Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

‹‹ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ አይደለም፣ የእናንተም ነው›› እስክንድር ነጋ (ኤልያስ ገብሩ ጎዳና)

$
0
0

በኤልያስ ገብሩ ጎዳና

‹‹ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ አይደለም፡፡ የእናንተም ነው፡፡ …››
‹‹በእስር ላይ የምትገኙ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ››

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

‹‹አሁን ደስተኛ ነኝ››
‹‹እስክንድርን ምግብ ማብሰል እያለማመድኩት ነው››

አቶ አንዷለም አራጌ

ከትናንት በስትያ ሰኔ 03 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ከቅርብ ጓደኛዬ እና የሙያ ባልደረባዬ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት [እስር ቤትም ነው] አምርተን ነበር- ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆኑትን አቶ አንዷለም አራጌን ለመጠየቅ፡፡ የተለመደውን የፖሊስ ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ስንዘልቅ የሰማያዊ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፈ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ፣ አቶ ሳሙኤል የተባሉ አባልና የ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እስክንድርን ሊጠይቁ ቀድመውን ደርሰው ነበር፡፡Andualem & Eskinder with family

…እስክንድርን እና አንዷለምን አስጠራናቸው፡፡ ሁለቱም ሲያዩን ደስ አላቸው፡፡ በተለይ በተለይ የእስክንድር ፈገግታ በጣም ደማቅ ነበር፡፡ ተከፋፍለን ከሁለቱም ጋር ሃሳቦችን መለዋወጥ ጀመርን፡፡

እስክንድር በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ “pen Golden of freedom 2014″ ተሸላሚ በመሆኑ ‹‹እንኳን ደስ ያለህ›› አልኩት፡፡ ‹‹አመሰግናለሁ፡፡ ትናንት አንድ ልጅ ሊጠይኝ መጥቶ ነግሮኛል›› ካለን በኋላ ደግመን ስለሽልማቱ በጋራ ሃሳብ መለዋወጥ ቀጠልን፡፡ እስክንድር ሽልማቱ አዲስ መሆኑን አላወቀም ነበር፡፡

በመሆኑም ስለሽልማቱ ሁኔታ፣ ማን እንደሸለመው፣ ሽልማቱ የት እንደተደረገ፣ ሽልማቱን ማን እንደተቀበለለት [ሽልማቱን የተቀበለው በኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ክስ ወንጀለኛ ተብሎ ከባልደረባው ፎቶ አንሺ ጋር 11 ዓመታት ከተፈረደበት በኋላ በይቅርታ የተለቀቀው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ ነበር]፣ የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ምን እንደሚመሰል፣ በሽልማቱ እነማን እንደተገኙ …ያወቅነውን ሁሉ ነገርነው፡፡

‹‹ይህንን አላዋኩኝም፣ ሰርካለም (ባለቤቱ) ለምን በቦታው አልተገኘችም?›› በማለት ጠየቀንና በድጋሚ ደስ ብሎት ጣቶቹን በሽቦ ውስጥ አሾልኮ ጨበጠን፡፡ ወዲያው ይህቺን መልዕክት ተናገረ፡-

‹‹ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ አይደለም፡፡ የእናንተም ነው፡፡ የኢትዮጵያዊ ጋዜጠኞች ነው፡፡ ሁላችንንም ይመለከተናል፡፡ ለሁላንችም ይገባናል፡፡ ይሄንን ሽልማት የምመለከተው ሐሳብን በነጻነት ከመግለጽ የመብት ጥሰት አኳያ ብቻ አይደለም፡፡ ለሌሎች የዜጎች መብቶች ሲሉ ለታገሉ እና እየታገሉ ላሉ ፖለቲከኞች፣ የሕሊና እስረኞችም ጭምር ነው፡፡ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከሌሎች ከተነፈጉ መብቶች ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡ ሁሉንም መብቶች እናገኛቸዋለን፣ ወይም እናጣቸዋለን፡፡ ለዚህ ደግሞ ጸንተን እንታገል፣ ትግላችን ግን ሰላማዊ ብቻ መሆን አለበት፡፡ …››

እስክንድር ደስ ብሎት ሃሳቡን መናገሩን ቀጥሏል፡፡ እኔ ለተወሰኑ ቀናት በማዕከላዊ መታሰሬን ሰምቶ ስለነበረም ‹‹ማዕከላዊ እያለህ የታሰሩትን ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች ለማግኘት ችለህ ነበር?›› ብሎ ጠየቀኝ፡፡ እነሱን በአካል ማግኘት አለመቻሌን ነገር ግን ከእነሱ ጋር ታሥረው የነበሩ ሌሎች ተጠርጣሪ ዜጎችን አግኝቼ በእስር ስላሉበት ሁኔታ መጠየቄን ነገርኩት፡፡

የታሰሩት ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖችን ቤተሰብ ማግኘት እችል እንደሆነና ከቻልኩም በእነሱ በኩል መልዕክቱ ይደርስለት ዘንድ በድጋሚ ጥያቄያዊ ሃሳቡን አቀረበልኝ፡፡ የተወሰኑ የእስረኛ ቤተሰቦችን ማግኘት እንደምችል አስረዳሁት፡፡

‹‹የታሰራችሁ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ፡፡ አከብራችኋላሁ፡፡›› ብለህ ንገርልኝ አለኝ – ደጋግሞ፡፡ …

በዕለቱ ከሰዓታት በፊት ሰናይት ታከለ የምትባል ወዳጄም እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ እንደምሄድ በነገርኳት ጊዜ ‹‹እንደማከብረው እና እንደማደንቀው ንገርልኝ›› ያለችኝን መልዕክት ለእስክንድር አደረስኩላት፡፡

እሱ ግን ሳቅ እያለ ‹‹ተሳስተሻል! …ተሳስተሻል! …ተሳስተሻል›› ብለህ ንገራት አለኝ፡፡ ‹‹ለምን?›› አልኩት፡፡ ‹‹ገና ምን ሰርቼ?›› በማለት በዚያ ትሁት አንደበቱ መለሰልኝ፡፡ በእውነት መልሱ አስደመመን፡፡ ዋይ እስክንድር፣ ፍጹም የተለየ ታላቅ ሰው!!!

እስክንድርን እናናግረው የነበርን ጠያቂዎች ወደ አንዷለም አራጌ ዞርን፡፡ አንዷለም ጋር የነበሩት ደግሞ ወደ እስክንድር፡፡

አንዷለም የስፖርት ቲ-ሸርት ከቁምጣ ጋር ለብሷል፡፡ ጥቁር መነጽር አድርጓል፡፡ ረጋ ብሎ ፈገግ በማለት ‹‹ምን አዲስ ነገር አለ?›› በማለት ጨዋታ ጀመረ፡፡ አንዷለም የእስክንድርን ሽልማት ሰምቶ ኖሮ፣ ‹‹አሁን ከምሳ በኋላ ጣፋጭ የለውዝ ሻይ እሱን እና ጓደኞቻችንን በመጋበዝ ‹እንኳን ደስ ያልህ!› በማለት ሰርፕራይዝ አደርገዋለሁ፡፡ ምግብ ማብሰል እያለማመድኩት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እኔ ነኝ ሰርቼ የማበላው፡፡ በልጅነቱ በበርገር ያደገ ልጅ አሁን ሽንኩርት እና ቲማቲም መክተፍ ችሏል …›› በማለት በቀልድ ነገረን፡፡

‹እነማን ከእናንተ ጋር አሉ? በአንድ ክፍል ውስጥስ ስንት ናችሁ? ጊዜያችሁንስ እንዴት ነው የምትጠቀሙበት?›› የሚል ጥያቄ አቀረብንለት፡፡

‹‹ለረዥም ጊዜ፣ በጣም አስቸጋሪ ክፍል ውስጥ፣ መሬት ላይ ስንከባለል ነበር በእስር ያሳለፍሉት፡፡ አሁን አቶ ስዬ አብርሃ ታስሮ በነበረበት ጥሩ በሚባል ክፍል ውስጥ ለአምስት ታስረን እንገኛለን፡፡ አቶ መላኩ ተፈራ፣ አቶ መላኩ ፈንታ ና አንድ ባለሃብት አብረውን ናቸው፡፡ አሁን አልጋ ላይ መተኛት ጀምሬአለሁ፡፡ ይሄ ለእኔ እንደ አዲስ ሕይወት ነው፡፡ አሁን ደስተኛ ነኝ፡፡ …ጊዜያችንን በጥሩ ሁኔታ ከፋፍለን እየተጠቀምንበት ነው፡፡ እናነባለን፣ እንወያያለን፣ የምንፈልጋቸውን መጽሐፍት ግን በምንፈልገው ጊዜ አናገኝም፣ በዚህ በኩል መጠነኛ ችግር አለ፡፡ በተረፈ ደህና ነኝ፡፡ እኔ ተስፈኛ ነኝ፡፡ እናንተም በተሰማራችሁበት ዘርፍ የምትችሉትን ሁሉ ለሀገራችሁ ለውጥ መታገል አለባችሁ…››

ከሁለቱም ጋር የነበረንን የ30 ደቂቃ ቆይታ ሳንጠግብ ‹‹በቃችሁ›› የሚለው የፖሊስ ድምጽ ተሰማ፡፡ ‹‹እናመሰግናለን፣ በቃ ሂዱ›› ሲል አንዷለም በእርጋታ ተናግሮ በሽቦ ስር አሾልኮ እጆቻችንን ጨበጠን፡፡

እስክንድር ደግሞ ‹‹‹ሲመቻችሁ ብቻ መጥታችሁ ጠይቁን፣ ሥራ እንዳይበደል!፡፡ ሥራችሁን ሥሩ›› በማለት ለእኛም ያለውን አሳቢነት ከምክሩ ጋር ደጋግሞ ገለጸልን – ሁሉንም ሰላም በሉልኝ በማለት፡፡ እንግዲህ እስክንድርን የምትሉ ሁሉ ሰላምታውን በእኔ በኩል አድርሻለሁ፡፡


Sport: አፍሪካ- ‹‹ክሮስ ኤክስፖርት እናደርጋለን›› –የዓለም ዋንጫ ዕይታ በገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

$
0
0

ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

(ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ)

(ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ)


በዚህ አለም ዋንጫ ላይ የአፍሪካን ቡድኖች ስመለከት ምንም እድገትና ተስፋ አላየሁባቸውም፡፡ በአውሮፓ ስመ ጥር ተጨዋቾች ይዘው በእንቅስቃሴ ለመብልጥና በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሸነፍ የሚያስችል ነገር አይታይባቸውም፡፡ጋና ከአሜሪካ ጋር ሲጫወት ተጀምሮ እስኪያልቅ ጋና ክሮስ ሲያደርጉ ነበር፡፡ በቀኝ በኩል ሮጠው ይመጡና ያሻማሉ፡፡እንደገናም ያሻማሉ …አሁም ያሻማሉ፡፡ገና ወደዚያ ሲመጡ እንደሚያሻሙ ያስታውቃል፡፡ ሻሞ መሆኑን የአሜሪካ ተጫዋቾች ብቻ ሳይሆኑ ሜዳ ያለውም ተመልካችን በቴሌቪዥን መስኮት ስር ያለው ሁሉ ያውቃሉ ፡፡ የአሜሪካ ተጨዋቾች ረጃጅም ናቸው፡፡ ዝላይም ከጋና ይሻላሉ ፡፡ኳሱን አሜሪካኖች እንደሚያገኙ እየታወቀ ክሮስ ሲያደርጉ ለምን ይሄን እንደማይቀይሩ ግልጽ አልነበረም፡፡ያንን ሁሉ ክሮስ አሜሪካኖች በቴስታ መመለሳቸው ብቻ ሳይሆን ጋና እየተጠቃ የነበረው ራሳቸው ክሮስ አድርገው ከሚመለሰው ኳስ መሆኑ ሲታይ ዋጋ ቢስ ክሮስ ነበር፡፡የሚገርመው በቀኝ ያን ሁሉ ክሮስ አድርገው ባከነና አንድ ኳስ በግራ ሄደው ልጁ ስላልተመቸው ለአዩ በተረከዝ አቀበለው፡፡አዩ አገባው፡፡አሜሪካኖቹ እንዲህ አይነቱ አመጣጥ ይቸግራቸዋል፡፡ልጁ ለአዩ በተረከዝ ያቀበለው ስላልተመቸው ነው እንጅ ክሮስ ነበር የሚያደርገው፡፡መቀባበሉ የሚያዋጣ ቢሆንም ጋና የተቃኘው በክሮስ ነው፡፡እርግጥኛ ነኝ አሰልጣኙ በተረከዝ በመስጠቱ‹‹እንዲህ አይነት የቄንጥ አጨዋወት አልፈልግም ››እንደሚሉት ነው፡፡መቀባበሉ ከእዚያ በኋላ ሳይደገም በክሮስ ዘለቀ፤ አለቀ፤ ተጠናቀቀ፡፡ ካሜሩን ክሮስ፤ ናይጀሪያ ክሮስ…..የአፍሪካ ቡድኖች ክሮስ ኤክስፖርት የሚደርጉ ይመስል ስራቸው ይሄ ሆነ፡፡ ናይጀሪያ ከደካማ ኢራን ጋር አየነው፡፡ አንድ ተጨዋች ማለፍ እንኳን ቸግሯቸው ኳሱ ሲበላሽ የኛ ቡድን ቀሽም መሆኑ እንጂ ናይጀሪያ በዚህ አቋሙ ማለፍ አልበነበረበትም፡ናይጀሪያ ነጣቂ ቡድን ነው ፡፡ጉልበተኛና በመደምሰስ አጨዋወት ላይ ያተኮረ ሆኖ እነርሱ ጠንካራ በሆኑበት በጉልበት ጨዋታ ገባንና ተበልጠን ተሸነፍን፡፡ የተሸነፍነው ለመሸነፍ ስለገባን ነው፡፡እኛ ጥሩ በሆንበት ነገር ናይጀሪያን ብነገጥም እንጥለው ነበር፡፡አሁን ያየሁት ናይጀሪያ ደካማ ነው፡፡ ጨዋታወም አይስብም፡፡
song
…..በ1998 አለም ዋንጫ የነበረው ናይጀሪያ ከመቼውም የተሻለ ነው፡፡ ከፊት የሚመሩት እነካኑ፤ፊኒዲ፤ኦኮቻና ነበሩ፡፡ ካኑና ፊኒዲ መሮጥ አይችሉም፡፡ በረጅሙ ሲጣልላቸው አይታጉሉም ይተውታል፡፡ወደፊት ተቀባብለው ሲሄዱ ጎል እንደሚያገቡ፤ሊያገቡ እንደሚችሉና ተጋጣሚን ስጋት ውስጥ አንደሚከቱት ያስታውቃል፡፡እነርሱ መቀባበላቸው ብቻ ሳይሆን እዚያ ቡድን ውስጥ ኳስ የማይችሉትን እንደግድግዳ ተጠቅመው እያስገቡ ይጫወቱ ነበር ፡፡ይሄ ቡድን ከሁለት አመት በፊት በአትላንታ ኦሎምፒክ በብራዚል 3ለ0 ተመርቶ 4ለ3 ሲያሸንፍ በክሮስ ሳይሆን እነካኑ የኳስ ሂደቱን ስላሳመሩት ነው፡፡ ቡድኑ ወደ ፊት ሲሄድ እንደሚያገባና እንደሚያስጨንቀ ያስታውቃል፡፡ያሁኑ ቡድን ኳስ ይዞ ለማጥቃት ሲሄድ ያ ኳስ እነርሱ ላይ ተመልሶ ጫና እንደሚፈጥር ያስታውቃል፡፡

……ካሜሩን ነገሮችን ሁሉ በጉልበት ለመጠቀም ይፈልጋሉ፡፡ በጉልበት ቢበልጡም፤ ደምስሰው ኳስ ቢቀሙም ያገኙትን ኳስ በትክክል ማቀበል አቅቷቸው ለባለጋራ እየሰጡ መጨረስ ብቻ ሳይሆን ተስፋ ያለው ነገር እንኳን አልታየባቸውም፡፡ያገኙትን ኳስ በማባከን ጨረሱ፡፡ ክሮሽያ 4ለ0 ሲያሸንፋቸው ጨዋታው ይደገም ቢባል እንኳን ካሜሩን በልጦ ላመሸነፍ እንኳን የሚችልበት ነገር አልነበረም፡፡ጉልበት ላይ መመስረታቸው ነገሮችን የሚቃኙበት እውቀት አልነበራቸውም፡፡ በክርን መትቶ በቀይ የወጣውም አፈጻጸሙን ሀይል ላይ ማድረጉ ቡድኑ የተመሰረተበትን ነገር ለማሳየት ይመስላል፡፡ ካሜሩን እንዲህ እንዲጫወት ጋና ክሮስ እንዲያደርግ ናይጀሪያ የግርግር ጨዋታን እንዲመርጥ መደረጉ አፍሪካ ውስጥ በእውቀት የሚጫወት ሰው ያለመኖሩ ሳይሆን አሰልጣኞች የመረጡላቸው አጨዋወት እንደሆነ ያሳያል፡፡ካሜሩን ፍጹም ከኳስ ውጭ ሆኖ ክሮስ ብቻ ሳይሆን ርግጫን ማዕከል ያደረገ ነበር፡፡1990አለም ዋንጫ የነበረው ካሜሩን መራገጥና ኳስ መጠለዝ ብቻ ነበር ፡፡ቡድኑ መልክ የሚይዘው ሮጀር ሚላ ሲገባ ነው፡፡ ሚላ እድሜው 38 ነበር፡፡ መሮጥ አይችልም (ከሌሎቹ ጋር ሲነጻጸር)ጉልበትአይጠቀምም፡፡፡ በተለይ ከእንግሊዝ ጋር ሲፋለጡ ተቀይሮ ገብቶ ጓደኞቹን እንደግድግዳ እየተጠቀመ ኳስ እየሰጠና እየተቀበለ እንግሊዝን ምጥ ውስጥ አስገብቶ ነበር፡፡ እሱ ሲገባ ክሮስ ቀረና ሚላ ላይ ተመሰረተ፡፡እሱ ሱገባ ካሜሩን ያስፈራለል ፡፡እሱ ቤንች ላይ ሆኖ ካሜሩን ይጠልዛል፡፡ ጉልበት ለመንጠቅ እንጅ ኳስ ለመቀባበልና ተቀባብሎ ባለጋራን ለማስጨነቅ አይጠቅም፡፡በካሜሩንና በእንግሊዝ ጨዋታ ላይ ሜዳውን ሚላና ጋስኮኝ ተቆጣጥረውት ነበር፡፡በተለይ እንግሊዝ ጋስኮኝ ላይ ተንጠልጥላ ጥሩ ለመምሰል ሞክራ ነበር፡፡ እንግሊዞች ከዚህ በፊትና አሁን ድረስ ከኋላ የተገኘውን ኳስ ለአጥቂ መጣልና ክሮስ በማድረግ የሚታወቁ ቢሆንም ጋስኮኝ በግሉ ይሄን እንዲቀይሩ ምኪንያት ሆኖ ነበር፡፡ ጋስኮኝ ደፋርነቱ ብቻ ሳይሆን ኳስ መቻሉ ከተከላካዮች ጋር ሄዶ በድፍረት ይቀበላል፡፡ ፊታቸውን አዙረው ለመሄድ ለተዘጋጁት እየጠራ ይሰጣል፡፡ እንደገና ይቀበላል፡፡ እንዲህ ሲያደርግ መሀል ሜዳው ከሁለት ወደ አራትና አምስት እያሳደገ የሰው ቁጥር እየጨመረ ወደ ፊት ፎርም ሆነው ስለሚሄዱ ማጥቃቱን በብዙ ቁጥር ከማሳደጉ ሌላ ባለጋራ ኳስ እንዳያገኙ አስችሎ ነበር፡፡ በታሪኳ እንግሊዝ ኳስ ተጫወተች የሚባለው ያኔ ነበር፡፡ይህም ጋስኮኝ ፎርም ባደራጋቸው ቅኝት ውስጥ በመግባታቸው ነው፡፡ ከዚያ በኋላ እነ ቤካም መጡ፡፡ ቤካም የመሀል ሜዳውን በቁጥር ማሳደግ ቀርቶ ያገኘውን በረጀሙ ለአጥቂ ሲጥል ጋዜጠኞችም አደነቁት ፡፡ያ ኳስ ግን እየመጣ እንግሊዝን ጫና ውስጥ እንደሚከታት እንዴት እንደጠፋቸው አስገራሚ ነበር፡፡ ጋስኮኝ መሀል ሜዳው ላይ ሁለት የነበሩትን ወደ አምስት ያሳድጋል፡፡ ቤካም መሀል ሜዳ አራት የነበሩት ወደ ሁለት ያወርድና ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ እንግሊዝና በእውቀት መጫወት እስከዛሬ ተጣልተው‹‹ጊዜ ከሚባክን ኳስ ይባክን››በሚለው ስልት ቶሎ ጎል ጋር ለመድረስ ያገኙትን ከየትም እየጠለዙና ተጠልዞ በሚመለሰው ኳስ እጠየተጠቁ አሉ ፡፡

………. ሰሞኑን አልጀሪያንም አየሁት፡፡አልጀሪያ ዘጠና ደቂቃ ሲከለከል ለአንድ አጥቂ እየጣሉ የተጣለለትም ሳያገኝ እንዲሁ ባከኑ፡፡መርተውም ተመርተውም ሲከላከሉ አፍሪካ የግርግር ቡድን እንደሆኑ እያስመሰከሩ ነው፡፡ በ12ተኛው አለም ዋንጫ ጀርመንን የመሰለ ሀያል ቡድን አልጀሪያ መጫወቻ አድርጎት ነበር፡፡ የተከላከለው ጀርመን ነበር፡፡አልጀሪያ 2ለ1 እየመሩ ያጠቁ ነበር፡፡አጥቂው መስመር ሳላ አሳድ፤ላካድራ ቤሉሚና ራባህ ማጃር እየተመራ በኳስ ቅብብል ጀርመንን አርበድበደውት ነበር፡፡የዛሬው አልጀሪያ ግን እነዚያን መምስል ቀርቶ ማስታውስ አልቻለም፡፡በተለያ አሳድን የመሰለ ቴክኒካል ተጫዋች አልጀሪያ ቀርቶ ለአፍሪካ እስካሁን አላፈራችም ፡፡ያሁኑ አልጀሪያ ፈጣንና ተከታካች ነው፡፡እንዲህ ሲባል ደግሞ ቀላል ነው ተብሎ በነሀሴ አዲስ አበባ ላይ የሚደረገው ግጥሚያ….ግን ያን ግዜ እንዴት ነው መግጠም ያለብን?

በሩጫ..በርግጫ…..በጡጫ..በቁንጥጫ…በቡጥጫ….ፈጣንና ጉልበትን ጠንከር ያሉ ስለሆነ ማስቸገራቸው አይቀርም፡፡ በተለይ ብቻ ለብቻ ካገኙ አስቸጋሪ ናቸው፡፡ቤልጀም ኳስ ስለሚቀባበል ነው ያስቸገራቸው፡፡ቤሌጅየም በጉልበት ቢገባ አልጀሪያ ማሸነፍ ይችል ነበር፡፡አሁንም እኛ በጉልበት ላይ ከተመሰረትን አልጀሪያ ደስ ነው የሚለው‹‹በምፈልገወው መንገድ መጣችሁልኝ›› ብሎ ፈገግ ብሎ እንደሚቀበለን ነው፡፡የኛ ትልቁ ችግራችን የኛን ጠንካራ ነገርና የነርሱን ደካማ ነገር ሳናውቅ መግጠማችን ነው፡፡ አሁን እንደተለመደው በጉልበት ለመቋቋም መሞከራችን አይቀርም፡፡ በጉልበት አንችላቸውም ካሁኑ በኳስ ለመብለጥ መዘጋጀት ካልቻልን ያገኘውን ኳስ እየሰጠን ለመንጠቅ መሯሯጥ ነው፡፡……….
spain

ስፔይን ወይስ እንግሊዝ?

ስፔይን ትላንትና በቺሊ ተሸንፎ ከአለም ዋንጫ በጊዜ ተሰናብቶ ተመልካች ሆኗል፡፡ ዣቪ ቤንች ላይ ነበር፡፡እዚያወ ቤንች ተቀምጦ ሲመለከት‹‹ይሄ ቡድን እንግሊዝ ነው ስፔይን?›› ብሎ እንደሚጠይቅ ይገመታል፡፡ በስፔይን ማሊያ እንግሊዝ፡፡ ፈጣንና በመልሶ ማጥቃት እንዴት እንደሚጫወቱ አሳዩን፡፡ ከቲኪ ታካ ወጥተው በተቃራኒው ሲሄዱ እንዳላዋጣቸው በዚህ ሁለት ጨዋታ አይተውታል፡፡ በቲኪ ታካ ሁለት የአውሮፓ ዋንጫና የአለምን ዋንጫ አግኝተዋል፡፡አሁን ግን ቲኪ ታካን እየተገበሩ እንዳልሆነ እየታየ ነው፡፡ የቲኪ ታካ ዘመን አበቃለት እየተባለ ነው፡፡ቲኪ ታካን እየተጫወቱ ከተበለጡ ነው ዘመኑ አበቃለት የሚባለው፡፡

ስፔይን በተለይ በዚህ ሁለትጨዋታ ቲኪ ታካ ውስጥ የሉበትም፡፡ ኮስታ ላይ ነው የተመሰረቱት ‹‹ሁሉም ነገር ወደ ኮስታ›› ብለው ጎል ፍለጋ ማዕከል አድገው ነበር የገቡት፡፡ቲኪ ታካን እየተጫወቱ የአውሮፓና አለም ዋንጫ ሲወስዱ ባለጋራ እንደይተገብሩ ሲሞክር አልቻለም፡፡አሁን ግን የሚተገብሩት ከቲኪ ታካ ውጭ ባለ ነገር ነው፡፡ አሁን እነርሱ ቲኪ ታካን እየተጫወቱ ተጋጣሚ ይሄን እንዳይተገብሩ ስለከለካቸው አልነበረም፡፡እንደዚህ ቢሆን ኖሮ ተቸግረው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እነሱ ሳይከለከሉ ከዚህ ነገር ወጥተዋል፡፡አሁን ድሮ ስፔን ወደነበረችበት አጨዋወት ነው የገቡት፡፡በዚህ ደግሞ ጉልበት ስለሌላቸው(ከሌላው ጋር በንጽጽር) ተጋጣሚን መብለጥ አልቻሉም፡፡ ቶሎ ቶሎ ነው ወደ ግብ የሚሄዱት(ይሄ ደግሞ የቲኪ ታካ ባህሪ አይደለም)፡፡አካሄዳቸው ደግሞ በግል ነው፡፡ሲፈጥኑ ይበታተናሉ፡፡ ሲበታተኑ በግል ይገኛሉ፡፡ በግል ሲገኙ ደግሞ ባለጋራ ለመንጠቅ አመቺ ሆነለት፡፡በፊት አንድ ሰው ኳስ ሲይዝ ብዙ ተቀባይ አለለት። ተቀባይ እንዳለው እሱ ስለሚያውቅ ወደ ግል አይገባም፡፡ ኳሱም ከአደጋ የተጠበቀ ነው፡፡አሁን ግን አንድ ሰው ኳስ ሲይዝ ከሚረዳው ይልቅ ነጣቂው ቀድሞ ይደርሰበታ፤ ይሄን ግዜ ወደ ግል ይገባል፡፡ ኢኔስታ ብዙ ኳስ ተነጥቋል፡፡በፊት ኳስ ሲነዳ ሌሎችን ለማስለቀቅ ቢሆንም ተቀባይ አለው፡፡ አሁን ግን የሚቀበለው ስለሌለ አፍርጠው ይቀበሉታል፡፡ ስፔይን በቲኪ ታካ አጨዋወት ግብ ጋር በብዙ ንክኪ ይደርሳሉ፡አሁን አሎንሶን ሆነ ከኋላ ያለው ራሞስ ኮስታን ነው የሚፈልጉት፡፡ ምክንያቱም ግብ ቶሎ ይፈልጋሉ፡፡ግቡን በሂደት ሳይሆን ከዚያ ውጭ ባለው ነገር ነው የሚፈልጉት፡፡ለዚህም ነው ወደ ፊት ቶሎ ቶሎ የሚጥሉት፡፡ ይሄ ደግሞ ቡድኑ እንዲበታተን ምከንያት ሆኗል፡፡ሰሞኑን ባደረጉት እንቅስቃሴ አንድ አክሽን ተጀምሮ እስኪያልቅ ሶስትና አራት ሰው ቢሳተፍ ነው፡ሌላው ሲባክን ይውላል፡፡በፊት ቲኪ ታካ ሲያደርጉ አንድ አክሽን አስኪያልቅ ሃያ እና ሀያ አምሰት ሰው ይሳተፋል(አንድ ሰው ሁለትና ሶሰት ጊዜ ስለሚነካ)..አሁን ቶሎ ስለሚሄዱ ኳስ የሰጠ ባለበት ለሚቀር ኳሱ ባለጋራ ሜዳ ሲገባ የሰው ቁጥር ያንስና ይነጠቃሉ፡፡ስፔን አሁን ባለጋራውን ሊያጠቃ በሚሄድበት መንገድ እነርሱም በዚሁ መንገፈድ ስለሚገኙ ተቸገሩ፡፡(ከቺሊ ጋር ተመሳሳይ አጨዋወት ውስጥ ስለገቡ)፡፡ ስፔይን በራሱ መንገድ ሳይሆን በቺሊ አጨዋወት ስለገባ ቺሊ አልተቸገረም፡፡ስፔይን ሁለቱንም አጨዋወት አይተውታል፡፡(ቲኪ ታካውና ከዚያ በተቃኒ ያለውን) የትኛው እንደሚያዋጣ አይጠፋቸውም፡፡ ግን እንዴት እንመልሰው ነው ጥያቄው፡፡አሁን ኳስ ከኋላ ሲበላሽ እርምት ተብሎ የሚወሰደው ኳሱን ከዚያ ማራቅ ነው በፊት፡፡ ከኋላ ሲበላሽ ተጫዋቹ የተበላሸበት ረዳት በማጣቱ እንደሆነ ያውቁና ብዙ ሆነው በመምጣት በመርዳት ተያይዘው ወደ ፊት ይሄዳሉ፡፡አሁን ነገሮች በግል ለማረም ይሄዳሉ፡፡ከተጨዋች ይልቅ የነጣቂ ቁጥር እያበዙ ነው፡፡ በፊት ብዙ ሆነው ስለሚሄዱ ቦታዎችን እየዘጉ ስለሚጓዙ ቢነጠቁ እንኳን እዚያው ይነጥቃሉ፡፡ ተጋጣሚም ቢነጥቅ መውጫ አያገኝም፡፡አሁን ተበታትነው ስለሚሄዱ ቡዙ ክፍተት ስላለ በተከፈተው ቦታ ይጠቃሉ፡፡በዚህ ሁለት ጨዋታ ቡድኑ ከቲኪ ታካ ወጥቶ ታይቷል፡፡የትኛው እንደሚያዋጣ እነርሱ ያወቁታል፡፡ ጀርመን በጉልበት አጨዋወት የታወቀ ነው፡፡በጉልበት ጨዋታ በአውሮፓና በአለም ሻምፒዮነ ተደጋጋሚ ዋንጫ ወስደውበታል ፡፡ነገር ግን ዋንጫ የወሰዱበትን የጉልበት ጨዋታ ትተው ወደ ኳስ ቅብብል መጥተዋል፡፡አሁን በያዙት ጨዋታ ዋንጫ ባያገኙም አልተውትም፡፡
england world cup
ዋንጫ ባገኙበት የጉልበት ጨዋታ ማንም አያደንቃቸውም ነበር፡፡የአለም ህዝብ ጀርመንን ማንሳት የጀመረው ከደቡብ አፍሪካ የአለም ዋነጫ በኋላ ነው፡፡ይሄንን እነርሱም አውቀውታል፡፡ባለፈው አለም ዋንጫ ሻምፒዮና ባይሆኑበትም ይሄን ጨዋታ አያዋጣም ብለው አልተውትም ፡፡እነርሱ ይሄን ጨዋታ ሲተገብሩ ተጋጣሚ እንዳይጫወቱ ሊያደርግ አልቻለም፡፡በዚህ ጨዋታ ለማሸነፍ አልተቸገሩም፡፡ይሄን አጨዋወት ራሳቸው ካልተውት በስተቀር ባለጋራ ለማቆም ይቸገራል፡፡ በነገራችን ላይ ጀርመኖች በተፈጥሮ ቴክኒካል ተጫዋች ባይኖራቸውም ኳስ መቀባበል ከጉልበት አጨዋወት ይሻላል ብላው እየሞከሩም እየበለጡበትም ነው፡፡( መሀል ላይ ከኢትዮጵያ ሰፈር ውስጥ 3 የሚያህል ተጫዋች ቢወሰዱ እንደ ስፔን ጥግ ይደረሱ ነበር) ስፔይን ግን በራሱ ነው ከዚህ ነገር የወጣው፡፡የህብረት ስራ ማህበሩ ከፈረሰ ወደ ግል ይዞታ ተጠቃለለ ማለት ነው፡፡ስፔን በፊትም እነ ዣቪ ላይ ነው የተመሰረተው እንጂ አሰልጣኙ ለዚህ የሚሆን ተጫዋች መርጦ ስልጠናውን ሰጥቶ የሰራው ቡድን አይደለም፡፡ ቢሆን ኖሮ ይህንኑ እንቅስቃሴ የሚቀጥሉ ልጆች እያስገባ ከዚያ ነገር እንዳይወጡ ያደርግ ነበር፡፡ አጨዋወቱን ቢፈልገውም የሚያስገባቸው ልጆች እንቅስቃሴውን የሚያሳድጉ ሳይሆን የሚያበላሹ ናቸው፡፡ እንግሊዝ በ1990 አንድ ጋስኮኝ ለብቻው ፎርም አድርጎ ኳስ እንዲጫወቱ ያደርግ ነበር፡፡ ጋስኮኝ ሲወጣና ቤካም ሲመጣ ነገሩ ተለያየ፡፡

ነውረኛዋና ሰላይዋ ዝማም (ኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

ከኢየሩሳሌም አረአያ

10414
ዝማም ትባላለች፤ የሕወሐት ታጋይ ናት። ባለቤቷ አቶ ቢተው በላይ ይባላሉ። ቢተው እስከ1993 ዓ.ም የደቡብን ክልል በበላይነት ሲያሽከረክሩና ሲመሩ የቆዩ ናቸው። በመጋቢት 93 ከአቶ መለስ ጋር በተፈጠረ የፖለቲካ ውዝግብ ከሌሎች ጋር ተነጥለው ወጡ። ከዚያም ከደቡብ ክልል ፕ/ት አባተ ኪሾ ጋር በሙስና ተከሰው ዘብጥያ ወረዱ። ፍ/ቤት መቅረብ እንደጀመሩ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ጋር ለዜና ዘገባ ስንመላለስ የቢተውን ባለቤት ዝማምን ተዋወቅኳት። በክልል 14 ቢሮ ተመድባ ነበር የምትሰራው። ባለቤትዋ ከታሰረ በኋላ ግን ዝቅ ተደርጋ በቀበሌ ደረጃ ተመደበች። ዝማም በርካታ ምስጢሮችን ታውቃለች። አርከበ ወደ ከንቲባነት ሊመጡ እንደሆነና ሌሎች ቁልፍ መረጃዎችን አቀብላኝ በኢትኦጵ ጋዜጣ ሰርቼዋለሁ።

..ዝማምን ዛሬ እስር ቤት የሚገኘው የደህንነት ሹም ወ/ስላሴና አየር መንገድ ያለው ሃይሌ አጠመዷት። የሕወሐት ነወረኛ ደህንነቶች ጋር መጠጥ እየተጋተች አንሶላ እንደተጋፈፈች ስገልጽ ከልብ እያዘንኩና ይህን ዘገባ ለምታነበው ሴት ልጇ እየተሸማቀቅኩ ነው። ነገር ግን ይህን ነውረኛ ድርጊቷን ባልዋ አቶ ቢተው እስር ቤት ሆኖ ያውቅ ነበር። እቤቱ ውስጥ በፓርቲው አንጃዎች ይካሄድ የነበረ ስብሰባ እየተቀረጸ አቶ መለስ ዘንድ ተልኳል። ይህ ሁሉ በዝማም የተከናወነ ነበር።… ሳይታወቅ የቆየውን “ኢየሩሳሌም አ..” የብእር ስም በመጠቆምና ለነወ/ስላሴ አሳልፋ በመስጠት የግድያ ሙከራ እንዲፈጸምብኝ ያደረገችው ዝማም ናት።

ንጉሴ የተባለ መቶ/አለቃ ተገድሎ ሬሳው ጅብ እንዲበላው የተደረገው በዝማም የሴራ ተባባሪነት ነው። (ታሪኩ ረጅም ሲሆን ይህን ጠንቅቀው የሚያውቁት መጽሃፍ ጽፈው ሲያበቁ ይህን ታሪክ አለማካተታቸው ያሳዝናል) ..እንደ ዝማም ሁሉ ባለቤትዋ ከ6 አመት እስር በኋላ ሲፈታ ያሳየው መገለባበጥ አሳፋሪ ነበር። ከአቶ መለስ ተጠግቶ የአፋር ክልል ባለስልጣን ሆነ። ከዚያም ወደ መከላከያ ኢንጂነሪንግ አመራ።ጭራሽ በዚህ ዓመት በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ “አስታራቂ” ሽማግሌ ሆኖ ተሰየመ። የስብሃት ተከታይነቱንም አረጋገጠ። ባልና ሚስት እጅግ የለየለት ርካሽ ቁማር የተጫወቱ ናቸው። …ባለፈው ሳምንት አንድ ወጣት ልጃቸው በሞት መለየቱን ሰማሁ። ከነርሱ ተግባር ጋር ልጁ የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ በመሞቱ ከልብ አዝኛለሁ። ፈጣሪ ነፍስ ይማር!!

(ነውረኛዋና ሰላይዋ ዝማም ይህቺ ናት)

የአቶ ሬድዋን ሁሴን የ”Corporal Interest” ትንታኔ

$
0
0

እርሳሱ መሬ

Ersasumere@gmail.com

redwon Hussein

ሬድዋን ሁሴን

በኢህአዲግ ውስጥ ካሉት ቁንጮ ባለስልጣናት መካካል በሞጋችነታችው እና የተሳካለት የቃላት መደርደር ችሎታቸው አቶ ሬድዋን ሁሴንን የሚተካከላቸው አለ ብዬ አላምንም:: እናም በዚያን ሰሞን የአውራምባው ጋዜጣ ባለቤት አቶ ዳዊት ከበደ እኝሁን ባለስልጣን ቃለ መጠይቅ ሲያደርግላቸው የተለመደውን ባዶና ካድሬያውዊ መልሳቸውን አፈሰሱት:: ታዲያን የእኔን ቀልብ የሳበው ነገር ደጋግመው የጠቀሱት ”Corporal Interest” ብለው የደነቀሩት ቃላትና ስለ ምንነቱም የእኔ መንግስት ጭብጥ ግንዛቤ ነው ብለው ያሉት ነገር ነበር:: አዎን ቃላቱ ልክ እዚህ  እንደምታነቡት ነው ጥቅም ላይ የዋለው። ለእንደኔ ብጤው እንግሊዝኛ እንደ ቁምጣ ለሚያጥረው አንድ በቋንቋው ተክኛለሁ የሚል የዚህን ቃል ትርጉምና አጠቃቀም እስካላስረዳኝ ድረስ አባባሉ ሰውየው እንደተጠቀሙበት አይነት አጠቃቀም አንብቤም ሰምቼም ነበር ለማለት ድፍረቱ የለኝም። ትልቁ ትዝብት ያለው ዘጠና ሚሊዮን ህዝብ እየገዛ ካለ መንግስት አፈ ቀላጤ አሳፋሪ ሊባሉ የሚችሉ የአቅም ማነስና የብስለት መታጣት መንፀባረቃቸው ላይ ነው። ለነገሩ በዚያች ሀገር ማፈር ከጠፋ ሰንበትበት ብሏል።ሌላው ቢቀር ቢሯቸውና የስልጣን ቦታቸው የሰጣቸው አጋጣሚና የተመቻቸ ዕድል ከጥቅም ላይ አውለው የራሳቸውን ግላዊና ቡድናዊ የዕውቀት አድማስ ማበልፀግ አለመቻላቸው ወይም አለመፈለጋቸው ዋነኛው አሳዛኝ ነገር ነው። በጣሙን የምንሽማቀቀው ደግሞ ይህን መሰሉ ክስተት ምሁር ነን ፣ ተምረናል ከሚሉ የመንግስቱ ባለሟሎች ጎራም ስናያ ነው።

በአንድ ወቅት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የህግ ምሁሮች በአሜርካን የተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ዲሞክራሲና ተጠያቂነት እንዲኖር ሊደነግጉት ባሰቡት ሰነድ ላይ ሊተቹ ከተሰበሰቡት መካከል አንዱ ሰነዱን የ”Human Right (watch)” ያቀረበው ነው ብሎ ንግግሩን ሲጀምር ብዙዎች ስል እሱ አፈር በገባሁ ብለው እንዳሉ አስታውሳለሁ። በምሁሩ ዘንድ “HR 2003” ከአሜርካን “House of Representatives “ የወጣ ሰነድ መሆኑን አጣርቶ ሳያውቅ ነው እንግዲህ ምሁራዌ ትችት ልስጥ ብሎ የተነሳው። እንዲም ሆኖ ዝርዝሩ ላይ ፍሬ ያለው ነገር ቢናገር ደህና ነበረ። ሰነዱ ዳግም ውጫሌን ሊያመጣብን ነው ፣ ቅብርጥሴ ሲል ነው የተደመጠው። በዚህ ዙሪያ አንድ በለን ካላችሁኝ በዚያኛው ሰሞን ስለ ፕሬስ ነጻነት ሲውያዩ አንዱ የምዕራቡን አለም አውቀዋለሁ የሚል የሚመስል ተከራካሬ በሙሉ ልብ ሲደሰኩረው የነበረውን ላካፍላችሁ። እንደ ሰውየው አባባል አሜርካን ኢራቅን እንድትወር ያደረጉት ጋዜጠኞችና የሚዲያ አባላት ናቸው።ይህን ሰው ጨምሮ በርካታ የኢህአዲግ ባለስልጣኖች ለንጽጽር ይረዳቸው ዘንድ የአሜርካንን ሚዲያ በተለይም “CNN” እና “FOX NEWS”ን እንደ ምሳሌ ሳያጣቅሱ ያለፉበትን ጊዜ አላስታውስም:: እነዚህ ሁለት  ተቋማት ተቃራኒ የሚመስሉ ሃሳቦች ያናጸባርቃሉ ማለቱ ተገቢ ቢመስልም የኢህአዲጎቹ ችግር ግን የአሜርካን ሚዲያ ማለት ቆጥረው የሚጨርሱት፣ልክ በኪሳቸው እንዳለው እና እነሱ ብቻ እንደሚዘውሩት የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን አድርገው መውሰዳቸው ላይ ነው::

ስለ ቃላትና ሃሳብ አገላለጽ ግድፈት ይህን ያህል ካልን ከላይ የጠቀስናቸው አቶ ሬድዋን ሁሴን ለማሳተላለፍ ስለፈለጉት ፍሬ ነገር እናውራ። እኔ እንደገባኝ ሚንስቲሩ የሚያወሩት የነበረው የጊዜው የኢህአዲግ ነጠላ ዜማ ሆኖ ዳናኪራ የሚመታበት ጋዜጠኝም ይሁን ሌላ “በነውጥ ስርአቱን ሊያፈርስ” የሚነሳውን ቡድን ከውጪ ሃይሎች ጋር የማያያዝ ጨዋታ ነው።የሚገርመው ነገር ይህ የውጪ ሃይል የተባለው ከወደ አሜሪካን የሚመነጨው የ”Corporate Interest” ተደርጎ የመወሰዱ ፌዝ ነው:: ኢህአዲጎች በአጭሩ የሚሉት ከዩክሬኑ የቀለም አብዮት እስከ አረቡ ስፕሪግ የተደረገውን የለውጥ  እንቅስቃሴ ከኋላ ሆነው የመሩት አሜሪካን  ሃገር የሚገኙ ተቋማት ናቸው:: እንደ የአቶ ሬድዋን ሁሴን መንግስት እምነት የነዚህ ተቋማት ቀዳሚ ፍላጎት በሃገሮች ውስጥ እነሱ እንደሚሉት ዲሞክራሲ ለማምጣትና ሰባዓዊ መብቶችን ሊያከብሩ የሚችሉ ቡድኖች መንግስት እንዲሆኑ ለማስቻል  ሳይሆን የገዛ ራሳቸውን የ”Corporate Interest” ለማሳጠበቅ ብቻ ነው። ያም ሆኖ ግን ጥረታቸው ሁሉ ሳይሳካ እንደቀረና ይልቁንም አብዮት የተደረገባቸው ሃገራት ወደ ከፋ ችግር ውስጥ እንደገቡ ነው ለማሳየት የሚሞከረው። ዞሮ ዞሮ ይህ የኢትዮጵያ መንግስት አመለካከት ከምን እንደመነጨ ማንም ሰው የሚያውቀው ነው። ኢህአዲጎችም በደንብ እንድናውቀው ነው የሚሹት::ለምን ቢባል የዞን ዘጠኝ አባላትን ወንጀለኛ ለማድረግ አዋጪ መስሎ የታያቸው ይህንኑ ውሃ የማይቋጥር ክርክራቸውን በህዝቡ ጭንቅላት ውስጥ ማስገባት ስለሆነ ይመስለኛል።ህዝቡ ይቀበለዋል አይቀበለውም ሌላ ጨዋታ ነው:: ባይቀበልስ ምን ያመጣል የሚለውም እንደዚሁ::

 

 

ይህን በመሰለው ህሳቤ ነበር አቶ ሬድዋን በቀጥታም ባይሆንም “Human Right Watch” ፣ “Freedom House” እና መሰሎቻቸው የዞን ዘጥኝ አባላትን በማስልጠንና በገንዘብ እየረዱ ነው የምትል ክስ ብጤ የሰነዘሩት:: ይህን የሚያደርጉት ደግሞ የራሳቸውን ርዮት አለም ለማስፋፋት ነው ብለዋል:: የዚህ እውነታማ እስከዛሬ ድረስ እንዴት እንዳልተገለጠላቸው ከገረሙኝ ነገሮች አንዱ ነው:: መጋፈጥ የነበረባቸው ይህ ጊዜ የፈተነውንና ብዙዎች የአለማችን ሃገሮች እሰየው ብለው የተቀበሉት ርዮት አለም ለኢትዮጵያ ይጠቅማል ወይም አይጠቅምም የሚለውን ክርክር ነበረ:: አይጠቅምም ብለው የሚሉበት አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ስለማይችሉ ይህቺን መሰሏን ክርክር ደፍረው አይነኳትም:: እረስተውት እንደሆነ ነው እንጂ የራሳችው ፓርቲ የአልባንያና የሌላም ሶሻሊዝም ዝባዝንኬ እርግፍ አርጎ ትቶ ነበር እኮ የምዕራቡን  ርዮት አለም ተቀበልኩ ያለው:: እንዲያው ለመሆኑ ይህ ከውጪ ሊጫንብን ነው ከሚሉት ርዮት አለም የትኛው ይሆን ለሃገራችን የማይጠቅመው ወይም የሚጎዳው:: ዲሞክራሲ አስፍኑ ፣ የሰውን ልጅ እንደሰው በእኩልነት ተመልከቱት ብሎ ማለት ምኑ ላይ ይሆን የሚያስፈራው? ርዮት አለሙ ሲሰራጭ አብሮት ስርጭቱን የሚያቀላጥፍ  ብዙ ገንዘብ ይሰጣል።ህይወት አትራፊው ስንዴማ ያለ ርዮት አለሙም ይመጣል:: አቶ ሬድዋን ዳር ዳሩን እያሉ የፎክሩትማ እንዳው በታሪካችን የውጪ ሃገሮች በሚሉን ስለማንሄድ አሁንም የባህር ማዶ ሰዎች አድርጉ ለሚሉል ነገር ደንታ የለንም የሚሉ ይመስላሉ:: እኔ እስከማውቀው ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት ላለፉት ጥቂት አመታት ብዙ ቢሊዮን ዶላር እርዳታ የጎረፈለት ምዕራባውያኑ ለእነሱ የሚበጃቸውን ተግባሮች አድርግ ሲሉት እሺ ጌቶች ብሎ ተግባሮቹን ስለፈጸመ ብቻ ነበር::

አቶ ሬድዋን እዲህና እንዲያ እያሉ ነበር ቃለ መጠይቃቸውን ገፍተው አንድ እሳቸውንም ሆነ የሚውክሉትን መንግስት በእጅጉ የሚያሳንስ አስተያየት የሰነዘሩት:: ሚንስትሩ “Human Rights Watch” እና  “Freedom House” ከመሰሎቻቸው ጋር በመሆን በመንግስታቸው ላይ ሊሰሩት የተዘጋጁትን ክፉ ነገር እናውቃለን በሚል እንድምታ በድርጅትቹ ውስጥ ያሉት እያንዳዳቸው ግለሰቦች ማን ማን እንደሆኑና ከዚህ ቀደም ምን እና የት ይሰሩ እንደነበረ ጭምር መንግስታቸው ጠንቅቆ እንደሚውቅ ከእኛ ወዲያ ላሳር በሚል መተማመን ተናገሩ:: ለምን እንደሆነ ባላውቅም  ይህን ስሰማ በአእምሮዬ ድቅን ያለብኝ ያ የቦሌው ፖሊስ የቪኦኤን ጋዜጠኛ ያለህበት መጥቼም ቢሆን አስርሃለሁ ያለው ነገር ነበረ:: ምናልባትም አቶ ሬድዋንም ፣ ያም ፓሊስም የሚናገሩትን የማያውቁና  የማመዛዘንና ጉድለት ያለበት አእምሮ ተሸካሚዎች ስለሆኑ ይሆናል:: ለነገሩ ኢህአዲግ ያፈራቸው ደናቁርት ባለስልጣኑ የተናገሩትን ከጠቢብና ምሁር እንደወጣ አድርገው ሊወስዱት እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም:: ነገር ግን እንደው አገሪቷ ውስጥ ሰው ከተገኘ ስለተቋማቶቹ ማንነትና ስለሰዎቻቸው በቀላሉ እየድህረ ገጾቻቸው ሄዶ ማወቅ ይችላል:: የእናቶ ሬድዋንን ለእኛ ብቻ ነው የተገለጥን የሚባለውን ዲስኩር ሳይሰማ ማለት ነው:: እኔም ያደረኩት ይኸው ነበረ:: በሁቱም  ተቋሞች ድህረ ገጾች ላይ ድርጅቶቹ መቼና እንዴት እንደተመሰረቱ መርሆቻቸዎ ምን እንደሆኑ ምን እንደስሩና ማን ገንዘብ እንደሚለግሳቸው በግልጽ ተቀምጧል:: የቦርድ አባላቶቻቸውና መሪዋቻቸው ማን እንደሆኑ የት ይሰሩ እንደነበረ በይፋ ይታያል:: ሰዎቻቸው በመንግስትም ይሁን በግሉ ዘርፍ በጣም ውጤታማ ስራ ሰርተው የተደላደለ ኑሮ እንዳላቸው ይገመታል:: አዋን አሚሪካኖች ከግል ምቾታቸው ባላነሰ ለሰው ልጅ ደህንነት ሲባል የሚችሉትን ሲረዱ የህሌና እረፍት ያገኛሉ:: ለዚያም ነው እነዚህ ተቋማት እንደ ኢትዮጵያ ባሉት ሃገሮች የሰው ልጅ መብት ይከበር ዲሞክራሲም ይበጃችኋል እያሉ ሃባታቸውን የሚያፈሱት::የመርህ ሰዋችና ፈሪሃ እግዛብሔብር ያደረባቸው ስለሆኑና በስራቸውም የህሌና ደስታን ስለሚያገኙ ብቻ:: የለም ለእነ ሬድዋን ይህ አይደለም ምክንያቱ:: ሌላ “Corporate Interest” የሚሉት ድብቅ አላማ አለ:: አቶ ሬድዋን ይህ ድብቅ አላማ ምን ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል:: እንድ እሳቸው ከሆነ እነዚህ ድርጅቶች ጠንክረው የሚንቀሳቀሱት በማዕድን ሃብት በተንበሸበሹ ሀገሮች ላይ ነው:: መዕልክቱ ልክ እንደ ድሮው ዘመን የደሃ አገሮችን ሃብት ሊዘርፉ ነው የሚል ይመስላል:: ጉድ በሉ አንባብዮች:: አቶ ሬድዋን አክለውም ተቋማቱ የኢትዮጵያን የመንግስት ባንኮችንና ቴሌን ወደ ግል ይዞታ ቀይሩ ብለው የሚወተውቱት እራሳቸው ሊግዙት ስለ አሰቡት ነው ብለው ያምናሉ። እንደዛማ ካልሆነ ሪፎርም አድርጉ እያሉ መጨቅጨቅ፣የዞን ዘጠኝ አባላትን ማሰልጠንን ምን አመጣው ብለው ይጠይቃሉ::

የተፈጥሮ ሀብት ፍለጋ አሜርካኖች አለምን ሲያስሱ የነበረበትን ዘመን አላስታውስም:: ያ ዘመን አለ ቢባልም እንኳን አፍሪካ ላይ እምብዛም ነው ባይ ነኝ:: እንዲው ለነግሩ በጣም የሚፈልጉትን ነዳጅ እንኳን በሱዳን ላይ እያዩት አልፈውት የለም:: እዚህ ላይ ግን መታወቅ ያለበት የአሜርካን ኩባንያዏች የአለም ሃገራት በሙሉ ወደ ሃገራቸው መጥተው መዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ሲለምኗቸው ነው የሚታየው:: እስኪ የአቶ ሬድዋንና የመንግስታቸውን የአስተሳሰብ ችሎታ መዝኑልኝ:: እስከ ትሪሊየን ዶላር በ”Asset” የሚያንቀሳቅስ አንድ የመሜሪካን ባንክ ይህችን ከትንሽ ምንዛሪ በላያ የማታወጣን የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ ለመግዛት ሲል በእነዛ ተቋሞችና ዘጠኝ ብሎግሮች በኩል መንግስት እንዲወድቅ ሲያግዝ ይታያችሁ:: ወይም በመቶ ሚቆጠሩ ሃገራት እየሰራ ያለ የሜሪካን የስልክ ኩባንያ የኢትዮጵያውን ቴሌ ለመግዛት ሲል ስርአቱና የስርዓቱ ፓሊሲዏች ይቀየሩ ብሎ ሲለፋ አስቡት:: የሚግርመው ነገር እንዲህ የውጪን “Corporate Interest” ፈራነው የሚሉት እነሬድዋንና መንግስታቸው ከነጻ ቀጥሎ ባለ ዋጋ የሃገሪቱን ለም መሬት ገበሬና ሰራተኛ ሳይቀር ይዘው ለመጡት ህንዶችን ቻያናዋች መቸብቸባቸው ነው:: እግዛብሔር ብሎትማ አሜሪካኖቹ ወደ ሀገራችን መዋለ ንዋይ ሊያፈሱ ቢመጡ ሌላው ቢቀር ፍታሃዊ ክፍያ፣ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በርካታ ስራና የመንግስት ገቢ ያመጡ ነበር::

በመጨረሻም የዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነውን ካለ መጠይቅ ያደረገው የአውራምባ ታይምሱ አቶ ዳዊት ከበደ ይህቺንም መጣጥፍ በድህረ ገጹ ላይ በመለጠፍ ሚዛናዊነቱን እንድናወድስ ቢያደርግ ደስ ይለኛል::

 

 

“ስለ … ። ሲባል ምርጫ ይቅር” …። ትግልም ይቁም ወይ?

$
0
0

የትግራይን መስቀል ስለመሸከም (ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

Download (PDF, 465KB)

ተመስገን ደሳለኝ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ዕለቱ የሁለት ሺ ሶስት ዓመተ ምህረት የመስቀል በዓል የተከበረበት ማግስት፤ ሰሜናዊቷ የኤርትራ አዋሳኝ  ወልቃይት ገና ከእንቅልፏ ሙሉ ለሙሉ ባለመንቃቷ፣ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ጎፈሪያቸው  የተንጨ(ባረረ ፋኖዎች በውስጧ ካሉ ተቋማት ወደ አንዱ እያመሩ ስለመሆኑ የጠረጠረች አትመስልም፤  ከኤርትራ የተነሱት ፋኖዎች መዳረሻ በወረዳዋ ታዋቂ የሆነው አወርቅ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት  በመሆኑ፤ ማንም ልብ ሳይላቸው ልክ እዚያው እንደደረሱ፣ ከፊሎቹ በሰለጠነ ወታደራዊ ስልት ትምህርት  ቤቱን ከአጥር ውጪ በመክበብ ድንገተኛ ጥቃት የሚሰነዝር ኃይል ከመጣ ለመከላከል ሲያደፍጡ፤ የተቀሩት  ደግሞ ወደ ውስጥ በመግባት በግቢው የሚገኙ መምህራን ሜዳው ላይ እንዲሰበሰቡ ቀጭን ትዕዛዝ  አስተላለፉ፤ በጥቂት ደቂቃዎችም ውስጥ ሁሉም በተባለበት ቦታ ተሰበሰበ፤ እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በዕቅዱ  መሰረት መፈፀሙን በጥንቃቄ ሲከታተል የነበረው የቡድኑ መሪ በቅድሚያ ስለራሱና ጓደኞቹ ማንነት እና  ስለወከሉት ድርጅት አጭር ማብራሪያ ከሰጠ በኋላ፣ የትግሉን ዓላማ በስፋት አብራርቶ አስረዳ፤ ሌሎች ጓዶቹም የፖለቲካ -—[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—-

“ሁለቱ ታላላቅ ዕቅዶች” ክፍል 2 (ዮፍታሔ)

$
0
0

ዮፍታሔ

ሦስቱ ክልሎች
ትግራይ

- ዕቅዱ ከኢትዮጵያ ተለይቶ አገር መመሥረት ቢሆንም ሕወኀት ከሌሎች የተማረው ትልቅ  ተመክሮ አለው። አንድ ጠንካራ አገር የሚያስፈልጉትን ቁሳዊ መስፈርቶች አስቀድሞ ሳያዘጋጅና  ሳያሟላ ይህን ለማድረግ መሞከር ለዚያውም ይህ ሁሉ “ጠላት” ዙሪያውን ባለበት ሁኔታ ራስን  በራስ የማጥፋትን ያክል (suicide) ትልቅ ስህተት ይሆንበታል። ከመጀመሪያውም ዕቅዱ  አይሳካም። ቢሳካም አይዘልቅም። ከዚህም በላይ አዲስ የምትመሠረተው አገር በሕወኀት ቁልፍ  ባለሥልጣናት አስተሳሰብ በኢትዮጵያዊነቱ ኩሩ በሆነው በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ወደጎን  እንዳትተውና በሱዳን ሕዝብና መንግሥት ዓይን ሚዛን የምታነሣና ሱዳን የሌላትን እንዲኖራት  በማድረግ ለሱዳን የምታጓጓ አገር ማድረግም ይጠይቃል።  –[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—

 

Comment

ይናገረው ዘመን –ይዳኘው መንገዱን! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

ከሥርጉተ ሥላሴ 20.06.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

…. ለቀጣዩ ቀናት

…. ውል ብሏል ለ

…. ሽውታ ለናፍቆት

              ሕትምት!

አደራውን ልኳል

ወገኑን – ተማምኗል

አርበኝነት ሆኗል፤

           ተጥዷል!

የብዕር አባቱ

80 ነው ባቱ

ብራና እትብቱ

ትህትና ነው ቤቱ

          በኽረነቱ!

የቁምነገር ሃብቱ

ፍልስፍናው በርቱ!

ጽናቱ – ስበቱ

ትዕግስቱ – ውበቱ

ማሰብ ነው ዕለቱ

ቀን – ተሌት፣ –  ህብስቱ፤

ተስፋ  – ማ –  ሟተቱ

ያሥራቱ!

ይናገረው – ዘመን

ይዳኘው – መንገዱን፤

ይሄው ነው ዕውነቱ፤

ድርጊት ባለቤቱ

          ችሎቱ!

የግንባር ሥጋ ነው

ለሃቅ ያደረ ነው።

መሠረተ – ህብር

የሥጦታው – ደንበር

የመከራ ገበር።

ጥማቱ …

ፍጥረቱ —

ፈቅዶ – ህማማቱ

ፍቅረ – መለኮቱ

ህይወቱን – ለናቱ

ውስጡን – ለልዕልቱ

           መክሊቱ!

አልፋ ነው መለከት

ኦሜጋማ – ስብከት

             አብነት!

ተግባሩ ነው ልፍል

ፏፋቴ ለፈል

ተናግሮታል ወለል

ዓለም መስክሮታል፤

መንፈስ – መዝኖታል

ምርጥ ሰው ብሎታል።

ሰማይም ሰጥቶታል

ቀድሞ ቀብቶታል፤

ሁሉን ሽልሞታል

ቅብዕ —– ሰክኖለታል!

                                                  ለአባ ትርጉም ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የእንኳን ደስአለህ ሥጦታ፤ 19.06.2014 ዙሪክ ሙዚዬም – ፓርክ።


የ2007 የመንግሰት በጀት ሚስጥር

$
0
0

(ግርማ ሰይፉ)

(ግርማ ሰይፉ)

ከግርማ ሰይፉ ማርይ
(የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል)

የኢትዮጵያ በጀት በደንብ አድርጎ ለመረመረው ሀገሪቱ ያለችበትን ፖለቲካ ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም ማለት በበጀቱ ውስጥ የቻይና፣ ምዕራባዊያን ሀገሮች እንዲሁም የምዕራብ ሀገሮች ይዞታ የሚባሉት አለም አቀፍ ባንኮች እጅ በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ እንደምታውቁት መንግሰት ለ2007 ዓመተ ምህረት ያቀረበው በጀት ብር 178.6 ቢሊዮን ነው፡፡ ዘጠኝ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ማለት ነው፡፡ መደበኛው ወጪ እና የክልሎች ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ የሚሸፈን ሲሆን ዋና ዋና የካፒታል በጀት ደግሞ ከመደበኛ ወጪ እና ክልሎች ድጋፍ ከሚተርፈው አነሰተኛ የሀገር ውስጥ ገቢ እና ለበጀት ጉድለት ለመሸፈን ከታሰበው ከሀገር ውስጥ ባንኮች ብድር ይሸፈናል ተብሎ የሚጠበቅ ነው፡፡ ከአጠቃላይ በጀቱ 19.2 በመቶ ከእርዳታና ብድር ይሸፈናል በዝርዝር ሲታይ ግን የመደበኛ በጀቱ 21.8 ከመቶ፣ የካፒታል በጀቱ ደግሞ 36.5 ከመቶ የሚሸፈነው ከብድርና እርዳታ ነው፡፡
ስንት ሰው እንደሚያስታውስ ባላውቅም የቀድሞ አዲስ ጉዳይ ጋዜጣ (ሁሌም ጋዜጣ ሳስብ የሚናፍቀኝ) በአንድ ወቅት የቀረበን በጀት ይህ በጀት ኢትዮጵያዊ በጀት ነው ወይ? የሚል ጥያቄ አንሰቶ ነበር፡፡ የበጀትን ዜግነት የጠየቀበት ገፊ ምክንያት በዚያን ሰሞን መወያያ፤ በአሁኑ ጊዜ ጠርናፊ ህግ የሆነውን የሲቪል ማህበራት ህግ ነበር፡፡ ይህ አፋኝ ህግ ማነኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሰቪል ማህበር በጀቱ ከአስር በመቶ በላይ ከውጭ ከሆነ ኢትዮጵያዊ አይደለም ነው የሚለው፡፡ አሁን በሀገራችን የሚንቀሳቀሱት ብዙዎች መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተመዘገቡት በኢትዮጵያዊነት ሳይሆን “ረዚደንት” በሚል ቅፅል ነው፡፡ አዲስ ጉዳይ ጋዜጣ ይህን በጠየቀበት ወቅት የሀገሪቱ በጀት ከ40 በመቶ በላይ ከውጭ እርዳታ ሰለነበር ይህ መንግሰት ይህን ያህል ከውጭ የሚያገኝ ከሆነ ኢትዮጵያዊ አይደለም የሚል መከራከሪያ ይዞ ወጥቶ ነበር፡፡ ይህን ሰፋ አድርገው በመተርጎም አንድ አንድ ሰዎች የገቢ ምንጭ ዜግነት የሚወስን ከሆነ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ከውጭ ከሚኖሩ ዘመዶቻቸው በሚላክላቸው ገንዘብ የሚተዳደሩ ስለሆነ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ መሆን የለበትም ብለው ነበር፡፡ ስላቅ መሆኑ ነው፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ የሚልኩላቸው ዘመዶቻቸው ዜግነት ያልቀየሩ በመኖሪያ ፍቃድ (ረዚደንት) የሚኖሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ethiopia-parliament
የሰዎችን ወይም የድርጅቶችን ዜግነት ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ ለማድረግ የገቢ ምንጭ መስፈርት መሆን የለበትም የሚለውን መከራከሪያ መንግሰት በዋዛ ያለፈው እንዳይመስላችሁ፡፡ መፍትሔ ብሎ የያዘው በተቻለ መጠን መንግሰት በጀቱን በመከፋፈል እና የተወሰኑት ወደ ጎን በማድረግ የብድርና የእርዳታ ገንዘቡ እንዳይታይ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም ነው መንግሰት ከፍተኛ መዋለ ንዋይ ከሚፈስባቸው የመሰረተ ልማቶች ውስጥ ዋና ዋና የሆኑትን ለምሳሌ እነ ቴሌ፣ መብራት ሀይል፣ ባቡር፣ የመሳሰሉት በሪፖርት ውሰጥ በስፋት እንደሰኬት ተካተው በበጀት ውስጥ ግን አይታዩም፡፡ ሉሎች ፋብሪካዎች ለምሳሌ ስኳር ፋብሪካ፣ ማዳበሪያ ፋብሪካ የመሳሰሉት ትልልቅ የመንግሰት ፕሮጀክቶቸ በበጀት ውስጥ የሉም፡፡ እነዚህ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ የፈሰሰላቸው የመንግሰት ኢንቨስትመንቶች ከበጀት ውሰጥ እንዲወጡ የተደረጉት ደግሞ ብዙዎች በብድር የሚሰሩ ናቸው፡፡ የእነዚህ ፕሮጀክቶች የብድር ሂሣብ በበጀት ውስጥ ቢደመር የመንግሰትን በጀት ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ላይሆን ነው ማለት ነው፡፡ ለነገሩ በሲቪል ማህበራት ትርጉም እነዚህ ሁሉ ተቀንሰው አሁን የቀረበው የመነግሰት በጀት ኢትዮጵያዊ በሚያደርገው ደረጃ ላይ አይለም፡፡ ምክንያቱም ከአጠቃላይ በጀቱ 19.2 በመቶ ከውጭ ብድርና እርዳታ የሚገኝ ስለሆነ ማለት ነው፡፡

መንግስት በበጀት ውስጥ ያካተታቸው በእርዳታና ብድር የተገኙ አብዘኞቹ የካፒታል ወጪዎች ለኤኮኖሚ ሴክተር መንገድ፣ ግብርና እና ውሃ ሲሆን፤ እርዳታው ደግሞ ለጤናው ሴክተር የተመደበ ነው፡፡ የእነዚህ ገንዘቦች ዋናኛ ምንጮች ደግሞ የኒዎ ሊብራል አራማጆች የሚባሉት መንግሰታት እና የእነዚሁ መንግሰታት ይዞታ ናቸው የሚባሉት ባንኮች የሰጧቸው ብድሮች ናቸው፡፡ እነዚህ መንግሰታት እና በቁጥጥራቸው ስር ያሉት የፋይናንስ ተቋማት ኢትዮጵያዊያን ጤናቸው እንዲጠበቅ የተሻለ መንገድ እንዲኖረን፣ ምርታማ ግብርና እንዲሁም ንፁህ ውሃ እንዲኖረን ዕርዳታና ብድር እየሰጡን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ብጥብጥ እንዲነሳ የቀለም አብዮት ይደግፋሉ ብሎ ስጋት ውስጥ መውደቅ አይቃረንም ወይ? ይህ በእውነት የአብዮታዊ ዲሚክራሲ ወይም የልማታዊ መንግሰት ቅዠት ይመስለኛል፡፡
በጣም የሚያስገርመው ደግሞ በዋነኝነት ከፍተኛ እርዳታ የሚሰጡን መንግሰታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በኩል አድርገው በቀለም አብዮት ሊያጠፉን ነው የሚባሉት የኒዎ ሊብራል አራማጅ ተብለው የተፈረጁት ሀገሮች መንግሰታት ናቸው፡፡ ከነዚህ ውሰጥ ቻይና እንደ መንግስት የምትሰጠን እርዳታ በሀገር ውስጥ ከውጭ ሀገር ዜጎች ምዝገባና የስራ ፈቃደ ከምናገኛው ያንሳል፡፡ ከሌሎቹ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ ከአንድ መቶኛ ያነሰ ነው፡፡ ቻይና ሀገራችን በበጀት ውስጥ ከተካተተው ብድር ከ59 በመቶ በላይ ሰጥታናለች፡፡ ይህ ቻይና የሰጠችን ብድር ብዙ ስለሆነ ሳይሆን መንግሰታት ለኢትዮጵያ የሰጡት ብድር እጅግ ዝቅተኛ ከመሆኑ የመጣ ከፍተኛ የመቶኛ ድርሻ ነው፡፡ ቻይና በጀት ውስጥ ባልገባው ብድር ከፍተኛ አበዳሪያችን ነች፡፡ የቻይና ብድር በዋነኝነት በበጀት ውስጥ ባለተካተቱት ከፍተኛ የመንግሰት የመሰረተ ልማቶች እና የኤኮኖሚ ሴክተሮች ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ ከበጀት እንዲወጣ የተደረገውን የቴሌን ማስፋፊያ ብቻ ብንወሰድ ወደ 32 ቢሊዮን ብር ወይም 1.6 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር በ2007 በጀት ተብሎ የተያዘውን 18 ከመቶ ይሆናል፡፡ ይህ ገንዘብ በጀት ውስጥ ቢታይ እና የመንግሰትን የዜግነት መስፈርት ብንጠቀም መንግሰት ኢትዮጵያዊ ነው ለማለት ይቻላል ወይ? በጀት የመንግሰትን አቅም የሚያሳይ መለኪያ ነው በሚለው ልማዳዊ መለኪያ ለመጠቀም ለሚፈልግ ለቀጣይ ዓመት የቀረበው በጀት ትክክለኛውን የመንግስት ጡንቻ የሚያሳይ ነው ብለን ለመውሰድ እንቸገራለን፡፡

የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒሰትሩ አቶ ሶፊያ አህመድ በዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ በግንባር ቀደምነት የሚያነሱት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዕዝ ኢኮኖሚ በሚባለው በደርግም ጊዜ ቢሆን ሪፖርቱን በይፋ ያቀርባል አቶ ሶፊያ ግን ይህን እንዲያደርግ ያለበትን ዓለማ አቀፋዊ ጫና የምንረዳ አይመስላቸውም፡፡ ያለበለዚያ ቦይንግ መግዣ ገንዘብ ሊገኝ እንደማይችል ግልፅ ነው፡፡ አሁን እኛ የግልፅነት ችግር አለባቸው እያልን ያለነው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪን የሚባለው አስማተኛ ድርጅት የሚሰራው ሰራ የሚያገኘው ገቢና ወጪው በግልፅ አይታወቅም ነው፡፡ እጅግ ብዙ ሀብት ፈሶበትም የሚያመጣው ትርፍ ተመጣጣኝ አይደለም እያልን ነው፡፡ በቅርቡ ከመንግሰት ድርጅቶች ይገዛው የነበረውን የወዳደቁ ብረቶች ግዢ እንዲያቆም መታዘዙ ይታወቃል፡፡ ለምን? የፀረ ሙስና እና ሰነምግባር ኮሚሸን እነዚህ ተቋማት ለምዝበራ የተጋለጡ እንደሆነ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ለነገሩ ይህ ድርጅት ተጠሪነቱም ለመንግሰት የልማት ድርጅት አይደለም፡፡ ሌሎቹም ኮርፖሬሽኖች ለምሳሌ የሰኳር ኮርፖሬሽን ስር ነው የሚባለው ተንዳሆ የሰኳር ፕሮጀክት ያለበትን ጉድ የማያውቅ ያለ አይመስለኝም፡፡

በጀት ውስጥ የገባውን የመከላከያ በጀት ስንመለከት ደግሞ በየሳምንቱ እሁድ በሚያቀርበው የቴሌቪዥን ፕሮግራ በነፃ ገበያ ሰርዓት እየተወዳደረ መነገዱን ቢነግረንም፡፡ በግልፅና በሰውር የሚሰራቸው የገቢ ማስገኛ ገንዘቦች እንዳሉት እየታወቀ ከውስጥ ገቢ የሚባል አንድም የገቢ ርዕስ በጀቱ ላይ አይታይም፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ የመከላከያ በጀት ይህ ብቻ ነው ብሎ ለመውሰድ አይቻልም፡፡ የመንግሰት ጡንቻ በመከላከያ በኩል ከዚህ እንደሚበልጥ ለማወቅ ደግሞ ልዩ እውቀት አይጠይቅም፡፡ ለዚህ ነው የመንግሰትን ትክክለኛ ቁመና የሚያሳይ በጀት አይደለም የምንለው፡፡

እነዚህ እርዳታ እየሰጡን ብድር የማይሰጡን መንግሰታት ምክንያታቸው ምንድነው? ብሎ መጠየቅም ተገቢ ይመሰለኛል፡፡ በኒዮ ሊብራል አሰተሳሰብ ተፈርጀው ሀገራችን ላይ የቀለም አብዮት ሊያመጡ ያሴራሉ የሚባሉት ሀገራት በዋና ዋና የንግድ እና ኢንቨስትምነት ውስጥ እጃቸውን ለማስገባት ወደኋላ ያሉት ለምንድነው? በተቃራኒው ደግሞ ቻይና በእነዚህ ወሳኝ የኤኮኖሚና የንግድ ኢንቨስትመንት ውስጥ እጇን በሰፊው የምትዘረጋው ለምንድነው? ብሎ መጠየቅ እና መልስ መሻት ግድ ይላል፡፡

በእኔ እምነት የምዕራባዊያን መንግሰታት በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የኢኮኖሚ መስኮች ውስጥ ለመሳተፍ ውሳኔ የሚሰጡት መንግሰታት ሳይሆኑ በየሀገሮቻቸው ያሉት የግል ባለሀብቶች ናቸው፡፡ የመንግሰታት ድርሻ ለባለሀብቶች ትክክለኛ መረጃ እንዲደርሳቸው ማድረግ እና ተገቢውን ከለላ መስጠት ነው፡፡ የግል ባለሀብቶች ደግሞ መረጃ የሚያገኙት ከኢቲቪ አይደለም፡፡ በተለያየ መልኩ በሀገራችን ያለውን ሁኔታ አብጠርጥረው ያውቁታል፡፡ እንደ ምሳሌ በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተው ዓይነት ብሔርን መሰረት ያደረገ ብጥብጥ ከፍተኛ ትርጉም አለው፡፡ አንድ አንዶች እንደሚያስቡት በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች የተቀናጀ ማሰትር ፕላን ዝግጅት ነው ብለው አይወስዱትም፡፡ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችና የሰጋት ደረጃ የሚተነትኑ ድርጅቶች የሚያወጧቸው ሪፖርቶች ትርጉማቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ በሀገሪቱ ውሰጥ ያለው የዲሞክራሲያዊ ሰርዓት በተለይም በየምርጫ ወቀት የሚፈጠሩ ሰጋቶች፤ መንግሰት የሚያወጣቸው አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ተገማችነት፤ በአጠቃላይ ለኢንቨስትመንት ያለው ምቹ ሁኔታ ወሳኝ ግብዓቶች ናቸው፡፡ ዝም ብሎ በኢቲቪ የሚለፈፍ የገፅታ ግንባታ ፕሮፓጋንዳ ተጠቅመው የኢንቨስትምነት ውሳኔ አይሰጡም፡፡
በተቃራኒው የቻይና መንግሰት በከፍተኛ ደረጃ አፍሪካን ለመቆጣጠር ባለው ፍላጎት መነሻ እንዲሁም ውሳኔ የሚሰጡት የግል ባለሀብቶች ሳይሆን የቻይና መንግሰት በመሆኑ ውሳኔዎች በአብዛኛው ኤኮኖሚያዊ አዋጭነት ብቻ ሳይሆኑ የፖለቲካ ጭምር ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቻይና በዓለም ላይ ከፍተኛ ብድር ሰጪ ሀገር ነች፡፡ ለአማሪካ ጭምር፡፡ በቻይና የግል ሴክተሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢንቨስት ለማድረግ ገና አልደረሱም፡፡ ቻይና እንደ ሀገር ያላትን ከፍተኛ ቁጠባ በዓለም ላይ ኢንቨስት ለማድረግ እየተጠቀመችበት ነው፡፡ ቻይና በሙሉ በሚባል ደረጃ የምትሰጠንን ብድር የሚጠቀሙበት የቻይና ኩባንያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ያለውን ስጋት በሚያካክስ ደረጃ ትርፋቸውን በአጭር ጊዜ ለማግኘት ይገባሉ በአሁኑ ሰዓት ቴሌን የወሰዱት ሁለት የቻይና የመንግስ ኩባንያዎች ናቸው፡፡ በተለያየ ስም የሚሰሩ፡፡ ቻይና የምታስገርመው እነዚህ የመንግሰት ኩባንያዎች ጉቦ የመሰጠት ጭምር አቅም አላቸው፡፡
እንደ ማጠቃለያ ለኢትዮጵያ የተበጀተው በጀት ብር 178.6 ቢሊዮን በጀት እንደ ሀገር ሲታይ አጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ ኢትዮጵያ 90 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት ከመሆኗ አንፃር እና በቅርቡ ደግሞ ዓመታዊ የነብስ ወከፍ ገቢያችን ብር 11 ሺ (550 የአሜሪካ ዶላር) ደርሶዋል ከተባልን ይህ በጀት ከእያንዳንዱ ሰው በወር የገቢውን 1.5 ከመቶ መዋጮ ሊሸፍነው የሚችለው ነው፡፡
ቸር ይግጠመን

የሎሬት ህመሙ ቢያመኝ!

$
0
0

የሎሬት ህመሙ ቢያመኝ …
———–//———
ይሞላ ብዪ ስኳትን ፣
ህልሜ እልም እያለ ቢፈትነኝ
ለህሊናየ አድር ብዪ ስማስን ፣
ድካሙ ቢሸበርክኝ
ተስፋ አልቆርጥም ባልኩ በተጋሁ፣
ህመሙ ቢደቁሰኝ
ብላቴን ጌታ ታወሰኝ ፣
ጸጋየ ህመሙ ዘልቆ ወጋኝ
የጸጋየ ህመሙን ታመምኩ
መላ ቅጡን አስጠፋኝ ።
ውስጤ ቢደማ ቢታወክ ፣
የጸጋየ ሮሮ በአይነ ህሊናየ መጣብኝ
የመጨረሻው እስትንፋስ ቃሉ ፣
ሎሬት ህመሙ አመመኝ
“እኔ ለእኔ ኑሬ አላውቅም ” ብሎ ያለን
የስንብት ጸጸት ቃሉን አዘከረኝ ፣
……. …….. ……. ……… …….. ……
የጸጋየ ጸጸት …
“የማይሰማ ወጨት ጥጄ –
እፍ ስል የከሰመ ፍም፣
ውርዴም ይፈወሳል ብዬ -
የሰው እከክ ስዘመዝም፣
በሰው ቁስል መቁሰል በቀር –
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም፡፡
የማይነጋ ህልም ሳልም –
የዘመን ደዌ ሳስታምም፣
የማያድግ ችግኝ ሳርም –
የማይድን በሽታ ሳክም፣
የሰው ህይወት ስከረክም –
እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም፡፡ ”
…… …….. ……. …….. …… ….. ……
ባይሰማ ባያየኝ አባት አለም ፣
ተስፋው በኖ የተለየንን
የቅኔው አባት መምህሩን ፣
10311727_10204297604786213_1298964279299971454_n
የጥበብ ሎሬት ፈላስፋውን
ድካም ልፋቱ መና ቀርቶ የታየውን ፣
“ግዴለም በተስፋ እንኑር አልኩት !” ጸጋየን
መላው ጠፍቶ ቢጨንቀኝ ፣
በተስፋ እኖር መስሎኝ ሳታልላት ደካማ ነፍሴን …
* ብላቴን ጌታ ጸጋየ ፣ ነፍስህን አራያ ገነት ያኑራት: (
በተጎዳ ስሜት … ይህችን ታክል ካልኩ ይብቃኝ! :(
ነቢዩ ሲራክ

ግልጽ ደብዳቤ!

$
0
0

ለሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች!
ለጋዜጠኛ መብት ተከራካሪዎች!
ህሊና ላላቸው ወገኖች በሙሉ!
የዓለም ስደተኞች ቀን ጁን 20 በመላ ዓለም ይከበራል። በየዓመቱ አስደሳች መፈክሮች ይጻፋሉ።ይለጠፋሉ።ስብስባዎች
ይካሄዳሉ።ታላልቅ ሰዎች መልዕክት ያስተላልፋሉ።ስደት በዓለም ላይ እንደኑሮ ውድነት እየጨመረ ነው።ችግሩ የአፍሪቃ
መሆኑ ቀርቶ አውሮፓና ኤዢያንም እያዳረሰ ነው።እኔ እንኳን ከተሰደድኩባት Dec 9,2005 ወዲህ
ኬንያ፥ሊቢያ፥ቱንዚያ፥ሴንትራል አፍሪቃ ሪፐብሊክ፥ቻድ፥ደቡብ ሱዳን፥ሶርያ፥ዩክሬን ወዘተ ፡ተጨማሪ ስደትን የቀመሱ
ሐገሮች ናቸው።ነገ ወደስደት እንደማይገባ ማንም ርግጠኛ መሆን አይችልም።እኔ ከጥቅምት ወር 1998ዓ/ም ስደት
በሕይወቴ ውስጥ ይከሰታል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር።ዛሬ ቅልጥ ያልኩ ስደተኛ ሆኜ የኔ ጦስ ለባለቤቴም
ተርፏል።ሃገር አልቦች ሆነናል።
ባለፉት ስድስት አመታት በዩጋንዳ ካምፓላ በተለያዩ ስፍራዎች “የዩኤንኤችሴር” አጋፋሪ በሆነው “ኢንተር ኤድ”
አስተባባሪነት በተከናወኑ የስደተኞች ቀን በዓል ላይ ኮከብ ተሳታፊ ነበርኩ። ዘንድሮም ዕለቱን ማክበሬ የማይቀር
ነው።
በደም የተቋጨው ምርጫ 97 የበርካት ንጹሃንን ደም ገብሮ ካለፈ ዘጠኝ ዓመታት ተቆጥሮአል።ገዳዮቹ ዛሬም ለፍርድ
አልቀረቡም።ሃገሪቱም በከፋ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።ጋዜጠኞችና ጦማሪያን በፈጠራ ክስ እስር ቤት ታጉረዋል።
ዴሞክራሲ በገዢዎች መልካም ፈቃድ የምትሰጥ ብርቅ ስጦታ ሆናለች።የስደተኛው ቁጥር እያሻቀብ ነው።እንኳን የኔ ብጤ
ስደተኛው ወደ ትውልድ ሃገሩ ሊመልስ ይቅርና ሃገር ቤት ያሉትም መውጫ አጥተው ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው።ሃገር
ቤት።
በመጪው 2007 ዓ/ም በኢትዮጲያ ምድር የሚከናወነውን ብሄራዊ ምርጫ በነጻና ፍትሃዊ መንገድ ለማከናውን ቀድመው
መመቻቸት ያለባቸው ጉዳዮች
እስካሁን መተግበራቸውን እጠራጠራለሁ።
ነጻን ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ በአዲስ መልክ አልተዋቀረም።
የሚዲይ በነጻነት የመጠቀም ጉዳይ እልባት አላገኘምም።
ገዢው ቡድን ልቡን ለነጻ ምርጫ ያዘጋጀ ለመሆኑም ከተፈጥሯዊ ባህሪው አኳያ እስካሁን ማረጋገጫ አልሰጠም።
ምርጫውን በአስፈላጊው ዘዴ በመጠቀም ዘላለማዊ ገዢ ለመሆን ይጠቀምበታል እንጂ ለማንም 1 ወንበር ማጋራት
አይፈልግም።የግርማ ሰይፉም በአፓርላማው መኖር ሳያቃጥለው አይቀርም፡
የኔ ስጋት በ2007 ምርጫ ማግስት የከበዱ ሁኔታዎች በሃገሬ ላይ እንደሚከሰቱና የዓለም የስደተኞች ቀን በ2015
ሲከበር የኢትዮጲያዊያን ቁጥር እንደሚያሻቅብ ብገልጽ ማሟረቴ አይሆንም።
ከ1997 ዓ/ም ወዲህ በተፈጠረው ሃገራዊ ቀውስ ምክንያት በርካታ ኢትዮጲያዊያን የፖለቲካ ስደተኞች በኡጋንዳ
የምንኖር ሲሆን ባለፉት 8 ዓመታት “በዩኤንአኤችሴር” ካምፓላና በዩጋንዳ መንግስት ያሉበት የደህንነት ስጋት
ምክንያት ወደ 3 ኛ ሃገር” ሪስትልመንት” አግኝተው የበረሩት “የቶንቦላው ባለዕድሎች” ጥቂቶች ሲሆኑ በርካቶች
አሁንም ደጅ እየጠኑ አሉ።እኔ ደጅ ጥናቴን አላቋረጥኩም።
እኔ ራሴ በቅርበት የማውቃቸው 3 የፖለቲካ ስደተኞች ባለፉት 2 ዓመታት በህመምና ስደቱ ባስከተለባቸው መራራ
ህይወት ተስፋ በመቁረት ወደ አይቀሬው መቃብር ወርደዋል።
3ቱም (UNHCR) ቢሮ ለዘመናት ሲመላለሱ ከርመው የዩጋንዳን አፈር ለብሰው ቀርተዋል።
የኔና የባለቤቴም ጉዳይ ላለፉት 6 ዓመታት ውሳኔ ሳያገኝ በተስፋ ዕድሚያችንን እያቃጠልን ነው።የኔስ የመረጥኩት
መንገድ ስልሆነ ነው።ባለቤቴ ግን ከዱባይ መጥታ ስደተኛ ሆና ያለስራ መጉላላቷ የሚያሳዝን ጉዳይ ነው።
የኔ ሕይወት በኡጋንዳ ምድር ልዩነቱ ሃገር ቤት ከባልደረባዬ እስክንድር ነጋ ጋር ቃሊቲ አለመታሰሬ እንጂ የቁም
እስረኛ ወይም በግዞት እንደሚኖር ሰው ነኝ ብል አልተጋነነም።
ላለፉት 7 ዓመታት በዩጋንዳ ቆይታዬ ገና ለጋ ስደተኛ ሳለሁ የኢትዮጲያን ሚሊኒየም ሲከበር ፕሮግራሙን
ከማስተባበር ጀምሮ በወቅቱ ከወያኔ ቆንስላ ጋር ሚሊኒየሙን በጋር ለማክበር ሲደረግ የነበረውን “መሞዳሞድ”
በመቃውም በዓሉን ወያኔን ባላሳተፈ ሁኔታ በድምቀት እንዲከበር ባደረኩት የጎላ ተሳትፎ “የወያኔ ክልል 16″(
ካምፓላ) ጥቁር መዝገብ ከሰፈሩት “አሸባሪዎች”(ወያኔ ያልተመቹትን ሰዎች የሚለጥፍባቸው ዓለም አቀፍ ታፔላ
ነው)ቁጥር ሁለት መስመር ላይ እንደምገኝ ይታውቃል።
የኢትዮጲያን ማህበረስብ በዩጋንዳ (ethiopian comunity) ከAug,2007 ጀምሮ የበጎ ፈቃድ ተስትፎ
ሳደርግ በመቆየት Nov2010 በተደረገ ጠቅላላ ጉባዔ በቦርድ አባልነት ተመርጬ እስከ አሁን ድረስ በማደርገው
እንቅስቃሴ ያልተደሰቱ ሃይሎች ኮሚኒቲውን ለመቆጣጠር በመፈለግ በሚያደርገው ሴራ አመራሩን ለማዳከም የሚደረገውን
ተግባር በመቃወሜ በጠላትነት ተፈርጄ እንቅስቃሴዬ ስጋት ላይ ወድቋል።
ከጃንዋሪ 2008 ጀምሮ በስደተኛው ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በሚመራው የስደተኞች ቤተክርስትያን የሰበካ ጉባዔ ስራ
አመራር ሆኜ በማገልገል ላይ ስሆን ከጁን 2010 ጀምሮ በተፈጠረው ውዝግብ የጥቃት ዒላማ ሆኜ በርካት መከራ
ደርሶብኛል።ድብደባም ተፈጽሞብኛል።(የካዛንቺስ ልጅ ተደብደቦ ዝም ባይልም ባለኝ ማህበራዊ ሃላፊነት ለሌሎችአርአያ
ለመሆንና መሰናክል ላለመሆን በማንም ላይ ዕጄን አላነሳሁም።ወደፊትም አላነሳም።) በተቀነባበረ ወጥመድም በፈጠራ
ክስ እስከ መታሰርና ዲፖርት ለማስደረግ የተሞከረው ደባ በወገኖቼ ርብርብና በአምላክ ፈቃድ እንደከሸፈ በቂ መረጃ
አለ።
አሁንም ክትትሉና ማወከቡ በመቀጠሉ እንድልቤ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ተቸግሬያለሁ።
#ለተወሰነ ጊዜ የብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤቱ የዩጋንዳ ሪፕረዘንታቲቭ ዲፕሎማት ሆኜ በቆየሁበት ወቅት በጣት
ክሚቆጠሩ ወዳጆቼ በቀር አብሮኝ ሻይ የሚጠጣ ወገን እስከማጣት የደረስኩበትና የፖለቲካ ሰው እስክመስል ድረስ(
በወዳጅም በኢ-ወዳጅም)በፖለቲካ አክቲቪስትነት ተፈርጄ መራራ ወቅቶችን አሳልፌያለሁ።አሳዳጆቼ መውጫ መግቢያ
በማሳጣት ሐገር ለቅቄ እንድጠፋ ቢፈልጉም ሃገር አልባው የትም ልሄድ እንድማልችል ግን አላወቁም።
በየጊዜውችግሬን ለሚመለከታቸው አካላት ባቀርብም ዘላቂ መፍትሄ አላገኘሁም።ውሎዬ በጠላት በተወረረ ፈንጂ ወረዳ ውስጥ ነው።
የተለያዩ ጹሁፎችን” በኢትዮጲያን ሪቪው” ኦን ላይን ላይ ፖስት በማድረግ ሃስብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነቴን
ኤክሰርሳይስ ሳደርግ ብቆይም ከዲሴምበር 2013 አጋማሽ በሳውዲ የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን የሰባዊ መብት
ረገጣ በመቃውም ለዓለም ህብረተሰብ ድምጻችንን ለማሰማት ህዝባዊ ስብሰባ በኮሚኒቲ ደረጃ ለማዘጋጀት በማስተባበሬ
የወያኔ ቆንስላ ለዩጋንዳ መንግስት ደብዳቤ በመጻፍ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ ከኮሚኒቲ ለቀመንበራችን አቶ ዘለቀ ጀበሮ
ጋር ተጠርተን ስብሰባውን እንድናቆም በከፍተኛ የፖሊስ ኮማንደሮች ጥብቅ መመርያ ተሰጥቶን ስብሰባውን ለመሰረዝ
ተገደናል።
በጉዳዩ ዙርያ ያማከርኩዋቸው “የሰባዊ መብት ተከራካሪ ድርጅትና” “የኢንተሬድ ሌጋል ኦፊሰር” እንደነገሩኝ
የማደርጋቸውን ተግባራት እንዳቆምና በሃገሬ ዙርያ የምጽፋቸውን ስራዎች ማቆም እንድሚገባ በማስጠንቀቃቸው
“ከኢትዮጲያን ሪቪው” ኦን ላይን ድረ ገጽ ዜናዎችናጹሁፎች ማተሜን አቁሜያለሁ።
አማካሪዎቼ እንዳሉት ሐገር አልባ ስደተኛ በተሰደደበት ሐገርና በስደት በሚኖርበት ሐገር ጉዳይ ላይ መሳተፍ
እንደማይችል ዩጋንዳ በ2006 ያወጣችው “የሪፊውጂ አክት “ይጠቅሳል።
#ሃገር አልባ(stateless)ዝም ማለት አለበት እንደማለት ነው።
ስደተኞች የራሳቸውን ማህበር መመስረት አለባቸው የሚል ሃሳብ ከጥቂት መሰል ወገኖች ጋር ከMar 2013 ጀምሮ
በርካታ ውይይቶች በማድረግና አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም የማስታወቅያ ስራዎችን በመስራቴ ካምፓላ
ለኔ የስጋት ስፍራ ሆናለች።
እንደ ጋዜጠኛና ሰባዊ መብት ተሟጋች እየጻፍኩ ለመኖር አስጊ ሁኔታ ላይ መሆኔን ማን ሊረዳልኝ እንደሚገባ ምላሹን
ከአንባቢ እጠብቃልሁ።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኜ ነው አለማቀፉን የስደተኞች ቀን ኡጋንዳ ላይ ለስድስተኛ ጊዜ ለማክበር በዋዜማ ላይ የምገኘው።
የዘንድሮው የስደተኞች ቀንን ለኔ ልዩ የሚያደርገው “ለዓመታት የደከምንበት “በዩጋንዳ የኢትዮጲያዊያን ስደተኞች
ማህበር በዩጋንዳ”የመመስረት ሂደት በጣት የሚቆጠሩ ቀናት በቀሩበት ሁኔታ በመሆኑ የህሊና ዕርካት እንደተሰማኝ
ለመግለጽ እወዳለሁ።
ዓለማቀፉ የሰባዊ መብትና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ግለስቦች ለኔና መሰል ስደተኛ ወገኖች ተጨባጭ
የሆነ መፍትሄ ይዘው እንዲቀርቡና( ከሙታን በላይ ከቋሚ በታች ) ከሆነው ሕይወታችን እንዲታደጉን የሁሉ መፍትሄ
ምንጭ በሆነው 1አምላክ ስም ጩኸቴን አሰማለሁ።
በምስራቅ አፍሪካ ያለን ጥቂት ያካባቢው ስደተኛ ጋዜጠኞች በዩጋንዳ ጋዜጠኞች ዩኒየን ቢሮ ከ Dec 2012 ጀምሮ
ለመሰባሰብ ብንሞክርም ሁኔታዎች ባለመመቻቸታቸው እንደባለሙያ የጎላ ተግባራት ባናከናውንም በስም ደረጃ
ተደራጅተናል።
ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት የአለም አቀፉ የስደተኞች ቀን ሊከበር ቀናት በቀሩበት ሁኔታ ለኔና ከኔ ጋር
ከSep2007 ጀምሮ የመከራ ሕይወት የምትገፋውና ለኔ ብላ ስደተኛ ለሆነችው ባለቤቴ ምን አዲስ ተስፋ ይዞ
እንደሚመጣ የምናየው ይሆናል።
ፍትህና መፍትሄ ለኛ በ2014 በአምላክ ፈቃድ ይሁን!!!
ደረጀ በጋሻው(penethiopian)
የምስራቅ አፍሪቃ ስደተኛ ጋዜጠኞች ማህበር ሊቀ መንበርና
የኢትዮጲያ ማህበረሰብ በዩጋንዳ ማህበራዊ ጉዳይ ተጠሪ
ካምፓላ ኡጋንዳ
ሰኔ 11ቀን 2006 ዓ/ም(June 18,2014)
እግዚአብሄር አምላክ የስደትና የመከራ ዘመኔን መፍትሄ ይስጠው።
+256782302124

እራህብ!

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)
እርሃብ እያገላበጠ ይቆላናል። ሲያስፈልገውም ይፈጨናል። ሲያሰኘው እንደ ድልህ ይደቁሰናል። ሲያሰኘውም መለመላችን እንዲህ ይገርፈናል። ወህ! ገና ሳልጀምረው እንዲህ ድክምክም አለኝ። ታካች —
የእኛው ድንቁ ኢትዮ – አፍሪካዊ ክቡር ይድነቃቸው ተሰማ በርትተው የታገሉበት። መንፈሳዊ ሃብታቸውን ሳይሰስቱ የገበሩለት። ሥልጡኑን ብቃታቸውን በገፍ የመገቡት፤ የነጭን የበላይነት በረቂቅ ብልሃዊ ስልት ታግለው ያሸነፉበት፤ ዬታላቁ ኢትዮ አፍሪካዊ ውለታን በስውር የሰነቀው ዬዐለሙ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ከፍ ካለ ደረጃ ደርሶ እንሆ በብራዚል የሚሊዮንን መንፈስ በቅርብም በሩቅም ከተሞ ሲያፍነከንክ፤ ሲያስጨፍር፤ ሲያስደንስ፤ ማጫ ሲያማታ፤ ምሾ ሲያስደርድርም፤ ወይንም መወድስ ሲደረደርለት፤ እንዲሁም በሰላ አንደበት ሲሳሳልም በቀለማምሙ ፍቅር በመስተዋድድ አጭቶ ሲያጋባ፤ ሲያጣምር …. ፍልቅልቅ …
ኮቢው- ብራናው ሲያሸበሽቡለት፤ እልልታው፤ ፉከራው፤ እልሁ፤ ቅጣቱ፤ ዳኝነቱ፤ የሜዳ ፍንጠዛ፤ የመረብ ኩልልታ፤ የድንብልብ ፍጥጫ፤ የአራጋቢ ሩጫ፤ የተፈጥሮ ኩልኩልታ፤ የሰንደቅዓለማ ሽለላ፤ የማህል ዳኛ ነጋሪት -ጉስምታው፤ የአሰልጣኙ ቁጭ ብድግ ቡረቃ፣ የእግረኛ ሰርገኛ – የቴስተኛው ቅልቅል፤ የበረኛ ፈረሰኛ፤ ውሃውም አድሎት ዘንድሮ በቸረቸራ ታድሟል። አቤት! ያቺ 90 ደቂቃ የሞት የሽረት ትግል፤ የውጭ ግቢ ነፍስ ስንደቃ። ግን የፍሰሃ አውደ ምህረት። እማማ አፍሪካ በመታደሟም የደም ህትምት ሂደቱ ሆነ ውስጣዊነቱ ከልብም ነበር ማለት ይቻላል – ለእኔ።
ነገር ግን ተሳታፊ ሃገሮች በቀረቡ ቁጥር ልቤ ቁስል – ክስል – እርር – ትክን – ቅስሜ ስብር ይላል። የተፈጥሮ መስኮቶቼ ተከፍተው ጠብታቸውን ያለ ይግባኝ በተፋሰሳቸው ይለቁታል። እኔም እንዳሻችሁ ብዬ ፈቀድኩላቸው። ፍል!
አንዲት ታላቅ ሀገር፤ የሰው ልጅ መፈጠሪያ ሀገር፤ የነጻነት የተግባር ትምህርት ቤት ሀገር ዛሬ አንድ መለያ ወላዊ የሆነ የጋራ መዝሙር የሌላት፤ በነፃነት የመኖሯ ትርጉም ተቀጥቅጦ መቅኖው የተዘረፈበት፤ ከአለም ማዕቀፍ ተነጥላ በበቀል የምትከተከት፣ በጠላቷ ሉዑላዊነቷን የተቀማች ሀገር፤ ለዛውም ከአብራኳ በበቀሉ ተወሳኮች – የምትቀጣ። ወያኔ እንዲህ አድርጎ ነው ኢትዮጵያዊነትን የተለተለው – በበቀል። ይህ ዘመን እንዴት ይነበብ? እንዴት ይደመጥ? ለመሆኑ ከልባችን ገብቷልን? ስርስር አድርጎ አጥንታችን ፈትሾታልን? እህህህ!
የዛሬዋ ብራዚል የፖርቹጋል ቅኝ ተገዢ ነበረች፤ በጠቅላላ የላቲን አሜሪካ ሀገሮችም፤ ዛሬ በ60 ዎቹ ነፃነታቸውን ያገኙት አፍሪካዊት ሀገራት ሳይቀር አንገታቸውን ቀና አድርገው ብሄራዊ መዝሙራቸውን በጉልበታማ የተመሰጠ መንፈስ በህብረት ይዘምሩታል፤ የአብነቷ ሀገር ኢትዮጵያ ልጆች ግን …. ተርጉሙት አቅም ካላችሁ … እባካችሁ?!
እያንዳንዱ ሀገር ከነደጋፊው ወደ ብራዚል ተጓጉዟል። ቤት ሆኖ የሚመለከተውም በመንፈሱ ከዛው ከደራው የኳስ ድለቃ ፌስታ ነው። እኛም እንደ ህዝብ እንደ ዓለም ታዳሚነታችን ከጥበቡ ፍቅር ጋር ያለን ሰወች በትጋት እንከታተላለን። ግን በሀዘን ድንኳናችነን ጥለን ትካዜን እዬዘገን።
የትካዜው ምንጭ የይድነቃቸው ልጆች ባለመሳተፋቸው አይደለም – በፍጹም። ያን የተከተረ በምናምን የተተበተበ ድሪቶ ጉድ ጥሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ማጣሪያው ላይ ነበሩ። በአፍሪካ ዋንጫም ላይ ታዳሚ ነበሩ። ላደረጉት መልካም ተሳትፎ ይመስገኑ። እኔ የሚያርመጠምጠኝ ግን ከጽንፍ አስከ ጽንፍ እያንዳንዱ ሀገር „አንድ ህዘብ አንድ ቡድን“ ብሎ ብሄራዊ መዝመሩን በህብርት ሲዘምርና በብሄራዊ ስሜት በፍቅር፣ በሲቃ ፍንድቅድቅ ብሎ እንደዛ ተመስጦ ወጥነቱ ሲያምርበት፤ ሲያለቅሱም ሳይ ሃዘኔን ለመግለጽ አቅም ያንሰኛል። እኛስ? ይህ ነው ኮረኮንቹ ህመም፤ ይህ ነው የቋቁሻማው ዘመን መርዝ፤ ይህ ነው የዚህ ጠቀራማ ዘመን ዬዞገኝነት ኪሳራ ሂደት? በአለም ተለይታ ህዝቦቿ የሚስማሙበት አንድ ብሄራዊ መዝሙር የሌለት ሀገር – ኢትዮጵያ!
ያ … ውስጥን ገልጦ፤ አኃታዊነትን በፍቅር ፈጥሮ፤ እናትና ልጅን የሚያገናኘው የጋራ ብሄራዊ ጸሎት – የጋራ ልዑቅ ዝማሬ – የወል መንፈሳዊ ቅኔዊ ሃዲድ የክብር – የሞገስ መግለጫ ስብርብር አደረገው – ወያኔ። እራሱ የመንፈሱን ቁመና መለመለው። የዚህ ውስጥን ትክን – ከእሳት እንደገባ ፕላስቲክ ከሙትርትር የሚያደርገው ደባ ሥሩን ስናገኘው፤ ልዕልት ኢትዮጵያ – እመቤት ኢትዮጵያ – ንግሥት ኢትዮጵያ በባዕድ በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ለዛውም በበቀል በመሸገ አኳኋን ታሽጋና ታፍና እዬተገዛች – እዬተገዘገዘች ያለች መሆኗን ያመሳጥርልናል።
ይህን ትውልዱ ከቶውንም መመዘኛ ከቶ ሊገኝለት የማይችለውን፤ የሞት ሞቱ ጥቃቱን ከውስጡ ሆኖ ውስጡን በመፈተሽ፤ መፍትሄውን በማያዳግም ሁኔታ ማመንጨት ያለበት ይመስለኛል። ከዚህ በላይ አንገት የሚያስደፋ ሥር ሰደደ ውርድት የለምና። እኔ የለሁም። አንተም የለህም። እርሶዎም የሉም። አንቺም የለሽም። ሃቁ ይህ ነው። በአጥንትና በደም የቆዬች፣ የኖረች ሀገር ብሄራዊ መዝሙር አልባ – በእኛ ዘመን።
የወያኔ መዝሙር ለእኔ ምኔም ነው። እንዲያውም አላውቀውም። ማወቅም አልፈልግም – ማድመጥም። ኢትዮጵያዊነትን ለረገጠ ለጎሳ ነጋዴ መንፈሴን አልፈቅድለትምና። ይህን ረመጥ ለመታደግ – በምን ቋንቋ? በምን ፍልስፍና? በምን ዶግማ? ያን የቀደመ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለምን በውስጥነት የሚያውለበለበውን ሞገዳማ ንጹህ መንፈስ የሚፈጥር፤ ውስጥን ፈንቅሎ የሚወጣውን የቃል ኪዳን ማደሻ ሥርዓተ – መወደስ መፍጥር ይቻላል? መቼስ? እንዴትስ?! አቅም ይገዛል ወይንስ ይወለዳል? መልሱ የቤት ሥራ – ለእኔዎቹ። ጌጦቼ የሐገሬ ልጆች – ያጣነው ብዙ ክብር ነው። የተራቆትነው ከመጠነ ሰፊ የእኛነት ረቂቅ ንጥረ ቅማማት ነው። የተነጠልነው ከደማቁ ውበታችን ነው።
አለሁልሽ እናቴ! ከአንቺ በፊት እኔ! ቃሌ ይታደስ – በፊትሽ! እኔነቴን እንሆ ተቀበይኝ! ውሉ እንዴት ይታሰር ….?! እንዴት? እንዴት? እንዴት? መከራዋን በአብሮነት ለመታገስ፤ ሐሤቷን ለመታደም – ፍላጎቷን ለመከወን፤ ትእዛዟን ለመቀበል እንዴት ይቻል? ይህ አኮ በጋለ ማረሻ ልብን የመተርተር ያህል ነው – ህመሙ ከተሰማን? ? ?
ህቃታ ተሸክሞ
መንፈስሽ እንዲህ ተሰንጎ – ታርሶ – ታሞ
ታወከ በግርግር – በአታሞ!
መወድስሽ አለቀሰ
እንደራበው – በቋሳ ተጠበሰ – ተበጠሰ። አለቀሰ – አስለቀሰ!
የጠብታ ስብስብ -
ኤሉሄን ይሰብስብ!
ነገን አምጦ ይውለድ
እንዲወለድ!
የእኔ ውቦች የሐገሬ ልጆች አለመሸነፋችን የሚረጋገጠው ወያኔ ባሰናዳው መጠራቅቅ ገብተን አለመቀርቀራችን ስናረጋግጥ ብቻ ነው። መርዝነቱን በአትኩሮትና በማስተዋል መርምረን ከራሳችን ጋር መታረቅ ስንችል ብቻ ነው። ማሸነፍ! አዎን – እራስን ማሸነፍ ግማሹ የመፍትሄ ድላችን ነው። በማሸነፍ ሙቀት እኛን ከነተፍጥሯችን ማግኘት ይቻላል። በስተቀር ግን – እም!
እንዳመመኝ = እንደ ተከዝኩ = አንገቴን እንደ ደደፋሁ ልሰናበት። ጊዜው ከኖራችሁ በዚህ ሊንክ Radio Tsegaye ወይንም www.tsegaye.ethio.info Aktuell Sendung „የተሰፋ ናፋቂን ግጥም“ አዳምጡ ትእዛዝ አይደለም ትሁት አስተያዬት እንጂ። የ19.06.2014ን ፕሮግራም። አመሰግንኳችሁ ከልብ – በፍቅር። ቸር እንሰንብት – ቸር ያሰማን። አሜን!

የራበው ዕህል ፍለጋ ይማስን – ነገን ማኖር እንዲችል!
የጎጥ ጋጥ – ማጥ!

እግዚአብሄርይስጥልኝ!

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትን የደፈጠጡ አገር አልባ ናቸው!

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ወንጀል ፍፃሜ መሪ ተዋንያን ሆነው ከቆዩ በኋላ በመሰደድ በአሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው በተቀመጡ የሰብአዊ መብትደፍጣጮች ላይ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ መምሪያ ጥቆማእንዲቀርብለት ኢትዮጵያውያንን/ትን በማበረታታት ላይ ይገኛል፡፡

እነዚህ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ ጨካኞች በሰው አገር ሄደው ተደብቀዋል፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በበማታለል ገብተው ለ30 ዓመታት ተደብቀዋል፡፡ እነዚህ በሰው ደም የተዘፈቁ ወንጀለኞች በቀላሉ ሊያዙ በሚችሉበት አገር በመሄድ ለድፍን ሶስት ዓመታት የተደበቁም አሉ ፡፡

ETHIOPIAN-CRIMINALS-300x152እነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ወንጀለኞች ከኒዮርክ እስከ ሎስአንጀለስ ባሉ ታላላቅ ከተሞች እራሳቸውን ደብቀው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የፉኝት ዘሮች ማንም አይነካንም በሚል የእብሪት ስሜት ህዝብ በሚሰበሰብባቸው የአደባባይ ቦታዎች እና በእምነት ተቋማት ሳይቀር ደረታቸውን ገልብጠው ይንፈላሰሳሉ፡፡ በየቡና ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ሲወጡ ሲገቡ ይውላሉ፡፡ በጎዳናና በመንደር መንገድ ላይ ይንፏቀቃሉ፡፡ የተማሩም አሉባቸው ያልተማሩም አሉባቸው፡፡ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዚያት የዘረፏቸውን ገንዘቦች በውጭ ባንኮች አጭቀዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የንግድ ተቋማትን በማንቀሳቀስ ንብረት አፍርተዋል፡፡ ሌሎቹም ኑሯቸውን ለመምራት እና ዓላማዎቻቸውን ለማሳካት የአገልግሎት ሰራተኞች ሆነው ህይወትን በችግር መግፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከንጹሀን የግፍ ሰለባዎች ጋር የሞት ዋስትና ተፈራርመዋል፡፡ ንጹሀን ዜጎችን ጨፍጭፈዋል፣ አስጨፍጭፈዋል፣ ረሽነዋል፣ አስረሽነዋል፣ ገድለዋል፣ አስገድለዋል፣ ፈጅተዋል፣ አስፈጅተዋል፡፡

በምርመራ ላለመያዝ የሀሰት ስሞችን በመቀያየር ማንነታቸውን በመደበቅ ሲንገዋለሉ እና ሲንከላወሱ ይውላሉ፡፡ ሲገርፏቸው እና ሲያሰቃዩአቸው በነበሩት የወንጀል ሰለባዎቻቸው እና መብቶቻቸውን በተደፈጠጡት ወገኖች በውል ይታወቃሉ፣ ሆኖም ግን እነዚህ የግፍ ሰለባዎች እነዚህን ጨካኝ አረመኔ ወንጀለኞች ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ አካላት በምን ዓይነት መንገድ ለህግ እንደሚያቀርቧቸው አያውቁም፡፡ የግፍ ሰለባዎቹ እነዚህን ሲያሰቃዩአቸው የነበሩትን ወንጀለኞች በየቀኑ ባዩ ቁጥር የቅዥት ህይወትን በመምራት ላይ ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ ግድያ፣ ማሰቃየት፣ እና ሌሎች በሰው ልጆች ላይ ወንጀል የፈጸሙ ግፈኞች በእነርሱ የእውቀት ደረጃ ምንም የሚመጣብን ነገር የለም በሚል ትዕቢት በመታበይ በሰላም እና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንደሚኖሩ እምነት አድርገዋል፡፡

እነዚህ ግፈኛ አረመኔዎች የሰው ልጆችን ሰብአዊ መብቶች የደፈጠጡ እና በአሁኑ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው የሚገኙ የቀድሞው የኢትዮጵያ የደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ባለስልጣናት ናቸው፡፡

እነዚህ ግፈኛ አረመኔዎች የሰው ልጆችን ሰብአዊ መብቶች የደፈጠጡ እና በአሁኑ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው የሚገኙ የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት) እና እራሱ ቀፍቅፎ የፈጠረው የይስሙላው እራሱን “የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሚክራሲያዊ ግንባር” እያለ የሚጠራው ቡድን ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ባለስልጣናት ናቸው፡፡

እነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች በለመደው አጭበርባሪ አንደበታቸው የአሜሪካንን የጥገኝነት እና ዜግነት መስሪያ ቤት ተቋም ስርዓትን በማታለል የአሜሪካንን የኗሪነት ወይም የዜግነት ፈቃድ ያገኙ ናቸው፡፡

እነዚህ ወንጀለኞች የገዳይ እና አስገዳይነት ወንጀላቸው ተረስቶ ምንም ነገር እንደማያመጣባቸው በማሰብ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በምቾት እና በተድላ መኖር እንደሚችሉ እምነት አላቸው፡፡

እነዚህግፈኞችለአሜሪካፍርድቤቶችለፍትህለፍርድ መቅረብአለባቸው!

እነዚህ በአሜሪካ አገር እራሳቸውን ደብቀው የሚገኙ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ የኢትዮጵያ ግፈኞች አንዳንድ ጊዜ ወንጀል ከፈጸሙባቸው የግፍ ሰለባዎቻቸው ጋር በአጋጣሚ ይገናኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 2011 ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ (ተለዋዋጭ ስም የሚጠቀም ፣ ሀብታብ በርሄ ተማኑ፣ “ቱፋ“፣ ከፈለኝ ዓለሙ) የተባለው ጨፍጫፊ ወንጀለኛ ኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት ሲያሰቃያቸው ከነበሩት የግፍ ሰለባዎች መካከል ከአንደኛው ጋር ዴንቨር ኮሎራዶ ከተማ ፊት ለፊት ተገናኙ፡፡ ከፈለኝ ወርቁ እ.ኤ.አ በጁላይ 2004 ሀብታብ በርሄ ተማኑ በሚል የሀሰት መታወቂያ በመጠቀም ነው ስደተኛ በመምሰል ወደ አሜሪካ የገባው፡፡ እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ መጨረሻ አካባቢ እራሱን “ደርግ“ እያለ የሚጠራ ጨካኝ አረመኔ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጭ ንጹሀን ዜጎችን የሚገድል እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የሚያሰቃይ “ቀይ ሽብር” የተባለ ዘመቻ አወጀ፡፡ በዚያን ጊዜ ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የእስር ቤት የጥበቃ አባል ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1978 ሳሙኤል ከተማ የተባሉ የፖለቲካ እስረኛ አብረዋቸው የነበሩትን እስረኞች ይህ ወርቁ የተባለ ጨፍጫፊ ሲያሰቃይ እና ሲገድል የነበረ መሆኑን የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1977 አበበች ደምሴ የምትባል የ16 ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረች እስረኛ “ወርቁ እየተኮሰ ሰዎች ገና አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን ጨምሮ ሲገድል አይቻለሁ“ የሚል የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ወርቁ “በወለሉ ላይ የፈሰሰውን የሟቾቹን ደም በተገኘው ሁሉ በምላሳችንም ጭምር እንድናጸዳው“ ለሌሎቻችን እስረኞች ትዕዛዝ ሰጥቷል ብለዋል፡፡ ወርቁ በአበበች ጭንቅላት ላይም ኤኬ – 47 አውቶማቲክ ጠብመንጃ አነጣጥሮ የነበረ ቢሆንም በእግዚአብሔር ታምር ህይወታቸው የተረፈ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንደ ፍርደ ቤቶች ዘገባ ከሆነ እ.ኤ.አ በ2013 ወርቁ በህገወጥ መልክ ዜግነትን በመግዛት ወይም በማግኘት፣ ማንነትን በመደበቅ ወንጀል፣ በማጭበርበር እና ህገወጥ ቪዛ በመውሰድ እና በመጠቀም፣ እንዲሁም ሌሎች የተጭበረበሩ ሰነዶችን በማቅረብ የሚሉ የተለያዩ ክሶች ቀርበውበታል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የወረዳ ፍርድ በ5 ቀናት የፍርድ ቀጠሮ ሂደት እ.ኤ.አ ሜይ 23/2014 በዋለው ችሎት ወርቁ በሁሉም ክሶችጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ 22 ዓመታት እስር እንዲቀጣተበይኖበታል፡፡ በአጠቃላይ ከዜግነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ መልኩ ለሚሰሩ ወንጀሎች በፌዴራል እስር ቤት ከ18 ወራት በላይ የእስራት ብይን አይሰጥም፡፡ ሆኖም ግን ብይኑን የሰጡት ዳኛ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ዳኛ ጆን. ኤል. ካኔ የወርቁ የጥፋተኝነት ወንጀል በጣም አስደንጋጭ እና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ዳኛ ካኔ እንዲህ በማለት ገለጻ አድርገዋል፣ “ይህችአሜሪካ አገር የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች መጠለያ ዋሻ የመሆን አደጋ ጋር በተያያዘ መልኩ ከፍተኛው የእስር ብይን መሰጠቱ ተገቢ ነው“ ብለዋል፡፡

ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የፍርድ ሂደት ጉዳይ ይዘውት የነበሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ጠበቃ ጆን ዋልሽ እንዲህ በማለት አውጀዋል፣ “የእኛ የፍትህ ስርዓት በአንድ ወቅት አሸባሪው ወንጀለኛ ተከላካይ ሲያሸብረው ከነበረው ስደተኛ ማህበረሰብ ላይ በተሳካ ሁኔታ እንዲወገድ አድርጓል፣ እናም ይህንን በማድረግ የእኛን ህጎች ብቻ አይደለም ከጥፈተኝነት ነጻ ያደረግነው ሆኖም ግን እዚህ እኛ አገር ውስጥ እየኖሩ ያሉትን የተከላካዩን የግፍ ሰለባዎች መብት ማስከበር ጭምር እንጅ፡፡“ በአሁኑ ጊዜ ፍትህ ተረጋግጧል/ሰፍኗል፡፡ የወንጀሉ ተከላካይ የሆነው ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ ለሰራው ወንጀል ከፍተኛ የሆነውን የእስር ብይን በመወሰን “ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የኗሪነት እና የጥገኝነት ህጓን በማጭበርበር ከለላ ለማግኘት ከውጭ ሲገድሉ እና ሲያሰቃዩ ቆይተው ወደ አሜሪካ ለሚመጡት ወንጀለኞች በሰላም ለመኖር መደበቂያ ዋሻ አትሆንም” በማለት ዳኛ ጆን ካኔ ጠንካራ የሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት በስደት በአሜሪካ አገር የሚኖረው የኢትዮጵያ ታዋቂው የምርመራ ጋዜጠኛ አበበ ገላው አንድ ቴዎድሮስ ባህሩ የሚባል “የኢትዮጵያ ሰይጣናዊ አቃቤ ህግ የነበረ“ (አሜሪካ ሊታይ በሚችል ቦታ ላይ እራሱን ደብቆ) አግኝቷል፡፡ ቴዎድሮስ ባህሩ ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ በሚባል ቦታ ኗሪ የሆነውን “በሰላማዊ አመጸኞች፣ በነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና በተቃዋሚ የፖለቲካ አባላት ላይ የጸረ- ሽብር አዋጅ እየተባለ የሚጠራውን የንጹሀን ዜጎች ማጥቂያ መሳሪያ በማድረግ ፍትሀዊ ያልሆነ እና ከህግ አግባብ ውጭ የዘፈቀደ እስራት ላይ የሙሉ ፈቃደኝነት ተዋናይ ሆኖ በመስራት “ በሚል ክስ አበበ ገላው መስርቶበታል፡፡ እንደ አበበ ገለጻ ከሆነ ባህሩ “ወንጀላቸው የህወሐትን ሙስና እና አምባገነናዊ አገዛዝ መቃወማቸው ብቻ በሆኑት ንጹሀን ዜጎች ላይ ለቁጥር የሚያዳግቱ የፍብረካ የአገር ክህደት እና የሽብር ወንጀል ክሶችን በመዘርዘር ዜጎች ያለስራቸው በሀሰት አንዲሰቃዩ እና ስብዕናቸውም እንዲገፈፍ በማድረግ ታላቅ ወንጀል ሰርቷል የሚል ነው፡፡“

አበበ ውንጀላውን እንዲህ በማለት አቅርቦታል፣ “ቴዎድሮስ ባህሩ ከህወሐት (በኢትዮጵያ የገዥው አካል ፓርቲ) ዓቃብያነ ህጎች መካከል አንዱ ሲሆን በፖለቲካ እስረኞች ላይ ማለትም በእነ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ በሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪዎች ላይ እና ጆሀን ፔርሰን እና ማርቲን ሽብዬ በተባሉ ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ የሽብር ክሶችን እንዲፈበርክ ሰልጥኖ እና ተቀጥሮ በወሰደው ስልጠና መሰረት ሲያስፈጽም የቆየ“ ተጠርጣሪ ነው የሚል ነው፡፡ አበበ በመቀጠልም “ባህሩ የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ያገኙትን እና ሌሎችንም ንጹሀን ዜጎች ማለትም ኦባንግ ሜቶን፣ ኒያሚን ዘለቀ፣ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ፋሲል የኔዓለም፣ መስፍን ነጋሽ እና አብይ ተክለማርያምን በሽብርተኝነት ክስ እንዲመሰረትባቸው አድርጓል“ ብሏል፡፡

በኤሌክትሮኒክ በተደረገ ግንኙነት ባህሩ ለአበበ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላልፏል፣ በሀሰት የተፈረከውን የእስክንድር ነጋን እና የሌሎችን ከላይ የተጠቀሱትን ተከላካዮች ሳቀርብ “ስራዬ ትዕዛዞችን ብቻ መቀበል ነበር“፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ቴዎድሮስ ባህሩ የናዚ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ወንጀለኞች “በኑርምበርጉ የጦር ፍርድ ቤት” ቀርበው በተጠየቁበት ጊዜ ያነሱትን መከላከያ ሀሳብ እንዳለ ደግሞታል፡፡ በዚያን ወቅት አዶልፍ ኤክማን የተባለው ወንጀለኛ በጦር ፍርድ ቤቱ የፍርድ ሂደት እየተካሄደ ለጥያቄ በቀረበበት ጊዜ እንዲህ የሚል የምስክርነት ቃል ሰጥቶ ነበር፣ “እራሴን ለስልጣን ስራዎቼ ለቢሮዬ ቃልኪዳን ታማኝ ሆኘ እራሴን ማስገዛቴ እና ታዛዥ ሆኘ በማስፈጸሜ ጥፋተኛ ነኝ፡፡ አይሁዶችን ሆን ብዬ በማጥቃት እና በስሜታዊነት እንዲገደሉ አላደረግሁም፡፡ ያንን ያደረገው መንግስት ነው፡፡“ ከዚህ ጋር በተመሳሰለ መልኩ ቴዎድሮስ ባህሩም ለስልጣን ስራው ሲል ንጹሀን ዜጎችን አልነካሁም ነው የሚለው፡፡ትእዛዝ ብቻ ነው የተቀበልኩት :: ለዚህ በሸፍጥ ለተሞላው የወንበዴ ቡድን ታማኝ ሎሌ እና አገልጋይ በመሆን ለሰራቸው ጥፋቶች ሁሉ ኃላፊነት የለኝም ነው የሚለው፡፡ እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን ወይም ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎችን “ሆን ብሎ እና በስሜታዊነት” አላጠቃሁም፣ ያንን የፈጸመው መንግስት ነው ይላል ቴዎድሮስ ባህሩ ፡፡

ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ የመሰረተቻቸው ክሶች፣

የህወሐት ገዥ አካል እርሷን እና ባለቤቷን እስክንድር ነጋን ወደ እስር ቤት እስከወረወረበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ጋዜጠኛ እና አሳታሚ ሆና ስትሰራ በቆየችው ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ በጣም ጠንካራና ማስረጃ የሞላው ክስ አቅረባለች፡፡ ሁለቱም ሰርካለም እና እስክንድር (በአሁኑ ጊዜ በሀሰት የሸፍጥ ክስ ተመስርቶበት የ18 ዓመታት እስራት ተበይኖበት ከመሀል ከተማ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኘው በታዋቂው የ “መለስ ዜናዊ የቃሊ እስርቤት”በመማቀቅ ላይ ያለው) በዘመናዊ የአፍሪካ የነጻ ጋዜጠኞች ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በገዥው አካል ጥቃት የተፈጸመባቸው እና ከፍተኛ የሆነ ዓለም አቀፋዊ አድናቆትን ያገኙ ሰላማዊ ጋዜጠኞች እስክንድርና ሰርካለም ናቸው፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውሰጥ እስክንድር እያንዳንዱን ታዋቂ እና ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ የፕሬስ ሽልማቶች አሸናፊ ነበር :: ከሁለት ሳምንታት በፊት በተወካዩ አማካይነት የተቀበለውን የ2014 ወርቃማ የብዕር የነጻነት ሽልማት ጨምሮ በዓለም ታዋቂና ተወዳጅ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሰርካለምም እንደዚሁ “ዓለም አቀፍ የሴቶች ሜዲያ ፋውንዴሽን” ከተባለው ዓለም አቀፍ የፕሬስ ድርጅት አደጋ ተደቅኖ ባለበት ሁኔታ የተለዬ ጀግንነትን ለሚያሳዩ ጋዜጠኞች ”ለደፋር ጋዜጠኝነት ሽልማት“ የሚለውን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ሽልማቶችን አግኝታለች፡፡

በተቀዳ የድምጽ/ኦዲዮ ቃለ መጠይቅ ሰርካለም ቴዎድሮስ ባህሩ በቀላሉ “ትዕዛዝን ብቻ በመቀበል” የሰራ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከፍርድ ቤቶች ውጭ ወደ እስር ቤት እንዲገባ እና እንዲወጣ ትዕዛዝ ከሚሰጡት ሰዎች አንዱ ነበር ብላለች፡፡ ሰርካለም በተጨባጭ እንዳስቀመጠችው ባህሩ ባለቤቷን የገዥውን አካል ትዕዛዝ ተቀብሎ ከመተግበርም ባሻገር “ሆን ብሎ እና ስሜታዊነት በተሞላበት ሁኔታ” ሲያሰቃየው እንደደነበረ ገልጻለች፡፡ እንደ ሰርካለም አባባል ከሆነ ባህሩ ቁጡ፣ ጨካኝ፣ ችግር ፈጣሪ፣ ምህረት የለሽ እና ሩህሩህነት የማይሰማው አረመኔ አቃቤ ህግ ነበር ብላለች፡፡ እንደ ባለሙያ ዓቃቤ ህግ የሚገባውን ህጋዊ ስርዓት ተከትሎ የሚሰራ ሳይሆን እንደ ፖለቲካ አቃቤ ህግ ተከላካዮችን ያድን ነበር፡፡ ባህሩ ተከላካዮችን አሳንሶ ለማሳየት በፍርድ ቤቱ ችሎት ፊት ሁሉንም አጋጣሚዎች ሁሉ ያደርግ ነበር፡፡ ተከላካዮች ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩ ነጻ መሆናቸውን ሊያስረዱ የሚችሉ ሰነዶችን እና ምስክሮችን በሚያቀርቡበት ጊዜ ሁሉ እነዚህን በሚያስተባብል መልኩ ተቃውሞዎችን እያቀረበ ይከላከል ነበር፡፡ ተከላካዮች ፍትሀዊ ብይን እንዳያገኙ እና ማለቂያ በሌለው ረዥም ቀጠሮ እየተመላለሱ እንዲጉላሉ በማሰብ እንዲሁም የፍርድ ሂደቱን ስርዓት በማጣመም ከፍትህ አካላት የአሰራር መርህ ውጭ በሆነ መልኩ ፍትህን ሲያዛበ ነበር፡፡ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማሰጠት በማሰብ የተፈበረኩ እና የሀሰት ማስረጃዎችን ያቀርብ ነበር ብላለች፡፡

ሰርካለም በተለየ መልኩ ቴዎድሮስ ባህሩ በእራሱ አቅም እና እንደ መንግስት ዓቃቤ ህግ እያወቀ ሆን ብሎ እና የያዘውን ስልጣን ለእኩይ ተግባር በማዋል በእርሷና በባሌቤቷ የክስ ሂደት ላይ የህግ የበላይነትን ሲያጣምም ቆይቷል በማለት ውንጀላ አቅርባበታለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ባህሩ በባለቤቷ ላይ መሰረተ ቢስ ክስ በመመስረት፣ የሀሰት ማስረጃ እና የሀሰት ምስክር በማቅረብ እውነታውን እያወቀ ሆን ብሎ ሲያጣምም ነበር በማለት ወንጅላዋለች፡፡ ሰርካለም ውንጀላዋን በመቀጠል ባህሩ እስክንድርን የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራራ በመሆን ወጣቶችን እየመለመለ ለሽብር ጥቃት ሲዳርግ ነበር ብላለች፡፡ ባህሩ ይህንን ውንጀላ ለማስተባበል የሚያስችል ምንም ዓይነት ማስረጃ ለማቅረብ አልቻለም፡፡ ሆኖም ግን የሸፍጥ ስራውን ለማከናወን ከዳኞች ጋር የሸፍጥ ዱለታ በማካሄድ ጥፋተኛ እንዲባል አስደርጓል፡፡ ሰርካለም ባህሩ እና ብርሀኑ ወንድምአገኝ የተባሉ ሁለት ዓቃብያነ ህጎች በግል የቤተሰቦቿን ንብረቶች፣ ቤቶቻቸውን፣ መኪኖቻቸውን እና ሌሎችን የግል መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ከህግ አግባብ ውጭ እንዲነጠቁ በማድረጉ ሂደት ላይ ተባባሪ ነበሩ በማለት ውንጀላ አቅርባባቸዋለች፡፡ ባህሩ እያወቀ ስልጣኑን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም ሆን ብሎ እና ሌሎችን የኢትዮጵያን የነጻውን ፕሬስ ጋዜጠኞች ለማጥቃት እንደ ሰርካለም አባባል ዓለም አቀፍ የፕሬስ አሸናፊ ተሸላሚ የሆኑትን እነ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እና ሌሎችም ፍትሀዊ ዳኝነት እንዳያገኙ በማድረግ ደባ ፈጽሟል ብላለች፡፡

ሰርካለም በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ ያቀረበችው ውንጀላ በተለይም የህግ የበላይነትን ከማስጠበቅ አኳያ እና የመንግስት ዓቃብያነ ህጎች ንጹሀን ዜጎች የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ሰለባ እንዳይሆኑ በመከላከል ሂደት ላይ የሚጫወቱትን ቁልፍ ሚና በሚመለከት በርካታ የህግ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርገዋል፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ ዓቃብያነ ህጎች የሰብአዊ መብት ጥበቃ ንቁ ተከላካይ መሆን እንዳለባቸው እና የአገር እና ዓለም አቀፍ ህጎች ታማኝነት እና የሰብአዊ መብት መርሆዎች በከፍተኛ ደረጃ መጠበቅ እንዳለባቸው ይጠይቃል፡፡ ዓቃብያነ ህጎች ለፍትሀዊ ዳኝነት ሂደት እና ለፖለቲካ ዓላማ ሲባል ኃላፊነቶቻቸውን በአግባቡ ሳይወጡ የሚቀሩ ቢሆን የህግ የበላይነት መርሆዎችን ብቻ አይደለም እየጣሱ ያሉት፣ ሆኖም ግን ቆመንለታል የሚሉትን የፍትህን ጠቅላላ መጨንገፍ የሚያመላክት ስለሆነ የእነርሱ መኖር በእጅጉ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

ሁለቱም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ እና ዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ስምምነቶች/ሲፖመስ (ዩናይትድ ስቴትስ ሲፖመስን በኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀጽ 13(1)) ላይ የተቀመጠውን “እያንዳንዱ ሰው በነጻ እና ገለልተኛ በሆነ የፍትህ አካል ችሎት ፍትህን የማግኘት እና የመደመጥ መብት እንዳለው እና ማንኛውም በግለሰቦች ላይ የሚመሰረትን የወንጀል ክስ ለመከላክል መብት እንዳለው የሚደነግገውን እና እ.ኤ.አ በ1992 ያጸደቀችውን፣(ሰፖመስ በአንቀጽ 14፡ የአፍሪካ ቻርተር ሰዎች እና በህዝቦች መብቶች (አቻሰህመ) ከአንቀጽ 6-8 የተዘረዘሩትን መመልከት ይቻላል)፡፡ የሮማ ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) የወንጀለኞች ፍትህ የማግኘት መብት መርሆዎችን በግልጽ ያስቀምጣል (ከአንቀጽ 22-33) እና የፍትሀዊ ዳኝነት (ከአንቀጽ 62 – 67) በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ለሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሰላባዎች ካሳ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግ እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግ መጣስን አስመልክቶ (በተባበሩት መንግስታት የጠቅላላው ጉባኤ የዴሴምበር 16/2005 ጉባኤ ውሳኔ ቁጥር 60/147) እንደሚገልጸው መንግስታት በሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩትን እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶችን ጥሰዋል የሚባሉትን መብት ደፍጣጮች የመዳኘት ኃላፊነት እንዳለባቸው በግልጽ ተደንግጓል፡፡“

በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ፈጽመው በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ተደብቀውበሚገኙ የኢትዮጵያ ወንጀለኞች ላይ ጥቆማ እንዲደረግ የቀረበ ጥሪ፣

እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 2012 “የአፍሪካ አምባገነኖች፡ የትም ሮጠው ሊያመልጡ አይችሉም፣ የትም ተደብቀው ሊያመልጡ አይችሉም!“ በሚል ያቀረብኩት ፅሁፍ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ደፍጥጠው ወደ ውጭ በመኮብለል በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ እየኖሩ የሚገኙትን መብት ደፍጣጮች አሳድዶ በማደን ስማቸውን እና ያሉበትን ልዩ ቦታ ለአሜሪካ ባለስልጣኖች ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ግዴታዎቻችሁን እንድትወጡ እና የወገኖቻችሁ ደም ደመከልብ ሆኖ እንዳይቀር የሚል ጥሪ አስተላልፌ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ እየተጠናከሩ በመጡት ምርመራዎች እና የሰብአዊ መብቶችን በመደፍጠጥ ወደ አሜሪካ በማታለል እና በህገወጥ መልክ የገቡትን ወንጀለኞች አሳድዶ በመያዝ በተለይም ለአሜሪካ ባለስልጣኖች ለህግ ማቅረብ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለዜግነት እና ለጉምሩክ አስፋጻሚ ፣ ለአገር ውስጥ ደህንነት ጉዳይ ፣ ለሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና ለጦር ወንጀለኞች ቡድኖች እና ለብሄራዊ ደህንነት የምርመራ ክፍል መ/ቤቶች መጠቆም ትችላላችሁ፡፡ ያሜሪካ መንግስት የጦር ወንጀለኞች፣ የዘር ማጥፋት ወንጀለኞች፣ የአሰቃዮች እና ሌሎች በዓለም ላይ ግጭትን ሊያመጡ የሚችሉ የሰብአዊ መብቶች ደፍጣጮች ኮሚሽን መደበቂያ ገነት እንዳትሆን ለመከላከል ጠንካራ ምርመራዎችን ያደርጋል፡፡ የውጭ ተጠርጣሪ የጦር ወንጀለኞች፣ አሰቃዮች እና የሰብአዊ መብት ድፍጣጮች ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የግዛት ክልል ውስጥ መኖራቸው በሚታወቅበት ጊዜ የምርመራ ቡድን ሙሉ የህግ ኃይሉን እና ስልጣኑን በመጠቀም ለማጣራት፣ ለመዳኘት እና በሚቻልት ሁኔታ ሁሉ እንደዚህ ያሉ ሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን ከአሜሪካ ለማስወገድ ጥረት ያደርጋል፡፡

ባለፉት አስርት ዓመታት ያሜሪካ መንግስት በመቶዎች በሚቆጠሩ ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ መልኩ በወንጀለኛ እና/ወይም ስደተኞች ምርመራ ላይ ስኬታማ ሆኗል፡፡ የዚህ ቡድን የዳታ መሰረት በርካታ የታወቁ ተጠርጣሪ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን ስም ዝርዝር አካትቶ ይዟል፡፡ የዳታ ቋቱ የታወቁ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለማድረግ ጠቃሚ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዜጉአ ወደ100 አካባቢ ከሚሆኑ ከተለያዩ አገሮች የመጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ላይ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሰብአዊ መብት ድፍጣጮች እና ከተለያዩ የወንጀለኛ እና/ወይም ከስደተኝነት ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር ስር አውሎ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩትን ታዋቂ ወይም ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ደግሞ ከዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በማስወጣት ወደ አገራቸው እንዲጋዙ አድርጓል፡፡

በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ እና በአሜሪካ እየኖሩ ያሉ የኢትዮጵያወንጀለኞች ለምርመራ ለዜጉአ ሰመደጦወቡ ጥቆማ መቅረብ ይኖርባቸዋል፣

በኢትዮጵያ በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች እና የጦር ወንጀሎች መረጃዎች በተሟላ ሁኔታ ተተንትነው እና ተጠቃለው ተዘጋጅተው ተይዘዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 በኢትዮጵያ ያለው የህወሐት ገዥ አካል አጣሪ ኮሚሽን ባቀረበው ዘገባ መሰረት የ2005 ድህረ ምርጫ ውዝግብን ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ 193 ሰላማዊ ዜጎች የተገደሉ፣ ሌሎች 763 ሰዎች ቁስለኛ እና ሌሎች ወደ 30 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ከህግ አግባብ ውጭ ለዘፈቀደ እስራት የተዳረጉ መሆናቸውን በተጨባጭ መረጃ አስደግፎ አቅርቧል፡፡ በዚህ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተዋንያን የነበሩ 237 ግለሰቦች ታውቀዋል፣ እንዲሁም ከዚሁ ጋር ንክኪ ያላቸው ተጠርጣሪዎች ተለይተዋል፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር 2003 በኢትዮጵያ በጋምቤላ 424 ንጹሀን ዜጎች ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ ለህወሐት ታማኝ በሆኑ የደህንነት ኃይሎች ተገድለዋል፡፡ በኦጋዴን ላይ በሚደረገው ጭቆና እ.ኤ.አ በ2008 ሂዩማን ራይትስ ዎች ባወጣው ዘገባ መሰረት “150 የተገደሉ ግለሰቦች“ እና ሌሎች 37 ተጨማሪ ሰላማዊ ዜጎች በጦር ወንጀለኝነት ተጠያቂ በሚሆኑ በኢትዮጵያ ወታደሮች ትዕዛዝ እና ተሳታፊነት በተደረገ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ተመዝግቦ ተይዟል፡፡ ይህንን የጦር ወንጀል የሚያወቁት ወይም ደግሞ እንደዚህ ያለ ወንጀል እንደሚፈጸም ማወቅ ያለባቸው ሆኖም ግን ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰዱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የሲቪል ባለስልጣኖች እንደ ትዕዛዝ ሰጭነታቸው በወንጀሉ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተስፋፋው እና ስልታዊ በሆነ መልክ በሶማሊ ክልል በእያንዳንዱ መንደር ላይ እየተካሄደ ያለው ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ የሚደረገው ግድያ፣ ማሰቃየት፣ አስገድዶ መድፈር፣ እና አፍኖ መሰወር በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ ገዥ አካል የመጨረሻውን ተጠያቂነት ሊወስድ የሚችልባቸው እና ሊጠየቅባቸው የሚችሉ በሰው ልጆች ላይ እየፈጸማቸው ያሉ ወንጀሎች ጠንካራ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ከብዙው በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ተደብቀው በሚገኙ የኢትዮጵያ ወንጀለኞች ላይጥቆማ ለማድረግ ለምን ተነሳሽነት ማሳየት እንዳለብን፣

ምናልባትም ባለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያውያን/ት ዘንድ በተደጋጋሚነት ሲቀርቡልኝ ከነበሩት ጥያቄዎች ውስጥ “እኔ እንደ ግለሰብ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ለማሻሻል ምን ማድረግ እችላለሁ?“ የሚሉ ነበሩ፡፡

በርካታ ኢትዮጵያውያን/ት በተለይም የዲያስፖራው ማህበረሰብ በግለሰቦች አቅመቢስነት ተስፋ እየቆረጡ የመጡ ይመስላል፡፡ በተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች መካካል የሚታዩትን የአንድነት መላላት በመመልከት እና መቋጫ በሌለው መልኩ እየተሰነጣጠቁ ሲፈረካከሱ በማየታቸው በሀዘን በመሞላት ከዳር ቆመው በመመልከት ላይ ይገኛሉ፡፡

ባለፈው ሳምንት በኮካ ኮላ ኩባንያ እና በሚያመርታቸው 114 ምርቶቹ ላይእንዳንጠቀም የሚቀሰቅስ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ ኮካ ኮላ 32 የዓለምለዓለም እግርኳስ የመክፈቻ ስነስርዓት ማድመቂያ የሚሆን ምርጥ አገራዊ ሙዚቃቸውንእንዲያቀርብ 32 ታዋቂ ሙዚቀኞች ጋብዞ ከእነዚህ ውስጥ31ዱን በመምረጥ ሲለቅቅ አንዱን ብቻ ነጥሎ በማውጣት የኢትዮጵያውን ወደ ጎን አሽቀንጥሮበመጣሉ ኮካ ኮላን ገሀነብ ግባ!!!” በማለት እቅጩንነግሬዋለሁ፡፡ በምንምዓይነት መልኩ የኮካ ኮላን ምርት አልገዛም፣ በፍጹም አልጠቀምም፣ እንዲሁምሌሎች የኮካ ኮላን ምርት እንዲገዙ ወይምእንዲጠቀሙ አላበረታታም፡፡ግለሰቦች በተናጠል እና እንዲሁም በጋራ በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችያለምንም ጥርጥር ለውጥ ያመጣሉ፡፡ ኮካበጭራሽ በፊቴ አይዞርም!

ባለፈው ሳምንት በኮካ ኮላ ምርት ላይ ላለመጠቀም የሚቀሰቅሰው ጥሪ መተላለፉን ተከትሎ በእስፔን አገር ከፍተኛ የሆነ የኮካ ኮላ ምርት ሽያጭ ቅነሳ ተስተውሏል፡፡ በእስፔን የኮካ ኮላ ምርት ሽያጭ በግማሽ ቀንሷል ምክንያቱም የእስፔን ህዝብ የኮካ ኮላ ኩባንያን ገሀነም እንዲገባ ስለነገረው ነው!!!

(በኢትዮጵያ ኮካ ኮላን ባለመጠቀም ጸጥ በማለት ውጤታማ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆኑን ተጨባጭ መረጃዎች ያመላክታሉ)፡፡

እስፔኖች ኮካ ኮላን አሽቀንጥረው ከጣሉት ኢትዮጵያውን/ትስ ምን ይሳናቸዋል?

ኢትዮጵያውያን/ት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለአሜሪካ የዜጎች እና ጉምሩክ አስፈጻሚ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና የጦር ወንጀለኞች ቡድን ለምን መጠቆም እንዳለባቸው በማስረጃ እና በመረጃ የተደገፉ በርካታ ምክንቶች አሉ፡፡

1ኛ) በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ወንጀል ሰርተው በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሄደው ተደብቀው የሚኖሩትን መጠቆም በምንም ዓይነት ሊታለፍ የማይችል በቀጥታ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ/ት ወይም ደግሞ በሌሎች ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመ ለመሆኑ እውቀቱ ያለው የሞራል ሰብዕና ተግባር በመሆኑ ነው፡፡ በሰው ልጆች ላይ እንደዚህ ያለ ወንጅልን የሚፈጽሙ ወንጀለኞች መጋለጥ እና ከአሜሪካ ህብረተሰብ መካከል መወገድ ይኖርባቸዋል፡፡

2ኛ) በእነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ላይ ጥቆማ ማካሄድ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቀው ላሉት ባለስልጣኖች አሜሪካ የሰብአዊ መብትን እየደፈጠጡ ለሚመጡ ወሮበላ ወንጀለኞች የሀሰት እና የተጭበረበረ የጥገኝነት ቪዛ እያመጡ በሰላም ለመኖር አሜሪካ በተጨባጭ መደበቂያ ገነት የማትሆን መሆኗን የሚገልጽ ጠንካራ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች አሜሪካ ቢገቡ እንኳ ወደ እስር ቤት እንደሚጋዙ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ምክንያቱም ለፖሊስ ጥቆማ በማቅረብ ለፍትህ ይቀርባሉ፡፡

3ኛ) በዚህ ጥቆማ ላይ የሚደረግ ሰፊ የሆነ ተሳትፎ ኢትዮዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት የገዥው አካል አባላት አስቀያሚ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በመሄድ አሜሪካንን የሚረግጡ ከሆነ በአሜሪካ ባንኮች የደለበውን የባንክ ሂሳቦቻቸውን ብቻ አይደለም የሚያጡት፣ ሆኖም ግን የእራሳቸውን ነጻነትም እንደሚያጡ ጠንካራ የሆነ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ የመጨረሻዎቹን ቀናት በአሜሪካ እስር ቤቶች ሊያሳልፉ እንደሚችሉ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

4ኛ) የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች አሜሪካ የእነርሱ መደበቂያ ገነት ዋሻ እንደማትሆን እሰካመኑ ድረስ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሰብአዊ መብቶችን ጥሰት ከመፈጸም እኩይ ተግባራት ይታቀባሉ፡፡ ሁሉም የገዥው አካል አመራር አባላት በሚባል መልኩ እና የእነርሱ ታማኝ ሎሌዎች በአሁኑ ጊዜ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነ እና በኢትዮጵያ ለውጥ ከመጣ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን የፍርጠጣ ጉዞ በመሰረዝ ወደ ሌላ አዲስ ቦታ ጉዞ እንደሚያርጉ ይታመናል፡፡ እንደገና ቢያስቡ የተሻለ ይሆናል!

በኢትዮጵያ ወንጀል ፈጽመው ወደ አሜሪካ በመሄድ ተደብቀው የሚኖሩወንጀለኞች እንዳሉ እያወቁ አለመጠቆም እና ለፍትህ እንዲቀርቡአለማድረግእና እንዲኖሩም መፍቀድ በእራሱ ወንጀል ነው፡፡ ወንጀል ከተሰራ በኋላለወንጀለኞች ተባባሪ መሆን ወንጀል ከመስራት ጋር እኩል ነው፡፡እነዚህ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ፈጽመው በአሜሪካን አገር ተደብቀው የሚገኙ ወንጀለኞች ፍትህ እንደዘገዬ ባቡር መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

የጥቃት ሰለባዎች ለጥቂት ጊዜ መታገስ ይኖርባቸዋል፣ ሆኖም ግን በመጨረሻው ሰዓት ፍትህ በሙሉ ኃይሉ ታጅቦ ይመጣል፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 23/2014 ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የተማረው ይህንን ሀቅ ነው፡፡ ያ በአሜሪካ ግልጽ ተደብቆ እየኖረ ያለው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ/ት የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ በየዕለቱ ሊማርበት የሚገባ አብይ ትምህርት ነው፡፡ ያ ሁኔታ አሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትን እየደፈጠጡ ያሉ እና አሜሪካ ሄዶ ከመደበቅ ይልቅ ወደ ሌላ አዲስ ቦታ ለመሸሽ ዕቅድ የሚያወጡት ወንጀለኞች ሊማሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

ለሁሉም ኢትዮጵያውያን/ የሚሆን ፍትህ ትምሀርት

ባለፈው ሳምንት በፊላደልፊያ ግዛት ለ65 ዓመታት ከኖረ በኋላ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ የእስር ቤት ጥበቃ አባል በመሆን በታዋቂው አውሽውዝ እየተባለ ይጠራ በነበረው የጦር ካምፕ እና በሌሎች ቦታዎች ላይ በሰራው ወንጀል በጦር ወንጀለኛነት በመጠርጠር ጆሀን ብሪየር የተባለው የ89 ዓመት አዛውንት ወንጀለኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ብሪየር እ.ኤ.አ 1952 ወደ አሜሪካ በመሄድ ተፈናቃይነት በሚል ምክንያት ዜግነትን ጠይቋል፡፡ ይህ ወንጀለኛ 1.1 ሚሊዮን ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች ያለቁበትን ወንጀል ተሳታፊ ነበር ፡፡ የጀርመን ባለስልጣኖች ከ216, 000 በላይ የሚሆኑ የአውሮፓ አይሆዶችን በመግደል በሚል በጥፋተኝነት በመንጀል በሪየር ላይ ክስ መስርተዋል፡፡

ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የናዚ እስር ቤት የጥበቃ አባል የነበረው ጆሀን ሪየር ከሰራው ወንጀል በምንም ዓይነት መንገድ አይለይም፡፡ ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት የእስር ቤት ጥበቃ አባል ነበር፡፡ እንደ ብሪየር ሁሉ ወርቁም የሰብአዊ መብት እልቂትን ፈጽሟል ወይም ደግሞ ያልተነገረ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ነው፡፡ በማሰቃየት እና በመግደል በርካታዎቹን የግፍ ሰለባ አድርጓል፡፡ እንደ ሪየር ሁሉ ወርቁ በዩናይትድ ስቴትስ ጥገኝነት በጠየቀበት ጊዜ የእራሱን ማንነት እና ጥፋተኝነት ለመደበቅ እንዲሁም በቀይ ሽብር በተካሄደው እልቂት የእራሱን ሚና አሳንሶ ለማቅረብ ጥረት አድርጓል፡፡ ወርቁ እንደ ሪየር ሁሉ ከፍትህ ለማምለጥ ሙከራ አድርጓል፣ ሆኖም ግን እንደ ሪየር ሳይሆን ፍትህ በ10 ዓመታት የጊዜ ገደብ ውስጥ አሳድዳ ያዘችው፡፡

እውነታው ሲገመገም ግን በአሜሪካ የሚኖሩት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች በደርግ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት የቆሸሸ ስራ የሰሩት ብቻ አይደሉም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ሌሎች በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የህወሐት ወይም ተባባሪዎቻቸው በርካቶች አባላት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብት ደፍጠጣ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁሉም በተጠናከረ ጥቆማ እና ምርመራ እየተለቀሙ ለፍርድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የስድስት ዓመትም ይሁን የስድሳ አምስት ዓመታት እነዚህ የህወሐትም ይሁኑየደርግ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለፍትህ መቅረብ አለባቸው፡፡

በፍትህ ላይ የሚሰናሰል ምንም ዓይነት ነገር እንደሌለ ሊገነዘቡ ይገባል! በእነዚህ በመሀከላችን በነጻነት በሚኖሩ ወንጀለኞች ላይ የሚደረግ ልዩነት ማብቃት አለበት!

ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያትን አንድ ቀላል የሆነ ጥያቄ ላቀርብላቸው እወዳለሁ፡፡ ይህም የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ መምሪያ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ሰርተው በአሜሪካ አገር እራሳቸውን ደብቀው የሚኖሩ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ጥረት እያደረገ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያን/ት እነዚህን በደም የተጨማለቁ ወንጀለኞች ከእያሉበት በመጠቆም ለምርመራ መምሪያው ተባባሪ መሆን ሊበዛብን ይችላልን?

እራሳቸውን በአሜካ ደብቀው የሚኖሩ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን እየጠቆሙ ማሳወቅ ቀላል ነገር ነው፣ ጥቆማ በምታደርጉበት ጊዜ ስማችሁንመስጠትአይጠበቅባችሁም፡፡

በሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ወይም በሰብአዊ መብት ረገጣ ወይም በጦር ወንጀለኝነት በሚጠረጠሩ በውጭ ዜጎች ላይ ማስረጃ ወይም መረጃ ካላችሁ ICE HISየስልክ ቁጥር 1-866- 347- 2423 በመጠቀም እና online tip form ያጠናቅቁ፡፡

ጥቆማ በምታካሂዱበት ጊዜ ስም መስጠት አስፋለጊ አይደለም!

በሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና የጦር ወንጀለኞች ቡድን ያላችሁን ማስረጃ እና መረጃ በኢሜል አድራሻ VRV.ICE@ice.dhs,gov ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡

ለሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሰለባዎች እገዛ አለ፡፡ ለICE confidential victim/witness hotline toll free number at 1-866- 872- 4973 ጥሪ ያድርጉ፡፡

“ዩናይትድ ስቴትስ የእራሷን ሰላማዊ የዜግነት መብት ህጎቿ አታላዮች እና አጭበርባሪዎች ተበውዘው ከውጭ የሚመጡ ገዳዮች እና አሰቃዮች መደበቂያ ዋሻ አትሆንም“ (የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ጠበቃ ጆን ዋልሽ)

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ሰኔ 17 ቀን 2006 ዓ.ም

የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት የአራተኛ መደበኛ ስብሰባ የአቋም መግለጫ

$
0
0

በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ተቃዋሚነት ጎራ የተሰለፉ ኃይሎች በቅድሚያ ትግላቸውን በብሔራዊ ነፃነት ዙሪያ ያድርጉ!

እኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት ከሰኔ ፲፬ – ፲፭ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. (June 21 – 22, 2014) አራተኛ መደበኛ ስብሰባችንን በተሣካ ሁኔታ አካሂደናል። በሁለት ቀናት ጉባኤያችን የሥራ አስፈጻሚ እንዲሁም የቁጥጥርና ፍተሻ ኮሚቴዎች ያቀረቧቸውን የ፮(ስድስት) ወራት የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርቶችን አዳምጠን ጠቃሚ ውይይት አድርገናል። ድርጅቱ ያከናወናቸው መልካም ተግባሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በአፈፃፀም የታዩ ድክመቶች እንዲታረሙ በማስገንዘብ፣ ለድርጅቱ ዓላማ ዳር መድረስ የሚያግዙ የሚከተሉትን አቋሞች ወስደናል።
፩ኛ) የኢትዮጵያውያን ሉዓላዊነት፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም መከበር እና የግዛታዊ አንድነት መጠበቅን በተመለከተ፦

በዘረኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሉዐላዊ መብቱን የተነጠቀ፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅምም ለባዕዳን ተላልፎ የተሸጠና የአገሪቱ ግዛታዊ አንድነት ፈጽሞ ያልተጠበቀ መሆኑን ከቀረቡት ተጨባጭ ማስረጃዎች ተገንዝበናል። የአገሪቱን የባሕር በር ወያኔ ተገዶ ሣይሆን ወዶ እና ፈቅዶ ለሻዕቢያ ከሸጠው ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ የተነሣም ኢትዮጵያ መተናፈሻ የሌላት ዝግ መሬት ሆናለች። ስለዚህ ኢትዮጵያ የወጪ እና የገቢ ንግዷን ጂቡቲን በመሣሰሉ ትናንሽ አገሮች መልካም ፈቃድ ላይ እንዲመሠረት በማድረጉ በዕድገቷ ላይ ከፍተኛ መሠናክል ሆኗል። «ወደብ ለሌለው አገር ስለ ዕድገት አይታሰብም» ማለት ባይቻልም እንኳን፣ የዕድገት ግስጋሴው ግን ወደብ ካላቸው ጋር ፈጽሞ ሊወዳደር አይችልም።

ከዚህ በተጨማሪ በመሬት ስፋት አንፃር ከአየርላንድ ሪፑብሊክ ግዛት የሚበልጥ ከ፰(ስምንት) ሚሊዮን ሄክታር በላይ የሆነ የአገሪቱ ለም እና ድንግል መሬት ለ፺፱(ዘጠና ዘጠኝ) ዓመታት ለሕንድ፣ ለቻይና፣ ለፓኪስታን፣ ለግብፅ፣ ለጅቡቲ እና ለሌሎችም አገሮች ባለኃብቶች በጣም በርካሽ ገንዘብ ተሸጦ ገበሬው ጦም አዳሪ እና አገር-የለሽ ሆኗል።

ከምዕራባዊ የአገሪቱ ድንበር በቁመት ከሰሜን ወደ ደቡብ ፩ሺህ፮፻(አንድ ሺህ ስድስት መቶ) ኪ.ሜ.፣ በወርድ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ፶(ሃምሣ) እስከ ፷(ስድሣ) ኪ.ሜ. ጥልቀት ያለው ለሙ እና ድንግሉ መሬት ለሱዳን በገጸ-በረከትነት ተሰጥቷል።

በቋንቋ ላይ የተመሠረተው የፌደራል አገዛዝ አደረጃጀት የሕዝቡን ነባር የአንድነት እና የአብሮነት ስሜት ንዶታል። ይህንንም ወያኔ ሆን ብሎ ኃይልን በአካተተ ፕሮፓጋንዳ ጭምር በመታገዝ የሕዝቡን የአንድነት እና የኢትዮጵያዊነት ስሜት በእጅጉ እንዲሸረሸር አድርጓል።

በዛሬዋ ኢትዮጵያ ከዐማራ የጸዱ ክልሎች ለመመሥረት በተያዘው ዘር የማጽዳት እና ዘር የማጥፋት ዘመቻ ዐማራው የማይኖርባቸው ክልሎች ተፈጥረዋል።

ይህ አጠቃላይ ሁኔታ ተዳምሮ ሲታይ የሕዝቡ ሉዓላዊነት፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም እና ግዛታዊ አንድነት ያልተጠበቀ እና ያልተከበረ መሆኑን ለመገንዘብ አይከብድም። በመሆኑም ዛሬ በትግሬ-ወያኔ ተቃዋሚነት ጎራ የተሰለፉት ኃይሎች የትግል ሥልታቸውን ዳግም ሊመረምሩ ይገባል። በአንድ አገር ላይ ሰላም፣ ዕኩልነት፣ ዲሞክራሲ እና ፍትኅ የሚሠፍኑት በቅድሚያ አገሪቱ ኅልውናዋ ሲጠበቅ ነው። ስለሆነም «በቅድሚያ የመቀመጫዬን» ነውና፣ የተቃዋሚ ድርጅቶች የትግሉን አቅጣጫ በቅድሚያ በብሔራዊ ነፃነት ዙሪያ እንዲያደርጉት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።

፪ኛ) በዐማራው ላይ የሚካሄደውን ሁለንተናዊ ጥቃት በተመለከተ፦

ባለፉት ፶(ሃምሣ) እና ፷(ስድሣ) ዓመታት ብቻ ሣይሆን፣ ከዚያም ቀደም ሲል ጀምሮ፣ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሱ የውጭ እና የውስጥ አጥፊ ኃይሎች የመጀመሪያው የጥቃት ዒላማቸው የሚያደርጉት «ዐማራ» የተሰኘውን ነገድ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም የረዥም ዘመናት ታሪካችን አሻራዎቻችንም ሆነ ዛሬ በዐማራው ነገድ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ አጉልተው ያሣያሉ። ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ዐማራው በኢትዮጵያ ምድር የመኖር መብቱን ተገፍፏል፤ በአገሩ ውስጥ ተንቀሳቅሶ በፈለገው እና ባሻው የሥራ መስክ ተሠማርቶ የመሥራት የዜግነት መብቱን ተነጥቋል፤ በነገዱ ማንነት ብቻ ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንገድ በጅምላ ተሠልቧል፣ ጭፍጨፋ እና ግድያ ተፈጽሞበታል፤ እህቶቻችን እና እናቶቻችን ጡታቸው ተቆርጧል፤ ዐማራው ኃብት እና ንብረቱን ተነጥቆ፣ በአገሩ እንደ ባይተዋር ተቆጥሮ በግፍ ከመኖሪያው ተባርሯል።

ለአብነት ያህል ባለፉት የ፮ ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ካድሬዎች እና በተላላኪዎቻቸው ከተፈፀሙት ግፎች መካከል፦
· በመጋቢት ወር ሁለተኛ ሣምንት መጀመሪያ በአምቦ ከተማ አካባቢ፣ ዳኖ ወረዳ (ከምዕራብ ሸዋ) በመቶዎች የሚቆጠሩ የዐማራ ተወላጆች በኦሕዴድ ካድሬዎች አማካይነት «አገራችሁ አይደለም እና ውጡ» ተብለው ተባርረዋል፤ ፳፮(ሃያ ስድስት) ዐማሮች በአሠቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በተለይ አቶ ጌጡ ክብረት የተባሉት የዐማራ ተወላጅ በአሠቃቂ ሁኔታ በገጀራ ተቆራርጠው መገደላቸው ተዘግቧል።

· በግንቦት ወር «የአዲስ አበባን ከተማ መስፋፋት እንቃወማለን» በሚሉ አክራሪ የኦሮሞ ብሔረተኞች በሚመራው እንቅስቃሴ ተሣታፊዎች፦ በአምቦ፣ በዓለማያ፣ በነቀምት እና በሮቤ (መዳወላቡ) ዩኒቨርስቲዎች በሚማሩ የዐማራ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እና አልፎ ተርፎም ኢሠብአዊ ግድያ ፈፅመዋል። በተለይም በነቀምት ዩኒቨርስቲ ይማሩ የነበሩ ፯ ተማሪዎች በትግሬ-ወያኔ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ተገድለዋል። በመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ትማር የነበረችዋን የዐማራ ተወላጅ ከፎቅ ፈጥፍጠው ገድለዋታል። ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. በቅፅ ፪፣ ቁጥር ፳፩ ባወጣነው መግለጫችን በይበልጥ እንደተብራራው፣ በጊምቢ ከተማ እና አካባቢው (ምዕራብ ወለጋ) ከሚኖሩት ዐማሮች መካከል በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩት ቤት፣ ንብረታቸውን ተነጥቀው እንዲፈናቀሉ ሆኗል። በአጠቃላይ በጊምቢ ከተማ እና በአካባቢው ይኖሩ ከነበሩት ዐማሮች የንብረት ይዞታ ውስጥ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል። ከዚህ በተጨማሪም በግንቦት ፮ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. የአካባቢው የኦሕዴድ ካድሬዎች በዐማራ ተወላጆች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ፈፅመዋል። ከስቡ ስሪ ወረዳ (ምሥራቅ ወለጋ) ፪መቶ ዐማሮች ‹‹ይህ አገር የእናንተ አይደለም፣ አገራችሁ ግቡ፤›› ተብለው ኃብት፣ ንብረታቸውን ተነጥቀው ተባርረዋል። በወለጋ በአክራሪ ኦሮሞዎች እና በኦሕዴድ ካድሬዎች አማካይነት በዐማሮች ላይ በስፋት የሚፈፀመው ግፍ አሁንም ያልተገታ መሆኑን የመገናኛ ብዙሃን እስካለፈው ሣምንት መጨረሻ ድረስ የዘገቡት ጉዳይ ነው።

· በዘንድሮው ዓመት በ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ብቻ የትግሬ-ወያኔ ካድሬዎች «ሕገ-ወጥ ግንባታ አካሂዳችኋል» እና «ቦታችሁ ለልማት ይፈለጋል» የሚሉ ሠንካላ ምክንያቶችን በመደርደር፦ በአዲስ አበባ፣ በጎንደር፣ በባህርዳር፣ በደብረማርቆስ፣ በደሴ፣ በሐረር እና በሌሎችም ከተሞች በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን በግሬደር እና በሰው ኃይል አፍርሰዋል። የትግሬ-ወያኔዎች በየዓመቱ ይህን አረመኔያዊ ድርጊት የሚፈፅሙት ሆን ብለው የክረምትን ወቅት ጠብቀው ነው። የዚህ ድርጊት ቀዳሚ ተጠቂዎች ደግሞ ዐማሮች መሆናቸው ይታወቃል።

በአንድ ቃል በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ዐማራው በየዕለቱ የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈፀምበት፤ ቀኑ የጨለመበት፤ ድምፁ ሰሚ ያጣበት፤ ግፉን ተመልካች ያላስተዋለለት ሆኗል።

ሐ) በዐማራው ላይ በሚደርሰው ግፍ እና በደል የተቃዋሚ ድርጅቶች እርምጃ፦

በሚያሣዝን ሁኔታ «በኢትዮጵያዊነት» ስም የተደራጁት የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች እንኳን ስለዐማራው ችግር ተቆርቁረው የሚያደርጉት ረብ ያለው ሥራ የለም። በዐማራው ላይ የሚፈፀሙትን ግፎች እና በደሎች «በዐማርኛ ተናጋሪዎች ላይ የደረሰ» እየተባሉ የሚሰጡት መግለጫዎች ዛሬ የዐማራውን ኅልውና ሆን ብለው የሚክዱ መሆኑን እና ለችግሩም የሚሠጡትን ዝቅተኛ ግምት በገሃድ ያሣያል።

መ) ዐማራው ኢትዮጵያዊነቱን ሣይለቅ በዐማራነቱ የመደራጀቱ አስፈላጊነት፦

አሁን ያለውን «የዐማራውን ጉዳይ ሆን ብሎ የማጣጣል» ሁኔታ መለወጥ የሚችለው፣ የዐማራው ልጆች ተደራጅተው «አለንልህ» ሲሉት እና ከጠላቶቹ አንፃር አቻ ወይም ጉቢ ኃይል ሲፈጥሩ ብቻ እንደሆነ የምክር ቤቱ አባላት ባደረጉት ሠፊ ውይይት ሙሉ በሙሉ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ስለሆነም ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የጀመረውን ዐማራን የማደራጀት ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል፤ አባላት እና አካላትም ሳይሰለቹ እና ሳይታክቱ የእያንዳንዱን ዐማራ በራፍ በማንኳኳት የድርጅቱ አባል እንዲሆን፤ ድርጅቱንም በዕውቀት፣ በገንዘብ፣ በመረጃና በመሳሰሉት እንዲደግፍ እንዲያደርጉ ጥሪውን ያስተላልፋል።

 

moreshዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

 

የወያኔን የጥፋት ድግስ እናምክን!

$
0
0
Weekly_Editorial_Tumbnailኢትዮጵያን የሚገዛው ጉጅሌ ሀገራችንን እየወሰደበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ አሳሳቢ ከመሆን አልፎ የአደጋውን መራራ ፍሬ ማየት ከጀመርን ሰነበትን። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወሳኝ ከሆነው የወደፊቱ የጋራ ጥቅማቸውና ህልውናቸው በበለጠ ልዩነታቸውና ያለፈ ታሪካቸው እንደዋናው ነገር እየተቆጠረ ለሚሰበከው ስብከት የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ባይሆን ኖሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት በደረሰ ነበር።
ህወሃት በህዝቡ ውስጥ የኖረውን ልዩነት የጠብ፣ የግጭትና የመፈራራት መሰረት በማድረግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ካለው ምኞት የተነሳ በመደዴ ካድሬዎቹ አማካኝነት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ በማቃቃር እኩይ ተግባር ላይ ተጠምዶ ይገኛል።
ህወሃት ይህን የማጋጨት ስራ በተለይ በስልጣን የመቆየት ፍርሃት ባባነነው ቁጥር የሚጠቀምበት መሳሪያ አድርጎታል። በባህርዳር ላይ የብሄረሰቦች ኳስ ጭዋታ ውድድር ምክንያት አድርጎ፣ መደዴ ካድሬዎቹን አሰማርቶ ስታዲዮም ውስጥ ኦሮሞዎች እንዲሰደቡ ካደረገ በኋላ ነገሩን ከማረጋጋት ይልቅ በኦሮሞኛ የቴሌቪዥንና ሬድዮ፣ ኦሮሞዎች በአማራዎች ተሰደቡ ብሎ ያስነገረው ለምንድን ነው? ከዚያ በኋላ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ቁጣና ጠብ ለመቀስቀስ ብሎም በዚህ ጠብ ውስጥ ገላጋይ በመምሰል የአንዱ ብሄር ጠባቂ መስሎ ለመታየት ጉዳዩን ባልተረዱ የዋሆች ውስጥ ለመግባት ይፈልጋል። በአማራ ተወላጆች አካባቢ እኛ ከሌለን ኦሮሞ ይፈጇቹኋል፤ በኦሮምያም በሶማሊያም እንዲሁ በተዘጋ በር ውስጥ በተቃራኒው ዘረኝነትንና መከፋፈልን በመስበክ ንጹሃኑ ህዝብ ከፍርሃት ተነስቶ ተገዥ ደጋፊዎቹ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ መሆኑንም ያልገባቸው የዋሆች ይኖራሉ። ህወሃትንና ባህርዩን በቅጡ ለምናውቀው ወገኖች ግን ይህ ተንኮሉ ትልቅ ሚስጥር አይደለም።
የጉጅሌው ቡድን የራሱን ስልጣንና የዝርፊያ ኢኮኖሚ ኮርቻ ለማደላደል እስከረዳው ወይም የሚረዳው መስሎ እስከታየው ድረስ ደሃ ገበሬዎችን ማፋጀትን፣ ህዝብን እርስበርስ ማናከስን፣ የቂም መርዝ መዝራትን የሚያየው እንደ ፖለቲካ ጥበብ ነው።
ጉጅሌው ብልጠት መስሎት የጎሰኝነትንና የማንነትን ደመነፍስ የሚነካ ፕሮፖጋንዳ በህዝቡ ውስጥ በመንዛት ሊያደርስ የፈለገው ጥፋት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ስላልሰራለት የራሱን ሎሌዎችና ተካፋይ መደዴ ካድሬዎችን በማሰማራት የጭካኔ ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኑን በብዙ መረጃዎች አረገጋግጠናል። በአሁኑ ወቅት በየቦታው የሚካሄደውን የህዝብ ማፈናቀልና ግጭት የሚመራው ራሱ ህወሃት ያሰማራቸው ካድሬዎች እንጂ በራሱ በህዝቡ ተነሳሽነት እንዳልሆነ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል። በዚህ ሳይጣናዊ አካሄድ ለምትደርሰው ለያንዳንዷ ጉዳት ሀላፊነት የሚወስደውም ራሱ ህወሃት መሆኑን ግንቦት 7 አጥብቆ ያምናል።
ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ የሚደግስልንን የጥፋት ድግስ ለማምከን የየብሄረሰቡ ልሂቃን ሁሉ አንድ ላይ ሆነን ህዝባችንን እንድንታደግ ግንቦት 7 ለሁሉም የነጻነት ሃይሎች ጥሪውን ያቀርባል።
ግንቦት 7 በዚህ የህወሃት የጨለማ መንገድ ላይ የሚያበራውን የብርሃን ችቦ ይበልጥ በማብራት ላይ ይገኛል። ሁላችንም በምናገኘው የብርሃን ሃይል ጨለማው ላይ እያበራን ከማሳየት አልፈን ወደ መቃብሩ ልንገፋው ይገባል።
ግንቦት 7 በኢትዮጵያ የማንነትና የብሄር ብሄረሰብ ጉዳዮች በሰለጠነ መንገድ እና በመደማመጥ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደረግ መንገድ መፍታት እንደሚቻል ያምናል። ይልቁንም የወደፊቱ የህዝባችንና የሀገራችን ጥቅም ይበልጥ የሚከበረው በስብጥርነታችን ላይ በምንገነባው አንድነት መሆኑን ያምናል።
የተከበራችሁ የአገራችን ዜጎች የነጻነታችን ጊዜ ቅርብ ነው። ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ ያዘጋጀልንን የጥፋት ድግስ፣ ሀገራችን የጋራ ጠላት በመጣባት ጊዜ ሁሉ እንደምታደርገው በአንድ ላይ ታግለን የጋራ ታሪክ እንሰራ ዘንድ የዘወትር ጥሪያችን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!
Source: ginbot7

የታላቁን ወር ረመዳን መግባት አስመልክቶ ከታሳሪ ጀግኖቻችን የተላለፈ አጭር የ‹‹እንኳን አደረሳችሁ›› መልእክት –ከድምጻችን ይሰማ

$
0
0

የታሰሩት ኮሚቴዎች

የታሰሩት ኮሚቴዎች


አርብ ሰኔ 20/2006

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው!
ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን!
እንኳን ለ 1435 ዓ.ሂ ታላቁ የረመዳን ፆም አደረሰን!

የዘንድሮ ረመዳን በመብት ትግላችን ውስጥ ሆነን ያገኘነው ሶስተኛው ረመዳን ነው፡፡ መብታችንን ለማስከበር በጀመርነው ሰላማዊ ትግል ውስጥ ያሳለፍናቸው ረመዳኖች አንድነታችንን ለመበታተን ያሰፈሰፉ ሃይሎች የበረቱበት እና ህዝባችንን በፍርሃት ለማሸማቀቅ ቀን ከሌት የተደከመባቸው ነበሩ፡፡ አካላዊ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ በህዝባችን ላይ የስነ ልቦና ሽንፈት ለመፍጠር ቀን ከሌት የተሰራባቸው ጊዜያትም ነበሩ፡፡ መጪው ረመዳን እነዚያን ትላልቅ ፈተናዎች ተሻግረን ዛሬም በአንድነታችን እና በትግላችን ላይ ፀንተን የምንገኝበት ወቅት መሆኑ ወሩን በልዩ ትኩረት እንድንቀበለው የሚያበረታታን ነው፡፡

በዘንድሮው ረመዳን በተዘነበለ ፍትህ ምክንያት በርካቶች የቀደሙ ረመዳኖችን አብረው ከፆሟቸው የቤተሰብ አባላት ጋር አይፆሙም፡፡ የዜግነት መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ በሞት፣ በስደት እና በእስር የተለያዩ ቤተሰቦች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ይህም ሆኖ ግን ዛሬ ገሃድ ሆኖ ያየነው መጪው ጊዜ ለዲን የሚከፈል መስዋእትነትን የመቀበል አቅማችን የደነደነ እና ለድልም የበለጠ የቀረብን መሆናችንን አመለካች መሆኑን ነው፡፡

ይህንን ለማለት ያስቻሉን በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እዚህ ሳንጠቅሰው የማናልፈው አንዱ ምክንያታችን ግን ለታሪክ ግብኣት ይሆን ዘንድ በምንታደመው የፍርድ ቤት ሂደት ላይ በምስክርነት የሚቀርቡ ወንድም እና እህቶቻችን ላይ ያስተዋልነው አስደናቂ በራስ የመተማመን መንፈስ ነው፡፡ ለትግሉ ያላቸው የቁርጠኝነት መንፈስ በእርግጥም የሚደንቅ ነው፡፡ ምስክሮች እየሰጡ ያለው ምስክርነት ለእኛ የፍርድ ሂደት ካለው ታሪካዊ ፋይዳም ባለፈ ተወክለንበት ስንንቀሳቀስበት የነበረው ሰላማዊ ህዝባዊ ትግል ምን ያክል ህዝባዊ መሰረት እንደያዘ የሚያረጋግጥ ክስተት ነው፡፡ ህዝባችን ዛሬም መስዋእትነት በከፈለለት ትግል ፅኑ እምነት እንዳለውም ያሳያል፡፡ ይህንን ከታሰርን በኋላ በነበሩት ወቅቶች በአካል ለመታዘብ የቻልንባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው፡፡ በመላው ሃገሪቱ፣ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ከእኛ መታሰር በኋላ እየተካሄዱ ያሉ ግዙፍ ተቃውሞዎችም በምስክሮቻችን እና ለጉብኝት በሚመላለሱ ወገኖቻችን ላይ እንዳየነው ሁሉ ለትግሉ ካላቸው እውነተኛ ተቆርቋሪነት የሚመነጭ መሆኑን ማወቅ ለእኛ ከምንም በላይ ትልቅ እርካታ የሚሰጥ ክስተት ነው፡፡

የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች!

ኢስላማዊ ስነምግባሮች ይበልጥ ጎልተው ለሚወጡበት እና የለውጥ ዋነኛ ጊዜ ለሆነው ለተከበረው ወረሃ ረመዳን በድጋሚ እንኳን አደረሰን፡፡ ረመዳን ለቤተሰብ እና ማህበረሰብ ለውጥ ዋነኛ መነሻ ወቅት ነው፡፡ በኢስላም ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ክስተቶች በዚሁ ወርሃ ረመዳን ተከስተዋል፡፡ ለእኛም ትግላችንን አስፍተን ለመቀጠል ከረመዳን የተሻለ አጋጣሚ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ያነሳናቸው ሶስት ቀላል ጥያቄዎች ሙሉ ለሙሉ አልተመለሱም፡፡ መንግስት የሚሊዮኖችን ድምፅ በማፈን የወሰዳቸው ህገ ወጥ እርምጃዎች በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ተቀባይነት አጥተዋል፡፡ ባለቤትነቱ የሰላም ወዳዱ ሰፊ ህዝበ ሙስሊም የሆነው መንፈሳዊ ድርጅታችን ቅቡልነት ባጣ ቀበሌኛ የሹመት ሥነ-ሥርዓት አማካኝነት በመጡ ህገ-ወጥ ሹማምንት እጅ ወድቋል፡፡ ይህም በመሆኑ መንግስት ከድርጊቱ እንዲታቀብ፣ እርምጃውንም በድጋሚ እንዲያጤነው ህዝበ ሙስሊሙ ያደረጋቸው ያላሰለሱ ጥረቶች ሰሚ ጆሮ በማጣታቸው ሳቢያ የሹመት ሥርዓቱንም ሆነ ህገ ወጥ ሹማምንቱን ቅቡልነት ነፍጓል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸው ህጋዊ የመብት ጥያቄዎች አለመመለሳቸው ሳያንስ የመሰረታዊ መብቶቻችን ንጥቂያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቀጥሎ መገኘቱ ጉዳዩ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ትኩረት በሚያሻው ወቅት ላይ መድረሳችንን ያመላክታል፡፡ ይህ የመብት ጥሰት እየጨመረ መቀጠሉም ህዝበ ሙስሊሙን ተግባራዊ የሆኑ ጫናዎችና እርምጃዎችን እንዲወስድ የሚያስገድድ እንደመሆኑ መጠን በአገሪቱ ከሚካሄዱ ሁለንተናዊ ማህበረ ፖሊቲካዊ ሂደቶች ጋር ትግላችንን በመቃኘት ለተሻለ ውጤት መታገል የግድ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህ ረመዳንም ለእኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ፈተናው በውጤት የሚለወጥበት ጊዜ እንዲሆን እንመኛለን፤ እንደሚለወጥም በአላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ላይ ያለን እምነት ፅኑ ነው!

በመጨረሻም በረመዳን ቤተሰባዊ አንድነታችንን በማጠናከር የተለመደ ኢስላማዊ እና ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት ባህላችንን በመጠቀምና ይበልጥም በማጠንከር ከመካከላችን ለችግር የተጋለጡ፣ በተለይም መብት በመጠየቃቸው ምክንያት ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመንከባከብ ላይ አደራ እንላለን::

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በረመዳን ከሚጠቀሙት ያድርገን!
========================================

ትግላችን እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

የአማራን ህዝብ በማጥፋት ወያኔና ተቃዋሚው በጋራ እየሰሩ ነው – ከወለጋ ከቄለም አካባቢ እና ከግንቢም ቁጥራቸው ከ2 ሺ እስከ 3 ሺ የሚደርስ የአማረኛ ተናጋሪዎች ተባረሩ

$
0
0

amharas-displaced-guraferdaአቶ አዲሱ አበበ አርብ ጁን 20 2014
welkait.com

በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ያስተላለፉትን ቃለ መጠይቅ ቃል በቃል በጽሁፍ ገልብጨ ከአውዲዮው ጋር እንድልክላችሁ ያነሳሳኝ ሆን ተብሎ በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ዘር ማጥፋት፣ ድርጊቱን ቀጥታ በሚፈጽሙት አካላት ብቻ ሳይሆን የወያኔ ትግሬዎችን የጎሳ ፖለቲካ እንቃወማለን የሚሉ ሳይቀሩ ሆን ብለው የተሰሳተ መረጃ በመስጠት በአማራው ህዝብ ላይ የክህደት ስራ እየሰሩ ለመሆኑ ለመጠቆም እና አንባቢም ቃለ መጠየቁን በማንበብም ሆነ ቃለ መጠየቁን ከተለያዩ ድህረገጾች በመስማት ያራሱን ፍርድ እንዲሰጥ ነው። በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ በወያኔና የሱ ተናካሽ ውሾች በሆኑ የብሄር ድርጅቶች ብቻ ሳይሆን፤ በኢትዮጵያ ስም የተደራጁ ፓርቲዎች፣ ድርጅቶች፣ ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ ድህረገጾች ወዘተ ጭምር በጋራ የሚተባበሩበት ለመሆኑ የሚጠይቅ አይምሮ ያለው ያስተውለው።

ተፈናቃዮች አማራ ናችሁ ተብለንከወለጋ ተፈናቀልን እያሉ፤ አቶ አዲሱ አበበ አማረኛ ተናጋሪዎች ተፈናቀሉ ይላሉ። በአማረኛ ተናጋሪነት ከሆነ ከወለጋ የተጠየቁ አፈናቃዮችኮ በአማረኛ ነው ከአቶ አዲሱ አበበ ጋር የሚነጋገሩት፤ አቶ አዲሱ አበበ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋዜጠኛ ስለሆኑ፣ እንዲሁም የአሜሪካ መንግስት ከምንም ጊዜ ይበልጥና ከማንም በላይ የወያኔ ትግሬዎችን መንግስት በገንዘብና በሰው ሀይል ስለሚረዳ አቶ አዲስ አበበ ከቀጣሪያቸው አቋም ውጭ ሊሆኑ አይችሉም ብንል፡ ከአማራው ኪስ በሚወጣ መዋጮ የሚንቀሳቀሱ እንደ ኢሳትና ሌሎችም በየሀገሩና በየከተማው የተቋቋሙ ሬዲዮ ጣቢያዎችና ድህረገጾች፣ የአማራው ህዝብ አማራ በመሆናችን ብቻተነጥለን፤ ሀብትና ንብረታችን ተዘርፎ፣ ተደብድበን፣ ከፊሎችም ተገለው ከሞት አምልጠን እዚህ ደረሰን ሲሉ፣ ”ከባለቤቱ ይበልጥ ያወቀ ቡዳ ነው” እንደሚባለው፤ አማራ ስለሆኑ አይደለም፤ አማረኛ ተናጋሪ ስለሆኑ ነው ብለው በአማራው ህዝብ ላይ አማራ በመሆኑ ብቻ ወንጀል እንደላልተፈጸመበት አድርገው የተዛባ ማስተባበያ ለህዝብ ጀሮ ያቀርበዋል።  ከዚህ ተጨማሪ ስለዚህ መፈናቀል የዘገቡ ኢትዮጽያዊ የሚባሉ ድህረገጾችና ሬዲዮ ጣቢያዎች ብዙም ባይሆኑ፣ ለይስሙላ የዘገቡም ዘግበውም በነጋታው ከድህረገጻቸው ያነሱ ድህረገጾችንም ታዝቤአለሁ።

ብአዴን ማን ነው ሲሉ አቶ ገብረመድህን አርአያ ሰፋ ያለ መረጃ ሰጠውናል። ብአድኖች ከመጀመሪያው ”አማራ ህዝብ ጠላት አይደለም” ያሉትን የገደሉና ከዚያም በአማራው ህዝብ ላይ በየክፈለሀገሩ እየዞሩ የአማራውን ህዝብ ነጥለው በመሪነት ያስገደሉና ያሰደዱ ለመሆኑ መረጃዎች አሉ። አሁንም ከዚህ ቃለ መጠየቅ እንደምንረዳው የኦሮሞና የአማራው ክልል ባለስልጣኖች ይሄን ያህል አፈናቅሉ፤ ይሄን ያህል ግደሉ፤ ይሄን ያህል ደግሞ ለፖለቲካ መልሱ እየተበሉ በእቅድ የሚፈጽሙት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል መሆኑን ቃለ መጠይቁ ይጠቁማል።

በአቶ አዲሱ አበበና በሬዲዮ ጣቢያቸው ላይ እንዲያውም ስለመፈናቀሉ በመዘገባቸው ባለውለታ እንጂ ቅሬታ የለኝም። ሌሎች በተቃዋሚነት ተሰልፈናል የሚሉ ግን አሁንም ቢሆን ለይስሙላ የሚጠይቁት ”ወደ ቀያቼው እንዲመለሱ” የሚል ነው። አንድ ሰው አማራ በመሆኑ ብቻ ሀብት ንብረቱ ተዘርፎ፤ አቅመ ደካማ የሆኑ ሚስት ልጆቹ፣ በእድሜ የገፉ እናት አባት ተገለው፤ ቤቱ ተቃጥሎ ”ወደ ቀያቸው ይመሰለሱ” የሚለው ፍርድ በአማራው ህዝብ ላይ ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና ማጥዳት ወንጀል ተባባሪነት ካልሆነ በቀር ትክክለኛ ፍርድ አለመሆኑን ህሌናችሁ ፍርድ ይስጥ።

አንድ ሰው አማራ በመሆኑ ብቻ ሀብት ንብረቱን ተቀምቶ፣ የተገደለው ተገሎ የሚፈናቀል ከሆነ፤ አንድ ከአማራ ወላጆች የተወለደ ኢትዮጵያዊ መብቱ ተከብሮ ለመኖሩ የጊዜና የቦታ አለመገጣጠም ካልሆነ በቀር ዛሬ ወለጋ በሚኖሩ አማሮች ላይ የደረሰው መገደልና መፈናቀል በሱ ወይም በሷ ላይ እንደማይደርስ ምንም አይነት መተማመኛ የለም። ብሄረተኝነት የግለሰቡን ብሄር አንጂ የግለሰቡን ሰብአዊ ባህሪ አይቶ ይህ ደግ ነው ተወው፣ ያ ክፉ ነው በለው አይልም። ስለዚህ ማንም ከአማራ ወላጆች የተወለደ ሁሉ በወያኔ ትግሬዎችና የነሱም ተናካሽ ውሾች በሆኑ የብሄር ድርጅቶቹ አንዲሁም ከሀገር ውጭ መረጃ በማጣመም፣ በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን ወንጀል በማስተባበልና ማእቀብ በማድረግ ከወያኔ ትግሬዎች ጋር በአጋርነት የተሰለፉ ሬዲዮ ጣቢያዎችና ድህረገጾች የአማራን ህዝብ በማጥፋት ወንጀል እየተባበሩ ለመሆኑ ከኔ ጽሁፍ ይልቅ ትንሽ ማሰብ የሚችል ጭንቅላት ያለው ሰሞኑን በወለጋ በአማራው ህዝብ ላይ በተፈጸመው ግድያና መፈናቀል ድህረገጾችን አይቶ፣ ሬዲዮ ጣቢያዎችን አዳምጦ ይፍረድ።

ከግለሰብ የተወረወረ ትዝብት

ቃለ መጠይቁን ለማዳመጽ ይሄንን ይጫኑ፣ በጽሁፍ ለማንበብ ከታች ያለውን ይመልከቱ

http://www.ethiopatriots.com/sound/AmarawMefenakel140619Welega.mp3

አሜሪካ ራዲዮ ጣቢያ ከተፈናቃዮች ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ፣

ጁን 20 2014

ከወለጋ በተለይም ከግንቢና ከቄለም ከግንፍሌ ወረዳ ተባረርን ደግሞ ቤት ንብረታችን ተቃጠለ ያሉ የአማረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት ባህር ዳር እንደሚገኙ ይናገራሉ። ቁጥራቸው እስከ 3000 ይደርሳል የሚሉ እነዚህ ተፈናቃዮች የአማራው ክልል አስተዳደር መፍትሔ እንዲፈልግላቸው በመጠባበቅ ላይ መሆኑንም ተመልክቷል። የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት በበኩሉ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ100 በታች ነው ይላል። አዲሱ አበበ ተፈናቃዮችንና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት አነጋግሮ ተከታዩን አጠናቅሯል።

አቶ ጋሻው ፈቃደ የተባሉና ሌላ አንድ ስሜ አንዳይገለጽ ያሉ ተፈናቃይ ጨምረን አወያየን፣ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉት የምእራብ ወለጋ ዞን ተፈናቃዩ ከወር በላይ ሆኖናል ብለው ይጀምራሉ።

አሁን 1 ወር ከምናምን እየሆነው ነው ምክንያቱ የድሮ ታሪክ ነው የሚያነሱት፤ ሚኒሊክ እንደዚህ አድርጎን፣ እንዲህ አድርጎን ነው የሚሉት፤ በጣም አሳደዱነ፤ የከተማው ህዝብ እንዳለ ወጥቷል እንደገና ባለስልጣኖች ደግሞ አሉበት፡ ፖሊሶች እነዚህ አድማ በታኝ የሚባሉት አብረው ነው ሲዘርፉና ሲደበድቡን የዋሉ ማለት ነው። አማራ የተባለውን።

እኮ ምክንያቱ ምንድነው አሉዋችሁ፤ በትክክል?

ምክንያቱ የድሮ ታሪክ ነው፣ እነሱ እንገነጠላለን ምናምን ነው የሚሉት፤ እራሳችን ነጻ እናወጣለን፤ አማራን አንፈልግም፣ አማራ ይውጣልነ ነው። እና ህይወታችን የተረፈው በስንት ነገር ነው። ኮርኒስ እየገባን ጫካ እየገባን በስንት ነገር ነው። ብዙ ሰው ሞቷል።

ስንት ጊዜ ሆኖት እርሶ ወለጋ ሲኖሩ?

እኔ 11 ዓመቴ ነው፣ ወደ 5 ቤተሰብ አስተዳድራለሁ፣ ሱቅም ነበረኝ፣ ጣቃ አከፋፍል ነበር፣ ጣቃውን እንዳለ ዘርፈውኛል።

ስንት ሰው ከዚያ ተሰደደ? ከወለጋ ከግንቢ በተለይ? እርሶ ካሉበት

ቢያንስ ከ8000 የማያንስ ህዝብ ነው።

ባህርዳር የአማራው አስተዳደር አለ እዚያ ደግሞ ሄዳችሁ አላመለከታችሁም? ምን አሉዋችሁ?

ወደ ቤታችሁ ተመለሱ ነው የተባልነው፣

ወዴት ወደቤታችሁ?

ወደነበራችሁበት ተመለሱና እናረጋጋለን ምናምን ነው ያሉን፤ እነሱ ደግሞ አሁን እራሱ አልተውም

ሌላው አቶ ጋሻው ፈቃደ ይባላል፤ የመፈናቀላችንን ምክንያት በውል አልተረዳነውም፤ ይሉና ይቀጥላሉ።

ምክንያቱ ምን  እንደሆነ እኛ ያወቅነው ጉዳይ የለም፣ ለኛ በኳስ ነው ምናምን ነው የሚሉት

ኳስ ማለት

በባህርዳር ከተማ ላይ ኳስ ጨዋታ ተካሂዶ ነበር፣ የአማራ ክልል ህዝብ ኦሮሞዎችን ጋላ! ጋላ! አሉን፣ እና የኛ ሰው ደግሞ የተደበደበ ሰው አለ። እያሉ ነው ለኛ ሲናገሩት የነበረው።

እናንተ እዚያ አልሄዳችሁም? ለምን እናንተን ውጡ አሉዋችሁ ብዬ ነው?

እኛም ግራ የገባን እኮ እሱ ነው፣ ከዚያ ወደዚያ ሰው ተይዞ መመከር እያለበት ለምን በስመ አማራ ለምን እኛ ይሄን ያክል መበደል አለብን የሚለውንኮ አቤቱታ ስናቀርብ አቤቱታችንን እዚህ ደግሞ አልቀበልም ያሉ።

ስንት ሰው ነው በጠቅላላ የተፈናቀለ ወይም እንዲወጣ የተደረገው?

ቢያንስ ከግንቢ ከተማ ብቻ አንድ 3000 ሰው ይሆናል። ያልወጣም እዚያ የቀረም ህዝብ አለ፤ በቃ ህይወታችን እስከሚያልፍ መጠበቅ ነው እንጂ ያለብን እንዴት እናደርጋለን?

ሌላ ሰው ሳናግር እንዲሁ ከ2000 ሰው በላይ ነው የሚሉኝ፤ ይሄን ያህል ሰው ሲፈናቀል እዚያ አካባቢ አስተዳደሩ፤ የፖሊስ ጣቢያው፤ የመንግስት ባለስልጣናት የሉም? ወይም እናንተ ሄዳችሁ አቤት ለማለት አልሞከራችሁም? አቶ ጋሻው።

ሄደን አቤት ብለናል፤ ግን ሊቀበሉን አልቻሉም፣ ሄደንም አመልክተናል አቤቱታችንን እያቀረብን ነው እኛ ያለነው አሁን ለነሱ

ለማን ነው አቅርበን እንቢ አሉን የሚሉኝ?

ርእሰ መስተዳደር ሄደን ነበር እኛ፣ ርእሰ መስተዳደሩ

ለማን ነው አቅርበን ነበር የሚሉኝ፣ ለባህርዳር?

አዎ ባህርዳር ከተማ ላይ፣

እና ምን ተባል…?

ከ5 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ተቀጠርን፣ 8 ሰዓት ደግሞ ውጡ አሉን።

ሰው ምረጡ ተብሎ ሰው መርጣችሁ ከላካችሁ እንዴት እንደገና ውጡ ይላሉ ብዬ ነው። ማ ቢሮ ነበር ልትገቡ የፈለጋችሁ?

እዚያ እርሰ መስተዳደሩ ላይ፤ በቃ አስተዳደሩ፤ እሱን ፈልገን ነበር እኛ ርእሰ መስተዳደሩን

ፕሬዜዳንቱ ቢሮ ነው ወይስ ምክትላችው ወይስ ጸሀፊ ጋ ወይም

አዎ፣ ርእሰ መስተዳደሩ ቢሮ ነው እንጂ

ለመሆኑ የአካባቢው ባለስልጣናት ምን አሉ? እናንተስ አቤት ብላችሗል? ላልሁት ጥያቄ የጸጽታ ሀላፊ ናቸው፤ እርሳቸው ሁሉንም ያውቃሉ፤ በማለት የአንድ ሰው ስምና ቁጥር ሰጠውኝ ደወልሁ

አቤት፤ አቤት

እንደምን ዋሉ? አቶ አወቀ

አቤት፤ ማን ልበል?

አዲሱ እባላለሁ፤ ከዋሽንግቶን ነው የምደውለው፤ ከአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ

ይሄን ስልክ አላውቀውም፤ ከየት ነው?

እንዳልሁት ከአሜሪካ ነው የምደውለው፤ ከአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ፣ ከዋሽንግቶን፣ ከቪኦኤ

ከዚያ አካባቢ ተፈናቀልን የሚሉ ሰዎች ኢንተርቪው አድርጌ ነበር፤ እና እርሶ የሚያውቁትን ነገር ቢነግሩኝ?

ከየት?

ከቄለም አካባቢ፤ ከግንቢም አማረኛ ተናጋሪዎች

የት ሄድን? ወዴት ተፈናቀልን አሉ?

ተባረው ባህር ዳር ጎጃም ውስጥ ነው  ያሉት፤ ሰፈራ ጣቢያ አግኝተው?

ማን ነው ያባረረው?

እርሶ የሚያውቁትን እንዲነግሩኝ ነው አቶ አወቀ፤ አሁን የምደውለው ነዋሪዎችም ባለስልጣናት ናቸው ያባረሩን ይላሉ፤ ሁለቱንም

እነማን ናቸው እነሱ መጀመሪያ?

የሰዎቹን ስማቸውን ነው የሚፈልጉት?

አዎ

በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው፤ ነገረ ግን ጥያቄዬ ከቄለምና ከግንቢ አካባቢ እንዲባረሩ ሆኖዋል ወይ? እንዲወጡ ተደርጓል ወይ? የጸጽታ ክፍሉ የሚያውቀው ነገር አለ ወይ? እምሎት።

እኔ የጸጽታ ክፍል አይደለሁምና ከህዝብ ነኝ፤ እና ማን ነው ያለ? መጀመሪያ ንገረኝ፣

እርሶ ……

ከዚያ በሗላ ነው የማውቀውን የምስጥህ እንጂ የሆነም ያልሆነም ነገር ልሰጥህ አልችልም ማነው ያለህ?

አቶ አወቀ የጸጽታ ሀላፊ ናቸው ተብሎ ነው ስልኩ የተሰጠኝ ልክ አይደለም?

ውሸት ነው፤ የጸጽታ ሀላፊ አይደለሁም። እኔ ሌላ ስራ ነው ይዤ ያለሁ፤ የጸጽታ ሀላፊውን ልትጠይቅ ትችላለህ።

እርሶ በምን ውስጥ ነው ያሉት? ስለዚህ ጉዳይስ የሚያውቁት ጉዳይ የለም።

እኔ የድርጅት ጽህፈት ቤት ነኝ

የተባረሩ አማረኛ ተናጋሪዎች ስለመኖራቸው አያውቁም?

የተባረሩ የሉም። ያባረረም የለም።

የእርሶ ቢሮ ሀላፊነቱ ምንድን ነው? አቶ አወቀ፤ የድርጅት ጉዳይ ሲሉ ምንድን ነው የምትሰሩት?

የኦህዲድ የድርጅት ጉዳይ ነው

እና የኦህዲድ ጽህፈት ቤት ይሄን አያውቅም?

የተባረረ ሰው የለም እያልሁህ እኮ ነው፣ በራሳቸው ፍላጎት ሊሄዱ ይችላሉ እንጂ ያባረረ ሰው የልም፡ እያልሁህ እኮ ነው፤ ቄለብ ወለጋ ስትል ከቄለብ ወለጋ የተባረረ ሰው የለም። እንደዞኑ የምናውቀው ነገር የለንም።

ከትናት በስቲያ ማክሰኞ ወደ ኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ደወልሁና የቢሮ ሀላፊዋን ወይዘሮ ራዲያ ኢሳን አገኘሁ። ምንም የምናውቀው ነገር የለም አሉኝ። ዛሬስ ያውቁ እንደሆን ብዬ እንደገና ወደ ወይዘሮ ራዲያ ቢሮ ደወልሁ፣ በቁጥሩ ላይ ነው ያልተስማማነው እንጂ ማወቁን ያውቃሉ።

ሁለት ሺ ሶስት ሺ ተፈናቀለ የምትለው አይደለም

ከነሱ የሰማሁትን ነው

መቶ የማይሞሉ ሰዎች ናቸው

ከሁለት ቦታ ነው የሰማሁት ከግንቢና ከቄለም

አዎ ቄለም ወለጋ አሼ ቀበሌ ነች አይደለ፤

አዎ አሼ ቀበሌ ነው ያሉኝ

የሆነ ወንጀል ተፈጽሞ ነበረ

ማን ነው የፈጸመው?

እንድ ሰው ሞቶ ነበር፤ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ የሆነ ቀጥሎ ደግሞ ሁለት ሰዎች ባልታወቁ ሰዎች ተገለዋል፤ ከፍርሀት ተነስተው ነው እነዚህ ሰዎች ክልል ሶስት የሄዱት፤ መንግስት ..

ከፍርሃት ማልት?

መንግስት፤ ፖሊስ፤ እዚያ ያለው አስተዳደር የሚባለው ስህተት ነው። አሁን እንዲያውም ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው ያለው

ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ፤ ነገር ግን ሰዎቹ ሁለት ሺ ሶስት ሺ ይላሉ፤ እርሶ 100 አይሞላም ይላሉ። ግን በፍርሀት ነው የወጡት የሚሉኝ ለምን ነው የፈሩት?

ነገርሁህ እኮ፤ በዚያ ቀበሌ አካባቢ ወንጀሎች ተፈጽመዋል፡ እንደነገርሁህ ወንጀሉን ይፈጽማሉ ተብሎ የሚገመተው ያው እየተፈለገ ነው።

ሁለት ሰው ወይም ሶስት ሰው ወንጀል ተፈጸመበት ሞተ ብለውኝል፤ መቶ የማይሞሉ ሰዎች ደግሞ ፈርተው ወጡና፣ እነዚህ ሁሉ የሚፈሩበት ምክንያት በመጠርጠር ስማቸው ተነስቶ ነው? ነገሩ ትንሽ የሚየያዝ አልሆነልኝም።

የተጠረጠሩ አይደለም። እኔ እስከማውቀው ድረስ ፍርሀት በቃ፤ አሁን ነገርሁህ እኮ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ አስተዳደሩም እየሰራ ነው፤ ወደ ንብረታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ነው።

እነዚህ ከመቶ የማይሞሉ እርሶ እንዳሉት ሲሰደዱ ወይም መፈናቀላቸውን መቼ ነው የእርሶ ቢሮ ያወቀው?

እንደ መንግስት ይሔን ሁለቱም የክልሉ መንግስታት ያውቁታል፤ የምናስተዳድረው ያው አንድ ሀገር ነው፤ ያው ክልሎች እራሳቸውን ያስተዳድሩ እንጂ መናበቡ ነገር አለ።

ይሄ ከሆነ መናበቡ አለ፣ ትናት ስደውል ምንም የምናውቀው የለም ብለውኛል። እና መቼ ነው ያወቁት? የእርሶ ቢሮ ያወቀው

አሁንም አሁንም አንተ የምትለው ከ2000 እስከ 3000 የምትለው አንተ ያነሳህልኝ ቁጥርና እኔ የማውቀው ቁጥር በጣም ስለሚለያይ

ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ፤ አንድም ሰው ቢሆን ብዙ አመት ከኖረበት መፈናቀሉ ሊያሳስበን ይገባል ማለቴ ነው። ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ፤ አሁን ደግሞ ፌደራል እዚያ ሄዶ እንዲያረጋጋ ተብሏል ተባለ፤ ነገር ግን ፌደራል አልሄደም። እንዲያውም እዚያ ያሉት ሰዎች እንዲወጡ እየተደረገ ነው የሚሉኝ ሰዎቹ።

እንግዲህ እኔ አሁን ያለኝን ትክክለኛ መረጃ ነው እየሰጠሁህ ያለሁት

እሺ

መንግስት እዚያ ያለው አስተዳደር የማረጋጋቱ ስራ ሌሎችም እንዳይፈናቀሉ ማለት የወጡትም ደግሞ እንዲመለሱ አማራ ክልል መንግስት ጋርም እየተናበቡ እየተሰራ ነው።

በጣም አመሰግናለሁ ሰላም ይዋሉ

እሺ

ለመሆኑ የአማራው ክልል ርእሰ መስተዳድር ምን እያደረገ ነው? ወደ አማራው ብሄራዊ ክልል መንግስታዊ ጽህፈት ቤት ደውዬ ፕሬዜዳንቱ የሉም ስለተባለ ወደ ሌላው ከፍተኛ ባለስልጣን ወደ አቶ ሰማ ቢሮ ተመራሁ፤ ከባለጉዳይ ጋር መሆናቸውን የገለጹልኝ ጸሀፊያቸው ወይዘሮ አዝመራ ከ 5 ደቂቃ በሗላ እንድደውል ነገሩኝ፣ ደወልሁ፤ አሁንም ከባለጉዳዩ ጋር እንዳሉ ናቸው ተባለ፤ ከ15 ደቂቃ በሗላ ደውል ተባልሁ፤ ደወልሁ፣ አስቼኳይ ስራ ገጥሟቸው አሁን ከቢሮ ወጡ ተባለ፤ በዚሁ አበቃሁ። በሌላ ጊዜ እንሞክራቸዋለን፤ የተፈናቃዮችን ሁኔታም እንከታተላለን፤ ላሁኑ በዚሁ ላብቃ፣ ሰላም።

Source- http://welkait.com/

“ሁለቱ ታላላቅ ዕቅዶች” ክፍል 3 (ዮፍታሔ)

$
0
0

በመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍሎች ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ጎሳን መሠረት በማድረግ ከተዘጋጁ ሁለት የተለያዩ “የኢትዮጵያ ካርታዎች”  በመነሣት የሕወኀት ሁለቱ ታላላቅ ዕቅዶች ተጠቅሰዋል። የመጀመሪያው ከትግራይ ክልል ጋራ የቤንሻንጉል ጉሙዝና የጋምቤላ  ክልሎችን በመቀላቀል ከኢትዮጵያ ተለይቶ አገር መመሥረት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ይህን ለማስፈጸም ከፍ ያለ ግጭት በቀሪዎቹ  የኢትዮጵያ ጎሳዎች (ይልቁንም በአማራና በኦሮሞ ጎሳዎች) መካከል መቀስቀስና እነዚህ ቀሪዎቹ ጎሳዎች ዕቅዱ እንዳይፈጸም፤ ቢፈጸምም  እንዳይዘልቅ በማድረግ ሊኖራቸው የሚችለውን ተጽእኖ ማስወገድ ናቸው። ከካርታዎቹ አንዱ መነሻ ቢሆንም የመጀመሪያውን ዕቅድ  ለማስፈጸም በትግራይና በሁለቱ ሌሎች ክልሎች እስካሁን የተደረጉና እየተደረጉ ያሉ ሌሎች ዋና ዋና ዝግጅቶች በአጭሩ ተጠቅሰዋል።  የአፋር፣ የጅቡቲና የሱዳን አስተዋጽኦ ምን ሊሆን እንደሚችል በአጭሩ ቀርቧል። ሁሉም መንገዶች ወደአንድ መድረሻ የሚወስዱ ሆነው  ይታያሉ። የሁለተኛው ዕቅድ በገሀድ መከናወን እንደጀመረ የሚያሳዩ ድርጊቶች ከመቸውም ይልቅ ዛሬ ለሁሉም ግልጽ ናቸው።--– [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—-

 

Comment

ምርጫ ይራዘምን ምን አመጣው? ማንን ይጠቅማሌ?

ዐማራውም በደል አልመረው አለ! ጠላቶቹም የላም አሸናፊ ሆኑ!

$
0
0

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት        እሑድ ሰኔ ፳፪ ቀን ፪ሺህ፮  ዓ.ም.          ቅፅ ፪ ፣ ቁጥር ፳፭

  • የዘመኑ «የትግሬ-ወያኔ ተቃዋሚዎች» ተብዬ ዘዬ፦ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንጂ የዐማራ ነገድ ተወላጆች አልተፈናቀሉም፣ አልተገደሉም፤

moreshባለፉት ፷(ስድሣ) እና ፸(ሰባ) ዓመታት ውስጥ፥ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ውስጥ «ተፈጠሩ» ለሚባሉ ሁለንተናዊ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ ተደርጎ የሚቀርበው እና በተገኘበት ቦታ ሁሉ የግፍ እና የሥቃይ ዓይነቶችን እንዲቀበል የሚደረገው የዐማራው ነገድ መሆኑን እያዬን እና እየሰማን ነው። ከሁሉም በላይ በትግሬ-ወያኔ ዘረኛ የአገዛዝ ዘመን፣ የዐማራው ነገድ ተወላጆች በጅምላ የአገሪቱ ነገዶች እና ጎሣዎች አውራ ጠላት እንደሆኑ ተቆጥረው በተገኙበት ሁሉ፥ እንዲገደሉ፣ እንዲታሠሩ፣ እንዲሰቃዩ፣ እንዲሣደዱ፣ እንደ ሙክት ተዘቅዝቀው ተሰቅለው ቆዳቸው እንዲገፈፍ፣ በቤት ውስጥ ተዘግተው በእሣት እንዲቃጠሉ፣ ከነሕይዎታቸው ታስረው ገደል እንዲወርወሩ፣ ነፍሰጡር የዐማራ እናቶች ሆዳቸው በሣንጃ ተተልትሎ ሽል እንዲሰለብ፣ ኃብት ንብረታቸውን ተነጥቀው ከአያት ከቅድመ-አያቶቻቸው ጀምሮ ከኖሩባቸው ቀዬዎች እንዲባረሩ ወይም ደግሞ በሥነልቡና ጫና ለዘመናት ከኖሩባቸው አካባቢዎች ተሸማቅቀው እንዲለቁ፣ በዐማራነታቸው እና በኢትዮጵያዊ ማንነታቸው እንዲያፍሩ፣ እየተደረገ መሆኑን ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነው። በዐማራው ነገድ ላይ ለሚደርሰው አሣዛኝ እና አሣፋሪ ክስተት፣ ከድርጊቱ ተላሚዎች እና ፈፃሚዎች ባልተናነሰ ሁኔታ፣ ከራሱ ከዐማራው አብራክ የወጡ ልሂቃን፣ በተለይም «የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንዘውራለን» የሚሉቱ፣ የሚፈፅሙት የክህደት እና የባንዳነት ተግባር፣ ለታሪክ እና ለትውልድ ትልቅ ጠባሣ ትቶ እንደሚያልፍ ማንም አመዛዛኝ ኅሊና ያለው ሰብዓዊ ፍጡር የሚገነዘበው ጉዳይ ነው። ለአብነት ያህል በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ከተፈተባቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች መካከል በተለይ ከአምቦ እስከ ደምቢ-ዶሎ ባሉት አካባቢዎች ከ፲፱፻፹ ዓ.ም. ጀምሮ የሚፈፀሙትን ግፎች አለፍ አለፍ እያልን እንመልከት።

  • በ፲፱፻፹ ዓ.ም.  በወቅቱ አጠራር በወለጋ ክፍለሀገር፣ አሶሳ አውራጃ፣ ባምቤሲ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ሸርቆሌ በሚባለው ቀበሌ ይኖሩ በነበሩት ዐማሮች ላይ በሻቢያ አመራር ሠጪነት፣ የኦነግ ሠራዊት ፬፻(አራት መቶ) ዐማራዎችን ሰብስቦ፣ የስዊድን ተራድዖ ድርጅት ባሠራው የ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ በማጎር፣ በሙሉ ከእነሕይዎታቸው በእሣት አጋይቷቸዋል።
  • በ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. በወቅቱ አጠራር በወለጋ ክፍለሀገር፣ አሶሳ አውራጃ፣ በአሶሳ ከተማ ይኖሩ በነበሩት ዐማሮች ላይ በሻቢያ አመራር ሠጪነት፣ የኦነግ ሠራዊት ፭፻(አምሥት መቶ) ያህሉን ሰብስቦ፣ በጥይት ረሽኗቸዋል፣ ከፊሉን ደግሞ ከእነሕይዎታቸው በእሣት አጋይቷቸዋል።
  • ከ፲፱፻፺፪ – ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. በነበረው ጊዜ በምሥራቅ ወለጋ የወያኔ/ኦሕዴድ ካድሬዎች እና ታጣቂ ነፍሰ ገዳዮች የአካባቢውን የኦሮሞ ተወላጆች በማነሣሣት በሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን በጥይት ቆልተዋል፣ በገጀራ ጨፍጭፈዋል፤ ከ፳ሺህ የማያንሱትን አፈናቅለው ወደ ቡሬ(ጎጃም) አባርረዋቸዋል። የ«ዐማራ ክልል» የሚባለውን የሚገዛው ሌላው የትግሬ-ወያኔ ሎሌ የሆነው ብአዴን፣ እኒያን በኦሕዴድ ግፍ የተፈናቀሉትን ዐማሮች በወባ ወረርሽኝ በሚያልቁበት በጃዊ (አገው ምድር) ቆላማ ሥፍራ በተናቸው። ዛሬ ከእኒያ መከረኞች መካከል በሕይወት የሚኖሩ ካሉ በተዓምር የተረፉት ብቻ ናቸው።
  • በመጋቢት ወር ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ከምዕራብ ሸዋ (አምቦ ዳኖ ወረዳ) በመቶዎች የሚቆጠሩ የዐማራ ተወላጆችን የትግሬ-ወያኔ ተላላኪ በሆነው የኦሕዴድ ካድሬዎች እና ታጣቂዎች አማካይነት «አገራችሁ አይደለምና ውጡ» ተብለው ተባርረዋል፣፳፮ (ሃያ ስድስት) የሚሆኑት በአሠቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፣ አቶ ጌጡ ክብረት የተባሉት ዐማራ በአሠቃቂ ሁኔታ በገጀራ ተቆራርጠው ተገድለዋል።
  • በግንቦት ወር ፪ሺህ፮ ዓ.ም. በወለጋ ክፍለሀገር በጊምቢ እና በቄለም አውራጃዎች ይኖሩ በነበሩ፣ በቁጥር ከ፫ ሺህ እስከ ፰ሺህበሚደርሱ ዐማሮች ላይ፣ የትግሬ-ወያኔ/ኦሕዴድ ካድሬዎች እና ታጣቂ ነፍሰገዳዮች አሠቃቂ እና ዘግናኝ የሆኑ ግፎችን በመፈጸም፣ ኃብት ንብረታቸውን ነጥቀው አባርረዋቸዋል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን ጨፍጭፈዋቸዋል። በተለይ አርብ ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺህ፮  ዓ.ም.           በቅፅ ፪፣ ቁጥር ፳፩ባወጣነው መግለጫችን በዝርዝር እንዳብራራነው በጊምቢ ከተማ እና በአካባቢው ይኖሩ በነበሩት ዐማሮች ላይ የደረሰው ግፍ እና በደል ዘግናኝ ነው።

ይህ በዐማራው ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ እና ስቃይ ሰሚ እና ሃግ ባይ ያጣው፦ አንድም ዐማራው የሚፈጸምበትን በደል አለመረዳቱ፣ አልያም በአብዛኛው የዐማራው ነገድ ልሂቃን ዕምነት «የትግሬ-ወያኔ እና ተከታዮቹ በደሉን የሚፈጽሙት ከዘር ጥላቻ ተነስተው ሣይሆን፣ ከማንኞቹም አምባገነን ገዥዎች ድርጊት ባልተለዬ ሁኔታ ነው፤» ከሚል የተሣሣተ መነሻ፤ ወይም ደግሞ በሁለቱም ምክንያቶች ነው። በሌላው ወገን ደግሞ «አሸናፊዎች ነን፣ ገዥዎች ነን» የሚሉት የትግሬ-ወያኔ እና በሥሩ የተደራጁት ዓላማ አስፈጻሚዎች የ«ላም አሸናፊዎች» በመሆናቸው ነው። የዐማራው ጠላቶች ዐማራው በዘር ተደራጅቶ የማያውቅ እና ዘረኛም እንዳልሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስለዚህ ዐማራው እነርሱ በከፈቱት መንገድ ከተጓዘ «ልንቋቋመው አንችልም» ብለው ስለሚያምኑ፣ ገና ሳይደራጅ ዘሩን ማጥፋት አለብን ብለው፣ እንደላም አሸናፊ ዐማራውን በተናጠል እየተከታተሉ ይመነጥራሉ። የሚያሣዝነው ግን የዐማራው ነገድ ችግር፣ በራሱ ነገድ አባሎች በተለይም በልሂቃኑ ጭምር በችግርነቱ አለመታየቱ፣ ለችግሩ መባባስና ከዚህ ደረጃ ላይ መድረስ የራሱን አስተዋፅዖ አድርጓል። ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ግፍ ከመብዛቱ የተነሣ ኢትዮጵያን በጠቅላላ እና መላውን ምሥራቅ አፍሪቃ በተመሠቃቀለ የእርስ በእርስ ፍጅት የሚከት የብሶት ማዕበል እየተንተከተከ መሆኑን መገንዘብ ብልህነት ነው። ስለሆነም የዐማራ ልጅ የሆንክ ይህን ግፍ ማስቆም የሚቻለው በመሸሽ፣ በመፍራት፣ ለሌላ አካል «አቤት» በማለት ብቻ አይደለም። ግፉ፣ እንግልቱ፣ መሣደዱ፣ ንብረት መቀማቱ፣ በኢትዮጵያዊ ዐማራ ማንነት መሸማቀቁ የሚቆመው እያንዳንዱ ዐማራ ኅሊናው ሲሸፍት፣ ከዚያም «እምቢ ለነፃነቴ! እምቢ ለኃይማኖቴ! እምቢ ለንብረቴ! እምቢ ለአገሬ! በቃ!» ብሎ የራሱን ዕርምጃ ሲወስድ ብቻ ነው። በመሆኑም በየትኛውም አኅጉር፣ በየትኛውም ሥፍራ የምትኖሩ የዐማራ ነገድ አባሎች በዘራችን ምክንያት እየተፈጸመብን ያለውን የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመቋቋም የምንችለው፣ የችግሩ መፍቻ ቁልፍ በእጃችን መሆኑን ስናምን ብቻ ነው።  ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ለመመሥረት የበቃውም በዐማራው ላይ በተከታታይ ጊዜያት የሚደረጉት ግፎች ባስከተሉት ጉዳት በተቆጩ የዐማራ ልጆች ነው። ስለሆነም ሞረሽ ወገኔ ትላንትም ሆነ ዛሬ በዐማራው ላይ የሚደርሰው ግፍ እና ሠቆቃ እንዲቆም በዓለም ዙሪያ ያሉት የነገዱ አባሎች እንዲቀላቀሉን፣ ኃይላችንንም አስተባብረን ለተገፉት እና ለሚበደሉት ወገኖቻችን አለኝታ እንድንሆን ጥሪውን ያቀርባል።   ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን! የዐማራው ደም የውሻ ደም ሆኖ አይቀርም! ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው! ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>