Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

እረ ለመሆኑ ከአንድነት ወዲያ ለኦሮሞ ማን ሊመጣ ነው? 

$
0
0

ተስፋዬ ዋቅቶላ (የአዳማ አንድነት ፓርቲ የሕ/ግንኙነት)

“….ያኔ እንተያያለን…”

በትላንትናው ዕለት የአዳማ አንድነት ሰልፍ ፈቃዳችንን ከ20ቀናት ደጅ ጥናት በኋላ ወስደናል፡፡ግን ከአስገራሚ ገጠመኞቹ ጥቂቱንም ቢሆን ማካፈል ግድ ይለናልና እነሆ፡፡ፈቃዱን ከመስጠታቸው በፊት ከከተማው ጸጥታ ክፍል ሶስት ሰዎች መጥተው ከንቲባው ጽ/ቤት ተጠርተው ገቡ፡፡እኛ በዚህ ዕለት ካልተሰጠን ላንወጣ ተነጋግረን ገብተናልና “ቶሎ ድረሱልኝ” ያላቸው ሰዎች መምጣት ደስ ብሎናል እንጂ አልፈራንም፡፡ሆኖም ነገርየው ለካ ማስፈራራት ነበር፡፡

በተለያዩ መንገዶች ትንኮሳ ቢደረግብንም ለትንኮሳው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ህጋዊውን ወረቀት መያዝ ቅድሚያ ሰጥተን ይዘን ወጥተናል፡፡ከትንኮሳዎቹ ሁለቱን ልጥቀስ፡፡

1. የጸጥታው ክፍል ኀላፊ ሻ/ቃ ዘሪሁን የመረጣችሁት መንገድ ትራፊክ የሚበዛበት ማደያዎች፣ባንኮች እና ገበያዎች ያሉበትበመሆኑ አንፈቅድላችሁም ልሂድ ብትሉ ያኔ እንተያያለን በማለት ሊያሰገድደን ሞክሯል፡፡

2. ልትይዙ ካስገባችኋቸው መፈክሮች “ ‘የኦሮሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄ በሕጋዊ አግባብ ይመለስ!’ የሚለው ተሰርዞ መውጣት አለበት::” በማለቱ ከፍተኛ ክርክር ገጥመን ልንግባባ አልቻልንም፡፡በዚሁ የተነሳ ሻለቃው “ይህን መፈክር ይዘህ ብትወጣ አስገባሃለሁ!” በማለት ዝቶብኛል፡፡በተጨማሪም አብራ የነበረች ሴት “እናንተ ስለኦሮሞ ምንአገባችሁ!” በማለት ልታጣጥለን ሞክራለች፡፡

እረ ለመሆኑ ከአንድነት ወዲያ ለኦሮሞ ማን ሊመጣ ነው?…ደግሞስ ሕብረብሔራዊ ፓርቲ አንተ ለዚህ ብሄር አያገባህም ሊባል የሚያስችለው ምን መንገድ አለ?…እረ ኢህአዴግ ሆይ በህገ መንግስታዊ መብትና ዲሞክራሲዊ መብታችን ላይ የሚጣልብንን ማዕቀብ በሕግ አምላክ ጠብቅልን-ኋላ የመንግስትነትህ ድርሻ የት ገባ ተብለህ ቀንህ ሲደርስ ትጠየቃለህ !

ተስፋዬ ዋቅቶላ (የአዳማ አንድነት ፓርቲ የሕ/ግ)

UDJ Head


የቴዲ አፍሮ እና የኮካ ጉዳይ

$
0
0

ሁኔ አቢሲኒያዊ

ይህንን ፅሁፍ ከጥቂት ወራት በፊት ዘሐበሻ ድሕረ ገፅ ላይ ፅፌው የነበረ ሲሆን ኮተታም ካድሬዎች ስላልተስተካከሉ ከጥቂት ማስተካከያዎች ጋር እነሆ በድጋሚ ለጥፌዋለው
ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) በብዙዎች ሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ወጣት ከያኒ ነው፤ በሙዚቃዎቹ በሚያነሳው ሀገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ታሪካዊና ወቅታዊ ጉዳዮች የተነሳ የብዙዎችን ቀልብ ለመግዛት የቻለ ይመስለኛል፡፡ የእርሱን ታላቅነት መግለፅ የዚህ ጹሑፍ ዓላማ፣ ጥያቄም፣ የማወቅም ፍላጎት አይደለም፡፡

teddy afroይልቁንም ለዚህ አጭር መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ ከሰሞኑ በአንዳንድ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኮካዎች(ኮተታም ካድሬዎች) የቴዲ አፍሮን ከብራዚል መቅርት ምክንያት አድርገው ሰሞንኛ ትችታቸውን በመሰንዘራቸውን ምክንያት እኔም የተሰማኝን ልጨምር በሚል ነው፡፡
እኛ ሐገር እንደፋሽን ከተያዙት ፖለቲካዊ እሳቤዎች መካከል ዋነኛው ጠርዝ ይዞ የመከራከር ልማድ ነው ይህ መንገድ የት እንደሚያደርሠን ባይታወቅም እንደኢትዮጵያዊ ግን አሳፋሪ እና የአለም ጭራ ሆነን እንድንቀር እያስደረገ ያለ ተግባር ነው፡፡ ከሠሞኑ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ለ2014ቱ የብራዚል የአለም ዋንጫ ማጀቢያ የሚሆን ከሌሎች የአፍሪካ ድምፃውያን ጋር በመሆን እየሠራ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን እስከአሁን ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባልታወቀ ጉዳይ ቴዲ ከኮካ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉን ከቴዲ ህጋዊ ድህረ ገፅ ላይ ማንበብ ችለናል ይህም በበርካታ የማህበራዊ ድሕረ ገፅ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ የመወያያ አጀንዳ ሆኗል፡፡

በተለይ በኮካዎች ዘንድ (በነገራችን ላይ ኮካ ኮተታም ካድሬ እንደማለት ነው) የቴዲን ከአለም ዋንጫ ውጭ መሆን እንደትልቅ እድል በመቁጠር ፌስቡካዊ በዓል እያከበሩ ይገኛሉ፡፡ ቴዲ አፍሮ መጥላትም ሆነ መውደድ መብት ቢሆንም ሐገራዊ ጉዳዮችን የምንመለከትበት መነፀር መስተካከል እንዳለበት ይሠማኛል፡፡

ቴዲ አፍሮ ብቻ አይደለም ከብራዚሉ የአለም ዋንጫ ውጭ የሆነው የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ፣ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያም ነች ከውድድሩ ውጭ የሆነችው ነገር ግን ይህንን የቴዲ አፍሮን ከብራዚሉ የአለም ዋንጫ ውጭ መሆን አጋጣሚ በመጠቀም የእንኳን ደስ አላቹህ መልዕክት መለዋወጥን የመሠለ አሳፋሪ ተግባር የለም ነገር ግን ይህ ጉዳይ ዞሮ ዞሮ መድረሻውን ወደ አንድ ቦታ ይወስደዋል ወደጠባብነት ኢህአዴግን ከምቃወምበት ጉዳይ መካከል አንዱ ይህንን ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ ሴራው ነው ለዚህ ሴራው ውጤታማ መሆን ደግሞ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን በአደባባይ የሚናገሩ እና የህዝቡ icon የሆኑ ሠዎች በድብቅ መምታት አንዱ ነው የዚህ ሠለባ ከሆኑት መካከል እንደ ታማኝ በየነ፣ አስራት ወ/የስ፣ ብርሐኑ ነጋ፣ ጥላሁን ገሠሠ እና ቴዲ አፍሮ የመሣሰሉት ተጠቃሾች ናቸው ሆኖም ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ሊጠፋ አልቻለም አይችልም፡፡

በአንድ ወቅት ቴዲ አፍሮ ስለምን ስለ አክሱም ሐውልት መመለስ አልዘፈነም ብሎ የፃፈ አንድ ኮካ ፌስቡከኛ (ኮካ ፌስቡከኛ ያልኩት ስሙን መጥራት ስላፈርኩኝ ነው) ሠሞኑን ቴዲ ከብራዚል በመቅረቱ ውስጡ በሐሴት ተሞልቶ ደስታውን እየዘረገፈልን ነው፡፡ አሁን እንደዚህ አይነት ሠው ባንዳ ቢባል መቀየም ይኖርበታል፡፡
ለማንእንደምናውቀው ቴዎድሮስ ካሣሁን በዚህች የሙዚቃ ህይወቱ ከዛቻ እስከመታሰር ድረስ የደረሰ መሆኑ እሙን ነው ይህም የደረሰበት የተለየ ሰው ስለሆነ ነው
ቴዲ ሺህ ዘመናት ስልጣኔያችንና ታሪካችን፣ ጥበባችን በፍቅር፣ ፍቅራችን በጥበብ የተገመደበት ውሉ ከየት ተጀምሮ የት እንደተቋረጠ ታሪክን እንጠይቅ ዘንድ እንዲህ ሲል በቅኔው ተመራምሮ ያመራምረናል፡-
ብራናው ይነበብ ተዘርግቶ ባትሮኖሱ ላይ፣
የእነ ፋሲለደስ የእነ ተዋናይ፣
የት ጋር እንደሆነ ይታይ የእኛ ጥበብ መሰረቱ…፡፡

እናም እስቲ ታሪክ ይታይ፣ ይመርመር፣ ዘመናትን ያስረጁና የተሻገሩ ብራናዎቻችን ይውጡ፣የሺህ ዘመን የሃይማኖት፣ የጥበብ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔና የፍልስፍና ድርሳኖቻንን ይታዩይመርመሩ… በአክሱም ስልጣኔ፣ በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ትንግርት፣ በጎንደርበእነ ፋሲለደስ የስልጣኔ አየር ዝናዋ የናኘላት፣ እነዛ ፍቅርን በጥበብ አስውበው በቅኔያቸውናበማኅሌታቸው ሰማይ ሰማያትን ሰንጥቀው በመንፈሳቸው ጸባዖት የደረሱ፣ በፍቅር ጧፍ የነደዱበማሕሌታዩ ያሬድ መንፈስ የተነሱ እንደ ተዋናይ ያሉ የቅኔ የጥበብ ጉልላቶች እንደ አጥቢያኮከብ በደመቁባት ምድር ዛሬን ፍቅር የተራብን፣ ጥበብን የተራቆትን፣ ስለ ፍቅር የደከመንምንድነው ምክንያቱ የሚል ይመስለኛል ቴዲ…፡፡

ቴዲ በሙዚቃው ለታሪክ ያለውን ስሱነትና (sensitivity) እውቀትም (Indigenous Knowledge)አሳይቶናል፡፡ ተዋናይን ስንቶቻችን እናውቀዋለን ተብለን ብንጠየቅ የሚያስተዛዝበን ሳይሆን ይቀራል፡፡ በተለይ ደግሞ ለዘመናችን ትውልድ ለአፉም ለልቡም ቅርቦቹ እነ አርሴናል፣ቼልሲ፣ ሜሲ፣ ሮናልዶ፣ እነ ፊፍቲ ሴንት እነ ቢዮንሴ፣ ወዘተ… የባሕር ማዶዎቹ ዝነኞች ናቸውእንጂ እነ ተዋናይን እነ ቅዱስ ያሬድን፣ እነ አጼ ፋሲልን ሊያስባቸው ወኔው ያለውአይመስልም፣ ኅሊናውንም ይደክመዋል እናስ እንዴት፣ ምን ሲደረግስ ሊያስባቸው ይችላል የኔትውልድ፡፡ በቅኔው የተራቀቀና በመንፈሳዊ እውቀቱ አንቱ ስለተባለው ስለ ተዋናይለመስማትም ሆነ ለማወቅ የታሪክ መዛግብትን ማገላበጥ ግድ ይላል፡፡ አሊያም ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች እግር ስር ቁጭ ማለት ያስፈልግ ይመስለኛል፡፡

ቴዲ በየትኛው መንገድ የሀገሩንና የቤተ ክርስቲያኑን የጥበብ እና የሥልጣኔ ከዋክብቶችን ሊያውቅ እንደቻለ ባይነገረንም የትናንትናዎቹን የሀገራችንን ባለውለታዎችና የዘመንፈርጦች ማንነት ለማወቅ እና እንዲሁም ታሪኩን ለመመርመር ግን የተጋና የሰላ አእምሮ እንደተቸረው/እንዳለው የግጥሞቹ መልእክቶች ይነግሩናል፡፡ እናም ከታሪካችንና ከስልጣኔያችን መሰረት ከአክሱም ተነስቶ በጊዜና በታሪክ ሃዲድ ላይ አሳፍሮን በትላንት ታሪካችን ውስጥ ራሳችንን እንድንመረምር፤ ራሳችንን እንድናይ ይወተውተናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ይለናል ቴዲ ስለ ፍቅር ዜማው ውብ የግጥሞቹ ስንኞች፡-
. . .የኋለው ከሌለ የለም የፊቱ፣
ሳይራመድ በታሪክ ምንጣፍ፣
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ፡፡
በማለት ከታሪካችን ጋር እጅ ለእጅ በምናብ ሊያጨባብጠንና ሊያስተያየን ይፈልጋል፤ እናምያለ ትላንት ዛሬ የለም፣ ያለ ዛሬ ደግሞ ነገ አይታሰብም በሚል የመጣንበትና የተጓዝንበትንአኩሪና አሳፋሪ የታሪካችንን ምእራፍ ለማገላበጥ ለደከምን ለእራሱ እና ለእኛ ትልቅ ቁም ነገርያለው ምክር ያስተላልፋል፡፡ ይህ የከያኒው የግጥም ስንኝ የሮማውን ታላቅ የሕግ ሊቅ፣ፈላስፋና አስተማሪ የሆነውን የሲስሮን አባባል አስታወሰኝ፡- ‹‹ከመወለዳችን በፊት ያለውንታሪክ ካላወቅን ዕድሜ ልካችንን ሕጻን ሆነን እንቀራለን፡፡›› ታሪካችንን ለመመርመር እናከታሪካችን ለመማር የደከምን እኛ ዛሬም እንደ አዲስ ሰናፈርስ ስንጀምር ከመጀመር ሀ ሁሳንወጣ እንደ ህጻን ባለህበት እረገጥ የሆንበትና ታሪክን እንድንደግም የተፈረደብን ምስጢሩምን ይሆን በማለት ታሪክ ጠያቂ፣ የታሪክ ወዳጅ፣ ከታሪክ የምንማር እንድንሆን ያተጋናል፡፡
ከምንኮራበት ታሪካችንና ስልጣኔያችን ባልተናነሰ አንገት የሚያስደፋ ስማችንና ማንንታችን በዓለም ፊት በቀየረብን በበርካታ የራብ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና መበላላት ታሪክ ዘመናትን ውስጥ አልፈናል፡፡ እናም የመጣንበት መንገዱ ረጅም ዘመናቶቻችንም መከራ ሰቆቃና ዋይታ የነገሰባቸው ናቸው ሲል የትናንቱን ታሪክ ለመድገም የተፈረደብን ይመስል ታሪክ ደጋሚዎች እንድንሆን የሆንበትን እውነታ መመርመርና ማየት እንችል ዘንድ ትልቅ ጥያቄ ያጭርብናል፡፡ ዛሬም እግራችን መሄድ ተስኖት ቆመናል የእርሱ ደጋፊዎች እንዳሉ ሁሉ የእርሱ ተቃዋሚዎች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ነው ነገር ግን በአሉባልታ የቴዲን ስራዎች ጥላሸት ለመቀባት የሚደረግ ትግል ወይ ቅናት ነው አልያም ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንደሚባለው ይሆናል፡፡
ደበበ ሠይፉ ቀጣይ ግጥሙን ለኮካዎች የፃፈው ይመስለኛል
ጥሬ ጨው – ደበበ ሰይፉ
————
መስለውኝ ነበረ ፣
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች ፣
ለካ እነሱ ናቸው ፣
ጥሬ ጨው..ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች ፣
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት-መቀየጥ
ገና እሚቀራቸው ፣
“እኔ የለሁበትም !”
ዘወትር ቋንቋቸው ።
………. እኔም የዘመኑ ካድሬዎችን ጥሬ ጨው ብያቸዋለው

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተላለፈ ጋዜጣዊ መግለጫ “ሕዝባዊ አንድነት ለነፃነት

$
0
0

udJ&AEUPለአለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት የሕዝብን መብት በመቀማትና አፍኖ በሥልጣን ላይ የሚገኘው የህወሃት/የኢህአዴግ መንግሥት ዜጐች በአገራቸው ውስጥ በመዘዋወር ሰርተው እንዳይኖሩ ያገደ ብቻ ሳይሆን በተወለዱበትና እየኖሩበት በአለው ቀያቸውም የገዠው ፓርቲ አባል ካልሆኑ ወይም ደግፈው ካልቆሙ ይሰደዳሉ፣ ይበታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፤ በተለያዩ ምክንያቶችም ንብረታቸውን ይቀማሉ፡፡ የተቀዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አባል ከሆነ ደግሞ ጫናው ምን ያህል እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ በዚሁ መመሪያቸው መሠረትም በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የመኢአድ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡ ከሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከልም ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህልም፡-


1. በደቡብ ክልል በሰሜንአሪ ወረዳ በጉዛ ዚፍቲ ቀበሌያት የሚኖር ሕዝብ ሕገ-መንግሥታዊ መብቻውን ተጠቅመው በመኢአድ ጥላ ሥር ስለተደራጀና ጽ/ቤት ስለከፈቱ ብቻ ሦስት (3) አመራሮቻቸው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍትህም ተከልክለው ሰሚ አካል ሊያገኙም አልቻሉም፡፡


2. በጐፋ ልዩ ዞን የሚገኙ የመኢአድ አመራሮችና አባላት ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ስለተደራጁ ብቻ ከፍተኛ ድብደባና እስር ደርሶባቸዋል፤ የፓርቲው መታወቂያቸውንም እንዲነጠቁ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜም አስራ ሁለት (12) የመኢአድ አባላት በሳውላ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡


3. በደቡብ ክልል በደራሼ ልዩ ወረዳ የመኢአድ የወጣቶች የአመራር አባል በጩቤ ተወግተው ለፍትህ አካላት አቤት ቢሉም መልስ አጥተው በችግር ላይ ይገኛሉ፡፡
4. በአማራ ክልላዊ መንግስት በአንካሻ ወረዳ የሚገኙ የመኢአድ አመራር በኢህአዴግ ካድሬዎች ተደብድበው በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከትናንት በስቲያ ማለትም ሚያዚያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በጐንደር ከተማ በመንግሥት ታጣቂዎችና በሕዝቡ መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የብዙ ዜጎች ሕይወት እንዲጠፋ ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ብዙ ዜጎችም ከቤታቸው እየታፈኑ ወደ አልታወቀ ቦታ እንዲወሰዱ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡


5. በተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር በአደረጉት ግጭት ምክንያት ብዙ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተው፤ ብዙ ንብረትም ወድሟል፡፡


ይህ የሚያሳየን የህወሃት/ኢህአዴግ መንግሥት የማስተዳደር ስልት ችግሩን በዘዴ በመፍታትና በማግባባት ሳይሆን ኃይልን በመጠቀም ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን ነው፡፡
በአጠቃላይ እንደዚህ ያሉ የከፉ የሰብአዊ መብት ረገጣ አገር ተረካቢውን ወጣት ምሁር ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡


ስለዚህ የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመቃወምና ከተበዳዮች ጐን የቆመ መሆኑን ለማሳየት “ሕዝባዊ አንድነት ለነፃነት” በሚል መሪ መፈክር በመላ አገሪቱ ሕዝባዊ ንቅናቄ ለመፍጠር ከዜጎች ጐን የቆመ ድርጅት መሆኑን ለማሳየት ሰላማዊ ሰልፎችን አዘጋጅቷል፡፡ በዚሁ መሠረትም እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2006 ዓ.ም በጐፋ ልዩ ዞን በሳውላ ከተማ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አድርጓል፡፡


ስለዚህም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነት ሲል ከጐናችን እንዲሰለፍ ታላቅ ሕዝባዊ ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ፕሮፌሰር መስፍን ለሰማያዊ ፓርቲ እራት ግብዣ የ20 ሰው ትኬቶችን እንደገዙ የፌስ ቡክ ጉዋደኞቼ ጽፈው አነበብኩ

$
0
0

 

Prof. Mesfin Woldemariam

Prof. Mesfin Woldemariam

ከልጅነታቸው እስከ ሽምግልናቸው ለዚች ሀገር ያላቸውን ሁሉ ሳይሰስቱ የሰጡት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ሌላው ቀርቶ የግላቸው የሆነ መኖሪያ ቤት እንደሌላቸው የምናውቅ ስንቶቻችን እንሆን?
አዎ! ለነ አባዲ ዘሙ ድንቅ ቪላ የገነባች ሀገር ባለፉት ረጅም ዓመታት ለፕሮፌሰር መስፍን አንድ ክፍል ቤት አልሰጠቻቸውም። ለአያሌ ዓመታት የኖሩት እና አሁንም እየኖሩ ያሉት ፒያሳ በሚገኝ የኪራይ ቤቶች ህንጻ ውስጥ ተከራይተው ነው።
ይህ ስለሆነ ፕሮፌሰር ፦ “ኢትዮጰያ ሀገሬ ሞኘ ነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ፣ የገደለሽ በላ” እያሉ በቁጭት አላንጎራጎሩም። ይልቁንም በምርጫ 97 ወቅት ለወጣቶች ባደረጉት አንድ ገለጻ ላይ ፦”እቤቴ ስገባ አፍራለሁ”ሲሉ ነው የሰማሁዋቸው። የገረመኝም ይኸው ነው።
“ማደሪያ የሌላቸው በርካታ ዜጎች መንገድ ላይ ወድቀው እያየሁ ማታ እቤቴ ስገባ አፍራለሁ፣ ጎዳና የሚያድሩትን እያሰብኩ እንቅልፍ አይወስደኝም፣ አሁን የምኖርበት የኪራይ ቤት በዝቶብኛል” ነው ያሉት ፐሮፌሰር መስፍን።
ጤና እና ረጅም እድሜ ለጋሽ መስፍን!

Dereje Habtewold

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ? – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ታላቅ የሕዝብ ቅልቅል ተካሂዷል። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል፦ የአህመድ ግራኝ ወረራ፣ የኦሮሞ ወረራ፣ በዘመነ መሣፍንት የነበሩት የእርስ በእርስ ጦርነቶች፣ ፈፃሜ-ዘመነ መሣፍንትን ያበሠሩት የማዕከላዊ መንግሥትን እንደገና የማዋቀር ጦርነቶች እንዲሁም ሁለቱ የኢጣሊያ ወረራዎች የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚያ ጦርነቶች እና የእርስ በእርስ ግጭቶች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሕዝብ ክፍል ሕይዎት እንዳሣጡ አይካድም። ያንንም ተከትሎ ከኑሮ አስገዳጅነት እና በአገዛዝ ኃይሎች የበላይነት የያዘው አካል በሚፈጥረው የፖለቲካ አሠላለፍ መለዋወጥ ምክንያት የአንዱ ጎሣ ወይም ነገድ አባሎች በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመጥፋት ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ ዋና ዋና ነገዶች እና ጎሣዎች መካከል፦ በምዕራብ ኢትዮጵያ ነዋሪ የነበሩት የጋፋት ነገድ በኦሮሞ ወረራ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ ሆነዋል ወይም ማንነታቸውን ተገድደው ለውጠው «ኦሮሞዎች» ወይም «ዐማራዎች» ወይም በሌላ ነገድ ስም ይጠራሉ፤ የሜያ ነገድ ተወላጆች ደግሞ በግራኝ አህመድ እና በኋላም ተከትሎ በመጣው በኦሮሞዎች ወረራ ምክንያት ቁጥራቸው በእጅጉ ተመናምኖ ዛሬ በዝዋይ ኃይቅ ውስጥ በሚገኙ ደሴቶች እና አካባቢው ብቻ ተወስነው ይገኛሉ። ጥንት በባሊ (ባሌ) እና ፈጠጋር (አርሲ) ተስፋፍተው ይኖሩ የነበሩት ሐዲያዎች እና ከንባታዎች በኦሮሞዎች ወረራ ተጨፍልቀው «ኦሮሞዎች» ሲባሉ ቀሪ ወገኖቻቸው በደቡብ ምዕራብ ሸዋ በአንድ ጠባብ አካባቢ በተጨናነቀ ሁኔታ እንዲኖሩ ተገድደዋል። ከዚህ በተጨማሪም፦ አርጎባዎች፣ ቀቤናዎች፣ ወርጂዎች፣ አላባዎች፣ ሲዳማዎች፣ ወዘተርፈ በኦሮሞዎች ወረራ ምክንያት ማንነታቸውን እንዲቀይሩ ተገድደዋል፤ ከዚያም አልፎ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። በእናርያ ንጉሥ ግዛት ሥር የነበሩት ጃንጀሮዎች (የም) በኦሮሞ ቆሮዎች (በእነ አባ ጅፋር) በገፍ በባርነት ተፈንግለዋል። የዳውሮ እና የገሙ ሰዎች ደግሞ ግዛታቸውን በኦሮሞ ወራሪዎች ተነጥቀዋል። በመሆኑም የዘመናዊት ኢትዮጵያን የሕዝብ አሠፋፈር ጥንቅር ለውጥ ለመገንዘብ ከአህመድ ግራኝ ወረራ ጀምሮ ማዬቱ ለበለጠ ግንዛቤ ይረዳል።

ግራኝ አህመድ በኢትዮጵያ ላይ ወረራውን የጀመረው የንጉሡ የአፄ ልብነድንግል ሹም እና የደዋሮ (ምዕራብ ሐረርጌ) ገዢ ከነበረው ከአዛዥ ፋኑኤል ጋር በ፲፭፻፲፯ ዓ.ም. ባደረገው ውጊያ ነበር። ግራኝ አህመድ ዘንተራ (ደንቢያ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ጣና ሐይቅ አጠገብ) በአፄ ገላውዲዎስ ሥር ሲዋጉ በነበሩት የፖርቱጋል ወታደሮች የጥይት አረር ተመትቶ በየካቲት ፳፯ ቀን ፲፭፻፴፭ ዓ.ም. እስኪገደል ድረስ ኢትዮጵያን ለ፲፱ ዓመታት ያህል በጦርነት አመሠቃቅሏታል፤ ዜጎቿን ኍልቆ-መሣፍርት ለሌለው ግፍ እና በደል ዳርጓቸዋል። የእርሱን የወረራ ፍፃሜ እግር በእግር ተከትለው የመጡት የኦሮሞ ወራሪዎች ደግሞ ከ፲፭፻፵ዎቹ ጀምረው ከደቡብ ከነጌሌ ቦረና አካባቢ ተነስተው ከፊታቸው የነበረውን የሌላውን ነገድ እና ጎሣ ሕዝብ ዕድሜ እና ፆታ ሣይለዩ በጅምላ እየፈጁ እስከ ትግራይ ድረስ ዘልቀዋል። ኦሮሞዎች አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል በተከታታይ ወረራዎች ለመያዝ የፈጀባቸው ጊዜ ከ፫፻ ዓመታት ይበልጣል። ስለዚህ ዛሬ ያለውን የኢትዮጵያን የሕዝብ አሠፋፈር በቅጡ ለመረዳት ያለፈውን የ፩፻፳ ያመታት ብቻ ታሪክ ሣይሆን አህመድ ግራኝ ኢትዮጵያን ከወረረበት ከ፲፭፻፲፯ ዓ.ም. ጀምሮ የነበረውን ሁኔታ መመርመር የግድ ያስፈልጋል። ሆኖም ባለፉት ፵ እና ፶ ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ «መሪዎች ነን» ብለው የተነሱ ልሂቃን የኢትዮጵያን የረዥም ዘመን የታሪክ ጉዞ በ፻ ዓመታት ብቻ በመገደብ በጉንጭ አልፋ ውዝግብ ሕዝብን ሲያተራምሱ ይታያሉ። በተለይም ለዚህ ውዝግብ ቀዳሚዎቹ የትግሬ እና የኦሮሞ ልሂቃን ሲሆኑ እንደ ዋለልኝ መኮንን ዓይነቶቹ ጥራዝ ነጠቅ የዐማራ ልሂቃንም በዚህ ክበብ ውስጥ ይገኙበታል።

ታሪካቸውን በቅጡ ያልተረዱ ጥቂት፣ አክራሪ እና ዘረኛ የሆኑ የኦሮሞ ልሂቃን፣ ከጀርመናውያን የኃይማኖት ሠባኪዎቻቸው የተጋቱትን ለኢትዮጵያዊነት እና ለዐማራ ያላቸውን ጥላቻ እንደበቀቀን ደግመው፣ ደጋግመው ሲጮኹ ይሰማሉ። ለመሆኑ የዚህ አስተሣሰብ ምንጩ ከዬት ነው? በዘመነ ቅኝ አገዛዝ የአፍሪካ ቅርምት ወቅት፣ እንግሊዞች፥ «ግብፅን መቆጣጠር ማለት ቀይ ባሕርን መቆጣጠር ማለት ነው፤ ቀይ ባሕርን መቆጣጠር ማለት ደግሞ መላውን የመካከለኛውን ምሥራቅ መቆጣጠር ነው፤» ብለው በማመን ግብፅን «የገንዘብ ብድር ዕዳን» ሠበብ በማድረግ ከቱርኮች ነጥቀው ቅኝ ግዛታቸው አደረጓት። እንደዚያም ሁሉ፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሠባኪዎች «ቻይናን ስጡን እና እስያ የእኛ ትሆናለች» ብለው ሰላዮቻቸውን በኃይማኖት ሠባኪነት ሽፋን በቻይና አሠማሩ፥ ቻይናም ቀስ በቀስ በምዕራባውያን ተፅዕኖ ሥር ወደቀች። የኦነግ እና የኦሕዴድ የንስሃ አባታቸው የሆነው ጀርመናዊው ሰላይ ዩሓን ክራፍ በበኩሉ «ጋሎችን ስጡን እና መላው የመካከለኛው የአፍሪቃ ክፍል የኛ [የጀርመኖች] ይሆናል፤» በማለት ጀርመን የኦሮሞን ነገድ ተጠቅሞ ምሥራቅን እና መካከለኛውን የአፍሪቃ ክፍል በቅኝ ግዛቱ ሥር የሚያውልበትን መንገድ መጥረጉን እናያለን። ስለሆነም «የነፃ ኦሮሚያ» ዓላማ አራማጆችም «ኦሮሚያ» ከሚባለው አዲስ ወያኔ-ሠራሽ ግዛት ጀምሮ የሚያራግቡት ተግባር ሁሉ፣ በ፲፱ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሠፊውን የኢትዮጵያ አካል ቆርሶ ለጀርመን የቅኝ ግዛት ለማድረግ የታቀደው ሤራ በዚህ በእኛ ዘመን ታድሶ መቅረቡን መገንዘብ ያስፈልጋል።

ከዚህ በተጨማሪ ዩሓን ክራፍ፣ ጀርመን በአውሮፓ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ የበላይነቱን እንድትይዝ ያለውን ፍላጎት እንደሚከተለው ገልጿል፥ «“ጋሎችን” መያዝ መካከለኛው አፍሪቃን ለመቆጣጠር ከማስቻሉም ሌላ፣ በቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኙትን አገሮችን መያዝ ከንግድ መቆጣጠሪያነት ባሻገር፣ ጀርመን በአውሮጳ ያላትን የበላይነት ማረጋገጥ እና የጀርመንን ሥልጣኔ በዐረቦች ምድር፣ በአበሻ እና በመላው ምሥራቅ አፍሪቃ ማስፋፋት ነው። የጀርመን በምሥራቅ አፍሪቃ መስፋፋት፣ የእስልምና ኃይማኖት በዐረብ ምድር እና በአፍሪቃ ጠረፎች የሚያደርገውን መስፋፋት የሚያዳክም፣ የዐረቦችን የባሪያ ንግድ የሚቀንስ፣ እንዲሁም የምሥራቅ አፍሪቃን ሕዝብ አረመኔነት በክርስትና ሥልጣኔ መዋጋት ነው። ከአበሻ በስተደቡብ ያሉት “ጋሎች” የሠፈሩበት ቦታ ለአውሮጳውያን ሠፋሪዎች ምቹ ቦታ ነው፤» በማለት ጀርመን የኦሮሞዎችን ልብ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት በማውጣት ምሥራቅን እና መካከለኛውን አፍሪቃ እንዴት በቁጥጥሩ ሥር ማዋል እንደሚችል «ወንጌላዊው» ክራፍ ምክሩን ለግሷል፤ ምክሩም የመከነ አይመስልም፤ ኦነግን እና መሰል ድርጅቶችን አፍርቷል። ለአብነትም ያህል ለኦነግ መመሥረት እና መጎልበት የስካንዴኔቪያን አገሮች፣ ጀርመኖች እና ሌሎችም የቅኝ ገዢነት ቅዠታቸው ያልለቀቃቸው አውሮጳውያን የሚያደርጉትን ሁሉን-አቀፍ ድጋፍ ልብ ይሏል!

በማስከተልም ዩሓን ክራፍ፣ ከሸዋ በስተደቡብ የሚኖሩት “ጋሎች” ብዛት ያላቸው መሆኑን ገልጦ፣ የእስላሞችን የመሥፋፋት ወረራ ሊመክቱ እንደሚችሉ እና የአፍሪቃ ጀርመኖች ሊሆኑ እንደሚችሉ ዕምነቱን አስረድቷል። ዩሓን ክራፍ ምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪቃ በጀርመን ቁጥጥር ሥር እንዲውል የነደፈው አንዱ ሥልት፣ ሚሽነሪዎችን በወንጌል ማስፋፋት ስም በአካባቢው በማሠማራት፣ የየአገሮቹ ልዩ ልዩ ነገዶች እና ጎሣዎችን ሊለያዩበት እና ሊናቆሩበት የሚችሉበትን ዘዴ ማጥናት፣ እንዲሁም ያገኟቸውን የማናቆሪያ ቀዳዳዎች ማስፋት ነበር። ለዚህም ዩሓን ክራፍ ያቀረበው ኃሣብ፦ «በደቡብ እና በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆችን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ነገዶች በመለዬት፣ በተቃራኒው ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን የኦሮሞ ጎሣዎች አንድ የሚያደርግ አዲስ መጠሪያ ስም በመስጠት፣ በዚህ አዲስ ስም የሚታወቅ የአካባቢ ስም ፈጥሮ፣ ያን አካባቢ ከቀረው የኢትዮጵያ የሚገነጥል ብሔርተኛ ቡድን በጀርመን ሁለንተናዊ ርዳታ ማጠናከር፤» የሚለው ነበር። ለዚህም «“ጋላ” የሚለው ስም ሁሉንም የነገዱን አባሎች አጠቃሎ ለመጥራት አያስችልም» የሚል ምክንያት በመስጠት፣ «ኦርማኒያ» ከሚለው ስም «ኦሮሚያ» የሚል ቃል በማውጣት ጥንት “ጋላ” በመባል የሚታወቀው ነገድ በዚህ እርሱ ባወጣው አዲስ ስም እንዲጠራ እና «ኦሮሚያ» ለሚባል ክልል ነፃ መውጣት እንዲታገል በወንጌል ማስፋፋት ስም አስተማረ፣ ሰበከ። በዚህ መሠረት ዩሓን ክራፍ ራሱ «ኦሮሚያ» ብሎ የሰየመውን የኢትዮጵያ አካል መቆጣጠር ማለት፣ ምሥራቅን እና መካከለኛውን አፍሪቃ መቆጣጠር እንደሆነ በማመን የጀርመን ተስፋፊዎች ዓይናቸውን ኢትዮጵያን በማፍረስ ላይ እንዲያነጣጥሩ ምክር ለገሠ።

የዩሓን ክራፍ እና የመሠሎቹ ምክር በጀርመን ቅኝ ገዢዎች ልብ ውስጥ መስረፁ ማስረጃው ጀርመን በአፍሪቃ አኅጉር ላይ ትከተል በነበረው የቅኝ ግዛት ፖሊሲ ላይ ጉልህ አሻራ አኑሯል። በዚህ ረገድ እስከ ፩ኛው የዓለም ጦርነት ድረስ ጀርመኖች ከምሥራቅ አፍሪቃ፥ ታንዛኒያን፣ ሩዋንዳን እና ብሩንዲን፤ ከምዕራብ አፍሪቃ ቶጎን፣ ከፊል ጋናን እና ካሜሩንን፤ ከደቡባዊ አፍሪቃ ደግሞ ናሚቢያን በቅኝ ግዛትነት በያዙበት ወቅት ከእንግሊዞች፣ ፈረንሣዮች እና ጣሊያኖች በከፋ ሁኔታ ያካሄዱት የከፋፍለህ-ግዛው የቅኝ አገዛዝ አካሄድ አይረሣም። ከሁሉም መዘንጋት የሌለበት አብይ ነጥብ፥ በ፲፱፻፹፮ ዓም በሩዋንዳ በሁቱዎች እና በቱትሲዎች መካከል የደረሠው የዘር ዕልቂት እና በብሩንዲም በየጊዜው በዘር ልዩነት ምክንያት የሚደረገው መተላለቅ ሠንኮፉ በጀርመን ቅኝ ገዢዎች የተተከለ እና በኋላም ጀርመኖቹን በተኩት ቤልጂጎች ዳብሮ በዘመናችን ደግሞ በፈረንሣዮች የተተበተበ የተንኮል ድር ድምር ውጤት መሆኑን ነው። በእኛም አገር በኢትዮጵያ፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት በዩሓን ክራፍ መሠሎቹ አመለካከት ተኮትኩተው ያደጉ የኦሮሞ ልሂቃን የሚያቀነቅኑት አስተሣሰብ አለ። ይኼውም፥ የያዙትን የኢትዮጵያዊነት ማንነት ለማስጠበቅ ሣይሆን ለማጣት በሚያስገድድ መልክ በራሣቸው ላይ ዘመቻ ከፍተው፣ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ቀርቶ ለራሳቸው ሊሰሙት የማይፈቅዱትን ጩኸት ሲያሰሙ ይደመጣሉ።

ለመሆኑ ጥቂት የኦሮሞ ልሂቃን ነገዳቸውን “ጋላ”፣ ቋንቋቸውን “ጋልኛ” የሚለውን ዐማሮች እንደሰጡዋቸው አድርገው የሚያቀርቡት ታሪካዊ መሠረት አለው? በመሠረቱ “ጋላ” እና “ጋልኛ” የሚሉትን ስሞች ዐማራው አላወጣቸውም። እንዲያውም የኦሮሞን ታሪክ በስፋት እና በጥልቀት ያጠኑ ሰዎች እንደሚያስገነዝቡት “ጋላ” ማለት እስላምም፣ ክርስቲያንም ያልሆነ ማለት እንደሆነ ያብራራሉ። የቃሉም ምንጭ ሶማሊኛ እንደሆነ ያስገነዝባሉ። በሌላ በኩል “ጋላ” ማለት ግመል ማለት ነው የሚሉም አሉ። ሌሎች ደግሞ “ጋላ” የሚለው ቃል «ገላ» ከሚለው የኦሮሚኛ ግሥ የወጣ መሆኑን እና ትርጉሙም «ወደ ቤታችን መሄድ ፈለግን፣ ወደ ቤታችን ሄድን ወይም ገባን» ማለት እንደሆነ ያስረዳሉ። ይህም ትርጉም ኦሮሞዎች በሶማሌና በባንቱ ጎሣዎች ተገፍተው፣ ከነበሩበት ከምሥራቅ አፍሪቃ የሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻዎች ፈልሰው ወደ ደቡብምሥራቅ ኢትዮጵያ ግዛት፥ ወደ ባሌ፣ የተጠጉበትን ዘመን በማውሣት፣ በሰላም ተረጋግተው የሚኖሩበትን ሥፍራ ፈልገው ማግኘታቸውን የሚያመለክት ስያሜ እንደሆነ ብዙዎች በትርጉሙ ይማማሉ። ስለዚህ ጥቂት ዘረኛ የኦሮሞ ልሂቃን «“ጋላ” የሚለውን የስድብ ስያሜ የሰጠን ዐማራው ነው፤» የሚሉት የራሣቸው የማንነት ቀውስ ያስከተለባቸው ግራ መጋባት ከመሆን ውጭ ሌላ አሣማኝ ምክንያት የላቸውም። «ዐማራ ይህንን መጠሪያ ሰጠን» የሚሉትም ውንጀላ ፍፁም መሠረተ-ቢስ ሐሰት ነው። በአንፃሩ «ኦሮሞ» እና «ኦሮሚያ» ለሚሉት መጠሪያዎች የታወቀ ፈጣሪ አላቸው፦ እርሱም አፍቃሬ ቅኝ ገዢዎች የነበረው ጀርመናዊው ዩሓን ክራፍ ነው።

ዩሓን ክራፍ «ጋላ» የሚለውን ቃል ለመቀየር ያነሣሣውን ኃሣብ ሲያስተነትን፦ «ጋላ» የሚለውን ቃል ሲተረጉም «ስደተኛ» ማለት እንደሆነ እና ይህም መጠሪያ በዐረቦች እና በ«አበሾች» የተሰጠ እንደሆነ ይገልፃል። በአንጻሩ እርሱ የፈጠረው «ኦርማ» ወይም «ኦሮማ» ማለት ትርጉሙ «ጎበዝ» ማለት እንደሆነ ያምናል። በእርሱ አባባል «ጋሎች» ለራሣቸው እና ለሚኖሩበት አካባባቢ አጠቃላይ የወል መጠሪያ ስለሌላቸው «ኦርማኒያ» ተብለው እንዲጠሩ ኃሣብ አቅርቧል። ሆኖም ይህንን የዩሓን ክራፍን ኃሣብ የእርሱ-ቢጤ የሆኑ የዘመኑ ሚሽነሪዎች እና ተመራማሪዎች እንኳን አልተቀበሉትም። ለምሣሌም ያህል፦ ኢትዮጵያን ያጠኑ እንደ ዶክተር ቻርለስ ቴ ቢክ ያሉ የመልከዐምድር ተመራማሪዎች፣ ለኦሮሞዎች «ጋላ» የሚለውን ስም የሰጡዋቸው ዐረቦች እና «አበሾች» አለመሆናቸውን እና ስሙ ከራሣቸው ቋንቋ የተገኘ እንደሆነ ይሞግታሉ። ይሁን እንጂ፣ ዕውነቱን ትተው ውሸቱን፣ ሠፊውን ጠልተው ጠባቡን፣ የሚያኮራውን ንቀው የሚያቀልለውን፣ የሚያስከብረውን አውግዘው የሚያዋርደውን፣ የመረጡት ጥቂት «ተማርን ያሉ» የኦሮሞ ልሂቃን፣ የዩሓን ክራፍን ስብከት አምነው ተቀብለው፣ ዐማራን እና ኢትዮጵያን ከምድረ-ገፅ በማጥፋት፣ «ኦሮሚያ» የተባለ አዲስ አገር በመመሥረት እንቅስቃሴ ላይ ከተሠማሩ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ አድርገዋል። ወራሪ የሆኑትን ኦሮሞዎችን እንደ ተወራሪ በመቁጠር፣ ወያኔም ዮሓን ክራፍ የሰጠውን የአካባቢ መጠሪያ በማፅደቅ፣ ዐማሮችን እና ሌሎችን ኢትዮጵያውያን ከአፅመ-ርስታቸው በማባረር፣ «ኦሮሚያ» የሚል አዲስ ግዛት ፈጥሮላቸዋል።

«እንግዳ ሲሰነብት፣ ባለቤት የሆነ ይመስለዋል፤» የሚሉት አባባል አለ። እንግዶቹ እና ወራሪዎቹ ኦሮሞዎች፣ የነባሮቹን የኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች ግዛቶች በወረራ ይዘው፣ የገደሉትን ገድለው፣ የሠለቡትን ሠልበው፣ ጡት ቆርጠው ሲያበቁ፣ ተበዳዮቹ «ይህ በደል ተፈፀመብን» ሣይሉ፣ እንዲያውም እነርሱ «ተበደልን» ብለው በወረራ የያዙትን አገር እንገንጥል ይላሉ፣ ነባሮቹን ኢትዮጵያዊ ነገዶች እና ጎሣዎች ያፈናቅላሉ። እነርሱው ነባር የአካባቢ ስሞችን ለውጠው እና በነገዳቸው ስም ቀይረው መያዛቸው እየታወቀ፣ «ዐማራው ስማችን እንድንቀይር አስገደደን፤ ቋንቋችንን፣ ባህላችንን እና የየአካባቢ ስሞችን ለወጠብን» እያሉ ስም ሲያጠፉ ይሰማሉ። ሃቁ ግን የአካባቢ ስሞችን በመለወጥና በራሱ ነገድ ስም በመጥራት የሚታወቀው የኦሮሞ ወራሪ ኃይል ነው። የታሪክ ሠነዶችን ማጣቀስ ካስፈለገም፥ በ፲፮፻ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን ከጎበኙት እና በአገሪቱም ተቀምጠው የሕዝቡን የአኗኗር ልማድ እና ዘይቤ በቅርበት እያጠኑ የታሪክ መድበሎችን ካበረከቱልን የአውሮፓ ሊቃውንት መካከል ፔድሮ ደ-ኮቪልኻም፣ አባ ፍራንሴስኮ አልቫሬዝ እና ሌሎችም የፖርቱጋል ዜጎች አያሌ ጠቃሚ የታሪክ ማስረጃዎችን ትተውልን አልፈዋል። እንዲሁም አህመድ ግራኝን ተከትሎ የዘመተው፣ እርሱ ባደረጋቸው ወረራዎች ሁሉ የቅርብ ተሣታፊ የነበረው የመናዊው ሺሃብ አድ-ዲን አህመድ ቢን አብድልቃድር ቢን ሣሌም ቢን ዑትማን፣ «ፉቱህ አል-ሓበሻ» በተባለው የታሪክ ድርሣኑ የዚያን ዘመን የኢትዮጵያን የሕዝብ አሠፋፈር ቅጥ በዝርዝር መዝግቦት ይገኛል። በእነዚያ ጽሑፎች ውስጥ «ጋላ» ወይም ኦሮሞ የሚባል ነገድ ዛሬ «ኦሮሚያ» ተብሎ በተከለለው አብዛኛው የኢትዮጵያ ግዛት ስለመኖሩ በአንዱም ጭራሽ አልተጠቀሰም። ስለዚህ የዛሬው ዘመን የኦሮሞ ልሂቃን የጥንት አባቶቻቸው በወረራ የያዙትን ግዛት እንደ አፅመ-ርስት ቆጥረውት ሌላውን ኢትዮጵያዊ ሲያፈናቅሉ ሃግ ሊባሉ ይገባቸዋል። ከኦሮሞ ወረራ በፊት ዛሬ ወለጋ፣ አርሲ፣ ወሎ፣ ኢሉባቡር፣ ወረኢሉ፣ ወረሂመኖ፣ ወዘተርፈ በመባል የሚታወቁት የቦታ (የአካባቢ) ስሞች የሚታወቁት እና የሚጠሩት በሌሎች ስሞች ነበር። የሚከተለውን ሠንጠረዥ እንዲሁም አባሪ ካርታዎችን ፩ እና ፪ ልብ እንበል።

ከኦሮሞ ወረራ በፊት ዛሬ ወለጋ፣ አርሲ፣ ወሎ፣ ኢሉባቡር፣ ወረኢሉ፣ ወረሂመኖ፣ ወዘተርፈ በመባል የሚታወቁት የቦታ (የአካባቢ) ስሞች
ተ/ቁ ነባር ስም በኦሮሞዎች የተሰጠው ስም የትኞቹን አካባቢዎች እንደሚገልጽ በአካባቢው ነዋሪ የነበሩ ነገድና ጎሳዎች
1 ቢዛሞ ቄለም ምዕራብ ወለጋ ጋፋት፣ ዐማራ፣ ሽናሻ፣ ቤንሻንጉል፣ አንፊሎ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
2 ዳሞት ሌቃ ምሥራቅ ወለጋ ጋፋት፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
3 እናርያ ኢሉ አባቦራ ኢሉባቦር ዐማራ፣ ከፊቾ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
4 ገሙ ጂማ ጂማ የም (ጃንጀሮ)፣ ገሙ፣ ዳውሮ (ኩሎ)፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
5 ገንዝ ጅባት እና ሜጫ ምዕራብ ሸዋ ጋፋት፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
6 ግራርያ ሰላሌ ሰሜን ሸዋ ጋፋት፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
7 እንደጥና እንጦጦ፣ ጉለሌ፣ የካ አዲስ አበባ ዙሪያ ሜያ፣ ዐማራ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
8 ኦ(ወ)ይጃ የረር እና ከረዩ ምሥራቅ ሸ ሜያ፣ ሐዲያ፣ ዐማራ፣ ከምባታ፣ ሲዳማ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
9 ፈጠጋር አርሲ አርሲ ሐዲያ፣ ከንባታ፣ ሜያ፣ ዐማራ፣ አዳል (አፋር)፣ ሲዳማ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
10 ደዋሮ ጭሮ ምዕራብ ሐረርጌ ሐዲያ፣ ከምባታ፣ ዐማራ፤ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
11 ላኮመልዛ ወሎ ደቡብ ወሎ ዐማራ፤ አዳል (አፋር)፣ አገው፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች
12 ቤተ-ጊዮርጊስ ወረኢሉ ወረኢሉ ዐማራ
13 ቤተ-ዐማራ ወረሂመኖ ወረሂመኖ ዐማራ
14 አንጎት ራያ ሰሜን ወሎ ዐማራ፣ አገው፣ አዳል (አፋር)
15 ባሊ ባሌ ባሌ ሐዲያ፣ ከንባታ፣ ሜያ፣ ዐማራ፣ ሲዳማ፣ ሌሎች፣ እንዲሁም የጠፉ ነገዶች እና ጎሣዎች

ስለዚህ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባን «ፊንፊኔ»፣ ናዝሬትን «አዳማ»፣ ደብረዘይትን «ቢሾፍቱ በሉ» እያሉ ለማስገደድ ለሚሞክሩት ዘመነኞች እኛም፥ ወለጋን ቢዛሞ እና ዳሞት፣ ኢሉባቡርን እናርያ፣ ወሎን ላኮመልዛ፣ አርሲን ፈጠጋር፣ ሐረርጌን ደዋሮ፣ ወዘተርፈ ብለን በጥንቱ ስማቸው የምንጠራ መሆናችንን እንዲያውቁት እንሻለን። ወደፊት ካላረፉም በእንግድነት ከኖሩበት አገር «ውጡ» የምንል መሆኑን ሊያውቁት ይገባል። የኦሮሞ ቀለም-ቀመስ ትውልድ ዐማራን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ፣ ክንዱን አስተባብሮ ሊያጠፋው ሲነሣ፣ ዐማራው በተቃራኒው እጁን አጣጥፎ ተቀምጦ ይጠብቀናል ብለው ካሠቡ በእጅጉ ተሣስተዋል። በመሆኑም ለማንኛችንም የሚበጀው እኛ ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ አንዳችን ለሌላችን ቀና መተሳሰቡ እንጂ፣ ፍጭው ፈንግጭው ከሆነ ዬትም አንደርስም። እንዲያውም ከኖረው መልካም ባህላችን ውስጥ የቀረንን አብሮ እና ተቻችሎ የመኖር መልካም ባህላችንን እንኳን ለማጣት እንገደዳለን። ስለሆነም ከዚህ ተነስተን «ወደፊት እንዴት እንጓዝ?» የሚለውን ጥያቄ አንስቶ በጋራ በሚደረስበት ውሣኔ የተሻለች ኢትዮጵያን በመገንባቱ ላይ ማተኮሩ ዐዋቂነት ብቻ ሣይሆን ብልኅነትም ነው። በየትኛውም መልኩ የትናንት ኢትዮጵያን ካነሣን፣ በዳዩ «ተበደልኩ» ባዩ፣ ወራሪውም «ተወረርኩ» የሚለው የኦሮሞው ልሂቅ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ሞረሽ ወገኔ በተለይ በአሁኑ ወቅት ራሱን በኢትዮጵያዊነት ጭንብል ውስጥ ሸፋፍኖ፣ ለጥፋቱ ሁሉ የሩቅ ተመልካች ሆኖ ለሚታዘበው የተማረው የዐማራ ተወላጅ የሚያስተላልፈው ግልፅ መልዕክት አለ፦ ወገናችን ከምድረ-ገፅ እየጠፋ ዝምታው እስከመቼ ነው? «ትውልድ ትውልድን ተክቶ ያልፋል፣ ታሪክም ይመዘገባል» ተብሏልና ዛሬ ለወገኖቻችን ካልደረስን ነገ እያንዳንዳችን የትውልድም፣ የታሪክም ተጠያቂ ከመሆን እንደማንድን መካድ አይቻልም። ስለዚህ በወገኖቻችን በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ በትግሬ-ወያኔ እና በተባባሪዎቻቸው ላይ የሚደርሰው ሠቆቃ ከዚህ በላይ በዝምታ እና በቸልተኝነት ሊተው ከማይችልበት ምዕራፍ ላይ መድረሱን ተገንዝቦ ለወገን ጥሪ ተጨባጭ የተግባር ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል።

ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደግ!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በታማኝ ልጆቿ መስዋዕትነት እና ትግል ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ? – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ( PDF)

MWAO_V2No23_map1

ካርታ ፪፦ (ምንጭ፦ ፕሮፌሠር ጌታቸው ኃይሌ፣ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም.። የአባ ባሕርይ ድርሰቶች፤ ኦሮሞችን ከሚመለከቱ ሌሎች ሰነዶች ጋራ። ገፅ ፲፪።)

 

moreshሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

“በቅሎ አባትህ ማነው ቢሉት ፈረስ አጎቴ ነው አለ” የኢህአዴግ የሃያ ሶስት ዓመት ጉዞ –ከሙሼ ሰሙ

$
0
0

mushe semu“ከአዲስ ጉዳይ መጽሄት የተወሰደ”

ለ23 ዓመታት የዘለቀው የኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ስር ከሰደደ ድህነት፣ ከኑሮ ውድነት፣ ከረሃብ፣ ከሰብአዊ-መብት ረገጣ፣ ከእስርና እንግልት በተለይ ደግሞ ከመበታተን ስጋትና አደጋ ሊታደገን እንዳልቻለ የእለት ተእለት ኑሮችን በቂ ምስክር ነው፡፡ ከሃያ ሶስት ዓመታት አንጻራዊ የሰላም ጎዞ በኃላ በየክልሉ የሚታዩት ግጭቶች፣ መፈናቀልና መሰደዶች ዛሬም እጅግ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ የመበታተን አደጋ እንደጃበብን እያረጋገጡ ነው፡፡ እዚህም እዚያ ብልጭ ድርግም የሚሉት ልማቶችም ከኢቲቪና ሬድዮ ዲስኩር አልፈው የኑሮውድነቱን፣ ግሽበቱን፣ ሙስናውን፣ ስራ-አጥነቱንና ስደቱን ማስቀረት አልቻሉም፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ኢ- ፍትሃዊው እስሬ! እየፈሩ ጋዜጠኝነት የለም!

$
0
0

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና

(ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታችን ትልቅ አደጋ ላይ ነው)

elias Gebru

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጎዳና

አርብ ግንቦት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ከወዳጄ ጋዜጠኛ ዳዊት ሠለሞን ጋር ቀጠሮ ነበረኝ፡፡ ረፋድ 5፡25 ሰዓት ላይ የሞባይል ስልኬ ጠራች፡፡ ከአምባሳደር ወደአራት ኪሎ በሚጓዝ ታክሲ ውስጥ ተሳፍሬ ነበር፡፡ የመስመር (የቢሮ) ስልክ መሆኑን አየሁትና “ሃሎ” አልኩኝ፡፡ ‹‹አቶ ኤልያስ፣ የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ?›› የሚል የሴት ድምጽ ተሰማኝ፡፡ ‹‹አዎን›› ስል መለስኩላት፡፡ ብዙ ጊዜ አንባቢዎች ስለሚደውሉ፣ ምን ዓይነት ግብረ-መልስ (feed back) ይኖራት ይሆን ነበር ሀሳቤ፡፡ ሳይሆን ቀረ፡፡ ‹‹የምደውለው ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ነው፣ በአንድ ጉዳይ ላይ ስለምንፈልግዎት ቃልዎትን መጥተው እንዲሰጡን ነበር፡፡›› …‹‹እሺ፣ ሰኞ ጥዋት ልምጣ?›› በማለት ጠየኳት፡፡ ‹‹ቆይ አንዴ?›› ብላኝ ባልደረቦቿን ካነጋገረች በኋላ ‹‹ይቻላል›› አለችኝ፡፡ ቀጭን የጌታ ትዕዛዝ፡፡ ከዚህ የስልክ ጥሪ በኋላ የመጽሔቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ (ፍቄ) ደውሎልኝ ስለጉዳዩ ሐሳብ ተለዋወጥን፡፡ ሰኞ በጥዋት ለመገናኘት ተቀጣጥረን ስልኩ ተዘጋ፡፡

ለምርመራ መጠራቴ በኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ ሕይወት ውስጥ የሚያጋጥም፣ የተለመደ ጉዳይ በመሆኑ ብዙ አልተገረምኩኝም፡፡ በቀድሞ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ እሰራ በነበረበት ወቅት አሸባሪ ተብሎ በፓርላማ በተሰየመው የ‹‹ግንቦት 7›› የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች እና በአገር ውስጥ በነበሩ ከፍተኛ ጄኖራሎች፣ የመከላካለያ ሰራዊት አባላትና ሌሎች ዜጎች ላይ ከባድ ክስ ቀርቦ ነበር፡፡ የፍርድ ሂደቱን ተከታትዬ የምዘግበው እኔ ነበረኩ፡፡ እኔ ከሰራሁት ዘገባ ጋር በተያያዘ አቃቤ ሕግ ክስ አቅርቦ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ከባልደረባዬ ጋዜጠኛ ፍጹም ማሞ (ዋና አዘጋጅ የነበረ) ተጠርተን ቃል በመስጠት በ5000 ሺህ ብር ከወጣን በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበን ነበር፡፡ ፍ/ቤቱም ክሱን ተመልክቶ ለእኔ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሰጠኝ አጋጣሚ ስለነበረ ጉዳዩን አስታውሼ በአዕምሮዬ ለአፍታም ቢሆን ማሰላሰሌ አልቀረም ነበር፡፡

ሰኞ ግንቦት18 ቀን 2006 ዓ.ም ጥዋት ከባልደረባዬ ፍቃዱ ጋር ቀጠሮ ስለነበረን ወደ ቢሮ አመራሁ፡፡ በአጋጣሚ ፍቃዱ ያለወትሮው ቢሮ አልነበረም፡፡ ስልኩ ይጠራል፣ ግን አይነሳም፡፡ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ገደማ ፍቃዱ ደወለልኝ፡፡ ሞባይል ስልኩን ያላነሳው ጓደኛው ቤት ረስቶት በመውጣቱ ምክንያት መሆኑን ነገረኝ፡፡ ከሰዓት የተጠራሁበት ቦታ ለመሄድ በድጋሚ ተቀጣጠርን፡፡ ከሰዓት በኋላ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ እና ነብዩ ሐይሉ ተቀላቅለውን አራት ሆነን ወደማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ሄድን፡፡

ምርመራ ቢሮ ቁጥር – 76

እኔ እና ፍቃዱ ተፈትሸን እና ሞባይላችንን ጥበቃ ጋር አድርገን ወደቢሮ ቁጥር 76 አቀናን፡፡ እኔ አንኳኩቼ ወደ ቢሮዋ ገባሁ፡፡ ፍቃዱ ውጭ ቁጭ አለ፡፡ አንድ ወንድ እና ሴት የመ/ቤቱ ባልደረቦች ቢሮ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከየት እንደመጣሁ ነገርኳቸው፡፡ ‹‹ቁጭ በል›› ተባልኩ፡፡ ‹‹ጥዋት ነበር እመጣለሁ እኮ ያልከው?›› ብሎ ወንዱ ፖሊስ ሀሳቡን ሰነዘረ፡፡ ‹‹አዎን›› ካልኩት በኋላ ጠዋት ያልመጣሁት በሁኔታዎች አለመመቻቸት መሆኑን አስረዳሁት፡፡ በምን ጉዳይ ልጠራ እንደቻልኩ መረጃው ካለኝ እንድነግረው ፈገግ እያለ ወዲያው እኔኑ ጠየቀኝ፡፡ መረጃው እንደሌለኝ ነገርኩት፡፡ አንድ የክስ መዝገብ ሲገልጥ የመጽሔታችንን ቁጥር 113ኛ ዕትም አየኋት፡፡ በመጽሔቱ ፊት ገጽ ላይ ‹‹በቃን! የጠባብ ብሔርተኝነት ዘመቻ›› በሚል ትልቅ ርዕስ ሥር የቀድሞ ጠ/ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ፣ የቀድሞ ም/ ጠ/ሚንስትር አቶ ታምራት ላይኔ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የኦነግ መስራች አቶ ሌንጮ ለታ፣ የቀድሞ ም/ ጠ/ሚንስትር እና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ለገሰ፣ የቀድሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር እና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ተፈራ ዋልዋና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን ፎቶግራፎች አለ፡፡ ይህ ጽሁፍ መጽሔቷ ዝግጅት ክፍል የተሰራ እና ከወራቶች በፊት አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ሕዝብ ጸያፍ ስድቦች መሳደባቸውን ተከትሎ መሰል ድርጊቶች ሥርዓቱ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በተለያዩ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት፣ በኤርትራው ፕሬዚዳንት እና በቀድሞ የኦነግ መስራች መደረጋቸውን በማስታወስ ጠባብ ብሄርተኝነትን የሚቃወም እና ለችግሩ መፍትሄ ጠቋሚ ጽሁፍ ነበር፡፡
በዚያን ዕለት ለፖሊስ ቃሌን እንድሰጥ የተጠራሁትም በዚሁ ጽሑፍ መስሎኝ ነበር፡፡ መርማሪ መሆን አለመሆኑን ያላረጋገጥኩት እያነጋገረኝ ያለው ወጣት ግን የተጠራሁት በቅርቡ በኦሮሚያ ክልሎች በተነሳው ግጭት እና ብጥብጥ ጋር በመሆኑ ላይ ጥቁምታ ሰጠኝ፡፡ በአጋጣሚ በእጅ ላይ ሁለት የዕንቁ መጽሔት ዕትሞችን ይዜ ገብቼ ነበር፡፡ ወጣቱ ልጅ ‹‹አንዴ ልመልከታቸው?›› ብሎኝ ግንቦት 20 በተመለከተ ባለፈው ቅዳሜ የወጣውን የመጽሔቱን ዕትም ሰጥቼው እያገላበጠ ተመለከታቸው፡፡ ከሌላ ክፍል የመጣ አንድ መርማሪም ክስ ያቀረበብኝን ዕትም ከፋይሉ ውስጥ ነጥሎ በመውሰድ የሆነ ጽሑፍን በተመስጦ አንብቦ ክፍሉን ለቅቆ ወጣ፡፡

ወጣቱ ልጅ፣ ‹‹ያው ጥዋት እመጣለሁ ብለህ እኛም ስንጠብቅህ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ እኛ በተራችን እናስጠብቅሃለን፡፡›› አለኝ – ፈገግ እያለ፡፡ ፈገግታው ከልብ የመነጨ ነው ለማለት ግን እቸገራለሁ፡፡ ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ አንዲት ወፈር ያለች፣ የፖሊስ ማዕረግ ያለው የደንብ ልብስ የለበሰች ሴት ወዳለሁበት ክፍል መጣች፡፡ ‹‹ኤልያስ አንተ ነህ?›› አለችኝ፡፡

‹‹አዎን›› አልኳት፡፡

‹‹መጣሁ›› ብላኝ ከአፍታ ቆይታ በኋላ ተመልሳ በመምጣት እኔ የተቀመጥኩበት ወንበር ጋር ባለው ሰፋ ያለ ጠረጴዛ ትይዩ ተቀመጠች፡፡

‹‹ጥዋት ለምን አልመጣህም?›› የመጀመሪያ ጥያቄዋ ነበር፡፡

በአጋጣሚ በተፈጠረ ጉዳይ መምጣት አለመቻሌን አስረዳኋት፡፡ በዚህ ጊዜ ወጣቱ ልጅ አድራሻዬን፣ ዜግነቴን፣ የትውልድ ቦታዬን፣ የተማርኩባቸውን ትምህርት ቤቶች እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ የሰራሁባቸውን የሚዲያ ድርጅቶች፣ የትዳር ሁኔታ …እየጠየቀኝ ፎርም ላይ እየሞላ ነበር፡፡

‹‹ብሔርህስ?›› አለኝ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያዊ›› አልኩት፡፡

‹‹ያ’ማ ዜግነት ነው፣ መናገር አለብህ›› አለኝ፡፡ በግሌ የማልወደው ጥያቄ መሆኑን ነገርኩት፡፡ [የሰው ልጆች በሙሉ ምንጫችን አንድ ነው ብዬ አጥብቄ ስለማምን የዘር ጥያቄ ከልጅነቴ ጀምሮ የማይመቸኝ እና የማላምንበት የግል ጉዳይ ነው] ስለብሄር ሊያስረዳኝ ሞከረ፡፡ መታወቂያዬ ላይ የተጻፈውን ነገርኩት፡፡
ወ/ሮ በላይነሽ የተባለችው ምርማሪዬ ፋይሉን ተቀብላ እና በመጽሔቱ የተከሰስኩበትን ጉዳይ ነገረችኝ፡፡ በታሪክ አምድ ሥር ‹‹የተገነቡት እና በመገንባት ላይ ያሉት የመታሰቢያ ሐውልቶች የእነማን እና ለእነማንስ ናቸው?›› በሚል ርዕስ ሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን የተባለው ጸሐፊ በጻፈው ጽሑፍ ውስጥ የኦሮሞን ብሔር የሚያጥላላ፣ ዘርን ከዘር የሚያጋጭ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ የመጣ መሆኑን የሚጠቅስ፣ ለኢትዮጵያ እንግዳ ሕዝብ መሆኑን የሚናገር …ወዘተ በጣም ጥሩ ያልሆነ ጽሑፍ መሆኑን ነገረችኝ፡፡ አያይዛም ይህን ጽሑፍ ተከትሎ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ቁጣ መቀስቀሱን፣ ተማሪዎች ጽሑፉን የጻፈው ግለሰብ ለሕግ እንዲቀርብ ሁለት ጊዜ ያህል ለዩኒቨርሲቲው የሚመለከተው አካል በደብዳቤ ቢያሳውቁም መልስ ሳይሰጣቸው በመቅረቱ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸውን፣ መስታወቶች መሰባበራቸውን፣ ንብረቶች መውደማቸው፣ በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ሆስፒታል ገብተው በሞት እና በሕይወት መካከል ያሉ ተማሪዎች መኖራቸውን፣ የመማር ማስተማር ሒደት መስተጓጎሉን …ወዘተ ዘርዝራ አስረዳችኝ፡፡

እኔም እኛ (የመጽሔቱ አዘጋጆች እና ባልደረቦች) ኢትዮጵያን አንድ የሚያደርግ እንጂ ዘርን ከዘር የሚከፋፍል ሥራ አለለመስራታችንን፣ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 29 መሰረት ሕግን በማክበር ጽሑፎችን መጻፋችንን እና የተለያዩ ግለሰቦችን ሐሳቦች ማስተናገዳችንን፣ ይህንንም መመልከት እንደሚቻል ከጠቀስኩላት በኋላ የተባለው ጽሑፍ የመጽሔቱ ሳይሆን የግለሰቡ የግል ግለ-ሀሳብ መሆኑን አሰረግጬ ነግሬያት ነበር፡፡

መርማሪዬም ‹‹ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በሕገ-መንግሥቱ ተደንግጓል ብላችሁ የመጣላችሁን ጽሑፍ በሙሉ ታትማላችሁ ማለት ነው?›› በማለት ቆጣ በማለት ለመናገር ሞከረች፡፡ የመጡልን ጽሑፎች ሁሉ እንደማይታተሙ፣ እንደዋና አዘጋጅነቴ መስተካከል ወይም መታረም ያለባቸውን ጽሑፎች በአግባቡ እንደምመለከት፣ ሌሎች የመጽሔቱ አዘጋቾችም መሰል ሥራዎችን ተጋግዘን እንደምንሰራ ረጋ ብዬ አስረዳኋት፡፡

በክፍሉ ውስጥ ያሉት ሶስቱም የፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦች በጽሑፉ ምክንያት የጠፋ ንብረት እና የአካል ጉዳት መኖሩን አጽንኦት በመስጠት ‹‹አጥፍታችኋል›› በሚል ተቆጥተው ሊናገሩኝ ሞከሩ፡፡ የእኔም ስሜት በተወሰነ ደረጃ መቀየር ጀመረ፡፡ እመን አትመን ክርክር ውስጥ ለአፍታም ቢሆን ገባን፡፡ ‹‹እነዚህ ሰዎች የፍርድ ቤትንም ሥራ ደርበው ይሰራሉ ወይ?›› ስል ታዘብኩ፡፡

ንግግሬን ቀጥያለሁ፡፡ በቅድሚያ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተፈጠረ ለተባለው ነገር መጽሔታችን መነሻ መሆኑን ለመቀበል እንደምቸገር፣ መጋቢት ወር ላይ የወጣ ጽሁፍ አደረሰ የተባለውን ችግር ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት እዚህ ምርመራ ክፍል ውስጥ መሆኑን፣ በጽሑፉ የተቆጡ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለዝግጅት ክፍላችን አለመግለጻቸውን፣ ተማሪዎቹ ያቀረቡትን ቅሬታ ዩኒቨርስቲው መደበኛ በመሆነ መልኩ ለመጽሔታችን ዝግጅት ክፍል ምንም ነገር አለማቅረቡን፣ ቅሬታ ቀርቦ ቢሆን ኖሮ ተፈጠረ የተባለውን ችግር ለመፍታት እኛም የራሳችንን ሥራ መስራት እንችል እንደነበረ፣ ማስተባበያ ጽሁፍ ወይም ጽሑፉን የሚተች ሌላ ጽሑፍ ቢመጣ ኖሮ በተመሳሳይ ገጽ እና ይዘት እንደምናስተናግድ፣ ለዚህም ኃላፊነት እና ግዴታ እንዳለብን ተናገርኩ፡፡

በዚህም ብቻ አቆምኩም፣ በዚሁ መጽሔት ላይ የፖለቲካ አቀንቃኑ እና የኦሮሞ ጉዳዮች ዋነኛ ተማጋች መሆኑ የሚታወቀው ጃዋር መሐመድ የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄዎች ከነመፍትሄዎቹ በተመለከተ የሰጠንን ሰፊ ቃለ ምልልስ ማስተናገዳችንን፣ አቶ ኦባማ አንሰርሙ የተባሉ ጸሐፊም ስለኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ ሰፊ ጽሁፍ አቅርበው በመጽሔታችን ላይ ማስተናገዳችንን ዋቢ በማድረግ አስረዳኋቸው፡፡ እኔም ብሆን በግሌ የትኛውም ዘር ከየትኛውም ዘር እንደማይበልጥ እና እንደማያንስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ረዥም ታሪክ ያለው ትልቅ ህዝብ መሆኑንና ከገዳ ሥርዓትም ዓለም ዴሞክራሲን እንደተማረ የግል ዕምነት እንዳለኝ ሀሳቤን ሰነዘርኩ፡፡
በቢሮው ውስጥ የፖሊስ ልብስ ለብሳ ኮምፒውተር ላይ ጽሑፍ በመተየብ ላይ ያለች አንዷ የተቋሙ ባልደረባ ጽሑፉ ግጭት ማስነሳቱን እና ጉዳት ማድረሱን ደጋግማ በመናገር ጥፋተኛ መሆናችንን ለመናገር ጥረት አድርጋ ነበር፡፡

እዚህ ጋር ለፖሊሷ ምሳሌ አነሳሁላት፣ አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ የ100 ዓመት ነው›› ብለው ተናግረዋል በሚል በአንድ ወቅት መስማቴን በመጥቀስ ይህ የግላቸው ዕምነት መሆኑን፣ እኔ ደግሞ ኢትዮጵያ ከ3000 ዓመታት በላይ ታሪክ እንዳላት እንደማምን እና የሳቸውን ሀሳብ መቃወም ካለብኝ መስታወት በመስበር እና ብጥብት በማስነሳት ሳይሆን በሀሳብ ሞግት ብቻ መሆን እንዳለበት አስረዳኋት፡፡ ምሳሌዬ ባይወጥላትም ዝም አለች – ሌላም ምሳሌ አንስቼላት ነበር፡፡ አቶ መለስ ‹‹የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው›› ብለው ነበር፡፡ ስላት፡፡ ‹‹አዎን፣ ምኑ ነው›› ብላ በፈጥነት መለሰችልኝ፡፡ ግን ትሰማኛለች እንጂ አታዳምጠኝም፡፡ ምናልባት እርሷንም ያስከስሳት ይሆን ማድመጧ!

…ሰዓቱ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ሆነ፡፡ መርማሪዬ ወደቤቷ ለመሄድ የቸኮለች መሰለኝ፡፡ ቃሌን ለመስጠት በነጋታው ከእሷ ጋር ተቃጣጠርን፡፡ በዋስ መውጣት እንደማልችል አረዳችኝ፡፡ እኔም በክፍሉ ውስጥ ካደረግነው ንግግር እና ፊታቸውን በማንበብ ቀድሜ ተረድቼ ነበር፡፡ ባልደረባዬ ፍቃዱን አስጠራሁት፡፡ ዋስትና መከልከሌንም ነገርኩት፡፡ ለእናቴ ስለጉዳዩ ነግሮ እንዲያረጋጋት ስልኳን በወረቀት ላይ ጽፌ ሰጠሁት፡፡ የቤቴን ቁልፍ ለአናንያ ሶሪ እንዲሰጥልኝ ነግሬም ቻው ተባብለን ተሰናበትኩት፡፡ እንግዲህ እንዲህ ነው እስር፣ በስልክ ጠርቶ ቡና ከበጋበዝ ይቀላል – ለመንግሥታችን፡፡

…ይቀጥላል!

የጎንደር መንፈስ ይጠራል (ክፍል –አራት) ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ጎንር ክፍል – አራት
የጎንደር መንፈስ ይጠራል።
ከሥርጉተ ሥላሴ 05.06.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

Gondor„የበለጠና የከበደ ኃላፊነት እንደሚጠብቀኝ ባውቅም ለእኔ የከበደኝ ግን ከጎንደር ህዝብ መለዬቴ ነው“ጓድ አበበ በዳዳየጎንደር ክ/ ኢሠፓ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ለጂንካ የክ/ ኢሠፓ አንደኛ ጸሐፊ ሆነው ሲሄዱ መሸኛቸው ላይ የተናገሩት ነበር። የጎንደር አቀራረብና የአያያዝ ሙያው ከውስጥና በመሆን ሰንደቅ የከበረ ነው። ጎንደር ኖሮ መለዬት ትዝታዎቹ በቀላሉ ሊፋቁ የማይችሉ፤ እንዲያውም ትውስታዎች እያመረባቸውና ወዘናቸው እዬፈካ በናፍቆት አሳምረው የሚያሹ፤ በራሳቸው ጊዜ በመንፈስ ቤተኛ መሆን የሚችሉ፤ ተመክሮን ያስመቹና ያሰበሉ የመልካምነት ማሳ ናቸው።

የማከብራችሁና የምናፍቅቻሁ የሀገሬ ልጆች ጹሑፉ ተከታታይ ይሆን ዘንድ ክፍል ሦስት ማጠቃለያው እንዲህ ይል ነበር።  — ሌላው ቀርቶ የታሪካችን አካል የሆነው የግራኝ መሐመድ እረፍት እኮ ጎንደር ነበር። ደንቢያ ላይ የግራኝ በር ይባላል። በነገራችን ላይ በዛ ዘመን የትግራዩ እንደርታና የጎንደሩ ደንቢያ በከንቲባ የሚተዳደሩ ዕውቅና የነበራቸው ከተሞች ነበሩ። ዛሬ ግን የእንደርታን ባላውቅም፤ አይደለም ደንቢያ ጎንደር አንዲት መንደር ናት በጨለማው ዘመነ በወያኔ – የታሪክ ረግረግ። ታሪክ ማለት እንደ ሥርጉተ ዕይታ – የህዝብ ወላዊ አዎንታዊና አሉታዊ አምክኖዊ፣ ክስተታዊ ክንውኖች ዕደሜ ጠገብ ሲሆኑ ታሪክ ይባላል። ይህን መክፈል ወይንም እንደ ዶሮ መበለት አይቻልም። ታሪክ ከአንገት በላይና በታች፤ ወይንም ሲሶና እርቦ ተብሎ ሊከፈል ከቶውንም አይችልም። አሉታዊም ሆነ አዎንታዊው ክንውኖች ለታሪክ ወጥ ገፀ – ባህሪው ወይንም ሙሉ ቁመናና መልኩ ነው፤ ታሪክ የትርጉም ሥራ አይደለምና።

ጎንደር ክፍል አራት ማጠቃለያ።

እንደ መግቢያ በር —- ድርጊት በድርጊት ላይ እዬተባ ውጤት ላይ ሲውል በዚያ ስሜት ውስጥ እራስን ማዬትና መመዘን የተገባ ነው። ሃሳብን አዞ ሃቅን በምልሰት በማሰማራት ለህሊና ችሎት ማብቃት የተገባ ትውልዳዊ ድርሻ ይመስለኛል። አንድ የጥበብ ሰው ገጠመኞቹን ገልቦ ወይንም ጨልፎ አላዬሁም አልሰማሁም ማለት አይችልም። ይህን ካደረገ እሱ በመኖር ውስጥ እዬኖረ ሳይሆን መኖር እሱን እዬኖረበት ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ክስተታዊ ሁነቶች የታላቁን ሰብዕና ጸጋ እንዲጋፉ ፈቅዷል ማለት ይሆናል። ህም! እራስን ይግባኝ አልባ መደፍጠጥ። በተለይም የጥበብ ቤተኛ የማህበረሰቡን ህይወት እንደዋዛ ሳይሆን በጥንቃቄ ያሰተውለው ዘንድ የከያኒነት ገመናው ግድ እንደሚለው አውቆ፤ የህይወቱን ልምድ ለማበልጸግ፤ ያለውንም ለማካፈል መትጋት ከጥበብ ፍቅሩ ተግባር የመጀመሪያው ሊያደርገው ይገባል። አንድ ጸሐፊ ዛሬን ተሻግሮ ትናትንም መኖር አለበት፤ ትናንት የኖረበት ማህበራዊ እውነት ውበት ነውና። ውበት ያለ እውነት፤ እውነት ያለ ውበት አይኖርም። ውበትን ካለ እውነት እውነትን ካለ ውበት ማሰብ የቃር አቸቶ ነው እልለሁ – እኔው።

የጎንደር መንፈስ አሳምሮ ይጠራል።

„ ቡልጋ በሚባለው አገር ይቀመጡ የነበሩ ህዝቦች በ484 ዓ.ም ጥር 11 ቀን በአለ ጥምቀትን ለማክበር ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች ካህናቱ በማኃሌት፤ ጨዋው በዘፈን ሲወዛወዙ ሰዐተ ቅዳሴው አለፈባቸው። በዚህ ጊዜ አንድ ባህታዊ ድንገት ደርሶ ቅዳሴውን ከእግዚአብሄር የታዘዙ ግሁሳን ቀድሰውታል በናንተ ግን ማት ታዞባችኋልና መዳኃኒተ ነፍሳችሁን ፈልጉ ብሎ ስለነገራቸው፤ ምን ብናደርግ ይምረን ይሆን  ብለው ጠዬቁት። እሱም እዬሩሳሌም ሄዳችሁ የጌታችን መቃብር ብትሰሙ ይቅር ይላችኋል አላቸው። እነሱም ወደ ቤታቸው ሳይመለሱ ታቦታቸውን እንደያዙ ለቅን አሳብ ወደ እዬሩሳሌም ለመሄድ ጉዞዋቸውን ቀጥለው ሲሄዱ የእነሱን መሄድ የሰሙ ባጠገባቸው ያሉት ህዝቦች ሁሉ ተከተሏቸው ። “  ዬእግዚአብሄር መንፈስ መንገዱን እንዴት ቀዬሰላቸው? „ መንገዳቸው በቀጥታ ወደ ስሜን የነበረውን ትቶ ወደ ስሜን እዬመራ ጎንደር አድርጎ ስቋር አደረሳቸው። በዓፄ አላሜዳ ቀዳሜ መንግሥት በ485 ዓ.ም መጋቢት 27 ቀን አብርንታት ደረሱ። ከአማራ ሳይንት ጀምሮ ያለፉባቸውን ቦታዎች ሁሉ ሥም እዬሠጡ ነበር የተጓዙት።“  (ገጽ 38 – 39)*  „ እነዚህ አቨው ሥርዓተ ገዳሙን ጠብቀው 278 ዘመን ከቆዩ በኋላ በ852 ዓ.ም ጉዲት በሰይፍ አስፈጃጃቸውና የጉዲት ዘመነ መንግሥት አልፎ አንበሳ ውደም እስኪነግሥ ድረስ በስውር ካሉት ግሑሳን በቀር በቦታው በግልጽ የሚታዩ መነኮሳት አልነበሩም። እግዚአብሄር በቸርነቱ ብዛት የጉዲትን ዘመነ መንግሥት አሳልፎ አንበሳ ውደምን በአባቱ ዙፋን ባስቀመጠው ጊዜ በ891 ዓ.ም ከሽዋ400መናኞች መጥተው ተሰውረው ከቆዩት ከፊተኞች አቨው ምንኩስናን ተቀብለው ተቀመጡ። እነዚህ 400 መናኞች ገዳሙን አጽንተው የመጣውን እያመነኮሱ እነሱ ሲያልፉ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውን እዬተተኩ 389 ዓመት ያለሁከት በሰላም ከኖሩ በኋላ በ1277 ዓ.ም በዐፄ አግባ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ገዳሙ ጠፋ። 40 ዘመን ጠፍ ሆኖ ከቆዬ በኋላ በ1319 ዓ.ም በአንደኛው አምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ሳሙኤል ዘዋልድባ ወይም ዘገዳመ ዋሊ የተባሉት አቡነ ሳሙኤል መጥተው ገብተው ጠፍቶ የነበረውን ገዳም አቋቁመው 70 ዓምት በገዳሙ ቆይተው በ1389 ዓ.ም በዚሁ ገዳም አረፉ።“ (ገጽ 43)* የማክበርችሁ መግቢያው ላይ በርካታ ዝርዝር ታሪኮችን ዘልያለሁ። እንዳይበዛባችሁ በማሰብ፤ የተወሰነውን ከፊል ክፍል በቀደመው የጸጋዬ ራዲዮ በ2013 አርኬቡ ላይ ትረካው ስላለ ወደ ኋላ ሄዳችሁ የ2013ን በቅደም ተከተል ታገኙታላችሁ። ዋናውመሰረታዊ ሃሳብ ግን ጎንደር ወገኖቹን እቅፍ ድግፍ አድርጎ፤ ጸጋቸውን አክብሮ፤ አባትነታቸውን ከልብ ተቀብሎ፤ ቤተክርስትያን በስማቸው አስቀርፆ ገዳምትን በስማቸው ሰይሞ መኖር ተፈጥሮው ብቻም ሳይሆን የኖረበት መክሊቱ ስለመሆኑ ለማጠዬቅ ነው።

ከገዳመ ዋልድባ ሳልወጣ ማህበረ ምእመናን መጋቢት 27 ማዬ ዮርዳኖስ በዓል ለማክበር ከዬትም የሀገራችን ክፍል ሲመጡ፤ በተጨማሪም ቀብራቸው ከዛ ቅዱስ ቦታ እንዲሆን የወሰኑ ወገኖች እሬሳ ይዘው ሲያልፉ የሚደረገውን ተልምዶዊ ባህል ሊቁ ጸሐፊ አቶ በሪሁን ከበደ እንዲህ ገልጸውታል። „ አባቴ ግራዝማች አስናቀው አበራ ይኖሩ የነበረው ወደ ገዳሙ በሚወስደው መንገድ ዳር ምዝክር አቦ ከተባለው ቦታ ላይ ስለሆነ 3ጋን ጠላ 3 እንቅብ ቆሎ ተዘጋጅቶ ማንም ሰው አስከሬን ይዞ ለቀብር ወደ ገዳሙ ሲያልፍ ይቀርብለታል። እንዲህ የሚደረገው በሳምንት አንድ ቀን ወይንም በወር ሁለት ቀን ሳይሆን ለምሳሌ በ30 ቀን 30 ሬሳ ወደ ገዳሙ ቢያልፍ ለ30ው ቀን ሁሉ የተደገስው ድግስ ያለማቆራጥ ይቀርባል። በዚህ መልክ 25 አምት አገልግለዋል። ምስክሩም ገዳሙና የጠለምት ህዝብ ነው። አባቴ ሲያልፉም ወንድሜ በቦታው ተከትክቶ ተግቶ ይከውናል“ (ገጽ 98 – 99)* ከገዳሙ በእጅ የተጻፈላቸው የምስጋና ደብዳቤም መጸሐፉ ውስጥ ተያይዟል። ለክብረ በዐል የሚመጣውም በሚደርስበት ቦታ ሁሉ ማህበረሰቡ እዬተነጠፈ እዬተጎዘጎዘ ፍቅር በሩን ከፍቶ ይጠብቀዋል።

ክብረቶቼ – ጎንደር እኮ ጥሩ ሰው፣ መልካም ሥነ – ምግባር ያለው እኮ ታጭቶ ነው የሚገባው። ሊቃናት ልቅናቸውን በሚያገኙበት የቅኔ የንባብ የእድምታ የሚስጥራት አብነት ት/ ቤቶች የቆሎ ተማሪዎች ውስጥ አራት ዓይናማዎችን ጎንደር ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ዝም ብሎ አይሸኛቸውም። ሞኝ አይደለም። መምህሩ ሴት የደረሰች ካላቸው የራሳቸውን፣ በስተቀር የቅርብ ዘመድ ተፈልጎ ይህም ሳይሳካ ቢቀር ከሀገሬው ቆንጆ ልጅ ተምርጣ፤ ያ ሙሑር በጋብቻ ታስሮ እንዲቀር ይደረጋል። ይህ ለጎንደር ክህሎቱ ነው – ልዩ ሥጦታው። ታናሼ ተክሌሻ በ2010 በሁለት ክፍል የጻፈው ነበር። ጹሑፉን ሳነብ እስቅበት ነበር …. ምክንያቱም ልጥፍ ግምት ስለነበረ። ሊቃውንት አያቶቼ ቁጭ አድርገው የቆሎ ተማሪነት ጊዜያቸውን እንደ ትልቅ ይነግሩኝ ነበር። ሰፊ ቤተሰብ ውስጥ ለእኔ የተለዬ አያያዝ ነበረኝ። አባቴ እራሱ ሲያሳድገኝ አሳ ዘይት እያጠጣ ነበር። አሁን እኔ ሙሉ ዕድሜ ላይ ነኝ – ምን ያህል የቀደመ ህዝብ ነው – እሰቡት።

ጎንደርና አብነቱ – በጥቂቱ፡

በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ የደረሰው ግፍና መከራ ከቦታው የነበሩ ወገኖች አሉበት። እኔ መግለጽ የምፈልገው ባለቤት ያልነበረው፤ ከእሳት ወጥቶ ቋያ ውስጥ ዬተርመጠመጠው ዬኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበተን በለስ በቀናው አኳኋን ተጉዟል። ወደ ጎንደር አቅጣጫ የተጓዙት ወገኖች በምን ሁኔታ ማህበረሰቡ ተቀበላቸው የሚለውን ተከድኖ የተቀመጠ የድርጊት ልዩ ጸጋ መተንፈሻ እስኪ ይሠራለት በማለት ነው።

የሠራዊታችን አባላት ከጎንደር ደንበር ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ህዝቡ በተለዬ ሲቃ በክብር ነበር የተቀበላቸው። አብሶ ወደ ጎንደር ከተማ እዬቀረቡ ሲመጡ የጎንደር ከተማ ህዝብ ከ20 እስከ 30 ኪ.ሜ  እስከ ኮሶዬ ድረስ ተጉዞ ነበር ድንኳን እዬጣለ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ያደረገላቸው። ሁላችሁም እንደምታውቁት በርሃ – ለበርሃ ለረጅም ጊዜ ካለቅያሬ ልብስ ሲከላተም የቆዬ ወገን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚሆን እሰቡት። በመንፈሱ የመሸነፍ – ድቀቱ፤ እልሁ፤  የመስዋዕትነቱ ዋጋ አልባነት፤ የትዳሩ – የቤቱ – የጎጆው – የወጣትነቱ መስዋዕትነትና አዝመራው – ከንቱነት፤ መግቢያ ቤቱም የሚጠብቀው የተቆለፈ የቋሳ ክምችት ሁለመናው ውልቅልቅ ያደረገው የተጎሳቆለ አካል ነበር።

በዚያ የመከራ፤ በዚያ የፈተና ጊዜ ግን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ወገኖቻቸው በመደገፍ፤ በሙሉ አለንላችሁ በማለት፤ መንፈስን በማጽናናት ነበር የተቀበሏቸው። እያንዳንዱ ነዋሪ በነፍስ ወከፍ እስከ 10 የሠራዊቱ አባላት ነበር እየተቀበለ ያሰነበተ። ኑሮው እራሱ ምስቅልቅል ባላበት፤ የራስን ቤተሰብ ለማስተዳደር በተበተነ ሃሳብ በሚባዘንብት፤ ሰላሙ ባልተረጋጋበት ሁኔታ በርሃ የከረመን ጎስቋላ እንግዳን ችሎ ማስተናገድ ከፈተና በላይ ውሃ ያዘለ ተራራ የመሸከም ያህል ነበር። ነገር ግን ጎንደር ተወጣው። ከእኔ ከወላጅ እናቴ ቤት አባትዬው በአባት ጦር፤ ልጅዬው በመደበኛ የሄዱ አባትና ልጁ በተለያዬ አቅጣጫ ተጉዘው እዛው ከእናቴ ቤት ተገናኙ። የልጁ እናት፣ የአባወራው ባለቤት ከአዋሳ ድረስ መጥተው ቤተሰቡን ተዋውቀው መልካም ቀጣይ ግንኙነትም መስርተው በፍቅር ተሰነባብተዋል። ይህ ዘመኑና ታሪክ የፈጠረውን ወላዊነት ኢትዮጵያዊነትን አብዝቶ ያዘመረ የተባ የተግባር ዓዕምድ ዓውድም ነው – እንዳሻው እዬተደፈጠጠ የሚደመጠው።

እንግዳ መጥቶ ወደ ቤቱ ለመሄድ ሲነሳ ጎንደር ላይ አስተናጋጆች በሙሉ ሊሸኙት አብረው ይወጣሉ። ከሊቅ አስከ ደቂቅ፤ ሲወጡ ቤታቸውን ከፍተው ነው። አንዳንድ ጊዜ እንግዳውን ከቤቱ አድርሶ መመለስ አለ። ለዚህም ነው „ሲሻኛኙ አደሩ“ የሚል ብሂል የኖረው። ከተማ ላይ አስፓልቱ ሞልቶ ለአንድ እንግዳ መላ ቤተሰቡ ወጥቶ ይሸኛል። ገጠር ላይ ወንዝ አሻግሮ ነው የሚመለሰው እንግዳ አሰንባቹ። ከእንግዳ ጋር ለመለዬት በጊዜያዊነት እንኳን ፍቅሩ ማህተም ነው። ከዚህ ጋር አንድ በኽረ ጉዳይ ላንሳ። ሻብያና ወያኔ ኢትዮጵያን የማፍረስ የጫጉላ ጊዜያቸውን ዕርገት የተከወነው ኤርትራውያኑን ንብረት አልባ በመመለስ ነበር። ሁሉንም መከራ የኢትዮጵያ ህዝብ በትዝብት አይቶ ቀን ሲሾልክ ግን፤ ንብረታቸውን ተረክቦ በተገኘው መገናኛ ሁሉ እዬሸጠ እዬላከላቸው ነው። ጎንደር ያኖሩበት የሚገኝበት፤ በማተቡብም የጠና ነው የሚባለውም እንዲህ መሰል ፈተና ሲገጥም ግራ ቀኙን አስቀምጦ ፈርኃ እግዚአብሄር ያለው ተግባር ስለሚከውን ነው። ወገኖቼ ተረት ተረት አይደለም የምናግራችሁ የሆነውና የተደረገውን ነው። ቂም ዕዳ ነው – እዳነቱ ደግሞ የነፍስ ነው ብሎ ማህበረሰቡ በጽኑ ያምናል። አሁን ወያኔ ይህን ያህል ቀጥቅጦ እዬገዛ ነው። ቢሰናበትም ጎንደር እንደ ተፍጥሮው ይቀጥላል። አብሮ መብላትና መጠጣት፤ አብሮ መኖርና ሃዘን ተፍሥኃውን መጋራት ሃይማኖት ነው ብሎ ያምናል – ጎንደር።

የጎንደር ያልመከነ መከራው – በጥቂቱ።

እኔ የማውቃቸውን ጥቂት ነገር ልብል። ትግራይን ብቻ አይደለም የደርግ መንግሥት ዬለቀቀው። ሰቲት ሁመራንና አብደራፊንም ጭምር ነበር። ሲለቀቅ የፓርቲው አካላትም አብረው ከህዝቡ ጋር እንዲለቁ ነበር የተወሰነው። ለእነሱ ለብቻ መጓጓዣ አልተላከም ነበር። የሰቲት ወረዳ ኢሠፓ የሥ/አ/ኮሜቴ አባል የሆነ ወጣት አንድ ጹሑፍ ስለ ጉዞው ጽፎ ነበር። ንዑስ እርእሱ „የጎተተኝ“ ይል ነበር። „አንዲት አራስ አብራን ትጎዝ ነበር። አቅም አንሷት ስለነበር ወደ ኋላ ነበረች። ውሃ ጥማቱ መካራ ስለነበር አራስ ልጇን ከግራር ሥር አድርጋ ውሃ ልትጠጣ ሄደች። ስትመልስ አራስ ልጇ አልነበረም። በጣም ስትጮኽ ወደ ኋላ ተመልሰን አገኘናት። የሆነውን ነገረችን። ያለን ምርጫ ወደ ፊት መሄድ ስለነበርን አብራን እንድትመጣ ነገርናት። በርሃ ነው የሚያቃጥል – ቋያ። እሷ ግን አሻም አለች። ልጄን ትቼ አልሄድም አለችን። አራሱ ህፃን የለም አንቺ ከእኛ ጋር ነይ ብለን በዛለ አቅማችን ለመናት። ግን አልቻለችም። አስገድደን ተሸክመን ለመጓዝ እሷን፣ እኛም አቅማችን እዬሟሸሸ ነበር – አልቻልነም። ትናነት መጣን፤ እኔ ብመጣም ግን ወደ ኋላ የሚጎተኝኝን ትቼ ነው። ዓይኗ መከራውን አያይም ነበር። ልጇን ፍለጋ ይማስን ነበር እንጂ። ምንግዜም ጸጸቴ ነው“ ይል ነበር ጸሐፊው። ይህ መከራ በወሎም እንደተፈጸመ አስባለሁ። አሁን የሚያስፈልጉን መሪዎች ይህን የመከራ ጊዜ መርምረው የሚችሉትን ለማድረግ ሰብአዊነት የሚመራቸውን ነው። መንግሥት ህዝብን ከቦታ ሲያስለቅቅ የሚደርሰው ሰቀቀን መከራ በቃላት መንዝሮ ለመግለጽ አይቻለም። ተርፈው የመጡትስ? ይህም ሌላ ጥያቄ ነው።

በተፋፋመ ውጊያ ላይ እያለን ጎንደር የነበሩ የሠራዊቱ ማዕከሎች ተነቅለው ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ተደረገ። የጨለማ – ደባ ነበር። የነበረው ምርጫ በሀገሬው ሃይልን አጠናክሮ መቀጠል ነበር። እርግጥ ሠራዊት ከማዕከል ለማምጣት አንድ እድል ነበር፤ ዳኮታ የሚያሰርፍ ቦታ ማዘጋጀት። ለዛ ደግሞ አዬር ማረፊያውው አይችልም ነበር። ስለዚህ ነዋሪው ጊዜያዊ መጠለያ ተሰርቶለት በፍጥነት የዳኮታ ማረፊያ ማሰራት ነበር። ነዋሪው በድንገት አፈር ለብሶ በዘመቻ በሚሠራለት ጊዜያዊ መጠለያ መጠለል ግድ ሆነ። ፈቃድም – ንግግር የለም። ከዛው እዬታደረ ያለ የሌለው ሃይል ሁሉ ተሰማራ ለድርብ ግዳጅ። ዳኮታ የሚያሳርፍ ጊዜያዊ አውሮፕላን ማረፊያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሰናዳ። እኔ የአንድ ኮሜቴ ሰብሳቢ ነበርኩኝ። አንድ እድል ብቻ ነበር። ምን እንደተላከ ታውቃላችሁ። ዳኮታው እንደተነሳ የራዲዮ መልእክቱ ስንቅ እንደተላከ ነበር መርዶው። ስንቁን እኮ የጎንደር ህዝብ ያቀርብ ነበር። የተፈለገው ሠራዊት ነበር። ብቻችን ነበርን። ደንቀዝ ላይ የሚለቀቀው የጠላት ከባድ መሳሪያ በቀጥታ አውሮፕላን ማረፊያውን ዒላማ ያደረገ ነበር። ከዚያ በኋላ ዳኮታውን ማሳረፍ አልተቻለም።

ያ ንጹህ የአዬር ማረፊያ ኗሪ የጦርነት ጊዜ ስለነበረ ካለ ካሳ ህፃነት – ሽማግሌ – የታመመ – በቃሬዛ፤  ነፍሰጡር ሁሉም ቤታቸው ፈርሶ ሜዳ ላይ እያሉ ወያኔ ገባ። ….. ባለቤት የሌለው ህዝብ በቀን ወደ 20 ቆርቆሮ ማልበስና የመጀመሪያ ምርጊቱን ማጠናቀቅ ነበር ዘመቻው፤ ባዶ ግድግዳ እንደቆመ፤ ወይንም ቆርቆሮ ሳይለብስ በቃ እንደተበተነ ሁሉም ተበተነ። ያ መከረኛ ህዝብ በግራ በቀኝ ተማገደ። በደልጊ በደንቢያ ዞን ክፍት ነፃ መሬት ነበር። የተንጣለለ ቦታም ነበር – አዬር ወለድ ለማምጣት እሱንም ቁብ የሰጠው የበላይ አካል አልነበረም። ለዛውም በደንቢያ በኩል የማልናገረው የተሻለ ሁኔታ ነበር …. አልሆነም። በኢዲዩም፤ በኢህአፓም፤ በደርግም፤ በወያኔም ዛሬም በአርበኛ ያው ቦታው በጦርነት ቀጠናነት ይማገዳል። ከዚህ ሌላ ወያኔ መሽጓል የሚል የተሳሳተ መረጃ እዬተሰጠ ያለቀ መንደር እናቱ ትቁጠረው ….. መናገር የቻለ ሁሉ ደግሞ እስካሰኘው ድረስ ይወቃዋል።

በጦርነቱ ጊዜ በሰማይ የመንግሥት በምድር የወያኔ መሳሪያ ከጫፍ አስከ ጫፍ ገበሬ – መንደር – እርሻ – የተፈጥሮ ሃብት – ነደደ – ተቃጠለ – ተርመጠመጠ። የሰውን ልጅን እራስ ውሻ …. እም ነው! ይህንን የገዘፈ መከራ ይፍታኃ ዬሚል  ቅዱስ መንፈስ መፍጠር የትግሉ መሰረታዊ መንገድ ይመስለኛል።

እንቡጢጣ -ማከያ ። ሻ/ ገብረህይወት የሚባሉ የደርግ አባል ነበሩ። የስሜን አውራጃ አስተዳደሪ ነበሩ። ከመንግሥት መዋቅር ህግና ደንብ ውጪ አስተዳደሪ ያላቸው አውራጃዎች የበላይ ሆነው እንዲያሰተዳድሩ በተሾሙበት ጊዜ፤ ጌታ አልነበራቸውም። ለአሰሳ ሲወጡ ጥቃት የሚሰነዘርበት ኢህአፓ ብቻ ነበር። ለወያኔ ግን አልጋ ባልጋ ነበር። ሹመታቸው ለስሜን – ለጭልጋና – ለወገራ አውራጃዎች ነበር። የሦስቱም አውራጃ ገበሬዎች ሰፊ ቅጣት ነበራቸው። እኔ የማውቀውን ልናገር። ባለፈው ጊዜ ጋዜጠኛ አብርኃም ደስታ ጮንጮቅ ላይ ወያኔ ያደረስውን መከራ ዘግቦ ነበር። እጅግ አመሰግነዋለሁ። ጮንጮቅ በጭልጋ አውራጃ የሚገኝ የምክትል ወረዳ ዋና የገጠር ትንሽዬ ከተማ ናት። 5 ቆርቆሮ ቤቶችና ሌሎች ግን በርካታ ጎጆ ቤቶች ነበሯት። በእግር ከጭልጋ ከተማ 4 ሰዓት ለኮበሌ ነው።  ከዛ የመጡ ገበሬዎች ልጆቻቸውን ይዘው አንድ ቀን እንዲህ አሉኝ „ እሙሃይ ነበር የሚሉኝ፤ እሙኃይ ሁሉን ለገብርህይወት ሰጠን አሁን ሁሉንም ጨረስን፤ የቀሩን ልጆቻችን ነውና ተምኖ ይውሰዳቸው“ አዎን በዬገብያው የሴት ቀሚስ እዬለበሰ የሚንጠለጠለው እጅግ በርካታ ገበሬ ነበር። ሦስት ጓደኞሞች ዘመቻ ጀመርን። አልቻልነም ይህን ተሸክሞ መኖር። ዘመቻችን ጭልጋ አውራጃ ሰላማዊ አስተዳደሪ ስላለው በእራሱ አስተዳደር ይመራ ነበር ፍሬ ነገሩ። ሻ/ ገብረሕይወት ይነሳ ነበር ጉልበታሙ አድማ።

በዛው ሰሞን ሻ/ ገብረህይወት የጭልጋን ህዝባዊ ድርጅቶች ቢሮ ገንዘብ ልመና ወጣቶችን ሰብስቦ ወደ ጎነድር ይዘውን ሄዱ። ቋራ ከሚባል የመንግሥት ሆቴል „ምግቡ በቅደም ተከተል ይቀርብ ነበር“ ለእኔ የቀረበውን አልበላሁም። የወጣልኝ ደፋር ነበርኩ። ብይ ስባል ደም አልበላም አልኩኝ። በህይወት ያሉት ይመሰክራሉ። በጥርስ የገባሁበት ቀንም ነበር። በቃ እኔ ብቻ ነበርኩኝ ያልበላሁት። ደግሞም ልክ ነበርኩ ጽዕዱ መሆን የልብ ያደርሳል – እንደ ልብም እንዲህ ያናግራል። አንዱ የሰከነው ጓዴ በህይወት የለም ኬኒያ ላይ አልፏል። ጓድ ዬኋንስ የኋላ ይባል ነበር። እንዳንታፈን ሻ/ ገብረህይወት ከመምጣታቸው በፊት መረጃ ለሦስታችንም ይሰጠን ነበር። ወጥተን እንድናድር፤ በኋላ ብልሁ ጓድ ገ/መድህን በርጋ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊና ጓድ ወንደወስን ኃይሉ የርዕዮተ ዓለም ጉዳይ ኃላፊ የወቅቱ የፓርቲው አደራጆች ሁለታችን የካቲት 66 ፓለቲካ ኢንስትቲዩት አንዱን ጀርመን ሀገር ላኩት። ከትምህርት በኋላ ወደ ጎንደር እንዳልመለስም የተደረገው ምክንያትም በዚህ ነበር። ጥሩ እድል ነበር አርሲን ዬመሰለ ሀገር፤ ያን ፍቅር የሆነ የጢቾ አውራጃ ህዝብ ጋር እንድሰራ አጋጣሚ አገኘሁ። በተጨማሪም ጓድ ስለሺ መንገሻን የመሰለ ለስላሳ – ሥልጡን – ፈጣን የአርሲ ክ/ ኢሠፓ ኮሜቴ ተጠሪ ለማዬት በቃሁ። በእውነት የተለዩ ነበር። እሳቸውን የሚያጅብ አንድም ስፔሻል የሚባል አልነበረም። እንዲያውም ተንጠልጥለው „አንተ“ ነበር የሚባሉት።  ጠባቂያቸው ህዝቡ ነበር። እሳቸውም ወጣት ነበሩ። ከወጣቶች ጋር ኳስ የሚጫወቱ፣ ሙዚቃ መኪና ውስጥ የሚያዜሙ ነበሩ። ልጅ ስለነበርኩ ናፍቆቱን ስላልቻልኩ ብቻ በለቅሶ በሃዘን በዬቦታው ልዩ ዝግጅት ተደርጎልኝ ተሸልሜ ወደ ጎንደር ተመልስኩኝ። ዕድለኛ ወጣት ነበርኩኝ። ሁሉም የሚሳሳልኝ።

እንዲህ ሆነላችሁ — ሻ/ ገብረህይወትም  ከሰቲት ሁመራ ወደ ጎንደር በጦር ኤሊኮፍተር ሲበሩ ሰማይ ላይ አመድ ሆኑ – በሁለት ቢላዋ እንደበሉ ነደዱ። ሬሳቸው እራሱ አልተገኘም። የጭልጋ፤ የወገራ፤ የስሜን አውርጃ ህዝብ አረፈ – ተገላገለ ከሃሞራቢ የቋሳ ሽምቅ ቅጣት – ተመስገን! ምንም እንኳን ዛሬም መከራው ተግ ባይልም።

እርገት ይሁን። ግለሰብ ጥፋት ወንጀል ሊፈጽም ይችላል። አጥፊውን ነጥሎ መውቀስ መንቀስ ይቻላል። የአካባቢው ህዝብና የአለም ውርስና ቅርሶች ያሉበትን የታሪክ ማህደርን ግን ግፍ ነው። ትውፊቱ ህዝቡ ቅርሱ የመንፈስ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል። ጎንደር በዚህ ዘመን እልፈቴ ነበር ብሎ የሚናገረው የሰላም ጊዜ ታሪክ የለውም። ይህም ሆኖ ባህሉን፤ ልማዱን፤ ወጉን፣ ትውፊቱን፤ ታሪኩን፤ እምነቱን ጠብቆ የኖረ ህዝብ ነው። „በሚስትና በሀገር ቀልድ የለም“ እዬተባለ ያደገ ስለሆነ ትንፋሹ ድፍረት፤ ትጥቁ ጽናት የሆነ። በማተቡ አዳሪ። ለቃሉ ተገዢ። አደራ አውጪ። ፍቅሩ ጽኑ የሆነ ህዝብ የመብቱ ዳር ድንበር ሊከበርለት እንደሚገባ በአጽህኖት እያሳሰብኩ ጹሑፌን እደምድማለሁ።

የእኔ ክብሮች ትእግስታችሁን ሳተሰስቱ ሸልማችሁ አብረን በአንድ መሰረታዊ ጉዳይ ዙሪያ ሰነበትን። እግዚአብሄር ያኑርልኝ። አምላኬ ይጠብቅልኝ። የ05.06.2014 የጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራሜ ዘና ያለ ናፍቆትን ብቻ ያጫወተ፤ የመግቢያ ትውውቁ – የዝግጅቱ ሆድ ዕቃ፤ ስንበቱን አክሎ በሥነ ግጥም ነበር። ትንሽ ግር እንዳይላችሁ እንደዚህም ዓይነት መንገዶችም መለመድ አለበት ነው ቁም ነገሩ። ኩምትርትር ያለ መንፈስ አስቲ በአመት አንዲት ሰዓት እንኳን የእርፍት ቀን ሊኖረው ይገባል ብሎ  የአብርኃሙ የጸጋዬ መሠሪያ የሥነ ግጥም ቀን ነበረው Tsegaye Radio Lora Aktuell Sendungen ብላችሁ ለጉግል ነፍሱ ስትነግሩት፤ ወይንም በቀጣዩ ሊንክ አምጣልን ብላችሁ ስታዙት ይዞ ከች ቀልጣፋው።  www.tsegaye.ethio.info ነገ ፓስት ያድርጉታል፤ ጊዜው ሲኖራችሁ ጎራ በሉ …. ደግሞ በቀጣዩ ለምለም ዝግኗን እንደትጠብቅ ….. ቸር ያገናኘን።

የቀደሙት ሊንኮች ….

ክፍል አንድ http://en.wikipedia.org/wiki/User:Aatebeje

ክፍል ሁለት http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30526#respond

ጎንደር ክፍል ሦስት http://www.zehabesha.com/amharic/archives/30763

  • ኮከብ ያለባቸው አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ መጸሐፍ በሊቁ ጸሐፊ ከአቶ በሪሁን ከበደ የተወሰደ ሲሆን፤ መጸሐፉም ተሽጦም ገቢ የሆነው  ለአብረንታት ዋልድባ ገዳም ነው።
  • ዓ.ምህረቱ በግእዝ ስለሆነ ብዙ ነገር ስለረሳሁ ግድፈት ካለ ይቅርታ ዝቅ ብዬ ሎሌያችሁ እጠይቃለሁ።
  • ግሑሳን – በአይን ማይታዩ የተሰወሩ ግን ለአግልግሎት በቋሚነት የተሰማሩ ንዑዳን፤

 

ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር ኢትዮጵያዊነት።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 


Ethiopian-American author Dinaw Mengestu and the aura of estrangemen

$
0
0

Hannah Black
June 5, 2014 

 

140609417The Ethiopian-American author Dinaw Mengestu’s third novel, All Our Names [Amazon.com], tells the story of Isaac, a name stretched to fit not one but two characters whose lives unfold in alternating narratives. In one of these narratives (Isaac), two men form a close friendship in Kampala during a coup, and in the other (Helen), set a year or two later, one of them attempts a love affair with an American woman in a small town in the Midwest. 

 

In the Isaac narrative, we are guided around the revolutionary foment of Amin-era 1970s Kampala by a young man who will eventually take the name of his best friend Isaac when he leaves Uganda for the US. He is a foreigner in Kampala, recently arrived from Ethiopia with ambitions to become a university student and a writer. Over the novel’s first few pages, Mengestu gradually draws out the revelation that even the first of these dreams is impossibly unrealistic.

 

Mired in poverty, neither of the two friends has the means to do more than spectate at the edges of a college scene that is already a palimpsest of imitations. Real and aspiring students alike model themselves on famous figures. The narrator cannot afford even this imitation, but there is some comfort, in this novel, in the fact that imitations are all there is to be had. The dreams of the immediate aftermath of colonialism are turning sour and in the new postcolonial mode, students imitate revolutionaries, the state imitates a state and the narrator simply follows his friend around as he lives out his fantasies.

 

Helen’s town, where she and the man she knows as Isaac meet after he leaves Uganda, is also freighted with unreality. The location is obviously intended to convey the purest essence of Middle America, so much so that the character herself often refers to “the rural mid-west” in a way that could reflect not just the structural needs of the novel but a not-implausible self-­consciousness about her origins. Her relationship with Isaac gives her a new vision of herself, as if from outside; she reflects on how her life would have been had he not arrived, as if this unlived life remains palpable to her. Mengestu sketches out the love affair between Helen and Isaac with the same hazy mix of broad strokes and sharply rendered detail that characterises the Kampala scenes.

 

In Mengestu’s Uganda, everything is constantly, violently changing, so much so that specific events blur and lose distinction. There are struggles to survive poverty, an attempt to overthrow a dictatorship, a bloody civil war, but all these unfold gently, without dramatic tension. As nameless corpses pile up in nameless villages, the narrator notes down his observations of the landscape. Mengestu zooms in on details: a grey suit that matches the grey radio on which a state of emergency is announced over and over again; the wet towel with which the narrator cleans his face after being beaten.

 

But one senses that Mengestu’s intentions have defeated him a little. The attempt to render both the voice of a traumatised refugee with literary ambitions and that of a white American woman who has never left her home state is virtuosic in intention, but not quite in execution. Both characters seem to remain far away from us, and from themselves. Perhaps this poor rendering of character is itself a kind of virtuosity, reminding us that vehicles like literature, or even language, are imperfect vessels for conveying a world of wildly different real experiences, whether those of a frustrated Midwestern social worker or of a helpless witness to atrocities.

 

The novel’s most impressive quality is this pervasive aura of estrangement, as if reality were interchangeable for some other state of affairs, and therefore only minimally possible to describe. But this effect is also a kind of failure. Poor black Africans are only too often represented in this way, as remote and essentially unknowable. Western media coverage of events in ­Nigeria or the Democratic Republic of the Congo, for example, tends to paint specific political formations as if they were incomprehensible eruptions of evil. Africans, we are led to believe, are subjects of trauma so great that it exceeds even the limits of the concept of trauma. Their names change, they appear in one place and disappear in another. Against this erasure, it feels important to remember the former Haitian president Jean-Bertrand Aristide’s dictum that “every person is a person”. Mengestu’s rendering of this hovers in a fascinating limbo, at times seeming to resist the pervasive negation of African subjectivity and at times coming uncomfortably close to simply repeating it.

 

Hannah Black’s writing has been published in Mute, Dazed Digital and The New Inquiry, where she is also a contributing editor.

 

thereview@thenational.ae

 

የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ፍቅረኛሞች በአዲስ አበባ – [አሪፍ የፍቅር ታሪክ)

$
0
0

በአዜብ ታምሩ

ወጣቶች ናቸው፡፡ ዓለምፀሀይ ዘላለምና አበራ ተካ ይባላሉ፡፡ ኑሮን በጎዳና የሚገፉ፤ ተቃቅፈው ውለው ተቃቅፈው የሚያድሩ፤ ማንንም ለመስማት ጊዜ የሌላቸው፤ ከጥቂት ቡቱቶዎቻቸውና ከትንሿ ውሻቸው ውጪ ምሳ ካገኙ ስለራት የማያስቡ ከፍቅር ሌላ ምንም የሌላቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ መሀል አውቶቡስ ተራ አዲስ ከተማ መሰናዶ ት/ት ቤት ጀርባ ከሚገኘው መንደር የኢትዮጵያ ህፃናት መርጃ ድርጅትን አጥር ተገን አድርገው የሚኖሩ ፍቅረኛሞች ናቸው፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ነጋ ጠባ የሚገረሙባቸው፤ ቤት ውስጥ ያጡት አንዱ ላንዱ መስዋዕትነት የሚከፍልለት ፍቅር እዚህ መገኘቱ አጀብ የሚያሰኛቸው፡፡
179 - Kumneger Cover
በነዚህ ወጣቶች ፍቅር ከሚገረሙት ሰዎች መካከል አንዱ አቶ በላይ ይባላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ህፃናት መርጃ ድርጅት የቴአትር ክፍል ሀላፊ የሆኑት እኒህ ሰው ናቸው ስለወጣቶቹ የነገሩኝ፡፡ ከእለት ጉርሳቸው ውጪ ሌላ የሌላቸውና ከማንም ምንም እንደማይፈልጉ የሚናገሩት ወጣቶቹ በቀላሉ ያዋሩኛል ብዬ
አልጠበኩም፡፡ እንዳሰብኩት ግን አልሆኑም፡፡ ከኔ ጋር ለማውራት ፍቃዳቸውን አልከለከሉኝም፡፡ ጥግ ይዘን ማውራት ጀመርን፡፡ እየሆነ ያለውን የሰሙ የአካባቢው ወጣቶች ተሰበሰቡ፡፡ ግርግሩን ፈራሁ፡፡ ወደ ድርጅቱ ግቢ ተያይዘን ገባን፡፡ የአካባቢው ልጆች ግን ‹‹ስለነሱ እኛን ጠይቂን፤ ነጋ ጠባ የምናያቸው የሚያስፈልጋቸውን የምናውቅ እኛ ነን›› አሉኝ፡፡ ያለ ምክንያት አይደለም እንዲህ ማለታቸው፤ እንደኔ ለአካባቢው እንግዳ የሆነ ሰው በመጣ ቁጥር ፍርሀታቸውን ያውቁታልና ሁሌም እንዲያ ይላሉ፡፡

“ፈራን መለያየት ፈራን” ይላል የሁለቱ ወጣቶች ልብ፡፡ የከበቡዋቸው የዚያ ሰፈር ልጆችም ‹‹እናንተን የሚለየው ሞት ብቻ ነው፡፡›› ይሏቸዋል፤ ግን ከዕለት ያለፈ ነገር ሊያደርጉላቸው አልቻሉም፡፡ እሱ ለሷ፤ እሷ ለሱ በሚሆኑት ነገር ተደንቀው የቀን ትዕይንት ካደረጓቸው ግን ከራረሙ፡፡ ዓለምፀሀይ ዘላለም ‹‹እድሜዬ 27 ነው›› አለችኝ፡፡ በደንብ ተመለከትኳት፤ ከዚህ አታልፍም፤ ጥቂት እውነት ብዙ መዘባረቅ የተቀላቀለበት ንግግሯ ከሚደጋገሙት መሀል እውነቶቹን እንድመርጥ አስገድዶኛል፡፡ በንግግሯ መሀል የእንግሊዝኛው ቃላት መደጋገም ሌላ ጥያቄ ያጭራል፡፡ አለምፀሀይ ጎበዝ ተማሪ ነበረች፤ ደብረ ማርቆስ ከተማ በሚገኘው ዋሸራ ብሮድቪው ኮሌጅ የሁለተኛ ዓመት የሴክሬተርያል ሳይንስ ተማሪ ሳለች የአእምሮ ህመም ስለገጠማት ትምህርቷን አቋርጣለች፡፡ (እሷ“ነቅዬ” ነው ትለኛለች ደጋግማ) አክስቶቿ ለማስታመም በሚል ወደ አዲስ አበባ ካመጧት በኋላ ረስተዋታል፡፡ ሄድ መለስ እያለች
ነገሮች እየተደበላለቁባት ስትነግረኝ አዲስ አበባ ከመጣች ሦስት ዓመት አልፏታል፡፡

ዝም ብለው ሲመለከቷት ከንግግር ቅልጥፍናዋና ጥንቅቅ ከማለቷ የአእምሮ ችግሯን ታስረሳለች፡፡ በቀላል ህክምና ለውጤት የምትበቃ ትመስላለች፡፡ ነገሩን የሚያውቅላት ይኑር አይኑር እንጃ እንጂ ብዙ ያነበበችም ለመሆኗ በንግግሯ የምታነሳሳቸው የዓለማችን ፀሀፍትና ፈላስፋዎች ምስክር ናቸው፡፡ እነሶቅራጥስ፣ አርስቶትልና ሌሎችም በአንደበቷ ሲጠቃቀሱ ይቺ ልጅ የሆነ ከአቅሟ በላይ የሆነባት፤ ሰው አልረዳ ያላት ነገር ቢኖርስ ብዬ ገመትኩ፡፡ ደግሞም ጠየኳት “በልጅነትሽ ምን መሆን ትፈልጊ ነበር?” ስል፡፡ ‹‹ሳይንቲስት መሆን፣ የፊዚክስ ሊቅ መሆን ፣ጠፈር ላይ መውጣት…” ለምጠይቃት
የምትሰጠኝ መልስ መጨረሻው ብቻ ነው ፈሩን የሚለቀው፡፡ በአብዛኛው በትክክል እየነገረችኝ ቆይታችን ቀጠለ፡፡

በወጣትነት እድሜ በተለይ በሃያዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የውስጥ ፍላጎቶቻችን የሚጋጩ ይመስለኛል፡፡ የሚያደምጥ የሚረዳ ሲጠፋ የሚፈልጉት ሳይገኝ ሲቀር ደግሞም የሚናገሩት ከማህበረሰቡ ለየት ሲል ‹‹ለየላት›› መባል ከዚያም ቤተሰብ መፍትሄ የሚለውን ሲያደርግ የአእምሮ ውጥረት ሲባባስ ጭንቀት ሲበረታ የባጥ የቆጡን መቀባጠሩ ቢያይል አይገርምም፡፡ በአለም ፀሀይ ህይወት ውስጥ ተመሳሳይ ነገር እንደተከሰተ ለመገመት አይከብድም፡፡ እሷንና ተወልጄ አድጌበታለሁ ያለችኝን ደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ ሰባት ሸዋ በር ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ከፖሊስ ጣቢያው ወረድ ብሎ ያለውን መንደር አስተያየኋቸው፡፡ የእሷ ፍላጎት ከማህበረሰቡ አመለካከት ጋር ሲጋጭና የምታነሳቸው የተለዩ ሃሳቦች ‹አበደች. እያስባላት በድግግሞሹ ተገፍታ ለአዕምሮ ህመም እንደተዳረገች ያስታውቃል፡፡

አበራ አጠገባችን ተቀምጧል፡፡

የምናወራውን እየሰማ ነው፡፡ አንዳንዴ በወሬያችን መሃል ሳቅ ይላል፡፡ ቀይ ረዥም ቆንጆ ወጣት ነው፡፡ “አበራ ተካ እባላለሁ፡፡ ተወልጄ ያደኩት አዲስ አበባ መነን አካባቢ ነው፡፡ እድሜዬ አስርን ሳይዘል ከቤተሰቦቼ ጋር ጥሩ ኑሮ ስንኖር ከሌሎች ዘመዶቻችን ጋር ተቀላቅለን መኖር ጀመርን፤ ያኔ ወላጆቼ ለዘመዶቻችን ጥለውኝ ሲሄዱ እኔም ከቤት ወጣሁ፤ የጎዳና ተዳዳሪ ሆንኩ፡፡ ዛሬ እድሜዬ ሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ይገኛል፡፡ አብዛኛውን እድሜዬን ያሳለፍኩት ጎዳና ላይ ነው፡፡” እያለ ስለራሱ አጫወተኝ፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች፣ በባህርዳር፣ ምዕራብ ሸዋ ጎዳናዎች ብዙ ክረምትና በጋዎች ዝናብና ፀሀዩ ተፈራርቆበታል፡፡ የሌት ቁሩ የቀን ወበቁ ገርፎታል፡፡ እናም ዛሬ ከተላመደው የጎዳና ህይወት ከመውጣት ሞት የሚሻል የሚመስለው አበራ ቀለል አድርጎ ‹‹ቀን ያገኘሁትን እሰራለሁ፤ ማታ ማታ እዚህ አድራለሁ›› በማለት የየዕለት ኑሮውን በአጭር ዓረፍተነገር ገለጸልኝ፡፡ በነአበራ ህይወት ውስጥ ማንም አብሮ ከሚኖረው የተለየ ብዙዎች ያጡትን የማፍቀርና የመፈቀር ህይወት በፍቅር ውስጥ ቢታመሙ አስታማሚ፣ ቢራቡም ቢጠግቡም የሚያወሩት የማያልቅ፣ ደስታ የማይለየው ለሌሎች ቦታ የሌለው መሆን ብዙዎች ያልታደሉት እንዲህ ባዶቤት እንዳንለው ጎዳናላይ ሲገኝ ለየት ያለ ስሜት መፍጠሩ አይቀርም፡፡ሁለቱ ወጣቶች ስለተገናኙበት አጋጣሚ አበራ ያስታውሳል፡፡ “ አውቶቡስ ተራ ጀርባ ሰላም ጂም አካባቢ ቁጭ ብዬ መጣችና አጠገቤ ቁጭ አለች፡፡ ከዚያ ካንተ ጋ መሆን እፈልጋለሁ፤ አለችኝ ተግባባን፤ አብረን መኖር ጀመርን” ይላል፡፡ እሷም “በቃ ስለወደድኩት አብረን መኖር ጀመርን” ትላለች፡፡ የዚያ መንደር ወጣቶችም “እዚህ አካባቢ የመጡ ሰሞን ማንም ትኩረት አይሰጣቸውም ነበር፤ እየቆየ ግን እንደሌሎቹ የጎዳና ልጆች አለመሆናቸውን ስናይ በነሱ ተሳብን” ይላሉ፡፡

እሱ ማንም እንዳይነካት ጠባቂዋ ነው፡፡ የመንፈስ ጭንቀቷ አይሎ መረበሽ ስትጀምር ወደ ደረቱ አስጠግቶ ወደ ራሷ ይመልሳታል፤ አብረው ያገኙትን ተቃምሰው ተቃቅፈው ውለው ያድራሉ፡፡ ‹አንድም ቀን ከዚህ የተለየ ነገር አላየንባቸውም› ሲሉ ይናገራሉ ነጋ ጠባ የሚያዩዋቸው፡፡ እሱም “ ታሳዝነኛለች፤ ታውቂያለሽ ይቺ ልጅ ትረበሻለች፡፡ እኔ ሳባብላት ነው ዝም የምትለው፡፡ ደግሞ እወዳታለሁ” ይላል፡፡ ይህንን የተመለከቱ እውነተኛ ፍቅር ማለት ይሄ ነው አሉኝ፡፡ ከነሱ ውጭ የሆኑ የትዳርና የፍቅር ሕይወቶችን እያነሳሱ፡፡

እንደ ምሳሌ ከጠቀሱልኝ መሀል የሰሞኑን ሰርጎች ከውጥን እስከመጨረሻቸው ለተመለከተ የትዳር መሰረት የሆነውን ፍቅራቸውንም ለመዘነ በየፍርድ ቤቱም ሳይጋቡ ተፋቱ አይነት የፍቺ ጥያቄዎችን መብዛት ላየ ደግሞም የፍቺ ጥያቄ የሚቀርብባቸው ምክንያቶች ግልፅ የማይሆኑና ስስ መሆናቸውን ለሰማ
የጋብቻ ትርጉም ቢደናገረው አይገርምም፡፡ ሲዘፈን እንደምንሰማው ተፅፎም እንደምናነበው የትዳር መሰረቱ ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ደግሞ ብዙውን ጊዜ ሳይታሰብ አንዳንዴም በመላመድ ይፈጠራል፡፡ የቱ ከልብ የሆነ የትኛው እውነተኛ ነው የሚለው በእያንዳንዱ ሰው ልብ የሚመዘን ነው፡፡ ፍቅር ሲታሰብ ምን አላት? ምን አለው? ከሚሉት ጀምሮ ከአቋም እስከ ዘሩ ከእውቀት እስከ አስተሳሰቡ ለክተው እስከሚጠብቁት ብዙዎችን አይተናል፡፡ ኑሮን ሀ ብለው ሲጀምሩም እንዲህ መሆኑን ባውቅ መች እገባበት ነበር? የሚሉት ብዙዎች ናችው፤ የሰው ባህሪ የጎደለውን መፈለግ ስለሆነ ሲይዙት ባዶ ቢመስል አይገርምም፡፡ ኑሮ ካሉት ሁለቱ ይስማሙ እንጂ የትም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ ለመመስረቱ ብዙዎችን ስንሰማ ኖረናልና የእውነተኛ ፍቅር ምሳሌዎች ይኸው እነዚህ ተገኝተዋል፡፡ ለመገናኘትም አብሮ ለመኖርም ምክንያታቸው ፍቅራቸው ነውና ፡፡

“አንድ ቀን” አለኝ አብዲ የተባለ ወጣቶቹን የሚያውቅ የዚያ ሰፈር ወጣት፡፡ ‹‹ሀይለኛ ዝናብ እየዘነበ ወደቤት ለመግባት እየሮጥኩ ስመጣ እነሱ ግን ድንጋይ ላይ ተቃቅፈው ቁጭ ብለው ዝናቡ በላያቸው ላይ ይወርዳል፡፡ በጣም ደነገጥኩ፤ እነሱ ጋ የማይዘንብ ሁሉ መሰለኝ፡፡ ቀስ እያልኩ መራመድ ስጀምር ተመስጠው እያወሩ መሆናቸውን ልብ አልኩ፡፡ በፍቅራቸው እንደሁልጊዜው ቀናሁ፡፡ ፅናታቸውም አስገረመኝና ምነው በሞቁት ቤቶች መሀልም ይህን መሰሉ ፍቅር በሞላ አልኩ፡፡” ሌላዋ ወይዘሮ ደግሞ በትዳር መሀል ሳይቀር የሚያጋጠሙትን እያነሳን ሁሌም እንገረምባቸዋለን አለች፡፡ ”ዛሬ ማነው የአእምሮ ህመምተኛ የሆነችኝ ሴት እንዲህ በትዕግስት ተንከባክቦ ከችግር፣ ከረሀብና ከጥማት ጋር ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ እየኖረ የሚያስታምም? ከሞቀ ቤታቸው እንኳ ብዙዎች የጎደለባቸውን ፍለጋ ሲሄዱ ነው የምናየው፡፡ እነዚህ ወጣቶች ግን ሲያማት እዚሁ እያስታመመ አብረው እየኖሩ ነው፡፡ነገረ ስራቸው ሁሉ እውነት ነው፡፡ እሱም መስራት የሚችል ቆንጆ ወጣት ነው፡፡ እሷም የተማረች ቀልጣፋ ወጣት ናት፡፡ ትንሽ ህክምናና ምክር ድጋፍ ቢያገኙ ተቆርቋሪ ሀላፊነት የሚሰማው ሰው ቢያግዛቸው በቀላሉ ራሳቸውን ችለው የሚያስመሰግኑ ወጣቶች ይሆኑ ነበር” አሉኝ፡፡

እነዚህ ወጣቶች በተለይ እሷ አዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ አክሰቶች እንዳሏት ትናገራለች፡፡ በየጊዜው መንገድ ላይ እንደምታገኛቸው ስትነግረኝ በአካባቢው ያሉ ወጣቶች ደግሞ በአንድ ወቅት ዘመዶችዋ መጥተው የተፈጠረውን አወጉኝ ፡፡ “አንድ ቀን ሁለት አክስቶችዋ መጡ፡፡ ከዚያ ልጃችንን ይዘን መሄድ እንፈልጋለን አሉ፡፡ እና ምን እናድርግላችሁ ስንላቸው ከሱ ነጥሉልን አሉን፤ መጀመሪያ ደብቆ ያመጣት መስሎን ውሰዷት ብለን ነበር፡፡ በፍፁም እሱንና ውሻዬን ትቼ አልሄድም፡፡ ስትል የሆነ ብር ወርውረውላት ሄዱ፡፡ ከዚያ በኋላ ለበዓል እንኳን መጥተው አላዩዋትም፡፡ ስለዚህ ቢወስዷትም የሱን ያህል ስለማያስታምሟት እሱ ይሻላታል›› ይላሉ፡፡

በነበረን ጥቂት ቆይታ ስለጎዳና ህይወት አስከፊነት አበክሬ ለመናገር ብሞክርም ሀሳቤ መፍትሄ መፈለግ መሆኑ ያልገባቸው ሁለቱ ወጣቶች በጥላቻ የተመለከቱኝ መሰለኝ፡፡ እሱን ወደ ስራ እሷን ወደ ህክምና የሚወስዳቸው ቢገኝ የሚለውን የልቤን ሀሳብ ካወቁ ቢታዘቡኝ አይገርምም፡፡ እነሱ የዘወትር ፍርሀታቸው መለያየት ነውና፡፡ እናም የዛሬው ፀሀይ የመጪው ክረምት ዝናብና ጎርፍ ቢያሰጋቸውም ይኸው አሉ፡፡ ለኛ ብዙ ነገር የጎደላቸው ቢመስለንም ፍቅር ህይወታቸውን ሙሉ አድርጎላቸዋል፡፡ የአብሮነት ኑሮአቸውን ይቀጥላሉ፤ መለያየትን ብቻ እንደፈሩ፡፡

(በአዲስ አበባ የሚታተመው ቁምነገር መጽሔት ላይ ታትሞ የወጣ)

እንደ ዘበት ያለፉት ነፍሶች – (እውነተኛ የወንጀል ታሪክ)

$
0
0

እነዚህ ሁለት የወንጀል ታሪኮች የተፈፀሙበት ጊዜ ጥቂት ዓመታት ወደኋላ ይርቃል፡፡ ሁለቱም ወንጀሎች የተለያዩና የሚያገናኛቸው ነገር የሌለ ቢሆንም ማጠቃለያቸው ግን ሞት መሆኑ ያመሳስላቸዋል፡፡ በተለይ በተለይ የህይወት ህልፈቱ ሳይታሰብ እንደዘበት መፈጠሩ ‹የተቆረጠለት ቀን› የሚባለውን አይነት አሟሟት ያስታውሳል፡፡ ሁለት ነፍሶች በተለያየ ዓመት በተለያየ ሁኔታ በተለያዩ ቀናትና በተለያየ ምክንያት እንደዘበት አልፈዋል፡፡ ሳይታቀድና ሳይታሰብ ህይወታቸውን የተቀሙት ሰዎች መቃብር ውሎባቸው- ገዳዮቹም አስር ቤት አሽጓቸው ተረሳስተዋል፡፡

Crimestopperslogo 

አንድ

 

ቀልድ የጠራው ሞት

ጥር ወር 1996 ዓ.ም

አዲስ አበባ

የየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 ነዋሪ ‹አንዳች እንከን የማይወጣለት ፍቅር ያላቸው ናቸው› ይላል፡፡ ለዓመታት በመቀራረብና በመተሳሰብ የዘለቁት ጓደኛሞች ፍቅራቸው ለብዙሃን ምሳሌ ሆኖም ኖሯል፡፡ በመካከላቸው ያለው የእምነት ልዩነት፤ የህይወት ፍልስፍና አለመገናኘት፤ የቤተሰብ ሁኔታ አንድ አለመሆንና ሌሎችም የጋራ ያልሆኑ መለያዎቻቸው ቢበዙም ከዚህ ሁሉ በላይ ገዝፎ የወጣ የጓደኝነት ፍቅራቸው ሁሉን አስረስቷቸው አንድ አድርጓቸዋል፡፡ እንደብዙዎቹ እምነት የጓደኝነት ሙሉ ትርጉም ስፍራ ይዞ የሚታየውና ጎልቶ የሚንፀባረቀው በእነዚህ ሰዎች ነው፡፡

ሁለቱ ወዳጆች አብረው የሚበሉ አብረው የሚጠጡ መሆናቸው ብቻ አይደለም ‹ጓደኛ› የሚለውን ስያሜ ያሰጣቸው፡፡ ሁለቱም ከመብላትና ከመጠጣት በላይ የህይወታቸውን ክፍተት የሚሞሉበትን ፍቅር መሰጣጣት የቻሉ ነበሩ፡፡ አንዱ ሲቸግረው ሌላው እየረዳው፤ አንዱ ሲጨንቀው ሌላው እያዋየው፤ አንዱ ደስ ሲለው ከሌላው እየተካፈለው ስሜታቸውን እየተጋሩት ኖረዋል፡፡ መወለድ ቋንቋ ነው እስከሚባል ድረስ ሁለቱ ወዳጆች አምሳልነታቸውን አንድ አድርገው ዘልቀዋል፡፡ ዓመታትን የተሻገሩትና የወዳጅነታቸውን ዘመን ትሩፋት የተቋደሱት በመካከላቸው ባለው ፍቅርና መቻቻል ነው፡፡ ለዚህም ይሆናል አንዱ ሌላውን ሲያስተዋውቅ ‹ጓደኛዬ ነው› የሚለው ቃል ብቻውን የሚወክልለት የማይመስለውም፡፡ ‹እንደወንድሜ የማየው ጓደኛዬ ነው› በሚል ቃል የወዳጅነታቸውን ልክ ሞቅ አድርጎ መግለፅን ነው የሚያዘወትሩት፡፡

ብዙዎች የእነዚህን ወዳጅነትና ፍቅር ይቀኑበት ነበርና የአብሮነታቸው ‹ሳይንስ› ለማወቅ ይጥሩ ነበር፡፡ ከሁለቱም ጋር የቅርብ እውቂያ የነበረው ወጣት እንደገለፀው ጓደኛሞቹን አንድ ያደረጋቸው ነገር ሁለቱም ቀልድና ጨዋታ መውደዳቸው ነው፡፡ ‹‹መጫወትና መቀለድ ይወዳሉ፡፡ እንደ ህፃን ልጅ ይላፋሉ፡፡ ይደባደባሉ፡፡ ሰዎች እስከሚገርማቸው ድረስ አይለያዩም፡፡ እንደውም አንዱ ሌላውን ካጣው ‹ሳላይህ ስውል ትናፍቀኛለህ› የሚባባሉ ወጣቶች ናቸው፡፡ ይህ ቅርርባቸው አንዱ ሌላውን እንደራሱ አድርጎ እስኪያውቀው ድረስ ልብ ለልብ ያጣመራቸውን ሁኔታ ፈጥሮም ነበር፡፡

አልፎ አልፎ ቢጋጩም ፀባያቸው ብዙም አይከርርም ነው የሚሉት የሚያውቋቸው፡፡ አንድ ሰው ‹‹ሁለቱም ለሳቅና ለጨዋታ ቅርብ የመሆናቸውን ያህል ለኩርፊያም ያንኑ ያህል ናቸው፡፡ ነገር ግን ኩርፊያቸው ራሱ የቀልድ ስለሆነ የሚያመር የለም፡፡ ለምን አኮረፍከኝ ብሎ መጠያየቅም የለም፡፡ ራሳቸው ማንም ሳይመጣ ይቀራረቡና መኮራረፋቸውን እንኳን ይረሱታል፡፡ ኩርፊያ ሲባል ታዲያ ከሰዓታት ያልዘለለው ዓይነት እንጂ ቀናት የሚፈጀው አይደለም›› ብለዋል፡፡

ጥር 23 ቀን 1996 ዓ.ም

ቀን ላይ ሁለቱም ከየዋሉበት መጥተው ተገናኙ፡፡ የዋሉበትም እዚያው ቀበሌ 15 ክልል ‹‹ኬር ኢትዮጵያ እርዳታ ድርጅት›› አካባቢ ነው፡፡ በተለመደው ፍቅርና ሰው ባወቀው የወዳጅነት ውሏቸው ነው ዛሬም የቀጠሉት፡፡ የሚያወቋቸው ሰዎች በሁለቱም ላይ ያነበቡት የተለየ ገፅታ የለም፡፡ የተለመደው ሳቅ- የተለመደው ጨዋታ- የተለመደው ልፊያ- የተለመደው መጎነታተል ዛሬም አለ፡፡ ያያቸው ማንነታቸውን እንኳ ከማወቁ በፊት የአብሮነታቸውን ፍቅር ከፊታቸው የሚቀዳባቸው ሁለቱ ጓደኛሞች ዛሬን እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ያሳለፉት ከዚህ ባልተለየ ሁኔታ ነው፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን አንድ ቃል ከሁለቱ ፍቅር መሀል ጥለቅ አለች፡፡ ‹‹ሸፋፋ›› የምትል ቃል፡፡

ተናጋሪው የዘወትሩ ንግግሩን ውጤት የጠበቀ ከፈገግታና ከሳቅ ጋር የሚመላለስ ምላሽ ውስጥ ነው፡፡ አንደኛው እግሩ በመጠኑ ዘወር ያለ መሆኑን አይቶ ነው ሌላውን ሸፋፋ ብሎ የሰደበው፡፡ በእርግጥ ከዚህ ቀደም ይህንን ቃል ተጠቅሞበት አያውቅም ነበር፡፡ ተሰዳቢው ‹ሸፋፋ› የሚለውን የቀልድ ስድብ ሲያደምጥ ውስጡ አንዳች ቁጣ የተተራመሰ መሰለው፡፡ ዘወትር እንደሚያደርጉት ያለ መተራረብ ነውና ተናጋሪው ከአፉ ለወጣው ቃል ቀልብ የሰጠው አልመሰለም፡፡ ከዚህ ቃል በኋላ የዕለቱ የፍቅር ውሏቸው ተቋጨና ተለያዩ፡፡ ተናጋሪው በውስጡ ነገን እየናፈቀና አብረው የሚውሉበትን ሰዓት እያሰበ ወደ ቤቱ ሲገባ ‹ሸፋፋ› የተባለው ደግሞ ከራሱ ጋር እያወራና ብስጭቱ ያመጣበትን ግልፍተኝነት ለማረጋጋት እየሞከረ ሄደ፡፡ ጥቂት ሰዓታት አለፉ፡፡

ተናጋሪው ሰውዬ ከቤቱ ወጣ፡፡ ሚስቱና ልጁን ሰላም ብሎ ወደ ጎረቤት ነበር አወጣጡ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቴሌቪዥን ለማየት ነው፡፡ ቤቱ ቴሌቪዥን የሌለ በመሆኑ ጎረቤት ወዳለው ጓደኛው ነበር የሄደው፡፡ እዚያ እየተጫወተና በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ሙዚቃ እየኮመኮመ ቆየ፡፡ ቀኑ ማመሻሸት ጀምሮ ነበርና ልቡ ወደ ቤቱ በመሄድና እዚያው በመቆየት መካከል ሲወላውል ስሙ ሲጠራ የሰማ መሰለው፡፡  የልጁ ድምፅ ነው፡፡ ‹አባዬ ና ትፈለጋለህ› ሲል ሰማው፡፡

ይህን የ10 ዓመት ህፃን የላከው የአባቱ ጓደኛ የሆነው ያ ‹ሸፋፋ› ተብሎ የተተረበ ሰው ነው፡፡ በልቡ ያሰበውን እኩይ ተግባር አንግቦ ወደዚህ ወዳጁ ቤት ሲመጣ በዚያ እሳት የለበሰ ስሜቱ ውስጥ እንዳለ ሆኖ የፈለገውን ማግኘት አልቻለም፡፡ የሰውየው ሚስት ‹ባልሽ የት ሄደ?› ተብላ ስትጠየቅ ነገሩ ስላላማራት ቤት አለመኖሩን ትናገራለች፡፡ ምንም የማያውቀው የ10 ዓመት ህፃን ደግሞ ብቅ ብሎ ‹አለ- ጎረቤት ቴሌቪዥን ሊያይ ሄዶ ነው› በማለቱ ነው ጥራው ተብሎ የጠራው፡፡

የሚፈልገው ሰው ማን እንደሆነ ለማወቅ ብቅ ያለው ወጣት ጓደኛው መሆኑን ሲያውቅ ፈገግ ብሎ ተናገረው፡፡ ‹‹ምነው በሰላም ነው? አብረን ውለን ትፈልገኛለህ?› ብሎ ነበር የጠየቀውና ወደ ቆመበት የተጠጋው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሚስትና ህፃን ልጅ ቆመው ይመለከታሉ፡፡ ወደ ጠሪው ሲቃረብ ያ ‹ጥሩልኝ› ያለ ወጣት በጥፊ ተቀበለው፡፡ ራሱን ለመከላከል ሙከራ በሚያደርግበት ወቅት ደግሞ ያላሰበውን ጩቤውን ከጎኑ አውጥቶ አንገቱ ላይ ሽጦበት ሮጦ ሄደ፡፡ ልጁና ሚስት በሁኔው ተደናግጠው ሲጮሁ የተወጋው ሰው ጥቂት ለመንገታገት ሞክሮ ባለመቻሉ በቁሙ ተዘረረ፡፡ ጎረቤቶች ጩኸት ሰምተው ሲወጡ ከተጎጂው አንገት ስር የሚወርደው ደም አካባቢውን አበላሽቶት ነበር፡፡ ወደ ሕክምና ሊወስዱት ሲያነሱት ግን ህይወቱ አልፋለች፡፡

ማንም ባላሰበውና ባልገመተው ሁኔታ ገዳይ ‹ሸፋፋ አለኝ› በሚል ምክንያት ቤቱ ገብቶ ጩቤ ታጥቆ ለግድያ መውጣቱ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ቀናቸውን በመተራረብና በመሳሳቅ የሚያሳልፉ  ሁለት ጓደኛሞች በግድያ የቆየ የወዳጅነት ፋይላቸውን ሲዘጉ መስተዋሉም ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነበር፡፡

ተጠርጣሪው ከሸሸበት በህዝቡ ትብብር ተይዞ ሲጠየቅ ‹በፈለገው ነገር ቢቀልድ ምንም አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን በተፈጥሮዬ እንዴት ይቀልዳል?› ነበር ያለው፡፡ ሁሌም የለመዱት መተራረብና መሰዳደብ ላልታሰበ ግምት ሊያደርሳቸው እንደሚችል የጠረጠረ የለም፡፡ ሟችም ሀገር አማን ብሎ የተቀመጠ- እንኳን በጓደኛ በሌላ ሰው እጠቃለሁ ብሎ የማያስብ እንዲሁም እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ለገዳዩ የነበረው ፍቅር ያልቀነሰ ምስኪን ነው፡፡ በአንዲት ቃል ህይወት ጠፋ፡፡ የጓደኛው ሞት ያሳዘነው የሚመስለው ገዳይ ‹‹ሳላስበው ሰይጣን አሳስቶኝ ያደረኩት ነገር ነው›› አለ፡፡ የሁለቱ ፍቅር በመቃብርና በእስር መደምደሙ ግን ግድ ሆነ፡፡ እናትና ልጅም እያዩት አባወራቸውን ቀበሩ፡፡

 

ሁለት

የ‹ዱብ ዕዳ› ምሽት

ነሐሴ ወር

1998 ዓ.ም

መሽቷል፡፡ አፋር ኬክ ቤት አካባቢ ከፒያሳ ወደ ሰይጣን ቤት በሚስደው ቁልቁለት መንገድ ላይ የክረምቱ ዝናብ መውጫ መግቢያ አሳጥቶት የዋለው አዲስ አበቤ በየካፌዎቹና በየሬስቶራንቱ ተጠልሎ ጋብ ሲልለት ነው ወደ አስፓልቶቹ ወጣ ያለው፡፡ በአንፃሩ ሌሎች በየቤታቸው ተቀምጠው የነበሩ ወደ ካፍቴሪያዎች ‹ሞቅ ላለ ሻይ› ጎራ ብለዋል፡፡ ጭር ያለው የክረምት ቀን ምሽቱ አካባቢ ደመቅ ያለ ይመስላል፡፡

ስዩም የ27 ዓመት ወጣት ነው፡፡ የዚያን ዕለት ከእናቱ ጋር ነው የዋለው፡፡ ወደ አመሻሹ ላይ ሲወጣ እቁብ ክፈል ተብሎ የተሰጠውን አንድ ሺ ብር ይዞ ነበር፡፡ ብቻውን ወደ አፋር ኬክ ቤት ጎራ ያለው ሻይ ለመጠጣት ብሎ ነበር፡፡

የስዩም ሰፈር እዚያው አካባቢ ነው፡፡ ቴዎድሮስ አደባባይ አስከሬን አበባ የሚሸጥበት በተለምዶ አበባ ሰፈር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በአካባቢው ልጆች ጋር የሚቀራረብ ቢሆንም ብዙዎች ግን የግሩፕ ፀብ የሚወዱ በመሆናቸው ብዙም ሊጠጋቸው አይፈልግም፡፡ የዚህ ወጣት ስራ መማር መስራት ህይወቱን በአግባቡ መምራት ብቻ ነው፡፡

ሻዩን ጠጥቶ ሲወጣ ከ3 የሚበልጡ ወጣቶች ቆመዋል፡፡ አያውቃቸውም፡፡ እነርሱ ግን የሚያውቁት መሰለው፡፡ አስተያየታቸው አላማረውም፡፡ ከምሽቱ 2 ሰዓት ሆኗል፡፡ አንደኛው ‹ና ወደዚህ› አለው፡፡ ስዩም አካባቢውን ቃኘት አደረገ፡፡ ብዙ ሰው የለም፡፡ ፈራ፡፡ የጠሩት በሰላም እንዳልሆነ ገብቶታል፡፡ ነገር ግን አማራጭ አልነበረውምና ተጠጋቸው፡፡ አጠገባቸው ከደረሰበት ደቂቃ ጀምሮ መጨረሻ እስከሆነው ነገር ድረስ ያዩ ሰዎች ነገሩን ለፖሊስ ተርከውታል፡፡

‹‹ተጠጋቸው፡፡ በዚህ መሀል ወዲያው በላይ የተባለው አንደኛው ጠጋ አለና በያዘው ጫፉ ላይ ብረት ያለው ዱላ አናቱን መታው፡፡ ስዩም ወደቀ፡፡ በወደቀበት ቦታ ጥለውት ይሄዳሉ ሲባል ከየት እንደመጡ ያልታወቁ 11 ወጣቶች ድንገት ደረሱና በወደቀበት ቀጠቀጡት፡፡ ጌቱ የተባለ አንድ ወጣት  የስዩም መቀጥቀጥ አልበቃ ብሎት ድንጋይ አምጥቶ ጭንቅላቱን መታው፡፡ ስዩም ጣር ላይ ነበር፡፡ ድንገት ብድግ ብሎ ከዚያ ውርጅብኝ ለማምለጥ ሮጠ፡፡ ብዙ ርቀት ግን አልተጓዘም፡፡ ተደናቀፈና ቦይ ውስጥ ወደቀ፡፡ በዚው ቀረ፡፡ ይህን ያዩና ሲሮጥ የተከታተሉት ደብዳቢዎቹ አልተዉትም፡፡ እዚያው የየድርሻቸውን ደብድበውት ጥለውት ሄዱ፡፡ በዚያን ጊዜ የአካባቢው ሰዎች ለማገላገል ያደረጉት ሙከራ የለም፡፡ የቡድን ፀብ በጣም ይፈራ ስለነበር ነገሩን በዝምታ ከመከታተል ውጪ ምርጫ ያለው አልነበረም፡፡ በቅፅበት ውስጥ የተከናወነው ድብደባ ደግሞ ፖሊስ ለመጥራት አመቺ አልነበረም፡፡ ያም ሆነ ይህ ትቦ ውስጥ የወደቀውን ተደብዳቢ ለማንሳት ወደ ስፍራው የሄዱት የአካባቢው ሰዎች ወጣቱ በዘግናኝ ሁኔታ መሞቱን አወቁ፡፡ በጨለማ ድብደባው ወቅት ሌዘር ጃኬቱን፣ ያጠለቀውን የወርቅ ሀብልና ኪሱ ውስጥ የተገኘውን 1 ሺ ብር የወሰዱት ደብዳቢዎች ተሰውረዋል፡፡

ጥቂት ቀናት ከፈጀ ምርመራና ክትትል በኋላ የተያዙት 11 ተጠርጣሪዎች ግድያውን አንዱ በአንዱ ላይ ሲያላክኩ ቆዩ፡፡ በተለይም የገደልኩት እኔ አይደለሁም ለማለት ከፍተኛውን የድብደባ ደረጃ ወደ ሌላ ለማዞር ጥረት ተደርጎም ነበር፡፡

የግድያው መነሻ የተባለው ነገር ነው ለሁሉም አስገራሚ የነበረው፡፡ ሁሉም ተጠርጣሪዎች ስዩምን አያውቁትም፡፡ ከሁሉም ውስጥ አንዱ ‹ና› ብሎ የጠራው ብቻ ስዩም ‹የአበባ ሰፈር› ልጅ እንደሆነ ያውቃል፡፡ ስዩም ተማሪ ይሁን አስተማሪ ሰራተኛ ይሁን ስራ አጥ የሚያውቅ የለም፡፡ ነገር ግን አንድ እውነት አለ፡፡ ስዩም የአበባ ሰፈር ልጅ ነው፡፡ በአበባ ሰፈር ነዋሪዎችና በእነዚህ ወጣቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ፀብ አምርቶ አሁን ሁለቱም ሰፈሮች ለጥቃት ተዘጋጅተው የተቀመጡ ናቸው፡፡ ይህን ደግሞ አንድም ወጣት ቢሆን ‹ሰፈሩን ላለማስደፈር› እንዲነሳ አድርጎታል፡፡ ይህም የቡድን ፀብን አስፋፍቷል፡፡

ስዩም አንዳች በማያውቀውና በማይጠረጥረው መንገድ ህይወቱ ሲጠፋ ለሰሚ ግራ የሚያጋባ ነበር፡፡ የቡድን ፀብ ተሳታፊ ሳይሆን አበባ ሰፈር የሚኖር ሰው በመሆኑ ብቻ የፀበኞች ጥማት ማስታገሻ መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡

ለዚህ እንደዘበት ያለፈ ህይወት ብዙዎች ‹ቀኑ ከዚህ አትለፍ ቢለው ነው› በማለት ሃሳባቸውን ሊሰጡ ቢሞክሩም ይህን መሰል ክስተቶች ማመዛዘንና ማሰብ በተሳናቸው ሰዎች ወደሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች እንደሚመራ ፖሊስ ተናግሯል፡፡

የቡድን ፀብ የአዲስ አበባ ከተማ ዋነኛ ችግር በነበረበት በዚያን ዓመት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የሚፈፀሙ ወንጀሎች ተበራክተው- ብዙዎችም ከህይወት ህልፈት እስከ ንብረት ውድመት ደርሶባቸው መኖራቸው ፖሊስ ችግሩን ለመከላከል ጠንካራ አሰሳ እንዲያደርግ አድርጎታል፡፡ የዚያም ውጤት ነው እነዚን ከ11 ያላነሱ የቡድን ፀብ ተዋንያን ለዚህ አንድ ነፍስ መጥፋት ዋና እና ተባባሪ ወንጀለኛ አድርጎ እንዲከስሳቸውና ወደ ዘብጥያ እንዲያወርዳቸው ምክንያት የሆነው፡፡

ሥለምን ወያኔን ከሥር መንቀል ያስፈልጋል? ሰማዕታት ሲታሰቡ (ከሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ሰማዕታት ሲታሰቡ።
ከሥርጉተ ሥላሴ 08.06.2014 (ሲወዘርላንድ – ዙሪክ)
Sirgut

ሰማዕታት ሲታሰቡ፤ ከቅርንጫፉ እ! ውጋት ነው። ከወገቡ እ! መጋኛ ነው። ከቋንጃው እ! ቁርጠት ነው። ከእጁ እ! ካንሰር ነው። ወያኔ ከሥረ መሰረቱ ነው መነቀል ያለበት። ስለምን የኢትዮጵያን ሉዕላዊ ህልውና አደጋ ላይ የጠላ ትውልድን ያሚያጠቃ ማነፌስቶ ስላለው። የወያኔ ማኒፌስቶ አንድን ዘር ብቻ መሰረት አድርጎ የተነሳ የጎጥ ማንፌስቶ ነው። ስለሆነም ነው ህልውናውን ለማቆዬት መል ተለጣፊ የጎጥ ድርጅቶችን ፈብርኮ የኢትዮጵያን ችግር ወስብስብ፣ ትብትብና ዳጥ ያደረገው።

 

በጎጥ ተመርቶ ለድል የበቃ፣ የህዝብን ጥቅም በእኩልነት ያስጠበቀ አንድም ሀገር ለናሙና ማቅረብ ፈጽሞ አይቻልም። የለም እንጂ – ቢኖርም እንኳን ለኢትዮጵያ እንደ ተፍጥሯዋ የራሷ አምክንዮዊ መንገድ ሊኖራት ይገባል። ልዕልት ኢትዮጵያ በኩረጃ ንድፍ ልትመራ የምትችል ሀገር አይደለችም። አሁን ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዛውም በአንሳው ጎሳ ስብስብ ነው እዬተጎረደች ያለችው። የአንድ ጎጥ ድርጅት ማዕከሉ ጎጡ ብቻ ነው። ከዚህ የሚያልፍ ራዕይና አመለካከት የለውም። ሊኖረውም ፈጽሞ አይችልም። በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ሀገራዊ ሃብታት በሙሉ ይጠቀጠቃሉ – ይደፈጣጣሉ። ሃብታት ሲባል የሃብት ሃብት የሆነውን የሰለጠነውን የሰውን ልጅን ጨምሮ።

የሰውን ልጅ እኩልነት ማዕከል ያላደረገ አስተዳደር ደግሞ ትንፋሹ ጥፋት ነው። ጥፋቱ ምትክ የማይገኝለትን የህዝብና የሀገር ፍልሰት ምድረ – በዳነት ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን እንደ ቤተ ሙካራ ጥንቸል ሁሉ ተሞክሮባታል። የዐፄ ሥርዐት ለዘመናት፤ የሶሻሊስት ሥርዐት ለ17 ዐመታት፤ ቋንቋን መሰረት ባደረገ ፌድራዚም የጎጥ አስተዳደር ደግሞ ለ23 ዓመታት። ሁሎችም ግን የህዝብን መከፋት ያደመጡ ባለመሆናቸው ሁልጊዜም ከስሜን እስከ ደቡብ፣ ከደቡብ እስከ ምስራቅ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለውን የህዝብ ችግር መፍታት አልቻሉም። ትናንትም እንባ ዛሬም እንባ …. ኑራቸው ሆኗል። የእንባና የደም መኖር። ቀረ የሚባል አንዳችም የሙከራ ጣቢያ፤ ሆነ ሥልት የለም። የቀረው ነገር „ሀገር አለኝ“ ማለት አፋፍ ላይ ያለበት ሁኔታ ብቻ ነው። በዘመነ ወያኔ – ስለትናንት የሚናገሩ ማናቸውም ሃብታት ተቀጥቅጠዋል፤ በፋስ ተፈልጠዋል፤ በገጆሞ ተከታትፈዋል። አፈሩም – ተፈጥሮውም – አዬሩም አልቀረለት። የትኛውም መሥሪያ ቤት ለመግባት የመጀመሪያው መጠይቅ ብሄረሰብህ ከዬት ነው? ዜግነትን ዘቅዝቆ ያንጠለጠለ – ደም የሚያዘንብ የመገለ ዘመን። የሁሉም ነገር ልኬታ መስፈሪያ ወቄቱ ጎሳ …. ጠቀራ! እንዲያውም በተገላቢጦሽ ኢትዮጵያዊነትን ለማወጅ ወንጀል የሆነበት የተኮደኮደ ዘመን፤ ኩፍትርትር የነቀዘ የጨቀጨቅ ወቅት፤ እጅግ የተማረረና ያለቀሰ ዘመን። ህም!

 

ከእንግዲህ በኋላ ለሁሉ መዳህኒት የሆነ የአቅም ጥሪት መሰብሰብ ግድ ይላል። የአቅም ምንጩንም ሚስጥር ለማግኘት ተግቶ መባተል። ይህ የአቅም ጥሪት አነሳው ብዙኃኑን ወይንም ብዙኃኑ አናሳውን ሊጨቁኑ ወይንም ሊድጡ የማይችሉበት ወጥ ሥርዓት መፍጠር ነው – ሥርዬቱ። የትርጉም ሥራ ለኢትዮጵያ ጠፍ ፍልስፍና ይመስለኛል። አቅብቅበው የሚጠብቁ ባዕዳን ስሜቶች አሉ። ቅስማቸው የሚሰበረው ከራሳችን – ከውስጣችን መነሳት ስንችል ብቻ ይሆናል። ኢትዮጵያዊነት እኮ ከሰማዩ ፈጣሪ በስተቀር የትኛውም ፕ/ ሆነ ሳይንቲስት አንቦልቡሎ ወይንም ጠፍጥፎ ሊሠራው ከቶ የሚችል አይደለም። አንዷን ነገር ነጥለን አውጥተን የማን ነሽ? ማን ፈጠረሽ? መቼ ተገኘሽ? ብለን ብንመረምራት? ሃብትነቷ የሁላችንም መሆኑን በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ በልበ ሙለነት ትነግረናለች።

 

ይህንን እርቀን – ከማንርቀው፤ ገፍተን – ከማንገፋው ወይ ካለባበሳችን፤ ወይ ከአመጋገባችን፤ ወይ ከጋብቻ ሥርዓታችን ብቻ አንዷን ዘለላ አንሱና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጧት፤ እናንተም በክብር ወንበራችሁን ይዛችሁ ተቀመጡ። ተወያዩ! ጣዕሙ – ጠረኑ የሚውደው ባለቤትነቱ የእኔም – ያንችም – የእርሶዎም መሆኑን ነው። ሰውሰራሽን መጸሐፍ ማንበብ ይቻላል። መተርጎምም ይቻላል። በብዙ ጥልቅ ቅመም የተቀመረን – የነጠረ አንቱ የማንነት ተፈጥሮን ግን በእውነቱ አይቻልም። ይህንን ነው ወያኔ የተዳፈረው። ይህን ነው ደቁሶ አቃጥሎ አመድ ለማድረግ እዬታገለ ያለው። ይቻለዋልን? ወደ ራሳችን ተመልሰን ራሳችን እንጠይቅ። መልሱ አቅማችን ይለካል። መልሱ ትውልድን ታሪክን ሀገርን ይታደጋል ወይ ያከስላል። እራስን ማሸነፍ ድፍረትን ይጠይቃል። ራስን ሃቅ ማንተራስም ወኔን ይሻል። ራስን መሆን መቻልም ክህሎት ነው። እንደ እራስ ለመኖር መቁረጥም ቁሞ ያስኬዳል። አንገትን ቀና አድርጎ እኩል አፍሪካዊነትን ያጎናጽፋል፤  ልብን አደላድሎ ዓለምአቀፋዊነት ይሸልማል።

 

ስለሆነም ይህን መንገድ ለማግኘት በጎጥ ተደራጅቶ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። ወይንም በዕምነት ተደራጅቶም የማይታሰብ ነው። አንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ ዘግቶ መኖርን እሰቡት። ይህ ለኑሮ አፍ ያለው መቃብር ነው – እን። የታሪኳ፤ የባህሏ፤ የቀለሟ፤ የሥልጣኔዋ፤ የተፈጥሮ ሃብታቷ፤ የእምነት ውርርሷ፤ የመልካዕ – ምድራዊ አቀማመጧ፤ የህዝቦቿ  ሥነ-ልቦናዊ አመለካከት – ውበቷ፤ ከጎረቤት ሀገሮች ጋር የነበራት የባህል – የወግ – የልማድ የመልካም ጉርብትና ውርርሷ፤ የተፈጥሮዋ ጥልቅነት ተመርምሮ መነሻውም መድረሻውም፤ ጎጠኝነትን አላይህም አለስማህም የሚል የእንቢተኝነት መንፈስ መፍጠር ያስፈልጋል። እኩልነትን ያደመጠ፤ ማስተዋልን የሰነቀ፤ ሰብዕዊነትን ማዕከል ያደረገ፤ ነፃነትን የኳለ ኢትዮጵያዊ ንድፍ –  ነድፎ ተግባራዊ ማደረግ ሲቻል ያን ጊዜ የተበተነ ሃሳብ፣ የተጎዳ መንፈስ፣ የቆሰለ አካል፣ የጎሳቀለ ህሊና ፈውሱ ይገኝለታል። በእያንዳንዱ ዜጋ ያለውን የታሰረ ፍላጎት ሊፈታ የሚችለው በበዚህ መንፈስ ስንሰባሰብ ብቻ ይሆናል። የኮሰሰ ወይንም የኮሰመነ ስሜትንም ወደ እራስ አስጠግቶ ሃብት ማድረግ የሚቻለው ያሰረንን ትብትብ እራሳችን በራሳችን ይፍታህ ስንለው ብቻ ነው። በዚህ ዙሪያ እኮ ብዙ አንደበቶች ታስረው ነው የሚታዩት ….

 

ከሞት በላይ ምን የከፋ ነገር አለ?! በተለይ ለአንዲት እናት ሀገር፣ ሆነ ለወለደች እናት ልጇን ከማጣት የበለጠ ምን መራራ አሳንጋላ ነገር አለ?! እጅግ ከመከራዎች ሁሉ ጎምዛዛው የልጅን መከራ ቆሞ ማስተናገድ ነው፤ በወያኔ መርዝ ይህንን እንኳን በእኩልነት ለማስተናገድ ተፈጥሮን የጋጠ ገጠመኝ ነው ያለው። ስለምን? መከራን መጋራትን ሸሽተናዋል። እንዲያውም በአንዱ መካራ ሌላው ያላጋጣል፤ በሌላው ጥቃት አንዱ ይስለቃል። ይህ ዛሬን ያሳድራልን? ይህ ነገን በብሩህ ተስፋ ያጫልን? እእ! እርግጥ ነው ለዚህ ተፈጥሮን የዘለለ ሰብእናን የጨፈለቀ የግዴለሽነት የመንፈስ ሆነ ዬበረሃማናት ባዕዳዊ ስሜት ወያኔ ጸንፆ ኮትኩቶ ያሳደገው ነው። ይበል እያለም ግርማ ሞገስ እልብሶ አሽሞንሙኖ የዳረው የኳለው መርዝ መሆኑ ይረደኛል። ግን ነገር ግን ይህ ለእኛ መዳኛችን ሳይሆን መጥፊያችን ነው። ይህን አሸንፈን ጥሰን የወጣን ዕለት ትንሳኤ ነው። በስተቀር ግን ከዚህ የባሰና የከፋ የተጋጋጠ እንዲሁም የደማ – በበቀል እርር ኩምትር ያለ ጥንዙል ነገ ከፊት ለፊታችን ያፋጠናል። እጅግ የምናፍቃችሁ ወገኖቼ የሀገሬ ልጆች – እኛም በዚህ ዙሪያ ወስጥ ወይንም ውጪ መሆናችነን ከራሳችን በላይ ሌላ የፖሊስ መርማሪ የለምና እንፈትሽ ….

 

ወያኔ ሌባ ነው። በዙ ነገራችን ቀምቶናል። ከሥር እንዲነቀል የሚያስፈልግበትም መሰረታዊ እውነት ከዚህ ይመነጫል ወያኔ እኛን ዘርፎናል። ሀገራችንንም አዋርዷል። ልዑላዊነቷን አስደፍሯል። ሽጧታል። ለነገም ተክፍሎ የማያልቅ የዕዳ ባለቤት አድርጓታል። በማወዕለ ንዋይ ብቻ ሳይሆን በመንፈስም። የቤት ሥራችን የገዘፈና የገረዘዘም ነው። የዘረፈንን እኛነት ማስመሰለስ ደግሞ ከእያንዳንዱ በግል ከሁላችንም በጋራ የሚጠበቅ ግዴታ ነው። ለወያኔ ፓሊሲ አለመጠቃታችን ማወቅ የሚቻለው ፈተናውን ስናልፍ ብቻ ነው። ፈተናውን ለማለፍ እራስን ከጋለ ምጣድ ላይ አስቀምጦ እዬተገላበጡ መኮረጅ ነው፤ በትልቅ ብርት ድስት ውሃ አፍልተን ስሜታችን ጨምረን እንፈትሸው። ይመቻል? ይደላል? የሰርግ ሽርሽር ነውን? –  በባሩድ በዬጊዜው የሚቃጠሉትን፤ በቤንዚን እዬነደዱ የሚያልቁትን፤ በስደት ሆነ በሀገር ውስጥ በሳንጃ የሚሸነሸኑትን፤ ከቀያቸው በግፍ የሚፈናቀሉትን ወገኖች የእኔ ነው አይደለም ብልን እራሳችን አፋጠን በምናገኘው ምላሽ ነገ እራሱን አምጦ ይወልዳል።

 

የትም ቦታ የሚቃጠለው ቤት፤ የትም ቦታ የሚፈሰው ደም፤ የትም ቦታ ለባዕድ ተቆርሶ የሚሰጠው መሬት፤ የትም ቦታ የሚገፋው ወገን የሥጋ ቁራጭ ነው። የደም ዘር ነው። ልንገፋው፣ አልሰማነም አላዬንም ብለን ልንሸሸው የምንችለው አይደለም። የትውልዱ አደራ እያነባ ይጠብቃል – እኛኑ፤ ግን መልሱን ፈርተነዋልመድፈር ተስኖናል። ስለምን እኛ ያለነው በግል ጎጇችን እንጂ በአዳራሳችን ውስጥ አይደለምና።

 

የእንግዲህ ትግላችን በቅጣቱ ሰለባነት የሚጠዘጥዘን ስሜት አሻግረን ወያኔ ላይ በመጣል ብቻ ሳይሆን፤ ወያኔ በእኛ ላይ አቅም የሌለው መሆኑን በአይኑ እንዲይ ወስነና ቆርጠን ተግባር ላይ መገኘት ስንችል ብቻ ነው። ይህም ከተቀበርንበት አሸዋ ወጥተን ቁልጭ ባለ ግልጽ ፍላጎት መስመራችን ፈለግን ማግኘት ስንችል ብቻ ይሆናል – መፍትሄው። የእትዮጵያ ህዝብም ባልታዬው የጎሳ አስተዳደር አሳሩን ከፍሏል። በማያውቀው ዕይታ ፍዳውን ከፍሏል። ባልኖረበት ማንነቱ በመጤ ማንነት እንዲጫረስ እንዲፋጅ ተዶልቶበታል፤ ጨዋው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለንትነውን ባከሰላው የጎሳ አስተዳደር መስመር ያለውን ጉዞ ሁሉ በቃኝ ማለት ይኖርበታል። ይበቃዋል። ከዚህ በላይ ምን የፈተና ጊዜ አለ? እሳቱ እኮ ሁሉንም አዳረሰ። ይህ ሁሉ ጦስ የጎጥ ማኒፌስቶ  የአመጣው መርዝ ነው። ሌላ የጎጥ ዘመን ናፍቆተኞችንም ፍላጎታቸውን የሚያመክንበት መንሹ ያለው በእጁ ነው። ከዚህ ሌላ እራሳቸውን ሰውረው በብሄረሰብ ወይንም  በእምነት ተቆርቋሪነት ሰም የደም ነጋዴዎችንም መርምሮና ፈልፍሎ ለመለዬት ማንዘርዘሪያም የሚስፈልግበት እጅግ ፈታኝ የጠቆረ ወቅት ላይ እንገኛለን። ከማን ጋር ነኝ? የእኔ ነውን? እንዳቀርበኩት አቅረቦኛልን? ቅንነቴን አክብሮታልን? ግልጽነቴን አድምጦታልን …. ንጹሑን ውስጤንስ ጨፍሮበታል ወይንስ ቦታ መድቦለታል? …. በሁሉም አቅጣጫ በጥንቃቄ ከቋሳ በጸዳ ሁኔታ መመርመር የተጋባ ይመስለኛል። ዝንቅ ህይውት ለማህበራዊ ኑሮ ሸጋ ነው፤ ቀለማምም ነው። ኑሮ ያመርበታል – ጌጣማ። ለፖለቲካ አብሮነት ግን ….. እህህህ!

 

እንደ እኔ እንደ ሥርጉተ ዕይታ – በጎጥ የሚያስብ ሰው ሰብዕዊነትን ለመተርጎም አቅም ያንሰዋል። በጎጥ የሚየስብ ሰው ርህርህናን ለመተርጎም አቅሙ የሟሟ ነው፤ በጎጥ የሚያመልክ ሰው አህጉራዊ ዕይታዎችን ለማስተናገድ ሽባ ነው። በጎጥ የሚይ ሰው ዓለም ዓቀፋዊነትን ለመቀበል ደረጃው አይፈቅድለትም። በጎጥ የሚተነፍስ ሰው ዘመኑ ከሸለማቸው ሥልጣኔ ጋር ለመኖር ዳፍንት ይዞታል። ሌላው ቀርቶ በጎጥ የሚየስብ ሰው ከጎረቤቱ ቀርቶ ከትዳር አጋሩና ከልጆቹ  ጋር ተስማምቶ ለመኖር ሚያስችለው ተፈጥሮው ተፍቆበታል። በጎጥ ማሰብ ስለ ሰው ልጅ ኃላፊነት በማይሰማው የህልም አለም ግን ጉድጓድ ውስጥ መኖር ማለት ነው – እንደ እኔ። ይህ የእክሌ – ተከሌ በሽታ አይደለም። ተሸፍነን ከመጋረጃው በስተጀርባ የምናሽሞነሙነው ሰብዕናን አጋድሞ የሚርድ የአብዛኞቻችን ገመናችን ነው። ዬቅርባችን ብቻ ነው ዓይናችን የሚፈቅደው። የአብዛኞቻን ችግር ይህ ነው። ከዚህ ጋር መፈታት መቻል ነው ስለ ነገ ራዕይ አለን ማለት የሚያስችለው ፍሬ ነገር። ቀን ደግሞ አድመኛ ነው። ትንሽ ነገር ብቅ ባደረገ ቁጥር ፈትለክ እያልን  የአደባባይ ሲሳይ እንሆናለን። ተከድኖ የሚቀር ነገር የለም – አይኖርምም።

 

አውነት ለመናገር አብዛኞቹ ወጣቶች እኮ በጣም በልጠውናል። እጅግ ከእኛ በጣም ሩቅ ተጉዞው ነው ብሩሁን ቀን የሚያስቡት። ያስቸገርነው እኛ ቀደም ብለን የተፈጠረነው ነን። ይህም በመሆኑ እነሱ ያልበሉትን እዳ እንዲከፍሉ መደረጋቸው አልበቃ ብሎ የሚከፍሉትን መስዋእትንትም ዋጋ እያሳጣነው ነው። ያረመጠመጣል። እንደ እኔ ነገ በጎሳ በጎጥ ቲወሪ ፈጽሞ መታለም የለበትም ባይ ነኝ። ቲወሪው የሀገር ሉዕላዊነት፤ የህዝብን ክብርና ታሪክ የሚደረምስ አሲድ ነው። በጎሳ የተደራጀ አካል ጥላቻው በቀልን ያረገዘ ደም የጠማው ነው። በቀሉ ደግሞ አይደለም ነገን ዛሬን ክው አድርጎ የሚያድርቅ እጅግ ኋለቀር ኢሰብዕዊ መንገድ ነው። መማር – መሰልጠን – ማወቅ ማለት ከዚህ ኋላቀር አስተሳሰብ ጋር መፋታት ካልተቻለበት መማሩ ሥጦ ወይንም ውሃ ሲሄድበት የከረመ አለት ነው – ለእኔ።። መማር መብለጥ ነው፤ መቅደም ነው። መማር ለመልካም ነገሮች ሁሉ አብነትነት ነው። መማር ዓለምን አልፎ ፕላኔቶችን መመርምር ማለት ነው። መማር መሰልጠን ነው። ተፈጥሮን መተርጎም ማለት ነው። የሰው ልጅ ውበትን አድንቆ በውስጡ መኖር እንጂ የዚህ ተጻራሪ ሆኖ በአንድ እግር ተንጠልጥሎ መቆም መማር አይደለም።  የጉም ሽንት ዓይነት ልበለው ….  እራሱን መተርጎም የተሳነውም – ወይንም እራስን ለመተርጎም አስተርጎሚ ተበዳሪ እሳቤ -  እንደ ሥርጉተ ማህይምነት በስንት እጁ ጣዕሙ -

 

እርግጥ ነው ወያኔ ከሥሩ እስኪነቀል ድረስ ተጓዳኝ የትግሉ ዘርፎች ይዘለሉ ማለት አይደለም። ወያኔ ያበቀላቸው እሾኾች ሁሉ በተገኘው አጋጣሚ መነቀል አለባቻው። የተሟላና የተደራጀ የህሊና ሥራም መሰራት አለበት። በግንባር ያሉ ፈተናዎችን ከእግር እግሩ እዬተከተሉ እዬተነተኑ እርቃኑን ማስቀርት – ማደረቅ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ዘላቂ ፍላጎትን ለማሟላት እራስን አሸንፎ በታቀደ፤ ህዝብን መሰረት ባደረገ፤ ነገ ከመምጣቱ በፊት ለምልሞ እንደሚጣ በሚያደረግ በተጠና መርኃ ግብር በቋሚነትና በተከታታይነት ሥራ ላይ መገኘት ያስፈልጋል።

 

ከውና – አንድ ነገር ወያኔ በለኮሰ ቁጥር ከዋናው ፍላጎት በመውጣት፤ ወይንም በደራሽ ችግሮች ላይ አትኩሮ ዋናውን ፍላጎት የሚሻውን ትኩረት ሆነ አቅም መንፈግ የተገባ አይደለም። ለአንድ መንገድ የተለያዩ ስልቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ግን ተቀናጅተው አንዱ የዘለለውን ወይንም ያላዬውን ሌላው ክፍቶቹን እዬሞላ እዬተደጋገፉ እኛኑ ሊውጠን ካሰፈሰፈው የጠላት ሁለገብ ሴራ እራስን ማዳን ዬቅድሚያ ትንፋሻችን ብቻ ሳይሆን መንፈሳችን ሊያርፍበት ዬሚገባው ዓይናማ አመክንዮ ሊሆን ይገባል እላለሁ። ለይደር የሚቀጠር ምንም ነገር የለም። አዳሩም ሞት ውሎም ሞት፤ አዳሩም ጥቃት ውሎም ጥቃት። አዳሩም ወርደት ውሎም ውርደት። ስለሆነም ሰቅስቆ ከሥሩ አረምን ማስወገድ፤ ማሳን አለስልሶ ቡቃዮዎችን ማስበል …. ከሁሉ በላይ የነፃነት ትግል ሰብዕዊነትን ይጠይቃል። ሰማዕታት ሲታሰቡም እራስን ከእሥር መፍታት በአጽህኖት አብዝቶ ይጠይቃል። በስተቀር የትውፊት ተደሞ ይታዘበናል። ። ልብ ያለው ሽብ። የኔዎች እኔ እንዲህ ታይቶኛል። ከክብሮቼ ጋር ውስጤን እንዲህ አውጥቼ ከመግለጽ በላይ ገነት የለም። አመሰግናችኋለሁ – በፍቅር። ኑሩልኝ።

 

እራሳችን የምናዳምጥበት አቅም አምላካችን ይስጠን። አሜን!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

የትግራይ ህዝብ የወያኔ ስርአት ተጠቃሚነው! (አንዷለም አስራት )

$
0
0

ከአንዷለም አስራት Andasr1983@gmail.com

Tigray_in_Ethiopia.ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ በቅርቡ የማከብራቸውና የሶስት አፋኝ መንግስታትን ጭቆና ከህዝብ ጫንቃ ላይ ለማንሳት እየታገሉ ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እና የአረና ትግራይ አባል የሆነው አብርሃ ደስታ የትግራይ ህዝብ የወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ እንዳልሆነ ለማስረዳት የሞከሩት ስህተት መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ አገልግሎት፣ በመሰረተ ልማትና በልማት ባለፉት 23 አመታት በአንጻራዊነት ከሌሎች ክልሎች በተሻለ ሁኔታ ተጠቃሚ እንደሆነ ለማስረዳት እሞክራለሁ። ይህን ስል የትግራይ ህዝብ አልፎለታል ፤ በልጽጓል፤ ከድህነት ወጥቷል እያልኩ ሳይሆን ህዋሃት በሚያደርገው በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አድልኦ ምክንያት ከሌሎች ክልሎች የተሻለ የስራ እድል ተፈጥሯል ፤ የተሻሉ የአገልግሎት ተቋማት አሉ፤ እንዲሁም ከፍ ያለ የገንዘብ ፍሰት አለ ይህም የሆነው የሌሎችን ክልሎች ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ነው የሚለውን ለማስረዳት ነው። ከመጀመሪያው ማስረገጥ የምፈልገው ግን ለወያኔ ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም።

1. በፖለቲካ

ወያኔ በትግራይ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው ፣ የወያኔን ዓላማ የማይደግፍ ትግረኛ ተናጋሪ በጣም ጥቂት እንደሆኑ ይታዎቃል፡፡ አብዛኛዎቹ ትግርኛ ተናጋሪ የህዋሃት ተቃዋሚዎች አላማውን ሳይሆን ግለሰቦቹን የሚጠሉ መሆናቸው የታዎቀ ነው፡፡ እነ ገብሩ አስራት ፣ ስየ አብርሃ ፣አረጋዊ በርሄ የመሳሰሉት ከወያኔ የተለዩት አላማውን ጠልተው ሳይሆን መለስ ዜናዊና መሰል አምባገነኖችን በመጥላት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ አንጋፋው ገብረ መድህን አርአያ ግን የወያኔን አላማ የማይቀበል እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ሁኖም የሁሉንም ትግርኛ ተናጋሪዎች የፖለቲካ አቋም አውቃለሁ ብየ አልታበይም ሌሎችም የወያኔን እኩይ ተግባር የማይደግፉ ይኖሩ ይሆናል ግን አብዛኛው ደጋፊ መሆኑ አሊ አይባልም።

ስለዚህም ወያኔ የትግርኛ ተናጋሪ ምሁራንን ሙሉ አቅም በሁሉም የስራ መስኮች ይጠቀማል፣ ኢትዮጵያ እንደ አዲስ በክልል ከተዋቀረችበት ጊዜ ጀምሮ የትግራይ የተለያዩ ቢሮዎች በአንጋፋና የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው የቢሮ ሃላፊዎች ሲመሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚሁ ምሁራንም የውስጥ ነጻነታቸው የተጠበቀ በመሆኑ በሙሉ አቅም ይሰራሉ፡፡ በተቃራኒው የሌሎች ክልሎች ተዎላጅ የሆኑ አብዛኛዎቹ ምሁራን የወያኔን አላማ ከመጀመሪያው የተጸየፉ በመሆናቸውና ወያኔም ገና ከጅምሩ በጣላቻና በጥርጣሬ ስላያቼውና እንዲጠጉ ስላልፈለገ በተለጣፊ ድርጅቶች መዋቅሮቹ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ በዚህም ምክንያት በሌሎች ክልሎች ከክልል አስተዳዳሪዎች ጀምሮ ትምህርትም ፣ብቃትም፣ ልምድም የሌላቼውና ጠርናፊ ወያኔዎች ሲጠሩዋቸው አቤት ሲልኳቸው ወዴት የሚሉ ፣ ታማኝነታቼውንም ለማሳየት የተሻለ ነገር ከመስራት ይልቅ በሚገዙት ህዝብ ላይ ቀንበር የሚያጠቡ ደካሞች ክዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ስልጣን ተሰግስገውበታል፡፡ ለዚህ አለምነው መኮንን አይነቶችን እንደምሳሌ ማየት ይቻላል፣ አለምነው መኮንን መለስ ዜናዊን ያመልክ እንደነበር ይነገራል ፣አለቆቹ የመለስን ራእይ ማስቀጠል ሲሉ ሰምቶ እሱም ራሱን ጭምር አይሰድቡ ስድብ ሰደበ፡፡

ስለዚህም ትግራይ የተሻለ ትምህርት፣ ልምድ፣ ብቃት፣ ዝግጁነት እና ሙሉ ስልጣን ባላቸው ሰዎች የሚተዳደር ክልል እና ህዝብ በመሆኑ ተጠቃሚ ነው፡፡

በአንጻራዊነት መልካም አስተዳደርም አለ ማለት ይቻላል፤ ፖለቲካውን እስካልነካ ድረስ ማንኛውም ትግራዊ በትግራይ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ክልሎችም አቅሙ የፈቀደውን ይሰራል። አሁን ያለው የፖለቲካ ስርአት ቢቀየር የትግራይ ህዝብ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ምናልባት አምልካከታቸውን ቀይረው ዲሞክራቶች ይሆናሉ ብለን እናስብ እንደሆነ እንጅ የተለዩ ሰዎች ያገኛል ብየ አላስብም ፤ ምክንያቱም የአረናና የህዋሃት ልዩነት የግለስቦች ጸብ ብቻ ነው ብየ አስባለሁ።

በኢኮኖሚ

ሀ. በኢትዮጵያ በጣም ሀብታሙ ድርጅት ኢፈርት ነው፣ ኢፈርትም ትግራይ ውስጥ ከሃያ በላይ ግዙፍ ድርጅቶች አሉት፣ የነዚህ ድርጅቶች ክፍተኛ ገቢ የት እንደሚገባ መረጃው ባይኖረኝም እነዚህ ድርጅቶች ግን በጣም ብዙ የስራ እድል ትግራይ ውስጥ ከፍተዋል፣ ብዙ የትግራይ ወጣቶች በትግራይ ውስጥም ሆነ ከትግራይ ውጭ የዚህ ህገውጥ ድርጅት ተቀጣሪ በመሆን የሌሎች ክልሎች ወጣቶች ያላገኙትን እድል አግኝተዋል፡፡ በነገራችን ላይ የኢፈርት የገንዘብ ምንጭ በጦርነቱ ወቅት ከወሎ፣ ከጎንደር፣ ከጎጃምና ከወለጋ አካባቢዎች የተዘረፈ ገንዘብና እንዲሁም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ልማት ባንክ በትእዛዝ የተወሰደና ከጊዜ በኋላ እንዲሰረዝ የተደረገ ብድር ነው፡፡ በሌሎች ክልሎች የሌሉ በርካታና ብዙ ቢሊዮን ብር ኢንቭስት ያደረጉ ድርጅቶች የስራ እድል ሲፈጥሩ የክልሉ ህዝብ አልተጠቀመም ማለት አይቻልም።

ለ. ህወሃት በጠባብ አላማው ከጎንደርና ከወሎ በጣም ሰፊ ለም የእርሻ መሬት ዘርፏል፣ ይህንንም የእርሻ መሬት ለአባላቱና ሌሎችም የትግራይ ተዎላጆች ብቻ አከፋፍሏል፣ እንዲሁም በርካታ የትግራይ ገበሬዎች በነዚህ ለም መሬቶች ሰፍረዋል፣ እነዚህ መሬቶች ቀደም ሲል በሌሎች ሰዎች የተያዙና የሁመራ አካባቢ ደግሞ የመንግስት እርሻ የነበረ ነው፡፡ ይህንኑ የዘረፈውን መሬት ህጋዊነት ለማረጋገጥ ይመስላል ወያኔ በተለይ በወልቃይት አካባቢ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካሂዷል፣ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፣ ታፍነው ተወስደው የደረሱበት አይታዎቅም፡፡ በነዚህ መሬቶች መወሰድ ምክንያት በርካታ የጎንደር ስዎች ተፈናቅለዋል፤ ተጎድተዋል፡ የትግራይ ሰዎች ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቅመዋል።

ከዚህ ጋር የተያያዙ በተለይ በሁመራ አካባቢ የተደረጉ ሶስት ነገሮችን ልጥቀስ፤

በተፈጥሮ በተራቆቱ የጎንደርና የወሎ አካባቢዎች የሚኖሩ ገበሬዎች በቂ የእርሻ መሬት ስለሌላቸውና በለም አካባቢዎችም መስፈር ስለማይፈቀደላቸው ወደሁመራ አካባቢ እየሄዱ በቀን ሰራተኛነት ህወሃትን ያገለግላሉ፣ እነዚሁ ድሆች ከደጋው አካባቢ የመጡ፡በመሆናቸው ለወባና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎች በቀላሉ ይጋለጣሉ፣ መጀመሪያም እንደሰው የማይቆጥሯቸው የትግራይ ባለሃብቶችም ሲታመሙ አውጥተው ይዎረውሯቸዋል በርካቶችም በዚህ ሁኔታ ይሞታሉ፡፡ ይህን ሪፖርት ያደረገው በጊዜው በቦታው እርዳታ ይሰጥ የነበር የ MSF ሰራተኛ ፈረንጅ ነው። በጊዜው ሰው እንዴት በሰው ላይ እንደዚያ እንደሚጨክን በግርምት ያውራ ነበር። እንደዚህ አይነት ሰዎች ወደሁመራ ለስራ መሄድ በደርግ ጊዜም የነበረ ሲሆን በዚያን ጊዜ ግን በቂም ባይሆን እንደሰው ህክምና የማግኘት እድል ነበራቸው፡፡

ሌላው ባለፈው አመት በሚድያ እንደተነገረው በህዋሃት ካድሬዎች ደባ የቀን ሰራተኞቹ የወሎና የጎንደር በሚል በቡድን ተከፋፍለው ለሳምንታት ሲጨራረሱ የአካባቢው ፖሊስም ሆነ የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ግጭቱን ለማስቆም አጥጋቢ እርምጃ አልወሰዱም፡፡

ሶስተኛውና ከአመት በፊት ከስፍራው ከመጣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረ ወጣት የተገለጸው የቀን ሰራተኞቹ የሰሩበት ደመዎዝ ተከፍሏቸው ከወያኔ እርሻዎች ሲወጡ በቅርብ ርቀት በሽፍቶች በተደጋጋሚ መዘረፋቸው ነው፣ በኋላ የቀን ሰራተኛ የነበረው ይህ ወጣት ያረጋገጠው ነገር ቢኖር ግን በሽፍታ መልክ መልሰው የሚዘርፉትም ቀደም ሲል ደመወዝ ከፋይ የነበሩት የእርሻዎቹ ባለቤቶች የሆኑት የህዋሃት ካድሬዎች ናቸው፡፡

በሶስቱም መንገድ የህዋሃት ካድሬዎች በነጻ ጉልበት ስራቸውን ያሰራሉ፡፡ ድሆቹ ገበሬዎች ደግሞ ወደቤተሰባቸው የመመለስ እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ብዙዎቹ በበሽታና በእርስ በርስ ድብድብ ያልቃሉ ቀሪዎቹም በተደጋጋሚ የሰሩበት በቀጣሪዎቹ ስለሚዘረፍ ወያኔ ያዘጋጀላቸውን የባርነት ኑሮ ይቅጥላሉ።

ሐ. በኢትዮጵያ የወታደራዊ (90% በላይ የኢትዮጵያ ጀኔራሎቹ ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው)፣ የደህንነት፣ የጉምሩክ፣ የኢምባሲ፣ የቴሌ፣ የመብራት ሃይል፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር በተለይ በክፍለ ከተማና በወረዳ (አብዛኛዎቹ የአዲስ አበባ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው) ፣የአየር መንገድ፣ የፖስታ ቤት፣ የስኳር ፋብሪካዎችና ሌሎችም በፌደራል መንግስት ስር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ቁልፍ ቦታዎች በአብዛኛው የተያዙት በትግርኛ ተናጋሪዎች ነው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የእርዳታ ድርጅቶች የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ትግርኛ ተናጋሪዎችን በብዛት እንዲቀጥሩ እየተደረገ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሰዎች የሚመጡት ከትግራይ ነው ስለዚህም ትግርኛ ተናጋሪዎች ከሌላው ክልል ተወላጆች የበለጠ የስራእድል አላቸው ማለት ነው፡፡ እነዚህ አዲስ አበባን የሰማይ ጠቀስ ፎቆች ባለቤት ያደረጓት ጀኔራሎች ትግራይ ውስጥ ምንም ኢንቭስት አያደርጉም አይባልም፡፡ የየመስሪያቤቶቹን ቁንጮ ስልጣን የያዙት ትግረኛ ተናጋሪዎች በክልላቸው ኢንቨስት አያደርጉም ማለት ዘበት ነው። በአንድ ወቅት “አዲ በግዲ” ተብሎ ሁሉም ከትግራይ ውጭ የሚኖር የክልሉ ተዎላጅ በትግራይ ከተሞች ቤት እንዲሰራ ተደርጎ እና በርካታ ቤቶች ተሰርተው ተከራይ ጠፍቶ እንደነበር ይታዎሳል።

መ. የትግራይ ተወላጆች በፈደራል መንግስትና በሌሎችም ቦታዎች ባላቸው ስልጣን ተጽኖ በማድረግ በርካታ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ትግራይ ውስጥ ፕሮጄክት እንዲኖራቸው ይታዘዛሉ አንዳንዶችም ፕሮጄክቶቻቼው በቀና መንገድ እንዲሄዱላችው ቀድመው ትግራይን ይመርጣሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ትግራይ ውስጥ ቅርንጫፍ የሌለው፡የውጭም፡ሆነ የአገር በቀል ድርጅት ጥቂት ነው ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ ትግራይ ውስጥ ደግሞ ማንም የውጭ ሆነ የአገር ውስጥ ድርጅት የሌላ ክልል ተወላጅ መቅጠር አይታሰብም ቋንቋ እንደምክንያት ይቆጠራል፤ በተቃራኒው የትግራይ ተዎላጆች በሌሎች ክልሎች ውስጥ በብዛት ይሰራሉ።

2. በማህበራዊ አገልግሎት

የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲወዳደር የተሻለ የትምህርትና የጤና አገልግሎት ያገኛል፣ በምሳሌ ላስረዳ ወያኔ ብዙ ያዎራለትን የጤና አገልግሎት ብናይ በ2000 አ. ም እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሪፖርት በትግራይ ለሚኖር 4.5 ሚሊዮን ህዝብ 15 ሆስፒታሎችና 123 ጤና ጣቢያዎች ይህም ለ304333 ህዝብ አንድ ሆስፒታልና ለ37113 ህዝብ አንድ ጤና ጣቢያ ሲሆን በአማራ ደግሞ ለ20.1ሚሊዮን ህዝብ 20 ሆሰፒታሎችና 183 ጤና ጣቢያዎች ይገኛሉ፡ ይሕም አንድ ሆስፒታል ለ1ሚሊዮን ህዝብ እና አንድ ጤና ጣቢያ ለ110636 ህዝብ ይደርሳል፡፡ ይህ ቁጥርን በሚመለከት ሲሆን በአማራ ክልል ያሉት ሆሲፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በመስፈርቱ መሰረት የተሟላ አገልግሎት የሚሰጡ ሳይሆኑ የተሾሙ ናቸው [የተሾሙ ማለትም በወያኔ ሹመት ብቃት ስለማይጠይቅ ያለብቃታቸው ለፖለቲካ ጠቀሜታ የተሰየሙት ጤና ድርጅቶችና ትምህርት ቤቶች የተሾሙ ይባላሉ]በዚህ በወያኔ ዘመን የሚአርጉ ድርጅቶችም እንዳሉ ስነግራችሁ የቀልድ ይመስላችሁ ይሆናል፣ የአረጉ ማለት ያልተሰሩ ግን እንደተሰሩ ተደርገው ሪፖርት የሚደረጉና እንደተሰሩ ተደርጎ የወጣው ገንዘብም በየደረጃው የሚወራረድ ማለት ነው፡፡ ከጥቅሙ ተካፋይ ያልነበረ ተቆጣጣሪ ሲመጣ ድርጅቱ ማረጉ ይነገረዋል፡፡

3. በመሰረተ ልማት

ትግራይ በመሰረተ ልማት ማለትም በመንገድ ፣ በቴሌኮሙኔኬሽን ፣ በመብራት ከሌሎቹ ክልሎች በተሻለ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በቅርቡ ሪፖርተር የሚገርም ዜና አውጥቷል አንድ ትግራይ ውስጥ ለሚሰራ መንገድ ሱር ኮንስትራክሽን የ2ቢሊዮን ብር ውል ፈረመ የመንገዱ ርዝመት 53ኪሚር ሲሆን ለአንድ ኪሎ ሜትር 40ሚሊዮን ብር ይከፈለዋል፡፡ እስካሁን በአገሪቱ ለኮንትራክተር የተሰጡ መንገዶች በኪሎሜትር ከ20ሚሊዮን አይበልጥም ነበር ይላል፡፡

4. በልማት

ባለፉት 23 አመታት ትግራይ ውስጥ በአድዋ፣ አዲግራት ፣ መቀሌ ፣ ማይጨው በርካታ ፋብሪካዎችና የአገልግሎት ሰጭ ትቋማት ተሰርተዋል እነዚህም ድርጅቶች ለብዙ ሰዎች የስራ እድል ፈጥረዋል፡፡

ከዚህ በላይ የቀረቡት መረጃዎች የሚያሳዩት ትግራይ ውስጥ የተሻለ መሰረተ ልማት ፣ ማህበራዊ አገልግሎትና በጣም የተሻለ የሰራ እድል መኖሩን ነው፡፡ ወያኔ ማእከላዊ መንግስቱን በመቆጣጠሩ ለወጣበት ክልል ልጆች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡ ወያኔ ለትግራይ ወጣቶች ያመጣላቼው ግን የተሻለ የስራ እድልና ገንዘብ ብቻ አይደለም፤ በየሄዱበት በጥርጣሬ መታየትን በአንዳንድ ቦታም መጠላትን ጭምር እንጅ።

ይህ የወያኔ አንድን ክልል ለብቻው ሌሎችን ክልሎች በሚጎዳ መልኩ ለማሳደግ የሚደረግ ጥረት ፍሬ እያፈራ ነውን? የሚል ጥያቄ መጠይቃችን አይቀርም። መልሱ አዎ የትግራይ ህዝብ የተሻለ የትምህርት ደረጃ ፤ ዝቅተኛ የስራ አጥ ቁጥርና በተለይ በህጻናት ሞት ዝቅተኛ መጠን አስመዝግቧል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2011 በአሜሪካ የእርዳታ ድርጅትና በማእከላዊ ስታቲስቲክስ ድርጅት በተደረገ የህዝብና የጤና ጥናት (Demographic and health survey) መሰረት ክጥናቱ በፊት ባሉት 12 ወራት ውስጥ ምንም ስራ ያልሰሩ ወይም ያልተቀጠሩ ሴቶች በመቶ ሲለካ በትግራይ 24.8%፣ በአማራ 38.4%፤ በኦሮሚያ 43.9% ና በደቡብ ህዝቦች 44.8% ነበር። በተመሳሳይ ጥናት መሰረት በእርግዝናቸው ጊዜ በሰለጠነ ባለሙያ ምርመራ የተደረገላቸው እርጉዞች በመቶ የሚከተለውን ይመስል ነበር፤ ትግራይ 50.1% ፤ አማራ 33.6% ፤ ኦሮሚያ 31.5% ፤ የደቡብ ህዝቦች 27%. ከዚህ ላይ የትግራይም ሽፋን ቢሆን በቂ ነው ማለት አይደለም ግን ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲውዳደር ከፍተኛ ነው።

በተመሳሳይ ጥናት መሰረት ክትባት የተከተቡ ህጻናት በመቶ ትግራይ 73.4%፤ አማራ 38.4%፤ ኦሮሚያ 26.8% ና ድቡብ ህዝቦች 38.1% ነበር።

በዚሁ ጥናት መሰረት ከአንድ አመት በታች የሆኑ ህጻናት ሞትና (IMR) ከአምስት አመታት በታች ባሉ ህጻናት የሞት መጠን በሚቀጥለው ሰነጠረዥ ቀርቧል

Tigray region got better

ከዚህ በላይ እንደሚታየው ትግራይ በሁሉም መለኪያዎች የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል። ትግራይ በ 2005 የደረሰበት ደረጃ ሌሎቹ ክልሎች በ2011 ማለትም ከ5 አመታት በኋላም አልደረሱም ፤ በሌላ አነጋገር ሌሎቹ ክልሎች ትግራይ የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ከ7-8 አመታት ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው።

በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ውስጥ አንድ ቀልድ አለ እሱም ቀደም ሲል አንድ ወጣት ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ? ሲባል ፓይለት ፤ ዶክተር ማለት የተለምደ ነበር፤ ያሁኑ ወጣቶች ግን ምን መሆን ትፈልጋለህ ሲባሉ ቶሎ ብለው “ትግሬ” ይላሉ። አሁን ባቋራጭ ሀብታም የሚያደርገው ፓይለትነት ወይም ዶክተር መሆን ሳይሆን ከገዥ ጎሳ መወለድ በመሆኑ ነው።

ለማጠቃለል ያህል በሁሉም መስፈርቶች የትግራይ ክልልም ሆነ ግለሰብ ትግርኛ ተናጋሪዎች የወያኔ ከፋፍለህ ግዛ ስርአት ተጠቃሚዎች እየሆኑ ነው ይህም እንዲቀጥል ወያኔ ሌሎች ክልሎች ብቃት ባላቸው ሰዎች እንዳይተዳደሩና ለእድገት ጥረት እንዳያደርጉ ሌሊት ከቀን ተግቶ ይሰራል። የክልል ፕሬዘዳንቶችን ይሽራል፤ ይሾማል፤ ይቆጣጠራል። ህዝብን ከህዝብ ያጋጫል ፤ ያፈናቅላል። ሲፈልግ አመጽ ያስነሳል፤ አመጹን ልቆጣጠር በማለት ይገድላል ፤ ያስራል፤ ከስራም ያፈናቅላል።

የዚህ ሁሉ ግፍ ቁናው ሞልቶ ዶክተር መረራ በተደጋጋሚ እንደሚሉት የሚበላው ያጣ ህዝብ መሪዎቹን ሳይበላ ሊታሰበብት ይጋባል እላለሁ።

ቸር ይግጠመን።

አባይን እነማን መቼ ይገድቡት?

“ነጻነትነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም!”

$
0
0

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች ያስተላለፈው ግልጽ መልዕክት

የተወደዳችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤

Obangበቅድሚያ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የአክብሮት ሰላምታ በማቅረብ በትግሉ መስክ የምትከፍሉትን መስዋዕትነት የሚያደንቅ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ምህዳሩ እጅግ ጠብቦ የለም የሚባልበት ደረጃ በደረሰበት ወቅት በምታገኙት ስንጥቅ ሁሉ እየተጠቀማችሁ ለህዝባችሁ የብርሃን ጭላንጭል ስለምትፈነጥቁ አኢጋን ሥራችሁን ያደንቃል፤ ያከብራል፡፡ እኛ በሥራችሁ ስኬት የምንመኘው ለቆማችሁለት የፖለቲካ ዓላማ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት አቅቷቸው መፈናፈኛ ላጡትም የመወሰን ኃይል እንደምትሰጧቸው በማመን ነው፡፡

አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ የበርካታዎች ጥያቄ “ህወሃት/ኢህአዴግን በምን ዓይነት የተሻለ አስተዳደር እንዴት መለወጥ ይቻላል የሚለው ነው?” ይህ ጥያቄ “እኛ ኢትዮጵያውያን የዘርና የጎሣ ትንንሽ አጥሮቻንን አፍርሰን ሁሉን አቀፍ ትግል ለማድረግ ተዘጋጅተናል ወይ?” ብለን ራሳችንን መልሰን አንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ እንዲሁም ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠት ሁሉም ነጻ ሳይወጣ ራሳችንን ነጻ ለማውጣት እንችላለን ወይ? ብለንም እንድንጠይቅ የሚያስገድደን ነው፡፡ …

ሽንፈት ላይ እያተኮሩና የጠላትን ኃይለኛነት እየሰበኩ ድል አይገኝም፡፡ ልዩነትን እያራመዱ ኅብረትና አንድነት ተግባራዊ መሆን አይችልም፡፡ ለአገራዊ ዕርቅ እንሰራለን እያሉ በፓርቲ መካከል ከዚያም በታች በግለሰብ ደረጃ መተራረቅ ካልተቻለ ብሔራዊ ዕርቅ ከቀን ቅዠት አያልፍም፡፡ እያንዳንዳችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ፣ መኢአድ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ ኦህኮ፣ አረና፣ እና ሌሎች እጅግ በርካታ ፓርቲዎች የተቋቋማችሁትና ዓላማ ያደረጋችሁት ኢህአዴግን እየተቃወማችሁ ለመኖር እንዳልሆነ የፓርቲ ፕሮግራማችሁ ይመሰክራል፡፡ ወይም ዓላማችሁ የራሳችሁን የፓርቲ ምርጫ የማድረግና ፕሬዚዳንት (ሊቀመንበር)፣ ምክትል፣ ሥራ አስፈጻሚ፣ … በመምረጥ አዙሪት ውስጥ ራሳችሁን ላለማሽከርከር እንደሆነ ከማንም በላይ ራሳችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ከዚህ አንጻር በጥንቃቄና በብዙ ጥናት የተቀመጠው የፓርቲያችሁ ፕሮግራምና ዓላማ ለአገራችን አንዳች ለውጥ ሳያመጣ እንደዚሁ እንዳማረበት ቢቀመጥ ለሕዝብ የሚያመጣው ትርፍ ምንድርነው? እናንተንስ ለመቃወም ብቻ የምትሰሩ አያደርጋችሁምን? … (ሙሉውን መልዕክት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)


የሕዳሴ አብዮት አተገባበር! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )

$
0
0

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ)

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከታታይ ባቀረብኳቸው ጽሑፎች ገዥው-ግንባር የመረጠው ስሁት መንገድ፣ ኢትዮጵያችንን ለሳልሳዊው አብዮት እያዘጋጃት መሆኑን ማውሳቴ ይታወሳል፡፡ ይህ የለወጥ መስመርም “የሕዳሴ አብዮት” የሚል ስያሜ ኖሮት፣ ሁሉን አሳታፊ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ንቅናቄ በመፍጠር አገሪቱን በዳግም
ውልደት ለማንፃት ብቸኛ አመራጭ የመሆኑ ጉዳይ በስነ-አመክንዮ ተሰናስሎ ቀርቦበት ነበር፡፡ በዚህ ተጠየቅ ደግሞ አብዮቱን ከዳር ለማድረስ ሊተገበሩ የሚችሉ (በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ) ስልቶች እና በመጀመሪያው የንቅናቄው ምዕራፍ ሥርዓቱ ለመመለስ ሊገደድባቸው የሚገቡ ጥያቄዎችን እንዳስሳለን፡፡

ለምን እንሞታለን?

የዓለም ታሪክ አምባ-ገነኖች እብደታቸውን እንዲተገብሩ የሚያስችላቸው የታጠቀው ኃይል (ጦር ሠራዊት፣ ደህንነት እና ፖሊስ) ስለመሆኑ አያሌ ማሳያዎችን ዘርዝሮ ያስረግጣል፡፡ የኢትዮጵያችን የቅርብ ጊዜ ታሪክንም ብንመለከት፣ የአፄ ኃይለስላሴ ጨቋኝ አስተዳደርን ግማሽ ክፍለ ዘመን አፋፍ ድረስ ተሸክመው የተጓዙት እነዚህ ኃይሎች መሆናቸው ጉዳዩን አምነን እንድንቀበል ያስገድደናል፡፡ የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በላኤ-ሰብ ዘመን በታሪክነት ተመዝግቦ ለመታወስ የቻለውም ይህንኑ ክፍል አጥብቆ በመያዙ መሆኑ የትላንት ክስተት ነው፡፡ ባለፉት ሁለት አስርታት ያስተናገድነው የኢህአዴግ ብልጣ ብልጥ አምባ-ገነን አስተዳደርም ከከፋፍለህ-ግዛ ስልቱ በተጨማሪ ዋና መሰረቱ ጠብ-መንጃ አንጋቹ አካል ለመሆኑ ይህ ትውልድ የአይን እማኝ ነው፡፡ አዲሱ የሕዳሴ አብዮታችንም በዚህ ኃይል ላይ ትኩረት ያደርግ ዘንድ የተገደደበት መግፍኤ ይኸው ነው፡፡

ከግፉአኑ (ከጭቁኖቹ) አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊት ‹‹ተኩስ!?›› ተብሎ በታዘዘ ቁጥር ስለምን አምሳያው የመከራ ተቸንካሪ ላይ ሁሌ ጥይት እንደሚያዘንብ እጅግ ግራ አጋቢ ነው፡፡ እውን የህፃናትን ግንባር የሚበረቅሰው፣ እህት-ወንድሙን አነጣጥሮ የሚጥለው ሥርዓቱን ተቀብሎት፣ ትዕዛዙንም አምኖበት ነው ወይ? በጉልበትም ሆነ በሥነ-ምግባር ከሚልቃቸው ግለሰቦች የሚተላለፍለትን መመሪያ እየተገበረ ሰጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛው የግል ጥቅም አመዝኖበት? ወይስ ለአለቆቹ የዘፈቀደ ተግባር ሎሌ ሆኖ? …የደህንነት መ/ቤቱ አባላትስ እንዲህ ታች ወርደውና አጎንብሰው የፓርቲ አገልጋይ የመሆናቸው ምስጢር ምን ይሆን? ከገዥው-ግንባር የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ድርጅቶች ቢሮ፣ አመራሩን እና ጋዜጠኞችን በመሰለል መጠመዳቸው የ‹‹እንጀራ›› ጉዳይ ብቻ ሆኖባቸው ነውን? ንፁሀንን በጠራራ ፀሀይ ሳይቀር አፍነው ለስቅየት አሳልፈው እንዲሰጡ የተገደዱበት መነሾስ ምንድር ነው? …የፖሊስ ሠራዊትስ የሥርዓቱ የማጥቂያ መሳሪያ በመሆን እንዲህ ማዕረጉን አቅልሎ ለሀፍረት የተዳረገበት ጉዳይ በማን እርግማን ይሆን? …እኮ ለምንድር ነው የእነርሱንም ጭምር ነፃነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያውጅ ጥያቄ ባነሳን ቁጥር ደማችንን ደመ-ከልብ የሚያደርጉት?

እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሰፊ ጥናት የሚጠይቅ መሆኑ ሳይዘነጋ፣ የንቃተ ህሊና ማነስ እና ነፍሰ-ገዳይን አወዳሹ ነባር ባሕላችን ከገፊ- ምክንያቶቹ መካከል ስለመጠቀሳቸው ለመናገር ግን የምሁራን ትንተና የሚያስፈልገው አይመስለኝም፡፡ ከዚህ አኳያም ሕዳሴን መሰረት የሚያደርገው አብዮታችን ከትኩረት ማዕከሉ ቀዳሚ አድርጎ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳና የንቃት ሥራ በመስራት፣ ባለፉት ዘመናት የጭቆናው አስፈፃሚ ሆኖ በታሪክ ጥቁር መዝገብ የሰፈረውን ታጣቂ ኃይል፣ ወደ ተባባሪነት (ሕዝባዊነት) መለወጥ እንደሚኖርበት ተረድቶ መፍትሔ ካላበጀለት በታሪክ ፊት ከሥሉስ ውድቀቱ የሚታደገው አይኖርም፡፡ በአናቱም አብዮቱ ክብሩን ሊመልስለት እንጂ፣ ነቅንቆ ሊበትነው የተነሳሳ እንዳልሆነ ታጣቂ ኃይሉን ማሳመን የእኛ ዓብይ ተግባር ነው፡፡ እነርሱ አንድም በኑሮ ውድነት፣ ሁለትም ነገን በመስጋት ስር እንዲያድሩ ተቀይደው ነጻነታቸውና መብታቸው የተገፈፈ የመሆኑን እውነታ አስረግጦ ነግሮ ከሕዝብ ጎን በመቆም ሚናቸውን ይወጡ ዘንድ ማግባባት አብዮታዊ ግዴታ ለመሆኑ ነጋሪ አያሻም፡፡ ከለውጡ በኋላም ሠራዊቱ ከአገር አለኝታነቱ በዘለለ፣ ከአድሎአዊነትና ከእርስ በርስ (ከዘውጋዊ) ጥላቻ በፀዳ ፍትሓዊ አስተዳደር ተጠቃሚ የመሆኑን ጉዳይ ማሳመኑ በቀውጢው ሰዓት ወሳኝ ድጋፍ ለማግኘት ጠቃሚ ነው፡፡ የጥቂት ጀነራሎች የሙስና ወንጀልም፣ አቻ ባልደረቦቻቸውንም ሆነ መላ ሠራዊቱን የሚወክል አለመሆኑን ከዘለፋ በራቁ ጨዋ ቃላት መወትወት ጉልህ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ይህን ታላቅ ተልዕኮ ለማሳካት በተለይም የአዛዦቹም ሆነ የተራው ወታደር ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ ጓደኞች፣ ዘመድ-ወዳጅ ወገኖች ቀዳሚውን ኃላፊነት መሸከም ይጠበቅባቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡

የትግሉ ስልቶች…

‹‹የከፋ ጭቆና ቢኖርም ሥርዓቱን የተሸከሙት ብዙ ሰዎች ለረጅም ጊዜ ትብብር ከነፈጉት ጨቋኙ አገዛዝ ተዳክሞ በመጨረሻ መውደቁ አይቀርም›› የሚለው ጄን ሻርፕ፤ የትብብር መንፈግ ፅንሰ-ሀሳብን የሰላማዊ ተቃውሞው ዋነኛው የትግል ማዕከል አድርጎ ያቀርበዋል፡፡ ለዚህ ስልት መተግበር ሀሳብን የማሰራጫ መንገዶች ያስፈልጋሉ፡፡ በይፋ የማይታወቁ የትግሉ መሪዎች/ቡድኖች፣ ሐሳቡ ጨቋኞቹን ለመጣል በሚካሄደው መሬት አንቀጥቅ አብዮት ላይ እንዴት ከፍተኛ ሚና ሊኖረው እንደሚችል፣ ለማሕበረሰቡ ማስገንዘብ ይገባቸዋል፡፡ ይህን ማሕበረሰባዊ ጠንካራ መረዳት ለመፍጠርም፣ በራሪ ጽሑፎችን፣ ማሕበራዊ ድረ-ገፆችን፣ ሕብረ-ዜማዎችን፣ አጫጭር አነቃቂ ፊልሞችንና የሞባይል ስልክ መልዕክት መለዋወጫ ዘዴዎችን ጨምሮ የተለያዩ የምስልና የድምፅ ሚዲያዎችን ማመቻቸት (መዘርጋት) ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነዚህ ከግብፅ እስከ ዩክሬን ተሞክረው የተሳኩ አማራጮችን በኢትዮጵያችንም ለመተግበር፣ በሚገባ መደራጀትና በኃላፊነት መስራት በእጅጉ አስፈላጊና ግዴታ የመሆኑ ጉዳይ አያከራክርም፡፡ እንዲሁም ከሕዝበ-ሙስሊሙ የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የተፈተነ እንቅስቃሴ ስኬታማ ተሞክሮዎችን ማጎልበትና ወደ ፖለቲካዊው ተቃውሞ መቀላቀል እንደሚቻል መዘንጋት የለበትም፡፡ የአደባባይ ተቃውሞ የሚፈቅደውን ሕገ-መንግስታዊ መብት በምልአት አንጠፍጥፎ መጠቀም ለሰላማዊ ትግሉ ዋነኛ መሰረት እንደሆነ አምኖ መቀበልም ሌላው መረሳት የሌለበት ጭብጥ ነው፡፡ እነዚህን ኩነቶች ለመተግበር የማይነጣጠሉትን እንቅስቃሴዎችም በሶስት በመክፈል በደምሳሳው እንመለከታቸዋለን፡፡

የአደባባይ እምቢተኛነት…

ዛሬ ላይ ስለመታገያ መንገዶቹ ብዙ ነጥቦችን ዘርዝሮ ማቅረቡ ላያስፈልግ እንደሚችል ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም በአገዛዝ ውስጥ የሚመረጡ የትግል ስልቶች በይፋ ከመቅረብ ይልቅ፣ በተቃውሞው አደረጃጀት ጥልቅ ዝግጅት እንደየአውዱ እየተመረጡ ቢተገበሩ የተሻለ ውጤታማ እንደሚሆኑ አምናለሁና፡፡ ሆኖም በዚህ መነሻነት ጥቂት ነጥቦችን ብቻ አንስቼ አልፋለሁ፡፡ በእነ ጄን ሻርፕ እና መሰል የትግሉ መምህራን ተደጋግሞ የሚጠቀሰው ‹‹የአደባባይ መቀመጥ›› የሚባለው ለሰላማዊው አመፅ ግንባር ቀደም ተደርጎ ይጠቀሳል፡፡ ለረዘሙ ቀናት/ሳምንታት አደባባዮችን ሞልቶ፣ ተጨባጭ ፖለቲካዊ ማሻሻያም ሆነ መሰረታዊ የሥልጣን ሽግግር እስኪደረግ ድረስ የመተካካት ስልት በተከተለ እና ግላዊ የዕለት ተዕለት የኑሮ መመሰቃቀሎችን ባገናዘበ (በእጅጉ ጉዳቶቹን በሚቀንስ) መልኩ በፈረቃ ፕሮግራም የሚደረግ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በትእምርትነትም የእስልምናን፣ የክርስትናን እና የአይሁድ እምነት ምልክቶችን ለመሰባሰቢነት በመጠቀም፣ በዋና ዋና ግልፅ ሕዝባዊ የመሰባሰቢያ ስፍራዎች ላይ የሰላም ድንኳኖችን መዘርጋት፣ የመማፀኛ ፊርማ ማሰባሰብ፣ በሕንፃዎች አናትና በግድግዳዎች ላይ ለውጥ የሚጠይቁ መፈክሮችንና ምስሎችን መለጠፍ፣ የመኪና ጥሩንባንና ሌሎች ከፍተኛ ድምፅ ሰጪ መሳሪያዎችን ያለማቋረጥ ማስጮኽ፣ የቤት ውስጥ መቀመጥ፣ የሥራ፣ የትምህርትና የረሃብ አድማዎችን መምታት፣ በማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ ማደም፣ በየእምነት ተቋማቱ በጋራ ፀሎት ማድረግ… በዚሁ ስር የሚካተቱ ተግባራት ናቸው፡፡

በርግጥ ይህ ሁሉ ሲሆን የአገዛዙ መሪዎች ሕዝባዊ አብዮቱን በታጠቀው ኃይል ለመቀልበስ ሙከራ ማድረጋቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ይሁንና በዚህን ጊዜ ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር እሰጥ-ገባ ውስጥ ባለመግባት፣ ምንም አይነት አፀፌታዊ ግብረ-መልስ ባለመስጠት፣ በተንኳሽ የቁጣ ቃላት በመጎነታተል ለማበሳጨት ባለመሞከር፣ ተቀጣጣይና ስለት ነገሮችን ከአካባቢው በማራቅ ወይም በፍፁም ባለመያዝ… የተቀኙ ስልቶችን መከተል የሕዳሴ አብዮታችን መገለጫ ነውና፤ በዚሁ መንገድ መፅናት ግዴታ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ይህ አካሄድ በአንዳንድ አገራት እንደተስተዋለው አጋጣሚውን በመጠቀም አብዮቱን ለመጥለፍም ሆነ ሰርገው በመግባት ወደ ደም-አፋሳሽ ነውጥ ለመግፋት የሚሞክሩትን ለመከላከል ያስችላል፡፡

ሌላኛው ጭብጥ፣ የትግሉን ግብ በግልፅ ቋንቋ ካስቀመጡ በኋላ፣ የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት ለሥርዓቱ የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቋርጡ መወትወት ነው፡፡ ቀጥታዊዎቹን ሰብአዊ ዕርዳታዎች ሳይጨምር ኢህአዴግ በቀዳሚነት የባጀት ድጋፎቹን ከነዚህ ሀገራትና ተቋማት እንዳያገኝ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጫና የሚካሄድበትን ስልት መቅረፅ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ አፈናውን ለማራዘም በርትተው በሚሰሩት የሥርዓቱ ፊት-አውራሪዎች ላይ፤ የጉዞ ማዕቀቦችን ጨምሮ ሌሎች ወደ ድርድሩ ማዕቀፍ እንዲመጡ የሚያስገድዱ ግላዊ ጫናዎች እንዲጠናከሩባቸው መጣር፣ ተጨማሪ የትግሉ መንገድ መሆን ይኖርበታል፡፡

አብዛኛዎቹ የአለማችን ጨካኝ አገዛዞችን ለታሪካዊ ሽንፈት የዳረገው ሌላው የመታገያ ስልት፣ አፋኝ ሕጎቻቸውን በግልጭ መጣስ መሆኑ በቀዳሚነት የሚወሳ ነው፡፡ በእርግጥ ይህን መሰል የአደባባይ የኢ-ፍትሓዊ ሕጎች ጥሰት ብዙ ዜጐችን ለእስር ይዳርጋል፡፡ ሆኖም የሰላማዊ አብዮት ውጤት መገለጫ፣ የዜጐች እስርን የመዳፈር ብርታት እንደሆነ ከመታወቁ አኳያ፣ ይህኛው አካሄድ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ በእኛም ምድር እስርን የሚዳፈሩ ብርቱና ቆራጥ ጎበዛዝት በተበራከቱ ቁጥር፣ የተቃውሞ አድራጊዎች መጠን በሂደት እየጨመረ እንደሚመጣና ግንባሩም ስጋት አድሮበት ከአፈና እርምጃዎቹ መቆጠቡ ስለማይቀር፣ ለምንፈልገው ሥርዓታዊ ሽግግር አስገዳጅ ፈቃደኝነት ውስጥ ልንከተው እንደሚቻለን ማመን ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ይሁንና ውጥረቱ እየበረታ በሄደ ቁጥር ሥርዓቱ ተቃውሞውን ለማክሸፍ በብዛት ወደ እስር መላኩ አይቀሬ ቢሆንም ‹ስለኔ አታልቅሱ› እንዲል መጽሐፉ፣ በእርምጃው ሳይደናገጡ በአቋም በመፅናት ከአደባባዩ ሳያፈገፍጉ፣ ታሳሪዎቹን በጀግንነት እያወደሱ፣ ለእስር የሚዳርጉ ሕጎችን በመጣስ ጀግኖቹን መቀላቀልና ማጎሪያዎቹን አለቅጥ ማጨናነቅ አገዛዙን ለማሽመድመድ ጠቃሚነቱ በተግባር የተሞከረ ስልት መሆኑን ማስታወስ ያሻል፡፡ ነፃነቱን በነፃ ያገኘ ከቶም ቢሆን የለምና! በሰላም ጊዜ እንጂ በእንዲህ አይነቱ የንቅናቄ ወቅት እስር ቤት ቅንጣት ታህል የሚያስፍራ አለመሆኑን በልበ-ሕሊና ማሳደሩ ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

ኢኮኖሚያዊ ትብብር መንፈግ

ስለትብብር መንፈስ መንፈግ ጉዳይ አስቀድመን ልናነሳው የሚገባን ኢኮኖሚ ተኮር የሆነውን የትግል ስልት ነው፡፡ ይህ ሥርዓት ለጭቆናው መሰረት ካደረጋቸው መካከል፣ በዝባዥ የምጣኔ-ሀብት ተቋማትን ማቋቋሙ አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እናም የኢኮኖሚ ትብብር መንፈግን ቀዳሚው የትግል አማራጫችን ብናደርገው የሕዳሴውን አብዮት ግቦች በአጭር ጊዜ ለማሳካት የማስቻሉ ዕድል የሰፋ ይሆናል፡፡ ለዚህም በዋናነት ልናተኩርባቸው የሚገቡ ሁለት ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው በማዕከላዊ መንግስቱ በቀጥታ እንደሚመሩና እንደሚደገፉ ከሚነገርላቸው ድርጅቶች፣ ምርቶችን ባለመግዛትና የምርት ሂደቱንም ከውስጥ በማጨናገፍ፣ እንዲዳከሙ ማድረግን የሚመለከት ነው፡፡ ረዥሙ ትግል ከባድ ዋጋ እንደሚጠይቀን ከተማመንን፣ ለህልውናችን የቀን ተቀን ኑሮ እጅግ ወሳኝ የሆኑትን የምርት ውጤቶች ከመንግስታዊ ተቋማቱ አለመግዛት፣ ሥርዓቱን ለማሽመድመድ ውጤታማ መሆኑ አይቀርም፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞችንና መሀከለኛ የአመራሩን አባላት፣ የምርት ሂደቱን እንዲያስተጓጉሉ በማግባባት፣ ተቋማቱን በዝግመታዊ ሂደት አቅማቸውን ማድቀቅ አንዱ የትብብር መንፈግ አማራጭ ነው፡፡ ይህ መንገድ ከዛሬው ነባራዊ ሁኔታችን አንፃር የማይቻል ቢመስልም፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ‹‹በርግጥ! እንችላለን!!›› እንዲል፤ እኛም የነቃንለትን ሃሳብ ለመፈፀም የማንፈነቅለው ድንጋይ እንደማይኖር በተግባር ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡ ደግሞም በቀላሉ በማይደበዝዝ መነቃቃት ካልታደስን መጪው ጊዜ አደገኛ ይሆን ዘንድ እንደመፍቀድ ይቆጥራልና፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ መንግስታዊ የንግድ ተቋማት ውስጥ ያሉትን ሠራተኞች በአንድ የግንኙነት መስመር በማስተሳሰር ሁኔታዎች ግድ ባሉ ቀን በተመሳሳይ ጊዜ በማንቀሳቀስ፣ ሥርዓቱን ክፉኛ ማዳካሙ ተግዳሮት የበዛ አለመሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ የኢኮኖሚ ትብብር መንፈግን የግድ የሚያደርገው ሌላው ጉዳይ፣ ግብር (ታክስ) ያለመክፈል ሕዝባዊ እምቢተኝነትንም ስለሚያጠቃልል ነው፡፡ የጭቆናው አገዛዝ ተጠናክሮ የቆመው በታክስ ሥርዓቱ ላይ መሆኑንም ሆነ ለሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያው መጥቀሙን በቅጡ መገንዘብ ከቻልን ታክስ ባለመክፈል፣ የቆመበትን መሰረት መቦርቦር የሚቻልበት ዕድል መኖሩን ማስታወስ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያችን ነባራዊ ሀቅ፣ አብዮቶቹ ከተተገበረባቸው ሀገራት አንድ ለየት የሚል ገፅ ያለው ከመሆኑ ጋር የሚነሳ ነው፡፡ ይኸውም የገዢው ግንባር አባላት ተከፋፍለው በሀገሪቷ ኢኮኖሚ የአንበሳውን ድርሻ መያዛቸው ነው፡፡ ከማዕድን ቁፋሮ እስከ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ፤ ከፋይናንሺያል ተቋማት እስከ አልኮል ምርቶች ድረስ የተቆጣጠሩበትን መንገድ ማዳከም፤ ሕዝባዊ ጉዳት ሳይከተል ቀጥታ የሥርዓቱን የመጨቆኛ ምንጭ ማድረቁን ቀላል ያደርገዋል፡፡ በርግጥ አገዛዙ ከእነዚህ የፓርቲዎቹ ተቋማት ምንም አይነት አገልግሎት ላለመጠቀም የሚደረገውን አድማ በመመዝመዝ፣ ሂደቱን በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ያነጣጠረና ብሔሩን ሆን ተብሎ ለመጉዳት ታስቦ እንደተደረገ አስመስሎ የሚነዛውን መርዛም ፕሮፓጋንዳ ከወዲሁ ለማጨናገፍ፣ ከድርጅቶቹ ምርቶቹን ያለመግዛት ውሳኔ፣ ከማንኛውም ብሔር ጋር እንደማይገናኝ ማመን እና መተማመንን መፍጠር ቀዳሚው ተግባር መሆኑ ይኖርበታል፡፡ በ‹‹ኤፈርት›› የበለፀገች ትግራይ፣ በ‹‹ዲንሾ›› ያደገች ኦሮሚያ፣ አልያም በ‹‹ጥረት›› የተጠቀመ የአማራ ክልል አለመኖሩን፣ መጀመሪያውኑ ከልብ ተገንዝበን ከተንቀሳቀስን፣ ፓርቲ ተኮር ድርጅቶቹን ማግለል አስቸጋሪ አይሆንብንም፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ቀጣይ ቅቡል መሪዎችም ይህን ጭብጥ ሕዝቡ ዘንድ በሚገባ ማስረፅ አንዱ ኃላፊነታቸው መሆኑን ሊዘነጉት አይገባም፡፡

የገዥው ፓርቲ አባላት…

ሶስተኛው ልንዘጋጅበት የሚገባው ጉዳይ፣ በመጀመሪያው የአብዮቱ እርከን ለዘብተኞቹን የግንባሩ አባላት በእንቅስቃሴው እንዲሳተፉ ማመቻቸት ነው፡፡ በተለይም ከድህረ-97ቱ የምርጫ ፖለቲካ ድቀት እና ይህን ተከትሎ በመጣው የተቃውሞ ስብስብ መዳከም የተነሳ፣ ‹ፓርቲውን በአዝጋሚው መንገድም ቢሆን እየገሩ መሄድ ይቻላል› በሚል የተቀላቀሉ እንዳሉ ይታወቃልና፤ እነዚህን ወንድሞችና እህቶች በሂደቱ ውስጥ ለማሳተፍ፣ የአብዮቱን መሪ ህልም እንዲያምኑበት ማድረጉ የግድ ነው፡፡ እነርሱን እያካተትን በተጓዝን መጠን፣ ሌሎቹም የፓርቲው አባላት ትግሉን በመቀላቀል፣ የራሳቸውን ጥያቄዎች አንግበው ሥርዓቱ ወደመነጋገር እንዲመጣ ያስችሉታል ብዬ አምናለሁ፡፡ የታቀደ አብዮት ስኬቶችን ስንመረምር እነዚህን መሰል ክስተቶችንም የለውጡ አካል ማድረጉን መረዳታችን አይቀርም፡፡ በነገራችን ላይ በመታደሳችን ዘመን ለቀደሙ ወንጀሎችም ሆነ ሀገራዊ ውድመቶች ሂሳብ ማወራረድን ታሳቢ ማድረግ ፍፁም አብዮቱን መጎተት ከመሆኑም በላይ፣ የታሪካችንን አስቀያሚ ገፅ በመድገም ቁልቁል መዝቀጥ እንደሆነ መተማመን ይኖርብናል፡፡ ግባችን ኢትዮጵያን እያደሱ ወደፊት ማራመድ እስከሆነ ዘንዳ፣ የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የመፍጠሪያው መንገድ ላይ ብቻ ማተኮር ብቸኛው መፍትሄ ነው፡፡ ያለፈው ዘመን ሰማዕታትን እየዘከርን፣ ለአጥፊዎቹ ምህረት እያደረግን በይቅርባይነትና በመቻቻል ላይ የምታብበውን ኢትዮጵያን መመስረት የሕዳሴው አብዮት ግብ ሊሆን ይገባል፡፡

የንቅናቄው ፊት መሪዎች

ይህን የለውጥ መንፈስ በፊት መሪነት ማስተባበር የሚችሉ ጠንካራ የሲቪክ ተቋማት በሀገሪቱ ያለመኖራቸው ጉዳይ፣ ለሂደቱ መፍጠን የግድ ሌላ አማራጭ እንድንፈልግ ያስገድደናል፡፡ በርግጥ አንዳንድ ወገኖች ለእንዲህ አይነቱ ጊዜ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መጠቀምን ይመክራሉ፡፡ ይህ ግን አደገኛና ያልተጠበቀ ክስረት ሊያስከትል የሚችል ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ድርጅቶቹ የየራሳቸው የተለያየ ዓላማ አንግበው የሚታገሉ በመሆኑ ከተሳታፊነት አልፈው በመሪነት መምጣታቸው፣ ሁነቱን ከሁሉን አሳታፊነት ወደ ቡድንነት፤ ከዲሞክራሲያዊ ሽግግር ወደ ሥልጣን ነጠቃነት (መፈንቅለ መንግስት) የመቀየር አደገኛ ክስተት ውስጥ ሊያስገባው ይችላል፡፡ ይህ አካሄድ በሌሎች ሀገራት ለከሸፉ አብዮቶች በማሳያነት መጠቀሱንም ታሳቢ በማድረግ፣ ለእኛ ችግር መፍትሔውን አዲስ (ከዚህ ቀደም ያልተሞከረ) አማራጭን ከራሳችን ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር መፈለግ ላይ ማተኮሩ ይበጃል፡፡ በግሌም ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ግዴታ ለመሸከም የተሻሉ ናቸው ብዬ የማስበው ዩንቨርስቲዎቻችንን ነው፡፡ በመላ ሀገሪቱ በተመሳሳይ ወቅት መጀመር የሚኖርበትን የሕዳሴ አብዮት፣ ሁሉም መንግስታዊ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙበትን ከተሞች ጨምሮ አጎራባች አካባቢዎችን ለማስተባበር ኃላፊነት የሚወስዱበት መንገድን ማማቻቸቱ የሚሳካበትን ስልት ከወዲሁ መቀየስ የሚቻል ይመስለኛል፡፡

ርግጥ ነው በዛሬው እውነታ ላይ ሆነን በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገዢው ፓርቲ የፖለቲካ መናኸሪያ የመሆናቸውን ነገር ግምት ውስጥ አስገብተን ስናምሰለስለው፣ ሁነቶቹ አልጋ በአልጋ ሊሆኑ እንደማይችሉ ከማንም የተሰወረ አይሆንም፡፡ ግና፣ በየተቋማቱ የየትኛውም ፓርቲ አባል ያልሆኑ ለውጥ አራማጅ መምህራንና ተማሪዎች በራስ ተነሳሽነት በመሰባሰብ የማስተባበሩን ኃላፊነት ተረክበው ከፊት መስመር እንዲሰለፉ የማንቃትና ማብቃት ሥራ ቢሰራ፣ አንድም እዚህ ግባ የሚባል ተግዳሮት ባለመኖሩ ሂደቱን ለማፋጠን ይጠቅማል፤ ሁለትም ከንቅናቄው ስፋት አኳያ ለከበደ መስዋዕትነት የመዳረጉ አጋጣሚ እጅግ የጠበበ በመሆኑ ግንባር ቀደም ተሰላፊ ደፋሮችን ማግኘት አዳጋች አያደርገውም፡፡ ይህ ዕቅድ የሚሳካ ከሆነ ደግሞ ዩኒቨርስቲዎቹ በዕኩል ውክልና የጋራ ማዕከል (አዲስ አበባ ለዚህ አመቺ ሊሆን ይችላል) አቋቁመው አብዮቱን በሀገርና ሕዝብ ጥቅም አስተሳስረው መምራት እንደሚኖርባቸው እንደማይዘነጉት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የአብዮቱ የመጀመሪያ ጥያቄዎች

ሕዝባዊ ንቅናቄው በሚገባ ተጠናክሮ ከቀጠለ በኋላ መንግስት እጁን ተጠምዝዞ እንዲተገብራቸው መነሳት ያለባቸው ቀዳሚ ጥያቄዎች (ለለውጡ መደላድል የሚሆኑት) የሚከተሉት ቢሆኑ መልካም ነው፡- በመላ ሀገሪቱ ባሉ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ፣ የሕሊና እና የሀይማኖት እስረኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት፤ በውጪ ሀገር ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እና የመብት ተሟጋቾች ያለልዩነት ወደ ሀገር ቤት ገብተው በነፃ እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የወጡ አፋኝ ሕጎችን መሰረዝ፤ በሀገሪቱ የመንግስት ምሥረታ ላይ የአፈና መዋቅር ሆኖ የሚያገለግለውን ምርጫ ቦርድ አፍርሶ አብዛሃ ኢትዮጵያዊን ሊያሳምን በሚችል ገፅ እንደገና ማዋቀር፤ ለዴሞክራሲ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ተቋማትን ነፃ ማድረግ፤ የብዙሃን (የመንግስት) ሚዲያን እውነተኛ የሕዝብ ልሳን የሚሆኑበትን አሰራር መዘርጋት፤ መከላከያ ሰራዊቱ፣ የደህንነት ሰራተኛው እና የፖሊስ አባላት በነቢብ ሳይሆን በገቢር ተጠሪነታቸውን ለሕገ-መንግስቱ ማድረግ… ሲሆን፤ እነዚህ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላ በ2007 ዓ.ም. የሚካሄደውን ምርጫ ለተጨማሪ አንድ አመት በማራዘም፤ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች (ለነባሮቹም ሆነ አዲስ ለሚደራጁት) መድረኩን ክፍት አድርጐ የሕዳሴውን አብዮት ለውጥ መተግበር ይቻላል ብዬ አምናለሁ፡፡ እዚህ ጋ መዘንጋት የሌለበት ዋነኛው ጉዳይ አብዮቱ በራሱ በገዥው-ፓርቲ ውስጥ ያሉ በፖለቲካ ቀኖናዊነት ያልተጠለፉና ሀገራዊ ለውጥ ፈላጊ የአመራር አባላት ‹የኢህአዴግ መንግስት ወይም ሞት!› የሚሉ ግትር ጓዶቻቸውን አግልለው፣ ይህንን ኃላፊነት እንዲወስዱ ጫና ማድረግ ላይ የሚያተኩር እንጂ፤ በደፈናው ግንባሩን በጠላትነት ፈርጆ የሚያሳድድ አለመሆኑን ግንዛቤ መውስድ ያስፈልጋል፡፡ የሕዳሴው አብዮታችን የ‹ጊሎትን› ማሽን የማይታጠቅና ልጆቹንም የማይበላ፤ በአጥፍቶ መጥፋት ጨዋታ ሕግ የማይመራ መሆኑን ማስረገጥ ቀዳሚው ተግባር ይሆናል፡፡ ጎን ለጎንም የለውጡን (የጥያቄዎቹን) መፈፀም የሚከታተል ከንቅናቄው አስተባባሪዎች፣ ከንግዱ ማሕበረሰብ፣ ከኃይማኖት ተቋማት፣ ከሲቪክ ማሕበራት፣ ከልሂቃኑ እና ከሀገር ሽማግሌዎች መካከል በተወጣጡ ግለሰቦች የጋራ ምክር ቤት አዋቅሮ ቁጥጥር ማድረግ የሚቻልበትን አሰራር መቀየሱ ሌላኛው ጠቃሚ ክዋኔ ነው፡፡ ይህ መንገድ በድህረ-ኢህአዴጓ ኢትዮጵያችን ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ምስቅልቅሎሽ ቦታ እንዳይኖራቸው የመታደግ አቅምንም ለመገንባት ማስቻሉ መዘንጋት የለበትም፡፡

የተባረከችዋ ቀን መቼ ትሆን?

ይህን መሰል የለውጥ ጥያቄ ማቅረቡ ሥርዓቱ ከሃያ ሶስት ዓመት በላይ ከመቆየቱ አኳያ የተቻኮለ እንደማይሆን አምናለሁና፤ ከላይ ከተጠቀሱት ዋና ዋና አብዮታዊ ጉዳዮች አንፃር፤ እንዲሁም በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹ልጄ ፋኖ ተሰማራ እንድትል አልፈልግም›› እንዳለው ሁሉ፤ ህወሓት የታሪካችን የመጨረሻው ‹‹ነፃ አውጪ›› ድርጅት ይሆን ዘንድ የሚታወጅበት ዕለትን ከወዲሁ መወሰኑ ላይ ከተስማማን፣ የ2007ቱ ወርሃ መስከረም በሁለት ጉዳዮች ቢመረጥ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ የመጀመሪያው በቀጣዩ ዓመት የሚደረገውን አምስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫን የማራዘሙ አስፈላጊነት ከሕዝባዊ ጥያቄው መካከል ግንባር-ቀደም በመሆኑ ለአገዛዙ በቂ የጥሞና ጊዜ መስጠት የማስቻሉ ጠቀሜታ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የአዲስ ዓመት ጅማሮ ከመሆኑ አኳያ ባሕላዊም ሆነ ስነ-ልቦናዊ መነቃቃት የመፍጠር አቅሙ የራሱ በጎ አበርክቶ ይኖረዋል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡

ከሞላ ጎደል ለሶስት ሳምንታት ያህል የተነጋገርንባቸው እነዚህ ታላላቅ አጀንዳዎች እውን ይሆኑ ዘንድ ቀጠሮውን በልቦናችን ይዘን፣ ራስን በውስጥ ዝግጅት ማሰናዳቱ ለነገ የማይተው የቤት ስራችን መሆኑንም ጨምሮ መረዳት ያሻል፤ በዚህም የሕዳሴያችን ንቅናቄ እንደ ቀዳሚዎቹ ሁለት አብዮቶች አዲስ መዘዝ፣ ሳይሆን አዲስ ተስፋ እንዲያመጣ እናስችላለን ብዬ አስባለሁ፡፡ በመጨረሻም ያቺ ትንሳኤ አብሳሪ ዕለት በኢትዮጵያችን ምድር ከቶም ቢሆን አቻ የላትምና፣ በአያሌ ናፍቆት ስለመጠበቋ ዛሬ ላይ እንዲህ መመስከሩ ከምኞት የተሻገረ መሆኑን አስረግጬ ብናገር ማጋነን አይሆንም፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

“እኛና አብዮቱ” በሚል ርእስ በተፃፈው መፅሓፍ ላይ የቀረበ የግል አስተያየት

$
0
0

የመፅሃፉ ደራሲ፤ ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ

አስተያየትና ማስተካከያ ሃሳብ አቅራቢ፤ ላቀው አለሙ (ዶ/ር)

አጠቃላይ አስተያየት፣

115ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ መፅሃፍ ማሳተማቸውን እንደሰማሁ መፅሃፋቸውን አግኝቼ ለማንበብ በጉጉት እጠባበቅ ነበር። ዘግይቶም ቢሆን በአንድ ወዳጄ አማካኝነት መፅሃፉ እጄ ገብቶ አነበብኩት። ደራሲው በዚያ የአብዮት ዘመን ስለተከናወኑ ተግባሮች አጠር ባለና በጥሩ አቀራረብ ፅፈዋል። በሂደቱ ውስጥ ላለፍነውም ሆነ ለአዲሱ ትውልድ ጠቃሚ መረ

ጃዎችን መፅሃፉ አካቶ ይዞዋል። የሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ አስተዋፅኦ የሚደነቅ እና እርሳቸውም ላደረጉት ጥረት ሊመሰገኑ ይገባል።

አነሳሴ በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ መፅሓፍ ላይ ሁለንተናዊ ግምገማና ትችት ለማቅረብ አይደለም። መፅሃፉን ካነበብኩ በሁዋላ በአዕምሮዬ ውስጥ ሲጉላሉ ለነበሩ ጥቂት ጉዳዬች አጭር አስተያየት እና ማስተካከያ ለማቅረብ ነው። በቅድሚያ በወቅቱ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች በተለይም መኢሶንና ኢህአፓ ስለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ከነበራቸው የተለያየ ግምገማ በመነሳት ያከናወኑዋቸው ተግባሮቶች እና በዚያም ሳቢያ ስለደረሱ ጥፋቶች ከመፅሓፉ ያገኘሁትን ግንዛቤ አሰፍራለሁ። በሁለተኛ ደረጃ ታላቅ ወንድሜ ሻምበል አለማየሁ ሃይሌን በተመለከተ ደራሲው ከፃፉት ሃሳቦች አንዳንዶቹ የተሳሳቱ በመሆናቸው እውነተኛውን ነገር ካለኝ መረጃ በመነሳት ላብራራ እሞክራለው ።

በቅድመ አብዮት ኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ መሰረት አልነበራም። በድርጅታዊ አቅም እና   በልምድ የዳበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችም በህብረተሰቡ መካከል አልነበሩም። የንጉሳዊ አገዛዙ እያቆጠቆጠ ከነበረው ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ወደሁዋላ ቀርቶ ስለነበር የህብረተሰቡን የለውጥ ፍላጎት እና ጥያቄዎች ለማስተናገድ አቅም አልነበረውም። ስለሆነም ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ብሶት ወደ ብሄራዊ የአመፅ እንቅስቃሴ ወይም አብዮት ተሸጋገረ። በአብዮታዊ እንቅስቃሴው ውስጥ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም የተሻለ የድርጅት አቅም የነበረው የወታደሩ ክፍል የህዝቡን ብሶት እየተከተለ ፀረ መንግስት እርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ። በሂደትም ንጉሳዊ ስርአቱን አስወግዶ ስልጣኑን ተቆጣጠረ ። ይህ የወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ የፈጠረውና የህብረተሰቡ ግፊት የታከለበት አስገዳጅ ክስተት እንደነበር ከመፅሃፉ ይዘት መረዳት ይቻላል።

ንጉሳዊ ስርአቱ እንደተወገደ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች በህብረተሰቡ መካከል እንቅስቃሴ ማካሄድ ጀመሩ። ሆኖም በመካከላቸው በነበረው የአላማና የአካሄድ ልዩነቶች እንዲሁም ስልጣን በያዘው ወታደራዊ ደርግ ላይ በያዙት አቋም እርስ በርስ በመጠላለፍ ተግባር እና የፖለቲካ ሽኩቻ ውስጥ ገቡ። በዚህም ተግባራቸው የትውልድ ጥፋትና ክስተት እንዲደርስ አድርገዋል። ለጋ እድሜ የነበራቸው እነዚህ የፖለቲካ ድርግቶች ከሌሎች ሃገሮች የቃረሙትን ንድፈ ሃሳብ በድፍኑ በማንበልበል ከእገሪቱ እውነታና ከህዝቡ የግንዛቤ ደረጃ በመራቅና በስሜት እየተገፉ የስልጣን ፍላጎት ላይ  ብቻ በማተኮራቸው በወቅቱ ለደረሱት ጥፋቶች የበኩላቸውን አስተዋፆ አድርገዋል።

ወታደራዊ ደርግ በጊዜው ህዝቡ ላነሳቸው መሰረታዊ የኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ተገቢና ስር ነቀል እርምጃዎችን ወስዷል። የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቹ (reforms) ላአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ጠቀሜታ የነበራቸውና ለተከታታይ እድገትም ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ነበሩ። ይሁን እንጂ ለሁለንተናዊና ቀጣይነት ላለው የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት ወሳኝ የሆነው የፖለቲካ ጥያቄ ተገቢውን መፍትሄ ሳያገኝ በመቆየቱ ችግሮች ይበልጥ ተወሳሰቡ፤ ያልተፈለገ ጥፋትም በሃገሪቷ ላይ ደረሰ። ተራማጅ ነኝ ይል የነበረው የምሁሩ ክፍል ብስለት ማጣትና ለስልጣን መስገብገብ እንዲሁም ለደርግ ከነበራቸው ንቀት የተነሳ ለፖቲካዊ ችግሮች መወሳሰብ አስተዋፆ ማድረጋቸውን የሻ/ል ፍቅሬን መፅሃፍ በጥንቃቄ ላነበበ ሁሉ በግልፅ ይታያል። ከነዚህም በተጨማሪ የቅርብና የሩቅ ሃገሮች ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና ግፊት ሌላው የችግሩ ምንጭ እንደነበር የግል ግንዛቤና አስተያየት አለኝ።

የደርግ አባላት በተለይም ሊ/መንበር መንግስቱ ኃ/ማሪያም ብልሃት በጎደለው የኢትዮጵያዊነትና የሃገር ፍቅር ስሜት በመገፋፋት የፖለቲካውን ውስብስብ ችግሮች በሃይል ብቻ ለመፍታት በመሞከራቸው በትውልዱ ላይ ከፍተኛ መከራና ጥፋት እንዲደርስ አድርገዋል። አልፎ ተርፎም ሃገራችን ዛሬ ለምትገኝበት የችግር ማጥ ዳርገዋት ሄደዋል።

ሻምበል ፍቅረስላሴ ከላይ ያነሳኋቸውንና ሌሎች የወቅቱን አበይት ክስተቶች በመፅሃፋቸው ውስጥ ለመዳሰስ ሞክረዋል። አያሌ ቁምነገሮችና ጠቃሚ መርጃዎች በመፅሃፉ ውስጥ ተካተው ስለቀረቡ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው ብዬ አምናለው። ሻምበል ፍቅረስላሴ በቅርበት የሚያውቋቸው ሌሎች ቀሪ ጉዳዬች ቢኖሩም በመፅሃፉ ውስጥ የቀረቡ ማብራሪያዎች በአብዛኛው ሚዛናዊ ናቸው ብዬ እገምታለው።

ሻምበል አለማየሁ ኃይሌን በተመለከተ፣

ሻምበል አለማየሁ ከኦሮሞና ከከፋ ብሄረሰቦች እንደሚወለዱ ሻምበል ፍቅረስላሴ በመፅሓፋቸው ጠቅሰዋል። ይህ ፈፅሞ ትክክል ያልሆነ መረጃ ነው። ምንም እንኳ የወላጆቻችን የትውልድ ሃረግ ከኦሮሞ፤ ከጉራጌና ከአማራ  ብሄረሰቦች የሚመዘዝ ቢሆንም የወላጆቻችንና የእኛ ስብዕና በአብዛኛው ኦሮሞነትን መነሻ አድርጎ በኢትዮጵአዊነት ስነልቦና የተገነባ ነው። ስለዚህ ሻምበል አለማየሁ ብሄረሰቡ ኦሮሞ እንጂ ከከፋ ብሄረሰብ ጋር በቀጥታ የሚያገኛኘው ነገር የለም። ይሁን እንጂ እንደአብዛኛው ኢትይጵያዊ በጋብቻ የተነሳ በከፊል ከከፋ፤ ከሲዳማና ከሃዲያ ብሄረሰቦች የሚወለዱ የሩቅ ዘመዶች እንዳሉን መካድ አይቻልም።

ሻምበል ፍቅረስላሴ በደርግ ውስጥ በእነ አለማየሁ ወገንና በሊ/መንበር መንግስቱ ደጋፊዎች መካከል ስለነበረው ቅራኔና በመጨረሻም ስለተወሰደው እርምጃ (የመንግስት ግልበጣ) ባብራሩት የመፅሃፋቸው ክፍል ውስጥ፣ ሻምበል አለማየሁ የኢህአፓ አባል እንደነበር፤ የታገለውም ኢህአፓን ስልጣን ላይ ለማውጣት እንደነበር ፅፈዋል (ገፅ 310)።  እውነቱ ግን  በፍፁም ከዚህ የተለየ እንደነበር እኔ በቅርብ የማውቀው ጉዳይ ነው። በመጀመሪያ ነገር አለማየሁ የኢህአፓ አባል አልነበረም። ይህንኑ ሃቅም የኢህአፓ አንዱ መሪ የነበሩት አቶ ክፍሉ ታደሰ በመፅሃፋቸው ውስጥ ገልፀዋል (ያ ትውልድ)። የአለማየሁ እምነትና ፍላጎት ደርግ ለኢትዮጵያ ህዝብ በይፋ ቃል ገብቶ ስልጣንን በጊዚያዊነት የያዘ ኃይል እንደመሆኑ፤ የአብዮቱ ወገን የሆኑና ኃላፊነት የሚሰማቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ተባብረውና የጋራ ግንባር ፈጥረው በህዝብ ይሁንታ ስልጣኑን እንዲረከቡ ይፈልግ ነበር። የደርግ አባላትን በተመለከተ ምርጫ በማድረግ ወደ ፈለጉት ድርጅት ውስጥ ተጠቃለው ትግሉን መቀጠል ይችላሉ ወይም ሌሎች የግል ምርጫዎችን መውሰድ ይችላሉ ብሎ ያምን ነበር። ደርግ በመንግስትነት ሚናው ለሁሉም ፓርቲዎች መድረኩን በእኩልት ማመቻቸት አለበት እንጂ አንዱን ድርጅት አገልግሎ፣ ሌላውን ማቅረብ የለበትም የሚል አቋም ነበረው። ለአብዮቱ የቆሙትን ኃይሎች ሁሉ በእኩል አይን በማየት፤ በማዕከልነት ማስተባበርና እኩል ድጋፍ መስጠት የደርግ ኃላፊነት መሆን አለበት ይል ነበር።

ለዚህም ሲባል እያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት በተለይም መኢሶንና ኢህአፓ አቋማቸውን አስተካክለው የአብዮቱን አላማ፤ የሀገሪቱን ጥቅምና የህዝቡን ፍላጎት እንዲከተሉ አለማየሁ በግሉ ይወተውታቸው እንደነበር በቅርብ አውቃለሁ። የመኢሶን መሪዎችን “እኛን ብቻ ማለትን መተው አለባችሁ።” ኢህአፓዎችን ደግሞ “የግለሰቦችን ግድያና ንብረት ማውደምን አቁሙ።” በማለት ሁለቱን ወገኖች በግልፅ  እየወቀሰ እንዲቀራረቡ ጥረት ያደርግ ነበር፡፡ መኢሶንና ኢህአፓ እንዲሁም ሌሎች ህቡዕ የፖለቲካ ድርጅቶች በማሌ እርዮተ አለም ዙርያ ተሰባስበው በመሰረታዊ የፖለቲካና ሃገራዊ አጀንዳዎች ላይ ተግባብተው በጋራ ግንባር ስር እንዲሰባሰቡና እንዲሰሩ አለማየሁ ብርቱ ፍላጎት ነበረው፡  መኢሶንና ኢህአፓ በብቸኝነት ስልጣን ላይ ለመውጣት ሲሉ እርስ በርስ ለመጠላለፍ ያደርጉ የነበረውን እሩጫና በሴራ የታጀበ የትግል ሥልታቸውን አለማየሁ ፈፅሞ አይደግፍም ነበር። የእርስ በርስ ሽኩቻና የመጠላለፍ አካሄድ በአገሪቷ ላይ የግለሰብ አባገነንነትን ያስከትላል፣ በዘላቂነት ደግሞ አገራችንንና ህዝቡን ይጎዳል ብሎ ያምን ነበር። ከዚህ ውጪ አለማየሁ በግሉ የስልጣን ፍላጎት ወይም ኢህአፓን በብቸኝነት ለስልጣን ለማብቃት አቅዶ አልተቀሳቀሰም። የእርሱ ጥረት እያሰጋ በመምጣት ላይ የነበረውን የግለሰብ አባገነንነት ወይም ብቸኛ የስልጣን ማዕከልነት ለማስወገድ ብሄራዊ እርቅና የፖለቲካ ትብብር ተፈጥሮ ለኢትዮጵያና ለህዝቡ ጥቅም በጋራ የሚሰራበት ሁኔታ መፍጠር ነበር።  ዳሩ ምን ያደርጋል የፖለቲካ ድርጅቶች ያነገቡት ድብቅ ፍላጎትና ይህንኑ ለማሳካት የቀየሱት የሴራ መንገድ ሻምበል አለማየሁን እና ሌሎች አያሌ ሀቀኛ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆችን ላልተጠበቀ መስዋዕትነት ዳርጓል፡፡

ሻምበል አለማየሁ  አላማውን ለደርግ ከማቅረቡ አስቀድሞ እርሱና ጓደኞቹ ስለ ህቡዕ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋምና አሰራር ጥናትና ግምገማ አድርገዋል፡፡ ሻምበል ፍቅረስላሴ ቢያንስ የዝያን ታሪካዊ ፅሁፍ ይዘትና ዓላማ ለምን በመጽሓፋቸው ውስጥ ለመጥቀስ እንዳልፈለጉ አስገርሞኛል፡፡ ጥናታዊ ፅሁፉ በደርግ አባላት መካከል ለተፈጠረው የሐሳብ መለያየትና ደርግ በአዲስ መልክ ተዋቅሮ የስልጣን ክፍፍል እንዲደረግ የረዳ በ45 ገፅ የተጠናከረ መሰረታዊ ሰነድ ነበር፡፡ ሻምበል ፍቅረስላሴ እንደፃፉት (ገፅ 305)፣ ሰነዱ በኢሕአፓ ተዘጋጅቶ ለነአለማየሁ የተሰጠ ሳይሆን ለዚሁ ተብሎ በተቋቋሙ ኮሚቴዎች የተጠና እና ረቂቁ በአለማየሁ ተስተካክሎ በደርግ ስብሰባ ላይ ለወይይት እንዲቀርብ የተደረገ ነበር፡፡ በተቋቋሙት የጥናት ኮሚቴዎች ውስጥ በህቡዕ የሚሰሩ የፖለቲካ ድርጅቶች አባላት በአባልነት ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል::

እስከማቀው ድረስ ወንድሜ ሻምበል አለማየሁ በባህሪው ግልፅ፣ ነገሮችን በቀና መንገድ የሚመለከት፣ ለግል ጥቅም የማይጓጓ፤ ወዳጆቹን ከልብ የሚወድና የሚያምን፣ ላገሩ ከፍተኛ ፍቅር የነበረው ወጣት መኰንን ነበር፡፡ የነገሮችን አመጣጥ ፈጥኖና አስቀድሞ የመረዳት ችሎታ የነበረው ቢሆንም የፖለቲካ ብልጠት፣  አሻጥር እና ሴራ ግን በፍፁም አያውቅም፡፡ አለማየሁ ሁሉ ነገሩ ፊት ለፊትና በቀጥታ ነበር፡፡ በኔ ግምት ይህ የግልፅነት እና የየዋህነት ባህሪው እንዲሁም በወቅቱ በደርግ ውስጥ ለጊዜው ታይቶ የነበረው የዲሞክራሲ ጭላንጭል አለማየሁን እምነት ስላሳደረበት በፍርሃትና በአድር ባይነት ከመጓዝ ለአመነበት ዓላማ መስዋእትነትን ከፍሎ ማለፉን እንዲመርጥ አድርጎታል፡፡ ይህንን ሁኔታ እኔና ወንድሞቼ እንዲሁም ሌሎች የአለማየሁ የቅርብ ወዳጆች እስከዛሬ በታላቅ ቁጭት የምናስታውሰው ጉዳይ ነው።

ጥር 26 ቀን 1969 የደርግ አባላት ስብሰባ ላይ እያሉ መፈንቅለ መንግስት ተደርጎ አለማየሁንና ሌሎችን ለሞት ያበቃው እርምጃ ታስቦበትና በከፍተኛ ሚስጥር በጥንቃቄ እንደተዘጋጀ የሚታወቅ ነው፡፡ ለዚህ ዝግጅት መጀመር ፋና ወጊ የነበሩት ሻምበል ፍረስላሴ ወግደረስ እንደነበሩ፣ የሰውና የጽሁፍ ማስረጃዎች አሉ።  የደርግ አባል የነበረው ወታደር እሸቱ አለሙ የፃፈው መፅሓፍ የሚጠቀስ ነው። እነ አለማየሁ በበኩላቸው ከሊቀመንበር መንግስቱ ሊደርስባቸው የሚችለው አደጋ እውን ከመሆኑ በፊት ቀድመው እርምጃ ለመውሰድ ሻምበል ፍቅረስላሴ እንደፃፉት (ገፅ 316)፣ በእርግጥ ዝግጅት ነበራቸው።  በዚህ መሰረት ሊቀመንበር መንግስቱ ጥር 28 ቀን 1969  በቁጥጥር ስር ውለው፣ አድርሰዋል ለተባሉት ጥፋቶች ሁሉ በህግ እንዲጠየቁ ቀደም ሲል ወስነው ነበር፡፡ ይህ የተወሰነው በብርጋዴር ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ሰብሳቢነት የተወሰኑ የደርግ አባላት በተገኙበት ስብሰባ ሲሆን፣ ሻምበል ፍቅረስላሴም የዚህ ስብሰባ ተሳታፊና የውሳኔው ተካፋይ ነበሩ፡፡ ታድያ ጥር 28 ቀን ሊታሰሩ የነበሩት ሊቀመንበር መንግስቱ እንዴት ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ጥር 26 ቀን 1969 መፈንቅለ መንግስት ለማካሄድ እድሉን አገኙ? እርሶን በቀጥታ የሚመለከተው የዘማቾች በጀት ጉዳይ ከመደበኛ የቅዳሜ ስብሰባ በፊት  ሀሙስ እለት በአስቸኳይ አጀንዳ ተይዞ ለውይይት እንዲቀርብ አለማየሁ በዋና ፀሀፊነቱ እንዴት አምኖ ሊቀበል ቻለ? ማንስ አነጋግሮ አሳመነው? ይህ ጉዳይ በቀጥታ እርሶን የሚመለከት ስለሆነ እባክዎትን ሻምበል ፍቅረስላሴ ሃቁን አፍረጥርጠው ይንገሩን፡፡ ከንግዲህ በኋላ ያለው ነገር ሁሉ ፋይዳው ለትውልድና ለታሪክ ስለሆነ የተደበቁ እውነታዎች በሙሉ ይፋ መሆን አለባቸው የሚል ብርቱ እምነት አለኝ፡፡

ሻምበል አለማየሁ ከፖለቲካ ልዩነት ባሻገር በሊቀመንበር መንግስቱ ላይ የግል ጥላቻና ቂም አልነበረውም፡፡ በህይወታቸውም ላይ ጥፋት ለማድረስ አላማና ሃሳብም አልነበረውም፡፡ ሊቀመንበር መንግስቱ ሊያጠፉት እንዳሰቡ ካወቀ በኋላ እንኳን “መንግስቱን እንምታው” እያሉ ለሚጎተጉቱት ወገኖች እንኳን “ይህ ትክክል አይደለም፣ እኔ በነፍስ ማጥፋት አላምንም፣ ጥፋት ካለ ታይቶ በህግ መጠየቅ አለበት እንጂ ለምን ይገደላል?” እያለ ይመልስላቸው ነበር፡፡ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነና “ለምሳ ሲያስቡን ለቁርስ አደረግናቸው” ተብሎ በአደባባይ የተፎከረው በሃቅ ላይ ያልተመሰረተ የሴረኝነት እና የጭካኔ መግለጫ ከመሆን ውጪ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡

ሻምበል አለማየሁ ሊቀመንበር መንግስቱ ላይ የነበረው ቅሬታ ስልጣን በብቸኝነት ጠቅልሎ ለመያዝ የነበራቸው ከፍተኛ ፍላጎትና ጭካኔ የተሞላው ተግባራቸው ብቻ ነበር፡፡ እንደዚያም ሆኖ ሊቀመንበሩ በነበራቸው የማስተባበር ችሎታ ዘወትር አድናቆቱን ይገልፅ እንደ ነበር አውቃለሁ፡፡

በመጨረሻ ሻምበል ፍቅረስላሴ ሻምበል አለማየሁ ታታሪና ጎበዝ ሰራተኛ እንደነበር  አያሌ ስራዎችን በብቃት በማከናወን ደርግ ስርአትን ተከትሎ እንዲሰራ ከፍተኛ ጥረትና አስተዋፅኦ ማድረጉን በመፅሐፋቸው ውስጥ ጠቃቅሰዋል፡፡ በቅንነት ላቀረቡት የምስክርነት ቃልም በበኩሌ ላመሰግን እፈልጋለሁ፡፡

መልካም ጊዜ ለሁላችን !

ላቀው አለሙ (ዶ/ር)

Email ፡ lakewalemu@Yahoo.com

Mobile፡ 202 492 0674

 

የሻምበል አለማየሁን የግል የህይወት ታሪክ በዝርዝር ለማጀጋጀት ስለታሰበ በተለያየ መልኩ ለመተባበር የምትፈልጉ ሁሉ በአድራሻዬ  ልታገኙኝ ትችላላችሁ፡፡

በዕውነት ፕሮፌሰር መሥፍን እንደሚሉት ፣የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አይደለም?

$
0
0

tekele Yeshaw(ተክሌ የሻው፣የግል አስተያዬት) ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም”የወያኔ ጥላቻ ፍሬ» በሚል ርዕስ የጻፉትና በተለያዩ ድረ-ገጾች የወጣው ነው። ፕሮፌሰሩ በዚህ ፍሑፋቸው፣ የትግራይ ሕዝብ በዘመነ ወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አይደለም፤ ተጠቃሚዎቹ “ጥቂቶች ናቸው» ብለው የደመደሙት ሀሳብ ዕውነት አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ክህደት በመሆኑ፣ ትግሬዎች በዘመነ የወያኔ አገዛዝ እንዴት ተጠቃሚዎች እንደሆኑ ተጨባች ነቃሾችን በማቅረብ የፕሮፌሰር መሥፍንን ሀሳብ መሞገት  [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]

 

የትግራይ ብሄርተኝነት እንዴት ወደ ፋሽስት ስርዓትነት እያመራ እንደሆነ ለማሳየት እንሞክር(ክፍል 1) (ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ)

$
0
0

የትግራይ ብሄርተኝነት እንዴት ወደ ፋሽስት ስርዓትነት እያመራ እንደሆነ ለማሳየት እንሞክር(ክፍል 1)
(ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ)tgh

የሰው ልጆች አብረው በማህበረሰብ ለመኖር ይቻላቸው ዘንድ ለአብሮ መኖር ፀር የሆኑ ምግባሮችንና ባህሪዎችን ማስቀረት መቻል አለባቸው። አለበለዚያ ማህበራዊ ኑሮ ሊታሰብ አይችልም። ሰውን ከእንሰሳየሚለየው ከስሜት ባሻገር የማሰብና የማመዛዘን ክህሎቱ ነው። ህሊና አንድ ሰው በጎና ክፉውን፤ መጥፎና ጥሩውን፤ ትክክለኛና ሃሰተኛውን ነገር ለይቶ እንዲያውቅ የሚያስችለውን ችሎታ ወይም ክህሎት አመልካች ነው። የሰው ልጅ የማሰብና የማሰላሰል ልዩ ችሎታ ስላለው በሚኖርበት ማህበራዊ ስፍራ የሚከሰቱትን ነገሮች ሊገነዘብና ሊዳኝ ይችላል። ልጅ ሲያድግ በጎውና ክፉውን እየለየ የሚያውቀው ከአሳዳጊ ቤተሰቦቹ፣ ከጎረቤቱ፣ በሚኖርበት አካባቢ ከሚገኙ ሰዎች፣ ተቇሞች፣ ትምህርት ቤት፣ መስጊድ፣ ቤተ ክርስቲያን ወዘተ ነው። የህሊና ዳኝነትና ለሱ መገዛት መቻል የአንድን ሰው ነፃ መሆንና በራሱ ነፃነት በጎናክፉውን የመወሰን ችሎታን ያሳያል። በጎሳ ብሄርተኝነት የተለከፈ አንድ ሰው አንደ ራስ-በቅ(self reliant) ሰው በራሱ ሀሳብና ፈቃድ ተመርቶ ማህበራዊ ህይወቱን ሊመራ አይችልም። በዚህ አይነት በጎሳ ብሄርተኝነት አይምሮአቸው የተመረዙ ሰዎች የግል ማንነታቸው መገለጫ የሆነውን እንደ ሰው የማሰብ ችሎታቸውን ለጎሳ መሪዎቻቸው አሳልፈው ስለሚሰጡ የአንድ በጎሳ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በሙሉ የጎሳ መሪዎቻቸው የሚነግሯቸውን እየሰሙና እየተከተሉ እንደ አንድ ሰው ወይም እንደ ጎሳ መሪያቸው ማሰብ ይጀምራሉ። ይህ ፈረንጆች “group thinking” የሚሉትና የአንድ አክራሪ የጎሳ ድርጅት ተከታዮች አንድ ወጥ የሆነ አስተሳሰብ (homogenization of thought) ተሸካሚዎች የሚሆኑበት ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት በአክራሪ የጎሳ አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በጎሳ መሪዎቻቸው ትዕዛዝ(ውሳኔ) ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል። የጎሳ መሪዎቹ የወደዱትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ። የጎሳ መሪዎቹ የመረጡለትን ነገር ሁሉ አንድ ሰው ለመቀበል ይገደዳል። ምን እንደሚያስብ ፤ ከማን ጋር ቡና መጣጣት እንዳለበት፤ ከማን ጋር መወያየት፤ ማንን ማፍቀር ማንን መጥላት፤ በየትኛው የፖለቲካ ስብሰባ ላይ መሳተፍ ወይም አለመሳተፍ እንደሚገባው ወዘተ የጎሳ መሪዎቹ ይነግሩታል። በዚህ አይነት የግል ማንነቱን ያጣ ሰው ይሆናል። በአለም ላይ ሰዎች የጎሳ ብሄርተኝነትን፣ አክራሪ የሃይማኖት ፍልስፍናን ወዘተ በመሣሠሉ መርዘኛ አመለካከቶችን በሚያራምዱ ፍልስፍናዎች ምክንያት የህሊና ዳኝነት ችሎታቸውንም ሆነ ክህሎታቸውን አሽቀንጥረው የጣሉበት ሁኔታ እንደነበረ ታሪክ ዘግቧል። ለምሳሌ በናዚ ጀርመን ውስጥ ሰዎች እንደ ሰው ለህሊናቸው መገዛትን አቁመው ህሊና ቢስ በመሆን በጥላቻ የሰከሩ መሪዎቻቸውን እነ ሂትለርን፤ በጣሊያን እነ ሞሶሎኒን በጭፍን የተከተሉበት ሁኔታ እንደነበር በ ሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት አይተናል። በዚህ ወቅት በናዚ ፍልስፍና መስፋፋት የተነሳ ብዙ ጀርመኖች ህሊናቸውን ስተው የሂትለር ፖርቲ ደጋፊና አጫፋሪ ሆነው ስለነበር ከብዛኞቹ የጀርመን ተወላጆች ሰው የሚያሰኛቸውን የህሊና ዳኝነት ክህሎት አሽቀንጥረው በመጣል የግል ማንነታቸውን አጥተው የናዚን ፋሽስት የፖለቲካ ፍልስፍና ስርዓት ተከታዮችና አቃፊ ደጋፊዎች ሆነው ነበር። የናዚም ሆነ የፋሽስት አክራሪ የጎሳ ብሄርተኝነት ተከታዮችን ከሰውነት ተራ በመውጣት የግለሰብ ማንነታቸውን አጥፍቶ እንደ እንሰሳት መንጋ የአንድን የጎሳ ድርጅት መሪዎች በጭፍን እንዲከተሉ ያደርጋል። እነዚህ በመሪዎቻቸው ሀሳብና ትዕዛዝ በጭፍን የሚመሩ ህሊና ቢስ የተደረጉ በጎሳ ብሄርተኝነት ስሜት የሰከሩ የአንድ ጎሳ ተወላጆች የሆኑ ጀሌዎች መሪዎቻቸው አድርጉ ያሏቸውን ነገሮች ሁሉ ካለ አንዳች ማወላወልና ማንገራገር ይፈፅማሉ። በዚህ አይነት ህሊናቸውን ያጡ ጀሌዎች በበዙበትና ስልጣን በተቆናጠጡበት ሃገር ውስጥ ሊከሰት የሚችለው አደጋ የብዙ ንፁሃን ዜጎችን ህይወት ሊቀጥፍ ይችላል፤ ሀገርን ያፈርሳል፤ ህዝብን ይበትናል። ትላንት የናዚ ጀርመኖች ፍልስፍና ገዥና ዋና አስተሳሰብ (dominant ideology) በነበረበት ግዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዳዊያን፣ እስላሞች፣ ጂፕሲዎች ወዘተ በገፍ እየተነዱ ሲፈጁ አብዛኛው የጀርመን ህዝብ ድርጊቱን ሳይቃወም እንዲያውም ሲደግፍ ታይቶ ነበር። በዛን ጊዜ በርካታ ጀርመናዊ በናዚ ጭፍን የጀርመን የበላይነት ፍልስፍና ( Deutschland ueber alles) ወይም ጀርመን ከሁሉ በላይ በሚለው የአርያን የዘር የበላይነት በሚያንፀባርቅ አስተሳሰብ አይምሮው ተመርዞ ነበር። በዚህ ምክንያት የጀርመን ህዝብ በጎውና መጥፎውን የሚለይበትን ህሊናውን አሽቀንጥሮ በመጣል የራሱን ማንነት አሳልፎ ለናዚ መሪዎች በገፀ-በረከትነት ሰጠ።
ዛሬ በኢትዮጲያችን ተመሣሣይ ሁኔታ እየታየ ነው ብዬ እሞግታለሁ። የወያኔ ድርጅት ትግል ሲጀመር የዚህን ድርጅት እኩይ አላማ በመቃዎም የተገረፉ፣ የተገደሉ፣ የተሰደዱ የትግራይ ተወላጆች እንዳሉና ለነዚህም ከፍተኛ አክብሮት እንዳለኝ ልገልፅ እፈልጋለሁ። ለሀገራቸው ያደረጉትንም ውለታ አልረሳም። ይሁን እንጂ ለ 17 አመታት በጦርነት እንዲሁም ላለፉት 38 አመታት ወይም 39 አመታት በፀረ ኢትዮጲያ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ አብዛኛው የትግራይ ተወላጅ በተለይም ቀለም ቆጠረ የሚባለው ክፍል በዛሬው ወቅት የመርዘኛው የትግራይ ብሄርተኝነት ሰለባ በመሆን የዚህ ያለው ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ የወያኔ አገዛዝ ደጋፊና አቃፊ ከሆነ ውሎ አድሯል። በዚህ ምክንያት የወያኔ ስርዓት በሌሎች የኢትዮጲያ ጎሳዎች ላይ የሚፈፅመውን ግፍ ከመቃወም ይልቅ በርካታ የትግራይ ተወላጅ ይህንን የወያኔን ስርዓት በፅናት ከሚቃወሙ ኢትዮጲያውያን በተቃራኒ ጎን መቆምን መርጧል። ይህንን ገደምም ጠመምም ሳላደርግ ባለፉት 21 አመታት ስናገር እንደቆየሁት ዛሬም በናንተ ፊት በአደባባይ እናገራለሁኝ። የዚህንም አደገኛ አዝማሚያ አውዳሚ ፍፃሜ አመለክታለሁኝ። እስቲ በቅድሚያ የቀድሞ የወያኔ ትግሬዎች መሪ መለስ ዜናዊ ለትግራይ ህዝብ ካደረገው እጅግ እብሪትና የማን አለብኝነት ከተጠናወተው ንግግሩ አንዱን ጠቅሼ የትግራይ ብሄርተኝነት ከምን አደገኛና ወደ ሗላ ሊመለስ ከማይችልበት ጫፍ እንደደረሰ መስረጃ አቅርቤ ላስረዳ ልሞግት። ይህ ከዚህ በታች የምጠቅስላችሁ ንግግር መለስ ዜናዊ መቀሌ ውስጥ የወያኔን የድል በዓል ሲያከብር በመቶ ሺዎች ለሚቆጠር የትግራይ ህዝብ ካደረገው ንግግር ነው፦

“ይህ ህዝብ እንኯን የሌሎች ባዕዶች ያልሆነ። እንኯን ከእናንተ ተፈጠርን። ይህ የእያንዳንዱ ታጋይ እምነት ነው። እንኯን ከእናንተው ማህፀን ተፈጠርን። እንኯን የኛ ሆናችሁ። እንኯን የሌላ የባዳ አልሆናችሁ። እንኯን በማዶ እያየናችሁ የምንቀናባችሁ አልሆናችሁ።”

በዛው እለት በተያያዘ ንግግሩ መለስ ለትግራይ ወጣቶች እንዲህ ብሎ መልዕክቱን አስተላልፎ ነበር፦

“እናንት ወጣቶች እዚህ ያላችሁበት መድረክ እንድትደርሱ ሲባል ታላላቆቻችሁ ላባቸውንና ደማቸውን አፍስሰዋል። ታላላቆቻችሁ በየጉራንጉሩ በየሸለቆውና በየተራራው ቀርተዋል። ታላላቆቻችሁ አጥንታቸው በየተራራው ተበትኗል። አጥንቶቻቸው በየተራራው የተበተነበት ምክንያት ትግራይ እንድትለማ በሚል ነው። እነኚህን አጥንቶች እንዳትረግጧቸው እንዳታረክሷቸው፤ ሁኔታውን ካመቻቹላችሁ በሗላ እንዳትከዷቸው ሌት ተቀን መጣር ይኖርባችሗል። “

ይህ ንግግር አንድ በብሄርተኝነት የሰከረ እነ ሂትለር ካደረጏቸው የእብሪት ንግግሮች የላቀ ነው።ዛሬ በዚህ የተቀሰቀሱ ልባቸው ያበጠ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ተፈጥረዋል።
ዛሬ የወያኔ ትግሬዎችና በስራቸው ያሰለፏቸው የጎሳ ተከታዮቻቸው በአብዛኛው ህሊና እንዳለው ግለሰብ በጎውንና ክፉውን አመዛዝኖ ፍርድ ከመስጠት ይልቅ በወያኔ ድርጅት ትዕዛዝ እንደ መንጋ በጀሌነት የሚመሩ ፍጡራን ሆነዋል። የአንድ ጎሳ ተወላጆች የራሳቸው ጎሳ ተወላጆች የሆኑ ሰዎች በሌሎች ከነሱ ጎሳ ውጪ ባሉ ተወላጆች ላይ የሚፈፀሙትን ማናቸውንም ህሊና ያለው ሰው ማየት የሚችለውን ጥፋትና ግፍ ለማየት ይሳናቸውና የጎሳ መሪዎቻቸው የሚሏቸውን እየሰሙ ይህን ግፍ ለሚፈፅሙት የጎሳ መሪዎቻቸው ጭፍን ድጋፋቸውን ሲሰጡ ይህ ሁኔታ ለአንድ ሃገር ታላቅ አደጋን ይጋብዛል። የጎሳ ፍጅት (Genocide) መነሾም ይሆናል። በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ የታጠቁ የትግራይ ተወላጆች በሃይል ከጎንደር ተቆርሶ ወደ ትግራይ ክልል የተጠቃለለውን ለም መሬት ይዘው አሻፈረኝ ያለውን ነባሩን ህዝብ ገድለው ከፊሉን የተወለደበትንና ያደገበትን ቀዬ ጥሎ ወደ ሱዳን ፣ አዲስ አበባና ጎንደር እንዲሰደድ ማድረጋቸው የወያኔ ትግሬዎች የተፀናወታቸውን ህሊና ቢስነትና አመለካከታቸው በጎሳ አስተሳሰብ የተመረዘበትን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በቅርቡም የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ታሪካዊውን የዋልድባን ገዳም የትግራይ ክልል አካል ነው በማለት በገዳሙ ውስጥ የነበሩትን የትግራይ ቀሳውስትና መነኮሳት በጎሳ ስሜት ቀስቅሶ ከጎኑ በማሰለፍ የወሰደው ገዳሙን የመቆጣጠር እርምጃ ይህንኑ ህሊና ቢስነትና የአንድ አናሳ የጎሳ ተወላጆችን እብሪት የሚያሳይ ድርጊት ነው። እንደ ኢትዮጲያ ግፍ ሞልቶ በፈሰሰበት ሀገር ውስጥ ይህ አይነቱ ጭፍንነት ሗላ ጎሳን መሠረት ላደረገ ከፍተኛ ፍጅት(Genocide) የሚዳርግ ነው። ዛሬ የአማራን ህዝብ ከሶማሌ ከቤኒሻንጉል ከደቡብና ከኦሮሚያ ክልል እንዲዎጡ የተደረገበት በፋሽስቱ የጣሊያን የወረራ ግዜ እንኯን ያልተፈፀመ ዘግናኝ ድርጊት ሲፈፀም የዚህን የአማራ የጎሳ ጥቃት እያስፈፀሙ ያሉት የወያኔ ትግሬዎች መንግስት፣ የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ከላይ እስከታች የዘረጋው የስለላ መረብ አዛዦችና የወታደራዊ ጭፍሮቻቸው እንደሆኑ አንዘንጋ። ~ ~

በክፍል ሁለት የወያኔ መንግስት አንዳንድ ፋሽስታዊ ጠባዮችን እንመለከታለን።

ቅድመ-ውህደቱና ልዩ ገጠመኞቹ

$
0
0

በ  ዘሪሁን ሙሉጌታ
ሰንደቅ

 

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የቅድመ ውህደት ስምምነት ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተካሄደው የግማሽ ቀን ስነ-ስርዓት ተከናውኗል። በስነስርዓቱ ላይ በርካታ ታዋቂ ሰዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና ዲፕሎማቶች ተገኝተው ነበር

የቅድመ-ውህደቱ አጠቃላይ ይዘት

Politiczedየውህደቱ የፊርማ ስነ-ስርዓት በተካሄደበት ወቅት የሁለቱ ፓርቲ አመራሮች ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል። የሁለቱም መሪዎች ንግግር ውህደቱ ከመዘግየቱ በስተቀር አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ከቅድመ ውህደት ስነ-ስርዓት ፊርማው በኋላ ለጋዜጠኞች አጠር ያለ ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ስለነበር በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ ጋዜጠኞች ለሁለቱ ፓርቲ መሪዎች ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር።

ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል በቀጣይ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የሚመሰረተው ፓርቲ ስያሜ ምን ይሆናል የሚል ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ስያሜው የሁለቱን ፓርቲዎች ስያሜ ባቆራኘ መልኩ አዲስ ስም ይወጣል ብለዋል። ስያሜው የሚፀድቀው በአዲሱ ውህድ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ መሆኑንም አስረድተዋል።

በተመሳሳይ ሌሎች ፓርቲዎችን ታሳትፋላችሁ? ለሚለው የጋዜጠኞች ጥያቄ መኢአድና አንድነት በመዋቅር ጥንካሬና በአባላት ብዛት በአንፃራዊ ደረጃ ከሌሎች ፓርቲዎች የተሻሉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ይህ ብቻ በቂ ባለመሆኑ ሌሎች ፓርቲዎች እንዲገቡበት በማድረግ ኢህአዴግን የሚፎከር አብይ ብሔራዊ ፓርቲ ለማቋቋም መታሰቡን ገልፀዋል። የአሁኑም የአንድነትና የመኢአድ ቅድመ-ውህደት እንደ ውህደት ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በአንድ ወር ውጥ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ አዲሱን ውህድ ፓርቲ ለመፍጠር የአቅም ጉዳይ በጋዜጠኞች ተነስቶ የነበረ ሲሆን፤ “ችግራችን የአመራር እና ድርጅታዊ አቅምን የማንቀሳቀስ እንጂ የአቅም አይደለም። አባላቶች በከፊልም ቢሆን የራሳቸውን ወጪ በመሸፈን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የሁላችንንም ፍላጎት እናሳካለን” ሲሉ ኢንጂነር ግዛቸው መልሰዋል። በቅርቡም የሁለቱም ፓርቲዎች ብሔራዊ ም/ቤት የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ በመሰየም ሁኔታውን ያፋጥናል ብለዋል። አዲሱ ውህድ ፓርቲም ከሁለቱ ፓርቲዎች የተውጣጣ 400 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ይኖሩታል ብለዋል።

ቀደም ሲል በመኢአድ በኩል “አንድነት ከመድረክ ካልወጣ ውህደቱ አይሳካም” የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለተነሳው ጥያቄ ጉዳዩ በሕግ ባለሙያዎች ታይቶ በመድረክም ሆነ አዲስ በሚፈጠረው ውህድ ፓርቲ ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ እንደሌለ መረጋገጡ፣ አንድነት ከመኢአድ ጋር ውህደት በሚፈፅምበት ወቅት ሕጋዊ ሰውነቱን ወዲያውኑ ስለሚያጣ ከመድረክ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ወዲያውኑ የሚቋረጥ በመሆኑ ችግር እንደማይፈጠር ተረጋግጧል ሲሉ ኢንጂነር ግዛቸው ተናግረዋል።

ሌላው ከጋዜጠኞች የቀረበው ጥያቄ፤ ቅድመ ውህደቱ የተሳካው በፓርቲዎቹ አመራሮች ሳይሆን፤ በሽማግሌዎች ግፊት ስለሆነ ምን ያህል ዘላቂነት ይኖረዋል የሚል ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢንጂነር ግዛቸው፤ በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የውህደት ፍላጎት መንፀባረቅ የጀመረው ከአራት ዓመት በፊት መሆኑን አስታውሰው፤ ለመዋሐድ ፍላጎቱ የመጣው ከአባሉና ከአመራሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፤ ነገር ግን ሽማግሌዎቹ የመጡት በመጨረሻ ውህደቱ እንዲፋጠን ድጋፍ ለማድረግ ነው ብለዋል።

አቶ አበባው መሐሪ (የመኢአድ ሊቀመንበር) በበኩላቸው አንድነት ከመድረክ ጋር ስላለው ግንኙነት ሲመልሱ፤ እስካሁን ድረስ ውህደቱን ሲያጓትት የቆየው የአንድነትና የመድረክ ግንኙነት የጠራ ባለመሆኑ ነው ብለዋል። መኢአድ ከአንድነት ጋር ሲዋሐድ ይሄው ችግር ወደ ውህዱ ፓርቲ እንዳይሄድ በመፍራት ጥያቄው በመኢአድ በኩል መነሳቱን ገልፀዋል። ሆኖም ችግሩን የሚያጠና ሁለት ገለልተኛ የሕግ ባለሙያዎች ተመድበው የመድረክና የአንድነት እንዲሁም የመኢአድ ከምርጫ ቦርድ ሕግና ደንብ ጋር ታይቶ በመጨረሻ ወደ ውህዱ ፓርቲ ሊተላለፍ የሚችለው የገንዘብና የንብረት እንጂ የፖለቲካ ባለመሆኑ በዚሁ በመተማመን የቅድመ-ውህደት ሰነዱ ሊፈረም መብቃቱን ተናግረዋል።

ሽማግሌዎቹ በአደራዳሪነት ይሳተፉ እንደነበር የጠቀሱት አቶ አበባው፤ የሽማግሌዎቹ በጎ አስተዋፅኦ ቢኖርም፤ አሁን ግን ሁለቱ ፓርቲዎች ድርድሩን በራሳቸው የጨረሱት መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪነት ከጋዜጠኞቹ የቀረበው ጥያቄ ፓርቲዎቹ የውስጥ ችግራቸውን ሳይፈቱ ወደ ቅድመ-ውህደት ፊርማ ለምን መጡ? የቅድመ-ውህደት ፊርማው ከማካሄዱ በፊት በር ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ የነበሩ ወገኖች ነበሩ ለሚለው ጥያቄ፤ አቶ አበባው ሲመልሱ በዚህ ወቅት ፓርቲዎቹ በውስጥ ችግር ላይ አለመሆናቸውን ይልቁኑ ቅድመ ውህደቱን እንዳይፈረም ሁከት የፈጠሩት የመኢአድ አባላት ሳይሆኑ የአዲስ አበባ የኢህአዴግ አባላት ናቸው ብለዋል። “የኢህአዴግ አባል የመኢአድን የውስጥ ችግር ይፈታ የማለት መብት የለውም” ሲሉ በመግለፅ ጉዳዩ ፓርቲዎቹን ውህደት እንዳይፈፅሙ በመንግስት በኩል የተቀናጀ ጥረት መኖሩን የሚያመለክት ከመሆኑም በላይ ኢህአዴግ ጠንካራ ፓርቲ እንዳይፈጠርና በሕዝባችን ላይ የጭቆና ቀንበር ጭኖ ለመቀጠል መፈለጉን የሚያመላክት ነው ብለዋል።

ፓርቲዎቹ ከሚያደርጉት ውህደት ጎን ለጎን በ2007ቱ ምርጫ የሚኖራቸው ተሳትፎና ለዚያም የሚሆን ስትራቴጂ ምን እንደሆነ ከጋዜጠኞች ተጠይቀው የነበረ ሲሆን፤ ምርጫውን በተመለከተ የውህዱ ፓርቲ የሚወስነው እንደሆነ ኢንጂነር ግዛቸው ጠቅሰው፤ በአጠቃላይ ሁለቱም ፓርቲዎች የምርጫ ፓርቲዎች እንደመሆናቸውና በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ በመሆኑ ምንጊዜም ለምርጫ ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል። በአንድነት ፓርቲ በኩል አማራጭ ፖሊሲ የምርጫ ስትራቴጂ፣ ማኒፌስቶ፣ ማዘጋጀት ዕጩዎችንና ታዛቢዎችን እየፈተሸ መሆኑንና በመኢአድም በኩል ይሄው ጉዳይ ስለሚኖር የሁለቱንም አጣምረን እንቀጥላለን ብለዋል። በምርጫ መሳተፍ፣ አለመሳተፉ ግን ወደፊት እንደሚወሰንና የዴሞክራሲ ተቋማቱ ነፃ መሆንና መጠናከር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።

በጋዜጠኞች ከተነሱ ሌሎች ጥያቄዎች መካከል ከፓርቲዎች ውህደት በኋላ አንጃዎች የመፈጠር ሁኔታዎች ስለሚስተዋል ለዚህ ችግር የተቀመጠ ስትራቴጂ አላችሁ ወይ የሚል ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢንጂነር ግዛቸው፤ ውህደቱን ተከትሎ አንጃ መውጣቱ ፓርቲዎቹን እንደማያሳስባቸው ነገር ግን የሚወጣው አንጃ ስርዓት አልበኛ ሲሆን ነው ችግሩ ብለዋል። አንጃ የሚወጣ ከሆነም ሁለቱ ፓርቲዎች በተቀመጠው መዋቅር በዴሞክራሲያዊና በሰለጠነ መንገድ መወጣት ይቻላል። ነገር ግን በስርዓት አልበኝነት ቢሮ በመውረር ከኢህአዴግ ጋር በመገናኘት መሰናክል የመፍጠሩ አካሄድ አንጃ መፍጠር አይደለም ብለዋል።

“ውህደቱ አልተስማማኝም የሚል ቡድን ካለ መብቱ ነው። ሌላ ፓርቲ ማቋቋም ይችላል። የሰለጠነ ፖለቲካ ለማካሄድ የጉልበት፣ የመደባደብና ከባህል ውጪ የሆነ ነገር ሲሆን ግን ያሳፍራል” ሲሉ ኢንጂነሩ የገለፁ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ከዚህ አንፃር በአንድነት በኩል የሚያሰጋ ነገር የለም ብለዋል።

ውህደቱ በመዘግየቱ እንደተቋም ሁለቱን ፓርቲዎች በፍጥነት ባለመስራታቸው ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ሁለቱም አመራሮች ገልፀዋል። በተለይ አቶ አበባው መሐሪ ውህደቱ ለምን ዘገየ ለሚለው የጋዜጠኞቹ ጥያቄ ሲመልሱ፤ የፓርቲዎችን መዋቅርና የፖለቲካ ፕሮግራም በማጣጣም ሂደት እንጂ ከግል ፍላጎት አለመመቸት ጋር የተያያዘ አይደለም ብለዋል። በአጠቃላይ ከአንድ ወር በኋላ በሚጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ከመኢአድ 200 ከአንድነት 200 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት አዲስ ውህድ ፓርቲ ይፈጠራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቅድመ-ውህደቱ ልዩ ገጠመኞች

የቅድመ-ውህደት ስነ-ስርዓቱን ልዩ ካደረጉት አጋጣሚዎች መካከል የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢዴፓ) አመራር አባል የሆኑት አቶ ሞሼ ሰሙ በፕሮግራሙ ላይ መገኘት አንዱ ነበር። የእሳቸው በቦታው መገኘት ከምርጫ 97 በኋላ ከፖለቲካ ልዩነት ባሻገር በግለሰብ ደረጃ የተፈጠረውን መቃቃር ሊያለዝብ የሚችል ጥሩ ጅምር እንደሆነም እየተገለፀ ነው። የአንድነትም ሆኑ የመኢአድ የፓርቲ አመራር አባላት ለአቶ ሞሼ ሰሙ ያሳዩት አዎንታዊ አቀባበል በዕለቱ የነበሩ ጋዜጠኞችን ትኩረት ስቦ ነበር። አብዛኛዎቹ የአንድነትና የመኢአድ አመራሮች አቶ ሞሼን ያገኙዋቸው ከምርጫ 97 በኋላ መሆኑን በአድናቆት ሲናገሩ ታይተዋል።

አቶ ሞሼ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰፊ የፖለቲካ ተሳትፎ እያሳዩ የመጡ ፖለቲከኛ ናቸው። በገዢው ፓርቲ ፖሊሲዎች ላይ ከሚያነሱዋቸው የሰሉ ትችቶች ባሻገር ለሀገሪቱ ፕሬስ መጠናከር የሚሰጡዋቸው ገዢ ኀሳቦች በመስኩ ባለሙያዎችና አጋሮቻቸው ጭምር እውቅና እየተሰጠው ነው። አቶ ሞሼ በሰኔ አንዱ የመኢአድና የአንድነት የቅድመ ውህደት ስምምነት ስነ-ስርዓት ላይ በድፍረት በመገኘታቸውም በኢዴፓ እና በሌሎች ተቃዋሚዎች መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን ያለመተማመን ስሜት በመጠኑም ቢሆን እንዲለዝብ ምክንያት ሊሆን ይችላል ብሎ መገመት ይቻላል።

ሌላው በዕለቱ ስነ-ስርዓት ላይ ከታዩ አወዛጋቢ ጉዳዮች መካከል ሊጠቀስ የሚገባው የቅድመ ውህደት ስምምነቱን ለመረበሽ የተደረገው ጥረት ነው። የውህደቱን ስነ-ስርዓት ለማወክ የተደረገው ጥረት እንደ ሀገር የሚያሳፍር፣ እንደ ዜጋም የሚያሳዝን ነው።

ከአስተባባሪዎቹ ገለፃ መረዳት እንደሚቻለው የውህደት ስምምነቱ እንዳይካሄድ በር በመደብደብና ፀያፍ ቃል በመናገር ሲበጠብጡ የነበሩት ሦስት ግለሰቦች ነበሩ። በእርግጥ ስነ-ስርዓቱ ወደሚከናወንበት ስፍራ እንዲገቡ የተፈለገው አስቀድመው የተጠሩ እና ለዚያም ልዩ ባጅ ያደረጉ ብቻ ነበሩ። ሆኖም የተወሰኑ ሰዎች “ልግባ፣ አትገባም” የሚል ውዝግብ በሩ ላይ ይስተዋል ነበር። በመጨረሻም ውዝግቡ ተባብሶ በር እስከመገንጠልና ድንጋይ እስከመወራወር ተደረሰ። በመሀሉም በተወረወረ ድንጋይ በመኢአድና በአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ላይ የጥርስ መውለቅ አደጋ በመድረሱ ሁኔታውን አሳዛኝ ትዕይንት አድርጎታል። በዕለቱም ስብሰባውን ከረበሹ ሦስት ሰዎች መካከል አንዱ የኢህአዴግ አባል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቅርቡ ሃያ ሦስተኛው የግንቦት ሃያ በዓል ሲከበር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከተናገሩዋቸው በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ለሀገሪቱ መድበለ ፓርቲ መዳበርና ለተቃና የምርጫ ስርዓት ከተቀመጡ ሕጎችና አሰራሮች ባሻገር ኢህአዴግ አባላቱን በስነ-ምግባር በማነፅ ተከታታይ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን፣ በሂደቱም የሚያጠፉ አባላቱን ለመቆጣጠር ከድርጅቱ የማንንም ምክር ሳይፈልግ በራሱ የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ መግለፃቸው አይዘነጋም።

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>