የስፖርት ጋዜጠኞች የተያያዙት ማዝናናት ወይስ ማዘናጋት?
እሽሩሩ ማሞ –በ አሥራቴ ወርቁ
በረከተ መርገም (አንተነህ ሽፈራው)
Smart Car: ስለአዲሱ ኒውዮርክ የፖሊስ መኪና ምን ያህል ያውቃሉ?
የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት አባላት በሚንሸራሸሩባቸው የከተማይቱ ጎዳናዎች ሁሉ ሲሆን የሚውለውን እና የሚያድረውን ለማወቅ ምን ቢኳትኑ አደጋች ነው፡፡ ታዲያ የከተማይቱ ፖሊስ ዲፓርትመንት ቀደም ሲል ሲጠቀምባቸው ከነበሩ የወንጀል መከታተያያ ዘዴዎች የላቀ ብቃት የለበሰ ስለመሆኑ የተነገረለት የዘመኑ ምጡቅ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነ የፖሊስ ተሸከርካሪ ፈጣሪዎቹ እነሆ ብለዋል፡፡
ይህ ዘመን አፈራሽ ቴክኖሎጂ የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት አባላትን የሥራ ጫና በእጅጉ የሚያቀል ስለመሆኑም እየተነገረለት ይገኛል ‹‹ስማርት ካር›› ሲሉ ፈጣሪዎቹ የሰየሙለት ይህ ተሽከርካሪ የሕዝቡን ደህንነት በተገቢው ሁኔታ ለመጠበቅ በሚያስችሉ ሙሉዕ በኩለሄ በሆኑ መረጃ ሰብሳቢ መሣሪያዎች የተደራጀ ነው፡፡
ተሸከርካሪው በተገጠሙለት ሁለት የኢንፍራሬድ መቆጣጠሪያዎች ያያቸውን ቁጥሮች ሁሉ ይመዘግባል፡፡ የተፈቀደለት ሰሌዳና አድራሻም ጭምር የመለየት አቅም ያለው ይኸው በተሽከርካሪው ላይ የተገጠመ ኢንፍራሬድ በዚያው መጠን የተጭበረበሩ ሰሌዳዎችና ሀሰተኛ አድራሻዎችንም ጭምር በመለየት የማጋለጥ ስራ ይሰራል፡፡ ዘመናዊ እና ‹‹ስማርት ካር›› የተስኘው የፖሊስ ተሸከርካሪ የክትትል ካሜራዎች የተገጠሙለት ሲሆን የሚቃኛቸውን አካባቢያዊ ጠባያት ሁሉ ወዲያውኑ ወደ ፖሊስ ዲፓርትመንት ማዕከል የመላክ ብቃትም የለበሱ ናቸው፡፡
የ‹‹ስማርት ካር›› ፕሮጀክት በረጅም ጊዜ ዕቅድ ሊከናወኑ ከተያዙት BYPO 2020 መጠነ ሰፊ ፕሮጀክቶች አንዱ ሲሆን የ ‹‹ስማርት ካር›› ፕሮጀክት የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት እስከ 2020 ሊያከናውናቸው ይዟቸው ከነበሩ በርካታ ዕቅዶች መካከል አንዱ እንደሆነ የገለፁት ኮሚሽነር ሬይምንድ ኬሊ በ2011 ከማክ ኪንሲና ኩባንያው ጋር የተጀመረው ፕሮጀክት ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ለዲፓርትመንቱ የሚጠቅሙ የመንገድ ላይ ካርታዎች ለመስራት ዕቅድ ሰንቋል፡፡
የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት በቅርቡ ሊተገብራቸው የያዛቸው 260 ያህል ፕሮጀክቶች ያሉ ሲሆን የተቋሙ ሰባት ያህል ሰዎችም ቴክኖሎጂውን ለማምረት የሚያስችለቸው ክህሎት እንዲለብሱ ተደርጓል፡፡
የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት የስማርት ካርን ጽንሰ ሃሳብ ያመነጨው ትኩስ የምስልና መስል መረጃዎችን ለማሰባሰብ የሚያስችለውን አዲስ አስራር ለመዘርጋት ከማስቡ ጋር ተያይዞ ሲሆን ክስተቱን የሚመለከቱ ባለስልጣናት ሊደረጉ የሚገባቸውን በተመለከተ መዲያውኑ መመሪያ እንዲያወርዱም ያስችላቸዋል፡፡
እነዚህ ሙሉ መሣሪያዎች የተገጠሙላቸው ‹‹ስማርት ካር›› የተሰኙት እነዚህ ተሸከርካሪዎች ቁጥራቸው እምብዛም ባይሆንም ቀጣይ ግን የጣት አሻራ ሊቀበሉ እና የፊትን ገጽታ ለመለየት የሚያስችል መሳሪያ የተገጠመላቸው የፖሊስ ተሽከርካሪዎች የኒዮርክ ፖሊስ ዲፕርትመንት የአጭር ጊዜ ዕቅድ ናቸው፡፡ ይህ ሁናቴ የፖሊስ መኮንኖቹ ሙሉዕነት ያለው መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ ስራቸውን ቀና የሚያደርግላቸው እንደሆነና ውሳኔ ለመስጠት ችግር እንዳይገጥማቸው እንደሚረዳቸውም እየተነገረ ነው፡፡
በከተማ ውስጥ ሊኖር የሚችል ስውር የሽብርተኝነት ሴራ ለማጋለጥና ለትራፊክ አደጋ መከላከል ሰራተኞች ተጠርጣሪዎችን ለመለየት ዘመን አፈራሹ የፖሊስ ተሸከርካሪ ፍቱን ነው ተብሏል፡፡
በአስተዳደራዊ ስራ ረገድም የኒዮርክ ፖሊስ አባላትን ከዚሁ ዘመነኛ የቴክኖሎጂ ውጤት ጋር ማስተዋወቅም የኒዮርክ ፖሊስ የቤት ስራ እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡
የፖሊስ ዲፓርትመንቱ ፈተና እንደሆነ እየተነገረለት ያለ እውነትም አለ፡፡ የበጀት ጉዳይ ብዙዎቹ ሥራዎች ሊሠሩ የታቀዱት ዘመናዊ ፈጠራዎች በተሳካ ውጤት ይታጀቡ ዘንድ በየጊዜው የማሻሻያና የጥገና ሥራዎች ሊከናወኑለት እንደሚገባ ነው እየተገለፀ ያለው፡፡
እነዚህ ዘመነኛ የፖሊስ ተሸከርካሪዎች የዘመነ ወንጀል በተንሰራፋባቸው ታላላቅ ከተሞች ልበ ብርሃን በሆነው የማየት፣ የመቅመስ፣ የማሽተትና የማድመጥ ችሎታቸው ታግዘው ለፖሊስ ዲፓርትመንቶች የሚመጣበት መረጃ የዋዛ አይደለም፡፡ ዝ
ኑ! እንዋቀስ፤ ኢህአዴግንም እናፍርሰው! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)
(ይህ “ኑ! እንዋቀስ” የሚለው ስር ነቀል የለውጥ ጥሪ ቀጥታ የሚያነጣጥረው በኢህአዴግ አባላት ላይ
ብቻ ነው፤ አመራሩን በፍፁም አይመለከትም)
ኢህአዴግ ራሱ በይፋ ሲናገር እንደተደመጠው፣ በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር ወደ ሰባት ሚሊዮን ገደማ
ደርሷል፡፡ ይህም የአገሪቱ ቁጥር አንድ ግዙፍ የፖለቲካ ፓርቲ ያደርገዋል፡፡ በርግጥ ግዙፍ እንጂ ጠንካራ
እንዳላልኩ ልብ ይሏል፡፡ ምክንያቱም ጥንካሬ የሚለካው በአባላት ቁጥር ሳይሆን በድርጅት ፍቅር፣
በዓላማ ፅናትና በሚሰጡት ልባዊ አበርክቶ ነው፡፡ እንዲህ ያለ አቋመ-ብርቱነት ደግሞ ድሮ በያ ትውልድ
ጊዜ ቀርቷል፡፡ በዘመነ-ኢህአዴግ የተንሰራፋው ጥቅመኝነት (በእነርሱ ቋንቋ ኪራይ ሰብሳቢነት) ብቻ
ነው፡፡ ለዚህም በደቡባዊቷ አዋሳ ከተማ ስድስተኛው የድርጅቱ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት፣ አቶ በረከት
ስምኦን በብስጭት እየተትከነከነ በደፈናው ለጥቅም ድርጅቱን የተቀላቀሉ አባላት በርካታ መሆናቸውን
አምኖ በአደባባይ መናገሩ አስረጂ ሊሆነን ይችላል፡፡ ይህን ንግግሩንም አፍታተን ስናብራራው
እንደሚከተለው ሆኖ እናገኘዋለን፡- የግንባሩ አባላት ቁጥር ሰባት ሚሊዮን ገደማ የደረሰው በጥቅም በመደለል፣ በአንድ ለአምስት የጥርነፋ
መዋቅር በፍርሃት ተጠፍንጎ በመያዙና በመሳሰሉት ነው (መቼስ አቶ በረከት ከድርጅቱ ጉምቱ መሪዎቹ አንዱ ነውና ዘርዝሮ እንዲያስረዳን
አይጠበቅበትም)
የሆነው ሆኖ አባላቱ እንዲህ የመብዛታቸው ምስጢር የድርጅቱ አምባ-ገነንነት ባህሪይ መገለጫ እንጂ አመላይ አጀንዳ አሊያም
ምትሀታዊ ችሎታ እንዳለው የሚያሳይ አይደለም፡፡ ይህ የትኛውም መሰል ሥርዓት ከተጠናወተው ሁሉንም ከመቆጣጠርና መጠቅለል
(Totalitarianism) አስተሳሰብ የሚሰርፅ ማኪያቬሊያዊ አስተምህሮ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ‹‹አምባገነኖች የአንድ እናት መንትያ ልጆች
ናቸው›› እንዲሉ፤ በ‹‹ቆራጡ መሪ›› ዘመነ-መንግስትም በጊዜው ከነበረው የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር አኳያ መሳ-ለመሳ ሊባል በሚያስደፍር
ሁኔታ ሳር ቅጠሉ ሁሉ ሰማያዊ ካኪ ለባሽ የኢሠፓ አባል ሆኖ ነበር፡፡ ግና፣ ያ ካኪ ለባሽ ሕዝብ፣ የልቡን በልቡ ይዞ ‹‹ቪቫ መንጌ!›› እያለ
አሳስቆ በስተመጨረሻ ጉድ እንደሰራው ሁሉ፤ ‹‹ይህ የህዝብ ማዕበል…›› ተብሎ በአቶ መለስ ዜናዊ የተሞካሸው የ97ቱ የቅዳሜው መሬት
አንቀጥቅጥ የሰልፍ ትዕይንትም፣ በድጋፍ ሳይሆን በግዳጅ የሰመረ መሆኑን ለማየት፤ አይቶም ለመመስከር ከሃያ አራት ሰአት ጊዜ በላይ
አልወሰደብንም፡፡ እንዴት? ቢሉ በማግስቱ (ሚያዚያ 30) ለተቃውሞ ከወጣው ሕዝብ የቅዳሜዎቹም በብዛት መሳተፋቸውን በራሳቸው
አንደበት ‹‹ትላንት ለቲሸርት፤ ዛሬ ለነፃነት!›› በሚል ሕብረ-ዝማሬ ከአደባባዩም አልፎ ከተማዋን በሚያናውፅ የለውጥ ጩኸት
የመሰከሩበት ‹‹ፖለቲካ›› መቼም ቢሆን አይዘነጋምና፡፡
እንግዲህ ይህ ሁሉ ታሪካዊ ሀቅ የሚገልፅልን አንድ ታላቅ እውነት-በጥቅም እየደለሉ አባልን ማብዛት በክፉ ቀን የማይታደግ መሆኑን ነው፡
፡ ጥቅመኝነት ግፋ ቢል የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ‹‹ፀበል›› ያስጠምቅ፣ ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው!›ን ያስፎክር ያሸልል ይሆናል እንጂ
የኢትዮጵያን ትንሳኤ መሻትን አያስቀይርም፡፡ ነብር ዥንጉርጉርነቱን እንደማይለውጠው ሁሉ የኢህአዴግ አባላትም ምንም ቢሆን ምን፣
እንደሌላው ሕዝብ የሀገር አንድነት የሚያሳስባቸው፣ ብሔራዊ ውርደት (ረሀብተኝነት) በቁጭት የሚያንገበግባቸው፣ ከዘውግ ልዩነት
የሕዝብ ለሕዝብ መተማመንና አንድነታዊ ጥንካሬው የሚበልጥባቸው፣ የኃይማኖት ነፃነት የሚያስተቃቅፋቸው… ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡
ምክንያቱም ጥቅመኝነት የእጦትን ክፍተት ለመሙላት ለጊዜው ያሰግዳል እንጂ ክብርንና ማንነትን አስሽጦ በባርነት ቀንበር አያሳድርም-
በተለይም ዥንጉርጉርነቱን ጠንቅቆ ለሚያውቀው ኩሩ-ሀበሻ!
ደግሞስ ምን ያህሉ አባል ነው፣ የድርጅቱን መታወቂያ በመያዙ ብቻ የረባ ጥቅም ያገኘው? በግላጭ እንደሚታየው በግል ጥቅምም ሆነ
በተጭበረበረው የዘውግ ፖለቲካ ሳቢያ ኢህአዴግን የተቀላቀሉ የአብዛኞቹ አባላት የኑሮ ደረጃ ዛሬም እንደ ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ህዝብ
ከችግር የመቆራመድ አስከፊ ሕይወት አልተላቀቀም፡፡ ፓርቲውን መታከካቸውም በማይጨበጥና በማይታይ እንቅልፍ የለሽ ሕልም
አናውዞ ይበልጥ ደቁሷቸዋል እንጂ በቀን ሶስቴ መመገብ እንኳ አላስቻላቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ የድርጅት አባልነታቸው እንደተርታው
ሕዝብ በአድሎአዊ አሰራር መማረርን እንዳላስቀረላቸው በርግጠኝነት መመስከር ይቻላል፡፡
ይህ አይነቱም እርግጠኝነት ነው ‹ኑ! እንወቃቀስ (እንነጋገር)፤ እንተማመንምና ሀገርና ትውልድ እየገደለ ያለውን ፓርቲያችሁን አብረን
ተጋግዘን እናፍርሰው› የሚል የማንቂያ ደውል ላሰማችሁ ገፊ-ምክንያት የሆነኝ፡፡ እናም ድርጅታችሁን ትመረምሩ ዘንድ ወደድኩ፡-
ድርጅታችሁ ሥልጣን ላይ ተፈናጥጦ ባሳለፋቸው ሁለት አስርታት የተጓዘበትን መንገድ በአስተውሎት ብትመረምሩ፤ በእርግጠኝነት እንደ
ግዙፍ ዐለት ካገጠጡ ሀገራዊ ውድመቶች እና ከበባድ ኪሳራዎች ጋር መፋጠጣችሁ አይቀሬ ነው፡፡ ይህም ሆኖ በቅድሚያ በተልካሻ
ፕሮፓጋንዳ ያሰለቸንን የብሔር ጉዳይ (የተወሰኑ ሰዎችን አማልሎ አባል ለማድረግ አስተዋፆ እንዳለው ባይካድም) ወደጎን ብለን፤
የትኛውም ብሔረሰብ ባህላዊ እሴቶቹን ማክበር፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋው መጠቀም… የፖለቲካ ፓርቲ በችሮታ የሚሰጠው ሳይሆን፣
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
2
የማንም ተፈጥሮአዊ መብት መሆኑን ማስረገጥ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ ይህ ማለት ግን የድርጅታችሁ ሀቲት፡- ‹አንዱ በሌላው እድሜውን
ሙሉ ሲጨቆን እንደኖረ፤ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየ እንደሆነ፤ ከብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ይልቅ የክልሉን እንዲያስቀድም
መቀስቀስና መስበክን የብሔር ብሔረሰብ መብትን ማክበር ነው› የሚለውን አምኖ መቀበል አይደለም፡፡ በግልባጩ ስርዓቱ እንዲህ አይነት
ጉዳዮችን ሰማይ ጥግ አጉኖ፣ ሕዝብን ከፋፍሎና በጥርጣሬ (በጎሪጥ) ወደሚተያይበት ጠርዝ ገፍቶ፣ የሥልጣን ዕድሜውን ያራዘመበት
ሁለት አስርታትን ያሳለፈ ስልቱ መሆኑን መረዳት አይሳናችሁም ብዬ አስባለሁ፡፡
ሌላ ሌላውን ትተን እንኳ የኢህአዴግን አመሰራረት ብንመለከት ግንባሩን ከፈጠሩት አራቱ ድርጅቶች መካከል ከሞላ ጎደል ህወሓት እና
ኢህዴን/ብአዴንን እንደ ፖለቲካ ድርጅት መውሰድ ይቻል ይሆናል እንጂ፤ ኦህዴድና ደኢህዴን፣ በህወሓት ‹‹አባ መላ››ዎች እንደ
የፋብሪካ ሳሙና በሚፈለጉበት መጠንና ቅርፅ ተጠፍጥፈው ከተሰሩ በኋላ በኦሮሞና በደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆች ላይ እንደ አለቅት
የተጣበቁ የመሆናቸውን ምስጢር እነርሱም ራሳቸው የሚክዱት አይመስለኝም (ምናልባት በሽግግሩ የመጀመሪያ ዓመት ላይ
እንደአስተዋልነው ከኦህዴድ ይልቅ፣ ኦነግ ኦሮሚኛ ተናጋሪዎችን ወክሎ ቢቀጥል ኖሮ ይህ ጉዳይ በዚህ አውድ ላይነሳ ይችል ነበር፡፡ የሆነው
ግን ተቃራኒው ነው፤ የራሱ የፖለቲካ ቁመናና ራዕይ የነበረው በኃይል ተገፍቶ፤ በምትኩ በሌሎች እስትንፋስ ህልው ሆኖ
‹‹የሚያስተዳድረው››ን ሕዝብና ራሱንም ጭምር ቀን ከሌት ‹‹ከብሔር ጭቆና ነፃ አወጣናችሁ›› ስለሚሉት ሞግዚቶቹ ገድል መተረክን
‹‹ፖለቲከኛነት›› አድርጎ የወሰደው ኦህዴድን ያነገሰ ነውና)
በነገራችን ላይ የፖለቲካ ፓርቲን እንደ ፋብሪካ ምርት ጣጣ-ፈንጣጣው ተጠናቅቆለት ሲያበቃ የመጫኑ አሰራር በሁለቱ ክልሎች ብቻ
ተገድቦ የቀረ አይደለም፤ አጋር ፓርቲዎችንም ይመለከታል፡፡ ከአፋር እስከ ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል፤ ከሀረር እስከ ሶማሌ ሲተገበር
በትዝብት የተመለከትነው ጉዳይ ነው፡፡ መቼም ገና ከስር መሰረቱ ‹‹እኛ እናውቅልሀለን!›› በሚሉ ‹‹የፖለቲካ ሞግዚቶች›› የተፈጠረ
ድርጅት በምደባ ቦታውን ያገኙ የአመራር አባላቱን በቅምጥል ኑሮ ከማንፈላሰስ በዘለለ፣ ‹‹እወክለዋለሁ›› ለሚለው ሕብረተሰብ ትርጉም
ያለው ስራ ይሰራል ተብሎ የሚታሰብ አይደለምና ‹በኦሮሚያ ሙስና እንደሰላምታ እጅ መጨባበጥ ተዘውታሪና ተራ ነገር ነው›፣ ‹በአፋር
ባጀት መቀለጃ ሆኗል›፣ ‹በሐረር ቤተሰባዊ ኢምፓየር ተገንብቷል›፣ ‹ቤንሻንጉል በድህነት ማቀቀ›፣ ‹ሶማሌ ክልል የአስተዳዳሪው አብዲ
ርስተ-ጉልት ሆነ› ጂኒ ቁልቋል እያሉ ሮሮዎችን ማሰማት ለውጥ አያመጣም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ህወሓትን እንደ ‹‹ግል አዳኝ››
በመቀበላቸው ብቻ ‹‹የአስተዳዳሪነት›› ካባ የተደረበላቸው ምስኪን የአመራር አባላት በቀላል ጉዳይ ላይ እንኳ የመወሰን ሥልጣን
የላቸውምና ነው፡፡
ይህ እንግዲህ በቀጥታ ከኢህአዴግ ስነ-ተፈጥሮ ጋር የሚጋመድ ችግር ነው፡፡ ሆኖም የመንግስት ሥልጣን መዘውር ከጨበጠ በኋላ
የጨፈለቃቸውን የዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች ተከትሎ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የደረሱ የአያሌ ሰላማዊ ዜጐች ግድያ፣ እመቃ፣
ከስራና ቤት ንብረት መፈናቀል፣ ስደትን… አንድ በአንድ ጠቅሰን ለማውገዝ ብንሞክር ሰማይ-ብራና፣ ቀይ ባህር-ቀለም ሆነው
ካልተመቻቹልን በቀር የሚደፈር አይመስለኝም፡፡ በርግጥ በኢህአዴግ ውስጥ ታላቅና ታናሽ ንጉሠ-ነገሥት የሆኑት ህወሓትና ብአዴን
ብረት ነክሰው፣ ሳንጃ ወድረው በትጥቅ ትግል ያለፉ ከመሆናቸው አኳያ ለየትኛውም አይነት ቅራኔም ሆነ ልዩነት ከመግደልና መጋደል
ውጪ ያለ ሌላ ሰላማዊ አማራጭ ላይዋጥላቸው እንደሚችል መዘንጋት የለበትም፡፡ ኦነግ ከሽግግር መንግስቱ ከተገፋበት ጊዜ አንስቶ
በኦሮሚያ፣ በአዋሳ፣ በሶማሌ… ግፉአን ያለቁበትን፤ እንዲሁም በድህረ-ምርጫ 97 የታየው የጎዳና ላይ ጭፍጨፋ ይህንኑ ሀቅ ያስረግጣሉ፡፡
ኩነቱም ግንባሩ በመጣበት አይነት የነፍጥ የበላይነት ያለፉት ሶቪየት ህብረት፣ ቻይና፣ ቬትናም፣ ኩባ፣ ኤርትራ ባሉ ሀገራት ከታየው
የሕዝቦች እልቂት፣ የተቀናቃኝ ድምፆች መታፈን፣ የጋዜጠኞች መጨፍለቅ… ጋር ቀጥታ ዝምድና አለው፡፡ እነዚህ ሀገራትንም ሆነ
ኢህአዴግን የተለየ ሃሳብ ለማስተናገድ ትዕግስቱም ፍላጎቱም እንዳይኖራቸው ያደረገው ይህ ከውልደታቸው ጀምሮ ከደም-አጥንታቸው
ጋር የተዋሃደው ተፈጥሮአቸው ይመስለኛል፡፡
በአናቱም ኢህአዴግ ከአባላቱ ይልቅ የአመራሩ ‹‹ፓርቲ›› ብቻ ስለመሆኑ ለመረዳት የውስጥ አሰራሩን መፈትሽ የተሻለ ይሆናል፤
እናንተም በቅርበት እንደምታውቁት በድርጅቱ ያልተፃፈ ሕግ ከላይ ወደታች የሚወርድ መመሪያን ትክክል ሆነም አልሆነ ‹‹ለምን?›› ብሎ
መጠየቅ የሚያስቀስፍ ሀጢያት ነው፡፡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመወያየት መሻት፣ ጥያቄ ማቅረብ፣ ሃሳብን መቃወም፣ ስህተቶችን
ማጋለጥ… አሳድዶ በድንጋይ የሚያስወግር አሊያም ከሀገር ሀገር የሚያሰድድ ታላቅ ጥፋት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ይህ ሁናቴም ነው
የአስተዳደር ድክመቶቹንም ሆነ አውዳሚ ጉድለቶቹን በፍጹም ለሕዝብ እንዳይደርሱ ገትሮ መያዝን የማይዘናጋበት ዋነኛ መንግስታዊ ስራ
ያደረገው (የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በውሃ ቀጠነ ወደ እስር ቤት ሲያግዝ መክረሙን ልብ ይሏል)
በጥቅሉ ድርጅቱ ለአመራሮቹ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በተደረገባቸው ዘመናዊ “V8” መኪናዎች እንዲምነሸነሹ እና በቢሊዮን
የሚቆጠር የሀገር ሀብት እንዲዘርፉ የሚያስችል ስልጣን ከማጎናፀፉ ባለፈ፤ እናንተ (ብዙሀኑ አባላት) ያተረፋችሁት ምንድር ነው?
በአነስተኛና ጥቃቅን ከመደራጀት፣ ‹‹ኮብል-ስቶን›› ፈልጦ ከመደርደር የዘለለስ ማን ምን ሊጠቅስ ይችላል? እስቲ! የተራቆተችና በድህነት
ወጀብ የተንገላታች ሀገራችሁን በዓይነ-ልቦናችሁ ለማስተዋል ሞክሩ፡፡ ያን ጊዜም ገና ጀንበር ስታዘቀዝቅ ስጋቸውን ለመቸርቸር ጎዳናዎችን
የሚያጥለቀልቁ እምቦቀቅላ እህቶቻችን፣ ‹‹ማምሻም ዕድሜ ነው›› እንዲሉ የመፅዋች ዓይን እየገረፋቸው በልመና ቁራሽ ሕይወታቸውን
ለማቆየት የሚውተረተሩ አዛውንትና ህፃናት፣ በየጎዳናው በየሰፈሩ ሲንገላወዱ የሚውሉ ስራ-አጥ ወጣቶች፣ በቀን አንዴ ለመመገብ ላይ
ታች የሚማስኑ ለፍቶ አዳሪዎች… ምድሪቷን እንዳጨናነቋት ይገለፅላችኋል፡፡ የዚህ ሁሉ መንስኤም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ፅንፈኛው
3
ድርጅታችሁ በሚከተለው በተግባር ያልተፈተነ (የሀገሪቱን ተጨባጭ እውነት ያላገናዘበ) ርዕዮተ-ዓለም፣ ፖሊሲ፣ አድሎአዊ አሰራር፣
ሙስና እና ለኃላፊነት የማይመጥኑ ‹‹አስፈፃሚዎች›› ችግር ስለመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ጥርጣሬ አይግባችሁ፡፡ እናም ጉዳዩ የሀገር ነውና
በግልፅ እንወቃቀስ (እንነጋገር)፤ ስለምንድነው በአባልነት በምታገለግሉት ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ‹ዛሬም በስኬት ጎዳና
እየጋለብኩኝ ነው› ብሎ እንደ ቁራ እየለፈፈ በተግባር ግን፡- መብራት፣ ውሃ፣ መንገድ፣ ኔት-ወርክ እንደ አደይ አበባ በዓመት አንዴ ብቻ
ብቅ የሚለው? በአገልግሎት ተቋማት መጠቀምስ እንዲህ የአሲምባን ያህል ያራቀው ማን ነው? ፍትሕን የጠሉትን መበቀያ መሳሪያ
አድርገው ያረከሱት እነማን ናቸው? ሰርቶ መብላት የማይጨበጥ ጉም የሆነብንስ በማን የተነሳ ነው? …በርግጥ ይህንን ጥያቄ ለጠቅላይ
ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ብናቀርብለት እንደ መለስ ዜናዊ በተረት መሳለቁ ባይሆንለትም፣ ‹‹ሰለሜ ሰለሜ››ን እየጨፈረ፤
እነ‹‹ሚካኤል ስሁል›› በቀደዱለት ልክ ዳናኪራውን እያስነካው ‹‹ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም!›› ብሎ ከመዘባበት አይመለስም፡፡
መቼስ እንደዚህ ሕዝብ የተናቀ የትም አይገኝም፡፡
ኢህአዴግ መፍረስ ያለበት ለምንድን ነው?
ይህንን አጀንዳ ለማንሳት መግፍኤ የሆነው ከላይ ለማሳያ ያህል የተጠቀሱት ስርዓታዊ ጥፋቶች በግላጭ የመታየታቸው እውነታ ብቻ
አይደለም፤ ይልቁንም ድርጅቱ ከስሁት መንገዱ ለመታረም (ለመታደስ) ፍፁም ዝግ-በር የመሆኑ ጉዳይ ጭምርም ነው፡፡ አዎን፣ እነዚህ
አሁን ሁላችንንም እያማረሩ ያሉ አብዛኞቹ ችግሮች የተከሰቱት አንጋፋው ድርጅታችሁ የ‹‹ኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ
ግንባር›› የሥልጣን መሰረቱን ለማፅናት ይሁነኝ ብሎ ከደፈጠጣቸው መብቶች ጋር ተያይዘው ከመሆናቸው በዘለለ ለኢኮኖሚያዊ
ጥያቄዎች በቂ ምላሽም ሆነ ሁነኛ መፍትሔ የሌለው ፀረ-ሕዝብነቱ የተረጋገጠ፣ ለመታረም ዝግጁ ያልሆነ፣ ተስፋችንን ያሟጠጠ ስርዓት
ስለሆነም ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመሪያ እነበረከት ስምኦን ልባቸው ከኢህአፓ ለመኮብለሉ አብይ ምክንያት አድርገው ያቀረቡትን ችግር
ታዬ የተባለ ታጋይ ‹‹ሞናሊዛ›› በሚለው ግጥሙ ግሩም አድርጎ ገልጦት እንደነበረ በ1993 ዓ.ም ‹‹ፅናት›› በሚል ርዕስ የተጋድሎ
ታሪካቸውን ባሳተሙበት መጽሐፍ ላይ ተርከውታል፡፡
‹‹አንተ ሌዎናርዶ የሮማ ጅል
የሰራሀትን ልታሻሽል
ልታፈርሳት ልትገነባት
ደግመህ ደጋግመህ ልትሰራት
ሰልሰህ ልትሰራት ስትችል
ጣኦት አደረግካት በሞትህ አጉል አጉል
ለራስህ ፍጡር እግዚኦ ልትል››
ይህ ግጥም በሰፈረበት ገፅ ላይ የተጠቀሰው የግርጌ ማስታወሻ ደግሞ ሊተላለፍ የተፈለገውን መልዕክት እንዲህ በማለት አብራርቶታል፡-
‹‹ታዬ የሚባል የኢህአፓ ታጋይ ‹ራሳችን የፈጠርነውን ድርጅት ማስተካከል አለብን› የሚል እምነት የነበረው ሲሆን፣ ዳ ቪንቺ እራሱ
ለሳላት ሞናሊዛ ፍቅር እንደተማረከ ሁሉ እኛም የፈጠርነውንና የተበላሸውን ድርጅት አመለክነው፤ ማስተካከልም ተሳነን በማለት ፓርቲው
ላይ እምነት ማጣቱን ‹ሞናሊዛ› በሚል ርዕስ በፃፈው ውብ ግጥም ገለፀ፡፡›› (ገፅ 61)
እነሆም አብዮታዊ ግንባሩ፣ ከመስራቾቹ አንዱ የሆነው ኢህዴን/ብአዴን፣ ያን ጊዜ ኢህአፓን መክሰሻ ባደረገበት ‹‹ድርጅታዊ አምልኮ››
ራሱም ተጠልፎ ከወደቀ ዓመታት ነጉደዋል፡፡ ታዬ እንዳለውም መሪዎቹ ኢህአዴግን ናቡከደናፆር አሰርቶት እንደነበረው አይነት እጅግ
ግዙፍ ‹‹አምላክ›› (ጣኦት) አድርገው ሀገርና ሕዝብን እየገበሩለት (እየሰዉለት) ነው፡፡ ርዕዮተ-ዓለምም ሆነ ፖሊሲ (በተለይ መሬትን
በተመለከተ) ‹‹የሚቀየረው በመቃብራችን ላይ ነው›› ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ የትምህርት ፖሊሲውም እንዲህ ትውልድን
እየገደለም እንዲሻሻል ያልተሞከረው በዚሁ እምነታቸው ይመስለኛል፡፡ ይህ ሁኔታም ነው እናንተም የምትስማሙባቸውን ታላላቅ ሀገራዊ
ችግሮችን ለመፍታት ኢህአዴግን ከማፍረስ ውጪ አማራጭ እንዳይኖር ያደረገው፡፡ ከእንግዲህ ወዲያም ከጥፋቱ ታርሞ ለሀገር የሚጠቅም
ዲሞክራሲያዊ የህዝብ ሥርዓት ሊያነበር ይችላል ብሎ ተስፋ ማድረግ ተላላነት ነው፡፡ እንኳን እናንተ ከተማ ላይ የተቀላቀላችሁት አባላት
ቀርቶ፣ ከበርሃ አቅፈው ደግፈው እዚህ ያደረሱት አንጋፋ ታጋዮችና አንዳንድ አመራሮቹም በድርጅቱ ተስፋ ቆርጠው ጥለውት መሄድ
ከጀመሩ ሰንብቷል፡፡ ታጋይ የውብዳር አስፋው ‹‹ፊኒክሷም ሞታ ትነሳለች›› በሚለው መጽሐፏ እውነታውን እንዲህ በማለት ገልፀዋለች፡-
‹‹የድርጅቱ አመራር የወሰዳቸውን የተሳሳቱ እርምጃዎች ቀድሞ ከነበረኝ የድርጅቱ ግንዛቤ ጋር በማጣመር ለዓመታት የታገሉለትንና
የደከሙለትን አባላት በነፃ እንዲንቀሳቀሱ ያላስቻለ ድርጅት፣ ለሕዝብ ነፃነትና ለዲሞክራሲ እታገላለሁ ቢል ከይስሙላ የማያልፍ ከንቱ
መፈክር መሆኑን ደምድሜ፣ ከመጋቢት 5 ቀን 1993 ዓ.ም ጀምሮ ራሴን ከድርጅቱ አገለልኩ፡፡ ይህም በሕይወቴ ጉዞ ዋነኛውና ወሳኝ
እርምጃ ነበር፡፡›› (ገፅ 16)
እንግዲህ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የድርጅት፣ የሴቶች ጉዳይና የመንግስት ሥራዎች ተሰማርታ ልጅነቷን በትግል የጨረሰችው የአቶ
ገብሩ አስራት ባለቤት፣ የውብዳር አስፋው እንዲህ አይነቱን ከባድ ውሳኔ በማሳለፍ ከኢህአዴግ ከተቆራረጠች እነሆ አስራ ሶስት ዓመታት
4
ነጉደዋል፡፡ በግልባጩ እናንተ ደግሞ እስካሁን ድረስ አንቀላፍታችኋል-ገና አልነቃችሁም፡፡ እናም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- ከዚህ
በላዔ-ሰብ ሥርዓት ለመገላገል የምንችለው፣ ዛሬውኑ ይህንን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ዋነኛና ወሳኝ እርምጃ በቆራጥነት መውሰድ
ስትችሉ ብቻ ነው፡፡ አለበለዚያ…
(የዚህ ጽሑፍ ሃሰበ-መልዕክትን በቅንነት ትቀበሉታላችሁ በሚል መተማመን አፈፃፀሙን፡- በምን አይነት መንገድ ተቀራርበን ልንወያይ
እንችላለን? በየትኞቹ ጉዳዮች ላይ መግባባት ይቻላል? ሃሳቡንስ ከግብ ለማድረስ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል? የሚሉትንና መሰል
ጥያቄዎችን በሌላ ዕትም ተገናኝተን በስፋት እንመክርባቸዋለን)
አትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ለምን ከምንወዳት አገራችን እንሰደዳለን? ክፍል 1 (በይበልጣል ጋሹ)
ከምንወዳት፣ ከአደግንባት፣ የማይረሳ የልጅነት ጊዜያችንን ካሳለፍንባትና አገራችንን ጥለን/ለቀን በባዕድ አገር በስደት በእምነት፣ በባህል፣ በቋንቋ እንዲሁም በአመለካከት ከማይመስሉን ጋር በተለያየ ፈተናና ውጣ ውረድ እና ለአፍታ በማይዘነጋ አገራዊ ትዝታ እንድንኖር ያደረገን ትልቅ ምክንያት ይኖረናል፤አለንም። ማንም ሰው በአገሩ በሰላም እና በደስታ ባሳደገው ማህበረሰባዊ ባህል መኖር እና ማደግ ይፈልጋል። የራሱ የሆነ በቂ ምክንያት ከሌለው በስተቀር ስደትን ቤቴ ብሎ የሚኖር የለም። ባገሩ በሰላም መኖር የሚችል ሰው የስደትን አስከፊነት እና ትግዕስት አስጨራሽነት ተቋቁሞ መኖር ባልቻለ ነበር። ግን እርሱ ባለቤቱ የሚያውቀው አሳማኝ ምክንያት አለው።
በእርግጥ ዛሬ ላይ ዓለም ሁሉ ለስደት የዳረገንን ምክንያት ዘመኑ በወለዳቸው ብዙኃን መገናኛዎች ምስክርነት መስጠት ከጀመሩ ጊዜያትን አሳልፈዋል። እውነታውንም በሚገባ ተገንዝበው ለሰሚዓን ምስክርነቱን ቀጥለውበታል። ከፊሎች ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ስሜት የለለውን የመንግስትን ከእውነታ የራቀ ተራ ወሬ ተከትለው ስደተኞችን ሲተቹ እና ሲያንገላቱ ይታያል። እርግጥ ነው ብዙዎች የአፍሪካ መሪዎች የስልጣን ዘመናቸውን የሚያስረዝሙት በሀሰት እና በኃይል ረግጠው እናስተዳድረዋለን እንመራዋለን በሚሎት ህዝብ ላይ የመከራ ቀንበር በመጫን እና በማስጨነቅ ነው። የኢትዮጵያ መሪዎችም የስልጣን ዘመናቸውን ለማስረዘም ያዋጣናል የሚሉትን ማንኛውም መንገድ ይጠቀማሉ። ሲፈልጉ ያጸድቃሉ፤ ሲፈልጉ ይኮንናሉ፤ይሾማሉ፣ይሽራሉ፤ ይገድላሉ፣ ያኖራሉም።
በአገራችን አንድ ገሀዳዊ እውነታ አለ። ህዝቡ አገሩ ከመኖር ይልቅ ወደ ስደት ዓለም የሚሄድባቸውን መንገዶች በማፈለለግ ከጊዜ ወደ ጊዜ የስደተኛው ቁጥር በእጅጉ እየበዛ እና እየጨመረ መምጣቱ ዓለም በአንድ ድምጽ የሚመሰክረው እውነታ ነው። አገርን ያሳድጋል ያለማል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የተማረው ዜጋም ስደትን በመቀላቀል ግንባር ቀደም ቦታን ይዟል። ለአንድ አገር እድገት አይደለም የተማረ ዜጋ ቀርቶ ማንኛም ሰው በተፈጥሮአዊ እውቀቱ፣ ጉልበቱ እና ገንዘቡ አገርን የመለወጥ አቅም አለው። የአደጉ አገሮችን ታሪክ ብንመለከት ወደ ብልጽግናው ዓለም የተቀላቀሉ ያላቸውን የሰው ኃይል በሙሉ በነጻነት ለአገሩ ተቆርቋሪ ሁኖ በቻለው መጠን እንዲሰራ በማድረጋቸው ነው።
ወደ ኢትዮጵያ አገራችን ስንገባ ግን በተቃራኒው ሁኖ እናገኘዋለን። በጣም የሚያሳዝነው የሚሰራ ሰው፣ የሚናገር ሰው፣ ለእውነት የቆመ ሰው እንዲኖርባት ያልታደለች አገር መሆኗ ነው። የዓለም መነጋገርያ የሆነውን የትናቱን የረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET702 ይዞ ኢጣሊያ መግባት የነበረበትን ወደ ሲዊዝ ጀነባ መሄዱን መመልከት ከበቂ በላይ የነጻነት እጦትን ያረጋግጣልናል።
በብዙ ምክንያቶች ዜጎቿ ስደተኞች ሁነውል። በሚገርም ሁኔታ በአገር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቿም አብዛኞቹ ወደ ስደት የሚወጡበትን አጋጣሚዎች በመጣባበቅ የመንፈስ ስደተኞች ሁነዋል። በተለያየ አጋጣሚ ወደ ውጭ የሚወጣው ዜጋ ወደ አገሩ የሚመለሰው ቁጥር በእጅጉ አናሳ መሆኑን ጥናታዊ ባልሆነ መንገድ የምንሰማቸው እና የምናያቸው መረጃዎች ህያው ምስክሮች ናቸው። ግን ለምን? እንዴት? እስከ መቼ? ህዝቦቿ በስደት የሚሰቃዩት መልስ የለለው የዘወትር ጥያቄየ ነው። ለስደት የዳረገንን አንዱን እና ትልቁን ምክንያት ለማንሳት እሞክራለሁ።
ነጻነት፣ ነጻነት፣ ነጻነት???
ነጻነት የሚለውን ቀጥተኛ ትርጉም በአጭሩ ከዚህ በፊት “ነጻነት ወይስ ቅኝ ግዛት” በሚል ባወጣውት ጽሁፌ ላይ ለመግለጽ ሞክሬ ነበር። (ነጻነት ወይስ ቅኝ ግዛት/ባርነት) በዚህ ጽሁፌ ደግሞ የነጻነት እጦት ምን ያክል ለስደት እንደዳረገን ውስጣዊ ስሜቴን ለመግለጽ እዎዳለሁ።
ነጻነት ተፈጥሮአዊ ነው። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው ትልቁ ጸጋ ነጻነት ነው። እሱን እንድናመልከው እንኳ ነጻ ፈቃድ ሰጥቶናል፤ አላስገደደንም። እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ሳያስገድድ የኢትዮጵያ መሪዎች ግን እነሱ ባልፈጠሩት፣ ባልሰሩት፣ ምንም ዋጋ በአልከፈሉበት ህዝብ ላይ አምባ ገነናዊ አገዛዛቸውን አስፍተው እኛን ሲጨቁኑን እና መከራ ሲያበዙብን እናያለን። እነርሱ እና የእነርሱ አጫፋሪዎች በነጻነት ይኖራሉ። ብዙኃኑ ህዝብ ግን በነጻነት እጦት ብዙዎች ተሰደዱ፣ ተንገላቱ፣ መከራን ተቀበሉ። ብዙዎችም ነጻነት ይኑር ብለው በመናገራቸው ተገደሉ፣ ታሰሩ፣ ሃብት ንብረታቸው ተወረሰ፣ የሚናገሩበት አንደበት እንዲዘጋ ተደረጉ፣ ለነጻነት የሚጽፉበት ብዕራቸው ተወረወረ እጃቸውም ታሰረ። ቤተ እምነቶችም ሳይቀሩ ነጻነትን በመስበካቸው የአምልኮ ስርዓታቸውን እንዳያካህዱ ተደረጉ። የአምልኮ ቦታዎች በምክንያት እንዲፈርስ ተደረገ። ባህላችንን፣ ታሪካችንን እና ማንነታችንን እንድናጣ ተደረግን።
የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም መስክ ነጻነቱ ተገፏል፤ በነጻነት መናገር፣ በነጻነት መጻፍ፣ በነጻነት መደራጀት፣ በነጻነት መሰብሰብ፣ በነጻነት ማህበራዊ ተግባራትን ማካሄድ፣ በነጻነት መስራት እና በነጻነት መንቀሳቀስ እንዲሁም በነጻነት ማምለክ ታሪክ ሆኖብናል። ህዝቡ በእጅጉ ነጻነትን ይፈልጋል። ነጻነት ፍለጋም ስደትን እንደ አንድ ዓቢይ ምርጫ አድርጎ በየቀኑ በብዙዎች የሚቆጠሩ ይፈልሳሉ። የስደትን አስገፊ ህይወት በጸጋ ተቀብሎ መኖር አማራጭ የለለው መፍትሔ አድርገነዋል። የዱር እንስሳት እንኳ ሳይቀሩ የእለት ከእለት ኗሯቸውን በነጻነት ማካሄድ የማይችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር ነጻነት ወደሚያገኙበት ቦታ/ጫካ ይሰደዳሉ። የሰው ልጅ ደግሞ ከእንስሳት በተለየ የአስተሳሰብ አድማሱ ሰፊ በመሆኑ ነጻነትን ከምንም በላይ ይፈልጋል። “ጎመን በጤና ይላል” እንዲሉ ነጻነትን ተነፍጎ የቁም እስረኛ ከመሆን ይልቅ በነጻነት በድህነት መኖር አእምሯዊ ረፍት ይሰጣል።
ስለዚህ የስደታችን ዋነኛ ምክንያት የነጻነት እጦት ነው። የህዝብ ነጻነት እስካልተመለሰ ድረስ ከስደት ወደኋላ ይላል ብሎ ማሰብና መፍረድ የቁም እስረኛ ሁኑ ብሎ እንደመፍረድ ይቆጠራል። ህዝብ ነጻነቱን ካገኘ ሁሉን ነገር ማድረግ ይችላል፤ ሰርቶ ድህነትን ማሸነፍ ይችላል፤ ማህበራዊ ህይወቱ ሰላማዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እድገቱ እውነታ ያለው እድገት እና ፖለቲካዊ አመለካከቱ የሰላ እና ዲሞክራሲያዊ ይሆናል።
የኢትዮጵያ መንግስት ሆይ ነጻነታችንን መልሱልን!
አገራዊ ስሜታችንን ጠብቁል እናተም አገራዊ ስሜት ይኑራችሁ!
ተውን በነጻነት እንጻፍ፣ እንናገር፣ እንቀሳቀስ፣ እንስራ!
አምልኮታችንንም ለአምላካችን በነጻነት እናቅርብ!
የመስዋዕትነት ወንጌል –ከጸጋዬ ገ.መድኅን አርአያ
[የሚኒሶታውን ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ ለምትከታተሉ ሁሉ] ቅጥፈታቸው ሲጋለጥ
ለሰላምና ለአንድነት የቆሙ ምዕመናን 3/24/2014
ቅጥፈታቸው ሲጋለጥ
ቤተክርስቲያናችን ተክሷል ስለዚህም ጠበቃ ቀጥረናል እያሉ ሲያወናብዱ የከረሙት አንዳንድ ሕገ-ወጥ የቦርድ አባላት ባለፈው ቅዳሜ 3/22/2014 መድኃኔዓለም በቤቱ አጋልጧቸዋል። ምንም አይነት ሕጋዊ የቅጥር ውል ስምምነት ፊርማ ከቤተክርስቲያኑ ጋር ሳይኖራት የቤተክርስቲያናችን እና የቦርዱ ጠበቃ ነኝ ስትል የከረመችው ግለሰብ በህዝብ እና በጠበቆች ፊት ቤተክርስቲያኑን ለመወከል ምንም አይነት የጽሑፍ ስምምነት እንዳልፈረመች ተናግራለች። በቤክርስቲያናችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት በሕጋዊው የቤተክርስቲያናችን ሊቀመንበር ላይ ከስልጣንህ ወርደሃል ከቦርዱም ተባረሃል በማለት ደብዳቤ በመጻፍ እንዲሁም ፖሊስ በሃሰት በመጥራት የቤተክርስቲያኑ ጠበቃ ነኝ ለምትለው ግለሰብ የቤተክርስቲያናችን አንድነትና ሰላም የሚገዳቸው አባላት ባለፈው ቅዳሜ 3/22/2014 በቤተክርስቲያናችን በመገኘት የተለያዩ ጥያቄዎችን ባቀረቡበት ወቅት ግለሰቧ ስማቸውን ለመግለጽ ያልፈለገቻቸው አንዳንድ አሁን ያሉና የቀድሞ ቦርድ አባላት በቃል በነገሩኝ መሠረት ብቻ ቤተክርስቲያኑንና ቦርዱን ወክዬ እየሰራሁ ነው ስትል የሕግ ሰው ነኝ የምትለው ግለሰብ ሕገ-ወጥነቷን በአደባባይ ገልጻለች።
በእለቱ ሕገ-ወጥ የቦርድ አባላት ሕዝቡ ተፈራርሞ ባቀረበው አጀንዳ መሠረት የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ አንጠራም በማለት ከፍርድ ቤት በተመደቡት አደራዳሪ ዳኛ በኩል አቋማቸውን በማሳወቃቸው የቤተክርስቲያናችንን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለማስጠበቅ እንዲሁም ሕገ-ወጥ የቦርድ ስብሰባን ለማስቆም
ወደ ቤተክርስቲያን የተመሙት ምእመናን የቤተክርስቲያኑ ጠበቃ ነኝ ስትል ከከረመችው ግለስብ ጋር ባደረጉት የጥያቄና መልስ ግብ ግብ ቤተክርስቲያናችንን ለመከፋፈልና ሰላሟን ለመንሳት እየሰሩ ያሉትን አንዳንድ የቦርድ አባላት የማጭበርበር ሥራ ያጋለጠ ነበር።
ውድ የደብረሰላም መድኃኔዓለም ምእመናን ላለፉት አንድ ዓመት ከአራት ወራት ያህል ሰላማችን ታውኮ፣ አንድነታችን ተናግቶና ሕሊናችን አዝኖና ከርሟል። ይህም ሁሉ ትዕግስት የተደረገው ለቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት ሲባል ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እንዲህ አይነት ከፍተኛ የማጭበርበር ሥራ እየተካሔደ ያለ በመሆኑና ቤተክርስቲያናችንን ፈጽሞ ለማዘጋትና ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኃይሎች ስላሉ ቤተክርስቲያናችንን ከእንደነዚህ ዓይነት ሰርጎ ገቦች የማጽዳት ሥራ የሁላችንም መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል። ለዚህም በመጪው ሜይ 11/2014 ዓ.ም በሚደረገው የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በነቂስ በመገኘት እና ኃላፊነት የሚሰማቸውን አዳዲስ የቦርድ አባላት በመምረጥ ቤተክርስቲያናችሁን እንድትታደጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ያለ ሕጋዊ ውልና ፊርማ የቤተክርስቲያናችን ጠበቃ ነኝ በማለት በውስጥ ጉዳያችን በመግባት ስትንቀሳቀስ በነበረችው ‘የሕግ
ባለሙያ’ እና ይህንንም ድርጊት ባልተሰጣቸው ስልጣን ቤተክርስቲያኑን ወክይ ብለው በቃልም ሆነ በጽሑፍ ውለታ የገቡትን ግለሰቦች በሕግ የምንጠይቅ መሆኑን እንድታውቁ እንወዳለን። የሕግ የበላይነት በሰፈነበት ሃገር እንዲህ አይነቱ ሕገ-ወጥ ድርጊት መፈጸሙ ሁላችንንም ሊያስቆጣን ይገባል።
መድኃኔዓለም የቤተክርስቲያናችንን አድነት ይጠብቅልን።
[የሃረሩ እሳት ቃጠሎ ጉዳይ] –የእሳት ፖለቲካ በኢትዮጵያ (Fire Politics in Ethiopia) –ይሄይስ አእምሮ
በሃይማኖት መሪዎችና አገልጋዮች ዙሪያ ሰሞኑን አንዲት መጣጥፍ ጽፌ ለድረ ገፆች ልኬ ነበር፡፡ ለኅሊናቸው ተገዢ የሆኑ አወጡት – አስነበቡን፤ እግዚአብሔር ይስጣቸው፡፡ ለባህልና ለይሉኝታ ያደሩት እንዲሁም እነሱ በሚፈልጉት ሙዚቃ ብቻ ታንጎና ማሪንጌ መደነስ የሚፈልጉት ወደቅርጫታቸው ከተቱት – ይክተቱት፡፡ ሁሉም የመሰለውን የማድረግ መብት አለውና ያነበበም ያስነበበም፣ ያፈነም ያሳፈነም የኅሊናው ዳኝነት ይፍረደው ከማለት ውጪ በዚህ በውዥንብር ዘመን መወቃቀሱም ሆነ መካሰሱ ፋይዳ የለውም፡፡ ግን ግን የእውነት አምላክ ለሁላችንም እውነተኛውን የልቦናና የኅሊና ሚዛን እንዲሰጠን እጸልያለሁ፡፡ ሁለትና ሁለት ሲደመር አራት ብቻ የሚሆንበት ሃቀኛ ዘመን እንዲመጣልንም እንዲሁ፡፡ በተረፈ የልጆቼ ልጆች “Mother stomach is ranger.” ሲሉ እሰማለሁና በዚያ “ሜጀር” የተቃኘ የቅሬታ ዘፈኔን ጋብዣቸው በገዢዎቻችን አነጋገር ንቅድሚት እላለሁ፤ ሕይወት እንዲህ ናትና፡፡
አንድ የብዕር ወዳጄ ያቺን መጣጥፍ ካነበበ በኋላ በነካ እጄ በዚህች ወያኔያዊ የእሳት ፖለቲካ ላይ ጥቂት ነገር እንድል አሳሰበኝ፡፡ ርዕሲቱንም የሰጠኝ እርሱ ራሱ ነው – Please take the credit dear Mr. Thingummy, wherever you may be.
ሀገራችን ተመልካች ያጣ የሕዝብ ብዛት ብቻ ሣይሆን ጭንቅት የሚያዞሩ እጅግ በርካታ ችግሮች የሚርመሰመሱባት በመሆኗ አንባቢን ላለማስቸገር ወይም ብዙ አንባቢ የለም በሚል ተስፋ መቁረጥ ወይም “አድማጭና የእርምት እርምጃ ወሳጅ ኃላፊነት የሚሰማው ጤናማ ወገን በሌለበት የኳስ አበደች ሀገራዊ ምስቅልቅል ሁኔታ ውስጥ ተነቦስ ምን ፋይዳ ሊያመጣ?” ከሚል ብሶት የተነሣ ሆን ብለን እየተውነው እንጂ መጻፍ የምንፈልግ ዜጎች የምንጽፈበት ጉዳይ በሽበሽ ነው፤ በበኩሌ አድማጭ ቢኖር ሃያ አራት ሰዓት ብጽፍ የማይደክመኝና የሚያጽፍ ጉዳይም ሞልቶ የተረፈ መሆኑን የምገልጸው የሚያፍኑኝን ድረ ገፆች ደስ አይበላቸው በሚል የመከፋት ስሜት ሳይሆን ተናግረን አድማጭ ባለመኖሩ ሳቢያ በእጅጉ የምቆረቆር መሆኔን በሚጠቁም የቁጭት ስሜት ነው፡፡ የወያኔው የዘረኝነት አባዜ ካስከተለብን ተነግሮ የማያልቅ ሰቆቃና የግፍ አስተዳደር ጀምሮ እነሚሚ ስብሃቱን የመሳሰሉ የሥርዓቱ ዘውጋዊ አባላትና እበላ ባይ ሆዳም ደጋፊዎቻቸው ባቋቋሟቸው የሠራተኛ አስቀጣሪ ድርጅቶች አማካይነት የሚካሄደውን ዘመናዊ ባርነት ብንመለከት ጉዳችን በጽሑፍም ሆነ በቃል ተዘርዝሮ የማያልቅ አስገራሚ ፍጡራን ሆነናል – እኛ “ኢትዮጵያውያን”፡፡ ቴዲ አፍሮ “እዚህ ጋ’ም እሳት፣ እዚያ ጋ’ም እሳት፣ እሳት፣ እሳት፣እሳት…” ሲል እንዳቀነቀነው ሀገራችን ወያኔያዊ እቶን ላይ ተጥዳ በየአቅጣጫው እንደባቄላ አሹቅ እየተንገረገበች ናት፡፡ ፖለቲካው እሳት፣ ሃይማኖቱ እሳት፣ ፌዴራሉ እሳት፣ ፖሊሱ እሳት፣ ቀኑና ሣምንቱ እሳት፣ ወሩና ዓመቱ እሳት፣ ኑሮው እሳት፣ ባለሥልጣናቱ እሳት፣ ነጋዴው እሳት፣ ዳኛው እሳት፣ በሽታው እሳት፣ ርሀቡ እሳት፣…፡፡ ሁሉም በእሳት አለንጋ ይጋረፋል፤ ይጠብሳል፤ ይሸነቁጣል፤ የት እንድረስ? የትስ እንግባ? ከነዚህ ከሲዖል ካመለጡ ሽፍቶች የሚታደገን ማን ነው? አምላከ ኢትዮጵያ ወዴት አለ? ኤሎሄ! ኤሎሄ! ኤሎሁም! በዚህ መከራችን ላይ ነው እንግዲህ ወያኔ በሐረርም በአዲስ አበባም እንደዚያች ተዘውትራ እንደሚነገርላትና “እዚህ አካባቢ እሳት ይነሳል ብያለሁ” ብላ ባስጠነቀቀች ማግስት ራሷ እንደምትለኩሰው የደሴዋ ዕብድ ሴት በሹምባሾቹ አማካይነት በሚፈልጋቸው ቦታዎች ላይ እሳት እየለኮሰ፣ እንዳይጠፋም ከልካይ ዘብ እያቆመ በሀገር ሀብትና በሕዝብ ዕንባ እየተዝናና የሚገኘው፡፡ ለማንኛውም አስታዋሼን ላመስግንና በጠቆመኝ ሃሳብ ዙሪያ እንዳመጣብኝ ትንሽ ልብከንከን፡፡ እውነትን ላለማየት ዐይነ ኅሊናቸው የታወረ፣ እውነትን ላለመስማት ዕዝነ ልቦናቸው የተደፈነ፣ አእምሯቸው በፀረ-ለውጥ ቫይረስ ለፈውስ ባስቸገረ ሁኔታ “corrupted” ለሆነ የ“ሚዲያ ሰዎች”ም የቮልቴርን አባባል ባስታውሳቸው ቅር አይለኝም – ቮልቴር እንዲህ አለ አሉ፡- “በምትናገረው ሁሉ ባልስማማም መናገር የምትፈልገውን ጉዳይ በነፃነት መናገር እንድትችል ግን ሕይወቴንም ቢሆን እገብርልሃለሁ!” አይ ኢትዮጵያ! በሁሉም ድሃ፡፡ ግን ተስፋ አለኝ – ትልቅ ተስፋ፡- ወደፊት አንድ ቀን ይህ ሁሉ ድንቁርናችንና ከንቱ ትምክህታችን እንደጤዛ ሲረግፍልን ሰው እንደምንሆን፡፡
በዓለማችን የፖለቲካ ዓይነቶች ብዙ መሆናቸው ከናንተ የተሠወረ አይደለም፡፡ የድንበር ፖለቲካ፣ የውኃ ፖለቲካ፣ የዘር ፖለቲካ፣ የዘውግ ፖለቲካ፣ የውጭ ብድርና ዕርዳታ ፖለቲካ፣ የሀገር ውስጥ የድርቅ ጊዜና የርሀብ ወቅት ዕርዳታ ፖለቲካ፣ የሃይማኖት ፖለቲካ፣ … ዝርዝሩ ብዙና ኪስን ሳይሆን አንጎልን የሚቀድ ነው፡፡ ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ ያልሞከረው የፖለቲካ ዓይነት ደግሞ የለም፡፡ እርግጥ ነው ወያኔ ብቻውን አይደለም፡፡ ይህ ቀረሽ የማይባል ሁለንተናዊ ድጋፍ ለወያኔዎች በገፍ እየሰጡ በ17 ዓመታት ውስጥ የሰው ኃይሉን ከሰባት ሰውነት ወደሚሊዮንነት በማሳደግ ፀረ-ኢትዮጵያ አቋማቸውን በተግባር የገለጡት የውጭ ጠላቶቻችንም በዚህ ኢትዮጵያን ወደፖለቲካዊ ቤተ ሙከራነት የመለወጡ ሂደት ውስጥ ያሳዩት ጉልህ ተሳትፎም ለአፍታ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ከዓለም ሕዝቦች መካከል እኛ ኢትዮጵያውያን ላይ ያልተፈተሸ ፖለቲካዊ መርዝ የለም፡፡ ባጭሩ የወያኔ ብቻ ሣይሆን የፈረንጆቹም guinea pig ሆነን የቀረን ብቸኛ መዘባበቻ ዜጎች ብንኖር እኛ ኢትዮጵያውያን ነን፡፡ እርግጥ ነው እነኢራቅንና አፍጋኒስታንን ብንረሳ አግባብ አይደለም – እኛን እየገረፈን ያለው የኃያላኑ የእሳት ወላፈን እነሱንም እየጠበሰ ነውና፡፡ “አልማሊኪ ቡሽ፣ ካርዛይ ቡሽና መለስ ቡሽ እያሉ ሃቀኛ ሰላም አይኖርም፡፡”
ወያኔ ተግባር ላይ ካዋላቸው ሕዝብን የማሰቃያና ሀገርን የማውደሚያ መንገዶች አንደኛው እሳት ነው፡፡ እንዲህ የምላችሁ ወዳጄ አሁን ስላስታወሰኝ ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ ከጥንትም በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡ ለነገሩ ጨካኝና አምባገነን መንግሥታት ለዓላማቸው ስኬት የማያደርጉት ነገር የለም፡፡ ደርግም በተወሰነ ደረጃ ይህን የእሳት ፖለቲካ ይጠቀምበት እንደነበር በጊዜው ሰምቻለሁ፡፡ ሞኙ ደርግ እሳትን ይጠቀምበት የነበረው ኮንትሮባንድን ከመቆጣጠር አንጻርና በጣም በጥንቃቄ እንደነበር በወቅቱ የነበሩ አሁን ድረስ ያስታውሳሉ፡፡ የወያኔ ግን የተለዬ ነው፡፡
በመሠረቱ ወያኔ ምን እንደሆነ መናገር የዐዋጁን በጆሮ ነው፡፡ ይሁንና ወያኔዎች በተጣባቸው የትውልድ መርገምት ምክንያትም ይሁን በሌላ ከሆዳቸውና ያሻቸውን እንዲሠሩ ከሚጠቅማቸው የጨበጡት ሥልጣን በስተቀር የኢትዮጵያዊነት ስሜት በጭራሽ የሌላቸው፣ እንዲያውም ከያዙት ጥቅምና ሥልጣን ያስወግደናል ብለው የሚፈሩት በቀን ሰመመንና በሌት ቅዠት የሚያባትታቸው የኢትዮጵያዊነት ስሜት በመሆኑ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚልን ዜጋ ሁሉ በየሄደበት እያሳደዱና እየገደሉ በደም ባሕር እየዋኙ የሚኖሩ፣ ጥላቸውንም የማያምኑ የከተማ ወሮበሎች መሆናቸውን እዚህም ላይ በድጋሚ ማስታወሱ በአሰልችነት ሊያስወቅስ አይገባም፡፡ እናም አስታውሱ – ወያኔ የዜጎችን የላብ ውጤት የሆነ ሀብትና ንብረታቸውን ማቃጠል ብቻም ሣይሆን ሕዝብን በሠልፍ ኮልኩሎ እንደሂትለር የኦሽትዊዝ ቻምበር የማይፈልጋቸውን በጋዝ እየለበለበ ቢፈጃቸው የሰይጣናዊ ተፈጥሮው የሞራል ምሰሶ ክፋትና ጥፋት ነውና ደስታን የሚያስገኝለት እንጂ ሰብኣዊነት የሚሰማው ሩህሩህ ፍጡር አይደለም፡፡ ሰብኣዊነትና ወያኔ ዐይንና ናጫ ናቸው፡፡
ወያኔዎች እንደገቡ ሰሞን የምንሰማቸው ብዙ የእሳት አደጋዎች ነበሩ፡፡ እነዚያ እሳቶች እንደሰሞነኞቹ የሕዝብን አንጡራ ሀብትና ገንዘብ ለማቃጠል የታለሙ ሣይሆኑ ጫካና ደን የማያውቁት መደዴዎቹ ወያኔዎች ደቡብ ኢትዮጵያንም እንደሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለማራቆት የታቀዱ ደኖችን የማቃጠል ወያኔያዊ የክተት ዘመቻዎች ነበሩ፡፡ በርካታ የደቡብና የኦሮሞ ብሔር መኖሪያ አካባቢዎች በነዚያ ወያኔ በቀሰቀሳቸው የሰደድ እሳቶች ተቃጥለዋል – አንጀታቸው ለተፈጥሮም የሚጨክን አረመኔዎች ናቸው፡፡ በምክንያትነት ሲቀርብ የነበረው ግን የኦነግን ሸማቂዎች ከምንጫቸው ለማድረቅና መደበቂያ ቦታ ለማሳጣት የሚል ነበር፡፡ ትግራይ ውስጥ ወያኔን ሊደብቅ የሚችል ዋሻ ካልሆነ በስተቀር ደንና ጫካ እንዳልነበረ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ጫካ ቢኖር ኖሮ ወያኔን ለማጥፋት በሚል ሰበብ የደርግ መንግሥት ነዳጅ በቦቴ መኪናዎች ጫካ ውስጥ እየደፋ በአብሪ ጥይትም በአሻጋሪ እየለኮሰ ሀገር ለማቃጠል የሚያበቃው የሞራል ድቀት ውስጥ እንዳልነበረ ያንጀቴን እመሰክራለሁ – ሰው ካልሞተ ሚስትም ካልተፈታች ወይ ካልሞተች አይመሰገኑም ወንድማለም፡፡ ደርግ ዜጎችንና ሀገርን በእሳት አይቀጣም፤ ደርግ ኢትዮጵያዊ ጨካኝ እንጂ እንደወያኔ ወፍዘራሽ የባንዳ ውላጅ አልነበረም፡፡ እሳት ባለጌ ነው፡፡ እሳት እጅግ መጥፎ ነው፡፡ ምሕረትን አያውቅም፡፡ እንኳንስ ዜጋህን ጠላትህንም ቢሆን በአግባቡ ውጋው እንጂ፣ በአግባቡ ቅጣው እንጂ ኢ-ሰብኣዊ በሆነ ሁኔታ በእሳት አትገርፈውም፡፡ እነሂትለርና ሙሶሊኒ እንኳንስ ዜጎቻቸውን ጠላቶቻቸውንም ቢሆን በሰደድ እሳት አልቀጡም፤ በእሳት መቅጣት የጀግና ሙያ ሳይሆን የፈሪ ዱላ ነው፡፡ ወያኔ ግን ከየትኛው የጀሃነብ ሰማይ እንደወረደብን አይታወቅም ይሄውና ጫካና ደንን ከማቃጠል አልፎ የምሥኪን ዜጎችን ቤትና ንብረት እንዳሻው በሚያዛቸው ኅሊናቢስ ጀሌዎቹ እያቃጠለ ይገኛል፡፡ ወያኔ እኮ በእሳትም ብቻ ሳይሆን እንደተራ ተንኮለኛ ዜጋ ምግብንና መጠጥን በመመረዝና የታወቀ ጠንቋይ ቤት ድረስም በመሄድ የሚጠላቸውን የሚያስወግድ ጉደኛ ፍጡር ነው፡፡ ኪሮስ አለማየሁ እንዴት ሞተ? አለማየሁ አቶምሳስ? በውነት ቆሻሾች ናቸው፡፡ ምን አድርገን ይሆን ፈጣሪ እነዚህ ለቅጣት የሰጠን ግን? እስኪ ወደዬኅሊና ጓዳችን እንግባና ራሳችንን በቅጡ እንመርምር፡፡
በዚያን ሰሞን ሐረር ውስጥ የተቃጠለው መንደር የዚሁ የወያኔን ዜጎችን በእሳት የመቅጣት የእሳት ፖለቲካ ያሳያል፡፡ የኢትዮጵያን ገንዘብ ለራሱ ፖለቲካ በመጠቀም ዜጎችን በአነስተኛና ቀጫጭን የሚባል አዲስ ፈሊጥ እያደራጀ አንዱን ርሃብተኛ ሌላውን ጥጋበኛ እያደረገ እናያለን፡፡ በጥቃቅን የማይደራጅን በጠላትነት በመፈረጅ በገቡበት እየገባ ያሳድዳቸዋል፡፡ ከወያኔ የተለዬ ነጋዴ ኑሮውና ግብሩ እሳት ሆነው እንዲያቃጥሉትና ከሀገር እንዲጠፋ ወይም በርሀብ አለንጋ ተገርፎ እንዲሞት ሲደረግ ወያኔን የተጠጋ ሆድ አደር ግን እምብርቱ እስኪገለበጥ እየበላና እየጠጣ ተንደላቅቆ ይኖራል፡፡ እንዲህ እንዲኖርም በመዥገሮች የተወረረችው እናት ሀገር በወያኔዎቹ አማካይነት ለአንዱ የእንጀራ እናት ለሌላው ደግሞ የእውነት እናት ሆና ለሆዳም ጥገኞቹ ሁሉንም ነገር እያመቻቸችላቸው ትገኛለች፡፡ ለምሳሌ በወያኔ ማኅበር ያልተደራጀ ዜጋ ሁለት በሁለት ለሆነች የንግድ ቤት ከገቢው ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን እጅግ ከፍተኛ ኪራይና ግብር እንዲከፍል ሲገደድ (ሂድ አትበለው እንዲሄድ ግን አድርገው በሚሉት ፈሊጣቸው) ለሆዳሞቹ ግን ካስፈለገ ካለኪራይና ካለአንዳች ግብር በሕዝብ ገንዘብ እንደፈለጉ ይሆናሉ፡፡ ባንኮች ሳይቀሩ ለነሱ የግል ጥገቶች ናቸው፡፡ የሀገር ስሜት ዛሬ ያልጠፋ ታዲያ መቼ ይጥፋ?
ይህ መሰሉና ሌላው ግፍ ሁሉ አልበቃ ብሎ ነው እንግዲህ የእሳቱ ፖለቲካ በሀገር ደረጃ እየተፋፋመ የሚገኘው፡፡ እንደሰማነው በሐረር ከአንዴም ሁለት ጊዜ ቃጠሎ ተነስቶ በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ብርና ሀብትና ንብረት ወድሟል፡፡ ይህ የሆነው በወያኔው ፈቃድና ይሁንታ መሆኑን የምንረዳበት መንገድ ደግሞ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ሲደረግ አስቀድሞ የተዘጋጀው የወያኔ ጦር እሳቱን ከብቦ አላሰቀርብም ማለቱና የእሳት አደጋ ሠራተኞችም እሳቱ የሚፈለገውን ጥፋት ካገባደደ በኋላ ሥራቸውን እንዲሠሩ መፈቀዱ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ግፍ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚደረግ አይመስለኝም፤ እንዲያውም አይደረግም፡፡ ምክንያቱም የሀገር ዜግነቱን የካደና ሀገር እየቸረቸረ የሚሸጥ የሀገር መሪ ከኢትዮጵያ ውጪ በየትም ሥፍራ ይኖራል ብዬ አላምንምና፡፡
የሐረሩ እሳት መንስኤው ወያኔ ሆኖ ዓላማው ደግሞ ቦታውን ለወያኔያዊ ባለሀብቶች ለመስጠትና በእግረ መንገድም ተቀናቃኝ ኢ-ወያኔያዊ ባለሀብቶችን ለማክሰም ነው – ይህን እውነት ለማወቅ ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም፡፡ በጣም ግልጽ ነው፡፡ መንታ ዓላማ ያነገበ ቃጠሎ ነበር ማለት ነው፡፡ አንደኛውና ዋነኛው በሥርዓቱ የማይፈለጉ ዜጎችን ማደኽት – ሁለተኛው በነሱ ቦታ ደግሞ ለሥርዓቱ ዕድሜ ቀን ከሌት ተንበርክከው ሰይጣንን የሚለምኑ ፍቁራን አባላትንና ደጋፊዎችን ማቋቋም፤ በቃ፡፡ በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ ይባላል፡፡ በኢትዮጵያ መሬት፣ በኢትዮጵያውያን ሀብትና ንብረት ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑ የመንግሥትን ሞሰብ ገልባጮችና ደጋፊዎቻቸው ይገባበዙበታል፤ ይጠቃቀሙበታል፡፡ እንግዴ ልጅ ሀገር ሻጭ ማዕዱን ሲጫወትበት ልጅ ከበይ ተመልካችነትም ወርዶ የሥቃይ ሰለባ ሆኗል፡፡ እየተራቡ በሀገር መኖርም ክልክል ሆኖ ለሞትና ለስደት መዳረግ ዕጣችን እንዲሆን ተፈርዶብናል፡፡ ይህን ቅሚያና ዘረፋ፣ ይህን የግፎች ሁሉ የበላይ የሆነ ግፍ በእሳት አማካይነት እውን ለማድረግ ደግሞ የኢትዮጵያን መለዮ ለባሽ ይጠቀማሉ -በዓይነቱ ልዩ የሆነ የታሪክ ምፀት ማለት ይህ ነው፡፡ ዋ እኔን! ይህች ቀን ልታልፍ እምቢልታው ሲነፋ እነዚህ ጉግማንጉጎች ምን ይውጣቸው ይሆን?
አዲስ አበባም ውስጥ በትንሹ ሁለት ያህል ቃጠሎዎች በነዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ ተከስተዋል፡፡ አንደኛው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሲሆን ሌላኛው በአንድ ግለሰብ ቤት የደረሰና የሦስት ሰዎችን ሕይወት የጠየቀ ቃጠሎ ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡ ነፍሳቸውን ይማር፡፡ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤቱ ግን ያጠያይቃል፡፡ እርግጥ ነው – ቃጠሎው ተፈጥሯዊ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደማንኛውም አደጋ ሆን ተብሎ ሳይሆን ድንገት ሊነሳ የመቻሉ ዕድል እንዳለ ሆኖ ከወያኔ ባሕርይ ተነስተን ስንገምት መነሾው ፖለቲካዊ አንድምታም ሊኖረው እንደሚችል ብንጠረጥር “ጠርጣሪዎች(skeptics)” ተብለን ልንታማ አይገባም፡፡ እንዲያውም ስንትና ስንት ጥበቃ የሚደረግለት ትልቅ ድርጅት በቀላሉ ለእሳት ይዳረጋል ብሎ ከማሰብ አለማሰብ ይሻላል ብለን ብንከራከር የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ስለሆነም ከድንገቴ አደጋነት ይልቅ የወያኔው ተንኮል እንደሚኖርበት መገመት አይከብድም፡፡ ወያኔ ለምን ብርሃንና ሰላምን ያቃጥላል? ምን ያገኛል? ከመገመት ባለፈ እውነተኛውን ነገር ማወቅ ሊከብድ ይችላል፤ መገመት ደግሞ ለማንም የማይከለከል የሁሉም መብት ነው፡፡
ከሁሉም በፊት ግን አንድ አጠቃላይ እውነት መኖሩን እንመን፡፡ ያም እውነት ወያኔ ቢቻል ቢቻል ኢትዮጵያ እንዳለች ብትቃጠል ወይም እንጦርጦስ ብትወርድ ደስ ይለዋል እንጂ የማይከፋ መሆኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ስሟ ሲነሳ የሚዘገንናቸውና ጠበል በመጠመቅ ያለ ሰው ላይ እንደተከሰተ ሰይጣን የሚያንዘረዝራቸው እነበረከትንና ሣሞራን የመሳሰሉ መፃጉዕ ዜጎች የሚገኙበት መንግሥታዊ መዋቅር የኢትዮጵያ ታሪክ የሚዘከርበትና አእምሯዊ ቅርስ የሚቀመጥበት ማዕከል ቢቃጠል አይደሰትም ብሎ ማሰብ የዋህነት ይመስለኛል፡፡ በዕንቆቅልሽ ሀገር ውስጥ ልንጠብቅ የማይገባንን ነገር ብንጠብቅ ብልህነት እንጂ ትዝብት ውስጥ ሊያስገባን የሚችል ሞኝነት አይደለም፡፡
በመሆኑም ወያኔ ይህን የእሳት ፖለቲካውን በመጠቀም ዜጎችን ራቁታቸውን ማስቀረቱንና ወደበረንዳ ሕይወት መለወጡን እንዲያቆም፣ የዘመናት ቅርሳችንን እያቃጠለ ታሪክ አልባ ሆነን እንድንቀር ማድረጉን እንዲገታና እስከተቻለ ደግሞ ነፃነታችንን እውን ለማድረግ የምንችልበትን የጋራ ሥልት መቀየስ እንድንችል የጋራ ጥረት እንድናደርግ ጥሪየን አቀርባለሁ፡፡ ሰላም፡፡
የተቃዋሚዎች ኅብረት የድል ዋስትና ነው
ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር – 5 ቁልፍ አገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን ይዛ እነሆ በPDF ያንብቧት
እውነተኛው አ.ኢ.ግ.ተ. (EITI) ወይስ የማዳም ክላሬ የሙስና ማጋበሻ ቡድን? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ማዳም ክላሬ አሸንፈዋል! እንኳን ደስ ያለዎት፣ ማዳም ክላሬ!
ባለፈው ሳምንት የ “አምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ሊቀ መንበር የሆኑት ማዳም ክላሬ ሾርት ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም እና በማስፈራራት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የሙስና ማጋበሻ ቡድናቸው አባል እንዲሆን ለማስቻል የEITI የቦርድ አባላት ድምጻቸውን እንዲሰጡ በማድረጉ ጥረት ሲያካሂዱት የቆዩት ዥዋዥዌ ጨዋታ ተሳክቶላቸዋል፡፡ ማዳሟ አሮጌውን እና ያረጀ ያፈጀውን የአሰራር ሂደትን ማለትም እጅ በመጠምዘዝ፣ በኃይል በማስፈራራት፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም በማስገደድ፣ ከኋላ ሆኖ በማስተኮስ፣ ስልጣንን መከታ በማድረግ ከህግ አግባብ ውጭ በግድ እንዲያምኑ በማድረግ፣ አሰልች እና የምጸት ቃላትን በመጠቀም እና የህጻናት ዓይነት እሽሩሩ ዘይቤ ቁጣን በመከተል ለርካሽ ጥቅም ሲባል የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ሀቅን በመደፍጠጥ በሸፍጥ ለጊዜውም ቢሆን ሀሳባቸውን አሳክተዋል፡፡ ማዳሟ በእንደዚህ ዓይነት እኩይ ምግባራቸው የተካኑ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2003 እንግሊዝ እና አሜሪካ በኢራቅ ላይ ወረራ ለማካሄድ በተዘጋጁበት ጊዜ ማዳም ሾርት በቶኒ ብሌር ላይ ጠንካራ የሆነ ትችት በማቅረብ ከመንግስታቸው ዓለም አቀፍ የልማት ጸሐፊነት ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደሚለቁ በማስፈራራት ሁኔታውን በመቃወም የኃይል ትችት አቅርበው ነበር:: ብሌርንና የአሜሪካን መንግስት ሲተቹ አንዳሉት “ሆኖም ግን በዚያም ተባለ በዚህ የጦርነቱ መካሄድ አይቀሬነት በተረጋገጠበት ወቅት፣ ሌሎችን አገሮች በኃይል እና በማስፈራራት ለጦርነቱ መካሄድ ድጋፍ እንዲሰጡ ያስገድዱ ነበር፡፡“
አንደ ኢራቁም ጉዳይ: ማዳም ክላሬ “በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ድምጽ በማግኘት የEITI አባል እንዲሆን ከህግ አግባብ ውጭ ስልጣንዎን በመጠቀም የቦርድ አባላትዎን ያስገድዱ እና ያሳምኑ እንደነበር እናውቃለን፡፡“ እንኳን ደስ ያለዎት! ድል ተቀዳጅተዋል፡፡ የድል ደረጃ አድርገው ይውሰዱት፣ ጣራውን ከፍ ያድርጉት፡፡ “ለሰብአዊ መብት የሚሟገቱትን ድል አድርገዋል፣ በእራስዎ ቦርድ ያሉትን የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችን በመላው ዓለም ፊት አዋርደዋል፣ እናም ዕድለቢሶችን እና ድምጽ አልባ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላትን አባርረዋል፣ “መብቶቻቸውንም” ደፍጥጠዋል፣ አሁን አዲስ አበባ በመሄድ የስኬት በዓልዎን ቸበርቻቻ ማክበር ነው፡፡ በትግል ያገኙት ውጤት ነውና፡፡ ቻምፓኝ እና ኮኛክ እንደ ጅረት ውኃ ይፍሰስ፡፡ አሁን EITIን የእርስዎ የግል ንብረት አድርገውታል፡፡ የእራስዎ ህጻን ነው! ለ EITI አዲስ ስም ያውጡለት፡፡ የማዳም ክላሬ የሙስና ማጋበሻ ድርጅት በሉት? ጥሩ የእምነተቢሶች የመጠሪያ ስምን ይዟል፡፡
በጣም የሚያስደንቀው እውነታ ግን የማዳም ሾርት ፍልስፍና (እራሳቸው “መርህ” እያሉ የሚጠሩት) በብዙ በሙስና በተዘፈቁ አገሮች የማዕድን እና አምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ላይ ዕዉን እየሆነ መጥቷል፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል የEITI አባል በማድረጉ እረገድ ማዳም ሾርት የማዕድን ሙስናን ለመቆጣጠር የሚያስችል ቀላል እና በሚከተለው ዳህራ ላይ ትኩረት ያደረገ በአጭር ርቀት ላይ የተመሰረተ ድሁር ህልዮት ቀምረዋል፤ ህልዮቱም እንዲህ ይላል፣ “በዓለም ላይ በጣም በሙስና የተዘፈቁ ገዥ አካላት የይስሙላ የግልጽነት እና ተጠያቂነት ካባን ደርበው የEITI አባል እንዲሆኑ መፍቀድ፡፡“ ከዚያም እግሮችን በማንሸራተት መደነስ እና ማቀንቀን፡፡ ስለግልጽነት እና መልካም አስተዳደር ጥቂት አስመሳይ ቃላትን እና ሀረጎችን በማነብነብ የህዝብ እምነትን ለማግኘት የማታለያ ጥረት ማድረግ፡፡ የውሸት በእመኑኝ ላይ የተመሰረቱ ጥሩ የሚመስሉ የቢሮክራሲ ፍሬ ከርስኪ የታጨቁበት የማመልከቻ ቅጽ መሙላት፡፡ ከዚያም በማዕድን ዘርፍ ስራው ጥሩ ተሞክሮ እና ታማኝ መሆናቸውን በመግለጽ የአባልነት ጥያቄውን የምስክር ወረቀት ለማግኘት መጠየቅ፡፡ በመጨረሻም ከደስታ የመጨረሻው ከፍተኛ እርከን ላይ በመድረስ ሰርግ እና ምላሽ ማድረግ ትልቁ ግባቸው ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ማዳም ክላሬ ሾርት ገዥውን አካል የጸረ ሙስና ተዋጊ ጦር አስመስሎ በማቅረብ እንዲሁም ወሮበላ ዘራፊዎችን እና ሸፍጠኛ ወንጀለኞችን በእራሳቸው ተለክቶ የተሰፋ የማስመሰያ ካባ በማልበስ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት የተከበሩ የአገር መሪዎች አስመስሎ ለማሳየት እና ለቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ያለምንም እንከን የጥሩዎች ሁሉ ተምሳሌት አድርጎ ለማቅረብ የተቀመረ ስሌት ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ መንገድ ነው በአፍሪካ እና በሌሎች አገሮች ያለው በሙስና የበከተው የማዕድን እና የተፈጥሮ ጋዝ ዘርፍ በማዳም ክላሬ ሾርት ከሙስና የማጽዳት የአሰራር ዘይቤ የተቃኘው፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የEITI አባል እንዲሆን የተሰጠው ውሳኔ ፍጹም በሆነ ሙስና የተደረገ እና የማስመሰያ የአባልነት ተውኔት ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 ገዥው አካል ለአባልነት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ በተደረገበት ጊዜ የተሰጠው ምክንያት:- “የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ’ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች በነጻነት እንዳይንቀሳቀሱ በሂደትም ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዳያደርጉ ደንቃራ ሆኗል ወደፊትም ይሆናል፤ ስለሆነም ‘የበጎአድራጎትእናማህበራትአዋጅ’ እስካልተወገደድረስኢትዮጵያየEITIአባልእንድትሆንእንደማይወስን በተጨባጭ ገልጾ ነበር፡፡ በ EITI ታሪክ በእንደዚህ ያለ የአፋኝነት ህግ መሰረት ከሰብአዊ መብት አጠባበቅ ጋር በተያያዘ መልኩ አንዲት አገር የድርጅቱ አባል እንዳትሆን የአባልነት ጥያቄው ውድቅ ሲደረግ የመጀመሪያው እና ብቸኛው ክስተት ነው፡፡ (የተሰመረው አጽንኦ ለመስጠት ነው)፡፡
ታዲያ ኢትዮጵያን በአሁኑ ጊዜ በአባልነት ለመቀበል የተቻለው በስራ ላይ እየተተገበረ ያለው “የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ” ተለውጦ ነው? እ.ኤ.ኤ ከ2010 ጀምሮ በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ላይ ምን የተለወጠ ነገር አለ? “በአዋጁ” መውጣት እና በስራ ላይ መዋል ቀጥተኛ እንደምታ ምክንያት እ.ኤ.አ በ2010 ብዛታቸው 4,600 የነበሩት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአስደንጋጭ ሁኔታ ቁጥራቸው አሽቆልቁሎ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ በዓመቱ መጀመሪያ አካባቢ 1,400 ሊሆኑ ችለዋል፡፡ “ከእነዚሁ ከተረፉት እና በሞት የሽረት ትግል ውስጥ በመንፈራገጥ ላይ ከሚገኙት ድርጅቶች ውስጥ ደግሞ በአዋጁ አሳሪነት ምክንያት 90 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆነውን የሰው ኃይላቸውን እንዲቀንሱ ተገደዋል፡፡”
በሶስት ወራት ውስጥ በአንድ ጊዜ እርምጃ ብቻ “አዋጁ” በኢትዮጵያ 70 በመቶ የሚሆኑትን የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ከስራ ውጭ አድርጓቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ በፌብሯሪ 2010 ገዥው አካል ከተመሰረተ ብዙ ጊዚያትን ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤን እና የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን በተጨባጭ የእነዚህን ሁለት ጠንካራ ተቋማት አቅም ሽባ ለማድረግ፣ እንዲሁም ደግሞ ሊያሳኩ የሚያስቧቸውን የተቋቋሙባቸውን ዝንባሌዎች እና ዓላማዎች ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ ለማስተጓጎል በማሰብ ሀብታቸውን እንዳያንቀሳቅሱ አገደ፡፡
የEITI የቦርድ አባላት እ.ኤ.ኤ በ2010 የገዥውን አካል የአባልነት ጥያቄ ውድቅ ካደረገ በኋላ በእርግጠኝነት አንድ ነገር ተለውጧል፡፡ እ.ኤ.አ በማርች 2011 ማዳም ክላሬ ሾርት የEITI የቦርድ ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ማዳም ሾርት ለብዙ ጊዜ ተደናቂ መሪ እና በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል ሻምፒዮን እንዲሁም በቅርቡ የአረፉት የአቶ መለስ ዜናዊ ከፍተኛ አድናቂ ናቸው፡፡ በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ ያመልካሉ፡፡ የሚያመልኳቸው ግን በጥሩ ነገር ተምሳሌትነታቸው አይደለም፡፡ ምናልባትም እ.ኤ.አ በ2010 ገዥው አካል የድርጅቱ አባል እንዳይሆን ውድቅ ያደረጉትን የEITI የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች እና የስራ ባልደረቦቻቸውን ክብር እና ሀሳብ ለማንኳሰስ እንዲሁም በወሰንየለሽ አፍቅሮ የተዘፈቁበትን ገዥ አካል ሽንፈት ለመበቀል ያደረጉት ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የገዥው አካል የአባልነት ጥያቄ ውድቅ በተደረገበት ጊዜ በ EITI ታሪክ በእንደዚህ ያለ የአፋኝነት ህግ መሰረት “በግልጽ ከሰብአዊ መብት አጠባበቅ” ጋር በተያያዘ መልኩ አንዲት አገር የድርጅቱ አባል እንዳትሆን ውድቅ ሲደረግ የመጀመሪያው እና ብቸኛው ክስተት ስለነበረም ነው፡፡ ማዳም ሾርት በአቶ መለስ ዜናዊ እና ኩባንያቸው ላይ የደረሰውን “ውርደት” ለመበቀል ዕቅድ በማውጣት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት የአቶ መለስን የመጀመሪያ የአባልነት ጥያቄ ውድቅ በማደረግ ቁልፍ ሚና የተጫወቱትን የEITI የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮችን ማዋረድ ላይ ያጠነጠነ ነበር፡፡ ማዳም ክላሬ፣ በቀልተኛዋ አሁን የበቀል እርምጃዎን ወስደዋል፡፡!
ማዳም ክላሬ በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል በመወገን እ.ኤ.አ ማርች 11/2014 ግልጽ ደብዳቤ በመጻፍ ድፍረት የተሞላበትን የዘመቻ ውትወታ (በማስገደድ አላልኩም) ሲጀምሩ በEITI በቦርድ አባልነት ባሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች እንደ አላዋቂ ልጅ አጥፊዎች ያህል አውርደው በመመልከት የቁጣ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ አምባርቀውባቸዋል፡፡ እብደትን የተላበሰ የሚያስገርም ምልከታም አድርገዋል፡፡ እንዲህ የሚል ምልከታ፣ “የEITI መርሆዎችን የሚተገብሩ አገሮችን ሁኔታ በመምለከትበት ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ሁኔታ በሌሎች አገሮች ከሚታየው በብዙ መልኩ የከፋ ነው የሚለውን አባባል አልቀበለውም፣“ በማለት ለእራስ ታላቅ ክብርን የሰጠ የድንፋታ ንግግር አሰምተዋል፡፡ ማዳሟ ይህንን ንግግር ሲያደርጉ ምን ለማለት ፈልገው ነው? ለመሆኑ የEITI አባላት እነማን ናቸው?
EITI በአሁኑ ጊዜ 40 ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ አባል አገሮች አሉት፡፡ ብዙዎቹ አባል አገሮችም በዓለም ላይ በሙስና በበከቱ እና ጨቋኝ መንግስታት መዳፍ ስር እግር ከወርች ተተብትበው የሚገኙ ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አፍጋኒስታን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ካሜሩን፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሬፑብሊክ፣ ቻድ፣ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ፣ ጊኒ፣ ካዛኪስታን፣ ላይቤሪያ፣ ማሊ፣ ማውሪታንያ፣ ሞዛምቢክ፣ ኒጀር፣ ናይጀሪያ፣ የኮንጎ ሬፑበሊክ፣ ሴኔጋል፣ ሴራሊዮን፣ ታዣኪስታን እና የመን ይገኙበታል፡፡ “የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሌሎች የከፋ አይደለም” ከሚለው ማነጻጸሪያቸው አንጻር ማዳም ሾርት በእርግጠኝነት አንድ ሊካድ የማይችል ሀቅን ተናግረዋል፣ ይኸውም በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ከሌሎች በገፍ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ከሚፈጽሙት የEITI አባል አምባገነን አገሮች የከፋ አይደለም፣ ወይም ደግሞ ከብዙዎቹ የተለየ አይደለም ብለዋል፡፡ ሁሉም በሙስና የበከቱ ናቸው፡፡ ሁሉም የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማትን ህልውና ግብአተ መሬት የፈጸሙ ናቸው፡፡ እናም የመመንተፊያ የቆዳ ቦርሳዎችን ተሸክመው ክው ክው የሚሉ ዘራፊዎች እና ወሮበሎች ናቸው፡፡ ማዳሟ ለቦርድ አባላቱ፣ ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ለኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ለማስተላለፍ የፈጉት ትክክለኛው መልዕክት ግልጽ ነበር፡፡ “ሁሉንም ጸጥ ለማድረግ” ነው፡፡ ከተሰጣችሁ ቁመት በላይ አትንጠራሩ፡፡ በሙስና የበከቱ ዘራፊዎችን ሊፒስቲክስ በመቀባት የተለመደውን የቢዝነስ ስራ እናስቀጥል፡፡ በዚህ መንገድ መጓዝ አንችልምን?
ባራክ ኦባማ እጩ ፕሬዚዳንታዊ ተመራጭ በነበሩበት ጊዜ ከተናገሩት ጋር እስማማለሁ፣ “አሳማን ለማቆንጀት ሊፒስቲክ (የከንፈር ቀለም) መቀባት ይቻላል፣ ሆኖም ግን አሁንም ያው አሳማ ነው፡፡ አንድን ትልቅ አሳ በወረቀት መጠቅለል ይቻላል፣ እናም ለውጥ ብለን ልንጠራው እንችላለን፣ ሆኖም ግን መጠንባቱን አያቆምም ፡፡“ EITI ለዘራፊዎች በልክ ዩኒፎርም አሰፍቶ ማስመሰያ በማልበስ “ግልጽነት” እና “ተጠያቂነት” ብሎ ሊጠራቸው ይችላል፣ ሆኖም ግን ያው አሁንም ዘራፊዎች ናቸው፡፡ ሙስናን በEITI አርማ መጠቅለል ይቻላል እናም ንጹህ ብሎ መጥራት ይቻላል፣ ሆኖም ግን እስከ አሁንም መጠንባቱን አያቆምም ፡፡ EITI የአፍሪካ ዘራፊ ገዥዎችን ንጹህ እና ጨዋ ለማስመሰል የሚቀባ ሊፒስቲክ ነው፡፡
አዲስ በሆነ መልኩ ማዳም ሾርት በእርግጠኝነት ትክክል ናቸው፡፡ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እጠይቃለሁ! ብዙዎቹ በEITI አባል የሆኑ የአፍሪካ አገሮች በተኩላ ዘራፊ ሙሰኛ ገዥ ቡድኖች የሚሽከረከሩ ናቸው፡፡ “ዘራፊነት የአፍሪካ አምባገነናዊነት ከፍተኛው ደረጃ” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት ህልዮት ቀምሬ ነበር፡፡ ማዳም ሾርት በገንዘቡ በኩል ትክክል ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን ዘራፊ ገዥ አካል በEITI ካለው ከትክክለኛ ቦታው ታላቁ የሙስና ጠረጴዛ ላይ ለምን ነጠሉት? በእውነት ይህ ጉዳይ ፍትሀዊ አይደለም፡፡
የበለጠ ከዚህ በተለየ መልኩ ማዳም ሾርት የእኔን ነጥብ በትክክል አረጋግጠውታል፡፡ በእርግጥ EITI ማዕከላዊ የማዕድን ሙስና ቡድን ነው፡፡ አሊባባን እና 40ዎቹን ሌቦች አስታወሰኝ፡፡
አሁንም በጣም በተለየ መልኩ ማዳም ሾርት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የአባልነት ጥያቄው ተቀባይነት እንዲያገኝ እና በEITI ሲስተም እንዲገባ ለማድረግ በግልጽ ደብዳቢያቸው ላከናወኑት የሞት የሽረት ትግል በጣም ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ፡፡ ከልብ በመነጨ መልክ ላደረጉት የትግል መንፈስ አደንቃቸዋለሁ፡፡ ማዳም ሾርት በእርሳቸው መንገድ የማይቆሙትን ማንንም ቢሆን የማዋረድ ስብእና ያላቸው ሰው ናቸው፡፡
የገዥውን አካል የአባልነት ጥያቄ ቦርዱ እንዲያጸድቀው በማስገደድ ማዳም ሾርት ታላቅ አገልግሎት አበርክተውልናል፡፡ ምንም በውል ሳያጤኑት EITI በእውን ምን ዓይነት ተቋም እንደሆነ እንዲሁም በህገወጥ መንገድ ጥቅም ለማግኘት የማስጠበቂያ የጫጫታ ቡድን መሆኑን አጋልጠዋል፡፡ በተደራጁ የወንጀለኞች ድርጅቶች የጥቅም ማስጠበቂያ የጫጫታ ቡድኖች የፖሊስ እና የፍትህ አካላቱ በትክክል ህዝቡን ማገልገል ሲሳናቸው ወይም ደግሞ ለማህበረሰቡ የህግ ጥበቃ ማቅረብ ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰቱ ናቸው፡፡ “በጥቂት የክፍያ ገንዘብ” ሰበብ በሸፍጥ የተካነው ወንጀለኛ ለደንበኞቹ “ህግ እና ስርዓትን” ያስከብራል፣ እናም በሌሎች ወሮበሎች እና አዲስ ወንጀለኞች እንዳይዘረፉ ጥበቃውን ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡
አብዛኞቹ የEITI አባል አገሮች በራሳቸው የህግ ተቋማት ሙስናን የመቆጣጠር አቅሙ የላቸውም፡፡ ብዙዎቹ አባል አገሮችም የአንድ ሰው፣ የአንድ ፓርቲ የፈላጭ ቆራጭነት ስርዓትን የሚያራምዱ ናቸው፡፡ የፖለቲካ ተቋማቱ እስከ አጥንታቸው ድረስ በዘለቀ የሙስና ነቀርሳ የበከቱ ናቸው፡፡ የይስሙላ ፓርላሜንታሪ ስርዓቶች አሏቸው፡፡ አቃቢያነ ህጎቻቸው በትምህርት፣ በማህበራዊ እና በሞራል ስብዕና አቅመቢስ የሆኑ ድሁር ወሮበላ ዘራፊዎች እና ጽናት የሌላቸው የእመኑልኝ የህግ መጽሐፍትን በብብታቸው ሸጉጠው የሚዞሩ የፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ የፍትህ ስርዓቱ ከገዥው አካል አመራሮች የኋላ ኪስ የሚገኝ ስርዓት ነው፡፡ የጸረ ሙስና ኮሚሽኖች የፖሊቲካ ተቀናቃኞቻቸውን፣ በገዥው አካል ላይ የሚነሳሱትን ሰላማዊ አመጸኞችን ጨምሮ ለማጥቂያነት በእራስ የተሞሉ የርቀት አነጣጣሪ ሚሳይሎች ናቸው፡፡ የህግ የበላይነት የለም፣ ያለው የደናቁርት የዘራፊዎች ህግ ብቻ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ EITI በአፍሪካ እና በሌሎችም አገሮች ለዘመናት የሚዘልቅ የማዕድን ሙስና የተንሰራፋበት አዲስ ዓለም አቀፋዊ ስርዓት ለማንበር ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ ላለፉት አስርት ዓመታት EITI ያከናወናቸው ተግባራት እንግዲህ ይህንን ጉዳይ እውን ለማድረግ ነው፡፡ እውነት ለመናገር EITI በእራሱ የሙስና ቡድን በሙስና የተዘፈቁ ገዥዎችን ለመከላከል የተቋቋመ ቡድን ነው፡፡ የአገራቸውን የተፈጥሮ ሀብት የዘረፉትን እና የመዘበሩትን ወሮበላ ዘራፊዎች መልሶ ለመዝረፍ የተቋቋመ ሰላማዊ ድርጅት ነው፡፡ ሁሉም በሙስና የተዘፈቁ ገዥ አካላት እንደገና ለመወለድ እና የEITIን ስርዎ መንግስት ለመቀዳጀት የሚከተሉትን ሂደቶች መከተል ይጠበቅባቸዋል፡፡ 1ኛ) የአባልነት መጠየቂያ ቅጹን መፈረም እና የEITIን የጥያቄ እና መልስ መዝሙሩን ደጋግሞ ማነብነብ፣ 2ኛ) መጠመቅ እና በ EITI ቄሶቹ መቀባት፣ 3ኛ) ቀደም ሲል ለተሰሩት ጥፋቶች በህዝብ ፊት ጥቂት ንስሀ የመግባት ተግባራትን ማከናወን፣ 4ኛ) ቀደም ሲል ለተፈጸሙ የሙስና ተግባራት ሁሉ ይቅርታ ማድረግ፣ 5ኛ) ከሙስና ወደ ንጹህነት እስኪመለሱ ድረስ የሶስት ዓመታት የዝግጅት ጊዜ መስጠት የሚሉት ናቸው፡፡
ለዘራፊ ገዥ አካላት ይህ ታላቅ ቅሌት ነው፡፡ የEITIን የከሀዲነት ባጅ ለማጥለቅ እና ከሙስና ምን ያህለ ነጻ እንደሆኑ በባዶ ኩራት በታጀለ መልኩ ለማሳመን በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ የEITI ባጅ በኢትዮጵያ ላሉት በሙስና የተዘፈቁ ዘራፊዎች የባዶ ዲስኩር የጉራ ችርቸራ መብትን ያጎናጽፋቸዋል፡፡ የEITIን የአባልነት ፈቃድ በማግኘት በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና በኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ላይ በእውነተኛነት ላይ ተመስርቶ የተገኘ ፈቃድ አስመስሎ ለመቅረብ በሸፍጥነት መጠቀሚያ ያድርጉታል፡፡ ” ሂዩማን ራይትስ ዎች አፍንጫችሁን ላሱ! የኢትዮጵያ የዲያስፖራ አፍንጫችሁን ላሱ! እዩ እንግዲህ ተመልከቱ እንደ አዳኝ ውሻ ጥርስ ንጹህ ነን እናም ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም ይህንን ልናረጋግጥላችሁ እንችላለን!“:: የማዕድን ሙስናውን ከጥርጣሬም በላይ ከተጨባጩ ሁኔታ በላይ፣ ከቦርዱ በላይ እና ከህግ በላይ አጠናክረው ይቀጥሉበታል፡፡ የEITI የአባልነት ፈቃድ በመስጠት ለመስረቅ፣ የተፈጥሮ ሀብትን ታማኝነት በጎደለው የጮሌነት አካሄድ ጥቅምን ለማግበስበስ ለማይጠረጠሩ ባለሀብቶች በመስጠት የሞራል ልዕልና በጎደለው መልኩ ተበዳሪዎችን እና ለጋሽ ድርጅቶችን በመጭመቅ ሌላ ተጨማሪ ገንዘብ ማጋበስን የሚያስችል መብትን ይሰጣቸዋል፡፡
የEITI አባል ለመሆን የተዘጋጁት ደረጃዎቹ እና መስፈርቶቹ ጸጥ የማድረጊያ የማስመሰያነት ዘዴዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ጸጥ የማድረጊያ ስልቶች ከውጭ የሚሰነዘሩባቸውን ትችቶች ለመሸበብ ብቻ አይደለም የተዘጋጁት ሆኖም ግን ከውስጥ ለሚነሱባቸው ሰላማዊ አመጾች ማዳፈኛ እንዲሆኑ ጭምር እንጅ፡፡ EITI በአሰልች እና ተደጋጋሚነት ባለው የቢሮክራሲ ውጣውረድ የተተበተበ ፍሬከርስኪ የበዛበት የአባልነት መቀበያ መስፈርቶች፣ ተጠያቂነት እና ግልጸኝነት ያለው መሆኑን ከጉራ ባልዘለለ መልኩ ዲስኩር ሲያደርግ ይደመጣል፡፡ ማዳም ሾርት ግልጽ ደብዳቤ ብለው አዘጋጅተው በለቀቁት ደብዳቤ ላይ ለድርጅቱ እጩነት ለመብቃት “ከEITI ጋር አብሮ ለመስራት በግልጽ እና በቀላል መንገድ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርቶች በቂ ምህዳር መኖር አለመኖሩ” ሁሉንም የህዝብ ግንኙት ስራዎች ሁሉ አፈር ድሜ አብልተውታል፡፡ ሌሎችስ በጣም አስመሳይ የሆኑ የባለስልጣን መስፈርቶች እንዴት ይታያሉ? እንዲሁ ዝም ብሎ የባህላዊ ጭፈራ እና ዳንስ ነውን?
በማንኛውም ትክክለኛ በሆነ መለኪያ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የEITI አባልነት ተቀባይነት ማግኘት የድርጅቱ መስፈርቶች ባዶ እና ወና መሆናቸውን ያመላክታል፡፡ EITI የእራሱን ቡድን ለመቀላቀል “አንድ መንግስት የድርጅቱ አባል ሲሆን ምን መስራት እንዳለበት እምነቱን የሚገልጽ እና EITIን ለማጠናከር ያለውን ጽኑ የሆነ መግለጫ አዘጋጅቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡” እውነት! ትልቅ ነገር! በመቀጠልም መንግስት “የEITIን ተግባራት ለማከናወን ሃላፊነት ያለው ከፍተኛ ባለስልጣን መሾም አለበት፡፡” እርግጥ ነው ሙሰኛ አሻንጉሊት የድርጅቱን ተግባራት መከናወናቸውን የሚከታተል ሌላ ሙሰኛ አሻንጉሊት ይሾማል፡፡ መንግስት “ከሲቪል ማህበረሰቡ ጋር መስራት ይጠበቅበታል፡፡” የትኛው ሲቪል ማህበረሰብ? ምንም ችግር የለም፡፡ ሙሰኛ ዘራፊዎች በሀገሮቻቸው ውስጥ እውነተኛ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ስለሚያጠፏቸው እነዚህ ዘራፊዎች ለእነርሱ የሚበጁትን የይስሙላ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መቀፍቀፍ እንዲችሉ የፈቃድ ሰርቲፊኬቱን EITI ይሰጣቸዋል፡፡ ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የ “ኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረት” የሚል ሆድአደር ተለጣፊ ድርጅት በመፍጠር ሌሎችን እያሳደደ በማጥፋት ላይ ያለው፡፡ እንዲህ ያለ ቀልድ!
ከመሀል አዲስ አበባ ወጣ ብሎ የሚገኘው የአቶ መለስ የቃሊቲው የእስረኞች የማጎሪያ ማዕከል እውነተኛ ለፍትህ እና ለሀቅ የቆሙ ዕውቅናን ያተረፉ ጋዜጠኞች እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ውድ እና ላቅ ያለ ደረጃ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ሽልማቶች እየተቀበሉ የሚገኙት በርካታ ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ የመሳሰሉትን ጀግና ጋዜጠኞች ውጦ የምጻት ቀኑን የሚጠባበቅ የሰላማዊ ዜጎች የማሰቃያ ተቋም ነው፡፡ እስክንድር ነጋ በቅርቡ በህይወት በተለዩት በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ ትችት በማቅረቡ እና በአረቡ ዓለም እየተካሄደ ባለው የጸደይ አብዮትን በማስመልከት በሰጠው ትንታኔ ብቻ ለ18 ዓመታት በእስር ቤት እንዲማቅቅ ያለምንም ሀፍረት ተበይኖበታል፡፡ ርዕዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ በየሳምንቱ በሚወጣ መጽሄት ላይ ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ብቻ እያንዳንዳቸው በ14 ዓመታት እስር እንዲቀጡ በማንአለብኝነት በይስሙላው/የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ህሊናየለሽ ውሳኔ ተበይኖባቸዋል፡፡
ከተለጣፊው “ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረት” ስለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ የተጠያቂነት እና ግልጸኝነት ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት መጠበቅ ማለት የዶሮዎችን መጠለያ ቤት እንዲጠብቅ ኃላፊነት ከሚሰጠው ቀበሮ አንድም ዶሮ ላለመጥፋቱ ትክክለኛ የሂሳብ ሪፖርት እንዲያቀርብ መጠየቅ እንደማለት ነው፡፡ በEITI ገዥ አካሎች መሰረታዊ ሀሳብ መሰረት ህብረተሰቡን ያለምንም ተጽዕኖ የበላይ ተመልካችነት እና የተቆጣጣሪነት ስልጣን በመስጠት በቀጥታ ተሳታፊ በማድረግ በማዕድን እና በተፈጥሮ ጋዝ ዘርፉ ላይ ትክክለኛ እና በዘርፉ ሊረጋገጥ የሚችል መረጃን አዘጋጅቶ የማውጣት ስራን በማቀላጠፍ ሂደቱን የማሳለጥ ተግባራትን የማከናወን ስራ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ የመጨረሻው ግቡ ደግሞ “ከተፈጥሮ ሀብት ተፈብርኮ የሚገኘው የምርት ገቢ በትክክል ያለምንም ሙስና ለህዝቡ ጥቅም እንዲውል መራጋገጫ የሚሰጥ ነው፡፡”
መረጃን በተመለከተ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል አስቀያሚ የመረጃ መቀቀያ ቶፋ አለው፡፡ “የአቶ መለስ ዜናዊ ምዕናባዊ የምጣኔ ሀብት“ እና “የአቶ መለስ ዜናዊ የውሸት የምጣኔ ሀብት” በሚሉ ርዕሶች ሳቀርብ እንደነበረ ሁሉ የአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ በእርሳቸው አመራር ኢትዮጵያ አስር ዓመት ሙሉ ያለምንም ማቋረጥ “ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ መጣኔ ዕድገት አስመዘገበች” በማለት ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ብቻ የውሸት መረጃ በመረጃ መቀቀያው ቶፋ እየታጨቀ የሀሰት መረጃ ሲሰራጭ ቆይቷል፡፡ እውነታው ግን ላም አለኝ በሰማይ ነው፡፡ ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም በቀን ሶስት ጊዜ አንድ ጊዜ እንኳን ለመብላት እየተቸገረ ነው ያለው፡፡
በጣም የሚያስደንቀው ነገር ደግሞ አቶ መለስ በብልጣብልጥነት የእራሳቸውን የቅጥፍና የኢኮኖሚ የዕድገት መረጃ አሀዝ ለዓለም ባንክ እና ለዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የመመገባቸው ጉዳይ ይህንንም ተከትሎ እነዚህ ዓለም አቀፍ ተቋማት የእርሳቸውን ጥሩንባ የመንፋታቸው ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከማንም በተሻለ መልክ ግንዛቤው ያላቸው ቢሆንም የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ታላቅ እና ድፍረት የተሞላበት የውሸት የኢኮኖሚ ዘገባ በማቅረብ ወንጀለኛ ገዥ አካላት ዕኩይ ድርጊታቸው የሀሰት ዘገባዎችን እንዲያቀርቡ እየገዟቸው ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በEITI የቀሚስ ጉንፍ ውስጥ ተወሽቆ በማዕድኑ ምርት እና ገቢ ሁሉምን ዓይነት የሀሰት የመረጃ አሀዞችን በመቀፍቀፍ እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠር አንጡራ የሀገሪቱን ሀብት ወደ ውጭ በማሸሽ ውጭ አገር በሚገኙ የግል የባንክ ሂሳቦቻቸው ላይ በማስቀመጥ ላይ እንደሆኑ እና እንደዚህ ያሉ ተመሳሳይ የማታለል ድርጊቶችን በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ የክርክር ጭብጤን ላቀርብ እችላለሁ፡፡ ወደፊት “በEITI ጋሻጃግሬነት እየተካሄደ ያለ የኢትዮጵያ የማዕድን ሙስና ተምኔታዊ የመረጃ አሃዞች” በሚል ርዕስ ስር ትችት አቀርባለሁ የሚል ዕቅድ አለኝ፡፡
EITI ጥሩ የሚመስሉ መስፈርቶችን በማቅረብ ሆኖም ግን በአፍሪካ እና በሌሎች ታዳጊ አገሮች ለሚካሄዱት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ሙስና የህጋዊነት ሽፋን በመስጠት የህጋዊነት ሀሳባዊነትን፣ ታማኝነትን ግልጽነት እና ተጠያቂነት ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ EITI “የድብቅ ቴክኖሎጅን” የሚጠቀም በመሆኑ በአፍሪካ እና በሌላው ዓለም ያሉ በሙስና የተዘፈቁ ገዥ አካላት ያለምንም ስጋት እና ጥርጣሬ የህዝቦቻቸውን ሀብቶች ለመዝረፍ ሲሉ ተቋሙን መቀላቀል ይፈልጉታል፡፡ EITI እምነት ከማይጣልባቸው፣ በሙስና ከተዘፈቁ እና አስጸያፊ ባህሪያትን የተላበሱ፣ እንዲሁም ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በዓለም መድረክ ላይ በመጀመሪያ እምነቱን በማግኘት በኋላ የሚከዳበት ዓይነት ጨዋታ ከሚደረግባቸው ድርጅቶች መካከል አንደኛው ነው ማለት ይቻላል፡፡
ሁለት ጊዜ ይቅርታ መጠየቅ እና አንዱን በጽናት መያዝ፣
“የማዕድን ሙስና በኢትዮጵያ፡ ለማዳም ክላሬ የተሰጠ መልስ” በሚለው የመጀመሪያው ትችቴ ላይ ማዳም ክላሬ የኢትዮጵያን የEITI አባል መሆን አስመልክቶ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከጉዳዩ ውጭ እንዲሆኑ ስላደረጓቸው አሰልች ቀኖናዊ ህጎች ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ይቅርታ እንዲያቀርቡ ሀሳብ አቅርቤ ነበር፡፡ ማዳሟ “የቦርድ አባላቱ የኢትዮጵያን የተባበረ የሲቪል ማህበረሰብ ድምጽ እንጅ የተቃዋሚ ዲያስፖራ ድምጾችን መስማት እንደሌለበት ተማጽዕኖ አቅርበው ነበር፡፡” ውጤታማ በሆነ መልኩም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ድምጽ መዘጋት እንዳለበት ሞግተዋል፡፡
“ግልጽ እና የተባበረው የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ” የማዳም ሾርት ፍጹም የሆነ ምዕናባዊ የሆነ እና የተረጋጋ ስሜት እንዳይኖር በማድረግ ዓላማ ላይ የሚሽከረከር ሆኖ ይገኛል፡፡ ትክክለኞቹ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከዓመታት በፊት ጀምሮ ታፍነው ተሸብበው ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን ማዳም ሾርት በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ የሌለውን አለ የሚል ቅዠት ለማንበር ይፈልጋሉ፡፡ ምናልባትም የእርሳቸው የስሜት ጓደኛ እንደሆኑት እንደ አቶ መለስ ዜናዊ የመኝታ ጊዜ ትረካዎችን መናገር መውደድ አለባቸው፡፡ እኔ በትረካዎች ላይ በእርግጠኝነት ትዕግስት ማድረግን እከተላለሁ፣ እንደ ዶ/ር ሰውስ ተረት:- “ ተረት ተረት የላም በረት: አንድ ዓሳ፡፡ ሁለት ዓሳዎች፡፡ ቀይ ዓሳ፡፡ ሰማያዊ ዓሳ፡፡” ተረት ተረት አንድ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት፡፡ ሁለት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፡፡ ሰማያዊ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት፡፡
በእርግጠኝነት ለተቀደሰ ተግባር፣ የተከበረ እና ሩህሩህነት የተንጸባረቀበት ሀሳብ ሲባል ማዳም ሾርት ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን/ት የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባት ይኖርባቸዋል የሚል ተስፋ ነበረኝ፡፡ ምናልባትም “ከተናገርኩት ውጭ የስህተት ግንዛቤ ተይዟል ይቅርታ” ሊሉ ይችሉ ይሆናል፡፡ እንደ ቆንጆ የህዝብ ግንኙነት ስራ በእርግጠኝነት ላይሉም ይችላሉ፡፡ ማዳም በእርሳቸው የተዛባ ጥላቻ ሰበብ የጥቃት ሰለባ ለሆኑት ወገኖች ይቅርታ ለመጠየቅ ለጋስነቱ ያላቸው አይመስልም፡፡ የዘመኑን የወጣቶችን ንግግር ለመጠቀም ማዳም ሾርት ሰዎችን በመበጥበጥ ከዘራፊዎች ድንበር ተርታ ጋር የሚያመሳስል የረዥም ጊዜ እውቅና አላቸው፡፡ ማዳም ሾርት በብርሀን ፍጥነት ተናዳጅነታቸው እና ግንፍልተኝነታቸው ይታወቃሉ፡፡ ሪቻርድ ዶውደን የተባለው የእንግሊዝ ታዋቂ ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ በ2011 ከማዳም ሾርት ትረካውን እንዲህ አቅርቦታል፡፡ “በአንድ ወቅት በአውሮፕላን ላይ ቃለ መጠይቅ እያደረግሁላቸው ሳለ እና ስለሩዋንዳ የሰብአዊ መብት ሁኔታ ትኩረት በመስጠት ጥያቄዬን ሳቀርብ ማዳሟ እኔን ለመወርወር በሚያስችል ዓይነት ሁኔታ አስፈራሩኝ፡፡ በዚያን ወቅት በጊኒ የአየር ክልል ላይ ስለነበርን ከዚያ በኋላ አቆምኩ፡፡ አሁን ደግሞ የተዋበ፣ ሰላም እና መረጋጋት በሰፈነበት በለንደን የጋራ ሀብት ክለብ ተገናኘን፣ እናም ማዳሟ እርጋታ የሚታይባቸው እና ሀሳብ የሚሰጡ ሆኖም ግን በማንም ዘንድ ጠንካራ ትችት የሚያቀርቡ የሚያደርጉትንም በብልኃት መያዝ የማይችሉ ሆነው ነው ያገኘኋቸው፡፡“ ማዳም ሾርት ቀልድ አያውቁም! ቶኒ ብሌር ሃሰባቸውን እንዳይገልጹ ለማድረግ በሀይል አፋቸውን ያስይዟቸው ነበር፡፡ (ብሌር የተናገሩት አያስደነቅም:- ”እንደተዋረደች እና ሀሳቧን እንዳትገልጽ በኃይል እንደተያዘች ሚስት ነው የተሰማኝ፡፡” ያሉት ሲያመናጭቁአቸው:: ይህ አካሄድ የማዳም ሾርት አጭሩ ጎዳና ነው! ቢሆንም ለማዳሟ ክብር እሰጣቸዋለሁ፡፡ ለሚያምኑት ይቆማሉ: ይዋጋሉ:: በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት ገዥ ዘራፊዎች በጽናት ይቅርታ የሚያቀርቡ ሴት ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላትን ይቅርታ መጠየቅ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ማዳም ሾርት በድርጅታቸው ያሉትን የሰቪል ማህበረሰብ ድርጅት ተወካዮችን ማለትም ዓሊ ኢድሪሳን፣ ንዋዲሺን ጂን ክላውዲ ካቴንዴን እና ሌሎችን የከፈለህን አትም አባላት ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ይህንን በጥብቅ እጠይቃለሁ! ማዳሟ “በግልጽ ደብዳቢያቸው” ፍትህዊነትን በጣሰ መልኩ አስደናቂ ተዋንያን በመሆን በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ላይ አምባርቀውባቸዋል፡፡ “የተለየ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች ጠንካራ ድምጾችን በማሰማት ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚደረግ ጥረት እንዳለ እና እንዲያውም የሰሜን ደቡቡን እንዲወስንለት በታቀደ ዘይቤ የሚመሩ ናቸው በማለት ክስ አቅርበውባቸዋል፡፡” የኢትዮጵያ ገዥው አካል የEITI አባል እንዳይሆን ተቀዋሚዎች ተቃውሞ በማሰማት የEITIን ዕድል ተፈታትነዋል በማለት ማዳሟ ጩኸታቸውን አሰምተዋል፡፡
ኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴን በማክበር ለማዳም ሾርት ግልጽ ደብዳቤ ግልጽ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ እንዲህም ብለዋል፣ “የኢትዮጵያ የEITI የአባልነት ጥያቄ በቀጣናው ስብሰባ እዲቀርብ በአጀንዳችን ውስጥ አልነበረም በእርግጥ ይህ ጉዳይ የከባቢ ሁኔታ ግምገማዎችን እያደረግን ባለንበት ሁኔታ ነው የመጣው፡፡“ በወቅቱ ሁለት ገዥ ሀሳቦች ተነስተው አንደኛው በመቃወም ሁለተኛው ደግሞ በመደገፍ ክርክር እንደነበር ገልጸዋል፡፡ “ገለልተኛ” በሆነ መልኩ ማዳሟን እንዲህ በማለት ሞግተዋል፣ “ኢትዮጵያ የEITI አባል እንድትሆን ግልጽ አቋም በመያዝ ወገንተኝነት አሳይተዋል፣ ከገለልተኝነት መርህ ጋር በተጻረረ መልኩ በድርጅቱ ሊቀመንበርነትዎ ላይ ጥያቄ ሊያስነሳ የሚችል ድርጊትን ፈጽመዋል፡፡ የድርጅቱ ታማኝ የመሆን ጠቀሜታ መሰረት የሚለካው በዚህ ጠቃሚ መርህ ነው፡፡” በዚህ አስፈሪ ግልጽ ደብዳቤ እንቆቅልሽ የሆነባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ “በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጹ ደብዳቤ ለተውሰኑ ጥቂት ሰዎች ማሳወቅ ሲገባ ለምን ለህዝብ ይፋ እንደተደረገ ግልጽ አለመሆኑን ለመጠቆም እንፈልጋለን… እንደዚሁም የእኛም ደብዳቤ እርስዎ ለህዝብ ለአደባባይ እንዳቀረቡት ሁሉ በEITI ድረ ገጽ ላይ እንዲታተም እንጠይቃለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ዓለም አቀፍ ድረ ገጽ ለጥምረት አባሎቻችን በሙሉ ሊለቀቅ ይገባል፡፡“ የሚል ነው፡፡
ማዳም ሾርት ለኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ በቀጥታ ሳይሆን በጸሐፊያቸው በጆናስ ሞበርግ በኩል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የተሰጠው መልስ በቁስል ላይ ጨው መነስነስ ያህል ነበር፡፡ ማዳሟ በግልጽ ደብዳቢያቸው ለኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ ደብዳቤ መጻፉ ችግር እንደሌለባቸው በመጮህ የተናገሩ ሲሆን ቀደም ሲል የዓለም ማህበረሰብ ከማወቁ በፊት መደረግ እንደነበረበት ተናግረዋል፣ ሆኖም ግን በኋላ ደፍረው ሲመልሱ አንዴት ተደርጎ!? በተለመደው ቦታቸው አርፈው እንዲቀመጡ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሞበርግ ይህንን ቆሻሻ ስራ የተሰጠው ሰው ነው፡፡ እኔ በግሌ የሚከተለውን ሳነብ እንደተዋረድኩ እቆጥረዋለሁ፣
“ማዳም ክላሬ ለእናንተ ደብዳቤ ምላሽ እንድጽፍ ጠይቀውኛል፡፡ ያቀረባችኋቸው ነጥቦች በሙሉ ማስታወሻ ተይዞባቸዋል፣ የሊቀመንበሯን ገለልተኛነት ተብሎ ከሚጠራው ነጥብ በስተቀር፡፡ ለጂን ክላውዴ እንደገለጽኩት ሁሉ ሊቀመንበሯ ገለልተኛ እንዲሆኑ አይጠበቅባቸውም፡፡ እንደማንኛቸውም የእኛ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ሁሉ ገለልተኛ መሆን እንዳለባቸው አይነት በመሆን ሊሰሩ አይችሉም፡፡ ሊቀመንበሯ EITIን ነው የሚያገለግሉት ምክንያቱም በድርጅቱ መርሆዎች ላይ እምነት ስላላቸው ነው፡፡ እነዚህን መርሆዎች የመጠበቅ ኃላፊነት እና የEITIን ጥቅም ማስጠበቅ አለባቸው፣ እናም ለእናንተ ደብዳቤ በጻፉበት ወቅት ያደረጉት ነገር ቢኖር ይህንኑ ነው፡፡ በደብዳቢያቸው ላይ የሊቀመንበሯን ሚና የሚጥስ ነገር አልታየም፡፡”
ኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ ከክብርትነታቸው በቀጥታ የሚጻፍ ደብዳቤ እንደክብርቷ አመለካከት ከሆነ አይመጥናቸውም፡፡ በሌላ አገላለጽ የማዳሟን ክብር ዝቅ የሚያደርግ ነገር ነው፡፡የሞበርግን ደብዳቤ በድጋሜ ሳነበው በጫካ እንደሚኖረው ባለረዥም ጅራት ቆርጣሚ አውሬ በንዴት ብግን ነው ያልኩት፡፡ ማዳም ሾርት ምን ያህል ደፋር መሆናቸውን የሚያሳየው በጸሐፊው አማካይነት ምላሽ የሰጡ መሆናቸውን ስናስተውል ነው! ማንም ጭራቃዊነት የሰራው እርሳቸው አይደሉምን?! በፍጹም የማለት ሞገስ ሊኖራቸው አይችልምን! ቀላሉ ዘዴ በጸሐፊያቸው አማካይነት የማርቀቅ እና እርሳቸው ፈርመው መላክ ነው፡፡ በግልጽ ለመናገር ማዳም ሾርት ለኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ ግልጽ መልዕክት ማስተላለፍ ፈልገዋል፡፡ ማን አለቃ እንደሆነ እና አጠቃላይ ሁኔታውን ለማሳወቅ ፈልገዋል፡፡ እርሳቸው አለቃ ናቸው፣ ስለሆነም ስለማንኛውም ነገር ደንታ የላቸውም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ማዳም ሾርት ስለኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ስለካቴንዴ ጉዳይ ደንታ የላቸውም!
ስለሰው ልጅ ስብዕና፣ ክብር እና ሞገስ ስል በኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ ስም እኔ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተገናኝቸ ወይም ደግሞ ተነጋግሬ አላውቅም፡፡ ሆኖም ግን እንደ አንድ አፍሪካዊ ወገኖቼ የእነርሱ ውርደት የእኔም ውርደት እንደሆነ እንዲገነዘቡልኝ እፈልጋለሁ፡፡ በእንደዚያ ዓይነት አያያዝ ሲስተናገዱ ስመለከት እንደ አፍሪካዊ የእኔ ኩራት ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ሆኖም ግን እንዲያውቁልኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር ጠንካራ ኩራት እና ኃይል ይሰማኛል፡፡ ለማዳም ሾርት አስደንጋጭ ግልጽ ድብዳቤ የሰጡት ምላሽ የአስተዋይነት፣ የምክንያታዊነት እና የተለምዷዊ በጎ ምግባር ተምሳሌት ነበር፡፡ እነዚህ አፍሪካውያኑ በምላሻቸው ላይ ቁጥብነትን፣ ባለሞያነትን፣ታጋሽነትን እና ታማኝነትን አሳይተዋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ “አፍሪካዊ ትውልዶቻቸው እሺ! አቤት ወዴት! እርስዎ እንዳሉት ጌታዬ!” እያሉ ስብዕናቸውን ዝቅ ማድረግ በፍጹም እንደሌለባቸው በተጨባጭ አሳይተዋል፡፡ ማዳም ሾርት እና መሰሎቻቸው አዲሱ የአፍሪካ ትውልድ ለማንም ሎሌ እንደማይሆን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሰውን ባለቃነቱ ብቻ “አዎ አዳኙ ጌታዬ” የሚባለው ተረት ተረት ጊዜው ያለፈበት እና ያፈጀበት ዘመን ላይ ነን፡፡ ሁላችንም አፍሪካውያን በጀግኖቹ ኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ ልንኮራ ይገባል፣ ምክንያቱም ክብርን በደፈጠጠ እና ባዋረደ ጭራቃዊ መንፈስ ላይ የብዕር ጦራቸውን በመስበቅ ክብር እና ሞገስን እንድንቀዳጅ አስችለውናል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ የፈጸሙት ተግባር ነው፡፡ ይሄ ነው ጀግኖች! እናደንቃችኋለን ኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ፡፡
በተጨማሪም ማዳም ሾርት በተደጋጋሚ በተናገሩት አቁሳይ እና ከስልጣን ገደባቸው ውጭ በመሄድ ላሳዩት ትዕቢት በተቀላቀለበት ድንፋታ ስሜታቸው እንዳይጎዳ መጽናናትን እንዲያደርጉ እማጸናለሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ማዳም ሾርት በቅርቡ በህይወት የተለዩት የአቶ መለስ ዜናዊ አምላኪ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2013 ማዳም ሾርት በአንድ የመታሰቢያ በዓል ላይ በመገኘት አቶ መለስ “ታላቁ” ሰው በማለት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንዲህም ብለዋል፣ “አቶ መለስ በህይወት ዘመኔ ካየኋቸው ሁሉ የመጠቀ እውቀት ያላቸው ፖለቲከኛ ናቸው” በማለት አሞካሽተዋቸዋል፡፡ (ቶኒ ብሌር፣ ጎርደን ብራውን፣ ሃሬት ሃርማን፣ ኢድ ሚሊባንድ፣ ዴቪድ ካሜሩን፣ ጆህን ሜጀር፣ ታቼርን ቅርጫት ደፉባቸው፡፡ ማዳም ሾርት ደስ ያላልዎትን የሚያስጨንቀዎን ነገር መግለጽ ይችላሉ!) እኔ በበኩሌ “አቶ መለስ ሁሉን ነገር አዋቂ” መሆናቸውን አላውቅም፣ ይልቁንም አነጣጥሮ ገዳይ እና አስገዳይ ተራ እርባናቢስ ለሰው ክብር የሌላቸው ዉዳቂ የነበሩ ለመሆናቸው ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለኝም፡፡ እስቲ አካባቢያችሁን ተመልከቱ፣ ሁሉም ጭራቸውን ይቆላሉ፡፡
አቶ መለስ እንደ ማዳም ሾርት ሁሉ እርሳቸውን የተቃወሟቸውን ወይም በእርሳቸው ላይ ትችት ያቀረቡትን ሁሉ “ድራሻቸውን የሚያጠፉ” በእብሪት የተሞሉ ሰው ነበሩ፡፡ የእርሳቸውን ተቀናቃኞች በተደጋጋሚ “ደደቦች”፣ “ቆሻሾች”፣ “የጭቃ ጅራፎች”፣ “ስግብግቦች” እና “ለምንም የማይጠቅሙ እርባና ቢሶች” በማለት ይፈርጇቸው ነበር፡፡ እንደዚሁም በሰለጠነ ህብረተሰብ አጠራር መሰረት ደግሞ ለመጥራት ጸያፍ የሆኑ ስሞችን ይለጥፉ ነበር፡፡ አቶ መለስ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ሊቀመንበር የነበሩትን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ወደ እስር ቤት ወርውረው ለብቻ በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲታሰሩ ካደረጉ በኋላ እንቅስቃሴ ባለማድረጓ ምክንያት የመወፈር ነገር ይታይባታል የሚል ምጸት አሰምተዋል፡፡ አቶ መለስ በፓርላሜንት ጉባኤ ላይ የሚገዳደሩ ጥያቄዎችን በማንሳት ወይም ሌላ ለየት ያለ አካሄድ እንዳለ ለማሳየት ሀሳብ የሚያቀርቡ ተወካዮችን በማዋረድ እና በመዘለፍ በሚፈጽሟቸው ጭራቃዊ ድርጊቶቻቸው ይደሰቱ እና እርካታን ያገኙ ነበር፡፡ የእርሳቸው ሰውን አሳንሶ የመመልከት፣ ምጸታዊ ንግግር፣ እና ለሚጠየቋቸው ጥያቄዎች የሚሰጧቸው ንቀት የተሞሉባቸው መልሶች በጣም አዋራጅ እና የተጠየቁ ጠቃሚ ነገሮችን ነቅሰው በማውጣ መልስ እንዳያገኙ የመዝለል ሁኔታዎች አንዳንድ ድፍረት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ተወካዮች በድፍረት ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች የሚሰጧቸው ምላሾች እና የመድረክ ተውኔቶች ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ በሜይ 2010 የተደረገውን ሀገር አቀፍ ምርጫ 99.6 በመቶ የተገኘው የድምጽ ውጤት በመጭበረበሩ ምክንያት የተገኘ መሆኑን የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን አቶ መለስን ከእውነታው ጋር አፋጥጠው ሲይዟቸው አቶ መለስ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎች ቡድንን ዘገባ “ወደ ቅርጫት መጣል ያለበት ቆሻሻ ነው” በማለት በጅምላ አውግዘዋቸዋል፡፡ ምን ማለት እችላለሁ? እራስን በአምላክነት ሰይሞ ተከታይ እንዲኖር መፈለግ!
ማዳም ሾርት የEITIን መርሆዎች እሰከብረዋል ወይስ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ተሟጋች/ወኪል ነበሩ?
ማዳም ሾርት በሞበርግ አማካይነት ለኢድሪሳ፣ ንዋዲሺ እና ካቴንዴ በሰጡት ምላሽ ለኢትዮጵያ ወገንተኛ ያልነበሩ ብቻ ሳይሆን የEITIን መርሆዎች ለማስጠበቅ እና ለEITI ጥቅም ተግተው በመስራት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የሚገልጽ ነበር፡፡ እርግጠኛ ነዎትን?
ማዳም ሾርት “የEITIን መርሆዎች አስጠብቀው” ነበር ወይስ ደግሞ በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል ወግነው ነው ይህን የሚከተለውን ግልጽ ደብዳቤ የጻፉት የሚለውን ማየት ለግንዛቤ የበለጠ ይረዳል፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ሁኔታ ከሌሎች በርካታ አገሮች የከፋ ነው የሚለውን አልቀበለውም፡፡
በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያለው ውይይት ጠቀሜታ በሌለው መንገድ የተለየ ፍላጎት ባላቸው እና ሙሉ ትርጉም ባለው “የሰሜኖች ለደቡቦች መናገር አለባቸው በሚለው የአሰራር ዘየ” በተገመደ ጠንካራ ድምጽ ተጽዕኖ ስር የወደቀ በመሆኑ ላይ መናገር አለብኝ፡፡
የአትዮጵያን የአባልነት ጥያቄ ውድቅ ማድረግ ማለት የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ የትም እንዳይሄዱ ማድረግ ማለት ነው፡፡
ከኢትዮጵያ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ተቃውሞዎችን ከመስማት ይልቅ በኢትዮጵያ ግልጽ እና የተባበሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ድምጽ መስማት ያለብን በመሆኑ ላይ ያለኝን እምነት መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡
በጥሩ ሁኔታ መስራት የሚችሉ በጣም ጠንካራ የሆኑ ሌሎችን የአፍሪካ አገሮች ሊቀላቀሉ የሚችሉ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች እንዳሉ ከሀሳባዊነት በራቀ መልኩ ምንም ዓይነት ጥርጥር የለኝም
አንድ ዓይነት ወጥነት የሌላቸው መስፈርቶች መኖርም ሌላው ታላቅ ችግር ነው፡፡ ለምሳሌ በሀገሬ የቅዱስ ፓውሎስ ካቴድራል ውጫዊ ክፍልን በኃይል የተቆጣጠሩትን ተቃዋሚዎች ማባረረን አስመልክቶ የሚነገር ጉምጉምታ አለ፡፡ የጓንታናሞ መኖር እና ማሰቃየትን የመተግበር ሁኔታ አስመልክቶ ዩናይትድ ስቴትስ ጉዳይ ለአባልነት ጥያቄ ሲቀርብ አልተነሳም፡፡
EITI የዘመቻ አድራጊዎች መሳሪያ ተደርጎ የሚታይ ከሆነ ውጤታማ እና ድጋፍ የሚኖረው ሊሆን አይችልም፡፡
ጎራዴው ለምን ማጥቂያነት ይውላል?
ማደም ሾርት ገዠው አካል የEITI አባል መሆን እንዲችል ጉሮሮ ለጉሮሮ በመተናነቅ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡ በግልጽ ድብዳቢያቸው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል አባል እንዲሆን ሽንጣቸውን ገትረው የውትወታ ተግባራቸውን አከናውነዋል፡፡ ማንም ሽንጡን ገትሮ ላመነበት ጉዳይ ትጋድሎ የሚያደርግን ሰው በሀሳብ የማንግባባ ቢሆንም እንኳን አከብራለሁ፡፡ ማዳም ሾርትም ላመኑበት ጉዳይ በጽናት መቆማቸውን አደንቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን እደነቃለሁ፣ በእርግጥም በጣም እደነቃለሁ! ማዳሟ ላደረጉት የጽናት ተጋድሎ ዋጋቸው ምን ሊሆን ይችል ይሆን? በኢትዮጵያ ላሉ ዘራፊዎች ማዳም ሾርት ያደረጉት ተጋድሎ ዋጋ ምን ያህል ይሆን? የማዳም ነብስ ዋጋው ምን ያህል ይሆን?
በእርግጠኘነት ስለEITI ከልብ የሚቆረቆረው ማን ነው?
EITI፣ CCC፣ EEITI ማንም ይሁን! ማን ነው ያገባኛል የሚለው? ማን ነው ትኩረት አድርጎ የሚይዘው!? አሳማን ሊፒስቲክ መቀባት ይቻላል፣ ሆኖም ግን አሁንም ያው አሳማ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ሁሉንም የአፍሪካ ዘራፊ አምባገነኖች የEITI አባል ማድረግ ይቻላል፣ እናም ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት ብሎ መጥራት ይቻላል፡፡ በቀኑ መጫረሻም ያው አንድ ዓይነት ዩኒፎርም የተሰፋላቸው የዝርፊያ ቦርሳዎችን ይዘው የሚዞሩ ዘራፊ አምባገነኖች ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ መሰቃየት፣ ኃይልን መጠቀም እና ጭካኔ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመቀጠል ላይ ይገኛል፣
ማዳም ሾርት ለአንድ አፍታ እንዲህ በማለት አሰቡ፣ ”እኔ እንደማስበው መሰቃየቱ፣ በኃይል መጠቀም እና ጭካኔ የተሞላበት ሁኔታዎች በጓንታናሞ እስር ቤት እና በኢራቅ ላይ ቀጥለዋል፡፡“ ደህና፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያ በተመሳሳይ መልኩ አስባለሁ፡፡ በኢትዮጵያ የሚደረገው ማሰቃየት፣ የኃይል እርምጃ እና ጭካኔ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀጠለ ነው፡፡ ጋዜጠኞች ይታሰራሉ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይዘጋሉ፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እንዲሸማቀቁ እና በፍርሀት ቆፈን እንዲጠመዱ እና እንዲታሰሩ ይደረጋሉ፣ ሰላማዊ አመጸኞች በኃይል እንዲጨፈለቁ ይደረጋሉ፣ እንዲሁም ምርጫዎች በጠራራ ጸሐይ ይጭበረበራሉ፡፡ ይህ ሁሉ ግን ሰላማዊ የሽግግር ለውጡን ሊያቆመው አይችልም፡፡ ያ ሁኔታ ይቀጥላል፣ ይቀጥላል… የኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች እና ወንዶች ይነሳሉ እናም ለነጻነታቸው እንዲህ በማለት ይጮሃሉ፣
“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ተርበናል! ነጻነት እንፈልጋለን! ነጻነት እንፈልጋለን! እስክንድር ይፈታ! አንዷለም ይፈታ! አቡባከር ይፈታ! ርዕዮት ትፈታ! የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ! ፍትህ እንፈልጋለን! ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት! አትከፋፍሉን! ኢትዮጵያ አንድ ነች! አንድ ኢትዮጵያ! ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ውኃ ናፈቀን! መብራት ናፈቀን! ተርበናል!…“
በጓንታናሞ እና በኢራቅ ውስጥ የሚካሄዱትን ስቃዮች፣ የኃይል እርምጃዎች እና ጭካኔዎች በሚመለከት ማዳም ሾርት የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶችን ተጠያቂዎች እንዳደረጓቸው ሁሉ እኔ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጠቅላላ ከጠፉ በኋላ ማዳም ሾርትን ተጠያቂ አደርጋለሁ፡፡
ማዳም ክላሬ ሾርት፣ “ተከሰዋል…!”
“እውነትን በዘጉ ጊዜ እና ከመሬትውስጥበቀበሯትቁጥር ድርጊቱን ማድረግ ይቻላል፣ ሆኖም ግን እውነት እያደገች፣ እየጠነከረች ትሄዳለች፣ እናም በአንድ ላይ ተሰባስባ የሚፈነዳ ኃይል ትፍጥራለች፣ በምትፈነዳበት ዕለት ሁሉም ነገር እራሷ በቀየሰችው መንገድ ይፈነዳል፡፡“ ኢሚሌ ዞላ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ለአማራ ወያኔዎች የመጀመሪያና የመጨረሻ መልእክት
ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
“መልእክት” ያልኩት አቀራረቤን ቀለል በማድረግ የአንባቢያንን ቀልብ ላለመግፈፍ ነው፡፡ እንጂ መነሻየ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነው፡፡ ማስጠንቀቂያም ይባል መልእክት ዋናው ጉዳይ በግሌ የተሰማኝንና የማምንበትን ለወገኖቼ ድኅነት ስልም የምጽፈው ነገር ለባለአድራሻዎቹ መድረሱ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉንም ድረገጾች ትብብር በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ እባካችሁን ለሁሉም ካድሬ መልእክቴን አድርሱልኝ፡፡
ሰው ክርስቶስን መሆን እንዳይችል ጠላት መንገድ እየዘጋበት መቸገሩ የሚታወቅ ነው፡፡ መሆን ቢፈልግ ግን ይችላል፤ የሚከለክለው አንዳችም ነገር የለም፡፡ ክርስቶስ ራሱም ያለው “እንደኔ ሁኑ፤ እኔን ምሰሉ” ነው፡፡ ችግሩ ክርስቶስን ለመሆን ወይም ቢያንስ ለመምሰል የእምነት ጽናትና እውነተኛ ፍቅርን የተላበሰ ስብዕና ማጣት ነው፡፡ ተራራን ሊያዞር የሚችል እምነት፣ የሚጠላንን ብቻም ሳይሆን የሚገድለንንም ጭምር የሚያፈቅርና ለጨካኞች የሚራራ ልብ፣ የማይወላውል እምነትንና የማያዳላ ፍቅርን የሚገልጥ በጎ ሥራ ካለ ከፈጣሪና ከአንድያ ልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ውህደት መፍጠርና ጓደኛ መሆን የማይቻልበት ምክንያት የለም፡፡ የሚጠይቀው እውነተኛ የልብ መሰበርን ብቻ ነው፡፡
ክርስቶሳዊ ተምሳሌትነትን በተወሰነ ደረጃ በመውሰድ አካሄድን ማረቅና ማስተካከል ይቻላል፡፡ ከወቅቱ አቢይ ሃይማኖታዊ ክንውን እንጀምር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከፆመ በኋላ በሰይጣን ሦስት ጥያቄዎች ቀርበውለት በአሸናፊነት ተወጥቷል፡፡ የመጀመሪያው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር፤ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እስኪ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ”፡፡ የክርስቶስም መልስ “ ‹ሰው የሚኖረው እግዚአብሔር በሚናገረው ቃል እንጂ በእንጀራ ብቻ አይደለም› ተብሎ ተጽፏል፡፡” አዎ፣ ለአስተዋይ ሰው በእንጀራ ብቻ መኖር እንደማይቻል ግልጽ ነው፡፡ እርግጥ ነው ሰይጣን በሚያስፈልገን ነገር ይመጣብናል፡፡ ሰይጣንና የስለላ ድርጅቶች ተመሳሳይነት አላቸው፤ በምትወደው ነገር ይመጡብህና ወጥመዳቸው ውስጥ ይከቱሃል(cf. blackmailing)፡፡ ክርስቶስንም በዚያ ቀዳዳ የመጣበት አርባ ቀንና አርባ ሌሊትን ካለምንም ምግብ በመክረሙ ተርቦ ነበርና ይሸነፍልኛል ብሎ ነው፡፡ እንዳሰበው ግን አልሆነለትም፡፡ ያ ምናልባት ሥነ መለኮታዊ ጣጣ ስላለው ለምድራዊ ሕይወት ጥሩ አብነት ላይሆን ይችላል፡፡ እናም የአርባ ቀኑን የክርስቶስ ፆም እንርሳውና አብዛኛው የአሁኑ ዘመን ሰው አንድ የምግብ ሰዓት አልፎበት አይደለም ትንሽ ሆዱ ጎደል ካለ እናቱን ከመሸጥ እንደማይመለስ እናስብ፡፡ አሰብን?…
ፈተናዎች በጥቅሉ የሥጋና የነፍስ ተብለው በሁለት ዐቢይ ክፍሎች ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ በአማርኛ ፈተናን የሚገልጡ ቃላት ውሱን ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ እንግሊዝኛው ሳይሻል አይቀርም፡፡ “test, quiz, exam, examination, temptation, assessment …” የሚባሉ ቃላት አሏቸው፡፡ እነዚህ ቃላት በዐውድ ውስጥ መገኘት ሳያስፈልጋቸው በቁማቸው የሚሰጡት የተወሰነ ምስል አለ፡፡ እኔ አሁን እዚህ ላይ ልጠቅሰው የምፈልገው የፈተና ዓይነት በእንግሊዝኛው አጠራር temptation የሚለውን ነው፡፡ የአባታችን ሆይ ጸሎት ውስጥ “ Our Father who art in heaven … lead us not into temptation but deliver us from evil.” እንደሚል፡፡
ከመጽሐፍ ቅዱስ ሳንወጣ የክርስቶስን ደቀ መዝሙርና የግምጃ ቤት ኃላፊ የአስቆሮቱ ይሁዳን እናስታውስ፡፡ ከገቢ ገንዘቦች አሥር መቶኛውን ለራሱ እንዲያደርግ ተፈቅዶለት የነበረው ይሁዳ በገንዘብ ፍቅር ክፉኛ የተለከፈ ነበር – ልክ እንደወያኔ፡፡ ይህ በሽታው ተባብሶበት በመጨረሻው ክርስቶስን ራሱን በሠላሣ አላድ ለጠላቶቹ አሳልፎ ሸጦታል፡፡ ገንዘቡን ግን አልተጠቀመበትም፡፡ ያልተጠቀመበትም ምክንያት ክፍያውን እንደተቀበለና ክርስቶስን ያሳድዱት በነበሩ አይሁዳውያን እንዳስያዘው የሰረፀበት ሰይጣን ለጸጸት አጋልጦት በመለየቱ ምክንያት ራሱን ሰቅሎ ስለሞተ ነው፡፡ የይሁዳ ነፍስ አልተማረችም፡፡ ይህን እውነት ከመጽሐፍ ቅዱስ እናገኘዋለን – ሊማር አለመቻሉንም ጭምር፡፡
ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ወደፈተና ይገባል፡፡ ለሆዱና ስለሆዱ በሆዱ የሚፈተን አለ፤ በሆድ መፈተን መጥፎ ፈተና ነው፡፡ ሀገርን የሚያሸጥ የሆድ ፍቅር የተጠናወተው ሰው ደግሞ በሕይወት ዘመኑ በሚኖረው የስብዕና መመሰቃቀል ብቻም ሣይሆን ልጆችን ወልዶ ቢያልፍ በሀፍረት አንገታቸውን ይደፋሉ፤ በሕዝብ ዘንድም መጠቋቆሚያ ይሆናሉ፡፡ታሪኩ የጠቆረና የትውልድ ማፈሪያ ይሆናል – አሁንም እንደወያኔ፡፡
አንድ ሰው ፈተናን ወደቀ የምንለው ነባር እምነቱንና ታማኝነቱን ለሆነ ጥቅም ሲል ክዶ ከትክክለኛው መንገድ ሲወጣ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ታሪክ ስንመለከት ሁለት በፈተና የወደቁ አካላትን እናገኛለን፡፡
ዋናው ተፈታኝና ፈተናውን ከመነሻው የወደቀው ከትግሬው ብሔር የወጣውና ሕወሃት በመባል የሚታወቀው ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሕዝብ ኃይል ነው፡፡ ለዚህ ድርጅት በፈተና መውደቅ መንስኤው ዓላማና ለጥቅም ነው፡፡ የሚታወቅን ነገር መዘርዘር አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡
ሁለተኞቹ ተፈታኞች ሁሉን ነገር እያወቁ ለፍርፋሪ እንጀራና ለማያዙበት የይስሙላ ሥልጣን ሲሉ በሕወሃት ሥር በባርነት አድረው የወጡበትን ሕዝብ ለወያኔ የሸጡ ይሁዳ አማሮች – ብአዴን ተብዬዎቹ – ናቸው፡፡ በሃይማኖታዊ አገላለጽ ሕወሃትን ልምጭ አስይዘውና በሁለንተናዊ ዘመናዊ መረጃ ደግፈው ጃዝ ብለው የላኩት የታላቁ ወንድም (The Big Brother) ባለሟሎችን የሉሲፈር ደቀ መዛሙርት ልንላቸው እንችላለን፡፡ ታሪካዊ ቂም በቀል አርግዘው ኢትዮጵያን ለማጥፋትና በእግረ መንገድም ቤት ያፈራውን ሥልጣንና ሀብት በግል ለመቆጣጠር የተነሡ የትግሬ ወያኔዎችን በሉሲፈር አጣማጅ በሰይጣን በራሱ ልንመስላቸው እንችላለን፡፡ ለሆዳቸው ያደሩ በተለይም የዕልቂት ዐዋጅ ከታወጀበት የአማራው ሕዝብ እንደተገኙ የሚነገርላቸው ከሃዲዎችን ደግሞ በሰይጣን አገልጋይነት ልንፈርጃቸው እንችላለን፡፡ የሆነው ሆኖ ትግሬም ይሁን አማራ ወይም ሌላ ከእውነተኛው የጤናማ ኅሊና መንገድ ወጥተው ኢትዮጵያን ለማውደም እስከተሰለፉ ድረስ ሁሉም የጥፋት ወኪሎችና የክፉ መንፈስ ምርኮኞች ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ያለው አጥፊ ኃይል ደግሞ የዓለም አቀፉ የጥፋት ኃይል ቅርንጫፍ ነው፡፡ ይህ በከፍተኛ ጥንቃቄና የሸር ጥልፍልፍ ወይም ሤራ (Conspiracy) የሚካሄድ የዓለምን ፖለቲካና ኢኮኖሚ የመቆጣጠር ዕቅድ ጅማሮው ቀደም ቢልም በሁሉም አቅጣጫ በተቀነባበረ ዘመቻ ወደስኬት ጫፍ የደረሱ የመሰሉት ግና አሁን በምንገኝበት የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው – የመሠረት ግንባታው ደርዝ መያዝ የጀመረው ግን የዛሬ 300 ዓመታት አካባቢ በ18ኛው መ/ክ/ዘመን መግቢያ አካባቢ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የሚያሠማሯቸው ጉዳይ አስፈጻሚ ተላላኪዎች ዘርና ቀለም፣ ፆታና ሃይማኖት ሳይገድባቸው እንደ እስስት ከየሚሄዱበት አካባቢ ሕዝብ ጋር እየተመሳሰሉ ሀገርንና ሕዝብን በቅርበት ይቆጣጠራሉ – ሲያሻቸው መጽሐፍ ቅዱስ ሲያሻቸው ደግሞ ሽጉጥ በመያዝ በመስቀል ከቀላጤ ‘politico-psuedo-religious’ ዘመቻ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስና የባሕርይ አባታቸውን ሊቀ ትጉሃን ዲያብሎስን ለማስደሰት ይጥራሉ፡፡ በመንግሥታት ጀርባ ሥውር መንግሥታትን በማቋቋም ሁሉንም ነገር በዐይነ ቁራኛ ይከታተላሉ – ሊያውም በ“ሁሉን ተመልካች” አንዲት ዐይናቸው! በዓለም አቀፍ ግዙፍ ካምፓኒዎቻቸው አማካይነትም የዓለምን ሀብትና ንብረት ይዘርፋሉ፤ ነዳጅና የተፈጥሮ ማዕድናትን እያሰሱ ለማይጠረቁት ሥውር ቱጃሮቻቸውና የምሥጢራውያን ድርጅቶቻቸው አለቆች ያስረክባሉ – ሁሉ በጃቸው ሁሉ በደጃቸው፤ ጦሩም ስለላውም አስተዳደሩም ምኑም ምናምኑም በነሱው ቁጥጥር ስለሚገኝ የ‹ሪሶርስ›ና የሰው ኃይል ችግር የለባቸውም፡፡ ጦርነቶችን ይፈጥራሉ፤ ሲፈልጉ ያጣላሉ – ሳይፈልጉ ያስታርቃሉ፡፡ መሣሪያዎቻቸውን ለተዋጊ ወገኖች በግልጥና በድብቅ ይሸጣሉ፡፡ ትውልድን ከሃይማኖትና ከባህል አውጥተው መና ለማስቀረት፣ ከሞራልና ሥነ ምግባር ማዕቀፎች ለይተው ባዶ ለማስቀረት እነሆሊውድን ከመሳሰሉ ተቋሞቻቸው ባፎሜታዊ ፊልሞችንና ሙዚቃዎችን በዓለም ይበትናሉ፡፡ ሀሺሺንና መጠጦችን በማምረት በሥውር ያሰራጫሉ፡፡ የሚገርመው እነዚህ ኃይሎች ፀረ-ሀሽሽ መስለው ቢቀርቡም ውሸታቸውን ነው፤ ከአፍጋስታን እስከ ኮሎምቢያና ሜክሲኮ የዐደንዛዥ ዕፅ ምርትና ገበያን የተቆጣጠሩት እነሱው መሆናቸውን የሚገልጡ መረጃዎች የአደባባይ ምሥጢር ከሆኑ ሰንብተዋል፡፡ ወያኔም እንደዚሁ ወጣቱን በጫትና በመጠጥ እያደነዘዘ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዳይኖር መጣሩን አንርሳ፡፡ በብዙ ነገር መመሳሰላቸውን ልብ እንበል፡፡ ወያኔን የሚገዛ ህግ እንደሌለ ሁሉ እነሱንም የሚገዛ ህግ የለም፡፡ የነሱን ደንቆሮ በሀሰት የዶክትሬት ዲግሪ የምስክር ወረቀት ለዓለም አቀፍ ተልእኮ ቢያሰማሩት ታማኝነቱ እንጂ ትምህርቱ ብዙም ፋይዳ ስለሌለው በአጭበርባሪነት የሚጠይቀው የለም – በወያኔ ቤትም ለባለሥልጣን ያልተበተነ የዲግሪ ዓይነት የለም – ባዶ ጭንቅላት ላይ ጥቁር ቆብና ጥቁር ካባ፡፡ ከነሱ ቁጥጥር የሚወጣን ሀገር መሪ(ዎች) በስለላ ድርጅቶቻቸው ልዩ ኮማንዶና በጨረር አነጣጥሮ ተኳሽ የፓራትሩፐር እስኳድ ያስወግዳሉ – ለሀገሩ የሚቆምን ሀገር ወዳድ ግለሰብም በዚህ መልክ ደመ ከልብ ሆኖ እንዲቀር ያደርጋሉ (ነፍስ ይማር – ኢቅእ(?))፡፡ (ቅን ታዛዦቻቸው ሊያፈነግጡ ወይም ጌታ ሊለውጡ ካሰቡም ይሄው የቅጣት በትር አይቀርላቸውም (ነፍስ ይማር – መዜአ (?))፡፡ … በሚያስወግዷቸው ምትክም የነሱን ፍላጎትና ጥቅም የሚያስከብር መለስ ዜናዊን የመሰለ ፀረ-ሕዝብና ፀረ-ሀገር ወሮበላ በዴሞክራሲ ጭምብላቸው ለላንቲካው ይጎልቱታል – ዋናውን መዘውር በእጅ አዙር የሚይዙት ግን እነሱው ናቸው፡፡ በዓለም ባንክና በአይ ኤም ኤፍ፣ በኔቶና በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አማካይነትም በማይወዱት ሀገር ላይ የኢኮኖሚና ወታደራዊ ማዕቀብ ይጥላሉ፤ እንዳስፈላጊነቱም ጦርነት ያውጃሉ፡፡ ከነሱ ዕይታና ቁጥጥር ውጪ የሚሆን አንዳችም ነገር የለም፡፡ ነፍስና ሥጋህን ብቻ ሳይሆን የምታስበውንም ሁሉ ጭምር በ“Mind Control system” ሊቆጣጠሩ ይሞክራሉ፡፡ ከፈለጉም በሰው ሠራሽ የመሬት መናወጥና ሱናሚ አንድን ሀገር ሊያደባዩ፣ አለዚያም በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መራጃ ዝናብን ከልክለው በድርቅ ሊመቱ፣ በሌላም በኩል ከመጠን በላይ ዝናብን አዝንበው በጎርፍና በመሬት መንሸራተት ናዳ ሕዝብንና መንግሥታትን ሊያስለቅሱ ይችላሉ፡፡ በአጭሩ የማያደርጉት ነገር የለም፡፡ ደግሞም እውነት ነው፡፡ ወያኔዎችስ? ሥልቱና አፈጻጸሙ ይለያይ እንጂ አንድና አንድ ናቸው፡፡
የወያኔዎች የአንድ ለአምስት የጥርነፋ ሥልት የዚሁ የዓለም አቀፍ ዘመቻ አካል ነው፡፡ በአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ዕዳ ውስጥ የሚዶሉህም በዐይናቸው ሥር አውለው ሊቆጣጠሩህ ነው፡፡ በብድር የተያዘ ሰው ደግሞ ታውቃለህ – ውልፊት ሊል አይችልም፡፡ ሌላ ነገር አምሮህ ብታንጋጥጥ- ማንጋጠጥም አይደለም ለማሰብም ብታስብ ራሱ ያስወነጅልሃል፡፡ ያኔ በአሸባሪነት ባትጠየቅ እንኳን በገንዘብ ዕዳ ያለህን ንብረት ያሸጡሃል ወይም የፍትሃ ብሄር ወንጀልህ ተቀባብቶ ወደ ተሟላ ደረቅ ወንጀል ይዞርብህና ቃሊቲ ልትወርድ ትችላለህ፤ ለማንኛውም እሥር ቤት ውስጥ ነህ – የእሥር ቤቱ ስፋትና ጥበት ላይ የጋራ መግባባት ላይ እስከደረስን ድረስ፡፡ በቤትህ ውስጥ ሳይቀር ከአንተ ዕውቀት ውጪ ተከታታይ ሊመደብብህና መላ እስትንፋስህ ወደ ማዕከላዊ መረጃና ደህንነት መሥሪያ ቤት ሊያመራ ይችላል፤ ስልክህ ሊጠለፍ፣ ኢሜልህ ሊጠለፍ፣ ፌስቡክህ ሊጠለፍ፣ ሚስትህ ልትጠለፍ፣ ልጆችህና ጓደኞችህ ጭምር ሊጠለፉ፣ አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ሁሉ አንተ ራስህም ልትጠለፍና የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ብዙ ሰይጣናዊ ነገሮች ሊደርሱብህ ይችላሉ፡፡ የእነአልማዝ ሠይፉን፣ የእነብርቱካን ሚዴቅሳን፣ የእነደበበ እሸቱን፣ የነስዬ አብርሃን ዝምታ ያዬ አንዳች ነገር ቢጠረጥር ሊፈረድበት አይገባም፡፡ በስማም የተባለበት ሰይጣን ይመስል በአርምሞ የተቀመጡበትን ምክንያት ከነሱ በስተቀር ማንም አያውቅም፡፡ አሣሪህና የስቃይህ ምንጭ ሲደርቅ ጮቤ መርገጡ ዲያብሎሳዊ መሆኑ እርግጥ ቢሆንም ለሰባት ቀን ሀዘን መቀመጡና በፈጣሪ ሥራ ገብቶ በ“ለምን ወሰድክብኝ” እዬዬ ማለቱ ሃይማኖታዊ መደላድል ያለው አይመስለኝም – የቃል መቀነት መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ የተገኘውም ይህን ዕንቆቅልሽ በአመስጥሮ ለመጠቆም ነው (አመስጥሮው እዚህ ላይ አበቃ እንጂ)፡፡ ለማንኛውም በዲያብሎስ ግዛት መብቴ ተረገጠ ሰው መሆኔ ተዘነጋ ብሎ መጠየቅ ሞኝነት ነው፡፡ ከሁሉ በባሰ ሁኔታ የጎንህ ፍላጭ ሚስትህ ወይም የአብራክህ ክፋይ ልጅህ ሊሰልሉህ ቢችሉ የዘመኑ የትልቁ ወንድምህ ፋሽን ነውና አይግረምህ፡፡ ወያኔ የትልቁ ዓለም አቀፍ ዘመቻ የምሥራቅ አፍሪካ ዋና መሥሪያ ቤት (Head Quarter) ነው ቢባል ያስኬዳል፡፡ ከጆርጅ ኦርዌል ድንቅ መጽሐፍ (ከ “1984” ውስጥ) እስኪ ቀጣዩን ጥቅስ እንመልከት፡፡
He [Winston Smith] took a twenty-five cent piece out of his pocket. There, too, in tiny clear lettering, the same slogans were inscribed, and on the other face of the coin the head of Big Brother. Even from the coin the eyes pursued you. On coins, on stamps, on the covers of books, on banners, on posters, and on the wrappings of a cigarette packet—everywhere. Always the eyes watching you and the voice enveloping you. Asleep or awake, working or eating, indoors or out of doors, in the bath or in bed—no escape. Nothing was your own except the few cubic centimetres inside your skull.
ተዛማጅ ትርጉም፡- (ዊንስተን ስሚዝ) ሃያ አምስት ሳንቲም ከኪሱ አወጣ፡፡ በዚያች ሣንቲም ላይም በአንደኛው ገጽ በጥቃቅን ፊደላት የተለመደው መፈክር ተጽፏል፤ በሌላኛው ገጽ ላይ ደግሞ የታላቁ ወንድም የራስ ምስል ጉብ ብሏል፡፡ [(መፈክሩ - ‹ ጦርነት ሰላም ነው፤ ነጻነት ባርነት ነው፤ ድንቁርና ጥንካሬ ነው፡፡› የሚል ነው1፡፡)] ከዚህች ትንሽዬ ሣንቲም የምታየው የታላቁ ወንድም ዐይኖች ትክ ብለው ሲያዩህ መግቢያ ያሳጡሃል፡፡ በሣንቲሞች፣ በቴምብሮች፣ በመጽሐፍ ሽፋኖች፣ በዓርማዎች፣ በፖስተሮች፣ በሲጋራ ወረቀቶች፣ የትም ይሁን የትም እነዚህ የታላቁ ወንድም ዐይኖች ያፈጡብሃል፡፡ ምን ጊዜም ዐይኖቹ መግቢያ መውጫህን ይከታተላሉ፤ ድምፆቹም የጆሮ ታምቡርህን ያለ ዕረፍት ይጠልዛሉ፡፡ ተኝተህም ሆነ ሳትተኛ፣ ሥራ ላይም ሆንክ ምግብ ላይ፣ ከቤት ውስጥም ሆንክ ከቤት ውጪ፣ መታጠቢያ ቤትም ውስጥ ሁን በአልጋህ ላይ … የትም ሁን የት ከታላቁ ወንድም ዐይኖችና የዘወትር ክትትል ማምለጫ የለህም፡፡ ጭንቅላትህ ውስጥ ከሚገኘው ነጭ አንጎል ውጪ የኔ ነው የምትለው የግል ንብረት እንዲኖርህ አይፈቀድልህም፡፡ [እርሱንም ቢሆን አንተ አታዝበትም!]
በዲያብሎስ መንፈስ የሚነዳውን የአፍራሽ ኃይል (The Negative Energy) ዓለማቀፋዊ የጥፋት አድማስ በአጭሩ ለማሳየት የሞከርኩት የሀገራችን ጉዳይም ከዚሁ ኃይል ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ከዘመን ፍርድ ማምለጥ አስቸጋሪ ነውና፡፡ ዓለማችን የሁለት ተፃራሪ ኃይላት መስተጋብራዊ ውጤት ናት፤ እነሱም ገምቢ ወይም አወንታዊ ኃይልና አፍራሽ ወይም አጥፊ ኃይል ናቸው፡፡ ማንም ሰው ከነዚህ ሁለት እርስ በርስ ተጠፋፊ ነባራዊ ሁኔታዎች ውጪ አይደለም፡፡ በምንገኝበት መሬታዊ/ምድራዊ ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት አንዱ ካለ ሌላው አይኖሩም፡፡ ገምቢ ካለ አፍራሽ አለ፡፡ በዬቋንቋዎቻችንም ደግ – ክፉ፣ ፍቅር – ጥላቻ፣ ቸር – ንፉግ፣ ሃቀኛ – ዋሾ፣ ወዘተ. የመኖራቸው እውነታ ይህንን ለማጠየቅ ይመስላል፡፡ ችግሩ ምጣኔያቸው ላይ የሚታየው የሚዛን መዛነፍ ነው፡፡ አንዱ ከሌላው ግዘፍ ነስቶ ከታዬ ለምሳሌ የክፋት መንፈስ ከተንሠራፋ ሀገርና ሕዝብ ይጎዳሉ፤ እንደሀገረ ኢትዮጵያ ለአጠቃላይ ውድመት ሊዳረጉም ይችላሉ፡፡ ይህ ዓይነት አስቀያሚ ሁኔታ የሚፈጠረው ኅሊናን በመሸጥ ለሆድና ለጥቅም ማደር ሲከሰት ነው፡፡ ሰዎች ኑሯቸውን ያሸነፉና ያለፈላቸው እየመሰላቸው ብዙ ጣጣ ውስጥ ይገባሉ፤ በዚያም ሳቢያ ከፍለው የማይጨርሱት ዕዳ ውስጥ ይነከራሉ፡፡ የብአዴኖች ወንድምና እህቶቻችን ዕኩይ ተግባርም ከዚህ የሚመደብ ነው – በደቂቃዎች ውስጥ ዕዳሪና ሽንት ለሚሆን የሆድ ቀለብ (እህልና ውኃ) ሀገርንና ሕዝብን የመሰሉ ዘላለማውያን ኅላዌያት ሲክዱ ማየት የታሪክ አሰቃቂ ፍርድና ምፀት ነው፡፡
ሕወሃት ኢትዮጵያን እያጠፋ ያለው ለዓላማና ለጥቅም ነው፡፡ የሕወሃት ተባባሪዎች የሆኑት ብአዴንና ሌሎቹ ኢትዮጵያን በማጥፋት ላይ ከሚገኘው ሕወሃት ጋር እየተባበሩ ያሉት ወገኖች ግን ለዓላማ ሣይሆን አንድም በድንቁርና ነው፤ አንድም በሆዳምነት ነው፡፡ አማራ አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ዓላማ ነድፎ ከፀረ-አማራ ኃይሎች ጋር በማበር ሊንቀሳቀስ ይችላል ተብሎ መቼም አይጠበቅም፤ በውነቱ የብአዴኖችን ነገር ስናጤነው የእርግማን ካልሆነ የሌላ አይመስልም፤ ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ አማራ ካልታመመ በስተቀር ዘመዶቹን ለመፍጀት በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ ሳይቀር በመታገያ ዓላማና ግብነት ቀርፆ የሚንቀሳቀስን ሰይጣናዊ ኃይል ሊተባበር አይችልምና ነው፤ በምንም ዓይነት መንገድ፡፡ ተጠየቃዊ አካሄዱም ይህን ታሪካዊ ህፀፅ ሊዳኝበት የሚያስቸለው ክፍተት የለውም – “ዕብደት ነው!” ብሎ የሚያልፈው ካልሆነ በስተቀር፡፡ በመሆኑም ብአዴን ውስጥ የሚገኙ አማሮች በየትኛውም ሚዛን ቢለኩ አንድም የለየላቸው ዕብዶች ወይም የለየላቸው ደናቁርት ማይማን ወይም ደግሞ ፀላኤ ሠናያት የሠፈረባቸው የክፉ መናፍስት ዋሻዎች ቢሆኑ እንጂ ለአማራ የሚቆረቆሩ አማሮች ሊሆኑ አይችሉም – ቃል ቢቸግረኝ እንጂ “ማይም” ማለቴ ራሱ ስህተት ነው፡፡ ማይምነት ከሀገር መሸጥና መለወጥ አይገናኝምና፡፡ ብአዴኖች አማራ አይደሉም ሲባል ደግሞ የደምና የአጥንት ጉዳይ ሳይሆን በፍካሬያዊ ትርጉሙ ነው፡፡ አማራን ከሚያጠፋ፣ ኢትዮጵያን ለመቅበር ጉድጓድ ከማሰ፣ ሀገርን ከሸጠና ከለወጠ ኃይል ጋር ያለ ሀፍረት አብሮ እየሠራ የሚገኝ “ሰው” አማራ ነኝ ቢል እንዴት ማመን እንደሚቻል ብአዴኖችን ራሳቸውን መጠየቅ ነው፡፡ በጣሊያን ጊዜ ከቅኝ ገዢው ባዕድ ወገን ጋር በባንዳነት ያገለግሉ የነበሩ ብዙዎቹ የዛሬዎቹ ገዢዎቻችን ወላጆች በንጽጽር ከብአዴኖች ይሻላሉ፡፡ ምክንያቱም የዚያኔዎቹ ባንዳዎች የካዱት መላዋን ኢትዮጵያን እንጂ የወጡበትን ጎሣና ነገድ አልነበረምና፤ በዚያ ላይ ጣሊያንም ቢሆን የወያኔን ያህል ቀርቶ ካልነኩት የማይነካና በጭካኔው ከወያኔ ፍጹም የማይወዳደር በአንጻራዊ አነጋገር እጅግ ሲበዛ ሰብኣዊ የነበረ ኃይል ነው፡፡ የኒህኞቹ ድርጊት ግን ዘግናኝ ወንጀል ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ወንድምህን፤እህትህን፤ አባትና እናትህን፣ በጥቅሉ በዘመኑ ቋንቋ ዘርህንና ቤተሰብህን እንደዐይጥ ከሚጨፈጭፍ የባንዳ ውላጅ ጋር መተባበር፣ ከዚያም ባለፈ ሰሞኑን እንደምንሰማው የጠላትን አንደበት በመዋስ በእንደራሴነትም ቢሆን የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ በአደባባይ መዝለፍ በምንም ዓይነት መለኪያ ጤናማነትን አያሳይም፡፡ (Shall we say proxy badmouthing or insulting?) ይህ ዓይነቱ የብአዴን ድፍረት የኅሊና መታወርንና የአንጎል ጤንነት መቃወስን በግልጥ የሚያመለክት ነው፡፡ የአእምሮ ህክምናም ሳያስፈልገው አይቀርም፡፡…
አሁን ምን ማድረግ ይቻላል? በዚህ መቀጠሉ ያዋጣል ወይ? እስከመቼስ በባለ አንድ ጥርስ ማርሽ ብቻ ማሽከርከር ይቻላል?
ሰዎች ከፈለጉ ለማንኛውም ችግራቸው መፍትሔ መፈለግና ማግኘትም ይችላሉ፡፡ ዋናው ነገር ችግር ውስጥ መገኘትን ማወቅ ነው፡፡ ይህ በራሱ የመፍትሔውን ግማሽ መንገድ እንደመጓዝ ይቆጠራል፡፡ ከዚያም ንስሃ መግባት ነው፡፡ ንስሃ መግባት ሲባል በዚህ ዐውድ መሠረት በሆነ ታሪካዊ አጋጣሚ በተፈጠረ ስህተት ገብተው የሚዋኙበትን የጥፋት ባህር ተረድቶ ከዚያ ለመውጣት ከልብ መጸጸት ማለት ነው፡፡ ጥፋት ሰብኣዊ ነው፡፡ ማንም ሰው ትንሽም ይሁን ትልቅ ስህተት ይሠራል፡፡ ከስህተት ጎዳና ለመውጣትና ተበዳይን ከልብ ይቅርታ ጠይቆ ለመካስ የሚተጋን ሰው ደግሞ ፈጣሪ ይወደዋል፡፡ ሰው ሲባል ከሌሎች እንስሳት የሚለየውና ክፉንና ደግን መለየት የሚያስችለው አንጎል ያለው በመሆኑ ከስህተቱ እየተማረ፣ ደካማ ጎኑን እያስወገደና ጠንካራ ጎኑን ይበልጥ እያሻሻለ ወደበለጠ አእምሯዊና አካላዊ ዕድገት መራመድ ይጠበቅበታል፡፡ ጥፋቱን እንደልማት ቆጥሮ በኩራት የሚጀነን ሰው ከወያኔ የሚመደብ የመከነ አእምሮ ባለቤት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደምናነበው ብዙዎች ቅዱሳንና ሰማዕታት ስህተትን ይሠሩ ነበር፡፡ ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ እነቅዱስ ዳዊት፣ እነሶሎሞን፣ እነጴጥሮስ … ሁሉም ይሳሳቱ ነበር፡፡ ግና በጸጸት ዕንባቸው ስህተታቸውን እያጠቡ ከእግዚአብሔር ምሕረትን እንዳገኙ ቅዱሣት መጻሕፍቱ ያስረዳሉ፡፡ ክርስቶስንና ክርስቶሳውያንን በጦር ያሳድድ የነበረው ኃጢኣተኛው ሳዖል፣ በኋላ ላይ በደገኛው የኢየሱስ መንፈስ ተመርቶ አንገቱን ለሠይፍ እስኪሰጥ ድረስ የክርስቶስ አገልጋይ ሊሆንና በቅዱስ ጳውሎስነቱ ሊታወቅ በቅቷል፡፡ አንድ ነገር እንድገም፡- አንዱ “ወንድሜ ሰባት ጊዜ ስህተትን ቢሠራብኝ ሰባት ጊዜ ሁሉ ይቅር ልለው ይገባኛልን?” ሲል ክርስቶስን ይጠይቀዋል፤ በርሱ ቤት ሰባት ብዙ ቁጥር መሆኑ ነው፡፡ ክርስቶስ ግን በሚገርም ሁኔታ “ሰባት ጊዜ ብቻ አይደለም፤ ሰባት ጊዜ ሰባም ቢሆን ይቅር በለው” ሲል ነው የመለሰለት፡፡ አራት መቶ ዘጠና ጊዜ ቆጥረህ ይቅር በል ለማለት አይደለም – ይቅር ባይነት ገደብ እንደሌለው ነው የዚያ አስተምህሮ ማዕከላዊ አንድምታ፡፡ ይህ ምሳሌ ሁለት መልእክት አለው፡፡ አንዱ ለበዳዮች – ሌላኛው ለተበዳዮች፡፡ በበዳይ ወገን በኩል ያየነው እንደሆነ “ብዙ በድያለሁና ይቅር ስለማልባል በጥፋት ጎዳና እንደተጓዝኩ ዕድሜየኝ ልፍጅ” ከማለት ያድናል፡፡ በተበዳይ ወገን በኩል ሆነን ያየነው እንደሆነ “ዕድሜ ልኩን ሲጫወትብኝ ኖሮ አሁን እንዲህ እንዲህ ያለ ነገር እንዳይደርስበት ስለፈራ ልታረቅህ ይለኛል፤ ደግሞስ ለስንት ጊዜ ያህል ከበደለኝ በኋላ ለምን ብዬ ነው ይቅርታውን የምቀበለው?” ከሚል ሰይጣናዊ ግብዝነት ይታደጋል፡፡ እናስ ምን እናድርግ?
ንስሃ ለመግባት ቅድመ ሁኔታ የለውም፡፡ አንድ ሰው ንስሃ መግባት የሚያስፈልገው ጥፋት በማጥፋቱ ነው እንጂ ባያጠፋማ ለምን? ለይቅርታ ደግሞ የጥፋት ደረጃ ማነስ ወይ መብዛት ለድርድር አይቀርብም፡፡ ዋናው ከልብ መጸጸትና ጥፋትን እርግፍ አድርጎ መተው ነው፡፡
በኢሳት እንደምንከታተለው ከብአዴኖች ምሥጢር እየሾለከ ወደተቃውሞው ጎራ እንደሚገባ ተነግሯል – ከኢሳት አንጻር የመረጃ ምንጭን የማጋለጥ ምሥጢሩ እስካሁን ባይገባኝም (ይህ ዓይነቱ ልበ ሙሉነት የመረጃ ምንጭን በማድረቅ ረገድ አሉታዊ ሚና እንደማይጫወት ባውቅ ደስ ባለኝ)፡፡ ለማንኛውም ይህ መልካም ጅምር ነው፡፡ በራሱ ግን በቂ አይደለም፡፡ በጣም ኢምንት ነው፡፡ ሙሤን ማስታወስ ይገባል፡፡ ሙሤ በፈርዖን መንግሥት ውስጥ ሆኖ ወገኖቹን ከሚጨፈጭፍ ኃይል ጋር – ሳያውቅ ነው – ይሠራ ነበር፡፡ ማንነቱን ከተረዳ በኋላ ግን 40 ሺህ እስራኤላውያንን ይዞ ከምድረ ግብጽ በመውጣት ሕዝቡን ከአስከፊ አገዛዝ ነጻ አውጥቷል፡፡ ብአዴኖችም ይህን ለማድረግ መረጃ ከመስጠት ባለፈ ብዙ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በሰፊው የአማራ መሬት የአፓርታይድንና የፋሺዝምን ሥርዓት ሕዝባቸው ላይ መጫናቸውን ትተው ከነፃነት ታጋዮች ጋር በኅቡዕ ኅብረት መፍጠርና የነፃነትን ጊዜ ማፋጠን አለባቸው፡፡ እስካሁን የሠሩት ጥፋት ፊታቸው ላይ እየተደቀነ ሊረብሻቸው አይገባም፡፡ ያን በንስሃ ማጠብ የሚቻለው የሠሩትን ስህተት የሚክስ መልካም ሥራ ሢሰሩ ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰው ንስሃ ሲገባ ያጠፋ የነበረውን ጥፋት ዳግመኛ ላለመሥራት ቃል የሚገባበትና የዚያን ተቃራኒ ደግ ሥራ ለመሥራት በዚያውም በደሉን ለማካካስ (atonement) ሌት ተቀን የሚተጋበት ዕድል ያገኛል፡፡ ንስሃ መግባት ሲጀመር ከሙስናና ከደም ማፍሰስ፣ ንጹሓንን በፖለቲካ ሰበብ ከማሰርና ከማንገላታት መቆጠብ ይገባል፡፡ በተመሳሳይ ቅኝት የሚጓዝ ሕይወት መጨረሻው አያምርም፡፡ ብአዴንም ሆነ ሌላው የወያኔ ተባባሪ እሚበላው ያው አንዲት እንጀራ ናት – ከዚያች አታልፍም፡፡ በተረፈ በቅንጦቱ ረገድ ቢጠጣ ዊስኪና ቢራ ነው፡፡ ቢተኛ ሞዝቮልድ አልጋ ላይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ይሰለቻል፤ በወንጀልና በኃጢኣት ወገንን ሸጦ በሚገኝ የደም ገንዘብ ተንፈላስሶ መኖር የሚቻለው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ሰው የሆነ ሰው በደም ደለል ውስጥ መንቦራጨቁ እየተከሰተለት ሲመጣ በሂደት አእምሮውን የሚያስጨንቅ ነገር ይገጥመዋል፡፡ ጭንቀትን ለመሸፈን ከጧት እስከማታ በመጠጥ ብርጭቆ ውስጥ ቢወተፉ ኅሊና ቀስ እያለ መንቃቱ አይቀርምና በሁለትዮሽ የዞረ ድምር – በመጥፎ ሥራና በመጠጥ – መሰቃየት ይከተላል፡፡ ያኔ የሚከሰተውን የኅሊና ጅራፍ ደግሞ የሚቋቋመው የለም፡፡ ስለዚህ ብአዴኖች ከገባችሁበት አረንቋ በአፋጣኝ እንድትወጡ ብታውቁትም ባታውቁትም በኅያው እግዚአብሔር ስም እማጸናችኋለሁ፡፡ ይህን የምላችሁ ለሕዝብ በማዘን ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ የምትሠሩት መጥፎ ሥራ ከሚያመጣባችሁ የዕልቂት ማዕበል እንድትተርፉ በቅንነት ለእናንተም በማሰብ ጭምር ነው፡፡ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ነፍሱን ግን ማትረፍ ካልተቻለው ምን ይጠቅመዋል? ይላል መጽሐፉ፡፡ የምሕረት በር ሳትዘጋ አሁኑኑ በንስሃ ታጠቡ፡፡ ሕዝባችሁ አምርሮ ጸልዮኣል፤ ጸሎቱም ተሰምቷል፡፡ እግዚአብሔር ይመስገንና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ክብርንና ሞጎስን አግኝቶ መልስ የሚሰጥበት ጊዜ ተቃርቧል፡፡ ምልክቶቹም ሁሉ እየታዩ ነው፡፡ አንዱን ልንገራችሁ – ያ ወጣት ብላቴና ረዳት አብራሪ – ምንም ነገር ሳይቸግረው – ከነአውሮፕላኑ ለምን ያን የመሰለ ታሪክ የሠራ ይመስላችኋል? አስቡት፤ አስቡበትም፡፡ በዚህ መልክ ጥሪው የሚተላለፍላቸውና የነፃነት ፍልሚያውን የሚቀላቀሉ ወጣቶች በሠልፍ እየተጠባበቁ ናቸው፡፡
አፄ ቴዎድሮስ በጣም ጨካኝ እንደነበሩ ይነገራል፤ ምናልባትም በሁኔታዎች አስገዳጅነት ወደዚያ ደረጃ ተገፍተውም ሊሆን ይችላል፡፡ እርሳቸውም ያን ጠባያቸውን እንደሚያውቁና ሕዝብን ለመቅጣት ከፈጣሪ እንደተላኩ ለሚቀርቧቸው ይናገሩ እንደነበር ተጽፏል፡፡ አንድ ወቅት መነኮሳትን ከያሉበት ይጠሩና በየተራ እያስገቡ “ለመሆኑ እግዚአብሔር አሁን ምን እየሠራ ነው?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ሁሉም የመሰለውን ይመልሳል፡፡ እርሳቸውን ያስደሰተች መልስ ግን አንድ ኮሣሣና ለነፍሳቸው ያልሳሱ (ሞትን የናቁ ማለቴ ነው) መነኩሴ “እግዚአብሔር በአሁኑ ሰዓት ቁናውን እየሰፋ ነው!” ሲሉ የተናገሩት ነው፡፡ አዎ፣ እሳቸውም አመኑበት፡፡ የሠሩትን ጥፋት ስለሚያውቁ፣ በሠፈሩት ቁና መሠፈርም ደንብ መሆኑን ስለሚረዱ አንገታቸውን ነቅንቀው በአግራሞት ነበር ያን መልስ የተቀበሉትና ባህታዊውን አመስግነው ወደመጡበት በክብር የሸኙት፡፡ ሌሎችን በትዝብት ዐይናቸው መግረፋቸውን ማስታወስ ካስፈለገ ግን ይሄውና አስታወስኩ፡፡
ወያኔንና ግብረ አበሮቹን ለመቅጣት እግዚአብሔር ቁናውን ሠፍቶ ጨርሷል፡፡ ወያኔን ያሣወረው ትዕቢት መቃብር ካልከተተው የማይለቀው ሆኖ እንጂ የወያኔ ጉድጓድ ከተማሰ፣ ልጡም ከተራሰና የመግነዝ በፍታውም ከተዘጋጀ ቆይቷል፡፡ የሚቀረው ሥርዓተ ግንዘቱና ጉዞ ፍትሃቱ ብቻ ነው፡፡ ያም በቅርቡ ይከናወናል፡፡ ለመሆኑ አሁን ሀገሪቷን ማን እያስተዳደራት እንደሆነ በግልፅ የሚያውቅ አለ? እኔ ከፈጣ ውጪ በሰው ደረጃ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድር ሰው አላውቅም፡፡ እርግጥ ነው የሆነ የወያኔ ቡድን መኖሩን አልክድም፤ ዋናው ግን በኪነ ጥበቡ እንደምንለው በዚያ ልዩ መለኮታዊ ኪነ ጥበብ ነው ውለን የምንገባው፡፡ ለማንኛውም መላው የኢትዮጵያ ጠላቶች ሂሳባቸውን የሚያወራርዱበትና በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ወያኔ የናኘው ማንኛቸውም የዘረኝነትና የጎሰኝነት አቧራ እንደጉም በንኖ የሚጠፋበት የነፃነት ዘመን ደጅ ላይ ቆሟል፡፡ ይህን ነፃነት ማንም ፈቅዶ አይሰጠንም፤ ማንምም ታግሎ አይነጥቀንም፡፡ የዕንባችን፣ የጸሎታችንና የመገፋታችን ውጤት፣ በወያኔዎች ደባ ለዓመታት የፈሰሰው ደማችን የሚያመጣልን መለኮታዊ ፀጋ እንጂ የሰው ስጦታ አይደለም፡፡ በየከተማው እንደሚያፋድሱት እነአባ መሸ በከንቱን የመሰሉ ሳይሆን በሩቅ ገዳማትና በሥውር ሥፍራዎች ቀን ከሌት ወደፈጣሪ የሚያለቅሱ አባቶችና እናቶች አሉን፡፡ ቢያንስ እነሱን አያሣፍራቸውምና መልሱን በቅርብ እንጠብቃለን፡፡ ኢትዮጵያችን ጥቂቶች በቁንጣን የሚሰቃዩባትና ሚሊዮኖች በጠኔ የሚረፈረፉባት ሀገር ሆና እንደማትቀር ቃል ኪዳን አለ፤ ሀገራችን የቃል ኪዳን ምድር ናት፡፡ እናም አይዞን!!!
ብአዴኖች ግን ወደ ኅሊናችሁ ተመለሱ፡፡ ይህ ጥሪየ ዘርን መሠረት ባያደርግብኝ ደስ ባለኝ፡፡ ነገር ግን ይበልጥ የሚያሣዝኑኝ እነሱ በመሆናቸው ነው ይህን የተለዬ ጥሪ እነሱ ላይ በማተኮር ማስተላለፍ የወደድኩት፡፡ ፈጣሪ መንሹን ሊጨብጥ – ገለባን ከምርቱ ሊለይ የማበራያ ዐውድማውን ለቅልቆ ጨርሷል፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፤ ከያዘው አሼሼ ገዳሜና አሥረሽ ምቺውም ይመለስ፡፡ የዚህ ዳንኪራና ጮቤ ወጪ የሚሸፈነው ከምሥኪኑ ሕዝብ እየተመዘበረና በሙስና እየተዛቀ መሆኑ የማይካድ ነው፡፡ በዚህ የጥፋት መንገድ እየነጎዳችሁ ያላችሁ ወገኖችም ለቁሣዊ ፍላጎቶቻችሁና ለሰይጣናዊ ሱሶቻችሁ ልጓም አብጁላቸው፡፡ ይህን ስል ወንድም በወንድሙ ላይ የሚፈጽመውን ግፍና በደል ያቁም፣ ወደኅሊናውም ተመልሶ ለሁሉም እኩል በሆነ ህግ ይተዳደር ለማለት እንጂ ሃይማኖታዊ ንስሃ ግቡና ፁሙ ቁረቡ ለማለት ፈልጌ አይደለም፡፡ ለዚያ ዓይነቱ ስብከት ይህ መድረክ ምቹ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ ሰላም ክረሙልኝ፡፡
መሰነባበቻ፡-
To the future or to the past, to a time when thought is free, when men are different from one another and do not live alone—to a time when truth exists and what is done cannot be undone: From the age of uniformity, from the age of solitude, from the age of Big Brother, from the age of doublethink—greetings!
ውርስ ትርጉም፡- ይድረስ የማላይህ የወደፊቱ ወይም ያልኖርኩብህ የኋለኛው ዘመን ትውልድ – በነፃነት ማሰብ ላልተከለከልከው፣ ሰብኣዊ ልዩነቶችህን ተረድተህ በሰላምና በፍቅር ተግባብተህ መኖር ለቻልከው፣ አምነህበት የምትሠራውን የሚያጨናግፍብህ ሳይኖር በእውነትና ስለእውነት መኖር ለበቃሃው ዕድለኛ ትውልድ ሰላምታየ ከዚህ ከተመሳስሎ የመኖር ዘመን፣ ከዚህ የብቸኝነት መንፈስ ሰውን ከሚያሰቃይበት የብህትውና ዘመን፣ ከዚህ ከታላቅ ወንድም የሰቆቃ ዘመን፣ ከዚህ ከአድርባይነትና አስመሳይነት ዘመን ባለህበት ይድረስህ፡፡ (ጆርጅ ኦርዌል፣ “1984”)
1 WAR IS PEACE
FREEDOM IS SLAVERY
IGNORANCE IS STRENGTH
አስማተኛው የኢኮኖሚ እድገት! (በ ገብርኤሉ ተስፋዬ)
ከየት ጀምሬ ወደየት እንደምሄድ አላውቀውም፣ አሁን አሁን የእድገት መለኪያው ምን እንደሆነ እንኩዋን ግራ ገብቷችዋል:: ወይስ የኢኮኖሚ እድገቱ ለኢትዮጲያውያን ሳይሆን ኢትዮጲያን ለሚያስተዳድሯት ብቻ ነው ወይ? እውነቱ በገሀድ ግልፅ ብሎ እያለ ካለፉት አስር አመታት ጀምሮ ጆሮዋችንን በሁለት ዲጅት ሀገሪቱ አድጋለች እያሉ ሲያደነቁሩን ከረሙ:: ለኔ እድገት የሚለው ቃል በአሁን ሰሀት ስድብ መስሎ እየታየኝ ነው:: የተወሰኑ ሰዎች ብር በብር ላይ አካበቱ፣ሀፍታም ሆኑ፣ ህንፃ ገነቡ፣ከመኪና መኪና ቀያየሩ ወዘተ እየተባለ በኢትዮጲያ ስም መነገዱ አግባብ አይደለም:: ለመሆኑ የኢትዮጲያ ህዝብ ጠግቦ የሚበላው ሀሁን ነው ወይስ የዛሬ 10 እና 20 አመት በፊት ነው? መልሱን የሁላችንም ልቦና ያውቀዋል! ህዝቡ አንገቱን ደፍቶ ሁሉን ነገር ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶ እንዳላየ ዝም ሲል ጅል የሆነ መሰላችው:: እስቲ የኢትዮጲያ እድገት ተብየው ያመጣውን ለውጥ ለመመልከት ልሞክር::
በመጀመሪያ መመለከት የምፈልገው የምግብ ዋስትናን ነው::የምግብ ዋስትና ማሽቆልቆሉን የማያምኑ ለሆዳችው የሞቱ እነሱ ብቻ ሲበሉ ሌላውም የበላ የሚመስላችው ብዙ አሉ:: ሆኖም ግን እውነት እውነት ነች እና ምንም ምንም ቢሉ እውነትነቷን አትቀይርም:: ስለምግብ ዋስትና ለመናገር በአዲስ አበባ ስለሚኖረው ህዝብ መናገርን መረጥኩ ምክንያቴም አዲይስ አበባ የኢትዮጲያ ዋና ከተማ እንደ መሆኑዋ መጠን፣የኢህአዴግ አመራሮች ስለእድገት ሲያወሩ የሚጠቅሱዋት ከተማ ስለሆነች እና በጣም ብዙ ህዝብ(ከ 5 እስከ 6 ሚልየን) ስለሚኖርባት ነው:: እዝይጋ ሥራ አልባ የሆኑትን፣ሚበላ የሌላችውን ብዙዎቹን የማሀበረሰባች አካላትን ሳይሆን ማየት የምፈልገው ስራ አገኘው ብሎ በመንግስት መስሪያቤት ተቀጥሮ የሚሰራውን ነው:: አንድ የመንግስት ሰራተኛ የድግሪ ምሩቅ የሆነ በወር 1600 ብር የሚያገኝ ሲሆን ከዚያ ላይ 250 እስከ 300 ግብር ይከፍላል በእጁ ላይ 1300 ይቀረዋል እንበል ፣ የቤት ኪራይን በተመለከት በአሁን ሰሀት በአዲስ አበባ አንድ ክፍል ቤት በትንሹ ከ 700 እስከ 800 ብር የሚያወጣ ሲሆን ከ 1300 ላይ ይሄን ብር ስናነሳ 500 ብር አካባቢ ይቀረዋል፣ በየቀኑ ለትራንስፖርት በትንሹ 3 ብር አወጣ ቢባለ 400 ብር እጁ ላይ ቀረው ማለት ነው:: እስቲ ይሄ ሰውዬ ሙሉ ጤነኛ ነው የህክምና ወጪ አያስፈልገው ቤተሰብ (ልጆችም) የሉትም ብንል እንኳን 400 ብር አያምስት ኪሎ ጤፍ ወይም 4 ኪሎ ሥጋ በወር አይገዛለትም:: በአስማት መኖር ማለት ይሄ ነው!! በየቦታው እንደምንሰማው ከ100,000 በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎች በአዲስ አበባ ብቻ ይገኛሉ:: እነሱም ከእድገቱ ጋር ነው አብረው የመጡት እያሉን ነው! ብሎ ብሎ ጉርሻ መሸጥ የተጀመረበት አገር እድገት አለ ከሚሉ አስማት አለ ቢሉ ይሻላል::እርግጥ ነው የተወሰኑ ሰዎች በአዲስ አበባ የምግብ ዋስትናችው የተጠበቀ ነው ከነርሱም ብዙወቹ የገዝው ፓርቲ አባላት ናችው:: እና ስለ እድገት ሲወራ የኢትዮጲያ ህዝብ በልቶ ጠግቦ አደረ የሚለው ተረት ባይተረክ መልካም ነው እላለው::
በመቀጠል ማየት የምፈልገው ማንኛው የምራባውያን ሀገር የኢኮኖሚ እድገት መጣ ብለው ሲያወሩ ለማሀበረሰባችው የተሻለ የስራ እድልን ፈጥረው ሲገኙ ነው:: በአሁን ሰሀት አብዛኛው የኢትዮጲያ ወጣት የት ነው የሚገኘው ጫት ቤት፣ መጠጥ ቤት፣ሺሻ ቤት፣ ወይስ ኑሮውን ለማሸነፍ ከሀገር ወቶ ተሰዶ በረሀ በልቶት ቀርቷል:: ማንም በአገሩ መኖርን የሚጠላ የለም! ወጣቱ ከሀገር ተሰዶ ሲወጣ ነጮቹ ናፍቀውት አይመስለኝም:: ከሀገር ተሰዶ በረሀ ላይ መሞት እንዳለ፣ በሀር ውስጥ የሻርክ እራት መሆን፣መደፈር፣ ከህንፃ ላይ ተወርውሮ መሞት አልፎ ተርፎም የሰውነት አካላችው እስከመሸጥ እንደሚደርስ እያወቁ ሀገራችውን ጥለው የሚሄዱት ቁጥር መጨመሩ ምንን ያሳያል? ምን ያህል ወጣቱ በኢህአዴግ አመራር እንደተማረረና ተስፋ እንደቆረጠ ነው የሚያሳየን:: ሌላው የሴት እህቶቻችን ቁጥር በወሲብ ንግድ ላይ እየጨመረ መሄዱ በካንፓስ ደረጃ መርጠው የተማሩት ፊልድ ነው ብዬ አላምንም ለኔ ይሄ የሚያሳየው ወጣቱ ከስራ ማጣት የተነሳ ኑሮን ለማሸነፍ የማይፈልገው አዝቀጥውስጥ እየገባ እንዳለ ነው:: ከሰሞኑ ደግሞ ይባስ ብሎ እድሜያችው ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጅ አገረዶችን በየድረ ገጹ ለወሲብ ሽያጫ አቅርበዋል፣ የሚገርም ነው እዚም ዘመን ላይ ደረስናል ያስብላል!
በሶስተኛ ደረጃ ማየት የምፈልገው ከምግብ ውጪ ለሰው ልጅ መሰረታዊ ነገሮች ብዬ የምላችውን የውሀና የመብራት አቅርቦትን ነው:: በአዲስ አበባ ከተማ የመብራትና የውሀ ነገር አነጋገሪ ከሆነ ሰንብቷል:: አብዛኛው የከተማው ክፍሎች ውሀና መብራት በፈረቃ ነው የሚያገኙት:: ጥቁር አንበሳን የሚያህል ሆስፒታል በየህለቱ በጣም ብዙ በሽተኞችን የሚያስተናግድ ሆኖ ሳለ ለዚህ አይነቱ ችግር መጋለጡ በጣም አሳዛኝ ነው:: የእድገት አንዱ መሰረቱ የህዝብን የ መጠጥ ውሀ እና የመብራት አቅርቦት ማሟላት ወይም ስርጭቱን መጨመር ሲሆን በአዲስ አበባ የምናየው ነገር ግን የተገላቢጦሽ ነው::
የህዝቡን የምግብ ዋስትና ካልጠበቁ ወይም ካላሻሉ፣ ለወጣቱ የስራ እድል ማመቻችት ካልቻሉ፣ በቂ ወይም ተመጣጣኝ የውሀ እና የመብራት አቅርቦት መስጠት ካልቻሉ ታዲያ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከህዝቡ ህየዘረፉ በሚወስዱት ብር የሚገነቡት እንፃን በማየት ነው እድገት መጣ የሚባለው:: ኢትዮጲያ በየአመቱ በቢልየን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ በእርዳታ መልክ ታገኛለች ከዚህ ውስጥ ብዙው ገንዘብ የሚጠፋው በ ጥቁር ፕሮጀክት(Black project) ነው:: የ ጥቁር ፕሮጀክት ማለት መንግስት በህዝብ ስላልተመረጠ ስልጣኑን ለማቆየት ሲል ለማሀበረሰቡ ብልፅግና የሚውለውን ገንዘብ ቀይሶ ለካድሬወችና ለሰላዮች(ለሆድ አደሮች) እድሜውን ለማራዘም እንዲሁ የሚበትነው ብር ነው:: ከሰሞኑም እንደሰማነው መንግስት የተቃዋሚ ፓርቲን እና አባላታችውን ለመሰለል በሚልዮን ዶላር የሚቆጠር የህዝቡን ንብረት እንደሚጠቀም(እንደሚበትን) ተገልጿል::ሌላው በሀገሪቷ ውስጥ መጣ እየተባለ የሚያወሩለት የኢኮኖሚ እድገት መሰረት አልባ ስለሆነ መሰረታዊ ለውጦችን ሊያመጣ አልቻለም ይህን ልል የቻልኩበት ምክንያት
1. ስለኢኮኖሚ እድገት ሲወራ ብዙም ጊዜ ትኩረት የማይሰጠው ግን ለኢህአዴግ ዋንኛው የገንዘብ ምንጭ የሆነው የስራአጥ እህትና ወንድሞቻችን በየሀገሩ የሚሰደድ ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መሄዱ ነው::ይሄን ስል በአሁን ሰአት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያን በየአገሩ ተበትነው የሚገኙ ሲሆን በየ ወሩ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለቤተሰቦቻችው ይልካሉ:: በተዘዎዎሪ ይሄን ብር ኢህአዴግ የኢኮኖሚ እድገት ነው ይላለ:: ዕህት እና ወንድሞቻችንን በተለያዩ ሀገሮች በትኖ በነሱ ጀርባ ላይ ቁጭ ብሎ መሰረታዊ እድገት ሊመጣ አይችልም::
2. በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦችን ለብዙ ሺ አመታት ከኖሩበት ቦታ አፈናቅሎ ለተለያዩ የእንድ እና የውጭ ሀገር ባለሀፍቶች መሬታችውን በመሸጥ የኢኮኖሚ እድገት አመጣን ማለት አይቻልም::እነዚ ሰዎች መሬታችው ሲወሰድ በመንግስት ብዙ ነገር ቃል የተገባላችው ቢሆንም አንዳችውም ግን እውን አልሆኑም:: በአሁን ሰሀት ከተወሰኑት በስተቀር በሙሉ በኬንያና በተለያዩ ቦታወች ተሰደው ሲገኙ በተቃራኒው ደግሞ የኢህአዴግ ካድሬዎች የከበሩበትን መንገድ እናያለን:: ማንኛውም አይነት እድገት በመጀመሪያ ደረጃ አላማ ሊያደርግ የሚገባው የመሀበረሰቡን ጥቅም ማስከበር ነው::
3. ምህራባዊያን(mainly US,UK and ISREAL) ኢትዮጲያ ያላት የጆክራፊ አቀማመጥ ቴሬሪስትን ለመዋጋት ያመቻል ብለው ስለሚያምኑና የኢትዮጲያ መንግስትም ጥቅሙን ለማስከበር አሽከር እንደሆነ ስላዩ በየአመቱ የሚሰጡት እርዳታ እየጨመረ መሄዱ ይህን እና የመሳሰሉትን አጋጣሚወች በመጠቀም በኢትዮጲያ እድገት አመጣው እያሉ ያወራሉ:: መሰረታዊ ችግሮች እየተባባሱ ህዝቡም ኑሮ እያሰቃየው፣ ወጣቱም ሥራ አልባ ሆኖ በየአረብ አገሩ እየተንከራተተ እድገት መጣ ማለት አይቻልም!! በሀገሪቷ ውስጥ የሚገባውን ገንዘብ በሙሉ ኢህአዴግ እና ካድሬዎቻችው አፍኖ በመብላት መሰረታዊ ለውጦች ሊመጡ አይችልም:: ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጲያዊ የተሻለ አመራር ያለው መንግስት ለማምጣት የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ አለብን!!!!!!!!!
ፍቅር ለኢትዮጲያ ህዝብ!!!
አስተያየት ያላቹ በዚ ኢሜል ልታገኙኝ ትችላላቹ ( allforethiopia@gmail.com).
ዕንባ! (ሥርጉተ ሥላሴ 27.03.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)
ዕንባ የድረሱልኝ ጥሪ ነው። ዕንባ የችግር አዋጅ ነው። ዕንባ የፈተና ነጋሪት ነው። ዕንባ የሰቀቀን ውስጣዊ እሳታዊ መግለጫ ነው። ዕንባ የመንፈስ ጭንቀት ረመጣዊ ተፋሰስ ነው፤ ዕንባ የጭምትነት ቁስለት እዢ ነው። ዕንባ የታመቀ ነበልባላዊ ጎመራ ነው። ዕንባ ውስጥን መለኪያ ነው። ዕንባን ለማስቆም ለመነሳት ሆነ፤ ለዕንባ ለመድረስ ደግሞ „ቅድመ ሁኔታ“ አያስፈልግም። እራሱ „ቅድመ ሁኔታ“ የሚለው ቃል ዕንባን ፈጽሞ አይመጥንም። ፍሉ ዕንባ ጥሪውን ሲያስተላልፍ ብስል ከቀሊል ሳይለይ ለሁሉም ሆኖ፤ ግን የሚማገዱት ጥቂቶች የቆረጡት ብቻ ናቸው። ሁላችንም መቆስቆሻ እንፈልጋለን። መቆስቆሻ ባያስፈልገው እንኳን ለዬግል የመንፈስ ምቾት አብዛኛዎቻችን እናዳላለን። ታዲያ ዕንባና ጥሪው ዬት – ከምን ይጠጉ? በዘመነ – ጠቀራ።
እጅግ የማከበራችሁ የሐገሬ ተስፋዎች፤ ይህን ዘመነ – ህማማት መመርምር ማገናዘብ አቃተን ማለት ባላችልም ጊዜው ያልደረሰ የግንዛቤ ችግር ግን ያለብን ይመስለኛል? ሰሞኑን የደንበር ጉዳይ በሚመለከት ተዘውትሮ የምስማው መሰረታዊ ጉዳይ አለ …. „የጎንደር መሬት፤ ጎንደሬ በሱዳን ተመታ“ ወዘተ …. ህም! እም! አደዋ የትግራይ ነበርን? ማይጨውስ የትግራይ ነበርን? ሐረርስ የሐረር ሰው ነበርን? ጎሬስ የኢሊባቡር ነበርን? ይህን መመለስ ስንችል ዛሬ መስጥረን የምንደልቅ እብኖች አይናችን ይከፈታል። ደንበሩ ሲጣስ ማህሉ ደንበር ይሆናል። የሱዳን ይሁን የግብጽ ዘመን የተሻገረ ፍላጎት የአውሮፓ ራዕይ ነው። ቀደምትን ሀገረ – ኢትዮጵያን ለማከሰም የተተለመ። ወያኔ የባንዳነቱን ተግባር እዬፈጸመ ስለሆነ ነገ እንደ ኩርድሾች የቁራጭ አፈር ለማኞች መሆን አይቀሬ ነው በዚህ ከቀጠለ። „የፉክከር ቤት ሳይዘጋ ያደራል“ ….. እንደሚባለው ….
ከዚህ ጋር ተያይዞ ያን ድንቅ ሰላማዊ የዕምነት እኩልነት ትግል „የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ“ ለማስቆም በምሽት የተበተነ በራሪ ጹሑፍ የሚያጨፋጭፍ ነበር። ባለቤቱ ማን ነበር? ተከትሎም ሳውዲ ላይ እህትና ወንድሞቻችን ተለይተው „ኢትዮጵያዊ“ እዬተባሉ በባዕድ ሀገር ደመ ከልብ ሲሆኑ ተባባሪው ማን ነው? የኢትዮጵውያን ከጽንፍ እስከ ጽንፍና ቁጣ „ኢትዮጵዊነትን“ አጉልቶ ሲወጣ ከነፃነት ታሪካችን ፍቀት ጋር የተላተመው ዘመቻስ ማን ነበር ያዘጋጀው? አሁን ትናንት አንቦ አካባቢ የሚኖሩ ወገኖች አካላቸው ዓይኑ በቢላዋ ገብያ ላይ አደባባይ ወጥቶ እንደ ሀሞራቢ ዘመን ተቀጥቅጦ ሲገደል፤ እንዲሁም ወደ 600 አባወራዎች ተፈናቅለው ልምና ሲፈረድባቸው ሴረኛው ማን ነው? „የኦሮምያን አዬር ከባዕዳን ወረራ አድነነዋል ስለዚህም ቀጣይነቱ በእጃችሁ ነው ያለውና ጠብቁት“ ተብሎ የተሰጠው ግንጥል ስሜትስ ጅረቱ ዬት ይወስደናል? ይህ ጥቃትን እዬጠጡ መኖርስ አንድነትን ፈጥሮ ትብሺ ትብስ ብሎ ለመሰለፍ አቅምን ካለይግባኝ ወና ማደረጉስ ምን ሊባል ይሆን? በእርግጥም ዕንባው ጎርብጦናልን? መሮናል? አንገፍግፎናል? ከቶስ ይህ አረሮ ዘመንስ አልሰለቸንም ይሆን? ስደቱስ?! —-
ለወጡ ወደ ወያኔ ከመሄድ በፊት እያንዳንዱ የወገኔ ዕንባ – ዕንባዬ ነው፤ የአካሌ ሰቆቃ – ሰቆቃዬ ነው? የአካሌ ችግር – ችግሬ ነው የሚል ሁሉ በብራና ላይ የሚኩለውን መግለጫውን ይዋጠውና እራሱን ሰለመለወጡ በቅድሚያ ያረጋግጥ? ከራስ ሲነሱ ሙሉዑ ብቃት ያለው አቅም ይኖራል። እራስን መለወጥ ሲቻል አብነቱ ሃይልና ብርታት ያስገኛል። እራስን መቅጣት ሲኖር ድፈረት ይፈጠራል። እራስን ከስህተት አርሞ ይቅርታን ተላብሶ ሲነሱ እርግጠኝነት ይኖራል። በስተቀር ግን ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው። ክብሮቼ ወገኖቼ፤ ጠላትን መብለጥና በጠላት መበለጥ ዬት ላይ ስለመስከናቸው እስኪ እባካችሁን መዝኑት – በህሊና አደባባይ።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ህዝቦቿ ከስሜን ወደ ደቡብ፤ ከደቡብ ወደ ስሜን፤ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ፤ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ በሽግሽግ – በውርርስ – ከቦታ ቦታ በመዘዋወር - ተዋህደው የኖሩባት የአብሮነት ተምሳሌት ሀገር ናት። ይህ የዘመናት ሂደት የታሪኳ እንብርት ነው። የጥንካሪያዋ ምንጭም ይሄው ነው። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ይወለዳል። ስለሆነም የእያንዳንዱ መክሊት መስተጋብር ተዋህደው፤ በተፈጥሮ ተቀምረው፤ በጋብቻ አደብ ገዝተው፤ በማህበራዊ ኑሮው ተመክሮ መስኖ ለምተው፤ በፈቃደ እግዚአብሄር ተመርቀው ገናናዋን ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያን ገነባ – መሰረተ።
እናት ሀገራችን ኢትዮጵያን የዛሬ ታላላቅ ሀገሮች በዲታነት በቁስ ቢበልጧትም፤ በመንፈስ ሀብታትና በውስጥ ብቃቷ ሆነ ጥራቷ እንዲሁም ከፈጣሪያዋ ጋር በአላት የቀረበ ግንኙነት ልዑቅ መሆኗን እነሱው እራሳቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ – ባዕዳኑ፤ አፈር በቀል አንጡራ ጠላት ባንደዎችም ጭምር። ኢትዮጵውያን የትም ይሁን የትም ውስጣቸው ፍሬ ዘለቅ ዕንቁ ነው። ሀገራቸው ኢትዮጵያ ወተቷን አጠጥታ እንደማሳደጓ፤ እሷም በልጃቿ አቻ የሌላት ሀገር መሆኗ ልብ ልክ ነው። ይህ ደግሞ በመንፈስ ብቃትና ብልህነት እያዬነው ነው። ሰለጠነ ከሚባለው ሀገር ከተማራው ዜጋ ያልተማረ አንድ ኢትዮጵዊ፤ በተፈጥሮ የፈጠራ ብቃቱ ሆነ አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅ አቅሙ ሆነ ችሎታው ዬት እዬሌለ ነው … አይገናኝም። ባያስመካም፤ ባያስኮራም ሥልጡኑ ጸጋው ሃብቱ ስለመሆኑ ግን መዘለል የለበትም።
የኢትዮጵዊነት የአብሮነቱ ፍቅሩም በሸቀጥ የተገዛ አለነበረም። መከባባሩ ገብያ አልነበረም ለአፍታ ሞቅ ብሎ የሚፈታ፤ ዬእናት ሀገራችን የኢትዮጵያ ታሪካዊ የአርበኝነት ጥንካሬዋ ምድራዊም አልነበረም። ዘንበል ብሎ የሚያደምጣት አምላክ ያላት ሀገር ከመሆኗ ላይ ነው – ረቂቁ አንድምታ። በህገ ልቦና አምላኳን አምና ከነበረችበት ዘመን ጀምሮ እምነቷ ሆነ ትምክህቷ በፈጣሪዋ ነው። በእኛ ዕድሜ እንኳን ዝናብ ሲጠፋ ለእስልም እምነት አባቶች ይነገራል። እባካችሁ „ድዋ“ ያዙ ተብሎ፤ መዕት ሲመጣም „ምህላ“ እንዲያዝ ለተዋህዶ አባቶች ይነገራል።
ደስታውንም ሀዘኑንም በእትብት ሀዲድነት ልባዊነት ጎልብቶ ገቢራዊ የሆነባት የጥቁር በዕት – ኢትዮጵያ እመቤት ነበረች። ወያኔ ሀገርን ለማፍለስ ሲነሳ ይህን አስፈሪ የውህደት ጥንካሬ መበተን ነበረበት – ለስትንፋሱ። በፋሳ ከሰሰከሰው። ኮሳሳ ኢትዮጵያን አልሞ እዬሄደበት ነው። ዛሬ እኮ „ኢትዮጵያዊ“ ማለት ወንጀል ነው። አረንጓዴ ቢጫ ቀይን ሰንደቅአላማ መልበስ ያሳስራል። ያሰድዳል፤ ያስደበድባል። አሳሬ ህግም ተደንግጎለታል – ለሰንደቅአላማ …. የዘመን አረማሞ ወያኔ – ግባዕቱ መቼ ይሆን ?ወደ ሄሮድስ መሪው አፈር ሊያጫውት የሚሄደው በእጅጉ ይናፍቃል —- መሬት ስትርድበት ወያኔን ማዬት —–
ጥንካረዋና ብርቷቷ የኢትዮጵያ እንቅልፍ የነሳቸው የውጪ ኃይሎች አጋጣሚውን ይጠብቁ ስለነበር ብቃቷን ሊሸረሽር የሚችል ሥርዓት ለማምጣት ተግተው ሲሰሩ ኖሩ። በለስ ቀናቸውና አሁን የልባቸውን የሚያደርስ ሽፍታ ወያኔ በማግኘታቸው ትራሳቸውን ከፍ አድርገው በመተኛት የእርስ በርስ ጦርነት ሊያስነሱ የሚችሉ ጥቃቶችን ወሸኔ እያሉ፤ እያጀቡ እርዳታ ለሽፍታው ወያኔ ያጎርፋሉ።
አዬን አኮ ከሰሞናቱ ለአንዲት ወንዝ ገብ ክሪሚ ምን ያህል ጊዜ፤ መንፈስ፤ ገንዘብ፤ አቅም እዬፈሰስ እንደ አለ ….. የኃያላን ሀገር መሪዎች ከዙፋናቸው ወርደው ለክሪሚ ሲያሸበሽቡ ….ፕሬዚዳንት ፑቲን አርቀው መተንፈሻ ቧንቧ ለመንሳት ፊት ለፊት ወጥተው ሲፋለሙ …. በተጨባጭ ተመለከተን። እኛማ እንደ ሰው መታዬታችንም እንጃ ነው …. ያቺ ገናና የነፃነት አንባ፤ የአፍሪካ የነፃነት ተቋም፤ ኢትዮጵያማ …. ማን አስታውሷት? የተከበሩትን ኔልሰን ማንዴላ የነፃነት አባትነትን የሸለመች ድንቅ ሀገር – ኢትዮጵያ፤ መላ አፍሪካን ከቅኝ ግዛት ያወጣች የሞገዳማ ጥንካሬ ብቸኛ ባለቤት ምንጩ – ከሰው ፍጥረት መገኛ ከምንጩ ነበር።
ታዲያ እኛ ምን እንጠብቃለን? ስለ እኛ ዋቢ ጠበቃ የሚሆን ባዕድ ማግኘት ይቻላልን በዚህ አያያዝ? የኢትዮጵያን ታላቅነት ለማን ሲመቸው ነው? ይህነን መርምሮ ማግኘት እንዴት ይሳነን? ይህንን ብናውቅ እኮ የምናቀርበው የድርድር ቅድሚያ ሁኔታ ባልነበረ? ሰው ልህሊናዊ ጉዳዩ የምን „ቅደመ ሁኔታ ነው“ ዕንባው ቅርባችን አይደለንም?! ብናውቅስ የምንመካበት ሰበብ ባልነበረ? ለስበብ የምናጠፋው ጊዜም ባልኖረ? ለጥሎ ማለፍ ሽኩቻም የምናቃጥለው ቆራጣ ጊዜ ባልኖረን? ያገባኛል ለምንልለት „ኢትዮጵያዊነት“ ዕንባ ጥሪውን በምን ክህሎት ይሆን ምላሽ ሰጥቶ ለስኬት የሚበቃው? ማናቸውም የወያኔ ጥቃት የእኔ ጥቃት ብሎ የመንፈስ መስማማት እንዴት ይፈጠር?! ግልጽነት ዘመኑን እንዲመራን መቼ ይሆን ይለፍ https://www.zehabesha.com/amharic/archives/13892 የሚያገኘው?!
እኔ እንደ ሥርጉተ እማስበው ማሸነፍ ከወያኔ በፊት እራስን ነው። ሙሉ ትጥቅና ስንቅ የጎደለው መንፈስ እሽሩሩ እያልን አብዛኞቻችን እስከመቼ? …. ጥቃቱ ይቀጥላል …. ዕንባውም ይጎርፋል …. ሽንፈቱም ይናኛል ….. እግዚአንሄር እኮ ነው በኪነጥበቡ ጠብቆ ያቆያት ኢትዮጵያን እንጂ እንደ እኛማ መትበስበስ እንደ ወያኔ የጥፋት ዕወጃ ቢሆን አልነበረችውም።
እጅግ የሚያሰፈራ ነገር ፊት ለፊት ደግሞ አለ። …. በዬቦታው ዜጋ አይደለህም እዬተባለ የሚነቀል፤ የሚሰቀል መንፈስ ብድሩን ለመመለስ ከተሰናዳ የሚያቆመው አይኖርም። አንድ የማወቀውን ነገር እስኪ ልንገራችሁ። ጎንደር የጓንግን ወንዝ ተከትሎ በአርማጭሆና በጭልጋ መካከል „የጋላ አገር“ የሚባል አለ። ስለ ቃሉ ይቅርታ እኔ የሰጠሁት አይደለም። በጣም ብዙ ቦታዎች በተለያዬ ሁኔታ ዘመኑ የፈቀደው ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። ለነገሩ አሁን የእስራኤላውያን ስም ሥልጣኔ ይሁን አላውቅም ሥራዬ ብለን ተያይዘነዋል። የባዕድ ፊደላትንም እንዲሁ፤ ድምጸቱ ፍሰቱ የእኛ ያልሆኑ እንደ እራስ አድርገን ተቀብለናል። „ጨጸ“ በቁቤኛው የሉም። እነዚህ ከነድምጻቸው ደግሞ ከእኛ ተፈጥሮ ጋር ኖረዋል በአንድ ምድጃ።
ስለሆነም የባዕዱ ሲመጣ አናውቅህም ብለው ትርጉም አልባ ያደርጉታል ወይንም የስያሜው መንፈስ ጥንዙልና ፍዙዝ ይሆናል። „ጸጋዬ“ የታላቁ የቅኔው ልዑል ሥያሜ ነው። ልዩ ስጦታ፤ መንፈሳዊ ሃብት፤ የውስጥ ክበረቴ፤ የማንነቴ ረድኤት ከአምላኬ ብቻ የተሰሰጠኝ እንደማለት ነው። ይህን ተፈጥሯዊ ጌጣችን እያፋለሰው ግን ተቀበልናል በዚህ ዘመን። ስለሆነም የቦታው ስያሜ እኔ ተቀብዬ የጻፍኩት አይደለም – ከቀደመው ዘመኑ የሰዬመው እንጂ።
…. ለማንኛውም በዚህ አካባቢ ለዘማናት የኦሮሞ ልጆች ተዋልደው ተጋብተው ኑሯቸውን መስርተው ያሉ እጅግ ብዙ ወገኖቻችን አሉ። ዋልድባ ገዳም ሲመሰረት ሆነ ከግራኝ ጥቃት በኋላም አባቶቻችን የመጡት ከሽዋ ነው። ሌላ ጊዜ ታሪኩን እምለስበታለሁ። የዘመነ መሳፍንት ታሪኩ መሰል ነው፤ የክፈለ-ጦሮች ሰራዊት አሰፋፈርና ኑሮም በመሰል ሁኔታ ተከናውነዋል። አሁን ጎንድር ከተማ አዬር ማርፊያ አዘዞ ጡረታ ሰፈር ወዘተ በጣም በርካታ ቅይጥ ሁኔታ ነው ያለው፤ በጣሊያኑ ንድፍ አስፈፃሚ በወያኔ ደግሞ „በታላቋ ትግራይ“ ዶክተሪን ጎንደርና ወሎ ተመሳሳይ የህዝብ ሰፈራ ተከናውኗል። ይህ ሁሉ እሳት ቢነሳ ማነው ማጥፋት የሚችለው ነው ጥያቄው? መተላለቅ ብቻ።
… እሳት የሚተፋ ዕንባ ይንቀለቀላል … ሁሉም ነገር የዶግ አመድ ነው የሚሆነው። አብሶ የቆላማ አካባቢ ነዋሪዎቹ ተዋጊዎች ናቸው። ቦታውም እራሱ ተዋጊ ነው። እንቅልፍ ወስዶታል ብላችሁ „አያ እከሌ“ ብላችሁ ውድቅት ሌሊት ላይ ብትጠሩት ትራሱ ያዘጋጀውን መሳሪያ መዥልጦ ብድግ ነው …. ቆለኛ ተረጋግቶ ተኝቶ አያውቅም፤ ከትዳር አጋሩ ይልቅ አቅፎ የሚተኛው መሳሪያውን ነው። አልሞም አይስትም። ቆቆች ናቸው። የቆለኛ ሴቷ እራሷ አለባበሷ እንደ ደገዋ አይደለም። ነጠላዋን በቀኝ እጇ አውርዳ ታደገድገዋለች። ስትቀመጠም ቁርጢጥ ብላ እንጂ ዘርፈጥ ብላ ሙሉ አካሏን አደላድላ አይደለም። ዝግጁ ናት …. ለማናቸውም ጉዳይ … ይህ እንግዲህ የአንድ በጣም ውስን አካባቢ ምስል ነው። ሌላውም አካባቢ መሰል ጉዳዮች አሉ። …. ዕንባው ፈንድቶ እሳት መትፋት ሲጀምር የሚያስቆመው አጋዚ የለም።
በሌላ በኩል መቼም ሽማግሌ ግራጫማ መካሪ የጠፋበት ጠፍ ዘመን ላይ እንገኛለን። ነገር ግን በትእግስት – በአርምሞ – በተደሞ ሆነው የሚኖሩት ኢትዮጵውያን በደሉ ሲባዛ፤ እንዲህም ሲከረፋ የነገ ተስፋዎች ወጣቶቹ በውስጣቸው ሽበት ያበቅሉ ናቸውና የተገባ አይደለም፤ ግፉ በዝቷል ወገኖቻችን እዬተገፉ ነው በማለት፤ በነቂስ እየተለቀሙ ሀገር አልባ፣ መሬት አልባ፣ ዜግነት አልባ፣ ማንነት አልባ፣ መኖሪያ አልባ ሆኖ ከሚጠቃው „አማራ ብሄረሰብ“ ጎን ይቆማሉ። በተጨማሪም አማራ አካባቢዎች እትብታቸው የተቀበሩውም ማዕከላዊ ግንዛቤ ያላቸው ወደ ጎሳዊ ስሜትና ግንዛቤ አንወርድም በማለት እራሳቸውን በተዕቅቦ ያቆዩትም ቢሆኑ የለዬለት ድርሻቸውን ለመወጣት ይቆርጣሉ …. ይወስናሉ። ሲበዛ ይገለማል። ሲከርም ይበጠሳል። የማይቻለውን አስኪ ሻግት ተቻለ —- ቀጣዩ መራራ ኮሶ፤ አሰንጋላ እንዳይሆን ሙሴዎችን በትዝብት ይጠብቃል።
ፍትጊያው – ትግሉ – ጦርነቱ – ተከትሎ ሀገርና ህዝብ፤ ትውልድና ታሪክ፤ ከሁሉ በላይ አብሮነትና ፍቅር አፈር ድሜ ይግጣሉ። ኢትዮጵያ ወያኔ የሳላት ኢትዮጵያ ብጥቅጥቅ እንድትል ታጥቆ የዶለተባት ኢትዮጵያ አይሆኑ ትሆንና …. የወያኔ ፍላጎት ሳይሸራረፍ ተግባር ላይ ይውላል። የጣሊያንም ህልም ይሳካል። የባዕዳን ራዕይ ይመሾራል። ግን እኛ ሀገርና መሬት አያስፈልግንም? አትናፍቅም ያቺ ውድ ሀገር ኢትዮጵያ!?!
ለመሆኑ መሰሉ እርምጃ ቢወሰድ፤ በእጥፍ ድርብ ቢወራረድ፤ ይህ ለነገ ይጠቅማል ወይ? ሀገር አልባነት – አፈር አልባነት – ኩራት አልባነት – መመለሻ ቤት አልባነት – ዘር አልባነት – ውርስ ቅርስ ትውፊት አልባነት – መሳቂያነት መኖር ወይንስ ምን ይባል ይሆን? …. ወላጅ አባቴ ሲበዛ ጭምት ነበር። ተራማጅም አስተሳሰብ ነበረው – ያው መምህርነት ልዑቅ ሙያ ነውና። አልፎ አልፎ ምን እዬታዬው እንደሆነ አላውቅም በልጅነቴ ደጋግሞ ያዜመውና ይወደው የነበረ ስንኝ ነበር ሙዚቀኛው ማን እንደ ነበር አላውቅም … ይቅርታ
„እናት አባት ሲሞት በሀገር ይለቀሳል
እህት ወንድም ሲሞት በሀገር ይለቀሳል
አክስት አጎት ሲሞት በሀገር ይለቀሳል
ሀገር የሞተ እንደሆ ወዴት ይደረሳል?“
ሀገር አልባነት ውርዴት ነው፤ አደራ መብላት ነው፤ አንገት መድፋት ነው፤ በራስ መተማመን እንደ አወጣ ገብያ ላይ አውጥቶ መሸቀጠም ነው ፤ ሰንደቅአላማን መጠቅጠቅ ነው። ይህ የሚያረመጠምጥ ከሆነ መከራን ለማስቆም እራስን መለወጥ በእጅጉ ለምን ያቅተናል? ለእኔ ይህ ገና ነው። ፍላጎቱ ብቻ እንጂ መሳሪያውም ማሳውም አልተሰናዳም። በደሉም ሰርስሮ ውስጣችን ገና አልገባም፤ ለዚህም ነው ነገሮችን ሁሉ ሳንመረምር እንደወረደ እያዋህድን መንፈሳችን የሚታወከው። ቁጣችን ቁስለትን የማያተርፈው። ቁሰለት ትርፍ ከሆነ መሸነፍ ያከትምለታል።
መሬት ላይ ያለው እውነተኛ ነገር በወያኔ ላይ ድል ያደረገው እኔ የማልደግፈው ድርጅት ከሆነ ጆሮ ማን ሲሰጠው። ቃለ ምልልስም ከሆነ ማን ቁብ ሰጥቶት ሲያዳምጠው። ማንስ ውጤቱን ሲያደንቀው – ሲያከበረው። ወገኖቼ – የኔዎቹ ቢያንስ „አክሱም ለጋንቤላው ምኑ ነው?“ ሲሉ ሄሮድስ መለስ ሲሳለቁ ያን ጊዜ በነፍስ ወከፍ የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች ቆሰልን። ግን ይህነን ንጹህ ቁስለኝነት እኛ ሸፍነን ወይንም አከናንበን ወይንም ሸጉጠን ከምናስተናገደው የዛሬ ጉድ ጋር ፊት ለፊት ተቀመጠን እስኪ እንመዝነው …. ሃቅን አንፍራ! ቢያንስ ለህሊና። ለእኛ ሲሉ ባሩድ ኑሯቸውን የነጠቀው፤ ትዳርና ቤታችን፣ ልጅና ኑሯቸውን ወጣትነታቸውን፤ የማይጠገበውን የልጅነት ክፈለ ጊዜያቸውን ለካቴና ለፈቀዱትም ትንሽ እንሰብ …. ምስጋናው፤ ዬክበር ቀኑ ማሰናዳቱ መልካም ሆኖ ሳለ ውስጥን አሸንፎ ወቅቱ ለሚጠይቀው ሁኔታ መገዛት አለመቻል ጥሬ ነገር ነው – ጠጠር። ፍልሚያ —-
ሌላው ሳቢያ ተኮር መሆናችንም ሊመረመር የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ጊዜ እንዲበላ የምንፈቅድለት እንደ እውነቱ ከሆነ ለሳብያ ነው። ስምምነቱም – ድርድሩም – ውሉም – ቃል ኪዳኑም ለሳቢያ የሰገደ ነው። ለዚህም ነው አድሮ ጥጃ የሚኮነው። „ቂም ይዞ ጸሎት ነው“ ነገሩ። አቅም ማጣትን የፈቀድንለት እኛ እንጂ ዕንባማ የዘወትር ጥሪው አቅም ለድል እንደሚያበቃ ጠንቅቆ ያውቃል። ለድል የሚየበቃው ወሳኝ ነገር የችግሩን ምክንያት ማወቅ ነው።
አጀንዳውም መሆን ያለበት ይሄው ነው። አቅምም – ጊዜም – ገንዘብም – መደመጥም ያለበትም ምክንያታዊ ጉዳይ ላይ መሆን አለበት። ይህ ከሆነ ከሽንፈት ጋር ሳይሆን የቀጠሮ ዝርዝር መርኃ – ግብራችን ከማሸነፋችን ሚስጢር ጋር ይሆናል። ማለምና መከወን ፍሬ ማዬትም ይሆናል ሰነዳችን። ይህን ነው በውስጣችን መዋጥ ያለብን አምክንዮ። የመደራጀትም አስኳል፣ የሩጫውም መስመር ዬድካሙም ዲካ መለካት ያለበት ከዚህ አንጻር ይመስለኛል። ይህ ከሆነ አቅም ሳይባክን፤ ወቅትም ሳያመልጥ፤ ምቹ ጊዜም ሳይሾልክ ሁሉ ነገር ምክንያታዊ ከሆነው ፍላጎታችን ላይ ከዋለ ነገን ማግኘት ይቻላል። ይህ ማለት መቁረጥ መወሰን መሆን መቻል ሦስቱ ሥላሴዎች ማሸነፍን አምጠው ይወልዳሉ …. በተረፈ አንድነት ከአንቦ ለተፈናቀሉ የዕንባ ቤተኞች ለወገኖቻችን ብቸኛ መጠለያ ጥግ ዕንባን አድማጭ በመሆናችሁ አመሰግናችኋለሁ። እንደ እናታቸው ጓዳም ቤት ያፈራውን ማካፈላችሁ ውስጥን ይመረምራል።
ክውናዬ ለዛሬ „ከቶ ዬት ይሆን ዬፍላጎታችን ሴሉ ያለው?“ ብዬ በ23.03.2014 በጻፍኩት ላይ የተከበሩ አቶ ምስክር እውነቱ የሰጡት ገንቢ አስተያዬት ይሆናል። „ዲቃላ አታድርጊው“ እሺ ብያለሁ የእኔ ጌታ። ሲቸገር ነው እንጂ እኔም አልወድም። 17 ዓመት ተግቼ ስጽፍ አይደለም ጋዜጣ ላይ የዋሉት፤ ያልዋሉትን ጌጠኛ ቃላትም ተግቼ መጠቀሜ ለቋንቋው ካለኝ ቀናዒነት ነው። መጻህፍቶቼም በሙሉ ይህን መርህ የተከተሉ ናቸው። ነገር ግን አማርኛ ቃላት የሌላቸው ፊደላት አሉ። „ጰ ና ፐ“ ከሁለቱም የሚፈጠሩ ቃላት የትውስት ናቸው። በተጨማሪም ከዘመን አመጣሹ ኢንተርኔት ጋርም ተዛመጆች አቻቸውን በአማርኛ ማግኘት ይቸግራል። ቃላት እንደ ሥልጣኔ ይሰደዳሉ፤ ይወራረሳሉ፤ ከዚህ ሌላ በሥነ – ግጥም ዘርፍ ገጣሚ በአንድ የግጥም እርእስ ሥር የፈለገውን ቋንቋ ቀላቅሎ የመጠቀም ሙሉ ዓለምዓቀፋዊ መብት አለው። ሌላው ፎንቱ ደቀቀ ስላሉት የድህረ ገጹ ባህሪ ነው። ኢትዮ ዛሬ እኮ ከዘሃበሻም የከሳ ፊደላትን ይጠቀማል። እጅግ የማክብረዎት የሀገሬ ልጅ እኔም እማነበው በመነጸር ነውና እርሰዎም እንዲሁ ያድርጉ ። በተረፈ እኔ በምመራው ድህረ ገጽ ያሉትን ገባ ብለው የቀደሙትና ዋጋቸው ያልቀነሱትን ይመልከቱ፤ በፒዲኤፍ የተሰሩ ናቸውና ማዬት ይችላሉ። www.tsegaye.ethio.info በርከት ያሉ አውዲዎችም አሉ፤ ጊዜ ካለዎት የዳምጧቸው። በተለይ „ተስፋ“ ላይ የመስቀል ባዕልን ምክንያት በማደረግ በ2001 የተሰራ ልዩ አውድዮ አለ …. ይወዱታል። „ስለ ድርጅት“ ጽንሰ – ሃሳብም „ማዕዶት“ ላይ … እርሰዎን ይጠብቃሉ – በተጠንቀቅ ….
የኔዎቹ ላበቃ ነው ፍቅርን ከውስጤ ሰጥቼ። መቆዬት መልካም ነው የምለው ኢትዮጵያን ለማዬት ካበቃ ብቻ ነው ለእኔ።
የዕንባ ቋሚ ጠበቃ መዳህኒዓለም ብቻ ነው።
እልፍ ነና እልፍነታችን እልፍ እናድርገው – በተግባር!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
የፓልቶክ ቦለቲከኞችን ማን ሃይ ይበለን (ቶኩማ አሸናፊ)
የፓልቶክ ታዳሚ ነኝ ። ሃሳቤን በፓልቶክ ክፈሎቸ ማሰተላለፍ አይከብደጘም። ግፋ ቢል በቀይ መታሰር ሲበዛም ( ባውንስ) ሃሳብን በቁም መግደል አለበለዚያም ወያኔ ደርግ ጽንፈኛ አድርባይ ሻቢያ ግነቦት 7 ኦነግ ጎሰኛ ብቻ አንዱን ስም ተለጥፎብኝ እንደምወጣ ሂደት አስተምሮኛል። የፓልቶከ ቦለቲካ ያስተማረኝ አንዱ መጥፎ ገጽታ ነው።በፓልቶከ ክፍሎች አንዳንዴ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሲጠፋ የተለያዩ መጣጥፎቸን ማንበብ የተለመደ በመሆኑ እራሳቸውን አጀንዳ ለማድረግና ምናልባትም ጊዜና ጉልበታቸውን ገንዘባቸውንም ጭምር መሰዋእት በማድረግ ለትግሉ አስተዋጽኦ ለማድረግ ደፋ ቀና ለሚሉ ወገኖቼ እራሳችንን እንድናይና የሳይበሩን አለም በተሻለ መንገድ እንድንጠቀምት ለመገፋፋት በብእሬ ትንሸ ለመኮርኮር ተነሳሳሁ። ማይክ የቸበጠ ሁሉ ወይም በሎቢ ላይ ቃላት የወረወረ ሁሉ ፖለቲክኛ በሚመስልበት የፓልቶከ መድረክ ቦለቲከኛውን ከፖለቲከኛ መለየት አስፈላጊነቱ ወቅታዊ ነው።
በመጀመሪያ ፖለቲከኞች የምላቸው በኣንድ ህበረተሰብ ውስጥ የሚታዩትን ፖለቲካዊ አኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት የፖለቲካ ስርኣቱን ለመለወጥ ወይም ለማሻሻል በግንባር ቀደምትነት የተሰለፉና ኣላማቸውንም ለማስፈጸም በጠራ የፖለቲካ ኣስተሳሰብ የታነጸ መነሻና መድረሻ ባለው የፖለቲካ ኣጀንዳ ስር የተሰባሰቡ ግለሰቦችን ነው፤፤ የፖለቲካ ስራ የሚሰራውም የማንኛውም ስርኣት ኣንቀሳቃሽ ህዝብ በመሆኑ ፖለቲከኞች ከህዝብ ጋር ያላቸው ግንኙነት ወሳኝ ነው።
ለዚህ መነሻ ሃሳብ ያነሳሳኝ ከጊዜ ወደጊዜ አየዘቀጠ የመጣው የዲያስፖራው በተለይም የሳይበሩ ኣለም “ቦለቲከኛ” መብዛት ነው፤ ቦለቲካ የሚለውን ቃል የሰማሁት ድሮ ልጅ ሆኜ በጣም ብዙ የሚያወሩና የሚያወሩት ነገርም እውነትም ዪሁን ውሸት ነገር ግን ሌላውን ለማሳመን የሚጠቀሙበት ቁዋንቁዋ የኣድማጭን ቀልብ የሚስብና ሃሰቱን እውነት እውነቱንም ሃሰት ኣድርጎ የማቅረብ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች” እሱ እኮ ቦለቲከኛ” ነው ሲሉት ትዝ ይለኛል።
ታዲያ ዛሬ ቴክኒዎሎጂ በፈጠራቸው የመገናኛ ብዙሃን በደምጽ በሚሰሙት ራዲዮ ቴለቭዥን ፓልቶኮች በኣንድ ጊዜ በበዙ ሰዎች ሰለሚደመጥ ቦለቲከኞችን ከፖለቲከኞች ለመለየት የተቸገርንበት ለመሆኑ በእርግጠኝነት ለመናገር ይቻላል ፡፡ መነሻዬ የዲኣስፖራው ፖለቲከኞች መድረክ የሆነውን ፓልቶክ ክፍሎችና ተዋንያን ቦለቲከኞችን በመሆኑ በዚሀ ጽሁፌ እሱ ላይ አተኩራለሁ።
አሁን ባለንበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚጠነሰስበት የሚፈጭበት የሚጋገርበት መድረክ ፓልቶክ ሆኖኣል ማለት ይቻላል። የሃገሪቱ ባለስልጣናት ወያኔ ኢሃደግ ደጋፊዎች ኣባላትም ጭምር ጀምሮ ተቃዋሚ ነን የሚሉ የፖለቲካ ድርጅች መሪዎች ተገንጣዩም አስገንጣዩም ኣንድነት ባዩም ጠባቡም ትምክህተኛውም ኣፍቃሪ ሃይለስላሴና ደርግ ስርኣቶችም ጭምር በኣጠቃላይ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ የዲያስፖራውም ሆነ የሃገር ቤቱ ፖለቲከኛም ቦለቲከኛም የሚሳተፍበት ዋነኛ መድረክ ሆኖኣል ፥፥ በፓልቶክ ከፍሎች የእምነት የማህበራዊ ጉዳዮች የፖለቲካ ተደማምሮ ከ ሶማሊያ ቀጥለን በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምንገኝ የመሆናችን ምክንያቱ ብዙ ምርምር የሚያስፈልገው ሳዪሆን የብዙ ፈርጅ ችግርተኞች አንደሆንን የሚያረጋግጥ ነው፥፥ የሁዋላ ቀርነት መለኪያም ነው፤፤ የዲሞከራሲ እሴት ደሆች መሆናችንም ነው ፥፥ ዝብርቅርቅ ታሪክ ኣስተሳሰባችን ላይ የቀረጸው ዝብርቅርቅ ኣመለካከት ነው ፥፥ ይህ ራሱን የቻለ ርዕስ ስለሆነ ወደፊት በሰፊው ለማሳየት እሞክራለሁ፥፥የኣሁኑ ተኩረቴ ግን የፖለቲካ ከፍሎችን ነው፥፥
ለፖለቲካ መወያያ መድረክነት የተፈጠሩ ከፍሎችኣደረጃጀት የተለያየ ነው፥ እንደሃገር ቤቱ በቈዋንቁዋ ላይ የተመሰረቱ ክልሎች በስም ጭምር የኣሮሞ የትግሬ የኣማራ የሃረሪ ወዘተ የክልል ፓልቶኮች
በሃሳብ ከኢትዮጵያ ተገንጥለው ነጻ መንግስት የመሰረቱ ክፍሎች ሚኒለከ ጅኖሳይድ
የስርኣቱ ዋና ደጋፊ የሚባሉ የሚታወቁ እንደ ገዛ ተጋሩ Eprdf ካናዳ ኢትዮ ሲቪሊቲ በግልጽ የሚታወቁ
በተቃዋሚች በኩል የተወሰኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ኣስተሳሰብ የበላይነትን የያዙባቸውና በርካታ የድርጂት ደጋፊዎችን ያቀፉ ዲሞክራሲ በገደብ የሚሉ
እንደ ኢካዲኤፍ ( ግንቦት ፯ ደጋፊዎች የሚበዙበት)
ቃሌ ( መድረክ መኢኣድ ኢዴፓ ኢህአፓ ደጋፊዎቸ የተደበላለቁበት )
EFND (ኢህአፓ) የመሳሰሉ
በሌላ በኩል የሁሉንም ኣስተሳሰብ እናንሸራሺራለን የሚሉ ነገር ግን ኣብዛኛው ስርአቱን ሂሳዊ ድጋፍ እንሰጣለን በሚል የተዋቀሩ በፖለቲካ የሃይል አስላለፍ መመዘኛ ግን የሰርኣቱ ደጋፊዎች ጎልተው የሚታዩባቸው እንደ ቅንጂት ስዊዘርላንድ ፡ ኢትዮ ዲኣስፖራ አይነቶችና በመጨረሻም ተጀምሮ አስከሚጨረስ ተቃዋሚንት እነጂ የት ነው ያሉት የሚያስብልና የስድብ ትምህርት ቤት ይመስል የነበረው ደብተራ ክፍሎች (አሁነ ግን ስድበ ተቅንሶአል)
በየክፍሎቹ ውስጥ የሃገራቸው ጉዳይ የሚያንገበግባቸው ነገር ግን ሃሳባቸው የበላይነትን ይዞ ያልወጣና ኣሰባሳቢ ኣመለካከት ስር ያልሰደደ በመሆኑ በድምጻውያን ቢዋጡም በርካታ ቅን ዜጎችና በሃሳብ የበሰሉ ዜጎች ለፓልቶኩ ፖለቲካ ዉበት ናቸው ። እጂግ በዝተው የሚታዩት ግን ቦለቲከኞች ናቸው፥፥
የቦለቲከኞቹን መገለጫ ከማየቴ በፊት ስለ ክፍሎቹና የኣንዳንድ ቦለቲከኞች nick name ትንሽ ልበል፥፥ ኣብዛኛዎቹ የፓልቶክ ከፍሎች ስምና ማነነታቸው ኣይጣጣምም ፥፥ ለምሳሌ ኢካዴፍ ቃሌ ቅንጂት ስዊዘርላንድ ደብተራ ሊክስ ሞረሽ ጀኖሳይድ ወዘተ ስማቸውና ውስጣዊ ማንንታቸው የተለያዩ ናቸው።
የፓልቶክ ታዋቂ ስሞች ለምሳሌ ኣባመላ፡ ሎሬት ጸጋዬ፡ ደብተራው የመሳሰሉ ስመ ጥር የሃገራችን ታላላቅ ሰዎች ስም ሲሆን ስሙን የያዙት ሰዎችና የፓልቶክ ባህሪያቸው ፈጽሞ አይገናኝም ፥፥ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን በስሙ የሚቀርበውን ፓልቶከኛ የስድብ ቃላት ከሞት ተነስቶ ቢያዳምጥ ፊታውራሪ አባመላ በዘመናችን የፖለቲካ መለኝነት ምን እንደሚመስል ቢሰሙ ተመልሰው መሞትን ይናፍቁ ነበር፥፥ የፓልቶክ ፖለቲካ የበሺታ ምንጭ ሃላፊነትና ተጠያቂነት የጎደለው በውጭ እየኖረ ሃገር ቤት ያለው ጥቅም የሚነካበት የሚመስለው በኮምፒውተር ጀርባ ያለ ፈሪ ቦለቲከኛ ነው።
ወደ ዋናው ነጥብ ልመለስና በእኔ እምነት የፓልቶክ ቦለቲከኞች መገለጫ
፤ እውነትን ሽምጥጦ መካድና ሃሰትን እውነት ኣስመስሎ የማቅረብ ችሎታ
፥ የፖለቲካ ግጭቶችን ልዩነቶችን ፍጹማዊ ማድረግ 100% መደገፍ ወይ መንቀፍ
፤ በመሰረታዊ ጥያቄዎች ፕሪንስፕልስ ላይ በየጊዜው ተገለባባጭ ኣቍም መያዝ (ኣካሄድ ሊለዋወጥ ይችላል
፤ የውይይት ቁዋንቋቸው (ቶን) የማያደርጉትን የሚያደርጉ መስሎ መቅረብ
፥ ፥የኢትዮጵያ መጻኢ እድል ወሳኝ ሃይሎች ሆኖ መታየት ብቸኛ ኣክቲቪስት ተንታኝ መስሎ መታየት
፤በፓልታልክ ኣበባ የሚፈነድቁ ለራሳቸው የሚሰጡት ግምት የተቆለለ ቦለቲካ መሆኑ ኣበባ ባዩ ቁጥር ደምጻቸው ከፍ እያለ የሚሄድ የሎቢ ጉበኞች
፤ የኣስተሳሰብ ድሀነትን በስድብ ባለጸግነት ለማካካስ የሚፈለጉ ስድብና ፖለቲካ የተቀላቀለባቸው
፥ ያነበቡትን ሁሉ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ መደንቀር የሚፈልጉ ከነባራዊ ሁኔታ የተፋቱ
፥ ሌላው በተናገረው ላይ ብቻ ለመናገር ማይክ ለመያዝ የሚሽቀዳደሙ የራሳቸው ምንም ግባት የሌላቸው
፤ የፖለቲካ መሰረቱ ህዝበ መሆኑን ያልተረዱ በህዝብና በፖለቲካ ድርጅት መካከል ያለውን ኣንድነትና ልዩነት ለመገንዘብ የማይፈልጉ ዘረኛ ሆነው ዘረኝነትን የሚያወግዙ የ ጎሳ ፖለቲካን በኣፍ የሚጠየፉ ነገር ግን ወሳኝ ነገር ሲመጣ የዘር ጉዋዳ የሚያንጎዳጉዱ።
፤ ስለ ዲሞክራሲ ስለፍትህ ስለ እኩልነት የሚሰብኩ በተግባር ዲሞክራሲን የሚገሉ ፍትሃዊ ወይይትን የሚገድሉ እኩልነትን የሚንዱ
እነዚህ በፓልቶኩ ፖለቲካ በየትኛውም ክፍል የሚታዩ የቦለቲካው መገለጫዎች ናቸው፤፤ ኣንዳንዱ ብዞዎችን ባህሪያት ያሙዋላል አንዳንዱ በተወሰኑት ስር ይወድቃል፥፥ ፖለቲከኛ ሳይሆኑ ቦለቲከኞች ይበዛሉ ያልኩት ከዚህ በመነሳት ነው፥፥ሽፋኑ ደግሞ ሃገር ወዳድነት ነው፤፤ በእርግጥም ብዙው ሃገሩን ይወዳል ያፈቅራል ። ታዲያ መውደድና ማፍቀር በኣግባቡ ካልተያዘ ኣደጋም እንዳለው መረዳቱ ደግሞ ኣስፈላጊ ነው፥፥ ብዙ ኣፍቃሪዎች ፍቅረኞቻቸውን ገድለው ለምን አንደገደሉ ሲጠየቁ ስለሚያፈቅራቸው መሆኑን ይናገራሉ ። የነሱ ብቻ እነዲሆኑ ስለሚፈልጉ። የአንዳንዶቻችንም የሃገር ፍቅር እንደዚያ ይመስላል። ሃገርን በግል ኣፍቅረህ በግል ችግርዋን ኣትፈታም፥፥
ዛሬ የደረስንበት የፓልቶክ ፖለቲካ ደግሞ ቅጥ ኣምባሩ የጠፋ ሆኖኣለ ፥፥ በተለይ የሲቪሊቲ ባለቤትና በፓልቶክ የሚታውቀው ቦለቲከኛ ኣባ መላ(ለጊዜው የፓልቶክ ስሙን እጠብቅለታለሁ የፓልቶክ መጠሪያው ነውና ) በ ፓልቶልክ ፖለቲካ ውስጥ እራሱንም እየገነባ የፓልቶክ ታዳሚውም እየገነባው መጥቶ እነሆ በራሱ ቦለቲካ ሆኖኣል፥፥ የግለሰቡን ማነነት ወይም ሰብእና ቁመት ውርደት ሆድ ኣፍንጫ መነጸር ወዘተ ወይም የጥንት ማንነቱን ለመመርመር ከአንድ ወር ቦለቲካ ሆኖኣል፥፥በበኩሌ ፖለቲከኛ ሳይሆን ቦለቲከኛ ለመሆኑ በመመዘኛዎቼ ኣስቀምጬ ኣብዛኛውን መስፈርቶቼን ከሚያሙዋሉት ኣንዱ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል ፥፥ እስቲ እያንዳንዱ እራሱን ይመዝን፥፥ ሰለኣባመላም ወር የፈጀ ውይይት የሚያደርጉ ወገኖቼንም በዚሁ መመዘኛ ኣስቀምጡዋቸው፥፥
የኣባመላ የኣቋም ለውጥ በኣንድ የፖለቲካ ድርጅት ቢሆን የኣቁዋም ለውጡን መመርመር በሱም ላይ ጊዜ ማጥፋት የተገባ ነው፥፥ ምክንያቱም ሃገርን እንመራለን የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ኣቍዋም ለውጥ በሃይል ኣሰላለፍ ላይ ትልቅ ጫና ስለሚያሳርፉ በፕሮግራማቸውም ጭምር ሚዛን ስለሚቀይር ነው፥፥ የሲቪሊትይ ኣቋም ለውጥ ወይም የኣባመላ ኣቋም ለውጥ ከዲያስፖራው ቦለቲካ ኣልፎ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል የሚል ኣመለካከት ካለ ኣሁንም የቦለቲከኞች ችግር ነው የሚሆነው:: እዚህ ላይ ኣባመላን ያነሳሁት የወቅቱ የሳይበሩ ቦለቲካ ሰለሆነ፡ አበመላም ከአርብ እስከእሁድ ታዳሚውን በራሱ ቦለቲካ ዙሪያ ደፋ ቀና እያለ የትላንት ሰዳቢዎቹን የማሰባሰብ ዘመቻ ስለ ያዘ ነው ።
በበኩሌ ኣባመላ ኣቋም ለውጫለሁ ያለባቸውን ፍሬ ጉዳዮች ትላንትም የምደግፋቸው ዛሬም አንዲራመዱ የምፈልገው ነው።
፩፡ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ያለመደራደር
፪፥ የሻቢያን ቀንደኛ ጠላትነት ማወቅ
፫፥ ለሃገር የሚጠቅም ልማትን የፖለቲካ መጠቀሚያ ኣለማድረግ።መሰረተ ሃሰቡ እሰማማዋለሁ ወያኔ ኢሃዴግ ልማት ልማት ሰልሚል ተቃዋሚ ከሆንኩ የልማት ተቃዋሚ መሆን ኣለብኝ ወይም
ተቃዋሚነት ምንም ዪሁን ምን የምትቃወመውን መቶ በመቶ መቃወም አለብህ የሚል ጨለምተኛ አመለካከት የትም አያደረሰንም።
የሰርአቱ ደጋፊዎችና አባመላም ጭምር አንድ ሰሞን መለስ ማለት አባይ ነው፡ ራእዩ ነው ብለው በአባይ ስም መለስን ከነምናምኑ እንድንደግፈው ሲያደርጉት የነበረው ፕሮፓጋንዳ አልሰምር ሲል አሁን ደግሞ አባይን አለመደገፍ የግብጽ ወዳጅ መሆን ነው በሚል ተራ ፐሮፓጋነዳ ተተክቶአል።
የኣባይ ጥቅም ላይ መዋል ከጥንት ነገስታት ጀመሮ የህዝብ ፍላጎት የነበር በአጼ ሃይለ ስላሴ
በሎኔል መንግስቱም አባይን ለመገደብ ፍላጎቱና ምኞቱ አልነበረም ማለት አይደለም።
በርግጥም ብሄራዊ ጥቅማችንንና ፖለቲካውን እንዴት እንደምናጣጥመው በወያኔ አኢሃዴግ ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ ተቃዋሚ ሃይሎችም ችግር አለ። የፖለቲካ ስልጣን ጥያቄ ብሄራዊ ጥቅምን ጭምር የሚገዳደረው ከሆነ አጥፊ ፖልቲካ ነው። አንዱና ዋነኛው ስርአቱን ምንቃወምበት ለ ፖለቲካ ስልጣን ብሎ የሃገሪቱን ጥቅም አሳልፎ ሰጥቶአል የምንለው። ታዲያ በዚሀ ረገድ ተቃዋሚው የአባይ መገደብ ላይ የሚታዩ ቴክኒካዊ ችግሮችን ከዘላቂ ብሄራዊ ጥቅም ጋር አለ ማጋጨት ተገቢ ይመስለኛል። በሌላ በኩል የአባይን ቦንድ መግዛት ይጠቅመኛል ያለ ሊገዛ ያልጠቀመው ሊተው መብቱን ማክበር ተገቢ ይመስለኛል። ምክንያቱም ከብሄራዊ ጥቅም ባሻገር ከአንቨስትመንት ጋርም የተያያዘ በመሆኑ ነው፥፥ኢንቨስትመንት ደግሞ በፓልቶክ ወይም በፖለቲካ ድርጅቶች የሚወሰን ሳይሆን ግለሰቡ ያዋጣኛል ያተርፈኛል በሚለው መስክ ነው ኢንቨስት የሚያደርገው። ኣሜሪካ ውስጥ ቤት ገዝቼ ኢንቨስት ኣደርጋለሁ የሚል ኣሜርካ ኢንቨስት ማድረጉን ለማንም አንደማያማክር ማለቴ ነው፥፥ ጉዳዩን ወያኔ ኢሃዴግ ቦለቲካ ሲያደርገው ፤ እኛም ቦለቲካ ኣናድርገው ነው፥፥ ይህ ማለት የወያኔ አሃዴግን ጩሀት ኣብረን እንጩህ ማለት ኣይደለም ፥፥
ብሄራዊ ጥቅምን ወይም ውያኔ ኢሃዴግ የስልጣኑ ዋና ማራዘሚያ የሆነውን የብሄረሰብ ችግር ወደ ጎሳ ፖለቲካ ለጥጦ ጥዋትና ማታ ብሄር ብሄረ ሰብ ስለሚል በመሬት ላይ ያለውን ችግር በመካድ የብሄረ ሰቦችን ችግር ማንሳት አያስፈልግም የሚል ወይም ያነሳን እንደ ዘረኛ መቁጠር አንድነትን ያመጣል ማለትም አይሆንም። የተጠቀሱትን ነጥቦች ያነሳሁት አባ መላን ቦለቲካ ለማድረግ ሳዪሆን አባ መላ በነዚህ ጥያቄዎች ዙሪያ ማለትም
የሻቢያን ጠላትነትና ወዳጀነት
የልማትና እድገት ጥያቄ ክዚሁ ጋር የአባይ መገደብ አሰፈላጊነት ክብሄራዊ ጥቅም አንጻር ማየቱንና የብሄራዊ ጥቅም አጀንዳ ደግሞ በየጊዜው ምትቀያይረውና ከፖልተካ ድርጂቶች ጋር በሚኖር ጸብና ኩረፊያ ላይ የተመሰረተ አቅዋም አለመሆኑን ለማሳየት ነው። አባ መላ የሚወቀስበትም የብሄራዊ ጥቅም አጀንዳን አንደፈለገ ማሽከርከሩ የኣባይ መገደብን እንደ ፈለገ ሲቦተልክበትና የብሄረ ሰብ ጥያቄና ቺግሮቹን የተለያየ ኣቋም መውሰዱ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የተቃዋሚወን ጎራ ኣስተካክለዋለሁ በሚል ኣጉል ጀብደኝነት የተለያዩ የፖለቲካ ኣጀንዳዎች ለምሳሌ የኣማራውንና የኦሮሞውን ኢሊት አስታርቃለሁ; አለም አቀፍ የተቃዋሚ ግራስ ሩት እመሰርታለሁ ;የኣለም ኣቀፍ አርዳታ ቡድን ቃለኣቀባይ ሆኜአለሁ በሚል ተስፈንጣሪ ፖለቲካና የራስ መካብ ቦለቲካ ውስጥ ተዘፍቆ የፓልቶክ ቦለቲከኞቺን እያንጫጫ ያለው ።
ሌላው አባመላ ወስጃለሁ የሚለው አቅዋም ወደመሀል ፖለቲካ መጥቻለሁ
የሚል ነው:: ወደመሀል ፖለቲካ መምጣትና ወደነበሩበት አቁዋም መመለስ ይለያያሉ። የመሃል ፖለቲካ ለሀገራችን ይበጃል የሚል እምነት ካላቸው ወገኖች አንዱ ነኝ። አገራችን ካለቺበት ወሰብሰብ ቸግር ልተወጣ የምትችለው ጫፍና ጫፍ የተጣረዘ ፖለቲካ ሳይሆን የብሔራዊ መግባባት ፖለቲካ መስፈን አማራጭ የሌለውና ወደመሀል መምጣት ከሁሉም አቅጣጫ ሊበረታታ ይገባል የሚል አምነት አለኝ ወደመሀል ሰንተር ፖለቲክስ መምጣት ማለት ግን በነባራዊ አውነታዎች ላይ ተመርኩዞ ያሉትን የተለያዩ ቅራኔዎች ቅደም ተከተል አስቀምጦ በሂደት ሊፈቱ የሚችሉትን ጊዜ ሰጥቶ ከሁሉም በላይ መፋጠጥን አስቀርቶ የመቻቻልና ተፋላሚ ቡድኖች ሁሉ ተጠቃሚ የሚሆኑበት መፍትሄ ማቅረብ እንጂ አንዱን ደግፎ ሌላውን በመርገምና በመኮነን ላይ ያተኮረ ፖለቲካዊ አካሄድ አይደለም :: አባመላ ሲፈልግ ተቃዋሚውን ሃይልና ግለሰቦችን ሲፈልግ መንግስትና ደጋፊዎቹን ሰብእና የጎደለው ተራ ስድብ እያወረደ ለዲያሰፖራው የፓልቶክ ቦለቲከኞችና ፓልቶክን መደበሪያ ላደረጉ ብቸኞች መዝናኛ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም።
ከዚሁ ጋር ሌሎች ቦለቲከኞቻችን ወደመሀል መምጣትን ከግራ ዘመሙ የፖለቲካ አስተሳሰብ በተቀዳው አድርባየነት ስፈርጁት ይታያሉ :: ዓለም በተለያዩ ቅራኔዎች በተወጠረችበት በዚህ ዘመን ፖለቲካዊ ቅራኔዎችን ለማርገብና በተለያየ መልኩ ሴንተር አቅዋም አንደመሳሪያ ሆኖ ያገለግላል :: በፖለቲካ የተነሳ የብዙ ሕዝብ ህይወት የሚቀጥፉ ፖለቲካዊ ችግሮችን መፍቻ
አንዱ ዘዴ ነው ።ይህም አቅምን ለመገንባትና የሃሳብ የበላይነትን ለመያዝ የሚያስችል አትሞስፈር መፍጠር ማለት ነው ። ወደ መሃል መምጣት” ምን ተቃዋሚ አለና” እየተባለ አይደለም። ቀስ በሎ ወደ ነበሩበት ለመመለስም መሸጋገርያ መንገድ ሊሆን አይችልም።
ሰለዚህም አባ መላ የስርአቱ ደጋፊ ነኝ የማለት መብቱ የተጠበቀ ሲሆን የፖለቲካ
ተርሚኒዎሎጂዎችን ይዘታቸውን ለራስ እነዲጠቅሙ በመመጠን ግራ የተጋባወን የድአስፖራ የፓልቶክ ቦለቲከኛ ማስጨብጨብ ከተራ ፕሮፓጋንዳ ውጭ ሊሆን አይችልም ።
ከላይ የውቅቱ የፓልቶክ ቦለቲካ ምን አንደሚመስል አንዱን ክስተት ብቻ በመሰረታዊ ጥያቄዎች ዙርያ ለማሳየት ያህል አንጂ ሰለአባመላ ብዙ ለመጻፍ ፈልጌ አይደለም :: የችግሩን ተጠያቂነትም ለአባመላ ለመስጠት አይደለም።የሚወራው ሰለአባመላ ሆድና ቁመና ሰለ ቀድሞ ማንነቱ ከመሆኑም በላይ ፓልቶከኛ ተቃዋሚው ትግሉን ወዴት እየወሰደው ነው ? የሚለው የዝቅጠት ፖለቲካ እነዲያቆም ለመገፋፋት ነው። ከሁሉም በላይ የስርአቱ ደጋፊዎች ምን ያህል እንደወረዱ የሚያሳየው ተመለሰልን ብለው የተፉትን ምራቅ ለመላስ አንድ ሳምንት ጊዜ እነኩዋን ለአባመላ የማሰቢያ ጊዜ አለመስጠታቸው ነው፡፡ ቦለቲካ ማለት ይህ ነው።
የፓልቶክ ቦለቲከኞች አስደናቂ ባህርይ አባመላን በሀሳብ ዙሪያ ሳይሆን ልክ የአባ መላ የአቀራረብ ባህሪይ ያለው የአራዳ ልጅ ተፈልጎም ይሁን ራሱ ፈልጎ ስለ አባመላ ህይወተ ፖለቲካ በአራዳ ቁዋንቁዋ ከ800 በላይ ቦለቲከኞች ቁጭብለን ሰናዳመጥ አጃኢብ ያሰኛል :: በርግጥ በተነሱት የአቅዋም ጥያቄዎች ላይ አጀንዳ ይዘው የተወያዩ ከፍሎች የሉም ማለት አይደለም : በእንዲህ አይነቱ ውይይት ላይ የሚሳተፉት እድምተኞች ግን ቁጠራቸው በጣም ትንሽ ነው :: ይሄም የሚያሳየን ዲያሰፖራው ፓልቶክን የመማሪያና የሃሳብ መለዋወጫ ለትግሉና ለሀገርም የሚበጁ የሃሳብ መፍለቂያዎች ከመሆን ይልቅ የቦለቲካ ኮሜዲያን ማፍለቂያ መድረክ እንዳይሆን ከልባቺሁ ለለውጥ መሳሪያነት ለመጠቀም የምትፈልጉ ወገኖች በያላችሁበት እራሳችሁን ፈትሹ። እንፈትሽ።
በመጨረሻም ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አባባል ልዋስና ” ኑ እንዋቀስና ኢሃዴግን እናፍርሰው”
ቶኩማ አሸናፊ
ያልታሰረው ማን ነው?? (ከአንተነህ መርዕድ)
ሰሞኑን አንድ ኢትዮጵያዊ በቶሮንቶ የህሊና እስረኞችን ለመዘከር በግሉ አዳራሽ ተከራይቶ የአንዱዓለም አራጌን “ያልተሄደበት መንገድ” የሚለውን መጽሃፍ ለሽያጭ በአቀረበበት ቦታ ተገኝቼ ነበር። በዚህ አዳራሽ አንዱዓለምን፣ እስክንድርን፣ ርዕዮትን …ወዘተ ለመዘክር ብለው የተሰባሰቡ ሰዎች ብዛት ስመለከት “በእውነቱ እስረኞች እኛ ነን ወይስ እነ ዓንዱአለም?” የሚል ጥያቄ ጫረብኝ። አገርን ያህል ትልቅ ነገር ከራሳችን የፖለቲካና የግል ጠባብ ፍላጎት ዙርያ ቀንበበን ልንከተው ስንቸገርና አልሆንልን ሲል ደግሞ እርስ በርሳችን ስንጎነታተል አሁን አለንበት የመከራ ዘመን እንድንቆይ በራሳችን የፈረድን መሆኑ ግልጽ ይሆናል።
ትንሹን ህይወታቸውንና ጠባቡን የግል ፍላጎታቸውን በትልቁ ለሚያይዋት ኢትዮጵያ የሰውትን ወንድሞቻችንን ልናስታውስ በሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ ብዙዎቻችን በተረባረብንና የነሱን ከባድ መስዋዕት በትንሽ በትንሹ በተጋራናቸው ነበር። እውነቱ ግን ያ አይደለም። ለብዙዎች የእንቅስቃሴያችን ማዕከል ሁሉ “እኔ” ስለሆነ ከዚያ የተለየን ማውገዝ፣ ማደናቀፍ፣ አለመተባበር…ተግባራችን የሆነ ይመስላል።
አንዱዓለም እንዳለው ከዚህ በፊት ያልተሄደበትን የመቻቻልና የመከባበር መንገድ መጀመር የጊዜው ጠቃሚ እርምጃ ነው። ይህ ሁኔታ መጽሃፍ ቅዱስ ላይ የዮሃንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ቁጥር3 እስከ 11 “ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘች ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርስዋን አቁመው መምህር ሆይ ይች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴ እንደነዚህ ያሉትን እንዲወገሩ በህግ አዘዘን። አንተስ ስለእሷ ምን ትላለህ? አሉት።….ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በደንጋይ ይውገራት አላቸው።…እነሱ ይህንን ሲሰሙ ህሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ” ይላል። ከኛም መካከል ህሊናው የሚወቅሰው ካለ ከተሳሳተ ድርጊቱ መቆጠብ አለበት። በዚሁ መጽሃፍ ቅዱስ የሉቃስ ወንጌል ላይም “በወንድምህ ዐይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፤ በራስህ ዐይን ግን ያለውን ምሰሶ ለምን አትመለከትም?” ሲል ይደግመዋል። እያንዳንዳችን የምንከተለው መንገድ ትክክል ሊመስለን ይችላል። የሌሎችን ሆነ የእኛን ትክክለኝነት የሚዳኘው ተግባራችንና ጊዜ ነው። እስከዚያው ግን መከባበርና መተባበርን የመሰለ ትልቅ ነገር የለም።
ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት ሰዎች ሆነ ተራው ግለሰብ የራሳቸውን ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ስህተት ላይ ብቻ ማተኮር ሲጀምሩ የውድቀታቸው መነሻ ይሆናል። ማንም ሰው ሲሠራ ሊሳሳት ይችላል። መጥፎው ነገር ከስህተት አለመማር ነው። ስህተቱን በጸጋ የሚቀበልና የሚያርም ትልቅ ነው። በእስልምና እምነትም ሃዲስ ላይ (በትክክል መጥቀስ ባልችል ይቅርታ ይደረግልኝ) እንዲህ ይላል “የማያውቅ ሆኖ የማያውቅ መሆኑን ማወቅ የማይፈልግ ቂል ስለሆነ ሽሸው። የማያውቅ ሆኖ አለማወቁን የሚያውቅ ከሆነ ልጅ ነውና አስተምረው። የሚያውቅ ሆኖ አዋቂ መሆኑን የማያውቅ ከሆነ ቀስቅሰው፤ ተኝቷልና። አዋቂ ሆኖ አዋቂነቱን የሚያውቅ ከሆነ ጥበበኛ ነውና ተከተለው” የብዙዎቻችን ባህሪ ባንዱ ሁሉ የሚካተት ነውና ቦታችንን ማወቅና እርምጃችንን ማስተካከል የተገባ ነው። ስለሆነም የታሰሩ ወንድምና እህቶቻችን የተሸከሙት እዳ ከግላችንና ከቡድናችን ፍላጎት በላይ አገራዊ ስለሆነ ከመጎነታተል፣ ከመከፋፈል ወጥተን አገራዊ ስፋት ባለው አላማ ዙርያ በጋራ መቆም ይኖርብናል።
ወደ ተነሳሁበት ርዕስ ልመለስና “ኢትዮጵያ የብሄረሰቦች እስር ቤት ናት” የሚለው ለትናንቶቹና ለዛሬዎቹ ጠባቦች መንደርደርያ ማዕከላዊ ሃሳብ ቢሆንም ደጋግመው እንደሚናገሩት ይህንን ብሂል በሃቅ ለብሄር ብሄረሰብ ነፃነት አልተጠቀሙበትም። ያ ቢሆን ምንኛ በታደልን። ድርጊታቸው ግን ተቃራኒ በመሆኑ ኢትዮጵያን ወደ ገሃነምነት ቀይረዋታል።
በአምደጽዮን፣ በፋሲለደስ፣ በቴዎድሮስ፣ በዮሃንስ፣በምኒልክ፣ በሃይለስላሴ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ማበብ ነበረበት ብሎ የሚያስብ አእምሮ ቅንነት አለው ብለን አንጠብቅም። እነዚህ ነገስታት ግዛታቸውን ለማስፋት፣ በስልጣናቸው ላይ ለመቆየት ባደረጉት እንቅስቃሴ ጭካኔ የተሞላበትን መንገድ መሄዳቸው ግልጽ ነው። በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እናስተዳድራለን ብለውም አያውቁምና የሚጠብቅም አልነበረም። ዳኝነታቸው ርህራሄና ፈሪሃ እግዜብሄር ያለበት እንዲሆን ሁሌ ባያከብሩትም ይናገራሉ፤ ህዝቡም ይጠብቃል።
ዛሬ በትናንት ታሪክ ታስረን፣ ለዚያ የከፋ ድርጊት ከመካከላችን ተጠያቂ ፍለጋ ስንኳትንና አጽም ለማውጣት መቃብር ስንቆፍር የሁላችን መቀበርያ አዳዲስ መቃብር እየተዘጋጀልን መሆኑን ዘንግተናል። በተለይም በዴሞክራሲ ስም እየማሉ የገዙን ሁለቱ ስርዓቶች ማለትም ደርግና ወያኔ ካለፉት ነገሥታት በባሰና በዘገነነ ሁኔታ ጨካኞች ናቸው። አገሪቱንም ወደ ሙሉ እስር ቤትነት የቀየሯት እነዚህ አምባገነኖች ያለፉትን አገዛዞች በኮነኑበት አንደበት የራሳቸውን ትልቅነት ከመስበክ ወደ ኋላ አላሉም። በነዚህ አገዛዞች “ኢትዮጵያ የዜጎች ሁሉ እስር ቤት ናት” የሚለው ከፀሃይ የደመቀ ዕውነት ነው።
ይህን ዓለም ያወቀውን እውነት በመካድ የትናንቶቹ አምባገነኖች መንግስቱ ኃይለማርያምና ፍቅረስላሴ ወግደረስ የነሱ አገዛዝ ፍትህ የሰፈነበት፣ ዴሞክራሲ የሞላበት የሚያስመስል ስንክሳራቸውን አሳትመው እንደጲላጦስ እጃቸውን ሊታጠቡ ይዳዳቸዋል። ፍቅረስላሴ “እኛና አብዮቱ”ባለው መጽሃፉ ቢያንስ ለታሪክና ለህዝብ ክብር ትንሽ የቅንንነት ጥፍጣፊ እንኳ ጨምሮበት ‘ሰርተን ያለፍነው ስህተት ይህ ነበር፣መጪው ትውልድ ከእኛ ስህተት ተምሮ መልካም አገር መገንባት አለበት’ የሚል እውነት በመጠኑም ይዞ ይቀርባል ተብሎ ሲጠበቅ ለብቻቸው ያዝዟቸው በነበሩት ሠርቶ አደር ጋዜጣ፣አዲስ ዘመን፣ የዛሬይቱ፣ ሄራልድ፣ ሬድዮና ቴሌቪዥን ላይ ሲያደነቁሩን የኖሩትን ፕሮፓጋንዳ ሃያ ሶስት ዓመታት ሲያመነዥከው ቆይቶ ለህትመት ሲያበቃ የህዝቡንም የማስታወስ ችሎታ መናቁን አሳይቷል። ፍቅረስላሴ በእስር ባሳለፈው ሃያ ዓመታት ወደ ኋላ በትዝታ መለስ ብሎ የሄዱበትን መንገድ ሁሉ በመቃኘት ወደ እውነቱ ቀርቦ መገኘት ሲገባው ሲታሰር ተኝቶ ሲፈታ የነቃ ይመስል። የኢትዮጵያ ህዝብ ቀድሞ ያለፈበትን የመከራ ዘመን ሆነ አሁን እየደረሰ ያለበትን ጭቆና ዳግም እንዳይመለሱ በመታገል ላይ እያለ ፍቅረስላሴ ባንኖ በመንቃት ድሮ የጻፈውም ሜሟር እንዳለ ይዘምርልናል። “በማይጨው ጊዜ የደነቆረ ስለማይጨው ሲተርክ ይኖራል” እንዲሉ ስልጣን ሲለቁ እንደደነቆረና ከዚያ ወዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ በምን አስተሳሰብ ላይ እንዳለ ለመገንዘብ ያልታደለ መሆኑ እንድናውቅ ያደርጋል።
ፍቅረስላሴ አሁን ድረስ የሚያመልክበትና በፍርሃት የሚያሸረግድለት መንግስቱ ኃይለማርያም ብቸኛ አላማው የሆነውን የስልጣን ጥማቱን ለማርካት የህዝቡን ለጋ ወጣቶች ብቻ ሳይሆን በእድሜና በልምድ መከበር የሚኖርባቸውን አዛውንት ኢትዮጵያውያንን፣ ጓደኞቹን ሳይቀር ተራ በተራ ሲያርዳቸው ቆሞ ሲንቀጠቀጥ፣ ማረጃ ሰይፍ ሲያቀብል እንዳልነበረ የነሱን የፍጅት ዘመን ከወያኔ ጋር እያነጻጸርን እንድንናፍቀው በተዘዋዋሪ ሊነግረን ይሞክራል።
የኢትዮጵያን ጠላቶች በየፈፋው ያርበደበዱት እነጄኔራል ታሪኩ ላይኔ፣አማን አንዶም፣ አምሃ ደስታ፣ ፋንታ በላይ ….ወዘት ዛሬ ተርፈው የተንሸዋረረ ታሪክ ሊነግሩ እንዳሉት በፍርሃት አልራዱም። አምባገነኑን አምባገነን ነህ እያሉ ነው የሞቱት። ታሪካቸውን ራሳቸው ባይናገሩም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ያውቀዋል። ሲያከብራቸውም ይኖራል። እነሱንና አገሪቱ የገደሉት የታሪክ ዝቃጮች ስለሥራቸው ምን ቀለም ቢቀባቡ ማንነታቸውን ሊደብቁ አይችሉም።
ለመሆኑ የአስራ ሰባት ዓመቱ የ“እኛና አብዮቱ” ውጤት ምን እንዳስገኘ ፍቅረስላሴ ይዘረዝረዋል? ህዝቡንና አገሪቱን ቀፍዶ አስሮ ለወያኔና ለሻዕብያ ያስረከበው ማን ነው? “ወርቅ ሲያነጥፉለት ፋንድያ የሚመርጥ” ብሎ መንግስቱ ሃይለማርያም የሰደበውን ህዝብ አንተም በተጠያቂነት ታቀርበው ይሆን?
አዎ ኢህአፓዎች፣ መኢሶኖች፣ወዝሊጎች፣ ማልሬዶች፣ ሻዕብያዎች፣ ወያኔዎች፣ ኦነጎች…..በዚች አገር ውድቀት አውቀውም ሆነ ሳያውቁ አስተዋጾ ማድረጋቸውን ለማወቅ ህዝቡ የፍቅረስላሴንና የጓደኞቹን ምስክርነት የሚፈልግ አይደለም። ምንም እንኳ ይህ ነበር የኛ ድርሻ ለማለት ድፍረቱን ባያገኙትም ህዝብና ታሪክ የሁሉንም አስተዋፆ አይረሳውም።
ቀበሌዎችን፣ የጦር ካምፖችን፣ መኖርያ ቤቶችን፣ ትምህርት ቤቶችን ሁሉ ወደ እስር ቤትነት የቀየረ፣ ወላጆች የልጆቻቸውን አስከሬን ለመቀበል የተገደሉበትን ጥይት ዋጋ ያስከፈለ፣ አልቅሰው እርም እንዳያወጡ የከለከለ፣ አዛውንቱን ኃይለስላሴን ያለፍርድ ገድሎ መቃብራቸው ላይ መፀዳጃ ቤት የሰራ…ወዘተ ይህን ሁሉ ያደረገ የደርግ ስርዓትና መሪዎቹ የሌሎችን ያነሰ ስህተት የሃጢያታቸው መጠራረጊያ ፎጣ ሊያደርጓቸው የሚያስችል የሞራል ብቃት የላቸውም።
የመሬት አዋጅን እንደትልቅ ድል ደጋግሞ ማንሳቱም የሚገርም ነው። ብዙ ኢትዮጵያውያን የተዋደቁለ የመሬት ጥያቄ በደርግ ሆነ በወያኔ አልተመለሰም። አዋጁ መሬትን ከመሬት ከበርቴዎች ነጥቆ ገበሬውንና መሬቱን የአምባገነኖች ንብረት ነው ያደረገው። ወያኔዎችም ካባታቸው ደርግ ደህና አድርገው ተምረዋልና ኢትዮጵያዊ የመሬት ባለቤት የሚሆነው “በኢህአዴግ ሬሳ ላይ ነው” ሲል መለስ ዜናዊ ደምድሞታል።
ከገበሬው የወጣን ነን የሚሉት የደርግ አባላት ሆኑ ለገበሬው ቆሜያለሁ የሚሉት ወያኔዎች በካድሬዎቻቸው አማካይነት ንብረቱና ራሱን ገበሬውን የራሳቸው የግል እቃ፣ በቤቱም ውስጥ እስረኛ አድርገውታል። በህብረት እንዲያርስ የተገደደውና በችጋር የተጠበሰው የአርሲ ገበሬ “በናንተ ህብረት እርሻ ያተረፍነው በርሃብና በተባይ ማለቅን ነው” ብለው ብልቃት ሙሉ ቅማል ለደርግ ባለስልጣን ማሳየታቸውን በወቅቱ በቦታው የነበርነው ጋዜጠኞች ተመልክተናል። ይህን እውነት በአብዛኛው አገሪቱ ለሥራ በተዘዋወርሁባቸው ወቅት ባይኔ አይቻለሁ።
ደርግ የጀመረውን የአፈና መንገድ ወያኔዎች በረቀቀና በሰላ መልኩ ተጠቅመውበታል። የመሰረት ደንጋዩን ያስቀመጡላቸው ግን እነፍቅረስላሴ ናቸው። ወያኔ አገርን በመበተን ከደርግ የከፋ ቢሆንም የደርግን ዘመን የሚናፍቁ ካሉ የዚያ ስርዓት ተዋናዮችና ተጠቃሚዎች የነበሩ ብቻ ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከሁለቱም አምባገነኖች የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይገባዋል።
ወደ ተነሳሁበት የእስር ጉዳይ ልመለስና በደርግ ሆነ በወያኔ መታሰርን በተደጋጋሚ ቀምሼዋለሁ። ለምን ታሰርሁ ብዬ አልቆጭም። ከህዝቡ መከራ የተጋራሁበት እውነተኛ የህይወቴ ምዕራፍ ስለነበር ባሰብሁት ቁጥር መጠነኛ የመንፈስ እርካታ ይሰማኛል። ሁለቱም ስርዓቶች በጣም ፈሪዎች ስለሆኑ በጣም ጨካኞች ናቸው። የተማሩትንና ለስልጣን ተቀናቃኝ ይሆናሉ ያሉትን ማሰርና በግፍ መግደላቸው እንዳለ ሆኖ በሁለቱም ስርዓቶች የሰባና የሰማንያ ዓመት በጤና የደከሙ ከፊሎችም ዐይናቸው የታወሩ አዛውንቶች ያለፍርድ እስር ቤት ቀስ እያሉ በሞት ሲያሸልቡ አይቻለሁ። መደገፍያ ከዘራቸውን ማንሳት የማይችሉትን አዛውንትና ክፉና ደግ የማያውቁ ህፃናትን የስርዓታቸው ተቀናቃኝ አድርገው የሚባንኑ አምባገነኖች ናቸው ሁለቱም።
ያ ሁሉ መጨፍጨፍ፣ ያ ሁሉ እስር የደርግን ስርዓት ከመፈራረስ፣ መንግስቱን ከመፈርጠጥ፣ ጓደኞቹን እነፍቅረስላሴንና ለገሰን እንደበግ ከመጎተት አላዳናቸውም። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ወያኔዎች ግድያውን፣ እስሩን ካስተማራቸው ከደርግ በባሰ ሰልጥነው ውድቀቱንም እየወረሱት ነው። የተፈጥሮአቸው እድገት ጣርያ (ክላይማክስ)ላይ ደርሰው ቁልቁለቱን ጀምረዋል። የገነቡት ሁሉ እየተናደ እንዳይቀብራቸው ራስን የማዳን ጥድፊያ ላይ ተጠምደዋል። ይህ መንፈራገጥ ግን የበለጠ ሚዛናቸውን እያሳታቸው ቁልቁል ይወረውራቸዋል። ሲወድቁ በሚያደርጉት መንፈራገጥ ብዙ ጉዳት ማድረሳቸው ግን የተጠበቀ ነው። የወያኔ የአጥቂነት ጊዜ አልፎበት አሁን በመከላከል ላይ ተጠምዷል። ጅኒው ከጠርሙሱ ወጥቷልና መልሶ የመክተት አስማት የሚሠራ አልሆነም።
ታላቁ ሩስያዊ ደራሲ፣ የታሪክ ምሁርና የሶብየትን አምባገነንነት አጥብቆ ይተች የነበረው አሌክሳንደር ኢሳየቪች ሶልዝሄንጺን የሩሲያውያንን መከራ ለዓለም በሚገባ ካሳወቀባቸው በርካታ ሥራዎቹ ዘ ጉላግ አርፒላጎ የዘረዘራቸውን ስናነብ ደርግና ወያኔዎች ያንን እያነበቡ የፈጸሙ ይመስለናል። በአንደኛው ጽሁፉ “እኛ በሚሊዪን የንምቆጠር ሩስያውያን ሴቶችና ወንዶች ከቀን ቀን፣ ከዓመት ዓመት ራሳችንን ደፍተን ወደ እስር የምንጎተትበት ምክንያት ይህ ነው። የማስጠንቀቂያ ደወል አናጮህም። በጎዳናዎች ተቃውሟችንን አናሰማም። እንዲያውም በተቃራኒው በጎዳና ላይ በጓደኞቻችን ፊት ስንነዳ እኛ ግዞተኞች ምንም እንዳልተፈጸመብን ፊታችንን ቅጭም አድርገን አንገታችንን ደፍተን፤ እነሱ የነገ ግዞተኞችም እኛን እንዳያዩ ዐይናቸውን መሬት ላይ ተክለው እንተላለፋለን። ህዝባችን ይህንን ድርጊት ሂደቱን ሳያዛባ ተግባራዊ ማድረጉን ተክኖበታል። በብዙ ማሰቃየት የታጀበው ምርመራ ሲጠናቀቅ እኛ ትንንሾቹ አሳዎች መረባቸው ውስጥ ዋኝተን እንገባላቸዋለን። …ባህሩን የሞላን ጥሩ አሳዎች፤ የአጥማጆቻችንን መንጠቆ ጉሮሮአችን ውስጥ ለማስገባት የምንሽቀዳደም፤ እኛን በመጎተት እንዳይደክሙ ወደ ላይ ቀዝፈን የምንቀርብላቸው…..” እያለ ለአምባገነኖች የመከራ ማገዶነት ምንም ሳይንፈራገጡ ወደ ማረጃው፣ ወደ እስሩ የሚሽቀዳደሙ ሩሲያውያንን የሸነቆጠበት አነጋገር እኔንም እንዳለንጋ መንፈሴን ይተለትለዋል።
በአሁኑ ሰዓት በመደበኛ እስር ቤቶች፣ በጦር ካምፖችና በድብቅ እስር ቤቶች የሚማቅቀውን ኢትዮጵያዊ ቁጥር ማወቅ ይከብዳል። በደፈናው እኛና ዓለም የሚያውቃቸው ደፋርና ለዴሞክራሲ ስርዓት ማበብ ከፍተኛ መስዋዕት በመክፈል ላይ ያሉትን አንዱዓለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ፣ አቡበከርና ጓደኞቹ ……እያልን ብንዘረዝር ቁጥራቸው የትየለሌ ነው።
እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው በአካል የተገደቡ እስረኞች ናቸው ብንልም በመንፈስ ልዕልና ያላቸው ንፁሃን ናቸው። በእኔ አስተያየት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ቀሪው ኢትዮጵያውያን ነን እስረኞች እላለሁ። እስክንድር፣ አቡበከር፣ ውብሸት፣ ርዕዮትና አንዱዓለም በአካል ከታሰሩበት ወህኒ ዘልቀው በመንፈስ ነጻ መሆናቸውን አሳውቀውናል። ያሉበትን መከራ እንደ ኢምንት በመቁጠር የምንከፍለው ቀላል ነው እያሉ ምንም ለመክፈል ያልተዘጋጀነውን፣ ከዳር ቆመን በፍርሃት የምንርደውን ህሊናችን እንዲሞግተን በመተው ባለ እዳ አድርገውናል።
ርዕዮት፡ “በኢትዮጵያ ፍትህ ማጣትና ጭቆና የተንሰራፋ በመሆኑ ለህይወቴ አዳጋ ይኑረውም አይኑረው ለእውነት እቆማለሁ” ብላለች። ይብላኝ ለእኔና ለእናንተ ዳር ለቆምነው።
አንዱዓለም፡ “ያልተሄደበት መንገድ” በሚል ርዕስ ከእስር ቤት ጠባብ ክፍል በጻፈው መጽሃፉ “እስር የስቃይ ብቻ ቢሆንም ከነፃነትና ከዴሞክራሲ እጦት አይከብድምና በጸጋ መቀመል ነበረብኝ” ሲል የአካል ስቃይን ፈርተን ህሊናችንን ለአሰርነው አማራጩን ይነግረናል። ከዚያም አልፎ “ይህ ሁሉ የመከራ ሸክም የማን ነው? የታሳሪ ፖለቲከኞች ብቻ ወይስ የነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን ሁሉ?” በማለት የፍትህና የነፃነት ናፍቆታችን አፋዊ በመሆኑ ህሊናችን እንዲወቅሰን ጥያቄውን ወረወረልን።
እስክንድር፡ ሰሞኑል ለልጁ (ርዕሱ ለልጁ ይሁን እንጂ መልዕክቱ ለእኛ ነው) ከእስር ቤት በፃፈው ደብዳቤ “በጣም ናፍቄሃለሁ። እናትህንም ጭምር። ስቃዩ አካላዊ ስቃይ ብቻ ነው የሚሆነው። የቤተሰባችን ስቃይ ለረጂም ጊዜ መከራ ከተሸከመው ህዝባችን ተስፋ ጋር የተቆራኘ ነው።ከዚህ የበለጠ ክብርም የለም።ስቃዩን ሁሉ በመቋቋም፣ የሚቻለውን ሁሉ ርቀት በመሄድ፣ማንኛውንም አቀበት በመውጣት፣የትኛውንም ባህር በማቋረጥ ነፃነት ላይ በመድረስ ጉዞአችንን ማጠናቀቅ አለብን። ከዚህ ያነሰ ትግል ህሊናን ማደህየት (ባዶ ማስቀረት)ነው” ሲል ጽናቱንና የምንሄድበትን እርቀት አመልክቶን “አምባገነንነት ፍርሃት የነገሠበት በመሆኑ መንግስታዊ ሽብር፣ እስራትና ማሰቃየት ዋነኛ ተግባሩ ነው። በዚህ መንገድ ግን ሁሉንም ህዝብ ማንበርከክ አይቻልም። ነገር ግን የተወሰኑ ሰዎችን የጥቃት ኢላማ በማድረግ ብዙውን ሰው በፍርሃት ማደንዘዝ ይችላሉ። በጥቁር ዓለም ጥንታዊ የመሆናችን የጋራ ኩራት ይህንን አስማት ለመጨረሻ ጊዜ እንድንሰብረው ያስገድደናል” ሲል በነሱ መታሰርና መሰቃየት ሩቅ ሆነን በፍርሃት ተሸብበን የታሰርነውን ሊፈታን ይታገላል።
ሌሎችም እስረኞች ደጋግመው በተለያዬ መልክ ያስተላለፉልን መልዕክት ይሄው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ህዝብ በአጠቃላይ እስረኛ መሆኑ ቢታወቅም ውጭ ያለነው እንኳ በፍርሃት፣ በራስ ወዳድነት፣ በክፍፍል፣ በመከነና የትም ባላደረሰን የትናንት አስተሳሰብና ከዚያም አልፎ በስሜታዊነት እስረኛ ነን። አንዱዓለም፣ እስክንድርና ሌሎችም የሚሉን ‘አሳሪ ሳይኖራችሁ ራሳችሁን ያሰራችሁ ራሳችሁን ነፃ አውጡና ትልቅ አገራዊ ዓላማ ይዘን አገር ነፃ እናውጣ’ ነው የሚሉን።
የጽሁፌ ማጠቃለያው ሁላችንም እስረኞች ነን።በመጀመርያ ራሳችንን ነፃ እናውጣ። ከዚያ የታሰሩ ወንድሞቻችንን፣ እህቶቻችንንና አገራችንን ነፃ ማውጣት እንችላለን።
ግለሰብ ሆኖ በህሊናው፣ ድርጅት ሆኖ በአሰራሩ ነፃነት ከሌለው ለነፃነት ቆሜያለሁ ማለት ከአፋዊነት አይዘልም። እስከ አሁንም የሆነውና ያየነው ይህንኑ ነው። ራሳችን ለራሳችን የነፈግነውን ነፃነት ከአምባገነኖች በልመና አናገኝም።
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ!
ጸሃፊውን በamerid2000@gmail.com ማግኘት ይቻላል
አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ የጥፋት ሐዋርያ ሲሆን
(ከአሌክስ አብርሃም)
ዛሬ ማታ ማለትም በ 20 /07/ 2006 ዓ/ም በሰይፉ ፋንታሁን እየተዘጋጀ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው ሾው ላይ የተመለከትኩት አሳፋሪ ድርጊት ይህን እንድፅፍ አነሳስቶኛል !
የሰይፉ እንግዶች አርቲስት አለማየሁ ታደሰ ፣ አርቲስት ግሩም ኤርሚያስና ኮሜዲያን ደረጀ ሃይሌ ነበሩ … (በዚህ አጋጣሚ ሶስቱንም እስከዚህ ጊዜ ድረስ የማከብራቸውና የማደንቃቸው አርቲስቶች መሆናቸውን እወቁልኝ ) እናም ሰይፉ ስለስራቸው ስለግል ሂወታቸው እየጠየቃቸው ውይይቱ ሞቅ ብሏል … (ወደ 33ኛው ደቂቃ አሳልፈው ያዳምጡት)
በመሃል ሰይፉ ቀለል አድርጎ አንድ ጥያቄ ለአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ አቀረበ
‹‹ በቀረፃ ላይ ላለ ፊልም የአንድ ‹ድራግ› ተጠቃሚን ወጣት ገፀ – ባህሪ ተላብሰህ ስትጫወት ድራግ ወስደህ ነበር ይባላል ..እውነት ውሸት ?
ሚሊየን ኢትዮያዊያን ወጣቶች ታዳጊወችና ህፃናት የሚያውቁት አርቲስት ግሩም ሚሊየኖች በሚመለከቱት ፕሮግራም ላይ እንዲህ ሲል መለሰ
‹‹እውነት !! ››
‹‹እንዴት ነበር አጋጣሚው ምንስ ተሰማህ›› ሰይፉ ጠየቀ
‹‹ በትወና ላይ ማስመሰል ሳይሆን ሁኖ መስራት የሚባል ነገር አለ… መምህሬ አለማየሁ ሊረዳኝ ይችላል (አለማየሁ በመስማማት ራሱን ነቀነቀ ) እናም በጭስ ተከልየ (?) የሚል ፊልም እየሰራን ነው … ቀረፃው ላይ የወከልኩትን ገፀ ባህሪ ወክየ ሳይሆን ‹ ሁኘ › ለመስራት ሃሽሽ (ድራግ) ወሰድኩ ..በቃ ጉልበቴ ተንቀጠቀጠ ዞረብኝ …..›› ሲል ሰፊ ማብራሪያ ሰጠ …
ይህን ፀያፍ ድርጊት እንደትልቅ የጥበብ ክስተት ማውራቱ ሳያንስ ጭራሽ በሃሽሽ ደንዝዞ መናገር ሁሉ አቅቶት ቀረፃ ላይ ባጋጣሚ የተወሰደውን ምስል በመሃል አስገብተው ያሳዩት ጀመረ … ይህ አሳፋሪ ቪዲዮ ታይቶ ሲያበቃ በአዳራሹ የታደመው ሰው ሞቅ ያለ ጭብጨባ ‹በሃሽሽ ደንዝዞ› ለታየው ‹‹አርቲስት ›› ለገሰ …..ሰይፉን ጨምሮ ! አለማየሁ ታደሰና ደረጀ ሃይሌን ጨምሮ !
1ኛ . በኢትዮጲያ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ (ኧረ በብዙ የአለማችን አገራት ጭምር) አደንዛዥ እፆችን መውሰድም ይሁን በማንኛውም መንገድ ማቀባበል ይዞ መገኘት ቁልጭ ብሎ የተቀመጠ ወንጀል እንደሆነ ሰምተናል ( በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን ) ይህን ፀያፍ ድርጊት አደባባይ አውጥቶ በትወናም ይሁን በሌላ ተልካሻ ምክንያት በሚሊየን ለሚቆጠሩ ወጣቶች ማሳየት ምናይነት ሃላፊነት አለመሰማትና ስርአት አልበኝነት ነው ?
2ኛ . አንድ ትልቅ እውቅና ያለው አርቲስት በርካታ ኢትዮጲያዊያን ተመልካቾች ባሉት ሾው ላይ በሃሽሽ ደንዝዞ ሲቀባጥር የሚታይበትን ቪዲዮ ማሳየት (ያውም እንደታላቅ ክብር በጭብጨባ ታጅቦ )የብሮድካስት ባለስልጣን መስሪያቤት …የኢቢኤስ ቴሌቪዥን አስተዳዳሪወች እንዲሁም የሾው ባለቤት ሰይፉ ፋንታሁንን የሚያስወቅስ (ጠያቂ ቢኖር በህግም የሚያስጠይቅ) ፀያፍ ተግባር ነው ! ምስሉን ካሳዩ በኋላ ‹‹ድራግ አይጠቅምም ጎጅ ነው ምናምን እያሉ ማውራቱም ቢሆን ከድርጊቱ በላይ ተፅእኖ የሚያሳድር ምክር አይደለም ) እዚች አገር ላይ ለትውልድ የሚገደው ማነው …የሚዲያወቻችን ስርአት አልበኝነትስ ሃይ የሚባለው በምን መንገድ ይሆን ?
3ኛ. በትወና ሰበብ ስክርቢቱ ላይ ድራግ መውሰድ ስለተፃፈ ስሜቱን ለመሞከር እና ‹‹መስሎ ሳይሆን ሁኖ›› ለመስራት ይህን ማድረጉ እንደአንድ የጥበብ መንገድ ከተወሰደ ( መምህሩ አለማየሁ ታደሰም ስላረጋገጠ) ወሲብ ነክ ስክርቢቶች ላይም ወሲብ መፈፀም ሙያዊ ፈቃድ ሁኖ ሊታይ ነው ማለት ነው ?
በዚህ አይነት አገራችን ላይ ከስር እንደአሸን የሚፈላው ፊልም ሰሪ ወጣት ሁሉ ‹‹መስሎ ሳይሆን ሁኖ›› ለመስራት በሚል ሰበብ ‹‹ወደ ፊልም ኢንዳስትሪ›› ሳይሆን ‹‹ወደብልግና ኢንዳስትሪ›› እንዲጎርፍ አንጋፋወቹ መንገድ እየከፈቱለት መሆኑን መታዘብ ይቻላል (አውቀውም ይሁን ሳያውቁ )
በአጠቃላይ ይህን ፀያፍ ድርጊት ለፈፀመው ግለሰብ …ምስሉን እንደደህና ነገር በጭብጨባ አሳጅቦ ላቀረበው የዝግጅቱ ባለቤት እንዲሁም ለህዝብ እንዲደርስ ላደረገው የቴሌቪዥን ጣቢያ ድርጊቱ ከእናተ የማይጠበቅ እጅግ የወረደና በ ሱስ አፋፍ ላይ የቆመውን በርካታ ወጣት ወደሱስ አዘቅት የሚገፋ ድርጊት መሆኑን መዘንጋት የለባችሁም እላለሁ !
ከፍ ያለ አደራ የተጣለበት የጥበብ ሰው እንኳን በአደባባይ በጓዳውም ቢሆን ትውልድን የሚያንፅ ወደበጎ ነገር የሚመራ ድርጊት ይፈፅም ዘንድ የሙያው ድስፕሊን በራሱ ያስገድደዋል ! መንግስትም ይሁን የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ ዝም ቢልም በበኩሌ ይህን የአርቲስቱን ድርጊት በፅኑ እቃወመዋለሁ ! አጥፊና ፀያፍ ድርጊት ነው ግሩም ኤርሚያስ አዝናለሁ !!
ኢህአዴግን የምደግፍበት አንድ ነገር አገኘሁ- መሬት አይሸጥም አይለወጥም! –ፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)
መሬት የሃብት ሁሉ ምንጭ ነው፤ መሬት ያለው “ምንም” ነገር ባይኖረው ሃብታም ነው። ከጊዜ በሁዋላ እንኳንስ የእርሻና የቤት መስሪያ ቦታ ማግኘት ቀርቶ ለመቀበሪያ የሚሆን ቦታ ማግኘትም ጭንቅ ይሆናል – የሰው ልጅ እንደ አሜባ በፍጥነት ይራባል፣ መሬት ደግሞ በዛው ልክ እየጠበበች ትሄዳለች። እናም ይህን ብርቀየ ሃብት በስርዓት መንከባከብ ግድ ይላል።
መሬት በግለሰቦች እጅ መሆኑ ምርትን ለማሳደግ ይጠቅማል የሚለው መከራከሪያ አሳማኝ ነው ። ኢህአዴግ ገበሬውንና የከተማውን ሰው እንደፈለገ የሚቆጣጠረው መሬት የመንግስት ስለሆነ ነው የሚለው መከራከሪያም እንዲሁ አሳማኝ ነው። ለመሬቱ ሲል ፈቅዶ የኢህአዴግ ባሪያ ለመሆን የመረጠ ብዙ ወገን አለ፤ መሬትን ነጻ ማድረግ ኢህአዴግ ከዘረጋው የባርነት ቀንበር ነጻ ለመውጣት አንድ እርምጃ ነው ተብሎም ሊታሰብ ይችላል። እርግጠኛ ባልሆንም እያመነታሁ እቀበለዋለሁ። ። በአጭሩ መሬት ወደ ግለሰቦች መዞሩን በመርህ ደረጃ እደግፋለሁ። ነገር ግን ዘረኝነትና ሙሰኝነት ባህሪው በሆነው መንግስት ስር ሆነን፣ መሬት ወደ ግል ይዙር ቢባል ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን ይመስለኛል ፣ ከኢህዴግ ባርነት ነጻ እንወጣለን ስንል የዘመናት ባርነትን እንዳንከናነብ እሰጋለሁ ። ኢህአዴግ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ መሬትን ወደ ግል የማዞር ብቃት የለውም። ይህን ደግሞ በ1980ዎቹ፣ በአማራ ክልል የመሬት ክፍፍል በተደረገበት ወቅት አይተነዋል። ሰዎች በፖለቲካ አቋማቸው ብቻ መሬት እንዳያገኙ መደረጉን በጊዜው ይወጡ የነበሩትን ዘገባዎች አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል።
አዲስ ስርአት እስኪመጣ መሬት ወደ ግል ባይዞር በብዙ መልኩ ተመራጭ ነው።
ባለፉት 23 ዓመታት ዋና ዋና የሚባሉ የከተማ መሬቶችን የህወሃት ሹሞችና ተላላኪዎቻቸው ተቆጣጥረዋቸዋል። ከከተሞች አልፎ በገጠር ለም የሚባሉትን የእርሻ መሬቶችንም እየተቆጣጠሩዋቸው ነው። ጋምቤላ፣ ኦሮምያ፣ ቤንሻንጉል፣ አፋር እንዲሁም ሰሜን አማራ ብትሄዱ ሰፋፊ መሬቶች በዘመኑ ሰዎች የተያዙ ናቸው። በአዲስ አበባ በአንድ ወቅት በተደረገ ጥናት አብዛኞቹ የከተማዋ ቁልፍ መሬቶች በህወሃትና ተላላኪዎቻቸው የተያዙ መሆኑ ተረጋግጧል ። መሬትን እየተሽቀዳደሙ የመያዙ እሩጫም በቀላሉ የሚቆም አይመስልም፣ አይቆምም። በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ( ኢህአዴግ በህይወት ከኖረ) እስካሁን ያልተያዙት ሰፋፊ የእርሻና የከተማ ቦታዎች በጥቂት የዘመኑ ባለሃብቶች ቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ለመተንበይ ሼህ ጅብሪል ወይም የፍጥሞውን ዮሃንስ መሆንን አይጠይቅም። ምክንያቱም ግልጽ ነውና ። መሬት የሃብት ምንጭ ነው፤ ሃብት ያለው ጉልበት አለው፤ ጉልበት ያለው ስልጣን አለው፤ ስልጣን ያለው ሁሉም አለው ።
አሁን ባለው መንግስት መሬት ወደ ግል ይዞታ ይዙር ማለት ላለፉት 22 ዓመታት ሰፋፊ መሬቶችን ዘርፈው የያዙ የዘመኑ ባለሃብቶች የግል መሬት እንዲኖራቸው መፍቀድ ማለት ነው። የሚመጣው መንግስት የእነዚህን ባለሃብቶች መሬት ቀምቶ ለማከፋፈል ቢሞክር ከአለማቀፍ ድርጅቶች ሳይቀር ከፍተኛ ተቃውሞ ይገጥመዋል። በደርግ ዘመን የግል ባለሀብቶች ንብረት ወደ መንግስት በዞረበት ወቅት ከምእራባዊያን አገራት ትልቅ ተቃውሞ መነሳቱን አንዘነጋም። አሁን ባለው የአለም ስርአት የግል ባለሀብቶችን መንካት ማለት ከምእራባዊያንና ከገንዘብ ተቋሞቻቸው ጋር መላተም ማለት ነው። ይሄ መንግስት እስከሚለወጥ መሬት በመንግስት እጅ ከቆየ፣ መጪው መንግስት የእነዚህን ሰዎች መሬት ቀምቶ ለማከፋፈል ቢሞክር ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ አይደርስበትም፣ ምክንያቱም መሬት የመንግስት ነውና። ” አስፈላጊው ካሳ ተሰጥቷቸው መሬታቸው ቢቀማ ተቃውሞ አይኖርም ” ቢባል እንኳ፣ በህገወጥ መንገድ ለያዙት መሬት ካሳ መክፈል የሞራልና የፍትሃዊነት ጥያቄ ያስነሳል። አዲሱ መንግስት የኢትዮጵያን የመሬት ስሪት በደንብ አጥንቶና ሁኔታዎችን ሁሉ አመቻችቶ መሬት ወደ ግል ቢያዞር ያን ጊዜ ቁጥር አንድ ደጋፊ እሆናለሁ። ዝምባብዌ ነጻ ከመውጣቱ በፊት መሬት የመንግስት ቢሆን ኖሮ፣ ነጻ በወጣ ማግስት መሬት ከግለሰቦች እየቀማ ያከፋፈለው የዝምባቡዌ መንግስት አሁን የገጠመውን ተቃውሞ ያክል አይገጥመውም ነበር፤ ደቡብ አፍሪካም ነጻ ሲወጣ መሬት የመንግስት ቢሆን ኖሮ፣ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ለብዙ ጥቁሮች መሬት እንደፈለገ ለማከፋፈል አይቸግረውም ነበር። በኢህአዴግ ዘመን መሬት ቢከፋፈል የዝምባብዌና የደቡብ አፍሪካ እጣ ይገጥመናል። መሬቱ ሁሉ በጥቂት የዘመኑ ሰዎች እጅ ይገባና እነሱ ” ነጮች” እኛ “ጥቁሮች” እንሆናለን። መጪው መንግስት መሬትን በፍትሃዊነት ማከፋፈል ይችል ዘንድ መሬት በመንግስት እጅ ሆኖ መቆየት አለበት። ኢህአዴግ መውደቁን ካወቀ፣ መሬትን ወደ ግል አዙሮ ለመጪው መንግስት ችግር አውርሶት ያልፍ ይሆን እያልኩ እሰጋለሁ።
በኢህአዴግ ዘመን መሬትን ወደ ግል እንዲዞር መፍቀድ ማለት እነዚህ ጥቂት የዘመኑ ሰዎች አሁን ከያዙትም በላይ ሰፋፊ መሬቶችን በፍጥነት እንዲያግበሰብሱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ማለት ነው። ዘመነኞቹ “መሬት ወደ ግል ሊዞር ነው” የሚለውን ሲሰሙ፣ በውጭ ባንኮች የከዘኑትን ገንዘብ እያወጡ መሬት በፍጥነት ለመግዛት ይጣደፋሉ። ስርአቱም የተወሰኑ ሰዎች ሰፋፊ መሬቶችን እንዲይዙ ሁኔታውን ያመቻችላቸዋል። ያልተያዙ መሬቶችን ለመግዛት ገንዘብ ቢያጥራቸው እንኳን የባንክ ብድር ይመቻችላቸዋል። የመንግስት ድርጅቶች ወደ ግል ሲዞሩ ያየነው ህገወጥ አሰራር በመሬት ሽያጭ ላይ እንደማይደገም ምንም ማረጋገጫ የለም ። የሻኪሶ ወርቅ ማእድን በስንት ነው የተሸጠው? በርካታ የመንግስት የንግድ ድርጅቶች እንዴት ነው ወደ ግለሰቦች የዞሩት? የተሸጡበት ገንዘብ መጠን ለህዝብ ተነግሮ ያውቃል? ገንዘቡስ መንግስት ካዝና መግባቱ ይታወቃል?
ቅንጅት አዲስ አበባን ሲያሸንፍ፣ የስርአቱ ልጆች ሰፋፊ መሬቶችን መቀራመት ጀመሩ፣ ኢህአዴግም ሆን ብሎ ሁኔታዎችን አመቻቸላቸው። ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ስር ያለች ትመስል ነበር። ቅንጅት ቢጨንቀው ” የመሬት ዝርፊያው በአስቸኳይ እንዲቆም” የሚጠይቅ መግለጫ አወጣ። የሚሰማ ግን አልነበረም። አላሙዲ ሳይቀር ጊዮርጊስ መሃል አደባባይ ላይ ለአመታት አጥሮ ያስቀመጠውን ቦታ እንዳልቀማ ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ አረሰው። ከዚያ ወዲህ ድፍን አስር አመት ምንም ስራ አልሰራበትም። ቅንጅት አዲስ አበባን እንደማይረከብ ሲያውቅ፣ ኢህአዴግ በመናኛ ገንዘብ ያዘረፈውን መሬት መልሶ ለመሰብሰብ ተሳነው። መሬት ወደ ግል ሊዞር ነው ቢባል ተመሳሳይ ነገር እንደሚፈጠር አልጠራጠርም።
በዚህ በዘርና በጥቅም በተማከለ ስርዓት ውስጥ ሆኖ መሬት ወደ ግል ይዙር ብሎ መጠየቅ በራስ ላይ እባብ እንደመጠምጠም ይቆጠራል ። ስለመሬት መሸጥና መለወጥ ለማውራት ኢህአደግ መቃብር እስኪገባ ድረስ መጠበቅ ግድ ይለናል። መታገል ያልብንም ኢህአዴግን ወደ መቃብር ለመሸኘት ነው። በእርሱ መቃብር ላይ አዲስ ስርአት ስንፈጥር ፣ ያን ጊዜ፣ ሁሉንም በማያስደስት ፣ ሁሉንም በማያስከፋ መልኩ መሬት ማከፋፈል ይቻላል።
ኢህአዴግ እስኪወድቅ መሬት በመንግስት እጅ መሆኑን በጽኑ እደግፋለሁ!
( ማሳሰቢያ ይሄ የግል አቋሜ ነው። አንድነት ፓርቲ በቅርቡ
ካስተዋወቀው የሚሊዮኖች ድምጽ ጋር በፍጹም አይያያዝም። ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ Wealth Over Work- በሚል ርዕስ ፓውል ክሩግማን The New York Times ላይ የጻፈው ጽሁፍ ነው። በዚህ ዙሪያ ሰፊ ክርክር እንደሚኖር እጠብቃለሁ)
የፍቅሩም ሆነ ፍቱኑ መፍትሄ አሁንም ያው ነው። (ዳዊት ዳባ)
አንድን አገር የመከፋፈል አደጋ የሚገጥመው ስልጣንና መሳርያ የያዘው ክፍል በግድ የተሳሳተ አማራጩን ተፈፃሚ ስላደረገ ወይ በሚፈፅማቸው ደባና ስህተቶች እንዲሁ መገነጣጠል ፋላጎቱና አላማው ስለሆነ ብቻ አይደለም። ለለውጥ የሚታገሉ ክፍሎች ሲበዙና ልዩነታቸውን አቻችለው በቀጣይ ሀላፊነቱን በጋራ ለመቀበል ሳይዘጋጁና ችግሩን በአግባቡ ተረድተው መከላከያውን የሁሉን ቡድንና ዜጋ ፍላጎት በሚያስማማና በአንድ ሊያሰልፍ በሚችል ብለሀት ሰፊ የጋራ መፍትሄ ሊሰሩለት ሳይችሉ ሲቀሩ ነው። በእርግጥም ያገራችን የወደፊት እጣ ፋንታ በጥሩ ወይ በመጥፎ ፍፃሜ የሚያገኘው በወያኔ ብቻ አይደለም። በድብቅም ሆነ በግልፅ ዘረኛ አጀንዳቸውን የያዙ ጎልበት ሲያገኙ ወይ ስልጣን ላይ ከተፈናጠጡ አደጋው አይቀሬ ነው። ሁሉ በየዘሩ ተደራጅቶ ባለበት ያገራችን እውነታ ይሄ ወይም ያንኛው ክፍል አንድነቷ እንደተጠበቀ እንዲቀጥል የፀና ፍላጎታችን ነው ቢሉም በምንም ደረጃ የሚገለፅ ዘረኛና አግላይ አጀንዳ በጉያቸው እስከያዙ ችግሩን አጋግለው የመጨረሻ ውጤቱ ተመሳሳይ ወይም የሚፈራው ነው የሚሆነው። ዘረኛ ቢሆኑም ለህልውናችን ስጋት አይሆኑም የሚለው ፈሊጥ በኛ አገር ነባራዊ ሁኔታ አይሰራም። ይህም ብቻ አይደለም ዘረኛ አጀንዳ ኖሮ አይደለም የሚመጣው ለውጥ ብዙና የተለያየ የሆነውን ሀሳብ፤ ፍላጎትና ስጋት የሚሸከምና አስማምቶ የሚሄድ ካልሆነም አደጋ አለው።
የኛን አገር ሁኔታ ልዩ የሚያደርገው ኢትዬጵያ የምትኖረው እኛ ስልጣን ላይ እስካለን ብቻ ነው የሚሉ ዘረኛ ውላጆች ናቸው ስልጣኑ ላይ ያሉት። ይህን አላማቸውን አልደበቁም። በጠራራ ፀሀይ ሁላችንም እንድናየው አድርገው እየሰሩበት ነው። በቀላሉ ተፈጻሚ ለማድረግ ያስፈልጋሉ ያሏቸውን ነገሮችን አመቻችተዋል። ላለመቀበል ካልወሰንን በቀር ይህንን ሁላችንም እናውቃለን። እንደውም ጠቅላላ ሁኔታዎች የሚያሳዩት ለውጥ መጥቶ ሳይጠራርጋቸው በፊት ይህን እኩይ አላማ ተፈፃሚ ለማድረግ ከጊዜ ጋር እየተሽቀዳደሙ እየሰሩበት እንዳሉ ነው። ለለውጥ የሚታገለው ክፍል እዚህ ያፈጠጠ ችግር ላይ ካለው ጠቅላላ ግንዛቤና የሰጠው ትኩረት ከችግሩ ክብደት አኳያ ባዶ ሊሰኝ የሚችል ነው። ይባስ ብሎ የበዛው ዜጋም ሆነ ፖለቲከኛ ዘርን መሰረት ባደረገ እኛና እነሱ በሚል መነሻ ነው ጠቅላላ አገራዊ እይታው የተቃኘው። ስለዚህም ችግሩ ላይ ያለው መረዳት ከተጨባጩ እውነታ በጣም የራቀ ነው። ያዋጣል ብለው እየሰራንበት ነው የሚሉትና የያዙት መፍትሄ የተሳሳተ መሆኑ ተደምሮ ገዥዎቻችን የወሰኑ ጊዜ በቀላሉ ይህን ተግባራዊ አድርገው እስታ ማለት የሚከብዳቸው አይደለም።
ይህ አፈራራሽ አገራዊ ችግር የተለያየ ፍላጎት ቢኖራቸውም በለውጥ ፈላጊዎች በሙሉ ድርሻ በሚያደርጉበት ሰላማዊ የጠረቤዛ ዙሪያ ውይይት ከሚመጣ ስምምነት መፍትሄ ሊሰራለት ይገባል። ይህን ማድረግ ይቻላልም። በተወሰኑ ቡድኖች ዘረኝነት፤ጥላቻና ጠባብ እይታ ተውጠን ወይ ተሸንፈን ነው እንጂ ኢትዬጵያዊነት ሰፊ ነው። የማይመልሰው የመብት ጥያቄ፤ የማያካትተው ሀሳብ፤ የማይሞላው ፍላጎትና የማይሸከመው ልዩነት የለም። አፈጣጠሩም ሆነ መሰረቱም ድሮም ቢሆን በልዩነት ላይ ነው። ብዙ በተሸከመ ቁጥር እየጠነከረ እንጂ እንዲዳከም ሆኖ ያለ አይደለም። ከንደዚህ አይነት ጥልቅ መረዳት የሚነሳ መፍትሄ ስራው መጀመር ያለበት ዛሬ ነው። ለነገ ስንተወውና አንድ ቀን ተኝተን ስንነሳ ብንን ብሎ ይጠፋል የሚመስለው በብዙ ፖለቲከኞችና ተቆርቋሪ ዜጎች የሚራመድ ሀሳብ ስህተትነትም አደጋም እንዳለው ለማሳየት የሚሰማ ጠፋ እንጂ በተደጋጋሚ ተሞክሯል።
ለጊዜው የሚያስከፍለውን ግዚያዊ ፖለቲካዊ ኪሳራ። ሊፈጠር የሚችለውና ጫጫታ ሳይፈሩ እዚህ አገራዊ ችግር ላይ በውይይትና በመቀራራብ የሚመጣ መፍትሄ አገራዊ ፋይዳው ግዙፍ ነው።ትግል ላይ እንዳለ አንድ ክፍል መሰዋትነት በቀነሰ በቶሎ አሸናፊ ለመሆንም የተባበረ ሀይልን የመጠቀም ወሳኝነት ትክክለኛ ፖለቲካዊ እርምጃ አድርገው ወስደውት የሞከሩት በእርግጥ አሉ። እነዚህ ክፍሎች ከዚህ አትለፉ የሚለውን ያደጋ ምልክት ያለበት ማስፈራራት ተላልፈው ለመቀራራብና ተባብሮ ለመታገል ሞክረዋል። ከዛም በላይ በውይይት ከሚመጣ መቀራረብ አንድነታችንን ባስተማማኝ ሁኔታ ለማስቀጠል የሚያስችል መነሻ የሚሆን አንድ አይነት ስምምነት ለመቋጠር ጥረት ያደርጋሉ።
ሁላችንም እንደምናውቀው ማበላሸትና እንቅፋት መሆን እንደመስራት ከባድ አይደለም። ትናንሿንም ሙከራ ከስር ከስር እየተከታታሉ አምርረው የሚቃወሙና በተቀናጀና በተባበረ መንገድ እንዳይሳካ የሚሰሩ ነበሩ። አሁንም አሉ። እነዚሁ ክፍሎች ናቸው ዛሬ ጎራ ለይተው እያየነው ያለነውን አደገኛ፤ ከፋፋይና አብሮነታችንን የሚገዳደር መዘረጣጥና እንኪያ ሰላንታ ውስጥ ያሉት። በጥቂቶች የተሞከረው ልዩነትን የማጥበብና የመተባበር ጥረት የራስ ዳሸንን ተራራ ያህል ገዝፎ ሲነገረን የነበረውን የልዩነት ግንብ ሰብሮ እታች ህዝብ ውስጥ ድረስ የሚታይ ትብብርን፤ አብሮነትንና ያንድነት መንፈስ ያጸና ነበር። በርግጥም ትክክለኛና ተስፋ ሰጪም ጅማሮ ነው።
በእርግጥ ይህ መፍትሄ ከዚህና ከዛ ወገን በተነሳ ተቃውሞ ቢደበዝዝም ዘረኛ ውላጆች ጉለበት ያገኙ በመሰላቸው ጊዜ ሁሉ የበለጠ ተፈላጊ፤ ፍጽም መፍትሄ ሆኖ ባብዛኛው ዜጋ ተቀባይ የሚሆን ነው። በርግጠኛነት ሞተ ሲሉ አፈር እየላሰ ይነሳል። ምክንያቱም ያገራችን ችግር ሌላ አቋራጭም መፍትሄም የለውም። በውይይትና በመቀራረብ የሚመጣና ፍቅር የሚገለጽበት መፍትሄ ላይ ስንደርስ ብቻ ነው ነፃነታችንን የምናቀርበው። አንድነታችን አስተማማኝ መሰረት ላይ የሚቀመጠው። ይህን ማድረግ ካልቻልን ወደፊት መራመድ አይደለም አስከዛሬ ከሄድንበት ወይ ዝንፍች። ሲተውላቸው እንዴት እንደሚያጨማልቁት እያየን ነው።
አፅኖት ሰቶ ለተከታተለው በጥቂቶች በመለስተኛ ደረጃ የተሞከረው ለወደፊቱም አገራዊ ችግሮቻችን ላይ አስተማማኝ መፍትሄ ለመስራት ትክክለኛውም የሚሰራው አንድና አንድ ይህው መንገድ ብቻ መሆኑን ያየንበት ነው። መልካምና ትክክለኛ የነበረውን ጅማሮ የምር ተደርጎ ግን አልተያዘም፤ ዛሬ ጎራ ለይተው ለመላተም ቀንዳቸውን ወደታች ቀስረው በጎሪጥ እየተያዩ መሬት የሚደበደቡ ክፍሎች የሚያሰሙት ጫጫታ ሲበዛ በፅናት አልተቀጠለበትም። በቂ ክትትልና ያብዛኞቻችንን ድጋፍና እርብርቦሽ ስላላገኘ ዛሬ ለምናየው አፍራሽና አሳፋሪ አገራዊ ክስተት ቦታውን ሰጥቷል። ፖለቲካችን ዘር ተለይቶ አንዱ ሌላው ላይ በሚያሳየው ጥላቻ ንቀትና ስድድብ ተሞልቷል። ወያኔን መታገል ተረስቶ የተጨቋኞች የርስ በርስ ልፊያ ትግል ሆኗል። በድጋሚ ለወደፊቱም ለነዚህ ክፍሎች የበላይነቱንና ተሰሚነትን እንዲያገኙ በፈቀድን ቁጥር የሚፈጠረው ዛሬ እየታዘብን ያለነው አፍራሽና አገዳዳይ ድርጊት እየጨመረ መሄድ ብቻ ነው። መዳረሻችንም የሚሆነው መከፋፈልና የዜጎች እርስ በርስ መጎዳዳት ነው።
ዘረኛ ውላጆች በድርጅታዊ ጥንካሬ ፤ በገንዘብ አቅም፤ ተከታዬችን በማብዛት፤በመገናኛው ዘርፍ። በሚያሳዝን ሁኔታ አንቱ የተባሉ ዜጎችን ምሁራንን አሰልፈዋል። ማሰለፍ ብቻ አይደለም እውቀታቸውን ሊዚህ አፍራሽ ሚና እየተጠቀሙበት ነው። በአጠቃላይ እነዚህ ቡድኖች ሁለንተናዊ የበላይነት የያዙበት ፖለቲካዊ አየር ነው አሁን ያለው። ይህንን አይነቱን የበላይነት ያገኙት ሁሌም እርምጃቸው ውስጥ ሁሉ ዘረኝነት ስላለበት ነው። የዘር አቁፋዳቸው ውስጥ ያልከተተውን ስለሚያስፈራሩና ስለሚያገሉትም ነው። ሁሌም ሁሉን ነገር ሀላፊነት በሌለበትና በማን አለብኝነት ስለሚሰሩ ነው። ውሸትን አብዝተው ይጠቀማሉ። የመጨረሻው ደረጃ ድረስ ወስደው ቆምንልህ የሚሉትን ዘር አባላት ሊበላህ ነው ጅቦ ይሉታል። ሽብር አብዝተው ይነዙበታል። የመልክታቸው ፍሬ ነገር ሲጨመቅ የዛ ዘር መኖር ለኛ መጥፊያችን ነው የሚመስለው። ሁሉንም አጋጣሚ ይጠቀማሉ። አፄ ሚኒሊክን መቃወም አማራን ማጥቃት ነው። አፄ ሚኒልክን ማወደስ ኦሮምን ለማጥቃት አድርገው ይጠቀሙበታል። ታሪክን፤ የጋራ የሆነውን ጭቆና፤ በውድድር ያሸነፈ እስፖርተኛ፤ ወይ አገዛዙን የተጋፈጠን ጀግና…. ሳይቀር ዘሩን አጣርተው ይጠቀማሉ። በተጨማሪ ወያኔዎችም ጉልበት ሰጥተዋቸዋል። ስልጣን ይዞ ለመቀጠል ሁሌም ሲጠቀሙበት የነበረና ለወደፊቱም በእጅጉኑ የሚያስፈልጋቸው ስለሆነ ይህን ማድረጋቸው ግን አይገርምም። ቤንዚን በማቅረብና ክብሪት በመስጠት እየተባበሯቸው ነው። ሀውልቶች እየገነቡላቸው ነው። ጥንካሬውን እያገኙት እና ሀይል እየተሰማቸው እንደሆነ ሁለቱም ጎራዎች አውቀዋል። ዘረኝነት፤ ንቀትና ብልግና ልጓማቸውን በጥሰው እየቧረቁ ነው። ወንጀሉና ብልግናው አድጎ እንደሁሌው ግለሰቦችና ድርጅቶች ወይም ቡድኖች ላይ ያለመና የሚያቆም አልሆነም።
ዳባ የሚል ስም ይዞ በዚህ ፖለቲካዊ አየር ይህን አይነት እውነት መናገር ምን ያህል ሚዛናዊ ተደርጎ ሊወሰድና ተቀባይ ሊሆን እንደሚችል ደጋግሜ እራሴን ጠይቄአለሁ። ለወትሮው ሀይ የሚሉ ሰዎችን ብጠብቅ ዝምታን ስለመረጡና ይባስ ተብሎ ጓሮ ጓሮውን ሲራመድ የነበሩ የከፉ ዘረኝነቶችና ጥላቻዎች ለለውጥ የቆሙ ወይም እኔንም ጨምሮ አብዛኛው ዜጋ የሚጠቀምባቸው መገናኛዎች ላይ ሽፋን እያገኘ ስለሆነ። ለዛውም ሚዛናዊ ባልሆነና በጥሬው መሆኑን ስለታዘብኩ ልፅፍበት ተገድጃለው። ዘር እየጠሩና እየለዩ ህዘብ ላይ የሚፈፀም አፍ መክፈትና ወንጀል በየቀኑ እየጨመረ ነው። እውነትነት ስላለውና ሚዛናዊ ለመሆን ግን ለወትሮው በጅምላ አማራው እንዲህ ነው ከሚለው ወንጀል ዛሬ ዛሬ ኦሮሞ ወይ ሙስሊሙ የሚለው እጅጉኑ አይሏል። ይህን ምስክርነቴን ለመቀበል የተቸገረ ነገር ግን ነገሮችን ሁሉ አጥርቶ በማወቅና በሚዛናዊነት የሚያይ አንባቢ እንደጥቆማ ወስዶት አስተርጓሚም እየተጠቀመ ቢሆን ከዛሬ ጀምሮ የራሱን ክትትል ማካሄድ ይችላል። ድምዳሜው እኔ ከገለጽኩትም በላይ የሚያስደምም ሊሆን ይችላል።
ታላቅ በሆነው ኢትዬጵያዊነት ስር ተሸጉጦ ለየትና ረቀቅ ባለ መንገድ የሚራመድ ዘረኝነት ለሌሎች ያለ ጥላቻ፤ ንቀትና ወንጀል እየደባበቅነው ነው እንጂ የቆየና ስር የሰደደ ችግር ነበር። ነውም። ዛሬ ለገባንበት ማጥ ውስጥም የከተተን ይህው ነው። ሀይላችንን አስተባባረን ዘረኛ አንባገነኖችን ከላያችን እናዳናራግፍ አላራምድ ብሎ በጭቆና ስራ እንድንኖር ካደረጉን ምክንያቶች አንድም ነው። ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ላይ ከዘመኑ ጋር የሚስማማ፤ ከጠረቤዛ ዙሪያ ውይይት የሚወለድ ሰላማዊ መፍትሄ እስቀምጠን ተባብረን ነጻ እንዳንወጣና ወደ ብልፅግናው ጎዳና እንዳንገባ እንቅፋት ነው። ይህን አይነቱን ዘረኝነትና የነዚህን ዜጎች ወንጀል ዛሬ እነደከዚህ በፊቱ ለመሸፋፈንም ሆነ ለማስተባበል የማያቻልበት ደረጃ ደርሷል።
ኢትዬጵያዊነት ትልቅም ጠንካራም ነው። ለረጅም አመታት በግልጽ በየጎጡ ተደራጅተው ዘረኝነትና ልዩነት ላይ የሚሰሩ ብድኖችን ማዳከም መቋቋም ችሏል። ስልጣኑ ላይ ያለው አገዛዝ ዘረኝነትና አድሏዊነትን በከፋና ለማንኛችንም በሚሰማና በሚያም መንገድ ለረጅም አመታት በሚራመድበት እውነታ ውስጥም ። አሁን ጉልበት እያገኘና እያገጠጠ የመጣው በሽፋንና በመሸጎጥ በዛ ላይ ከኛ በላይ ላሳር ኢትዮጵያዊ በሚል ማጭበርበሪያ የሚካሄድ ዘረኝነት ግን ሊያስከትል የሚችለው አደጋ በቶሎ ካልተገታ በጭራሽ በጭራሽ ቀላል ሆኖ አልታየኝም። ለማንኛውም እስከሚቀጥለው ምርጫ የጥላቻና የዘር ፖለቲካ ናላችንን እንደሚያዞረን እንጠብቅ። ተቃዋሚዎች በሙሉ ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለዚህ ተመቻችተው ነው ያሉት። ለነገሩ ጣት ይቀሳሰራሉ እንጂ ሁሉስ መቼ ፅዱ ናቸው። ለማንኛውም በሚያናድድ ሁኔታ ከሂደቲ ተጠቃሚ ሆኖ የሚወጣው እንደሁሌው አርቆ የሚያቅደውና መጠቀምን የሚችልበት ይሆናል።
ዳዊት ዳባ Sunday, March 23, 2014 dawitdaba@yahoo.com