Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ከዛሬ ጀመሮ የዞን ዘጠኝ ኩሩ አባል መሆኔን አረጋግጣለሁ –ግርማ ካሳ

$
0
0

zone9-e1398747809895

ርዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ …….እያልን ስሞችን መዘርዘር እንችላለን። በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ  ዜጎች ሕገ ወጥና ኢፍትሃዊ  በሆነ መንገድ የታሰሩ ወገኖቻችን፣  ከእሥር እንዲፈቱ ስንጠብቅ ፣ ሌሎች እየተጨመሩ ነው። ከቃሊት ዉጭ ሆነው እነ ርዪትን ሲጎበኙ የነበሩ አሁን እነ ርዮት አለሙን እየተቀላቀሉ ነው።

 

ዞን ዘጠኞች ፣ እነ ጋዜጠኛ ተስፋአለም፣ የሚጽፉትን ፣ የሚጦምሩትን እኛም አንብበነዋል። በድብቅና በሚስጠር አልነበረም ሃሳባቸውን ሲያካፍሉን የነበሩት። የኛ አካል ናቸው። እነማን እንደሆኑ እናውቃቸዋለን። የታሰሩት ወንጀል ስለፈጸሙ አይደለም። ሕግን ስለጣሱ አይደለም። ወንጀላቸው አገራቸውን መዉደዳቸው ነው። ወንጀላቸው ለፍትህ መቆማቸው ነው። ወንጀላቸው ዶር መራራ ጉዲና እንዳሉት፣  ከጫካ የወጡ ግን ጫካ ከነርሱ ያልወጣ፣  ከበስተጀርባ ሆነው እነ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እያዘዙ የሚፈልጡና የሚቆርጡ፣ ከሕግ በላይ የሁኑና ለሕግ ደንታ የሌላቸው፣  ጥቂቶች እንዲጽፉ የማይፈልጉት ስለጻፉ ነው። «እነዚህን የሳይበር ስፔስ አርበኞች ልክ ብናገባቸው፣  ሌሎችም ፈርተው አርፈው ይቀመጣሉ»  የሚል የተሳሳተና እንጭጭ አስተሳሰብ ስላላቸው ነው።

 

እንግዲህ ጥያቄዉ «የኛ ምላሽ ምንድነ ነው የሚሆነው ? »  የሚለው ነዉ። የአለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በግለሰብ ደረጃ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተሰማንን ሐዘንና ንዴት ገልጸናል። ተገቢም ነው።

 

ነገር ግን ከዚያ አልፈን መሄድ መቻል ያለብን ይመስለኛል። አገዛዙ ዋና ግቡ እኛን ተስፋ ማስቆረጥ ነው።  ገዛ ተጋሩ በሚባል የፓልቶክ ክፍል አንዲት የአገዛዙ ካድሬ ትሁን ደጋፊ፣  አገዛዙ ላይ ችግር ያለንን  ሰዎች  »ፓፕ ኮርኖች» (ፈንድሻውች) ነበር ያለችን። ለጊዜ ቡፍ ብለን ጸጥ የምንል !!!!!!

 

እንግዲህ ምርጫዉ የኛ ነው። እኛ ሚሊዮኖች ነን። እነርሱ ጥቂቶች ናቸው። እኛ ፍቅርን ፣ ሰላምን፣ እኩልነትን አንድነት እንፈልጋለን። እነርሱ ዘረኝነትን፣ ጭካኔን፣ ግፍን፣ መከፋፈልን ይሰብካሉ። እኛ አገራችን በፍቅር እንገባ እንላለን። እነርሱ ግን «እኛ ስልጣን ላይ እንቅይ እንጂ አገር ብትፈልግ ትፈራርስ» ይላሉ። እኛ የዘር፣ የሃይማኖት የጾታ፣ የእድሜ ልዩነት ሳይኖር እያንዳንዱን ዜጋ፣ አዎ ከጠ/ሚኒስተሩ ጀመሮ እስከ ሊስትሮዉ ፣ በስብእናዉና በኢትዮጵያዊነቱ የከበረ ነው እንላለን። እነርሱን ግን« ሁሉንም  አዋቂዎች፣ ፖሊሱም ፣አቃቢ ሕጉም፣ ዳኛዉም፣ ሕግ አውጭዉም፣ ሕግ አስፈጻሚዉም፣ ኢኮኖሚስቱም፣ ኢንጂነሩም እኛ ብቻ ነን። ሌላዉ ከጫማችን በታች ተረግጦ መቀመጥ ነው ያለበት» ይላሉ።

 

እንግዲህ ምርጫው የኛ ነው። እንደ እንስሳ አንገታችን ላይ ማነቆ ታስሮ፣  ጥቂቶች እየጎተቱን እና እንደፈለገ እየተጫወቱበን መኖር፣ ወይም ነጻነታችንን ማወጅ። ዝም ብለን ለጊዜው ብቻ የምንጮህ ፓፕኮርኖች መሆን ወይም አለትን የሚሰባብር ዳይናሚት መሆን። እነርሱ እንደሚፈልጉትና እንደሚመኙት፣ ዝምታን መርጠን፣ አፋችን ዘግተን መቀመጥ፣ ወይም ዳግማዊ ዞን ዘጠኖች በመሆን  የዞን ዘጠኝ  አባላት ቁጥርን ከስድስት፣  ወደ 6 ፣ ስድሳ ሚሊዮን ማሳደግ።  የናንተን አላውቅም እኔ ግን፣ ከዛሬ ጀመሮ የዞን ዘጠኝ ኩሩ አባል መሆኔን አረጋግጣለሁ።

 

መርዛማ እባብ ከመንደፍ ዉጭ፣  ሌላ ነገር አያውቅም። እነርሱም ማሰር እንጂ መፍታት አያውቁም። ዜጎችን ማሸበር እንጂ ማረጋጋት አያውቁም። ኢትዮጵያዉያንን ማዋረድ እንጂ ማክበር አያውቁም። ይህ ለሃያ አመታት የዘለቀ ግፍ አንድ ቦታ ላይ መቆም አለበት። አሁን መቆም አለበት። ሊያስቆሙት የሚችሉት ደግሞ እነ ጆን ኬሪ አይደሉም። እኛ ብቻ ነን።

 

ሚያዚያ 26 (ሜይ 3 ቀን) በአንድነት ፓርቲ የተዘጋጀ የእሪታ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ከብዙ ግፊትና ትግል በኋላ አስተዳደሩ ለሰልፉ እውቅና ሰጧል። ሰልፉ ሰላማዊና ሕጋዊ ሰልፍ ነው። የምንፈራበትም፣  የምንሸሽበት ምንም ምክንያት የለም። ሰልፍ የምንወጣዉ ለፖለቲከኞች ወይንም ለአንድ ፓርቲ ፣ ወይንም ለሌሎች አይደለም። ሰልፍ የምንወጣው ለራሳችን ስንል ነው። «በአዲስ አበባ እድገት አለ። ዴሞክራሲ አለ። ስርዓቱ መቀጠል አለበት። ኢሕአዴ ጥሩ እያደረገ ነው። የታሰሩትም መታሰራቸው ተገቢ ነው» የሚሉ እነ ሚሚ ስብሀቱ ሰልፍ ባይወጡ ብዙ አያስገርምም። ግን በልባችን ለውጥ እየፈለግን፣ መሰረታዊ የመብትና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች እያሉን፣ ዝምታን ከመረጥን ግን፣ ይሄን የሚያዚያ 26ቱን ሰልፍ እንደ አንድ መድረክ ተጠቅመን ድምጻችንን ማሰማት ካቃተን ግን፣  ታዲያ እንዴት እንዘልቀዋለን ?

 

እንግዲህ  ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁ እላለሁ። እንዉጣ። ድምጻችንን እናሰማ። መብታችንን እናስከበር። የሕዝብ ጉልበትና አቅም ምን ማለት እንደሆነ እናሳይ። ለታሰሩ አጋርነታችንን እንግለጽ። ስድስት ዞን ዘጠኖች ቢታሰሩ ሚሊዮኖች እንደተወለዱ  እናስመስክር።

 

እመኑኝ የሕዝብን ጉልበት ሊቋቋም የሚችል ማንም ኃይል የለም !!!!!!


በሰፊው የኦሮሞ ህዝብ እና ልጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ በአጽንኦት እናወግዛለን!!!

$
0
0

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመሬት ስሪት ላይ ግልፅ አቋም እና ፖሊሲ ያለው ፓርቲ መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በዚህም መሰረት መሬት በሦስት መሰረታዊ አውድ ላይ እንዲመሰረት ይህም ማለት በወል፣ በመንግስትና በግል ይዞታነት እንዲከበር አቋም ይዞ ይታገላል፡፡ ነገር ግን ከወልና ከመንግስት ውክልና ውጪ ያሉት ይዞታዎች በግል ይዞታነት እንዲከበሩ አቋም ይዞ ይታገላል፡፡ ኢህአዴግ የገጠሩ መሬት የግል ከሆነ አርሶ አደሩ መሬቱን እየሸጠ ወደ ከተማ ይፈልሳል ብሎ ያምናል፡፡ ከምንም የተነሳ ስጋት ነው ባይባልም አንኳ ኢትዮጵያውያን ከመሬት ጋር ያለንን ስነልቡናዊ፣ ማህበራዊና ሁለንተናዊ መስተጋብርን ያላገናዘበና የተጋነነ ስጋት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከመሬት ጋር የተለየ ቁርኚት እንዳላቸሰው ለማወቅ ሞታቸውን ሲያስቡ እንኳ “የሀገሬ አፈር ይብላኝ” ሲሉ መመኘታቸው በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ኢህአዴጎቹም በቀድሞ ስርዓት ሲተገበር የታገሉትን የመጨቆኛ መሳሪያ ለራሳቸው ሲሆን ተጠቀሙበት፡፡ የሆኖ ሆኖ ይህ የኢህአዴግ ስጋት እውነት ነው እንኳ ቢባል ኢህአዴግ የከተማውን መሬትስ የግል ይዞታ ያላረገው ከተሜው ወዴት እንዳይሰደድ ነው?
2_n
ዋናው የገዥው ፓርቲ ፍላጎት መሬትን በጁ በማድረግ የዜጎችን ነፃነት በዚያኑ ያክል ለመሸበብ ነው፡፡  አርሶ አደሩም ሆነ የከተማው ህዝብ መሬት የኔ ነው ብሎ ካመነ ለኢህአዴግ ጫና ስለማያጎበድድ መያዣ ለማድረግ ነው፡፡ የህዝቡ የመሬት ባለቤትነት ቢረጋገጥ በመንግስትና ለኢንቨስትመንት በሚፈለጉ መሬቶች ላይ የመደራደር አቅሙ እጅግ ከፍ ይላል፡፡ መሬቱን በመልቀቁ በሚሰጠው ካሳ (ዋጋም) በቂ የኑሮ ዘዬ ሽግግር የሚያገርግበት አጋጣሚ ይፈጥራል፡፡ ይህ ሊሆን አልቻለም፡፡ በ02/ 08/ 06 ዓ.ም ቡራዩ አካባቢ በተደረገ የመሬት የሊዝ ጨረታ ለተነሺው አርሶ አደር በካሬ 10 ብር የታሰበለት መሬት በጨረታ በካሬ 17 ሺህ ብር መሸጡን ፓርቲያችን ያሰባሰበው ማስረጃ ያሳያል፡፡ በ10 ብር የታሰበለት አርሶ አደር የሚሰደደው በዚህ መልኩ መንግስት ሲቀማው እንጂ የመሬቱ ባለቤት ሆኖና ተደራድሮ በሚሸጥበት ወቅት አልነበረም፡፡

መሬት የምርጫ ድምፅ መያዣ፣ ለኢህአዴግ ገንዘብ ማሰባሰቢያ እና የድጋፍ ምንጭ ሆኗል፡፡ በቅርቡ በጉጂ ዞን ኦዶ ጉዶ አካባቢ ለ2007 ዓ.ም ምርጫ ሞዴል የተባሉ አርሶ አደሮች በቁጥር ከፍ እንዲሉ እንደሹመት ተሰጥቷቸው ሲያበቃ 500 ብር እንዲያዋጡ የመሬት ይዞታቸው ለማስፈራሪያነት መዋሉ እንደማሳያ ሊወሰድ ይችላል፡፡

በሌላ በኩል ምንም አይነት ህዝባዊ ውይይት ሳይደረግበት ከሰማይ ዱብ ያለው የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የልማት መሪ ፕላን ያስቆጣቸው የኦሮሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰልፍ በማድረጋቸው የደረሰባቸውን ህገ ወጥ ድብደባና እስራት አንድነት በእጅጉ ይቃወማል፡፡ ለእውነተኛ ልማት ነው እንኳ ተብሎ ቢታሰብ ኢህአዴግ ካለበት የተአማኒነት ችግር የተነሳ ተማሪዎቹ ለተቃውሞ አደባባይ ቢወጡ ተፈጥሯዊ እና ህገ መንግስታዊ መብታቸው ሊከበር በተገባ ነበር፡፡ ነገር ግን ሁሉን ነገር ካልጋትኳችሁ የሚለውና ለዴሞክራሲያዊ ሽንፈት የማይገዛው ኢህአዴግ በተማሪዎቹ ላይ ያደረሰውን እንቃወማለን፡፡ የታሰሩ ተማሪዎችም በአስቸኳይ እንዲፈቱም እንጠይቃለን፡፡ የኦሮሞ ተማሪዎችን በገፍ ከዩኒቨርሲቲ የትምህር ገበታቸው በማባረር የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት ከዚህ ተደጋጋሚ ተግባሩ ታቅቦ ልጆቹን በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመልስ እንጠይቃለን፡፡

በአጠቃላይ መሬት የዜጎች መያዣ መሆኑ እንዲቀር እንታገላለን፡፡ ዜጎች በመሬታቸው የመደራደር እውነተኛ መብት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ተቃውሞ የሚያነሱ ዜጎችም ድምፅ እንዲሰማ እናሳስባለን፡፡

                                                             አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ

                                                                 ሚያዚያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም

                                                                           አዲስ አበባ  

 

UDJ Head

 

በቅሎን አባትህ ማን ነው? ቢሉት “አጎቴ ፈረስ ነው አለ”አሉ፤ ምንነትና ማንነት፡ የዘመኑ አንገብጋቢ ጥያቄ

$
0
0

Pro Mesfinከፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም
ሚያዝያ 2006

ምጽዓት የቀረበ ይመስላል፤ ብዙ ሰዎች ሳይጠየቁ በቁሎው የተጠየቀውን ጥያቄ ራሳቸውን ጠይቀው አጎቴ ፈረስ ነው የሚለውን መልስ እየመለሱ ናቸው፤ ስለምንነታቸውና ስለማንነታቸው በውስጣቸው አንድ አስጨናቂ ነገር እንዳለባቸው ግልጽ ነው፤ የጎዶሎነት ስሜት ስለሚሰማቸው የድረሱልኝ ጥሪ በጩኸት እያሰሙ ነው፤ ግንባር ቀዳሚ መለከት ነፊም አለ፤ እውነት ግን አይደፈጠጥም፤ እየዘለለ ያፈጥባቸዋል፤ አጎቴ ፈረስ ነው ባሉ ቁጥር፣ አባትህስ እያለ ያፈጥባቸዋል! በፈረስ አጎትነት የአህያን አባትነት መደምሰስ አይቻልም፤ ነገር አፍጥጦ ከመጣ አፍጥጦ ከመግጠም የተሻለ መልስ አይገኝለትም፤ ተቅለስልሰው ሊያልፉት ሲሞክሩ በኅሊና ውስጥ ተቀርቅሮ ይደበቃል፤ ለራስም ለማኅበረሰብም ክፉና ዘላቂ በሽታ ይሆናል፤ ኢትዮጵያዊነት ማንነቱን የሚክድ ኢትዮጵያዊ ሲያቃዠው ያድራል እንጂ ፍቆ አያጠፋውም፤ አንድ ጊዜ በጀኒቫ በአንድ የአበሻ ምግብ ቤት ስበላ አንድ ዱሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዬ የነበረ የኤርትራ ተወላጅ ሲገባ ተያየን፤ እየሳቅሁ ደሞ እዚህ ምን ልታደርግ መጣህ ስለው፣ ከዚህ ማምለጥ እኮ አይቻልም፤ አለኝ፤ እንዴት ብሎ!

ምንነት ከማንነት የተለየ ነው፤ ምንነት ከማንነት ይቀድማል፤ ምንድን ነህ? የሚለው ጥያቄ ከተመለሰ በኋላ ነው ማን ነህ? መልስ የሚያስፈልገው፤ የምንነትን ጥያቄ የማያውቁ የማንነትን ጥያቄ ፍልስፍና አዋቂዎች መስለው የተውሶ ሀረጎችን ጣል ጣል እያደረጉ ተደናግረው ለማደናገር ይሞክራሉ፤ ከንቱ ድካም ነው፤ ማንነት ከምን ተነሥቶ ነው ራሱን ችሎ የሚቆመው? ራስን ሳያውቁ ሌላውን ለማወቅ መሞከር፣ ራስን ሳያሳምኑ ሌላውን ለማሳመን መሞከር፣ ያልሆኑትን ለመሆን ከመሞከር የሚቀልለው ራስን መሆን ነው፡፡

በቁሎው አባትህ ማን ነው ተብሎ ሲጠየቅ የነፍሱ ቁስል ተነክቶበታል (ለነገሩ በቁሎ ነፍስ የለውም)፤ ለዚህ ነው እያወቀ ጥያቄውን የሳተው! አሁን ሌላ ጥያቄ ሊያስፈልግ ነው፤ በቁሎው የካደው አባቱን ብቻ ነው? በአባቱ በኩል አጎቱ አህያ ነው፤ በእናቱ በኩል አጎቱ ፈረስ ነው፤በቅሎ አንግዲሀ አጎቴ ፈረስ ነው ሲል የካደው አባቱን ብቻ አይደለም።

በቁሎ አጎቴ ፈረስ ነው አለ የተባለውን ሳስብ የአባቴ ሸክሊት የምትባለዋ በቁሎ ትዝ አለችኝ፤ ማይጨው ዘምታለች! እሷ ትዝ ስትለኝ የማላውቃቸውን ወላጆችዋንም አሰብሁ፤ አንድ ወንድ አህያና አንዲት ባዝራ (ሴት ፈረስ)፤ ለመሆኑ አጎቴ ፈረስ ነው ያለው አህያ አገሩ የት ይሆን? ለመሆኑስ አጎቴ ፈረስ ነው ሲል ምን ማለቱ ነው? የሸክሊትን ዘር በአጭሩ ብናየው እንደሚከተለው ይሆናል፤–

አንደኛበቁሎው በአባቱ በኩል አንድ ወንድና አንዲት ሴት አያት አህዮች አሉት፤
ሁለተኛበቁሎውበእናቱበኩልአንድወንድናአንዲትሴትፈረስአያቶችአሉት
ሦስተኛ አባቱ፣ አህያው፣
አራተኛ እናቱ ፈረስዋ (ባዝራዋ)፣
አምስተኛ አህያ አጎትና አህያ አክስት፣
ስድስተኛ ፈረስ አጎትና ፈረስ አክስት፣

ከአንድ በቁሎ ተነሥተን ወደአንድ አህያና ወደአንድ ፈረስ ተሸጋግረን ስንት አህያና ስንት ፈረስ አዛመድን!

ስለኢትዮጵያ ሕዝብ ጎንደሬው የሲዳሞ ሰው፣ መሀንዲሱ፣ የሕግ ባለሙያው ደመቀ መታፈሪያ ያደገበትንና ያየውን በልብ-ወለድም በታሪክም እያቀነባበረ ከአርባ ዓመታት በፊት ጀምሮ ደጋግሞ ጽፎበታል፤ ብዙዎቻችን አልተማርንበትም፤ አላሰብንበትም፤ አልተወያየንበትም።

በማእከላዊ እስር ቤት፣ ከዚያም በቃሊቲ ከአንድ የወላይታ ወጣት ጋር (በአለበት ይቅናውና) ወዳጅነት ጀምረን ነበር፤ ስለወላይታ ለመማር ፈልጌ ገና ጥያቄዎችን መጠየቅ ስጀምር ወላይታ ውስጥ ብዙ ጎሣዎች መኖራቸውን ነገረኝ፤ ብዙ ነገር ለመማር ተዘጋጅቼ ሳለሁ መቼም ሁሌም በባርነት ውስጥ ስላለን እንደፈቀድን ለመሆንና እንደፈቀድን ለማድረግ አይፈቀድልንምና ለያዩን (ይለያያቸውና)፤ ያሰብሁትን ሳልፈጽም ቀረሁ፤ ቢሆንም ወላይታ ብዙ ከሌሎች የኢትዮጵያ ጎሣዎች ጋር ዝምድና ያላቸው ጎሣዎች መኖራቸውን ለመገንዘብ ችያለሁ፤ የደመቀ መታፈሪያን ሀሳብ በትንሽዋ ወላይታ ውስጥ ለማየትና ሀሳቡን ለማረጋገጥ አስችሎኛል፤ መማር ለፈለገ ቃሊቲም ትምህርት ቤት ነው።

ከብዙ ዓመታት በፊት አንድ የተምቤን ሰው ከጻፈው እንደተገነዘብሁት፣ በአንድ ዘመቻ ጊዜ ከሸዋ ከዘመተ ሰው መወለዱን በዳዊት መጽሐፍ ላይ ተጽፎለት ያገኝና የቅኔ ትምህርቱን ሲጨርስ አባቱን ፍለጋ ወደሸዋ ይመጣል፤ ቡልጋ ይደርሳል፤ እየጠየቀ የአባቱን ዘመዶች ያገኛል፤ የአባቱ ልጅ (ወንድሙ) አዲስ አበባ መሆኑ ይነገረውና አዲስ አበባ ይመጣል፤ በእንግሊዝ አገር ተምሮ የተመለሰውን ወንድሙን ያገኛል፤ ሥራ ያስገባዋል፤ የፈረንጁን ትምህርት ይማራል፤ ራሱን ችሎ ይኖራል፤ ወንድሙን ከነልጁ ደርግ ይገድለዋል፤ የተምቤኑ ተወላጅ ለሸዋው ወንድሙ ለቅሶ ይቀመጣል።

ከአንድ ሳምንት በፊት አንዲት ሴት አራት ልጆች ይዛ በአጠገቤ ስታልፍ ሳቅ ብላ አንገትዋን ሰበር አድርጋ ሰላምታ አሳየችኝ፤ አወቅኋት፤ ከአምስት ስድስት ዓመታት በፊት በዚያው በእኔ ሰፈር አካባቢ ትለምን የነበረች የመቀሌ ሴት ናት፤ በዚያን ጊዜ አርግዛ ሳያት የመጣሽው ከነባልሽ ነው ወይ ብዬ ስጠይቃት ወንድ ልጅዋ አባቱ እንዳልመጣ ነገረኝ፤ እርግዝናዋ ድንገተኛ አደጋ መሆኑን ነገረችኝ፤ በጣም ትልቅ ሆና ስለነበረ ወደሀኪም ቤት እንድትሄድ ገንዘብ ሰጠኋት፤ ከወለደች በኋላም አንድ ጓደኛዬ መሣፈሪያ ሰጣትና ወደመቀሌ ተመለሰች፤ አሁን እንደገና መጣች፤ ስጠይቃት ሁሉም ነገር ተባብሷል፤ የማዳበሪያ እያሉ ያስጨንቁናል፤ አለች፤ በይ አሁን ደግሞ ተጠንቀቂ ብዬ ተሳስቀን ተለያየን፤ ችግርም ያዛምዳል።

እንደመደምደሚያ አድርጌ ቢትወደድ አስፍሐን ላንሣ፤ ቢትወደድ አስፍሐ ለኢጣልያ ያደሩ ባንዳ ነበሩ፤ በመጨረሻም በጎንደር ላይ ኢጣልያ ድል ሲሆን ከጌታቸው ጋር ነበሩ፤ ኢጣልያኑ ጌታቸው ወደአገሩ ሲሸሽ ቢትወደድ አስፍሐን ይዞ ለመሄድ ፈልጎ ነበር፤ ቢትወደድ አስፍሐ ግን ለሁለተኛ ጊዜ አልከዳም ብለው በአገራቸው ቀሩ፤ የዱሮዎቹ ሰዎች ያላቸው ሰብአዊነትና አብሮ የመኖር ጥበብ ቢትወደድ አስፍሐን ከራስ አበበ አረጋይ ጋር አገናኛቸው፤ ታላቁ ባንዳ የትግራይ ገዢ ለነበሩት ለታላቁ አርበኛ ረዳት ሆኑ፤ ራስ አበበ ስለቢትወደድ አስፍሐ ያላቸውን አስተያየት ለማወቅ ዕድሉ አልገጠመኝም፤ ቢትወደድ አስፍሐ ስለራስ አበበ ያላቸውን አስተያየት ግን በመጠኑም ቢሆን ለማወቅ ችዬአለሁ፤ ቢትወደድ አስፍሐ ራስ አበበን በጣም ያከብሩአቸዋል፤ በጣም ያደንቁአቸዋል፤ የቢትወደድ አስፍሐ አማርኛና የኢትዮጵያ ታሪክ እውቀት ሳይተላለፍልን በመቅረቱ በጣም አዝናለሁ፤ ስለኤርትራ ‹ናጽነት› ድምጽ እንዲሰጥ ወያኔ በሚገፋፋበት ጊዜ ቢትወደድ አስፍሐ በሙሉ መንፈሳዊ ወኔ የወያኔንና የሻቢያን ጫና ተቋቁመው ኢትዮጵያዊነታቸውን አልክድም ብለው በኩራት ቆሙ፤ ባንዳው አርበኛ ሆኑ! ንስሐ ያጸዳል! ንስሐ ነጻነትን ያጎናጽፋል፤ የደበቁት ኃጢአት ግን በቀን ያቃዣል!

ባንዳና የባንዳ ልጅ ሁሉ የአርበኛ ስም ሲጠራ ያቃዠዋል! አጎቴ ፈረስ ነው! ይላል።

ሰሚ ጆሮ ያጣ የሕዝብ እሮሮና ጩኸት እስከመቼ? (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

$
0
0

ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና

Gezahegn Abebeዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካለችበት የኢህአዲግ ስርአት ለመላቀቅ እና ከገባችበት ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሜያዊ ውድቀት ወጥታ ህዝቡም ከወያኔ ስርዓት ተላቋ ወደ ተሻለ እና ወደ ተረጋጋ ሕይወት ለመድረስ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እና በሁሉም አቅጣጫ እና በሚችለው መንገድ መታገል ይጠበቅበታል:: ዛሬ ላይ ወያኔ ኢህአዲግ የእምነታችንን ነጻነት እያሳጣን የዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት እየረገጠ እና የዜግነት ክብራችንን እና ነፃነታችንን በመግፈፍ የባርነት ኑሮ እየኖርን እንገኛለን::  መቼም በአሁኑ ጊዜ በጨቋኙ የወያኔ ስርአት ያልተማረረ የህብረተሰብ ክፍል ያለ አይመስለኝም ስለሆነም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ሀይማኖት፣ ዘርና፣ቋንቋ ሳይዘው ሊጠይቀው የሚገባ የመብትና የነጻነት ጥያቄ ሊሆን የሚገባው  እስከ መቼ ? በወያኔ መንግስት የግፍ ስርዓት  እየተጨቆኑ መኖር ብለን እራሳችንን ልንጠይቅ ያስፈልጋል::

በርግጥ በአሁኑ ሰአት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሀገር ቤትም የሚኖረው ከሀገር ውጭ ተሰዶ የሚኖረውም (ዲያስፖራ) ኢትዮጵያዊ በሚችለው መንገድ ሁሉ ወያኔንን በመቃወም እና በመፋለም የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውንም ግፍ እና በደል ለአለም ህዝብ እና መንግስታቶች ለማሳወቅ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ  እንዳለ ይታወቃል::በተለይም  በወያኔ መንግስት ጨቋኝ እና ዘረኛ አገዛዝ ተጠቂ የሆነው በሀገር ውስጥ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሕዝባችን ከማንኛውም ጊዜ  በባሰ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ እና እየደረሰበት ካላው ችግር የተነሳ በየጊዜው ድምጹን እያሰማ እንዳለ ይታወቃል:: በሀገር ውስጥም ሆነው መሰዋህትነትን  እየከፈሉ ያሉ  በሰለማዊ ትግል የወያኔን አቅም ማሽመድመድ እና ከስልጣን ማስወገድ ይቻላል በማለት አምነው እና ቆርጠው የተነሱት እንደ ሰመያዊ ፓርቲ እና አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የመሰሉ ፓርቲዎች ሕዝቡ ብሶቱን እና ምሪቱን በአደባባይ እንዲያሰማ  እያደረጉት ያለው ሰላማዊ ትግል የሚያስመሰግናቸው ነው :: እነዚህ ፓርቲዎችም  የኢትዮጵያ ሕዝብ ህገ መንግስታዊ መብቱን እንዲያስከብርና ለነጻነቱም እንዲታገል እያነቁት ሲሆን ፣ በአሁኑ ሰአት ለመብቱ እና ለነጻነቱ በየጊዜው ድምጹን እያሰማ እና በአደባባይ እየጮኸ  ይገኛል :: ቢሆንም ሀገርን እመራለው ሕዝብንም አስተዳድራለው ብሎ ከተመጠው መንግስት ነኝ ባይ አካል ግን ምንም አይነት የሕዝቡን እሮሮና ጩኸት አዳምጦ የሕዝብን ጥያቄ የመመለስ ነገር አይታይም::

የኢትዮጵያ ሕዝብም ሕገ መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ ሀገርን እመራላው ብሎ ለተቀመጠው አካል ድምጹን ማሰመትና መብቱን መጠየቅ ሕገ መንግስታዊ መብቱ ቢሆንም ነገር ግን ይሄ መብቱ ሲከበርለት አይታይም :: በወያኔ መንግስት በኩል በተቃራኒው የሚሆነው ግን ሌላ ነው ሕዝቡ ብሶቱን ለማሰማት በተነሳ ጊዜ ዜጓችን ማዋከብ፣ ማስፈራራት፣ ማሰርና፣ የተለያዩ በደሎችን በዜጎቹ ላይ መፈጸመ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣ አሳሳቢ የሆነና የወያኔ መንግስት የለመደው የእለት በእለት ተግባሩ ሆኖል::

በርግጥ በአሁኑ ጌዜ የምርጫም ጊዜም እየደረሰ ከመሆኑም የተነሳ ሕዝብን ለማታለልና በኢትዮጵያ ላይ ዲምክራሲ እንዳለ ለማስመሰል በምህራባውያን ዘንድ የፖለቲካ ቁማሩ እንዳይበላሽበት በፓርቲዎች ጥያቄ ሳይወድም ቢሆን በስንት መከራ ሰላማዊ ሰልፎችን የማድረግ መብትን የፈቀደ ቢመስልም  ሕዝብን እና የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችን ግን በአይነ ቁራኛ በመከታተል ፣ በማዋከብ፣በማሰር ላይ ይገኛል:: ሕዝቡ በተለያያ ጊዜ በሰላማዊ ሰልፎች በየጊዜው ጩኸቱን እያሰማ ቢሆንም የሕዝብ ጩኸት ግን  አዳማጭ ያገኘ አይመስልም:: በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ሕዝቡ  እየጠየቀ ላለው ጥያቄ የወያኔ መንግስት የሕዝብን ጩኸት ሰምቶና አዳምጦ መልስ ይሰጣል ብሎ ማሰብ ሲበዛ እጅግ የዋህነት ይመስለኛል:: የወያኔ መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር፣ መከራ ምንም የማያሳስበው መንግስት እንደሆነ በተለያየ ጊዜ ያየነውና የተረዳነው ነገር ሲሆን በአለም ላይ በተለያዩ ሀገራት ከሚኖሮ ሕዝቦች መካካል በአሁኑ ጊዜ እንደ ኢትዮጵያ ሕዝብ እየተዋረደና መከራ እየደረሰበት የሚኖር ያለ ሕዝብ ያለ አይመስለኝም በቅርቡ እንኮን እንደምናስታውሰው በሳውድ አረቢያ በጨካኝ አረመኔ አረቦች ሕዝባችን በአደባባይ እንደ በግ ሲታረድ በአለም ዙሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከዳር እስከ ዳር በአንድነት በኢትዮጵያዊ ስሜት በጩኸት ድምጻቸውን ሲያሰሙ በጊዜው በወያኔ መንግስታቶች ዘንድ የሕዝባችን እንደ በግ በአደባባይ መገደል እንደ ምንም ነገር ቦታ ያልተሰጠው ጉዳይ እንደነበር እና የወያኔን መንግስት በብዙዎች ዘንድ ለትዝብት የዳረጋቸው ክስተት እንነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ::

ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገሩ ላይም መኖር አቅቶታል ጮኸቱንም ያሰማል የሕዝቡም ጩኸት ማብቂያ ያለው አይመስልም ሰመያዊ ፓርቲም ቢሆን አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በአሁን ሰአት ሕዝቡ ብሶቱንና በመንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ እንዲያሰማ በየጊዜው የሰለማዊ የተቀውሞ ሰልፎችን እያዘጋጁ እና በወያኔ መንግስት ላይ የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ቢሆኑም  የወያኔ መንግስት ግን የሕዝብን ጥያቄ የመመለስ አዝማሚያ አይታይበትም  ነገር ግን  በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሕዝብን እሮሮና ብሶት ማዳመጥ ሕገ መንግሥታዊ ግዴታው ነው፡፡ እነ እስክንድር ፣ርዕዮትና ፣ አንዶለም ሌሎቹም የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች  በየእስር ቤቶች ውስጥ በእስር በማቀቅ ላይ ባሉበት ሁኔታ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የአለም የሰባሃዊ መብት ተከራካሪዎች ሳይቀሩ ያለበደላቸውና ያለሀጢያታቸው በግፍ በእስር ላይ ያሉ እስረኞች  ከእስር እንዲፈቱ በየጊዜው በመጠየቅና በውጭ ሀገርም በሀገር ውስም የሚኖሩ ኢትዮጵያ ዜጎች በተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች በመሰብሰብ ስለወገኖቻችን ቢጮኽምጩኸቱም ሰሚ ጆሮ ያጣ እየሆነ ይገኛል::

የኢትዮጵያ ሕዝብ በየጊዜው ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች ከእስር እንዲፈቱ በሰላማዊ ሰልፎች ይጮኻል ነገር ግን የወያኔ መንግስት ህገ መንግስቱን አክብሮና የሕዝብን ጩኸት ሰምቶ ለሕዝብ ጥያቄ መልስ መስጠት ሲገባው ያለምክንያት ያስራቸውን ዜጓች ከእስር ከመፍታት ይልቅ የሕዝብን ጩኸት ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ከቀን ወደ ቀን ሕዝብን በማተራማስና ሌሎች ንጹሃን ዜጎችንም እያደኑ በመያዝና በማሰር ስራ ላይ ተደምጦል::

 እነ አንዷለም አራጌ ፣እነ በቀለ ገርባ ፣ እና ናትናሄል እና ሌሎችም እስረኞች ከቃሊቲ እንዲወጡ ሕዝብ እየጮኸ ባለበት ሁኔታ ሌሎች በብዙዎች የሚቆጠሩ አንዷለሞች፣ ሌሎች በቀለዎች፣ ሌሎች ናትኖሄሎች ለእስር እየተዳረጉ ነው እነ ርዕዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸትንና ሌሎች በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ እየጮኽን ባለንበት ሁኔታ ሌሎች ርዕዮቶችና ሌሎች እስክንድሮች፣ ሌሎች ውብሸቶች ወያኔ በሚያቀርባቸው የሃሰት ውንጀላዎች እየተከሰሡ ወደ እስር ቤት እየተወረወሩ ሲሆን  ሰሞኑንም እያየን ያለነው ያለነው ይኼንኑ ነው :: ሕዝብን አስሮ የማሰቃየት ሀባዜ የተጠናወጠው አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት በማን አለብኝነት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሌሎች  ጋዜጠኞችን በማያዝ አስሯቸዋል::እነዚህ ወገኖቻችን  ምንም የተደበቀ አጀንዳ የሌላቸው ግን ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈረው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይከበር ያሉና በህገ መንግስቱ መስረት የሕገ መንግስቱን አንቀፅ እየጠቀሱ የሃሳብ የመግለፅ መብታቸውን የተጠቀሙ ሶስት ጋዜጠኞችን እና ስድስት ብሎገሮችን በተለያየ የሀሰት ወንጀል በመወንጀል ለእስር መዳረጉ ወያኔ ምን ያህል በእምቢርተኝነት ልቡን እያደነደነ ያለ አንባ ገነን መንግስት እንደሆነ በገሃድ ቁልጭ አድርጎ ያሳይ ሀቅ ነው::  ይህ ሁሉ ግን የሚያሳያው ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ዜጎችን በተለያየ የሀሰት ውንጀላ በመወንጀል ማሰረኑንና ሕዝብን ማሰቃየቱ እንደማይቀር የሕዝቡም ስቃይ፣ መከራ፣ እስራታ እና ግድያ እስከ መቼ እንደዚህ ይቀጥላል ? የእኔም ጥያቄ የብዙዎቻችን ጥያቄ የወያኔ አንባ ገነንተ እስከ መቼ ? ሰሚ ጆሮ ያጣው የሕዝብ ሮሮ እና  ጮኸትስ እስከ መቼ ?

እንደእኔ አመለካከት ህዝባችን በሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፎች አረመኔው የወያኔ መንግስት ለሕዝቡ ጥያቄ  መቼም ቢሆን መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ  ይሆናል ብዪ አላስብም::ነገር ግን የወያኔን መንግስት ይበልጥ ሊያዳክሙ የሚችሉትን ስልቶችን ( strategy) በመንደፍ ትግላችንን ብንቀጥል ወያኔን ማንበርከክ ይችላል የሚል እምነት አለኝ:: ለነገ የሕዝብ እሮሮ እና ጩኸት ተሰምቶ ህገ መንግስቱ የሚከበርባትንና ዜጎች በነጻነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን እየተመኛው ለዛሬ ጹሁፊን ላጠቃል ::

ውድቀት ለአንባ ገነኖች!!
  gezapower@gmail.com

አንድነት ሕዝቡን ለመድረስ የዘዉግ ድርጅቶች የግድ አያስፈልጉትም (አሰፋ ቤርሳሞ)

$
0
0

አሰፋ  ቤርሳሞ

(abersamo@gmail.com)
unityበመድረክ እና በአንድነት መካከል ስላለው ግንኙነት ሁለት ኢትዮጵያዊያን የጻፉትን አነበብኩ። ዶር መሳይ ከበደ፣ መድረክ ዉስጥ ባሉ የዘዉግ ደርጅቶች እና በአንድነት ፓርቲ መካከል ያሉት የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነቶች የማይታረቁ መሆናቸውን  በመገልጽ፣  አንድነት ጊዜዉን እና ጉልበቱን እነዚህ የዘዉግ ድርጅቶችን በማባበል ላይ ከማጥፋት፣ ከሌሎች አገር አቀፍ ድርጅቶች ጋር አብሮ እንዲሰራና እንዲዋሃድ ይመክራሉ።

አቶ ዳዊት ተሾመ በበኩላቸው፣ ለዶር መሳይ መልስ ይሆን ዘንድ ባቀረቡት ጽሁፍ ፣ የዶር መሳይን አቋም በኢትዮጵያ ያለዉ ፖለቲካ ወደ ጫፍና ጫፋን እንዲሄድ የሚያደርግ የማክረር ፖለቲካ ነው ሲሉ ጠንካራ ትችት ያቀርባሉ። በመድረክ እና በአንድነት መካከል ለተፈጠረዉ ችግር በዋናነት የአገር አቀፍ ድርጅቶችን (እነ አንድነትን) ተጠያቂ ያደርጋሉ።

«The main causes of conflict between UDJ and other ethnic-based Medrek members parties emanate from endogenous (i.e. UDJ elites’ political calculus and the modus operandi of Mederk) and exogenous (i.e. Semayawi party’s, diasporas’ and All Ethiopian Unity Party (AEUP)’s pressure) factors which, for the last few years, cause either the centrifugal or centripetal political trends.» ሲሉ ነበር አቶ ዳዊት፣  አንድነት፣ ሰማያዊ ፣ መኢአድና ዳያስፖራው ላይ ያነጣጠሩት።

አቶ ዳዊት፣ በመድረክ እና በአንድነት መካከል የነበሩትንና ያሉትን መሰረታዊ ችግሮች የተረዱ  አልመሰለኝም። የሰማያዊ ፓርቲ በቅርብ የተመሰረተ ድርጅት ነው። በመድርክ እና በአንድነት መካከል የነበሩት ችግሮች ከዚያ በፊት በርካታ አመታት ያስቆጠሩ ናቸው። መኢአድን ከወሰድን ደግሞ ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአመራር አባላቱ ለአመታት እርስ በርስ ሲናጡ የነበሩበት ሁኔታ ነው የነበረዉ። ወደ ዳያስፖራዉ ከተመለስን፣  መድረክ በተለይም በዉጭ ባሉ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች ዘንድ ትልቅ ድጋፍና ተቀባይነት እንደነበረው የሚታወቅ ነው። ዶር መሳይ ከበደም እራሳቸው፣ የመድረክን ራእይና አላማ ይደግፉ እንደነበረም አስቀምጠዋል። መድረክ በጣም ተቀባይነት ነበረዉ።

ስለዚህ በአንድነት እና በመድርክ መካከል ያለው ችግር፣ በመኢአድ፣ ሰማያዊ ወይም ዳያስፖራዉ፣ በአንድነት ላይ ጫና ስላደረጉ ነው የሚለው መከራከሪያ ትንሽ ዉሃ የሚቋጥር አይመስለኝ።

መድረክ እንደተመሰረተ፣ ከምርጫ 2002 በፊት እና ከዚያ በኋላ የአንድነት ፓርቲና አረና፣  መድረክ እንዲዋሃድ ገና ከጅምሩ ግፊት ያደርጉ እንደነበረ በስፋት ተዘግቧል። መድረክ መዋሃድ እንዳለበት፣ አቶ ዳዊት እንዳሉት፣ የአንድነት ፓርቲ ለፖለቲካ ስሌት ሲል አሁን የያዘው አቋም ሳይሆን፣ ከጅምሮ ሲስራበት የነበረ ጉዳይ ነው። መድረክ ወደ አንድነት እንዲመጣ ወደ አምስት አመት ገደማ ፣ ብዙ ዉይይቶች ተደርገዋል። ነገር ግን የአረና እና የአንድነት ጥያቄ በሌሎች ድርጅቶች ዉድቅ በመደረጉ መድረክ ሊዋሃድ አልቻለም።

ለዚህም ዋናዉ ምክንያት፣ ዶር መሳይ ከበደ እንዳሉት፣  የፖለቲካ ፕሮግራም ልዩነቶችን ማጣበብ ስላልተቻለ ነው። በእንጥልጥል የቆዮ፣ እንደ መሬት ፖሊሲና የፌደራል አወቃቀር ያሉ ጥቂት፣ ግን ቁልፍ የፖለቲክ ፕሮግራም ልዩነቶች ላይ  ስምምነት ሊደረስ አልተቻለም። የዘዉግ ድርጅቶች አሁን ያለው በቋንቋ ላይ የተመሰረተው፣ በኃይል በሕዝቡ ላይ የተጫነው ፌደራል አወቃቀር እንዲቀጥል ይፈልጋሉ። በመሬት ፖሊሲ ዙሪያ አሁን ካለው የመሬት ፖሊሲ የተለየ አቋም የላቸውም፡፡ ዶር መሳይ ከበደ እንዳሉት መድረክ ዉስጥ ያሉ አንዳንድ የዘዉግ ድርጅቶች ከአንድነት ይልቅ በፖለቲክ ፕሮግራሞቻቸው ከኢሕአዴግ ጋር ነው በጣም የሚቀራረቡት። ይሄ ከድሮም ይታወቃል። ነገር ግን አንድነትዮች ሰጥቶ በመቀበል መርህ መሃከል የሆነ ቦታ መድረስ ይቻል ይሆናል የሚል እምነት ስለነበራቸው ነው።

«መድረክ መዋሃድ ካልቻለ፣ ያሉ ልዩነቶችን ይዞ ለምን በግንባርነት አይቀጥልም ? » የሚል መከራከሪያ ሊነሳ ይችላል። የተከበሩ ዶር ነጋሶ ጊዳ መድረክ ዉህደት ሊፍጠር እንደማይችል፣ ነገር ግን ፓርቲዎች በግንባርነት፣  በመለስተኛ ፕሮግራም ዙሪያ፣ መስራቱ እንደሚያዋጣቸው በመግለጽ፣ መድረኩ ጠንካራ የተቃዋሚዎች ስብስብ እንዲሆን ጠይቀው ነበር።

እርግጥ ነው እንደ ግንባር ለመቀጥል ሙሉ ለሙሉ የፖለቲካ ፕሮግራም መጣጠም መኖር የለበትም። ፓርቲዎች ያሏቸውን ልዩነቶች ይዘው፣ በሚስማሙበት ጉዳይ ላይ ግንባር ፈጥረው፣  አብረዉ መንቀሳቀስ ይችላሉ። ታዲያ «የአንድነት ፓርቲ ለምን በመድረክ ዉስጥ፣  ተዋህዶ ካልሆነ በቀር፣ እንደ ግንባርነት መቀጠል አልፈለገም ? » የሚለው ተከታዩ ጥያቄ ነው የሚሆነው።

በዋናነት አንድነት በመድረክ ዉስጥ እንደ ግንባር አብሮ የመስራት ችግር ያጋጠመው፣ ብዙዎች የሚዘነጉት፣ ምናልባትም አቶ ዳዊት ልብ ያላሉት፣  መድረክ ዴሞክራሲያዊ የሆነ አሰራር ስላልነበረው ነው። በመድረክ ዉስጥ ያለው ቢሮክራሲ ብዙ ስራዎች እንዳይሰሩ ትልቅ ማነቆ ፈጥሯል። መድረክ ዉስጥ በጉልህ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በዋናነት የአንድነት ፓርቲ እና አረና ናቸው። ሌሎች የመድረክ አባል ድርጅቶች ምን ያህል አባላት እንኳን እንዳላቸው አይታወቅም። አንዱ ድርጅት በዶር መራራ ጉዲና የሚመራዉ ኦፌኮ ነው። ሌላው ደግሞ በነ ዶር በየነ ጴጥሮስ የሚመራዉ ቡድን ነው። እነዚህ ሁለት ምሁራን ምን ያህል በድርጅታቸው ዉስጥ ዴሞክራሲያዊ  አሰራር እንደሚፈቅዱ ለማወቅ ትንሽ ያስቸግራል። ምን ያህል በድርጅታቸው ዉስጥ ተጠያቂ እንደሆኑ አይታወቅም። ነገር ግን በመድረክ ዉስጥ፣ በድርጅቶቻቸው ስም፣ እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ካልተስማሙ ምንም የሚሆን ነገር እንደሌለ፣ በአጭሩ፣  ዶር በየነ እና ዶር መራር በመድረክ ዉስጥ ቪቶ ፓወር እንዳላቸውና የምንሰማው።

ይህን አይነቱ አሰራር እንዲለወጥ፣ መድረክ ሪፎርምድ እንዲሆን፣ በአንድነት በኩል ጥረቶች ሲደረጉ አመታት አስቆጠሩ። በተለይም በዶር ነጋሶ ጊዳዳ የሚመራዉ፣  በመድረክ የአንድነት ተወክዮች ቡድን፣ መድረክ ዉጤታማ ሆኖ እንዲወጣ ብዙ፣ እጅግ በጠም ብዙ ደክሟል። ነገር እንደታሰበውና እንደተደከመበት አልሆነም።

በመድረክ ዉስጥ ያለ መዝረክረክ እና ጸረ-ዲሞክራስያዊ አሰራር፣ በርካታ የአንድነት አመራር አባላትና ደጋፊዎች በመድረክ ላይ ጥያቄዎችን እንዲያስነሱ አደረጋቸው። የሚነሱ ጥያቄዎች ከግዜ ወደ ጊዜ ፣ ከአመት ወደ አመት እየጨመሩ ሲመጡ፣ የአንድነት ፓርቲ የበላይ አካል የሆነው ብሄራዊ ምክር ቤቱ፣ ለሕዝቡ፣ ለአባላትና ለደጋፊዎቹ ተጠያቂ በመሆኑና በአባላቱ ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎችን የማስተናገድ ግዴታ ስላለበት፣ በመድረክ ዙሪያ መከረ። አንድነት ከመድረክ ጋር ያለዉን ግንኙነት በተመለከተ፣ መረጃ ላይ ያተኮረ ጥናት ተደርጎ ሪፖርት እንዲቀርብለት ኮሚቴ አቋቋመ። ኮሚቴዉ በታዘዘው መሰረት ሪፖርቱን አቀረበ። ምክር ቤቱ በመድረክ ዙሪያ ማሻሻያዎችን እንዲደረጉና ፣ ያሉ  የፖለቲካ ልዩነቶችን ማጣበብ ተችሎ፣ መድረክ ወደ ዉህደት እንዲመጣ ግፊት እንዲደረግ ወሰነ።

መድረክ በአገራችን ለዉጥ እንዲመጣ ሊረዳ የሚችል አማራጭ መንገድ እንጂ፣ በራሱ ፍጻሜ አይደለም። መድረክ የታሰበለትን ግብ ማስፈጸም ካልቻለ፣ መድረክ እንዲሻሻል ግፊት ማድረጉ ተገቢ ነበር። የአንድነት ፓርቲም ያደረገው ይሄንኑ ነው። ይሄ ሊያስወቅሰው በጭራሽ አይገባም።

የመድረክ አባል ድርጅቶች በመድረክ የአሰራር ለዉጥ እንዳይመጣ በር ዘጉ። የአንድነት ፓርቲ በፊቱ የሚቀረው አማራጭ፣ ከመድረክ ዉጭ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ሆነ። የሚሊዮኖች ድምጽ በሚል መርህ በመላው ኢትዮጵያ መንቀሳቀስ ጀመረ። የመድረክ ሌሎች አባል ድርጅቶች ደስተኛ አልሆኑም። አንድነትን ለስድስት ወራት አገዱ።

የአንድነት ፓርቲ፣ የፖለቲካ ፕሮግራሞችን ማጣጣም እስከተቻለ ድረስ፣  አገር ዉስጥ ከሚንቀሳቀስ የዘዉግ ይሁን አገር አቀፍ ደርጅቶች ጋር መዋሃድ በአምስት አመት እቅዱ ካስቀመጣቸው ፖሊሲዎቹ  አንዱ ነው። ከአምስት አመታት በላይ ከመድረክ ጋር በዉህደት ዙሪያ ሲሰራ ነበር። ብርሃን ለፍትህና ለዲሞክራሲ ከተባለ ድርጅት ጋር ዉህደትን መስርቷል። ከመኢአድ እና ከአረና ጋርም ለመዋህድ እየተነጋገረ ነው። (መሰናክሎች በሂደት ቢያጋጥሙም) ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የሚደረግ የዉህደት ዉይይት እንዳለ እስከአሁን አልሰማንም። ሰማያዊ ለብቻው መጓዝ የሚፈልግ ፓርቲ እንደሆነ ነው የነበረን መረጃ የሚያሳየው። ያ ተለዉጦ ንግግሮች ከተጀመሩ፣ እሰየው ነው የምንለው።

አቶ ዳዊት ለማንጸባረቅ እንደሞከሩት፣ አንድነት ከሰማያዊ ወይንም ከመኢአድ ጋር ለመዋህድ ሲል ፊቱን ከመድረክ አላዞረም። መድረክ ነው አንድነትን እየገፋ ያለው። የመድረክ ድርጅቶች ናቸው ኢሕአዴጋዊ የሆነ የፖለቲካ አቋማቸዉን ለማቻቻል ፍቃደኛ ያልሆኑትና መድረክ የተኛ ስብስብ እንዲሆን ያደረጉት።

አቶ ዳዊት «The greater danger lies for Ethiopian unity, as a State, is not from any secessionist movements/parties but from how pro-unitary parties handle the case and portray ethnic-based parties.» ሲሉ እንደ አንድነት ፓርቲ ያሉ አገር አቀፍ ድርጅቶች፣  በዘዉግ የተደራጁ ድርጅቶችን እንዲለማመጡ የሚፈልጉ ይመስለኛል።

አቶ ዳዊት ተሾመ አንድ የዘነጉት ጉዳይ ቢኖር፣ በአገራችን እየገዙ ያሉት የዘዉግ ድርጅቶች እንደሆኑ ነው። ፖለቲካ በማስፋራርት አይሆንም። ብዙ የዘር ድርቶችና አክራሪዎች «ይህ ከሆነ ጦርነት ይመጣል፣ አገር ትገነጠላለች …» እያሉ በባዶ ማስፈራራቱ አንዱ ትልቁ መሳሪያቸው ነው። ፖለቲካችን በመርህ ላይ መመስረት አለበት። በዘር ተደራጅተናል የሚሉ፣ ሕዝቡን በምንም መስፈርትና ሚዛን የማይወክሉ መሆናቸውንም መገንዘብ አለብን። የአንድነት ፓርቲ ሕዝቡ ጋር ለመድረስ የዘር ድርጅቶች አያስፈልጉትም። በስለጠነ መልኩ፣ የሕዝቦች መቀራረብና መተሳሰር ላይ በማተኮር፣ የኢትዮጵያዉያን መሰረታዊ የዴሞክራሲ፣ የመብት፣ የኢኮኖሚ ጥያቄዎች እንዲፈቱ ከታገለ ፣ ኦሮሞዉ ከኦሮሞ ድርጅቶች ይልቅ አንድነትን፣ በደቡብ ያሉ ብሄረሰቦችም ከደቡብ ድርጅቶ በላይ አንድነት የማይደግፉበት ምንም ምክንያት የለም።

ለዚህም ነው፣  ኦሮሞው፣ ትግሬው፣ ጋሞዉ፣ ሃመሩ …ቅልቅሉ ከአንድነት ኋላ ተሰልፎ በየክልሉ የመብትን ጥያቄ የሚያነሳዉ። የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚለው ዘመቻ፣ የአንድነት ፓርቲ በደቡብ ክልል በጂንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በወላይታ ሶዶ ሰላማዊ ሰልፎች ያደረገ ሲሆን፣ በሁለተኛው ዙር ዘመቻ ደግሞ፣  እንቅስቃሴዎችን በአዋሳ፣ እንደገና በጂንካ፣ በቁጫ ይደረጋሉ። (5 ከተሞች በደቡብ ክልል) ። እንደ አንድነት፣  ሌላ በደቡብ ያለ የዘዉግ ድርጅት የሕዝብን ጥያቄ ያጎላ አለን?

በኦሮሚያ ክልል ደግሞ በፍቼ፣ በባሌ/ሮቢ፣ በአዳማ እንቅስቃሴዎች የተደረጉ ሲሆን፣ በቅርቡ ደግሞ እንደገና በአዳማ፣ በነቀምቴ በአምቦና  በለገጣፎ አንድነት ሕዝቡን ያንቀሳቅሳል ( 6 ከተሞች በኦሮሚያ) ። እስቲ ኦሮሞዉን እንወክላለን ብለው ከሚያወሩት ቁጥራቸው ከማይታወቅ የየኦሮሞ ድርጅቶች መካከል ኦሮሚያ ዉስጥ እንደ አንድነት ፓርቲ የሚንቀሳቀስ አለን ? «ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት፣ አዲስ አበባ ኦሮሚያን ወረረች፣ የአኖሌ ሃዉልት መሰራቱ አኮርቶናል . ወዘተረፈ » እያሉ ለሕዝብ የማይጠቅም፣ ሕዝብን  ከሕዝብ የሚለያይ ጠባብ ፖለቲካ ያራምዳሉ እንጂ ምን የፈየዱት ቁም ነገር አለ?

በአማራው ክልል በደሴ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር ሰልፎ የተደረጉ ሲሆን፣ በደብረ ታቦርና በድብረ ማርቆስም ይቀጥላል። (6 ከተሞች በአማራዉ ክልል) ከትላልቆቹ ክልሎች በተጨማሪ በአዲስ አበባ፣ በድረደዋ፣ በመቀሌ፣ በአዋሳ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ።በተለያዩ ብሄረሰቦች ዘንድ በመዝለቅ ልዩነትን ሳይሆን አንድነትን ፣ ጥላቻን ሳይሆን ፍቅርን አንድነቶች እየሰበኩ ናቸዉ።በዚሁ ይቀጥሉ ባይ ነኝ።

የመድረክ ራእይ ጥሩ ነበር። ግን አልሰራም። መድረክ ዉስጥ ገብተው ለመስራት ያኔ መሞከራቸው ስህተት አልነበረም። ስህተት የሚሆነው ግን መድረክ እንደማይሰራ ታውቆ፣ ከአሁን በኋላ በመድረክ ዉስጥ መቀጠል የሚፈልጉ ወይም የሚያቅማሙ ከሆነ ነው።  የዶር መሳይ ከበደን ሃሳብ በመጋራት አንድነት ከመድረክ ጋር ያለውን የቀረ ጣጣ አስወግዶ፣ ትኩረቱን ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር ማድረጉ ያዋጣዋል ባይ ነኝ።

ዶር መሳይ ምናልባትም አንድነት ከመኢአድ ፣ ከሰማያዊ ከመሳሰሉት ጋር እንዲዋሃድ ነው የሚፈልጉት። እኔም ያ ፍላጎት አለኝ። ነገር ግን ፕራክቲካል መሆን ሊያስፈልገን ይችላል። ሰማያዊ ፓርቲ ለብቻቸው መስራት የሚፈልጉ ናቸው። የትብብር ትቅም ያልገባቸው ገና በስሜት የሚጋልቡ።  እነርሱን ካልፈለጉ መለማመጥ ተገቢ አይመስለኝም። መኢአድ ዴሞክራቲክ ድርጅት ነው ብዬ አላስብም። የመኢአድ የበላይ ጠባቂ የሚባል አለ፣ አቶ ኃይሉ ሻዉል የሚመሩት። (በኢራን እንዳሉት አያቶላ ማለት ነው)። አሁን ያሉት የመኢአድ ሊቀመንበር፣ ይመስለኛል፣ ለአቶ ኃይሉ ሻዉል እንጂ ለመኢአድ ላእላይ ምክር ቤት ተጠያቂ አይደሉም። ያ ቢሆን ኖሮማ፣ የላእላይ ምክር ቤቱ ዉህደቱን ተስማምቶ ሊቀመነበሩ፣ በሁለት ቀኑ የተለያዩ ምክንያት እያቀረቡ፣  በአቋራጭ የምክር ቤቱ ዉሳኔን ባልቀለበሱ ነበር። ከዚያም በተጨማሪ መኢአድ በሕዝብ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት እዛ ማዶ ታች ወርዷል። ስለዚህ መኢአድ ላይም ብዙ ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግም። አባላት አመራር አባላቶቹን ተጠይቂ አድርገው ፣ የአባላት ፍላጎት ተግባራዊ ቢሆንም ፣ አንድነት እና መኢአድ ገና ድሮ ይዋህዱ ነበር።

አንድነት ትኩረቱን አረና ላይ ቢያደርግ በጣም ጥሩ ሊሆን ይችላል። አረናዎች የመዋሃድ ትልቅ ፍላጎት አላቸው። ለምን ዉህደትን ከልብ የሚፈልግ፣ እንደገና የሚታዩ ተጨባጭ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ካለ ድርጅት ጋር ዉህደት እንዲፈጠር ቅድሚያ አይሰጠዉም ? የአረና አባሎችን አንድነቶች በትግራይ እጅና ጓንት ሆነው ነው የሚሰሩት። ያሉ ወይንም ሊኖሩ የሚችሉ ልዩነቶችን በማጣበብ በቶሎ ቢዋሃዱ ጥሩ ነው።

በአረና አንዳንድ አመራሮች ዘንድ አሁንም በመድረክ ላይ ተስፋ የማድረግ ነገር ያለባቸው ይመስለኛል። አንድነት በመድረክ ዉስጥ እንዲቀጥል ዉስጥ ዉስጡን ለማግባባት ይሞክሩ ይሆናል። ነገር ግን ጥረታቸው ዉጤት ያስገኛል ብዬ አላምንም። በዚህ ረግድ አቋሞቻቸውን ግልጽ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ወይም በመድረክ ይቀጥሉ፤ አሊያም ከአንድነት ጋር ይዋሃዱ።

 

ጃዋር ነበር የሚለው፣ አሁን ግን የኦሮሞ ተማሪዎችም ደገሙት –ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት (ናኦሚን በጋሻዉ)

$
0
0

ናኦሚን በጋሻዉ
naomibegashaw@gmail.com

 

በዉጭ አገር የሚኖሩ የኦሮሞ ብሄረተኖች፣ በዶር መራር ጉዲና የሚመራዉን ኦፌኮ ጨምሮ በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች እና አንዳንድ የኦሮሞ ሜዲያዎች ያቀረቡትን ጥሪ በመቀበልና አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃዉሞ ማሰማታቸው በስፋት ተዘግቧል።

መቅደም ያለበትን ላስቀድም። ተማሪዎቹ ጥያቄዎቻቸዉን ያነሱት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ነው። በፌደራል ፖሊስ የደረሰባቸው ድብደባ ልብን የሚያቆስል ከመሆኑም ባሻገር  መወገዝ አለበት። በዚህ ጉድያ ላይ፣  ሌላ አቋም ይዞ የሚከርከር ካለ፣ ለሰብአዊነት ደንታ የሌለው ሰዉ ነው ብዬ ከማለፍ ዉጭ ብዙ የምለው አይኖረኝም።

የኦሮሞ ድርጅቶች ሆነ ተማሪዎች አዲሱን ማስተር ፕላን የተቃወሙበት ሁለት ጥንድ ምክንያቶች ሊኖሯቸው ይችላል ብዬ አስባለሁ። አንደኛው፣ በልማት ስም የኦሮሞ ገበሬዎች አግባብ በሌለው መልኩ መፈናቀል የለባቸውም የሚል ነው።

በልማት ስም፣ ወይንም የአንድ ቋንቋ ተናገሪ በመሆናቸው ምክንያት ሰላማዊ ዜጎችን የማፈናቀሉ ተግባር፣  ላለፉት ሃያ አመታት በአገራችን በስፋት ሲታይ የነበረ አሳዛኝ ክስተት ነው። እነዚህ የኦሮሞ ድርጅቶች፣  የኦሮሞ ገበሬዎች ለምን ተፈናቀሉ በሚል አሁን እየተከራከሩና እየጻፉ እንዳሉት፣ በኦሮሚያ ዉስጥ «ይሄ አገራችሁ አይደለም እየተባሉ» ዜጎች ሲባረሩና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሲፈጸምባቸው፣ በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች በልማት ስም ቤቶች ሲፈርሱ»  ለምን ብለው ድምጻቸውን አሰምተውን ቢሆን ኖሮ ለነርሱ የበለጠ ከበሬታ ይኖረን ነበር።

የኦሮሞ ገበሬዎች በኦሮሚያ ዉስጥ በጂማ፣ በኢሊባቡር፣ በወለጋና  በመሳሰሉት   በኦሮሚያ ክልል መንግስት ተፈናቅለው መሬታቸው ለባለ ሃብቶች የተሰጠበት ሁኔታ  እንዳለ እናውቃለን። ገበሬዎቹን ሆነ ሌሎች ዜጎችን የማፈናቀል ተግባር፣ ከኦሮሞነት ጋር፣ ወይንም በአዲስ አበባ ስር ከመሆን ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። ዜጎችን በቅያቸው የማፈናቀሉ ጉዳይ መንግስት ከሚከተለው የመሬት ፖሊሲ ጋር የተገናኘ ነው። መሬት የመንግስት እስከሆነ ድረስ በኦሮሚያ ክልል አስተዳደሪ ትእዛዝ ይሁን፣ በአዲስ አበባ ከንቲባ ትእዛዝ ፣ ዜጎች በግፍ ፣ በቂ ካሳ ሳይከፈላቸው እንዳይፈናቀሉ የሚገታ ምንም ነገር የለም። ስለዚህ የሚበጀው ፣ የኦሮሞ ገበሬዎችን ጨምሮ ማንኛዉም ዜጋ የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ መታገሉ ነው።

ሁለተኛው ተቃዉሞ የተሰማበት ምክንያት፣  በቀጥታ ተቃዉሞ እያሰሙ ካሉ የኦሮሞ ተማሪዎች ጋር በሃሳብ የሚያላትመኝ ጉዳይ ሆኖ ነው ያገኝሁት። «ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት። ፊንፊኔ የኦሮሞዎች ናት»  የሚለው መፈክራቸው ፣ እጅግ በጣም መርዛማ ከመሆኑም የተነሳ አገሪቷን ወደ ከፋ የዘር ጦርነት የመዉሰድ አቅም ያለው ነው። ይህ አይነቱ ፖለቲካ ከዉጭ በነጃዋር ሞሃመድ እየተጠነሰሰ ሲሠራበት የነበረና፣ በየድህረ ገጹና ሶሻል ሜዲያዉ የተረጨ  ሲሆን  ይኸው ዉጤቱም በመጠኑም ቢሆን በአንዳንድ የኦሮሞ ተማሪዎች ሲንጸባረቅ ለማየት እየቻልን ነው። ይህ መርዝ በአስቸኳይ እንዲመክን ካልተደረገ፣ በኦሮሞዎች እና በአማራዎች፣ በኦሮሞዎች እና በጉሙዞች፣ በኦሮሞዎችና በሶማሌዎች፣ በኦሮሞዎች እና ከፊቾዎች …መካከል የዘር ግጭት በስፋት ሊሰራጭ ይችላል። ይህም ደግሞ በዋናነት የኦሮሞ ማህበረሰብን ከሌላው ጋር በማጋጀት ፣ በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያመጣል።

ይህ አይነቱን ፖለቲካ ፊት ለፊት መጋፈጥና መቃወም ያስፈልጋል። ከአሁን ለአሁን የተቃወሙት አገዛዙን  ነው በሚል፣ ዝም ተብለው ሊታለፉ አይገባም።

«ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ ናት። ኦሮሚያ እየተወረረች ነው ! ፊንፊኔ የኦሮሚያ ናት…» የመሳሰሉትን  ከፋፋይና ጠባብ መፈክሮች ሲያሰሙ የሰማናቸው እነዚህ የኦሮሞ ተማሪዎችና በዉጭ ያሉ የኦሮሞ አክራሪዎች፣ ከገበሬዉ የሰብአዊ መብት ይልቅ፣  ከሃያ አመታት በፊት በኦነግ እና በሕወሃት በኃይል በሕዝቡ ላይ የተጫነዉን የኦሮሚያ ካርታ፣ መለወጡ ያሳሰባቸው ነው የሚመስለኝ። ከአሁን ለአሁን አዲስ አበባ ከሰፋች፣ ማስተር ፕላኑ ከጸደቀ፣ ኦሮሚያ ለሁለት ትከፈላለች የሚል ፍርሃት ሳይገባባቸው እንዳልቀረ ነው። ምናልባትም ኦሮሚያ ሬፑብሊክን የመመስረት እድላችንን ያጨልምብናል የሚልም ስጋት ሊኖራቸውም ይችላል።

ነገር ግን አንድ የዘነጉት ነገር አለ። አብዛኞቻችን ዝም ስንልላቸው፣ እነርሱ የሚጩኹት ጩኸት የበለጠ ተሰሚነት ያገኝ እየመሰላቸው ነው። አዲስ አበባ ዋና ከተማችን ናት። ማስተር ፕላን ኖረም አልኖረም አዲስ አበባ ትሰፋለች። እስከአሁንም የሰፋችው ማስተር ፕላን ኖሮ አይደለም። አዲስ አበባ ኦሮሞዉ፣ ሱማሌዉ፣ ትግሬው፣ አማራዉም ፣ ድብልቁም ..ሁሉም ያለ ፍርሃትና ያለ ሰቀቀን የሚኖሩባት ከተማ ናት። አዲስ አበባ በኦሮሚያ እንዳሉሌሎች ከተሞች፣ ኦሮሞዎች ብቻ የሚመረጡበትና የሚመርጡባት፣ ሌሎች በሰቀቀን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የሚኖሩባት፣ አፓርታይድ የሰፈነባት ከተማ አይደለችም። አዲስ አበባ የሁሉም ናት። ሕዝቡ ከሁሉም አቅጣጫ በአዲስ አበባ መኖር ይፈልጋል። በዘረኝነት አጥር መታጠር አይፈልግም። መሻሻል ይፈልጋል። ወደ አዲስ አበባም ይጎርፋል። በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ አደገች። የሕዝቧም ቁጥር ጨመረ።

በቅርብ ጊዜ ዉጥ ናዝሬት እና አዲስ አበባ ፣ አዲስ አበባ እና ደብረ ብርሃን፣ አዲስ አበባና ወሊሶ፣ አዲስ አበባና አምቦ ይገጥማሉ ተቦ ይጠበቃል። ከአዲስ አበባ ናዝሬት ያለው ሰፊ መንገድ ተጠናቋል። በኢኮኖሚና በሕዝብ ለሕዝብ ትስስር አኳያ ካየነው ፣ አዲስ አበባ እና አዳማ ገጥመዋል ማለት ይቻላል።  አዲስ አበአ እየኖሩ ናዝሬት የሚሰሩ፣ ናዝሬት እየኖሩ አዲስ አበባ የሚሰሩ ቁጥራቸው እየበዛ ነው። በቦሌ ያለው ኤርፖርት ብቃት ስለሌለው ፣ አዲስ አይሮፕላን ማረፊያ በቴሲ ከተማ ሊሰራ ነው። ቴሲ፣ ሰበታን አልፎ በአዲስ አበባ እና በወሊሶ መሃከል ያለች ናት። ኤርፖርቱ ሲጠናቀቅ ፣ የዚያኑ ያህል የኢኮኖሚክ እንቅስቃሴውም ያድጋል። አካባቢዉ ከአዲስ አበባ ጋር ትስስሩ የበለጠ እየጨመረ ይመጣል። ይሄም ደግሞ የሆነው በማስተር ፕላኑ ምክንያት አይደለም። የሕዝብ እንቅስቃሴ ነው። የሕዝብ እንቅስቃሴን ደግሞ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንደ በርሊን ግንብ አይነት ፣ ካልተሰራ ማቆም አይቻልም። እነርሱ የሕዝብን እድገት ማፈን፣ ህዝቡን በዘር አጥር አሸገው ማስቀመጥ ቢፈልጉም፣ ህዝቡ ግን አይሰማቸው። ተሸናፊ የሚሆኑት እነርሱ እርሳቸው ናቸው። (በነገራችን ላይ የዉሸት አፈታሪክ ላይ ተመርኩዘው የአኖሌን የጥላቻ ሃዉልት የገነቡ፣ ነገ የአዲስ አበባን ግንብ እንገባ ቢሉ የሚያስደንቅ አይሆንም)

እንግዲህ «አዲስ አበባ ለምን አደገች፣ ተወረርን» የሚለውን ጠባብ አመለካከት መያዝ ሳይሆን  የሚያዋጣዉ፣ «አዲስ አበባ በምታድግበት ጊዜ ሁሉንም በጠቀመና ፍትሃዊነት ባለዉ መልኩ ይሁን» በሎ መከራከሩ ነው። በተለይም ከላይ እንደገለጽኩት መሬት የመንግስት ነው በሚል ዜጎችን በኃይል የማፈናቀል  ተግባር እንዲቆም አስፈላጊዉን ግፊትና ጫና ማሳደሩ በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። ይህ የዘር ወይንም የጎሳ ጉዳይ ሳይሆን የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው።

የኦሮሞ ተማሪዎችንም ሆነ ድርጅቶች የኦሮሚያ የዘር ጠባብ ጥያቄዎችን ማንገብ አቁመው፣ የሰብአዊ መብት ጥያቄዎች ያንግቡ እላለሁ። ያኔ እኛም ከጎናቸው እንቆማለን። አሁን ግን «ኦሮሚያ ለኦሮሞዎች» ካሉ መንገዱን ጨርቅ ያርግላቸው። እነርሱን ከማንም በላይ  የምንታገልና የምንቃወም እንጂ የምንደግፍ አንሆንም። አዲስ አበባ የሁላችንም ናት። ቡራዪ፣ ሰበታ፣ ለገጣፎ፣ አምቦ፣ ወለጋ፣ ኢሊባቡር የሁላችንም ናቸው።

 

 

ክብርነቶ  በተናገሩበት  ሳመንት? (ከዳዊት ዳባ)

$
0
0

ከዳዊት ዳባ

Sunday, April 27, 2014

Commentሰኞ መያዚያ 13 2006  ባሌ ውስጥ የሁለት ንፁሀን ዜጎችን መገደል በመስማት ሳምንቱን ጀመርነው።  አገዳደላቸው    ወንጀላችሁን ከባድ ያደርገዋል። የመጀመርያው ልጅ በቁጥጥራችሁ ስር ነበር። በህግ አግባብ መጠየቅ ስትችሉ ነው በነጻ እርምጃ የገደላችሁት። አፉ ውስጥ ሽገጥ አስገብታችሁ ተኩሳችሁ። በሚቀጥለው ቀን ይህን ግፍ ዜጎች ስለተቃወሙ  ሌላ ዜጋ ደግሞ በቀን ብረሀን ገደላችሗል።

ማክሰኞ  መያዝያ 14 2006  አፋር ውስጥ አስር ንፁሀን ተገለዋል። ከቦታው ያንድ እህት ምስክርነት።” እኔ አራሴ  የቆምኩት ስምንት እሬሳ ላይ ነው። ይህ የመጀመርያ አይደለም። በየቀኑ አምስት ልጅ፤ ስድስት ልጅ፤ ሰባት ልጅ፤ ስምንት ልጆች እየቀበርን ነው። ገዳዬች ፌደራል ፖሊሶች ናቸው። እጅግ ለጆሮ በሚከብድና በሚያሳዝን ሁኔታ ልጆ መገደሉ ሳያንስ ነብሰ ጡር  እህትም በጽኑ ተጎድታለች። ይህቺ እህታችን ሳትሞትም አልቀረችም’”። በዚሁ ቀን ጋንቤላ ዲማ ላይ መከላከያ ሰራዊት አባለት አስገድደን ፍቶወት ካልፈጸምን ብለው ባስነሱት አንባጓሮ ከመከላከያ ሶስት ከፌደራል አንድ ሞተዋል። “ጋዜጠኛ መሳይ ዝሆኖች ሲጣሉ” ብሎ እንደገለጸው ይህ ገጠመኝ ቁጥሩ ከራት በላይ የሆኑ ንፁሀን ዜጎች ሂወት ያለአግባብ እንዲጠፋ አድርጓል  ። ህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚታገሉት ድርጅቶች ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ አስራ ስምንት አባላቱ ምንም ወንጀል ሳይሰሩ በዚሁ እለት ታስረውበታል።   የአገሪቷ ህግ ተቃውሞ ለማድረግ ፍቃድ የማያሻ መሆኑን ቢደነግግም በዚሁ እለት አንድነት  ፍቃድ ከለከልንህ ብላችሁታል።

እሮብ መያዝያ 15 ካመት በፊት ዴሬደዋ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ በተያያዘ የታሰረ ዳንኤል ጎሳ የሚባል ዜጋ አሰቃይታችሁ ገድላችሗል። ይህ ወገን ደብደባ ሲፈፀምበት ነበር። ለእሬሳ ምርመራ ፖሊስ ከቤተሰቡ ጋር ወደ አዲስ አበባ ተልኳል። የተላከው ፖሊስ ገዳዩ  እራሱ አለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም።  የሬሳ ምርመራው አምስት ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ተጠናቋል። ሐኪምቤቱ የሬሳ ምርመራ ውጤት ቅጂውን እንኳ  ለቤተሰቡ አልሰጥም ነው ያለው። ባንፃሩ አባት አበበ ጎሳ ልጄን ገድሏል ብለው ከጠረጠሩት አካል ነው የምርመራውን ውጤት ያገኛሉ የተባሉት። አቶ አበበ ያላቸው አንድ  ልጅ ብቻ ነው። እሱኑ ነው የገደላችሁባቸው።  ልጅ የሙት ልጅ ነው። አባት በወንድ አቅማቸው  ብቻቸውን ሆነውና መከራ አይተው ያሳደጉት መሆኑን ተናግረዋል። እናንተ እንዳላችሁት እራሱንም ያጥፋ ወይ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ይገደል በናንተ እጅ እያለ ስለሞተ መንግስቶት ተጠያቂነት አለበት።

ሐሙስ መያዚያ 16  ጎንደር ጪንጋ ላይ ዜጎች ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ የመብት ጥያቄ ማንሳት ከጀመሩ ቀናቶች ተቆጥረዋል። ይህን ምክንያት አድርጋችሁ አራት ዜጎችን ገድላችሗል። እንዲሁ አንድ ፖሊስ ሞታል ሌላ ቆስሏል። ነዋሪው ተቃውሞ ሲያሰማ የነበረው መሳርያ ሳይዝ ስለነበር ህዝብ  ፖሊሶቹ እርስ በእራሳቸው ተጋዳድለዋል እያለ ነው። እነዚህ ፖሊሶች የሞቱትም ሆነ የቆሰሉት በየትኛውም መንገድ ይሁን ወናው ጉዳይ  እናንተ   በተሸነፋችሁ ጊዜ ወይ ከዛም በሗላ አልቻልንም ብላችሁ ስልጣን ስላለቃቅችሁና ሁሌም ችግሮችን ሁሉ  በምትፈቱበት የሀይልና ግጭት ያለበት መንገደ ምክንያት  ስለሆነ አሁንም ለነዚህም ዜጎች ሞትም በቀጥታ ተጠያቂ ናችሁ። በዚሁ እለት  የቆሰሉት ዜጎች ብዙ መሆናቸውና ባህር ዳር ሆስቢታል ልህክምና መግባታቸውን ሰምተናል።  አስራ ስድስት ተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ማታሰራቸውንም በዚህ ቀን ነው የሰማነው።

አርብ መያዚያ 17 የሰላማዊ ፓርቲ ሰላሳሶት አባላት ሊቀመንበሩን ጨምሮ መታሰራቸውን ሰምተናል። እነዚህ ዜጎች ያለምንም ጥፋት የታሰሩት  ለሰላማዊ ሰልፍ ህዘብን ሲቀሰቀሱ በነበረበት ጊዜ ነው። የጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ዘግናኝና ልታፍሩበት የሚገባ ግብራችሁን  የሰማንበትም ቀን ነው። የዞን ዘጠኝ ስድስት አባላትም መታሰራቸውን የሰማነው በዚሁ ሳምንት ነው። መብራት አገልግሎት ለረጅም ጊዜ እያገኘን አይደለም ያሉ የሽሮ ሜዳ አካባቢ ነዋሪዎችን አፍሳችሁ አስራችሗል።

ቅዳሜና እሁድ ዜና ሰለሌ ነው እንጂ ግድያው፤ እስሩ፤ ማንገላታቱ ይኖራል። ግፋችሁን በማጋለጥ እንኳ እኩል ልንራመድ አልቻልንም። ጨርሼ ሳለቀው ሌላኛው ሰኞ መጥቶ ይህም ሳምንት እንዲሁ በመገደል በማሰር በማሸበር መጀመሩን እየሰማው ነው። በቀጣይ ያንድነት ሰላማዊ ተቃውሞ አለ። የስልምና እምንት ተከታይ ወንድሞቻችን ጥያቄያቸውን ለማስመለስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አለ። አስተዳድራችሁ አድሏዊ ሆኖ እያለ አዲስ አበባን እናስፋፋለን በሚል ደሀ ዜጎችን ከመሬታቸው ለማፈናቀልና ለማኝ ለማድርግ የዘየዳችሁት እቅድ መረረ ተቃውሞ ከዜጎች እየስነሳ ነው። ጎንደር፤ ጋንቤላ ባጠቃላይ በመላ አገሪቱ የለውጥ ፍላጎት እየተንቀለቀለ ነው። ሰንቱን ገድላችሁ፤ ስንቱን አስራችሁና አሰቃይታችሁ እንደምትወጡት የምናየው ይሆናል።

ይህን እንዳስብ ያደረገኝ ሰባቱንም ቀን በየቀኑ በግፍ ስለተገደሉ እንሰማባቸው የነበሩ ሳምንታት እጅግ ብዙ መሆናቸውን ስለታዘብኩ ነው። በሳምንት አምስቴ፤ ሶስቴ ወይ አንዴ መስማት የተለመደ ነው። የታሰረውን፤ ግፍና ስቃይ የተፈፀመበትን  ወይ ያሰደዳችሁትን ዜጋ ጨምረን እንይ ካልን ይህን አይነቱ ወንጀል ሳይፈፀምና እኛም ሳንሰማ ያሳለፍነው ቀን ማግኘት  አይቻልም። ይህ እንግዲህ የመገናኛ ሽፋን ለማግኘት የቻለው ብቻ  ተወስዶ ነው።

በእርግጥ ንፁሀን ዜጎችን መግደል ማሰር ማሰቃየት ማሰደድ ትግል ላይ እያሉም ያለቆቾ  ዋና ሞያቸው እንደነበረ ብዙዎች መስከረዋል። ሚኒልክ ቤተ መንግስት ከገባችሁ ሀያ ሶስትኛ አመታችሁ ላይ ናችሁ። ታዲያ ከሀያ ሶስት አመት በሗላ ዛሬስ ነጻ እርምጃን  ማቆም ቻላችሁ ወይ ነው ጥያቄው?።  የለመግባባቶችን፤ ልዩነትን ሳትገድሉን ዜጋውን ሳታሸብሩ መፍታት ትችላላችሁ ወይ ነው ጥያቄው?። ከላይ እንዳዩትና ልትክዱት የማያችላችሁ ይህ ችግር ከአመት አመት የሚጨምር እንጂ የሚቀንስ በጭራሽ አልሆነም። ስለዚህ መልሱ ባጭሩ አልቻላችሁም ነው። በእርግጥም ይህን የሀያሁለት አመት እብደት ላየ  መግደልና ግፍ መፈፀም እንዳትችሉ እስክናደርጋችሁ ወንጀላችሁ አይቆምም ብሎ ድምዳሜ ዜጋው ላይ ባይደርስ ሲፈጥረው ጅላንፎ ሆኖ ነው ማለት ይቻላል። እርሶ እራሶ ዘላለማዊ ከብርና ሞገስ ብለው ማሀላ ፈፅመው  ስልጣን ከያዙ በሗላ እንኳ ብዙ ንፅሀን ዜጎች በነጻ እርምጃ ተገለዋል። ያለጥፋታቸው ዜጎች በገፍ እየታሰሩና ስቃይ እየተፈፀመባቸው ነው። የታዘለች ህፃንም አልቀረላትም። ይህን አይነት መንግስታዊ ሽብር በሚፈፀምበት አገር ለአፍ ካልሆነ ፖለቲካ ማህደሩ ስፍቷልም ጠቧልም ብሎ መከራከር ልብ ድክም ማድረግ ነው።

በጠቅላላው የስልጣን ዘመናችሁ የፈፀማችሁት ፍጅት ቢወዳደር ከደርጉ የሚብስ ይመስለኛል። ምክንያቱም  በዚህ ደረጃና በማያባራ ሁኔታ በየቀኑ በግፍ ስለሚገደሉ ስለሚታሰሩ ሰቆቃ ስለሚፈፀምባቸው ንፁሀን ዜጎች በኔ እድሜ ያኔ አይሰማም ነበር። በርግጠኛነት ግን እስቲ ቦንብ አፈንድተን ሀያ ሰላሳ ሰው እንግደልና የዜጋውን ስሜት እናጥና ወይ ፖለቲካ እንስራበት ብለው ፍጅት የሚፈፅሙ መሪዎች አልነበሩም።” ጦርነት ሰርተን” የምትባለው አለቆቾ የሚወዷት የጫወታ አይነትን ማለቴ ነው።

ደርጉም አንባገነን ስርአት ስለነበር ሰፈራ የመሳሰሉ ግብታዊና ጎጂ እቅዶችን ተግባራዊ አድርጓል። ዜጎች ያልተስማሙባቸውና አምርረው የተቃወሟቸው ቢሆንም  እንደናንተ ያጉረመረመውን ሁሉ በገፍ መግደል ወና የቅዱ ማስፈፀሚያ  ግን አልነበረም።  ሰበብ አይሁን ለማለት ነው። ህንፃ ለመግንባት፤ መንገድ ለመስራት፤ አበባ ለመትከል  የንፁሀን ሂወት እስርና ስቃይ የግንባታዎቹ ሁሉ መሰረቱ እኮ ነው የሆነው።  ይህ የባህሪያችሁ ከመሆኑም በተጨማሪ ሁላችሁም ጋር ከፍተኛ የማስተዳደር እውቀት አለ ማለት ብቻ ነው የሚቻልው።

ክብር የሆነው ለሰው  ልጅ ሂወት የሚሰጠው ዋጋ ከፍተኛ በነበረበት ዘመን ዜጎች ግዛው ለምን ለምን ሞተ? ማርታ ለምን ለምን ሞተች ብለው ጉሮሮ ሊይዙ ይደርሱ እንደነበር ያውቃሉ። ዛሬ ከአንድ እስከ አስር ዝም ብሎ ዜናችን ነው። ለምን ተብሎ መጠየቅ አይደለም ገደሏቸው እኮ ተብሎም በቀጣይ አናወራበትም። ሀምሳ፤ መቶና ሶስት መቶ አዲስ ቁጥር አየደለም። ከዚህ በፊት አድርጋችሁታላ። ያዋጣል ካላችሁ ግን ለወደፊቱም በርቱ። ይህን በሚመስል እውነታ ውስጥ ጊዜና ሁኔታ ይመቻቻል። ያኔ  ገደላችሁ አይደለም ገላመጣቸሁ የስልጣናችሁን ፍፃሜ እንደሚያደርገው  እነግሮታለው።  ማወቅ ያለቦት የተለወጠ ነገር የለም ያው ኢትዬጵያዊ ነው።

በግሌ  ስልጣኑ የያዙ ለት ያደረጉትን ንግግሮትን ካዳመጥኩበት ጊዜ ጀምሮ ሁሌም ሳዮትም ሆነ ስሰማዎት አብሮአደጌን ሞዘዘኝን ነው የሚያስታወሱኝ። በዛኑ  ሰሞን በፃፍኩት ፅሁፍ ስለዚሁ ጉዳይ ልነግሮት ነበር። ሰው ናቸው የሚሉ ሲበዙ አልቸኩል ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ተውኩት። ይህን ክፍል ጎርጄ በሌላ ገፅ ላይ አኖርኩት። ዛሬ ኮፒ ፔስት ነው ያደረኳት። በርግጥ ሰበአዊነት ያለበትና ልጆቼ ተቆጡኝ። ፀለይኩኝም የምትለዋ ቃለ መጠይቆት አጭበርብራኝለች።

ልጆች ሆነን ከልጅነቱ ጀምሮ የመጨረሻ ገንገበት የነበረ ልጅ ነበር።  ለዚህ ልጅ የሆነ ጊዜ ላይ ይህን ባህሪውን ያየ ሌላኛው አብሮ አደጌ  ሞዘዘኝ ብሎ የቅጥል ስም አወጣለት። ገንገበቶች ገገማ ስለሆኑ   እንደተጠመቀበት ወይ እንደሰለጠኑበት ጉዳይ ነው ለመሀበረሰቡ  ጠቃሚም ጎጂም የሚሆኑት። አክራሪ የእምነት ሰው፤ ወይ ገገማ  ቀልደኛ፤  ጨካኝ መርማሪ ወይ ለእውነት  የሚሞት ዳኛ ወይ የሚያናድድ ሊስትሮ ጠራጊ ሊሆኑ ይችላሉ። ሞዘዘኝ ከፍ ሲል የሰፈር የጠብ ቡድን አገኘው። ከዛ  አንዷን ጡቷ ላይ በጩቤ ወጋት፤ እትዬ እንትናን በድንጋይ ፈነከታቸው። የዛን ሰፈር ልጅ በብረት ሰንሰለት ቀጠቀጠው። ብቻ ስሙ ባንዴ ዝነኛማ ተፈሪም ሆነ። የጠብ ቡድን ውስጥ ደግሞ ድርሻቸው ማካበድና ማሟቅ የሆነ አሉ። ሀይ ሀይ ስለበዛበት ሞዘዘኝ እስታ ሊል አልቻለም። ቆያይቶ  ተገደለ።

እርሶን ሳይ ትግሬ ተጋዳላዮች ምርጥ መጠቀሚያ ነው ከመንጋው መዘው ያወጡት እላለው። ገንገበቶችን  እንዲሞቃቸው በማድረግ ብቻ እንደፈለጉ ሊነዷቸው መቻላቸውን አውቀዋል። የዚህ አይነት ሰዎችን ምንም አይነት ወንጀል ማሰራት ቀላል ነው።  የሚፈልገው  ጎሽ አበጀህ፤ አቤት ድፍረት፤ ለርሶ ሲሆን ባለእራዩም እንዲህ ሊያሳምረው አይችልም ነበር። እስከዛሬም ተሳስተናል አይነት ሙገሳን መጨመር ነው።  በርግጠኛነት ከበቀደሙ የፓርላማ ውሎዎ መልስ ብዙዎች ይህን አይነት አስተያየት ሰጥተዎታል። ከዋኖዎቹ ለዚሁ ጉዳይ ተደውሎሎታል። ሙገሳ ያለበት ተመሳሳይ ነገርን ብለዎታል።  ለሁሉም መልክቴን ጠቅላይ ሚንስትሩ ሞዝዘውኛል።  ብዬ አቆማለው።

 

የሕግ አምላክ የሞተባት አገር፤ በሕገ መንግሥት ሳይሆን በወያኔ የጫካ ሕግ ለሃያ ዓመታት (ያሬድ ኃይለማርያም)

$
0
0

ያሬድ ኃይለማርያም

ከብራስልስ፣ ቤልጂየም

ሚያዝያ 23፣ 2006

Commentለከት ያጣው የወያኔ ጭካኔ እና የማይነጥፈው የሕዝብ ትእግስት ኢትዮጵያን ወዴት እየወሰዷት እንደሆነ አገሪቱ ዛሬ ያለችበት ውጥንቅጥ ሁኔታ በግላጭ ያሳያል። በመግደል አባዜ የተለከፉት የወያኔ ተጋዳላዮች ዛሬም መግደላቸውን ቀጥለዋል። ለይስሙላ በወረቀት ላይ የሰፈረው ሕገ-መንግስት እና በውስጥ የያዛቸው መሰረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች ለወያኔ ተጋዳላዮች ምናቸውም እንዳልሆነ በተደጋጋሚ እያሳዩን ነው። በአገሪቱ ውስጥ ያለው የሕግ ማእቀፍ (አንዳንዶቹ ሕጎች በራሳቸው የማፈኛ መሳሪያ ተደርገው የተቀረጹ መሆኑ ሳይረሳ) ለወያኔ ተጋዳላዮችና ተራ ካድሬዎች ሳይቀር ምናቸውም አይደለም። ሲሻቸው ይገድላሉ፣ ያፍናሉ፣ ይሰውራሉ፣ ባደባባይ ይደበድባሉ፣ ሺዎችን በየማጎሪያው ያሰቃያሉ፣ ያዋርዳሉ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ ይሞስናሉ፣ ይሰርቃሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ያስፈራራሉ፣ ሴቶችን ይደፍራሉ፣ ህዝብን ያሸብራሉ፣ ምኑ ቅጡ።

እንግዲህ የሕግ አምላኩ ሲሞት ሥርዓት አልበኝነት ይነግሳል፤ ዘራፊዎች ይበራከታሉ፣ ገዳዮች ባደባባይ ገድል ይጥላሉ፣ ሙሰኞች አገርን እና ሕዝብ ይቆጣጠራሉ፣ የአገር ሃብት ያሸሻሉ፣ በድሆች ጉሮሮ ላይ ቆመው በሃብት ይጨማለቃሉ። በዚህ ላይ ጎጠኝነት ሲታከልበት መላ ቅጡ ይጠፋል። ብዙዎቹ እየከሰሙ ያሉ አገሮች (failed states)እየተባሉ በየጊዜው የሚጠቀሱ አገሮች በእነዚህ ችግሮች ውስጥ የሚማቅቁ ናቸው። ወያኔም ለኢትዮጵያ የዋለላት አንዱ ትልቁ ነገር ከእነዚህ አገሮች ተርታ እንድትሰለፍ ማድረጉ ነው። እንደ ታላቅ ስኬት የሚቦተለክለት የዛሬዋ የኢትዮጵያ ልማት ውስጡ ሲገባ ላዩ አሮ ውስጡ ሊጥ እንደሆነ ዳቦ ስለመሆኑ ምንም ጥናትና የተለየ ምርምር ሳይጠይቅ 95% የሚሆነውን የአገሪቷን ሕዝብ ኑሮ ማየት በቂ ነው። አንጻራዊ በሆነ መልኩ በወያኔ ዘመን የመጀመሪያዎቹ አሥር አመት ውስጥ እንኳን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያገኛቸው የነበሩትን እንደ መብራት፣ ውኃ፣ የጤና አገልግሎትና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶቹ ዛሬ ተነፍጓል። የደብል ዲጂት ልማታዊነት ነጠላ ዜማዎች በወያኔ እና ባጫፋሪዎቹ የአለም አቀፍ ‘የልማት’ ተቋማት ጆሮዋችን እሲደነቁር በሚዘፈንበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ አስከፊ በሆነ የኑሮ ዋስትና ማጣት ውስጥ ሆኖ የመከራ እንቆቆውን እየተጋተ ይገኛል። የእነዚህ የመሰረታዊ አቅርቦቶች በዚህ ደረጃ ላይ አቆልቁሎ መገኘት አንኳን የቀለም አብዮት፤ ሌላም መገለጫ የሌላቸው አመጾችንና እልቂትን ቢወልድና በአገሪቱን ወደ ከፋ ብጥብጥ ቢከት የሚገርም አይደለም። ይሁንና እንደ ወያኔ ያለ ክፉ፣ መረን የማያውቅ እና ጨካኝ ሥርዓት እድለኛ ሆኖ ሆደ ሰፊ፣ የማይቻለውን ሁሉ የሚችል፣ ጨዋና ታጋሽ ሕዝብ ሲጋጥመው ጭካኔውን እያበረታ፣ የአፈና ሰንሰለቱን እያጠበቀ፣ አባላቱን በአሃብት እያሞሰንነና እያጎለበተ ይንሰራፋል። የአገር መፍረስ ወይም አደጋ ላይ መወደቅ የራሳቸውን ጥቅም አደጋ ላይ እስካልጣለ ድርስ ግድ የማይሰጣቸው ጎጠኛ ፖለቲከኞችም በደሃው ሕዝብ ላይ ይሰለጥኑበታል፤ ይሰይጥኑበታልም።

ሰሞኑን በአገሪቱ ውስጥ የሚስተዋለው የፖለቲካ ድባብ ወያኔ ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ አገሪቱን የሚዘውርበት መሪ ከቁጥጥሩ ውጭ እንዳይወጣ እየተውተረተረ ያለ መሆኑን ነው። ለዚህም ይመስላል ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ባንዲራና መፈክር ይዘው በተንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፤ በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን አስሮ እያሰቃየ ያለው። ለዚህም ነው በማኅበራዊ ድኅረ ገጾች በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የውይይት መነሻ ሃሳቦችን እያጫሩ ሕዝቡ እንዲወያይ ይጋብዙ የነበሩ የዞን 9 አባላትን ለቃቅሞ አጉሮ እያሰቃያቸው የሚገኘው። ይህም አልበቃ ብሎ ባለፉት ሦስት እና አራት ቀናት ውስጥ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ (ጥያቄያቸው ምንም ይሁን ምን) እያቀረቡ ያሉ የኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪ ዩንቨርሲቲ ተማሪች ላይ የተለመደውን የጭካኔ እርምጃ እየወሰደ ያለው። ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንደተገለጸው ከሆነ በርካታ ተማሪዎች በታጠቁ ሃይሎች የጭካኔ እርምጃ ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል። በተለይም በአንቦ ከተማ ተማሪዎች በግፍ ተገድለዋል። የወያኔ መንግሥት ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በተማሪዎች ላይ ተደጋጋሚ የጭካኔ እርምጃዎችን ወስዷል። በመላ አገሪቷ በወያኔ እርምጃዎች ከተጠቁት ተማሪዎች ውስጥ ግን ትልቁን ግፍ የተቀበሉት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ስለመሆናቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚመለከቱ ሪፖርቶች ይመሰክራሉ። በሥራዬ አጋጣሚ እኔም ይህን አረጋግጫለሁ።

ዛሬ ላለንበት ጠቅላላ አገራዊ ክሽፈት፣ ውርደት እና የመከራ ሕይወት ከላይ እንደጠቀስኩት ለከት ያጣው የወያኔ ጭካኔ እና አፈና፤ እንዲሁም የአለማችን ተጭባጭ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን  የማይነጥፈው የሕዝብ ትእግስት እና ዝምታም ትልቁን አስተዋጾ አድርጓል። በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ተማሪዎች ላይ፣ በጋዜጠኞች ላይ፣ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና ደጋፊዎች ላይ፤ እንዲሁም በኃይማኖት መሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል በጋራ ልናወግዘው እና ልንታገለውም ይገባል። በፍትሕ እና በኢ-ፍትሐዊነት፣ በጭቆና እና በነፃነት  መካከል ገለልተኛ ሆነው የሚንጠለጠሉበት ገመድ ወይም የሚቆዩበት ደሴት የለም። ፍትሕ ሲጓደል እያዩ እንዳላዩ መሆን በራሱ ኢ-ፍትሐዊነት ነው። መብት ሲጣስ እያዩ እንዳላዩ መምሰል በራሱ የጣሹ ግራ እጅ መሆን ነው። ንጹሃን ዜጎች በግፍ ሲገደሉ፣ ሲደበደቡ፣ ሲታሰሩ እና በሃሰት ክስ እየተፈረደባቸው በእስር ሲማቅቁ እያዩ ገለልተኛ መሆን አይቻልም። የፖለቲካ ገለልተኝነትን እና ለፍትሕ፣ ነጻነት እና ለህሊና መቆምን ባናምታታቸው ጥሩ ነው።

 

ለፍትህና ለነፃነት በመቆም የሰውነትም፤ የዜግነትም ግዴታችንን እንወጣ!

http://humanrightsinethiopia.wordpress.com/


ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!

$
0
0

ginbot 7ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲንቅናቄ፣ ዘረኛው ወያኔ በኦሮሚያ ሕዝብና ወጣቶች ላይ እያካሄደው ያለውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ እስርና አፈናን በጥብቅ ይቃወማል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ያስገነዝባል።

የአሮሚያ ወጣቶች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም የድሀ ገበሬዎች መፈናቀልን መቃወማቸው ፍትሀዊ ነው። የወያኔ “ማስተር ፕላኖች” የወያኔ የዘረፋ እቅዶች መሆናቸው በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው። ነዋሪዎቹን ያላማከረ፣ ግንባር ቀደም ባለጉዳዮችን ባለቤት ያላደረገ፣ የሕዝብ ይሁንታ ያላገኘ ማስተር ፕላን ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም።

ወያኔ ኦሮሚያን ብቻ ሳይሆን መላዋን ኢትዮጵያ በምስለኔዎቹ አማካይነት እየገዛ የኢትዮጵያን ውድ ልጆች በራሳቸው ጉዳይ ባይተዋር አድርጓቸዋል። ኦህዴድ በወያኔ ቅጥረኛነት የኦሮሚያ ወጣቶችን በማስጨፍጨፍ ላይ ያለ እኩይ የአድርባዮች ስብስብ ነው።  ወጣቶች የተቃወሙት ይህንን ነው።እነዚህ ወጣቶች በአካባቢያቸው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባቸዋል። ድምፃቸው ሊሰማ ይገባል። የሌላው አካባቢም ወጣት የኦሮሚያ ገበሬ መፈናቀል ያገባዋል። ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረግ ጉዳይ ሁሉ ያገባናል። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ወያኔ የራሱን እቅድ እንዲጭንብን አንፈልግም።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ወጣቶች ጥያቄ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ አድርጎ እንዲወስድ ጥሪ ያደርጋል።  በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል የተጀመረው መፈናቀል ዛሬ አዲስ አበባ አጎራባች ከተሞች ደርሷል። በአምቦ ይህንን የተቃወሙ ወጣቶች በግፍ ተጨፍጭፈዋል፤ በሌሎች ቦታዎችም ላይ ግድያውና እስሩ በርትቷል። ወጣቱ  የጥይት እራት ሆኖ እስኪያልቅ መጠበቅ አንችልም፤ ሁሉም ትግሉን ይቀላቀል።

የወያኔ የጥቃት ሰለባ የሆኑት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይን ያነሱ ወጣቶች ብቻ  አይደሉም። በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የወያኔን አምባገንነት የተቃወሙ በሙሉ የጥቃቱ ሰላባዎች ናቸው። ለሰልፍ ቅስቀሳ አደረጋችሁ በሚል የታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ሰልፉ ተደርጎ  ካለቀ በኋላም አልተፈቱም።  ይህ ሰቆቃ ማብቃት አለበት።

ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

አንድነት ፓርቲ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ “የእሪታ ቀን” በሚል ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ ይቀላቀሉ! (ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር)

$
0
0

ጤና ይስጥልኝ !

 

ግዛቸው ሽፈራው እባላለሁ። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር ነኝ።  አንድነት በኢትዮጵያ ሕጋዊ ፍቃድ አግኘቶ፣ በአገሪቷ ባሉ ክልሎች ሁሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀሰ ድርጅት ነው። አንድነት ከማንም ግለሰብና ድርጅት ጋር ፀብ የለዉም። የአንድነት ፖለቲካ የኢትዮጵያዊነት፣ የፍቅርና የመቻቻል ፖለቲካ ነው።  አላማችን ፣ የበለፀገች፣ ልጆቿ፣ በዘር ፣ በሃይማኖት፣ በጾታ ልዩነት ሳይደርገባቸው እኩል የሆኑባት፣ አንድነቷና ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን መመስረት ነው።

GizachewShiferaw

ግዛቸው ሽፈራው , የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀመንበር

 

አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢሕአዴግ መራሹ መንግስት፣  ግልጽነት የጎድለው፣ ተጠያቂነት የሌለው፣ በሙስና የተዘፈቀና የመልካም አስተዳደር ችግር ያለበት እንደመሆኑ፣  በሕዝብ ላይ ትልቅ በደል እያደረሰ ይገኛል። የሚከተለው የተሳሳተና ጎጂ የመሬት ፖሊሲ፣  ዜጎች፣ በልማት ስም፣ በቂ ካሳ ሳይከፈላቸው፣ ከቤታቸው እና ከእርሻ ቦታቸው በኃይል እንዲፈናቀሉ እያደረገ ነው። የሰብአዊ መብት ረገጣው፣ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ….. በግፍ መታሰራቸው፣ የኑሮ ዉድነቱ ሕዝቡ ከሚሸከመው በላይ እየሆነበት ነው።

 

ሕዝባችን ከዚህ የተሻለ ይገባዋል።  ኢትዮጵያዉያን አሁን ያለውን አሳዛኝ ሁኔታ አንቀበለም በማለት፣ ለዉጥ መጠየቅ፣  ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረግ ይኖርብናል።

 

ሕዝቡ ድምጹን ማሰማት የሚችልበት መድረክ ያገኝ ዘንድ፣ አንድነት፣ በሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እውቅና ያገኘበት፣ ሁለት ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎችን ፣ እሑድ ሚያዚያ 26 ቀን፣ በአዲስ አበባ እና በደቡክ ክልል በምትገኝ የድራሼ/ጊዶሌ አዘጋጅቷል። የአዲስ አበባ እና የጊዶሌ ነዋሪዎች፣ በነቂስ ወጥተው ድምጻቸውን እንዲያሰሙ በአክብሮት ጥሪ አቀርባለሁ።

 

ነጻነት ነጻ አይደለም። ነጻነትን ከሌሎች አናገኝም። ነጻነትን እኛዉ እራሳችን ነን ለራሳችን ማወጅ የምንችለው። እራሳችንን በግል ካያነው፣ ምንም ማድረግ የማንችል፣  አንድ ተራ ሰው አድርገን ልንቆጠር እንችላለን። ነገር ግን ተራ ሰዎች፣  በሚሊዮን ሲቆጠሩ፣ እነርሱን ማነቃነቅ የሚችል ምንም ኃይል አይኖርም። እንነሳ። ሰልፍ እንዉጣ። ድምጻችንን እናሰማ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን ! እራሳችንን ነጻ በማወጣት አገራችንን ነጻ እናውጣ !

 

እንግዚአብሄር አገራችን ኢትዮጵያን ይባርካት

 

ግዛቸው ሽፈራዉ

 

 

 

 

የአዲስ-ኦሮምያ ጉዳይ በመቐለ-እንደርታ ዓይን –ከአብርሃ ደስታ

$
0
0

Wallaggaa2014_3

ስለ አዲስ አበባ ማስተር ፕላንና የኦሮምያ አርሶአደሮች መፈናቀል ጉዳይ በፃፍኩት ላይ “የኦሮሞ ተማሪዎች ዓመፅ ከብሄር አንፃር አትየው፤ መታየት ካለበት አርሶአደሮቹ ከቀያቸው ካለመፈናቀል መብት አንፃር ነው” የሚል አስተያየት ደርሶኛል። እኔም ይሄን ጉዳይ በቅርበት ከማውቀው የመቐለ እንደርታ አርሶአደሮች ልምድ አንፃር ልየው ይፈቀድልኝ።

በመቐለ የከተማ ዕድገት ፕላን መሰረት አንዳንድ በከተማው ዙርያ የሚገኙ የገጠር መንደሮች ወደ መቐለ ከተማ ይገባሉ። ይህንን ዉሳኔ ባከባቢው አርሶአደሮች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞታል። አርሶአደሮች የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ሞክረዋል። የክልል ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጣልቃ ገብተው የኃይል እርምጃ ወስደው ሰልፈኞቹን ደብድበው፣ አስረው፣ ገድለው ዓመፁ ለግዜው አስቁመውታል። ጥያቄው ግን እስካሁን ድረስ አለ። በዚህ ምክንያት ያከባቢው አርሶአደሮች የመንግስት አገልግሎት ተነፍገዋል። አርሶአደሮቹም ከመንግስት ጋር ላለመተባበር አድመዋል። ለምሳሌ የእግሪሐሪባ አርሶአደሮች ልጆች የመማር መብታቸው ተነፍጓል። የነዚህ አርሶአደሮች ልጆች ለምን እንዳይማሩ ተከለከሉ? ወላጆቻቸው መሬታቸው ወደ ከተማ መግባቱ በመቃወማቸው ምክንያት ነው። የትግራይ ክልል ባለስልጣናት “የወላጆቻቹ መሬት የከተማ እንዲሆን ካልፈቀዱ እናንተ ህፃናት እዚሁ ትምህርትቤት አትማሩም። ምክንያቱም ይሄ ትምህርትቤት የከተማ ሆኗል” አሏቸው። እናም እስካሁን ድረስ እነኚህ ልጆች የመማር መብታቸው እንደተነፈጉ ነው።

“የገጠር መሬት ወደ ከተማ ሲገባ ለምን ይህን ያህል ተቃውሞ ይነሳበታል?” የሚል ጥያቄ መነሳቱ ተገቢ ነው። ከተማ ማደግ አለበት። ከተማ ሲያድግ በዙርያው ወዳለ የገጠር መንደር ይሰፋል። ግን ለምን አርሶአደሮች አምርረው ይቃወሙታል?

(አንደኛ) አርሶአደሮች ከቀያቸው መፈናቀል አይፈልጉም። ለመሬታቸው ልዩ ፍቅር አላቸው። የያለ መፈናቀል መብትም አላቸው (በመርህ ደረጃ)። አንድን አርሶአደር ያለፍቃዱ ከቀዩ መፈናቀል የለበትም። ግን መንግስት በኃይል ያፈናቅላቸዋል። መንግስት በአንድ በኩል “አርሶአደሮች መሬት ከተሰጣቸው ሽጠው ከቀያቸው ይፈናቀላሉ፣ ስለዚህ መሬት ሊሰጣቸው አይገባም” በሚል ስሌት መሬት የመንግስት አድርጎታል። በኢትዮጵያ ታሪክ አርሶአደሮች ከቀያቸው የሚፈናቀሉ በኃይል እንጂ በፍቃዳቸው አይደለም። በዘመነ መሳፍንት ግዜ አርሶአደሮች መሬት አልባ ጭሰኛ የሆኑ በኃይል እንጂ በፍቃዳቸው አልነበረም። አሁንም በመንግስት ትእዛዝ እንጂ በፍላጎቱ ከቀዩ የሚፈናቀል የለም። ስለዚህ ተቃውሞው ከቀያቸው ላለመፈናቀል የሚያደርጉት ትግል ነው።

ግን አርሶአድሮች ከቀያቸው ያለመፈናቀል መብት ካላቸው ለምን ወደ ተቃውሞና ዓመፅ ይሄዳሉ? አርሶአደሮች መፈናቀል አይፈልጉም። መንግስት በኃይል ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ያስገድዳቸዋል። መንግስት እንዲፈናቀሉ ሲያስገድዳቸው ለምን አቤት አይሉም? አቤት ለማለት’ኮ ገለልተኛ የፍትሕ አካላት መኖር አለባቸው። የፍትሕ አካላት ሲኖሩ ደግሞ የያለመፈናቀል መብት በሕግ የተደነገገ መሆን አለበት። ከመሬት የያለመፈናቀል መብት በሕግ የተደነገገ እንዲሆን መሬት የዜጎች መሆን አለበት።
mekele
አሁን በኢህአዴግ ሕገመንግስት መሰረት ዜጎች መሬት ተከራይተው የመጠቀም መብት እንጂ የመሬት ባለቤት የመሆን መብት የላቸውም። መሬት የዜጎች ሳይሆን የመንግስት ነው። ስለዚህ ዜጎች መሬት የመከራየት (ሊዝ የመሬት ኪራይ መሆኑ ነው) መብት አላቸው። ባለቤትነቱ ግን የመንግስት ነው። ስለዚህ አንድ ተካራይ ከተከራየሁት ቤት (መሬት) መልቀቅ (መነሳት) የለብኝም ብሎ መከራከር አይችልም። ተግባሩ ግን መቃወም ይችላል።

እናም አርሶአደሮቹ ከመሬታችን አንፈናቀልም ሲሉ መሬትኮ የመንግስት እንጂ የናንተ አይደለም፤ ስለዚህ ትነሳላቹ ይሏቸዋል። አርሶአደሮቹም “መሬትኮ የመንግስት መሆን የለበትም” ሲሉ “መሬት የመንግስት ካልሆነማ መሬታችሁን ሽጣቹ መሬት አልባ ትሆናላቹ። መሬት በጥቂት ሃብታሞች እጅ ይገባል” የሚል መልስ ይሰጣቸዋል። መሬታቹ ሌሎች ሊወስዱት ስለሚችሉ ቀድመን እኛ ወስደነዋል ዓይነት ማለት ነው።

ስለዚህ አርሶአደሮቹ መሬታችን አንሰጥም ብለው በሕግ ፊት እንዳይከራከሩ ሕጉ አይደግፋቸውም። ምክንያቱም ሕጉ መሬት ለዜጎች ሳይሆን ለመንግስት ነው የሰጠው። ስለዚህ የሕግ ድጋፍ የላቸውም። የህግ ድጋፍ ባይኖራቸው እንኳ ተግባሩ ትክክል አለመሆኑ ያውቃሉ። እናም ይቃወሙታል። መቃወም ሳይፈቀድላቸው ሲቀር ያምፃሉ። ሲያምፁ በኃይል ይደፈጠጣሉ። እናም አማራጭ ስለሌላቸው አኩርፈው ይቀመጣሉ። በኦሮምያ ግን ዓመፁን አቀጣጠሉት።

ስለዚህ የችግሩ መንስኤ የመንግስት የተሳሳተ የመሬት ፖሊሲ ነው። መሬት የህዝብ (የዜጎች) ቢሆን ኑሮ አርሶአድሮች ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብታቸው በሕግ ይከበርላቸው ነበር (ገለልተኛ የዳኝነት ስርዓት ሲኖር ማለት ነው)። ምክንያቱም መሬት የአርሶአደሮች ከሆነ ማንም ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ አያስገድዳቸውም ነበር። መሬት ለራሹ ከተሰጠ አርሶአደሮች ያለ ፍቃዳቸው ከመሬታቸው (ከቀያቸው) አይፈናቀሉም። ካልተፈናቀሉ ደግሞ መሬታችን ወደ ከተማ ይገባል ብለው ዓመፅ አይቀሰቅሱም ነበር። ስለዚህ የችግሩ ምክንያት የመሬት ፖሊሲው ነው።

(ሁለት) አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ አርሶአደሮች የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ይሄ የሚሆነው ግን አርሶአደሮችን በማሳመን (በፍቃዳቸው) ሁኖ ለመሬታቸው ተገቢ ካሳ (ራሳቸው በጠየቁት መሰረት) ሊከፈላቸው ይገባል። በመቐለ ዙርያ ያሉ አርሶአደሮች ግን ከመሬታቸው ተፈናቅለው ሲያበቁ በቂ ካሳም አይሰጣቸውም። የካሳ መጠን የሚወስነው መንግስት ነው (ካሳ የማያገኙም አሉ)። መሬታቸው አጥተው በቂ ካሳ ካላገኙ ከዚህ የባሰ መነቀል አለንዴ? ይህ ሲሆን እንዴት አይቃወሙም? የኦሮምያ ጉዳይም ተመሳሳይ ስጋት ሊጭር ይችላል።

(ሦስት) “መሬታቹ የከተማ አካል ሁኗል” በሚል ምክንያት አርሶአድሮች ከቀያቸው ያለፍቃዳቸውና ያለ በቂ ካሳ ከተፈናቀሉ በኋላ መሬቱ በሙስና ለሙሰኞች ይቸበቸባል። መሬት የመንግስት በመሆኑ እንዲሁም መንግስትና ገዥው ፓርቲ በመቀላቀላቸው ምክንያት የገዥው ፓርቲ ጥቂት ካድሬዎች መንግስት ሁነዋልና ከአርሶአደሮች የተረከቡትን መሬት እንደፈለጉ ለፈለጉትን ባለሃብት ይሸጡታል። መሬት ከአርሶአደሮች ነጥቀው ለራሳቸው ያደርጉታል። ወይ ይሸጡታል ወይም ደግሞ ህንፃ ያቆሙለታል። መሬት አይሸጥም አይለወጥም እየተባለ የመንግስት አካላት ግን እንደፈለጉ ይሸጡታል፣ ይለውጡታል። መሬት እንዳይሸጥ እንዳይለውጥ የተከለከለ አርሶአደሮቹ እንጂ መንግስትማ የፈለገ ያደርጋል። እናም ከአርሶአደሮች የተነጠቀ መሬት ለግል ሃብታሞች እየተሸጠ እየተመለከቱ እንዴት አይቃወሙም? እንዴት ለመሬታቸው አያምፁም? በኦሮምያም በእንደርታ የተተገበረውን እንደማይደረግ ምን ማረጋገጫ አለን?
ስለዚህ የመቐለ እንደርታ አጀንዳ በመውሰድ የአዲስ አበባ ኦሮምያ ጉዳይ መገመት ይቻላል። ጉዳዩ ከመንግስት የመሬት ፖሊሲ ጋር ይገናኛል።

“የኦሮምያ ተቃውሞ ፖለቲካዊ አጀንዳ አለው” ካላችሁኝም ያው ፖለቲካዊ ተልእኮ ሊኖረው ይችላል። ፖለቲካዊ ተልእኮ ያለው ዓመፅ ሲቀሰቀስምኮ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ መሰረት አድርጎ ነው። ፖለቲካዊ ዓመፅ የሚቀሰቀሰው ጭቆና ሲኖር ነው። የፍትሕ እጦት ሲኖር ነው። የዴሞክራሲ እጦት ሲኖር ነው። ነፃነት ሲታፈን ነው። ስለዚህ ዓመፁ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያለው ከሆነም ያው መንስኤው ደግሞ የኢህአዴግ ጨቋኝ አገዛዝ መሆኑ ነው። ምክንያቱም በሀገሪቱ ፍትሕ ቢሰፍን ኑሮ ዜጎች ፖለቲካዊ አጀንዳ ይዘው አያምፁም ነበርና ነው።
የፖለቲካዊ ዓመፅ መንስኤ ጭቆና ቢሆንም ዓመፅ ግን የጭቆና ነፀብራቅ እንጂ ጭቆና የሚወገድበት ትክክለኛ ስትራተጂ አይደለም። በዓመፅ ጨቋኞችን ከስልጣን ማባረር ይቻል ይሆናል። በዓመፅ ጭቆናን ማስወገድ ግን አይቻልም። ጭቆና የሚወገደው ዴሞክራሲ በማስፈን ነው። በዓመፅ የሚገነባ ዴሞክራሲ ደግሞ የለም። የዴሞክራሲ መንገድ ዴሞክራሲ ነው። ዓመፅ የሰው ህይወትና ንብረት ይበላል። በዓመፁ ምክንያት ህይወታቸው ላጡ ተማሪዎች ጥልቅ ሐዘን ይሰማኛል።

የነፃነት – ቃና። (ከሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.05.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

pic2የነፃነት ቃና የነገሮች ሳይሆን ይልቁንም ሰው የመሆን ልዩ ቃና ነው። ቃና መሆን እራሱ ሲያንሰው ነው – ለነፃነት። ነፃነት ትርጉም ያለው መኖር ማለት ነው። መኖር ሲተረጎምም ነፃነት ማለት ይሆናል። ነፃነት እንደ ጎረቤት ሳይሆን እንደ እራስ ሆኖ መኖር የሚያስችል ቀለማም የመብት ባላቤትነት ልዩ እርስተ – ጉልት ነው። የህይወትም እርእስም። ነፃነት ውስጥን ፈቅዶ የመተርጎም አቅም ካለምንም ተጽዕኖ ወይንም ፈቃድ ሰጪ ኃይል ወደ ተግባር ለመተርጎም የሚያስችል የብቃት ብቸኛ ማውጫ ነው። ነፃነት እራስን እንደ ፈለገ ገልጦ አንብቦ መኖር ማለት ነው። እርግጥ ነፃነት ጣሪያና ግድግዳ አለው። መብትና ግዴታ። መብትን ለማግኘት ግዴታን መወጣት። ግዴታን ተወጥቶ የመብት ባለቤት መሆን። ቀደምቶቹ የመብታቸውና የግዴታቸውን ጣሪያና ግድግዳ በአግባቡ ስላወቁ ነፃነታቸውን ለማግኘት ተሰዉ። በነፃነታቸውም በሀገራቸው ዳር ደንበር በወጥ ማንነት ኮርተው ኖረው – አለፉ። ዬድርሻቸውን ዬተወጡት አይደለም እናት ኢትዮጵያን አፍሪካን በአለም የተበተነው የዘረ ጥቁር ተፈጥሮ በተግባር አነጠሩት። መወደሱን ለማንነት በፈቃድ ሸልመው ዙፋኑን ጭነው  -አነገሡት። ኑሯቸው ህይወት — ማለፋቸውም ሕይወት ሆነ። መፈጠርን – ተጠበቡበት። አይደለም ትናንት ዛሬም በራስ የመተማመን ጥገትን በውስጣችን በደማቸው አተሙ። – ብሩካኑ በኢትዮጵዊነት የተካኑ።

የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ጥሬ ሀብትን ብቻ ሳይሆን እርካሽ ጉልበትን ለማጋበስ አፍሪካን እንደ ቅርጫ በተከፋፈሉበት ዘመን አባቶቻችንና እናቶቻችን በከፈሉት የህይወት መስዋዕትነት ሰውነታችን ተከብሮ እንደ እራሳችን በጣዕማችንና በጠረናችን እንኖር ዘንድ አስቻሉን። ነፍሳቸውን ኤልሻዳይ አርያም ገነት ያስገባለን። አሜን!  የትጉኃኑን አቨውን ዘመን የባረከ አምላክ እኛምንም በበረከቱ ይጎብኘን። አሜን! የቀደሙት የኢትዮጵያ መሪዎች እርብኝነታቸው ከዘመኑ ብቃት በላይ ስለነበረ ከባርነት ያወጡን የነፃነት አባቶቻችንና እናቶቻችን ናቸው። ደግመው ወለዱን – ለክብር።

ኢትዮጵያ ሀገራችን በታላቅ ክብር ከአፍሪካ ተለይታ እንድትኖር ካደረጉት የተግባር ተጋድሎዎች አንዱ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ የራሷ ብርቅና ውድ የፊደል ገበታ ያላት መሆኑ ነው። ይህ ዕጹብ ድንቅ ገቢራዊ ቅርስ እኛነታችን ከሰጡን ታላቅ ባላውለታዎቻችን ደምና አጥንት መስዋዕትነት ውስጥ የተገኘ ልዩ ጥሪታችን፤ የጋራ የመንፈስ ሃብታችን ድህነታችንም ነው። ምልክታችን፤ እኛነታችን ነው።

አማርኛ ቋንቋ ቃናው ነፃነት፤ ጣዕሙ ደግሞ ታላቅ የዕውቀት ዘርፍ ነው። አያሌ ሰዎች የሚስማሙበት ቋንቋ መግባቢያ ነው ብለው ነው። ለእኔ መግባቢያ ብቻ ሳይሆን ቋንቋ የዕውቀት ዘርፍም ነው። ዬዓለም የመተንፈሻ ሳንባዋ ቋንቋ ነው። ቋንቋ ሙያም ነው። ባህልን ወግን ልማድን እምነትን ማንነትን ቀምሮ እራስን መግለጽ የሚያስችል የሀገር አንበደት ነው – ቋንቋ። የህዝብ ልሳን ነው። ቋንቋ ተቋምም ነው። እንደ ኢትዮጵያ ላላ ለታደለ ሀገር ደግሞ የነፃነት በኸረ ልጅ ነው።

አማርኛ ቋንቋ ያደገ፣ የሰለጠነ – ብልህ ወታደር ነው። እናት ሀገሩን ከነፃነት የታደገ ታላቅ ባለውለታም ነው። ጠላትን ቀጥቶ ለማንበርከክ ወጥ አንደበት ባይኖር ትጥቅና ሥንቁ፤ ፍላጎትና ራዕዩ የባቢሎን ግንብ በሆነ ነበር። ሥልጡኑ አማርኛ ግን ግዳጁን በከፍተኛ ደረጃ የተወጣ ሰማዕት፣ አርበኛና አደራ አውጪም ነው።

pic1አማርኛ ቋንቋ ፍሰቱ – ርባታው – ለዛው – ቃናው – ጣዕሙ – ዜማው – አወራረዱ ሳቢና አጓጒ ነው። አማርኛ ቋንቋ ውበቱ ልዩ ነው። ደማም – ዓይነ – ገብም። እያንዳንዱ ነጠላ ፊደል ቅርጽና ይዘታቸው ተደላድለው የተፈጠሩ እንደ አራስ ልጆች ታይተው የማይጠገቡ ብርቅ የዓይን አበባዎች ናቸው።  በሌላ በኩል አማርኛ ቋንቋ አንባሳደራችንም ነው። ከአፍሪካ የተለዬች ኢትዮጵያን ያደረጋት ታላቁ ሚስጥር ቀለማሙ የፊደል ገባታ ሥህናዊ ተፈጥሮ ነው። ለላቀው ብቃቱ ዘመንን እዬሸኜ ፈተናን እዬረታ፤ ጠላቶቹን እያስተማራ አምሮበት አለ። ባሰኜው ቀለም በሀገሩ ወግና ልማድ ትውፊትና ማንነት ፈክቶ  - አብቦ አለ። መፈጠርስ እንደ አንተ-  መኖርም እንደ አንተ – ማወቅም – ማደግም እንደ አንተ፤ መማርም መመራመርም እንደ አንተ -  ባለ ግራጫ ግን ሁል ጊዜም ዕንቡጥ።

የጹሑፌ መግቢያ ፎቶ በ2012 ዓለም ዐቀፍ የፊደላት ቀን ሲከበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተመረጡት ፊደላታ ጋር አማርኛ ቋንቋ ቤተኛ ሆኖ ፍላየሩ ውስጥ ነበር። ይህ ሁለተኛው ፎቶ ደግሞ እነዚህ የምታዮዋቸው ፊደሎች ለናሙና የተሰሩ ናቸው። ከተመረጡት ዬ17 ሀገሮች የፊደል ገበታዎች ውስጥ አንዱ የእኛው ጀግና ነበር። ይህ ለአንድ ወር በዘለቀው ኤግዚቪሽን መክፈቻ በር ላይ የነበረ ሲሆን „የገደል ማሚቶ“ በሚል እርእስ ሥር በተመረጡት ቋንቋዎች ተተርጉሞ በአንድ መጸሐፍና በድምጽም ንባቡ አብሮ ተያይዞ ቀርቦ ነበር። የአግዚቢሽኑ በር ሲከፈት ደግሞ ውስጡ  ሃብታችን በተሟላ መልኩ ነበር። ለዚህ ክብርና ዝና እንዲህ ያበቁን ኢትዮጵያዊነታችን እንድንሳሰለትና፤ እንድናደንቀው ያደረጉት ቀደመቱ ማስተዋሉን ፈጠሪ አምላካችን አብዝቶ የሰጣቸው ቀንዲሎቻችን ነበሩ።

„የእኛ ታሪክና የፖለቲካ ውጥንቅጥ“ ዲያቆን ኒቆዲሞስ እርቅይሁን ተችተው አኔን እንደጻፉኝ ኢትዮጵያዊነቴ ተጭኖኝ ሳይሆን ሙሉዑ ሰው እንድሆን በደም ፍሳሽና በአጥንት ክስካሽ የተሰጠኝ ውስጤ  - ብርቄም – የመኖሬ ስዋሰውም መኖሬም በመሆኑ ነው።

ለነገሩ እንደ ጸሐፊው አገላለጽ ወቀሰው ለእኔ ክብሬ በመሆኑ ለዚህ የወቀሳ ምስክርነት ላበቃኝ አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው። እንኳንስና ይሄ በኢትዮጵያዊነቴ ምክንያት በድንጋይ ተደብድቤ እንድሞት ቢወሰንብኝ እዬዘፈንኩ የምቀበለው ስለመሆኑ የጹሑፌ ታዳሚነታቸውን ስለገለጹልኝ ለክቡርነታቸው ሆነ የእሳቸው ጹሑፍ ታዳሚ ለነበሩ ቅኑ ወገኖቼ አበክሬ በተደሞ መግለጽ እሻለሁ። አሁንም የሰው ሰው መሆኔን የሰጠኝ ኢትዮጵያዊነቴ ክብር -ምስጋናና – ልዕልና ለምንጊዜም እመኝለታለሁ።

pic3በተረፈ መልስ መጻፍ ያለስፈለገኝ ምክንያት ከቅርንጫፍ ጋር ሳይሆን እኔ ከግንዱ ጋር ስለሆነ ግብግቡ ግንዱን ወዳጄን ተክሌሻን እዬጠበኩ ነበር። እምለው ከኖረኝ የታናሼ ቃና የብዕር ውበት ግጥሜ ስለሆነ ደስ እያለኝ ከተክሌሻ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር እእ! በተረፈ ሰማዕታት አማርኛ ቋንቋን እስከነ -ሙሉ ትጥቁ፤ እስከነ – ስንቁ ስለሸለሙኝም ዱዳ ሳልሆን ምንም እንኳን በሥነ -ንግግር ጥበብ  ዕድሉን አግኝቼ በሥልጣና ክህሎቴ ቢታገዝም በተፈጥሮዬም ብቁ ተናጋሪ፤ የወጣልኝ አድማጭ፤ ጸሐፊ፤ ገጣሚና ባለቅኔ እንዲሁም በትሁት እርግጠኝነት፤ በፈካ በራስ የመተማመን ስሜት እንዲኖረኝ አባቶቼና እናቶቼ ስለ አደረጉ አውዳቸዋለሁ፤ አከብራቸዋለሁ።  ስለዚህም በሙሉ ሰውነት አለምን በግልቡ ሳይሆን ከልቡ ገብቼ እንደፈትሽው በሚገባ ጠርበው ቀርጸውኛል። ጌጦቼ – ዋርካዎቼ  - ጉልላቶቼ ቀደምቶቹ የነፃነት ሊቀ – ሊቃውንታት።  http://www.ethiomedia.com/14news/our_complex_history.pdf

 

አሁን ወደ ቀደመው — ሁላችሁም እንደምታወቁት ሲዊዘርላንድ የሥራ ቋንቋዎች አራት ሲሆኑ ሶስቱ ጎልተው የወጡ በመሆኑ ዕርእሱ የአምርኛ ፊደል የሚለው በጀርመንኛ፤ በጣሊያንኛና በፈረንሳይኛ ሲሆን … በጎን ያሉት ደግሞ ሲጻፍ ከቀኝ ወደ ግራ እንደሆነ፤ ሲነበብ ከቀኝ ወደ ግራ ስለመሆኑና ከላይ ወደ ታችም እናት ፊደልን ማንበብ እንደሚቻል ተብራርቷል፤ ዝቅ ብሎ የእናት ፊደሎችና የልጅ ፊደላት እርባታን ለአብነት ተስርቷል። ከዚህ ባለፈ ስለ ቋንቋው አጠቃላይ ዜማዊ ድምጸት፤ ስለ ሰዋሰዋዊ ፍሰት፤ ግሳዊ እርባታ፤ የአናባቢና ተነባቢ ፊዳላት ጠባያት፤ በሌሎች ቋንቋዎች የሌሉ ፊደላትና የድምጽ ተዋፆዖ፤ የትውስትን ቃላትን ብቻ ስለሚያስተናግዱት ሁለት ፊደላት ማለትም „ጰ እና ፐ“ እና  የአማርኛ ቋንቋ ፍጥረቱ – እድገቱ – ደረጃውና የወደፊት ዕጣውን በሚመለከት ሰፊ ገለጻ / ፕረዘንቴሽንም / ነበር …. ይህ ብቃት ምንጩ የዛሬ አይደለም የትናንት ዓይነታ ሃብት እንጂ። አንገትን ቀና አድርጎ፤ ልብን ነፋ አድርጎ፤ እኛ አራሳችን የፊደል ገበታ አለን የሚስብል ጉልበታም ፕላኔት በመዳፋችን አለን። የማንም የትውስት ወይንም የብድር ያልሆነ፤ ተሸብቦ ወይንም ተሽበልብሎ ወይንም ተኮፋትሮ ወይንም ተትርትሮ ሳይሆን እራሱን ገልጾ፤ ብቃቱን ሊያሰጎበኝ የሚችል የሊቀ ሊቃውንታት ዕውቀት ጭማቂ ማለት አስችሎናል …. የነፃነት ባለቃናውን ዬአማርኛ ቋንቋ።

 

አማርኛ ቋንቋ ጥልቅ የመሆኑን ያህል አተረጓጎሙ እኔ ነኝ ካለ የቋንቋ ፊደላት ሆነ ሥርዓተ – ህግጋት ቢበልጥ እንጂ የሚያንስ አንዳችም ነገር የለውም። የቀደሙት ከፊደል ቀረጻ ጀምሮ የሠሩለት ሥርዓት አማርኛን እራሱን አስችሎ ቀጥ አድርድርጎ አቁሞ ዓዕምድ እንዲሆን አስችሎታል። አማርኛ ቋንቋ ምርኩዝ – ከዘራ አይሻም። ወይንም ደንበር ዘለል ኩባንያዎች አይለማመጥም – ክፉሉ አይደለምና። ተፈጥሮውም አይፈቅድለትም። ነፃነትን አምጪው ኃይል እራስ በመሆኑ ይህንንም ጀግናው በቃና እና በቅኔ፤ ብብቃትና በስልት – ከውኖታል።

pic1

ሲወዘርላንድ በዙሪክ ክፈለሀገር ቪንተርቱር በሚባል ከተማ በቀን 2000 እንግዶችን በፍቅር የሚያስተናግደው የኢንተግሬሽን እና የህዝብ ቤተ መጸሐፍት የሚገኝበት ህንፃ ከሦስት መቶ ዓመት በላይ የኖረ በመሆኑ ካቩ ሆነ የጣሪያው እንጨት እንደተፈጠረ ውበቱ ከሩቅ ይጠራል። ከላይ ወደ ታች ፍላዬሩ ተሰርቶ ስለነበረ ታሪካዊ ህንጻ ጣሪያውንም ስለሚያሳይ እንዳለ ማቅረቡን መርጫዋለሁ።  „ወ ና ጀ“ ይታያሉ። ስታተልቁት ደግሞ ሌሎችም ይወጣሉ።

 

አማርኛ ያማረ የተዋጣለት ትዕይንታዊ ኪናዊ ቋንቋ ነው። አማርኛ ለፍቅርም ምቹ የሆነ ጣዕም አለው … ሥንኞቹ ዓይናማ ናቸው። ግጥሞቹ ኮልኮዮች ናቸው፤ ቅኔዎቹ ውስጥን ያስነብባሉ  - ርቀው ሊቅነትን ይሸልማሉ። ድርሰቶቹ ተሳለሙኝ ባዮች ናቸው። ተረትና ምሳሌዎቹ ዕውደት ይናፍቃቸዋል፤ ሥነ ቃሎቹ ትውፊትን ይጣራሉ። ቅጽል፤ መስተዋድድ፤ ተወሳከ ከግሥ፤ መስተጻምር ግሥ – ያነግሳሉ።  አደብ የገዛ አደብን ያበረከተ – እጬጌ!

አማርኛ ቋንቋ እራሱን ሲገልጽ በነፃነት ነው። ነፃነቱን የሰጠው እሱ እራሱ ነበር። ነፃነቱን አምጦ አርበኞችን በአኃቲ ልቦና በፍቅር ገዝቶ ባዕቱን አስከብሮ እሱም ከበረ። ቋንቋው የሚርቅ ሳይሆን አቅርቦ እርስዎን እዬፈታተሸ እሱ ደግሞ በተራው በህግ ሥርዓቶቹ ይፈትሽዎታል። ዘንበል ያሉ ግድፈቶችን ትህትናን ለግሶ እያባበለ፤ እያቆላመጣ ያስተምራል።

pic4ባልተወለዱን፣ በቀለም በማንገናኛቸው ዘንድም እንዲህ ይወደዳል። ተከብሮ ያስከብራል። አንገትን ቀና አድርጎ ማንነትን ያበራል። አማርኛ  የኢትዮጵያ ሀገራችን የወል ሃብትና መግለጫ ነው። ንብረትነቱ ግላዊ ሳይሆን እናት ሆዱ በመሆኑ ሁላችንም በእኩልነት ያለአድሎ ያስተናግዳል። ግንኙነታችን የሰመረና ያማራ እንዲሆን ይጓጓል። በዬትኛውም ዘመን የተነሱ ቅኝ ገዢ ፍላጎቶችን ሰብሮ – አዋርዶና – አሳፍሮ የመለሰ የጀግኖች ቁንጮ ነው። ፍላጎታቸውንም አባክኖ ውኃ የበላው ቅል አድርጎታል – አርበኛው።

አማርኛ ቋንቋ በዘመነ ወያኔ በክፉ አይን የሚታይ፤ ስር በሰደደ ጥላቻ ጦርነት የታወጀበት፤ ፍዳውን የከፈለ፤ በረቀቀ ሆኔታ ታቅዶ ሞት የተበዬነበት ነበር። ግን አልሆነም። ወያኔ በፈለገ መልኩ አጠቋቁሮ፤ በባሩድ አቃጥሎ ሊደምስሰው ቢሻም እንሆ ተወደደ ተከበረ ተፈቀረ – ነገም። አማርኛ ቋንቋ ዘመኑ የፈቀደለትን ሥልጣኔ የተቋደስው ከሰማይ በወረደ መና አልነበረም። እሱም ታግሎ ደምቶና ተሰውቶ ነው። ስለዚህ የለመደውን መሰዋዕትነት እንደ ዘምኑ ማስተናገድ የመቻል ሙሉ አቅምና ሥነ – ተፈጥሮ አለው። ለዚህም ነው ገደልነው ሲሉ እያተ የሚሄደው፤ አጠፋነው ሲሉ እያበለ የሚገኘው፤ ደመሰስነው ሲሉም ቀድሞ ድል ላይ የሚፈርሸው፤ ሊከተክቱት ባዘጋጁት ገጀሞ እንሱን እዬከሰከሰ የሚያሸንፋቸው። ወያኔ ሰው በማያውቀው ደረጃ በጣም ብዙ ነገሮች ነው በአዲስ አባባ ዩንቨርስቲ እንዲከስሙ ያደረገው። ግን ሥራዬ ብለን ተግተን የምንታገልለት ኃይሎች ስላላን ምን አልባት አንድ ቀን የአፈኑት የኢጎ አርበኞች ሲበኑ ሌላም ታእምር ወያኔ ያያል።

አዎን ቋንቋችን አማርኛ ማደግ ስላለበት ዘመኑን የቀደሙ ተግባራት ተከውነውበታል። ትናንት ሲዊዘርላንድ ላይ ጄኔባ ድብልቅ ያሉ ሁለት ፍሬ መጸሐፍቶች፤ ቪንተርቱር ላይ ሙዚዬም ቤተ መጸህፍት ሁለት የአዲስ አባባ ዩንቨርስቲ የሥነ ቃል ጥናታዊ ወረቀቶችና አንድ የሥነ ቃል  መጸሐፍ ብቻ ነበሩ። ዛሬ ግን 6 ጊዜ አስተውሉ 6 ጊዜ በሲዊዝ ብሄራዊ  የኢንተግሬሽን ቤተ መጸሐፍት ብሄራዊ ጉባኤ ስለ አማርናኛ ቋንቋ የአዋቂዎችና የልጆች መጸሐፍት ፍላዬሩን በሀገሬው ቋንቋ እራሳቸው ሰርተው ማብራሪያ ተስጥቶበታል። እናም አብዛኞቹ የኢንተግሬሽን ቤተ መጸሐፍት አዲስ መምሪያ ከፍተው በፍቅር እያስተናገዱት ይገኛል። ትግሉ ይቀጥላላ ውጤቱም ይታፈሳል ……

ሌላም ይታከል – በሥነ ሥርአት፣ በንድፍ የተሰሩት ግጥሞች በቂ ጊዜ ተስጧቸው ለኤግዚቢሽን በቅተዋል። አለ ሌላም ቤተ መጸሐፍት ታዳሚዎቻቸውን የአማርኛ ቅኔ ሲዘረፍ በጣዕማዊ ቃና አስኝቷቸው ውሎ አበሉን ትራንስፖርቱን ክፍለው ቁጭ ብለው አዳማጡት። ይደገምልን እያሉ፤ በመጨረሻም „ የምሽት ማህሌት“ ሲሉ አደነቁት።

 

ግን ምን ያደርጋል? እንዲህ በሰው ሐገር የሚደከምለት ወያኔም በአንጡራ ጠላትንት ፈርጆ የሚደቁሰው አማርኛ ቋንቋ ንዑድ መንፈስን የሰነቁትን ማዬትም መስማትም አንሻም ሲሉ የኢጎ አርበኞች በዬኑበት።  አዎን! በ2013 የካቲት 4 ሲዊዘርላንድ ጄኔባ ላይ የኢሳት ፈንድ ራይዚንግ ነበረ። እንዲሸጥ በጊዜ ተጠዬቀ። ፈቃዱን ማግኘት አልተቻለም። ማስታዋቂያ ብቻ መናገር ይቻላል ተባለ። ይህ ስለተባለ ገንዘብ – ጊዜ  - ጉልበት ፈሶ ከእያንዳዱ ለናሙና 3 ሲደምር 18 መጸሐፍት 4 ሰአት ተጓዙ ወገኖቻቸውን ሊዩ – ጓጉ። ያው ከወገኖቹ ጋር ውስጥ ባይፈቀድላቸውም ውጪ ኃይለኛ በረዶ ነበር እንሞክራለን አለችኝ ክብሬና እህቴ ወ/ሮ ምስራቅ መንገሻ ይዘን ሄድን። ይህም አልሆነም። በቃ ይህ ነው የነፃነት ትግል።

እህቴ አረረች ማስታገስ ስለነበረብኝ ወቅቱ ያልነበረውን አዲስ ፕሮጀክቴን ነገርኳትና እንድትረሳው አደረኩኝ። እኔን ነፃ ሊወጣ በተደራጀ ሚዲያ ላይ የነፃነት ቃና ውበት ታሸገ። እኔን ግን አስቆመኝ?! እእ! አንድ ወንድሜ በጥልቀት ያውቃል። እንዲያውም ተጨማሪ ገንዘብ ላኩ „ እንቅልፍ አልባዋ ሥርጉተ ሥላሴ“ እስከ ማለት ያስቻለው የማይታይ ተግባር ከወንኩ። የወጣው ገንዘብ ቀላል አልነበረም። በወቅቱ ዓይኔን ኦፕራሲውን አድርጌም ስለነበር ያልተጋባ እርምጃ ነበር የወሰድኩት። ግን አረመኔዎች ናቸው። ትንሽ ብጣቂ አንጀት ያልሰራላቸው። አሁን ወያኔ ቢሆን ስንቱን ባል ነበር። ለእነዚህ በነፃነት ሀገር ነፃነቴን ለሚነጥቁ  — ለሚጨፈልቁ – ለሚረማማዱበት —- ሰዎች ፍርድና ዳኝነትን ከጌጦቼ ስለላ የቤተ ሥራውን ለእናንተ ልስጥ። አይካድ ነገር ሶስት እህቶቼ – ተሳትፈውበታል። ያውም እኮ እኔ ከሞት የተረፍኩ ነገ ምን ሊሆን እንደሚችል የማላውቅ ነኝ። አይታፈር ስሞትላቸው ለቀብር ይመጡ ይሆናል። „አሻም“ አልፈልግም።

ህም!  እንኳንስ 18 መጸሐፍት ከሁለት ኪሎ በላይ በሃኪም የተከለከልኩ ነኝ። ክብሮቼ  እናት ሆዱ ሁነና ግፍና በደሉን መርምሩት። እግዚአብሄር ይመስገን። አሁን ማስታወቄውን በብላሽ ኢትዮ ሚዲያና ሞረሽ ወገኔ ሠሩት፤ ከዚህ በኋለ ሊንኩን ወገኖቼ በሙሉ እዬተሻሙ ተረባረቡበት። ጭንቀት ነበረኝ አዲስ ሥራ ስለሆነ እንዳልዘረፍ። አሁን ግን መንፈሴ አረፈ።  ዘሃበሻም ማህበራዊ ድህረ ገጽ ደግሞ ቀዳ እያደረገ ልሳኑን በፍቅር ተቀበለ። በጉልበተኛ አቅመ ቢስ ኢጎ ታፍኖ የነበረው በር ቧ አድርጎም ከፈተለት። እንዲህ ተገናኝ እንጂ ተለያይተን እኮ ነበር። ከ2009 እስከ 2014 ብዙ ነው መርግም። ግን ተቻለ። እጅግ አመስግናችኋለሁ። ነፃነትን በእናንተ አዬሁኝ። ለዛውም ለሴት! ድንቅ ነው። ተመስገን! እንኳንም 2011 አልሞትኩኝ።

 

የሰማይን ጸጋ መገደብ አይቻልም – ፈጽሞ። ሥጦታው የመዳህኒት ነውና። የተዘጋ ተከፈተ። ማን ያውቃል ነገ እናንተን ሊይ ወደ እምትኖሩበት ባዕት ብቅ ይል ይሆናል። ሲዊዞች ጣዕሙን የሚለኩትን እናንተም ትቋደሱት ይሆናል። ተክሌሻ ወንድምአለም እዬሰማህ ነው? ለመሆኑ አለህ ከእኔ ጋር ነህን? መቼም እኔ ካለአንተ ብዕር አይሆንልኝ። እስቲ አንድ መላ በል አባቱ። መቼም እኔና አንተ ፍቅር በፍቅር ሆነናል። አንድ ጊዜ የዶር/ አረጋይ መጸሐፍን ተሳታፊው ምጥጥ አደረገላቸው ስትል ትንሽ ዜና ቢጤ አኮምኩመህን ነበር። እዚህ ደግሞ ግልምጫውም ጥፊውም ተችሎም ጋዳ ነው – ተራራ። ገደሉኝ ስልህ! በሽታሽቶ።


ሲዊዝ የአንድነት ድጋፍ ድርጀት እናት ድርጅቱ እውቅና እንዲሰጠው ያልታከተ በሳል ጥረት አድርጎ አልተሳካለትም። ሲዊዝ ውስጥ ያለው ትሬኮላታ ታገለው። በመጨረሻ አባላቱ ተዘርፈው የሀቅ አርበኞች ተገፈተሩ። ሲዊዝዬም ከአንድነት ረድኤት ውጪ ሆነች። ሥርጉተን የተከላት ኢሠፓ ፓርቲዋ ነው። ያበቀላት ደግሞ ገበረመድህን በርጋ ነው። ገብረመድህን በርጋ ማለት ጎንደርን ፓሪስ የማድረግ ንዑድ አቅም፤ ኢትዮጵያን የመሥራት ጥልቅ ጥበብ የነበረው፤ ትውልድ ሊተካው ከቶውንም የማይችል የድርጅት ናሙና  ነበር። ስለሆነም ሥርጉተን ጠቅላል አድርጎ ቆሻሻ ውስጥ መጨመር አይቻልም ቁርጠችሁን እወቁ – ።

ቅኑ ጎጄ ወንድሜ መከፋትህን ጥቃቴ ውስጥህ እንደ ገባ ጥቅምት 12.2013 ዙሪክ ላይ ሳገኝህ  በአይኔ አይቻለሁ። ዬአንተን ፈቃድ ስለሟላሁ፤ ሁለት ጊዜ ሙሉ በራሴ ወጪ ፍርንከፈርት አማይን በግንቦት 7 ስብሰባ መገኘቴ የተከለውን ቋሳ በምልሰት ትመረምረው ዘንድ በአጽህኖት አሳስብኃለሁ። ለእኔ አይደለም ለነፃነት ትግሉ አይበጅም። አፋፍ ላይ የተንጠላጠለ፤ በብዙ ዝንቅ ፍላጎት የታመለ ስሜት ይዘን የታላቋን ኢትዮጵያን ህልም መመኘትም ጅልነት ይመስለኛል።

ሌላው አስደሳቹ ዜና ስለ ፍቅር ሥርጉተ እምትለው ስለነበራት አሁንም 7ኛው መጸሐፏ መንገድ ላይ ነው //// 8ኛውም እርማት ላይ ነው – ይቀጥላል በዚህ በያዝነው አምት //// ሌላም ስለ አማርኛ ቋንቋና ስለ ኢትዮጵያ መታዳም ሰሞኑን ትንሽዬ ቀዳዳ አግኝቻለሁ። ተመስገን! እግዚአብሄር አብሮ ካለ ሁሉም አለ። የሰማይን መክሊት ከቶ ማንም ሊገድበው አይችልም …. ገና ያፈራል  - ይጎመራል። ወርቅ ይፈልቃል እንጂ አይማርትምና። አማርኛ ቋንቋ ቤቱ ውስጥ ሆኖ ውስጥነቱን ያዘራል። ሥርጉተም ትግሏን በመቀጠል ታንቆጠቁጠዋለች። የተደራጀው አደራጅ ግጥሙ ነውና።

 

የሚገርማችሁ ነጮቹ ይወዱታል አብሶ ለፊደልና ለተስፋ መጸሐፍት  ፍቅራቸው ጥልቅ ነው። ስለሆነም በጉባኤዎች፤ በኤግዚቢሽኖች በገለጣ ጣቢያዎች ከነፃነት – ቃናችን ጋራ ይገናኛሉ – እኛስ ነው ጥያቄው? ግን 613 ግጥሞችን በሶስት መድብል በአንድ ጊዜ አፍ ባላው የመቃብር ኑሮ  - ያሳተመ ሰምታችሁ ታውቃላችሁን? ሥርጉተ በ2010 አድርጋዋለች። በ2012 በአንድ አመት ብቻ ሶስት መጸሐፍትን አሳትማለች። የሥርጉተ ሥላሴ የመንፈስ ሰብል።“ ይህቺን ቃል ጉግልን ብታጎርሱት ይነግራችኋል። ጉግል ጉቦ ይወዳል። ታዲያ ጉርሻው እንደ „ባለታክሲው ፊልም“ በቢላዋ እንዳይሆን አደራ! ብረት ግጥሙ አይደለም። በዘንካታ እጣት። ጉግልንም ባህላችን እናስተምረው – ይሁን በሉ።

 

እንደ መደምደሚያ – ቋንቋ ሰው ሰው የሚሸት ቃና እና ናርዶስ አለው። ቋንቋ ጌጥ ነው – ልዩ። ውስጥን የሚሳይ ዘመናዊ መስታውት ነው። ስለ ውስጥ የሚናገር ርትዑ ነው። ቋንቋ ከተናጋሪው ቀድሞ ተናጋሪውን የማንበብና የመተርጎም ጸጋ አለው። ቋንቋ ንዑድ መንፈስ ስላለው ርህርህናው ጥልቅ ነው – እርግብ። እኔ „እኔን“ ከምገልጸው በላይ በተብራራ መልኩ አማርኛ ቋንቋ „እኔን“ ተርጉሞኛል ብል ግነት አይደለም።

 

የኔዎቹ ጨረስኩኝ። ዕለተ ሃሙስ ያው በተለመደው ጊዜ የቻላችሁ አዬር ላይ፤ ያልቻላችሁ ደግሞ አርኬቡ ላይ ግንቦት 8. 2014 እንገናኝ። www.tsegaye.ethio.info Tsegaye – Radio Lora Aktuelles ወይንም www.lora.ch.tsegaye ብዕሬን ብቻ ሳይሆን እኔን እህታችሁን ናፍቆት ብትክትክ አድርጎ ሲነዳድለኝ ታዳምጣላችሁ። ጀግኖቻችንም አብረን እናከብራለን። ጀግናን አብረን እንናፍቃለን …. እሺ ….. መልካም የንባብ ጊዜ ሰንበት ተመኘሁላችሁ እኔ ሎሊያችሁ ሥርጉተ ሥላሴ።

 

  • ፎቶዎቹ የተገኙት ከሲዊዞች ጋራ ስለተሰራ ነው እንጂ በተለያዬ ሁኔታ ከኢትዮጵውያን ጋር የተሰሩ ቪዲዮዎች ፎቶዎች ማግኘት አልቻልኩም – እንኳንስ አኔ በሚቀርቧቸው ሰዎች እንኳን ተሞክሮ አልተቻለም – ጉበልበተኞች። ተዳፈን። እረመጥ ነው ፍሞ ያበስላለ …..

 

 

ነፃነት የገባው ማንነት ለነፃነት ክብር አለው። ግን ማንነቱ እራሱን ማግኘት ከቻለ ብቻ!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

በሚኒሶታው መድኃኔዓለም ቤ/ክ ስም መነገድ ይቁም!!! [አቡነ ማርቆስ ቤ/ክርስቲያኑንን አሳማ ያርቡበት ያሉበት አነጋጋሪ ቪዲዮ]

$
0
0

በቀጣይ ያስተናገድንላችሁ መልዕክት ለሰላም እና ለአንድነት ከቆሙ የሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምዕመናን የተላለፈውን ጥሪ ነው።

debereselam Minnesota
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
5/3/2014

የቤተክርስቲያናችንን አንድነትና ሰላም ለመናድ እየተንቀሳቀሰ ያለው ቡድን በታላቁ ደብራችን በደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ስም የሐሰት ዘመቻ እያደረገ ስለሚገኝ የቤተክርስቲያናችን አባላትና ሌላውም ኃይማኖቱንና አገሩን የሚወድ ሁሉ እየተነዛ ካለው የሐሰት ቅስቀሳና አሉባልታ እራሱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

የቤተክርስቲያናችን የሚኖሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የገለልተኝነት አቋም አሁንም ያልተቀየረና የተጠበቀ ሲሆን በቅርቡ የዚሁ የሰላምና አንድነት አፍራሽ ቡድን ዋነኛ አንቀሳቃሽ ከሆኑት ግለሰቦች መካከል አንዱ ወደ ኢትዮጵያ በመሔድ ሥልጣን ላይ ባለው ኃይል 6ኛ ፓትርያርክ ተብለው ለተቀመጡት አባት ሜኖሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ባለው ሲኖዶስ ሥር ለመተዳደር ወስኗል በማለት የተሰራጨው የድምጽና የቪድዮ መልእክት ፍጹም ከእውነት የራቀ እንደሆነ ሁሉም እንዲያውቀው እንወዳለን።

ሰላምና አንድነትን አሻፈረኝ በማለት የቤተክርስቲያኑ አባላት ተሰብስበው የመጨረሻ ውሳኔ እንዳያስተላልፉ መሰናክሎችን ሲፈጥር የነበረው የዚህን ቡድን ሕገወጥ አካሔ በፍርድ ቤት አስገዳጅነት የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ለሜይ 11 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲካሔ ከተወሰነ በኋል የሚያደርጋቸውን ሕገወጥ
አካሒዶች መቀጠል ስላልቻለና በጉባኤውም ተሸናፊነቱን አስቀድሞ በማወቁ ራሱን በእለተ ሆሳዕና ከቤተክርስቲያን ለይቷል። በቅርቡ ተወካዩን ወደኢትዮጵያ በመላክም ሕዝቡ ሳይወስንና ስብሰባም ሳያደርግ ሚኖሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በእናንተ አመራር ሥር ለመሆን ወስኗል
በማለት የሐሰት ወሬ ለፓትርያርክ አባ ማቲያስ የተነገረውና እርሳቸውም ያስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ቤተክርስቲያናችንን በማይወክሉ እወደድ ባዮች የተፈጸመ ማወናበድ ስለሆነ ደብራችን ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አሁንም ሆነ ወደፊት በአባቶች መካከል ያለው መለያየት ተፈትቶ አንድ ሲኖዶስ አንድ ፓትርያርክና አንድ አመራር እስከሚፈጠር ድረስ በገላጋይነት አቋም የሚጸና መሆኑን ለአንድነትና ለሰላም የቆምን ብዙኃን የቤተክርስቲያኑ አባላት ሁሉም እንዲያውቀው በአጽንዖት እናሳስባለን።

ከዚህም በተጨማሪም በበራሪ ወረቀቶችና በራድዮ እንዲሁም በየዌብ ሳይቱና በፌስ ቡክ ቤተክርስቲያናችን ሰባኪያንን እና ዘማሪያንን በማስመጣት ጉባኤ ያዘጋጀ እንደሆነ ተደርጎ እየተላለፈ ያለው ቅስቀሳም ሐሰት መሆኑን እንገልጻለን። የተባለው ስብሰባ የተዘጋጀውና የሚመራውም በዚሁ ራሱን ለእምነትና ለእውነት ሳይሆን ለፖለቲካ መሳሪያነት ባዘጋጀው ቡድን ስለሆነ ምእመናን ጥሪው የቤተክርስቲያን እንዳልሆነ እንዲያውቁት እንወዳለን።

በቤተክርስቲያናችን ችግር በመፍጠር ሰላማችንን የረበሹትን የቦርድ አባላት ሽሮ በምትካቸው አዳዲስ የቦርድ አባላትን ለመምረጥ እና በዲሴምበር 15/2013 በከፍተኛ ድምጽ ቤተክርስቲያናችን ባለችበት የገለልተኛ/ገላጋይነት አቋም ትቀጥል ተብሎ የተወሰነውን ውሳኔ ለማጽደቅ ሜይ 11/2014 በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ድምጽ መስጠት የምትችሉ የደብራችን አባላት ሁሉ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በዚህ አጋጣሚ ላለፉት ዓመታት ተከብሮ የቆየውን የእግዚአብሔርን ቤት ይኸው የሰላም እና የአንድነት አፍራሽ ቡድን የጋበዛቸው አቡነ ማርቆስ “ህንጻ” እያሉ ሲያቃልሉትና “አሳማ ያርቡበት” ያሉበትን ቪድዮ በድጋሚ ትመለከቱት ዘንድ፤ ላላዩትም ታሳዩ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። አቡነ ማርቆስ ደብረሰላምን አሳማ ማርቢያ አድርጉት ቢሉም የእግዚአብሄር ቤት የአሳማ ማርቢያ አይሆንም።

ወ ስብሐት ለእግዚአብሔር!

“ኢንሔሊ ተቃርኖተ ጽድቅ” “ከእውነት ጋራ የሚጋጭ ነገር እየሰራን ለመኖር አንድፈር” –ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

$
0
0

ቀሲስ አስተርዕየ

ቀሲስ አስተርዕየ

አቡነ ማቲያስ

አቡነ ማቲያስ

nigatuasteraye@gmail.com
ሚያዚያ ፳፻፮ ዓ.ም.

ማሳሰቢያ፦
እንደሚታወቀው ከዚህ ቀደም በተከታታይ ያቀረብኳቸው ጽሁፎች፤ አንባቢ በግልጽ ወደሚያያቸው ክስተቶች ቀጥታ ዘልዬ በመግባት አይደለም። ይህም ባለመሆኑ፤ ከነገረ መለኮት ውስጥ ሳልገባ ህዝባውያን የሆኑትን ነገሮች ብቻ ባቀርብ ላንባቢ እንደሚቀል የተለያዩ ምክሮችና ሀሳቦች ከተለያያችሁ ወገኖቼ ቀርበውልኛል። እንደናንተ ሀሳብ ቢሆን ኖሮ ፤ ላንባቢ ጥልፍልፍ ከሚሆንበት ነገረ መለኮት ከመግባት ይልቅ፤ ወቅታውያን የሆኑትን ነገሮች ብቻ እንደክር በመምዘዝ ለማሳየት በቀለለኝ ነበር። ምክራችሁ ትክክል ቢሆንም፤ ለመቀበል ከዚህ በታች በገለጽኳቸው ምክንያቶች እንደምቸገር ተረዱልኝ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ወደ ህሊናችን እንመለስ (አንተነህ መርዕድ)

$
0
0

 

Landindየመሬት ጥያቄ ብዙ መስዋዕት የተከፈለበት ቢሆንም አሁን በባሰ ሁኔታ ወያኔ ከሁሉም ዜጋ ነጥቆ በግሉ አድርጎታል። ማንም ኢትዮጵያዊ የሃገሩ፣ የመሬቱ ባለቤት አይደለም። ከዚህ የባሰ ዜጎችን የማዋረድ ተግባር የለም። አባቶቻችን መሬታቸውን ለባዕድ አንሰጥም በማለት ህይወታቸውን ከፍለው አቆይተውናል። ዛሬ እኛ የራሳችን መሬት ባለቤት እንዳንሆን ሁላችንንም መሬት አልባ ያደረገን ስርዓት ዜጎችን አፈናቅሎ ካድሬዎቹን በመሬት ችብቸባ አሰማርቷል። ለባዕዳን ከመሸጥ አልፎ “እኛም የመሬት ባለቤት ልንሆን ይገባናል” ያሉትንና ይህንኑ የዜጎችን ህጋዊ መብት የጠየቁትን ሁሉ በጠራራ ፀሃይ ባደባባይ ይገድላል።

ጋምቤላዎች፣ አፋሮች፣ ሲዳማዎች፣ ጉጂዎች፣ ሶማሌዎች ዛሬ ደግሞ አምቦዎችና ጎንደሮች የተገደሉት መሰረታዊ የሆነውን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በማንሳታቸው ነው። በየቦታው እያናጠለ ዜጎችን የሚገድለው የወያኔ ስርዓት በቀነበበልን ጠባብ መንደር ተከልለን ጥቃቱ ወደየቤታችን እስኪመጣ የምንጠብቅ ገልቱዎች መሆናችንን ከብዙ የህይወት መስዋዕት በኋላ እንኳ የተማርን አይመስልም። ትናንት አገራዊ አጀንዳ ይዘው የመታገልና መስዋዕት የመክፈል ታሪክ ያላቸውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች “የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሶማሌ…” እያለ ከፋፍሎ በወንድሞቻቸው ላይ የሚደረገውን ጥቃት በጋራ  እንዳይከላከሉ እስከ ማድረግ ደርሷል። አያቶቻችን ከሰሜን ከደቡብ፣ ከምስራቅ ከምዕራብ ተጠራርተው ጠላታቸውን በመከላከል ተደራርበው የወደቁባት ይህች አገር የማን ናት? ኦጋዴን፣ ኤርትራ፣ መተማ ወዘተ. የወደቁ አባቶቻችንን አጥንት የየትኛ ጎሳ አባል እንደሆኑ መለየት እንችላለን?

ከመቶ ዓመት በፊት ተገደሉ የተባሉ ዜጎቻችንን ካረፉበት መቃብር እየተቆፈረ ለፖለቲካ ፍጆታ፣ ለከፋፋይ ዓላማ የሚያናፍሰው ስርዓት በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ዜጎች መሰረታዊ መብታቸውን በሰላማዊ መንግድ ስለገለጹ ብቻ እየገደለ ነው። ሰሞኑን ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራሊስት አመራር አባላት እንደገለጹት ያለፈ ታሪክ ስህተትን ስንቆፍር አዲስ ኢትዮጵያን በጋራ ለማለም አልቻልንም። ተባብረን አሁን በተከሰተ ችግር ዙርያ እንታገል ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢ ነው።

ከሁለቱም ወገን ያሉ ጽንፈኞች የሚያካሂዱትን የጥላቻ ዘመቻ ችላ ብለን አሁን ባለ የጋራ ችግር ዙርያ ትግልን በማቀናበር የምንመኛትን ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያ ለመገንባት መተባበር የወቅቱ አብይ ቁም ነገር ነው።

የሁሉም ኢትዮጵያውያን ህይወት ክቡር ነው። ለንጹህ ዜጎች መሞትና መታሰር ሃላፊ የሆኑትን ሁሉ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ መብት ተቋማት፣አክቲቢስቶች፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰቦች እየመዘገቡ መያዝ ያስፈልጋቸዋል። ሁሉም በሰራው ነገ ተጠያቂ መሆኑ አይቀርምና።

የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ከደርግ አወዳደቅ ለመማር ጊዜው ሩቅ አይደለም። መንግስቱ ኃይለማርያምና ከጥቂት ባልደረቦቹ በቀር አብዛኞቹ ላለፈ ተባባሪነታቸው ዋጋ ከፍለውበታል። ከሁሉም በላይ ግን የህሊና ጠባሳቸው ቀላል አይደለም። አቅፋችሁና ደግፋችሁ የያዛችሁት ስርዓት ተጠቃሚዎችና ወንጀለኞች ጥቂትና በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ለማምለጫቸው ቦታ፣ ለኑሮአቸው ከፍተኛ ንብረት አሽሽተው የመጨረሻውን ቀን እየተጠባበቁ ነው። እነሱ ሲሄዱ በጠራራ ፀሃይ ልጆቻቸው የተገደሉባቸውን፣ መሬታቸውንና ንብረታቸውን ተነጥቀው የተፈናቀሉን፣ በየእስር ቤቱ በግፍ ሲማቅቁ የነበሩትን፣ ባጠቃላዩም ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ግፍ ሲፈጽምባቸው የነበሩ ኢትዮጵያንን ቀና ብላችሁ ማየት የማትችሉበትና ለድርጊታችሁ ተጠያቂ የምትሆኑበት ጊዜ ይመጣል። ወደ ህዝባችሁ መመለስ ካለባችሁ ጊዜው አሁን ነው።

ሁላችንም ወደ ህሊናችን እንመለስ። እየጠፋ ያለው ነገ አገሪቱን የሚረከቡ ወጣቶች ህይወት ነው። በደርግ ወቅት በእርስ በርስ መጨራረስ ከተሞች ወስጥ ያለቀው፣ በኦጋዴን በረሃ፣ በኤርትራና በትግራይ ጋራዎች የረገፉ ወጣቶቻችን፤ ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮ-ኤርትራ ትርጉም አልባ ጦርነት እንዲሁም በየቦታው የተገደሉ ዜጎች ቁጥር የባከነውም ንብረት አገራችንን አሁን ላለችበት የዓለም ጭራነት ዳርጓታል። ከዚህ በኋላ ሌላ ውድ ህይወትና የአገር ሃብት ማጥፋት የማንኛውም ቅን ኢትዮጵያዊ አላማ አይሆንም። ችግራችን የጋራ ነው። አገሪቱም የጋራችን ናት። የገራ የሆነ አገርና ህዝብ ደህንነት የሚጠበቀው በጋራ ተሳትፎ ነው። ድብቅ አጥፊ ዓላማ ካላቸው በቀር ሁላችንም ለጋራ ቤታችንና ህዝባችን ባንድ እንቁም።

ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርክ

አንተነህ መርዕድ  amerid2000@gmail.com

ሜይ 2014

 

 

 


ህመሙ የጋራ ሀመም ነው ጩኸቱም የሁላችንም ጩኸት ነው (የአቋም መግለጫ እና ምክር ብጤ!)

$
0
0

ከአቤ ቶክቻው

በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ክልል ሁሉም አካባቢዎች ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ እያሰማ ነው። መንግስትም በበኩሉ የፈሪ ዱላውን እያወረደው ይገኛል። እውነቱን ለመናገር መፍራት ተቃወሞ የሚያመጣ ተግባር ሲፈጽሙ ነበር እንጂ ተቃውሞውን አለነበረም።
Wallaggaa2014_3
ኢህአዴግዬ በክላሿ ተማምና ያላስቀየመችው የህብረተሰብ ክፍል ካለ እርሱ ኢህአዴግን እንደ ግል አዳኙ የተቀበለ ብቻ ነው። ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላየ እየተወሰደ ያለው ርምጃ በተመሳሳይ መልኩ በአማራ ክልል ጎንደርም እየተወሰደ ይገኛል ይሄው አይነት ከዚህ በፊት በጋምቤላ፣ በአዲሳባ፣ በደቡብ ብሄር በሄረሰቦች ክልል ሀዋሳ እና ተረጫ ወረዳ ላይ እንዲሁም በቅርብ ጊዜ በሀረሪ ከልል ሀረር ላይ ሲወሰድ ነበር። (እነዚህ በቀላሉ ያስታወስኳቸው ናቸው ማስታወሻ ብናገላብጥ ደግሞ ሌላም ሌላም ይገኛል)

በጥቅሉ እነደ ኢህአዴግ ያሉ ”ፋራ” አምባገነኖች ለሰላማዊ ተቃወሞ ሰላማዊ ምላሽ ሲሰጡ ታይቶም አይታወቅ። እኛ የምንጸለይ የነበረው ኢህአዴግ ገደላውን ትታ የምትጠየቀውን እንደ ዘመናዊ ገዢ ፓርቲ፤ በቅጡ ብትመልስ ነበር። ግን አልሆነም። በዚህም የተነሳ እስከ አሁንም ድረስ በኦሮሚያ ክልል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰላማዊ ዜጎች በአልሞ ተኳሾች እና ሳያልሙ ተኳሾች ተገድለዋል ቆስለዋልም።

ይህ ህመም የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች እና ዘመዶቻቸው ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያውያን ነው። ሰለዚህም ሁሉም በያለበት እና በየ አቀሙ ጩኸቱን ሊቀባበል ይገባል የምለው።

“አንተ ውጪ ቁጭ ብለህ….”

ወጪ ሀገር የሚገኝ ሰው የሚገጠመው ትልቁ ፈተና ይሄኔ ነው። ጩኸቱ የጋራ ነው ብዬ ስናገር አንዳንድ ወዳጆች ገና አንብበው ሳይጨረሱት ሁላ “አንተ ውጪ ቁጭ ብለህ እኛን ልታስጭርስ” የሚል አስተያየት ለመጻፍ ሲያቆበቁቡ ይታየኛል። በተወሰነ ደረጃ እወነትም ውጪ ሃገር የሚገኝ ሰው “አይዟችሁ አትፍሩ በረቱ…” ብሎ ለማለት የሞራል የበላይነት እንደሌለው አምናለሁ።

ስለዚህም አትፍሩ ብዬ አልመክርም። ነገር ግን እየፈራንም ቢሆን፤ ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ጩኸቱ የጋራችን እንደሆእነ ልናሳይ ይገባል፤ ይሄ ማለት የግድ አደባባይ ውጡ ብሎ ማደፋፍር አይደለም። ቢያንስ ግን ከገዳዮቹ ጋር ባለመተባበር ጩኸቱ እና ኡኡታው የእኛም መሆኑን ማሳየት እንችላለን ለማለት ነው።

በተጨማሪም በተለያዩ ሰለፎቻችን ላይ፤ ለምሳሌ ነገ በሚካሄደው የአንደነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ የእሪታ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ ከሚያሰማቸው እሪታዎች አንዱ በኦሮሚያ እንዲሁም በአማራ ክልል ጎንደር ላይ እየተደረገ ያለውን የሰላማዊ ዜጎች ጭፈጨፋ የሚያወግዝ ሊሆን ይገባዋል የሚል እምነቴን ለማካፈልም ነው።

ከዚህ በተጨማሪም በጎንደርም ሆነ በኦሮሚያ አካባቢዎች እየተደረገ ያለውን ግድያ በሶሻል ሚዲያዎቻችን እና ባገኘነው አጋታሚ በማሰራጨት ጩኸቱ የጋራችን መሆኑን እናሳይ ለማለትም ነው። ምክንያቱም አንድም ዛሬ በተለይ በኦሮሚያ ክልል እየደረሰ ያለው ትላንት ብብዙዎች ላይ ደርሷል፤ ነገም በእያንዳንዳችን እንደማይደርስ ዋስትና የለንምና ነው!

በመጨረሻም

ህይወታችውን ላጡ ነፍስ ይማርልን!
ለቆሰሉት ምሀረትን ይስጥልን!
የሚገድሉትንም ክላሻቸውን ያክሽፍልን!

አሜን!

(የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ) ሁሉም ለበጎ ነው

$
0
0

debereselam-medhanialem
በቀለ ገብርኤል (ሲሳይ) – ከሚኒሶታ

እስኪ ወደ ኋላ ሄድ ብለን ያለፍንበትን መንገድ በትዝታ እንቃኝ – ጥናታዊ ጹሑፍ በሁለቱም ወገን ይቅረብ ተብሎ ለወራት ከተዘጋጁ በኋላ፣ የቀረበውን ካዳመጥንና ከሰማን በኋላ ስድስት ሰዓት የፈጀው ስብሰባችንን ማንም ሰው ረግጦ ሳይወጣ ድምጽ ቢሰጥበትም ኮረም አልሞላም በሚል ወዝግብ ተነስቶ አሁን ላለንበት ደረጃ ደርሰናል። ፍረድ ቤት ጣልቃ ገብቶ ይገላግለናል ያልነው፣ ምንም እንኳን ጠቅላላ ጉባሄ እንዳይጠራ ቢሞከርም፣ ነገር ግን እኛው እንድንወስንበት ጉዳያችንን ተመልሶ ወደ እኛ መጥቷል።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የአራቱ ሃዋርያት በትግራይ ጉብኝት አነጋጋሪ ሆኗል (ከአስገደ ገ/ስላሴ)

$
0
0

ከአስገደ ገ/ስላሴ፣ መቐለ

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ

ሰሞኑን ባልተለመደ መንገድ ከትግራይ ክልል የሰልጣን መዋቅር እርከን ወጣ ያለ የክልሉን ስልጣን የተጋፋ (የነጠቀ) የስለላ ስራ የሚመስል እንቅስቃሴ ከ23 አመት የህ.ወ.ሃ.ት አገዛዝ በኃላ አራት አዛውንት የለውጥ ሃዋርያት መስለዉ በመላው ትግራይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ ከዛም አልፎ በቀበሌ  ከተሞች ሳይቀር በልዩ ሃይል ታጅበዉ እየዞሩ ሰንብተዋል። -- ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ—

 

የቁጥር ጨዋታ?! – ፂዮን ግርማ

$
0
0

ጠ/ሚ ኃይለማሪያም በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ

(በፋክት መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 33 የካቲት 2006 ታትሞ የወጣ)

fukitሕፃን እዮሲያስ የጓደኛዬ ልጅ ነው። በሰባት ዓመቱ ሁለተኛ ክፍል ገብቷል። ፈጣንና መጠየቅ የሚወድ ታዳጊ ነው። ባገኘኝ ቁጥር በጥያቄ ልቤን ጥፍት ያደርገዋል። አብዛኛው ጥያቄዎቹ ትምሕርት ቤት ከጓደኞቹ ጋራ ከሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚመነጩ ናቸው። ባለፈው ሰሞን እንዲህ ብሎ በእንቆቅልሽ መልክ ጠየቀኝ። ለእኔም አጠያየቁ ልጅነቴን ስላስታወሰኝ በትዝታ ፈገግታ ታጅቤ “ምናውቅልህ” አልኩት። ”እ … ቢሄዱ፣ ቢሄዱ የማይሰለቻቸው?” አለኝ። ጥያቄውን እኔ ከለመድኩት የልጅነት የእንቆቅልሽ መልስ ጋራ ለማዛመድ የዱር አልቀረኝ የቤት መንገድ አይሰለቻቸውም ስል ያሰብኳቸውን እንስሳት ማሰላሰል ቀጠልኩ። የመሰሉኝንም ስማቸውን ደረደርኩለት፤ አልተሳካልኝም።

እዮሲያስ አገር ስጭኝ አለና በሰጠኹት አገር ላይ ፍልስስ ብሎ፤ ”ቢሄዱ፣ ቢሄዱ የማይሰለቻቸው … እ … ውሃ፣ መብራት እና የስልክ ኔትወርክ” ሲል ያልጠበኩትን ምላሽ ሰጥቶ በደንብ አስፈገገኝ። ዐዋቂን እንጂ ሕፃናትን የሚያሳስባቸው የማይመስለን የውሃ፣ የመብራት እና የስልክ አገልግሎት መጓደል ከማሳሰብ አልፎ በእንቆቅልሻቸው ውስጥ አስገብተው እንደ ሥነ-ቃል በየቦታው እንዲያዛምቱት እንዳስገደዳቸው ተገነዘብኩ። ቤት ውስጥ በተደጋጋሚ የሚሰሙት “ውሃ ሄዳለች፣ መብራት ጠፍቷል፣ ኔትወርክ የለም” የሚለውን ነው፤ መሄድ፣ መጥፋት እና አለመኖር የሚዛመዱት ደግሞ ከመንገደኝነት ጋር ነውና ስለእንቆቅልሹ ለእዮሲያስ እና ለጓደኞቹ አጨበጨብኩላቸው።

ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ “አዲስ አበባ ውስጥ ሃያ አራት ሰዓታት ውሃ የሚያገኘው የከተማው ክፍል ሰባ አምስት በመቶ ነው” ብለው የሕፃን እዮሲያስ እንቆቅልሽ ፈገግ እንዳደረገኝ ሁሉ እርሳቸውም ፈገግ አሰኙኝ። እንደ እርሳቸው አባባል፤ ሰባ አምስት በመቶ የሚኾነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ ያለመቋረጥ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሲያገኝ ሃያ አምስት በመቶ የሚኾነው ነዋሪ ደግሞ በተለያየ ደረጃ ያገኛል።አንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ደግሞ ዐሥራ አምስት ቀን ቆይቶም ቢኾን ውሃ ያገኛል።

በውሃ እና በመብራት እጦት የአዲስ አበባ ሕዝብ እየተሰቃየ መኾኑን በመጥቀስ ጥያቄ ላነሱላቸው ጋዜጠኞችም ጥያቄው አጠቃላይ ስዕሉን የማያሳይ እና በተሳሳተ መረጃ ላይ የተመሰረተ መኾኑን በመጠቆም “አጠቃላይ ስዕሉን ካላየን በስተቀር የተሳሳተ ስዕል እንዳንሰጥ መጠንቀቅ አለብን” ሲሉ ማስጠንቀቂያ ቢጤም ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኅብረተሰቡን ችግሩ ያጡታል ብሎ ግምታዊ መላምት ማስቀመጥ ቢከብድም ምናልባት በማስታወሻ መያዣቸው ላይ የተሰጣቸውን መረጃ ሲያሰፍሩ ቁጥሩ ተገላብጦባቸው ሊኾን ይችላል ብሎ መገመት ግን ትክክለኛነት ይመስለኛል።

ምናልባት በቅርቡም “እኔ ለማለት የፈለኩት በተለይ ባለሥልጣናት በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ ያሉትን ጨምሮ ሃያ አምስት በመቶ የሚኾነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ሃያ አራት ሰዓት ንጹህ የመጠጥ ውሃ ያገኛል። ሰባ አምስት በመቶ የሚኾነው ደግሞ በአጭር እና በረጅም ጊዜ ተራ ውሃ ያገኛል።” የሚል መግለጫን ይሰጡ ይኾናል ብሎ መጠበቅ ሳይሻል አይቀርም። ለነገሩ ይቺ የቁጥር ጨዋታ የገዢዎቹ የተለመደ የጋዜጣዊ መግለጫና የፓርላማ ሪፖርት ማዳመቂያ መኾን ከጀመረች ከራርማለች።

ባለፈው ጊዜ እንዲሁ የጋዜጣ ማተሚያ ቤትን በተመለከተ ጥያቄ ቀርቦላቸው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጋዜጣን በጥራት እና በብዛት የማተም አቅም ያለው ብቸኛ ማተሚያ ቤት “ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት” ነው። እንዲሁም በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን ጋዜጣ ማተም የሚችል ማሽን ያላቸው ማተሚያ ቤቶች ከሦስት አይበልጡም እነርሱም ቢሆኑ ከላይኛው አካል ፍቃድ ካላገኙ በስተቀር ለማተም ፍቃደኛ አይደሉም። ታዲያ እውነታውን ያጡታል ተብለው የማይታሰቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደረሰኝና የአድራሻ መያዣ ካርድ የሚያትሙትን ጥቃቅን ማተሚያ ቤቶች ሳይቀር ተደምረው ሲሰጣቸው እንደወረደ ተቀብለው አገሪቱ ላይ ወደ ሁለት መቶ ሃምሳ የሚጠጉ ማተሚያ ቤቶች እንዳሉ ጋዜጣ ማሳተም የሚፈልግ አካል ካለም ወደ እነዚህ ማተሚያ ቤቶች ሄዶ ማሳተም እንደሚችል ሲመክሩ ሰምቼ፤ ”የእነዚህ ማተሚያ ቤቶች አድራሻ የት ይኾን?” ስል ልጠይቃቸው ፈልጌ ነበር።

አሁን ደግሞ በእርሳቸው የመንግሥት አስተዳደር ሥር የሚተዳደሩ ብዙኀን መገናኛ ሳይቀሩ በየጊዜው የሚያነሱትን የአዲስ አበባ ከተማ የውሃ ችግር በምን ስሌት እንደተሠራ በማይታወቅ መልኩ ሰባ አምስት በመቶው የከተማው ነዋሪ የተሟላ አገልግሎት እንደሚያገኝ ደምድመው ተናገሩ። እነ ሕፃን እዮሲያስ እንኳን “መንገደኛ” ያደረጉትን “ውሃ” እርሳቸው “የትም ንቅንቅ ብሎ አያውቅም” ሲሉ የቤት ልጅ አደረጉት። የአዲስ አበባ ከተማ የውሃ ሽፋን በመቶኛ እያደገ መሄዱንማ አገልግሎቱን የሚሰጠው የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣንን በየቤቱ በዘረጋው የውሃ መስመርና የቧንቧ ቆጣሪ ቁጥር ልክ ለክቶ ሁሌም በሚሰጠው መግለጫ ሲነግረን ቆይቷል። ከዛም በላይ በአንዳንድ አካባቢዎች የከፋ የውሃ እጥረት ሲያጋጥምም በውሃ ማከፋፈያ መኪና ውሃን ለኅብረተሰቡ የማድረስ አገልግሎት እንደሚጀምርም ጭምር ሲናገር ተሰምቶ ነበር። ጥያቄው “በየቤቱ ባሉት የውሃ ቧንቧዎች አማካኝት ሊወርድ የሚገባው ውሃ መቼ ነው ከሄደበት የሚመለሰው?” የሚለው ነው።

ነዋሪዎች በየመንደሩ ውሃ መጣ አልመጣ እያሉ፣ በርካቶች የሌሊት እንቅልፋቸውን መስዋዕት አድርገው ሲያገኙ እያጠራቀሙ ሲያጡ ደግሞ ከያለበት እያስቀዱ በሚኖሩባት ከተማ “ሰባ አምስት በመቶው በተሟላ ሁኔታ ውሃ ያገኛሉ” ማለት ተናጋሪውን ትዝብት ላይ ይጥላል። ይህን መግለጫ በየቤቱ ሆኖ የሚከታተለው “ውሃ አጥ” ነዋሪ ምናልባት በያለበት ሆኖ “ ውሃ የጠፋው እኛ አካባቢ ነው እንጂ ሌላ ቦታ ውሃ አለ ማለት ነው” በሚል ሊያስብ ስለሚችል ቁጥሩን አምኖ ይቀበላል በሚል ከኾነ ያስኬዳል። ነገር ግን እኔ እንኳን በግሌ ለማረጋገጥ ከሞከርኳቸው አዲስ አበባ ውስጥ ካሉ፤ የረር ጎሮ፣ አያት፣ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፣ አስኮ፣ ዊንጌት፣ ኮተቤ፣ ፈረንሳይ፣ ሽሮሜዳ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ለቡ፣ መገናኛ፣ ሃያ ሁለት፣ በአብዛኛው የኮንደምኒየም ቤቶች እና ሌሎች ቦታዎች ያሉ ነዋሪዎች ውሃን በየተራ እንደሚጠቀሙ ነው። እነዚህ አካባቢ የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በስንት በመቶ ታስበው ይኾን? ጠቅላይ ሚኒስትር።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እንደ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፍ ቢያደርግለትና ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ሃያ አራት ሰዓት ውሃ ቢያገኝ፤ እንዲሁም በከፊል የሚያገኘው የኅብረተሰብ ክፍል ሃያ አምስት በመቶው ብቻ ቢኾን ኖሮ ችግርን በሂደት የመላመድ ባሕል ባለው በዚህ ማኅበረሰብ ውስጥ ፍጹም የውሃ እጥረት እንደ ችግር አይነሳም ነበር። ምናልባት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትክክለኛውን ቁጥር ለማግኘት የአዲሱን ባቡሩን ቀለም ለመምረጥ በየቦታው እንደተቀመጡት መዝገቦች ዓይነት በየአካባቢው በማስቀመጥ መረጃን ለማሰብሰብ ቢሞክሩ የተገላበጠውን ቁጥር ያገኙታል ብዬ እገምታለሁ።
***********
በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የተንቀሳቃሽ ስልክ፣ የመደበኛ እና ኢንትርኔት አገልግሎት ተገቢ አገልግሎት አለመኖር እና ጥራት መጓደል ተጠቃሚውን እጅግ ካስመረሩት ጉዳዮች አንዱ ነው። “ኔትወርክ ተጨናንቋል፤ እባክዎትን ትንሽ ቆይተው ይደውሉ፤ የደወሉላቸው ደንበኛ መሥመሩን እየተነጋገሩበት ነው፣ እባክዎትን ደግመው ይሞክሩ፤ የኔትወርክ ሽፋን የለም” የሚሉት በኢትዮ-ቴሌኮም አገልግሎት ላይ የተለመዱ ምላሾች ናቸው። ስልክ ሲደወል ከስልኩ ውስጥ ድምጽ አለመስማት፤ ስልኩ ከተነሳ በኋላ የራስን ድምጽ መልሶ መስማት፣ እያወሩ የራስን ድምጽ እንደ ገደል ማሚቱ ከሥር መስማት የተለመዱ የአገልግሎቱ አካል ናቸው። ወደ ባንክ እና በኢንተርኔት አገልግሎት ወደሚሰጡ መሰል ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ሲኬድም “ኮኔክሽን የለም ትንሽ ጠብቁ “የሚሉት ምላሾች እንደተገቢ ምላሽ መቆጠር ከጀመሩ ሰንብተዋል።

እነሕፃን እዮሲያስ “መንገድ የማይሰለቻቸው” ሲሉ በእንቆቅልሽ መልክ ካስቀመጧቸው ውስጥም የቴሌኮም አገልግሎትን በሚመለከት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ሲናገሩ፤ በቴሌኮም አገልግሎት ሥር ያሉት የተንቀሳቃሽ፣ የኢንተርኔት እና የመደበኛ አገልግሎት መቆራረጥ የተከሰተው አሠራሩን ዘመናዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመሳሪያ ለውጥ ሂደት አገልግሎት መዛነፍ መኖሩን ገልጸው ይህ መዛነፍ በተቀመጠለት የስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚስተካከል እርግጠኛ ሆነው ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀናት በፊት “ከስድስት ወራት በኋላ” ሲሉ ያስቀመጡትን የጊዜ ገደብ የኢትዮ – ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊው አቶ አብዱራሂም አሕመድ፤ ችግሩን ለማስወገድ መሠረተ ልማት ለመቀየር የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑን እና በጥቂት ወራት ውስጥ በጣም በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ለዚህ ሲባልም የቅድሚያ ቅድሚያ ተሠጥቶት ዝርጋታውን የማቀላጠፍ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ከተናገሩ ስምንት ወይም ዘጠኝ ወራት መቆጠሩን አስታውሳለሁ። ባለሥልጣናቱ በቁጥር እየተጫወቱ የሚዘልቁት እስከመቼ ይኾን?

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፤ ኢትዮጵያ የመረጠችው የቴክኖሎጂ ኩባንያ፤ ”ዴንማርክ”፣ “ኖርዌይ”፣ እና “እንግሊዝ” የሚጠቀሙበት “ሁዋዌ” የተሰኘውን ኩባንያ መሆኑን በኩራት ሲናገሩ ተሰምተዋል። ሌላውን ቁሳቁስ ቢሆን እነ “ዴንማርክ”፣ “ኖርዌይ”፣ እና “እንግሊዝ” እና የመሳሰሉት አገራት ኢትዮጵያ ከምታመጣበት “ቻይና” አይደል እንዴ የሚያስመጡት? ዋናው ጥያቄ የሚነሳው ለእነዚህ አገራት የሚገባው ዕቃ ጥራት እና ኢትዮጵያ የሚገባው ዕቃ ጥራት አንድ ዓይነት መሆን አለመሆኑ ላይ ነው። እነዚህ አገራት ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቁጥጥር አንድ መሆን አለመሆኑ ላይ ነው። በእነዚህ አገራት ያለው ሙስና እና በኢትዮጵያ ያለው ሙስና አንድነት እና ልዩነት ላይ ነው።

ጥያቄው መሆን ያለበት “ሁዋዌ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘረዘሯቸው አገራት ካሉት አስተዳዳሪዎች ጋራ ያለው የሥራ ግንኙነት እና ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አስተዳዳሪዎች ጋራ ያለው የሥራ ግንኙነት ምን አንድነት አለው የሚለው ላይ ነው። ሌላው ጥያቄ ደግሞ የእነዚህ አገራት ገዢዎች ለሕዝባቸው ያለባቸው ተጠያቂነት እና የኢትዮጵያ ገዢዎች ያለባቸው ተጠያቂነት ነው። የ”ዴንማርክ”፣ የ”ኖርዌይ”፣ እና የ”እንግሊዝ” ገዢዎች በየስምንት ወሩ እየመጡ “ጥቂት ወራት ታገሱ፣ ከስድስት ወራት በኋላ ይጠናቀቃል፣ ዕድገቱ የፈጠረው ችግር ነው” የሚሉ ምክንያቶችን እየደረደሩ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም እንደማይሞክሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ያጡታል ብዬ አላስብም። ለማንኛውም ስድስት ዓመት መታገስ ለለመደ ሕዝብ ስድስት ወር እሩቅ አይደለምና “ኔትወርኩ አያሰማማም፣ ኢንትርኔቱ ኮኔክሽን የለውም፣ የቤቱ እና የቢሮው ስልክ አይሠራም” እየተባባሉ ስድስት ወር መጠበቅ ብዙ የሚከብድ አይመስለኝም።
የአሁኑም የቀድሞውም ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሲሉ እንደተሰሙት፤ መንግሥት የቴሌኮምን አገልግሎት ወደ ግሉ ዘርፍ ማስተላለፍ የየማይፈልገው፤ ቴሌ ገንዘብ የሚታለብበት ተቋም በመኾኑ ነው። ምናልባት ለኅብረተሰቡ የሚከብደው ስድስት ወር መጠበቁ ብቻ ሳይሆን ባልተገኘ አገልግሎት መታለቡ ሊኾን ይችላል። በአሁኑ ወቅት ባለው አገልግሎት በአብዛኛው አንድ ሰው ወደ ሚፈልገው ሰው ስልክ ደውሎ ለማግኘት ከአምስት እና ከስድስት ጊዜ በላይ ደውሎ የራሱን ድምጽ እየሰማ ለመዝጋት የሚገደድ ሲኾን ለዚህም ቴሌ የአገልግሎት ክፍያውን ያገኛል። እንደጠቅላይ ሚኒስትሮቹ አገላላጽ፤ ቴሌ ባልሰጠው አገልግሎት ኅብረተሰቡን ያልባል ማለት ነው። ስለዚህም ከባድ የሚመስለው ስድስት ወር መጠበቁ ሳይሆን ባልበላ አንጀት መታለቡ ነው።

የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ ቁጥርን በሚመለከት በ2003 እና በ2004 ዓ.ም. ከዕቅዱ በላይ ማሳካቱን የገለጸው ኢትዮ-ቴሌኮም ለ22 ሚሊዮን ሕዝብ ተንቀሳቃሽ ስልክ በመስጠት በሞባይል አገልግሎት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ስድስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ሲናገር ተሰምቷል። የተለመደው የቁጥር ጨዋታ ኾኖ ነው እንጂ፤ ደረጃው የአገልግሎት ጥራትን መሠረት አድርጎ የወጣ ቢኾን ኖሮ አገሪቷ ከአፍሪካ የመጨረሻው ተርታ ላይ ትሰለፍ ነበር።

***********
ሕፃን እዮሲያስ “ቢሄድ፣ ቢሄድ የማይሰለቸው” ካላቸው መንገደኞች ውስጥ አንዱ የመብራት አገልግሎት ነው። የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሠራተኛ የኾነ ታማኝ ምንጭ በአንድ ወቅት፤ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ድርጅት ውስጥ የምትሠራ ነገር ግን ልዩ ልዩ የጥቅማ ጥቅም ድጋፍ ይደረግላት የነበረች አንዲት ጋዜጠኛ ለኮርፖሬሽኑ በርካታና አስቸኳይ የኾኑ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነቶች እንዳለባትና ለዚህም አገልግሎት መብራት እየጠፋ ስለሚያስቸግራት የግል ትራንስፎርመር እንዲገጠምላት መጠየቋን ይነግረኛል። እርሱን ያስገረመው እርሷ ምን ዓይነት ኃላፊነት ላይ ብትኾን ለግሏ ትራንስፎርመር መጠየቋ ነበር። እኔ ደግሞ ምን ዓይነት ምላሽ እንደተሰጣት ጓጉቼ ጠየኩት። “ከአንቺ በፊት በጣም በርካታ ባለሥልጣናት ስለጠየቁ፤ ተራ ጠብቂ “ተባለች አለኝ። ምናልባት የአገሪቱ ባለሥልጣናት ለኅብረተሰቡ ችግር ቦታ ሳይሰጡ በቁጥር የሚጫወቱት፤ የውሃ፣ የመብራት እና የስልክ አገልግሎት ተራ እየጠበቁ በየግላቸው ስለሚያገኙ ይኾን?

tsiongir@gmail.com

ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰቀለ? (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

$
0
0

በዚህ ርእስ ላይ የምጽፈው ሃይማኖትን ለመስበክ ፈልጌ አይደለም፤ ከውስጥ የሚኮረኩረኝን ነገር ለማውጣት ነው፤ በኢትዮጵያ የተስፋ ሕልም አይታየኝም፤ የሚታየኝ የጥፋት ቅዠት ነው፤ ከሃያ ዓመት በላይ በመለስ ዜናዊና በጓደኞቹ በኩራትና በእብሪት የተዘራው ጥላቻ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልቡ የደም መግል እንዲቋጥር አድርጎታል፤ ይህንን የማይገነዘብ ያለ አይመስለኝም፤ ነገር ግን ባህል ሆኖብን አደጋ ማስጠንቀቂያን አንወድም፤ በአንጻሩ ግን በባዶ ሜዳ ለሽለላና ለፉከራ የሚጋብዘንን እንወዳለን፤ እኔ ማንንም የሚያስፎክር ነገር አይታየኝም፤ ማንንም የሚያሳብይ ነገር አይታየኝም፤ ክርስቶስ የተሰቀለበት ምክንያት ግን በድፍን ጨለማው ውስጥ ብልጭታን ያሳየኛል፤ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዋናው ምክንያት ‹‹ክፉን በክፉ አትመልሱ ስላለ ነው፤ የኢየሱስ ክርስቶስ አብዮት ይኸው ነው።

Pro Mesfin

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

‹‹ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደተባለ ሰምታቸኋል፤ እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሟችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉ፤ስለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ፤›› ማቴ. 5/43

አልፎ አልፎም ቢሆን እያንዳንዳችን ራሳችንን ልንጠይቀው የሚገባ ጥያቄ ነው፤– ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰቀለ? የኢየሱስ ክርስቶስ መሠረታዊው ትምህርት ክፉን በክፉ አትመልሱ የሚል ነው፤ እስቲ ይህንን የምታነቡ ሰዎች ይህን ሦስት ቃላትን ብቻ የያዘ ዓረፍተ ነገር ደጋግማችሁ አንብቡት፤ ቀላል ነው ብላችሁ አትለፉት፤ ይህ ትምህርት እንዴት ነው አስጊ ሆኖ የታየው? እንዴት ነው ለስቅላት የሚያበቃ ወንጀል የሆነው?\

እንራመድና ሌላ ጥያቄ እንጠይቅ፡- ዛሬ ከሁለት ሺህ ዓመታት በኋላ የክርስቶስ ትምህርት ገብቶናል ወይ? በየአህገሩ፣ በያገሩ‹ በየመንደሩ ስናይ የሰው ልጆች የክርስቶስን ትምህርት የሰሙ አይመስልም፤ ወይም ሰምተው ክርስቶስ የተናገረው ለመላእክት ነው ብለው ይሆናል! በአለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ውስጥ የሰው ልጆች በአጠቃላይ በተለይ ክርስቲያኖች ስንት ጦርነቶችን አካሄዱ? ስንትስ ሚልዮን ሰዎች አለቁ? ስንት ሚልዮን ተፈናቀሉ? ስንት ለዕድሜ ልክ አካለ-ስንኩላን ሆነዋል? ከሁሉም ይበልጥ በመስቀሉ ላይ ሆኖ ፍቅርን የሰበከውን የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ለጥልና ለመነታረኪያ እየተጠቀሙበት ነው።

ለትንሣኤ ለመብቃት ከሞት ጋር መጋፈጥ ያስፈልጋል፤ ያውም ተራ ሞት አይደለም፤ ለዓላማ በፈቃደኛነት የሚቀበሉት የመከራ ሞት ነው፤ መስዋእትነት የሚባለውም ይህ ነው፤ የኢትዮጵያ ዜና ማሰራጫ ሰዎች ሞት የሚለውን ቃል ይፈሩታል፤ አይጠቀሙበትም፤ ህልፈት በሚል ቃል ተክተውታል፤ እንደመለስ ያለ ሰው እንዴት ይሞታል፣ ያልፋል እንጂ! እንደዓለማየሁ ያለ ሰው እንዴት ይሞታል ያልፋል እንጂ! ይበልጥ የሚያስደንቀው በክብር ተሸኝተው የሞቱትን መስዋእት ሆኑ ማለታቸው ነው! ሞትን ስሙን እንክዋን ለመጥራት እየፈሩት መስዋእትነትን ሊያከብሩ ይከጅላቸዋል፤ ክርስቶስ ተደብድቦና ተገርፎ፣ በምስማር እጆቹና እግሮቹ በአንጨት ላይ ተከርችሞበት፣ በራሱ ላይ የእሾህ አክሊል አስቀምጠውበት ሰቅለው ከሞተ በኋላ ቀበሩት፤ በሞቱም ለሰው ልጆች ኃጢአት ራሱን መስዋእት አደረገ፤ ሞትንም፣ መቃብርንም አሸንፎ ተነሣ፤ ትንሣኤ ይህ ነው፤ ይህ ከባድ ነው፤ ክፉን በክፉ አትመልሱ የሚለው ትምህርቱ ከሁለት ሺህ ዓመታት በኋላ ያልገባን ለዚህ ነው።

በሌላ በኩል ስናይ አንዳንድ ሰዎች እንደእናት ቴሬዛ፣ እንደእናት አበበች ጎበና፣ እንደወንድም ብንያም (የመቄዶንያ)፣ … ያሉ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ለክርስቶስ ትምህርት ቅርብ ሆነው እናገኛቸዋለን፤ አብዛኛው በጣም ሲርቅ እነዚህ ሰዎች አብዛኛዎች ሰዎች የተሸነፉበትን ዳገት አንዴት ወጡት? እነሱ በብዛት ያገኙት ጸጋ ለሌሎች እንዴት አልደረሰም? እንደሚመስለኝ ሳይደርስ ቀርቶ አይደለም፤ ይኸው ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች አይገዛም ብሏልና በሁለት እጆቻቸው ሌላ ነገር እንቅ አድርገው የያዙ ሰዎች ጸጋውን የሚቀበሉበትና የሚይዙበት እጅ የላቸውም፤ የክርስቶስ ጸጋ ማጋበስን ይጠየፋል፤ የጤፍ ቅንጣት ያህል እምነት ቢኖራችሁ ተራራውን ና ብትሉት ይመጣል፤ ሂድ ብትሉትም ይሄዳል፤ ያለውንም እናስታውስ፤ ቀይ ባሕርን ለሁለት ከፍሎ፣ በአምስት ዓሣዎች አምስት ሺህ ሰዎችን መግቦ በተግባር አሳይቷል።

በኢትዮጵያውያን መሀከል የሚካሄደውን ንትርክ በጥሞና የተከታተለ ሰው አንድ አገር አንድ ማኅበረሰብ መሥርተን አንድ ሕዝብ ሆነን የምንቀጥልበት መንገድ አለ ወይ ብሎ ለመጠየቅ ይገደዳል፤ በአንድነት እንድንቀጥል የሚፈልጉትም ራሳቸውን ያታልላሉ፤ በታትነን እንቃረጣለን የሚሉትም ራሳቸውን ያታልላሉ፤ በሁለቱም ወገን ያሉት ለሚፈልጉት ነገር አልተዘጋጁም፤ ያቀፉት ተቃራኒ ምኞቶችን ብቻ ነው፤ የአንዱ ጥላቻ አባትና እናቱን እንዲያፋታ ይገፋፋዋል፤ የሌላው ጥላቻ ደግሞ የተጣሉ እናትና አባቱን አንድ ቤት ውስጥ ቆልፎባቸው፣ በግድ ተፋቀሩ! ይላቸዋል፤ ሁለቱም ከየራሳቸው ምኞት ውጭ የሚያዩት የለም፤ በአርሲ የተገነባውን ሐውልት እንዴት ያለ አእምሮ ጸነሰው? ጡት መቁረጥ የየት አካባቢ ባህል ነው? የኦሮሞን ባህል አያስታውስም? እኔ በሻሸመኔ ያየሁት በጦር ተገድሎ የተሰለበው ሰውዬስ ሐውልት የሚቆምለት መቼ ይሆን? እንዲህ ዓይነቱ ቁስል መፋቅ አብሮ የሚያኖር አይደለም።

ባህል ያልሆነ በጦርነት ጡትን መቁረጥ ከባህላዊው እንትንን ከመቁረጥ የበለጠ ሆኖ ሐውልት የሚሠራለት አዙሮ ማየት ሲጠፋ ነው፤ ራስን ሰድቦ ለሰዳቢ መስጠት የሚባለው ይህ አይደለም? ዶር. በድሉ ዋቅጅራ እንዳለው ‹‹ኑ ሀውልት እንስራ!! … ኑ ሀውልት እንስራ ለልጅ ልጅ የሚዘልቅ፣

የጥላቻ ጥንስስ
የቂም በቀል ድግስ።››

መጥፎ ምርጫ ነው፡- እየተደባደቡ፣ እየተጋደሉ ሲመች ለወንጀሉ ሐውልት እየሠሩ ማለፍ አንድ ምርጫ ነው፤ አንዱን ሰው ከታችም ይሁን ከላይ ምኑንም ይሁን ምኑን የቆረጠውን ኮንነን፣ ክፉን በክፉ አትመልሱ የሚለውን አርማ ይዘን ለአዲስ ግንባታ በኅብረት ወደፊት መገስገስ ሁለተኛ ምርጫ ነው፤ የክርስቶስን ትምህርት ብንከተል ከዚህ ያወጣን ነበረ፣ እንግዲህ በጥበቡ ያውጣን

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>