Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የኢትዮጵያ የቀድሞ ዘመናዊ የጦር ሰራዊትን ታሪክ ሳንዘክር ስለ ኢትዮጵያ ማውራት አንችልም

$
0
0

የኢትዮጵያ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት መሰረቱ በዳግማዊ ምንሊክ ዘመን ይጣል እንጂ በተደራጀ መልክ የተመሰረተው ከፋሽሽት ኢጣልያ መባረር በኃላ መሆኑን በርካታ ድርሳናት ያስረዱናል።ዛሬ ቀና ብለን ስለ ኢትዮጵያ መናገር የቻልነው በጥንት አባቶቻችን ተጋድሎ ብቻ አይደለም።የቀድሞ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት ገድልም ትልቅ አስተዋፆ አለበት።ሱማልያ ”ቁርስ ድሬዳዋ ምሳ አዲስ አበባ” በሚል መፈክር በ1969 ዓም በከፈተችብን ጦርነት ከሞቃዲሾ በምታስተላልፈው የአማርኛ ራድዮ ፕሮግራም ፎክራብን ነበር።ምስራቃዊውን የሀገራችንን ክፍል ይዛ ነበር።
በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሚሊሻ ከመደበኛ ሰራዊት ጋር እልህ አስጨራሽ ውግያ አድርጎ ነፃነታችንን እና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ያስከበረው የቀድሞ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት ነው።ኢትዮጵያውያን ብዙ ያልገቡን፣ክብር መስጠት ሲገባን ክብር ያልሰጠናቸው ክቡራን አሉን።
ክብር ለቀድሞ ዘመናዊ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት! የኢትዮጵያ የቀድሞ ዘመናዊ የ ጦር ሰራዊትን ታሪክ ሳንዘክር ስለ ኢትዮጵያ ማውራት አንችልም።

Source: ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG


የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው?

$
0
0

ፐሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

989TeddyAfro_NYC_26

አርቲስት ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)


ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤  በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ  የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

 

 

በቴዎድሮስ ላይ ከባድ ተንኮል ሲፈጸምበት የሰማሁት በመጀመሪያ ዛሬ በስደት ላይ ባለው « አዲስ ነገር» የሚባል ጋዜጣ ላይ ነበር፤ ጋዜጣው ቴዎድሮስ በሙያው ያገኘውን መልካም ስም በሰፊው ጥላሸት ቀብቶት ነበር፤ በጣም ሰፊ የሆነ ሀተታ በቴዎድሮስ ዘፈኖች ላይ በማቅረባቸው ምን ያህል አንገብጋቢ የአገር ጉዳይ አግኝተውበት ይሆን ብዬ አነበብሁት፣ ምንም ለአገር  የሚጠቅም ጉዳይ አላገኘሁበትም፤ በዘፈኖቹ ላይ በተደረገው ሂስም ከጋዜጠኞቹ መሀከል የሙዚቃ ሙያ ባለቤት እንዳለ ብጠይቅም ጋዜጣው ባለሙያ እንደሌለውና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለሙያ ማማከራቸውን ነገሩኝ፣  ስሙ  እንዲጠቀስ የማይፈልግ ባለሙያ፣ ባለሙያ አይባልም፣ እንኳን በሙያው በራሱም አይተማመንም ማለት ነው፤ በዚህ በራሱ በማይተማመን ሰው ምስክርነት ላይ በተመሰረተ ረጅም ነቀፌታ ቴዎድሮስን ደበደቡት፤

 

ሁለተኛው የቴዎድሮስ ጣጣ በመኪና ሰው ገጭቷል ተብሎ መከሰሱ ነው፤ በሌሊት፣ በጨለማ ነው፤ ቴዎድሮስ እንደሚለው  «እኔ ወደአገሬ የገባሁት ሰውዬው ሞተ በተባለበት ቀን ማግስት እንደሆነ ቪዛዬ ያረጋግጣል፣»  (ነጋድራስ መስከረም 30/2001 ዓ.ም. ) በኋላም ከዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የተገኘው መረጃ ይህንኑ የሚያረጋግጥ እንደነበረ ተነግሮአል፤  በዚሁ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ የሚከተሉት መረጃዎች ተጠቅሰዋል ፦

  1. ቴዎድሮስ ከውጭ የተመለሰው በ22/2/1999 ዓ.ም መሆኑ
  2. ሰውዬው በ 22/1/1999 ሞቶ አስከሬኑ በ22/2/1999 ዓ.ም መመርመሩን የጽሑፍ ማስረጃ፣
  3. ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ በሆስፒታሉ የተገለጸው የምርመራ ቀን እንዲለወጥ መጠየቃቸው፣
  4. ከአሥራ ሦስት ቀኖች በኋላ በተደረገ ምርመራ መኪናው ላይ ምንም ደም አለመገኘቱን፣

ይህ ሁሉ ሆኖ በቴዎድሮስ ላይ ተፈርዶበት ወህኒ ወርዶ ጊዜውን ጨርሶ ከወጣ ቆይቶአል።

 

ከዚያ ወዲህ ደግሞ በተቀነባበረ ሁኔታ ቴዎድሮስ ካሣሁን በዘፈኑ ያገኘውን ዝና ለማጉደፍና በሥራውም የሚያገኘውን ጥቅም ለመቀነስ ተግተው የሚሠሩ ሰዎች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ነገሮች አሉ፣ በመጀመሪያ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው በደል ከአለ ግልጽ ሆኖ ቢወጣና ሁላችንም ብናውቀው ጥሩ ነው፤ አለዚያ ግን እየተደራጁ አንድ ግለሰብን ለማጥቃት የሚደረገው እርምጃ የሚወገዝና ልንቃወመው የሚገባ ጉዳይ ነው፣  አንድን ሰው በእምነቱ፣ በአስተያየቱ፣ ወይም ስኬታማነቱን በመመቅኘት ለመጉዳት ዓለም -አቀፋዊ ሴራ ማካሄድ ክፋት ነው፤ ይህንን ክፋት አምጠው የወለዱትና ለማሳደግ የሚሞክሩት ሰዎች፤ የማሰብ ችግር ያለባቸውና ክፋታቸው ተመልሶ እነሱኑ የሚያጠቃ መሆኑን የመገንዘብ ችሎታ  እንኳን የሌላቸው ናቸው።

 

ሦስተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የበደሌ ቢራ ፋብሪካ በቴዎድሮስ ዘፈን ለመጠቀም ሲፈልግ፣ የጨለማ ሰዎች ተሰብስበው በቴዎድሮስ ዘፈን የታጀበውን የበደሌ ቢራ እንደማይጠጡ በመዛታቸው ኩባንያው ከቴዎድሮስ ጋር የነበረውን ውል መሰረዙ ነው፤  እንደተገነዘብሁት ቴዎድሮስ ትንሽ በቁንጫ ተሰቃየ እንጂ ክፍያው አልቀረበትም፣ ነገር ግን ቴዎድሮስን አንደሰው፣ እንደኢትዮጵያዊ፣ እንደዘፋኝ የሚያውቁት ሰዎች የሉም፤ ወይም በጨለማዎቹ ሰዎች ተሸንፈዋል፤ ወይም በፍርሃት ቆፈን ደንዝዘዋል! የጨለማ ሰዎቹ ቴዎድሮስ ካለበት አንጠጣውም የተባለው ቢራ ለቴዎድሮስ ወዳጆች እንዴት ጣፈጣቸው?

 

አራተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የመጣው ሦስተኛውን ጥቃት ለመቋቋምና ለማረም ምንም ዓይነት የማረሚያ እርምጃ ስላልተወሰደ ነው፤ የበደሌ ቢራ ኩባንያ እንዳደረገው ሁሉ የኮካኮላ ኩባንያም ቴዎድሮስ ካሣሁንን ለአሻሻጭነት መረጠ፤  የጨለማዎቹም  ሰዎች እንደገና ተነሡ፤  ቴዎድሮስን ካልሻራችሁ ኮካ ኮላ አንጠጣም  ብለው የቴዎድሮስ ውል እንዲፈርስ አደረጉ፤  አሁንም ቁንጫው ትንሽ ምቾቱን ከመቀነሱ በስተቀር ቴዎድሮስ ገንዘቡን አላጣም፤ አሁንም የቴዎድሮስ ወዳጆች ነን የሚሉ ኮካ ኮላ እየጣፈጣቸው ይጠጣሉ፤ ትንሽ ቆራጦች የጨለማ ሰዎች  በአደባባይ ምላሱን እየሳለ እልል ከሚለውና ከሚጨፍረው ነፍሰ-ቢስ ስብስብ ምን ያህል እንደሚበልጡና ውጤታማ እንደሚሆኑ ያሳያል።

 

የቴዎድሮስ ካሣሁን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው፤ የጨለማ ሰዎቹ ግን ወደግለሰብነት ደረጃ ገና ያልደረሱ ናቸው፤ ስለዚህም ቴዎድሮስን እንደሰው እንዳያዩት እዚያ ገና አልደረሱም፤ እንደኢትዮጲያዊ እንዳያዩት መናፍቃን ናቸው፤ እንደዘፋኝ እንዳያዩት ጆሮአቸው አይሰማም።

 

በአዲስ ነገር ተጀምሮ እስካሁን አልበርድ ያለው ቴዎድሮስን ነጥሎ የማጥቃት ዘመቻ ምክንያቱ ምንድን ነው? በጥሞና ሊታይና ሊመረመር የሚገባው በአዲስ ነገር ጋዜጣና በጨለማዎቹ ሰዎች መሀከል ያለ የሚመስለው ድርጅታዊ ግንኙነት ነው፤  የአንድ ግለሰብን ሰብዓዊ መብቶች እየደጋገሙ በመርገጥ አጋጣሚ እየፈለጉ ማጥቃት የሚጎዳው ተረጋጩን ብቻ ሳይሆን ረጋጮቹንና የጋን ወንድሞችንም ነው፤ አንድ ቀን ግፍ ወደተነሣበት ይመለሳል።

Health: ዲ.ኤን.ኤ – DNA ለምን ጉዳይ? እንዴት? መቼ?

$
0
0

 

ዲ.ኤን.ኤ (Deoxy Ribonucleic Acid) /DNA/ በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ሌሎች በሙሉ የያዟቸው የሞለኪውል ቅንጣቶች ሲሆኑ፤ ገና አንድ ጽንስ ተፅንሶ የተሟላ አካል ባለቤት እንዲሆንና የህይወትን አካላዊ ተግባር እንዲያከናውን የሚረዳ ነው፡፡

የዲ.ኤን.ኤ ቅንጅታዊ ስርዓት (DNA sequence) በዚህች ምድር ላይ ያሉ ሰዎችን በሙሉ ልክ እንደ አሻራ መለየትና የማጣመር ብቃት አለው፡፡ በዚህም ሰዎችን በተለያዩ ነገሮች እንዲለዩ ማድረግ ያስችላል፡፡
dna zehabesha
የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ምንነትና የህጋዊነት ክርክሮች

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ የሚከናወነው እጅግ ግላዊ ለሆኑ ጉዳዮች ለምሳሌ ለበሽታዎች ስለሚኖር ተጋላጭነት ሲሆን፤ በተለያየ ሁኔታ ለንግድ የተቋቋሙ ኩባንያዎች የሰዎችን የጤና ምስጢር ለመግለፅ ሳይሆን የዲ.ኤን.ኤ ቅደም ተከተል መለያና ከሰው ሰው የሚለየው ሾርት ታንደም ሪፖርትን /Short Tandem reports/ በመመርመር ሁለት ሰዎች የሚገናኙት ወይም የሚለያዩ መሆኑን ነው የሚያጣሩት፡፡ የፖሊስ ሳይንቲስቶች ኢስ.ቲ አርስ የተባለውን ምርመራ ይጠቀማሉ፡፡ በትዳር ላይ መማገጥንና ማታ አንሶላ ከተጋሩዋትና በራስ ዲኤንኤ መካከል ያለውን መጣጣም ለማወቅም ይቻላል፡፡ እንደ ባለሙያዎች አገላለፅ ሰዎች የዲኤንኤ መመርመሪያን በቀላሉ ሊገዙት ስለሚችሉ ወደ ምርመራ ቢዝነሱ ይሮጣሉ እንጂ ስለ ህግ ጉዳየችም ሆነ የሌሎችን ግለሰባዊ መብት ስለመጋፋታቸው ለማሰብ ጊዜ አይኖራቸውም፡፡

በበርካታ ሀገራት የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ከሚያስከትለው ጉዳት በተጨማሪ ከፍተኛ የህግ ፈተና ገጥሞቷል፡፡ በብዙ ሳይንቲስቶች ጥናታዊ ምርመራ በዓለም የጄኔቲክ ምርመራ እጅግ ትልቁ ገበያ ያላት ሀገር አሜሪካ በእያንዳንዱ ግዛት ስለግለሰቦች መብትና ስለሚከለከሉ ህጎች ምንም መረጃ የለም፡፡ በርካታ ግዛቶች በትዳር ላይ ስለሚኖር መማገጥም ሆነ አባትነትን ለመለየት ዲ.ኤን.ኤ የሚሰበስቡና ቢዝነስን የሚያከናውኑ ድርጅቶች ያሉ ቢሆኑም በየትኛው ህግ እንደሚዳኙ ምንም ማስረጃ ለማግኘት አልተቻለም፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ 1996 ድረስ ማንኛውም የኒዮርክ ግዛት ነዋሪ የሆነን ሰው ጄኔቲክ ምርመራ ወይም ያለፍላጎቱ ውጤቱን መግለጽ ህገ ወጥ ነበር፡፡ ያለ ግለሰቡ ፍቃድ የሚደረግ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ብዙዎችን ለስጋት ሲዳርግ፤ የህክምና ማህበረሰቡን የህግና የስነ ምግባር አጣብቂኝ ውስጥ ከቷል፡፡

ኢንተርኔት አዘውትሮ የመጠቀም ዕድል ያለውና የጤና ድህረ ገጾች የሚጎበኝ ሰው የሚወሰልት የትዳር ተጓዳኝን ለማወቅ፣ የልጅዎ አባት መሆን አለመሆንዎና መሰል ጥርጣሬዎችን ለማረጋገጥ ከፈለጉ ‹‹እኛ ዘንድ ይምጡ!›› የሚሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የንግድ ማስታወቂዎችን የማንበብ አጋጣሚ ይኖረዋል፡፡ ሆኖም የምርመራውን ትክክለኛነት፣ ስለ ህጋዊ ተቀባይነትና ስለሚያስከትለው የስነ-ልቦና ቀውስ ማንም ያስተዋለ ባይኖርም ተግባሩ አለመወገዙን ነው የተለያዩ ሚዲያዎች የሚዘግቡት፡፡ በእንግሊዝም ተግባሩ ህገ ወጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ቀስ በቀስ የምርመራው ጥቅም እየጎላና እያደገ በመምጣቱ ታላቅ ይፋዊ ተግባር በመሆን ላይ ነው፡፡

 

ዲ.ኤን.ኤ ምርመራ – ለአርኬዎሎጂ

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ በአርኪዎሎጂ ምርምር ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡ ይህም የተለያየ የጀኔቲክ ኮዶችንና ቅደም ተከተሎችን (Genetic Codes and Sequences) በመጠቀም ከብዙ ዓመታት በፊት በምድር ላይ ህይወት ምን እንደሚመስልና ተያያዥ የቀደምት የአኗኗር ሁኔታን ለመጠቆም የሚያስችል ነው፡፡ ይህ ደግሞ በተለያየ ወቅት የምድራችንን የስነ ህይወት ገፅታዎችን ከማንፀባረቅም በተጨማሪ ተያያዥ የሆኑ ምርምሮች የበለጠ እንዲደረጉ አስተማማኝ መረጃን ለመስጠት ያስችላል፡፡

 

የወላጅነት ማረጋገጫ – በዲ.ኤን.ኤ ምርመራ

የተለያየ አጋጣሚ የልጆቻቸውን ማንነት መለየት ላቃታቸው የአብራካቸውን ክፋይ በምርመራው ማረጋገጥ የሚያስችል ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ ድብቅ በሆነ የወሲብ ውስልትና ውስጥ የሚፈጠሩ የመደፈር፣ የማርገዝና የተወለደ ልጅን የእኔ አይደለም ብሎ ላለመቀበል መደፋፈርና ከህግ ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታትም የተሻለና አማራጭ የሌለው ሆኗል፡፡

 

የወንጀል ነክ ጉዳዮችን ለማሳወቅ

ወንጀለኞች ወንጀል ሰርተው በሚጠፉበት ጊዜ ከአካላቸው ጋር ከተነካኩ ነገሮች በሙሉ በሚወሰዱ ናሙናዎች የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ በማድረግ ከማንነታቸው ጋር የማዛመድ ስራ በመስራት ተጠርጣሪዎችን ለማግኘት ያስችላል፡፡ በየጊዜው እየተሻሻሉ በሚመጡ የዲ.ኤን.ኤ የምርመራ ቴክኖሎጂ ከምርምሩ ጥበብ መሻሻል ጋርም እጅግ የረቀቁ አካሄዶችን በማድረግ በዙሪያው የሚጠረጠሩ ሰዎችን ለማግኘት ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይህ ታዲያ ከአሸባሪነት ጋር በተያያዘም ራሱን የቻለ አስተዋፅኦ ሊያደርግም ይችላል፡፡

 

የጠፋ የቤተሰብ አባልን ለማግኘትና የዘር ሐረግን ለመፈለግ

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ በተለይም በትውልድ ሐረግ ውስጥ የማይቀየረውን ዋይ ክሮሞዞም (Y chromosome) መሰረት ባደረገ መልኩ የቤተሰብ የዘር ሐረግ ተለይቶ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡ ይህም የተረሱ የዘር ሐረግንም ሆነ በአንድ አካባቢ ተለይተው የሚገኙ ሰዎችንም ከሌሎቹ ለመለየት ያስችላል፡፡ በዚህም ለምሳሌ ልክ ለረዥም ጊዜ እንደተለያዩት የደቡብና የሰሜን ኮሪያ ዜጎች ከረዥም ዘመናት በኋላ የቤተሰብ ማንነታቸው ተለይቶ እንዲገናኙም ይረዳል፡፡ በሳይንሳዊው ምርምር ለሚጠቀምበት ብቻ ማለት ነው፡፡

 

የተሻለ ጤንነት ያለው ልጅ እንዲወለድ

ከወሊድ በፊት በእናት ሆድ ውስጥ ያለውን የልጆች የጤንነት ደረጃ በማወቅ በጊዜው በቂ የሆነ ለውጥ የሚያመጣበትን እንክብካቤና ምርመራ ለማድረግ የዲኤንኤ ምርመራ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በተለይም ህፃናት የማይድኑ አስቸጋሪ ህመሞችን ይዘው እንዳይወለዱ ችግራቸው በጊዜ ታውቆ ቁጥጥር እንዲደረግበት ለማድረግ የዲኤንኤ ምርመራ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

 

በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን ለማወቅ

ከላይ ከተጠቀሰው የጤና እንከን በተጨማሪም የዲኤንኤ ምርመራ በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመታደግ በተለይም ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዳይተላለፉና አንድ ትውልድ ላይ እንዲገታ ትልቅ እርዳታ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም እንደ ካንሰር ያሉ ህመሞች የሚበዙበት የሴሎች ደረጃና ሁኔታም ሆነ ምክንያቱን ቫይረስም ይሁን ሌላ ነገር ለመለየት ያስችላል፡፡ ታዲያ ይህ ከተለያዩ ህዋሳት በሚገኙ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራዎች የተዛማጅ ስራዎች በማነፃፀርም የሚከናወን ነው፡፡

 

የአዲስ ስነ ፍጥረት ግኝትን ለመጠቆም

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ የተለያዩ አዳዲስ ስነ ህይወታዊ ግኝቶችን የብቃት ሁኔታና በህይወት የመቆየት እድላቸውንም ለመመርመርና ለመጠቆም የሚረዳ ነው፡፡ ይህም የአንድን ዝርያ አመጣጥ ለማሳወቅ ወይም ከሌሎች ነባራዊ የስነ ፍጥረት አካላት ጋር ያላቸው ተዛማጅነትንም ለማጥናት የሚረዳ ነው፡፡

 

የሙታንን አካላት ለመለየት

በተለያየ አጋጣሚ የሚዋደዱ ሰዎች አንዳቸው ተለይተው መጥፋትና ሞተው አስክሬናቸውንም ለመለየት መቸገርን የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ የሚፈታው ይሆናል፡፡  በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ በአውሮፕላን መከስከስ በሚደርስ ችግር ባህር ውስጥ ሰጥመው የሚገኙ አስከሬኖችን ለመለየት የሚጠቅመው የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ነው፡፡ ይህ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ በውሃ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ኬሚካሎችንና ውሃውም ራሱ በሚፈጥረው ተፅዕኖ የሰዎች አካላት ሊጎዳ ስለሚችል ማንነታቸውን ለመለየት ያስቸግረናል፡፡ ስለዚህም ከአስከሬኑ በሚወሰድ ናሙናና ከመሰል የሌላ ሰው ናሙና ጋር በማመሳከር በአስከሬኑ ዙሪያ በቂ መረጃ እንድናገኝ ያስችላል፡፡ የአስክሬኑ የዝርያ ምንጭ፣ ሀገሩንና የህዝቦቹን ማንነት የመግለፅ አጋጣሚም እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

 

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ በታዋቂ ሰዎች ላይ የደቀነው ስጋት

በቀዳሚነቱ የሚነገርለት የእንግሊዝ የዲ.ኤን.ኤ ስርቆሽ ህግ የታዋቂ ሰዎች ጄኔቲክ መለያቸው በአንዳንድ ፕሬስ ላይ ሊቀርብ ይችላል የሚለውን ስጋት ለማስወገድ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2002 የንጉስ ሀረይ ፀጉርን በመውሰድ የቀድሞ ልዕልት ዲያና አፍቃሪ የነበረው ጀምስ ሔዊት ልጅ መሆኑን ለማረጋገጥ መስረቁን ዘገባዎች አቀረቡ፡፡ ይህን የዩኬ የሰው ልጅ ጄኔቲክ ኮሚሽን የሰዎችን ጄኔቲክ መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ ህጉ ጠበቅ እንዲል ጥሪ አቅርቧል፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 በእንግሊዝ ያለግለሰቡ ፈቃድ የሰውን ዲ.ኤን.ኤ መመርመር ወንጀል እንዲሆን ተደረገ፡፡ ያም ፀጉርን፤ ምራቅንና ማንኛውንም የሰው ህዋስን ያለፍቃድ መውሰድ ህገ ወጥ ተግባር እንደሆነ ያጠቃልላል፡፡ ማንም ተይዞ የተቀጣ ባይኖርም ድርጊቱን መፈፀም በገንዘብና በሶስት ዓመት እስራት ያስቀጣል፡፡

እንግዲህ ከላይ በዝርዝሩ እንደተገለፀው የዲኤንኤ ምርመራ ለበጎ ተግባር /ለህክምና/ መሆኑ ቀርቶ ለማህበራዊ ጉዳዮች በማዋል ሰፊ የቢዝነስ መስክ እየሆነ መምጣቱ የግለሰብ መብት መጋፋቱ የህግ ጥያቄን አስከትሏል፡፡ በርካታ የዓለም አገራት ቴክኖሎጂው ያላቸው በስፋት እየተከራከሩበት እንደሆነ ቢታወቅም ሌሎች ያልተዳሰሱት ሀገራት ጉዳዩን ህጋዊ እልባት ይሰጡት ይሆን ብሎ ከጠየቀ በኋላ ያ እስከሚሆን መጠበቅ የለብንም ሲል ያስጠነቅቃል፡፡ ይህም ማለት የዘር ህዋስ መታወቂያ ካርዶችን በየዞርንባቸው ስፍራዎች ጥለናቸው ስለምንነሳ የግለሰብ ነፃነትና መብት ለብዙ የማናውቃቸው ሰዎች ምርመራ የተጋለጠ ነው፡፡

 

 

በአንድነታችንና በሰላም ለመኖር ወደ 1966 ክልላችን መመለሱ ይመረጣል (ብርሃነ ደስታ ሃይለየስ)

ሕብረት እንዴትና ከማን ጋር? (ይታያል በላቸው)

$
0
0

አገራችን ኢትዮጵያ የገጠሟትን ውስብስብ ችግሮች ለማስወገድ አብሮ መስራት ወሳኝ መሆኑን  የተረዱና፤ተረድተውም በሃሳቡ ተመርተው በአንድ ላይ በመደራጀት ፣በፖለቲካው ትግል ውስጥ ገብተው  አለአንዳች ውጤት እንደጉም በነው የጠፉ ብዙዎች ናቸው።በተደጋጋሚ የሕብረት ጥሪ ይሰማል፤የዚያን  ያህል በድርጅቶችና በአባሎቻቸው ላይም የህብረቱን ጥሪ ለማስተናገድ ጫናው ተበራክቷል።ትግሉ  ትክክለኛውን ፈለግ ይዞ ይሂድ ሲባል ትክክለኛው ሕብረት እንዴትና በምን ሁኔታ እንደሚፈጠር  ተፈጥሮም ዕድሜ እንዲኖረውና ከግቡ እንዲደርስ ብልሃትና ስልት ያስፈልጋል።ይህን ሳያረጋግጡ ለዜና  ፍጆታ ብቻ መሰረት የሌለው ስምምነት ላይ ቢደረስና ሕብረት ተፈጠረ ቢባል ሕብረቱ ወደለመድነው  ውድቀትና ተስፍ አስቆራጭ ውጤት ያሸጋግረናል። ሙሉውን በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ

 

Comment

 

 

 

 

የነፃነት ትግል ሁሉንም መራራ መከራ ለመቀበል መፍቀድ ነው። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 01.07.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

andargachew

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

የነፃነት ትግል መከራን ለመቀብል ተፈቅዶና ተወዶ የሚወሰድ እርምጃ ነው። የነፃነት ትግል የጫጉላ ጊዜ ሽርሽር አይደለም። ሊሆንም ከቶውንም አይችልም። ስለዚህ ዛሬ በግንቦት 7 ጸሐፊ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የደረሰው እግታ ከትግል መስምር አንዱ በመሆኑ ሊያደናግጥ የሚገባው የዓለም ፍጻሜ አይደለም። ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን እራሳቸውን ሰጥተው ነው ኢትዮጵያ ሀገራችን ከክብሯ ጋር ያቆዩን። ኢትዮጵያ በቀደሙት ጠላቶቿ ላይ ድልን በድል አነባብረው ነጻነትን ዘምን ከዘመን የቀለቡት – ለትውልዱ። ዐፄ ቴውድሮስ እራሳቸውን በሽጉጥ የገደሉት በመሬታቸው ነበር። ሌላ መሬት ሄደው አልነበረም። ይህ ለነፃነት የሚሰጥ የከበረ ስጦታ ነው። ዛሬ በወያኔ እስር ቤት የሚገኙት ጀግኖቻችንም ዬትም ሄደው አይደለም በመሬታቸው ላይ ነው ስቃያቸውን የሚያዩት። ዘርአይ ደረስ ደግሞ ገድሉ ዕጹብ ነው። አብዲሳ አጋ፤ ሞገስ አስገዶም፤ አብርሃም ደቦጭ ሁሎችም የተፈቀደላቸውን ጀግንነት የከወኑት በተሰጣቸው ቦታና በተፈቀደላቸው ጸጋ ነበር።  ለጀግና ሁሉ ቦታ የድርጊት መስኩ ነው። ሁሉ አጋጣሚ መሪውና መርሁ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌም ለድሎት ሄደው አይደለም የታገዱት። ለምንመኛት አንዲት ኢትዮጵያ፤ ለውዱ  - ለክብሩ  - ለፍቅሩ ኢትዮጵያዊነት እንጂ። ይህ የትውልዱን አደራ በድርጊት ያዘከረ ሰማዕትነት ነው – ለእኔ ለሥርጉተ።

ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ ስንት ጀግኖች በመሬታቸው መሥራትን፤ መኖርን፤ መተንፈስን፤ ማደግን፤ ታግደው ለእስር ለሞት፤ ለስደት፤ ለፍርሃትና ለስጋት፤ ለባይተዋርነትና ለሞት ተጋልጠዋል። ስለዚህ አንድ እራሱን ቆርጦ ለነፃነት ትግል ለሰጠ ጀግና የቃሉ መፈፀሚያ ውሉ ወርቅ ቀለበቱ ስለሆነ ጀግንነቱን ቢያፈልቀው እንጂ ፈጽሞ አያደበዝዘውም። ለወያኔ ሻ/ አጣናው ዋሴን ሱዳን አሳልፋ ከሰጠች በኋላ ገድሏቸዋል። ይህ ደም የጠማው አረመኔ የለመደበት ነው። መክለፍለፉ ሆነ አጋጣሚ ጠብቆ ማጥቃት መቻሉ የሚጠበቅ ነው። ቋሳ እኮ ለወያኔ የተፈጠረበት የተፈለፈለበት እጭነቱ ነው።

ወያኔ ፍጥረተ ነገሩን ሲመረመር በቀል ነው። ደሙ ትንፋሹ አካላቱ በሙሉ በጎሰኝነት የሰመጠ እንደ አራዊት የሚያስብና የሚኖር ሆኖ አብዛኞቻችን ግን የጠላታችን ማንነት ለመግለጽ ተሸማቀን ወያኔ ለማለት ድፈረት አንሶን ኢህአድግ እያልን እናቆለባብሰዋለን። እነሱ ያላፈሩበትን። ደፈረው የሚናገሩትን። ቁስለት!

የወያኔ ሃርነት ትግራይ እያፈረሰን እንዲቀጥል የፈቀድንለት እኛ እንጂ እሱ አቅም ኖሮት ፈጽሞ አይደለም። ካለ አቅምና ወርዱ የተሸከመው ህዝባዊ ሃላፊነት ስላልቻለው እንዲህ ነገን ፈርቶ ዙሪያ ገባውን በእሾኽ አጥሮ አልፎ ተርፎ ባህርማዶ ተሻግሮ በቀሉን ለማሳካት የሚንፈራፈረው። ስንት የማይታወቁ ኢትዮጵውያንን ሱዳን፤ ጁቡቲ፤ ኬኒያ፤ በመላ አረብ ሀገር ላይ እዬታፈኑ እጅግ በሚዘገንን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው ታሪክና ነገ የሚያወጡት ሃቅ ይሆናል።

ለዚህም ነው ጠላታችን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ስለመሆኑ ጠንቅቅን በሚገባ ማወቅ የሚገባን። አሁንም ትግሉ ተጠናክሮ መከራው አስተቃቅፎን፤ ፈተናው ውስጣችነን አገናኝቶት፤ ጥቃቱ እልህን አመንጭቶ እንዲመራን መፍቀድ ከእያንዳንዱ በግል ከሁሉም በጋራ የሚጠበቅ ግዴታ ይመስለኛል።

የዛን ብልህ ጀግና አበራ ሀይለመድህን ጥበብ ማንበብ – መተርጎም – ማመሳጠር የሚገባውም ከዚህ አንፃር ነው። ጀግናው የጠላቱን ብልቱን አገኘው። ድሉን በእጁ አስገባ። ስለምን ጣሊያን ወይንም ወደ ጀርምን ሄዶ እጁን አልሰጠም እያሉ ሲሞግቱኝ ለነበሩት የፋሽስቱ አስትንፋስ ዬት ድረስ ሊያካልል እንደሚችል ማመዛዘን የሚያስችል  ይመስለኛል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለእኔ አሁንም ጀግናዬ ናቸው። ጀግንነታቸው ላመኑበት ፍላጎት እራሳቸውን በመስጠት መቁረጣቸው ብቻ ሳይሆን ማናቸውንም መከራ ፈቅደው በመቀበላቸውም ነው። ተፈጥሯቸውም ለድርጅታዊ ተግባር ፍጹም የሰጠና ብቁ ነውና።

በተረፈ ግንቦት 7 እንደ ድርጅትነቱ፤ አባላቱ እንደ አባልነታቸው በመሰምራቸው የሚሰጣቸውን ግዳጅ ሊከውኑ ይችላሉ። ወይንም መመሪያ ሊጠብቁ ይቸላሉ።  ሌሎቻችን ግን በጠገግ ከግንቦት 7 መመሪያና መርህ ለማንጠብቀው የጠራ አቋም ይዘን በድፍረት ፊት ለፊት ወጥተን ድርጊቱን ማውገዝ አለብን። እንደ ተለመደው ትግላችን በግል እንቅስቃሴ ለማድረግ የፈቀድነው በጀመርነው መስመር መረጃውን መላክ አሁኑን ያስፈልገናል። ፍጥነት ድል ነው። ለዚህም መዳህኒቱ ኢጎን መታገልና ማሸነፍ –  ከውስጥ። በወያኔ እርር ድብን አደረገን እንላለን። ግን የእውነት ነውን?! ከሆነ — ቁስሉ የወያኔ ማሸንፍን እንዳያውጅ በአንድነት መነሳት ነው። እኔ ከዬትኛውም ድርጅት አመራር አልጠብቅም። ስለምን የራሴ መሪ እራሴ ነንኝና። ቁስለቴ ይመራኛል። እህህን ታቅፌ አልተኛም። የሚጋፉኝን እዬተጋፋሁ ሰላቢዎችን ሊጎትቱኝ የሚፈልጉትን እዬገፈተርኩ ከራሴ ጋር ታርቄ ለህሊናዬ አድራለሁ።

ዛሬ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የደረሰው ነገር በማናቸውም የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች በአነሰ – በበዛ ሊከሰት የሚችል ስለሚሆን ጠንቃቃነት ጠረናችን ሊሆን ይገባል። ችግሩን ቋያውን አብሮ ለመጋፈጥ መወሰን መቁረጥ መገኘት።  የፋመ ግፊት – የፋመ ድርጊት በፍጥነት! እርግጥ ነው ጉዳዩ ባለቤት አለው። ይህ መልካሙ ነገር ነው። ነገር ግን „ ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው።“ ዕድል ያላቸውም ወገኖች ይኖራሉ። ሊደመጡ የሚችሉ። ቀንም ዕድል አለው። ቦታም ዕድል አለው። ስለዚህ ሁሉም በመክሊቱ የተሰጠውን ለመከወን ይተጋ ዘንድ ዝቅ ብዬ እኔ ሎሌያችሁ አሳሰብኩኝ።

 

እርገት። በተረፈ አሁን ወደ ኋላና ፊት እዬሄዱ፤ የፖለቲካ ትንተና የሚሰጥበት ክፍለ ጊዜ ሳይሆን፤ እኔ – ለእኔ፤ ለራሴ ላደርግ የሚገባውን መከላከል ስጀምረው ሀገሬ ኢትዮጵያን አድብቶ እያጠቃት ካለ ባንዳ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጥቃት ትድናለች። ማልቀስን ለማስቆም በሁለት እግር ቆሞ ጠላትን በማናቸውም ሁኔታ መመከት። አቅምን አክብሮ – በአቅም በአግባቡ ለመጠቀም ጥሩ አደራጅና ጥሩ መሪ መሆን። ቅንንት። መጀመሪያ ግን እራስን ማደራጀት።

 

ኢትዮጵያዊነትን የሚጠብቅ አምላክ ጀግኖቻችን ይጠብቅ! አሜን!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

የአንዳርጋቸው ጉዳይ በውጭ ሚዲያዎች ለምን ሳይዘገብ ቀረ? – (በመታሰራቸው ዙሪያ የኔ 3 ጥያቄዎች)

$
0
0

andargachew
ስታየሁ ከዋሽንግተን ዲሲ

በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ ትናንት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መንግስት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ታሰሩ የሚል ዜና ካነበብኩ በኋላ የተለያዩ ጥያቄዎች በጭንቅላቴ ላይ ተመላለሱ።

የመን በመንግስት አሰራር ደረጃ ከአፍሪካ ሃገራት የማትሻልና በሙስና የተጨማለቀ አሰራር ስላላት አቶ አንዳርጋቸው እንዴት ለትራንዚትም ቢሆንም መመረጣቸው ድፍረታቸውን ባደንቅም ውሳኔያቸው ገርሞኛል። ጫት በሚቅሙ የመንግስት ሃይሎች የምትመራው የመን በተለይም አቶ አንዳርጋቸውን በጫት ንግድ ልትለውጣቸው ትችላለች የሚለው የብዙዎች አስተሳሰብ ባይስበኝም እኔን የገረመኝ አቶ አንዳርጋቸውን የሚያህል ትልቅ የተቃዋሚ ድርጅት መሪ የመታሰር ዜና አንድ ሳምንት ሙሉ በሌሎች የውጭ ሚዲያዎች አለመዘገቡ ገርሞኛል።

ዜናውን ከዘ-ሐበሻ ካነበብኩ በኋላ በግንቦት 7 ድረገጽ፣ በኢሳት ዝርዝሩን ሰማሁ። ከዛም ወደ የመን ሚድያዎች ጋር በኢንተርኔት አሰሳ ጀመርኩ። ከዚህ በፊት የግድያ ሙከራ በአስመራ ሊደረግባቸው ታቅዶ ከሸፈባቸው ስለተባሉት አቶ አንዳርጋቸው አንዳችም ጉዳይ የሚያወራ ነገር አላየሁም። በአንዳችም ሚድያ ስለመታሰራቸው የተዘገበ ነገር አለመኖሩ ገርሞኛል።

በተለይም የእንግሊዝ ሃገር ፓስፖርት አላቸው የሚባሉት አቶ አንዳርጋቸው እውነት የእንግሊዝ ፓስፖርት ካላቸው እንዴት እንግሊዞች ዝም አሉ? አንድ ዜጋቸው እንዲህ ያለ መታፈን ውስጥ ሲወድቅ ሚዲያዎቻቸውም መንግስታቸውም እንዴት ዝም አለ?

የኤርትራ ባለስልጣናትም ዝም ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ያሉት ነገር የለም። ምንድን ነው ጉዱ? እንደሚባለው ግንቦት 7ና አለኝ የሚለው ኃይል ቀስ በቀስ ከአስመራ ለቆ ለመውጣት ካለው እቅድ ጋር በተያያዘ አቶ አንዳርጋቸው አንድ ነገር ደርሶባቸው ይሆን?

አልጀዚራን የመሳሰሉ ለኢትዮጵያ ጉዳይ ዜናዎች ቅርብ የሆኑ የሌላ ሀገር ሚዲያዎችስ ይህን ዜና አለመዘገባቸው የሚያሳዩን ነገሮች ምንድን ናቸው?

እስኪ ተወያዩበት።

የአማራ ጉዳይ፤ አለ? ወይስ የለም?

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም

ግንቦት 2006

mesfinተናግሬ ነበር ማለት ዋጋ የሌለው የወሬ ማጌጫ ነው፤ እስቲ ፍቀዱልኝና ልጠቀምበት፤ ከወያኔ ዋና ምሁር፣ ከመለስ ጋር ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት-ለፊት በቴሌቪዥን በተገኛኘን ጊዜ ‹‹አማራ የሚባል ጎሣ የለም፡›› በማለቴ መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ ብቻ ሳይሆኑ ‹‹አማራ-ነን ባዮች›› በቃልም፣ በጽሑፍም፣ በቴሌፎንም ልክ-ልኬን እየነገሩኝ አንጀታቸውን ቅቤ አጠጥተው ነበር፤ ‹አንዲት ሴት ደውለው እብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል፤› ብለውኛል፤ አንድ ሰው የተናገረው ስሕተት ከሆነ ስሕተቱን በማስረጃ ማጋለጥና የራስን ሀሳብ በማስረጃ መትከል ነው፤ እውቀት የሚዳብረው፣ ሰዎች የሚማሩትና በእድገት ጎዳና የሚጓዙት በተጨባጭ ማስረጃ መነጋገር ሲችሉ ብቻ ነው፤ እኔ አማራ የለም፣ ዜሮ (0) ነው፤ አልሁ፤ አማራ አለ፣ አንድ አለ፤ (1) ነው ያለ ሰው የአንድን ዋጋ ማሳየት አለበት፤ አማራ የለም የሚል ዜሮ ነው ማለቱ ስለሆነ ከሌለ ነገር ምንም አይጠብቅም፤ ከአለ ነገር (ከ1) ብዙ ነገሮችን መጠበቅ ይቻላል።

ዱሮ በልጅነታችን ጭራቅ የሚሉት ማስፈራሪያ ነበረ፤ በአለፉት ሃያ ሦስት ዓመታት አማራ የሚባል ጭራቅ ማስፈራሪያ፣ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ቋት እንደሆነ ሲነገር ቆየ፤ መለስ ዜናዊም እየደጋገመ ‹አከርካሪቱን ሰብረን ሁለተኛ እንዳያንሰራራ› እናደርገዋለን እያለ እንደዛተ የተሰበረውን አከርካሪት ሳያይ ሞተ፤ በሕይወትም እያለ ቢሆን መለስ ዜናዊ አከርካሪቱን እሰብረዋለሁ የሚለውን አማራ የተባለ ስያሜ እንደሹመት ለነበረከት ስምዖንና ለነተፈራ ዋልዋ ይሰጥ ነበር፤ የክብር ጎሣ እንበለው! ራሱም ቢሆን ከዚህ የክብር ጎሣ ቤተሰብነት አልራቀም፤ አከርካሪቱ እንኳን ሊሰበር አልተገኘም!

ስንት ሺህ ሰዎች አማራ ናችሁ እየተባሉ ከስንት ስፍራ ተፈናቀሉ? አማራ ማለት እነዚሁ የተፈናቀሉት፣ በየጫካው የተገደሉትና የተሰደዱት ብቻ ናቸው? ሌሎችም ካሉ የጎሣ ዝምድና ሳይስባቸውና ከተፈናቀሉት ጋር አብሮ ለመቆም ለምን አልቻሉም? በጋምቤላ በደረገው ጭፍጨፋ የተጨፈጨፉት ጎሣዎች በጣም ትንሽም ቢሆኑ ከካናዳ እስከ አውስትራልያ ዓለምን ያዳራሱት የጎሣ ዝምድና ስሜት ለምን ለእነዚህ አማራ ለተባሉት ተፈናቃዮች አልሠራም? እንግዲህ አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉትና የሚሰቃዩት ዘመድና ደጋፊ የሌላቸው ሰዎች ናቸው ማለት ነው፤ ሰውነታቸውም ቢሆን በሕግ ያልተረጋገጠላቸው፣ ሕግ የማይመክትላቸው ናቸው ማለት ነው፤ ይህንን ክርክር ከገፋንበት ዜግነታቸውንም የምንጠራጠርበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን፤ ደርግ በጎሣ ላይ የተመሠረተ የውትድርና ሥልጠና ያደረገ ይመስለኛልና በዚህ ጉዳይ ላይ የደርግ ባለሥልጣኖች፣ በተለይም ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አንድ ቀን የሚነግሩን ይኖራል የሚል ግምት አለኝ።

አጥቂና ጨቋኝ ነፍጠኛ የሚባለው ሕዝብ ሲጠቃና ሲበደል ከኡኡታ በቀር ድምጹ የማይሰማው ትርጉሙ የህልውና ነው? ወይስ የወኔ? በሌላ አነጋገር አማራ የሚባል ጎሣ በእርግጥ አለ? ወይስ የለም? ከአለ የሚወራለትን ነፍጠኛነትና ወኔ ምን ዓይነት ብል በላው? ይህ ክርክር ከሃያ ሦስት ዓመታት በፊት አማራ የሚባል ጎሣ አለ ብለው የሞገቱኝን ሰዎች (የሞተውን መለስንና ያሉትን ጓደኞቹን ጭምር)፣ የመላው አማራ ይባል የነበረውን ድርጅት፣ ብአዴን የሚባለውን የወያኔ ድርጅት መሠረተ-አልባነት ለማሳየት እንጂ የሌለውንና ከዚህ በፊት ተቆስቁሶ ያልተነሣውን ጎሣ ለማነሣሣት አይደለም፤ የሌለ ነገር ቢቆሰቁሱት አይነሣም,

በአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን፣ የሚገደሉትን፣ የሚሰቃዩትን ሁሉ ‹‹ሰዎች›› ብናደርጋቸውና ሰዎች ብንላቸውስ? ሰው መሆን የተፈጥሮ ነው፤ ልለውጥህ ቢሉት አይለወጥም፤ ሰው ሆኖ ተወልዶ ሰው ሆኖ ይሞታል፤ ሰው መሆናቸውን ወንጀል የማድረግ ዝንባሌ የሚኖረው ሰይጣን ብቻ ይመስለኛል።

ወይም አማራ የክርስቲያን ሃይማኖትን ተከታይነት የሚገልጽ ስያሜ አድርገን ብንወስደው የእነዚህ ሰዎች መፈናቀል፣ መገደል፣ መሰቃየትና መሰደድ ክርስቲያኖች እንዲጠፉ ለማድረግ ነው? ይህ ከሆነ አንድ ጸረ-ክርስቲያን ኃይል አለ ማለት ይመስለኛል፤ ይህ መደምደሚያ ችግር አለበት፤ ፓትርያርክና ሊቃነ ጳጳሳት ሰይሞ ጸረ-ክርስቲያን ተግባር ነጋ-ጠባ ማከሄድ አታላዩንና ተታላዩን ለመለየት ያስቸግራል።

እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን ‹‹ኢትዮጵያውያን›› ብንላቸውስ? ኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ ዜግነት ነው፤ ዜግነት አንድ ሕዝብ በደሙና በአጥንቱ የሚገነባው ነው፤ ዜግነት የሕግ ከለላ አለው፤ ይህንን የሕግ ከላላ ተነፍገው በኢትዮጵያ ምድር ከያለበት የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉት፣ የሚሰቃዩትና የሚሰደዱት ኢትዮጵያዊ ዜግነትን ለማጥፋት የተደራጀ ኃይል አለ ማለት ነው።

አንግዲህ አማራ የሚባሉት ነፍጥ የሌላቸው ነፍጠኞች በምድረ ኢትዮጵያ ሰዎችም ሆነው፣ ክርስቲያኖችም ሆነው፣ ኢትዮጵያውያንም ሆነው መኖር አይፈቀድላቸውም ማለት ነው ወደሚል መደምደሚያ በግድ መድረሳችን ነው፤ ያዋጣል ወይ?

ግራም ነፈሰ ቀኝ አማራ የሚባል ጎሣ እንደሌላ በስያሜው ላይ የሚደርስበትን ጥቃት ለመመከት እንኳን ባለመቻሉ አስመስክሯል፤ በሕይወት ላለ በህልውና ላይ የሚደርስበትን ጥቃት መመከትና መከላከል የተፈጥሮ ነው፤ ይህ ሳይሆን ሲቀር ህልውና የለም።


‘ክርስትና የዋህንን በአድርባይነት መርዝ እየወጉ እና እየተሽሞነሞኑ የሚኖሩበት ሕይወት አይደለም” በክርስትና ስም ”አትናገሩ” ለማለት ለሚዳዳቸው የበግ ለምድ ለባሾች ምላሽ ትሁንልኝ

$
0
0
ዛሬ (ስሙን አልጠቅሰውም) ማንነቱን የማላውቀው ግን ፋይሉ አናት ላይ ነጠላ ለብሶ የተነሳ ፎቶ በትልቁ የለጠፈ የፌስ ቡክ ገፄ አባል እንዲህ የሚል መልዕክት በውስጥ መስመር ላይ ለጠፈለኝ። ” አይ ክርስትና—–ቤተክርስቲያንን ማገልገል አይሻልህም? ” ወዘተ የሚሉ ቃላት ይዟል።ግለሰቡን ከእዚህ በፊት ስለማላውቀው ፋይሉን ከፍቼ ማየት ጀመርኩ።ፕሮፋይሉ ላይ በትልቁ ነጠላ ለብሶ የተነሳውን ፎቶ ለጥፏል።ከወደ አናቱ የሀገራችን ክፍል መሆኑን ፋይሉ ይናገራል።ወደውስጥ ገባሁ።አንዱ ክፍል ላይ አቶ መለስን ፎቶ በትልቁ ለጥፎ የአምላክ ያህል ”ውዳሴ መለስ” ድርሰት ብጤ ለጥፏል።ቀጠልኩ መጎርጎሬን በሌላ ቀን አቶ ኢሳያስን ለጥፎ ከውክሊክ ያገኘውን ታሪካቸውን ተርጉሞ ምንጭ ውክሊክ ብሎ አያይዞታል።በተለይ በእዚህኛው ክፍል ላይ አቶ ኢሳያስ ”በነፃ ምርጫ የተመረጡ በዲሞክራሲ የሚያምኑ” የሚል ጨምሮበታል። እናም ቀደም ብዬ ከቅንነት ሃሳብ የሰጠ የመሰለኝ ሰው አሳዘነኝ እና ለእርሱ እና በቤተክርስቲያን ስም ለሚያጭበረብሩ ሁሉ እንዲህ ማለት ፈለኩ።
ለወዳጄ እና ለመሰሎችህ (የማስታወሻዬ አርዕስት ነች)
138ክርስትና የማጭበርበርያ ጉረኖ አይደለም።ክርስትና እንደ እባብ እየተቅለሰለሱ የዋሃንን የሚነድፉበት የሸለምጥማጦች ጅራፍ አይደለም።ሰው በክርስትና ውስጥ ሲኖር ፍርሃት፣አድርባይነት፣ጥቅምን ማስቀደም እና እኔ ብቻ ‘ደረቴ ይቅላ ሆዴ ይሙላ’ የሚል ከሆነ ክርስቲያን ባይሆን ይመረጣል።ክርስቲያን በመንግስት ዘረኝነት ሲታወጅ ከንፈር እየመጠጠ ዘረኝነትን የሚጠየፈውን መፅሐፍ ቅዱስ ይዞ ሕዝብ ከሚያታልል እራሱን ወደ ትልቅ ባህር ቢወረውር ይሻለዋል።ክርስቲያን የሰው ዘር በሙስና እና በአድልዎ ሲሰቃይ መቃወም ካልቻለ ባይፈጠር ይበጀዋል። ክርስቲያን ሰዎች ሲሰደዱ ያሰደዳቸውን ቡድን ከመውቀስ ይልቅ በቤተ ክርስቲያን ስም በስዱዳን ቁስል ላይ የመርዝ እንጨቱን ከላከ ፍርዱ አይቀርለትም።ክርስቲያን ሰዎች ሲታሰሩ ለታሰሩት መጮህ ካልቻለ እራሱን በራሱ በሰይጣን የጥቅም አሽክላ እንደተበተበ እና ቤተክርስቲያን እየሄደ የዋሃንን የሚሸነግል ይሁዳ ቢባል ሲያንሰው ነው።
በሀገራችን ዘረኝነት ነገሰ በክርስትና ስም እንዳላዩ ያለፉ ቃል ላልተነፈስን ወዮልን፣
በሀገራችን የዋሃን ንፁሃን ምንም የተደበቀ አጀንዳ የሌላቸው መውጫ መግቢያቸው የሚታወቅ (ዞን 9 መጥቀስ ይቻላል) በግፍ ታሰሩ።በክርስትና ስም እኛ የቤተክርስቲያን ነን እያልን ቃል ያልተነፈስን ወዮልን!
በሀገራችን ሰዎች በዘራቸው እና በቋንቋቸው ብቻ እየተለዩ ከኖሩበት ስፍራ በግፍ ተባረሩ (ሐረር፣ወለጋ፣ጉርዳፈርዳ፣ጅጅጋ፣ወዘተ) አይናችን እያየ በክርስትና ስም እኛ የቤተክርስቲያን ነን እያልን ቃል ያልተነፈስን ወዮልን!
የሀገራችን ድንበር እየተቆረሰ ለባዕዳን በሙስና እና በሀገር ክህደት ተቸበቸበ።በክርስትና ስም እኛ የቤተክርስቲያን ነን እያልን ቃል ያልተነፈስን ወዮልን!
ኢትዮጵያውያን በባዕዳን እየታሰሩ በእየቦታው ሲንገላቱ ”ታስሬ አልተየቃችሁኝም” የምትለዋን ቃል ወደጎን ትተን በክርስትና ስም እኛ የቤተክርስቲያን ነን እያልን ቃል ያልተነፈስን ወዮልን! ለታሰሩት፣በዘር እና በቋንቋ አድልዎ እየተደረገባቸው ለተንገላቱት፣በኢትዮጵያዊነታቸው እየተለዩ ለሚታሰሩት መጮህ ክርስትና ነው። ክርስትና በሙስና ፊታቸው ለሚያብለጨልጩ እና በዘረኝነት ለሰከሩ እና ሃገራቸውን ለጥቅም ለሸጡ ወንጀለኞች በመቆም ወይም በአድርባይነት ዝም በማለት አይገለጥም።ክርስትና የዋህንን በአድርባይነት መርዝ እየወጉ እና እየተሽሞነሞኑ የሚኖሩበት ሕይወት አይደለም።
ጉዳያችን
ሰኔ 25/2006 ዓም (ጁላይ 2/2014)

Source: gudayachn

የሙስሊሞች ተቃውሞ እንደገና (የሙስሊሞችን ተቃውሞ እደግፋለሁ፣ ከተቻለም እሳተፋለሁ)

$
0
0

Abrha Destaየመጀመሪያው የከተሞች ምድብ ተቃውሞው የሚካሄደው በከፍተኛ የድምጽ ተቃውሞ ሲሆን ተቃውሞው የሚደረግባቸው ከተሞችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1) በአዲስ አበባ ከተማ
2) በኦሮሚያ:- መቱ እና ዶዶላ ከተማ

ከላይ በተጠቀሱት ሶስት ከተሞች ተቃውሞው የሚከናወነው በድምጽ ይሆናል፡፡ በአዲስ አበባ ተቃውሞው የሚከናወነው በታላቁ አንዋር መስጂድ ላይ ሲሆን በሌሎቹ ደግሞ የትግሉ ማእከል በሆነ የተመረጠ የከተማው መስጂድ ላይ ይሆናል፡፡

ለተቃውሞው ከሚከተሉት 6 መፈክሮች መሀል የገራልንን መፈክር በወረቀት ላይ አስፍረን ይዘን በመምጣት በተቃውሞው ላይ ከፍ አድርገን እናሳያለን፡፡ መፈክሮቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

‹‹ለሀይማኖታዊ መብታችን በፅናት እንቆማለን!!››

‹‹ፍትህ ይስፈን – የታሰሩት ይፈቱ!!›› ‹‹መጅሊስ ለህዝበ ሙስሊሙ ይመለስ!!››

‹‹የእምነት ነፃነታችን ይከበር!!››
‹‹አፈና፣ ግፍ እና ማስገደዱ ይቁም!!››
‹‹የእምነት ቤቶቻችን ክብር ይጠበቅ!››

በእለቱ የምናከናውነው ተቃውሞ ዝርዝር መርሀ ግብር እንደሚከተለው ነው፡-

1. ለ3 ደቂቃ ሰላት እንዳለቀ አንድነታችንን እና ፅኑ መሆናችንን ለማሳየት እጅ ለእጅ በመያያዝ ባለንበት እንቆማለን፤

2. ለ3 ደቂቃ ይዘነው የምንመጣውን መፈክር የሰፈረበት ወረቀት ከፍ በማድረግ የዚያን ጀግና የሀበሻ ልጅ ቢላል (ረ.ዐ) ድንቅ ፅናት በውስጣችን በማሰብ ‹‹አሃዱን አሀድ!! አሃዱን አሀድ!!›› የሚል መፈክር በአንድ ላይ እናሰማለን፤

3. ለ3 ደቂቃ የሃይማኖት እና የሰብአዊ መብቶቻችን በከፍተኛ ሁኔታ እየተጣሱ መሆናቸውን በመቃወምና ሰላማዊ ትግላችን መብት የማስከበር ትልቅ ዓላማ እንዳለው ለማሳየት ‹‹መብታችን ይከበር!›› የሚል መፈክር እናሰማለን፤

4. ለ3 ደቂቃ በዚህ የተከበረው የረመዳን ወር ሀያሉ አላህ ነስሩን እንዲለግሰን ከልባችን ዱዓ እናደርጋለን፤ በመጨረሻም ወደየመጣንበት ሰላማዊነታችንን አንደጠበቅን እንመለሳለን!

ድምፃችን ይሰማ

ድምፃችን ይሰማ

Abraha Desta

“በእኔ ስም አይሆነም!”“NON IN MIO NOME”–ሕዝብን የጨፈጨፈ ገዳይ ጀግና አይደለም!

$
0
0

በልጅግ ዓሊ

ክፍል አንድ


ሕዝብን የጨፈጨፈ ገዳይ ጀግና አይደለም!

ልቤ ተሸበረ ከሩቅ ስትጣሪ ሰማሁሽ ሃገሬ፣
ስንቱን ብሶት ላውራሽ እናቴ ዘርዝሬ፣ . . . .

ሀገሬ ድምጽሽን ቀርቤ እንዳልሰማ ፤
አላጥፍ አልጠቀልል መሬት አይደለም ሻማ
ክል እያለ መጥቶ የዝማሬሽ ቃና
ያማልለኝ ገባ ያዘናጋኝ ገባ ከሩቄ ሆነና።

ከሩቅ ቢሆንም ድምጽሽ እንኳን አልጠፋ
ሕያው ያደረገኝ ነፍሴን ያወጀልኝ ነው የልቤ ተስፋ።

Non in Mio Nomeዮሐንስ አድማሱ
ልቤ ተሸበረ /1957

ጣሊያን ቲቮሊ ከተማ የሚገኘው ፍርድ ቤት ሜይ 6/2014 በሰዎች ተሞልቷል። ፍርድ ቤቱ ፍርዱን በሚከታተሉ በመሙላቱ ምክንያት ከፍርድቤቱ ውጭ የፋሽሽቶች ደጋፊዎችም ይሁኑ ተቃዋሚዎች ተሰባስበዋል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታገትና ለወያኔዎች ተላልፎ መሰጠት ለተቀዋሚዎች የማንቂያ ደውል ነው

$
0
0

(ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌ)

የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው በየመን መታፈንን ከሰማን ጊዜ ጀምሮ አብዛኛው ሀገር ወዳድና የኢትዮጵያን የነጻነት ቀን ናፋቂ ወገኖችን ያሳሰበና እረፍት የነሳ ጉዳይ እንደሆነ በየቀኑ በየማህበራዊ ድህረ ገጽ ከሚወጡት ነገሮች መረዳት እንችላለን :: በርግጥ ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች ብዙ የተማሩ ኢትዮጵያን ሙህሮች፣ ብዙ የፖለቲካ ሰዎች በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ ለብዙ ነገር ሰላባ ሲሆኑና ህይወታቸውን እስከሚያጡ ድረስ ሆነዋል :: ሰሞኑን ግን በነጻነት ታጋያችን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ በየመን የደረሰው እገታና ለነብሰ በላው የወያኔ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱ እውን እንደሆነ ስሰማ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በእኔም ላይ በጣም ከባድ የሆነ የሀዘን መንፈስ የፈጠረብኝ ሲሆን በወያኔ መንግስት ላይ ያለኝን ጥላቻ ይበልጥኑ ከፍ እንዲል ያደረገ ክስተት ሆኖል እንዳርጋቸው ወደ ትግል ሲገባ እራሱን ለሞት በማዘጋጀት ሊደርስበት ያለውን ማንኛውንም መሰዋትነት ለመክፈልና ሁሉንም መከራ ለመቀበል ዝግጅነቱን በማሳየት እንደሆነ ከሚሰራቸው ስራዎች መረዳት ይቻላል ::በርግጥ እውነተኛ ትግል መስዋህትነትን እንደሚያስከፍል ባውቅም የእኝህ እድሜያቸውን በሙሉ ለነጻነት ሲታገሉ የኖሩ የነጻነት ታጋይ ላይ የደረሰው ነገር ግን በውስጤ ሁለት ነገሮችን ጭሮብኛል ያለፈ ሲሆን አንድን ነገር ግን እንዳውቅ ረድቶኛል:: አንዱ እንዳርጋቸው ቢታሰርና የፈለገው ነገር በእሱ ላይ ቢደርስ እንኮን ለወያኔዎች የእግር እሳት የሆኑ እንዳርጋቸው የወለዳቸው ብዙ ሚሊዩኖች የነጻነት ታጋዮች ኢትዮጵያኖች በየስፍራው ተወልደዋልና ደስ ይለኛል::

Photo: የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው በየመን መታፈን ሁላችንንም ኢትዮጵያኖችን የወያኔን መሰሪነት አውቀን በቁጣ በወያኔ መንግስት ላይ መነሳት ይገባናል ::የወያኔ መንግስት እሱን በሚቃወሙ ባሉ ሰዎች ላይ ሁሉ እየወሰዳቸው ያለው በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ምን ያህል አንባገነን መንግስት እንደሆነ አመላካች ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታፈንም አመላካች ሲሆን በወያኔ ሴራ የተቀነባበረ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም :: የወያኔ መንግስት ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር በነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ላይ የሆነው ነገር የኢትዮጵያን ሕዝብና ተቃወሚዎችን ይበልጥ የሚያጠነክርና ለትግል ይበልጥኑ እንዲነሳሱ የሚያደርግ መሆኑ ነው:: የእንዳርጋቸው በየመን መታሰር ለተቃዋሚ መሪዎች ሊያነቃቸው ያለ ትልቅ ደውል የተደወለ ነው የሚመስለኝ :: በሀገርም ውስጥ በውጭም ያሉ የተቀዋሚ ድርጅቶች አንድ በመሆንና በመተባበር ልዮነታችንን ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብንም  በማስተባበር በጋራ ጠላታችን ላይ በመዝመት ይሄን አረመኔ መንግስት ለማስወገድ በጋራ እንናሳ::  ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ውድቀት ለወያኔ!!

Photo: የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው በየመን መታፈን ሁላችንንም ኢትዮጵያኖችን የወያኔን መሰሪነት አውቀን በቁጣ በወያኔ መንግስት ላይ መነሳት ይገባናል ::የወያኔ መንግስት እሱን በሚቃወሙ ባሉ ሰዎች ላይ ሁሉ እየወሰዳቸው ያለው በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ምን ያህል አንባገነን መንግስት እንደሆነ አመላካች ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታፈንም አመላካች ሲሆን በወያኔ ሴራ የተቀነባበረ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም :: የወያኔ መንግስት ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር በነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ላይ የሆነው ነገር የኢትዮጵያን ሕዝብና ተቃወሚዎችን ይበልጥ የሚያጠነክርና ለትግል ይበልጥኑ እንዲነሳሱ የሚያደርግ መሆኑ ነው:: የእንዳርጋቸው በየመን መታሰር ለተቃዋሚ መሪዎች ሊያነቃቸው ያለ ትልቅ ደውል የተደወለ ነው የሚመስለኝ :: በሀገርም ውስጥ በውጭም ያሉ የተቀዋሚ ድርጅቶች አንድ በመሆንና በመተባበር ልዮነታችንን ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብንም
በማስተባበር በጋራ ጠላታችን ላይ በመዝመት ይሄን አረመኔ መንግስት ለማስወገድ በጋራ እንናሳ::
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ውድቀት ለወያኔ!!

አሁን ላይ ነገሮች ሁሉ የተቀየሩ ነው የሚመስለው የአቶ እንዳርጋቸው ጉዳይ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ከመሆን አልፏል :: በአሁኑ ሰአት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ እና የአመለካከት ልዩነቱን ወደ ኋላ በመተው እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ቃል ጉዳዮን በንቃት እየተከታተለው ሲሆን የታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መያዝና በወያኔ እጅ ላይ መውደቅ ለአንዳንድ ሆድ አደር ወያኔዎች ብቻ ፈንጠዝያ የፈጠረና ያስደሰተ ቢመስልም ብዙ ኢትዮጵያ ወገኖችን ግን ከሌላዉ ጊዜ በተለየ መልኩ በእልህና በቁጭት ለትግል እንዲነሳሱ ያደረገ ክስተት እንደሆነ በፊስ ቡክ በውስጥ መልክት ከሚደርሰኝ ደስ የሚልና የሚያበረታታ ጽሁፍ ለመረዳት ችያለው::

ድርጊቱ ለተቃዋሚዎች የማንቂያ ደውል መሆን ይገበዋል ለነጸነት እንታገላለን የሚሉ ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ለነጻነት እየታገልን ያለን ኢትዮጵያኖች የወያኔን መሰሪነት አውቀን ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ በቁጣ በወያኔ መንግስት ላይ መነሳትና በወያኔ ላይ ያለንን የከረረ ጥላቻ በእንቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ ልንገልጽ ይገባናል ::የወያኔ መንግስት ስልጣኑን በሀይልና በጉልበት ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ እሱን በሚቃወሙ ባሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ ሁሉ ይኼው አረመኔው የወንበዴ ስብስብ እየወሰዳቸው ያለው በግፍ የተሞሉ እርምጃዎች ምን ያህል አንባገነን መንግስት እንደሆነ አመላካች ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታፈንም የዚሁ አመላካች ነው::ዛሬ ላይ የአንዳርጋቸው መታፈን በርግጥ የወንበዴዎችን ቡድን ጮቤ እያስረገጣቸው እንደሆነ አስባለው የወያኔ መንግስት ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር በነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ላይ የሆነው ነገር የኢትዮጵያን ሕዝብና ተቃወሚዎችን ይበልጥ የሚያጠነክርና ለትግል በጥንካሬ እንዲነሳሱ የሚያደርግ መሆኑ ነው:: የእንዳርጋቸው በየመን መታገትና በወያኔዎች የተቀነባበረ ሴራ ለወያኔዎች ተላልፎ መሰጠት የየመንን መንግስት ባደረገው ከህግ ውጭ የሆነ አሳፋሪ ድርጊት ለወደፊት የታሪክ ተወቃሽ የሚያደርገው ቢሆንም የመኖች በሰሩት ስራ ወደ ፊት ተጠያቂ እንደሚሆኑበት ምንም ጥርጥር የለኝም::ዋናው መታወቅ ያለበት ግን ድርጊቱ ለተቃዋሚ መሪዎች ትልቅ የቤት ስራ የሰጠና ሊያነቃቸው ያለ ደውል የተደወለ ነው የሚመስለኝ ::

በሀገርም ውስጥ በውጭም ያሉ የተቀዋሚ ድርጅቶች በስሜትና፣ በደመነብስ የምንጓዝበት ዘመን ያብቃ፣ እየሰራን ያለውንም ስራ እንመርምር ፣እንንቃ የወያኔን መሰሪ ሴራ ለማክሸፍ አንድ በመሆንና በመተባበር ልዮነታችንን ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብንም በማስተባበር ነጻነታችንን ህውን ለማድረግ በጋራ ጠላታችን ላይ በመዝመት ይሄን አረመኔ መንግስት ለማስወገድ በጋራ እንናሳ::

በመጨረሻም ለወያኔዎች የማስተላልፈው መልእክት ቢኖር እውነተኛ ታጋይ ሊታሰር ሊሞትም ይችላል የተጀመረውን ትግል ግን ልታስሩትም ሆነ ልትገሉት ከቱ አትችሉም ::ኢትዮጵያ አንድ እንዳርጋቸው ብቻ ሳይሆን ሚሊዮን እንዳርጋቸው ፈጥራለችና በከንቱ አትደከሙ:: ወደዳችሁም ጠላችሁም የእንዳርጋቸውን ፈለግ በመከተል ሁላችንም የነጻነት ታጋዮች ነን!!!

አቶ አንዳርጋቸው አምላክ ከአንተ ጋር ይሁን

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
gezapower@gmail.com

በዚህ ሙቀት መቀጠል ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ያድናል –ወያኔንም ከሥሩ ይመንጥራል!

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 04.07.2014 (ሲውዘርላንድ – ዙሪክ)

573C78Cየምልዕቱ ሙቀቱ የፈላ፣ የማያቋርጥ ጠላትን የሚያርገበግብ፣ የጠላትን መጋኛ የሚያናውጥ ከሆነ ድንበር አልቦሽ የነፃነት እንቅስቃሴ እልህን አመንጭቶ ቁርጠኝነትን መንበር ላይ ያወጣል። ቁርጠኝነቱም በፈንታው ደግሞ እራሱን ወልዶ ተግባራትን በቅድመ ተከተል በስክንት አልምቶ ግንባርን ባለማጠፍ ፍሬ – ዘር የሚያመርትብት አዲስ ምዕርፍን በተደሞ ያውጃል።

ማፈርና አንገቱን ዘቅዝቆ መሄድ ያለበት ታሪክን የገደለ፤ የቀደምት አርበኛ አባቶቻችነን አጽማቸውን ከመቃብር እያወጣ መስዋዕትነታቸውን ዋጋ አልቦሽ ያደረገው፤ ያፈሰሱትን የድል ደም ነጋሪት ለባዕድ ውጭ ወራሪ የሚቸረችረው የማንነት ነጋዴው ሙጃው ወያኔ እንጂ የአባቶቹን አደራ ተረክቦ ለአንዲት ቀደምት ሉዕላዊት ሀገር የሚታገል የነፃነት መንፈስ ሊሆን አይገባም – ፈጽሞ።

በዬትኛውም መስፈርት ቢሆን በቀደሙት ኢትዮጵውያን ደምና አጥንት የቆዬውን የማንነታችን ተቋማት በስልትን በቋሳ መዶሻ የተረተረ፤ በፋስ የፈለጠ፤ በረግረግ አስውጦ የደረመሰ ጃርት የ90 ሚሊዮን የ80 ህብረ ብሄር ቀላማትን ያበበን ማንነት ያቀላ፤ የጥቁር ህዝብ አብነታዊነትን ትርጉምን ያበለዘ – ያፈለሰ ይህን መንፈስ የመምራት አቅምም ተፈጥሮውም ፈጽሞ የለውም። ይህንን ነው በላዩ ላይ እዬተናደ እዬፈረሰ ያለውን ማንነትን ተገንዝቦ በጽናት በህብረትና በአንድነት የቆሰለንውን ዜግነት እንታደገው ዘንድ ዘመኑ በአጽህኖት የሚያስተምረው። በዬትኛውም ሁኔታ ኃላፊነቱን የዘለለ ትውልድ ከተጠያቂነት አይድንም። ሳቢያ ማስታገሻ ቢሆን እንጂ እርግማንን አይፈውስም። ስለሆነም አትኩሮቱ ምክንያታዊ በሆነው እራስን ሆኖ በሁለት እግር የመቆም ጉዳይ ነው።

ለአንድ ጎሳ እጅግ ለወረደ የዘር ትርምስና የጥላቻ ጫጩትን ፍልፍሎ ለሞሸረ ሀገር በቀል ባንዳ ጥቃት እጅ መስጠት እውነትም ደማችን ተበርዟል፤ ተስልበናል ማለት ነው። ስለዚህም ከበፊቱ በበለጠ በጠነከረ – በተሰበበሰ – በሰከነ መንገድ አቅምን ያዳመጠ፤ አቅምን በአግባቡ ሊመራ የሚችል ዘርፍ ብዙ ዘላቂ በመርህ ላይ የተመሰረተ፤ መርህ የሚመራው ጽኑ አለታማ አንድነት ፈጥሮ በመንቀሳቀስ የልብን ማደረስ ይቻላል።

አኃታዊ እራይ የሁለመና ብቁ ወታደር እንዲሆን የምንፈቅድበት አራት ዓይናማው መንገዳችን ደግሞ ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረው አለምን የፈጠረው ሚስጥር ኢትዮጵያዊነት ጄኒራላችን ሊሆን ይገባል። በዚህ ማቀፍ ውስጥ መደማመጥ ከተቻለ የምንፈልገውን ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገን ማግኘት እንችላለን።

መቻቻል ችሎቱ

እንደተረገዘ ህይወቱ።

ይህቺ ግጥም በአንድ ወቅት የቋጠርኳት ነበረች። አሁን ከእኛ የሚጠበቀው ደግሞ፤

የመቻቻል ችሎቱ

በኢጎ ላይ መዝምቱ።  ይህ ከሆነ – እልህ እራሱ፤ እራሱን አፍርቶ መንገዳችን ይጠርጋል። ከግባችንም ያደርሳል። የጠላትህን ብልት ለመርታት የአንተን ብልት ስታሰናደው ብቻ ይሆናል። ለማሸነፍ ሆድ ዕቃውን ማወቅ አለብህ። ስታውቀው ታሸንፈዋለህ። ለማሸነፍ ግን መጀመሪያ ህሊናህን አሸንፈው። ጠላትህን በስሱ ብልቱ ገብተህ ማረድ የምትችለው የታላቁን ራዕይ የጥሪ ድምጽ ለማድመጥ ሥልጡን መንፈስ ሲኖርህ ብቻ ነው።  ቅን ልቦናህን ገቢር ላይ ማዋል ስትችል ብቻ ጠላትህን ታራግፋዋለህ እስከነ ጉቶው።  የቆረጥክ ዕለት በተፈለገው ግዳጅህ ላይ ከነፍስህ ያለህ ወይንም ያልተዛበህ ወይንም ያልሾለክ መሆንህ ታውቀዋለህ። ያን ጊዜ ከቀደምት አደራ በይነት ፍውሰት እንደ ዋጋህ ይከፈለሃል።  ይህ ደግሞ ቢመቱም ቢኖሩም ህይወት ነው። ጧፍ።

ይህ ያሰፈራው ያርበተበተው ወገቡን ሲያልፈሰፍሰው የነበረው ወያኔ የሚወስዳቸው ግልጽ ወይንም ስውር ጥቃቶች የታላቁን ሀገራዊ የአደራ ራዕይ የሚያፍታታ – የሚመክት እያንዳንዱ ስለመፈጠሩ ምክንያታዊነት መተርጎም እንዲያስችለው ይረዳዋል። ይመራዋል። ከጎን ሊቀመጥ የሚገባው መንፈስ ከፈቀደልክለትህ የጀግናህ ሊሆን ይገባል።

የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የእኛ ናቸው። የነፃነት ትግሉ አካል ናቸው። የኢትዮጵያዊነት ረቂቅ መንፈስ ወስጣቸውን አብዝቶ የጎበኘው ነው። የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ  የሠራ አካላት ሴሌ ናቸው። እንጎልም። ስለሆነም ጥቃታቸው ከጎረበጠን ወለም ዘለም ቆሞ፤ ወጣ ገብ ትግል ቆሞ፤ ኢጎ ተገፍትሮ ተቀብሮ – ግልጽ የጠራ መስመርን እንድንከትል አስተምሯል። ቆሞም ይሰብከናል። አባትም ሆኖ ይመክረናል። ይህን ስንተላለፍ ዘመነ – ህግጋትን፤ መርኃ  ነፃነትን፤ ጊዜ ጠገብ አደራን ተላልፈናልና እርግማን ይሆንብናል። እርግማኑ ውስጥን ማጣት ነው። ይህ ደግሞ ከንቱነት ነው።

የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ማናቸውም እንግልትና መከራቸው ለእኛ ከብረት የተሰራ ቁርጥራጭ ጽናትን ለእሳቸው ደግሞ ክስተታዊ (phenomenal) ሰብዕናቸውን የበለጠ ያነጠረዋል። ከመከራ በሰተጀርባ ታላቅ ክብር አለና። ለ እናት ሐገራችን ለኢትዮጵያ ክስተት (phenomenal) ናቸው።

የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፍቅራቸውን ፍላጎታቸውን መውረስ ይቻላል። የሳቸውን የተከደነ ሲሳይ፤ አዳዲስ የሠላጡኑ ጸጋዎችንና ጸሐይ ያልነካቸውን ግኝቶችን፤ የተመክሮ ዝቀሽ ትጋታቸውን መተካት ግን አይቻልም። አንድ ሰው መሰሉ ምንጩ ያልተደባለቀ – ዋና (original) ብቻ ነው ያለው። ለዚህም ነው አሻራችን የተለያዬ የሚሆነው። የውስጥ ቅመማቸው ከነተፈጥሮው ከባለቤቱ ዘንድ ብቻ ነው የሚገኘው።  ይህ ስምዬለሽ ህመም የሚሰማን ከሆነ  ቢያንስ  በእጃችን ላሉት የተገባውን ክብር ለመስጠት፤ ለመንፈሳቸው ጥበቃ ልናደርግላቸው ይገባል። ትውልዱ ሲያጣው ሳይሆን ሃብቱን በእጁ የሚገኘውን ብቃቱን በዝብዞ ለፍላጎት ተጠቃሚ መሆን ብልህንትን ማዘከር ይመስለናል። ለዚህ ደግሞ እኛ አልታደልንም። እስኪ ልብን ይስጠን። አሜን! አብሶ ለዬት ብለው የሚፈጠሩትን ለማግኘት የአንድ ትውልድ ዘመንን ይጠይቃል። ማን የቅኔው ልዑልን ሎሬት ጸጋዬ ገብረምድህንን ተከ? ማን የተከበሩ ፕሮፌስር አስራት ወልደዬስን ተካ? ማን የንጉሦች ንጉሥን ዐጼ ሚኒሊክን ተካ? በጠራ ቋንቋ ትውልድ ሊተካቸው የማይችሉ ብልህ አምድ ወይንም ምሰሶ  (pillar) መሪ አጥተናል። መምራት ሥነ – ጥበብ ነው። ተሰጥዖ። እርግጥ ጥበቡ በክህሎት ሊበለጽግ ይችላል። ይህም ቢሆን በቋንቋ ዶክትሬቱን የወሰደ ሁሉ አይጽፍም። ዬሚናገር ሁሉ የሚዲያ አንባቢ ሊሆን አይችልም፤ የሚጽፍም እንዲሁ። አርቀው አስበው ሥልትን በሥልት አዋቅረው መወደድን ያህል ዲታነትን ማግኘታቸው ግን ለትውልዱ ቅምጥ ሃብት ነው። አብነት – በግንባር ሥጋነት።

ሌላው እውነት ለመናገር ጠላታችን ማን ነው? ዬጠላታችን ፍላጎታችን ለማወቅ የጠላታችን በደል ሥር አለማግኘት ነበር ማለት እችላላሁ። ዛሬስ?! የኔዎቹ የጥንካሬ ምንጩ እኛው ነን። ዓለምን የፈጠረውን ዶግማ በአግባቡ ማድመጥ ከቻልን። ምን ቀረኝ? „ስለምን እንዲህ ሆነ? ስለምን ዜናው ዘገዬ? የምንል እንኖራለንለን።“ ከእግዚአብሄር ፈቃድ ውጪ አንዲት ስንዝር መራመድ አይቻልም። ይህን የሚያውቀው ቀኑን የወሰነው ባለቤቱ ብቻ ነው። „ነገር ሁሉ ለበጎ ይሆን ዘንድ ግድ ነው“ የነፃነት ትግሉ ከእሬት በላይ መራራ ነው። መራራ የሚያደርገው ደግሞ ጦርነቱ የእርስ በርስ መሆኑ ነው። ቀለብ የሚሰፈርልት ሆድ አደረሙ በከብትንት እዬተነዳ ነው። ውስጥን የሚያነብ ዘመን አመጣሽ መሳሪያ እስኪገኝ ድረስ ከመቼውም በበለጠ ጠንቃቃነት በብልህነት፤ ሚዛናዊነት በማስተዋል ይምራን፤ ግብታዊነትን አለመረጋጋትን ሆነ አፍ እላፊን እንግታ። „ሙያ በልብ ይላል“ ጎንደሬ …. አንድ ልከል „ልብ ያለው ሸብ።“ የመከራ እንቅብ ሲሞላ ይፈሳል – ሲከርም ይበጠሳል። ቀጣዩ የወያኔ ጥቃት በዚህ መልክ አይመጣም። ዌኢ ምግብን በመበከል። ወይ የቤተሰብን ሰላም በማወክ። ወይ መኪና ኪስ ውስጥ ፈንጂ በመቅበር ሊሆን ይችላል። ግንባር ላይ የወጣችሁ ወገኖቼ „ሃበሻ ቤት ግብይታችሁን በልክ ታደርጉት ዘንድ በአጽህኖት አሳስባለሁ።

በተረፈ ሽልማቴን ግን በዬትኛውም ሁኔታ በዬትኛውም ቦታ የፈጠራቸው አምላክ ለሰጣቸው መክሊት ጥበቃ ያደርጋል ብዬ አስባለሁ። የተፈቀደ መከራ የተማሰነለት ነውና ይመቻል። አባቶቻችን ፈተና ሲጠፋ ሁለት ሦስት ሱባኤ ይዘው ፈተና ዘገይብን ብለው አምላካቸውን ይጠይቁበታል። ከምድራዊ በረከት የሰማዩ ዝልቅ መሆኑን የማመሳጠር አቅሙም ህይወቱም ስላላቸው። ለአቶ አንዳርጋቸውም ከዚህ በላይ ትርጉም የሚያስፈልገው አይመስለኝም።

አዎን! ነገ ሌላ ቀን ነው። የእኛ ሆኖ ሊመጣ ይችላል። ከዚህ ሌላ የፖለቲካ ድርጅት ሆነ ንቅናቄ የቁብ ማህበር አይደለም። ሥርዓት አለው፤ ደንብ አለው። ከደንቡና ከፕሮግራሙ የመነጨ ደግሞ የውስጥ መመሪያ አለው፤ ከሁሉም የፈለቁ የአፈጻጻም ዝርዝር መመሪያዎች አሉት። በስሜትና በግባታዊነት አንድ ሰው ብቻውን ተነስቶ የሚወስነው ምንም ነገር የለም። አንድን ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት አጋጣሚዎች ሊመሩት አይችሉም። ለዚህም የአደረጃጃት መርሁ ዴሚክራሲያዊ ማዕከላዊነት ዶግማው ነው። የተደራጀ – ድርጅት ባልተደራጀ ሁኔታ ለምን አልተንቀሳቀሰም ተብሎ ሊኮነን ግንቦት 7 በፍጹም አይገባም። የሆኖ ሆኖ አቅም ያላቸው ወገኖች በዬትም አቅጣጫ የሚነሳውን በትእግስትና በችሎት የተገባውን ግንዛቤ በማስጨበጥ አቅምን ማሰባሰብ፤ እቅምን በእጅ ለማቆዬት መባተል ያለባቸው ይመሰለኛል። ሰው ለሰው መዳህኒቱም መፍትሄውም ነው። ሰው ሲጨምር ኃይል ይኖራል። መክሊቱም በመጠንም በአይነትም ይጨምራል። ወቅታዊው ጉዳይ የገጠመን ፈተና ባለቤትነት ሁለንትና ሁላዊነት እንዲሆን ግን የእያንዳንዱ በግል ሁሉም በጋራ መሆን እንዲችል – ማድመጥ – ማስረዳት – መንገድ ማሳዬት ይገባል።

ጌጦቼ — እልህን አርግዞ ድልን ባሰላ እናታዊ ፍቅር ልሰናበት ፈለግሁ። ነገር ግን ቀድም ብዬ በ2013 በመስከረም ጽፌ አዲስ ቦይስ አውጥቶልኝ ከነበረው ውስጥ አንዱን ላላነበባችሁት ወገኖቼ እንሆ በታላቅ ትህትና። የቃላት እርማት ጭማሬ የለበትም። ሊንኩ ከሌላ ድህረ ገጽ አግኝቸዋለሁ  ማመሳከር ትችሉ ዘንድ – እሺ ውዶቼ!

ማሰብ ከመፈለግ በፊት ይቀድማል!

ማንነትን ማን ያክበረው? የሰከነ – ድርጊት!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

ያንዳርጋቸው መንገድና የኔ ጡመራ!

$
0
0

በደረጀ በጋሻው ከምስራቅ አፍሪቃ

አንባገነኖች ባህሪያቸው ተመሳሳይ በመሆኑ በማምን ላይ ሲሞዳሞዱ ህሊናቸውን አይቆረቁራቸውም።

የመን የምትባል ከቀይ ባህር ማዶ ያለች የአረቦች ምድር ሰሞኑን የፈጸመችው የልወደድ ባይነት ፖለቲካዊ “ግልሙትና”ታሪክና ትውልድ በመሪር ትዝታው ሲያስታውሱት የሚኖር ወራዳ ተግባር ነው። ሀገሪቱን ድሮም አትጥመኝም። አሁን ጨርሶ ጠላኋት።

ወገኔ አንዳርጋቸው በምርጫ 97 ማግስት ከወዳጄ ያሬድ ጋር ዝዋይ ማጎርያ ካምፕ መከራ የቀመሰና ወያኔን አብጠርጥሮ የሚያውቅ ፥”ነጻነትን የማያውቅ ነጻ አውጪ”በተሰኘው ምርጥ መጸሐፉ ገዢውን ሃይል በጥልቀት እንድናውቅ የበኩሉን ድርሻ የተወጣና የአውሮፓ ዮሮም ሆነ የንግስት ኤልሳቤጥ ባውንድን በጡረታ እየተቀበለ እንደማንኛውም ዲያስፖራ ፖለቲካን የቢራ ላይ ጨዋታ ማድመቅያ ያላደረገ የነጻነት ፋኖ ነው።

ዛሬ በግፍ አንበሶች ጉድጓድ እንደተጣለው ዳንኤል ከአንድዬ በቀር ምንም ሊታደገው የማይችል ምስኪን መሆኑን ስሰማ ውስጤ ይደማል። ያቺ ሐገር ሊታደጓት የሚባዝኑ ልጆቿን ለነጣቂ አውሬ የምትገብር ምድር በመሆኗ መጨረሻዋ የናፍቀኛል። የኔን ዕድሜ ሙሉ መከራ ስትዝቅና እኔንም ለ18 ዘመናት ስታዝቀኝ መኗሯ ዕድሏና ዕድሌ መጣመሩ በውስጤ እንድብሰከሰክ አድርጎኛል።

ዩጋንዳ ሸራቶን ሆቴል ሚሊኒየሙን ድል ባለ ድግስ የወያኔን ቆንስላ ሳንጨምር ያከበርንበትን ምክንያት አንድ ከካናዳ መጥቶ የነበረ ዲያስፖራ ጠይቆኝ በወቅቱ የጣልነው ዕገዳ ወያኔን “ኢትዮጲያዊ አይደልህም ማለታችን ሳይሆን አላግባብ ያሰራቸውን ጋዜጠኞች፥የሰባዊ መብት ተሟጋቾችና የቅንጅት አመራሮችን ሳይፈታና በሩን ለብሔራዊ ዕርቅ አስካልከፈተ ድረስ” ቢፈልግ የሚቀጥለውን ሚሊኒየም ያክበር ብለን አልነበረም። ዲያስፖራው ወዳጄ ቀደም ሲል እንደኔ ዲያስቁራ በነበረ ጊዜ የንበረው ሐገራዊ ወኔ ኮንዶሚኒየም ቤት ለማግኘት ከተመዘገበበት ጊዜ ወዲህ ሸርተት ያለና ተለጣፊ የሚመስል ማንነት ካነገበ ወዲህ በምናደርጋቸው የሃሳብ ልውውጦች ውስጡ መቦርቦሩን ቆሌዬ ነግሮኛል።ምንም ሆነ ምንግን እውነቱን መንገር የኔ ዐቢይ ተግባሬ ነበርና ጋትኩት።ካስመለሰውም ጉዳዩ የርሱ ይሆናል።

ዛሬም ካለንበት ብሔራዊ ቀውስ ለመው

የድምጻችን ይሰማ ወቅታዊ ጽሑፍ፡ ሺህ ሆነን እንደ አንድ፤ አንድ ሆነን እንደ ሺህ –የፅኑዎች ትግል

$
0
0

ከድምጻችን ይሰማ የተላለፈ ወቅታዊ ጽሁፍ
ቅዳሜ ሰኔ 28/2006

የኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ የከፈተው ሁለንተናዊ ጥቃት እና ጭቆና በብዙ ሚሊዮናት ዜጎች ላይ የተከፈተ ጥቃት ቢሆንም እኛ … ብዙ ሚሊዮናት… ዜጎች ግን ብዝሃነታችን፣ የቋንቋችን መለያየት እና የብሔራችን አንድ አለመሆን እክል ሳይፈጥርብን በእምነት ገመድ ተሳስረን የተከፈተብንን ጥቃት ስንመክት እነሆ ሦስተኛ ረመዳናችንን ያዝን።
muslim1
በእነዚህ አመታት ውስጥ ‹‹ወርቅ በእሳት ይፈተናል!›› እንዲሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ከባድ የእንግልት እና የመከራ ጊዜያትን አሳልፈናል። መንግስት አንድ መንግስት በዜጎቹ ላይ ሊያደርሰው የሚችለውን ሰቆቃ አንድም ሳያስቀር አሟጦ በእኛ ላይ አድርሶብናል። የሐምሌ 6/2004 የሌሊት ጭፍጨፋ፣ የአርሲ አሳሳው ግድያ፣ የገርባ፣ የደጋንና የሀረሩ ሕይወት ቀጠፋ፣ የዒድ ሶላቱ ህፃንን ከአዛውንት፣ ወንድን ከሴት ያልለየ ድብደባና ግድያ፣ በማእከላዊ በወኪሎቻችን እና በበርካታ ወንድም እና እህቶቻችን ላይ የተፈፀሙ ዘግናኝ እና ኢሰብአዊ አካላዊ ጥቃቶች፣ እንዲሁም ተቆጥረው የማይዘለቁ የእስር፣ የድብደባ እና አካል የማጉደል ጥቃቶች ወሰን ያለፉና መንግስታዊ ጭካኔ የታየባቸው የሰቆቃ ዳራዎች ነበሩ።

የእነዚህ ሁሉ እርምጃዎች የመጨረሻ ግብ ደግሞ አንድነታችንን መበተን፣ ተስፋችንን ማጨለም እና ወደ አፄው ዘመን የተሸማቀቀ ማንነታችን መመለስ ነበር። ዳሩ ግን በፍየል ዘመን በግ ሊያደርጉን ለሚሹ አካላት እጅ ባለመስጠት እና አንድነታችንን በማጠናከር፣ ‹‹ብልጦች አይደለንም! ብልጣ ብልጦች ግን አያታልሉንም!›› እያልን የተቃጡብንን ጥቃቶች ስንመክት ከርመናል። ወደ ፊትም በአላህ (ሱ.ወ) እርዳታ በዚሁ የአንድነት መንፈስ የሚደርሱብንን ጥቃቶች በሙሉ መመከታችንን እንቀጥላለን!
ሺህ ሆነን እንደ አንድ አካል እንድንታገል መሠረቱን የጣሉልን ደግሞ ‹‹አንድ ሆነው እንደ ሺህ›› መታገል የቻሉት ብርቅዬ ወኪሎቻችን ናቸው። አዎን! ወኪሎቻችን አንድ ሆነው እንደ ሺህ ታግለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ የተሰነዘረውን ዱላ ብቻቸውን በማእከላዊ ተጋፍጠውታል፡፡ አቋማቸውን ለማስለወጥ፣ ቅስማቸውን ለመስበር እና ተስፋቸውን ለማጨለም ታቅዶ የደረሰባቸው ኢሰብአዊ ጥቃት ሳይበግራቸው ከብረት ጀርባ ሆነው አቋማቸውን ለህዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡ ስቃዩን እየተሰቃዩለት ላለው የኢትዮጵያ ሙስሊምም የእንኳን አደረሰህ መልእክት አድርሰዋል፡፡ ፅኑ ሆነው ፅናትን አስተምረውናል።

ፅናት ሰላማዊ ትግል ግቡን ይመታ ዘንድ ትልቁ መስፈርት ነው። በዓለም ዙሪያ ግባቸውን መምታት የቻሉ ሰላማዊ ትግሎች አመታትን የወሰዱ፣ የታጋዮችን ፅናት የፈተኑ እና አሜኬላቸው የበዛ ነበሩ። የእኛ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ትግልም ከዚህ የተለየ ሊሆን እንደማይችል መገመት ይቻላል። የትግሉን የመጨረሻ ፍሬ ለማየት ምናልባትም የትውልድ ቅብብሎሽን የሚፈልግ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ ግን እንደ አላህ (ሱ.ወ) ፍቃድ በቅርቡ ድላችንን እንደምናየው ተስፋ እናደርጋለን።

ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ… ‹‹እንደ ታጋይ በዚህ ትግል ውስጥ ማበርከት ከምንችለው አስተዋፅኦ ምን ያህሉን አበርክተናል? ትግሉን እስከ ድል ደጃፎች ድረስ በፅናት ለመቀጠል ዝግጁነታችን ምን ይመስላል? በትግሉ ዙርያ ምን ያህል የመረጃ ልውውጦችን እናደርጋለን?››

እኒህን እና መሰል ጥያቄዎችን ራሳችንን እየጠየቅን እኛም እንደወኪሎቻችን ሁሉ ሺህ ሆነን እንደ አንድ ከመታገል በዘለለ አንድ ሆነን እንደ ሺህ የምንታገልበትን እና የድሉን ጊዜ የምናቃርብበትን መንገድ ማየት ያስፈልገናል።
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!


“ሁለቱ ታላላቅ ዕቅዶች” ክፍል 4 (የመጨረሻ) (ዮፍታሔ)

$
0
0

ለሕወኀት ቀኑ በፍጥነት እየጨለመ መሆኑ ግልጽ ቢሆንም እስካሁንም ምንም ዓይነት የማስተካከያ ርምጃም ሆነ  የመለሳለስ አቋም ከማሳየት ይልቅ በተለመደው እብሪቱ የመቀጠሉ ምክንያት ሊሠራ የሚችል ዕቅድ አለኝ ብሎ  ከማመን ነው። ከሰሞኑ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን አግቶ እስከመውሰድ ድረስ የደፈረበት ድርጊት አገዛዙ  የደረሰበትን የፍርኃት ደረጃ በግልጽ የሚያሳይ ቢሆንም ‘መውጫ ቀዳዳ አለኝ’ ብሎ የሚያስበው አስተሳሰብ  ሥር የሰደደ መሆኑን የሚያመለክትም ጭምር ነው። ‘እነዚህን ዕቅዶች ብዙ ሠርቸባቸዋለሁ፣ ዝግጅቶቸን  ወደማጠናቀቅ ደርሻለሁ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እየኖሩ ከመሥጋት እጅግ የተሻለ ዕቅድ ነው’ ብሎ ያምናል።  [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]

Comment

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UNO) ሁላዊ ህገ መንግሥቱ ለፎቶ እንድናዬው ወይንስ –ሚዛን?

$
0
0

ከሥርጉተሥላሴ 06.07.2014 (ሲዊዘርላንድ -ዙሪክ)

Andargachewእንደ መግቢያ – አውሬነትና ሰብዕዊነት ሲፋጠጡ ዳኛው የዓለም አቀፉ ህገ – መንግሥታዊ ዓውጅ ነው ለገኃዱ ዓለም። ግን ይቻለዋልን አውሬን ጠርቦ ለመግራት ….. !?! ድርጅቱ የተባባሩት መንግሥታት (UNO)ፍጥረተ ነገርና ነፍሱ፣ ደሙ ሆነ ፕላዝማ (plasma) እንዲሁም የሠራ አካላቱ ድንጋጌዎቹ ሲንቀሳቀሱ ህልው መሆኑን ያውጃሉ። ድንጋጊያት ድርጊት ላይ ተግተው ሲገኙ እስትንፋስ እንዳላቸው ያበሥራሉ። ካልሆነ ግን ያማረ ትጠቅ ብቻውን ፋሽኮ ነው – ለሥርጉተ። ትጥቅ ከተከላካይነት አልፎ እንደ ፊፋዋ ድንቡልቡል መረብ ላይ ጎል ማስቆጠር ሲችል – የዓለሙን የሰብዕዊ መብት ምልከተ ዐጤ (UNO) ህልውናውን በተገባው ሁኔታ እንደ ተፈጥሮው ሊያብራራ ይችላል። የልቡ ትርታ በትክለኛው ምት ላይ ስለመሆኑ ያውጃል። አቅም የሚለካው ከሸር ከታጠበ መቻል ይመስለኛል  [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—

 

 

ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል፤የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል። ነጋ አባተ (ከእሥራኤል)

$
0
0

ይህቺ እራፊ የምትመስል እና ህልቅ መጠቅለያ የሆነች ብሂል ከአበው የተወረሰች ግን ደግሞ  ያልመነዘርናት ከባለጠጋ ድሆች የተገኘች ሃብት ናት ። በነገራችን ላይ እኔ በምኖርባት በሃገረ  እሥራኤል ትውልደ ኢትዩጵያውያን የሆኑ ተረትና ምሳሌዎች ወደ ዕብራይስጥ ቋንቋ ተተርጉመው  በተውኔቱም ፦በሥነ_ጽሁፉም ውስጥ እየተዶሉ ሲቀርቡና ትውልዱ ሲታነጽባቸው ሳይ እኛ የእኛን  እየጣልን ፤ የሩቅ አሻግረን እያየን በምኞት የምንከንፍ ምስኪን ህዝቦች መሆናችንን እያየሁ  እገረማለሁ። በእጃችን ባለው አስተውለን የማንማር በመሆናችን! ። ይቅርታ በወቀሳ በመጀመሬ። —-[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—–

Comment

እኔም አንዳርጋቸው ነኝ! እኔም ግንቦት ሰባት ነኝ! (በአበበ ገላው)

$
0
0

የአፓርታይድ ስርአት መገለጫዎች አድልኦ፣ የዘር መከፋፈል፣ ጭቆና፣ ምዝበራ፣ ዝርፊያ፣ የመሬት ንጥቂያ፣ ግድያ፣ እስራት፣ ግርፊያ፣ ሰቆቃ፣…ዋነኞቹ ናቸው። እነዚህም የአፓርታይድ ስርአት መገለጫዎች ከደርግ የከፋው የህወሃቶች ስርወ መንግስት ዋነኛ ባህሪያት መሆናቸው አለም ያወቀው ጸሃይ የሞቀው እውነታ ነው።
abebe
ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ፣ ህወሃት መራሹ ፋሺስታዊ ስርወ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በርካታ ዘግናኝ ወንጀሎችን ፈጽሟል። በኦሮሚያ ክልል ገበሬዎች ያለ አግባቡ ከመሬታቸው መፈናቀላቸውን የተቃወሙ ተማሪዎች ላይ ተኩስ በመክፈት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያና የአካል ጉዳት ፈጽሟል። ከዚህም አልፎ በሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎች የጅምላ እስር፣ አፈና፣ ሰቆቃና ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀል ገጥሟቸው ህይወታቸው ተመሰቃቅሏል፣ ህልማቸው ጨልሟል።
ህገመንግስታዊ መብታችን ይከበር ከማለት ያልዘለለ ጥፋት ያላጠፉ የዞን ፱ አባላትን ያለምንም ማስረጃና ክስ በህገወጥ መንገድ በእስር ቤት በማጎር ከፍተኛ የአካልና የስነ ልቦና ጥቃት እንዲፈጸምባቸው ተደርጓል። ከወለጋ በሺ የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በኦህዴድ መሪነት በደረሰባቸው ከፍተኛ ጥቃት ሳቢያ ቤትና ንብረታቸውን ትተው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። የቀድሞው የጋምቤላ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ እና ሌሎች ሰባት የክልሉ ተወላጆች ከደቡብ ሱዳን በህወሃት የጸጥታ ሃይሎች ታፍነው፣ ከፍተኛ ድብደባና ሰቆቃ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ በሽብር ወንጀል ተከሰዋል።
በተመሳሳይ በየመን በኩል ወደ ሶስተኛ አገር ይጓዙ የነበሩት የግንቦት ሰባት ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመንና የህወሃት የደህንነት ሃይሎች ታፍነው ወደ አዲስ አበባ ተወስደው ከፍተኛ ድብደባና ሰቆቃቃ እንደተፈጸመባቸው ለማወቅ ተችሏል። በመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል እንጂ የህወሃቶችና የጋሻ ጃግሬዎቻቸው ወንጀል ተዘርዝሮ አያልቅም።
ህወሃት የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ገንጥዬ ሪፐብሊክ አቋቁማለሁ በሚል ጠባብና ዘረኛ አላማ ጫካ ከገባ የዛሬ ፵ አመት ጀምሮ በአገራችን እና በህዝቧ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፍና በደል መፈጸሙ ያደባባይ ምስጢር ነው። ህወሃቶች በየእለቱ በሚፈጽሙት ፋሺስታዊና አንባገነናዊ ወንጀሎች ሳቢያ የኢትዮጵያ ህዝብ ክብሩ፣ ነጻነቱ፣ ሰብአዊ መብቱ፣ ዜግነቱ፣ ክብሩና ማንነቱ ተገፎ በጨቋኞች ጫማ ስር አስከፊ የመከራ ህይወት እንዲገፋ የተገደደ ሲሆን ህወሃቶችና ፍርፋሪ የሚጥሉላቸው ሎሌዎቻቸው ህዝብ በጠራራ ጸሃይ እየዘረፉ፣ እያሰቃዩ፣ በኑሮ ችግር እግር ከወርች አስረው እየገርፉና እየገደሉ ተንደላቀው ለመኖር ሲጥሩ ይታያሉ።
እኔም እንደ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በወያኔ የሚፈጸሙ መንጀሎችን ለማጋለጥና፣ የህዝባችንን ብሶትና መከራ አጉልቶ ለማሳየት የበኩሌን አስተዋጽኦ ለማበርከት አቅሜ የፈቀደልኝ ሁሉ በግሌ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ። ምንም እንኳ በየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲም ይሁን ንቅናቄ ላለመግባት ውሳኔ አድርጌ የቆየሁ ቢሆንም፣ ከቅርብ ግዚያት ጀምሮ ግን ታግሎ ሊያታግል የሚችል ድርጅት ወስጥ በመግባት የበለጠ አስተማጽኦ ማበርከት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው በመረዳቴ የግንቦት ፯ የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄን ተቀላቅያለሁ።
እንደ ማንም ድርጅት ግንቦት ፯ ድክመትም ጥንካሬም ያለው ሲሆን የድርጅቱን ጥንካሬዎች የበለጠ አጎልብቶ ለመታገል በቁርጠኝነት ተነስቻለሁ። እኔም ድርጅቱ ጥንካሬዎቹን አጎልብቶ ድክመቶቹን አርሞ የበለጠ ህዝባችንን አደራጅቶ ታግሎ እንዲያታግል አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚቻለኝን ሁሉ ጥረት አደርጋለሁ።
ህወሃቶችና የወንጀለኛ አፓርታይድ ስርአታቸው ተጠቃሚዎችና አገልጋዮችን በያሉቡትና በየገቡበት አምርረን በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ መታገል የዚህ ትውልድ ታሪካዊ ፈተና ነው። በተለያዩ ግዚያትና የታሪክ አጋጣሚዎች የተቋቋሙ ድርጅቶች ሁሉም ለጋራ እራእያችን መሳካት በህብረት ህዝባችንን የበለጠ አደራጅተው እንዲታገሉም ያላሰለሰ ጥረት ለማድረግ ቃል እገባለሁ።
እነ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ አንዱ አለም አራጌ፣ ርዮት አለሙ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ ኡስታስ አቡበከር አህመድ እና በርካታ ኢትዮጵያዊያን የጋራ ራእያቸው የሆነውን የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እውን ለማድረግ እጅ ለጅ ተያይዘን እንታገል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን በትግሉ እንዲቀዳጅ በህብረትና በጋራ አምርረን ለመታገል በያለንበት እንደራጅ። ኑ በጋራ እንነሳ፣ ሀገራችንን ከአውሬዎች ለማታደግ ሁለገብ ትግል በያለንበት እናፋፍም።
እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ! እኔም ግንቦት ሰባት ነኝ! እኔም አሸባሪዎችን በነጻነት ጥሪ የማሸብር አሸባሪ ነኝ!
ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!
ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት!

እኔ የማይገባኝ እንዴት 23 አመት ሙሉ ዜጎችን እያሰሩ ይቀጥላሉ ?

$
0
0

ግርማ ካሳ

ሃብታሙ አያሌው ፣ ዳንኤል ሺበሺ እና የሺዋስ ከበደ ወደ ማእከላዊ መዉረዳቸዉን የሚገለጽ ዜና ተመለከትኩ። በጣም አዝኛለሁ።

habtamu ayalew

ሃብታሙ አያሌው

ሃብታሙ አያሌው በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ትልቅ ሥራ እየሰራ ያለ፣ በቅርቡ ወዳጅ አባቷን ያጣችው እህታችን ባለቤት እና የአንዲት ቆንጅዬ ልጅ አባት ነው።የአንድነት ፓርቲ እና መኢአድ የቅድመ ዉህደት ስምምነት ፈርመው ፣ ዉህደቱን ለማስፈጸም ያቋቋሙት የጋራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነው። ያ ብቻ አይደለም የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ሆኖ ሰርቷል ፣ አቶ ሃብታሙ።
ዳንኤል ሺበሺ የአንድነት ት ጉዳይ ሃላፊ ም/ሰብሳቢ ነው። የአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቀሩን በአገሩቷ ሁሉ ለማጠናከር እየሰራው ባለው ስራ፣ ወጣት ዳንኤል ሺበሺ ትልቅ ሚና የነበረው ወጣት አመራር ነው።

የሺዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ ነው። በቅርቡም ሰማያዊ ፓርቲ ለሰፍ ቅስቀሳ በሚያደርግበት ጊዜ ታግቶ ከሳምንት በላይ ውህኒ የተወረወረ ወጣት ነው።

ምርጫው እየተቃረበ ሲመጣ፣ ጠንካራ ፉክክር እንዳይኖር ፣ «ከወዲሁ ተቃዋሚዎችን ማዳከም አለብን» የሚል ዉሳኔ ኢሕአዴግ የወሰደ ይመስለኛል። የአመራር አባላትን የማሰሩ አሳዛኝ ተግባር፣ በተለይም ደግሞ የአንድነት እና መኢአድ ዉህደት እንዳይፈጸም፣ በአገር ቤት ያሉ ሰላማዊ ታጋዮች እንዲፈሩና እንዲሸማቀቁ ለማድረግ ሆን ተብሎ የተደረገ ለመሆኑ ብዙ አርቆ ማሰብ አይጠይቅም። አይሳካላቸዉም እንጂ።

yeshiwas

የሺዋስ ከበደ

ከጥቂት አመታት በፊት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ኢሕአዴግ አሰረ። እንደ አንዱዋለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን ያሉ ተነሱ። የወ/ት ብርቱካን መታሰር ትግሉን አላቆመዉም። እነ አንዱዋለም አራጌን ደግሞ «ሽብርተኞች» ናችሁ ብሎ አሰረ። ትግሉ አላቆመም። ኢሕአዴግ ማሰሩን ቀጠለ። አቶ አስራት ጣሴ፣ አቶ ዳንኤል ተፈራን ለተወሰነ ጊዜ አስሮ ፈታ። አሁን ደግሞ ይኸው እንደ ሃብታሙ ያሉ ፣ በሰላም አገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያዉያንን አግቶ የት እንዳደረጋቸው አይታወቅም። በቶርቸር በሚታወቀው ማእከላዊ ነው ይባላል።

እኔ የማይገባኝ፣ እንዴት 23 አመት ሙሉ ዜጎችን እያሰሩ ይቀጥላሉ ? ሰው እንዴት አይሻሻልም ? እስከመቼ ነው የጫካ አስተሳሰብ የሚገዛቸው ? ይቅርታ ይደረግልኝና ይሄስ እርግማን ነው !!!

10494588_750671571658261_8784450188684809422_n

ዳንኤል ሺበሺ

በቅርቡ ሰላማዊ ወጣቶችን በአምቦ፣ በጊምቢ … በጥይት ረፈረፏቸው። ፌስ ቡክ ላይ በመጻፋቸው ዞን ዘጠኞችን አስረው ይኸው እያሸማቀቋቸው ነው። ነገ ደግሞ ምን እንደሚያደርጉ አናውቅም። ይሄንን ሕዝብ ምን አድርግ ነው የሚሉት ? እንዴት ነው ኢሕአዴግ ዉስጥ ልብ ያለው ፣ «ይሄ ነገር ትክክል አይደለም። ለኛም ለአገርም አይጠቅም። መካረርና ጥላቻን ያሳድጋል» ብሎ የሚያከላክል የለም እንዴ ?

ነገሮች በጣም እየከረሩ ነው። ብዙዎች እየተናደዱ ነው። ሁኔታው በጣም አስፈሪ ነው። ኢሕአዴግ ቀይ መስመር ላይ የቆመ ይመስለኛል። የሚያደርጋቸዉን እና የሚወሰናቸው ዉሳኔዎችን አስቦና ተጠንቅቆ እንዲወስድ እመክራለሁ። በአስቸኳይ ማእከላዊ እሥር ቤት ጨምሮ፣ በተለያዩ እሥር ቤቶች በግፍ ያጎራቸውን ሰላማዊ ዜጎች እንዲፈታ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዲያሰፋና ለብሄራዊ እርቅም እንዲዘጋጅ፣ አኩረፈው ነፍጥ ካነሱ ወገኖች ጋር ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ዉይይት እንዲጀምር፣ እመክራለሁ። አስጠነቅቃለሁም።

ጆሮ ያለው ይስማ ! ልብ ያለው ይስተዉል !

 

 

 

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live