Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

እሰይ! ድል ለወጣቱ ትውልድ!!! (ከሮበሌ አባቢያ)

$
0
0

ከሮበሌ አባቢያ፣ 5/5/2014

addisdemo3የአንድነት ፓርቲ ያቀረበውን እጅግ በጣም ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ፣ አይኖቼ እምባ እያቀረሩ፣ ልቤን ደስታ ፈንቅሏት ነው እኔም እንደ ሰልፈኞቹ መፈክር እያሰማሁ ከናት  ሀገሬ ውጪ ከምኖርበት ከተማ በቴሌቪዥን ከመኖሪያ ቤቴ ተቀምጬ ነበር  የተመለከትኩትት።
እሰይ! ድል ለወጣቱ ትውልድ!!! በማለት ይህቺን መጣጥፍ ለመክተብ ተነሳሳሁ። ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንደጻፍኩት ግትር ኢትዮጵያዊ ነኝ። ያ እንዳለ ሆኖ፣ አንድነት ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ የተገኙት ታዳሚዎች በኦሮሞ ተማሪዎችና በደጋፊዎቻቸው ላይ የደረሰውን ፋሺስታዊ ጭፍጨፋ አበክረው በማውገዘቸው በወገኖቼ ኢትዮጵያን ኮርቻለሁ፤ አድሮብኝ ከነበረው ጥልቅ ሀዘንም ተፅናንቻለሁ፤ ለሰብአዊ መብት ዓላማ ስኬት ለመታገል ቃልኪዳኔን አድሻለሁ።

 ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ—


‹‹ትንሹ›› ተስፋዓለም (ከጽዮን ግርማ)

$
0
0

በአነጋገሩ ቀጥተኛና በጠባዕዩ ገራገር ነው፡፡ ‹ጥርስ ያሳብራሉ› በሚባሉ ስብሰባዎች፣ በኃይለ ቃል በተሞሉ የኤዲቶሪያል ውይይቶችና ግምገማዎች ሳይቀር ስሜቱን ውጦ በተረጋጋ መንፈስና በለዘብታ ቃል መመላለስ ጸጋው ነው፡፡ በኤዲቶሪያል ጠረጴዛዎችና ዴስኮች ዙሪያ በሐሳብ ለመግባባት ከሚደረጉ ግብግቦች ውጭና ባሻገር ቂምና በቀል አያውቅም፡፡ በደሙ ውስጥ ከሚዘዋወረውና ራሱን ከሰጠለት የጋዜጠኝነት ሞያውና የጋዜጠኝነት መርሕ የተነሳ ሌላ ዓለም፣ ሌላ ጥቅም፣ ሌላ ኑሮ ያለም አይመስለው፡፡ ለእርሱ ኑሮው፣ ለእርሱ ዓለሙ ተጨባጭ መረጃን ከወገናዊነት በጸዳ መልኩ ለሕዝብ ማድረስ ነው – ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፡፡
አሁን ተስፋዓለም በማኅበራዊ ደረ-ገፅ ላይ ‹‹ዞን 9›› በሚል መጠሪያ ገጽ ከፍተው በመጦመር ከሚታወቁ ስድስት ጦማርያንና (Bloggers) ኹለት ጋዜጠኞች ጋራ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ከታሰረ ዛሬ ዘጠኝ ቀን ኾኖታል፡፡ ተስፋለምን ጨምሮ ዘጠኙ ተጠርጣሪዎች የታሠሩት፤[ራሱን የመብት ተሟገች ነኝ ብሎ ከሚጠራ የውጭ ድርጅቶች ጋራ በሐሳብና በገንዘብ በመረዳዳት ማኅበራዊ ድረገፆችን በመጠቀም ሕዝቡን ለአመፅ ለማነሳሳት የተለያዩ ቀስቃሽ መጣጥፎችን ለማሰራጨት ሲዘጋጁ ተደርሶባቸዋል፡፡] በሚል እንደኾነ ፍርድ ቤት የቀረቡበት የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ያስረዳል፡፡
tesfalrm
ተጠርጣሪዎቹ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት አርብ ሚያዚያ 17 ቀን ማምሻውንና ቅዳሜ ሚያዚያ 18 ቀን ነው፡፡ እሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ በመዝገብ ቁጥር 118722 የቀረቡት የ‹‹ፎርቹን›› ጋዜጣና ‹‹የአዲስ ስታንዳርድ›› መጽሔት ፍሪላንስ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ከፍተኛ አዘጋጅ ከአስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምሕርና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘለዓለም ክብረት ለ29/08/2006 ተቀጥረዋል፡፡በመዝገብ ቁጥር 118721 የተካተቱት የአዲስ ዘመን ጋዜጠኛ የነበረችው ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎቹ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃነ ሲሆኑ ለ29/08/2006 ተቀጥረዋል፡፡ እንዲሁም በመዝገብ ቁጥር 118720 ሦስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን ለሚያዝያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የምርመራ መዝገቡን ያዩት ዳኛ፣ ተጠርጣሪዎቹ በቀጠሮው ዕለት ጧት አራት ሰዓት እንዲቀርቡ አዘዋል፡፡
ተስፋዓለም ተይዞ በተወሰደበት ዕለት ምሽት ድርጊቱን በአካል ተገኝቼ ተመልክቻለኹ፡፡ ጎረቤታሞች እንደመሆናችን የተስፋዓለም አንድ ትርፍ የቤት ቁልፍ በእኔ ቤት ይገኛል፡፡ እናም የቤቱ ቁልፍ በአጋጣሚ አንድ ሌላ ጓደኛችን ጋር ነበር፡፡ ባለፈው ዓርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ከሠላሳ ደቂቃ አካባቢ የቤቴ በር ተንኳኳ፡፡ በወቅቱ ሰዓቱ መሽቶ ስለነበር እኔም ኾነ ቤት ውስጥ የሚገኙት እኅቶቼ በጣም ደነገጥን፡፡ በሩን ከመክፈቴ በፊትም ያንኳኳውን ሰው ማንነት ጠየቅኹ፡፡
ማንነቴን በስም ከጠራ በኋላ እንድከፍት አዘዘኝ፡፡ በድጋሚ ማንነቱን ጠየቅኹ፡፡ የተስፋዓለምን ስም ሲጠራ ደነገጥኹና ተንደርድሬ ከፈትኹ፤ ምክንያቱም እንዲህ ያለ ጥሪ አጋጥሞኝ ስለማያውቅ ችግር ገጥሞት ሊሆን ይችላል ብዬ ጠረጠርኹ፡፡ ተደናብሬ ስወጣ ፊቱ በቁጣ የሚንቀለቀል ወጣት ተስፋዓለም ስለተያዘ እንደምፈለግና ወርጄ እንዳናግር አዘዘኝ፡፡ እየሔድን መረጋጋት ስላቃተኝ ማንነቱንና የተፈጠረውን ነገር እንዲነግረኝ ጠየቅኹት፡፡ ‹‹ማንነቴ ምን ያደርግልሻል፤ እርሱን በኋላ ታውቂዋለሽ፤ አኹን ወደ ተጠራሽበት ሒጂ፤›› አለኝ፡፡
ቅርብ ለቅርብ ስለነበርን ወዲያው ደረስን፡፡ ትንሹ ተስፋዓለም ከእርሱ በገዘፉ ወጣቶች ተከቦ ሜዳ ላይ ቆሟል፡፡ ከእግሩ ሥር በፌስታል የተቆጣጠሩ ነገሮች ተቀምጠዋል፡፡ ኹለቱ ፌስታሎች የሚለበሱ ነገሮች መኾናቸውን አስተውያለሁ፡፡ ኹኔታው በእጅጉ ግራ ስለገባኝ ምን እንደተፈጠረ መወትወት ጀመርኹ፡፡ የተፈጠረውን የሚነግሩኝ ሳይሆን የሚቆጡኝ ድምፆች በረቱ፡፡‹‹የሚነገርሽን አዳምጪ፤ አንድ ትርፍ የቤት ቁልፍ አንቺ ጋር አለ አይደል?›› አሉኝ፡፡ ቁልፉ እኔ ጋር እንዳለ ነገር ግን የሚገኘው ሌላ ጓደኛችን ጋር እንደሆነ ነግሬ እኔን ወደ አሳሰበኝ ጉዳይ ተመለስኹ፡፡
ተስፋዓለምን ለምንና የት እንደሚወስዱት ለማወቅ ጎተጎትኹ፡፡ ሁለት እጆቹን በደረበው ሹራብ ኪሱ ውስጥ ከቶ መካከላቸው የቆመው ተስፋዓለም የሚሔደው ማእከላዊ እንደኾነና ከሥራ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መኾኑን እንደተነገረው ነገረኝ፡፡ ከያዙት ወጣቶች መካከል ጭንቀቴን የተረዳው አንዱ ይህንኑ ደግሞ ኹለት የፖሊስ ልብስ የለበሱትን ሰዎች አመጣና ‹‹የሚወሰደው ሕጋዊ ቦታ መኾኑን እነርሱን አይተሸ አረጋግጪ››፤ አለኝ፡፡ ቤቱ ቢከፈትና ንብረት ቢጠፋ ተጠያቂ መኾኔን ከማስጠንቀቂያ ጋር በመንገር ትንሹን ተስፋዓለምን ብዙ ኾነው ይዘውት ሔዱ፡፡

ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን አባይ ምንጭ እና ተስፋ ኮከብ በሚባሉ ትምህርት ቤቶች፣ የኹለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በ‹‹ከፍተኛ አራት›› አጠናቅቋል፡፡ አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሥር የሚገኘው የቀድሞው ማስሚዲያ ማሠልጠኛ ኤጀንሲ የጋዜጠኝነት ትምህርቱን በመከታተል ላይ ሳለ ‹‹ሰብ ሰሃራን ኢንፎርመር›› የተባለ የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ላይ በገጽ ሥራና ቅንብር ባለሞያነት ተቀጠረ፡፡
ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላም የመዝናኛ ዜናዎችን በማዘጋጀት የጋዜጠኝነት ሥራን በዚኹ ጋዜጣ ላይ መሥራት ጀመረ፡፡ ቀጥሎም ‹‹ፎርቹን›› በተባለው ሳምንታዊ እንግሊዘኛ ጋዜጣ ላይ ተቀጥሮ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ዘገባዎችን መሥራት ጀመረ፡፡ የ‹‹ፎርቹን›› ጋዜጣ አደረጃጀትና ኤዲቶሪያሉ ጠንካራ ስለነበር የጋዜጠኝነት ችሎታውን ለማሳደግ በጋዜጣው ላይ የሠራባቸው ዓመታት አግዘውታል፡፡
ከ‹‹ፎርቹን›› በኋላ የቀድሞው የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ባለቤት የነበሩት ዶ/ር ፍሥሓ እሸቱ ባለቤትነት የሚዘጋጅ ደረጃውን የጠበቀና በዲዛይን ውበቱ ትኩረት ሳቢ የነበረውን ‹‹ማይ ፋሽን›› የተሰኘ እንግሊዘኛ መጽሔት ገጾች ዲዛይን ይሠራ የነበረው ተስፋዓለም ነበር፡፡ ከዚኹ መደበኛ ሥራው ጎን ለጎን የአሶሺየትድ ፕረስ የዜና ወኪል ረዳት በመኾን ለውጭ ሚዲያዎች መሥራት ጀመረ፡፡
‹‹ማይ ፋሽን›› መጽሔት ከተዘጋ በኋላ በከፍተኛ ደረጃ ተነባቢነት የነበረውን ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ ከሞያ ጓደኞቹ ጋራ መሠረተ፤ የጋዜጣው የዜናና ማኅበራዊ ፊቸር ገጾች አርታዒም ነበር፤ በዚኹ ወቅትም በተባበሩት መንግሥታት ሥር ለሚገኘውና በሰብአዊ ጉዳዮች ላይ ዜናና ትንታኔ ለሚያቀርበው ዓለም አቀፉ ኢሪን (IRIN) የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ኾኖ ይሠራ ነበር፡፡
በመንግሥት ጫና ምክንያት የአዲስ ነገር ጋዜጣው ከመዘጋቱ አንድ ወር በፊት በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ጋዜጠኞች (EEJA) ማኅበር በኩል በዩጋንዳ የአንድ ዓመት የሥራ ላይ ልምድ ልውውጥ ዕድል አግኝቶ ስለነበር ወደዚያው አመራ፡፡ በፕሮግራሙ አጋጣሚና ከልምድ ልውውጡ ጎን ለጎን በዩጋንዳ የተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎችና ‹‹ሩድሜክ›› በተባለ ሚዲያ ላይ ለአንድ ዓመት በሞያው ሲሠራ ቆይቷል፡፡
በዩጋንዳ የነበረውን የአንድ ዓመት የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም ካጠናቀቀ በኋላ ቆይታውን በማራዘም ‹‹ሐበሻዊ ቃና›› የተባለ መዝናኛ ላይ የሚያተኩር ባለቀለም የአማርኛ ጋዜጣ ማዘጋጀትና ማሳተም ጀመረ፡፡ ጋዜጣው በአቅም ማጣት ምክንያት እስከተዘጋበት ጊዜ ድረስ በዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያና ደቡብ ሱዳን ውስጥ ይሰራጭ ነበር፡፡
በመጨረሻም ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ የጋዜጠኝነት ሥራውን ፍሪላንስ ኾኖ በመቀጠል ለ‹‹አዲስ ፎርቹን›› እና ‹‹አዲስ ስታንዳርድ›› የእንግሊዘኛ ጋዜጣና መጽሔት መሥራት ጀመረ፡፡ ቢቢሲን (BBC) ጨምሮ ከተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች ጋራም በፍሪላንሰርነት መሥራቱን ቀጠለ፡፡ ከወራት በፊት የ‹‹ቢቢሲ››ዋ ዜና በዳዊ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ጋራ በአዲስ አበባ ያደረገችውን ‹‹ሃርድ ቶክ›› የቴሌቭዥን ፕሮግራም በረዳትነት ያዘጋጀው ተስፋዓለም ነበር፡፡
ተስፋዓለም የሚሠራው ዘገባ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ የሶማልያ ቀውስ በተባባሰበትና የኢትዮጵያ ጦር በአልሸባብ ላይ በዘመተበት ወቅት ስፍራው ድረስ ተጉዞ ዘገባዎች አስነብቧል፡፡ በተለይ ለምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጥ ሲኾን የሰሜንና ደቡብ ሱዳን ጉዳይን በሚመለከት በቦታው ተገኝቶ በቅርብ እየተከታተለ በ‹‹ፎርቹን›› ጋዜጣ ላይ ዘገባዎቹን አቅርቧል፡፡ ተስፋዓለም የወቅቱ የአካባቢ ጥበቃ ጋዜጠኞች ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ ከመኾኑም በላይ የአፍሪካ ኅብረትና ሌሎች ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፍረንሶች ላይ በመካፈል ዘገባዎችን ሠርቷል፡፡
በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ጋዜጠኛ ከየትኛውም ዓለም አቀፍ የዜና ተቋም ጋራ ሲሠራ ለኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅበታል፡፡ የየትኛውም ድርጅት የዜና ወኪል ይኹን ጥናት አድራጊ የውጭ ዜጋ ወደ ኢትዮጵያ ለሥራ ሲገባ ስብሰባው ወይ ጥናቱ የት እንደሚካሔድ፣ ማንን እንደሚያናግር አሳውቆ ፈቃድ ማግኘት አለበት፡፡ በዚህ አሠራር መሠረት ተስፋዓለም ከበርካታ ዓለም አቀፍ የዜና ወኪሎችና አጥኝዎች ጋራ የነበረው ቆይታ ከኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዕውቅና ውጭ አልነበረም፡፡
ተስፋዓለም በዕድሜው ሠላሳ አንድ ዓመቱ ነው፡፡ በጋዜጠኝነት ሞያ ላለፉት ዐሥር ተከታታይ ዓመታት አገልግሏል፡፡ ሥራ ሲጀምር በጣም ትንሽ ስለነበር ‹‹ትንሹ ተስፋዓለም›› የሚል ቅጽል በጓደኞቹ ተሰጥቶታል፡፡ በልጅነት ገጽታው ታላላቆቹ፣ ታናናሾቹም ኾኑ የዕድሜ አቻዎቹ እንደ ወንድም ስለሚቆጥሩት ‹‹ትንሹ›› የሚለው ቅጽል እስከ አሁን የሚታወቅበት ነው፡፡
ተስፋዓለም ግን ከስያሜው በላይ በእጅጉ ልቆ በሞያው ትልቅ ኾኗል፡፡ በሞያው የረገጣቸው አባጣ ጎርባጣዎች አብስለውት በሳልና በካር አድርገውታል፡፡ አንባቢነቱ፣ ነገሮችን በትኩረትና በተለየ መንገድ መመልከቱ፣ የማይሰለች ጠያቂነቱ፣ ተግባቢነቱና ጋዜጠኝነቱ ሰብእናውን አግዝፈውታል፡፡ ኹለቱንም ወላጆቹን በትምህርት ቤት ሳለና ገና ሥራ በጀመረበት ወቅት በሞት በማጣቱ እርሱና በሥሩ ያለችውን እኅቱን አይዟችኹ የሚላቸው ሰው አልነበረም፡፡ እናም ተስፋዓለምን በወጣትነቱ ማለዳ የተሸከመው የቤተሰብ ሓላፊነት እንደ አለት አጠንክረውታል፡፡ ‹‹ትንሹ›› ተስፋዓለም ማኅበራዊ ሓላፊነቱን ከኋላ ተሸክሞ እውነተኛ ጋዜጠኝነትን ለመተግበር በአያሌው ተግቷል፡፡
ተስፋዓለም ከኢትዮጵያ ውጭ ለመኖር የሚያስችሉት በርካታ ዕድሎች አዘውትረው ከፊቱ ይመጣሉ፡፡ እርሱ የሚመርጠው ለጋዜጠኝነቱ እገዛ ሊያደርጉለት የሚችሉ አጫጭር ሥልጠናዎችን እየወሰደ ወደ ሀገሩ መመለስ ነው፡፡ አገር ውስጥ የሚሰጡ ሥልጠናዎችም ተስፋዓለምን አያልፉትም፡፡ ‹‹ከኢትዮጵያ ከወጣኹ ከሞያዬ እለያያለኹ›› የሚል ስጋት ስለሚያድርበት አገሩ ላይ ኾኖ ክፉውንም ደጉንም እየተጋራ፣ ለሞያው ሥነ ምግባር ራሱን አስገዝቶ በሀገሩ ቁጭ ብሎ ይሠራል፡፡
ለሥራው ጥራት፣ ተጨባጭነትና ሚዛናዊነት ሟች የኾነው ተስፋዓለም የሚጠቅመውን መረጃ ለማግኘት ማንኛውንም መሥዋትነት ስለሚከፍል ሠርቶ ከሚያተርፈው ደመወዙ ይልቅ መልሶ ለሥራው የሚያውለው ወጪ ይበልጣል፡፡ እርሱ ኹሌም የገንዘብ ድኻ ነው፡፡ ያጠለቀው ጫማ በላዩ አልቆ እስኪቀደድ ድረስ ራሱን ለሥራው አሳልፎ የሚሰጥ የሳንቲም ድቃቂ የጨርቅ ዕላቂ ድኻ ነው!! ለዚህ ጠባዕዩና አኗኗሩ ከልጅነት እስከ ዕውቀት የሚያውቁት በርካታ ጓደኞቹ በምስክርነት ሳይቆጠሩ ምስክርነታቸውን ሰጥተውለታል፡፡
የተስፋዓለም ጓደኝነት ስለማይቆረቁር ባልንጀርነቱ ለብዙዎች ነው፡፡ ጋዜጠኝነት ከሚሰጣቸው ዕድሎች ዋነኛው ሠርክ አዲስ ሰው መተዋወቅ ነው ብሎ ስለሚያምን ወዳጆቹ በርካታ ናቸው፡፡ ኹሉንም ጓደኞቹን እንደየባሕርያቸው እስከአሁን አብሮ አቆይቶአቸዋል፡፡ ሰው ያሻውን ያኽል እንኳ ቢያስከፋው እንደ መሬት ነገር ቻይ እንጂ መከፋትን፣ መበቀልንና መቀየምን አያውቅም፡፡
እኔና ተስፈዓለም የምንተዋወቀው ፎርቹን ጋዜጣ በሠራንበት ወቅት ነው፡፡ ለጋዜጠኝነት እጃችንን ካፍታታንበት ፎርቹን ጋዜጣ ጀምሮ እስከ አሁንም ድረስ የልብ ጓደኛሞች ነን፡፡ ካለፈው አንድ ዓመት ተኩል ጀምሮ ደግሞ ጎረቤታሞች ኾነናል፡፡ተስፋዓለም መረጃ ለማግኘት በሚያደርገው ጥረት ሁሌም አደንቀዋለኹ፡፡በኦሞ የተከሰተው ጎርፍ በኮረንጋት ደሴት የሚገኙትን ዳሰነችና ኛንጋቶም ቀበሌ ነዋሪዎች ጠራርጎ እየወሰዳቸው መኾኑን እንደሰማ በቦታው ተገኝቶ ዘገባውን ለመሥራት፤ጭነት በያዘ አይሱዙ መኪና ላይ ከጭነቱ ላይ ተቀምጦ ሌሊቱን በሙሉ በመጓዝ አርባ ምንጭ ገብቶ ያደረውን መቼም አልረሳውም፡፡
ተስፋዓለም የመታሰሩ ወሬ እንደተሰማ ስለተስፋዓለም አስተያየት የሰጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ በተለይ በየፌስ ቡክ ገጾቻቸው እየወጡ ስለእርሱ “one of the prominent journalist” በሚል የመሰከሩለት የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ የኹሉም አስተያየት ግን እርሱ ለጋዜጠኝነት ሞያው የሚሰጠው ክብርና ዋጋ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡
የረጅም ጊዜ ጓደኛውና የቀድሞ የሥራ ባልደረባው ስመኝሽ የቆየ (ሊሊ) ‹‹ተስፋዓለምን የተዋወቅኹት ሥራ እንደጀምርኹ እርሱ ፎርቹን እኔ ደግሞ ሰብ ሰሃራን እየሠራሁ ነው፡፡ ገና ስቀጠር በጊዜው የሥራ ባልደረባዬ የነበረ ጋዜጠኛ እንዴት ጠንካራ ጋዜጠኛ መኾን እንዳለብኝ እየመከረኝ በየመሀል እንደ ትልቅ ምሳሌ ያደርግ የነበረው አንድ ሰው ተስፋዓለም የሚባል ፎርቹን የሚሠራ ጋዜጠኛ እያለ ነበር፡፡ ጽሑፎቹንም እንዳነብና እንዴት የተሟላ ዘገባ መጻፍ እንደምማር ይመክረኝ ነበር፡፡›› ትላለች፡፡
አያይዛም‹‹ከሳምንታት በኋላ ተስፋዓለምን ሳገኘው ከተባለው በላይ ለሞያው ያለውን ታታሪነት በተግባር አየኹት፡፡ በሥራው ላይ ምንም ነገር ጣልቃ እንዲገባበት አይፈቅድም፤ አካሉም፣ አእምሮውም ልቡም ለጋዜጠኝነት የተሰጠ ነው፡፡ ጓደኝነታችን ጠንክሮ ዐስር ዓመት ሲዘልቅም አንድም ቀን ገንዘብ ሳያጓጓው አብዛኛውን የሕይወቱን ክፍል ከሰጠለት ሞያ በሻገር የዋህነቱን፣ ቀጥተኛነቱን፣ ለሰው ደራሽነቱን እና ጠንካራነቱን እያየሁ አብረን ኖርን፡፡ ተስፋለም ለኔ ከሞያ ባልደረባ አልፎ ጓደኛና ወንድም ኾነኝ፡፡›› ብላለች- ለፋክት በሰጠችው አስተያየት፡፡
‹‹ለመጀመሪያ ጊዜ ይዤ የመጣሁትን ዜና እንዲያርምልኝ ሰጥቼው፤ ወደጀመርኩት የኢኮኖሚ ጽሑፍ ተመለስኩ። ነገር ግን አፍታም ሳይቆይ በንዴት እየቀዘፈ መጥቶ “አሁን በዚህ ሌሊት ይህ ዜና ተብሎ ይሠራል….›› አለኝ ተስፋዓለም ለሞያው የሚቆረቆር። አንዳች ስሕተት መስሎ የሚሰማውን ፊት ለፊት ከመናገር የማይቆጠብ ነው፡፡ያን ሌሊት በብዙ ጭቅጭቅና ንትርክ ዜናው ተሠርቶ ወጣ። አጋጣሚው ግን ልዩነታችን በጋዜጠኝነት ፍልስፍና ላይ እንደኾነ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር። እርሱ “ሚዛናዊ” ብሎ የሚሟገትለት ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርዓት አንዳች የማያራምድ ይልቁንም ጋዜጠኝነትን አሽመድምዶ ልሳን የሚሸብብ መኾኑ ሊያግባባን አልቻለም። እኔ “balanced journalism is a zero-sum game in Ethiopia” ብዬ እሞግተዋለኹ፤ እርሱ በየትኛውም የመንግሥት ሥርዓት ቢኾን የጋዜጠኝነት ሕግጋት የማይጣሱ ደንቦች ናቸው ይላል። ይህን ደግሞ በሥራው ያሳያል፡፡ጋዜጠኝነትን ሕይወቱ ያደረገው ተስፋዓለም በምንም መልኩ ቢኾን ሞያው በትምህርት ቤት ያገኛቸውን የጋዜጠኝነት መርሖዎች እንዲቃረን አይፈልግም። ዜናዎች ሲያዘጋጅ “ሚዛናዊነት” የሚለው መርሕ አለመጣሱን ሲያረጋግጥ ብቻ ነው ወሬው የኅትመት ብርሃን የሚያየው።›› ሲል በፌስ ቡክ ገጹ ስለ ተስፋዓለም ያሰፈረው የቀድሞ የ‹‹አዲስ ነገር›› የሞያ አጋሩ ጋዜጠኛ ዘሪሁን ተስፋዬ ነው፡፡
ከተስፋዓለም ጋር አብሮት የሠራው የቀድሞ የ‹‹አዲስ ነገር›› ባልደረባ ዳኝነት መኮንን፣ ‹‹ኹሌም ስለጋዜጠኝነት አለባውያን፣ መሠረታውያን፣ ቀመርና ሥነ ምግባር አብዝቶ የሚጨነቅ ምናልባትም ብቸኛው ጓደኛችን ነው። ጋዜጠኝነት ማለት accuracy, balance, clarity, and neutrality ከኾነ የማውቀው አንድ ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ ነው። የዜና ዘለላ መቁጠር፣ የፊቸር አለላ ማሰባጠር ማን እንዳንተ ተስፍሽ! ዜናና ታሪክ ሲሠራ ቀዳሚና ፊተኛው፤ እስረኞችን ቃሊቲ ወርዶ በመጠየቅ ታታሪው ወንድሜ ጠያቂና ስንቅ አሳሪ ያብዛልኽ።›› ብሎታል፡፡
‹‹ተስፋዓለም የግል ፖለቲካዊ አመለካከቱ ከጋዜጠኝቱ ጋራ እንዳይጋጭበት የሚጠነቀቅ ወጣት ነው። ለጋዜጠኝነት ከፍ ያለ ክብርና ዋጋ ይሰጣል። አንዳንዴ እቀናበታለኹ። ስለሚዛናዊነት፣ ስለተገቢነትና ስለእውነተኛ ዘገባ አብዝቶ ይጨነቃል። ማንኛውም ዐይነት ዘገባ ከትክክለኛው ወንዝ ተቀድቶ እንዲፈስ ይመኛል፤ ያደርጋል፤ ይጓዛል። መጀመርያ ለሞያው ታማኝ መኾንን ያስቀድማል። ከተስፋዓለም ጋራ ሳወራ ከታናሽ ወንድሜ ጋራ የማወራ ነው የሚመስለኝ። ኢሕአዴግ እንደ ተስፋዓለም መሥመራቸውን ጠብቀው ለሚሠሩ ሰዎች የማይመለስ ይኾናል ብዬ አስቤ አላውቅም። አኹንም መታሰሩን ማመን እውነት አልመስልኽ ብሎኛል! የሚሰማኝ፣ እልኽ፣ ቁጭት፣ ተስፋ ቢስነትና ቁጣ ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ ተስፋዓለም የማንም ወገን አይደለም። ብቻውን በራሱ የቆመ ጋዜጠኛ ነው፣›› ያለው የቀድሞው የ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ ባልደረባው ማስረሻ ማሞ ነው፡፡
ከጋዜጠኝነት ት/ቤት ጀምሮ እስከ አኹን ጓደኛው የኾነው ጋዜጠኛ ደረጀ ብርሃኑ÷ ‹‹ተስፋዓለም ከኹሉም ጋራ ለመግባባት የሚሞክር፣ በት/ቤት በነበረበት ወቅት ጋዜጠኛ ለመኾን ከፍተኛ ፍላጎት ስለነበረው ሥራ የጀመረው ከኹላችንም ቀድሞ ትምሕርቱን ሳይጨርስ ነበር፡፡ ተስፋዓለም ኹልጊዜም አብረውት ቢኾኑ የማይሰለች፣ ጓደኝነቱና ጨዋታው የሚናፈቅ፣ ስለ ጋዜጠኝነት መሠረታዊ ቀመርና ሥነ ምግባር ቢያወራ የማይታክተው ጋዜጠኛ ነው፤›› ብሎታል፡፡
በ‹‹ሰብ ሰሃራ››ና ‹‹ማይፋሽን›› በሠራበት ጊዜ አለቃው የነበረው ዓለማየሁ ሰይፈ ሥላሴ፣ ‹‹ተስፋለም በየዕለቱ ለመለወጥ የሚጥር ታታሪ ልጅ ነው፤ ፍጹም ሞያዊ ጋዜጠኝነት ለማምጣትና ሚዛናዊ የኾነ ዘገባ እንዲሠራ ለማድረግ የሚጣጣርና የሚተጋ ጋዜጠኛ ነው፤ ይህን የሚያደርገው ደግሞ ራሱ ብቻ ሳይኾን ሌሎችን በመጎትጎት ጭምር ነው፡፡ የጋዜጣና የመጽሔት ዲዛይኖች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ኾነው እንዲሠሩ ለማደረግ የሚጥር፣ ከሌሎች ልምድ የሚቀስምና የራሱን ልምድ ለማካፈል ወደኋላ የማይል ጠንካራ ጋዜጠኛ ነው፤›› ብሎታል፡፡
የእውነትም ‹‹ትንሹ›› ተስፋ ዓለም ይኸው ነው፡፡ ማኅበራዊና ግላዊ ችግሮቹን ተቋቁሞ ስለ ጋዜጠኝነት ማውራትና ጋዜጠኛ ኾኖ መኖር የማይሰለቸው የአማናዊ ጋዜጠኝነት ተስፋ – ተስፋ ዓለም!!

ብአዴን ማን ነው? (ገብረመድህን አርአያ፣ አውስትራሊያ)

$
0
0

(ገብረመድህን አረአያ ከፐርዝ አውስትራሊያ)

(ገብረመድህን አረአያ ከፐርዝ አውስትራሊያ)

የአንድን ድርጅት ማንነቱን ከማቅረብ በፊት ቀደም ብሎ የተፈጸመውን ስህተት፣ ቀጥሎም ኢህአፓን ለማጥፋት በህወሓት እና በሻእቢያ የደረሰበትን ጥቃት አጠር ባለ መልኩ ማቅረብ አስፈላጊ ይሆናል።
የስትራተረጂ ስህተት ለከባድ ወድቀት ይዳርጋል።

ኢህአፓ ትግሉን የጀመረው ገና በ1960 መጀመሪያ ነበር። አብዮቱ እየተቀጣጠለ ሃገር አቀፍ ሆነ። ዘውዳዊ ስርዓት ወድቆ በማርክሲዝም ሌኒኒዝም ርእዮተ ዓለም የሚመራ ሶሻሊዝም የኢትዮጵያ ስርአት እንዲሆን ነበር። ይህ ግራ አክራሪ ስታሊኒዝም በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ ይማሩ በነበሩ የተሰባሰበ ቡድን፣ የወቅቱ አብዮተኞች ተገቢውን መልክ የያዘ አደረጃጀት ያልነበረው፣ አብዮተኛ የሚል ስም በማግኘታቸው ብቻ “ዲሞክራሲያ” ተብሎ የሚታወቀውን የኢህአፓ ልሳን በየሳምንቱ በመበተን አሁን ኢትዮጵያ የደረሰባትና እየደረሰባት ያለው ከባድ ችግር የከፈተው እነ ዋለልኝ መኮንን እና የኢህአፓ ግብረአበሮቹ የስታሊን ደቀ መዛሙርት ኢትዮጵያን አደጋ ወስጥ ጣሏት። በዚህ ወቅት ሰፊውን ትኩረት የሰጡት፤

1. በኤርትራ ጥቅያቄ ላይ ኢህአፓ ያለው አቋም ኤርትራ ከዚህ ቅኝ አገዛዝ ነፃ በመሆን ተገንጥላ ነፃ መንግሥት ማቋቋም ሙሉ መብቷ መሆኑን ያምናል፤

2. ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች ወህኒ ቤት እንደመሆኗ የኢህአፓ አቋም በዚሁ ጥያቄ ላይ ርቱእና ግልጽ ሲሆን፣ ብሄር ብሄረሰቦች የራሳቸውን እድል በራሳቸው በመወሰን እስከ መገንጠል መብታቸው ያልተገደበ ነው ይላል።

ይህ ትንታኔ ማንም ኢትዮጵያዊ በተጨማሪ ለማረጋገጥ ክፈለገ “ዲሞክራሲያ” ቅጽ 8 ቁጥር 1፣ የካቲት 23 ቀን 1973 የታተመውን ሙሉ ሃሳቡን በድጋሚ ጽፎታል፣ የቃላት ለውጥ በትንሹ ቢኖርበትም። ይህንን ጽሑፍ ለማግኘት EPRP በሚለው ድረገጽ በመግባት የዲሞክራሲያን እትም ከ1961 እስከ ዛሬ የሚለውን ፈልጋችሁ አንብቡ። ይህ ጽሑፍ የሚያሳዝነው ኢህአፓ አሲምባ እንደገባ ታጋዮቹ በፈጠሩት ጫና በሻእቢያ 1ኛ ጉባኤ 1969 መጨረሻ የአቋም ለውጥ በማድረግ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ናት፤ የኤርትራ ጥያቄ የዲሞክራሲ ጥያቄ በመሆኑ ትግሉ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ስለሆነ ኤርትራም የዚሁ አካል እንጂ ቅኝ ተገዢ አይደለችም በማለት በጉባኤው የሰጠው ውሳኔ ቅጥረኛው ህወሓት ታህሳስ 1972 የኢህአፓ ተዋጊ ክንፍ ሰራዊት ከባድ መስዋእትነት ክፍሎ በወያኔ ተደመሰሰ። በውጭ ሃገር የሚኖሩ የኢህአፓ አመራር በየካቲ 1973 በዲሞክራሲያ ልሳን ያወጡት ጽሑፍ የኢህአፓው ተዋጊ ክንፍ ኢህአሠ ታጋይ ለናት ሃገሩ ኢትዮጵያ የከፈለውን መስዋእትነት ውድቅ ለማድረግ የታቀደ ነው፤ ለምን?

ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ነጥቦች የኢህፓ አመራር በዲሞክራሲያ ልሳኑ ደጋግሞ በመዘርዘር ጠባቦችና ጸረ ኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ሃይሎች እንዲፈጠሩ አደረገ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የኃይለማርያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች –ከተመሰገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

$
0
0
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

በ2005 ዓ.ም መጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም “ጠቅላይ ሚኒስትር” ተደርጎ በኢህአዴግ ሲሾም፤ በፓርቲው ውስጥ አክራሪ ብሔርተኛ የአመራር አባላት ከመኖራቸው አኳያ፤ መቼም ቢሆን “ራሱን ችሎ ይቆማል” ብሎ መጠበቁ ተምኔት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ኃይል እንኳን እንደ ኃይለማርያም ላለ የድል አጥቢያ መሪ ቀርቶ፣ ከድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ እስከ ምኒሊክ ቤተ-መንግስትም ድረስ ታላቅ የተጋድሎ ታሪክ ለነበረው አቶ መለስም ቢሆን ክፍተት ካገኘ አለመመለሱን የ93ቱ ሣልሳዊ ህንፍሽፍሽ በግልፅ አሳይቶ ማለፉ አይዘነጋም፡፡ በተጨማሪም ራሱ መለስ ዜናዊ በድህረ ምርጫ 97 የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ዘብጥያ ወርደው የነበሩትን የቅንጅት አመራሮች “ከእስር እንዲፈቱ ብፈልግም አክራሪው ኃይል ተቃወመኝ” ማለቱን ዊክሊክስ የተሰኘው የመረጃ መረብ የአሜሪካ አምባሳደርን ጠቅሶ ይፋ ማድረጉ ይህንኑ ያስረግጣል፡፡ የአምባሳደሩ መረጃ የተጋነነ፤ አሊያም “ተጋግሮ የቀረበለት ነው” ሊባል ቢችል እንኳ “ጭስ በሌለበት…” እንዲሉ፤ በግንባሩ ውስጥ አክራሪ ኃይል ለመኖሩ በጠቋሚነት ሊወሰድ ይችላል፡፡Temesgen Desalegn “Fact” Ethiopian Amharic newspaper editor

ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ መለስን ከተካበት ዕለት አንስቶ፣ ያደረጋቸው ዲስኩሮችም ሆኑ ለቀረቡለት ጥያቄ የሰጣቸው ምላሾች በአክራሪው ኃይል ተጽእኖ ሥር ማደሩን ያሳያል፡፡ የድርጅቱ የታሪክ ንባብም ቢሆን፣ በአቅመ ደካማ የመጠቀም የፖለቲካ ጨዋታው የሰነበተ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ኃይለማርያም ከሹመቱ በኋላ ከባሕሪው አፈንግጦ፣ ዝነኛዋን የመለስ ዜናዊን ሕዝባዊ ሽብር መፍጠሪያ ‹‹ቀይ መስመር››ን፤ ‹‹እሳት መጨበጥ›› በሚል ተክቶ የተቃውሞ እንቅስቃሴን በሙሉ እስከማስፈራራት መገፋቱም የዚሁ ውጤት ይመስለኛል። በተቀረ እርሱ ወደ ሥልጣን በመጣበት መጀመሪያ አካባቢ፣ ‹‹ኃይማኖተኛ››ነቱን ብቻ በመጥቀስ ‹‹ቤቴን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› በሚል ሥርዓታዊ ማፍያነትን ባደራጁ ጓደኞቹ ላይ ጅራፍ እስከማወናጨፍ ይደርሳል ተብሎ መገመቱ፣ በግንባሩ ውስጥ የተንሰራፋውን አክራሪ ኃይል በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ እዚህ ጋ ሳይጠቅስ የማይታለፈው ጥቅምት 10 ቀን 2005 ዓ.ም የወጣው ‹‹ሪፖርተር ጋዜጣ›› በልዩ እትሙ፣ ኃይለማርያም ‹‹ቄስ›› ተብሎ ሊቀባ አንድ ወር ሲቀረው በትምህርት ምክንያት ከሀገር እንደወጣ ካስነበበበት ጋር የሚያያዘው ነው፡፡ ወደ ፖለቲካው ከመቀላቀሉ በፊት የሚያመልክበትን ‹‹የኢትዮጵያ ሐዋርያት ቤተክርስቲያን›› ቄስ ህዝቅኤል ጎዴቦን ‹‹ፖለቲካ ውስጥ መግባት ሀጢአት አይሆንብኝምን?›› ሲል መጠየቁን ጋዜጣው አትቷል፡፡ ግና፣ ምን ዋጋ አለው? ባልተጠበቀ ፍጥነት ከተራ ፖለቲከኝነት አልፎ የሀገሪቱ መሪ ለመሆን በመብቃቱ፣ ‹‹ቅስና››ው በመንገድ ሊቀር ተገደደ እንጂ፡፡ እርሱም ቢሆን ዛሬ እንዲህ አይነት ጥያቄ አያነሳም፤ በፈሪሃ እግዚአብሔሩም ቦታ፣ ፈሪሃ ኢህአዴግ ተተክቷል፡፡ እናም ከእስልምና መንፈሳዊ መሪዎች እስከ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ያሉ ንፁሀን፣ በራሱ አነጋገር ‹‹እሳት በመጨበጣቸው›› ወደ ‹‹ቃሊቲ›› ተላልፈው ምድራዊውን ገሀነም ይቀበሉ ዘንድ ቡራኬ ሰጥቷል፡፡ Dead end - Copy ሰሞነኛው ጉዳይ

አቶ ኃይለማርያም በስድስት ወር (በጥር) ለተወካዮች ም/ቤት ማቅረብ የነበረበትን ሪፖርት በዘጠኝ ወሩ ባለፈው ሳምንት ባቀረበበት ወቅት፣ ከምርጫው በፊት የፖለቲካ ማሻሻያ መጠበቁ የዋህነት እንደሆነ የጠቆመን፣ የም/ቤቱ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የጠበበው ምህዳርን አስመልክቶ ላቀረበለት ጥያቄ ‹‹ዲሞክራሲ በአንድ ሳምንት ተበጥብጦ አይጠጣም (ፓርቲው ሥልጣን ከያዘ በቀጣዩ ወር ሃያ ሁለተኛ አመቱን መድፈኑን ልብ ይሏል)፣ ዲሞክራሲ ህልውናችን ነው፣ ቀይ ምንጣፍ አናነጥፍም…›› ጅኒ ቁልቋል በሚሉ የእብሪት ገለፃዎች ማለፉ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ሪፖርቱ በሀሰተኛና በማደናገሪያ ዘገባዎች የታጀለ እንደነበረ መታዘብ ተችሏል፡፡ ለማሳያነትም ያህል ጥቂቶቹን በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡- ‹‹ዕድገት›› ሲባል… የኢኮኖሚ ዕድገትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሪፖርቱ ላይ ‹‹የሀገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት ሂደት ሲታይ ላለፉት አስር ዓመት (ከ1996-2005) በየዓመቱ በአማካይ 10.9 በመቶ በማደግ ከፍ ባለ የእድገት ጉዞ (Trajectory) ውስጥ መሆኑን አመላክቷል›› ሲል ነግሮናል፡፡ ይሁንና አስሩን ዓመት ትተን የዘንድሮውን በመሬት ላይ ያለውን እውነት እንኳ ብንመለከት የሚያሳየው ተቃራኒውን ስለመሆኑ ለራሱም ቢሆን ይጠፋዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በአገሪቱ ሥራ-አጥነት (በከተሞች 40 በመቶ መድረሱን ጥናቶች ይጠቁማሉ) በአስከፊ መልኩ ተንሰራፍቶ፣ ስደት ዕጣ-ፈንታ ተደርጎ ኩብለላ የዕለት ተግባር በሆነበት፣ ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ በኑሮ ውድነት እንደ ከባድ ማዕበል ወደላይ ጎኖ፣ ቁልቁል በአናት እየተተከለ በሚንገላታበት፣ ጎዳናዎች ቀን ቀን ልመና በወጡ ምንዱባን፣ ማታ ማታ ደግሞ ነፍሳቸውን ለማቆየት የሚውተረተሩ በዕድሜም በአካልም ትናንሽ የሆኑ ሴተኛ አዳሪዎች ተጥለቅልቆ… ባለበት በዚህ ዘመን ‹በየዓመቱ በአማካኝ 10 በመቶ እያደግን ነው› የሚልን አላጋጭ ሪፖርትን ሰምቶ በቸልታ ማለፉ ሰው የመሆን ጉዳይንም ፈተና ላይ መጣሉ አይቀርም፡፡ በዚህ ለሶስት ወራት በዘገየው ሪፖርት የዋጋ ንረትን ከአንድ አሃዝ እንዳያልፍ እየተሰራ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ከየምርጫው አንድ ዓመት በፊት በመለስ ዜናዊ ይቀርቡ የነበሩ ሪፖርቶች እንዲህ አይነት የዋጋ ንረት እንደሚቀንስ የ‹‹ሚያበስሩ›› እንደነበር ይታወሳል፡፡ የኃይለማርያምም ሪፖርት፣ ፓርቲው በምርጫ ዘመቻው ወቅት ሁሌ እንደ ስልት የሚጠቀምበትን ይህንን ጉዳይ አስጩኾ ከተለመደው የግብይት ሥርዓት አፈንግጦ መጠነኛ የዋጋ ማረጋጊያ በማድረግ የእሳት ማጥፊያ ሥራ ለመስራት ከመዘጋጀት ያለፈ ትርጉም ያለው ነገር የሚያመጣ ሆኖ አይደለም፡፡ አብዮታዊ ግንባሩም ቢሆን የምርጫው ማዕበል የሚጠራርገውን ጠርጎ፣ የሚወረውረውን ወርውሮ ማለፉ ላይ እርግጠኛ እንደሆነው ሁሉ፣ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የዋጋ ንረቱ ተመልሶ የቱንም ያህል ወደላይ ቢስፈነጠር የተቆጡ ድምፆች አደባባዩን እንደማይሞሉት ጠንቅቆ ያውቀዋል። ሌላው የሪፖርቱ አስቂኝ ክፍል የግብርናውን ዘርፍ የተመለከተው ነው፡፡ ይኸውም ካለፈው ዓመት የዘንድሮው በእጅጉ ማደጉን ገልፆ እንደምክንያት ያቀረበው ‹‹ዋናው የዕድገት መሰረት በመሬት ማስፋት ሳይሆን በምርታማነት የመጣ መሆኑን የሚያሳይ ነው›› የሚል ነበር፡፡ ይሁንና እዚህ ጋ የሚነሳው ጥያቄ የዘርፉ ባለሙያ መሆንን የማይጠይቅ ቀላልና ግልፅ ነው፡- የግብርና ቴክኖሎጂ መሻሻል በሌለበት፣ የሰው ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመጣበት (አማካይ የመሬት መጠን ከአንድ ሄክታር ያነሰ ሆኖ)፣ ማዳበሪያ ለፓርቲ አባላት ብቻ በሚታደልበት፣ የዝናብ ወቅትን ብቻ ጠብቆ በሚዘራበት እና መሰል ችግሮች ባጨለሟት ኢትዮጵያችን ምርታማነት ከመቼውም ጊዜ በላይ አደገ መባሉ እንዴት ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል? …መቼም በመለኮታዊ ኃይል ከሰማይ በወረደ መና ነው ሊሉን አይችሉም፡፡ ካሉ ግን ምን ማድረግ ይቻላል! ሰውየው ኃይለማርያም፣ ፓርቲውም ኢህአዴግ ነውና፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው የእነርሱ ዕድገት፣ ምርታማነት… ቅብርጥሶ የሚለው ፕሮፓጋንዳ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በምግብ እጦት መጠቃታቸውን ዓለም አቀፍ ተቋማት እየዘገቡ ባለበት ወቅት መሆኑ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም የኢንዱስትሪው ዘርፍ እንደ መስከረም አደይ አበባ በየሜዳው መፍካቱን አብስረውናል፡፡ ይሁንና ሀገሪቱ እንኳን ለግዙፍ ፋብሪካዎች የሚሆን የኃይል አቅርቦት ቀርቶ፣ አነስተኛ ፍጆታ ያለውን የከተማ ነዋሪ የመብራት ፍላጎትም ማሟላት ያለመቻሏ ጉዳይ ፀሀይ የሞቀው፣ ዝናብ ያጨቀየው የአደባባይ እውነታ ነው፡፡ የግልገል ግቤ 3 ፕሮጀክትም ቢሆን፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደደሰኮረው በሚቀጥለው ዓመት ሥራ የሚጀመር አለመሆኑን ግንባታውን የሚያካሄደው ካምፓኒ አስቀድሞ ማሳወቁን ሰምተን አረጋግጠናል፡፡ ሌላው በሪፖርቱ ከተጠቀሱ ጉዳዮች ውስጥ ግርምት የሚያጭረው ከወራት በፊት በሳውዲ አረቢያ አሰቃቂ ጭካኔ የተፈፀመባቸውን ወንድም-እህቶችን በተመለከተ በአምስት መስመር ብቻ ተቀንብቦ የቀረበው ዘገባ ነው፡፡ የዚህን ሥርዓት ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ከመራቅም በላይ፣ መበስበሱን የሚያስረግጠው እንዲያ በ21ኛ ክ/ዘመን ሊፈፀም ቀርቶ ይታሰባል ተብሎ በማይታመን ጭካኔ ደማቸው ደመ-ከልብ ሆኖ ስለቀረውና አስክሬናቸው በጎዳና ላይ ስለተጎተተው ወገኖቻችን፡- ‹‹የሳዑዲ መንግስት በተለያየ ምክንያት ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃዳቸውን ማስተካከል ያልቻሉ ኢትዮጵያውያን አገር ለቀው እንዲወጡ በወሰነው መሰረት…›› በማለት በሪፖርት ተብየው አቃሎ ማቅረቡ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ሁለት ነገር ያመላክታል፡፡ የመጀመሪያው ሥርዓቱ ለዜጎቹ ደህንነት ደንታቢስ በመሆኑ ቢያንስ በወረቀት ላይ እንኳን ነውረኛውን የሳውዲ መንግስት ለማውገዝ እና ወደፊትም ከእንዲህ አይነቱ ዲያብሎሳዊ ተግባሩ እንዲታቀብ ለማስጠንቀቅ አለመድፈሩን ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በዚህን መልኩ ከተባረሩ ስደተኞች መካከል አሁንም ወደዛው የሞት ቀጠና ተመልሰው መሄዳቸው፣ ጠ/ሚንስትሩ እንዲያ የተዘባነነበትን ‹‹ዕድገት›› ልብ-ወለድ ማድረጉን ነው፡፡ መልካም አስተዳደር ሲባል… የኃይለማርያም ደሳለኝ ሪፖርት በደምሳሳው እውነት ለመናገር የሞከረው መልካም አስተዳደር ያለመኖሩን በተመለከተ ብቻ ነው፡፡ ለማሳያነትም የሚከተለውን ልጥቀስ፡- ‹‹በአገራችን ከፌዴራል ተቋማት ጀምሮ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ደረጃው የተለያየ ቢሆንም፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደሚታዩ ሕዝቡ በተለያዩ መድረኮችና አገልግሎት በሚያገኝባቸው ሥፍራዎች ቅሬታዎች እያነሳ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡›› ከዚህ በተጨማሪም መንግስታዊ ጉድለቱ ከኪራይ ሰብሳቢነት አንስቶ፤ በመሬት አስተዳደር፣ በታክስ አሰባሰብ እና የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት በማስፈፀም ሂደት፣ በአገልግሎት ተቋማት ውስጥ የሚታይ የአመለካከት ችግር፣ የሥራ ተነሳሽነት አለመኖር፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት መጥፋትንም እንደሚጨምር ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ይሁንና ሰዎቹ እንዲህ በድፍረት ያነበሩት ሥርዓትን ክሽፈት ቢያውጁም፣ ቅንጣት ታህል ‹የሕዝብ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል› የሚል ስጋት የለባቸውም፡፡ ስለምን? ቢሉ፣ በአንድ በኩል ስለዲሞክራሲ ማበብና የሕግ የበላይነት እየዘመሩ፤ በሌላ በኩል በእነዚህ ሁሉ ችግሮች ተተብትበው ሥልጣንን በገዛ ፍቃድ ካለመልቀቅም አልፎ ቀጣዩን ምርጫ አጭበርብሮ እና ተቀናቃኞችን ጨፍልቆ ለማሸነፍ ዝግጁ መሆን የሚቻለው በእኛይቱ መከረኛ ኢትዮጵያ ብቻ እንደሆነ ገና ድሮ ገብቷቸዋልና፡፡ ሌላው የአገሪቱን ሀብት በጠራራ ፀሀይ የመዝረፍ እውነታውን ለመረዳት ጠቅላይ ሚንስትሩ ሪፖርቱን ካቀረበበት ሁለት ቀን ቀደም ብሎ (በ14/8/06 ዓ.ም) የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2005ቱን የበጀት ዓመት በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርት ማየቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ መስሪያ ቤቱ በተለያየ ምክንያት ከመንግስት ተቋማት በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ እንደባከነ የገለፀው የገንዘብ መጠን በድምሩ 3,207,752,247.05 (ሶስት ቢሊዮን ሁለት መቶ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ሁለት ሺ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ብር ከዜሮ አምስት ሳንቲም) መሆኑን በግላጭ አስቀምጧል፡፡ ይህ እንግዲህ በቀጥታ ከጥሬ ገንዘብ ጋር የተያያዘ ውድመት ነው፡፡ ከዚህ ሌላ በርካታ ችግሮችና ዘረፋዎች መኖራቸውን ሪፖርቱ በስፋት ዘርዝሯል፡፡ ለምሳሌ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያን የተመለከተውን ማየት ይቻላል፡፡ ይህ መሳሪያ ሥራ ላይ መዋል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2005 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ለግብር ከፋዩ ከተሸጠው ውስጥ 89 በመቶው አገልግሎት ላይ ቢውልም፣ የሽያጭ መረጃን ወደ መረጃ ቋት የሚያስተላልፈው 12 በመቶ ብቻ ሲሆን፤ የተቀረው 88 በመቶ ምንም ነገር እንደማያስተላልፍ ተገልጿል፡፡ እናሳ! ይህ ስለምን ሆነ? ለግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤቱ መረጃ የማያስተላልፉት የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችስ በእነማን ድርጅቶች እጅ ውስጥ የሚገኙት ይሆኑ? …እውን! ጠቅላይ ሚንስትሩ ለዚህ መልስ ይኖረዋልን? የስኳር ኮርፕሬሽኖችን በተመለከተ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሪፖርቱ ላይ ‹‹(አዳዲሶቹ) አብዛኛው የስኳር ፋብሪካዎቻችን በቀጣይ ዓመት ወደ ማምረት ተግባር ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል›› በማለት ቢገልፅም፤ የኦዲት ሪፖርቱ ግን ተቃራኒውን ነው የሚያረዳን፡፡ ይገነባሉ የተባሉት ፋብሪካዎች በኮርፕሬሽኑ የአምስት ዓመት ዕቅድ መሰረት ሁለመናቸው ተጠናቅቆ ወደ ማምረት እንደሚገቡ መገለፁ አይካድም፡፡ ነገር ግን የጣና በለስ ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት ግንባታ እስከ ጥቅምት 2005 ዓ.ም ያልቃል ቢባልም፤ በዛው ዓመት መጨረሻም ቁጥር አንድ 45 በመቶ፣ ቁጥር ሁለት 39 በመቶ ብቻ ሲጠናቀቅ፤ በኦሞ-ኩራዝ ደግሞ የፋብሪካው ግንባታ መጠናቀቅ በነበረበት ዓመት 42 በመቶ ብቻ የተሰራ መሆኑን ሪፖርቱ አጋልጧል፡፡ እንዲሁም እስከ ጥቅምት 2006 ዓ.ም ይጠናቀቃል የተባለው የወልቃይቱ ፋብሪካ የኦዲት ሪፖርቱ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ምንም አይነት የግንባታ ሥራው እንዳልተጀመረ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም የተንዳሆ ስኳር ልማት ፋብሪካ በታቀደለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ ምክንያት 5146.09 ሄክታር መሬት ላይ የነበረው የሸንኮራ አገዳ ምርት ዕድሜው በመራዘሙ ተበላሽቶ እንዲወገድ በመደረጉ፣ ፋብሪካው ማግኘት የሚገባውን 102,440,145.00 (አንድ መቶ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ አርባ ሺህ አንድ መቶ አርባ አምስት) ብር ተገቢ ባልሆነ መንገድ ያሳጣው እንደሆነ የኦዲት ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ታዲያ ጠቅላይ ሚንስትራችን ‹በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ይጀምራሉ› የሚለን የትኞቹን የስኳር ፋብሪካዎች ይሆን? እግዜር ያሳያችሁ! እንዲህ አይነት ያፈጠጠ ነጭ ውሸት የሚነግረን፣ ፕሮጀክቶቹን እስከዚህ ዓመት መስከረም ወር መጀመሪያ ድረስ በበላይነት ይመራ የነበረው አባይ ፀሀዬን አማካሪው አድርጎ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ይህ ሁኔታ የሚያመላክተው ሌላ ጉዳይ ቢኖር አቶ ኃይለማርያም ዛሬም ‹‹እመራዋለሁ›› ለሚለው አብዮታዊ ድርጅቱ ሩቅ የመሆኑን ምስጢር ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትርነት በተሾመ ማግስት፣ አቶ መለስ ማሌሊትን ቀብሮ ስለልማታዊ መንግስት ከማንችስተር እስከ ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲዎችና ዓለም አቀፍ የአደባባይ መድረኮች መከራከሩን ያልሰማ የሚመስለው ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በመጀመሪያው ከውጭ ጋዜጠኛ (ከቪኦኤው ፒተር ላይን) ጋር ባደረገው ቃለ-መጠየቅ ላይ ‹‹እኛ ተራማጅ ግራ-ዘመም ነን›› ሲል የተደመጠበትም መግፍኤ ይኸው ይመስለኛል፡፡ ኤርትራ ሆይ! ብረሳሽ… ጠቅላይ ሚንስትሩ ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት፣ አቶ ግርማ ሰይፉ መንግስት የኤርትራንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማቀራረብ የሚያደርገውን ጥረት አስመልክቶ ያለውን አቋም በተመለከተ ላነሳው ጥያቄ፣ የሰውየው ምላሽ ከእውነታው ፍፁም ያፈነገጠ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የኃይለማርያም ማብራሪያ ሁለቱ ሕዝቦች የቀድሞ ግንኙነታቸውን መልሰው እንዲያጠናክሩ ‹‹ኢትዮጵያውያን የኃይማኖት አባቶች እና ምሁራኖች ለሚያደርጉት ጥረት መንግስት ድጋፍ እያደረገ ነው›› የሚል ሲሆን፤ ኤርትራን በተመለከተ ደግሞ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በአሸባሪነት ፈርጆ ማዕቀብ ጥሎ እያሰቃያት ከመሆኑም በላይ በአካባቢው ከኢትዮጵያ በስተቀር ተሰሚነት ያለው ሀገር ያለመኖሩን የሚያመላክት አንድምታ አለው፡፡ ይህ ግን ምን ያህል እውነት ነው? ብለን ስንጠይቅ፤ በኤርትራ መገንጠልም ሆነ በለንደኑ ኮንፈረንስ የህወሓትን የበላይነት ያስረገጡትና በአሜሪካን አስተዳደር ተሰሚነት ያላቸው አምባሳደር ኸርማን ኮኽን ኤርትራን ከ‹‹ብርዱ›› ለማውጣት አሜሪካም ሆነች የተባበሩት መንግስታት የጣሉትን ማዕቀብ እንዲያነሱ እና ድንበሩ እንዲሰመር በአደባባይ መጮኽ ከጀመሩ መሰንበታቸውን እንረዳለን፡፡ እንዲሁም ሌላኛው አምባሳደር ዴቪድ ሺንም ኢትዮጵያ ባድመን እስከመስጠት ከሄደች በሁለቱ ሀገራት ሰላም ማምጣት እንደሚቻል ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ እናም እነዚህን ሰዎች ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ አሜሪካውያን ፖለቲከኞች ኤርትራ እ.ኤ.አ. ከ2009 ዓ.ም ወዲህ ሽብርተኝነትን ከመደገፍ መቆጠቧን ጠቅሰው በመከራከር ላይ መገኘታቸው እውነታውን ፍንትው አድርጎ ሳያል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ኢትዮጵያውያን የኃይማኖት አባቶችና ምሁራኖች…›› ንግግርም በሬ ወለደ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ባለፈ የሀገሬ መንግስት ለተከታታይ አስራ ስድስት አመታት ‹ኤርትራ ሆይ! ብረሳሽ ቀኜ ይርሳኝ›ን የሚዘምረው ሀገር-በቀል ተቀናቃኞቹን በስመ-ሻዕቢያ መጨፍለቅ ሲፈልግ ብቻ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ እኛ ቀጥለናል! ግንባሩ ‹‹ባለራዕይ›› በማለት ካቆለጳጰሰው የቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ህልፈት በኋላ፣ በጠባብ ብሔርተኞችና ጥቅመኞች በመሞላቱ መተካካቱን ተከትሎ ይፈረካከሳል የሚል ከውስጥም ከውጪም የሚሰማ ሹክሹክታ ነበር፡፡ በርግጥም የኃይለማርያም ወደ መንበሩ መምጣት ‹‹በአማራና ኦርቶዶክስ የምትመሰለው ሀገር፣ የአናሳውም ሆናለች›› ከሚለው የአቦይ ስብሐት እንቶ ፈንቶ ውጪ፣ ከተጠበቁት ሁነቶች ብዙዎቹን (በተለይ ሥርዓታዊ ልልነት ይፈጠራል የሚለው) በገቢር ከመስተዋል አልታደጋቸውም፡፡ ለዚህም ሁለት ማሳያዎችን እጠቅሳለሁ፡፡ የመጀመሪያው ባሳለፍነው ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀረበው ሪፖርትና ማብራሪያ ላይ ተደጋግሞ የተነሳው ‹‹የአፈፃፀም ችግር›› የሚለው ነው፡፡ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተብሎ ከበሮ ከተደሰቀለት የተቀመጠ ግብ አኳያ፣ ነባራዊው ሁኔታ ስምም አለመሆኑን ራሱ ኃይለማርያምም ‹‹የአፈፃፀም ጉድለት›› በሚል የዳቦ ስም ሊያሳብብ ከመሞከር በቀር አልካደውም፡፡ አንድ ማዕከላዊ መንግስትን የሚመራ ግንባር፣ ሊያውም እስከ ቤተሰብ የወረደ የኃይል ማዕከል ለመገንባት የሚጥር ስብስብ፤ ከተሞችን እያሰቃየ ላለው የመሰረታዊ ግልጋሎቶች ዕጦትና የተቀመጡ ዕቅዶች አለመሳካት ይህን በመከራከሪያነት ማቅረቡ፤ የስርዓቱ ተቋማት መፈረካከስን ከማስረገጥ ያለፈ የሚነግረን ምስጢር የለውም፡፡ ሌላኛው የአማካሪዎቹ ስብስብ ጉዳይ ነው፡፡ ሰውዬው ከጎኑ የሰበሰባቸውን ጉምቱ ፖለቲከኞች ትተን፤ ለእያንዳንዱ ጉዳይ ካውንስል የማቋቋም ፍጥነቱን ብናስተውል ስርዓቱ በመለስ ዘመን የነበረውን ጥብቅነት አጥቶ መዋለሉን እንረዳለን፡፡ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ እንዲመራ ካስቀመጠው ዶ/ር ደብረፅዮን ውጪ፣ ‹‹የኢኮኖሚ ካውንስል›› በሚል አይረቤ ስም ለማቋቋም መሞከሩ ሳይበቃ፤ በባጀት ዕጥረት እየተሰቃየ ያለውን አስተዳደሩን ለመታደግ የፋይናንሻል ምንጮችን ከውጪ የሚያፈላልግ ሌላ ካውንስል መሰል ስብስብ ማደራጀቱን ስንታዘብ፤ ስርዓቱ ቢያንስ እንደ መለስ ዘመን መቀጠል በማያስችል ወላዋይነት /Brittle state/ ለመፈተኑ ጥቁምት ይሰጠናል ብዬ አስባለሁ፡፡ በተለይም ጠቅላይ ሚንስትሩ በሪፖርቱ ላይ የአገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማሟላት መንግስት የሐዋላ አግልግሎትን ማጠናከር እንዳለበት ከመግለፅ ባለፈ፣ ከ2000 ዓ.ም መጀመሪያ አንስቶ የህንዱን ካራቱሪ እና ሳውዲ ስታርን ጨምሮ ለበርካታ ባለሀብቶች ስለተሰጠው ሰፋፊ የእርሻ መሬት አንዳችም ነገር ትንፍሽ አለማለቱ የክስረቱ ዋነኛ ማሳያ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በወቅቱ ከመሬት ቅርምት ጋር አያይዘው የተቃውሞ ድምፃቸውን ላሰሙ ምሁራንም ሆነ ‹‹አንድ ሄክታር መሬት በሃያ ብር›› መሰጠቱን በመኮነን የድርጊቱን ኢ-ፍትሓዊነት በዘገባው ለገለፀው ታዋቂው ‹‹ኒዎርክ ታይምስ›› ጋዜጣ፣ መለስና ጓዶቹ መከራከሪያ አድርገው ያቀረቡት ‹‹በአጭር ጊዜ ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ችግራችንን ይቀርፋል፣ የቴክኖሎጂና የሙያ ሽግግር እንዲደረግ ያስችላል›› የሚል እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ ግና፣ ዛሬ ይህ ጉዳይ ሕልም ሆኖ ለውጭ ምንዛሪ ሐዋላን የሙጥኝ መባሉን እየሰማን ነው፡፡ እንዲሁም በራሱ በመለስ ዜናዊ በ2005 ዓ.ም በርግጠኝነት መውጣት እንደሚጀመር የተነገረለት የነዳጅ ክምችትም ቢሆን፣ ‹‹ውሾን ያነሳ…›› እንዲሉ የተዘጋ ፋይል ሆኗል (በነገራችን ላይ በፓርላማው. የፓርቲው ካድሬዎች ባለስልጣናቱ ላይ የሚያዘንቡት የጥያቄ እሩምታ የሚያመለክተው፣ ፓርላሜንታዊ ዴሞክራሲ ዘግይቶ ወደ ኢህአዴግ ሰፈር መምጣቱን ሳይሆን፣ የፓርቲውን የውስጥ የዕዝ ተዋረድ መሰነጣጠቁን እና ቡድንተኛነት ግንባሩን እያመሰው መሆኑን ነው፡፡ በተቀረ ከዚህ ውጪ ያለው መከራከሪያ ሁሉ ጥሩ የአደባባይ ቧልት ከመሆን የሚያልፍ አይመስለኝም) የሆነው ሆኖ ከላይ ኃይለማርያምን ያብራሩልናል ብዬ ለመጥቀስ ከሞከርኳቸው ጭብጦች በእጅጉ ባለፈ፣ ሪፖርቱን ያቀረበበት ተአብዮ እና የማንአለብኝነት መንፈስ በቅድመ-ምርጫው አንድ ዓመት ውስጥ አንዳችም የፖለቲካ ማሻሻያ እንዳትጠብቁ የሚለው ዋነኛው ሲሆን፤ አቦ ሌንጮ ለታ ‹‹ሰዎች አሳስተውታል›› እንዳለው፤ ዙሪያው ያሉት አለቆች እንዳዘዙት፤ ‹እኛ እየረገጥናችሁ እንቀጥላለን፣ እናንተም በተጨቋኝነታችሁ አዝግሙ› የሚለው ደግሞ ሌላኛው ውስጠ-ወይራ ጥብቅ መልእክቱ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ በመጨረሻም ጠቅላይ ሚንስትር ኃ/ማርያም ጥር 2003 ዓ.ም. ‹‹ምዕራፍ›› ከተሰኘ ኃይማኖታዊ መጽሔት ጋር ቃለ-መጠይቅ ባደረገበት ወቅት ‹‹ከመጽሐፍ ቅዱስ ደስ የሚልዎት ቃል የቱ ነው?›› በሚል ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠውን ምላሽ፣ አንድም ዛሬ የሚከተለውን መንገድ ቆም ብሎ እንዲፈትሽ ለማስታወስ፤ ሁለትም ለዚህ ተጠይቅ መደምደሚያ ይሆን ዘንድ ወደጃለሁና እንደሚከተለው አሰፍረዋለሁ፡- ‹‹መጽሐፍ ቅዱስን እወደዋለሁ፡፡ የዮሴፍ፣ የዳዊት፣ የሙሴ ሕይወት በጣም ይለውጡኛል፡፡ የእነዚህ ቅዱሳን ሕይወት በጣም ያንጹኛል፡፡ ዳንኤልም በጣም ጠቢብ ነው፡፡ ስለዚህም እንደርሱም መሆን መልካም እንደሆነ አስባለሁ፡፡›› ወንድም ኃይለማርያም ደሳለኝ፡- የልብህን መሻት አምላክ ይሙላልህ!!

 መታሰቢያነቱ በግፍ ለተገደሉ የዮኒቨርቲ ተማሪወች።

$
0
0

ብርሀን አህመድ

       መንገድ ላይ ቀረሁ!!
የልቤን፣አውጥቸ__ ሳልናገር፣ለስው፣
አድካሚ፣ጉዞየን__ ሄጀ፣ሳልጨርሰው፣
እንዳሻኝ፣እንደልብ__ ሳልፅፍ፣ሳይነበብ፣
በቡቃያኔቴ__ አፍርቸ ሳላብብ።

ተምሪ፣ጨርሸ__ ሀገሬን፣ሳልጠቅም
አግብቸ፣ወልጀ__ ልጅ፣አቅፊ፣ሳልሰም፣

እናቴን፣ሳልጦራት__ አባቴን፣ሳልረዳ
አምሮብኝ፣፣ሳልታይ__ ወጥቸ፣ከጋዳ
አናቴ ላይ ጥይት __ ጉኔን፣ሰለት ወግቶተኝ
በወጣትነቴ መንገድ ላይ ቀ  ረ ሁ  መሪ።

pen

(የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ) ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት!!

$
0
0

ከኢትዮ ተዋሕዶ

ህሊናዬ ያለእረፍት ይናጣል በሃሳብ ቅብልብሎሽ አድማስ ይሻገራል፡፡መቸም ህሊናችን አንድ ግዜ ክፉውን ሌላ ጊዜ በጎውን ማውጠንጠኑ የተለመደ ገቢር ቢሆንም ህሊናዬን በቁጣና በቁጭት ያደነቆረኝን ነገር በልቤ አብሰልስዬ በአንደበቴ መስክሬ የእርካታ ጣሪያ ላይ መድረስ አልተሳነኝምና ቁጭት ያቀረረ ብእሬን አንስቼ በጦማር ልፋለመው ገባሁ፡፡በቅድሚያ ክቡር ንዑድ የሆነ ሰለምታዬ ይድረሳችሁ፡፡
debereselam Minnesota
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለዘመናት በሊቃውንት አባቶች ከታላቁ መፃህፍ ከመፅሐፍ ቅዱስ በተጨማሪ ህገ መንፈሳዊ በሆኑት ፍትሃ ነገስት(The Law of the Kings)፣ቃለዓዋዲ፣ ሐይማኖተ አበው እና ሌሎችም አዋልደ መፃህፍት በመታገዝ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን ቅዱሳን አባቶች ስለ እውነት ብለው እንደ ስንዴ ተቆልተው እንደ አክርማ ተሰንጥቀው በዱር በገደል እንዲሁም በበረሀ ተቅበዝብዘው ቅጠል በልተው አፈር ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው የቤተክርስቲያንን ህልውና ከፀና ሰርዓቷ ጠብቀው አኖረዋል፡፡

የጉድ ሃገር ገንፎ እያርደ ይፋጃል” እንዲሉ አለማዊ ክብርና ዝናን ለመላበስ በመሻት ከሙሽራው ክርስቶስ ውዳሴ በላይ የኔ ስምና ክብር ይቅደም በማለት በበዓለ ሆሳዕና ቅዳሴ የተስተጓገለበትን የሚኖሶታው ደብረ ሰላም መድሐኒያለም በአርምሞ ማለፍ ከህሊና ጋር መቃቃር እንዲሁም የልቦና መባከን ስለሆነብኝ ትንሽ የግሌን የአስተሳሰብ ልኬት እና ግንዛቤ ከመንፈሳዊ ህግ ጋር በማዋሃድ ላወጋችሁ ወደድኩ ፡፡ሆሳዕና በልዩ ሁኔታ የሚከበር ጌታችንን ክርስቶስ በእየሩሳሌም ከሚጠቡ ህፃናት አንደበት አንስቶ እሰከ ቤተፋጌ ድንጋዩች ድረስ “ሆሳዕና በዓርያም በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ አርሱ ብሩክ ነው″ ብለው ያመሰገኑበት ተዓምራታዊ እለት እና አንደኛው አበይት በዓል ነው፡፡ እናም በዚህ እለት ኢትዮጳያ ካለው ቅዱስ ሲዲኖዶስ ለኒዮርክና አካባቢዋ የተላኩት አቡነ ዘካሪያስ በስርዓተ ቅዳሴው የእኔን ስም በመግለፅ ሊቀደስ ይገባል ካለሆነ ቅዳሴው ተስተጓግሎ ቤተክርስቲያኒቷ እንድትዘጋ የሚል ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ለሃያ አመታት በዚህ ስርዓት ሲተዳደሩ የነበሩ ህገ እግዚአብሄርን የሚያከብሩ ካህናትና ዲያቆናት ከህዝበ ክርስቲያኑ ጋር ጌታን ሲያመሰግኑ ዋሉ፡፡ የነገስታቱ ምድራዊ ጥንካሬና ጉልበት ያስፈራቸው ካህናት ቅዳሴውን ትተው ምድራዊውን ንጉስ ሊያመስግኑ ከሆሳዕና ተለዩ ከፈሪሳዊያንም ጋር አበሩ፡፡ከሙሽራው በላይ መድመቅና መክበር የፈለጉ ሚዜዎች መሆን ፈልገው እንጂ ከማያልፈው የክርስቶስ ክብር የእነሱን ዘለቄታ የለሽ ዝና ማስቀደም አልነበረባቸውም(የመንግስት ቀኝ ክንፍ ካለሆኑ በቀር) ደግሞም ቤተክርስቲያን ስለአለም ሁሉ የምትማልድ እንጂ ለህዝብና አህዛብ፣ ለቤተክርስቲያን ኃላፊዎችና ለቤተመንግስት ባለስልጣን አልያም ላለው ለሌለው ብላ እግዚኦታ የምታስብል አይደለችም፡፡ ለቤተክርስቲያን አገልጋይም በተለየ መልኩ በማዕረግ ፀሎት መደረግ አለበት ከተባለ በስርዓተ ቅዳሴው “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ቀሳቀወስት ወዲያቆናት” በሚል ሀረግ ይማልዳል፡፡

ስለውግዘት መፅሐፍ ቅዱስ (መፅሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ 36 ቁጥር 15) እንዲህ ይላል፡- "የማይገባ ግዝትን ለምትፈፅሙ ለናንተ ወዮላችሁ ስለ ኃጢያታችሁ ድህነት ከናንተ ይራቀ እንደስራችሁ መጠን ፍዳውን ትቀበላላችሁና ለባልንጀራችሁ ክፉ ምላሽ ልምትመሱ ለናንተ ወዮላችሁ"፡፡ በፍትሃ ነገስትም ላይ እንዲህ የሚል ኃያል ቃል እናገኛለን "አለቃው ህዝቡን የሚመክራቸው በውግዘት ያይደል በመስቀል የሚያስራቸው ይሁን በማይገባ አያውግዝ፡፡ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለት ፈልጎ በማይገባቢያወግዝ እርሱ ከእግዚአብሐየር ዘንድ የታሰረ የተወገዘ ይሁን፡፡ ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት ይላል፡፡ በተፃራሪ ለግል ክብርና ዝና ውግዘት ማድረግ ተገቢ አይደለም ተደጋጋሚ ምክር ሳይደረግ ሊቃውንተ ቤተክረስቲያን ጉባዔ ሳይቀመጡ ውጉዝ ከመዓርዮስ ማለት ወፈ ገዝት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ሰለስቱ ምዕት(318ቱ ሊቃውንተ ቤተክርሰቲያን) አርዮስን በተደጋጋሚ መክረውና ዘክረው በነቂያ ጉባዔ እንዳወገዙት ልብ ይሏል ይህም የሆነው ለግል ክብርና ዝና ሳይሆን ከባድ ሐይማኖታዊ ክህደት በመፈፀሙ ነው፡፡

ስለውግዘት መፅሐፍ ቅዱስ (መፅሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ 36 ቁጥር 15) እንዲህ ይላል፡- “የማይገባ ግዝትን ለምትፈፅሙ ለናንተ ወዮላችሁ ስለ ኃጢያታችሁ ድህነት ከናንተ ይራቀ እንደስራችሁ መጠን ፍዳውን ትቀበላላችሁና ለባልንጀራችሁ ክፉ ምላሽ ልምትመሱ ለናንተ ወዮላችሁ”፡፡ በፍትሃ ነገስትም ላይ እንዲህ የሚል ኃያል ቃል እናገኛለን “አለቃው ህዝቡን የሚመክራቸው በውግዘት ያይደል በመስቀል የሚያስራቸው ይሁን በማይገባ አያውግዝ፡፡ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለት ፈልጎ በማይገባቢያወግዝ እርሱ ከእግዚአብሐየር ዘንድ የታሰረ የተወገዘ ይሁን፡፡ ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት ይላል፡፡ በተፃራሪ ለግል ክብርና ዝና ውግዘት ማድረግ ተገቢ አይደለም ተደጋጋሚ ምክር ሳይደረግ ሊቃውንተ ቤተክረስቲያን ጉባዔ ሳይቀመጡ ውጉዝ ከመዓርዮስ ማለት ወፈ ገዝት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ሰለስቱ ምዕት(318ቱ ሊቃውንተ ቤተክርሰቲያን) አርዮስን በተደጋጋሚ መክረውና ዘክረው በነቂያ ጉባዔ እንዳወገዙት ልብ ይሏል ይህም የሆነው ለግል ክብርና ዝና ሳይሆን ከባድ ሐይማኖታዊ ክህደት በመፈፀሙ ነው፡፡

ደግሞም እኮ በድርጊት እንጂ በስም ሰማዕትነትን የተቀበለ የሰው ዘር የለም (መብራቱን እስከ ዘይቱ የያዘም አይደል ከሙሽራው ጋር ሰርጉን የሚታደም?)፡፡

ከታሪክ የማይማር ታሪክን ይደግማል እንዲሉ ፈሪሳውያንና ሰዱቃዊያን በሆሳዕና እለት ህዝቡ የዘንባባ ዝንፃፊ እና የለበሱትን ልብስ በማንጠፍ ጌታ በውርንጭላይቱ ላይ ሆኖ እንዲያልፍ በማድረግ “ሆሳዕና በዓርያም በእግዚበሔር ስም የሚመጣ አርሱ ብሩክ ነው″ ብለው ሲያመስግኑ ለእነሱ አልተዋጠላቸውምና መምህር ሆይ ለምን ዝም በሉ አትላቸውም አሉት ምስጋና የባህሪ ገንዘቡ ነበርና እነሱ ዝም ቢሉ የቢታኒያ ድንጋዮች ያመሰግኑኛል አላቸው፡፡ እውነትም ድንቅ ነበር የቤተ ፋጌ አለቶች ድምፅ አውጥተው አመሰገኑት ዛሬም ይሄ ነው የተፈፀመው ፈሪሳውያንና ሰዱቃዊያን አናመሰገንም ሲሉ በበዓለ ሆሳእና በደብረ ሰላም መድሐኒያለም የቤተ ፋጌ አለቶች ድመፅ አውጥተው አመሰገኑት (ከቢታኒያ ድንጋይ ከማነስ ይሰውረን)፡፡ አቡነ ዘካሪያስም መፅሐፍ ቅዱስ በማይፈቅደው ከቤተክርስቲያን የህግ መፅሐፍ ከሆነው ከፍትሃ ነገስት ጋር በሚጣረስ መልኩ የግዝት ትዕዛዝ አስተላለፉ (እንደማስተባበያ ሥልጣነ ክህነታቸው ተያዘ እንጂ አልተወገዙም የሚል ጉንጭ አልፋ ምክንያት እንደ ምክኒያት ቢቀርብም &እዚች ጋር አንድ ቀልድ ቢጤ ትዝ አለችኝ ሰዎቹ በሰውዬው ሀብትና አውቀት እጅጉን ይቀኑና ህይወቱን እስከማጥፋ የሚደረስ ቅናት ያድርባቸዋል እናም በሚመላለስበት ቦታ አዘውትረው ይጠብቁት ነበርና አንደ ቀን አድፍጠው በሚጠብቁበት ሰዓት የሰውየው የበኩር ልጅ ያገኛቸዋል ወትሮውንም አባቱን ሊያጠፉት እንደሚፈልጉ ይሰማ ነበርና የያዙትን ስለት በማየት አባቴን ልትገሉት ነው አይደል ሲላቸው አንደኛው ፈጠን ብሎ አይደለም ባክህ የእናትህን ባል ነው አለው፡፡ግዝትና ክህነትን መያዝ ምን አለያየው ሁለቱም ግልጋሎትን የሚከለክሉ አይደሉም እንዴ ቂቂቂቂቂ)

ግዝት በቤተክርስቲያን ሃይማኖትን ለካዱ እና በነውር ለተገኙ ሰዎች በተለይም በካህናት ላይ የሚተላለፍ የመጨረሻው የፍርድ ውሳኔ ነው።ይህ አንድን ካህን(ሰው) ከማኅበረ ክርስቲያን የመለያ ውሳኔ የሚተላለፈው ደግሞ ተጨባጭ የሆኑ የኃይማኖት ክህደትና የምግባር ብልሹነት ሲቀርቡ ብቻ ነው።
ስለውግዘት መፅሐፍ ቅዱስ (መፅሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ 36 ቁጥር 15) እንዲህ ይላል፡- “የማይገባ ግዝትን ለምትፈፅሙ ለናንተ ወዮላችሁ ስለ ኃጢያታችሁ ድህነት ከናንተ ይራቀ እንደስራችሁ መጠን ፍዳውን ትቀበላላችሁና ለባልንጀራችሁ ክፉ ምላሽ ልምትመሱ ለናንተ ወዮላችሁ”፡፡ በፍትሃ ነገስትም ላይ እንዲህ የሚል ኃያል ቃል እናገኛለን “አለቃው ህዝቡን የሚመክራቸው በውግዘት ያይደል በመስቀል የሚያስራቸው ይሁን በማይገባ አያውግዝ፡፡ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለት ፈልጎ በማይገባቢያወግዝ እርሱ ከእግዚአብሐየር ዘንድ የታሰረ የተወገዘ ይሁን፡፡ ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት ይላል፡፡ በተፃራሪ ለግል ክብርና ዝና ውግዘት ማድረግ ተገቢ አይደለም ተደጋጋሚ ምክር ሳይደረግ ሊቃውንተ ቤተክረስቲያን ጉባዔ ሳይቀመጡ ውጉዝ ከመዓርዮስ ማለት ወፈ ገዝት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ሰለስቱ ምዕት(318ቱ ሊቃውንተ ቤተክርሰቲያን) አርዮስን በተደጋጋሚ መክረውና ዘክረው በነቂያ ጉባዔ እንዳወገዙት ልብ ይሏል ይህም የሆነው ለግል ክብርና ዝና ሳይሆን ከባድ ሐይማኖታዊ ክህደት በመፈፀሙ ነው፡፡

መቸም ዲያብሎስ በእድሜ እንጂ በተንኮል የማይበልጠን ተመፃዳቂ ለምድ ለባሽ ተኩላዎች ስለሆንን እንጂ ከእውቀትና ከመንፈሳዊ ብስለት ጋር የማይስማማ ቅዱሳን በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ከፃፏቸው የህግ መፅሕፍት ጋር በሚጣረስ መልኩ ባልተባረከነ በአራቱም የቤተክርስቲያኑ አቅጣጫ በቅብዓ ሜሮን ባልተባረከበት ብዙ ተገቢ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ባለተፈፀመበት አዲስ ቤተክርስቲያን ከሶስት ሳምንት በላይ ስርዓተ ቅዳሴ መፈፀም ምን ይባላል? ደግሞስ ለብዙ ዘመናት የጌታ ስጋና ደም ሲፈተትባት የነበረችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ይሄንን በረት አሳማ አርቡበት ብሎ ናቡከደነፆራዊ ድፍረት የተሞላበት ስድብ መሳደብ መቸም ሚኒሊክ ቤተመንግሰት ካሉት ነገስታት የተላከ እንጂ ከሰማዩ አባት የተወረሰ መንፈሳዊ ብስለት አይደለም፡፡

ሌላው አስነዋሪ ክስተት አላዋቂ መካር የፍዳ ማከማቻ መሆኑ ያልተረዱት የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የበላይ አሰተዳዳሪ አባ ዘርዓ ዳዊት በትንሳኤ ሌሊት አለም ከአመተ ፍዳ ወደ አመተ ምህረት በተሸጋገረበት አዳም ከዲያብሎስ እስራት ወጥቶ በክርስቶስ እቅፍ በዋለበት በዚያች የድህነት ብስራት በሚበሰርበት የምህረት እምቢልታ በሚለፈፍበት የነፃነት ነጋሪት በሚጎሰምበት ትንሳኤ ክርስቶስ በሚዘመርበበት እለት የአስታራቂነት ሚና ከሚጠበቅበት መንፈሳዊ አባት ቤተክርሲቲያኗ ግልፅ ያልሆነ በጉባዔ ባለተወሰነ የካህናቱና ዲያቆናቱ ምግባር ፅድቅ ይሁን ኩነኔ ባልተለየበት ለማህበረ ምዕመኑ የካህናቱንና የዲያቆናቱን ውግዘትና የስልጣነ ክህነት እስር መለፈፍ ምን ይሉታል? (እስራት የባህሪ ገንዘቡ ከሆነው የኢትዮጵያ መንግሰት ካልተላኩ በቀር)፡፡ እናም ቅዱስ አባታችን የቀደመውን አስቡ እግዚአብሔር ለሁለት አምላክ መገዛት አትችሉም በማለት ቀናተኛ አምላክ መሆኑን በአውደ ምህረቱ ትሰብኩልን የለ እናንተም ወይ ምድራዊ ክብራችሁን አልያም በመስቀል ላይ የዋለውን አምልኩ አልያ ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት ሆኖ በቤተክርስቲያን መክበር አይቻልም፡፡
ናቡከደነፆራዊ ድፍረታችሁን ትታችሁ የቀደመውን አስቡ!!!

እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያናችን ህብረትን ፍቅርን አንድነትም ይስጥልን!!!

የማለዳ ወግ …ዞን 9 ኞችን አደግፋለሁ !አግብቷቸው ስለጦመሩ መብታቸው መገፈፍ የለበትም (ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0
ነቢዩ ሲራክ
የማለዳ ወግ …ዞን 9 ኞችን አደግፋለሁ !
አግብቷቸው  ስለጦመሩ መብታቸው መገፈፍ የለበትም  !

zone 9999 ዞን 9 ኞችን አከብራቸዋለሁ ፣ እዎዳቸዋለሁ!” የሃገር የህዝባችን ጉዳይ ያገባናል !” በሚል በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ህይዎታችን ዙሪያ የሚያቀርቧቸው መጣጥፎች አስተማሪ ለመሆናቸው እማኝ ነኝ  !  ጦማርያኑ ቀፍድዶ ከያዘን ፍርሃት ወጥተን ህገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ ለመብታችን እንድንተጋ ማነቃቃታቸው ቢያስመሰግን እንጅ የሚያስኮንን ፣ የሚያስወግዝ ፣ ብሎም ወህኒ የሚያስወርድ ነው አልልም።

ዞን 9 ኞችን የምንወድ የምንደግፍ  እኔና እኔን መሰሎች ጥቂቶች አይደለንም ። እልፍ አእላፎች ነን ። ቢያንስ እኔ በግል የወጣት ጦማርያኑ እንግልትና ጉዳት የሃገር  ጉዳት ነው ብየ አምናለሁ ። እልፍ  አእላፎች ጦማሪዎች ” ህገ መንግስቱን አልጣሱም “ስንል  ” ህገ መንግስቱ ይከበር ፣ ዞን 9ኞች ይፈቱ !” ዘንድ ድምጻችን ከፍ አድርገን እናሰማለን  !

የዞን 9 ጦማርያን የመጻፍ የመናገር መብታቸውን ተጠቅመው ተደራጅተው በሰለጠነና በዘመነ አካሔድ ፍርሃት ዝምታችን ሰብረውልናል።ስለዚህም የሃገርና የህዝብ ድንቅ ልጆች እንጅ በጠላትነት ሊፈረጁ አይገባም። “የህዝብ የሃገር ጉዳይ ያገባናል!” ብለው ግንባራቸውን ለመስዋዕት የሰጡት ወጣቶች የህግ ከለላ ያስፈልጋቸዋል እንጅ ህግ እየተሸራረፈ መብታቸው መጣስ የለበትም።

ዞን 9 ኞች የማይወዷቸው የማግፈልጓቸው ” ሃገርና ህዝብ በድለዋል ፣ በብዕራቸው ሰላም አደፍርሰዋል!” ካሉ  የተጨበጠ መረጃ ይዘው አይሞግቷቸው አልልም። ጉዳያቸው በህግ ማዕቀፍ ተመርምሮ እና የዋስ መብታቸው ተከብሮ ትክክለኛ ፍትህን ሊያገኙ  ይገባል። ይህ ሳይደረግ የሳሾቻቸው አቤቱታ ብቻ እየተሰማ ፣  ባልረባባ ምክንያት እየወነጀሉ ዞን 9ኞችን ሊያዳክሙና ከአደባባይ መድረኩ ሊያጠፏቸው አይገባም ።

በዚህ ረገድ የፍትህ አካላት የሃገርንና የህዝብን ደህንነት ከማስጠበቁ ባልተናነሰ  የታዳጊ ወጣት ጦማሪዎችን መብት የማስጠበቅ ሰው የመሆን የሞራል ግዴታ አለባቸው  !

“የህዝበና የሃገር ጉዳይ ያገባናል!” ያልን ፍዳችን በዝቷል ። ያም ሆኖ ዝም አንልም ፣ ያገባናልና በአደጋ ተከበን እንጦምራለን  !  አዎ  ! ያገባናልና !

ሰላም …

ነቢዩ ሲራክ

Sent from Samsung Mobile
zone-9-300×300.jpg

“የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሐዊና ሕጋዊ ነው”

$
0
0

ሰንደቅ ጋዜጣጋዜጣው ሪፖርተር

አቶ አባዱላ ገመዳ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔ

 በአዲስአበባ ዙሪያያሉትን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚተዳደሩ ከተሞችን ከአዲስአበባ ጋር በማስተሳሰር በጋራ ለማልማት የወጣውን የተቀናጀ መሪዕ ቅድ በመቃወም ሰሞኑን በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የተካሄደው ተቃውሞ ተከትሎ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። በአዳማ፣ በድሬዳዋ፣ በጅማ፣ በመደወላቡ፣ በአምቦ፣ በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎችና በጠቅላላው በ11 ዩኒቨርሲቲዎች የተቀጣጠለው ተቃውሞ መነሻው የአዲስአበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ትግበራ ጉዳይ ነው። ዕቅዱ “የኦሮሚያ ከተሞችን በመቁረስ ወደአዲስአበባ ለማጠቃለል የታቀደ ነው፣ በርካታ ኦሮሞዎች ከቤት ንብረታቸው ሊፈናቀሉ ነው” የሚሉ አስተያየቶች በተለይ በማህበራዊ ድረገጾች በስፋት በመሰራጨታቸው ተማሪዎች ግራ በመጋባት የወሰዱት እርምጃ እንደሆነ ይታመናል። መንግሥታዊ አካላትም በወቅቱ ሕዝቡን በማሳተፍ ስለፕላኑ (ዕቅዱ) በቂና ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን አለማድረጋቸው ለግጭቱ መነሳት አንድ ምክንያት መሆኑ እየተነገረ ነው።

ቶ አባዱላ ገመዳ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔ

ቶ አባዱላ ገመዳ
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔ

የመንግሥት ኮምኒኬሸን ጽ/ቤት ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በመደወላቡ እና በአምቦ ዩኒቨርሲቲዎች ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ 10 ሰዎች መሞታቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ እግርኳስ በመመልከት ላይ ባሉ ተማሪዎች ላይ ባልታወቁ ሰዎች በተወረወረ ፈንጂ 70 ያህል ተማሪዎች ሲቆስሉ አንድ ተማሪ መሞቱን አስታውቋል።

ጽ/ቤቱ በዚሁ የመንግሥትም አቋም በገለጸበት መግለጫው በፌዴራልና በክልል የፀጥታ ኃይሎች ትብብር ሁከቱ በተፈጠረባቸው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት መቻሉን ጠቅሶ እስካሁን በተደረገው ማጣራት ከበስተጀርባ በመሆን ሁከቱን በማነሳሳትና በማቀነባበር ተግባር ላይ የተሰማሩት ጥቂት ፀረ ሰላም ኃይሎች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል ብሏል። ከዚሁ ግርግር በስተጀርባ የቆሙትና ከዚህ ቀደም በነበሩ ግጭቶች እጃቸውን ሲያስገቡ የነበሩ የአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ያሉ ኃይሎች በሚቆጧጠሯቸው ሚዲያዎች እየታገዙ ይህንን የተማሪዎችን ጥያቄ ለጥፋት ዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ መንቀሳቀሳቸውን በመግለጫው አስታውቋል።

በተፈጠረው ሁከት ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸውና ወገኖችና ቤተሰቦቻቸው መንግስት የተሰማውን ሐዘን የገለጸ ሲሆን የጥፋቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ የነበሩትን ተከታትሎ ለፍርድ ለማቅረብ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉትን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚተዳደሩ ከተሞችን ከአዲስ አበባ ጋር በማስተሳሰር በጋራ ለማልማት የወጣውን የተቀናጀ መሪ ዕቅድ ጋር ተያይዞ በተማሪዎች ስለተነሳው ጥያቄና በመንግሥት ስለተወሰደው እርምጃ የአሜሪካ ድምጽ አማርኛ ክፍል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔ የሆኑትን አቶ አባዱላ ገመዳን ከትላንት በስቲያ አነጋግሯል። እንደሚከተለው ቀርቧል።

ጥያቄ፡- ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ብዙ ሰዎች ሞተዋል። ሰልፉ የተካሄደው ባልታጠቁ ተማሪዎች ነው። በሮቤ፣ በአምቦ፣ በጅማ፣ በነቀምት፣ በመዳወላቡ፣ ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። መንግሥትም ራሱ ሐሙስ ዕለት ባወጣው መግለጫ እስከ 10 ሰዎች መገደላቸውን አምኗል፣ በዚህ ላይ የሚሰጡን ምላሽ ምንድነው?

አቶ አባዱላ፡- እውነት ነው፤ በኦሮሚያ ክልል ባሉት ዩኒቨርሲቲዎች የተነሳ የተቃውሞ ጥያቄ አለ። ጥያቄው የተነሳው በኦሮሚያና የአዲስ አበባ የጋራ ማስተር ፕላን በሚመለከት የተነሳ የተቃውሞ ጥያቄ ነው። በሁሉም አካባቢ ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ ፍትሃዊና ሕጋዊ ነው። እነዚህን ፍትሃዊና ሕጋዊ ጥያቄ በየአካባቢው ያሉት፣ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደርም ሆነ በየአካባቢው ያሉት አስተዳደሮች ለመመለስ ጥረት አድርገዋል። ጉዳዩን በቅርበት ይከታተሉ የነበሩ የመንግሥት ኃላፊዎችም በጉዳዩ ሒደት ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሞክረዋል። ይሁንና አንዳንድ ቦታ ተማሪዎቹ ጠየቁ፣ በቂ መልስ አላገኘንም አሉ። ለበላይ አካልም ጥያቄያቸው እንዲሄድላቸው ጠየቁ፣ ግን ደግሞ ያ-ምላሽ ከመምጣቱ በፊት ነው ሰልፍ ወጡ። እንግዲህ ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣት ሕገ-መንግሥታዊ መብት ነው። ይህ በሕገ-መንግስቱ የተቀመጠ ነው። ይሄ እንደተጠበቀ ሆኖ ሠላማዊ ሰልፍ ሲወጣ አስቀድሞ ማሳወቅ እንደሚገባ ይደነግጋል። ይሄ የሚሆነው በአካባቢው ያለ የመንግሥት አስተዳደር ሰልፍ የወጣው ሕዝብ አንድም ጉዳት እንዳይደርስበት ለመከላከል ነው። ሁለተኛ ደግሞ በሌላው ዜጋ ንብረትና ሐብት ጉዳት እንዳይደርስ ለመጠበቅ ነው። እነዚህ ሁለቱ ካልተሟሉ ችግር ሊከሰት እንደሚችል በአገራችንም በሌሎች ዴሞክራሲያዊና ባደጉ አገራትም ይታወቃል። መጀመሪያ ተማሪዎቹ ጥያቄያቸው ፍትሐዊ ሆኖ ሠላማዊ ሰልፉ ሕጉን ተከትሎ ያለማካሄድ ችግር ያጋጠመበትና ሳያሳውቁ በኃይል ስለተወጣ ከተማ ላይ በንብረት ላይ የደረሰ ኪሣራ አለ። ይሄ ወደባሰ ችግር እንዳይሰፋ የፀጥታ ኃይሎች ለመከላከል የወሰዱት እርምጃ አለ። የፀጥታ ኃይሎች አድማ ለመበተን ጢስ እና ውሃ ተጠቅመዋል። ይህን አልፎ ለሕይወት መጥፋትና ለሌሎችም ችግሮች የተከሰቱበት ሁኔታ አለ።

ጥያቄ፡- የተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሐዊና ሕጋዊ ነው ብለዋል። ሠላማዊ ሰልፍ ደግሞ በሕገመንግሥቱ የተቀመጠ መብት ነው ብለዋል። ሠላማዊ ሰልፍ ማድረግ የሚፈልግ ለመንግሥት አካላት ማሳወቅ ነው ብለዋል። ነገር ግን የታጠቁ ኃይሎች ልጆቹ ላይ ተኩስ እንደከፈቱና በዚህም ምክንያት የማይተካ ሕይወት እንደተሰዋ ነው የሚነገረው። ጥያቄያቸው ትክክለኛ እስከሆነ ድረስ ለዚህ ግድያ ምን መልስ ይሰጡናል?

አቶ አባዱላ፡- በመጀመሪያ ይህ መምጣት የሌለበት ነው። ሕይወትም ንብረትም መጥፋት በጣም የሚያሳዝን ነው። መንግሥትም ሐዘኑን ገልጿል። እኔም በቦታው ደርሼ አይቻለሁ፣ አዝኛለሁ። መሆን የማይገባው ጉዳይ ነው። በቦታው በኃይል ለመመለስ ወይም በጥይት ለመመለስ አይደለም ዝግጅቱ። አንድ ምሳሌ ለማንሳት ልሞክር። የአድማ በታኝ የፌዴራል ፖሊስ በቦታው የደረሰው ብዙ ተሽከርካሪዎችና ንብረት ከተቃጠለ በኋላ ማታ ላይ ነው። ማምሻውን 11 ሰዓትና ከዚያ በኋላ ነው የደረሰው። ቃጠሎው እየሰፋ ሲሄድ ነው፣ የክልሉ መንግሥት ይሄ ነገር የከፋ ሕይወት ሊያጠፋ ስለሚችል የሚቆጣጠር ኃይል መግባት አለበት ብሎ ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ አቅርቧል።

ጥያቄ፡- ተማሪዎቹ መኪናዎችን ሲያቃጥሉ ነበር ነው የሚሉኝ?

አቶ አባዱላ፡- እንግዲህ በአምቦ ከተማ ቀደም ሲል ሠላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ማሳወቅ ይገባል ያልነው ባመፈፀሙ፣ ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ፣ ተማሪዎቹ በግቢያቸው ውስጥ የመጨረሻውን ዝግጅት አድርገው የወጡ ቢሆንም፤ ከውጪ ግን ተማሪዎችን የተቀላቀለ ብዙ ኃይል አለ። የዘረፋ ፍላጎት ያለው፣ የማውደም ፍላጎት ያለው ኃይል ተቀላቅሏል። ከተቀላቀለ በኋላ ለምሳሌ በአምቦ አበበች መታፈሪያ የሚባል ሆቴል ተዘርፏል። ሆቴል ውስጥ የነበሩት የቱሪሰት መኪናዎች ተቃጥለዋል። እንደዚህም የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ተቃጥሏል። የምዕራብ ሸዋ ፍ/ቤት ዶክመንቶችና ፍ/ቤቱ ራሱ ተቃጥሏል። እንዲያውም ተማሪዎች ናቸው ለማለት የማያስችለው ከጥበቃ ኃይሎች ትጥቅ በመቀበል ወደተኩስ የተገባበት ሁኔታ ነበር። ይሄ ነገር ሄዶ ሄዶ ብዙ ሕይወት፣ ብዙ ንብረት እንደሚያወድም ይታወቃል። መንግሥት ይህን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት።


(የተማሪዎቹ ግድያ ጉዳይ) ከማስተር ፕላኑ ግጭት ባሻገር

$
0
0

***** (ዜና መዋዕል)27/8/06

የሰሞኑን የአዲስ አበባንና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን ተከትሎ የተነሳውን ተቃውሞና ግድያ በሚመለከት እንደ አንድ ግፍንና በደልን እንደሚጠላ ዜጋ ጥልቅ ሃዘን ይሰማኛል፡፡ ነገሩ በኛ ሀገር ሆነና ነው እንጅ ስልጣን የሚያስለቅቅና በግድያው የተሳተፉትንም በህግ የሚያስጠይቅ በሆነ ነበር፡፡ በየትኛውም ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን የሚያቀርብ ዜጋ እንኳን ሞት ድብደባም አይገባውም፡፡ ረብሻና ሁከት ፈጣሪዎች እንኳ ሲያጋጥሙ በሰለጠነ መንገድ በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ ማቅረብ ተገቢ ነበር፡፡ ይህ ግን በኛ ሀገር ሊታሰብ የሚችል አይደለም፡፡ ከግጭቱ ባሻገር ግን ሰከን ብለን ልናነሳቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፤ እኔም በዚህ ጽሁፍ የማተኩረው በዚሁ ነው፡፡
tplf killing ethiopians
ከ85% በላይ የሆነው ህዝብ ኋላ ቀር በሆነ የግብርና ዘዴ ህይወቱን በሚመራባት ሀገራችን የከተሜነት ወይም የኢንዱስትሪውና የአገልግሎት ሰጪው ዘርፍ መስፋፋት ጠቀሜታው አሌ የሚባል አይደለም፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ አካባቢዎችም ከአ/አበባ በረከቷንም ሆነ ርግማኗን መካፈላቸው አልቀረም፡፡ በተለይም ከከተማዋ መስፋት ጋር በተያያዘ በዙሪያው ያሉ የኦሮሚያ ገበሬዎች ይዞታቸውን ባልተጠናና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እየሸጡ እርሻቸውን እያጠበቡ፤ ከተሞቹም ለዘላቂ ልማት አመቺ ባልሆነ መንገድ እየተስፋፉና ከአ/አበባ ጋር እየገጠሙ መሆኑን እያየን ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ገበሬው ባለችው ጥሪት የሚያስተምራቸው ልጆቹን አምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ ተስፋፍተው ካልቀጠሩለት ስራ አጥ ልጁ ተመልሶ የእሱኑ መሬት እየተቀራመተ ድህነቱን ማባባሱ አይቀርም፡፡
በመሆኑም በማስተር ፕላኑ በዙሪያው ያሉ የኦሮሚያ አካባቢዎች ወደ አ/አበባ ተካለሉም አልተካለሉ ይህንን የከተሜነት ወይም የኢንዱስትሪና አገልግሎቱን ዕድገት ታሳቢ አድርጎ በቅንጅት መስራቱ ለኔ በግሌ ጥቅሙ እንጅ ጉዳቱ አይታየኝም፡፡ ነገር ግን ከቀደመው የመንግስት አፈፃፀም ግድፈቶችና ከአጠቃላይ የስርዓቱ ችግር ስንነሳ የምንቃወምባቸው በቂ ምክንያቶች ይኖራሉ፡፡

ምንም እንኳ የጋራ ማሰተር ፕላኑ ለውይይት በቀረበበት ወቅት የኦሮሚያ ካድሬዎች ያቀረቧቸው ጥያቄዎች በህገ መንግስቱ መሰረት ክልሉ ከአ/አበባ ሊያገኛቸው ስለሚገባው ጥቅሞች ቢሆንም በቀጣይ ባለድርሻ አካላት ይወያዩበታል መባሉ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጅ፡-
1- ባለድርሻ አካላት ተወያይተው የጋራ ማስተር ፕላኑ ይቅር ቢሉ እንኳ መንግስት ከማድረግ ወደኋላ የማይልና የሚስማሙለትን ብቻ መርጦ የሚያወያይ፣ ውሳኔውንም የሚያስደግፍ መሆኑን ከቀደመው የመንግስት አካሄድ የምንረዳ መሆኑ፤
2- ገበሬዎቹም በልማት ስም ሲነሱ የሚሰጣቸው ካሳ በዘላቂነት ህይወታቸውን ለመምራት የማያስችላቸው መሆኑ፤
3- ስርዓቱ ለገበሬው ዝቅተኛ ካሳ ከፍሎ በከፍተኛ የሊዝ ዋጋ የሚሸጠው መሬት ገንዘቡ ኃላፊነትና ተጠያቂነት በተሞላበት መንገድ ለህዝብና ለሀገር ጥቅም መዋሉን እንድንጠራጠር የሚያደርገን የመንግስት ባለስልጣናት ሃይ ባይ ያጣው ዘረፋና ሙሰኝነት፤
4- እንዲሁም መሬቱን በፍትሃዊነት ሀገርና ህዝብን ለሚጠቅሙ ሳይሆን የስርዓቱን ደጋፊዎችና ተጠቃሚዎች የኢኮኖሚ የበላይነት ለማስቀጠል ሲባል በአሻጥር እነዚሁ ልማታዊ ተብዬ ባለሀብቶች የሚቃረጡት መሆኑ ጥያቄ እንድናነሳ ከበቂ በላይ ምክንያቶች ይሆናሉ፡፡
ጥያቄውን የምናነሳበት መንገድና ዘዴ ግን የምንፈልገውን ምላሽ ለማግኘት ያለንን ዕድል ይወስናል፡፡ ጉዳዩን የአንድ ብሄር ችግር አድርገን የምናነሳው ከሆነ ትልቁ ችግር እዚያ ጋ ይጀምራል፡፡ ሲጀመር በጋምቤላ ነዋሪዎቹ እየተፈናቀሉ ከህንድና ከአረቢያ የመጡ ኢንቨስተር ተብየዎች ከነፃ ባልተሸለ ዋጋ መሬቱን ሲነጥቁት አብረነው ስላልጮህን ዛሬ አብሮን ላይቆም፤ አማራው ህይወቱን መስርቶ ተረጋግቶ ሲኖርበት ከነበረው ቀዬ አማራ በመሆኑ ብቻ ሲፈናቀልና ከክልላችን ውጣ ሲባል የአማራው ችግር ብቻ አድርገን በማየታችን ዛሬ አብሮን ላይቆም ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ገዢዎቻችን (ይቅርታ መሪዎቻችን ወይም አስተዳዳሪዎቻችን አልልም) እስካሁን ሲጠቀሙበት ለነበረው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲያቸው መጠቀሚያ መሆናችንን ነው፡፡ በተለያየ ጊዜና ሁኔታ ለያይቶ የሚያጠቃን ስርዓት ዋናው ዓላማ ተባብረን እንዳንቆምና መብቶቻችንን እንዳንጠይቅ ነው፡፡
ይህ ደግሞ ተሳክቶላቸዋል፡፡ በሰሞኑ ተቃውሞ እንኳ ብሄር ለይቶ ከመቋሰሉ በተጨማሪ ጥያቄውን ሌላ መልክ ለማላበስ ምንም እንኳ ጥያቄውን ያነሱት ተማሪዎች ዓላማቸው ነበር ብለን ባንገምትም እሱን ታከው በአንዳንድ ቦታዎች ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሱት፣ ንብረት ያወደሙትና የዘረፉት የራሳቸው ግብ እንደነበራቸው መካድ አይቻልም፡፡

ወደ እውነታው ስንመጣ ሱሉልታና ጫንጮ ለሚኖረው ኦሮሞ ባሌና ሐረር ከሚገኘው ኦሮሞ የሰሜን ሸዋ አማራ በባህልም በእምነትም ይቀርበዋል፡፡ አብሮ የኖረውን ሕዝብ አማራ ስላልሆነ ብቻ ሲጠቃ ዝም ይላል ማለት አይደለም፡፡ ኦሮሞውም አማራ ሲጠቃ ዝም አይልማ፡፡ ምናልባት ራሱን የተማረ ብሎ ከሚጠራውና በተግባር ግን ካልተማሩት አባቶቹ ካነሰው እንዲሁም ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍና ሕዝብና ሕዝብን በማጋጨት ሆዳቸውን ለመሙላት ከሚያስቡ ደም አፍሳሾች ውጭ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተቻችሎ ተከባብሮና ተፈቃቅሮ የሚኖር መሆኑን አንዱ ካንዱ ተጋብቶ ወልዶን ስላሳደገንና አብረንውም ስለምንኖር እናውቀዋለን፤ ይህንንም ለመረዳት ነጋሪ አያሻንም፡፡

ስለሆነም የሕዝቡን የመብት ጥያቄ በጠባብ ብሄርተኝነትና ጽንፈኝነት ተመርቶ ከማጥበብ ይልቅ፡-
- የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ፣
- በማንኛውም ቦታ ሰዎች ያለአግባብ እንዳይፈናቀሉና አስፈላጊ ከሆነም ፍትሃዊና ተገቢ ካሳ እንዲያገኙ፣
- በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሕዝቡን የስልጠን ባለቤትነት እንዲያከብርና ህገመንግስታዊ መሰረት የሌላቸውን አፋኝ ህጎቹን እንዲያሻሽል፣
- የስርዓቱ ብልሹ አስተዳደር እንዲሻሻል ካልሆነም ስልጣን እንዲለቅና
- ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነትና በነፃነት የሚኖርባት ለሁላችንም የምትመች ሀገር እንድትኖረን ተባብረን በጋራ መቆምና መታገል ይገባል፡፡
ከሁከትና ብጥብጥ እንዲሁም ሌላውን ከማግለልና ከጥላቻ ፖለቲካ ከጥቂት አውቅልሃለሁ ባዮች ውጭ እንደሕዝብ የምንጠቀመው ስለሌለ በተለይ የተማረውና የሚማረው የህብረተሰቡ ክፍል ይህን ነቅቶ ሊከላከለው ይገባል፡፡
አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ!

የገንዘባችን ዋጋ ስንት ነው?

$
0
0

ኤድመን ተስፋዬ *
* (የግብርናና ኢኮኖሚስት እና የገጠር ልማት ባለሞያ)

ethiopia-100birr
የ ፅሁፌ ትኩረት የገንዘባችንን ዋጋ በመፈተሸ ከንድፈ ሀሳብ እና ከሀገራት የኢኮኖሚ ታሪክ መነሻነት መንግስት ለዋጋ ግሽበቱ የሚሰጠውን የኢኮኖሚ እድገት ምክንያትነት ከመሞገት በተጨማሪ ከዋጋ ግሽበቱ ጀርባ አጮልቆ ማየት ነው፡፡ መነሻችን ኑሮአችን ነው ኑሮአችን ስንል ደግሞ ገንዘባችን አንዱ ና ዋነኛው ከመሆኑ አኩአያ እንቆቅልሽ የሆነብንን የገንዘባችን ዋጋ ከመግዛት አቅሙ አንፃር ዋጋውን በመፈተሽ በዋጋ ግሽበት አማካኝነት ገንዘባችንን መሰረቅ አለመሰረቃችንን መፈተሽ የሚያስፈልግ ይመስለኛል፣ የምን መሰረቅ ካሉ ከዛሬ አንድ ወር በፊት ዘንቢል ይዘው ወደ ገበያ ወጡ እንበል በ መቶ ብር ዘንቢሎን በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ሞልተው ተመለሱ እንደገና ከ አንድ ወር ወይም ከ አራት ወር በሁአላ በተመሳሳይ መልኩ ከአንድ ወር በፊት የሸመቱትን እቃ ለመሸመት መቶ ብር ይዘው ሲወጡ መቶ ብሮ ሊገዛሎት የቻለው እቃ ከዘንቢሉ ግማሽ አላለፈም እንበል ምክንያቱ ደግሞ በገንዘቡ የመግዛት አቅም መቀነስ የተነሳ በኪሶ የያዙትን ገንዘብ በመሰረቆኦ ነው:: ይህም ማለት የአንድ ብር ኖት የዋጋ ግሽበቱ 30 ፐርሰንት በሆነበት ሁናቴ ያለው ዋጋ (1 /1.30) 0.76 ወይም ሰባ አምስት ሳንቲም በመሆኑ ሃያ አምስት ሳንቲም ከአንድ ብር ላይ እንደ መሰረቅ ማለት ነው ፡፡ ስለ ገንዘብ የመግዛት አቅም መቀነስ ወይም ስለ ዋጋ ግሽበት ሲነሳ በአሁኑ ወቅት ምሳሌ የምትሆነው የሮበርት ሙጋቤ ሀገር ዙንባቤ ነች፣ የዙንባቤ ገንዘብ ከመውደቁ የተነሳ በዙንባቤ ከተሞች በፌስታል ሙሉ ገንዘብ ቢያዩ ከገንዘቡ ይልቅ ፌስታሉ ዋጋ እንዳለው ማወቅ አለቦት በሚል ደረጃ እስኪቀለድበት ድረስ ገንዘባቸው የማገበያየት አቅሙ ሞታል፡፡ በሀገራችንም በአብዛኛው ህብረተሰብ ምነው ገንዘባችን የሱማሌ (ሱማሌ ከወራሪው ዚያድባሬ መውደቅ ጀምሮ እሰከ አሁን ምን ያህል ገንዘቡአ የማገበያየት አቅሙ እንደሞተ ልብ ይሉአል) ብር ሆነ በሌላ በኩል የኛን መቶ ብር ከ ከጃማይካዊው ዩዝየን ቦልት ጋር በማመሳሰል ዩዝየን ቦልት መቶ ሜትሩን ከ አስር ሰከንድ እንደሚገባው ሁሉ የኛም የመቶ ብር ኖት ተዘርዝሮ ለማለቅ ከአስር ሰከንድ ያላነሰ ጊዜ ነው የሚወስድበት የሚል እና ሌሎች ተመሳሳይ ማህበረሰባዊ ትዝብቶች እና ብሶቶች የገንዘባችንን የመግዛት አቅም መድከምን እና የኑሮ ውድነትን ተንተርሶ ይነሳሉ፡፡ በአንድ ወቅት በፖርላማ የሀገራችንን የዋጋ ግሽበት አደገኛነት በመግለፅ የግሽበቱን ምክንያት ከመንግስት ቅጥ ያጣ የገንዘብ ወጪ ስርአት ጋር የተገኛኘ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት እንዲሁም መንግስት የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት ተጨማሪ የገንዘብ መጠን ወደ ኢኮኖሚው በማስገባቱ ግሽበቱን እንዳባባሰው በመግለፅ መንግስት ወጪውን እንዲቀንስ በአንድ የተከበሩ የፓርላማ አባል ለተነሳው ጥያቄ ነብሳቸውን ይማርና የቀድሞው የሀገራችን ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ በሰጡት መልስ ከኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ የዋጋ ግሽበት ( inflation) መከሰቱ አዲስ ነገር አለመሆኑን በመግለፅ የዋጋ ግሽበቱ ከኢኮኖሚው እድገቱ ጋር በተመጣጠነ መልኩ የተከሰተ መሆኑን በማብራራት ለዋጋ ግሽበቱ ሲባል የሚቀነስን የመንግስት ወጪ ልማትን ከመቀነስ ጋር አያይዘው ጫማ ጠበበኝ በሚል እግር አይቆረጥም ሲሉ ኬይኔዥአዊ መልስ ሰጥተዋል፡፡ የኬይኒዝ የኢኮኖሚክስ ንድፈ ሀሳብ እንደ ሚያወሳው መሀከለኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት የኢኮኖሚ እድገትን በማቀላጠፍ የኢኮኖሚ እድገት አቀጣጣይ መሳሪያ ሊሆን ይችላል ይህ ሊሳካ የሚችለው ግን እንደ ኬይኒዝ የኢኮኖሚክስ ንድፈ ሀሳብ መሰረት መሀከለኛ (moderate) የሆነው የዋጋ ግሽበቱ የመቆጠብ አቅማቸው አናሳ ከሆኑት የሰራተኛው እና የአርሶ አደሩ መደብ ሀብትን ወደ ካፒታሊስቱ በማሸጋገር የመዋእለ ነዋይ ፍሰትን በማስፋፈት እና በማቀላጠፍ ለኢኮኖሚ እድገት አዎንታዊ ሚና መጫወት ሲችል ነው ይህንን ለማሳካት ደግሞ የኢኮኖሚ ስርአቱ በፍላጎት እና በአቅርቦት መርህ መመራት ይኖርበታል ፡፡ በኢኮኖሚ ውስጥ ሙሉ የስራ እድል ወይም ሙሉ ሰራተኛ መኖርን እንደ ቅድመ ሀሳብ (Assuption) እንደመነሻ በመውሰድ የዋጋ ግሽበትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ዝምድና የሚተነትነውን የሞላ የስራ እድል (full employment model) የሚባለውን የኢኮኖሚክስ ሞዴል መነሻ ብናደርግ የስራ እድል ወይም ሰራተኛ ሙሉ በሆነበት የኢኮኖሚ ስርአት የኢኮኖሚ እድገት ከኢኮኖሚ እድገቱ ስፋት አኩአያ ላልተጠበቀ የዋጋ ግሽበት ምክንያት ሊሆን ይችላል ነገር ግን የድህነት ስፋቱ በገዘፈበት ሀገር ከ 10-12 % የኢኮኖሚ እድገት በተመዘገበበት ሁናቴ 35-40 % የዋጋ ግሽበት ተከስቶ ከኢኮኖሚ እድገቱ ጋር ማያያዝ የተጋነነ ሲሆን እንዲያውም በእንደዚህ አይነት የኢኮኖሚ እድገት መጠን ይህ አይነቱ የዋጋ ግሽበት የኢኮኖሚውን ጤናማ አለመሆን አመላካች ነው፡፡

የዋጋ ግሽበት ምክንያቶች ስንል

በኢኮኖሚ ስርአት ውስጥ ከልኬቱ ያለፈ የዋጋ ግሽበት ወይም የገንዘብ የመግዛት አቅም መውደቅ( inflation) በሀገር ላይ ከኢኮኖሚያዊ መመሰቃቀል ባለፈ ለማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መመሰቃቀል ምክንያት ሊሆን ይችላል፣ የገንዘብ ኢኮኖሚስቶች የዋጋ ግሽበትን ወይም የገንዘብ የመግዛት አቅም መውደቅን (inflation) በዜጎች ላይ የሚፈጸም ስርቆት በማለት ይገልፁታል፡፡ የዋጋ ግሽበት ወይም የገንዘብ የመግዛት አቅም መውደቅን የሚያስከትሉ መንስኤዎች ፍላጎታዊ ( demand pull) እና ወጪያዊ ግፊቶች (cost push) ሲሆኑ በወጪያዊ ግፊቶች ምክንያት የሚባለው የሰራተኛ ዋጋ መናር፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ፣ የግብርና ግብአቶች መወደድ ፣ በምንዛሬ መወደድ የተነሳ ከውጪ የሚገቡ ግብአቶች መወደድ፣ በሀይል ዕጥረት የተነሳ የምርታማነት ግብአቶችን መወደድን ተከትሎ አምራቹ አካል ኪሳራን በመፍራት በሚጨምረው የእቃዎች ዋጋ ምክንያት የሚከሰት የዋጋ ግሽበት ሲሆን ፍላጎታዊ ምክንያት የሚባለው ደግሞ ከገቢ መጨመር ጋር የተያያዘ የፍላጎት መጨመር እንዲሁም የአቅርቦት ማነስ ( ሸማቾች አንድአይነት እቃዎችን በተለይ የፍጆታ እቃዎችን የመግዛት ፍላጎት ከአቅርቦት ማነስ ጋር ተያይዞ የሚፈጥረው የዋጋ ንረት)፣ ከመንግስት የበጀት ጉድለት ጋር ተያይዞ የገንዘብ ኖት አቅርቦት መጨመር ጋር ተያይዞ የሚከሰት የዋጋ ግሽበት ነው፡፡ የገንዘብ የመግዛት አቅም መውደቅ( inflation) እስከ 2 % ብቻ ከሆነ በኢኮኖሚው ላይ ይሄነው የሚባል ችግር ሊፈጥር ስለማይችል ጤናማ ለባል ይችላል ከ 2 % በላይ ከሆነ ግን እንደየደረጃው በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሲኖረው በተለይ ሀይፐር ( hypher) የሚባለው ደረጃ ከተደረሰ የመገበያያውን ገንዘብ እስከ መለወጥ እንደሚያስደርስ አብዛኛዎቹ የገንዘብ ኢኮኖሚስቶች ይገልፃሉ፡፡

የአንድ ብር የገንዘብ ኖትን ለማተም ወጪው 0.25 ሳንቲም ከሆነ 0.75 (ሰባ አምስት ሳንቲም )ሳንቲሙን ትርፍ የሚያገኘው አንድ ብር አሳታሚው አካል እንደሆነ ለማወቅ የተጋነነ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ መሆን አስፈልግም፣ ይህ አይነቱ ንድፈ ሀሳባዊ ምሳሌ መንግስታት የበጀት ጉድለታቸውን ለመሸፈን ከኢኮኖሚው አቅም በላይ ተጨማሪ የገንዘብ ኖትን ብሄራዊ ባንክን በመጠቀም ማተም እንደ አማራጭ የሚወስዱበትን ምክንያት በትንሹ ለመረዳት ያስችለናል፡፡የሀገራት የኢኮኖሚ ታሪክ እንደሚነግረን ደካማ እና በሙሰኛ አመራሮች የተሞላ የመንግስት ስርአት ወጪውን እና የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን እና ለበጀቱ ምንጭነት መበደርን እና የብድርን ምንጭ ከልኬቱ ባለፈ (ከገቢው በላይ) መልኩ ያለ ቅድመ ሁኔታ መጠቀም ሲሆን በዚህም የተነሳ ከመንግስት ስርአቱ ገለልተኛ በመሆን የኢኮኖሚውን የገንዘብ ፍሰት መቆጣጠር እና ማስተካከል የሚገባውን ብሄራዊ ባንክ በፍፁም ገለልተኛ እንዲሆን አይፈቅዱም፡፡ የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋአም በተደጋጋሚ ሁኔታ እንደሚገልፀው በሀገራችን ካለፉት ስምንት እና ዘጠኝ አመታት ወዲህ በኢኮኖሚው ውስጥ የገንዘብ አቅርቦት በተለየ ሁነታ መጨመሩን ሲሆን በባንኮች ያለው የተትረፈረፈ የገንዘብ ክምችት ደግሞ በካሽ ያለውን ብዛት ያለው የገንዘብ ኖት በኢኮኖሚው ውስጥ መኖሩን ማሳያ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ እውቁ ኢኮኖሚስት ፍሪድማን አገላለፅ የዋጋ ግሽበት በከፈተኛ መጠን ቀጣይነት ባለው መልኩ ከተከሰተ የገንዘብ አቅርቦቱም በኢኮኖሚ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ዶ/ር አሳየሀኝ ደስታ Economic Growth for Inflation: The Ethiopian Dilemma በተባለው ጥናታዊ ፅሁፋቸው ሀገራችን በዋጋ ግሽበት አዙሪት ውስጥ ለመገኘቱአ በዋናነት የሚያነሱት ምክንያት የገንዘብ ኖት አቅርቦቱን መጨመር ሲሆን ለዚህም ማሳያነት እ.ኤ.አ በ 2002 19.4 % የነበረው የገንዘብ አቅርቦት በ 2006 ወደ 23.3 % መጨመሩን ሲሆን ይህ ሁናቴ ደግሞ ከ 2002- 6 በአማካይ የተመዘገበውን 6.8 % የኢኮኖሚ እድገት ጋር (የኢኮኖሚ እድገቱ በራሱ ግሽበታዊ በሆኑ ምክንያቶች የተሞላ መሆኑ እና በክፍለ ኢኮኖሚዎች ትስስር ላይ የተመሰረተ አለመሆኑ እንዳለ ሆኖ) የገንዘብ ክምችቱን ለማስተካከል የገንዘብ አቅርቦቱን በ 18 % መጨመር ያስፈለገ ሲሆን ይህ ሁናቴ ደግሞ ባለው የዋጋ ግሽበት ላይ በአማካይ ለተጨማሪ የ 12 % የዋጋ ግሽበት ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ በዚህ ሁናቴ ውስጥ የመንግስት የበጀት ጉድለት ኔጋቲቭ መሆኑን በመጥቀስ ምንም እንኩአን የገንዘብ አቅርቦቱ መጨመር ለመዋእለ ነዋይ ፍሰቱ ምክንያት ቢሆንም እንኩአን የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር የመንግስትን የበጀት ጉድለት ማእከል ካልተደገ ዋጋ ቢስ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡

በሀገራችን የምግብ ፍጆታዎች የሆኑት የግብርና ምርቶች እጥረት ለምግብ ፍጆታዎች ዋጋ ንረተ በምክንያትነት በሚበቀርብበት ወቅት መንግስት የሚሰጠው ምላሽ የምግብ ፍጆታ የሆኑት ምርቶች ዋጋ ሊንር የቻለው በኢኮኖሚ እድገቱ የተነሳ እና አምራቹ ገበሬ ለምርቱ ትክክለኛ ዋጋ በመፈለጉ እንደሆነ ነው ይህም ማለት የግብርና ስራው ህይወቱን ስለ አሻሻለለት ለእለት ፍጆታው ሲል ብቻ ምርቱን ያለ ዋጋው ስለማይሸጥ እንደ ማለት ነው ነገር ግን የአለም አቀፉ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ድርጅት (UNICEF) ሆነ የተባበሩት መንግስታት በሀገራችን በየአመቱ ለምግብ እጥረት የሚጋለጡት ሰዎች ህፃናትን ጨምሮ 26 ሚሊዮን እንደሚደርስ በሚገልፁበት ሁናቴ መጋቢያችን የሆነው አርሶ አደር በግብርናው እንቅስቃሴ የተነሳ ህይወቱ መለወጡን እና ሀብታም መሆኑ ሲገለፅ ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም፡፡

ያለአግባብ የኬሚካል ግብአቶችን ለ ግብርና በመጠቀም የተነሳ ሀገራችን ከአፍሪካ ከፈተኛ የፀረ ተባይ (pesticides) መድሀኒት ክምችት የሚገኝባት ቀዳሚ ሀገር መሆንዋን ኤድዋርድ የተባሉ አጥኚ Greening Ethiopia for self-sufficiency. በተባለው ጥናታዊ ጽሁፋቸው ይገልፃሉ፣ በከፍተኛ ደረጃ የኬሚካል ማዳበሪያ መጠቀምን ተከትሎ የገጠሩ አምራች የሆነው የግብርና መሬት ለስነምህዳራዊ ችግር የተጋለጠ ሲሆን የችግር መጠኑም ከ መሬት ምርታማነት መውደቅ እስከ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያትነት የሚደርስ ሲሆን ይህም በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነውን የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ሲሆን ይህም የሚያሳየን የግብርና ምርቶች ዋጋ መናር መንስኤን ውስን የሆነ የግብርና ምርታማነት ቴክኖሎጂ በገጠሩ አካባቢ በመኖሩ የተነሳ የሚለው የሚገልፀው ይመስለኛል ፡፡

ከዋጋ ግሽበት ጀርባ

ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ቀጣይነት ባለው መልኩ በሚከሰትበት ሁናቴ በኢኮኖሚው ስርአት ውስጥ የሚተገበር የወለድ ተመን ፖሊሲ የዋጋ ግሽበትን መጠን ማእከል በማድረግ የኢኮኖሚ ስርአቱን ሚዛናዊነት በጠበቀ መልኩ እና የዋጋ ግሽበቱን ከመቀነስ አኩአያ በተመቻመቸ መልኩ ተግባራዊ ካልሆነ በባንኮች ና በፋይናንስ ተቋአማት ውስጥ የሚሰጠውን የቁጠባ ና የብድር አገልግሎት በተበዳሪ ሰራቂነት እና በቆጣቢ (በአበዳሪ) ተሰራቂነት መሀል የወደቀ አገልግሎት ያደርገዋል በመሆኑም ትልቁ ጉዳይ ከዋጋ ግሽበት ጋር ተያይዞ የሚፈጠረው የቆጣቢ በ ተበዳሪ መሰረቅ ነው፡፡ የቅርቡን የብሎንበርግ 29.6 % በአማካይ የሚለውን የሀገራችንን ያለፉትን አምስት አመታት የዋጋ ግሽበት መነሻ ብናደርግ ከወለድ ተመኑ (አማካይ ከ 8-10%) ጋር ባነፃፀረ መልኩ የዋጋ ግሽበቱን ያማከለው የወለድ ተመን ኔጋቲቭ 20 % መሆኑን እንረዳለን ይህ ማለት ደግሞ አንድ ተበዳሪ ( ከባንክ ተበዳሪ የሆነ ግለሰብ) ከአበዳሪ (ብሩን በባንክ ውስጥ ቆጣቢ ከሆነ ግለሰብ) 100 ብር ቢበደር አበዳሪው ተጨማሪ 20 ብር ገንዘቡን እንዲጠቀም ለተበዳሪው መክፈል እንደማለት ነው ይህን ወደ ጠቅላላው የኢኮኖሚ ስርአት ስንመልሰው በዋጋ ግሽበት አማካኝነት ባንክ ውስጥ ቆጣቢ ከሆነው ግለሰብ ወደ ባንክ ተበዳሪው ግለሰብ የሚሸጋገርን ሀብት መነሻ በማድረግ በዋጋ ግሽበት አማካኝነት በጠቅላላው ኢኮኖሚ ውስጥ የሚፈጠርን የሀብት ሽግግር ለመገንዘብ አዳጋች አይሆንም በተጨማሪም በዋጋ ግሽበት ወቅት በቢሮክራሳዊ እና በጥቅመኝነት የተነሳ የተወሰኑ አካላትን እና ድርጅቶችን ብቻ ያማከለ ከፍተኛ መጠን ባለው የብር መጠን ደረጃ የብድር አገልግሎት መኖሩ ሰራቂን ማዘጋጀት እንዳለ ለመገንዘብ አዳጋች አይደለም፣ የትኛው ኢኮኖሚስት ነበር ለሰላምታ እንኩአን ለፖለቲከኞች እጆቼን ከዘረጋውላቸው እና ሰላምታ ከተለዋወጥን በሁአላ ጣቶቼን እቆጥራቸዋለው ምክንያቱም ሊሰረቁ ይችላሉና በማለት የተናገረው፡፡

በሬየን አልሸጥም –አጭር ወግ –በሄኖክ የሺጥላ*

$
0
0

Henok Yeshitila

አዲሱን (የነበረውን ግን ሰሞኑን የሾረውን) የ “ኦሮሞ ወጣቶች ” ግድያ። በነገራችን ላይ ለምንድን ነው “የኢትዮጵያ ወጣቶች ” የማንለው? ማለት ስለማንፈልግ? ወይስ ብንል ባንል ምን ይጠቅማል ( ምንስ ይጎዳል በሚል ሃሳብ?) ሁለቱንም ያዙልንና እንቀጥል።

ሰሞኑን አምቦ ላይ የተፈጸመውን ግድያ  ተከትሎ ወዳጆች ” ልጅ ሄኖክ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር በል እንጂ “ጠላቶች ደሞ ” አንተ ምንትስ አማራ አሁን አማራ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ መከራ የደረሰበት አምሳ ገጽ ጽፈህ ፣ ነገሩን ለውጠሕና ለጥጠህ ባቀረብከው ነበር ” የሚሉ መልዕክቶችን አስቀምጠውልኛል። እኔም እንደ ለገዳዲ ሬዲዮ ” ጦማሪዎችች ሆይ ምልእክታችሁ  ደርሶኛል ለሁሉም እንደነገሩ ለመመለስ እንሆ–”

በነገራችን ላይ አማራ ስለመሆኔ እኔ በበኩሌ እርግጠኛ አይደለሁም ፣ ቢያንስ እርግጠኛ እስክሆን ብትታገሱኝ ምን ነበረበት ( ስለ-ኔ ከኔ በተሻለ መልኩ የምታውቀው እናቴ እንኩዋ እንዲህ በሙሉ አፍዋ “አንተ አማራ!”  ብላኝ  አታውቅም። ታዲያ የምታውቀው ነገር ቢኖራትም አይደል ? አለበለዚያ ማኛና ሰርገኛ በሚል ማህበረስብ ውስጥ አድጋ እኔን በደም ስሜ መጥራት ባልዳገታት ” እስኪ ለናቴ ጊዜ እንደሰጠሁዋት እናንተም ለኔ ጊዜ ስጡኝ ” ደሞ ለዘር ፣ እድሜ ለወያኔ እንኩዋን የሰው  የንብ ሰፈር እንኩዋ በታወቀበት ዘመን የምን መንገብገብ ነው!) ።  አቦ እናት ለዘላለም ትኑር ! ቀጣዩን ሃሳብ በሚቀጥለው መስመር ላይ ያንብቡት።

መልስ አንድ:  ለሞቱት ስንገጥም

 

ሲረግጡን ታግሰን

ሲሰድቡን ታግሰን

ይሄን ሁሉ ዘመን ብሶት ተንተርሰን

ሃዘን አኮራምቶን

መላ ቅጡ ጠፍቶን

ሁሉም ግራ ሆኖ

በሃሳብ ተውጠን

ከሥጋ ስማችን

ያፈሩ ከበደን ።

 

እና አይሆንም አልን

ሕጉ ይስተካከል

ይሞረድ ይቦረሽ ባለ ጥርሱ መድብል

ድንበሬን መልሱ ክብሬን እንዳሻችሁ

ነጻነቴን ቀሙኝ ስሜን እባካችሁ።

 

አልጻፍ አልናገር

አልሰለፍ ይቅር

ባልበላም ግድ የለም ዘመን ጾሜን ባድር

አይከፋኝም ከቶ ብሰደድ በገፋ

ሃገሬ ቢቆረጥ ታሪኬ ቢጠፋ

 

አይሞቅ አይበርደንም እኛ ግድ የለንም

ሰው ቢፈናቀል ቢራቆት ቢራብም

 

ወደብ አልባ ብሆን ወይም ወኔ አልባ

እሱ አይደልም ለኔ ከቁብ የሚገባ

 

እያልኩ ልቀጥል አሰብኩና ተውኩት።  እውነት እውነት እላችሁዋለሁ ሰው እንዳይከፋው እያሰቡ ለመጻፍ ከማሰብ የበለጠ  የሚከብድ ነገር ዕኔ በበኩሌ አላጋጠመኝም። ስለ መፈናቀል ጽፈ ሳልጨርስ ስለ አፈናቃዮች መጻፍ በጣም ይከብዳል፣ ስለ ዘረኛ ስርዓት ጽፈ ሳልጨርስ ስለ ዘረኛ ተጨቁዋኝ መጻፍ አሁንም ይከብዳል። ስለ ኢትዮጵያ ተናግሬ ሳልጨርስ ስለ መንዝ ወይም ስለ ኦሮሚያ መጻፍ ይደብታል። ስለ ትግሬ አምባገነን ተናግሬ ሳልጨርስ ስለ አማራ ወይም እሮሞ ታዳጊ አምባገነን ወግኖ መናገር ይከብዳል ።  የነገሩን ውስብስብነት ተረዱልኝ። በደላቸው፣  ስቃያቸው፣ መታሰር መገደላቸው፣ ሁሉም እውነትነት አለው። ግን   ሀሳባቸው ከደረሰባቸው በደል ያንሳል ፣ ስሜታቸው ካሳለፉት መከራ አንጻር ኢምንት ( ታልኢት) ነው፣ ጉልበታቸውን የማያውቁ በትንሽ ነገር የተጠመዱ ታጋዮች ሆኑብኝ፣ ወንድሞቻቸውን የሰዉለትና የምሰዉለት አላማ ከማንነታቸው ይደቃል፣ ጉዋዶች የተሻል ጥያቄ አለ ( ፍንጭ ልስጣችሁ አይደልም ኦሮሚያ  ኢትዮጵያ የኔ ነች የሚል )።   እስኪ አንድ ወደ ሁዋላ እንመለስና እናስብ። ስናስብ ደሞ በርጋታ እናስብ።

አንድ ወደ ሁ-ዋላ

በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ክፍላተ ሃገራት እንዴት ይካለሉ እንደነበር እናስብ ( ስለ ደርግ ጠቅላይ ግዛት አሰያየም  ብዙ ማውራት አልፈልግም፣ ማወቅ የፈለገ ያንብብ )  ፣ ከዚያ ” የዘመናት ብሶት የወረሰው ጀግናው የ ትግራይ ሰራዊት ( ስሙን ቀይሮ የ ኢህአዲግ የተባለው ) አዲስ አበባ ገባና ዔርትራን ለማስገንጠል የሚመች ሕግ አወጣ፣  በዚህም ሕጉ ኤርትራን  ብ ቻ ሳትሆን የልጅነት ( የእቃቃ ፍቅረኛዬም ) ከነ ኮካ ኮላ ኮርክያችን ( ጥሪታችን) ጋ አብራ ተገነጠለች (የሚገርመው ኮርኪ ሰለሆነ ነው መሰለኝ ይዘሽ መወጣት አትችይም አልተባለችም )። በመቀጠልም 70 ምናምን  ሺ  ሰው የጨረሰውና ያስጨረሰውን   ጦርነት አካሄአዱ ( በቴዲ አፍሮ ቁዋንቁዋ ” ሁለቱ ዝሆኖች”) በኔ ቁዋንቁዋ ዘ-ለቱ  እባብስ።

ያ ጦርነት አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ ለሰራው ሥራ የማህተም ማድረቂያ ካሳ ነበር።  ከዛ የመሃል ሀገር ሰው ጨዋተው የተጀመረ መስሎት በደስታ ፓርላማ ውስጥ ጨፈረ ( አንዳንዱ ኮፍያውና ሽርጡ እስከሚወልቅ ድረስ ) እና በየቤቱ የዘሩን ቆዳ የስል ጀመር። ጀግናው የኢህአዲግ ሰራዊት ግን ልጅነት ደጎሰ ጨዋታ ፈረሰ አለ ። ድሮስ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚሀብሄር ነሳ እንዳለው እዮብ ወያኔ ሰጠ ወያኔ ነሳ ሆነ  ( ስለዚህም ይህ የዘመን ብሶተኛ  ለኤርትራ በደም ለተቀረው ሕዝብ ደሞ በቾክ  ያሰመረውን ሕግ መርገጥ ጀመረ ) እና ከተሜ እንዴት ተደርጎ አለ። እኛ ስንት ነገር ስናስብ የምን ዘሎ መቀላቀል አይነት ነገርም አንዳንዶች ሲናገሩ ሰማናቸው። አንዳንዶቹ ልጆቻቸው በበሽታና በድንቁርና ከማለቃቸው የበለጠ የልጆቻቸው አማርኛ መማር አሳሰባቸው፣ በ 2006  መሬታቸውን ከቀማቸው ይልቅ ከመቶ ዓመት በፊት ቸፍጭፎናል የሚሉትን ሚኒልክን  መውቀስ ቀለላችው፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል በሚለው ይጠደሰጡት ፣ የአንድን ግለሰብ ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱን ተቃወሙ እና በታንክ እና በ መትረይስ ከሚደበድባቸው ወያኔ ይበልጥ የቴዲ አፍሮ ዘፈን አመማቸው እና በጠራራ ጸሓይ እየተገደሉ  ወያኔ ይሙት ይላሉ ስል ” ቴዲ አፍሮ ይታሰርልን አሉ” ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ። ለዚያ ነው እየከፈሉት ያለው መስዋትነት ከያዙት ሃሳብ ይበልጣል ያልኩት ።  ነብሳቸውን አይማረውና የጎሳ ማይክሮ ባይሎጅስቱ ( መለስ )  ይህንን  ቆመው ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን ? እንደኔ እንደኔ ” አዋ ይሄኛው ባክቴሪያ ልክ እንደታሰበው ነው ሪ- አክት እያደረገ ያለው፣ ያኛው አሁንም ቢሆን ትንሽ ራይቦሶማል ትራይባል ሴንስ ኢንሰርት ሊደረግበት ያስፈልገዋል ” የሚሉ አይመስላችሁም? አይ እሳቸው ! አይ እኛ !

አንድ ወደ-ፊት 

የትግል ስያሜ ያላማ ግብር ይሆናል ማለት ዘበት ነው። ለምሳሌ ( የትግራይ ነጻ አውጪን እንመልከት)። በመጀመሪያ ትግራይ ማለት ከየት እስከየት ነው ? የመሃል ሃገሩን ትግራይ ይጨምር ነበር ? እንደዚያ ከሆነ የትግራይ ሕዝብ ሳይሆን የትግራይ ኑዋሪዎች ነጻ አውጪ ነበር መባል የነበረበት። ምክናይቱም ትግሬ ትግራይ ውስጥ ብቻ አይደልምና  የሚኖረው። ለምሳሌ የኛ ጎረቤት የነበሩት እማማ ሐዳስ ( እድሜ ለ ወያኔ የተንጣለለ ቤት ሰርተው ወደ ሳር ቤት ገቡ እንጂ ትግሬ ነበሩ። ግን ነጻ ስለመውጣታቸው እርግጠኛ አይደለሁም።

አሁንም ወደ ነገሬ ልመለስ ( ማንሽ አንቺ በዛሁ የጠፋሁ እንደሁ መልሽን )። ይሄ በተያያዘ ሃሳብ የመጥፋት ችግር አለብኝ ”

አሁንም የስያሜ ጦርነትን የሚቀድም ነገር ያለ ይመስለኛል ( እንዲሁ ሳስበው ፣ አያርገውና የኦሮሞ ሕዝብ ምናምን የሚባል ድርጅት አዲስ አበባን ” ፍንፍኔን በሸዋኛ ” ወይም ” ፊንፍኔ በኦሮምኛ” እዚህ ጋ ቶሎሳ እና ተሎሳ ብለው ሲጣሉ ስላየሁ ጥንቃቄ ቀድሜ ባረግ ብዬ ነው፣ ለማስመልስ ባደረጉት ጥረት ወያኔን ሳያስቡት ገለበጡት እንበል ( ልክ ወያኔ ሳያስበው አዲስ አበባ እንደደረሰ ) ከዛ ምን የሚሆን ይመስላችሁዋል ? እናንተ ለመመለስ ትፈሩ ይሆናል ሌኔ ግን የሞተው መለስ  በኦሮሞ ልጆች ስም; በኦሮሞ ልጆች ደም ፣ በኦሮሞ ልጆች አፈር ብቅ የሚል ይመስለኛል። ከስያሜ ማንነት ይቀድማል። ማንነታችንን ሳናስከብር ስለ ምንነታችን መናገር አንችልም ( ” መ ስፍን ወ/ማርያም እንዳሉት)።  መቼ ነው የነሱን ጨዋታ መጫወት የምናቆመው ? መቼ ?

 

ወግ

አንድ ገበሬ እጅግ የሚወደው በሬውን ሊሸጥ ገበያ ይዞ ይወጣና ሳይሸጥ  ይዞ ይመለሳል።

ዘመድ “ምነው ጃል በሬህን የሚገዛ ሰው አጣህ?”

ገበሬ ” አይ በሬዬን  ሊገዙ ከመጡት ሰዎች መሃል አንዳቸውም  ለበሬው የሚሆን ድርቆሽ ( መኖ ወይም ሳር ) አልነበራቸውም፣ ስለዚህ በሬየን ሽጬ በረሀብ ከምገልው ብዬ ነው ሳልሽጥ  ይዤው የተመለስኩ ”

እኔም እንዲህ ነው የሚታየኝ።  ወያኔ መውደቅ ስላለበት ተብሎ በሬዬን በርሃብ ለሚገል ገበያተኛ ነጻነቴን አልሸጥም። እንሱም (ወያኔዎችም) ቢሆን  ሲጠነሰሱ እርሾዋቸው ዘረኝነት ነበረና። በሬዬን ልተገዛ ከፈለክ መጀመሪያ ሳር ይኑርህ ፣ መጀመሪያ የሚገዛ ሃሳብ ይኑርህ፣ መጀመሪያ ስለ በሬ እወቅ።  አስራ ስምንት ሚሊዮን ጭቁን፣  አስራ ስድስት ሚሊዮን ጭቁን ቢጠላ ጥላቻው  ወተት አይወጣውም እሱንም የሚጠላውንም  ይዞ ይጠፋል እንጂ።  ብሬ መግዛቱ አይደልም ቁም ነገሩ ፣ ቁም ነገሩ እስክታርደው ድረስም በሬነቱን መገንዘብ ነው።

ገበያ ወጥቶ ሸማች መሆን አይደለም ቁም ነገሩ፣ ቀም ነገሩ ቢያንስ የሸማች ባህሪ ይዞ መገኘት ነው።

በአንድነት ለመቆም አንድ አይነት አመለካከት የግድ ሊኖር ይገባል በሚለው ሃሳብ ብስማማም በይበልጥ የሚያስማማኝ አንድ አይነት አላማ ሊኖር ይገባል የሚለው ነው።

እስከሚገባኝ የታጋይ ሃሳብ የጨቆኑትን ከማሸነፍ፣ የገደሉትን ከማንበርከክ፣ የበደሉትን ከመበደልም የራቀና የላቀ መሆን አለበት ብዬ አስባለው። በታጋይና በበቀልተኛ መሃከል ያለው ልዩነት ይሄም ይመስለኛል። ታጋይ አንድን ስርዓት ሲቃወም ወይም ሲታገል፣ ስርዓቱ ማድረግ የነበረበት ግን ያላደረገውን ነገር ለመለወጥ ይመስለኛል፣ አንድ ታጋይ አንድን ስርዓት ለመለወጥ ሲነሳ ፣ ኢ-ፍትሃውነትንም ሆነ የአስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እውቀቱና ብቃቱ እንዳለው አምኖ ያ እውቀቱና ብቃቱ ስልጣን ላይ ባለው ስራዓት ( ስርዓቱ በሚፈቅደው መንገድ ታግሎ ) እውቅናን ሲነፈግ ፣ ያ የሚያልመውን ለውጥ ለማምጣት እምቢ ያለ አካል ነው ብዬም አስባለሁ። በቀልተኛ ግን የድሮ ቁስሉንና ብሶቱን ከማሰብ እና ብድሩን እንዴት እንደሚመልስ ከማውተንተን ያለፈ ሕልም የለውም፣ ለሱ የሥርዓት ለውጥ ማለት የበደሉትን ( ወይም በድለውኛል በሎ የሚያምነውን) ማህበረሰብ መበደል ነው፣ ለሱ ትግል ቂሙን የሚወጣበት ፣ እልሁንና ቁጭቱን የሚገልጽበት አጋጣሚ መፈለግ ነው። ወያኔ የተፈጠረው በዚህ መንገድ ነው፣ ሌላውም በዚህ መንገድ መሄድ ይፈልጋል ፣ እንደ ዜጋ የተሻለ ሃሳብ ከሌለህ፣ ከቂመኛነት ወደ ታጋይነት፣ ከባለ አረርንት ወደ ባለ ር-አይነት መለወጥ ካልቻልክ በሬየን አልሸጥም።

ቸር ይግጠመን

 

 

 

* ገጣሚው

 

ድምጻችንን ሰጥተን ውሳኔውን ለመቀበል ዠግጁ ነን?

$
0
0

debereselam-medhanialemየሚኒሶታ ደብረሰላም መድሐኒአለም ቤተክርስቲያን አንድ ምራፍ ጨርሶ ወደ ሁለተኛው ሊዞር በ ጣት በሚቆጠሩ ቀኖቶችብቻ ነው የቀረው። አንደኛው ምን ምን አስመዝግቦ አለፈ ቀጣዩስ ምን ምን ይዞ ይመጣል ብሎ ማሰላሰል ካለፈው እንድንማር ለወደፊቱ እንድንሰናዳ የጠቅማል። ታዲያ ባለፉት ሁለት አመታት በየምክንያቱ ሁለትና ከሁለት በላይ ሆነን  በተገናኘንበት ስፍራዎች ሁሉ ከምንወያይባቸው አርስቶች አነዱና ዋንኛው የቤተክርስቲየናችን ጉዳይ ነበር ።-[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]

“የኢትዮጵያ የብሔሮች ጥያቄና መፍትሔዉ” እስክንድር ነጋ(ከቃሊቲ እስር ቤት)

$
0
0

 

እስክንድር ነጋ

እስክንድር ነጋ

የዲሞክራሲያዊ መብቶች ጋር ተያይዞ፣ የብሔረሰቦች የእኩልነት መብት በቃልና በፕሮግራም ብቻ ሳይሆን፣ በግብር መታወቅ አለበት፡፡ የእያንዳንዱም ብሔረሰብ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖትና ሌሎችም መለያዎች በእኩልነት መታወቅና መከበር አለባቸዉ፡፡ ብሔሮች ሁሉ ትልቅም ሆነ ትንሽ የራሳቸዉን የወደፊት ዕድል የመወሰን መብት መታወቅና በትክክል ከስራ ላይ መዋል አለበት፡፡ ብሔሮች ቋንቋቸዉንና ጠቃሚ የሆኑትን ባህሎቻቸዉን በነፃ እንዲያዳብሩ መደረግ አለበት፡፡ ማንም ሰዉ በዉስጥ አስተዳደራቸዉ ላይ ጨቋኝ ተፅዕኖ እንዳያደርግ መከላከል አለበት፡፡ ኢትዮጵያን ከብሔሮች እስር ቤትነት ወደ ብሔሮች ማበቢያ ሥፍራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይቻላልም፡፡ የሕዝቦች አንድነት፣ በሳንጃና በመድፍ በተቋቋመዉ አንድነት ፋንታ፣ በመግባባትና በመፈቃቀድ ላይ ሊመሠረትና እንደአለት ጸንቶ ሊኖር የሚችለዉ በዚህ መንገድ ብቻ ነዉ፡፡ በንጉሱ እና በደርግ ጊዜ የብሔርን ጥያቄ አንግበዉ የተነሱ አካላት ሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ(ሻቢያ)፣ ሕወሓት እና ኦነግ ነበሩ፡፡ በአሁን ግዜ ግን ነፃ አዉጭ ብሔር የሌለዉ የደቡብ ክልል ብቻ ነዉ ይህም ሊሆን የቻለዉ እንደሚመስለኝ የጎሳዎች ብዛት እና የመልክአምድራዊ አቀማመጥ ብሎ ነግሮኛል፡፡ አምባገነን ባለበት አገር ላይ የብሔር ጥያቄ የሚያነሱ አካላት እየበዙ እንጅ እያነሱ አይሄዱም፡፡ እንደ ምሳሌ ታላቋን ሩስያ ማንሳት በቂ ነዉ፡፡ በእስታሊን አምባገነንነት ምክንያት አብዛኞቹ አገሮች ለመገንጠል ምክንያት ሆናቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የዩጎዝላቪያ፣ የራሽያ እና የሶማሊያ እጣ ፋንታ ሳያጋጥማት እኛ ቀድመን ልናድናት ይገባል፡፡ ይሄም ሊሆን የሚችለዉ በአንድ እና አንድ መንገድ ብቻ ነዉ፡፡ እሱም በሰላማዊ ትግል ወያኔን ስናስወግድ ብቻ፡፡ከዛም ስራዉ የኛ የጋዜጠኞች እና የፖለቲከኞች ይሆናል፡፡ የብሔር ፖለቲካ የበሰበሰ እና ያለፈበት መሆኑን ምርጫ 1997 አስተምሮን አልፏል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ኤርትራ እንዳትገነጠል የበኩልን ድርሻ ቢወጣም በወያኔ እንቢተኝነት በ1984 ዓ.ም ምህረት ህዝቡን አሰሩ፣ ገደሉ አቆሰሉ፡፡ ይህም አልበቃ ብሏቸዉ የኤርትራ ህዝብን በምርጫ በማወናበድ ምርጫቸዉን አሳኩ፡፡ በየት አገር ነዉ ባርነት ወይስ ነፃነት የሚል ምርጫ የተካሄደባት አገር አለች፡፡የኤርትራ ህዝብ ግን የጣሊያን እና የእንግሊዝ አስተዳደር አሻፈረኝ ብሎ ወደ እናት አገራቸዉ ለመመለስ የበኩላቸዉን ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የታሪክ ድርሳናቶች ይናገራሉ፡፡ ሁለት ኤርትራዊያን ግለሰቦችን ማንሳት ያዉም በቂ ነዉ ዘርዐይ ደረስ ጣሊያኖች በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ሲቀልዱ በመበሳጨት ጣሊያኖች ላይ ጉዳት አድርሷል፤ አብርሃም ደቦጭ በግራዚያኒ ላይ ቦምብ በመወርወር የመግደል ሙከራ ያደረገ እና ያቆሰለ፡፡ህዝቡም ሲጠይቅ የነበረዉ ኢትዮጵያዊነት ነዉ፡፡ይህንንም አሳክተዉ ከ60 ዓመታት በኋላ ተመልሰዋል፡፡ ለዚህ ሁሉ መሳካትም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስተር የነበሩት የአክሊሉ ሀብተወልድ ድርሻ ላቅ ያለ ነበር፡፡


“ኢትዮጵያ ወይም ሞት” በማለት በሀገር ፍቅር ማህበር ስር የተሰለፉ ሀገር ወዳድ ኋይሎች ህዝቡን በማስተባበር በነቂስ ወጥቶ የኤርትራን ግዛቶች ሲያጥለቀልቅ እንደነበርም ይታወሳል፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር አብረዉ ለመኖር የሚፈልጉ ህዝቦች ነበሩ፡፡ ሁሉም የኤርትራ ህዝብ ለመገንጠል ከሻቢያና ከወያኔ ጋር አብረዉ ቁመዋል ማለት ከእዉነት የራቀ ነዉ፡፡ የኤርትራ መገንጠል ለአስገንጣኞች አካላት ብቻ ነዉ የጠቀመዉ፡፡ ኤርትራ በመገንጠሏ የኤርትራ ህዝብ ምን አገኘ? የኢትዮጵያ ህዝብስ ምን አገኘ? አሁንም የኤርትራ ህዝብ በጭቆና፣ በርሀብ፣ በስደት እና በበሽታ እያለቀ ነዉ፡፡ መገንጠል እንደማያዋጣ የኛዉ ኤርትራ አስተምራናለች፡፡
እስክንድር ነጋ የሚፈልገዉ እኩልነትና ነፃነት የሠፈነበት፣ የህዝቦቿ አንድነት ከብረት የጠነከረባትና ብሔረሰቦች ሁሉ ያበቡባት፣ የማንም ተመፅዋች ያልሆነ በራሱ የሚተማመን በማንም ፊት የባታችነት ስሜት ሊኖረዉ የሚችል ህዝብ እንዲይፈጠር ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል የፈጀዉን ጊዜ ቢፈጅምና የፈለገዉን ያህል መሥዋዕትነት ቢጠይቅም፣ ብዙ ችግሮችና መሰናክሎችን ከፊታችን ቢደቀኑም፤ የዚች ዓይነት ኢትዮጵያ እንድትመሰረት እስከ መጨረሻዉ ለመታገል ቆርጨ ተነስቻለዉ፡፡ የእናት አገራችን ህልዉና ላያስጠብቅ የሚችለዉ ለ22 ዓመታት ፈላጭ ቆራጭ ጫማ ስር የተረገጠችበት ብሔራዊ ነፃነቿን ክብሯ ተገፍፎ የቆየችበት ዓመታት ነዉ፡፡ በሁሉም ወገን የሚደረገዉ መሯሯጥና መሰናዶ ሲታይ አበረታታች ነዉ፡፡ ወሳኝ የሆነዉ ፍልሚያ ገና ከፊታችን እንደሚጠብቀን ምንም ጥርጥር ሊኖረዉ አይችልም፡፡
የግንቦት 7 መስራች እና መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በሚመለከት ከግብፅ መንግስት እርዳታ ተቀብሏል ተብሎ ወሬ እየተናፈሰ መሆን ስጠይቀዉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ብርሃኑ የሚያደርገዉ አይመስለኝም ካደረገዉ ግን በጣም አዝኘበታለዉ፡፡ ለምንድን ነዉ አባቶቻችን የሰሩትን ስህተት የምንደግመዉ፡፡ መኢሶን፣ ኢህአፓ፣ ጀብዐ እና ወያኔ በአንድ ይሁን በሌላ መልኩ የዉጭ እርዳታን እየተቀበለዉ፡፡ አገራችን እና ህዝቧን ጎርቷል፡፡ ኤርትራን እንድናጣ ሁነናል፡፡ አሁንም መናገር የምፈልገዉ ኢህአዴግን እና ኢትዮጵያን ለይተን ማዬት አለብን፡፡ ኢህአዴግን የጎዱ እየመሰላቸዉ አገራችንን እያደሟት ነዉ፡፡
ለተቃወሚ ፓርቲዎች እችን መልዕክት አስተላልፏል፡፡
1.የዉጭ ኋይሎች ድጋፍ የዚችን ኩሩና ታሪካዊ አገራችንን ብሔራዊ ክብርና ነፃነት የማይነካ፣ ራስን ለመቻል የምታደርገዉን ጥረት የሚያግዝ እንጅ የማያደናቅፍ እርዳታ መሆን አለበት፡፡
2. ማንኛዉም ህዝብ በዉጭ እርዳታ ላይ በመተማመን አብዮቱን ከግብ ለማደረስ እችላለሁ ብሎ ካሰበ ራሱን ማታለሉ ብቻ ሳይሆን አብዮቱንም ብሔራዊ ነፃነቱን ያጣል፡፡ ማንም ህዝብ በተለይም ደግሞ እንደኢትዮጵያ ሕዝቡ ኩሩና ባለታሪክ ሕዝብ ከሆነ ለገዛ ነፃነቱ፣ ለገዛ ለዉጡ ለገዛ ክብሩ ከሁሉም በፊት መተማመን ያለበት በራሱ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ስለሆነም የዉጭ እርዳታን በሚመለከት በኩል ብሔራዊ ክብርና ነፃነት እንደዚሁም ከሁሉ በፊት በራስ መተማመን የሚለዉ ዋናዉ መመሪያችን ይሆኑ፡፡
እስክንድር ነጋ
ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ጊዜያቸዉን ማባከን የለባቸዉም የሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲ የሰላማዊ ትግል መንገድ መቀላቀል አለባቸዉ፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲ “ሰላማዊ ትግሉን(አብዮቱን) እኛ ካልመራነዉ አብዮት አይሆንም” ከሚል አመለካከት መጀመሪያ መላቀቅ አለባቸዉ፡፡ትግሉን ማንም ይምራዉ ማን ሕዝቡ ለትክክለኛዉ የስልጣን ባለቤት መሆን አለበት፡፡ ዛሬ የሚወነጃጀሉት ኢህአፓ፣ መኢሶን፣ ማሌሪድ፣ ሰደድ፣ ወዝ ሊግ፣ ሻዕቢያ፣ ህወሓት ይህን የህዝብ መብት ረግጠዉ እና አፍነዉ በህዝቡ ቦታና ጥያቄ እራሳቸዉን መተካታቸዉ ሲሆን ዋና የህዝቡን የበመደል መነሻ ምክንያት ይህ ነዉ፡፡ በመሆኑም በአንዳንድ ታዳጊ አገሮች ዉስጥ ሕዝቡን በዙሪያቸዉ አጠቃለዉ ለማሰለፍ አይነት ተግባራዊነት ታላላቅ ሰዎችን የመሰሉ እንኳን ለማፍራት አልቻለችም፡፡ ከዚህ አኳያ ጋንዲን ያፈራች ህንድ፣ ማኦን ያፈራች ቻይና፣ ማንዴላን ያፈራች ደቡብ አፍሪካ እና ፓትርስ ሉሙባን ያፈራች ኮንጎ ጋር ሀገራችን በአቻ አትታይም፡፡ እነዚህ ታላላቅ ሰዎች ከሀገራቸዉ አልፈዉ የአለም ሰዎች ሁነዉ ኑረዋል፡፡እየኖሩም ነዉ፡፡ እንዲያዉም ኢትዮጵያ ዛሬ የጎደላት ነገር ቢኖር እኒህን የመሰሉ ቅን ሰዎችን ማግኘት ነዉ፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንኳን የብሔረሰቦችን የአመለካከት ድንበር አቋርጦ በማለፍ የህዝቦቷን አመኔታ ሊያገኝ የቻለ የፖለቲካ ሰዉ መፍጠር ቀርቶ ለተወለደበት ብሔረሰብ ለመቆም የቻለ ሀቀኛ የህዝብ ሰዉ መፍጠር አልተቻለም፡፡
በመጨረሻም እስክንድር ልብን በሚማርክ ሁኔታ ስለ ኢትዮጵያ እናት እና አባቶቻችን ለብዙ ዓመታት ታግለዉና ተዋግተዉ ነፃነታቸዉን ያወጁት፡፡ ስለዚህ ይህ ትዉልድ ጭቆናና ግፍ በቃኝ ብሎ የራሱን መሪዎች ገርስሶ መጣል አለበት፡፡
“እኔ ለዲሞክራሲ ስል ታሰርኩ እንጅ ሌላ ምን ሆንኩኝ ለነፃነት የምከፍለዉ መስዋዕትነት እስከ ሞት ድረስ ነዉ”
እስክንድር ነጋ
“እኔ ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለኝም የምታሰርባት፣ የምገረፍላት፣ የማለቅስላት፣………. በቃ በአጭሩ እኔ የምሞተዉ በአገሬ በኢትዮጵያ መሬት ነዉ፡፡ ነፍሴም የምታልፈዉ ሥጋዬም የሚፈርሰዉ በምወዳት አገሬ ኢትዮጵያ ነዉ”
እስክንድር ነጋ
“ብሔሮች በጋራና በሰላም ለመኖር ዘላለማዊ ዋስትናቸዉ ደግሞ ዲሞክራሲያ መንግስት ነዉ”
እስክንድር ነጋ
ጠያቂዎቹ እየበረከቱ ሲመጣ ቻዉ ተባብለን ተለያየን በሌላ ቀን እነዚህን አይጠገቤ ወሬዎችህን እንደምትደግምልኝ ተስፋ አረጋለዉ፡፡
አምላክ ከአንተ ጋር ይሁን ብዬ ወጣዉ፡፡
ከእስክንድር ዐይን ርቄ በሄድኩኝ ቁጥር ሆድ ባሰኝ አቅም አነሰኝ ይህን ንፁህ ሰዉ ማሰር ምን ይሉታል፡፡
በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ሳሞራ የኑስ…………… ተዉ ፍቱ ይህን ጀግና፡፡
ተዉ ተዉ ተዉ………… ከሆስኑ ሙባረክ፣ ከጋዳፊ ተማሩ፡፡
ቅዳሜ ጧት 3፡00-3፡30(ከቃሊቲ እስር ቤት)
አብዲሳ አጋ(ገሞራዉ)

ብአዴን ማን ነው (ከገብረመድህን አርአያ )

$
0
0

የአንድን ድርጅት ማንነቱን ከማቅረብ በፊት ቀደም ብሎ የተፈጸመውን ስህተት፣ ቀጥሎም ኢህአፓን ለማጥፋት በህወሓት እና በሻእቢያ የደረሰበትን ጥቃት አጠር ባለ መልኩ ማቅረብ አስፈላጊ ይሆናል።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በድር ድርጅታችን ወደ የት እያመራ ነው? (ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን)

$
0
0

በግንቦት ወር የተከሰቱ 11 ታሪካዊ ሁነቶች

$
0
0

Meles zenawi

ከአቤኔዘር ይስሃቅ

1. ግንቦት 1, 1947 ዓ.ም ሀገራቸውን ከድተው ለጣሊያን በባንዳነት ሲያገለግሉ የነበሩት የአስረስ ተሰማ የልጅ ልጅ የነበረው የቀድሞው አምባ-ገነኑ፣ ከፋፋዩና ጎጠኛው መሪ ለገሰ/መለስ/ ዜናዊ የተወለደበት ቀን።

2. ግንቦት 8, 1981 ዓ.ም የሀገሪቱ ጄኔራሎች በመንግስቱ ሀይለማሪያም ላይ የመፍንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉበት ቀን።

3. ግንቦት 8, 1982 ዓ.ም በመንግስቱ ኃይለማሪያም ላይ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉት ጄኔራሎች የተረሽኑበት ቀን።

4. ግንቦት 13, 1983 ዓ.ም አምባ-ገነኑ፣ ሰው በላውና ጨፍጫፊው መንግስቱ ኃይለማሪያም ሀገሪቱን ጥሎ ወደ ዚምባቡዌ የፈረጠጠበት ቀን።

5. ግንቦት 16, 1983 ዓ.ም ሻዕቢያ የኢትዮዽያ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የነበረችውን አሥመራን የተቆጣጠረበት ቀን።

6. ግንቦት 20, 1983 ዓ.ም አምባ-ገነኑ ኢህአዴግ የቀድሞውን አምባ-ገነን ደርግን የተካበት ቀን።

7. ግንቦት 4, 1990 ዓ.ም ሻዕቢያ ኢትዮጵያን የወረረበት ቀን።

8. ግንቦት 7, 1997 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በነቂስ ወጥቶ በምርጫ የራሱን መሪዎች የመረጠበት ቀን። /በኋላ ኢህአዴግ ቢያጭበርብረንም/

9. ግንቦት 7, 1997 ዓ.ም ማታ ላይ መለስ የራሱን ሕገ-መንግስት ጥሶ ከግንቦት 8, 1997 ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት ከቤት ውጪ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ መከልከሉን ያወጀበት ቀን። ከ8 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ከመለስ ሞት በኋላ በመለስ የታወጀው ሕገ-ወጥ ክልከላ እንዲሻር ማድረጉ ይታወቃል።

10. ግንቦት 8, 1997 ዓ.ም በሀገሪቱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የምርጫ ቆጠራው ሳይጠናቀቅና ምርጫ ቦርድም ምንም አይነት መግለጫ ከመስጠቱ በፊት ኢህአዴግ ከአዲስ አበባ በቀር በሁሉም የሀገሪቱ ክልል ምርጫውን ማሸነፉን በጉልበት ያወጀበት ቀን።

11. ግንቦት 10, 2004 ዓ.ም አበበ ገላው በአሜሪካ የመለስን ቀልብ የገፈፈበትና መለስም በአደባባይ ሲደነግጥ የታየበት ቀን። ከድንጋጤው ሳያገግም ከዚያ በፊት የነበረበት ህመም ተባብሶበት ከ2 ወር በኋላ በዚያው ሞተ። የተረሳ ካለ ጨምሩበት።

ምናባዊ ቃለምልልስ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር

$
0
0

meles zenawi
ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ው/ልደታቸውን አስመልክቶ የተደረገ ምናባዊ ቃለ ምልልስ

ልማጠኛ (ልማታዊ ጋዜጠኛ)፡-
እሺ በቅድሚያ ጊዜዎን ሰውተው ስለውልደትዎ ለማውጋት እዚህ ያለሁበት ምናባዊ ስቱዲዎ ድረስ በመንፈስ ስለተገኙልኝ በፌስቡክና በመላው የሽሙጥ ማህበረሰብ ስም ለማመስገን እወዳለሁ፡፡ እስቲ ያሉበትን ሁኔታ በአጭሩ ቢያስረዱ፡፡

መለስ፡-
ያለሁበት ሁኔታ ግልጽ ነው፡፡ በምድር ሳለሁ ለሰራሁት ስራ ጥሩም ሆነ መጥፎ ሂሳቤን በሙሉ ኦዲት እያደረኩ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እዚህ እያንዳንዷ ነገር ሁሉ የራሷ አካውንት አላት፡፡ ያው ባላንሴ ዴቢት እና ላያቢሊቲ ብቻ ሆኖብኝ መጨነቄን ልትገምት ትችላለህ፡፡ ብዙ አታስገባኝ ወደሱ፡፡

ልማጠኛ፡-
እሺ ይተዉት እሱን፡፡ ዛሬ የልደትዎ ቀን ነው፡፡ በእርስዎ መወለድ ዓለም ምን ተጠቅማለች ብለው ያስባሉ፡፡ ምንስ ጉዳት ተከስቷል?

መለስ፡-
ዌል እንግዲህ በእኔ መወለድ ብዙ ጥቅም እና ጥቂት ጉዳቶች መከሰታቸውን በመረጃ ብቻ ሳይሆን በማስረጃም ጭምር ማሳየት እችላለሁ፡፡ ግን አንተ ማወቅ የፈለግከው ከልጅነቴ ጀምሮ የነበረውን ነው ወይስ ስልጣን ላይ በአሚር ሙጫ ከተጣበቅኩ በኋላ ያለውን ጊዜ ብቻ ነው?

ልማጠኛ፡-
የወጣትነትዎና የትግሉን ዘመን ለጊዜው ይተዉት፡፡ ብዙም የሚያወያይ ነገር ላይኖረው ይችላል፡፡ በይበልጥ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ጊዜዎትን ነው ማወቅ የፈለግኩት፡፡

መለስ፡-
ይሁንልህ፡፡ እኔ ተወልጄና አድጌ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆንኩ ጀምሮ በርካታ ጥቅሞች ተገኝተዋል፡፡ ለምሳሌ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከዋልኩት ውለታዎች አንዱ በቀን ሶስት ጊዜ መብላት የሚባለውን ነገር በወሬ ደረጃ ማስተዋወቄ ነው፡፡ እምልህ… ተግባር ሌላ ነገር ነው፡፡ ግን እውን ባይሆንም እንኳ ሶስቴ የመብላትን ተስፋ ለድሆች መስጠት ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ሶስት ቀን ባይችሉ እንኳ በሶስት ቀን አንዴ መብላት ላይከብዳቸው ይችላል፡፡ ኢንፋክት ከእኔ ጠቅላይነት በኋላ በአንድ ጊዜ ከ5 ሚሊየን ሰው በላይ ሲራብ አልታየም፡፡ ሁሌም ከ5 ሚሊየን እስከ 4 ሚሊየን 999 ሺ 999 ሰው ብቻ ነው ሲራብ የነበረው፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ እኔ ለፍቼና ላቤን አንጠፍጥፌ፣ ድንቅ የሚባል የኢኮኖሚ እውቀቴን በመጠቀም እንዲከሰት ባደረግኩት የኑሮ ሁኔታ የሰዎች የምግብ አምሮት እንዲጨምር አድርጌያለሁ፡፡ አፒታይት ማለቴ ነው፡፡ ዱሮኮ ስጋ በሳምንት ሶስቴ ወይ ሁለቴ ይበላ ነበር፡፡ ማንም አይናፍቀውም፡፡ አሁን ግን የፍቅር ዘፈን ተዘፍኖለት ‹‹ቁርጤ ቁርጠቴ›› ተዘምሮለት ነው የሚገኘው፤ በክብር.. ለዚያውም ደሞዝ ተጠብቆ! ህዝብ ይንቃቸው የነበሩት ጣፊያና አንጀት እንኳ ዛሬ አዲሳባ ላይ መበላት መጀመራቸው የኔ ውለታ ነው፡፡ ሸኾና ራሱ በእነሱ ቀንቶ ‹‹እኔስ መቼ ነው የምብበላው?›› የሚል ንቅናቄ ሊጀምር መሆኑን ሰምቻለሁ፡፡

ልማጠኛ፡-
ለጊዜው አገሪቱ ውስጥ ያለው ህጋዊ ንቅናቄ የ‹‹ቐ›› ንቅናቄም ብቻ ነው ክቡርነትዎ፡፡ ለማንኛውም ይቀጥሉ እስቲ!

መለስ፡-
መልካም፡፡ እንደውም የስጋ ነገር ሲነሳ በግ ትዝ አለኝ፡፡ ዱሮ ትዝ ይልሀል በየሰፈሩ በአምስት ብር በሚቆረጥ ሎተሪ በግ እንደሽልማት ይደርስ ነበር፡፡ እንደውም ትዝ ይለኛል ገና ምኒሊክ ቤተ መንግስት እንደገባን አንዱ የበግ ሎተሪ ሲያዞር አዜብ አግኝታው የእኔ 6ሺ ብር ደሞዝ እስኪደርስ ከጓደኞቿ ተበድራ ገዝታ ነበር አልደረሳትም እንጂ፡፡ እሱን የበግ ሎተሪ ደርግ ነው ያስጀመረው ታውቅ ከሆነ፡፡ ያው ደርግ በበግ ሎተሪ አስጀመረ… እኔ ደግሞ በኢኮኖሚ ፖሊሲዬ በበዓል እንኳ የሚታረደውን በግ ሎተሪ አደረግኩት፡፡ አሁንኮ በግ ገዝቶ ማረድ ሎተሪ እንደማሸነፍ ሆኗል አሉ፡፡ በግ ተገዝቶ ሲገባ ሰፈር ውስጥ እንደሙሽራ ተጨብጭቦለት የሚገባ መሆኑን ሰምቻለሁ፡፡ በዚህ ታዲያ ሌላው ቢቀር የበግ መብት ተቆርቋሪዎች ሁሉ ሳይደሰቱ ይቀራሉ ብለህ ነው? እንግዲህ የኔ ሌጋሲ ነው ይሄ!

ስኳርስ ቢሆን! ከእኔ በፊት የተናቀና በየወረቀቱ ተጠቅልሎ የሚሸጥ ‹‹ርካሽ›› ነገር አልነበረም እንዴ? ታምራት ላይኔ እንኳ ገና እንደገባን ስንቴ ሲልሰው ነበር! ዘይትም ቢሆን ያምስት አምስት ነበር ዱሮ፡፡ ዛሬ እቴ … እኔ ልመስገን እንጂ ስኳርና ዘይት ትንሽ ጠፋ ካለ ለትዳር ሽማግሌ እንደሚላከው ለቀበሌ ካድሬ አማላጅ ተልኮ ተለምኖ ነው በክብር በሰልፍ ቀብረር ብሎ የሚመጣው፡፡ አንዳንዱ እንደውም እንደዱሮው ትዳር ጠለፋ ምናምን ሁላ ይሞካክር ነበር፡፡

ልማጠኛ፡-
ክቡር ጠቅላይ… እስቲ ምግቡን ይተዉት ለጊዜው፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ፡፡ ዜርፎር ስጋ ራሱ ከበላሁ ትንሽ ቆይቻለሁ፡፡ በጎመን ብዛት ቬጂቴሪያን ከሆንን ቆየን፡፡ አምሮቴን ከሚቀሰቅሱ ወደሌሎች ውለታዎችዎ ብናልፍ፡፡

መለስ፡-
ኦኬ! ከዩኒቨርሲቲ ሳንርቅ እንይ፡፡ ኮብልስቶን በማን ዘመን ነው ክብር ያገኘችው? ማንንም ጠይቅ! ወላ አውሮፓ ወላ አሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ቀመስ ባልሆኑ ሰዎች እጅ ስንት ዘመን ቅኝ ተገዝታለች? እኔ አይደለሁም እንዴ በዩኒቨርሲቲ ምሩቃን እጅ ማእረግ አግኝታ እንድትስሰራ ያደረኳት? ‹‹የተማረ ይፍለጠኝ›› ብላ የተረተችው የኮብልስተን ንግስት ለዚህ ምስክር መሆን ትችላለች፡፡

ሌላው ደግሞ ዱሮ ኤለመንታሪ ትምህርት ቤት በመደዳ ግርፊያ የሚባል ትዝታ ነበረን፡፡ ሰክሮ የመጣ አስተማሪ ረበሻችሁ ብሎ በመደዳ ይገርፍ ነበር ተማሪውን፡፡ ያ የተማሪዎች ቋሚና የሚናፈቅ ትዝታ ሆኖ አልፎ ነበር፡፡ ያንን ትዝታ ለናፈቃቸው ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፓዮኔርነት አስተዋውቄያለሁ፡፡ አንድ ተቃውሞ ሲያነሱ ፌደራል ገብቶ በመደዳ የቀጠቀጣቸው በእኔ ዘመን ብቻ ነው፡፡ በዚህም የዱሮ ትዝታቸውን የማመንዠግ እድል አግኝተዋል፡፡ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎችም የናፈቃቸውንና በፊልም ብቻ ይሰሙት የነበረውን የጥይት ድምጽ እንዲሰሙ አድርገናል፡፡ ቀላል ነው እንዴ ይሄ? እነሱምኮ ትንሽ አክሽን ትሪለር ምናምን ነገር ያስፈልጋቸዋል! ይኸው በቅርቡ እንኳ በአምቦና በሌሎችም ከተሞች የኦሮሚያ ከተሞች ተማሪዎችን የዚህ በረከት ተቋዳሽ ማድረግ የተቻለው በእኔ ሌጋሲ ነው፡፡ ስንቱ ተቀነጨለ በግርግር፡፡

ልማጠኛ፡-
እስቲ አሁን ደግሞ ወደተቋማት ይምጡልኝ፡፡ ተቋማት በእርስዎ ዘመን ምን ተጠቅመዋል ብለው ያስባሉ?

መለስ፡-
ብዙ ተጠቅመዋል፡፡ ለምሳሌ ማረሚያ ቤት ተቋምን ውሰድ፡፡ ወላ ቃሊቲ ወላ ቅሊንጦ ዱሮ ከሞላ ጎደል የወንጀለኞች ቦታ ነበር፡፡ አሁን ግን ለቦታው መሰጠት ከሚገባው ክብር አንጻር ምርጥ ምርጥ የሚባሉ ሰዎችን ከየአቅጣጫው በመምረጥ እንዲታሰሩበት አድርገናል፡፡ ዛሬኮ እስር ቤት ያልገባ የለም፡፡ እንደውም ‹‹የጀግና ቤቱ እስር ቤት ነው›› የሚል ተረት ሁላ ተጀምሯል ሰምተህ ከሆነ፡፡ እስር ቤት በቅርብ ታሪካችን እንዲህ አይነት ክብር አግኝቶ አያውቅም፡፡ ወላ ፖለቲከኛ፣ ወላ ተቃዋሚ ፓርቲ፣ ወላ ጋዜጠኛ፣ ወላ የሃይማኖት አባቶች የት ነው ያሉት ዛሬ? እስር ቤት አይደለም እንዴ? ኦፍኮርስ! ሌላው ቀርቶ በርካታ ባለስልጣናት እንኳ እየገቡ ነው በስኳር ጦስ፡፡

ደግሞ እስር ቤት ብቻ አይምሰልህ ክብር ያገኘው፡፡ አግአዚ ክፍለ ጦርስ ቢሆን አልተከበረም እንዴ? ዱሮ ማን ያውቀው ነበር? እኔ ነኝ ከወደቀበት አንስቼ በሺዎች በሚቆጠሩ እናቶችና አባቶች አፍ ያስገባሁት፡፡ በእርግማን መሆኑን አትይ ዋናው መነሳቱና ዝናው መናኘቱ ነው፡፡ ዱሮ ክፍለጦሩ ጥይት እንኳ የሚተኩሰው ልምምድ ላይ ብቻ ነበር፡፡ አሁን ግን ክብር ተሰጥቶት የትም ቦታ ተቃውሞ ላይ ቀይ ኮፍያውን ለብሶ ከች ይላል፡፡ ‹‹ተኩስ!›› ሲባል ብቻ በስናይፐር መቀንደብ ነው! ‹‹ቋ! ጧ! ጯ!›› ያረጋል እያነጣጠረ! ህጻን መምረጥ የለ አዋቂ! ይህን የመሰለ ዝና ታዲያ ከየት ነው የሚመጣው? አንድን ተራ ክፍለጦር ከሂትለር የ‹‹ፖግሮም›› ፖሊስ እኩል ዝና ማቀዳጀት ቀላል ነው እንዴ?

ለማእከላዊ ምርመራ ጣቢያም ሆነ የአገር ፍቅር ለሚለበልባቸው ገራፊዎቹ የዋልኩት ውለታም የሚረሳ አይደለም፡፡ በደርግ ዘመንኮ ገራፊዎች በግልጽ ስለሚገርፉ ብዙ ወቀሳ ይደርስባቸው ነበር፡፡ በእኔ ዘመን ግን ህጋዊ ሽፋንና ጠለላ አግኝተዋል፡፡ የጸረ ሽብር ህጉ ተመቻችቶላቸዋል፡፡ የግርፋት ጊዜያቸው አጭር ነበር በፊት፡፡ እኔ ነኝ ከብዙ ጥረት በኋላ በፍርድ ቤት ፈቃድ ለ4 ወራት ያክል በነጻነት መግረፍ እንዲችሉ ያመቻቸሁት፡፡ ትቢተኛ ዳኞችን እንኳ እኔ ነኝ ‹‹እንዳላየ ሆናችሁ እለፏቸው፤ ተባበሯቸው፤ ህጋዊ ሂደቱን አሳልጡላቸው›› ብዬ አስጠንቅቄ ቀና ብለው እንዳያዩዋቸው ያደረኩት፡፡ ማንም ተራ ዳኛኮ የማእከላዊ ገራፊን እንደዱሮው ሊናገረው አይችልም፡፡ መገልመጥ ቀርቶ በዓይኑ ቂጥ ሊያየው አይችልም፡፡ ተቋማዊ መከባበሩ ሰፍኗል፡፡ በዚህ ምን ያክል እንደሚደሰቱ ገምት፡፡ ተቋማዊ ነጻነት ያለውን አስፈላጊነት የሚረዱ ሁሉ ሲያመሰግኑኝ ይኖራሉ በዚህ!

ልማጠኛ፡-
እስቲ ለህዝቡ የዋሉለት ካለም ቢጨምሩልን፡፡

መለስ፡-
ለሀዝቡ በዋነኝነት ዋልኩት ውለታ ለአገሩ መሞት እንዲችል ማድረጌ ነው፡፡ ይሄ ትልቅ ክብር ነው ያው፡፡ የተለያዩ ጭቆናዎችን በማድረግ ሰዎች በግልም በቡድንም ለትግል እንዲነሳሱና በሂደቱም ለአገራቸው ነፍሳቸውን እንዲሰጡ አመቻችተንላቸዋል፡፡ ይሄ ደብል ጥቅም ነው ያለው፡፡ ለህዝቡም ለአገር የመሞትን ክብር እንደሚያቀዳጅ ሁሉ ለፌደራልና አግአዚም ነጻ የሰው ዒላማ ይሰጣቸዋል፡፡ ውትድርና ስትሰለጥን ያው መተኮስ ሊያምርህ ይችላል፡፡ ይህ አምሮት ባለፈው ጎንደር ላይ አንዱ ፌደራል አስራ ምናምን ሰው እንደገደለው በህገወጥ መልኩ ከሚተገበር የሰላማዊ ተቃዋሚ አጋጣሚ ሲገኝ እንደ97ቱ፣ እንደአኙዋኩ፣ እንደጋምቤላው፣ እንደደሴው፣ እንደጎንደሩና ትግራዩ፣ እንደሱማሌ ክልሉ፣ እንደአሳሳውና ኮፈሌው፣ እንደአምቦው ወዘተ በህጋዊ መልኩ ቢተገበር ይሻላል ከሚል መነሻ ነው የተነሳነው፡፡

ሌሎችንም አጋጣሚዎችን ፈጥረናል፡፡ ለምሳሌ በባድመ ጉዳይ እንደቀልድ ከኢሳያስ ጋር በርጫ ላይ የፈጠርናትን ጨዋታ የምር አድርገናት ‹‹ለምን ፉል ፍሌጅድ ጦርነት አድርገነው በኋላ አንሸማገልም›› በሚል ተነጋግረን በኢትዮጵያ በኩል ወደ 70 ሺ ሰው አካባቢ ለእናት አገሩ የመሞት እድል ፈጥረናል፡፡ መሬቱን ያው ጦርነቱ ሲያልቅ መልሰንለታል ለኢሴ፡፡ ይህ ለህዝብ ከዋልኳቸው ውለታዎች አንዱ ነው፡፡

ልማጠኛ፡-
ብዙ ውለታ ነው የጠቀሱልኝ፡፡ ይህ ሁሉ ውለታ በእርስዎ ሞት መቋረጡ በእርግጥም አሳዛኝ ነው፡፡ እንዳልኩዎት…

መለስ፡-
ኖ! ኖ! አትሳሳት! እኔ በበሞቴ የተቋረጠ ውለታ የለም! አሁንምኮ እነዚህ ነገሮች ቀጥለዋል፡፡ በኔ ሌጋሲ አይደለ እንዴ አገር እየተገዛ ያለው! እነ ሃይለማሪያም ደሳለኝ እና ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሁሉ በእኔ ሌጋሲ አይደል እንዴ እየተንደላቀቁ ያሉት?

ልማጠኛ፡-
ሁለቱ አይለያዩም ጌታዬ? አቶ ሐይለማርያምኮ ጠቅላይ ሚኒ…..

መለስ፡-
አይለያዩም ባክህ! ጆብ ስፔሲፊኬሽናቸው ሁሉ አንድ ነው!

ልማጠኛ፡-
በመጨረሻ የሚጨምሩት ነገር ካለ እድሉን ልስጥዎት፡፡

መለስ፡-
ብዙ የምለው እንኳ የለኝም፡፡ ህዝቡን ብቻ ማመስገን ነው የምፈልገው፡፡ እንደአንድ ጣኦት ልመለክ የምችልበትን እድል ለማመቻቸት ለሚደክሙት ካድሬዎችም ሰላምታ ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ እዚህ ፌስቡክ ላይም የተወሰኑት እየሰሩት ያለውንም ስራ አይቻለሁ፡፡ ምንም አይልም፡፡ ትንሽ ብቻ አንዳንዴ እያበዙት ጥርስ እያስነከሱብኝና የማንም መቀለጃ እያረጉኝ ከመሆኑ በስተቀር ጥሩ እየለፉ ነው፡፡ ምኞታቸው ተሳክቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ እመለካለሁ የሚል ተስፋ ባላደርግም እታገሳለሁ፡፡ ይብቃን ለዛሬ፡፡

ውይ ረስቼው! ሜሮን ጌትነትንም ሰላም በልልኝ በናትህ፡፡ እሷ ልጅ ጥያቄና መልስ ውድድር ላይ በሌጋሲዬ ስም ያልተመለሰ ጥያቄ ሁሉ ነጥብ ትሰጣለች አሉ! ለካ ለልማታዊ አርቲስቶችም ብዙ ውለታ ውያለሁና!

ልማጠኛ፡-
አመሰግናለሁ አቶ መለስ!

መለስ፡- አመሰግናለሁ! ሙድህ ከጣመኝ ወደፊትም ብቅ እያልኩ ቃለ መጠይቅ ልሰጥህ እችላለሁ!
===================================

(ማሳሰቢያ፡- ይሄ ቃለ መጠይቅ ምናባዊ ነው፡፡ ዓላማው መለስ በስልጣኑ ከሰጠው ጥቅም ይልቅ በጨቋኝ ስርአቱ ያዘነበብን ጉዳት በጣም እንደሚከፋ ማሳየት ነው፡፡ መለስ አንዳችም ጥሩ ነገር አልሰራም ለማለት አይደለም፡፡ ጥሩ ነገሩ በ99.6 በመቶ ተጋኖ በኢቲቪና አንዳንዴም በፌስቡክ አሰልችቶናል፡፡ ጭቆና የቀደመ በጎ ስራን እንደእሳት ይበላል፤ ለዚህ አትጠራጠሩ፡፡ የመለስ ልደት በዓል ለሆነላችሁ የስርአቱ ተጠቃሚዎችና ቅልብ ካድሬዎች ደግሞ ሙት በመውቀስ ጽንፍ ረግጬ ከሆነ ይቅርታችሁን እለምናለሁ፡፡ አንድ ቀን እንደምትወለዱ ተስፋ በማድረግ! መልካም ልደት!)

‹‹ያለምንም ደም››
‹‹ሌጋሲው ይቅደም!›› ቂቂቂ

የሄንሪ ቀመር በአንፊልድ ሊቨርፑል (ልዩ ትንታኔ)

$
0
0

የትልቅነት ማዕረጉን ተገፍቶ የቆየው ሊቨርፑል ወደ ክብሩ እየተመለሰ መሆኑን የዘንድሮ ስኬታማ ግስጋሴው ይጠቀላል፡፡ ለቀዮቹ ጥንካሬ ብሬንዳን ሮጀርስ ትልቅ አድናቆት ቢገባቸውም የክለቡ የሽግግር ጉዞ ዋናው ቀያሽ ጆን ሄንሪ ናቸው፡፡ አሜሪካዊው በአዲስ አስተሳሰቦች ስኬትን እንዴት ማምጣት እንደሚቻል የተገነዘቡ ናቸው፡፡ ይህንን አቅማቸውን በቢዝነሱ እና በስፖርቱ እንዴት መጠቀም እንዳለባቸውም ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ አዲስ እና የተለዩ ሀሳቦችን እያፈለቁ ውድቀትን ሳይፈሩ ያሰቡትን ይተገብራሉ፡፡
ሄንሪ በአሜሪካ ቦተን ሬድ ሶክስ የተሰኘውን ክለብ በባለቤትነት ሲረከቡ በቤዝቦል ስፖት እጅግ ስኬታማ ተብሎ ይጠቀስ ከነበረው ኒው ዮርክ ያንኪስ ጋር የነበረውን ሰፊ ልዩነት ለማጥበብ አንድ የተለየ ሀሳብ ማፍለቅ ነበረባቸው፡፡ የአሜሪካው ኦክላንድ አትሌቲክ በቤዝቦል ስፖርት ራሱን መልሶ ለማጠናከር ጥናት ማድረጉን ያውቁት ሄንሪ በተመሳሳይ ሬድ ሶክስን መልሰው ለመገንባት ሊጠቀሙበት ሲንቀሳቀሱ ማንም አልፈቀደማቸውም፡፡
የውድቀት ፍርሃት’
liverpool
ሊቨርፑል በሮጀርስ ስር ሲሰለጥን አንዱ የጠቀመው ከውድቀት ፍርሃት ነፃ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ያለመፍራት መንፈስ ደግሞ ከክለቡ አናት የመነጨ ነው፡፡ ሄንሪ እና የፌንዌይ ስፖርትስ ግሩፕ (FSG) ቀደም ሲል ስህተቶች ሰርተዋል፡፡ ነገር ግን በስህተቶቻቸው እየተማሩ ሊቨርፑል ከሌሎች ተቀናቃኞቹ ጋር ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ሞክረዋል፡፡ የአሁኑ የሊቨርፑል ትልቅ የጥንካሬ ባህርይ የክለቡን የስልጣን ተዋረድ ተጠቅሞ ከላይ የወረደ ነው፡፡
ሊቨርፑል የተለየ ነገር መሞከር ለመፈለጉ አንዱ ማስረጃ ዳሚዬን ኮሞሊን መሾሙ ነው፡፡ ሆኖም ይህ እንዳልሰራ ሲመለከቱ በቶሎ ሀሳባቸውን አረሙ፡፡ በዝውውር ገበያ ላይ አብዝቶ መሳተፍ ስኬትን እንደማያረጋግጥ ተገነዘቡ፡፡ ስለዚህ ሌላ አይነት ቀመር መሞከር ነበረባቸው፡፡
ሄንሪ ሁልጊዜም በሊቨርፑል ሰፋ አድርገው ማሰብ እና ጠቅለል ያለ ስዕል መመልከት ይፈልጋሉ፡፡ ሰውዬው ለሚፈጠሩ አደጋዎች መፍት ለመስጠት እጃቸውን አጣምረው የሚጠባበቁ ሳይሆኑ እያንዳንዷን እርምጃ አስቀድመው አስበው በስትራቴጂ መሄድ የሚመርጡ ናቸው፡፡ ደጋፊዎች እንደ ትልቅ ስህተት የሚመለከቱትን እርሳቸው የስኬታቸው ግስጋሴ ምስክር አድርገው በበጎ ያዩታል፡፡ በእግርኳስ የተለዩ እና አዳዲስ አስተሳሰቦችን ማራመድ ከባድ ነው፡፡ ምክንያቱም ደጋፊዎች ምንም አይነት ውድቀትን አይታገሱም፡፡ ሆኖም ከውድቀቶች እየተማሩ እንጂ በቀጥት ስኬት ጋር አይደርስም፡፡
አለማችን ካፈራቻቸው ድንቅ እና ታላላቅ ስፖርተኞች አንዱ የሆነው ማይክል ጆርዳን በአንድ ወቅት ይህንን ብሏል፡፡ ‹‹በህይወት ዘመኔ ደጋግሜ ውድቀትን ተጎንጭቻለሁ፡፡ የተሰካልኝም ለዚህ ነው፡፡ ሄንሪ እና FSG ለፈጠራ በሰላም አዕምሮ ቢዝነስን ማሳደግን ያውቁበታል፡፡ ሊቨርፑልን እና ሬድ ሶክስን እያስተዳደሩ ያሉትም በዚህ መንገድ ነው›› ሄንሪ ይህንን ቀመር ወደ ውጤት ለማድረስ እና ሊቨርፑልን መልሰው ሃያል ለማድረግ የተከተሏቸውን መንገዶች መቃኘት እንችላለን፡፡
የሮጀርስ ሹመት
ሄንሪ የሊቨርፑልን ህዳሴ በበላይነት ይምሩ እንጂ ራዕያቸውን የሚጋራ፣ አዳዲስ ሀሳቦችን በመሞከር የሚያምን እንዲሁም ቡድኑን ሜዳ ላይ የሚመራ ሰው ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ ሮጀርስ ይህንን ሁሉ በውስጣቸው የያዙ እውነተኛ መሪ መሆናቸውን አሜሪካዊው አመኑበት፡፡ ወጣቱ አሰልጣኝ ሜዳ ላይም አዳዲስ ሃሳቦችን እየተጠቀመ ለስኬት እንደሚሰራ እርግጠኛ ሆኑበት፡፡ ሄንሪ ሮጀርስን ሲሾሙ የእግርኳስ ፍልስፍናቸውንም እንዲያራምዱ ፈቀዱላቸው፡፡ ሮጀርስ ሄንሪን አላሳፈሩም፡፡ በተለይ መንገድ ሊቨርፑልን ውጤታማ አደረጉት፡፡ ሰውየው በቡድኑ የተለዩ ሁኔታዎችን ፈጥረዋል፡፡ የሊቨርፑል ተጨዋቾች ለግጥሚያ በአዕምሯቸው ዝግጁ እንዲሀኑ በዓለም ላይ የላቁ ከሚባሉት የስፖት ስነ ልቦና ባለሙያዎች አንዱን አስቀጥረዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ በቀጥታ ቡድኑ ላይ የፈጠሩት ተፅዕኖ በጥናት ባይረጋገጥም የዘንድሮው የሊቨርፑል ተጨዋች አካላዊ እና አዕምሯዊ ጥንካሬ ግን አስገራሚ ሆኗል፡፡
ሮጀርስ ተጨዋቾቻቸውን ሲያቀናጁም እንደዚሁ የፈጠራ አቅማቸው ይንፀባረቃል፡፡ ከግጥሚያዎች በፊት ሊቨርፑል በየትኛው ጨዋታ ምን አይነት አጨዋወት ይዞ እንደሚቀርብ መገመት ያስቸግራል፡፡ ሮጀርስ የመጠቁ ታክቲክ አዋቂ ተብለው ባይፈረጁም ቡድናቸውን የማይገመት ማድረግን ያውቁበታል፡፡ ዘንድሮ ከቡድኑ የጥንካሬ ሰበቦች አንዱ ይኸው የማይጨበጥ የጨዋታ ስትራቴጂ ይዞ የመገኘት ባህሪዬ ነው፡፡ ይህ የሮጀርስ የፈጠራ ዝንባሌ በሄንሪ ፍላጎት እየተበረታቱ የሚተገብሩት ነው፡፡
የዝውር – ኮሚቴ
የኮሞሊ መምጣት እንደታሰበው ስኬታማ ሆኖ አይገኝ እንጂ ሀሳቡ በራሱ ስህተት አልነበረም፡፡ ሰውየው የተሾሙት በዝውውር ገበያው ሰዎች በቀላሉ ከሚያዩት አልፈው እንዲመለከቱ ነበር፡፡ ሆኖም አሰራሩ ችግር እንደነበረው ለማወቅ የአንዲ ካሮል ግዢ በቂ ነበር፡፡ ሉዊስ ሱአሬዝን የመሰለ ኮከብ በ22 ሚሊዮን ፓውንድ የገዙት ሰው ለቀድሞው የኒውካስል ወጣት ዝውውር 35 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲከፍል መስማማታቸውን ማመን ያስቸግራል፡፡
በዚህ የዝውውር ሂደት መቀጠል እንደማይችሉ የተገነዘቡት ሄንሪ በ2012 ክረምት የዝውውር ኮሚቴ አቋቁሙ፡፡ በእርግጥ የኮሚቴ አሰራር አዲስ አልነበረም፡፡ ብዙዎቹ ክለቦች እንዲህ አይነት መዋቅር አላቸው፡፡ የሊቨርፑሉ ኮሚቴ ግን በተለየ መልኩ የተጫዋቾችን ባህላዊ የምልመላ ስርዓት ከስታስቲካዊ ትንታኔዎ ጋር አነፃፅሮ የጋራ ስምምነት ላይ ይደርሳል፡፡ ከኦክላንድ አትሌቲኮ ሞዴል የተቀዳ ሳይሆን አይቀርም ተብሎ የሚገመተው ይህ አሰራር ምናልባት በእግርኳሱ ለቦሩሲያ ዶርትሙንድ የዝውውር ስትራቴጂ ይቀርባል፡፡
ኮሜርሺያል
የአሁኖቹ የሊቨርፑል ባለሀብቶች ከቀድሞዎቹ በተለየ መልኩ ክለቡ በኮሜርሺያል እንዲያድግ የትኛውን አካባቢ ኢላማው ማድረግ እንዳለበት ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ አዳዲሶቹ የክለቡ የቢዝነስ ዲፓርትመንት ሰዎች የሊቨርፑል ገቢ ያሳደጉበት ፍጥነት ያስደንቃል፡፡ ሬድ ሶክስ በFSG ባለቤትነት ስር ከገባ ወዲህ ከኒውዮርክ ያንኪስ ጋር የነበረውን ሰፊ ርቀት ለማጥበብ 90 የሚደርሱ ተጨማሪ የቢቢነስ አጋሮች ጋር በኮንትራት ተጣምሯል፡፡
የአሜሪካዊያኑ አዳዲስ ሃሳቦች ሊቨርፑል ለወደፊቱ የተደላደለ እና አስተማማኝ ፋይናንስ እንዲኖረው የሚያደርጉ ስትራቴጂዎችን ይዘዋል፡፡ በዓለም ዙሪያ እጅግ ከፍተኛ ደጋፊ ያለው የመርሲ ሳይዷ ክለብ መልካም አጋጣሚዎቹን ሁሉ ቀስ በቀስ በመጠቀም የገበያውን ስፋት ወደ ገንዘብ የመቀየር ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ለጊዜው የሊቨርፑል አጠቃላይ ሂብ ኪሳራ ቢያሳይም የኮሜርሺያል ትርፉ እያደገ ነው፡፡ የክለቡ ኮሜርሲያል ስትራቴጂ ምናልባትም በጥቂት ዓመታት ወስጥ ትርፋማ አድርጎት የቡድኑን ተፎካካሪነትም ከፍ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ምናልባትም በፋይናንሱ የበረታው ክለብ በዓለም ላይ አሉ የተባሉ ምርጥ ተጨዋቾችን ወደ አንፊልድ ይስባል፡፡
ስታዲየም
አንፊልድን የማስፋፋቱ ሀሳብ የሚሳካ አይመስልም ነበር፡፡ የሊቨርፑል ከተማ ምክር ቤትም ፈቃድ የመስጠት ምልክት አላሳየም፡፡ ስለዚህ ምናልባትም ክለቡ ይህንን ሀሳቡን ትቶ አዲስ ስታዲየም ለመገንባት ቢያቅድ እንደሚሻል ሲነገር ነበር፡፡ ሄንሪ ወደ እንግሊዝ ከመጡ በኋላ ግን ሁሉም ነገር ተለወጠ፡፡ አንፊልድን የማስፋፋቱ ሀሳብ የሚቻል መስሎ ታየ፡፡ እንዴት?
ይህ የሄንሪ ሁኔታዎችን ‹‹አይቻልም›› ከሚለው አልፎ የመመልከት ባህሪይ ያመጣው ነው፡፡ ለፈጠራ አዕምሮውን ክፍት ያደረገ ሰው ችግሮን ለማለፍ መፍትሄ ይመከታል እንጂ ወደ ኋላ አይመለስም፡፡ አሁን ሊቨርፑል ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚስማማ ስታዲየም እየተመለከተ ነው፡፡ ይህ ስታዲየም አንፊልድ ራሱ ነው፡፡
የFSG ሰዎች ለቦስተኑ ክለባቸውም ተመሳሳይ ዘዴ ተጠቅመዋል፡፡ በዚያም አይቻልም እየተባሉ በተለየ ብልሀት የቤዝቦሉን ክለብ ስታዲየም አግዝፈው ተጠቅመውበታል፡፡ ሰዎቹ ለስኬት አይተኙም፡፡ በሩጫቸው ሁሉ የሚገጥማቸውን ውድቀት ተቀብለው እና ተምረውበት ቀጣዩን እርምጃ ይጀምራሉ፡፡ በሬድ ሶክስ ደጋግሞ ውድቀት ቢጎበኛቸውም በመጨረሻ የስኬቱን ቀርም አግኝተውት በ10 ዓመታት ውስጥ ሶት የWorld Series (የአሜሪካ ቤዝቦል ሻምፒዮና ውድድር) አሸንፈዋል፡፡ አሁን FSG የቀደመ ልምዱን ታጥቆ ሊቨርፑልን በድጋሚ ትልቅ ሊያደርግ ተነስቷል፡፡ እያንዳንዱን እርምጃውንም በጥናት እና በእቅድ ተያይዟል፡፡ አሜሪካዊያኑ ሮጀርስን በአሰልጣኝነት ሲቀጥሩ ሰውየው ከገንዘብ በላይ ጊዜ እንደሚያስፈልገው አውቀዋል፡፡ የአንፊልዱን ክለብ በሶስተኛው ዓመት ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ሊመልሱ ቃል ይገቡት አሰልጣኝ በሁለተኛ ዓመታቸው ሊቨርፑልን የዋንቻ ተፎካካሪ አድርገውታል፡፡ ከሜዳ ውጪ ደግሞ የክለቡ የኮሜርሺያል ባለሙያዎች የሊቨርፑልን ገበያ እያሰፉ እና የቢቢነስ ሽርኮቻቸውን በቁጥር እያሳደጉ አስገራሚ ግስጋሴ ላይ ናቸው፡፡ የሄንሪ ቀመር እየሰራ ነው፡፡

የሜርሲሳይድ መነቃቃት
በሜርሲ ሳይድ በአይነቱ ልዩ የሆነ መነቃቃት እየታየ ነው፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን የሊቨርፑል ከተማዎቹ ሁለት ክለቦች አስገራሚ ብቃት በማሳየት ላይ ናቸው፡፡ የውድድር ዘመኑ ሲጀመር ተሰጥቷቸው ከነበረው ግምት በላይ መሆን ችለዋል፡፡

ከሊቨርፑል ምን ተጠብቆ ነበር?
ሊቨርፑል የውድድር ዘመኑን የጀመረው ቅይጥ የሆነ እምነት እና ግምት ይዞ ነው፡፡ በ2012-13 የውድድር ዘመን ቡድኑ ያስመዘገበው ውጤት የተገለፀው ‹‹ከተጠበቀው በታች›› ተብሎ ነው፡፡ ይህም አንባቢዎችን ‹‹ውድቀት›› ከሚለው ቃል ለመከለል የተደረገ ጥረት ነበር፡፡ የአዲሱ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ አጀማመር አስከፊ ነበር፡፡ ይህም የክለቡ ዝነና አሰልጣኝ ከኃላፊነት መነሳታቸው ስህተት ወይስ ለስራው ዕጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት አንድሬ ቪያስ ቦአስ እድሉ ሊሰጣቸው ይገባ ነበር? የሚሉ እና መሰል ጥያቄዎች በደጋፊው አዕምሮ ውስጥ እንዲመላለስ አድርጎ ነበር፡፡ ቀዮቹ የውድድር ዘመኑን የጀመሩት በቀድሞው የኬኒ ዳልግሊሽ ረዳት ስቲቭ ክላርክ በሚመራው ዌስት ብሮም በአሳማኝ ሁኔታ 3-1 ተሸንፈው ነበር፡፡ ይህ አጋጣሚ በራሱ ስቲቭ ክላርክ ኃላፊነቱ ሊሰጣቸው ይገባ ነበር ወይ? የሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡ አጀማመሩን ይበልጥ አስከፊ ያደረገው በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ቡድኑን የተቀላቀሉት ጆአለን፣ ፋቢዮ ቦሪኒ እና ኦሳማ አሳይዲ ውጤታማ መሆን አለመቻላቸው እና ክሊንት ደምፕሴይን ለማስፈረም የተደረገው ጥረት መክሸፉ ነበር፡፡ ተጫዋቹ በይፋ የቀረበለትን ጥያቄ አለመቀበሉ የክለቡን ታማኝ ደጋፊዎች እንኳን ትንሽ ራቅ ባለ ጊዜ ቢሆንም ስሙ ከስኬት ጋር ተያይዞ ይጠቀስ በነበረው ቡድናቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ አስገድዶ ነበር፡፡ ሆኖም ውጤታማ በነበረው የጃንዋሪ የዝውውር መስኮት ክለቡ ዳንኤል ስቴሪጅ እና ፊሊፔ ኩቲንሆን ወደ ቡድኑ መቀላቀሉ መረጋጋትን አሰፈነ፡፡ የውድድር ዘመኑም ቅርፅ እየያዘ መጣ፡፡ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ሆኖ የውድድር ዘመኑን ያጠናቅቃል ተብሎ ተፈርቶ የነበረበት ወቅት ነበር፡፡ ነገር ግን ሰባተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ፡፡ እንደ አጀማመሩ ቢሆን ከዚህም የከፋ ውጤት ይዞ ሊያጠናቅቅ ይችል የነበረበት ሰፊ ነበር፡፡ የውድድር ዘመኑ ሁለተኛ አጋማሽ ግን ጥርት ባለ መልኩም ባይሆን በቀጣዩ የውድድር ዘመን የሊቨርፑል ደጋፊዎች ምን ሊመለከቱ እንደሚችሉ የጠቆመ ነበር፡፡

2013-14 ዓለም አቀፍ ክብር
ፍፁም ተቃራኒ በሆነ መልኩ ሊቨርፑል የዘንድሮውን የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ሶስት ጨዋታዎች በሙሉ አሸነፈ፡፡ ይህንንም ድል ያላሳከው ያለ ኮከብ ተጫዋቹ ልዊስ ሱአሬዝ እገዛ ነበር፡፡ እንደ ሲሞን ሚኞሌ እና ማማዱ ሳኮን የመሳሰሉ ተጨዋቾች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ቡድኑ መቀላቀሉ እጅጉን ጠቅሞታል፡፡ የአያጎ አስፓስ እና ኮሎ ቱሬ ዝውውር ግን ያገኘው ድብልቅ ምላሽ ነው፡፡ ከሊቨርፑል ተጠብቆ የነበረው ደጋፊዎቹ በሹክሹክታ ‹‹ቀጣዩ የውድድር ዘመን የእኛ ነው›› ሲሉ መስማት ነበር፡፡
ከተጫዋቾቹም የተጠበቀው አራተኛ አሊያም አምስተኛ ሆነው ለማጠናቀቅ የቻሉት ያህል እንዲታገሉ ነበር፡፡ በእርግጠኝነት ያልተጠበው ነገር ዘጠን ጨዋታዎችን በተከታታይ ማሸነፉ ነበር፡፡ ቡድኑ ‹‹ጥልቀት እንደሌለው›› እየተነገረ ባለበት ሰዓት ከ34 ጨዋታዎች በኋላ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላ ይቀመጣል ብሎ የረጠረጠ አለመኖሩ እውነት ነው፡፡ ሌላው ያልተጠበቀ ነገር ባርሴሎና ብሬንዳ ሮጀርስን ወደ ባርሴሎና ለማስኮብለል ሙከራ እያደረገ ነው መባሉ ነበር፡፡ ምን ይሄ ብቻ ፔፕ ጋርዲዮላ ሊቨርፑል በውድድር ዘመኑ እያሳየ ያለውን ብቃት አድቆ የአንፊልዱ ክለብ ዳግም በቻምፒዮንስ ሊግ ሲጫወት መመልከት እንደሚፈልግ ይናገራል ብሎም የጠበቀ አልነበረም፡፡

ኤቨርተን፡- ሞዬስ ተረስተዋል
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኤቨርተን በፕሪሚየር ሊጉ ድብልቅ ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን በዴቪድ ሞዬስ የተመሩት ቶፊስ ስድስተኛ ሆነው አጠናቀቁ፡፡ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ከከተማ ተቀናቃኛቸው ሊቨርፑል በላይ ሆነው መጨረሳቸው ነበር፡፡ የገዘፈ ስም የነበራቸው እና እንደ ‹ጣኦት› የሚቆጠሩት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ሲወስኑ ዩናይትድ ሞዬስን ወደ ኦልድትራፎርድ ወሰደ፡፡ ኤቨርተንም አሰልጣኝ አልባ ሆነ፡፡ በቀጣዩ የውድድር ዘመን እንዲመሯቸውም ሮቤርቶ ማርቲኔዝን ሾሙ፡፡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ስፔናዊው ከዓመት በፊትም ‹‹ንጉስ›› ዳልግሊሽን እንዲተኩ በሊቨርፑል ኃላፊነት በዕጩነት ከቀረቡ አሰልጣኞች መካከል ግንባር ቀደም ነበሩ፡፡
ማርቲኔዝ የአሰልጣንነት ዘመናቸውን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገሩት ስዋንሊ ሲቲን የታችኛው ዲቪዚዮን ሻምፒዮን በማድረግ ነበር፡፡ በዊጋን በነበራቸው ቆይታም ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ቡድኑን ከመውረድ በመታደግ አድናቆት አትርፈዋል፡፡ በአራተኛው የውድድር ዘመን ግን ዊጋንን ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን ከመውረድ ሊታደጉት አልቻሉም፡፡ ነገር ግን ባዶ እጁን አልሸኙትም፡፡ የማርቲኔዝ ልጆች የሮቤርቶ ማንቺንውን ማንቸስተር ሲቲ በማሸነፍ የኤፍ.ኤ ካፑን ድል ማጣጣም ቻሉ፡፡ ኤቨርተን እንዲህ ያለውን አሰልጣኝ ሲሾም ወደ ፊት እንዲያራምደው አስቦ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ
ማርቲኔዝ በተጫዋቾች ዝውውር በኩል ድንቅ ስራ ሰርተዋል፡፡ በተለይ በውሰት ውል ያስፈረሟቸው ተጫዋቾች ብቃት ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ኤቨርተን እስካሁን ላደረገው ግስጋሴ በጊዜያዊነት ቡድኑን የተቀላቀሉት የዤራርድ ዴሌፋ፣ ጋሬት ባሪ እና ሮሜሉ ሉካኩ ሚና የጎላ ነው፡፡ ማርቲኔዝ ተጨዋቾቻቸውን የሚያስተምሩበት መንገድ ሙገሳን አስገኝቶላቸዋል፡፡ ሮስ ባርክሌይ ‹‹ቅን ሰው›› ብሎ ከገለፃቸው በኋላ ‹‹በርካታ የታክቲክ ልምምዶችን እንሰራለን፡፡ ይህ ደግሞ ለእኔ መልካም ነው፡፡ ወጣት በመሆኔ ብዙ እማራለሁ›› ሲል ለአሰልጣኙ ያለውን አክብሮት ገልጿል፡፡
ከኤቨርተን የተጠበቀው ምን ነበር? አምስተኛ አሊያም ስድስተኛ ሆነው እንዲያጠናቅቁ እና ታላላቆቹ ክለቦች በሚወዳደሩበት መድረክ የመሳተፍን ዕድል ለማግኘት መጣር ነበር፡፡ ከዚያም እንደተለመደው ባዶ እጅ መመለስ እና ከከተማ ባላንጣቸው ሊቨርፑል ጋር የበላይ ሆኖ ለመጨረስ እርባና ቢስ ፉክክር ማድረግ ተጠብቋል፡፡ ሆኖም ግምቶችን ሁሉ ውድቅ በማድረግ የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ የሚያስገኘውን ስፍራ ይዞ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ እንዳውም በአሁኑ ወቅት ቢያንስ በሂሳብ ስሌት ደረጃ የጉዲሰን ፓርኩ ቡድን ከአርሰናል በተሻለ አራተኛ ሆኖ የመጨረስ ዕድል አለው፡፡ ሌላው ቢቀር ባለፈው ክረምት ከፍተኛ ወጪ ካወጣቸው ቶተንሃም እና ከሞዬስ ዩናይትድ በላይ ሆኖ የማጠናቀቁ ነገር እርግጥ እየሆነ መጥቷል፡፡ በውድድር ዘመኑ መገባደጃ በርካታ ክለቦች ጫና ውስጥ በሚወድቁበት ሰዓት ስድስት ጨዋታዎችን ያለከልካይ ማሸነፍ ችሏል፡፡

የሜርሲ ሳይድ ደስታ እና ጥርጣሬ
ሁለቱ የመርሲ ሳይድ ክለቦች ምርጥ እግርኳስ ይጫወታሉ፡፡ የሚፈልጉትን ውጤት ማስመዝገባቸው ብቻ ሳይሆን ኳስን የሚጫወቱበት መንገድ በራሱ አስደናቂ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በፕሪሚየር ሊጉ ሲያጠቃ እጅግ የሚያስፈራው ቡድን ሊቨርፑል ነው፡፡ በመልሶ ማጥቃት ቡድኖችን ከጥቅም ውጪ የሚያደርግበት መንገድ ለተመልካች አዝናኝ ነው፡፡ ኤቨርተንም ቢሆን መልካም እግርኳስ ይጫወታል፡፡ በተለይ በክንፍ በኩል ማጥቃት አሁንም የኤቨርተን መታወቂያው ነው፡፡ ስቲቭ ፒናር እና ሌይተን ቤይንስ በግራ መስመር የሚሰነዝሩት ጥቃት በሞዬስ ዘመንም የነበረ ነው፡፡
ሺመስ ኮልማን እና ኬቪን ሚራላስ በቀኝ መስመር የፈጠሩት የማጥቃት አማራጭ ግን የማርቲኔዝ ውጤት ነው፡፡ ባሪ እና ጀምስ ማካሪቲ የመሀል ሜዳውን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ያላሰለሰ ጥረት አማካይ ክፍሉ የበለጠ የተረጋጋ ሆኗል፡፡ ሁኔታውን ትኩረት ግቢ የሚያደርገው ኤቨርተን የከተማ ተቀናቃኙ ሊቨርፑል ለዋንጫ የሚያደርገውን ጉዞ ማገዙ ነው፡፡ ኤቨርተን የሚገኘው ቀሪዎቹን ጨዋታ በሙሉ የሚያሸንፍ ከሆነ ቻምፒዮንስ ሊግ መሳተፍ የሚያስችለው ደረጃ ማግኘት በሚችልበት ሁኔታ ነው፡፡ በመሆኑም ሊቨርፑል በማሸነፉ የሚገፉበት ከሆነ እና ኤቨርተን በሜዳው ከሲቲ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ የከተማ ተቀናቃኙ ሻምፒዮን እንዲሆን የበኩሉን አስተዋፅኦ አበረከተ ማለት ነው፡፡ አንዳንድ የኤቨርተን ደጋፊዎች ግን መራራ ባላንጣቸው ሊቨርፑል ለ19ኛ ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሲሆን ከመመልከት ይልቅ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ቢቀርባቸው እንደሚመርጡ በመናገር ላይ ናቸው፡፡
ሆኖም እንደ ስልቨ ደስቲን እና ሮስ ባርክሌይን የመሳሰሉ ተጨዋቾች የቻምፒዮንስ ሊግ ምሽቶች ወደ ጉዲሰን ፓርክ ቢመጡ ደስታቸው ወደር እንደማይኖረው በመናገር ላይ ናቸው፡፡

ገንዘብ ተሸንፏል
ሊቨርፑል እና ኤቨርተን በብሪታኒያውያን ተጨዋቾች ዙሪያ ቡድናቸውን መገንባታቸው ድንቅ ሀሳብ እንደሆነ በፌዝ መልክ በተደጋጋሚ ተነግሯቸዋል፡፡ አባባሉ የመነጨው በክለቦች የሚያድጉ ተጨዋቾች ከሌሎች ሊጎች ከሚመጡ ተጨዋቾች በብቃት ያነሱ ናቸው ከሚል እሳቤ ነው፡፡ ምፀታዊው ነገር ግን ሮይ ሆጅሰን ወደ ብራዚል ይዘውት በሚሄዱት ስኳድ ውስጥ ቢያንስ ስምንት ተጨዋቾችን ከሜርሲ ሳይድ ሊመርጡ የሚችሉ መሆኑ ነው፡፡ ስቲቨን ዤራርድ፣ ዳንኤል ስቱሪጅ፣ ራሄም ስቴርሊንግ፣ ጆርዳን ሄንደርሰን፣ ግሌን ጆንሰን፣ ሌይተን ቢይንስ፣ ፊል ጃግዬልካ እና ሮስ ባርክሌይ ወደ ደቡብ አሜሪካዊ ሃገር የመጓዝ ዕድላቸው የሰፋ ነው፡፡ ሊቨርፑል ዳግም እንደሚያንሰራራ አሊያም ወደ ክብሩ ሰገነት እንደማይመለስ ተገንብዮ ነበር፡፡ ኤቨርተንም ቢሆን የውጭ ባለሀብት የክለቡን ባለቤት ቢል ኬንራይትን እስካልተካ ድረስ ምንም የተለየ ነገር እንደማይፈጥር ተደምድሟል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ሁለቱ የሊቨርፑል ክለቦች በእግርኳስ ከገንዘብ ይልቅ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባው ቴክኒክ፣ ክህሎት እና ጥሩ አሰለጣጠን ለመሆናቸው ጥሩ ማሳያ ሆነዋል፡፡ በቅርቡ ሊቨርፑልን የተቀላቀሉት ተጨዋቾች በሙሉ ለሊቨርፑል መነቃቃት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዳበረከቱ አይካድም፡፡ ሱአሬዝን ማቆየት ከፍተኛ ወጪ እንደጠየቀም አይታበልም፡፡ ሲጀመር እርሱን ማግኘት በራሱ ፈተና ነበር፡፡ ነገር ግን ሁሉም ነገር የተቀባባ አልነበረም፡፡ ሊቨርፑል በፕሪምየር ሊጉ አሁን ያለበትን ደረጃ የተቆናጠጠው ባለፈው ዓመት ባፈሰሰው መዋዕለ ንዋይ ምክንያት አይደለም፡፡ ከሰባተኛ ወደ አንደኛ ደረጃ መምጣት የማይታሰብ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ አድናቆት ሊቸረው የሚገባ ነው፡፡ ኤቨርተንም ቢሆን ይህን ያሳካው በገንዘብ እርዳታ ብቻ አይደለም፡፡ አሰልጣኛቸው አዲስ ታክቲክ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በሜዳ ውስጥ እና ከሜዳ ውጪም ብልህ ነበሩ፡፡ ይህም ልፋታቸውም አንፀባራቂ የውድድር ዘመን አስገኘላቸው፡፡ ከነበሩበት ተራነትም ወደ ከዋክብትነት ተለወጠ፡፡
ሊቨርፑል እና ኤቨርተን የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ ክስተቶች ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ቀጣዩ ዓመት ለከተማዋ በጣም አስደሳች መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ የቻምፒየንስ ሊግ ምሽቶች ወደ ከተማዋ የሚመለሱ ከሆነ በርካታ ጎብኚዎች መጉረፋቸው ስለማይቀር የከተማዋ ገቢም እመርታን ያሳያል፡፡ ከእግርኳሷዊ አንፃር ብቻ ከተመለከትነው ሁሉም ተገንታኞች፣ አሰልጣኞች እና የሌሎች ክለብ ደጋፊዎች ቆም ብለው እነዚህን ሁለት ክለቦች ለማየት ይገደዳሉ፡፡ አምነው ባይቀበሉም እንኳን በእነዚህ ሁለት ቡድኖች ትንሣኤ መማረካቸው እውን ነው፡፡

የአበበ ገላው “ጩኸት”አንደምታ (ዳጉ ኢትዮጵያ)

$
0
0

ዳጉ ኢትዮጵያ (dagu4ethiopia@gmail.com)

620አንድ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ወዳጄ “በአበበ ገላው የሰሞኑ ድርጊት ምን አስደሰተህ?” ሲል ግራ በመጋባት ጠየቀኝ፡፡ የወዳጄ ጥያቄ የአበበ ገላው በፕሬዚደንት ኦባማ ፊት የኢትዮጵያውያንን የነፃነት ጩኸት ማስተጋባት በኔ በኢትዮጵያ ምድር የምኖር ዜጋ ላይ ስለሚኖረው አንደምታ በጥልቅ እንዳስብ አደረገኝ፡፡

ዜጎች ሐሳባቸውን በነጻነት መግለጽ በማይችሉባት ሐገር፤ ይልቁንም “ለዚህ ሥርዓት ጥሩ አመለካከት የለህም፣ የወጣት ሊግ፣ የሴቶች ፎረም፣ የነዋሪዎች ፎረም ወዘተ በተሰኙ የስርዓቱ አደረጃጀቶች አልተሳተፍክም” በሚል – መገለል፤ ባስ ሲልም መዋከብና ከስራ መፈናቀል በሚደርስበት ሐገር የማስበውን የሚተነፍስልኝ፣ አንደበት የሚሆንልኝ ሳገኝ ብደሰት፣ ባሞግሰው – ጀግና ብለው ምን ይገርማል? የህዝቡን ይሁንታ አግኝቼ ተመርጫለሁ፣ ኮንትራት ተሰጥቶኛል ወዘተ የሚል ማመካኛ እየደረደረ በምከፍለው ግብር የሚተዳደሩ የህዝብ ንብረት የሆኑ ሚዲያዎችን ወደራሱ የግል ንብረትነት አዛውሮ ጠዋት ማታ ሳልጠግብ – ጠግበሃል፣ በሥራ አጥነት እየተንከራተትኩ – ሥራ በሽ በሽ አድርጌልሃለሁ፣ የኑሮ ውድነቱ አጉብጦኝ – ኑሮህ ተሻሽሏል እያለ የራሱን ሹማምንት ምቾት የኔ እንደሆነ አድርጎ ለኔው የሚለፍፍ ስርዓት ባለበት ሐገር የነጻነት ጥማቴን የሚናገርልኝን አበበን ባወድሰው የሚያስገርመው ምኑ ነው?

በአምቦ፣ ሐሮማያ፣ አፋር፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ተምቤን፣ ጎንደር ወዘተ በወንድም እሕቶቼ፣ በእናት አባቶቼ ላይ የሚደርሰውን አፈና፣ ግርፋት፣ ከመኖሪያ ማፈናቀል፣ ግድያ፣ አላግባብ ከስራ ማባረር ወዘተ ሳወግዝ “የ… ከተማ ነዋሪዎች መንግስት የወሰደውን እርምጃ አደነቁ… ከግድያው የተረፉትም አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠየቁ” እየተባለ በስርአቱ የፕሮፖጋንዳ አንደበቶች ጩኸቴን ስቀማ – ያልኩት ቀርቶ ለመንግስት ጆሮ የሚጥመው በኔ ስም ሲነገር – አበበ ትክክለኛውን ጩኸቴን ሲጮህልኝ እልል ብል፣ ትክክለኛ ብሶቴን ለአደባባይ ሲያበቃልኝ አበጀህ ብለው ተሳሳትክ የሚለኝ ማነው?

በሐገር ውስጥ በመሆን ስርዓቱ ያሰፈነውን የፍርሐት ቆፈን ወግድ ብለው በብዕራቸው ብሶቴን የተነፈሱልኝን፣ ጩኸቴን የጮሁልኝን ተቃዋሚዎች፣ በጋዜጠኝነት ሙያቸው አገዛዙ ያመጣብኝን የመረጃ ረሐብ ሊያስታግሱልኝ የሞከሩ ጋዜጠኞችንና ጦማሪያንን ሰብስቦ በፈጠራ ክስ በእስር ሲያጉራቸው አሰፈንኩት ብሎ ያሰበውን የህዝብ ድምጽ እርጭታ በነጎድጓዳማ ድምፁ የሰበረልኝን – ስርዓቱ ለሚዘጋው እያንዳንዱ በር በአንጻሩ በትግል የሚከፈት ሌላ በር እንደሚኖር በተግባር ያረጋገጠልኝን አበበን አበጀህ የኔ አንደበት ብለው ወዴት ላይ ነው ጥፋቴ?

“የዋህ ነህ – የአበበ ገላው ድምጹን ማሰማት ስርዓቱን አያፈርሰውም፣ ኦባማ በስርዓቱ ላይ ማዕቀብ እንዲጥል፣ በአደባባይ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል እንዲያወግዝ አያደርገውም” ይሉኛል፡፡ እኔስ እሱን መች ጠበቅኩና? ለተበዳይ በደሉ መሰማቱ በራሱ የድሉ መጀመሪያ መሆኑን አታውቁም? ለታፈነ ሰው ጩኸቱ ለአደባባይ መብቃቱ፣ በደሉ ለጆሮ መድረሱ በራሱ ስኬት ነው፡፡ እንጂማ ጀርባዬ ላይ ሆኖ የሚያጎብጠኝን፣ እንደ እንስሳ ስለ ሆዴ እንጂ ስለ ነጻነቴ እንዳልጠይቅ የሚያስፈራራኝን፣ ስራ፣ የመኖሪያ ቤት ወዘተ በጥረቴ ሳይሆን ለስርዓቱ ባጎበደድኩት መጠን የማገኘው ድርጎ ያደረገብኝን ስርዓት ወግድልኝ ብሎ የማሽቀንጠሩ ኃላፊነት የኦባማ ሳይሆን የኔ መሆኑን መቼ አጣሁት? ገዢዎቼ የወንበር ስስት፣ የስልጣን ስጋት ስላለባቸው የአቤን ድርጊት ከወንበራቸው ከመነቅነቅ አንጻር ሊመዝኑት ይፈልጋሉ፡፡ የኔ መስፈሪያ ሌላ ነው፡፡ የማይወክለኝን ከወንበሩ የመነቅነቁ፣ ከምርጫ ኮሮጆ በመጣ የዜጎች ይሁንታ ሳይሆን ከሩስያ በመጣ የኤኬ 47 ጠመንጃ ጉልበት መንግስትነትን የያዘውን ስርአት የማንኮታኮቱ የቤት ሥራማ የኦባማ አስተዳደር ሳይሆን የኛ የኢትዮጵያውያን የመሆኑን ሐቅ መቼ ሳትኩት?

ደግሞስ እውነትን በሐይል ለስልጣን መናገር ያለውን ጉልበት መቼ አጣችሁት? ይኸው አበበ አይደል እንዴ በሐገር ውስጥ በጠመንጃና በእስር ቤት ሐይል፣ በውጪ ሐገር በብልጣ ብልጥነት ሸፋፍነው ይዘውት የነበሩትን የአምባገነንነት ማንነት በአለም አደባባይ እርቃኑን አስቀርቶ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ለክውታ (ምናልባትም ለህልፈት)፣ የስርአቱን ቲፎዞዎችም ለከፍተኛ ብስጭት የዳረገው? ትግሉ ፈርጀ ብዙ መሆኑን አትርሱ እንጂ፡፡ የቀድሞው መሪ ድምጻችን ይከበር ብለው ወረቀት ይዘው አደባባይ የወጡ ወንድሞቻችንን ግንባር በአልሞ ተኳሾቻቸው አስነድለው መቼ ዝም አሉ? “ባንክ ሊዘርፉ ሲሉ ተገደሉ” ብለው በወጣቶቹ ወላጆች ላይ የስነ ልቦና ጦርነት አልከፈቱም? ይህን ግፍ ያዩ ብዙዎች በኢትዮጵያ ሰማይ የእውነትና የፍትሕ ፀሐይ መቼም አትወጣም ብለው ተስፋ እንዲቆርጡ አልደረጉም? ስለዚህ የአበበ ድርጊትም አፋኞቻችንን – “እውነት ታፍና መቼም አትቀርም፤ ጠመንጃም የእውነትን ወሊድ ያዘገየው ይሆናል እንጂ እስከወዲያኛው አያስቀረውም” የሚለውን ሃቅ በአእምሯቸው እንዲያቃጭል ማድረጉ በራሱ ድል አይደለም? ይልቁንም ክስተቱ የተፈፀመው የስርአቱ ጥቅመኞች ቀድሞ በአካል፣ ሞተውም በ”ራዕይ” የሚመሯቸውን ግለሰብ ልደት ለማክበር ተፍ ተፍ ሲሉበት በነበረው ወቅት መሆኑ በስርአቱ ደጋፊዎች ላይ የፈጠረውን የስነ ልቦና ጉዳት እስኪ ወደ ማህበራዊ ድረ-ገፆች ጎራ በሉና ታዘቡ!

“አበበ አንድ ግለሰብ ነው… ጩኸቱም ምንም ለውጥ አያመጣም” ይላሉ፡፡ እንዴ… የነፃነት መንፈስ እኮ ሁሌም ሲጀመር በአንድ ወይም በጥቂት ሰዎች ነው፡፡ ደግነቱ ግን ቶሎ ይዛመታል፡፡ ውቂያኖስ ሳይገታው፣ ፖለቲካዊ ድንበሮች ሳያስቆሙት፣ የመረጃ አፈና ሳያግደው ወደሺዎች ከዚያም ወደ ሚሊዮኖች ይጋባል፡፡ ምርጫ 1997ን ማስታወስ ይቻላል፡፡ ጥቂቶች የነፃነት መንፈስን ከታሰረበት ፈተው ለቀቁት፡፡ በወራት ጊዜ ውስጥ ከገጠር እስከ ከተማ – ከድሐ ጎጆ እስከ ቤተ መንግስት ተቆጣጠረው፡፡ ዛሬም በአበበ ገላው የተለኮሰው የነጻነት ችቦ የነጻነት እጦት ብርድ ሆኖ ያንዘፈዘፈንን በሙቀቱ ሲያፍታታን፤ የአምባገነንነት ትኩሳት ጭንቅላታቸው ላይ የወጣውን ገዢዎቻችንን ነበልባል ሆኖ ሲፈጃቸው መመልከታችን አይቀሬ ነው፡፡

እናም … እናም… እናም… በወንድሜ አበበ ገላው ሥራ ደስ ተሰኝቻለሁ – ተነቃቅቻለሁ – ተስፋንም ሰንቄያለሁ፡፡ ነገ ይህ የነፃነት ስሜት በአእላፋት ላይ ተጋብቶ ገዢዎቻችንን በየሔዱበት ሲያስጨንቅ፣ አንገት ሲያስደፋ፣ ሲያብረከርክና ሲያፍረከርክ አሻግሬ እያየሁ…

 

የእስረኛው ‹‹ጋዜጠኝነት›› ሌላ ፈተና –በጽዮን ግርማ

$
0
0

tsiongir@gmail.com
(ፋክት መጽሔት ላይ የታተመ)

የ2012ቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳታዊ ምርጫ ከመከናወኑ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ስለምርጫውና የአሜሪካ የጋዜጠኝነት ኹናቴ እንዲወያዩ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አዳራሽ ከተጋበዙና ከሰማንያ የዓለም አገሮች ከተውጣጡ አንድ መቶ ሠላሣ ተሳታፊ ጋዜጠኞች መካከል አንዷ ነበርኹ፡፡ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ከተጋበዙ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጠኞች መካከል ታዋቂው የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ ቦብ ውድዋርድ አንዱ ነበር፡፡
zone 9999
ቦብ በስቴት ዲፓርትመንት ሕንፃ አዳራሽ ከሌላ አገር ለመጡ ጋዜጠኞች፤ በምርመራ ጋዜጠኝነት ሥር አጨቃጫቂና አንገብጋቢ ጉዳዮችን ሲዘግቡ በአሜሪካ መንግሥት የሚያጋጥማቸውን ፈተና እየዘረዘረ፣ ዓለም የሚደነቅበትን የአገሩን የመናገርና የመጻፍ ነፃነትና ‹ዴሞክራሲያዊ› የምርጫ ሂደት የፕሬዝዳንት ኦባማን ስም ሳይቀር በስም እየጠቀሰ በሒስ ሲሰልቀው ከፍርሃት ነፃ በኾነ ከፍተኛ የራስ መተማመን መንፈስ ተሞልቶ ነበር፡፡

በወቅቱ የስቴት ዲፓርትመንት ከፍተኛ ባለሥልጣናት “The price of politics” የሚለውን ባለሠላሳ ዶላር መጽሐፉን ፈርሞ በቦታው ለተገኘነው ጋዜጠኞች በስጦታ እንዳበረከተልን ተናግረው ሲያስጨበጭቡን ቦብ በስጨት ብሎ በማቋረጥ፣ ‹‹መጽሐፌን ለማንም በነፃ አልሰጠኹም፤ ስቴት ዲፓርትመንቱ ነው ገዝቶ የሰጣችኹ›› በማለት ሲያሸማቅቃቸው በፈገግታ ነበር ያለፉት፡፡ እንግዲህ የዓለም ጋዜጠኞች በተሰበሰቡበት በኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዳራሽ አንድ አንጋፋ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ መሪውንና ሥርዓቱን ሲተች በምናብ ማየት ነው!!

ውይይቱ ሲያበቃም ለጋዜጠኛው ክብር ሲባል በየቡድናችን እየተጠራን ባለበት ሔደን የማስታወሻ ፎቶ እንድንነሣ ስንጋበዝ ባለሥልጣናቱ ለጋዜጠኛው ያላቸው ክብር በግልጽ ይታይ ነበር፡፡ ሞጋች ጋዜጠኞች ከሚሰደዱበት፣ ከሚታሰሩበት አልያም በፍራቻ ሥራ ከሚያቆሙበት ወይም ከፍ ዝቅ ተደርገው እየተመናጨቁ መረጃ ከሚከለከሉበት፣ ከፖለቲካዊና ገዢዎችን ከሚነካ ዘገባ ይልቅ ወደ ማኅበራዊና መዝናኛ ጉዳዮች እንዲያተኩሩ በእጅ አዙር ከሚገደድበት አገር ለሔደች ለእንደኔ ዓይነቷ ጋዜጠኛ የስቴት ዲፓርትመንቱ ባለሥልጣናት ለአንጋፋው የዋሽንግትን ፖስት ጋዜጠኛ ቦብ ውድዋርድ የቸሩት አክብሮት ቢያስደምመኝም የጋዜጠኝነት ሞያ እንዲያ ተከብሮ የሚያስከብር መኾኑን አላጣኹትም ነበር፡፡

ጋዜጠኝነት እንደሞያ እጅግ የተከበረ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት በአቀራረቡ ባለብዙ መልክ ቢኾንም የብልሹ አስተዳደርና አሠራር ችግሮችን ነቅሶ ለማውጣት፣ ከሕዝብ የተሰወሩ በደሎችን ለማጋለጥ፣ ከሕግና ሥርዓት ውጭ የኾኑ ባለሥልጣናትን በዐደባባይ ለመተቸትና ለማጋለጥ፣ ለሕዝብ ዋስ ጠበቃ በመኾን የሚያገለግል በተለምዶ አጠራር ‹አራተኛ መንግሥት› ነው፡፡

ከሚዛናዊነት፣ እውነትና ፍትሕ ጋር የሚሠራ “ሞያዊ ጋዜጠኛነት” (Professional journalism) ለዴሞክራሲዊ አስተሳሰብና ተግባር ዋናው አንቀሳቃሽ ሞተር ነው፡፡ ከፍርሃትና ስጋት የተጠበቀ፣ ከተገዢነትና አገልጋይነት የጸዳ ጋዜጠኝነት የሚወደድ ሞያ ነው፡፡ ሞያዊ ጋዜጠኝነት አገልጋይነቱ በቀጥታ ለሕዝብ ስለኾነ ኹሌም ለውጥ በማምጣት ሒደት ውስጥ ዋና ተሳታፊ ነው፡፡ ሞያው ነጻ በወጣባቸው አገሮችም ልክ እንደ ቦብ ውድዋርድ ተከብረው የሚያስከብሩ ጋዜጠኞች ይፈጠራሉ፡፡

በጋዜጠኝነት ሞያ የኢትዮጵያን ነባራዊ ኹኔታ ብናይ፤በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በአገሪቱ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንደተከበረ በተለያየ መንገድ ያውጃል፡፡ መልሶ ደግሞ ይህን መብት ገደብ አልባ በኾኑ የተለያዩ መንገዶች ሲያፍነውና ሲጨቁነው ይታያል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው አሠራር በተለይ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው ነጻነት ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ወድቋል፡፡ ለግል የተፈቀዱት ከአንድ እጅ ጣቶች የማያልፉ ሬዲዮ ጣቢያዎችም ቢኾኑ ነፃነታቸው የተረጋገጠው በመዝናኛ ዝግጅቶችና በጥቂት የማኅበራዊ ጉዳይ ዘገባዎች ብቻ ነው፡፡ የኅትመት ብዙኃን መገናኛን በሚመለከትም በርካታ ጋዜጣና መጽሔቶች በየወቅቱ ቢታዩም በተለያየ ምክንያት ስለሚቋረጡ በገበያው ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆዩት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

እስረኛው ‹‹ጋዜጠኝነት›› በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ውስጥ የጋዜጠኝነት ሞያ በራሱ ነፃ ያልወጣ እስረኛ ነው፡፡ በገዢው ግንባር ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ብዙኃን መገናኛዎች በመንግሥት ጥቅም ልክ የሚሠሩና ድጋፍ ብቻ የሚሰጡበት ‹‹ጋዜጠኝነት›› ነው፡፡ ከግንባሩ አስተሳሰብና አሠራር የሚነጨው ይኸው የሞያው እስረኝነት ላለፉት ኻያ ሦስት ዓመታት ሲሠራበት የቆየ ነውና አያጠያይቅም፡፡ በግለሰብ ባለቤትነት በሚመሩ የኅትመት ብዙኃን መገናኛዎችና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተጀመረው የዲጂታል ሚዲያ ላይ ተግባራዊ የሚደረገው ጋዜጠኝነትም በበርካታ ተጽዕኖች ሥር የወደቀ ጋዜጠኝነት ነው፡፡ በተለይ ከምርጫ 97 ጀምሮ ጠንካራ ክንድ ተጭኖ ይዞታል፡፡

የመንግሥት ባለሥልጣናት በሚሰጧቸው መግለጫዎች ጋዜጠኛውን የሚያንቋሽሹ ቃላትን በመጠቀም በግል ብዙኃን መገናኛ ላይ የሚሠሩ ጋዜጠኞች አገሪቷን ወደተሳሳተ መንገድ የሚመሩ አጥፊዎች አድርጎ መሣል የተለመደ ነው፡፡ የወንጀል ሕጉ ውስጥ ጋዜጠኛን በሚመለከት የተካተቱት አንቀጾች፣ የመገናኛ ብዙኃን ዐዋጅና የፀረ ሽብር ዐዋጁ ጋዜጠኝነትን አስረው የሚያስቀምጡ መቆጣጠሪያ መሣሪያዎች ናቸው፡፡

በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ባሉ የኤሌክትሮኒክስና የኅትመት ሚዲያ አማካይነት በየዕለቱ በጋዜጠኞች ላይ የወቀሳ ናዳ በማውረድ ሞያው ነፃነቱን እንዲያጣ ያደርጉታል፡፡ በመንግሥት ብዙኃን መገናኛዎች ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች የነፃነታቸው ጉዳይ ሳያሳስባቸው በግል የሚሠሩ ጋዜጠኞችን የሚያንኳስስ ተደጋጋሚ ዘገባ ማቅረብን ለአለቆቻቸው እንደ እጅ መንሻ ይጠቀሙበታል፡፡

በኾነው ባልኾነው ጋዜጠኞችን እየጠሩ ማስፈራራት፣ መክሠሥና ማሰር ሞያውን የበለጠ እንዲኮሰምን ያደርገዋል፡፡ መተቸትን አብዝቶ የሚጠላው መንግሥት በአገዛዙና በሥርዓቱ ላይ ጠንካራ ትችት የሚያቀርቡ ጋዜጠኞች ሲወጡ ‹‹ከጀርባቸው እገሌ የሚባል አሸባሪ ድርጅት አለ›› ወይም ደግሞ ‹‹እገሌ ከሚባል አገሪቱን ለማተራመስ ከሚሠራ አካል ላይ ገንዘብ ተቀብለዋል›› በሚል ፈርጆ ሞያውን አስሮ ያስቀምጠዋል፡፡ ለመረጃ ነፃነትና ለጋዜጠኝነት ሞያ ድጋፍ በመስጠት ከማሳደግ ይልቅ ገና ብቅ ሳይል አናት አናቱን በማለት እዛው ያስቀረዋል፡፡

በሌላ በኩል የመንግሥት ተፎካካሪ የኾኑ የተቃዋሚ ፓርቲ ድርጅቶችም ምንም እንኳን ራሳቸው በበርካታ የመንግሥት ጫና ሥር የሚገኙ ቢኾኑም ትችት የሚያቀርብባቸውን ጋዜጠኛ ላይ ተጽዕኖ ለማሳረፍ አይሰንፉም፡፡ እነርሱን የሚተች ጋዜጠኛ ቅጥያ ይለጠፍበትና የመንግሥት ደጋፊ ተደርጎ ይፈረጃል፡፡ በተለይ እርስ በርስ ስምምነት በሚያጡበት ጊዜ ኹሉም ጋዜጠኛውን ወደ ራሳቸው ጎራ ለመጎተት ይሞክራሉ፡፡ እንቢተኝነትን ያሳየ ወይም ደግሞ ድርጊቱን የተቃወመ ጋዜጠኛ ስሙ ከአንዱ ድርጅት ወይም ግለሰብ ጋር ተዳብሎ ሞያዊ ክብሩን ይገፈፋል፡፡

ጥቂት በማይባሉ አንባብያን ዘንድ ደግሞ ጋዜጠኛው ያቀረበውን መረጃ ትክክለኛነት በሒደት መዝኖ እውነቱን ከማወቅ ይልቅ ፍረጃውን ተከትሎ አብሮ የመዝመም ዝንባሌ ይታያል፡፡ በፍረጃ ፍዳውን ባየ ጋዜጠኛ ላይ ውግዘት ይጨምርበታል፡፡ የማንበብ ፍላጎቱም የሚዘልቀውም የኾነውን የተፈጠረውን ሳይኾን እርሱ እንዲኾን የሚፈልገውን ብቻ ነው፡፡ ጉዳያቸው ብዙኃን መገናኛ ላይ ለመቅረብ ብቁ የኾነም ያልኾነም ግለሰቦች፣ የንግድ ተቋማት፣ አርቲስቶችና ሌሎች አካላትም የሚጻፉት ነገሮች ኹሉ በእነርሱ ፍላጎት ልክ እንዲኾን ይወተውታሉ፡፡ ከፍላጎታቸው ውጭ ከተጻፈና ከተዘገበ ደግሞ ከቻሉ መክሰስ ካልኾነ ደግሞ ጋዜጠኛውን ማንቋሸሽና ጠልፎ ለመጣል ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ ምንም እንኳን ሕትመቱ ከመውጣቱ በፊት ቅድመ ምርመራ (censorship) ባይኖርም ከማቀድና ከመጻፍ በፊት ጋዜጠኛው በግሉ ፤የራስ በራስ ምርመራ (self censorship) በማድረግ የሞያውን ነጻነት አሳልፎ ይሰጣል፡፡

ሞያው ነጻነት ባጣ ቁጥር ዕድገቱ እየኮሰመነ ስለሚሄድ የሞያው ተፈላጊነት ይቀንሳል፡፡ በዕውቀትና በክህሎት ብቁ የኾኑ አብዛኞቹ ባለሞዎች ሥራቸውን ይቀይራሉ አሊያም አገር ጥለው ይሰደዳሉ፡፡ ዕለት ከዕለት ሞያውን የሚቀላቀሉት ባለሞያዎችም ብቃት አነስተኛ ስለኾነ ቁንጽል የሆኑ የጋዜጠኝነት መርሆዎችን ብቻ አንጠልጥለው በመያዝ ሞያውን የበለጠ ያዘቅጡታል፡፡ እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ሞያውን በተቀላቀሉ ቁጥር ገዢው ፓርቲ ይደሰታል፡፡ የጋዜጠኝነት መርሕ ተጥሶ ዘገባ ሲቀርብ የመናገርና የመጻፍ ነፃነት መብት በአገሪቱ ላይ መከበሩንና ጋዜጠኞቹ ግን ይህን መብት እንዴት እየተጠቀሙበት እንደኾነ ለዓለም ሕዝብ ለማሳያነት ይጠቀምበታል፡፡

በጋዜጠኝነት ዘርፍ ወደ ተለያየ የዓለም አገራት ተጉዘው ትምሕርት ቀስመው የመጡ ምሑራንም ስለ ጋዜጠኝነት ሞያ አስተያየት ሲጠየቁ ችግሩ ከሥሩ መርምረው ሞያው ነፃነት ያጣበትን ምክንያት ከእነ መፍትሔው በማስቀመጥ ለመቀየር ከመሞከር ይልቅ በነፃነት ዕጦት በኮሰመነው የግል ብዙኃን መገናኛ የሕትመት ውጤትና ጋዜጠኝነት ላይ ውርጅብኝ ያወርዱበታል፡፡ በከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት የጋዜጠኝነትና ሥነ ጹሑፍ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ሳይቀሩ በአብዛኛው ለመመረቂያ ጹሑፋቸው የሚመርጡት ርእስና የሚሠሩት ጥናት የጋዜጠኝነትን ነፃነት የበለጠ የሚያሳጣ ነው፡፡
እነዚህ ኹሉ ችግሮች ተደማምረው ሞያውን አክስመውታል፡፡ አኹን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጋዜጠኝነት ከእስር፣ከስደት፣ከፍረጃ፣ከፍርኃት የተረፈ ‹‹እስረኛ›› ጋዜጠኝነት ነው፡፡ ጋዜጠኝነት በአብዛኛው የራስ በራስ ቅድመ ምርመራ ራሱን ጠፍንጎ ባሰረ ባለሞያና ለሞያው የጠለቀ ዕውቀት በሌላቸው ሰዎች የመጨረሻ እስትንፋስ እየተንገታገተ ያለ ሞያ ነው፡፡ በመንግሥት በኩል ደግሞ ይቺኑ ትንሽ እስትፋስ እስከ መጨረሻው ለማጥፋት በሚደረገው ጫና ያሉት ጋዜጠኞች ሞያው የሚጠብቅባቸውን መረጃን ለሕዝብ የማስተላፍ ሥራን ከመሥራት ይልቅ ራስን ወደ መከላከል ሥራ ተሸጋግረዋል፡፡ በተለይ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ ያሉት ጋዜጦችና መጽሔቶች የፊት ገጽ ሽፋንና የድረ ገፆች ዋና መነጋገሪያ ርእስ ጋዜጠኞች ላይ የሚደረግ እስርና ጫና ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ የማዳከሚያ ስልት ሊኾን ይችላል፡፡

በየአራት ዓመቱ በሚካሄደውና ለሦስተኛ ጊዜ በተደረገው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት መድረክ ላይ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ተሳታፊ ኾና ቀርባ ነበር፡፡ ስብሰባው የሚደረገው በ197 የዓለም አገሮች መካከል ሲኾን ሲኾን አገራቱ የሰብዓዊ መብት አያያዛቸውን በሚመለከት ሪፖርት የሚያቀርቡበት እንዲኹም የሚቀርብባቸውን ወቀሳና ትችት አዳምጠው የሚያሳሽሉትን ‹‹አሻሽላለሁ›› የሚሉበት ያልተስማሙበትን ደግሞ ያልተስማሙበትን ምክንያት የሚያስረዱበት ስብሰባ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በዚህ ስብሰባ ላይ በ2010 ላይ ስትሳተፍ የመጀመሪያዋ ቢኾንመ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን በሚመለከት 159 ጉዳዮችን እንድታሻሽል ተነግሯት ዘጠኛ ዘጠኙን መቀበሏን ስልሳውን ግን እንደማትቀበለው ተናግራ ነበር፡፡ስብሰባው በቀጥታ ከጄኔቭ በቴሌ ኮንፍረንስ የተመራ ሲኾን እያንዳንዱ አገራት ከሚገኙበት አገር ኾነው በስብሰባው እንደተሳተፉት ኹሉ ማክሰኞ ዕለት በተደረገውና ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በተሳተፈችበት በዚህ የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ የተመራና ከአምስት በላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ምክትል ሚኒስትሮችን የያዘ ቡድን አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ጽ/ቤት ተገኝተቶ በውይይቱ ተሳትፎ ነበር፡፡

በልኡካን ቡድኑ አማካኝነት የኢትዮጵያ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ፤ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ፣ የበጎ አድራጎትና ማኅበራት ዐዋጅን በተለመከተና የፀረ ሽብር ሕጉን በሚመለከት በከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟታል፡፡ በስብሰባው ላይ የተሳተፉት አብዛኛው አገራት ኢትዮጵያ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ኢትዮጵያ የፀረ ሽብር ሕጉን የመናገርና የመጻፍ ነፃነትን እንዲሁም የፖለቲካን ተቃውሞ ለማፈን እየተጠቀመችበት ስለኾነ ሕጉን እንድታሻሽልና ሕጉም ሲሻሻል የፖለቲካ ተቃውሞን ለማፈን እንዳትጠቀምበት ዋስትና የሚሰጥ መኾን እንዳለበት በመግለጽ ጠንካራ ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል፡፡
የልኡካን ቡድኑ አባል የነበሩት የኮሚዩኒኬሽን ምክትል ሚኒስትሩ አቶ ሽመልስ ከማል በአገራቱ የቀረበውን ወቀሳ አጣጥለው፤ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብር ሕጉ ሰበብ ተደርጎ የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ እንደሌለ ጠንከር አድርው በመናገር የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ ተይዘው የታሠሩና ከዚህ ቀደም በጋዜጠኝነት ሥራ ላይ ይሠሩ ነበር የሚባሉ እስረኞች ቢኖሩ እንኳን የታሰሩት ከጋዜጠኝነት ሞያቸው ጋር በተያያዘ ሳይኾን በፈጸሙት የሽብር ወንጀል መኾኑን አበክረው ተናግረዋል፡፡

አቶ ሽመልስ እንዲህ ያለ መከራከሪያ ሲያቀርቡ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አገር ውስጥ ያሉም የውጭ ጋዜጠኞች ሲጠይቋቸውም ይህንኑ ነው የሚመልሱት፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሪፖርት ሲያወጡም የሚመልሱት ይህኑ ነው፡፡ አሁን ደግሞ የዓለም አገራት ተሰባስበው ኢትዮጵያ የመናገርና የመጻፍ ነፃነት አፈናን እንድታቆም፣በፖሊስ፣በመከላከያና በደህንንት ሰዎች የሚፈጸመው ‹‹ቶርቸር›› እንዲቆም ፀረ ሽብር ሕጉን ጋዜጠኞችን ለማሠር እንዳትጠቀምበት የዓለም አገራት ተሰባስበው ቢመክሩም የአቶ ሽመልስ ከማል ምላሽ ተመሳሳይ ኾኗል፡፡ በርካታ ችግሮችን ተቋቁሞ የሚውተረተረው የእስረኛው ‹‹ጋዜጠኝነት›› ትልቁ ፈታናም እዚህ ጋር ኾኗል፡፡ ጋዜጠኛ ይታሰራል ሲታሰር ደግሞ ‹‹በጻፈው ጹሑፍ ሳይኾን በሽብር ተግባር ላይ ስለተሳተፈ ነው›› የሚል ታፔላ ይለጠፍለታል፡፡ ይህ ደግሞ ሞያውን የበለጠ ችግር ውስጥ ይዘፍቀዋል፡፡ የ‹‹እስረኛው›› ጋዜጠኝነት ሌላ ፈተና ማብቂያ እንደተባለው ኢትዮጵያ የፀረ ሽብር ሕጉን፣ የመናገርና የመጻፍ ነፃነትን እንዲሁም የፖለቲካን ተቃውሞ ለማፈን እየተጠቀመችበት ነው በሚል እየተወቀሰችበት ያለውን ሕግ ስታሻሻል ይኾን?

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>