እንዴት ጀመራችሁ ከየትስ መጣችሁ
ያረጀ መሣሪያ እንደታጠቃችሁ
ክፋት ምቀኝነት ተንኮሉን አዝላችሁ
እሹሩሩ ልጄ እያባበላችሁ
ህዝብን በማሣሣት ሰይጣን ተጣብቷችሁ
ወይ ለህዝብ ሳይሆን ፍትህ ለተራበው
ችግር ለደቆሰው እርሃብ ለጎዳው ለተጎሳቆለው
አሁን ተረዳነው እራስን መውደድ ነው
በሰይጣን ፈረስ እየጋለባችሁ
በሱዳን ምህታት እያታለላችሁ
ወንድምን በመግደል ወንድምን በማሰር እየፎከራችሁ
አገር ለመገንጠል እየዶለታችሁ
ለአንድነት ለህብረት የቆመውን ሁሉ እየገደላችሁ
የመናገር መብቱን ከህዝቡ ነፍጋችሁ
ውሸት ዲሞክራሱ እያራመዳችሁ
በዘር በሃይማኖት ህዝብን ከፋፍላችሁ
በቋንቋ መሰረት ሃገር በጣጥሳችሁ
ለመንገስ ለመክበር ነበር እቅዳችሁ
የእናንተ ውሸት ባቡር የማይችለው
በከንቱ አትድከሙ ህዝባችን ንቁ ነው
ትዝብት ይታወስ
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር
ሕዝባችን ንቁ ነው
ኃይለማርያም ደሳለኝ እና አባዱላ ገመዳ ከ”ተንባዩ”ጋር ታዩ፤ “ቡራኬ ሰጥቻቸዋለሁ”ይላል (ፎቶ ተይዟል)
”ትንቢተኛው” ከጠቅላይ ሚኒስትራችን ጋር ምን ይሰራል ?
ከአቤ ቶኪቻው
ሰሞኑን ጠቅላያችን አንዴም ሲደንሱ አንዴም ”ሲቀደሱ” በየሚዲያው እያየናቸው ነው። እሰይ እንዲህ ነው እንጂ የኔ አንበሳ በዬ ላደንቃቸው እፈልጋለሁ። ይሄንን ፎቶ ያገኘሁት ከፌስ ቡክ ተሰውረው በትዊተር የመሽጉ ጎበዞች ዘንድ ነው። ከዛም በማስፍንጠሪያ ተስፈንጥሬ ”ትንቢተኛው” ድረ ገጽ ውስጥ ብገባ በኢትዮጰያ ቆይታው አባ ዱላ ገመዳ እና ሃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ ለሌሎችም ባለስለጣኖች ቡራኬ እንደሰጠ ይናገራል።
እግረ መንገዱን ባለስልጣኖቻችን እስር እና ግርፉን እንዲተዉ ስልጣንም ከእግዜር እንጂ ከጠብ ምንጃ ዘንድ እንዳልሆነ ነግሮልን ከሆነ ደህና ነው!
ዝም ብሎ የወደፊት እጣ ፈንታቸውን ብቻ ነግሯቸው ከተመለሰ ግን ዝም ብሎ ነው የለፋው፤ የባለስልጣኖቻችንን እጣ ፈንታ እኛም እንነግራቸው ነበር። (አያያዙን አይቶ… ) እንዲል የሀገሬ ሰው ማለት ነው።
ማላዊውን ትንቢተኛ እንደኔ ለማታውቁት ከዩቲዩብ ላይ ያገኝሁት አንድ ስራውን በድረ ገጻችን ውስጥ እንደሚከተለው አሰቀመጠዋለሁ፤
የምር ግን ለጠቅላያችን እና እና ለአባዱላችን ምን ተንብዮላቸው ይሆን… ?
በቪዲዮው ውስጥ አንዷን ደርባባ (ማሊያዊት ሳትሆን አትቀረም) ከአንድ እውቅ እና ትልቅ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ጋር የፍቅር ቁርኝት መስርታ እንደነበር ህዝብ ፊት ሲነግራት አይቼ ያ ባለስልጣን ማን ይሆን… ብዬ ለማወቅ ጓጓቴንም አልደብቅዎትም፤ ማን ያውቃል ባላየነው ቪዲዮ ደግሞ ባለስልጣኖቻችንን ከማላዊት ኮረዳ ጋር ፍቅር የመሰረትክ ውጣ… ብሎ አስለፍልፏቸው ይሆናል።
ጭማሪ፤
ባለስልጣኖቻችን ግን እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ”በበረከቱ ይጎብኛት” ሲባል እንደዛ እንዳልሳቁ ዛሬ ምን ታያቸው… ወይስ የኢትዮጵያ እግዜር እና ”የትንቢተኛው” እግዜር ይለላያያሉ… ?
[የሃረሩ ቃጠሎ ጉዳይ] መቃጠል መቃጠል መቃጠል –ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)
የ ደ ሶቶን ሃሳብ ለማየት በአዲስ አበባ የተገነቡ የጨረቃ ቤቶችን እንመልከት። ነዋሪዎቹ ቤቶችን ለመስራት ብዙ ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ አፍስሰዋል፣ ይሁን እንጅ የመንግስትን የባለቤትነት ማረጋገጫ ቁራጭ ወረቀት ለማግኘት ባለመቻላቸው የሰሩት ቤት ሃብት ሊሆን አልቻለም። ቤታቸውን መሸጥ፣ መለወጥ እንዲሁም በባንክ አስይዘው ገንዘብ መበደር አይችሉም። እነዚህ ሰዎች የባለቤትነት ካርታ እስካላገኙ ድረስ ቤታቸው ሃብታቸው ነው ማለት አይቻልም። ነገር ግን የይዞታ ማረጋገጫ ብጣሽ ወረቀት ባገኙ በሰከንድ ውስጥ ቤታቸው ሃብታቸው ይሆናል፣ መሸጥ መለወጥ፣ ቤታቸውን አስይዘው ከባንክ መበደር ይችላሉ። በአንድ ወረቀት የቤቶቹ ባለቤቶች ከድህነት ወደ ሃብት ባለቤትነት ተሸጋገሩ፣ በሌላ አነጋገር የድህነትን መጋረጃ ቀደዱ ማለት ነው። መንግስት ህጋዊ እውቅና ለሌላቸው ሌሎች ቢዝነሶችም ህጋዊ እውቅና ቢሰጥ ፣ ሰዎችን ባለሀብት ማድረግ ብቻ ሳይሆን መንግስትም ከእነዚህ ቢዝነሶች ብዙ ግብር መሰብሰብ ይችል ነበር። በኢትዮጵያ ያለው የገዢዎች ስብስብ ግን ንብረት በማውደም የሚደሰት ይመስላል። ቤት ማፍረስና ንብረት ማቃጠል ልዩ መልክቱ ሆኗል። ባለፉት 22 ዓመታት ስንትና ስንት ቤቶች ፈረሱ፣ ስንቶቹ ተቃጠሉ፣ ስንትና ስንት የአገር ሃብት አብሮ ወደመ፣ ስንቶቹ ደኸዩ፤ ወረቀት በማደል ህጋዊ ማድረግ ሲቻል ሳይቻል ቀረ።
ከረጅም አመታት በሁዋላ የደ ሶቶን መጽሃፍ እንዳስታውስ ያደረገኝ በሀረር በተደጋጋሚ የሚታየው የእሳት ቃጠሎ ነው። የንግድ ቤቶችን የሚያቃጥላቸው መንግስት ከሆነ የመንግስት የድንቁርና ብዛት ልክ ማጣቱን የሚያመለክት ነው። መንግስት ቤቶችን ሲያቃጥል፣ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ሰዎች ወደ ድህነት ጎራ መግባታቸውን አያውቅም ለማለት አልደፍርም። እነዚህ ሰዎች ህጋዊ እውቅና የላቸውም ቢባል እንኳን፣ የህጋዊነት ማረጋገጫ ብጣሽ ወረቀት በመስጠት፣ ህጋዊ በማድረግ ድህነትን እንዲሻገሩ ማድረግ ይቻል ነበር። ንብረትን በእሳት በማጋየት የሚገኝ የኢኮኖሚ እድገት ምን እንደሆነ በፍጹም አይገባኝም፤ የማውደም ኢኮኖሚክስ የሚባል ነገር መኖሩንም አላውቅም።
መንግስት አነስተኛና ጥቃቅን እንዱስትሪ የሚለው ነገር አለ። ሃሳቡ ፖለቲካዊ ይዘት ባይኖረው ጥሩ ነው። አውሮፓኖች ያደጉት በተለያዩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች በጊዜው አጠራር ( ጊልዶች) ነው። የዛሬዎቹ ግዙፍ የአውሮፓ ኢንዱስትሪዎች በተለያዩ አነስተኛ ጊልዶች የተመሰረቱ ናቸው። በእኛ አገር ግን መንግስት ጥቃቅንና አነስተኛ የተባሉትን ድርጅቶች ከቢዝነስ አውጥቶ የፖለቲካ ስራ ስለሚያሰራቸው ተደካሙ፣ እነዚህ ድርጅቶች የቢስነዝ ድርጅቶች ከሚባሉ፣ ጥቃቅንና አነስተኛ የፖለቲካ ድርጅቶች ቢባሉ ይቀላል። መንግስት እነዚህን ድርጅቶች በመደገፍ ወደ መለስተኛ እንዱስትሪነት እንዲለወጡ ከማበረታታት በራሱ ትላልቅ ግንባታዎችን ያካሂዳል። አምባገነን መንግስታት ሁሌም ትላልቅና ብልጭልጭ ግንባታዎችን መስራት ያስደስታቸዋል። ግንባታዎቹ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ይኑራቸው አይኑራቸው፣ በህዝቡ እስከታዩና “ ዋው” እስካስባሉ ድረስ ግድ የላቸውም። ለምሳሌ የተከዜን የሃይል ማመንጫ እንመልከት። የወጣበት ገንዘብ የትየለሌ ነው፣ ጠቀሜታው ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ፣ ግልገል ጊቤም እንደዛው ነው። በአባይ ግድብ ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት ላይም ጥርጣሬ አለኝ- በተለይ ከደለል ጋር በተያያዘ የሚፈጠረው ችግር በቀላሉ አይፈታም። በአዲስ አበባ የሚገነባው ባቡር ብዙ ጦሶችን ይዞ እንደሚመጣ እድሜ ከሰጠን እናየዋለን። መንግስት ለታይታም ቢሆን በሚያስገነባቸው ግዙፍ ግንባታዎች አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ተረስተዋል፣ በዚህም የተነሳ እድገቱ መሰረት የሌለው የእቧይ ካብ ሆኗል።
በሃረርና በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ነጋዴዎችን ንብረት ከማውደም በአነስተኛ ማህበራት እያደራጁ የኢኮኖሚው መሰረት እንዲሆኑ ማድረግ ይቻል ነበር፤ ነገር ግን ለዜጎቹ የሚቆረቆር መንግስት የለምና ሁሉም ነገር በምኞትና በነበር ይቀራል።
የጠፋውን የማሌዥያ አውሮፕላን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፤ (ከዚህ በፊት 5 አውሮፕላኖች ጠፍተው እንደነበር ያውቁ ኖሯል?)
ከአትላንታው አድማስ ራድዮ
ስለ ማሌዢያው የበረራ ቁጥር 370፣ የተሰወረ አውሮፕላን መዘገብ እጅግ ከባድ ነው። ምክንያቱም ነገሮች በየደቂቃው ይቀያየራሉና። ገና ሲጀመር፣ አውሮፕላኑ ለመጨረሻው ጊዜ ድምጽ ያሰማበት ሰአት ልክ አልነበረም፣ ከዚያ ቀጥሎ ሁለት ጥቁሮች በሃሰት ፓስፖርት ተሳፍረዋል ተባለ፣ ጥቂት ቆይቶ ጥቁር አይደሉም፣ ኢራናውያን ናቸው ተባለ፣ .. ከዚያ በኋላ 6 ሰዎች አውሮፕላኑ ውስጥ ሊገቡ ካሉ በኋላ ሃሳባቸውን ቀይረዋል ተባለ፣ ጥቂት ቆይቶ ስድስት አይደሉም 2 ናቸው፣ እነሱም ገና ከቤታቸው ሳይወጡ ሃሳባቸውን የቀየሩ ናቸው ተባለ ….፣ ከዚያ ደግሞ አውሮፕላኑ ከጠፋ ከ 48 ሰአት በኋላ የአንዳንድ ተሳፋሪዎች ስልክ ይጠራል ተባለ . ጥቂት ቆይቶ ፣ ውሸት ነው የማንም ስልክ አይጠራም ተብሎ ተነገረ …፣ ከዚያ በኋላ ቻይናዎች በአንድ የቻይና ባህር ላይ የአውሮፕላኑ ስባሪን አይተናል አሉ ተባለ ..፣ ጥቂት ቆይቶ ውሸት ነው አላዩም በሚል ተስተባበበለ።
እያንዳንዱ የሚነገር ጉዳይ ልብ የሚያንጠለጥል ቢሆንም፣ በዚህ በዓለማችን የበረራ ታሪክ እጅግ ውስብስብና አሰገራሚ የሆነ መሰወር ጉዳይ ሁሉም መላምቱን ለመስጠት ቢቸኩል የሚፈርድ አልነበረም። እንደተባለው አውሮፕላኑ በቴክኒክ ችግር አይደለም ድምጹን ያጠፋው፣ እንደተባለው ካቅሙ በላይ የሆነ ነገር ገጥሞትም አይደለም።
ምናልባት ያለፉትን ሰባት ቀናት የተለያዩ ነገሮችን ሰምታችሁ ይሆናልና ቀጥታ ወደፊት በመፈናጠር ዛሬ ጉዳዩ ከደረሰበት ነገር እንጅምር። ከዚያ በኋላ ከዚህ በፊት የጠፉ አውሮፕላኖችን ታሪክ እናሳያችኋለን።
ዛሬ ጠዋት የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአየር ሃይል ሃላፊያቸው ያሉበትን ደረጃ ለመናገር ብቅ ብለው ነበር። በነሱ መረጃ መሰረት ዛሬ የተነገረው ትልቁ ነገር አውሮፕላኑ በቴክኒካል ችግር ሳይሆን ሆን ተብሎ ድምጹን ማጥፋቱንና ፣ ምናልባትም የመጨረሻውን ግንኙነት ከተቆጣጣሪዎች ጋር ካደረገ በኋላ ቢያንስ 7 ሰአት ያህል ሳይበር እንዳልቀረ መናገራቸው ነው፡፡ ያ ማለት አውሮፕላኑ ተጠልፏል ወይም ታግቷል። ይህ የሆነው ደግሞ ወይም ከተሳፋሪዎች መካከል በአንዱ ወይም ደግሞ እንደ ኢትዮጵያው አየርመንገድ በራሱ ፓይለት ተጠልፎ ነው ማለት ነው።
ይህ የዛሬው ውጤት እስካሁን አውሮፕላኑ ሲፈለግ የነበረባቸውን ቦታዎች ሁሉ ፉርሽ እንደነበሩ የሚያሳይ ነው። ለመሆኑ አውሮፕላኑ ከምድር ተቆጣጣሪዎች ጋር እንዳይገናኝ፣ ሆን ብሎ መገናኛውን የነቀለው ሰው ማነው? ይህ ሊሆን የሚችለው እንደ አቪየሽን ሃላፊዎች ወይ በራሱ በፓይለቱ ነው፣ ወይም ደግሞ በጣም ጥሩ የሆነ የፓይለትነት ችሎታ ባለው ጠላፊ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ አውሮፕላኑ ቢያንስ ለሰባት ሰአት ያህል በምዕራብ አቅጣጫ ከተጓዘ ሊደርስ የሚችለው ሁለት ቦታ ነው፣ አንዱ አንዳማን ደሴቶች ሲሆን ሁለተኛው ህንድ ውቂያኖስ መካከል ነው። እንደ ማሌዥያ ባለሥልጣኖች ገለጻ አውሮፕላኑ የያዘው ነዳጅ ቢያንስ ሰባት ሰአት ያህል ያስኬደዋል። ያ ማለት ከዚያ በላይ መሄድ ስለማይችል፣ ወይም አንዱ የተደበቀ ደሴት አርፏል፣ ወይም ህንድ ውቂያኖስ መካከል ተከስክሷል። አሁን ያለው መላ ምት ይህ ነው።
ይህም ቢሆን እንቆቅልሹን የሚፈታው አይደለም። ለመሆኑ ከአየር መንገዱ ጋር ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ የቆየው ፓይለት፣ የቤተሰብም የሆነ የሌላ ችግር ያልታየበት፣ .. ጥሩ ምግባር እንዳለው የተመሰከረለት፣ በትዳሩ ከ20 ዓመት በላይ የቆየው ፓይለት እንዴት ሆን ብሎ አውሮፕላኑን ይዞ ይሰወራል? ይህ አንዱ ጥያቄ ነው፡ በሌላ በኩል የ 27 ዓመቱ ረዳት ፓይለት አብዱል ሃሚድ፣ ከአየር መንገዱ ጋር ለ7 ዓመት ሰርቷል፣ የተከበረና ምንም አይነት የሚያጠራጥር ነገር የለሌበት ነው። ርግጥ ከዓመታት በፊት ከተሳፋሪዎች መካከል ሁለት ሴቶችን ውስጥ ድረስ ጋብዞና አጠገቡ አስቀምጦ መጓዙ ቢነገርና ይህም የአየር መንገድ ህግን መተላለፍ ቢሆንም፣ በጉርምስና ተሳብቦ ከመቅረቱ በቀር ሌላ እንዲህ ያደርጋል ተብሎ የሚያስገምት ነገር ምንም አልተገኘም።
ከመንገደኞች መካከል ከሆነስ የአውሮፕላን እገታው የተደረገው ማን አደረገው? ለምንስ አደረገው? ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። ከመንገደኞቹ አብዛኞቹ ቻይኖች እንደመሆናቸው አልቃይዳና ታሊባን በዚህ ድርጊት ይኖራሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። ርግጥ አንዳንድ ተንታኞች ከቻይና አንድ ግዛትን ለመገንጠል የሚታገልና ከዚህ በፊት አንድ የቻይና አውሮፕላን ለመጥለፍ የሞከረ አንድ ድርጅት እንዳለ በማስታወስ ይመዝገብልን እያሉ ነው። አስገራሚው ነገር ግን፣ ይህ ከሆነ ጠላፊዎቹ ወይም አጋቾቹ ወይም ድርጊቱ የፈጸመው ማንም ይሁን ማን፣ እንዴት ምክንያቱንና የሚፈልገውን አልተናገረም? እንዲሁ ዝም ብለን እንሙት፣ ድምጻችንን እናጥፋ ብሎ እንዴት ይወስናል? ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው።
ነገር ግን አሁን ባለው የነገሮች ግጥምጥም አውሮፕላኑ የቴክኒክ ብልሽት አልገጠመው ይልቁኑ ሆን ተብሎ ታግቶ ወይም ፓይለቱ ራሱ አግቶት የሆነ ቦታ ወስዶታል ወይም ውቂያኖስ መካከል ከስክሶታል። ይህ ደግሞ በቅርብ ከሆነውና የራስን አውሮፕላን ጠለፈ ከተባለው የኢትዮጵያው ሃይለመድህን ታሪክ ጋር ለማመሳሰል የሞከሩም ነበሩ።
ከዚህ በፊት የጠፉ አውሮፕላኖች ተገኝተዋል? የጠፉስ አሉ?
አዎ አሉ።
- ለምሳሌ በሜይ ወር 2003 ዓ.ም የኡጋንዳ ንብረት የሆነው ቦይንግ 727 ድንገት ሳይፈቀድለት ከአየር ማረፊያው ተነስቶ በመብረር ያልታወቀ ቦታ ሄዷል – እስካሁንም የት እንደገባ አልተገኘም። ፓይለቱና ረዳቱ ብቻ እንጂ ተሳፋሪ አልነበረውም።
- የፈረንሳይ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 447 በ2009 ዓ.ም ድንገት ጠፍቶ ፣ ስብርባሪው ህንድ ውቂያኖስ ላይ የተገኘው ከሁለት ሳምንት በኋላ ነበር።
- የትራንስ ዎርልድ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን በበረራ ቁጥር 800 ጉዞ ከጀመረ በኋላ አየር ላይ በመፈንዳቱ 230 ሰዎች አልቀዋል። ይህ የሆነው በ1996 ዓም. ነው።
- የታይገር አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ፣ በበረራ ቁጥር 793 ጉዞ ከጀመረ በኋላ 106 ሰዎችን እንደጫነ የት እንደገባ አልታወቀም ፣ ይህ ይሆነው በ1962 ዓ.ም ቢሆንም፣ ዛሬም ድረስ ምን እንዳጋጠመው የሚያውቅ የለም።
- በ1957 ዓ.ም የፓን አሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን ቦይንግ 337 44 ሰዎችን እንደጫነ አየር ላይ ጠፋ፣ከአንድ ሳምንት በኋላ ስብርባሪው ውቂያኖስ ላይ ተገኘ።
እነዚህ ሁሉ አስገራሚ ታሪኮች ናቸው። አንዳንዶቹ ምናልባት ቴክኖሎጂ በጣም ባልዳበረበት ወቅት ሊሆኑ ይችላሉ። አሁን 43 መርከቦች፣ 58 አውሮፕላኖች፣ 14 አገሮች ፍለጋውን እያጣደፉ ቢሆንም፣ የመጥፋቱ እንቆቆልሽ ግን ፣ አገር ስጠኝ ብለን የምንፈታው አልሆነም።
ሃገራዊ ጥሪ ከ 2007 ምርጫ በፊት!
ስለ ሃገራችን ኢትዪጵያ መከራ፣ ስለ ህዝባችን ስቃይ፣ ስለ ኢህኣዴግ ግፍ፣ ስለ ተቃዋሚዎች ህብረት ኣልባ መሆን፣ ሌላም ሌላም ከሚገባው በላይ ተጽፈዋል፣ ተነግረዋል፣ ነገር ግን ያመጣነው ለውጥ የለም – እንዲያውም የባሰ መለያየት፣ መወቃቀስ፣ ማጥላላት፣ እና የኢህኣዴግን ኪስ እንዲሰፋ ኣስተዋጽኦ ኣድርገናል። ኣሁንም ኣሁንም ለውጥ ከተፈለገ እኛ ራሳችን መለውጥ ኣለብን: የሃገር ሃገራዊ ራእይ ኣግኝተን መስማማት የግድ ይላል።
ኣሉታዊ ኣስተዋጽኦ
በብልጣብልጥ እና በኣጭር ጊዜ ስልጣን ለመጨበጥ የሚደረገው ሩጫ ካለፈው 20 ኣመት እንዳየነው የትም ኣያደርስም። ለስልጣን መውጣጫ የሚደረጉ ኣስመሳይ ፈጠራዎች ሁሉም ነቅቶባቸዋል፣ ሰዎች ዝም ይበሉ እንጂ በልባችው መሳቃቸው ኣልቀረም። በዘር፣ በጎሳ፣ በጥቅማጥቅም ወዘተ የሚደረጉ ስብስቦችና መሳጥሮች ስንቶችት በታትነዋል:: በኣንጻሩ ደግሞ ኢሕኣዴግን ከነበረው ደካማነት ኣጠናክረውታል።
ስለዚ መጠላለፉ እና ሩጫው ይቅርና ረጋ ብለን ተሰባስበን፣ ተነጋግረን፣ ተመካክረን፣ ላይ ታች ብለን፣ ግዝያዊ የሃገር ኣመራር መመስረት የግድ ይላል። ወደ ሌላ ውጥን ሳንሄድ በቅድሚያ ያሉትን ድርጅቶች ተሰባስበው ግዝያዊ የሽግግር መድረክ እና ስርኣት – መመስረት ኣለባቸው። ከፓሪስ ኮንፈረንስ፣ ከኢድሃቅ ፣ ከህብረት፣ ከቅንጅት….መማር መቻል ኣለብን።
ስላለው የድሮ ታሪካችን ብቻ እያወራን እኛ ግድፈት የሞላበት ታሪክ እየሰራን መሆናችን ማወቅ ኣቅቶናል። ኣገራችን ለመጀመርያ ግዜ ወደብ ኣልባ ሁናለች (የተጀመረው ግን ከዓድዋው ጦርነት ጣልያን መረብ ምላሽ ሲቆጣጠር ነው) ፣ ገበሬዎች ከርስታቸው እየተፈናቀሉ; መሬታቸው ለባእዳን በርካሽ ዋጋ እየተክራየ ይሰቃያሉ፣ መንግስት ህገ መንግስት ተገን ኣድርጎ የፈለገው ያስራል፡ ያሰቃያል፡ ይገድላል፡ ይበትናል ወዘተ፣ ለሱዳን መሬት እየተሸጠ ነው፣ ፍርድ ቤቶች የመንግስት ፓለቲካ መሳርያ ሁነዋል፤ ታዲያ ከዚህ ሁሉ የባሰ ምን ሊመጣብን ነው። ይህን ሁሉ ማገናዘብ ኣቅቶን ለመፍትሄ መተባበር ሰንፈን መጠላለፍ ማንነታችን ኣድርገነዋል።
ትምክህተኝነት ከዛም ጠባብነት እንዲሁም መጠላለፍ ኣሁን ደግሞ ሙስና ኣገሪትዋን እየዶቆሳት ነው። ከጅማሪዎች የነበረች ሃገር። ታሪኳና ባህልዋ እያከሰምን ወደ ታች ዓዘቅት እየከተትናት መሆናችን እና ጸጸቱ ኣብሮን እንደሚቀበር ማወቅ ኣለብን። ከዚህ ውርደት ተስማምተንና ተከባብረን በሰላም መኖር እንዴት ያቅተናል። ጣልያንን ያሸነፉ ኣያቶቻችን እኮ ወድ ህይወታችው ገብረው ነው እንጂ እንደኛ እየተለጣጠፉ ኣልነበሩም።
ሁላችን ማውቅ እና መቀበል ያለብን ኣንድ ድርጅት ብቻው ስልጣን ልይዝበት የሚችል ግዜ ኣብቅተዋል። እስካሁን ድረስ በነበሩት ኣስከፊ የከፋፍለህ ግዛ ስርዓቶች ምክንያት በህዝብ ላይ ነቀርሳ ፈጥረዋል። የይቅርታና የእርቅ ስራ ኣልተሰራም። ሰለዚህ መተማመን የለም። ሙሱናም የሰዎች ራእይ ሁነዋል:: ይህ ለመንቀል የተደራጀ ሃይልና ህግ ያስፈልጋል። ይቻላልም።
ስለዚህ ከዚህ ሁሉ ውጣ-ውረድ ተምረን በህይወታችን መልካም ስራ ሰርተን ለመኖር እንብቃ። ለራሳችን ቃል ገብተን እንነሳ። የሌሎች ተበደልን የሚሉትን ወገኖች ብሶት ለማዳመጥ ትእግስት ይኑረን። ያኔ ነው ተግባብተን ለመስራት የሚቀለን። ከሙሱና ነጻ ሁነንም ገለልተኛ የፍትህ ተቋማት እያስፋፋን ህዝባችንን እያስተባበርን እየተረዳን፣ መልካም ስራ በመስራት ራሳችንን ደስ ኣሰኝተን፣ ሃገራችንን እየረዳን፣ ለተተኪ ትውልድ ገንቢ ባህል እያስተላለፍን፣ ሌሎችም በድህነት ሳይሆን በክብር እንዲያውቁን ማድረግ የምንችለው።
ኣወንታዊ ኣስተዋጽኦ
ኣሁን ተቃዋሚ ድርጅቶችን የሚያጣላቸው ፕሮግራም ወይም ፓሊሲ መኖር ኣልነበረበትም: ከነጻ ምርጫ ስርዓት ጋር ተያይዞ ህዝቡ ሊቀበላቸው ላይችል እኮ ይችላል፣ ግዜው እንዴት እየተለዋወጠ እንዳለ ለምን ኣይረዱም; ቢሆንስ ፍጽማዊ የሆነ ፕሮግራም እኮ የለም ዋናው በሰላም መመካከር እንጂ።
1. በሃገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች ተባብረው ለመስራት በንኡስ ፕሮግራምም ቢሆን መስማማት ኣለባቸው።
2. በውጭ ያሉት ተቃዋሚ ድርጅቶችም የበለጠ ሰፊ ስብስብ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል።
3. የሃገር ውስጥና የውጭውን ደግሞ የመንግስት ተንኮል ግምት ውስጥ በማስገባት ግንኙነቱ በዚህ ኣንጻር ሊከናወን ይችላል; ዋናው መተማመን እና ላንድ ኣላማ መቆም ነው።
የተቃዋሚ ድርጅቶች፡ ኣንድነት (USA)፣ ሸንጎ፣ ግንቦት 7፣ ኦነግ፣ ኢህኣፓ፣ መኢሶን ሌሎችም ተባብራችሁ ማእከላይ ኣመራር መስርታችሁ፣ የውጭውን ግፊት መምራት እና በሃገር ውስጥ ላሉት ተቃዋሚዎች የሚገባውን ድጋፍ እና ኣጋር መሆን ነው። ሌላ ኣማራጭ ኣለን የሚል ካለ መልካም። ከኢሳያስ ኣፈወርቂ በኩል የሚደረግ ስልታዊ ትብብር ግን ከጠቀሜታው ጉዳቱ ከመጠን ያለፈ እንደሆነ ያለፍት 40 ኣመታት ተመኩሮ ኣስተምሮናል። የጋራ ማእከላይ ኣመራሩ ከተቀበለው ግን ልንስማማበት እንችላለን።
ልዩነትን ተቻችሎ ሀገር መገንባት
እስካሁን ድረስ እንደታዘብነው እርስ በርሳችን መጠላለፍ፣ ለኢህዓዴግ በጎሳና በዘር እየፈረጅን እኛው ራሳችን በጎሳና በዘር ተሰባስበናል፣ ተበደልን የሚሉት ሳናዳምጣቸው ኣልተበደላችሁም እንድያውም ደልትዋችሃል ብለናቸዋል፣ ብሄራዊ ማንነታችን ያለ ህብረት ሊጎለብት ኣይችልም; ህብረት ደግሞ ኣላከበርንም; ተከተሉን እናውቅላችሃለን በዝተዋል። ሀገር ለመገንባት ልዩነትን ኣቻችሎ መደማመጥ; መከባበር; ለበጎ ስራ መትጋት ይጠበቃል። ሁላችን መሪዎች መሆን ኣንችልም ኣንድ መሪ ግን ማስቀመጥ ኣለብን። ትእግስትና ስብእነት ያስፈልጋል።
ኢህኣዴግ መውደቁ ሲቃረብ የተኪው ህብረት ጎልብቶ መውጣን ደግሞ ኣይታይም፣ እንዲያውም ሻክረዋል። ይህ ኣይነት ሂደት የሶማልያ የኢራቅ የኣፍጋኒስታን የመሳሰሉትን ሁኔታዎች እንዲከሰት በር ከፋች ነውና። ኢህኣዴግ ቢውድቅ ምን የፈጠርነው ኣብሮ የመስራት ባህል ኣለና? ልዮነትን ኣክብሮ መሰረታዊ በሆኑ ኣበይት ሕጎች ኣብሮ የመስራት ጅማሮ ማሳየት ኣለብን። የጓደኝነት ይሉኝታ ኣስወግደን ዘላቂ ሃገራዊ ራኢይ ውስጥ እንሳተፍ።
ታደሰ ገብረስላሰ
የታሪክ ጥናት አብነት -የታሪክ ትምህርት ተግዳሮት
(በካሣሁን ዓለም-አየሁ )
ታሪክ ማጥናት አያሌ ጠቀሜታዎች አሉት ።ታሪክን የምናጠናው በተለያዩ ምክንያቶች ነው ።ለታሪክ ማጥናት የመጀመሪያው አስባብ የአእምሮን እድገት ለመለኮስ ግልጋሎት መዋሉ ነው ።ታሪክ ማዕምራዊ ብስለትን ያነቃል።ሁለተኛው ምክንያት ደሞ፣ ለመልካም ዜግነት መሰረት መጣል ነው ።ሶስትም፣ ምግባራዊ ግዴታዎችን ለመፈፀም በብርቱ ያግዛል።በአራተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የታሪክ ጥናት ዞግ ታሪክ ባህልን ለመገንዘብ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ነው።በመጨረሻም፣ ታሪክ ለዉጥን ለማገናዘብ አስፈላጊነቱ መጉላቱ ።
አሜሪካዊው የታሪክ ምሁር ዋልተር ማክዱጋል ታሪክን መረዳት ለምን እንደሚጠቅም ባስተነተነበት የምርምር ወረቀት ላይ፣ ሶስት አበይት ምክንያቶችን እንደመደምደሚያ አቅርቧል ፣እንዲህም ይነበባል ። ” የታሪክ ትምህርት የአንድን ሀገር ህዝብ አእምሮአዊ እድገት የሚያነቃቃ፣አስፈላጊ የሆነዉን የዜግነት ድርሻ ለመትግበር የሚያተጋ እና ስነ-ምግባራዊ አገልግሎት እንዲወጡ የሚያዘጋጅ ግዙፍ መሳሪያ ነው ።” ታሪክ የወጣቶችን ሕሊና በምክንያት እንዲመራ የሚገራ ፣የሰው ልጆችን ህይወትና አኗኗር ጥልቀት፣ስፋት፣ክብረት(ሪችነስ) ለማድነቅ የሚያስችል ፣ስለ ሰው ልጅ አሳዛኝ የኑሮ መዋዕል የሚያስገነዝብም ትዉስታ የሚያድል ኃይል ነው።የታሪክ እዉቀት በሌሎችም ስነ- እውቀታት(ዲስፕሊንስ) ለምሳሌ ስነፅሁፍ፣ስነ -ልሳን፣ ስነ-ፍጥረት(ሳይንስ ) ፣ነገረ- መለኮት(ትዎሎጂ ) ፣ስነ- ሰብ(አንትሮፖሎጂ )፣ስነ-ሕብረተ ሰብ(ሶስዮሎጂ ) ፣ስነ -ቅሪት ቁፋሮ(አርኬዎሎጂ )፣ፍልስፍና፣ስነ -ህንፃ(አርኪቴክቸር) ወዘተ መሰረት የሚሆን የሚጣጣም አውድ እንደሚፈጥር ለግንዛቤ ከበቃ ሰንበትበት ብሏል ።ታሪክ የማንኛዉም ዘርፈ- ትምህርት ማዕምራዊ ግብዓት፣የአስተምህሮዎች መሰረት መሆኑን በምርምር የተራቀቁ በሰሎች በአፍም በመፅሃፍም ሲያውጁ ነው ዘመናት የተቆጠሩት ።
አሜሪካዊው የስነ- ትምህርት ተጠባቢ ሊኔ ማንሰንም በበኩሉ ስለ ታሪክ እዉቀት ፋይዳ ሲናገር ፣ “ታሪክ ስላለፉት ሁነቶችና ሰብእናዎች እርባና በማስተማር፣ ከራሳችን ህይወትና አኗኗር ጋር በማዛመድ አስተያይተን ይዞታችንን የምናበለፅግበትን መንገድ ለመቀየስ ያግዛል።ሰዎች በሃላፊው ዘመን የሰሩትን የፈፀሙትን በማወቅ ፣የራሳችንን አኗኗር በሰፊ ማዕቀፍ ዉስጥ እያስተዋልን በመመጪ ዘመን ማድረግ የምንችለዉን እንድንተልም የሚያበቃ የጥበብ አቅል ያድለናል።”ብሎ ያሰምርበታል ።ማንሰን ለትንታኔው ማሳረጊያ ያደረገው አረፍተ -ነገር እጅጉን ቀልብ የሚስብ ነበር ፣ ” ካለ ታሪክ እዉቀት ፣ አለምህ በጣም ትንሽ ናት። ” ያለው የብዙሃኑን ትኩረት ማርኩዋል ።ይህም የታሪክን ትምህርት ሁለንተናዊ ረብ ፣ታሪክ መማር ማጥናት የሚኖረዉን ታላቅ ቁብ ለፅድቅ የሚያበቃ ሆኖ እናገኘዋለን ።
የታሪክ ትምህርት አቀናቃኞች የታሪክን ስነ-ዜጋዊና ምግባራዊ አገልግሎት በተመለከተ እንዳብራሩት ከሆነ፣ የታሪክ ትምህርት ምናልባትም ከማንኛዉም የትምህርት ዘርፍ በበለጠና በላቀ ሁኔታ፣ ሰዎች እንዴት ኃላፊነት የሚሰማቸው ሆነው እንደሚቀረፁ፣እንደምን በህብረተሰቡ ዉስጥ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ ዜጎች ሆነው እንደሚታነፁ ያስተምራል።ለዚህ ነው እውቁ የታሪክ ተመራማሪ ማክዱጋል ታሪክ “በዘመናዊ ስርዓተ – ትምህርት ዉስጥ ያለ/የሚገኝ ሃይማኖት ” ነው እስከማለት ርቆ የሄደው ።
ለግላጋዎቹ ወሬዛዎች በሚኖሩበት ሀገር የተገነቡትን እሴቶች ሲማሩ፣ሁነኛ አምሳሎችን (አይድያልስ) ለመጠበቅና ለማስከበር የተደረጉትን ጦርነቶች ሲረዱ ፣የተለያዩ መሪዎችን ድል አድራጊነትና ሽንፈት ሲያጠኑ የራሳቸው ህብረተሰብ እንዴት እንደተበጀና መልክ እንዳበጀ እንዲሁም የነሱ ሚና በዚህ ዉስጥ ምን እንደሆነ በተሻለ መንገድ ደህና አድርገው ይረዳሉ ፣ይገነዘባሉ ።
የታሪክን እውቀት ግንዛቤ መታጠቅ ፣የታሪክን ውል ማስተዋል ማጥበቅ ወጣቶች ያለፉትን ግለሰቦችና ህብረተሰቦች አሳዛኝ ስህተት የሚማሩበትን አጋጣሚ ሁኔታ ሲያዘጋጅላቸው ፣ተመሳሳይ ስህተቶች እንደገና እንዳይሰሩና እንዳይከሰቱ የሚከላከሉበትን አመቺ ምህዳር ያደላድልላቸዋል።
ከዚህም ባሻገር የታሪክ ግንዛቤ ፣ወጣቶች ከቀደሙት ታላላቅ ሰዎች ዉሎ መንፈስ ተምሳሌት ተዉሰው ትላልቅ ህልሞች እንዲያልሙ ያነቃቃል።ባለፉት ግዙፍ ሰብናዎች ገድል አርአያነት ተገርተውና ተቃኝተው በሕይወታቸው ዉስጥ ድንቅና እፁብ ነገሮችን እንዲከዉኑ ዉስጣዊ ኃይል ለማፍለቅ ያበቃል ያጠረቃል ። የታሪክ ምርምር ሊቁ ማንሰን አክሎም ሲያትት ፣” ወደአለም የሚወስዳቸዉን የሚያደርሳቸውን አስፈላጊ እዉቀት የሚቸራቸው የሊበራል አርቶች እዉቀት ነው ።እናም ታሪክን ማጥናት የብልህ ምርጫ ነው ።” ሲል የታሪክን ትምህርት ንዑድነት ያደመቀበት ቀለም በእማኝነት የፀደቀ ብሂልነትን ተክኖ ዘልቁዋል።
በዚህ ፀሐፊ አገማገም፣ የታሪክ ጥናት ባህልንም ለመረዳት ያለው ጠቀሜታ እጅጉን የጎላ ነው ።የታሪክ እዉቀት ባህልን ለመመርመርና ለመተንተን በቁልፍ መሣሪያነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ።ጠለቅ ዘለቅ ያለ ታሪካዊ ግንዛቤ ሳይጨብጡ ባህልን ለመግለፅ የሚደረግ ሙከራ “ሳያጣሩ ወሬ፣ ሳይገሉ ጎፈሬ” ይሆናል ትርፉ ።ወደሁዋላ መለስ ብለው ታሪክን ካልዳሰሱ ፣የታሪክ መዛግብትን አገላብጠው ካልከለሱ የተለያዩ ባህሎችን መገንዘብ አዳጋችም አታካችም ነው የሚሆነው ።አንድን ባህል ጠንቅቆ ለማወቅ ከሁሉም የሚልቀው ሁነኛ አቀራረብ ባህሉ የተመሰረትበትን ፣ባህላዊ ገፅታው የተንሰራፋበትን አካባቢ ታሪክ በማጥናት ነው ።ስለ ባህል የሚያጠኑ በሳል ተጠባቢዎች እንደሚያስተምሩን ፣ባህል አጠቃላይ(ጀነራል ) እና ልይ ወይንም ዉሱን(እስፐስፊክ ) ተብሎ የሚደለደል ሲሆን ፣ሁለቱንም ባህላዊ ምዳቤዎች በቅጡ ለመረዳት የታሪክ እዉቀት እገዛ በፍጡነ-ረድኤትነት የሚስተዋል ሆኖ ይገኛል ።ታሪክ አጠቃላዩን ሃገራዊ ባህል የምናነፅርበት ፣ልይና ዉሱን የሆነዉን ግላዊና አካባቢያዊ ክበበ-ባህል የምናስተዉልበት መነፅር ሆኖ ያገለግላል ።እንዲህም ሲሆን ፣ታሪክ ለመልካም ዜግነት እዉንታ መሰረት የሚሆነዉን የራስን ልይና ዉሱን እንዲሁም አካባቢያዊ ባህል ጠንቅቆ ለማወቅ፣ የሀገርን የመንግስትን ስርወ- ታሪክ ልብ በማለት ብሔራዊ (ናሺናል )፣ሃገረ መንግስታዊ (እስቴት )፣እና አካባቢያዊ (ሎካል) ሆነው የፀኑ ሕግጋትን ፣ወጎችን ፣ልማዶችን ፣ግዕዛትን (ኖርምስ )፣ትዉፊቶችን ወዘተ ለመተዋወቅና ለመለማመድ አመቺ ጎዳና ይጠርግልናል።
በሌላም በኩል የታሪክ ጥናት እርባና ከሚገለጥባቸው የአተያይ ዘዌዎች(አንግልስ ) አንዱ ለዉጥን ለመረዳት የሚፈይደው ፋይዳ ገሃድነት ነው ።ለውጥ ከያንዳንዱ እለት ህይወት ማህፀን ዉስጥ የሚፈለቀቅ የሕይወት ዘር ነው ። ለዉጥ የህይወትም ቅመም እንደሆነ የሚያወሱ ሃታትያን በርካታ ናቸው ።የህልዉናን ፍሰት ለማስመር ለዉጥን በቅጡ ማየት፣መመርመርና መፍትሄ መሻት ወይ መላመድ ተፈጥሮአዊ ሕግም ጭምር ነው። ” ታሪክ ራሱን ይደግማል “ሲባል ስንሰማ አድገናል።ኖረናልም ።ታሪክ ራሱን ሲደግም ለማስተዋል የታደልንም በአሀዝ እንገዝፋለን መቼም ።ታሪክን ማጥናት እንዴት ለዉጥን በአግባቡ ማጤንና መወጣት እንደሚገባን ያስተምረናል ።ለዉጥ ሲከሰት ዞር ብሎ ኃላፊዉን ጊዜ መመልከት እጅግ ብልህነት ነው።ለዉጡ በተሸኘው ዘመን የነበረዉን ሁኔታ መፈተሽ፣እኛም ሆነ በቅርብ የምናውቃቸው ወይም ታሪካቸዉን የሰማንላቸው ሰዎች፣ቡድኖችና ሰብአዊ ስብስቦች ፣ማህበረሰቦች ፣ህዝቦች ፣ሀገሮች ወዘተ እንዴት ለዉጡን በማስተናገድ ተሻግረን /ተሻግረው ማለፍ እንደቻልን/እንደቻሉ ልብ የምንልበትን አስተዉሎት ይለግሰናል።ይህንንም አስተዉሎት ለገዛ ራሳችን ህይወት አርአያ ምሳሌ አድርገን ልንገለገል እንችላለን ።ከዚህም በተጨማሪ ፣ታሪክ ለዉጥን በወርደ -ስፉህ(ላርጅ ስኬል ) መልኩ አብራርቶ ለማስተንተን አቅል ይቸራል።ለምሳሌ አንድ ሰው ለምን የኑሮ ዉድነት እንደተከሰተ ፣የኑሮ ዋጋው ንሮ ስለምን ህዝቡን በችግር እንዳባዘተ ለማወቅ ቢሻ ፣ታሪክን ዳግም በመፈተሽ የምጣኔ ሃብታዊዉን ዝቅጠትና ድቀት ገፅታ ሊቃኝ፣መንስኤዎቹንና የስፍነቱን መጠን መርምሮ ሊያገኝ አይሳነዉም።ይህም በታሪክ የተፈሸነ፣በታሪክ ተዳውሮ የተሸመነ ግኝት አሁን ባለንበት ወቅት በቃሪያ ጥፊ እሚያጮለንን ዉጥንቅር ፣እግር ከወርች ቀይዶ አላላውስ ያለልን ዉንክርክር ድንግርግር በወጉ ሊያመላክተን ይበቃል።
ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረዉና ሁላችንም እንደምናውቀው የታሪክ ትምህርት እንደው ታሪክን ለማተት ብቻ የሚሰጥ ትምህርት አይደለም ። ታሪክ ብዙ እጅግ ብዙ ነገሮችን ያስተምረናል ።ታሪክ የትውልድን አእምሮ በማንቃት ፣የወጣቱን ሕሊና በቁም ነገር በማጠርቃት ወደ ብስለት ያሥገሰግሰዋል።እርምጃዉን ያፋጥናል ።የታሪክ እዉቀት የመልካም ዜግነት መስረት ፣የዜግነት ግዳጅን በስኬታማ መልኩ ለመወጣት የሚያስችል ፣የግንዛቤ አብነት የሚያድል ሲናዊ ክህሎት ያላብሳል።ከዚህም ተያይዞ ፣ታሪካዊ እዉቀት ያለንበትን ማህበረሰብና ሕብረተ -ሰብ ወግና እድር ፣ትውፊቶችና ግዕዛት፣ፍቁዶችና አይነኬዎች ጠንቅቀን፣ ድረ-ገብ ባህርያት አዳብረን በምግባረ -ሰናይነት ኑባሬያችንን እንድናስመሰክር ኮትኩቶ አሳዳጊያችን ነው ።ወደ ባህላዊው ዳራ ስንዘልቅም፣የታሪክ እዉቀት ባህልን በጥራት በምልዓት ለመገንዘብ አይናችንን በሚከፍትልን የብርሃን ዘሐ ይመሰላል ። ታሪክ ማጥናት በእለት ተዕለት ሕይወታችን፣በዙሪያችን በሚፈጠሩት ለዉጦች መሃል እንዴት መኖር እንደምንችል ፣እንደምን የለዉጡን ማዕበል ዋኝተን እንደምንሻገር የሚያግዘንን ኃይል ያስታጥቀናል።
ታሪክን የሸመገለው ዘመን አስታዋሽ ፣ያልሰለጠነና ሁዋላ ቀር ትዉልድ ትዝታ ቀስቃሽ ብቻ አድርጎ መመልከት በራሱ ካለመሰልጠን የሚመጣ ግድፈት ሆኖ የሚታይ ነው ። ጥበባዊ በረከት ይደርጅለትና በሳሉ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፣
“የት ጋ እንደሆን ይታይ የኛ ጥበብ መሰረቱ ፣
የሁዋላው ከሌለ የለም የፊቱ ።
ሳይራመድ በታሪክ ምንጣፍ ፣
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ።”
ያለው የብዙዎችን ትኩረት የማረከው በዋዛ አይደለም ።ታሪክ የትላንት መሰረታችን ከዛሬ ይዞታችን ተነፃፅሮ፣ ነገያችን በተራዘመ አተያይ ታልሞ፣ ተተልሞ የሚገራበት ወደረኛ የኑባሬ ጉባኤችን ነው እኮ። ታሪክ የምንነታችን ፣የእንዴትነታችን ፣የማንነታችን የከየት ወዴት አሻራችን ነዉና ልናውቀው ልንጠብቀው ይገባል።
ታሪክ ሊከበር ይገባል ።ታሪክ ከምናብ ተፈልቅቆ ፣በግለሰባዊ የፈጠራ ግፊት ብቻ ተጨምቆ የሚነገር ተረት ፣የሚፃፍ የፈጠራ ድርሰት /ወግ አይደለም ።ወይም ቡና በአቦል ተቀድሶ በበረካ እስኪያሰልስ እርስ በርስ የሚተጋተጉበት ተረብና የነገር ጉሸማም አይሆንም ፣ከቶም ቢሆን። ታሪክ አግቦና አገም ጠቀምም አይደለም ።ያለ የነበረን የዘመን ዉሎና አዳር ፍርድ ሳያዛቡ ገልፀው ፣ግራና ቀኝ አይተው ያለአድልዎ በይነው ተንትነው ፣ለመጪው ትዉልድ ቅርስ ማስተላለፍ ነው። ታሪክን ማዛባት ፣የተወናከረ ታሪክ ማስተማር ፣ማስራጨት ማስተጋባት ያስጠይቃል ።ያጠያይቃል።ታሪክንም እንዳይማሩ መከልከል ማገድ፣የታሪክ ትምህርትን ቢጋር ከሥርዓተ ትምህርቱ ደልዞ መፋቅ ፣ከፍተኛ ትምህርት ተቁዋማት፣ዩኒቨርስቲዎች የታሪክ ትምህርት እንዳያስተምሩ በመግለጫና ሰርኩላር ማገድ ሃገርን መግደል መሆኑ ሊጤን ይገባል።ሀገራችን በአያሌ አይ-አዎዎች (ፓርዶክሥስ ) አየታመሰች ነው ።ግብርና -መር የኢንዱስትሪ እድገት ለእዉንታ የሚያበቃ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ መታወቂያ ዉሌ ነው ያለው መንግስት፣ ከትምህርት አይነቶች ማዕድ እርሻና ከብት እርባታዉን አካቶ የሚያቅፈዉን የግብርና ትምህርት ድራሹን ካጠፋ ሰንብቷል ።በዚህም የገበሬው ልጅ ወላጆቹን እንዳቅሙ ሊመክር የሚያስችለው አንዳች እይታ እንዳያጎለምስ ድድር ግርዶሽ ጋርዶበታል፣ትንሽም ቢሆን ምርት ማሳደጊያ ምክርና አስተያየት እንዳይሰነዝር ዕድል ነፍጎታል።የታሪክ ትምህርት ወቅታዊ ተግዳሮትም በመፃኢ እኛነታችን ላይ የሚቆልለው አስከፊ ጫና የትየለሌነቱ ካሁኑ ይታየኛል።በረከት ስምዖን ድርሰት የተለማመደበትንና ፣እስከዛሬም ፈውስ ባላገኘለት የንክነት (ንዩሮሲስ ) ሕማሙ መዳፍ ስር ተጨብጦ፣ ፍርሃትና ጭንቀት ተልትሎ በከታተፈው ፣ እብድ እንደያዘው በሶ በነፋስ ተበታትኖ በተዘራ መንፈስ የጫረዉን “የሁለት ምርጫዎች ወግ” ነው የታሪክ አባሪ የምናደርገው ?ተዋደው ተዛምደው ፣ተፋቅረው ተከባብረው የኖሩትን ህዝቦች በጎሳ ነቀርሳ ልክፍት አናቁሮ በማበላላት ፣ለኢሕአዴግ መንሰራፋት አመቺ መንገድ በክፋት ለመቀየስ፣ የሻቢያው ሰላይ ተስፋዬ ገብረአብ ህዝብን በህዝብ በማያባራ ግጭት ለማፋጀት የፃፈዉን “የቡርቃ ዝምታ” ብቻ ነው ታሪክ ብለን የምናወርሰው ?የኤርትራ ታሪክ ሟቹ መለስ ዜናዊ ደደቢት በረሃ ዉስጥ መሽጎ በፃፈው ብቻ ተወስኖ መቅረት አለበት ?የጅማ አባጅፋርን ቤተ- መዘክር ትተን ነው የአኖሌን ሃውልት የምናስጎበኘው ?መምህር ወልደኪዳን በሚያሳዝን ቅጥፈት የደጎሱትን የተንሻፈፈ ተረት ነው ለልጆቻችን አደራ የምናኖረው ? ታዋቂ ምሁራንንና ተመራማሪዎችን ያፈራው ፣በበርካታ ሺዎች የሚሰሉ አፍሪቃዊ የታሪክ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ወግ ማዕረግ ላለው አላማ ያደረሰው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ለመዘጋት መቃረቡ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት ነቢይነትን አይጠይቅም ።እጅግ አሳዛኝ ሁነትነቱ ከማንም የተሰወረ አይደለም ።ሁላችንንም ሊያሳስበን ግን ይገባል። አሁን ነው ስለ ታሪክ ማሠብ ። የዛሬን ቱማታ ብቻ ሳይሆን ነገንም ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው።መንግስት በታሪክ ትምህርት ላይ የተከሰተዉን ችግር አስተዉሎ አሰብ እንዲያደርግ ጊዜው ትልቅ ጥያቄ ደቅኖበታል።እንዴት እንደሚዳኘው ከርመን እናየዋለን ።የነገ ሰው ይበለን ።
ጀግንነት የሁለት ፊደላት ፍጥረት ነው ። ሥራ!
(ልክ የዛሬ ወር ነበር ረ/አውሮፕላን አብራሪ ሀይለመድህን አበራ ሲዊዘርላንድ – ጄኔባ ላይ የሠራው – ጀግንነትን)
ሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
ዕለተ ሰኞ 17.03.2014 ብሄራዊ ቀኔ ቅኔዬም ነው – ለሥርጉተ። ነገ ደግሞ በብሄራዊ ደረጃ እንዲከበር ይሠራበታል። የነፃነት ቀን በአዬር መንገዳችን ልዩ ምልክት ይሆናል። ከሥራ የተፈጠረው ጀግንነት መጠነ ሰፊ አክባሪም በቂ አድማጭም አለው። በጣም በእርግጠኝነት። ቀለሙ ሰንደቁ ነውና። ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ሀይለመድህን አበራ ተገኘ የፈጸመው ተግባር በእግረመንገድ የተከወነ ሳይሆን በውስጡ ባለው ፈቃደ እግዚአብሄር ነው። ገሃዱ ይህ ነው።
(„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል። እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። ምሳሌ ምዕራፍ 16 ቁጥር 9)
ወጣቱ ሀይለመድህን አበራ ውስጡ የተሰማውን ጥልቅ ስሜት በሰለጠነ ህሊና ገለጸ። ይህ ደግሞ ክህሎት ነው። ስሜት ለሰጠው እውነት ለመገዛት ወስኖ ፈጣን ምላሽ ሰጠ። የገለጸውም ለሰላማዊ የነፃነት ትግል ትርጉም በሚሰጥ ሁኔታ ነበር። ከዚህ በኋላ ነው ቴክኒካል ነገሮችን ማዬት የሚቻለው። ያስተዋለውን እውነታ ከምክንያታዊ ጭብጦች ጋር አጋብቶ አበለጸገው። ስለሆነም ክህሎቶ በሥነ – ጥበብ ቁመትና ወርድ መለካት አለበት እላለሁ እኔው ሥርጉተ ሥላሴ። በሊቀ -ሊቃውንታት ዓይንም ሊዳሰስ ይገባዋል ባይም ነኝ። የበራ አፈፃፀሙ በራስ የመተማመን ጉልበቱ ነበርና። ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ሀይለመድህን አበራ የተነሳው ከገሃዱ አለም ማዕከላዊ ጭብጥና ከነባራዊ ሁኔታውም ነው። በዚህ ሂደት የብዙኃኑ ስሜትና ፍላጎት በአኃቲነት በውህደት ተጋብተዋል።
ሙያ በሥልጠና የሚገኝ ቢሆንም አገልግሎቱ ለህዝብ ስሜት ቅርብ ሲሆንና ማደማጥ ሲችል፤ የሙያው ክህሎት ሆነ ብቃቱ ውስጥን ገላጭ ስለሚሆን ውጤቱን ዓይነ – ገብ ያደርገዋል። ወጣት ሀይለመድህን አበራ እሱ ራሱ የገህዱ ዓለም ታዳሚ በመሆኑ ቅርበቱን የበለጠ ጉልህ ስለሚያደርገው እርምጃው የለማ ትራስ ሆነ ድልዳል አለው። በሥልጠና ያገኘው የክብር ስያሜም ከተግባር ሥራው ጋር ሆኖ ቋሚ ትምህርት ቤት ሊሆን መቻሉ በቂ አድናቂና ቋሚ የድርጊቱ አድማጭ እንዲያገኝ ጉልበት ሆኖታል።
ስሜቱን ኮርኩሮ ለዚህ የላቀ ተግባር ያበቃው ሚስጢር አዳራን ከብዙኃን ውክል ስሜት ጋር ሚዛን ላይ አስቀምጦ የደፋውን እርምጃ የችሎቱን ድምጽ መውሰዱ ነው። ዬሚመጣውን ማናቸውንም መስዋዕትነት አዝናንቶ ለማስተናገድ የቆረጠው የህሊናውን አድማጭነት፤ እንዲሁም ከወገኖቹ የሚያዬውን ብቻ ሳይሆን መሆን የሚችለውን የውስጡን ፍላጎት አድምጦ መወሰን መቻሉና ከዛ ላይም መነሳቱ የአቅሙን ብቃት በጉልህ ያብራራል። የብልህነቱን ጥልቀት ለማዬት አጅግ በርካታ የዝምታ ክንውኖችን ማንሳት ቢቻልም ጸጋውን አውቆ በጥዋቱ ተግባር ላይ ማዋሉ ዘመናትን ሊያሻግር የሚችል ዓምደ ተመክሮ ነው – ለእኔ።
ጀግናዬ ሀይለመድህን አበራ ዛሬ በውል ሊታዬን ያልቻለም ሚስጢር በውስጡ እንደ ጸነሰም ለእኔ ይሰማኛል። በጥሞና የመረመረው፤ የገጠመኝ ዘለላዎቹን ሁሉ ንጹህ ጥሬ ሀብቱ እንዲሆኑ አድርጎለታል። ፊድ ባኮቹ ከውጣ ውረዱ ማሳ ያፈሰውን ትልቁና ብቸኛ የወርቅ እንክብል በመሆናቸው „እኔስ? ምን?“ የሚሉትን የህሊና ጥያቄዎች፤ የግራ፣ የቀኝና የማህል ዳኛ፤ እንዲሁም አቃቢ ህግ፤ በተጨማሪም ጠበቃ ሆኖ በሙሉ ልብ ብይን ሰጥቶበታል። የተከደነ ሲሳይ ይሏችኋል ይህ ንጡርነት፤ መረቅነት፤ ክውንነት ነው። ፍላጎቱን ከመንፈሱ ጋር፤ ስሜቱን ከተፈጥሮው ጋር፤ ድርጊቱን ከኃላፊነቱ ጋር አስማምቶ ሙቀት ሸልሞናል። ቅዝቃዜና ብርድ በእሱ የጭምትነት ተልዕኮ የሉም። ጥበቃ አስቀድሞ የደነገገላቸው ተግባራቱ ጥናታዊና ምርምራዊ ናቸው። ፍልስፍናዊና አምክኗዊ ማለትም ይቻላል።
„አሻምን“የገለጸበት መንገዱ ከዚህ በፊት ያልታዩ፤ ፈጽሞም ሊታሰቡ የማይችሉ ክጥፋትና ከትርምስ የዳኑም ናቸው። ይህ „ፍቅር“ የሚባለው የመስዋዕትንት የቆረጠ አርበኛ የሚሻ የኑሮ፤ የህይወት፤ የነፃነት፤ የመብት፤ የብሄራዊ ግዴታ አስኳል ታዬ። አውነታዎች ከሚታዩ ገጠመኞች አውድማ
ለሰንደቅዓላማ፤ ለዳር ደንበር፤ ለህግ የበላይነት፤ ጧሪ ጠዋሪ ላጡ የአደራ ውርስና ቅርሶቻችን ሁሉ ከፍቶ ገብሯል። ወጣቱ ሀይለመድህን አዬር ላይ ሆኖ ከአንዱ ገጸ ባህሪ ወደ ሌላው ገጸባህሪ ሲሸጋገር በቁጥብነት፤ በድንበር፤ ልኩን ለክቶ ሊገለጽ በማይችል ርጋታና በስክነት፤ ሥራን ከግድፈት በብልህንት ነጻ በማውጣት ጀግንነትን ነፍስ ዘራበት። ላላጣጠመው የወጣትንት ቀንበጥ ህይወት መራራን ጽዋ በፍጥነት ቀድሞ እራሱን ሰጠበት። ከምንም ነገር ጋር ንክኪ የሌለው „ፍቅር“ ማለት ይህ ነው።
እኛ አብዛኞቻችን የተሳነን ደግሞ ይህን ማድረግ ይመስለኛል። የምንፈልገውን ሆነ የምንወደውን ነገር እራሱ በቅጡ የማወቅም ተዛነፍ ዕያታ ነው ያለን። ፍላጎታችንም በነፍሳችን ውስጥ ተጠላይ ነው ወይንም ጭሰኛ። አብዛኛውን ጊዜ ጥግና ሳቢያ መፈለግ። ይህም ማለት እኔን የሚኮለኩሉ ጉዳዮች በመጡ ቁጥር ወይ ኮማ ውስጥ መሆን ወይንም ኩብለላ ያሰኘኛል። በዬፌርማታው መሽሎክ። ስለሆነም ፍላጎት ሲባዝን፤ ወይንም ሳይረጋ ወይንም አፈር ሳይለብስ ክው ብሎ ደርቆ በኖ ይቀራል። ፍርፋሪና እንጥፍጣፊ የተሰናበተበት ምኞት። ምክንያቱም ቋሚ ፍላጎትን በውስጥ የማነፅ፤ በጽናት አበክሮ የማበቀል ብቃቱ ውሽልሽል ስለሚሆንም ነው። ልጅም፣ ታናሽም የሆነው የትናንት አንድ ፍሬ „ሥራ“ በአጽህኖትና በተደሞ የሰበከው ይህንኑ የውስጥ ግድፈታችን እንድናርም ነው። አንድ ፍጥረት የ30 ዓመት ወጣት ትንፋሽን ሳቢና ጉልበታም አቅም ኖሮት እንዲህ የዓለም አጀንዳና ፊኖሚና ለመሆን በቃ። በቃ! ያበቀለው የሥነ – ህይወት ዋርካ። እራሱን ለፍላጎቱ የማስገዛት ጥንካሬውም አይነታ ብሂል ነው የመሆን አንጎል።
ገና በጋሜነት በኩብልና፤ እጅግ በሚያሳሳው አፍላነት ዕድሜው ለተሰጠው ጸጋ ራሱን የሚያስገዛ ፍጡር ፍላጎቱና አሱ ህይወትን በፍጥነት መረዳቱ ብቻ ሳይሆን፤ በጥልቀት የማጤን፤ ስለነገ ብቁ ግንዛቤ የመኖር ብሩህ ህሊና ላላቸው ፤ እንደ ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ሀይለመድህን አበራ ተገኘ ላሉ ብቻ የተሰጠ መክሊት ነው። ድርጊቱ ከገሃዱ ዓለም ጭብጥ ገዝፎ የወጣ በመሆኑ ጥልቅ ተግባሩ ጀግና ሊያሰኘው መቻሉ ቢያንሰው እንጂ የሚበዛበት ሊሆን ከቶም አይገባም። ድምጽን በዳጣ አንባገነን ለተገፋ ብዙሃን ህዝብ ለዘመኑ ፍትህ ርትህም ነው። በዚህ ሥም ነገ ሚሊዮኖች ይጠሩበታል። ታሽቶና ነጥሮ የወጣው ተግባሩ ውበቱ ያለው ከእውነታው ማዕከል በመሆኑ ፈተናን የመርታት አቅሙም የዚያኑ ያህል ጉልበታም እንደሚሆን ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።
ህይወት ወይንም መኖር ሲባል በማህበረሰቡ የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ በንቃትና በባለቤትነት ስሜት መሳተፍ ማለት ነው። በሌላ አገላለጽ አንዲህ ላቅ ብሎ ለተሰጣቸው ሰዎች የህብረተሰቡ ችግር፣ ሰቆቃ ሆነ መከፋትም ከሌላው የህብረትሰብ ክፍል ይልቅ ቀድሞ ያሳስባቸዋል – ይታያቸዋልም። ለዚህም ነው መግቢያ ላይ ሥራው በሥነ – ጥበብ ዓይን ሊታይ ይገባዋል ያልኩት። ስለሆነም ሃይላችን የህዝባችን የመንፈስ ውጥረታዊ ፍርሃት፤ ዬየጓዳው ጃንቦ ስጋት፤ የተስፋ ድርቀት፤ ዬህልም ርቀትን በጥንቃቄ በማስተዋል፤ መቼቱንም አዋቅሮ ለራሱ ሳይሰስት፤ ግጭቶችንም በማስማማት ለወቅቱ ዬተፈቀደለትን የሙሴነት ተስጥዖ ሳያልፈው ወይንም ሳይዘለው ወይንም ሳያፍነው በመሆን በዝምታ ድባብ ቀደሰው። ስለዚህ ለእኔ ከጀግንነትም አልፎ የህይወቴ ነው ማህደሬም።
ወጣት ሀይለመድህን የህውከት ጦሮ የሚንጠውን አዬር ራሱ ነፃ አውጥቶታል። ማህል ላይ የተገተሩ ዥንጉርጉር፤ ስርክራኪ፤ ሸውራር ተዛነፍ ፍላጎቶችን ሁሉ በዝምታ በማረቅ፤ መስመራቸውን በፍጥነት እንዲያስተካክሉ በማድረግ የኃይል አሰላለፉን እንደ ገና ሪባይዝ በማደረግ ጥንቃቄና ጥራትን አውጆለታል። እንዲሁም ካለገላጋይ ከቁንጨጮ ላይ ወጥቶ የሚያተራምሰውን የግል ኢጎም ዘቅዝቆ አንጠልጥሎታል። ለሌላው መኖር – ክብርም ለህዝብ ፍላጎት መቅድምነት በማለት ወጤታማ ተግባር ከውኗል። ስለሆነም ጀግናዬ ሀይለመድህን አቅምን ሳያባክን የአደራን ጥሪ „እሺ“ ብሎ ስለፈቀደ እንሆ ተወደደ።
እንደ መቋጫ – „ጀግናችን አጀንዳችን“ ብዬ በጻፍኩት ላይ „አመላችሁ ነው። የሰሞናት ነው፤ የወረት ነው“ የሚል አስተያዬት ከአንድ የጹሑፌ ታዳሚ አንብቢያለሁ። የተከበሩ የሀገሬ ልጅ ጹሑፌን ጊዜ ወስደው ስላነበቡልኝ ከፍ ያለ ክብር አለኝ። አመሰግነወትምአለሁ። ልነግረውት የምሻው ቁምነገር ግን አለኝ። ያዳምጡኝ። ሥርጉተ ሲዊዘርላንድ እያለች የማነን ጎፈሬ ታበጥር ይመስለወታል? ሥራዬ ምን ሆነና?! „ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት“ መደበኛ የህይወቴ አጀንዳዎች ናቸው። ጠረኖቼ ትንፋሾቼም መሆኑንም ልግለጽልዎት እሻለሁ። በጣም በእርግጠኝነት ልነግረዎት የምሻው ለእኔ ወጣት ሀይለመድህን መስቀሌ መሆኑን ነው — ተግባባን ወዳጄ።
ከሚያዚያ 10 ቀን 2014 ጀምሮ ደግሞ በቅኔው ንጉሥ በጸጋዬ ድምጽ ራዲዮ ፕሮግራሜ በዬ15 ቀኑ ቋሚ ዓምድ ይኖረዋል „የተስፋ ማህጸን“ www.lora.ch.tsegaye. ይጠብቁኝ። ግን እርሰዎ „የኢትዮጵያ ምድር ጦር፤ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል፤ የኢትዮጵያ አዬር ኃይል፤ ኢትዮጵያን ያስቀደሙ የሲቢክስ ማህበራት፤ ድርጅቶች ሁሉ በነቂስ እዬተለቀሙ ወያኔ በዱድማ ህሊናው ሲንዳቸው ከቶ የት ነበሩ?!“ የአንጋፋው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ሙሴ ሰማዕት አሰፋ ማሩ በጠራራ ጸሐይ በባሩድ ሲንድ —- በደል አይረሳም ያገረሻል እሺ። ይበሉ እንደ አውሮፓውያኑ ሰዓት አቆጣጠር ከ15 እስከ 16 ሰዓት ሚያዚያ 10.2014 አዬር ላይ እንገናኝ። ለሚመድቡልኝ ጊዜም በቅኑ መንፈስ የቅድሚያ ምስጋና ተላከ – ለእርሰዎ- ለጌታው።
ውዶቼ የእኔዎቹ ብትክትኮች፤ አፋፍ ላይ የተንጠለጠሉ፤ ማጣፊያ ያጠራቸው፤ እንደሚሉን ሳንሆን እንደ ፍላጎታችን ጠንካሮች እንሁን። ቀዳዳውን ሁሉ የምናሸፍንበት ዘመን መሆን አለበት። በተለይም ሴቶች፤ እሺ ልዕልቶቼ። ክብረቶቼ የሀገሬ ልጆች ዛሬ በአጭር ትጥቅ ዕይታዬን አጋርቼ ሽው ልል ነው …. የጀግንነት የአንደኛ ወሩ „የተስፋ ማህጸን“ ዝክረ ሀይለመድህን በዚህ መልክ ማህሌት ተቆመለት። ሙሉቀን ከድንግል እግር ሻማ ይበራል። ወገኖቼም ፌስቡካችሁን ቲውተር አካውንታችሁ በጀግናቹሁ አንቆጥቁጡት። ፈቅዳችሁ ለሰጠችሁኝ ጊዜ አከበርኳችሁ። ወደድኳችሁም። መልካም የተግባር ጊዜ – ለሁላችንም። ሥራችን – እንሥራ!
እግዚአብሄር ስለሚሰጠን የመንፈስ ማረፊያ ጀግና አድናቆታችን ለዘለአለም ነው!
ፈተናን ከመፈጠሩ በፊት አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
በነፃነት ቀን ነፃነት ማጣት !
ከይድነቃቸው ከበደ
ሰብአዊ መብቶች እያንዳንዳችን ሰው በመሆናችን ብቻ የሚገቡን ከሰብአዊነታችን ተለይተው ሊታዩ የማያችሉ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስታት እነዚህን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ሰብአዊ መብቶች ለማክበር ለማስከበርና ለማሟላት በቀዳሚነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት ኃላፊነት ከፈረሙ ቀደምት አገራት መካከል ኢትዩጵያ ትገኝበታላች፡፡
ይሁን እንጂ የሴቶች ሰብአዊ መብቶች በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ ካለመሆኑ ባሻገር ኢ-ፍትሃዊነት እጅግ የበዛ ነው፡፡ ይህም በመሆኑም እ.ኤ.አ. በ1908 በአሜሪካ ኒወርክ ከተማ በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩ ላብአደር ሴቶች ‹‹ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያና የተመቻቸ የሥራ ሰዓት ለሴቶች›› በሚል መፈክር የሥራ ማቆም አድማ በማካሄድ የሴቶች ድምፅ እንዲስተጋባ አድርገዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የዓለም ሴቶች በማህበር በመደራጀት ትግላቸውን በማጠናከራቸው የዓለም መንግስታትን አስተሳሰብ በመለወጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል አገሮች የሴቶች መብት ስምምነት/ኮንቪክሽን/ እንዲፈራረሙ እብይ ምክንያት ሆነዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ1910 በኮፕን አገር ከተማ በተደረገው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ጉባሄ ላይ የመነሻ ሃሳብ በማቅረብ ማርች 8 በየዓመቱ እንዲከበር ያደረጉት ሴቶች ለመብታቸው ያደረጉትን አስታውጾ ለመዘከር ዓለም አቀፍ መድረክ ለማመቻቸት በመቻላቸው ስማቸው በአክብሮት ይነሳል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓሉን ያከበሩት ጀርመን፣አውስትራሊያ፣ሲውዘርላንድ እና ዴንማርክ ለመሆናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከዚሁ የአንድነት ተምሳሌትነት በመነሳት በዓለማ አቀፍ ደረጃ ማርች 8 የሴቶች ቀን በማድረግ ዓለም አቀፍ ስያሜዎችን በመስጠት አገራችን ኢትዮጵያ ጨምሮ በተለያየ መልክ ሲከበር አመታትን እቆጥሯል፡፡ የዘንድሮዉም ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን እስከ ዛሬ በአገራችን በተከታታይ የኢትዮጵያ ሴቶች ካከበሩት በዓላት የሚለየው ሁሌም የምኮራባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሠላማዊ ታጋይ ሴቶች የፈፀሙት ገድል ነው፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ የዜጎች መብት በእኩልነት ተጠብቆ በሴቶች ላይ አጥልቶ የኖረው የጾታ ጭቆና እስከዛሬ ምላሽ ያላገኘ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡በተለይ በወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት የስልጣን ዘመን የሴቶች ጭቆና እና የመብት እረገጣ በህግ ማቀፍ ውስጥ መሆኑ ይብልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ይህን ለማለት የሚያስደፍረው የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው በሚባለው ህገመንግሰት የፆታን አድልዎ የሚቀርፍ እና የሴቶችን መብት የሚያመላክት ድንጋጌዎች በውስጡ አካቶ የያዘ ቢሆንም ተግባሪዊነቱ ፕ/ር መስፍን እንዳሉት ‹‹የተፃፈበትን ወረቀት ያህል ዋጋ የማያወጣ ነው››፡፡ ዋጋ አለው እንኳን ከተባለ የትርፉ ተካፋይ የሆኑት የገዥው መንግሰት አጨብጫቢዎች እና የጡት ልጆች ብቻ ናቸው፡፡
በአገራችን መከበር ከጀመረ ከሦት አስርታት በላይ ያስቆጠረው ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለሴቶች በሴትነታቸው ከሚደርስባቸው ጾታዊ በደል እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ያስቀረላቸው አንድም ነገር የለም፡፡ በተለይ ከላይ እንደተገለፀው በወያኔ/ኢህአዴግ መንግሰት ሴቶች በህግ እና በመብት ጥላ ስር ከፍተኛ የሰብአዊና የዲሞክራሲ ጥሰት እየተፈፀመባቸው ይገኛል፡፡
እጅግ አስገራሚው ክስተት ደግሞ የኢህአዲግ ሴቶች ሊግ ፣ የሴቶች ፎረም ኢህአዲግ የሚያዘው እና አገዛዙ ያስተባበራቸው በርካታ የሴት ማህበራት ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለወያኔ መንግስት ስርአት ነው፡፡ ስርአቱ ደግሞ የመላው ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እና ይሁንታ ያላገኘ መሆኑ ነው፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከመንግስት ድጋፍ ውጪ በራሳቸው ፍቃድና አቅም አንድም የተደራጀ ማህብር የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ እርግጥ ነው የሴቶች የፅዋ እና የእድር እንዲሁም የዕቁብ ማህበራት በአገራችን ለቁጥር የሚታክቱ ነው፤ግን እነዚህ ማህበራት የሴቶችን ሁለንተናዊ ችግሮችን የሚቀርፉ አይደለም፡፡
ለመደራጀት ሳይሆን ለማደራጀት ትኩረት እና ድጋፍ የሚሰጠው መንግሰት በሴቶች ላይ ማላገጥን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል፡፡ለዚህም እንደማሳያ ከታችኛው የቀበሌ ባለስልጣን ጀምሮ እስከላይኛው የአገር መሪ የሴቶች እኩልነት እና የመደራጀት መብት በህግ የተጠበቀ እንደሆነ ሳይታክቱ የሚገልፁት ነገር ነው፡፡ይሁን እንጂ የሴቶች እኩልነት እና የመደራጀት መብት ለኢህአዴግ አባልነት እና ቤት ለቤት ቡና እያጣጡ የተነገራቸው መልሰው ከማውራት ከቅያስ ወይም ከጎሮ ከድሬነት ያለፍ ተሳትፎ ከተደራጁበት ሳይሆን ከደራጃቸው አካል ያተረፉት ነገር የለም፡፡ ከላይ የተጠቀሰው አሳብ ለመረዳት እና ለመታዘብ ብዙ መራቅ አያስፈልግም በህገመንግስቱ መሰረት ተደራጅተዋል የተባሉ ማናቸውም እንዲሁም በየትኛውም ቦታ የሚገኙ የሴት ማህበራት ከመንግሰት ተፅኖ ውጪ ላለመሆናቸው ከማህበራቸው የስም አወጣጥ ጀምሮ ተግባራቸው በመመልከት በቀላሉ ማህበሩ እና ማህበርተኞችን እነማን እንደሆኑ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ለዚህ ፁሑፍ መነሻ የሆነው አሳብ ዘንድሮ ተከብሮ ሳይሆን ተደፍሮ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ማርች 8 መሰረት ያደረግ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የባለፈው እሁድ ማርች 8 አስመልክቶ የሴቶች 5 ሺህ ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር ተካሂዶአል፡፡ በውድድሩ ላይ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶች ተሳትፈዋል ፤ከተሳታፊዎቹ ብዛት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ በአነስተኛ እና ጥቃቅን መንግስት ያደራጃቸው ሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች አደባባይ ይዘው የወጡት አሳብ ጥቃቅን መሆኑ በእርግጥም ማህበርተኞቹ ምን ያህል አንድ ለአምስት ‹‹እደተጠረነፉ›› የሚያሳይ ነው፡፡ የጉዳዩ አሳሳቢነት የሚጀምረው እነኚህ ጢቂት ‹‹የተጠረነፉ›› ሴቶች በነፃነት ቀናቸው ነፃነት የተነፈጋቸው መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እሩጫው ላይ የተሳተፉት በራሳቸው ፍቃድ ሳይሆን በድረጅታቸው ትዕዛዝ ነው ሊያስብል የሚያስችል የተለያየ ‹‹ልማታዊ›› የሆነ መፈክሮችን ሲያሰሙ ተደምጠዋል፡፡በመንግሰት ልዩ ድጋፋ የተደረገላቸው እነኚህ ሴቶች ለሚደግፉት ሳይሆን ለተገደዱበት ዓላማ የመሰላቸውን መፈክር እና ቀረርቶ በማሰማት እንዲሁም የተለያዩ ፖስተሮችን በመያዝ በዕለቱ ሲንቀሳቀሱ ታይተዋል፡፡
ይሁን እንጂ ለመንግስት ደጋፊዎች የተፈቀደው ለሌሎች ለመንግሰት ተቃዎሚ ሴቶች ፖሊስ ያደረገው ክልከላ እና እስራት ክስተቱን አስገራሚ ብቻ ሳይሆን አሳሳቢያ ደርገዋል፡፡ እንደሚታወቀው ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ነው፤ ይህ ቀን ሴቶች ተሰባስበው ከበሮ ይዘው የሚደልቁበት ቀን ሳይሆን ለነፃነታቸው ቀደምት ሴቶች ያደረጉትን ተጋድሎ በመዘከር ያሁኖቹ ሴቶች ለበለጠ እኩልነት እና ነፃነት በጋራ የሚቆሙበት የቃል ኪዳን ቀን ነው፡፡ ይህም እንደሆነ የተረዱ ሴቶች በነፃነት ቀናቸው ስለነፃነታቸው ከፍ ባለ ድምፅ ሲዘምሩ ማየት ምንኛ መታደል ነው ! ይህን በድፍረት ላደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች አድናቆት ሊቸራቸው እና ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሴቶች በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ በአደባባይ ታፍሰው ለእስር የበቁት በእኔ ዘመን ይህ የመጀመሪያ ነው ፡፡የኔ ዘመን ደግሞ 23 ዓመት ሙሉ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ የበላው ጅብ አልጮው ብሎ ተቸግረን የከረምንበት ወቅት ነው፡፡ እርግጥ ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ለማወቅ እና ለመዘርዘር ሰፊ ጥናት ያስፈልጋል፡፡ የችግሩ አሳሳቢነት እንደተጠበቀ ሆኖ እንቢ ለነፃነቴ በማላት አደባባይ በመውጣት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች ‹‹ እኔ የጣይቱ ልጅ ነኝ ! እስክንድር ይፈታ ! እርዮት ትፈታ ! አብበከር ይፈታ ! አንዱአለም ይፈታ ! መብራት እና ውሃ ናፈቀን ! ፍትህ እንፈልጋለን ! ›› እና የመሳሰሉትን መፈክር በልበ ሙሉነት በማሰማት ያሳዩት ቆራጥነት ታሪክ መቼም የሚዘነጋው አይደለም፡፡ በይበልጥ ደግም በዚሁ የፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ብቻ ለእስር መዳረጋቸው የመንግስት ስርዓት ምን ያህል አምባገነን እና ጨቋኝ እንደሆን በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡
የቁልቁለት መንገድ! – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
በማስመሰል ታጥሮ መሆን በጠፋበት
ምን አገባኝ የሚል በተከማቸበት
የባይተዋር መንፈስ ከሞላ ባገሩ
ዘመኑን ማወቂያ ይሄ ነው ሚስጥሩ
ይሄን ጊዜ ጠርጥር እንደጠፋ ዘሩ፡፡
(ገጣሚ ደምሰው መርሻ/ያልታተመ)
አዎን፣ ገጣሚ ደምሰው እንዳለው እኔም በዚህ ዘመን “ዘሩ እንደጠፋ” አሊያም ሊጠፋ እንደተቃረበ እጠረጥራለሁ፡፡
ስለምን? ቢሉ …በኢትዮጵያችን ለህሊናው፣ ለሕዝብና ለሀገሩ የሚቆረቆር፣ የእውነት ተሟጋችና የሞራል ልዕልናን የተቀዳጀ ሙሉ ሰው ፈልጎ ማግኘት እጅግ አተካች ሆኗልና፡፡ የግል ጥቅም አሳዳጅ፣ አፋሽ-አጎንባሽ በሞላበት፣ እንደ ቴዎድሮስ ለሀገር ቤዛ መሆን፤ እንደ ግርማሜዎቹ እና ወርቅነህ የራስን ምቾት ወዲያ ጥሎ በጠገበ ሆድ ከወገን ጋር መራብና ከጎኑ መቆም፤ እንደ አቶ ሽፈራው ደሳለኝ አስፈሪ ሞት ከከበበው ሸለቆ ውስጥ በህይወት ለመውጣት ሲባል የጠላትን ጫማ ከመላስና ያላመኑበትን ተናግሮ ምህረት ከመጠየቅ ይልቅ በድፍረት ሞትን ፊት ለፊት መጋፈጥ ወይም ግንባርን ለአረር መስጠት እንደ ተረታ-ተረት ከተቆጠረ ዘመናት አልፏል (አቶ ሽፈራው ደሳለኝ ማን ናቸው? ለሚለኝ አንባቢዬ ‹‹የታኀሣሡ ግርግር እና መዘዙ›› የተሰኘውን የብርሃኑ አስረስ መጽሐፍ ገፅ 302ን እንዲያነብ እጋብዘዋለሁ) አሊያም ደግሞ የሰው ዘር በመሆን ብቻ የሚገኘውን የሞራል ልዕልና ከትውልድና ሀገር ጥቅም አኳያ ለማጠየቅ በዚህ አውድ ለማነሳው ተጠየቅ በአንፅሮ ለማፍታታት ይጠቅመኝ ዘንድ እኔው ራሴ እዚሁ ጠቅሼው አልፋለሁ፡፡
የመጽሐፉ ደራሲ ‹‹በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጊዜ የድጋፍ ንግግር አድርጋችኋል በማለት በመንግስት ተይዘው ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ከተላኩት አንዱ የሆኑት…›› ብለው ከአቶ ሽፈራው ደሳለኝ ጋር ከአስተዋወቁን በኋላ እንዲህ በማለት ትርክታቸውን ይቀጥላሉ፡- ‹‹…አቶ ሽፈራው ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ተልከው ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ ዳኛው ‹ሠርተሃል ለተባለው ወንጀል ጥፋተኛ ነህ፣ አይደለህም?› ይላቸዋል፡፡ ‹የቱን ወንጀል?› ሲሉ አቶ ሽፈራው ዳኛውን ይጠይቃሉ፡፡ ዳኛው አቶ ሽፈራው ሠርተዋል የተባለውን የወንጀል ቃል ሊናገሩት አልወደዱም አልደፈሩምምና ‹አንተ የሠራኸውን?› ብለው ጠየቁ፡፡ አቶ ሽፈራው ‹እስቲ ወንጀል የተባለው ይነበብልኝ› ብለው አጥብቀው ይጠይቃሉ፡፡ ይሄን ጊዜ ዳኛው ሳይወዱ ‹ይህን ጣሳ እግዚአብሔር ገላገለን፣ አወረደልን ማለትህን፤ …ለዚህ ጥፋተኛ ነህ አይደለህም?› ይሏቸዋል፡፡ ‹የለም ተስተካክሎ ይጻፍልኝና እምነት ክህደቴን ልናገር› ይላሉ፡፡ ‹የለም በዚህ ላይ ጥፋተኛ ነኝ በል› ይሏቸዋል፡፡ ‹ትክክለኛ ቃሌ ይጻፍና ነው እንጂ እንዲሁ ጥፋተኛ ነኝ፤ አይደለሁም፤ አልልም› ብለው ይመልሳሉ፡፡ ‹እሺ ምን ተብሎ ይስተካከል› ሲሏቸው፤ ‹ይህን የበሰበሰ የተጠረማመሰ አሮጌ ጣሳ እግዚአብሔር ገላገለን ነው ያልኩት› ሲሉ ዳኞቹ የተባለውን አልሰማንም ለማለት ራሳቸውን ጠረጴዛ ስር አግብተው ተደበቁ፡፡››
በዚህ ዘመን ራሳቸውን ጠረጴዛ ስር አግብተው እንደ ሰጎን አንገታቸውን ቀብረው በፍርሃት የሚኖሩ አድር፣ እበላ-ባይ፣ ፈሪ ሰዎች የአቶ ሽፈራውን ባመኑበት መቆም እንደ አጎል ጀብደኝነትና ሞኝነት ቢቆጥሩት አስገራሚ አይሆንም፡፡ የሆነው ሆኖ እንደ ብልህነት አሊያም ብልጥነት ተደርጎ የሚወሰደውን የአድርባይነት ‹‹ስልት›› ለማሳየት አንዲት ሀገርኛ ምሳሌ እዚህ ጋ ለንፅፅር ላቅርብና እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ለራሴ ጽሑፍ ‹‹F›› ከመስጠቴ በፊት ወደ አጀንዳዬ ልዝለቅ፡፡
ታሪኩ ዝናው በስፋት የናኘ ሽፍታ የመሸገበትን (ግዛቱ ያደረገ) ጥቅጥቅ ያለ ጫካ አቋርጦ ስለሚያልፍ መንገደኛ ገጠመኝ ነው፡፡ መንገደኛው ለሰዓታት ከተጓዘ በኋላ ድንገት ሽፍታው እጅ ይወድቅና ስንቅ የቋጠረበትን ስልቻ ጨምሮ ከላይ እስከታች ይበረበራል፤ ሆኖም ሰባራ ሳንቲም ሊያገኝበት ባለመቻሉ ከመጠን በላይ የተበሳጨው አያ ሽፍታ ሆዬ ንዴቱን ለማብረድ ሲል ‹‹ውዳሴ ዜማ አቅርብልኝ!›› በማለት ቀጭን ትዕዛዝ ይሰጠዋል፤ በፍርሃት ነፍሱ እጉሮሮው የተወተፈችበት መንገደኛም ተንፈስ ብሎ ለመረጋጋት እየሞከረ እንዲህ ሲል አቀነቀነለት ይባላል፡-
‹‹አይኑ የተኳለ ጠላት የሚጋረፍ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ 2
ጠብ-መንጃ ገስጋሽ ጉብታ ተሻግሮ
ከዘብጥ የሚናደፍ
እንደሚካኤል ነህ ጠላትህም አይተርፍ!››
እነሆም የሀገሬ ምድር እንዲህ ባሉ ሀሞተ-ቢስ አወዳሾችና አስመሳዮች ተጥለቅልቃ እጆቿን ወደ ሰማይ ከዘረጋች (ሱባኤ ለመግባት) ሰነበተች፡፡ በርግጥም ከብዙሀኑ በተሻለ ማንሰላሰል ይሳናቸዋል ተብለው የማይታሰቡ ‹‹ምሁራን››ም ሆኑ ‹‹መንፈሳዊ››ነታቸው የበዛ የኃይማኖት መሪዎች በግል ጥቅመኝነት ታውረው ከስርዓቱ ጋር እጅና ጓንት በመሆን የጭቆና አገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም በሀሰት መስካሪነት የቅጥፈት ምላሳቸውን ሲያንበለብሉ መስማት ‹እግዚኦ› የሚያስብል አስደንጋጭ መናፍቅነት መሆኑ ቀርቶ እንደ ተራ ነጋዴ ንግግር፣ ተራ የዕለት ተዕለት አጋጣሚ ከሆነ ዘመናት ተቆጠሩ፡፡ ‹‹መንፈሳዊያን›› አባቶች በተከበረው ቤተ-መቅደስ ምኩራብ ላይ ከመእምናኑ ፊት ለፊት ቆመው ቃየልን ‹‹አቤል››፣ በርባንን ‹‹መሲህ›› በማለት ሲሰብኩም ለአመል እንኳ ድንቅፍ አያደርጋቸውም፤ ከግላዊ ጥቅማቸው አሻግረው የግፉአንን የስቃይ እሮሮ ማድመጥም ሆነ ለሌላው ማሳወቅ ጭራሹንም አይሞክሩትም፡፡ ‹‹ምሁራን›› ተብዬዎቹም አርቲስት ሰለሞን ተካልኝ ‹‹ውበት ከቅንድቡ የሚፈስ›› እንዲል፤ ‹አይኑ የተኳለ› እያሉ በሕፃናት ደም ሳይቀር የጨቀየውን ኢህአዴግ መራሹን መንግስት እንዴት እንዴት ‹ብፁእ› አድርገው የውዳሴ ከበሮ ሲመቱለት እንደሚያድሩ እዚህ ጋ ዘርዝሮ ለማቅረብ ማሰብ አባይን በጭልፋ አጋብቶ ለመጨረስ እንደመሞከር ያለ ዕብደት ያስቆጥራል፡፡
ወጣም ወረደ እንዲህ አይነቱ የሞራል ዝቅጠት በትላንት ወይም በዛሬ የእድሜ ገደብ የሚለካ አለመሆኑን በድፍረት መናገር ይቻላል፤ ምክንያቱም በነገሥታቱ የአገዛዝ ዘመን የጀመረና በጣሊያን የአምስት ዓመቱ የወረራ ወቅት እንደወረርሽኝ የተስፋፋ ስለመሆኑ በቂ ማሳያዎች አሉ፡፡ ይህ እንግዲህ ‹‹ሀገር›› ለተሰኘ ማህተም መስዋዕት የሆኑትን አቡነ ጴጥሮስን የመሳሰሉ ታሪክ በታላቅ አክብሮት የሚዘክራቸውን ቀዳማይ አባቶችና እናቶችን ሳንዘነጋ ነው፡፡ እናም የሩቁን ትተን ከ1983ቱ የመንግስት ለውጥ ወዲህ ያለውን እንኳ ብንመለከት ይህን መሰሉ ክስረት ዙሪያችንን ከቦ ሊውጠን የቀረው ስንዝር ታህል ርቀት ብቻ መሆኑን ለመረዳት የማሕበራዊ ሳይንስ ምሁራን ትንታኔን ማገላበጥ አይጠይቅም፡፡ ያኔ ገና በለውጡ ማግስት ህወሓት እና ሻዕቢያ በአንድ አንቀልባ ካልታዘልን በሚሉበት የ‹‹ጫጉላ›› ዘመን፣ ከኤርትራ ምድር የወርቅ ጥርሳቸው ሳይቀር በጭካኔ ወልቆ ባዶ እጃቸውን የተባረሩ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በጉምቱው ምሁር ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ የተመራው አጣሪ ቡድን ‹‹ውሸት ነው! ይህ አይነቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ኤርትራ ይኖሩ
በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ አልተፈፀመም!!›› በማለት አይኑን በጨው አጥቦ በድፍረት ሲያስተባብል፣ አንጀታችን እያረረ ‹‹ይሁና!›› ብለን በትዝብት ማለፋችን እውነት ቢሆንም፤ የዝምታችን ውስጠ-መልዕክት ያልገባው ፕሮፌሰሩ ግን ያረረው አንጀታችን ይበልጥ እርር ይል ዘንድ በተለመደው ቅጥፈቱ ታላቁ የዐድዋ ድል ባለቤትነትን ከሀገር ከፍታ፣ ቁልቁል ወደ ጎጥ ለማውረድ ያልፈነቀለው ቋጥኝ፣ ያልማሰው ስር አልነበረም (በነገራችን ላይ ህወሓት ዛሬም ከዐድዋ ድል ጀግኖች ጋር ጥቁር ደም እንደተቃባ በግላጭ የሚያመላክተው በዘንድሮው 118ኛው ክብረ በዓል ላይ የተስተዋለው አሳፋሪ ትእይንት ነው፡፡ ይኸውም በታሪካዊቷ ዐድዋ ከተማ በሚገኘው ሶሎዳ ተራራ ስር ‹ድሉን ለመዘከር› ከተሰቀሉት የእቴጌ ጣይቱ፣ የራስ አሉላ አባነጋ፣ የባልቻ አባነፍሶ እና የባሻ አውዓሎም ግዙፍ ምስሎች መሀል የተሸናፊው ሀገር ህዝብ ሳይቀር በድሉ ዕለት ሮማ በተሰኘው አደባባዩ ‹‹ቪቫ ምኒሊክ›› እያለ በታላቅ ጩኸት ያወደሰው የታላቁ ንጉሠ ነገሥት ምስል አለመካተቱ ነው፡፡ …መቼም ይህ ለምን ሆነ? ብለን የክልሉን አስተዳዳሪ ጓድ አባይ ወልዱን ብንጠይቀው ‹‹በጦርነቱ ወቅት ምኒሊክ መሸሽ ጀምሮ ነበር›› የሚለውን ዝነኛ ህወሓታዊ ትርክት ገልብጦ፣ ‹‹በስራ መደራረብ በተፈጠረ ስህተት ነው›› ብሎ በክፍለ ዘመኑ ታላቅ ሽርደዳ አንጀታችንን ይበልጥ ድብን እንደሚያደርገው ቅንጣት ታህል አትጠራጠሩ)
ለማንኛውም እንደ ፕሮፌሰር እንድሪያስ ያሉ በድሃው ሕዝብ ጥሪት የከፍተኛ ደረጃ የትምህርት ዕድል ማግኘት የቻሉ በርካታ እበላ-ባይ ‹‹ምሁራን›› ስርዓቱ የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም የሚያምታታበትን ‹‹የሁለት ዲጂት የኢኮኖሚ ዕድገት›› የፈረንጅ ጥናቶችን በጥራዝ-ነጠቅነት እያጣቀሱ ምክንያታዊ መስለው ሊያሳምኑን በከንቱ ብዙ ደክመዋል፡፡ በአናቱም የመከላከያ ሠራዊቱ ለባዕድ ሀገር ጥቅም ሲባል ሶማሊያን በወረረበት ወቅት አንዳንድ የዩንቨርስቲ መምህራን እና ‹‹የፖለቲካ ተንታኞች›› በመሬት ያለውን ተጨባጭ እውነታ ይሁነኝ ብለው ወደጎን ገፍተው አገዛዙ ቀን ከሌት ‹‹እመኑኝ!›› በሚል ጩኸት ያሰለቸንን ሰበብ፣ በጥናት እንደተረጋገጠ አስመስለው ለመተንተን ያደርጉት የነበረው እሽቅድምድም ሁሌም በሀዘን የምናስታውሰው ነው፡፡
የኃይማኖት መሪዎችም ምንም እንኳ በነቢብ የአገልግሎታቸው ዋጋ በፈጣሪ መንግስት መሆኑን ደጋግመው ቢነግሩንም፣ በሀልዮ የሚታየው የአሸርጋጅነት ግብራቸው ግን ምድራዊውን ጨቋኝ ስርዓት ደግፎ የሚይዝ ምሰሶና አቅፎ የሚያሞቅ ክንድ ከሆነ በርካታ አስርታት ተቆጥረዋል፡፡ የእስልምና እምነት የበላይ ወሳኝ አካል የሆነው መጅሊስ መእምናኑ ያነሱት ፍትሃዊው የመብት ጥያቄ ተቀልብሶ፣ ሕዝባዊ ውክልና የተሰጣቸው የኮሚቴ አባላት ለአስከፊው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የተዳረጉበትን መንግስታዊ ሽብርተኝነት ለመሸፋፈን ከመተባበርም አልፎ ቅዱስ ቁራንን አዛብቶ እስከመጥቀስ መድረሱ በትዝብት ያሳለፍነው የትላንት ኩነት ነው፡፡ የክርስትና እምነት መሪዎችም በተመሳሳይ ሁናቴ የስርዓቱን የጭካኔ እርምጃዎች እንደ ቅዱስ ተግባር ለማፅደቅ ያልረጩት ጠበል፣ ያልጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አልነበረም፡፡ ሌላ ሌላውን እንኳን ትተን በቅርቡ ህይወቱ ያለፈው የኦሮሚያ ክልል አስተዳዳሪ የአለማየሁ አቱምሳ ስርዓተ ቀብር ላይ ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ‹ዲሞክራሲን ለማስፈን መስዋዕትነት የከፈለ፤ ሩጫውን የጨረሰ፤ ተጋድሎውን
በብቃትና በንቃት የተወጣ…› እያሉ አፋቸውን ሞልተው የምስክርነት ቃላቸውን ሲሰጡ ሀፍረት ብሎ ነገር ለቅፅበት እንኳን ዝር 3 አላለባቸውም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ በሰውየው ህልፈት እጃቸው እንዳለበት የሀሜት ወሬ የሚናፈስባቸው እነዚያ ጲላጦሳውያን ጓዶቹ እንዳሻቸው ቢያንቆለጳጵሱት መቼስ የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው ብሎ በቸልታ ማለፍ ይቻል ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሰማዩን መንግስት ብቻ ያገለግሉ ዘንድ በቃሉ እንዲመላለሱ ግድ የሚላቸው ‹‹መንፈሳውያን››፣ እንዲያ የገዛ ወገኑን ‹‹ኦነግ!›› በሚል የሀሰት ውንጀላ በጥይት ሲደበድብና ሲያስደበድብ፤ መከራን በሕዝብ ላይ እንደምርጊት ሲለስን፤ አምባገነን ስርዓቱን በታማኝነት ሲያገለግል… ያለፈን ሰው ‹‹ዲሞክራት›› እያሉ በአደባባይ ማወደስ በቤተ-ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ራሱ የተነቀፈውን ለእግዚአብሔርና ለቄሳር ዕኩል መገዛትን እንደትክክለኛ ተግባር አምኖ መቀበል ነው ወደሚል ጠርዝ መገፋታችን አይቀርም፡፡
በግልባጩ በሁሉም እምነት ያሉ ‹‹መንፈሳዊ›› መሪዎች ስርዓቱ በድህረ-ምርጫ 97ም ሆነ በተከታዮቹ ዓመታት የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባላትን እና ጋዜጠኞችን እንደ ጥጃ እያሰረ በግፍ ሲያሰቃይ ድርጊቱን ለመንቀፍም ሆነ ዘላቂ ዕርቅ እንዲወርድ ለመማለድ አንዳች ሙከራ አለማድረጋቸው በታሪክ ጥቁር መዝገብ በጉልህ ቀለማት ሰፍሮ የሚኖር ሀጢያታቸው ነው (የቅንጅት እስረኞችን ለማስፈታት የተሄደበት የ‹‹ሽምግልና›› መንገድ የአቶ መለስ ዜናዊ ቧልት ስለመሆኑ ከቶም ማንም ሊጠራጠረው አይችልምና እዚህ መጥቀሱ አስፈላጊ አይመስለኝም)
ሌላው የማሕበረሰባችን የሞራል እሴት በእጅጉ መዝቀጡን የሚያስረግጥልን ብዙሀኑ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በተዘፈነበት ለመደነስ፣ በተደገሰበት አሳላፊ ለመሆን የሚያደርጉትን መገፋፋት ስናስተውል ነው፡፡ ስርዓቱ ከሚያራምደው ‹‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ›› ርዕዮተ-አለም የተቀመረውን ‹‹ፌደራሊዝም አወቃቀር››ን ተንተርሶ ሀገሪቱን በዘውግ ከፋፍሎ እና በሕዝብ መካከል የጥርጣሬ መንፈስ አንብሮ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሙን በግጥምና ዜማ ማወደስ የእህል-ውሃ ጥያቄ ካደረጉት በርካታ ዓመታት ነጉደዋል፡፡ እንዲህ አይነት የሙዚቃ ስራ በአንዳንድ ክልሎች መሬት የሚያሸልም ፈጣን አዋጪ አድርባይትመንት (ኢንቨስትመንት ላለማለት ነው) እስከ መሆን መድረሱ ከታፊና ነጋዴ አርቲስቶች በዘውጉ ዙሪያ ይረባረቡ ዘንድ ታላቅ ልማታዊ አብነት ሆኗቸዋል፡፡ ይህ ሁናቴም በኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብን የንፁሃን መታጣት ከድንጋይ ወገራ የታደጋትን የኦሪቷ ዘማዊት ከማስመሰልም አልፎ እንደ ነገሥታቱ ዘመን የአዝማሪ ጨዋታ፤ የቤተ-መንግስቱ መዝናኛ እና አጀንዳ ማራገቢያነት እስከ መሆን ሞዴል ተሸላሚ አድርጓታል፡፡ ይሁንና ቁጥራቸው ጥቂት ቢሆንም ቴዎድሮስ
ካሳሁንን (ቴዲ አፍሮን) የመሳሰሉ መክሊታቸውን እንደ ጉሊት ሽንኩርት ለሽያጭ ያላቀረቡ ከያኒያን፣ ደራሲያን፣ ገጣሚያን… የመኖራቸውን እውነታ ሳንዘነጋ፤ ሀገሪቱ ‹‹ሰው አይብቀልብሽ!›› ተብላ የተረገመች እስኪመስል ድረስ ብሔራዊ ጥቅም፣ ህሊና፣ ሞራል፣ እውነት የረከሱበትና የተዋረዱበት ዘመን ላይ መድረሷን የሚያስረግጡልን በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡
ከጥቂት ወራት በፊት በብአዴኑ ካሳ ተክለብርሃን ፊት-አውራሪነት የሶማሌ ክልልን የጎበኙት አርቲስቶቻችን፣ ገና ድሮ ጆርጅ ኦርዌል ‹‹Animal Farm›› ብሎ በሰየመው መጽሐፉ ‹‹አራት እግር ጥሩ፤ ሁለት እግር መጥፎ›› እያሉ በመንጫጫት ስብሰባን ለመረበሽና ተቃውሞን ለማጨናገፍ አሳማው ናፖሊዮን እንዳሰለጠናቸው አይነት በጎች፤ ኢህአዴግ በጎጥ የካፋፈለውን ሕዝብ ‹‹በታሪኩ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን አንድ ሆኗል!!›› በማለት በሬ ወለደ የሀሰት ምስክርነታቸውን አምነን እንድንቀበል ለማድረግ ለሳምንታት ተንጫጭተው ሊያደነቁሩን ሞክረዋል፡፡ እነዚህ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የክልሉ ነዋሪዎች ገና ዛሬ (በኢህአዴግ እፁብ ድንቅ እና ፍትሀዊ አስተዳደር) ኢትዮጵያዊነት እንደተሰማቸው፤ ገና ዛሬ በፍቃደኝነት ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ አስመስለው ለማሳመን የሄዱበት የቁልቁለት መንገድ አጥንት ድረስ በሚዘልቅ ሀዘን እንዳኮራመተን እነርሱም ይጠፋቸዋል ብዬ አላስብም፡፡ ጉዳዩ ሆድ ሌላ፣ እውነት ሌላ ሆኖባቸው እንጂ፡፡ ግና፣ የቄሳሩ ጲላጦስም ‹‹እውነት ምንድር ነች?›› እንዲል፣ እውነት ለእነርሱ ዋጋዋ ስንት ነው? መቼም ከእውነት ይልቅ ግድ የሚሰጣቸው የሆድ ነገር ነው፤ እበላ አዳሪዎች ናቸውና፡፡
በጥቅሉ በኢትዮጵያችን ከምሁር እስከ ተርታው፤ ከጳጳሳት (ፓስተራት) እና ሼሆች እስከ መናፍቃውያን፤ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ፤ ከጄነራል እስከ ወታደር፤ ከከያኒ እስከ ጽሑፍ ገልባጭ፤ ከቱጃር እስከ ጥሮ-ግሮ አዳሪ፤ ከመምህር እስከ ተማሪ… ስር የሰደደ አድርባይነት እና የሞራል ክስረት ለመንሰራፋቱ አይነተኛ ማሳያው አምባገነኑ ኢህአዴግ እንዲህ ሚሊዮኖችን ረግጦ እየጨፈለቀ፣ አስሮ እያንገላታ፣ ከሀገር እያሰደደና እየገደለ… ከሁለት አስርት በላይ መቆየት የመቻሉ ምስጢር ነው፡፡ ግና፣ የሕዝብን መከራ በማራዘም ኪስን ማደለብ፣ ግላዊ ፍላጎትን ማርካት ሁሌም አትራፊ ሊሆን እንደማይቻል መዘንጋት የለበትም፡፡ ማን ነበር ‹የተከፋፋለና አድርባይ ሕዝብን ከጭቆና ማላቀቅ፣ ሰማይን የማረስ ያህል አዳጋች ነው!› ያለው?
አዎን፣ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ በጉልበታም ስርዓታት የጭካኔ መዳፍም ሆነ በግላዊ ጥቅመኝነት እየተናዱ የመጡት የባህል እና የሞራል እሴቶች ትውልዱን ዛሬ ላይ ለደረሰበት አስከፊ ማሕበራዊ ቀውስ መዳረጋቸው አሌ የማይባል ነው፡፡ ርግጥ ነው የችግሩ ስፋትና ጥልቀት እንደ ስርዓቱ የፖለቲካ ፍልስፍና በዘውግ የተከፋፈለ አይደለም፤ ብዙሀን እና ህዳጣን የሚል መስፈርትንም የተከተለ አይደለም፤ ኃይማኖታዊ መለያም የለውም፤ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች አለቅጥ መንሰራፋቱ በግላጭ ይታያልና፡፡ ይህም ነው መፍትሔውን ስር ነቀል የማሕበራዊ አብዮት (ለውጥ) ብቻ እንዲሆን ያስገድደው፡፡
የቀደሙት ሁለት አብዮቶች በዋናነት ያነሷቸው የብሔር እና የመሬት ጥያቄ መክሸፋቸው (መቀልበሳቸው) ዛሬም ሶስተኛ አብዮትን የማይቀር ዕዳ አድርጎ የመውሰዱ ሁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ሥራ-አጥነት፣ ከነባሩ ባህል ማፈንገጥ፣ ሙስና፣ በሕብረተሰቡ ዘንድ አክብሮትና 4 ተሰሚነት ያላቸው ታላላቆችን አለማደመጥ፣ አድርባይነት፣ ደንታቢስነት፣ ዶሮ ሳይጮኽ ደጋግሞ መክዳት፣ የ‹‹ስቀሎ፣ ስቀሎ…›› ሀሰተኛ ድምፅ መበራከት፣ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች እና የመሳሳሉት ትውልድና ሀገር ገዳይ ደዌዎችን ለመፈወስ ከማሕበራዊ አብዮት ያነሰ መፍትሔ እንደሌለ ከተለያዩ ሀገራት ታሪክ መረዳት ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ ኢህአዴግ በየትኛውም የዓለማችን ሀገራት የተከሰተ ሕዝባዊ አብዮት እንቅልፍ እንደሚነሳው በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ለተከታታይ ቀናት ‹‹ተንታኝ›› ጭምር በመጋበዝ፣ ምስራቅ አውሮፓ ድረስ ተጉዞ የተሳካውን የዩክሬን አብዮት ከቀለም ጋር በማያያዝ ለማውገዝ ያቀረባቸው ፕሮግራሞች የፍርሃቱ መጠን አንዱ ማሳያ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላል፡፡ ግና፣ እውነት እውነት እልሀለሁ በመቶ ሺህ የሚቆጠር የታጠቀ ኃይል ቢሰለፍ፣ እልፍ አእላፍ ፊርማቶሪዎች በሕዝብ መሀል ቢሰገሰጉ፣ ሚሊዮናት ካድሬዎች ሀገር-ምድሩን ቢያጥለቀልቁ፤ አገዛዛዊ ጭቆና እና ማሕበራዊ ክስረት እስካለ ድረስ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ፣ የትኛውም ምድራዊ ኃይል ሊያመክነው የማይችል አብዮት መቀጣጠሉ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ በመጨረሻም ይህንን ጽሑፍ ጄነራል መንግስቱ ነዋይ በተለምዶ ‹‹የታሕሳስ ግርግር›› እየተባለ የሚጠራውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፍ ተከትሎ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት በሰጠው ቃል እቋጨዋለሁ፡-
‹‹…ዋ! ዋ! ዋ! ለእናንተም ለግዥአችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀሳቤ በዝርዝር ገብቶት በአንድነት በሚነሳበት ጊዜ የሚደርስባችሁ መዓት የሚያሳቅቅ ይሆናል፡፡››
ትንቢቱ ከ13 ዓመት በኋላ ከእጥፍ በላይ መፈፀሙን ስናስታውስ፣ በጥቅመኝነት ስሌት ከስርዓቱ ጋር ተወዳጅተው የግፉአንን የመከራ ዕድሜ የሚያራዝሙ አድርባዮችም ሆኑ የአገዛዙ ልሂቃን ሕዝቡ ‹‹ሆ!›› ብሎ በአንድነት የተነሳ ዕለት ከመዓቱ ያመልጡ ዘንድ አይቻላቸውምና ዛሬውኑ ‹ንሰሀ ግቡ!› ብሎ ማሳሰብ ግድ ይላል፡፡ …ዋ! ዋ!! ዋ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ቀዳማይ ወያኔ፤ ዓድዋ እና የካቲት 11 በወያኔ ትግሬዎች ዕይታ –ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ)
ብዙዎቹ በዚህ ጽሑፍ የቀረቡ መረጃዎች እና ትንታኔዎች በሂደት ላይ ካለ ከሚቀጥለው አዲስ መጽሐፌ የተገኙ ምንጮች ናቸው።እኛ በታሪክ አጋጣሚ ተገኝተን ጸረ ወያኔ አቋም ይዘን የምንተነትን ጸሐፊዎች የተቻለንንን ያህል የወያኔ ቅጥፈቶች እያጠናን ስናቀርብ ማንበብ ሰልችቶአቸው ግማሽ ገጽ አንብበው ወደ ቀላል ዜና እና ትንታኔ የሚሮጡ ብዙ እንደሆኑ አገምታለሁ።እንዲህ ዓይነት ልምድ ጥልቅ እውቀት እንዳይኖረን ያግደናል።እንድያ ከሆነ የሚሞግቱንን ጠላቶች በማስረጃ ለመመከት ደካሞች እንሆናለን።መረጃ ሲያጥረን ሕዝቡ የጠላት ‘ፕሮፓጋንዳ’ ተማሪ ይሆናል።። ስለዚህም ብርቱ ድካም፤ምርምር ጌዜ እና መስዋእት የተደረገባቸው ጽሑፎች ማንበብ ድርሻችሁ እንደሆነም አትዘንጉ።
ባለፈው በክፍል ፩ “የወያኔ ትግሬዎች በጉንደት፤በጉራዕ፤በዶጋሊ ፤….ጦርነቶች የሚዋሹት ውሽት ሲመረመር” በሚል ለብዙ አመታት ሲነግሩን የነበረውን “የወቅቱ ጦርነቶች” የገጠሙት ትግሬዎች ብቻ ነበሩ፤ እያሉ የሌሎች ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎ ዋጋ በማሳጣት ሲዋሹን የነበረው ጀብደኛ ትምክሕት በጐንደር፤በጐጃም፤በወሎ እና በሸዋ ጦር ተዋጊዎች ጭምር እየታገዙ ጦርነቱን ገጥመው ድል የተቀዳጁ አንደነበር አንጂ ትግሬ ብቻውን እንዳልተዋጋ እና ድሉም የብቻችን ነው የሚለው የወያኔ የታሪክ ቅሚያ እንደበፊቱ በቸልተኛነት መታለፍ እንደሌለበት ከሃቅ የራቀ ውሸታቸውን በወቅቱ የተጻፉ መረጃዎች በማስረጃ አጋልጫለሁ። ክፍል ፪ “የዓፋሮች እና አፄ ዮሐንስ ፍትግያ” የሚለው ጽፌ አዘጋጅቼው ልለጥፈው ነበር፤ እሱን ወደ ክፍል ሦስት በማቆየት ይህ ክፍል ሁለት ብለን በመሰየም እናንብበው።
“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል!” –ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ!
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እ.ኤ.አ ማርች 9/2014 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀቶ በነበረው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶችም ተሳትፎ አድርገው ነበር፡፡ ከዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባፈነገጠ መልኩ በኃይል በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጠው ስልጣንን የሙጥኝ በማለት ከህግ አግባብ ውጭ በህዝብ ላይ ደባ በመፈጸም ላይ የሚገኙትን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ዕኩይ ምግባር የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘበው በማሰብ ወጣት ሴቶቹ እውነታውን ያለምንም መሸፋፈን በማጋለጥ እምቢ አሻፈረኝ በማለት ተቃውሟቸውን ለዓለም በይፋ አሰምተዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ተቃውሟቸውን አጠናክረዋል፣
“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ተርበናል! ነጻነት እንፈልጋለን! ነጻነት እንፈልጋለነ! እስክንድር ይፈታ! አንዷለም ይፈታ! አቡባከር ይፈታ! ርዕዮት ትፈታ! የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ! ፍትህ እንፈልጋለን! ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት! አትከፋፍሉን! ኢትዮጵያ አንድ ነች! አንድ ኢትዮጵያ! ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ውኃ ናፈቀን! መብራት ናፈቀን! ተርበናል!…“
ለሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች ባርኔጣዬን ዝቅ በማድረግ ከወገቤ ጎንበስ በማለት ያለኝን አድናቆት ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ፡፡ በእነርሱ እጅጉን ኮርቻለሁ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ሰማያዊ ፓርቲን ለምን እንደደገፍኩ እና በጽናትም ከፓርቲው ጎን ለምን እንደምቆምኩ በርካታ ሰዎች ጥያቄዎችን አቅርበውልኝ ነበር፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ቁጥር አንድ አድናቂ (አንደኛ ቲፎዞ) ለምን እንደሆንኩ ማንም ቢሆን ጥያቄዎች ካሉት/ካሏት ይህንን ቪዲዮ (እዚህ ይጫኑ) እንዲመለከቱት እጋብዛለሁ፣ እናም መልሱን ከእዚያው ያገኙታል፡፡
አረመኔው ገዥ አካል በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያን ወጣት ሴቶች እና ወንዶች በዱላ እየደበደበ እና እንደ እባብ እየቀጠቀጠ ሁሉንም የጭቆና ዓይነቶች በእነርሱ ላይ እየተገበረ ባለበት ሁኔታ ከዳር ቆሜ ለመመልከት ህሊናዬ ሊፈቅድልኝ አይችልም፡፡ የመናገር መብታቸውን ተጠቅመው ሀሳባቸውን ለመግለጽ በመሞካራቸው ምክንያት ብቻ የኢትዮጵያ ወጣቶች ሲታሰሩ፣ ሲደበደቡ፣ ሲሰቃዩ እና ግፍ ሲፈጸምባቸው በዝምታ አልመለከትም፡፡ በወጣቶቹ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እና ስቅይት የእነርሱ ድምጽ በመሆን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እናገራለሁ፡፡
ወጣት ሴቶቹ ተቃውሟቸውን የገለጹት በሰላማዊ መንገድ ነው፡፡ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በማሰማታቸውም በጨካኙ የገዥ አካል ማሰቃየት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ በሰላማዊ እና ከአመጽ በጸዳ መልኩ በአገሪቱ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ሲሉ ነው በአሁኑ ጊዜ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በመሰቃየት ላይ የሚገኙት፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች እና አባላት እንደማንኛውም ሰው ሁሉ የ5 ኪ/ሜ ሩጫውን ተቀላቀሉ፡፡ በሰላማዊ መንገድ እሮጡ እና ከማጠናቀቂያ ቦታው ደረሱ፡፡ ምንም ዓይነት ህግ አልጣሱም፡፡ አንድም ጠጠር አልወረወሩም፡፡ በማንም ላይ ጥቃት አልፈጸሙም፡፡ ምንም ዓይነት ሁከትን በሚያመጡ ተግባራት ላይ አልተሳተፉም፡፡ ከአንድ ሺህ በላይ ሯጮች በተሳተፉበት በዚያ ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች እና አባላት በመሳተፋቸው (ወይም በሌላ ምክንያት) በአንድም ሰው ላይ ጉዳት አልደረሰም፡፡ ቅንጣት ያህል ንብረት ላይ ጉዳት አልተፈጸመም፡፡ አንድም ባለስልጣን ማስፈራሪያ አልደረሰበትም ወይም ደግሞ የጥቃት ሰለባ አልሆነም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ምንም ዓይነት የዘለፋ ቃላት እንኳ አልተጠቀሙም፡፡ ሁሉምን ነገር በሰላማዊ መንገድ፣ ሞገስን በተላበሰበ መልኩ እና በሚያስደምም ሁኔታ ነው ያከናወኑት፡፡ እነዚያ ጀግና ወጣት ሴቶች የምርጥ ተደናቂነት ተምሳሌት ቀንዲል ናቸው! በእነዚህ ወጣቶች እጅግ ኮርቻለሁ እናም ባርኔጣዬን ዝቅ በማድረግ አድናቆቴን ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ፡፡
በዕለቱ የተከበረውን በዓል ኃላፊነት በመውሰድ ያዘጋጀው የገዥው አካል የሴቶች፣ የህጻናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ነበር፡፡ የገዥው አካል የዕለቱ መፈክር “የምርጥ ሴቶች የመጀመሪያው ዙር የ5 ኪ/ሜ ሩጫ“ የሚል ነበር (ምን ለማለት እንደተፈለገ ግልጽ ባይሆንም)፡፡ ገዥው አካል ዕለቱ ከ10,000 በላይ ሴቶችን እና ልጃገረዶችን ያሳትፋል በማለት ዲስኩር አድርጎ ነበር፡፡ ገዥው አካል በበዓሉ ዕለት ሴቶች እንዲሳተፉ በስፋት የጥሪ ማሳሰቢያ ሲያደርግ ጠንካራዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች ማሳሰቢያውን ሊሰሙት እንደሚችሉ እረስቶት ኖሯል፡፡ መንፈሰ ጠንካራዎቹ ወጣት ሴቶች ግን ማድረግ ያለባቸውን ነገር በሚያስደምም ሁኔታ አደረጉት፡፡ ወጣት ሴቶቹ ለገዥው አካል ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሳይሆን ብጫ ካናቴራ በመልበስ ተልዕኳቸውን ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡ እዚያ የተገኙት ለመሮጥ ነበር፣ ለነጻነታቸው ለመሮጥ፣ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ለመሮጥ፣ የኢትዮጵያ እስረኞች እንዲፈቱ ለመሮጥ፣ በመሰቃየት ላይ ላለው እና ተስፋ ለራቀው ህዝብ ትኩረት በመሳብ ለመሮጥ፡፡ ወጣቶቹ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች አረመኒያዊ እና ጨካኝ እየተባለ በሚታወቀው ገዥው አካል ፊት ደፋርነታቸውን ማሳየት መቻላቸው ብቻ አይደለም አስደናቂ የሚሆነው ሆኖም ግን የእራሳቸውን የብልህነት ፈጠራ በመጠቀም የስርዓቱን ዕኩይ ምግባር በማጋለጣቸው ጭምር እንጅ፡፡
የአምስት ኪሎ ሜትሩ ሩጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ሰባት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፣ ተደብድበዋል እንዲሁም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ የሰብአዊ መብት እረገጣው ሰለባ ከሆኑት ውስጥ፡ ሜሮን ዓለማየሁ፣ ምኞቴ መኮንን፣ መታሰቢያ ተክሌ፣ ወይኒ ንጉሴ፣ ንግስት ወንድይፍራው፣ ወይንሸት ሞላ፣ እና እመቤት ግርማ ይገኙበታል፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ ጌታነህ ባልቻ (የድርጅተ ጉዳይ ኃላፊ)፣ ብርሀኑ ተክለያሬድ (የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) እና አቤል ኤፍሬም (የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል) የተባሉ ሌሎች ሶስት ወጣት ወንዶች ደግሞ እስረኛ ሴቶች ያሉበትን ሁኔታ ለመጠየቅ በሄዱ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለው እነርሱም ለእስር ተዳርገዋል፡፡
የጣይቱ እና የምኒልክ ልጆች በይስሙላው/በዝንጀሮዎች (ካንጋሩ ኮርት) ፍርድ ቤት፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የይስሙላ ፍርድ ቤት ስርዓት በአገሪቷ ዘርግቶ በመተግበር ላይ ይገኛል በማለት ሁልጊዜ ስናገረው የቆየሁት ጉዳይ ነው፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተመሰረቱት “ክሶች” የገዥው አካል የይስሙላ ፍርድ ቤቶች እንዴት ባለ ሁኔታ እየተካሄዱ እንዳሉ ከምንም ጥርጣሬ በላይ በግልጽ ያመላክታሉ፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተመሰረቱት ክሶች በባዶው የትወና መድረክ ላይ ብቻ የሚከናወኑ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የይስሙላው ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ ማርች 14/2014 ያደረገው የሁለተኛው ቀን “የችሎት” ትወና በሳሙኤል በኬት፣ ኢጀን ኔስኮ፣ ጂን ገነት ወይም ካፍካ ላይ የተደረገ ያለቀለት የትያትር ትወና ይመስል ነበር፡፡ የህጋዊነት ትወናው በምግባር የለሾች፣ በስም የለሾች፣ የማስተዋል ብቃት በሌላቸው፣ በህሊና የለሾች፣ በሀሳብ የለሽ ደነዞች፣ታማኝነት በሌላቸው ፖለቲከኞች እና ዋናው ተግባራቸው ህዝቡን ማሰቃየትን እና መከራ ማሳየትን እንደመርሀ የሚከተሉ አስመሳዮች በግልጽ በማይታይ መልኩ የሚጦዝ የውሸት የህጋዊነት ሽፋንን ተላብሶ እየተተገበረ ያለ ኃላፊት የጎደለው እና የተዋረደ የመድረክ ተውኔት ነው፡፡ ፍትህ ፊት የሌላት እና ቅርጿ የተበላሸ የይስሙላ ስርዓት ዘርግታ ትገኛለች፡፡ ፍትህ በሚያስገርም ሁኔታ በመደምሰሷ ምክንያት አካል የላትም፡፡ በኢትዮጵያ የፍትህ ፊት እና አካል በይስሙላው ፍርድ ቤት በርቀት በቁጥጥር ስልት መጠቀሚያ መሳሪያ ተይዞ የሚመራ እና በጌቶቹ ትዕዛዝ እንዲያደርግ የተሰጠውን ብቻ ያለምንም ኃፍረት ተቀብሎ እንደበቀቀን የሚደግም የሮቦት ዳኛ (አንደየተሞላ አሻንጉሊት) የተሰማራበት ሆኗል፡፡ የፍትህ አካሉ በዘራፊዎች ቁጥጥር ስር ዉሎአል፡፡
በ “ችሎቱ” ክፍል እንደ አንድ ተመልካች ዘገባ ከሆነ “የማታ” በሚል ስም የሚታወቅ “የፖሊስ መርማሪ” የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች የጣይቱ ልጆች ነን (የ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንግስት የነበሩት) እና የእምዬ ምኒልክ ልጆች ነን (በ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ እና የንግስት ጣይቱ ባለቤት የነበሩት) በማለት በአደባባይ በመጮህ በሽብር ተግባር ላይ ተዘፍቀው ታይተዋል በማለት የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ “መርማሪው” በተጨማሪም ተከሳሾቹ እየተራቡ ያሉ መሆናቸውን እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ማለትም ርዕዮት፣ እስክንድር፣ አንዷለም እንዲሁም ሌሎች እንዲፈቱ” እያሉ በአደባባይ ጩኸት እያሰሙ ነበር ብሏል፡፡ እንግዲህ ይኸ ነው በሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ተፈጸመ የተባለው “የሽብር ተግባር” ይዘት፡፡
የችሎት ስነስርዓቱ ከታቀደለት በአንድ ሰዓት ዘግይቶ ነው የተጀመረው፣ ምክንያቱም የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች በሰልፉ ላይ ለብሰዋቸው የነበሩትን ካናቴራዎች ወደ ችሎቱ ሲቀርቡ እንዲቀይሯቸው ቢጠየቁም ለመቀየር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነበር፡፡ ፖሊሱ እስረኞቹን ከነካናቴራቸው ወደ ፍርድ ቤቱ እንዲቀርቡ መፍቀድ የፖለቲካ እምቢተኝነትን አምኖ እንደመቀበል ያስቆጥራል የሚል እምነት አደረበት፡፡ እንደ ዘገባው ከሆነ ሴቶቹ ወደ “ፍርድ ቤቱ” ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት የለበሷቸውን ካናቴራዎቻቸውን በማስገደድ እንዲቀይሩ ለማድረግ ፖሊ ሁከት ፈጥሮ እንደነበሩ ታውቋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች እስከሚወሰዱ ድረስ በተያዙበት ቦታ እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡ “የፍርድ ቤቱ” ክፍል በተመልካች ተጨናንቋል፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም በሙሉ ተገኝተው ነበር፡፡
የፌዴራል አቃቤ ህግ ጉዳዩን ለመመርመር እና መረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜ እንዲሰጠው ሴት እስረኞችም በእስር እንዲቆዩ ጠየቀ፡፡ (በቁጥጥር ስር የማዋል ልምድ እና ተጠርጣሪን በእስር ቤት አውሎ ለጥፋተኝነት መረጃዎችን ለመፈለግ መሞከር የገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤት አሰራር ዋናው መለያ ባህሪው ነው፡፡ አንድ ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት የሚደረገው አሳፋሪ ዘዴ በእያንዳንዱ ከፍተኛ የወንጀል ጉዳይ ከሁለት ደርዘን ወይም ከዚያ በላይ በሚሆኑ በቀድሞዎቹ ባለስልጣኖች እና ባለፈው ዓመት ደግሞ በንግዱ ማህበረሰብ አባላት ላይ ሙስና በሚል ሰበብ የተደረገው እስራት ሲታይ ገዥው አካል ካለፉት አስርት ዓመታት በላይ ሲፈጽመው የቆየ ተግባር መሆኑን ነው፡፡ አቃቤ ህጉ እስከ አሁንም ድረስ ለሙስናው መረጃ ፍለጋ በሚል ሰበብ ጊዜ እየነጎደ በሄደ ቁጥር እነርሱ በእስር ቤት ተረስተዋል፣ ገዥው አካል ጉዳዩን ለሁለት ዓመታት ያህል ምርመራ እየተካሄደበት ነው በማለት በይፋ የገለጸ ቢሆንም)፡፡
የይስሙላ አቃቤ ህጉ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የዋስትና መብት መሰጠት እንደሌለበት ተከራክሯል፣ ምክንያቱም “ዋስትናው ከተሰጠ አሁን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ያሉት ታሳሪዎች መረጃዎችን ያጠፋሉ፣ እናም ምስክሮች የምስክርነት ቃላቸውን እንዳይሰጡ በማንገራገር እና በማስፈራራት እንዳይመሰክሩ ሊያደርጉ ይችላሉ” ብለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ መከላከያ ጠበቃ አቶ ዓለሙ ጎቤቦ (በእስር ቤት የምትገኘው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን ያተረፈችው ርዕዮት ዓለሙ አባት) ጉዳዩ የፖለቲካ ባህሪ ያለው ስለሆነ ልጆቹ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከውጭ ሆነው እንዲከራከሩ እንዲደረግ በማለት የክርክር ጭብጣቸውን አቅርበዋል፡፡ ቀጥለውም እንደ ህጉ ከሆነ ደንበኞቼ የዋስትና መብት እንዲያገኙ ይፈቅዳል፣ እናም ይህንን ላለማድረግ እየተከናወነ ያለው የዳኞቹ ተቃውሞ ተጠርጣሪዎቹን በእስር ቤት ለማማቀቅ የተደረገ ደባ ነው ብለዋል፡፡ “ዳኛው” የዋስትና ጥያቄውን አልተቀበሉትም፣ እናም የዳኝነት ሂደቱን ቀጠሉ፡፡ (ባለፉት በርካታ ከፍተኛ የሆኑ የፍርድ ቤት ጉዳዮች የፍርድ ሂደት ላይ እ.ኤ.አ የ2006 የቅንጅት ፓርቲ አመራሮችን “የፍርድ ሂደት” ጉዳይ ጨምሮ ገዥው አካል ምስክሮችን በማስፈራራት፣ ጉቦ በመስጠት፣ በሙስና አማልሎ ተጽዕኖ በማሳደር እና ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ ቃለመሃላን በመጣስ የውሸት የምስክርነት ቃል እንዲሰጡ በማድረግ ዕኩይ ምግባር ላይ ተዘፍቆ ይገኛል)፡፡
እንደ ፍርድ ቤት ተመልካች ታዛቢዎች ከሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች በእስር ቤቱ ውስጥ በቁጥጥር ስር ሆነው እያለ ከህግ አግባብ ውጭ በፖሊስ እና በደህንነት ኃላፊዎች አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው እንዲሁም የማስፈራራት ሰለባ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ለይስሙላው ፍርድ ቤት ተናግረዋል፡፡ በሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ ቅጥረኛ እና ሰላይ እንዲሆኑ ብዙ ገንዘብ ቀርቦላቸዋል፡፡ ከተከሳሾቹ መካከል ትዕግስት ወንድይፍራው የተባለችው ባለፈው እኩለ ሌሊት ላይ ሶስት ወንድ ፖሊሶች እርሷ ወደታሰረችበት ክፍል መጥተው እንድትወጣ ትዕዛዝ እንደሰጧት “ለፍርድ ቤቱ” ተናግራለች፡፡ ከኃላፊዎች መካከል አንደኛው ዱላ በማንሳት በማወዛወዝ ካልተባበረች በስተቀር እስክትሞት ድረስ እንደሚደበድቧት ማስፈራራታቸውን ገልጻለች፡፡ ሌሎችም ሴቶች ተመሳሳይ የማስፈራሪያ ዛቻ እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ ሴቶቹ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የሚያደርጉትን ንቁ የአባልነት ተሳትፎ እና ጓዳዊ የትግል መንፈስ እንዲተው እና ከድጊታቸው እንዲታቀቡ በመደብደብ እንዳዋረዳቸው እና እንዳስፈራራቸው ያላቸውን ምሬት ገልጸዋል፡፡ በተመልካቾች ዕይታ “ብቃት የለሽ” ተብሎ የተፈረጀው የዕለቱ የችሎት ዳኛ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅቆ እ.ኤ.አ ለመጋቢት 18/2014 እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት አሰናብቷል፡፡
በይስሙላው ፍርድ ቤት ያለውን ኃይል መገዳደር፣
የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና የፍርድ ሂደታቸው እንዲታይ ማድረግ እ.ኤ.አ በ2015 ይካሄዳል ተብሎ በሚታሰበው አገር አቀፋዊ ምርጫ ሰማያዊ ፓርቲ እንዳይሳተፍ እና ለመዝጋት በደጋኑ የተተኮሰ የመጀመሪያው ቀስት ነው፡፡ ገዥው አካል ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልጽ እና ግድፈት ሊደረግበት የማይችል ሀቅ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ በአንክሮ ሲታይ በቅርቡ ባረፉት በአቶ መለስ ዜናዊ የተጻፈው የባለ ሶስት ድርጊት የረዥም ጊዜ ተውኔት ተከታይ ነው፡፡ እነዚህ የተውኔት ድርጊቶችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ ድርጊት አንድ፡ “ምርጫው” ከመድረሱ በፊት የሰማያዊ ፓርቲ, አመራሮችን እና አባላትን የይስሙላውን ፍርድ ቤቶች በመጠቀም ማሰቃየት፣ ማስፈራራት፣ ሽባ እና አቅመቢስ ማድረግ፡፡ በዚያ መንገድ ሌላ ተጨማሪ የኃይል እርምጃዎች ቢወሰዱ በህዝቡ ዘንድ የተለመደው አካሄድ እንጅ የበቀል እርምጃ አይደለም የሚል እንደምታ እንዲኖር ከመሻት የመነጨ ነው፡፡ ድርጊት ሁለት፡ ምርጫው ከመድረሱ ጥቂት ወራት በፊት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን ሰብስቦ በእስር ቤት ማጎር፡፡ ይሄም የይስሙላውን ፍርድ ቤት አንደውነት የፍርድ ሸንጎ የሚሰራ ለማስመሰል ነው፡፡ ድርጊት ሶስት፡ ከምርጫ በኋላ እ.ኤ.አ በ2005 (1997 ምርጫ) የተደረገውን ጭፍጨፋ ድርጊት መድገም ነው፡፡!
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን የህግ ሂደት እና ጥቃት በተመለከተ ሁለት አማራጮች አሉ፡፡ 1ኛ) በይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ላይ ተስፋ በመቁረጥ እራስን መነቅነቅ እና በመሰላቸት ጥሎ መሄድ 2ኛ) እንደ ኪልኬኔ አገር ድመቶች ከይስሙላው ፍርድ ቤት ጋር ጎሮሮ ለጉሮሮ መተናነቅ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን መብት ማስከበር፡፡
ገዥው አካል ኢትጵያውያን እና ሌሎች በይስሙላው ፍርድ ቤት የውሸት ማስመሰያ ምክንያት እራሳቸውን በመነቅነቅ ሁሉንም ነገር ይተውታል ወይም ደግሞ ትችት በመስጠት ብቻ ጥለው ይሄዳሉ የሚል እሳቤ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ገዥው አካል በጊዜ ሂደት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም እንደ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ አንዷለም አራጌ፣ አቡባከር አህመድ እና ሌሎችም በእስር ቤት ታጉረው “ይረሳሉ” የሚል ስሌት አለው፡፡ ገዥው አካል የይስሙላው የፍርድ ቤት ማስፈራሪያ ዘመቻ በከፍተኛ ውጤታማነት እና ብቃት ላይ ተመስርቶ የሚቀጥል ላለመሆኑ ትንሽም እንኳ ቢሆን ጥርጣሬ የለዉም፡፡
የሰላማዊ ትግል ዋና ዓላማው የጨቋኙን አካል ተቋማት እና ህጎች በመጠቀም በጨቋኙ አካል ላይ ትግሉን በሰላማዊ መልኩ በማፋፋም መቀጠል ነው፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያለው ምንም ዓይነት የተፈጸመ ስህተት የለም፡፡ በገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤቶች ዘንድ የፍትህን ጥላ እንኳ ማግኘት እንደማይችል ማንም መገመት ይችላል፡፡ ማንም ቢሆን በውሸት እምነት ላይ በተመሰረተው የይስሙላው ፍርድ ቤት ፍትህ ሰበብ መሰቃየት የለበትም፡፡ ወደፊት ምን ሊከሰት እንደሚችል በእርግጠኝነት እናውቃለን፡፡ የክስ ሰነዱ ቀደም ሲል ተጽፎ ተዘጋጅቷል፣ በግልጽ ለመናገር ቀደም ሲል የነበረዉን የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ክስ ስማቸውን በመለወጥ፣ በማደስ እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን በማካተት የክስ ሰነዶቹ እነዚህን ለመዳኘት በስራ ላይ ይውላሉ (በግልጽ አባባል ለማጥቂያነት ይውላሉ)፡፡
ያንን ትያትር ቀደም ሲል አይተነዋል፡፡ ክስ የቀረበባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት በየጥቂት ሳምንታት ልዩነት ከማጎሪያ እስር ቤቶች ወደ የይስሙላው ፍርድ ቤት እንዲመላለሱ ይደረጋል፡፡ የገዥው አካል አቃቤ ህግ ማስረጃ ለመፈለግ (የሩጫው ዕለት የተጠናቀቀ ስለሆነ እና ሌላ ተጨማሪ ማስረጃ ማግኘት የተሳሳተ እና ውኃ የሚቋጥር ባይሆንም) በሚል ስልት ብዙ የማዘግየት ስራዎችን በመስራት የተለመደውን የገዥውን አካል የበቀልተኝነት የሱስ ጥማት ለማርካት ጥረት ያደርጋል፡፡ የዋስትና መብት ጥያቄዎች ተከልክለዋል፣ ሺህ ጊዜ የሚጠየቁ ቢሆንም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ይደበደባሉ፣ ህግወጥ አያያዝ ይፈጸምባቸዋል፣ እናም በእስር ቤት የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ይፈጸምባቸዋል፡፡ እርስ በእርሳቸው ላይ መተማመን እንዳይኖርም ጫና ይፈጸምባቸዋል፡፡ ህሊናቸውን እንዲሸጡ ገንዘብ እና ሌላ ሌላም ነገር ይሰጣቸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲን ከፍተኛ አመራሮችን እንዲክዱ ላቅ ያለ ዋጋ የሚያወጡ ጌጣጌጦችን ይሰጧቸዋል፡፡ በጓደኞቻቸው፣ በፓርቲ አባላት እና አመራሮች እንዳይጎበኙ ክልከላ ሊጣል ይችላል፡፡ ለብቻ በአንድ ክፍል ውስጥ ሊታሰሩ ይችላሉ፡፡ የህክምና እርዳታ እንዳይደረግላቸው ክልከላ ሊደረግ ይችላል፡፡ በገዥው አካል በተቀጠረ ባለሙያ እንደተገለጸው እነዚህ እስረኞች “በሚከረፋው እስር ቤት” የገሀነም ህይወት እንዲገፉ ሊደረግ ይችላል፡፡ ይህ ጉዳይ ለብዙ ጊዜ ማለትም እ.ኤ.አ በ2015 እስከሚደረገው አገር አቀፍ “ምርጫ” ድረስ ቀጣይነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ዘዴው ቀላል ነው፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ሃሳብ ማስቀየስ፣ ማሸማቀቅ፣ ማስፈራራት፣ ከመሰረታዊ ዓላማቸው እንዲርቁ ማድረግ እና በአጠቃላይ መልኩ ደግሞ ምርጫ እየተባለ ከሚጠራው የይስሙላ ምርጫ ተሳትፏቸውን ሽባ ማድረግ ነው፡፡
ገዥው አካል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ያለምንም ውይይት በፍጥነት ወደ እስር ቤት የመውሰዱን ሁኔታ በተመለከተ በእራሱ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ለምን ሊጠየቅ እና ሊሞገት እንደሚገባው አራት አሳማኝ ምክንያቶች አሉ፡፡ በመጀመሪያ የጅምላ ሰብአዊ መብት ረገጣው ተግባራዊ እንዲሆን የሚያግዙት የገዥው አካል ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች (በተለይም የምራብ መንግሥታት) እነርሱ በሚያደርጉት ልገሳ ድርጊት እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ በተጨባጭ እንዲያዩት ይገደዳሉ፡፡ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲስፋፋ እና ሰብአዊ መብት እንዲጠበቅ ደንታ አንደማይሰጣቸው የታወቀ ነው፡፡ ሁለተኛ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የይስሙላ የፍርድ ሂደት በእራሱ በይስሙላው ፍርድ ቤት ላይ አንዲፈረጅበት ማድረግ ያስፈለጋል፡፡ ገዥው አካል እራሱ ለይስሙላው የፍርድ ቤት ሂደት መቅረብ አለበት፡፡ ሶስተኛ የይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ዛሬ በፍትህ ወንበር ላይ ተቀምጠው (እና ሌሎች ከመጋረጃ ጀርባ ተቀምጠው በዳኝት ወንበር ላይ የተሰየሙትን ዳኞች ጣቶች የሚጠመዝዙ) በእራሳቸው ዳኝነት ነገ እንደሚዳኙ በመገንዘብ ከፍተኛ ተቃውሞ መኖር አለበት፡፡ ዛሬ ከህግ አግባብ ውጭ ለመፍረድ በወንበር ላይ የተቀመጡት ሰዎች ከፍትህ ረዥም ክንድ ሊያመልጡ እንደማይችሉ የኑረምበርግ የፍርድ ሂደትን፣ የካምቦዲያ ፍርድ ቤት ልዩ የፍርድ ቤት ሂደትን፣ የሩዋንዳ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደትን፣ የደቡብ አፍሪካ የእውነት እና የዕርቅ ኮሚሽንን፣ የቻርለስ ቴለር የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደትን እና የቦካሳን እና ሌሎች የአገር ውስጥ የፍርድ ሂደቶች ሊያስታውሱ ይገባል፡፡ ሁኔታዎች ሁልጊዜ ይገለባበጣሉ፡፡ ስለ ሁኔታዎች መገለባበጥ ጉዳይ እስቲ ደጋግማችሁ አስቡ፡፡ ሁልጊዜ ይገለባበጣሉ!
ከደቡብ አፍሪካ ታሪክ ብዙ ቁም ነገሮችን ልንማር እንችላለን፡፡ እ.ኤ.አ በ1964 የአፓርታይድ ገዥ አካል የአፍሪካ ኮንግረስ መሪዎችን እና ሌሎች የጸረ አፓርታይድ ተሟጋቾችን ኔልሰን ማንዴላን፣ ዋልተር ሲሱሉ፣ ጎቫን ኢምቤኪ፣ ራይሞንድ ሃላባ፣ አህመድ ካትራዳ፣ ኤሊያስ ሞሶሌዲ እና ቢሊ ኔይር ሰብስቦ በይስሙላው የአፓርታይድ የፍትህ ችሎት ፊት ገተራቸው፡፡ እነዚህ ሰባት አመራሮች እንደ “ጣይቱ ሰባት” የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሁሉ በአፓርታይድ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ፍትህን እናገኛለን የሚል እምነት አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም ግን መሰረተ ቢስ ክሱን አጥብቀው ተቃውመውታል፡፡ ይህንንም በማድረጋቸው ለደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው ዓለም ታሪክ ሰርተዋል፡፡ የሰባቱ የጸረ አፓርታይድ መሪዎች የሪቮኒያ የፍርድ ሂደት ለዛሬዋ ደቡብ አፍሪካ ፍትህ መስፈን መሰረትን የጣለ ነው፡፡
አራተኛው እና ምናልባትም በጣም ጠቃሚው ነገር የይስሙላውን ፍርድ ቤት አጥብቀን መዋጋት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በህግ የበላይነት ለሚያምኑ ሁሉ ለህጉ ተገዥ ላልሆኑት ወንጀለኞች የህይወት እና የመተንፈስን ያህል ጠቃሚ መሆናቸውን ሊያስተምሩ የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ በህግ የበላይነት ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው ስለወንጀለኞች ማስተማር እና መጮህ ያለባቸው፡፡ እራሱ ያወጣቸውን እና ያጸደቃቸውን ህጎች የሚደፈጥጥ ወሮበላ መንግስት በእራሱ እና በህግ የበላይነት ላይ ንቀትን የሚፈለፍል ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የህግ የበላይነትን ለመያዝ እና ለመንከባከብ ከማንም የተሻለ መሆን አለበት፡፡
“የጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድን (ድጎማ/ዝክር)” እንደግፍ፣
Semayawi Party Legal Defense Fund 2ሁሉንም አንባቢዎቼን “ለጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድ (ድጎማ/ዝክር)” እንድታዋጡ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ የሰኞ ትችት መጣጥፌን ለበርካታ ዓመታት ስታነቡ የቆያችሁ በርካታ ወገኖቼ እንዳላችሁ እገነዘባለሁ፡፡ የሰኞ ትችት መጣጥፌ አሁን ስምንተኛ ዓመቱ መሆኑ ነው፡፡ አንዳንዶች ከእኔ ጋር በሁሉም ነገር በሀሳብ የማይግባቡ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ እንደዚሁም በርካታ ለመቁጠር የሚያስቸግር ብዛት ያላቸው አንባቢዎቼ ደግሞ ቢያንስ በጥቂት ነገሮች ላይ ከእኔ ሀሳብ ጋር እንደሚስማሙ እገነዘባለሁ፡፡ የእኔ አቤቱታ የቀረበው ለእነዚህኛዎቹ ወገኖቼ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት እየተሰቃዩ ያሉትን “የጣይቱ ሰባት” ጀግኖችን በመርዳቱ ጥረት እያንዳንዳቸው ማገዝ እንዲችሉ ያቀረብኩትን ሀሳብ በመደገፍ በተግባር እንዲያሳዩ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ እርዳታ እንዲያደርጉም በአጽንኦ እማጸናለሁ፡፡ ምንም ትንሽም ቢሆንም እንኳን ስጋት አይደርባችሁ፣ ትልቅ ጋን በትንሽ ጠጠር ይደገፋል ነውና፡፡ ባለፉት ዓመታት ምን ለመስራት እንዳቀድኩ አድናቆታቸውን የገለጹልኝ በርካታ ኢትዮጵያዊያን/ት ወገኖቼን በተለያዩ ጊዚያት አግኝቸ ነበር፡፡ ምንም ይሁን ምን ለሰራሁት ሁሉ ምስጋናን አልሻም፣ በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብት ያለመሻሻል ሁኔታን ስመለከት ካሁን የበለጠ ሺ አጥፍ መሆን የሆነ ስራ መስራት ነበረብኝ በማለት አራሴን ወቅሳለሁ፡፡
የዛሬ ሰባት ዓመት በዚሁ ወር “ትንሿ ወፍ እና የጫካው እሳት: የዲያስፖራው ማህበረሰብ የሞራል ትረካ” በሚል ርዕስ ስር በትችት መጣጥፌ ላይ ምን ለመስራት እንዳሰብኩ ለአንባቢዎቼ ተናግሬ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት ማድረግ የምችለውን ሁሉ እያደረግሁ ነው፡፡ አሁን አንባቢዎቼን መጠየቅ የምፈልገው ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ ነው፡፡ እስቲ በጥሞና አስቡት ወገኖቼ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ትናንሽ ወፎች አንድ ላይ ተባብረው በመስራት የጫካን እሳት መግታት ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የ”ጣይቱ ሰባት” ጀግኖች በአረመኔው ገዥ አካል የእሳት ማቀጣጠያ ጉድጓድ ውስጥ ናቸው፡፡ ሲቃጠሉ መመልከት አለብን ወይም ደግሞ ከእነርሱ ጎን በመቆም ታግለን ለድል መብቃት አለብን፡፡ “ለጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድ(ድጎማ/ዝክር)” እርዳታችሁን እንድታደርጉ እማጸናለሁ፡፡ ለወደፊቱ የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ተቆርቋሪነታችሁን አሁኑኑ በተግባር አሳዩ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲን ሴት ጠይቁ…
Free the Taitu Seven Amharicከቀድሞዋ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ማጊ ታቼር ጋር በብዙ ነገሮች ላይ እንደማልስማማ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሯ በሴቶች የፖለቲካ አመለካከት ላይ በነበራቸው እምነት ምንም ዓይነት ያለመስማማት አዝማሚያ አልነበረኝም፡፡ “በፖለቲካው ዓለም የተነገረ ምንም ነገር በፈለጋችሁ ቁጥር ወንድን ጠይቁ፡፡ የተሰራ ምንም ነገር በፈለጋችሁ ጊዜ ግን ሴትን ጠይቁ“ ነበር ያሉት፡፡ ሰለሆነም ለእነዚህ ወጣት ሴት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት አንድ ነገር እናድርግ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች እሩጡ፣ እሩጡ…! ለነጻነት የምታደርጉትን ሩጫ በጽናት ቀጥሉበት…
በዚህ ድረ ገጽ የእርዳታ እጃችሁን ለምትዘረጉ: http://www.semayawiusa.org/donate/
በባንክ ሐዋላ ለመርዳት ለምትፈልጉ፡
ለሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ድጋፍ የሚከፈል (የአሜሪካ ባንክ (Bank of America)
የሂሳብ ቁጥር፡ 435031829977
የመላኪያ ቁጥር፡ 051000017
በቼክ ለመርዳት ለምትፈልጉ፡
ለሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ድጋፍ የሚከፈል
የ.ፖ ሳ.ቁ 75860
ዋሽንግተን ዲሲ. 20013
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
መጋቢት 9 ቀን 2006 ዓ.ም.
[ሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] “ለቤተክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት ስንል ዝም አንልም”–ለቤ/ክ ሰላምና አንድነት ከቆሙ ምዕመናን
3/19/2014
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ፤ አሜን !
ለቤተክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት ስንል ዝም አንልም።
ለቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት ከቆሙ ምዕመናን።
ቤተክርስቲያናችን ደብረሰላም መድኃኔዓለም በይፋ ከተምሠረተችበት ከ 1994 ዓ.ም እ.ኤ.አ ጀምሮ በብዙህ ሺህ ለሚቆጠሩ ስደተኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እጅግ በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ስትሰጥ ቆይታለች፤አሁንም በመስጠት ላይ ትገኛለች። የቤተክርስቲያን ሕይወትና ጉዞ ግን ቀላልና አልጋ በአልጋ ስላልሆነ በየጊዜው ብዙ ፈተናዎች ያጋጥማሉ። የዚህ የዛሬው መልዕክት ዋና አላማም በቤትክርስቲያናችን ጉዞ ውስጥ አንዱና ትልቁ የሆነውን በአሁኑ ሰዓት ያጋጠመንን ፈተና ከሥር ከመሠረቱ ለሁሉም ለማሳወቅ ነው።
ሁላችሁም እንደምታውቁት ቤተክርስቲያናችን ደብረሰላም ፍጹም የኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት፣ ቀኖና፣ትምሕርትና ትውፊት የሚፈጸምባት ብቻ ሳትሆን የሚሰጠው አገልግሎትም በኢትዮጵያ ካሉ ታላላቅ አድባራትና ገዳማት ጋር የሚተካከልና ዝናዋም በመላው ዓለም የገነነ ነው። ይህች ቤተክርስቲያን ገና ሥትመሰረት ጀምሮ በገለልተኛ አስተዳደር እንድትመራ በወቅቱ የነበሩ መሥራች አባላት ተስማምተው ያደረጉት እንደሆነ ሁሉም የሚመሰክሩት ነው። ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት በወቅቱ በሥልጣን ላይ የነበሩት ፓትርያርክ በመንግሥት ጣልቃ ገብነት ተነስተዋል በሚልና የተሾሙትም አባት የመንግሥት ብርቱ ደጋፊ እንደነበሩ ይነገር ስለነበረ በተጨማሪም በምዕራቡ ዓለም ለረጅም ጊዜ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ያገለገሉት አባት (አቡነ ይስሐቅ) የፕትርክና ሹም ሽሩን ድርጊት በመቃወማቸው ቤተክርስቲያኗ ከየትኛውም አስተዳደር ሳትወግን በአስተዳደር ገለልተኛ ሆና በሜኖሶታ የቤተክርስቲያናት ማቋቋሚያ ሕግ እንድትተዳደርና ለውስጥ አሰራርም መተዳደሪያ ደንብ እንዲዘጋጅ ተደርጓል።
በተግባርና በመረጃ እንደታየውም በኢትዮጵያ በሥልጣን ላይ የተቀመጡት አባት በርግጥም የመንግሥት ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ ለቤተክርስቲያንና ለምእመናንን ብዙም ደንታ የነበራችው ስላልነበሩ፤ ከስልጣን የተባረሩት አባትም በወቅቱ እንደተባለው በህመም አለመሆኑና በመንግሥት ትእዛዝ እንደተነሱ መረጃዎች በመውጣታቸው በአንዲት ቤተክርስቲያን ሁለት ፓትርያርክና ሁለት አመራር ሊኖር አይገባም የተለያዩት አባቶች አንድ እስኪሆኑና አንድ አመራር እስኪሆን ድረስ ቤተክርስቲያኗ በገለልተኝነት አቋማ እንድትቀጥል ሆኗል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ የመለያየት መንስዔ ሳይፈታና ምንም ዓይነት ለውጥ ሳያሳይ ከተስፋ መቁረጥና ከእምነት ጽናት ማነስ በመነጨ ይህን የገለልተኝነት አቋም ለመቀየርና ኢትዮጵያ ካሉት አባቶች/ሲኖዶስ ጋር የመቀላቀል ጥያቄ በሰንበት ት/ቤት በቀረበ። በጥያቄውም መነሻነት ጁን 2 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ አብዛኛው የቤተክርስቲያኗ አባላት ቤተክርስቲያናችን ባለችበት አቋሟ እንድትቀጥል የሚፈልጉ መሆናቸውን ባቀረቧቸው አስተያየቶችና የውሳኔ ሐሳብ ቢገልጹም በቤተክርስቲያኗ ተቀዳሚ ካሕን ውግዘት መስይ ቃል ውሳኔ ሳይሰጥ ጉዳዩ በይደር ተይዞ የበለጠ ግንዛቤ እንዲኖር በሚል በፓናል ውይይት እንዲቀርብ ተደረገ። ዲሴምበር 15 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው የፓናል ውይይት ላይ ባለንበት እንቆይ በሚለው እና ኢትዮጵያ ባለው ሲኖዶስ እንተዳደር በሚለው ሃሳብ የተዘጋጁት ቡድኖች ከጉዳዩ ጋር ይገናኛል ብለው ያመኑበትን ጥናት በጽሑፍ ካቀረቡና ለተለያዩ
ጥያቄዎችም ማብራሪያዎች ከተሰጡ በኋላ( ለ6 ሰዓት የቆየ ስብሰባ ነበር) አባላት ድምጽ እንዲሰጡበት ተደርጎ በስብሰባው ተካፋይ ከሆኑት አባላት ከፈተኛ ቁጥር ያላቸው ቤተክርስቲያኗ ባለችበት የአስተዳደር ገለልተኝነት አቋም እንድትቀጥል ወስነዋል።
ይህንንም ውሳኔ ተከትሎ በተደረጉ የአስተዳደር ቦርድ ስብሰባዎች ላይ አንዳንድ የአስተዳደር ቦርድ አባላት በወቅቱ የስብሰባው ምልዐተ ጉባዔ/ኮረም/ ስላልሞላ ውሳኔውን አንቀበልም በማለታቸውና በተቃራኒው ደግሞ የአስተዳደር ሊቀመንበሩና ሌሎች የቦርድ አባላት የኅዝብን ውሳኔ ማክበር ይገባናል ውሳኔን የመሻር መብት ያለው ጠቅላላ ጉባዔ ብቻ ነው ሲሉ የተለያየ አቋም በመያዛቸው በአስተዳደር ቦርዱ አባላት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ሊቀመንበሩ ጉዳዩን ባለቤቱ ኅዝቡ ተመልክቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት አጠቃላይ የስብሰባ ጥሪ ለፌብረዋሪ 16 2014 ጠሩ። ነግር ግን የኅዝቡን ውሳኔ መቀበል ያልፈለጉት የአስተዳደር ቦርድ አባላቱ ጄንዋሪ 23 2014 ባደረጉት ህገወጥ ስብሰባ ሊቀመንበሩን ከሥልጣናቸው አውርደናል ሲሉ ተናገሩ። መጀምሪያ ግን ይህ ሊቀመንበሩ ከሥልጣናቸው ወርደዋል የሚለው ትእዛዝ የመጣው ‘የቤተክርስቲያኑ ጠብቃ ነኝ’ ከምትል አንዲት የሕግ ባለሙያ ሴት ነው። ለዚህች ሴት ማን ቤተክርስቲያኑን እንድትወክል ውል እንደፈረመላት ባይታወቅም የተቀጠረችው በግለሰቦችና በአንዳንድ የቦርድ አባላት እንደሆነ ይነገራል። በቤተክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ቤተክርስቲያኑን ወክሎ ማናቸውንም ሰነድ የሚፈርመው ሊቀመንበሩ ብቻ እንደሆነ በአንቀጽ 6 ክፍል 3 ‘ሀ’ 7) ላይ ተደንግጓል። እዚህ ላይ ልብ ሊሉት የሚገባው ነገር ሊቀመንበሩን አውርደናል ባሉበትና ሌላም ባልተሾመበት ሁኔታ ማን በቤተክርስቲያኑ ስም ውል እንደፈረመ ነው። አሁንም ይህ ጠበቃ ለቤተክርስቲያኑ ቀጥረናል ተብሎ የተላለፈው መልእክት ግልጽ አይደለም።
ሊቀመንበሩን ከሥልጣናቸው ለጊዜው አግዶ ለጠቅላላ ጉባዔ ማቅረብ የሚቻልበት የውስጥ አሰራር እያለ ለምን ጠበቃ መቅጠርና ከፍተኛ ወጪ ማስክተል አስፈለገ? ይህ አላስፈላጊ አካሔድ ያሳሰባችው የቦርድ አባላት ሊከተል የሚችለውን ከፍተኛ ወጪ ለማስቆምና የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ ለማስጠበቅ ሲሉ የእገዳ ይጣልልን አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቅርበዋል።
ስለሆነም እነኝህ ያለአግባብ እየሔዱ ያሉ የቦርድ አባላት የቤተክርስቲያናችንን ሊቀመንበር አውርደናል ካሉ በኋላ የቤተክርስቲያኑን ንብረትና ገንዘብ ለመጠበቅ ሲባል እንዲሁም እየተከሉት ያለውን ከመተዳደሪያ ደንቡና ከስቴቱ የቤተክርስቲያናት ሕግ ወጪ የሆነ አካሔድ ለማስቆም ሲባል ከፍርድ ቤት አስቸኳይ የእገዳ ማዘዣ ለማውጣት የተወሰደውን ርምጃ ነው ቤተክርስቲያኑ ተከሷል በማለት ሕዝቡን ለማደናገር እሞከሩ ያሉት። እውነታው ግን ሕዝቡ ተሰብስቦ በተከሰተው ጉዳይ ላይ ተነጋግሮ ውሳኔ እንዳይሰጥ እንቅፋት የሆኑት እነኝሁ የሕዝቡን ውሳኔ አንቀበልም በማለት ቤተክርስቲያናችንን አሳልፈው ለመስጠት ሁሉንም ሕገ-ወጥ አሰራር እየገፉበት ያሉት የቦርድ አባላት ናቸው። ከጄነዋሪ 11/ 2014 የአስተዳደር ቦርድ ስብሰባ በኋላ ምንም አይነት የአስተዳደር ቦርድ ስብሰባ ተደርጎ አያውቅም። በዚህ ሁኔታ ቤተክርስቲያኑ ተከሷል ጠበቃ ገዝተናል እንዴት ሊባል እንደተቻለም ግራ የሚያጋባ ነው።
ከአራት መቶ በላይ የሚሆን ህዝብ ፔትሺን ፈርሞ አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ እንዲደረግ ቢጠይቅም በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ፌብረዋሪ 5 2014 ጉዳያችሁን በጠቅላላ ስብሰባ ፍቱትና አስታውቁኝ በማልት ማሳሰቢያ ቢሰጥም አሻፈረኝ በማለት ያለሕዝቡ ፈቃድና እውቅና ጠበቃ በመቅጠር ከፍተኛ ወጪ ስለተጠየቀ ይህንንም ከፍተኛ ወጪ ከቤተክርስቲያኑ አካውንት የሚያውጡበት አሰራርና ሕግም ስለሌለ ሕዝቡን ‘ቤተክርስቲያናችን ተከሰሰ’ በማለት ከእውነታው የራቀ ውዥንብር አሰራጭተዋል። ለመሆኑ ቤተክርስቲያኑ በምን ጉዳይ ላይ ነው የተከሰሰው??? በወንጄል ነው በፍታብሔር ??? ቤተክርስቲያኑ ማንን ምን ስላደረገ ነው የተከሰሰው ??? ማነውስ የራሱን ቤተክርስቲያን የሚከሰው ???
ከላይ እንደተጠቀሰው የሕዝቡን ውሳኔ አንቀበልም ያሉ የቦርድ አባላት በቤተክርስቲያኑ ገንዘብ ላይ ብክነት እንዳያስከትሉና ያለሕዝቡ ፈቃድ ወደ ኢትዮጵያው ሲኖዶስ ተቀላቅሏል እንዳይሉ የእገዳ ማእቀብ ይደረግን የሚል ጥያቄ ብቻ ነው ለፍርድ ቤት የቀረበው። ይህም ጥያቄ የአራት የቦርድ አባላት ብቻ ሳይሆን ከአራት መቶ በላይ የሆኑ አባላት ፔትሺን የፈረሙበት ጉዳይ ነው። አሁንም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሕዝቡ ባስቸኳይ ተሰብስቦ በቦርዱ አባላትም ሆነ በማንኛውም ጉዳይ ላይ ውሳኔውን እንዲያሳልፍ የሽምግልና ሒደት/mediation/ እየተከናወነ ሲሆን አሉ የሚባሉ ጉዳዮችን ሁሉ ለሕዝቡ በጠቅላላ ጉባዔ ላይ መግለጽ እየተቻለ ሕዝብን ለማሸበርና ያልተደረገውን ተደርጓል ተብሎ የተላለፈው መልእክት ውሸት መሆኑን ሁሉም እንዲያውቀው እንወዳለን።
በመጨረሻም የሁሉም ጉዳይ ባለቤትና የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ስለሆነ የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ በቀረቡት ፔትሺኖች መሠረት ባስቸኳይ እንዲጠራ እናሳስባለን።
መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያናችንን በሰላምና በአንድነቷ ያጽናልን። አሜን!
አባ መላ ሳይበላ ተበላ! –ሆዳም! ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም!
አባ መላ ነኝ የሚለው የፓልቶኩ ብርሃኑ ዳምጤ ሰሞኑን የሰራው ስራ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው። ከአንድ ድርጅት ውልቅ ብለው በዚያው ጀንበር ሌላው ድርጅት ጥልቅ የሚሉ፤ ያም ሳይጥማቸው ወይም ሳይመቻቸው ይቀርና ወዲያው ደሞ ወደ ሌላ 3ኛ 4ኛ….. ድርጅት ጥልቅ ውልቅ የሚሉ ጥቂት የማይባሉ ቅብዝብዞችን አውቃለሁ።እነኚህ አይነቶቹ የቻሉትን ያህል እንደ ፌንጣ ዘለው ዘለው በመጨረሻ እዩኝ እዩኝ ያለ ……እንዲሉ፦ ራስን ብቻ አባል በሚያደርገው ዲፕሬሽን ወደ ተሰኘው ድርጅት ይገቡና ፍጻሜያቸውም እዛው ይሆናል።
ሰሞኑን በአባ መላ የታየው ዝላይ ግን በፌንጣ ተምሳሌት ከተገለጹት ቅብዝብዞች የተለየ ነው፡፡ አባ መላ ውልቅ ካለበት የወያኔ ጓዳ ያሞሌ ተመኑን ቀንሶ ዳግም ጥልቅ ብሏል። ስለዚህ ለአባ መላ ተግባር በተምሳሌነት የምትጠቀሰው ፌንጣ ሳትሆን የተፋውን መልሶ የሚውጠው ጉማሬ ይመስለኛል ።
ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን ወያኔን ጉማሬ ብለው የገለጹበትም ምክንያት ይህው ነበር፡፤ በነገራችን ላይ ብርሃኑ ዳምጤ በአንድ ቃለ ምልልስ ላይ “አባ መላ” የሚለውን ቅጽል ያወጡለት ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን መሆናቸውn (he was my best friend) አይነት ድምጸት) ሲናገር ሰምቸዋለሁ፡፤ የሞተ አይጠይቅ ሆነና ዝም ብለን ሰማነው።
ይሁን እንጂ በበኩሌ እንደሚታየኝ ብርሃኑ ዳምጤ የተሰ|ኘ የተሰፋ ሙዝ የሚሸጥ የምናለሽ ተራ ቁጭ ይበሉ (ምንጭ አብሮ አደጉ)ና የብርቅየውን ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬን ጓደኝነት እንኳን በዕውን በልቦለድ ድርሰትም ቢካተት ለአንባቢ የሚጥም አይመስለኝም፡፤ ልቦለድም ቢሆን እኮ የገሃዱ ዓለም እንጂ የከሃዲው አለም ነጸብራቅ ነው አልተባለም።….
ወደ ቀምነገሩ ልመለስ፦ አዎ ብርሃኑ ዳምጤ እነ ሎሬት ጸጋዬን እየጠቃቀሰ ፕሮፊይሉን ከፍ ከፍ እያደረገ ቢቆይም ሰሞኑን በሰራው ታሪካዊ ክህደት ያበገነው አብሮ አደጉ ያለ ከፈን ምናለሽ ተራ ቀብሮታል።
ለዚህም ነው ብርሃኑ በሰሞኑ ተግባሩ ከማንም በላይ የጎዳው ራሱን ነው ያልኩት፡፤
ከልብ አጢናችሁት ከሆነ የብርሃኑ ዳምጤ ችግር “ሞራል አልባ” መሆኑ ነው። ሞራል አልባ ሰዎች የሌላውንም ሞራል ለመጨፍለቅ ሁለቴ ማሰብ አያስፈልጋቸውም። ሞራል አልባ ሰዎች ፤ ምን ይሉኝ? አይሉም።ምን ይሉኝ የሚለውን ጥያቄ በአግባቡና በቦታው ማንሳት፤ የሞራል ድቀት ከሚያስከትል አደጋ ያድናል። ብርሃኑ ዳምጤን መሰል ሰዎች ይህን ጥያቄ አያውቁትም።
ለዚህም ነው ትናትና እንኳን ለተሰዳቢው ለሰሚው በሚዘገንን ጸያፍ ስድብ ያበሻቀጣቸውን የወያኔ ባለስልጣናት ዛሬ “ማሪኝ ብዬሻለሁ” እያዜመ የሚለማመጠው።
ግን ለምን?
ጥሩ ጥያቄ ነው…ሞራል አልባ ሰው የማንነቱ ነገር ብዙም አያስጨንቀውም። ተደፈረብኝ። ተገሰሰብኝ የሚለው እሱነት የለውም። ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም። ለሱ ማንነት? ከሚለው “የስብዕና” ጥያቄ ይልቅ ምቾት፤ ድሎት፤ ቅንጦት፤…..የተመቸ ህይወት ቅድሚያ አላቸው። በአጭሩ ሞራል አልባ ሰዎች ከምንም ከምንም ይልቅ ለሆዳቸው ቅድሚያ ይሰጣሉ።ብርሃኑ ዳምጤም ያደረገው ይህንኑ ነው።
ከወያኔ ኩብለላ
የወያኔ ባለ ስልጣናት የአውራቸውን ሞት ተከትሎ በራሳቸው የውስጥ ችግር ተንጠው፤ ውጭ ለታሰሩት ውሾች ይሰ|ጡ የነበሩትን መደበኛ መሽሩፍ አቋረጡ። በዚህ ምክንያት አለን ከሚሏቸው ተናካሽ ውሾቻቸው አንዱ (አባ መላ) ሰንሰለቱን በጥሶ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ተቀላቀለ።
በተቃዋሚው ጎራ ቆይታ፦
ሰንሰለቱን በጥሶ የመጣው አባ መላ አክቲቪስት ተባለና(ይታያችሁ ሞራል አልባ ሰው የሰባዊ መብት ተሟጋች ሲሆን) የድሮ ጌቶቹን አብጠለጠለልን። ሙታንታ ማድረግ የማያውቁ ፍልጦች የሚል ኢ.ሞራላዊ ስድብ አወረደባቸው። እግረ መንገዱንም ሙታንታን ያህል የግል ገበና ሁሉ አውቃለሁ አይነት ራሱን አካበደ።
የጦር ሃይሎች ኤታ ማዦር ሹሙን በዓለማችን የመጨረሻው ደደብ ጀነራል ሲል ተሳለቀበት። የጀኔራሉ ህጻን ልጅ የኦሮሚያውን ፕሬዘዳንት በልምጭ ሲገርፈው “ አባዱላ እንደ ፈርስ ያስካካ እንደነበር ገለጸልን፡፤ ሞራል አልባው አባ ዱላ ለሆዱ ብሎ በህጻን ተገረፈ ብሎ እራት ግብዣ ላይ ያየውን ተረከልን። እረ ማን ቀርቶ… የአዜብን አካላዊ ገጽታ አብጠለጠለ … የበረከትን ሴረኝነት አማሰለ…ስብሃትን በዝሙት በስካርና በገዳይነት ወነጀለ … ብቻ አብዛኞቹ ቱባ ቱባ ባለስልጣናት እጅግ በሚዘገንነው በምናለሽ-ተራ ጩቤ ምላስ ተተለተሉ።ባለ ስልጣናቱ ተዘናግተው ምሱን ባለመስጠታቸው … በሞራል አልባ አንደበቱ ዘመተባቸው። የአዜብ አፍንጫ ጠማማነት ምን የፖለቲካዊ ፋይዳ እንዳለው ባይገባንም ፈገግ ማለታችን አልቀረም።
ብርሃኑ ዳምጤ እንዲህ እንዲህ እያለ በተቃዋሚው ጎራ ቆየ፡፤ ወደ ኢሳት ቢያንዣብብም …. በወያኔ የጎደለበትን ምሱን የሚተካበት ምናምኒት ሊያገኝ የቻለ አልመሰለኝም። ቀጠለና በሳውዲ መንግስት ግፍ የተፈጸመባቸውን ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳት በተቋቋመው አለም አቀፍ ግብር ኃይል ገብቶ እድሉን ሞከረ፡፤ እንደ ልኳንዳ ቤት ውሻ አይኑ እየተንከራተተ ምራቁን ገርገጭ አድርጎ ከመዋጥ በስተቀር አሁንም ጠብ የሚል ነገር አልተገኝም። በዚህን ግዜ ብርሃኑ ዳምጤ፤ ከወያኔ ጉያ መውጣቴ ታሪካዊ ስህተት ነው ሲል፡ ታሪካዊ ስህተት ያለውን በታሪካዊ ሞት ሊያርመው ወሰነ።አመቺ ግዜም ጠበቀ።ረዳት ፓይለት ኃይለ መድህንን በቴሬሪስትነት በመፈረጅ ለወያኔ የመጀመሪያውን የምህረት ጥየቃ ደውል ደወለ! ኦሮማይ…….!
ዳግም ወደ ወያኔ…
ብርሃኑ በደርሶ መልሱ ጉዞ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው ያልኩት ያለ ምክንያት አይደለም። በክብር የያዙትን ጌቶቹን አስቀይሞ ሲያበቃ ዛሬ ተመልሶ ለምህረት ደጅ መጥናቱ፤ ዋጋውን ዝቅ አድርጎ ራሱን ለዳግም ሽያጭ ማቅረቡ፤ እንደ ፖለቲከኛ ብቻ ሳይሆን እንደ ሰውም ስብዕናውን ማዝቀጡ እየታየኝ እንጂ ።
ከበድን መሃል ምኑን ይመርጧል አትበሉኝ እንጂ፦ በኔ እይታ ዛሬ ከሰሎሞን ተካልኝና ከቤን የዘቀጠ ሞራል ላይ የሚገኘው ብርሃኑ ነው። ይህን ለመረዳት ደግሞ ከቤን ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ማድመጥ ብቻ በቂ ነው፡፡ በ
ቃለ መጠይቁ ቤን ሌጌቶቹ ባለው ታማኝነት በመኩራራት የሚሰነዝራቸው አስተያየቶችና ጥያቄዎች “ደግ አላደረክም ቢሆንም እንምርሃለን” አይነት ድምጽ ነበራቸው፡፤ አባ መላም በአንጻሩ ጭራውን እየነሰነሰ ጌታው እግር ሥር እንደሚንከባለል ውሻ አይነት በልምምጥ ስሜት ነበር የሚመልሰው፡፤ ከባሪያም ተራ…..!
ከሞተ ወዳጅ የቆመ ጠላት ይሻላል!
ከብርሃኑ ዳምጤ ድፍረት ሁሉ ያስገረመኝ ፡ ታማኝ በየነንና ማንጓጠጥ መሞከሩ ነው። በርግጥ ወያኔ ከማንምና ከምንም በላይ ታማኝ ቢዋረድላት እንደምትደሰት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፤ በዚህ ስሌት ይመስላል ብርሃኑ ዳምጤ ታማኝን ለማብጠልጠል የሞከረው። ነገር ግን አልተሳካም፡፤ ወያኔም ቢሆን ጀግና ታከብራለች ሲሉ ሰምቻለሁና ከብርሃኑ የገለማ ቃል ይልቅ የታማኝን ግልጽ ጠላትነትን የምታከብር ይመስለኛል፡፤ ከሞተ ወዳጅ የቆመ ጠላት ይሻላል ይባል የለ። ብርሃኑ ለኛም ለወያኔም ሞቷል።
ይህን የምለው በታማኝ በየነና በአባ መላ መካከል ያለው ፍጹም የሆነ ልዩነት እየታየኝ ነው፡፤ ቃላቶች ካልተመሙብኝ እስኪ በንጽጽር ልግለጻቸው።
ታማኝ ከአላሙዲን የዶላር ማማ ላይ “እረ ወግድልኝ!” ብሎ ወርዶ ከተገፋው ወገኑ ጎን በመቆም ከፍተኛ የሞራል እርከን ላይ የሚገኝ የህዝብ ልጅ ነው።
ብርሃኑ ደግሞ በአንጻሩ በደም ከጨቀየው ከወያኔ ደጅ የወዳደቀ ምንምን አይቶ፤ ይሁን እስቲ ካወጣነው የሞራል ማማ ላይ ቁልቁል ተምዘግዝጎ የወረደ የግፈኞች ወዶ ገብ ባሪያ ነው።አለቀ።
በነገራችን ላይ ብርሃኑ የወያኔን የምህረት ደወል በቤን አማካኝነት ሲያስደውል፤ አብሮም የኢሳትንና የግንቦት ሰባትን ብዙ ሚስጥር ገጸ በረከት እንደሚያቀርብ ነግሮናል። እውነት እውነት እላችኋለሁ ብርሃኑ እስካሁን ከቀበጣጠራቸው ነገሮች ውጭ አንድም የሚያውቀው ነገር የለም። ለምን በሉኝ? ምክንያቱም ዋናው ቁጭቱ ወደ ሚስጥሩም ወደ …ካዝና ሊያቀርቡት አለመፍቀዳቸው በመሆኑ ነው።ጨዋታ በጋራ ሂሳብ በግል ተባለ….አልወደደውም።
አክቲቪስት ስለመባሉ….
በኢሳት ጋዜጠኞች አክቲቪስት መባሉ ለኔ ብዙም እንደ ጥፋት አልታየኝም። አክቲቪስት የሚለው ስያሜ እንደ ወታደር ቤት በአገልግሎት ዘመን ተመዝኖ የሚሰጥ ሹመት ሳይሆን አመለካከትን ብቻ መሰረት አድርጎ የሚስጥ በመሆኑ ብርሃኑም ወያኔ ማብጠልጠል በጀመረበት ቅጽበት አክቲቪስት መባሉ አልተገቢነቱ አይታየኝም፡፤ በኔ አመለካከት
በእጅጉ የሚያስቆጨኝና ስህተት የምለው “አክቲቪስት” የሚለውን መጠሪያ መስጠቱ ሳይሆን አንድ የ11ኛቢ ተማሪ (ከአብሮ አደጉ የሰማሁት ነው) የምናልሽ ተራ ቁጭ በሉ እነ ሙሉጌታ ሉሌን ከመሰሉ በሳል ሰዎች ጎን ፖለቲካ ሊተነትን መቀመጡ ነው። የሚያናድደኝ ከነታማኝ በየነና አበበ ገላው ሌሎችም ብርቅዬ ኢትዮጵያዊያን እኩል አለም አቀፍ ግብር ኃይል ውስጥ መግባቱ ነው። “እኩያ ቢስ ..!” ይሉ ነበር ቀኛዝማች እንቶኔ እንዲህ አይነቱ ያለአቻ… ….ሲገጥማቸው። ይህ አይነቱ ስህተት እንዳይደገም ሊታሰብበት ይገባል ይመስለኛል።
አሁንም በኔ እይታ ብርሃኑ ዳምጤ (ከሟቹ አለቃው ከጠ/ሚ አጸያፊ አባባል ልዋስና) ከመበስበስ… ወደ.. መታደስ…. እንደገና ወደ መበስበስ ያደረገው የደርሶ መልስ እንቅስቃሴ በአጭሩ ሲቀመጥ፡
እንሆ ብርሃኑ ዳምጤ ጥቅም(ሆዱ) ስለጎደለበት ወያኔን ከድቶ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ገባ። የወያኔ ባለስልጣናትን በአጸያፊ ስድብ ማዋረድን ለተቃዋሚው ጎራ እንደ ገጸበረከት አቀረበ።አሁንም በተቃዋሚ ጎራ ለህሊና እንጂ ለሆድ የሚሆን ነገር በማጣቱ የአሞሌ ተመኑን ቀንሶ ራሱን ለቀድሞ ጌታው ዳግም ለሽያጭ አቀረበ። ይህው ነው። መጣ እነሱን ሰደበ …ሄደ..ራሱን ሰደበ!
ብርሃኑ ዳምጤ ከዚህ በኋላስ?
ብርሃኑ ከዚህ በኋላ አይደለም ፖለቲካዊ ህይወት ሰዋዊም ህይወት የሚዋጣለት አይመስለኝም።በቅርቡ አንድ አብሮ አደጉ ብዙ ብዙ አሉታዊ ባህሪያቱን እንዳጋለጠው ሰምተናል። ብርሃኑ የሰሞኑ ተግባሩ ከራሱ ሌላ ማንንም ላለመጉዳቱ ሌላው መገለጫ በይደር ተይዞ የነበረ፤ በቀይ ሽብር ዘመን ከኢህአፓ ውልቅ ደርግ ጥልቅ ብሎ ያስቀጠፋቸውን ሁለት ወጣቶች ጉዳይ ከሟች ቤተሰቦች አንደበት ለማሰማት እንቅስቃሴ መጀመሩ ነው።ይህ ማስፈራሪያ ሳይሆን በቅርብ የማውቀው ወዳጄ እየሰራበት ያለ ጉዳይ ነው።
በኔ እይታ ብርሃኑ የወያኔ ባለስልጣናትን ከሰደባቸው አጸያፊ ስድብ አኳያ እጃቸውን በምህረት የሚዘረጉለት አይመስለኝም። እንደ ሰሎሞን ተካልኝ “የቅንድቡ ውበት” አይነት ሙገሳም የሚያዋጣ አይሆንም። እናም አባ መላ በፓልቶክ ውስጥ ተፈጥሮ በፓልቶክ ውስጥ ኖሮ በፓልቶክ ውስጥ ሞተ ! የሚለውን ዜና የምንሰማበት ግዜ እሩቅ አይሆንም።አባ መላ ሳይበላ ተበላ! ይሏል ይህ ነው…..
ለድህረ ገጾች
ኢሳቶችና ድህረ ገጾች ብርሃኑ የወያኔ ባለስልጣናት በአጸያፊ ስድብ ሲያዋርዳቸው የተቀዳውን ኦዲዮ እየመረጣችሁ በማስደመጥ የምህረት ጥያቄው ተቀባይነት እንዳይገኝ ብታደርጉ እኔን ያየህ ተቀጣ! ነውና አስቡበት….. እያልኩ ከአጼ ቲዎድሮስ ታሪክ ላይ በተዋስኳትና ስሟን ወደ ራሴ በቀየርኳት ስንኝ ልሰናበታችሁ….
ይህንን ሲሰማ ያጓራል ላመሉ
ማናትም ቢላችሁ አዜቧ ናት በሉ!
አዜብ ጌታቸው
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ለአልሙዲ “ማፅናኛ”
(ከጋዜጠኛ ተስፋዬ ተሰማ)
በቅርቡ ባህርዳር ላይ በተካሄደው የኢትዮጵያ ስፖርት በአል ሼኽ አልሙዲ በክብር እንግድነት ተጋብዘው ነበር። የበአሉን መክፈቻ በቲቪ ስከታተል አንድ ጥያቄ ወደ በአእምሮዬ መጣ። አልሙዲንን የክብር እንግዳ አድርጐ መጋበዙ ለምን አስፈለገ?..ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። “የገዢው ፓርቲና የባለስልጣናቱ ታማኝ ወዳጅ ስለሆኑ፣ በባህርዳሩ ስታዲየም ግንባታ ድርጅታቸው ስለተሳተፈ ወይም ሼኹ ለስፖርት ያላቸውን ፍቅር በማየት..” የሚሉ ነገሮችን መደርደር ይቻላል።
በእኔ ግምት አልሙዲ በባህርዳሩ በአል በእንግድነት የተጋበዙት በሰሜን አሜሪካ ስፖርት በአል ላይ ስለተዋረዱ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት የፈጠርዋት ማፅናኛ ትመስለኛለች። ባለፈው አመት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ ሳምንት ሁለት የኢትዮጵያ ስፖርት በአል ተከበሮዋል። አንድኛው በሼኽ አልሙዲና የዳይስፖራውን ማንነትና ፍላጐት ባልተገነዘቡ ወዳጆቻቸው የተዘጋጀ ነበር። በነዚህ ወገኖች ግምት “ዳያስፖራው በተወሰኑ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት ካድሬዎች የሚሽከረከር የዋህ ህዝብ” አድርገው ይወስዱታል።
አሜሪካ ሀገር ከኅይለስላሴ ጀምሮ በደርግ ጊዜ ከዛም በኋላ የመጣው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ (በምንም መንገድ አሜሪካ ይምጣ) ለዘሩ፣ ለጐሳው ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነቱ ጥልቅ የሆነ ፍቅርና ክብር አለው። በዚህ ምክንያት የኢህአዴግን የዘር ፖለቲካ አይደግፍም። ከደጋፊዎቹም ጋር የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ የገባው በዚህ አገር ወዳድ አቋሙ ነው። ይህ እውነት ያለገባቸው አልሙዲና ተከታዮቻቸው በስፖርቱ አስታከው ዳያስፖራውን እንቆጣጠራለን በማለት በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ቢከሰክሱም አልተሳካላቸውም። ባዶ ስታዲየም ታቅፈው ነው የቀሩት። ሁለተኛው ኢ.ኤስ.ኤፍ.ኤን የሚባለው ኢትዮጵያዊ ፌዴሬሽን የነሱን ያክል ገንዘብ ሳይኖረው በርካታ ህዝብ ከጎኖ ማሰለፍ ችሎዋል። እንዲያውም ስታዲየሙ ሞልቶ ሰው እስኪመለስ ድረስ። በዚህ በአል ከፍተኛ የሆነ የአንድነትና የአገር ፍቅር ስሜት የታየበት፣ የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ ብሎ በብዛት የተውለበለበበትና ያሸበረቀበት፣ ሰዎች ከብሄራቸው ይልቅ ኢትዮጵያዊነታቸውን ያገነኑበት ትልቅ በአል ነበር።
ባዶ ስታድየም የታቀፉትና አፍረው በውርደት ለተመለሱት አልሙዲ የባህርዳሩ እድል በማፅናኛነት ተሰጣቸው። ኢትዮጵያዊያን በነፃነት በሚኖሩበት አሜሪካ ግን አልሙዲ በገንዘባቸው የህዝብን ድጋፍ መግዛት አይችሉም። በገንዘብ ምንም ማድረግ እንደማይችሉም ሊያውቁት ይገባል።
አፍንጫህን ላስ –አቶ ሂደት።
ከሥርጉተ ሥላሴ ሲዊዘርላንድ ዙሪክ
እኔ ነኝ አቶ ሂደትን አፍንጫውን እንዲልስ የፈለኩት። ሃሳቤን የሚጋራ ትብብር ካለም ደስታውን አልችለውም። በ16.03.2014 ጀንበር ዘቅዘቅ ከመለቷ በፊት ዘሀበሻ ስገባ አንድ አዲስ መረጃ አገኘሁ። የአንድነትና የመኢአድ ቅድም ውህደት መሰናዶ።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13623 ዘግዬት ብሎ ደግሞ ማምሻ ላይ ለሁለተኛው ቀን በደብተራ ክፍል አዲሱን ዜና አበሰሩ ለታዳሚው የአንድነቱ አቶ ሃብታሙ አያሌው። እንደ ድሮው ቢሆን እንዴት? ወዴት? ለምን? እያልኩ መንፈሴን አመሰው፤ አውከው ነበር። አሁን ግን አዳማጠኩ አቶ ሂደትን ማዬት ነው ፍሬውን። በቃ! ጅልነት ቀረ ወላለቀም። ነገም የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ከባዶ ሳጥን ቆጠራ በኋላ አቶ ሂደት ሌላ ትዕይነት ይዞ ከች ቢል አፍንጫህን ላስ በመጣህበት መንገድ ብዬ ቅንጡን አብርሬ ማሳፈር። ሞኙን ይፈልግ …. ይበቃል የተዳቀቅነው —-
ይልቅ አቶ ሀብታሙ በ16.03.2014 በነገሩን ሰበር ዜና ላይ የተፈለፈለ ቁምነገር አብሬ አዳመጥኩኝ። ኮረቻ ላይ ቁጢጥ ያለ „ኢጎ“ አላሰራም ካላ በመጣበት መንገድ ለመሸኘት መወሰኑን። ይህ ማለፊያ ነገር ነው። ግን ላይ ብቻ ነው „ኢጎ“ ያለውን አቶ ሀብታሙ? ታችም አለና ታቹም ላዩም በተገባው ይቃኝ ባይም ነኝ። እንዲውም መጋኛው ያለው ከታች ይመስለኛል። ለማንኛውም እኔ ጅልነትን ስለቀበርኩት አቶ ሂደት በፈለገው ቅርጽና ይዘት ሊያወናብድ ቢያነፈንፍ ቅስሙን እንኩት። የጀመረውን የማተራመስ ማሳ ለቀቅም አድርጌለት ከቻልኩ ማገዝ በሰተቀር ግን መፈሳፈስ፤ መፈራረጅን፤ አጋ ለይቶ በገጀሞ መከታከትን እሱ እንደሚጠብቀው ስለማውቅ አፍንጫህን ላስ ብዬዋለሁ። አሁን ተዋውቀናል። በዛች ቆልማማ አፍንጫው እሱ ከመሳቁ – ከመሳለቁ በፊት እኔ ቅድም …. ማን ሞኝ አለ።
ሌላው አቶ ሂደትን የምጠብቀው ቁም ነገር እንዳለ እስቲ ላስታውስህ። በዚህ ገጥመህ በሰፋኽው ማሳህ ብቃት ያላቸው ሴቶች ከገንዘብ ያዥነት ወይንም አቻዎቻቸውን ከሚመሩበት „የሴቶች ጉዳይ ክፍል“ ሸገር ያለ ወንዝ የሚያሻግር ላቅ ያለ ድርሻ እንዲያው ታምነው ይስጣቸው ይሆን?! ያው በአጭሩ ቢቀረጠፍም አንድነት የመጀመሪያው ፓርቲ ነው ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳን የሊቀመንበርነቱን ቦታ ሲሰጥ። ለዚህም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ከአንድ ብሄራዊ ፓርቲ መሪዎች ዝርዝር ታሪክ ውስጥ አይኔ በክብር አለችና።
ከዛም በኋላ ምን ነበረ? ርዕዮትዬን ስጠብቅ ጭራሽ ተፈናቃይ አደረጋት አቶ ሂደት። አሁንስ ከቶ ምን እዬተመከረ ይሆን? …. እርግጥ እነ ወይንዬም ጠንከር ብለው ጎልተው እዬወጡ ነው። …. „በሴትነታችን ሳይሆን በብቃታችን“ በማለት …. ለማንኛውም ዘመነኛው ሂደት ይጠበቃል። መፍትሄውን እዬዘለለ ይህ ሂደት የሚባል ጉድ እኛንም አሞ ከሞ ያጫውተናል እንጂ የድሉ መናገሻ ፍሬ ነገር እኮ ይታወቃል። እነ ሚሚ እነ ቱቱ እነ እሙዬ እነ ሜላት ተናገሩ እኮ! ውይ! አንድ ነገር ረስቼ „ነገረ ሴቶችን“ የሚያዳምጥ ጆሮ የሚገዛበት ቦታ የምታውቁ አላችሁን? ከሰማችሁ እባካችሁ ….?! ለሚነግረኝ ትንሽ ሽልንግ ቢጤ በመቀነቴ ቆጣጥሬ እዬጠበኩ ነው ….
ሌላ ምን ነበር? ብቃትና አቅም አዬሁኝ ከ15.03.2014 ከአቶ ሃብታሙ አያሌው የደብተራ ሩም ቆይታ። ወያኔ አዘጋጅቶ በነበረው የሚዲያ ፓናል ዲስክሽንም ክርክም ያለች፤ ክሽን ያለች አንጀት አርስ ቦንብ ነበር ያጎረሱት ሽፋታውን ወያኔ፤ ወያኔ ከጫካ ወደ ከተማ ኑሮውን ሲያደላድል የ2ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩት አቶ ሃብታሙ አያሌው። ለነገሩ አዲስ አበባም እኮ ለወያኔ ጫካው፤ መንፈሱ ጫካ፤ ህሊናው ጫካ …. ለአራዊትነት የተፈቀደ ግዛት ….. በጫካ ቲወሪ መደናበር —-
የአንድነት አዲስ መዋቅር፤ የመድረክ ምስረታ ሰሞናትም የአደራ ጠባቂው አቶ አንዶአለም አራጌ እንዲህ ከዓይን ያውጣህ የተባለ መንፈሰ ሊጋባ ነበር። የእኔ ስጋቴ እንዲህ ጎልብቶ የወጣ አቅምን ማዬት የሚፈልጉ፤ ማድመጥ የሚሹ፣ እንደ ብርቅ የሚያዩ፣ ይህን ሃብት ጥቅም ላይ ለማዬት የሚጓጉ የመኖራቸውን ያህል ተመሳስለው ያሉ የግል ኢጎ ቁስለኞች ደግሞ ከአረሙ ጋር በማበር ሌላ የጨለመ ትዕይነት እንዳይመጣ እንቅልፍ አለባው ሥርጉተ ትሰጋለች። ይፈቀዳል አይደል መስጋት …. ? ? ?
እኔ እነዚህ የትውልድ አዲስ ተረካቢ ወጣቶቹ ጥንካሬ ፈጽሞ የማይጠበቅ እዬሆነበኝ ነው። ግንዛቤያቸው፣ ዕያታቸው ከምኑ ነው የዛቁት? ይገርማል – ይገራል። ከመራራው የዕንባ ጅረት ሳይሆን አንደማይቀር ሰማይ ቤት ላይ ያለው የክሮስፖንዳንስ ሠረተኛ ጠቁሞኝ ነበር አንድ ቀን እንደ ዋዛ። …. ታዲያ እኛ ይህን የሚያሰተናግድ ንጡህ መንፈስ አለን ነው ጥያቄው … ከዚህው ከአቶ ሃብታሙ ማህደር ሳልወጣ ትንሽ ቆዬት ባለቸው የቃሌ ክፍል ቃለ ምልልሳቸው „መንገዱ ተጀመረ“ ልጃቸውን የትዳር ጥንዶቹ በጉራጌኛ የጠሩበት ስያሜ ነው። የኢትዮጵያን ቀለማም ማንነት እንዲህ ፈቅደው ያስጌጡ ናቸውና ተዚህ ላይ አቶ ሂደትን ቸር ወሬ ስላሰማኝ ለጥ ብዬ አመሰገንኩት። ውሳኔው ያስተምራል – ይመራል። የአዲሱን ትውልድ መንፈስም አሳምሮ ያሳያል …. ሌሎቻችንም ይልመድብን። እኔ ትርጉም የሚሰጡኝን ነገሮች በአግባቡ ነው አክብሬ የምይዛቸው። ጠብ ብላ የምትፈስ ጠበል የለችም። ሥጋና ምን ተባለዬ ቤት አይደለሁም ….
ገጥሞ መስፋት ያልኩት በአሉታዊ እንዳይታይብኝ። አዎንታዊ ነው። አኔ እራሴ ተገጥሜ ተሰፍቼ ነው በህይወት ቁሜ እንደ ጥንቱ ከሞት ተርፌ ሰው ሆኜ ቆሜ ያለሁት። የእውነት እምተርፍበት ሁኔታ በጣም ስስ ነበር። ግን ፈጣሪ ይመስገን ተገጥሜ ከተሰፋሁ በኋላ ሶስት ዓመት ተጨመረልኝ። በኋላም ይመጣሉ ተብለው የተሰጉት ነገሮችም በሃኪሞቼ እንደተተነበዩት አይደለም በጣም በእጅጉ የቀነሰ ነው።
ሌላ አንድ ነገር የቀረ ደግሞ አለኝ። አቶ ሂደት አለህ? ሆሆ ትሰማኛለህ? ከልብህ እባክህ አዳምጠኝ – ቢተ? (bitte? እባክህ?)? ገጥመህ ስትሰፋ ደስ ብሎህ ፍንክንክ ፍልቅልቅ ብለህ ተቀበሉኝ እንደምትለን ሁሉ „ተገጥሜ ለመሰፋት ጊዜዬ ገና ነው“ ላላው ልጅህ ደግሞ ነፃነቱን ፈቃዱን ጠብቅለት። ከነፃነቱ ጋር እዬሄድክ አትላተም። „ጊዜ ገቢረ ለእግዚአብሄር“ ይላል ወንጌሉ። እሱን መለስ በልና ገልበጥ አድርገህ ከቃሉ ጋር ጥድፊያህን አሰማማው። „ሲሮጡ የላኩህም“ አትሁን። አደብ የትውልዱ መንፈስ ነው፤ ለነገሩ ይሄ ሚስጥር ጠጠር ብሎብሃል አይደል?። ከሌለህ ደግሞ ቅዱስ ወንጌል ያለውን ይሄው እኔው እህትህ አስታወስኩህ። ካለጊዜው የተፈጸመ ድርጊት ታምራዊ አንድ ነገር ብቻ ነበር። የቃና ዘገሊላ የድንግል ማርያምና የልጇ ፍቅራዊ ሂደት። „መጠበቀን“ የመሰለ ነገር የለም። መጠበቅ ለእኔ የዲያመንድ ጮራ ነው።
ለነገሩ አንተ መስማማትን አትወድም። በምን አቅልህ? እንደ ሽፍታው ወያኔ እኮ አቅልህ የተዘቀዘቀ ሸውሻዋ ነህ። ደግሞ ታስፈራራለህ ወዮ! እያልክ አትስማሙ እያልክ፤ በእንትን በቅብጥርስ እያልክ ስታምሰን ከረምክ። አሁን ተነቃብህ። አፍንጫህን ላስ ተበላክ …. ጉድህ ፈላ …..። እዬተወላገዱ ሙድ ማሳት ተመነጠረ። አዬህ አቶ ሂደት …. መንፈስ ሲሰበሰብ አቅም ወግ ይደርሰዋል።
ብቻ አደራ እንደዚህ ለግለግ እያሉ የሚወጡትን ቀንበጦቼን ወደ ቃሊቲ …. እንዳታስባቸው እንጂ፣ እኛም ልክ እንደ ጀግናው አበበ ቢቂላ ቀደመንህ ልብ ገዛን። ከአንተ ጋር አብረን ወገኖቻችን በሰባራ ሰንጣራው መውቃት፤ መድቃት፤ ማብጠልጠል ቅርት፤ ምን ይውጥህ? ትላንትን አሳዬህን፤ ዛሬንም ሻምላ ጋሬጣ አዘጋጅተህ በሉ ልያችሁ የማን ደም ፈሰሰ ቀረ። „አሞራው በረረ ቅሉ ተሰበረ“ ሆነልህ – ትልምህ። እኛ ምናችን ሞኝ?! እቴ! ሞኝህን ፈልግ ብለን … በተደሞ ማዬትን መረጥን። ስንችል ደግሞ የምንችለውን ማጉረስ። ምን ይውጥህ?! ….. አንተ ምንትሶ – ቅብጥርሶ፤ ደልቅ ከዘመንኛው ጥጋበኛ ወያኔ ጋር … አንድ ቀን አንተም እንዲህ እዩዩኝ ስትል እንክት ትልና …. እንደ ጦር የምትፈራው „ገናናው ኢትዮጵያዊነት“ በአኃቲ ማዕዶት … በሽንጣም ሞሰብ ቅብጥን ቅልጥ በማለት በናፍቆት ማር የምታዘንበው ሀገራችን ላይ … ተግባባን ጌታው አቶ ሂደት። ለነገሩ ሰንደቅአላማን ገንባሌ አድርጎ ቀን ሳይታደል ካለአለአቅሙ፣ ካለወርዱም የተኮፈሰው ውሽልሽል የጎጥ ቅራቅንቦ „ኢትዮጵያዊነት“ ከእኔ ወዲያ ላሳር እያለ ነው አሉ …. አያልቅበት ቀዳዳ ዲሪቶ መጣፍ። ሰው ይተዘበኛል አይል? አይኑን በጥሬጨው ያሸ ጉድ …. „መሳቂያው ፓርላማ“ አለ አቤ ቶኪቻው። በል ከመሰናበቴ በፊት ተጠይቅ አስሰኪ አንድ ጥያቄ ከቶ መቼ ነው ከዚህ ኪስ አውላቂ የድቡሽት ቤት ጎጠኛ ሽፍታ ጋር የምትፋታው? የናፈቀኝ አሱ ነው …. ህልም አይከለከል ነገር ..
የእኔዎቹ እንዴት ናችሁልኝ። አብረን በመቆዬታችን ደስ ሲለኝ ስንበቱን ሳስብ ደግሞ ክፍት አለኝ። ባር ባር እያለኝ ናፍቆቴን በፍቅር ጥበብ አሳምሬ ቸር እንድተሰነብቱልኝ ተመኝቼ ልሰናበት። መልካም ጊዜ። ማይክ ፍሪ ….
እልፍ ነንና እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።
እግዚአበሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ ሥላሴ።
“ሰው በላ” በሆኑት የኢህአዴግ ሙሰኞች ላይ ኮሚሽኑ ለምን ይሽኮረመማል?
ሳሙኤል ተወልደ በርሔ/ሃርስታድ ኖርዌይ/
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በነበሩበት የጠቅላይነት ዘመን የተጀመረው እና ቀጣይነት እንደሚኖረው የተነገረለት የከፍተኛ ባለስልጣናት ‹‹የሀብት ምዝገባ››ን የበላው ጅብ ምነው አልጮህ አለ?…ጥያቄው ይህ ነው፡፡ የሚመለከተውም ጸረ ሙስና ኮሚሽንን ነው፡፡ ጸረ ሙስና ኮሚሽን የገቢዎች ባለስልጣናቱን እነ አቶ መላኩ ፈንቴን በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ ካሳሰራቸው በኋላ ፀረ ሙስና ስሙ የመታደስ አዝማሚያ ታይቶበት ነበር፡፡ ትናንሽ ባለስልጣናት ላይ እንደሚበረታ የሚነገርለት ፀረ ሙስና ኮሚሽን የነ አቶ መላኩ ፈንቴን በቁጥጥር ስር መዋል ተከትሎ ከአይን ያውጣህ ተብሎ ነበር፡፡
ይህ ራሱን የቻለ ጉዳይ ቢሆንም፣ ለዚህ መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ ግን ተጀምሮ የተቋረጠው ወይም ወደፊት ይፋ ይሆናል ተብሎ በእንጥልጥል የቀረው የከፍተኛ ባለስልጣናት የሐብት ምዝገባ ይፋ የማድረግ ሒደት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ሙስና እና ሙሰኞች እንዳሉ ባለጉዳዩ ኢህዴግም ያምናል፤ ያውቃል፡፡ የሀገር እና የህዝብን ሀብት የተለያየ ቅርንጫፍ ካለው የሙስና ግንድ መታደግ የሚቻለው ባለስልጣናትን በማሰር ብቻ አይመስለኝም፡፡
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን በአንድ ወቅት፡- “መለስ የ6 ሺ ህብር ደመወዝተኛ ነበር፡፡ ቤተሰቡን ከወር እስከወር ያስተዳድር የነበረውም መንግስት በሚከፍለው ደመወዝ ብቻ ነበር…” በማለት እንደተናገሩ (እንደተሳለቁ) አይዘነጋም፡፡ ለተቀረው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ ለራሱ ለኢህአዴግ አባላት እንኳን ፌዝ የሆነው የወ/ሮ አዜብ መስፍን ንግግር በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዘንድ እንዴት እንደሚታይ (እንደሚተረጎም) አላውቅም፡፡ ኮሚሽኑ “በ6 ሺህ ብር ደመወዝ ነበር የምንተዳደረው” ከሚለው የወይዘሮዋ ንግግር ተቃራኒ የሆነ የሀብት ክምችትን ያጋልጥ ይሆን?…ወይስ ወይዘሮ አዜብ እንዳሉት “የመለስ ቤተሰብ በ6 ሺህ ብር ይተዳደር ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን ከሚቆረጥላቸው የባለቤታቸው የጡረታ ገንዘብ ውጪ ቤሳቤስቲን የላቸውም” በማለት ፖለቲካዊ ጥብቅና ይቆምላቸው ይሆን?…አብረን የምናየው ይሆናል፡፡
“ዓላማዬ ሙስናን እና ሙሰኞችን ማጋለጥ ነው፡፡ ህብረተሰቡም ይተባበረኝ…” እያለ በተደጋጋሚ የሚደሰኩረው ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለረዥም ጊዜ አፍኖ ያቆየውን (“ሲመዘግብ የነበረውን”) የባለስልጣናት ሀብት ያለ አንዳች “ሴንሰር” ወይም ኦርጂናሉን ንብረታቸውን ይፋ እንደሚያደርግ ሰሞኑን በድረ-ገፆች ከተሰራጩ መረጃዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ እዚህች ጋር ጥያቄ አለኝ፤ ኮሚሽኑ “ይፋ” የሚያደርገው የባለስልጣናት ሃብት በምን ዓይነት የምርመራ ስትራቴጂ የደረሰበት ነው?…ወይስ ባለስልጣናቱ “እኔ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ፤ ከዬት አምጥቼ ሀብት አከማቻለሁ?…ያለችኝ ይቺ ናት” ብለው የተናዘዙትን ጥቃቅንና አነስተና ንብረት ነው “ይፋ” የሚያደርገው?
“ያለቺኝ ይቺ ናት፤ ይህችኑ መዝግብ” ተብሎ የተሰጠውን ሀብት ይፋ የሚያደርግ ከሆነ በህዝብ ንብረት ላይ መሳለቅ ነው የሚሆነው፡፡ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት በቢሊዮን የሚቆጠር በሕገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ከኢትዮጵያ ወደ ውጪ እንደሚኮበልል በየጊዜው ያጋልጣሉ፡፡ እንዲህ ያለ ዘግናኝ ገንዘብ መቼም በተራ ኢትዮጵያዊ ወደ ውጪ ይኮበልላል ማለት የዋህነት ነው፡፡ በኮበለለው እና ወደፊትም በሚኮበልለው የህዝብ (የሀገር) ገንዘብ ውስጥ የቱባ ባስልጣናት እጅ እንዳለበት አያጠራጥርም፡፡ ታዲያ ኮሚሽኑ በምን መንገድ ነው በከባድ ሙስና ኮብልሎ በውጪ ሀገር ባንኮች የተከማቸውን ገንዘብ የሚያጋልጠው?…የሚለው ጥያቄ የግድ አጥጋቢ ምላሽ ማግኘት አለበት፡፡
ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የነ አባዱላ ገመዳን፣ የነበረከት ስምኦንን፣ የነዶ/ር ደብረፅዮንን…ትክክለኛ ሀብትና ንብረት ካላሳወቀን ኮሚሽንነቱ ቀርቶ እንደ መርካቶ “ቁጭ በሉ” እያታለለን ቢኖር “መልካም” ነው፡፡ ምክንያቱም፡- የመርካቶ “ቁጭ በሉ” ለተነሳለት “ዓላማ” ባዳ በመሆኑ የትኛውም ዓይነት ኃላፊነት ደንታ አይሰጠውም፡፡ ስለሆነም በኮሚሽነር አሊ ሱሌይማን የሚመራው ፀረ-ሙሽና ኮሚሽን የበረከት፣ የደብረፂዮን ወይም የአዜብ “ዓይን ገረፈኝ” ብሎ የተዛባ መረጃ የሚያቀርብልን ከሆነ “ውጉዝ ከመ አርዮስ” ከመባል አይድንም፡፡
ምክንያቱም ከዚህ ምስኪን ሕዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ እንደ “ቦዘኔ” ልጅ የትም ወጥቶ ሲቀር ከማየት በላይ የሚያስቆጭም የሚያናድድም ድርጊት የለም፡፡
ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ከደብረፂዮን ጋር ሲሆን ሕወሓትን፣ ከበረከት ጋር ሲሆን ብአዴንን፣ ከአባዱላ ጋር ሲሆን ኦህዴድን…መምሰሉን ትቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ዘብ እንዲቆም ከዛሬ ጀምሮ በአስቸኳይ ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ ካለበለዚያ ካገኘው ወይም የሩሲያ ቮድካ ከጋበዘው ባለስልጣን ጋር ሁሉ እንደ እስስት እየተመሳሰለ የኢትዮጵያን ህዝብ ላብ እንደ ደም መምጠጥ እንደሌለበት ካሁኑ መገንዘብ አለበት፡፡ እንዲሁም እንደ ልጃገረድ መሽኮርመሙን አቁሞ የባለስልጣናቱን ሀብት “ይፋ” ማድረግ አለበት፡፡ ምክንያቱም ሙስና የገንዘብ ዝርፊያ ቢሆንም፤ እንደ “ሰው በላ” አውሬ ሀገሪቱን ቀርጥፎ ይጨርሳታል ባይ ነኝ፡፡
ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ያላቸውን ሀብት በይፋ ካስመዘገቡ እና የተመዘገበው ሀብታቸው ለህዝብ ይፋ ከሆነ፣ ከደሞዛቸው በላይ የሆነ መኪና ለመንዳት ብዙም ድፍረት እንደማያገኙ ይታመናል፤ ምናልባት ዓይን በጨው በማጠብ የመጣው ይምጣ ብለው ካልፎከሩ በስተቀር፡፡ እናም ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሆይ ያኔ ማለትም የዛሬ ሁለት እና ሶስት ዓመት ገደማ የከፍተኛ ባለስልጣናት ሀብትን መዝግበህ አንደነበር አይዘነጋም፡፡
ወይስ የከፍተኛ ባለስልጣናቱ ፊት እንደ እሳት ገረፈህና የነሱን የሀብት መጠን ለማሳወቅ ጉልበትህ ከዳህ? በርግጥ ልክ ነህ፤ የቱባ ባለስልጣናቱን ሀብት መዝግበህ ይፋ ከምታደርገው የሀብት መጠን በላይ ህንፃ ሲገነባና መኪና ሲሸጥ ያገኘኸውን አይነኬ ባለስልጣን መንካት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ አናጣውም፡፡
ይህ ማለት ግን በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት የህዝብ ሀብት ሲመዘበር መሽኮርመም አለብህ ማለት አይደለም፡፡ ኃላፊነትህ ሀገር እና ወገንን ከምዝበራ ማዳን እስከሆነ ድረስ በአብዛኛው በልመና እና በእርዳታ የምትተዳደር ሀገርን አሳልፈህ መስጠት የለብህም፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም የሚመጣው የእርዳታ እና የልመና ገንዘብ የተለመነለትን አላማ ሳያሳካ የሚቀርበት ጊዜ እንዳለ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡
ይሄ ጉዳይ ደግሞ ከማንም በላይ ሊያሳምመው የሚገባው በኮሚሽነር አሊ ሱሌይማን የሚመራውን የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንን ነው፡፡ እንደ እንጉዳይ እየበቀሉ የሚያድሩ ከሚመስሉት የአዲስ አበባ ዘመናዊ ህንፃዎች መካከል ምን ያህሎቹ ለሐሜት የተጋለጡ እንደሆኑ እናውቀዋለን፡፡
ይሄ ህንፃ እከሌ የተባለ ባለስልጣን ንብረት ነው፤ ያኛው ድርጅት የእገሌ ነው ለሚል የአደባባይ ሐሜት የተጋለጡ ንብረቶች መኖራቸው ፀረ ሙስና ኮሚሽንን እንቅልፍ ሊነሳው በተገባ ነበር፡፡ እንዲህ አይነቱ የአደባባይ ሐሜት ተመርምሮ እና ተጣርቶ ተጠርጣሪዎቹ ማግኘት የሚገባቸውን ቅጣት እንዲያገኙ ያስችላል በሚል ምክንያት የሐብት ማሳወቂያ እና ማስመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ወጥቶ ስራ ላይ ከዋለ ሰነባብቷል፡፡ በነገራችን ላይ አዋጁ ወጥቶ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ በመጀመሪያው አመት ማለትም በ2003 ዓ.ም 18ሺህ 94 ሰዎች ሐብታቸውን አስመዝግበዋል፡፡
ከነዚህም መካከል የኤፌድሪ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና ፌዴሬሽን ም/ቤቶች አፈ ጉባኤዎች፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሀብታቸውን እንዳስመዘገቡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡ ግን የትኛው ባለስልጣን ምን ያህል ሀብት እንዳለው ኮሚሽኑ ይፋ አላደረገም፡፡ ይህን ማድረግ እያለበት ያላደረገበት ምክንያት ነው ሊያነጋግር የሚገባው፡፡
የከፍተኛ ባለስልጣናቱ ሀብት መመዝገብ አንድ ርምጃ ነው፤ ዋናው ስራ ግን ሀብታቸውን ይፋ የማድረጉ ሒደት ይመስለኛል፡፡ አቶ በረከት ስምኦን፣ ወይዘሮ አዜብ መስፍን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ አባዱላ ገመዳ…ወዘተ ሀብታቸው እንደተመዘገበ ቢነገርም የሀብታቸው መጠን ይፋ አለመሆን ህብረተሰቡ ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሊጫወት የሚገባውን ሚና አዳክሞታል የሚሉ አስተያየቶች ይደመጣሉ፡፡
አቶ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ‹‹ዜጎች ከታችኛው አስከላይኛው መዋቅር የመንግስት አካል ድረስ ሙስና እንዳይኖር የሚያስችል ከባቢ መፍጠር አለባቸው›› ማለታቸውን አስታውሳለሁ፡፡ እኔ ደግሞ እንዲህ እላለሁ፡- ዜጎች እንዲህ አይነቱን ከባቢ መፍጠር የሚችሉት ፀረ ሙስና የመዘገበውን የባለስልጣናት ሀብት ለህዝብ ይፋ ሲያደርግ ነው እላለሁ፡፡
አንድ ባለስልጣን ካስመዘገበው ሀብት በላይ ሲቀማጠል ያየው ሰው ለሚመለከተው አካል ጥቆማ ሊሰጥ የሚችለው የባለስልጣናቱ ሀብት አስቀድሞ ይፋ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ በተረፈ ጠንቋይ በመቀለብ ሙስናን መዋጋት አይቻልም፡፡ እንደ ፀረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ ከሆነ ከላይ የጠቀስኳቸውን ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ጨምሮ 393 ከፍተኛ ተሿሚዎች፣ 498 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ 10334 የሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተሿሚዎች እና የመንግስት ሰራተኞች፣ 3225 የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ተሿሚዎች እና የመንግስት ሰራተኞች፣ 3644 የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሰራተኞች በአጠቃላይ 18ሺህ 94 ሰዎች ሐብታቸውን ቢያስመዘግቡም፣ አሁንም ድረስ የመንግስት ኃላፊዎች ሀብት ምን ያህል እንደሆነ ጸረ ሙስና እና እግዜር ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ እንደው ፀረ ሙስና እግዜር ረድቶት የቱባ ባለስልጣናትን የሀብት መጠን ቢያሳውቀን ጥሩ ነበር፤ ደግሞም ያጓጓልም፡፡
የኃይለማርያም ደሳለኝ ሀብት ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ የማይፈልግ ሰው አለን? የበረከት ስምኦን እና የአዜብ መስፍን ሀብት ስንት እንደሆነ ማወቅ አያጓጓምን? የሌሎቹንም ባለስልጣናት ሀብት ማወቅ ከልብ አንጠልጣይ ፊልም በላይ ያጓጓል፤ ያቁነጠንጣል፡፡ እናም ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሆይ ለመጓጓታችን ብቻ ሳይሆን ለፀረ ሙስና ትግሉ ስትል ጭምር የባለስልጣኖቻችንን ሀብት በፈጠረህ አሳውቀን፡፡ አለበለዚያ የፀረ ሙስናውን ትግል ራስህ እንደ ጀመርከው ራስህ እዛው ትጨረስዋለህ፡፡
ህብረተሰቡን የትግሉ ተሳታፊ ማድረግ የሚቻለው፣ ትግሉ በድል እንዲጠናቅ የሚያስችሉ መረጃዎችን ይፋ በማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን ኮሚሽኑ መረጃዎቹ ላይ አንጥፎ ተኝቶ ህብረተሰቡ የነቃ የፀረ ሙስና ትግል እንደሚያካሂድ መመኘት እንደማሞ ቂሎ ፍሬ አልባ መሆን ነው፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሊ ሱሌይማን የባለስልጣናቱን የሀብት ምዝገባ መረጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ በማድረግ አባክዎን ትግሉን ያጧጡፉ!!!
የአባ በላ ፍቅር እስከ መቃብር (ማህሌት ነጋ)
በማህሌት ነጋ
“ሃይለማሪም ደሳለኝ አብዩዝድ ነው። እንደውም ማታ ማታ (በህወሃቶች) ሳይገረፍ አይቀርም!” ብሎ ነበር ብርሃኑ ዳምጤ ከጥቂት ወራት በፊት በፓልቶክ ላይ።….
“ስለ አንድ ሰው ስንጽፍና ስንናገር ቢቻል አዎንታዊና መልካም ከሆኑ ነገሮች መጀመር ጥሩ ነው” ይሉ ነበር “የኔታ” በሚል ቅጽል ስም እንጠራቸው የነበሩ የዘጠናኛ ክፍል የአማርኛ አስተማሪያችን። ቀጭንና የዋህነት የተላበሰ ፊታቸው ላይ ችፍ ብሎ የማርክስን ግርማ ሞገስ ያጎናጸፋቸውን ገብስማ ሪዝ በእጃቸው እየዳበሱ ያስተማሩኝ ትዝ አለኝ።
ነገሩ የድሮ ትምህርት ቢሆንም የተማርኩትን በማሰብ እንደ አዞ ደንዳና ቆዳ ስለ ታደለው ብርሃኑ ዳምጤ ለመጻፍ ስነሳ ከልቅ አፉ ባሻገር ከማደንቅለት ባህሪው ብጀምር መልካም ነው ብዬ አሰብኩ።
ማንም በቀላሉ ሊክደው የማይችለው ሃቅ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) የፍቅር ሰው ነው። ብርሃኑ ለፍቅር ሲል ብዙ መስዋእትነት ከመክፈል አልፎ በስደት ዘመኑ ሳይቀር እንደ ዘላን ብዙ ተንከራቷል። የሚገርመው ነፍስ ካወቀ ጀምሮ እስካሁን ያፈቀረው አንድ ብቻ ነው። ለፍቅረኛው ሲልም ብዙ ተሰቃይቷል፣ ወደ ፊትም መሰቃየቱ አይቀሬ መሆኑን ለመተንበይ ቀላል ነው።
ታዲያ ብርሃኑ “ሆዴ! ያላንቺ ማን አለኝ!” እያለ በፍቅር የሚያቆላምጣት አይኗ የሚያማልሉ፣ አፍንጫዋ ሰልካካ፣ ጸጉሯ የሃር ነዶ የሚመስሉ የቆንጆ ቆንጆ የሆነች ኮረዳ እንዳትመስላችሁ። በተቃራኒው፣ አፍንጫም፣ አይንም የሌላት ትልቅና ወደፊት የተገፋ ጆንያ የሚመስል ግንባር ብቻ ያላት መሆኗን ጠንቅቆ ያውቃል። ያለባት አንድ ትልቅ ችግር የመኖ ነገር አይሆንላትም። በቀላሉ አትጠረቃም። ቢሆንም ነፍሱ እስኪወጣ ይወዳታል።
በፍቅር “ሆዴ! ሆዴ! ” የሚላትም ሌላ ሳትሆን በስተርጅና አክሮባት የምታሰራው ሆዱን ነው።
“ሆድ፣ ሆዴ! ያላንቺ ማን አለኝ!” እያለ ዘውትር በፍቀር የሚዳብሳት ፍቅረኛ። የሚያቃጥል ፣ የሚያንቀዠቅዥ፣ ህሊና የሚያስት ፣የሚያክለበልብ፣ ቀልብ የሚያሳጣ ከሁሉም በላይ የሚያዋርድ የሆድ ፍቅር ቢባል ማጋነን እንደማይሆን እርግጠኛ ነኝ።
የታደለ ለነጻነት፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለሰላም መስዋእትነት ሲከፍል፣ በየእስር ቤቱ ሲሰቃይ የቁብና የእድር ዳኛ ለመሆን ብቃት የሌለው አጭቤ ግን በሆድ ፍቅር ተቃጥሎ የሆድ ማንዴላ ሆኖ እንደ ረከሰ ሴተኛ አዳሪ በየአደባባዩ ከንቱ ስብእናውን በስሙኒ እየቸረቸር ለከፈሉት ሁሉ እየደነሰ ይኖራል። ኑሮ ካሉት…መሆኑ ነው።
ታዲያ ሰሞኑን ከተቃዋሚ ጎራ አመለጥኩ እያለ እያለከለከ ቤን (ሆድፈርስት) እና ሰለሞን ቅንድቡ በተባሉ እርካሽ የሆድ ውጠራ የትግል አጋሮቹ በኩል የለመደውን ቱሪናፋ ሲቸረችር አያቴን አስታወሰኝ። አፈሩ ይቅለላትና አያቴ የአባ መላ አይንቱን የመለፍለፍ ልክፍት ያለበትን ቅል ስታይ “አሻሮ የበላ አሻሮ ያገሳል” ነበር የምትለው።
እውነት ለመናገር ነገሩ ሁሉ ብርሃኑ መኖ ፍለጋ መጣ መኖ ፍለጋ ተመለሰ ወይንም ተገለባበጠ መሆኑን ስለምናውቅ እራሱን ማግዘፍ ያልተሳካለት ምስኪን ሆድ ወዳድ ምን ቢናገር ሊያስከፋን አይችልም። በነገራችን ላይ አባ መላ የሚለው ስም ስለሚያንስበት ከዚህ በኋላ አባ በላ በሚል የማእረግ እድገት እዲሰጠው ፍቃዳችሁ ይሁን።
አንድ ምስክር እንዳለው አባ በላ መብላት የሚያቆመው ሲጠግብ ሳይሆን ሲደክመው ብቻ ነው። ታዲያ አባ በላ በመፈረካከስ ላይ ካለው ከወያኔ መንደር አምልጬ መጣሁ ብሎ እያለከለ እንደመጣ መጀመሪያ ያቀረበው ጥያቄ የመኖ ነበር። “ይከፈለኝ” አለ። ለከፋዮቹ ችግር የሆነው ምን ሰርቶ ምን እንደሚከፈለው ማጣራት ነበር። ከፓርክንግ ሎት ምንተፋ ባሻገር ሙያ የለው፣ ትምህርት የለው፣ እውቀት የለው፣ አመል የለው፣ ግብረገብ የሌው፣ ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ነበር።
የመጣው ባዶ እጁን ግን ደግሞ ትግስት የሌለው ቀዥቃዣ ቢሆንም “ሆደ ሰፊ” መሆኑ የታወቀ ጉዳይ ነው። ይከፈለኝ ሚስጥር ይዤ መጥቻለሁ፣ የወያኔ ሰላዮች በአሜሪካና በአውሮፓ ስምዝርዝርና አድራሻ አለኝ አለ። በርግጥ ለዚህ ጠቃሚ መረጃ ክትፎ ምናምን ተገዝቶለት መረጃውም ለሚመለከታቸው የአሜሪካና አውሮፓ መንግስታት መመራቱን ሰምቻለሁ።
በኢሳት ላይ ካልወጣሁ፣ መድረክ ካልሰጣችሁኝ አለ። የሚገርመው ግን በኢሳት ላይ ቃለምልልስ ለማድረግ እንኳን ይከፈለኝ አለ። ኢሳቶችም ለዚህ አንከፍለም አሉት። ምንም እንኳን መጀመሪያ ይከፈለኝ ሲል የቀረበው በስካይፕ ቢሆንም ቢያንስ ለትራንስፖርት ይከፈለኝ አለ።። የሆድ ነገር፣ የሆድ ፍቀር፣ የሆድ ትግል ነው ነገሩ ሁሉ።
የተቃዋሚው ጎራ አስቸጋሪ ትግል እንጂ መኖና አረቄ እንደሌለው ሲገባው ነገሩ ሁሉ ሊጥመው አልቻለም። እርሱ ሃሳቡ ሁሉ በቀላሉ የማትረካውን ፍቅረኛውን “ሆዴን!” ሞልቶና ሸንግሎ ማሳደር ነው።
ያም ሆነ ይህ ስለ አባ በላ ብዙ መጻፍ አያስፈልግም። ጓዙን ጠቅልሎ፣ ሆዱን ታቅፎ እያለከለ በመጣበት መንገድ ሄዶ የድሮ ጌቶቹ እግር ስር እያለቀሰ ማሩኝ ቢልም እኛ ድምጹን ቀርጸን ስላስቀረን ይሂድ ተውት። ድሮም ቢሆን ጅብ በጨለማ እንጂ በብርሃን ኑሮ አይሳካለትም።
ያልተማረው ተንታኝ አባ በላ እንደ ጀብድ የሚቆጥረው ስራ ፈቶ ፓልቶክ ላይ ተጥዶ የቆጥ ያባጡን መቀባጠሩን ነው። ለማንኛውም አባ በላ መንግስት የለም ወያኔ አልቆለታል እያለ ከዘፈናቸው ዘፈኖች መሃል አለፍ አለፍ እያልን እናዳምጥ። ወጪት ሰባሪ የሆነው አባ በላ ጌቶቹን የሚያጋልጡ በርካታ ዘፈኖች ስለዘፈነ ቀስ በቀስ እያወጣን እንዝናናባቸዋለን። እነዚህን ከታች ለናሙና የመረጥኳቸውን የውስጥ አዋቂው የአባ በላን ንግግሮች (ዘፈኖች) በጥሞና ይከታተሉ።
ሃይለማሪያም ደሳለኝ “አብዩዝድ” ነው
ይለማሪያምን ተዉት፣ እኔ ለሃይለማሪያም ማዘን ጀምሪያለሁ። እኔ እንደውም ከሳውዲ ከተመለሱት ሰዎች አንዱ ይመስለኛል። ምክንያቱም የት ጠፋ ይሄ ሰውዬ። በሳውዳአረዲያ ነበረ ማለት ነው። እና ሰሞኑን እንሰማለን ማለቴ ነው። አንዱ abused የሆነ ሰው ነው ማለቴ ነው። እርሱ እኮ ሰልፍ ሊወጣለት የሚገባው ሰው
ነው። ግን ጥሪ ለምን እንደማያቀርብ አይገባኝም። አለ አይደለም እንደዚህ abused እደረጋለሁ፣ እንደውም ማታ ማታም ሊገረፍ ይችላል። ምክንያቱም በጣም
ተደነባብሯል።
የሚያወራው ነገር ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። እርሱን ተዉት እንደ መሪም አትቁጠሩት። እሱ እንደ ሰው ህሊና ቢኖረው immediately resign ማድረግ
አለበት። እውነቴን ነው፣ ከልቤ ነው። መናቄ አይደለም። ምክንያቱም authority ሲባል de facto power ሊኖረው ይገባል። ዝምብሎ መቀለጃ ስትሆን፣ you have to resign። ብዙ ስራ አለ ለሱ የሚሆን። ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የኮብል ስቶን ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አለ። አንዱን ሊመራ ይችላል። በደቡብ የሚካሄደውን የኮብል ድንጋይ ምንጣፍ ቢከታተል ይሻለዋል። ምን አጨቃጨቀው ከነዚህ ሰዎች ጋር።
ሳሞራ ዘረኛ ነው
አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ስትመለከት structurally እከሌ ሚኒስትር ነው ይሉሃል ምክትሉ ደግሞ ሌላ ሰው ነው። ዋነው ሰውዬ አይደለም አለቃው፣ ምክትሉ ነው አለቃው። እኔ በቅርብ ቦታውን አልጠቅስልህም የመከላከያ ሚኒስትሩ እዚህ መጥተው ነበር፣ ዋሺንግተን ዲሲ። አብሯቸው ኢታማዦር ሹሙ ሳሞራ ነበር።
የውጭ አገር ሰዎች ሁሉ ያሉበት ዲነር ነው። ሌሎችም ባለስልጣኖች ነበሩ። እኔም ነበርኩ። ኢታማዦር ሹሙ መከላከያ ሚኒስቴሩን ይሰድበዋል፣ በዘሩ። ፈረጆች ባሉበት እኮ ነው። ቀለድኩ ነው የሚለው። እንዲህ አይነት ቀልድ አለ እንዴ። በወታደራዊ ስርአት ውስጥ መከላከያ ሚኒስቴር ማለት ትልቅ power ነው ያለው።
አንተ አስር አለቃ ሆነህ ሃምሳ አለቃው ሲመጣ ቆመህ ነው ሰላምታ የምተሰጠው… አንድ ኤታማዦር ሹም፣ምንም ልምድ የሌለው ጎሬላ ነው። በጣም ጨዋ ሰው
ነው መከላከያ ሚኒስቴሩ፣ እኔ ስለማውቀው ነው። በጣም ነው የተናደደው (አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ)። ደሞ እኮ አስተርጉሞ ለፈረንጆች ሊነግራቸው ይፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዘናዊ አሉ ብሎ ነው የሚያወራው። የዚህን ሰውዬ ብሄረሰብን እንደ ሌባ አድርጎ ነው ይሚቆጥረው።…እኔ እንደዛን ቀን ደሜ ፈልቶ አያውቅም።
ብዙ ሰዎችም የሚያውቁት በብዙ ነገር ነው፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አንዱ መቼም የሚፋረደው እሱን (ሳሞራን) ነው። በመከላከያ ውስጥ የተጠላ ሰው ነው። ይሄንን ሰውዬ ሲያዋርደው ስታይ really በዚያን ለት ዲነሩ አንዳለ ነው የተበላሸው…። አንተ ሚኒስቴር ስለሆንክ አይደለም ዘበኛው (ህወሃት ከሆነ) ሊኒቅህ ይችላል።…አንድ ስርአት structural problem ካለብት ሚኒስቴሩን ሹፌር የሚያዘው ከሆነ…አሁን እዚህ ዋሺንግተን ኤምባሲ አንድ ሰለሞን የሚባል ሃያ አመት የሚያውደለድል አለ። ምን እንደሚሰራ አይታወቅም፣ ።።ሰላይ ነው ልጁ መሰለኝ…ሰላሳ አምባሳደር ይቀያየራል። እርሱን የሚነካው የለም። ሾፌር ነው መደበኛ ስራው። ግን he is powerful than the ambassador, even ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ የበለጠ። እንደዚህ አንደዚህ አይነት ሰዎች ናቸው እዚህ የሚመደቡት።….
አዜብ መስፍን አጭበርባሪ ናት
ባክህ ተው አዜብ ምናምን ይለኛል። በሶስት መቶ ብር፣ በሁለት መቶ ብር ነው የምኖረው ምናምን ትላለች። ያልጠየቋትን ትለፈልፋለች። በሁለት መቶ ብር ነው እንዴ አሜሪካ በየግዜው የምትመጣው። ምን አይነት የምን ገንዘብ ነው? እኔ እሱ አይደለም፣ ስለሱ ችግር የለብኝም።…ይሄንን የሚገዛ ሰው ካለ ይግዛ stupid ሰው ካለ እንጂ አራት ሺ ብር ደሞዝተኛ የ100ሺ ብር ቦርሳ የምትገዛ ሴትዮ “አራት ሺ ብር ምናምን” ትላለች። በቃ ይሄው ነው።
First of all, የምትሰጣቸው ኮሜንቶች backfire የሚያደርግ ነው። መለስ መንጃ ፍቃድ የለውም፣ ባንክ አካውንት የለውም …ምን ማለት ነው? ቤተሰቡን take care የማያደርግ ፍጡር ምን አይነት መሪ ነው? እንዴት ነው መንጃ ፈቃድ የሌለው መሪ የሚኖረው በአለም ላይ?…እንዴት ነው ባንክ አካውንት የሌለው መሪ የሚኖረው? ይሄ irresponsibility ነው። ቤለሰብህን handle ማድረግ አለብህ…. መታወቂያ ሊኖርህ ይገባል። መታወቂያ የሌለው መሪ ነው እንዴ ሲመራ የነበረው። ምንድን ነው የሚያወሩት?…ስለገንዘብ የማያውቅ መሪ ነው?… እንዴት ነው ስለገንዘብ የማያውቅ ሰው ስለሃገር ኢኮኖሚ ሲወስን የነበርው? ይሄ ጥሩ ነገር አይደለም። ለማን ተይ እንዳላሏት አልገባኝም።
እሷ ገንዘብ የሚመስላት በቼክ የሚሰጥ ነው። How about የቤተ መንግስት ኦዲት የማይደረገው ገንዘብ…እማይወራረድ ገንዘብ አለ፣በሚሊዮን የሚቆጠር። ገንዘብ ሚኒስቴር የማያውቀው። እሱ ገንዘብ አልመሰላትም እንዴ?….How about ኤፈርት? የኤፈርት ስራ አስኪያጅ አይደለችም እንዴ?… ስለዚህ እንደዚህ አይነት ነገር ያመኛል። እንደዚህ አይነት childish የሆነ ፉገራ። እንደ ሃገር ደግሞ ሊያመን ይገባል።…አውቃለሁ የዚህ የዶክተር ጌታቸውም ጠበቃ እርሷ ነች። I know that, አጭበርባሪ ነች። የኢህአዴግ ዘጠነኛ ጉባኤ አድርባይነትን ተዋጉ ብሎናል ይሄ ሩም በአር ያነት እራሱን አስቀድሞ በአድር ባይነት ላይ ዘመቻ አውጇል።
የአቋም ለውጥ
ታዲያ ዛሬ አባ በላ ግርማ ብሩ አሞሌ ጨውና ብር ሲያሳየው እንደልማዱ ከሻቢያ አምልጨ ተመለስኩ እያለ ልፈፋ ጀመረ። አይ አባ በላ! በኢሳት ላይ በግንባር ሲቀርብ ሲሳይ አጌና “ከወያኔ ካምፕ ምን አስወጣህ?” ብሎ ሲጠይቀው ደረቱን ነፋ አድርጎ “ህሊናዬ እንቅልፍ ነሳኝ” አለ።
በረጅም አረፍተ ነገርም እንዲህም አለ፣ “በየግዜው የምናያቸው ነገሮች እየተሻሻሉ መምጣትን ሳይሆን እጅግ በሚያሳዝን ሁናቴ በአገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ ማህበራዊ ህይወት ውስጥ በተለይ ዲሞክራሲን ፍትህን፣ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት ህሊናህ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እየሆነ ሲመጣ ፣አገሪቱ የጥቂቶች ሆና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ባእድ ሆነው፣ ወጣቶች ሌት ተቀን ከዛች አገር እግራችን ይውጣ በሚል አገራቸውን እስከሚጠሉበት፣ ሴት እህቶቻችን በየአረብ አገሩ በሚሸጡበት፣ ጋዜጠኞች በመጻፋቸው እድሜ ልክ በሚፈረድበት፣ የኑሮ ውድነት በአለም ደረጃ ፍጹም ልትሸከመው በማትችል ደረጃ፣ ዛሬ ኢትዮጵያዊ ውስጥ የመንግስት ሰራተኛ እንዴት አድርጎ እንደሚኖር ሁሉ የማያውቅበት ሁናቴ ሲፈጠር ያንን ጉዳይ እንዲታረም ባለን ‘አክሴስ’ ሃላፊዎቹን ሁሉ እንትን ማድረግ እንሞክር ነበር።….ስር አቱ እርስበርስ መናበብም አልቻለም።….በጣም እሮሮ ያለብት ስርአት በመሆኑ ከዚህ መንግስት ጋር ሆነህ ለማስተካከል የምታደርገው ጥረት ዝም ብሎ ግዜ ማጥፋት ስለሚሆን እንደውም በሚሰራው ስተትና ወንጀል ላይ ታሪካዊ ሃላፊነት ይኖራል የሚል እንትን ስላለኝ ካለብኝ የዜግነትና የሞራል ጉዳይ አንጻር ጥያቄው አገር የማስቀደም፣ ህዝብን የማስቀደም ጉዳይ ስልሆነና የግል ጉዳይ ስላልሆነ የግዴታ ይህንን ስርአት በማንኛው መልክ ለማስተካከል ወይንም ለመለወጥ ከሚታገሉ ጎራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ጋር አብሮ መስራቱ ለአገር ይጠቅማል የሚል እምነት ላይ ደርሻለሁ። እና አሁን ሲሪየስ አቋም ነው ያለኝ።….”
“መቼም ይሄ በረጅሙ “በጄጄጄ!” የሚያስብል ጉዳይ ቢሆንም አያቴ “ጦጣ መንና ጫካ ገባች” የምትለው ተረቷን አስታወሰኝ።
አባ በላም ዝም ብሎ ህሊናዬ እንቅልፍ ነሳኝ የሚል ጨዋታ ጀመረ እንጂ አፈጣጠሩ ለህሊና ሳይሆን ለሆድ ስለሆነ ብዙ በአደባባይ መለፍለፉን ትቶ ሆዱን እየጠቀጠቀ ቢኖር ይመረጣል። እኔን ከአባ በላ በላይ የሚያሳዝኑኝ “የጨነቀው እርጉዝ ያገባል” እንዲሉ እርኩስ ጥንባቸውን ያወጣ ሆድ አደር ድጋሚ መቀጠራቸው ነው። ሳሞራ ዘረኛ፣ ሃይለማሪያም እርባና ቢስ አሻንጉሊት፣ አዜብ አጭበርባሪና ሙሰኛ፣ ስብሃት ሰካራምና ሴሰኛ፣ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ሌባ፣አባይ ወልዱን መሃይም፣ ቴድሮስ አድሃኖም ህጻንና እንጭጭ፣ ሽመልስ ከማል የማይረባ አድርባይ፣ አባ ዱላ ላንቲካ፣ ግርማ ብሩ እግር አጣቢ፣ በረከት ሴሰኛ….እያለ ፓልቶክ ላይ እንዳልጨፈጨፋቸው ዛሬ ሻቢያን ለመዋጋት ተመልሼ መጣሁ እያለ ያጃጅላቸዋል።…
አባ በላ ጠመዝማዛ መንገድ በከንቱ ተጓዘ እንጂ እውነታው እንዲህ ነው። የእርሱ ፍቅር እስከ መቃብር እንደነ ሰብለወንጌል የፍቅር ታሪክ የሚያማልል አይደለም። አባ በላ የሚያፈቅረው አብሮት የተወለደውን ሆድ ስለሆነ ጥቂት ቆይቶ አብሮት ይቀበራር። እኛም የሆድ ፍቅር እስከ መቃብር የሚለውን ታሪኩን ጽፈን የቀብሩ ስነስርአት ላይ እናስነብብለታለን። ምስኪን የሆድ አርበኛ! ስለ ህሊና ሳትናገር ዝም ብለህ የሰጡህን መኖ ጠቅጥቅ። መልካም መኖ ይሁንልህ ብለናል!
ያረጋገጥነው የምግብ ኢ_ዋስትናን (ዋስትና አላልኩም) ነው –ክፍል 5 [የመጨረሻው ክፍል]
ሠሎሞን ታምሩ ዓየለ
ይህንን ክፍል ስጀምር አንባቢያንን እንዲህ በማለት ነው። በሕዝቦቿም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረክ ሥራቸውና መልካም ተግባራቸው የተመሰገነላቸው፤ የተወደሰላቸው፤ የተጨበጨበላቸውና ውዳሴ የተቸራቸውን ድንቅዬዎቹን ኢትዮጵያውያን ሁሉንም ባይሆን ጥቂቶቹን ለሰከንድ በኅሊናችን እንድናስባቸው በመጠየቅ ነው። እነርሱ ለኛ ሻማ ናቸው። እራሳቸውን በጥረታቸው አብርተው ብርሃኑን ለኛም እንዲደርሰንና እንድንገለገልበት መንገዱን መርተውናል። እኛ ግን እርኩስና ስንኩል መንገድ ይሻላል ብለን የራሳችንን ፍልስፍናና የኑሮ ዘይቤ ትተን የሌሎቹን የማናውቀውንና ለኛ ኅ/ሰብ ምቹ ይሁን አይሁን በቅጡ ሳናረጋግጥ የተበላሸና የማይሰራ መንገድ መርጠን እነሆ ስንገታገት ግማሽ ምዕት ዓመት ሊሞላን አንድ አሥር ዓመት ቀረን። አንዳንዶቻችን የአዳምና የሔዋን ልጆች መሆናችንን እረስተን በማንነት ዙሪያ ብቻ ስናወራ ጊዜው በረረ። ሐረር የኖራችሁ ታውቁታላችሁ ብዬ አስባለሁ። ይህ ሰው የ፫ተኛው ክፍለ ጦር ኦጋዴን አንበሳ የሙዚቀኛው ክፍል (የቀላድ አምባው) ድምጻዊ ነው። መስፍን ከበደ ይባላል ። ሹመቱን እረሳሁኝ። ወታደር ሲኖርም፤ ሲሞትም በማዕረግ ስሙ ነው የሚጠራው። አስቀድሞ ታይቶት ነው መሰለኝ በ1960ዎቹ አጋማሽ እንዲህ በማለት አቀንቅኖ ነበር፦ ትውልዳችን የዓዳም አንድ ነው ደማችን፤ ከቶ ለምን ይሆን ዘር መለየታችን? ለውጥ በኑሮአችንና በአስተሳሰባችን ሲያልፍም አልነካን። በጊዜ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከፋም ለማም በሆነ ነገራቸው ለውጥ መታየት ነበረበት። በምሳሌም እንደተማርነው ” ምንም ያህል ዘመን በውሃ ውስጥ ቢኖር መዋኘት የማይማረው ድንጋይ ብቻ ነው” ተብሎ በተለይ የምዕራብ አፍሪካ ሰዎች ነገር በምሳሌ እንዳላቸው አንድ ወቅት ላይ ከረፖርተር ጋዜጣ ላይ ያነበብኩኝ መሰለኝ። ለማለት የፈለኩት እኛም በቂ እንዳልተማርንና ስህተትን በሌላ ስህተት ከመተካት በስተቀር ትርፍ ያመጣና ሕይወታችንን ከጎስቋላው ኑሮ ፈቀቅ ያደረግ እርምጃና ለውጥ አለማየታችንን ለመናገር ፈልጌ ነው።
ለዘመናትና ዛሬ ድረስ የኢትዮጵያ ገበሬ የተለያዩ የዕጽዋት ዝርያዎችን በመስኩ ላይና በጎተራው በመንከባከብና በመጠበቅ የሰው ልጅ ህልውና ታሪክ ከምድረ ገጽ እንዳይጠፋና እንዲቀጥል የበኩሉን ድርሻ እንደ አቅሚቲ ተወጥቷል። ለዓለምም ሕዝብ እንደ ቡና፤ እንሰት፤ ኑግ፤ ኮረሪማና ሌሎች ቅመማ ቅመሞችን፤ ኦክራ (የሴት ጣት)፤ ጤፍ፤ የተለያዩ የገብስ ሰብል ዓይነቴዎችን፤ ባህላዊ መድሃኒት የሆኑትን የኮሶና የድንገተኛ ዕጽዋቶችንና ሌሎች ሰብሎችንና እንስሳቶችን ጠብቆና በእንክብካቤ አቆይቶ ፤ ለራሱ ሳያልፍለት ለሌሎች አቀብሎና ሰጥቶ ቆይቷል። መልሶም የእነርሱ ተረጂም ሆኗል። ለዚህ ሁሉ ተግባሩ ደግሞ የአገሬ ገበሬን ዕውቅና ቢቸረው ቢያንስበት እንጂ አይበዛበትም። ለምሳሌም ያህል ለመጥቀስ የአሜሪካን የገብስ ሰብል ገበሬዎች ይህንን ውለታውን ጠንቅቀው ያውቁታል። ለምን ይህ ሁሉ የሰው ሃብትና እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶች ኖሮን እንዲህ ምድር ለኛ ብቻ ሲዖል የሆነችብን ብለን መጠየቅም ተገቢ ነው። ይህንንም ገጥታችንን ለመቀየር መፍትሄው እኛ ዘንድ እንጂ ሌላ ስፍራ እንደማይኖር ተገንዝበን ቀናውን መንገድ መከተል የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለን መነሳት እንዳለብን ለመጠቆምም ነው።
ግብርና የአገራችን ዋነኞ ኢኮኖሚ መሰረት ነው። ለዕድገታችንም መሰረቱ ግብርናው ነው ካልን አገራችን የገበሬ ምድር ናት ማለት ነው። አዎን! አገራችን ኢትዮጵያ፦ የአፈር ገፊው፤ የእንስሳት አርቢው፤ የዓሳ አስጋሪው፤ የደንና ዱር አራዊት ጠባቂው፤ የንብ አናቢውና የማር ቆራጩና የሌላም ልጆች አገር ነች። ለምን ቢባል በክፍል 4 መጨረሻ ላይ ጠቀሜታው ተገልጾአል። ግብርና ክቡር ሙያ ነው። ገበሬም እንደዚያው ማለፊያና ደግ ነው ። የአገራችን ኢኮኖሚ ምን ያህል ከግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ጋር የተቆራኘ ለመሆኑ ተደጋገመው የሚነገሩትን አኅዛዊ መረጃዎች መመልከቱ ይበቃል። እጅግ በድህነት አረንቋ ውስጥ ለሚገኘው 80% በላይ ለሆነው የአገራችን ሕዝብ ለኑሮው መሰረቱና መደበኛ ሥራው ነው። ከጠቅላላው የአገሪቱ ምርትም ውስጥ ድርሻው 50 % ነው። የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ወደ ዓለም ገበያ ከሚጓዙት ሸቀጦቻችንም እስከ 85% ድርሻ አለው። ዋነኛ የኤክስፖርት ምርታችን ብለን የምንጠራው የኮኖሚው ዋልታ ቡና ቡና 25% ድርሻ አለው። በተጨማሪም የእንስሳት ሃብታችንም ቢሆን ለብቻው ከጠቅላላው የግብርናው ምርት ውስጥ 15% ስፍራን ይይዛል።
የአገራችን ግብርና ዋና ዋና ገጽታዎቹ ምንድር ናቸው? በዋናነት የሰብል ልማት ላይ ያተኮረው ግብርናችን የዝናብ ጥገኛ ነው። የዝናቡ ተስተካክሎ በጊዜው መምጣት፤ መጠኑና ሥርጭቱ ለምርቱ ብዛትም ሆና ጥራት ወሳኝ ናቸው። የምግብ እህሎች የሚባሉቱ የብርዕና የአገዳ (ጤፍ በቆሎ ማሽላ ስንዴ ገብስ አጃ ዳጉሳ) ፤ ጥራጥሬ (ባቄላ አተር ምስር ሽምብራ አኩሪ አተር አደንጓሬና ሌሎች)ና የቅባት (ኑግ ሰሊጥ ተልባ ለውዝ) እህሎች በዋነኛነት የለማውን ማሳ (ከ80 _90%) እጅ ሸፍነውት ይገኛሉ። እንደ ጠቅላይ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት የ2005 የግብርና እንቅስቃሴ ናሙና ጥናት ረፖርት መሰረት ( አሃዙን ለማንበብ እንዲመች ወደ ሚቀርበው ለማጠጋጋት ተሞክሯል) በምግብ ሰብል ምርት የተሸፈነው ማሳ በጠቅላላው (በአነስተኛና በዘመኑት እርሻዎች በመኽርና በበልግ ወራት) መጠን 12 1/4 ሚሊዮን ሄክታር ሲደርስ ከእዚሁ ማሳ ላይ ብቻ ወደ 231 ¼ ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ እህል እንደተሰበሰበ ተገልጾአል ። እስቲ ስለዚህች አሃዛዊ መረጃ መሰረት አድርጉና ለጠቅላላው ሕዝብ ቁጥር ግምት አካፍሉትና የሚሰጣችሁን የነፍስ ወከፍ ዋጋ ተመልከቱት። ምን ይሰማችኋል? ይሄ የነፍስ ወከፍ ዋጋ የአትክልትና ፍራፍሬ፤ የሥራ ሥሩንና የቅመማ ቅመሙንና ሌሎችን ውጤት እኮ አይጨምርም። ታዲያ ውጤቱ ትክክል ነው ብለን የምናምን ከሆነ፤ ለምን በረሃብ ፤ በችጋርና በጠኔ እንሰቃያለን? ግብርናችን አንድ ቦታ ላይ በችግር ተውተውትቧል ማለት ነው። በተደጋጋሚ ለእርሻ አገልግሎት የዋሉት ማሳዎች የለምነት ደረጃቸው የቀነሰ ነው። አስተራረሳችን በአብዛኛው እጅ ዛሬም ጥንታዊና በዘልማድ ላይ የተመሰረት ነው። በኢትዮጵያ ምድርና ማሳዎች ላይ ብዙ ትራክተሮችና ተጎትተው የሚሽከረከሩ መሳሪያዎች አያጔሩም፤ የማጨዳ መውቂያና መፈለፈያ መኪኖች አይሽከረከሩባትም። በአገሪቱ አገልግሎት ላይ የትራክተሮች ብዛት ለሚታረሰው መሬት ወይም ደግም ለገበሬው ቁጥር ቢካፈል ድርሻው በጣም አነስተኛና ደካማ ነው። ይህም ማለት ግብርናችን በአብዛኛው በእጅ ሃይል የሚከናወን ነው ማለት ነው። የምርት ማሳደጊያዎች አጠቃቀማችን እንዲሆን ከምንፈልገው እጅግ ወደ ታች የተጎተተና የራቀ ነው ። በአትክልትና ፍራፍሬ፤ የሥራ ሥር ተክሎች የተሸፈነው ማሳም ስፋት ትልቅ ነው። የኢኮኖሚ ዋልታ ቡናችንም ለብቻው የያዘው የማሳ ስፋት ክ1/2 ሚሊዮን ሄክታር በላይነው። የጫት ተክሉም ቢሆን ቀላል ግምት የሚሰጠው አልሆነም ። ከፍተኛ የሰው ኃይል የተሰማራበት ይህ የሰብል ልማት ንኡስ ክፍል ምርትና ምርታማነቱ እጅግ በአነስተኛ ደረጃ ለይ ነው። ለምርትና ለምርታማነቱ መጨመር ተገቢው ስፍራ የተሰጣችው የግብአት ( ምርጥ ዘር፤ የመሬት ማዳበሪያ ፤ ጸረ_ተባይና ሌሎች) አጠቃቀሙ በዝቅተኛ ደረጃ ለይ ነው በተለይ በግብርናቸው ዕድገት ላይ የጎላ ለውጥ ካስመዘገቡት አገሮች ተርታ ሲነጻጸር። ዛሬም ብሐራዊ የበቆሎ ምርት አማካዪ ከ25 _30 ኩንታል/ ሄክታር በላይ አልዘለለም። በምርምር ጣቢያዎች፤ በአንዳንድ ሠፋፊ እርሻዎችና በጣት የሚቆጠሩ የገበሬዎች ማሳ ምርቱ ከፍ ያለ እንደሆን ይነገራል። የምንኮራበት የጤፍ ሰብልም በአስራዎቹ የመጀመሪያ ረድፈ እንጂ ከአስራዎች ግማሽ በላይ አልወጣም፤ ማሽላም ከ20 ኩንታል/ ሄክታር በላይ አልዘለለም፤ የባሌና አርሲ የስንዴ ሰብል ቀበቶዎች ብለን የምንጠራችው ስፍራዎችም የሚመዘገበው አማካይ ምርት ከሄክታር ከ20 ኩንታል በቅጡ አልተሻገረም። ይህ ማለት ደግሞ ከዚህ በላይ መጓዝ አይችሉም ማለት እንዳልሆነ አንባቢ ግንዛቤ እንዲያገኙ ይጠየቃሉ። ባጭሩ ሁኔታዎቹ ተሰፋ አስቆራጭ ናቸው ማለት አይደለም። በተቃራኒው መቆም የሚያስችል ችሎታ በገበሬውም በተፈጥሮም አሉ። ዋነኛ የግብርናው ተዋንያኖቹ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው ከእጅ ወደ አፍ የሚያመርቱ በመጨረሻው የድህነት መስመር ላይ የተሰለፉ ግፉአን አምራቾች ናቸው። የይዞታ መጠናቸውም ከድሮው እጅግ በፍጥነት እያሽቆለቆለ መጥቶ ከ 1 ሄክታር በታች መሆኑ ከተገለጸ ሰነባበተ። ቁጥራቸው በዛ ያለ ገበሬዎችም ከኩርማንና ከበሬ ግንባር ያላነሰ መሬት መጠን ይዘው ይማስናሉ። መቼስ የአባ ወራው ሆነ የእማ ወራው ብዛት ስንት እንደሆን በቅጡ አይታወቅም። ከጠቅላዩ ስታትስቲክስ የተለቀቁት መረጃዎች እንደሚጠቁሙትና እነሱንም መሰረት በማድረግ የቤተሰቡን ቁጥር ሳይጨምር ከ14 ሚሊዮን በላይ ሳይገመት አይቀርም። ከእዚህ ውስጥ ምን ያህሉ ወንድ ?ምን ያህሉ ሰቶች? እንደሆኑ የሚታወቅ አይመስልም። በእድሜ ደረጃም ቢሆን፤ በመደበኛ የትምህርት ችሎታቸው ተለይቶ የተቀመጠ መረጃ ለማግኘት ያስቸግራል። ሌላም ልጨምር በየተሰማራበት ንዑስ የሥራ ክፍልም ምን ያህል እጁ እንደሆነ የሚገልጥ ቀጥተኛ መረጃ በቀላሉ ማግኝት አይቻልም። ይሄን ጊዜና ነው የጠቅላይ ስታትስቲክስ መ/ቤት እጅግ አስፈላጊነትና መልካም መግለጫ ሰጭነት ስፍራው። ” ሃሎ ሃሎ ሃሎ ሃሎ ጠቅላይ ቢሮ “ በ1950ዎቹ የተጫወተው ባህታ ገ/ሕይወትም አይደል። መረጃ ዘርዘርና ረቀቅ ተደርጎ ሲቀርብ ለሚተነትነው አካልም ሆነ መረጃውን መሰረት አድርጎ አገልግሎቱን አዘጋጅቶ ለተጠቃሚው በበቂ ለማድረስ ደፋ ቀና ለሚሉት ተቋሞችና ድርጅቶች እጅግ ይጠቅማል፤ ያግዛልም፤ ይረዳልም። ይህ ስራው ሁሉ ከእጅ ወደ አፍ ብቻ የሆነው ገበሬ ለዕለት ተዕለት ለቤተሰቡና ለራሱ ምግብ ፍጆታ የሚውል ምግብ እንጂ የሚያመርተው እንዲህ ተርፎት የከተማውን ነዋሪ ለማጥገብ ተገቢውን ድጋፍ ከሚመለከታቸው ካልተቸረው በስተቀር የዳገትን ያህል አስቸጋሪ ነው። እንግዲህ ሰለ ግብርናው ልማትና ዕድገት ሰናወራና መግለጫ ስንሰጥ በቅድሚያ ስለሱ መሆን አለበት። ችሎታውን ሳንንቅ፤ አቅሙንና ክህሎቱን ሳንለካ ብዙ ጊዜ አላዋቂነቱን እንሰብካለን። ገበሬ አካባቢውን ጠንቅቆ ያውቀዋል። ጥሩ ተመራማሪ ነው። የተመራማሪው ሳይንቲስት ሥራ መሪውና መምህሩ ገበሬ ነው። ከእርሱ ችግሮቹን ጠይቆና ለይቶ ቅደም ተከተል አስይዞም አይደል ፤ ለችግሮቹ መፍትሄ ለማበጀት ምርምሩን በመስክና በቤተ ሙከራ የሚያደርገው። እኛ እናውቅልሃለን የምንለው የምንበልጠው ችሎታችንን በወረቀት ላይ ባማስፈርና ሰነዶችን በማዘጋጀት፤ ለስብሰባ ብቁ እንዲሆኑ በማቅረብ ነው ብል ብዙ ስህተት ላይ አልወድቅም። ታዲያ ሁላችንም ብንሆን ለሃገሪኛው ዕውቀትና ክህሎት ተገቢውን ስፍራ ብንሰጥ ማለፊያ ስራ ነው ለማለት ይቻላል። በተጨማሪም እኒሁ ገበሬዎች እንደ መንግስት ሹመኞች፤ የፖለቲካ አዋቂዎችና ሌሎች አካላቶች ሁሉ ሰዎች መሆናቸውን አንዘንጋ። በቂ ችሎታና ክህሎት ያላቸውና ሥራን እንደ አቅሚቲ በመፍጠር ኑሯቸውን ለማሸነፍና ለማሻሻል የሚፍጨረጨሩና እምቅ ሃይልና በተስፋ የሚኖሪ፤ ከዛሬ ነገ ይሻላል ብለው የሚጓዙ መሆናቸውንም ከግምት ውስጥ እናስገባ። የዚህን ሰብል አብቃይ አነስተኛ ይዞታ ለይ የሚገኙትን ገበሬዎች በመርዳትና በማገዝ በብዛትና በዓይነት ምርት አምርቶ ወደ ገበያ በማውጣትም ለኑሯቸው በቂና አስተማማኝ ገቢ አግኝተው ወደ ተሻለ የኑሮ ደረጃ የሚረማመዱበትን መንገድ አቅጣጫ ማስያዝ አጣዳፊ ተግባር ነው። ይህንን ስንፈጽም ብቻ ሰለ ምርትና ምርታማነት ከፍ ሲልም ስለ ምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የምናወራው።
ከእንሰሳት ሃብታችንም የምናገኘው ጥቅም በበቂ አገልግሎ ት ላይ የተመሰረተ ነው ብሎ አፍን ሞልቶ ለመናገር ያስቸግር ይሆናል። ቢሆንም ይኽው ሃብታችንን እንዳያድግ ቀፍድዶ የያዘንን ችግሮች ለይተን አውቀን ቅደም ተከተል አስይዘን ተገቢውን ድጋፍና እገዛ ለአርቢዎቻችን ካደረግን ተጠቃሚ የማንሆንበት ምክንያት የለም። ከጠቅላይ ስታትስቲክስ ቢሮ የተለቀቀ የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያመለክተው (2005 እ ኢ አ) አገራችን ወደ 50 ሚሊዮን የሚደርሰ የከብቶች፤ ከ20 ሚሊዮን በላይ የበጎች፤ ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍየሎች፤ ወደ 45 ሚሊዮን የሚጠጉ ዶሮዎችና 2 ሚሊዮን ተግማሽ የሚደርስ የንብ ቀፎ የተሰማራባት በለሃብት ነች። ፈረስ፤ አህያ፤ በቅሎንና ግመልን መረጃው ስላላስፈለገኝ አልጠቀስኩትም። ይኽው ዋነኛ የአገራችን የመረጃ ምንጭም ጽ/ቤት ከላይ በተጠቀሰው ዓመት ብቻ የዘመናዊውን የእንሰሳት እርሻዎች ምርት ሳይጨምር ወደ 3 1/3 ቢሊዮ ን ሊትር ወተት፤ 176 ½ ሚሊዮን ሊትር ጥቂት ፈሪ የግመል ወተት፤ ወደ 40 ሚሊዮ ን ኪሎ ግራም የማር ምርት፤ ወደ 94 ½ ሚሊዮን በቁጥር የዕንቁላል ምርት (ትንሽ ነው፤አንድ ዕንቁላል ለአንድ ሰው እንደማለት ነው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከዕንቁላል በሚገኘው ፕሮቲን ዕጥረት ይሰቃያል ማለት ነው።) ከአነስተኛ ይዞታ ካላቸው አርቢዎች አገሪቷ እንደሰበሰበች ገልጿል። የነፍስ ወከፍ ድርሻችንን ለማወቅ ያው እንደተለመደው ማካፈል ነው ለሕዝብ ቁጥር። ትክክለኛ ቁጥር ከሆነ ይናገራል፤ ይገልጻል፤ ዓይን ይከፍታል። የውሸት ከሆነ ደግሞ አይታይም፤ ምኞት ነው። ስለሆነም ኩነቶችን በአግባቡ አይገልጥም፤ አያስረዳምም። ጉም ነው። ጥጥ ነው። ብን ብሎ ይጠፋል።
በዋናነት የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ በፍጥነት ለማሳደግ የሚረዳው መንገድ የገበያና የኢንዲስትሪ መሰረትን ሊያስጥል የሚያስችለን በዘመናዊ ዘዴ እርሻ የሚያርሱና የሚያበቅሉ እንዲሁም እንስሳትን የሚያረቡና ተዋጽዖዎችን በብዛትና በጥራት ለተጠቃሚው በተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ የሚያከፋፍሉ እርሻዎችን ማስፋፋትና ቁጥራቸውንም በየጊዜው እንዲጨምሩ በማድረግ ነው። እነዚህኑ ገበያ መርና የዘመኑትን እርሻዎች ማብዛትና ማስፋፋት በአነስተኛ ይዞታ ላይ የሚገኙትን ሰብል አብቃዮችን ሆነ እንስሳት አርቢዎችን እንዲሁም ንብ አናቢዎችንና ዓሳ አስጋሪዎችን ጨምሮ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፤ በጠቃሚም ሆነ በጎጂ ጎኖች እየታየና ውጤቱም በአግባቡ እየተገመገመ በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ለውጥና ግፊት እንዲያመጣ ዝግጅቱን ከወዲሁ ማጠናቀቁ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። እነዚህ ሰፋፊ እርሻዎችን ዓይነትና የይዞታ መጠናቸውን ለመግለጽ የተደራጀ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። ብዙም ሰለነሱ ማውራትም ያዳግታል። ምን አልባትም ከመንግስት የመሬት መቀራመት ዝብርቅርቅ አሰራር ጋር ያስከተለውን ችግር ተመልክቶም ሊሆን ይቻላል።
ለመሆኑ ከእዚህ አስፈላጊና መሰረታዊ ብለን ከጠራነው ክፍለ ኢኮኖሚ ጀርባ የትኞቹ ተቋሞች ናቸው የሚገኙት? በእኔ ዕይታ በዋናነት ብዬ ከምጠቅሳቸው ልጀምር።
ፓርላማ (ምክር ቤት)
የአገሪቱ የምትደዳርበትን ሕግ፤ ደንብ፤ ሥርዓትን ከሚቀርጸውና ከሚያጸድቀው የሕዝብ ተወካዮችና የፌደራል ምክር ቤት ብንጀምርስ? ይህ በሕዝብ ድምጽ የበላይነት አግኝቻለሁ ብሎ በየአዳራሹ ሰብሰባ በማድረግ የሚያስተላልፈው ውሳኔ መንግስት የሚባለውን ተቋም ፍላጎት ወይስ የአርሶ አደሩን ጥቅም አስጠባቂ ነው? የሕዝብ መሰረታዊውን ፍላጎት ተመልክቶና ተከታትሎ ነውን የተጣለበትን ኅላፊነት የሚወጣውን? ለመሆኑ ስለ አገሪቱ ግብርና ይዞታ በየዓመቱ ስንት ጊዜ እንደ ዋነኛ አጀንዳ ቆጥሮ ተወያይቶበታል? ምንስ ያህል ጠቃሚ ውሳኔዎችን አሳልፏል? በመገናኛ ብዙሃን ዜና እንደምንሰማው የም/ቤቱ አባላት ጎበኙ፤ አደነቁ፤ የሚኒስቴሮችን ረፖርትአዳመጡና ማብራሪያ ሃሳብ ጠየቁ? በቃ ይሄው ነው እርምጃችሁ? አለቀ ደቀቀ! ሕዝብ ስራችሁን የሚገመግመው መንግስት ለማድረግ የፈለገውን በመደገፍ ብቻና በምታወጡት እጅ እንዳልሆነ ስንቶቻችሁ ታውቁት ይሆን? ከተከበሩት የፓርላማው ተወካዮች ተነሳሽነት አሳይተው ከላይ ለጠየቅሁት ጥያቄ ተገቢ መልስ የሚሰጥ ይኖር ይሆን ?
ግብርና ሚኒስቴርና የክልል ግብርና ቢሮዎች
እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር በንጉሥ ምንይልክ አስተዳደር ዘመን በአዋጅ በ1907 ዓም የተቋቋመው የአሁኑ ግብርናና የገጠር ልማት ሚኒስቴር ቀደም ሲል ጀምሮ ለበርካታ ጊዜያት ስሙንም ቀያይሯል። ለመጥቅስም ፦ የእርሻ፤ የእርሻና ሕዝብ ማስፈር፤ የእርሻና የመሬት ይዞታ፤ የእርሻ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት፤ የግብርናና የአካባቢ ጥበቃ ስሞቹ ለአብነት ከሚጠቀሱቱ ዋነኞቹ ናቸው። ቁም ነገሩ ከስሙ ምን አለን ነው የሚባለው። ከፊታውራሪ፤ብላቴና ደጃዝማች ማዕረጎችን ጨምሮ በትምህርታቸው የዶክተር ማዕረግ ያላቸውንና በዕውቀታቸው በልምዳችው፤ በክህሎ ታቸውና በአስተዳደር ችሎታቸው የተከበሩና የተመሰገኑ ትጉህ የሆኑት ጨምሮ የወያኔ/ ኢሕአደግ የጦር አበጋዝ የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሠን በሚንስትር ማዕረግ መርተውታል። አንዳንዶቿም ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሚ ተሹማዋል። ለመጥቀስም፦ ዶ/ር ገረመው ደበሌና አቶ ዘገዬ አስፋው ናቸው። ፎቷቸውም በካዛንቺስ በሚገኘው የሚኒስቴሪ ጽ/ ቤት መግቢያ አዳራሽ ተስቅሏል። ጠቅላላ ቁጥራቸውን ለማወቅ ከጽ/ ቤቱ ማግኘት ይቻላል። አንዳቸውም ግን የአገሪቱን ግብርና ኢኮኖሚ ከፍ አድርገው ጥግ አልያሲያዙትም ወይም አላነሱትም። ነገር ግን በቀድሞዎቹ ሚንስትሮች ጊዜ አገሪቷ እንዲህ እንዳሁኑ የችጋር፤ የረሃብን የድርቅ ምሳሌ ሆናና ለዜጎቻ ማፈሪያ የሆነችበት ጊዜ ከ1966 ዓም ድርቅ በስተቀር የከፋ ጊዜ በታሪኳ አታውቅም። አንድ የጋራ የሆነ ጠባያቸው አላቸው። ይኽውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጥረታቸው አድናቆትን አልቻራቸውም፤ አላጨበጨበላቸውም፤ ዘፈንም ሆነ ግጥም አልዘፈነምም፤ አልገጠምምም። እኔ የማስታውሰው የዶ/ር ገረመውን መንበር በ1975 ዓም የተረከቡት አቶ ተኮላ ደጀኔ ግን በወሰዱት የፈጣን የመዋቅር ማሻሻያና ማስተካከያ እርምጃ በዋናውና በየክፍለ ሃገሩ ዋና ከተሞ ች ለይ ብቻ ተኮልኩሎ የተቀመጠውን የሰው ሃይል ገበሬውን ተጠግቶ አገልግሎቱን እንዲቸረው በማሰብ በተወሰደው እርምጃ ሰለባ የሆኑቱ እንዲህ ባማለት ተቀኝተው ነበር። በተኮላ፤ ጉዴ ፈላ።
በመሠረቱ ይህ የሚኒስቴር መ/ቤት ሲዋቀር በዋናነት ኃላፊነት የተሰጠው የአገሪቱን ግብርና ልማት ለማስፋፋትና ለማሳደግ ሲሆን በተጨማሪም የተገቢ ፖሊሲ ሃሳብ በማመንጨትና ለተግባራዊነቱም አርሶ አደሩን ማዕከል በማድረግ የአኗኗር ዘይቤውን ደረጃ በደረጃ ለመለወጥ ነበር። ግብርና ሚኒስቴር እኔ እስከማውቅው ድረስ የሰራው መዋቅር እራሱኑ መልሶ አላሰራው እያለ ማነቆ ስለሆነበት እንዲሁ ራሱን በማዋቀር ጥሩ የሥራ ጊዜውን ያጠፋ መ/ ቤት ነው። ዋናው ግብርናን ተልዕኮ የሚያስፈጽመው ክፍል ተገፍቶ ድጋፍ ሰጪና የአስተዳደርና የፋይናንስ ክፍሉ አንበሳ የሚሆኑበት ጊዜ ይበዛል። መዋቅሩ በቀላሉ ስራን በመደገፍ የሚያቀላጥፍ ሳይሆን ትከሻቸውንና ኃያልነታቸውን ለማሳየት ብቻ በሚሞክሩ አለቃዎች ተሞልቷል። መዋቅሩም ቢሆን ግዙፍና ቦርቃቄ ፤ በእዝ ሰንሰለት የተንዛዛ ነው። ዛሬ ደግሞ ይህ መዋቅር በክልል፤ በዞንና እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ የተዋቀረ ነው። ጥያቄው ለምን ተዋቀረ ሳይሆን ተልዕኮውን የአቅሙን ያህል ድርሻውን ይወጣል ነው። አንድ የጥበብ ሰው ሠዓሊን ግብርና ሚ/ርን ሳለው ተብሎ ሥራ ቢሰጠው በብሩሹ እጅግ ግብዳ፤ ግዙፍና ቅርጽ የሌለው ሰው አድርጎ ሰርቶ ያስቃችኋል። ግብርና ሚ/ ር በተማረ የሰው ኃይልም ቢሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ቢበልጥ እንጂ አያንስም። ምሁራኖቹን በአግባቡ የተጠቀማባቸውና በችሎታቸው ያሰማራቸው አይመስልም። የግብርና ሚ/ር ካለው ነገር ሁሉ የዘመቻ ስራ ይወዳል። ደራሲ በዐሉ ግርማ በኦሮማይ መጽሃፉ እንደጠቀሰው ለቀይ ሽብር ዘመቻ፤ ለአረንጓዴው ዘመቻ፤ መሃይምነትን ለማጥፋት ዘመቻ፤ የቀይ ኮከብ ጥሪ ዘመቻና ሌሎችም ማለቂያ የሌላቸው ዘመቻዎች አይነት እኔ በማውቀው ግብርና በሽ ነበር። ዛሬም ቢሆን ይህ በሽታ ጠፍቷል ከነጭርሱ ብሎ ለመናገር አይቻልም። የዘመቻ ሥራ የአንዴ ተግባር ስትሆን ተሰተካክላ በሯሷ አትቆምም፤ አትቀጥልምም። ምንአልባት የዘመቻ ሥራ ለሃገር መካላከያ ሠራዊት በፍጥነት ጠላት ሳይደራጅበትና መሬት ሳይዝበት ሊጠቅመው ይችላል። ለሁሉ ነገር ግን ዘመቻን እንደ ዋነኛ የስራ ስልት አድርጎ መቀጠል ሥራን ያበላሻል። የሕግ አስፈጻሚነት ድርሻውን ከኤክስቴንሻ ን አገልግሎቱ መለየት መቻል አለበት። የሚያወጣቸው መረጃዎቹና የሰብል ግምገማ ረፖርቶቹ መሆን ያለባቸው በተጨባጭ በተሰበሰቡና እውነትነት ኖሯቸው በሚያሳምኑና ምክንያት ባላቸው ላይ ተመስርተው እንጂ የባለሙያውን ግምት፤ፍላጎትና ዕውቀት ብቻ መሰረት አድርገው መሆን የለባቸውም። ጥሩ ምርታማነት በተወሰኑ በጣት የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችን ውጤት ብቻ እያጎላን ስለ ተቀረው ገበሬ ጭምር አድርገን የምናወራና ረፖርት የምናደርግ ከሆነ እየሰራን ሳይሆን ምኞታችንን እያጋነንን ነው የምንገልጸው። በተጨማሪም ነፍሳችንን ነው ደስ ያሰኘናት እንጅ በተጨባጭ ያረገገጥነው የለም። ዛሬም ቢሆን የኢትዮጵያ ገበሬ ምርታማነት በዓለም በሚገኙት ገበሬዎች ሁሉ በአብዛኛው ምርቶቹ በዝቅተኛ ደረጃ ለይ ነው። በ1980ዎቹ መጨረሻና 1990ዎቹን ይዞ በዘመቻ መልክ የተጀመረው “ኤክስቴንሺን ፓኬጅም” በአንዳንድ ስፍራዎች ምርትና ምርታማነተን ቢያጎናጽፍም በሌሎች አስፈላጊ ተብለው በተጠቀሱ ስልቶች ስላልታገዘ የተፈለገውን ውጤት ያመጣ አይመስልም። “የኤክስቴንሺን ፓኬጁም” በአንዳንድ ክልሎች፤ ዞኖች፤ ወረዳዎችና በተለያዩ ልማት ጣቢያዎች የፉክክርና የመበላለጥ ስሜት የነገሰበት አሰራር እንዲነግስ መንገድ በመክፈቱ ስራዎቹን ለመከታተል የልማት ሰራተኞቹ በውጥረት እንዲሰሩ አስገድዷቸው እንደነበር በገሃድ የታየ ሃቅ ነበር። እንደ ኢትዮጵያ ሬዲዮ የአንድ ሰሞን የዜና ዘገባ መሰረት ክልሎችም ሆኑ ወረዳዎች ጤናማና አካባቢን ያላገናዘበ ውድድር ውስጥ የገቡ ይመስል ይሄን ያህል ገበሬዎች በዚህ ፓኬጅ ታቀፉ፤ ይሄን ያህል መሬት በዚህ ሰብል ተሸፈን፤ ይሄን ዓይነት ግብዓት በዚህ መጠን ለገበሬው ተሰራጨ፤ ይሄን ያህል ምርት ተሰብሰቦ ይሄን ያህል የሚገመት ብር ገበሬው አገኘ፤ የገበሬው ምርታማነት ጨመረ የሚል የተጋነነ ወሬ መልቀቅ ስራዬ ተብሎ ተይዞም ነበር። አንዳንዴም ታረሰ የሚሉትና ተገኘ ብለው የሚዘግቡት ደግሞ ከሰብሉ የዘር መጠን በብዙ የዘለለ አይመስልም ( አጃይባ ነው)። እነዚህ የተጋነኑና እጅግ ጥቂት ገበሬዎችን የሚገልጹ ረፖርቶች ከፕሮፓጋንዳ ከመንዛት የዘለለ ለድሃው አርሶ አደር አስገኝተውለታል ተብሎ የሚነገር የኑሮ ለውጥም፤ ሸማቹንም ህብረተሰብ ጨምሮ ካለምንም ማጋነን የለም። ይህንንም ስል ስራዎቹ አልተሰሩም፤ አልተለፋም፤ አልተደከመም፤ አልተወጣምና አልተወረደም ለማለትና ለማጣጣል ፈልጌ አይደለም። ስንቱ በየክልሉ፤ በዞን፤ በየወረዳውና በየልማት ጣቢያው የሚገኝ የልማትም ሆነ ከስራው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የሌላችው ሁሉ ባጭር ጊዜ የመስክ ስልጠና በዘመቻው ላይ ተሳትፈዋል። ይህንንም በዓይኔ በብረቱ ያየሁት ነው። ችግሩ ግን ጋዜጠኞች ተብዬዎቹ ስራውን በአፋቸው ላይ በፕሮፓጋንዳ ጨረሱት። የበረከተውና የተለቀቀው ” የዜና ምርት “ እንጂ የእህል ምርት ሆኖ አልተገኘም። በቁጥርና በአኅዝ የገበሬውን ቤት ምርት በምርት አደረጉት። ይገኛል ተብሎ ተገምቶ የተሰጣቸውን ምርት በመሰላቸው ዋጋ እያባዙ ጭቁኑን ገበሬ ብር በብር አደረጉት። አሁንም ደግሜ እናገረዋለሁ እነዚሁ ጋዜጠኞች ከሂሳብ ትምህርት ጥሩ አድርጎ የገባቸው መደመርና ማባዛት ብቻ ነው። አንድ ገበየሁ ውቤ ለአንድ ሺ የዘመኑ ጋዜጠኞች ተብዬዎች ይበቃል። ይህንንም ስናገር ታዲያ የተከበሩና በዘገባቸው የተደነቁና የሕዝብ ይሁንታ የተቸራቸውም የሉም ለማለት ግን አልደፍርምም፤ አይዳዳኝምም። ሁሉም ስራው ያውጣው!
አብረሃም ሊንከልን የተባሉት የተባባሩት አሜሪካ መንግስት የቀድሞ ፕሬዚዳንት የሳቸውን መንግስት የግብርና ዴፓርትመንት “ the people’s department,” ብለው ይጠሩት እንደነበር ከአንድ ” አሜሪካኖችና ግብርናቸው” ከሚል የቆየ መጽሔት ላይ አየሁት። እንግዲህ እንደሳቸው አባባል “ሕዝባዊ “ ማለታቸው አይደል። አዎን! ሕዝብ እየራበው፤ ጠኔ እያዳፋው፤ በምግብ እጥረት በሽታ እያንገላታው እያለ ስለ ሌላ ልማት ብንነግረው ትርጉም የለውም። በቂ ምግብ ካላገኘ የማሰብም፤ የመስራትም፤ የማምረትም፤ የመጀገንም አቅምና ታሪክ የመስራት ችሎታውም ይቀንሳል። ረሃብ ክፉ ነው። ቅስም ይሰብራል፤ ያስከፋል፤ ከሰውነት ጎዳና ያወጣል፤ ያሳፍራል፤ ያሰድዳል፤በመጨረሻም ይገድላል። ሕዝብ የመብላትም ሆነ ጤናውን የመጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው መንግስታዊ ተቋሞች ሁሉ ይህንን ኃላፊነታቸውንና ግዴታቸውን ተገንዝበው ነው ወደ ሥራቸው መግባት የሚችሉት እንጂ እንዲሁ ግድ የለሽ ሆኖ ሥራን መጀመር ያስጠይቃል።
ሌሎቹን ተቋሞችም እንዲሁ በጨረፍታ ወይም በወፍ በረር ቃኘት አድርጎ ማለፍም ተገቢ ነው። እነሆ! በጥቂቱ።
የግብርና ምርምር ተቌሞች
ከተመሰረተ ግማሽ ምዕተ ዓመት እያስቆጠረ ያለው የግብርና ምርምር ተቋም ዛሬ ላይ ራሱን በፈዴራልና በክልል በሚተዳደሩና በአገሪቱ የተለያዩ የግብርና ሥነ ምህዳር ቀጠና በመከፋፈል ምርምሩን እነደሚሰራ ይታወቃል። ዛሬ ቁጥሩ 55 የሚደርስ የምርምር ተቋም፤ ማዕከልና የሙከራ ጣቢያዎች እንዳሉት ይገለጻል። በመሠረቱ ምርምር ሁልጊዜ ከምርት ቀድሞ ይገኛል። ዛሬ የተገኘውን የምርምር ውጤት በአንድ ጀምበር ማሰራጨት አይቻልምም፤ አይታሰብምም። ነገር ግን የምርምሩ አካሄድ መሆን ያለበት በቅደም ተከተል የአገሪቱ ግብርና ዕድገትና ልማት ላይ ማነቆ በሆኑ ችግሮች ላይ ቅድሚያን ያስቀምጣል። መጨመር የምፈልገው ነገር ቢኖር ሌሎች አገሮች ጫፍ የደረሱበትንና የተራቀቁበትን እኛ ግን በሰለጠነ የሰው ኃይል፤ በመሳሪያዎች፤ በበጀት ዕጥረትና በአሰራር ደንብ ባልተዘጋጀንበት የምናስበውን ለጊዜው ትተን፤ ምርምሩ የአካባቢ ገበሬውን ዕውቀትና ክህሎት መሰረት አድርጎ ቢንቀሳቀስ ወደ ተግባር ለመለወጥ ያፈጥናል። ትኩረት ለሃገሪኛ ዕውቀትና ልንሰራ በምንችላቸውና ፈጣን ለውጥ ልናገኝባቸው፤ ወደ ተግባር በቀላሉ በሚመነዘሩት ላይ አትኩሮት ማድረግ ሳይሻል አይቀርም በማለት አስተያዬቴን በዚህ ተቋም ላይ ልቋጭ።
የግብርና ትራንስፎርሜሺን ኤጃንሲ
አዲስ የተቋቋመው የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲም ያዘጋጀውን ሰነድ መሰረት አድሮጎ መንቀሳቀስ ተቻለ መሰረት ለመጣል ደግ እርምጃ ነው። መቼስ በወረቀት የሰፈረና ያማረ ነገር የሃሳብ ነጸነት በሌለበት አገር ወደ ተመኘው ለመጓዝ እክል አያጣውም። ነገር ግን የመንግስት ዶማዎች፤ ቡሾች፤ “ቹሽኪዎች” እየቆፈሩ በአሰራሩ ለይ ማነቆ እንዳይሆኑበት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያሻዋል። “ቹሽኪ” በቡልጋሪኛ ቋንቋ ቃሪያ ማለት ሲሆን ቃሉንም አንዳንድ እድሜ ጠገብና ነገር በምሳሌ ዕውቀታቸው ልክ ጥግ የደረሰባቸው አዋቂዎች ብቻ ይጠቀሙበታል። እንግዲህ በኛም ቢሆን ቃሪያ አንድም ይለበልባል፤ ያቃጥላል፤ ሰው ይፈጃል። ከፍ ሲል ደግሞ እንዲህ ” የበሬ አፍንጫ “ አይነቱ ትልቁ ቃሪያ ደግሞ ውስጡ ባዶ ቦሸቃ ስለሆነ መሰለኝ እኒያ ቡልጋዎቹ ይህንን የሚናገሩቱ። ሰለ ወደፊት ዕጣው በጎ ከመመኘት በስተቀር ለወቀሳ ገና ልጅ “ሙጫ” ነው። እንደ ስሙ ያድርግለትና ለውጥ ለማምጣት ያብቃው። ኤጀንሲውም አሜን እንደሚል ተወዲሁ ይታየናል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞች
የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞችም በዘርፉ የተማረና የሠለጠነ የሰው ኃይል አምራቾችና አቅራቢዎ ች ስለሆኑም ልዩ ትኩረትን ይሻሉ።በትምህርቱ ዝግጅትም የሚያስተምሯቸውን ወጣቶች የኢትዮጵያ ግብርናን የሚገልጽ በኮርስ ደረጃ አዘጋጅተው እዚያው በትምህርት ላይ ሳሉ መተዋወቁ እጅግ አስፈላጊ ነው። ምሩቃኑ ወደ አገልግሎት መስጠት ሲሸጋገሩ በቀላሉ ችግር የመፍታት አቅማቸው ይዳብራል። አለባለዚያ እንደገና አዲስ ተማሪዎችና ሠልጣኞች ይሆናሉ። ትምህርት ቤቶቻችን የድምጻዊያንና የገጣሚያን ጥበ ብ ተሰጥኦ ያላቸውን ማሳያ መድረክ መሆኑ እንዳለ ሆኖ፤ ይህንኑ መሰረት በማድረግም ተማሪዎቻችን የሂሳብ ፤ የሳይንስ፤ የምህንድስና፤ የጤና፤ የምግብ ቴክኒዎሎጂና ሌሎች ተዛማጅ ዕውቀቶች ችሎታ ያላቸው መገኛ (መናኽሪያ ) መሆናቸውን ጭምር ማሳየት መቻል አለብን። ከበቂና ከተሟላ ዝግጅት ጋርም የተማሪውን ብዛትም ሆነ ጥራት ለማስተካከል ለአፍታ ቸል መባል የማይገባው ጉዳይ ነው። ብዛቱን ከጥራቱ ጋር ጎን ለጎን ለማስኬድ የሚያስችል አማራጭም አስቀድሞ እንዳለ መገንዘብ አለብን። በዚህ ጎዳይ ላይ አስተያየት የሚሰጡ ምሁራንን ሃሳብ አለመረጃ ማጣጣል ተገቢም አይደል፤ እንዲያውም ይወገዛል። አስተምራ የልጆቻን ዕውቀት የምታባክን አገር ብትኖር እምዬ ኢትዮጵያ ነች። የሰው ሃይልም በአግባቡ ካልተገለገሉበትም እንደ ሌሎቹ ሃብቶች ይባክናል፤ መቅኖ ያጣል። የወደፊቱ ምሁራኖች ተቀርጸው የሚወጡበት ማዕከልም በመሆኑ፤ ተማሪዎች በፍርሃት ሳይሆን በነጻነት ሃሳባቸውን የሚገልጹበት መድረክ መሆንም ሲችል ጭምር ነው። በአገራችን የመጀመሪያው የእርሻ ትምህርት ተቋም አምቦ ከተማ የሚገኘው የዛን ጊዜው የአምቦ እርሻና ቴክኒክ ትምህርት ቤት እንደሆነ ያውቃሉን? በ1939 ዓም እ ኢ አ የተመሰረተው ይኽው የእርሻ ትምህርት ቤት ፶ ኛውን የወርቅ ኢዬቤልዩ በወርሃ የካቲት 1989 አክብሯል። እኔም በቦታው ተገኝቼአለሁ። ፸፭ኛውን ለማክበር ደግሞ በ2014 ዓም ዕድሜ እንመኛለን። ቪቫ አምቦ እርሻ ተቋም!!! ዛሬ አምቦ ዩኒቨርስቲ።
የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅቶች
ሌላዎቹ ደግሞ የግብርና ምርት ማሳደጊያ አቅራቢዎ ች ናቸው። የመሬት ማዳበሪያና ጸረ ተባዮች ኬሚካሎችን በማቅረብ ይታወቃሉ። በተለይ የመሬት ማዳበሪያ አቅራቢዎቹ በመንግስትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ንብረት ናቸው። በገበሬው ልፋትና ኪሳራ ንግዳቸውን በትርፍ ያጣድፋሉ። ለገበሬው በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባሉ ፤አያቀርቡም መንግሥትስ ገበሬውን በዋጋ ይደጉማል፤ አይደጉምም መረጃው የለኝም። ቀደም ሲል የነበሩት የግል አስመጬዎች ግን ከጨዋታው ውጭ እንደሆኑ የኢትዮጵያ አማልጋሜትድ ኃ/ተ/ማን ብቻ ማስታወሱ ይበቃል። በርካታ የግል ካምፓኒዎችም በጸረ ተባይ አስመዝጋቢነትና የተመዘገቡትን ጸረ ተበዮች ወደ አገር ውስጥ በፍቃድ በማስገባት ያከፋፍላሉ። ገበያ መር ላልሆኑ ገበሬዎች ግን አንዳንዶቹ ዋጋቸው ከገበሬው የመግዛትና የመጠቀም ጥቅም አንጻር ሲታይ በለው የሚያሰኝ አይዶለም ። ለኢትዮጵያ ገበሬዎች የተሻሻሉና የተመረጡ ዘሮችን በማቅረብ በዋናነት የሚታወቀው የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት የሚባለው መንግሥታው ድርጅት ሲሆን በአነስተኛ መጠን ደግሞ የግልም እንዳሉ ይጠቀሳል። ቢሆንም የገበሬውን የምርጥ ዘር ፍላጎት በዓይነትም፤ በብዛትም ለማሟላት አልቻሉም። ዘርን በማምረትና በማከፋፈል እንቅስቃሴ መሳተፍ ለሚፈልጉ ባለ ሃብቶች መስኩ ብዙ ተወዳዳሪ የሌለበት መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ እገልጻለሁኝ። ባልተፈታው የመሬት ጥያቄ ምን ያህል ያስኬዳል? መልስ የለኝም።
የገበያ ሥርዓት ማስፋፊያ ድርጅቶች
የግብርና ምርት የገበያ ሥርዓት ምን ይመስላል የሚለውን ለመመልከት በቂ መረጃ ባይገኝም በገበያው ሥርዓት ገበሬው ላለመጠቀሙ ግን በተዘዋዋሪ መናገር ይቻላል። የቀድሞው የእርሻ ሰብል ገበያ ድርጅት አሰራር ግን በአምራቹ ገበሬ ላይ ተመልሶ እንዳይመጣ ለማስገንዘብ እንወዳለን። እ ሰ ገ ድ ገበሬውን እያስለቀሰና እንደ ኩዳዴ ወር (የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች የሚጾሙት ነው) ድመት (ሰሞነኛ አባባል ነች። ቃሉን ከመገናኛ ብዙሃን እሰጥ እገባ ነው ያገኘሁት) እያከሳ ፤ዓይጥና ዓይጠ መጎጥ ግን እያኮራና እያወፈረ መኖሩን በጀብራሬዎች አንደበት ሲገለጽ እንደነበረው “ ኩራ እንደ እ ሰ ገ ድ ዓይጥ” እንደተባለው ዓይነት ጨዋታ ግን መስማት አንፈልግም። ለገበሬው ምርት በጥናት ላይ የተመሰረተ ዋጋ እንዲከፈለው እንጂ በርካሽ ዋጋ ተገዝቶ መንግስት ለሸማቹ ኅ/ሰብ ዋጋ ለማረጋጋት በሚል ሽፋን ብቻ ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ የሚደረገው ጨዋታ መቆም አለበት።
የመስኖ ልማት ድርጅት
የመስኖ እርሻ የሚሰጠውን ጥቅም ማውራት እንደው ለቀባሪው አረዱት እንዳይሆንብኝ ጥቂት ብቻ ልበል። የአሜሪካውን ካሊፎርኒያ ግብርና ያየ ደግሞ አብዛኞውን የካሊፎርኒያ ደረቅ ሸለቆዎችን እንዴት በቋሚተክሎች ፍራፍሬዎች፤ በአትክልቶች፤ በሩዝ ሰብል፤ በጥጥና በከብቶች መኖ ምርት አልምቶ የዛሬዋን ካሊፎርኒያ የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ የ40 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት አድርጎ በአገሪቱና በዓለም ደረጃ ቀዳሚ ስፍራ እንዳስያዛት መናገር ደግሞ አስፈላጊ ይመስላኛል። ስለኛ ግን መናገር የምፈልገው ነጥብ አለኝ። ይኽውም በመስኖ ልናለማው የሚችል በሚሊዮኖች የሚገመት መሬት እንዳለንና ይህም ስታትስቲክስ ከዘመነ ደርግ ብዙም ፈቀቅ እንዳላለ ነው የምንረዳው። የመስኖ ውሃ ለረዥም ጊዜ አገለግሎት ለይ በአግባቡ እንዲውል ካስፈለገ የመስኖ ሥራ መዋቅር በመስክ ላይ ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን ለውሃው አስተዳደርና ፍትሃዊ አጠቃቀም ከወዲሁ እንዲታሰብበት ለማስገንዘብ ጭምር ነው። የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ወሃ አጠቃቀም ነገን ጭምር ማሰብ አለበት። መንግስት እንዲህ ዓባይን ለመገደብና የኃይል አጠቃቀማችንን ከፍ ለማድረግ የሚሰሩትን ሥራም ጎን ለጎን የተገኘውንም ዕውቀትና ክህሎት ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ዋነኛው የሆኑት የውሃ ምንጫችን ወንዞቻችንን በመጥለፍ በዓመት ሁለቴና ከተቻለ ከዚያም በላይ እንድናመርት ቢያደርጉን ምንኛ በታደልን። አዋሽ፤ ባሮ፤ ጊቤና ግልገል ጊቤ፤ ሶርና ገባ፤ ዴዴሳ፤ ዳቡስ፤ ዋቢ ሸበሌ፤ ሻያ፤ ቦርከና፤ ጀማ፤ ጉደር፤ ያዩ፤ ፎገራ፤ የጨዋቃ፤ ኦሞና በዕውቀት ማነስ ምክንያት ያልጠቀስኳቸውን ሁሉ ጨምሮ በምድራችን በደጃፋችን አይደል የሚፈሱት።በእጃችንና በደጃችን ያለውን የውሃ ሃብትም ከምርጥ የአገሪቱ መሃንዲሶች ጋር መክረው መስኖ በመስኖ ቢያደርጉን ምን ገዶአቸው። ተው ስማኝ አገሬ ማለትስ ይዀው አይደለምን? በ1971ዎቹ የተጀመረው የአረንጓዴው ዘመቻ ያስከተላቸው ጥፋቶች ነገር ግን ምንም ያልተነገረላቸው የውሃ ሃብት አጠቃቀም ችግሮች ነበሩብን። እንዲህ ልግለጸው። የጨፌ መስኮችንና ረግረግ መሬቶችን በማጠንፈፍ ወደ ልማት ማምጣት በሚል አደገኛ ስልት ስንት እርጥብና ረግረግ መስኮችን አድርቀን ዛሬ ወደ ሜዳነት የለወጥናቸው ሥፍራዎች እንዳሉ አንባቢያን እንዲረዱልኝ፤ የልማት አርበኞቻችንም ግንዛቤ እንዲጨብጡልኝ ፈልጌ ነው። እርጥብ መሬቶችና ረግረግማ ሥፍራዎች ለወንዞቻችንና ለጅረቶቻችን መጋቢ አናት መሆናቸናውን እንኳን እኛ ድኩማን የግብርና ባለሙያዎቹ ግንዛቤ ሳንጨብጥ ፤ በአንድ ወቅት የኢሉባቦር ዋና አስተዳዳሪ ተብለው የተሾሙት በልማት ስራቸውና ሕዝብን በልማት ማሰማራት ዋና ሃይል እንደነበር በአመራራቸው የታወቁቱ አቶ አንሙት ክንዴ በአንድ የግብርና ልማት እንቅስቃሴ ሥራ ዓመታዊ ግምገማ ላይ ነበር የኛዎቹ የግብርናው ልማት ስራ መሪዎቹ ረፖርታቸውን ሲያቀርቡ ልክ ግዳይ እንደጣለ አንበሳ ይሄንን ያህል የጨፌና ረግረግ መሬት ወደ ልማት አመጣን እያሉ ለተሰብሳቢው ሲደሰኩሩ አዳምጠው ጉዳዩ ልማት ሳይሆን ለነገው የውሃው ሃብታችን የጥፋት መጀመሪያ መሆኑን በመብለጥ የተናገሩት። የአለም ማያ፤ የአደሌና የላንጌ ሐይቆች፤ አናታቸው የጨፌ መስክ የነበሩት የሐረር ሐማሬሳ ከተማ ከበው ወደ ፈዲስ የሚፈሱት ሁለት ወንዞችና የኢሉአባቦር እርጥብና ረግረግ መሬቶች ዛሬ ደርቀውና አንዳንዶቹ በአደገኛ ሁኔታ ላይ ለመገኘታቸው ለእኔ ዓይነተኛ ምሳሌዎችና አስረጅ ናቸው። እንክብካቤና ጥበቃ ለርጥብና ረግረግንም ሥፍራዎች ጠቃሚና ዓይን ከፋች ስልት ነው።
የገጠር መሬት ሃብት አስተዳደር ተቋም
የኢትዮጵያ መሬት የኢትዮጵያውያን አንጡራ ሃብት በመሆኑ አገልግሎቱም በቅድሚያ ለኢትዮጵያዊያን ገበሬዎች መሆን ይገባዋል። ኢትዮጵያዊያን በመሬታቸው የበቀሉትን ምርቶች ቅድሚያ ተጠቃሚ እንጂ ተመልካች መሆን የለባቸውም። አገራቸው ያፈራውን ምግብ እነርሱ ሳይቀምሱና ሳያጣጥሙ የሌላ አገር ሰዎችን መቀለብ ከሞራል ጥያቄም ባሻገር መብታቸው መሆኑን አስረግጬ መናገር እሻለሁ። ግብርናውን ለማዘመን በሚል ፈሊጥ ለዘመናት በመሬቱ በዘልማድ መንገድ ሲንከባብና ለምነቱን ሲጠብቅ የኖረውን አገሪኛ ሰዎች እያፈናቀልን ለውጭ ኢንቨስተር መሬትን የሚያክል ንብረት እዚህ ግባ በማይባልና የነዋሪውን ጥቅም ባላገናዘበ መልኩ የሚካሄደው የመሬት መቀራመት የኋላ የኋላ የሚጎዳው አገርና ሕዝብ ነው። ጥቂት ባዕዳንን ሃብት በሃብት ላይ እንዲጨምሩ ብቻ በማሰብ፤ድሃን ከሚወዳት መሬቱ ማፈናቀል ሃጢአት ነው። የሕዝቡን ህልውናና ደህንነት ሳይሆን እያስከበርን ያለነው በላዩ ላይ አደጋና ተጨማሪ ስጋት ነው እያስቀመጥን ያለነው። በተጨማሪም በስራ ፈጠራና በቴክኖሎጂ ሽግግር ስም ጥቂቶች እንዲከብሩና የሃብት ደረጃቸውን ከፍ ባማድረግ የሚቀመጡበትን ልክ እንጂ ያሻሻልነው የሕዝቡን የምግብ ዋስትና አይደለም እያረጋገጥን ያምንገኘው። ሃብት ፈጣሪው ሕዝብ ይሄ ስንኩልና ጎዶሎ አሰራር ይጎዳዋል፤ በአገሩም ባይተዋርና የበይ ተመልካች ያደርገዋል። ከልቡም ልማት ተብዬው እንቅስቃሴም አያሳትፈውም። የውጭ ኢንቨስተመንት በሌሎች የስራ መስኮች ተጨማሪ ሃብት ማስገኘት ይቻል ይሆናል። በግብርናው ክፍለ እኮኖሚ ግን በተለይ ከመሬት ጋር በተገናኘ ላይሰራ ይቻላልና ጠንቀቅ ማለቱ ከፖለቲካ ዝርክርክነትና አስቸጋሪነት አንጻር ሲታይ ማለፊያና ይበል የሚያስኝ ሙያ እንዳይደለ መሬቱን እየቸረቸሩት ለሚገኙት የመንግስት ተቋም ሹመኞችና ጥቅመኞች ጉዳዩን በትኩረት እንዲመለከቱት ይሁን ስል እጠይቃለሁ። እስከዛው ግን መስራት በምንችለው አቅማችን ቅድሚያ ለኢትዮጵያዊያኑ ይሁንልን። ለውጭ ባለ ሃብት የከፈትነውን ዕድል ሳናጓድል የአገሪቱን ባለሃብቶች እንዲጠቅም አድርጎ ማሳተፉ ተገቢ ነው።
የሙያ ማኅበሮቻችን
በአገሪቱ በርካታ የሙያ ማኅበሮ ች አሉ። ለመጥቀስም፦ የሰብል ሳይንስ፤ የአዝርዕት ጥበቃ፤ የኢኮኖሚክስ፤ የየደን ልማት፤ የእርሻ መሃንዲሶች፤ የምግብ ጥናት፤የጤና፤ የገበያ ጥናት፤ የሥነ ሕይወት፤ የአፈር ሳይንስ፤ የኮንስትራክሺን፤ የሜካኒካል መሃንዲሶ ችና ሌሎችም። አንዳንዶቹ ዕድሜ ጠገብ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ገና ሙጫ ናቸው። የምግብ ዋስትናቸው ከእድሜያቸው አንጻር ገና አልተሟላም። በምግብ እጦት፤ በጠኔ፤ ችጋርና ድርቅ ምክንያት በእድሜያቸው ማስመዝገብ ያለባቸውን ቁመትም ሆነ ክብደት ገና አልደረሱበትም። ዓመታዊ ጉባኤ ያካሂዳሉ፤ የምርምርም ሆነ የልማት ጥናት ወረቀቶች ይቀርባሉ። ውይይት ይደረግባቸዋል፤ ጥያቄዎች ይቀርባል መልስ ይሰጥባቸዋል። ዕውቀት ይጨምራል፤ ልምድ ይካበትበታል፤ ማን ምን እንደሆንና ምን እንደሚሰራ ይታወቃል። ጥሩ ነው። ዕውቀት ለብቻው ከሆነና ወደ ተግባር በሰንካላ አመራርና ፖሊሲ ካልተተረጎመ እንደምን ይጠቅማል? ምሁራን ስለሙያቸው ዋጋ ትክክለኛውን ካላወሩበት፤ የተሳሳተውን ካላስተካከሉበት፤ ሁሉ ነገር ፖለቲካ ነው ብለው ካመኑበት፤ ዕውቀት ከጋን ውስጥ መብራትነት አልወጣችም ማለት ነው። ትምህርት ለምርምር ለምርትና ለችግር መፍቻነቷ ታዲያ ለመቼ ነው? ምነው ስለ ሙያችን አንደበታችን ተዘግቶ የፓርቲ ፖለቲከኞች ስለ ሙያችን ደግመው ሲያስተምሩን ለመማር ፍቃደኞች ሆንን? በሙያችን ቀድመን መታየት ሲገባን ዛሬም ተማሪዎች ነገም ተማሪዎች ሆነን መታየት ፈለግን? ዕውቀታችንን መሰረት አድርገንማ ሃሳባችንን መግለጽና ማብራራት ካቃተን አካላችንንም ሆነ ኀሊናችንንም ጭምር ምርኮኛ አድርገናል ማለት ነው። እግዚኦ ከዚህስ ይሰውረን! ካለፈ በኋላስ ቢናገሩት ማንን ሊጠቅም? ትንሽ፤ ትንሽ ካሁኑ ጀምሮ እንናገር። ትንሽ ትንሽ መስዋዕት እንሁን። እንግዲህ ሺ ዓመት አይኖር።
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች
ከዚሁ የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ጀርባ ደግም መንግስታዊ ያልሆኑ የሚባሉ ምግባረ ሠናይ ድርጅቶች አሉ። በንጉሱ ጊዜ በቁጥርብዛታቸው በአስራዎቹ ሲገመቱ፤ በደርጉደግሞ በመቶዎቹ ነበሩ። ዛሬ ግን ቁጥራቸው ከ1500 በላይ እንደሆኑ በቅርቡ የኢሳ ቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንግዳ አድርጎ ያቀረባቸው ባለሙያ በቃለ መጠይቅ ወቅት መግለጻቸው ይታወሳል። አብዛኛዎቹ በገጠር የሚገኘውን የሕዝብ ክፍል ለመርዳትና በአኗኗሩ ላይ ለውጥ ለማምጣት የተሰለፉ አጋዥ ኃይሎች ናቸው። በሰብል ልማት፤ በውሃና አፈር አጠባበቅ፤ በአነስተኛ መስኖ አገልግሎት፤ በደን ልማት፤በሰብል ዘርና ሌሎች የተክል መራቢያ አካሎች በማቅረብ፤ በጤናውና በኑሮ ዘዴውና በሌሎችም ለተጠቃሚው አገልግሎ ቶችን በማቅረብ ይታወቃሉ። አገልግሎታቸው ምን ያህል ጠቅሟል የሚለው ውስጥ ለመግባት ሌላ ክትትልና ጥናት ስለሚያስፈልገው እዚያ ውስጥ የምገባበት ችሎታውም አቅሙም የለኝ። እዚሁ ዘንድ ላቁም። ብቻ ከገበሬው ኑሮ ጋር እንደተሰለፉ ለመግለጽና ለመረጃ ያህል ነው ያቀረብኩት።
ታዲያ ይህ ሁሉ የተቋምና የሰው ሃይል ተሰልፎና ተግባሩን ካከናወነ ለምንድነው ከዚህ አ ስከፊና ጎስቋላ ኑሮ እኛ ኢትዮጵያዊያኑ መውጣት ያቃተን? የኔም፤ የናንተም ፤ የሌሎችም የኛን ችግር መስማት የሰለቻቸው የዓለም ህብረተሰብ ክፍሎች ዋነኛ ጥያቄ ነው። አገራችንን ሁላችንም በምንፈልገው ና በወደድነው መልኩ ተርጉመናታል፤ ተረድተናታል። ቁም ነገሩ ግን ያለው መለወጥ (ቃሉን ጠበቅ ተደርጎ ይነበብ) መቻሉ ላይ መሰለኝ።
ለማጠቃለል ሙከራ እናድርግ። ላለፉት 6ትና 7 ዓመቶች መሰረታዊ የሚባሉት የምግብ እህሎችና ውጤቶች ዋጋቸው በፍጥነት ዕለት በዕለት እየናረ አይቀመሴ ደረጃ ለይ ደርሷል። በውጤቱም በሚሊዮን የሚቆጠሩት የኅብረተሰብ ክፍሎች በልቶ ማደር ምኞት ሆኖባቸዋል። የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሰማይ ያህል እርቋቸዋል። ትናትን ማመስገን ከተጀመረ ሰነባብቷል። ኑሮ ተወደደ፤ መብላት አልቻልንም የየዕለት የሕዝብ እሮሮ ነው። ጋሽዬዎችና አባቶች ኪሳቸው ባዶ ነው፤ እትዬና እናቶችም የእጅ ቦርሳቸው ለስሙ ነው ያለው። ደፍሮ የመግዛት አቅማቸው ተሟጧል። ጥያቄው ከገዢዎችችን መልስ ጋር አልተጣጣመም። የጥያቄው መልስ በተጓዳኝ መስመሮች መንገድ ላይ ነው እየተጓዘ የሚሄደው። ተጓዳኝ መስመሮች አይነካክም፤ አይገነኙም። ጉዟቸው አይደረሰበትም፤ የትዬሌሌ ነው። ምግብን በገበያ ላይ ማየት እንጂ ገዝቶ መጠቀም አቅም ቀን በቀን እየተሸረሸረና እየጠፋ ነው።
ምግብ መብት ነው ተብሎ አገሮች ሁሉ መሰረተ ሃሳቡን ከተቀበሉትና ያንንም ለመተግበር በየዓመቱ መሃላና የድርጊት ፕሮግራም ከተነደፈለትም ሰነባብቷል። በርግጥም ሰናስበው ደግሞ መራብና በችጋር ጠኔ ስቃይ ማየትም መብት ነው ብሎ የሚከራከር ጤናማ አእምሮም ያለው ሰው ያለም አይመስለኝም። ያለመራብ መብት እንጂ የመራብ ግዴታ የለብንም። ባጭር አገላለጽ መራብን የሰው ልጆች ሁሉ ሊጠሉትና ልንጠየፈው የሚገባ ውጉዝ ሁነት ነው። ዱሮ እንደምናስበው የ 40 ቀን ዕድልና ዕጣም አይደለም፤ የእግዜርም ቁጣም ሊሆን አይችልም። እንደ ዜጋ ሁሉም ሰዎች ለኑሯቸው የሚበቃ አስፈላጊውን አልሚ ምግቦ ች የያዘ ምግብ ማግኘት አለባቸው። ምግብ መብት ነው ሲባል ደግሞ መንግስት የሚባለው ተቋም በየቤቱ እየዞረ ምግብ ያድል ማለትም አይደለም። ነገር ግን በዋናነት ሰው በፈጠረውም ሆነ በተፈጥሮ አደጋ ችግር ምክንያት በጊዜያው፤ በአጣዳፊና ሥር በሰደደ የምግብ እጦት ችግር ሰለባ የሆኑትን የኅብረተሰብ ክፍሎች አለምንም አድልዎ ሰው በመሆናቸው ብቻ መታደግ እንዳለበት ለመግለጽ ነው። የመንግስት አንዱ ተግበር በግዛቱ ውስጥ የሚኖሩትን የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ደህንነትና ጤናቸውን መጠበቅ ነው። ይህም በመሆኑ መንግስት ለአሰራር ያመቸው ዘንድና ተጠያቂነቱንና ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት የምግብ ዋስትና ሕግና ደንብ አውጥቶ ካለምንም አድልዎ መተግበር አለበት። ለዜጎቹ መራብና መጎሳቆል ሃላፊነቱ የመንግስት እንጂ የሌሎች እንዳልሆነ ጠንቅቆ ማወቅ ያሻዋል። የኢትዮጵያ ምድር አንዱ በልቶና ጠግቦ የሚያደርገውን ያጣበት ሌላኛው ደግሞ ረሃብን እያሰበና እየተጨነቀ የሚኖርባት ምድር መሆኗ ማቆም አለበት። ምግብ አንዱን ወገን ጠቅሞ ሌላውን መጉጃ መሳሪያ መሆን የለበትም። ክቡሩን የሰው ልጅ ማስራብና በጠኔ ማንገላታት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ስለሆነ ” ውጉዝ ከመአርዮስ” መባል ያስፈልገዋል። ወንጃልም ስለሆነ እንደየደረጃው ያስጠይቃል፤ ብያኔም ያሰጣል ፤ ያሳስራል፤ ምህረትም አያሰጥም፤ ከፍም ካለ በሞት ያስቀጣል። ድሃን መርዳት እንጂ በረሃብ መቅጣትም በሃይማኖቱም አስተሳሰብ ቢሆንም ኩነኔ ና ሃጢአት ነው። ከአካል ሞት በኋላም ላለው መንፈሳችን በመንግስተ ሰማያትም አያስገባምም ፤ እንዲያውም በጀሃነም ያስቀጣል። በአንድ አገር፤ ክልልና ቀዬ የሚኖሩ ሕዝቦች እንዲህ ቅጥ ያጣ የተመሰቃቀለ ኑሮ የሚገፉበት ዐብይ ምክንያት የፖለቲካው ምስቅልቅልና በጥቅም የተሳሰረ የኢኮኖሚ መዋቅር በመሆኑ፤ ይህ ችግር ሳይቃለለ የምግብ ዋስትናን ከቃላት ባሻገር ልናገኘው እንደማንችል መገንዘቡ ጠቃሚ ነው። ጠቅለል ባለ አነጋገር የምግብ ዋስትና ችግር ምርት በመጨመር በሚደረገው ሩጫ ብቻ የሚፈታ ሳይሆን ፖለቲካዊም ችግር ጭምር ነው። ፖለቲካ ደግሞ ሰው ሰራሽ ነው። ስለሆነም ፖለቲካዊ መፍትሄ በሰዎቻችን መልካም ፍቃድ ያስፈልገዋል ማለት ነው። የተዝረከረከና የተጨማለቀ፤ የተወሰኑ ቡድኖችን ጥቅም ብቻ ለመጠበቅ የቆመ ፖለቲካ ደግሞ ችግሩን ሊፈታ የሚያስችል ተቋማዊም ሆነ ሰዋዊ አቅምና ችሎታ የለውም፤ አይጠበቅምም።
ሌላው ሳልጠቅሰው ማለፍ የማልፈልገው ነጥብ ደግሞ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄን ጉዳይ ነው። ለገበሬው ያለችው አንድ ትልቁ ሃብት መሬት ብቻ ናት። ገበሬው የመሬቱ ባለቤት ከሆነ ንብረቱን ጥሎ ከተማም አይሰደድም። ማነው ሃብቱን ንብረቱን ጥሎ ንብረት አልባ ለመሆን የሚመኘው። እንደውም ብዙ እንዲያመርት እንደ ማትጊያ ዘዴ ይሆነዋል። የኪራይ ንብረት ሲሆን ግን ያልተሟላ ዕለት ሲመጣ ጥሎት ወደ ከተማ ይሰደዳል። ገበሬም እንደኛው ሰው ነው፤ነገን ከኛ በተሻለ ያስባል ፤ ስኬታማ ኑሮን ለመኖር ይታገላል፤ ይጥራል። በዚህ ጉዳይ ላይ የገበሬው ድምጽና ፍላጎት ይጠና ፤ ይጠየቅ። ገበሬውም ድምጹን የሚያሰማበት የራሱ ብቻ የሆነ ማኅበርም ከቀድሞዎቹ የገበሬ ማኅበር በተለየ ሁኔታ በራሱ አነሻሽነትና ጥያቄ መመስረት አለበት። ከመንግስት ሰዎች የሚጠበቀው ደግሞ የመሬት ይዞታውን ማሻሻል እንጂ ማጃጃል መሆን የለበትም። የበለጠ የገጠሩን ኑሮ ምቹ ካደረግንለት ወደ ከተማ ስደት አይጠበቅም። የከተማ ከንቲባዎቻችን ከተሞቻቸውን ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ እንፈልጋለን የሚሉትን ዲስኩር በገጠሩ ማስፋፋት ይጠበቅብናል። ገበሬን በሽታ እንዳይነካው ጤንነቱን በቅርብ እንጠብቅለት። ገበሬ ሲታመም፤ አገርም ይታመማል። መሬት ጦም ማደር ትጀምራለች። ጦም ያደረ መሬት የሚያበቅለው አረሞችን ነው። ገበሬም አይሙት፤ የሞተ እንደሆን ዕውቀቱንና ክህሎቱንም ጭምር ይዞ ነው የሚሞተው። የዕውቀትና የክህሎት ድርቅ ደግሞ ውጤቱ አስከፊ ነው። ምች ይመታናል፤ አጠውልጎም ያጠፋናል። እግዚዎ! መሃረነ ክርስቶስ! ጸሎቱን ጨርሱ። እኔስ አበቃሁኝ ያሰብኩትን ቢሆንም ባይሆንም፤ ቢያስከፋም ቢያስደስትም ተነፈስኩኝ። አሜን!!!!!
በሌሎች መጣጥፍ ዐርዕስት እስከምንገናኝ ጤና ይስጥልኝ!!!
ሠሎሞን ታምሩ ዓየለ
አንዳንዴ ኑሯችን በራሳችን እንድንቀልድ ያስገድደናል (ዳዊት ከበደ ወየሳ)
አንዳንዴ ኑሯችን በራሳችን እንድንቀልድ ያስገድደናል:: ካለፉት በርካታ አመታት ጀምር በአዲስ አበባ የሚታየውን የመብራት መቆራረጥ የተመለከተ ሰው በሙሉ ያዝናል:: ይህ ሃዘን ወደ ብሶት ቁጣ ተቀይሮ ሰሞኑን በተከታታ ህዝቡ በመብራት ሃይል ላይ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ቁጣውን እየገለጸ ነው:: አንድነት ፓርቲም ይህን አስመልክቶ “የ እሪታ ቀን” ብሎ የሰየመውን የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል:: እኛ ከውጭ ሆነን ነገሮችን ስንመለከታቸው እውነት የማይመስሉ እውነቶችን እያየን መገረማችን አልቀረም:: ይህንን ግርምት በቀልድ ቢጤ ብናዋዛው ብለን ስናስብ ደግሞ የሜትሮሎጂ አየር ትንበያ ታወሰን:: መብራት ሃይል በሜትሮሎጂ ዜና አይነት የሰሞኑን የመብራት መጥፋት እና መጥፋት ዘገባ ምን ብሎ ቢያቀርብልን ይገርመናል:: እስኪ በራሳችን እየሳቅን የመብራት ሃይልን… ሜትሮሎጂያዊ ዜና ከዚህ በታች እናንብብ::
የሰሞኑ የአዲስ አበባ የመብራት ሃይል… ይቅርታ የመጥፋት ሃይል ትንበያ ከዚህ በመቀጠል ይቀርባል:: በሰሜን አዲስ አበባ… ከበላይ ዘለቀ ጎዳና እስከ ፒያሳ፣ ውቤ በርሃ፣ አራዳ፣ ዶሮ ማነቂያ፣ ሰራተኛ ሰፈር፣ ከቸርችል ጎዳና እስከ ቴዎድሮስ አደባባይ ድረስ መጠነኛ የሆነ የመብራት መቆራረጥ ይደርሳል:: ከዚያ ወረድ ብሎ በስቴዲየም እና አካባቢው, መስቀል አደባባይ, ከእስጢፋኖስ እስከ መገናኛ 22 ማዞሪያ እና ኮተቤ ድረስ… እንዲሁም በካዛንቺስ አካባቢ ደብዛዛ እና ፈዛዛማ የመብራት ብርሃናት ይታያሉ::
በቦሌ እና ቦሌ ቡልቡላ መብራት እንደበጋ መብረቅ ብልጭ ድርግም ይላል:: ከላፍቶ እስከ ሳሪስ; ወሎ ሰፈር፣ ጎፋ ማዞሪያ፣ ቄራ፣ ሳር ቤት፣ እንዲሁም ከአየር ጤና እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ነጎድጓዳማ የመብራት መቆራረጥ ያጋጥማል:: በጨርቆስ እና አካባቢ… እንደከዚህ ቀደሙ ደረቅ አየር እና ድፍን ጨለማ ሆኖ ይሰነብታል::
የአዲስ አበባ ምእራባዊ ዞን… ከተክለሃይማኖት ሰፈር ጀምሮ በአብነት አድርጎ እስከ ሰባተኛ እና መርካቶ ድረስ፣ መሳለሚያ፣ ኮልፌ ከዊንጌት እስከ ቡራዩ ድረስ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ ስለማይኖር ከመብራት አደጋ ነጻ ይሆናሉ::
በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን፤ በተለይም የንግዱ ህብረተሰብ ይህንኑ አውቆ አካባቢ በካይ የሆኑ የናፍጣ ጄነሬተሮችን እንዲጠቀም እናሳስባለን:: የባንክ አገልግሎት ሰጪዎች፣ የኮምፒዩተር ቤቶች… መብራት ቢመጣም እንኳን ኔትዎርክ ስለሌለ፤ ጽጉር ቤት እና ምግብ ቤቶችም… መብራት ብንሰጣችሁ ውሃ ስለማይኖር፤ ይህንን ተግዳሮት ግምት ውስጥ በማስገባት ነፋሻማ የሆነውን ቫት እና መብረቃማውን የሽያጭ ታክስ በመክፈል የዜግነት ግዴታችሁን እንድትወጡ ከወዲሁ እናሳስባለን::
በአጠቃላይ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ምሽቱን ጧፋማ፣ ኩራዛማ እና ሻማማ በመሆን ይሰነብታሉ:: ዛሬ ከሳተላይት ያገኘነው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚያሳየው… አዲስ አበባ ከላይ ወደ ታች ስትታይ እንደክሪስማስ ዛፍ ብልጭ ድርግም ትላለች:: በዚህም ምክንያት ምሽት ሲሆን; አዲስ አበባን በአነስተኛ አውሮፕላን የሚጎበኟት ቱሪስቶች ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል:: ከዘርፉ የሚገኘው የገቢ መጠን በመጨመሩ መንግስት ለዚህ አዲስ የስራ መስክ ትኩረት በመስጠት የማበረታቻ ገንዘብ እንደሚመድብ አስታውቋል:: ለስራውም መሳካት… መብራት ሃይል የሰፈር መብራቶቹን በፈረቃ በማብራት እና በማጥፋት; ምሽቱን “በብልጭ ድርግም” የሚያደምቀው መሆኑን በደስታ ገልጿል::
ከቶ ዬት ይሆን ዬፍላጎታችን ሴሉ ያለው (ከሥርጉተ ሥላሴ)
ከሥርጉተ ሥላሴ 23.03.2014 ( ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
በእኔ ውስጥ እኔ ነኝ ያለሁት። እማስበውም አምጽፈወም በነፃ ዕይታ መንፈሴን ቃልቲ ወይንም ቂልንጦ ሳልክ ውስጤ የሚለኝን በድፍረትና በልቡ ሙሉነት ነው። ስለዚህ እኔ „እኔን“ ስገልጽ ተሸማቅቄ ወይንም ምን ይሉኝ ብዬ ወይንም አዩኝ አላዩኝ ብዬ ተሸፋፍኜ አይደለም። በዬትኛውም ዘመንና ጊዜ እኔ „እኔን“ ተውሶት ወይንም ተበድሮት አያውቅም። በጣም ብዙ ሰዎች በተለያዬ አጋጣሚ ከልጅነት እስከ እውቀት ሥርጉተን ያውቋታል። ጊዜና ሁኔታ ሲፈቅድም ቆመው ይመሰክራሉ። ባነብም ባዳምጥም እምኖረው ግን እራሴን ሆኜ ነው – በጣም በእርግጠኝነት። ተዳብሎ የሚኖር ፍላጎት ሆነ ጭሰኛ ወይንም ሞፈር ዘመት ስሜቴ ያዘለ ወይንም የሙጥኝ ብሎ ጥገኝነት የጠዬቀ ፍላጎት ኖሮኝ አያውቅም። ለዚህም በሙሉ መንፈስ እራሴን ሆኜ እንድኖር መንፈሴን በማያቋርጥ የራስ መተማማን መስኖ አልምተው ያሳደጉኝን ወላጆቼንና እጅግ የሚናፍቀኝን ማህበረሰቤን አመሰግናለሁ።
ስለዚህም እኔ ለምሰጠው አስተያዬት እኔን የወከለ ስለሆነ ጊዜ ወስዳደችሁ ለምታነቡት ወገኖቼ እንዲሁም፤ አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ አስተያዬት ለምትሰነዝሩት ወገኖቼ እኩል አክብሮት አለኝ። እማርበታለሁም። አመሰግናችኋላሁ። አለፍ ብላችሁ መሄድ ካሰኛችሁም ሥርጉተ ጠጥታው ያደገችው ፈተና ሆነ ተመክሮ ሁሉንም ለማስተናገድ ስለመቻሏ መለኪያዋ ስለሚሆን አዝናንታ እንደምታስተናግደው ተሰፋ አላት – እራሷ።
ትናንት ነበር ያነበብኩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ፓርቲያቸውን ወክለው ወደ አሜሪካ የተዘጋጁበት ጉዞ እንደ ታገዱ ከዘሃበሻ። ከዚህ የባሰ ፈተና ብጠብቅም አዘንኩኝ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13729
እጅግ ያሳዘነኝ ደግሞ ከአንባብያን የተጻፉት አስተያዬቶች ናቸው። ለመጻፍም ያነሳሳኝ ይሄው ነው። አንዱ ወያኔ ያዘጋጀው ነው አትመኑት የሰማያዊ ሊቀመንበር እንደ ልደቱ ነው ይላል። ሁለተኛው ደግሞ ወርዶ ታች ሰፈር ይቆጥራል። ወያኔ ከወሰደው የእገዳ እርምጃ ሁለቱም አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ አስተያዬቶች አሳዘኑኝ። ሰው እንዴት እራሱን ማሸነፍ ይሳነዋል። እኛ እንዲህ መንደር ካሰኘን፤ ስለምን ወያኔን እንነቅሳለን። ለሁላችንም መዳኛችን ኢትዮጵያዊነታችን ነው። ማናቸውም ሰው ሲያጠፋም ሆነ በጉ ሲሰራ መመዘን ያለበትም በዜግነቱ መሆን አለበት እንጂ ጎጡ?! ክብርና ግርማ፤ ፍቅርና ትህትና፤ ናፍቆትና መሆን ያሉት ከሚስጥሩ እንብርት ከኢትዮጵያዊነት ላይ ነው። የትናንት ጀግኖቻችን ናሙናነት ወተታቸው የታለበው፤ የሞቱት የተሰዉት ለሚስጥርነታቸው ነው …. ጠበል ቢጤ በዬጓዳው ሳያስፈልግ አይቀርም …. እኔ እማውቀው የሰማያዊ ሊቀመንበር ኢ/ ይልቃል ጌትነት ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ነው። ከዚህ ባለፈ መንፈሳችን ተቋማቱ ላይ እናሳርፍ፤ ፍቅራችንም እምነታችንም ከጋራው አመራር ላይ …. ከፓርቲው ንጥር መርህ፤ ይህ ከሆነ በስበብ አስባቡ በሚፈጠሩ ስንጥሮች አንታወክም ….
ሌላው ያነበብኩት አስተያዬት ብቃትን ማዬት የሚናፍቀን እንዳለን ሁሉ፤ ዓይንህ ላፈር የምንል መኖራችን ፍላጎታችን ጋር ምን ያህል እዬተላለፍን እንደመንባዝን ሰፊ ስዕል ነበር። ሰማያዊ ሲመሰረት ጀምሮ እኔ ከልብ ሆኜ እከታተለዋለሁ። አሁን ባላቤት ያላቸው ይመስለኛል ውጪ ሀገር። የሎቢ ተግባር የሚሰራላቸው። ቀደም ባለው ጊዜ ባልነበራቸው ሰዓት የሚያቅዷቸው፤ ሃላፊነት ወስደው የሚወስዷቸው ፈጣንና ደፋር እርምጃዎችና ውጤቶቻቸው፤ ፈተናዎቻቸውና ፈተናውን ተከትለው የሚያሰዮዋቸው ጥንካሬ ሁሉ ይደንቁኝ ስለነበረ ከረንት ላይ አንብቤ አስተያዬት ከሥር በጣም በትጋት እጽፍበትም ነበር።
ጉልህ ድፍረታቸውን ያዬሁበት የመጀመሪያው እርምጃቸው የሙሶሎኒን ግፍ ሊዘከር አይገባውም በሚል መንግሥት ነኝ የሚለው አካል ተቀምጦ እነሱ ነበሩ ቀዳሚውን የመከራውን ገፈት ፉት ያሏት፤ ከዛም በኋላ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ግልጽ ያለ አቋም መወሰዳቸው ብቻ ሳይሆን ተግባር ላይ መገኘታቸው አበረታች ነው – ለእኔ። በዛ ላዩ ታች እሳት በሚጋረፍ ቃጠሏማ ወጀብ ሆነው ዕለታዊ ቋያውን ተቀብለው በቅንነትና በሃቀኝነት እዬተንገረገቡ መገኘታቸው ወያኔ ሊያሰኛቸው ከቻለ እውርነት ነው። ሰማያዊ እንደ ተቋም ጠንካራ ራዕይና ጠንካራ ፍላጎት ይዞ በድፍረት እዬተንቀሳቀሳ ያለ ቀንበጥ ፓርቲ ነው – ለእኔ። ነገ ምን ይሆናል? ሥርጉተ ጠንቋይ አትቀልብም።
አሁን ባለው ሁኔታ ግን መሰረት የያዘ የተግባር ትልማና ክንውን እያዬሁ ነው። አንጋፋ የሚባሉት አብሶ ለህሊና መሰናዶ ቁብ ሲሰጡት አይታዩም። እነሱ ግን ህሊናን ከማሰናዳት ጀምሮ ያለው መንፈስ ጠንካራ ነው። አጋዥ ተቋማትን ወይንም ክንፎችን አጠናክሮ ማውጣት ብቻ ሳይሆን እንደዬባህሪያቸው „የእንቢታን“ተግባር መሸለማቸው በራሱ የብርታት መለኪያ ነው። አጋጣሚዎች ሳይበክኑ አቅምን ከሥር በመገንባት እረገድ ጅምሩም ፍሬ አዘል ነው። በአጭር ጊዜ ዘለግ ያለ ተግባርና ተመክሮውም ጠቋሚ ተስፋ አለው። ይህ ውጤታማ የግልና የቲም ተግባር ተናጠላዊ ፍርጃ የሚያሰጥም አይደለም። አመራሩ መደማመጥ፤ መከባበር መተማመን አስከቻለ ድረስ አውዱ ሰላም ነው፤ በሰላም መስመር ደግሞ ትርፍ አለ ….
ከኢንጂነር ይልቃል ጌትነት አንድ ሥንኝ ልዋስና „የድርሻ ልውውጡ“ ሰርቷል የሚያሰኘው ቁምነገር ያለውም ከዚህ ላይ ነው። ወጣት ለመኖር የሚጓጓ ቢሆንም ከፍላጎቱ በታች ባለው እንጂ በላይ ባላው ነገር አይደለም። እውነት ለመናገር ወጣቶች ለግል ኑሯቸው ስስታሞች አይደሉም። እንዲያውም የወያኔ መሰሪነት ዶክተሪን ለግል መኖር ነበር። ግን ተፈጥሯቸው አልፈቀደላቸወውምና በዬአጋጣሚውም የምናዬው የወያኔ ፍላጎት አብሶ ኢትዮጵያን በሚመለከት ተዘቅዝቆ ሲንጠለጠል ነው። ስለሆነም በዚህ ጠቀራማ ዘመን ብሄርና ብሄረሰብ እዬተባሉ ያደጉ የትናንት ለጋዎች በንጹህ መንፈስ ስለ አንድ ህዝብና አንድ ሀገር ፊት ለፊት ወጥተው፤ በባንዳነት ሀገርን በመበተን ላይ ያለውን ወያኔ እዬተፋለሙ መገኘታቸው ሊያስመሰግናቸውና እግዚአብሄር ይስጣችሁ ሊያሰኛቸው ይገባል። ይህንን በማደረጋቸውም በዚህ ዙሪያ ቅሬታ ያላችሁ ወገኖች ድምጻችሁን አትስጡን ሲሉም አዳምጫቸዋለሁ። በጣም ደፋር እርምጃ ነው። ስለምን ትግላቸው ትውልድና ታሪክን፤ ሀገርን ከማዳን ላይ በጽኑ የተገነባ ስለሆነ ነው እንጂ በነፍስ ወከፍ የነበራቸው ቦታ ሆነ ኑሮ በቂ ነበር …. ማለት ይቻላል።
ግን አኛ አልታደለንም፤ የሚሻል፣ የሚበልጥ፣ የተወጣላት ነገር የማዬት። እንዲያውም የነጻነት ትግሉ ቤተሰቦች ሆነን አሁን በተገኘው እውቅናና ወያኔ በወሰደው የጉዞ እገዳ እርምጃ መስጥረን ደስ ሚለን የምንኖርም እንኖራለን። የእኛ ጀግናችን አደባባይ ወጥቶ እልፎችን አሰልፎ ወደ ፊት ሲገሰግስና ትርፍን ሲዝቅ ሳይሆን፤ ይልቁንም በጠላት እጅ ገብቶ ሲታሰር፤ ሲታፍን በጠራራ ጸሃይ በባሩድ ሲነድ፤ ወይ እንደ የኔሰው ገብሬ በቤንዚን እራሱን አርከፍክፎ አቃጥሎ አምድ ሲሆን፤ ወይን ሀገር ጥሎ ተሰዶ ፊት ለፊት መጋፈጡን ሸሽቶ ለዕለት ኑሮው ሲያድር ብቻ ነው። በቃ ያልተሰረ ታታሪ፣ ያልተፈነ ባተሌ ስለነገ የሚፈለገውን ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት እወስዳለሁ ብሎ ለሚገፋጥ ከወያኔ በበለጠ እኛው ስናሸው ሲሰኘንም ወያኔ በማለት ወስደን ከጠላት ጋር ስንለጥፈው – አለመታዳል።
ከዚህ በተጨማሪ እኔ በግሌ „ሰማያዊ ጊዜ ገና ነው ተገጥሜ ለመሰፋት እኔ ለጋ ነኝ። መሬት ረግጬ እራሴን ችዬ ለመንቀሳቀስ ጊዜ እሻለሁ፤ ወይንም እራሴን ችዬ እድሌን እሞክራለሁ“ ማለቱን እራሱ ልናከብርለት ይገባል። ከእንጨትም፣ ከተራራም፣ ከቀንም፣ ከቤትም፣ ከሰውም፣ ከመሬም ዕድል አለ። እንታገልለታለን የምንለው ነፃነት እኮ ይህው ነው። ልንጫነው በፍጹም አይገባም። በተገኘው አጋጣሚም ካላፍላጎቱ በተጽዕኖ አቅጣጫውን ልናስተው አይገባም። በመንገዱ ላይ ጋሬጣ ልንሆንበት አይገባም፤ እንደ ገራራ የማይገራ ኢጎም አድረገን ልናዬው አይገባም፤ ጉዙውን ሆነ ፍላጎቱን በፖዘቲብ ልናይለት ይገባል። ካለፉት ስህተቶች ተምሮ፣ በአገኘው ተመክሮ ተነስቶ ለትውልዱ አዲስ መንፈስ ምቹ የሚሆን ሽግሽግ ማደረጉ ራሱ ለእኔ በግሌ በጣም በጎ ነው። በራስ መንገድ፤ በራስ መርህ፤ በራስ ቴስት መንፈስን ለመምራት መወስንና መቁረጥ አንድ ጥበብ ነው። ወቅትንና ጊዜን፤ ፍላጎትንና ተስፋን ማድመጥ መቻል የአቅም ሥነ – ሥርዓት ነው።
በአንፃሩ ተናጠላዊ ትግሉ ጎድቶናል፤ ፍላጎታችን አጓቷል፤ ራዕያችን አርቋዋል፤ ተስፋችን አጫጭቷል፤ ለጠላት ኢላማ የቅርብ ተጠቂ አድርጎናል፤ ጉልበታችን – ተመክሯችን – መክሊታችን ብናስተጋብረው የበለጠ ህዝብ በማሰለፍ አቅምና ችሎታ ይኖረናል፤ በአንድ ላይ ሆነን አብረን እንሰራለን፤ ተዋህደን ወይ ተቀናጅተን የሚሉም ከተገኙ ወሸኔ ነው። የእነሱንም ነፃነት ልናከብርላቸው ልናዳምጣች ይገባል። የሚመቻቸውን የሚያውቁት እነሱ መሬት ላይ ያሉት እንጂ እኛ አይደለንም።
በተረፈ ዬፓርቲዎች ፉክክር ለእኔ በጎ ነው። ለሚደግፉት ፓርቲ የበለጠውን ጊዜ መስጠት ወይንም ፕሮሞት የሚያደርጓቸውም ኃይሎች የሚወስዱት እርምጃ በጎ ነው። ችግሩ ያለው ነፃነት ለራሳችን የምንፈልገውን ያህል ከሌላው ላይ ሲደርስ ወይንም ለሌላው ለመስጠት ንፉጎች መሆናችን ነው። እንደ እኔ አንዱ በአቅደው ላይ ነፃነቱን ጠብቆለት ሌላው በመሳተፍ በማገዝ፤ ሌላው በአቀደው ላይ ሌለኛው ኃላፊነቱን ወስዶ በመጋራት ፍላጎታችን ዕውን ማደረግ ይገባል እንጂ አንዱ በሌላው ላይ በመንፈስ በማማጽ፤ ወይንም ልብን በማሸፈት በጠላት ላይ የሚገኝ ድል ምንም የለም። አብሶ ይህን ቆርጠን ከምንቀጥለው የወያኔ ተለጣፊ የምንለውን ስያሜ ነገር በእጅጉ ልንቆጠብበት ይገባል። የተያዘ የተረዘዘውን ሁሉ እንዲህ እያደረግን ለምለምን ማደረቅ ምን ሊባል እንደሚችል ሂዱበት ….
ይከወን። ግን እኛ የእውነት ወያኔ እንዲወድቅ እንፈልጋለን? የትም ሳንሄድ ወደ ጎረቤትም እስኪ እራሳችን እንፈትሸው? ምኑ ይሆን የሚያስደስተን? ምኑ ይሆን የሚያስከፋን? ከቶ የት ላይ ይሆን የፍላጎታችን ሴል ያለው? ለነበረን ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ – የኔዎቹ – ክብረቶቼ ቸር ሰንብቱልኝ።
ፍላጎቴን ሳውቅ ቀን እኔ በእኔ ውሰጥ አለመሽሎኩን አረጋግጣለሁ።
ፈተናን ከመፈጠሩ በፊት አሸንፎ የተፈጠረ ኢትዮጵያዊነት።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።