Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም

ሚያዝያ 2006

mesfin n

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።

የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።

ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፤ ስለዚህ ያስፈራል፤ በደቡብ ሱዳን ሁለት መቶ ሰዎች በዘር ተለይተው ታረዱ ሲባል ያስፈራል፤ በናይጂርያ፣ በኮንጎ የሚካሄደውን የዘርና የሃይማኖት እልቂት ስንሰማ ያስፈራል፤ በ1997 ዓ.ም. መለስ ዜናዊና አዲሱ ለገሰ እንዳስታወሱን የሩዋንዳ የጎሣ እልቂት በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ አለ፤ የቅርብ ተኳሽ የሆነው የአግዓዚ ጦርም አድፍጦ መጠበቅ ያስፈራል፤ ሌላውም ይህንን አውቆ አድፍጦ መጠበቁ ያስፈራል፤ ሰማይ ጠቀስ የሠሩት፣ የሥልጣን ኃላፊነትን ችላ ብለው በሥልጣን የሚነግዱና የሚከብሩት፣ የማይኖሩበትን ሕንጻ የሚክቡት፣ ከሕዝብ ጋር ያላቸው የአይጥና የድመት ኑሮ ያስፈራል፤ አቶ አስገደ ወያኔ መደንገጡን ይነግረናል፤ መደንገጥ የማይቆጣጠሩት ፍርሃት ነውና አደጋ ያመጣል፤ አደጋው አደጋን ይጠራል፤ ይህም ያስፈራል።

በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው? የትግራይ ሕዝብ በየትኛው አቅጣጫ ነው አንደልቡ እየተዘዋወረ ለመሥራትና ለመኖር የሚችለው? ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤ በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው።

ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ጥላቻ ወደንዴት፣ ንዴት ወደቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደአውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።

ሌላ አገር እንዲህ አልሆነም፤ እዚያ አገር እንዲህ አልሆነም፤ የሚባል ነገር የለም፤ እኛ ዘንድ ሌላ ነው፤ የኢትዮጵያ ደሀዎች እንባ የእግዚአብሔርን ሰማይ አጨቀየው!

ክፋት እንደእሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደዓምድ ይወጣል፤ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቁጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም፤ ሰው በቀኙ በኩል ይነቅላል፤ ይራብማል፤ በግራም በኩል ይበላል፤ አይጠግብምም፤ እያንዳንዱም የክንዱን ሥጋ ይበላል፤ ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤… ኢሳይያስ 9/18-21

ትንቢተ ኢሳይያስ ለሩዋንዳውያን ብቻ አይደለም፤ ጥላቻና ክፋት በተዘራበት ቦታ ሁሉ ውጤቱ ጥፋት ነው፤ ምናሴ ኤፍሬምን በልቶ አይቀርም፤ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላዋል።


15 Health Benefits of Eating Apples (Amharic Video)

$
0
0


What makes apples so great?

In 2004, USDA scientists investigated over 100 foods to measure their antioxidant concentration per serving size. Two apples—Red Delicious and Granny Smith—ranked 12th and 13th respectively. Antioxidants are disease-fighting compounds. Scientists believe these compounds help prevent and repair oxidation damage that happens during normal cell activity. Apples are also full of a fibre called pectin—a medium-sized apple contains about 4 grams of fibre. Pectin is classed as a soluble, fermentable and viscous fibre, a combination that gives it a huge list of health benefits.
15 Health Benefits of Eating Apples (Amharic Video)

ዓባይ እንደዋዛ–“ኢትዮጵያ ሃገሬ ናት፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ ነው” ክፍል ሶስት (ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

$
0
0

 

ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

ክፍል ሁለት ዓባይና ኢትዮጵያ አንድና የተያያዙ መሆናቸውን ያሳያል። አንድና የተያያዙ ናቸው የሚለውን ሃሳብ ከተቀበልን ዓባይ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እስካገለገለና ኑሮውን እስካሻሻለ ድረስ የኢትዮጵያን ይገባኛልነትና የሚሰሩ መሰረተ ልማቶች መቀበል የኢትዮጵያውያን ግዴታ ነው። ዓባይ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥሪት መሆኑን አምናለሁ። ጎሳዊ ወይንም ክልላዊ ሃብት አይደለም። ስለሆነም፤ ዓባይን የምንታደገው “ኢትዮጵያ ሃገሬ ናት፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ ነው”–-[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—

ጥሩ የመንፈስ ፍላጎትን አድምጭነት –ልዩ መክሊት ነው –ለእኔ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 12.04.05 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

ዛሬ እንዲህ ወደ ሀገረ አሜሪካ ጉዞ አማረኝ። ስለምን? የንግግር ሥነ – ጥበብ ህግጋት መከበሩ መንፈሴን ስለገዛው።

Commentሥነ – ንግግር ጸጋ ነው። ሥነ – ንግግር ሙያም ነው፤ ሥነ – ንግግር ሁለት መንትያ ልጆች አሉት። እንደ ቤተሰብ የሚያቸውም የቅር ሥጋዎቹ አሉት። ሥጋዎቹን በቀጠሮ ልተውና የሥነ – ንግግር ባላና ወጋግራ የሆነው ጉልቻው ያፈራቸውን ልጆች እስኪ በጥቂቱ እንይ። የመጀመሪያ ልጁ „ተናጋሪ“ ይባላል። ሁለተኛ ልጁ ደግሞ „አድማጭ“ ይባላል። ሁለቱም እንደ ጸጋነታቸው በክህሎት ሊዳብሩ፤ በሥልጠና ክህሎታቸው ጥንግ ድርብ የሆነ ብቃትን ሊጎናጸፉ ይችላሉ። ሁለቱንም የተሰጣቸው ፍጡራን የታደሉ ናቸው። ወይንም አንዱን ብቻም የተሰጣቸው ግማሽ እድለኞችም ሊኖሩ ይችላሉ። በሌላ በኩል አንዱ ደመቅ ብሎ ዘለግ ሌላው ደግሞ ዝቅ ያለ ሁነትም ይገጥማል። ይህ በሂሳብ ስሌት ሩቦ የጎደለው ወይንም ሦስት አራተኛው የተሟላ እንደ ማለት፤ ወይንም ሶስቱ እጅ እንደማለት …..

 

የሥነ ንግግር ጥበብና ዕድገት ዝርዝር ሁነቶች፣ የአንድን ጥሩ ተናጋሪ መስፈርቶችን በሚመለከት 8ኛ መጸሐፌ ላይ ከተገናኘን መጠንኛ ግንዝቤ ለማስገንዘብ ትንሽ ነገር ብያለሁ። ስለዚህ ዘርዝር ያሉትን ነገሮች ገታ አድርጌ አሁን ወደ ተነሳሁበት መሰረተ ሃሳብ ስንሄድ፤ እንደ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሩ ተናጋሪም፤ ጥሩ አድማጭም መሆኑን  አሁን ለተነሳሁበት መሰረታዊ ጭብጥ ይመቸዋል። በነፍስ ወከፍ ስመጣ በሥነ ንግግር ህግጋት መስፈርቱን ያማሉ አብሶ አድማጭነት ቁሞ በእግሩ ሲሄድ ያዬሁት በጓድ ገ/መድህን በርጋ ነበር። ጓድ ገ/መድህን በርጋ የሀገር ውስጥ ንግድ ሚ/ር ቋሚ ተጠሪ፤ የጎንደር ክ/ሀገር ኢሠፓ ኮሜቴ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፤ በኋላም የሚዛን ተፈሪ ክ/ ሀገር የኢሠፓ ኮሜቴ ተጠሪ የነበሩ ናቸው። የጓድ ገ/መድህን ጥሩ ተናጋሪነታቸው ንጥርነት የመነጨውም ቃላቶች ቢደረደሩ ሊገለጸው ከማይቸለው የምድመጥ ወደር የለሽ መክሊታቸው ነበር። የጓድ ገ/መድህንን የማድመጥ ሥነ ውበትን ለመተንተን ብዕሬ አቅም ፈጽሞ የላትም። የሥነ ንግግር ሙሉዑነት ብቃታቸው ፏፋቴ  ፍጽምና የተላበሰው ከማድመጥ መክሊታቸው ይቀዳ ነበር። አባይን ከምንጩ ከአናቱና ከሞገዳማ ፏፏቴው ጋር እሰቡት – እንደዛ ነው።

 

የጋዜጠኛ አበበ ገላው ፍላጎቱን የመደምጥ ብቃቱ የማዬው እኔ ከዚህ አንጻር ነው። በአፍሪካ ቆይታው የገጠመውን ዕድል ሳያሳልፍ ውስጡን በጥቂቱ ከፈት አድርጎ በጥንቃቄ ለሄሮድስ መለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ቴስት የሰጠበት ነበር፤ በኋላም ሁኔታውና አጋጣሚሚውን ሳያሾልክ ወይንም ሳይዘል የመንፈሱን ፍላጎት ድምጸት አደባባይ አውሎ በድምጹ ብቻ ፈቃደ እግዚአብሄር የሰጠውን ታላቅ ኃላፊነት ታምርም ተወጣ። ያ የሬገን ህንፃ ሞገዳማ ድምጽ በጣም ብዙ ትርፍ አስገኝቷል። እርግጥ ውጤቱ የመንፈስ ስለሆነ በኪሎ ወይንም በጆንያ ወይንም በወራንታ መለካት አይቻልም።

 

እኔ እንዲህ እላላሁ፤ የሰው ልጅ መጀመሪያ የተሰጠውን ጸጋ ማወቅ አለበት። ሁለተኛው ደግሞ የተሰጠውን ጸጋ ለመፈጸም መፍቀድ አለበት። ሶስተኛው የተሰጠውን ጸጋ ለማድመጥ የተመቼ መሆን አለበት። አራተኛው የተሰጠውን ጸጋ ለመፈጸም የሚያስችሉ ሁኔታዎችን፣ ወቅቶችንና፣ አካባቢዊ አምክንዮችን ገምቶ መወሰን – መቆረጥና ከትክለኛው የፍላጎቱ ድምጽ ጋር መገናኘት ያስፈልገዋል። ሦስቱንም ጊዜም ጋዜጠኛ አበበ ገላው በተግባር አንቆጥቁጦታል። ጸጋው ይህ ነው፤ መክሊቱ ይህ ነው። ከሰማዬ ሰማዬት የተሸለመው የቤት ሥራውም ይህው ነው።

አቤዋ በእጁ በገባ ማናቸውም አጋጣሚ ሁሉ የፍላጎቱን እንብርት ለማሟላት አብዝቶ የሚባትል፤ ለትውልዱ የረቀቀ ሥጦታ ነው። አብሶ ወጣቶች አብነትነቱን ተከትለው መሰሉን ተግባር ለመከወን ከተጉ፤ ኢትዮጵያ ሀገራችን ፈተናዋም ሆነ የመፍትሄ መንገዶቿ ቀና ይሆናሉ። ለዚህም ነው በ2013 ዘሀበሻ አዘጋጅቶት በነበረው „አመታዊ የምርጥ ሰው“ የድምጽ አሰጣጥ ሥርዓት ላይ እኔ አንደኛ ጋዜጠኛ አበበ ገላውን፤ ሁለተኛ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን፤ ሥስተኛ አቶ ገ/መድህን አርያን አቅርቤ የነበረው። መጨረሻ ላይ „ማገዶው አቶ አንዶአለም አራጌ“ ማሸነፉም አስደስቶኛል።

 

አሁን ወደ ቀደመው። ቀደም ብዬ ያነሳሁትን ነጥብ መንገድ የተከተለው ጋዜጠኛና ገጣሚ ሳዲቅም በሀገረ አሜሪካ አቮይን ቀልባቸውን ገፎ ቁፍ ያላች ዶሮ አድርጓቸዋል። እነዚህ ወጣቶች ለእኛ ልዩ ምልክቶቻችን፤ የተግባር አርማዎቻችን፤ የድርጊት አዛውንቶቻች፤ የሥራም ልዩ እርስቶቻችን ናቸውና ከልብ ልናከብራቸው፤ ልናደንቃቸው ይገባል። የእውነት አሳራቶቻችንም ናቸው።

 

የማከብራችሁ ወገኖቼ የሰው ልጅ ለራሱ መኖር ከፈለገ ሁሉም ይሆናል። መንገዱም እጅግ ሰፊና በድሎት የሰገረ ነው። ይህን አሻም ላላ፤ የህዝብ ዕንባ ለሚጎረብጠው፤ እራሱን ፈቅዶ በመስጠት ኑሮውን የኮረኮንች – የዳገት – የፈተና ለማደረግ ፈቅዶ፤  ለምልዕትና ለሀገረ ኢትዮጵያ  ዕንባ ቅርብነቱን በድርጊት ለሚያቀልም ጀግና ውሎው አዳሩ በፈቀደው የዕንባ ዙሪያ ይሆናል። ይህ ደግሞ መታደል ነው። እኔ እንደማስበውም ምድራዊም ብቻ አይደለም። መዳህኒታዓለም አባታችን ፍቅሩን የገለጸበትን ሚስጥር በአምሳሉ በፈጠራቸው ፍጡራን ሲይ፤ እንዲህ መስዋዕትነቱ መክኖ አለመቅረቱን ሲመለከት በሰማይ ሳይቀር ታላቅ ደስታ ይሆናል። ሁልጊዜም ለተገፋ፤ ለተጨቆነ፤ ባሩድ በዬዕለቱ ለሚቀቅለው ወገን መጮኽ — መጮኽ  —- መጮህ —- መጮኽ ——- መጮኽ ———- ከዶሮ ጩኽት – እስከ ዶሮ ጩኽት ———ጩኽቱ እስኪሳማ ድረስ መጮኽ —- አሁንም መጮኽ —— ነገም መጮኽ —— ከነገ ወዲያም መጮኽ — የቅኑ አቤዋ መንገዱ ይህ ነው። የተፈቀደለትም ይኽው ነው። ወደ ፋመው ፈተና ፈጥኖ መገስገስ …. ስለሆነም ስለ ህዝብ ፍቅር አቤዋ መጻፍም መናገርም ይችላል። ሙሉዑ መብት አለውና! ሆኖታል – ተገኝቶበታል፤ ተስጥቶታልም።

 

አቤዋ አብዝቶ ቅን ነው። ሰውን በጣም ያምናል። ማንንም – በምንም ሁኔታ ይመጣል ብሎ አይጠረጥርም። ንጹህ ፍንትው ያለ ልብ አለው – ወገኖቹን በፍቅር የሚያቀርብበት፣ ፕሮቶኮል ሆነ ሲናርዮ ግጥሙ አይደለም። የወገኖቹ ጉዳይም ባለቤትነት አብዝቶ ይሰማዋል። የፈለገ ከመጠን ያለፈ ቢሆን ድካም ዝር አይልበትም – በተለይ ለችግር ቅርብ ነው። ክብርና ኩራትም አይሻም። ጥሩ አድማጭ ነው። ከግለሰብ ጀምሮ የአካሉን ችግርን ለመጋራት የወደደ ነው። ወገኖቹ ስለሚያደርጉት መልካም ነገር አንደበቱን ከፍቶ ያደንቃል – ያበረታታል – ተስፋ ይሆናል – ስለነገ ብሩህ ቀን ዘለግ አድርጎ በጎ ያስባል – አውንታዊ ነው። እንደ ታናሽነቱም ቀልጣፋ ታዛዥም ነው። ድፍረቱ ያጠግባል፤  የማይመቸውን ነገር ፊት ለፊት ወጥቶ ይናገራል – ስለሆነም የግንባር ሥጋ ነው። በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ ለተሰማሩት ወገኖቹ ለሚታሰሩት –  ለሚሰደዱት – ለሚገፉት – ለሚገለሉት ደግሞ ማገራቸውና ልዩ ድምጻቸው ነው። የሙያ ቤተሰቦቹን እንደ እራሱ የአብራክ ልጆቹ ነው የሚያያቸው የትም ይኑሩ የትም። ጠበቃቸው – ዋቤያቸውም ነው። እውነትን አቤ ይወዳል። አቤ የኢጎ በሸተኛ አይደለም። ያልተገባ ክብር ፈጽሞ አይሻም – አይቀበልምም። አሁን እኔ „ጋዜጠኛ“ ከሚለው ቃል በተጨማሪ አንዲት ቃል ባክል አይፈልግም – አይወደውም።

 

እጅግ የማከብራችሁ የሀገሬ ልጆች  እግዚአብሄር አምላክ የሰውን ልጅ ሲፈጥር እንድናመሰግነው ብቻ እንጂ እሱ ምን ጎድሎበት? ከእኛስ ምን የሚፈልገው ነገር ኖሮ? ጋዜጠኛ አበበ ገላው  እንደ አናንያ፣ እንደ አዛርያ፣ እንደ ሚሳኤል ገብቶ ከጋመው እሳት የተማገደው፤ ኑሮው የተበተነው፤ ከቦታ ቦታ የተንካራተተው እለበቃ ብሎ እንሆ ዛሬም የአለሙን መሪ ፕ/ ባራክ ኦባንም መድረክ ላይ መጎተ። ህሊናቸውን ፈተነ። መንፈሳቸው ላይ በትልቁ ጥያቄ ምልክት በቃለ አጋኖ አስቀመጠ። ተባረክልኝ ወንድምአለም – የእኔ ብርቅ ታንሽዬ።

 

የእኔ ክብረቶች ወገኖቼ —  ዕንባ እንዲህ – ይደመጣል። ዕንባ እንዲህ  ይተረጎማል – በትውልዱ። የዛሬ ጹሑፌ መሰረታዊ አላማ አቤዋን እግዚአብሄር ይስጥልን እናትዬ፤ ኑርልን የኔ አባት፤ ድንግልዬ ጥላ ከለላ ትሁንልህ፤ አንተ ኩራት ነህ ለማለት ነው። አቤዋ „ጠንቃቃነት ያተርፋል እንጂ አያከስርምና፤ ከሰማይ በታች ባለ ነገር ሁሉ አደራ ጠንቃቃ ሁን!“ ጦርነቱ የእርስ በእርስ ነው። በዚህ ውስጥ የማይታዩ ዲቃላ ፍላጎቶች፤ የከሱ የሚመስሉ አንገታቸውን ደፍተው የታቆሩ ጥቁር ስሜቶች፤ ኮሳሳ መስለው ቀን የሚጠብቁ ሴራዎችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ምንጊዜም ማሰብና ስንዱ መሆን ይሻል። ቅንነትን ማስንበት የሚችለው መኖር ሲቻል ብቻ ነው። ለመኖር ደግሞ በተጓዳኝ ያሉ ነገሮችን ሁሉ በማስተዋል ጥንቃቄን ገበራቸው ማድረግ መሰረታዊ ነው። ከዚህ የበለጡ ህዝበ ጠቀም ተግባራትን ሆነ ገድላትን መፈጸም የሚቻለው በህይወት መኖር ሲቻል ብቻ ነው። እርግጥ አንድዬ አለ። ፈጣሪ አምላክ የሰጠውን ለማቆዬት ጥበቃው ይኖራል። ነገር ግን ሰውም የተገባውን ያህል ለራሱ ጥንቃቄ ማደረግ አለበት። ጥንቃቄ በራሱ ነገን ይወልዳልና።

መከወኛ። አቤዋ! ሁልጊዜም አንተ እሳት ውስጥ ገብተህ መርመጥምጥ የተፈጠርክበት፤ እግዚአብሄር አምላክ መርቆና ቀብቶ የሰጠህ ብቸኛው መንገድህ፤ ቀበቶህም ነውና መልካምና ቀጣይ የመስዋዕትነት ጊዜ – ከድል ጋር እህትህ -አድናቂህና አክባሪህ ተመኘሁልህ። ቤተሰብህን እግዚአብሄር አምላክ ጥበቃ ያድርግ። አሜን።

 

የኔዎቹ በ8.04.2014 በነበረኝ የራዲዮ ፕሮግራምም ስለ አቤዋ በተደጋጋሚ ያልኩት ነገር ነበረኝ። ወፊቱ ሹክ ብላኝ ይሆን? አላውቅም። ብቻ ግን ማድመጥ ትፈልጋላችሁ? መልሱ „ተገኝቶ ነው“ አላችሁ አይደል። የቀረ የለም ዝልዝሉ ጥበሱ ድውለቱ ሽሮም ጨጨብሳውም ያቺ ልስልስ እጅ ቁርጥም የምታደርገው ቡላዬም አለች  www.tsegaye.ethio.info Aktuell Radio Lora www.lora.ch.tsegaye ጎራ በሉና ዘንጣፌ ጤፍ እንጀራ ጋር ታደሙ። ግን ትእዛዝ አይደለም ማስታወስ …. መንፈስን በስንቅ ለሚያኖሩት የመስዋዕትንት ውዶቻችን እንዲሁም እናንተስ ልምን ይቅርባችሁ፤ ናፍቆት የሆናችሁትን አድማጮቼን ጨምሮ አባታችን ይጠብቅልኝ። አሜን! ጨረስኩ – ለዛሬ።

 

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

“መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ”መጽሐፍ ላይ የተደረገው ውይይት

የመደብ ወይስ የብሄር ጭቆና?! (ከአብርሃ ደስታ)

$
0
0

እንዲህ ተጠይቋል
“ባለፉ ስርዓታት የነበረ የማሕበረ ፖለቲካ መዋቅር የመደብ የትግል (ጭቆና) መሰረት ያደረገ ነበር ወይስ ብሄር?”
ባለፉ ስርዓታት ጭቆና ነበረ (አሁንም አለ)። በኢትዮጵያ ታሪክ በህዝብ የተመረጠ ህዝብን ለማገለግል የተነሳ መንግስት አልነበረም (የለም)። ስለዚህ ጭቆና አለ። ጭቆናው ምን መሰረት ያደረገ ነው? ብሄር ወይስ መደብ? በኔ እምነት ጭቆናው ከሁለቱም ዉጭ ነው። በኢትዮጵያ የመደብ ጭቆና አልነበረም (የለም)፤ የብሄር ጭቆናም አልነበረም (የለም)። የነበረው (አሁንም ያለው) ጭቆና የኤሊት (Elite) ጭቆና ነው።
እስካሁን ድረስ የመደብ ፖለቲካ የለንም። የመደብ ፖለቲካ ከሌለ የመደብ ጭቆናም የለም። የብሄር ጭቆናም አልነበረም፣ የለም፣ ሊኖርም አይችልም። የመደብ ጭቆና ግን ለወደፊቱ ሊኖር ይችላል።
ያለፉ የኢትዮጵያ ገዥዎች ስልጣን ለመያዝ እንዲሁም በስልጣን ለመቆየት ሲሉ በህዝቦች ላይ በደል አድርሰዋል። በደል ሲያደርሱ ብሄር ወይ መደብ መሰረት አድርገው አይደለም። መደብ ጭራሽኑም አልነበረም፣ የለም። ብሄር ነበር፤ ግን ጭቆናው ብሄር መሰረት ያደረገ ሳይሆን ስልጣን መሰረት ያደረገ ነበር፣ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ Class Based Or Nation Based Struggle ሳይሆን Elite vs People Based Power Struggle ነው።
ገዥዎች ስልጣን መያዝና እስከ ህልፈታቸው በስልጣን መቆየት ይፈልጋሉ። ለስልጣናቸው ሲሉ ታድያ ይደግፈናል የሚሉትን የሕብረተሰብ ክፍል ይጠቅማሉ፤ ለስልጣን አደጋ ነው በሚሉት ህዝብ ወይ ግለሰብ ደግሞ ጉዳት ያደርሳሉ፤ ስልጣናቸውን ለማጠናከር። ግን በፖለቲካ አንድን የሕብረተሰብ ክፍል መጥቀም አይቻልም፣ ይከብዳልና። ስለዚህ በሕብረተሰቡ ስም የተወሰኑ ግለሰቦች እንዲጠቀሙ ይደረጋል። ግለሰቦቹ ሲጠቀሙ የመጡበትን ሕብረተሰብ እንደተጠቀመ ተድርጎ ይታሰባል: ለፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ሲባል። ህብረተሰቡ በስልጣን ላይ ያለ ስርዓት “የኛነት” ስሜት ያሳድራል። ለዚህም ፕሮፓጋንዳ ይሰራል። ምክንያቱም የተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ ነው መጥቀም የሚቻለው። ለስልጣን የሚረዳው ግን አብዛኝው ህዝብ ነው። ተጠቃሚ ግለሰቦች ታማኝ የስርዓቱ አገልጋዮች ይሆናሉ። በነሱ ታማኝነት ስርዓቱ ዕድሜው ያራዝማል።
ለስልጣን አደጋ የሚሆን ግለሰብ ወይ ማሕበረሰብ ደግሞ የጥቃት ዒላማ ይሆናል። የስልጣን ዒላማ የሚሆነው በመደቡ አልነበረም (በመደቡ ዒላማ ሊደረግ ይችላል ግን መደብ አልነበረም)። በብሄሩም አልነበረም። በግዜው ካልተመቱ የስልጣን ስጋት ይሆናሉ የተባሉትን ግለሰቦች ወይ የሕብረተሰብ ክፍሎች ይጠቃሉ፤ ብሄራቸው ምን ይሁን ምን። ግን በኢትዮጵያ ታሪክ አንዳንድ ብሄሮች የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ለምን? በብሄራቸው ምክንያት? አይደለም። ለስርዓቱ ታማኝ አይደሉም፤ ስጋት ይሆናሉ ስለተባሉ ብቻ ነው።
በኢትዮጵያ ታሪክ የመጎዳትም የመጠቀምም መስፈርት ብሄር ወይ መደብ አይደለም፤ የፖለቲካ ታማኝነት (Political Patrimonial-ism) ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልምድ መሰረት የፖለቲካ ታማኝነት የሚገናኘው ከብሄር ጋር ነው። ሙሉ በሙሉ ባይባልም አንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች የበለጠ ይተማመናሉ (ምክንያቱም ፖለቲካችን መርህ መሰረት ያደረገ ሳይሆን ስሜት መሰረት ያደረገ ነው። በስሜት መነዳት ደግሞ አለመሰልጠን ነው)። አማርኛ ተናጋሪ ስልጣን ከያዘ አማርኛ የሚናገረውን (ሌላ ቋንቋ ከሚናገር) የበለጠ ያምናል። ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞን የበለጠ ያምናል። ትግርኛ ተናጋሪ ትግራዋይን የበለጠ ያምናል። በዚህ መሰረት አማራኛ ተናጋሪ ስልጣን ሲይዝ አማራዎችን ያስቀድማል (ለስልጣኑ ሲል)። ሌሎች ደግሞ ቅሬታ ያድርባቸዋል። ከዛ ለስርዓቱ ታማኝ አይሆኑም። ታማኝ ካልሆኑ በጠላትነት ይፈረጃሉ። በጠላትነት ሲፈረጁ ተጎጂ ይሆናሉ። እነዚህ የስርዓቱ ተጠቃሚ የሚደረጉ ታማኞች ግለሰቦች ናቸው። ብሄር ሙሉ ተጠቃሚ ማድረግ አይቻልምና። ተጎጂዎች ግን ብሄር ሙሉ ወይ የሀገር ህዝብ በሙሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ ተጠቃሚዎች ታማኝ ግለሰቦች ናቸው። ተጎጂዎች ግን ብሄር ሊሆኑ ይችላሉ። አንድን ብሄር ሌላኛው ብሄር እየበደለ ነው ይባላል። በዳዮቹ ግን ኤሊቶች (elites) ናቸው። ይህን ነገር ጉዳዩ የብሄር ጭቆና ያስመስለዋል። የብሄር ጭቆና ሊኖር ግን አይችልም።
ስለዚህ ባለፉ ስርዓታት (አሁንም ጭምር) በህዝቦች የሚደርስ በደል አለ። ይህንን በደል ብሄሮች የሚፈጥሩት አይደለም። ያለው በደል በብሄሮች ላይ የተፈፀመ የelites በደል ነው። ኦሮሞዎች የተበደሉ ኦሮሞ ስለሆኑ አልነበረም። ለተመሰረተው ስርዓት ተቀብለው አሜን ብለን እንዲገዙ ለማድረግ የተቃጣ ጥቃት ነው የተፈፀመባቸው። ስለዚህ ጥቃቱ ስልጣን መሰረት ያደረገ ነው። ዒላማው የፖለቲካ ታማኝነትን መሰረት ያደረገ ነው።
አማርኛ ተናጋሪ ንጉሶች ታማኝ ባልሆነ ማንም ሰው እርምጃ ይወስዳሉ። ለዚህም ነው በሁሉም ህዝቦች (አማራን ጨምሮ) በደል የደረሰው። ትግርኛ ተናጋሪ ገዥዎች ታማኝ ባልሆነ ማንኛውም ሰው እርምጃ ይወስዳሉ፤ ለስልጣን ሲሉ። ምሳሌ ህወሓት የትግራይ ልጆች በሆኑ እነ ስየ አብርሃ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ አስገደ ገብረስላሴና ሌሎች ታጋዮች ላይ መጥፎ እርምጃ የወሰደው እነኚህ ሰዎች ትግርኛ ተናጋሪ ስላልነበሩ አይደለም። ለስርዓቱ ታማኝ ስላልሆኑ እንጂ።
ስለዚህ በኢትዮጵያ ምድር የደረሰውን እንዲሁም እየደረሰ ያለው ጭቆና ብሄር ወይ መደብ መሰረት ያደረገ ሳይሆን የፖለቲካ ታማኝነት መሰረት ያደረገ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያውያን ጭቆና የብሄር ወይ የመደብ ሳይሆን የፖለቲካ ነው።
It is so!!!

ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ውርደት ጥቁር ቀን (ሮበሌ አባቢያ)

$
0
0

ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ውርደት ጥቁር ቀን ከሮበሌ አባቢያ፣ 27/52014   tplf-addis-620x310

በአምቦ ከተማና በሌሎች የኦሮምያ ክልል ውስጥ የዩኒቭርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያቀረቡት ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ በጨካኙ የአግዓዚ ጦር አልሞ ተኳሾች በጥይት መደብደብን ስለሆነ፣ ይህንን አሰቃቂ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ ያውም ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰብአዊ መብት መከበር ግምባር ቀደም መመሪያ ሆኖ በዓለማችን ላይ በገነነበት ጊዜ በመፈፀሙ፣ ወንጀለኞች ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም። ይህንን የተገነዘበው የባእዳንን ዓላማዎች ለማስፈፀም በጫንቃችን ላይ የተኮፈሰው የወያኔ መንግሥት አገልጋዮቹ ለፈፀሙት ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ወንጀሉን በመሸፋፈን የሕዝብ ትኩረት ወደ እርሱ ሙገሳ እንዲዞር እነሆ 23ኛውን የወረራ በዓሉን ሲያከብር በመፍጨርጨር ላይ ይገኛል። ነገር ግን ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ውርደት ጥቁር ቀን ተብሎ መዘከሩ አይቀርም።

ወያኔና ከርሱ በፊት የነበሩት ሁለት መንግሥታት 

ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ጀምሮ ጥቂት ምሳሌዎቸን ጠቅሼ በማወዳደር  የወያኔን ውሸት ላንባብያን ላቅርብ፦

1.   የ1997 ምርጫ አለደም መፋሰስ የሥልጣን ሽግግር የተደረገበት ታሪካዊ ወቅት ነው ሲል ነውረኛው የወያኔው አምባገነን መሪ መለስ ዚናዊ ሲመፃደቅ በኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ታይቷል። ያ አልበቃ ብሎት፣ ወያኔ በ99.6% አሸንፌያለሁ ብሎ የቀጠፈበት የ2002ቱ ደግሞ በጥራቱ እንከን ያልተገኘበት ምርጫ ነበር እያለ መለስ ዚናዊ ሲያፌዝብን አዳምጠናል። በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች፦ የሕዝብ ደምና ሕይዎት ተሰውቷል፣ የመራጮች ድምፅ ተሰርቋል፣ ድላቸው ተቀምቷል፣ አሸናፊዎች ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተወርውረዋል፣ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ በተለይ ወጣቶች የምርጫውን መጭበርበር በአደባባይ ስለተቃወሙ በግፍ ታስረዋል። ይህንን አረመኔያዊ የወያኔ ፋሺስታዊ ተግባር፣ ታሪክ ምንጊዜም አይረሳውም።

2.   የብሔር ብሔረሰቦች ጉዳይ ሲነሳ አፄ ኃይለ ሥላሴ በድል አድራጊነት ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ ሕዝባቸው በቆየው እምነቱ፣ ባሕሉና ልማዱ መሠረት መብቱ እንዲጠበቅለት ወዲያው አውጀዋል። በዘመነ መንግሥታቸው የባህል ሚዩዚየም እንዲከፈት አድርገዋል። አፄው ባመቻቹላው አዋጅ መሠረት፦ ሀ) በአዲሰ አበባ ጊፍቲ (እመቤት) ጂፋሬ የተባሉት ባለውቃቢ የጥንቆላ አገልግሎት ይሰጡ ነበር፤ አልተባበርህም ያሉትን አርበኛ አባታቸውን ፋሺስት ኢጣልያ ቁልቆል ዘቅዝቆ በመግደሉ ይህ እንደ ውለታ ተቆጥሮ፣ ወ/ሮ ጂፋሬ “የኢትዮጵያ ሀገር ፍቅር ማህበር” ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል፤ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ፣ ልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን በቀብር ሥነሥርዓታቸው ላይ መገኘታቸውን አውቀለሁ፤ ለ) አምቦ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ደንፋ እየተባሉ የሚጠሩ በንጉሠ ነገሥቱ የሚታወቁ ባለውቃቢ እንደነበሩ አውቃለሁ፤ አፄው አዘውትረው አምቦን ይጎበኙ ስለነበር፣ ደንፋ ፈረሰኞች እስከ ጊንጪ(36 ኪሎሜትር ከአምቦ) ድረስ ልከው እንደሚያሳጅቧቸው ይታወቃል፤ ሐ) ሕዝብ ታዋቂ የማምለኪያ ቦታዎች፣ የየረሩ ንጉሥ ተብሎ የሚጠራው ባለውቃቢ የሚኖርበት በአዲሰ አበባ አካባቢ፣ ሆራ አርስዴ በቢሾፍቱ፣ የአርሲ እመቤት መኖሪያ በአርሲ፣ ሶፍ ዑመር በባሌ እንደነበሩ ይታወቃል።

3.   የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ዛሬ መሬቱ የሚነጠቀው የኦሮም ተወላጅ አያት/ቅድመ አያት የአካባቢወ ሕዝብ ማንም ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ሳያዘው ለጥምቀት በዓል ወደ ጃንሜዳ እየጎረፈ እጅግ የሚማርኩ የየባህሉን ዘፈኖች፣ ጭፈራዎችና ውዝዋዜዎች  መመልከት ለኢተዮጵያን ኩራትና ፈንጠዝያ፣ እስከ ዛሬም ለቱሪስቶች መስህብ ሆኖ በመገኘቱ የወያኔ መሪዎች ዶላር ያፍሱበታል። በሕግ የተደነገገ የአለባበስ ኮድ ስላለነበረ ሁሉም በየባህሉ ልብስ አጊጦ ጃንሜዳን አጥለቅልቆ ያውባት ነበር። በወያኔ አበረታችነት ሳይሆን እስካሁንም እንደዚያው ነው።

4.   በደርግ ዘመነ መንግሥት የብሔር ብሔረሰቦች ኢንስቲቱት ተቋቁሞ ነበር። “የዘር የሃይማኖት ልዩነት አንሻም፣ ይላሉ ልጆችሽ ኢትዮጵያችን ትቅደም”፣ ተብሎም ተዘምሯል። የባህል ዘፈኖችና ቲያተሮች በየክፍላተ ሀገር አብበው ነበር።

5.   የወያኔ ዘመነ መንግሥት እስር ቤቱ በኦረሚፋ ተናጋሪዎች ታጭቋል ተብሎ ተነግሮለታል… የብሔር ብሔረሰቦች ወያኔ ለፖለቲካ ፍጆታ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የማሞኛ በዓል ከመሆን አልፎ፣ የ83ቱንም ብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋዎችንና ልማዶች አቆይቶ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ የሚዘልቅ አይደለም።

6.   ረሀብን በማስወገድ ረገድ ሶስቱም መንግሥታት ሀላፊነታቸውን ሙሉ በሙሉ አልተወጡትም። የአፄው አገዛዝ የወሎውን ረሀብ ለመሸሸግ መሞከሩ ሊወገዝ ይገባዋል። የደርግ መንግሥት ረሀብ በሀገሪቱ ውስጥ እያለ ሥልጣን ላየ የወጣበትን 10 ዓመት ለማክበር የአልኮል መጠጦችን ከውጪ ሀገር በዶላር ማስገዛቱ ያስወግዘዋል። ወያኔ የሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አሰመስግቤያለሁ እያለ ሲፎልልባት በቆየበት ሀገር 6.5 ሚሊዎን ረሀብተኞች ኸተባበሩት መንግሥታት የምግብ እረዳታ ይጠብቃሉ መባሉ የአገዛዙን ጭካኔ ያመለክታል።

7.   የወያኔ መንግሥት መሪዎች ለሱዳን መሬት ቆርሰው ለመስጠት እየተሯሯጡ ነው። የቀድሞ መንግሥታት እንኳን ሊያደርጉት የማያስቡት ወራዳ ድርጊት በታሪክ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል

8.   ወያኔ ኢትዮጵያን አስገንጥሎ ወደብ-አልባ ያደረጋት ሞራላዊም ሆነ ሕጋዊ ብቃት የሌለው ቅጥረኛ መንግሥት።

9.   መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን ረገጣ በተመለከተ የወያኔ መንግሥት ሬኮርድ አሳፋሪና ዘግናኝ መሆኑን ዓለም ያወቀው ሐቅ ነው። እነዚህን መብቶች ለማስከበር የወያኔን አገዛዝ በተባበረ ተቃውሞ ማንበርከክ ግድ ይላል።

10. በአፄው ዘመነ መንግሥት በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመሥራት ጥናቱ ተጠናቆ ነበር፤ ሆኖም በገንዘብ እጦት ምክንያት ግድቡ አልተሰራም። የግብፅ ኤክስፐርቶችም በአባይ ወንዝ ላይ እስከ 40 ግደቦች ለመሥራት እነደሚቻል በጠናት አረጋግጠው፣ ችግሩ የገንዘብ ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል። የህዳሴው ግድብ የሌሎችን የልማት ፕሮጄክቶች በጀት የሚሻማ የመዝረፊያ  ፕሮጀክት ከመሆኑም በላይ፣ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል የሦስትኦሽ ወገን ውይይት ተደርጎ ስምምነት ካልተደረሰ በስተቀር፣ ውጤቱ ንትርክና አልፎም ወጣቱን ትውልድ በማያባራ ጦርነት ውስጥ መዝፈቅ ይሆናል። የአባይ ውሀ የገዘፈው ከአማራውና ከኦሮሚያ ክልሎች በሚያፈሱለት ገባር ወንዞች አማካይነት ነው። ታዲያ ሁለቱ ክልሎች ከህዳሴው ግድብ የሚያገኙት ድረሻቸው ምን ያህል ነው? የብሔር ብሔረሰቦችን ከፋፋይ ፖሊሲ በውስጥ እያዳከመን እያለ ሁኔታውን በሚያባብስ ተግባር ላይ ማተኮር የሚያስከትለው አደጋ ከባድ ስለሚሆን በቀና መንፈስ መወያየት ለሁሉም ይበጃል።

አለመታመን፣ ለወያኔ ሰቀቀን

ዋሽቶ ማስዋሸት የወያኔ ቁንጮዎች የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ ቆይቷል። ሆኖም ዛሬ፣ ውሸት አገዛዙን የሕዘብ ተዓማኒነት አሳጥቶት ውድ ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል። ጉዳቱ ለምንወዳት ሀገራችንም ጭምር ነው። ምክንያቱም የውጭ ጠላት መጥቶባት ክተት ቢታወጅ፣ የተለመደ ውሸቱ ነው በማለት ወያኔን የሚያምን ኢትዮጵያዊ ስለማይገኝ በቆየው ባህላችን መሠረት ሆ! ብሎ የሚነሳና አጥቂውን ለመፋለም ፈቃደኛ ተዋጊ እንደማይገኝ አምናለሁ።

በደርግ ዘመነ መንግሥት ማብቂያም ውሸት ስለበዛ፣ የአካባቢ ወጣቶች እንደተለመደው በአርበኝነት ወኔ ተነሳስተው የክተት ጥሪ ለመቀበል ፈቃደኞች ሁነው ስላልተገኙ፣ በቀበሌዎችና በገበሬ ማህበራት አስገዳጅነት እየታፈሱ ለለብ ለብ ሥልጠና ወደ ወታደራዊ ተቋማት ከተላኩ በሗላ በውጊያ ልምድ ያዳበረውንና በአረቦች ፔትሮ-ዶላር ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታቀውን የወያኔ ሠራዊት እንዲገጥሙ የተገደዱትንና የረገፉተን ወጣቶች ማሰታወስ ግድ ይላል። አስከፊው ሁኔታ እዚያ ደረጃ ላይ እሰኪደርስ ድረስ ደርግ ወያኔን እንደ ተራ ሺፍታ እያቃለለ ፕሮፓጋንዳውን ይነዛ ነበር። የሥልጣን ባለቤት የሆነውን ሕዝብ መዋሸት፣ የሚያስከትለው መዘዝ ብዙ ነው።

ከእንግሊዞች ፖለቲካ ምን ይማሯል?

ፀሐይ በእንግሊዝ ግዛት ከቶም አትጠልቅም (The sun never sets on the British Empire”) ተብሎ ሲጠቀስ ከልጅነቴ ጀምሮ እሰማ ነበር። የጥቅሱም ትርጉም፣ እንግሊዝ (ብሪቲሽ) የቅኝ ግዛቶቿን ጨምሮ በዓለማችን ላይ የነበራት ግዛት እጅግ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ፣ ጀምበር አንዱ ጋ ስትጠልቅ ሊላው ጋ ትወጣለች ማለት ነው። ዛሬ ደሞ፣ ጀምበር በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገሮች ላይ አትጠልቅም ለማለት እደፍራለሁ። አዎ! በያዝነው 21ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ ቋንቋዎች እየከሰሙ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንደሚተኩ አዝማሚያው  በሂደት እየታየ ነው። አንዳንድ ጥናቶች ይህንኑ አዘማሚያ እያሳዩ ነው። የቋንቋዎች ብዛት እያነሰ በሄደ ቁጥር፣ የሰው ልጆች የርስ በርስ መግባባት እየጨመረ እንደሚሄድ የሚያጠራጥር አይመስለኝም።

እንግሊዞች ፖለቲካቸው የሚሳካላቸው በእራሳቸው ላይ መሳቅ ስለሚችሉ ነው ተብሎ ሲነገርም ሰምቻለሁ። በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ ህብረት ውሰጥ እንቆይ በሚሉት በሌበር ፓርቲ እና ሊብራል ፓርቲ ባንድ ወገን፣ እና የለም ከህብረቱ እንውጣ በሚለው የወግ አጥባቂው ፓርቲ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ እንደሚሄድ የተገነዘቡት ሌሎች አውሮፓውያን፣ እንግሊዝ የሌለችበት ፖለቲካ አይጠፍጥም እያሉ ሲተቹ ይሰማሉ፡፤

በኢትዮጵያ ሀገራችንም ቢሆን አማራና ኦሮሞ የማይሳተፉበት የጋራ ፖለቲካ ከሌለ፣ ኢትዮጵያ እንደ ውሁድ ሀገር አትኖርም፤ የአፍሪካ ሕብረትም ሕልውና አጠራጣሪ ይሆናል። ታዲያ የጥቁሮቹ የኩሽ፣ የካምና የሴም ልጆች እጣ ፋንታ ምን ሊሆን ነው?  አዎ! የዛሬን ስናነሳ ትናንትን ሳንረሳ አስታውሰን በሞኝነታቸን ላይ ስቀን ስህተታችንን አርመን ወደፊት መጓዝ ብልህነት ነው።

በሀገራችን በኢትዮጵያም ቢሆን የቋንቋዎች ብዛት እያነሰ መሄዱ አይቀሬ መሆኑን ካሁኑ አምኖ መቀበል ብልህነትና አርቆ አስተዋይነት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም። በዚህ አስተሳሰብ በመጓዝ፣ ወያኔ ከጫነብን ደም አፋሳሽ የጎሳ ፖለቲካም ለመገላገል ፍቱን መድሐኒት አአአእናገኛለን።

የግል ሚዲያ/ነፃ ፕሬስ መታፈንና መዘዙ 

በእድሜዬ ዘመን ያጋጠሙኝን ሶስት መንግሥታት ላንሳ። እነዚህም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ የመንግሥቱ ኃይለማርያም (ደርግ) እና  እንደወራሪው ፋሺስት ጣልያን ኢትዮጵያውያንን በጥይት የሚቆላው ወያኔ ናቸው። ሦስቱም የነፃ ፕሬስና መሠረታዊ የሕዝብ መብቶች በተለያየ ደረጃም ቢሆን አንቀው በመያዛቸው ይታወቀሉ። በዚህ ምክንያት ሁለቱ ከሥልጣናቸው ተዋርደው ሊወድቁ በቅተዋል፤ ወያኔም ተመሳሳይ ዕጣ ይጠብቀዋል። ተንሽ ላብራራ፦

1.   ጃንሆይ ያፈኑትን የፕሬስ ነጻነት ደርግም ወርሶ በሥራ ላይ ስላዋለው፣ በመንግሥት ሙሉ ቁጥጥር ሥር በሚገኙ ሚዲያዎች ለሚነዛባቸው የሃሰት ፕሮፓጋንዳና የስም ማጥፋት ዘመቻ ዓፄውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው በነፃ ፕሬስ አማካይነት አጸፋዊ መልስ ለመስጠትና እራሳቸውን ለመከላከል አልቻሉም። ለምሳሌ ገና ወጣት ሳሉ በደጃዝማችነት ማዕረግ የአስበ ተፈሪ አውራጃ ገዢ ሆነው የከተማውን መሬት ሸንሽነው አላንዳች አድልዎ በርስትነት ማከፋፈላቸው፣ በ1946 ዓ.ም በፕሬዚዳንት አይዘንሐወር ጋባዥነት ከአሜሪካ ጉብኝት በሗላ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ፣ ሕዝቡ ታጥቆ በመነሳት በርሻ ልማት እንዲሰማራ ለማረስ ለሚፈልግ አትዮጵያዊ በነብስ ወከፍ አንዳንድ ጋሻ የገጠር መሬት እንዲሰጥ አውጀው እንደ ነበርና በዚህ አዋጅ የሰፈሬ ሲቪሎች ተጠቃሚ እነደበሩ አውቃለሁ፣ከኔ ጭምር በርካታ የአየር ሀይል መኮንኖች በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ነጭ ሳር ተብሎ በሚጠራው ቦታ የተሰጠንን አንዳንድ መሬት ለማልማት በዝግጅት ላይ ነበርን። ጃንሆይ ሌሎች አያሌ አኩሪ ሥራዎችን ማከናወናቸው ሐቅ ነው፡፡ ነፃ ፕሬስ ቢፈቀድና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተፈጥረው ቢሆን ኖሮ እነዚህን አኩሪ ክንውኖችን በመጥቀስ ደጋፊዎቻቸው ሊከራከሩላቸው በቻሉ ነበር፡፡ ግና፣ የአምባገነን ትዕቢታቸው ስላልፈቀደላቸው ነፃ ፕሬስ መፍቀድ አልተዋጠላቸውም። ሰለዚህ ተዋርድው ከዙፋናቸው ወረዱ፤ የሌሎችም ዲክታተሮችም ዕጣ ፋንታ ከዚህ የተለየ እንደማይሆን ታሪከ አስተምሮናልና።

 

ብዙዎቻችን አጥብቀን የታገልንለት የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ንጉሠ ነገሥቱ በሕይዎታቸው እያሉ አቆጥቁጦ እያደገ ከእርሳቸው ሕልፈት በሗላ የእንግሊዞችን ሞዴል የመሰለ ሞናርኪ ሊፈጠር በቻለ ነበር። እኔም የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲፈጠር ሁኔታ እንዲመቻችና ነፃ ፕሬስ እንዲፈቀድ ያቀረብኩት ተማጽኖ በኢትዮጵያን ሄራልድ ላይ በ1966 ዓ.ም ታትሞ ነበር። ግን ሰሚ አላገኘም፤ ለዚያውም በዚያን ጊዜ ማን ተደማምጦ።

 

2.   የደርጉ ሊቀ መንበር ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም ነሐሴ 12 ቀን 1966 ዓ.ም በቁጥር አ/ኮ/072/66 ለሁሉም ወታደራዊ ክፍሎችና  በየጠ/ግዛቱ ለተቋቋሙት ንዑስ ኮሚቴዎች በያሉበት ከጻፈው ደብዳቤ ጋር አያይዞ ሀያ (20) ነጥቦችን የያዘ አንድ ገጽ የሥራ ዝርዝር መመሪያ ልኮ ነበር።

የአየር ኃይል ንዑስ ደርግ ከመመሪያው ውስጥ የተወሰኑትን መርጦ በተለይ በተራ ቁጥር 15 የተገለጸውን ቅድሚያ በመስጠት ነሐሴ 17 ቀን 1966 ዓ.ም. ቁጥር ፦ አሀ/ንደ/  //  /66 በጻፈው ደብዳቤየሚከተለውን መልስ ሰጥቷል

 

“ጉዳዩ፦ በአየር ኃይል ንዑስ ደርግ የቀረበ ሀሳብ

ለጦር ሀይሎች፣ ለፖሊስ ሠራዊትና ለብሔራዊ ጦር አጠቃላይ ደርግ

የአየር ሀይል ንዑስ ደርግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እንዲፈጸሙለት በአየር ሀይል ሠራዊት ስም ይጠይቃል፦

የተጀመረው ንቅናቄ “ብሔራዊ” እንዲሆን የሰላማዊ ሕዝብ ተካፋይ መሆን አለበት። ስለዚህ ለምሳሌ፦

ሀ.   ከኢትዮጵያ ሠራተኞች አንድነት ማህበር፣

ለ.   ከአሠሪዎች ማህበር፣

ሐ.   ከዩኒቨርስቲ መምህራን፣

መ.   ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣

ሠ.   ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣

ረ.   ከብሔራዊ ሸንጎ /ፓርላማ/

ሰ.   በቻርተር ከሚተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች፣

ሸ.   ደርጉ ከሚያምንባቸው ልዩ ልዩ ሌሎች ክፍሎች መወከል አለባቸው።”

 

ቀን የደረስንበትን ውሳኔ ልዕልቲቱ ማታ ታሽረዋለች እያሉ ጠቅላይ ምኒስትሩ ያማርራሉ ተብሎ ስለተወራ፣ የታሠሩትባለሥልጣኖች የቴሌቪዠን ሰዓት ተሰጥቷቸው አመራር ለመስጠት የተቸገሩበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንዲገልፁ ይደረግ ዘንድ በሻለቃ አዲስ ተድላ በኩል በጽሑፍ የቀረበው ሀሳብ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከባድ ስህተት ሊፈፀም ችሏል። ምክር አልሰማም ባይነቱ የደርግን መንግሥት አንኮታኮተው!

 

3.   ነፃ ፕሬስ፦ በሰው ልጆች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሕይዎት ውስጥ ወሳኝ ሚና አለው። ነፃ ፕሬስ የዜጎች እኩልነት መለኪያ ነው፤ የግለሰብ ነፃነት ዋስትና ነው፤ የሥልጣኔ ምልክት ነው፤ የሕዘብን ብሶት መግለጫ ነው፤ የመልካም አስተዳደር መንገድ ጠቋሚ ነው። እነዚህን ለመረዳት ያልፈለገው የወያኔ አገዛዝ ገና ሥልጣን እንደያዘ ማበብ ጀምረው የነበሩትን ድንቅ ጽሑፎች አከሰመ፤ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት አውታሮች በሙሉ በአገዛዙ ጥብቅ ቁጥጥር ስር ዋሉ። ስለዚህ ከሕዝብ ተለይቷልና የሕወሐትም ሞት አይቀሬ ነው!

 

ወያኔና ሙስና

 

የወያኔ ቁንጮ መሪዎችና ቡችሎቻችው ከማይወጡበት የሙስና ባህር ውስጥ ገብተው በመስጠም ላይ ናቸው።

 

ኢኮኖሚያቸው በአሁኑ ጊዜ እየመጠቀ በመሄድ ላይ የሚገኘው የቻይና ኮሙኖስት ፓርቲ መሪዎች፣ በሀገራቸው ስር የሰደደ  ሙስና የቱን ያህል እንዳሳሰባቸው ለመግለፅ እነዲህ ብለው ነበር፦

“ይህንን ጉዳይ ቆጣጠር ካቃተን፣ ፓርቲውን ለሞት ከሚዳርግ አልፎም ከሚገድል፣ ሀገሪቱንም ለውድቀት የሚያበቃ ሁኔታ ሊመጣ  ይችላል (“If we fail to handle this issue well, it could prove fatal to the Party, and even cause the collapse of the Party and the fall of the state”. ) ብለው የፓርቲው ዋና ጸሐፊ የተነገሩትን እንደ አውሮፓ ኖቬምበር 15 ቀን 2012  “Reform in China vs crisis within EPRDF” በሚል ርዕስ ከተብኩትን ጽሑፍ በድረ-ገጾች ላይ አስለጥፌ አስነብቤያለሁ።

 

ቅጥረኛው የወያኔ ነውረኛ አገዛዝ ላለፉት 23 ኣመታት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች ሲያዳሽቅ፣ ንብረቷን ሲመዘብርና ንዋይና የቡና ምርት የመሳሰሉትን ሀብት ሠርቆ ወደ ውጪ ሀገር በስውር በማሸጋገር ከብሮና ብቸኛው ባለመሬት ሆኖ፣ የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ የበላይነትን አስፍኖ፣ የዴሞክራሲ ግብዓቶቸን በሙሉ ተቆጣጥሮ እነሆ ዛሬ በማንአለብኝነት ሙስና አለቅጥ ባልጎ እንዳሻው እየገደለ፣ እያሰረ፣ ዜጎችን ከመኖሪያቸው እያፈናቀለ፣ ይገኛል። የወያኔ ቁንጮ መሪዎችና ቡችሎቻችው ከማይወጡበት የሙስና ባህር ውስጥ ገብተው በመስጠም ላይ ናቸው።

 

ይህ መውደቂያው አይቀሬ፣ ከአንድ አናሳ ጎሳ ከተውጣጡ በዘረፋ የከበሩ  ጄኔራሎች የሚደገፈው መንግሥት እስከ አሁን ካደረሰው ዘግናኝ በደል በላይ ሌላ ሳጨምር በአፋጣኝ በቃህ ሊባል ይገባል!!!

 

 

ስለ የሙስና ንግሥት ሕዝቡ ምን ይላል?

 

ወልቃይት ብናስጠይቅ አሉን እዚያ የለች

ቀዳማዊ እመቤት ታዲያ ወዴት ሄደች

የሙስና ንግሥት ዘርፋን የከበረች

ፈልጓት ባካችሁ የት እንደ ደረሰች

እንድንፋረዳት ፍርድ ቤት አቅርበን

መች እንዲህ እንቀራለን ተገድለን ተገርፈን

ባባታችን ሀገር ተዘርፈን ተዋርደን

የመብት ጥያቄ ስናነሳ ታስረን

መለስ የዘራውን የጎጠኞች ፍሬ

አድጎ ሳይስቸግር እንቅጨው በጥሬ

ማምከን በተግባር ነው አይደለም በወሬ

ይህ ነው የኔ ምኞት ለኢትዮጵያ ሀገሬ

ንግሥቲቱን አየን ጥቀር ለብሳ ከስማ

በጣይቱ ከተማ ተደብቃ ከርማ

ወንጀሏ ይዘርዘር አንዱ ይንገር ላልሰማ

ወህኒ ቤት እንስደድ አዜብ ጎላንማ

ኑሮን ያልጠገቡ የኦሮሞ ልጆች ወጣት ተማሪዎች

ሕይዎታቸው ጠፍቶ፤ ደማቸው ተረጭቶ ባጋዚ ተኳሾች

አርፋ አትቀመጥም ሕዝብን ካለጋጨች፤ ካላተራመሰች

ታዲያ እንዴት ይኖራል አዜብ ተጠፍራ ቶሎ ካልታሰረች

 

ጸሎቴና አድናቆቴ

በ24/5/2014 መድረክ አዲስ አበባ ላይ ባካሄደው ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታየው የተቃዋሚ ሀይሎች አስደናቂ ትብብር የበለጠ አይሎ፣ ጎልብቶ፣ አድጎና ፈርጥሞ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ለማንበርከክና በእናት ሀገራችን ውስጥ ጎጠኝነት ፈጽሞ እንዲከስም የዘወትር ጸሎቴ ነው።

ኦቦ ቡልቻ ደመቅሳ ላሳዩት ሞራል ገንቢ ተሳትፎ አድናቆቴን ከልብ እገልጻለሁ፤ ለመድረክ አመራሮችና አባላት ልባዊ መሥጋናዬን አቀርባለሁ።

የታሰሩት የፖለቲካና የህሊና እስረኞች አለምንም ቅድመ-ሁኔታ በአስቸኳይ ይፈቱ!

በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ወንጀል የፈፀሙ ሁሉ ለፍርድ የቅረቡ፤ ለሞቱት ተማሪዎች ቢተሰቦች መንግሥት ካሳ ይክፈል!

 

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

rababya@gmail.com

 

 

የመብት ረገጣውንና የከፋፋዮችን ሤራ በጋራ እናስወግድ! (ሸንጎ)

$
0
0

shengo

ግንቦት 19 2006 (ሜይ 27 2014)

 

ሁሉ ከገዥው ቡድን የሚሰጠው ምላሽ የሚያነሳውን ጥያቄ በመመርመር፣የደረሰበትን ብሶት በማዳመጥ ሰላማዊ መፍትሄ ከመሻት ይልቅ ድብደባ፣ እሥራት፣ ስቃይና ግድያ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ይህ ለሃያሦስት ዓመታት ሳያባራ የቀጠለው የግፍ ተግባር እነሆ በቅርቡ በአምቦ፤ በነቀምት፤ በጊምቢና በሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች ውስጥበዘግናኝ መልኩ ተደግሟል። ጨካኙ የህወሓት፨ኢህአዴግ አገዛዛ በሥርዓቱ ፖሊሲ ላይ ተቃውሟቸውን ለማሰማት ሰላማዊ ሰልፍያካሄዱ ተማሪዎችን፣ ከአሁን በፊት በጎንደር፣ በአዋሳ፣ በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች እንዳደረገው፣ ዛሬም በጥይት ደብድቦ ብዙዎችንገድሏል፤ ሌሎችንም አቁስሏል።

 
ደግመን ደጋግመን እንደገለጽነው፤ ይህ ሰብዓዊ ርህራሄ የጎደለው ተግባር በኢትዮጵያውያን ሁሉ መወገዝ አለበት። በሀገራችን ምድርውስጥ በፍጹም እንዳይደገምም ሁሉም ተባብሮ ሊነሳና አምቢ፤ በቃ ሊል ይገባዋል። ይህን ዓይነት አስከፊ ወንጀል የፈጸሙ ሁሉለፍርድ መቅረብ ይኖርባቸዋል።

 
አገዛዙና በግድያው የተሳተፉት ሁሉ ሊገነዘቡት የሚገባው ነገር ቢኖር የዚህ ዓይነት ጭፍጨፋና መንግሥታዊ ሽብርተኝነት የሕዝብንብሶት አባብሶ፣ ሰሜቱን እንዲሸፍት እንደሚያደርገው እንጂ አፍኖ ማጥፋት በፍጹም እንደማይቻል ነው። የሕዝብን ተቃውሞበጉልበት ማጥፋት የሚቻል ቢሆን ኖሩ ለ፪፫ ዓመታት የተካሄደው ማለቂያ የሌለው ግፍ ሕዝቡን ሰጥለጥ እንዲል ባደረገው ነበር።
በሀገራችን ውስጥ ያለውን እውነታ በትክክል መረዳት ለሚፈልግ ሰው የገዥው ቡድን የግፍ ተግባር እየከፋ በሄደ ቁጥር የሕዝቡምእምቢኝ ባይነት እየጠነከረና እየተስፋፋ መሆኑን በቀላሉ ማየት ይችላል።
ህወሓት፨ኢህአዴግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የመብት ረገጣ ብቻ ሳይሆን ሕዝባችንንም እርስበርሱ በጥርጣሬና በጠላትነት እንዲተያይ አንዲሁም የአንዱ ቋንቋ ተናጋሪ የሌላው ቋንቋ ተናጋሪ፤ የአንዱ ሃይማኖት ዕምነት ተከታይ የሌላው ሃይማኖት ዕምነት ተከታይ ጠላትእንደሆነ አድርጎ የሚያራመደው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የሀገራችን ችግር መንስዔ መሆኑን በገልጽ መረዳት ይቻላል።
አገዛዙ ሲያራምደው የቆየው የሃያ ሦስት ዓመት ከፋፋይ ፖሊሲው በአሁኑ ወቅት አስከፊ ገጽታው በተለያየ መልክ በመገለጥ ላይ ነው። ዜጎች በፍቅርና በሰላም ተከባብረው ተረዳድተውና አንድ ሆነው መኖር ሲገባቸው እርስበርስ እንዲጋጩ እየተደረገ ነው። አንዱኢትዮጵያዊ ሌላውን ከአካባቢው ለቅቆ እንዲሄድ የማስጨነቅ፣ የማሰፈራራት የማስገደድ ተግባሮች ከቀን ወደቀን እጅግ አሳሳቢ በሆነመልኩ እየተካሄደ ይገኛል።

 
የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ይህ ተግባር የሚፈጸመው በአብዛኛው ባለሥልጣኖችና ካድሬዎቻቸው አማካኝነት ነው። ለምሳሌከጉራፈርዳና ከሌሎችም የቤነሻንጉል አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲባረሩ የተደረገው፡ በአካባቢው ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ትዕዛዝ ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት ከወለጋ ንብረታቸውን ተነጥቀው በጉልበት ተፈናቅለው የተባረሩት በሺዎች የሚቆጠሩወገኖቻችንም ግፍ የተፈጸመባቸው በአገዛዙ ባለሟሎች አጋፋሪነት ነበር። ይህ የአንዱን ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ የሌላው ጠላት እንዲሆን፤ የአንዱን ኅብረተሰብ ክፍል ጥቅም ለማስጠበቅ ሌላውን ማግለል እንደሚገባው በሚያደርግ ከፋፋይና አርቆ አሳቢነትየጎደለው አመለካከት በፈጠረው አጥፊ ሁኔታ ተጠቅመው የአገዛዙ ባላሟሎች ብቻ ሳይሆኑ ጠባብ ብሄረተኞችም በሕዝባችን ውስጥ አለመተማመን፣ ጥርጣሬና መርዘኛ ክፍፍል ለመንዛት መሞከራቸው አልቀረም። በቅርቡ በአንዳንድ ቦታዎች የተከሰቱት ሁኔታዎች የሚያመለክቱትም ይህንኑ ነው።

 
ዓይኑን ጨፍኖ በክህደት ውስጥ የሚገኘውና የከፋፋይነትን መርዝ የዘራው የህወሓት፨ኢህአዴግ አገዛዝ ግን በሀገሪቱ ውስጥ ሰላምእንደሰፈነ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ነገር ተንበሽብሾ ሕዝቡም የደስታ ኑሮ እየኖረ እንደሆነ ሊነግረን ይሞክራል። ሃቁ ግን የተገላቢጦሽ በመሆኑ በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ራስን ለማታለል ካልሆነ በስተቀር ሕዝብን መሽንገል እንደማይቻል ግልጽ መሆን አለበት።
ሕዝባችን መሠረታዊ በሰላም የመኖር መብቱን ከተገፈፈ ቆይቷል። የህልውና ዋስትናውን አጥቷል። በሰላም ገብቶ የመውጣት፣ ውሎየማደር መብትና ዋስትና ሊያገኝ አልቻለም። ይህ አደገኛ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ሀገራችንንም ሆነ ሕዝባችንን እጅግ ዘግናኝ ሁኔታይጠብቃቸዋልና ዛሬውኑ እንዲቆም የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን። ከዚህ ዓይነቱ የርስበርስ ጥላቻና ግጭት የሚጠቀም ማንም እንደማይኖር መረዳት ያስፈልጋል።

 
በኢትዮጵያችን ውስጥ በሁሉም ላይ አስከፊ የመብት ረገጣ እየተካሄደና የሕዝባችንም ስቃይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነው። በመሆኑም የሀገራችንን ችግር ለመፍታት የትግል ትኩረታችን ከፋፋዩንና ጨቋኑን የህወሓት፨ኢህአዴግ የግፍ አገዛዝ በጋራ አስወግደን በምትኩ አንድነቷ በተጠበቀ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም ዜጋ በእኩልነት የምታስተናግድ ዴሞክራሲያዊና ህገ፡መንግሥታዊሥርዓት የሚያከብር ሕዝባዊ ሥርዓት መመሥረት ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የከፋፋዩችን ሴራ

 

 

 

 

 

 

 

 


አቶ መለስ ዜናዊ በአፍሪካ የጋራ መገማገሚያ መድረክ ላይ የፈፀሙት አሳፋሪ ወንጀል ሲጋለጥ…(በትረ ያቆብ)

$
0
0

በ በትረ ያቆብ

betre yacobከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአፍሪካ ምድር ላይ ሰላምና ብልፅግና እዉን ያደርጋል ተብሎ በአፍሪካ ህብረትና በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋት ታምኖበት የተቋቋመዉ እና “የአፍሪካ የጋራ መገማገሚያ መድረክ” (African Peer Review Mechanism) የተሰኘዉ ተቋም በአጭር ጊዜ ዉስጥ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የተነሳለትን አላማ እንደሳተ እና ከጥቅም ዉጭ እንደሆነ እየተነገረ ነዉ፡፡ በተያያዘም በተደራጀ የሙስና ሰንሰለት ተጠልፎ የግለሰቦች ኪስ ማድለቢያ እንደሆነም እየተገለፀ ይገኛል፡፡ ከዚህ ብዙ አፍሪካዉያንን ካሳዘነ ጉዳይ ጋር በተያያዘም በቀዳሚነት የቀድሞዉ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ፓርቲያቸዉ ህወሐት/ኢህአዴግ አብረዉ እየተወነጀሉ ነዉ፡፡

ይህን አሳፋሪ የአቶ መለስን እና የፓርቲያቸዉን ተግባር በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ መረጃ የደረሰኝ ከሶስት ወር በፊት ሲሆን ፡ መረጃዉን ለጓደኛየ የላከችለት አንዲት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ያካሄደችና ብዙ ዘገባዎችን የሰራች አፍሪካዊ ጋዜጠኛ ነበረች፡፡ የላከችዉም ኢትዮጵያዉያን ሊያዉቁት ይገባል በሚል ነበር፡፡ ባደረግኩት መጠነኛ ጥናት እንደተረዳሁት ጉዳዮ ባልታወቀ ምክንያት ተዳፍኖ እንዲቆይ ህብረቱ ብርቱ ጥረት ያደረገ ሲሆን ፤ ህወሃት/ኢህአዴግም ጉዳዮ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጀሮ እንዳይደር ብዙ ጥሯል፡፡ ያም ሆኖ ግን ጉዳዩን በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች ከዚህ በፊት በአንዳንድ የአፍሪካ ሚዲያዎች አማካኝነት ለህዝብ ይፋ ሊሆኑ ችለዋል፡፡ ነገር ግና እስከ አሁን ግልፅ በሆነ መንገድ መረጃዉ ለህዝብ እንዳልደረሰ ይነገራል፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት “የአፍሪካ የጋራ መገማገሚያ መድረክ” (African Peer Review Mechanism) የተቋቋመዉ በ2003 ዓም ሲሆን ፤ የተቋሙ አላማም የእያንዳንዱን የሕብረቱ አባል ሀገር አጠቃላይ የፖለቲካ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በተመለከተ በገለልተኝነት ጥናት እና ግምገማ ማድረግ እንዲሁም ከዚህ በመነሳት የፖሊሲ አቅጣጫችን ለኃብረቱ በማቀበል ኔፓድ ግቡን እንዲመታ ማድረግ ወይንም የአፍሪካን ሰላም እና ብልፅግና ማረጋገጥ ነዉ፡፡ በተለይም ተቋሙ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ፣ በመልካም አስተዳደር ፣ ሙስና እና የሀብት አጠቃቀም ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡ ተቋሙ በእነዚህ እስትራቴጅክ የአፍሪካ ሀገራት ችግሮች ላይ መስራትና ለዉጥ ማምጣት ከተቻለ አፍሪካን ካለችበት ኋላ ቀርነትና ድህነት ማዉጣት ይቻላል የሚል እምነት አንግቦ የተነሳ ነዉ፡፡

ተቋሙ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት መሪዎችን አቅፎ የያዘ ሲሆን ፤ የተቋሙ ፖሊሲ እንደሚጠቁመዉ በዋና ማስተባበሪያ ፅሕፈት/ቤቱ ስር በየሀገራቱ የሚቋቋሙ በገለልተኝነት የየሀገራቱን ሁኔታ የሚገመግም እና የሚተነትን ገለልተኛ አካላት አሉት፡፡ የእነዚህን አካላት ጥናትን መሰረት በማድረግም የየሀገራቱ መሪዎች በየጊዜዉን እየተገናኙ ይመካከራሉ ፤ ፖሊሲዎችን ይነድፋሉ ፣ መፍትሄ ያፈላልጋሉ፡፡

ከእጄ የገቡት መረጃዎች እንደሚያስረዱት የአፍሪካ የጋራ መገማገሚያ መድረክ አጀማመሩ የተሳካ የሚባል ነበር፡፡ በአጭር ጊዜ ዉስጥም በርካታ ሀገራትን በአባልነት ማቀፍ ችሎ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ብዙም ሳይቆይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምንም እንኳን ከተቋሙ ምስረታ ጋር በተያያዘ ትልቅ ድርጃ የነበራቸዉ ሰዉ የነበሩ ቢሆኑም እንዲህ አይነት ገለልተኛ ተቋም በሚያፈቅሩት መንበራቸዉ ላይ የሚፈጥረዉን አደጋ ከጅምሩ በመረዳት በተቋሙ ላይ ጥቃት እንደሰነዘሩበት እነዚህ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

እዚህ ላይ ለምን እና እንዴት ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነዉ፡፡ የተቋሙ ፖሊሲ እና ህግ ሶስት የተቋሙ ንዑሳን ክፍሎች በየአንዳንዱ ሀገር ይደነግጋል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ “የአፍሪካ የጋራ መገማገሚያ መድረክ የብሄራዊ አስተዳደር ጉባኤ” የተባለዉ የተቋሙ ዋና እስትራቴጅክ አካል ሲሆን ፤ ተግባሩም ግምገማና ጥናት በሚወክሉት ሀገር ላይ በማካሄድ ሪፖርት እንዲያዘጋጁና ለተቋሙ የበላይ አካል ማቅረብ ነዉ፡፡

የተቋሙ ፖሊሲ እና ህግ ይህ ንዑስ ክፍል የሚያካሂደዉ ጥናትና እና ግምገማ ነፃና ገለልተኛ እንዲሆን እና የሚያዘጋጀዉ ሪፖርትም ትክክለኛ ፣ ታማኝ እንዲሁም የሀገራቱን እዉነተኛ ገፅታ የሚያሳይ እንዲሆን በማሰብ ንዑስ ክፍሉ ፍፁም ከመንግስት ገለልተኛ እንዲሆን በግልፅ ደንግጓል፡፡ በዚህም መሰረት ክፍሉ  ከፖለቲካዉ ገለልተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ፣ ከተለያዩ ሲቪክ ማህበራትና ተቋማት የተዉጣጡ ግለሰቦችን ፣ ምሁራንን ፣ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚወከሉ ፖለቲከኛዎችን እና የመሳሰሉትን የሚያቅፍ ሲሆን ፤ ተቋሙን የሚመሩ ግለሰቦችም ፍፁም ከመንግስት ገለልተኛ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ይህ የተቋሙ ፍፁም ገለልተኛ መሆን በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና በፓርቲያቸዉ ፍፁም አልተወደደም ነበር፡፡ በህዝባቸዉ ላይ የሚፈፅሙትን ዘግናኝ ወንጀል ለዓለም ህብረተሰብ አጋለጡብኝ በሚል እንደ ሂዉማን ራይቶች ያሉን አለም አቀፍ ተቋማትን አይን ላፈር ያሉት እና በሀገሪቱ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ ሲቪክ ማህበራትን ጉሮሮ ያነቁት አቶ መለስ ያንን መሰል ጠንካራ ተቋም በፍፁም የሚታገሱት አልሆነም፡፡ በተለይም በተቋሙ የሚካሄደዉ ጥናት እና የሚዘጋጀዉ ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት ከሀያላኑ ሀገራትና እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲሁም ከተለያዩ ምዕራባዊ ተቋማት በሚያገኘዉ ብድርና እርዳታ ላይ ችግር የሚፈጥርባቸዉ በመሆኑ ተማቋሙን በመዳፋቸዉ ጠልፎ ለመጣል እንዲንቀሳቀሱ እንዳስገደዳቸዉ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ እናም አቶ መለስ ጊዜ አላባከኑም ነበር ፤ በፍጥነት በሀገር ዉስጥ በተቋቋሙት የተቋሙ ንዑሳን ክፍሎችን ዉስጥ ጣልቃ በመግባት ተቀዋማቱን በቁጥጥር ስራቸዉ እንዲዉሉ ለማድረግ ደፋ-ቀና ይሉ ጀመር፡፡ በመጨረሻም ጥረታቸዉ ሰምሮ ተቋማቱን በመዳፋቸዉ ማስገባት ቻሉ፡፡ በተለይም “የአፍሪካ የጋራ መገማገሚያ መድረክ የብሄራዊ አስተዳደር ሸንጎን” የህዝብ ዉክልና በማሳጣት በኢህአዴግ የፖለቲካ ካድሬዎች እንዲሞላ በማድረግ እና የተመረጡ ካድሬዎችንም በመሪነት ቦታ ላይ በማስቀመጥ መንግስት በሀገሪቱ ላይ የሚፈፅመዉን ወንጀል በማጋለጥ የህብረተሰቡ ድምፅ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀዉን ተቋም ጠመዘዙት፡፡

በወቅቱ ይህ አቶ መለስና ህገ-ወጡ ፓርቲያቸዉ የፈፀሙትን እኩይ ተግባር የአፍሪካ ህብረትና አባል ሀገራት ሊታገሉት እና ለምን ሲሉ ሊጠይቁ ይገባ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ያለመታደል ሆኖ ያንን ያደረገ አካል አልነበረም፡፡ እንዴዉም ብዙ የአፍሪካ መንግስታት በሀገራቸዉና በህዝባቸዉ ላይ የሚፈፅሙትን አሳፋሪ ተግባር ለመሸፈን ሲሉ የእነ አቶ መለስን ተግባር እንደ ጥሩ ተሞክሮ በመዉሰድ በየሀገራቸዉ ተግባራዊ ያገርጉት ጀመር፡፡ ይህም ተጠናክሮ ቀጥሎ በስተመጨረሻ ተቋሙን የፖለቲከኞች መሰብሰቢያ እና መፈንጫ አደረገዉ፡፡ በጉጉት ይጠበቅ የነበረዉ ተቋም በዚህ ሁኔታ ከሸፈ፡፡ ከታለመለት መስመር ወጣ፡፡

አቶ መለስ እዚህ ላይ ብቻ አልተገቱም ፤ ጥረታቸዉን አጠናክረዉ በመቀጠል በስተመጨረሻ በተቋሙ አህጉራዊ ዋና ማስተባበሪያ ፅህፈት/ቤት ዉስጥ የራሳቸዉን ሰዉ ህገ-ወጥ በሆነና በሚያሳፍር መንገድ አስርጎ እስከማስገባት ደረሱ፡፡ ይህንንም በማድረጋቸዉ ተቋሙን በመዳፋቸዉ አስገብተዉት እንዲቆዩ እስችሏቸዋል፡፡

በአቶ መለስ አሻጥር የተቋሙ አሀጉራዊ ፅ/ቤት ሐላፊ ሆነዋል በሚል በተለያዩ የተቋሙ የቀድሞ ባለስልጣናትና አፍሪካዊ ጋዜጠኞች የሚወነጀሉት ግለሰብ አቶ አሰፋ ሽፋ በመባል የሚታወቁ የኢህአዴግ ሰዉ ሲሆኑ ፤ ሰዉየዉ ከህግ ዉጭ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ ቆይተዋል፡፡  ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ የቀድሞ  የተቋሙ ባለስልጣን የነበረ ሰዉ ለአንድ ጋዜጠኛ ሲናገር “ምንም እንኳን የማስተባበሪያ ፅ/ቤቱ ሐላፊ በየአመቱ በጠቅላላ ጉዳኤ የሚመረጥ ቢሆንም ይህ አሰራር ግን በአቶ አሰፋ ላይ አልተተገበረም ነበር፡፡” ሲሉ ይናገራሉ፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አቶ አሰፋ ወደ መንበረ ስልጣኑ የመጡት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የተቋሙ የኢትዮጵያ ተወካይ በነበሩትና በመንግስት ታማኝነታቸዉ በሚታዎቁት በአቶ ንዋይ ገብረአብ  ተፅፎ በወቅቱ የፓነሉ (Panel of Eminent Person) ሰብሳቢ ለነበሩት ለፕሮፌሰር ሳዌር በተላከ ደብዳቤ ብቻ ነበር፡፡ ይህ አሰራርም ከተቋሙ ፖሊሲ ጋር ፍፁም የሚጋጭ ነበር፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አቶ መለስ ይህንን ህገ ወጥ ተግባር በሚፈፅሙበት ወቅት የዚህን ትልቅ ራዕይ ሰንቆ የተነሳ አሀጉራዊ ተቋም ጠቅላላ ጉባኤ በሊቀመንበርነት ይመሩ የነበረ ሲሆን ይህም ለአላማቸዉ መሳካት ሳይጠቀሙበት አልቀሩም፡፡ በተያያዘም አንዳንድ አፍሪካዊ ጋዜጠኞች ሰዉየዉ በተቋሙ ዉስጥ የነበራቸዉ ተቀባይነትም በተወሰነ መንገድ ጠቅሟቸዋል ሲሉ ይናገራሉ፡፡

አቶ አሰፋ ሽፋ የመጡበት መንገድ ከዚህም በላይ አስገራሚ ነበር፡፡ ጉዳዩን ሲከታተሉ በነበሩ አፍሪካዊ ጋዜጠኞች የወጣዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ሰዉየዉ ማስትሬት አለኝ ብለዉ የትምህርት ማረጃ ለተቋሙ አቅርበዉ አቅርበዉ ነበር ፣ ያቀረቡት ማስረጃም  ደቡብ አፍሪካ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ እንደተማሩ ያትታል፡፡ ሆኖም ግን ጋዜጠኞቹ ወደ ተባለዉ ዩኒቨርስቲ በመሄድ የሚመለከታቸዉ አካላትን ሲጠይቁ ያገኙት መልስ የሚያስደነግጥ ነበር፡፡ ዩንቨርስቲዉ እንዲህ የሚባል ሰዉ አላስተማርኩም በማለት አቶ አሰፋ ያቀረቡት ማስረጃ የሀሰት እንደነበር ገልጠዋል፡፡

ይበልጥ የሚያሳፍረዉ ግን አቶ ሽፋ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የተፈፀሙ አስነዋሪ ተግባራት ናቸዉ፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሰዉየዉ እንዳሻቸዉ የፈለጉትን ያህል ዶላር እየመዠለጡ ያሻቸዉን ከማድረግ ባለፈ ተቋሙንም ለከፋ ሙስና አጋልጠዉታል፡፡ ተቋሙን ጠያቂ የሌለበት ቤት አስመስለዉት አልፈዋል፡፡ በዚህም አልበቃ ብሎ ሰዉየዉ የፈለጉትን ያህል እስኪበቃቸዉ እንዲመዘብሩ ኮንትራታቸዉ እየተራዘመ በስልጣን ላይ ለተከታታይ አመታት እንዲቆዮ የተደረገ ሲሆን ፤ ይህም የተቋሙን አሰራር የተላለፈ ነበር፡፡ እዚህ ላይ አቶ መለስ ይህንን አሳፋሪ ጉዳይ እያዎቁ ዝም ብለዋል ሲሉ ጋዜጠኞች ይዎነጅሏቸዋል፡፡

የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ዛሬ በዚህ አፍሪካዊ ተቋም ዉስጥ ከሙስና ባሻገር የለየለት አንባገነናዊ እና ብልሹ አሰራርም ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡ ይህም ተቋሙን ግልፅ የሆነ የኦዲት ስርዓት እንኳን የሌለዉ እስከመሆን አብቅቶታል፡፡ ኦዲት ቢደረግ እንኳን ለይስሙላ እንጅ ተግባራዊ በሆነ መንገድ ወጭንና ገቢዉን ለመቆጣጠር እና ችግር ሲኖር የእርምት እርምጃ ለመዉሰድ አልነበረም የሚያስብሉ በርካታ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ አንድ በዉጭ ሀገር ተቋም በተሰራ ኢዲት አቶ አሰፋ ሽፋ በግልፅ ያለ አግባብ የወሰዱት ገንዘብ እንዳለ በማሳየቱ ገንዘቡን ገቢ እንዲያደርጉ ቢጠየቁም ሰዉየዉ ግና የዉስጥ ግብረ አበሮቻቸዉን መከታ በማድረግ አሻፈፈረኝ ብለዉ የወሰዱትን ገንዘብ ሊመልሱ አላቻሉም፡፡ ቆይቶም ይህ አሳፋሪ ተግባር እንዲሁ ታልፏል፡፡

በወቅቱ የተፈፀሙት የሙስና ወንጀሎችና ሌሎች ተግባራት እንደ አፍሪካ ህብረት ባለ ተቀዋም ዉስጥ ይፈፀማል ተብሎ የማይታ ሰብ እጅግ አሳፋሪ ነበር፡፡ መረጃዉን ለመጀመሪያ ግዜ ይፋ ያወጣችዉ አፍሪካዊ ጋዜጠኛ እንደጠቆመችዉ ለዚህ ሁሉ ስርዓት አልበኝነት ምክንያቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ናቸዉ ያለች ሲሆን፡፡ ሰዉየዉ ኔፓድን እና ተቀዋሙን በቁሙ ቀብረዉታል ትላለች፡፡

ኢህአዲግ ከ70 ዓመት በፊት በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን በተገነባ ስታዲዮም ውስጥ ሆኖ ግንቦት 20 እያከበረ ኢትዮጵያ አድጋለች ይላል

$
0
0

ለዘንድሮው በዓል ክብረ በዓል በመላ ሀገሪቱ ከግማሽ ቢልዮን (500 ሚልዮን) ብር በላይ ወጪ እንደሆነ እየተነገረ ነው።

OLYMPUS DIGITAL CAMERAበአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ለማወቅ ብዙ ምርምር የሚጠይቅ አይደለም።ህዝቡ የመሰረታዊ ፍጆታዎችን የመግዛት አቅሙ ተዳክሟል።ቀድሞ እናት ልጇን እንጀራ በሽሮ ብቻ ማብላቷ ያሳስባት ነበር።ዛሬ ይህ ዘመን በተለይ በከተሞች አካባቢ በቁጥርም ከፍተኛ በሆነው ሕዝብ ዘንድ ችግሩ ከፍቶ ዳቦ ገዝቶ ማብላት ከባድ ሸክም ሆኗል።አብዛኛው ሕዝብ ስለ ዳቦ ብቻ አይደለም ጭንቀቱ።የሚጠጣ ውሃም ነው። በአዲስ አበባ ብቻ ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጋ ሕዝብ የሚናፍቀው እና ለማግኘት የሚታትርበት አንዱ ተግባሩ ሆኗል የውሃ ነገር።ውሃ ፍለጋ ጀርካል ይዘው የሚንከራተቱ ሕፃናት እና እናቶችን ማየት የተለመደ ነው።በአዲስ አበባ ብቻ አደለም ሐረር፣ድሬዳዋ፣ሐዋሳ እና በርካታ ከተሞች የውሃ እጥረት ላይ ናቸው።

ይህ ከሰው ልጅ መሰረታዊ ፍጆታ አንፃር ብቻ የምናየው ኢህአዲግ/ወያኔ 23 ዓመት ሙሉ ሊያስተካክለው ያልቻለውን ጉዳይ ጠቀስኩ እንጂ ባለፉት 23 ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ በፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብት ዘርፍ ሁሉ ወደ አደገኛ መንገድ እያመራች ነው።እርግጥ ነው ከስርዓቱ በመጠቀማቸው የሀገራቸውን ችግር እና የሌላውን እሪታ ላለመስማት የወሰኑ ወገኖች የሚሉት በተቃራኒው ነው።እውነታው ግን ከእነርሱ አስተሳሰብ ብዙ የራቀ ነው።

ፖለቲካው

- ፖለቲካው በጥቂት በጎሳ የሚያምኑ ኢትዮጵያዊነትን በሚያጥላሉ እና የጎሳ ግጭትን ለመለኮስ እስከ 20 ሚልዮን ብር አውጥተው የእጅ እና የጡት ሃውልት በሚሰሩ ጉድ አመራር ስር ነው፣
- ፖለቲካው ለኢህአዲግ/ወያኔ ማጎብደድ እና መልመጥመጥን ብቻ እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ እና በዙርያው ተስፋ ቢስ ግን ለገንዘብ እና ለጥቅም ባደገደጉ አድር ባዮች ተከቧል፣
- ፖለቲካው ዲሞክራሲ ላይ እየተሳለቁ እና እያፌዙ በሚናገሩ የተቀመጡበትን የህዝብ ትከሻ በዘነጉ ባለግዜዎች ተተራምሷል፣
- ፖለቲካው በአንድ ወቅት በጠበንጃ ስልጣን በያዙ ኃይሎች ስር ወድቆ ለዘላለም ገዢዎች እኛ ነን ብለው እራሳቸውን በሾሙ ሹመኞች ተይዟል።

ምጣኔ ሃብቱ -

- ምጣኔ ሃብቱ አቅጣጫውን የማያውቅ በፖለቲካው እና በጎሳቸው ስም በተሰበሰቡ ግለሰቦች ፍላጎት እንጂ በሀገር ራዕይ እና እድገት መሰረት አይመራም፣
- ምጣኔ ሃብቱ ከ70 በመቶ በላይ በስርዓቱ ስር በተደራጁ ኩባንያዎች የሚሽከረከር እና ሀብት ለማጋበስ ባሰፈሰፉ የውጭ ጥቅመኞቹ እየታገዘ በአስፈሪ እና አደገኛ ኃይሎች እየተሽከረከረ ነው።
- ምጣኔ ሃብቱ ሙስና የገንዘብ ብቸኛ ምንጫቸው የሁኑ ግለሰቦች ኢንቨስተር ተብለው የሚጠሩበት ነው፣
- ምጣኔ ሃብቱ ብሔራዊ ባንክ የተጭበረበረ ወርቅ ከመግዛት አንስቶ እስከ ግምሩክ ኃላፊ ድረስ በሀብት የሚ ምነሸነሹበት ተቋማት ሆኗል።

ኢትዮጵያ ከምንገምተው በላይ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነች

ኢህአዲግ ኢትዮጵያን የዛሬ 23 ዓመት ከነበረችበት ከፍ አደረኩ እያለ ቢናገርም ዕውነታው ኢትዮጵያ ከምንገምተው በላይ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነች።ከምጣኔ ሃብቱ እና ከፖለቲካው የተገለለው ሕዝብ ምሬቱ ገፍቶ የሚወስደው ጫፍ ለማወቅ ይከብዳል።የእዚህ ዓይነቱ ምሬት የኃይል እርምጃም ስለማይቀርለት ከትናንቱ ይልቅ መጪው አስፈሪ እንዲሆን አድርጎታል።

የዘንድሮው ግንቦት 20 እንደባለፈው ሁሉ ካለፈው ይልቅ መጪውን አስፈሪ አድርጎታል።ሃያ ሶስት ዓመት ደቡብ ኮርያ እና ብራዚል የድሃ ህዝባቸውን ቁጥር ቀንሰው ሀብት በፍትሃዊነት እንዲከፋፈል ያደረጉበት እረጅም የተባለ ብዙ ታምር የሚሰራባቸው ዓመታት ናቸው።በኢትዮጵያ ደግሞ 23 ዓመታት ሀብት የተወሰኑ ቡድኖች ውስጥ የተሰበሰበበት፣ ከአስር ሺዎች ወደ መቶ ሺህ ሕፃናት የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑባቸው ዓመታት ናቸው።ህንፃ እና መንገድ መስራት ሕዝብ ማስተዳደር አደለም።የአረና አባል አቶ አሰግደ እንዳሉት ”መንገድ መስራት አስደናቂ ነገር አደለም።ጣልያን በአምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ቆይታው ከስድስት ሺ ኪ ሜትር በላይ መንገድ ሰርቷል።ይህንን ማድረጉ ፋሽሽታዊ ስራው ይቀጥል አያስብልም።

የሆነው ሆኖ ኢህአዲግ ከ70 ዓመት በፊት በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን በተገነባ ስታዲዮም ውስጥ ሆኖ ግንቦት ሃያን እያከበረ ኢትዮጵያ አድጋለች ይላል።ከየቀበሌው እና ትምህርት ቤቶች በልፈፋ አዲስ አበባ ስታድዮም ውስጥ ለተሰበሰበው ሕዝብ አቶ ኃይለማርያም ሲናገሩ ”በምግብ እራሳችንን ችለናል” ሲሉ ተደምጠዋል።”የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም” እና ይችን ንግግር በመጪው የእህል መሰብሰብያ ወቅት ላይ እንደማይደግሙት እራሳቸውም ያውቁታል።እንዳፋቸው ቢሆንልን ጥሩ ነበር።እውነታውን እርሳቸው የቤተ መንግስት እንጀራ ከሚበሉት ይልቅ የሚያውቀው ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።

ለዘንድሮው በዓል ክብረ በዓል በመላ ሀገሪቱ ከግማሽ ቢልዮን (500 ሚልዮን) ብር በላይ ወጪ እንደሆነ እየተነገረ ነው።የግማሽ ቢልዮን ብር ብክነትን አስቡ እና በውሃ ጥም የሚንከራተቱ የከተማ እና የገጠር ነዋሪዎችን አስቡ።ስንቱ በእዚህ ገንዘብ ንፁህ ውሃ ባገኘበት ነበር። ስንት ገበሬ ከባህላዊ የበሬ አስተራረስ ወደተሻሻለ የትራክተር ማረሻ በተሻገረበት ነበር።ከሃያ ሶስት ዓመታት በኃላም በበሬ እያረስን ነው።ቀ 3 አመታት በኃላም ኢህአዲግ/ወያኔ ከ70 ዓመት በፊት በተሰራ ስታድዮም ውስጥ ሆኖ አደጋችሁ እያሉ መፎከር የጤና ይሆን?

ጉዳያችን
ግንቦት 20/2006 ዓም/ ሜይ 28/2014

Source: gudayachn

ጎንደር –ክፍል ሦስት (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ክፍል ሦስት

ከሥርጉተ ሥላሴ 29.05.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

Gondor„ለመደመጥ የጥሩ አድምጩን የጎንደርን ህዝብ ሥነ ልቦና በጥንቃቄ መርምሮ ማወቅ ይገባል፤ ጎንደር መሆን ነውና!“ ጓድ ገብረመድህን በርጋ የጎንደር ክፍለ ሀገር የኢሠፓ ዬድርጅት ጉዳይ ኃላፊ በነበሩበት ጊዜ በአጽህኖት – በተደጋጋሚ የሚቃኙት ቅኔ ነበር። ሲገፉም አብሮ ለመሰለፍ ያስቻለው፤ ቋሚ ጽናት የመነጨው ከዚህ ንጹሕ ፍቅርና እርግጠኝነት እንዲሁም የበቃ አቅማቸው የተፈለፈለ ነበር። እስከ መጨረሻዋ ቀን ድርስ አብረን ነበርን። ማናቸውንም መስዋዕትነት ከፍለን። ጓድ ገዛህኝ ወርቄና ጓድ ገ/መድህን በርጋ አብረው የመሥራት አጋጣሚ ኖሯቸው ቢሆን ኖሮ ህዝበ – ጠቀም  ትዕይንቱ ጎንደር ላይ እጬጌ በሆነ ነበር። ሁለቱም በቂና ሙሉ የመምራት አቅምና ብቃት፤ የህዝብ የጸዳ ንዑድ ፍቅር፤ ከቶውንም ሊገለጽ የማይችል የሥራ ፍቅር ጉልታቸው ነበርና። ለእኔ ህሊናዎቼ ናቸው – ዬምኮራባቸው።

እጅግ የማከብራችሁ የሀገሬ ልጆች ባለፈው ጊዜ ክፍል ሁለትን በዚህ መልኩ ነበር የደመደምኩት። እንዲህ …

ክፍል ሁለት ማጠቃለያው — በዬዘመናቱ መበደሉን እያወቀ ግን በአርምሞና በትእግስት የላቀውን ዬእናት ሀገሩን ጉዳይ በማስቀደም በተደሞና በአርምሞ እንዲሁም በጭምትንት የተቀመጠን ህዝብ ሰብዕና፤ ከእኛም አልፎ ዬዐለም ሃብትና ቅርስ የሆኑ ውድ ጌጦቻችን ያበረከተ ንቁ ህዝብ፤ ለማንኛውም ቋያ ነክ ግዳጅ መቆስቆሻ የሆነውን ወርቅ ህዝብ ዛሬ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይብጠለጠላል በሦስት ተመድቦ …. ይከተከታል መረማመጃም ሆኗል። ግን ለምን?!!!

ጎንደር – ክፍል ሦስት።

እንደ መግቢያ – ጣዕሙን ስፈትሽው እኔን ውስጤን እንዲያሳይ እያስገደደ ነው። እሱን ስገለጥው እኔን እራሴን በሃቅ መተርጎም እችል ዘንድ ሚዛን ላይ አስቀምጦ እዬፈተሸኝ ነው። ስመሰክር ውስጤን አደባባይ አውጥቼ በእርግጠኝነት እንዳቀርብ እዬመከረና ቆሞም እዬጠበቀኝ ነው። የጎንደር እውነትነትና ትውፊትነት እንዲሁም የታሪክ ተመክሯዊ መስታውትነት፤ በተጨማሪም የባህል ልዕቅና ጉልበታምነት ሆነ፤ የተባ ዬተግባር ፍቅር ጉልህነትን፤ በአንክሮ ችዬ መግለፄን ፈተና ላይ አስቀምጦ ለማድመጥ በዝግጁነት ነው። እኔ ደግሞ ፈተናውን እንዳልወድቅ ቢያንስ 50% ቁንጥጧን ማግኘት እችል ዘንድ ጥሬ እዬታገልኩ ነው። ግን እችል ይሆን?

ውጪ ሀገር በምንኖረው በእኛም ብቻም ሳይሆን አፍ እላፊው ሆነ ቅጥዬለሹ ድልደላው እንዲሁም ምደባው በሽታሽቶ በዬዘመኑ የሚወቀጠው፤ በክፉ አይን የሚታዬው ያ መከረኛና አሳረኝ ሀገርቤት ያለውንም ህዝብንም – ረመጡ ይኽ ነው። ዘመንና እርግማን ….

ሀ. „የወያኔ ሙሉዕ ደጋፊነት፤“

ለ. „የአማራነት አክራሪነት፤“

ሐ. „ለነፃነት ደንታ ቢስነት“ አራተኛም አለ „መሃል ሰፋሪነት“ – ያንገሸግሻል – ለመስማትም- ምግለት።

በቅድሚያ ወደ ዝርዝሩ ከመግባቴ በፊት አንድም አካባቢ ተነቅሶ በተገኘው አጋጣሚ መጠቃጠቂያ የሆነ የለም። በጠላትም በወገንም በኩል አለመሰልጠኑ፤ ቁምጣ ለባሽነቱ፤ ደንታቢስነቱ፤ ባላገርነቱ፤ ውጪ እንኳን ወጥቶ ከታክሲ ሹፌርነት ውጪ ሥልጣኔ – ገብ አለመሆኑ በአነጋገር ዘይቤው ሁሉ ይወቀጣል – ጎንደር ብቻ። ኧረ ስንቱ?

-       ለዛውና ዘይቤዊ አነጋገሩ ሆኑ ልዩ ግርማ ያላቸው ሙሽራ ቃላቶቹ በቋሚነት በኤሎትሪክስ ሚዲያ ሆነ በፕሬስ እንዲሁም በመጸሐፍት ህትምት ተጠናክሮ ይቀጥላል። እራስን ተበድሮ ወይንም ተውሶ መኖር ተፈጥሮው ስላልሆነ።

-       በኢትዮጵያዊነቱ የመኖር አቅሙ ዛሬ ሳይሆን፤ አርቲፊሻል ሳይሆን ሆኖ የኖረበት አብነት ስለሆነ ንቅንቅ አይልም። ተፈጥሯውን አይዘልም ወይንም አይደፈጥጥም።

-       ቁምጣ ለባሽነቱ የአርበኝነት መለያ ምልክቱ ስለሆነ ትውፊቱን አበልጽጎ ይቀጥልበታል – አጉልቶ።

-       ባለገርነቱ – አዎን ሀገር አልባ አይደለም በነፃነት የኖረች እናት ሀገር አለች – ፈተናን እንደአመጣጡ እያሸነፈች የኖረች ገናና – ኢትዮጵያን የመሰለ የሰው ልጆች መፈጠሪያ አለችው – ይኮራባታል ቃናውም ቅኔውም – ዜማውም – መዝሙሩም -ማዕዛውም ናት።

-      አለመሰልጠኑ ቅርሶቹ ለዓለም አቀፍ ውርስና ቅርስ መብቃታቸው ህሊናን ሚዛን ላይ ያሰቀምጣል። ከዚህም ባለፈ ከዬትኛውም አካባቢ ከሚመጡት ወገኖቹ የሚመጥን የሥልጣኔ አቅም አለው። የቀለም – የዘር – የሃይማኖት ልዩነት በሌለበት ሁኔታ ሰልጥነዋል ከሚባሉት ሀገሮች ህዝቦች ጋር በተሻለ አቀራረብ መስሎ ሳይሆን መጥኖ የመኖር መክሊቱ ትርፋማ ነው። ይህም ተጨባጭ ነው።መረጃው መዳፍ ላይ ይገኛል።

እርግጥ ነው የወያኔ አሙካዎች የወጣላቸው የወያኔ ሃርነት ትግራይ አባላት ፓልቶክ ላይ ሥማቸውን ብታዩት „ማይዘጎንደር፤ በለሳ፤ አርማጭሆ፤ ጎንደር፤ አመድወንዝ፤ አንገረብ፤ አንባጊዮርጊስ“ ወዘተ ነው። ይህ ምክንያታዊ ነው። በሁለት የሚሰነጥቅ። አንደኛው ጎንደር አረሙን ወያኔን ከልቡ ተቀብሏል – ደጋፊ ነው ለማሰኘት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የነፃነት ትግሉ ቤተሰብ ጥርጣሬ እንዲሰፍንበት ሆን ተብሎ የተሸረበ ሴራ ነው። የሆነ ሆኖ መሆንን ለሚያውቅ ቅን ዜጋ መንፈሱ የረጋ፤ የብረት ማገር ነውና ከፍላጎቱ ሆነ፤ ከአንጡራ የመንፈስ ቅርሰ – ሃብቱ ጭብጦ መስረቅ  ጠላት አይችልም። እኔ የምታዘበው በሁሉም አቅጣጫ ተነጥሎና ተለይቶ በይፋም ሆነ በሽምቅ ጎንደር ሲነሳ መታመስን ነው፤ ይህ ለእኔ የሚሰጠኝ ጉልህ ምላሽ የበታችነት ስሜት የወጠነው ወይንም ያስታጠቀው እራሱን መሸከም ያልቻለ ለጋ ስሜት ይመስለኛል – ብዕር የሚያነሳውም፤ የማይክ ተጠቃሚውም – ሽምቅ ተዋጊውም፤ ይህ የበለጠ ለጥንካሬ የሚጋብዝ እንጂ ጉልበትን የሚያሞሽሽ፤ ወይንም ጥንካሬን የሚሸበሽብ ሊሆን አይችልም። በጠራ ቋንቋ ምን እንዳለን – ምን እንደምንፈልግ – ምን እንደምንችልና ምን እንደተፊቀደልንም በሚገባ እናውቃለን።     

ሀ. „የወያኔ ደጋፊነት“ … ወይንም የባንዳ ደጋፊነት። ቃሉ እንዳይጠጋኝ በጥቅስ ውስጥ ይቀመጥ። ብራናዬም ይቀፋታል። ከምን አንፃር? ከዚህ በላይ ምን በደል አለና? ከአፈር – ከመሬት፤ ከድንበር በላይ ምን ጥቃት አለና? ወልቃይትና ጠገዴ – አዲረመጽና አዳርቃይ – ሰቲትና አብደራፊ አሁን ደግሞ ድንቁ ዋልድባ ገዳምን፣ ስሜን ፓርክንም ጨምሯል መሬቱ መወሰዱ ብቻ መሰላችሁ። በዬዕለቱ በነዋሪዎች መንፈስ ላይ የሚጫነው በበቀል የጨቀዬ ድቀት ቅጣቱ፣ ውርድቱ፣ ግልምጫው፣ የበታችነቱ፤ በስላቅ መገፋቱ – መገፍተሩ፤ የአጽም – ፍልሰቱ፤ የአዛውንታት አፈናውና – ድራሻቸው ጥፋቱ፤ የአንስት እህቶች ከፍቃድ ውጪ መደፈሩ፤ የነፍስ ልግጫው፤ በእርስታቸው ላይ ባይታዋርነቱ፣ በህዝብ ማህል መሳቂያነቱ ይህ ክብር ነውን? ይህ ደስታን ያመነጫልን? ዕድሜ ዘለቅ ቅርሶች መዘረፋቸው – መቃጠላቸው፤ ታሪካዊ ዝክሮች በስውር መጥፋታቸው፤ ይህ መንፈስን ለጠላት ይሸልማልን? በፍጹም! ውርደትን ተቀብሎ ድጋፍን ከመሰጠት አፈር መልበስ ይበልጣል። በብረት ብቻ ሳይሆን በብረትና በድንጋይ መዶሻ ተቀጥቅጦ መሞት ይሻላል – ሙጃን ከመደገፍ። እንተዋወቃለን እኮ ጫካ ላይ ምን እና ምን እንደ ነበሩ – እርቃኑን የቀረ ደመ – ነፍስ መንፈስ እንዴት ተብሎ ይደገፋል?! በምን ስሌት?! ህልም ነው።

አንድ የወልቃይት የጠገዴ ኗሪ ከተማ መኖር ቢያምረው በመንፈሱም አያስበውም ትግራይ ሄዶ መኖርን፤ እንኳንስ ገንዘቡን ሆጭ አድርጎ ቤት ሊገዛና ሊሠራ ቀርቶ። ፈጽሞ! ባዕቱን ፈልጎ ሄዶ ጎንደር ላይ ይሠራል – ይኖራልም ደስ ብሎት። የትግራይን ህዝብ ጠልቶ አይደለም፤  አንድ ጊዜ ስለ አይሁዲት ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ከሀገርቤት ፕሬስ ጋር በነበረው ቆይታ „አዜብ አጀንዳችን“ አይደለችም ብሎን ነበር። እንደዛ ነው ነገሩ። ጠረኑም አይጠጋም። የፈለገ ቢበደል ወይ ወደ ማህል ሀገር በስተቀር እርግጫውን ቀምሶ ይኖራል እንጂ ፍትህ ፍለጋ „ትግራይ“ አይታሰብም። ቅርጥምጣሚዎች አሉ ውጪ ሀገር የሚኖሩ እነሱ እንኳን ወደ ሀገር ሲሄዱ ትኬታቸው ጎንደር ይላል። በጎንደር አድርገው ሰቲት እንጂ በትግራይ እእ፤ ለወላጆቻቸው የሚያደርጉት ነገር ካለም ጎንደር ላይ። በመንፈስ ፈቃድ መገዛትና በመንፈስ  ሽፍትንት መገዛት በጣም የተለያዩ ናቸው። ሊቀራረቡም የማይችሉ የሩቅ ገደል ግልም – ጎርማዳና የዶዶሙ ዕይታዎች ናቸው። አይታሰብም።

ነገር ግን በአብሮነት ሂደት ውስጥ ያለው አምክንዮ ደግሞ ሌላ ውብ እርእስ ነው። አፈሩ መርግ ሆኖ ይክበዳቸውና ሄሮድስ መለስ በቦታው ተገኝተው ጠይቀው ነበር  „ሊጠይቁን የሚፈልጉትን ነገር አናውቀውም ነበር ያላቸው“  ማናቸውም ኢትዮጵያዊ  ጎንደር ላይ ሲኖር ደንበር አልቦሽ ሆኖ ነው። ተግባር ይመሰክረዋል። ጎንደር ላይ እኮ „የቴወድሮስ ከተማ የለም“ ዬየኋንስ ከተማ እንጂ። አብዛኛውን የጎንደር ሰው ከፋሲል ይልቅ ምርጫው የኋንስ ነው። ከአንድ ቤተሰብ በጣምራ የኋንስን ይጠሩበታል – ከፍቅሩ ከአክብሮቱ የተነሳ። በሃዘን ተፍሰኃው፤ በቤተ እግዚአብሄር ውሎም ቢሆን የመንፈስ አባቶቻቸውን አክብረውና አቅርበው እንጂ አጋ ለይተው አይደለም – አብረው ናቸው። ነገር ግን ጠላቱ ማን እንደ ሆን? ስለምንስ እንደ ሆነ? አስተርጓሚ አያስፈልገውም – ወይንም ቀስቃሽ። አሳምሮ ጠፈፍ አድርጎ ጎንደር ያውቀዋል።

ከዚህ በላይ በዬዘመኑ ማገዶነት – የግንባር ሥጋነት የማን መለያ እንደሆን ታሪክ ቆሞ ይመሰክራል። የሀገርን ልዑላዊነትን ለማስከበር ከሁለቱ የጫካ አራዊቶች ጋር በነበረው ፍልሚያ እሳትን እዬቀደመ ይረመጠመጥ የነበረው ማን እንደ ነበር በህይወት ያሉ የሠራዊታችን ከፍተኛ መኮንኖችም ሆኑ ባልደረባዎቻቸው ሀቁን መናገር ይችላሉ። ግንባር ላይ የሚሸሽ አንድም የጎንደር እትብት ኖሮም አያውቅም። እንዲህ ዓይነት ወንድ ልጅ የጎንደር እናት አምጣ አትወልድም – በፍጹም።  እስቲ ከቻላችሁ የድንቁን ጸሐፊ የአቶ ገሪማ ታፈረን „ጎንደሬ በጋሻውን“ አንብቡት። ሴቶች ሳይቀሩ ሥማቸው ተዘርዝሯል የጣሊያንን መሪዎችን አንገት እንዴት እንደቅል ይሰዬፉ እንደ ነበር። መርምሩ – በውስጡ መኖር ያስችላችኋል። የአርበኝነት እውነት በልጽጎ የአልገዛም ባይነት ብርታት ፈክቶ ፈልቆም ጎንደር ላይ እትብት

ለ.የአማራነት አክራሪነት፤“ „አማራነት“ የሚለውን እራሴን ነው ለናሙና ዬማቀርበው። ሲዊዝ እራሱ ቅርበቴ ከእነማን ጋር እንደሆነ የሚያውቀው ያውቀዋል። ለመንፈሴ የሚመች የሀገሬ የኢትዮጵያ ልጅ ዬልቤ ነው። ከዚህም ባለፈ ገደብ አልቦሽ የበዙ ሲዊዞችን ጨምሮ በርካታ ግንኙነት፣ ጠንካራም ትስስር ከሌሎች ሀገር ዜጎችም ጋር ነው ያለኝ። ባይኮራበትም በእርግጠኝነት ሙሉዑነት መግለጽ ያስችላል።። በቃ! ስለ „አማራነት“ እኔ እራሴ አላውቀውም። ቤተሰቦቼ እራሳቸው የሚያውቁት ስላልነበረ፤ ቤተሰቦቼ „አማራ“ ነሽ ብለው አላሳደጉኝም። ቤተሰቦቼ የማያዋቁትን እኔ ዬት አባቴ አምጥቼ ላውቀው እችላለሁ? ለዚህም ነው ብዙ ነገሮች የማይመቹኝ። እምወደው ፓርቲዬ ኢሠፓ ቆርጦ በሚገስጻቸው ወይንም በዲፕሎማሲ ቋንቋ ከቦታ ወር በሚያደርጋቸው ጓዶቼ ጎን እስከመጨረሻው ነበር እምሰለፈው። በድፍረት። ያላደኩበትን ዬት አባቴ አምጥቼ እሆነዋለሁ። ጓድ ወንደወስን ኃይሉ የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሜቴ ተለዋጭ አባል የቺኮዝላባኪያና የሀንጋሪ አንባሳደር ሲሆኑ ከሥርጉተ ጋር በማናቸውም ሁኔታ ይገናኙ ነበር። ጓድ ገ/ መድህን በርጋ ጎንደርን እንዲለቁ ሲወሰን አብራቸው ሥርጉተ ነበረች፤ የሚዛን ተፈሪ ክ/ ሀገር አንደኛ ጸሐፊ ሆነው ከፓርቲያቸው ያፈነገጠ አንጃ ፈጥረዋል ተብለው ማዕከላዊ ሲታሰሩ በግልጽ ደብዳቤ ፈቃድ ጠይቃ እሳቸውንም ቤተሰባቸውን ሄዳ ጠይቃላች – ሥርጉተ፤ ጄ/ አሰፋ ሞሲሳ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲገጥማቸው ሆለታ ገነት ድረስ ሄዳ አይታቸዋለች፤ አሁንም ሌትና ቀን የምትባትለው ስለ ታላቁ ኢትዮ – አፍሪካዊ የቅኔ ንጉሥ ስለ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ድህን ነው። የምትከሰበት፤ የተገለለችበት አምክንዮ አንዱም ይሄው ነው። ሲዊዝ ውስጥ አንድ ቀን ከአንድ ጎንደሬ ጋር ቡና ጠጥታ አታውቅም፣ ወይንም ስትጓተት አትገኝም። ሃጢያት ሆኖ ግን አይደለም። ቀድሞ ነገር ጎንደር እትብታቸው የተቀበረ ወገኖቼ ከዚህ ሲዊዘርላንድ ምን ያህሉ ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም። ስለምን? አላደገችበትም። እነሱም አይፈልጓትም። ያለደጉበትን ከዬት አምጥተው። እንዲህ ቢሆኖ ስንቱን መከራ አብረዋት በታገሱ ነበር …..

ሐ. „ለነፃነት ደንታ ቢስነት።“ ማን እዬከፈለን ይሆን እንዲህ መቆስቆሻ የምንሆነው? ስንት ባውንድ ይሆን በዬወሩ የተቆረጠልን?! በኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ላይ ጎንደሬን ዘጭ ያደረገ ንግግር በተደጋጋሚ በጆሮዬ አድምጫለሁ። አላዝንም። ስለምን? እራሳችን እናውቃለን። የበታችነትም ፈጽሞ አይሰማንም። ያጣነው ነገር የለም። ማለት የመንፈስ ደሃዎች አይደለንም። የትም ቦታ የሚመጥን አቅም እንዳለን አሳምረን እናውቃለን። ከሁሉ በላይ „ሙያ በልብ ነው“ መርኃችን። ብዙ ነገሮች ድከምቶች በሉት ወቀሳዎች ተነቅሰው ተሸከም ይባላል – ህዝቡና ልጆቹ።  በድንበሩ ጉዳይ „ሰማያዊ ፓርቲ“ ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጅቶ ብዙ ሰው አለውጣም ተብሎ ጎንደር እስኪበቃው ሲከተከት ነበር። ቃሉን ብገልጸው እራስን መስደብ ይሆናል። ግን ስለምን? ብሎ መጠዬቅ መልካም ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ጉዳዩን በቅርበት አድምጦ እርምጃ መውሰዱ ፍጥነቱ አንቱ ነው። ነገር ግን መሬት ላይ የሰከነ የሚሠራ ነገር ካልኖረ በጥድፊያ ጎንደር ላይ  ምንም ነገር መከወን አይቻልም። ሥልጣን ያለው አካልም ቢሆን በፈለገው ነገር ላይ ይመካ – አይችልም። አቅም ሆነ ጉልበት ይኖረው እማይቻለው ነገር ጎንደር ላይ አይቻልም። ሥጋን መግዛት እንጂ መንፈስን መግዛት አይቻልም። አንድ ምሳሌ እንዳነሳ ይፈቀድልኝ። እትብቴ በተቀበረበት ተወልጄ ሳድግ፣ ስኖርና ሥሰራ በውጩ ሆኜ ሳይሆን በውስጡ ስለነበርኩ ደልዳላ መረጃዎች አሉኝና።

በደረግ ጊዜ መንደር ምስረታ ለማስፈጸም ከፍተኛ ችግር ነበር። እኔ ጋይንት ዞን ነበርኩኝ። የጋይንት ህዝብ ጥንካሬ ብርታት ታታሪነት መግለጽ አልችልም። ስለምን? ከአቅሜ በላይ ነውና። ቤታቸው ጅብ ገል ይባላል። ክዳኑ በእሳር የሚሠራ ሆኖ፤  ግማሹ ግድግዳ በድንጋይ ወጥ ሆኖ ይሠራል፤ በሌላ በኩል ሥራ ወዳዶችም ስለሆኑ የተሻለ ኑሮ ያላቸው ቤታቸው ደርብና ምድርም ነው። በጣውላና በድንጋይ የተሠራ። ይህን አስፈርሶ መንደር ለመመስረት እጅግ – እጅግ ከባድ ዳገት ነበር። ከባድ የጦር መሣሪያ ለአስፈፃሚነት ነበር የተሰናዳው። መሣሪያ ቢጠመድ ግን የጋይንት ህዝብ – ይስቃል። እንደሚያሸንፍ ያውቀዋል። ልበ ሙሉ ነው። ደፋርም ነው። የዬትኛውንም ህዝብ ሥነ – ልቦናውን ስታውቁት መፍትሄው ከቅርብ ነው። 14 ቃላት በሁለት ዐረፍተ ነገር ግን ደንዳናውን ልቦናቸውን አራርቶ አሸነፈ። እንዲያውም እኛ እንበልጥ እኛ እንበልጥ ውድድር ጀምረው ካለምንም ብጥብጥ፤ ከመንግሥት ጋርም ሳይጋጩ ቡድኑም ሳይተዋክ በለሰለሰ ሁኔታ፤ ትህትናን በሰነቀ አኳኋን መርኃ ግበሩ ተፈፃሚ መሆን ቻለ። የተጠመደው መድፍና መትረዬስ አልነበረም ያሸነፋቸው። ከልባቸው ጠብ ያሉ ሁለት ስንኛት ነፍሳቸውን ገዝተው ፈቀዱ – በደስታ።

ሌላም – ጎንደር እንደ ሻ/ መላኩ ተፈራ የበደለ ልጅ የለውም። አይናቸው ደስ ብሎት እንኳን የሚመሩትን ህዝብ የማዬት አቅም አልነበራቸውም። እንዲህ ብዬ ልለፈው። በኋላ ጓድ ገዛህኝ ወርቄን ሰጥቶ በትህትና ሁለት ሦስት ሰዓት ነበር ቢሮቸው መግቢያ ላይ ቀጥ ብለው የተበደለን በማዳመጥ፤ ከዛው በዘቦች ስልክ ደውለው ጉዳዩን ለሚመለከተው ክፍል እራሳቸው በባለቤትነት ስሜት በመከወን፤ ሁሉም ይቅር ያ የሚበራ ግንባራቸው ብቻ ይበቃ ነበር አይደለም ሌላው። „ከፍትፍቱ ፊቱ“ ይላል ጎንደሬ – ለማንኛውም ወያኔ በስሱ ገብቶ ፍርደ – ህዝብ፣ ድምጽ – ህዝብ በሻ/ መላኩ ተፋራ ላይ ለማሰጠት ሞክሮ ስብሰባ አብዮት አደባባይ ላይ ጠራ፤ ቻለን አረሙ ወያኔ? እእ! አልቻለም። የጎንደር ህዝብ የበቃ መንፈሱን ከሱቅ ተሂዶ የሚገዛ ደጋፊነት ሆነ ተቃዋሚነት የለም። በመንፈሱ ዲታ ነው ሃብታም። በራስ የመተማማን ብቃቱ ያጠግባል – ጉልበታምም ነው። ድፍረቱ ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራ – የሚመክት ነው። ውሳኔው ህይው፣ ውበታማ ጸዳሉ ቆሻሻን የመርገጥ አቅሙ – አንቱ ነው። ለማናቸውም ፍላጎቱና እምነቱ ጽናቱ የማይበገር ማገር ነው። በሃይማኖቱ ያለው ፍቅር ከእንቁላል ውሃ የተገነባ ነው። አሁን በሥርጉተ ልብ ውስጥ ልቡን ገጥሞ እንደ ቦይ ውሃ ሊያፈስ የቻለ ማን ነው? ይቻላል? ማንም አይችልም። አይታሰብም። እንደ ተፈጥሮዬ – እንደ መንገዴና እንደ መርሄ ነው የምኖረው። ይህ ከታሪካዊው እትብቴ አፈር የተቀመመ የውስጤ መልክ ነው። ሳምንና ሲገባኝ ብቻ ነው መገኘት የምችለው።ነገር ቀድሞ ይገባናል እንደዛ ነው ….

ጎንደር ለረጅም ጊዜ ማዕከላዊ የኢትዮጵያ መዲና መሆኗ፤ በዬጊዜው በሚቀሰቀሱ ጦርነቶች የሚቀሩ የበቁ ማህበራዊ ህሊናዊ ዕሴቶች፤  ኢሠፓም ሆነ ኢህአፓ የፈጠረው ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ታክሎ፤ ከሁሉም በላይ የሃይማኖታዊ የቀደመ የሚስጥራት ጥልቅና የዳጎሰ ዕድምታ – ትርጓሜ፤ በተፈጥሮ የሚገኙ የትውልድ ውርርስ ጸጋዎች ተዳምረው የዳበረና የሰከነ፣ የሠለጠነ ብጡል ብቃት በመንፈስ ላይ አጽንተው ገንብተዋል። በቀለሉ የማይናድ – በቀላሉ የማይገባበት። ይህ በድንገተኛ አቀራረብና አያያዝ የሚደፈር አይደለም ወይንም በታንኳ እንደ አሻው የሚቀዝፍበት አይደለም። የእንቁላል ግንብ ነው። ወያኔን እኮ ዬትኛው አካባቢ ነው ሽንጡን ገትሮ የተዋጋው ከአንቦ በስተቀር ጎንደር ነው ፊት ለፊት በጣም ለርጅም ጊዜ የታገለው፤ ወያኔንም  የተረፈረፈው።

ያው ይታወቃል ጎንደር ሲባል ብዙ ሰው መስጥሮ ዓይኑ ይቀላል። ጸጉሩ ይቆማል፤  የንጉሦችን ንጉሥ ዐፄ ሚኒልክን አትንኩ የሚል አርበኛ የንጉሦችን ንጉሥ ዐፄ ቴወድሮስን ቀጥቅጡ ሲል ትሰማላችሁ። የጓጎለ ያልጠና የመንፈስ ድህነት። የጸሎት መጸሐፍት የሚጽፉት እንኳን „ታምረ ማርያምን“ እስኪ አንብቡት በሞቴ ሁለቱም የንጉሦች ንጉሥ ዘመናቸው የፈቀደላቸውን ከውነዋል። እንዲያውም ከዘመኑም የቀደሙ ነብይም ነበሩ – ሁለቱም። ይህ ሃቅ ለእኔ የሚሰጠኝን የዳበረ ትርጉም ያህል ለሌላው አይሰጠውም። ስለምን? የነፃነት ቃናን፣ የኢትዮጵያዊነት ህግጋትን የመተርጎም ሆነ፣ ጥልቅ የማንበብ አቅምን ይጠይቃል። አንድ ኢትዮጵያዊ ዐፄ ቴወድሮስን አልቆ ዐፄ የኋንስን ወይንም ባልቻ አባነፍሶን ቢያል ለእኔ መራራ ነው። ጎንደርም ሥርጉተን መታዘብ አይደለም ድቅቅ እንድል ይረግመኛል

እንደሚታወቀው ሃይማኖታዊ ዶግማዎች ብጥብጦች ከተነሱ ለማስከን እጅግ ከባድ ነው። ያን የታመሰ ዬኦርቶዶክስ ተዋህዶ የዶግማ ሆነ የቅኖና ውቂያ ዬት ላይ ነበር በዴሞክራሲያዊ መፍትሄ አምንጭነት ለዛውም በዛ በጥንት ዘመን መልክ ያዬዘው? የዘመኑ ልዩ ሥጦታ በነበሩት በዐፄ ፋሲል ዘመን።  ሊቃውነተ – ቤተክርስትያናት ካራ – ጸጋ – ቅባት በሚባል ሃይማኖታዊ ዶግማ ሲከታከቱ ኖረዋል። ወደዛ መግባት ጸጋዬ ስላልሆነ ዘልዬ ጦር አማዞ፣ አጋ አስለይቶ ሲያፋልጥ የኖረውን እንዴት እንደ ነበር? እንዲህ ይሉናል አራት ዓይናማው ሊቅ ሊቃውንቱ ጸሐፊ ተክለፃድቅ መኩሪያ

„ ከሦስቱ ወገኖች ማናቸው እውነትን ዬያዙ እንደሆነ ለማረጋገጥ ዬአውራጃ ሊቃውንት በሻና በአንጎ ላይ ተስብስበው እንዲከራከሩ ንጉሥ ዐፄ ፋሲልና ጳጳሱ አቡነ ማርቆስ አዘው ነበር። ከጎጃም ከቅባቶች ወገን ዋናው ተከራካሪ ዘእያሱ የሚባለው ነው። ከደብረ ሊባኖስ ተዋህዶዎች ወገን አዳም ዘእምፍራዝ የሚባለው ሆኖ ብዙ ጥቅስ እያጣቀሱ ተከራከሩ። በመጨረሻም አዳም እምፍራዝ ተዋህዶ አሸነፈ። ዘእዬሱስ ቅብዕት ተሸነፈ ተብሎ ጉባኤው ተፈታ። የቅባቶች ወገን ከጎጃም በተለይ ደብረ ወርቆች ናቸው። ተዋህዶ ግን በደብረ ሊባኖስ፣ በሽዋ፣ በጎንደር፣ በትግሬ ነው። ጸጋዎች ግን ይበልጥ የሚገኙት በሽዋ ነው ይባላል“ ገጽ (ገፅ 148-149 )* በዚህ መልክ በተለይ በተዋህዶዎችና በቅባቶች መሃከል ተነስቶ የነበረውን እሳት የሚያጠፋ ፍጥጫን ከሥሩ የነቀለ፤ የዳበረ ሥልጡን የዴሞክራሲ ያደገ ልምድ ፤ በመንፈስ የዳጎሰ መረቅ ቅርሱ በትውልድ ውስጥ ገንብቶ በትውፊት ማብቀሉ መንፈስን ልምድ ጠገብ አንዲሆን አድርጎታል – ፍሬ ዘሩ ዲታ እንዲሆን አግዞታል። ይህ እንግዲህ የፈረንሳይ አብዮት ተነስቶ „ነፃነት፤ እኩልነት፤ ወንድማማችነት“ የሚል ዓለምዓቀፍ ዴሞክራሲያዊ መንፈስ ከመፍጠሩ በፊት ቀድሞ እጅግም በጣም ቀድሞ ዕውን ሆኗል።

ይህ በራሱ አቅም ያለው የመንፈስ ውርስ ነው – ትውፊት። ትውልድ ከቶውን ሊተካቸው የማይችሉት ኢትዮ አፍሪካዊ የጥበብ ቅርስ ህይወትም የነበሩት ሰአሊ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ የማስተር ፒሳቸው  „እናት“ ነፍስ የዘራች – መንፈሳዊት፤ ወጥ ሀገር በቀል ልዑቅ ተግባር ቀልብ ያረፈው ከአዲስ ዘምን ሊቦ ወደ ጎንደር ሲኬድ ያለ ዬሜሮናዊ ተራራ ትርጉም ነው። ተራራውን እንዲሁ ስታዩት ያቺ ቀደም በሰው እጅ ያልተሰመረችውን ወ/ሮ ኢትዮጵያን ቁጭ። እንደ ግሼ! ኢትዮ አፍሪካዊው የቅኔው ንጉሥም የሎሬት ዕዝለ መንፈስ ያረፈበትን „ሊማሊሞን“ እንዲህ ይለዋል በጥቂቱ ከአባቴ – ጽዑም ቅኝት እንሆ -

„ሊማሊሞ“

„ ….. ክንፉ ከነካስማው ዘሞ

ከጽንፍ ጽንፍ አርምሞ

ከደበራቅ እስከ አዲ አርቃይ

አለት ከደመና በላይ

አዘንብሎ እንደ ሰማይ

እንደጠፈር ሽቅብ ሲታይ፤

ጉም አጥልቆ እንደቀሚሱ

ፀሐዩን እንዳንገት ልብሱ

ተከናንቦ ተሸላልሞ

ተንደላቆ ሊማ – ሊሞ  /// ///

የቅኔው ንጉሥ ዝቅ ብሎ ደግሞ ወደ ማጠቃለያው …. እንዲህ ለዛዊ ተፈጥሮውን ከሰማዬ ሰማያት ይቀዳዋል …..

የጉም ክናዱን እንደጣር፣ ወደ ምድር ማኀፀን ልሞ

እንደባቢሎን ግንብ አጥር፣ ቋንቋ ለቋንቋ አሳድ

አልበገር አልደፈር፣ አልሰበር ያለን ከርሞ …….“  ( እሳት ወይ አበባ ከ114- 115)

አቤት! ዜማ አቤት! ውበት አቤት! ጣዕም …. አዬ ሊቁ አንተም በሥጋ ትሞትን?! ጌታዬ ተራቆትን አንተን በማጣታችን።

ሊማ – ሊሞን … ገታ ላድርግና ሌላ ማከያ አለኝ ከዚህ ንዑድ ጥልቅ መንፈስ ሳንወጣ። የሥነ – ጥበብ ዓራት ዓይናማ ሊቀ – ሊቃናት እንዴት ጎንደር ላይ ቅዱስ መንፈሳቸው ያርፍበት እንደ ነበር ለማጠዬቅ የእሳት ወይ አበባ መድበል ግጥም „ይድረስ ለወንድሜ ለማላውቅህ“ መግቢያው በጎንደር በር ተሟሸ። ሥጦታውም እዛው አረገ። እኔ እላለሁ ጋሼ ጸጋዬ አንድ ሰው አልነበረም ህዝብ እንጂ።

„ይድረስ ለወንድሜ ለማላውቅህ „

„ ….ርቀህ ተብርህ ሰንብተህ

የቱሪስት ካርድ የሳበህ

አንተ ማነህ?

እኮ ማነህ ወንድምዬ፣ ደራሲ የሚቃኘው

ሣአሊ የሚነድፍብህ

ቀሲስ የሚቀስብህ

የቱሪስት የጋዜጠኛ፣ ካሜራ እሚጋብዝህ

የሚተች የሚተረጉም፤ የሚነድፍህ የማንም እጅ

የማነህ ደም የማነህ ቅጅ?

አንተ የእማማ ኢትዮጵያ ልጅ  (ገጽ 26)

ያ የሚስጥራት የዜማ ጣዝማ የነበረው የቅዱሱ መንፈስ ያሬድስ የመክሊቱ መና አህዱነት – ያው ጎንደር።

እንደ መሰብሰቢያ — ሌላው ቀርቶ የታሪካችን አካል የሆነው የግራኝ መሐመድ እረፍት እኮ ጎንደር ነበር። ደንቢያ ላይ የግራኝ በር ይባላል። በነገራችን ላይ በዛ ዘመን የትግራዩ እንደርታና የጎንደሩ ደንቢያ በከንቲባ የሚተዳደሩ ዕውቅና የነበራቸው ከተሞች ነበሩ። ዛሬ ግን የእንደርታን ባላውቅም፤ አይደለም ደንቢያ ጎንደር አንዲት መንደር ናት በጨለማው ዘመነ በወያኔ – የታሪክ ረግረግ። ታሪክ ማለት እንደ ሥርጉተ ዕይታ – የህዝብ ወላዊ አዎንታዊና አሉታዊ አምክኖዊ፣ ክስተታዊ ክንውኖች ዕደሜ ጠገብ ሲሆኑ ታሪክ ይባላል። ይህን መክፈል ወይንም እንደ ዶሮ መበለት አይቻልም። ታሪክ ከአንገት በላይና በታች፤ ወይንም ሲሶና እርቦ ተብሎ ሊከፈል ከቶውንም አይችልም። አሉታዊም ሆነ አዎንታዊው ክንውኖች ለታሪክ ወጥ ገፀ – ባህሪው ወይንም ሙሉ ቁመናና መልኩ ነው፤ ታሪክ የትርጉም ሥራ አይደለምና።

ውዶቼ ዘመን ጠገብ ተመክሮ፤ ወገን ጠቀም የበቃ ተሳትፎ፤ ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ይፈጥራል። ምንጮቹ በሥርዓት ሲፈተሹ የማንነት መነሻ ይታወቃል። የመነሻው ነፍስ ውስጥን ይሠራል። ሥራው ደግሞ ጥልፍ ነው – ውጽፈተ ወርቅ – ዬትውልድ የዕንቁ  ልቅ፤ ቀጥ ያለ ዓዕማደ የምሰሶ – ዓውድ! ስለነበረን መልካም ጊዜ ውስጤን ለውበቶቼ ለእናንተ ሸልሜ ክፍል አራትን በቀጠሮ አሳድሬ አክብሬና ወድጄ ልሰናበት ነው፤ አኔው ሎሌያችሁ ሥርጉተ ሥላሴ። ቸር ያገናኘን – አምላካችን በፋቃዱ።

ክፍል አንድ http://en.wikipedia.org/wiki/User:Aatebeje

ክፍል ሁለት http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30526#respond ንባቡ ተከታታይ ይሆንላችሁ ዘንድ ሊንኮቹ እነዚህ ሲሆኑ ኮከብ ያለበት – ምንጭ ከዐጼ ልብነ ድንግል እስከ ዐጼ ቴውደርሱ ከሊቁ የተወሰደ ነው – በትህትና።

ትውልዳዊ ድርሻችን በህብረትና በአንድነት እንወጣ!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ልማታዊ ፓትርያርክ (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

$
0
0

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
nigatuasteraye@gmail.com
ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.

መግቢያ

abune mathiasይህችን ክታብ በዚህ ርእስ እንዳዘጋጅ ያነሳሳችኝ “ልማታዊ መንግስት-እንደ ቻይና፤ ነገሩስ ባልከፋ” በሚል ርእስ ዶ/ር ደስታው አንዳርጌ ግንቦት ፲ ቀን ፪ሺ፮ ዓ.ም ያቀረቡልን ክታብ ናት።  ከ’ሀ’ እስከ ‘ሠ’ ተዘርዝራ የቀረበችውን ይህችን ክታብ ሳነብ፤ እንደኔ ያለውን እንቅልፋም ተማሪ ቀስቃሽ ምሁር፤ በክታባቸው አማካይነት ጣቴን ይዘው ወደ ጠቀሷቸው አገሮች ወደ እስያ፤ ቻይና፤ ታይዋንና ጃፓን በመንፈስ ወሰዱኝ።

ተመልከት! ልማታዊ መንግስት ይሉሀል:: ሰላም በምድራቸው፤ በጎ ፈቃድ በዜጎቻቸው አዕምሮ እና ስነ ልቡና ላይ ልማትን የመሰረቱ እነዚህ የቻይና የጃፓንና የታይዋን መንግስታት ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት የዘረጋው የልማት ግን፤ በጅብና በአህያ፤ በተኩላና በበግ፤ በጃርትና በዱባ መካከል የተዘረጋ የልማት ተቃራኒ ጥፋት ነው።” እያሉ በማነጻጸር ያስጎበኙኝ መሰለኝ።

ቀጥለውም፤ “የኢትዮጵያን ግማሽ ህዝብ ያቀፈችውን ኢትዮጵያዊቷን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን እመራለሁ ብለው ፓትርያርክ ነኝ የሚሉት “ካዲስ አበባ ወጥቼ በየገጠሩ ስዘዋወር ዓለም ያደነቀው ልማት ሲጣደፍ አየሁ” እያሉ ሲናገሩ ሰምተሀል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በዘረጉት ያብነት ጉባዔ ተሳትፌያለሁ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ትክክለኛ ቄስ ነኝ የምትል ከሆነ፤ ያስጎበኘሁህን አይተህ፤ የነገርኩህን ሰምተህና ተረድተህ፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መምህራን ካስተማሩህ የልማት ዘይቤ ጋራ አነጻጽረህ፡ በክህነታዊ ሀለፊነትህ የምትለው ለማለት አትፍራ” ያሉኝም መሰለኝ።

በዚህ ስሜት ላይ ሆኘ ክታቧን ለመጨረስ ቀጥየ ሳነብ፤ በተራ ዝርዝር ሐ ላይ “የአገር ፍቅርና የሃላፊነት ስሜት” በምትለው አንቀጽ ስር፤ እኛ ኢትዮጵያውያን የተሰለፍንበት መስክ የሚጠይቀንን ሀላፊነት መውሰድ የማንችል ደካሞች መሆናችንን ለማሳየት፡ እኒሁ የተከበሩ መምህራችን ብዙ ምሳሌዎችን ከጠቀሱ በኋል፤ “ለበጎውም ለክፉውም ተጠያቂው ሁልጊዜ ሌላ ነው። . . . . . . . ራስን መጠየቅ፤ እውነትን መጋፈጥ መንፈሳዊ ወኔ ይጠይቃላ።” ካሏት እንደ ጦር ፍላጽ ከምትናደፈው ቃለ አጋኖ ላይ ደረስኩ።

 [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ተረግመሻል ይሆን????!!

$
0
0

..<< ተረግመሻል ይሆን????!! >>..

ከድር አብዱ

ሰማይሽ ቢቋጥር፣ ደመናሽ ቢያጠላ፤
ወንዞችሽ ቢንቧቡ፣ ኩሬሽ ምን ቢሞላ፤

የ13 ወር ፀሀይ፣ገፅሽን ቢያሞቀው፤
የተፈጥሮሽ ፀጋ፣ግርማሽን ቢያገዝፈው፤

በደጋጎች ልሳን፣በድሆች አንደበት፤
በቅጥርሽ በምድርሽ፣ሰላም ላይወርድበት፤
የነፃነት ሰንደቅ፣ ፍትህ ላይፀናበት፤

ተይዘሽስ እንደው!!

በሰራሽው ስራ፣ እጅሽ ባስቀደመው
ሞገስሽ ተረስቶ፣ክብርሽ የነጠፈው

የተጣባሽ መጥኔ፣ ክፉሽ የመብዛቱ፤
የጠፍሩ ሲሄድ፣ የልጓም መምጣቱ፤

(ጠፈር በሊታ ሲሄድ ልጓም በሊታ መጣ ) ነው ተረቱ

መች ይሆን ትንሳኤሽ…..እማማ ኢትዮጵያዬ

tplf-addis-620x310

ዓባይ እንደዋዛ፤ ግድቡን ከጥላቻ አንጻር ማየት አደገኛ ነው

$
0
0

ክፍል አራት
አክሎግ ቢራራ ዶ/ር

ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

የዚህ ተከታታይ ፅሁፍ መሰረታዊ ሃሳብና ትንተና፤ ኢትዮጵያ ዓባይንና ሌሎች ወንዞቿን የራሷን ኢኪኖሚ ዘመናዊነት፤ ለሕዝቧ የምግብ ዋስትና ስኬታማነት፤ እያደገ ለሄደው ወጣት ትውልድ የስራ እድል የመፍጠር ወዘተ መብት ያላት መሆኑን የሚያጠናክር ነው። The Nile is African and Ethiopia is its hub በሚል አርእስት ለአለጀዚራ ያቀረብኩት ፅሁፍ ይኼን ይገባኛልነት በማስረጃ ተደግፎ ያሳያል። በአረብኛ የተተረጎመው ትንተና የብዙ አንባቢዎችን አስተሳሰብ እንደቀሰቀሰ ሰምቻለሁ፤ አሉታዊና ነቀፋ ያለበት ትችት አልደረሰኝም። የኢትዮጵያን ይገባኛልነት ሌሎች የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች እንደሚደግፉም አሳይቻለሁ። –[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—

ግንቦት 20- የመከራ የስደትና ዘረኝነት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ

$
0
0
Weekly_Editorial_Tumbnailወያኔ ለንግሥና የበቃበትን ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓመተ ምህረት መታሰቢያ በአል ለ23ኛ ጊዜ ለማክበር ሰሞኑን ደፋ ቀና ሲል ሰንብቷል። በኢትዮጵያ ግብር ከፋይ ህዝብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃንና በተለያዩ የውጪ አገራት የተመደቡ የወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤቶች በዚሁ የግንቦት 20 በአል አከባበር ሥራ ተጠምደው ከርመዋል። ለኢትዮጵያ አገራችንንና ለህዝቦቿ ባርነትን ለህወሃትና ለግብረ አበሮቹ ደግሞ አልመውት የማያውቁትን ድሎትና ብልጽግናን ያጎናጸፈው ግንቦት 20 በየአመቱ ሲዘከር ልብ ልንላቸው ከሚገቡ በርካታ ትሩፋቶቹ ጥቂቶቹ ማስታወስ ይችላል፦
  1. ኢትዮጵያ አገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአብራኳ በተገኙ ከሃዲዎች መዳፍ ውስጥ ወድቃ ሉአላዊነቷና አንድነቷ የተናጋበት ሁኔታ መፈጠሩ፤
  2. በዘመናት ጥረት የተቋቋመው ህብረ ብሄር የአገር መከላኪያ ሠራዊታችን ፈርሶ በምትኩ ለጠባብ የዘውግ ጥቅም የተሰባብሰቡ መንደርተኞች ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠሩት ተቋም መመስረቱ፤
  3. በከፈሉት የህይወት መስዋዕትነት አገራችንን ከውጪ ጠላት ተከላክለው ነጻነት ያወረሱን ጀግኖች አባቶቻችን ታሪክ እየተብጠለጠለ በታሪካችን እንድናፍር መደረጉ፤
  4. ዜጎች በብሄር ማንነታቸው ከመንግሥት ሥራና የግል ይዞታ የሚፈናቀሉበት ዘመን መፈጠሩ፤
  5. የመንግሥትና የህዝብ ሃብት የነበሩ የንግድና የአገልግሎት መስጫ ተቋሞች በሙሉ ወደ ህወሃት የግል ይዞታነት መዛወራቸው፤
  6. የዘር የሃይማኖትና የቋንቋ ልዩነት መስፈርት የሆነበት ሥርዓት ተቋቁሞ ዜጎች እርስ በርስ የሚላተሙበት ፤ ለዘመናት በሰላም ከኖርበት ቀያቸው በነቂስ የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ደጋግሞ መከሰቱ፤
  7. በልማትና እድገት ሥም ሰፋፊ የእርሻ መሬቶቻችን ለህንድ፤ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በመቸብቸቡ የነገው ትውልድ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ውስጥ እንዲወድቅ መንገዶች መመቻቸታቸው፤
  8. በሚሊዮን የሚጠጉ ለጋ ወጣቶች ተስፋቸው ተሟጦ ለአሽከርነትና ለግርድና ወደ አረብ አገር የሚፈልሱበት ችግር እየተባባሰ መምጣቱ፤
  9. በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ስደትና እንግልት ሰለባ መሆናችን ወዘተ
  10. ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና የመደራጀት መብት ተጥሶ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአስተሳሰባቸውና በአመለካከታቸው በእስር ቤት እንዲማቅቁ፣ እንዲገደሉና እንዲሰደዱ ተደርገገዋል ።
ወያኔ ሰሞኑን ባወጣው “የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ” የግንቦት 20 ድል በሀገራችን ለዘመናት ተንሰራፍቶ የነበረውን የዓፈናና የጭቆና ስርዓት የተወገደበትና በምትኩ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችል ፅኑ መሰረት የተጣለበት ፣የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችና ነፃነቶች በተለይ ደግሞ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነት የማረጋገጥ ቁልፍ ጥያቄ ምላሽ ያገኘበትበመሆኑ ልዩ ቦታና ክብር ይሰጠዋል። የግንቦት 20 ድል ሀገራችን ተደቅኖባት የነበረውን የመበታተን አደጋ በመታደግ የኋልዮሽ ጉዞዋን በአስተማማኝ ሁኔታ በመቀልበስ ድሮ ወደነበረችው የስልጣኔ ማማዋ ለመመለስ የሚያስችል በህዝቦች ይሁንታና መከባበር ላይ የተመሰረተ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መሰረት የተጣለበት የህዳሴአችን ጮራ የፈነጠቀበት የድል ቀን ነው።” ብሏል።
ይህንን መግለጫ እንዳነበብን ወይም እንደሰማን የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሰን እንድንጠይቀው ግድ ይለናል።
  • በአገራችን ተንሰራፍቶ የነበረው አፈናና ጭቆና ደጋግመህ እንደምትነግረን ተወግዶአል ለማለት የአንድ ብሄር የበላይነት የሰፈነበት መከላከያ ሠራዊትህ መላው አገሪቱን በመቆጣጠር በአሶሳ፤ በአርሲ፤በሃረር ፤ በኦጋዴን ፤ በጋምቤላ ፤ በአዋሳ፤ በዋካ፤ በአረካ ፤ በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖች ፤ በጎንደር፤ በአዲስ አበባና በሌሎችም በርካታ ቦታዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ የፈጸማቸው ግዲያዎች፤ እስርና እንግልት በምን ቋንቋና መስፈርት ነው በቀድሞ ስራዓቶች ከተፈጸሙት ተሽለው የተገኙት?
  • የደህንነት ሃይሎችህ በዜጎች ላይ የሚወስዱት ዘግናኝ እርምጃዎችና አብዛኛውን ህዝብ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ የከተተው አንድ ለአምስት ጥርነፋህ እንዴት ተደርጎ ነው የሰብአዊና የዲሞክራሲ መብቶች ግንባታ ጽኑ መሠረት የሆነው?
  • ትናንት በበረባሶ ጫማ አዲስ አበባ የዘለቀው ወታደርህና ቤሳ በስቲን ያልነበራቸው መሪዎቹ ዜጎችን ከቄያቸው በማፈናቀል በተቀራመቱት የከተማ ቦታዎች የጦፈ ንግድና በጨበጥከው የመንግሥት ሥልጣን በተመቻቸ ዘረፋ የገነቡት የንግድ ድርጅቶች፤ ህንጻና ከአለም አቀፍ አበዳሪዎች በተገኘ ገንዘብ የተሠሩ መንገዶች እንዴት የዲሞክራሲና የልማት መሠረት ሊሆኑ ይችላሉ ?
  • በምስሌኔዎችህ የምታስተዳድራቸው ብሄር ብሄረሰቦች የእጅ አዙር አገዛዝህን አንፈልግም በስማችን አትነግድብን እያሉህ ከትውልድ መንደርህ ጀምሮ ነፍጥ እያነገቡ እያየህና እየሰማህ ስለየትኛው የብሄር ብሄርሰብ እኩልነትና ነጻነት ነው የምትደሰኩረው?
  • ከውጭ በተገኘ የመሳሪያና የትጥቅ ድጋፍ የሰሜኑን የአገራችንን ክፍል ለማስገንጠል 17 አመት ሙሉ አገራችንን የወጋህ አንተው ሆነህ እያለህ ከየትኛው የአገር መበታተን አደጋ ነው እንደታደከን መላልሰህ እየነገርክ የምትደነቁረን ?
  • የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ነው በማለት የኩራት መሠረታችንን ስታፈርስ ከኖርክና በተለይ አዲሱን ትውልድ ታሪክ አልባ አድርገህ ካበቃህ ቦኋላ በየትኛው ዘመን ወደነበረው የሥልጣኔ ማማ ልትመልሰን ነው ባለ አዲስ ራዕይ የሆንክልን ?
” ጆሮ ለባለቤቱ …” እንዲሉ እነዚህ ጥያቄዎች ሲነሱ ወያኔ እንደለመደው ” የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች ፤ጸረ ሠላምና ጸረ ልማት ሃይሎች ፤ የብሄር ብሄረሰብ መብት የማይዋጥላቸው የአማራ ትምክህተኞች ፤ የኤርትራ የጥፋት መልዕክተኞች ፤ ሽብርተኞች” የሚሉ አራምባና ቆቦ የሆኑ መልሶችን እንደሚሰጥ መጠራጠር አይቻልም። የወያኔ ታሪክ ሁሌም የክህደት፣ የውሸት፣ የማስመሰል እና የማጭበርበር መሆኑን ሁሉም ህዝብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በየአመቱ የሚያከብረው ግንቦት 20 ደርግ የንጉሰ ነገሥቱን ዘውድ ገርስሶ ሥልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ ተገፍቶ ከስልጣን እስከወደቀበት ዕለት ድረስ ያከብረው ከነበረው መስከረም 2 የተለየ ነው ብሎ አያምንም። ወያኔ ደርግን በሃይል ከሥልጣን የገረሰሰበትን ግንቦት 20ን በመስከረም 2 እንደተካው ሁሉ ህዝብ ለነጻነቱ የጀመረው ትግል ተጠናክሮ ወያኔን በሃይል ከሚቆጣጠረው ሥልጣን ሲያሽቀነጥረው የግንቦት 20 በአከባበርም አብሮት እንደሚያከትም ነጋሪ አያሻውም። ህዝብ በዘር በተሰባሰቡ ባንዳዎች መዳፍ ውስጥ የገባበትን ዕለት ፤ብሄራዊ ኩራቱንና ማንነቱን የተነጠቀበት ቀን፤ በገዛ አገሩ የበይ ተመልካች የሆነበትን የወያኔ የድል ቀን መልሶ የሚዘክርበት ምክንያት አይኖረውም። ወያኔ በየአመቱ የሚያከብረው ግንቦት 20ንና የድል ፍሬዎቹን ህዝብ እንደማይጋራው ግንቦት 7 ቀን 1997 ህዝብ በግልጽ ተናግሯል።
የግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና የትግል አላማ ነጻነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ግንቦት 7 ቀን 1997 ያስመዘገበውን ድል መልሶ እንዲቀዳጅ ማድረግ ነው። ስለዚህም ሰላም ፍትህና እኩልነት የተጠማኸው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ፤ በገዛ አገርህ ሠርቶ የመኖር ተስፋህ ተሟጦ ለስደት በባህርና በየብስ ለማምለጥ እያኮበኮብክ ያለህ ወጣት፤ በየስፍራው የተቀጣጠለውን ህዝባዊ አመጽ ለማፈን እየተላክ ከገዛ ወገንህ ጋር ደም እየተቃባህ ያለኸው ወታደር፤ የገዥዎችን የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም በፖሊሲ ሃይል፤ በደህንነትና ጸጥታ ጥበቃ የተሰማራሃው ወገን ፣ ግንቦት 7 የጀመረው የነጻነት ትግል እናንተንም ጭምር ከአፈናና ከጉስቁልና ነጻ ለማውጣት ስለሆነ ዛሬውኑ ትግሉን ትቀላቀሉ ዘንድ ድርጅትህ ግንቦት 7 ወገናዊ የትግል ጥሪውን ያቀርብልሃል።
የግንቦት 20 ድል መቀሌ ውስጥ የአፓርታይድ ሠፈር የገነቡ የሥርዓቱ ቅምጥሎች ፤ አዲስ አበባ ውስጥ የመቀሌ ሠፈር ተብሎ የተሰየመውን ህንጻ ያሳነጹ ሌቦች ፤ በጋምቤላ፤ በአፋር፤ በቤነሻንጉልና ማሃል ኦሮሚያ የእርሻ መሬት እየዘረፉ የተቀራመቱ ህወሃቶችና የጥቅም ተካፋዮች እንጂ የሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ አለመሆኑን በተግባር ለማሳየት ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የወያኔን የአገዛዝ ሥርዓት ከላያችን ላይ አሽቀንጥረን ለመጣል ከምንጊዜውም በላይ መነሳት ያለብን ጊዜው አሁን ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ኢትዮጵያ እውነተኛ ልጇን አጣች

$
0
0

ብዙ የውጭ ሃገር ሰዎች ሃገራችንን ይወዳሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የኦስትርያ ተወላጅ የሆነው ካርልሃይንዝ ቦይም(Karlheinz Böhm ) ነበር። ነገር ግን ካርልሃይንዝ የዓለም ዜጋ(Weltbürger) ነኝ ብሎ ነበር የሚያምነው። ቢሆንም ካርልሃይንዝ 2003 የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት ተቀብሏል።

ይህንን ታላቅ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ኢሊባቡር ውስጥ ጉመሮ ሻይ ተክል መጥቶ በነበረበት ወቅት ነው። በዚያ ወቅት የተነገረን የፊልም ተዋንያን መሆኑን ብቻ ነበር። ጀርመን ከመጣሁበት ቀን ጀምሮ ስለዚህ ሰው ደግነት በሰፊው ልረዳ ችያለሁ።

ካርልሃይንዝ በተወለደ በ86 ዓመቱ ያለፈው ሐሙስ ሌሊት ሳልዝቡርግ – አውስትሪያ ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

karl
ካርልሃይንዝ በኦስትርያ፣ በጀርመን እና በሲዊዘርላንድ የተከበረ የፊልም ተዋንያን ነበር። ካርልሃይንዝ የታወቀው ንጉስ ፍራንዝ( Kaiser Franz Joseph) ሆኖ በሠራው ፊልም ነበር። ከዛም በኋላ በተከታታይ ብዙ ፊልሞች ሰርቷል። ይህ ሰው በፊልም ታዋቂነቱ ሳያግደው ፣ የተንደላቀቀው ኑሮው ሳያጓጓው የሃገራችንን ሕዝብ ኑሮ እዛው እየኖረ ሕዝብን መርዳት የወሰነው 1976 ኬንያ ውስጥ ሆኖ ስለ አፍሪካ ችግር ባወቀበት ወቅት ነበር።

በጀርመን፣ በኦስትሪያና በስዊዘርላንድ ለሦስት ሃገሮች በሚተላለፈው የቴሌቪዥን የውድድር ፕሮግራም (“Wetten, dass..?”) ላይ በ1981 በእግድነት ቀርቦ ከሕዝቡ ጋር የውድድር ሃሳብ ያቀርባል ። በአፍሪካ ለደረስው ችግር እርዳታ የሚሆን ይህንን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከሚመለከተው ሕዝብ አንድ ሦስተኛው . . . አንድ የጀርመን ማርክ ወይም አንድ የስዊስ ፍራክ ወይም 7 የኦስትሪያ ሽልንግ ከሰጠ ችግሩ ባለበት ቦታ ሄጄ እረዳለሁ ብሎ ይወዳደራል።

ካርልሃይንዝ ምንም እንኳን በሚሊዮን የሚቆጠር እርዳታም ቢያገኝም የተከታተለው ሕዝብ አንድ ሦስተኛው የተወዳደረበትን ገንዘብ አልሰጠም። በዚህ ምክንያት ውድድሩን ያሸንፍና ወደ አፍሪካ መሄድ ግዴታው አይሆንም። ቢሆንም ግን ይህ ታዋቂ የፊልም ሰው ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በዓላማው በመጥናት የተንደላቀቀውን ኑሮውን እርግፍ አድርጎ በመተው ኢትዮጵያ ውስጥ የችግረኛውን ኑሮ እየኖረ እርዳታውን ለመስጠት ወሰነ። ከ1982 ጀምሮ ከፊልም ስራው ተለያይቶ በእርዳታው ላይ ብቻ አተኮረ።

ካርልሃይንዝ “ሰው ለሰው“ . . . “Menschen für Menschen” የሚባል ድርጅት አቋቁሞ ከ1981 ጀምሮ እርዳታ ሲደርግ ቆይቷል። እዛው ሃገራችን ውስጥ ካርልሃይንዝ ከወይዘሮ አልማዝ ጋር ተጋብቶ ይኖር ነበር። ወይዘሮ አልማዝ ካርልሃይንዝ ከታመመበት ጊዜ ጀምሮ የእርዳታ ድርጅቱን ሲመሩ ቆይተዋል። ካርልሃይንዝ 7 ልጆች ሲኖሩት ሁለቱ ከወይዘሮ አልማዝ የተወለዱ ናቸው።

ለካርልሃይን ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ።

በዚህ አጋጣሚ የድረገጽ ባለቤቶች የዚህን ታላቅ ሰው ፎቶ በመለጠፍ ለሃገራችን ብዙ ላገለገለው ሰው ሃዘናችንን እንድንገልጽ ታደርጉልን ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ።

http://www.dw.de/the-two-lives-of-karlheinz-böhm/a-17672792

በልጅግ ዓሊ – ፍራንክፈርት – 30.05.2014

የሚሊዮኖች ድምጽ ግብረ ኃይል በዳያስፖራ –ዝምታችን እስከመቼ ?

$
0
0

በቅርቡ አንዲት ታላቅ ጥቁር አሜሪካዊት የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ከዚህ አመት በሞት አልፈዋል። ማያ አንጀሎ ይባላሉ። እኝህ ታላቅ ሴት ጸሃፊ፣ ገጣሚም ነበሩ። አንድ ጊዜ ማያ አንጀሎ ሲናገሩ ፡ “We may encounter many defeats but we must not be defeated.” ብለው ነበር።

በዚህ አለም ስንኖር፣ በግለሰብ ደረጅ፣ በቤተሰብ፣ በአገር የተለያዩ ፈተናዎች ያጋጥሙናል። ስህተቶች እንሰራለን። እንወድቃለን። ሽንፈቶች ያጋጥሙናል። የምናቀርቅርበት፣ የምናዝንበት፣ የምናለቅሰበት ጊዜ አለ። በአገር ጉዳይ ያለውን ሁኔታ እንኳን ስንመለከት፣ ከስድሳዎች የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ ፣ በተለይም በአገራችን እኩልነት፣ ዴሞክራሲ፣ ሰላም፣ የሰብአዊ መብቶች መከበር፣ የሕግ የበላይነትን በተመለከተ ፣ ከተገኙት ድሎች ይልቅ፣ ሽንፈቶቻችን በጣም ይበዛሉ። በስድሳዎቹ የነበረው የለዉጥ እንቅስቃሴ መስመር ስቶ ወደ ማይሆን ቦታ ወሰደን። በዚያ ጠባሳ ምክንያት ፖለቲክ እንደ ኮረንቲ ይፈራ ጀመር።ደርግ ወድቆ ኢሕአዴግ ሲተካ፣ «አዲስ ንጉስ እንጂ ለዉጥ መቼ መጣ» እንዳለው ዘፋኙ የታሰበለትም የተጠበቀው ሳይሆን ቀረ። በዘጠና ሰባት ታሪካዊ የሆነ የቅንጅት እንቅስቃሴ ታያ። የኢሕአዴግ ዱላ ተጨምሮበት፣ በመሪዎቹ መካከል የተፈጠረው ልዩነት የትግሉን ግለት አወረደው። እንደገና ሽንፈት አጋጠመን። እንደገና አምባገነኖች ለጊዜ ተሳካላቸው።

ላለፉት አንድ አመት፣ የሚሊዮኖች ንቅናቄ በሚል መርህ ፣ የወዳደቀዉን በማንሳት ፣ የተሰባበረዉን በመጠገን፣ ብዙዎች ለአሥርተ አመታት መስዋእትነት የተከፈለበትን ትግል ከግብ ለማድረስ፣ ተጨባጭ የሆኑ ሥራዎችን መታየት ጀምረዋል። ለዉጥ ሊያመጣ የሚችለው ኃይል የህዝብ ኃይል ብቻ ነው። ይህንን ኃይል ከማደራጀት፣ ከማንቃት፣ ከማሰባሰብ ዉጭ ሌላ የተሻለ አማራጭ የለም። ሕዝብን ከጎኑ ያላደረገ ትግል ዋጋ የለውም። የሚሊዮኖች ንቅናቄ ሕዝብን ማእከል ያደረግ የሚሊዮኖች ንቅናቄ ነው።

ብዙዎች ከጊዜ ወደ ጎዜ ከሚሊዮኖች አንዱ ነን እያሉ ትግሉን እየተቀላቀሉ ነው። የሶሊዳሪቲ ንቅናቄ፣ የብዙ ደርጅቶች ስብስብ የሆነው ሸንጎ፣ የሽግግር ምክር ቤቱ እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች የሚሊዮሞች ንቅናቄ አካል ሆነው በጋራ እየሰሩ ነው። በሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል ዙርያ መሰባሰቦች እየታዩ ነው። ይህም አስደሳች ዜና ነው።

ነገር ግን አሁንም ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆነ ወገኖቻችን ያለፉትን ጠባሳዎችን እየተመለከቱ፣ ተስፋ ቆርጠው፣ እጃቸውን ለፍርህትና ለባርነት አሳልፈው ሰጠው፣ ዝም ማለትን የመረጡ አሉ። ለነዚህ ወገኖቻችን የማያ አንጀሎ አባባል ልናካፍላቸው እንወዳለን። “We may encounter many defeats but we must not be defeated.” እንላቸዋለን። «ዝምታችን እስከመቼ ነው ?» እንላቸዋለን።

የሚሊዮኖች ንቅናቄ መጪው እንቅስቃሴዎች በአዳማ/ናዝሬት፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ታቦር ይሆናል። ከነዚህ ከሶስት ከተሞች በተጨማሪም፣ ከሃላፊዎች እውቅና ከተሰጠ ፣ በአርማጭሆ፣ በወገራ እና በቁጫ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ። ቢያንስ በአንድ ቀን ብቻ፣ ከሶስት እስከት ስድስት ባሉ ከተሞች የአንድነት ፓርቲ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው። ሕዝቡ ፍርሃትን አውልቆ፣ ያለፉት ሽንፈቶች ተስፋ ሳያስቆርጡት፣ ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለሕግ የበላይነት፣ ለፍትህ ፣ ለዲሞክራሲና ለእኩልነት ድምጹን ለማሰማት መዘጋጀቱ ትልቅ ድል ነው።

እንግዱህ ይሄንን ታሪካዊና አገራዊ እንቅስቃሴ እንቀላቀል። ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ። ነጻነት ዋጋ ያስከፍላል። ሌሎች ትልቅ ደረጃ የደረሱት ጥረው ግረው ነው። ሌሎች ነጻነታቸው ያገኙት መስዋእትነት እከፍለው ነው። እኛም እንደዚሁ ዋጋ ለመክፈል እንዘጋጅ። ለኛ መብት ሌሎች እንዲጮሑልን መጠበቅ የለብን። ለመብታችን እያንዳንዳችን እንነሳ ።ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን።

MILLIONS OF VOICE FOR FREEDOM !

 

የሕዳሴ አብዮት! (ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ)

የዛሬይቱ ኢትዮጵያችን ‹‹አብዮታዊ ሁኔታ›› ላይ ለመድረሷ በብዙሃን ዜጐች ዕይታም ሆነ፤ ሂደቱን በተከታተሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ምሁራን ምልከታ የማይታበል ሐቅ ሊሆን መቃረቡ በዚህ ተጠየቅ ለማነሳው አጀንዳ ገፊ-ምክንያት ነው፡፡ በአናቱም ባለፈው ሳምንት ‹‹የ‹ቀለም› አብዮት ናፍቆት›› በሚለው መጣጥፍ ላይ ለማሳያነት የጠቀስኳቸው ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ነገረ-ንዋያዊ ችግሮች ተደማምረው፣ ሀገሪቷን በርቀት እንደታዘብናት ሶቪየት ሕብረት፣ አሊያም በቅርበት እንዳስተዋልናት ሶማሊያ በመጪዎቹ ጥቂት ጊዜያት የመፈራረሷን አይቀሬነት ማስረገጣቸውን ልብ እንላለን፡፡ ከዚህ ክፉ የታሪክ ዕጣ ለመታደግም ከሁለት አስርታት በላይ ያስቆጠረውን ይሄን አሮጌ ሥርዓት መቀየር ብቻውን ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ እንደማይችል ዛሬ ግልፅ እውነታ ሆኗል፤ ምክንያቱ ደግሞ ለዘመናት በገዥነት የተንሰራፋው የፖለቲካ ባሕልም አብሮ ካልታደሰ ነገሩ-ሁሉ ‹‹ታጥቦ ጭቃ…›› ከመሆን አለመዝለሉ ነው፡፡

እናም ወደዚህ ከፍታ ለመሻገር ሶስተኛው አብዮት ብቸኛ መፍትሔ የመሆኑ ጉዳይ አከራካሪ አይደለም፤ ይህ ታላቅ ንቅናቄ ‹‹የሕዳሴ አብዮት›› በሚል ስያሜ ቢጠቃለል፣ ሂደቱ አንድም ኢህአዴግን ከክፉ ስራዎቹ ከመግታት ባለፈ፣ ኢትዮጵያን በሁለንተናዊ መልኩ የማደስና የተረጋጋ የፖለቲካ ማሕበረሰብ መፍጠርን የመሳሰሉ ተልዕኮዎችን በቀላሉ ወደ መሬት ለማውረድ ያስችላል፤ ሁለትም ከለውጡ ጋር የተያያዙ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ከስያሜው አንድምታ አንፃር እየቃኙ በቀላል መንገድ ለመተንተን ጠቀሜታ ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ አምኜም በአዲስ መስመር የሕዳሴን ታሪካዊ ዳራ፣ አተገባበር እና ተያያዥ ጉዳዮችን እየጠቃቀስኩ ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡

 ‹‹ህዳሴ›› ሲባል…

በ5ኛው ክፍለ ዘመን ከጀርመን የተነሱ ጎዝ፣ ቫንዳልና ቡርጉንዲያኖችን ጨምሮ ሰባት ጎሳዎች፣ በወቅቱ ከፊል አውሮፓን ያስተዳድር የነበረውን ልዕለ-ኃያል የምዕራብ ሮማ ኢምፓየር አንኮታኩተው ግብዓተ-ፍፃሜውን ዕውን አደረጉት፡፡ ይህም የኃያሉ አገዛዝ ፍፃሜ ፕላኔታችን በአዲስ የፖለቲካ ባሕል እንድትዋጅ ሌላ የታሪክ ምዕራፍ ከፈተ፡፡ የዚህ መነሾም አሸናፊዎቹ ጀርመናውያን ጎሳዎች የአስተዳዳሪነት ችሎታም ሆነ ልምዱ ስላልነበራቸው የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም የሮማ ቤተ-ክርስቲያን እና ፊውዳሎቹ ሥልጣኑን ሙሉ በሙሉ በመቀራመታቸው ነበር፡፡ መላ ግዛቱም ሥልጣኔ-ጠል (Barbarism) እየተባለ የሚጠራውንና እስከ 15ኛው ክፍለ ጊዜ ድረስ በዘለቀው ‹‹የጨለማው ዘመን›› ውስጥ ያልፍ ዘንድ ተገደደ፡፡ ይህን ተከትሎ ትምህርትም ሆነ መንግስታዊው አስተዳደር በኃይማኖታዊ ቀኖና እንዲበየን ተፈረደበት፡፡ በወቅቱ አብያተ-ክርስቲያናት በብዛት ከመታነፃቸው ባለፈ አይን የሚሞላ መሰረታዊ ልማት ባለመዘርጋቱ፣ ከተሞች እጅጉን ቆርቁዘው የገጠሩን ገፅታ እስከመላበስ ደርሰው ነበር፡፡ ከሁሉም የከፋው ደግሞ መመራመር፣ መጠየቅና አለማዊ እውቀትን መፈለግ ከደመ-ቀዝቃዛዎቹ ‹‹መንፈሳዊያን›› አስተዳዳሪዎች ዘንድ ምድራዊ ፍዳን ለመቀበል መዳረጉ ነበር፡፡

በዚህ መልኩ ክፍለ-አህጉሩ ሰባትና ስምንት መቶ የመከራ ዓመታት ካሳለፈ በኋላ፣ የጣሊያኖቹ ፍሎረንስ፣ ቬነስ እና ሮማ ከተሞች ከዘመኑ በተለየ እውቀት ፈላጊና አንሰላሳይ ልጆቻቸው መናጥ ጀመሩ፡፡ ይህንን የመነቃቃት መንፈስ በሥራዎቹ በማካተት የዘመኑ ዝነኛ ባለቅኔ ዳንቴ አሊጋሪ በቀዳሚነት ይታወሳል፡፡ በ15ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ደግሞ መነቃቃቱ መላ ጣሊያንን በማዳረስ በምርምር ውጤት (በሳይንስ) መቃብር ላይ ተንሰራፍቶ የነበረውን ኃይማኖታዊ አስተዳደር ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎ አፈራረሰው፡፡ ይህ አይነቱ የለውጥ መንፈስ ከጣሊያን ባሻገር ከአልፕስ ተራሮች ጀርባ ባሉ የአውሮፓ ሀገራት ድረስ በመዛመቱም ታሪክ ይቀየር ዘንድ ግድ ሆነ፡፡ ለሁነቱም ዋናው ተዋናይ ሕዝባቸውን ከተዋጠበት የጨለማ ዳዋ ለማላቀቅ ሲሉ የጥንታዊያኑ ግሪክ እና ሮማ የተዘነጉ የአሰላሳዮችን የአእምሮ ውጤት መመርመር ቀዳሚ ስራዎቻቸው ያደረጉት የጊዜው ጠቢባን እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ባህል፣ ስነ-ጽሁፍ፣ ሞራል እና መሰል ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ እውቀቶችን መልሶ በመመርመር ጠቃሜታውን ለይቶ ማሰራጨትን የቀን ተቀን ሥራ ማድረጋቸው የማታ ማታ ለስኬት አብቅቷቸዋል፡፡ እነሆም የታሪክ ምሁራን ‹‹ሕዳሴ›› (Renaissance) ብለው የሚጠሩት ይህንን ሁነት ነው፡፡

በርግጥም ሕዳሴ የታሪክ ሀዲድን ተከትሎ የኋሊት በመመለስ የማንፃት (የመታደስ) ተግባር የሚያከናውን የሳይንስ ዘርፍ ነው፡፡ ይህም ጥንታዊውን ዘመን ዛሬ ላይ እንዳለ ማንበር ሳይሆን፤ የቀደመውን ሥልጣኔ የወደቀበትን ህፀፅ መርምሮ ለዘመኑ የሚበጀውን አንጥሮ በማውጣት፣ ያረበበውን ማሕበራዊ ፍዝነት እና ኋላቀርነት አንገዋሎ በመጣል ላይ የሚያተኩር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፍልስፍና መሆኑ አፅንኦት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ምዕራባውያን ለደረሱበት የሥልጣኔ ከፍታ ዋናው መሰረት የተጣለው በሕዳሴው ዘመን ስለመሆኑ ራሳቸው ይመሰክራሉ፡፡ ኮፖርኒከስ፣ ጋሊሊዮ፣ ቦይል፣ ሀአርቬይ፣ አይዛክ ኒውተን፣ ሊዎናርዶ ዳቪንቺ፣ ሚካኤል አንጀሎን የመሳሰሉ ጉምቱ ጠቢባን የሥራ ውጤትም አብርሆት (ኢንላይትመንት) የሚባለውን ዘመን ወልዷል፤ ይህም ወደ ኢንዱስትሪ አብዮት አሸጋግሮ ለዛሬው ዘመናዊነት መደላድልን ስለማመቻቸቱ የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ፡፡

በወቅቱ የሕዳሴው መንገድ ቀያሽ ተደርጎ የሚጠቀሰው ገዥ-ሃሳብ፣ የሰውን ልጅ በቀዳሚነት በሚያጠናውና ሰዋዊነት (Humanism) ተብሎ በሚጠራው ዘርፍ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ ይህ አስተሳሰብ በሀገረ-እንግሊዝ በተስፋፋበት በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳው ፀሐፌ-ተውኔት ዊሊያም ሼክስፒር፣ ኃይማኖታዊ ክብረ በዓላትን፣ ስሜት-ተኮር እንቅስቃሴዎችንና ሥነ-ምግባር ላይ ብቻ ያውጠነጥን የነበረውን የድራማ ዘውግ፣ ወደ አለማዊ ይዘትነት በመቀየር ለሀገራዊ ፍቅር መነቃቃት እና የአርበኝነት መንፈስን በማስረፅ ረገድ ወደር የማይገኝለት ሚና ለመጫወቱ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቹ ግንባር ቀደም ምስክሮች ናቸው፡፡ በጥቅሉ የ‹‹ሕዳሴ›› (Renaissance) ፅንሰ-ሀሳብ የግሪክና የላቲን ብሉይ መድብሎች ላይ ቆሞ ፍልስፍናን እና መሰል የእውቀት ዘርፎችን መተርጎምን የያዘ የብርሃን ንቅናቄ በመሆኑ፤ የግለሰብን አለማዊ ከፍታ ለማስረገጥ፤ የሰውን ልጅ ምክንያታዊነት፣ የምርምር ክሂልና የኪነ-ውበት ፈጠራ ማሳደግን ዋነኛ ማዕከሉ ያደረገ ብርቱ የለውጥ መንፈስ ነው ተብሎ ቢደመደም ማጋነን አይሆንም፡፡

 የኢትዮጵያ ህዳሴ

በሚሊኒየሙ አከባበር ዋዜማ ይህንን ቃል በጥራዝ ነጠቅነት የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መጠቀሙን ተከትሎ፣ ከክቡራን ሚንስትሮች እስከ የቀበሌ ካድሬዎች የንግግር መክፈቻና መዝጊያ ሆኖ ዛሬም ድረስ በማጭበርበሪያነት እያገለገለ ይገኛል፡፡ በአባይ ወንዝ ላይ እየተሰራ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫንም «የሕዳሴ ግድብ›› ሲሉ ሰይመውታል፤ ምንም እንኳ የትኛውን ያለፈ ታሪካችንን እንደሚያድስ አፍታተው ባይነግሩንም፡፡ ሰሞኑን የተከበረውን የግንቦት ሃያ በዓል በማስመልከት በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ በወሬ ደረጃ የሚያውቀውን ገድል እየተደነቃቀፈ የተረከልን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም ቢሆን ‹‹የግንቦት ሃያ ድል ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ገናናነቷ እንድትመለስ /እንድትታደስ/ የጠቀመ ነው›› ከሚል መታበይ አልፎ፣ የትኛውን የገናናነት ዘመናችንን ለመመለስ እንደተቻለ ለይቶ አላስቀመጠልንም፡፡ በርግጥ እርሱ እያወራ የነበረው የአክሱም ስልጣኔን በተመለከተ ከሆነ፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ታላቁ ስላቅ ተብሎ በታሪክ ማህደር ሊመዘገብ ይገባል፤ በተለይም የአቶ መለስ ዜናዊን ‹‹የአክሱም ሀውልት ለወላይታው ምኑ ነው?!›› ሽርደዳን ስናስታውስ፡፡ በተቀረ ‹‹ሕዳሴ›› ብሎ ለመሰየም በቅድሚያ መታደስ የሚገባው ጥንታዊ ሥልጣኔ ስለመኖሩ ማመን እንደሚጠይቅ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፕሬዚዳንት ለነበረ ሰው ይጠፋዋል ብዬ አላስብም፡፡

በአናቱም ጀግናው ኢህአዴግ ከምንሊክ በፊት የነበረችዋን ኢትዮጵያ እንደማያውቃት ሲለፍፍ እና የኢትዮጵያ ታሪክን በ100 ዓመት ገድቦ፣ የቀደመው የሥልጣኔ አሻራ የአንድ ወይም የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ማሕበረሰብ ግንጥል ውበት እንደሆነ ለሃያ ሶስት አመት ሙሉ ሲሰብክ ኖሮ፣ ዛሬ ‹የጥንቱን ገናናነት እንመልሳለን› ማለቱ፤ ራሱ ካነበረው የሥርዓት አወቃቀር ጋር ፊት ለፊት እንደሚያላትመው የዘነጋው ይመስለኛል፡፡ ይህም ሆኖ ‹‹ስለሕዳሴ የማወራው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ አይደለም!›› ካለን ደግሞ፣ የኢትዮጵያን የ3ሺህ ዘመን ቀደምት ታሪክ በይፋ አምኖ መቀበሉን ያወጀ ያህል አድርገን ልንወስደው እንችላለን፤ ግና፣ ይህ አይነቱ አቋም ድንገት በሞቅታ የሚለወጥ ሳይሆን፣ ብዙ ማብራሪያዎችን እና ደም ያፋሰሱ ጠማማ ታሪኮችን የማቃናት ከባድ ሥራ የሚጠይቅ ነው፡፡ በተረፈ የሕዳሴው ልፈፋ በታሪክ ብያኔው ያኮረፉትንና ‹ቅድሚያ ኢትዮጵያዊነት› የሚሉትን ስብስብ በሀሳዊ የፕሮፓጋንዳ ማግኔት ወደፓርቲው ለመጎተት የሚጠቀምበት ተራ የማጭበርበሪያ ስልት ከመሆን የሚዘል አይመስለኝም፡፡

የሆነው ሆኖ በዚህ አውድ መከረኛይቷን ኢትዮጵያ ከአደገኛው ማዕበል የሚታደጋት ቀጣዩ ሕዝባዊ ንቅናቄ ‹‹የሕዳሴ አብዮት›› በሚል ማዕቀፍ ስር ይወድቅ ዘንድ ገፊ-ምክንያቱ፣ የሥርዓት ለውጥ ብቻውን ለሀገሪቱ ትንሳኤ በቂ አለመሆኑን አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡ ስለምን? ቢሉ፣ በተለይም ከ1983ቱ የመንግስት ቅያሬ በኋላ የተከሰቱ አስጨናቂ ችግሮች መፍትሄ ያገኙ ዘንድ ዳግም የመታደስ (እንደገና የመወለድ) አስፈላጊነትን አማራጭ አልባ ምርጫ በማድረጋቸው ነው፡፡ በተለይም የብሔር ፖለቲካው የወለደው የጎሳ ክፍፍል፣ ከባህላዊ እሴቶች ማፈንገጥ፣ የትምህርት ጥራት ማሽቆልቆል፣ የኃይማኖት መቻቻል ወደ ታሪክነት መቀየር፣ የህሊና ታማኝነት መደብዘዝ እና ከሰው ልጅ ይልቅ ቁስ መከበሩ… ከሞላ ጎደል አብዮቱን በታሪክ ማንፃት መካከል የማለፍ ተልዕኮ እንዲያነግብ ገፍቶታል፡፡ በተጨማሪም የቀድሞ የታላቅነት መገለጫችን የሆነው የአክሱም ሥልጣኔ ክቡድ መንፈስ ለዚህ ዘመን መዋጀት የሚበቃ ሽራፊ ምስጢረ-ጥበብን ሸሽጎ ስለመያዙ ከቶም ቢሆን ቅንጣት ታህል የማንጠራጠር መሆናችን ሕዳሴን አጀንዳ እንድናደርገው ያስገድደናል፡፡

ከላይ እንዳየነው የአውሮፓን ሥልጣኔ በፅኑ መሰረት ላይ ያስረገጡት አሰላሳዮቻቸው እንደሆኑ ሁሉ፤ በእኛም አውድ ሀሳቦቻቸውን ወደ አደባባዩ ተዋስኦ አብዝተን ልናካትትላቸውና የሕዳሴያችን ምሁራን ሊሆኑ ይገባል ብዬ የማምንባቸው ሶስት መምህራን አሉ፡፡ መስፍን ወልደማርያም፣ መሳይ ከበደና ተከስተ ነጋሽ፡፡  አዛውንቱ ጠቢብ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በተለይም ‹‹መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ›› በሚለው መጽሐፋቸው፣ የኋላው መዘንጋቱ የችግሮቻችን ምንጭ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡ በገፅ 12 ላይም እንዲህ በማለት በቁጭት ይጠይቃሉ፡-

‹‹ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዓመታት በፊት ሰረገላ ነበር፣ የመስኖ እርሻ ነበር፣ የግንብ ቤት ነበር፣ ሕዝብ የሚገበያየው በገንዘብ ነበር፤ ከአራት መቶ ዓመታት በፊት ጋሪ ነበር፣ ድልድይና የግንብ ቤቶች ተሰርተው ነበር፤ የዚህ ሁሉ የሥራ ጥበብ ለምን ከሸፈ? የአክሱም ሀውልቶችን የመስራት ጥበብ ለምን ከሽፎ ቀረ? የላሊበላን ከድንጋይ የተፈለፈሉ አብያተ ክርስቲያናት የመስራት ጥበብ ለምን ከሸፈ? የጎንደርን ቤተ-መንግስቶች የመስራት ጥበብ ምን አክሽፎ አስቀረው? እነዚህ ሁሉ የድንጋይ ስራ ጥበቦች በሚታዩበት አገር በደሳሳ ጎጆ ውስጥ መኖር ከትውልድ ወደትውልድ የሚተላለፍ ባሕል መሆኑ በምን ምክንያት ነው?››

ቀድሞ ግራ-ዘመም የነበሩት የፍልስፍና መምህር ፕ/ር መሳይ ከበደ ደግሞ ሌላኛው የሕዳሴው ምሁር ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ፤ በተለይም ከ40ዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ጋር በተባረሩ ማግስት ባሳተሟቸው መጻሓፍት፣ የቀደሙ ሀገር-በቀል የኢትዮጵያ ሊቃውንትን ሙግቶች በማብራራት ይታወቃሉ፡፡ ‹ወደ ምንጫችን የመመለስን› ጥሪ የሚያስተጋቡት ፕሮፌሰሩ፣ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ማጥ ለመውጣትም ሆነ ወደፊት እንድትገፋ፣ ለረዥም ዘመን ካስተናገደቻቸው ዕሴቶች መካከል ረብ ያላቸውን መመለስ እንደሚገባት አብዝተው ተከራክረዋል፡፡

አስመራ የተወለዱት የታሪክ አጥኚው ፕ/ር ተከስተ ነጋሽም ሌላው ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የትምህርት ስርዓቱ ላይ ባደረጉት አበርክቶ በዚህ አውድ የማነሳቸው እኚህ ምሁር፣ እንደ ፕ/ር መሳይ ሁሉ፣ ዘመናዊው የትምህርት ስርዓት አውሮፓ ተኮር እና ኢትዮጵያ-ጠል በመሆኑ ወደፊት መራመድ እንዳላስቻለን ደጋግመው ከመናገር ባለፈ፤ ቋንቋ የሚሸከመውን ሀገራዊ ማንነት ከመረዳት አኳያ አማርኛን እና ኦሮምኛን የስርዓተ-ትምህርቱ ቋንቋዎች ማድረግ ብቸኛው ከውድቀታችን መውጫ መንገድ መሆኑን ያምናሉ፡፡ …በጥቅሉ እነዚህ አንጋፋ ጠቢባን (ያልጠቀስኳቸው ሌሎችም እንደሚኖሩ ሳልዘነጋ) አውሮፓውያን ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ከጨለማ የወጡበትን ብልሃት መመርመርን ይበልጥ አጠንክረው በመከተል፣ ሀገር የመታደግ ተልዕኮዎቻቸውን ከዳር ያደርሳሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ይሁናቸውና!

መጪው የሕዳሴ አብዮት በዋናነት የሚያተኩርበት ሌላው ጉዳይ፣ ከአራት አስርታት በፊት በያ ትውልድ ፈታኝ የትግል ጉዞ ላይ ትልቅ ተሳትፎ የነበራቸውን እንስቶች የተኳቸው የዛሬዎቹ የፆታ አቻዎቻቸው ለምን ከእንቅልፍ በከበደ አርምሞ ውስጥ ሰጠሙ? የሚለው ነው፡፡ ከአውሮፕላን ጠላፊዋ ማርታ መብራቱና ታደለች ኪዳነማርያም እስከ የመኢሶኗ ወሳኝ መሪ ንግስት አዳነ፤ እንዲሁም ከእልፎቹ የኢህአፓ ትንታግ ጓዲቶች እስከ ወያኔዎቹ አረጋሽ አዳነ እና ቀሺ ገብሩ ያሉ ተዘርዝረው የማያልቁ የዚያ ዘመን የአናብስት እንስቶች እንቅስቃሴ እንደዋዛ አክትሞ፣ በብርቱካን ሚደቅሳ፣ ርዕዮት አለሙና ፈቲያ መሀመድን በመሰሉ ጥቂት ጀግኖች ተገድቦ መታየቱ፣ በቀድሞው ታሪክ መታደስን አማራጭ የለሽ ያደርገዋል፡፡ በርግጥ የእንስቶቻችንን ፊኒክስነት ለመመለስ ከጥንቱ ይልቅ የትላንቱ የእናቶቻችን ጊዜ በተምሳሌነቱ ተስተካካይ የለውም፡፡ እነርሱ በያ ትውልድ ተጋድሎ የጊዜውን ጎታች የፆታ አመለካከት በመጋፋትና የወንዶችን ትምክህታዊ ዓለም በመነቅነቅ ታሪክ ለመስራት የታደሉ ፈርጦች እንደሆኑ አስመስክረዋል፡፡

የእኔ ዘመን አብዮተኛ ሴቶችም፣ በኮታ ሳይሆን በእውነተኛው እኩልነት እንዲገለጡ ግዴታቸውን ከወዲሁ መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ከወቅታዊው የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር እኩሌታውን የሚይዙት እንስቶቻችን በነቂስ ያልተሳተፉበት አብዮት በየትኛውም መስፈርት ውጤታማ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በግልባጩ እነርሱን በዕኩልነት ማካተቱ ካልተሳካ ለውጡ ሊዘገይም ሆነ ክፉ ጠባሳ ሊኖረው ስለሚችል፣ ‹‹ያለሴቶች ተሳትፎ የኢትዮጵያ ሕዳሴ እውን አይሆንም!›› ከሚለው ዘመነኛ ኢህአዴጋዊ ቧልት እና ፕሮፓጋንዳ በተለየ መልኩ ተግባራዊ የሚሆን የንቃት ሕዳሴ ትኩረት ሊሰጠው ይገባዋል ብዬ አምናለሁ፡፡

ሌላው ጉዳይ ኢትዮጵያ በ66ቱ እና በ83ቱ የአብዮት ሀዲድ ላይ የመጣችበትን የማሕበረ-ፖለቲካ ታሪኳን ግድፈቶችና ስኬቶች በምክንያታዊነት መመርመር ለሁለንተናዊ ዳግም ልደት (ሕዳሴ) እንድንዘጋጅ መደላድል የመፍጠሩ እውነታ ነው፡፡ ይህ የዳግም ልደት አብዮታዊ ጉዞ ደግሞ በዋነኝነት የሁለት ማሕበረሰቦችን ቅሬታ የሚያቅፍ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይኽን የምለው የሌሎቹን ዋጋ በመዘንጋት ሳይሆን፣ በቀዳሚነቱ ስለማምን ነው፡፡

የብሔር ጥያቄ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ መንግስት ለመናድ ቅርብ የነበረባቸው ዘመኖችን ተመልክተናል፡፡ በዚህ መንገድ አልፈንም በዋናነት በአግባቡ መመለስ ካቃቱን ጥያቄዎች መካከል በኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚነሳው ዋነኛው መሆኑ አያከራክርም፡፡ ይህ ጥያቄ ጠርዘኛ ልሂቃኑ በሚያቀርቡት ልክ ባይሆንም፤ መሬት የረገጡ ማንነታዊ ቅሬታዎችን ተንተርሶ መነሳቱ ግን መካድ የለበትም፡፡ እናም ኢትዮጵያችንን በማደስ ጉዞ፤ ኦሮሞነት ከሀገሪቱ ምንነት ብያኔ የተነጠለ ሆኖ የመጣበትን የታሪክ አጋጣሚ ሂደት በመግታት፣ የብሔሩን መለዮዎች የኢትዮጵያዊነት ብያኔ ገዢ መተርጎሚያና መዳረሻ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሌላኛው ጭብጥ ደግሞ የኢትዮጵያን እስልምና ነባራዊነት ማፅናት ነው፡፡ ኃይማኖቱም ሆነ ተከታዮቹ በአፄያዊዎቹ አፈና ውስጥ ለሺ ዓመታት የመቆየታቸውን እውነታ ተቀብለን፤ በኢትዮጵያዊነት ትእምርታዊ ገፆች ውስጥ ቀዳሚ አዋጭነታቸውን መቀበል የመታደሳችን ግብ ሊሆን ይገባል፡፡ ለነዚህና ለሌሎች መዘርዘር ለማይቻሉን የሀገሪቷ መከራዎች፣ መውጫው ኢትዮጵያን በማደስ የሚደመደም አብዮት ከሆነ ዘንዳ፣ የብሔራዊ ዕርቅ ጉዳይ ከዋነኛ የሽግግር ሂደቶች መካከል ከፊት የሚቆም እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ በእርግጥ ርዕሰ-ጉዳዩ በተነሳ ቁጥር፣ ‹ማን ከማን ጋር ነው የሚታረቀው?› እያለ የሚቀልድ ኢህአዴግ መራሹን መንግስት የመሰለ ቢኖርም፤ እየመጣ ካለው መዓት ሀገሪቷን ለማዳን፣ ብሔራዊ እርቅ ምቹ ድልድያችን መሆኑን ማመን ያስፈልጋል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በበላይነት የሚዘውሩት ልሂቃንን በአንድ የጋራ መድረክ ላይ ማሰባሰብ፣ በቀጣይ እንድትኖረን በምንሻት ሀገር ምንነት ማዕቀፍ ውስጥ የሚያርፉ ተመጋጋቢ አመለካከቶችን ለመቅረፅ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

የሆነው ሆኖ ይህን ተምኔት የመሰለ፣ ነገር ግን ሊከወን የሚችል የሕዳሴ አብዮት ያለእንቅፋት ለማሳለጥ፣ በቅድሚያ ገዥዎቻችን ‹በአንድ ክፉ አጋጣሚ ስልጣኑን ብናጣ ያበቃልናል› ከሚለው ነቢባዊም ሆነ ተጨባጭ ስጋት እንዲላቀቁ ዋስትና መስጠት ላይ መግባባት የግድ ይላል፡፡ በመገዳደል ከተበከለው የግራ-ቀኝ ፖለቲካ ለመንፃት፤ ከነነውረኝነታቸው ሀገሪቷ የእነርሱም እንደሆነች አምነው እንዲቀበሉ ማድረግ ብቸኛው መፍትሔ ነው፡፡ በመጪዋ ኢትዮጵያ አንዱ ልዩ ቀናዒ፣ ሌላኛው ደግሞ ተጠርጣሪ እንደማይሆንባት መተማመን፣ ለሕዳሴው የሚኖረንን ተስፋ ያጎለብታል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፡፡

(የሕዳሴው አብዮትን ማስፈፀሚያ ሃሳብን በተመለከተ ሳምንት እመለስበታለሁ)

“በጨለማዋ አህጉር” ዋሻ ጭላንጭል ብርሃን ይታያልን?

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 

africa

 

በየጊዜው ተስፋቢስነቷ እየጨመረ የመጣው የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታአወዛጋቢ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡  አንዳንዶቹ ጨለምተኝነትን በሚያንጸባርቅ መልኩ በሙስና በተዘፈቁ መሪዎቿ እና ሥር በሰደደው ጥልቅ ድህነት ሳቢያ በመጥፎ ሁኔታ ላይ ተንጠልጥላ ያለች ዕድለቢስ አህጉር በማለት ሲፈርጇት ሌሎቹ ብሩህ ተስፋ የሚታያቸው ሰዎች ደግሞ በአህጉሩ ለውጥ ለማምጣት ተስፋቸውን በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ጥለዋል፡፡     


(
የጸሐፊው ማስታወሻ፡ ይህ ትችት የአፍሪካ አህጉር ዕጣ ፈንታ በያዝነው ምዕተ ዓመት አጋማሽ ምን እንደሚመስል ለመገምገም ተዘጋጅቶ በፓምባዙካ ድረ ገጽ/Pambazuka.org   እ.ኤ.አ ሜይ 29/2014 የታተመ ነው፡፡ እንደ ፖለቲካ ሳይንቲስት እና የህግ ባለሙያነቴ የእራሴን የመከራከሪያ ጭብጦች በማቅረብ የእራሴን ሙያዊ የ “ትንበያ” ግምገማ አድርጊያለሁ፡፡)

ታዋቂው የአሜሪካ የዱላ ክዋስ (ቤዝ ቦል) የነበረው ላውሬንስ ዮጊ ቤራ ቀልድ በሚመስል መልኩ ሲናገር : “ትንበያ” መስጠት አስቸጋሪ ነገር ነው በተለይም ስለወደፊቱ ብሏል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ እ.ኤ.አ በ2050 እና ከዚያም በኋላ ባሉት ጊዚያት በተለይም ከጨለማው የአፍሪካ አህጉር ዋሻ መጨረሻ ብርሃን ስለመኖር እና አለመኖሩ፡፡ ባለፉት ግማሽ ምዕተ ዓመታት በነበሩ ነባራዊ እውነታዎች ሁኔታ ላይ በመመስረት ስለአፍሪካ ትንበያ መስጠት ትንበያ ሰጭውን ሟርተኛ ወይም የመጥፎ አጋጣሚ ትንበያ ሰጭ የሚል ፍረጃ ያሰጠዋል፡፡ በኋላ መስታወት ሳይመለከት ለመተንበይ የሚሞክር ጠንቅዋይ ነው  ፡፡ ከዚህ አንጻር እኔ ከሁለቱም አይደለሁም፡፡

እንደ ፖለቲካ ሳይንቲስት በታዋቂው የዘመናዊ የፖለቲካ ሳይንስ ‘መስራች አባት‘ ኒኮሎ ማካቬሊ ያለዉን እከተላለሁ: “ማንም የወደፊቱን ለማየት የሚፈልግ ሁሉ ያለፈውን ክስተት መዳሰስ አለበት፣ በሰዎች ላይ የሚፈጸሙ የወደፊት ክስተቶች ካለፈው ታሪክ ጋር ተመሳሳይነት አላቸውና”፡፡ ማካቬሊ ሰዎች ከስህተታቸው የመማር አቅም ያላቸው ለመሆናቸው ጨለምተኝነት የተንጸባረቀበት አስተሳሰብን አራምደዋል፡፡ የሰው ልጅ ከስህተቱ ሊማር  አይችልም የሚል አምነት ነበረው::

እንደ ህግ ባለሙያነቴ የምከተለው  ደግሞ “የሰው ልጅ በነፃነት እንዲኖር ተፈርዶበታል፣ ምክንያቱም ወደዚህች ዓለም ከመጣ ጀምሮ ለማንኛውም ለሚሰራው ስራ ሁሉ ሰው ኃላፊነትን ይወስዳል“ በማለት ጂን ፓውል ሳትሬ ያወጁትን ማሳሰቢያ እወስዳለሁ፡፡ ሳትሬ ከእርሳቸው በፊት በነበሩት ጃኩ ሩሶ በተባሉት ምሁር አስተሳሰብ አንፀባርቀዋል፡፡ ጃኩ ሩሶ እንዲህ በማለት አውጀዋል፣ “የሰው ልጅ ነጻ ሆኖ ተፈጥሯል፣ ግን በየትኛውም ቦታ ነፃነቱን አጥቶ ታስሯል፡፡ እራሳቸውን የሌሎች ጌታ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች እራሳቸው ከሌሎች የባሰ  የበታች ባሮች ናቸው፡፡” ሰለዚህ አፍሪካውያን/ት በህግ የበላይነት፣ ፍትሀዊ እና ትክክለኛ ህጎች ጥላ ስር ነጻ ሆነው ይኖራሉ? ወይስ ደግሞ ቀደም ሲል በቅኝ ገዥዎች እና በኋላም በእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ጌቶቻቸው አገልጋይ ሆነው ይቀራሉ?

የያዝነውን ምዕተ ዓመት አጋማሽ የወደፊት ትንበያ በመስጠት ረገድ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ እመራለሁ፡፡ እነርሱም 1ኛ) የአፍሪካ ‘የወደፊት ታሪክ’ ‘ባለፈው ታሪክ’ የሚወሰን ነው ወይስ ደግሞ ገና ባልተወለዱት ነጻ አፍሪካውያን/ት የሚጻፍ ታሪክ ነው? 2ኛ) የሰው ልጅ መፈጠርያ የሆነችው አህጉር እ.ኤ.አ በ2050 እና ከዚያ በኋላ የነጻነት እና የሰብአዊ መብቶች መቃብር ልትሆን ትችላለችን?

የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመተንበይ የኋላ መስተዋት መመልከትን፣ የዕጣ ፈንታ ነጋሪ ጠንቋዮችን ወይም ደግሞ የሂሳብ ሞዴል ቀመሮችን አልጠቀምም፡፡ ይህንን ጉዳይ ለወደፊቱ ለፕሮፌሽናሎች እና ትንበያ ሰጭዎች እተወዋለሁ፡፡ እንደ ፖለቲካ የህግ ባለሙያነቴ እና  የሰብአዊ መብት ተሟጋችነቴ የምያሳሰበኝ ጥያቄ የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሁኔታ በደብዛዛው መስታወት ፍትህን፣ ነጻነትን፣ የህግ የበላይነትን፣ እኩልነትን እና ሌሎችን ከፍተኛ የሞራል ስብዕና የሚጠይቁትን ጉዳዮች ለመመልከት እመርጣለሁ፡፡ ለእኔ ጥያቄ ሆኖ የሚቀርበው የህዝብ ስብጥር እና ውልደት፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጥ፣ የከባቢ አየር ሁኔታ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2050 እና ከዚያም በኋላ የአፍሪካን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሊወስኑ የሚችሉ የሰዎች የልማት ጉዳዮች አይደለም፡፡ እነዚህ ጉዳዮች ለእድገት ለደህነነት ያለምንም ጥርጥር ወሳኞች ናቸው፡፡ የእኔ የትኩረት አቅጣጫ ያነጣጠረው በአፍሪካ አህጉር የህግ የበላይነት እና መልካም አስተዳደር፣ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የፖለቲካ እና የአካባቢ ስነምህዳር የውድመት አማራጭ የምጻት ቀንን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ለማመላከት ነው፡፡

አንድ የኡጋንዳውያን/ት የቆየ እንዲህ የሚል የማስጠንቀቂያ አባባል አለ፣ “ወደየት እንደምትሄድ ካላወቅህ/ሽ ማንኛውም መንገድ እዚያ ያደርስሀል፡፡“ በቀጣዮቹ 50 ዓመታት አፍሪካ ወደየት ነው የምትሄደው? አፍሪካውያን/ት የማንዴላን ረዥሙን የነጻነት እና የብልጽግና ጉዞ በመከተል እ.ኤ.አ በ2050 እና ከዚያም በኋላ ግባቸውን ለማሳካት ጥረት ያደርጋሉ ወይስ ደግሞ በድህነት አዘቅት ውስጥ እና በአምባገነኖች ወጥመድ ተጠፍረው የእርስ በእርስ የጎሳ ጥላቻን፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን፣ ሙስናን እና ያልተገደበ የህዝብ እድገትን የምጻት ቀናቸውን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ? በ2050 እና ከዚያ በኋላ ተስፋ የተጣለባት አፍሪካ ለአፍሪካውያን/ት ትሆናለች ወይስ ደግሞ አዲስ የማትመች እና አሁን አንዳለችበት ሁኔታ ‘የለማኞች አህጉር’ ትሆናለች? አፍሪካ በ2050 እና ከዚያ በኋላ አሁን እንደምናውቃት አፍሪካ ልትኖር ትችላለችን? በአሁኑ ጊዜ ስለአፍሪካ መተንበይ እርባናየለሽ ተግባር ነውን?

የፖለለቲካ ሳይንቲስቱ የማካቬሊ ነብያዊ ቃላት በእኔ ጆሮ ውስጥ እንዲህ በማለት ያንሾካሹካሉ፣ “አፍሪካ ከነጭ አምባገነናዊ የቅኝ ግዛት ጭቆና በመላቀቅ ብቻ በጥቁር አፍሪካውያን/ት መዳፍ ስር ወድቃ በመማቀቅ ላይ ትገኛለች፡፡ ለ50 ዓመታት በዘለቀው የነጻነት ጉዞ አፍሪካ መረን በለቀቀ አምባገነናዊ ስርዓት፣ ሙስና፣ ድህነት፣ ጦርነት፣ የጎሳ ጥላቻ፣ ረኃብ እና በሽታ ተንሰራፍተውባት ትገኛለች፡፡ 2050 ለአፍሪካ የምጻት ቀን ነው፡፡ አፍሪካ በ “ፕሌቶ ዋሻ” ጥላውን እንጅ ብርሀንን ሳታይ እስረኛ ሆና ትቀጥላለች፡፡ የዓለም ፍጻሜ ይሆናል፡፡ አፍሪካ ብሩህ ተስፋ አይታይባትም፡፡“

እንደ የመከላከል የህግ ባለሙያነቴ የብሩህ እና የደስታ ቃላት እንዲህ በማለት በጆሮየ ላይ ያቃጭላሉ፡፡ “የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንደ ጸሐይ የሚያበራ ነው፡፡ በአፍሪካ እያስገመገመ በሚመጣው የህዝቦች የነጻነት ፍላጎት ምክንያት አምባገነናዊነት እንደቆሻሻ ተጠራርጎ በታሪክ የቆሻሻ ማስቀመጫ ቅርጫት ውስጥ ይጣላል፡፡ የአንድ ፓርቲ የፈላጭ ቆራጭነት ስርዓት ተገርስሶ እውነተኛ በሆነ የብዙሀን ፓርቲ ስርዓት ይተካል፣ ኢፍትሀዊነት እና አድሏዊነት በህግ የበላይነት ይወገዳል፣ ሙስና በግልጽነት እና በተጠያቂነት ብርሀን ተንኖ ይጠፋል፣ ብልጽግና ድህነትን ያስወግዳል፣ ሰላም በጦርነት ላይ ድልን ይቀዳጃል፣ የጎሳ ጥላቻ በጎሳ ፍቅር እና መተሳሰብ ይተካል፣ ረሀብ በተትረፈረፈ ምርት ይወገዳል፣ ድርንቁርና በትምህርት ብርሀን ይገፈፋል፡፡ ከዋሻው መጨረሻ ደማቅ ብርሀን የምታበራ ጸሐይ ትታያለች፣ የህግ የበላይነት በህገ አራዊት ላይ ድልን ይቀዳጃል፡፡ ያ ጊዜ በአፍሪካ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ በመሆን የመጀመሪያ ሆኖ ይመዘገባል፡፡“

ስለሆነም እ.ኤ.አ በ2050 እና በኋላ በአፍሪካ በፖለቲካ ሳይንቲስት እና በህግ ባለሙያ የተተነበዩ ጥቂት ሆኖም ግን ጠንካራ ተስፋዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

የፖለቲካ ሳይንቲስት፡ እ.ኤ.አ በ2050 እና በኋላ የአፍሪካ ዋናው ችግሯ ረሀብ እና ቸነፈር ወይም ደግሞ ዓለም አቀፍ የድህነት ወትወዋቾች በሚስማማቸው መልኩ እንደሚጠሩት ‘የምግብ ዋስትና እጦት’ ነው፡፡ አሁን ያለው 1.1 ቢሊዮን የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ ብዛት በመጨመር በ2050 ቢያንስ 2.4 ቢሊዮን እንደሚሆን ይገመታል፡፡ የናይጀሪያ 174 ሚሊዮን የሆነው ህዝቧ በ2050 በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ 440 ሚሊዮን ይደርሳል፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 በዩናይትድ ስቴትስ የስታቲስቲክስ ቢሮ በቀረበው ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ በተለየ መልኩ የአንድ እናት የውልደት መጠን 6 ልጆች በመሆን በ2050 በዓለም አቀፍ ደረጃ በህዝብ ብዛት ከፍተኛ ከሆኑት አገሮች በ13ኛ ደረጃ ላይ ከነበረችበት በመውረድ ወደ 7ኛ ደረጃ ላይ በመሆን በሶስት እጥፍ በማደግ አሁን ካለችበት ከ91 ሚሊዮን ወደ 278 ሚሊዮን ይደርሳል፡፡  በ2050 አፍሪካ በድህነት ወጥመድ (በመልካም አስተዳደር እጦት እና የኢኮኖሚ አመራር ብልሹነት ምክንያት ትውልድ አቀፍ ድህነት) ውስጥ እራሷን እንደምታገኝ እና ‘የማልቲሲያን ህልዮት’ (የህዝብ ብዛት የምግብ አቅርቦትን እንደሚበልጥ) እንደምትተገብር ይገመታል፡፡ አፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን ህዝቧን ለመመገብ የሚያስችል የምግብ እህል አቅርቦትን ለማሳደግ አትችልም፡፡ ‘የህዝብ ብዛት ቦምብ’ በምዕተ ዓመቱ አጋማሽ የአፍሪካን ህዝብ ይጭርሳል፡፡ 

የህግ ባለሙያ፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ 70 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ እድሜው ከ35 ዓመት በታች ያለ ነው፡፡ የወጣቱ የህብረተሰብ ከፍል ብዛት በምዕተ ዓመቱ የበለጠ የሚጨምር ይሆናል፡፡ ለአፍሪካ ወጣቶች ጥራት ያለው ትምህርት አስፈላጊነት እና የወጣቶች ፍላጎቶች እና እሴቶች መቀያየር ትልቅ የነበረውን ባህላዊውን የቤተሰብ ብዛት እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡ አዲሱ ትውልድ የቤተሰብ ምጣኔ እና የወሊድ መከላከያ ዘዴዎች እና አገልግሎቶችን ተጠቃሚ በመሆን የውልደት መጠንን የማዘግየት ልምዶችን በስራ ላይ ያውላል፡፡ የአፍሪካ ወጣቶች የአዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና የስራ ፈጠራ ዕድሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ወጣቶች የመንግስት የስልጣን ልጓምን በመጨበጥ መልካም አስተዳደርን በማጎልበት እና በማጠናከር የስርዓቱ እሴት እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡ አፍሪካ እውነተኛ የሆነ የብዙሀን ፓርቲ ስርዓት ዴሞክራሲ እንዲኖራት በማድረግ በነጻነት የሚሰሩ የፍትህ አካላት፣ ዳኝነት፣ ነጻ እና ወገንተኛ ያልሆነ ፕሬስ እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት እና በየተወሰ ጊዜ የሚካሄዱ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫዎች እንዲኖራት ያደርጋሉ፡፡ አፍሪካ በታደለቻቸው ለም መሬቶቿ እና በአህጉሩ ባሉት የውኃ ኃበቶቿ ጸጋዎች የዓለም የዳቦ ቅርጫት ትሆናለች፡፡ የአፍሪካ ብሩህ ቀኖች በመምጣት ላይ ናቸው!

የፖለቲካ ሳይንቲስት፡ ጆርጅ አይቴይ እንዲህ ብለዋል፣ “አፍሪካ ደኃ ናት ምክንያቱም ነጻ አይደለችም፡፡” በእርግጥ አፍሪካ ደኃ አይደለችም፡፡ አፍሪካ በተፈጥሮ ኃብት ረገድ በጣም ኃብታም አህጉር ናት፡፡ አፍሪካ ደኃ ናት ምክንያቱም አመራሩ በሞራል ዝቅጠት የበከተ ነው፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ለምንም ነገር የማይውሉ አምባገነኖች፣ በሙስና የበከቱ እና እርባናየለሾች ናቸው ፡፡ በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት አለ እየተባለ ቢነገርም (ባለፉት አስርት ዓመታት በከፍተኛ ደረጃ እድገት ካስመዘገቡት አስር አገሮች ውስጥ ሰባቱ ከአፍሪካ ናቸው) እየተባለ በዓለም አቀፍ የድህነት ወትዋቾች እና ለውጥ ለማምጣት ፍላጎቱ የሌላቸው የምዕራቡ ዓለም የዜና ባለሙያዎች ቢደሰኮርም ሀቁ ግን ድህነት ከ85 በመቶ በላይ ከሚሆነው እና በቀን ከአንድ ዶላር በታች እያገኘ ከሚኖረው የአፍሪካ ህዝብ ህይወት ጋር በቅርበት ተቆራኝቶ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ በ2050 ድህነት እና በሽታ የአፍሪካውያንን/ትን አማካይ የመኖር አድሜን ከ37 ዓመት በላይ እንዳይዘል በማድረግ ቀንሶታል፡፡ ስለሆነም አፍሪካ በድህነት እና በአምባገነናዊ የወጥመድ ድር በመተብተብ ተይዛ ትቆያለች፡፡       

የህግ ባለሙያ፡ የሚመጣው አዲሱ የአፍሪካ ትውልድ አሁን ባለው የድህነት እና አምባገነናዊ የወጥመድ አሽክላ ተጎጂ ይሆናል፡፡ በምዕራቡ ዓለም እርዳታ ተመጽዋችነት እራሳቸውን ተገዥ አያደርጉም፡፡ ይልቁንም ይህንን የለማኝነት ባህል ከናካቴው ያጠፋሉ፡፡ አፍሪካን ከችግር ለማላቀቅ እና ከድህነት ወጥመድ ውስጥ ለማውጣት ወጣቶቹ የእራሳቸውን እውቀት እና ቴክኖሎጂ ይጠቀማሉ፡፡ ለሚገጥማቸው ውድቀት እራሳቸውን ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡ በቅኝ ግዛት፣ በኢምፔሪያሊዝም፣ ኮሙኒዝም እና በሌሎች ለአፍሪካ ውድቀት ተጠያቂ ናቸው እያሉ ጊዜ በማባከን ላይ አያሳብቡም፡፡ የአፍሪካን ድህነቶች በሙሉ አያስወግዱም ሆኖም ግን በእርግጠኝነት የአፍሪካን የአመራር ሽባነት ያስወግዳሉ፡፡ ወጣቶቹ በእራስ የመተማመን ጠንካራ ስሜታቸው አፍሪካን ከድህነት እና ከአምባገነናዊ የወጥመድ አሽክላ ውስጥ መንጥቀው ያወጣሉ፡፡

የፖለቲካ ሳይንቲስት፡ “ራዕይ በሌለበት ጊዜ ህዝቦች ይጠፋሉ“ ተብሎ ተጽፏል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አፍሪካውያን/ት በደቡብ ሱዳን፣ በመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ፣ በማሊ፣ በቻድ፣ በሶማሌ እና በሌሎቸም እያለቁ ነው፡፡ አፍሪካ ራዕይ በሌላቸው (ድሁር እና እውር) አምባገነን መሪዎች እየተሰቃየች ነው፡፡ የሞ ኢብራሂም የአፍሪካ አመራር ሽልማት ከዓለም ትልቁ በየዓመቱ የሚሰጥ ሽልማት (በ10 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እና የህይወት ሙሉ ኢንዶውመንት ሁለት መቶ ሺ ዶላር)  እ.ኤ.አ በ2007 ከተመሰረተ ጀምሮ ሶስት ጊዜ ብቻ ሰጥቷል፡፡ ተሸላሚዎቹ ከሞዛምቢክ፣ ቦትስዋና እና ኬፕቬርዲ አገሮች የመጡ ናቸው፡፡ ‘አዲሱ የአፍሪካ መሪዎች ዝርያ’ እየተባለ በቢል ክሊንተን እና በቶኒ ብሌር ሲዘመርላቸው የነበሩት አምባገነኖች አንዳቸውም ከዚህ ሽልማት በር ላይ እንኳ አልደረሱም፡፡ በአፍሪካ ያለው የአመራር ቀውስ እ.ኤ.አ በ2050 እና በኋላ አፍሪካን በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ይዘፍቃታል፡፡

የሀግ ባለሙያ፡ እ.ኤ.አ በ2050 የአፍሪካ መሪዎች በሰከነ መልክ አስበው የሚሰሩ እንጅ እንደ ቀደምቶቹ ነገርን የሚያጦዙ አምባገነን መሪዎች አይሆኑም፡፡ በጥሩ ሁኔታ የተማሩ እና ስልጠና የወሰዱ (በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው እንደሚገኙት መሰኛ የደናቁርት ስብስብ አይሆኑም) የሚሆኑ ናቸው፡፡ ችግሮችን ከጅምሩ ለመፍታት በሰከነ መንፈስ አስበው እና አቅደው የሚንቀሳቀሱ እንጅ እንደቀደምቶቹ ችግርን በችግር ላይ የሚቆልሉ አምባገነኖች አይሆኑም፡፡ እንደሁኔታው እራሳቸውን ከአዳዲስ ክስተቶች ጋር አጣምረው የሚሄዱ እና ከነገሮች ጋር እራሳቸውን ማዛመድ የሚችሉ ናቸው፡፡ የአዲሱን ትውልድ ድምጽ የሚሰሙ እና ፍላጎታቸውን አጥንተው የሚተገብሩ ናቸው፡፡ አእምሯቸው ለበጎ ነገሮች እና ለለውጥ ክፍት እንዲሁም የሚመጡ ችግሮችን አስቀድመው መተንበይ የሚችሉ እና መፍትሄ መስጠት የሚችሉ ናቸው፡፡ በ2050 እና በኋላ የአፍሪካ መሪዎች ታማኞች፣ ግልጽነትን የተላበሱ፣ ተጠያቂነት እና በእራስ የመተማመን ስሜት የሚታይባቸው እንዲሁም የፈጣሪነት እና የተነሳሽነት ስሜት የሚስተዋልባቸው ናቸው፡፡ የሚከተሉትን የማንዴላን መርሆዎች እና ትዕዛዞች ተከትለው የሚሄዱ ናቸው፡ 1ኛ) ከኋላ ሆኖ መምራት ሌሎችን ከፊት ሆነው እንዲመሩ በማድረግ በተለይም መልካም ነገሮች ከተከናወኑ በኋላ በሚደረግ የድል አከባበር ስርዓት ላይ ማሳተፍ፣ 2ኛ) አደጋ በሚኖርበት ጊዜ ከፊት ሆኖ መምራት፣ በዚህም ሳቢያ ህዝብ ይወድሀል እምነትም ይጥልብሀል፡፡

የፖለቲካ ሳይንቲስት፡ ‘አፍሪካ የጨነገፉ መንግስታት አህጉር ናት፡፡ አፍሪካ የጨነገፈች አህጉር ናት፡፡’ በምዕራቡ ዓለም የመገናኛ ብዙሀን ብዙ ነገር እየተባለ የተለያዩ ትርጉሞች ይሰጣሉ፡፡ የጨነገፉ እና በቋፍ ላይ ያሉ አገሮች የሚለው ትርጉም ያፈጠጠውን እና ያገጠጠውን እውነታ ለመደበቅ ሲባል የሚውል የማደናገሪያ ስያሜ ነው፡፡ እውነታው ግን የአፍሪካ አገሮች መሪዎች የወሮበላ ስብስቦች፣ መንታፊ ዘራፊዎች እና  በሙስና የበከቱ ሞራለቢሶች ናቸው፡፡ የአፍሪካ መንግስታት የአገሮችን ግምጃ ቤቶች እና ብሄራዊ ሀብቶች ዘርፈው ወደ ውጭ አገር ባንኮች በእራሳቸው የሂሳብ ደብተር የሚያስቀምጡ የታወቁ የማስመሰያ የወንጀለኛ ተቋሞች ናቸው፡፡ ከአፍሪካ አህጉር በስተቀር በመሬት ላይ በየትኛውም የዓለም ክፍል ቢሆን እንደ አፍሪካ ያለ በሙስና የበከተ፣ በብልሹ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አያያዝ ስርዓት የተተበተበ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ የተንሰራፋበት አይገኝም፡፡ በ2050 ሁሉም የአፍሪካ መንግስታት በሚባል መልኩ የጨነገፉ መንግስታት ወይም ደግሞ በዘራፊዎች የሚጦዙ ወሮበላ መንግስታት ይሆናሉ፡፡ ጥቂት የአፍሪካ መንግስታት በጣም ወሳኝ የሆኑ የፖለቲካ ትሩፋቶችን ለእራሳቸው ዜጎች ይሰጣሉ፡፡ ጥቂት መንግስታት በእራሳቸው ዜጎች ዓይን እይታ ህጋዊነትን ይላበሳሉ፣ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሁሉም የአፍሪካ አገሮች በእራሳቸው ዜጎች  እና በሌሎችም ይዘለፋሉ፡፡ የአፍሪካ መንግስት በዓለም ላይ የተዋረደ እና የተናቀ ይሆናል፡፡ በቅርቡ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር የሆኑት ጆን ማኬይ እንዲህ ብለው ነበር፣ ናይጀሪያ በመሄድ ቦኮ ሀራም በተባለ አሸባሪ ቡድን ተጠልፈው የተሰወሩትን 300 ልጃገረዶችን ከአደጋ ለማዳን “ጉድላክ ጆናታን ከሚባል አንድ ሰው የሆነ ፈቃድ መሳይ ነገር አልጠብቅም፡፡“ ጉድላክ ጆናታን ልጃገረዶች ያሉበትን ቦታ ፈልጎ ከአደጋ ሊታደጋቸው የሚችል የጦር ኃይል ገና እያሰማሩ ነው፡፡ ናይጀሪያ ልጃገረዶችን ከአደጋ ለማዳን በምታደርገው እንቅስቃሴ በእራሷ ልትወጣው ስላልቻለች የናይጀሪያን የጦር ኃይል ለመርዳት ዩናይትድ ስቴትስ ወታደር እና ሰው አልባ አውሮፕላን አሰማርታለች፡፡ ‘የታላቋ አፍሪካ’ ዕጣ ፈንታ እንግዲህ እንደዚህ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ፣ ኮትዲቯር እና ማሊ ውስጣዊ ቀውስ እና ጥላቻ በገጠማቸው ጊዜ እራሳቸውን ከእራሳቸው ለመጠበቅ ለድሮ ቅኝ ገዥዎቻቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በምዕተ ዓመቱ አጋማሽ አፍሪካ በጣም ትንንሽ ወደሆኑ ብጥስጣሽ የወሮበላ ግዛቶች (መቶ የሚሆኑ የተበጣጠሱ በወሮበላ አምባገነኖች ንጉሶች እና ባንዳዎች ቁጥጥር ስር የሆኑ መንግስታት) ትከፋፈላለች፡፡ አፍሪካ ከጨነገፉ እና በቋፍ ላይ ካሉ መንግስታት አህጉርነት ፍጹም ወደ መከኑ እና የወደቁ መንግስታት አህጉርነት ትቀየራለች፡፡

የህግ ባለሙያ፡ አፍሪካ በምዕተ ዓመቱ አጋማሽ ከአምባገነናዊነት ወደ ብዙሀን ፓርቲ ዴሞክራሲ ሽግግሯን ታጠናቅቃለች ምክንያቱም ከጥፋተኝነት ነጻ ትሆናለች፡፡ በ2050 እና በኋላ አብዛኛው የአፍሪካ ክፍል እንደ አሁኗ ቦትስዋና ይሆናል (በቦትስዋና መንግስት የ “ሳን” ህዝብን (“የጫካ ህዝቦች”) ማፈናቀሉን እና ማስፈሩን በመመርመር አውግዣለሁ)፡፡ ነጻ እና ፍትሀዊ የሆነ የብዙሀን ፓርቲ ምርጫዎች ይኖራቸዋል፡፡ የአፍሪካ ህዝቦች እንደ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ በአቦ ሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) እየተመሩ የዴሞክራሲያዊ መንገድን ይከተላሉ፡፡ ጠንካራ ተቋማት ማለትም ነጻ ፍርድ ቤቶችን፣ ፕሮፌሽናል ሲቪል ሰርቫንቶችን እና የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማትን ጨምሮ ይመሰረታሉ፡፡ የህግ የበላይነት ተቋማዊ ይሆናል እናም ሰብአዊ እና የንብረት ባለቤትነት መብት ይከበራሉ፡፡ የአፍሪካ አዲሱ ትውልድ የግልጽነት እና የመቻቻል ባህሉን በማጠናከር እራሱን ከፍ ወዳለ ደረጃ ያዘጋጃል፡፡ አህጉሩን የማህበረሰቦች ጭራ እንዲሆን ጠፍንገው የያዙትን በህግ ያለመጠየቅ ወንጀልን እና ሙስናን ያወግዛል፣

የአፍሪካ ባለብሩህ አእምሮ ባለቤቶች የሆኑት የተማሩ ወጣቶች የአህጉሩን ዕጣ ፈንታ መወሰን እና መቆጣጠር ይጀምራሉ እንዲሁም የነቀዘውን እና የነፈዘውን የቀድሞውን ትውልድ ኋላቀር ልማድ እና አሰራር ያስወግዳሉ፡፡ በምዕተ ዓመቱ አጋማሽ የግንኙነት ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ውጤታማ በሆነ መልኩ በመጠቀም የአፍሪካ አህጉር የነበረባትን የዴሞክራሲ ጉድለት ታካክሳለች፡፡ የአፍሪካ ወጣቶች ከዓለም ወጣቶች ጋር የግንኙነት መስመራቸውን በማጠናከር በመላው አፍሪካ ያልተጠበቀ እና ታላቅ ለውጥ ለማምጣት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ የአፍሪካ ችግሮችን ለመፍታት ከሌሎች አገሮች በትውስት እና በኩረጃ የተገኘውን እውቀት፣ ብልሀት እና የተወሳሰበ ቴክኖሎጂን መጠቀም ብቻ ሳይሆን በአፍሪካውያን/ት ባህል ላይ የተመሰረቱ ወጥ ሀሳቦችን፣ ማህበረሰቦችን እና ራዕዮችን አስተባብሮ በስራ ላይ ያውላሉ፡፡ በምዕተ ዓመቱ አጋማሽ የአፍሪካ ረዥሙ፣ ቀዝቃዛው እና ጠንካራው የክረምት አምባገነንነት፣ ድህነት እና የደስታ እጦት የብሩህ አእምሮ ባለቤቶች በሆኑት ወጣቶች የአፍሪካ የጸደይ አብዮት ተካሂዶ ፍቅር የነገሰባት እና ዴሞክራሲ ያበበባት አህጉር ትሆናለች፡፡

በጨለማ ውስጥ ጨለማውን አህጉር በመስታወት ውስጥ በመመልከት ከዋሻው መጨረሻ ያለውን ብርሀን ማየት አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ የአምባገነኖች ጭጋግ፣ ሙስና እና ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም በአህጉሩ ላይ ተንሰራፍተው የሚገኙት በቀላሉ ብርሀንን ለማየት የሚፈቅዱ አይደሉም፡፡ ያልተገደበ የህዝብ እድገት፣ ቁጥጥር የማይደረግበት የከተማ እድገት፣ ስር የሰደደ ሙስና፣ በዜጎች መካከል የሚከሰት ከፍተኛ የሆነ የገቢ ልዩነት፣ አውዳሚ የሆነ የአየር ንብረት ለውጥ፣ መረን የለቀቀ የምሁራን ፍልሰት እና በተደጋጋሚ የሚደርስ ግጭት እና ጥላቻ ከዋሻው ጫፍ ያለውን ብርሀን ለማየት በጣም አስቸጋሪ አድርገውታል፡፡ እንደዚህም ሆኖ ጸሐይ ነገ እንደምትወጣ እርግጠኛ ሆኘ መናገር ስለምችል ለጨለማው አህጉር በ2050 እና በኋላ ብሩህ ተስፋ ይፈነጥቅበታል፡፡ ከሙያ እና ከስራ አድሏዊነት በጸዳ መልኩ ስለአፍሪካ ብሩህ ተስፋ አላሚ ሰው ነኝ፡፡ ከሁሉም በላይ በአፈጣጠሬ ተምኔታዊ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡

ለጨለማው አህጉር ከዋሻው መጨረሻ ብርሀን የለም፡፡ ብሩህ የአፍሪካ ጸሐይ ነው ያለችው!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ግንቦት 25 ቀን 2006 ዓ.ም

ሰኔ 1 ቀን ትኩረቱ አዳማና ደብረ ማርቆስ ላይ ነው -አማኑኤል ዘሰላም

$
0
0

የአሥራ ስድስት አመት ወጣት ነበረች። ይሄን ጊዜ ከኮሌጅ ተመርቃ፣ ሥራ ይዛ ምናልባትም ተድራ፣ የልጆች እናት ትሆን ነበር። አሁን ግን የለችም። ኮተቤ አካባቢ ነበር፤ ከአጋዚ ጦር አንዱ በተተኮስ ጥይት ተመታ ወደቀች። ሰኔ አንድ ቀን 1997 ዓ.ም።

shibre-desalegn

የአሥራ ስድስት አመት ወጣት ነው። በእጆቹ ድንጋይ አልያዘም። ተማሪ ነበር። ወደቤቱ ሲመለስ፣ በአካባቢዉ ግርግር ተፈጠሮ ስለነበረ፣ ሰላምና መረጋጋት እናመጣለን ባሉ ታጣቂዎች ተገደለ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት በጊምቢ ወለጋ። ያኔ ደም ፈሰሰ። አሁንም ደም እየፈሰሰ ነው። ያኔም ድብደባ ነበር አሁን ድብደባ ነው።፡ያኔ መታሰር፣ መታፈስ ነበር፣ አሁንም መታሰር፣ መታፈስ ነው። ያኔም አንገት ደፍቶ አቀርቆ ባርያ ሆኖ መኖር ነበር። አሁን አንገት ደፍቶ መኖር ነው። ያኔም ዜጎች ከቅያቸው ይፈናቀሉ ነበር። አሁንም ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው። አይበቃም እንዴ ወገን ? ?

አንድ ነገር መርሳት የሌለብን ነገር አለ። ይሄ ሁሉ በአገራችን እና በሕዝባችን ላይ እንዲኖር የፈቀድነው እኛዉ እራሳችን ነን። አምባገነኖችን ማማረርና መራገም ማቆም አለብን። እነርሱ አሁን እያደረጉት ያለውን እንዲያደርጉ የፈቀድንላቸው እኛው ነው።

አንዳንዶቻችን ትችት እንወዳለን። «ይሄ ለምን አልተሰራም፣ ተቃዋሚዎች እንደዚህ ናቸው….» ማለት እንወዳለን። አገር ቤት ያሉ ታጋዮች ትንሽ ስህተት ከሰሩ ፣ ስህተታቸውን አጋነን እናወራለን። የተሰሩ መልካም ስራዎችን ላይ አናተኩርም። ነጻነትን እንፈልጋለን። ግን ሌሎች ታግለው ነጻነትን እንዲያመጡልን ነው የምንጠብቀው። ይሄ አይሆንም !!! ይሄ አይሰራም። ዳር ቆም ትችት ያለፈበት ፖለቲካ ነው።

ለዉጥ ከፈለግን ፣ ሌሎች ለምን ይሄን አያደርጉም ማለት አቁመን፣ እኛ ምን እያደረግን ነው ብለን መጠየቅ አለብን። ያልተሰራ ነገር ካለ፣ ሰብሰብ ብለን፣ ጓደኞቻችን ይዘን እኛው እንስራው። በአገራችን ጉዳይ ላይ ነጋሪና ጎትጓች ሊኖረን አይገባም። ትግሉን ለመርዳት ተሯሩጠን መምጣት አለብን እንጂ መለመን የለብንም። በአገራችን ሰለምና ደሞክራሲ ኒኖር እኮ፣ እስክንደር ነጋ ወይንም አንዱዋለም ወይንም አገር ቤት እየተጋሉ ያሉቱ ብቻ አይዴልም የሚጠቀሙት። እያንዳንዳችን ነው የምንጠቀመው። ኢትዮጵያ ስትመነጠቅ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነው የሚመነጠቀው። ስለዚህ የምንታገለው ፣ ባናስተዉለው ነው እንጂ፣ ለራሳችን ነው።

ለበርካታ አመታት የአንድነት ፓርቲ ላይ ከፍተኛ ትችት ይቀርብ ነበር። «ምን እየሰሩ ነው ? ለምን አያታግሉንም ? ..» እያሉ የሚጮሁ ጥቂት አልነበሩም። እነሲህ ሰዎች ያኔ ትክክል ነበሩ። አዎን አንድነት ተኝቶ ነበር። ግን ያለፈው አመት የተለየ ሁኔታ እያየን ነው። ባህር ዳር፣ ደሴ፣ ጊዶሌ አዲስ አበባ ….ይመስክሩ። አንድነት አስደሳች በሆነ ሁኔታ የተጨበጡ ስራዎችን እየሰራ ነው። ታዲያ ትላንት አንድነትን ለምን አልሰራም ብለን ስንተች የነበረን፣ ዛሬ ድምጻችን ለምን ጠፋ ? ታዲያ የኛንስ ድርሻ ለመወጣት ለምን ዘገየን ?

እንግዲህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከራሱ ጋር እንዲነጋገር እጠይቃለሁ። የፊታችን እሁድ ሰኔ 1 ቀን በአዳማና በደብረ ማርቆስ ታልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል። ባለስልጣናት ለሰልፉ እውቅና ሰጥተዋል። እንግዲህ በአዳማ እና በደብረ ማርቆስ ያለን በነቂስ እንወጣ። ድምጻችንን እናሰማ። «ነጻነት ፣ ነጻነት፣ ቢሊሱማ ! ቢሊሱማ» እያለን እንጩህ። በራሳችን እንተማመን። እነርሱ ምንም ማድረግ እንደማንችል ነው ደጋግመው ሊነግሩን የሚፈልጉት። ያንን ከማለትና ልቦናችንን ለመስለብ ከመሞከር ዉጭ ሌላ አማራጮች የላቸውም። እኛ ግን ልባሞች እንሁን። አንፍራ። በደብረ ማርቆስና በአዳማ የነጻነት ደዉል ይሰማ።

በተቀረው የኢትዮጵያ ግዛት እንዲሁም በዉጭ አገር ያለን፣ በመንፈስ ሰልፉን እንቀላቀል። በሶሻል ሜዲያዎች ዘምቻዉ ፣ ቅስቀሳው ይጧጧፍ። በስካይፕ፣ ቫይበር፣ ኢሜል ወዳጅ ዘመዶቻችንን ወደ ሰልፉ እንዲወጡ እናበረታታ። እንነቃነቅ!!!!!!

በዉጭ አገር ላለን በተለየ ሁኔታ ሌላ ትልቅ ሃላፊነት አለብን። ገዢው ፓርቲ እንዳለ ኢኮኖሚዉን ተቆጣጥሯል። የአገሪቷ ካዝና በ እጃቸው ነው። የህዝብን ጥያቄ አንግቦ የሚንቀሳቀሰው የሚሊዮነሞች ንቅናቄ፣ የጀርባ አጥንቱ ህዝብ ነው። እኛ ነን። በዚህ ጊዜ አገር ቤት ያለው ሕዝባችን ፈታኝ ትግል እያደረገ ባለበት ወቅት፣ በዉጭ ካለን ብዙ ይጠበቃል። ለሌሎች ፣ ሌሎች ጉዳዮች ብዙ ገንዘብ እየተሰበሰበ ባለበት ሁኔታ፣ ወሳኝ ለሆነው ነገር ዝምታዉና መቀዝቀዙ ትክክል አይደለም። ዳያስፖራው ፕራዮሪቲዉን ማስተካከል አለበት።

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>