። ነገር ግን አንድነቶች፣ ዋጋ እየከፈሉ፣ ቲዮሪ እየደረደሩ ማውራት ሳይሆን፣ ትግል ማለት ምን ማለት እንደሆነ በተግባር እያስመሰከሩ ናቸው። ከደሴና አካባቢው ሕዝብ ጋር ሆነው፣ እያነቁትና እየቀሰቀሱት፣ ሕዝቡ ደፍሮ ድምጹን እንዲያሰማ ማድረግ መቻላቸው ትልቅ ነገር ነው። ከዚህ የበለጠስ ምን አለ ? ለዉጥ ሊያመጣ የሚችለው እኮ ሕዝቡ ብቻ ነው !

በሶስተኝነት፣ አዎን፣ የደሴን አስተዳደር ላመሰግን እወዳለሁ። አንዳንዶች «መስራት ያለባቸውን ስለሰሩ ለምን ይመሰገናሉ ?» ሊሉ ይችላሉ። ልክ ነው፣  ሕግን አክብረዉ፣ ዜጎች ሰለማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ መፍቀድ ስራቸው ነው። ነገር ግን እንደ አዲስ አበባ ፣ ባሌ/ሮቢ ፣ መቀሌ……ካሉ፣ ሕገ-መንግስቱን ንቀዉ የዜጎችን መብት በመጋፋት ሰላማዊ ሰልፎ እንዳይደረጉ ከሚያግዱ አስተዳደሮች ጋር፣ የደሴ አስተዳደር ሲነጻጸር በጣም የተሻለ ሆኖ ነው የተገኘው። በጎን ሕግን እንዲያፈርሱ የሚደረግባቸውን ጫና ተቋቁመው፣ ሕግን ማክበሩን መምረጣቸው ያስመሰግናቸዋል።

 

በቅርቡ እንደተከታተልነው፣ አንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደሚያደርግ ባሳወቀ ጊዜ ፣ አስተዳደሩ ሕግ ወጥ ደብዳቤዎችን በመጻፍ ለሰልፉ እውቅና አልሰጥም ብሎ እንደነበረ ይታወቃል። ከዘጠኝ ወራት በፊት፣ የሚሊዮኖችም ድምጽ ለነጻነት፣ ክፍል አንድ፣ እንቅስቃሴ ወቅት፣ አሁንም የአንድነት ፓርቲ በመቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ቅስቀሳዎች አድርጎ፣ ሰልፉ  ነገ ሊደረግ ዛሬ፣  «መቀሌን እንኳን አንድነት ቅንጅትም አልደፈራትም» በሚል፣ የአንድነት መራር አባላትን በማሰርና የቅስቀሳ መኪናዎችን በማገት፣ የመቀሌ የሕወሃት አስተዳዳሪዎች ሰልፉ እንዲጨናገፍ ማድረጋቸው በወቅቱ ተዘግቧል። በባሌ/ሮቢ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የቅስቀሳ ዘመቻ ተደርጎ፣ የሰልፉ ቀን በጠዋቱ፣  ሰልፍ ከተደረገ ከፍተኛ ደም መፋሰስ ይኖራል የሚል ዛቻ በመሰጠቱ፣ ለሕዝብ ደህንነት ሲባል ሰልፍ እንዳይቀጥል የተደረገበት ሁኔታም ነበር። ታዲያ ደሴዎች አስር እጥፍ አይሻሉም ?

እንግዲህ ሌሎች የአገራችን ባለስልጣናት፣ ከደሴ አስተዳደር ይማሩ እላለሁ። «ፖሊሶች ፣ ዜጎችን የሚደበድቡና የሚያወኩ፣ የጥቂት የአገዛዙ ባለስልጣናት አገልጋዮች የሆኑ፣ ሕዝብን የሚያስጨንቁ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ የሚሰነዝሩ፣ በሕገ መንግስቱ የተደነገጉ ሕጎችን የሚሸረሽሩ ሳይሆን፣ በደሴ ሰልፍ እንዳየነው፣  ከሕዝብ ጋር እየሄዱ፣  ሕግና ስርዓትን እያስጠበቁ፣  ሕዝብ የሚያገልግሉና ለሕግ የሚገዙ ይሁኑ» እላለሁ።

 

ለአገራችን የሚያዋጣዉ ሁላችንም በሕግ ፊት እኩል ስንሆን ነው። ባለስልጣናት ሕግን ካከበሩ አገር ሰላም ይሆናል። በደሴ እንዳየነው ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች በሰላም ተጀመሮ በሰላም ይጠናቀቃል። እንግዲህ ሁላችንም ለሕግ ተገዥዎች ሆነን አገራችን በፍቅር እንገባ።

የድንበሩና የዐባይ ጉዳይ!! (አንተነህ ሽፈራው)

የኢትዮጵያ ሽግግር ምክር ቤቱ ኢፕሪል 13 ስብሰባን በተመለከተ (ከሚሊዮኖች አንዱ)

$
0
0

ከሚሊዮኖች አንዱ

comment_stage_5የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ንቅናቄ በሚል የጀመረው እንቅስቃሴ፣ በዉጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ድጋፍ እያገኘ መጥቷል። ኢትዮጵያዉያን በአካባቢያቸው ካሉ የአንድነት ድጋፍ ማህበራት ጋር በመሆን ከሚደግፉት በተጨማሪ፣ የተለያዩ ሲቪክ ማህበራት፣ በዉጭ አገር ያሉ የፖለቲካ ደርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች ሳይቀር፣ ጉዳዩ የአንድ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ጉዳይ ነው፣ በሚል ከሚሊዮኖች አንዱ ነን እያሉ ነው።

ከነዚህ፣ አገር ቤት እየተደረገ ያለዉን እንቅስቃሴ ከሚደግፉ ድርጅቶች መካከል፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት አንዱ ነው።  ምክር ቤቱ የራሱ አላማና ግብ ይዞ እየተንቀሳቀስ ያለ ደርጅት ነው።

በኢትዮጵያ የሚደረገዉን ሰላማዊና ሕጋዊ እንቅስቃሴ ምክር ቤቱ እንደሚደግፍ ብዙ ግዜ አሳዉቋል። አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል የምክር ቤቱ መሪዎችና አባላት  ያሳነሱበት፣ ያንቋሸሹበት፣ «አይሰራም፣ ጊዜ ማጥፋት ነው» በሚል በተዘዋዋሪ መንግስት ሕዝቡ ድጋፍ እንዳይሰጥ የሞከሩበት ጊዜ የለም። ይልቅስ ፣ የሽግግር ምክር ቤቱ፣ በዳያስፖራ ያለው የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል ተወካዮችን ልኮ አብሮ የሚሰራ ከመሆኑም ባሻገር፣ በተለያዩ መግለጫዎቹ አገር ቤት ለሚደረገው ትግል ያለውን ሶሊዳሪቲ በገሃድ ያሳየ ድርጅት ነው።

ለምሳሌ ኦክቶብር ፣ 2013  የሽግግር ምክር ቤቱ «በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉን ትግል እንደግፋለን» በሚል ርእስ ያወጣዉን መግለጫ ማንበብ እንችላለን። መግለጫዉ «የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ለነዚህ ቆራጥ የፖለቲካ ድርጅቶች በተለይም ለሰማያዊ ፓርቲና የአንድነት ድርጅት አመራርና አባላቶች፤ እንዲሁም በየእስር ቤት ተወርውረው ለሚገኙት የኢትዮጵያ የክፉ ቀን ደራሽ ጀግኖች የድርጅት መሪዎችና ጋዜጠኞች፤ ያለንን ከፍተኛ አድናቆት ከመግለጽ ባሻገር፤ ይህንን ግፈኛ ስርአት በህዝባዊ አመጽ መታገልና ማስወገድ የድርጅታችን መርህ ከመሆኑ አኳያ ሙሉ ድጋፋችንን የምንሰጥ መሆኑን እናረጋግጣለን» ሲል ነው፣  አገር ቤት ላሉት ታጋዮች ምክር ቤቱ አጋርነቱን የገለጸው።

ምክር ቤቱ የአንድነት ፓርቲም ሆነ ሌሎች ሰላማዊ በሆነ መንገድ ታግለው፣ በምርጫ አሸንፈዉ፣ በሕጉ መሰረት ሕገ መንግስቱን አሻሽለው፣ ለሁሉም ዜጎች እኩል የሆነች፣ አንዲት፣ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ብትመጣ ፣ እንደ ማንኛዉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የሚመኙትና የሚናፍቁት ነው። ለዚህም ነው ድጋፋቸዉን እየሰጡ ያሉት።

ነገር ግን ነገሮች እንደተጠበቁ ላይሄዱ ይችላሉ። «በአገራችን ኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ቀዉስ የበለጠ እየከረረ፣ ኢሕአዴግ እርሱ ባወጣዉ ሕግ አልገዛም ብሎ፣  ሕገ ወጥና አምባገነናዊ እርምጃዎች በመዉሰድ ፣ ወደ አላስፈላጊ ደረጃ ከተኬደ፣ በኢትዮጵያ አናርኪ እንዳይፈጠር፣ ከወዲሁ አማራጭ መፍትሄ  ማዘጋጀት ያስፈልጋል» ብለው  በሽግግር ምክር ቤቱ የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ያምናሉ። አሁን በስልጣን ላይ ያሉት አምባገነኖች ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል የሚል እምነት በመኖሩም፣ ከወዲሁ በተለይም በዉጭ ያለውን ኃይል በማሰባሰብና ወደ አንድ በማምጣት፣ ተጠባባቂ PLAN  B ለማዘጋጃት እየሰሩ ነው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የሚል ስያሜም ለራሳቸው የሰጡት በዚህ ምክንያት ነው። ስልጣን ለመጨበጥ ሳይሆን፣ ነገሮችን በፈራረሱበት ወቅት፣ የሽግግር መንግስት ተቋቁሞ አገራችን እንደ አገር የምትቀጥልበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ።

አገር ቤት ያለዉ ትግል ተጨባጭ ዉጤት አምጥቶ፣ በኢሕአዴግ እና በተቃዋሚዎች መካከል መግባባት ተፈጥሮ፣ አሁን ያለው ሕገ መንግስት ተሻሽሎ፣  ነገሮች ሁላችንም እንደምንፈልገው ቢሄዱና የሽግግር መንግስት ምክር አላስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ ቢከስም፣ ሁላችንም የምንመኘው ነው። ነገር ግን ያ እስኪሆን፣ «ምናልባት» በሚል መጠንቀቁ አስተዋይነት ነው። ለዚህም ነዉ ጥረታቸው ሊደገፍና ሊበረታታ የሚገባው።

የሽግግር ምክር ቤቱ፣ የፊታችን ሚያዚያ 5 ቀን በዋሺንግተን ዲሲ ስብሰባ ያደርጋል። ስብሰባዉን  ላይቭ በፓልቶክ፣ ወይንም፣ ቴሌኮንፈራንስ የሚተላለፍ ከሆነ ለመከታተል እሞክራለሁ። በዲሲ አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያዉያን በአካል ስብሰባዉን እንዲካፈሉ፣ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣ ሃሳባቸውን እንዲገልጹም አበረታታለሁ። በአገር ጉዳይ ላይ መመካከርና  መወያየት ምንጊዜም ጠቃሚ ነውና።

ስብሰባው፣ ብዙ ጊዜ በዳያስፖራ ከተለመደውና አሰልቺ ከሆነው፣ አገዛዙን ከማዉግዝና ከመስደብ ፖለቲካ ያለፈ፣ የተጨበጡና ሥራ ላይ ያተኮሩ፣ ኢትዮጵያዊያን ማሰባብስ የሚችሉ፣ በሰለጠነ መንፈስ የሚቀርቡ፣ አንኳር ቁም ነገሮችን ጉዳዮችን አንስቶ እንደሚወያይ ተስፋ አደርጋለሁ።

 

 

ስለፍትሕ ሲባል፤ ሥርዓቱ ይፍረስ! (ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

Temesgen-Desalegn4ባለፉት አራት አስርታት ሀገሪቱ አያሌ ተግዳሮቶችን መጋፈጧ ባይዘነጋም፤ በተለያየ ጊዜ ሚሊዮኖችን ካረገፈው አሰቃቂው ረሃብ በማይተናነስ መልኩ ሕዝቦቿን ዋጋ ያስከፈለ ጉዳይ ቢኖር የፍትሕ አለመከበር ያስከተለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍሩ በርካታ ማሳያዎች አሉ።

የየካቲቱን አብዮት ጠልፎ ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ወታደራዊው ደርግ፣ የፍርድ ቤት ደጆችን በጓጉንቸር ቆልፎ ሲያበቃ፣ የራሱ አባላት እጃቸውን እያወጡ ድምፅ በመስጠት በአፄው ባለስልጣናትንም ሆነ ግብረ-አበሮቹ በነበሩ መኮንኖች ላይ የሞት ቅጣትን ያህል የመጨረሻ ከባድ ውሳኔ የማሳለፍን አስደንጋጭ ክስተት ጨምሮ፤ ከከተማ እስከ ገጠር ያደራጃቸው የአብዮት ጠባቂዎችና የገበሬ ማሕበራት ከየቤቱ አንቀው እያወጡ “ነፃ እርምጃ” እንዲወስዱ፣ ከየእስር ቤቱ እየለቃቀሙ በጅምላ እንዲረሽኑ በአዋጅ የፈቀደበት ጊዜ የፍትሕ ምኩራቡ ፈርሶ በግላጭ የተቀበረበት ዕለት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በርግጥ ይህ የማን-አለብኝነት አረመኔያዊ አገዛዝ የታቃውሞውን ጎራ በማጠናከር ታሪካዊ ውድቀቱ እንዲፋጠን ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ እንደነበር ለመረዳት 17 ዓመታትን መውሰዱ አይዘነጋም።

“ፍትሕ አልባው አምባ-ገነናዊ የደርግ ስርዓት አማርሮ በርሃ ያስወጣንና ብሶት የወለደን የለውጥ ሃዋርያት ነን፤ በመቃብሩም ላይ ፍትሕ-ርትዕ የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት አገር እንመሰርታለ” በማለት ከበሮ ይደስቁ የነበሩት የያኔው “ነፃ አውጪዎች”ም፣ ደርግ አፍርሶ የቀበረውን የፍትሕ ምኩራብ አመዱን አራግፈው ቢያነሱትም፤ ባነበሩት አስመሳይ ሥርዓት በኩል በዘውግ ማንነት፣ በሙስናና በሙያ አልባ ዜጎች በክለው ክብር የለሽ ሲያደርጉት በጣት የሚቆጠሩ ወራት እንኳ አልፈጀባቸውም። ‹‹አዲስ ንጉስ አንጂ ለውጥ መቼ መጣ!›› እንዲል ከያኒው፤ ካስወገዱት የደርግ መንግስት ጋር ልዩነታቸው-ደርጉ ያልቻለበትን የተቃውሞ ድምፆች በአዋጅ እንዲንቀሳቀሱ በአንድ በኩል ፈቅደው፣ በሌላ በኩል መልሶ ለመጨፍለቅ የፍርድ ቤቶችን ባረኮት የመጠቀም ባለ ሁለት ገፅ ብልጠታቸው ብቻ ነው።

 

ይህ አይነቱ አገዛዝም ሥልጣን በያዘ ማግስት ሀገሪቱን እንዳሻው ለመርገጥ ሲቪል ቢሮክራሲውን ብቻ ሳይሆን የፍትሕ ስርዓቱንም በአምሳሉ አፍርሶ መስራት ነበረበት። ይሁንና ተቋሙን በዚህ መልኩ ለማዋቀር ጊዜ እንደሚያስፈልግ በመረዳቱ አሁን ድረስ በቂ መከራከሪያ ሊቀርብላቸው የማይችሉ ጉዳዮችን ከፍትሕ ሥርዓቱ ነጥቆ ሕገ-መንግስቱ ውስጥ በመዶል ለሌሎች ሰጥቷል። ለዚህ ደግሞ በቂ ማሳያ የሚሆነው፤ ሕገ-መንግስታዊነትን አስመልክቶ የሚነሱ የማጣራት ኃላፊነቶችን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መስጠቱ ነው። በርግጥ አንዳንድ የወቅቱ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሕገ-መንግስቱ በተረቀቀበት ሰሞን፣ ከሕገ-መንግስቱ የሚጣረሱ አዋጆች፣ ክሶች አሊያም ኩነቶች ሲፈጠሩ፣ የማጣራቱ ኃላፊነት የፍርድ ቤት መሆን አለበት ሲሉ የተከራከሩ ድምፆች ነበሩ። ዳሩ ውሎ-አድሮ ምን እንደሚሰሩ አስቀደመው የሚያውቁት ታጋዮች፣ በዛ ካድሬ-ዳኞች ባላፈሩበት ወቅት እንዳሻቸው ሕገ-መንግስቱን እየናዱ ቢያስሩ፣ አዋጅ ቢያወጡና ቢያስፈርዱ ድጋፉን የሚሰጣቸው ተቋም፣ በኢሠፓውያን እንደተሞላ የሚጠረጥሩት ፍርድ ቤት ሳይሆን፣ እንደ ልብ ሊቆጣጠሩት የሚችሉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑን በመረዳታቸው፣ በፓርላሜንታዊ ሥርዓት ትመራለች በተባለች ሀገር ብዙም ባልተለመደ አኳኋን ሕገ-መንግስታዊ ትርጉም የሚሻቸውን ጉዳዮች የማጣራት ስራን ለዚሁ ምክር ቤት ሰጡት፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የፍትሕ ተቋሙን በፓርቲ ፖለቲካ የተተበተበ፣ ለጉልበተኛ የሚገብር፣ ገንዘብ ሊገዛው የሚችል፣ ተቀናቃኝ ድምፆችን የማፈኛ መሳሪያ… አድርጎ የመቅረፅ ዓላማቸውን ማሳካት ችለዋል፡፡ በውጤቱም ተቋሙ የህግ የበላይነት የተደፈጠጠበት አድሎአዊና በየጊዜው ደካሞችን የሚያጠቃ ከሆነ እነሆ ከሁለት አስርት በላይ አስቆጥሯል።

 

የሆነው ሆኖ የሥርዓቱን ፍትሕ ረጋጭነት በተጨባጭ ፍፃሜዎች አስደግፎ ለማቅረብ ሁለት አብነቶችን እጠቅሳለሁ፡፡ ቀዳሚው የበርካታ ግፉአንን እሪታ ሲወክል፤ ተከታዩ ደግሞ የገዥዎቹን የሙስና እና የጓዳ ፖለቲካ ትስስሮች ይጠቁመናል ብዬ አምናለሁ።

 

የሞገስ ወልዱ-ጩኸት

ሰማይ ከመፍገጓ በፊት፣ ሁሌ ንጋት ላይ ኮተቤ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ተነስቶ፣ በእግሩ ሰከም ሰከም እያለ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ግድም ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይደርስና ዋናው በር ፊት ለፊት ቆሞ ከአንድ ሰዓት ላላነሰ ጊዜ ‹‹ሌባ ዳኛ!›› እያለ ይጮኻል፡፡ ያፏጫል፡፡ ‹‹እናንተ ገላችሁኛል፤ ቀብራችሁኛል፤ አምላክ ፍርዱን ይሰጣል!›› በማለትም ተስፋው በሰማያዊው መንግስት ላይ ብቻ እንደሆነ ያውጃል፡፡ …ይህ ሰው እንደምን ያለ ከባድ በደል ቢደርስበት ይሆን ምሬቱ እንዲህ ጣራ የነካው?

 

አሳዛኙ የሞገስ ታሪክ እንዲህ ይጀምራል፡- በ1997 ዓ.ም የወላጅ እናቱን ወ/ሮ አስካለ ቢፋ ህልፈት ተከትሎ፣ ወንድሙ ኃይሉ ወልደአማኑኤል የወራሽነት ድርሻውን እንዲያካፍለው ክስ መስርቶ ሲያበቃ፤ ሶስት ጥያቄዎችን ለፍርድ ቤቱ ያቀርባል፡-

 

‹‹ንብረትነቱ የእናታችን የሆነ ቀበሌ 14/15 ውስጥ የሚገኝ 250 ካሬ ሜ. ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት፣ ሁለት ማሳ የእርሻ መሬት እና በንግድ ባንክ አራት ኪሎ ስላሴና መገናኛ ቅርንጫፍ የተቀመጠ መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብን ያካፍለኝ፡፡››

 

የከሳሽ ወንድም የሆነው ኃይሉም ፍርድ ቤት ቀርቦ ‹‹ቤትም ሆነ የእርሻ መሬት የሚባል ነገር የለም፤ በባንክ አለ ስለሚባለው ገንዘብም አላውቅም፤ እናታችን በሞተችበት ወቅት ስሟን ለማስጠራት ስል የእርሷ የነበረውን መሬት በ30 ሺህ ብር ሸጬ፤ ለአርባ፣ ለመንፈቅ፣ ለተስካር 10 ሺህ ብር ያወጣሁ ሲሆን፤ ቀሪውን 20 ሺህ ደግሞ ለወንድሜ ማረፊያ የሚሆን ቤት ሰርቼበታለሁ›› ሲል ምላሽ ይሰጣል፡፡ ችሎቱም ‹ቤቱንና የእርሻ መሬቱን በተመለከተ የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩን› ገልፆ ‹የ30 ሺህው ጉዳይ ግን ያለይግባኝ ባይ ፍቃድ ወጪ የተደረገ ስለሆነ፤ የገንዘቡ ግማሽ 15 ሺህ ብር ድርሻው ስለሆነ እንዲሰጠው› በማለት ወስኖ መዝገቡን ይዘጋል፡፡

 

በውሳኔው እጅግ በጣም የተበሳጨው ሞገስ፣ ጉዳዩን በይግባኝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይወስደዋል፤ ይግባኝ ሰሚውም ‹‹ቤቱ ይገኝበታል›› የተባለው ቀበሌ የእናታቸውን ማህደር እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ግና፣ ሀገሪቷ ኢትዮጵያ ናትና፤ ቀበሌው ማህደሩ መጥፋቱን፣ ሟችም በተከሳሽ ቤት ይኖሩ እንደነበረ በደብዳቤ ያሳውቃል፡፡ ሆኖም ቀበሌው ይህንን ምላሽ ከሰጠ ከ14 ቀን በኋላ ‹የቀድሞውን አስተዳደር ጠይቄ ያገኘሁት መረጃ ነው› በማለት ለፍርድ ቤቱ እንዲህ የሚል ሌላ ደብዳቤ ይልካል፡- ‹ወ/ሮ አስካለ የግል መኖሪያ ቤት የነበራቸው ሲሆን፣ ቤቱ ያረፈበት መሬት ለ‹‹ሪል እስቴት›› በመሰጠቱ፤ ምትክ ቦታና ስድስት ሺህ ብር ወስደዋል›። የሰው ምስክሮችም ቀርበው ሟች እናት ቤት ሰርተው እንደነበረ ያረጋግጣሉ፡፡ ይህም ሆኖ የወ/ሮ አስካለ ማህደር ከቀበሌው ‹‹ጠፍቷል›› በመባሉ ምንም አይነት ማስረጃ ስላልቀረበ የቀድሞው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ችሎትም ሊለወጥ አልቻለም፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ላለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛው ፍርድ ቤት በር ላይ ቆሞ መጮኽን ስራዬ ብሎ ይዞታል፡፡ በርግጥ ከቀን ቀን አካላዊ መዳከም እየበረታበት መሄዱ በግልፅ ቢታይም የ40 ዓመቱ ጎልማሳ ሞገስ ወልዱ ዛሬም ከፍርድ ቤት ደጅ ቆሞ መጮኹና ማፏጨቱ የበርካታ ግፉአንን ድምፅ የሚወክል ይመስለኛል።

 

ይህ ጉዳይ የሚያሳየው፣ የመንግስት ደመወዝ እየተከፈላቸው በዜጎች ሕይወት ላይ ሊወስን የሚችል እንዲህ አይነቱን ማስረጃ ያለአንዳች ጭንቀት ‹‹ጠፋ›› ብሎ ለመናገር የሚደፍሩ፣ ስለሕዝብ ብሶትና ችግር ምንም ግድ የሌላቸው ካድሬዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም እንደ ሞገስ ያሉ የፍትሕ እጦት ረመጥ ሆኖ ያንገበገባቸው ምስኪኖች በአደባባይ ሲጮኹ ውለው፤ ሲጮኹ ቢያድሩ ‹‹ምን ይሆን ችግራቸው?›› ብሎ ለማድመጥ የሚሞክር አንድ እንኳን ባለሥልጣን መታጣቱንም ጭምር ነው። ‹‹ሳይሰሙ ቀርተው ይሆናል!›› ማለቱን ከባድ የሚያደርገው ደግሞ፣ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ የሚተላለፉ መንገደኞችም ሆኑ ወደ ተቋሙ የሚመጡ ባለጉዳዮች ክስተቱን የማወቃቸው እውነታ ነው፡፡ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሰዎችን የችሎት ውሎ ለመሰለል ከተከሳሾች ቀድመው የሚደርሱ የደህንነት ሰራተኞችም ሞገስን ለማወቃቸው እኔው ራሴ ምስክር ነኝ። በአናቱም ከዚህ ቀደም በሸገር ራዲዮ ‹‹ኧረ በሕግ›› የሚል ፕሮግራም ያዘጋጅ የነበረውና በአሁኑ ወቅት በ97.1 ኤፍ.ኤም ‹‹የእኔ መንገድ›› የተሰኘ በተመሳሳይ ጭብጥ ዙሪያ የሚያተኩር ፕሮግራም የሚያዘጋጀው በሳሉ የሕግ ባለሙያ ሰለሞን ጓንጉል፣ ይህንን ታሪክ ከአንዴም ሁለቴ ለአድማጭ አድርሶታል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ነው ከቀበሌ አንስቶ ላይ ድረስ ያሉ መንግስታዊ መዋቅሮችን የዘረጋውና የሚቆጣጠረው የኢህአዴግ አመራር አባላት፣ የሞገስን ጩኸት ‹‹አልሰሙም›› ማለቱን ከባድ ያደረገው (በነገራችን ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ ለአስር አመት ያህል በየቀኑ እየተመላለሱ የሚቆሙ አንዲት አዛውንት እና በፍትሕ ሚኒስቴር በር ላይ ቆማ መዋል ከጀመረች ስድስት ዓመት ያለፋት ራሄል የተባለች አቤት ባይ እንስት… መኖራቸውን አልዘነጋሁም)

 

ሙስና እና የጓዳ ፖለቲካ ትስስሮሽ

አገሪቷ በዚህ ሁሉ መፍትሔ እጦትና በፍትሕ መዛባት እየተመሰቃቀለችና በሕዝቦቿም ዋይታ እየተናወፀች ቢሆንም፤ መጽሐፉ ‹‹ዓይን አላቸው አያዩም፤ ጆሮ አላቸው አይሰሙም›› እንዲል፤ ገዥዎቻችን ይህን መሰሉን የድሆችና የአቅመ ደካሞች ብሶት መስማትን ፍፁም አይሹም። እነርሱ የታጋሉትም ሆነ የሚሰሙት አለቆቻቸውንና ባለፀጋዎችን ብቻ እንደሆነ ከሚያሳዩን በርካታ ማስረጃዎች መሃል ለአብነት አንድ ምሳሌ ላቅርብ፡-

 

ጉዳዩ በሙስና ተጠርጥሮ በእስር ላይ ከሚገኘው የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ዳይሬክተር መላኩ ፈንቴ ጋር ይያያዛል፡፡ ከዚህ ሰው ሃያ አንድ ገፅ ከፈጀ የእምነት ክህደት ቃል ውስጥ ኮነ ምህረቱ የተባለ ግለሰብ በአራጣ ማበደር ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ‹‹እነአየለ ደበላ ለዳኛ ጉቦ ሰጥተው በዋስ ከእስር ተፈትተው፣ ከሀገር ለመውጣት ያስባሉ›› የሚል ‹‹መረጃ›› በመስጠት መተባበሩን ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ እንደነገረው ገልፆ፣ ከእስር እንዲለቀቅ መደረጉን እናገኛለን፡፡ መቼም በሙስና ወንጀል ከተጠያቂነት የሚድን ተከሳሽ የሚሰጠው መረጃ ተጠርጣሪዎችን በሕግ ለመጠየቅ የሚጠቅም ሲሆን እንጂ፤ እንዲህ ባለ ከዋናው ክስ ጋር በማይዛመድ ተራና የአሉ-ባልታ ወሬ አለመሆኑን እነገብረዋህድና እነመላኩ ቀርቶ ማንኛውም መንገደኛ እንኳ ሊጠፋው አይችልም፡፡ አውቆ የተኛ… እንደሚባለው ካልሆነ በቀር።

 

የሆነው ሆኖ ከመላኩ ፈንቴ የእምነት-ክህደት ቃል ትኩረት የሚስበው፣ ግለሰቡ በዚህ መልኩ ከሱ ተነስቶለት ከእስር ከተፈታ በኋላ ንብረቱና የባንክ ሒሳቡ መታገዱን አስመልክቶ የተፈጠረው ኩነት ነው፡፡ አቶ መላኩ ጉዳዩን ለመርማሪዎቹ ሲያብራራ ቃል-በቃል እንዲህ ነበር ያለው፡-

 

‹‹አቶ አባይ ፀሀዬ እና አቶ ደመቀ መኮንን ደውለው ‹ግለሰቡ አቤቱታ እያቀረበ ነው፡፡ ለምን አታዳምጡትም? ሲሉኝ፤ እኔም ከዚህ በኋላ ነው ግለሰቡን እቢሮዬ አግኝቼ ከላይ በገለፅኩት ሁኔታ እንዲስተናገድ ያደረኩት።››

 

እነዚህ ሰዎች ‹‹ነፃ አወጣነው›› የሚሉትን ሕዝብ ለስቃይ ዳርገው፣ ጥቂት ባለፀጎችን ብቻ ለማገልገል የቆሙ መሆናቸውን ለማስረገጥ ከዚሁ የእምነት-ክህደት ቃል አንድ ማሳያ ልጨምር፡- ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የተባለ የአዲስ ልብ ህክምና ክሊኒክ ባለቤት ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የሕክምና መሳሪያዎች (የልብ ፒስ ሜከር ተብሎ ተጠቅሷል) በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያስገባ በቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ሠራተኞች እጅ ከፍንጅ ከተያዘ በኋላ መለቀቁን በተመለከተ የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባል የሆነው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም ስልክ ደውሎ ‹‹ክሱን ብታነሱላቸውና በአስተዳደራዊ መፍትሔ ብትሰጧቸው›› ብሎ ከመንገሩም በላይ የግለሰቡ ክስ እንዲቋረጥ የሚጠይቅ ደብዳቤ እንደፃፈላቸው መላኩ ፈንቴ ለመርማሪዎቹ መናገሩ በመዝገቡ ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ይህንን ሁናቴም ከወቅቱ የፖለቲካ አሰላለፍ አኳያ ስንተነትነው አቶ መላኩ ‹ዶ/ር ቴዎድሮስን መስማት፤ ህወሓትን እንደመታዘዝ ነው› የሚል እምነት አድሮበት የተባለውን ፈፀመ ብለን ብንደመድም ተምኔታውያን አያሰኘንም፡፡

 

እነዚህ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ያውም ሀገር በሚጎዳ ወንጀል የተከሰሰ ተጠርጣሪን በተመለከተ ከሥልጣን ገደባቸው አልፈው ‹‹አድምጥ!›› እያሉ የማዘዛቸው ምስጢር ሥርዓቱ ለፍትሕ ያለውን ግድየለሽነት እና በዚህ ሥርዓት የሕግ የበላይነት ብሎ ነገር እንጦሮጦስ መውረዱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል ብዬ አምናለሁ፡፡ በርግጥ ይህንን ጉዳይ ለጥጠን ከተመለከትነው ‹‹…ለምን አታዳምጡትም?›› የምትለዋን ቃል ሰምና ወርቅ የለበሰች ቅኔ አድርገን በመውሰድ ልንፈታት እንችላለን፤ በተለይም መላኩ ፈንቴ ከዚህች ጥያቄ መሰል ትዕዛዝ በኋላ ግለሰቡን ቢሮ ጠርቶ ማስተናገዱን ስናስተውል፡፡ ምንም እንኳን አባይ ፀሀዬ በጊዜው በጉዳዩ ላይ መላኩን ሊያዝበት የሚያስችል መንግስታዊ ሥልጣን /የዕዝ ተዋረድ/ ባይኖረውም፤ አንጋፋ የህወሓት አመራር አባልና የበለጠ የፖለቲካ ጉልበት ያለው መሆኑ፤ ደመቀ መኮንን ደግሞ በብአዴን በኩል የአለቃነቱ ነገር ሲታሰብ፣ አሁንም መላኩ ፈንቴ የተጠየቀውን ‹‹ጥያቄ›› ከማስተናገድ ውጪ ሌላ አማራጭ አይኖረውም ወደሚል ጠርዝ ይገፋናል፡፡ በርግጥ እውነታው ይህ ቢሆንም፣ መላኩ ዛሬም እስር ቤት ውስጥ ሆኖ የቀድሞ አለቆቹንም ሆነ ራሱን ተጠያቂ ለማድረግ አልደፈረም፡፡ በግልባጩ ለቀረቡበት ክሶች በሙሉ ተጠያቂው ገብረዋህድ እንደሆነ ከመናገሩም በላይ እንዲህ በማለት ወንጅሎታል፡-

 

‹‹የአያት ባለቤት በግብር ማጭበርበር ተከሶ በነበረበት ወቅት የተከሳሹ ቤተሰብ የሆነ ሰው እቢሮዬ መጥቶ ‹ገብረዋህድ ምንም ጥፋት ሳያጠፋ ነው የአያት አክሲዮን ማሕበር ባለቤትን ያሳሰረው፤ አሁንም አንድ ሚሊዮን ብር ካመጣችሁ ከእስር ይፈታል ብሎናል› የሚል ጥቆማ አመጣልኝ፡፡ …ገብረዋህድ እና ነጋ ገ/እግዚአብሔር (የነፃ ትሬዲንግ ባለቤት ነው) ጓደኛሞች ናቸው፡፡ ነጋ ዕቃ ሲያስመጣ አያስፈትሽም፤ የነጋም ጓደኞች እነ አልሳም፣ ጌት አስ የመሳሰሉት ድርጅቶች ዕቃ በቀላል ቀረጥና ታክስ እንዲሁም አልፎ አልፎ ሳይፈተሹ ያልፋሉ፤ …ባለቤቱ ሃይማኖትም፣ በነጋ ድርጅት ውስጥ ትሰራለች…››

 

መላኩ ፈንቴ ይህንን ጉዳይ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መናገሩንና ጠቅላይ ሚኒስትሩም፣ ፀጋዬ በርሄን ‹‹ተከታተል›› ብሎት እንደነበረ ከአስረዳ በኋላ እንደሚከተለው ይቀጥላል፡-

 

‹‹ገብረዋህድ በኋላ እንደነገረኝ ባለቤቱን ከነጋ ድርጅት አስወጥቶ በአዜብ ትዕዛዝ መሰረት ኤፈርት ውስጥ ያስቀጠራት መሆኑን ገልፆልኝ ‹አንተም ላይ የሚወራው ስለምትታገል ነው ብላኛለች አዜብ› ሲለኝ እኔም ተከታትዬ ፀጋዬ በርሄ ከምን እንዳደረሱት አልጠየኩም፡፡ መጠየቅ ነበረብኝ፤ ጥፋት ነው፡፡ በአጠቃላይ ገብረዋህድ ላይ ብዙ ነገር ይባል ነበር፡፡››

 

መቼም ይህ ምላሽ በ1981 ዓ.ም ከአስመራ ዩንቨርስቲ በኢኮኖሚክስ ዲግሪውን፣ ከአውስትራሊያ በገቢ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪውን፤ ከለንደንም በቢዝነስ አስተዳደር በተመሳሳይ መልኩ ትምህርቱን ካጠናቀቀና የረዥም ዓመታት የስራና የፖለቲካ ተሞክሮ ካለው ሰው የተሰጠ መሆኑን ስናስተውል፤ ሀገሪቱ የአምባገነን ባለሥልጣናት መቀለጃ ብቻ ሳትሆን፤ የሰዎቹንም የአቅም ማነስ ያመላክታል፡፡ እንዲሁም እነሞገስ ሰሚ ያላገኙበትን ምክንያትም ሆነ በዚህች ሀገር ገንዘብ ያለው የፈቀደውን መፈፀም የመቻሉን ምስጢር ይገለፅልናል።

 

ኢህአዴጋዊ ዕድሜ ማራዘሚያ…

ገዥው ስብስብ የፍትሕ ስርዓቱን ተቋማዊነት ሳይነካ፣ ለጨቋኝነቱ መጠቀሚያ የሚያደርግበት አንዱ መንገድ ከጠቅላይ እስከ ታች በተዋረድ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ድረስ ያሉ ዳኞችን የሚመድብበት አካሄድ ነው፡፡ በርግጥ እንዲህ አይነቱ ሀገርና ሕዝብ አልያም ሞራላዊ ልዕልና እና የሕግ-የበላይነት የማያስጨንቀው አገዛዝ፣ የፍትሕ ስርዓቱ ቅጥ የለሽ ተባባሪነት ሳይታከልበት የሥልጣን ዕድሜውን ማራዘም እንደማይችል መረዳት አይሳነውም፡፡ ይህን ለማድረግም ያለው ብቸኛ ምርጫ ዳኞቹን ከስሩ መሰብሰብ ይሆናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢህአዴግ መሩ-መንግስት ሁለት አካሄዶችን ለመተግበሩ ያሳለፋቸው ሁለት አስርታት በሚገባ ያሳያሉ።

 

የመጀመሪያው የሚሾሙት ዳኞች፣ የግንባሩ ከፍተኛ የካድሬ ማሰልጠኛ እንደሆነ ከሚነገርለት ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ተማሪዎች መካከል ማድረጉ ነው፡፡ ከዚህ ‹‹የትምህርት›› ተቋም ውስጥ የሚወጡ የሕግ ምሩቃን ደግሞ ስለጥልቅ ዘመናዊ የሕግ ፅንሰ-ሃሳብ ለማወቅ ከመትጋት ይልቅ፤ የኢህአዴግ ፖሊሲዎች እና አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሕግን እንዴት ‹‹ለመደብ ጠላት›› መጠቀም እንደሚያስችሉ በሚሰብኩ መምህራን ስር እንዲያልፉ ይገደዳሉ (ስለመምህሮቹ ምሁራዊ ልሽቀት ለመረዳት የሕዝብ ሙስሊሙን ጥያቄ በሽብር ተግባር ለመፈረጅ እና ማሕበረ ቅዱሳንን በአክራሪነት ለመወንጀል በ‹‹ጥናታዊ ጽሑፍ›› ስም የተጓዙበትን ርቀት ማየቱ ብቻ በቂ ይመስለኛል)፡፡ ተማሪዎቹም በዚህን መሰሉ የካድሬ ተቋም ስልጠና ስር ሰንብተው ሲወጡ፤ በፍፅምና ሊታመኑላቸው ይገቡ የነበሩትን ፍትሓዊ ዳኝነትና ህሊና የሚባሉ ጉዳዮችን ጨፍልቀው፣ በተለይም ፖለቲካዊ ነክ በሆኑ አይረቤ ክሶች ፊታቸው በሚቆሙ ንፁሀን ዜጎች ላይ መከራን የሚያዘንቡ አሽከሮች ይሆናሉ፡፡ ይህንን አስነዋሪነት ካለመታከት የሚፈፅሙትም፣ ሥልጣንን እና ተያያዥ ጥቅማ-ጥቅሞችን እያጋበሱ ወደ ከፍታ ሲወጡ ተመልክተናል።

 

ሁለተኛው የግንባሩ አካሄድ ከካድሬ ማሰልጠኛውም ሆነ የተሻለ ነው ከሚባለው የአ.አ.ዩ. የሕግ ፋካሊቲ የሚመረቁትን፣ በተከታታይ ርዕዮተ-ዓለማዊ ጠመቃ የሥርዓቱ ጋሻ-ጃግሬ ማድረግ ላይ ያተኮረው ነው፡፡ በሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ሲያገለግሉ ቆይተው ስደትን የመረጡ ዳኞችና ዐቃቢ-ህግያት በተለያየ ጊዜ እንደ መሰከሩትም አሰልቺ የርዕዮተ-ዓለም ጠመቃ የፍትሕ ሥርዓቱን ነፃነት ጽልመት ካላበሱት ሂደቶች በዋነኛነት ተጠቃሽ ነው፡፡ በአንድ ወቅትም ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ የሀገሪቱን ዳኞች ሰብስቦ ስለሕገ-መንግስት እና ሕገ አተረጓጎም መርህ ሲያስተምር ለማየት የተገደድነው የዚሁ የጠመቃው አንድ አካል በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ዳሩስ፣ ይህማ ባይሆን ኖሮ እስክንድር ነጋ ላይ 18 ዓመት መፍረድ ሕሊና እንዴት ይፈቅድ ነበር? ኦልባና ሌሊሳንስ ለ11 ዓመታት ወህኒ ያስወረወረው ጥፋት ምን ተብሎ በአሳማኝ መልኩ ሊጠቀስ ይችል ይሆን?

…ቀሪው ለሳምንት ይቆየን!


ኢትና አሸሮች፥ የህወሃት የድሜ ልክ እስረኞች (ሳዲቅ አህመድ)

$
0
0

ገና ወጣት ሳሉ የደርግን ስርዓት በመሸሽ ወደ ጠረፍ ያቀኑ ናቸዉ። ዲሞክራሲያዊ መሆን ይቃጣዉ የነበረዉ ህወሃት ሁለት አማራጭ የሰጣቸዉም ነበሩ፤ ደርግን በጦር መታገል ወይም ሱዳን ገብቶ ስደተኛ በመሆን ወደ አዉሮፓ፣ዩናይትድ እስቴትስ ወይም ካናዳ በመሰደድ ህወሃትን በገንዘብና በፖለቲካ መርዳት። ወደ ጦርነት አዉድማ የገቡት ኢትና አሸሮች  እንዳሉ ሆነዉ ሱዳን መግባት የመረጡት በተባበሩት መንግስታት (UNHCR) በኩል ወደ ምእራቡ አለም የመጓዛቸዉ ህልም እዉን እስኪሆን ድረስ በሱዳን ዉስጥ “ኢትና-አሸር” የሚባል ህገወጥ (ሐራም) ስራ ነበራቸዉ። ለአያሌ አመታት በዚህ ህገወጥ ስራ በመሰማራት ህወሃትን የደገፉ ሲኖሩ እነዚሁ ኢትና አሸሮች ዛሬም ካሉበት ቦታ የህወሃት የቁም እስረኞች ሆነዉ ህወሃትን እያገለገሉ ይገኛሉ።

ኢትና አሽር (አስራ ሁለት)የስራ ዘርፍ ምን እንደሆነ ለኔ ለመጻፍ በጣም ያሳፍረኛልና ሱዳን ከነበሩ ኢትዮጵያዉያን ጠይቃቹ ተረዱ። ሰዎችን በሙስና ይዞ ሎሌ ሚያረገው ህወሃት፤ እነዚህንም ኢትና አሽሮች ባሰራቸዉ አሳፋሪ ወንጀል ዛሬም ከርቀት ሆኖ ይቆጣጠራቸዋል።አንዳንዶቹ ንሰሃ አርገዉ ቤተ-ክርስቲያን ወይም ተዉበት አርገዉ መስጊድ ቢገቡም፤ የካድሬነት ስራ ይሰጣቸዋል። ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ባላዉቅም ስለ መስጊዱ ትንሽ ልበል…

ኢትና አሸሮች ምን ያደርጋሉ?

ስርዓቱን ሊነካ የሚችል ስራ ለመስራት ስብሰባ ቢጠራ ስብሰባዉን ንግግር በማስረዘም ማበላሸት፣ከተሰብሳቢዉ ጋር ችግር በመፍጠር ስብሰባዉን የጭቅጭቅ ማድረግ፣ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠራ ቢቻል ሰላማዊ ሰልፉን ማስቀረት ካልሆነ ሰላማዊ ሰልፉ ደካማ እንዲሆን ማድረግ፣ሚስጥርን ለህወሃት አሳልፎ መስጠት፣ “እኔ ከዚህ ዘር ስለሆንኩኝ ነዉ የማልታመነዉ” በማለት ማለቃቀስ፣ በህዝብ ዘንድ የማይደገፍ ሐሳብ ሲሰነዘር ደካማዉን ሐሳብ በመደገፍ ተክቢርን ማዥጎድ ጎድ፣ ፊትና (መከፋፈል) መጣ ብሎ በማልቀስ የሰዉን ልብ በልቶ አቅጣጫ ማስቀየር፣ስርዓቱን በጽኑ የሚቃወሙ ግለሰቦችንና ሚዲያዎችን ስም ማጥፋትና ተዓማኒነትን ማሳጣት ወዘተ የገኙበታል።

ኢትና አሸሮች ዲያስፖራ ባሉ ቡድኖች በቦርድ-በሃላፊነት ተመርጦ ለመስራት የማያቅማሙ ሲሆኑ በተለያዩ ኮሚኒቲዎች በሃላፊነትም ይሰራሉ፤ አንዳንድ የኑሮን እንቅፋቶች ህወሃት ሰለሚያነሳላቸዉ ከሌላዉ የበለጠ ግዜን መለገስ ብቻ ሳይሆን ዳጎስ ያለ ገንዘብን አዉጥቶ በመርዳት የሰዉን አፍ ለማዘጋት ይሞክራሉ። ሰዎችን በጥቅም ለመደለል የሚያረጉት ሙከራ የላቀ ነዉ፤ በመንግስትና በዲያስፖራዉም መሃከል ድልድይ በመሆን ባመራር ደረጃ ላይ ላሉ ወገኖች በኢንቨስትመንት ስም መሬት በማሰጠትና ሌሎችንም ለሙስና የሚመቹ ጉዳዮችንም ያስፈጽማሉ።

ምክር፥ ዉድ ኢትና አሸሮች! ዉድ የሆነዉን ህይወት ለህወሃት አሳልፎ ሰጥቶ የቁም እስረኛ ከመሆን የትላንቱ ታሪካቹ የትላንት ነዉና ዛሬ የናንተን የበደል ገፈት የቀመሱ እህቶችን ይቅርታ ጠይቃቹ፤ አምላክቹን ጥልቅ በሆነ ንሰሃ (ተዉባ) ተማጸኑትና እራሳ ሁን ከህወሃት ቀንበር ነጻ አዉጡ።

ምክር፥በኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የእምነት ማእከላትና ማህበራት ዉስጥ ተሸጉጣቹ የሙስሊምን ሰላማዊ ትግል እንቀለብሳለን ብላቹ የምታምኑ ከሆነ ከንቱዎች ናቹ። የሰሞኑም ግርግራቹ አልሰራም(ያዲሳባዉም ጭምር)፤ እናንተ ለሰራቹት የኢትና አሸር ሐጢዓት ይቅርታ ጠይቁ እንጂ ድምጻችን ይሰማ” የሚለዉ ጀግና ትዉልድም ሆነ መሪዎቹ ከማፍያዉ ህወሃት የላቁ በመሆናቸዉ ይቅርታ አይጠይቁም። ግዜዉ ሳይረፍድ የህወሃትን ሲህር (መተት) ከላያቹ ላይ ገፋቹ ጣሉና ከጀግናዉ ትዉልድ ጋር አብራቹ ጀግኑ።

ዉዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! እነዚህ ኢትና አሸር የምንላቸዉ ንዑሳንን ሴራ ለማሳየት በጃችን ያለዉን የድምጽና የቪዲዮ መረጃ ብንለቀዉ “ለካስ አልቀናል” ብሎ ብዙሓኑ ይደናገጣል። ተወደደም ተጠላም  ለህዝብ በነጻ (ሊላሂ) እንሰራለን የሚሉ የዲያስፖራ ቅምጥሎች ይህን ሰላምዊ ትግል ለማዳከም እንዳልዳከሩት የለም…ግን ዉድቀት ታትማባቸዉለች አሸናፊ አይሆኑምና ልብ ያለዉ ልብ ይበል!

ሳዲቅ አህመድ

 CLK

 

 

ብርሃኑ ዳምጤ –ደቡር አባ መላ ዘአገምጃ

$
0
0

 መስፍን ቀጮ/ወፍ
ከጠቅላይ ቢሮ አዲስ አበባ

Aba-Mela  የሚቀጥለውን ትረካ ለመጻፍ ብዙ ሀሳብ ውስጥ ገብቼ ነበር፡፡ ብጽፈውስ ምን ዋጋ አለው የሚል ስሜትም ተጭኖኝ ነበር፡፡ ሆኖም ‹ጅብ በማያውቁት ሀገር ቁርበት አንጥፋልኝ› እንዲሉ ከላይ የተጠቀሰው ብርሃኑ ደቡር አባ መላ በአዲሶቹ አለቆቹ የተረቀቁለትን ቃለ መጠይቆች ሲያነበንብ መስማቱ ስለሰለቸኝ ‹ማን ያውጋ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ› በማለት የልጅነት ጓደኛዬን ሳልወድ ለማጋለጥ ወሰንኩ፡፡

እኔና ብርሃኑ ዳምጤ በአንድ ማዕድ እየበላን በሰፈር ወንዝ እየተራጨን እየተንቦራጨቅን ብይና አርቦሽ እየተጫወትን ሌላም ሌላም ነገር እየሰራን ያደግን ልጆች ነበርን፡፡ ብርሃኑና እኔ ት/ቤት ስንገናኝ እንዲሁ ጓደኛሞች ሆነን እኔ ከእሱ በዕድሜ አራት ዓመት አንስ ስለነበር ትምህርት የጀመርኩት ከሱ በኋላ ነበር፡፡ አንደኛ ክፍል ስገባ እሱ ወደሶስተኛ ተዛውሯል፡፡ ከሱ በእድሜ ከማነሴ በላይ ደቃቃ በመሆኔ ‹ቀጮ› የሚል ቅፅል ስም ወጥቶልኝ ነበር፡፡ ብርሃኑ በዚያን ጊዜ ከክፍል ልጆች በዕድሜ ይበልጥ ነበር፡፡ በትምህርቱ ደካማ ስለነበር ክፍል ስለሚደግም ታናናሾቹ ይደርሱበትም ይቀድሙትም ነበር፡፡ ለዚህም ነው እኔና እሱ ስድስተኛ ክፍል ላይ የተገናኘነው ብርሃኑ በጣም ወፍራምና ለፍላፊ ነበር፡፡

ሲለፈልፍ በፍንጭቱ ይረጨው የነበረው ምራቅ ከውፍረቱ ጋር ሆኖ ትርክርክነቱን ያጎላው ነበር፡፡ አንድ የጠቅላይ ግዛት ልጅ ‹የድሃ መሃቻ› (ሊጥ ማቡኪያ) ብሎ ጠራው፡፡ ከዚያ በኋላ የድብቅ መጠሪያ ስሙ ሆነ፡፡ ብርሃኑ ምግብ በተለይ ጥሬ ሥጋና እንቅልፍ ከሁሉም በላይ አብልጦ የሚወድ ልጅ ነበር፡፡

ከስድስተኛ ክፍል በኋላ እኔና ብርሃኑ በጣም ጥብቅ ጓደኛሞች ሆንን ብርሃኑን የተጠጋሁት የሰፈር ጉልቤዎች በሚተናኮሉኝ ጊዜ ይከላከልልኝ ስለነበር እሱ የወደደኝ ደግሞ ክፍል ውስጥ የቤት ስራም ሆነ ፈተና ስለማስገለብጠው ከዚያም አልፎ ከትምህርት ቤት በኋላ እቤቴ ሸኝቶኝ ምግብ በልቶ ስለሚሄድ ነበር፡፡ በወላጆቼ በኩል ከቀልደኝነቱ ባሻገር አንድ ልጃቸው በመሆኔ እንደ አይነ ብሌናቸው ያዩኝ ስለነበር ወንድም በማግኘቴ ደስ ብሏቸው ይወዱት ነበር፡፡

የስድስተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈትነን ውጤት ሳንሰማ በክረምት ወር አባቴ በመስሪያ ቤቱ ትዕዛዝ ወደ ጠቅላይ ግዛት በመዛወሩ እኔም አብሬ ተጓዝኩ፡፡ በሶስተኛ ዓመት ክረምት ላይ ለዕረፍት አዲስ አበባ መጥቼ ስለነበር ጓደኛዬን ለማግኘት ሰፈር ስሄድ አያቶቹን ሊጠይቅ አገምጃ ጉራጌና ኦሮሞ አገር መሄዱ ተነገረኝ፡፡ በነገራችን ላይ ብርሃኑ በአባቱ መንዜ ሲሆን በእናቱ ደግሞ የአገምጃ ጉራጌና ኦሮሞ ነው፡፡ ሳላገኘው በመመለሴ እያዘንኩ ወደ ጠቅላይ ግዛት ተመለስኩ፡፡ በዓመቱ አባቴ እንደገና ወደ አዲስ አበባ በመዛወሩ ተመልሼ አዲስ አበባ መጣሁ ብርሃኑንም ወዲያው አገኘሁት፡፡

ብዙ ገጠመኞቻችንን እየተለዋወጥን እንደቀድሟችን አብረን መጫወትና መዋል ቀጠልን፡፡ ታዲያ መስከረም ጠባና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታችንን ስንጀምር እኔ ከአስረኛ ክፍል ልጆች ጋር ስሰለፍ ጓደኛዬ ከዘጠነኞች ጋር ተሰልፎ አየሁት፡፡ ሚኒስትሪ በመውደቁ አንድ ዓመት ደግሟል፡፡ አልገረመኝም ጓደኛዬን ስለማውቀው!

ከስልሳዎቹ መጀመሪያ የኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚያንቀሳቅሱት የመንግስት ተቃውሞና አመጽ እየበረታ  በሄደበት ወቅት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ቀልብ ስቦ የእንቅስቃሴው አጋርና ደጀን አድርጓቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ስድስትና አራት ኪሎ በተነቃነቁ ቁጥር መላው የአዲስ አበባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ወረቀት ይበተናል፣ የከተማ አውቶቢስ ይሰባበራል፡፡ ሌላም ብዙ ሌላ ነገር ይደረጋል፡፡ በዚያን ወቅት የመርካቶን ተማሪዎች የምናስተባብረው ብርሃኑ፣ እኔ፣ ተስፋዬ የማነና ሌሎም ነበርን፡፡ ተስፋዬ የማነ ችኩል ቅብጥብጥ ግብታዊና ደፋር ነበር፡፡ ይህን ስለምናውቅ አደገኛ ሁኔታዎችን እንዲፈጽም እናደርገው ነበር፡፡ አንድ የማልረሳውና እስከ አሁን ድረስ የሚፀጽተኝ ነገር ላውራችሁ፡፡ ከሰፈር ወጥተን ልክ ጠቅላይ ቢሮ ስንደርስ ሹፌሩ ብቻ ያለበት አንድ አውቶቢስ ቆሞ እናያለን፡፡ አውቶቢሱ ብቻ ለምን እንሰብራለን ሹፌሩም መመታት አለበት አለ ብርሃኑ ችኩልና ቅብጥብጡ ተስፋዬ ዕብድ በሚያክል ድንጋይ የሾፌሩን አናት ተረከከው፡፡ ምስኪኑ ሹፌር

የተማሪዎች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የየካቲትን አመጽ አስከተለ፡፡ አመጹ በመካሄዱ ላይ እንዳለ ከውጪ የመጡ ምሁራንና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየፊናቸው ሕቡዕ ጥናት ክበቦችን በማቋቋም ወጣቱን መመልመል ተያያዙት፡፡ በዚህም መሰረት ኢህአፓና መኢሶን ወጣቱን እየተቀራመቱ በየጎራቸው ኮለኮሉት ታዲያ ብርሃኑ፤ ተስፋዬና እኔ የኢህአፓ ሰለባዎች ሆንን፡፡ እንደማንኛውም ወጣት የድርጅቱ ተገዢና ደጀን ለመሆን በሙሉ ልብ ተሰናዳን፡፡ ከብዙ ፈተናና ምስጢራዊ ግምገማ በኋላ ታማኝነታችን በመረጋገጡ ከበላይ አካል የሚሰጠንን ሚሽኑ (ግዳጅ መፈጸም ጀመርን) በዚህ ወቅት ነበር፡፡ ብርሃኑ ዳምጤ ‹‹ደቡር›› የተሰኘውን የኮድ ስም የተጎናጸፈው እኔም ከቀጮ ወደ ‹‹ወፍ›› ተቀየርኩ፡፡ የተስፋዬን ረሳሁት፡፡ በድርጅቱ መዋቅር መሠረት እኔ በቅርብ እንዳውቃቸው የተደረጉት ተስፋዬና ብርሃኑ ደቡር ብቻ ነበሩ፡፡ በደቡር በኩል እየተነገረኝ ከበላይ የሚፈሰውን መመሪያና ግዳጅ መፈጸም የቀን ተቀን ተግባራችን ሆነ፡፡

ከትዝታዎቹ አንድ ቀን ደቡር ግዳጃችንን ነገረን ይኸውም ምዕራብ ሆቴል ጀርባ አንድ ሀብታም ነጋዴ የቀን ገቢውን ማታ ማታ ቤቱ ይዞ ስለሚሄድ መኪናው አካባቢ በመቆየት ገንዘቡን ተረክቦ መሄድ ስለሚሆን ሁለት የታጠቁ ጓዶች በአካባቢው እንደሚገኙና ወፍ የተቀዳደደ ልብስ ለብሰህ ማዘናጋት ትጀምራለህ ተባልኩ፡፡ ወዲያውም ጓዶቹ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳሉ፡፡ ሰውየውን ገና ስጠጋው ጓዶቹ ከመቅጽበት መጥተው ገንዘብ ተረክበው ይባስ ብለው የሰውየውን ፔጆ መኪና ቁልፍ ነጥቀው አስነስተው ፈረጠጡ ወደ መደበቂያችን ቦታ ሄድኩ፡፡ ደቡርና ተስፋዬ ቤቱን አሟሙቀው ጫት እየቃሙ ደረስኩ፡፡ በምርቃና የተለያዩ እቅዶችን ስናወጣና ስናወርድ ቆይተን ወደ ጨብሲ ተዘዋወርን፡፡ ብዙ ስንገነባና ስናፈርስ አድረን፡፡ የበላይ አካልን ትዕዛዝ እንጠብቃለን፡፡ ራሳችን በግብታዊነት፣ በጠላት ስም ሰዎችን እረሽነናል፡፡ ሚሽን ከሌለን ሥጋ መጠጥና ጫት አስገዝተን ለሌላ ግድያ እንዘጋጃለን፡፡ ቀልቤሳ በቀበሌ የኛ ግፍና ጭካኔ ደግሞ ከሱ ቢበልጥ እንጂ አያንስም፤ ምን ዋጋ አለው ለአንባቢያን ማቅረቡ እኔን ራሴን ስለሚዘገንነኝ ዝም ብዮ እዘጋዋለሁ፡፡ ባለፈረሱ ብርሃኑ ደቡርስ ምን ይሰማው ይሆን? እንደ አርበኞችና ጀግኖች እሱም ባለፈረስ ሆነ አባነብሱ፣ አባዳኜ፣ አባጠቅል፣ ሲባል ሰምቶ ብኩን አረመኔ!

ትግሉ እየጋለ በሄደ ቁጥር የመኢሶንና የኢህአፓ ጦርነት እየተፋፋመ ሄደ፡፡ በዚህም ጊዜ ራስን ለማዳን ወይም ለአላማ ብዙ ጓዶች ተገድለዋል፡፡ እኛም ብዙ ረፍርፈናል፡፡ ብዙ ሀብታሞችን አስገብረናል፡፡ የንጹህ ሰዎችንም ደም በከንቱ አፍሰናል፡፡ ቤት ይቁጠረው፡፡ ከአሜሪካን ግቢ ጀምሮ አደሬ ሰፈርን ሰባተኛን ኮልፌን አካሎ በአሸባሪነትና በገዳይነት የታወቀው ስም ደቡር የዛሬው አባመላ ከነህዋሱ ነበር፡፡ ሁኔታዎች እየከፉ ሄደው በቀበሌና በደርግ ፖሊሶች ኢህአፓ፣ መመታት ጀመረ፡፡ ይባስ ብሎም ኢህአፓ ለሁለት ተከፈለ፡፡ በመሆኑም የኢህአፓ መዋቅር ውዝምብር ውስጥ በመግባቱ ግማሹ ወደ አሲንባ፣ ሸዋና ወሎ ገጠር ውስጥ ሲገባ ግማሹ ደግሞ ከተሞች ውስጥ መፍጨርጨር ጀመረ፡፡ እኔ አዲስ አበባ ስቀር ደቡርና ተስፋዬ ወደ አጋምጃ ሸፈቱ፡፡ ሩቅ ሳይሄዱ አንዲት ትንሽ ሆቴል አልቤርጎ ውስጥ ተማርከው ወደ አዲስ አበባ ተወሰዱ፡፡ ወሬውን ስሰማ በጣም አዘንኩ፣ ተደናገጥኩ፡፡ ተደብቆ መኖርንም ተያያዝኩት፡፡ ከጥቂት ወራቶች በኋላ ተስፋዬን አገኘሁት፡፡ እንደኔው ተጨናንቆና ተደናግጦ ነበር፡፡ ከእስር እንዴት እንደተፈታ አላጫወተኝም፡፡ የመጨረሻ መተያየት ሆነ፡፡ ሰንብቼ ስጠይቅ ተስፋዬ የማነን እህቶቹ ወደ አሜሪካ እንደወሰዱት ሰማሁ፡፡ አይ ቅብጥብጡ ተስፋዬ አሁንስ ሰክኖ ይሆን?

ከኢህአፓ መሰነጣጠቅ በኋላ ብዙ ጓዶች ለደርግ እጃቸውን ሰጡ ይቅርታ እየጠየቁ፡፡ አንድ ምሽት በተደበቁበት ቦታ ከብርሃኑ ደቡር የኮድ መልዕክት ደረሰኝ፡፡ በጣም በመገረም ወደ ቀጠሮው ቦታ ሄድኩ፡፡ በኮድ መሠረት ወደተባለችው ላንድክሩዘር ተጠጋሁ፡፡ ደቡር ጋር አይን ለአይን ተያየን፡፡ መኪናው ውስጥ ገባህ ተሳሳምን፡፡ መኪናዋ መንቀሳቀስ ጀመረች፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ መኪናውን ከሚሾፍረው ሰው ጋር አስተዋወቀኝ፡፡ ቀጥሎም መጠነኛ የፖለቲካ ትንታኔ ካደረገልኝ በኋላ ግራ የሚያጋባ ሚሽን (ግዳጅ) እንዳለን ገለጸልኝ፡፡ ይኸውም ጓዳችን የሆነው ጩልሌ (መላኩ) መመታት እንዳለበት በበላይ አካል መወሰኑን ነገረኝ፡፡ ጥርጣሬ ላይ ወደቅሁ፡፡ በማን? በደርግ? ወይስ ከሁለቱ የኢህአፓ አንጃዎች ባንዱ? ግራ ገባኝ፡፡ ብርሃኑ ደቡርና ሰውየው ጉንጫቸው በጫት ተወጥሮ ነበር፡፡ ጨብሲ እናድርግ ብለው ሰንጋ ተራ አካባቢ መኪናዋን አቆሙ፤ አንዲት ትንሽ መጠጥ ቤት ገብተን ቢራዎች መጠጣት ጀመርን፡፡ ከሁለት ሰዓት ቆይታ በኋላ ከቤቷ ወጥተን ወደ ተክለሃይማኖት አቀናን ጎላ ሰፈርን እንዳለፍን የተዋወቅኩት ሾፌር መኪናዋን አቁሞ ወረደ፤ ከመንገዱ ዳር ካለች የተዘጋች ኪዩስክ ጠጋ ብሎ ከአንድ ህፃን ጋር ተነጋግሮ ወደ መኪናው ተመለሰ፡፡ ወዲያውኑ ደቡር ክላሽንኮቭን ከመኪናው ወለል አንስቶ የመኪናውን የጎን መስታዋት አወረደ፡፡ ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ ጩልሌ (መላኩ) ከመንገዱ ዳር ሲደርስ ብርሃኑ ደቡር የያዘውን ክላሽ አቅንቶ ጥይቱን አርከፈከፈበት፡፡ በሰኮንዶች ጊዜ ብትንትኑ ወጥቶ መሬት ላይ ተዘረረ፡፡ መኪናዋም በሀይለኛ ፍጥነት እየበረረች ሰፈሩን ለቀቅን፡፡ ብዙ ግድያዎች ላይ ተሳትፌአለሁ፡፡ እንደዛች ቀን ግን ደንግጨና ፈርቼ አላውቅም፡፡ እስከዛሬ ህሊናዬን የሚያስጨንቀኝ ነገር ቢኖር ጩልሌን ለምን? ነበር፡፡

ደቡርስ አሁን ምን መልስ ይሰጠን ይሆን ወይስ እንደጲላጦስ እጁን ታጥቧል፡፡ ጉዞዋችንን በመቀጠል ፒያሳን ካቋረጥን በኋላ በራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ እንደገና አንድ ቡና ቤት ውስጥ ገባን፡፡ እኔ እየተርበተበትኩ ነው፡፡ እነሱ ግን በጫቱና በጨብሲው ምክንያት የደፈረሱትንና ቦታ የጠበባቸውን አይኖቻቸውን እያጉረጠረጡ እንደገና አልኮል መገልበጥ ጀመሩ፡፡\ከትንሽ ጊዜ በኋላ ብርሃኑ ወሬውን ቅደድ ጀመረ፡፡ የኢህአፓን ከንቱነትና መፈረካከስ አመራሩን እየኮነነ ከዘላበደ በኋላ በሱ እምነት ደርግ ጋር ተጠግቶ በኢህአፓ ላይ ቀይ ሽብር ማፋፋም የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑን ገለጸልኝ፡፡ አያይዞም የጩልሌ እምቢታ ምን እንዳመጣበት አበክሮ አሳሰበኝ፡፡ ላብ በላብ ሆኜ እየተብረከረኩ እምቢታዬን ገለጽኩለት፡፡ ብዙ ሊያግባባኝ ሞከረ፡፡ ምንም እንኳ በሁኔታው ብደናገጥና ብፈራም ፍንክች አላልኩለትም ነበር፡፡ በግልጽም ነገረኝ፡፡ በጨካኙ የደርግ ምርመራ ሹም በሻለቃ ብርሃኑ ከበደ ሥር እንደሚሰራና ብዙ የኢህአፓ ጓዶችን ወደ ደርግና ወደአብዮቱ እንዲመለስና እምቢተኞችም እንዳስመታ ገለጸልኝ፡፡ አሁን ተደናገጥኩ ፍርሃቴም ቀጠለ፡፡ ብርክ ያዘኝ ከህሊናየ ጋር እየተሟከትኩ ቡና ቤቱን ለቀቅን፡፡ መኪናዋ ወደ አራት ኪሎ አመራች፡፡ በመካከላችን ፀጥታ ሸፍኗል በመጨረሻም ሰተት ብላ ሚኒልክ ግቢ ገባች፡፡ ከመኪና ወረድን በእግራችን ትንሽ ከሄድን በኋላ አንድ በጩኸትና በለቅሶ የተሞላ ቤት በረንዳ ላይ አስቀመጡኝ፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ አንድ የሰከረ መርማሪ በጥፊ እያዳፉ አንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ አስገብቶ አግዳሚ እንጨት ላይ ገልብጦኝ፡፡ ወዲያውኑ አንዲት በደም የተጨማለቀች ኳስ ቢጤ አንስቶ ወደ አፌ ሊወትፍ ሲል ብርሃኑ ደቡር ብቅ አለና ስሙን ጠርቶ ቆይ አለው፡፡ በቅጽበታዊ ገለል ብሎ ቆመ፡፡ ከሁኔታው ደቡር አለቃው መሆኑን ተረዳሁ፡፡ ‹‹እሱን ለኔ ተወው›› በማለት ከመጀመሪያው ጥፊ በቀር ተገልብጦ አዳነኝ፡፡ ብርሃኑ ደቡር ጓደኛዬን ማመን አቃተኝ የአብሮ አደግነት ቆሌ ከሰባተኛ ተነስታ መርካቶን ፒያሳን  ቤተመንግስት ገብታ አዳነችኝ፡፡ ክብር ምስጋና ይግባትና ከዚያ በኋላ አንድ በእስረኞች የተጣበበች ግማት በግማት ክፍል ውስጥ አጎሮኝ ተሰወረ፡፡ እዚያች ጠባብ ግም ክፍል ውጥ የሚዘገንኑ ትርኢቶች አጋጠመኝ አንድ ሁለቱ አዲስ ግርፎች ስለነበሩ ነባር እስረኞች ቁስላቸውን በቆሻሻ  ጨርቅ ሲጠርጉና ሲሸፍኑላቸው ተመለከትኩ፡፡ ቁስለኞቹም የስቃይ ድምጽና ለቅሶ ሲያሰሙ ታዘብኩ፡፡ በአጠቃላይ ሀያ ከሚሆኑ እስረኞች መሀል ሳልገረፍ የገባሁት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ አይ! የመርካቶዋ አድባር ቆሌ! ሺህ አድባር ውለታሽን ይክፈሉሽ አልኩ በልቤ፡፡ እዚያች ክፍል ውስጥ ሳለሁ ከተመለከትኩት አዲስ ቁስለኛ ሲመጣ የከረመው ወደ ሌላ ቦታ ይወሰዳል፡፡ ማገገሚያ ጣቢያ አይነት ነበረችና አንዳንዴም ባሳቻ ሰዓት የተወሰኑ ሰዎች ይወስዳሉ፡፡ ዕጣ ፋንታየ ምን እንደሆነ ሳላውቅ ይኸው አስር ቀን ሆነኝ፡፡ በአስራ አንደኛው ቀን ሰባት የምንሆን እስረኞች ስማችን እየተጠራ እንድንወጣ ተደረገ፡፡ ምን ይሆን እያልኩ ስጨነቅ ከሌላ ቦታ ከመጡ አምሳ ከሚሆኑ እስረኞች ጋር በአንድ አዳራሽ ውስጥ ተደባለቅን ከጥቂት ጊዜ በኋላ የስብሰባው አስተናባሪ የዕለቱን አንቂና ተናጋሪ በአንዲት በር በኩል አስከትሎት ገባ፡፡ ሌሎች ይወቁት አይወቁት እንጃ እኔ ግን ጓደኛየን ደቡርን ሳየው ስላላስገረፈኝ ከልቤ እያመስገንኩ የሚለውን ለመስማት በጉጉት መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ከንግግሩ ምንም የተለየ ነገር አልሰማሁም ያው እንደለመደው ኢህአፓን አጥብቆ አወገዘ ወደ አብዮቱ ካምፕ መመለስን አበክሮ ከአስገነዘበ በኋላ ምርምራችን ተጣርቶ ንጹህነታችን ስለተረጋገጠ ምህረት እንደተደረገልንና ከአሁን በኋላ ሰላማዊ ኑሮ እንድንጀምር አበክሮ ከአሳሰበን በኋላ ወዲያውኑ በተነን፡፡ ከደስታ ብዛት ግማሹ ያለቅሳል ሌላው ይስቃል አንዳንዱ ደግሞ የድጋፍ መፈክር ያሰማል ሳይጠየቅ ታዲያ ሌላ ምን ያድርግ? አይ የነፍስ ነገር የሆነው ሆኖ ከአዳራሹ ስንወጣ ደቡር ወደ ቢሮው ወሰደኝና ጥቂት ምክር ከሰጠኝ በኋላ ለታክሲና ለምግብ የሚሆን አስር ብር ሰጥቶኝ እንድሰወር ነገረኝ፡፡ አይ አብሮ ማደግ እያልኩ አመስግኘው ተለያየን፡፡

ህቡዕ በነበርኩበት ጊዜ ሁሉን ነገር በሬዲዮና በጋዜጣ እከታተል ነበር፡፡ በተለይም በ1968 እና በ1969 ኢህአፓ በከተማ ውስጥ በመደምሰሱ መኢሶንም ፍርጠጣውን ተያይዞት ስለነበር፤ ደርግ በነበረበት ፍልሚያ የውስጥ ተቀናቃኞችን መደምሰስና ማስወገድ ነበር፡፡ ባልታሰበ ሁኔታ ሰናይ ልኬና ኮሌኔል ዳንኤል አስፋው በሻለቃ ዩሃንስ እንደተገደሉ የወዝ ሊግ መዋቅር ከመቅጽበት ፍርስርሱ ወጣ፡፡ በወቅቱ በተራ ካድሬዎች ቀርቶ በራሳቸው በደርግ አባላት የሚፈራው ሻለቃ ብርሃኑ ከበደ የብርሃኑ ደቡርና የሌሎቹ መርማሪ ነፍስ ገዳዮች አለቃ ከወዝ አደር ሊግ መፈራረስ በኋላ ባንዲራው በመውደቁ ያ ጨካኝ አውሬ ነፍስ በላ በደርግ የመረሸን ፅዋ ደረሰው፡፡

በሁኔታው የተደናገጡት የወዝ ሊግ አመራር አባላት ይቅርታ እየጠየቁ ለመንግስቱ ሀይለማርያም ገበሩ በተዋረዱም ብርሃኑ ደቡርና መሰል ጓደኞቹ አለቃቸውን ሻለቃ ብርሃኑ ከበደን እየኮነኑና እያወገዙ ነጻ ሆኑ የዛን ጊዜዎቹ ጲላጦሶች! ደቡር ለተወሰነ ጊዜ ድምፁ ጠፋ፡፡ እንደ እኔ ህቡዕ ገባ ወይስ ከአገር ወጣ እያልኩ አብሰለስል ነበር፡፡

ከወራቶች በኋላ የዳምጤ ልጅ ደቡር የሰደን ካባ ለብሶ ከፍተኛ ካድሬነት መከሰቱ ሰማሁ፡፡ ‹‹ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል›› እንዲሉ ብዙ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሚካሄድበት ፒያሳ አካባቢ ነበር የተመደበው፡፡ እሳቱ ደቡር በስልጣኑ በመመካትና በማስፈራራት ብዙ ገንዘብ ዘርፏል፡፡ በነፃ ከሚጠጣውና ከሚመገበው ባሻገር በጣም የሚያሳዝነው እሱና ግብረ አበሮቹ በፀረ አብዮት ሰበብ ብዙ ወጣት ልጃገረዶችን እያሰሩ ደፍረዋል፣ አበላሽተዋል፡፡ በርብርቦሽ አባት አልባ ልጆችን አስወልደዋል፡፡ የርብርቦሽ ዲቃላዎች ማሳደግ አቅቷቸዋል፡፡ ብርሃኑ ደቡር በየሆቴሉ እየገባ በነፃ መብላትና መጠጣት መብቱ አድርጎት ነበር፡፡ ካስቴሊ በነፃ ይመግበውና ያጠጣው ነበር፡፡ ከምግብ ሁሉ ጥሬ ሥጋ አብልጦ ስለሚወድ በአራዳ ልኳንዳ ቤቶች በነፃ ትኩስ ብልቶች መብላት ሥራው ነበር፡፡ ሆዳም! ይህም ድርጊቱ የአደባባይ ምስጢር እየሆነ በመምጣቱ በቀንደኛው ደርግ አባልና የሰደድ የበላይ አካል በጋሻው አታላይ ክትትል እንዲደረግበት ታዘዘ፡፡ ክትትሉ ውጤት አስገኘ ኮንትኔንታል ቡና ቤት አጠገብ ወደ እርይ በከንቱ መውረጃ ላይ ፒዜሪያ የምትባል የጣሊያን ምግብ ቤት አለች፡፡ ጣልያናዊው ባለቤት ከለውጡ በኋላ ለላብ አደሮቹ መርቆ አገር ለቆ ሄደ፡፡ ላብአደሮቹ ለጥቂት ጊዜ አብረው ከሠሩ በኋላ በስምምነት ኤርትራዊ ላብአደር ምግብ ቤቱን ጠቅልለው ይህ ሰው በአካባቢው ቀበሌ ተመራጮች በፈለጉት ጊዜ መጥተው በነፃ ይመገቡ ጀመር፡፡ በተጨማሪም ገንዘብ ያስገብሩት ነበር፡፡ ችግሩን መሸከም ሲያቅተው በሰዎች ምክር አቤቱታውን ለከፍተኛው ካድሬ አሰማ፡፡ ደቡር አጋጣሚውን በጣም ወደደው፡፡ ቀበሌዎችን አስፈራርቶ ዘረፋውን አስቆመ፡፡ በምትኩ ቀበሌዎቹን ተክቶ በተራው ምግብ መጠጥና ገንዘብ መብላትና መጠጣት መዝረፍ ጀመረ፡፡

ይህ ሲሆን የቀበሌ ተመራጮቹ አልተኙለትም ነበር፡፡ ብዙ ጭብጥ መረጃዎች አጠናቅረው ለበጋሻው አታላዩ አቀረቡለት፡፡ የዳምጤ ልጅ እንደለመደው ፒዜሪያ ገብቶ ሰዎች ጋብዞ እየበላና እየጠጣ ተዝናንቶ ሲወጣ እጅ ወደላይ ተብሎ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ በማግስቱ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ሆዳሙ ካድሬ ብርሃኑ ዳምጤ በሚል መግለጫ ግፉና ድርጊቱ ተነበበ፡፡ ከጥቂት ወራቶች እስር በኋላ በምህረት ተፈታ እስሩን አላከረሩበትም፡፡ ሁሉም ካድሬዎች የሱ አይነት ድርጊት  ይፈጽሙ ስለነበር፡፡ ከተፈታ በኋላ በአንዳንድ ጓደኞቹ እርዳታ ግብርና ሚኒስቴር ተቀጥሮ አጋርፋ እርሻ ማዕከል ተመደበ፡፡ እዚያ እየሰራ ሳለ እንደገና ታሰረ ምክንያቱን አላውቅም፡፡ በብዙ አማላጅና በሚኒስትሩ በዶክተር ገረመው ደበሌ ግፊት በእስር ተፈትቶ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ፡፡ በወቅቱ ደርግ በመላው ምስራቅ አውሮፓ ኮሚኒስት አገሮች የፖለቲካ ስልጠና እንዲገኙ ካድሬዎችን ይልክ ነበር፡፡ ታዲያ ቀልጣፋው ብርሃኑ ደቡር ተሰባብሮ ከአንድ ቡድን ጋር ወደሶቭየት ዩኒየን ለአስር ወራቶች የፖለቲካ ትምህር ተላከ፡፡ ከትምህርት መልስ ግብርና ሚኒስትር ተመለሰ፡፡ ሥራውን ጀመረ፡፡ ትንሽ ሰንበት ብሎ ወደ ዋናው ግብርና ሚኒስቴር ዕቃ ግዢ ክፍል ተመድበ፡፡ በመሆኑም ለሆዳሙ ጓደኛዬ ደቡር ሌላ አመቺ የዝርፊያ ሁኔታ ፈጠረለት፡፡ ከነጋዴዎች ጋር በመስማማት ገንዘብ ማካበት ጀመረ፡፡ ምርጥ ምርጥ ልብሶችና ጫማዎች መቀያየር ጀመረ፡፡ ቀን በቀን በውስኪ መታጠብ ጀመረ፡፡ በ247 ብር ደሞዝ ደርግ ድንብርብር ባለበት ዘመን ብዙ ፕሮግራሞ ያወጣ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት የኢሠፓን ካድሬዎች ለልማትና ለመንደር ምስረታ በሚል በየክፍለሀገሩ በተበተነበት ጊዜ ብርሃኑ ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር ዘመተ፡፡ ተልዕኮውን ጨርሶ ሲመለስ አጅሬ ደቡር ‹‹ምን ይገደው›› ተገለባብጦ የኢሰፓ የአባልነት ቀይ ደብተር እጁ ውስጥ አስገባ፡፡ በዚህም ቀይ ደብተር ብዙ ነገደበት፡፡ ዘረፈበት ሌላም ሌላም ብዙ አደረገበት፡፡ ትዝ ከሚሉኝ አንዱ የግርማ ቢራቱ ነገር ነበር፡፡ ግርማ ቢራቱ የአባቱን ንግድ መርካቶ ውስጥ ያካሂዱ ነበር፡፡ ደስተኛ፣ ተጫዋች ሴት አሳዳጁና መጠጥ ወዳጁ ግርማ በጊዜው ተገጥሞለት ነበር

‹‹ከሰው ግርማ ቢራቱ

ከመኪና ቶዮታ ማርክ ቱ››

የዘመኑ የመርካቶና የአራዳ ልጆች ያስታውሱታል ብዮ አምናለሁ፡፡ ሞቷል ነፍሱን ይማረውና ታዲያ የብርሃኑ የገንዘብ ምንጭ ሆኖ ነበር፡፡ ወዶ ሳይሆን በመፍራት ሌሎች የሰፈራችን ነጋዴዎችና የቡና ቤት ሴት ባለቤቶች ገንዘብና ሩካቤ ስጋ ይለግሱት ነበር፡፡ ሳይወዱ በፍርሃት የደቡር ጉዞ ሁሌ እንደቀጠለ ነው፡፡ በተለመደው ‹‹አፍዝ አደንግዝ›› በነያሬድና በነአሳየ ብርሃኑ አማካይነት ደስ አለኝ ቤዛን ገልብጦ የግብርና ሚኒስቴር ቋሚ ካድሬ ሆነ፡፡ ደሞዙን ከ247 ብር ወደ 710 ተወረወረ ‹‹የባለ ማስትሬት›› ደሞዝ!!! ዶ/ር ገረመውን እያጫወተና እያሳቀ እንዳያፈናቅለው አደረገ፡፡ ይህም ሽፋን በዶክተሩ ስም እየነገደ ጉቦ መቀበል እንዲችል ረዳው፡፡ የግብርና ሚኒስቴርን የፋይናንስ መምሪያ ሃላፊዎች ብዙ ያልተወራረደ ገንዘብ እንዳለበት ተረጋግጦ እያለ እንዲመልስ አልተጠየቀም ካላበደ በቀር ማን ደፍሮ ሊጠይቅ! የብርሃኑ ዝርፊያ ብዙ አይነት ነበር፡፡ በብዙ መቶዎች የሚያስተናግደውን የሰራተኞች ክበብ መሪዎቹን አባሮ ክበቡን በቁጥጥሩ ሥራ ካደረገ በኋላ ከመርካቶ (ከሰፈሩ ሰባተኛ) ጩልሌ ልጆች ቀጥሮ የክበቡን ገቢ እየሰነጠቀ ሙልጭ አርጎ በልቷል፡፡ ሲሾም ያልበላ አይነት! ለምንስ አይዘርፍ ማን ሊጠይቀው! እንደገና ደርግ ሊወድቅ በሚንገዳገድበት ጊዜ የሞት የሽረቱን የኢትዮጵያን ወጣቶች እያስገደደ ለብሄራዊ ውትድርና ይመለምል ነበር፡፡ ካድሬዎች በየቀጠናው ኢሰፓ አንደኛ ፀሐፊዎች አመራር በኮሚቴ ምልመላውን ተያይዘውት ነበር፡፡ ብርሃኑ ደርቡም የአንዱ ቀጠና ኮሚቴ አባል ነበር፡፡ በወቅቱም ሀብታሞች ልጆቻቸው እንዳይዘምቱባቸው ለአንድ ልጅ እስከ 2000 ብር ይከፍሉ ነበር፡፡ እያንዳንዳቸው ቀጠናም የተወሰነ ኮታ መምታት ስለነበረበት ጉቦውን ከበሉ በኋላ በምትካቸው የድሃ ልጆችንና የጎዳና ተዳዳሪዎችን እያፈሱ ኮታቸውን ያሟሉ ነበር፡፡ ደቡርና መሰል ጓደኞቹ!

ብርሃኑ ደቦር የዳምጤ ልጅ ይሁን አባ መላ ምን ያላደረገው ነገር አለ፡፡ በስልጣኑ በመጠቀም መሬት ተመርቶ ጉለሌ ጳውሎስ ሆስፒታል ጀርባ ቪላ ቤት መሥራት ጀመረ፡፡ ቤቱም በሚያስደንቅ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገባደደ፡፡ አያስገርምም፡፡ ጥሬ እቃዎቹ በሙሉ የተበረከቱት በልዩ ልዩ ነጋዴዎች ሲሆን መሃንዲዎቹና እንጨት ማገሩን የግብርና ሚኒስቴር ነበሩ፡፡ በነገራችን ላይ አምፑል እንኳን ከኪሱ አውጥቶ አልገዛም፡፡ ምላጩ ደቡር አባመላ በዚህ አላበቃም ቤት መሸጥ መለወጥ በተከለከለበት ዘመን አንድ ቀን እንኳ ያላደረበት ቤት ጠግሮ ዶላሩን አጥቁሮ ማንም ሳይሰማ ሽል ብሎ አሜሪካ ገባ፡፡

ያ ተበድሮ ያላወራረደው ገንዘብ በግብርና ሚኒስቴር የፋይናንስ ሰራተኞች ደመወዝ እየተቆረጠ ለመስሪያ ቤት ገቢ ተደረገ ‹‹አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ›› አይነት!

ከላይ የብርሃኑ የዘር አመጣጥ የጠቀስኩት ያለ ምክንያት አልነበረም፡፡ ብርሃኑ የቀንደኛው ወያኔ ግልገል የግርማ ብሩ የአክስት ልጅ ነው፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለግርማ ብሩ አጎቱ ነው፡፡ በግርማ ወልደጊዮርጊስ ልጀምር ይቅርታ በአክብሮት ባለመጥራቴ አክብሮት አይገባውምና! ይህ ሰው ሁለት ዘመን እያምታታና እያጭበረበረ የኖረ ሲሆን አሁን በሶስተኛው መንግስት ፕሬዚዳንት ሆነ፡፡ በንጉሱ ዘመን የፓርላማ አባልነቱን ወደ ኋላ ትቼ በደርግ ጊዜ የፈፀማቸውን ድርጊቶች ላውሳ፡፡ የኤርትራ ክፍለ ሀገር ሲቪልአቪየሽን ሀላፊ ሆኖ ተሾመ፡፡ ከጥቂት አገልግሎት በኋላ በይዘቱም ይሁን በቅርፁ ከርሳሙ መቶ አለቃ ግርማ ተስባብሮ የኤርትራ የትራንስፖርት አላፊ ለመሆን በቃ ቦታውን የፈለገው ያለ ምክንያት አልነበረም፡፡ ‹‹ቦታው የወርቅ ማዕድን ነበርና›› በወቅቱ በደርግ አሰቃቂ ግፍ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ንብረታቸውን እየተው ሀገራቸውን ጥለው ወደ ውጪ ሀገር ወይም ወደበረሃ የሚጠፋበት ጊዜ ነበር፡፡ ምስኪኖች ሞትን ፈርተው! ‹‹ቀልጣፋው›› መቶ አለቃ ግርማ የየብሱና የባህሩ ትራንስፖርት ሀላፊው በመሆኑ የኤርትራውያኑን ምርጥ ምርጥ መኪናዎች ከምጽዋ አሰብ እየላከ በልጁ በሰለሞን ግርማ አማካኝነት አዲስ አበባ መሃል አገር እየቸበቸበ ብዙ ገንዘብ ካዝናው ውስጥ አስገብቷል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በልጁ ስም አንድ የንግድ ድርጅት አቋቁሞ ከሩቅ ምስራቅ የተዋጊ አውሮፕላኖችን መለዋወጫ የአውሮፕላን ቦንቦችና ሌላም ነገሮች መንግስት በማቅረብ ከፍተኛ ገንዘብ በኮሚሽን አግኝቷል፡፡ ‹‹ወያኔ እንደገባ በመገናኛ አውታሮች ሰለሞን ግርማ በወንጀል እንደሚፈለግ የለፈፈውን ያጤኗል እንደ አባት እንደልጅ እንዲሉ›› ሰለሞን ተቀለጣጥፎ ሩቅ ምስራቅ ኮበለለ፡፡ አሁን የት እንዳለ አላውቅም፡፡ መቶ አለቃ ግርማ ይበልጥ የሚታወቀው በስነ ምግባር ብልሹነቱና በሴሰኝነቱ ሲሆን የአስራ አራትና የአስራ አምስት እድሜ ያላቸውን ወጣቶች በሌሊት ሶስትና አራቱን እያበላሸ ያድር እንደነበር ይታወቃል፡፡

ለምሳሌ ያህል ከሁለት ወጣት እህትማማቾች ልጆች ማስወለዱም ይታወቃል፡፡ አብረኸት የተሰኘችውን የ12ኛ ክፍል ውሽማውን የምጽዋ ትራንስፖርት ሃላፊ በማድረግ የምሁራን ሠራተኞችን ሞራል አዳሽቋል ከርሳሙ መቶ አለቃ ግርማ የአሁኑ ፕሬዚዳንት! ያች ልጅ ‹‹Suger Dady›› ብላ የፃፈቸውን ያጤኗል፡፡

ግርማ ብሩን በተመለከተ ጎበዝ የቀለም ተማሪና በጣም ቀዝቃዛ ሰው ነበር፡፡ ከአብዮቱ ፍንዳታ በኋላ በኢህአፓነት ተጠርጥሮ ደብረዘይት ከተማ ታስሮ ሲያበቃ የተፈታ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲውን ከጨረሰ በኋላ አንገቱን ደፍቶ በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ወንበር ያሞቅ ነበር፡፡ ወያኔ ከገባ በኋላ ከአጎቱ ከግርማ (መቶ አለቃ) ጋር በመሆን የሶዶ ጅዳ ተወካይ በመሆን ተሽሎክልኮ ባልዋለበት የኦህዴድ አባል በመሆን እስከ ሚኒስቴርነት ደረሰ፡፡ ይህ የድንጋይ ስር እባብ ምን ያህል ጨቋኝ አድርባይ ስለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነውና ብዙ አልዘበዝብም፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሶስት ዘመዳም ጉዶች አጋምጃን ይወክላሉ? የባልቻ አባ ነፍሶ አገር እነዚህን ጎዶች ታብቅል? ባልቻ አባ ነፍሶስ ምን ይሰማው ይሆን መልሱን ለአባ  ነፍሶ አፅም ትቸዋለሁ፡፡

በቸር ይግጠመን

መስፍን ቀጮ/ወፍ

ከጠቅላይ ቢሮ አዲስ አበባ

 

 

ሙክታር ከድርና የኦሮሞ አክራሪዎች –ናኦሚን በጋሻዉ !

$
0
0

ናኦሚን በጋሻዉ !

Muktar-Kedir1

ሙክታር ከድር

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው አገልግሏል። አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ትልቅ ክልል የምትባለው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳነት ሆኗል። ሙክታር ከድር ይባላል። የኢህአዴግ አንዱ  የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክርሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ነው።

ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ 150 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኝ ሄቶሳ በምትባል የአሩሲ መንደር አንድ ትልቅ ግንባታ ለማስመረቅ በክብር እንግድነት ይገኛል። አንድ ወንዝ ተገድቦ፣ ወይንም የጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት ተሰርቶ ለመመረቅ አይደለም የመጡት። እልም ባለ ገጠር መሃከል፣ አካባቢዉ ሁሉ ሜዳና እርሻ በሆነበት ቦታ፣ አንድ ትልቅ በአይነቱም፣ በይዘቱም የተለየ፣  ፈረንጆን እንደሚሉት ዊርድ የሆነ ሃዉልት ቆሟል። የአኖሌ ሃዉልት ይሉታል።

በቀድሞ ጊዜ በገዳ ስራአት ጀግና የነበሩ የኦሮሞ መኮንኖችን  ገድል የሚዘክር፣ ወይም በቅርብ ታሪካችን እንደ አብዲሳ አጋ፣ ባልቻ አባ ነፍሶ የተሰኙ የኦሮሞ ጀግኖችን የሚያሳይ ሃዉልት ቢሆን ሸጋ ነበር። ነገር ግን ሃዉልቱ ጡት የያዘ አንድ እጅን ያሳያል። ከመቶ አመት በፊት የሚኒሊክ ወታደሮች የአርሲ ኦሮሞዎችን ጡት ቆርጠዋል የሚሉትን የሌለ የፌጥራ አፈታሪክ ለማስታወስ ነዉ ብለው የቆሙት ሃዉልት። ያዉ በሚሊዮኖች በሚቆጠር ከሕዝብ ካዝና በተወሰደ ብር የተሰራ ሃዉልት። «አማራዎች እንደዚህ ጡት ቆራጮች ናቸው!» የሚለው የጥላቻ መልእክት በኦሮሞ ወጣቶች ላይ ከልጅነታቸው ጀምሮ ለማስረጽ ሆን ተብሎ የቆመ ሃዉልት። ኦሮሞው አማራዉን እንዲጠላ፣ እንድ እፍልስጤምና እስራኤል በመሃከላቸው ግድግድ ተፈጥሮ  እንዳይተማመኑ  እንዲተላለቁ ለማድረግ የቆመ ሃዉልት። የሰይጣን የዲያብሎስ ሃዉልት!!!

በአኖሌ በአጼ ሚኒሊክ ወታደሮች ተደረገ የተባለው  ጡት ቆረጣ መደረጉን የሚያረጋግጥ ምን አይነት የጽሁፍ መረጃ የለም። ዶር ነጋሶ ጊዳዳ በፓልቶክ ሲጠየቁ «ምንም አይነት የጽሁፍ ማስረጃ የለም፤ ግን በአፈ ታሪክ ነው የተላለፈው» ነበር ያሉት። የአጼ ሚኒሊክ ወታደሮች አያታቸውን አስረዉ ወፍጮ እንዲፈጩ ማስገደዳቸዉን የተናገሩት ዶር ነጋሶ ፣ በወለጋ የሚኒሊክ ወታደሮች ጡት ቆርጠው እንደሆነ ሲጠየቁ «ወለጋ እንደዝያ አልሆነም» ነበር መልሳቸው። አጼ ሚኒሊክ በጎጃም በሃርረ፣ በወላይታ በበርካታ ቦታዎች ወታደሮቻቸው ልከው አስገብረዋል። በአርሲ ተደረገ ከሚባለው ማረጋገጫ ካልቀረበበት  አፈ ታሪክ ዉጭ በሌሎች ቦታዎች የጡት ቆረጣ ተደረገ የሚል በአፈ ታሪክም አልተሰማም።

እንግዲህ እንደዚህ ዉሸት የሆነን አፈታሪክ በማራገብ ፣ ት/ቤቶችና  ክሊኒኮች በመሳሰሉ ቁም ነገሮች ላይ ገንዘብ ከማጥፋት ይልቅ፣ ዘረኛዉና ጠባቡ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይህ አይነቱን፣  ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቃቅር፣ ዜጎችን ወደ እልህና ወደ ጦርነት እንዲሄዱ የሚገፋፋ፣ ጥላቻን በሰዎች ልብ ዉስጥ የሚዘራ፣  አሳዛኝና አስቀያሚ ሃዉልት ማቆሙ፣ ምን ያህል  ለአገር ጥቅም ሳይሆን ለአገር መጥፋት እየሰራ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

እስቲ ወደ ሙክታር ከድር መልሼ ልዉሰዳችሁ። በቅርቡ ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣  በኦሮሚያ ዉስጥ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያንን በተመለከተ በኦህደድ ወንጀሎች ስለተሰሩ ግፎች ሲናገሩ፡

«I do know that there are Oromo individuals who do say “ non-Oromos  or those who do not speak Afan Oromo,  have no rights. They are second citizens.” I have expressed already that I am against such people. This brings me back to the OPDO “Gimgama” of 1989. OPDO was then confronted with serious problems of human rights violation, corruption and anti-democratic Oromo nationalism. We evaluated the leadership, the cadres and members of OPDO under the motto “Clean OPDO from OLF attitude (anti-democratic/narrow) and Naftagna (please note that Naftagna is not equal to Amhara) practices (violation of democratic and human rights including corruption). The result of the “Gimgama” was that thousands were found out to have anti-democratic attitudes and carried out Naftagna practices. 189 cadres were imprisoned so that they are brought to justice because of high corruption and serious human rights violation. Thousands were expelled because of their bad attitudes and bad practices. Only about 300 were kept after receiving warnings»  በማለት ነበር በኦህድድ አክራሪዎች የተፈጸሙትን ወንጀሎች የዘረዘሩት።

 

ማስጠንቀቂያ ተሰጧቸው ከነበሩ  አክራሪ ዘረኞች መካከል  ማን የሚገኝ  ይመስላቹሃል ? የአኖሌ የጥላቻ ሃዉልት መራቂ የሆነው ኦሮሚያን ኦሮሞ ካልሆኑት የማጽዳት አላማ በዉስጡ ያለው፣ የኢትዮጵያዉ  ጀነራል ምላዲቹ ፣ ሙክታር ከድር አንዱ ነበር።

«Among these were Alemayehu Atomsa and Muktar Kadir. Anyway, what was going on then was really very sad. Non-Oromo Ethiopian investors and traders were not welcome. Documents for bids for land were leaked out to Oromos so that they could win against non Oromo (for example against the 7 rich Gurage in Jimma). Shops were closed down. Boards to guide people were written only Qube (no Amharic and English translation). Appeal documents written in Amharic were rejected. Schools refused to give lessons in Amharic. (With silly arguments “we were formally forced to learn in Amharic, now it is their turn to be forced to learn in Afan Oromo.) We will not pay money for Amharic teachers and books”). Unfortunately, I hear that the attitude and practice still lingers.» ይላሉ ዶር ነጋሶ በጽሁፋቸው።

ታዲያ የሙከታር ከድር ዘረኛና የጥላቻ ታሪክ እየታወቀ፣ የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት  ማድረጉ፣ የአኖሌን የጥላቻ ሃዉልት ማቆሙ፣  ኦሮሞዉን ለመጥቀም ነው ወይንስ ኦሮሞውን ከሌላ ህዝብ ጋር ለማጋጨት ?  ኦሮሞው ከሌላው ሕዝብ ጋር የተዛመደ፣ የተዋለደ፣ የተሳሰር አይደለምን ? ለዲሞክራሲ ቆመናል የሚሉት፣ የኦሮሞ ድርጅት መሪዎችስ ይሄን የነሙክታር ከድር መርዝ ማዉገዝ የለባቸውምን ?  ለኦሮሞው ከአማራዉ፣ ከጉራጌዉ፣ ከጉሙዙ፣ ከቡርጂዉ፣ ከሲዳማው፣ ከጌዴዎው፣ ከሶማሌው ጋር አብሮ ተከባብሮ፣ ተስማማቶ መኖር አይሻለዉምን ? ለምንስ  እነዚህ አካራሪ ኦሮሞዎች ጠብ ይፈልጋሉ ? ለምን ተነጥለው ለመታየት ይሞክራሉ ? የሚያስተሳሰር፣ የሚያቀራራብ፣ አንድ የሚደርግን ማብዛትና ማስፋፋት እንጂ የሚያጣላና የሚያቃቅር ነገር ለምን እንጭራለን ?

አክራሪዎች በአኖሌ እንዳየነው አይነት ካከረሩ፣ ኦሮሞ ለኦሮሞዎች በሚል፣ ባለፈበትና በማይሰራ ባዶ ፉከር ከተነሱ፣  በዚያኛዉ ወገን ያሉት ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ዘነጉትን? ወይስ «በዙሪያችን ካሉ ሌሎች ሕዝቦች እዚያ ማዶ ያለው የትግሬ ጦር ይጠብቀናል» የሚል ግምት አላቸው ? እነዚህ አክራሪ ኦሮሞዎች ሰው ዝም ሲላቸው ትንሽ ልባቸው ያበጠ መሰለኝ። አላወቁትም እንጂ፣  እንዲሁ በባዶ ባበዱ ቁጥር እራሳቸዉን ነው የሚያስገምቱት። አለም በግሎባላይዜሽን በተሳሰረችበት ዘመን፣ ምን ያህል ኋላ ቀሮች መሆናቸዉን ነው የሚያሳዩት።

 

እንግዲህ ልብ ይገዙ ዘንድ እመክራቸዋለሁ። ጥላቻ ለማንም አይጠቅም። እልህ ለማንም አይጠቅምም። ዘረኝነት ለማንም አይጠቅምም።

 

 

በዘሀበሻ ላይ የወጣውን የቅዳሜ ዕለት የደብረሰላም መድሐኒአለም ውሎ ተከታትዬ በጣም አዘንኩኝ (ታዛቢ)

$
0
0

debereselam Minnesotaበሚኒሶታ መድሐኒአለም ታሪክም ላይ ጥቁር ነጥብ ጥሎ ያለፈ እለት መሆኑንም ነው የተረዳሁት። የሚኒሶታ መደሐኒአለምን ቤተክርስቲያንን ውዝግብ በቅርብ ሆኜ የምከታተል አባል በመሆኔም ባለፉት 15 አመታት የመጡትን የሄዱትን የወረዱትን ጠንቅቄ አውቃለሁ በተለይም ባለፈው 1 አመት  ከ 6 ወራት ውስጥ ያለውን ሒደት።ለዛሬው ብዙም ወደ ዋንኛው ችግር ጠልቄ ገብቼ ባልናገርም ነገር ግን ቤተክርስቲያኗ በአጣብቂኝ መንገድ ላይ እንዳለች ሁላችንም የምናውቀው ነው። የወደፊቱን አቅጣጫ ለመወሰን የሁለቱም ጎራ የተሰለፉት ጉዳያቸውን  በፍርድቤት አሲዘው ለ ሜ 11 ቀን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ቀጠሮ መያዙን ወቅታዊው ሊቀመንበር በቤተመቅደሰ ፈትለፈት ቆመው 20 ቀናት በፊት ነግረውናል። –- ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ—

ኋላ የመጣ ዓይን አወጣ! (ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

$
0
0
ጌታቸው ረዳ

ጌታቸው ረዳ

The first part of this commentary is been written in Amharic. Unfortunately, I deleted it by accident and my Amharic font program got corrupted. And had no option, but to replace it in English whatever memory I had in mind from the deleted portion. So, my apology to my readers for presenting the article half English and part also Amharic.

On 6 April, 2014, I was contacted by a friend via text to listen a Pal Talk room namely “Debtera Leaks Political Secrets of Ethiopia –Voice Room” edited by a lunatic, drunkard and annoying type by the name Bruk (Brook) where the Ethio- media Editor Abraha Belay was interviewed.

Unfortunately, I was not able to listen to it and asked another friend to record the interview for me. My friend responded “I stopped going there a long time a ago. it is not a place where test of maturity is conducted. Especially, the editor is self deluded and a noisy moron.”- said my friend.

Since, I was in a situation where unable to listen to the interview, after a little while, he called me back and decided to journey there to the room and recorded Abraha Belya’s interview. He sent me a limited part of the recoded interview, because he got there after almost at the end of the interview.

This room, ‘Debtera Leaks Political Secrets of Ethiopia –Voice Room’, which is administrated by a certain name ‘Buruk/Brook’ whom I (after listening to the recoded audio what he was referring to particular opposition like me and few of my friends with the same position regarding our view that (“Tigrayans as beneficiary of TPLF”) deem to be indeed a psycho. He referred as “extreme right wingers”.

How pathetic this noisy moron could referred as such for arguing our views which any normal mind can see that for the last 22 years, the rulers are Tigrayans and the investment, the Defense, the Diplomacy, the Airline, the bank, the business, the political power, the armament, the money, the mining, the land is all at the hand of “MAJORITY” Tigrayans from the top tycoon to the lower Tigrayan strata.

As far as I know the name ‘Buruk/Brook’ means blessing, however, the experience was closer to a curse based on his smearing against us.

Later after I came home, my friend chatted with me via a phone, that he was ready to ask the editor of the room and Abraha Belay with regard to his insult against those of us. It was also perfectly obvious to my friend that entering such room, meant entering a room full of sealed minded elements, and ‘apologies’ will be confronted with violent insult and some intimidation and endless nonsense rhetoric, including an admin that would continually victimize his opponents by red doting by blocking text and muting their voices. So, he decided to restrain himself from commenting or asking for the sake of waiting to record the interview for me.

Now, let me take you to Mr. Abraha Belay and Mr. Buruk short interview as a sample sent to me by a friend.

Before that, I like to escape what Abraha Belay had to say about Media and fairness and the father of the TPLF General Haylom Araya.

He talked few distorted story regarding the father of Haylom contrast with the father of Tedros Hagos (TPLF elite). But, failed to tell us, why Hayelom’s father was also in prison for over 10 years. I have no idea when, Tedros’s father was Awraja GeZZi in Shire (since I was born in Axum and grew up for certain period with a family in a deep village called Semema and also in Indasilasse capital city of Shire (walking from Semema by foot and stay week in the capital back to my home village on Friday evening) for schooling when I was a small boy, before I moved back again to Axum). All I know is he was not Awraja Gezzi, but Prince Mengesha’s secretary.

There were two other Shire Awraja Gezzi when I was a little boy as far as I remember. Perhaps could be. The point is why also did not tell us Hadush Araya’s (Hailom’s) father was in prison for so many years during that era. He tried to labeled Araya as ArbeNga and Hagos as Banda. I doubt the allegation was right. Anyway, let me move on to the other issue.

According to another witness which I will quote him at the end of my comment here, Balambaras Hagos (the same name and title as my mother’s grand father) and the all TPLF founders/leaders as the children of Nobles from Tigray. I will quote all of them by name later. I will send the audio evidence from Berhe Hagos from one of the Geza Tegaru admin (an ethno-centric room and directed by a fanatic Amhara hater a lady named “Hidiyat Raya”- remember she was the one said “Gojame are ZikiteNga, Idiot, Subhuman” and for the Gondere as ‘Telat’ ). Berhe told us in the audio “TPLF leaders are all children of nobles and feudal who are the other side copy of Ras Mengesha and the likes who were repressive feudal of Tigray. “Amhara was not our repressors but the Tigrayan feudal oligarchies and barons” said Berhe. Though Berhe is unpredictable, he is all the time fluctuating with no coherent ideology. But, at time, he has some valid points such as this one here.

The other issue is a waste of time to deal with his (Abraha Belya’s) “fair media” nonsense rhetoric he was talking about, as if he too is not one of the Diaspora pathetic media personality.

We have so many evidence for the last 8 or so years as editor of Ethiomedia- he is nothing but a click for the certain moron individuals (many of them hard line ethno- nationalist secessionists like Negasso, Bulcha and the rest of the criminal OLF goons) and certain white collar elites who are nothing but basket of naïve elites nick named “Doctor Zero-0) and the rest of religious Mujahedeens and Jawars.

I really do not want to go further, – it makes me so sick when I heard this fellow talking about fairness media. Let me omit his nonsense freedom of media and information rhetoric aside for another time.

Let me also escape what he said in regard to the question “who is ruling Tigray?” Few of us said yes, Eritreans are ruling our people and our country. But, it is not entirely true that only Eritreans are ruling Ethiopia/Tigray as Abraha Hagos seemed to response.

Tigrayans are in power. Not Eritreans. There are individuals with Eritrean blood, but, there is nothing we can do if they said they are Ethiopians. The fact the matter is, there are many Tigrayans also worst than Eritreans who advocate for Eritrea and also for blockage of our sea ports. The entire TPLF is crazily in love about Eritrea. These elements have been deluded by false propaganda pumped to their soft head through teachings of a sophisticated psychological subversion from Ethiopia’s enemies of all corners.

Though, there is some truth to it that there are Eritreans in power glued inside TPLF, let us also not confused the ethno nationalist of Weyane Tigray of Tigray origin are responsible group for every crime done. They are majority in number.

If the rulers are Eritreans, whose fault is this? Tigrayans or Eritreans? Is it not Tigrayans especially Abraha Belay’s community/Awaraja “May Chew” (Raya ena Azebo) who are crazily in love with Weyane Tigray to the extent majority of that Awaraja new born youth are named after Hayelom Araya? Common now!

I will deal about this next time. Majority followers/puppets of Weyane Tigray are currently from Enderta and MayChew Awraja.

We ask why the shift from አሽዓ (Axum, Shire, Adua) to those known hereditary rulers of Tigray feudal territories (Enderta and Raya) responsible for First Weyane (ቀዳማይ ወያነ) whom at this time population in particular the youth and the farmers are seen as fanatic supporter of Weyane Tigray?

We ask why the shift now, where these two Awraja were known for their melting pot and somewhat friendly society as good Ethiopians who tend to be somewhat neutral from being hardliner ethicist than the other Awraja before TPLF created. Thorough Research needs to be studied.

The Ethiomedia editor Mr. Abraha Belay also amazed me when he said “if there was a hero like Alemayohu who exposed the hidden secret of Meles Zenawi inside TPLF as Alemayohu exposed the hidden secret of the Shaabiya spy Tesfaye Gebreab- Ethiopia or TPLF; as organization or society of Tigray people would have not been hijacked by Eritreans to favor Eritreans”.

How premature, how silly one can be than this argument off line?

Meles Zenawi was not doing his subversive mission secretly as Abraha thought Meles was secretive. None of them did secretly. Including the Tigrayans in higher position or lower position. They wrote books, they argued, they openly intimidate, arrest, murdered anyone who do not accept the theory of colonialism by Ethiopians and safety and security to benefit Eritrea before Ethiopia.

They never was secretive to it! All of them be it Eritrean born blood or Tigrayan born blood from their jungle all the way until now: Seye, Gebru, Tsadkan, Meles, Abay, Seyoum, Sebhat, Tedros….all were and still in power continue to defend their original position.

Infact Asgede told us in his book. that at one time, Meles Zenawi was against sending Tigrayan fighters to Eritrea and was against EPLF (though, hard to understand why) when other Tigrayans went the contrary.

For your surprise brother Abraha Belay- it was openly given millions of Dollars and Airline, banks and dual citizen passports/sometime with no passport of Id card-to Eritreans that all the rights Ethiopians did not given.

This was openly carried. There was no secret. The chief designer for the Weyane Kililization apartheid admonition in Ethiopia was Meles. And that was supported and crazily loved by Tigrayans for implementing such Bantustan policy in Ethiopia. The Tigrayans were part and participants of the destruction and the pillage of Ethiopia with no secret attached to it. The subversion was and still is openly operating.

Ethiopians were removed by force from Eritrea their property taken away from them. Some killed, disappeared and raped. There was no secret. When Melese Zenawi openly support the ethnic cleansing by Eritreans again Ethiopians, the Tigray elite in power also went along with him. He did not do it in secret as you claimed foolishly and compared with Tesfaye Gebreabs secret spy mission.

It irritated me. Let me stop here.

Now to Bruk and Abraha Belay’s Mabo Jumbo accusation.

Mr Buruk: asked Abraha Belay- “…..ይህንን የሚያነሱ አንዳንድ ግለሰቦች ‘ኢትዮጵያዊያን ነን’ የሚሉ በተቃዋሚ ውስጥ ያሉ አክራራ right wing ምናልባት የቲ ፒ ኤል ኤፍ ተቀጣሪዎችም ሊሆኑ ይችላሉ፤ (እነሱ) ምንድ ነው የሚሉት “በዲያስፖራ ያለው የትግራይ ተወላጆች ወያኔን የሚቃወሙት በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ አብዛኛው (የትግራይ) ሰው ግን ቲ ፒ ኤል ኤፍን ይድግፋል፤ እንዲሁም ትግራይ ውስጥ ዲቬሎፕመንት አለ፡ እያሉ ይህንን ፕሮፓጋንዳ ሊጠቀሙበት ይሞክራሉ። እኛም ውስጥ እንግዲህ ተቃዋሚዎች ነን ብለው ማንነታቸውን አናውቃቸውም፤ ነግር ግን ((ትግራይ ተጠቃሚ ነው የሚሉ) እንደዚያ የሚሉ ሰዎች/ተቃዋሚዎች አሉ። ለነሱ የሚሰጡት መልስ ምንድ ነው አቶ አብርሃ?”

የአብርሃ በላይ መልስ ከማየታችን በፊት፤ መጀመሪያ በፓልቶኩ አዘጋጅ “አቶ ብሩክ” ልጀምር (ግን ብዙ ልሄድበት አልፈልግም)። በብሩክ አመለካካት “የትግራይ ተወላጆች ወያኔን የሚቃወሙት በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ወይንም ትግሬዎች በወያኔ ጊዜ ከተቀሩት ጎሳዎች ተጠቅመዋል።” የምንል ተቺዎች፤ “ማንነታችን የማይታወቅ፤ ቀኝ/አክራሪ፤የወያኔ ተቀጣሪዎች፤ፕሮፓጋንዲስቶች” ብሎናል።

ይህ ‘ደነዝ’፤ በቀኝ አክራሪ እና በወያኔነት አንዲሁም ማንነታችን በማይታወቅነት አድርጎ ሲስለን፤ አስገራሚው ነገር ፦ እኛ ትግሬዎች “ትኩስ ዕብድ” በከተማው ስናይ ሰውየው “ይህ አዲስ ነፋስ” ከየት መጣ የምንለው ዓይነት ስፓኒሾች “ሎኮ” የኒሉት ‘ዕብድ’ ሆኖ ነው ያገኘሁት።

ይህ ደብተራው ሊክ የተባለው ፓልቶክ “ኢካድ ፎረም/ካረንት አፈይር” የተባለው “የስሜተኞች፤ የሰካራሞች፤የሻዕቢያው የግንቦት 7 ደጋፊዎች እና የጎጠኞች ስብስብ” የተካው ይመስላል። አሁን የካረንት አፈይር እብዶች እና የአባ መላ እብዶች ወደ “ደብተራ ሊክ ፓል ቶክ” የኮበለሉ ይመስለኛል። ቁጥሩም የበረታበት ዋናው ምክንያት የኮብላዮቹ ዓይነት ይመስለኛል። የበርካታ ‘ጂሃዲሰት ኢስላም’ ክፍሎች ስትመለከቱ ክፍላቸው ከማንኛውም ፓል ቶክ ታዳሚ በቁጥር የበዛነው። በመርህ ከተመሮከዘ ይልቅ በርካታ ተጃጃሊ እና የቀወሰ ስሜተኛ ማስመጣት በጣም ስለሚቀል፤ ጎብኚው “በተከታታይ” የበረከተ ይሆናል።

አንድ ወዳጄ ሲነግረኝ ‘አዘጋጁ’ (ቡሩክ ማለቱ ነው) የሆነ ነገር እያነበበ “አበሻ” የተባለ ስም ትግራይ ውስጥ አንዳለ ካነበበ በሗላ “አያችሁ ‘አበሻ’ የሚል ስም ትግራይ ወንድሞቻችን ውስጥም ነበር ማለት ነው” ብሎ ሲል በሰውየው ትንሽ ጭንቅላት በሳቅ ነበር የተንከተከትኩት ብሎ ነግሮኛል።

አብርሃስ ምን መልስ ሰጠ? አብርሃ በላይ፤ ያመናቸው፤ያሞገሳቸው፤በድረገጹ ሲያሸበርቃቸውየነበሩት አርበኞቹ በየወቅቱ እየተንሸራተቱበት የተቸገረ ይመስላል። ስየ አብርሃ ሲንሸራተትበት አሁን ደግሞ፤ አብርሃ ደስታ የተባለ አዲስ አርበኛ አግኝቷል። ቋሚ አርበኛው ሆኖ የቆየው አስገደ ገብረስላሴ ብቻ ነው። አስገደ ደግሞ አርበኛ በመባሉ ተገቢ ነው። እኔም እስካሁን ድረስ በአድናቆት እና በጐ ዓይን የምቸረው ታጋይ ነው።በዛው ችግር የለብኝም።

እንዲህ ይላል አብርሃ በላይ

“ አዎ፣ አዎ፤ አየህ አብርሃ ደስታ አንድ ነገር ሲለጥፍ ተሽቀዳድመው ወድያውኑ ትችት የሚሰጡ እነኚህ የምትላቸው ሰዎች ናቸው።” ሲል በአብርሃ ደስታ ‘ቅዱስነትና ሙሉእነት’ የተማረከው አብርሃ በላይ፤- “አብርሃ ደስታን” መተቸት ማለት ቡሩክ እና አብርሃ አንደሚሉን “አክራሪ ቀኝ ሃይሎች፤ወያኔዎች፤ማንንታችን የማይታወቅ ግለሰዎች…” ነን ማለት ነው።

ይህ አዲስ እብደት አይደለም። በአብርሃ በላይ ብቻ አልተጀመረም። ስየ አብርሃ ሲመጣ፤ስየን በመተቸታችን፤ ስየ ጸረ ወያኔ ነው፤አዳኛችን ነው ተብሎ ሽር ጉድ ሲሉ በነበሩበት ወቅት፤ የሕግ ምሑር እና የሕግ አስተማሪው “አል ማርያም” በወቅቱ ‘ሲኒክስ’ ብሎናል። አብርሃ በላይ “የትግራይ ሕዝብ እንዲሸማቀቅ የሚያደርጉ፤ ጸረ አንድነት ሃይሎች ወዘተ…” ብሎናል። ስለ ነጋሶ ጊዳዳ ስለ ቡልቻ፤ ስለ ብርቱካን ስለ ኦ ኤል ኤፍ፤ ስለ ግንቦተ 7፤ ስለ ጃዋር…ስለ በየነ ጴጥሮስ” በተቸን ቁጥር ያልተባልነው ነገር አልነበረም። ሁሉም በየተራ ሲወድቁባቸው፤ ግን እነ …እነ…..እነ,፣ ይቅርታም አልጠየቁንም።

አብርሃ ደስታን አንዳትነኩት፤ወዮላችሁ እያሉ የሚሰድቡን በርከት በርከት ብለዋል። የአብርሃ በላይ አዲሱ አርበኛ ‘አብርሃ ደስታም’ እኮ “ትግሬ ተጠቅሟል፡ የሚሉ “የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ናቸው፤ደርጎች ናቸው ብሎናል”። ትግራይ እሱ ብቻ ወይንም እነሱ ብቻ የተወለዱባት መሬት መስሎ የሚታያቸው “ብዙ ከብቶች” አሉ። በነዚህ ትንንሽ “ጎሰኞች” ጭንቅላት የትግራይን ሕዝብ ነባራዊው ሃቅ ስለተናገርን፤ “ትግሬነታችን” የመስጠት ወይንም የመንጠቅ ሥልጣን ያላቸው መስለው እየታያቸው ነው። እነ አብርሃ በላይ እና አብርሃ ደስታ እኮ “ፋሺስት ወያነ ትግራይ” የሚለንን እኮ ነው እየደገሙት ያሉት። ስለ ትግሬዎች ፖለቲካ የሚተች ሁሉ፤ “የትግሬ ጠላት” “ወይንም “ትግሬዎች አይደሉም፤ ሽዋውያን ተጋሩ ናቸው” ብሎ ድሮ በወጣትነታቸው ወያኔ ያስተማራቸውን ዝባዝንኬ ነው እየደገሙት ያሉት። እንዲህ ብሎ ለሚወላፈጥ ግለሰብ መልስ እና ትችት መተቸት፤ በአብርሃ በላይ እና ባንዳንድ ትንሽ ጭንቅላቶች “አክራሪዎች/ቀኞች እና የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ነን” ተብለናል።

አስገራሚወ ነገር ለበርካታ አመታት እኛ ጥቂት ሰዎች ወያኔን ስንቃወም የኖርነው ሰዎች፤ ወያኔን ሲያገለግሉበት ከነበሩበት ኢትዮጵያ ወደ እዚህ መጥተው እኛን ‘ፀረ ሕዝብ ፤አክራሪዎች ብሎው ሲሰይሙን ትግራይ ውስጥ የኖሩ ትግርኛ ተናጋሪ አማራዎች ለዛ ባለው ምላሳቸው “ወይ ትገርምኒ” (ትግርሚኛለሽ) የሚሉት ነገር ነው።

አብርሃ ደስታ ወያኔን መቃወሙ የሚጠበቅ እና የሚያስመሰግነው ነው። ነገር ግን አማራን ከተወለደበት አገሩ ይባረር የሚለትን አን ጃዋር መሐመድን እና የሻዕቢያው ተስፋዬ ገብረአብን “ይመቹኛል፤ አትንኳቸው፤ይቀጡሉበት” እያለ ሲወላፈጥብን እና በአማራ ሕዝብ ሕይወት አንደ የፖለቲካ መጫወቻ ካርድ ሲመለከተው መተቸታችንን በአብርሃ በላይ እና በስሜት የሚወነጨፉ መሰል ጋላቢዎች ስንዘለፍ “ከትገርምኒ” በላይ ነው። ዛሬ አስተዳዳሪው ትግሬ ሳይሆን ሌላ ተመሳሰሳይ ዱርየ ሥልጣኑን ይዞ ቢሆን ኖሮ እና ትግሬ ከኦሮሞ፤ከጋምቤላ…እየተገደለም ግማሹም ከያለበት እየተጎተተ ወደ ትግሬ ሲባረር ብያይ፤ ወይንም በየዳር ትምህርት ቤቱ በየደረንዳው ተጥሎ የትግሬ ህፃናት ከእናታቸው ጉያ ተለጥፈው በብርድ እየተሰቃዩ ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ በቲቪ፤ በሬዲዮ በቃለ መጠይቅ (አሁን እንደ አማራዎቹ እየተደረገ እንዳለው) ቢያዳምጥ ኖሮ፤ ለጃዋር እና ለተስፋየ ገብረአብ የሰጠውን ማአዛዊ ፍቅር ያሳይ ነበር? አይመስለኝም; ስሜቱ እጅግ ይለዋወጥ ነበር። አይደለም እነ ጃዋርን እና እነ ተስፋዬን አትንኩብኛ እና የአማራን መጠቃት በጽሑፍ ከማውገዝ ይቅርና ፤ ትግሬዎች ቢጠቁ ኖሮ ‘ ምድረ ትግሬ’ ጸጉሩን አቁሞ ፤ ዓይኑን ደም አልብሶ ነበር ዓለምን በሞላ ‘መሬት ቀወጢ” ያደርግ የነበረው።

አብርሃ በላይ የሚገርመው ደግሞ “እባካችሁ አስተምሯቸው” ብሎ ደግሞ ለደብተራ ፓልቶክ ታዳሚዎች ይማጠናል። እኛኑን ማለት ነው። “ትግሬ ስልጣን ላይ አይደለም፤ አብዛኛው ትግሬ የወያኔ ተጠቃሚ እና ደጋፊ ነው” ማለታችንን እንድናቆም የፓልቶከክ ፕሮፌሰር “አዋቂዎች” የሆኑት ማንነታችን የማይታወቅ የትግሬዎች የጎሳ ፖለቲካ የምንተች እኛኑን ሊያስተምሩን ማለት ነው። እሱ እራሱ ሊያስተምረን ያልቻለውን እነ ብሩክ ሊያስተምሩን ማለት ነው። “ወይ ትገርምኒ”!

ትግሬው የወያኔ ደጋፊ ካልሆነ ተቃዋሚም አይደለም። መረጃው ከአብርሃ በላይ የቅርብ ወዳጁ ምን አንዳለን እነሆ ላስቀምጥ እና ልደምድም።

መኮንን ዘለለው ይባላል። የታንድ አመራር አባል ነው። ወያኔን ይቃወማል። ስለ ትግሬዎች የሚነግርን አንድ ነገር አለ። ይህ የምጠቅሰው ጥቅስ እኔ ለመኮንን ዘለለው ባንድ አጋጣሚ የሰጠሁት መልስ የተቀነጨበ ነው።

እንዲህ ይላል፤- ልጥቀስ፡-

አዎ ትግሬዎች በጣም ጥቂት ካልሆኑ በቀር፤ ወደ ትግሉ አልተቀላቀሉም። ይኼ ደግሞ ፓልቶክ ሩም ሆነህ መቀላቀላቸው ብትመጻደቅና ትግሬዎች ተቀላቅለው እየታገሉ፤ ጌታቸው ረዳ ግን ትግሬዎች ወደ ትግሉ አልገቡም፤ አልታገሉም፤ ይለናል፤ ብለህ ብታወግዘኝም። ከኔ ይልቅ አንተ በራዲዩ ቃለ መጠይቅ ተጠይቀህ ምን እንዳልክ ባጭሩ ልግለጽልህ እና አውነተኛው እና ሃሰተኛው ማን እንደ ሆነ ለአንባቢ እንዲመች ቃልህ ይኼው፡

የሚከተለው ‘መኮነን ዘለለው’ ከአዲስ ደምፅ ጋር ያደረገው ምልልስ ነው።

ጥያቄ፦ አበሁኑ ሰዓት የትግራይ ተወላጆች በትግሉ ጎራ ለመቀላቀል ፍላጎት እንደሌላቸው በግልጽ የምናየው ጉዳይ ነው፡ ለምን እንዲህ ሆነ?

ከዚህ ቀጥሎ የመኮንን መልስ ግን ቃል በቃሉ ምንም ሳይታረም አቀርባለሁ። በቅንፍ ሲሆን ግን አማርኛውን ለማቃንት የተጨመረ ነው። መኮንን ዘለለው፦ የትግራይ ሕዝብ 90% ወይንም 100% (90 ከመቶ ወይንም 100 በመቶ) የመንግሥት ተቃዋሚ ነው። ሚስቱ የከዳቺው ሰው(ባል) ለመታገል ዝግጁ የሆነ አይመስለኝም።

የትግራይ ሕዝብ ባሳደጋቸው በልጆቹ የተከዳ ሕዝብ ነው። አንድ ሰው የሚያምናት ሚስቱ በሚስቱ የተከዳ ሌላ ሚስት ለማግባት የሚሮጥ አይመስለኝም። ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልገዋል። የትግራይ ሕዝብም እንደዛው ነው።

ትናንትና ልጆቼ ብሎ ወደ ትግሉ የላከ ልጆቹ ራሳቸው የከዱት ሕዝብ ነው እና አሁን በቀጥታ ወደ ትግሉ ለመግባት በማሰብ ላይ ነው። አርቆ የሚያስብ እውነተኛ የሚታመን የትግል ድርጅት እስካሁን አልተገኘም። እከሌ አለ የምትልም አይመስለኝም። አሁን

የትግራይ ሕዝብ በጠቅላላ አሁን ኢትዮጵያዊ እምነት ያለው የትግራይ ሕዝብ እየጠፋ ነው።

አሁን ያለው የትግራይ ሕዝብ ማን አለ እስቲ ከኢሕአዴግ ሃይል የተሻለ የሚል ነው። የተቆረቆረ የትግራይ ሕዝብ የምንሰማው እና ከዚህ መንግሥት የተለየ ጠባይ የተለየ አቀራረብ እንዲኖረን ያስፈልጋል።….”

በማለት የትግራይ ሕዝብ የወያኔ ደጋፊ እንደሆነ/እንደነበረ በቃልህ ነግረኸናል። የትግራይ ሕዝብ ከወያኔ የተሻለ ተቃዋሚ የለም እንደሚል ነግረኸናል። እንደገና ወያኔዎች ስለከዱት ወደ ትግሉ ጎራ መግባት አልፈለገም። ብለሃል። ስለዚህ ጌታቸው ረዳ ምን ባጠፋሁ ነው፤ “ትግሬዎች አይታገሉም ይላል፡ ብለህ በኔ ላይ ውርጅብኝ የወረድከው? ይኼ አቋምህም እኮ ከነ ታማኝ በየነ ጋር በአዲስ ደምጽ ራዲዮ ተከራክረሃል/ደግመኸዋል። ታማኝ ምን ብሎ እንደመለሰልህ/እንደጠየቀህ አንተ ምን ብለህ እንደተናገርክ ታስተውሰው ይሆናል።

እኔ ያለ መረጃ ሰውን አልነካም ፤ ሲነኩኝ ነው እኔም ሃቁን ለማውጣት ሁሌም ራሴን ለመከላከል የምጋፈጠው። ከማንኛችሁም ጋር የምጋፈጠው ስለ አገር እንጂ በግል ተነሳስቼ የማገኘው ነገር ወይንም ጥቅም እንደሌለ ይታወቅልኝ። ማንም ሊወደኝ ወይንም ሊጠላኝ ይችላል; ሁለቱም የየሰው መብት ነው፤ አከብረለታለሁ። አንድ መታወቅ ያለበት ግን እዚህ ትግል ስገባ “ሰውን ለማስደሰት/ለማስቀየም/ለመወደድ/ ለመጠላት/ለመሾም/ዝና ለማትረፍ/ለመዋረድ ለማዋረድ/ በሚል አይደልም። የሚሰድቡኝ ካሉ ይበልጥኑ እራሳቸው ተመልሰው ማየት ይኖርባቸዋል። እንደ ማልምራቸው የምታውቁት ነው። አገርን መዝለፍ ያልከበዳቸው እኔን አንድ ግለሰብ መስደብ ይከብዳቸዋል የሚል ሕልም የለኝም። ስለዚህ ክቡራን ወንድሞቼ ምስኪኑ ጌታቸው ረዳን በየፓል ቶኩ ስሜን ባታነሱ እና የማቀርበውን ትችት ብትጋፈጡ ይመረጣል። አቶ መኮንን ለትግልህ እና ለዕድሜህ አክብሮት እሰጣለሁ።”

ስል ባንድ አጋጣሚ መልስ ሰጥቸው ነበር። ይህ ያመጣሁት አብርሃ በላይም ሆኑ መሰሎቹ ማስተዋል ያለባቸው ነገር፤ መኮንን ዘለለው የሚለንን በቅጡ እንዲመረምሩት እና እኛን መዝለፍ አንዲያቆሙ ነው። ከዚህ የምንማረው አንግዲህ የትግራይ ሕዝብ አቋም ከነመኮነን ዘለለው ወዲያ የሚያውቅ ያለ አይመስለኝም። መኮንን የነገረን ደግሞ ሃቁ ከላይ ጠቅሻለሁ።

ስለዚህ አብረሃ በላይም ሆነ ሌሎቻችሁ ከላይ ያቀረብኩትን ነጥብ መምታት ከቻላችሁ ‘እሰየው” ይኸው ሜዳው እና ፈረሱ። እኛን ያለ ማስረጃ መከራከር ግን ወያኔዎችን ለዘመናት የታገልነው ሰዎች አክራሪዎች/ቀኝ/ወያኔዎች/የማይታወቁ ሰዎች ወዘተ… እያላችሁ መሳደቡን ትንሽ እፈሩበት። ዓየሩን ቀድመን የተነፈስነው እያለን? ኋላ የመጣ ዓይን አወጣ! አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay)getachre@aol.com  

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live