Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የሞረሽ እንቅስቃሴ ላልተገለጸለን አንዳንድ ነጥቦች

$
0
0

ከሞረሽ ደጋፊ፣ ረቡዕ ሰኔ ፫ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም.

moresh
ሞረሽ ወገኔ በወያኔ ዘረኛ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ እቅድና እንቅስቃሴ መሠረት፣ በአገራችን በኢትዮጵያ በአማራ ጎሳ ላይ በየአቅጣጫው እየደረሰ ባለው መጠነ ሰፊ ጉዳት ምክንያት ብሶት የወለደው ድርጅት ነው። በሀገራችን ታሪክ ብዙ ሳንጓዝ «አምባገነን» የሚባለው የወታደራዊው ደርግ የግዛት ዘመን ሳይቀር፣ ጎሳዎችን ሳይለይ በፖለቲካ አመለካከት ምክንያት ኢትዮጵያውያንን በግድያ ንብረታቸውንም ለመንግሥት በማድረግና በመውረስ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰባቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። የአማራው ጎሳ አባላት እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ተጠቂ የነበሩ መሆናቸው የሚካድ አይደለም። በኢሕአፓም ሆነ በሌሎች የተቃውሞ ትግሎች የተሳተፉ፣ መስዋዕትነት የከፈሉ፣ በደርግ በኩልም በመሆን በተቃዋሚዎቹ ዒላማ ተደርገው የተገደሉ የዚሁ ጎሳ አባላት ብዙ ናቸው። ከዚያ በፊት የነበረውንም የቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት «ፍትሐዊ አይደለም» ብለው ከተነሱት የእንቅስቃሴ መሪዎችና ሰለባዎች ውስጥ ከአማራው ጎሳ የተወለዱ፣ ብዙ ለፍትሕ የቆሙ እንደነበሩ፣ ወያኔዎች ሳይቀር ይመሰክራሉ። ለአብነትም እነ የንዋይ ወንድማማቾች ብርጋዴር ጄኔራል መንግሥቱ እና ግርማሜ ንዋይ፣ ዋለልኝ መኮንን እና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል። እነዚህ «የኢትዮጵያ አስተዳደር ትክክል አይደለም» በሚል መስዋዕትነትን የከፈሉ ከአማራ ጎሳ የተወለዱ ኢትዮጵያውያኖች እንጂ «አማራ ነን» በሚል የተንቀሳቀሱ አልነበሩም።


ወያኔዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥር አናሳ መሆናቸውን ስለሚገነዘቡ፣ በስልጣን ይቀናቀነኛል የሚሉትን ወገን ሌሎችን አስተባብሮ ማጥቃት እንደ ስትራተጂ የሚጠቀሙበት ነው። በመሆኑም በኢትዮጵያ ተፈጥረው ለነበሩ ችግሮች ብቻ ሳይሆን ያልነበረ ችግርን እንደነበረ አድርጎ፣ ለዚህም የአማራውን ጎሳ ተጠያቂ ማድረግ፣ የአጭር ጊዜ ፍላጎቱን እንደሚያሳካለት በማሰብ ነው። ስለሆነም በትላልቅ ጎሳዎችም ሆነ በአናሳ ጎሳዎች እንዲጠላና ዘመቻ እንዲካሄድበት፣ ከፍተኛ የሆነ የጥፋት ሥራ ሠርቷል። የዋህ የሆኑ የዚህ የወያኔ እኩይ የሆነ አስተሳሰብ ሰለባ የሆኑ ጎሳ አባላትም ለዘመናት አብረዋቸው የኖሩ የአማራ ጎሳ ተወላጂ የሆኑ ጎረቤቶቻቸው ላይ ከ«ውጡልን» አንስቶ እስከ ግድያ የሚደርሱ ብዙ በደሎች ሲደርስባቸው በጥቃቱ በመተባበር ወይም ዝም በማለት አሳልፈዋል፣ ወይም በማሳለፍም ላይ ናቸው። ይህንን በአማራው ጎሳ ላይ ያነጣጠረ ጭፍን ጥላቻ ማንኛውም ፍትሕን የሚሻ ዜጋ ሁሉ ሊቃወመውና ሊያስቆመው ይገባ ነበር። ሆኖም ግን ወያኔ አገሪቱን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በአማራው ጎሳ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት በተጠናከረ መልኩ ሲፈጸም እናያለን።


በተደራጀ ኃይል ጥቃት የሚደርስባቸው ተጠቂዎች ከሚደርስባቸው ጥቃት ሲሸሹና የመጠቃት ፍራቻ ሲኖራቸው በጋራ መከላከልን መሻት ተፈጥሯዊ ክስተት ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ዘርን መሠረት ያደረገ የፖለቲካ አደረጃጀት መኖር እንደሌለበት የሞረሽ ወገኔ መሥራቾች ጠንቅቀው ያውቃሉ። የፖለቲካ ድርጅቶች ዘርን መሠረት ሲያደርጉ የእድገት ደረጃን ያለማወቅና ሰዎችን አንድ የሚያደርጋቸው ቀለማቸው፣ ቋንቋቸው ወይም ባህላቸው ብቻ ሳይሆን አመለካከታቸው መሆኑን አለመገንዘባቸውን የሚያሳይ ነው። የሞረሽ መሥራቾች የወያኔን የጎሳ ፖለቲካ ቢቀበሉት ኖሮ ቀደም ብለው የፖለቲካ ድርጅት በመሠረቱ ነበር። ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ መጠበቅም ባላስፈለገ ነበር።


ሞረሽ እንደ መርህ በየትም ቦታ የተረገጠች ፍትሕን ትክክል አይደለም ብሎ ያምናል፣ እንዲስተካከልም ድምጽ ያሰማል። በመሆኑም በኦሮሞም፣ በጋምቤላም፣ በሶማሌም፣ በትግሬም ወይም በሌሎች ጎሳዎች በገዢውም ሆነ በሌላ ሥልጣን ፈላጊ ቡድን የሚደርሰውን ጥቃት ሁሉ አጥብቆ ይቃወማል። ሞረሽ ኢትዮጵያ የብዙ ጎሳዎች ደሴት እንደመሆኗ መጠን አንዱ ጎሳ ተጎድቶ ወይም አንዱ ጎሳ የሌለበት ኢትዮጵያ አትኖርም ብሎ ያምናል። ስለሆነም የአማራ ጎሳ የሌለባት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አትባልም፣ የኦሮሞ ጎሳ የሌለባት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አትባልም፣ የትግሬ ጎሳ የሌለባት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አትባልም እንዲሁም ሌሎች ጎሳዎች የሌሉባት ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ አትባልም። በመሆኑም አንዱ ሲበደል ተበዳዩ ብቻ ሳይሆን ሌላውም ሁሉ ቁጭቱን ሊገልጽና ድርጊቱን ሊቃወመው ይገባል። ያ ሲሆን የሚፈራው ሥልጣን የያዘው ሳይሆን ሕዝብ ይሆናል ማለት ነው። ትክክለኛው ፍርሀትም ይሄው ነው።


ሞረሽ በዚህ መርሁ የማንኛውም ጎሳ አባላት በግልም ይሁን በቡድን መበደል የተቃውሞ ድምጹን አጉልቶ ያሰማል። ሌሎች ጎሳዎች በዛ ያሉ ድምጽ የሚያሰሙ ቡድኖችና ድርጅቶች ቢኖሯቸውም የአማራው ጎሳ ግን በታላቁ የኢትዮጵያ ልጅ በፕሮፌሰር አሥራት ተጀምሮ ከነበረው መአሕድ በስተቀር ለጎሳው አቤቱታ የሚያሰማ፣ እየደረሰበት ያለውን ጉዳት የሚቃወም፣ የተሰባሰበ ቡድን የለውም። በሌላ በኩል ግን በወያኔ መንግሥት አስተባባሪነት በአማራው ጎሳ ላይ በየቦታው እየደረሰ ያለው ጉዳትና ጥቃት ለመለካት የሚያስቸግር ነው። በመሆኑም ሞረሽ ወገኔ በአማራው ጎሳ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማሳወቅ አቅሙ የፈቀደውን ትግል የሚያደርግ ከመሆኑም በተጨማሪ ሌሎች አግባብነት ያላቸው መንገዶችን በመጠቀም በደል የሚፈጽሙትና የሚያስፈጽሙትን ከሕግ ፊት ለማቅረብ የበኩሉን ጥረት ያደርጋል። ሞረሽ ወገኔ ለአማራው የሚመኘውን ሰብአዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች መብቶች ለማንኛው የሀገሪቱ ጎሳ አባላት እንደሚመኚና ለተፈጻሚነቱም ድምጹን በማሰማት የመታገያ ስልቱ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል። በዚህ አጋጣሚ ሞረሽ ሊገልጸው የሚፈልገው ነገር ቢኖር አሁን ባለበት ሁኔታ የሲቪክ ድርጅት እንጂ የፖለቲካ ድርጅት አለመሆኑን ነው። እንደ ሞረሽ እምነት የጥቁሮችን መብት በማስከበር በእንቅስቃሴ ውስጥ ነጮች እንደተሳተፉና መስዋዕትነት እንደከፈሉ ሁሉ የአማራው ጎሳ የሚደርስበትን በደል «አግባብ አይደለም» ለማለትና የሚደርስበትን በደል ለማስቆም የየትኛውም ጎሳ አባላት ተሳትፎ ማድረግ አግባብነት አለው ይላል።


የሀገራችን ታሪክ እንደማንኛውም ሀገር ታሪክ መልካምም መጥፎም ገጽታ ይኖረዋል። የሰው ልጅ የሠራው ሥራ የሚገመገመውም በወቅቱ ባለው መለኪያ እንጂ ዘመናትን አሻግሮ በማይመሳሰሉ ዘመናት ባሉ መለኪያዎች መሆን የለበትም። ያለፈውን መልካም ነገር መሠረት አድርጎ ከተሠሩ ስህተቶች ተምሮ መልካም ነገርን ማምጣትና በእጁ ያለውን የአሁኑን ጊዜ በሚገባ በመጠቀም ወደፊት የሚፈጠር እውነታን መቀየርና የሚጻፍ ታሪክን መልካም እንዲሆን ማድረግ ተገቢ ነው። ይህ ለጋራ ዕድገት የተሻለ ነገርን ያመጣል። ያለፈ አፈ ታሪክ ላይ በማተኮር እድገት አይመጣም። እድገት የሚመጣው በአግባቡ የተተለመ ራዕይ ላይ በማተኮርና ተገቢውን በመተግበር ነው። በጥላቻ እድገት አይመጣም። ጥላቻ የሚያመጣውን ውጤት ለማየት ብዙ መመራመር አያስፈልግም። በዓለም ላይ ያሉ ትላልቅ ችግሮች የጥላቻ ውጤቶች ናቸው። ሞረሽ ይህንን ጠንቅቆ ያውቃል። በአማራው ላይ በወያኔ መሪነት በመጀመሪያ በሌሎች ጎሳዎች ጥላቻ እንዲደርስበት ከዚያም በመቀጠል በንብረቱና በሕይወቱ ላይ ጉዳት እንዲደርስበት ሲደረግ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። ልብ እንበል፥ በእናት ማህጸን ውስጥ ያሉ ያልተወለዱ ጽንሶች፣ ምንም የማያውቁ ሕጻናት ሳይቀር ታርደው እንዲገደሉ ተደርጓል። ሠርተው ከመብላት ውጭ ምንም የፖለቲካ አስተሳሰብና የሥልጣን ፍላጎት የሌላቸው ገበሬዎች ከኖሩበትና ሀብትና ንብረት ከአፈሩበት ቦታ ያለምንም ነገር ባዶ እጃቸውን ተፈናቅለው ቤት አልባ መንገድ ተዳዳሪ ለማኞች እንዲሆኑ ተደርገዋል። ይህንን ድርጊት በተደራጀ መልኩ መቃወምና ማስቆም የግድ ይሆናል። ለዚህም ነው ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት የተቋቋመው። በመሆኑም ሞረሽ በወያኔ የፖለቲካ ፍልስፍና መሠረት የተፈጠረ ሳይሆን በወያኔ እኩይ ሥራ ምክንያት መጠነ ሰፊ የሆነ የጥፋት ዘመቻ እየደረሰበት ያለውን የአማራ ጎሳ ለመታደግ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ የተቋቋመ ነው።


የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን ማን ይፈራቸዋል?

$
0
0
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እስክንድር ነጋን፣
 ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችንማን ይፈራቸዋል?
bloggersየኢትዮጵያ የነጻው ፕሬስ እና ጦማርያን ቁንጮ የሆነው እስክንድር ነጋ ሀሳቡን በነጻ በመግለጹ ብቻ በአምባገነኑ የወሮበላ ቡድን ስብስብ የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት የ18 ዓመታት እስር ተበይኖበት በገዥው አካል የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ሟቹ መለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ እስክንድር ነጋ በቁጥጥር ስር እንዲውል እና የ18 ዓመቱ የሸፍጥ እስራት እንዲበየንበት ተደርጓል፡፡ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ማናቸውም ጋዜጠኞች የበለጠ እስክንድር ነጋን ይፈራዉና ይጠላው ነበር፡፡ ዝሆን አይጦችን “ይፈራል” ከሚለው ኢ-ስነ አመክንዮ አንጻር በተመሳሳለ መልኩ መለስም እስክንድር ነጋን እንደጦር ይፈራው ነበር፡፡
በቅርቡ እስክንድር ከማጎሪያው እስር ቤት ለ8 ዓመት ልጁ ለናፍቆት እንዲህ የሚል ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል፣ “እንዲያው ሁኔታውን ሳየው እያለሁ የሌለሁ የዘፈቀደ አባት ሆኛለሁ፣ ምክንያቱም በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፈረንሳዮች ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍቅር እያሉ ደጋግመው ይጠሯቸው የነበሩትን ሶስት ቀላል ቃላትን በመውሰድ እኔም በሀገሬ ነጻነት፣ እኩልነት እና ፍቅር እንዲሰፍን በማሰብ እነዚህን ቃላት በማስተጋባቴ ነው በሸፍጠኞች ለእስር የተዳረግሁት“ ብሏል፡፡ እስክንድር ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለአብሮነት ፍቅር ጦማሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ለእኔ የጀግናዬ ተምሳሌት የሚሆነው!
የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል ጀግናዋ የ34 ዓመቷ ወጣት ርዕዮት ዓለሙ በተመሳሳይ መልኩ በአቶ መለስ ዜናዊ የ14 ዓመታት እስር በይኖባታል፡፡ ይህች ጀግና ወጣት በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ “እውነት ተናጋሪዋ ኢትዮጵያዊት እስረኛ” በመባል ትታወቃለች፡፡ ርዕዮት ለእስር የተዳረገችው የግድብ ፕሮጀክት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን በተመለከተ በገዥው የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ጠንካራ ትችት በማቅረቧ እና በቅርቡ በህይወት የተለዩት የሊቢያ አምባገነን መሪ ሙአማር ጋዳፊ እና መለስ ዜናዊ ከአንድ ባህር የሚቀዳ ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው መሆናቸውን በይፋ በመግለጿ ነው፡፡ ርዕዮት በእስር ቤት ተዘግቶባት እና አፏን ተሸብባ ለመቀመጥ ባለመፍቀድ በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ ስልጣኖቻቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በህገወጥነት ለሚጠቀሙት ህገወጦች እና ትዕቢተኞች እውነት እውነቱን እንዲህ በማለት እቅጬን ተናግራለች፣ ”የተሻለች ኢትዮጵያን ለማየት እኔ በግሌ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ማበርከት አለብኝ የሚል እምነት አለኝ፣ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ኢፍትሀዊነቶች እና ጭቆናዎች ተንሰራፍተው ስለሚገኙ እነዚህን እኩይ ተግባራት በምጽፋቸው ትችቶቸ ማጋለጥ እና ከንቱ መሆናቸውን መቃወም አለብኝ… ለዚህ በጎ ዓላማ በድፍረት ትግል በማካሂድበት ወቅት ሊያስከፍለኝ የሚችለውን ዋጋ ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ“ በማለት ከእስር ቤት አፈትልከው በሚወጡ የእጅ ጽሁፎቿ ገልጻለች ጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ፡፡ በማይበገረው እና በማይንበረከከው ትክክለኛ የጽናት አቋሟ ምክንያት ገዥው አካል ሰብአዊነት የሚባለውን ክቡር ነገር በመደፍጠጥ የህክምና አገልግሎት እንዳታገኝ ቅጣት ጥሎባታል፡፡ መቀመጫውን ሎንዶን ያደረገ የህግ መከላከል የተነሳሽነት ሜዲያ/Media Legal Defense Initiative የተባለ ተቋም በአልጃዚራ ባቀረበው ዘገባ መሰረት ርዕዮት “በሰውነት አካሏ ላይ የተከሰተ እብጠት የተገኘ ቢሆንም ተገቢ የሆነ ህክምና እየተሰጣት እንዳልሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡ ምንም ዓይነት የሰመመን መስጫ ማደንዘዣ ሳይሰጣት በጡቷ ላይ የቀዶ ህክምና ስራ በማከናወን የቀዶ ህክምና መስፊያ ክሩ ከጡቷ ሳይወጣ ከዓመት በላይ ከመቆየቱም በላይ ከደህረ ቀዶ ህክምናው በኋላም ቢሆን ተገቢ የሆነ ህክምና የተሰጣት አይደለም“ ብሏል፡፡ ለእኔ ርዕዮት የጀግና ተምሳሌታዬ ናት!
የማይበገረው ጋዜጠኛ እና አርታኢ ውብሸት ታዬ የመናገር አንደበቱን ተሸብቦ በመለስ ዜናዊ ዝዋይ በሚባል አስፈሪ እና ጭራቃዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ በእርሱ ላይም የ14 ዓመታት እስራት ተበይኖበታል፡፡ ውብሸት የገዥውን አካል ሙስና እና ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን አስመልክቶ በጋዜጣ ላይ የሚያቀርባቸውን ትችቶች እና አስተያየቶች በፍጹም አያቋርጥም፡፡ ውብሸት ለሚጠዘጥዝ የኩላሊት ህመም ተጋልጦ የሚገኝ ቢሆንም እርሱም ህክምና እንዳያገኝ ተደርጎ በመሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ በማጎሪያው እስር ቤት ለሚገኙት የህሊና እስረኞች የህክምና አገልግሎት መንፈግ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እለት በእለት የሚፈጽማቸው በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ የቅጣት ወንጀሎች ናቸው፡፡ ፍትህ እየተባለ የሚጠራው የውብሸት የአምስት ዓመት ልጅ እንዲህ በማለት ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል፣ “ሳድግ እና ለአቅመ አዳም ስደርስ እኔም እንደ አባቴ ሁሉ ወደ እስር ቤት እጋዛለሁን?“ ሕፃኑ ፍትህ በአሁኑ ጊዜ አጥር የሌለው እስር ቤት ውስጥ እየኖረ መሆኑን ሊገነዘብ አይችልም፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት “የኢትዮጵያ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች” (የፖለቲካ እስረኞችን ከያዘው ከመሀል ከተማ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘው የ “መለስ ዜናዊ ታዋቂው የቃሊቲ እስር ቤት” ህንጻዎች ቀጥሎ የተሰየመ) እና ሌሎች ጋዜጠኞች በስም አጥናፍ ብርሀኔ፣ ዘላለም ክብረት፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋቤላ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና ኤዶም ካሳዬ የክሱ ጭብጥ ባልታወቀበት ሁኔታ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ውለው ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ፖሊስ በእነዚህ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ላይ ምን ዓይነት ክስ መመስረት እንዳለበት ገና በመለግ ላይ ይገኛል፡፡
(የገዥው ቡድን ፖሊስ የሚጠረጥረውን ዜጋ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር አውሎ እና እስርቤት በማጎር እያሰቃዬ ተሰራ ለተባለው ጥፋት ማስረጃ እና መረጃ በመፈለግ በዜጎቿላይ ሰብአዊ መብትን በመደፍጠጥ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ብቸኛዋ አገር ናት!!!የይስሙላዎች የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች በዘፈቀደ ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስርለዋሉት ዜጎች ዋስትና በመንፈግ ፖሊስ እና አቃቤህግ የሚባሉ የገዥው አካልየማጥቂያ መሳሪያ ሎሌዎች የሚፈበረኩ የፈጠራ ውንጀላዎችን አቀነባብረውእስኪያቀርቡ ድረስ የተንዛዙ እና አሰልቺ የሆኑ ማያልቅ ቀጠሮዎችን በመስጠት እናየይስሙላውን ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ከሚገባው በላይ በማዘግየት በንጹሀን ዜጎችላይ የቁማር ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ነው አነዚህን ፍርድቤቶችን “የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች እያልኩ የምጠራቸው፡፡” እውነተኛው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ወንጀል ሀሳብን በነጻ በመግለጽ የሚያምኑበትን ነገር በነጻ ማራመዳቸው እና እነርሱ የተሻለች ኢትዮጵያ በማለት ስለሚጠሯት ኢትዮጵያ ህልም ማለማቸው ነው፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንን ጉዳይ የሚመለከተው በቅርቡ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የዳኝነት ችሎት ለህዝቡ እና ጉዳዩን በቅርበት ለሚከታተሉት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ዝግ ነበር፡፡
እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንንየሚፈሯቸው ለምንድን ነው?
ናፖሊዮን ቦና ፓርት የተባሉት የፈረንሳይ አምባገነን መሪ በዚያች አገር የነጻው ፕሬስ ላይ ጦርነት ባወጁበት ወቅት “ከአንድ ባታሊዮን ጦር ይልቅ አራት ተቃዋሚ ጋዜጦች የበለጠ ይፈራሉ“ የሚለውን እውነታ የበለጠ ግልጽ አድርጎታል፡፡ ላለፉት 23 ዓመታት በኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር በስልጣን ላይ ተጣብቆ ለሚገኘው ገዥ አካል ኤኬ – 47 ከታጠቀ አንድ ባታሊዮን ጦር ይልቅ ብዕር እና የኮምፒውተር ኪይ ቦርድ የያዙ ጥቂት ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን የበለጠ ያስፈሩታል፣ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ እንዲወሸቅ ያደርጉታል፣ ያርዱታል፣ ያስደነብሩታል፣ የሚይዝ የሚጨብጠውን ያሳጡታል፣ የቀን ቅዠት ይፈጥሩበታል፣ በላብ እንዲጠመቅም ያደርጉታል፡፡ በታሪክ መነጽር ሲታይ እና ሲገመገም ሁሉም አምባገነኖች እና ጨቋኞች የነጻውን ፕሬስ የእውቀት እና የክህሎት ኃይል አጥብቀው ይፈሩታል፡፡ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተንፈራጥጠው የሚገኙት አምባገነኖች ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው ከታቀው እና በልዩ ልዩ የጦር ክፍሎች ተዋቅሮ በጠላት ላይ ቅጽበታዊ ድልን የመቀዳጀት አቅም ካለው እና የጠላትን ኃይል በማያንሰራራ መልኩ ከሚያደባይ የጦር ኃይል ይልቅ የነጻውን ፕሬስ የዕውቀት እና የክህሎት ኃይል አጥብቀው ይፈራሉ፡፡
ጠቅላላ የብዙሀን መገናኛዎችን እና ነጻውን ፕሬስ መቆጣጠር የገዥዎች እኩይ ምግባር ነው፡፡ የመረጃ ፍሰቶችን በመቆጣጠር በኃይል የሚገዙትን ህዝብ ልብ እና አእምሮ የተቆጣጠሩ እንደሚመስላቸው እምነት አላቸው፡፡ የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎችን በመቆጣጠር እንደ በቀቀን እየደጋገሙ ከሚቀፈቅፉት ነጭ ውሸታቸው እውነትን የሚፈበርኩ ይመስላቸዋል፡፡ ነጻውን ፕሬስ አፈር ድሜ በማብላት ሁሉንም ህዝብ ሁልጊዜ ማሞኘት የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን “እውነት ለዘላለም ተቀብራ እንደማትቀር እና ግፈኞችም በጉልበት ነጥቀው በያዙት የስልጣን ዙፋን ወንበር ላይ ለዘላለም ተጣብቀው እንደማይቆዩበት ድንጋይ በሆነው ልባቸው ያውቁታል፡፡“ ሁልጊዜም ስልጣናቸውን የሚያጡ እየመሰላቸው እለት በእለት የውሸት ድሪቷቸውን እየደረቱ ኑሮ አድርገው ይዘውታል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቆ የሚገኘው አረመኔ አምባገነን ገዥ ከብዙ ዓመታት በፊት ናፖሊዮን ተጋፍጦት የነበረውን ዓይነት ሁኔታ ተጋፍጦ ይገኛል፡፡ “ጋዜጠኛ የህዝቡን እሮሮ የሚያሰማ፣ ስህተትን አራሚ፣ ምክርን የሚለግስ፣ የሉዓላዊነት ወኪል እና የአገሮች መምህር ነው፡፡“ ጋዜጠኛ “አገርን የሚያስተምር” ነው፣ መረጃን ለህዝብ የሚሰጥ ነው፣ ህዝቡን በእውቀት የማነጽ እና የማስተማር ኃላፊነት አለው፡፡ እንግዲህ እነዚህ እውነታዎች ነበሩ ናፖሊዮን ነጻውን ፕሬስ እንዲፈሩት ያስገደዳቸው፡፡ የነጻው ፕሬስ ኃይል የናፖሊዮንን አምባገነናዊ አገዛዝ ትርጉም ባለው መልኩ እንደሚያጋልጠው እና በህዝቡ ዘንድ ተጠያቂ እንደሚያደርገው ናፖሊዮን ይገነዘቡ ነበር፡፡ ናፖሊዮን የፈረንሳይን ህዝብ ለማስፈራራት በማሰብ መጠነ ሰፊ የሆነውን የስለላ መረባቸውን በመዘርጋት ሲያካሂዱት የነበረውን ስለላ ሲያጋልጡ የነበሩትን ጋዜጠኞች ለማስፈራራት፣ በእስር ቤት ለማጎር፣ በስራዎቻቸው ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እና አንደበታቸውን ለመሸበብ ጊዜ አላባከኑም፡፡ ነጻው ፕሬስ የናፖሊዮን ወታደራዊ እቅድ መክሸፉን አጋልጧል፡፡ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ማንንም ሳይለይ በጅምላ በዋና ዋና መንገዶች ላይ የተካሄዱትን ጭፍጨፋዎች እና የእርሳቸው የፖለቲካ ተቀናቃኝ በሆኑት ቡድኖች እና ግለሰቦች ላይ የተካሄደውን እስራት፣ ማሰቃየት እና ግድያ አውግዟል፡፡ በኢትዮጵያ እንደ መዥገር በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቀው የሚገኙት አምባገነኖች በናፖሊዮን ቅዠት በመውደቅ በተመሳሳይ መልኩ ወጣት ጦማሪያንን እና የነጻው ፕሬስ አባላትን ያስራሉ፣ ያሰቃያሉ፡፡ እውነታውን በመፍራት እንቅልፋቸውን አጥተው በነጭ ላብ ተዘፍቀው ያድራሉ!
የኢትዮጵያ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ልዩ የኢትዮጵያ ጀግናዎች እና ጀግኒቶች ናቸው፡፡ የእውነት ተናጋሪ ተዋጊዎች ናቸው፡፡ አረመኔ አምባገነኖችን በብዕሮቻቸው እና በኮምፒውተር ኪቦርዶቻቸው ይዋጋሉ፡፡ የእነዚህ ወጣቶች ጥይቶች እውነት፣ ቃላት፣ ሀሳቦች፣ እውነታዎች እና እምነቶች ብቻ ናቸው፡፡ የተንሰራፉትን ውሸቶች በእውነት ጎራዴ ይከትፏቸዋል፡፡ መጥፎ እና መሰሪ ሀሳቦችን በጥሩ ሀሳቦች ያሳድዷቸዋል፣ እናም ያረጁ እና ያፈጁ፣ እንዲሁም የጃጁ፣ እና የበከቱ አሮጌ አስተሳሰቦችን በአዲስ እና ተራማጅ በሆኑ አስተሳሰቦች ለመተካት የማስተማር ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡ የህዝቦችን ተስፋቢስነት በመዋጋት በተስፋ ቃላት ያለመልማሉ፡፡ ፍርሀት በጀግንነት እና በደፋርነት ድል እንደሚመታ ለህዝቡ ያስተምራሉ፡፡ ድንቁርናን እና ኃይለኛ ደንቆሮዎችን በእውቀት እና በምክንያታዊነት ይዋጋሉ፡፡ በእብሪት እና ትእቢት ለተወጠሩት የገዥው አካል አባላት በሰለጠነ መልኩ ለማስተማር እና ለማግባባት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ትዕግስትየለሽነትን በታጋሽነት፣ ጭቆናን ከመሸከም በጽናት ታግሎ በማስወገድ እና በጥርጣሬ ከመሸነፍ በሙሉ እምነት አሳድሮ ድል በመምታት ለመቀየር ይፈልጋሉ፡፡ የህዝቡን ልብ እና አእምሮ ለመያዝ በሚደረገው የትግል አውድ እንደ ወሮበላው የገዥ አካል ስብስብ በተራ የውሸት ፕሮፓጋንዳ እና በኃይል በጉልበት ጨፍልቆ ለመያዝ ሳይሆን እውነታውን እና እውነቱን ብቻ ለወገኖቻቸው በማሳየት በብዕሮቻቸው እና በኮምፒውተር ኪቦርዶቻቸው ይታገላሉ፡፡
ክህደት፣ ውሸት እና ፍርሀት በተንሰራፋባት ምድር ላይ መኖር፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እውነት ውሸት በሆነባት፣ እውነት በእየለቱ በምትደመሰስባት እና ሸፍጠኛ አታላዮች በፍርሀት ተዘፍቀው የሚኖሩባት የእራሳቸውን ምድር ፈጥረዋል፡፡ ገዥው አካል እንዲህ የሚለውን የካርቴሲያንን መርህ አዛብቷል፣ “በኛ አስተሳሰብ ብቻ ነገሮች ሁሉ ህልውና ይኖራቸዋል ወይም ደግሞ ህልውና አልባ ይሆናሉ“፡፡ መለስ ዜናዊ የክህደት አለቃ ነበር፡፡ ሁልጊዜ በሱ የማጎሪያ አስር ቤቶች ውስጥ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኛ የለም በማለት ሽምጥጥ በማድረግ ይክድ ነበር፣ እንዲህ በማለት፣ “በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኛ የለም፡፡ በእስር ቤት ያሉት አመጸኞች እና አሸባሪዎች ናቸው፡፡ እናም በእስር ቤቶቻችን የፖለቲከ እስረኞች አሉ ብሎ ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው ምክንያቱም የፖለቲካ እስረኞች አይደሉምና፡፡ በሱ የንጉስነት ወቅት ምንም ዓይነት ረሀብ እና ቸነፈር እንዳልነበረ ሙልጭ አድርገው በመካድ እንዲህ ብሎ ነበር፣ በጣም ጥቂት የሆኑ በጣት የሚቆጠሩ በምግብ እጥረት ጉዳት የደረሰባቸው በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የወረዳ ኪስ ቦታዎች እና በሶማሊ ክልል አካባቢ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ብቻ ነው የነበሩት በማለት ዓይኔን ላፈር ብለዋል፡፡ በአገሪቱ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ያፈጠጠ እና ያገጠጠ እውነታ ሙልጭ አድርገው በመካድ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብአዊ መብት ጥሰት የለም“ ብለዋል፡፡ ይህንን ለማስረገጥ በማሰብ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኦጋዴን አካባቢ መንደሮችን አቃጥለዋል እየተባለ ውንጀላ ቀርቦብናል፡፡ ሆኖም ግን በእርግጠኝነት ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፤ ኑስ አንድ መንደር እንኳ አልተቃጠለም፡፡ እናም እኔ እስከማውቀው ድረስ አንዲት ጎጆ አልተቃጠለችም፡፡ እኛ እየተከሰስን ያለነው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ቀድሞ ከነበሩባቸው መንደሮች በማንቀሳቀስ ወደ መጠለያ ካምፖች በማስገባታችን ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅንጣት መረጃ ሊቀርብ አይችልም“ ብሎ ነበር፡፡ የአሜሪካ የሳይንስ እድገት ማህበር/American Association for the Advancement of Science በኦጋዴን መንደሮች ላይ የተካሄደውን የጅምላ የመንደሮች ማቃጠል ወንጀል በሳቴላይት ምስሎች የተረጋገጠው እውነታ ለመለስ ምድር ምናባዊ ህይወት ምንም አይደለም፡፡ አደናጋሪ የፕሬስ ህግ አዋጅ በማውጣት በደርዘን የሚቆጠሩ ምርጥ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ለእስር እና ግዞት ሲዳረጉ የሌባ አይነ ደረቅ እንዲሉ በሀሰት በነተበው አንደበታቸው መልሰው “ከዓለም የተሻለ ምርጥ የፕሬስ ህግ” በማለት ያደናግራሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 የተካሄደውን አገር አቀፋዊ “ምርጫ” ተከትሎ መለስ ፓርቲው ምርጫውን በ99.6 በመቶ ያሸነፈ መሆኑን በኩራት ተናግሮ ነበር፣ ምክንያቱም ህዝቡ ፓርቲያቸውን የሚወደው ስለሆነ ነው በማለት አፋቸውን ሞልተው ተናግረው ነበር፡፡ አቶ መለስ የኦርዌላን/Orwellian የእንስሳት ትረካ ዓይነት እውነታን የሚያራምድ ሰው ነበር፡፡ ውሸቱን ለመንዛት ሲፈልግ “የፖለቲካ ቋንቋን በመጠቀም የለየለትን ነጭ ውሸት እውነት እንዲመስል አድርገው በማቅረብ፣ ግድያ መፈጸም ወንጀል እና የስነምግባር ዝቅጠት መሆኑ ቀርቶ የሚያስከብር እንደሆነ አድርገው በማቅረብ ነጩን ውሸት የእውነት ቅርጽን እንዲላበስ አድርገው በማስመሰል የማቅረብ የባዶ ብልጣብለጥነት አካሄድ መንገድን ይጠቀሙ ነበር፡፡”
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተቀምጠው አገሪቱን እያተራመሱ በመግዛት ላይ ስለሚገኙት ስብስቦች አንድ የማይካድ ሀቅ አለ፡፡ ሁሉም በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቀው ነው እየኖሩ ያሉት፡፡ ያገጠጠውን እና ያፈጠጠውን እውነታ አየፈሩ ነው በመኖር ላይ ያሉት፡፡ የነጻው ፕሬስ ኃይል እውነታውን የሚያጋልጥ ስለሆነ የነጻውን ፕሬስ ኃይል በመፍራት ነው እየኖሩ ያሉት፡፡ በአንድ ወቅት የእነርሱ የአመለካከት ፍልስፍና አለቃ ቁንጮ የነበሩት ቪላድሚር ሌኒን አንዳለው “የመናገር ነጻነት እና የፕሬስ ነጻነት ለምንድን ነው የሚፈቀደው? ለምንድን ነው መንግስት ትክክል ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ሲሰራ ትችት እንዲቀርብበት የሚፈቅደው? ተቃዋሚዎችን የጠላት መሳሪያ እንዲሆኑ መንግስት መፍቀድ የለበትም፣ ሀሳቦች ከጠብመንጃ የበለጠ የገዳይነት ባህሪ አላቸው፡፡ ለምንድን ነው ማንም ሰው የማተሚያ ቤት እንዲገዛ እና የሚቀርቡ ሀሳቦችን አትሞ በማሰራጨት በስልጣን ላያ ያለውን መንግስት በተቀነባበረ ስሌት ለመተቸት እና ለማሳፈር እንዲችል የሚፈቀደው?“ ፡፡
እውነታውን በሚገባ ያውቁታል ምክንያቱም እውነታው ህዝቡን ነጻ እንዲሆንያ ደርገዋል፡፡ ነጻነትን ይፈራሉ ምክንያቱም አዲስ ሀሳቦችን ይፈራሉ፡፡ አዲስ ሀሳቦችን ይፈራሉ ምክንያቱም ለውጥን ይፈራሉ፡፡ ነጻ የሆነ ህዝብ የእውነትን ጥሩር ታጥቆ የሀሳብ ነጻነትን ተጎናጽፎ በእራሱ ፈቃድ የእራሱን የመንግስት ዓይነት ለመመስረት ሙሉ ነጻነት አለው፡፡
በኢትዮጵያ ላይ ስላለው ገዥ አካል ያለው እውነታ ምንድን ነው? እውነታው በሰው ልጆች ላይ ግፍን የፈጸሙ ወንጀለኞች ናቸው፡፡ ምንም ዓይነት ህጋዊነት የላቸውም፡፡ በጠብመንጃ ኃይል በጉልበት በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚገኙ አምባገነኖች ናቸው፣ ምርጫዎችን በመስረቅ እና በመዝረፍ ተመርጠናል እያሉ በማታለል ተክነዋል፣ በጥልቅ የሙስና ማእበል ውስጥ ተዘፍቀው የአገሪቱን ሀብት በማውደም ላይ ይገኛሉ፣ ስልጣናቸውን በህገወጥ መንገድ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፣ የህግ የበላይነትን በመደፍጠጥ በጫካው ህግ የሚገዙ ህገወጦች ሆነዋል፣ እውነታው ሲታይ በአጠቃላይ በሸፍጥ የታወሩ የጫካውን አስተዳደር ወደ መንግስታዊ አስተዳደርነት አዙረው ህዝብን በማተራመስ ላይ የሚገኙ የስግብግብ ወሮበላ ቡድን ስብሰቦች ናቸው፡፡ እውነታው በአጠቃላይ ሲታይ የአፍሪካን የጨካኝ ዘራፊነት ስርዓት በሀገራችን ላይ የሚተገብሩ ወሮበላ ዘራፊዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ወሮበላ ዘራፊዎች ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን ይፈራሉ ምክንያቱም እነዚህ ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪዎች አምባገነኖቹ የሚሰሯቸውን ወንጀሎች እና ሙስናዎች፣ የመከኑ እና የወደቁ ፖሊሲዎቻቸውን፣ የአቅም ድሁርነታቸውን እና ድንቁርናቸውን በማጋለጥ እውነታውን ያወጡባቸዋል፡፡ እነዚህ ጭራቃዊ ፍጡሮች በጫማቸው ስር እረግጠው የያዟቸው የግፍ ሰለባዎች ነጻ ቅዱስነት እና የያዙት ጸበል ስለሚያቃዣቸው ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን አጥብቀው ይፈራሉ፡፡ በያዙት ሁሉ ኃይል በመጠቀም እውነቱ ወጥቶ ለህዝብ እንዳይደርስ እና እንዳይታወቅባቸው ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም፡ የሳቴላይት ስርጭቶችን ሳይቀር አፍነዋል፣ የኢንተርኔት ግንኙነቶችን አቋርጠዋል፣ ጋዜጦችን በመዝጋት ጋዜጠኞችን በእየእስር ቤቶች አጉረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የአረብሳት ለዓለም አቀፉ የግንኙነት ህብረት/International Communication Union እና ለአረብ ሊግ/Arab League ኢትዮጵያ ስርጭቱን ያፈነች መሆኗን እና “ወንጀለኛውን ለመቅጣት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ” እና በዚህ ህገወጥ ድርጊት ምክንያት ለደረሰው ጉዳት ወይም በዚህ ህገወጥ የአፈና ተግባር ምክንያት ወደፊት ለሚደርስ ማንኛውም አደጋ ተገቢውን ካሳ እንድትከፍል እንዲደረግ ተማጽዕኖውን አቅርቧል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ገዥው አካል በገበያ ላይ የቀሩትን እና በገዥው አካል ላይ ጠንካራ ጥችት የሚያቀርቡትን ጥቂት ጋዜጦች በየመንገዶች እያዞሩ የሚሸጡትን ጋዜጣ አዟሪዎችን እያሳደደ፣ እያስፈራራ እና በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛል፡፡
እውነታው በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻ ከመግለጽ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እየተካሄደ ላለው ጭቆና እና አፈና የቻይናዎች ስውር እጆች ያሉበት መሆኑ ነው፡፡ ቻይናዎች ለገዥው አካል የማፈኛ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ማቅረብ ብቻ አይደለም የሚያከናውኑት፡፡ ሆኖም ግን ለተንቀሳቃሽ ስልኮች እና ለኢንተርኔት አገልግሎት የመሰረተ ልማት ስራዎችም ግንባር ቀደም ተዋንያን ናቸው፡፡ የመረጃ ፍሰት ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ እና ወደ ኢትዮጵያም እንዳይገባ ለመገደብ እና ለማቋረጥ የአንድ መስኮት ፈጣን የአግልግሎት መስጫ ኪቶችን ይዘዋል፡፡ ከዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ በፊት የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሄላሪ ክሊንተን ዛምቢያን በመጎብኘት ላይ ሳሉ የቻይናውያን በአፍሪካ አህጉር ላይ ያላቸውን ሚና በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “በቅኝ ግዛት ዘመን ጊዜ መምጣት እና ለመሪዎቹ ገንዘብ በመስጠት የተፈጥሮ ሀብቶችን ከአፍሪካ መውሰድ ቀላል ነበር፣ በምትለቅቅበት ጊዜ እዚህ ላለው ህዝብ ምንም ነገር ትተህ አትወጣም፣ በአሁኑ ጊዜ አዲስ ቅኝ ተገዥነት በአፍሪካ ማየት አንፈልግም“ ብለው ነበር፡፡ እውነታው ግን ቻይናውያን በኢትዮጵያ መቆየታቸው እና የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መያዛቸው ብቻ ሳይሆን ለገዥው አካል የቴክኒክ እገዛ በመስጠት፣ የኦዲዮ እና ቪዲዮ መሳሪያዎችን በማቅረብ የመረጃ ምርመራ በማድረግ እና በኤሌክትሮኒክ መገናኛ ብዙሀን ላይ አፈናዎችን በማካሄድ ነጻ አሰተሳሰብን በመጨቆን በዋናነት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
ነጻነትን ይፈራሉ፡፡ ነጻነት ምንድን ነው? የሁሉም የሰው ልጆች ነጻነቶች ባህሪያት ከፍርህት የሚገኙ ነጻነቶች ናቸው፡፡ በተግባራዊ ሁኔታ ሲታይ አንድ ሰው ያሰበውን ለመናገር መፍራት ወይም ደግሞ አንድ ሰው ደስ ያለውን መጻፍ መፍራት ወይም በአንድ ሀሳብ ማለትም ሀይማኖት ወይም ፍልስፍና ላይ ማመን እና አለማመንን መፍራት ወይም ደግሞ አንድ ሰው ከመረጠው ሰው ጋር አብሮ መገናኘት መፍራት ማለት አይደለም፡፡ ዋናው እና የመጨረሻው የሰው ልጅ ሁሉ ሊያደርገው የሚገባው ህዝቡ እራሱ ስልጣን የሰጣቸው በስልጣን ወንበር ላይ ያሉት ሰዎች ናቸው በህብረተሰቡ የኑሮ ሂደት ላይ መፍራት እና ህዝቡን ማክበር ያለባቸው፡፡
ሀሳብን ይፈራሉ፡፡ “ሀሳቦች ከጠብመንጃ የበለጠ ገዳዮች ናቸው“ በማለት ሌኒን አስጠንቅቀዋል፡፡ ሀሳቦች ሳይንስን፣ ፖለቲካን እና ማናቸውንም የሰው ልጅ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች ሁሉ የመለወጥ ኃይል አላቸው፡፡ ከምንም በላይ ዓለም ጠፍጣፋ አይደለችም፡፡ ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ያሉ ገዥዎች የአዲስ ጠፍጣፋ መሬት ባለቤቶች ናቸው፡፡ እንደ ጥንቱ ንጉሶች፣ ዛሮች፣ እና ማሃራጃሆዎች ሆነው ከህዝቡ ፈቃድ ውጭ ( በተሰረቀ ስምምነት) መሰረት መግዛት ይፈልጋሉ፡፡ ጥቂት ሞራላዊ ጠቀሜታ ያላቸው ሀሳቦች ሲኖሯቸው ነገሮችን በቀላሉ ለመገንዘብ እና አዳዲስ ሀሳቦችንም ለማድነቅ እና ተቀብሎ ወደ ተግባር ለማዋል የምሁርነት አቅሙ የሌላቸው የመንፈስ የአስተሳሰብ ድሁሮች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን የጎሳ ክፍፍልን ለማራመድ፣ ስግብግብነት እና ጥላቻን ለማምጣት፣ የጥላቻ ከባቢን የመፍጠር፣ ግጭትን የመጫር፣ ሙስናን ለማስፋፋት እና ለማጠናከር፣ ህብረትን በመናድና የጥላቻ መንፈስን በመዝራት እንዲሁም በሰዎች መካከል ጥርጣሬ እና አለመተማመን እንዲነግስ በማድረግ ጭንቅላቶቻቸው ዋና የዲያብሎሳዊነት ቤተሙከራዎች ናቸው፡፡ ህዝብን ሊያስተባብሩ እና ሊያፋቅሩ የሚችሉ ሀሳቦችን ለማመንጨት፣ በጎሳዎች መካከል ፍቅርን የማስፈን፣ ብሄራዊ አንድነትን የማምጣት፣ የጋራ መግባባትን የመፍጠር፣ የጓዳዊነት መንፈስ የማጠናከር እና እምነትን የማራመድ አቅመቢሶች ናቸው፡፡
አዳዲስ ሀሳቦችን የሚፈሩ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተቆናጥጠው የሚገኙ አምባገነኖች የአዲስ ሀሳብ አመንጭ እና ባለራዕይ መስለው ለመታየት ይሞክራሉ፡፡ ህዝቡ እና ዓለም ወደፊት ጥሩ ነገር የሚያስቡ መልካም ነገር አላሚዎችና ፈጣሪዎች እንደሆኑ አድርጎ እንዲመለከታቸው እና እምነት እንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡ ሆኖም ግን በህልም የቅዠት ፍርሀት ተዘፍቆ ያለ ማንም ሰው መልካም አላሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ባለራዕይ መሪዎች ለሚያደርጓቸው ማለትም ታማኝነት፣ ኃላፊነትነትን የመሸከም ብቃት፣ ሌሎችን አነቃቅቶ እና አሳምኖ በስራ የማሳተፍ ችሎታ፣ ያለፉትን ስህተቶች በግዴለሽነት እንዳሉ ከመድገም ይልቅ ከስህተት እና ከውድቀት መማርን፣ ስህተት በሚሰሩበት ጊዜ ይቅርታ አድርጉልኝ ብሎ መጠየቅን፣ ግልጽነት፣ ትክክለኛውን ነገር ለመስራት ፍትሀዊነት እና በፍቅር ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከመገኘት ተግባራት ጋር ሁሉ አይተዋወቁም፡፡ መጥፎ እና ዕኩይ ተግባራትን ለማድረግ ፍቅር ያላቸው መሰሪ መሪዎች ናቸው፡፡ ኪሶቻቸውን የሚወጥሩትን የተዘረፉ በርካታ ገንዘቦችን ዓይኖቻቸው በቀላሉ ማየት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን አሁን እየፈጸሟቸው ያሏቸው በርካታ ወንጀሎች በዘለቂነት ለወደፊት ሊያስከትሉት የሚችሏቸውን እንደምታዎች ለማየት የታወሩ ናቸው፡፡ ጠንካራን ሀሳብ ጊዜው እየመጣ ያለውን ሀሳብ የሚያቆመው ምድራዊ ኃይል የለም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነት የሚያደርገውን ተጋድሎ የሚያቆመው ኃይል የለም፡፡ አንዴ ከተጀመረ በመንገዱ ላይ ያለውን ጋሬጣ ሁሉ እየጠራረገ ወደፊት ይገሰግሳል፡፡
ለውጥን ይፈራሉ፡፡ ለውጥ ምንድን ነው? ለውጥ በሁሉም ነገር የሚከሰተውን የዕድገት እና የመበስበስ ዓለም አቀፋዊ ዘላለማዊ የለውጥ ህግ የሚገዛ ሂደት ነው፡፡ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው ገዥ አካል ለውጥን አጥብቆ ይፈራል ምክንያቱም በህበረተሰቡ ላይ ያላቸውን የኢኮኖሚ እና የፖሎቲካ የበላይነት ቦታ ስለሚያሳጣቸው ነው፡፡ ለውጥን ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት የሚንቀሳቀሱትን ማናቸውንም ሙከራ ሁሉ ይደመስሳሉ፡፡ ከዚህ አንጻር “በሰላማዊ መንገድ የለውጥ አብዮት እንዳይመጣ የሚከለክሉ ሁሉ የአመጽ ለውጥ በኃይል እንዲመጣ ይገደዳሉ“ የሚለውን ሀቅ ለመገንዘብ የተሳናቸው ይመስላል፡፡
በፖለቲካ ህጋዊነት ማጣት እና በመንግስት አቅም ማጣት ምክንያት ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በፖለቲካ መበስበስ የመጨረሻ ጠርዝ ላይ ያለችበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ የጨነገፈ መንግስት ሆናለች፡፡ ባለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት የጎሳ ክፍፍል ፖሊሲ (የጎሳ ፌዴራሊዝም) “ልማታዊ መንግስት” ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዘገብን በማለት የሚራገበው እርባናየለሽ ፕሮፓጋንዳ ቢኖርም እንኳ ኢትዮጵያን በሁለት አማራጮች ላይ ጥሏታል፡፡ የእነርሱ ነጭ ውሸት ብቻ ነው በባሁለት እና በባለሶስት አሀዝ እድገት ያስመዘገበው፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ቆማለች፡፡ እንደተባበረች ሀገር አንድ ሆና ወደፊት ትገሰግሳለች ወይም ደግሞ ወደተለያዩ ትናንሽ የተበጣጠሱ ክልሎች ትገነጣጠላለች፡፡ የአፓርታይድ ዓይነት ባንቱስታንስ በኢትዮጵያ ክልል እየተባለ በዘር እና በቋንቋ የተቀየደ የአገዛዝ ስርዓት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የተበጣጠሱ ግዛቶች ስብስብ የምትሆን ከሆነ የመጀመሪያው ቸግር ቀማሽ የሚሆኑት አሁን በስልጣን ላይ ተጣብቆ የሚገኘው ገዥው አካል፣ የእነርሱ ጋሻጃግሬዎች እና ደጋፊዎች ናቸው፡፡ በፖቲካ ስልጣን ማጣት ብቻ የሚቆም ሳይሆን ቢያንስ እስከ አሁን ድረስ በአገር ውስጥ የሚደረግ ለውጥ ዘግይቶ እንደደረሰ ባቡር ይቆጠራል፡፡ በምስራቅ አውሮፓ በመካከለኛው ምስራቅ ሲነፍስ የነበረው የለውጥ ነፋስ ያለምንም ጥርጥር በኢትዮጵያም መንፈሱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ሊነሳ የሚችለው ብቸኛ ጥያቄ ግን እነዚህ ነፋሶች ተስማሚ እና በሰላም የሚያልፉ ወይስ ደግሞ ሁሉንም ነገር እየገነደሱ እና እየቦደሱ የሚጥሉ ኃይለኛ የሁሪኬን/hurricane-force ሞገዶች ይሆናሉ የሚለው ነው፡፡
እውነት ነጻ ያወጣሀል ነጻ አስከሆንክ ድረስ ሆኖም ግን ነጻ ያልሆኑት ይሰቃያሉ፣
“እውነት ነፃ ታወጣሀለች” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ነጻነት እና ፍርሀት ለእየራሳቸው ተነጥለው የሚኖሩ ናቸው፡፡ የነጻው ፕሬስ እና ጦማሪያን ብቸኛው ተግባራቸው እንዳዩት እውነታውን ወዲያውኑ መናገር ነው፡፡ ስለ እውነታው ያላቸውን ሀሳብ የለምንም ፍርሀት የመግለጽ ነጻነት አላቸው፡፡ ሆኖም ግን ህዝቡ እውነታውን ቀድሞም ቢሆን ያውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች የሚለው ነጭ ውሸት ቢሆንም ህዝቦች እውነታውን ያውቁታል፡፡ የሚበላ በቂ ምግብ እንደሌለ ያውቃሉ፣ እናም ሚሊዮኖች በየቀኑ እየተራቡ እንዳሉ ያውቃሉ፡፡ እንዲሁም በቂ የውኃ አገልግሎት ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሌለ ያውቃሉ፡፡ አናሳ የህክምና አገልግሎት ነው እየተሰጠ ያለው፣ ወጣቶች ጥራት ያለው ትምህርት አያገኙም እናም ስራ አጦች ናቸው፡፡ ገዥው አካል በሙስና ማጥ ውስጥ የተዘፈቀ እና የበከተ ነው፣ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ይፈጽማል፡፡ ህዝቦች በግልጽ የአየር ድባብ ውስጥ እስረኛ ሆነው እንደሚኖሩ ያውቃሉ፡፡
የነጻ ጋዜጠኞች እና የጦማሪዎች ወንጀል የሚያውቁትን ነገር ለማያውቁት ወገኖቻቸው መግለጻቸው ብቻ ነው፡፡ የእነርሱ ወንጀል የማዕድን ሙስና እና ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን፣ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች እየቆፈሩ በማውጣት ማስረጃ በማቅረባቸው ነው፡፡ ለዚህም በስልጣን ላያ ያለው ገዥ አካል እየፈራቸው ያለው፡፡ ገዥው አካል እውነታው ሳይታወቅ ተቀብሮ እንዲቀር እና እንዲረሳ ይፈልጋል፡፡ ገዥው አካል እውነታው እንዳይታወቅ በመደበቅ፣ እውነት ተናጋሪዎችንም ጸጥ በማስደረግ እና በየእስር ቤቶች በማጎር ለዘላለም ጸጥ በማድረግ ትንፍሽ እንዳይሉ በማድረግ እውነትን የመግደል እምነት አለው፡፡ ጆርጅ ኦርዌል እንደጠቆሙት፣ ”የማጨበርበር እና የሀሰት ሸፍጥ በተንሰራፋበት ጊዜ እውነትን መናገር አብዮተኛነት ድርጊት ነው“ ብለው ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ጦማሪያን የኢትዮጵያ የማይበገሩ አብዮተኞች ናቸው፡፡
ፍርሀትን በብዙሀን መገናኛ እንደ መሳሪያ መጠቀም፣
በስልጣን ላይ ያለው ገዥ አካል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ዋና ድክመትን እንደ ትልቅ መጠቀሚያ መሳሪያ አድርጎ ይጠቀምበታል፡፡ ህዝብን ግራ ለማጋባት፣ እርስ በእርስ ለመከፋፈል፣ ለማታለል፣ ጥላሸት ለመቀባት እና ሀሳብን ከዋናው ጉዳይ አቅጣጫውን ለማስቀየስ ፍርሀትን በዋና መሳሪያነት ይጠቀምበታል፡፡ ማቋረጫ የሌለው የፍርሀት ዘመቻ በህብረተሰቡ ላይ ለመንዛት ሲፈልግ፣ ጥላሸት ለመቀባት እና ለማጠልሸት ሲፈልግ በህዝብ የግብር መዋጮ የሚተዳደረውን መገናኛ ብዙሀን ለእኩይ ምግባር ሌት ቀን ይጠቀማል፡፡ ገዥውን አካል የሚቃወሙትን ቡድኖች እና ግለሰቦች ጸጥ ለማድረግ ሲፈልግ እርባናየለሽ በውሸት ላይ ተመስርተው የተቀነባበሩ ዘጋቢ ፊልሞችን በመፈብረክ “አሸባሪ” የሚል ታፔላ በመለጠፍ በአሰልችው የመገናኛ ብዙሀን እንደበቀቀን ይደጋግማቸዋል፡፡ የውሸት ሸፍጥ በታጨቀበት እና ለመስማት እና ለማየትም አስቀያሚ በሆነው “አኬልዳማ” ብሎ በሰየመው ለምንም የማይውል እርባናየለሽ ዘጋቢ ፊልም ኢትዮጵያ በዲያስፖራው ተቃዋሚ ኃይል እና በአገር ውስጥ ባሉ የእነርሱ የግብር ተመሳሳዮች አማካይነት እንዲሁም ሌሎች አሸባሪ ቡድኖች ትብብር እና ርብርብ አደገኛ የሽብር አደጋ ተደቅኖባት እንደሚገኝ አደንቋሪ ጩኸታቸውን አሰምተዋል፡፡ “አኬልዳማ” በዓለም ላይ የተደረጉትን በጣም አስፈሪ እና አስቀያሚ ምስሎችን ሁሉ ለቃቅሞ በቪዲዮ በማሳየት በቅርቡ በህይወት የተለዩት አቶ መለስ ዜናዊ ተቃዋሚዎቻቸውን ጥላሸት በመቀባትና በሶማሌ የሚንቀሳቀሰው የአልቃይዳ እና አልሻባብ ቅጥረኞች ናቸው ብለው በአሸባሪነት በመፈረጅ የጥቃት ብቀላቸውን በንጹሁነ ዜጎች ላይ በሰፊው ተግብረውታል፡፡
በሌላ “ጅሃዳዊ ሀራካት” በተባለ እርባናየለሽ ዘጋቢ ፊልም በክርስቲያን እና በሙስሊሙ ህብረተሰብ መካከል ፍርሀት እና ጥላቻን ለማስፋፋት በማሰብ ጸረ እስልምና እሳትን የመጫር ሙከራ አድርገው በህዝቡ አርቆ አስተዋይነት እና የንቃት ደረጃ ምክንያት እኩይ ምግባራቸው ሳይሳካ መክኖ ቀርቷል፡፡ ለዘመናት አብሮ እና ተከባብሮ እየኖረ ያለውን የክርስቲያን እና የሙሰሊም ማህበረሰቡን በማጋጨት የእስልምና አሸባሪዎች በድብቅ ጅሀዳዊ መንግስት ለመመስረት ዕቅድ አውጥተው ተንቀሳቅሰዋል በማለት በሁለቱ ታላላቅ ኃይማኖቶች እምነት ተከታዮች መካከል የማያባራ እልቂት እና የደም ጎርፍን ለማዝነብ የታቀደ ዲያብሎሳዊ የድርጊት ዕቅድ ነድፈው ነበር፡፡ አሁንም ህዝቡ የነቃባቸው እና ከእነርሱ እኩይ አስተሳሰብ ውጭ የመጠቀ ሀሳብ ስላለው እና ስላወቀባቸው ዕቅዳቸው አሁንም መክኖ ቀርቷል፡፡
ፍርሀት እና ጥላቻን በህዝቡ ውስጥ ለማስፋፋት እና ምናባዊ የሆነ የዘር እና የጎሳ እልቂት እንዲሁም የኃይማኖት ጽንፈኝነት እልቂት እንደሚከሰት በመስበክ ይህንንም እልቂት ለማስወገድ ብቸኛ ቅዱሶች እነርሱ እንደሆኑ አድርገው በማቅረብ እና በማደናገር ጸረ ኢትዮጵያ እና ዘረኛ አስተሳሰብ የተጠናወታቸው ጎጠኞች መሆናቸውን በአደባባይ አስመስክረዋል፡፡ አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ አንዱን ጎሳ በሌላው ላይ በማስነሳት ለማጋጨት ሌት ቀን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ “የጎሳ ፌዴራሊዝም/ethnic federalism” በሚል እኩይ ስልት የዘር ማጽዳት ዘመቻቸውን ቀጥለውበታል፡፡ የጎሳ ጥላቻን ለመቀስቀስ ታሪካዊ ብሶቶችን እየፈበረኩ እና ጥቃቅን ነገሮችን እያጋነኑ በህዝቡ ዘንድ አለመተማመን እና ግጭቶች እንዲነሱ አበርትተው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ህዝቡ ግን ስለነቃባቸው በባዶነታቸው ቀልበቢስ በመሆን እንደ አበደ ውሻ ከወዲያ ወዲህ በመቅበዝበዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ የእራሳቸውን ፍርሀት እንደ መሳሪያ በመጠቀም ህዝቡን ለማደናገር ይሞክራሉ፡፡
በኢትዮጵያ ትንታግ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ላይ የተከፈተው ጦርነት በእራሷ በእውነት ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው፣
በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል በነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና በጦማሪያን ላይ ያወጀው ጦርነት በእውነት በእራሷ ላይ ያወጀው ጦርነት ነው፡፡ ገዥው አካል ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት በተደረጉት ጦርነነቶች እና ግጭቶች ሁሉ በድል አድራጊነት ተወጥቷል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ ጎራዴ እና ኤኬ 47 አውቶማቲክ ጠብመንጃዎችን በታጠቁ አምባገነኖች እና ብዕሮች እና የኮምፒውተር ኪቦርዶችን በሚጠቀሙ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን መካከል የሚደረገው ወሳኙ ፍልሚያ ተቃርቧል፡፡ ያ ጦርነት እና ፍልሚያ በኢትዮጵያውያን/ት ልብ እና አእምሮ ውስጥ ሰርጾ ሁሉንም ዜጎች ለወሳኙ ፍልሚያ እና ለድል ጉዞ ጥርጊያ መንገዱን የሚያመቻች ይሆናል፡፡ የዚያ ጦርነት እና ፍልሚያ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በእርግጠኝነት የምናገረው ነገር ቢኖር ፍልሚያው የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስን ይሆናል፡፡ በእርግጥ ያ ጦርነት በእውነት አራማጅ ወገኖች አሸናፊነት እንደተደመደመ እምነት አለኝ፡፡ ኤድዋርድ ቡልዌር ሊቶን የተባሉት ገጣሚ በትክክል እንዳስቀመጡት ጎራዴ በታጠቁት እና ብዕርን በጨበጡት ተዋጊዎች መካከል በሚደረግ የጦርነት ፍልሚያ በመጨረሻ ሁልጊዜ የወሳኙ ድል ባለቤት የሚሆኑት ብዕርን የጨበጡት ናቸው፡፡
እውነትን ጨብጠዋልና!
እውነት፣ ይህ!
ከሰዎች አገዛዝ ስር ሌላ ታላቅ ነገር አለ፣
ብዕር ከጎራዴ የበለጠ ኃይል አለው፡፡ አስተውል/ይ
ቀስት ተሸካሚዎች ይፈነድቃሉ፣ ግን ምንም የሚመጣ ነገር የለም!-
ልዩ ታምር ከጌታቸው እጀ ይቀበላሉ፣
እናም ቄሳሮችን በድን ለማድረግ ያምጻሉ
ታላቋ መሬት ትንፋሽ ያጥራታል!- ጎራዴውን ከዚህ ወዲያ ውሰዱ-
መንግስታት ከእርሱ ውጭ ሊጠበቁ ይችላሉና!
ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል ማዳን ወይስ ደግሞ የኢትዮጵያን ነጻ ፕሬስ እና ጦማሪያንን ማዳን የሚል ወሳኝ ጥያቄ ቢቀርብልኝ ቶማስ ጃፈርሰን እንደመረጡት ሁሉ እኔም የኋለኛውን ማዳን የሚለው እንዲጠበቅልኝ እመርጣለሁ፡፡ ቶማስ ጃፈርሰን እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው የሚከተለውን መልስ ሰጥተው ነበር፣ ”የእኛ መንግስት መሰረቱ የህዝብ ሀሳብ እንደመሆኑ መጠን የመጀመሪያው ዓላማ መሆን ያለበት ያንን መብት ማስከበር ነው፡፡ እናም ጋዜጦች የሌሉበት መንግስት ከሚኖር ወይም ደግሞ መንግስት በሌለበት ጋዜጦች ብቻ ከሚኖሩ የትኛው የተሻለ ነው የሚል ምርጫ ቢቀርብልኝ የኋለኛውን ለመምረጥ ለሰከንድ እንኳ ጥርጣሬ አይኖረኝም፡፡ ሆኖም ግን ይህን ስል ማንኛውም ሰው እነዚህን ጋዜጦች መቀበል እና ማንበብ መቻል አለበት፡፡“
በተመሳሳይ መልኩ ለእኔም ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን የሌሉበት ገዥ አካል ከሚኖር ወይም ደግሞ ገዥ አካል በሌለበት ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ብቻ ከሚኖሩ የትኛው የተሻለ ነው የሚል ምርጫ ቢቀርብልኝ የኋለኛውን ለመምረጥ ለሰከንድ እንኳ ጥርጣሬ አይኖረኝም፡፡ ከሁሉም በላይ ለዓላማ በጽናት የቆምኩ፣ ለምሰራው ትክክለኛ ስራ ሁሉ ኩራት የሚሰማኝ፣ ላመንኩበት ዓላማ ከልብ እና በወኔ የቆምኩ፣ ዓላማየን ለማስፈጸም በከባድ እርምጃ ወደፊት የምገሰግስ፣ ላልሰራሁት ወንጀል ይቅርታን የማልጠይቅ፣ በምሰራው ስራ ሁሉ የማላፍር፣ ቆራጥ እና የማያወላውል ባህሪን የተላበስኩ የኢትዮጵያ ጦማሪ ነኝ!!!
ኃይል ለነጻ ጋዜጠኞች እና የኢትዮጵያ ጦማሪያን!
ውድቀት እና ዉርደት ህዘብን በጠብመንጃ ኃይል አስገድደው ለመግዛት ለተነሱ የዕኩይ ምግባር አራማጆች!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ኦባንግ “ከምርጫው” በፊት ለተቃዋሚዎች “ምርጫ” አቀረቡ

$
0
0

Obang Methoለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በአገር ውስጥ ለሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና አግባብ አላቸው ለሚሏቸው አካላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተቀምጠው እንዲመክሩ ማሳሰቢያ ሰጡ፡፡ ኢህአዴግ በውስጥ ችግሩ፣ በውጭ ተጽዕኖ ወይም በፖለቲካው የተፈጥሮ ባህርይ የሚከስምበት ደረጃ መድረሱን ያሳሰበው በ”ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ስምና ፊርማ የተበተነው የአኢጋን ደብዳቤ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ልዩነታቸውን አጥብበው እንዲሠሩ ጠይቋል፡፡ ይህንን ለኢትዮጵያና ለሕዝባቸው ሲሉ መሥራት የማይችሉ ከሆነ ከኢህአዴግ በላይ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል፡፡

የፖለቲካ ዕርቅ በመጀመሪያ በተቃዋሚዎች ደጅ ሊተገበር እንደሚገባው ያሳሰበው አኢጋን፤ ይህንኑ ዕርቅ መሠረት በማድረግ ወደ ኅብረት እንዲመጡ በደብዳቤው ገልጾዋል፡፡ ወደ ኅብረት ሲመጡ የፖለቲካ ሥልጣን የመጨበጥ ዓላማቸውን ወደ ጎን መተው እንዳለባቸውና ኢትዮጵያን በማዳን ተግባር ላይ እንዲያተኩሩ በጥብቅ አሳስቧል፡፡

መግለጫው ሲቀጥልም “የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ካለው ግንኙነት አኳያ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰበስባል፡፡ በቅርቡ አንድ ታዋቂ የምዕራቡ ዓለም የፖሊሲ አውጪ ሲናገሩ ኢትዮጵያውያን የምዕራቡ ዓለም ነጻ ያወጣናል ብለውበጭራሽ ማመን የለባቸውም፡፡ ከውጭ ሚላከውን ዕርዳታና ድጋፍ ብናቆም እንኳን ይህ ሚሆን አይደለም፡፡ የለውጥ አራማጅና መሪመሆን ለባቸው ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ናቸው እንጂ ለጋሽ መንግሥታት አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህንን ሊረዱ ይገባል፡፡ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ከህወሃት/ኢህአዴግ የተሻለ አማራጭ በሚፈጥሩበት ጊዜ እኛ የግድ እንድንደግፋቸው ያደርጉናል በማለት ለጋራ ንቅናቄያችን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል” በማለት በመረጃ ላይ የተደገፈ ጭብጥ አቅርቧል፡፡

ሰሞኑን የዚህ ዓመት የSEED ተሸላሚ የሆኑት ይህ የአቶ ኦባንግ የምርጫ አማራጭ ግልጽ ደብዳቤ መጪውን ሁኔታ በሚከተለው ሁኔታ ገልጾታል፤ “አገራችን በበርካታ ድሎች ያንጸባረቀ ታሪክ ያላት ነች፡፡ ከሁሉ በበላይ የሚጠቀሰው የዓድዋ ድል ድጋሚ የሚፈጸምበት ጊዜቢኖር አሁን ነው፡፡ የዓድዋን የጦር ድል በፖለቲካው መድረክ እንድገመው፡፡ መጪውን ምርጫ ፖለቲካዊ የዓድዋ ድልየምንጎናጸፍበት እናድርገው፡፡ ነጻነታችን እንደ ዕርዳታ እህ ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም፡፡ ስለዚህ እኛው ራሳችን እንደአድዋ ድል አንድ ሕዝብ ሆነ በመውጣት የራሳችን የምናደርገበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ቅንነት ካለ የጦር ሜዳውን አድዋ በፖለቲካውሜዳ ላይ መድገም ይቻላል፡፡ አንድ ሊያደርጉን ሊያስተባብሩን የሚችሉ “ምኒልኮችን” ለመጠቀም ፈቃደኛና ቅን እንሁን፡፡

በአኢጋን አድራሻና በዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ይህ የማሳሰቢያ ግልጽ ደብዳቤ አኢጋን በተለይ በዕርቅ ዙሪያ የሚጠየቀውን ማንኛውንም ጥያቄ ድጋፍ እንደሚሰጥ ያረጋገጠ ነው፡፡ የደብዳቤው ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡


“ነጻነትነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም!”

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች ያስተላለፈው ግልጽ መልዕክት

የተወደዳችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤

በቅድሚያ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የአክብሮት ሰላምታ በማቅረብ በትግሉ መስክ የምትከፍሉትን መስዋዕትነት የሚያደንቅ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ምህዳሩ እጅግ ጠብቦ የለም የሚባልበት ደረጃ በደረሰበት ወቅት በምታገኙት ስንጥቅ ሁሉ እየተጠቀማችሁ ለህዝባችሁ የብርሃን ጭላንጭል ስለምትፈነጥቁ አኢጋን ሥራችሁን ያደንቃል፤ ያከብራል፡፡ እኛ በሥራችሁ ስኬት የምንመኘው ለቆማችሁለት የፖለቲካ ዓላማ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት አቅቷቸው መፈናፈኛ ላጡትም የመወሰን ኃይል እንደምትሰጧቸው በማመን ነው፡፡

አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ የበርካታዎች ጥያቄ “ህወሃት/ኢህአዴግን በምን ዓይነት የተሻለ አስተዳደር እንዴት መለወጥ ይቻላል የሚለው ነው?” ይህ ጥያቄ “እኛ ኢትዮጵያውያን የዘርና የጎሣ ትንንሽ አጥሮቻንን አፍርሰን ሁሉን አቀፍ ትግል ለማድረግ ተዘጋጅተናል ወይ?” ብለን ራሳችንን መልሰን አንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ እንዲሁም ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠትሁሉም ነጻ ሳይወጣ ራሳችንን ነጻ ለማውጣት እንችላለን ወይ? ብለንም እንድንጠይቅ የሚያስገድደን ነው፡፡

ህወሃት/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጣናው እንዲሁም ለመላው አፍሪካ “የሚተርፍ” እኩይ የዘርና የጎሣ ፖለቲካ በማስፋፋት አገራችንን እንደዚህ ባለ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በጣለበት በአሁኑ ወቅት የብዙዎች ጭንቀት አገራችን ወደ ምን ዓይነት አዘቀት ውስጥ እየገባች ይሆን የሚለው ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ነገር ግን ይህንን ፍርሃት ወደ ተስፋ የሚቀይር አማራጭ እስካሁን ተግባራዊ መሆን ባለመቻሉ አማራጭ የጠፋ ይመስል ህወሃት/ኢህአዴግም “እኔ ከሌለሁ …” እያለ ያስፈራራል፤ ተቃዋሚዎችም በእርስበርስ ሽኩቻ የህዝብ አመኔታ በማጣት ወደ አለመታመን ከመሄዳቸው የተነሳ መልሶ ተዓማኒነትን ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ገና ብዙ የሚቀር አለ፡፡ ይህም ሆኖ ግን ለኢትዮጵያ ሕጋዊ አማራጭ በመሆን ለሕዝባችን መፍትሔ የምታመጡበት ወሳኝ ጊዜ አሁን መሆኑን የጋራ ንቅናቄያችን ያምናል፡፡

እንደምታውቁት የዛሬ ዓመት ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ ነው፡፡ ምርጫውንና አመራረጡን ከሥሩ ጀምሮ የተቆጣጠረው ህወሃት/ኢህአዴግ ሆኖ ሳለ በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ይካሄዳል ብለን አናምንም፡፡ ሆኖም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል የሚፈለገው ተግባር ከተከናወነ በአገራችን እውነተኛ ለውጥ ይመጣል ብለን እናምናለን፡፡ ዓመኔታ የሚጣልበት አማራጭ ከተገኘ ዓለምአቀፉ ኅብረተሰብ ህወሃት/ኢህአዴግን አንቅሮ ለመትፋት ከምንጊዜውም ይልቅ ዝግጁ ነው፡፡ ይህንንም የምንለው ከምንም ተነስተን ሳይሆን ድርጅታችን በአውሮጳ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በሌሎች የዓለም ክፍሎች ባለው የግንኙነት መስመር ከሚያገኘው ተጨባጭና ተዓማኒ መረጃ በመነሳት ነው፡፡ በምዕራቡ ዓለም ዘንድ ህወሃት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያራምደው የዘር ፖለቲካ፣ የሚከተለው እጅግ ጭቋኝ ፖሊሲ፣ በየጊዜው በሚያወጣቸው አረመኔያዊ ህግጋት፣ ወዘተ ኢትዮጵያን ለከፍተኛ አደጋ የጣለና ለአህጉሩ መጥፎ ምሳሌ እየሆነ በመምጣቱ በኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ የመከሰቱ ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አሳማኝ የሆነበት ጊዜ ላይ ይገኛሉ፡፡ አሁንም ጥያቄው “ህወሃት/ኢህአዴግን ማን ይተካዋል?” የሚለው ነው፡፡ይህንን የመመለሱ ኃላፊነት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ የወደቀ ቢሆንም በተለይ አገር ውስጥ ያላችሁት የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅድሚያ ልትመልሱት የሚገባ ጥያቄ ነው፡፡ አመኔታ የሚጣልበት አማራጭ ሆናችሁ የመቅረባችሁ ሁኔታ ስለምርጫው ነጻና ፍትሃዊነት ከመጠየቅ ባልተናነሰ መልኩ ተጠይቆ መልስ ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡

አገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለእናንተ ማስረዳት የሚያስፈልግ አይመስለንም፡፡ በየቀኑ የሚፈጸመውን በደልና ግፍ መከታተል ብቻ ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ በበቂ ሁኔታ የሚያመላክት ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ እንደ ተቀጣጣይ (ክላስተር) ቦምብ በየቦታው የበተነው የጎሣ ፖለቲካ ፈንጂ ከፋፍሎ በመግዛት ለራሱ የሥልጣን ማቆያ ቢጠቀምበትም በአሁኑ ጊዜ አገራችንን ከላይና ከታች እያነደዳት ይገኛል፡፡ ከዚህ አኳያ በአገራችን ላይ ሊፈነዳ የሚችለው ነገር ሁሉንም የሚያሳስብ እንደሆነ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ራሱ በፈጠረው ችግርና በበተነው መርዝ ራሱን በራሱ ሊያጠፋው እንደሚችል ከድርጅቱ ውስጥ የሚታዩት የሥልጣን ሽኩቻዎች ሁሉም “ሳይቀድሙኝ ልቅደም” በሚል አስተሳሰብ እንደተወጠረ የሚያመለክት ነው፡፡ አገራችን ነጻነቷን ከመጎናጸፏ በፊት ይህንን ዓይነቱ የህወሃት/ኢህአዴግ እርስበርስ መበላላት የሚያሳስባቸው ኢትዮጵያውያን እጅግ በርካቶች ናቸው፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ እናንተ ባላችሁ ኃላፊነት ይህንን በውል የምታጤኑት እንደሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ያምናል፡፡

ህወሃት/ኢህአዴግ ከውስጥ በሚነሳበት ግፊትና የመበላላት ስጋት፤ ከውጪ በሚመጣበት ተጽዕኖ ወይም በሁለቱ ጥምረት ከሥልጣን መወገዱ የማይቀር ነው፡፡ ይህንን የሚቀበል ካልሆነም ሥርነቀል ተሃድሶ ማድረጉ እየጎመዘዘው የሚጠጣው ሐቅ ነው፡፡ በየትኛውም መልኩ የሚከሰተው ለውጥ አገራችንን መልሶ መልኩን ለቀየረ በዘር ላይ ለተመሠረተ አገዛዝ አሳልፎ የሚሰጣት መሆን የለበትም፡፡ ይልቁንም የሚመጣው ለውጥ ሕዝባችንን እውነተኛ ነጻነት የሚያጎናጽፍ፣ ፍትሕ የሚሰጥና ወደ ዕርቅ የሚመራ መሆን ይገባዋል፡፡ አገራችን በዚህ ጎዳና ላይ እንድትጓዝ የማድረጉ ኃላፊነት የእናንተ እንደሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ያሳስባል፡፡

ይህ ደግሞ ሥልጣን ከመጨበጥ ባለፈ ምኞት ላይ የተመሠረተና እያንዳንዱ ነጠላ ፓርቲ ከሌሎች ጋር በኅብረት በመሥራት ተግባራዊ ሊያደርግ የሚገባው መሠረታዊ ዓላማ ነው፡፡ አገራችን ካለችበት ታላቅ ችግር አኳያ የፓርቲዎች መተባበርና ከተቻለም መዋሃድ ወደ መፍትሔ በሚወስደው መንገድ ላይ የመጀመሪያው ስኬት ነው፡፡ ይህ ግን በቀላሉ አይገኝም፤ ሆደ ሰፊ መሆንን፣ ከራስ ይልቅ ለአገርና ለሕዝብ እንዲሁም ለመጪው ትውልድ ማሰብን፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ከፍተኛ የመንፈስ ልዕልናን የሚጠይቅ ነው፡፡ ሥልጣንን፣ የራስን ክብር፣ የበላይነትን፣ “እኔ ከሌላው የተሻልኩ ነኝ” ማለትን፣ ወዘተ እያውጠነጠኑ ለአገር አስባለሁ ማለት በእጅጉ አስቸጋሪ ነው፡፡ “ከጠላት” የላቀ የመንፈስ ልዕልና ከሁሉም ይጠበቃል፡፡

በመጪው ምርጫ ከምንጊዜውም በበለጠ በመጽናት ለለውጥና ለነጻነታችን የምንታገልበት ሊሆን ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የናፈቀውን ነጻነት ሊጎናጸፍ የሚችልበት አማራጭ ሊፈጠር እንደሚችል አኢጋን ያምናል፡፡ ይህ ሊከሰት የሚችለው በአገር ውስጥ ያላችሁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥቃቅን ልዩነታችሁን አስወግዳችሁ አጀንዳችሁን ሕዝባዊ በማድረግ በኅብረት ለመሥራት ስትወስኑ ነው፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ባደረገው ጥናት አብዛኞቻችሁ ያላችሁ ልዩነት መሠረታዊ እንዳልሆነ ለመረዳት ችሏል፡፡ ይህም የሚያሳየው እርስበርስ ከሚያለያያችሁ ነገሮች ይልቅ ሊያስማሟችሁ የሚችሉት በርካታዎች እንደሆኑ ነው፡፡ በተለይ በአመራር ላይ ያላችሁ በተለያየ ጊዜ ከሌሎች ጋር የተከሰቱ ልዩነቶችና ግጭቶች እንዲሰፉ ምክንያት ከመሆን ይልቅ ለአገርና ሕዝብ በማሰብ ኢትዮጵያን የመታደግ ኃላፊነት ወድቆባችኋል፡፡ አገር ከሌለ ምንም ሊኖር አይችልም፤ እንደ ትልቅ የያዛችሁት ልዩነትና ችግርም ከንቱ ይሆናል፤ አብሮ ይከስማል፡፡

በተደጋጋሚ የሚሰማው ነጠላ ዜማ “በኢትዮጵያዊ ውስጥ ተስፋ የሚጣልበት ተቃዋሚ ፓርቲ የለም” የሚል ነው፡፡ በእርግጥ ለዚህ ጥያቄ ዋንኛ ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው፡፡ ምክንያቱም በአስመሳይ ዲሞክራሲና ተግባራዊ ባልሆነ ሕገመንግሥት ሕዝባችንን ከመጠርነፍ አልፎ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም በተመሳሳይ ሁኔታ ሸብቧቸዋል፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው ፕሮግራም በኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ እንዳይኖር ያደረገ ለመሆኑ ማንም የሚክደው አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በኢህአዴግ ብቻ እያመካኙ መኖር ተቀባይነት የሌለው አካሄድ ነው፡፡እያንዳንዱ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲ ዓላማው የኢህአዴግን መሰሪነትና አፋኝነት ለመስበክ ሳይሆን ሕዝብን ለነጻነት ማብቃት ነው፡፡ እታገለዋለሁ ከሚለው አካል መላቅ ካልቻለ ለትግል ብቁ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡

ሽንፈት ላይ እያተኮሩና የጠላትን ኃይለኛነት እየሰበኩ ድል አይገኝም፡፡ ልዩነትን እያራመዱ ኅብረትና አንድነት ተግባራዊ መሆን አይችልም፡፡ለአገራዊ ዕርቅ እንሰራለን እያሉ በፓርቲ መካከል ከዚያም በታች በግለሰብ ደረጃ መተራረቅ ካልተቻለ ብሔራዊ ዕርቅ ከቀን ቅዠት አያልፍም፡፡ እያንዳንዳችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ፣ መኢአድ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ ኦህኮ፣ አረና፣ እና ሌሎች እጅግ በርካታ ፓርቲዎች የተቋቋማችሁትና ዓላማ ያደረጋችሁት ኢህአዴግን እየተቃወማችሁ ለመኖር እንዳልሆነ የፓርቲ ፕሮግራማችሁ ይመሰክራል፡፡ ወይም ዓላማችሁ የራሳችሁን የፓርቲ ምርጫ የማድረግና ፕሬዚዳንት (ሊቀመንበር)፣ ምክትል፣ ሥራ አስፈጻሚ፣ … በመምረጥ አዙሪት ውስጥ ራሳችሁን ላለማሽከርከር እንደሆነ ከማንም በላይ ራሳችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ከዚህ አንጻር በጥንቃቄና በብዙ ጥናት የተቀመጠው የፓርቲያችሁ ፕሮግራምና ዓላማ ለአገራችን አንዳች ለውጥ ሳያመጣ እንደዚሁ እንዳማረበት ቢቀመጥ ለሕዝብ የሚያመጣው ትርፍ ምንድርነው? እናንተንስ ለመቃወም ብቻ የምትሰሩ አያደርጋችሁምን? ለኢህአዴግና ወዳጆቹስ ጣት የሚጠቁሙበትን ዕድል እየሰጣችሁ እስከመቼ ትኖራላችሁ? ስለዚህ የእስካሁኑ በነጠላ የመጓዙ ጉዳይ ካልሰራ በኅብረት የመሥራቱ ጉዳይ የግድ ይሆናል፡፡ ይህ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ አኢጋን ያምናል፡፡

የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ካለው ግንኙነት አኳያ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰበስባል፡፡ በቅርቡ አንድ ታዋቂ የምዕራቡ ዓለም የፖሊሲ አውጪ ሲናገሩ “ኢትዮጵያውያን የምዕራቡ ዓለም ነጻ ያወጣናል ብለው በጭራሽ ማመን የለባቸውም፡፡ ከውጭ የሚላከውን ዕርዳታና ድጋፍ ብናቆም እንኳን ይህ የሚሆን አይደለም፡፡ የለውጥ አራማጅና መሪ መሆን ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ናቸው እንጂ ለጋሽ መንግሥታት አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህንን ሊረዱ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ከህወሃት/ኢህአዴግ የተሻለ አማራጭ በሚፈጥሩበት ጊዜ እኛ የግድ እንድንደግፋቸው ያደርጉናል” በማለት ለጋራ ንቅናቄያችን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ይህ ንግግር በአገር ውስጥ ለምትገኙት ብቻ ሳይሆን በዳያስፖራ ለምንገኘውም ልንገነዘብ የሚገባው ሐቅ ነው፡፡ ነጻነት ከምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን በዳያስፖራ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያንም ሊመጣ አይችልም፡፡ የነጻነታችንን ጥያቄ ተግባራዊ የሚሆነው እናንተ በአገር ውስጥ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኅብረት በመሥራት ሕዝባችንን ለለውጥ ስታስተባብሩት ብቻ ነው፡፡ እኛ ይህንን ከራሳችን ትከሻ ላይ ለማውረድና እናንተን በኃላፊነት ለመጠየቅ የምንጭነው ሳይሆን አገር ውስጥና ውጭ መሆናችን በታሪክም ይሁን በሌላ ምክንያት የተከሰተ በመሆኑ በቅንነትና በሐቅ የምንናገረው እውነታ ነው፡፡ እኛም ከአገር ውጭ ነን በማለት እጃችንን አጣጥፈን የምንቀመጥ ሳይሆን በአገር ውስጥ የሚካሄደውን ትግል የመደገፍ፣ የማገዝ፣ የምዕራባውያንን አመለካከት የማስቀየር፣ በአገር ውስጥ የሚካሄደውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የማሳወቅ፣ … ኃላፊነት እንዳለብን በመገንዘብ ነው፡፡ አኢጋን ይህንን ዓይነቱን ተግባር ሲያካሂድ የቆየ አሁንም ከአገር ውስጥ የሚመጣውን ጥያቄ ለመመለስና በሚችለው ሁሉ ለማገዝ ሙሉ ዝግጁ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡

ከዚህ በፊት በተካሄዱት ምርጫዎች እንደታየውና በፓርቲያችሁ ፕሮግራም ላይ እንደሰፈረው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ በምርጫ ተወዳድራችሁ ሥልጣን የመያዝ ዓላማ እንዳላችሁ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ግን ማናችሁም ብትሆኑ በነጠላ ፓርቲነት ተወዳድራችሁ ሥልጣን በመያዝ ለውጥ እንደማታመጡ በግልጽ ልንነግራችሁ እንወዳለን፡፡ በምርጫ አሸነፋችሁ ቢባል እንኳን ሥልጣን የሌለው ቢሮ ከመያዝና የህወሃት/ኢህአዴግ አሻንጉሊት ከመሆን እንደማታመልጡ እሙን ነው፡፡ ይልቁንም ይህ ዓይነቱ አካሄድ ህወሃት/ኢህአዴግ በተለይም ለምዕራቡ ዓለም ለሚደሰኩረው የይስሙላ ዴሞክራሲ ማረጋገጫ ሆኖ በማቅረብ የኢህአዴግ ዕድሜ መቀጠያ መድሃኒት ነው የምትሆኑለት፡፡ ስለዚህ ከመጪው ምርጫ አኳያ ትግሉ የተናጠል ሳይሆን ፓርቲዎች በኅብረት በመሆን ኢህአዴግን በእርግጠኝነት ሊተኩ የሚችሉበት አማራጭ ሊሆን ይገባዋል፡፡

በበርካታ አገሮች እንደሚታየው እናንተም በኅብረት በመሆን ኃይላችሁን አስተባብራችሁ ለሕዝባችሁ ስትሉ እርስ በርስ መጠላለፍ፣ መነቋቆር፣ መካሰስ፣ ወዘተ አሁኑኑ ማቆም ይገባችኋል፡፡ በእስራኤል፣ ብሪታኒያ፣ ጀርመን፣ … በተለያዩ ጊዜያት እንደታየው ፓርቲዎች ጥምር መንግሥት በመመሥረት ሕዝባቸውን ታድገዋል፣ አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያስ ይህ ሊሆን የማይቻልበት ምክንያት ምንድርነው? መልሱን መመለስ የሚገባችሁ እያንዳንዳችሁ የፓርቲ አመራሮች ናችሁ፡፡

ይህ ሳይሆን የሚቀር ከሆነ በቅርቡ የፖለቲካ ታሪካችን እንደታየው በዚህም ዘመን በተመሳሳይ መልኩ ይደገማል፡፡ በዘመነ አጼ ኃይለሥላሴ የተነሳው የህዝብ ብሶት ዳር ሳይደርስ ደርግ ለራሱ አስቀረው፡፡ በደርግ ዘመን መከራውንና ስቃዩን ያየው ሕዝብ ህወሃት/ኢህአዴግ “የሕዝብ ብሶት” የወለደኝ ነው ብሎ ሲመጣ የመከራው ዘመን ማብቂያው የደረሰ መስሎት ተስፋ አደረገ፡፡ “ብሶት” ወለደኝ ያለው ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ታይቶ በማይታወቅ የዘር “ድንበር” ከፋፍሎ የሕዝባችንን ብሶት ለ23ዓመታት በየቀኑ እያበዛው ይገኛል፡፡ አሁንም ጥንቃቄ ወስዳችሁ ሁላችሁም ለሕዝባችን የሚሆን መፍትሔ የማታመጡ ከሆነ የሕዝባችን ብሶት እንዲቀጥል የምታደርጉ ብቻ ሳይሆን በመጪው ትውልድም ከመጠየቅ አታመልጡም፡፡

በቅንጅት ጊዜ ሕዝብ እጅግ ተስፋ አድርጎ ውጤት ሲጠብቅ ቅንጅቶች “መቀናጀት” አቅቷቸው ጫፍ ላይ ደርሶ የነበረው የሕዝባችን ድል ገደል ገባ፤ በራሱ ተቀናጅቶ የነበረው ሕዝብ የህወሃት/ኢህአዴግ የበቀል እርምጃ ሰለባ ሆነ፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ወገኖች ጋር ባለው ግንኙነት አሁንም ተመሳሳይ ችግር ይፈጠራል እያሉ ስጋታቸውን የሚገልጹልን ቁጥራቸው በርካታ ነው፡፡ በአገራችን ላይ በርካታ ችግሮች የተጋፈጥን ቢሆንም ከፈጣሪ በኩል ግን ሁልጊዜ መፍትሔና የተበላሸውን የማስተካከል ዕድል አለ፡፡ ይህም ዕድል አሁን እንደሆነ አኢጋን ያምናል፡፡ ከዚህ አንጻር ጥቂት ሃሳቦችን ለማካፈል እንወዳለን፤

  1. በምንም መልኩ በኢትዮጵያ አማራጭ ፓርቲ የለም የሚለውን ተስፋ አስቆራጭ ንግግር አትቀበሉ፡፡
  2. ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብራችሁ ልትሰሩ የሚያስችላችሁን ነጥቦች ዘርዝሮ በማውጣት በሚያስማማችሁ ጉዳዮች ላይ የጋራ አስተሳሰብ ልትወስዱ የምትችሉበትን መንገድ አመቻቹ፡፡
  3. በዕቅዳችሁና ከሌሎች ጋር በጥምረት በመሆን ምንም እንኳን አስቸጋሪ ቢሆን በዋንኛነት በአገራችን የፖለቲካ ምህዳር የሚሰፋበትንና ዕርቅ የሚመጣበትን መንገድ ከመቀየስ ተስፋ አትቁረጡ፡፡
  4. የፓርቲ ፕሮግራምና ማኒፌስቶ ከሰማይ የወረደ፣ የማይገሰስ፣ የማይሻርና የማይለወጥ የፈጣሪ ቃል አይደለም፡፡ ስለዚህ ወደ ውኅደት በሚደረገው ጉዞ መሻሻል፣ መለወጥ፣ መስተካከል፣ የሚገባው የፕሮግራም አንቀጽ የፓርቲያችሁን ኅልውና አደጋ ላይ እስካልጣለ ድረስ ተፈጻሚ ለማድረግ ሆደሰፊ ሁኑ፡፡
  5. ከመሪዎች ጀምሮ በፓርቲያችሁ ውስጥ ውህደትን፣ ጥምረትን፣ … ተግባራዊ ለማድረግና በጋራ ለመሥራት ዕንቅፋት የሚሆኑ ግለሰቦችን በግልጽ መውቀስና እንዲታረሙ ወዲያውኑ ማድረግ ወሳኝነት ያለው ተግባር ነው፡፡ “እገሌን እንዴት እወቅሰዋለሁ” ወይም “አቶ እገሌ የፓርቲያችን የጀርባ አጥንት ነው እንዴት ተሳስተሃል እላልሁ” በሚሉ የይሉኝታ አስተሳሰቦች ለአንድ ሰው ሲባል አገርና ሕዝብ መከራና ስቃይ እንዲቀጥል መደረግ የለበትም፡፡ አገር ለመምራት ፓርቲ መሥርታችሁ ሕዝብን በይሉኝታ መንግሥት ማስተዳደር ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለይሉኝታ በራችሁን ዝግ ይሁን፡፡
  6. ሁልጊዜ ለመምራት ሳይሆን ለመመራት ተዘጋጁ፡፡ የሰላማዊ ትግል መሪ መመሪያ ይኸው ነው፡፡ ለመመራት የተዘጋጀ መሪ ለመሆን ምንም አይቸግረውም፡፡ ከሥልጣንህም ተነሳ ሲባል ፓርቲውን አይገነጥልም ወይም “እኔ ከሞትኩ …” በሚል ጭፍን አስተሳሰብ በሕዝብ ላይ የውድመት ተግባር አይፈጽምም፡፡ ይህ ምንም የምንደባበቅበት ነገር አይደለም በተግባር ሲፈጸም የኖረ ነው፤ መስተካከልና መሻሻል የሚያስፈልገው ነው፡፡ ከመገልገል ይልቅ ለማገልገል ትሁት ሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው ትክክለኛ አስተዳደር ነው እንጂ ህወሃት/ኢህአዴግን በሌላ መተካት አይደለም፡፡ ሕዝባችን ይህ ያንሰዋል እንጂ አይበዛበትም፡፡ ስለሆነም “ኢህአዴግ ይነሳ እንጂ” የሚለው ጠባብና ሰንካላ ሃሳብ የእውነተኛ ለውጥ መርህ ስላልሆነ በጭራሽ ለሕዝባችን አትመኙለት፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንግዲህ ወዲህ የሚያስፈልገው “ከጎሣና ዘረኝነት ይልቅ ሰብዓዊነት”የሚያብብባትና “አንዱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ነጻ የወጣባትን”፤ ፍትህ፣ ሰላምና ዕርቅ የሰፈነባትን አዲሲቷን ኢትዮጵያን ነው፡፡ ከዚህ ያነሰ ለውጥ በለውጥ ደረጃ ሊታሰብም ሆነ ሊታቀድ አይገባውም፡፡

እናንተ አገር ውስጥ ሆናችሁ በየጊዜው በምታደርጉት የመስዋዕትነት ተግባር የጋራ ንቅናቄያችን ከጎናችሁ ይቆማል፡፡ ሥራችሁንም በታላቅ አክብሮት ይከታተላል፡፡ የመስዋዕትነታችሁ ውጤት ፍሬ እንዲያፈራ የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ በውጭ ከበርካታ ወገኖች ጋር ባለን ግንኙነት ለምትፈልጉን ሥራ በምንችለው ሁሉ ለመተባበር ፈቃደኛ መሆናችን እንገልጻለን፡፡ በተለይ በዕርቅ መንገድ ላይ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚጠየቀውን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኝነቱን ይገልጻል፡፡ ይህ ጉዳይ በዚህ ደብዳቤ ላይ ለፕሮቶኮል ብለን የምንናገረው እንዳልሆነ እንድትረዱልን እንፈልጋለን፡፡

አገራችን በበርካታ ድሎች ያንጸባረቀ ታሪክ ያላት ነች፡፡ ከሁሉ በበላይ የሚጠቀሰው የዓድዋ ድል በድጋሚ የሚፈጸምበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ የዓድዋን የጦር ድል በፖለቲካው መድረክ እንድገመው፡፡ መጪውን ምርጫ ፖለቲካዊ የዓድዋ ድል የምንጎናጸፍበት እናድርገው፡፡ ነጻነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም፡፡ ስለዚህ እኛው ራሳችን እንደ አድዋ ድል አንድ ሕዝብ ሆነን በመውጣት የራሳችን የምናደርገበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ቅንነት ካለ የጦር ሜዳውን አድዋ በፖለቲካው ሜዳ ላይ መድገም ይቻላል፡፡ አንድ ሊያደርጉንና ሊያስተባብሩን የሚችሉ “ምኒልኮችን” ለመጠቀም ፈቃደኛና ቅን እንሁን፡፡

እርስበርሳችን እንደ ወንድምና እህት ለመተያየትና ለመግባባት ፈጣሪ ቅን ልብ ይስጠን፡፡ እናንተንም ለፍትሕ፣ ለነጻነት፣ ለሰብዓዊነት፣ ለፍቅርና ዕርቅ ስትታገሉ ማስተዋልንና ጥበብን ይስጣችሁ፡፡

ከአክብሮት ጋር ለአገራችን ፈውስ እንዲመጣ የትግል አጋራችሁ፤

ኦባንግ ሜቶ
ዋና ዳይሬክተር፤
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)

Email: obang@solidaritymovement.org
Website:www.solidaritymovement.org

የወታደራዊ አገዛዝ 40ኛ ዓመት ከግንቦት 1966 –ግንቦት 2006 ዓ.ም

$
0
0

የሺዋስ አሠፋ
(ለነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደጻፉት)

የአንድ ሀገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች በሙሉ መንግስት ጨቋኝ ቁጥጥር ስር ሲሆኑ፣ የህዝቡ እንቅስቃሴዎችና ክንውኖች ከመንግስት በሚወርድ መመሪያ ብቻ ሲመክኑ፣ በህጋዊ ውሳኔና በፖለቲካዊ ውሳኔዎች መካከል ምንም ልዩነት ሲጠፋ ያች ሀገርና በውስጧ ያሉ ዜጎች በወታደራዊ አገዛዝ ስር የወደቁ ናቸው፡፡ በሀገሪቱ ያለው አገዛዝ በግልፅና በስውር በሚያሰማራቸው ወታደሮች፣ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች፣ ደህንነቶች የነዋሪዎችን/የዜጎችን፣ የመንቀሳቀስ ሀሳብን የመግለፅና የመደራጀት መብት በቅርብ ክትትልና ቁጥጥር ስር ያለና የተገደበ ወይም ከፍተኛ ጫና ያለበት ይሆናል፡፡

mengistu hailemariam
የወታደራዊ አገዛዞች ሁሉም ለማለት በሚቻል መልኩ ወደ ስልጣን የሚወጡት በመደበኛ ጦርነት፣ በሽምቅ ውጊያ፣ በመፈንቅለ መንግስት ወይም በተለያዩ ሁኔታዎች በሚፈጠር የስልጣን ክፍተት ነው፡፡ በወታደራዊ አገዛዝ ካለፉ ሀገሮች መካከል ሶቪየት ህብረት፣ ምስራቅ ጀርመን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቺሊ፣ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ፓኪስታን፣ ኢትዮጵያ… ጥቂቶቹ ናቸው፡፡በሀገራችን እንዳየነውና ከሌሎችም ሀገሮች ተሞክሮ እንዳነበብነው የእነዚህ አገዛዞች ዋና ዋና ባህሪያት ከሚባሉት ውስጥ ከነሱ በፊት የነበሩ ስራዎችን መልካም ጅምሮችንም ጨምሮ መደምሰስና ማጥፋት፣ አዲስ መሰረትነው ለሚሉት ሀገርና ልማት ህዝቡን በእዝ ሰንሰለት በመጠርነፍ አስገድዶ ለማሰራት መሞከር፣ የሚከናወኑ ተግባራት በሙሉ በአስቸኳይ ጊዜና በዘመቻ ስራ እንዲሰሩ ማስገደድ፣ ስለተሰሩ ስራዎች ውጤት ሳይገመገም ሌላ ዘመቻ በማስከተል ህዝቡን ረፍት ማሳጣ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር አንድ ኃይል በጠላትነት መሳልና የህዝቡን አይን ከአገዛዙ ድክመት ወደሚመጣው ጠላት ማዞር፣ በሚቆጣጠረው ብዙሃን መገናኛ የህዝቡን ሕይወት በፕሮፓጋዳ መያዝ፣ የተለየ ሀሳብ ያላቸውን ከጠላት ጋር በመፈረጅ፣ ሀገር ጠባቂና ለህዝብ ተቆርቋሪ መስሎ መታየት፣ የሀገሪቱን ሀብት በመበዝበዝ የገዥዎችን የአስተሳሰብ ድክመት በገፍ በሚወጣ የሀገር ሀብት ለማካካስ መሞከርና መሰል ድርጊቶች መለያዎቹ ናቸው፡፡

የዘውዳዊ ስርዓት እያረጀና ማስተዳደር እየተሳነው ሲሄድ ከወታደሩ የተሰባሰቡና ራሳቸውን ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ብለው የሰየሙ፣ ከኢትዮጵያ መለዮ ለባሾች የተውጣጡ ለንጉሱ የማታለል ታማኝነትን እየገለፀ የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴን መንግስት የገለበጠው ወታደራዊ ቡድን ስልጣኑን ያዘ፡፡
ሻ/ል ተስፋዬ ርስቴ ‹‹ምስክርነት›› በሚለው መፅሐፋቸው እንደገለፁት ደርግ የራሱ የሆነ ርዕዮት ዓለም አልነበረውም፤ ድንገት በተሰባሰቡ መኮንኖች የተሞላ ነበር፡፡ ከየካቲት 1966 ጀምሮ ከ6 ወራት ባነሰ ስልጣኑን በእጁ ካስገባ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደር መንግስት በመመስረት መለዮ ለባሾችን በሚኒስትርነትና በኮሚሽነርነት ማዕረግ በማስቀመጥ ከጠመንጃ አፈሙዝ ያገኘውን ስልጣን ለ17 ዓመታት ገፋበት፡፡

ከተለያዩ የጦር ካምፖች የተውጣጡ መኮንኖች አራተኛ ክፍለ ጦር ጠቅላይ መምሪያ ከተሰባሰቡ በኋላ በቅድሚያ መነጋገር የጀመሩት ምን እናደርግ? በሚል አጀንዳ ነበር፡፡ ይህ ግንቦት 1966 ምንም መርህ ያልነበረው ወታደራዊ ቡድን ከመስከረም 1967 ጀምሮ ስልጣኑን ጠቅልሎ በመያዝ ሀገሪቱን የጦርነትና የዘመቻ ቀጠና በማድረግ ሲያተራምሳት ኖረ፡፡ በዚህ ወቅት ከተደረጉትና ተመልካቹን ካስደነቁት ነገሮች አንዱ የአብዮቱ መሪና የደርጉ ሊ/መንበር የነበሩት ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም ለጋዜጠኛ ሚሊዮን ተረፈ ሲመልሱ የሚሊቴሪ ልብሳቸውን በሱፍ ቀይረው እኔ ዋና ፀሐፊ ነኝ ‹‹ወታደራዊ መንግስት የታለ? አሁን ያለው መንግስት ሲቪል መንግስት ነው›› ሲሉ መደመጣቸው ነበር፡፡

ደርግ ሀገሪቱን ደቁሶ ከወደቀ በኋላ በእሱ እግር የተተካው ኢህአዴግ በሽግግር መንግስቱ ውስጥ ያካታተቻው ሚኒስትሮች ጋንታ መሪዎች፤ ተዋጊና አዋጊ ወታደሮች የነበሩ ሲሆኑ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጀምሮ ሁሉም ባለስልጣናት የወታደር ልብሳቸውን ለውጠው ሙሉ ሱፍ የለበሱ ወታደሮች ናቸው፡፡ ስብሃት ነጋ፣ ስየ አብርሃ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባይ ወልዱ፣ አዲሱ ለገሰ፣ በረከት ስምኦን፣ አባዱላ ገመዳ ወዘተ ሁሉም ወታደሮች የነበሩ ሲሆን አንዳንዶቹ ከጄነራልነት በቀጥታ አቶ ወደሚል ማዕረግ ወርደው አገዛዙን ሲቪል ለማስመሰል የተሞከረበት መንገድ ቢታይም እንደ 1997 ዓይነት ፈታኝ ጊዜ ሲመጣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ሁሉም አዋጊ ጄነራሎች ሆነው ታይተዋል፡፡

በብዙኃን ሲቪል ህብረተሰብ እንደሚታወቀው ወታደር በከፍተኛ ታዛዥነትና ዲሲፕሊን የሚያምን፣ ቀድሞ በገባ የሲኒየሪቲ ባህል የሚገዛ (ይሄ ዛፍ ከአንተ ቀድሞ እዚህ ግቢ የበቀለ በመሆኑ የሲኒየር ሰላምታ ስጥ ሲባል እስከመቀበል የሚደርስ)፣ ለ6 ወራት ባገኘው ስልጠና ከ60 ዓመታት በላይ
የሚኖርበት፣ በበዓልም ሆነ በአዘቦት፣ በሰርግም ይሁን በለቅሶ በጠዋት ተነስቶ እንቅስቃሴ የሚሰራ፣ ፂሙንና ፀጉሩን የማስተካከል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካልሰራ፤ ጫማው ካልተቀባ፣ የሸሚዙ ኮሌታ ካልነፃ፣ ሱሪው ቀጥ ብሎ ካልተተኮሰ፣ ቁርሱን የማይቀምስ ህይወቱን በሙሉ በተጠንቀቅ የሚኖር፣ ለሀገሩ ጋሻና መከታ የሚሆን፣ ሀገሪቱ በአገዛዝ ስር ስትሆን ደግሞ የአለቃው ዱላ የሚሆን ነው ወታደር ማለት፡፡ ይህን የወታደር ህይወት በመንግስት ስርዓት ውስጥ ስናየው ዛሬ ሀገራችን ያለችበት አጠቃላይ ሁኔታ ያሳየናል፡፡ ለሚከናወኑ ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ህዝብን አማክሮና የህዝቡን ይሁንታ አግኝቶ ከመንቀሳቀስ ይልቅ በተለመደው ወታደራዊ አሰራር የአንድን ግለሰብ ሀሳብ ባለው የጥርነፋ መዋቅር መሰረት ከላይ ወደታች ለማውረድና ለማስረፅ ሌት ከቀን በሚዲያ መለፈፉና በየቀበሌው ከአመት አመት ስብሰባ የካድሬዎቹና የህዝቡ ህይወት ሆኖ እያየን ነው፡፡

ለ23 ዓመታት በዚህ ሁኔታ የሚገዙን ግለሰቦች ከስማቸው በፊት ያለውን ቅፅል ቢቀይሩም፣ ወታደራዊ መለዮአቸውን ቀይረው የሲቪል ልብስ ቢለብሱም ሲያዋጉና ሲያዋጉ የኖሩ ናቸው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ለ17 ዓመታት በደርግ፣ ለ23 ዓመታት በኢህአዴግ በጠቅላላው ለ40 ዓመታት በወታደራዊ አገዛዝ ስር የምትማቅቅ ሀገር ናት፡፡የደርግ ባለስልጣናት የነበሩት መንግስቱ ኃ/ማርያም፣ አጥናፉ አባተ፣ ተፈሪ በንቲ፣ አማን አንዶም፣ መላኩ ተፈራ፣ ለገሰ አስፋው፣ ፍ/ስላሴ ወግደረስ እና ሌሎችም ይህንና ያንን ያደርግነው መጀመሪያ ኢህአፓ ስላደረገው ነው ወይም በመኢሶን ምክር ነው በማለት የአገዛዙን መጥፎ ድርጊቶች በሌላ ወገን ለማላከክ ቢሞክሩም የመንግስታቸውን ወታደራዊ አገዛዝነት አይከዱም፡፡
eprdf-tplf
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ግን ፈፅሞ በወታደርነት ያልተሰለፉ ለማስመሰል ከሲቪል መካከል በምርጫ የመጡ ተደርገው እንዲታዩ ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ እውነታው ግን በወጣትነት ጊዜያቸው በተቀረፀባቸው የአድርግ አታድርግ በወታደራዊ ትዕዛዝ የተቀየዱ መሆናቸው ነው፡፡ ይህ የወታደር መስመራዊ
ትዕዛዝ በዘርና በወንዝ ልጅነት ሲጠፈር ፍፁም የሆነ የጋሪ ፈረስ አይነት መከተልን ያመጣል፡፡ የችግሩም ምንጭ ጥልቀት ይሄን የተቀየደ አሰራር ወደ ሲቪል ተቋማት ለማውረድና በዚሁ መሰረት የጉልበትም ሆነ የአእምሮ ስራዎችን አስገድዶ ለማሰራትና ሀገርን ለማስተዳደር ሲሞክር ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽን መስሪያ ቤትን አስተዳደር ለፈረንሳይ ኩባንያ እንሰጣለን የሚል ትዕዛዝ መጣ፡፡ በወቅቱ ይህን ለማስፈፀም ላይ ታች ሲሯሯጡ የነበሩት አቶ ደብረ ጽዮን የተባሉ የህወሓት ወታደር የነበሩ በኋላ ልብሳቸውን ቀይረው ሚኒስተር የተደረጉ ሰው ነበሩ፡፡
በወቅቱ እዚያው እሰራ ስለነበር ከተሰብሳቢዎች መካከል ነበርኩ፤ በስብሰባው መክፈቻ ላይ እኒህ ግለሰብ ያስተላለፉት ትዕዛዝና ያንን ትዕዛዝ ለማስተላለፍ የተጠቀሟቸው ቃላት ቀጥታ ከኢታማጀር ሹሙ የተቀበሉትን ወታደራዊ ትዕዛዝ ለሰራዊቱ የሚያስተላልፉ ጄኔራል ይመስሉ ነበር፡፡ ስለ ጭቆና፣ ስለ
ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ስለሽብር፣ ስለመበታተን አደጋ ምንም የማይመለከተው ቦታ ላይ ተናገሩ፡፡ ስለቴሌ መፍረስና ስሙም አትዮ ቴሌኮም ወደሚል መቀየሩን፣ ሰራተኛ እንደማይቀነስ ወዘተ… ብዙ ተናገሩ፡፡ የእኛን ሀሳብ ግን አንዱንም ለማድመጥ ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ የመጡት ወታደራዊ ትዕዛዝ ማስተላለፍ ስለነበር፡፡ላለፉት 40 ዓመታት በባንክ፣ በቴሌ፣ በመብራት ኃይል፣ በአየር መንገድ፣ በህንፃ ኮንስትራክሽን፣ በመንገድ ትራንስፖርት ላይ በመሳሰሉት ተቋማት ወታደራዊ ትዕዛዝና የዘመቻ ስራ ትንፋሽ እስኪያጥራቸው ሲያዋልባቸው ኖሯል፡፡ የሚደንቀው ግን አስበውና አቅደው ሳይሰሩ ያለፈውን ተግባር ድክመ
ትም ሆነ በጥንካሬ መነሻ ሳያደርጉ ለማደግ መታሰቡ አልፎም አድገናል መባሉ ነው፡፡ በሰላም በምንገዛላቸው ጊዜ ይህን ቢያደርጉም ስልጣኑን የሚነቀንቅ ሁኔታ ሲከሰት ልብስና ማዕረግ ቀያይረው በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ማለት የነዚህ ወታደራዊ አገዛዝ መሪዎች ባህሪ ነው፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ
በሌሎች እንደ ኩባ፣ በርማ እና ደቡብ ሱዳን መሪዎች የቅርብ ጊዜ ትዝታዎቻችን ናቸው፡፡

የወታደራዊ አገዛዝን ከነፍሱ የሚጠሉት ጄን ሻርፕ አገዛዞች በጣም ብልጥና ውስብስብ ሆነዋል ይላሉ፡፡ ህዝቡን እርስ በርስ ከማጋጨት በተጨማሪ ከዲሞክራት መንግስታት ጋር ለመወዳጀት ይሞክራሉ፣ ህዝባቸውን በውሸት ምርጫ በማታለል ከሲቪሉ የተመረጡ ለመምሰል ይጥራሉ፡፡ ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተሳሳተ መረጃ በመስጠት በመሬት ላይ ከሚታየው ውጭ የሆነ እድገት ያስመዘገቡ ይመስላሉ ወዘተ፡፡ ስለዚህም ህዝቡ በመጀመሪያ የወታደራዊ አገዛዙን አመጣጥ፣ አሁን የቆመባቸውን ምሰሶዎችና፣ ወደፊትም በስልጣን ለመቆየት የሚፈነቅላቸውን ድንጋዮች ማወቅና መደራጀት ተገቢ ነው፡፡
በወታደራዊ አገዛዝ ለ40 ዓመታት እንደተያዝን እየታወቀ አሁንም በዚያው መንገድ ካለንበት ለመውጣት ሲታሰብ እጅግ ያስደንቃል፡፡ ወታደር ስሪቱ አንድ ነው፡፡ መጀመሪያ መደምሰስ፣ ቀጥሎ ማረጋጋት፣ ቀጥሎ ጊዜያዊ መንግስት መመስረት ቀጥሎ… አለቀ፡፡ ወታደራዊ አገዛዝን ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ የሚቻለው ህዝብ በቃኝ ሲል፣ በአንድ ድምፅ አልገዛምሲል ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ህዝቡ ማወቅ አለበት፡፡ ህዝቡ እንዲውቅ ደግሞ የህዝቡን ቀልብ የሳበና ህዝቡ የሚሰማውና የሚከተለው የፖለቲካ ድርጅት አስፈላጊ ነው፡፡በሀገሪቱ ያለው የመጨረሻው ትልቅ ኃይል ህዝቡ ነው፡፡ የፖለቲካ ድርጅት ህዝቡ እንደሚሰማው እርግጠኛ ከሆነ በሰላማዊ መንገድ አገዛዙን ሊያንበረክከው ይችላል፡፡ የአገዛዙ የመጨረሻ ጉልበት ወታደሩ ነው፡፡ ወታደሩን ዱላ በማድረግ ህዝቡን ማስፈራራት፣ ማሰር፣ መግደል የመጨረሻ አማራጭ ይሆናል፡፡ የፖለቲካ ድርጅቱ እያንዳንዱ ተራ ወታደር ከህዝቡ የወጣ እንዲሆነ በመገንዘብ ለእያንዳንዱ በተለያዩ ቦታ ለተሰማራው ወታደር ቅርብ እንደሆነ በመገንዘብ እያንዳንዱ በተለያዩ ቦታ ለተሰማራው ወታደር የቅርብ ዘመዴ ወይም ቤተሰቤ ከሚለውና መልዕክት/ደብዳቤ እንዲደርሰው ያደርጋል፡፡

በዚህ አይነት አንድ ወታደር ቢያንስ ከአምስት ሰዎች ከእኛ ጋር ቁም፤ ከወገንህ ጎን ቁም፤ የአምባገነን ዱላ አትሁን፣ ለሀገርህ እንጂ ለአገዛዙ አሽከር አትሁን የሚል ደብዳቤ ያደርሰዋል፤ የእነዚህን አይነት የሰላማዊ ትግል ስልቶች የህዝቡን የሞራል ልዕልና ከማሳደጋቸውም በተጨማሪ ለወታደራዊ አገዛዙ ፍፁም በማያዳግም ሁኔታ ሽባ የሚያደርጉና በአጭር ጊዜ ነፃነትን የሚያጎናፅፉ ናቸው፡፡ በሀገራችን የሰላማዊ ትግል ብዙ ያልተለመደና በህዝቡ ልብ ያልነበረ በመሆኑ ለ40 ዓመታት የተጫነብንን የብረት አገዛዝ ለመገርሰስ ሌላ ብረት በማንሳት መሞከር ወደሌላ አዙሪት እንደሚከተንም አብሮ መታሰብ ያለበት ሀቅ ነው፡፡ ሰላማዊና ህዝባዊ እንቢተኝነቱ የተሳካና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲያመጣ የፖለቲካ ድርጅትና የብዙኃን መገናኛዎች ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡ ጋሽ መስፍን (ፕ/ር መስፍን) እንደገለፁት የፖለቲካ ድርጅት ያስባል፣ ያቅዳል፣ ይወስናል፣ የብዙኃን መገናኛዎች ውሳኔውን ያስተላልፋሉ/ያሰራጫሉ፤ የትግሉ ዋና ኃይል የሆነው ህዝቡ ይፈፅማል/ይተገብራል፡፡ በዚህ አይነት የምንተገብራቸው፣ የ40 ዓመታት የጭቆና ቀንበር አሽንቀጥረን ለመጣል የሚያስችሉን 200 የሚደርሱ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው የሰላማዊ ትግል ስልቶች መኖራቸውንም ልብ ይሏል፡፡

ቸር ይግጠመን!

የመሬት ወረራን በመቃወሜ የተፈፀመብኝ በደል –አበበ ሆንጃ (ከሰበታ)

$
0
0

ነዋሪነቴ በሰበታ ከተማ አስተዳደር ወለቴ 03 ቀበሌ ጎጥ አራት ነው፡፡ የጎጥ ሰብሳቢ ሆኜ ለሁለት ዓመት ሰርቻለሁ፡፡ የቀበሌው የምክር ቤት አባል እና የኦህዴድ ኢህአዴግ አባል ሆኜ አገልግያለሁ፡፡ ድርጅታዊ እና ማንኛውንም ከላይ የሚወርደውን የመንግሥት መመሪያና ደንብ በህገ መንግሥቱ መሰረት
እንደ ዝቅተኛ አመራር ከድጋፍ ሰጪ አመራሮች በሚሰጠኝ መመሪያ እና ደንብ መሠረት በመፈጸም እና በማስፈፀም ሰርቻለሁ፡፡ የህዝብን ጥቅም ለማስከበር ለአካባቢ ፀጥታ፣ ልማት እና የህዝብን አደረጃጀት በቀበሌው ውስጥ ከየትኛውም የጎጥ አመራሮች በበለጠ ስሰራ ቆይቻለሁ፡፡ በ23/07/06 ዓ.ም ለቀበሌው የፀጥታ ዘርፍ በጎጡ ውስጥ ባለው ከፍታ ቦታም መሬት እየተወረረ ነው በማለት ሪፖርት ባደርግም የሚሰማኝ አላገኘሁም፡፡ የሚሰማኝ በማጣቴ መሬት እየወረሩ የነበሩትን ‹‹እየተሰራ ያለውን አቁሙ!›› ስላቸው ‹‹አንተ ምንድነህ? ከአንተ የበላይ የሚገኙት ባለስልጣናት ናቸው ያዘዙን!›› በማለት ስራቸውን ቀጠሉበት፡፡
addis-ababa-realethiopia-141
በማግስቱ ዓርብ ቀን 25/07/06 ዓ.ም ጧት 2፡00 ሰዓት አካባቢ ለቀበሌ 03 ሊቀመንበር ደውዬ ስለሁኔታው አስታውቄያለሁ፡፡ ሊቀመንበሩም ለደንብ አስከባሪዎች ደውሉላቸው በማለት መልስ ሰጥተውናል፡፡ ይህም በእንዲህ እንዳለ አንድ ምንም የሥራ ዓይነት የሌለው ደላላና የግንባታ ፈቃድ ሌላቸው የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት በመቸብቸብ ሀብት ያካበተ ግለሰብ ረቡዕ ማታ የደንብ አስከባሪዎች እየጠራ ገንዘብ ሲያፍስ እንደዋለ በዓይኔ አይቻለሁ፡፡ ይህ በሆነበት ማግሥት እርስ በእርሳቸው ጀርባ በመግጠም አራቱ ቤቶች ወደ ሰሜን፣ አራቱ ቶች ደግሞ ወደ ደቡብ፣ አራቱ ተዋቅረው አልቀው ቆርቆሮ ሊመቱ ሲል፣ አራቱ ደግሞ ገና ጉድጓድ ተቆፍረው እያሉ ተደረሰባቸው፡፡ ዓርብ ቀን በ25/07/06 ዓ.ም ከሰበታ ከተማ አስተዳደር የቀበሌያችን ደጋፊ ሰው አመራር የሆነውን ግለሰብ ደውዬ በግምቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በህገ ወጥ መንገድ የተሰሩት ቤቶች አስፈርሻለሁ፡፡

ይህንን የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት ከመሬት ወራሪዎች እጅ አስፈርሼ ስላስመለጥኩ የጥቅሙ ተካፋይ የቦታዎቹ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ እና ምንም ዓይነት የግንባታ ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦችና ባለስልጣናት ሥልጣናቸወን ተጠቅመው በደል አድርሰውብኛል፡፡ የመሬት ወረራ ያደረጉ ግለሰቦች በእኔ ላይ ተደራጅተው በደል እያደረሱብኝ ይገኛሉ፡፡ ዐቃቤ ሕግ፣ ፖሊስ እና አስተዳደር እና ፀጥታ ከፍተኛ አድማ፣ ተፅዕኖ፣ ማዕቀብ እና በኑሮዬ ላይ ችግር በመፍጠር ከቤቴ እንድወጣ አድርገውኛል፡፡ አሁን ተባባሪ ሆኛለሁ፡፡ ህገ ወጥ ቤትን በማስፈረሴና የመሬት መቀራመቱን ለማስቆም በጣርኩ በ8/8/06 ዓ.ም ስምንት ኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት እንዲሁም 11 አባላት የያዘ የከተማዋ ፖሊሶችን በመያዝ እንዲሁም 10 የሚደርሱትን የቀበሌ 03 ደንብ አስከባሪዎችን ግደሉት ተብለው መኖሪያ ቤቴን ከበው ውለዋል፡፡ እነዚህ አካላት የታዘዙት ከከተማው የፖሊስ አዛዥ ሲሆን በእኔ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ምክንያታዊ ባለመሆኑ ‹‹ለምን እንገድለዋለን?›› ብለው ከአዛዡ ጋር የተከራከሩ የፖሊስ አባላት እንዳሉም ሰምቻለሁ፡፡ ባለቤቴ ‹‹ባልሽን አምጭ!›› ተብላ ያለአግባብ የዋስትና መብትዋን በመንፈግ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታስራ ትገኛለች፡፡ ‹‹የመንግስት ያለህ›› በማለት ለህዝብ እና ለሀገር ታማኝ ሆኜ መሥራቴ፣ ከኪራይ ሰብሳቢዎች ጋር ለመተባበር ህገ-ወጥ ግንባታዎችን ማስፈረስ፣ አጥፉት፣ ግደሉት ያስብላል ወይ?

የአስተዳደር ፀጥታ ኃይሉ በሙሉ በእኔ ላይ ከፍተኛ አድማ፣ ተፅዕኖ፣ በመፍጠር ሊያጠፉኝ ተነስተዋል፡፡ ዛሬ ባለቤቴ ከመንግሥት ስራ ተፈናቅላ፣ እኔም እንዳይገሉኝ ሸሽቼ እገኛለሁ፡፡ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ አራት ልጆች ያሉኝ ሲሆን ሁለቱ ልጆቼ የወለድኳቸውና ሌሎች ወላጅ አልባዎች በመሆናቸው የማሳድጋቸው ልጆቼ ዛሬ ለጎዳና አዳሪነት ሊዳረጉ ስለሆነ ለሚመለከተው ሁሉ ከጎኔ እንዲሰለፉ የድረሱልኝ ጥሪዬን አቀርባለሁኝ፡፡

እልህ ያረገዘው –ያለወለደው። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 13.06.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

2005

ከዬት መጀመር እንዳለብኝ ሳላውቅ እንሆ ጀመርኩት። ለሁለተኛ ጊዜ እርእስ ሰጥቼ ለመጻፍ ተሰናደሁ። ግን ይቻለኝ ይሆን? አላውቀውም። ጉዴ ይታይ።

በጓጉሎ ቀናት መታሸት – እንደ ተልባ። በወለምታ በወላላቁ ፍላጎቶች መሾክሾክ – እንደ አጃ። ባለተደላደለ አለሎ መዳጥ – እንደ ጥጥ። በላተገራ መቀንጠቢያ መነን – እንደ ባዘቶ። ለቅሞ ማፍስስ አፍሶ መልቀም። እልህ ያረገዘው ግን ያልወለደው ትዕይንት የእኛ ሃብታችን መሆኑ። እም!

„ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“ „ኢትዮጵያ“  በምላስ መጋዘን ስትደገም – ስተሰለስ። ስትሞሸር – ዘውድ ስትጭን። ስትሽሞነሞን መንበር ላይ ከፍ ብላ ስትታይ ፍላጎት- ምኞት ህልም። መመኘት መልካም። ደስ ይላል። ይህን ቀን  ምኞት ማግኘት የሚቻለው ግን ማሸነፍ እራስን መርታት ሲቻል ብቻ ነው። ለማሸነፍ እልህን አግብቶ እልህን ማርገዝ። ማርገዙ ብቻውን ደግሞ ሸክም ነው። እልህ ያረገዘውን መገላገል ነው ብልሃቱ። በስተቀር ብልሃት የሌለው ቅላት።

ሰለ ወያኔ አስከፊነት ቀን እራሱ ከአመት አስከ አመት ታዳሚ ነውና ይናገራል;። ነገም ይናገራል ቢሄድም ተከታዩ ነገ መምጣቱን ስለሚያውቅ። ደንበሩም ወሰኑም ይናገራል – በቁሙ ታርዷልና። ዱሩ ጫካው ይናገራል – እርቃኑን ነውና። ካቴናው ይናጋራል ከእልፍ ጋር አብሮነቱ አና ብሏልና። ባሩዱም ይናገራል ሰፊ የሥራ መስክ ተክፍቶለታልና። መገፋቱም ይናገራል ከዳር እስከ ደንበር ተካልሏልና። ራህቡ ይናገራል ሁሉም ዓይነት ራህብ ድንኳን ጥለው ሃዘን ላይ ቁጭ ብለዋልና። መጠቃቱም ይናገራል ማህጸን ተቀጥቅጧል – አብራክም ተመትሯልና። መዋረዱም ይናገራል ክብር ተጥሷልና። ታሪክም ይናገራል – ምድማዱ ጠፍቷልና። እንዲያውም ብራና ላይ ያሉት ባህርማዶ የተሻገሩት ሳይቀሩ ሳንከሰል ድረሱልን እያሉ መልእክት እዬላኩ ነው።

ማንነታቸውን የተገፈፉት ትውፊት ገብ ቦታውች ትናንሽ መንዶሮች ሳይቀሩ ስማቸውን ተልጧል፤ እነሱም እራሳቸው አቤት ባዮች ናቸው ለሰማዩ ዳኛ። ቋንቋ የለም ጠፍቷል። ቋንቋው ጎሳ ሆኗል። ቅርሱ ተጥሷል ስለሆነም ይጮኃል ሰሚ ቢያገኝ። ይህ ሁሉ ሆኖ ግን እልሁ መጋኛ መሆን አልቻለም። እልሁ በሽታ መሆን አልቻለም። እልሁ በሽታ ከሆነ ለመዳን ትታገላለህ። ለመዳን የምትታገለው በሃኪም የተሰጠህን መዳህኒት ሳታቅማማ ተከታትለህ ከወሰድከው ብቻ ይሆናል። በስተቀር እንዲያውም ሌላ ጠንቅ ይዞ ከች።

ወይ መዳህኒተአለም አባቴ አሁን ደግሞ አንድ ነገር ነሰተኝ – መንፈሴ። ግን እሺ ንገረኝ አልኩት። „ዋናውን መሳሪያ አትዝለይ“ እያለኝ ነው። አስከትሎም እንዲህ አለኝ። …. „እልሁ እራሱ ከቦታው ስለመኖሩ አረጋግጪ“ እለኝ። እውነቱን።“ ግን ግን ጥቃቱን እንደ ክኒኗ ዋጥ ሰልቀጥ ሲደርግ የጤና ነውን? ይህም ሌላው ጉዳይ ነው። አፋቸውን ሞልተው ወያኔ ይሻላል። ይሄኛው በደል በዚህ ይካካሳል ይሉናል የጎጥ ጠበብቶች። ወያኔ „ኦሮምዬ“ የምትባል ክልል ፈጥሮልናል ቢያንስ በቋቋችን እዬተናገርን ነው በማለት በፍቅር ድብን ሲሉ አስተውላለሁ። ተጠቂሚ ነን ባዮች አልገባቸውም እንጂ እራሱ „የኦሮምያ ክልል“ የሚለው ስያሜ እኮ አንባገነን ነው። „የአማራ ክልል“ የሚለውም እንደዚሁ። „የደቡብ ህዝቦች ክልልም“ የሚለውም እንደዚሁ ወዘተ። ስለምን? በስውር ደባ፤ በረቂቅ ቋሳ የዋጣቸው ማንነቶች አሉና። የደፈጠጣቸው ማንነቶች አሉና። በእርህራሄ አልቦሽ የዳጣቸው ማንነቶች አሉና። ወለጋ እኮ የለም ወይንም አዋሳ፤ ወይንም ወሎ። እንደገና በቁጥራቸው አናሳም ቢሆኑ በአንድ ብሄረሰብ ልዩ ሥም በተከለሉ ቦታዎች ቁጥራቸው ያነሱ ኢትዮጵያዊ  ብሄረሰቦች አሉ። አሁን ወሎ አገው፣ ኦሮሞ አለ። ጎንደር ቅማንት ሽናሻ ወይጦ አለ። እኔ እንደማስበው እልሁ የሴራውን ሥር አላገኘውም። እልህ የለሾችም ቢሆኑ በወያኔ ቀለብ የሚሰፈርላቸው ከዘመንተኛው ጋር የመደቡት እራሳቸውን እዬፋቁ ስለመሆኑ አልተገለጠላቸውም። በነጠፈ ህልም ላይ እዬዳከሩ ነው ያሉት። ግርዶሽ ነገር አለባቸው። ወይንም እንደ አባት አደሩ ዓይነ ጥላ ነገር። እራሳቸው እኮ የለም። በሌለ ውስጥነት አለመኖርን እንደ መኖር አድርጎ መቀበል። የመንፈስ ድህነት ወይንም የተፈጥሮ ስጦታን ዝለት …. ዝግተም።

ክልል የሚለው ቃል እራሱ የሚከፍል የሚተረትር የሚሰነጥቅ ዲዲቲ ነው። አዲስ አበባ ክፈለ ከተማ በዚህ ስያሜ መንፈስ እንደ አወጣ ተሸኝሽኗል። ወረራው መጠነ ሰፊ፤ ወረደ ሰፊና ቁመተ ረጅም ነው።

በዚህ ስሌት በቦታ ስያሜ እንኳን ሳይቀር መብቱ የተጠበቀለት „የትግራይ ክልል“ ብቻ ይሆናል። ይህ ባለ ጊዜነትን የሚያውጅ ይመስለኛል። „ትግሬነት’ ቀን አልከዳውም እንደ ‚ኢትዮጵያዊነት“ የዚህ ሁሉ ደባ ፍሰት መነሻ መሠረታችን ያፈልሰዋል። ምድረበዳ ያደርገዋል። ይህን በትክክል ተረድትን ስንመረምረው መዳኛችን አንድ ብቻ ነው። ቀረመቱ ሳይሆን መሠረቱ ይሆናል – የፍላጎታችን አውራ ድልዳል። የመንፈሳችን ዓይነ ልቦና ሆነ እዝነ ህሊና መንሹ መሰረቱን ያውጃል። ፍሬ ዘር፤

ሥር ያለው የጥቃት ዓላማ እልህን ጠንስሶ ስለምን መገላገል አላስቸለንም? ምን አልባት በደሉ ግጥግጥ ሆኖልን? ወይንም ቅልቅል? ለዛውም በግንቦት ኢትዮጵያ ሠርግ አልተለመደም። ካልቸገረ በስተቀር … መሰረቱ መርዝ – ጣሪያው መርዝ -ግድግዳው መርዝ – ማገሩ መርዝ – መግቢያ መውጫ በሩ መርዝ።  በመርዝ ላይ ቁጭ ያለ ሰብእና እልህ ሰውነቱ እንዲፈጥር በማደረግና ባላማደረግ መሃከል ያለው ልዩነት እንደ ሰው መሆን ወይንም ይህን ጸጋና መክሊት ከመተላለፍ ይመነጫል።

ከዚህስ በኋላ ለእንጉልቻ የተፈጠረ ወይንም ቀንናና ሌሊት የእንቅልፍ ክኒኑን ወስዶ ለሽ፤ ወይንም የእልህን ትልሞች መቆጣጠር ተስኖት የዛለ አካል ተሸክሞ መኖር ዕጣው ይሄ ነው፤ እንደ እኔ እንደ ሥርጉተ ይህ አርበኝነትን ቅንቅን እዲበላው በሙሉ ድምጽ መፍቀድ ነው። አርበኝነት የግድ ነፍጥ ማንሳት ብቻ አይደለም። በሸር ላይ በመንፈስ መሸፈት። ልብን ቅርቅር አድርጎ በዳይን ፊት በመንሳት አርበኝነት አንቱ ይሆናል። መንፈስን አሸፍቶ በልብ ውስጥ ጫካን ማደራጀት፤ በተገኘው አጋጣሚ ፍቅርን ነፍጎ በቃህንን እያንቦለቦሉ ሰንጎ ማጉረስ። ለጠላትም ለግል ኢጎም። ልምምጥ ጎንበስ ቀና አያስፈልግም የዚህን ጊዜ እልህ ተፈጥሯል – የተፈጠረውም እልህ ተገላግሏል ማለት ያስቻላል። በስተቀር ኤሉሄ ነው።

እልህ የግል ሃብት ነው። የግል ንብረት ነው። እልህ እራስ ለራስ ችሎ የሚሰጠው ነፃነትም ነው። እልህ የድል መንበርም ነው። እልህ የራዕይ ጉልላትም ነው። በተለይ ተበደልኩ ለሚል ዜጋ እልህ የበሽታው ሁሉ መፈወሻ ነው። እልህ የቋሳ ሃጢያት የፈጠራቸውን ስንክሳሮች ሁሉ ይፍታህ ይላል እንደ አባቱ እንደ ጴጥሮስ። ስለሆነም የጡሑፉ ወጋግራ በሽታውን ለመፈወስ መጀመሪያ ከራሱ ይነሳ ነው አብዩ ዓምድ። በዙሪያው ያለውን ይቃኝ። እልሁን የሚመሳሳሉትን ደስ ብሎት ማቄን ጨርቄን ሳይል ይቀላቀል። ሲቀላቀል ግን ለማጥመድ ወይንም ለመጠመድ መሆን አይኖርበትም። እልሁን ለማድመጥ የእልህ ዘብ አደር ለመሆን እንጂ።

ይህም ማለት እልሁን ለመገላገል የእልሁን ሥነ ምግባር መፈጸም ግድ ስለሚለው፤ ቅንነነት – እውነት – ንጹህ ልብ – ግልጽነት – ቀጥተኝነት – ታማኝነት – አክብሮተ – ዕሴት – ውል – ለኪዳን ማደር – መሆን – ፈርኃ እግዚአብሄር –  ሁሉንም የመንፈስ ሃብቶች ሳይለግሙ ለማህበርተኞች ፈቅዶና ወዶ ግዙት – ንዱት በማለት መፍቀድ ይኖርበታል። ተጻራሪ ዕኩይነትን በመጸዬፍ መገፍተር —-

ይህን ጊዜ በደል ይረታል። መበደል ያሸንፋል። ግን ችለናል? ወይንስ ገና ታቱ ነው? የተሻለ ወያኔ ነው የሚሉ ጹሑፎችን አነባለሁ እንዲሁም አንደበቶችን አደምጥ ነበር አሁንስ? ቀንበጥ ከትምህርት ቤት ወጥቶ ሲቀር ይመቻልን? የጫጉላ ሽርሽር ነውን? እልሁ የት ላይ ይቀመጥ? የት ነው ያለው ባላንባራስ እልህ? ዳጥ። በኢትዮጵያዊነት ማእቀፍ ግን ጎጤን። „ስንት ጊዜ በንግግሩ ላይ „ኢትዮጵያን“ አነሳ“ ይህ ለአንድ በጎጡ ለሚያምን ታላቅ የተከበረ ሰው እንደ ብርቅና ድንቅ ይነገርለታል። ለእኔ ግን ስለጎጥ የሚያስብ  – የሚደክምም መንፈስ „ኢትዮጵያዊነትን“ ባያነሳ – ሳይፈጠር ቢቀርም ይሻለዋል። ውሃ መልኩ ምን ይመስላል?!!!! የእኔ ክብሮች? መልስ –  ውሃማ። ኢትዮጵያዊነትም እንደዛ ነው።

 

ክወና – ትናንትና 12.06.2014 ብራዚል ላይ አለምአቀፍ ድርጊት ተከወነ – ከተለመደው ውጪ። ነፃነቱን የተቀማ ህዝብ ባላበት ቦታ አንተ ባላህ ጉልበትና አቅም እንኳን አንደበትህን ማዘዝ እንደሚሳነህ ሃቅ እራሱን አስከበረ – አስረከበ። ገድል ነው። የፊፋው ፕሬዜዳንት ሆነ የሀገሪቱ መሪ ወሮ እዬቻሉ ግን ልሳናቸውን ማን ዘጋው? ነፃነት የሚገዛ ሸቀጥ አይደለም። ወይንም የምተሸጠው ሸቀጥ ወይንም በችርቻሮ የመትሸቅጠው – የምትሸቅጥበትም።

የእግር ኳስ እስፖርት አፍቃሪን በምልአት በመሩበት በድንቆቹ በነፔሌ በሀገረ – በብራዚል አንደበት ተከርችሞ የአሻንጉሊት ትርዒት ብቻ ቀረበ። ዳመናማ ነበር። ይህንን ዘመናችን ያበረከተልንን ትልቅ አጋጣሚ ሳናከባልለው ወይንም በኢጎ መርዝ ሳንበክለው ከራሳችን ጀመርን ይህን እናንብበው  - እንተርጉመው – እናመሳጠረው። ጩኸቱ ሌላው ላይ ሲሆን ወይንስ ከእኔም ላይ ባላው!?! ….. እንለካው።

የሬግኑ የ2012ቱ የክብር ጉባኤ አባልና የመንበር ተናጋሪ አፈሩ ይከብዳቸውና ሄሮድስ መለስ ዜናው ነበሩ። ግን ከታች የተቀመጠው ከብላቴናው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ንግግር በኋላ ያ – ክብር ልብን ነፍቶ መንቀሳቀስ፤ ያ ካለቦታ ተኮፍሱ እዩዩኝ ማለት-  ኩምሽሽ ብሎ ተኮመታተረ። የሚገርመው መሰንበት አልችል በሎ ጠንዝሎ ትንሽ ቀናት በደመንፈስ ዕብኑን ሞካከረ። ይህም አልሆነም ሰኔልና ቹቻን አዳብሉኝ ብሎ አለፈ …. ። የዚህ ዓመት የአቤዋ ድምጹም የዓለሙን መሪ ፕ/ ባራክ ኦባማን የቀጣይ የመሪነት ክብርና ዝና በምን ይዋጀዋል? መጠበቅ።

ይህ ሁሉም ሰው ባለው መድረክ፤ ባለው ዕድል፤ በእጁ በገባ ሥልጣን፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሊያስተውለው ዬሚገባ ዘመን ያፈራው ትልቅ አመክኖዊ – ክስታታዊ – ተቋም ነው። ለዛውም የዶግማ። በእጅህ ያለውን ነገር የምታከብረው ስታጠው መሆን አይገባውም። ይልቁንም ልብህ ከአንተ ጋር መሆኑን ካረጋጋጥክ ከማጣትህ በፊት ለሥነ ምግባሩ ፈቅደህ – ወደህ – ደስ ብሎህም መገዛት አለበህ። አፈና …. ለፈርዖን ለሄሮድስ – ለጋዳፊ – ለሙጋቤ – ለናዚ – ለሂትለር ለማንም አይሆንም ….። ማበጥ ——- መተርተርን – መፈንዳትን ያልማል። ጌጦቼ የእኔ ውቦች ይሄው ነው ዛሬ እኔና ብራናዬ የምናወጋችሁ።

መልካም የልደት በዓልን በፍቅር – በአክብሮት – በትህትና – ተመኘሁ ነፃነትን ለዛውም ለሴት ሳልጠብቀው ግን በተባረከች ቀን አገናኝቶ ላጎናጸፈኝ ለዘሃበሻ ድህረ ገጽ ዝግጅት ክፍል እና ታዳሚዎች።  እንኳን ለ6ኛ ዓመት ምስረታ ልደታችሁ አደረሳችሁ – አደረሰን። አዝመራማ አመትም ተመኙሁ  ከልብ – ለልቤዎቹ።

በተረፈ Radio Tsegaye Aktuell Sendungn ወይንምwww.tsegaye.ethio.info ጎራእያላችሁጊዜስታገኙበድምጽደግሞእንገናኝናፍቆትንእናወጋጋ።ኑሩልን – የኔዎቹ።

 

እልህን የምወደው የቆሰለውን ውስጤን ለመፈወስ አቅም እንዲኖራው አድርጌ መምራቴን ሳረጋግጥ ብቻ ነው!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ለመኾን እንደማይችሉ ያምናሉ

$
0
0

በአብዮቱ መባቻ ዓመታት ከደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት›› ጋራም በቁርኝት ሠርተዋል
ከደርግ ጋራ አብሮ በመሥራትና ደርግን በማውገዝ መካከል የሚታዩት የፓትርያርኩ የአቋም ጽንፎች ፀረ አማሳኝ መስሎ የአማሳኞች ከለላ ኾኖ የመገኘት ፍፃሜ ነው!!
(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፵፱፤ ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.)

ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያኒቱና መሪዎቿ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ሊኾኑ እንደማይችሉና መንግሥት በቤተ ክርስቲያኒቷ የአስተዳደር ጉዳይ ጣልቃ ቢገባ ሕገ መንግሥቱን እንደማይፃረር አቋም ይዘው መከራከራቸው ተገለጸ፡፡

የፓትርያርኩ አቋም የተንጸባረቀው፣ ከአንድ ሳምንት በፊት በተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶሱ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ለቀናት ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደነበር የስብሰባው የፋክት ምንጮች ተናግረዋል፡፡
abune matias
የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ ለካህናት ስለተከለከሉ ተግባራት አስመልክቶ፣ ጳጳሳትና በቤተ ክርስቲያኒቱ በሓላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ ካህናት ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ አባልነት ወይም አራማጅነት ነፃ መኾን እንደሚገባቸው ይደነግጋል፡፡

ስለ አንቀጹ አግባብነትና አስፈላጊነት በተሰጠ ማብራሪያ፣ ‹‹እስከመቼ ድረስ አንድ ላይ ተጣብቀን እንኖራለን፤ ሕገ መንግሥቱ እንደሚለው ነፃ መኾን አለብን፤ ነፃ መኾናችንን ለማረጋገጥ ጳጳሳትና በሓላፊነት ደረጃ ያሉ ካህናት ከፖሊቲካ እንቅስቃሴ አባልነትና አራማጅነት ነፃ እንዲኾኑ መከልከል አለብን፤›› መባሉ ተዘግቧል፡፡

ፓትርያርኩ አንቀጹን በመቃወም ‹‹ከመሐንዲስ፣ ከዶክተር ነፃ ልንኾን እንደማንችለው ከመንግሥት ጥገኝነትም ነፃ ልንኾን አንችልም፤›› የሚል አስተያየት መስጠታቸው ተዘግቧል፡፡ አያይዘውም በሕገ መንግሥቱ የተደነገገው መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ እንጂ በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጣልቃ ቢገባ ድንጋጌውን እንደማይፃረር የሚያሰማ አቋም አራምደዋል ተብሏል፡፡

አቡነ ማትያስ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ የመጨረሻ ወሳኝና ላዕላይ የሥልጣን መዋቅር ከኾነው ከቅ/ሲኖዶሱና አባላቱ ይልቅ ከመንግሥት ጋራ አላቸው የሚባለው ያልተገራና ያልተገደበ ግንኙነት የሊቃነ ጳጳሳቱን ቁጣ ቀስቅሷል በተባለበት ኹኔታ ይህን አቋም ማራመዳቸው እያነጋገረ እንደሚገኝ ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Patriarch Abune Mathias formerly known as Aba Teklemariam with Dergue’s Renewal committee membersሌሎች የፋክት ምንጮች በበኩላቸው፣ ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጋራ አላቸው በሚል በተቺዎቻቸው የሚጠቀሰው ልክ ያልኾነና ያልተገራ ግንኙነት ጵጵስና ከመሾማቸው አስቀድሞ የሦስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ በነበሩባቸው የአብዮቱ መባቻ ዓመታትም፣ የወቅቱን የሥርዓት ለውጥ በቤተ ክህነቱ ለማሥረጽና ተቃዋሚዎች (በተለይ ኢዲዩ) የሕዝብ ተቀባይነት እንዳያገኙ ወደ ስሜን ኢትዮጵያ ተጉዘው የፈጸሙትን ተግባር በአስረጅነት ይጠቅሳሉ፡፡*

›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››
*YeTahisas Girgir ena Mezezuበግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ከ፲፱፻፵፰ – ፶፫ ዓ.ም. በአገር ግዛት ሚኒስቴር የሕዝብ ፀጥታ ጥበቃ መምሪያ ሓላፊ ሌተና ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ ልዩ ረዳት የነበሩት አቶ ብርሃኑ አስረስ ‹‹ማን ይናገር የነበረ… የታኅሣሥ ግርግርና መዘዙ›› በሚል ርእስ በቅርቡ ለኅትመት ባበቁት መጽሐፍ፣ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የፊት ስማቸው አባ ኃይለ ማርያም እንደነበር የጠቀሱት በስሕተት ይመስላል፡፡

በ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. በወልቃይት፣ በፀገዴና በአርማጭሆ ቆላ ደርግን በመቃወም የተንቀሳቀሰውን የኢዲዩ ኃይል ለማቆምና ደገኛው ከቆለኛው ጋራ እንዳይተባበር ለመምከር በደርግ ተመልምለው ወደ በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ካቀኑት መካከል በወቅቱ አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት አኹን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አንዱ የቡድኑ አባል እንደነበሩ የመጽሐፉ አዘጋጅ ገልጸዋል፡፡

አባ ተክለ ማርያም በወቅቱ ‹‹የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አቡነ ቀሲስ፣ በኋላ አቡነ ማትያስ ናቸው›› የሚሉን ጸሐፊው፣ ከአባ ተክለ ማርያም ጋራ አለቃ ቀለመ ወርቅ(የቤተ ክህነት ደብተራ ይሏቸዋል) በቡድኑ ውስጥ የተካተቱት ‹‹ለሃይማኖት ነክ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደነበር›› አስፍረዋል፡፡

የሕዝብ ተሰሚነት አላቸው በሚል ከጠቅላይ ግዛቱ ሰባት አውራጃዎችና የጎንደርን ከተማ በመወከል ከተመረጡት መካከል በወቅቱ የደብረ ታቦር አውራጃ ተወካይ አቶ(በኋላ ሊቀ ማእምራንና ደርግ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደር በኅብተረሰብ ተሳትፎ ላይ መመሥረት በሚል ሐዋርያዊ አገልግሎቷን በሶሻሊስታዊ መንፈስ ለመቃኘት ያቋቋመው ጊዜያዊ ጉባኤ ጸሐፊ) አበባው ይግዛው አንዱ እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡

Patriarch Abune Mathias with renewal committeesከዘመቻው ጉዳይ ጋራ በተያያዘ ስብሰባ የተደረገው በጎንደርና ደብረ ታቦር ላይ ብቻ እንደነበር የሚገልጹት አቶ ብርሃኑ፣ ‹‹ኢዲዩ እየበረታ መጥቷል፤ እኛም በሰላም ተነጋግረን ደገኛውንና ቆለኛውን እንዳይተባበር ማድረግ አልቻልንም፤›› በማለት ዘመቻው ስኬታማ እንዳልነበር ጠቅሰዋል፤ አያይዘውም ‹‹ኹለቱ የሃይማኖት ሰዎች የተመለሱት አንድም አስተያየት ወይም ማብራሪያ ሳይሰጡ ነበር፤›› ብለዋል፡፡ (ገጽ 400 – 421)
***************************************************

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር ዶ/ር ውዱ ጣፈጠ ካሱ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ በሠሩት ጥናት፣ የሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ቀሲስ የነበሩት አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት (በኋላ ብፁዕ አቡነ ማትያስ) ደርግ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የለውጥ ጊዜያዊ ጉባኤ›› (the EOC provisional council or Renewal Council) በሚል ያቋቋመው ጊዜያዊ ጉባኤ አባል የነበሩ ባይኾኑም የምክር ቤቱ ሊቀ መንበር ከነበሩት ዶ/ር ክነፈ ርግብ ዘለቀ ጋራ በጥብቅ ቁርኝት መሥራታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጊዜያዊ ጉባኤው በነሐሴ ወር ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ምክትል ሊቀ መንበር ኮሎኔል አጥናፉ አባተ ቀጥተኛ መመሪያና ቁጥጥር የተቋቋመ ነበር፡፡ ከኹለተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ጋራ ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው ጊዜያዊ ጉባኤው፣ ቅዱስነታቸው በአራት መዋቅሮች(የፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት፣ የስብከተ ወንጌልና ማስታወቂያ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ፣ የውጭ ጉዳይና ልማት ኮሚሽን) የቤተ ክህነቱን አስተዳደር ለማጠናከር ያቋቋሙትን ኮሚቴ በመጋፋት ለውጥና መሻሻል ያመጣል ያለውን የራሱን ባለአምስት ኮሚቴዎች (የሕግና አስተዳደር፣ የስብከተ ወንጌልና ትምህርት፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ የታሪክና ባህል ጉዳዮች እና የአቤቱታ ሰሚ) መዋቅር ዘርግቷል፡፡

ከጊዜያዊ ጉባኤው ጋራ ያልተግባቡትና የማሻሻያ መዋቅሩን ያልተቀበሉት ቅዱስነታቸው በወርኃ የካቲት ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. ጊዜያዊ ጉባኤው ለደርጉ ባቀረበው የክሥ ሪፖርት ‹‹ሲጠበቅ የቆየ ፍርድ›› በሚል ዐዋጅ ከመንበረ ፕትርክናው ተገፉ፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱና በጊዜያዊ ጉባኤው መካከል ሽኩቻ የተካሔደበት ቀጣዩ የፕትርክና ምርጫ በጊዜያዊ ጉባኤው በኩል ታጭተው የቀረቡትን ሐዋርያዊውን ባሕታዊ አባ መላኩ ወልደ ሚካኤል – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በመንበሩ ሠየመ፡፡

ጊዜያዊ ጉባኤው በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫና ሹመት፣ በአህጉረ ስብከት ዝውውር እንዲሁም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሹመት በቀጥታ ይቆጣጠር የነበረ ከመኾኑም በላይ ከደርጉ ጋራ እጅና ጓንት ኾነው በአባልነት የሠሩ አባላቱ በዋና ሥራ አስኪያጅነትም ተቀምጠው ነበር፡፡ ጵጵስና እስኪሾሙ ድረስ የቅዱስነታቸው አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ የነበሩት አባ ተክለ ማርያም ዓሥራት ከጊዜያዊ የሃይማኖት ጉባኤው ጋራ በጥብቅ ቁርኝት መሥራት ብቻ ሳይኾን ወደ ስሜን ኢትዮጵያ ተነቃንቀው ስለ አብዮቱ ካስተማሩና የሥርዓት ለውጡን የሚቃወሙ እንደ ኢዲዩ ያሉ ኃይሎች የሕዝብ ተቀባይነት እንዳያገኙ ከቀሰቀሱ የደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት› አንዱ ነበሩ፡፡

“Before his appointment as bishop, Matyas had been Abune Qasis of Patriarch Abune Takla-Haymanot. Though not a member of the provisional council, he had closely worked with Dr. Kenafe-Regeb Zallaqa, chairman of the council, and was mobilized to northern Ethiopia with members of the council to teach and explain about the revolution.”(WUDU TAFETE KASSU,PhD; THE ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH,THE ETHIOPIAN STATE AND THE ALEXANDRIAN SEE: INDIGENIZING THE EPISCOPACY AND FORGING NATIONAL IDENTITY,1926 – 1921; p.366)

ማን ይንገርልን – ማን ይመስክርልን – (ከጸጋዬ ገብረመድህን አረአያ)

$
0
0

እንደ ልጄ የምቆጥረውና ከበኩር ልጄ ከዩሐንስ ጋር ያደገው ሳምሶን በሕክምና ኮሌጅ ይማር በነበረበት ዘመን በምሽቱ ሰዓት ላይ የ‹‹ፈገግታ ጊዜ›› በምንለው ግማሽ ሰዓት ያጫውተን ነበር፡፡ አዎን ሕይወት ውጥርጥር ባለበትና ጭንቀት ከቀበሌ ከሚወረወር ቀስት፣ ጭንቀት ከየካድሬውና ከየፖለቲካው ኅቡዕ ድርጅት ከሚወረወር ሌላ ቀስት፣ ጭንቀት፣ ከመስሪያ ቤት ጭንቀት፣ ከበላይ አካል ጭንቀት፣ ከበታች አካል ጭንቀት፣ ጭንቀት —- አንድ የድሮ ማስታወቂያ ሚኒስትር እንዳሉት ከላይ ከመሳፍንቱና ከመኳንንቱ በሚለቀቅብህ እሳት፣ ከታች ከሕዝቡና ከሠራተኛው ከሚነድድብህ እሳት የገና ዳቦ ትሆናለህ፡፡ ስለዚህ ‹‹በታይም አውት›› (ፋታ ልበለው) መልክ ከሳሚዬ ጋር የማደርገው የግማሽ ሰዓት ውይይት (ጨዋታ) ለእኔ “ማሳጅ” ነበር፡፡ መታሻ!
ethiopian flag
እንደ ወትሮው የዛሬው ወጋችን በክፍል ውስጥ ስለነበረው አጋጣሚ ነበር፡፡ በዚያው ዕለት በሕክምናው ኮሌጁ የመጀመሪያው ሰዓታት (ሦስት) አስተማሪው ዶክተር አሥራት ወልደየስ ነበሩ፡፡ “ዛሬ የማስተምራችሁ ስለ ጦር ሜዳ አነስተኛ የቀድዶ ሕክምና ነው” ይላሉ፡፡ አከታትለውም የጦር ሜዳውን “ሰገሌ እንበለው” ይላሉ፡፡ ይቀጥላሉ፡፡ ተፋላሚዎች በወሎው ጦር በኩል “ንጉሥ ሚካኤል” —- ይሉና ቆም ብለው ይመለከቱ ጀመር፡፡ እንዳጋጣሚ ከፊት ለፊት የተቀመጠውን አንዱን ተማሪ “ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስን ታውቃቸዋለህ? ብለው ይጠይቁታል፡፡ “አንተዋወቅም” ይላል፡፡ ሁለተኛው ጊዜ ሳይፈጅ ወደ መርካቶ ሲኬድ መግቢያው ላይ ድልድይ ያላቸው ሰውዬ ናቸው” ይላቸዋል፡፡ ሦስተኛው በሙሉ የአዋቂነት ኩሩ ስሜት ‹‹የአጤ ኃይለሥላሴ ቅድመ አያት ናቸው፡፡ ከአያቴ ጋር በጣም ይተዋወቁ ነበር›› አለ፡፡ ሌላው የፕሮፌሰር አሥራትን ከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት የበለጠ ለማጋጋል ፈለገና ይልቁንም እሳቸው በዛሬው ፕሮግራማቸው ስለጦር ሜዳ ሕክምና ለማስተማር የተዘጋጁ መሆናቸውን ስለተናገሩ “ኢትዮጵያ ከእንግሊዞች ጋር በተዋጋች ጊዜ የጦር መሪ የነበሩት አጭር፣ ፉንጋ ሰው ነበሩ፡፡ አጤ ኃይለ ሥላሴ ሠላሳ ዓመታት አሠሩአቸው” ይላል፡፡ ፕሮፌሰሩ ትንሽ ይደንቃቸውና “ኢትዮጵያ ከእንግሊዞች ጋር የተዋጋችው ትራፋልጋር ላይ ነበር ወይስ ወተርሉ ላይ ነበር?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ አራዳው ተማሪ “የለም ሰገሌና አንኮበር ላይ ነበር” ይላቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ እንግሊዞች በወተርሉና በትራፋልጋር ላይ ጦርነት የገጠሙት ከፈረንሳዩ መሪ ከናፖሊዮን በናፖርት ጋር ነበር፡፡) ፕሮፌሰሩ ቀልዱንም ሞክረውት ጥርሳቸው ሊላቀቅ አልቻለም፡፡ በጎጃም ቅኔ ቤት የሚወራ ጨዋታ ነበር፡፡ በጎንጅ የሚታወቁ አንድ የቅኔ መምህር ነበሩ ይባላል፡፡ እንደአጋጣሚ ሆኖ ጥርሶቻቸው ሽግናም ነበሩ፡፡ አንድ ቀን አንድ ወዳጃቸው ሰውን ሁሉ በጨዋታው ሲያስቅ ውሎአል፡፡ መምህር ሞገሴ ግን አንድም ጊዜ ፈገግ ሲሉ አልታዩም፡፡ ወደማታ ላይ ሰውየው “አባ ሞገሴ አንድ ደቂቃ እንኳ ሲስቁ አላየሁዎትም›› ይላቸዋል፡፡ ጥርሰ ሽግናሙ መምህርም ‹‹መቼ የምስቅበት ጥርስ ስጠኝና?” አሉ ይባላል፡፡ ለመሆኑስ በዚህ አገር ከማስለቀስ አልፎ የሚያስቅ ነገር ከወዴት መጥቶ! አባ ሞገሴ ጨርሰውታል፡፡ መቼ ለፈገግታ ታደልን፡፡

ሳምሶን (ከብዙ ዓመታት በፊት ጀምሮ ዶክተር) እንዳጫወተኝ ዶክተር አሥራት ወረቀቶታቸውን ሰበሰቡና፣ በጥቁር ሰሌዳው ላይ የጻፉትንም አንዳንድ የህክምና ዓይነቶች ጠራረጉና “በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካሉ ተማሪዎች ጋር አገርን በተመለከተ መነጋገር የሚያስቸግር አይመስለኝም ነበር፡፡ በተለይም ሀብተ ጊዮርጊስን ከማያውቅ የዩኒቨርሰቲ ተማሪ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ?” በማለት ክፍሉን ጥለው ወጡ፡፡ ከዚያ ወደ ቢሮአቸው ሄደው በትካዜ ባሕር ይሰጥማሉ፡፡ ያለፉትን ዘመናት ጦርነቶች፣ የጦር አገዛዦቹን ከነጀብዱዎቻቸው፣ በድል ጊዜ የነበረውን ሽለላና ፉከራ፣ የዘመቻ ባህልና የጦርነት መንፈስ አንብበዋል፤ ሰምተዋል፡፡ ፋሽስት ኢጣልያ አገራችንን በወረረችበት ዘመን የነበረውን ውጣ ውረድ፣ ማን ከማን ጋር እንደቆመ፤ ስለጀግንነትና ስለክህደት ሰምተዋል፡፡ ተከታትለዋል፡፡ ሲናገሩ ኖረዋል፡፡ እያደር አገሪቱን የጀግና ድርቅ እንደመታት፣ የእምነት ድቀት እንደወረደባት ብዙ የሚናገሩና ቁጭታቸውም የማይገታ መሆኑን ሰው ሁሉ የሚያውቅላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ ከክፍል ገብተው “ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስን ታውቃላችሁ አይደል?” ሲሉ የተሰጧቸው (እዚህ ላይ ያልተጠቀሱም አሉ) መልሶች አስደነቁአቸው፡፡ በእንግሊዝ አገር ይማሩ በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን እንደ ብርቅ ሕዝብ፣ እንደ ሰማያዊ ተዋጊ ኋይላት፣ የጥቁር ሕዝብ እንቁና እግዚአብሔር ለራሱ መከበርያ አድርጎ —– የፈጠረው ተደርጎ በብዙዎች ይታይ እንደ ነበር አስታወሱ፡፡ የአድዋው ጀግና መሪ የወቅቱን የአውሮፓ ኃያል መንግሥት ያንኮታኮተበትንና ጥቁሩን ሕዝብ እንዳኮራው ሁሉ ተፈሪ መኮንን ወደ ሥልጣን ሲመጡ ‹‹ይኸ ደግሞ ለእኛ ሁሉ የተወለደልን ነፃ አውጫችን ነው›› ብለው እንደ አዳኝና የአርነታቸው ምልክት አድርገው እንደ ተቀበሉአቸው አሰቡ፡፡ ራስ ተፈሪን እንደ አምላክ እንደሚያዩአቸውም አሰቡ፡፡ አድዋን እንደገና፣ ተድአሊን፣ ጉዳጉዲን በአእምሮአቸው አሰሱ፡፡ አጼ ኃይለሥላሴን የሚያደንቁአቸውን ያህል በእነ በላይ ዘለቀ፣ በእነ አቶ ፈጠነ፣ በአፈንጉሥ ታከለ—– በእነ ልጅ እያሱና በአባታቸው በንጉስ ሚካኤል ሞት የነበራቸው ቅሬታ ትዝ አላቸው፡፡ አጼ ኃይለሥላሴ ይቺን አገር ያስከበሩአት መሪ መሆናቸውን እያሰላሰሉ ደግሞ አወዳደቃቸውን፣ አሟሟታቸውንና አብሮአቸውም የሦስት ሺህ ዓመት የዙፋን አገዛዝ ምዕራፍ መዘጋቱን በአእምሮአቸው አወጡ አወረዱ፡፡ ሳያስቡት እንባ ወርዶአቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ታላቅነትና የሕዝብዋ አንድነት ግዙፍ ታሪክ እየወደቀ ይሆን? ብለውም መጨነቅ ያዙ፡፡

ይህ ትውልድ በዚህ ዓይነት ውጣ ውረድ ውስጥ አላለፈም፡፡ ወይም ያንን ዘመን በታሪክ ቅብብሎሽም አላወቀውም፡፡ በአንድ ወቅት እንደ ገለጡልኝ “ጀግና ስንፈልግ ባጀን” የሚለውን የእኔን የጦቢያ መጣጥፍ ካነበቡ በኋላ በአካል የሚያውቁአቸውን ቀኝ ጌታ ዩፍታሔ ንጉሤን አስታወሱ፡፡ ከዚያ በኋላ ቀኑን ሙሉ ተበጥብጠው ውለዋል፡፡ “ስማ! አሉኝ” አቤት አልሁ፡፡ “የሼክስፒየርን ሐምሌት አንብበሃል” አሉኝ፡፡ አዎን ብዙና ዋነኛ ስንኞቹ አሁንም በአእምሮዬ ውስጥ ቀርተዋል፡፡ በቃሌ ነበር የማንበለብላቸው አልኋቸው፡፡ ያነሱብኝ ሐምሌት ከመቃብር ቆፋሪው ሰውዬ ጋር ያደረገውን ንግግር ነበር፡፡ በቁም የሞቱ፤ ሞተው ያልተቀበሩ፤ ሞተውም አለን የሚሉ፤ አለንም የሚሉ ምውታን! ዶክተሩ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔን ያነሱበት ምክንያት ገብቶኛል፡፡ ዩፍታሔን እንደ ሼክስፒየሩ መስፍን (ልዑል ሐምሌት) በመቃብር ሥፍራ የሚባዝን ፍጡር አድርገው ነበር ያዩአቸው፡፡ አዎን ከሐምሌት የሚለዩት ዩፍታሔ ከሙታን መካከል ሕያዋንን የሚፈልጉ በመሆናቸው ነው፡፡ ዮፍታሔ ጀግና ናፈቃቸውና “ዓይኔን ሰው አማረው” አሉ፡፡ ባበደ ቅኔ

‹‹አጥንቱን ልቁጠረው መቃብር ቆፍሬ
ጎበናን ከጋላ አሉላን ከትግሬ
ስመኝ አድሬአለሁ ትናንትና ዛሬ ——
“ዓይኔን ሰው አማረው” አሉ?

የአገር ናፍቆት፣ የጀግና ረሃብ፣ የታሪክ ምርምር ፣ የእኔነት ፍለጋ አንድ ሕዝብ ከከፍተኛ ብሔራዊ ውድቀት ላይ በሚገኝበት ሰዓት የሚያጋጥም አባዜ ነው፡፡ የታሪክ ክፍተት፣ የእኔነትና የጋራ አገር ሳይታሰብ ከትልቅ እንቆቅልሽ ውስጥ መውደቅ፣ ወደማይታወቅ፣ ጉዞውም ወዳልለየ አቅጣጫ ይወስደዋል፡፡ ይህንን ወቅት ያሰላስሉአል፡፡ በነገራችን ላይ በብዙዎች መጣጥፎቼ ውስጥ ሐምሌትን ሳልጠቃቅስ አልቀረሁም፡፡

በቅን የኢትዮጵያ ልጅነት ከሚታወቁት ዶክተር ጋር የምር ንግግር ነበረኝ፡፡ ባለፈው መጣጥፌ (ጅብ ቲበላህ በልተኸው ተቀደሰ) ላይ ለማመልከት እንደሞከርሁትም በመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት ምክትላቸው ከነበሩት (በኋላ የቅንጅት ሊቀመንበር) ከአቶ ኃይሉ ሻውልም ጋር ስለዚህ አገር የጉዞ አቅጣጫ ቀን ከሌት የምንወያይባቸው ጊዜያት ነበሩ፡፡ ዋናው ጉዳይ አንደኛ የመጣውን አደጋ መመለስ ነው፡፡ ሁለተኛ ኢትዮጵያን በተመለከተ እዚህ ስንደርስ የተቀረጸውን ታሪክ ማቃናት ነው፡፡ ሦስተኛ በየትም አገር በማንኛውም ዘመን ብቅ የሚል ሥነ መንግሥት አለ፡፡ በእኛ እምነት በዚህ ወቅት የመጣብን ሥነ መንግሥት ጤና ጉዳይ አጠያያቂ ከመሆኑ ላይ ነው፡፡ ከሥርዓቱ ጋር ሊግባባ የሚችል ማን ጤነኛ ሰው አለ? ምን እናድርግ? ከዜሮ መነሳት ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡

የትናንቲቱ ኢትዮጵያ የዛሬውና የነገይቱ ኢትዮጵያ መሠረት ናት፡፡ የዛሬ ኢትዮጵያውያንም በትናንቲቱ ኢትዮጵያ መሥራቾችና የመሠረት ድንጋይ አቀባዮች ትከሻ ላይ የቆምን ነን፡፡ ይህን በመካድ አዲስ ታሪክ እንመሰርታለን ለሚሉ አጥፊ ኃይላት ሶማሌዎች አንድ አባባል አላቸው፡፡ “አዲስ ጫማ ከመግዛትህ በፊት አሮጌውን አትጣለው” ይላሉ፡፡ የወደፊቱን ተስፋ ሊያሳጡን የሚፈልጉት የዚህ መንግሥት ባለቤቶች የትናንት ደሆችና የዛሬ ውርስ የሌለው ሕዝብ አድርገው ፈርደውብናል፡፡ የሚያሳዝነው ለዚህ ሁሉ ሴራ የራሳቸው ትረካ፣ አዲስ ታሪክና ድርሰት ይዘው ሲቀርቡ የቅጥፈታቸው ሰለባ አለመታጣቱ ነው፡፡ አንድን ሕዝብ የጋራ ታሪክ አልባ ማድረግ፣ መነሻና መድረሻ የሌለው —— መሠረትና መንደርደሪያ አልባ ማድረግ በቀላል ቋንቋ የሚገለጥ ኃጢአት አይመስለኝም፡፡ በአንድ ሐረግ ለመግለጥም ሁላችንም እየተገረፍን እንደ ከብት ወደ ቄራ እየተወሰድን ነው፡፡ በጉልበት የምንጋተው መርዝ! ከዚህ ቀደም በተጠቀምሁበት ቋንቋ እንደገና እመለስበታለሁ፡፡ ለእነዚህ ነፍሳት እግዜሩም ሌላ ገሐነም ማዘጋጀት አለበት፡፡

minilikበመጀመሪያዎቹ አንቀጾች ለማመልከት እንደ ሞከርሁት የቅርቡንም ሆን የጥንቱን የኢትዮጵያ ታሪክ እኛም ከሰባው ዓመት ባሻገር የዘለልነው እምብዛም ክትትል በማጣት በተጨማሪም ወደ ሥልጣን እርካብ ላይ የወጣ ሁሉ ፀሐይ ብርሃንዋ መስጠት የጀመረችው በእነሱ አገዛዝ ጀምሮ መሆንዋን ለማስረገጥ ብዙ ትርምስ ሲፈጠር ኖርዋል፡፡ እውነት ነገር ይነገር፡፡ በአጼ ኃይለሥላሴም ዘመን ቢሆን የምኒልክም፣ የቴዎድሮስም፣ የዩሐንስም ታሪክ ጉልህ ሆኖ እንዳይወጣ ይፈለግ እንደነበረ ምስክር ነኝ፡፡ የዚህም ምክንያት በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመንና ታሪክ ላይ ምንም ጉዳይ ወይም ግለሰብ ጥላውን እንዳይጥል ስለሚፈለግ ነበር፡፡ በዘመናቸውም የነበሩትን አርበኞች ሁሉ ታሪክ ለቅመን በንጉሠ ነገሥቱ ትከሻ ላይ በመቆለል እውነተኞቹ አርበኞች ሳይታወቁ፣ ታሪካቸውን፣ በአፍ በመቀባበል እንጂ ተነግሮ ሳንጠግበው ሰዎቹ ወይ ተገድለዋል፡፡ በገመድ ተንጠልጥለዋል ወይም የእርሳስ ሲሳይ ሆነዋል፡፡

ያለፉትን መንግሥታት በመጠኑና ምናልባትም ይበዘባቸዋል በማይባል ሁኔታ ጀግንነትና ጀግናን ባለማክበር የተሰለፉትን አገር ሻጮችንና ለአገር ክብርና ሰማዕትነት የቆሙትን ወገኖቻችንን ሲገድሉና ሲያስገድሉ የኖሩትን ስንተች በጅተናል፡፡ አዝናለሁ፡፡ በባንዳነትና በአገር ጠላትነት የቆሙትን በየጊዜው ስናሳቅል (እኔን ጨምሮ) የቆየነውን ያህል ለዛሬውና ተረካቢው ስለ ጦርነቶታችን፣ ስለ መሪዎቻችን በጎ በጎ ምንባብ አቅርበን የምናውቅ አይመስለኝም፡፡ በዚህ የተነሳ እንደምትከታተሉት ሁሉ ውሸት ይነግሥ ዘንድ፣ የፈጠራ ታሪክ ተአማኒነት ያገኝ ዘንድ አስተዋጽኦ አድርገናል፡፡ የእውነት አለመነገር ለቅጥፈት ተቀባይነት አስተማማኝ ሁኔታዎችን አስገኝቷል፡፡

ውሸትን የመሰለ ጨካኝ ነገር የለም፡፡ ውሸት ደግሞ ሰው ሳይሆን ባሕርይ ነውና ያንን ገፋ አድርግን ካየነው እንደ ዋሾ ሰው ጨካኝ የለም ለማለት ይቻላል፡፡ ትንሽ ዕድሜህ ገፋ ሲልና በመሠረቱም በቤተሰብ በሚሰጥ ትምህርትና ግብረ ገብነት ተኮትኩተህ ካደግህ ተራራ የሚያካክለው የወያኔዎች ቅጥፈት ያሳብድሃል፡፡ ቀደም ሲል እንዳልሁት ደግሞ ይቺ አገር ከምንም ምንም የበለጠ ሀብትዋና ኩራትዋ የዘመናት ጀግንነትና ለአንድነትዋ የተከፈለው መስዋዕትነት ሆኖ ሳለ ያለንን አውቀን ያለማሳወቁ ጎዳን፡፡ ጎድቶናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ልጆቻችን እንኳ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን እየተመለከቱ “የፕሮፓጋንዳውን እውነት” ወደ ማመኑ አዘንብለዋል ባይ ነኝ፡፡ በተለይም መንግሥት ይዋሻል ብሎ ለማመን የማይፈልገው የዋሕ ሁሉ ደህና የፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆኖአል ባይ ነኝ፡፡ የማላስባቸው ሰዎች ሳይቀሩ እኔን አዋቂ አድርገው “ጋሽ ጸጋዬ ይኸ ቴሌቪዥን ላይ የሚቀርበው የምኒልክ ጭካኔ ምን ያህል እውነት ነው?” ብለው ይጠይቁኛል፡፡ እንደአጋጣሚ ደግሞ መኪናዬ ውስጥ በተለዋዋጩ የአየር ጠባይ የወየበች መጽሐፍ አለችኝ፡፡ Who will tell the people? የምትል፡፡ ለሕዝቡ ምን እንንገረው? የሚሉ ፋይዳዎችን የሚነካካ ነው፡፡ አዎን ለሕዝባችን —— በተለይም ለአዲሱ ትውልድ ምን እንንገረው? የእነማን ልጅ መሆኑን ——- በምን መሠረት ላይ የበቀለ መሆኑን እንዴትና በማን ይነገረው? አዎን ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ ምኒልክንና የአድዋ ጦርነትን ምኒልክንና አርሲን ——- በጠቅላላውም ምኒልክንና የታሪክ ዘመኑን በተመለከተ የሚቀርበው ፕሮግራም ደሙን ያላፈላው ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ የፈጠራ ድርሳንና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ እየሰጠመ የሚገኘውን የወያኔ መርከብ ለማዳን ሲባል የተፈበረከው ቅጥፈት መልስ የሚገባው አይመስለኝም፡፡ በእኔ በኩል ውሸትን ማስተባበል ሥራዬ ነው ብዬ አላውቅም፡፡ እውነትን በእውነቱና በሐቀኛ ቅርጹና መልኩ ማሳየት እርግጥ የአደጋ ጊዜ ግዴታ ይሆናል፡፡ አለዚያ ለፈጠራ ድርሳን ሁሉ እንደ አስተባባይና ተቃዋሚ ሆኖ መጮህ ተገቢ አይደለም፡፡

ፋሽስቶችና ናዚዎች አብረው የሚጓዙባቸው የጋራ ባሕሪያት አሉአቸው፡፡ ይኸውም በተደጋጋሚነትና በአሰልቺነት የሚቀርበው የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ የደገምሁት ካልሆነ በቀር ሙስሊኒ ራሱ “ማይክሮፎኑን” ከያዘ የሕዝብን ቀልብና ልብ መማረክ ዕዳው ገብስ ነበር፡፡ (ለእኔ ተውልኝ ነበር የሚለው) በዚህም የተነሣ የኢጣልያ ጎረምሶች ለእሱ ፕሮፓጋንዳ፣ የጀርመን ወጣቶች ከሒትለር ለምትወጣ አንዲት ቃል ተገዥ ሆኑ፡፡ ሕዝቦቻቸውም ወደ እልቂትና አገሮቻቸውም ወደ ፍጹም ውድመት መሩ፡፡

ሁላችሁም ልትስማሙኝ እንደምትችሉ አምናለሁ፡፡ በአንዲት ነጥብ ላይ ማለቴ ነው፡፡ ወያኔ በመጣበት እግር መውጣት ሳይሆን መጽሐፋችን እንደሚለው “በታላቅ መንቃቃት” የሚያልፍበት “የታላቁ መልአክ” እንቢልታ ከሚጮኽበት ደረጃ ላይ ደርሶአል፡፡ ይኸን ራሱም አላወቀውም አይባልም፡፡ ከሁለት ባላ ላይ ተንጠልጥሎ ሁለት አደጋ በማድረስ “የመጣው ይምጣ” ላይ ይገኛል፡፡ የጨረሳቸውን የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ፈለግ ተከትለው አመጹን የሚያፋፍሙ ወጣቶችን ጥያቄዎች ለማስተኛት ኦሮምኛ የሚናገሩ የመንደሩን ሰዎች የቴሌቪዥን እንግዶች እያደረገ ነው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ በማድረግ “የምኒልክ ሐውልት በፊንፊኔ መቆም ይገባዋል ወይ? የናዚ ሐውልት በለንደን እንዲቆም ይፈቀዳል ወይ?” በማሰኘት የዛሬን ጥያቄ በሌለ ታሪክ ሊለውጠው እየሞከረ ነው፡፡ በሌላም በኩል በአማራውና በኦሮሞው መካከል ያለውን የማያረጅና የማይፈርስ ድልድይ ለማቃጠልና ደም ለማፋሰስ እየሞከረ ነው፡፡ እውን ለዚህ ዓይነቱ ተለማማጅ ፕሮፓጋንዳ የምንፈታ ተራ ሕዝብ ነን?

በዚያን ሰሞን የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ መሪ ለሆነ ወዳጄ ስልክ ደውዬለት ነበር፡፡ “ምን እየተፈጠረ ነው?” አልሁትና “እባክህ በአገር ሽማግሌ ጠፍቶአል የማይባል ነገር የለም፡፡ የማይሰማ ታሪክ፣ የማይሰደብ ጀግና፣ ስለኢትዮጵያ አንድነት የማይነገር ተረት የለም” አለኝ፡፡ በዚህ መጣጥፍ ላቀርበው ላሰብሁት አሳብ ተጨማሪ ግፊት ፈጠረብኝ፡፡ የሽማግሌ ከአገር (በአገር) መጥፋት፣ የታሪክ ምስክሮች ከአገር (በአገር) አለመኖር፣ ሕሊና ያላቸው ሰዎች ወጣ ብለው ለመናገር ያለ መቻል (ጥቂቶችን በማኅበራዊ ድረ ገጽ ብናነብብም) በአገር ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ ምን ያህል ጎድቶታል? ብዙ ብዙ እንደሚባለውም አንድ አገር ላይ ሕሊና ቢሶች ከሚያደርሱባት አደጋ ይልቅ ተከናንበው የተኙ የእውነት ምስክሮች በዝምታቸው የሚያደርሱት አደጋ መቶ እጥፍ ነው፡፡

“ሽማግሌ ዜጋ ጠፋ” አለኝ ወዳጄ፡፡ ወያኔ እንደ መጣች ታሪክ መዘበራረቅና የጥላቻን ዘር መበተን እንደ ጀመረች “ኢትዮጵያን በትክክለኛ ቅርጽዋና ይዘትዋ የሚያውቁአት አረጋይ ዜጎች ነበሩ፡፡ በሚኒስትርነት፣ በአምባሳደርነት፣ ሕዝብን በማስተባበርና በጦር ሜዳም ውሎ የታወቁ አባቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ አባቶች ሁኔታው ሁሉ አገርን የሚያዋርዱና ቀስ በቀስም የእያንዳንዱን ዜጋ ሕልውና የሚጻረሩ መሆኑን በመረዳት ባለቀ ዕድሜያቸው ላይ “የኢትዮጵያዊነት ማኅበር” አቋቁመው ነበር፡፡ እነዚህም አቶ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ ቢትወደድ ዘውዴ ገብረሕይወት፣ ደጃዝማች ዶክተር ዘውዴ ገብረሥላሴ፣ ልጅ ሚካኤል እምሩ፣ ደጃዝማች ወልደሰማያት ገብረ ወልድ ፊታውራሪ ገብረሕይወት፣ አቶ በለጠ ገብረጻድቅና ዋናው ጸሐፊ አቶ ሳሙኤል ዓለማየሁ ነበሩ፡፡ የፖለቲካ ሥልጣንን አይተውትና ጠግበውት በመጨረሻ ዘመናቸው ላይ የነበሩትን እነዚህን አባቶችና ሁለት ሦስት ወጣትነት ያላቸው ቅን ዜጎችን ለማየት ያስደነገጣቸው ወያኔዎች ይኸ አጀንዳ ይፈርስ ዘንድ ያልጣሩት መስክ አልነበረም፡፡ በዚህም በስደቱ ዓለም ተመሳሳይ ጥረቶች መደረጋቸውን አውቃለሁ፡፡ ልብ በሉልኝና አረቡ ዲታስ አሜሪካ ድረስ መረቡን ዘርግቶ ወጣቶቻችንን ለመከፋፈል የሚያደርገውን ትከታተሉት የለም እንዴ? በስፖርቱ ስም!

“የሽማግሌ” ሚና ምንድን ነው? ታሪክ ሲዛባ፣ ሕግና የታወቀው ሥርዓት ሲናጋ፣ በሕዝብ መካከል ሰላም ሲታጣ መምከር፣ መገሰጽ፣ ማስተማር ነው፡፡ ይኸ ነበር ባህላችን! በዛሬው የእብደት ዘመን ግን እንደምከታተለው በእርግጥ የሽማግሌ ሚና ሊጫወቱ የሚገባቸውና በዚያ ሰልፍም ከመጀመሪያው ረድፍ መገኘት የሚኖርባቸው አንዳንድ ግለሰቦች ከአጥፊዎች ጋር ማኅበር በመጣጣት ላይ መሆናቸውን ተገንዝቤአለሁ፡፡ ይኸ የሚያስታውሰን ፈረንጆች “ንጉሡ ራቁታቸውን ናቸው” የሚሉትን ይትበሐል ነው፡፡ እንደሚባለው የንጉሡ ባለሟሎች በዓይነቱ፣ በጥራቱና በረቂቅነቱ እስከዛሬ የማይታወቅ ልብስ እየተሰራልህ ነው ብለው አእምሮውን አስተውታል፡፡ በመጨረሻም “በዓይን የማይታየውን ልብስ ለብሰሃል” ብለው በዙሪያው እየተሽከረከሩ በወደል ወደሉ ቋንቋ ያደንቁት ጀመረ፡፡ በፊቱ እየተንበረከኩም “ንጉሣችን ለዘላለም ይኑር! ዓይን አይቶት የማያውቀውን ረቂቅ ልብስ ለብሶ ለሕዝብ ይታይ ዘንድ ወደ አደባባይ ይወጣል” ብለው ከፊት ለፊቱ መሮጥ ይይዛሉ፡፡ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ያጨበጭባል፡፡ ሆታው ሌላ ነበር፡፡ ሁሉም አጨብጫቢ ነው፡፡ “ሆ” ባይ ነው፡፡ በመካከሉ አንዲት ትንሽ ልጅ ——– አእምሮዋ በቅጥፈትና በማጭበርበር ኃጢአት ያልተበከለ-ከአባትዋ ትከሻ ላይ እንደታዘለች “ንጉሡ ራቁቱን ነው፡፡ ንጉሡ ራቁቱን ነው” አለች ይባላል፡፡ ታዲያን እንደ የእውነት ምስክሮችና የአገሪቱ ሕሊናዎች አድርገን የምንመለከታቸው (በእኛም አገር ዛሬ) ሰዎች ራቁቱን ያለውን ንጉሥ ሲያቆላጵሱት እየሰማን ነው፡፡

የአድዋ ጦርነትና የምኒልክ ዘመን በሰባትና ስምንት ሺ ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደ “ትናንት” ማታ የሚታይ ይመስለኛል፡፡ እኔ አንድ ትሁት ኢትዮጵያ ዜጋ ደግሞ የተወለድሁት ፋሺስት ኢጣሊያ ከተባረረች በኋላ ሲሆን በምኒልክ ዘመን ሁነኛ ሥፍራ የነበራቸው ሰዎችን ለማወቅና ለማነጋገር ዕድል ገጥሞኛል፡፡ እንዲያውም የአክስቴ ባለቤት (የእናቴ ታናሽ እህት) ልጅ ደስታ ምትኬ የእቴጌ ጣይቱ የአክስት ልጅና ጸሐፊያቸውም ነበሩ፡፡ በተደጋጋሚ በመጣጥፎቼ የጠቀቀስኋቸውን ጋዜጠኛና ከንቲባ ደስታ ምትኬ፣ ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም (ዋየሕ) ደጃዝማች ከበደ ተሰማን፣ ፊታውራሪ እማኙ ይመርን ሌሎችንም አውቃለሁ፡፡ እንደማምነውም ዛሬም ጭምር በዚያ ዘመን የኖሩ ከአምስት እስከ አሥር ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ (ሰሞኑን ባለ 139 ዓመት ዕድሜ ኢትዮጵያዊ ብቅ አሉ ልበል?)

የምኒልክ ዘመን ወደ ኋላ ብዙ የዘመን ርቀት ሄደን በብዙ ውጣ ውረድ ታሪኩን የምንፈለፍልበት ጣጣ ያለው አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን ዕድሜ በምኒልክ ዘመን ሲወስኑት የኖሩት ወያኔ ገዥዎቻችን ግን መረጃው ያላረጀውን፣ ብል በልቶ ያላፈጀውን ቁልጭ ያለ ታሪክ በፈጠራ ድርሳን ለምን እንደ ለሰኑት፣ የፈጠራ ታሪክ ደራሲ (እነ ተስፋየ ገብረአብ) ለምን እንደሾሙብን ግልጽ ነው፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በታላቅና ታሪካዊ ሁኔታ የተመሰረተውን አንድነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ ለማፍረስ ያገኙት ስልት ይኸ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡

ለሕዝባችን ስለዚያ ዘመን ማን ይናገር? ማን የሕዝብ ሕሊና ሆኖ ይመስክር? ታሪክ ምን ይላል? ከመጠነኛ ንባቤ፣ ባለፉት ዘመናት በምኒልክ ዘመን ከነበሩ አዛውንትና አዋቂዎች ወግና ምስክርነት በመነሣት ያቅሜን ትንሽ “እውነት” ብተነፍስ ዛሬ ማታ ጥሩ እንቅልፍ የምተኛ ይመስለኛል፡፡ በቻይናዎቹ የታኦ ፍልስፍና እንደሚነገረው “ማለዳ ላይ ታኦ አንብበህ ማታ ላይ ብትሞት ደስ ይበልህ፡፡ የጽድቅ መንገድ ይኸ ነውና” ይላል፡፡

እምዬ ምኒልክ – ትንሽ ስለ ምኒልክ ስብእና

ስለ ልደታቸው፣ ስለ ትምህርታቸው፣ በአጤ ቴዎድሮስ ተወስደው እንደ አባት እንዳሳደጉአቸውና ልጃቸውን እንደዳሩላቸው ከመቅደላ አምልጠው እንዴት ወደ ሸዋ እንደ ተመለሱ ማውሳት ዝርዝርና መጽሐፍ የሚወጣው ይመስለኛል፡፡ ይልቁንም ስለ መንግሥት አመራር ስታይላቸው፣ ስለሕዝባዊነታቸውና ስለ “አረብ ዘመቻቸው” ብቻ ብናወራስ?

ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት የተባሉበት ጊዜና የአጤ ዩሐንስ መንግሥት ማክተሚያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጭካኔ ይልቅ ርህራሄና ፍቅር የተራበበት ዘመን ነበር፡፡ አጼ ቴዎድሮስን በነበራቸው ታላቅ ብሔራዊ ራእይ እስከ ወዲያኛው የምናከብራቸውን ያህል ወደ መጨረሻው ላይ ጭካኔያቸው ዳር ድንበር አጥቶ ነበር፡፡ በኋላም አጼ ዩሐንስ ጎጃምን በነቂስ አቃጥለው ቀጣሁት ብለዋል፡፡ “እስላም የሆንህ እስከ ሦስት ወር ድረስ ክርስቲያን ሆነህ ካልጠበቅኸኝ ማርያምን በሕይወትህ ቆርጠህ ጠብቀኝ” ስላሉ የወሎ፣ የሸዋ ሙስሊሞች በበኩላቸው ጎራዴ መሳል ጀምረው ነበር ይባላል፡፡ እስካሁን ስላም ጠፍቷል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ምኒልክ “ሁሉም በእምነቱ ይተዳደር፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልጄ ነው ብለው በአዋጅም በግንባርም ለሕዝባቸው በመግለጣቸው “እምዬ ምኒልክ” ሊባሉ ችለዋል፡፡

እውነት ይነገር! ምኒልክ ከመቅደላ አምልጠው ወደ ሸዋ ሲጓዙ በዛብህ አባደክር የተባለ ባላንጣቸው ብዙ ሠራዊት አደራጅቶ ሥልጣን አልለቅቅም ብሎ አፍቀራ (መንዝ) ላይ መሽጎ አስቸግሮ ነበር፡፡ ይሁንና ምኒልክ ጋደሎ እንደ ደረሱ የሱባ፣ የጥሙጋ፣ የአርጤማና የከረዮ ኦሮሞ ባላባቶች በደስታና በእልልታ ተቀብለው ንጉሥነታቸውን አውጀው ታላቅ ግብዣ አደረጉላቸው፡፡ በዚያ ግብዣም ላይ ምኒልክ (ያን ጊዜ ደጃዝማች) በተራቀቀ ኦሮምኛ ንግግር አድርገው ለባላባቶቹ ልዩ ልዩ ሽልማቶች ሰጥተዋቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ አጤ ምኒልክ ብቻ ሳይሆኑ አባታቸው ንጉሥ ኃይለ መለኮት፣ አያታቸው ንጉስ ሳህለ ሥላሴና የእሳቸውን አባት አዝማች ወሰን ሰገድ የተራቀቀ ኦሮምኛ ይናገሩና እድገታቸውና ክፍላቸውም ከኦሮሞዎች ጋር መሆኑ በጹሑፍም በቃልም የተረጋገጠ ነው፡፡

ምኒልክ በአባታቸው ዙፋን ላይ ለመቀመጥ ወደ ሸዋ በመጡ ጊዜ በባላንጣነትና በሥልጣን አላስረክብም መልክ አምጾ የነበረው በዙ አባደክር ኃይል ጠርቀምቀም ያለ ነበር፡፡ ይሁንና ከአባደክር ሠራዊት መካከል በርከት ያሉት በየጊዜው እጃቸውን ለምኒልክ በመስጠት ከሠራዊቱ ጋር ተቀላቅለዋል፡፡ አንደኛውም የበዙ አባደክር ወታደር ጎበና ዳጬ (አባጥጉ) ነበሩ፡፡ እኒህ የወታደርነት ቁመናና ግርማ ሞገስ የነበራቸው የበዙ አባደክር ወታደር ለምኒልክ ከገቡ በኋላ በፍጥነት የቤተ መንግሥቱ ባለሟል ሆኑ፡፡ ታሪካቸው እንደሚለው ደግሞ በዙ አባደክር እጁን ሰጥቶ ምህረት ጠይቆ ሲገባ ከጎበና ጋር ሲገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፡፡ (በነገራችን ላይ እንደ አስተማሪያችን ልናያቸው እንደ እውነት ምስክር ልንቀበላቸው የምንወድደው ክቡር ኦቦ ቡልቻ ስለምኒልክና ጎበና ግንኙነት የሚናገሩት ታሪክ ከየትኛውም የዘመኑ ፋብሪካ የወጣ መሆኑ አልገባኝም፡፡ የምኒልክና የታላቁ ጎበና ዳጨ ግንኙነት ይህን ሲመስል ከበዛብህ ጋር ሆነው ምኒልክን የወጉ በሙሉ ምሕረት መቀበላቸው እውነት ነው፡፡ በዛብህ ግን መላልሶ ምሕረት እየጠየቀ በመሐሉ እየሸፈተ ጥፋት በማድረሱ፣ ወዲህም ምኒልክን በግብዣ ላይ ለመግደል ሽጉጥ ስለተገኘበት፣ በተጨማሪም ስለ ሥልጣን አያያዝ ከሰዎች ጋር የተላላከው ደብዳቤ ስለተያዘበት መሳፍንቱና መኳንንቱ የሞት ፍርድ ፈረዱበት፡፡ ያን ጊዜ ነው እናት አይዋጁ የተባለች የዘመኑ የቡልጋ አዝማሪ (እንደ ዶክተር ሥርግው አገላለጥ)

“ጋላም አርፈህ ተኛ አውልቅ ጀልዶህን
ያማራውም ጎበዝ ፍታ ኮርቻህን
በእሳት አቃጠሉት የሚያባንንህን
“አንተም ጨካኝ ነበርህ ጨካኝ አዘዘብህ
እንደ ገና ዳቦ እሳት ነደደብህ”
አለች ይባላል፡፡ (እሳት ነደደብህ የተባለው በጥይት ሲደበደብ ከጥይቱ ጋር የሚበተነው አረር ልብሱ ላይ አርፎ እሳት ስለተያያዘ አካሉ በተጨማሪም በእሳት ስለተለበለበ ነው፡፡)

ምኒልክ ለበዛብህ ተደጋጋሚ ምሕረት ሰጥተው በሰላም ይኖር ዘንድ ያሳዩትን ፍቅር በመጣስ እስከ ግድያ ሙከራ መድረሱ የተጠቀሰውን ፍርድ መስጠት ግዴታ ሆኗአል፡፡ አለዚያ አጎታቸው ኃይለ ሚካኤል ሣኅለ ሥላሴ ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ባፈና ጋር አድማ አቀነባብሮ በሕይወታቸው ላይ ሲነሳ ምኒልክ የግድያ ትዕዛዝ ወይም በወቅቱ ይደረግ እንደነበረው ንብረት አልቀሙም፡፡ ስለዚህ የምኒልክን ደግነት፣ አዛኝነትና ርኅራሄ የተመለከተው ሰው ሁሉ “እምዬ ምኒልክ” ይላቸው ገባ፡፡

ስለባለቤታቸው ስለ ባፈና ትንሽ ነገር እንጨምርበት፡፡ ወይዘሮ ባፈና ምኒልክን ሲያገቡ ብዙ ልጆች የነበሩአቸውና በዕድሜም ረገድ ምኒልክን በብዙ የሚበልጡአቸው ነበሩ፡፡ (እቴጌ መነን አፄ ኃይለ ሥላሴን ስድስት ዓመት ይበልጡአቸው ነበር – የራስ እምሩን ማስታወሻ ያነብቡአል) ወይዘሮ ባፈና ከምኒልክ ልጅ ለመውለድ ስላልቻሉ አንዲት ልጃቸውን ከሣኅለ ሥላሴ ልጆች ለአንደኛው በመዳር ይህንን ክፍተት ለመሙላት ይሞክራሉ፡፡ ስለዚህ ኃይለ ሚካኤል የተባለውን ያልተሟላ ጤንነት ያለውን የሣኅለ ሥላሴ ልጅ አግባብተው ምኒልክን ለመገልበጥ ሞከሩ፡፡ ምኒልክ ይህን ሁሉ ይከታተሉ ነበር፡፡ በዚህ አድማ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑትን ሁሉ አስሮ መቅጣት የተለመደ በሆነ ነበር፡፡ ዳሩ ግን አጎታቸውንም ሚስታቸውንም አልቀጡአቸውም፡፡ ይልቁንም ባለቤታቸው ወይዘሮ ባፈና ከአፈንጉሳቸው ጋር እንደሚማግጡ ያወቁ ስለነበረ ሁለቱንም ከእልፍኝ አስጠርተው “ሁለታችሁን ልድራችሁ ነው” ማለታቸው በጽሑፍ ጭምር ተረጋግጦአል፡፡ በመጨረሻውም ለባፈና መተዳደሪያ የሚሆን መሬትና ሀብት ሰጥተው ከአፈንጉሥ በዳኔ ጋር አጋቡአቸው፡፡ የምኒልክ አርቆ አሳቢነትና ሰብዓዊነት ይህን መሳይ ነበር፡፡

እንደሚባለው አጼ ምኒልክ አፈንጉሥ በዳኔንና ባፈናን ፊት ለፊት ባነጋገሩበት ጊዜ “ሁለታችሁን ልድራችሁ ነው” ሲሉ ታማኝ አገልጋያቸው የነበሩት አፈንጉሣቸው “እንዴት ሲደረግ ጌታዬ ምኒልክ የገባበትን ጭን እኔ የምደፍረው” ሲሉ “ወስላቴ በምስጢር ስታደርገው ግን መቼ እንዲህ አልህ” በማለት አፊዘው ራሳቸው ደግሰው አጋቡአቸው ይባላል፡፡ አፈንጉሥ በዳኔ ለምኒልክ በሥራ በኩል እጅግ ታማኛቸውና በተሰማሩበት ኋላፊነት እንከን ያልነበራቸው ሰው እንደሆኑ ይወሳል፡፡

ስለ ምኒልክ ሰብዓዊነትና አርቆ ተመልካችነት ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ አንዱም በጦር ሜዳ ያሳዩት የነበረው ምሕረትና ርህራሄ ነው፡፡ እንደሚነገረው በራስ ጎበና የሚመራውን የሸዋ ጦር የጎጃም ጦር መሪ ራስ ደረሶ በየጊዜው ለፍልሚያ ሲፈታተኑት ቆይተው በኋላ እምባቦ ላይ ንጉሦቹ በተገኙበት ትልቅ ጦርነት ተካሂዶ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ቆስለው ተማረኩ፡፡ በዚህን ጊዜ ንጉሥ ምኒልክ የንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን ቁስል እየጠረጉ ፋሻ እያሰሩላቸው ጠቦት እያሳረዱ እንዳከሙአቸውና እቴጌ ጣይቱም ታላቅ እንክብካቤ እንዳደረጉላቸው ዜና መዋዕሉ ያወሳል፡፡ ይኸ ብቻ አይደለም፡፡ አጼ ሚኒልክ ከንጉሥ ተክለሃይማኖት ጋር የነበራቸው ቅራኔ በከፋና በወለጋ ግዛቶች ምክንያት ነበር፡፡ በኋላ ግን ከፋን መልሰው እንደ መረቁላቸው ታውቋል፡፡ (ለንጉስ ተክለሃይማኖት የንግሥናን ማዕረግ ንጉሠ ነገሥት ዩሐንስ ሲሰጡአቸው ንጉሠ ጎጃም ወከፋ ብለው ነበር) ንጉስ ተክለሃይማኖት በኋለኛው ዘመን ለወዳጆቻቸው “እባካችሁ ስለምኒልክ አንድም ክፉ ነገር እንዳትነግሩኝ፡፡ የምኒልክን ሞት ሳልሰማ መሞትን እመኛለሁ፡፡ ይሉ ነበር፡፡

በሌሎች መጣጥፎች ላይ እንዳመለከትሁት ምኒልክ ከአድዋ ጦርነት በኋላ የኢጣልያንን ምርኮኞች እያከሙና እያሳከሙ፣ እያስታመሙና እየቀለቡ ባሳዩአቸው እንክብካቤ አለም ዓቀፍ ክብርና ዝና ተቀናጅተዋል፡፡ ይኸ የሰብዓዊነት ማስረጃ በፈንጆቹ በኩል “ከአፍሪካ የማይታኝና የማይታሰብ ሥልጡን መሪ” ተብለው ተደንቀዋል፡፡ (ከተማረኩት የኢጣልያ ሠራዊት መሪዎች መካከል ጄኔራሎች፣ ኮሎኔሎች፣ ማጆሮችና ቲኒንቲዎች በብዛት ይገኙ ነበር፡፡

አጼ ምኒልክ ከሕዝብ ጋር የነበራቸው ትብብርና ፍቅር እጅግ ድንቅ እንደነበር የሚያስረዳ ሌላ ጉዳይ አለ፡፡ እንደሚባለው ንጉሠ ነገሥቱ በየሳምንቱ በበቅሎአቸው አዲስ ዓለም (55 ኪሎ ሜትር ርቀት) እየሄዱ አስቀድሰው ይመለሳሉ፡፡ ይህን ሁሉ ርቀት አብረዋቸው መሣሪያ ይዘው የሚከተሉአቸው በርካታ ሰዎች ደግሞ ነበሩ፡፡ ታዲያ መኪና መጣና ምኒልክም መንዳት በመቻላቸው በአራዳ ጊዮርጊስ የተሰበሰቡ የዘወትር አጃቢዎቻቸውን “እናንተም አርፋችሁ ጠብቁኝ፡፡ በአውቶሞቢል ሄጄ እመለሳለሁ” ብለው ተሰናብተዋቸው መንገዳቸውን ይሄዳሉ፡፡ እነዚያ አዎች ከአራዳ ጊዮርጊስ ሳይለዩ ሲጠብቁ ቆይተው ምኒልክ ሲመለሱ አገኙአቸው፡፡ ሰዎቹ አኩርፈዋቸዋል፡፡ ምኒልክ ቢለማመጡ ቢለማመጡ ሰዎቹ ይቅርታ ማለት አልሆነላቸውም፡፡ ከሕዝቡ ጋር የነበራቸው ግንኙነት የአባትና የልጅ ዝምድና ስለሆነ “እንግዲህ ካሳዘናችሁኝ ሰልሜ ታርፋላችሁ” አሉ ይባላል፡፡ ይኸ በዘመኑ እጅግ ከባድ አነጋገር መሆኑ ነው፡፡ እግረ መንገዳችውን መቀለዳቸው ነው፡፡

ቀደም ሲል እንደ ገለጥሁት ጎበና ለአጼ ምኒልክ የገቡት ከአባደክር ብዙ ሠራዊት ሲሆን ጎበዝና ደፋር ተዋጊ በመሆናቸው ከደጃዝማችም በላይ ራስ ተብለዋል፡፡ ራስ ጎበና ይህን ሹመት ያገኙት በአንድ ቀን ለእሳቸውና ለዳርጌ ሳህለ ሥላሴ በተሰጠው ሹመት ነው፡፡ ከንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ልጅና ከራሳቸው ከምኒልክ አጎት (መስፍን) ቀድመው ራስ መባላቸው ድፍን ኢትዮጵያን ያስደነቀ ሹመትና የምኒልክ ፍትሐዊነት መሆኑ ሲወሳ ኖሯል፡፡ እንዲያውም አጼ ምኒልክ ስለ ጎበና ሲያነሱ “ጎበና ጎበና የእኔ – አንተ የጦር ንጉሥ ያገር ንጉሥ እኔ” ይሉ ነበር ይባላል፡፡ በፍቅር፣ በአክብሮትና በአድናቆት! ታዲያ የራስ ጎበና ልጅ ደጃች ወዳጆ የምኒልክን ልጅ ወይዘሮን ሸዋረጋን አግብተው ልጅ እንደ ወለዱ ይነገራል፡፡ ወጣቶቹ ለምን እንደ ተፋቱና የተወለደውም ልጅ ዕጣ ፋንታ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡

የአረብ ዘመቻውና የኅብረቱ መሠረት

ከዚች አጭር መጣጥፍ ምን ዓይነት ውጤት እንደሚገኝ አላውቅም፡፡ አጀማመሬም ረጅሙን የምኒልክ ታሪክ በአጭሩ ለማስረዳት እችላለሁ ብዬ አይደለም፡፡ በታሪካችን ውስጥ በዚህ ጽሕፈት አማካይነት ምን ያህል ርቀት እንደምንሮጥ ለማየት ብቻ ነው፡፡ እስካሁን የሞከርሁት ምኒልክ የሚለው ስም ከዘመኑ በፊት የተከሰተ፤ ሰውየው ከዘመኑ በፊት የነቃ፣ ሥልጡን፣ በተፈጥሮው ሩኅሩህና ሰብዓዊ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ ዝርዝር ማስረጃውንና ታሪኩን ማንበልበል ቀላል ነው፡፡ እኔም እንዲሁ በአእምሮዬ ውስጥ ከመዘገብኋቸው ዓበይት ነጥቦች መካከል ትዝ የሚሉኝን ብቻ ነው ለዛሬ ያቀረብኩት፡፡ አለዚያ የምኒልክን ሰብዓዊነት በሚመለከት የፈረንጆችንም የኢትዮጵያውያንም ምስክርነት በሰፊው መዘርዘር ቀላል ነው፡፡ እሸት እሸት የሆኑ መረጃዎች አሉ፡፡

አጼ ምኒሊክ ቀደም ሲል ንጉሰ ነገስት ብለው ማሕተም አሳትመው ከአጼ ዮሐንስ ጋር በመጠነኛ ፍጥጫ ላይ ቆይተው ነበር። አጼ ዮሐንስ ምንም እንኩዋን የነጋሲነት ትውልድ ባይኖርባቸውም ጄነራል ናፒዮር በአጼ ቴዎድሮስ ላይ በነበረው ተልእኮ ተባባሪና ደጋፊ ስለሆኑ በርከት ያለ መሳሪያ መሸለማቸው ይታወቃል። እንግሊዞች ለዚህ ተልእኮአቸው ምኒልክም እንዲተባበሩ ቢጠይቋቸው ትብብር ሳያሳዩ ቀርተው ከመሳሪያ እርዳታው ተካፋይ አልሆኑም። ይልቁንም ምኒልክ ቴዎድሮስን እንደአባት ያዩአቸው ስለነበረ ከሴራው አልተሳተፉም። ራስ ጎበና ሁኔታውን ለመሰለል ሞክረው እንደነበረና ከእንግሊዞች ጋር ግን አለመገናኘታቸው ይወሳል። ለማንኛውም ንጉስ ምኒልክ አጼ ዮሃንስን በንጉሠ ነገስትነት በተቀበሉ ጊዜ በተስማሙት መሰረት ተበታትነው የኖሩትን የምእራብ ኢትዮጵያ ግዛቶች ወደ ውህደቱ በማስገባቱ ረገድ በሚያካሄዱት ዘመቻ አንዳች ተቃውሞና ጣልቃ ገብነት እንዳያስገቡ ንጉሠ ነገስቱ ተስማምተውላቸዋል። በሰሜኑ በኩል ውህደቱን በማምጣቱ ረገድ አጼ ቴዎድሮስ ስራውን በአብዛኛው ጨርሰውታል። ስለዚህ በምኒልክ በኩል በራስ ጎበና አዛዥነት በጉድሩና በአዋሽ ወንዝ አካባቢ የነበሩት ቀድሞም በአምሃየስ ፣ በአስፋወሰንና በሳህለስላሴ ዘመን በኅብረቱ ውስጥ ገብተው የነበሩትን ኦሮሞዎች በማስተባበር አንድነቱ የበለጠ ስር እንዲሰዽድ አድርገዋል። በሚቀጥለው ርምጃ የግቤ፣የጎጀብና የዴዴሳ አካባቢ ስፍራዎች በራስ ጎበና ልጅ በደጃዝማች ወዳጆ አማካይነት በውይይትና በድርድር ብቻ የውህደቱ ተሳታፊዎች ሆነዋል።

የጎበና “የአረብ እንቅስቃሴ” የተጀመረው በ1860-1870 ድረስ ባሉት አመታት ነው።በእነዚህም አስር አመታት የሊበንን ነዋሪዎች፣ በሙገር ጅረት አካባቢ ነዋሪዎች ከዚያም ጊቤን ተሻግረው ነዋሪዎቹን እያሳመኑና እያስተባበሩ በፈቃዳቸው ያለ ደም መፍሰስ ከውህደቱ ተሳታፊዎች ለመሆን ተስማምተዋል:: ከነዚህም መካከል የጅማው አባ ጅፋር ይገኛሉ:: የአባ ጅፋር እናት ህብረቱ ለሁሉም ጥቅም እንደሆነ በማወቅ ለልጃቸው በሰላም እንዲገቡ ምክር እንደሰጧቸው ገልጠዋል::

ከዚህ በኋላ ሁለተኛው የራስ ጎበና ውህደቱን የማጠናከር ተግባር የተከናወነውበ 1870 – 1880 ነበር፡፡ በዚህ ዘመቻ ጎበና አባ ጥጉ የሌቃ ነቀምቴና የሌቃ ቄለሞን ባላባቶች (መሪዎች) ኩምሳ ሞረዳና ጆቴ ቱሉን አንዲት ጥይት ሳትተኮስና በሰላም የአንድነቱ አቋም አባላት አድርገዋቸዋል:: የአጼ ምኒልክ የክርስትና ልጅ የሆኑት ደጅ አዝማች ገብረ እግዚአብሄር ሞረዳ (የሌቃ ነቀምቴው) እና የሌቃ ቄለሙ ደጅ አዝማች ጆቴ ቱሉ ከጦር ሚኒስትሩ ከራስ ጎበና፣ ከኢሊባቡር ገዥ ከራስ ተሰማ ናደው ጋር በመመካከር የኢትዮጵያ ዳር ድንበር እስከ ነጭ አባይ መሆኑን በማመን ዛሬ ኡ ጋንዳ እስከሚባለው አገር ድረስ ሄዶ የሚያቀና የጦር አስኳል ልከው ነበር:: ይሁንና አስመራ ላይ አንድ ችግር ተፈጠረ:: ጣሊያኖች ከህንድ ሀገር ያስመጡአቸው ላሞች በሽተኞች ሆነው ተገኙና ከዚያ የጀመረ የከብት በሽታ ወደ ኢትዮጵያ ተዛመተ:: “ ክፉ ቀን ” በተባለው በዚህ በሽታ እስከ ኢሉባቦር፣ ወለጋ፣ ሲዳሞና ከፋ ድረስ አያሌ ሺህ ህዝብና ከብት አለቀ፡፡ ሠራዊቱም የዘመቻ ተግባሩን ማቋረጥ ግዴታው ሆነ:: (የአረብ ዘመቻ ማለት የምእራብ ዘመቻ ማለት ነው፡፡ ቃሉ ግዕዝ ነው) ለነጭ ዓባይ ማስገበሩ ንቅናቄ የተመረጡት የጦር አዛዥ ከራስ ተሰማ ሠራዊት ፊታውራሪ ኀይሌ የሚባሉ ሲሆኑ ስምንት መቶ ወታደሮች ይዘው ዘምተው ነበር፡፡ እርሳቸው እንደ ምንም ብለው ከስፍራው ደርሰው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከሶባት ጅረት በስተግራ ሰቀሉ፡፡ እጅግ የሚጋረፈውን ንዳድ ለጠባቂ ለመተው አላስቻላቸውምና እርሳቸውም ሰው ሳያስቀሩ ወደ ጎሬ ተመለሱ፡፡ እንደሚባለው ከጥቂት ቀናት በኋላ ቢቸነር በሚባለው የጦር አዛዥ ሰራዊቱን አስከትሎ ከስፍራው ሲደርስ የኢትዮጵያን ይዞታ ለማስከበር ሰው ስላላገኘ ሰንደቅ አላማውን አውርዶ የግብጽን ሰንደቅ አላማ ሰቀለ፡፡ (ተክለ ጻድቅን፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይን፣ ሥርግው ሀብለ ሥላሴን፣ ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴን ወዘተ ወዘተ ያነብቡአል)

ዘመቻው በንዳድ፣ በሰውና በከብት እልቂት ብዙ ችግር ስላደረሰ እንደታሰበው እስከ ነጭ አባይ መፍለቂያ ሊሳካ ባይችልም በዚያው አቅጣጫ የሼህ ሆጀሌ ግዛት ቤኒሻንጉልና(ቤላ ሻንጉል) እና ቦረና ወደውህደቱ እንዲገቡ ራስ መኮንን ወልደሚካኤል ጉዲሳና ፊታአውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የቦረና፣ የጅባትና ጫጫ ገዢ ብዙ ደክመው ተሳክቶላቸዋል። ከነሱም እኩል የወለጋ ባላባቶች ደጃዝማች ጆቴና ደጃዝማች ገብረግዚአብሄር ተሳታፊዎች ሆነዋል። (በነገራችን ላይ ሼህ ሆጀሌ እስከ እድሜያቸው ፍጻሜ ድረስ ጽኑ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስሜት እንደነበራቸው ይነገርላቸዋል፡፡)

“በአረቡ ዘመቻ” ውህደቱን በመቃወም ጦርነት የከፈተው የከፋው ንጉስ ጋኪ ሼሮኮ ነው። ጋኪ ሼሮኮ ከአጼ ሰርጸ ድንግል በቀጥታ የትውልድ ሃረግ የሚመዝዝና በማንም ስር ለመሆን አልፈልግም የሚል ነበር።እርሱም ከራስ ወልደጊዮርጊስ ጋር ተዋግቶ ተማረከ። ጦርነቱ አንዳለቀ ግን የከፋ ሴቶች ባሎቻችንን እኛ ባልደገፍነው ጦርነት ውስጥ ማግዶ አስጨረሳቸው በማለት ከስሰው መሰቀል አለበት የሚል አቤቱታ አቀረቡ። አጼ ምኒልክ ግን ጋኪ ሼሮኮን ወደ አንኮበር በመውሰድ በእንክብካቤ አቆዩት ይባላል፡፡

ስለ አርሲ ምን የምንለው አለ? በሳህለ ስላሴና በንጉስ ሃይለመለኮት (የምኒልክ አባት) ጊዜ ጥቂት ኦሮሞዎች መሸፈታቸው ይነገራል። ይሁንና በአዝማች ሰይፉና በራስ ዳርጌ አማካይነት ወዲያው ሰላም መመስረቱ ይወሳል።ራስ ዳርጌ በቅርብ በህዝቡ ዘንድ ባገኙት እውቅና፣ መልካም ስነምግባርና ሃይማኖተኛነት እዚያ በገዢነት ተመድበዋል፡፡ አርሲ ከኢትዮጵያ ክፍላተ ሃገር ጠበብ ያለችና የህዝቡም ብዛት እስካሁን አንድ ሚሊዮን ስላለሆነ የራስ ዳርጌ ወራሾች እነ ራስ ካሳ ሃይሉ ብዙ የሰላሌ ተወላጆችን ወደዚያ በመውሰድ አስፍረዋቸዋል።

እንደ በቆጂ፣ ትንሳኤ ብርሃንና ጢቾ ባሉት ከተማዎችም ብዙሃኑ ነዋሪ ጉራጌ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ከምባታና ኦሮሞ ነው። የምኒልክ ጸሐፌ ትዕዛዞች ባቆዩን መዘክሮች መሰረት አጼ ምኒልክ ወደ አርሲ የሄዱት በጦርነትና ለጦርነት ሳይሆን የሃረሪው መሪ አሚር አብዱላሂ አልገብርም ብሏል በተባለ ጊዜ ወደዚያ ሲዘልቁ ነበር። የጨለንቆ ጦርነት እየተባለ በሚጠቀሰው ዘመቻ ደግሞ ሃሮልድ ማርከስ እንደገለጸው የአሚሩ አመጽ ያለቀው በአስራአምስት ደቂቃ ነው። ይህም በአለም ታሪክ ያልታየና ያልታወቀ ነው። አሚሩ ሁለት ሚስቶቹን ይዞ ሲጠፋ ወዲያው በከተማው ሰላም ነገሰ። ተስፋዬ ገብረአብና ቀደም ብሎም ወዳጄና የድሮ ተማሪዬ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እንዳሉት ሳይሆን በጨለንቆው ዘመቻ አንድም የኦሮሞ ተወላጅ ተሳትፎ አልነበረውም፡፡ እናት አይዋጁ የምትባል (ስርጕው ሃብተ ስላሴ እንደሚሉት)የቡልጋ የኪነት እመቤት(አዝማሪ) ከገጠመቻቸው ሁለት አናቅጽ ባቀርብላችሁ

ጎበና ጎበና ጎበና ፈረሱን አማን ቢያስነሳው
ዓባይ ላይ ገታው
ጎበና ፈረሱን ፋሌ ላይ ቢያስነሳው
አረብ አገር ገታው
ጎበና ፈረሱን ቼቼ ቢለው
ሱዳን ላይ ገታው
የመዳኒት ጥቂት ይበቃል እያለች
እጅጋየሁ አድያም አንድ ወልዳ መከነች

(እጅጋየሁ አድያም ሰገድ የአጼ ምኒልክ እናት ናቸው።)

የታላቅ ብሄራዊ ቤተሰብ ምስረታ

ጥንታዊት ኢትዮጵያ (“ወያኔዎች አጠራሩን ከፈቀዱልኝ”) ጥቁር አፍሪካን፣ አለዚያም እስከ ነጭ አባይና_ቤናድር (ሞቃዲሾ) የመንና ሐድራሞትን (የማውቀው አካባቢ ነው) ማጠቃለሉ ቀርቶ የአሁኑን ቅርጽ የያዘው በ19 ክፍለ ዘመን ፍጻሜና በሐያኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ ነው። እስካሁንም ይህን አንድነት የፈታው አንዳች ሃይል አልነበረም። የኢትዮጵያ ታሪክ በአጠቃላይና ይልቁንም የምኒልክን ዘመን ታሪክ በመከታተል የታወቁት ዶክተር ሃሮልድ ማርክስ በአንድ ጽሁፋቸው ላይ እንደገለጹት አጼ ሚኒልክ ኢትዮጵያን አንድ በማድረጉ ረገድ “አንድ ታላቅ ብሄራዊ ቤተሰብ” መስርተዋል። የዚህ “ብሄራዊ ቤተሰብ” ስርዓት ደግሞ በግዴታ ወይም በማስፈራት የመጣ አይደለም። በተፈጥሮ መጣ ይሉናል was not the outcome of coercion,it was what came naturally, አዎን እንደተባለውም የሸዋ ነገስታት በአብዛኛው ከምኒልክ ወደኋላ የምንቆጥራቸው ሁሉ ኦሮምኛ ስለሚናገሩ፣ በጋብቻ ከኦሮሞዎች ጋር በመተሳሰራቸውና ለሎችንም በዚህ ረገድ ስላደፋፈሩቸው ወዲህም የሞጋሳ (የጡት ልጅነት) ስርአት ስለተዘረጋ “አንድ ብሄራዊ ቤተሰብ” ሊመሰረት ችሎአል።

በሌሎች መጣጥፎቼ ያነሳኋቸውን ነጥቦች ላለመደጋገም እየሞከርሁ ነኝ። ከመቶ አመት በፊት ተበጣጥሶና በጎሳ መሪዎችና የክፍለ ሃገራት ወቅታዊ ገዢዎች _ዘመነ መሳፍንት _ተበታትኖ የኖረ አገር ወደ ህብረት የመጣበት ዘመንና ያንን ያስፈጸሙ የታሪክ ከዋክብት በአባትነት ሊከበሩ፣ በጀግንነት ሊዘከሩ ሲገባ ዛሬ ላይ የሚጨፈጨፉት ለምንድነው? የታሪክ ክብርና የብሄራዊ አላማ ጉዳይ እንደዘመኑ ገዢዎች ቅኝት ነው። ወዳጆቼና ወገኖቼ ለመሆኑ በህልማችሁም በቅዠታችሁም አገር የሚሸጥ መንግስት ይመጣል —- ይኖራል ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ለመሆኑ ሕዝብን ከህዝብ ለማጫረስ የሚፈልግ መንግስት ይኖራል ብላችሁ አምናችሁ ታውቃላችሁ? ለመሆኑ በሕልምም ሆነ በቅዠት መንግስት ከህዝብ ይቀማል፣ ይሰርቃል፣ ደም ያፈሳል፣ ቀምቶ ራሱን፣ ያበለጽጋል የሚል ወሬ ብትሰሙ ታምናላችሁን በሌላ አለም ማለቴ ነበር። ለመሆኑ ትልቁ ሌባ የመንግስት መሪ መለስ ነው ብሎ ጉግል (Google) ሲገልጥላችሁ ምን ተሰማችሁ? (ሶስት ቢሊዮን ዶላርስ)

በእኔ በኩል የርስበርሱ ጭፍጭፍ መሰናዶ እያስፈራኝ ነው፡፡ “የምኒልክ ሃውልት ይፍረስ” የቴሌቪዥን ጥሪ! “በኦሮሞ ጥያቄ ስም”! የወያኔ የጦር አዋጅ ነው። ከዚያው ከሰፈራቸው “ወያኔ” ከአስራአምስት ከማይበልጡት ሴረኛና ጠንቀኛ ማእከላዊ ገዢዎቻችን የሚገላግለንና ለእኛም ጋር የሚታረቅ ሽምብራ የሚያክል ወያኔ የለም? ኢትዮጵያን የሚያድን! ትግሬውንም የሚያድን?

በነገራችን ላይ የአጼ ምኒልክ ዘመን የኦሮሞ ልጆች ከትልልቁ የመንግስት ሃላፊነት፣የጦር አበጋዝነትና አስተዳደር ስራ ላይ የወሳኝነትን ሃላፊነት የተቀዳጁበት ነበር። ለመሆኑ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ከታሪካዊ የአገር አንድነት ተጋድሎ፣ውጤትና ታሪካዊ በረከት ሊያለያይ ይችላልን? ወያኔኮ ሺህ አመት የመግዛት ዕድል ቢኖረው አንዲት ትምህርት ላለመካፈል ጭንቅላቱን አውቆ የዘጋ የክፋት ሁሉ ምንጭ ነው፡፡ መሄድ ያለበት።


ወጣቶቹና –ቅዳሜ (ጽዮን ግርማ)

$
0
0

አንዷን ቅዳሜ በፍርድ ቤት

በዛሬው ችሎት ፖሊስ የሃያ ስምንት ቀን የምርምራ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደለት

ጽዮን ግርማ

ጽዮን ግርማ tsiongir@gmail.com

ጽዮን ግርማ
tsiongir@gmail.com

 

ለአብዛኛው ወጣት አዲስ አበባ ላይ ”ቅዳሜ” ትርጉም አላት። የሣምንቱን የሥራ ቀናት በየፈርጁ ያሳለፈው ኹሉም ወጣት ”ቅዳሜ”ን ደግሞ እንደየምድቡ ይውልባታል። እንደሰማኹት ከኾነ ለዞን ዘጠኝ አባላትና ጓደኞቻቸውም ቅዳሜ ልዩ ቀን ናት። ለወጣቶቹ አብሮነት የጡመራ መድረኩ ቢያግዛቸውም ከዛ በላይ ግን ጓደኝነታቸው ቤተሰባዊነትን ፈጥሮላቸው አብዛኛውን ቅዳሜ እንደየቅርበታቸው አብረው ያሳልፋሉ።

አብረው እስረኛ ይጠይቃሉ፣ የታመመን ያጽናናሉ፣ በጋራ ምሳ ይቋደሳሉ፣ የተለየ ዝግጅት ካለም አብረው ይሳተፋሉ። ከዚህ የተረፈ ጊዜ ካላቸው ደግሞ ፈጣንንና ነጻ የገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት በሚገኝበት ሆቴል ገብተው ዓለም በምን ኹኔታ ላይ እንዳለች ለመከታተል ይሞክራሉ። አገሪቷ ውስጥ ባለው ከፍተኛ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ችግር ምክንያት አብዛኛው ጋዜጠኛና ጥቂት ወጣቶች የእነዚህ ትልልቅ ሆቴሎች ገመድ አልባ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። በቅዳሜ ወደእነዚህ ሆቴሎች ጎራ ያለ ከጦማሪያኑ ወይም ከጋዜጠኛ አንድ ሰው ሊያገኝ ይችላል። በቃ ሲገናኙ ሰላም ተባብለው መቀላቀል ነው። እናም በአንድ ጉዳይ ጨዋታ ጀመራል። አብዛኛው ጨዋታ በአገር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሊኾን ይችላል። ኮምፒዩተሮቻቸውን እየነካኩ ስለ አገራቸው ግድ ያላቸውን ይነጋገራሉ፣ ይከራከራሉ አሊያም ይጨቃጨቃሉ። መሄጃው ሰዓት የደረሰበት ደግሞ ተሰናብቶ ይሄዳል። በእነዚህ ሆቴሎች በቀጠሮ የሚገናኝ ሰው የለም። ”የት ነህ? የት ነሽ?” የሚለው የስልክ ጥያቄም ለመገናኘት በቂ ነው።

የተስፋዓለም ቅዳሜ ደግሞ ሌላ ነበረች። ሥራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ አብዛኛውን አርቦች ከእነ ለሊታቸው በሥራ ያጠፋቸዋል። ቅዳሜንም ረፈድ አድርጎ ይነሳል። እናም የመጀመሪያ ሥራው ለሕትመት የበቁ ጋዜጣና መጽሔቶችን አበጥሮ ማንበብ ነው። በማንበብ ብቻም አያቆምም፤ ከዘገባዎቹ አብዛኖቹ የተሠሩት በጓደኞቹ አሊያም በሚያውቃቸው ጋዜጠኞች ስለሚኾን ስልክ ይደውላል። ከዘገባዎች ውስጥ ተስፋዓለምን የሚያስደስቱት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ሊኾኑ ስለሚችሉ የስልክ ልውውጦቹ ”እንዲህ ብታደርግ/ብታደርጊ ኖሮ፣ እንትናን ብታናግረው በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰጥህ ነበር፣ እዚህ ቦታ እኮ እንዲህ ዓይነት መረጃ ነበር፣ ይሄ እኮ ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ሕትመት ላይ ወጥቷል፣ እውነቱን ለመናገር ይሄ ለሕትመት የሚበቃ ዘገባ ነው ብዬ አላምንም” በሚሉ አስተያየቶች የተሞሉ ነበሩ። በዚያው ልክ ደግሞ የሚያስደስተውን ዘገባ ሲያነብ ወይም ፕሮግራም ሲሰማ አዘጋጁን አወቀው አላወቀው ስልክ አፈላልጎ በመደወል ያበረታታል። የተስፋዓለም ግማሽ ቅዳሜ የምታልቀው ይህን ሲያደርግ ነው።

አኹን እነዚህ ወጣቶች ቅዳሜያቸውን በፌደራል ወንጀል ምርመራ መምሪያ (ማዕከላዊ) ፖሊስ ተነጥቀዋል። ሃምሳ ቀናት ታስረው ዘጠኝ ቅዳሜን አጥተዋል። እንዳሻቸው የሚያደርጓትን ቅዳሜ አኹን እነርሱ አያዙባትም። ከጠዋቱ ዐስራ ሁለት ሰዓት ሲል ከእንቅልፋቸው ይቀሰቀሳሉ። ለቁርስ ዳቦ በሻይ ይሰጣቸዋል። (ቤተሰብ የሚያወስድላቸው ምግብ ቁርስ ከበሉ በኋላ ነው የሚደርሳቸው) እናም ተመልሰው ገብተው ይዘጋባቸዋል። አብዛኞቹ ለየብቻ ከሌሎች እስረኛ ጋር የታሰሩ ሲኾን ሁለት፣ ሁለት ተደርገው የታሰሩም አሉ። እናም ከምርመራ የተረፈ ቀናቸውን በዝጉና በጨለምተኛው ክፍል ያሳልፋሉ። በአንዷ ቅዳሜ ደግሞ እንደዛሬው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

አንዷን ቅዳሜ – በፍርድ ቤት

ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም.፤ ሦስቱ ወጣቶቹ እነርሱ በማያዙባት ቅዳሜ እጆቻቸውን በካቴና ታስረው ፒያሳ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ግቢ ውስጥ ሲደርሱ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ቁጥር ያለው በዐይን ግምት ሦስት መቶ የሚደርስ ችሎት ተከታታይ በግቢ ውስጥ ተገኝቶ ነበር። የዛሬዎቹ ጠባቂ የፌደራል ፖሊሶች ባለፈው ጊዜ ከነበሩት ሻል ያሉ ስለነበሩ ቤተሰቦች ችሎት ውስጥ ገብተው እንዲታደሙ ባይፈቀድላቸውም ግቢ ውስጥ ከመቆም የከለከላቸው ወይም ያመናጨቃቸው አልነበረም።

ከጠዋቱ አራት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ አካባቢ ሲኾን ችሎቱ በሴት ዳኛ በመሰየሙ፤ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎቹ ናትናኤል ፈለቀ እና አጥናፉ ብርሃነ እጃቸውን በሰንሰለት እንደታሰሩ ወደ ግቢው ገቡ። ዛሬ ወጣቶቹ በስስ ፈገግታ ”አይዞአችሁ ደህና ነን” የሚል የተስፋ ምልክት ለቤሰተቦቻቸውና ለጓደኞቻቸው አሳይተዋል። ከእነርሱ ቀጥለው በፖሊስ ታጅበው የገቡት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና የሕግ መምሕርና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘለዓለም ክብረት እጆቻቸው በካቴና እንደታሰረ ለቤተሰቦቻቸው ሰላምታን ሰጥተዋል። የእነርሱ ፈገግተኛ መኾን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለጓደኞቻቸውና ለወዳጆቻቸው ጥቂትም ቢኾን እፎይታን ሰጥቷል።

ተጠርጣሪዎቹ ችሎት የቀረቡት እንደወትሮው ኹሉ በሁለት መዝገብ ተከፍለው ቢኾንም ፖሊስ ያቀረበው ምክንያትና መከራከሪያ አንድ ዓይነት ነበር። ችሎቱ ከተሰየመ በኋላ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ቀጠሮ በርካታ ጉዳዮችን ሲመረምር መቆየቱንና አሁንም ያልተጠናቀቀ ምርመራ ስለሚቀረው ተጨማሪ ሃያ ስምንት ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል።

ጠበቃው አቶ አመሐ፤ ”ፖሊስ ከዚህ ቀደም በወሰደው ጊዜ ቀጠሮ ሰነድ ለማስተርጎም፣ የምስክሮችን ቃል ለመቀበል፣ ኢሜሎቻቸውን ለመፈተሽ እንዲሁም ያልተያዙ ግብረአበሮቻቸውን ለመያዝ ብሎ እንደነበርና አሁን ዝም ብሎ በጥቅሉ በርካታ ሥራዎችን ሠርቼያለሁ እንደገና ይጨመርልኝ ማለቱ አግባብ አይደለም” ሲሉ አመልክተው ነበር። ዳኛዋ ፖሊስ የሠራውን ሥራና የሚቀረውን ምርምራ እንዲያስረዳ በማዘዛቸው፣ ”ከሠራናቸው በርካታ የምርመራ ሥራዎች መካከል የተባባሪዎቻቸውን ቤት ፈትሸናል፣ ለተለያዩ ባንኮች የተጠርጣሪዎቹን ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን ጠይቀን ከተወሰኑት ምላሽ አግኝተናል፣ የተወሱ ምስክሮችን ቃል ተቀብለናል፣ ከትርጉም ሥራውም የተወሰነውን ሠርተናል። ግብረአበሮቻቸው ወደ ክፍለ ሃገርና ወደ ተለያዩ አገራት እየሸሹ መያዝ ስለተቸገርን የፖሊስ ኃይል አሰማርተን እያፈለግናቸው ነው እነርሱንም መያዝ ይቀረናል።” በማለት ተናግሯል።

አቶ አመሐ በበኩላቸው፤ ”ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ ሃምሳ ቀናት ሞልቶታል። እነዚህ የሚላቸውን ነገሮች አጠናቆ ለመጨረስ የነበረው ጊዜ ከበቂ በላይ ነው። አሁንም ቢኾን እነዚህን ምርመራዎች ለማድረግ ደንበኞቼን አስሮ ማስቀመጥ አስፈላጊ አይደለም፤ ስለዚህም ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቻውን ሊያከብርላቸው ይገባል። ይህን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ባይቀበለው እንኳን ከዚህ በኋላ ፖሊስ በሚሰጠው ሃያ ስምንት ቀናት ጊዜ ውስጥ ምርመራውን አጠናቆ እንዲመጣ፤ አጠናቆ ባይመጣ ደግሞ ጥያቄው ተቀባይነት እንደማይኖረው ተደርጎ ይመዝገብልን” በማለት ጠይቀዋል።

ዳኛዋ አቤቱታውን ካደመጡ በኋላ፤ ፖሊስ ከዚህ በኋላ ሲቀርብ ለተጨማሪ የምርመራ ቀነ ቀጠሮ መጠየቂያ አሁን የጠቀሳቸውን ምክንያቶች በምክንያትነት ይዞ እንዳይቀርብ በማሳሰብ የጠየቀውን የሃያ ስምንት ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፈቅደዋል።

በዛሬው ዕለት ችሎት ከቀረቡት መካከል ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፤ ከፍተኛ የኾነ የጀርባ ሕመም ስላለበት ወንበር እንዲገባለት መጠየቁንና እስካኹን ሊገባለት እንዳልቻለ ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት አመልክቷል። ዳኛዋ ከምንም ነገር በላይ የጤና ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ በማሳሰብ የጠየቀው ወንበር እንዲገባለት ሲሉ ተናግረዋል። በችሎት የተገኘው መርማሪ ፖሊስ፤ ”በአጋጣሚ የእርሱ መርማሪ እኔ ነኝ የጀርባ ሕመም እንዳለበት ነግሮኛል። ወንበር እንዲገባለት ግን አልጠየቀኝም። አሁንም ቢኾን ይህ በጣም ቀላልና እዛው እኛው ጋር ሊያልቅ የሚችል ነገር ነው። ችግር የለም እናስገባለታለን” ሲል ቃሉን ሰጥቷል።

እስረኞቹ ከችሎት ሲወጡ እንደ አገባባቸው በፈገግታ ሰላምታ እየሰጡ ሲኾን፤ ችሎቱን ለመከታተል መጥቶ ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ የቆመው ሰውም እጁን በማውለብለብ ተሰናብቷቸዋል።

“የትኛውም የሥራ ፈጠራ የሚመነጨው ከችግር ነው” –ከፎርጂዱ ዶ/ር ኢ/ር ሳሙኤል ዘሚካኤል ጋር የተደረገ ቃለምልልስ

$
0
0

የሰሞኑ አነጋጋሪ ሰው ፎርጂዱ ዶ/ር ኢ/ር ሳሙኤል ዘሚካኤል በአንድ ወቅት አድርጎት የነበረው ቃለምልልስ ስለግለሰቡ ግንዛቤ ይሰጣችኋል።

የዛሬ 35 ዓመት አንድ ሕፃን ከድሃ ቤተሰብ በጋንዲ ሆስፒታል ተወለደ፡፡ ያ ሕፃን ከተቀሩት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት የተለየ ችሎታ አልነበረውም፡፡ ቤተሰቦቹ ድሃ ስለነበሩ በእንክብካቤና በቅምጥል አላደገም፡፡ አባቱን አያውቃቸውም፡፡ የአምስት ወር ህፃን ሳለ ነው በሞት የተለዩት፡፡
ገና በወጣትነት ዕድሜ የትዳር አጋርን በሞት መነጠቅ ከባድ ፈተና መሆኑን መገመት አያዳግትም፡፡ ልጆቻቸውን የማሳደግና ቤተሰቡን የማስተዳደር ሸክም እናቱ ትከሻ ላይ ወደቀ፡፡ ኑሮና ብቸኝነቱን መቋቋም የከበዳቸው እናቱ፤ ሕፃኑ ሁለት ዓመት ሲሞላው “ከአንድ፣ ሁለት መሆን ሳይሻል አይቀርም” በማለት ባል አገቡ፡፡ አዲሱ ባላቸውም አላሳፈሯቸውም፡፡ ልጆቻቸውን፣ እንደ “እንጀራ አባት” ሳይሆን ከስጋ ልጆቻቸው እኩል ተንከባክበው አሳደጓቸው፡፡
ያ ከድሃ ቤተሰብ የተወለደው ሕፃን፤ በእልህ አስጨራሽ ትግልና ጥረት፣ በከፍተኛ የእውቀት ፍቅርና ትጋት ድህነትን ድል ነስቶ፣ ከራሱ አልፎ ለሌሎች ለመትረፍ በቃ፡፡ የድሃ ወንድም እህቶቹ መመኪያና መኩሪያ ሆነ፡፡ በአሁኑ ሰዓት 13 ወላጅ አልባ ህፃናትን እያሳደገ ያስተምራል፡፡ በተለያዩ ችግሮች የተነሳ የከፍተኛ ተቋም ትምህርታቸውን ሊያቋርጡ የደረሱ በርካታ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በገንዘብ በመደገፍ፣ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ አድርጓል፡፡
ዶ/ር ኢ/ር ሳሙኤል ዘሚካኤል በሙያው መሃንዲስ ነው፡፡ በ1995 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቴክኖሎጂ ፋኩልቲ የትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪውን በሲቪል ኢንጂነሪንግ አገኘ፡፡ ሁለተኛ ዲግሪውን በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት በ2000 ዓ.ም ከአውስትራሊያ ካምቢራ ዩኒቨርሲቲ፣ ሦስተኛ (ዶክትሬት) ዲግሪውን ደግሞ በአርባን ፕላኒንግ በቅርቡ ከአሜሪካ ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ መቀበሉንና ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንደተሰጠው ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም “ላይፍ ኮች ኤንድ ሞቲቬሽን ስፒከር” (የሕይወት ጥበብ አሠልጣኝና የሚያነቃቁ ንግግሮች አቅራቢነት) ሥልጠናዎችን በመውሰድ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ (ቢኤ) እንዳለውና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመዘዋወር ስለምህንድስና ትምህርት እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡
የአዲስ አድማሱ መንግሥቱ አበበ ከዶ/ር ኢ/ር ሳሙኤል ዘሚካኤል ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ እንድታነቡ ተጋብዛችኋል፡፡
eng samuel z
ከዩኒቨርሲቲ እንደተመረቅህ የት ነበር ሥራ የጀመርከው?

በጥሩ ውጤት ስለተመረቅሁ የመጀመሪያው ሥራዬ በዩኒቨርሲቲው ቀርቼ ማስተማር ነበር፡፡ ሁለተኛ ሥራዬ በአዲስ አበባ መስተዳድር የመሬትና ግንባታ ጉዳዮችን ማማከር ነበር፡፡ ዎርልድ ቪዥን በተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት፣ በኢንቨስትመንት ቢሮና በተለያዩ ተቋማትም ሠርቻለሁ፡፡

ከመንግሥት ሥራ የለቀከው ለምንድነው?

የመንግሥት ሥራ የለቀኩት በ1998 ዓ.ም ነበር፡፡ ምክንያቴ ደግሞ ሰነፍ ሆኜ ወይም በሌላ ምክንያት ሳይሆን የራሴን ሥራ ለመጀመር ነው፡፡

ያኔ ደሞዝህ ስንት ነበር? የጀመርከውስ ሥራ ምን ነበር?

ከቅጥር ስወጣ ደሞዜ 22ሺ ብር ነበር፡፡ ሥራ የለቀኩት፣ ደሞዝ አነሰኝ ብዬ ሳይሆን፣ በቀሰምኩት እውቀት የራሴን ሥራ ለመጀመር አስቤ ነው፡፡
አፍሪካን ቪዥነሪስ ዴቨሎፕመት ኩባንያን ከጓደኛዬ ጋር በአንድ ሚሊዮን ብር ካፒታል አቋቋምን፡፡ ለሁለት እናቋቁም እንጂ ገንዘቡ የእኔ ነበር፡፡ ይህንን ኩባንያ የመሠረትኩት፣ ራሴን እንደ አፍሪካዊ ባለራዕይ ስለምቆጥር፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ እኔ ካለፍኩ በኋላ የማይቆም (የማይቋረጥ) ኩባንያ እንዲሆን ስለፈለግሁ ነው፡፡ ብዙ ድርጅቶች ባለቤቱ ሲሞት ሕልውናቸው ያቆማል፡፡ የእኔ እንደዚያ እንዲሆን አልፈለግሁም፡፡

ኩባንያው ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን ነው የፈለግኸው?

አዎ! እዚህ በመዲናችን ሂልተን ሆቴል አለ፡፡ በመላው ዓለም በተመሳሳይ ስም የሚጠሩ በርካታ ሂልተን ሆቴሎች አሉ፡፡ ማክዶናልድ፣ በአንድ ሱቅ ነው የጀመረው፡፡ አሁን በመላው ዓለም 36ሺ ቅርንጫፎች አሉት፡፡ ስለዚህ አፍሪካዊ መለያ (ብራንድ) ያለው፣ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች እየተስፋፋ የሚሄድ፣ አፍሪካውያን የግዙፍ ኩባንያ ባለቤት የመሆን አቅም እንዳላቸው የሚያመለክት ድርጅት እንዲሆን በማሰብ የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

ተሳካልህ ታዲያ? ኩባንያህ አሁን ምን ላይ ደርሷል?

አዎ ተሳክቶልኛል፡፡ ከጠበኩት ፍጥነት በላይ እየተጓዘ ነው፡፡ የቱንም ያህል አድካሚ ቢሆንም ውጤታማ እየሆነ ይገኛል፡፡ እኔ ከተለያዩ ባንኮች ጋር ነው የምሰራው፡፡ መንግስት የቀረፃቸውን አሰሪ ፖሊሲዎች በመጠቀም በስፋት እየተንቀሳቀስኩ ነው፡፡ በነገራችን ላይ በርካታ ብልህ ሰዎች አንድን ስራ ለመስራት ከባንክ ጋር በጥምረት ይሰራሉ፡፡ እኔም ይንንን የስኬታማ ሰዎች መርህን ነው የምከተለው፡፡ ለምሳሌ በአገራችን ኢኮኖሚ ትልቁን ሚና እየተጫወተ የሚገኘው ደርባን ሲሚንቶ ከ360 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጥቶበታል፡፡ ከዚህ ውስጥ ባለሀብቱ ያወጡት 60 ሚሊዮን ዶላሩን ሲሆን ቀሪውን 300 ሚሊዮን ዶላር ግን ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና ከሌላ የፋይናንስ ተቋም ነው ያገኙት፡፡ እንደሚታወቀው ባለቤቱ የአለማችን ቢሊየነር ናቸው፡፡ ግን ይህንን የብልሆች መርህ ይከተላሉ እንጂ ያላቸውን ገንዘብ ሁሉ አንድ ፕሮጀክት ላይ አላዋሉም፡፡ እኔም እንደ አቅሚቲ የተከተልኩት ይህንን አለም አቀፍ የኢንተርፕረነሮች መርህን ነው፡፡
የዚሁ ኩባንያ አካል የሆነ የአፍሪካ ቪአይፒ (VIP) ክበብ ከጐረቤታችን ኤርትራና ከሰሜን አፍሪካዊቷ ሞሮኮ በስተቀር በተቀሩት የአፍሪካ አገራትና በአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ተመስርቶ በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ቀና አስተሳሰብ ያላቸው ባለራዕይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪችንና መምህራንን እያፈራ ይገኛል፡፡

አፍሪካ ቪዝነሪስ ዴቨሎፕመንት ካምፓኒ ምንድነው የሚሠራው?

ይህ ድርጅት በዋናነት ተግባሩ፣ የኮንስትራክሽን ሥራ ይሰራል፡፡ ኮፊ ላንድ ኮፊ የተሠኘ የወጪና ገቢ ንግድ ድርጅታችን፣ የኢትዮጵያን ቡና ወደ ውጭ ይልካል፡፡ ቀደም ሲል ከሌሎች አጋሮች ጋር በኢቴቪ “ባለ ራዕይ” የሚል ቶክሾው ነበረን፡፡ የሚዲያና የሞቲቬሽን ሥራዎች እንሠራለን፣ የአስጐብኚ ድርጅት አለን፡፡ ከሕንድ ኩባንያ ጋር በጆይንት ቬንቸር ጣና ሐይቅ ላይ የሪዞርት ሥራ ጀምረናል፤ በሀዋሳ ሐይቅ ላይም ሪዞርት ለመሥራት ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር የቦታ ጥናት እያደረግን ነው፡፡
ዴቨሎፕመንት ኢንስቲቲዩቱም ለተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሥልጠና ይሰጣል፡፡ ሥልጠናው በአብዛኛው በት/ቤት ከሚሰጠው የአካዳሚክ ሥልጠና የተለየ ነው፡፡ አንድ ሰው በዙሪያው ያለውንና በውስጡ የሚገኘውን እምቅ ችሎታና ኃይል እንዲያውቅ፤ እንዲፈትሽ፣ እንዲያይ፣ በውስጡ ያለውን መክሊት አውጥቶ በሚገባ እንዲጠቀም የሚያደርግ፣ ሥልጠና ነው፡፡ በአጠቃላይ አንድ ሰው ከራሱ አልፎ ለሌላው መትረፍ እንደሚችል የሚያግዙትን ሥልጠናዎች እንሰጣለን፡፡
ፍርሃታችንን እንዴት እንገራለን? የሚለው ከማኔጅመንት ሥልጠናዎች አንዱ ነው፡፡ አንዳንድ ሰው የራሱን ሥራ ለመሥራት ወስኖ ሲያበቃ፣ ያለውን ገንዘብ አውጥቶ ቢዝነስ ለመጀመር ይሰጋል፡፡ ሌላው ትዳር ለመያዝ ይፈራል፣ የተለያዩ የፍርሃት መንገዶች አሉ፡፡ ፍርሃት በተወሰነ ደረጃ ሲሆን መጥፎ አይደለም፤ ለጥንቃቄ ይረዳል፡፡ ከልክ ሲያልፍ ግን፣ እጅና እግር አሳስሮና ሽባ አድርጐ ያስቀምጣል፤ በድህነትና በችግር ታስረን እንድንኖር ያደርጋል፡፡ ይህንን ዓይነቱን ፍርሃት የሚያስወግድ ሥልጠና እንሰጣለን፡፡
ሁለተኛው ሥልጠና ሥራ ፈጠራ ወይም ኢንተርፕሪነርሺፕ ነው፡፡ ይህ ሐሳብ ብዙ ጊዜ ለበርካታ ሰዎች ግልጽ አይደለም፡፡ ሥራ መፍጠር ማለት በዙሪያችን ያሉትን ችግሮች መቅረፍ ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ አላቸው፡፡ ነገር ግን ገንዘባቸውን እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው አያውቁም፡፡ እኛ ችግራቸውን ተገንዝበን መፍትሔውን ከፈጠርንላቸውና ካሳየናቸው በገንዘባቸው ይገዙናል፤ እኛም በገንዘቡ እንጠቀማለን፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ችግር አለ ወይ? አዎ በሽበሽ ነው፤ ሞልቷል፡፡ ሥራ ለመፍጠር ዕድሎች አሉ ወይ? አዎ በጣም ሞልተዋል፡፡ ሥራ መፍጠር ማለት ይህ ነው፡፡
በነገራችን ላይ ትልልቅ ሕልም ያላቸው ሰዎች፣ ችግሮችን ከማማረር ይልቅ አንዳች ፈታኝ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው መፍትሔውን ወደመፈለግ ይሄዳሉ፡፡ ይህም አዲስና ሌላ ተጨማሪ የስራ እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ የትኛውም የሥራ ፈጠራና መፍትሔ የሚመነጨው ከችግር ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው፣ ወደዚህች ዓለም ሲመጣ፣ ችግር መፍቻ መክሊት ወይም መፍትሔ ይዞ ነው የሚመጣው፡፡

ቢል ጌት እንኳን ተወለደ – እሱ በመወለዱ የማይክሮሶፍት ሶፍትዌርን ማግኘት ቻልን!
ስቲቭ ጆብስ እንኳን ተወለደ – እሱ በመወለዱ የአይፎንን ምርቶች ማግኘት ችለናል!
ኼነሪ ፎርድ እንኳን ተወለደ – የሰውን ድካም የሚቀንስ መኪና ፈጥሯልና!
የራይት ብራዘርስ ወንድማማቾች እንኳን ተወለዱ – የእነሱ መምጣት፣ ከአንዱ የዓለም ጥግ ወደ ሌላው የምናደርገውን ጉዞ አሳጥሮልናልና!

የሕክምና የፈጠራ ሰዎች እንኳን ተወለዱ – በእነሱ መወለድ፣ ብዙ ሰዎች ከሕመምና ስቃይ ፈውስ አግኝተዋልና!

አንተ እንኳን ተወለድክ – ሰዎችን የሚያነቃቁ መረጃዎችን በጋዜጣችሁ በማውጣት፣ እኔን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ቅዳሜ ቅዳሜ አዲስ አድማስን በናፍቆት እንድንጠብቅ አድርገሃልና!…

እኔ የቱንም ያህል ብማር፣ ከማውቀው ይልቅ የማላውቀው፣ ከደረስኩበት ይልቅ ያልደረስኩበት፣ ከገባኝና ከተረዳሁት ይልቅ ያልገባኝ ይበልጣል፡፡ ምናልባት ኢንጂነር የሚለው ማዕረግ አብሮኝ ስላለ፣ አንዳንዶች ያወቅሁ፣ የተረዳሁ የጨረስኩ ሊመስላቸው ይችላል፡፡ የኢንጂነሪንግ ትምህርት 104 ዘርፎች አሉት፡፡ ቴክስታይል፣ ሌዘር፣ ኬሚካል፣ ዎተር፣ ረዚደንስ፣ ኃይዌይ ወዘተ…ኢንጂነሪንግ የተባሉ ብዙ ዘርፎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ እኔ የማውቀው አንዱን ቁንፅል ዘርፍ ነው – ሲቪል ኢንጂሪንግን፡፡

የበለጠ ለማወቅ ብዙ መረጃዎች መሰብሰብና ማንበብ አለብኝ፡፡ ስለዚህ የእናንተንም ጋዜጣ አነብባለሁ፣ ምክንያቱም አንተ የምታቀርበው የስኬታማ ሰዎች ታሪክ በጣም ያነቃቃኛል፡፡ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችን በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ ትምህርታችን የምንቀስመው እውቀት 20 በመቶ ነው፡፡ ቀሪውን እውቀት የምንማረው ከሌላ የሕይወት መስክ ነው፡፡ ት/ቤት ገብቶ መማር ጥሩ ነው፡፡ ግን በቂ አይደለም፡፡ ሁል ጊዜ ባለን ላይ መጨመርና ዘወትር ራስን ከዘመኑ እውቀት ጋር ማስማማት (አፕዴት ማድረግ) ያስፈልጋል፡፡ ሙሉ ሰው መሆን የምትችለው ያኔ ነው፡፡ አንተም እንኳን ተወለድክ ያልኩት፣ ሙሉ ሰው ለመሆን ስለረዳኸኝ ነው፡፡

ሥራ እንድንፈጥር የሚያደርገን ቀና አስተሳሰብ (ፖዘቲቭ ቲንኪንግ) ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች “ኢትዮጵያ ውስጥ ከምወለድ፣ አሜሪካ ውስጥ እንስሳ፣ ዛፍ፣…ሆኜ ብወለድ ይሻል ነበር፡፡ እዚያ እንስሳው ይከበራል፣ ዛፉም እንክብካቤ ያገኛል፡፡ እዚህ ግን…” በማለት ያማርራሉ፡፡ እዚህ ያለውን እውነት መቀበል ይቸግራቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ሰው ከመንግስት ይጠብቃል፡፡ ለእኔ ከመንግስት በፊት የሚቀርበኝ አንድ ሰው አለ፡፡ ያም ሰው እኔ ነኝ፡፡ ቀና አስተሳሰብ የምንለው እንዲህ ዓይነት አመለካከት እንዲኖረን የሚያደርግ ነው፡፡

ብዙ ሰው ራዕይ (ቪዥን) የለውም፡፡ ከአምስት ዓመት በኋላ የት እንደሚደርስ አያውቅም፡፡ የዛሬ ዓመት ምን ያህል ገቢ እንደሚኖረው አይረዳም፡፡ ዝም ብሎ በዘልማድ እየኖረ ይመሻል ይነጋል፡፡ የብዙዎቹ ኑሮ ተመሳሳይ ነው፡፡ ለአቅመ አዳም ወይም ለአቅመ ሔዋን መድረስ፣ ከዚያም ማግባት፣ የተገኘውን መስራት፣ ልጅ መውለድ፣ ሲሞቱ በዕድርተኞች ተሸኝቶ መቀበር ነው፡፡ ብዙ መስራትና ታሪክ መፍጠር እየቻለ የዚህ ዓይነት ተራ ህይወት ኖሮ እስከወዲያኛው የሚያሸልበው ሰው በርካታ ነው፡፡ እኔ ሳልፍ ግን ዕድር አያስፈልገኝም፡፡ ምክንያቱም በመሰረትኳቸው ድርጅቶች ውስጥ የተቀጠሩ ብዙ ሺ ሰራተኞች ወጥተው ይሸኙኛል፡፡ የማከናውናቸው ስራዎችም ብዙ አድናቂዎችና ወዳጆች ስለሚፈጥሩልኝ ወደ ማይቀረው ቤቴ የማደርገው ጉዞ አያሳስበኝም፡፡

አንዳንድ ሰዎች ሺ ዓመት ላልኖር ምን ያስጨንቀኛል? ይላሉ፡፡ ግን ከፈለጉ መኖር ይችላሉ፡፡ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ ላሊበላ ለብዙ መቶ ዓመታት እየኖረ ነው፡፡ ንጉሥ ላሊበላ በሌለበት ዘመን እኛ ስለላሊበላ እያወራን ነው፡፡ አክሱማውያን ስላቆሙት ሐውልት አሁንም እያወራን ነው፡፡ ስለውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ ስለአብርሃ ወአፅብሃ፣ ስለሶፍ ዑመር፣ ዛሬም ይወራል፡፡ እነዚህን ድንቅ የስልጣኔ ናሙናዎች የሰሩ ጠበብቶች ስማቸው ከመቃብር በላይ እየተነሳ ነው፡፡ ለእኔ ሺ ዓመት መኖር ማለት ይሔ ነው፡፡ እንግዲህ ሺ ዓመት መኖርን የሚያስቡ ዜጎችን ለመፍጠር ነው 52 ሥልጠናዎችን የምንሰጠው፡፡

በሚዲያና በምንሰጣቸው ስልጠናዎች የሰው አእምሮ በመለወጥ፤ ስራ ወዳድና ባለራዕይ፣ ባለፈጠራና ቅን አሳቢ … ለመሆን የሚረዱ መጻህፍት ከውጭ እያስመጣን ለዩኒቨርሲቲዎችና ለተለያዩ ድርጅቶች እናከፋፍላለን፡፡
ከዚህ ውጭ በአስጎብኚ (ቱር ኤንድ ኦፕሬተር) ዘርፍ፣ ቱሪስቶችን እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ስምንት ቪ 8 መኪኖችና በስድስት ቫን መኪኖች፣ ወደተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በመውሰድ እናስጎበኛለን፡፡ በግንባታ ዘርፍም ለምንሰጠው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መሳሪያዎችና መኪኖች አሉን፡፡

በምትሰጠው የማነቃቂያ (ሞቲቬሽን) ሥልጠናና በምታደርገው ንግግር የሰው አቀባበል
እንዴት ነው?

እኔ የምሰጣቸው ስልጠናዎች፤ ሰዎች በሚገጥማቸው ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ተስፋ እንዳይቆርጡ፣ ሌላ የተሻለ ቀን ከፊታቸው እንዳለ እንዲያስቡ፣ የሚያውቋቸው ትልልቅ ስኬታማ ሰዎች ሁሉ እነሱ በነበሩበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለፉ፣ እነዚያ ስኬታማ ሰዎች ከእነሱ የሚለዩት፣ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮችን ተስፋ በማስቆረጥ፣ ጨክነው በመሻገራቸው ውጤታማ እንደሆኑ … እንዲያውቁ ነው የማደርገው፡፡

ለምሳሌ፤ ዛሬ እኔ የደረስኩበትን በማየት አንዳንድ ተማሪዎቼ እንደ እድለኛ ሊቆጥሩኝ ይችሉ ይሆናል፡፡ በእርግጥም ዕድለኛ ነኝ፡፡ ሆኖም ግን የእኔ ዕድለኛነት ከእነሱ የተለየ አይደለም፡፡ አቃቂ ከተማ ውስጥ በፈረስ ጋሪ የጠዋት ተማሪ ስሆን ከሰዓት፣ የከሠዓት ተማሪ ስሆን ጠዋት እየሰራሁ ነው የተማርኩት፡፡ ሰው ቤት በእረኝነት ተቀጥሬ ከብቶች እየጠበቅሁና እያጠብኩ፣ አዛባቸውን እየጠረግሁ አበሳ አይቼ ነው የተማርኩት፡፡ በማገኘው ገንዘብ መጻሕፍት እገዛለሁ፣ ማንበብ ያለብኝን አነብባለሁ፡፡ እንዲህ አይነት አስቸጋሪ ፈተናዎች፣ በፅናት ተቋቁሜ በማለፍ ነው ዛሬ ለደረስኩበት ደረጃ የበቃሁት፡፡ ሰው ቤት በእረኛነት ተቀጥረህ እየሰራህ የ12ኛ ክፍልን መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና መውሰድ ይከብዳል፡፡ ነገር ግን የተሻለ ጊዜ ማየት ከፈለግህና ጎዳና ላይ ከመውደቅ እነዚያን አስቸጋሪ የሆኑትን ስራዎች በማከናወን ነገ የበለጠ አስቸጋሪ የሚሆነውን ጊዜ ልትሻገር የምትችልበትን ዕድል ትፈጥራለህ፡፡

አንድ የፈረንጆች አባባል አለ፡፡ Opportunity Plus Preparation = Luck፡፡ ዝግጁነትና አጋጣሚ ሲደመሩ ነው ዕድል የሚባለው፡፡ በዚህ ቀመር መሰረት፣ ሁሉም ሰው ዕድለኛ ነው፡፡ ሥራን ሳይንቅ ለመስራት ዝግጁ ከሆነ የማያሸንፍበት ምንም ምክንያት የለም፡፡

የቀድሞውን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት የክቡር ግርማ ወ/ጊዮርጊስን የሕይወት ታሪክ በአማርኛና በእንግሊዝኛ አዘጋጅቼ እየተጠናቀቀ ነው፡፡ የእሳቸውን ታሪክ አንዳንድ ሰዎች ያውቃሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ በጣም የሚገርም ታሪክ አላቸው፡፡ 12 ዓመት የቆዩበት ኢዮቤልዩ ቤተመንግስት ሲሰራ፣ በቀን ሰራተኛነት ተቀጥረው 1.50 ማሪያ ትሬዛ እየተከፈላቸው ድንጋይ አንጥፈዋል፤ አሸዋ አቡክተዋል፡፡ ከራሳቸው አንደበት ነው የሰማሁት፡፡ ሸቀጣ ሸቀጥ ነግደዋል፣ ከገጠር ዕንቁላል እየገዙ ከተማ አምጥተው ሸጠዋል፣ አንድ ወር ጨለማ ቤት ታስረው ያውቃሉ፡፡ በአንድ ወቅት ጦር ፍርድ ቤት ቀርበው ለሞት አንድ እርምጃ ሲቀራቸው ነው የተረፉት፡፡ እኚህ የፅናት ምሳሌ የሆኑ ሰው፤ የጥቁሮች የነፃነት ዓርማ እንደሆነች የሚነገርላትና የሰው ልጅ መገኛ የሆነች አገር ርዕሰ ብሄር መሆን የቻሉት፣ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮችና ውጣ ውረዶች አልፈው ነው፡፡

እንደሳቸው ያሉ ሰዎችን የሕይወት ታሪክ ከሰማህና ካነበብክ አንተም ተመሳሳይ ችግር ሲመጣብህ፣ የእነሱ ገጠመኝ ትዝ ይልሃል፡፡ ምን ዓይነት አቅም ይሰጥሃል መሰለህ! ተስፋ ቆርጠህ ለየትኛው ጊዜዬ ነው? ብለህ እርግፍ አድርገህ እንዳትተው ያደርግሃል፡፡ ከጨከንክና መከፈል ያለበትን ዋጋ ከከፈልክ ነገ ወደተሻለ ነገር ታልፋለህ፡፡ ይህንን ነው ታሪካቸው የሚናገረው፡፡ ብዙ ትንንሽ ሰዎች’ኮ ናቸው ትልልቅ የሆኑት፡፡ ከእናቱ ማኅፀን ሀብትን፣ እውቀትን ዝናን… ይዞ የመጣ ሰው የለም፡፡

ብዙ የሚያነቃቁ መጻሕፍት ተተርጉመው ገበያ ላይ ውለዋል፡፡ እነዚያን መጻሕፍት የሚያነቡ ሰዎች እምብዛም ሲለወጡ አይታዩም፡፡ ለምን ይሆን? ከአተረጓጎም ስህተት ነው ወይስ ሌላ ምክንያት አለ?

ለዚህ ጥያቄ ብዙ መልሶች አሉ፡፡ መጻህፍቱን አንብበው ለመለወጥ የሚያቅዱ ሰዎች ለእቅዳቸው ታማኝ አይደሉም፡፡ ጠዋት በ12 ሰዓት ብትመጣ እኔን ቢሮ ታገኘኛለህ፣ ማታ በ5 ሰዓት በዚህ ስታልፍ ብታየኝ አለሁ፡፡ የጻፍኩትን መጽሐፍ እኖራለሁ፣ የምኖረውን ነገር እጽፋለሁ፡፡ የስኬት መፃህፍትን የማነበው “ጎበዝ እንባቢ ነው…” ለመባል ሳይሆን፣ ያነበብኩትን በቀጥታ ለመተግበር ነው፡፡ ሁሌም ያነበብኩትን በተግባር እኖረዋለሁ፡፡ ስለዚህ መጻሕፍት ይጠቅሙኛል ማለት ነው፡፡

አንድ ሰው ማለት፣ የተማረው ትምህርት፣ ያነበባቸው መፃህፍት፣ ከሰው ታሪኮች የቀሰማቸው እውቀቶች… ድምር ውጤት ነው፡፡ አንዳንድ ግነት የሚበዛባቸው መጽሐፍት እንዳሉ ይገባኛል፡፡ ጥቂት መጻሕፍት ሲተረጎሙ፣ የእንግሊዝኛውን ትርጉም በትክክል ላያስተላልፉ ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ የተጻፈላቸውን ዓላማና ግብ እንዲመቱ ተደርገው ነው የሚቀርቡት፡፡ ችግሩ ዘርፈ ብዙ ቢሆንም ዋናው ግን የተፃፉትን መጻሕፍት ካነበቡ በኋላ፣ ወደ ህይወት ለመተርጎም አለመድፈር፣ አለመቁረጥ፣ አለመጨከን ነው፡፡ ብዙ ሰው ሀብታም መሆን ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ሀብታሞች የሚከተሉትን የአኗኗር መርህ ለመከተል ፈቃደኛ አይደለም፡፡

የሀብታሞች መርህ ምንድነው?

ብዙ ናቸው፤ ዋነኛው ግን ቁጠባ ነው፡፡ ትንሽ ገንዘብ ሲያገኝ ለዚህም ለዚያም እየጋበዘ ካባከነ፣ ትንሽ ሳንቲም ሲይዝ ሁሉ እያማረው ካጠፋ፣ እንዴት ነው ሀብታም የሚሆነው? መቆጠብና ማጠራቀም ያስፈልጋል፡፡ አቅሙ በሚኖርበት ጊዜ በዓለማችን አለ በሚባለው ሪዞርት ውስጥ ለአንድ ሌሊት ሺ ዶላሮች ከፍለህ ማደር ትችላለህ፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ ገበሬውን ብታየው ይሞታታል እንጂ ለዘር ያስቀመጠውን እህል አይበላም፡፡ መነሻ ካፒታል ማለት ዘር ነው፡፡ ብዙ ሰዎች መነሻ የሚሆናቸውን ካፒታል ያገኙና ያጠፉታል፡፡ አንዳንዱ ፍቅረኛውን ለማስደሰት ሲል በይሉኝታ ያባክናል፣ አንዳንዱ ከልማዳዊ የኑሮ ዑደት ጋር በተያያዘ ለ40፣ ለ80፣ ለሙት ዓመት፣ ለሰርግ፣… ሊያውለው ይችላል፡፡ ልማዳዊ ባህል እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ሟችን ሲሸኙ ድሆችን መርዳት ያለ ቢሆንም፣ ያለውን ሁሉ አውጥቶ ማባከን የሃይማኖቱ ትምህርት እራሱ የማይደግፍ መሆኑን አባቶች ሲናገሩ እየሰማን ነው፡፡ እነዚህ ልማዳዊ ድርጊቶች ያለንን ጥሪት አሟጠን እንድናጠፋ፣ ጊዜያችንን እንድናባክን ያደርጉናል፡፡

ሌላው ችግር ብዙ ሰው በትንሽ ነገር ይረካል፡፡ በትንሽ ነገር መርካት አያስፈልግም፡፡ እኔ በትንሽ ነገር አልረካም፡፡ ብልጽግና፣ ትልቅነት፣ አሸናፊነት ይገባኛል፡፡ በዓላማ ነው ወደዚች ዓለም የመጣሁት፡፡ ከራሴ አልፌ ለሌሎች መትረፍ ይገባኛል… ብዬ ውስጤን አሳምኜዋለሁ፡፡ የእኔ ወላጆች እንዲህ አምነው ቢሰሩ ኖሮ፣ ያሳለፍኩት ውጣ ውረድ አይገጥመኝም ነበር፡፡ በእኔ የትውልድ ሃረግ፣ ከአሁን በኋላ ድህነት እንደማይኖር እርግጠኛ ነኝ፡፡ አንደኛ ልጆች ስወልድ አባካኝ እንዳይሆኑና የስራ ሰው እንዲሆኑ ኮትኩቼ ነው የማሳድገው፡፡ ሁለተኛ፤ አባት ያቆየላቸውንና ሕይወታቸውን የሚለውጡበት ዘር ወይም እርሾ ያገኛሉ፡፡ የብዙዎቹ ሰዎች ችግር ይህንን አለማግኘት ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡

አዋዋልም ወሳኝ ነው፡፡ የአገሬ ሰዎች “አዋዋልህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ” የሚል አባባል አላቸው፡፡ እኔ ሕይወትን በትግል ካሸነፉ ሰዎች ጋር እንጂ አሉታዊ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር አልውልም፡፡ ምክንያቱም እምነቴን፣ ራዕዬንና ዕቅዴን እንዲያበላሹብኝ አልፈልግም፡፡ ሰው ውሎውን ነው የሚመስለው፡፡ እኔ የምውላቸው ሰዎች በአንድ የልብስ ስፌት መኪና ተነስተው ከ3ሺ ሰራተኛ በላይ መቅጠር ከቻሉ የጋርመንት፣ ሪልእስቴትና የሆቴል ባለቤቶች ጋር ነው፡፡ ከጣራ ጠጋኝነትና ከቀለም ቀቢነት ተነስተው ለ6,200 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ከቻሉ ሰው ጋር ነው የምውለው፡፡ ድሮ አንድ ጫማ እንደቡታጋዝ ክሮቹን እየቀየሩ ሶስት ዓመት ያደርጉ የነበሩ ሰው፣ በሚሊዮን ብሮች አምረው በተሰሩ ቤቶች ውስጥ ከሚኖሩ፣ ሶስትና አራት ሚሊዮን ብር ታክስ የሚከፈልባቸው መኪኖች ከሚያሽከረክሩ ሰዎች ጋር ነው የምውለው፡፡ አብሬአቸው ስውል የየዕለቱን የስራ ዲሲፒሊን፣ የገንዘብ አጠቃቀማቸውን፣ የሰራተኛ አያያዛቸውን፤… ዩኒቨርሲቲ ከምማረው በላይ ከእነሱ በቀጥታ የምቀስመው ነገር አለ ማለት ነው፡፡

እነዚህ ሰዎች ዛሬም ድረስ ተግተው የሚሰሩት ራዕያቸውን ለማስፈጸም እንጂ ለምግባቸውና ለልብሳቸው አይደለም፤ ለዚያማ ያላቸው በቂ ነው፡፡ ነገር ግን እንቅልፍ የማያስወስድ ራዕይ አላቸው፡፡ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የመትረፍ ሕልም አላቸው፡፡ ይህ ራዕይ፣ የእኔም ራዕይ ነው፡፡ ለእንጀራና ለምግብ ቢሆን፣ ስራ ለቅቄ ስወጣ የወር ደሞዜ 22ሺ ብር ነበር፡፡ እኔን በምቾት ለማኖር በቂ ነበር፡፡ ከስራ ስወጣ የከፈልኩት ዋጋ አለ፡፡ የተሰጠኝ መኪና ነበረኝ፤ ያንን ትቼ ታክሲ መጋፋት ጀመርኩ፣ ዝናብ ደብድቦኝ እቤት ስገባ ራዕዬ ያልታያቸው፣ ህልሜ ያልገባቸው እናት፣ እህትና ጉረቤቶቼ “እሰይ ይበልህ! ድሎት አስጠልቶህ የመረጥከው ሕይወት ነው፤…” ይሉኝ ነበር፡፡ ያኔ “ተሳሳትኩ እንዴ? ተመልሼ ልግባ?” የሚል ሃሳብ አልመጣልኝም ግን በውስጥህ የሚንቦገቦገው ህልም፣ ከፊት ለፊትህ የታየህን ራዕይ ለመጨበጥ እንድትቆርጥ፣ እንድትጨክን ያደርግሃል፡፡

ራዕይ እንዴት ይገለፃል?

ራዕይ ለሌሎች የማይታይ ነገር ማየት ማለት ነው፡፡ አዎ ለሌሎች የማይታየው ላንተ ቁልጭ ብሎ ይታይሃል፡፡

ኼነሪ ፎርድ፤ ዘመዶቹ፣ አክስት፣ አጎትና ጎረቤቶቹ፣…. በቅሎ፣ ፈረስ፣ አህያ… ሲጠቀሙ እሱ ዘመዶቹ ያልታያቸው መኪና ነበር የታየው፡፡ ይህ ነው ራዕይ፤ ሌሎች አይቻልም ያሉትን ይቻላል ብሎ ማድረግ፣ ሌሎች አይቻልም ብለው ፈርተው ያፈገፈጉበትን ይቻላል ማለት፣ ደፍሮ መግባት… ማለት ነው ራዕይ፡፡

ራዕይን በተመለከተ እኔ የምጠቀምበት አንድ መርህ አለኝ “ራዕይ ማለት የሚታትሩለት ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሚሞቱለት ጭምር ነው” የሚል፡፡ ልትሞትለት የተዘጋጀህለትን ራዕይ ለማሳካት እንቅልፍ ብታጣ ትልቅ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ልትሞትለት’ኮ ተዘጋጅተሃል፡፡ ለመሞት የተዘጋጀህለትን ለማሳካት በምታደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገጥምህ ውጣ ውረድ ከሞት ስለማይበልጥ፣ ችግሮቹን መቋቋምና መጋፈጥ አይከብድም፡፡

ራዕይን ለማሳካት መንገዱ ሁሉ አልጋ በአልጋ አይደለም፡፡ ሕይወት ራሱ’ኮ ያስተምረናል፡፡ ስንወለድ በእናታችን እቅፍ ውስጥ ነበርን፡፡ ከዚያ ዳዴ ማለት ብንጀምርም ወዲያው መራመድ አልቻልንም፡፡ ጠረጴዛ ይዘን እየወደቅንና እየተነሳን ደግሞ እየቆምን፣ የእናትን እጅ ይዘን እየተራመድንና እየወደቅን፣ በኋላ ደግሞ እየጠነከርን፣ …. ነው ያደግነው፡፡ እኔ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የማውቃቸው ስኬታማ ትልልቅ ሰዎች በሙሉ ያልወደቁ አይደሉም፤ ወድቀው የተነሱ ናቸው፡፡ ያልተፈተኑ አይደሉም፤ እንደወርቅ በእሳት ውስጥ አልፈው ተፈትነው ነጥረው የወጡ ናቸው፡፡ እጅህ ላይ ያለውን ወርቅ፤ “ምን ሆነህ ነው እንዲህ ያማረብህ? ዋጋህስ ከሌሎች ማእድናት ውድ የሆነው ለምንድነው?” ብለህ ብትጠይቀው “በእሳት ውስጥ ተፈትኜ ስላለፍኩ ነው” ይልሃል፡፡ በፈተና ውስጥ ማለፍ ዋጋ ይጨምራል ማለት ነው፡፡

ራዕይህን እንዳታሳካ አንዳንድ ነገሮች ሊያዘገዩህ ይችላሉ፡፡ የተወሰነ ወቅት ላይ ለስራ የማያመቹ ፖሊሲዎች፣ የብድር ማጣት፣ ሰው ሰራሽ አደጋዎች፣ የፋይናንስ እጥረት… ሊያዘገዩህ ይችላሉ፡፡ ወዲው መፍትሄ ስለምትፈልግለት ከግብህ ግን ሊያስቀሩህ አይችሉም፡፡ ይህንን ነገር ነው እንግዲህ ለተማሪዎቻችን የምንነግረው፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ከ32 ዩኒቨርሲቲዎች በ27ቱ ከአንድ እስከ ሶስት ሳምንታት፣ ለዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ ለመምህራን፣ ለአስተዳደር ሰራተኞችና ለተማሪዎች ያለምንም ክፍያ ሥልጠና ሰጥቻለሁ፡፡ እውቀቴን በጂዲፒ ፕሮግራሙ በማካፈል፣ የዜግነት ድርሻዬን በመወጣት ጥሩ ምሳሌ መሆን እፈልጋለሁ፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ ሰዓት ኬንያ በሚገኘው ናይሮቢ ናሽናል ኤይር ወይስ አምስት መቶ አርባ ሺህ ብር ከፍዬ የፓይለቲንግ ትምህርት እየተማርኩ ነው፡፡ ሳጠናቀቅ የግል ጀት የማብረሪያ ላይሰንስ (ፈቃድ) ይኖረኛል፡፡ በቀጣይም የግል ጀት እንደሚኖረኝ አምናለሁ፡፡ አየህ በዚህ ሁሉ ለተማሪዎቼ ምሳሌ ለመሆን እየጣርኩ ነው፡፡

በዚህ ስልጠና አንዳንድ ፈታኝ ሁኔታዎች ገጥሟቸው ትምህርታቸው ሊያቋርጡ የደረሱ ተማሪች፣ ለካንስ እንዲህ ነው ወይ? ብለው ጨክነው እንዲማሩ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ አይነት በየዩኒቨርሲቲዎቹ የአፍሪካ ቪአይፒ ክለብ አቋቁሜአለሁ፡፡ ይኼ የአፍሪካ ባለራዕዮች ክለብ ነው፡፡ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት አንድ ሚሊዮን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለማፍራት እየሰራሁ ነው፡፡

ተማሪዎቼ ራሳቸውን በጣም አስፈላጊ ሰው አድርገው ነው የሚቆጥሩት፡፡ ከተመረቁ በኋላ እንደ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ባለቤት እንደ አቶ ሳሙኤል 6,200 ሰራተኞች፣ እንደግሪን ኮፊ ባለቤት እንደ አቶ ታደለ አብርሃ 13ሺ ሰራተኞች፣ እንደ ኖክ ኩባንያ ስራ አስፈፃሚ እንደ አቶ ታደሰ ካሳና በአጋሮቻቸው እንደተቋቋመው የንግድ ድርጅት 15ሺ ሠራተኛ… መቅጠር ባይችሉም፣ እያንዳንዳቸው 100 ሰው መቅጠር ቢችሉ፣ ከ19 ዓመት በኋላ የእኔ ተማሪዎች ለ70 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ፡፡ ስለዚህ፣ አሁን ወገኖቼ ወደ ሱዳን የሚሰደዱባቸው መንገዶች፣ ሌሎች በመኪኖች ተሳፍረው ለስራ ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡባቸው ጎዳናዎች ይሆናሉ፡፡ ይህ ነው ራዕይና ግቤ፡፡ ይህ ምኞች ሳይሆን ራዕይ ነው፡፡ በምኞትና በራዕይ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ ራዕይ የሚታይና የሚጨበጥ እውነት ነው፡፡
አፍሪካ ቪዥነሪስ ዴቨሎፕመንት ካምፓኒ በአሁኑ ወቅት ለ144 ቋሚ ሰራተኞች ለ 122 ጊዜያዊ ሰራተኞች በአጠቃላይ ለ 246 ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ ካፒታሉም ወደ መቶ ሚሊየን ብር እየተጠጋ ይገኛል፡፡ በቀጣይም በሌሎች ዘርፎች ለመሰማራት እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፡፡
ዶ/ር ኢ/ር ሳሙኤል ለዛሬው ማንነቱ ያበቁት ሰዎች ባለውለታዬ ናቸው ይላል፡፡ የመጀመሪያዋ ድሃም ቢሆኑ ከልጅነት አንስቶ ጥሩ ሰብእና እንዲኖረው በስነ ምግባር ቀርፀው ያሳደጉትን እናቱን ወ/ሮ እኔቱ ወርቅነህ ናቸው፡፡ የእንጀራ ልጅ ነው ሳይሉ እንደወለዱት ልጅ ያሳደጉትን 12ኛ ክፍል ወድቆ ዝዋይ ሄዶ ሲማር ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉለትን ለአባቱ ለአቶ ዘሚካኤል ኃ/ኢየሱስ ከፍተኛ አክብሮት እንዳለው ገልጿል፡፡ በሮል ሞዴልነት ለቀረፀው ለኢ/ር ኤርሚያስ አሰፋና ነገሮችን ሁሉ ላሳካለት ለእግዚአብሔር ከፍ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
መቅድም

ከሁሉ በማስቀደም ይህንን መፅሐፍ ማዘጋጀት የምችልበትን እድል በማግኘቴ የተሠማኝን ወደር የለሽ ደስታ ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡ በእርግጥም ከትንሽ ነገር ተነስቶ ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደሚቻል በተግባር ያተረጋገጠ ጀግናን የህይወት ተሞክሮ የሚተርክ መፅሐፍን አዘጋጅቶ ማሳተም በራሱ ልብን በሐሴት ይሞላል፡፡ በተለይ እንባቢ እጅ ገብቶ እንዲህ ሚሊዮኖችን ለመልካም ሥራ ሲያነሳሳ ከመመልከት በላይ የሚያረካ ነገር የለም፡፡ የዚህ ታሪክ ባለቤት የሆኑት ክቡር ግርማ ወ/ጊርጊስ በጎ ተፅዕኖ ካሳረፉብኝ በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት ስኬታማ ሰዎች መካካል አንዱ ናቸው፡፡ ከታሪክ መዛግብት እንደተረዳሁት፣ ከአብሮ አደግ ጓደኞቻቸው እና በቅርብ ከሚያውቋቸው ወዳጆቻቸው እንዲሁም ረጅም ጊዜን አብረዋቸው ካሳለፉት ከስራ ባልደረቦቻቸው ምስክርነት እንደተገነዘብኩት ከሁሉ በላይ ደግሞ በአካል ቀርቤ እንዳረጋገጥኩት በእርግጥም የክቡርነታቸው የህይወት ተሞክሮ በአስገራሚ እና የትኛውንም ሰው የማነቃቃት ኃይል ባላቸው ገጠመኞች የተሞላ ነው፡ እኔ በበኩሌ ከፅናታቸው ፅናትን ተምሬያለሁ፡፡ ባስመዘገቧቸው ድሎች እና እጅግ በሚያስደምመው ስኬታቸው ብዙ ጊዜ ተነቃቅቻለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ተራው ያንተ ነው፡፡ ከርሳቸው ገድለ ታሪክ ብዙ ነገር እንደምትማርበት አምናለሁ፡፡ ይህንን መፅሐፍ ለማዘጋጀት የተነሳውበትም ዋነኛ ዓላማ የርሳቸውን ፈለግ የሚከተሉ ዜጎችን ለማፍራት ነው፡፡ ትዝ ይለኛል ከቀደሞው የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ክቡር ግራማ ወልደ ጊዮርጊስ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል የተዋወኳቸው ከዛሬ አስር ዓመት በፊት ነው፡፡ በወቅቱ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ ተማሪ እና የተቋሙ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ነበርኩ፡፡

መንግስትም ያን ጊዜ ከወጣቱ ይልቁንም ከዩንቨርስቲ ተማሪ ጋር ተቀራርቦ የመስራት ፍላጎት ስለነበረው በተደረገልን ጥሪ እና በተያዘልን ቀጠሮ መሰረት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት በታደሙበት ልዩ ፕሮግራም ላይ በብሔራዊ ቤተመንግስት ተገናኝን፡፡ እንግዲህ ከእዚያ የሚጀምረው የእኔና የእርሳቸው ትውውቅ ስር ሰዶ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ በተለይ ባለፉት ሰባት አመታት የጠበቀ ጥሩ ቅርርቦሽ ነበረን፡፡ እንደ ጌታ እና ሎሌ ሳይሆን እንደ አባት እና ልጅ እየተመካከርን በርካታ ወገኖችን የሚጠቅሙ ስራዎችን ሰርተናል፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ካላቸው የካበተ የሥራ ልምድ በመነሳት የሚያካፍሉኝ ገንቢ ሓሳብ ከብረት ይልቅ ብርቱ እና ጠንካራ እንድሆን አድርጎኛል፡፡ በዛ ላይ እንደ ወርቅ ተፈትኖ ነጥሮ የወጣው አስገራሚ የህይወት ተሞክሯቸው እና ጥልቅ የሆነው እውቀታቸው በራሱ መሳጭ እና ለላቀ ስራ የሚያነሳሳ በመሆኑ ሁልጊዜም ቢሆን እርሳቸውን ማግኘትም ሆነ ከእርሳቸው ጋር መስራት ያስደስተኛል፡፡ ጥናታዊ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ብዙ ትልልቅ ሰዎች በአንድ ወቅት ትንንሽ እና ታናናሽ ነበሩ፡፡ ይሁንና ግን በዚያ የብላቴናነት እድሜያቸው በዚያች ሚጢጢዬ ልባቸው ውስጥ ትልልቅ ህልም ነበራቸው፡፡ ያንን የልጅነት ህልማቸውንም እውን ለማድረግ መክፈል ያለባቸውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል የጨከኑ እና የቆረጡ ስለሆኑ ያስቡትን ከማሳካት ያገዳቸው የተመኙትንም ከመሆን ያስቀራቸው ነገር የለም፡፡ ከእነዚህ ከትንሽ ነገር ተነስቶ ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደሚቻል በተግባር ካረጋገጡ ህያው ምስክሮች መካከል አንዱ ክቡር ግርማ ወልደ ጊዩርጊስ ናቸው፡፡

በአፍሪካ በህዝብ ብዛቷ ሁለተኛ የሆነችን ታላቅ አገር በርዕስ ብሔርነት ለ 12 ዓመታት የመሩት እኚህ ሰው በእርግጥም ዘንድሮ ሳይሆን ድሮ ትንሽ ሰው ነበሩ፡፡ ትንሽ!!! እኚህ ሰው መራብንም መጠማትንም ያውቃሉ፡፡ ምንም እንኳ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር እስከመሆን ቢደርሱም አንድ ወቅት ግን እጅግ ዝቅ ብለው ሥራ ሳይንቁ በቀን ሰራተኝነት ተቀጥረው የሰሩ ሰው ነበሩ፡፡ እናም ከትናንት እስከ ዛሬ ህይወታቸው በይቻላል ባይነት መንፈስ የተሞላ እና በራስ የመተማመን መንፈስ የተቃኘ በመሆኑ ከታች ተነስተው እላይ ቢደርሱ አይገርምም፡፡

የያኔው ትንሹ ግርማ ትንሽ ሆኖ አልቀረም፡፡ ይልቁንስ ከራሱ አልፎ ለሌሎች ይተርፍ ዘንደ ሌሊትና ቀን ሲተጋ ኖረ፡፡ ተሳካለትም፡፡ ቀን አልፎ ቀን ሲተካ የእርሱም ህይወት እያደር እየተለወጠ እለት እለትም እኗኗር እየተቀየረ መጣ፡፡ ቀስ በቀስም ያ ትንሹ ልጅ ኑሮን ታግሎ በማሸነፍ የተደነቀ እና የተከበረ ሰው ሆነ፡፡ አሁን እኔ እንግዲህ ያዘጋጀሁት የዚህን ጀግና ገድለ ታሪክ ነው፡፡ ናፍቆቴ ከመሳጭ ታሪኩ ቁም ነገርን ቀስመህ አንተም ሌላ ታሪክ ሰሪ እንድትሆን ነው! ጋሽ ግርማ ይህንን መፅሐፍ በማዘጋጅበት ሂደት የህይወት ተሞክራቸውን ሲያካፍሉኝ እያንዳንዱ ገጠመኛቸው የሚያስደንቀኝ ከመሆኑ ባሻገር የማስታወስ ችሎታቸው ያስገርመኝ ነበር፡፡ እያንዳንዷን ክስተት እና ያሳለፉትን ነገር ሁሉ ከእነ ቀኑ ብቻ ሳይሆን እለቱን እና ሰዓቱን ጭምር በቀላሉ በማስታወስ ያለምንም የሐሳብ መደነቃቀፍ ነበር የሚተርኩልኝ፡፡ ቦታና የሰው ስምም ቢሆን በፍፁም አይጠፋቸውም፡፡ እያንዳንዱን ነገር ዛሬ እና አሁን እንደተደረገ ድርጊት በቀላሉ ሲገልፁ ግርምትን ያጭራሉ፡፡ በዛ ላይ ቁም ነገሩን በቀልድ እያዋዙ ስለሚናገሩ የአድማጭን ቀልብ በቀላሉ ሰቅዘው ይይዛሉ፡፡ እውነት ነው ጋሽ ግርማ ጨዋታ አዋቂ ናቸው፡፡ አይሰለቼ የሆነው ታሪካቸውን ሲያስከመኩሙ አፍ ያስከፍታሉ፡፡ ተስፋ አደርጋለሁ አንባቢም ተመሳሳይ ስሜት እንደሚሰማው፡፡ እኔ በበኩሌ በመኖሪያ ቤታቸው /Semi-palace/ በሚገኘው ቢሮአቸው ይህን መሳጭ ታሪካቸውን እየኮመኮምኩ አያሌ ቀናትን ሳሳልፍ በውስጤ ይፈጠር የነበረው አይነት መነቃቃት በአንባቢዬ ላይ እንደሚፈጠር አምናለሁ፡፡ በዛ ላይ በጨዋታችን መካከል ያልተነሳ ጉዳይ የለም፡፡ እርግጥ ነው ከአገር ደህንነት አኳያ መገለፅ ከሌለባቸው ጉዳዮች በቀር በወጋችን ያልተዳሰሱ ነጥቦች የሉም፡፡ ክቡርነታቸው በርዕዮት ዓለም እና በሚያራምዱት ፓለቲካዊ ፍልስፍና ወይም አይዶሎጂ የተነሳ ፍፁም ተቃራኒ በሆኑ ሶስት መንግስታት ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ሰርተዋል፡፡ ሆኖም ከጨቋኝ ገዢዎች እና ከአምባገነን መሪዎች ጋር ወግነው ህዝብን ያስመረሩበት አጋጣሚ የለም፡፡

ከሶስት መንግስታት ጋር መስራታቸው በራሱ የህዘብ ልጅ ለመሆናቸው በቂ ማሳያ ነው፡፡ እውነታው ይሄ ባይሆንማ ኖሮ እኮ በሶስቱም ዘመነ መንግስታት ህዝቡ በከፍተኛ ድጋፍ እና በሙሉ ይሁንታ መርጦ እንደራሴው አያደርጋቸውም ነበር፡፡ የሆነው ግን ይሄ ነው፡፡ እናም እምነት ጥሎ ድምፁን ለሰጣቸው ህዝብ ሲታገሉ ኖረዋል፡፡ እንደማንኛውም የአገሬ እና የወገኔ ጉዳይ ያገባኛል ብሎ ቆርጦ እንደተነሳ ባለ ራዕይ ወጣት ለህዝብ ጥቅም እና ለአገር ልማት መከፈል ያለበትን ዋጋ ሁሉ ከፍለዋል፡፡ ብዙዎችን ከአላማቸው አጨናግፎ ከመስመር ያስወጣቸው ራስ ወዳድነት እርሳቸውን የማንበርከክ ጉልበት አልነበረውም፡፡ በተለያየ አጋጣሚ ፅኑ አቋማቸውን የሚፈታተን መደለያ ቢቀርብላቸውም አንድም ቀን የግል ጥቅማቸውን አስቀድመው አገራቸውን እና ህዝባቸውን ለድርድር አቅርበው አያውቁም፡፡

በሰሩባቸው መንግስታዊ በሆኑና ባልሆኑ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ የግል ማህደሮቻቸውም የሚመስክሩት ይህንኑ ሀቅ ነው፡፡ እንዲያውም በስራ ባሳለፉባቸው ረጅም አመታት ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋፅዎ የተመለከቱ በርካታ ተቋማት በተለያየ ጊዜ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አበርክተውላቸዋል፡፡ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ከንጉሰ ነገስቱ እጅ ከፍተኛ የክብር ኒሻን ከተሸለሙ ጥቂት ኢትዮጵያውያን መካከልም አንዱ ናቸው፡፡ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፈው ያስመዘገቡትን ዘርፈ ብዙ ስኬት የተገነዘቡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለሰራቸው ስራዎች እውቅና በመስጠት አድናቆታቸውን ከአክብሮት ጋር ገልፀውላቸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ክቡርነታቸው ሶስት የክብር ዶክትሬት ዲግሪዎችን ተቀብለዋል፡፡ እርሳቸው አንድም ብዙም ናቸው፡፡ ጋሽ ግርማ ያለ አንዳች ግነት ያልተሳተፉበት የስራ ዘረፍ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ያሁኑ ሳይሆን የያኔው ትንሹ ግርማ የሸክም ስራ ሰርቶ ያውቃል፡፡ ባይገርማቸሁ ንግድን አሀዱ ብሎ የጀመረው ደግሞ እንቁላል በመሸጥ ነው፡፡ ደሞ ሌላ ጊዜ አንድ ጣልያናዊ ጋር በቀን ሠራተኝነት ተቀጥሮ ነበር፡፡ እኔ ከሁሉም በላይ የሚደንቀኝ ደግሞ በድንጋይ ጠራቢንት ፤ በአሸዋ አንጣፊነት እና በወለል ገንቢነት በዚያ ለጋ እድሜው ተቀጥሮ የሰራው ቤተመንግስት መሆኑ ነው፡፡ ታድያ ይህ ብላቴና ከአመታት በኋላ ርዕሰ ብሔር ሆኖ ዳግመኛ በዚያው ቤተ መንግስት ይኖራል ብሎ ማን ያስባል? በብዙዎች ዘንድ እዚህ ግባ በማይባል ዝቅተኛ የስራ መስክ ላይ የተሰማራ አንድ ቀን ሰራተኛ እዚህ ይደርሳል ብሎስ ማን ይገምታል? ያ ልጅ እንደ ተራ ሰው በሚቆጠርበት ስፍራ ታሪክ ተለውጦ ነገር ተገልብጦ የተለየ የክብርን ሥፍራ ያገኛል ብሎስ ማን ይጠረጥራል? በዛ ላይ ስልጣኑ የተገኘው እኮ በኃይል አይደለም፡፡ የአገሬ የዘመናት እውነታ እንደነበረው በደም መፋሰስ ወይም በተንኮል የተገኘም አልነበረም፡፡ እኔ እስከገባኝ ድረስ ሹመቱ የተገኘው በብቃት ነው፡፡ በብቃት፡፡
ለመሆኑ የዚያ የትንሹ ልጅ እና የእዚህ የትልቁ ሰው የስኬት ምስጢር ምንድን ነው? ከትቢያ ላይ ተነስቶ የሰው ልጅ መገኛ እና የጥቁር ህዝቦች የነፃነት አርማ የሆነች አገርን እስከ መምራት የደረሰው እንዴት ነው? እኔ በበኩሌ ገና ከ 10 ዓመቱ ጀምሮ አገሩን በታማኝነት አገልግሎ ከበቂ በላይ የዜግነት ድርሻውን እንደተወጣ ይሰማኛል፡፡ እውነት ነው በርዕስ ብሔርነት ባሳለፉባቸው ዓመታትም በደል የደረሰባቸው እና ፍትህ የተነፈጉ ዜጎችን ተቀብለው በማስተናድ ከህዝብ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ተወተዋል፡፡ በቅርበት እስከማውቀው ድረስ ቢሮአቸው ለማኛውም ባለጉዳይ ክፍት ነበር፡፡
ማንም እንደሚመሰክረው ዘመናቸውን ሁሉ ያሳለፉት የአገርን እና የህዝብን ጥቅም በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ እነዚያ ያሳለፏቸውን አመታት ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስታውሷቸው በእጅጉ እደሚደነቁ አጫውተውኛል፡፡ ባስመዘገቧቸው ተደራራቢ ስኬቶችና በተጎናፀፏቸው ድሎች መንፈሳዊ ኩራት እንደሚሰማቸው ጭምር ነግረውኛል፡፡ በአንፃሩም አንዳንድ አሳዛኝ እና የሚቆጩባቸውን ገጠመኞቻቸውንም ሳይነግሩኝ አላለፉም፡፡ በቅርቡ ዘጠና አመት ሞልቷቸው የልደት በዓላቸውን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የወዳጅ አገር አምባሳደሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አድናቂዎቻቸው እና ጓደኞቻቸው በተገኙበት ከቤተሰቦቻቸው ጋር በድምቀት ያከበሩት ክቡርነታቸው እዚህ እድሜ ላይ ደርሰው እንኳ ትንሽ ልረፍ ሳይሉ አሁንም ድረስ በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት እንዲፈታ የጀመሩትን የሰላም ጥረት እያቀላጠፏት ነው፡፡ ከድንበር ይገባኛል ጥያቄ ባሻገር ያለውን እንቆቅልሽ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት ከሚከለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመስራት ላይ ናቸው፡፡ ለመሆኑ ይህ የሰላም ጥረት ምን ደረጃ ላይ ደርሷል? ኤርትራውያንንስ እንዴት ይገጧቸዋል? ሲጀመር የችግሩ ዋነኛ ምንጭስ ምንድን ነው?

እንደሚታወቀው ኤርትራ እና ኢትዮጵያ በንጉሱ ዘመን በፌዴሬሽን ተጣምረው ይኖሩ ነበር፡፡ ይሁንና ግን ብዙም ሳይቆይ ይህ የጋራ መርህ ተጥሶ ያስተሳስራቸው ሰንሰለት ተበጣጠሰ፡፡ በዚህ ድንገተኛ ውሳኔ ያልተደሰቱ ወገኖች ነፍጥ አንስተው ሸፈቱ፡፡ ሌሎችም የመገንጠልን ዜማ እያቀነቀኑ ተቀላቀሏቸው፡፡ ትግሉም በዚህ መልኩ ተቀጣጥሎ የአንድ አገር ህዝቦች እርስ በእርሳቸው ለዘመናት ተላለቁ፡፡ ክቡርነታቸው ከዚህ ክስተት ጋር በተያያዘ የሚሉት ነገር አላቸው፡፡ ስለምን ንጉሱ ፊዴሬሽኑ እንደበተኑ ያጫውቱናል፡፡ የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ውሳኔንም “ታላቅ ስህተት” ብለው ይገልፁታል፡፡ ለምን? ስለዚህ ነገር ብዙ ብዙ ያወጉናል፡፡

በአንፃሩም እንደ ሰም እቅልጦ እንደ ገል ቀጥቅጦ 17 አመት ረግጦ ስለገዛን ስለ ደርግ እና ስለ ዋናው ሰውዬ ስለ ጓድ መንግስቱ ኃይለማርያ የሚያጫውቱን ነገር አላቸው፡፡ በተለይ በኤርትራ ስላሳለፏቸው ሁለት አስርት አመታት ይተርኩልናል፡፡ በነገራች ላይ ስለ ኤርትራዊያን ተናግረው አይጠግቡም፡፡ ስለዚያ ህዝብ ቅንነት እና ደግነት መስክረው አይረኩም፡፡ እነዚህ ከአንድ አብራክ እንደተወለዱ መንትያ ልጆች ከአንዲት ጥንታዊት አገር የፈለቁት ሁለቱ ህዝቦች አሁን ተለያይተው እና የቅርብ ሩቅ ሆነው ቢኖሩም እንኳ አንድ ቀን በመካከላቸው ያለውን ጠብ አብርደው እና እርቅ አውርደው ሠላማዊ ጉርብትና ይመሰርታሉ የሚል ፅኑ እምነት ስላላቸው የሁለቱን አገሮች እንቆቅልሽ ለመፍታት ዛሬም ድረስ እያደረጉ ያሉትን ጥረት ክቡርነታቸው ያጫውቱናል፡፡ በአንፃሩም ይበጃል ብለው የሚያምሩበትን የመፍትሄ ሃሳብንም ያካፍሉናል፡፡ ሌላው የሚያጫውቱን እንዴት ለኢ.ፌ.ድ.ሪ ፕሬዝዳንትነት እንደታጩ ነው፡፡

በተለይ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ሥርዓተ መንግስት ተበሳጭተው “ምን አለ አንድ ቀን መንግስት ብሆን” ብለው የተመኙት ምኞት ሰምሮ በፓርላማ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሆነው በተመረጡበት እለት ለመሆኑ ምን አይነት ስሜት ነው የተሰማቸው? በብሔራዊ ቤተመንግስት ያሳለፏቸው አስራ ሁለት አመታትስ ምን ይመስላሉ? እንደ ፕሬዝዳንትነታቸው በእነዚያ አመታት ሠራኋቸው ብለው የሚኮሩባቸው አበይት ተግባራት የትኞቹ ናቸው? ህገ መንግስቱ የሠጣቸውን ስልጣን እና ግለሰባዊ የመሪነት ነፃነታቸውን ተጠቅመው ካስተላለፏቸው ታላላቅ ውሳኔዎች መካከል ከፍተኛ የህዝብ አድናቆት ያተረፉባቸው የትኞቹ ናቸው? ምናለ ባላደርገው ኖሮ ብለው የሚፀፀቱበት ጉዳይስ አጋጥሟቸው ይሆን? ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስቡት የሚቆጫቸውስ ነገር አለ? እርሳቸው “አዎ አለ” ብለው አጫውተውኛል፡፡ እጅግ ደስ ብሏቸው እንደ እንቦሳ ጥጃ ስለ ቦረቁባቸው አያሌ ቀናት እና በተቃራኒው ክፉኛ ስላዘነባቸው ሶስት አጋጣሚዎችም ነግረውኛል፡፡ ለመሆኑ እነዚያ የፈነደቁባቸው እና የተከፉባቸው ጉዳዮች ምን ምን ናቸው?

በነገራችን ላይ ክቡርነታቸው በአንድ ወቅት በአገር ክህደት ወንጀል ተከሰው ያውቃሉ፡፡ በወቅቱ የተመሰረተባቸው ክስ እኪጠናቀቅ በእስር ላይ ከመንገላታታቸው ባሻገር የተጠቀሰባቸው የወንጀል ክስ የሞት ፍርድ የሚያስፈርድ ነበር፡፡ ያን አስቀያሚ እና አስደንጋጭ የሆነውን ክስተትንም ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስቡት በህይወት መኖራቸው ያስገርማቸዋል፡፡ ፊታቸው ላይም አንዳች የመደነቅ ስሜት እየተነበበባቸው “ልክ እንደ እስራኤል ንጉስ እንደ ቅዱስ ዳዊት ለሞት አንድ እርምጃ ቀርቶኝ ሳለ ለጥቂት እኮ ነው በተዓምር የተፈፍኩት” ነበር ያሉኝ የሁኔታውን ከባድነት በሚያስታውቅ ቅላፄ፡፡ እኔም ይህንን እውነተኛ ግን ደግሞ አስፈሪ ገጠመኛቸውን ሲያጫውቱኝ የሰማዋቸው ሲበዛ እድለኛ መሆናቸውን በውስጤ እያንሰላሰልኩ ነበር፡፡ ለመሆኑ ለእስር የዳረጋቸው እና የጦር ፍርድ ቤት ያቆማቸው ጉዳይ ወይንም ሰሩት የተባለው ወንጀል ምን ነበር? እንዴትስ ከዚያ ጨለማ እስር ቤት ወጡ? እንዴትስ ፊት ለፊታቸው ተደቅኖ ከነበረው ሞት አመለጡ? ምላሹን በዝርዝር ይተርኩልናል፡፡

ሌላኛው እኔን ያስደነቀኝ የህይወታቸው ክፍል ደግሞ ከግል ስብዕናቸው እና ከቤተሰብ አመሰራረታቸው ጋር ይያያዛል፡፡ ክቡርነታቸው አሁንም ድረስ ከእርሳቸው ጋር አብረው ከሚኖሩት ከወ/ሮ ሳሌም ጳውሎስ ጋር 66 ዓመታትን በጋብቻ ተጣምረው አሳልፈዋል፡፡ ይሄ ትዳር ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል፡፡ በተለይ ጅማሬው ላይ ጥንዶቹን የገጠማቸው ፈተና እንዲህ በቀላሉ በቃላት የሚገለፅ አይደለም፡፡ በሁለቱ ጥምረት ያልተደሰቱ ብዙዎች በርካታ ወጥመድ እየዘረጉ እና ነገር እየሸረቡ ቁም ስቅላቸውን አሳይተዋቸዋል፡፡ ይሁንና ግን “እንዴት ተራ ወታደር ታገቢያለሽ” በሚል ሽፋን የተነሳውን የተቃውሞ ማዕበል በፅናት የተቋቋመችውና በያኔው ግርማ ፍቅር የነሆለችው ትንሸ ሳሌም አልተበገረችም፡፡ እናም በፍቅር ከረታት ከተናቀው ከዚያ ምስኪን ጋር አብራ ተሰደደች፡፡ እርሱም ቢሆን አላሳፈራትም፡፡ ታላቁ መፅሐፉ “እምነት ፣ ተስፋ ፣ ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ፀንተው ይኖራሉ፡፡ ከእዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው” እንዲል በፍቅሩ ተማርካ የተከተለችው እና ጥሎ አይጥለኝም ብላ ልቧን ያሳረፈችበት ግርማ አንድ ቀን ትልቅ እና የተከበረ ሰው ይሆናል የሚለው ተስፋዋም አልተለወጠም፡፡ ይልቁንስ ካሰበችው እና ከገመተችው በላይ ያ ትንሽ ልጅ የተከበረ ታላቅ ሰው ሆነ፡፡ ገና ከመነሾው በፍቅሯ የተረታው ትንሹ ግርማ ስለ እርሷ ሲል ያላለፈው የመከራ ሸለቆ የለም፡፡ እርሱ ስለ ፍቅር ተሰዷል፡፡ ቀን በወጣላቸው በጊዜው ሰዎች መዳፍ ወድቆ እስር ቤት ተወርውሯል፡፡ ግና ያኔም ቢሆን ለውዱ የገባውን ቃል አላጠፈም፡፡ መሐላውንም አላፈረሰም፡፡ እኔ ይህንን ክስተት ከባለታሪኮቹ አንደበት ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁ እለት ተደምሜያለሁ፡፡ እናንተ ማንበባችሁን ቀጥሉ እንጂ እኔስ ይህንን የሁለቱን ጥንዶች የፍቅር ታሪክ አስኮመኩማችኋለሁ፡፡ ጋሽ ግርማ በትዝታ ማዕበል ውስጥ እየዋኙ ከ66 ዓመታት በፊት ያሳለፏትን የፍቅር ህይወት ሲያጫውቱኝ በህሊናዬ ውልብ ያለብኝ “ፍቅር አያረጅም” የሚለው ህያው ቃል ነው፡፡ እውነት ነው ፍቅር ሁለት ጥንዶችን አጣምሮ አብሮ ያስረጃል እንጂ እሱስ አያረጅም፡፡ ክቡርነታቸውን “ለእኔ ሳሌም ያኔም ዛሬም ያው ናት፡፡ በፍቅር የምወዳትና የማከብራት” ያሰኛቸውም ይሄው ሃቅ ሳይሆን ይቀራል? ነው እንጂ … አልያማ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

ይህ ትዳር 5 ልጆችን 15 የልጅ ልጆችን እና 28 የልጅ ልጆችን አፍርቷል፡፡ ከአብራካቸው ክፍያቸው አንዷ ባህር ማዶ የምትኖር ስትሆን ስሟ ከተቃዋሚዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ ይነሳል፡፡ እርግጥ ነው አባቷ ግርማ የገዢው ፓርቲ አባል ባይሆኑም ተቃዋሚ ግን አይደሉም፡፡ እርሷም ብትሆን የእርሳቸው አቋም የግድ መጋራት ላይጠበቅባት ይችላል፡፡ ይሁንና ግን ጥያቄው እንዴት በተቃራኒ ጎራ ልትቆም ቻለች? የሚለው ነው፡፡ ሌላው እውነታ ደግሞ እርሳቸው ሥልጣን ላይ እያሉ ወደ አገር ውስጥ ለስራ ጉዳይ በመጣችበት አጋጣሚ ልጃቸው ታስራ ነበር፡፡ ሆኖም ስልጣናቸውን ተጠቅመው ጣልቃ ከመግባት ይልቅ ስራዋ ያውጣት ብለው ነበር ዝምታን የመረጡት፡፡ ለመሆኑ ልጅቱ ማን ትባላለች? አሁን የምትኖረውስ የት ነው? እዚህ ያሉ ልጆቻቸው ስለ አባታቸው ምን ይላሉ? አባትና እናታቸውስ እንዴት ይገልጧቸዋል? ስለ እነዚህ ጉዳዮች ይህ መፅሐፍ በዝርዝር ያስረዳናል፡፡ ክቡርነታቸው ምን ያዝናናቸዋል? ከምግብና ከመጠጥ የትኛውን ያዘወትራሉ? ጉደኛ ዳንሰኛ እንደሆኑ ስለሚነገረው ጉዳይስ ምን ይላሉ? ሌላው በብዙዎች ህሊና ከሚመላለሱ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ከእርሳቸው በፊትም ሆነ አሁን ካሉት መሪዎች መካካል የማን አድናቂ ናቸው የሚል እንደሚሆን ይገመታል፡፡ እንዳጫወቱኝ ከሆነ ከአሜሪካ እና ከኢትዮጵያ የሚያደንቋቸው ሶስት መሪዎች አሉ፡፡ ለመሆኑ እነዚያ ሰዎች እነማን ናቸው? ስለምንስ ያደንቋቸዋል? ሮል ሞዴላቸውስ ማን ነው? በቅርቡ በሞት ስለተለዩን ስለ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር ስለ አቶ መለስ ዜናዊስ ምን ይላሉ? ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለቱ የተዋወቁት መቼ፤ እንዴት እና የት ነበር? ምን ያህልስ ይቀራረቡ ነበር? የስራ ግንኙነታቸውስ ምን ይመስላል? ጠቅላይ ሚንስትሩን እንዴት እና በምን ይሆን የሚገልፅዋቸው? ይህ መፅሐፍ ለእነዚህ እና ለመሰል ጥያቄዎች ቁልጭ እና ቅልብጭ ያለ ምላሹን ይሠጣል!

መግቢያ

ይህንን መፅሐፍ ለማዘጋጀት ካሰብኩ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ፍላጎቱም ያደረብኝ ለመጀመርያ ጊዜ ከተዋወኳቸው ቀን አንስቶ ነበር፡፡ በእለቱ ለእኔም ይሁን አብረውኝ ለነበሩ ታዳሚዎች የህይወት ተሞክሯቸውን ከረጅሙ በአጭሩ ከብዙ በጥቂቱ ሲያካፍሉ ያዳመጥኳቸው በመደነቅ እንደነበር ዛሬም ደረስ ትዝ ይለኛል፡፡ ከዚያ በኋላ ስለ እርሳቸው የሚያተርኩ ልዩ ልዩ አይነት መጣጥፎች እያነፈነፍኩ እከታተል ነበር፡፡ በተለይ አገሬን ወክዬ በምሳተፍባቸው አህጉር እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከእርሳቸው ጋር የምሰራበት እድል ያገኘሁባቸው አመታት እርሳቸውን በቅርበት እንዳውቃቸው ረድተውኛል፡፡ ይሄኔም ታሪካቸው፣ የህይወት ፍልስፍናቸው፣ ለአገር እና ለወገን ያላቸው ተቆርቋሪነት ይበልጥ እየሳበኝ መጣ፡፡ እያደርም ባዬግራፊያቸውን የያዘ መፅሐፍ የማዘጋጀቱ ፍላጎት እየጎለበተ ሄደ፡፡ አንድ ቀንም እዚያው ቤተመንግስት ቢሮአቸው ሳሉ ይህንን መሻቴን ገለፅኩላቸው፡፡ የእርሳቸውን የህይወት ተሞክሮ የሚያካፍል መፅሐፍ የማሳተም፣ ዘጋቢ ፈልም የማዘጋጀት እና በእውነተኛ ታሪካቸው ላይ የተመሰረተ ፊልም ለመስራት ፍላጎቱ እንዳለኝ ገለፅኩላቸው፡፡

እርሳቸውም በትህትና “ምን ሥራ ሠራሁና ነው ለጀግና የሚሰጠውን ክብር ልትሠጠኝ የወደድከው? ከሌላውስ ምን የተለየ ታሪክ አለኝና ነው? እንዲህ አይነት ለኔ የማይገባ ታላቅ ነገር ያሰብክልኝ” የሚል ጥያቄ አዘል ምላሽ ሰጡኝ፡፡ ይህ ትህትና የተሞላበት ምላሻቸው በፊት በነበረኝ መገረም ላይ ሌላ መደነቅ ጨመረብኝ፡፡ ወዲያውም አያቴ “ፍሬው የበዛ ማሽላ አንገቱን ጎንበስ ያደርጋል” ብላ በልጅነቴ የነገረችኝ ግሩም አባባል ከፊቴ መቶ ገጭ አለ፡፡ ወዲያውም “እውነቷን ነው እማማ” አልኩ በልቤ፡፡ እኝህን ሰው ለዚህ ክብር ያበቃቸው ይሄው ትህትናቸው ነው ብዬ ይበልጥ ተደመምኩ፡፡ ቀጥዬም ለጥያቄያቸው ምላሽ ይሆናል ብዬ ያመንኩበትን ምላሽ ሰጠኋቸው፡፡ ዋነኛ ዓላማዬንም በዝርዝር አስረዳኋቸው፡፡ ይሄኔም ጥያቄዬን በፀጋ ተቀብለው ሙሉ ፍቃደኝነታቸውን ገለጹልኝ፡፡ ከዚያም መጠነኛ ፕሮፖዛል ቀረጬ አቀረብኩላቸው፡፡ ወደዱትም፡፡ በመጨረሻም የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰን ስራዬን አሀዱ ብዬ ጀመርኩኝ፡፡ እርግጥ ነው የሙያዬም ሆነ የስራዬ ፀባይ ወደ ተለያዩ የአለም ክፍሎች እንድንቀሳቀስ ግድ ይለኛል፡፡ ይሁንና ግን በተቻለ አቅም አገር ውስጥ እስካለሁ ድረስ በሳምንት ሁለት ቀን ቃለ መጠይቅ /Interview/ አደርጋቸው ነበር፡፡ በተለይ ማክሰኞ እና ሐሙስ ጠዋት ጠዋት እየተገናኘን ከሦስት ሰአታት በላይ እናሳልፍ ነበር፡፡ ከዚያም ለሥራ ጉዳይ ወደ ባህር ማዶ ወጣ ስል በማርፍባቸው ሆቴሎች እስከ ውድቅት ለሊት ድረስ እየቆየሁ ቃለ መጠይቁን በጽሑፍ አሰፍረው ነበር፡፡ በቀሪዎቹም እለታት መረጃዎችን ከተለያየ ሥፍራ የማሰባሰቡን ስራ ተያያዝኩት፡፡

ከብሔራዊ ቤተመንግስት፣ ከፕሬዝዳንት ፅ/ቤት፣ ከቤተመንግስት አስተዳደር፤ ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ ከሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከትራንስፖርት ሚንስትር፣ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትውት፤ ከኢትዮጵያ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት፤ ከኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር፤ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፤ ከልዩ ልዩ የግል ሚድያ፤ ከኢትዮጵያ አየር ኃይል፤ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ከፌደሬሽን ምክር ቤት፤ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፤ ከአገር መከላከያ ሚንስቴር፤ ከላየንስ ክለብ፤ ከለም ኢትዮጵያ፤ ከስካውት ማህበር፤ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር፤ ከአዲስ አበባ እድሮች ህብረት፤ ከጥንታዊ ኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር፤ ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ጡረተኞች ማህበር፤ ከሆሎታ ወታደራዊ መኮንኖች ማሰልጠኛ፤ ከአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ እስከ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ፤ ከወጋገን ባንክ፤ ከግቤ እርሻ ልማት፤ ከቆርኪ ፋብሪካ፤ ከሜሪ ጆይ የልማት ተራድዖ ድርጅት እና ከብሔራዊ ቤተመዛግብት ልዩ ልዩ ሰነዶች እያገላበጥኩ ጠቃሚ ናቸው ብዬ ያመንኩባቸውን የድምፅ፣ የምስል እና የሰነድ መረጃዎችን ኮፒ በማድረግ አከማቸሁኝ፡፡ በተጓዳኝም ከአብሮ አደግ ጓደኞቻቸው፣ ከረጅም ጊዜ የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ከልብ ወዳዶቻቸው እና ከቅርብ ቤተሰቦቻቸው ጋር በቀጠሮ በመገናኘት ተጨማሪ ግብአቶችን አሰባሰብኩ፡፡ ቀጥሎም እያንዳንዱን መረጃ በመተንተን እና በማቀናጀት በግብዓትነት ተጠቅሜ መፅሐፉን በዚህ መልኩ ወደማዘጋገቱ ተሻገርኩ፡፡ ዋነኛ ዓላማዬም ሚሊዮኖች ከእርሳቸው የህይወት ተሞክሮ በርካታ ቁም ነገሮችን በመቅሰም የእርሳቸውን አሰራ ፍኖት እንዲከተሉ ለማድረግ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ እንዲህ ነው ብዬ የምገልፀው እውቀትን ከእርሳቸው ቀስሜያለሁ፡፡ አፌን ሞልቼ የምናገረውም ክቡርነታቸው የአላማ ፅናት፣ የውሳኔ ሰጪነት ብቃት፣ ኃላፊነትን የመሸከም ክህሎት፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በብልጠት የማለፍ ጥበብ፤ በራስ መተማመን፣ ቆራጥነት፣ ተዓማኒነት፣ ጥንቁቅነት፣ ግልፅነት እና የማሳመን ክህሎት ያላቸው ብቁ እና ግልፅ ሰው መሆናቸውን ነው፡፡ አዎ እርሳቸው የልጅነት ህልማቸውን እውን ያደረጉ ውጤታማ እና ስኬታማ ሰው ናቸው፡፡ ከትንሽ ነገር ተነስቶ ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደሚቻል በተግባር ያረጋገጡ እና በእሳት ተፈትነው እንደ ከበረ ማዕድን ነጥረው የወጡ የኢትዮጵያ ወርቅ ልጅ ናቸው፡፡ እርሳቸው ዘመናቸውን ያሳለፉት በድል ላይ ድል በመቀዳጀት ነው፡፡

በዛ ላይ ወድቆ መነሳትን፣ ታግሎ ማሸነፍን እና ተከራክሮ መርታትን ያውቁበታል፡፡ ይሁን አንጂ እንዳለመታደል ሆኖ እንደነዚህ ያሉ ምድራችን ያፈራቻቸውን እንቁዎች ስናጌጥባቸው አይስተዋልም፡፡ ለጥቂት ጀግኖቻችን እንኳ መታሰቢያ ያቆምንላቸው ካለፉ በኋላ ነው፡፡ በዚህ ረገድ እኔ ተሳክቶልኛል፡፡ እኚህ የአገር አድባር እና ተንቀሳቃሽ ቅርስ የሆኑ ሰው በህይወት ሳሉ ሊሞገሱ፣ ሊወደሱ፣ ሊዘከሩ፣ ሊሸለሙ እና ሊከበሩ ስለሚገባ አምቦ ዩኒቨርስቲ የሚገኘው ግዙፉ ላይብራሪ በእርሳቸው ስም እንዲሰየም ያቀረብኩት ኃሳብ በሴኔቱ ሙሉ ተቀባይነት አግኝቶ ተቋሙ ለክብርነታቸው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በሰጣቸው እለት ቤተ መፃህፍቱም በእርሳቸው ስም ተሰይሟል፡፡ ከዚህ የልቀት ማዕከልም በቀጣዮቹ አመታት በርካታ የነቁ እና የበቁ፤ ያወቁ እና የመጠቁ እንዲሁም የተማሩ እና የተመራመሩ ብዙ ምሁራን እንደሚፈልቁበት እልፍ ግርማዎችም እንደሚበቅሉበት አምናለሁ፡፡

የዚህ መፅሐፍ ዓላማ ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ዋነኛ ግቤ በእርሳቸው ስኬት ተነቃቅተው ለመልካም ስራ የሚነሳሱ ውጤታማ ዜጎችን ማፍራት ነው፡፡ ይህ ህልሜም ይህንን መፅሐፍ በሚያነቡ በርካታ ወጣቶች ላይ እውን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡ ሚሊዩኖች በይቻላል ባይነት መንፈስ ሲሞሉ እና በራስ የመተማመን አቅማቸውን ሲጎለብት ይታየኛል፡፡ የእኚህ በእውቀት የሸመገሉ እና ሽበታቸው ሺህ ውበት የሆነላቸውን ስኬታማ ሰው ፈለግ ከሚከተሉ ባለ ራዕዮች መካከልም አንዱ አንተ አንደምትሆንም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በመጨረሻም መልካም ንባብን እየተመኘሁ ወደ መፅሐፉ ፍሬ ሃሳብ እንድትገቡ በፍቅር እና በአክብሮት እጋብዛለሁ፡፡
ደራሲው

ሕዝበ ክርስቲያን በጰራቅሊጦስ መንገድ ሲሄዱ፤ ፓትርያርክ፤ ሊቃነ ጳጳሳት፤ መነኮሳትና ቀሳውስት በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ (ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

$
0
0

በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ!

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
nigatuasteraye@gmail.com
ሰኔ ፳፻፮ ዓ.ም.

ማሳሰቢያ፦

ቀሲስ አስተርዕየ

ቀሲስ አስተርዕየ

የዚህች ክታብ አላማ ነገረ መለኮት ለማስተማር አይደለም። ሆኖም አብዛኛዎቻችን ኢትዮጵያውያን እምነታችሁ ምንድነው ስንባል መልሳችን ክርስቲያን ነና! ነው። እንዲያውም ብዙዎቻችን በኩራት በልበ ሙሉነት ከዘመኑ ክርስትና በፊት በነበረችው በኦርቶዶክስ ተጠምቄ ያደኩ ነኝ እንላለን። በተለይም በአውደ ምህረት ላይ ቆመን እግዚአብሄር ይባርክ ለማለት ተክነናል የምንል ሰዎች፤ ስንጠየቅ ለክርስትናየ ደግሞ ምን ጥያቄ አለው! እንዲውም ባይደንቅህ ልብሴን ተመልከት! የጨበጥኩትንም መስቀል እይ! በደረቴ ያንዘረገኳቸውን ክርስቲያን ነክ ጌጣ ጌጦች ተመልከት የዚህች ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ቄስ፤ መነኩሴ፤ (ጉዳችን አያልቅምና በአቡነ ጳዎሎስ ዘመን የተለቀቀ ቆሞስ)፤ ጳጳስ ነኛ! እንላለን። በእምነት በታሪክ በባህል መኩራት ተገቢ ነገር ነው። የሚኮሩበትን ሳይጠበቁ መኩራራት ብቻ ግን ዝናብ የለሽ ባዶ ደመና መሆን ነው።

መጠበቅ መቻላችን የሚመዘንበት ጰራቅሊጦስ ነው። በሱ እየተመዘን ፤ እሱ ከሚጠላቸው ከዝሙት፤ ከሀሰት፤ ከስርቆት፤ ከስስት፤ ከክህደት ተጠብቀናል፤ ህዝቡንም፤ ጰራቅሊጦስ ከማይወዳቸው ነገሮች ሁሉ ራቁ እያልን፤ ራሳችንን ምሳሌ አድርገን እናስተምራለን። እግዚአብሄርን እንቀድሳለን፤ ህዝቡንም እናስቀድሳለን ቄስ፤ ቆሞስ ( መረን የተለቀቀ)፤ ጳጳስ ነን የምንል፤ በወያኔ ዘመን ያለን ካህናት፤ ከምን ላይ እንዳለን ማሳየት እችል ዘንድ፤ የጰራቅሊጦስን ሚዛንነት ለመግለጽ ወደ ነገረ መለኮቱ ገባ ብየ ለመውጣት እገደዳለሁና ለትእግስታችሁ ይቅርታ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በእስር ላይ የሚገኙት የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአቶ አንዷለም አራጌ መልእክት (ሊያነቡት የሚገባ)

$
0
0

Andualem & Eskinder with family

ኤልያስ ገብሩ (ጋዜጠኛ)

“‹‹የታሰራችሁ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ። አከብራችኋላሁ።›› ብለህ ንገርልኝ አለኝ – ደጋግሞ።…”
ከትናንት በስትያ ሰኔ 03 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ከቅርብ ጓደኛዬ እና የሙያ ባልደረባዬ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት [እስር ቤትም ነው] አምርተን ነበር- ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆኑትን አቶ አንዷለም አራጌን ለመጠየቅ። የተለመደውን የፖሊስ ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ስንዘልቅ የሰማያዊ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፈ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ፣ አቶ ሳሙኤል የተባሉ አባልና የ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እስክንድርን ሊጠይቁ ቀድመውን ደርሰው ነበር።

…እስክንድርን እና አንዷለምን አስጠራናቸው፡፡ ሁለቱም ሲያዩን ደስ አላቸው፡፡ በተለይ በተለይ የእስክንድር ፈገግታ በጣም ደማቅ ነበር። ተከፋፍለን ከሁለቱም ጋር ሃሳቦችን መለዋወጥ ጀመርን፡፡ እስክንድር በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ “pen Golden of freedom 2014″ ተሸላሚ በመሆኑ

‹‹እንኳን ደስ ያለህ››

አልኩት።

‹‹አመሰግናለሁ። ትናንት አንድ ልጅ ሊጠይቀኝ መጥቶ ነግሮኛል››

ካለን በኋላ ደግመን ስለሽልማቱ በጋራ ሃሳብ መለዋወጥ ቀጠልን። እስክንድር ሽልማቱ አዲስ መሆኑን አላወቀም ነበር።

በመሆኑም ስለሽልማቱ ሁኔታ፣ ማን እንደሸለመው፣ ሽልማቱ የት እንደተደረገ፣ ሽልማቱን ማን እንደተቀበለለት [ሽልማቱን የተቀበለው በኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ክስ ወንጀለኛ ተብሎ ከባልደረባው ፎቶ አንሺ ጋር 11 ዓመታት ከተፈረደበት በኋላ በይቅርታ የተለቀቀው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ ነበር]፣ የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ምን እንደሚመሰል፣ በሽልማቱ እነማን እንደተገኙ …ያወቅነውን ሁሉ ነገርነው።

‹‹ይህንን አላዋኩኝም፣ ሰርካለም (ባለቤቱ) ለምን በቦታው አልተገኘችም?››

በማለት ጠየቀንና በድጋሚ ደስ ብሎት ጣቶቹን በሽቦ ውስጥ አሾልኮ ጨበጠን። ወዲያው ይህቺን መልዕክት ተናገረ፡-

‹‹ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ አይደለም። የእናንተም ነው። የኢትዮጵያዊ ጋዜጠኞች ነው። ሁላችንንም ይመለከተናል፡፡ ለሁላንችም ይገባናል። ይሄንን ሽልማት የምመለከተው ሐሳብን በነጻነት ከመግለጽ የመብት ጥሰት አኳያ ብቻ አይደለም። ለሌሎች የዜጎች መብቶች ሲሉ ለታገሉ እና እየታገሉ ላሉ ፖለቲከኞች፣ የሕሊና እስረኞችም ጭምር ነው። ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከሌሎች ከተነፈጉ መብቶች ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡ ሁሉንም መብቶች እናገኛቸዋለን፣ ወይም እናጣቸዋለን። ለዚህ ደግሞ ጸንተን እንታገል፣ ትግላችን ግን ሰላማዊ ብቻ መሆን አለበት። …››

እስክንድር ደስ ብሎት ሃሳቡን መናገሩን ቀጥሏል፡፡ እኔ ለተወሰኑ ቀናት በማዕከላዊ መታሰሬን ሰምቶ ስለነበረም

‹‹ማዕከላዊ እያለህ የታሰሩትን ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች ለማግኘት ችለህ ነበር?››

ብሎ ጠየቀኝ፡፡ እነሱን በአካል ማግኘት አለመቻሌን ነገር ግን ከእነሱ ጋር ታሥረው የነበሩ ሌሎች ተጠርጣሪ ዜጎችን አግኝቼ በእስር ስላሉበት ሁኔታ መጠየቄን ነገርኩት።

የታሰሩት ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖችን ቤተሰብ ማግኘት እችል እንደሆነና ከቻልኩም በእነሱ በኩል መልዕክቱ ይደርስለት ዘንድ በድጋሚ ጥያቄያዊ ሃሳቡን አቀረበልኝ፡፡ የተወሰኑ የእስረኛ ቤተሰቦችን ማግኘት እንደምችል አስረዳሁት።

‹‹የታሰራችሁ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ። አከብራችኋላሁ።››

ብለህ ንገርልኝ አለኝ – ደጋግሞ።… በዕለቱ ከሰዓታት በፊት ሰናይት ታከለ የምትባል ወዳጄም እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ እንደምሄድ በነገርኳት ጊዜ ‹‹እንደማከብረው እና እንደማደንቀው ንገርልኝ›› ያለችኝን መልዕክት ለእስክንድር አደረስኩላት።እሱ ግን ሳቅ እያለ

‹‹ተሳስተሻል! …ተሳስተሻል! …ተሳስተሻል››

ብለህ ንገራት አለኝ።

‹‹ለምን?››

አልኩት፡፡

‹‹ገና ምን ሰርቼ?››

በማለት በዚያ ትሁት አንደበቱ መለሰልኝ፡፡ በእውነት መልሱ አስደመመን። ዋይ እስክንድር፣ ፍጹም የተለየ ታላቅ ሰው!!! እስክንድርን እናናግረው የነበርን ጠያቂዎች ወደ አንዷለም አራጌ ዞርን፡፡ አንዷለም ጋር የነበሩት ደግሞ ወደ እስክንድር።

አንዷለም የስፖርት ቲ-ሸርት ከቁምጣ ጋር ለብሷል። ጥቁር መነጽር አድርጓል። ረጋ ብሎ ፈገግ በማለት

‹‹ምን አዲስ ነገር አለ?››

በማለት ጨዋታ ጀመረ። አንዷለም የእስክንድርን ሽልማት ሰምቶ ኖሮ፣

‹‹አሁን ከምሳ በኋላ ጣፋጭ የለውዝ ሻይ እሱን እና ጓደኞቻችንን በመጋበዝ ‹እንኳን ደስ ያልህ!› በማለት ሰርፕራይዝ አደርገዋለሁ። ምግብ ማብሰል እያለማመድኩት ነው። ብዙ ጊዜ እኔ ነኝ ሰርቼ የማበላው። በልጅነቱ በበርገር ያደገ ልጅ አሁን ሽንኩርት እና ቲማቲም መክተፍ ችሏል …››

በማለት በቀልድ ነገረን።

‹እነማን ከእናንተ ጋር አሉ? በአንድ ክፍል ውስጥስ ስንት ናችሁ? ጊዜያችሁንስ እንዴት ነው የምትጠቀሙበት?››

የሚል ጥያቄ አቀረብንለት።

‹‹ለረዥም ጊዜ፣ በጣም አስቸጋሪ ክፍል ውስጥ፣ መሬት ላይ ስንከባለል ነበር በእስር ያሳለፍሉት፡፡ አሁን አቶ ስዬ አብርሃ ታስሮ በነበረበት ጥሩ በሚባል ክፍል ውስጥ ለአምስት ታስረን እንገኛለን፡፡ አቶ መላኩ ተፈራ፣ አቶ መላኩ ፈንታ ና አንድ ባለሃብት አብረውን ናቸው፡፡ አሁን አልጋ ላይ መተኛት ጀምሬአለሁ፡፡ ይሄ ለእኔ እንደ አዲስ ሕይወት ነው። አሁን ደስተኛ ነኝ። …ጊዜያችንን በጥሩ ሁኔታ ከፋፍለን እየተጠቀምንበት ነው፡፡ እናነባለን፣ እንወያያለን፣ የምንፈልጋቸውን መጽሐፍት ግን በምንፈልገው ጊዜ አናገኝም፣ በዚህ በኩል መጠነኛ ችግር አለ፡፡ በተረፈ ደህና ነኝ። እኔ ተስፈኛ ነኝ። እናንተም በተሰማራችሁበት ዘርፍ የምትችሉትን ሁሉ ለሀገራችሁ ለውጥ መታገል አለባችሁ…››

ከሁለቱም ጋር የነበረንን የ30 ደቂቃ ቆይታ ሳንጠግብ

‹‹በቃችሁ››

የሚለው የፖሊስ ድምጽ ተሰማ።

‹‹እናመሰግናለን፣ በቃ ሂዱ››

ሲል አንዷለም በእርጋታ ተናግሮ በሽቦ ስር አሾልኮ እጆቻችንን ጨበጠን። እስክንድር ደግሞ

‹‹‹ሲመቻችሁ ብቻ መጥታችሁ ጠይቁን፣ ሥራ እንዳይበደል!። ሥራችሁን ሥሩ››

በማለት ለእኛም ያለውን አሳቢነት ከምክሩ ጋር ደጋግሞ ገለጸልን – ሁሉንም ሰላም በሉልኝ በማለት። እንግዲህ እስክንድርን የምትሉ ሁሉ ሰላምታውን በእኔ በኩል አድርሻለሁ።

ለምን የሳሙኤል ዘሚካኤል ጉዳይ ያን ያህል ያስደንቀናል? (በትረ ያዕቆብ)

$
0
0

ከበትረ ያዕቆብ

በትረ ያዕቆብ

በትረ ያዕቆብ

ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፆች አካባቢ የህዝብን ቀልብ መሳብ የቻለና አሁንም ዋና መወያያ አጀንዳ ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ተከስቷል፡ የሳሙኤልዘሚካኤልየሀሰትዶክተር እናኢንጂነርነት፡፡ ጉዳዩ ብዙዎችን አጃኢብ አስብሏል ፤ አሁን በርካቶች ብስጭታቸዉን እና ቁጣቸዉን በተለያየ መንገድ እየገለፁ ይገኛል፡፡ ብዙ ሰዎች በአንድ ወቅት የስኬት ምልክታቸዉ እስከ መሆን የደረሰና አድናቆታቸዉን ያጎረፉለት ሰዉ ድንገት የሀሰት ሆኖ ሲያገኙት መደናገጣቸዉ አልቀረም፡፡

እርግጥ ነዉ ነገሩ ትንሽ የሚያስገርም ነዉ፡፡ ወጣቱ የሄደበት እርቀት ግራ የሚያጋባና ድፍረቱ የሚያስገርም ነዉ፡፡ ሌላዉን ትተን በሀገር ዉስጥ የሚገኙትን ዩንቨርሲቲዎች ስም ደጋግሞ እያነሳ ይህንን ሸለሙኝ ፣ ይህንን ሰጡኝ ፣ የረዳት ፐሮፌሰርነት ማዕረግ ተበረከተልኝ ወዘተ ማለቱ በእርግጥም ከማሰገረም አልፎ ብዙ ያስብላል፡፡ ያም ሆኖ ግን እኔን ይበልጥ ያስገረመኝ ጉዳዩ የዚያን ያልህ  እንደ ተዓምር የመታየቱ ነገር ነዉ፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ እየተደረገ ያለዉን ዉይይት ስመለከት እንዴ ነዉ ነገሩ ብየ መደነቄ አልቀረም፡፡

በዚህ ወጣት የተፈፀመዉ አሳፋሪ ተግባር ዛሬ የተከሰተ አዲስ ክስተት አይደለም ፤ የነበረና አሁንም  እየተፈፀመ ያለ ነገር ነዉ፡፡  እዉነቱን መነጋገር ካለብን መሰል ማጭበርበር ቤተ-መንግስት አካባቢ በጣም የተለመደ እና  ብዙዎች የተጨማለቁበት ተግባር ነዉ፡፡ ይታያችሁ ፣ ቤተ-መንግስት ነዉ ያልኩት፡፡ ይህንን ስናይ ወጣቱ የፈፀመዉ ተግባር የሚደንቅ አይመስለኝም፡፡ እንዴትስ ያስደንቃል፡፡

ዛሬ ሳሙኤልዘሚካኤልእድል ጥሎት ሁሉም ተረባረበበት እንጅ የኢህአዴግ ባለስልጣናት የትምህርት ማስረጃ ቢመረመር ስንት ከሱ የባሰ ጉድ ይገኝ ነበር፡፡ እንግዲህ ሀገርን ያህል ትልቅ ነገር እንመራለን የሚሉ  ግለሰቦች መሰል ተግባር በሚፈፅሙበት አገር የዚያ ወጣት ተግባር ጉድ የሚያስብልበት ምክንያት አይታየኝም፤፤ እንዴትስ ሊያስብል ይችላል፡፡ ከዚህ ይልቅ ቤተ-መንግስት ተቀምጠዉ አገርን የሚዘዉሩ ግለሰቦች ፣ በያንዳንዳችን እጣ ፈናታ ላይ የመወሰን ስልጣን በጉልበት የጨበጡ ባለስላጣናት የሀሰት ማስረጃ ሊያስደንቀን ፣ ሊያበሳጨን ፣ ሊያስደነግጠን ይገባ ነበር፡፡

ዛሬ በርካታ የኢህአዴግ/ህወሀት ጉምቱ ባለስልጣናት እንከዋን ትምህርት ቤት ገብተዉ ሊማሩ በበሩ እንኳን ሳይልፉ ባለሁለተኛ እና ሶስተኛ ድግሪ የመሆናቸዉ ጉዳይ ለብዙዎቻችን ሚስጥር አይመስለኝም፡፡ ዛሬ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲት ድግሪና ማስትሬት በቀጭን ትእዛዝ እንዳሻቸዉ የሚሰበስቡት ተራ ነገር ነዉ፡፡ ሲያሻቸዉም ከዉጭ በገንዘብ ይሸምቱታል፡፡ ሲልም እድሜ በሙያዉ ለተካኑ የቻይና እና የህንድ ዜጎች እንደፈለጉት አሳምረዉ አዘጋጅተዉ ኮንግራ ይሏቸዋል፡፡ከዛም ከለታት አንድ ቀን ብቅ ብለዉ ይህ አለን ይላሉ፡፡ ይህ ነዉ ለኔ አሳፋሪዉ ፣ አስደንጋጩ፡፡

በእንዲህ አይነት መልኩ በርካታ ትልልቅ ባለስልጣናት የሀሰት የክብር ካባ ለመደረብ ሞክረዋል፡፡ አሁንም ብዙዎች ይህንን መንገድ ቀጥለዉበታል፡፡ ከብዙ ወራት በፊት አንድ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዉስጥ የሚሰራ ወዳጄ ሲያጫዉተኝ “ዩንቨርስቲዉ በካድሬ መመራት ከጀመረበት እለት አንስቶ በርካታ የኢህአዴግ መኳንንቶችን በማዕረግ” አመርቋል” ነበር ያለኝ፡፡ ይታያችሁ እርሱ ያለዉ “በማዕረግ” ነዉ፡፡ ይህ ማለት ሳይማሩ ፣ ሳያጠኑ ፣ ሳይፈተኑ ኤ በ ኤ ይሆናሉ ማለት፡፡ ለኔ ይሄ ነዉ አስደንጋጩ ጉዳችን፡፡ ይህ ወዳጄ እንደነገረኝ አልፎ አልፎም በዉጭ ዩኒቨርስቲ መማር የሚፈልጉ ከተገኙም የሚፈልጉትን የትምህርት መስክ መርጠዉ የመዓረግ ተመራቂ ተብሎና ሁሉም ነገር ተሟልቶለት ይሰጣቸዋል፡፡ እኒህ ሰዎች ናቸዉ ዛሬ ሀገሪቱን የሚመሩት ፤ ከእኛ በላይ አዋቂ የለም የሚሉን ፣ የጭቆና ቀምበር ጭነዉ ፍዳችንን የሚያሳዩን፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁለት ግለሰቦች ማንሳት እዉዳለሁ፡፡ ይህ ለምሳሌ ያህል ብቻ ነዉ፡፡ የመጀመሪያዉ በአንድ ወቅት እንደ ምሁር ለመፈላሰፍ ሲቃጣዉ የነበረዉ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ነዉ፡፡ ሰዉየዉ ትምህርቱን ከዩንቨርሲቲ አቋርጦ በረሀ እንደ ወረደ እና ከ17 አመት የትጥቅ ትግል በኋላ በለስ ቀንቶት ቤተ-መንግስት እንደገባ ነዉ ነበር የምናዉቀዉ፡፡ ሆኖም ከእለታት በአንዱ ቀን አቶ ምን ይሳነዋል ባለሁተኛ ድግሪ ምሁር ነዉ ሲባል ሰማን ፣ ያም አልበቃ ብሎ ሌላም እንዳከሉበት የቀብሩ እለት ተነገረን፡፡ የአቶ ሳሞራ የኑስም ታሪክ ተመሳሳይ ነዉ፡፡ 11ኛ ክፍል አቅርጠዉ በረሀ ገብተዉ እንደታገሉ እንጅ ሌላ የምናዉቀዉ ነገር አልነበረም፡፡ ሆኖም  እርሳቸዉ ከ11 ክፍል በአቋራጭ ከፈለጉት ቦታ ላይ ጉብ አሉ፡፡ በሀዉልታቸዉ ላይም ባለ ሁለተኛ ድግር ምሁራ ናቸዉ ተብሎ ተፃፈ፡፡ እንዴት ብሎ የጠየቀም አልነበረም፡፡ እስከማዉቀዉ ድረስ በጉዳዮ ላይ ጥያቄ ያነሳ ብቸኛ ሰዉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ብቻ ነዉ፡፡ ዛሬ “ለእዉነት ቆሜያለሁ” የሚለዉ ሬድዮ ፋናም ያኔ አዳች ነገር ትንፍስ አላለም ነበር፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በቅርቡ ብዙ አፍሪካዊ ጋዜጠኞች  የተሳለቁበት በሀሰት የትምህርት ማሰረጃ በመንግስት ሴራ የአፍሪካ ህብረት አካል በሆነ ድርጅት ዉስጥ ትልቅ ስልጣን እስከመጨበጥ የበቃዉ የኢህአዴግ ካድሬም በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡

እንግዲህ ይታያችሁ እነዚህ ሰዎች ሀገር መሪ ነን ይላሉ፡፡ እነዚህ ናቸዉ የሀገሪቱን ፖሊሲና እስትራቴጅ ቀራፂያን ፣ እነዚህ ናቸዉ ሀገሪቱ እና እኛን ወክለዉ ከሌሎች ጋር የሚደራደሩት ፣ እነዚህ ናቸዉ ዛሬ በእያንዳንዳችን ህልዉን ላይ ወሳኝ ሆነዉን የሚገኙት፡፡ ይህ ነዉ እኔን ይበልጥ የሚያሳፍረኝ ፣ የሚያሰገርመኝ፡፡ ይህ ነዉ ለኔ ትልቁ ጉድ፡፡ እንዴት ነዉ እንዲህ አይነት የሀገር መሪዎች ባሉበት ሀገር አንድ ከደሀ ቤተሰብ የወጣ ልጅ የፈፀመዉ የማጭበርበር ተግባር የሚደንቀዉ፡፡ ነዉ ወይስ አላዉቅም ልንል ነዉ፡፡

ከባለስላጣናቶቻችን እና ከእኛ ዜጎች አልፎ ተርፎ እንኳ በየዩንቨርስቲዉ በዶክተር እና ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ስም የሚያጭበረብሩት የዉጭ ዜጎች በርካታ አይደሉም? የመጀመሪያ ድግሪ ይዘዉ በዶክተር ስም የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑ ወጣት ልጆች ላይ ሲቀልዱ አላየንም ፣ አልሰማንም ? ለምሳሌ እንኳን በቅርቡ ወደ አንድ የዉጭ ዩንቨርስቲ  ሁለተኛ ድግሪዉን ለመማር ያቀና ወጣት ዶክተር ነኝ ብሎ ካስተማረዉ የዩንቨርሲቲ መምህሩ ጋር በአንድ ክፍል ዉስጥ ለትምህርት እንደተገናኙ ሲተረክ ሰምተናል፡፡

በጥቅሉ እንነጋገር ከተባለ በርካታ ጉድ በዙሪያችን አለ፡፡ ዘርዝረን አንጨርሰዉም፡፡ በመሀከላችን በርካታ የቀበሮ ባህታዊያን እንዳሉ ልብ ልንል ያገባል፡፡ ይህ እየሆነ ባለበት አገር የሳሙኤልተግባር ለኔ ብዙ የሚያስደንቅ ነዉ ብየ አላስብም፡፡ እንዴዉም በአንድ ግለሰብ የማጭበርብር ተግባር ላይ ብቻ ማፍጠጡ ችግሩ እንደሌለ ያስመስለዋል ፤ ወደ መፍትሄም አይወስድም፡፡ ስለዚህም ችግሩን ሰፋ አድርጎ ማየትና አፍረጥርጦ መነጋገር ተገቢ ነዉ እላለሁ፡፡ ሬድዮ ፋናም ቢሆን “ለእዉነት ቆሜያለሁ” የሚል ከሆነ በአንድ ግለሰብ ተግባር ላይ ብቻ ከማንባረቅ በዘለለ የሌሎችንም በተለይም ሀገር እንመራለን በሚሉ የኢህአዴግ/ህወሀት አምባገነን ባለስልጣናት እየተፈፀሙ ያሉ ማጭበርበሮችን ሊያጋልጥ ይገባል፡፡ እርግጥ ኢህአዴግ አምጦ ከወለደዉ ተቋም ይህን መጠበቅ ሞኝነት ነዉ፡፡ ለሁሉም ቸር እንሰንብት !

የጀኔራሎቹ የጓዳ ሽኩቻ! –ቀጣዩ ኢታማዦር ማን ነው?

$
0
0

በላይ ማናዬ

(ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ በአዲስ አበባ የሚታተም)

‹‹ደመወዝ አነሰኝ ብሎ ጭማሪ የሚጠይቅ ካለ አሁንኑ ከሰራዊቱ መልቀቅ ይችላል፡፡›› ይህ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም የሆነው ጀኔራል ሳሞራ የኑስ ሁለተኛው የሰራዊት ቀን በተከበረበት ሰሞን ባህር ዳር ከተማ ሙሉዓለም አዳራሽ ከተሰበሰቡት የሰራዊቱ አባላት መካከል የደመወዝ ጭማሪን በተ
መለከተ ለተነሳለት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ የተናገረው ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከአጼ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ዘመናዊ ውትድርናና የጦር ስልት ሰልጣኝ ወታደሮችንና መኮንኖችን በተደራጀ ስልጠና ማፍራት መጀመሯ ይጠቀሳል፡፡ በሀረርና ሆለታ የጦር አካዳሚዎች በመታገዝ ዘመናዊ የውትድርና ሳይንስ ትምህርት መሰጠት የተጀመረው በዚሁ በንጉሱ ዘመን ነበር፡፡ በዚህ መልኩ እየተደራጀ የመጣው የሀገሪቱ ሰራዊት እስከ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን መምጣት ዘመን ድረስ የሀገሪቱ ብሄራዊ ሰራዊት ሆኖ ለመዝለቅ ችሏል፡፡ ሆኖም የደርግ ውድቀትን ተከትሎ በነበረው ጊዜ አያሌ የሰራዊቱ አባላት ለስደትና ሞት እንዲሁም ለብተና ለመዳረግ በቅተዋል፡፡
millitery ethiopian
(በእርግጥ ቀደም ብለው የተማረኩትን የቀድሞው የሰራዊቱ አባላት በኢህአዴግ ውስጥ ማግኘት እንደሚቻል ኩማ ደመቅሳ (የፖሊስ መቶ አለቃ እነደነበር ይነገርለታል)፣ እና ተራ ሚሊሻ እንደነበር የሚነገርለት አቶ አባዱላ ገመዳን ከፊት መስመር ላይ በማስቀመጥ መጥቀስ ይቻል ይሆናል፡፡ እንደነዚህ ያሉት የቀድሞው ሰራዊት አባላት ደርግ ከመውደቁ በፊት ከድተው የህወሓትንና የኢህዴንን ታጋዮች የተቀላቀሉት ናቸው፡፡)

እናም በጊዜው ታጋዮች ሀገሪቱን በሙሉ ለመቆጣጠር መቻላቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰራዊት (የደርግ ሰራዊት ብቻ ብሎ ማቃለሉን አልፈለግሁትም) ሜዳ ላይ ተበትኖ እንደቀረ ይታወሳል፡፡ ስለሆነም የኢህአዴግ ሰራዊት ሲያሸንፍ ሊያስተምሩት የሚችሉ አንዳንድ የቀድሞው ሰራዊት አባላት መኮንኖችን ብቻ አስቀርቶ ሌላውን ወደጎን ገፍቶታል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ሙሉ ለሙሉ ሲፈርስ ያለቀው ሰራዊት አልቆ በዚያው የሸሸውም የመን ላይ ለእስር ተዳርጎ ከፍተኛ ስቃይ መጋፈጡ የአደባባይ እውነት ሆኖ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያለ አንዳች ባህር ኃይል፣ ያለ አንዳች የተፈጥሮ የባህር በር የቀረች ሀገር ለመሆን ተዳርጋለች፡፡ አሁን ያለው መከላከያ ሰራዊታችን የምድርና የአየር ኃይልን ብቻ ያቀፈ ነው፡፡ የምድር ኃይሉ ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ በቀድሞ ታጋዮችና በቅርብ ጊዜ ምልምሎች የተደራጀ እንደሆነ ሲነገርለት፣ አየር ኃይሉ ላይ ግን ኢህአዴግ እንደገባ የአየር ኃይል ሳይንስን እንዲያስተምሩት የመረጣቸውን ጥቂት የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላትን በውስጡ የኋላ ደጀን አድርጎ ይዞ መቆየቱ ይነገራል፡፡

በአጠቃላይ ህወሓት/ኢህአዴግ ደርግን አሸንፎ ስልጣን ላይ እንደወጣ በትግል ይዞት የመጣውን ሰራዊት ‹‹ብሄራዊ ሰራዊት›› ለማድረግ ችሏል፤ ወዲያውም እዙ በመለስ ዜናዊ ስር እንዲሆን መደረጉ ታወቀ፡፡ ኢህአዴግ እንደገባ አካባቢ ብዙ ሰዎች ሰራዊቱን ‹የገበሬ ሰራዊት› እያሉ ይጠሩት እንደነበር
ይታወሳል፡፡ በሂደት ግን ቀድሞ የነበሩትንና ሌሎች አዳዲስ የወታደራዊ ትምህርት ቤቶችን በመጠቀም ሰራዊቱን የማዘመን ስራ ተሰርቷል፤ አዳዲስ የሰራዊቱ አባላትን በአዲስ ዘመናዊ ስልጠና ኮትኩቶ ወደሰራዊቱ ማካተት ተችሏል፡፡ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ሰራዊት ልክ እንደ አያቶቹና አባቶቹ ሁሉ ግዳጁን
በብቃት የመወጣት ተፈጥሮአዊ የጀግንነትና የግዳጅ ስብዕናን የተላበሰ እንደሆነ ብዙዎች ምስክርነታቸውን ይሰጡታል፡፡ በእርግጥም የሰራዊቱ ጀግንነት ሊካድ የሚችል አይደለም፤ ሀቅ ነውና፡፡ አንዱ ማሳያ የሚሆነንም በተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ግዳጆች ላይ አመኔታን አትርፎ በመመረጥ በተ
ሰማራበት ግንባር ሁሉ በሚገባ ግዳጁን ለመወጣት መቻሉ ነው፡፡

አሁን ያለው ሰራዊት በአዲስ መልክ ‹ብሄራዊ ሰራዊት› ሆኖ በአዋጅ የተደራጀው የካቲት 7/1988 ዓ.ም እንደነበር ይታወሳል፡፡ (ይህን ቀን ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ የሰራዊት ቀን በሚል ሰራዊቱ እንዲያከብረው ተወስኖ ሁለት ጊዜ ለማክበር ችሏል፤ የአድዋ ድል የተመዘገበበት ታሪካዊ ቀን እያለ ይህኛው እንዴት ‹‹የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቀን›› ተብሎ እንደተመረጠ አወዛጋቢ ቢሆንም ቅሉ!) ለማነኛውም በማደራጃ አዋጁ ላይ የመከላከያ ሰራዊቱን ግዳጅና ‹የማንነት› ተዋጽኦ በአጭሩ ለመግለጽ ተሞክሯል፤ ‹‹የሐገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር፣ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ፣ ከማናቸውም ፖለቲካ ድርጅት ወገንተኝነት ነጻ በሆነ ሁኔታ ተግባሩን የሚያከናውን ሰራዊት ማደራጀት…›› በሚል፡፡

ቃል የሚዋሸከው እንግዲህ እዚህ ጀምሮ ነው፡፡ ‹‹ሚዛናዊ ተዋጽኦ›› እና ‹‹ከማናቸውም ፖለቲካ ድርጅት ወገንተኝነት ነጻ…›› የሚሉትን ሀረጎች ወስደን ተግባር ላይ ያለውን ስናይ እውነታው ለየቅል መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ኢህአዴግ ነባሩን የኢትዮጵያ ሰራዊት አፍርሶ በምትኩ ተሸክሞ ይዞት የመጣውንና ለስልጣኑ ያበቃውን ሰራዊት ‹ብሄራዊ ሰራዊት› ነው ሲል ወገንተኛነቱ እንደምን ያለ ሊሆን እንደሚችል ቀድሞ የሚያውቀው ጉዳይ ይሆናል፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ካሉት አጠቃላይ የሐገሪቱ የጦር ጀኔራሎች መካከል ስንቶቹ የህወሓት ቀኝ እጅ እንደሆኑ ከኢህአዴግም ሆነ ኢትዮጵያ ህዝብ የተሰወሩ አለመሆናቸውን ኢህአዴግ ሊያጣው የሚችለው እውነታ አይደለም፡፡

እስካሁን ከነበሩትና አሁን ካለው የመከላከያ ሰራዊቱ ኢታማዦር ሹሞች መካከል ስንቶቹ የህወሓት እንደሆኑስ የማያውቅ ማን ነው? በእርግጥ አሁን ላይ በጣም አስቸጋሪ በሚባሉ የጦር ግዳጆች ላይ የትኞቹ የሰራዊቱ ክፍሎች በቀዳሚነት እንደሚመደቡ ይታወቃል፡፡ በመከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ክፍል ውስጥ የሚሰራ አንድ ባለማዕረግ የሰራዊቱ አባል ስለዚህ ሁኔታ ሲገልጽ፣ ‹‹ያስፈልገኛል የምትለውን መሰረታዊ ነገር ለማግኘት እንኳ በጣም አዳጋች ነው፡፡ ሌላው ቢቀር በተለያዩ የሀገሪቱ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ጥበቃ የሚያደርጉ በረሃ አካባቢ ያሉ የሰራዊቱ አባላት ምን አይነት የግዳጅ ሁኔታ ላይ እንዳሉ የሚያውቀው ያውቀዋል፡፡ ስለሰራዊቱ ብዙ መናገር አይቻልም እንጂ ስንት ነገር አለ መሰለህ? አድራጊ ፈጣሪዎቹ ግን እዚህ አዲስ አበባ ላይ ያሉት ሰዎች ናቸው፡፡ ምደባው ጎጠኝነትና ጎሰኝነትንም እንደ ስውር መስፈርት ያስቀመጠ ነው፡፡›› ይላል፡፡በእርግጥ የእነዚህ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ግዳጃቸውን የሚወጡ የሰራዊቱ አባላት ሁኔታ እዚህ መሀል ሀገርና አንጻራዊ ሰላም ባለበት ቦታ ላለነው ኢትዮጵያውያን በግልጽ ባይታየንም፣ በከፍተኛ የሀገርና የወገን ፍቅር ስሜት ሆነው ግዳጃቸውን ስለሚወጡ ግን ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ የእነዚህ ቆራጥ ወገኖቻችን ጥረት ነው ሀገርንና ህዝብን የሚ
ያስከብረው፡፡ ዳሩ ግን እንዲህም ሆነው ግዳጃቸውን ሲፈጽሙ ትንሽ እንኳ የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጥያቄ ሲያነሱ፣ ‹‹ደመወዝ አነሰኝ ብሎ ጭማሪ የሚጠይቅ ካለ አሁንኑ ከሰራዊቱ መልቀቅ ይችላል፡፡›› የሚል አግባብ ያልሆነና አሳፋሪ መልስ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህን መሰሉን መልስ የሚሰጡት ጀኔራሎች እዚህ አዲስ አበባ ላይ የተንደላቀቀ ኑሮ እየኖሩ፣ ምንጩ ያልታወቀ ሀብት እያፈሩ መሆኑ ደግሞ ግርምትን የሚያጭር ነው፡፡

አሁን አሁን ጄኔራሎቻችን የብዙ ኃብት ባለቤቶች እንደሆኑ ይነገራል፤ ይህ ፎቅ የጀኔራል እገሌ ነው፣ ያኛው ደግሞ የጀኔራል እገሌ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ጀኔራሎች ገቢያቸው ምን ያህል ነው ብለን ስንጠይቅ ግን ምላሽ አናገኝም፤ ገቢያቸው ይሆናል ብለን ከምናምነው ጋር ለማገናዘብ ከሞከርን ደግሞ ሰዎቹ ሙስና ውስጥ መዘፈቃቸውን ለመናገር እንደፍራለን፡፡ (በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ ተደርጎ የተሾመው ሰው ራሱን ከሙስና ያራቀ እንደሆነ የሚነገርለት ሲሆን በሌሎች ሰዎች ላይ ያለውን አሰራር በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ ምንጮች ያነሳሉ፡፡ ‹‹ተውአቸው የሰሩትን ፎቅ ይስሩ፤ በባንክም የሚያስቀምጡትን ያህል ያስቀምጡ፤ በቅርብ ጊዜ ግን ሀብቱ ለሚመለከተው የኢትዮጵያ ህዝብ ይመለሳል›› በማለት መናገሩንም የሚያስታውሱ አሉ፡፡ ይህን የሰውየውን ባህርይ ያጤኑት አንዳንድ ጀኔራሎችና ባለስልጣናት ታዲያ ሰውዬውን ከሙስናና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ለማነካካት ሙከራ ማድረጋቸው አልቀረም፤ እስካሁን እየተሳካላቸው እንዳልሆነ ቢነገርም ቅሉ፡፡) ዝሆኖቹ ጀኔራሎች ይህ ሁሉ ነገር አያሳስባቸውም፤ ተቆጭም ያላቸው አይመስሉም፡፡ እነሱን የሚያሳስባቸው በመካከላቸው ያለውና ሊኖር የሚገባው የእርስ
በእርስ የበላይነት ነው፤ በስልጣንም በሀብትም፡፡ ባለ አራት ኮከብ ጀኔራሉ ሳሞራ የኑስ በመለስ ዜናዊ ምርጫ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ተደርጎ የተሾመው የዛሬ ሰባት አመት ገደማ እንደነበር ይታወሳል፡፡ (የመጀመሪያው ባለ ሙሉ ጀኔራል ማዕረግ ያገኘ በሚል ምስሉ ብሄራዊ ሙዚየም የተቀመጠለት የጦር ሰው ሳሞራ የኑስ ነው፡፡) ይህ ሰው እስካሁን በስልጣን ላይ ለመቀመጡ ዋነኛ ምክንያት የሚባለው ለመለስ ዜናዊ የነበረው ቅርበትና ታዛዥነት ነው፡፡ በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድመው ኖሮ ሳሞራን ከኢታማዦርነቱ የማንሳት እቅድ እንደነበረው ይነገራል፡፡

ይህንን ጠንቅቆ ያውቅ የነበረው ጀኔራል ሳሞራ ታዲያ የሚሻርበትን ቀን ሲጠብቅ መለስ ህይወቱ በማለፉ በያዘው ቦታ ለመደላደል ስራዎችን መስራት እንደጀመረ ይወሳል፡፡በመለስ ዜናዊ እቅድ ውስጥ ሳሞራን እንዲተካው ተዘጋጅቶ የነበረው ደግሞ ሳሞራ የሙሉ ጀኔራልነት ማዕረግ ሲደፋለት በሁለተኛነት ደረጃ የሌትናት ጀኔራልነት ማዕረግን የተጎናጸፈው የ‹ብአዴኑ› ወጣቱ የጦር ሰው አበባው ታደሰ ነበር፡፡ ይህን የአበባው ወደ ኢታማዦር ሹምነት መምጣትን አጥብቀው ከማይፈልጉት ሰዎች ደግሞ ጀኔራል ሳሞራ ዋነኛው እንደሆነ ይነገራል፡፡ በዚህም የተነሳ የመለስን ህልፈት ተጠቅሞ ሳሞራ አበባውን ከሰራዊቱ የማግለል ስራ እንደሰራ የሚጠቅሱ አልጠፉም፡፡ እናም የማዕከላዊ እዝ ዋና አዛዥ የነበረውን ሌትናንት ጀኔራል አበባው ታደሰን በቦታው መቆየት ሳሞራ የፈለገው አይመስልም፡፡ አበባው ከማዕከላዊ እዝ አዛዥነት እንዲነሳ ተደረገ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ለሳሞራ እምብዛም ቅርብ እንዳልሆነ የሚነገርለትን ሌላው ‹ጠንካራ› ሰው ሌትናንት ጀኔራል ሳዕረ መኮንን (የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ የነበረ) ከኃላፊነቱ እንዲነሳ ተደረገ፡፡ አሁን ጀኔራል ሳሞራ ስጋቶቹን ያቃለለ መሰለ፡፡

ሂደቱ በዚህም የሚያበቃ እንዳልሆነ ነው ምንጮች የሚጠቁሙት፡፡ በተለይም በሌትናት አበባው ታደሰ ላይ ያለው ስጋት እሱን ከኃላፊነት በማንሳት ብቻ የሚያበቃ አልሆነም፡፡ በማዕከላዊ እዝና በሌሎችም በሰራዊቱ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዳለው የሚነገርለት በእድሜ ትንሹ ጀኔራል አበባው ታደሰ ኃላፊነቱ ከተነሳም በኋላ ከፍተኛ ክትትል እንደሚደረግበት ነው የሚነገረው፡፡ በተለይም ከሰራዊቱ ከአዛዥነቱ ከተነሳ በኋላ ምዕራብ ጎጃም አዊ ከሁለት ሲቪሎች ጋር አንድ ሻይ ቤት እንደታዬ መነገሩ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲነሳበት አስችሎአል፡፡ ይህን ተከትሎ በማዕከላዊ እዝ ሲደረግ በነበረው ግምገማ ወቅት አንዳንድ የሰራዊቱ አባላትን በጎጠኝነት ሰበብ የማደናገር ሁኔታ እንደታዬ ይጠቀሳል፡፡ አንዳንዶች በግልጽ ‹‹የአበባው አሽከር ነበርኩ ብለህ ሂስህን ዋጥ!›› እየተባሉ እንደተገመገሙ ምንጮች ያወሳሉ፡፡

በእርግጥም አሁን ጀኔራል ሳሞራ ጡረታ የሚወጣበትን ጊዜ በሚገባ ያራዘመ ይመስላል፤ ስጋት ያላቸውን ሰዎችም ከቁልፍ ቦታቸው ለማሸሽ ችሏል፡፡ በመከላከያ ሰራዊት ደንብ መሰረት ቅድሚያነትና ብቃት (ሲኔሪቲ) ትልቅ ተጽዕኖ አላቸው፡፡ ይህን ካየን ደግሞ አሁን ላይ ሰራዊቱ ውስጥ ካሉ ጀኔራሎች መካከል የሳሞራ ምትክ ሊሆን የሚችለው በቀዳሚነት ከሳሞራ አንድ ደራጃ ወረድ ብሎ የሚገኘውና ከሌሎቹ ቀደም ብሎ ሌትናት ጀኔራልነትን ያገኘው አበባው ታደሰ ነበር፡፡ ይህ እንዲሆን ያልፈለገው ሳሞራ ግን ሰውዬውን ገለል ማድረጉን መርጧል፡፡ ሳዕረንም እንዲሁ፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ጀኔራል ሳሞራ እንዲተካው የሚፈልገው አሁን በአብዬ የሰላም ማስከበር ግዳጅን በአዛዥነት የሚመራው ሌትናት ጀኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ነው፡፡ ይህ ሰው ሌትናት ጀኔራልነቱን ያገኘው በቅርብ ቢሆንም የእሱን ሲኔየሮች ከኃላፊነት ገለል በማድረግ እሱ ወደመሪነቱ እንዲመጣ የተፈለገ ይመስላል፡፡ ሌትናት ጀኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ከጄኔራል ሳሞራ ጋር ጥብቅ ወዳጆች እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ ዮሃንስ ከፍተኛ ሀብት እንዳካበቱ ከሚነገርላቸው ጀኔራሎች መካከል ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ደመወዙ በአስራ ሺ የሚቆጠር ዶላር እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ ቢሆንም ግን ሀብታምነቱ አሁን የዚህ ደመወዝ ባለቤት ከመሆኑም የቀደመ ለመሆኑ መረጃዎች ያሳብቃሉ፡፡ (ሌትናት ጀኔራል ዮሐንስ የደህንነቱን ስራ በኃላፊነት የሚዘውረው ጌታቸው አሰፋም ድጋፍ እንዳለው ይጠቀሳል፡፡)

በዚያም አለ በዚህ ግን አሁን ላይ ሳሞራ መለስ በህይት እያለ ከነበረው እቅድ በወጣ መልኩ በኢታማዦር ሹምነቱ መቆየቱ ሀቅ እንደሆነ ይገኛል፤ የጡረታ ጊዜውን ማንም ቆርጦ ማስቀመጥ የተቻለው የለም፡፡ በስብሰባዎች ወቅት በድፍረት እያንዳንዱን ነጥብ እያነሳ ይገስጻቸው ነበር የሚባልለት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አሁን የለም፡፡ ስለዚህም አሁን ሳሞራም ሆነ ሌሎች ጄኔራሎች ተቆጭ የሌላቸው እንደሆኑ ነው የሚነገረው፡፡ በትንሹም ቢሆን አቶ በረከት ስምዖን የመለስን ቦታ ተክቶ ለመገሰፅ የሚሞክርበት አጋጣሚ ቢኖርም እንደመለስ ግን አይደነግጡለትም፤ በስልጣናቸውም ላይ ለውጥ የሚያመጣ መስሎ አይሰማቸውም ነው የሚባለው፡፡ በመጨረሻም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ሚና እዚህ ላይ ማንሳቱ እምብዛም አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ በእርግጥ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ናቸው፡፡ ያም ቢሆን ግን ጀኔራሎቹ ለሰውዬው እንደቀድሞው አዛዣቸው መለስ ዜናዊ አድርገው የሚመለከቷቸው አይመስለኝም፡፡ እናም አሁን በሰራዊቱ ውስጥ ወሳኙ አድራጊ ፈጣሪው ሰው ሳሞራ የኑስ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ለዚያም ይመስላል ከሰራዊቱ ለተነሳለት ጥያቄ ‹‹ካልፈለግህ ልቀቅ…›› ምላሽ ለመስጠት የበቃው፡፡ ለዚያም ይመስላል ለቀጣይ የስልጣን ጊዜው ‹ስጋቴ› ናቸው ያላቸውን ሲኒየር ጀኔራሎችን ከአዛዥነት ያነሳቸው፡፡

ተባበር ወይንስ ተሰባበር!? (ዋስይሁን ተስፋዬ)

$
0
0

ሰኔ 10 ቀን 2006 እ.ኢ.አ.
ከዋስይሁን ተስፋዬ


በኢትዮጵያ ሃገራችን በፍቅር፣ በመተሳሰብና፣ በመቻቻል ለዘመናት የኖረ ህዝብ እርስ በርሱ በጥርጣሬና በጥላቻ ሲጎሻሸም፤ ቤተሰብ ከቤተሰብ መተማመን ጠፍቶ ግለኝነት ሲነግስ፤ የአብሮነታችን ማሰሪያ የሆነው ፍቅራችን ጠፍቶ አንዱ ብሄር በሌላው ብሄር ላይ ጥላቻን ሲዶልት፤ መከባበራችን ረክሶ አንዱ ሃይማኖት ሌላውን ሲጠራጠር፤ ባጠቃላይ በሃገሪቱ ፍቅር ጠፍቶ ጥላቻ ሲነግስ በማየቴ አዘንኩ። ገዢው የኢህአዴግ ከፋፋይ ሥርዓት የዘረጋው አፋኝ መዋቅር ህዝብ ከጥላቻ ውጪ ሌላ ምንም አይነት መረጃ እንዳያገኝ አፍኖ፤ በሃገሪቷ ሰላምና መረጋጋት እንዳይሰፍን፤ ብሎም ኢትዮጵያዊነት ቀስ በቀስ እየተሸረሸረና እየጠፋ እንደሆነ ሳስተውል ደግሞ ፈራሁ። በአንፃሩ ደግሞ ይህ አደገኛ ሁኔታ ለመናገር በሚዘገንን መልኩ አስከፊ በሆነበት በዚህ የጨለማ ዘመን፤ በተቃዋሚስምራሳቸውንሰይመው ‘እኔካልኩትበላይ ምንም ሊሆን አይችልም’በሚልአምባገነናዊአስተሳሰብ፤ በህዝብ ስምለህዝብነፃነትሳይሆን የራሳቸውንየግልፍላጎትለማሳካትየህዝብንበደልበማባባስ ላይ የተሰማሩ ስብስቦች እንደ አሸን በዝተው ስመለከት ተረበሽኩ። በመሆኑም በሃገራችን በጎ ነገር እንዲሰፍን በመመኘት፤ ያላስተዋለ ተገንዝቦ፣ አይቶ ዝም ያለም የሃገርና የህዝብ ውድቀት ነውና ማፈግፈጉን ትቶ ወደ እውነተኛው የህዝብ ነፃነት መንገድ ይራመድ ዘንድ፤  በዚህች አጭር ፅሁፍ ጥቆማዬን ለአንባቢያን ማቅረብን ፈቀድኩ።

ሁላችንም እንደምናውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነትና የሃገሪቱ ህልውና በኢህአዴግ መንግስት በጎ ፍቃድ ብቻ የሚወሰን መሆኑ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ግልፅ ነው። በመሆኑም መንግስት እንዳሻው ሃላፊነት በጎደለው አካሄድ ህዝብን ለዘመናት ሲያፈናቅል፤ ንጹሃን ዜጎችን መጥፎ ስም በመስጠት ባልሰሩት ሃጥያትና በተፈበረከ የሃሰት ውንጀላ በየእስር ቤቱ እንዲማቅቁ ሲያደረገ፤ የሃገሪቱን መሬት በፈቀደው መልኩ ለባእዳን ሃገራት ሲያድልና ሲሸጥና ብዙ ሌሎች በደሎችን በህዝብና በሃገር ላይ በተደጋጋሚ ሲፈፅም ማየት የተለመደ ሆኗል። በኔ አስተሳሰብ ኢህአዴግ ይህንን ማድረግ የቻለበት ዋንኛው ምክንያት የሚዲያ ተቋማትን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር በመቻሉ ነው። በሃገራችን የሚገኙት መንግስታዊ የሚዲያ ተቋማት የኢህአዴግን የዘረኝነት ፖሊሲ ብቻ በመስበክ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ስለ ሃገሩ አንድነት፣ ስለ ህዝቧ ፍቅርና፣ በሃገሪቱ ስላሉት የተቃዋሚ ድርጅቶች እንቅስቃሴ እንዳይሰማና እንዳያውቅ በማድረግ አስተሳሰቡ ከአካባቢው የማያልፍ ጠባብ አድርጎታል። ለዚህም በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲተውኑት ያየነው ትእይንት አይነተኛ ምስክር ነው። ለአንድ ሃገርና ህዝብ የወደፊት አቅጣጫና ህልውናን በመወሰኑ ረገድ ሚዲያ እጅግ ወሳኝ ድርሻ አለው።ኢህአዴግ በሚቆጣጠራቸው የሚዲያ ተቋማት የሚያሰራጨውን የዘረኝነትና የእርስ በርስ የጥላጫ መርዝ በመቋቋም የነፃነት ትግሉን ወደፊት መግፋትና ለውጤት ማብቃት የሚቻለው፤ ኢህአዴግ እየፈፀማቸው የሚገኙትን በደሎች ከማጋለጡ ባሻገር፤  ህዝቡ በተቃራኒው ስለአንድነትና ፍቅር እንዲሁም ስለተቃዋሚዎች በቂ እውቀት እንዲኖረውና፣ ልዩነቶቻቸውን አጥብበው በጋራ እንዲሰሩ የሚገባውን ጫና እንዲያደርግ፣ አልያም የመረጠውን መቀላቀል ይችል ዘንድ ሁለገብ መረጃዎችን በስፋት ለህዝብ ለማድረስ የሚሰራ የሚዲያ ተቋም መገንባት ሲቻል ብቻ እንደሆነ ይሰማኛል። በተለይ እንደ ኢህአዴግ የሚዲያ ጠላት በሆነና ህዝብን በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ ከፋፍሎ የእርስ በርስ ጥላቻና ቂም ለማስፋፋት ታትሮ በሚሰራ አረመኔአዊ አገዛዝ ስር ለወደቀ ህዝብ ነፃ የመረጃ ስርጭት እጅግ አስፈላጊ ነው።  

ሁላችንም እንደምናየው የኢትዮጵያ ህዝብ በአሁኑ ወቅት የተቃዋሚ ቡድኖች ከመጠን በላይ በመብዛታቸው ምክንያትና መረጃ በብቃት ስለማይደርሰው፤ የድርጅቶቹን አላማ፣ ግብ፣ ራእይ፣ በጎ ጎኖችና ግድፈቶች፣ እንዲሁም ሌሎች ልዩነቶቻቸውን በቅጡ መለየት ተስኖት፤ ምኑን ከምኑ፣ የትኛውን ከሌላኛው መለየት ባለመቻሉ ግራ በመጋባቱ ‘የነፃነት ትግል የውሸት፤ ፖለቲካ አይንህ ላፈር’ በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ተወስኖ፤ የሚደርስበትን ችግር ለማስቆም በጋራ ከመታገል ይልቅ በዝምታ መቀመጥን መርጦ ይገኛል። በመሆኑም የተቃዋሚ ድርጅቶች ያለ ህዝብ ተሳትፎ ብቻቸውን ሲያጨበጭቡ ይታያሉ።   

ከላይ ለመግለጽ የሞከርኳቸውንና ሌሎች መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ዋንኛ መሳሪያው ብቃት ያለው የሚዲያ ተቋም መኖር በመሆኑ የተለያዩ የተቃዋሚ ቡድኖች ተቋማትን መስርተው ሲንቀሳቀሱ እናያለን። ነገር ግን እዚህጋ ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ተቋማቱን መመስረት ብቻ ሳይሆን የሚያስተላልፉት የመረጃ ይዘቶችና አይነቶች እጅግ ወሳኝ መሆናቸውን ነው። በኔ እይታ የሚዲያዎች አትኩሮት በተለየ ሁኔታና በስፋት፤ በተቃዋሚዎች መካከል ያሉትን ልዩነቶች፣ የተቃዋሚዎችን በጎ ጎኖችና ግድፈቶች፣ ከገዢው መደብ ጋር ያላቸውን ልዩነቶች በመረጃ ማቅረብ፣  ለሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ያለ አድልዖ እኩል መድረክ የሚሰጡና በሃገሪቷ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተቃራኒ አመለካከቶች ያሏቸውን ምሁራንንና የፖለቲካ ሰዎችን በማወያየት ህዝብ በስነልቦና በእውቀት እንዲጎለብት በስፋት የሚሰሩ ሊሆኑ ይገባል። ከዚህ መነሾነት ሲስተዋሉ በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ መረጃን ለማስተላለፍ በሚል አላማ ከሚሰሩት የሚዲያ ተቋማት አብዛኛዎቹ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የኢህአዴግን መሰረታዊ አላማዎች ከማስተጋባት ያለፈ የሚጨበጥ ስራ ሲያከናውኑ አይታዩም። በእርግጥ አንፃራዊ በሆነ ሁኔታ ስመለከታቸው እንደ Addis Dimts Radio፣ SBS Australia፣ የVOA እሰጥ-አገባና እንወያይ የራዲዮ ዝግጅቶች ሊመሰገኑ  የሚገባ መሆኑን ለመጠቆም እወዳለሁ። 

ከአድማጮችና ከደጋፊዎች ብዛት አንፃር የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ስለሚመስለኝ ሃሳቤን ለመሰብሰብ ይሆን ዘንድ፤ ታዋቂ ሰዎችና የፖለቲካ መሪዎች ከአድማጮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በኢሳት ራዲዮ ምላሽ የሚሰጡበት፤ የ “ጥያቄ አለኝ” ዝግጅት ላይ፤ የኢሳት ቴሌቢዥንና ራዲዮ በማኔጅመንት ዳሬክተሩ በአቶ ነአምን ዘለቀና በጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ ትብብር መላሽ የነበረበትን ለሁለት ሳምንታት የተላለፈ ዝግጅት ላይ ከአንድ አድማጭ የቀረበ ጥያቄንና ከኢሳት የተሰጡ መልሶችን እንደምሳሌ ማንሳት አስፈላጊ ነውና ከዝግጅቱ ከታዘብኩት ጥቂት ልበል። እኝህ ኢትዮጵያዊ የኢሳት አድማጭ ለኢሳት ያቀረቡት ጥያቄ ከላይ ካነሳሁት መሰረታዊ ሃሳብ ጋር በፅኑ ስለሚገናኝና አድማጩ ኢሳትን ሊያስገነዝቡ የሞከሯቸው ጭብጦች በአምባገነን ስርዓቶች ለአመታት ሲሰቃይ ለኖረው ህዝብ ነፃነት መጎናፀፍ ጉልህ ሚና ስለሚኖራቸው፤ ጥያቄያቸውም የበርካታ ኢትዮጵያውያንም ጥያቄ እንደሆነ ስለምገምት ለአንባቢያን ጥያቄውን አቀርባለሁ።  

ምስጋና ይህን ወሳኝ ጥያቄ ላቀረቡት ለእኝህ ቀና ኢትዮጵያዊ የኢሳት አድማጭ ይድረስና፤ ባይሳካም የጉዳዩን ወሳኝነት ለማሳሰብ አቀራረቡን የበለጠ ግልፅ አድርገው በሁለተኛው ሳምንትም በድጋሚ ጠይቀዉት ነበር።  ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ልመለስና፤  እንደኔ አረዳድ የጥያቄያቸው መንፈስ ይህን ይመስላል፤ “እስካሁን ድረስ የተለያዩ መረጃዎችን ስትሰጡን ኖራችኋል። ነገር ግን የምትሰጡን መረጃዎች የኢትዮጵያ ህዝብን ወደ ድል ሊያበቁ አልቻሉም። ሁላችንም እንደምናየው ወያኔ የሚፈልገዉን ነገር ከማድረግ የሚያግደው ምንም ሃይል ሊፈጠር አልቻለም። የዚህ ዋና ምክንያት ደግሞ የምትሰጡት መረጃ ወያኔ በደሉን ከህዝብ ለመደበቅ የጭቆና ስልቱን በመቀየር ስህተቱን እንዲያርም ከማድረግና ከማገልገል በስተቀር ለህዝብ የረባ ፋይዳ አላስገኘም።  ለወያኔ ደካማ ጎኑን እንደምትነግሩት ሁሉ፤ ለተቃዋሚዎችም ስህተታቸውን እንዲያርሙ እንድታሳስቧቸው ዘንድ፤ ብሎም ተቃዋሚዎች እየሰሩት በሚገኙት በደል ምክንያት ለነፃነቱ ላለመቆም ሳይወድ እንዲሸሽ ለተገደደው የኢትዮጵያ ህዝብ ብርታት እንደሚሆነው በማስገንዘብ ከብዙ አድማጮች አስተያየት ቢሰጣችሁም፤ ተግባራዊ ልታደርጉ አልቻላችሁም። የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ሃይሎች ኢህአዴግ ከሚያጠፋው በላይ በኢትዮጵያ ላይ ትልቅ ጥፋት እያደረሱ ይገኛሉ፤ ምክንያቱም እኔ ካልኩት ሃሳብ በላይ ማንም ሊሆን አይችልም ብለው ስለሚያምኑ፤ ልስራ ብሎ የሚመጣውን አንዱ ሲያዳክም፤ አንደኛው ሌላኛውን ሲያጠፋ እያየን እንገኛለን።  ፊትለፊት አምጥታችሁ አገናኝታችሁ በጋራ እንዲሰሩ ልዩነቶቻቸውን ህዝብ አውቆ እንዲፈርድና የመረጠውን እንዲቀላቀል የማትረዱት ለምንድነው?”። 

ለጥያቄው በትብብር የሰጡትን መልስ መሰረት በማድረግ ለአቶ ነአምን ዘለቀና ለጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ ማሳሰብ የምፈልጋቸው ነጥቦች፤ የእኚህ  አድማጭ ጥያቄ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያከ መሆኑን፣ የተጠየቀው ጥያቄ እርስዎ(አቶ ነአምን) አስረግጠው እንዳስገነዘቡን የኢሳትን ነፃ ሚዲያነት የሚጋፋ ሳይሆን በተቃራኒው ኢሳት እንደ አንድ ለኢትዮጵያ ህዝብ መረጃ ለማቀበል የሚሰራ ነፃ የሚዲያ ተቋም በስፋትና በከፍተኛ ትኩረት ሊሰራበት የሚገባዉን ወሳኝ ጭብጥ የያዘ መሆኑን፣ ለህዝብ ነፃነት የሚበጀው አንድ የተቃዋሚ ድርጅት ትእይንት ባዘጋጀ ቁጥር ብቻ ወይንም ገዢው መንግስት በህዝቡ ላይ በደል በፈጠመ ጊዜ ብቻ የተቃዋሚ መሪዎችኒና ታዋቂ ግለሰቦችን ማነጋገር ሳይሆን፣ የህዝቡን የመረጃ ክፍተት መሰረት ያደረገና ዘላቂነት ያላቸው የተጠኑ ውይይቶችን ለህዝብ ጆሮ ማቅረብ እንዳለበት ለማስገንዘብ የቀረበ መሆኑን አውቃችሁ ግዴታችሁን ለመወጣት ብታተኩሩ መልካም ነው፣ የሚሉ ናቸው።

በዚህ አጋጣሚ የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሳቸውን በደሎች በማስተጋባት ብሶቱን ለማሰማት እለት ተለት የሚያደርገውን ጥረት ለማድነቅ እወዳለሁ። ሆኖም በኔ እይታ ይህ የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን ጥረት ብቻውን፤ ለህዝብ ብሶቱን ከማሰማት ያለፈ አስተዋዕፅዎ ይኖረዋል ብዬ አላምንም። በመሆኑም ኢሳት እንደ ነፃ የሚዲያ ተቋም ህዝቡ በቂ መረጃን አግኝቶ እየደረሱበት የሚገኙትን ከመጠን ያለፉ ችግሮች ለማስቆምና፤ ብሎም ለነፃነቱ በጋራ ትግሉን ይቀላቀል ዘንድ ለማስቻል፤ የህዝብ ብሶትን ከማሰማት ባለፈ እጅግ በጣም ብዙ መስራት የሚጠበቅበት መሆኑን በማስገንዘብ፤ የህዝብ ነፃነትን  እውን ለማድረግ በሚደረገው ትግል ላይ እንደ ሚዲያ ሃላፊነቱን ለመወጣት መጠነ ሰፊ የሆነ የዝግጅትና የአቀራረብ ለውጥ ማድረግ እንደሚኖርበት ጥቆማዬን አቀርባለሁ።

ይህን ሃሳብ ሳካፍል ፅሁፌን ያየ ያነበበ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ፤  እኔ የተረዳሁትን ተረድቶ መፍትሄውን እንዲፈልግ፤ አልያም ሃሳቤን ለማካፈል የሞከርኩት ነፃሚዲያያጎናፀፈኝንእድል’ተጠቅሜ ነውና፤ ከተሳሳትኩ የመታረም መብቴ የተጠበቀ መሆኑን እንዲረዳልኝ እጠይቃለሁ። ስለሆነም የኔ ማጠቃለያ የነፃ ሚዲያዎች ትኩረትና የአንባቢያን ጠቃሚ አስተያየት እንደሚሆን በእጅጉ ተስፋ አደርጋለሁ።

ቸር እንሰንብት

ከዋስይሁን ተስፋዬ

ttwasyhun@gmail.com

Comment

 


የልብ ርትዑ አንደበት! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 17.06.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)
Haile Medhin Aberaልክ የዛሬ አራት ወር ይህችን ዕለት ነበር ጀግና ካፒቴን አበራ ሀይለመድህን ሲዊዘርላንድ ጄኔባ ላይ ካለምንም እንከን፤ ካለምንም ግድፍት፤ ከለምንም ጥፋት ልቡ የተናገረውን ስኬታማ ክንውን ያደመጥነው።

የልቡ ርትዑ አንደበት መድረኩ ሆነ አድማጩ ድርጊቱ ብቻ እንዲሆን ወስኖ የማድረግ አቅሙን፤ የልቡን ፈቃድና ውሳኔ እንድናይ፤ እንድንማርበት ፈቀደልን። ተባረክ የእኔ ጌታ!

እንሆ የተባ ርትዑ የልብ አንደበት በሙሉ መስናዶ ተደራጅቶ የልብ ካደረስ ልክ ዛሬ አራት ወር ሆነው።

በዚህ በተሸኙ ወራቶች ስሜቱን? ፍላጎቱን? ውስጡን ማዬት ባይቻልም ልቡ የነገረውን፤ ልቡ የወሰነለትን፤ ዘመን የፈቀደለትን ተግባር ከዋኝ በመሆኑ መንፈሱ እረፍት ላይ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ከሁሉ በላይ ደግሞ የአንድም ፍጥረተ – ህይወት አካል ሆነ መንፈስ አደጋ ላይ ሳይጥል፤ ቂም ሳይተክል፤ ደም የሚያጋባ እርግማን ሳይፈጥር በጸጥታና በዝምታ የተከወነ መሆኑ ቁጭ ብሎ ሲያስበው ሆነ ሲመረምረው ሊጸጽተው የሚችል አንዳችም ነገር ከቶ እንደማይኖር ይሰማኛል።

ጀግና አበራ ሀይለመድህን የልቡ አንደበት ጥሩ ተናጋሪ የመሆኑን ያህል ጥሩ አድማጭም መሆኑን በቅደም ተከተል የወሰዳቸው እርምጃዎችና ፍሬዎቹ እራሳቸው መስካሪዎች ናቸው። ትውልዱ ከዘመኑ መቀደም ነገን አስልቶ ጥንቃቄን – በብልህንት፤ ብልህነትን – በማስተዋል፤ ማስተዋልን – በድርጊት ማስጌጥ አብነቱን አንቱ ያሰኘዋል። ዛሬ በዬዩንቨርስቲዎች የሚያልቁት ወጣቶች፤ በገፍ ወደ እስር ቤት የሚጣሉት ቀንበጦች፤ አብሶ ሴቶች ከግፉ በተደራቢነት በእዬስር ቤቱ የሚደርስባቸው ፆታዊ ጥቃቶች እና እንግልቶች ሁሉ ሲሰሉ ወጣት አበራ ሀይለምድህን ዬወሰደው እርምጃ አስፈላጊና የተገባ ወቅታዊ መሆኑን ያመሳጥርልናል።

ዕለታዊ ህይወት ለመምራት በስጋት ታፍኖ ራህብን ማስተናገድ፤ የመኖርን ነፃነት በጠራራ ጸሐይ ተቀምቶ ከሁለተኛ ዜግነት ደራጃ በታች መማቀቅ፤ የሰው ልጅ ለትንፋሹ እንኳን ይለፍ ደጅ ጥናት ወረፋ የሚጠይቀብት ቀን ላይ መደረስ፤ ዜጋ ለሚለብሰው ልብስ ቀለምን እንኳን ተሳቆ መሆኑ ሁሉም ሲጠቃለሉ በተለይ ነገ ኢትዮጵያን የሚረከቡ የብሩህ ራዕይ ባለቤት ወጣቶች „አሻምን“ በተገኘው መንገድ ሁሉ ለመግለጽ ቆርጠው በዬደቂቃው መሰዋታቸው ሲታሰብ ይህ ብርቅ ወጣት የወሰደው እርማጃ ሃቅን ያበራ፣ እውነትን ያነገረ፣ ለእውነት ዘብ አደር የሆነ ስለመሆኑ አስተርጓሚ ፈጽሞ አያስፈልገውም።

ዛሬ ዘመን ባመጣው የቴክኖሎጂና ሳይንስ የመረጃ ፍሰት የኢትዮጵያ ወጣቶች ትውልዳዊ ድርሻቸውን ለመወጣት ሌትና ቀን ሲባትሉ፤ ወያኔ ግን የሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት በመከተር ለእስር የዳረጋቸው ወጣት የብሎገር ትንታጎች፤ የሚረዷቸው ወላጆቻቸውን ሆነ የሚሳደጓቸውን ታናናሾቻቸውን ሜዳ ላይ ካለ ባሊህ ባይ ሲበተኑ ለሚያይ ህሊና በእርግጥም ጀግና አበራ ሀይለመድህን ዬወሰደው እርምጃ የጠራ – እውነትን የተንተራሰ ስለመሆኑ ያለ ይግባኝ ሊያስማማ የሚችል ፍሬ ነገር ሊሆን ይገባል።

ወጣት ጋዜጠኞች ብእራቸውና ጸጋቸው ያዬውን – ያደመጠውን ነው የጻፉት። ከዚህ ውጪ የፈጸሙት አንዳችም በደል የለም። ነገር ግን ከቅርብ ስለተገኙ ብቻ የቋሰኛው ወያኔ የጥቃት ሰለባ ነው የሆኑት። ታስረው በእግር ብረት እንደ ወንጀለኛ መቀጣጫ እንዲሆኑ ሲንገላቱ ቀን እራሱ ደም ያነባል። ምን አደረጉ እነዚህ ንጹኃን? ዘመን የሸለማቸውን ተጋሪ በመሆናቸው እንዴት እንደ ወንጀለኛ በሰንሰለት ይታሠራሉ?!

ስለሆነም ትውልዱ በወል መከራው – በጋራ እንባው፤ በሁለገብ ፍዳው ላይ ቢያንስ መስማማት ያለበት ይመስለኛል። ትውልዱ በተወለደበት በሀገሩ በመገለሉ – በመሬቱ ባይተር መሆኑ – በቀዩ መገፋቱ – በባዕቱ በጥቂቶች በመገላመጡ  እነዚህን ጉልህ ጥቃቶቹ አቅምን ፈጥረው የራዕይን ስምረት ሊያሳኩ የሚችሉ መንገዶችን እንዲጠረጉ መትጋት እንዳለበት ደወሉ ሊሆኑለት ይገባል እላለሁ፤ ካፒቴን አበራ ሀይለመድህን አበራ ያደረገው ይህንን ነው። ያደመጠውን — ያነበበውን —- አመሳጥሮ በተባ ድርጊት ተረጎመው። የልቡ አንደበት ማይክራፎን ወይንም ድምጽ ማጉያ ወይንም መንበር መድረክ አላስፈለገውም – በፍጹም። አጃቢም አላሰኘውም። የፕሮቶኮል ሥነ ምግባር ቅደመ ሁኔታ አልጠዬቀም – በፍጹም። ቁልፍ ከእጁ ነበር – መግል የሚያነባ የግለት ፍዳና ዕንባ። ስለሆነም በማድረግ ብቃት መሪነት „አሻፈረኝን“ ገለጸ።

የልብ ንግግር ህብር ነው። የልብ ንግግር – መስመር ነው። የልብ ንግግር – ደንበር ነው። የልብ ንግግር – የቁስለት ብር አንባር ነው። ዬልብ ንግግር ጥቃት አውጪ – የንቁ መንፈስ ሥር ነው። የልብ ንግግር አጃቢ አልቦሽ – ትጥቀ ሙሉ አሸናፊ ግብር ነው። የልብ ንግግር ለሽ ብሎ በተኛ በጠላት ሰራዊት ላይ ጥቃት ፈጽሞ ገዢ መሬቱን መቆጣጠር የሚያስችል ጉልተ ድል ነው። ረዳት ካፒቴን አበራ ያሰተማረው ምስክር ተግባሩ ይሄውን ነው።

ስለሆነም በተወሰን ደረጃ የእሱ ጉዳይ መልክ የያዙ ሁኔታዎች እንዳሉ ቢደመጡም በዚህ ዙሪያ አቅም ያላቸው ወገኖች ተግተው መሥራት ግን ይኖርባቸዋል። እርግጥ መረጃው እንደ ጠቆመው ፍሬ ነገሩ ትንፋሽን መሰብሰብ ያስችላል። ትንፋሹን በእርግጠኝነት እንዲቀጥል ለማድረግ ግን ጠንካራ ተከታታይነት ያለው ተግባር መሠራት አለበት።  ጊዜያዊ ነገር ጊዜያዊ ቋሚ ደግሞ ቋሚ ነው። ለቋሚ ዕውቅና በርትቶ መትጋት ያስፈልግ ይመስለኛል። ነገ ሌላ ቀን ነው። ሰው ይቀዬራል። ሁኔታም እንዲሁ። ቋሚ ከሆነ ግን መሬት ዬያዘ ይሆናል – እርግጠኝነትንም ያስውባል።

እግዚአብሄር ይመስገን ከሙያ አንፃር ዶር/ ሼክስፔር ፈይሳ ህይወታቸውን የሰጡበት ተግባር ከውነዋል። ጉዳዩ እትብታዊ ባለቤት ከሙያ አንጻር አለው። ይህም ቢሆን ጎን ለጎን እገዛው ፊርማ ማሰባሰቡ ወዘተ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ዘነፍ ያለች ነገር ቢፈጠር ጥቃቱ ብዙ ነገር ነው የሚያደቀው አምክንዮም እንዲሁ። ብዙ ተስፋን ነው የሚያራቁተው። ብዙ ነፍስ ነው ጥግ አልባ የሚሆነው። ስለሆነም እኔ እላለሁ ማሸነፍን በሁለት እግሩ ማቆም በእጅጉ ያስፈልግ ይመስለኛል። ሀገሩ ሲዊዝ ነውና።

በተረፈ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች የመወያያ መድረክ በቀጥታ ጉዳዩ ለሚመለከተው የሲዊዝ መንግሥታዊ አካል የጻፈው ደብዳቤ ከልብ የሚገባ ነው። አምላካችን የሰውን ልጅ ሲፈጥር እንዲያመሰግነው ብቻ ነው እንጂ ጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ ሁሉም ያለው የሁሉም ጌታ ልዑል ነው። የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች የመወያያ መድረክ በማህጸረ ስሙ ከረንት  ኃላፊነቱን ወስዶ እሳከሁን የሲዊዘርላንድ መንግሥት በረዳት አውሮፕላን አብራሪ አበራ ሀይለመድህን ጥያቄ ዙሪያ ለወሰዳቸው በጎ ምላሻዊ  ተግባራት እንዲሁም ቀጣይ እንክብካቤም ሁኔታውን ዘርዝሮ ምስጋና መጻፉ የላቀ ሥልጡን ተግባር ነው። ብልህነትም – መብልጥም፤ እንዲሁም ማስተዋልም ነው። ይህ በኸረ ተግባር ቀላል ሊመስል ይችል ይሆናል። እንደ እኔ በጥቂቱ ስሜቴ እንዲህ ነው ያዬው —-

  1. የጉዳዩ ባለቤትነትን አመሳጥሯል፤ አለሁ ባይነት ሲታደሉት ብቻ የሚገኝ ምርቃት – እናትነት!
  2. መስዋዕትንት ለመቅደም ፈቅዷል፤ በከፋ ቀን መገኘት – ማተበኝነት – ኪዳንም፤
  3. የጀግናውን ችግር ፈቅዶ በይፋ ተጋርቷል፤ አካላዊነትን በመሆን አቅልሟል።
  4. ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን አብራርቷል፤ የታሪካዊት ሀገርን የኢትዮጵያ ክብር ጠብቋል። አደራ አውጪነት!
  5. የመንፈስ ሥልጡን ህዝብ አምከንዮ በሚገባ ገልጧል፤ የራቀ የበለጠ አቅምን ማሳዬት ግልጽነት በብልህነት።
  6. የወገኖቹን ወላዊ የዕንባ አጋርነት ተስፋነትን አመሳክሯል፤ ብቻውን አለመሆኑን በቅኔ – ቃኝቷል።
  7. የጉዳዩ ተከታታይ ሂደትን – ወገኖቹ በንቃት መታደማቸውን  አሳምሮ ተርጉሟል፤
  8. ለነገን ቀና መንገድን ጠርጓል – ድልዳል አበጅቶለታል ለቀጣይ ፍላጎቱ — በትህትና።
  9. ለፈጣሪ አምላክም ተመችቷል። „ተመስገን!“ ማለት መምህር ነውና። „እናመሰግናለንም“ ትህትና በአክብሮት ነው።

http://ecadforum.com/2014/06/06/switzerland-thank-you-for-granted-resident-status-to-ethiopian-airlines-co-pilot/ ከረንት እኮ ከምሥረታው ጀምሮ እኔ ነኝ ያለ የፖለቲካ ድርጅት ባለነሰ እጅግ የላቀውን  ትውልዳዊ ሃላፊነት የከወነ የመወያያ መድረክ ነው። ሀገራዊ ጉዳዮች መሬት ይዘው በሁለት እግራቸው እንዲቆሙ –  መንፈስን በማደራጀት፤ ከግለሰብ ህይወት ጀምሮ እስከ ግዙፉ የፖለቲካ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ድረስ በመሆን ሸማ የከበረ ነው። መሬት የያዘ ጉልበታማ ሁለገብ  ክንውን ያበራ የመወያያ መድረክ ነው። የከረንት አንድ ሰው ባለበት ቦታ – አንድ እራሱ ግን እንደ አስር ነው። ከከረንት በፈለገው መልክና ሁኔታ አባልተኛው ቢለቅ እንኳን የከረንት ቤተኝነት ስሜትን ሆነ ንጹህ ፍቅር እኔ ነኝ ያለ ጀግና መፋቅ ከቶውንም አይችልም – ከረንት ባዕት ነው እንደዚህ ልበለው። እኔም የከረንት – ከረንትም የእኔ። እንደዚህ ባሉ ባለቤት ባጡ ጉዳዮች ደግሞ ከረንት እንዲህ የግንባር ሥጋ መሆኑ እጅግ ያስመሰግነዋል። የእኔም ብትሆኑ እግዚአብሄር ይባርካችሁ።

እርገት ይሁን — ልብ ያዘዘውን – ልብ የተለመውን – ልብ ያቀደውን – ልብ የቆረጠበትን – ልብ የወሰነለትን – ልብ የቆረበበትን የምልእተ ድምጽ ግፍ አድማጭ ሰው እራሱ ልብ ነው! አዎን! ጀግና አበራ ሀይለምድህን ልብም – የልብ -ልብም – ልባምም ነው። ሙያን በልብ የሞሸረ ጽናታዊ ዓዕማድ!

የኔዎቹ የፊታችን ሃሙስ በተለመደው ሰአት ከ15 እስከ 16 Radio Tsegaye  Aktuell Sendung www.tsegaye.ethio.info  አብረን ናፍቆትን እንታደም። ስለሆነም የቻላችሁ አዬር ላይ ያልቻላችሁ በማግስቱ ሲለጥፉት ከቻላችሁ አዳምጡ – በትህትና። በተረፈ ይህቺን ቀነ 17.06.2014 የጀግናን ፎቶ መንበር ላይ ማደረጉን አትዘንጉ እሺ! ሺዎችን ማፍራት የሚቻለው ከእጅ የገባን ድንቅ ማክበር ሲቻል ብቻ ነው …. ቸር ያሰማን –  ቸር እንሁን። አሜን!

 

ፈተናን ከመፈጠሩ በፊት አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር – ኢትዮጵያዊነት!

ልብ ያለው ጀግና የልቡን የሚያደርስልት እሱ እራሱ ብቻ ነው!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ኮካ ኮላ የተባለው መጠጥ አጠገቤ አይደርስም! (ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም)

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ኮካ ኮላ ትክክለኛ ነገር አይደለም!

boycottcocacola1-300x293የኮካኮላ ኩባንያ በታዋቂው የኢትዮጵያ ኮከብ ድምጻዊ ሙዚቀኛ በሆነው በቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ላይ ያደረገውን ስነምግባርን የጣሰ፣ የዘፈቀደ እና ፍትሀዊ ያልሆነ ድርጊት በማስመልከት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ በማህበራዊ እና በመገናኛ ድረ ገጾች ተቃውሞውን በመግለጽ የኮካ ኮላ ምርት እንዳይጠጣ ጥሪውን በማስተላለፍ ላይ ይገኛል፡፡ የዲያስፖፈራው ማህበረሰብ በማያያዝም የኮካ ኮላ ኩባንያ ተንኮልን ባዘለ መልኩ ቴዲን ነጥሎ በማውጣት የአድልኦ ሰለባ እንዲሆን አድርጓበታል በማለት ላይ ነው፡፡ የኮካ ኮላ ኩባንያ 32 የልዩ ልዩ አገሮች ሙዚቃ የቡድን አቀንቃኞችን ለብራዚል የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን/FIFA ዋንጫ የመክፈቻ ስነስርዓት ማድመቂያ ሙዚቃ አንድያቀነባበሩ አድርጎ ነበር፡፡ የኮካ ኮላ ኩባንያ በቴዲ አፍሮ ከተቀነባበረው የኢትዮጵያ ሙዚቃ በስተቀር የሁሉንም ዓይነት መሰል ሙዚቃዎች ለቅቋል!

አሁን የኮካ ኮላ ምርት እንዳይጠጣ የሚለውን መርህ እቀላቀላለሁ፡፡ ባለፉት ስምንት ዓመታት ሳቀርባቸው የነበሩትን ትችቶቸን ስትከታተሉ ለቆያችሁ በሚሊዮኖች ለምትቆጠሩ አንባቢዎቸ አሁን የኮካ ኮላ ምርት እንዳይጠጣ የሚለውን ቡድን እንድትቀላቀሉልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

የኮካ ኮላ ኩባንያ እና ተወካዮች በቴዲ ላይ ስህተት የፈጸሙ መሆናቸውን ከጥርጣሬ በላይ ተገንዝቢያለሁ፡፡ ስሙን አጥፍተዋል፣ ስብእናውን ዝቅ አድርገዋል እናም በአደባባይ በህዝብ ፊት አዋርደውታል፡፡ ይዞት የቆየውን ዝና እና ክብር ነፍገዋል፣ ስሙን ጥላሸት ቀብተዋል፣ እናም በስራው እና በጥሩ ስነምግበሩ ተጎናጽፎት የቆየውን ጥሩ ስሙን አጉድፈዋል፡፡ ፍትሀዊ ያልሆነ፣ ጨካኝነት የተሞላበት እና የሞራል ስብዕናን ባልተላበሰ ሁኔታ አስተናግደውታል፡፡

እ.ኤ.አ ጁን 7/2014 የኮካ ኮላ ኩባንያ ተወካይ የሆኑ ባለስልጣን የተናገሩትን ዘገባ በመጥቀስ እንደሚከተለው ቀርቧል፣ “ለፊፋ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ‘ዓለም የእኛ ናት‘ የሚለውን የኢትዮጵያ ልዩ ሙዚቃ ለማቅረብ ዓላማ በማድረግ ዜማውን እንዲያቀርብ እና እንዲቀረጽ እዚህ እኛ የኮካ እስቱዲዮ ድረስ ወደ አፍሪካ እንዲመጣ ተደርጎ ነበር፡፡ ከቴዲ አፍሮ ጋር የተደረገው የኮንትራት ስምምነት ‘ማንዳላ የተወሰነ’ በተባለ መቀመጫውን በናይሮቢ ያደረገ በሌላ ሶስተኛ አምራች ወገን የተፈጸመ ሲሆን ቴዲ አፍሮም ላደረገው ጥረት ሙሉ ክፍያ ተሰጥቶታል፡፡“ የባለስልጣኑ መግለጫ በመቀጠልም እንዲህ ይላል፣ “የድምጽ ቀረጻው ከተጠናቀቀ በኋላ ኮካ ኮላ ሴዋ የተባለ ኩባንያ የሚያዝዝበት የግል መጠቀሚያ ንብረት ነው፣ ሆኖም ግን ሙዚቃው እስከ አሁን ድረስ አልተለቀቀም፣ እናም በአሁኑ ጊዜም እንኳ ሙዚቃው ይለቀቃል የሚል ዕቅድ የለም፡“ በማለት አስተያየታቸውን ቋጭተዋል፡፡

እ.ኤ.አ ጁን 10/2014 በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የቴዲ አፍሮ ተወካይ ባለስልጣን የኮካ ኮላን አስደንጋጭ አዋጅ በማወጅ እና ቴዲ አፍሮ ሙያዊ ያልሆነ ባህሪ አሳይቷል በማለት በኮንትራት ስምምነቱ በግልጽ በተቀመጠው አንቀጽ መሰረት እምነትን የሚያጎድል ድርጊት ሲፈጸም ለህዝብ እንዳይለቀቅ የሚከለክል እንደሆነ አሳውቀዋል፡፡ መግለጫው በማያያዝም የኢትዮጵያን የዓለም ዋንጫ ልዩ ሙዚቃ ላይ ኮካ ኮላ ያልተገደበ ክልከላ ያደረገበትን ምክንያት ለማወቅ እኛ ጉዳዩን በድረ ገጽ ይፋ ከማድረጋችን በፊት ለእነርሱ ብናቀርበውም እስከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት ምላሽ ያለመስጠቱ እንቆቅልሽ ግራ እንዳጋባው ገልጿል፡፡ በዚህም መሰረት የኮካ ኮላ ኩባንያ መጥፎ እምነትን በማራመድ፣ እና “የእራሱን የኮኩባንያ የጽናት፣ የታማዕኒነት፣የህዝብ እምነት እና በእራስ የመተማመን መርሆዎች” በይፋ በመደፍጠጥ “በኩባንያ እብሪት” ተዘፍቆ ይገኛል በማለት ክስ አቅርቦበታል፡፡ የኮካ ኮላ ኩባንያ “የሚያዋርድ፣ የአድናቂዎቻችንን ስሜት እና የኮካ ኮላን ደንበኞች የሚጎዳ መግለጫ በመስጠቱ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡

የቴዲ አፍሮ ተወካይ የኮካ ኮላን ፍረጃ ሙሉ በሙሉ እንዲህ በማለት ውድቅ አድርጎታል፣ “ከቴዲ አፍሮ ጋር የተፈጸመው የኮንትራት ስምምነት ማንዳላ የተወሰነ/Manadala Limited በተባለው በናይሮቢ የሚገኝ የምርት ተቋም ሶስተኛ ወገንተኝነት አማካይነት ነው፡፡“ አቶ ምስክር ሙሉጌታ [የኢትዮጵያ እና የኤርትራ እንዲሁም የማናዳላ ቲቪ ብራንድ ማናጀር] የተባሉ የኮካ ኮላ ተወካይ ባለስልጣን እኛን ከቀረቡን በኋላ ተነሳሽነቱን በመውሰድ የኮካ ፕሮጀክትን ምርጫ እና በቀጣይነትም እኛን ወደ ኮካ ስቱዲዮ በማምጣት የኮካኮላ ማዕከላዊ፣ የምስራቅ እና የምዕራብ አፍሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ከማንዳላ ቲቪ ጋር የኮንትራት ስምምነት እንድንዋዋል አድርገዋል…” አቶ ምስክር እንደ ሰራተኛ እና ማንዳላ ቲቪ ደግሞ እንደ በርካታ የሙዚቃ ንብረት አገልግሎቶች ኃላፊ ለኮካ ኮላ ማዕከላዊ፣ የምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ተወካይ በመሆን በአንድ ዓይነት የህግ ማዕቀፍ እና በኮካ ኮላ ኩባንያ ላይ ለሚያስከትለው እንደምታ ዋና መስሪያ ቤቱን በአትላንታ ያደረገውን ተቋም በመወከል የተደረገ የኮንትራት ስምምነት ነው፡፡”

እንደዚሁም ደግሞ በኮካ ኮላ መግለጫ ላይ ጉልህ የሆኑ መጣረሶች የተስተዋሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የኮካ ኮላ ኩባንያ ከቴዲ አፍሮ ጋር ምንም ዓይነት የኮንትራት ስምምነት ግንኙነት ባይኖረው ኖሮ በእርሱ ላይ ያነጣጠረ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ለምን አስፈለገው? በሌላም በኩል ኮካ ኮላ ቴዲ አፍሮ “ላደረገው ጥረት ሙሉ ክፍያ ተፈጽሞለታል” ብሏል፣ እንዲሁም የኮካ ኮላ ኩባንያ ከቴዲ አፍሮ ጋር የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ማድመቂያ ሙዚቃን ለማሰቀረጽ የኮንትራት ስምምነት ባይኖረው ኖሮ “የተቀረጸው ሙዚቃ የኮካ ኮላ ሴዋ/Coc-Cola CEWA ንብረት ነው ማለት ለምን አስፈለገው?”

ኮካኮላን የዓለም እግር ኳስ የዋንጫ ጨዋታ ማድመቂያ የሆነውን ልዩ የኢትዮጵያን ሙዚቃ በይፋ እንዳይለቅቀው ያስገደደው ተቃውሞ ምንድን ነው?

ለዓለም የእግር ኳስ የዋንጫ ጨዋታ ማድመቂያ በወጣው የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ግጥም እና ቅላጼ ላይ ምንም ዓይነት የፖለቲካም ወይም ሌላ አወዛጋቢ ጉዳይ የለበትም፡፡ በእርግጥ ቴዲ ኮካ ኮላ ዴቪድ ኮሬይ አንዲገጥም ባደረገው ግጥሞች ውስጥ ቃላትን በቀጥታ ወስዶ “ዓለም የእኛ ናት” በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ ተርጉሞ ነበር ያቀርበው፡፡ ሌላ የጨመረውም ሆነ የቀነሰው ነገር የለም፡፡

ቴዲ አፍሮ ከ32 የዓለም የሙዚቃ ጥበብ ባለሙያዎች ለምንድን ነው እንዲነጠል የተደረገው እና የኮካ ኮላ የማዋረድ እና የዘለፋ ኢላማ እንዲሆን የተዳረገው? ኮካ ኮላ ለምንድን ነው የኢትዮጵያን ልዩ የቴዲ ሙዚቃ በአደባባይ ለመልቀቅ ያገደበትን ምክንያት? ለቴዲ ለግሉ ለመገለጽ ፈቃደኛ ያልሆነውስ? ኮካ ኮላ ለምንድን ነው ጉዳዩን ግልጽ በማድረግ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩት የቴዲ አድናቂዎች የኢትዮጵያ ልዩ ሙዚቃ እንዳይወጣ የተደረገበትን ምክንያት ለመናገር ያልፈለገው?

ኮካኮላን ለምን እደምማስወግደው፣

የኮካ ኮላ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የኢትዮጵያን ልዩ ሙዚቃ ላለመልቀቅ ያወጣው ይፋ የተቃውሞ መግለጫ ለቴዲ አፍሮ ጠላቶች የደስታ እና የደረት ድለቃ ምንጭ ሆኗል፡፡ በድል አድራጊነት እንዲህ በማለት ድሰታቸውን ገልጸዋል፣ “ኮካ ኮላ ቴዲን አሽቀንጥሮ ጣለው!“

ኢንዱስትሪዎች መርዛማ ኬሚካሎችን ወደ ቆሻሻ መጣያ ቦታ እደሚጥሉ ሁሉ እኔም እንደዚሁ ኮካ ኮላን ወደ መርዛማ የኬሚካሎች ቆሻሻ መጣያ ቦታ ጥየዋለሁ፡፡ ይህንን ተመሳስሎ አነጋገር በቀላሉ የምጠቀምበት አይደለም፡፡ “የኮካ ኮላ ኩባንያ ካንሰር አምጭ በሆኑት ፋንታ ፒንአፕል እና ቫውልት ዜሮ ቤንዚን (በሁለት ምርቶቹ ላይ) ያለውን መጠጦች በህግ ተከሶ በስምምነት ጉዳይዩን እልባት ሰጥቷል፡፡“ ኮካ ኮላ 114 የምርት ዓይነቶችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ አኳፑሬ ከሚለው ጀምሮ ዚኮ እስከሚለው ድረስ ድረ ገጹ ላይ ይፋ አድርጓል፡፡

አሁን 114 ምርቶቹን ላለመጠቀም የማይለወጥ ዉሳኔ አድርጌአለሁ፡፡ አኳፑሬን፣ ባርቅን፣ ኮካ ኮላን፣ ዳሳኒን፣ ኢቪያንን፣ ፉዝን፣ ጋላሴኡን፣ ቪታሚን ዋተርን፣ ሐይ-ሲንን፣ ኢንካኮላን፣ ጀሪኮንን፣ ኪንሌይንን፣ ሊፍትን፣ ሚኑት ሜይድን፣ ኖርዘርን ኔክን፣ ኦዱዋላን፣ ፓዎሬድን፣ ሬድ ፍላሽን፣ ስፕራይትን፣ ታብን፣ ቫውልትን፣ ወርክስ ኢነርጅን፣ ዚኮን… አነዚህን መጠጦች በምንም ዓይነት ሁኔታ አልገዛም ወይም በምንም ዓይነት መንገድ አልጠቀምም፡፡ ማንም ቢሆን እነዚህን ምርቶች እንዲገዛ ወይም እንዲጠቀም አላደፋፍርም ወይም ደግሞ ሀሳብ አላቀርብም፡፡ በዚህም እውነታ መሰረት በዓለም ላይ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አንባቢዎቼ እነዚህን ምርቶች እንዳይገዙ ወይም ደግሞ እንዳይጠቀሙ በአክብሮት እጠይቃለሁ!

ሁላችንም አንድ በመሆን እንተባበር እና ኮካ ኮላን እና 114 የሚሆኑ ምርቶቹን ባለመጠቀም ከገበያ ውጭ እናድርጋቸው፡፡

ለአስርት ዓመታት የኮ ካላ ኩባንያ ምርቶቹን በደስታ እና የደስታ ስሜት በተቀላቀለበት ዓይነት ሁኔታ እና መፈክሮችን ሊረሱ በማይችሉ ቃላት በማሽሞንሞን የኮርፖሬት ንግዱን ሲካሄድ ቆይቷል፣ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት እና አጠቃላይ የንግድ እሴቶቹን ሲያስተዋውቅ ቆይቷል፡፡ ባለም የተሰራጩት መፈክሮቹ እንዲህ ይላሉ፣ “ኮካ፡ እውነተኛ ነገር ነው“፣ “ከኮካ ጋር ነገሮቸ ሁሉ የተሻሉ ይሆናሉ“፣ “በአሁኑ ጊዜ ዓለም የሚፈልገው ኮካን ነው”፣ “ኮካ ይህ ነው“፡፡ ኮካ ኮላ እንዲህ ብሎ የሚጀምር የቴሌቪዥን የንግድ ሙዚቃ አለው፣ “የተሟላ ደስታ ባለበት ሁኔታ በመዘመር ዓለምን ለማስተማር እወዳለሁ“፣

ኮካ እንደ እስፕራይት እውነት ሳይሆን ዉሸት
በኢትዮጵያ ነገሮች ኮካ መራራ ያደርጋል፣
ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ ጥላቻ እንጅ በኢትዮጵያ ፍቅርን የሚያመጣ አይደለም፣
ኮካ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እድሜ ሳይሆን ጥላቻ ነው የጨመረው፣
ኮካ ኢትዮጵያውያንን ፈገግ የሚያደርግ ሳይሆን በጥላቻ እንዲሞሉ ያደረገ ነው፣
ብዙ የስኳርነት ባህሪው ስለሚያፍነኝ ኮካን አልጠጣም፣
የዓለም ህዝብ ኮካን ወይም ደግሞ ማንኛውንም 113ቱን የኮካ ምርቶች እንዳይገዛ እፈልጋለሁ፣
በአሁኑ ጊዜ የመጨረሻው እና የዓለም ህዝብ የማይፈልገው ነገር ቢኖር ኮካ ነው፣
ኮካ ዘበት ነው!

የኢትዮጵያ ታዋቂ ሙዚቃ በኩሩው የኢትዮጵያ ወፍ ሲዘመር እንዳይሰማ የተደረገበት ምክንያት ለምን እንደሆነ አውቃለሁ፣

ቴዲ አፍሮ የእራሱን ህዝብ እና አገር ይወዳል፣ ለዚህ ዓላማው አየተቀጣ ይገኛል፡፡

ውርደት ቀለቡ የሆነው እና የትንሽ ጭንቅላት ባለቤት የሆነው በኢትዮጵያ ህዝቦች ጫንቃ ላይ ከፍላጎታቸው ውጭ ተቆናጥጦ የሚገኘው ገዥው አካል ኮካ ኮላ የቴዲን ሙዚቃ እንዳይለቅቀው ተጽዕኖ ያደረገበት ለመሆኑ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ምክንያቱ ግልጽ ነው፡፡ እነዚህ በበቀል እና በጥላቻ የተሞሉት ገዥ ጽንፈኛ የወሮበላ ስብስብ ቡድን የቴዲ አፍሮ ትክክለኛ ጌታው ማን እንደሆነ ለማሳየት ያደረጉት ከንቱ ምግባር ነው፡፡ እነዚህ የበቀል እና የጥላቻ ቋቶች እንዴት ባለ የማታል ዘዴ እና የተለሳለሰ በሚመስል ማደናገሪያ እየተጠቀሙ በቴዲ እና በደጋፊዎቹ ላይ እየወሰዷቸው ያሏቸውን ዕኩይ ተግባራት ለማሳየት ነው፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከኮካ ኮላ ጋር የተደረገውን አጠቃላይ ስምምነት ብልግና በተቀላቀለበት መልኩ እየሳቁ ሲመለከቱት ቆይተዋል፡፡ እንዲቀጥልም ፈቅደዋል፡፡ እንዲህም ብለው ነበር፣ “ቴዲ ከልቡ ጥረት ያድርግ እና ቆንጆ የሙዚቃ ስራ ይዞ ይቅረብ“፣ መዳፎቻቸውን በማፋተግ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ጥሩ አድርገን በመበቀል ሊረሳው በማይችል መልኩ አርአያ የሚሆን ትምህርት እንሰጠዋለን“፡፡ በእነዚህ የእኩይ ምግባር አራማጆች የደም ስሮች ውስጥ ጥላቻ እና በቀልተኝነት ተዋህደዋል፡፡

በመጨረሻዋ ደቂቃ በኮካ ኮላ በኩል የበቀል እርምጃቸውን ወስደዋል፡፡ (ኮካ ኮላ እ.ኤ.አ በ2013 ሶስተኛውን የጠርሙስ ፋብሪካ በድሬ ዳዋ ከተማ ያጠናቀቀ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡) ኮካ ኮላ ገበያውን በኢትዮጵያ ለማስፋት ከፈለገ የቴዲ አፍሮን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ማድመቂያ ሙዚቃ መልቀቅ የለበትም፡፡ ምስኪኑ ኮካ ኮላ በሰይጣኖች እና በቴዲ አፍሮ መካከል በተያዘው ጉዳይ ላይ መሳሪያ በመሆን የይስሙላ መወዛወዝን ይዞ ቀትረ ቀላል ሆኖ ይገኛል፡፡

በእርግጥ ያ ሁሉ በገዥው አካል እየተደረገ ያለው በሸፍጥ የተሞላ እርባና የለሽ ድርጊት በቴዲ አፍሮ ስብዕና ላይ የሚያመጣው ነገር አይኖርም፡፡ ቴዲ በሚመስጠው ቅላጼው “ፍቅር ሁሉን ያሸንፋል” የሚል ሙዚቃውን ማሰማቱን ይቀጥላል፡፡ “ሙሉ ይቅርታን ከማድረግ በላይ በቀል የለም” የሚለውን መርህ ነው የሚከተለው፡፡ እሱን ጥፋተኛ ያደረጉትን ይቅርታ ያደርግላቸዋል (ጃህ ያስተሰርያል!)

በኢትዮጵያ ላለው ወሮበላ ዘራፊ ቡድን ማንኛውም ተመልካች የቴዲ አፍሮን ስም ጥላሸት ለመቀባት፣ ለማበሳጨት እና የአገሪቱ ብሄራዊ የአንድነት እና የክብር መገለጫ ምልክት የሆነውን ጀግና ታዋቂ የኢትዮጵያ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ስሜት ለመጉዳት በሚያደርጉት እርባና የለሽ የስነ ልቦና ጦርነት ላይ እንግዳ ሊሆንበት አይችልም፡፡ ለበርካታ ዓመታት እነዚህን ቆሻሻ የማታለል ድርጊቶቻቸውን በተቀናቃኞቻቸው ላይ ሲፈጽሙ ቆይተዋል፣ አሁንም ይህንን እኩይ ምግባራቸውን በተጠናከረ መልኩ ይቀጥሉበታል፡፡

እውነታው ግን የቴዲ አፍሮ የኪነ ጥበብ ሙያ ለኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት የማይሞተውን ጠንካራ ፍቅር አሳይቷል፡፡ በሁሉም ሙዚቃዎቹ እና ግጥሞቹ ቴዲ የኢትዮጵያን ክብር ከፍ አድርጎ አሳይቷል፣ እንዲሁም ለወሮበላ ዘራፊዎች እና ለከሀዲዎች እውነታውን ነግሯቸዋል፡፡ የእርሱ ሙዚቃ፣ መዝሙሮች እና ግጥሞች የአውዳሚነት ጥረቶችን በማዳከም በኩል የኢትዮጵያን ህዝብ እምነት እና ሞራል ከፍ በማድረግ ውጤታማ ክስተቶችን ፈጥረዋል፡፡ ቴዲ በግጥሞቹ እንዲህ በማለት አውጇል፣ “ያዙት፣ ጠበቅ አድርጋችሁ ያዙት! እርስ በእርሳችን ይቅርታ ካደረግን እና ከተፋቀርን የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቅርብ ነው፡፡“

ቴዲ ተያስተሰርያል በሚለው አልበሙ በቡድን የወሮበላ ስብስብ ወንጀለኞች የተያዘውን ዙፋን አጋልጧል፡፡ መዝሙሩን በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሁሉም የጎሳ መሰረት ያላቸው ህዝቦች በስምምነት፣ በሰላም እና በፍቅር በአንድ ኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር በህብረት እንዲኖሩ አዚሟል፡፡ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን የሙዚቃ ክህሎት በመጠቀም የክርስቲያን እና የእስልምና እምነት ተከታዮች እጆቻቸውን በማጣመር በአንድነት በሰላም እና በፍቅር እንዲኖሩ አስተምሯል፡፡ ቴዲ የታደለውን የዓላማ ጽናት ለእኩይ ምግባር እንዲሸጥ ለማድረግ ለመቁጠር ከሚያዳግተው በላይ በርካታ ሀብት እና ሽልማት ቀርቦለት ነበር፡፡ ሆኖም ግን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ነብሱን ለወሮበላ ዘራፊዎች ለመሸጥ እንደማያስብ ጽኑ ተቃውሞ አሳይቷል፡፡

ቴዲ አፍሮ በእርሱ የትውልድ ዘመን ካሉ የጥበብ ባለሙያዎች ሁሉ የበለጠ እና የላቀ ተነሳሽነት ያለው ወጣት ከያኒ ነው፡፡ ቴዲ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ወጣቶችን ቀልብ በመሳብ ዴሞክራሲ፣ ነጻነት እና ሰብአዊ መብቶች በአንዲት ኢትዮጵያ እንዲጠበቁ እና እንዲከበሩ አነቃንቋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የእኩይ ምግባር አራማጆቹ በሙዚቃው ያሳየውን አርበኝነት ለመበቀል አሁን ያዘጋጀው ሙዚቃ እንዳይለቀቅ በመከልከል “ዋጋ” እንዲከፍል እያደረጉ ነው፡፡ የእውነትን መዝሙርን በምንም ዓይነት መልኩ ማገድ እና ጸጥ ማድረግ አይቻልም፡፡

ቴዲ የሚሸጥ ዕቃ አይደለም! ቴዲ በኮካ ኮላ ወይም በወሮበላ ዘራፊ ቡድን ባለብዙ ቢሊዮን ገንዘብ ባለቤት ቱጃሮች የሚገዛ ሸቀጥ አይደለም፡፡ እርሱን ለማዋረድ እና ለመዘለፍ መሞከር ይችላሉ፡፡ ቀላሉ እውነታ ግን ቴዲ በእራሱ እና በሀገሩ ላይ የራስ ደጀን ተራራን የሚያህል ኩራት እና ክብር ያለው ትንታግ ወጣት መሆኑን ያለመገንዘባቸው ነው፡፡ ወሮበላ ዘራፊዎች ከህዝብ በሰረቁት እና በዘረፉት ኃብት ምንም ያህል ኃብት ቢያከማቹ ማጅራት መችዎች ለዘላለም የሚኖሩ ወሮበላ ዘራፊዎች፣ በጥባጮች እና ማጅራት መችዎች ሆነው ይቀራሉ፡፡ ይህም የሚያዋርድ የቋንቋ ቃላትን መደርደር አይደለም፡፡ ይህ እንደ ቀትር ጸሐይ የበራ ኃቅ ነው!

እባካችሁ ቴዲ አፍሮ በእራሱ እና በእናት ሀገሩ ላይ ኩራት እና ፍቅር ያለው ትንታግ ወጣት በመሆኑ ምክንያት ብቻ አትጥሉት! እርሱን አትጥሉት፣ ምክንያቱም የሀገር ምልክት ነው፡፡ እርሱን አትጥሉት፣ ምክንያቱም የሀገር አርበኛ ነው፡፡ ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ እንደዚያ ሆኖ ነው የተወለደው!

በኢትዮጵያ ያለው እውነተኛው ቴዲ አፍሮ እንጂ የኮካ ሸቀጥ አይደለም!

ዓለም እና አብዛኛው የዓለም ህብረተሰብ እንዲሁም የዓለም የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴዲ አፍሮን ይፈልገዋል፡፡ ቴዲ የአፍሪካ የሙዚቃ ሊቅ ነው፡፡ የእርሱ የሙዚቃ ግጥም “ፍቅር ሁሉን ያሸንፋል” በሚል መርህ ላይ የተዋቀረ ነው! አፍሪካውያን/ት ግጥሞቻቸውን እና የሙዚቃ ፍቅሮቻቸውን ወደ አንድነት መድረክ እንዲያመጡ እያደረገ ነው፡፡

ቴዲ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ታዋቂው የጥበብ ባለሙያ ነው ምክንያቱም የእርሱ ሙዚቃ ህዝቡን ወደ አንድነት እያመጣ ነው፡፡ ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያውያን/ት እና አፍሪካውያን/ት ፍቅርን፣ ሰላምን፣ አብሮነትን እና መልካም ነገርን ሁሉ ይዘምራል፡፡ የእምቢተኝነት መዝሙሮችን ይዘምራል፡፡ ስለእርቅ አስፈላጊነት፣ መግባባት እና ይቅርባይነት ይዘምራል፡፡ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት አጠንክረው ለሚሰሩ ሀገር ወዳዶች ሁሉ የስራ መዝሙሮችን ይዘምራል፡፡ ስለኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ ማራኪነት እና ስለህዝቧ ደግነት ይዘምራል፡፡ ቴዲ አፍሮ በአፍሪካ ላይ ስላለው ፍቅር ይዘምራል፡፡

የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ህይወትን የበለጠ አስደሳች አድርጎታል፡፡ የዓለም ህዝብ ቴዲ አፍሮ ሰለፍቅር ሲዘምር እንዲያዳምጠው ማየት እፈልጋሁ፡፡ በማያቋርጥ አምባገነንነት መዳፍ ስር ወድቃ ህይወት አልባ እና ደስታ ከራቃት አገር ይልቅ የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ህይወትን እና ደስታን ይጨምራል
ቴዲ አፍሮ እውነተኛ ነገር ነው! ቴዲ አፍሮ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ነው!

ቴዲ አፍሮ በቅርብ ጊዜ ያሳተመው “ጥቁር ሰው” የተባለው አልበሙ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1896 በኢጣሊያ ቅኝ ገዥ ወራሪ ኃይል ላይ የተቀዳጀችውን ድል የሚዘክር ነው፡፡ ያ አንጸባራቂ ድል በአፍሪካ እና በዓለም ታሪክ ላይ ጉልህ ምዕራፍን ይዞ ይገኛል፡፡ የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ስጋ ለመከፋፈል እና የአፍሪካን ህዝቦች በባርነት በመያዝ ጥሬ ሀብቷን ለመዝረፍ በማቀድ በበርሊን ከተማ ከተደረገው ጉባኤ ሁለት ዓመታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በኢጣሊያን እና በኢትዮጵያ መካከል በተደረገው የመጀመሪያው ጦርነት የኢትዮጵያው ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የኢጣሊያንን ወራሪ ወታደሮች በአድዋ ጦርነት ላይ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የሞቱት ሞተው የተረፉት እግሬ አውጭኝ በማለት ወደመጡበት እንዲመለሱ አድርገዋል፡፡ የአድዋ ጦርነት የአውሮፓ ኃያል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ወታደሮች ጉልበት ስር እንዲንበረከክ የተገደደበት ጊዜን ያስታውሳል፡፡ ፋሽስት ኢጣሊያ እንደገና እ.ኤ.አ በ1935 ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛትነት ለመያዝ ሁለተኛውን የኢጣሊያን እና የኢትዮጵያን ጦርነት ለኮሰች፡፡ በዚህም ጦርነት ለዘላለም ሊረሱት የማይችሉት የሽምቅ ውጊያን ሽንፈት ተከናንበው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ኢትዮጵያ (በአፍሪካ ከሌላዋ ላይቤሪያ በስተቀር) ነጻነቷን ጠብቃ የቆየች ከቅኝ ግዛትነት ነጻ የሆነች አገር ሆና እንድትቆይ አድርጓታል፡፡ ቴዲ አፍሮ ስለፍርኃት የለሽ መሪዎቿ እና ነጻነታቸውን እና ሉዓላዊነታቸውን ላለማስደፈር በቀስት እና በደጋን እንዲሁም ኋቀር በሆኑ ጠብመንጃዎች በመታገዝ ብቻ ሳይሆን በነበራቸው ኩራት እና ወኔ በጀግንነት ተዋግተው የሀገራቸውን ነጻነት እና ህልውና ላስከበሩት ተራ ኢትዮጵያውያን ጀግኖችም ዘምሯል፡፡

በቴዲ እና ልዩ በሆኑት የኪነ ጥበብ ስራዎቹ ኮርቻለሁ፡፡ ለኢትዮጵያ ልዩ ባህል እርሱ ላበረከታቸው እጅግ መጠነ ሰፊ በሆኑ አበርክቶዎቹ ሁሉ በጣም ኮርቻለሁ፡፡ በሙዚቃ ስራዎቹ አማካይነት ፍቅር፣ አንድነት እና በህዝቦች መካከል ብሄራዊ ዕርቅ እንዲወርድ ባደረጋቸው እልህ አስጨራሽ ጥረቶች ላይ እጅግ ኮርቻለሁ፡፡ ቴዲ ልዩ የመንፈስ ጽናት ያለው እና የውርደትን ትጥቅ ያስፈታ ትንታግ ከያኒ ወጣት ነው፡፡ የእርሱን ዝና እና ክብር ለማንቋሸሽ በተከታታይነት ዘመቻ ሲያደርጉበት ምንም ዓይነት ምላሽ አይሰጣቸውም፡፡ በእርግጠኝነት እንዲህ ብቻ ይላል፣ “ፍቅር ሁሉንም ያሸንፋል፡፡“ በጥላቻ የተሞሉ የእኩይ ምግባር አራማጆች ፍቅር ሁሉንም ያሸንፋል ብሎ የተነሳን ሰው በምንም ዓይነት መልኩ ሊያሸንፉ አይችሉም፡፡

አሁን በህይወት የሌለው መለስ እ.ኤ.አ በ2008 በሰው ላይ የመኪና አደጋ አድርሶ አምልጧል በሚል በውሸት የተቀነባበረ የሸፍጥ ክስ ሳቢያ ቴዲ አፍሮን ወደ እስር ቤት በወረወረው ጊዜ በቴዲ ጎን ቆሜ በዓለም ህዝብ የሕሊና ፍርድ ቤት ስከራከር ነበር፡፡ እንደዚሁም ቴዲ አፍሮ ፈጽሟቸዋል በሚል የፍብረካ ወንጀሎች በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ እንዲመሰረትበት መለስ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ የተቀነባበሩ 10 አገር ከመውደድ ጋር ተያይዞ የሰራዉን የ “ወንጀል ክሶች” ዝርዝር መዝግቤ ይዣለሁ፡፡ የመለስ እኩይ የሙት መንፈስ በቴዲ ግጥሞች በተገለጹ እውነቶች እና እምነቶች ሲወጋ እና ሲባንን ይኖራል፡፡

ቴዲ እ.ኤ.አ በ2010 ወደ ሎስ አንጀለስ በመጣበት ወቅት የእርሱን የሙዚቃ ትርኢት ተመልክቸ ነበር፡፡ የሙዚቃ ትርኢቱ አስደናቂ ነበር፡፡ የቴዲ የሙዚቃ ትርኢት ወጣት በነበርኩበት ጊዜ እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በመጀመሪያው እረድፍ ላይ ቆሜ ያየሁትን የታላቁን ቦብ ማርሌይን ካያ እና የህይወት ግብግብ ጎዞ/Kaya and Survival tour በሚል ርዕስ የቀረበውን ሙዚቃዊ ትርኢት እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡ ቦብ ማርሌይ በአፍሪካ ነጻነት እና በፓን አፍሪካኒዝም ላይ እንደነበረው ፍቅር ሁሉ ቴዲ አፍሮም በተመሳሳሳይ መልኩ በነጻነት፣ በአንድነት፣ ዕርቀ ሰላም በማውረድ እና በአትዮጵያ ህዝቦች ላይ ፍቅር እንዲሰፍን ይፈልጋል፡፡ እንደ ማርሌይ ሁሉ የቴዲ ሙዚቃም ቀስቃሽ፣ አስደማሚ እና ልብ አንጠልጣይም ነው፡፡ እንደ ማርሌይ ሁሉ ቴዲም ስለፍቅር፣ ሰላም፣ ተስፋ፣ እምነት፣ ለጋሽነት፣ ፍትህ፣ ዕርቅ፣ መግባባት እና ይቅርታ አድራጊነት ይዘምራል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ነገሮች ናቸው የቴዲ አፍሮን የሙዚቃ የቅላጼ ኃይል በኢትዮጵያውያን/ት ልብ እና ልቦና ውስጥ ዘልቀው በመግባት የተስፋ ማጣት ቁስልን፣ ማለቂያ የሌለውን ጭቆና እና ኢትዮጵያን ከአምባገነንነት መቃብር ለማዳን ለቀዶ ጥገናው ስራ በመስፊያ ክርነት እያገለገሉ ያሉት፡፡ ቴዲን በኢትዮጵያ ውስጥ ስለፍቅር፣ ሰላም እና ፍትህ ከመስበክ እና ከመዘመር የሚያግደው ምንም ምድራዊ ኃይል የለም፡፡

ቴዲን የኢትዮጵያ ጅግና የስነ ጥበብ ባለሙያ እና የእራሴም ግላዊ ጀግና አድርጌ እቆጥረዋለሁ!

ዓለም የእኛ ናት የኮካ አይደለችም፡፡ አንድ ኮካ ኮላን በአንድ ሰው ማስወገድ፣ አንድ ኮካ ጠርሙስ በአንድ ጊዜ ማስወገድ አለብን!

የእኔን ሳምንታዊ ትችቶች ለበርካታ ዓመታት በመከታተል ላይ ለሚገኙት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አንባቢዎቼ እኔን እዲቀላቀሉኝ እና “ኮካን ከመጠቀም እንዲያስወግዱ” የአክብሮት ጥሪየን አቀርባለሁ!

ኮካ ኮላ በጨለማ እንደሚካሄድ የኃይማኖት ክብረ በዓል የሻማ ብርሀን ይዘን ለተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ብንወጣ ጉዳዩ አይደለም፡፡ ኮካ ኮላ ስለእኛ ሞራል ዝቅጠት ጉዳይ ደንታ የለውም፡፡ የኮካ ኮላ ዋና ጉዳይ ከሁሉም በላይ ስለትርፍ እና ኪሳራ ማሰላሰል ብቻ ነው፡፡ ኮካ ኮላ ከ200 በላይ በሚሆኑ አገሮች ከ30 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ ዓለም አቀፍ ሽያጮችን ያካሂዳል፡፡ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለገበያ ማስተዋወቂያ ዘመቻ ወጭ ያደርጋል፡፡ ኮካ ኮላ በውል ሊገነዘበው የሚችለው ብቸኛው ቋንቋ የትርፍ እና ኪሳራ ቋንቋ ነው፡፡

በአንድ ጊዜ አንድ ሰው ኮካ ኮላን መግዛት እና መጠቀምን ቢያቆም እና የ114 የኮካ ኮላ ምርት ውጤቶችን መግዛት እና መጠቀምን ብናቆም ዓለማችንን ከኮካ ኮላ መዳፍ ስር በ114 ቀናት ውስጥ ማላቀቅ እንችላለን፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ አንባቢዎቼ ኮካ ኮላ መጠጣትን እንዲያቆሙ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ የእራሳቸው “የኮካ መጠቀም ማስወገጃ ቀን” እንዲኖራቸው እጠይቃለሁ፡፡ ሁልጊዜ ኮካ ሲቀርብ አሻፈረኝ አልፈለግም አንዲሉ !!!

ይህ የማስወገድ ስልት በኮካ ኮላ ላይ ብቻ የተወሰነ መሆን የለበትም፡፡ ስለኢትዮጵያ ብሄራዊ ኩራት ጭምር ነው፡፡ አገራችንን ከሶዳ ቸርቻሪ እና ከወሮበላ ዘራፊዎች ማላቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡

አንድ የካካ ኮላ ጠርሙስን ባንድ ሰው እንዋጋ እላለሁ፣ አንድ ሰው ኮካ ኮላ በአንድ ጊዜ ማስወገድ ይቻላል! እምቢ ኮካ አልፈልግም

ኮካ ኮላ እንዲህ በማለት ጉራዉን ይነዛል ፣ “ዓለም የእኛ ናት!“ አኛ ደግሞ ለ ኮካ ኮላ ኢትዮጵያ የእኛ መሆኗን ማሳየት አለብን!

በመጨረሻም የእኔ ኮካ ኮላን መጠጣት የማስወገድ ዓላማ ቴዲን ነጻ እንዲያደርገው በኮካ ኮላ ላይ ውጥረት ለመፍጠር አይደለም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ከጀርባ መጋረጃ ሆኖ የኮካ ኮላን እጅ ለሚጠመዝዘው ለአንደበተ ድሁሩ የገዥ አካል እውነተኛውን ነገር እስከ አፍንጫው ለመንገርም አይደለም፡፡ ይህንን የማደርገው ኢትዮጵያዊ በመሆኔ ስለሚሰማኝ ክብርና ሞገስ ስለማስብ ብቻ ነው፡፡

ተባበሩኝ እባካቸሁ ለክብራችሁ
ተባበሩኝ ለክብራችን
ውርደት እስከመቼ ተሸክምን እንችላለን?
ባንደበታችን መናገር ባንችል
ባንደበታችን የሚገባዉን ማስቆም አንችላለን ::

ተባበሩኝ ወገኖች ጀግኖች ለክብራችን !
ኮካ ኮላ ነው በሉ የሚያስጠላ፥ የሚያጣላ::

በግሌ የምለው አንዲህ ነው፥

ኮካ ኮላ ለዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ካዘዛቸው 32 አገራዊ ልዩ ሙዚቃዎች መካከል 31ዱን ከለቀቀ እና የታላቂቱ የኢትዮጵያን ልዩ ሙዚቃ አሽቀንጠሮ ከጣለ በበኩሌ ኮካ ኮላን የምለው “ተምዘግዝጋችሁ ገሀነም ግቡ” ነው!!!”

ኮካ ኮላ፥ የሚያስጠላ የሚያጣላ!!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሰኔ 10 ቀን 2006 ዓ.ም

የትግራይን መስቀል ስለመሸከም ….ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

$
0
0
ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ)

…ዕለቱ የሁለት ሺ ሶስት ዓመተ ምህረት የመስቀል በዓል የተከበረበት ማግስት፤ ሰሜናዊቷ የኤርትራ አዋሳኝ ወልቃይት ገና ከእንቅልፏ ሙሉ ለሙሉ ባለመንቃቷ፣ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ጎፈሪያቸው የተንጨ(ባረረ ፋኖዎች በውስጧ ካሉ ተቋማት ወደ አንዱ እያመሩ ስለመሆኑ የጠረጠረች አትመስልም፤ ከኤርትራ የተነሱት ፋኖዎች መዳረሻ በወረዳዋ ታዋቂ የሆነው አወርቅ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመሆኑ፤ ማንም ልብ ሳይላቸው ልክ እዚያው እንደደረሱ፣ ከፊሎቹ በሰለጠነ ወታደራዊ ስልት ትምህርት ቤቱን ከአጥር ውጪ በመክበብ ድንገተኛ ጥቃት የሚሰነዝር ኃይል ከመጣ ለመከላከል ሲያደፍጡ፤ የተቀሩት ደግሞ ወደ ውስጥ በመግባት በግቢው የሚገኙ መምህራን ሜዳው ላይ እንዲሰበሰቡ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፉ፤ በጥቂት ደቂቃዎችም ውስጥ ሁሉም በተባለበት ቦታ ተሰበሰበ፤ እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በዕቅዱ መሰረት መፈፀሙን በጥንቃቄ ሲከታተል የነበረው የቡድኑ መሪ በቅድሚያ ስለራሱና ጓደኞቹ ማንነት እና ስለወከሉት ድርጅት አጭር ማብራሪያ ከሰጠ በኋላ፣ የትግሉን ዓላማ በስፋት አብራርቶ አስረዳ፤ ሌሎች ጓዶቹም የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ዋና ዋና ርዕሶች የሚገልጹ በአማርኛና ትግርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶችን የማደል ስራቸውን በማጠናቀቃቸው እንደአመጣጣቸው በሽምቅ ተዋጊ ስልት ከአካባቢው ተሰወሩ፡፡ ይህ በሆነ በአስራ ሁለተኛው ቀን (መስከረም 30) ደግሞ እዛው ወረዳ ወደሚገኝ ሌላ ትምህርት ቤት ለተመሳሳይ ዓላማ ድንገት ተመልሰው መጥተው ነበር፤ ሆኖም መንገድ ላይ ካደፈጡ ፖሊሶችና ታጣቂዎች ጋር ፊት ለፊት ተገጣጥመው በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ከእነርሱ ወገን አንድ ሲሰዋ፤ ከፖሊስ አባላት አንድ ቆስሏል፤ አንድ መምህርም በገዛ ቤቱ በተቀመጠበት በተባራሪ ጥይት ቆስሏል፤ ፋኖዎቹም የዚያ ቀን ዓላማቸው ከሽፎ ወደመጡበት የኤርትራ በርሃ ተመልሰው ለመሄድ ተገድደዋል…Temesgen Desalegn “Fact” Ethiopian Amharic newspaper editor

ፊታችሁን ወደ ሰሜን…
ከወዳጆቼ ግርማ ሰይፉና በላይ ፍቃዱ ጋር መቀሌን ለመጎብኘት የነበረን ዕቅድ በተለያዩ ምክንያቶች እየተሰናከለ፤ መልሶ እየተወጠነ ጥቂት ለማይባሉ ወራት ሲጓተት ቆይቶ፣ በግንቦት መጨረሻ ዕለተ-አርብ ምሽት ላይ፣ ህወሓት እነ ለገሰ አስፋውን በኃይል አባርሮ በእጁ ወደአስገባት ሞቃታማዋ የትግራይ ርዕሰ-መስተዳድር መቀመጫ ደረስን፤ ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ከባድ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተፈጭተው የሚጋገሩባትን፣ የአጼ ዮሀንስ ከተማ ለአራት ቀናት ተቆጣጠርናት ስናበቃ፤ ‹ከእግር እስከ ራሷ…› ለማለት ባያስደፍርም፣ የቻልነውን ያህል በጉብኝት አካለልናት፤ በተናጠልም መነሻዬን ‹ሮሚናት› አደባባይ (መሀል እምብርቷን) አድርጌ በአራቱም አቅጣጫ ለመቃኘት ሞክሬያለሁ፤ በዋናነት ትኩረቴን የሳበው ከሰማዕታቱ ሐውልት በስተሰሜን ተንጣሎ የሚገኘው መንደር ነው፤ መንደሩ በዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ተውቦ ሲታይ፣ የደቡብ አፍሪካዋ ጽዱ ከተማ ኬብ-ታዎን ያሉ ቢመስልዎ ስህተቱ የእርስዎ አይሆንም፤ ስለምን ቢሉ? እየተመለከቱ ያሉት ስነ-ሕንፃ ውበት እጅግ በተራቀቁ ዘመን አመጣሽ የግንባታ ቁሳቁሶች የተንቆጠቆጠ መንደር ነውና፡፡ ወደቦታው ይዞኝ የሄደው ጎልማሳ የባጃጅ አሽከርካሪ ‹‹በትግራይ ክልል ባሉ 46ቱም ወረዳዎች በተለያየ ጊዜ በኃላፊነት ከተመደቡ አስተዳዳሪዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ እዚህ መኖሪያ ቤት አላቸው›› ሲለኝ ግን ማመን ቢያዳግተኝም አድናቆቴ ወደ ከፍተኛ ድንጋጤ ተቀይሯል፤ ምክንያቱም ቤቶቹ በመንግስት ደሞዝ ሊሰሩ ቀርቶ፣ ሊታሰቡ እንደማይችሉ በግልፅ ያስታውቃሉና ነው፤ ታዲያ! ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ምናልባት የአስተዳዳሪዎቹ ደሞዝ እንደ አክሱማውያን ዘመን በወቂት (በወርቅ ድንጋይ) ይሆን እንዴ?
የሆነው ሆኖ አንጋፋዎቹ ‹የታገለ-ያታገለ፣ በድል አጥቢያ አርበኝነት ያገለገለ፣ በሀገር ሀብት እንዳሻው የመምነሽነሽ መብት አለው› እንዲሉ፣ ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ አገሬውም ይህንን እውነታ አብጠርጥሮ በማወቁ አካባቢውን ‹‹ሙስና ሰፈር›› ብሎ እንደሚጠራው ስሰማ፣ ጎልማሳው የነገረኝን ወደማመኑ ጠርዝ ተገፋሁ፡፡ መደበኛ ባልሆነ መልኩ የተወያየኋቸው በተለያየ ዕድሜ ላይ የሚገኙ በዛ ያሉ የከተማዋ ነዋሪዎችም ባለንብረቶቹ የህወሓት ካድሬዎች እንደሆኑ መስማታቸውን አረጋግጠውልኛል፡፡ በይበልጥ ደግሞ ሁለት ልጆቻቸውን በትግሉ እንዳጡ ያወጉኝ አንድ አዛውንት ምንም እንኳ እተባለው አካባቢ ሄደው ቤቶቹን በአይናቸው አለማየታቸውን ባይሸሽጉኝም፣ በተሰበረ ስሜትና ምሬት በዋጠው ድምፅ ‹‹እነርሱ በእኛ ልጆች ደም ተረማምደው፣ ለድል ከበቁ በኋላ ዓላማቸውን ትተው የሀገርን ሀብት በመዝረፍ ራሳቸውንና ዘመዶቻቸውን ባለፀጋ ማድረግ እንደቻሉ በሰማሁ ቁጥር፣ ልጆቼ የተሰዉት በደርግ ወታደሮች ጥይት ሳይሆን በገዛ የበረሃ ጓዶቻቸው ክህደት እንደሆነ አድርጌ በማሰብ በቁጭት ስለምብሰክሰክ ሀዘኑ እንደ አዲስ ያንገበግበኛል›› ሲሉ መስማት ምንኛ እንደሚያሸማቅቅ ማንም ለመገመት አይከብደውም፡፡

የዚህ አይን ያወጣ ዘረፋ መነሾም ድርጅቱ በተለይም የ1993ቱን ‹ዳግማዊ ህንፍሽፍሽ› ተከትሎ ያጋጠመውን የታማኝ ሰው እጥረት ለማሟላት መስፈርቱ ‹‹ህወሓትን እንደ ግል አዳኝ›› መቀበል ላይ የሚያተኩር እንጂ፤ የስነ-ምግባር ጉድለት ኖረ አልኖረ አሳሳቢው ባለመሆኑ እንደነበረ ይነገራል፡፡ በዚህ ድምዳሜም የቀድሞ አመራሮቹ ጭምር እንደሚስማሙ አስተውያለሁ፡፡ እውነታውን የሚያውቀው የከተማዋ ነዋሪም ቢሆን፣ ደፍሮ ህወሓትን ‹‹ሌባ!›› ብሎ ባያወግዝም፤ ተቃውሞውን ለመግለፅ መንደሩን ‹‹ሙስና ሰፈር›› በማለት መሰየሙ በራሱ አንድ ማሳያ ነው፡፡ መቼም በመቀሌ እልፍ አእላፍ ሰላዮች ከመሰግሰጋቸውም ባለፈ፣ ከምሁር እስከ ሊስትሮ፣ ከነጋዴ እስከ አርሶ አደር በጠንካራ ጥርነፋዊ መዋቅር የተጠፈሩባት ከመሆኗ አኳያ፣ ግንባታውንም ሆነ ነዋሪው የሰጠውን ስያሜ፤ ትላንት መለስ ዜናዊ፣ ዛሬ ደግሞ እነ አባይ ፀሀዬ ‹አልሰሙ ይሆናል› ብሎ ማሰቡ “ፀሀይ በምዕራብ ትወጣለች” አይነት ጉንጭ አልፋ ክርክር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ሌላው የከተማዋ ‹‹ጥቁር ሐውልት›› ተብሎ ሊጠቀስ የሚችለው፣ ጋዜጠኛ ዮናስ በላይ በ2003 ዓ/ም በወርሃ ነሐሴ በታተመችው ‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ (በቅርቡ ባሳተመው ‹‹ወያኔዎቹና ሽፍቶቹ›› በተሰኘ መጽሐፉም አካቶታል) ‹‹ገረቡቡ-የመቀሌው አፓርታይድ መንደር›› በሚል ርዕስ ካስነበበን ‹‹የግንቦት ሃያ ፍሬ›› ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ዮናስ በጽሑፉ እንደገለፀው መንደሩ የተመሰረተው በድፍን መቀሌ በምቾቱ የተሻለ በሚባለው መልከዓ-ምድር ላይ ነው፤ ባለቤቶቹ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ጥቂት ባለሀብቶች መሆናቸውንም ሆነ፣ የደቡብ አፍሪካውን የጭቆና ስርዓት የሚያስታውሰው መጠሪያ ስሙ ከመንደሩ አጎራባች ያሉ የኤስ.ኦ.ኤስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዳወጡለት ወዳጃችን ዮናስ ጨምሮ ማስነበቡ አይዘነጋም፡፡ …እነሆም መቀሌ እንዲህ ነች፤ በጉራማይሌ ገፅታ የተገነባች፤ ህወሓታውያኑን በምቾት የምትንከባከብ፤ ሰፊውን ሕዝቧን ደግሞ ምድራዊ ፍዳ የምታስቆጥር፡፡

በነገራችን ላይ ከተማዋ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ መግዘፏን አስተውያለሁ፤ ይህ ግን የፈረደበት ድፍን ትግራዋይን በተለየ መልኩ ተጠቃሚ ሆኗል እንደማለት አይደለም፤ ዳሩ የዚህ አይነቱን የሕንፃ ጋጋታ ከክልሉ ውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያን የአድሎአዊነት ማሳያ አድርገው ሊወስዱት እንደሚችሉ አስባለሁ፡፡ ጥያቄው ግን ይህ አይደለም፤ ይልቁንም ሰማይ ጠቀሶቹ ፎቆቿም ሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎቿ አሊያም ቤተ-መንግስትን የሚያስንቁ መኖሪያ ቤቶቿ ለተርታው ነዋሪ ምን ፈየዱለት? የሚል እንጂ፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለም ይህ ኩነት በዋናነት የሚያመላክተው መቀሌ፣ በህወሓት መካከለኛና ከፍተኛ ካድሬዎች፤ እንዲሁም እነርሱን በተጠጉ ባለሀብቶች ወደ ሀጢአን ቅጥርነት እየተቀየረች መሆኗን ነው፤ ይህን ለማለት ያስደፈረኝ አንድም ብዙዎቹ ግንባታዎች ግለሰባዊ እንጂ መንግስታዊ አለመሆናቸው ሲሆን፤ ሁለትም ሕንፃዎቹ መኖሪያ ቤቶች እና ሆቴሎች በመሆናቸው ነው (እያወራን ያለነው ስለኢንዱስትሪዎች አይደለም)፡፡ እናሳ! ይህ አይነት ግንባታ ለንብረቱ ባለቤቶች ካልሆነ በቀር ለትግራይ ሕዝብ ምኑ ነው? …ርግጥ ነው እነዛ ለ17 ዓመታት ያህል የሰው ልጅ ይቋቋመዋል ተብሎ የማይታሰብ መከራ እየተቀበሉ ተራሮቹን ያንቀጠቀጡ ታጋዮች፤ ከድሉ በኋላ እሳት የላሱ፣ የመርካቶ ነጋዴን በብልጠት የሚያስከነዱ ሆነዋል፡፡
እዚህ ጋ ሳይነሳ የማይታለፈው ሌላው ነጥብ የከተማዋ ነዋሪ በፍፁማዊ ጨዋነት እንግዳ ተቀባይ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ያልኩት በጉዳዩ ላይ ጥናት አካሄጄ ሳይሆን፣ በየሬስቶራንቶች እና መንገዶች ላይ ካጋጠሙኝ በመነሳት በደምሳሳው የታዘብኩትን ተንተርሼ መሆኑን በትህትና እገልፃለሁ፡፡ ጓል መቀሌዎችንም፣ ‹‹የቐንየልና፣ ክብረት ይሃበልና!›› እላለሁ (ይህ ምስጋና ግን የደህንነት ሰራተኞችንም ሆነ፤ ችግር እንዳይፈጠርብን ሊጠብቀን እንደመጣ የገለፀውን የከተማዋ ፖሊስ አዛዥን አይመለከትም፡፡)
የሹክሹክታ ወሬ…
መቀሌ በከፍተኛና መካከለኛ ካድሬዎች የቅንጦት መኖሪያ ቤቶች ከመጥለቅለቋ በተጨማሪ፣ ገዥው-ፓርቲን በተራ ወቀሳም ቢሆን ስሙን ማንሳት ላልተጠበቀ የከፋ አደጋ የሚዳረግባት የአፈና መንደር መሆኗን ለመታዘብ ብዙ ድካም የሚጠይቅ አይደለም፤ በጥቂት ቀናት ቆይታዬም የታዘብኩት እውነታ አረናንና አንድነት ፓርቲን ተቀላቅለው ከሚታገሉ የከተማዋ ወጣቶች በስተቀር፣ በነዋሪው ላይ አስፈሪ ፍርሃት ማርበቡን የሚያስረግጥ ነው፡፡ በተለይም አድራሻና ማንነታቸው የማይታወቅ ‹‹ነጭ ለባሽ›› የሚል ተቀፅላ መጠሪያ ያላቸው ታጣቂዎች ‹በተቃዋሚነት የጠረጠሩትን በሙሉ አፍነው በመውሰድ ያሻቸውን ያደርጉታል› የሚል ወሬ በሹክሹክታ መዛመቱ፣ የፍርሃቱ አንድ መነሾ ሳይሆን አይቀርም ብዬ አስባለሁ፡፡ ወሬው በሕዝብ ዘንድ ይህን ያህል ስር የሰደደ ፍርሃት ማሳደር የቻለበት ምክንያት፣ ከበረሃው ዘመን ጀምሮ ‹‹ደርግን ይደግፋሉ›› ወይም ‹‹ይሰልላሉ›› ተብለው የተጠረጠሩ ነዋሪዎችን ድርጅቱ ለእንዲህ አይነት ተልዕኮ ባሰለጠናቸው አባላቱ ከመኖሪያ መንደራቸው በውድቅት ሌሊት እያፈነ ከወሰዳቸው በኋላ የደረሱበት አለመታወቁ ነው፤ ይህ ትውልድ ለፍርሃት እጅ መስጠቱም ከዚሁ ጋር እንደሚያያዝ ይነገራል፡፡ ካድሬዎቹም እንዲህ አይነት የበረሃ ወሬዎችን ሆነ ብለው እያጋነኑና እየቀባቡ በሕዝቡ መሀል ማናፈሱን ዛሬም ስለመቀጠላቸው ጥቂት የማይባሉ ወጣቶች አረጋግጠውልኛል፡፡ በአጠቃላይ በትግራይ፣ በቀድሞው የህወሓት መስራች አቶ አስገደ ገ/ስላሴ አገላለጽ ‹‹ሕዝቡ ሁሉ እስረኛ ነው››፡፡

ከአፈናዊ ማስፈራሪያዎችና ማሸማቀቂያዎች በተጨማሪ በከተማዋ ሥራ-አጥነት አለቅጥ መንሰራፋቱ እና አብዝሃው የበይ ተመልካች መሆኑ፣ የአዲሱን ትውልድ ልብ በህወሓት ላይ ካሸፈተው ውሎ ያደረ ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ከወደ ሸገር ተጋንኖ የሚወራውን ያህል ባይሆንም፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን በመውደድ ብቻ ድርጅቱን የሚደግፉ እንደነበሩ አይካድም፤ ግና፣ ይህም ቢሆን የሰውየውን ህልፈት ተከትሎ ታሪክ ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡ ሌላኛው የተቃዋሚውን ጎራ ያጠናከረው ምክንያት ከቀዳሚዎቹ ሁሉ የከፋ አምባገነን እንደሆነ የሚነገረው የአባይ ወልዱ ካቢኔ፣ በሙስናና መልካም አስተዳደር እጦት የሚቀርብበት ወቀሳ ነው፡፡ የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ደግሞ ‹‹ነፃ አውጪ››ውን ህወሓት እና መቀሌን ለሁለት ከፍሎ የማይተዋወቁ ዓለሞች አድርጓቸዋል ወደሚል ድምዳሜ ያደርሳል፡፡ ይህም ሆኖ ህወሓት በየትኛውም የትግራይ መሬት ተቃዋሚ ፓርቲ የመንቀሳቀስ ዕድል እንዳይኖረው ከጫካው ትግል ጀምሮ፣ በድርጅታዊ ቋንቋ ‹‹የትግራይ መሬት ከአንድ ፓርቲ በላይ መሸከም አይችልም›› የሚለውን ያልተፃፈ ሕግ ለማስፈፀም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፤ ለአፈናው ቀንበር መክበድም ቀንደኛው መነሾ ይህ ነው የሚለው ጭብጥ የተጋነነ አይደለም፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሀዬ፣ ስዩም መስፍን እና ፀጋዬ በርሄ፡- መቀሌ፣ አጽብሃ ወአብርሃ፣ ውቅሮ፣ አዲግራት፣ ፈረስ ማይ፣ አድዋ፣ አክሱም፣ ሽሬ እንደስላሴ፣ አላማጣ እና ማይጨው ከተሞች ተገኝተው ከነዋሪዎቹ ጋር ስብሰባ በመቀመጥ፤ እንዲሁም ከነበለት፣ ማይቅነጣል፣ ዕዳጋ ዓርቢ፣ እንዳባጉና እና ሽራሮን ከመሳሰሉ ወረዳዎች ደግሞ የተወሰኑ ግለሰቦችን በተወካይነት ወደ መቀሌ በማስመጣት ‹‹ችግራችሁ ምንድን ነው? አለ የምትሉትን ቅሬታና የጎደለውን ነገር በሙሉ ንገሩን?›› በሚል መንፈስ የተቀኙ ጥያቄዎችን በማቅረብ ውይይት አካሄደው እንደነበር ይታወሳል፤ በዚህ ስብሰባም ሕዝቡ በርካታ ችግሮችን ከመዘርዘሩ ባለፈ፣ በአብዛኛዎቹ መድረኮች ስሜት የፈነቀላቸው አረጋውያን ሳግ እየተናነቃቸው ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ሊጠቃለል የሚችል ተቃውሞ መሰንዘራቸውን ሰምቻለሁ፡-

‹‹እናንተ ክዳችሁናል! ለ17 ዓመታት ልጆቻችንን በጦርነት ማግዳችሁ ስታበቁ፤ ለትግራይ ሕዝብ አንዳችም የጠቀማችሁት ነገር የለም፡፡ እንዲያውም በሌሎች ክልሎች ላይ በሚገኙ ወገኖቻችንን ላይ በምታደርሱት በደል በጠላትነት እንድንመለከት ነው ያደረጋችሁን፡፡ ከዚህ በኋላ በምንም መልኩ አናምናችሁም!!››

የቀድሞዋ የድርጅቱ የአመራር አባል አረጋሽ አዳነም ‹‹እነዚህ ሰዎች (የህወሓት መሪዎች) የምር ኢትዮጵያን ይወዳሉ ወይ? የሚል ጥያቄ ተብላላብኝ›› ማለቷን ‹‹የትግራይ ሕዝብ፣ ወያኔዎቹና ሽፍቶቹ›› መጽሐፍ ገፅ 81 ላይ መገለፁ የአዛውንቶቹን አባባል ያስረግጣል ብዬ አስባለሁ፡፡

የሆነው ሆኖ እነ አባይ ፀሀዬ ከሕዝቡ የሰበሰቡትን ቅሬታ ይዘው (በርግጥ መጀመሪያውኑም ችግሩ ስለመኖሩ ሳያውቁ ቀርተው አይደለም)፣ ከክልሉ ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ ጋር ተወያይተውበት ነበር፡፡ ፕሬዚዳንት አባይም በድርጅታዊ መዋቅር የቀድሞ አለቆቹ እቢሮው ተገኝተው አንድ በአንድ የዘረዘሩለትን ችግር ካደመጠ በኋላ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፡- ‹‹እናንተ ያነጋገራችሁት ተቃዋሚ-ተቃዋሚውን ብቻ እየመረጣችሁ ነው፤ የመጣችሁትም ልክ እንደ ተቃዋሚዎች እንከን ፍለጋ ነው››፡፡

መቼም ከዚህ የበለጠ አስገራሚ የፖለቲካ ቀልድ ያለ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር ሄዶ ሄዶ አንድምታው ‹‹ህወሓት እኛ እንጂ እናንተ አይደላችሁም›› የሚል የልዩነት መልዕክት ይኖረዋልና ነው፡፡ ይህ ደግሞ በመለስ ህልፈት ማግስት ‹‹የአዲስ አበባው›› እና ‹‹የመቀሌው›› ተብሎ ለሁለት መከፈሉ ሲነገር የነበረው የህወሓት የውስጥ መተጋገል ገና መቋጫ ላለማግኘቱ አመላካች ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል (በነገራችን ላይ እነ አባይ ፀሀዬ በብዙ ሺህ ቅጂዎች የታተመ መጠይቅ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በትነው የነበረ ሲሆን፤ በቅርቡ ደግሞ የተሞላው መጠይቅ ተሰብስቦ ወደ አዲስ አበባ መላኩን ሰምቻለሁ፡፡ ይሁንና ውጤቱ ምንም ይሁን ምን አዲስ ነገር ይኖራል ብዬ ግን አላስብም፤ ምክንያቱም ከአስራ ሶስት ዓመት በፊት በዋነኛ መሪዎቿ አንደበት ‹‹ህወሓት ከአናቷ በስብሳለች›› ተብሎ ከተመሰከረባት ክፉ ህመሟ አለመፈወሷ ዛሬም በገሀድ ይታያልና)
የትግራይ እጣ-ፈንታ
በአስከፊው የትጥቅ ትግል ያለፈው የአካባቢው ነዋሪ፣ በህወሓት ላይ የነበረው ተስፋ መሟጠጡን የሚያስረግጥልን፣ ከላይ ያየነው የመቀሌ ገፅታ እና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ያሉ ነዋሪዎች ለጉምቱ የድርጅቱ ታጋዮች ያቀረቡት ብሶት ብቻ አይደለም፤ አርሶ አደሩም በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ በስቃይና በድህነት ኑሮውን የመግፋቱ ጉዳይ ጭምር እንጂ፡፡ በተለይም መሬትና ማዳበሪያ ወሳኝ የፖለቲካ ካርድ ሆነዋል፡፡ ማዳበሪያው በክልሉ በጀት የሚገዛ ቢሆንም፣ በዱቤ የማከፋፈሉን ስራ የሚያሳልጠው ደደቢት ብድርና ቁጠባ ነው፡፡ ብዙሃኑ አርሶ አደርም ከዚህ ተቋም በዱቤ የገዛውን ማዳበሪያ መክፈል ባለመቻሉ በዕዳ የመያዝ ክፉ ዕጣ-ፈንታ ይገጥመዋል፡፡ ስለዚህም ያለው አማራጭ ሁለት ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡ የመጀመሪያው ሚስቱንና ልጆቹን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ለልመና አሰማርቶ በሚያገኘው ገንዘብ እንደምንም ዕዳውን ከፍሎ፣ የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት መያዝ የሚችልበትን አጋጣሚ ማመቻቸት፤ ወይም ከህወሓት ጎን በመቆም ዕዳው ተሰርዞለት፣ የሴፍቲኔት ተጠቃሚም ሆኖ በጭቆና አገዛዝ ውስጥ ማዝገም ነው፡፡ ላለፉት ሃያ ሶስት ዓመታትም የሰሜን ኢትዮጵያ መልከዓ-ምድር ይህን በመሰለ ፍርሃትና በአንድ ርዕዮተ-ዓለም ተጠርንፎ ማደሩን ማን ይክደው ይሆን?
የመጪው ጊዜያት የብቻ ፍርሃት…
በዚህ አውድ የማነሳው የትግራውያን ከባድ ፍርሃት፣ ከክፉው የህወሓት አስተዳደር ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ በሀገሪቱ በነቢብ ገዥ-ፓርቲ ተደርጎ የሚታሰበው ኢህአዴግ መሆኑ ባይስተባበልም፣ ግንባሩን የፈጠሩት አራቱ ድርጅቶች በፖለቲካዊ ተፅእኖም ሆነ በአንዳንድ መንግስታዊ ቁልፍ ኃላፊነቶች ላይ እኩል ውክልና ያሌላቸው መሆኑ አያከራክርም፤ ይህንን ያፈጠጠ ሀቅ አምኖ አለመቀበሉም መፍትሔውን ሊያርቀው እንደሚችል መዘንጋት የለብንም፡፡ ለማሳያም እንደ ኢህአዴግ ባለ አምባ-ገነን አገዛዝ ውስጥ ከምንም በላይ ወሳኝ የሆኑት የደህንነት እና የመከላከያ ሠራዊቱ አወቃቀር በህወሓት የበላይነት መሆኑን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊም በመከላከያ ውስጥ ያለውን ፍትሓዊ ያልሆነ ውክልና ከማመኑም በዘለለ፣ በበረሃው ዘመን ታጋዩ በአብላጫው የህወሓት አባል የነበረ መሆኑን እንደ ምክንያት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ በአናቱም ድርጅቱ በመሀል ሀገር ያጣውን ድጋፍ ለማካካስ፣ ራሱን የትግራይ ብሔረተኛ አስመስሎ ከማቅረቡም ባለፈ፣ እንዲህ አይነት ከፋፋይ መንፈሶች እንዲናኙ በርትቶ ለመስራቱ በርካታ ማስረጃዎች አሉ፤ ‹‹እኛ ከሌለን የትግራይ ህዝብ ለአደጋ ይጋለጣል›› ከሚለው አፍራሽ ቅስቀሳው አልፎ፣ በ97ቱ ምርጫ ወቅት የኢንተርሃሞይ ጨዋታን ወደ ክርክሩ መድረክ ያመጣበትን አውድ እና በ2002ቱ ምርጫ አንድነትን ወክሎ በተምቤን ለመወዳደር የቀረበውን አቶ ስዬ አብርሃንም ሆነ አረና ፓርቲን ለማጥላላት የተጠቀመበትን ፖለቲካ መጥቀሱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በቅርቡ የሙስሊሙ መንፈሳዊ መሪዎችም ምርምራ የተደረገባቸውም ሆነ ስቅየት የደረሰባቸው በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ መርማሪዎች መሆኑን ለፍርድ ቤት መናገራቸው ተጨማሪ ማሳያ ነው፤ መቼም የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊዎች፣ ከሌሎች ብሔሮች የተገኙ መርማሪዎችም ሆነ ጨካኝ ገራፊ የፖሊስ አባላት አጥተው አይመስለኝም፤ እንዲህ አይነት አመለካከት በሕዝብ ዘንድ እንዲሰርፅ የሚሹ ፖለቲከኞችን ትዕዛዝ ማስፈፀም እንዲቻል እንጂ፡፡ ይህ እውነታም በአንዳንድ ቦታዎች ድርጅትንና ሕዝብን ቀላቅሎ ለጅምላ ፍረጃ ማጋለጡ አሌ አይባልም፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ደግሞ በክልሉ ላይ ብሔራዊ ሥጋት ፈጥረው ሕዝቡን አማራጭ አልባ አድርገው ድርጅቱን እንደጋሻ እንዲመለከት ቢያስገድዱ አስገራሚ አይሆንም፡፡
ሳልሳዊ ወያኔ
በብላታ ኃይለማርያም ረዳ ፊት-አውራሪነት በ1935 ዓ/ም ትግራይን በአፄው ላይ እንድታምፅ ያነቃቃው የወያኔነት እንቅስቃሴ፤ በያኔዋ የአፄው የክፉ ቀን ወዳጅ ታላቁ ብሪታኒያ ማበር ጭምር ሲቀለበስ፤ በክሽፈቱ ፅንስ ውስጥ ሌላ ትውልድ እንደሚገነግን ግልፅ ነበር፡፡ እናም የእነ ኃይለማርያምን ኢትዮጵያዊነት ጨፍልቀው የተነሱት እነ ስብሐት ነጋ፣ ያን ብርቱ የማህበረሰብ ክፍል ሰቆቃ ጠምዝዘው ከማህበረ-ባህሉ የተጣረሰ መንገድ መርጠው ሸገር ሲደርሱ፤ እነርሱኑ ካፈራ መሬት፣ የተቀለበሰውን ዳግማይ ወያኔ ረግጦ የሚነሳ ትውልድ እንደሚመጣ ዘንግተው ሰንብተዋል፡፡ ይሁንና ከላይ በመግቢያዬ የጠቀስኩትን የወልቃይቱን ትምህርት ቤት ኩነት በወቅቱ በቦታው የነበረው መምህር ሀጎስ አርዓያ (ስሙ የተቀየረ) እንደተረከልኝ፣ ራሳቸውን የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን/ ብለው በሚጠሩ ነፍጥ-አንጋች ፋኖዎች የተፈፀመ የመሆኑ እውነታ የህወሓትን የተሳሳተ ግምት ያስረግጣል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ የሳልሳዊ ወያኔ ወኪል እንደሆነ እየታመነ የመጣ የሚመስለው ስብስብ ሁመራ፣ ወልቃይትና ሽሬን በመሳሰሉ ከባቢዎች እንዳሻው የመንቀሳቀስ አቅም መገንባቱ ይነገራል፡፡ ድርጅቱ ከአስራ ሶስት አመት በፊት ወደ ኤርትራ በተሰደደው የህወሓት ሰው ፍሰሀ ኃይለማርያም ተድላ አስተባባሪነት መመስረቱ ይታወሳል፡፡ እንደ ትህዴን እምነት መሪው ፍስሀ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ መንግስት ደህንነቶች ነው የተገደለው፤ ከዚያን ጊዜም ወዲህ ሌላኛው የህወሓት አባል የነበረው ፀጋዬ ሞላ አስገዶም ከግማሽ መቶ ሺ አያንስም የሚባለውን ታጣቂ እንቅስቃሴ እየመራ እንደሆነ ንቅናቄውን በተመለከተ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ድርጅቱ ለፕሮፓጋንዳ ሥራው የራሱ ቴሌቪዥንና ራዲዮ፤ እንዲሁም ‹‹መጽሔተ ብስራት›› የተሰኘች በአማርኛና ትግርኛ የምትዘጋጅ የህትመት ውጤት እንዳለው ይታወቃል፡፡
ትህዴን የመረጠው የትግል ስልት ትክክል ነው አይደለም የሚለውን ሙግት ወደጎን ትተን፣ ኢትዮጵያን የሚመለከትበት መንገድ አስደማሚ ነው፡፡ በ1993 ዓ.ም አጋማሽ በለቀቀው የፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ እንደገለጸው፣ ዓላማው ‹‹አንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ነው››፤ የንቅናቄው ጠንከር ያለ የክልሉን የድጋፍ መሰረት ስናስተውል፣ የአንዲት ኢትዮጵያ መንፈስ የትግራዋይ ዋነኛው መለዮ መሆኑን ያስረግጥልናል፡፡ ‹ትግራይ የኢትዮጵያ መፈጠሪያ መሬት ናት› የሚለው የስብስቡ ድምፅ፣ ‹‹ትላንት የተፈጠረች›› ከሚለን ህወሓት ጋር ያለውን ተፃርሮሽ ፍንትው አድርጎ ያሳየናል፡፡ ፕ/ር መሳይ ከበደም፣ ከሳምንት በፊት በበተኗት መጣጥፍ ለድርጅቱ ቡራኬያቸውን እንዲሰጡት ያስገደዳቸው፣ ይኸው የአንዲት ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊነት ምስረታ ናፍቆት ይመስለኛል፡፡ አንቀፅ 39፣ ኢትዮጵያውያን እንዲበታተኑ የሚያደርግ በከፋፍለህ ግዛ የመገንጠል ፖሊሲ የተቀኘ እንደሆነ የሚከራከረው ንቅናቄው፣ ‹‹የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሉአላዊነት የሚያምን ነው›› ሲል ህወሓት የማያውቃትን ትግራይ ይነግረናል፡፡ መሪው ፀጋዬ ሞላም ‹‹የትህዴን አላማ የትግራይ ሕዝብ ጥያቄን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥያቄም ለመመለስ እንደሚታገል›› አበክሮ ይሟገታል፡፡ የሆነው ሆኖ የ17ቱ ዓመታት መራር የትጥቅ ትግል ዋና ገፈት ቀማሽ በሆነች ምድር፣ ዛሬም በተመሳሳይ መንገድ የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎቿ ‹‹ዱር ቤቴ!›› ማለታቸው ስለህወሓት ክሽፈት ‹‹ግዛቴ›› በሚለው መሬት በግላጭ መታወጅን ይመሰክራል፡፡

በመጨረሻም የለውጡ መንፈስ በመላ ሀገሪቱ እንዲናኝ ከትህዴን የጠቀስኳቸው መሰል መንፈሶች ጋር የሚስማማ አረዳድ ያለው አረና እና በስሩ የተሰባሰቡት ወጣቶችም ሆኑ የብሔሩ ልሂቃን፣ የትግራይን የመከራ መስቀል የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ግፉዓንም እንዲጋሩ የማሳመን ሥራ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በርግጥ ይህን መሰል የተንሸዋረረ አረዳድ ለመኖሩ ዋነኛው መነሾን ትህዴን በፖለቲካ ፕሮግራሙ እንዲህ ሲል መግለፁ መዘንጋት የለበትም፡-

‹‹ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ወያኔ (ማሌሊት) ለትግራይ ሕዝብ ብቸኛ ጠበቃ መስሎ በመቅረብ በሌሎች ሕዝቦች ላይ እየፈፀማቸው ባሉ ግልፅና ስውር ወንጀሎች ሳቢያ የትግራይ ሕዝብ በገዛ አገሩ በአይነ-ቁራኛና በጥርጣሬ እንዲታይ ማድረጉ ነው፡፡››

ያለፈው አልፏል፤ በመጪው ጊዜያት ይህን ፍርሃት አሸንፎ ትግርኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ የለውጡ አካል ለማድረግ፣ ለሥርዓት ቅየራው የሚካሄደው ትግል ዘርን መሰረት ያደረገ አግላይ የመከራ መስቀልን በጋራ ለመሸከም ዝግጁ መሆንን የሚያካትት ሊሆን ይገባል ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም ጠረጴዛው ላይ ያለው ምርጫ ሁለት ብቻ ነውና፤ ወይ አብሮ መውደቅ፣ አልያም በህብረት መነሳት፡፡ እስከዚያው እነ አባይ ፀሐዬን ከደርግ የሰማይ እሩምታ የከለሉ የትግራይ ተራሮች፣ ለትህዴን ጓዶችም እንደማይጨክኑ በመተማመን እናዘግማለን፡፡

ኢትዮጵያ: አሁንስ ተስፋሽ እግዚአብሔር አይደለምን? ዶ/ር ዘለዓለም እሸቴ ይመር

$
0
0

ነገሩ ግራ የገባው ነው!

ለመሆኑ አሳባችን ምንድነው? እንዲሁ ስንጨቃጨቅና ስንነካከስ ምን ያህል ልንዘልቅ  ነው? ንትርኩና መተላለፉ እጅ እጅ ብሎንና ሰልችቶን ሁሉን ትተን የእርቅ ያለህ!  ጊዜው ለመሆኑ መቼ ይሆን? ከጥል ወደ ፍቅር፤ ከመከፋፈል ወደ አንድነት፤  በስምምነት ለማደግ ቀጠሮ የያዝነው ለመቼ ነው?

ይህ የጋራ የሆነ የእርቅ ጉዳይ መደማመጥን ሊጠይቅ ነው። እኛ ደግሞ የለመድነው ሌላ  ነው። ታዲያ ስንተላለፍና ስንዘላለፍ ችግራችንን አክርረነው እና ነገራችንን እጡዘነው የባሰ  ተራርቀን እንታያለን። ሁላችንም ነገርን የምናየው በየራሳችን መነፅር ብቻ ስለሆነ ሌላው  የሚናገረው አይገባንም። ስለዚህ ሁል ጊዜ መተላለፍ ብቻ ሆኖብናል።  አይዞን!  እግዚአብሔር ስለ ተስፋው ቃል እንዲህ ሲል ይናገራል  “አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጥቅጠህ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን  ሰጠሃቸው።”(መዝሙር 74፥14)። “የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ  ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?” ይላ እግዚአብሔር(አሞጽ 9፥7) “ኢትዮጵያ  ፈጥና እጆቿን ወደ አግዚአብሔር ትዘረጋለች። (መዝሙረ ዳዊት 68፡31)  ምድራችን የመሪዎቻችንን ክብር ስታስተናግድ ለዘመናት ኖራለች። እጃችንን ስንዘረጋ  ደግሞ አዲሲቷ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔርን ክብር ታስተናግዳለች።

የእስራኤል ሕዝብ ጥሪ በአንድ ሰው ያውም በአብርሃም ላይ የተመሰረተ ነው። ስለሆነም  ያዕቆብ እስራኤል በመሆን የቃል ኪዳኑን ሕዝብ መሰረተ።ኢትዮጵያ ጥሪ ግን በሕዝብ ላይ የተመሰረተ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ እጆቿን በመዘርጋት የተስፋው ቃል ሕዝብ ትሆናለች። ለሕዝቡም ምግባቸውን ይሰጣቸዋል። ይህም ተጽፏል። ስለተጻፈም ይፈጸም ዘንድ ግድ ነው።  እግዚአብሔር የሰጠን ተስፋ ዓይናችንን ከሰው ላይ አንስተን ፈጣሪያችን ላይ እንድናደርግ  ይጠራናል። የሚያስተሳስረንም በእግዚአብሔር ያለን እምነት ብቻ ነው። እግዚአብሔር  ኢትዮጵያ የማንኛውም አንድ ሃይማኖት አገር ሳትሆን በእግዚአብሔር ስር ያለች የፍቅር  አገር ያደርጋት ዘንድ እናምናለን።  ምልክት ይሁነን!  ባንዲራችንን የቃል ኪዳን ምልክት እናድርገው።

መላ ከላይ ይምጣልን ስንል ለምልክት ባንዲራችን የተስፋችን አመልካች የሆነው የተዘረጉ  እጆች ይኑርበት። ስሙኝና።  ባንዲራችን እኛን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ኩራት እንደሆነ ይታወቃል። በባንዲራችን ላይ  ያለው አርማችን ግን መንግሥት በተቀየረ ቁጥር እየተቀየረ ዕድሜው በመንግሥታት ዕድሜ  ልክ ብቻ የሚቆጠር መሆኑ ይታወቃል።  መላው ጠፍቶን እጆቻችንን እንደዘረጋን አምላክ ይወቅልን ስንል ኢትዮጵያ ከጥሪዋ ጋር  የሚሄድ አርማ (የተዘረጉ እጆች) በባንዲራችን ላይ እንዲያርፍበት እናድርግ የሚል  ምኞት አለኝ።

ይህ ዓርማ ታሪካዊ በሆነው ባንዲራችን ላይ ቢቀመጥ ሊሰጠን ያለውን ምልክት በጥቂቱ እንመልከት።
1ኛ/ የተሰጠን ዓርማ ከአምላክ የተወሰነልንን የበረከት ጥሪ ለመቀበል እሺ በማለት  እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እንዲባርካት ፍቃደኝነታችንን ያሳያል።
2ኛ/ የተሰጠን ዓርማ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማንነት ያንፀባርቃል። የሰዎች ምኞት  የሚያንፀባርቅ ሳይሆን የተስፋው ቃል ሕዝብ ለመሆናችን ምስክር ይሆናል።
3ኛ/ የተሰጠን ዓርማ ከማናቸውም መንግሥታት ጋር ስለማይወግን ዘላቂነት ይኖረዋል።
4ኛ/ የተሰጠን ዓርማ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ሃሳብ እንጂ ኢትዮጵያዊ ሰው  የፈጠረው አይደለም። ስለዚህም ከአምላክ የተሰጠን ስጦታ ነው።
5ኛ/ የተሰጠን ዓርማ በሺህ የሚቆጠር ዘመን ታሪክ ያለው ታሪካዊ ነው። ስለዚህም ታሪካዊ  በሆነው ባንዲራችን ላይ ታሪካዊ ለሆነችው አገራችን ምቹ ነው።

6ኛ/ የተሰጠን ዓርማ ለኢትዮጵያ ብቸኛ መለያ ይሆናል። በሌላ በኩል ግን የብዙ አገሮች ባንዲራ ኮከብ አለበት።

7ኛ/ የተሰጠን ዓርማ ከማናቸውም ሃይማኖት ጋር አይወግንም። ከማናቸውም ሃይማኖት  ምልክቶች ጋር አይያያዝም። አይማኖት እንደማይከፋፍለን ምልክት ይሆንልናል።
8ኛ/ የተሰጠን ዓርማ በፊት ለአፍሪካ ኩራት የነበረውን ባንዲራችንን ለዛሬ የአፍሪካ ተስፋ  በማድረግ ይበልጥ ያከብረዋል።
9ኛ/ የተሰጠን ዓርማ ኢትዮጵያ የብዙ አይማኖቶች አገር ብትሆንም ቅሉ በአይማኖት  ሳንከፋፈል በመያያዝ እዲስ በሆነ መልክ የእግዚአብሔርን እርዳታ ጠይቆ ማግኘት ምን  እንደሚመስል ለዓለም ያበስራል።
10ኛ/ የተሰጠን ዓርማ እግዚአብሔር አዲሲቷን ኢትዮጵያ ገፅታ ለውጦ የዓለም ሞዴል  ሲያረጋት ለእግዚአብሔር ታማኝነትና ታላቅነት መታሰቢያ ይሆናል።  ኢትዮጵያ ሆይ፡ ምርጫሽ የቱ ይሆን?

Commentየዶ/ር ዘላለም ኢሜል ፡ one@EthioFamily.com

 

የሁለት ፈረሶች ጥያቄ (ዳንኤል ክብረት)

$
0
0
ዳንኤል ክብረት
ሁለት ፈረሶች እንደነበሩ ተነገረ፡፡ አንደኛው እጅግ ለምለም በሆነ ሰፊ ሜዳ ላይ ተሠማርቶ፣ ሲያሻው ደግሞ በግራ በቀኝ ገብስ ፈስሶለት፣ ሲጠማው የሚጠጣው ውኃ በሜዳው መካከል ኩልል ብሎ እየወረደለት፣ አውሬ እንዳይተናኮለው ዙሪያውን በውሻ እየተጠበቀ ይኖር ነበር፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሣር ዘር ለአመል ያህል ብቻ እዚህም እዚያም በበቀለበት፣ ጭው ባለ ደረቅ ሜዳ ላይ ተሠማርቶ ያገኛትን እየነጨ፣ ከዕለታት በአንድ ቀን ከደጋ የዘነበ ዝናብ በአካባቢው ሲያልፍ የሚያገኘውን ጥፍጣፊ ውኃ እየተጎነጨ፣ ሌትና ቀን ምን ዓይነት አውሬ መጥቶ ይዘነጥለኝ ይሆን? እያለ በሥጋት ይኖር ነበር፡፡
daniel-kibret-300x207

ዳንኤል ክብረት

ምንም እንኳን ሁለቱም ፈረሶች በኑሮ በማይቀራረብ ሜዳ ላይ በመከራና በቅንጦት ተለያይተው ቢኖሩም የኑሮ ጥያቄ ግን አገናኝቷቸው ኖሯል፡፡ ያ እንዲያ በለመለመ መስክ ተሠማርቶ እምብርቱ እስኪነፋ ሆዱ እስኪቆዘር እየበላ ሲተኛ ሲነሣ የሚውለው ፈረስ ‹‹ይኼ ሣር ያለቀ ዕለት፣ ይኼም ውኃ የነጠፈ ጊዜ፣ እነዚህም ውሾች እኔን መጠበቅ ትተው የሄዱ ጊዜ፣ ይኼስ ገብስ የጠፋ ቀን ምን ይውጠኝ ይሆን? ያስ ቀን መቼ ይሆን? ይል ነበር፡፡ ይኼ ጥያቄ ምንጊዜም ይረብሸው ነበር፡፡

 

 ያ በደረቅ ሜዳ ላይ እዚህም እዚያም የበቀለች ሣር እየነጨ ከርሱን ሲደልል የሚውለው ፈረስ ደግሞ ‹‹መቼ ይሆን አልፎልኝ ለምለም መስክ ላይ ውዬ፣ ከፈሰሰ ውኃ እንደ ልቤ ተጎንጭቼ፣ ያለ ሥጋት አድሬ የሚነጋልኝ? ያ ቀን መቼ ይሆን?ይል ነበር፡፡

እዚህ ሀገር ያለን ሰዎች በሁለቱ ፈረሶች ጥያቄ ውስጥ ወድቀናል፡፡ አንደኛው መስኩ ለምልሞለት፣ ውኃው መንጭቶለት፣ ሥጋቱ ጠፍቶለት፣ ሕይወቱ ቀንቶለት የሚኖረው ሰው ጥያቄ ነው፡፡ እንዴት ሜዳው ላይ እንደደረሰ አያውቀውም፤ ብቻ አንድ ቀን ተቀለጣጥፎም፣ ተጣጥፎም፣ ተለጣጥፎም፣ ራሱን ሜዳ ላይ አግኝቶታል፡፡ ለስንትና ስንት ፈረስ የሚበቃውን መስክ ብቻውን ተሠማርቶበታል፡፡ አገር የሚያጠጣውን ወንዝ ብቻውን ይንቦራችበታል፡፡ ጥጋብን ከልኩ በላይ፣ ምቾትንም ከመጠን አልፎ ቀምሶታል፡፡ ድህነትን ረስቶ የት መጣውን ዘንግቶታል፡፡ ግን ሥጋት አልለቀቀው ይኼ መሥመር የተበጠሰ ዕለት፣ ይኼ ሥርዓት ያለፈ ቀን፣ ከእገሌ ጋር የተጣላሁ ጊዜ፣ ቀን የዞረችበኝ ሰዓት፣ የተነቃ ለታ፣ ዕቁቡ የተበላ ጊዜ፣ ካርታው ያለቀ ቀን፣ መንገዱ የታወቀ እንደሆን፣ ሕግ የተቀየረ ቀን፣ ምን ይውጠኝ ይሆን? ያችስ ቀን መቼ ትሆን? እያለ ይጠይቃል፡፡ እየበላ ይሠጋል፣ እየጠጣም ይጨነቃል፤ አይቷል፣ ሰምቷል፡፡ ድንገት ለምለሙ ሜዳ ላይ ተገኝተው ድንገት ከሜዳው የጠፉ አሉና፡፡
አሁን ሆዱ ተቀይሯል፤ አንገቱ ተቀይሯል፤ እጁ ተቀይሯል፤ መቀመጫው ተቀይሯል፤ ማረፊያና መዋያው ተቀይሯል፡፡ ይህንን ያጣ ዕለት ምን ይውጠዋል?
ያኛውም ፈረስ አለ፡፡ እንደ ዐርባ ቀን ዕድል ሆኖ የደረቀ መስክ ላይ ውሎ እንዲያደር የተፈረደበት፤ ቢሄድ ቢመጣ፣ ቢወርድ ቢወጣ ከዚያ መስክ መላቀቅ ያቃተው፡፡ መቼ ይሆን የእኔስ ሜዳ በሣር ተሞልቶ እንደነዚያ ሣር የምጠግበው እያለ ምኞት የገደለው፡፡ የእኔስ ወንዝ መቼ ይሆን ውኃ ሞልቶት ሳልጨነቅ የምጠጣው? እያለ ሃሳብ ያናወዘው፡፡ የእርሱ ቤት እየፈረሰች ከጎረቤቱ ዘጠኝ ፎቅ ሲበቅል አይቷል፡፡ ስትተከል፣ ውኃ ስትጠጣ፣ አላያትም፡፡ እንዲሁ ብቻ ፎቋ በቀለች፡፡ ስትገዛ ያላያት፣ ፍንጥር ያልጠጣባት መኪና እንዲሁ ሽው እልም ስትል አያት፤ እናም ምን ዓይነት ፈረሶች ይሆኑ ለዚህ የሚበቁት እያለ ይጠይቃል፡፡ ዝርያቸው ምን ቢሆን ነው? መልካቸውስ ምን ቢሆን ነው? የፈረስ ጉልበታቸውስ ምን ያህል ቢሆነ ነው? ፍጥነታቸውና ቅልጥፍናቸውስ እንዴት ያለ ቢሆን ነው? ጌቶቻቸውንስ እንዴት አድርገው ቢያገለግሏቸው ነው? እንዲህ ለምለም መስክ ላይ የለቀቋቸው? እኛም ስናገለግል ኖረናል፤ ጋሪ ስንጎትት፣ እህል ስንሸከም፣ ዕቃ ስናጓጉዝ ኖረናል፤ ጌቶቻችን ሲጋልቡን ኖረናል፤ ግን እነርሱ ምን ያህል ቢያስደስቷቸው ነው ይህንን ዕድል የሰጧቸው? እያለ ይጠይቃል፡፡
ለመሆኑ እነርሱ ናቸው ወደ እኛ የሚመጡት ወይስ እኛ ነን ወደ እነርሱ የምንሄደው? ለመሆኑ የኛን ድህነት ነው ወይስ የእነርሱን ሀብት ነው የምንካፈለው? በርግጥ ከኛም የሄዱ አሉ፤ ከእነርሱም የሚመጡ አሉ? ይላል፡፡ አንዱ ሜዳ ላይ ተሠማርተን እንደ አቅማችንና እንደ ችሎታችን መጋጥ ሲገባን ለምን ሁለት ዓይነት ሜዳ ሆነ፡፡ አሁን እኛና እነርሱ እኩል ‹‹ፈረስ›› ተብለን እንጠራለን? እኛ ‹‹ሌጣ ፈረስ›› ነን፣ እነርሱ ደግሞ ‹‹ባለ ወግ ፈረስ›› ናቸው፡፡
ግን ይሁን፤ እሺ መቼ ይሆን እኛስ እንደነርሱ የምንሆነው? መቼ ይሆን ያለ ሥጋት ውለን የምናድረው? ለምለሙን መስክ ማን ይነካዋል፤ ላለው ነው ድሮም የሚጨመርለት፤ የኛ የድኾቹን መስክ ነው ለሀብታሞቹ የሚሰጡት፤ የድኾቹን ደረቅ መስክ ሀብታሞቹ የሚቀኑበትን ያህል እኛ በእነርሱ ለምለም መስክ አንቀናም፡፡ ደግሞ አንድ ቀን ይመጣሉ፡፡ ‹‹ይህንን መስክ ለምለም ማድረግ እንፈልጋለን›› ይላሉ፡፡ እኛም ደስ ይለናል፡፡ የዘመናት ምኞታችን አይደል? መንገዱ ጠፍቶን እንጂ እኛም ለምለም ማድረግ እንፈልግ ነበርኮ? መንገዱን ያወቀው ሰው ሲመጣ ለምን እንቃወመዋለን፡፡
ግን ይቀጥሉና ሌላ ነገር ይሉናል፡፡ ‹‹መስኩን ግን ለምለም የምናደርገው ለእኛ እንጂ ለእናንተ አይደለም›› ይሉናል፡፡ ለምን? ለምን? እኛ ለምለም ሣር አይወድልንም? እኛ ለምለም የምናደርግበትን መንገድ ለምን አያሳዩንም? ባያሳዩንስ ለምን አይፈቅዱልንም? ባይፈቅዱልንስ ለምን አይተውንም? እንላለን፡፡ ይህ ግን ጥያቄ ነው እንጂ መልስ የለውም፡፡ እኛም ጥያቄውን የምናውቀውን ያህል መልሱን አናውቀውም፡፡ ስንጠይቅም ‹‹ምላሽ›› እንጂ ‹‹መልስ›› የሚሰጥ አናገኝም፡፡
እኛም ከዚያ መስክ እንወጣለን፣ ወደሌላ መስክም እንዛወራለን፤ አሁንም ቅንጥብጣቢ ሣር እንፈልጋለን፤ ጥፍጣፊ ውኃ እናስሳለን፡፡ ያ እኛ የነበርንበት መስክ ግን በአንድ ጊዜ ይለመልማል፡፡ ውኅው ጅረት ሆኖ ይፈስበታል፡፡ ይገርመናል፡፡ እኛ እዚያ ሳለን፡፡ ውኃ አልነበረም፡፡ እንደ ወር በዓል ቀን ቆጥረን ነበር የምናገኘው፡፡ አሁን ግን ይንፎለፎላል? ለመሆኑ እኛ ምን ብለን መጠየቅ ነበረብን? ይኼ ራሱ ሌላ ጥያቄ ይሆንብናል፡፡ መቼ ይሆን እኛስ እንዲህ ባለው መስክ ላይ የምንሠማረው? እንላለን፡፡ የማይሳካ ምኞት እንመኛለን፤ የማይመለስ ጥያቄ እንጠይቃለን፡፡
እዚያም ቤት ሌላ ጥያቄ አለ፡፡ ፀሐይዋ እንደወጣች ትቀጥል ይሆን? ወንዙ እንደፈሰሰ ይቀጥል ይሆን? ነፋሱ እንደነፈሰ ይቀጥል ይሆን? ሣሩ እንደለመለመ ይዘልቅ ይሆን? እኔስ እንደተወደድኩና ሞገስ እንዳገኘሁ እኖር ይሆን?
ሰውየው ስለ አውሮፕላን አነዳድ የሚገልጥ ማኑዋል አገኘና አውሮፕላኑን አስነሥቶ አበረረ፡፡ ገጹን ይገልጣል፤ የተጻፈውን ይፈጽማል፤ አውሮፕላኑም ይበራል፡፡ በቀጣዩ ገጽ ላይ ምን እንዳለ የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ገጹ ተገንጥሎ ቢገኝ ምን ማድረግ እንዳለበትም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ብቻ ይገልጣል፣ ያነባል፣ ይነካካል፣ ይበራል፡፡ አውሮፕላኑ ተነሥቶ በሃያ አምስት ሺ ጫማ ከፍታ ላይ ሲደርስ የመጨረሻው ገጽ ላይ ደረሰ፡፡ ‹‹ክፍል ሁለትን በክፍል ሁለት መጽሐፍ ይመልከቱ›› ይላል፡፡ ክፍል ሁለት መጽሐፍ ግን የለውም፤ የት እንዳለም አያውቅም፡፡ ምን ማድረግ እንዳለበትም አልተዘጋጀም፡፡ ስለዚህም እንደወጣ መውረድ ጀመረ፡፡ ያውም በዝግታ ሳይሆን እየተምዘገዘገ፡፡
እናም እኛ በለምለም መስክ ላይ ያለን ፈረሶች፣ አንድ ክፉ ቀን መጥቶ ‹‹ክፍል ሁለትን በሌላ መጽሐፍ›› ቢለንስ? ምን ይውጠናል? ለመሆኑ ክፍል ሁለት የት ነው ያለው? እስካሁን ያሳየን የለም፡፡ እኛ የምናውቀው የየዕለቱን ምዕራፍ ብቻ ነው፡፡ ያንን እናነባለን፣ በእርሱ እንኖራለን፣ ቀጣዩን ምዕራፍ አናውቀውም? ስለዚህም እኛም እንጠይቃለን? እንዲሁ እንዘልቅ ይሆን? ብለን፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

Source: Danielkibret

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live