Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት እንዴት? (ሥርጉተ ሥላሴ )

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 03.10.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ዛሬ የተመለደውን የዘበኝነት ተግባሬን ልከውን – እነሆ መጣሁኝ።

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

እንዲህ ሆነ „በሳምንቱ እንግዳ“ የኢሳት ዝግጅት ክፍል ሁለት ላይ … አቶ ኤርምያስ ለገሰ „ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት“ በሚመለከት የሰጡት አሰተያዬት የግል ዕይታ ቢሆንም በህዝብ መገናኛ በመሆኑ ሰፊ አድማጭ እንደሚኖረው ስለተገነዘብኩኝ የትርጉም ማቃናት ያሰፈልገዋል በማለት ሃሳቤን ወይንም ግንዛቤዬን ላጋራ ወደድኩ። ቢቻል አቶ ኤርምያስ ከመርሁ ጋር እንዲታረቁልኝ፣ ባይቻል ደግሞ ሚዛኑን የጠበቀ ግንዛቤ በአድማጮች ዘንድ መኖር እንዳለበት በእጅጉ ፈለግሁኝ። በቅድሚያ ግን ማዶ – ለማዶ የነበረ ወገን እንዲህ በጠራ መስመር ተገናኝቶ ሃሳብን  – በሃሳብ ለማታገል የተቻለበት መሰረታዊ ምክንያት አቶ ኤርምያስ ለገሰ በመሆናቸው፣ የጎጥ አስተዳደርን አሻም ብለው የነፃነት ትግሉን በመቀላቀላቸው ነውና ለወሰዱት ሥር ነቀል እርምጃ ከልብ በአክብሮት ላመስግን እወዳለሁ። እንዲሁም ውይይቱን ልብ ብሎ ላዳመጠው በወያኔ ሥር የወደቀችው እናት ሀገራችን ኢትዮጵያና ልጆቿ የሚከፍሉትን አሳር እጅግ መራራነት በዬአጋጣሚው በመግለጸዎት ደስ ብሎኛል። እንኳን ወደ እኛ መጡ – አብረን ለመዝለቅም ያብቃን አምላካችን። አሜን!  http://ethsat.com/video/esat-bezih-saminte-with-tamagne-beyene-ermias-legesse-wendimagegne-gashu-august-10-2014-part-2/ የእኔን መንፈስ ያነሳሳው ሊንክ ይኸው ሲሆን፤ ከገለጻው ውስጥ ሥንኞቹ ከ45 አስከ 48 ደቂቃ ባለው ጊዜ ይገኛሉ። እርግጥ ነጥብ በነጥብ አልጻፍኩትም – አልሄድበትም  – እንዳላሰለች በማሰብ። በጥቅሉ ግን የጓጎለ መንፈሱን ትንሽ ለማለዘብ እንዲህም እላለሁ … እንሆ።

የዕለቱ ቃለ ምልልስ ከመከወኑ በፊት ከተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ተያይዘው የታሰሩ  ወጣቶችን ምክንያት በማድረግ ማጠቃለያ እንዲሰጡ ጋዜጠኛና ጸሐፊ /fact/* ሲሳይ አጌና ሲጠይቃቸው ከሰጡት መልስ ነው የምነሳው።  በጥቅሉ የመልሱ ጭብጥ መንፈስ እንዲህ ነው። ለተጠዬቁት ጥያቄ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ሲመልሱ እንዲህ ይሉናል። „ እኔ አልጠራጠርም እነዚህ ሰዎች በዶክመንተሪው /documentary/* ይሁን በክሱ ሂደት ላይ ከአቶ አንዳርጋቸው ክስ ጋር ተስታኮ እንደሚነሳ ለሰከንድ አልጠራጠርም። እነዚህን ሰዎች በተለይም ወጣቶች ለምን ታሰሩ? ለምንስ አሰሯዋቸው እነ አብርሃም ደስታን፤ እነ ሃብታሙን ለምንስ አሳደው ያዟዋቸው? የሚለውን ነገር የግሌን ግምት መስጠት እፈልጋለሁ። ኢህአድግ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የሚባል መርህ አለ እና ያ ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርህ በነገራችን ላይ አቶ አንዳርጋቸው ኢህአድግን ጥሎ ወጣሁበት ያለው አንዱ መጸሐፉ ውስጥ አይተኸው ከሆነ ይኼው ነበር። ባጭሩ ምን ማለት ነው። ዴሞክራሲያ ማዕከላዊነት ማለት ማዕከላዊ እስር ቤት ማለት ነው።“ ጋዜጠኛና ጸሐፊ /fact/ ሲሳይ አጌና ከማህል ገብቶ እንዲህ ሲል ጠዬቀ „በራስህ አስተሳሰብ ማለት ነው?“  አቶ ኤርሚያስ ቀጠሉ …

„አንድ ሰው ከላይ ይናገራል፤ አቶ መለስ ሊሆን ይቻላል። ከላይ አቶ መለስ የተናገረውን አርማጭሆ ያለው የገጠር አባላችን ሳይጨምር ሳይቀንስ ይናገራታል። ከአንድ ቦታ የሚፈስልህን ነገር መቀበል ማለት ነው። አንዱ ባህሪው ይኸው ነው። ታስታውስ ከሆነ በ1997 ዓ.ም የምርጫ ውደቀታችን ጋር ተያይዛ የተነሳች ቃል ነበረች እንግሊዘኛ ነበረች ….የተቃውሞ ድምጽ /protecting vote / “ አቶ መለስ ይህችን ተናገራት፤ ያቺውኑ ቃል አቶ በረከተ ደገማት፤ የቀበሌ አባላችን አርማጭሆ ደንበጫ ያለው ኦሮምያ ያለውም የገጠር አባላችን እንዲሁ።“

„ ዴሚክራሲያዊ ማዕከላዊነት በባህሪው ከአንድ ቦታ የሚፈስልህን መቀበል ማለት ነው። ኢህአድግ እስካለ ድረስ ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አለ። ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት እስካለ ድረሰ ደግሞ አድርባይነት አለ። አድርባይነት እስካለ ድረሰ ደግሞ የሚማር ድርጅት አይኖርም ማለት ነው። የኢህአድግ ዋነኛ መግለጫው አድርባይነት ነው። የአንድ ፓርቲ አመራር ብቻ እስካለ ድረስ የሚማር ድርጅት የለም። ኢህድግ የሚማር ድርጅት አይደለም ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ የሚማር ወጣት መፍጠር አይችለም። ይህ ድርጅት 20፣ 23፣ 22 አመት በሥልጣን የምታያቸው የሚማር ድርጅት ስለልሆነ ወጣቶችን መፈጠር አልቻለም ማለት ነው። ስለሆነም ኢህድግ የወጣት መሃን ሆኗል። አድርባይነት በሚመለከት እነሱ ራሳቸው አድርባይ ሆነናል ብለዋል?“ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ስለ አድርባይነት የሚሰማቸውን ስሜትና ህሊናዊ ፍርድ ከሰጡ በኋላ ንጽጽሩን ቀጥለው … „በተቃራኒው ዬተቃዋሚው ፓርቲዎች ማብራራት፣ ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ የሚችሉ ወጣቶች እዬፈለቁ ነው። እነዚህ ወጣቶች  ለኢህአድግ ከሚቀጥለው ምርጫ አኳያ እነ ሃብታሙ ያልካቸው ሰዎች“ /አቶ ሃብታሙ፣ ወጣት አብርሃም፣ አቶ ዳንኤል፣ አቶ የሺዋስ / ማለታቸው ነው „ሥጋት ናቸው። ዬምርጫ ክርክ ቢነሳ ከበረከት ጋር ሃብታሙ ይከራከራል ማለት ነው። የሁለት ትውልድ ሰዎች … “ በተጨማሪም አቶ ኤርምያስ የጋዜጠኛ አብርሃም ደስታንም የለውጥ ሃዋርያነት ለማነፃፀሪያ በማመሳከሪያነት አቅርበዋል።

እንግዲህ በነበራቸው የሦስትዮሽ ሁለተኛ ዙር „የሳምንቱ እንግዳ“ የኢሳት ቆይታ የወያኔ ሥርዓተ ሂደት በዴሞክራሲ ማዕከላዊነት የታሰረ ነው፤ አዳዲስ ዬወጣት ፖለቲከኞች መፈጠር ማህነነትም በአጽህኖት ከመርሆ የመነጨ ስለመሆኑ ገልጸዋል። ይህ አገላለጽ የትርጓሜ ማቃናት ሊደረግለት ይገባል ባይ ነኝ። ምክንያቱም ዴሚክራሲያዊ ማዕከላዊነት ዛሬ ብቻም ሳይሆን ነገ የብዙኃኑ ድምጽ እንዲሁም ብቃት እንዲመራት በምንመኝላት ልዕልት ኢትዮጵያ ተግባራዊ መሆኑ አይቀሬ ነው ባይ ነኝ። ዛሬም ቢሆን እያንዳንዱ ዬተቃዋሚ ፓርቲ መርሁን አጉብጦ ሳይሆን በትክክለኛ ትርጉሙ የአመራር ጥበብነቱን ህግጋት ጠብቆ ተግባር ላይ እስካዋለው ድረስ በውስጡ እዬኖረበት ነው ብዬ አስባለሁ። በጣም በሰከነ ሁኔታ መርሁና አድማጩ ከጽነሰ ሃሳቡ ትርጓሜና የአፈጻጸም ሂደት ፍትሃዊነት ጋር ተጣልቶ ከመቃብሩ አያቁመኝ እንዳይል ከወዲሁ በጥንቃቄ ሊያዙ የሚገባቸውን ጉዳዮች ማብራሪያ መስጠቱ በእጅጉ አስፈላጊ ነው። ነገ ሲታሰብ በዝልቦ ጉዞ ሳይሆን፤ ከድክመቶች ትምህርትን – ከጥንካሬዎች ደግሞ ፍሬን መዋራረስ ግድ ስለሚል።

ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት /Democratic centralism/  ምንድን ነው? ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የአንድ ድርጅት የአደረጃጀት መርህ ነው። የትኛውም ድርጅት እንደ ድርጀት በዚህ መርህ ዙሪያ ማለፉ ወይንም መኖሩ ወይንም ህልውናውን መገንባቱ ግድ ይሆናል። ፖሊሲዎችም እንዲሁ በዚህ መንፈስ ሊቀረጹ ይችላሉ። በተለይ ግራ ዘመም ከሆነ። አግባብነቱ ስለምን? ማዕከላዊነት ከልክ በላይ ከጠበቀ አንባገነንነት፤ ዲሞክራሲ ከመጠን ካለፈ ደግሞ ሥርዓተ አልበኝነት ድርጀቱን ይወረውና ህልፈቱን ያውጃል ከሚል ግንዘቤ ተነስቶ በሌኒንስቱ ዘመን ተግባር ላይ የዋለ ነው። መንፈሱ የፓርቲዎች ነፃ መፈጠር፤ ነፃ ውይይትና ፉክክር እንዲሁም የድምጽ ብልጫን የመምራት አቅምን ይግልጻል። ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አራት ሁልአቀፍ መርሆች አሉት፤ በዬርከኑ ፓርቲውን የሚመሩ አካላት ሁሉም አካላት በምርጫ ከታች ወደ ላይ የመመረጥ፤ ጥቂቶች ለብዙሃን ውሳኔ ዬመገዛት፤ ከታች ወደ ላይ በቀጥታና በውክልና የሚመረጡ አካላት በህዝብ ምርጫ ከላይ ደረሰው የሚወስኑት ውሳኔ ተፈጻሚ የመሆን ግዴታ … የፓርቲ ከፍተኛ መሪ አካላት የምርጫ ዘመን ውስኑነትና ተለዋጭነትን ያመለክታል ….

ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ተፈጥሮው ከአመራር የጥበብ ስልት ጋር የተዋዋጠ ነው – ህሊና ላላው ድርጅት። በቀላል አገለላጽ የመብትና ግዴታ ጋብቻ ማለት ነው። ሁለቱም ልክ እንደ አፍንጫ ቀዳዳ፤ ወይንም እንደ ሁለት ዓይን ተመሳሳይ ወርድና ቁመት፤ ስፋትን ጥበት ያላቸው ዬአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ለአንድ ድርጅት የሁለቱ ተስማምቶ መኖር የነፍሱ ማደሪያ- የሩኹ ማሳዳሪያ እንደመሆኑ ሁሉ መዛባታቸው ደግሞ ህልፈቱ ይሆናል። ለህዝብም ርትኃዊ ትንፋሽ ወሳኙ ክፍል ነው። በግልጽና በይፋ ይህን መርህ ተግባር ላይ በማዋል ደረጃ የሶሻሊስቱ ንድፈ ሃሳብ በማንፌስቶው ሆነ በደንቡ ቁልጭ አድርጎ የሚያስቀምጠው ሲሆን በካፒታሊስቱም ዓለምም በተግባርና በሂደት በአብዛኞቹ ጥቅም ላይ ሲውል የሚታይ መርህ ነው። መብትና ግዴታን አጣጥሞ አንባገነንትን አርቆ ሥርአት አልበኝነትን ማሰር የሚቻለው መርሁን በትክክል ተግባር ላይ ሳያጣሉ ማዋል ሲቻል ብቻ ነው። ሳያበላልጡ የተደላደለ መስመር በመዘርጋት።

መብት … የነፃነት ትልቁ መገለጫ ነው። አንድ ሰው መብት ሲኖረው መተንፈስ ይችላል። አንድ ሰው መብት ሲኖረው መኖርን ይጀምራል። መኖር ደግሞ ሥርዓትና ወግ አለው። ዬሥርአትና ወጉ መተላለፊያ የድርጊት በሩ ደግሞ የፍጥረት አውራ የሆነው ልዑቁ የሰው ልጅ ነው። አንድ ሰው መብት አለው የሚባለው በሀገሩ በነፃነት ለመኖር የሚያስችለውን የህጎች ዕንብርት በፈቃዱ ይሆነኛል ብሎ ማጽደቅ ሲችል፤ ለሚፈልገው መሪ ካለምንም ተጽዕኖ ድምጽ የመስጠት ወይንም የመንፈግ መብቱ የተረጋገጠለት ሲሆን፤ በዜግነቱ ብልጫ ወይንም ግት ወይንም መደፍጠጥ ሳይኖርበት እመጥናለሁ ብሎ ባሰበው የኃላፊነት እርከን በእጩነት እራሱን አቅርቦ በድምጽ ብልጫ የመሸነፍ ወይንም የማሸነፍ አቅሙ በአራዊት ግፍያ የማይጠወልግበት ሲሆን። ይመራኛል ብሎ የመረጠው አካል ቢያጠፋ የመገሰጽ፤ ሲበዛ በቃህኝ ብሎ በሰላማዊ መንገድ ከሥልጣን የማገድ እንዲሁም የማውረድ ህጋዊ ድጋፍ፤ የህግ ዕውቅና እንዲሁም ጥበቃ ሲኖረው፤ በዬትኛውም የሀገሪቱ ክልል የመኖር  – የመሥራት – የመዘዋወር – የማይገሰስ መብት ሲኖረው፤ ሀገሩ በምታስገኘው ጥቅም እኩል ተሳታፊ ሲሆን፤ በውጪ ሀገርም ቢኖርም ሀገሩን በፈለጋት ወቅትና ጊዜ ካለምንም ተዕቅቦ ተመልሶ ካለ ሥጋት መኖር ሲችል፤ አይቶ ለመመለሰም ቢሆን ያልታሰረ ፈቃድ ሲኖረው የመኖር – የመማር – የመሥራት – ሃብት የማፍራት ወዘተ … ያ ሰው ነፃነት ባለው ሀገር ነፃነቱ ተጥብቆለት ይኖራል ማለት ይቻላል።

ይህ ሙሉዑ መብት የተረጋገጠለት ሰው ግዴታው ደግሞ በሌላ ኃይል የተጫነበት ሳይሆን እራሱ ፈቅዶና ወዶ የተቀበለው የማድረግ ወይንም የመፈጸም ሂደቱ ነው። ከዚህ ላይ አንድ ምሳሌ ላንሳ … ይህ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የታዬው በዘመነ ቅንጅት ነበር። አሁን የተከበሩ ዶር/ ብርሃኑ ነጋ በህዝብ ሙሉ ፈቃድና ይሁንታ – ውዴታም ለአዲስ አበባ ከንቲባነት በ1997 የተመረጡ ህዝባዊ መሪ ነበሩ። ዕድሉን አግኝተው ቢሆን ኖሩ መሪና ተመሪ የፈቃድ ውርርስ ስለተከናወነ ሰምና ወርቅ የሆነ የአገልግሎት ጊዜ ይኖራቸው ነበር ማለት ነው። የሰላ የሰመረ መስመር …ô ከታች ወደ ላይ ተፈቅዶ ለተሰጠ መብት ከላይ ወደ ታች ህግ ሆኖ ሲመጣ ያለምንም እንከን ወይንም ማንገራገር ይፈፀም በነበረ …. ህልም …. ሆኖ የቀረ መራራ ስንብት ….

ሌላ ምሳሌ ትንሽ ዘርዘር አድርጌ ስለ እውነተኛው የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መንፈስ ላንሳ ….  የአንድ ሀገር ህዝብ የህጎች ሁሉ እናት ህግ የሆነውን ህገ መንግሥቱ ከረቂቁ ጀምሮ በስፋት እንዲወያይበት ይደረጋል። በራዲዮ፤ በጋዜጣ፤ በግልና በጋራ አስተያዬት ህዝብ ሃሳቡን እንዲሰጥበት ይደረጋል። ረቂቁ በህዝብ አስተያዬት ዳብሮ ወይንም ተሻሽሎ ተጠቃሎ ከታች ጀምሮ በበሰለ ሁኔታ እያንዳንዱ አንቀጽ ከነማብራሪያው – ከነማሻሻያ ሃሰቦቹ ቀርበው ከታች በመሰረታዊ ቀበሌው ምላዕተ ጉባኤ ካለምንም ተጽዕኖ ረቂቁ ይጽድቅና ለቀጣዩ አካል ሰነዱን ይላካል። በዚህ ሂደት ክንውኑ መብት ጎልቶ ይታያል ….

ከቀበሌ ቀጥሎ ያለው አካል የወረዳው ጉባኤ ነው። የወረዳው ጉባኤ እንደ ቀበሌው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ሳይሆን ከዬቀበሌው ይወክሉናል የተባሉ ውክል አካላት ብቻ የሚገኙበት ይሆናል። ማለት መሰረታዊው አካል ድምጹን የሰጣቸው በድምጽ ብልጫ ለቀጣዩ አካል ውክልና ያገኙ ማለት ነው። እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ አብስለው ለቀጣዩ አካል ያስተላልፉታል። በዚህ መልክ በአውራጃ፤ በክ/ሀገር በተመሳሳይ መልኩ ይከውንና …. ሀገራዊ የህዝብ ተወካዮች ጉባኤ ላይ የህዝብን ፍላጎት ያማከለው ከታች ጀምሮ እዬታሸ የዳበረው ረቂቅ፤ በውይይት እንዲጸድቅ ይደረጋል። ከመሠረታዊ ጉባኤ እስከ ሀገራዊ ሸንጎ ውሳኔ ድረስ ዬህዝቡ መብት በስፋት ጎልቶ ይታያል። ጉባኤው ውይይት ላይ እያለም የተሻለ አዲስ ሃሳብ ከዬትኛውም ወገን ከማናቸውም ዜጋ ከቀረበ ጉባኤው መርምሮ ሊጠቀምበት ይቻላል አዲሱን ሃሳብ። አሁን ከዚህ ላይ ሰባት ነገሮችን እናያለን።

  1. የነፃነት መንፈስን ንጡርነት፣
  2. አክብሮተ – የህዝብ ድምጽ ተደማጫንትን፣
  3. የበታች አካልና የበላይ አካል የመብት አፈፃፀም ዬእኩልነት ሂደትን፣
  4. የፍላጎት ሁለንትናዊነት – ሰላማዊ ቅብብሎሽን፣
  5. የአቅም ተደማጭነትና ተቀባይነትን፣
  6. የነፃነት ነፍስ ህልውና ድርጊት ላይ መገኘትን፤
  7. ፈቅዶ የሰጠው አካል ፈቃዱን የማንሳት መብትን / የመሻር/ የማሰናበት/የማግለል/ የመገሰጽ/

ዬሀገራዊው ጉባኤ ውክል አካላቱ በህዝብ ድምጽ ብልጫ የሚመጡ ናቸው። በተጨማሪም ህገ መንግሥቱን ፈጻሚው አካል ካስፈጻሚው አካል ጋር በፈቃድ የሚያገባ ሂደቶች በተገባው ሁኔታ ተከናውነዋል። ከዚህ በኋላ ብሄራዊው ጉባኤ በረቂቁ ላይ ተወያይቶ በድምጽ ብልጫ ያጸድቀዋል። እያንዳንዱ አንቀጽ በድምጽ ብልጫ ይጸድቃል። አሁን የመፈጸም ሂደቱ ምን ይሆናል ማለት ነው ግዴታ ይሆናል ማለት ነው። ግዴታው ግን ተወዶና ተፈቅዶ የሚቀበሉት ከመሆኑም በላይ ለአፈጻጸሙ ሠራዊቱ -ጠባቂው ህዝቡ ይሆናል ማለት ነው። ከዚህ ነጥብ ጋር በዬደረጃው በተካሄደው ውይይት ሆነ ጉባኤው ላይ ድምጽ የመስጠት፤ ድምጽ የመንፈግ። የመደገፍና የመቃወም መብቶች ክፍት ናቸው። ነገር ግን በአብዛኛው ድምጽ ከጸደቀ በኋላ ጥቂቶች ማለትም ያልደገፉት ለብዙኃኑ ድምጽ የመገዛት ግዴታ ይኖርባቸዋል። ይህ ማለት የተቃወሙት፤ የደገፉትና ድምጽ ያልሰጡት ለህገ መንግሥቱ ተፈጻሚነት እኩል ግዴታና ተጠያቂነት አላቸው ማለት ነው። በሌላ በኩል በብዙኃን ድምጽ የሚጸድቁ ጉዳዮች አሸናፊነታቸው ለሁሉ እንጂ ለደጋፊዎች ብቻ ባለመሆኑ አሸናፊዎች በተሸናፊዎች ላይ ቅንጣት ታክል ተፅዕኖ የማሳደር ኃይል የላቸውም። ይህ እንግዲህ ቁልጭ ያለው የዲሞክራሲያዊ ማዕካለዊነት የመብትና የግዴታ ማዕከላዊ መርህ ነው።

ይህ ማለት በብዙሃን ድምጽ ለምትመራ ለነገ የነጋላት ሀገር ለኢትዮጵያ ዬዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርህ በአግባቡ ተግባር ላይ እንዲውል ነው ምኞቱና ህልሙ። የበላይ አካላት ህግ አውጪው፣ ህግ ተርጓሚውና ህግ አስፈፃሚው ከታች በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ስለሚመረጡ፣ ከታች በስሎ ለውሳኔ የበቃውን ወደ ታች ሲልኩት ህዝቡ ላይ የሚጫን አይሆንም ô። ህዝቡ መብቱና ግዴታው ተስማምተው ዴሞክራሲን በህይወቱ ውስጥ ያለውን ድርሻ ይተገብረዋል – ፈቅዶ። ስለዚህ አስፈሪም – አሰፈራሪምገዢም ጨቋኝም  – ቀጥቃጭም አ -ንገራጋሪም በዚህ መስመር ድራሻቸው ይጠፋል። አንድ ሰው ነፃነቱ ከተከበረለት አድርባይ የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለውም። የተከደነበት ወይንም የተዘጋበት መድረክ አይኖርምና። የፈለገውን ነውና ድምጽ የሰጠበት። በትክክል በተፈጸም ሂደት – ሂደቱን ህዝቡ እንደ ሃይማኖታዊ ዶግማ ነው ወዶ ከደሙ ጋር የሚያዋህደው። ለተግባራዊነቱም ግንባር ቀደም ተዋናዩ ህዝቡ እራሱ ይሆናል። የህዝብ ጥበቃ ይደረግለታል። ስምምነት – መደማመጥ – ኑሮን መውደድ – ዘለግ ያለ ዕድሜን መመኘትም የሚመጡት በዚህ መልክ በተከወነ የመርሁ ጤናማ ….. ጉዞ እንጂ የሰው ልጅ እንደ በግ አረስቶ ሆኖ በቤንዝን አራሱን አቃጥሎ የሚሞትበት … ሁኔታ አይፈጠረም – በፍጹም።

ስለዚህ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት በአውሬያዊነት ተመክሮ ትርጓሜ ጽልመታዊ መልከና ገጽ ተስጥቶት እንደማስፈራሪያ፤ እንደ በቀል መወጣጫ ተቆጥሮ ለነገ አያስፈልግም እንዳይባል ጥንቃቄ በእጅጉ አስፈላጊ ነው። የተነሳውን ሃሳብ እንደ ወረደ ወይንም እንደ ተለቀቀ ዝም ብሎ ማለፍ አስፈላጊ ባለመሆኑም ማብራሪያ ሰጥቶ በትርጉም ማቃናት ሊታለፍ የማይገባው የሃቅ እንክብል ነው። ማብሰል የግድ አስፈላጊ ስለሆነ እንደ ተንጠለጠለ እንዳይቀር መሬት የያዘ፤ ቀለል ባለ የትርጓሜ ይዘት ማስተዳደር ለይደር ሊቀጠር ስለማይገባ እነሆ ልጽፍ የተገደድኩት በዚህው ምክንያት ነው።

አሁን በኢትዮጵያ ለዛውም ከአንድ ጎሳ ድርጅት የፈለቀ ነገር ሁሉ ኮሽ ሳይል የመፈጸም ድርብ ግዴታ አለ – ጫና አለ። በስለላና በስጋት በተወጠረ ሁኔታ ህዘብ አምጦ እንዲቀበል ተገዷል። ስለምን? ቀድሞውንም በወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ላይ መወያዬት የሚችሉት አባላቱ – ዝርያው ያላቸው ብቻ ናቸው። በአፈጻጸሙ ደረጃ ግን በውስጡ የሌለ አባል ለመሆን የማይፈቀድለት፤  በአካበቢ ዝር እንዳይል የተዘጋበት – ወይንም የተቆለፈበት ወገን ተገዶና ታስሮ በፍርሃት ተቀፍዶ እንዲቀበል ይገደዳል። ዘነፍ ያለች ጉዳይ ቢነሳ አሸባሪ ነው። ይታሰራል፤ ይገደላል። ይሰደዳል። ቢኖርም በስጋት ተንዘፍዝፎ ጥላውን እዬሸሸ እንዲኖር ይገደዳል። ቀድሞ ነገር መርሁና ትርጓሜው እኮ ለጎሳ አስተዳደር ተብሎ የተቀመረ አልነበረም። ለምልዕት ህዝብ ለሰለጠነ ህዝባዊ አስተዳደር እንጂ። አብሶ ንድፈ ሃሳባቸው የሶሻሊስት ርዕዮት የሆኑ ሀገሮች ህብረ ብሄራዊ የፓርቲ ሥርአትን ሳይሆን የአንዳዊነት ፓርቲ ሥርአትን ስለሚከተሉ ተወዳዳሪዎችም መራጮችም እነሱ በመሆናቸው ማዕከላዊነቱ እጅግ ጥብቅ፤ ያመራሩ ዝንባሌውም አንባገነናዊ ሊሆን ይችላል። ለዛውም ከአልባንያ ንድፈ – ሃሳብን የወረሰው ወያኔም ከዚህ ሊያመልጥ ከቶውንም አይችልም። እንዲያወም በከፋ ሁኔታ ጎሳዊነትን በሶሻሊስት ንድፍ፤ ነፃ የኢኮኖሚ ንድፍን ከዞጋዊ ጋር ቀላቅሎ የወዘተረፈ ስንክሳር መጨፈሪያ ነው ያደረገው መርሁን …. LMNO ይህ ነው የወያኔ ዴሞክራሲያዊ መግለጫው  – የጎበጠ – ጎብዳዳ ጉድ።

ወያኔ ሲያስፈልገው ሶሻሊስት፣ ሲያሰኘው – አረቢስት፣ ሲለው – ካፒታሊስት ለታላቋ ትግራይ ቅዠት እንደሚያመቸው ይጨፍርበታል። ሲጠቀለል ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርሁ እራሱ ለጫካ ተመክሮው አቅሙ አይደለም። መርሁ ለጎጥ አስተዳደርም ልኩ አይደለም። መርሁ ለኢሰባዊነት ድፍረታዊ አገዛዝ ግጥሙ አይደለም። ቀድሞ ነገር የወያኔ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት እኮ ቁመናው ሲታይ ሥር የሌለው ዕጽ ነው። ሥር የሌለው ዕፅ እራሱንም መሸከም አይችልም እንኳንስ ሌላውን ….

ለወያኔ ቀልቡ ረገጣ – ርግጫ – ፍጥጫ – ውንብድና – መቅጠፍ – ቃልን ቅርጭም አድርጎ መብላት –  መዝረፍ – ማስፈራራት አምሳያዎቹ ናቸው። ከዚህ ባለፈ ወያኔ እሾኽ ዘርቶ እሾኽ ያመረተ የዘመናችን ጃርታዊ አስተዳደር በመሆኑ ዘመኑ ፈቅዶለት ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ካገኘው የነፃነት ትንሳኤ ጋር አይተዋወቅም። „አንድ ሜትር በአንድ ሜትር“ የሰው ልጅ ታስሮ ውሎ አድሮ ህልፈቱን የሚጠብቅበት የድቅድቅ የጨለማ ዘመን። ቀና የዴሞክራሲ አስተሳሰቦች ባዕዱ ነው – ለአረሙ ወያኔ።  እንደ አንድ ልጅ እግር ኮበሌ እኮ አቅም የለውም። የማሰብ ህሊናው የተሰለበ ነው። አቅዶ ይዋሻል። አቅዶ ይበቀላል። አቅዶ ያጠፋል። አቅዶ ስህተት ይፈብርክና ያሰራል – ይገድላል – ያሳድዳል። ወጣት እያለሁ ያነበብኩት አንድ መጸሐፍ ነበር “ሞገድ“ ይባላል። ዬሞገድ መጽሐፍ ጭብጡ ዜና ዬሚሰራው በ500000 ከፍሎ ወንጀል ያሰራል። ሌሊቱን እራሱ ከፍሎ ያሰራውን ወንጀል እንደ ተጠናቀቀ በዚያው ቅጽበት ዜናው የተሰራበት ጋዜጣ ህትም ያወጣል። 10000000 ከዚህ በላይ ጋዜጣው ይሸጣል። የወያኔ ድራማ ብናውቀው ይሄው ነው። ሚዲያን በማዕከል የሚመራው ድርጅት በፖለቲካ ነክ ተግባሮች ላይ አይሳተፍም። ተግባሩን የሚሠራው ተዳብሎ -ተብድሮ ነው። ለእያንዳንዷ ስንኝ የነፃነት ነፍስ በጎጥ የተደራጀ የወሮበላ ቡድን አለው። ወያኔ አይደለም ወጣት አዲስ መንፈስ ያለውን ኃይል ማብቀል ቀርቶ እራሱንም ማዳን የሚችል ድርጀት አይደለም። ዘመኑ ለሰው ልጆች ከሰጣቸው የመንፈስ ዕሴቶች በእጀጉ ርቆ ሚገኝ የአራዊት ማፍያ ነው።

ወያኔ እኮ እንባ ጠበቂ ብሎ በሚ/ር ማዕረግ ጽ/ቤት አለው። ወይ ማላገጥ። ዕንባ ሲቃጠል ሲነድ ቤንዚን አብሮ አርከፍክፎ በአንባ የሚዘመን – ቢሮ። ወያኔ የሰብዕዊ መብት በሚመለከት ዓለም ዓቀፍ በዓላትን አክብራለሁ ይላል። ግን በ2014 እኤ.አ. በዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ምን እንዳደረገ የዓለም ህዝብ አይቶለታል። የሰብዕዊ መብት ጉባኤም ተለጣፊ አለው። ዜጎች በቤንዚን ተቃጥለው ሲሞቱ፣ ሴቶች እስር ቤት አርግዘው ሲወልዱ – እስር ቤት ሲደፈሩ፤ እስረኞች በካቴና ታስረው ቃለ – ምልለስ ሲደርግላቸው፤ ከነካቴናቸው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፤ በወንበዴ ሰራዊቱ የማገጠ ተግባር ሲፈጸምባቸው፤ ለሴቶች አስፈሪ የሆነው በሽታ የጡት ነገር ሆኖ ጆሮ አልባ ሲሆን፤ የሰሞናቱ እራሱ ከሁለተኛው ከተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቃለ ምልልስ ጋር የሰማነው የጣር የድረሱልኝ ሰቀቀን …. ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል …. የሰብዕዊ መብት አለ፤ በላቀ የዴሞክራሲ ምጣኔ እያለ ያላግጣል። ስለሆነም የዴሞክራሲ ማዕከላዊነት ሥሙ መጠራቱ ሳይሆን ቁም ነገሩ መርሁና ህግጋቱ ከአራዊት ተፈጥሮ ጋር አይተዋወቁም። እንዲያውም በመርሁ ውስጥ „ነባርና ወጣት“ መሪዎችን የማወራረስ፣ የማተካካት የተመክሮ ቅብብሎሽ መኖሩን አሳምሮ ይፈልጋል …. መርሁ። ይህ ማለት ባልተቋረጠ ሁኔታ ዬወጣት መሪዎችን ችግኝ ያፈላል ማለት ነው። ስለሆነም ማናቸውም የሰብዕዊ መብት መርህ በወርደ ጠባቡ ወያኔ ልኬታ መታዬት አይገባውም ባይ ነኝ። ይልቁንም ጠቃሚዎችን ከማይጠቅሙት ጋር በሚገባ እዬለዩ ጥናታዊ ተግባራትን በተከታታይ መከወን የነፃነት ትግሉ አውራ ተግባር ይመስለኛል። እያወላገደ የሚተረጉማቸውን የበቀል ጉርስና ስንቅ ያደረጋቸውን አሳሪ ህግጋቶቹን ሁሉ እያፍታቱ ለአደባባይ ማብቃትም ይጠበቃል።

እርገት ይሁን የኔዎቹ። ወያኔ በባህሬው የአንድ ሀገር ትውልድን የሚያጠፋ ድርጀት ነው። ስለሆነም ትውልዱ ከሚያጠፋው ጋር መተባበርን አይፈቅድም። ወጣቱ እንደ ዘመኑ መሄድ ይሻል። ወያኔ ደግሞ ከቤተሰብ ቀጥሎ ካለው የጎሳ ሥርዓት ላይ ነው ያለው። ወያኔ ከወጣቱ ራዕይና ከራሱ ከዘመኑ እድገት ወደ ኋላ የተመለሰ ነው ዙሮ የሚሄድ ነው። ወጣት ደግሞ ሲሆን ቀድሞ በስተቀር ከዘመኑ ጋር ተፈጥሮው የተዋህደ ነው። ስለሆነም „ለምን ወያኔ የወጣት መሃን ሆነ?“ ለሚለው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ዓለማቀፋዊ መርህ ተጠያቂ ሊሆን አይገባም። በሌላ በኩል ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የጥቂቶች መርህ ነው የሚለውም ቢሆን መርሁ ጥቂቶች ለብዙኃን ውሳኔ መገዛትን ነው የሚቀበለው። በተጨማሪም አድርባይነት መብቀያው ነፃነት አጥቶ ከመታፈን፣ ከፍርሃት እንዲሁም ከውጥረት የሚመጣ እንጂ ከዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አይደለም። ተግባራዊ ተሳትፎ ከቀጥተኛ ትርጉሙ እንኳን የሚፈልቅ ስላልሆነ።

ወገኖቼ በፖለቲካ ድርጅቶች ሆነ በሙያና ህዝባዊ ድርጀቶችም የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አፈጻጸም ሥርዓቱ ተመሳሳይ ነው። ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የፖለቲካ አመራር ሥልጣኔ ጥበብ ነው። የነፃነት ሂደት ተመክሯዊ መሰላል ነው። የፍትህ ድል ልዩ እርካብ ነው። ሃሳቤን በዚህ ከውኜ ብዕሬን ለሌላ ጉዳይ እንድተሰናዳ አሳስቤ እናንተንም ውዶቼ በመታደማችሁ አክብሬና አምስግኜ ልሰናበት እኔ ሎሊያችሁ ሥርጉተ።  መሸቢያ – ሰንበት።

  • ጋዜጠኛና ጸሐፊ ብዬ በቅንፍ /fact/ ብያለሁ። በኢትዮጵያዊው የሥነ ፁሑፍ ህግጋት አንድ መጸሐፍ ተራኪ፤ ገላጭ፤ ስዕላዊ ሊሆን ይችላል። መጸሐፍት ከሦስቱ አንዱን ወይንም ሁሉንም ሊሆኑ ይችላሉ። የጋዜጠኛና የጸሐፊ ሲሳይ አጌና መጸሐፍ ሶስቱንም አሟልቶ፤ ተተርጓሚነቱንም አክሎ፤ መረጃዊ – ሪፖርታዊ – ዘገባዊ ተንተኝነትንም አበልጽጎ እንዲሁም ታሪካዊ ቅኝቶችን ደምሮ መደቡ ህግና ህገ ነክ ጉዳዮችን ከሚካተቱበት መምሪያ  ውስጥ ስለሚመደብ ነው በቅንፍ ውስጥ ዬጸሐፊነቱን ደረጃ /fact/ ብዬዋለሁ።
  • Documentary ቀጥታ ትርጉሙ እውነትን ማንጸባረቅ፤ በማስረጃ የተደገፈ ዬፊልም – ዬቲቪ – ዬራዲዮ ዝግጅት፤ ማስረጃነት ያለው የጹሁፍ ቅኝት፤ ከመረጃ ጋር የተያያዘ፤ መረጃዎቹ እውነትን የሚያረጋግጡ ማለት ስለሆነ ወያኔ ግን በበቀል የበቀለ፤ በማሸበር – የሰከነ፤ በማስፈራራት – የተከዘነ ቁልጭ ያለ የመንፈስ ስርቆት ተግባር በራዲዮ ሆነ በቴሌቪዢን እንዲሁም በጹሑፍ ዝግጅት አዝለብልቦ ቢያዘጋጅ ለትርጉሙ Documentary አይመጥነውም እላለሁ።
  • ለእኔ ኢህአድግ የሚባል ድርጅት የለም። ቢኖርም ቅርፊት – የባህር ማሽላ አዘርዛሪ ዓይነት ነው አሮ ረግፎ የቀረ፤ ምንም ጥቅም የማይሰጥ። ስለዚህ በሌለ ነገር ላይ ሳይሆን ባለ ነገር ላይ ስለሆነ ሙግቴን ያቀረብኩት „ኢህአድግ“ እያሉ አቶ ኤርምያስ ለገሰ የተጠቀሙበትን ቅርቅር አድርጌ የዘጋሁት በመሆኑ በጭንብሉ ሳይሆን ገዢውን – ዘረኛውን በግልጽ ሥሙ በሚመካበትና በማያፍርበት ሥሙ ወያኔ እያልኩኝ ነው የፃፍኩት። ለእውነት ይቅርታ ቢጠዬቅበት ሰማይ ይፈርሳል …. እና ….

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

   እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 


የእርቅና የመግባባት ሂደት መመዘኛዎች (ዶ/ር ዘለዓለም እሸቴ ይመር)

$
0
0

peaceበኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ ምእራፍ እንዲኖር መፍትኤው ምንድነው? ያልተሞከረው ብቸኛ መፍትኤ እርቅና መግባባት ነው። ለመሆኑ እርቅና መግባባትን እምቢ ባዩ ማን ይሆን? መንግስት ወይስ ተቃዋሚ? ወይስ ዝምተኛው አብዛኛው ሕዝብ? ወይስ ሁላችንም? ሁሉም ክሱን ትቶ ራሱን ይመርምር። ራሳችንን እንድንመረምርበት የሚከተለውን ባለ 10 ነጥብ የእርቅና የመግባባት ሂደት መመዘኛዎች እንደ መንደርደሪያ አሳብ አድርገን እንውሰድ። ታዲያ በነዚህ ሚዛን ተመዝነን ቀለን እንዳንገኝ አምላክ የእሽታን መንፈስ ለሁላችንም ይስጠን። መንግስትን በተመለከተ
1ኛ/ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት ጁቢሊ (“Jubilee”) ማብሰር
2ኛ/ በፊታችን ያለውን ምርጫ ፍታዊ ማድረግ(በራስ መተማመንን ያሳያል)
3ኛ/ ተቃዋሚ የሚያቀርበውን መጥፎ አሳብ እያጋለጡ መልካም የሆነውን ግን በስራ ላይ ማዋል
ተቃዋሚን በተመለከተ
4ኛ/ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከመከፋፈል ይልቅ አንድነትን እንዲፈጥሩ (አንድነት ሃይል ነውና)
5ኛ/ የሰላም ትግሉ ከጦርነትና ከአብዮት አመፅ የፀዳ መሆኑን ከልብ ማስመር
6ኛ/ መንግስት የሚሰራውን ስህተት እያጋለጡ መልካም ስራውን አለመካድ
መንግስትና ተቃዋሚ (ሁለቱንም) በተመለከተ
7ኛ/ የንግግር ቃላት በፀጋና በቅንነት የተሞላ ይሁን(ሰውዬውን ወዶ አሳቡን መጥላት እንማር)
ገለልተኛው አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተመለከተ
8ኛ/ ዝምታውን አቁሞ ለእርቅና መግባባት ድምፁን እያሰማ መሟገት ይጀምር
ሁሉንም ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊን በተመለከተ
9ኛ/ ለኢትዮጵያ የጋራ በሆኑት ነገር ላይ አንድነትን መግለፅ (ኢትዮጵያ ከፖለቲካችን በላይ ናት)
10ኛ/ አምላክ ኢትዮጵያን እንዲባርካት እጆቻችንን ወደ ፈጣሪ መዘርጋት
ከሁሉም ወገን ልሰማ እወዳለሁና አሳባችሁን ፃፉልኝ: Z@myEthiopia.com

የደርግና የወያኔ የውይይት ክበብ –ከአንተነህ መርዕድ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ጥቅምት 2014 እ ኤ አ

ላለፉት አርባ አመታት በአምባገነኖች መዳፍና በካድሬዎች ቁጥጥር ስር ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘላቂ ነፃነት እስካላገኘ ድረስ የስርዓት መቀየር ብቻ ለነፃነቱ ዋስትና አልሆነውም፤ አይሆነውምም። አምባገነኖች ጉልበቱን ከመበዝበዝ፣ ከማሰርና ከመግደል አልፎ ስብዕናውን በመግፈፍ የጎደፈ አስተሳሰባቸውንና ፍልስፍናቸውን በዜጎች አዕምሮ በመሙላት አገዛዛቸውን ዘላቂ ያደረጉ ይመስላቸዋል። የሚገርመው ደርግ ሆነ ወያኔ የህዝብ መሰረት ሲያጡ፣ ዙርያ ገባው ገደል ሲሆንባቸው፤ በካድሬዎቻቸው ህዝቡን ሰብስቦ በፕሮፓጋንዳቸው ማጥመቅ ልትበጠስ የደረሰችውን በስልጣን ዘመን የሚያራዝምላቸው ይመስላቸዋል።
ደርግ በመጨረሻው ዘመን እንደ ወያኔ ህዝቡን እየሰበሰበ እውቀት በሌላቸው እበላባይ ካድሬዎች አማካይነት በግዴታ ማርክሲዝም ሌኒንዝምን ቋቅ እስኪል ለመጋት ታግሎዋል። የታለመው ህዝብን የማዘናጋትተልዕኮ አልሰራም፣ በውርደት ከመውደቅ ግን አላዳነውም። ይህንን ባንድ ምሳሌ ልቋጨው። በአዲስ አበባ ዩኒቭርሲቲ ዓለም ያደነቃቸው፣ በእውቀታቸው አንቱ የተባሉ ምሁራን እየተገደዱ በመኮንን አዳራሽ ከቢሮ ሰራተኞች፣ ከዘቨኞች፣ ከፅዳት ሰራተኞች ጋር ታጉረው በእድሜም በዕውቀትም እዚህ ግቡ የማይባሉ ውርጋጥ ካድሬዎች እንጨት፣ እንጨት የሚል የፍልስፍና ፕሮፓጋንዳ ይዥጎደጎድባቸዋል። ከግማሽ በላይ የሚሆነው የተሰላቸው ተሰብሳቢ በየጥጉ እንቅልፉን ይለጥጣል። እውነት መሆኑን ባላውቅም ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አሉት የተባለው እውነቱን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ጮርቃው ወጣት ተማሪ ካድሬ መምህሮቹን ጭምር ብዙ ለማስተማር ቀድሞ የተሞላውንና እሱም በቅጡ ያልገባውን ፍልስፍና ከቀባጣጠረ በኋላ ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካላችሁ በማለት ይጠይቃል። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እጃቸውን ያወጡና “ይህንን ነገር ደጋግምችሁ ስታስተምሩን ከረማችሁ። አሁን ፈትኑንና የወደቀ የወደቀውን እንደገና አስተምሩ” ብለው ተቀመጡ ይባላል። ግፍን ከመቃወም ግንባራቸውን የማያጥፉት ፕሮፌሰር መስፍን ይህንን ከማለት እንደማይመለሱ ሁላችንም እርግጠኛ ነን።
ethiopian flag
በተመሳሳይ ሁኔታ ሰሞኑን ወያኔ ስልጣኑን እንዳስረከበው ደርግ ዜጎችን እየሰበሰበ ብዙ ሚሊዮን ብር ወጭ አድርጎ በግዴታ አስተምራለሁ እያለ ይገኛል። የሚገርመው የወያኔን ትምህርት ተቃዋሚው መብዛቱ ነው። በሁሉም የአገሪቱ ክልል እንደሚደረገው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራኑን ሰብስበው የፌዴሬሽን ምክርቤቱ ሰብሳቢ ካድሬው ካሳ ተክለብርሃን ለምሁራኑ ትምህርት ሊሰጡ ሲሞክሩ ተቃውሞው የበረታ ነበር። እንደ ፕሮፌሰር መስፍን በሚገርም ሁኔታ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ “ለመሆኑ በየትኛው እውቀታችሁ ነው እኛን እናንተ የምታስተምሩት? ካንተ ብንጀምር እውቀትህ ምን ያህል ሆኖ ነው እዚህ ያለነውን ለማስተማር ያስደፈረህ? ለመሆኑ አታፍሩም?” በሚል መሽንቆጣቸውን ስሰማ ደንቆኛል። የበየነ ሃሳብ በከፍተኛ ጭብጨባ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪ የተቃውሞ ሃሳቦች በተሰብሳቢው ተደግፏ። ብዙዎችን ያስደነቀው የካሳ ተክለ ብርሃን ቻይነት ነው። ፀጥ ብሎ ወቀሳውንም ስድቡንም ጠጥቶ ስብሰባውን ቀጥሏል። ሌሎች ቢሆኑ በትነውት ይሄዱ ነበር ተብሏል።

አንባቢ በየነ ጴጥሮስን ከመስፍን ወልደማርያም ጋር እኩል ሚዛን ውስጥ እንዳያስቀምጥ አስጠነቅቃለሁ። መስፍን ወልደማርያም ያመኑትን ያለፍርሃት የሚናገሩ፣ የሚናገሩትን ደግሞ የሚያደርጉ፤ ለግል ዝና፣ ስልጣን ሆነ ሃብት የማያጎበድዱ በየጊዜው የተፈተኑ ደፋር ዜጋ ሲሆኑ በየነ ጴጥሮስ ከዚያ በታቃራኒው የቆሙ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል። ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል ይባላልና። የእናት ኢትዮጵያ ሆድ ዝጉርጉር ስለሆነ በየነ ጴጥሮስን ከመስፍን ወልደማርያም መዘነቅ አይቻለንም። ስለነዚህ ሁለት ሰዎች ብዙ ለማለት ቦታው አይደለም ሌላ ቀን እመጣበታለሁ፤ በተለይ ስለ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም። ወደተነሳሁበት ልመልሳችሁ።

የህዝቡ ፀጥ ረጭ ማለትና ታቃዋሚዎች ለሰልፍ ሲጠሩት ግልብጥ ብሎ መውጣቱ እንቅልፍ የነሳው ወያኔ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ የመንግስት ሰራጠኞችን፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን፣ የስርዓቱን ደጋፊዎችንና ባጠቃላይ ህዝቡን ከፍተኛ ወጭ አውጥቶ የሚያምስበት ብዙ ምክንያቶች አሉት። ዋና ናቸው የምላቸውን እንደዚህ ላስቀምጥ።

• ለመጭው ምርጫ ያደረበትን ስጋት ለማቃለል የውሃ ልኩን ለመለየት
• በስለላ መዋቅሩ ሊለዩ ያልቻሉና ይቃወሙኛል ያላቸውን ለቅሞ ለማወቅ
• ጥርሳቸው ያለቀ አገልጋዮችን ወርውሮ በአዳዲስ ምልምሎች ለመተካት
• እንደደርግ ማርክሲዝም በልማታዊ መንግስት ፅንሰ ሃሳብ ህዝብን ለማደንዘዝ
• እየከሸፈ ያለው ከፋፋይ የዘር ፖለቲካ እንዲያንሰራራና በተለይም ሁለቱን አንጋፋ የአማራና የኦሮሞን ህዝብ የተለያየ ስም በመስጠት አንገታቸውን ደፍተው እንዲቆዩ ለማድረግ
• የምርጫ ዘመቻ በይፋ ከመታወጁ በፊትና ታቃዋሚዎችም ወደ ህዝቡ ከመቅረባቸው ቀድሞ ለራሱ ጥርጊያ መንገዱን ለማመቻቸት የሚሉትና ሌሎችንም ታሳቢ አድርጎ እንድሆነ ያስታውቃል።

ወያኔ ኢህአዴግ አቅዶ ተነስቷል ካልሁዋቸው ነጥቦች ምን ያህል ተጠቃሚ እንደሚሆን ራሱም የሚያውቀው ጊዜም ቆይቶ የሚመሰክረው ሲሆን “አፋፍ ለአፋፍ መቀደስ የተኛ ሰይጣን መቀስቀስ” እንዲሉ ያልጠበቀውን አስቀያሚ ውጤት እያሳየው ለመሆኑ የኢሳትን ዘገባና ድረገጾችን የሚከታተል ሁሉ የሚገነዘበው ነው። የመጭውን ምርጫ ውሃ ልክ ለመለካት ጊዜና ጉልበት ማባከን ባልተገባው ነበር። በ1997 ዓ ም ምርጫ ወያኔን የማይመርጥ መሆኑን ያሳየ ህዝብ አሁን የባሰ ጭቆናና ግፍ ተንሰራፍቶ ያ ሁሉ በደል ተፈጽሞበት ለወያኔ የሚሳሳ ልብ አይኖረውምና።
ይቃወሙኛል ያላቸውን ለቅሞ ለማውጣትም ቢሆን ጣመን ሊመታው አይገባም። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎት ፍርሃትን አሽቀንጥረው በመጣል ያቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሉአላዊነት ጉዳይ፣ የጎጠኝነት ፖለቲካ ከፋፋፍ ደባ፣ የውሸት የኤኮኖሚ እድገት፣ የፍትህ እጦት፣ የህወሃት የበላይነትበሁሉም ዘርፍ መንገሥ፣ ወዘተ መድረኩ ላይ በግልጽ ተሞግቶባቸዋል። አፄ ምኒልክንና ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ይቅርና ደርግን እንኳ የሚወቅሱበት የሞራል ብቃት እንደሌላቸው በመድረኩ ተነግሯቸዋል “በራሷ መብራት እርቃኗን አዩባት” ይሏል የወያኔ የሰሞኑ የውይይት መድረክ ነው። ስለዚህ ስንቱን ለቅሞ አስሮና ተከታትሎ ይጨርሳል??

ልማታዊ መንግስት ማለት ጥቂቶቻችሁን አክብሮ ብዙዎቻችንን ማደህየት ነው? የሚለው ጥያቄ ብቻ የፅንሰሃሳቡን ፉርሽነትና የህዝቡንም ብስለት አረጋግጧል። ለሃያ ሶስት ዓመታት የተደለቀው የዘር ፖለቲካ ለአገሪቱ የተወው ጠባሳ ለመሻር ገና ብዙ መስዋዕት የሚጠይቅ ቢሆንም ኢትዮጵያ አልጠፋቸም። አትጠፋምም። በተለይ የኦሮሞና የአማራ ልሂቃን ካንቀላፉበት መንቃት እንዲሁም ከተሳሳተ አመለካከታቸው ወጥተው ለግል ጠባብ ፍላጎታቸውና ለዝናቸው ሳይሆን ለህዝባቸው ጠቃሚ ነገር ማሰብና መተግበር አለባቸው።

የዘረኝነት መሃንዲስ የሆነው መለስ ዜናዊ ህይወቱ ቢያልፍም እየቆየ የሚፈነዳ ቦምብ ቀብሮ ሄዷል። እንግሊዞች ቅኝ በገዙአቸው አገሮች የፈፀሙትን ያህል ሸር ሰርቷል። ማክሸፍ የኢትዮጵያዊ ሁሉ ሃላፊነት ነው። ሁለት ተጨባጭ ምሳሌ ልጥቀስላችሁ። በዚህ በኩል ትግርኛ ተናጋሪ ወንድሞቼ ብታግዙኝ ምንኛ ደስ ባለኝ። ይህንን ጉድይ በሚገባ የምታውቁትና ባርምሞ ብትቀመጡም እዳው የእናንተም ነውና እንረዳዳ። በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ ትግራይ ሄዶ የአገር አዛውንቶችንና ታዋቂ ግለሰቦችን ይሰበስብና “ምን አድርገናችሁ ነው ድጋፋችሁ የቀዘቀዘው? ተቃዋሚዎችን ለመስማትም ጆሮአችሁን የሰጣችሁት? ከተሳሳትን ታረሙ በሉን እንጂ አረናንና ነፍጠኞችን ለምን ትሰማላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። የአገር ሽማግሌዎች እየተነሱ “ከአብራካችን ልጆቻችንን ያስረከብናችሁና የሞቱት፣ ከሌለን አካፍለን አብልተን በደርግ ጦር እየተለበለብን የደገፍናችሁ አንተ፣ ስዩም፣ አባይ፣ ስብሃት ነጋና ጥቂቶቻችሁ ሚሊየነር ሁናችሁ እኛና ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ እንድንለያይ፣ በድህነት እንድንማቅቅ ነው?ምን ጥሩ ነገር ሰራችሁ?” የሚሉትንና ሌሎችን መሰረታዊ ጥያቄዎች ሲያቀርቡለት የመለሰላቸው እንዲህ ሲል ነው። “አዎን ያላችሁን ሁሉ ትክክል ነው። አጥፍተናል። ድጋፋችሁን አትንፈጉን እናርማለን። አንድ ትልቅ ጥሩ ነገር ግን መስራታችንን አትዘንጉ። ለትግራይ ህዝብ አንገት መድፋት ምክንያት የሚሆኑ አማራና ኦሮሞን ለያይተንላችኋል። አማራን ነፍጠኛ፣ ኦሮሞን ጠባብ ብለን ቅስማቸውን በመስበራችን ትግሬ አንገቱን ቀና አድርጎ የሄደበት ጊዜ እንደዛሬ አልተገኘም” አላቸው። ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ህወሃት በሚገባና በተሳካለት ሁኔታ የሰራውም ይህንን ነበር። ኦሮሞ ወይም አማራ ነኝ የሚልና በተዘጋጀለት ወጥመድ ውስጥ ራሱን አስገብቶ የሚንቀሳቀስ ሁሉ ከዚህ የባሰና የወረደ ድንቁርናና ጅልነት የት ይገኛል?

መለስ በዚህ አላበቃም አብዛኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች በክረምት ትምህርት ቤት ሲዘጋ በጫት፣ በሲጋራና ባልኮል እንዲናውዙ ሲድረግ የትግራይ ወጣቶች ክረምቱን ሙሉ ልዩ ስልጠናና ትምህርት ሲሰጣቸው ይከርማል። ይህ ገና ስልጣን በያዙ ማግስት ጀምሮ አብዛኞቹ አገሪቱ ውስጥ ያሉት ተቋማት ውስጥ ለትግራይ ወጣቶችና ሰራተኞች በየክረምቱ ልዩ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቶ አሁን አሁን ትግራይ በሚገኙ ተቋማት ያደርጉታል። በቂ ቦታ ገንብተዋልና። በየወቅቱም መለስ በመካከላቸው የገኝቶ ወጣቶቹን ያበረታታቸዋል። በሌላ ክልል ይህንን አድርጎ አያውቅም። የኢትዮጵያ መሪ ሳይሆንና ኢትዮጵያዊ ሳይሆን የሞተ ቢኖር መለስ ዜናዊ ብቻ ነው። በአንድ ወቅት ለሰበሰባቸው ሰልጣኝ ወጣቶች የተናገረው ግን ንፁህ ህሊና ያላቸውን ተሳታፊዎች አስደንጧል። ባጭሩ እንዲህ ነበር ያለው። “እናንተ እድለኞች ናችሁ። እኛ እንደናንተ በአካባቢያችን ሳንማር በወጣትነት መዳፍ የማትሸፍን ስኳር እየቃምን፣ አቀበት ቁቁለት ወርደን ተዋግተን፣ ሞተን፣ ቆስለን ነው ለዚህ የበቃነውና ለዚህ ያበቃናችሁ። እናንተ ይህችን አገር ለረጂም ጊዜ ለመምራት መዘጋጀት አለባችሁ። ይህ ደግሞ የሚሆነው በትምህርት ከሌላው ስትልቁና ኤኮኖሚውን መቆጣጠር ስትችሉ ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ ሁሉን አመቻችተንላችኋ። እናመቻችላችኋለንም። ይህ እድል ካመለጣችሁና አማራና ኦሮሞዎች ስልጣን ከያዙ ተስፋ አይኖራችሁም” ሲል በለጋ አእምሮአቸው ላይ መርዙ ለመጠቅጠቅ ሞክሯል።

መለስ ለትግራይ ሽማግሎችና ወጣቶች የተናገረው መራራ በዘረኝነት የተሞላው ቅስቀሳ ለነሱ በማሰብ ሳይሆን በስልጣን ለመቆየት የትግራይን ህዝብ መሰረት ላለማጣትና የበለጠም ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በጥርጣሬ እየተያየ እንዲኖር ለማድረግ ነው። የትግራይ ህዝብ ለጥቂት የህወሃት ባለስልጣናት ምቾትና ስልጣን ሲል ከዘላቂው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መለያየት የሚመርጥ አይደለም። ፕሮፓጋንዳውና ጊዜያዊ ጥቅማጥቅም ጥቂቶችን አማልልሎ እንደሆነ እንጂ ብዙሃኑ የትግራይ ህዝብ እውነቱን የሚረዳ ነው። ስለዚህም ነው የትግራይ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ በበለጠ አፈና ውስጥ የሚገኘው። በነፃነት ሃሳቡን እንዲገልፅና እንዲንቀሳቀስ ቢደረግ የትግራይ ህዝብ በትክክል ምርጫውን ያውቃል። ልክ እንደትናንቱ እንደ አፄ ዮሃንስ፣ እንደ አሉላ ኢትዮጵያዊነቱን ይመርጣል።

የሰሞኑ ትምህርት ያሳየን ነገር ቢኖር የህዝቡን ብስለትና የወያኔን የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው። ከኃይለስላሴና ከምኒልክ ያነሰች አገር ይዛችሁ እነሱን መውቀስ አትችሉም። ጦሩን ደህንነቱ፣ ሁሉንም ቁልፍ ቦታና ኤኮኖሚውን በአንድ መንደርልጆች አስይዛችሁ ዴሞክራሲ አለ ለምን ትላላችሁ? ሃያ ሶስት ዓመት መርታችሁ ከአለንበት ውድቀት የከተታችሁን አርባ ዓመት ለመግዛት እንዴት ትመኛላችሁ?…..የመሳሰለው ጥያቄ እንኳን ከቀሪው ህዝብ ሞሰብ መላስ ከሰለቻቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ ደህዴድ ዴድ…ዴድ ዴድ ከተባሉ ደጋፊዎቻቸው ጋር እንኳን የሚያካርማቸው አይደለም።
ቸር እንሰንብት
amerid2000@gmail.com

የፖለቲካ አመራሮቹ ችሎት ያለ ተከላካይ ጠበቃ ሲታይ፤ቀጣይ ቀጠሯቸው ግልፅ አይደለም

$
0
0

Habtamu abrhayeshiwas danielዛሬ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ፒያሳ አራዳ በሚገኘው የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የፖለቲካ  ፓርቲ አመራሮች ጉዳይ በዝግ ችከሎት ያለ ተከላካይ ጠበቃ ቀጠሮ መስጠቱ ተጠቆመ፡፡ የፖለቲካ አመራሮቹ አቶ ሀብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ የአንድነት ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ አብርሃ ደስታ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህርና የአረና ፓርቲ ምክትል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንዲሁም አቶ የሺዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ከተከላካይ ጠበቆቻቸው ጋር ሳይገናኙ ከቀጠሮ ሰዓታቸው አርፍደው ከቀኑ 10 እና 11 ሰዓት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

በነበረው የፍርድ ቤት ችሎት ተከላካይ ጠበቃ ደንበኞቻቸውን ህጉ በሚፈቅደው መሰረት በማዕከላዊ ሄደው መጎብኘትና መነጋገር ቢፈልጉም፤ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል “ማዕከላዊ” ፖሊስ ስላልተፈቀደላቸው ፍርድ ቤት መገኘቱ ለፕሮፖጋንዳ ካልሆነ ከህግ አግባብ ትርጉም ስለሌለው እንደማይገኙ አስቀድመው ማሳወቃቸው ተጠቁሟል፡፡ በችሎትም ቤተሰብ፣ ጋዜጠኛ፣ ዲፕሎማቶች እና ወዳጅ ዘመድ እንዳይከታተል መከልከሉም ታውቋል፡፡ የእስረኞቹ ቀጣይ ቀጠሮ መቼ እንደሆነ እስካሁን ከፍርድ ቤቱ ማግኘት ባይቻልም፤ እንደ ነገረ ኢትዮጵያ ዘገባ ከሆነ የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ አቶ ተክላይ ሹመት ተጠርጣሪዎቹ የተቀጠሩት ለጥቅምት 20 ቀን 2007 ዓ.ም. ሲሉ፤ ሌላ ፖሊስ ደግሞ ለጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ነው የሚል ጥቆማ መስጠታቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስረኞቹ እስካሁን በነበረው ምርመራ ፖሊስ ምንም ዓይነት ለወንጀል ክስ የሚያበቃ መረጃ ባለማግኘቱ፤ ወደ ኃይል እርምጃ በመሄድ ፖሊስ የሚፈልገውን ቃል እስረኞቹ ያልፈፀሙትን አስገድዶ የእምነት ቃል እንዳስፈረማቸው የማዕከላዊ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ይሄም ለህዝቡና ለመገናኛ ብዙኃን እንዳይገለፅና ፍርድ ቤትም በቅሬታ መልክ እንዳይቀርብ ስለተፈለገ ነው ተከላካይ ጠበቆቹ እንዳይጎበኙ የተከለከሉት ሲሉ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ በዚህም የዛሬው ችሎት ያለጠበቃ ጭምር በዝግ ችሎት መካሄዱ የተጠቆመ ሲሆን፤ የቀጠሯቸው ቀንም ከላይ ከተጠቀሰው ውጭ እስካሁን ትክክለኛውን ከፍርድ ቤቱ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ መረጃዎእ አመልክተዋል፡፡ ችሎቱን ለመታደም ወደ ስፍራው ያቀኑ ሰዎችም ፍርድ ቤቱ ግቢ ሲገቡ ከወትሮ በተለየ በፖሊሶች ከፍተኛ ፍተሻ፣ እንግልትና ወከባ እንደተፈፀመባቸው የዓይን እማኞች ገልፀዋል፡፡

8 ጊዜ የተቀያየሩትን የኢትዮጵያ ባንዲራ ዓይነቶች ያውቋቸዋል? (ካላወቁ ይመልከቷቸው)

$
0
0

በተለያዩ ጊዜያት በሃገራችን የነበሩ የሰንደቅ አላማዎች እንደሚከተለው እንመልከት
1

2

3

4

5

6

7

8

ኢትዮጵያ ዘመን ተሻጋሪ የሰንደቅ አላማ ታሪክ ካላቸው ሃገራት መካከል አንዷ ናት ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እስከ 1890ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ ድረስ በቀለማትም አንድ ወጥ አልነበረም ፤ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያሉት ሰንደቅ አላማ ቀለማት ወጥነት ባለው በተያያዙ አራትማእዘናት በጥቅም ላይ የዋሉት በ1890ዎቹ መጨረሻ ነው ፤ በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሰንደቅ አላማ ልዩትርጓሜና ስርፀት የተሰጠው በ1898 እንደሆነ ይነገራል ፤ ቢጫ የብርሃን፣ ቀይ የመስዋዕትነትና አረንጓዴ የተስፋምልክት ተደርጐ ይወሰዳል፡፡

ከዚህ በኋላ ሰንደቅ አላማችን አንድ ጊዜ መንፈሳዊ ሌላ ጊዜ ፖለቲካዊ ትርጓሜ እየታከለበት ዘመን ተሻግሯል ፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በሰንደቅ አላማችን ስም በጐም ሆነ መጥፎ ተግባራት በተፈፀሙባቸው ዘመነ መንግስታት ጭምር ለሰንደቅ አላማችን ያለን ፍቅርና ክብር እጅግ ጥልቅ ነው ፤ ጥንታውያንጀግኖች ወላጆቻችን ሰንደቅ አላማችንን ይዘው አስደናቂ ትግልና ውጊያ በማካሄድ ከባዕዳውያን ቀጥተኛ ተፅዕኖ ነፃ የሆነች ሃገር አስረክበውናል ፤ በአንዲት ባንዲራቸው ጥላ ስር በመሆን ወራሪውን ሃይል በእግዚአብሔር ረዳትነትና እና በታማኝ አርበኞች ጀግንነት ከቀኝ ግዛት ነጻ የሆነች ሀገር አቆይተውልናል ፡፡

ኢትዮጵያውያን ለአያሌ ዘመናት ብሔራዊ ክብራችንን ባዋረደና እንደ ህዝብ አንገታችንን ባስደፋን አስከፊ የድህነትማቅ ውስጥ ኖረናል ፡፡ አሁን ሰንደቅ አላማችን የጭቆናም የጭፍጨፋ አርማ አይደለም። የሰንደቅ አላማችን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት እንደ ዱሮው ሁሉ የልምላሜ የተስፋና ለነፃነት የሚከፈል መስዋዕትነት ምልክቶቻችን ናቸው ።

“አፍ ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም” እንደሚባለው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አውቀው ይሁን ሳያውቁ “ባንዲራ ጨርቅ ነው” በማለት በአደባባይ ሲናገሩ ጆሯን ሰምቷል ፤ በዚህ ንግግራቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን የባዲራው ነገር የገባቸው እጅጉን ውስጣቸው ተጎድቷል ፤ እድሜ ልካቸውን ለሀገር ብለው ከጠላት ጋር ጦር ሜዳ ለተዋደቁ አባቶቻችን ይህ አባባል አጥንት ዘልቆ የሚሰማ ስሜት ፈጥሮባቸው አልፏል ፤ አቶ መለስ ይህን በተናገሩ በሳምንታት ውስጥ አፋቸውን ሞልተው “ይቅርታ መናገር አልነበረብኝም ተሳስቻለሁ” የማይሉ ሰው ስለሆኑ ምን ማለት እንደፈለጉ በሌላ አባባል ንግግራቸውን መስመሩን ማስቀየር ችለው ነበር ፡፡

የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ቀን በዓል መከበር የጀመረው በአዲሱ ሚሊኒየም መጀመሪያ ላይ ነው ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀው የሰንደቅ አላማ አዋጅ በዓሉ በየአመቱ በመስከረም ሁለተኛ ሳምንት ሰኞ እንዲከበር ይደነግጋል ፤ አዋጁ መስከረምን የመረጠው ወሩ ለሃገራችን የዘመን መለወጫና አዲስ የተስፋ የስራና የለውጥ መንፈስ የሚፈጠርበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ይመስላል ፤

የሰንደቅ አላማችን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ህብረ-ቀለማት ያለፈውም ሆነ የመጪው ጊዜ በልማት የመለወጥ ፣ በነፃነትና በተስፋ የመኖር ራዕያችን አሻራዎች ናቸው፡፡ የአግድም ቀለሞች አረንጓዴ- ስራ፣ ልምላሜና እድገት ፤ቢጫ -የተስፋ፣የፍትህና የእኩልነት ቀይ- ለነጻነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡ ይህን የቀለም ህብረት ኢትዮጵያ መጠቀም የጀመረችው ከአድዋ ጦርነት በፊት መሆኑን ታሪክ ይናገራል ፤ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ይህን የቀለም ህብረት መጠቀም የጀመሩት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ ይታወቃል ፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነትና የቅኝ አለመገዛት ተምሳሌት የሆነች ሀገር በመሆኗ በርካቶች ይህን ለመጠቀማቸው ቀዳሚ ምክንያን መሆኑን የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ፡፡

ምንጭ፡ አንድ አድርገን

ጫልቱን የገደላት ወያኔ ኢህአዴግ ሆኖ ተገኘ

$
0
0

ገለታው ዘለቀ

የስደተኛው ማስታወሻ ከተሰኘው መጽሃፍ ውስጥ ኣንዲት ምእራፍ መዝዤ በዛ ላይ የሰላ ግምገማ ለማድረግ ነው የዛሬው ኣነሳሴ ። መጽሃፉን የጻፈው ተስፋየ ገብረኣብ ሲሆን በዚህ መጽሃፍ ውስጥ የተለያየ ጭብጥ ያላቸውን ጉዳዮች በየምእራፉ ያነሳ ሲሆን “ጫልቱ እንደ ሄለን” የሚለው የብዙዎችን ትኩረት እንደሳበ ሁሉ የእኔንም ስቦ ነበርና በዚህ ክፍል ላይ ያነጣጠረ ትችት ኣቀርባለሁ።መጽሃፉ ከተለቀቀ ዘግየት ቢልም የጫልቱ እንደሄለን ጉዳይ ግን መወያያነቱ ረዘም ላለ ጊዜ ቆይቶ ስላየሁ ነው ዛሬ የተነሳሁት።
yesidetegnaw
ደራሲው ይህን ክፍል ሲጀምር በፍቃዱ ሞረዳ በተባለ ገጣሚ የተደረሰ ግጥምን በማንበብ ነው። የዚህ ግጥም ይዘት ወይም ጭብጥ ከዘረኝነት ጋር የተያያዘ ነው። በዚህ ግጥም ብእሩን ያሟሽና ኣንዲት ጫልቱ የተባለች ቆፍቱ ተወልዳ ያደገች ውብ፣ የኣስራ ኣራት ኣመት ልጅ ጋር ያስተዋውቀናል ። ይህቺ ህጻን ቆፍቱ ውስጥ የታወቀች ፈረስ ጋላቢ እንደነበረች ይናገራል። ከወንዶች ጋር ሁሉ ተወዳድራ ፈረስ ግልቢያ እንዳሸነፈች በዚያም ምክንያት ፈረስ እንደተሸለመች፣በዚህም ስሟ እስከ ዋጂቱ፣ እስከ ወልመራ፣እስከ ሴራ፣ እስከ ደዋራ፣ እስከ በቾ፣ እስከ ጭቋላ፣ እስከ ድሬ፣ እስከ ጊምቢቹ ድረስ ተሰምቶ እንደነበር ያስረዳናል። ይህ የሆነው ከኣስራ ኣራት ኣመቷ በፊት በመሆኑ በርግጥ ይህቺ ህጻን ከቆፍቱ ትላልቅ የታወቁ ፈረስ ጋላቢዎች ጋር ተወዳድራ ኣሸነፈች? የሚለው የተኣማኒነትን ጥያቄ ያስነሳል። ወይ እንደሷ ከሆኑ ታዳጊ ህጻናት ጋር ተወዳድራ ከሆነ ደራሲው ኣንድ ይበለን እንጂ የኣስራ ሁለት የኣስራ ሶስት ወይም ከዚያ በታች ህጻን ሆና ከኣካባቢው ወንዶች ጋር ተወዳድራ ኣሸነፈች ቢለን ከመነሻው ተዓማኒነት የሚባለውን ጉዳይ እንድናነሳ ያደርገናል። ይሁን…. እንግዲህ….. ብለን ይህንን ጉዳይ ተወት ኣድርገነው ማንበባችንን ስንቀጥል ጫልቱ ብቻዋን በኣስራ ኣራት ኣመቱዋ ፈረስ ጋልባ ዘመድ ለመጠየቅ ጉዞ ስትጀምር ያሳየናል። ይህቺ ኣንድ ፍሬ ልጅ ብቻዋን ፈረስ ጋልባ ዘመድ እንድትጠይቅ ቤተሰብ መፍቀዱ ሌላው ኣንድ ኣንባቢ የሚጠይቀው ጉዳይ ሆኖ ለማናቸውም መንገድ ላይ ሊጠልፏት የከበቧትን ጎረምሶች በጣጥሳ እንዳመለጠች ይተርክልናል። ጋላቢ ስለነበረች ከዚያ ሁሉ ጎረምሳ ሽምጥ ጋልባ ኣመለጠች ይለናል። ምን ኣይነት ፈረስ ቢሆን? ምን ኣይነት ህጻን ጋላቢ ናት ያሰኘናል። ይሁን ብለን እንቀጥላለን….. ደራሲው ብዙ ሳይቆይ ጫልቱ በኣስራ ኣምስት ኣመቷ ከድሬ ለመጣ ታዋቂ የአድአ ቤተሰብ መዳሯን ያረዳናል። የሚገርመው ደራሲው ይህን መርዶ ለተደራሲያኑ ሲያቀርብ ኣለመከፋቱ ነው። በኣስራ ኣምስት ኣመት ትዳር መጀመርና መደፈር በጣም ኣሰቃቂ ጉዳይ ነበር። ደራሲው ለዚህች ህጻን ኣዛኝ ቢሆን ኖሮ ያለእድሜዋ በመዳሯ ብዙ ሊል ይገባው ነበር። ይህቺ ህጻን ያገባችው በኣስራ ሰባት ኣመቱዋ ኣይደለም። በኣስራ ኣምስት ኣመቷ ነው የተደፈረችው። ይህቺ እህታችን ምን ኣልባትም ገና የሴቶቹን ወግም ኣላየችም ይሆናል። በገጠር የሚወለዱ ሴቶች ቶሎ የሴቶችን ወግ የሚያዩ ኣይደሉም። ኣካሉዋና ስሜቱዋ(emotion) ለወሲብና ለትዳር ሳይበቃ መዳሩዋ ቀጣይ የህይወት ዘመኑዋን ሁሉ ሊያበላሸው ስለመቻሉ ጥያቄ የለውም።የስነ ልቡና ሰዎች እንደሚሉት ሴቶች ለኣቅመ ህያዋን ሳይደርሱ ወሲብ ሲፈጽሙ ህይወታቸውን ሁሉ የሚከተላቸው የስሜት ችግር ኣለ። ደራሲው ለዚህች ወጣት ስስ ስሜት እንዳለው እንደራራላት በዚህ ኣካባቢ ሳያሳየን መቅረቱ ለጫልቱ ያለውን ፍቅር ከወዲሁ እንድንመዝን ያደርገናል።

ጫልቱ ብዙም ሳትቆይ ጠፍታ ወደ ቤቷ ተመለሰች። ምነው ትዳር ይሻላል ቢሏት ሰካራም ነው ይደበድበኛል ኣለች። በርግጥ ከዚህ ሌላ በቃል ለመግለጽ የፈራችው ምክንያት እንዳለ ሁሉ ተሰምቶኛል። ችግሩዋን ማስረዳት ስለማትችል ይህንን ምክንያት በመስጠት እንቢኝ ማለት ፈልጋ ይሆናል። ለማናቸውም ይህን ክፍል ሳነብ ኣንጀቴን ያላወሰው ጉዳይ ያለእድሜዋ ምናልባትም የሴቶችን ወግ እንኳን በቅጡ ሳታይ ዘላ ሳትጠግብ የቤተሰብ ሃላፊነት ቀንበር ትከሻዋ ላይ መጫኑ ነው።

ጸሃፊው ወደ ኣዲስ ኣበባ ሊሸኛት ሲል የባህሪ ለውጥ ማምጣቱዋን ቁጡ መሆኑዋን ጥቂት ጠቆም ኣድርጎን እሱን ስላብከነከነው የሄለንና የጫልቱ ስያሜ ጉዳይ ያሮጠናል። ኣንባቢዎች እንከተልና ንባባችንን ስንቀጥል ከብዙ የቤተሰብ ምክር በሁዋላ ወደ ሸገር ሄዳ እንድትማር ተወሰነ ይለናል። ቤተሰብ ወደ ሸገር እንድትሄድ መወሰኑ ስለሸገር መልካምነት የሰማው ጉዳይ ቢኖር ነው ብለን እንድናስብ ያደርገናል። የጫልቱ ዘመዶች የሚወዱዋትን ቆንጆ ልጃቸውን ወደ ክፉ ቦታ ሂጂ ኣይሉም ብለን እናስባለን። ቆፍቱ ከኣዲስ ኣበባ ብዙ የማይርቅ በመሆኑ እነዚህ የጫልቱ ቤተሰቦች ተመላልሰው ኣይተውም ሊሆን ይችላል። ከሁሉም በላይ ኣዲስ ኣበባ ያለችው የጫልቱ ኣክስት ምስክርነትም ጥሩ ነበር ማለት ነው። የሆነ ሆኖ ጫልቱ ወደ ሸገር እንድትሄድና በዚያ እንድትማር ስምምነት በመያዙ ጫልቱ ሸገር ገባች። ሸገር ስትገባ ያረፈችው በኣክስቷ ቤት ነው። ኣክስቷ ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ከኣንድ መሬ ኣማራ ጋር ጋብቻ መስርታ በጥሩ ሁኔታ ትኖራለች። ጫልቱን ኣዲስ ኣበባ ጥሩ ኣርጋ ስተቀበላት ነው የምናየው። የኣክስቷ ባል ሲቆጣት እንኳን ኣናይም። ጫልቱ ኣዲስ ኣበባ ውላ ስታድር ተወደደች።ጎረቤቶች ሁሉ እንዴት ይገልጿት እንደነበር ደራሲው ሲገልጽ። እንዲህ ኣድርጎ በኣክስቷ በኩል ያቀብለናል።
“ሄለን የኔ ቆንጆ፦ ጎረቤቶቻችን ሁሉ ወደውሻል። ግልፅና ልበ ሙሉ ናት ብለው ነገሩኝ። ቁመናሽና መልክሽን የማያደንቅ የለም።”

ይህ የሚያሳየው ቆፍቱ ላይ ወጪ ወራጁ ይላት እንደነበረው ኣዲስ ኣበባም ተቀብላ ጫልቱን እያደነቀች እንደሆነ ነው። የምትኖርበት ኣካባቢ ኣእምሮ ብሩህ ቆንጆ እያለ ውስጥና ውጪዋን ኣድንቋል። በርግጥ ደራሲው ይህን ከነገረን በሁዋላ ኣክስቷ ስሟን መቀየር እንዳለባት፣ ትምህርት ለመማር ኣማርኛ መማር እንዳለባት ገለጸችላት ይለናል። በርግጥ ትምህርት ለመማር ኣማርኛ መማር ያለባት እዚህ ኣዲስ ኣበባ ስለመጣች ብቻ ኣይደለም። ቆፍቱ ሆና ትምህርት ለመማር ብታስብ ኖሮ በዚያን ጊዜ ቁቤ ኣልነበረምና ያው ኣማርኛ መማር ነበረባት። ይህ ጉዳይ ያሳዝነኛል። ሁሉም የሃገራችን ቡድኖች ሁሉ በቋንቋቸው መማር ቢችሉ ኖሮ ጥሩ ነበር። ባይልንጉዋል ሆኖ ማደግ ቀድሞ ቢቻል ኖሮ ጥሩ ነበር።

ለማናቸውም ጫልቱ ኣማርኛ ገና መልመድ መጀመሩዋ ሲሆን በዚህ ጊዜ ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ሊስቁብሽ ይችላሉና ቶሎ ቶሎ ኣጥኚ መባሉዋን ይነግረናል። በርግጥ እዚህ ጋር ልገልጸው የምፈልገው ኣለ። ደራሲው በዋናነት ለዚህች ውብ ወጣት የህይወት መጥፋት ተጠያቂ ለማድረግ የሚሞክረው የቋንቋን የስምንና የንቅሳትን ጉዳይ በማመናፈስ ስለሆነ ኣንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። እርግጥ ነው ኣዲስ ኣበባ በሄለን ቅላጼ (Accent) መሳቁዋ ኣይካድም። እዚህ ጋር ግን መነገር ያለበት ኣዲስ ኣበባ በቅላጼ የምትስቀው ጫልቱ ኦሮሞ ስለሆነች ኣይደለም። ኣዲስ ኣበባ ከኣዲስ ኣበባ ውጭ ተወልደው በመጡ ኣማሮች፣ ትግሬዎች፣ ዶርዜዎች፣ ጉራጌዎች ወዘተ እንደሳቀች ነው የምትኖረው። ይሄ ጉዳይ ደግሞ በጣም ክፉ (serious) ተደርጎ ኣይታይም ነበር። ከጫልቱ ኣማርኛ ይልቅ ኣዲስ ኣበባ በመንዞች ኣማርኛ ተንፈራፍረው ይስቃሉ። ለምን የራሴን ልምድ ኣልነግራችሁም። ኣዲስ ኣበባ በነበርኩበት ሰዓት ወላጅ እናቴ ከገጠር ኣንዲት የዘመዳችንን ልጅ ወደ ኣዲስ ኣበባ ይዛ መጣች። ይህቺ የዘመዳችን ልጅ ወደ ኣዲስ ኣበባ የመጣችው መሃን የሆነችውን ኣክስታችንን እንድታግዝ፣ በዚያውም ትምህርት እንድትማር ነው። ይህቺ ልጅ ተወልዳ ያደገችበት ቀበሌ ከስልጣኔ በብዙ ርቀት ወደ ኋላ የቀረ ነው። መኪና እንኳን ኣይታ ስለማወቋ እርግጠኛ ኣይደለሁም። ለማናቸውም ኣዲስ ኣበባ መጣችና ትምህርት ቤት እንዳስገባት ታዘዝኩ። ወደ ትምህርት ቤት ልወስዳት ስል ያሳሰበኝ ነገር የስሟ ጉዳይ ነበር። ስሟ በልጌ ነው። በዚህ ስም ልጆች ይስቁባትና ስሜቱዋ ይጎዳል ብየ ረድዔት ኣልኳት። በዚያ ስም ተመዘገበችና ትምህርት ቀጠለች። ኣልፎ ኣልፎ በንግግሩዋና በገርጋራ የገጠር እንቅስቃሴዎቹዋ ህጻናት ይስቁባት እንደነበር ተረድቼኣለሁ። በኣማርኛዋ የትምህርት ቤት ህጻናት ከሚስቁት ይልቅ እኛ ቤት ውስጥ የምንስቀው ኣይረሳኝም። ኣንድ ቀን እንደዚህ ሆነ። ምሳ ልንበላ በዝግጅት ላይ ሳለን ረድዔት ለማስታጠብ ትዘጋጃለች። በወጉ መሰረት ኣባወራ መጀመሪያ ይታጠባልና ማስታጠቢያውን ይዛ ወደ ኣክስቴ ባል ቀረበች። የኣክስቴ ባል ኣሁን ያስታውሱታል ብየ ኣስባለሁ። በዚያን ጊዜ እሳቸው ሬዲዮ ይጎረጉሩ ነበርና ረድዔት መቆሙዋን ኣላዩም። ትንሽ ጠበቀችና
“ኣብባ እጣትሁ ላይ ውሃ ላርግልሁ” ኣለቻቸው። የኣክስቴ ባል ዘወር ኣሉና
“ምን?”
“ጣትኩን ውሃ ኣስነኩት”

የኣክስቴ ባል ፈገግ ኣሉና ሌባ ጣታቸውን ብቻ ወደ ማስታጠቢያው ዘረጉ። ሁላችንም በሳቅ ኣለቅን። በረድዔት ቤት “ጣትኩን ውሃ ኣስነኩት” ማለት እጅሁን ታጠቡ ማለት ነው። እንዲህ ባሉ ዘየዎች ኣዲስ ኣበባ ትስቃለች። ይሁን እንጂ የምትስቀው መራራ ጥላቻን በሆዷ ይዛ ሳይሆን በቀልድ ነው።
በርግጥ እንደጫልቱ ከተለያየ ገጠር የሚመጡ ሁሉ ኣዲስ ኣበባ ሲገቡ ሊሰማቸው የሚችለውን ጫልቱም ሊሰማት እንደሚችል ስሜቱዋን ልንረዳላት ይገባል። የሆነ ሆኖ በኣጠቃላይ በጎረቤቶቹዋ ዘንድ ባለ ብሩህ ኣይምሮና ልበሙሉ ቆንጆ የተባለች ስለሆነች የተጋነን ችግር ኣልገጠማትም። እንዴውም መልካም ስም ወጥቶላታል። መልካም ልጅ ተብላለች። ከማሪቱ ጋር ያላት ግንኙነት በጣም ጥሩ ነበር። ብዙ ጊዜ በኣንድ ሰው ቤት ያለውን ንትርክ ሁሉ ጫልቱ ኣላየችም።
ጥሩ በሚባል ቤተሰብና ጎረቤት መሃል ቆየችና ኣማርኛዋ ሲሻሻልላት የማታ ትምህርት ገባች። የማታ ትምህርት በገባችበት ሰዓት ምንም መጥፎ ነገር ኣይገጥማትም። ነፍስ ካወቁ የማታ ተማሪዎች ጋር ምን ኣልባትም በጣም ጥሩ ግንኙነት ነበራት። ኋላ ላይ ለጫልቱ ቤተሰቦች ጫልቱን ወይም ሄለንን ወደ ቀን ማዛወሩ መልካም መስሎ ታያቸውና ወደ ቀን ስትዛወር ደራሲው በሚገርም መንገድ እንዲህ ሲል ልባችንን ያንጠለጥለዋል።
“የጫልቱ መራር ፈተና የጀመረው በዚህ ጊዜ ነበር።”…….

ምን ይሆን የሚገጥማት? ኣስተማሪ ምን ሊላት ነው? ምን ትሆን ይሆን? ………. ብለን ልባችን ይሰቀላል:: ደራሲው መጨረሻ ላይ ለደረሰበት ድምዳሜ ትልቅ ኣስተዋጾ ያደረገው ኣሁን በዚህ በትምህርት ቤት የምታሳልፈው የህይወት ልምዱዋ ነው ማለት ነው። ደራሲው ለጫልቱ ህይወት መመሰቃቀል ተጠያቂ የሚያደርገው ስርአታዊ ሽብር (systemic Violence) ነው ብሎ ያምናል። በራሱ ቋንቋ እንዲህ ይገልጸዋል።

“የሆነችውን አፍርሶ፣ ያልሆነችውን እንድትሆን ያደረጋት ማነው? ይህ ስርአታዊ ሽብር (systemic Violence) ስለመሆኑ ጫልቱ ግንዛቤው አልነበራትም።”

የሚገርመው ግን ለዚህ ስርዓታዊ ሽብር (systemic violence)ና ለጫልቱ ስሜት መጎዳት ዋና ተጠያቂ የሚያደርገው ህጻናትን ነው። ከፍ ሲል እንዳልኩት ጫልቱ ኣዲስ ኣበባ ስትመጣ ብዙም የሚያስከፋ ነገ ኣልገጠማትም። ነፍስ ካወቁ የማታ ተማሪዎች ጋር ስትማር የከፋ ችግር የመረረ ነገር የለም። ትልቁ ችግር የመጣባት ወደ ቀን ስትዛወር የሰባተኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት በትምህርታቸው ኣርባ ኣንደኛ የወጡ ሰነፎች እንደነ ሳምሶን ኣይነት ህጻናት ማብሸቃቸው ነው። የሚገርመው በትምህርት ቤቱዋ ውስጥ መምህራኖቹዋም ለጫልቱ ያደሉ ነበር። ይወዱዋት ነበር። ችግሩ የነበረው እነዚያ የኣስራ ሶስትና የኣስራ ኣራት ዓመት ህጻናት ጋር ነው። እነዚህ ህጻናት በጫልቱ ንቅሳትና ቋንቋ መሳቃቸው ጫልቱን ሊጎዳ የሚችል መሆኑ ኣያጠያይቅም። ነገር ግን ጫልቱ በነዚህ ህጻናት መጎዳቷ ስርዓታዊ ሽብር(Systemic Violence) ለሚል መደምደሚያ ኣያደርስም። ጫልቱ እኮ ወደ ማታ ተመልሳ በዚያ ትምህርቱዋን መቀጠል ትችል ነበር። ለምን ከነዚያ ህጻናት ጋር እያበሸቁዋት ትኖራለች።

እነዚህ ህጻናት ጫልቱን በማብሸቃቸው ከስርዓት ጋር ምንም የተያያዘ ነገር የለውም። ቤተሰብ ኣላስተማራቸው፣ ኣስተማሪ ኣላስተማራቸው ይህንን መሳቅ ከየት ኣመጡት። እነዚህ ህጻናት ከኣዲስ ኣበባው ዘየ ለየት ያለ ኣማርኛ ሲሰሙ መቀለዳቸው ኣይቀርም። ጫልቱ ኦሮሞ ስለሆነች ኣይደለም።
ደራሲው ኣንዲህ ይላል። ኣንድ ጋጠ ወጥ ተማሪ የሚለውን ይመስለኛል የሚገልጸው።

“ ቆንጆ ነሽ የሆንሽ ኒቂሴ ገላ ሆንሽ እንጂ”
በርግጥ ኣንድ የኣስራ ሶስት ኣመት ሕጻን “ቆንጆ ነሽ” ይላል? ኣይመስለኝም። ንቂሴ ገላ…. ሊል ይችላል። በርግጠኝነት ግን ጫልቱ ኦሮሞነቱዋን ሳትገልጽ ስሟንም ደብቃ “ሄለን ነኝ” ያለች ሲሆን ኣንድ የኣስራ ሶስትና ኣስራ ኣራት ኣመት ህጻን
“የጋላ ነገር ይህን የመሰለ ውበት ቸክችከው ቸክችከው ኣበላሹት” ኣይልም።

እንዴ?…. ህጻናት እኮ ናቸው:: ህጻናት የጠሉትን ንቅሳት ኣልፈው ሌላ ውበት በጫልቱ ፊት ላይ ማየት ኣይችሉም። ከሁሉ በላይ ደግሞ “የጋላ ነገር….” ኣይሉም።ይህንን ያለው ራሱ ተስፋየ ነው። ደራሲው ራሱ የፈለገውን መልእክት ለማስተላለፍ እነዚህን ህጻናት ለምን ወንጀል እንደሚያናግራቸው ኣልገባኝም። በደርግ ጊዜ እንኳን የኣስራ ሶስትና የኣስራ ኣራት ኣመት የኣዲስ ኣበባ ህጻን ይቅርና እኔ ራሴ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኘም ስለ ብሄር ብዙ ኣላውቅም። ትላልቅ የሆኑ ሰዎችም ብዙ ኣያውቁም ነበር። ሌላው ቀርቶ መንግስቱ ሃይለማርያም ኦሮሞ ይሁን ኣማራ ወይ ወላይታ ኣይታወቅም ነበር። ሁዋላ ላይ ዚምባብዌ ሳለ ኧረ ኣገሩ ሁሉ ዘሩን እየተጠየቀ ነው እርስዎ ከየት ነዎት? ተብሎ ነው ኦሮሞና ኣማራ መሆኑን ለ VOA ተናግሮ የታወቀው። ይህንን ስናይ በፍጹም ከእውነታው የራቀ ነገር እነዚህን ህጻናት ደራሲው እንዲናገሩ ያደርጋቸዋል። በዚህ ኣዝኛለሁ። ከሁሉ የሚያሳዝነው ጎረቤቱን፣ ኣስተማሪውን ሁሉ ለጫልቱ ጥሩ ኣድርጎ፣ የማታ ተማሪዎችን እንከን ሳያወጣ፣ የሰባተኛ የቀን ተማሪዎችን ለጫልቱ መሰበር ዋና ተጠያቂ ማድረጉ ብሎም የስርዓቱን ሽብር የፈጠሩት ዋና ተጠያቂ እነዚህ ህጻናት እንደሆኑ ኣይነት ድምዳሜ ማሳየቱ በጣም ገርሞኛል።

ከፍ ሲል እንዳልኩት ደራሲው የሚያሳየን እነዚህ ህጻናት ጫልቱ ኦሮሞ መሆኑዋን ያወቁት በንቅሳቷ ነው። ይሄ ደግሞ በጣም ይገርማል።በመጀመሪያ ደረጃ ንቅሳት የሚነቀሱት ከፍ ሲሉ ነው። ጫልቱ በስንት ኣመቷ ደረቷን ሁሉ ሳይቀር እንደተነቀሰች ኣላውቅም። ይሁን…. ኣልፎ ኣልፎ በኣስራ ኣንድ በኣስራ ሁለት ኣመት ጊዜ የሚነቀሱ ይኖሩ ይሆናልና ይህን እንለፈው። በመሰረቱ የኣስራ ሶስትና ኣስራ ኣራት ኣመት የኣዲስ ኣበባ ህጻን በዚያን ጊዜ ንቅሳት የኦሮሞ መገለጫ መሆኑን ኣያውቅም። ኣይደለምም። ንቅሳት ያለው እንዴውም በብዛት የሚታየው በኢትዮጵያ ኣይሁዶች፣ በዎሎዎች፣ በትግሬዎች፣ በመንዞች ኣካባቢ ነው። እነዚያ ህጻናት ንቅሳትን በማየት ሄለን ኦሮሞ ናት ሊሉ ኣይችሉም። ደራሲው ሊደርስበት ለፈለገው መደምደሚያ የወሰዳቸው መንደርደሪያዎች(premisis) ተዓማኒነት የጎደላቸው ከመሆናቸውም በላይ ህጻናት መራሽ ስርዓታዊ ሽብር የተፈጠረ ኣስመስሎ ማቅረቡ ይህን ክፍል ባዶ እንዳያስቀርበት እሰጋለሁ።ደራሲው ኣጥብቆ የሚታገለው ጫልቱ ስሟን መቀየሩዋ ከማንነት መምታታት(identity confusion) ጋር እንዲያያዝለት ነው። በመሰረቱ በቋንቋ ሳይንስም ቢሆን በስምና በተሰያሚ መካከል ምንም ዓይነት ተፈጥሮኣዊ ግንኙነት የለም።

እኔ ራሴ ስሜ ከኦሮሞ የተወሰደ እንደሆነ ብዙ ሰው ይነግረኛል። በዚህ ደስተኛ ነኝ። ወላጅ እናቴ ኦሮሞ ኣገር ደራ የተባለው ቦታ ኣድጋ ስለነበር ስለ ኦሮሞዎች ጥሩነት ኣውርታ ….ኣውርታ ….ኣውርታ……..ኣትጠግብም ነበርና በልጅነት ጊዜየ እኔም ኦሮሞ በሆንኩ ብየ ኣስቤ ኣውቅ እንደነበር ትዝ ይለኛል።
የስም ጉዳይን ይዘን ወደ ኣዲስ ኣበባ ስንመጣ ብዙ ኣስቂኝ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል። እርግጠኛ ነኝ እነዚያ የጫልቱ የክፍል ጓደኞች ከኣማራ ኣካባቢ የሄደች ኣንድ ንቅሳት ያላት ወጣት ክፍሉ ውስጥ ብትኖር ስሟ ደግሞ ቁንጥሬ ጭንቅል ቢሆን በስሟም በንግግር ዘየዋም መሳቃቸው ኣይቀርም። ኣንድ ኣምታታው ውርጋጥ የሚባል ወንድ ተማሪ ቢኖርም ክፍሉ በሳቅ ማለቁ ኣይቀርም። በዚህ በስም ኣካባቢ ብዙ ነገር ኣይቻለሁ። እዚህ ስማቸውን ብጠቅስ ጓደኞቼ ይቆጡኛል ብየ እንጂ የማውቃቸው ሰዎች ኣዲስ ኣበባ ሲገቡ ዘመንኛ ስም ለውጠው ኣይቻለሁ። ይሄ ደግሞ መራራ ከሆነ ስሜት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ሸገርን ለመምሰል ነው።እነዚያ ህጻናት ሃጎስ በሚለውም ስም መሳቃቸው ኣይቀርም። ሸምሱ በሚባል የጉራጌ ልጅም መሳቃቸው ኣይቀርም።ይህ ነገር መልካም ኣይደለም። ሕጻናቱ የሚስቁት ከብሄር ከደም ሃረግ ጋር ኣያይዘው ሳይሆን ኣዲስ ኣበባ ሰለጠንኩ ስትል ዘመንኛ ያለቻቸውን ስሞች ዘርዝራለች። ከጥንት ጀምሮ በገጠሩና በከተሜው መካከል ሰፊ ምጣኔ ሃብታዊና ማህበራዊ ክፍተቶች ተፈጥረው እየሰፋ በመምጣቱ ኣዲስ ኣበባ ለየት ማለቱዋን በስም ኣወጣጥ፣ በኣነጋገር ዘየ ለማሳየት ፈልጋ ነው። ይሄ ደግሞ እጅግ መራራ ነገር ኣይደለም። የገጠሩን ወንድሙዋና እህቱዋን ኣትጠላም።

ጸሃፊው የኣተቴን ነገር ኣንስቶ ጫልቱ በዚህም እንዳዘነች ይገልጻል። ያለችው እኮ ኣዲስ ኣበባ ነው።ርቃ ሄዳለች እኮ። የተለየ ባህል የተፈጠረበት፣ ኣዲስ ኣገር ነው ያለችው።ጫልቱ ለመልቲ ካልቸራሊዝም ክፍት መሆን ኣለባት እኮ። ቆፍቱ ያለው ኣተቴ እዚህ ባለመጠራቱ ልታዝን ኣይገባትም። እዚያው ኦሮሚያ ክልል ያሉ ብዙ የኦሮሞ ልጆች ኣይቀበሉትም። ወለጋ ያሉ ፕሮቴስታንት ኦሮሞዎች በየሱስ ስም እያሉ ነው የሚረግሙት። እዚያው ኦሮሞዎች መካከል ስትሄድም ልትጎዳ ነው ማለት ነው። ርቃ ስድትሄድ በተውጣጣ ማህበረሰብ ውስጥ ስትኖር በቀበሌዋ የነበረውን ባህል ሁሉ ታገኘዋለች ማለት ኣይደለም። ይህቺ ልጅ ይህን የኣተቴ ባህሉዋን እዚያው ቆፍቱ እያለች እንዳትንከባከበው የሚያደርግ ኣካል ቢፈጠርና ኣዘነች ቢባል ስሜት ይሰጣል። ይህንን መገንዘብ ያስፈልጋል። በተረፈ ግን ኣተቴ ያለው ኦሮሞ ጋር ብቻ ኣይደለም። ወሎና መንዝ ብንሄድ ብዙ ኣለ። ኣዲስ ኣበባ መጥታ ተይ ልጆቹን ስለ ኣተቴ ኣታስተምሪ መባሉዋ የመጨረሻ ስሜት ሰባሪ ነገር ተደርጎ መቅረቡ ትክክል ኣይደለም።

በመሰረቱ ማህበራዊ ለውጥ ኣይጠላም። ጫልቱ ጂንስ መልበሷ፣ ቦርሳ መያዟ፣ ከተሜ መምሰሏ ምንም ችግር የለውም። ዋናው ነገር ለለውጥ ስትዘጋጅ ኣንዳድ ጠቃሚ የሆኑ ባህሎቹዋን እንዳትጥል መምከር ነው። ስልጣኔ ሲመጣ ማህበራዊ ለውጥም ይመጣል። በዚህ ጊዜ ኣዳዲስ ባህሎችን ለመማር መዘጋጀት ማለት ነው እድገት ማለት።ይሄ ደግሞ ከማንነት መምታታት ጋር የተገናኘ ኣይደለም። ማንነት በነገራችን ላይ የሚቀየር፣ የሚያድግ ነገር ነው። ትናንትና ሙስሊም የነበር ዛሬ ክርስቲያን ቢሆን ማንነቱን ቀየረ ማለት ነው። ባህላዊ ማንነትም እየተቀየረ ሊሄድ ይችላል። ዜግነትም ይቀየራል። በመሆኑም እግራችን ሲርቅ ያለንበት ኣካባቢ ባህል ሲውጠን ስሜታችን ሁሉ ስብርብር ይላል ማለት ኣይደለም።

ወደ ጫልቱ የሰባተኛ ክፍል ብሽሽቅ ጉዳይ እንመለስና መምህር ጽጌ ያን ዱርየ ሳምሶንን ኣንዴ ሲዠልጡት ኣልቅሶ ቆይ ሰኔ ሰላሳ እንገናኛለን ነው ያለው። ጫልቱ ማድረግ የነበረባት ይህንን ነው። የሚሰድቧትና የሚያበሽቋት ህጻናት በኣስተማሪዎች የተላኩ ኣይደሉም። ስለዚህ ማድረግ የነበረባት ለመምህር ጽጌ መናገርና ጸጥ ማሰኘት ነው።

ደራሲው ጫልቱን ከሚገባው በላይ ስሜቷን ለመስበር ይሞክራል።ኣንባቢን ከንፈሩን ለማስመጠጥ ይሞክራል። ይሁን እንጂ የሄለንን ህይወት የወሰደበት መንገድ እሱ እንዳሰበው ኣንባቢ እንዲሰማው የሚያደርግ ኣይደለም። ራሱ ደራሲው እነዚያ የኣንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ስሜቱዋን ሁሉ ዖሮሞ ከመሆኑዋ ጋር ኣያይዞ እንዲሰብሩዋት ያደርግና በተሰበረ ስሜት ወደ ቆፍቱ ለእረፍት ይልካታል። በዚያ ደግሞ ስሟን በመቀየሯ መሳቂያ ያደርጋታል። ቆፍቱ ስትሄድ ኣክስቷ ኣማርኛ ብቻ ተናገሪ ኦሮምኛ ኣልችልም በይ ኣለቻት ይለናል። እንደዚህ ይባላል? ለማናቸውም እረፍት ጨርሳ ወደ ኣዲስ መጣች።ወዲያው ደግሞ በትምህርቷ ብዙ ሳትገፋ ከዘጠነኛ ክፍል ኣካባቢ ኣቋርጣ ትዳር መሰረተች ይለናል።

የሚገርመው ሄለን ያገባችው ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ነው። ስርዓቱ ምን ያህል ተቀብሏታል ማለትነው? ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ያለ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ጫልቱን ከነንቅሳቷ በፍቅር ወድቆ፣ ብዙ ቆንጆ ባለበት ኣዲስ ኣበባ ጫልቱ ኣሸናፊ ሆና ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ማግባቷ የሚያሳየው ከነዚያ ከህጻናት ከነሳምሶን ውጭ ከፍተኛ ከበሬታና ተቀባይነት ኣላት ማለት ነው። ባሏም ደስ ብሏት ኣብራው እየኖረች ነበር። ኣገር ዘመድ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ኣገባች ብሎ ሳይኮራ ኣልቀረም። በዚያን ጊዜ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ መወሸም እንኳን ለሴቶች እንደ ትምክህት እንደነበር ኣይዘነጋም።
ከዚህ ተነስተን የሄለን ህይወት ሰመረላት ኣለፈላት ወደሚባል የህይወት መስመር ውስጥ እንደገባች መረዳት ያስችላል። ይህቺ ልጅ ገረድ ኣይደለም የሆነችው። ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ነው ያገባችውና።
ደራሲው ሄለን ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ኣግብታ እያለ በመሃል ኢህዓዴግ ኣዲስ ኣበባን እንደተቆጣጠረ ይነግረናል። ከዚህ በሁዋላ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪው ባሏ ወደ ወህኒ ሲወርድ ምን ኣልባትም ሃብትና ንብረቱንም ኣጣ። የዚህን ጊዜ ሄለን ወይም ጫልቱ ትልቅ ችግር ላይ ወደቀች። ለባለቤቷ ስንቅ እንኳን ማቀበል ተሳናት። ትዳሯ ፈረሰ። ጎጆዋ ዘመመ። ከሁሉ የሚያሳዝነው ደራሲው በራሱ ኣንደበት
“ለባሏ ስንቅ ማቀበያ ቀርቶ ለራሷም የምትመገበው አልነበራትም።” ይላል።

ይልቅ ይሄ ኣንጀቴን በላው። የኣንድ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ሚስት ያላትን ሁሉ በኣጭር ጊዜ ውስጥ ኣጥታ የምትበላው ሁሉ ስታጣ የለውጡን ኣስከፊነት ያሳያል። የምትበላው ብቻ ሳይሆን ማደሪያም በመቸገሩዋ ኣንድ ካፌ ውስጥ እየሰራች መተዳደር ጀመረች። ትንሽ ቤት ተከራይታ መኖር ጀመረች። ቤታቸውም ተወረሰ ማለት ነው። ይህ ኑሮ ለኣንድ ኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ሚስት ከባድ ነበር። ስሜትን ይጎዳል።

ደራሲው ቀድሞ ለወሰነውና ሊያስተላልፍ ላሰበው ጭብጥ ሲል ሄለንን እንደፈለገው ሲያናግራት እናያለን። ወደ መጨረሻ ወጉን ሲቀጥልልን ይህቺ የኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ሚስት ደርግ ወድቆ ኢህዓዴግ በገባ ሰሞን ቴለቪዥን ትከታተል ነበር ይለናል። ከዚያ ኣንድ ቀን “ጭቆና” የሚለውን ቃል በቴሌቪዥን ስትሰማ ጊዜ ለመረዳት ጥረት አድርጋ ነበር ይላል ደራሲው። ይሄ ኣይመስልም። ይህቺ ልጅ በስርዓት ደረጃ ጭቆናን በህይወቷ ኣላየንም።ማነው የጨቆናት። የት ቦታ ጭቆናን ኣየች። እንዴውም ኢህዓዴግ ራሱ የጨቋኝ ሚስት ብሎ ኣለማሰሩም ኣንድ ነገር ነው። የኣንደኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ያውም እነሳምሶን ኣበሸቋት ማለት ወደዚህ ከፍ ያለ ማህበራዊ ጉዳይ ኣያመጣንም። ከሁሉ በላይ ማህበራዊ ለውጥ እንዲህ ቀላል ነገር ኣይደለም። በኣንዴ በቴለቪዥን ስታይ ኣሃ! ብላ ጭቆናን ተገነዘበች ለማለት ኣይቻልም።በቀጥታም ባይሆንም የኣውራጃ ኣስተዳዳሪ ባል ኣግብታ ያለፈውን ስርዓት የቀመሰች ሴት በትምህርት ቤት ብሽሽቅ “ጭቆና!” ትላለች ለማለት እኛ እራሳችን ልጅ መሆን ሊኖርብን ነው።

ደራሲው እነዚህን የማይመስሉ ነገሮች ሁሉ ኣንስቶ ጫልቱ የማንነት መምታታት ውስጥ እንደገባች ሊያሳየን ይሞክራል። በመሰረቱ የብሄርን ማንነት ከስም ጋር ኣያይዞ የማንነት መምታታት ውስጥ ለመግባትና ለመጨነቅ እውቀት ይጠይቃል። ስለብሄር ፖለቲካ መማር በዚያ መጠመቅ የመንፈስን መረበሽ ሊያመጣ ይችላል። ይህቺ ለግላጋ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ በስም ለውጧ ምክንያት ተጨንቃ፣ ኣሁን እኔ ሄለን ነኝ……. ጫልቱ ነኝ……..ጫልቱን ፈልጌ ኣጣሁት ከውስጤ…….. ብላ በመጨነቅ ሰውነቷ ከስቶ ለሞት ደረሰች ማለት በሬው ወለደ ከሚለው ጠብደል ፈጠራ ኣይተናነስም:: ታዲያ ጫልቱን ምን ገደላት? ካልን ወያኔ ኢሃዲግ ኣዲስ ኣበባ ሲገባ ትዳሯን ኣፍርሶ ሜዳ ላይ ጥሏት ስለነበረ፣ የሚበላ ስላጣች፣ ተስፋ ስለመነመነባት፣ በብስጭት ኩርምት ብላ ነው የሞተችው። ማን ገደላት ካልን ወያኔ ኢህዓዴግ ኣበሳጭቶ ተስፋ ኣሳጥቶ ለበሽታ ሰጥቶ ነው የገደላት ለማለት ጠንካራ መረጃ ኣለን። ይህቺ ልጅ የሁዋላ ታሪኳ ማለትም ያለእድሜዋ ማግባቱዋ፣ ሁዋላም ኣዲስ ኣበባ ስትመጣ ለባህል ግጭት (culture shock) መጋለጧ በተለያየ ደረጃ የጎዱዋት የህይወት ልምዶች ቢሆኑም ከዚያ በሁዋላ ኣግብታ ኣካባቢውን ለምዳ ትኖራለች ተብሎ ነው የሚታሰበው።
የዚህ ጽሁፍ ደራሲ በቅርቡ በኣንድ ስብሰባ ላይ ሲናገር ለጫልቱ ሃውልት ይገባታል ሲል ሰምቻለሁ። በዚያ ኣልከራከርም።ለሃውልት የሚያበቃ ነገር ካለ ችግር የለውም። በሚሰራው ሃውልት ላይ ግን የሚጻፈው የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ብሽሽቅ ሳይሆን ወያኔ ኢሃዴግ ትዳሯን ኣፍርሶ ሜዳ ላይ ስለጣላት ለሞት የተዳረገችው ጫልቱ ተብሎ መሆን ኣለበት።

ማጠቃላያ
“ጫልቱ እንደ ሄለን” ጭብጡ በጣም የቀለለብኝ የኣንድን ሰው ህይወት ኣንስቶ ማህበረሰብን ወክሎ ለማሳየት ስለሞከረ ኣይደለም። ደርሶ ማጠቃቃለል (hasty generalization) የሚባለው እዚህ ጋር ኣይሰራም። የኣንድ ሰውን ይወት እየተረኩ የማህበረሰብን ህይወት ቁልጭ ኣድርጎ ማሳየት ይቻላል። ዋናው ግን የተሳሉት ገጸ ባህርያት ያንን ልናሳይ የምንፈልገውን ማህበረሰብ ህይወት የሚወክል ባህርይ ስንፈጥርላቸው ይመስለኛል። ጫልቱ እንደ ሄለን በሚለው ውስጥ የኦሮሞ ወገኖቼን ብሶት ማሳየት ኣይቻልም። ከሁሉ በላይ ደራሲው የሲስተም ሽብር ያለውን ጉዳይ ለማሳየት ህጻናት ዋናውን ድርሻ መያዛቸው ልቦለዱ እንዲወርድብኝ ኣድርጓል።
ይህንን ካልኩኝ በሁዋላ ግን የኦሮሞ ህዝብ ብሶትና እንግልት ባለፉት ስርዓቶች ሁሉ ያሳለፈው ጉዳት ከስም ለውጥ ከኣተቴ ልምድ ያለፈ ነው። የኦሮሞን ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ክፍፍል፣ የፖለቲካ ውክልና ጥያቄዎች እንዲህ ባሉ በስያሜ በምናምን ማውረድ ተገቢ ኣይደለም።ኢትዮጵያን ከኦሮሞ ውጭ ማየት ኣይቻልም። ይህ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ታሪክ ያለው ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር ለሃገሩ መስዋዕት ሲሆን የኖረ ልበ ሰፊ ህዝብ ነው። ይሁን እንጂ በመጡት ስርዓቶች ሁሉ ተጠቅቱዋል። በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊው መስክ ተጎድቱዋል። ይህ ማለት ግን ሌላው ወገኑ ኣልተጎዳም ማለት ኣይደለም። ሁሉም ቡድኖች በተለያየ ቅርጽና ይዘት ተጎድተዋል። የኦሮሞው ህዝብ ኣሁን ያለው ፍላጎት ብሄርን ነጥሎም ይሁን በጅምላ የሚደረግ ጭፍጨፋ ይቁም እኩልነት በሃገራችን ይስፈን ነው። ይህ ጥያቄው ደግሞ ተገቢና እውነተኛ ነው። በቋንቋው በኩል ኦሮምኛ ኣንዱ ዋና መግባቢያ ቋንቋ መሆን ኣለበት። ከዚያ ውጭ ግን ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ሲኖር ኣንዳንድ የኦሮሞ ተወላጆች የኣማራ ስም ወይ የትግሬ ስም ወይ የወላይታ ስም ኣውጥተዋል ብሎ የሚከፋ ኣይደለም። ኣማራ ሆነው የኦሮሞ ስም ያላቸው ብዙ ኣሉ። የደቡብ ተወላጅ ሆነው የኦሮሞ ስማ ያላቸው ሰዎችና ቦታዎች ብዙ ናቸው። በመሆኑም የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ከፍ ኣርጎ ማየትና ከፍትሕ ከዴሞክራሲ ኣንጻር መመለስ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። በኢትዮጵያ የሚኖሩ ብሄሮች ሁሉ ኣንዱ የኣንዱን ብሶት በመረዳትና እውቅና በመስጠት ተከባብረው ሲኖሩ ጥያቄዎቻቸው ይፈታሉ። ከዚህ ውጭ ግን ባህል ለመካፈል፣ ባህልን ሰጥቶ ለመቀበል፣ ለዘመናዊነት ክፍት መሆን በጣም ኣስፈላጊ ነው።

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

geletawzeleke@gmail.com

ነገረ ህወሓት: ህወሓትና ‹‹ወያኔ›› ምንና ምን ናቸው? –ጌታቸው ሺፈራው (ጋዜጠኛ)

$
0
0

‹‹ህ.ወ.ሓ.ት›› የተሰኘው የፖለቲካ ቡድን ሙሉ ስሙ ሲዘረዘር ‹‹ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ›› መሆኑ ለማንም ግራ የሚያጋባ አይደለም፡፡ በተለይ በርሃ በነበረበት ጊዜ ከረዥም ስሙ ይልቅ ‹‹ወያኔ›› መጠሪያው ሆኖ አገልግሏል፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ይህን ስም ህወሓት ከዚህ በፊት የነበረ ታሪክ ቀጣይና የትግራይ ህዝብ ታሪካዊ እንቅስቃሴ አስቀጣይ (ወራሽ) ለመምሰል ተጠቀመበት፡፡ ህወሓት ‹‹ወያኔ›› የተሰኘ ስሙን በመጀመሪያዎቹ ለጥቂት ጊዜያት በተለይ ውስጥ ለውስጥም ሆነ በቀጥታ ካስተዋወቀ በኋላ ይህን ስሙን ሌሎችም እንዲለምዱት አደረገ፡፡ ይህን ያደረገበት ምክንያቱ ደግሞ ስሙ በታሪካዊነቱም ሆነ ትርጉሙ የህወሓትን ሰብዕና የሚገነባ በመሆኑ ነው፡፡
tplf-rotten-apple-245x300
‹‹ወያኔ›› ማለት በትግርኛ አብዮት ወይንም አመጽ እንደ ማለት ነው፡፡ ህወሓት ይህን መልካም መጠሪያ የወሰደው ደግሞ በ1935 ዓ/ም አካባቢ ተነስቶ ከነበረው ‹‹ወያኔ›› ከተባለው የአርሶ አደሮች አመጽ የቀጠለ ታሪካዊና አልጋ ወራሽ ለመምሰል ነው፡፡ ሆኖም በ1930ዎቹ መጨረሻ ትግራይ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የአገራችን ክፍሎችም ተመሳሳይ የአርሶ አደሮች አመጽ ተቀስቅሶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የ‹‹ወያኔ›› አመጽ የፊውዳሉ ስርዓት ከነበረው ብልሹነት የመነጨና በኋላም ለተማሪዎች አብዮትም ጭምር እንደ እርሾ እንዳገለገለ ከታሪክ መረዳት ይቻላል፡፡ የወቅቱ አማጺያን ህዝብ ይቀሰቅሱበት ከነበረው መፈክር መካከል ቀዳሚው ‹‹ሰንደቃችን የኢትዮጵያ ነው›› የሚል ነበረበት፡፡ በአጠቃላይ እንቅስቃሴው በኢትዮጵያ አንድነትን መሰረት ያደረገ እንጂ ህወሓት ‹‹ወያኔ››ን በቅጽል ስምነት አንጠልጥሎ ይከተለው ከነበረው ‹‹ተገንጣይነት›› ፖሊሲ ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው፡፡ የመጀመሪያው እንቅስቃሴ ‹‹ወያኔ›› ወይንም አመጽ ከስርዓት እንጂ ከአገር ‹‹ነጻ›› መውጣት ወይንም መገንጠልን ጋር የተገናኘ አልነበረም፡፡

ህወሓት ከአርሶ አደሮቹ አመጽ ብቻ ሳይሆን በነ መንግስቱ ንዋይ ከተሞከረው የመንግስት ለውጥ ሙከራ በተጨማሪ ‹‹መሬት ለአራሹ›› የሚል መፈክርን አንግቦ ለተነሳው የተማሪዎች አብዮት እርሾ እንደነበር ከሚነገርለት የአርሶ አደሮች እንቅስቃሴ እጅጉን ተቃራኒ ነው፡፡ ህወሓት ‹‹እየሱስ አምላካችን ነው›› የሚል መፈክር ካነገቡት አርሶ አደሮች ይልቅ የወቅቱ የማርክሲዝም አንድ መርህ ከነበረው ስለ መሬት ለአራሹ፣ ስለ ዓለም ላብ አደሮች ትብብር ከሚያወራው የተማሪው አብዮት ቅርብ ነበር፡፡ ሆኖም ከአርሶ አደሮቹ ይልቅ ለተማሪው እንቅስቃሴ አንድ አካል ነበር የሚባለው ህወሓት ከመሬት ለአራሹ ይልቅ ‹‹ስለ ትግራይ ህዝብ›› መሬት እንደሚጨነቅ አስመሰለ፡፡ ስለ ዓለም ላብ አደሮች ትብብር ሲያወራ ከነበረው የ1960ው አብዮት ወርዶ ለአንድ ብሄር ተወላጆች ትብብር፣ መገንጠል…የመሳሰሉት ተገንጣይ ጉዳዮች ቅድሚያ ሲሰጥ ነው ከተማሪዎች አብዮትም ያፈነገጠው፡፡ ሁለተኛው ‹‹ወያኔ››ነት (አብዮት) ይህኔ ነው ያከተመው፡፡ ከዚህ በኋላ ህወሓት ‹‹ወያኔ›› የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ አጥቷል፡፡ ምክንያቱም ከአርሶ አደሮችም ሆነ ከተማሪው አብዮት አፈንግጧልና ነው፡፡
ከተማሪዎች እንቅስቃሴ እንኳን ያፈነገጠው ህወሓት የቀዳማዊ ወያኔ ወራሽ ነኝ በሚል ዳግማዊ ‹‹ወያኔን›› በመጠሪያነት መጀመሪያ አካባቢ ተጠቀመበት፡፡ ህወሓት በደርግ ላይ ድል እያስመዘገበ ሲመጣ ‹‹ወያኔ›› በተለይ በወቅቱ ተቃዋሚዎች ዋነኛ መጠሪያው ሆነች፡፡ ስሙ ከመለመዱ የተነሳ እነ መንግስቱ ኃ/ማርያም ሳይቀሩ ተግባሩን ሲያወግዙ ከህወሓትና ከረዥም ዝርዝሩ ስሙ ይልቅ ‹‹በወያኔ››ነት መጥራቱን ተያያዙት፡፡ ይህ ለህወሓት መልካም ስም ነበር፡፡ እሱ ቢጀምረውም ትርጉምና ታሪካዊ ተያያዥነቱን ሳያጤኑ ያጋነኑለት የሚቃወሙትና የሚጠሉት አካላት ናቸው፡፡

የአርሶ አደሮች አመጽ በተቀሰቀሰበት ወቅት በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ተመሳሳይ አመጾች የነበሩ ቢሆንም ከህወሓት ጋር የተማሪው አብዮት አካል የነበሩት ወደ ትጥቅ ትግል ሲገቡ ‹‹ዳግማዊ፣ ሳልሳዊ…›› ብለው ስማቸውን አልወሰዱም፡፡ ወያኔ የአርሶ አደሮቹ አመጽ ኢትዮጵያዊ አላማ የነበረው ቢሆንም ልክ እንደ ህወሓት አሻፈረኝ ብለው ዱር የወጡትና ከእሱም የተሻለ አገራዊ አላማ እንደነበራቸው የሚነገርላቸውና ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ያፈነገጡት እንኳን ‹‹ወያኔ›› ነን አላሉም፡፡ በእርግጥ ህወሓት የአርሶ አደሮቹን ቀደምት አመጽ ከራሱ ጋር በማዛመድ ‹‹ዳግማዊ››ነቱን ያወጀው ከመርህና አላማ አንጻር ሳይሆን ከአርሶ አደሮቹ ጋር ‹‹በብሄር›› ግንኙነት እንዳለው ለመግለጽ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህም በአብዛኛው መርህና አላማ ከተማሪዎች አብዮትም ሆነ ከአርሶ አደሮቹ አብዮት የራቀና ያፈነገጠ ያደርገዋል፡፡ አሁንም አብዛኛዎቹ የህወሓት/ኢህአዴግ ተቃዋሚዎች ‹‹ወያኔ›› የምትለዋን ስም አሉታዊ አድርገው በስፋት ይጠቀሙባታል፡፡ እኔ በበኩሌ ይህ ስም ለህወሓት ኢህአዴግ አይገባውም ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ህወሓት ራሱን ኢትዮጵያዊ አቋም ከነበራቸው አርሶ አደሮች የቀጠለ መሆኑን ለመግለጽ ‹‹ዳግማዊ ወያኔ›› ብሎ የሚጠራበት አላማም ሆነ ታሪካዊ ትስስር ስለሌለው ነው፡፡

በነገራችን ላይ በእንግሊዘኛው ‹‹Tigray People Liberation Front›› ከተባለው ስሙ ውስጥ ‹‹ወያኔ›› ለሚባለው እኩያ ትርጉም አይገኝለትም፡፡ በቀጥታ እንተርጉመው ከተባለ ‹‹የትግራይ ህዝቦች ነጻ አውጭ ግንባር›› ነው የሚሆነው፡፡ Tigray ትግራይ ነው፡፡ People ህዝብ የሚለውን ይወክላል፡፡ Liberation አርነት (ኃርነት) ነው፡፡ Front ደግሞ ግንባር እንጂ አብዮት ሊሆን አይችልም፡፡ ስሙን እንዲሁ ለክብር ሲባል አገናኘው እንጂ ተያያዥ ትርጉም የለውም፡፡ ቃል በቃል ሲተረጎም ‹‹Front››ን ‹‹ወያኔ እንዳሉት እንረዳለን፡፡ ወያኔ የተሰኘው የአርሶ አደሮች እንቅስቃሴ የራሱ የሆነ እንቅስቃሴ እንጂ ‹‹ግንባር›› ወይንም ‹‹Front›› የሚባል አልነበረም፡፡ ከህወሓት ውጭ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (‹‹Tigray Liberation Front››) የሚባል ታጣቂ ቡድንም ነበር፡፡ ግን እንግሊዘኛ ስሙ ላይ ‹‹Front› የሚል ስላለው ብቻ ‹‹ወያኔ›› በሚል የሌሎችን ታሪክ ለመጋራት አልተንጠራራም፡፡

ምንም እንኳ በማርክሲሳዊ እይታ አብዮታዊ ባይሆንም ከህወሓት ይልቅ ኢዲዩ ራሱን ወያኔ ብሎ ቢጠራ ከህወሓት የተሻለ መሰረት ነበረው፡፡ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የኢዲዩ አባላት ከአማጺያኖቹ አርሶ አደሮች ጋር የሚያመሳስል የርዕዮተ ዓለማዊም ሆነ ሌሎች ትስስሮች ስለነበራቸው ነው፡፡ የተገንጣይ አላማም ሆነ በአገራቸው ላይ ጥላቻ አልነበራቸውም፡፡ ይህን ስንመለከት ህወሓት በበርካታ ምክንያቶች ‹‹ወያኔ›› የሚለው ስያሜ እንደማይገባው መገንዘብ ይቻላል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ‹‹ልማታዊ መንግስት››፣ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ››፣ ‹‹ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ››…..የሚባሉትን ስሞች ዝም ብሎ በሌሉበት የመለጠፍ ታሪኩ የሚጀምረው ‹‹ወያኔ››ን በመጠሪያነት ያለ አግባብ ከቀላቀለበት ጊዜ የጀመረ ይመስለኛል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ያነሳው ሁሉ በስፋት እንደሚጠላ ያውቀዋል፡፡ ይህን የማይገባውን የክብር ስምም ገና በርሃ እያለ አስተዋውቆ ዘወር በማለቱ በአብዛኛው አሉታዊ መስሏቸው ሌሎች ናቸው መጠሪያው ያደረጉት፡፡ በተለይ በተቃዋሚዎቹ ዘንድ የማይወደው መስሎ ሳይታያቸው አይቀርም፡፡ ስለሆነም አብዛኛዎቹ ተቃዋሚዎች ህወሓት/ኢህአዴግን ‹‹ወያኔ›› ብለው ሲጠሩት ግን ከሚገባው በላይ እንዳጋነኑለት፣ የማይገባውን ታሪክ እንዳወረሱት፣ አገር ወዳድና ቀናኢ አላማ እንዳለው አድርገው እየቆጠሩት መሆናቸውን መገንዘብ ይገባቸዋል፡፡ በተለይ ህወሓትን ጠበብ ብለው እየከሰሱ ቢሆን ህወሓትን ከትግራይ ህዝብ ጋር የማይነጣጠል፣ ለትግራይ ህዝብ የሚሰራ አድርገው የሚቆጥሩት ‹‹ወያኔ›› ብለው ሲጠሩ ህወሓትን ከሚከሱበት ጠባብነት አልወጡም ማለት ነው፡፡

‹‹ወያኔነት›› በገዥዎች ላይ እምብይ ባይነት ነው፡፡ የድሮዎቹ አርሶ አደሮች ይህን ስም የራሳቸው ያደረጉት በበዝባዡ ፊውዳል ስርዓት ላይ አምጸው ነው፡፡ አሁን ‹‹ወያኔ›› የሚባለው ህወሓት ዘመናዊ ፊውዳል ሆኗል፡፡ ራሳቸውን ‹‹ወያኔ›› ባይሉም የህወሓትን ዘመናዊ ብዝበዛ የሚቃወሙ እምብይ ባዮች አሉ፡፡ እነዚህ እምብይተኞች ህወሓት አሸባሪዎች ይላቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ወያኔ የሚባል አካል መባል ካለበት ግን ያለ ምንም ጥርጥር ከበዝባዡና ከዘመናዊ ፊውዳሉ ከህወሓት ይልቅ ይህን አፋኝ ስርዓት በመቃወም ላይ ለሚገኙት ደፋሮች የሚመጥን ስም ይሆናል፡፡ ችግሩ ግን ተቃዋሚዎች ራሳቸው ለራሳቸው የሚገባውን ስም ለበዝባዥ አሳልፈው የሚሰጡ መሆናቸው ነው፡፡ ይህ ለህወሓት መልካም ነገር ነው፡፡

እኔ በበኩሌ ‹‹ወያኔ›› ብዬ ጠርቼው አላውቅም፡፡ አይገባውማ! ያለ ታሪኩ!? ያለ አላማው!?

ማዕተቤን አልበጥስም

$
0
0

በአንድ ወቅት በጨካኝነቱ ተወዳዳሪ ያልነበረው የታላቋ ሩስያ መሪ የነበረው ስታሊን በአገዛዝ ዘመኑ የሩስያ ኦርቶዶቶዶክስን ለማጥፋት ያልወሰደው አረመኔአዊ ድርጊት አልነበረም ። ከእነዚህም መካከል የቤተክርስቲያኒቱን አማኞች በጥይት መግደሉ ጥይት ማባከን ነው ብሎ በማሰቡ ከፓትርያርኩ ጀምሮ እስከ አራስ ህፃናት ድረስ ያሉትን ኦርቶዶክሳውያን በግዙፍ መርከቦች እየጫነ ውቅያኖስ ውስጥ በመጨመር ለአሳነባሪዎች ቀለብ እስከማድረግ ደረሰ ። ይህን የመሰለው ግፍ ግን ኦርቶዶክሳውያኑን ከማጥፋት ይልቅ ይበልጥ ሃይማኖታቸውን እንዲያጠብቁ አደረጋቸው ። እንዲያውም በሩሲያ ታሪክ እንደዚያን ዘመን የኦርቶዶክሳውያን አማኞች ቁጥር በዝቶ የታየበት ዘመን እንደሌለ የታሪክ ፀሐፊዎች ይናገራሉ ።

የሁኔታውን አደገኛነት የተገነዘበው ስታሊን ፓርላማውን ሰበሰበና እንዲህ አለ ።” ጓዶች ይሄ አካሄዳችን አላማረኝም ከሃይማኖቱ ሰባኪዎች ይልቅ የእኛ ግድያ የሩስያ ኦርቶዶክስን እያለመለመ እና እያጠነከረ ይገኛል። እናም ግድያው ይቁም ። ምክንያቱም ከዚህ አይነቱ አካሄዳችን የተማርኩት ነገር ቢኖር ክርስቲያን እና ምስማር በመቱት ቁጥር እየጠበቀ መሄዱን” ነው ብሎ የሩሲያን ኦርቶዶክስ ማጥፋት ድክም ብሎት አቆመ ይባላል ።

ትናንት ከግሸን እንደተመለስኩ ለ 10 ቀናት ያህል የተለየሁትን የማኅበራዊ ድረገፆችን ለማየት ብከፍተው አንድ ደስ የማይል ዜና ብዙዎች ሲቀባበሉት ተመለከትኩ ። ብዙዎች የሚያወሩት በስሜት እንዳይሆን ብዬ ወደ አንድ ወዳጄ ጋር ብደውል ወሬ አለመሆኑን አረጋገጠልኝ ። እኔም ምንም ከሌሎች የተለየ ነገር ማለት ባልችልም የአቅሜን ታህል ድምፄን ላሰማ አልኩና ይኸው ብቅ አልኩኝ።

ክቡር ሚንስትሩ በሲቪል ሰርቪስ ስልጠና ላይ ግልፅ በሆነ አማርኛ ” የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ይሄን የኦርቶዶክሳውያን ማዕተብ መበጠሳችን አይቀርም ” ብለው መናገራቸውን ሰማን ። አንድን ሰው ወንጀለኛ አድርጎ ከባድ ፍርድ እንዲፈረድበት የሚያደርገው ደግሞ ምቹ ጊዜ ሰዓትና በተገቢው ሁኔታ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወንጀል መፈፀሙ ሲረጋገጥ መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ይናገራሉ ። አንዳንድ ሰዎች የሰው ህይወት በእጃቸው ጠፍቶ 3 እና 4 ዓመት የሚፈረድባቸው እና ሌሎች ደግሞ በተመሳሳይ መንገድ የሰው ሕይወት አጥፍተው ከ ዕድሜ ልክ እስከ ሞት ፍርድ ድረስ የሚያደርስ ቅጣት የሚወሰንባቸው ከ3 እና የ4 ዓመት ፍርደኞቹ በተለየ መልኩ በስህተትና በአጋጣሚ ሳይሆን ሆን ብለው አቅደው ፣ቅድመ ዝግጅትም አድርገው ሆን ብለው የፈፀሙት ወንጀል በመሆኑ ነው ቅጣታቸውን ከባድ የሚያደርገው ።

እኝህ ክቡር ሚንስትር በዚህች ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ላይ ደስ የማይሉ ንግግሮችን ቀን እየጠበቁ መናገራቸውን ከጀመሩ ቆየት ብለዋል ። እኝህ ሰው ዛሬም ሲናገሩ እግዚአብሔር በሰማያት ብዙዎቻችን በምድር እየሰማን ነው። ከሰመነው ሰዎች መካከልም፦

1. ቅዱስ ፓትርያርካችን ሰምተዋል ።
2. መላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሰምተዋል።
3. ካህናት እና ዲያቆናቱም ሰምተዋል።
4. መነኮሳቱና ባህታውያኑም ሰምተዋል።
5. የሊቃውንት ጉባኤ አባላትም ሰምተዋል።
6. የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በሙሉ ሰምተወል።
7. ዘማሪዎቻችንም ለዚህ የሚሆን ዜማ ባይደርሱም ሰምተዋል።
8. ፀሐፍያን ነን ብለው በየአጋጣሚው መከራ የሚያሳዪን ፀሐፍትም ሰምተዋል።
9. ከሁሉም በላይ ከየመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ተመርቀው የወጡና የአውደምህረት ላይ የስቱዲዮና የሲዲ ላይ አንበሶቻችንም በደንብ ሰምተዋል ። ግን ሁሉም ይስሙ እንጂ ምንም ሊሉን አልፈቀዱም።

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ክቡራን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከጥቂቶች በቀር ብዙሃኑ በእርግና ማእረግ ላይ የሚገኙ ያውም መቃብራቸው የተማሰ ልጣቸው የተራሰ ቢሆንም ዝም ብለዋል ። አረ ተዉ ውኃ ሽቅብ አይፈስም ነው እኮ የሚባለው። እናንተ ዝም ስላላችሁ እኮ ነው ፓስተር ዳዊት ነኝ የሚል ፍንዳታ ወጠጤ ተነስቶ እንደፈለገ ቅድስት ቤተክርስቲያንን የሚሰድባትን ሰው ነው እኮ እንዲያው ሰው የላትም ተብሎ ከሚቀር ከማለት እነ መምህር ምህረተአብ የአቅማቸውን ያህል የሚፍጨረጨሩት ። ሌሎችም እንዲሁ በየአቅጣጫው እየተነሱ የፈሪ በትራቸውን ሲያወርዱባት ምነው ዝምታችሁ በዛ ።

ሰባኪዎቻችንም እንደሁ ከጥቂቶች በቀር ብዙሃኑ እኛን ኢትዮጵያን አትልቀቁ ዲቪም አትሙሉ እያሉን እነሱ ግን በቦሌም በባሌም ፣ በሚስትም በሲስተምም እልም እያሉ መኖርያቸውን ከኢትዮጵያ ውጪ ከማድረግ በቀር ፣ ንግድ ሚንስቴር በማያውቀው ነፃው አውደምህረት ላይ በየ ስቱድዮው በመቀረፅ ያልበላንን በማከክ ከሚያራግፉብን ሸቀጦች ሌላ እና ለእርድ እንደተዘጋጀ የሐረር ሰንጋ ራሳቸውን ከማደለብ በቀር ምንም ሲፈይዱ አይታዪም ።

እስቲ ጥሩልኝ ኢትዮጵያ ውስጥ የቀረ ኑሮውን በምእራብ ሀገራት ያላደረገ ሰባኪ ። ከ ምህረተአብ በቀር እንደው በቤተክርስቲያን ላይ የሚወረወሩ ቀስቶችን ለመመከት የሚፍጨረጨር ማን አለ ? ንገሩኛ እከሌ በሉኝ ። ወይኔ ዛሬ እንኳን ሰው ይጥፋ ? እነ አትናትዮስን እነ ቅዱስ ጊዮርጊስን የወለደችው ቅድስት ቤተክርስቲያን የወላድ መካን ሆና ትታይ።

እኔ የምለው ክቡር ሚንስትር ይሄ አሁን ግዜ እየጠብቅንለት ነው ብለው የነገሩን ማዕተብ ከኦርቶዶክሳውያን አንገት ላይ የመበጠሱ ነገር የምእራብ ኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ባለፈው ዓመት ከምእራብ የሀገራችን ክፍል መጥተው ለቅዱስ
ሲኖዶሱ እንደተናገሩት …… ” ፖሊሶች በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች በራፍ ላይ በመቆም ከኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች አንገት ላይ እየበጠሱ ነው ያሉትን አቤቱታ መነሻ በማድረግ በዚያ የታየው ማዕተብ የማስበጠስ ስራ ተሞክሮው አበረታች ሆኖ በመገኘቱ ነው ለዚህ አዋጅ መሰል ዛቻ ያበቃዎት ?

ሲቀጥል ደግሞ እርስዎ የሚከተሉት ሃይማኖት ምን ይሆን ?

እኔ ግን እላለሁ

1. ባለፈው ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳንን የመጎነታተል ነገር ቢሞከር ከታሰበው በላይ ከማኅበሩ በተለያዪ ምክንያቶች የራቁትን ጨምሮ ሌሎች አዳዲስ አባላትን ወደ ማኅበሩ በማምጣት ማኅበሩን በሰው ኃይልእንዲጠናከር አድርጎታል።

2. በሻሻ የሚባል ቦታ በሀገራችን መኖሩን የሚያውቅ ከአካባቢው ሰው በቀር የሚያውቅ ብዙ ሰው አልነበረም ። ነገር ግን ጥቂት ብዙኃኑን የእስልምና እምነት ተከታዮች የማይወክሉ አሸባሪዎች ማዕተባችንን አንበጥስም ባሉ የተዋህዶ ልጆች ላይ በፈፀሙት ግድያ ምክንያት በሻሻ በዓለም ላይ ታወቀች። ዛሬ በሻሻ ልክ እንደ አክሱም ፅዮን ፣ ግሸን ማርያም ፣ ቅዱስ ላሊበላ ፣ ቁልቢ ገብርኤል ከመላው ዓለም በሚመጡ ምእመናን ይጨናነቃል ። በአክራሪዎቹ የወደመችዋ ደሳሳዋ የበሻሻ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያንም ዛሬ በሚገርም ካቴድራል ተተክቷል ። ለዚህ እውቅና ደግሞ ሀገረ ስብከቱ ምንም ያደረገው አስተዋፅኦ የለም ። የሰማዕታቱ መሰየፍ እንጂ ።
mahtebe
ይገርምዎታል ክቡር ሚኒስትር የበሻሻ ጉዳይ መች በዚህ ብቻ ያበቃል መሰልዎ ። አሁን መላውን ዓለም እያስደመመ የሚገኘው የወጣቶች የጥምቀት በዓል አከባበርን የወለደው እኮ የበሻሻ ሰማእታት ደም ነው። በዚህ ጉዳይ የአንድም ሰባኪ እጅ የለበትም ። ከግሪሳዎቹ የተሃድሶ ርዝርራዦች መካከል አንዱ ግሪሳ ብቻ ነው የእኛ የአገልግሎት ነው ወጣቱን እንዲህ እንዲነሳሳ ያደረገው ሲል የተሰማው። ይህ ግን ሀሰት ነው ግሪሳዎቹ ኪሎና የባንክ አካውንታቸውን ከመጨመርና ከማብዛት በቀር አንድም ምእመን ወደ ቤተክርስቲያን ጉያ አልጨመሩም ።

አሁን ደግሞ ምን እየሆነ መሰልዎት እርስዎ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ማዕተብ ማስበጠሳችን እንደሁ አይቀር አሉ ከተባለ ወዲህ ይገርምዎታል የኦርቶዶክሳውያኑን አንገት ቢመለከቱ ቀድሞ የሀብት መግለጫ የነበሩትን የወርቅና የብር ሐብሎች በሚያምሩና በወፋፍራም የማዕተብ ክሮች ተተክተው እየታዩ ነው ። የብዙኀኑ የፌስ ቡክ ፕሮፋይል ፒክቸሮችም በማዕተብ ክሮች እየተለወጡ ነው ። የማዕተብ ክር ነጋዴዎችም ገበያ ድርት ብሏል። ምነው ደግሞ ቅዳሴ ማስቀደስ ፣ ንስሀ መግባት ፣ ስጋወደሙ መቀበል ፣ ፆም መፆም የሚከለክል በመጣና ተአምር ባየን ። ከዘመኑ ሰባክያን ይልቅ ምእመናን ወደ ቅድስት ቤተክርስትያን ለመመለስ እግዚአብሔር ባወቀ በአንድም በሌላም መንገድ የአህዛብና የመናፍቃን መነሳሳት ሳይሻል አይቀርም ። እንደውም የዘመኑን ግሪሳ ሰባክያን እና ዘማርያን ልብ ብላችሁ አንገታቸውን ብታዩት ማዕተብ የለውም።

በመጨረሻም ክቡር ሚንስትር እኔ ማዕተቤን በአንገቴ የማስረው ለጌጥ ሳይሆን ጌታ በማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 10 ፣ 32 – 33 ላይ የተናገረውን አምላካዊ መመርያ መሰረት በማድረግ ነው። ” ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ ይላል። ይህ ማለት በአፌ ማንነቴን መግለፅ የማልችል ብሆንም እንኳን ማዕተቤን በአንገቴ ላይ ማሰሬ ብቻውን የክርስቶስ መሆኔን እርርሪሪ እያለ በመጮህ ይመሰክርልኛል ።

ግን ቆይ የማዕተብ ክር በአንገታቸው ላይ ያለውን እናቆይ እና ሌሎቹን በትግራይ ፣ በአማራ ፣ በኦሮምያ ፣ በደቡብና በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ያሉትን በግንባራቸዉ ፣ በአንገታቸው ፣ በክንዳቸው ላይ የተነቀሱ ኦርቶዶክሳውያን ዕጣ ፈንታስ እንዴት ሊሆን ነው ? ለዛሬ አበቃሁ ።

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ከግሸን ደብረ ከርቤ መልስ
መስከረም 26/ 1 /2007 ዓም
አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ


”እናመሰግናለን አሜሪካ!” Thank you America! ኢትዮጵያውያን ዛሬ በዋሽግተን ዲሲ በሰልፍ ወጥተው ያሰሙት ድምፅ

$
0
0

የጉዳያችን አጭር ጥንቅር

Ethio-America flag 1ኢትዮጵያውያን ዛሬ መስከረም 27/2007 ዓም (ኦክቶበር 7/2014) ዋሽግተን ላይ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (ስቴት ዲፓርትመንት ) ፊት ለፊት ተሰለፉ።ሰልፉ ባለፈው በዋሽግተን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኢትዮጵያውያን ላይ የተኮሰውን የኤምባሲ ሰራተኛ ከሀገር በማስወጣቷ አሜሪካንን ለማመስገን ሲሆን በሰልፉ ላይ ግለሰቡ የተኮሰበት ሽጉጥ አሁንም በኤምባሲው ውስጥ መገኘቱ እና ምርመራው ወደ አምባሳደር ግርማም እንዲዞር ይጠይቃል።በሌላ በኩል በወገኖቹ ላይ የተኮሰው ግለሰብን በመደገፍ እና ወደ ኤምባሲ የገቡትን ተቃዋሚዎች በመቃወም የተሰለፉትን ከዋሽግተን አትዮጵያ ኤምባሲ እና ከሌሎች ቦታዎች የአውቶብስ ተከፍሎላቸው የመጡ ሰልፈኞች ታይተዋል።በተለይ የስርዓቱ ደጋፊዎች ተሰላፊዎች ለመፈክር መፃፍያ እና ለአውቶብስ ከ2000 ዶላር በላይ ወጪ መደረጉን መረጃ እንደደረሳቸው በተቃዋሚ በኩል ከተሰለፉ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ ወቅታዊ የመወያያ መድረክ (ECADF) የቀጥታ ስርጭት ገልፀዋል።

በሰልፈኞች ላይ የተኮሰውን ደግፎ የሚሰለፍ የሰው ልጅ ይኖራል ብለው ያልገመቱት የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት ሰራተኞች በወገኖቹ ላይ የተኮሰውን ግለሰብ በመደገፍ የወጡትን በመገረም ተመልክተዋቸዋል።በአሜሪካ ሕግ ጠለላ ውስጥ ያለ ሰው እንዲህ በወገኖቹ ላይ የተኮሰ ሰውን ደግፎ ይወጣል ብለው አሜሪካኖቹ ፈፅመው ያልገመቱት የስቴት ዲፓርትመንት ሰራተኞች ቢገረሙ አይገርምም።በነገራችን ላይ በወገኖቹ ላይ የተኮሰው የኤምባሲ ሰራተኛ ላይ የአሜሪካ አቃቢ ሕግ የክስ ወረቀት ማውጣቱን ዛሬ ”ዘሀበሻ” በድረ-ገፁ ገልጧል።

በመጨረሻም ሰልፈኞቹ በመጪው ቅዳሜ የዓለም ባንክ ፊት ለፊት ለሌላ ሰልፍ ለመገናኘት ተቀጣጥረው ተለያይተዋል።በዓለም ባንክ ፊት ለፊት በመጪው ቅዳሜ የሚደረገውን ሰልፍ ዓላማ ለኢትዮጵያ ወቅታዊ የመወያያ መድረክ (ECADF) የገለፁት አንድ የሰልፉ አስተባባሪ እንደተናገሩት ” እኛ ለኢትዮጵያ ብድር አይሰጥ አንልም።ብድሩ ይሰጥ። ነገር ግን ወያኔ እጅ እንዳይገባ እና ለሙስና እንዳይጋለጥ ከፍተኛ ቁጥጥር ይደረግ” የሚል ጥያቄ ነው ለዓለም ባንክ የምናቀርበው ብለዋል።

ጉዳያችን
መስከረም 27/2007 ዓም (ኦክቶበር 7/2014)

ወያኔ ሲያስር አሜን….ሲገድልም አሜን

$
0
0

ነሚያህ

tplfብዕር የያዘ ማንም ሰዉ በዘመናችን ደግሞ የኮምፒተር መክተቢያ ፊቱ ላይ የደቀነ ሁሉ ከሱ ዉጭ ያለዉን ማንንም ሰዉ “ሌባ”፤ “ባንዳ” ወይም “ከሃዲ” እያለ እንዳሰኘዉ መጻፍ ይችላል። በተለይ በእንደኛ አይነቱ ሀላፊነትም ተጠያቂነትም በሌለበት ህብረተሰብ ዉስጥ ደግሞ የጓደኛዉ ሀሳብ ያልተስማማዉ ሁሉ እየተነሳ የገዛ ጓደኛዉን ባንዳና ከሃዲ አድርጎ ስለሚስለዉ የላይ የላዩን ብቻ ለሚመለከት ሰዉ አገራችን በባንዳና በአገር ወዳድ መሳ ለመሳ ለሁለት የተከፈለች ትመስላለች።  እግዝአብሄር ይመሰገን እዉነቱ ግን ከዚህ እጅግ በጣም የተለየ ነዉ። ርዕሴን የጀመርኩት አሜን ብዬ ነዉና እስኪ አንባቢዉ አንተም አሜን በል። ባንዳነትና ከሃዲነት ኃብታምና በእድገት ወደፊት የገፉ አገሮችን እየዘለለ ደሃና ኋላ ቀር አገሮችን ብቻ የሚጠናወት ተራ በሽታ አይደለም። ብዙዎቻችን አምባገነን መሪዎቻችንን ሸሽተን የተጠለልንባት አገር አሜሪካ እነ ሄንሪ ቤስትንና ጆን ብራዉንን የመሳሰሉ ከሃዲዎችን እንዳበቀለች ሁሉ ኢትዮጵያችንም ትናንት እነ ኃ/ሥላሤ ጉግሳን ዛሬ ደግሞ የኃ/ሥላሤ ጉግሳ የልጅ ልጆች የሆኑትን እነ መለስ ዜናዊን፤ አባይ ፀሐዬንና ሰብሃት ነጋን የመሳሰሉ የለየላቸዉ ከሀዲዎችን አፍርታለች። በነገራችን ላይ ሙስሊሙ በዱአዉ፤ ክርስቲያኑ በፀሎት፤ ጠቢብ በጥበቡ ፤ፀሐፊ በምናቡ የባንዳዉንና የከሃዲዉን ብዛት ለመቀነስ ካልተባበሩ በቀር “ወላድ በድባብ ትሂድ” ብለን ባንመርቃቸዉም የባንዳ አባትና አናት አስካሉ ድረስ ባንዳም መወለዱ አይቀርም።

ደጅአዝማች ኃ/ሥላሤ ጉግሳ ማንም ሳያስገድደዉ ወድዶና ፈቅዶ ለወራሪዉ የጣሊያን ጦር ካደረ በኋላ ከጄኔራል ደቦኖ ጋር ሆኖ እናት አገሩን ኢትዮጵያን ወግቷል። ጣሊያኖች ኃ/ሥላሤ ጉግሳ ከነተከታዮቹ ከጎናቸዉ ተሰልፎ አገሩን ሲወጋ ያደረጉት የመጀመሪያዉ ነገር ይህ ከሃዲ ሰዉ ከጎናቸዉ መሰለፉን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ለዓለም ህዝብ ማሰራጨት ነበር። ታሪክ እራሱን ይደግማል ሲባል አይኑ አላይ እያለዉ በጆሮዉ ብቻ ለሰማ ሰዉ ዛሬ ማረጋገጫዉ እነሆ በግልጽ ቀርቦለታል። ትናንት ማክሰኞ መሰከረም 27 ቀን የወያኔ ቴሌቭዥንና ሬድዮ ኢትዮጵያ ዉስጥ በጋዜጠኞች ላይ የሚፈፀመዉን እስርና ስደት፤ ወያኔ በወገኖቻቸን ላይ የሚፈጽመዉን የዕለት ከዕለት ሰቆቃና እንዲሁም በቅርቡ አምቦና ኦጋዴን ዉስጥ የተካሄዱትን የጅምላ ግድያዎች የሚደግፉ የዚህ ዘመን ኃ/ሥላሤ ጉግሳዎች ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ ያካሄዱትን የክህደት ሰለማዊ ሠልፍ በተደጋጋሚ ለህዝብ አቅርበዋል። እነዚህ ትናንት ክቡር ባንዲራችን በአለባሌ ሰዉ አንደበት “ጨርቅ” ተብላ ስትሰደብ ከተሳዳቢዉ ሰዉ ጎን ቆመዉ የሳቁና የተሳለቁ ከሃዲ ሆድ አምላኪዎች ዛሬ “ባንዲራችን ተደፈረ” ብለዉ የአዞ እምባ ያነቡብናል። የትኛዉ ባንዲራ?  ለመሆኑ እነዚህ “እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነዉ” ባዮች ጀግናዉ ዘርዐይ ደረስ ጣሊያኖችን በራሳቸዉ አደባባዮች አንገታቸዉን በጎራዴ የቀላዉ ለዬትኛዉ ባንዲራ እንደሆነ ያዉቃሉ? እነ አብዲሳ አጋ፤ በላይ ዘለቀ፤ ባልቻ አባ ነብሶና እልፍ  አዕላፋት የኢትዮጵያ ልጆች ምትክ የሌላትን ህይወታቸዉን የሰጡት ለዬትኛዉ ባንዲራ አንደሆነ ያዉቃሉ?

እነዚህ ወያኔ አዲስ አበባ ዉስጥ የገዛ ወገኖቻዉን ሲያስርና ሲገድል አሜን ብለዉ ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ ሠላማዊ ሠልፍ የሚወጡ የለየላቸዉ ከሃዲዎች ባንዲራ አዲስ መንግስት በመጣ ቁጥር እንደ ፖሊሲና እንደ ካቢኔ ሚኒስቴር የማይቀያየር ቋሚ የአገር ማንነትና የትዉልድ ትስስር መታወቂያ መሆኑን ሊገነዙ ይገባል። ባንዲራ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ሊቀየር ይችላል ብለን ብናስብ እንኳን ምን አይነት ሰዎች ብንሆን ነዉ ባንዲራን የመሰለ ህዝብና አገር ማስተሳሰሪያ ማተብ ኢትዮጵያንና ታሪኳን ከልቡ ለሚጠላዉ መለስ ዜናዊና   የትግራይ ሪፓብሊክ ካላቋቋምኩ ብሎ ይታገል ለነበረዉ ለከሃዲዉ  ስብሀት ነጋ የምንተዉላቸዉ? ደግሞም  እነዚህ ምናምንቴዎች አንደሚሉት ባንዲራችን ላይ ባዕድ አካል ሆኖ የተለጠፈዉና የኢትዮጵያ ህዝብ በተለምዶ “ባላ አምባሻዉ” እያለ የሚጠራዉ የወያኔ ጨርቅ እዉነትም ኢትዮጵያ ዉስጥ የብሄር ብሄረሰቦችን እኩልነት አረጋግጦ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አገራችን  በየቀኑ ብሄር ብሄረሰቦች ዉጣልኝ አልወጣም እየተባባሉ የሚተላለቁባት አገር አትሆንም ነበር።  አባቶቻችን የሞቱት ለአረንጓዴ፤ ብጫና ቀይ ባንዲራ ነዉ፤ እኛም ዛሬ በየተሰደድንበት አገር አገሬን እያሰኘ የሚያስጮኸን ይሄዉ አረንጓዴ፤ ብጫ ቀይ ባንዲራችን ነዉ። አገር ቤት ያለዉ ኢትዮጵያዊም አንዱን “ባላአምባሻዉ” ሌላዉን ደግሞ ባንድራዬ እያለ የሚጠራዉ ይህንኑ አረንጓዴ፤ ብጫና ቀይ ባንዲራዉን ነዉ። በአንዲት አገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ እነሱም እኛም ለየቅላችን  የኛ የምንለዉ ባንዲራ ሊኖር በፍጹም አይችልም። ይልቅ ወያኔዎች ሲጠፉ እነሱ ይዘዉብን የመጡት ኮተቶ ሁሉ አብሯቸዉ መጥፋቱ አይቀርምና ዛሬ “ባንዲራችን ተደፈረ” ብላችሁ የምታቅራሩ እዉሮች ነገ ከወያኔ በጸዳችዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ጭራሽ ባንዲራ ላይኖራችሁ ይችላልና መጀመሪያ ከራሳችሁ ጋር ቀጥሎም ከአገራችሁ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትታረቁ አጥብቄ እማጸናችኋለሁ።

የወያኔን ቂልነትና ባዶነት በሰብኩ ቁጥር ትዝ የምትለኝ አንዲት ቀልድ ብጤ አለችና እስኪ ለፈገግታ ትሆናለችና አዳምጡኝ። ሁለት አመት የፈጀዉ የኤርትራና የኢትዮጵያ አላስፈላጊ ጦርነት እንዳለቀ በጦርነቱ ወቅት ስንቅና ትጥቅ በማመላለስ ትልቅ ዉለታ የዋለች ኣንዲት አህያ ጦርነቱ አብቅቶ የድል በዐል ሲከበር መስቀል አደባባይ ተጋብዛ መለስ ዜናዊ ፊት ትቀርባለች፤ በቋንቋ ይግባቡ ነበርና መለስ ጎንበስ ብሎ በጆሮዋ አንድ ነገር ሹክ ሲላት አህይት በደስታ እየፈነጠዘች አደባባዩን መዞር ጀመረች። በልማታዊ አህይት ዝላይና ፍንጠዛ ግራ የተጋቡት የወያኔ ጋዜጠኞች ዜና ያገኙ መስሏቸዉ “ታላቁ መሪ” ምን አለሽ ብለዉ አህይትን ጠየቋት። የዕድሜ ልክ የህወሓት አባል ሆነሻል ተብያለሁ ብላ አህይት ዝላይዋንና ፍንጠዛዋን ቀጠለች።

ትናንት እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ የወያኔን ጭፍጨፋ፤ እስርና በዘር መድሎ የተጨማለቀ ስርዐት አበጀህ ቀጥልበት ብለዉ አደባባይ የወጡ ጥቂት ህሊና ቢሶችና እነሱን አመስግኖ የነጻነት አርበኞችን “ዱሪዬዎች” ብሎ የዘለፈዉ የአድር ባዮች ሁሉ አድርባይ የሆነዉ  ግርማ ብሩ ከዚያች ባድመ ላይ ብዙ ስንቅና ትጥቅ ካመላለሰችዉ ጎበዝ አህያ የሚለዩበት መንገድ ቢኖር አህያዋ ማሰብ ስለማትችል አለማሰቧ እነሱ ግን ማሰብ እየቻሉ አለማሰባቸዉ ብቻ ነዉ። በተረፈ እነሱም አህያዋም የወያኔ አባልነታቸዉ ያስደስታቸዋል፤ ምክንያቱም ሁለቱም አያስቡም። መቼም የገዛ ወንድሙና እህቱ ሲታሰሩ፤ ሲደበደቡና  ሲገደሉ አሜን ብሎ ተቀብሎ ነብሰ ገዳዮችን ደግፎ ሰላማዊ ሠልፍ የሚሰለፍ የሰዉ ዘር ያለዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ መሆን አለበት። ለዚያዉም በወያኔ ዘመን ብቻ!

እነዚህን ሆዳሞች ደግሜ ደጋግሜ እዉሮች እያልኩ የምጠራቸዉ አለምክንያት አይደለም። በእርግጥም ስለማያዩ ነዉ። ባለፈዉ ወር አዚህ አሜሪካ ሚዙሪ ግዛት ፈርግሰን የሚባል ከተማ ዉስጥ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች መሳሪያቸዉን ሰላማዊ ሰልፈኛዉ ላይ ስላዞሩ (ልብ በሉ ስላዞሩ ነዉ ያልኩት እንጂ ስለተኮሱ አላለኩም እነሱም አላደረጉትም) የአሜሪካ ህዝብ፤ መሪዎችና የህዝብ ተወካዮች ምን ያህል እንደተንጫጩ ሁላችንም ተመልክተናል። እነዚያ እዉሮች ያልኳቸዉ ወንድሞቻችንም  እኛ የተመለከትነዉን ተመልክተዉት ይሆናል፤ ግን እነሱ የአዕምሮ እዉራን ናቸዉና ስዕሉን ብቻ ነዉ እንጂ ቁም ነገሩን አላዩትም። ስለዚህም ነዉ የነሱ ድፕሎማት ተብዬዉ  ድንጋይ ራስ (ርዕስ እምኒ) አዲስ አበባ ዉስጥ ያለ መስሎት ሠላማዊ ሠልፈኛ ለመግደል ደጋግሞ ሲተኩስ አበጀህ ብለዉ ሠላማዊ ሠልፍ የወጡለት።  እግዚአብሄር ከዚህ አይነቱ የአዕምሮ እዉርነት ያድነን! እባካችሁ አሁንም አሜን በሉ። እኔ እያረረ የሚስቅ ማሽላ ብቻ ይመስለኝ ነበር . . . .  ለካስ የገዛ ወገኖቹ ሲገደሉ ደስ ብሎት የሚስቅ ሰዉም አለ። አቤት እግዚኦ!!!!

ሌላዉ የገረመኝ ነገር ቢኖር እነዚህ የአዕምሮ እዉራን ትናንት ረፋዱ ላይ ለአሜሪካዉ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ በጻፉት ደብዳቤ ግንቦት 7 ያ እንቅልፋም ፓርላማቸዉ “ሽብርተኛ” ብሎ የፈረጀዉ ድርጀት ነዉና ምነዉ ዝም ብላችሁ ታያላችሁ ብለዉ ኬሪን መወትወታቸዉ ነዉ። ኬሪ እንደነሱ ጨካኝና አምባገነን መሪዎች የማይወደዉንና የሚጠላዉን ሁሉ አይንህ አላማረኝም እያለ ማሰር የሚችል መስሏቸዋል። እነዚህ ሆዳቸዉ ልባቸዉን የሸፈነ ከሃዲዎች አይገባቸዉም አንጂ የነሱን “ግንቦት ሰባቶችን” እሰሩልን ብሎ ጥያቄ እንኳን ኬሪ የአለማችን ሀይለኛዉ መሪ አባማም ማስተናገድ አይችልም።  እኛስ ብንሆን የምንታገላቸዉ ለዚሁ ነዉኮ – ኢትዮጵያን የሚመራ ሁሉ ሀሳባችን ከሀሳቡ በተጋጨ ቁጥር አንዳያስረንና እንዳይደገድለን። እኔኮ ምን ይሻለኛል . . . . በአንድ በኩል ኢትዮጵያዉያን የወገኖቻቸዉን መገደል ተቃዉመዉ ሠላማዊ ሠልፍ ሲወጡ የወያኔዉ ተላላኪ ግርማ ብሩ የኤርትራን መንግስት ይከስሳል፤ የአይጥ ምስክር ድንቢጥ እንዲሉ የግርማ ብሩ ተላላኪዎች ደግሞ (የተላላኪ ተላላኪ ማለት ነዉ) ግንቦት ሰባት የሚረዳዉ በኤርትራ መንግስት ነዉና ስጋታችንን እዩልን እያሉ ኬሪን ይለማመጡታል። መቼም አዉቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም ነዉና የወያኔ ደጋፊዎች አይገባቸዉም አንጂ ለሻዕቢያ ጎንበስ ቀና እያሉና የሻዕቢያን መሪዎች እንደ ታቦት እየተሳለሙ ለዚህ ዛሬ ላሉበት ደረጃ የበቁት የወያኔ መሪዎች ናቸዉኮ። ዛሬ በባነኑ ቁጥር አንዴ ግንቦት ሰባት አንዴ ሻዕቢያ እያሉ ዛር እንደያዘዉ ሰዉ የሚያጓሩትም ተደምስሰዉ ከታሪክ ምዕራፍ የሚፋቁት በዚሁ እንደ ህጻን ልጅ እጃቸዉን ይዞ ለታሪክ ባበቃቸዉ በሻዕቢያ በኩል መሆኑን በሚገባ ስለሚያዉቁት ብቻ ነዉ። ምድረ የወያኔ አጎብጋቢዎች  ዛሬ እቅጩን ልንገራችሁ፤ ወደዳችሁም ጠላችሁ ይህ “ልማታዊ” ብላችሁ የምትጠሩት ነብሰ ገዳይ አገዛዝ ይደመሰሳል- ስጋታችሁ ትክክለኛ ስጋት ነዉ። ግን ከዚህ ስጋት የሚያድናችሁ ኬሪ ሳይሆን የራሳችሁ ሂሊና ብቻ ነዉና ሳይዉል ሳያድር ዛሬዉኑ ኑና ከህዝብ ጎን ተሰለፉ፤ አለዚያ ዕድላችሁ ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ይሆናል። መቼም እንደኔዉ የዚያች ምስኪን አገር ልጆች ናችሁና በተረት ብነግራችሁ ይገባችኋል ብዬ ነዉ እንጂ በእናንተና መወቀጥ በሚገባዉ ኑግ መካከል ምንም ልዩነት የለም።

የዘረኞቹ የወያኔ መሪዎችና እንደ ችግኝ ኮትኩተዉ ያሳደጓቸዉ ቡችሎቻቸዉ አስቂኝ ታሪክ በዚህ ብቻ አያበቃም፤ እነዚህ ጣምራ ጉደኞች ብዙ ተነግሮ የማያልቅ ጉድ አላቸዉ።  ወያኔዎች ጋዜጠኛ እያሰሩና ከአገር እንዲሰደድ እያደረጉ ተዉ ያላቸዉን ፀረ አገርና ፀረ ልማት ይሉታል፤ በየሰላማዊ ሠልፉ ላይ ንጹህ ዜጎችን በጅምላ ሲጨፈጭፉ ምነዉ ያላቸዉን ደግሞ ሽብርተኛ ብለዉ ያስሩታል። እነዚህ አረመኔዎች  ይህንን የመሰለ ለጆሮ የሚቀፍ ወንጀል በህዝብና በአገር ላይ ፈጽመዉ ሰዎች በነጻነት ወደሚኖሩበት አገር ሰዉ መስለዉ ሲመጡና ስንቃወማቸዉ ደግሞ እዚህ ዉጭ አገር ያስቀመጧቸዉ ተናካሽ ዉሾቻቸዉ “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት” የጎደላቸዉ ብለዉ ይዘልፉናል። ለመሆኑ ለእነዚህ እንደ ዉሻ ቁራሽ ስጋ በተወረወረላቸዉ ቁጥር ለሚያላዝኑ ምናምንቴዎች ማነዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንደነሱ ነዉርን አሜን ብሎ መቀበል ብሎ የነገራቸዉ? ዜጎችን አንደ እንስሳ አየጎተቱ ገድለዉ አስከሬኑን በሟቹ ወንድም እያስጎቱና ይህንን ነዉር በቪድዮ እየቀረጹ መሳቅና መሳለቅ ነዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ወይስ  ይህንን ኔሮና ሂትለር ምን አደረጉ የሚያሰኝ ጭካኔና አረመኔነት መቃወም ነዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት? አዲስ አበባ ዉስጥና እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ ተቃዋሚ ኃይሎችን “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት” የጎደላቸዉ ብለዉ የዘለፉት ሬድዋን ሁሴንና ግርማ ብሩ የዉኃ ጠብታን ያክል ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በደማቸዉ ዉስጥ ቢኖር ኖሮ “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት” የኢትዮጵያዉያንን ህይወት በየአደባባዩ መቀማት አይደለምና እናከብራቸዉ ነበር እንጂ በወጡና በገቡ ቁጥር ስማቸዉን እየጠራን ሌባና ከሃዲ እያልን አናሸማቅቃቸዉም ነበር። ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ስንታሰርና ስንዋረድ እልል፤ ስንገደል ደግሞ አሜን ብለን እንደ በሬ አንገታችንን ለቢለዋ መስጠት ማለት አይደለም። ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ለወገን ማዘን ነዉ፤ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ወገን ሲጎዳና ሲጠቃ ከለላ መሆን ነዉ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ዜጎች ሰቆቃ ሲፈጸምባቸዉና ሲገደሉ ቆሞ ከመመልከት ይልቅ ወይም የገዳዮች ጠበቃ ከመሆን ባጭር ታጥቆ  ነብሰ ገዳዮችንና የጭካኔ ምልክቶችን ከአገር አናትና ከህዝብ ጀርባ ላይ ማስወገድ ነዉ – ወላድ በድባብ ትሂድ – ይህንን የሚያደርጉ የቁርጥ ቀን ልጆች እናት ኢትዮጵያ ትናንንት ነበሯት፤ ዛሬ አሏት ነገም ይኖሯታል።

የጥይት ሩምታ በሰንደቅዓላማችን ላይ …. ጥጋቡ መረን ለቀቀ።

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 10.10.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/


“ያልወለድኩት ቢለኝ ባባ አፌን አለኝ ዳባ – ዳባ”
እኔ አይደለሁም ዘመኑን በተደሞና በአርምሞ እንዲሁም በፅሞና ሲከታተል ባጅቶ – የከረመው፤ እሰኪበቃው ድረስ በወያኔ 40 ዓመት ሙሉ በቋሳና በቁርሾ የተቀጠቀጠው የኢትዮጵያ ሰንድቅአላማ ነው በመንፈሱ  – የተቃኘው። ለመሆኑ ዬት የሚያውቀውን ሰንድቅዓላማ ነው እንዲህ ወያኔ የሚዘባነነው?! በዚህ ሰንደቅዓላማ ተከብራና ታፍራ የኖረች ሀገር አታስፈልገኝም፣ ገዝታኛለች በማለት አይደለም ትግራይን ከኢትዮጵያ ነጥሎ “የታላቋን ትግራይ” ህልም ለማሳካት እርጥብ ጌሾውን በቂም ምቸት ጠንስሶ ሲዳከር የኖረው። ቀድሞ ነገር በወያኔ ሃርነት ትግራይ ማዕቀፍ ውስጥ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የተፋቀ ነው። ከዚህ መንፈስ ሳትወጡ በጥልቀት መርምሩት …. በሌለ – ባልነበረ –  በአመለ መንፈስ የበቀለ የባዕድ ህልም ተጓዥ በምን ስሌት ነው ዛሬ አጃቢዎቹ ተቆርቋሪነቱን የሚያንኳኩለት ወይንም የሚያንኮሻኩሹለት? …. በዚህ ብሄራዊ ሰንድቅዓላማ ዙሪያ መንፈሱ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ኖሮ በፍጹም አያውቅም? መቼ – በዬትኛው ዘመንስ? እስኪ ጫካ እያለ የኢትዮጵያ ሰንድቅአላማ ንጹህ ምስሉን፣ ገጹን በወያኔ ሃርነት ጉባኤዎች ላይ ዬት ላይ ተከብሮ ታደመ? – እንዲሳተፍስ በዬትኛው የወያኔ ሃርነት ጉባኤ ላይ ተፈቀደለት? ምን ያህል ነፃነት ተሰጠው? ይህ እኮ ተፈጥሮው ያልተነነ የዕውነት መሰረተ – ጉልት ነው። ወያኔ በለስ ቀንቶት ከጫካ ወደ ከተማ ሲገባ ለምስል አንድ ቦታ ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅአላማ ያያዘ ሰራዊት ሆነ መሪ አይታችኋልን?! ፈጽሞ አኮ በኢትዮጵያዊነት ሙጣጭ መንፈስ በሌለው ጭድ ግንዛቤ እኮ ነው ሀገር እንዲህ እዬታመሰ ያለው። ወያኔ ከኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ውጪ የነበረ፣ ያለ – ወደፊትም የሚኖር መሆኑን እውነትን የመቀበል አቅማችን ጋር እባካችሁ ወገኖቼ እንነጋገር። የእኔ ያልሆነው የእኔ ሊሆን ከቶ አይችልም። ለዚህ ነው ከወያኔ አስተምኽሮ የመነሳትን አስፈላጊነት በአጽህኖት ሳልታክት የማሳስበው። ውዶቼ – የኔዎቹ ከዚህ ከተነሳችሁ መንገዱ ቀላል ነው ….

ethiopian-human-rights-activits

የእናት ኢትዮጵያ ያ ወ/ሮ ሞንዳላ ሙሉ ቅርፆዋ እኮ ለወያኔ በሽታው ነው የነበረው። በመንፈስና በአካሏ ተበትና አቅመ ቢስ ስትሆንለት የተነሳበትን ቁርሾ አሳካለሁ ብሎ አይደል ዘመን ይቅር የማይለውን ዘር አምካኝ ድርጅት ወያኔ ሃርነት ትግራይን የተከለው። አረሙ ወያኔ በተጠመጠመ ትብትብ ተብትቦ ነገር እያፈላ ዛሬ ያለችበትን የሞትና የህይወት ግብግብ አና ብሎ ፈጠረ። ተሳክቶለት ሁሉን የመያዝ ዕድሉን አግኝቶ እንኳን ለሰከንድ ሳይዘናጋ ዘነዘናዋን አስቀርቶ እዬገዘገዛት ይገኛል። ሰንደቅዓላማው መቼ ተፈጥረ ብሎ እንደዘገበው ተመልከቱት … “የተፈጠረበት ዓመት ሰንድቅዓላማው በግዕዙ የተጻፈው ቀን ሲተረጎም “ጥር 28 ቀን 1988 ዓም.” ምን? “የተፈጠረበት ዓመት” ታሪክን፤ ትውፊትን – የፈሰሰ ደምን፣ የተከሰከሰን አጥንት ሁሉ ዋጋ አልባ አደረገው። በቁሙ ገድሎ የሚቀብር ዝክንትል ህልም። ለዚህ የላሸቀ ብክነት ነው ፋሽኮው ቀለብ የሚሰፈርለት ሲጮህ የምታዳምጡት ….

http://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1

የኔዎቹ ውዶቼ – ማናቸውም አንጡራ የሃብት ዘረፋው ደግሞ የመንፈሱንም ጨምሮ ለዬትኛው ተልዕኮ ማስፈጻሚያ እንደሚውል “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ነው።” ጡጦ የሚጠባ ልጅ እኮ አይደለም የኢትዮጵያ ህዝብ። …. እራሱ ብክሉ መንፈስ ከዚህ አጥፊ ድርጅት አፈነገጥኩ የሚለው ጥንስስ ድርጅት ሁሉ ከዚህ አዟሪት የመውጣት አቅም የለውም። …. ሽባ ነው። ይህ ማለት ጥላቻው ሥር ሰደድ መርህ መሆኑን ማመሳክር ይቻላል። እሩቅ ሳይኬድ ይህችን ነጠላ አምክንዮ ይዛችሁ ብትፈትሿት።

እ.ኤ.አ ጥቅምት 5.ቀን 2014 እዚህ ሲዊዘርላንድ ዙሪክ በብራዚል ቆንሲላ ጽ/ቤት ብራዚላውያን በሀገራዊው ምርጫ ሲሳተፉ መዋላቸውን ቴሌ ዙሪ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሲዘግብ አዳመጥኩኝ። ሰልፉንም አዬሁኝ። ህሊና ያለው፤ ባለቤትነት የሚሰማው፤ የህዝብን ድምጽ የማይፈራ፤ ዬህዝብ ድምጽ አስፈላጊነት የመተርጎም አቅም የተሰጠው፤ እንዲሁም ዘመኑ ለሰው ልጆች የለገሰውን የመብት ነፃነት ያልነፈገ ተግባር እንዲህ ባደላቸው ሀገሮች ይፈጸማል። የሌሎች ሀገር ዜጎች ተሰደውም ሁነኛ አላቸው፤ እረኛ አላቸው፤ ባሊህ ባይ አላቸው – ።

ብራዚላውያን እዚህ ሲውዘርላንድ ላይ ምርጫው ላይ እንዲሳተፉ በክብር ተጠሩ፤ የቻሉት በቦታው ተገኝተው ሲመርጡ ዋሉ። አንዲት ቃለ ምልልስ የተደረገላቸው ወ/ሮ ሲገልጹ እንደሰማሁት ሶስት ሰአት እንደጠበቁ አዳምጫለሁ። ማለት በርካታ ብራዚላውያን ሙሉ ቀን ድምጻቸውን ሲሰጡ እንደዋሉ ተረድቻለሁ። አሁን ወደ እኛ የእንሰሳ አስተዳደር ስንመጣ፤ አይደለም ውጪ የሚገኘው ወገን በሀገሩ ጉዳይ እኩል መሳተፍ እንዲችል መብቱን በሚያረጋግጡ ማናቸው ተሰትፎዎች ተከብሮ መጠራቱ ቀርቶ፤ በሰላም ጥያቄ ሊያቀርብ የሚሄደውን ዜጋ በጽሞና በማዳመጥ ለቀጣዩ አካል ማስተላለፍ ሲገባ በባሩድ ሩምታ ዜግነት ከነአርማው ሲደበደብ አዬን። ከዚህ ሲዊዝ የተፈጸመው የሰው ልጆች የማይገሰስ መብት ተግባራዊነት ለብራዚላውያን፤ በአሜሪካ ደግሞ ኢትዮጵውያን ላይ የደረሰው በቋሳ የጨቀዬ ግፍና በደል ባልተራራቀ ሰሞናት የተከወነው ትዕይንት ምን ያህል የሰብዕዊ መብት ረገጣ ከሀገር አልፎ የዜጎችን ጉዳይ ይወክላል በተባለው ቆንጽላ ጽ/ቤት እንደ ተፈጸመ የሚያረጋግጥ የሀቅ ማህተም ነው። ለነገሩ ባለፉት ወራቶች አሜሪካን ሀገር ተካሂዶ በነበረው የአንባገነን አፍሪካውያን ዬመሪዎች ጉባኤ የህዝብን ሮሮ ያላደመጠው አካል፤ አሁን በዓይኑ፣ በብሌኑ አይቶ ይፈርድ ዘንድ የሰማዩ ዳኛ የላከው የምፅዓት ቀን ደወል ነው። ኢትዮጵያ አምላክ አላት። – አቅሟ – ኃይሏ  – መመኪያዋ  – መጠጊያዋ ፈጣሪያዋ ነውና።

በሌላ በኩል ውጭ ያለነው ተዘለን እንኳን፤ ሀገር ቤት ያለው ዜጋ በትክክል ለውሳኔው ድምጹን በነፃነት መስጠት ይችላል ወይ ለሚለው በስማ በለው ሳይሆን በ97 የተከወነው ጽልመታዊ አንበገነናዊ ድርጊት ምስክር ነው። የጠቆረው ታሪካችንም አካል ነው። ከአራት አመት በኋላም የአደራ አርበኛው አቶ አንዷለም አራጌ እስር ጨምሮ ከዚህው ስጋት የመነጨ ነበር። ለቀጣዩም ምርጫ ቁርሾን ከዝኖ ገና ከመምጣቱ አስቀድሞ እነ አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ አቶ ሺዋስ አሰፋ፤ አቶ ዳንኤል ሺበሺና ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ሰለባ የሆኑበት ምክንያት ይሄው ነው። ያደላቸው ደግሞ በተሰደዱበት ሀገር መብታቸው ተከብሮ በነፃነት ለወደዱት ድምጽ ሲሰጡ አዬን። ብራዚላውያን እርቀው ቢኖሩም መንግሥታቸው የሚያስባቸው መሆኑ፤ በራሱ በሚኖሩበት ሀገርም ተከብረው እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል። አንተ ላጣህ ሌላው ያገልሃል፣ ያቀልሃል ጉዳዩም አይደለም፤ “ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ፤ ባለ ዕዳ አይቀበለውም” እንዲሉ። አንተ ለኖረህ ደግሞ ሌላው ይንከባከበሃል – ያሽቃብጥልሃል – ያሸከሽክልሃል። እኛ ኢትዮጵውያን ግን የሁለት ሀገር ስደተኞች ነን። እረኛ አልባ … ምንዱባን …..

አልቀረለትም – ሰንድቅአላማችንም የመከራው ዘመን ታዳሚ ነውና በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲተኮስበት ታዬ – በባዕድ መሬት። ዜጎችም የነፃነት ጥያቄ ባቀረቡ ተመሳሳይ ዕጣ ገጠማቸው። እርግጥ ነው የጫካው አራዊት ወያኔ በጥርሱ ይዞ በጠላትነት ከፈረጃቸው ዬኢትዮጵያዊነት መግለጫዎች ታላቁ ሰንድቅአላማች ነው። ወያኔ ጫካ በነበረበት ጊዜ ሲሰኘው ሲያቀጥለው፤ ሲያሻው የአሞሌ መቋጠሪያ ሲያደርገው፤ ሲለው ደግሞ የእግሩ ገንባሌ አድርጎ ሳይሰቀጥጠው – ሲጠቀጥቀው፤ ከዚህም ባለፈ ሳይፈሩ፣ ሳያፍሩ በድፍረት ትዕቢተኛው የወያኔ መሥራች መሪው ሄሮድስ መለስ ዜናዊ በአደባባይ “ጨርቅ” እያሉ መሳለቃቸው የጨለማው ታሪካቸው ክፍለ አካል ሆኖ፤ ዛሬ ደግሞ በሌለ ልብጥ አርቲፊሻል መንጣጣት … አንገት – የለሽነት።

ወያኔ ቀድሞውን የተነሳበት ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያን ማጥፋት በመሆኑ በዚህ ዙሪያ ያሉ ተቋማትን ካላ ምህረት ነው በተከታታይ ከትክቶና ቀጥቶ ለማምከን የሚታገለው። ዛሬም ቢሆን እዬነጠሉ የእሳት እራት የሆኑ አርበኞቻችን በሰንድቅአላማቸው ላይ የማያወላውል ቁርጠኛ አቋም ያላቸው፤ የማይደራደሩም በመሆናቸው ብቻ ነው።

እዚህው ዘሃበሻ ላይ 8ጊዜ የኢትዮጵያ ሰንድቅዓላማችን እንደተቀያዬር የሚገልጽ ጹሑፍ አንብቤያለሁ። ምን ለማለት እንደሆነ ባይገባኝም፤ አስፈላጊነቱም ለአሁን ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ ባይረዳኝም፤ ምን አልባትም ለነገ የጠራ አቋም እንዲያዝ ታስቦበት ሊሆን ስለሚችል ሃቁን ማንጠር ያስፈልጋል። ከወያኔ በፊት በነበረው ጊዜ ሰንድቅዓላማችን ላይ ሌላ የመንግሥት ታካይ ውክል ፍላጎት ቢኖርበትም ሰንድቅዓላማችን በአዋጅ አልታሰረም፤ አልተረሸነም፤ ማዕቀብ አልተጣለበትም፤ አልተቃለለም፤ አልተንቋሸሸም፤ በክፉ ዓይን አልታዬም፤ አልተገላመጠም፤ በወንጀለኝነት ተጠያቂም አልነበረም – አልተገፋም እንዲያውም የሚያበረታታ ተግባር ነበር ሲከወን የኖረው። ክብሩ – ማዕረጉ –  ሙላቱ – ልክ አልነበረውም። ዋቢ ላለው ሀገራዊ ተልዕኮ እራሱ መሪ – ተመራጭ  – አደራጅ – አስተናባሪ – ግንባር ቀደም እንዲሆን ያልታሰረ ንጹህ ነፃነት ነበረው በግርማና በሞገስ ነበር።

በምልሰት የነበረውን ተደማጭነት ሆነ ተቀባይነት ሲገመገም፤ በዬጊዜው ማህሉ ላይ ተጨመረበት የሚበልለት ሰንደቅዓላማ የመንግሥት አካላት በቢሮቸው ከሚያስቀምጡት በስተቀር በዬትኛውም ቦታና ጊዜ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ለመላ ኢትዮጵያ ህዝብ የእትብት ውስጥነት መለያ ረቂቅ መንፈስ የነበረው፤ ለዜጎች የማንነታቸው መግለጫ፣ የሐሤታቸው ማፍኪያ፣ የሃዘናቸው ማስታገሻ – ማጽናኛ፤ እንዲሁም የዕምነታቸው – የአውዳማታቸው ሆነ የባህላቸው አባዎራቸው፤ ዓዕምዳቸው፣ አንጎላቸውና አንገታቸው የአድህኖ ምስላቸው ነበር – የነበረው። ዜጎች የዳር ደንበራቸው ልዩ የክብር ጌጥ አድርገው አምልከውትም ኖረዋል። ይህን በማድረጋቸው ደግሞ አይታሰሩም፤ አይንገላቱም፤ ወይንም አይሰደዱም ወይንም ሰው ሳያይ ሰንደቅዓላማቸውን እንደለበሱ በቂም በቀል አይገደሉም። ሆኖም ተደርጎም አያውቅም። ስለዚህ የዛሬው የበቀል ቅጥቀጣ ምንጩ አንድ ነው ባንዳነት ነው። ኢትዮጵያ በነፃነት ተከብራ መኖሯ፤ ሉዕላዊነቷ ተደንቆ – ደምቆ መኖሩ፤ የአፍሪካ ቀንድ ማዕከል መሆኗ የጎረበጠው የጫካ አራዊት ትናንትም ዛሬም – ነገም ለሰንደቅዓላማችን ጠላትነቱን በዬአጋጣሚው እዬገለጸ ነው።

በምንም ዓይነት መስፈርት በዐጤው ጊዜም ሆነ በዘመን ደረግ የነበረው የሰንድቅዓላማ የመንግሥት የጥበቃና የእንክብካቤ ደረጃ ከባንዳው ወያኔ ጋር ለማነፃፀሪ ማቅረብ በሥጋ የሌለች አንስት ነፍሰጡር መሆን ትችላለች ብሎ የማመን ያህል ነው ለሃቁ የሚርቀው – ለዬትኛውም የማነፃፀሪያው ሆነ ዬማካካሻ ድርድር። … በህግ አምላክ! እንዲህ ከተቀረቀረ መንፈስ ጋር ዬቀደምት ግርማ ሞገስ ከዚህ ጉማማ ዘመን ጋር አይነካካ። ከዚህ ባለፈ እማማ አፍሪካን የነፃነት ወተት አጥትቶ እራሷን ያስቻለ አንቱ ነው – የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ – የቅኔ ሊቃውንቱ። ድንበር አልቦሽ ተወዳጅና ተናፋቂ የበኽረ ነፃነት የጥቁር ዕንቁ አንድምታ ነው ሰንደቅዓላማችን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ።

ይህ ለዚህ ንቁ ትውልድ በእጁ ያለ፤ ክፉና ደግ የሚሰማበት፤ በጎሪጥ የሚታይበት፤ ብሄርተኛ እዬተባለ የሚገለልበትና የሚቀጠቀጥበት በመሆኑ ለቀባሪው አረዱት ይሆናል። ነገ ወያኔ ሊያደርገው የሚችል ቀጣይ ነገር ይኖራል። አንድነታችን እንዲሸረሽር ታስቦ በተዘጋጀው የመርዝ ስሌት ብቀላ ምስል ላይ በህዝብ ድምጽ በጉልበት እንዲጸድቅ ሊያደርገው ይችላል። ማዋጋት – ዕዳ ትቶ ማለፍ የወያኔ ህልሙ ነውና። ባህሪውም ይኼው ነው። ዜጎችን ሰላም መንሳት – ማወክ – መወጠር – መንፈስን ማባካንና ማፈናቀል። ነገር ግን ….  ኢትዮጵውያን ትናንት የሞቱለት ዛሬም የሚሞቱለት ሰንደቅዓላማ ግን መቼውንም ህያው ይሆናል። ይኼው ታሪክ እራሱን ደገመና ደረታቸውን ለጠላት ባሩድ የሰጡ ጀግኖች የወያኔን ምልክት በጀግንነት ከቦታው አወረዱትም። “ … ወደ ኤምባሲው ገብተው የነበሩት ኢትዮጵያውያንም በአሁን ወቅት የኢህአዴግ  መንግስት የሚጠቀምበትን ባለኮከብ ሰንደቅዓላማ በማውረድ የቀድሞውን ታሪካዊ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ለተወሰነ ጊዜ ሰቅለው ከግቢ እስኪወጡ ማውለብለባቸው በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ጠቁመዋል፡፡ https://addismedia.wordpress.com/tag/usa-ethiopian-embassy-tplf-eprdf/” ነገም ይቀጥላል። የናፈቃቸው፤ ዓይናቸው የራበው በተሰደዱበት ሀገርም ሰንደቅአላማችው ከንክብሩ ሲውለበለብ ማዬት ነበርና በጀግንነት ፈጽመው ቆይታቸውን ቀለማም አደረጉት – የዘመናት አብነታዊ ተቋማት። ኑሩልን – ጀግኖቻችን – ኩራቶቻችን።

ይህን በደማችን ውስጥ የሚንቀለቀለውን የብሄራዊ ስሜት መግለጫ ወያኔ ማምከን ፈጽሞ አይችልም። ደምና ሥጋ ነው ለእኛ ሰንደቅዓላማችን። መንገድ ላይ ፊት ለፊት ሰንደቃችን አጊጠንበት ከወያኔ ተላጣፊዎች ጋር ስንገናኝ እንዴት በመንፈሳቸው ላይ ቤንዚን እንደሚያርከፈክፍ ሰንደቅአላማችን የሚያውቀው – ያውቀዋል። የወያኔ ጀሌ መንፈስ ሰንደቃችን ለብሰን ሲዩ የተለበለበ ግንድ ነው የሚመስሉት። አሁንም ይሄን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል። የተሰወረው ጥቃት አውጪ ቦንብ ነውና። ነገ አዲሱ ትውልድ መታጋል ያለበት ምንም ያልተለጠፈበት ዋጋው ከፍና ዝቅ የማይል ዬኢትዮጵያ ሰንድቅዓላማ ብቻ ድምጽና ነፍሱ መሆኑን በድርጊት ለጠላቱ ማሳወቅ አለበት። የትኛውም ዓይነት መንግሥትና ሥርዓት ይፈጠር ከእንግዲህ ቢያንስ የሰንድቅዓላማችን ህልውና ቋሚ መሆን መቻል አለበት። ከዚህ ለሚወጣ ማናቸውም የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ኃይል ቢሆንም ድምጽን መንፈግ ግዴታችን መሆን ይገባዋል። ብሄራዊ ዓርማችን – ምልክታችን – የወልዮሽ ሃይማኖታችን ንጹሑ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ብቻ ይሆናል።

ለዚህ ደግሞ አዲሱ ትውልድ ጀምሮታል – ይቀጥላል። ደግሞ ወግ አይቀርም “ሰንድቅዓላማችን ተደፈረ” ተባለ። የት የሚያውቀውን ነው ወያኔ …. ያ … ጨርቅ እያለ ያላገጠበት፤ ያባጫለው፤ ገድለን ቀብረነዋል እያለ የቅራራበት እኮ ነው። ነገር ግን  ማንነት የትም ቦታ በዬትኛውም ሁኔታ ደም ነውና ጎልቶ ጎልብቶ ገኖ ደምቆ – ይጎመራል።

ትናንት የተፈጠሩ፤ ውጪ ሀገርም ተወልደው ያደጉ የተስፋ ዕንቡጦች ዛሬ ሰንድቅአላማቸው የትኛው እንደሆነ ለይተው በሚገባ ያውቁታል። እንዲህ በተመሰጠ – በድንግልና ጥልቅ መንፈስ እንሆ የነገ የተስፋ ልዕልት፤ የሰባዕዊ መብት ተሟጋቿ፤ የፓን አፍሪካኒስት ሩኽ መንፈስ ያልተለያት እመ – ትጉኋን ሳምራዊት ተሰማ ደግና ገዱን መንገድ ሐዋርያ ሆና እዬሰበከች ነው። ድንግልዬ ትጠብቅልን። ውስጧን አንብቡት የኔዎቹ። ሰንደቋ ታቦቷ ነው – ለትውፊት።

ቀደምት አርበኞች እለሞቱም አሉ። ደጎቹ – ደግን ይኼው ተክተዋል። ዓርማቸውን ከፍ አድርጋ አክብራ የምታስከብር አልማዝ እነሆ ሸልሞናል – አምላካችን። ተመስገን! እልፍ ናቸው ዬሰንደቅዐላማቸው ፍቅር ስፍስፍ ዬሚያደርጋቸው – ቀንበጦቻችን። የኢትዮጵያ ሰንደቅ መንፈስ ነው።  መንፈስ አይሸመትም  – አይበደሩትም። አይታመም – ሞትም ድርሽ አይልበትም። የማይለወጥ ቋሚ የደም ማገር ነውና።

የማከብራችሁ ወገኖቼ – በሀገረ አሜሪካ ሰንደቅዓላማችን እንደዛ ባሩድ ሲነጣጠርበት ማዬቱ እራሱ ይሰቅጥጣል። መታሰቡ እራሱ ያንቀጠቅጣል። ዜጎችን ለመግደል ብቻ ታስቦ አልነበረም የተተኮሰው። ሰንደቅዐላማችን ለመግደል – መንፈሱን ለማቁሰል – ቅስሙን በዓለም አደባባይ ለመስበር – ክብሩን ለማዋረድም ታስቦ ነበር። ግን ፍርዱ የሰው ሳይሆን የሰማይ ሆነና ያላመጠውን ሳይውጥ ወንጀል ፈፃሚው ተጠቅልሎ – ተቀጣበት። የቃልኪዳን ውል እንዲህ ይፈርዳል። ሌላም ይኖራል። ዬሰንድቅዓላማ ስጦታው በሰውኛ ፍቺ አይደፈርም – ከቶውንም። ለ1988 ተፈጠረ ለተባለ ልብድ ምስል አለንለት ብሎ አደባባይ መውጣትም – ዝልቦነት ነው። ማፈር- መሸማቀቅ ሲጋባ እንዲህ ጥጋብን አደባባይ ማውጣት የመጨረሻው እራስን ዬማነቅ ትዕይንት ይሆን – ይሆን? የእኔ ውዶች ፍቱት ወይ ተርጉሙት – አቅም ያላችሁ።

ክብረቶቼ ስንብት እናድርግ፤ የሃሳብ ልዩነትን በሰለጠነ መልክ ማስተናገድ ማለፊያ ነው። ስለሆነም በሁለቱም ወገን የታዬው ትክክል ነው የሚሉ ወገኖች ይኖራሉ። ይህ በሃሳብ ላይ አይደለም። በማንነት ላይ ነበር። ነገር ግን ቅኖች ወገኖቼ ልብ ሊሉት የሚገባው አብይ ጉዳይ በማንነት ላይ ውይይትም ድርድርም የለም። ለማንነት አጀንዳ አይያዝለትም። ስለዚህ በነፃነት ሀገር ሃሳብን በሃሳብ የማታገል መርሁ እንዲህ ተግባራዊ ሲሆን ማዬት መልካም ሆኖ ሳለ፤ በሰንደቅአላማችን የጥይት ሩምታ ጉዳይ ግን ቁርጥ ያለ አቋምና ውሳኔ፤ እንዲሁም የጠራ መስመርም መከተል አለብን። እኛ ብቻ እኮነን በቀደምትነት የሰው ልጅ መፈጠሪያ ሆነን የሚያስማማ ብሄራዊ መዝሙር፣ ሰንድቅአላማና ህገ መንግሥት በዓለም የሌለን ህዝቦች። ይህን መራራ ዘመን ለመዋጀት አለን የሚሉ ድርጅቶች ሁሉ የፍላጎታቸው አስኳል ሊያደርጉት ይገባል – አምክንዮ። በተረፈ የፊታችን ሃሙስ Radio Tsegaye 09.10.2014 የተለመደ ዝግጅት ይኖረዋል። የቻላችሁ እ.ኤ.አ ሰዓት አቆጣጠር ከ15 እስከ 16 ሰዓት ላይ፤ ያልቻላችሁ ደግሞ አርኬቡ ላይ ታገኙታለችሁ ማድመጥ ትችላላሁ – ፈቃዳችሁ ከሆነ። ደህና ሁኑልኝ – ኑሩልኝ።

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

የግንቦት 7 ወታደራዊ ጉዳዮች ቡድን የሕወሓት/ኢሕአዴግ ጀነራል መኮንኖችን ብቃት የገመገመበት ሰነድ ወጣ

$
0
0

Ginbot-7-Top-logo_4

የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በ23 ዓመት ው ያፈራቸው ጄኔራል መኮንኖች  ከወታደራዊ አመራር ይንስ ትምህርት እና ስልጠና አንር ሲመዘኑ

በግንቦት 7  የወታደራዊ ጉዳዮች ቡድን የተዘጋጀ ጥናታዊ ፅሁፍ  ክፍል 1

 

PDF-   የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በ23 ዓመት ጉዞው  ያፈራቸው ጄኔራል መኮንኖች

 

መስከረም 2007 ዓ..

የርዕስ ማውጫ

መግቢያ. 2

1…… የወታደርዊ አመራር ምንነትና ዋና ዋና የአመራር እርከኖች፤. 3

2…… የወታደራዊ አመራር የስልጠና እርከኖችና ወደ ወታደራዊ የትምህርት አካዳሚዎች መግቢያ መስፈርቶች.. 3

2.1. ወታደራዊ አካዳሚ፡ 4

2.2. ሰታፍ ኮሌጅ.. 4

2.3. የአዛዥነት እና የመምሪያ መኮንንነት አካዳሚ… 5

2.4 የጦር ኋይሎች ዋር ኮሌጅ(Armed Forces War College) 6

3…… የመኮንኖች የማዕረግ ዕድገት ሂደት.. 7

4…… የጄነራል መኮንንነት የማዕረግ ዕድገት.. 8

5…… የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮች የሥልጠና ሂደት፤. 10

6…… የአሁኑ  የሀገር መከላከያ መኮንኖች ከወታደራዊ አመራር ሳይንስና ጥበብ አንፃር. 11

7…… ማጠቃለያ. 13

8…… አባሪ ሰነድ- ፩ (Annex-1) 15

 

የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በ23 ዓመት ጉዞው  ያፈራቸው ጄኔራል መኮንኖች

ከወታደራዊ አመራር ሳይንስ ትምህርት እና ስልጠና አንፃር ሲመዘኑ

 

መግቢያ

የኢትዮጵያ ሠራዊት በዘመናዊ መልክ ከተቋቋመበት ከ1927 ጀምሮ  እስክ 1983 ዓ/ም ድረስ ጊዜው በሚጠይቀው ወታደራዊ ሳይንስ የተማሩ፣  ዘመናዊ ክህሎትንና  ሥንምግባርን የተላበሱ እና  በተግባር የተፈተነ ጀግና  የምድር ጦር፣ የባህር ኃይልና የአየር ሃይል ሠራዊትና መሪዎችን  ለማፍራት የቻለ ነበር::  በሂደቱም ሰራዊቱን  ፈታኝ በሆኑ የተለያዬ አውደ ፍልሚያዎች መርተው ለድል ያበቁ ከፍተኛ ወታደራዊ ምሁራንና መኮንኖችን አፍርቶ ማለፉ የሚታወስ ነው::  የማእረግ አሰጣጡም እንዳሁኑ ዘርን መሰረት በማድረግ ሳይሆን የትምህርት ዝግጅትን፣ ወታደራዊ ዲስፕሊንና ሥነምግባርን እንዲሁም በእየእርከኑ ያሳየው ብቃትና ተገቢውን የመቆያ ጊዜ መፈፀሙ ተረጋግጦ፤ ይህንን እንዲያስፈፅም በተዋቀረ ገለልተኛ አካል አቅራቢነት በሀገሪቱ መሪዎች ሹመት ሲሰጥ ኖሯል።
Samora Yenus
ቀደም ሲል በተገለፀው የማዕረግ እድገት አሰጣጥ ሂደት መሠረት በአጠቃላይ ከ1927 እስክ 1983 ሀገሪቱ 293 ጄኔራሎችን አፍርታ ነበር። በሌላ መልኩ ወያኔ የመንግሥት ሥልጣን ከወሰደበት ከ1983 ጀምሮ ዘርንና ታማኝነትን በቻ መሰረት በማደረግ ለ130  የቀድሞ ሽምቅ ተዋጊ መሪዎቹ ከብርጋዲየር እስከ ሙሉ ጄኔራልነት ማዕረግ አድሎአቸዋል። ከትምህርት ዝግጅት አንፃር 97 በመቶ (126ቱ) የሚሆኑት መደበኛ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀትና ከህሎት የሌላቸው ሲሆን ቀሪዎቹ 3 በመቶ የሚሆኑት ተገቢውን የወታደራዊ ሳይንስ የተማሩና በቂ ሙያዊ ክህሎትን ያዳበሩ አራት የቀድሞ ጦር አባላት ብቻ ነበሩ (አሁን ሦስቱ በጡረታ ሲገለሉ አንዱ በፖለቲካ ጉዳይ የተባረሩ ናቸው)። በአጠቃላይ ከነዚህ 130 ጄነራሎች ውስጥ 67ቱ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የሕወሓት አባላት ናቸው።

 

የዚህ ፅሁፍ አጠቃላይ ዓላማ ባለፉት 23 ዓመታት የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ያፈራቸውን ጄኔራል መኮንኖች ከወታደራዊ ሳይንስና ሙያዊ ክህሎት አንፃር መፈተሽና መገምገም ነው። በዚህም መሰረት ይህን መግቢያ (Introduction) ጨምሮ

1ኛ፡ የወታደራዊ አመራር ምንነት እና ዋና ዋና የጦር  አመራር እርከኖች፣

2ኛ፡ የወታደራዊ አመራር የስልጠና እርከኖችና ወደ ወታደራዊ የትምህርት አካዳሚዎች የመግቢያ መስፈርቶች፣

3ኛ፡ የመኮንኖች የማዕረግ እድገት፣

4ኛ፡ የጄኔራል መኮንኖች የማዕረግ እድገት፣

5ኛ፡ የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮች ትምህርትና የሥልጠና ሂደት፣

6ኛ፡ አሁን ያለው የጦር ሃይል መኮንኖች የአመራር ሥልጠናና ብቃት፣

7ኛ፡ ማጠቃለያ ሲሆኑ ከዚህ እንደሚከተለው በቅደም ተከተል ይቀርባሉ።

 

1.    የወታደራዊ አመራር ምንነትና ዋና ዋና የአመራር እርከኖች

 

ወታደራዊ አመራር በተፈጥሮው የሳይንስንና የጥበብን (both Science and Art) ዘርፍ አጣምሮ የያዘና የተከበረ የሙያ መስክ ነው። ይህም በመሆኑ ማንኛውም የጦር ኃይል አባል በአመራር ቦታ ላይ ከመቀመጡ በፊት ዘመኑ የሚጠይቀውን ለየሥልጣን እርከኑ ተገቢ የሆነውን ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ በመማርና እና ስልጠና በመውሰድ (Military Education and Training) በአጥጋቢ ሁኔታ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል።

 

የወታደራዊ አመራር (Military Leadership) ትምህርትና ሙያዊ ስልጠናውም በወታደራዊ የአመራር ንድፈ ሀሳብ ፣ ስትራቴጅና ታክቲክ ትምህርትና የተግባር  ሥልጠናን የሚያካትት ሆኖ መደራጀት ይኖርበታል።

meles and his millteryበጦር ሀይሎች ውስጥ አመራር የሚሰጡ የአመራር አካላት በሁለት ዋና ዋና ደረጃዎች ይከፈላሉ:: እነሱም:-

1.1.   የበታች ሹም (Non Commissioned Officer/NCO)

1.2.  መኮንኖች ናቸው (Commissioned Officers) ናቸው::

የበታች ሹም (Non Commissioned Officer/NCO)፦ የሚባሉት ሰራዊቱን በቅርብ የሚቆጣጠሩ፣ የሚያደራጁ፣ የሚያሰለጥኑ፣ የሚመሩትን ሀይል ለውጊያ የሚያዘጋጁ ከፍተኛ ሀላፊነት ያለባቸው የሰራዊቱ የጀርባ አጥንት ሆነው የሚያገለግሉ መሪዎች ናቸው:: በሰራዊቱ ውስጥ በግንባር መስመር ከበላይ አካል የሚሰጣቸውን ትእዛዝ ተቀብለው በተዋረዱ የሚያዙ የሚያዋጉ እና በየትኛውም የሰራዊቱ ጠቅላይ መምሪያ ውስጥ የስታፍ ስራዎችን በኃላፊነት የሚሰሩ ናቸው:: የአመራር ብቃታቸውንም ለማጎልበትም የወታደራዊ የአመራር ስልጠናም ይወስዳሉ:: በአጠቃላይ የበታች ሹሞች በተዋጊው ሰራዊትና በአመራር መኮንኖች መካከል እንደ ድልድይ ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው::

 

መኮንን (Commissioned Officer/CO)የሚባለው የወታደራዊ አመራር ጥበብን እና የወታደራዊ ስልት ስልጠናን ወስዶ በምድር ጦር፣ በአየር ሀይል (Pilot Officer) በባህር ኃይል (Ensign) በምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግ የተመረቀ(ች) ወይም ከዚያ በላይ እስከ ከፍተኛ ፊልድ ማርሻል ማዕረግ የደረሰ ሁሉ መኮንን ይባላል:: ስልጠና ያልወሰደ ግን መኮንን አይባልም፡፡ አንድ መኮንን በህግ የተሰጠውን ማዕረግና ሀላፊነት ከተቀበለ በኋላ በተመደበበት የጦር ክፍል የሚመራቸውን ክፍሎች ወይም ኃይሎች  በትዕዛዝ፣ በማነቃቃት እና በማግባባት ግዳጃቸውን እንዲፈጽሙ ተጽዕኖ የማድረግ ሀላፊነት አለበት::

 

2.   የወታደራዊ አመራር የስልጠና እርከኖችና ወደ ወታደራዊ የትምህርት አካዳሚዎች መግቢያ መስፈርቶች

 

ማንኛውም የሠራዊቱ አባል መኮንን ለመሆን ከዚህ እንደሚከተለው በተዘረዘሩት መሠረታዊ  የመኮንኖች የአመራር ሳይንስና ጥበብ ሥልጠና ተቋማትና እርከኖች ውስጥ በመግባት ተገቢውን እውቀትና ክህሎት በማዳበር የሚሰጠውን የተግባርና የንድፈ ኃሳብ መመዘኛ በጥሩ ሁኔታ ማለፍና መመረቅ ይኖርበታል።የወታደራዊ አመራር የስልጠና እርከኖችም የሚከተሉት ናቸው፦

2.1.   የእጩ መኮንኖች መሰረታዊ የአመራር ስልጠና

2.2.  የስታፍ ኮሌጅ

2.3.  የአዛዥነትና የመምሪያ መኮንንነት

2.4. የጦር ኮሌጅ ናቸው::

2.1. ወታደራዊ አካዳሚ፡

ይህ አካዳሚ የዕጩ መኮንኖች ማሰልጠኛ ሲሆን ተቋሙ እንደ የሀገሩ እና አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በጦር ኃይሎች ውስጥ እጩ መኮንኖችን መልምሎ ወታደራዊ የአመራር ጥበብና ሳይንስ በማስተማር ሠራዊቱን ለመምራት እና ለማገልገል የሚያዘጋጅና አጥጋቢ ውጤት ያመጡትን  አስመርቆ ወደ ተለያዩ የሠራዊቱ ክፍሎች እንዲሰማሩ የሚያስችል ተቋም ነው፡፡ ወደ አካዳሚው የእጩ መኮንነት ኮርስ መግባት የሚቻለው ከዚህ የሚከተሉት መስፈርቶች ተሟልተው ሲገኝ ብቻ ነው፡፡

ሀ. እድሜያቸው 17 እስክ 23 ዓመት የሆነ (የሆነች)፣

ለ. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን በሚገባ ያጠናቀቁ ሆነው በትምህርት ቤት ቆይታቸው ወቅት ከክፍል ወደ ክፍል በሚሸጋገሩበት ጊዜ በክፍል ውጤት ደረጃቸው ከ1ኛ እስከ 5ኛ የወጡ፣

ሐ. ከፍተኛ የትምህርት ተቋም/ኮሌጅ በዲፕሎማ በጥሩ ሁኔታ የተመረቁ፣

መ. ከዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ወይም የሁለተኛ ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ፣

ሠ. ከሰራዊቱ ውስጥ ከበታች ሹማምንት ውሰጥ ፲ አለቃ እና ከዛ በላይ ሆነው በአካዳሚ እውቀታቸውና ወታደራዊ አመራር ብቃታቸው የተረጋገጠላቸው፡;

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አሟልተው የተመለመሉ እጩ መኮንኖችም በአካዳሚው ውስጥ ከሦስት እስከ አራት ዓመት ለሚሆን ጊዜ  የአካዳሚክ፣ የወታደራዊ ስልቶች፣ መሰረታዊ የአመራር ሳይንስና ጥበብ፣ የአካል ብቃት፣ የሞራል እና የስነ ምግባር ትምህርቶችና የተግባር ሥልጠናዎችን በመማር የብቃት መመዘኛ ፈተናዎችን በአጥጋቢ ሁኔታ ሲያሟሉ እንዲመረቁ ይደረጋሉ፡፡ የብቃት ደረጃ የሚለካባቸው መስፈርቶችም፦ የአካዳሚ ብቃት 55% ፤ የወታደራዊ ብቃት 30% እና የአካል ጥንካሬና የአትሌቲክስ ብቃት 15% ይይዛሉ፡፡ ኮርሱን ሲጨርሱና በምዘናው አጥጋቢ ውጤት ሲያመጡ በመጀመሪ ደረጃ የሳይንስ (Bachelor of Science / B.Sc) ዲግሪና በምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግ  ይመረቃሉ፡፡ በአጠቃላይ አካዳሚው ተመራቂ መኮንኖችን በቆይታቸው ወቅት በሠራዊቱ ውስጥ የአንድ የመቶ ጦር (ኃይል) ለማዘዝ የሚያስችላቸውን  ወታደራዊ የአመራር ጥበብ ትምህርት እና የአካዳሚክስ እውቀት በሚገባ ታጥቀው እንዲወጡና በብቃት እንዲያገለግላሉ ያስችላቸዋል፡፡

2.2. ሰታፍ ኮሌጅ

 

ስታፍ ኮሌጅ ማለት የመካከለኛ መኮንኖች የአመራር ሳይንስና ጥበብ የሚማሩበት ተቋም ነው፡፡ በዚህ ኮሌጅ ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት የወታደራዊ አመራር ትምህርት፣ የአስተዳደር እና የስታፍ መምሪያ መኮንንነት ተግባር እና ሀላፊነት፣ የወታደራዊ ሥነምግባር፣ የወታደራዊ ሙያ ፖሊሲ እና የአካል ብቃት ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡ በኮሌጁም ውስጥ በሁለት ደረጃ የተከፈሉ ሥልጠናዎች ማለትም ጁኒየር እና ሲኒየር ኮርሶች ይሰጣሉ። ወደ እዚህ ኮሌጁ ለመግባት የግድ ማሟላት የሚገባቸው መሰፈርቶች በሲኒየር የሻምበልነት ወይም በሻለቃነት ማዕረግ ሰራዊቱ ውስጥ ግዳጅን መወጣትና  ማገልገል ናቸው፡፡

ሀ. የጁኒየር ኮርስ፡ ይህ ኮርስ ሲኒየር የሆኑና የሻምበል ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች ገብተው የሚማሩበት ፕሮግራም ነው። የሚሰጠውም የኮርስ ይዘት የወታደራዊ አመራር እና የስታፍ መኮንንነት ተግባራትን፣ የወታደራዊ ሥልቶችን እና የአካል ብቃት ሥልጠናን ያካተተ ነው፡፡ ኮርሱም የሚፈጀው ጊዜ ሃያ ሳምንት ሲሆን ኮርሱንም ሲጨርሱ የሻምበል አዛዥ ወይም በሻለቃ መምሪያ ውስጥ በስታፍ መኮንንነት የኃላፊነት ቦታ ይሰራሉ፡፡

ለ. የሲኒየር ኮርስ፡ ይህ ኮርስ ጁኒየር የሆኑ የሻለቃ ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች የሚሳተፉበት ኮርስ ነው፡፡ ትምህርትና የሥልጠናውም ይዘት ወታደራዊ የአመራር ሳይንስና ጥበብ፣ የወታደራዊ ሥልጠናዎች፣ የአስተዳደር እና የሎጂስቲክ ትምህርቶች፣ የስታፍ መኮንንነት ተግባር እና ኋላፊነት እና የአካል ብቃት ሥልጠናዎችን ያካትታል፡፡ የኮርሱም የቆይታ ጊዜ አንድ ዓመት ነው፡፡

መኮንኖቹ ኮርሱን ሲጨርሱ የሻለቃ አዛዥ ወይም በብርጌድ መምሪያ ውስጥ የስታፍ መኮንን ሆነው ያገለግላሉ፡፡ በአጠቃላይ የስታፍ ኮሌጅ ሥልጠና የጨረሱ መኮንኖች የሚሰጣቸው የትምህርት ማስረጃ  ዲፕሎማ ነው፡፡

2.3. የአዛዥነት እና የመምሪያ መኮንንነት አካዳሚ

 

ይህ አካዳሚ ሲኒየር ሻለቃዎች እና ሌ/ኮሌኔሎች በመቀበል ለከፍተኛ አመራር ሰጭነት  የሚያስተምር ተቋም ነው፡፡ ወደ አካዳሚው የመግቢያ መስፈርቱም  የጁኒየር እና የሲኒየር ስታፍ ኮሌጅ ኮርሱን ካጠናቀቁ መኮንኖች ውስጥ በአመራር ስጭነታቸውና በስነምግባራቸው የሚመረጡ ይሆናል፡፡ ኮርሱም በዋነኝነት  በወታደራዊ የአመራር ጥበብ፣ ፍልስፍና፣ በወታደራዊ ታሪክ፣ በወታደራዊ ሥልቶች፣ እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት እና የአካል ብቃት ትምህርቶች ያተኮረ ሆኖ ከ10-12 ወራት የሚሆን ጊዜን ይፈጃል፡፡ ኮርሱን አጠናቅቆ ለመጨረስ እንዲያስችላቸው  የመመረቂያ ጥናታዊ ፅሁፎችን አዘጋጀቶ ማቅረብና አጥጋቢ ውጤት ማምጣት ያስፈልጋል፡፡ መኮንኖቹም ትምህርታቸውን ሲጨርሱ በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ የማስተርስ (Master of Military Arts and Sciences) ዲግሪ ይሰጣቸዋል፡፡ ከሥልጠናው በኋላም የሥራ ኋላፊነታቸውም የሻለቃ ወይም የብርጌድ አዛዥ ወይም በክ/ጦር (በዕዝ) መምሪያ ውስጥ የመምሪያ መኮንን በመሆን ያገለግላሉ፡፡ መኮንኖቹ ከተመረቁና በያዙት ማዕረግ የተወሰነ አገልግሎት ከሰጡ በኋላ በዚሁ አካዳሚ ውስጥ እንደገና ሁለት ኮርሶችን ይወስዳሉ፡፡

እነዚህም፦

ሀ/ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥናትና

ለ/ የዕዝ አዛዥነት

እነዚህ ኮርሶች በዋናነት የሚያተኩሩት በወታደራዊ ስትራቴትጂክ ጉዳዮች እና የዕዝ አዛዥነት ንድፈ ሀሳብ ላይ ነው፡፡ ኮርሱንም ሲጨርሱ የወታደራዊ ዕቅድ ነዳፊዎች (Strategic Military Planners) ሆነው ይመደባሉ፡፡

 

2.4 የጦር ኋይሎች የጦር ኮሌጅ (Armed Forces War College)

 

ይህ ተቋም  በወታደራዊ የሥልጠና እርከን ውስጥ የመጨረሻው የስትራቴጂክ አመራር ሥልጠና (Strategic Leadership Training) የሚሰጥበት የጥናት እና የምርምር ማዕከል ነው፡፡ በዚህ ተቋም ውስጥ የኮርሱ ተሳታፊዎች የሚሆኑት በምድር ኋይል፣ በአየር ኋይል፣ እና በባህር ኋይል ውስጥ ስትራቴጂክ አመራር (Strategic Level Leaders) እየሰጡ ከሚገኙት እና   ከከፍተኛ ስቪል የመንግስት ባለስልጣናት ውስጥ ቢያንስ ማስተርስ ዲግሪ ያላቸውን ፖሊሲና እስትራቴጂ አውጪ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉትን በመቀበል ለከፍተኛ የሥልጣን ቦታ እና ሀላፊነት የሚያዘጋጅ የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ጥናት እና ምርምር ተቋም ነው፡፡

እንደ ተለያዩ ሀገሮች ተጨባጭ ሁኔታ በጦር ሀይሎቻቸው ውስጥ እራሳቸውን የቻሉ የምድር ሀይል የጦር ኮሌጅ፣ የአየር ሀይል የጦር ኮሌጅ እና የባህር ሀይል የጦር ኮሌጅ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ሆኖም በወታደራዊ የሥልጠና እርከን መሰረት ሁሉም ሀይሎች አመራር መኮንኖቻቸውን በየራሳቸው የጦር ኮሌጅ ትምህርታቸውን ካስጨረሱ በኋላ ወደ ዋናው የጦር ኃይሎች የጦር ኮሌጅ ገብተው እንዲሠለጥኑ ያደርጋሉ፡፡

ወደ ጦር ኋይሎች የጦር ኮሌጅ ለመግባት በቅድሚያ መሟላት ያለበት፦

  1. የአዛዥነትና የመምሪያ መኮንንነት ኮርስን መጨረስ፣
  2. በጦር ኃሎች የጦር ኮሌጅ የሚሰጠውን ኮርስ መጨረስ፣
  3. በሠራዊቱ ውስጥ በአመራር ሰጭነት ከ 22 ዓመት በላይ ማገለገል፣
  4. በወታደራዊ ሥነምግባር ምንም ችግር የሌለበትና፣
  5. የአካል ብቃቱ በሀኪም የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡;

ከላይ የተጠቀሱት መሠረታዊ መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆነው ወደ ጦር ኋይሎች የጦር ኮሌጅ የሚገቡት ለብርጋዲየር ጄኔራልነት የሚታጩ ስለሆነ በምድር ኃይል በሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ በአየር ኋይል ተመጣጣኝ በሆነው Group Captain እና በባህር ሀይል ደግሞ ካፒቴን (Captain) በአጠቃላይ ሁሉም በኮሎኔል ማዕረግ ደረጃ ሆነው በማገልገል ያሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

የኮርሱም ተሳታፊዎች መጠንም 75 በመቶ ከጦር ኋይሎች ከሦስቱም ኃይሎች ተመጣጣኝ ቁጥር ያላቸው ከፍተኛ መኮንኖችን እና 25 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከሲቪል የመንግስት ባለስልጣናት፣ ከሀገር ውስጥ ጉዳይ፣ (በአሁኑ የፌደራል ጉዳዮች)  እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ተመርጠው እንዲሣተፉ ይደረጋል፡፡ ኮርሱም የሚያተኩርባቸው ርዕሰ ጉዳዮችም የስታራቴጂክ አመራር ጥበብ፣ የብሔራዊ ደህንነት ስትራቴጂ ጥናት (National Security Strategy)፣ የግጭት ማስወገድ ጥናቶች (Conflic Resolution Research)፣ የህብረት ጥምር ውጊያ ፍልስፍና (War Games) እንዲሁም የጥናት እና ምርምር ንድፈ ሀሳብ ትምህርት የሚሰጥበት ማዕከል ነው፡፡ መኮንኖቹ ትምህርቱን ሲጨርሱም በስትራቴጂ ጥናት የማስተርስ ዲግሪ (Master Degree in Strategic Studies) ደረጃ  ይመረቃሉ፡፡ በጦር ኋይሎች ውስጥም የኮር ወይም የዕዝ አዛዥ ወይም በሀገር መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ የመምሪያ መኮንነት የሥራ ኋላፊ ሆነው እንዲሠሩ ይደረጋል። በጦር ሀይሎች የጦር ኮሌጅ ውስጥ ትምህርታቸውን ጨርሰው የተመረቁ መኮንኖች ምንም አይነት የዲሲፕሊን ችግር ሪከርድ የሌለባቸው ከሆነ በቀጥታ የብርጋዴር ጄኔራልነት ማዕረግ ይሰጣቸዋል፡፡ በአጠቃላይ ከላይ የተቀመጠው  መሠረታዊ የሆነው የመኮንኖች የአመራር ጥበብ ስልጠና ሂደት ከዕጩ መኮንነት ኮርስ እስከ ጦር ኮሌጅ የሚዘልቅና መንገዱም ሌላ አቋራጭ  የሌለው ረዥም እና አስቸጋሪ ውጣ ውረድ የበዛበት መሆኑን ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ ይህንን ረጅም መንገድ ያለፉ መኮንኖች ሁሉ የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት የተወጡ ስለመሆናቸው ያለፉት ታላላቅ አውደ ውጊያዎች(በምስራቅና በሰሜን ኢተዮጵያ) ምስክርና ማስረጃዎች ናቸው፡፡

 

3.    የመኮንኖች የማዕረግ ዕድገት ሂደት

 

የመኮንኖች የማዕረግ ዕድገት መነሻውም ሆነ መድረሻው ወታደራዊ ትምህርትና ሥልጠና ነው፡፡ የወታደራዊ አመራር ሳይንስ ጥበብ ደግሞ ለመኮንነት ማዕረግና ዕድገት የማዕዘን መሰረተ ድንጋይ ሲሆን በአጠቃላይ የመኮንነት የማዕረግ  ዕድገት በሥልጠና እየታገዘ የሚከናወን ቀጣይነት ያለው ሂደት  ነው፡፡ መኮንን ለመሆን በቅድሚያ የዕጩ መኮንንነት ኮርስ ወስዶ በሚገባ ማጠናቀቅን ይጠይቃል። የአንድ መኮንን የመጀመሪያው ማዕረግም በምድር ሀይል ምክትል መቶ አለቃ (Second Lieutenant) በአየር ሀይል ፓይለት መኮንን (Pilot Officer) በባህር ሀይል ደግሞ ኢንሳይን (EnSign ) ይባላል፡፡ ምክትል መቶ አለቃ ሆኖ የተመረቀ መኮንን ወደ ሚቀጥለው የማዕረግ ዕድገት ለማለፍ የግል ሪፖርቱ ተገምግሞ ምንም ዓይነት የዲሲፕሊን ችግር ከሌለበት በምድር ሀይል ሙሉ መቶ አለቃ (Lieutenant) በአየር ሀይል በራሪ መኮንን (Flying Officer) በባህር ሀይል ምክትል ሊዩተናንት (Sub – Lieutenant) ይሆናል ፡፡ በሙሉ መቶ አለቃ ማዕረግ ደግሞ አምስት ዓመት ካገለገለ በኋላ የሻምበልነት ማዕረግ ያገኛል፤ በሻምበል ማዕረግ ደግሞ አራት ዓመት ማገልገል አለበት፡፡ በአራት ዓመት የቆይታ ወቅትም የስታፍ ኮሌጅ ኮርሱን ካጠናቀቀና በቆይታ ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበው የወታደራዊ ዲሲፕሊን እና የሙያ ብቃቱ ተረጋግጦ በበቂ ሁኔታ ከአለፈ የሻለቃነት ማዕረግ ዕድገት ይሰጠዋል፡፡

በሻለቃ ማዕረግ የቆይታ ጊዜ አራት ዓመት ሲሆን  በአራት ዓመት ውስጥም የአዛዥነትና የመምሪያ መኮንንነት ኮርስ ይወስዳል፡፡ የሻለቃ የማዕረግ ቆይታውን ሲጨርስ በሠራዊቱ ሕገ ደንብ መሰረት በዋንኛነት የወታደራዊ ዲሲፕሊኑ፣ የአመራር ብቃቱ፣ በተዋረድ የወሰደው የወታደራዊ አመራር ስልጠና እና በቆይታው ጊዜ ባስመዘገበው ሪፖርት ተመስርቶ ይገመገምና ወደ ሚቀጥለው የማዕረግ ዕድገት የሚያልፍ ከሆነ የሌ/ኮሎኔል ማዕረግ ይሰጠዋል፡፡ የሌ/ኮሎኔል ማዕረግ ቆይታ አራት ዓመት ሲሆን በአራት ዓመት ቆይታው ወቅት የሚወስዳቸው ኮርሶች የአዛዥነትና የመምሪያ መኮንንነት ኮርስ እንዲሁም የምድር ኃይል ወይም የአየር ኃይል የጦር ኮሌጅ የአመራር ጥበብ ሥልጠናን ወስዶ ከጨረሰና በቆይታ ጊዜውም ውስጥ ምንም ዓይነት የዲሲፕሊን ችግር ከሌለበት የሙሉ ኮሎኔልነት ማዕረግ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

ከሙሉ ኮሎኔልነት ማዕረግ ወደ ቀጣዩ ማዕረግ ለማደግ ቢያንስ የአራት ዓመት የቆይታ ጊዜ ያስፈልጋል ፡፡ በአራት ዓመት የቆይታ ጊዜ ውስጥም የጦር ኃይሎች የጦር ኮሌጅ በመግባት የስትራቴጂክ የአመራር ጥበብ መውሰደና መመረቅ ይኖርበታል:: ኮርሱንም ከጨረሰ በኋላ በቀጥታ የወሰደው የአመራር ሥልጠና እርከን፣ የአመራር ብቃቱ እና አጠቃላይ የ22 ዓመት የአገልግሎት የቆይታ ሪፖርት ተገምግሞ ከአለፈ የብ/ጄነራልነት የማዕረግ ዕድገት ይሰጠዋል፡፡ ትክክለኛ የመኮንኖች የማዕረግ እድገት አሰጣጥ ሂደትና ይዘት ከላይ በተጠቀሰው የትምህርት፣ የስልጠና፣ የሥነምግባር አፈፃፀም ግምገማ  ውጤትን መሠረት ባደረገ መንገድ የሚከናወነው ብቻ ነው፡፡

 

4.    የጄነራል መኮንንነት የማዕረግ ዕድገት

 

የጄነራል የመኮንነት የማዕረግ ዕድገት መሰረታዊ የትምህርትና ሥልጠና ዝግጁነቶች እንደተጠበቁ ሆኖ በየሀገሩ ተጨባጭ ሁኔታ  መሰረት  ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ ያህል በአሜሪካ የጦር ኋይሎች ውስጥ የጄነራልነት ሹመት በፕሬዘዳንቱ አቅራቢነት በህግ መወሰኛው ምክር ቤት ይጸድቃል፡፡ በሌሎች ሀገሮች ግን የጄነራልነት ሹመት የሚካሄደው በመከላከያ ሚኒስቴር በሚቋቋመው የማዕረግ ዕድገት ቦርድ ወይም በመከላከያ ካውንስል በተቋቋመው በሰራዊቱ ህገ ደንብ መሠረት መመዘኛውን ያሟሉ ተመርጠው ለሀገሪቷ ፕሬዘዳንት ቀርቦ ይጸድቃል፡፡

የጄነራል መኮንንነት ማዕረግ ከፍተኛው የወታደራዊ ማዕረግ እርከን ሲሆን በጦር ኋይሎች ( በምድር ኃይል፣ በአየር ኃይል እና በባህር ኃይል) ከፍተኛውን ኃይል የሚመሩ ወይም የሚያዙ፣ ሠራዊቱን የሚያደራጁ፣ የሠራዊቱን ህግ ደንብ የሚያወጡ፣ ሠራዊቱ የሚዋጋበትን የጦርነት ህግ እና ሠራዊቱ የሚሰለጥንበትን የሥልጠና ፖሊሲ፣ የወታደራዊ ዶክትሪን እና ስትራቴጂ የሚቀርጹ፤ በአካዳሚም ሆነ በወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብ የተካኑ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው የጦር ኃየሎች ጄነራል መኮንኖች ናቸው፡፡

 

ሰንጠረዥ-ሀ፦ የጄነራል መኮንኖች የማዕረ አጠራር በተለያዩ የጦር ኃይል ክፍሎች

ተ.ቁ

በምድረ ኃይል

በአየር ኃይል

በባህር ኃይል

1

Brigadier General Air Commodore Commodore

2

Major General Air Vice Marshal Rear Admiral

3

Lieutenant General Air Marshal Vice Admiral

4

Full General Air Chief Marshal Admiral

5

Marshal or Field Marshal Marshal Air Forces Admiral of the fleet

 

ሀ. ብርጋዴር ጄነራል፡ ይህ ማዕረግ ከሙሉ ኮሎኔል ቀጥሎ የሚሰጥ ሲሆን የጄነራል መኮንኖች የመጀመሪያ ማዕረግ ነው፡፡ ከሙሉ ኮሎኔልነት ወደ ብርጋዴር ጄነራልነት ለመሸጋገር መመዘኛዎቹ፡

1)    በኮሎኔልነት ማዕረግ የአገልግሎት ዘመን፣

2)   የወታደራዊ የአመራር ጥበብ በተዋረድ የወሰደ፣

3)   በአገልግሎት ዘመኑ ያሳየው ዲሲፕሊን፣

4)   የወታደራዊ አመራር ብቃቱ እና ልምዱ፣

5)   በብ/ጄነራልነት ማዕረግ ሊሰራበት የሚችልበት የሥራ ቦታ ክፍት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

ብርጋዲር ጄነራል ማዕረግ ያለው መኮንን በጦር ኃይሎች የብርጌድ ወይም የክፍለ ጦሩ አዛዥ እንዲሁም የኮር እስታፍ ይሆናል፡፡ በያዘው ማዕረግም ከሁለት እስከ አራት ዓመት ያገለግላል፤ የጡረታ ጊዜውም በያዘው ማዕረግ አምስት ዓመት ከቆየና 30 ዓመት የአገልግሎት ዘመን ከሞላው ጡረታ ይወጣል፡፡ የጡረታ የዕድሜ ጣራውም 62 ዓመት ይሆናል፡፡

 

ለ.ሜጀር ጄነራል፡ ይህ ማዕረግ ከብ/ጀኔራል ማዕረግ ቀጥሎ ያለ ባለ ሁለት ኮከብ ማዕረግ ነው፡፡ ከብ/ጀ ወደ ሜ/ጀኔራል የማዕረግ ዕድገት ለመሸጋገር በቅድሚያ ፡-

  • ክፍት የስራቦታ መኖሩ (Number of Open Positions) ፣
  • በአመራር ብቃት የፈጸማቸው ግዳጆች፣
  • በወታደራዊ ሥነ ምግባር ምንም ችግር የሌለበት፣
  • የአመራር የሥልጠና እርከን በተዋረድ የወሰደ፣
  • የአገልግሎት የቆይታ ጊዜውን (Years of Services) የጨረሰ መሆኑ መታየት ይኖርበታል።

መኮንኑ ሜ/ጀኔራል ከሆነ በኋላ የሥራ ኃላፊነቱም የክፍለ ጦር ወይም የዕዝ አዛዥ ወይም በጦር ኃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ውስጥ የመምሪያ መኮንን ሆኖ መሥራት ነው፡፡ በያዘው ማዕረግም እስከ አምስት ዓመት ከአገለገለ በኋላ ወይም 35 ዓመት በጦር ኃይሎች ውስጥ አገልግሎት ከሰጠ ጡረታ ይወጣል፡፡ የጡረታ ዕድሜውም 62 ዓመት ነው፡፡ ከዕድሜው ጣራ ውጭ በተለየ ሁኔታ በሥራ አስፈላጊነት አራት ዓመት በተጨማሪ የመስራት አማራጭ አለው፡፡ እድሜውም እስከ 64 ዓመት ሊዘልቅ ይችላል፡፡

 ሐ. ሊዩተናንት ጄኔራል፡ ይህ ማዕረግ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ባለ ሦስት ኮከብ ከፍተኛ የጀኔራልነት ማዕረግ እርከን ነው፡፡ አንድ መኮንን ወደ ሌ/ጀኔራልነት ማዕረግ ከመድረሱ በፊት በጦር ኃይሎች ውስጥ በአመራር ከ 20 ዓመት ያልበለጠ አገልግሎት መስጠት አለበት፤ ከሜ/ ጀኔራል ማዕረግ ወደ ሌ/ጄነራል ማዕረግ ለመሸጋገር መሟላት ያለበት የአመራር ብቃቱ፣ በያዘው ማዕረግ የቆይታው ጊዜ፣ በወታደራዊ ሥነ-ምግባር ምንም አይነት ችግር የሌለበት፣ የአመራር የሥልጠና እርከኖችን ያለፈ፣ እና ክፍት የሥራ ቦታ መኖሩ ናቸው፡፡ ሌ/ጀኔራል ከሆነ በኋላ የሥራ ኃላፊነቱም የኮር ወይም የግንባር ወይም የህብረት የጥምር ጦር አዛዥ እና በሀገር መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ፣ የመምሪያ መኮንን ሆኖ ማገልገል ነው፡፡ መኮንኑ በያዘው ማዕረግ ቢያንስ ሦስት ዓመት ማገልገል አለበት ነገር ግን በያዘው ማዕረግ አምስት ዓመት ከአገለገለ እና በጦር ሀይሎች ውስጥም 40 ዓመት ካገለገለ በጡረታ ይገለላል፤ የዕድሜ ጣሪያውም 62 ዓመት ይሆናል፡፡

 

መ. ጄኔራል፡ ይህ ማዕረግ ከሌ/ጄነራል ቀጥሎ ከፊልድ ማርሻል  ዝቅ ያለ ባለ አራት ኮከብ ማዕረግ ሲሆን በጦር ኃይሎች ማዕረግ አሰጣጥም ከፍተኛው የሹመት እርከን ነው፡፡ ከሌ/ጀኔራልነት ወደ ሙሉ ጀኔራልነት የማዕረግ እድገት ለመሸጋገር በቅድሚያ ክፍት የስራ ቦታ ሲኖር፣ በጦር ሀይሎች ውስጥም 20-23 ዓመት ያገለገለ፣ የአመራር ብቃት እና ልምዱ ስኬታማ የሆነ፣ በወታደራዊ ሥነ ምግባሩም ምንም ዓይነት እንከን የሌለበት፣ ለአመራርነት የሚሰጠውን ከፍተኛ የሳይንስና የጥበብ ሥልጠና እርከኖችን በተዋረድ የጨረሰ መሆን ይኖርበታል፡፡ የሙሉ ጀኔራል የኋላፊነት ቦታም በጦር ኃይሎች ውስጥ የምድር ጦር ወይም የአየር ኃይል አዛዥ ወይም የህብረት ዕዝ አዛዥ ወይም የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ወይም የጦር ኃይሎች አዛዥ ሆኖ መሥራትን ያጠቃልላል፡፡ በያዘው ማዕረግ ቢያንስ አምስት ዓመት ያገለገለ ሆኖ በጦር ሀይሎች ውስጥ ያበረከተው የአገልግሎት ጣራ  40 ዓመት ከሞላ ጡረታ ይወጣል፡፡ የዕድሜ ጣሪያውም 64 ዓመት ይሆናል፡፡

የአንድ ሀገር የጦር ኃይል (የምድርኃይል፣ የአየር ኃይል፣ የባህር ኃይል) ከዚህ በታች በተጠቀሱት  ሦስት አይነት የአመራር ደረጃዎች  ማለትም፦

  1. በቀጥተኛ የግንባር መስመር አመራር መኮንኖች
  2. በከፍተኛ አመራር መኮንኖችና
  3. በስትራቴጂክ አመራር መኮንኖች የተደራጀ መሆን ይኖርበታል፡፡

በሰራዊቱ ውስጥ ጄነራል መኮንኖች የሆኑ ሁሉ የሥትራቴጂክ አመራር አካል ናቸው፡፡ አንድ መኮንን የብ/ጄነራል ማዕረግ ለመድረስ 22 ዓመት ማገልገል አለበት ከዚህ ውስጥ ከ7-8 ዓመታት ያለው ጊዜ የወታደራዊ የአመራር ጥበብ ሳይንስ የሚቀስምበት የዕውቀት ጉዞ መንገድ ነው፡፡

በአጠቃላይ የጄነራል መኮንኖች የወታደራዊ አመራር ጥበብ ሥልጠና መነሻው መሰረታዊ ከሆነው ከዕጩ መኮንንነት የሥልጠና እርከን ተነስቶ እስከ መጨረሻው የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ትንተና ጥናት እና ምርምር ተቋም እስከ ሆነው የጦር ኮሌጅ ድረስ ይዘልቃል፡፡ የአመራር የሥልጠና እርከኖችን ያላለፈ ጄኔራል የተሟላ ተክለ ሰውነት እንደሌለው ይታሰባል ወይም ይቆጠራል፡፡

 

5.    የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮች የሥልጠና ሂደት፤

 

በሀገራችን የመከላከያ ሠራዊት ታሪክ ውስጥ የወታደራዊ ትምህርትና ሥልጠና ከፍተኛ ቦታ እና ትኩረት ነበረው፡፡ በቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት የነበረው የመከላለከያ ሚኒስቴር ሁለት የጦር አካዳሚ ትምህርት ቤቶች ነበሩት፡፡ እነዚህም የሐረር ጦር አካዳሚና የሆለታ ገነት ጦር ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡ የሆለታ ገነት ጦር ትምህርት ቤት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በትንሽ ዓመት ቆይታ የተቋቋመ በርካታ ብርቅዬ የጦር መኮንኖችን በጥራት ያስመረቀ ተቋም ነው፡፡ ትምህርት ቤቱ ከ1ኛ ኮርሰ እስከ 54ኛ ኮርስ ድረስ መኮንኖችን ያስመረቀ ቢሆንም በደርግ ጊዜ በነበረው የርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የማሰልጠን ሥራውን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ማካሄድ ተስኖት ነበር፡፡

የሐረር ጦር አካዳሚ እ.ኤ.አ 1957 ከተቋቋመ አንስቶ እስከ ተዘጋበት 1977 ድረስ በርካታ መኮንኖችን አስመርቋል። አካዳሚው ለጎረቤት ሀገሮች ጭምር መኮንኖችን ያሰለጥን ነበር፤ ሁለቱም የጦር ትምህርት ቤቶች አለም ዓቀፍ የአመራር ስልጠና መመዘኛ ስታንዳርድን በጠበቀ መልኩ ተደራጅተው ብዙ አመራሮችን አሰልጥነው በማስመረቅ ለሃገሪቱ አበርክተዋል፡፡ ከእነዚህ የጦር አካዳሚ ት/ቤቶች ከተመረቁ መኮንኖች ውስጥ ከምክትል መቶ አለቃነት  እስከ ሌ/ጀኔራልነት ማዕረግ የደረሱ ይገኙበታል፡፡እነዚህ ጄኔራል መኮንኖች በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ የተካኑና በሥነምግባር የታነፁ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የተማሩ ከፍተኛ ብቃት እና ችሎታ ያላቸው ሀገራቸውን በወታደራዊ መስክ ያስጠሩ ብርቅዬ የኢትዮጵያ የሀገር መመኪያ ልጆች ነበሩ፡፡ የሐረር ጦር አካዳሚ  ከ1ኛ ኮርስ እስከ 21ኛ ኮርስ ድረስ በማስተማር አስመርቋል፡፡

 

በወቅቱ የነበሩት የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ጦር ኃይሎች የመከላከያ ሥልጠና ፖሊሲ በሚያዘው መሠረት ወታደራዊ የአመራር ጥበብና ሳይንስ በተገቢው ሁኔታ ከዕጩ መኮንን ሥልጠና እስከ ስታፍ ኮሌጅ ድረስ የዘለቁ 293 ጄነራል መኮንኖች ነበሩት(ሰንጠረዥ-ለን ይመልከቱ)።

ሰንጠረዥ–ለ፦ በሦስቱም መንግሥታት የተሾሙ ጄነራል መኮንኖች (1927–2007 ዓ/ም)

.

የማ ደረጃ

1927 እስከ 1983

ከ1983 ጀምሮ

ጠቅላላ ድምር

ኃይለ ሥላሴ

ርግ

ህወሓት/ ኢህአዴግ

1

ጄኔራል

0

0

1

1

2

ሌ/ጄኔራል

15

3

6

24

3

ሜ/ጄኔራል

6

32

24

62

4

ብ/ጄኔራል

63

174

99

336

ጠቅላላ ድምር

84

209

130

423

 

 

በአጠቃላይ እነዚህ ጄኔራል መኮንኖች በዚህ ጽሁፍ ዋና አካል ላይ የተቀመጡትን የወታደራዊ አመራር ሥልጠና እርከኖች ይዘት እና ሂደት አሟልተው የተመረቁና በተግባር በጦር ሜዳ ውሎአቸውም አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ እንደነበሩ ድርሳናቸው ያስረዳል፡፡

6.    የአሁኑ  የሀገር መከላከያ መኮንኖች ከወታደራዊ አመራር ሳይንስና ጥበብ አንፃር

 

የዛሬው የሕወሓት ሰራዊት ከሽምቅ ተዋጊነት በቀጥታ መደበኛ የሀገሪቱ ሠራዊት እንዲሆን በምድር ሀይልና በአየር ሀይል ተከፋፍሎ  እንዲደራጀ የተደረገ ሲሆን ሠራዊቱን እንዲመሩ የተመደቡት የበታች ሹሞችና መኮንኖች በሙሉ በምንም ዓይነት ወታደራዊ የአመራር ስልጠና ውስጥ ሳያልፉና ከወታደራዊ ሙያ ሳይንስና  ሕግጋት ውጭ በዘርና በፖለቲካ ወገንተኝነት ላይ በመመሥረት ማዕረግ በጅምላ የተሰጣቸው ናቸው:: ይህ ደግሞ በሀገሪቷ መጥፎ የታሪክ ጠባሳ እየጣለ ይገኛል።

በወታደራዊ የአመራር ስልጠና ታሪክ ያለምንም የአመራር ስልጠና የጄነራል መኮንነት ማዕረግ የሰጠች የመጀመሪያ አፍሪካዊት አገር ኢትዮጵያ ነች:: ሕወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ከ1983 ጀምሮ እስከ 2006 ዓ.ም. ድረስ ለ130 አባሎቹ (ለዝርዘሩ አባሪ ፩ን ይመልከቱ)  የጄኔራል መኮንነት ማዕረግ የሰጠ ሲሆን 97 በመቶ የሚሆኑት ተሿሚዎችም በምንም ዓይነት የወታደራዊ አመራር ሳይንስና ጥበብ ስልጠና ውስጥ ያላለፉ ናቸው። ወደ 52 በመቶ (67ቱ) የጄኔራል መኮንንነት ቦታም የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የህወሓት አባላት ተቆጣጥረውታል (ሰንጠረዥ-ሐን እና ሥዕል-አንድን ይመልከቱ)::

 

በአጠቃላይ ከላይ በሥዕሉና በሠንጠረዡ እንደተመለከትነው፤ ሂደቱ የሀገሪቱን የወታደራዊ ስልጠና ገጽታን ከማበላሸቱም በላይ መጥፎ የታሪክ ጠባሳ እየጣለ ይገኛል:: በሚገርም ሁኔታ የሀገር መከላከያ የስትራቴጂክ አመራር እንዲሰጡ በህዋሓት የተሾሙ ጄነራል መኮንኖች  መሰረታዊ የሆነውን የአመራር ስልጠና እንኳን ያልወሰዱ እና የአካዳሚክስ እውቀታቸው በጣም ዝቅተኛና በአብዛኛው ከ5ኛና ከ9ኛ ክፍል ያላለፈ መሆኑን የግል ሕይወት ታሪካቸው ያሳያል።

አንድን ሠራዊት ለመምራትም ሆነ ለማሰልጠን ቀድሞ ሰልጥኖ መገኝት ጥያቄ ውስጥ ሊገባና ሊጣስ የማይችል መርህ ነው:: የህወሓት መንግስት ከፈጸመው አስከፊ ወንጀል አንዱ ምንም ዓይነት የወታደራዊ አመራር ትምህርትና ስልጠና ሳያገኙ ጄነራል ብሎ በመሰዬም ሠራዊት እንዲመሩ ማድረጉ ነው:: የአሁኑ ጄኔራል መኮንኖች በአካዳሚክስም ሆነ በወታደራዊ ሳይንስና የአመራር ጥበብ ድህነት የተጎዱ፣ ጫካ በነበሩበት ወቅት መደበኛ ባልሆነ የሽምቅ ውጊያ ዕውቀት ብቻ ተኮፍሰው የኖሩ አሁንም በዚያው መንገድ የሚጓዙ ናቸው::

የህወሓት ጄነራል መኮንኖች  ስለወታደራዊ አመራር ጥበብ ስልጠና ምንነትና ይዘት እንዲሁም  ሂደት  ምን እንደሆነ ግንዛቤ የሌላቸውና የማወቅ ፍላጎት የሌላቸው ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት በአስተርጓሚ እንዲማሩ ተሞክሮ ነገር ግን ሳይሳካ መቅረቱ በተጨባጭ የሚታወቅ ነው፡፡ ምክንያቱም “አሁን እኛ ጄነራል መኮንኖች ስለሆንን አንማርም ምን ያደርግልናል” በሚል ነበር።  በአሁኑ ወቅት ሠራዊቱ እየተመራ ያለው በእነዚህ ዓይነት ሰዎች ነው! የሚገያስርመው ነገር በሚመሩት ሰራዊት ወስጥ የሚገኙ የመካከለኛ እና የዝቅተኛ አመራር መኮንኖች በወታደራዊ የአመራር ስልጠና ንድፈ ሀሳብም (Theory) ሆነ ተግባራዊ ስራዎች አለቆቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ይበልጧቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት እድሉ ቢሰጣቸው እነዚህን ጄኔራሎች በብቃት መልሰው ሊመሯቸው የሚችሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የወታደራዊ ሳይንስ ንድፈ ሀሳብ (theory) እንደሚያሳየው አንድ ወታደር መኮንን የሚባለው የአመራር ጥበብ በመውሰድ በተገቢ ሁኔታ ካጠናቀቀ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ንድፈ ሀሳብ  አንፃር ለህወሓት ጄኔራል መኮንኖች ምን ስም ቢሰጣቸው ይመጥናቸዋል? የበታች ሹም ቢባሉ፣ ለበታች ሹምነት ማዕረግ የሚያበቃውን የአመራር ስልጠና አልወሰዱም፡፡ ከበታች ሹም ቀጥሎ ወደታች ያለው ማዕረግ ቢሰጣቸው ደግሞ እሱንም እንኳን ለማሟላት መደበኛ የሆነውን መሠረታዊ የወታደራዊ  ስልጠናም አልወሰዱም፡፡ በዚህ ነባራቂ ሐቅ በመንተራስ ከተራ ወታደር በስተቀር ሊሰጣቸው የሚችል ምንም ዓይነት መጠሪያ ስም የለም፡፡ ሕወሓቶች ጫካ እያሉም ሆነ አሁን የሚጠራሩበት “ተጋዳላይ እከሌ” “ወዲ እከሌ” የሚለው መጠራሪያቸው የሚመጥናቸው ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ሌ/ጄነራል ብለው የሾሙትን ከፍተኛ መኮንን ወዲ ወረዳ እያሉ ይጠራሉ፡፡ ይህ ባጠቃላይ ሲታይ ሠራዊቱ የአንድ መደበኛ ሠራዊት አካልነት ባህሪም ሆነ ተግባር አይታይበትም።

የህወሓት ጄኔራል መኮንኖች የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ፣ ዕውቀትና አመራር አናሳና ደካማነት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በተጨባጭ በግልጽ የተከሰተበት የታሪክ አጋጣሚ ታይቶ አልፏል:: ይህ ጦርነት እልፍ አዕላፍ የሆኑ የደሃው ኢትዮጵያዊውያን/ት ልጆች ህይወት የተቀጠፈበትና የሀገሪቷ አንጡራ ሀብት የወደመበት አስከፊ ጦርነት ነበር:: ለዚህ ደግሞ ተጠያቂዎቹ:-

1ኛ፡ የሕወሓት ከፍተኛው አመራር እና

2ኛ፡ የህወሐት ስትራቴጂክ አመራር ሰጭ ጄኔራሎች ናቸው

ከላይ የተጠቀሱት የሕወሓት ጄኔራል መኮንኖች  የወታደራዊ ትምህርትና ስልጠና ሳይወስዱ ወይንም ሳይቀስሙ ሠራዊቱን እንዲመሩ በመደረጋቸው ከፍተኛ ጉዳትና አደጋ ደርሷል:: ይህ ሁኔታ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ውስጥ መኪና ያለመብራት መንዳት ወይም መኪናን ያለመሪ ለመንዳት እንደሚደረግ ሙከራ ያህል ይቆጠራል::

በአጠቃላይ የመኮንኖች የወታደራዊ አመራር ጥበብ ሥልጠና ምንነትና ይዘት እንዲሁም ሂደቱን እና የመኮንኖች የማዕረግ ዕድገት አሰጣጥ መነሻውም ሆነ መድረሻው የወታደራዊ ትምህርትና ስልጠና መሆኑን በሚገባ ከተጨባጭ ሁኔታ ጋር አይተናል፡፡

2.    ማጠቃለያ

 

ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ በአጠቃላይ የወታደራዊ ትምህርት እና ስልጠና ይዘትና ሂደት ምን እንደሚመስልና  አሁን ያለውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚመሩትን ጄኔራል መኮንኖችን  ዓለም ከደረሰበትና  ተቀባይነት ካለው የወታደራዊ ትምህርትና ስልጠና ስታንዳርድ እንፃር የሙያ ብቃት ደረጃቸውን በመመዘንና በመተንተን  በጥልቀት ለመዳሰስ ሙከራ አደርጓል። የወታደራዊ ሳይንስና የአመራር ጥበብ ሥልጠና በተዋረድ ከመሰረታዊ ሥልጠና ወደ ቀጣዩ ስልጠና እንዴት እንደሚሸጋገርና እንደሚገባ፣ ሥልጠናው የሚያካትታቸው የትምህርት ዓይነቶች ፣ ከሥልጠናም በኋላም በኃላፊነት ሊመሩት የሚችሉት ኃይልና የወታደር ብዛት፣ የሥልጠናው የቆይታ ጊዜ፣ እንዲሁም ሥልጠናውን ሲጨርሱ የሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ እና ከተወሰነ አገልግሎት በኋላ ከአንዱ የአመራር ሥልጠና ወደ ሌላው የአመራር ሥልጠና እርከን እንዴት እንደሚሸጋገሩ ሥዕላዊ በሆነ መለኩ በማቅረብ ሳይንሳዊ የሆነ የአመራር ሥልጠና ሂደት ዋነኛው እና ትልቁ መንገድ መሆኑን ያመለክታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አንድ ጀኔራል መኮንን በሚያዝዘው  ኃይል ውሰጥ ለየእርከኑ አመራር ሰጭ ሊሆኑ  የሚገባቸውን ማዕረጋቸውን፣ የኃላፊነት ቦታና ሠራዊቱ የሚዋጋበትን የጦርነት ህግ፣ ሰራዊቱ የሚሰለጥንበትን የስልጠና ፖሊሲ፣ የወታደራዊ ዶክትሪንና ስትራቴጂ  መቅረጽ መቻል ያለበት መሆኑን ያስረዳል:: አሁን መሬት ላይ ያለው ሐቅ የሚያሳየው ግን ተሿሚዎቹ ክህሎቱ እና ችሎታው የሌላቸው በመሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን አንድ ብቃቱ የተረጋገጠለት ጀኔራል መኮንን ሊፈፅማቸው የሚገባ ተግባራት በብቃት ማከናወን እንደማይችሉ ጥናቱ ያስረዳል:: የእነሱ ዶክትሪንና ስትራቴጂ ቀረጻ መሬት ወረራ ፣ ዝርፊያ፣ ምዝበራ፣ አፈናና ዜጎችን በውጭ ሀገራት ሳይቀር እንዴት መጥለፍ እንደሚቻል ያተኮረ ላቅ ያለ ተንኮል ብቻ ነው:: በአንድ ወቅት ሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጄነራል መኮንኖቹን ሲገመግሙ ያስቀመጡትን ድምዳሜ በመጥቀስ ፅሁፍን እናበቃለን። “እናንተ በቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴም ሆነ በደርግ ዘመነ መንግስት ከነበሩት ጄኔራል መኮንኖች ጋር ስትነፃጸሩ የሰማይና የምድር ያህል ትራራቃላችሁ:: የእናንተ ችሎታ አንድ ሻለቃ  ወይም 400 መቶ ሰው ያለው ሀይል ከማዘዝ  ያለፈ አይደለም!’’

በመጨረሻም ከዚህ በታች በተቀመጠው አባሪ ሰነድ ሰንጠረዥ ፩፤ ሕወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ከ1983 ዓ.ም. አንስቶ እስካሁን ድረስ የጦር ኃይሉ የተዋቀረው በአንድ ብሔር (በትግራይተወላጆች) የበላይነት፣ ያለአንዳች የወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ሥልጠና መሆኑን ማንም ሊያስተባብለው በማይችል መልኩ ጥሬ ሐቁ ተቀምጧል። ይህ በራሱ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለምን በዚህ አሳዛኝ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና፣ የማኅበረሰባዊ ዝቅጠት ላይ እንደምትገኝ ቁልጭ አድርገው ከሚያሳዩት ተግዳሮቶች (Factors) አንዱ ሊሆን ይችላል።

3.    አባሪ ሰነድ- ፩ (Annex-1)

 

ginbot 7 1 ginbot 7 2 ginbot 7 3 ginbot 7 4 ginbot 7 5 ginbot 7 6

ginbot 7 7 ginbot 7 8 ginbot 7 9 ginbot 7 10 ginbot 7 11 ginbot 7 12

ጃዋሪዝም (የማምታታት ፖለቲካ) በጌታቸው ሺፈራው

$
0
0

‹‹(ጠባብ) ብሄርተኝነት ልክ እንደ ርካሽ መጠጥ ነው፡፡ መጀመሪያ እንድትጠጣው ይገፋህና ያሰክርሃል፡፡ ቀጥሎ አይንህን ያውርሃል፡፡ ከዛም ይገድልሃል፡፡›› ዳን ፍሪድ

በጌታቸው ሺፈራው

(የግል አስተያየት)

Jawarጃዋር መሃመድ ከአመታት በፊት ከማደንቃቸው ኢትዮጵያዊ አክቲቪስቶች መካከል አንዱ ነበር፡፡ በተለይ ይህ ወጣት ከጥቂት አመታት በፊት እነ በረከት ስምኦንን አልጀዚራ ላይ ሲያፋጥጣቸው ሳይ አድናቆቴ ከፍ ብሎ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ጃዋር ወደ ሶማሊያ ዘው ብሎ ስለገባው ሰራዊት፣ ቋንቋ ሳይለይ በየትኛውም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚደርሰውን በደል ሽንጡን ገትሮ መከራከሩ ይታወሳል፡፡ ግን ምን ያደርጋል ይህ አቋሙ እንደተጠበቀው ሊዘልቅ አልቻለም፡፡ መሃል ላይ የ‹‹እኛ እና እነሱ›› ብልሹ ፖለቲካ ሰለባ ሆነ፡፡

በተለይ በአንድ ወቅት አልጀዚራ ላይ ቀርቦ ‹‹በቅድሚያ ኦሮሞ ነኝ›› ካለ በኋላ የፖለቲካ አቋሙ እየተንሸራተተ ሜንጫን እንደ ህጋዊ ነገር ማንሳት ውስጥ ገባ፡፡ አንዴ ‹‹ኢትዮጵያዊ ሙስሊም›› ሆኖ የኦሮሞ ሙስሊሞች ነጻነት ለሌላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ነጻነትም ወሳኝ ነው ሲል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኑን ኦሮሞ በሜንጫ አንገቱን ስለመቅላት ይሰብካል፡፡ (ይህን መረጃ የተቀነባበረ ነው የሚል መረጃ ያቅርብ)፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ክርስቲያኑን ኦሮምኛ ተናጋሪም ጭምር ወክሎ ‹‹ቅድሙያ ኦሮሞ ነኝ›› አለ፡፡

ከዚህ ውጣ ውረድ በኋላ ጃዋር በቅርቡ ከ‹‹ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ›› ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል፡፡ በቃለ መጠይቁ እስካሁን አሉ የሚላቸውን ብዥታዎች ለማጥራትና አቋሞቹንም ለማስረገጥ በሚመስል መልኩ የቀረበ ይመስላል፡፡ በዚህ ቃለ መጠይቅ ጃዋር ከዛ በፊት እንዳደረጋቸው አነጋጋሪ ነገሮች ባይኖሩትም ቃለ መጠይቁ በሙሉ ‹‹ምክንያታዊ ናቸው›› በሚላቸው ምክንያት አልባ የማምታታት ክርክሮች የተሞሉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡

በቃለ መጠይቁ አልጀዚራ ላይ ‹‹መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ›› ያለበትን አቋሙን የሚያጠናክርበት ነው፡፡ ‹‹በልጅነቴ ነው በፖለቲካው ተጠምቄ ያደኩት›› የሚለው ጃዋር ‹‹ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ እስከምሞትበት ጊዜ ድረስ ከምንም ከማን በላይ ራሴን እንደ ኦሮሞ ነው የማያው፡፡›› ሲል በ‹‹ማንነቱ›› ሁኔታ ላይ ይደመድማል፡፡ ግን በዚሁ ቃለ መጠይቅም ቢሆን ከአንድ አቋም ወደ ሌላ አቋም ሲዘል ታይቷል፡፡

ጋዜጠኛው ‹‹ኦሮሞ ፈርስት›› የሚለው ጉዳይ ከመነሳቱ በፊት ኢትዮጵያዊ በሆኑ አጀንዳዎች ይሳተፍ እንደነበር በመግለጽ ከዛ በኋላ አቋም መቀየር አለመቀየሩን ሲጠይቀው ‹‹አልቀየርኩም›› ይላል፡፡ መልሶ ደግሞ ‹‹አየህ! ከ2008፣ 2009 በኋላ ‹ኮንሸስ› የሆነ ምርጫ አድርጌያለሁ፡፡ በተለይ ከአማራ ልሂቃን ጋር በመገናኘት ለእነሱ ስለ ኦሮሞ ህዝብ ትግል በማስረዳት ከእነሱ ጋር አብሮ ለመስራት ይቻላል የሚል እምነት ነበረኝ፡፡ የአማራ ልሂቃን በኦሮሞ ትግል ላይ ያላቸው አመለካከት በጣም የሚያስደነግጥና በጣም የሚያስፈራ ነበር፡፡ በትምህርት ጥናቴም ሆነ ባለኝ ቀረቤት ችግሩ ምንድን ነው ብየ ሳስበው ምን አልባት ካለማወቅ (ኢግኖራስን) የመነጨ ነው የሚል ነበር፡፡ ሁለቱንም አካል ወደ መሃል በማምጣል አብሮ መስራት ይቻላል በሚል አምስት አመት ያህል ነው የሰራሁት፡፡ ነገር ግን ያለው ችግር የግዝብተኝነት (አሮጋንስ) ችግር እንዳለ ተረዳሁ፡፡ ኦሮሞ ፈርስት የሚለው ከመምጣቱ በፊት ስርቤይ አድርጌ ነበር፡፡ …27 ያህል ሰዎችን ደውየ 1 ወይም 2 ብቻ ናቸው የተቀበሉት፡፡ እንዲሁም የኦሮሞ ትግል እየተዳከመ በመጣ ቁጥር ያላቸው ንቀት እየተጠናረ ሄደ›› በሚል አቋሙን መቼ እንደቀየረ ለማስገንዘብ ሲጥር ‹‹ከተወለድኩ ጀምሮ እስከሞት ድረስ ኦሮሞ ነኝ›› የሚለው የ‹‹አሁኑ›› አቋሙንም ራሱ መልሶ ይከራከረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሌላ አቋሙን የቀየረበት ምክንያት እንዳለው ጃዋር እንዲህ ያስረዳል፡፡ ‹‹…በግብጽ የሚገኙ የኦሮሞ ስደተኞች በአባይ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያና ግብጽ ባለባቸው ችግር ጥቃት ሲደርስባቸው ‹‹እኛ ኦሮሞዎች ነን፡፡ ከኢትጵያ መንግስት ጋር ምንም ትስስር የለንም ሲሉ እንዴት አባታችሁ ኦሮሞዎች ነን ትላላችሁ የሚል በጣም አጸያፊ የሆነ የሚዲያ ዘመቻ ተጀመረባቸው፡፡ ያ ለእኔ ቀይ መስመሩን ያለፉበት እንደሆነና ……በዚህም በማንነታችን ላይ የተነጣጠረ ጥቃት ነው ወደሚል ገባሁ›› ይለናል፡፡ እንደ ጃዋር ከሆነ ግብጽ ውስጥ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ሲዳምኛ….. ተናጋሪዎች የሉም፡፡ አሊያም ጥቃት አልደረሰባቸውም፡፡ ወይንም ደግሞ ነገ ጃዋር ቆሜለታለሁ በሚለው ኦሮሞነታቸው ግብጾች ጥቃት የሚያደርሱባቸው ሲሆን ‹‹እኛ ኦሮሞዎች አይደለንም፣ ከኦሮሞ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለንም፡፡›› ቢሉ ትክክል ናቸው እንደማለት ነው፡፡

በዚህ ቃለ መጠይቅ ጃዋር ተራ የሀሳብና የአመክኖ ማምታታት ብቻ አይደለም የሚታይበት፡፡ አንዴ መለስ ዜናዊ፣ ሌላ ጊዜ ኦነግ፣ አሊያም ኦህዴድ የያዙትን አቋም አቋሙ አድር ሲከራከርበት፣ ‹‹እኛ›› እያለ ሲገልጽ ተስተውሏል፡፡

ለአብነት ያህል 27 ያህል የ‹‹አማራ ልሂቃንን›› አነጋግሬ አገኘሁት የሚለውን መደምደሚያ ሲገልጽ ነፍጠናውን አከርካሪው ሰብረነዋል የሚለውን አቶ መለስ አቋም በግልጽ እንደተጋራ ይታያል፡፡ ጃዋር ‹‹ይህን አሮጋንስ ማስተካከል የሚቻለው … ቀኝ ዘመሙን የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት አከርካሪውን በመስበር እጅ ማሰጠት ነው፡፡ ያ ፖለቲካ እንደማይሰራ ወደ ‹ኮምፕሊት ፖለቲካል ባንክራፕሲ› ማስገባት ግዴታ ነው በሚለው መደምደሚያ ደርሼ ነበር፡፡›› ይላል፡፡ ይህኔ ጃዋር መለስን መለስን ነው የሚመስለው፡፡

ኦህዴድ ከገዥው ቡድን ጋር ተባብሮ የኦሮሞን ህዝብ እየበደለ ስለመሆኑ ለተነሳለት ጥያቄ ጃዋር ኦህዴድን ምንም አቅም የሌለው አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ መልሶ ደግሞ ለህወሓት ፈታኙ ኦህዴድ ነው እያለ ያምታታል፡፡ ጃዋር መጀመሪያ ‹‹ለእኔ የኦህዴድ አመራሮችም ሆነ አባላት በአንድ ፋብሪካ የሚሰሩ የፋብሪካ ዩኒየን ያህል ጉልበት የሌላቸውና የማይፈቀድላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ከተፈጠረበት ጊዜ ድረስ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ድርጅታዊ ስብዕና የሌለው ድርጅት ነው፡፡›› በማለት ከምንም የማይገባ፣ ለምንም የማይሆን አቅመ ቢስ ያደርገዋል፡፡

ምንም አቅም የላቸውም ያለውን ተመልሶ ‹‹..ህወሓት እንደፈለገው ኦህዴድ ቡችላ የሚሆንለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ብዙ ያልነቁት በእድሜ እየገፉ በሄዱ ቁጥር፣ ከኦነግ ጋርም ለመሻማት የተማሩትን ወደ ድርጅቱ እየከተተ በሄደ ቁጥር፣ ኦህዴድ እንደ ድርጅት ባይጠናከርም ግለሰቦች በተቻለ መጠን የህዝቡን መብት ለማስጠበቅ እየተንቀሳቀሱ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እንዲያውም በአሁኑ ወቅት ለህወሓት ከማንም በላይ አስፈሪው ኦህዴድ ሆኖ ያለበትና ባለፉት ሁለት አመታት የምናየው ዳይናሚክስ ከፍተኛ አደጋ እየፈጠሩበት እንዳለ ነው የምናየው፡፡›› በማለት በቅጽበት ኦህዴድን ከአነስተኛ ፋብሪካ ዩኒየንነት ወደ ግዙፍና አስፈሪ ፓርቲነት ያሳድገዋል፡፡

ጃዋር መጀመሪያ ‹‹እንደ ድርጅት አልቆጥረውም፤ አቅመ ቢስ ነው፡፡›› ስላለው ኦህዴድ ይቀጥላል፡፡ ‹‹ያ ብቻ አይደለም የተማሩ ኦሮሞዎችን በግዳጅ ወደ ቢሮክራሲው አስገብቷል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ቢያንስ ከስርዓቱ ጋር እምብይ ማለት ቢያቅታቸው ‹አክቲቭሊ› ህዝቡን መበደል እያደረሱ አይደለም፡፡ …..ከዚህም የተነሳ በኦነግ የተጀመሩ ብዙ ፕሮጀክቶችን ወደማጠናቀቀ እየደረሱ ነው ያለው›› በማለት ኦህዴድን የኦነግ ‹‹ራዕይ አስቀጣይ›› ያደርገዋል፡፡ ይፈጽማል ከሚባለው ኃጥያት ነጻ ሊያወጣው ይሞክራል፡፡

ጃዋር ከአንድ የፋብሪካ ማህበር አይሻሉም የሚላቸውን ኦህዴዶች እንደገና ሲያማካሻቸው ጋዜጠኛው ‹‹ስለዚህ የኦህዴድ መኖር አስፈላጊ ነው?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ጃዋር ግን አሁንም ያምታታል፡፡ ‹‹አይደለም!›› ይላል፡፡ ግን ደግሞ ስለ ኦህዴድ አስፈላጊነት እንዲህ ይገልጻል፡፡ ‹‹በአሁኑ ወቅት ወደ 90 በመቶ የሚሆነው የኦሮሞ ልሂቃን ኦህዴድ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ቀጣዩ የኦሮሚያ እጣ ፈንታ በእነሱ እጅ ነው ያለው፡፡›› በማለት መኖሩ አስለላጊ አይደለም የተባለው ኦህዴድ የኦሮሚያ እጣ ፈንታ ሆኖት ያርፋል፡፡ ጃዋሪዝም እንዲህ በደቂቃዎች አቋምን የመቀየር፣ የመቀያየር፣ የማምታታት ፖለቲካ ነው!

ይህ እንግዲህ ጃዋር ነው፣ ፖለቲካው ደግሞ ጃዋሪዝም፡፡ ስለዚህ አሁንም ማምታታቱን ይቀጥላል፡፡ እናም በአዲስ አበባ ‹‹መሪ እቅድ ወይም ማስተር ፕላን›› ላይ ለተነሳው ተቃውሞ ኦህዴዶች አሉበት እንደሚባል ጋዜጠኛው ሲያስታውሰው ‹‹ማንኛውም ኦሮሞ ኦህዴድም ሆነ ኦነግ ‹‹ማንነት፣ ኦሮሞ የሚባል ነገርና አዲስ አበባ ጉዳይ አንድ ናቸው›› በማለት ኦህዴድን ከማህበር ወደ ለህዝብ እንደሚያስብና አላማ ያለው የፖለቲካ ድርጅት ያደርገዋል፡፡ በአብዛኛው የቃለ መጠይቅ ክፍል መጀመሪያ ላይ ‹‹የዩኒየን አቅም ያህል የሌላቸው›› ያላቸውን ኦህዴዶች ያሞገሰበት ነው፡፡ ‹‹የዛሬ 9 አመት አካባቢ ዋና ከተማው ወደ አዳማ ሲዛወር ኦህዴድ ከፍተኛ ተቃውሞ ማድረጉን፤ ወደ ዋና ከተማውን አዲስ አበባ ማስመለሳቸውን በመግለጽ ‹‹የዩኒየን ያህል አቅም የላቸውም፣ የፖለቲካ ድርጅትም አይደሉም ስላላቸው መወድስ ያቀርባል፡፡

አሁን በአዲስ አበባ በተፈጠረው ችግር ደግሞ ‹‹በኢህዴድ ውስጥ አንድም ልዩነት ሳይፈጠር በአመራሩ በአንድ አቋም የተቃወሙበት ነበር፡፡ በግልጽ የህወሓትን ሰዎች ተቃውመዋቸዋል፡፡ በህወሓትና በኦህዴድ ጉዳይ ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ የነበረውን ልዩነት ከአሁን ቀደም ኖሮ አያውቅም፡፡ ከዚያ አልፎ ያን ተቃውሞ ህዝቡ እንዲያውቀው በቴሊቪዝን አስተላልፈዋል፡፡ ይህን በማድረጋቸው ብዙ ሰዎች ለስራቸውም፣ ለህይወታቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ራሳቸውን አደጋ ላይ አጋልጠዋል፡፡ ወጣቱም እነሱን ተከትሎ ነው ወደ ትግል የገባው›› በሚል የትግሉ አንቀሳቃሽ ሞተሮች፣ ነጻ አውጭዎች ያደርጋቸዋል፡፡

‹‹በኦህዴድ ውስጥ እከሌን እናጥቃ እከሌን እንግደል ቢሉ የባሰ ችግር ውስጥ ስለሚገቡ እስካሁን እየተፋጠጡ፣ በተቻለ መጠን ኢህዴዶችን በሁለት ከፍለው እያጋጩ ለማዳከም ሙከራ እያደረጉ ነው ያሉት፡፡ ባለፈው ሳምንት ሁለት፤ ሶስት ስብሰባ ተደርጎ ኦህዴዶች በአንድ አቋም ነው ተስማምተው የወጡት፡፡ እናም (ህወሓቶች) የተሳካላቸው አይመስለኝም፡፡›› በማለት ከጠንካራው ኦህዴድ ጎን ሆኖ ህወሓት አቅመ ቢስ እንደሆነ ያወራል፡፡ መቸም መጀመሪያ ላይ ‹‹የዩኒየንን ያህል አቅም የለውም የተባለው ድርጅትና ይህኛው ኦህዴድ በአንድ ሰው፣ ደግሞም በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ፣ በሴኮንድና ደቂቃዎች ልዩነት የተነሳ መከራከሪያ ነው ብሎ ለማመን ይከብዳል፡፡ ግን የሆነው ይህ ነው፡፡ ምክንያቱም ፖለቲካው ማምታታት ነው፡፡ ጃዋሪዝም!

ጃዋር መጀመሪያ ላይ ‹‹አሽከር›› አድርጎ የሚያቀርባቸው ኦህዴዶች ወደ መጨረሻ አናብስት ይሆናሉ፡፡ እነዚህን ‹‹አናብስቶች›› የእራሱ አድርጎ ስለሚቆጥራቸው ኦህዴድን ሰራው የሚለውን ሁሉ ‹‹እኛ እንዲህ አድርገን›› እያለ ይገልጸዋል፡፡ ኦህዴድን እቃወማለሁ እያለ ኦህዴድ ሆኖ (እኛ እያለ) ኦህዴድ ስኬቴ ስለሚለው ‹‹ስኬት›› ይናገራል፡፡ ኦህዴድ አሰራኋቸው የሚላቸውን መሰረተ ልማቶች ‹‹የእኛ›› ሲል አፍለኛ የኦህዴድ ካድሬ ይመስላል፡፡ እንዲህ! ‹‹በተጨባጭ ያሳየነውም ይህንኑ ነው፡፡…….ህወሓት እምብይ እያለ የኦሮሞ ልሂቃን፣ የኦሮሞ ትምህርት ቢሮ በኦሮሚያ ውስጥ ያሉ አማሮችና ሌሎችም በቋንቋቸው መማር መብታቸው ነው ብለው ነው የደነገገሩት፡፡ ምክንያቱም የቋንቋ ጭቆና ምን እንደሆነ ስለምናውቀው በሌላ ጭቆና ማድረግ አንፈልግም፡፡›› ኦነግንም፣ ኦህዴድንም በዓላማ አስተሳስሮ ‹‹የኦነግ የፖለቲካ አላማ እና የአሁኑ የክልላዊ ህገ መንግስት ስታየው በኦሮሚያ ያሉ ዜጎች በሙሉ ኦሮሚያዊ ናቸው ነው የሚለው፡፡›› በሚል አንድም፣ ሁለትም፣ ሶስትም ነን ባይ ነው፡፡

‹‹ኢትዮጵያዊነት የተጫነብን ብልኮ ነው›› የሚለው ጃዋር ሌሎችን ‹‹ስትፈልግ ኢትዮጵያዊ ነኝ በል! ስትፈልግ አማራ ነኝ በል! ስትፈልግ ጎንደሬ ነኝ በል! ስትፈልግ የፈለገህን በል! በእኔ ላይ ግን የአንተን ማንነት ለመጫን አትሞክር….›› ብሎ በኃይለ ቃል ያስጠነቅቃል፡፡ በእርግጥም ምንም ሆነ ምን የእኔን ማንነት አሊያም እኔ የፈረጅኩትን ማንነት ተቀበል ማለት አግባብ አይደለም፡፡ ግን ጃዋር እንዲህ አስጠንቅቆ ሳይጨርስ እሱም ሌሎች ላይ የማፈልጉትን ብልኮ ይደርባል፣ እነሱ ነኝ በማይሉት ማንነት ይፈርጃቸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ በቀዳሚነት የሚነሱት ስለ አገር አንድነት የሚያነሱትን ወገኖች ‹‹አማራ›› የሚል ብልኮ የሚጭንባቸው መሆኑ ነው፡፡ በስልክ ደውሎ ከአነጋገራቸው በኋላ አቋሙን እንዳስቀየሩት የሚናገርላቸው ‹‹የአማራ ልሂቃንም›› እንዲህ ብልኮ የተደረበባቸው ናቸው፡፡ ስለ አንድነት ያነሳ እሱ ባያምንበትም በጃዋር መመዘኛ ግን ‹‹አማራ›› ነው፡፡

ጃዋር በአንድ በኩል ‹‹አማራ›› የሚላቸው ልሂቃን የያዙት አቋም የሰፊው የአማራ ህዝብ አቋም አይደለም ይላል፡፡ ተመልሶ ደግሞ ‹‹ኦሮሚያ ውስጥ ያደጉት የነፍጠኛ ልጆች የአማራው ህዝብ የተሳሳተ አመለካከት እንዲይዝ አድርገውታል፡፡ ኦሮሞ ገና ቃሉ ሲነሳ አገር አፍራሽ፣ ጠበኛ የሚል አመለካከት በህዝቡ ውስጥ እንዲመጣ አደርገዋል፡፡ ከአሁን በፊት የነበሩት የአማራ ገዥዎችም ህዝቡ የተሳሳተ አመለካከት እንዲይዝ አድርገውታል፡፡›› በማለት የ‹‹አማራ ህዝብ የአማራ ልሂቃንን አስተሳሰብ እንደያዘ›› በገደምዳሜው ይከሳል፡፡ መጀመሪያ ላይ ‹‹የአማራ ልሂቃን አስተሳሰብ የሰፊው የአማራ ህዝብ አስተሳሰብ አይደለም፡፡›› ያለውን ወርድ ብሎ ‹‹ህዝቡን የተሳሳተ አመለካከት እንዲይዝ እድርገውታል›› ይለናል፡፡

ጃዋር ለወቅቱ አቋሙ ምክንያት አድርጎ የሚወስደው አንድም ደውሎ ያናገራቸው የ‹‹አማራ›› ልሂቃን አስተሳሰብ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ግብጽ ውስጥ ‹‹ኢትዮጵያዊ አይደለንም›› ብለው ግን ‹‹በቀኝ ዘመሙ›› የፖለቲካ ኃይል (ሚዲያ) ዘመቻ ተከፍቶባቸዋል በሚሉት ኦሮምኛ ወጣቶች ምክንያት ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ጥቃት ቀዳሚ ትኩረት ማግኘት እንዳለበትና የአማራ ልሂቃን አስተሳሰብ አከርካሪውን መመታት እንዳለበት በመግለጽ ይህን የፖለቲካ ቡድን ቀዳሚ ጠላት አድርጎ ያቀርበዋል፡፡ ወደኋላ ላይ ደግሞ ጋዜጠኛ በፈቃዱ ሞረዳ ‹‹የኦሮሞ ህዝብ ጠላት ማን ነው?›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርብለት ‹‹የኦሮሞ ህዝብ በራሱ ላይ ነው ማተኮር ያለበት›› በሚል ጠላት የሚባል ነገር ላይ ትኩረት እንደማያደርግ ይገልጻል፡፡ ግን ፖለቲካው ጃዋሪዝም ነውና አሁንም ማምታታቱን ይቀጥላል፡፡ በዚህ ወቅትም ህወሓት ቀዳሚው ጠላት ይሆናል፡፡ ቀደም ሲል ያላቸውን ጣል እርግፍ አድርጎም ‹‹አሁን ባለው ሁኔታ ‹‹አክቲቭ ኢነሚ›› ብለን የምንጠራው ህወሓትን ነው፡፡ ምንም ምንም ጭቅጭቅ የለውም፡፡›› እያለ ይቀጥላል፡፡ በደቂቃዎች ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ሶስትና ከዛ በላይ ጠላቶችና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡት ግቦች ይቀመጡለታል፡፡ ‹‹የአንድነት ኃይሉን (አማራ ይለዋል) አከርካሪውን ከመምታት፣ በራሱ ላይ ትኩረት ማድረግ፣ ስርዓቱ (ህወሓት!) ላይ ‹‹ፎከስ›› ማድረግ….. ››

አብሮ ስለመስራትም ጃዋሪዝም ያው ማምታታት ነው፡፡ መጀመሪያ ላይ በደወለላቸው የ‹‹አማራ›› ልሂቃን መሰረት የኦሮሞ ህዝብ ራሱን ችሎ መስራት አለበት የሚል መደምደሚያ እንደደረሰ የሚናገረው ጃዋር ‹‹የእኛ እርሻ ላይ ዝናብ እየዘነበ ማንም ጋ አንሄድም፡፡›› ይላል፡፡ ትንሽ ቆይቶም ‹‹አብሮ ለመስራት መቼም ቢሆን ክፍት ነን፡፡›› በማለት ይህ ባህል ከድሮ የመጣ መሆኑን ያስረግጣል፡፡ ደግሞም እንደገና ‹‹ከሜጫና ቱለማ፣ እስከ መኢሶን፣ እስከ ኦነግ መሪዎች ለሁሉም የሚሆን መካከለኛ መንገድ ለመፍጠር ስርተዋል፣ መስዋትነትም ከፍለዋል፣ ያ መስዋትነታቸው ግን ሰሚ አላገኘም፡፡ እንዲናቁ ነው መንገድ የከፈተው፡፡›› በሚል ወደ መካከለኛ መንገድ ለመምጣት የሚደረገው ፖለቲካ መስዋዕትነት የሚያስከፍልና የማያወጣ አይነት እንደሆነ በገደምዳሜው ይገልጻል፡፡ አብረን መስራት አለብን፡፡ ዝግ አይደለንም እንዳላለ ‹‹እኛ ስንጎዳ ያ ጉዳት ዳግመኛ እንዳይደገም እርምጃ መውሰድ ያለብን እኛ ብቻ ነን፡፡›› በሚል ‹‹ብቻችን እንወጣዋለን!›› የሚል አቋሙን እንደገና ሊያጠናክር ይሞክራል፡፡

የ‹‹ብሄር/የእኛ እና እንሱ›› ፖለቲካ ስስ የሆነውን ጉዳይ በማጋጋል እውቅናን ማግኘት፣ ጥላቻ በመስበክ ደጋፊ ማሰባሰብ፣ ማምታታት ነው፡፡ ‹‹የእኛ እና እነሱ ፖለቲካ›› አመክኖ ሳይሆን የማነጻጸር አባዜ የተጠናወተው የማምታታት ፖለቲካ ነው፡፡ ይህ መነጻጸር የማይገባውን ነገር የማነጻጸር አባዜ የጃዋሪዝም ዋነኛ መገለጫ ነው፡፡

ምክንያታዊ ለሚባል ሰው፤ ሰው ምንም ይሁን ምን በህገ ወጥነት መታሰር የለበትም፡፡ አማርኛ ተናገረ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ ተናገረ፣ሶማልኛ አሊያም ሌላ ቋንቋ በህገ ወጥ መንገድ መታሰር የለበትም፡፡ የግድ ሶስት ወይንም አራት ኦሮምኛ ተናጋሪ በህገ ወጥ መንገድ ከታሰረ ይህን ህገ ወጥነት መቃወም እየተቻለ፤ አምስት ወይንም ስድስት አማርኛ ወይንም ትግርኛ አሊያም ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ዜጋ መታሰር ነበረበት የሚል የስካር፣ ‹‹ጠባብ ብሄርተኝነት›› ያወረው ክርክር ሊቀርብ አይገባም፡፡
ለጃዋሪዝም ግን ይህ ሰብአዊም ሆነ ህጋዊ አመክኖ አይሰራም፡፡ ጃዋር ‹‹ዛሬ እስር ቤት ብትገባ ምርጥ የኦሮሞ ልጆችን እስር ቤት ውስጥ ነው የምታገኛቸው፡፡ አንድ የአማራ እስረኛ ካለ 90 የኦሮሞ እስረኛ አለ፡፡›› በሚል በኦሮምኛ ተናጋሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ‹‹አልተበደለም!›› ከሚለው ‹‹አማራ›› ጋር በማነጻጸር ‹‹ለመከራከር›› ይጥራል፡፡ እንደ ጃዋር የበርካታ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች መታሰር ምክንያታዊ ሊሆን የሚችለው ሌሎች በህገ ወጥ መንገድም ቢሆን ከታሰሩ ብቻ ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ ልክ ርካሽ መጠጥ እንደሚያመጣው ‹‹ጠባብ ብሄርተኝነት›› የሚያመጣው ጭፍንና የማምታታት ፖለቲካ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ‹‹ማስተር ፕላን›› ለ‹‹ኦሮሞ ህዝብ ቆመናል›› የሚሉት አካላት አመክናዊ እንዳልሆኑ ካሳዩናቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ‹‹ፊንፊኔ የኦሮሚያ ናት›› ይሉ እንዳልነበር በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹አዲስ አበባ የኦሮሚያን መሬት እየወሰደች ነው፡፡›› የሚል የጃዋሪዝም ፖለቲካ ውስጥ ገቡ፡፡ በሂደት ስርዓቱ ‹‹ማስተር ፕላኑን›› የተቃወሙ ወጣቶችን በጠራራ ፀኃይ ጨፈጨፋቸው፡፡ በወቅቱ በተፈጠረው ችግር ሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎችም ‹‹ከኦሮሚያ ውጡ ተብለው ተደብድበዋል፣ ተገድለዋል፡፡›› በተለይ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት የሚያቀነቅኑ የፖለቲካ አካላት ጉዳዩን በግልጽ ለመደገፍ አልቻሉም፡፡ ምን ያህል ሰርተውበታል የሚለው እንዳለ ሆኖ ግድያውን ተቃውመው ሰልማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፣ ሻማ አብርተው ጭፍጨፋውን ተቃውመዋል፣ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ይህም ቢሆን በቂ ላይሆን ይችላል፡፡ ጃዋር ተቃዋሚዎች ያደረጉትን ትንሽም ነገር ቢሆን በቂ አይደለም ከማለት ይልቅ ማብጠልጠሉን ነው የመረጠው፡፡

በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ትንሽም ቢሆን የሰሩትን ተቃዋሚዎች እያብጠለጠለ ለህወሓት መሳሪያ ሆኖ ተማሪዎቹን ያስጨፈጨፈውን ኦህዴድን በ‹‹ማስተር ፕላኑ›› ዙሪያ ለህወሓት ፈተና፣ በ‹‹ፊንፊኔ›› ጉዳይ ከህዝብ አሊያም ለ‹‹ኦሮሚያ›› ከቆሙ ሌሎች ኃይሎች ጋር ተመሳሳይ አቋም እንዳለው፣ ትግሉንም በማቀጣጠል ለወጣቱ አርዕያ አድርጎ ማወደሱ ነው፡፡ ግድያውን የተቃወሙት ተቃዋሚዎች በጃዋር የተብጠለጠሉት ግን በተማሪዎቹ ላይ የተፈጸመውን ግድያ በሚገባ አልተቃወሙም በሚል አይደለም፡፡ ጃዋር አሁንም ያነሳው ለመከራከሪያነት የማይበቃ ‹‹የጠባብ ብሄርተኝነት›› ማነጻጸሪያ ነው፡፡ ጃዋር የፖለቲካ ቡድኖቹ ለኦሮምኛ ተናጋሪ ተማሪዎች ላይ የተደረገውን ግድያ አልተቃወሙም ለማለት ያነሳው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንን ነው፡፡ በኦሮሚያ ተማሪዎች በተፈጸመው ግድያ በቂ ምላሽ አልተሰጠም ብሎ ለመከራከር የዞን ዘጠኞች ላይ የተፈጸመው ህገ ወጥ እስር ተቃዋሚዎች ያሰሙት ተቃውሞ ተጋንኗል በሚል በመከራከሪያነት አቅርቦታል፡፡ ይህ ጃዋሪዝም ነው፡፡ የማይነጻጸረውን ማነጻጸር፣ በቅጽበት የተቃወሙትን መደገፍ፣ የደገፉትን መቃወም፣ አመክኖ ሲጠፋ ማምታታት!

Source – ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

ሕወሓትና በትግርኛ ተናጋሪዎች ሙሉ ቁጥጥር ስር የወደቀዉ መከላከያ ሠራዊት ከአራት አመታት በኋላ በድጋሚ ሲፈተሽ

$
0
0

Ginbot-7-Top-logo_4

ሕወሓትና በትግርኛ ተናጋሪዎች ሙሉ ቁጥጥር ስር የወደቀዉ መከላከያ ሠራዊት

ከአራት አመታት በኋላ በድጋሚ ሲፈተሽ

መስከረም  26 2007 ዓ..

ሕዝባዊ ሓርነት ወያኔ ትግራይ (ሕወሓት) ምን ያክል የኢትዮጵያን የፖለቲካ መዋቅሮች እንደሚቆጣጠር ለማወቅ በአገሪቱ የመከላከያ፣ የደህንነትና የፖሊስ ተቋሞች ዉስጥ ዋና ዋና የትዕዛዝ ሰጪና ቁጥጥር ቦታዎች ላይ በሀላፊነት የተቀመጡትን የትግራይ ተወላጆች ብዛት መመልከቱ በቂ ይመስለናል። የሕወሓት መሪዎች ስልጣን በያዙባቸዉ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት አመታት ዉስጥ እየገነቡት ላይ ያለዉን ስርዐት መልካምና ሁሉን አቀፍ ስርዓት ለማስመሰል አንዳንድ ከነርሱ ቁጥጥር ዉጭ መተንፈስ እንኳን የማይችሉ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆችን አልፎ አልፎ ስልጣን ላይ አስቀምጠዋቸዉ ነበር። ዛሬ ሕወሓቶችን እራሳቸዉን እጅግ በጣም በሚያሳፍር መልኩ እነዚህ በጥንቃቄ ለቅመዉ ያመጧቸዉንም የሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች ወደመጡበት መልሰዋቸዉ በሁሉም መስክ ቁልፍ የሆኑ የአገሪቱን  የስልጣን ቦታዎችን የሚቆጣጠረዉ የትግራይ ተወላጅ ሕወሓቶች ብቻ ሆነዋል። አያሌ ኢትዮጵያዉያን የህወሓትን አገዛዝ “ዘረኛ” አገዛዝ ነዉ ብለዉ የሚጠሩት ይህንን ሙልጭ ያለ በዘር ላይ የተመሰረተ ጭፍን አገዛዝ ተመልክተዉ ይመስለናል።

ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ ለፈጠረዉ ዘረኛ ስርዓት ብቸኛ ምሳሌ ሆኖ መቅረብ የሚችለዉ ደቡብ አፍሪካ ዉስጥ ነጮች የፈጠሩት ዘረኛ (Apartheid) ስርዓት ብቻ ነዉ። በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ በተለይ በቁጥሩ ከፍተኛ ብልጫ ያለዉና ትግርኛ ተናጋሪ ያልሆነዉ ሠራዊት እጅግ ያኮረፈ፤ የተቆጣና ያመረረ ሠራዊት ከመሆኑ የተነሳ እራሱን የሚመለከተዉ እንደ አገር መከላከያ ሠራዊት አባል ሳይሆን አንደ ህወሓት የቤት ዉስጥ አገልጋይ ባሪያ ነዉ። ይህ የሕወሓት ዘረኞች በሠራዊቱ ላይ የፈጠሩት የመገዛትና የበታችነት ስሜት በየቀኑ ከፍተኛ ቁጣና የዉስጥ ለዉስጥ ተቃዉሞ የሚገጥመዉ ቢሆንም ህወሓት በዘረጋዉ ከፍተኛ የአፈና መረብ የተነሳ የህዝብ መነጋገሪያ አርዕስት መሆን አልቻለም። የህወሓት መሪዎችም ቢሆኑ ይህንን ቁጣና ተቃዉሞ በሚገባ ስለሚያዉቁ “ግምገማ” እያሉ በሚያዘጋጇቸዉ መድረኮች ላይ እንደዚህ አይነቶቹን በእነሱ የበላይነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ማስተናገድ ቀርቶ ጥያቄዎቹ እንዲነሱም አይፈቅዱም። አንዳንዴ ደፍረዉ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሱ ግለሰቦች ሽብርተኛ፣ የደርግ ስርዐት ናፋቂዎች፣ ጠባብ ብሄረተኞች ወይም የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች የሚል ተቀጽላ ስም ይሰጣቸዋል። ዛሬ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዉ በተለያዩ የወያኔ እስር ቤቶች ዉስጥ የሚሰቃዩት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ለዚህ አሳዛኝ ሁኔታ የበቁት በመከላከያ ተቋሞች ዉስጥ ሠራዊቱን በየትኛዉም እርከን የሚመሩ መኮንኖች አመዳደብ ወታደራዊ አመራር ችሎታን፤ ልምድንና የብሄር ስብጥርን ያካተተ መሆን አለበት ብለዉ ደፍረዉ በመናገራቸዉ ነዉ።

ዛሬ የወያኔን መከላከያ ሠራዊት እየለቀቁ ከአገር የሚወጡ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል። እነዚህ ወታደራዊ መሪዎች፤ የበታች መኮንኖች፤ ባለሌላ ማዕረጎችችና ተራ ወታደሮች ከጠላት እንከላከላን ብለዉ የማሉላትን እናት አገራቸዉን እየለቀቁ የሚወጡት በወያኔ ጦር ዉስጥ ስር የሰደደዉ ዘረኝነትና በዚህ ዘረኝነት ላይ የተመሰረተዉ አመራር የሚያደርስባቸዉ በደል አንገፍግፏቸዉ ነዉ። በየጎረቤቱ አገር ተሰድደዉ በችግር ላይ የሚገኙ ምርጥ የኢትዮጵያ የወታደራዊ ሳይንስ አዋቂዎች ሁሉም በአንድ ድምፅ የሚናገሩት ሠራዊቱ ዉስጥ ይደርስባቸዉ የነበረዉ ንቀትና ዉርደት የሰዉ ልጅ መሸከም ከሚችለዉ በላይ መሆኑን ነዉ።

ሕወሓትን ለረጂም ግዜ የመራዉ መለስ ዜናዊና ጓደኞቹ ሥልጣን በያዙባቸዉ በመጀመሪያዎቹ ሁለትና  ሦስት አመታት ጊዜያት ቁልፍ የሆኑ ቦታዎች  ሰዎች መያዛቸዉን አስመልክተዉ ሲናገሩ ህወሓት ለ17 አመታት የደርግን አምባገነናዊ ስርዓት ሲዋጋ የፈጠረዉ ወታደራዊና ድርጅታዊ ግዝፈት አብዛኛዉ የወታደራዊና የደህንነት አመራር ቦታ በህወሓት ታጋዮች አንዲያዝ ምክንያት ሆኗል ብለዉ ከተናገሩ በኋላ ይህ አሰራር በሂደት ሙሉ በሙሉ እንደሚቀይርና የኢትዮጵያ የፖለቲካና ወታደራዊ የሥልጣን ክፍፍል የአገሪቱን ብሄር ብሄረሰቦች ጥንቅር ያገናዘበ ይሆናል ብለዉ ተናግረዉ ነበር። ሆኖም ዛሬ ይህ ከተነገረ ከሃያ አመታት በኋላና ይህንን የተናገረዉ መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት ከተለየ ከሁለት አመታት በኋላ የሕወሓት የሥልጣን ቁጥጥር ጭራሽ አጋሽቦ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከትግርኛ ቋንቋ ዉጭ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወደ ሥልጣን አይመጡም የሚባልባት አገር ሆናለች። በኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ በገነባዉ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ የዕዝ፤ የክፍለጦርና የመምሪያዎች አዛዥ ለመሆን ዋነኛዉ መለኪያ የትግራይ ብሄረሰብ ተወላጅና የሕወሓት ታማኝ አገልጋይ መሆን ነዉ እንጂ ችሎታ፤ ልምድ፤ ብቃትና የወታደራዊ ሳይንስ ክህሎት አይደለም። ችሎታ፤ ልምድና ብቃት መመዘኛ ሆነዉ የሚቀርቡት በመጀመሪያ ለሹመት የታጨዉ መኮንን የትግራይ ተወላጅ እና የሕወሓት ታማኝ አገልጋይ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ብቻ ነዉ።

የሕወሓት የስልጣን ሞኖፖሊ በወታደራዊ ደህንነት ተቋሞች ላይ ብቻ ተወስኖ አያበቃም። አብዛኛዉን የአገሪቱ የኤኮኖሚና ማህበራዊ ተቋሞችም ወይ ከላይ አለዚያም ከታች ሆነዉ የሚቆጣጠሩት የሕወሓት ታማኝ አገልጋይ ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸዉ። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለይስሙላ የተቀመጠና ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የመጡ ሰዎች የሚገኝበት አገዛዝ አለ፤ በዚህ አገዛዝ ዉስጥ ደግሞ አገሪቱን ወዳሰኘዉ አቅጣጫ በዘፈቀደ የሚዘዉረዉና ከትግርኛ ተናጋሪዎች ዉጭ ሌሎች የማይገኙበት በአገዛዙ ዉስጥ ሌላ ቡድናዊ አገዛዝ አለ። ዛሬ እነ ኃ/ማርያም ደሳለኝ፤ አባዱላ ገመዳና ደመቀ መኮንንን የመሳሰሉ ምስለኔዎች ስልጣን ላይ የተቀመጡ ነገር ግን የሕወሓት ጌቶቻቸዉ ከሚነግሯቸዉ ዉጭ በራሳቸዉ ምንም አይነት ትዕዛዝ መስጠት የማይችሉ አሻንጉሊቶች መሆናቸዉን እነሱ አራሳቸዉም የተገነዘቡት ይመስላል።

ግንቦት ሰባት- የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዛሬ አራት አመት (እ.ኤአ.በ2009) በዘር የተደራጀዉን የወያኔ መከላከያ ተቋም አደረጃጀት ምን እንደሚመስል በመረጃ አስደግፎ ለአለም ህዝብ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። ግንቦት ሰባት ይህ ይሻሻላል ወይም አደረጃጀቱ በሂደት ይለወጣል ተብሎ የተነገረለት የወያኔ መከላከያ ተቋም ጭራሽ ከድጡ ወደማጡ እያዘገመ መሆኑን በጥናታዊ መረጃዎች አስደግፎ እንደሚከተለዉ ያቀርባል። በዚህ ጥናት ዉስጥ የወያኔን መከላከያ ሠራዊት ይዘትና ቅርጽ በሚገባ የሚያዉቁ፤ ሠራዊቱን ለቅቀዉ የወጡና አሁንም በሠራዊቱ ዉስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ከፍተኛ መኮንኖች ተሳትፈዋል። ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበዉ ሠንጠረዥ የተለያዩ የመከላከያ ተቋም የስልጣን ቦታዎችን፣ በስልጣን ቦታዎችን እነ ማን እንደተቀመጡና  የተወለዱበትን ብሄረሰብም ጭምር ያሳያል።

Am1 (1)
Am2

Am3

Am4

Am5

Am6

‘አሸባሪ ብዕሮች’ (ክንፉ አሰፋ)

$
0
0

ክንፉ አሰፋ

ይህች አጭር ጽሁፍ የተወሰደችው በአውስትራሊያ ከምትታተም “አሻራ” ከተሰኘች መጽሄት ልዩ እትም ላይ ነው።

የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር “ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።” ነበር ያለው።

2053fountain_pen አንባገነኖች ፕሬስን ይፈራሉ። ይጠላሉም። የህዝብ መሰረት የሌላቸው፤ በራሳቸው የማይተማመኑ ሁሉ ነጻ ሃሳብን ይጠላሉ። ነፍጥን ብቻ ተማምነው በሕዝብ ጫንቃ ላይ የሚቀመጡ፤ እንደምን ነጻ አመለካከትን ሊቀበሉ ይችላሉ?  ፍጹም አንባገነናዊነት በሰፈነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች፤  ህግ አውጭው ህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ  የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ የለም። ይህንን ቁጥጥር በጥቂቱም ቢሆን ተክቶ ይሰራ የነበረው ነጻው ፕሬስ ነው። ከዚህም አልፎ ሕዝቡ መብቱን እንዲያውቅና መብቱንም እንዲያስከብር ብዙ ሰርቷል-ፕሬሱ። ሙስናን አጋልጧል፣ እንደ እንባ ጠባቂም እየሆነ የህዝብን በደልም ይፋ አድርጓል። ይህን የተቀደሰ ተግባር ማከናወን እንደወንጀል፤ ጠንከር ሲል ደግሞ እንደ ሽብርተኝነት የሚቆጠርበት ሃገር ሆናለች የዛሬይቱ ኢትዮጵያ።

መብትን ማወቅ እና ማሳወቅ፤ ‘ህዝብ ለጦርነት እንዲነሳ ማድረግ፤ ወይንም በስራዓቱ ላይ ጥርጣሬ መፍጠር  ነው’ ተብሎ ከተተረጎመ ደግሞ ጋዜጠኛን በአሸባሪነት መፈረጁ ብዙ ሊደንቀን አይገባም።

ኢትዮጵያ ላለፉት አስርት-አመታት ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ በቁጥር አንደኛ ደረጃ ላይ የነበረች ሃገር ናት።  አሁን ይህንን ደረጃዋን ለቃለች። እድገትና  ትራንስፎርሜሽኑን ተከትሎ ከመጡት ለውጦች አንደኛው መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ የአንደኝነት ደረጃዋን ያጣችው ታዲያ ትራንስፎርሜሽኑ ይዞት በመጣው መሻሻል አይደለም።  ነጻ ፕሬሱ ከሃገሪቱ እንዲጠፋ በተደረገ ሁለገብ ጦርነት እንጂ። አብዛኛው ጋዜጠኛ ተሰድዷል፣ ጥቂቶቹ ታስረዋል፣  አንዳንዶቹም  አቅማቸው ተሟጦ አልቆ፤ ዝም ብለው እንዲቀመጡ ተደርገዋል።  ለነጋሪ የተረፉትንም እስከዛሬዋ እለት ድረስ እያሳደዷቸው ይገኛሉ።

ከጅምሩ በፕሬሱ ላይ የተከፈተው የገዥው ፓርቲ ውግያ ቀላል አልነበረም። ፕሬሱ ግን እለት ተዕለት የሚያርፍበትን የአንባገነኖች ጡጫ ሁሉ ችሎ ብዙ ተጉዟል። እየተንገዳገደ፤ እየወደቀና እየተነሳ የህዝቡን የህሊና ንቃት እንዲሰፋ ከማድረጉም ባሻገር በኢትዮጵያ የማንበብ ባህል እንዲዳብር ነጻው ፕሬስ ተግቶ ሰርቷል።   የህትመት ዋጋ እስከ 500% እንዲጨምር ቢደረግም ፕሬሱ አልቆመም ነበር። ጋዜጠኞች እንደጥጃ እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣  እየተሰቃዩም  ስራቸውን ላለማቋረጥ መትጋታቸውን አላቆሙም። በካድሬ ዳኞች ፍርደ-ገምድል ፍትህ ሲሰጣቸው፤  ያለ አግባብ በእስርና በገንዘብ ሲቀጡም ሰራቸውን አላቋረጡም…

የአሜሪካው ፍሪደም ሃውስ በተከታታይ ባወጣቸው ዘገባዎች ኢትዮጵያን ፕሬስ (Status: NOT FREE) “ነጻ ያልሆነች” ሃገር ሲል ፈርጇል።  የፕሬስ አዋጁንም ፍጹም አፋኝ ሲል ይከሳል። የፈረንሳዩ ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ፣ የኒውዮርኩ ሲ.ፒ.ጄ. እና የብራስልሱ አይ.ኤፍ.ጄ. በሽብር ክስ የተያዙ የጋዜጠኖችን ሰነድ እያከታተሉ አሳፋሪነቱን ቢገልጹም አፍ እንጂ ጆሮ ከሌለው ስርዓት ያገኙት የስድብ ምላሽ ብቻ ነው። አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዋችም አፈናውን  ይፋ ማድረጉን ተያይዘውታል።  ከገዥው ፓርቲ የሚያገኙት ምላሽ “የኒዮ ሊበራል” አቀንቃኞች የሚል ስድብ እና ዛቻ ብቻ ነው።

ከምርጫ 97 ነኋላ ግን የህወሃት እድገት እና ትራንስፎርሜሽን፤  ጫን ያለ ነገር ይዞ ብቅ አለ።

ሽብርተኝነት!

ከዚህ በኋላ ጋዜጠኛ በህገ-መንግስት ሳይሆን፤ ህጉን በሚጻረረው አዋጅ መዳኘት እንዳለበት ተነገረ። ስርዓቱም በባሩድ ሳይሆን ይልቁንም በብእር ጫፍ እንደሚሸበር አረጋገጠ።

ይህ የሽብርተኝነት አዋጅ ቃል በቃል የተቀዳው ከአሜሪካ እና ከእንግሊዝ  መንግስታት ሰነድ መሆኑን ሃይለማርያም ደሳለኝ ለቢቢሲ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ድንቅ ነው። ሰውየው ግን ምን እየተናገሩ እንደሆን የሚያውቁት አይመስልም። በዚህች በሙት መንፈስ የምትመራ ሃገር ሌላም ብዙ እንግዳ ነገር እንሰማለን።  የቡሽ አስተዳደር ከቶኒ ብሌየር ጋር አልቃይዳ የተባለውን አደገኛ ሽብርተኛ ለማጥፋት የነደፉት ይህ ሰነድ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞችን ለማጥፋት እየተጠቀሙበት እንደሆነ ነው የሚነግሩን። የፈረንጆቹ ሽብርተኝነት (terrorism)  ሲተረጎም፤  “በሃይማኖት ወይንም በርዕዮተአለም ጥላ ስር ተደራጅቶ አመጽን የማድረግ ተግባር” እንደሆነ ይነግረገናል።

በሽብርተኝነት ተወንጅለው በየእስር ቤቱ የተጣሉት የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ የትኛውን ርዕዮተ-አለም ወይንም ሃይማኖት ተንተርሰው አመጽ እንደፈጠሩ፣  የትኛውን አውሮፕላን እንዳስጠለፉ፣ የትኛውን ህንጻ እንዳፈረሱ፣ የትኛውን ንጹህ ዜጋ እንደገደሉ አልተነገረንም።

እርግጥ ነው። የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እየተቹ ይጽፋሉ። ትችቱ ታድያ ለውጡ ላይ አይደለም። የለውጡ አቅጣጫ ላይ እንጂ። አቅጣጫው ትክክለኛ መስመር መያዝ እና አለመያዙን መተቸት “ወንጀል ነው” ሲባል ለቀረው አለም አዲስ ነገር ሊሆን ይችላል። ከዚያ የባሰም አለ። ገዢውን ፓርቲ መተቸት እና ስለ ለውጥ አስፈላጊነት መጻፍ በሽብርተኛነት ያስከሰሰ ወንጀል ሆኖ ሰማን። አስቂኙ ነገር፤ አዋጁ ለኦሳማ ቢን ላደን ሽብር በምእራባውያን ሀገሮች የረቀቀ የጸረ-ሽብር ህግ መሆኑ ነው።

ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ሲፈረጁ ነው ነጻው ፕሬስ በኢትዮጵያ አፈር የለበሰው። ይህ የመጨረሻ ጥይታቸው መሆኑ ነው። አለማቀፍ የጋዜጠኞች ተሟጋች ተቋማት ሳይቀሩ ተስፋ የቆረጡ እስኪመስል ድረድ  በዘንድሮ  አመታዊ  ዘገባቸው የኢትዮጵያን  ጉዳይ ችላ ብለውታል። እነዚህ ተቋማት በየአመቱ ስለኢትዮጵያ ፕሬስ ሁኔታ የሚያወጧቸው ዘገባዎች የሚዘገንኑ ነበሩ።  ወያኔን የማይማር፣ የደነዘዘ እና የማይለወጥ ስርዓት አድረገው ስላዩት ችላ ያሉት ይመስላል። ሃያ አመት የማይሰማ፣ ያሃ አመት የማይሻሻል፣ ሃያ አመት የማይማር ስርዓት… ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ሆነባቸው።

በምርጫ 97 ሰሞን በርካታ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች ቃሊቲ ተወርውረው ነበር። በጉዳዩ ላይ  የአምነስቲ  ኢንተርናሽናል  ዲያሬክተር  ከነበሩት ዶ/ር  ማርቲን  ሂል ጋር ስናወራ አንድ ጥያቄ  አነሱልኝ።

“ለመሆኑ ሰርካለም ፋሲል ላይ ለምን እንዲህ ጨከኑባት? ”  የሚል ነበር የማርቲን ጥያቄ። እኝህ ታላቅ ሰው ይህን ጥያቄ ለምን እንዳነሱልኝ  አሁን ነው የተገለጠልኝ።

የሰርካለም ፋሲልን ጉዳይ ማንሳቱ የኢትዮጵያን ፕሬስ የሰቆቃ ጉዞ በከፊልም ቢሆን ይገልጸዋል።

ሰርካለምን ከባለቤትዋ እስክንድር ነጋ ጋር አፍነው ወደ ቃሊቲ ሲወስዷት ነብሰ-ጡር ነበረች። የመውለጃዋ ቀን ሲደርስም ከእስር አልለቀቅዋትም። በምጥ ስቃይ፣ ነብስ ውጭ፤ነብስ ግቢ ሁኔታ ውስጥ ሆና እንኳን አሳሪዎችዋ ርህራሄ አላሳዩዋትም ነበር።   በመጨረሻ እዚያው ቃሊቲ እስር ቤጥ ናፍቆትን ተገላገለች።  በዚያ የጭንቅ ወቅት የሚይዘውን እና የሚጨብጠውን ያጣ ስርዓት ምን እያደረገ እንደነበር እንኳን በውል አየውቀውም።  “የመንግስት ጠላት”  የሚል ታፔላ ተለጥፎለት የሚንቀሳቀስ ጋዜጠኛ፤ ሊወድቅ ከሚንገዳገድ ስርዓት  ከዚህም በላይ ሊደረግበት እንደሚችል ለማስረዳት ሞከርኩ።

ነብሰ-ጡርዋ ሰርካለም የተከሰሰችው ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ እና ለማፍረስ፣ ጥላቻን የምታስፋፋ፣ ጥርጣሬን የምትነዛ… ተብላ ነበር። በ “ምህረት” ከእስር እንደተፈታች ወደ ኬንያ ተሰደደች። በኋላም ሀገር ሰላም የሆነ ሲመስላት ከስደት ተመለሰች። ይህች ወጣት እትብትዋ ወደተቀበረባት ሃገርዋ ብትመለስም እንደዜጋ የመኖር ዋስትናዋ ግን በአንባገነኖች መዳፍ ስር ሆነ። በኑሮዋ እና በትዳርዋ ዙርያ ካለፈው የባሰ ችግር መጣባት። ባለቤትዋ እስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት ተከሶ በፍርደ-ገምድል ዳኛ ለአመታት ተፈረደበት። ቤት ንብረታቸውም በግፍ ተቀማ። ከዚህ በኋላ በመኖር እና ባለመኖር የሚደረግ ምርጫ ውስጥ መግባት ግድ ሆነባት። እናም ባለቤትዋን ወህኒ ቤት ጥላ ዳግም ተሰደደች። እስዋም ሆነች በሰቆቃ የተወለደ ልጅዋ በመንገድ ከመወርወራቸው በፊት ያላቸው አማራጭ ይህ ብቻ ነበር።  የሚወዷት ሃገራቸውን ጥለው ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ስደተኛ ጋዜጠኞችን ተቀላቀሉ። እንደቀልድ የሚነገር ሌላም እውነታ አለ። ከ”ሽብርተኛ” ጋር በስልክም ሆነ በአካል ያወራ፣ አብሮ የታየ፣ አብሮ ሻይ የጠጣ፣ የተነካካ ሰው ሁሉ ሽብርተኛ  እንደሆነ አዋጁ ይደነግጋል። ሰርካለም እና ናፍቆት በእስር ያለው እስክንድር ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት ሽብርተኛ ተብለው ሊወነጀሉም ይችሉ ነበር።

በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ፍርሃት ውስጥ እንዳሉ ግልጽ ነው። በጋዜጠኛ የሚናድ ሀገ-መንግስት ይዘው ስንት አመት ሊዘልቁ እንደሚችሉ ባናውቅም፤ አሁንም ጋዜጠኞችን ሲያስሩ ይህንንኑ ዘፈን ይደጋግሙታል። 99.7 በመቶ በህዝብ የተመረጠ መንግስት መራጩን ሕዝብ ከቶውንም መፍራት አልነበረበትም። ነገሩ ስላቅ ነው።  ይህ ቀልዳቸው ግን የህዝቡን ንቃተ-ህሊና ዝቅ አድርጎ ከመመልከት የሚመጣ ይሁን እንጂ ጉዳዪ ሌላ ነው። አንባገነኑ ናፖሊዮን ቦናፓርት ብሎታል። ከሺ ሳንጃ አንድ ጋዜጠኛ ያስፈራል።  የጭቆና እና የአፈና ስርዓት ገንብቶ ለረጅም አመት የቆየ አንባገነን በታሪክ አልታየም።

የፈቀደውን መምረጥ የሚችልን ህዝብ አዲስ ዘመንን ብቻ እንዲያነብ መምከራቸው ብቻ አይደለም በሕዝብ ላይ ያላቸው ንቀት፤ የፍትህ ስርዓቱን ለበቀል የሚዘረጋ እጃቸው አድርገው ነጻውን ፕሬስ ለማጥፋት ሲጠቀሙበትም እጅግ ያንገበግባል።  የህግ የበላይነትን እንዲህ እያደረጉ ናዱት።

ኢሕአዴግ  የፕሬስ ነጻነትን  ለህዝቡ እንዳጎናጸፈ ይመጻደቃል።  ይህ ስህተት ነው።  መናገር፣ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ፣ መጻፍ፣ … ወዘተ መብት የሰው ልጅ የተፈጥሮ ጸጋ እንጂ አንድ ስርዓት የሚያጎናጽፈን ጉዳይ አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሀው ስርዓት እነዚሁኑ መብቶች እየጨፈለቀ እነሆ ሃያ ሶስት አመታትን ዘልቋል።

ነጻ ፕሬሱን ለምእራባውያን የዲሞክራሲ ማሳያ አድርጎ እንደተጠቀመበት እርግጥ ነው። የአለም ባንክ እና ለጋሽ ሃገሮች በኢትዮጵያ የሳንሱር አዋጅ እንደጠፋ ነው የሚነገራቸው። የእርዳታና ብድር እጃቸውን የሚዘረጉልንም ከቀድሞው የተሻለ የመጻፍና የመናገር ነጻነት አለ ብለው ስለሚያምኑ ይመስላል። ግና ይህ የሳንሱር አዋጅ በአእምሮ ሳንሱር መተካቱን  የምናውቀው እኛ ብቻ ነን። ሳንሱር ቢኖር ይህ ሁሉ ጋዜጠኛ ባልታሰረ፣ ባልተንከራተተ እና ባልተሰደደ ነበር።

ምርጫ መጣ! ጋዜጠኛ ይውጣ! እንዲሉ… በቅርቡ በስድስት ነጻ ፕሬስ ህትመቶች ላይ ከተመሰረተው ክስ ጋር በተያያዘ  አስራ ሁለት ጋዜጠኞች ለስደት መብቃታቸው ተዘግቧል። በጭላንጭል የነጻነት ድባብ ይንቀሳቀሱ የነበሩት፤ አዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ፣ ጃኖ፣ አፍሮ ታይምስ እና እንቁ ጋዜጦች እንዲቋረጡ ተደርጓል። ጋዜጠኞቹም በአሸባሪነት ሽፋን ተከስሰው  እስከ አስራ ስድስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተበይኖባቸው የነእስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርእዮት አለሙ እጣ ይደርሳቸዋል። እነዚህ ጋዜጠኞች የነበራቸው አማራጭ የሽብር አዋጁ ሰለባ መሆን አልያም አገር ለቀው መሰደድ ነው። ተሰደዱ።  የስደተኛ ጋዜጠኛውን ቁጥር ወደ 210 አሳደጉት።

ውንጀላው ግን በተያዘለት መርሃ-ግብር ቀጥሏል።  ሰሞኑን “ያልተገሩ ብዕሮች” በሚል ርእስ በኢቲቪ የቀረበውን “ዘጋቢ ፊልም” ያስተውሏል?  በአንድ በኩል የጋዜጠኖቹ ጉዳይ በህግ የተያዘ እንደሆነ ይነግሩናል። በሌላ በኩል ደግሞ “ልማታዊ” ተዋንያን እና የስርዓቱ አጎብዳጆችን በመገናኛ ብዙሃን አቅርበው ፍርድ እንዲሰጡ ያደርጓቸዋል። በእርግጥ በመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ አንድ ተጠርጣሪን በወንጀለኝነት መፈረጅ አዲስ ነገር አይደለም። የፍትህ አካሉ ውሳኔ ከመስጠቱ  በፊት ተጠርጣሪው በኢቲቪ የፖለቲካ ፍርድ ይበየንበታል።  ከዚያም እንደ “ዳኛ” ልዑል አይነት የሲቪል ሰርቪስ ምርቶች ውሳኔውን ያጸኑታል።

በዚያ የኢቲቪ ቅንብር ሃይሌ ገብረስላሴም ተዋንያን ነበር።  የሚናገረውም የትዬለሌ። “ትልቁ የጦር መሳርያቸው ፕሬስ ነው።… ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይባላል… ” ይለናል ሃይሌ ገብረስላሴ። “ዘጋቢ” ፊልሙም  የእነ እስክንድር ነጋን ፎቶ፣ የእነ ተመስገን ጽሁፎች ያሳየናል። የዚህ ድራማ ሌሎቹ ተዋንያን ከሙያው ጋር የተያያዝን ነን የሚሉ አድርባዮች ናቸው። ሃይሌ ግን ምን ቤት እንደሆነ ግልጽ አይደለም።  በየትኛውስ እውቀቱ ነው ፍርድ ሊሰጥ የደፈረው? “አንድ ጋዜጣ  የውሃ አምራች ድርጅትን እንዲዘጋ አድርጓል።”  ሲል ሃይሌ በዚያ “ዘጋቢ ፊልም” ይወነጅላል። አንድ ጋዜጠኛ እውነትን ጽፎ  የንግድ ድርጅትን ወይንም የመንግስት ተቋምን ማፍረስ ወይንም በተቋማቱ ላይ ጥርጣሬ መፍጠር ከቻለ እንዲያውም ጀግና ነው የሚባለው። ጋዜጠናው የሚጽፈው ውሸት ከሆነ ደግሞ ፍርዱን ለህዝቡ ለምን አይተውለትም?

አብራሃ ደስታ ሌላው በአሸባሪነት ሽፋን የተከሰሰ ጋዜጠኛ ነው።  አብርሃ አሸባሪ መሆኑ የተረጋገጠው ፍርድ ቤት ሲገባ እና ሲወጣ ነው።  ሲገባ በጭብጨባ ሲወጣ በጭብጨባ ተሸኝቷል። ህዝብ በነቂስ ወጥቶ  ኣብርሃ ጀግና! የነፃነት ታጋይ! እንወዳሃለን፤እናከብርሃለን ሲለው እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ የት ነበሩ?

ያልተገራ አንደበታቸውን በመገናኛ ብዙሃን ሲከፍቱ የነበሩት እነዚህ ተዋንያን የሚነግሩን እጅግ አሳፋሪ ነገር ነው።  አጠቃላይ ይዘቱ በመንግስት ላይ ምንም አይነት ትችት መቅረብ የለበትም የሚል እንድምታ አለው። የህወሃትን አንባገነናዊነት መተቸት፣ የስርዓቱ ፖሊሲዎች መንካትና በባለስልጣናቱ ላይ ጥርጣሪ እንዲኖር ማድረግ… ስርዓቱን ያፈርሰዋል ነው እያሉን ያለው።  ህግ አውጭው ከህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ  የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ በሌለበት ሃገር ነጻው ፕሬስ ከዚህ ውጭ ምን ይስራ ነው የሚሉት? ፕሮፓጋንዳ?

ለፕሮፓጋንዳውማ በርካታ አማራጮሽ አሉ። አዲስ ዘመን ጋዜጣም አለልን። ለ90 ሚሊዮን ህዝብ የቀረው ጋዜጣ።  አዲስ ዘመን  በቁጥር ስንት ሺ እንደሚታተም ባናናውቅም በኪሎ እየተሸጠ የሸቀጥ እቃ መጠቅለያ ሆነ እንጂ።  ‘የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተመረቁ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሱዳን ሄዱ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሱዳን ተመለሱ። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ 11 እጅ እንደሚያድግ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።’  …. የሚሉ ዘገባዎችን እየያዘ ከሸቀጥ እቃ መጠቅለያነት ውጭ ለሚመጻደቁለት እድገት ምንም እንዳልፈየደ እንኳ አያውቁትም።

የመገናኛ ብዙሃን አፈናው በነጻ ፕሬሱ ላይ ብቻ አልተገደበም። በኢትዮጵያ የመረጃ መረቦችም ታፍነዋል።  ከሰብ ሰሃራ አፍሪካ በኢንተርኔት ይዞታ እና አገልግሎት የመጨረሻዋ ሃገር ናት። ኢንተርኔቱን የሚቆጣጠረው መንግስታዊው ቴሌኮም ስርዓቱን የሚተቹ ድረ-ገጾችን በቻይና ቴክኖሎጂ እንዲዘጉ አድርጓል።  የዜጎችን ስልክ በህገወጥ ማንገድ መጥለፍ የተለመደ ተግባር ነው። እንዲሁም ስካይፕ እና ቫይበር ያሉ የቮይስ ኦቨር ስልኮች ደግሞ ፊን ፊሸር በተባለ የኮምፒዩተር ቫይረስ አማካኝነት ይጠለፋሉ።  እንዲህ እያሉ በዜጎች የግል ህይወት ሳይቀር እየገቡ ቴሌን ሙሉ በሙሉ የስለላ ተቋም እንዳደረጉት የአሜሪካው ሂዩማን ራይትስ ዋች ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያን ወደ ጨለማ ዘመን እየወሰዳት ያለው ይህ የህወሃት ስርዓት የኢንተርኔት ተጠቃሚው  እንዲያሽቆለቁል እየጣረ እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት። በተለይ የፌስቡክ አብዮትን ለመግታት ስለሚሻ የኢንተርኔት አገልግሎትን ማዳከሙ ላይ ጥብቅ አቋም ይዟል። መንግስት አልባዋ ሶማልያ እንኳን፣  ስድስት የቴሌፎንና ስልክ አቅራቢ ኩባንያዎች አሏት። በዚህ ቀላል ቴክኖሎጂ እንኳን ከሶማልያ በታች ሆኖ ስለ እድገት መመጻደቃቸው ሊያፍሩበት ይገባል።

እጅግ የሚያሳዝነው ይህ ስርዓት ለፈጸመው ለዚህ ሁሉ በደል ለሽልማት መብቃቱ ነው። ልማታዊው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ በአርቲስቶች ስም ለሟቹ ጠቅላይ ሚ/ር የወርቅ ብዕር ነበር ያበረከተላቸው። ብዕር ትልቅ ትርጉም አለው። ብእር የሚሸለም ሰው ለፕሬስ ክብር ያለው፤ ፕሬስን የሚያከብር ሰው ነው። ሰራዊት የወርቅ ብዕር እንዲሸልም አርቲስቶች አልወከሉትም ነበር።  ይህንን ሲያደርግ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እስር ቤት ውስጥ ይንገላቱ ነበር። ሰራዊት ይህንን ሲያደርግ  የአለም አቀፍ ህብረተሰብ ጠ/ሚኒስትሩን የፕሬስ አፈና በእጅጉ ያወግዝ ነበር።   እንደ ሰራዊት ያሉ ሃላፊነት የጎደላቸው ሰዎች ብዙ አይደሉም።  ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ሲሉ እንዲህ አይነት ስራ እየሰሩ በሰው በቁስል ላይ እንጨት ይሰድዳሉ። ታዲያ እንደነዚህ አይነቶቹ አድርባዮችም ለፕሬሱ መጥፋት ሚናቸው ቀላል አይደለም። የማያልፍ የለም። ሁሉም ያልፋል። መንግስትም እንደ አንሶላ ተጠቅልሎ ይሄዳል። ይህ ቀን አልፎም ለትዝብት ያበቃናል።

ማን ነበር “ፕሬስ  የሌለው መንግስት ከሚኖረን  መንግስት የሌለው  ፕሬስ  ቢኖረን  እንመርጣለን።” ያለው? እርግጥ ነው። ያለ ፕሬስ የሚኖር ህዝብ በጨለማ ነው የሚጓዘው። ያለ ነጻ አስተሳሰብ እና ያለ ነጻ ፕሬስ፣  እድገት ይመጣል ማለት አይታሰብም። እንዲያው የህዝብን ንቃተ-ህሊና ዝቅ አድርጎ መመልከት ይሆናል እንጂ።


ትምክህተኛና ጠባብ ማን ነው? –ከአስገደ ገ/ስላሴ መቀሌ

$
0
0

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ

የህወሓት ኢህአደግ መንግስት ፖሊሲና ስትራተተጂ ስልጠና በሚል ሽፋን ተማሪዎች በሃገር ደረጃ ከ300 ሺ በላይ የፍትህ አካላት ማለት ዳኞች ቸቃብያን ሕግ ፖሊሶች በሙሉ መጀመርያ በየ ክልሉ ለ15 ቀናት ስልጠና ተሰጣቸው በተለይ በትግራይ የፈትህ አካላት በውቅሮ 15 ቀን በአክሱም ከዛ በላይ እየሰለጠኑ ይገኛሉ::

በዚሁ ስልጠና በሁሉም ቦታ ማለት ይቻላል:: የድሮ ነገስት በማንሳት በፊሊም የተቀረፀ እነዛ ነገስታት የትምክህትና የጠባብነት ምንጭ መሆናቸው:: ሃገራችን ዘር ሃይማኖት ቢሄር ከቢሄር እያጋጩ የትምክህትና ጠባብነት መፈንጫ አድርጎዋታል በማለት ሲያማርሩ ከርመዋል:: በሌላ በኩል የህወሓት ኢህአደግ መንግስት ካለፉት ስርዓቶች የበለጠ ሃገራችን እንደቀየረ ሲነግሩን ከርመዋል::

በተሰብሳቢዎች ግን የምትነግሩን ያላቹሁ በንቃተህልናቸው አሁን ካለው ትውልድ እጅጉን የወረዱ ነበሩ:: ያም ሆኖ ሃገራችን አንድነቷና ሉኦላዊነቷ ጠብቃ እንድትኖር አድርጓታል:: እናንተ ግን የዚህች ሃገር ሉኦላውነቷ ያስደፈራቹሁ ናቹሁ:: ኢትዮዽያ የባህር በሯን አሳልፋቹሁ ሰጥታቹሁ በሁሉም ነገረ ጠገኛ አድርጋቹሁን አላቹሁ ሃገራችን በቋንቋ በወንዝ እንድትከለልና ዜጎች በፈለጉት በሃገራቸው ክልል ሰርተው እንዳይኖሩ በማደረግ ጠባብነና ትምክህት እንዲነግስ ከማድረጋቹሁ አልፎ የሃይማኖት የቢሄር ግጭት ተስፋፍቶ ዜጎች እርስ በእርሳቸው እንዳይተማመኑ አድርጋቹሁ እነ አፀይ ዩሃንስ አፀይ ምንሊክ የቴክኖሎጂ እውቀት ባልነበረባቸው ምንም እንኳ አንዳንድ ስህተቶች ቢኖሩዋቸው እቺ ሃገረ ስትደፈር የኢዮዽያ ህዝብ እንደ አንድ ሰው ሆኖው ሕብርና ሃገራዊ ወኔን በመፍጠር ሃገራችን ከባዕድ ወረራ ተከላክለው አቆይቶውናል:: እናንተ ግን በጥቂት የፓርቲ አመራር ውሳኔ ብዙ ስህተት ፈፅማቹሃል:: በተጨማሪም ለህዝቡ ይሁን ለመንግስት ሰራተኛ በአንድ ወጥ በማስተማር ፈንታ የትግራይና የኦሮሞ ህዝብ የአፀይ ምንሊክ መጥፎ ገፅታ በፊልም በማሳየት በአማራም በኦሮሞ ወይም የትግራይ ነገስታት መጥፎ ገፅታ በማሳየት በሌሎች ቢሄሮች ቢሄረሰቦችም እንደዚሁ እንዲናናቁ አድርጋቹሃል ተብለዋል::
በኔ እምነትም ትምክህትና ጠባብነት እንዲስፋፉ የሚያባብሱት ያላቹሁ የህወሓት ኢህአደግ መሪዎች ናቸው:: ስለዚህ ትምክህተኛና ጠባብ ማንው ለሚለው መልሱ ኢህአደግ ነው:: ይህ ደግሞ የኢህአደግ መሪዎች ሕብረተሰቡ በትምክህትና ጠባብነት ስሜት ካልከፋፈሉት ስልጣናቸው እድሜ የለውም:: ሌላ የኢህአደግ መሪዎች የትምክህት ቋት መሆናቸው መረጋገጫ በዚህች ሃገር ከኛ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ (አይዶሎጂ) ወዲያ የለም ከነሱ እምነት ውጭ የራሱን ሃሳብ ይዞ የተነሳ ፓርቲ ወይም ቡድን ወይም ግለሰብ እንቢ ላለ ሰው ጥይት አጉርሰው ነው መልሱ:: ሌላ ቀርቶ የሃገራችን የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ እየተነተኑ ለህዝብ መረጃ የሚያደርሱ ጋዜጤኖች አምዳውያን የደሀረ ገፅ ጦማርያን የፓርቲ መሪዎች ከሃገር ውጭ እንዲሰደዱ በወህኒ ቤት ታስረው እንዲበሰብሱ ሌሎችም ተሸማቅቀው እንዲኖሩ ተደርገዋል እየተደረጉን ናቸው::

መላው የኢትዮዽያ ህዝብ ሙሁራን ተማሪዎች የመንግስት ሰራተኖች የህወሓት ኢህአደግ መሪዎች አሰተሳሰብ ካልተቀበለ ከሁሉም የስራ እድል ጥቅማ ጥቅም የማግኘት ነፃ ሆኖ እንዳይንቀሳቀስ ተደርገዋል ድርጊቱ እየቀጠለ ነው:: አሁንማ የኢትዮዽያ ህዝብ የመሬት ባለቤትነቱ ተነጥቆ የኢሀአደግ መሪዎች ጢሰኛ (ተጠማኝ) እንዲሆን ተደርገዋል:: የሃገሪተቱ አበዛኛው ብዙ ገንዘብ ሊያስገኙ የሚችሉ የእንድስትሪ ማእከላት በኢሀአደግ መሪዎች ጠፍረው በመያዝ የግል ባለሃብቶች እንዲቆረቁዙ አድርጎዋቸዋል:: በሌላ በኩል የሞያ የሰራተኛ የሴቶች የወጣት ማሕበራት የእምነት ተቋማት በሙሉ የኢህአደግ አደረጉዋቸው:: እምነቶች በመመርያ ካልተጓዙ የማይኖሩበት ሁኔታ ተፈጥረዋል::

የተቃዋሚ ፓርቲዎች በአስሳሰብ የላቁ ሆኖው ካልተገኙ አስተሳሰባቸውን በሰላማዊ ውድድር እንደማሸነፍ መጥፎ ስሞች በመለጠፍ ትምክህተኛ ፈላጭ ቆራጭ ሕግ በማፅደቅ እንዲደቁ ተደርገዋል እየተደረጉ ይገኛሉ:: በዚሀ ምክኒያት የህወሓት ኢህአደግ ፓርቲ በፈጠረው የጠባብነት ባህሪያትና ተግባር ጠንቅ ብዙ የተቃዋሚ ኃይሎች ነፍጥ አነሱ ልክ ትምክህተኛው ህወሓት ወደ ስልጣን በመጣበት መንገድ ስልጣን ለመያዝ በረሃ ገብተዋል እየገቡም ይገኛሉ:: ሌሎችም በአሸባሪነት ሰበብ በየ ወህኒ ቤቱ ታጉረዋል:: የዚህ አደጋ ውጤት የህወሓት መሪዎች ከደርግና ሌሎች መንግስታት ትምክህትና ጠባብነት ከፈጠሩት ተሞክሮ እንደማሻሻል ፈንታ የባሰው ትምክህተኛ ጠባብነት አንግሰዋል:: ለዚህ ጉዳይ ቆም ብለው አስበው ሰክነው በሰላም ካልፈቱት ሃገራችን ኢትዮዽያ ከባድ አደጋ እያንጃበባት ነው:: ለሚፈጠረው አደጋ ደግሞ ተጠያቂዎች የህወሓት ኢህአደግ መሪዎች ናቸው:: የኢትዮዽያ ህዝቦች እንደሆን በቦታችን ነን አንበረከክም::

የሰሞኑ የሥልጠና ፓለቲካ

$
0
0

የስምኦን ልጅ በረከት ከመክተብም አልፎ የሃገሪቷን ልሂቃን ኢንዶክትሪኔት እያደረገ ይገኛል። እስከማስታውሰው ድረስ የበረከት የመጨረሻ ህልም በዩንቨርስቲ ተጋባዥ መምህር ሆኖ ሌክቸር መስጠት ነበር። እነሆ!የልብን መሻት በማየት በላቀ ደረጃ የሚሰጠው ” ልማታዊ መንግሥት ” የሌክቸረሮች ሌክቸረር አደረገው። ርግጥ የድርጅቱ ከአጠገቡ አለመኖርም ህልሙን ያለጊዜው እንዲሳካ ሳያግዘው አልቀረም ። እኔ እምለው እሱ ባይኖር ኖሮ ማን ጵፎ ማን ያሰለጥን ነበር? አደራችሁን! ዶክተር ደብረጲዬን ብላችሁ የሀይሌን ልብ እንዳታቆሟት። የሀይሌ ልብ ከቆመ ሀገሪቷ በሁለት አመት ውስጥ ሁለት ጊዜ መስቀለኛ መንገድ ላይ ስለምትቆም ማናችንም አንፈቅድም ። ከሀይሌ ጋር ያላባራ ፀብ የገጠመው በረከትም ቢሆን!
ወደ ቁምነገሩ ልመለስ ።ወዳጄ ሰነዶቹን ሲልክልኝ ከተለመደው ውጭ አዲስ ነገር አይኖረውም በማለት ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር። አላነበብኩትም ላለማለት ብቻ ስልኬን ከፈትኩ። ከሰነዶቹ ውስጥ ” የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትግላችንና ፈተናዎቹ” የሚለው ቀልቤን ሳበው ። አንብቤ ስጨርስ ውስን ነጥቦችን መዝዤ በማውጣት ከትላንትናው አስተሳሰብ ጋር ማገናዘብ ጀመርኩ። እናም ስልኬን አውጥቼ የሚከተሉትን ቁምነገሮች ለመክተብ በቃሁ ፣
1• Paradigm Shift
bereket
ይህ ሰነድ ስርነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ ያመጣው በስርአቱ አደጋ ላይ ነው። ድርጅቱ ከመሬት በታች ከመዋሉ በፊት በጳፉቸው ድርሳናትም ሆነ ገድሎች የስርአቱ አደጋ በዋነኛነት የሚመነጨው ከውስጥ ነበር። ቦናፓርቲዝም፣ ጥገኛ ዝቅጠት ፣ የመበስበስ አደጋ፣ እንደ አሣ ከጭንቅላቱ መሽተት ፣ ሙስና፣ ጠባብነት እና ትምክህት፣አድርባይነት… ወዘተ የውስጥ አደጋዎቹ መገለጫዎች ነበሩ።
ዛሬ የስምኦን ልጅ ምስጋና ይግባውና በዚህ ጉዳይ ላይ ስር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ በማድረግ ( ” የአስተሳሰብ እድገት” አለማለቴን ልብ ይሏል) የስርአቱ አደጋ ከኢህአዴግ ውጭ እንደሚመነጭ ያበስራል። ለዚህ እማኝ እንዲሆን በገፅ 24 ላይ ፣
“… በስልጣን ላይ ሆኖ አገሪቷን የሚያምሰ የትምክህት ሀይል የለም። … በሥልጣን ላይ ሆኖ አገሪቷን የሚያተራምስ የጠባብነት ሐይል የለም።” በማለት ይገልጻል።
ለዚህ አስተሳሰብ ማጠናከሪያ የሚሆነው በዚሁ ገጵ ላይ ፣
“… ይህ መሰረታዊ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ በሥልጣን ላይ ባለው ፓርቲና በመንግሥት መዋቅሮች የትምክህትና የጠባብነት አስተሳሰብን የሚያራምዱ ግለሰቦች አሉ።” በማለት ችግሩን በግለሰብ ደረጃ የሚገለፅ እንደሆነ ያሰምርበታል ።
ታዲያ የስርአቱ አደጋ የትነው ያለው?
2• ማነው ባለሳምንት?

የበረከት ማስታወሻ በኢህአዴግ ውስጥ ሰርጐ ገቦች መኖራቸውን አምኗል ። እነዚህ ሰርጐ ገቦች ከሌሎች ጋር በመቀናጀት ስርአቱ ላይ ፈተና እንደደቀኑበት በሚከተለው መልኩ በገፅ 24 ላይ ጠቅሶታል፣
“… ውጭ ሆነው ስርአቱን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ የትምክህትና ጠባብነት ሐይሎች ጋር በመቀናጀት ልዩ ልዪ ፈተናዎችን በመደቀን ላይ ይገኛሉ።”
ይህቺ አንቀጵ በንዴት እንደተጳፈች ታስታውቃለች። የንዴቱ ምንጭ የቅርብ ግዜውን የኦቦ አዲሱን እና የራሱን ቅሌት በማስታወስ የተጳፈች ትመስላለች ።
ኦቦ በንዴት ውስጥ ሆኖ፣
” … ሁለት ሶስተኛው መምህር የእኛ አባል ሆኖ በራሳችን ላይ ይሰለፉል” ነበር ያለው። የስምኦን ልጅ ደግሞ ቁርሴን ስበላ በሚል መንደርደሪያ የቅርብ ጓደኞቹ ሳይቀሩ ” ምርጫ የማይደርስ መስሎሀል?” በማለት እንደዛቱበት ተናግሯል ።
እናም አጨዳው ይቀጥላል ። ከበረከት ሰነድ ለመረዳት እንደሚቻለው ለመጠረግ የተዘጋጁት የአማራና ኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ የኢህአዴግ አባላት ናቸው።
ጠራጊው ማን ይሆን? ጠረጋው እስከየት ድረስ ይዘልቃል?

3• ትምክህት Vs አማራ
የበረከት ሰነድ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ትምክህት ለአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ልዩ ስጦታ በማድረግ አቅርቧል። ሌላው ቀርቶ ከአማራ ክልል ውጭ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ችግር ዋነኛ መንስኤ ” ከትግራይ የፈለቀው ገዥ መደብ እና ባለሟሎቹ” መሆኑን በመካድ በገፅ 29 ላይ፣
“… የዚህ አይነት ችግር ሲፈጠር በተጨባጭ የሚታወቁት መንስኤዎች ሁለት ናቸው ።አንዱ በራሳቸው የአማራ የተወሰኑ ወላጆች ዘንድ የሚታይ ችግር ሲሆን ፣ሌላው በሚኖርበት ህዝብ የተወሰነ ማህበረሰብ ዘንድ የሚታይ ችግር ወይም ድክመቶች ናቸው” በማለት ይገልጻል ።
አቶ በረከት ወክየዋለው የሚለውን የአማራ ብሔረሰብ በሌላ ክልል ሲኖር፣ የሚኖርበትን ብሄር ብሔረሰብ የሚንቅ፣የማያከብር፣ ማንነቱን የማይቀበልና የመጉዳት አዝማሚያ ያለው በማለት ይፈርጀዋል። ( የበረከትን ፅሁፍ ላለመዳችሁ አንባቢያን ” የተወሰኑ” ፣” ጥቂት”፣ ” እዚህ ግባ የማይባሉ”፣” እፉኚት” … ወዘተ የሚሉ የፊት ቅጥሎች (prefix) ካያችሁ እንደ ዳቦ ስም ውሰዷቸው)

4• ” የእኩልነት ጨዋታ ”
የበረከት ማስታወሻ በገፅ 34 ላይ ” የብሔር እኩልነት በተከበረበት የሌለ በማስመሰል።… በፌደራል ደረጃ እኩል የመሳተፍ መብት በተከበረበት በዚሁ አዲሱ ዘመን እነዚህ መብቶች እንደሌሉ ” በማለት የጠባብ ሐይሎች ተገቢ ያልሆነ ወቀሳ እንደሚያቀርቡ ያስገነዝባል። ይህን የአቶ በረከት መከራከሪያ እንደ ቅቡል ወስደን የሚከተለውን ጥያቄ እናንሳለት፣
* በፌደራል ደረጃ አራቱ ታዳጊ ክልሎች ዘወትር የውክልና ጥያቄ እንደሚያቀርቡ የዘወትር ሪፓርትህ ነው። እናም ስንት ሚኒስትር፣ ዴሬክተር፣ ስራ አስፈጳሚ… አለ? ( ከሀያ ሶስት አመት የሥልጣን ዘመን በኋላ የድሮውን መከራከሪያ እንዳታቀርብና እጄን በአፌ ላይ እንዳላገኘው።)
* አቶ በረከት ሠራዊቱን ለማመጣጠን እንደተቻለ በገፅ 31 ላይ አስታውቀሀል። ታዲያ ለምን የሐይማኖት ስብጥርን በአሃዝ አስደግፈህ እንዳቀረብከው የሰራዊቱን የአመራር ደረጃ በዛው መልኩ አቅርበህ አፉችንን አታዘጋንም?

5• አዲሳአባ

አቶ በረከት ያዘጋጀው ሰነድ ከአዲሳአባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ የነበረው ችግር ፣የሁከቱ ምክንያት እና መገለጫ የጠባብ ሐይሎች ዘመቻ እንደሆነ በገፅ 33 ላይ ያሳውቃል ። በርግጥ የኦህዴድ አመራር አባላትና የኦሮሚያ ሚዲያ ( ሳታቫኦ) እጃቸው አለበት ብሎናል። ከዚህ በተጨማሪም በዚሁ ገጵ ላይ፣
“… በአዲስ አበባ የፌደራል ዋና ከተማነትና በኦሮሚያ ክልላዊ ጥቅም መካከል ይህ ነው የሚባል ግጭት የለም” ይለናል ።
ጥያቄ አንድ: ማስተር ፕላኑ መጀመሪያ በተባለው መልኩ ሳይሸራረፍ ይፈፀማል ማለት ነው?
ጥያቄ ሁለት: የጥቅም ግጭቱ ከሌለ የኦሮሚያ ልዪ መብት እስከ አሁን ለምን አልተደነገገም?
ጥያቄ ሶስት: ችግር የፈጠሩት የኦህዴድ ባለሥልጣናት እነማን ናቸው? ( በነገራችን ላይ ኦቦ ጁነዲን ሳዶ አትላንታ ለሚገኙ ወዳጆቹ ” ያ! ማኪያቬሊ ሃገሪቷን የማትወጣበት አዘቅት ከቶ ሞተ ” እያለ እንደሚናገር ሰምተሀል መቼስ?)

6• ቤኔሻንጉል vs የደች በሽታ ( Dutch Disease)

አባይን መገደብ የማን አስተሳሰብ ነበር? የሚለው ጥያቄ ለጊዜው ይቆየንና ግድቡ እየተሠራበት ካለው ቦታ አንጳን አንድ ጥያቄ እናንሳ። በሕገመንግሥቱ የመገንጠል ጥያቄ ሊነሳ የሚችለው ከመከፉት( መበደል) ብቻ ሳይሆን ” የአይናችሁ ቀለም አላማረኝም፣ ብቻዬን መኖር ፈለኩ ” ከሚል ጫፍ የረገጠ ፈንጠዝያም ሊነሳ እንደሚችል ባለራእዪ መሪ ደጋግመው ነግረውናል። እናም ቤኔሻንጉሎች ” የመገንጠል ጥያቄ” ቢያነሱ ምላሻችን ምን ይሆናል?
( ምክር ቢጤ:የተሐድሶ ጊዜ ደጋግመን የዘመርናትን ” የደቾች በሽታ” በካሪኩለማችን ቢካተት ።)

7• የተዘነጋ ፍረጃ
ጓድ በረከት ለአማራ ህዝብ ትምክህት ፣ ለኦሮሞ ህዝብ ደግሞ ጠባብነት የሚባሉ ኢህአዴጋዊ ጥብቆ አጠለክ። የትግራይ ህዝብ የትኛውን ይልበስ?

በግልጽ እንነጋገር – (ይሉኝታ፣ ምሁራን፣ ትግልና ሀገር በኢትዮጵያ)

$
0
0

አንዱ ዓለም ተፈራ

የእስከመቼ አዘጋጅ

ጥቅምት ፫ ቀን ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት ( 10/13/2014 )

eskemecheበአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በኢትዮጵያ ያለውን ተጨባጭ የፖለቲካ ሁኔታ የማያውቅ ኢትዮጵያዊ የለም። ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁላችንም አንድ ስምምነት ላይ ነን። በአንድነት ያልተገኘንበት፤ ምን ይደረግ? በሚለው መፍትሔ መሥጠቱ ላይ ነው። መፍትሔ ደግሞ ከመቅረቡ በፊት፤ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አልፎ፤ በግንዛቤያችን ደረጃ ያለንበትን መመርመሩ ግዴታ ይሆናል። እንግዲህ የዚህ ጽሑፍ ማጠንጠኛ ይኼው የግንዛቤያችን ጉዳይ ነው። በትግሉ ዙሪያ፤ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ ግለሰቦች ሞልተናል። እያንዳንዳችን የምንፈልገውን እናውቃለን። የሚያስማማን ደግሞ እያንዳንዳችን ከምንፈልገው መካከል ያለው የጋራ ፍላጎታችን ነው። ይህ የየግል ፍላጎታችን በሀገር ደረጃ ሲቀመጥና የጋራ የሆኑት ከመካከሉ ተጎልጉለው ሲወጡ፤  ሀገራዊ መታገያ ዕሴቶቻችን ነጥረው ብቅ ይላሉ። በዚህ ጽሑፍ፤ የሀገራችን፣ የትግላችን፣ የምሁራን ሚናና የይሉኝታችንን አስተዋፅዖ አጤናለሁ። እነኚህ፤ በያዝነው ትግል ያላቸውን ድርሻ ተንትነን ስንረዳ፤ ውጤታማ ወደ ሆነ መንገድ እናቀናለን።

በይሉኝታ ትግል አይካሄድም። ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ መርምረን፤ ግስጋሴውን በማጥናት፤ በጎውን በመመዘገብና ችግሩን በመለየት እርማት አድርገን፤ መንገዱን የማቅናት ግዴታ አለብን። በየጓዳችን የምንናገረውና በአደባባይ የምናቀነቅነው አንድ ካልሆነ፤ አስመሳዮች ነን። በየጓዳችን፤ “አንድነት እኮ አንደያ ነው።” “መኢአድንማ ተወው።” “ግንቦት ሰባት እኮ እንዲህ ነው።” “ኢሕአፓ እኮ እንዲያ ነው።” “የሽግግር መንግሥት ባዮች ደሞ እንደዚህ ናቸው።” “የምን ሸንጎ አመጣህብኝ! ለመሆኑ እነሱ ማናቸው?” “የሚረባ ምን ድርጅት አለ ብለሽ ነው?” “አርፎ መቀመጥ ይሻላል።” “ሁሉም አይረቡም።” እያልን በአደባባይ ደግሞ፤ “ወያኔ ዛሬ ይወድቃል።” “ነገ ሕዝቡ ያቸንፋል።” “መተባበር አለብን።” “ሰላማዊ ሰልፍ እንውጣ!” “ለኦባማ ደብዳቤ እንጻፍ።” “ሀገሬን እወዳለሁ።” ብንል፤ ሌሎችን ሳይሆን ራሳችንን ነው ማታለል የያዝነው። ወይ አንድ ጊዜ ቅርጦ ከወያኔ መላተምና ለሆድ ማደር! አለያ ደግሞ፤ በቅጡ ሰፈር ለይቶ ከሕዝብ መወገን ነው። ይሉኝታ ቀን አይገፋም፤ አፍ ብቻ ነው የሚያለፋው። ራስን ብቻ ነው የሚያስገምተው። ድርጅት አለኝ ብሎ መንደላቀቅ፣ እየታገልኩ ነው ብሎ መኩራራት፣ ያለኔ ሁሉም አይሆንም ብሎ ማቅራራት፣ ታሪክ አለኝ ብሎ መደንፋት የትም አያደርስም። ለሕዝባዊ ትግሉ ጠብታ እንኳን አይረዳም። በግልጽ መነጋገሩና እውነተኛውን መንገድ መከተሉ ብቻ ነው የሚያዋጣው። በያንዳንዱ ድርጅት ጉድለት አለ። አዎ ጉድለት አለ። ባሁኗ ሰዓት መቶ በመቶ ትክክለኛ የሚባል ድርጅት የለም። እያንዳንዱ ድርጅት ደግሞ ጥሩ የሆነ ጎን አለው። ከያዝናቸው ሌላ ከሰማይ የሚመጣ የለም። ያሉትን በቀና መመርመርና አስተካክለን ወደፊት መጓዝ አለብን።ታዲያ ጥሩውን አጉልቶ፤ ለጎደለው ማስተካከያ አበጅቶ፤ አነፃጽሮ ቢያወጡት፤ ሁሉም ድርጅቶች አንድ ይሆናሉ።

ይህን ግልጽ ላድርገው። ሁሉም ድርጅቶች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መሆኑን ያውቃሉ። በሀገራችን ያለው መንግሥት፤ ፀረ-ኢትዮጵያ መሆኑን ይቀበላሉ። መወገድ እንዳለበት ያምናሉ። ሕዝቡ መብቱን አስከብሮ፤ የራሱን ምርጫ በትክክለኛ መንገድ በቦታው መተካት እንዳለበት ይቀበላሉ። እንግዲህ እነዚህ መሠረታዊ የሆኑ የጋራ የትግል ዕሴቶቻችን ናቸው። ዴሞክራሲያዊ አሠራርና የሕግ የበላይነት በሀገራችን እንዲሰፍን ሁሉም ይፈልጋሉ። ይህም በጣም ጠቃሚ ዕሴት ነው። በተጨማሪ፤ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተሳትፎ መደረግ ያለበት፤ በኢትዮጵያዊ ዜግነት ላይ የተመሠረተ፤ እያንዳንዷ ኢትዮጵያዊትና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በግለሰብ፤ የዴሞራሲያዊ መብቶች ተከብረውላቸው፤ በኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ መሆን እንዳለበት ያምናሉ። ይህ እንግዲህ መታገያና የምንታገልለት ጉዳይ ነው። ታዲያ ለዚህ ነው ሁሉም ድርጅቶች አንድ ይሆናሉ ያልኩት። ይህን የማይቀበል ድርጅት ካለ፤ ፈርተን ወይንም በይሉኝታ፤ ሕልውናው እንዲቀጥል መንገድ መጥረግ የለብንም። ይህ ይሉኝታ ሳይሆን ልበ ቢስነትና ተልፈስፋሽነት ነው። ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት መክፈል ቢያቅተን፤ ቢያንስ እውነቱን ተናግረን ራሳችንን ነፃ ማሳደር አይኖርብንም? ትግል እኮ፤ ራሳችንን ለሌሎች ሕልውና አሳልፈን መሥጠት ማለት ነው። የዚህ ሀ ሁ ደግሞ መጀመሪያ ለምናምንበት መቆም ነው። ወደ ምሁራን!

በያዝነው ትግል፤ ምሁራን ከፍተኛ ሚና አላቸው። በኛ ሀገር ባሁኑ ሰዓት ምሁራን በያሉበት፤ ግዴታቸውን፤ ማለትም ታሪካዊ ተግባራቸውን እያከናወኑ አይደሉም። ታሪካዊ ግዴታቸውን ለመወጣት፤ የአንድ ድርጅት አባል መሆን ወይንም አለመሆን መለኪያው አይደለም። ትግሉንና ሂደቱን መርምሮ፤ ትክክለኛ መፍትሔ ብሎ የሚያምንበትን በግልጽ ለሕዝቡ በማቅረብ፤ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ የምሁራኑ ተግባር ነው። ትግሉን ከመመርመር ይልቅ ላሉበት ድርጅት ተገዥ በመሆን፤ ሁሉንም ጉዳይ በድርጅቶቻቸው ዓይን የሚመለከቱ ከሆነ፤ ምሁር የሚያስብላቸውን መለኪያ አያሟሉም። አስተዋፅዖም የላቸውም። የድርጅታቸው እንጂ የሀገራዊ ጉዳዩ መልስ ሠጪ ባለመሆናቸው፤ ትግሉን እየጎዱ ነው። ለአንድ ምሁር፤ ሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታውን መዝኖ መፍትሔ ማቅረቡ፤ ከፖለቲካ ድርጅት አባልነቱ ጋር የተያያዘ አይደለም። መሆንም የለበትም። ይህ ለተጨባጩ ሁኔታ የሚሠጥ ተጨባጭ መልስ ነው። በአቀራረብና በቅደም ተከተል፣ በዘዴና በስልት፣ ወይንም ትግሉ ሊወስድ በሚችለው አቅጣጫና የሂደቱ ፍጥነት ላይ የተለያየ አመለካከት ይኖራል። ይህ በርዕዩተ ዓለምና ውጤቱን ከማፋጠን ወይንም ጉዳቱን ከመቀነስ ድርጅታዊ መልክ ይይዛል። ይሁን። ያኔ ምሁራን ጎራ ሊለዩ ይችላሉ። መሠረታዊ በሆነው ተጨባጭ የሀገራችን የፖለቲካ ሀቅና አጠቃላይ መፍትሔው ላይ ግን ልዩነት ሊኖር አይገባም። ተጨባጩ የፖለቲካ ሀቅ አንድ ነው። ከመልሶቹ ሁሉ ደግሞ ትክክለኛው አንድ ነው። ወደዚያ ለመድረስ በሚወስደው መንገድ መለያየት ይቻላል። ምሁራን በተጨባጩ ሀቅና በትክክለኛው መልስ አይለያዩም። ታዲያ ይኼን የኛ ምሁራን አልተገበሩትም።

የምሁራን ትኩረት መሆን ያለበት፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርን ተግባር መዘርዘርና ማውገዝ ሳይሆን፤ ወደፊት የሚያሳይ መፍትሔውን በመጠቆም፤ ምን መደረግ እንዳለብት ማሳየት ነው። እናም ለምን መተባበር አቃተን? ለምን ትግሉ ባለበት ይረግጣል? ድርጅቶች ትግሉን እየጠቀሙ ነው ወይንስ እየጎዱ? አደረጃጀታቸው ለያዝነው ትግል እየረዳ ነው ወይንስ እየጎዳ? ለምን የታጋዩ ጎራ ባንድነት አልተሰለፈም? ለአለመሰባሰባቸው አደረጃጀታቸው አስተዋፅዖ አያደረገ ነው ወይንስ አይደለም? የመታገያ ዕሴቶቻችን ምንድን ናቸው? ድርጅቶች ይሰባሰቡ ስንል በምን ዙሪያ ነው? መሰባሰቢያ ማዕከላዊ ጉዳይ ከሌላቸው ለምን ይሰባሰባሉ? ሀገራዊ ራዕያችን ምንድን ነው? የሚለውን፤ በየድርጅቶቹ መርኀ-ግብር ከሠፈረው ግባቸው በስተቀር፤ ሀገራዊ የሆነ መልስ የሠጡ ምሁራን አልተገኙበትም። እናም ምሁራን በምሁርነታቸው በቦታቸው አልተገኙም። አንድም ፈሪዎች በመሆንና በመደበቅ አንገታቸውን ደፍተዋል፣ ሌላም ለድርጅቶቻቸው አሽከር በመሆን በድርጅቶቻቸው መነፅር ብቻ ተመልካች ሆነዋል? አለያም ሌሎች ይሥሩት በማለት በየግል አጀንዳቸው ተጠምደዋል። ይህ ምሁራዊነት አይደለም። ምሁር ማለት፤ ጨለማውን ገልጦ የሚያጠራ፣ ያልተረገጠውን ዳስሶ የሚያሳይ፣ ያልተዳሰሰውን ደፍሮ የሚቃኝ፣ ማለት ነው። እናም ምሁራን በምሁርነታቸው በቦታቸው አልተገኙም።

ትግሉ የኛ እንጂ የመጪዎቹ ወይንም የሌሎች አይደለም። አንድነት ግዴታ ነው። ማድረግ ያለብንን እና የኛ የሆነውን ኃላፊነት፤ ለማንም ልናስተላልፈው አይገባም። ይህ በኛ ወቅት ያለና የኛ ሀገራዊ ግዴታ ነው። ሀገራችን አሁን ላለችበት የፖለቲካ ሁኔታ የትናንትኖችን መውቀስ ወይንም ለነገዎቹ ማስተላለፉ ተገቢ አይደለም። ይህ የራሳችን የአሁኑ ኢትዮጵያዊያን ኃላፊነት ነው። የያዝነውን ትግል በሚመለከት፤ ባሁኑ ሰዓት የታጋዩ ወገን አንድ ማዕከል የለውም። ባሁኑ ሰዓት የተጋዩ ወገን አንድነት የለውም። ባሁኑ ሰዓት የተጋዩ ወገን ትግሉን በትክክል አልተነተነውም። ባሁኑ ሰዓት የታጋዩ ወገን የአንድነት ሀገራዊ ራዕይ የለውም። ባሁኑ ሰዓት የተጋዩ ወገን በትክክል አልተደራጀም። ባሁኑ ሰዓት የተጋዩ ወገን በትክክል ትግሉን አልመራም፤ እየመራም አይደለም። ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ የታጋዩን ወገን፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የተሻለ ብሎ እንዳማራጭ እንዲወሰደው አስተማማኝ ሆኖ አልተገኘም። በርግጥ በማይካድ ደረጃ ሀገር ቤት ውስጥ ወደፊት የመንቀሳቀስ ሂደት ይታያል። አጥጋቢ አይደለም። ነገር ግን አጥጋቢ ባይሆንም፤ ያለው አማራጭ ያ ብቻ ሆኗል። ከዚያ የተሻለ ማድረግ እንችላለን። ትግሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ሆኖ የቀረበ አይደለም። በመኖርና ባለመኖር መካከል ግብግብ ሆኖ ስለተጫነው ብቻ ነው። እናም በማንም ውዴታ ወይንም ፍላጎት የተመሠረተ አይደለም። እኛ አስተዋፅዖ ለማድረግ ከፈለግን፤ የምንችለው፤ ጠንካራ የሆነ “የኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ” ማካሄድ ነው። ለዚህ ንቅናቄ ደግሞ መሠረታዊ የትግሉ ዕሴቶቻችን ከላይ የተጠቀሱት ናቸው። እኒህም፤

ሀ) የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ሉዓላዊነት መረጋገጥ፤

ለ) የኢትዮጵያ አንድ ሀገርነትና አንድ ብሔርነት መጠበቅ፤

ሐ) የሕግ የበላይነት በኢትዮጵያ መስፈን፤

መ) የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊትና የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር፤ ናቸው።

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ሁሉን የኢትዮጵያዊያንን ፍላጎትና አሁን ያሉትን ድርጅቶች በሙሉ ፍላጎት የሚያሟሉ የትግል ዕሴቶች ናቸው። በነዚህ ዙሪያ የሚደረገው ትግል፤ አስተማማኝ የሆነ የወደፊት እንዲኖረን ይረዳናል። በርግጥ አመራሩን የሚሠጡት ግለሰቦች ወሳኝነት አላቸው። በዙሪያቸው የሚኮለኮሉትም ወሳኝነት አላቸው። አቤት ወዴት ብሎ፤ ሎሌ ይመስል አብሮ የሚነጉድ ተከታይ አሽከር ነው፤ እንጂ የድርጅት አባል አይደለም። ዴሞክራሲያዊ አሠራር ባልዳበረበትና ለሕግ መገዛት ባልጠነከረበት ትግላችን ውስጥ፤ ግለሰቦች የሚጫወቱት ሚና ከባድ ነው። ይመለካሉ። እስኪ ተመልከቱ፤ በየድርጅቶቹ ውስጥ ያሉ መሪዎች፤ እንደግል ንብረታቸው፤ ድርጅታቸው ከተመሠረተ ዕለት ጀምሮ ብቻቸውን ሲያዙበት አንዳንዶቹ አስርታት አመታት፤ ሌሎቹ ደግሞ ድርጅታቸው ከተፈጠረ ጀምሮ ያለውን ዕድሜ አስቆጥረዋል። አንድም ተከፋፍለው፣ አለያም ተገደው ካልሆነ በቀር ለውጥ የለም። መወራረስና ወጣቶቹን ወደፊት ማምጣት ትልቁ ነውር ነው። ስም የማልጠቅሰው፤ ያልተጠቀሰ ይኖርና እኔ የለሁበትም እንዳይል፤ ሁሉም በሙሉ በዚህ የተዘፈቁ ስለሆነ ነው።

ለግለሰቦች ያለኝ መልዕክት፤ ትክክለኛ የሆነ ኢትዮጵያዊ መንግሥት በሀገራችን እንዲኖር ሁላችን እንፈልጋለን። በምንችለው ደግሞ እየጣርን ነው። በየጊዜው መስዋዕት እየተከፈለ ነው። ትግል የበኩሌን እስካደረግሁ ድረስ ሌላ ኃላፊነት የለብኝም ብለን የምንቀመጥበት ክስተት አይደለም። ትግል የኛን ጠንካራ አስተዋፅዖ ከሌሎች ጠንካራ አስተዋፅዖ ጋር በመደመር፤ ካለንበት ወደፊት የሚኬድበት ነው። ባለንበት ከረገጥን፤ መመርመር ያለብን ጉዳይ አለ ማለት ነው። አንድም ትክክለኛ ያልሆነ የትግል ግብ ነድፈናል አለያም ትግሉ ለሚጠይቀው ትክክለኛ ድርጅት ይዘን አልተገኘንም ማለት ነው። ይኼ መመርመር አለበት። እንዲህ ካላደረግን፤ እንዲያው የምናደርገውን የማናውቅ ነን ማለት ነው።

በታጋይ ድርጅቶቹ መሪዎች በኩል ለድርጅቶች ያለኝ መልዕክት፤ ስትታገሉበት ላለው መርኀ-ግብር፤ እስከዛሬ በአባላት ከፍተኛ መስዋዕትነት፤ የምትችሉትን እያደረጋችሁ ትግሉን አቆይታችሁታል። ከልባችሁ የሀገራችንን ነፃ መውጣት ፈልጋችሁ ጥራችኋል። በቂ ሆኖ አልተገኘም። እናም አንድም ትግሉን፤ አለያም አደረጃጀታችንን በጥያቄ ውስጥ ያስገባ ሀቅ በላያችን ላይ መጥቷል። አሁን ከሌሎች ጋር አንድ ሆናችሁ ብቻ ነው ወደፊት መቀጠል የሚቻለው። እናም መርኀ ግብራችሁ ላይ ከፍተኛ እምነት ካላችሁ፤ ለአሁኑ አቆዩትና፤ ሀገር ነፃ ሲወጣ ለሕዝብ ታቀርቡታላችሁ። አሁን መታገያ ዕሴቶቻችን ተቀይረው፤ መጀመሪያ ሀገር ብለናል። ስለዚህ፤ ሀገርን እናስቀድም። የየድርጅቶቻችሁ ንብረትም ሆነ ታሪክ ይቆያችኋል። ለአሁኑ ከሌሎች ጋር በመሆን ባንድ ሰፊ የኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ ሥር እንሰለፍ። በሀገር ጉዳይ ተመሣሣይና ተቀራራቢ አመለካከት ያላቸው፤ ነገር ግን የተለያየ ርዕዩት በሚከተሉ ድርጅቶች መካከል፤ የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ውድድር የሚደረገው፤ ነፃ ሀገር ሲኖር፤ ሕዝቡ የመምረጥ መብቱ ሲከበርለትና፤ ሕግን የሚያከብር መንግሥት በሥልጣን ላይ ሲሆን ነው። አሁን ትግሉ ያን ለማስከበር ነው። ስለዚህ የሁሉም ባንድነት፣ ባንድ ላይ፣ ባንድ ድርጅት መሰባሰብ የግድ ነው።

 

የተዋረደው ሰንደቅ አላማ ‹‹የክብር›› ቀን (ጌታቸው ሺፈራው)

$
0
0

ጌታቸው ሺፈራው

በዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑት ሰንደቅ አላማዎች መካከል የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በቀዳሚነት ይገኝበታል፡፡ በጸረ-ቅኝ ግዛት ትግሉ ወቅት በመላው ዓለም የሚገኙ ጥቁሮች ከነጻነት ምልክትነቱም በተጨማሪ አንዳች ኃይል ያለው አድርገው ወስደውታል፡፡ በተለይ ከቅኝ ግዛት ትግሉ በኋላ በርካታ የአፍሪካና የካሪቢያን አገራት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ምልክታቸው አድርገው ተጠቅመውበታል፡፡ ከዚህም የተነሳ በሰንደቅ አላማ ላይ ጥናት የሚያደርጉ ምሁራን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ የአፍሪካ ሰንደቅ አላማዎች ዘር ይሉታል፡፡

10482065_596327470492915_3458501353410632231_nየኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑት ከዓለም ሰንደቅ አላማዎች ቀዳሚው እንደመሆኑ ለሌሎች ህዝቦች ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ በራሱ መሪዎች የተዋረደው ብቸኛው ሰንደቅ አላማም ሳይሆን አይቀርም፡፡ በርካታ የአፍሪካና የካሪቢያን አገራት የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በምልክትነት ሲወስዱ የወቅቱ የኢትዮጵያ ገዥዎች ግን የኢትዮጵያውን ሰንደቅ አላማ ቀለም ትተው ከአውሮፓና ከአረብ አገር የተዋሱትን ሰንደቅ አላማ ክብር ከነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ጎን ያንጠለጥሏቸዋል፡፡

ሻዕቢያና ጀብሃ ሰንደቅ አላማውን ለማዋረድ (ጨርቅ ለማስመሰል) ከዓረብ አገራት በእርዳታ ያገኙት የነበረውን ዱቄትና በሰሜን ኢትዮጵያ የሚበቅለውን በለስ ቋጥረውበታል፡፡ ከሻዕቢያ ስር ሆኖ የጎለመሰው ህወሓት የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ስለማዋረድ ከሻዕቢያ ልምድ ቀስሟል፡፡ በመሆኑም እሱም እንደ ሻዕቢያ የዱቄት መቋጠሪያ አድርጎት እንደነበር ይነገራል፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ሰንደቅ አላማውን ‹‹ጨርቅ›› ያሉትም ከምንም ተነስተው ሳይሆን በአንድ ወቅት ሻዕቢያ ባስተማራቸው መሰረት እንደ ጨርቅ ሲጠቀሙበት ስለነበር ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ሰንደቅ አላማውን የማዋረድ ታሪክ ገና ከጫካ የጀመረ በመሆኑ ለሰንደቅ አላማው ያላው ንቀትና ጥላቻ በዚሁ መልኩ ደሙ ድረስ ዘልቆ ገብቷል ማለት ይቻላል፡፡ ለዚህም ነው አከበርኩ እያለ እንኳን ማክበር ያልቻለው፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ መጀመሪያ ላይ ንጹሁን ከዛም በኋላ ውሃማ ሰማያዊ ክብ ያለበት፣ በቅርቡ በ654/2001 ዓ.ም በወጣው የሰንደቅ አላማ አዋጅ ደግሞ ደማቅ ሰማያዊ መደብ ላይ ያረፈ ክብ ያለበት ሰንደቅ አላማን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አድርጎ እየተጠቀመበት ነው፡፡ በዚህም መሰረት በቅርብ አመታት የሰንደቅ አላማ ቀን በዓል እያከበረ ነው፡፡ ከውስጥ ያልመነጨን ነገር መተግበር አይቻልምና አከብራለሁ እያለም እያወረደው ዛሬ ድረስ ደርሷል፡፡ በሌላ በኩል ገዥዎቹ ለሰንደቅ አላማ ክብር የሌላቸው መሆናቸውና የአሁኑ ሰንደቅ አላማ (በተለይ መሃል ላይ ያለው ምልክት) ያለ ህዝብ ፈቃድ መለጠፉ አሁን ‹‹የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ›› የሚባለው ህዝቡም ከላይ የተጫነበት እንጂ የራሱ እንዳልሆነ በማመኑ በሁሉም ወገን ክብር ተነፍጎታል፡፡

የዚህ ጽሁፍ አላማም ኢህአዴግ ለሰንደቅ አላማው አዋጅ አውጥቶ፣ የክብር ቀን ቆርጦ አከብረዋለሁ ቢልም ለይስሙላህ እንጂ ክብር እንደማይሰጠው ለማሳየት ነው፡፡ በሰንደቅ አላማው አዋጅ በአንቀጽ 6/1 መሰረት ‹‹ሰንደቅ አላማው ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሃል ቢጫ፣ ከታች ቀይ›› ይኖረዋል ይላል፡፡ መሃል ላይ ያለው ኮከብ አቀማመጥንም ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን በየ ካፌው ሌላ ሰንደቅ አላማ (መሃል ላይ ክብ ያለውን) ከሌለው ንጹህ ሰንደቅ አላማ በማዳቀል (በክር ተሰፍቶ) የተሰቀሉት ይበልጣሉ፡፡ ምንም እንኳ በየካፌው ሰንደቁን መስቀል የማይፈቀድ ቢሆንም፣ ህጉ ተጥሶ በዘፈቀደ ተንጠልጥሎ ይገኛል፡፡

በአዋጁ ከተቀመጠው ቀለምና አቀማመጥ ውጭ የተሰቀለ ሰንደቅ አላማ በእስርና በገንዘብ እንደሚስቀጣ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ግን አዋጁን የደነገጉት አካላት አይጠቀሙበትም፡፡ ለአብነት ያህል አቶ መለስ ዜናዊ ከመሞታቸው ከወራት በፊት ኬንያ ላይ ሰንደቅ አላማውን ከላይ ወደታች ገልብጠውት ታይተዋል፡፡ በአዋጁ መሰረት አቶ መለስ ዜናዊ ቢያንስ በገንዘብ 3000 ብር አሊያም አንድ አመት እስር ይጠብቃቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን አቶ መለስ ዜናዊ ምንም ሲባሉ አላየንም፡፡

በዚሁ በማይከበረው አዋጅ 6/2 መሰረት ‹‹ቀለማቱ ብሩህና ደማቅ መሆን አለባቸው›› ይላል፡፡ ነገር ግን የተለያዩ ቁልፍ የ‹‹መንግስት›› ተቋማት ሳይቀሩ ይህን ህግ በሻረ መንገድ ሰንደቅ አላማውን ሲያውለበልቡ ይታያሉ፡፡ ለአብነት ያህል በሽብርተኝነት ተጠርጥረዋል ተብለው የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን የሚቀርቡበት የአራዳ ችሎት ለረዥም ጊዜ የተጠቀመበት የተበጣጠሰ ሰንደቅ አላማ (ሰሞኑን ቀይረውታል) በምሳሌነት ማንሳት ይቻላል፡፡ ከዚህም ባሻገር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ፓርላማ ያረጀና የተቀዳደደ ሰንደቅ አላማ ያውለበልብ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ሁለቱን መስሪያ ቤቶች ጨምሮ በበርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሰንደቅ አላማው ማታ ሲወርድ አይታይም፡፡ በአራዳ ችሎትና ፓርላማውን የመሳሰሉት ምን አልባትም ከአመት በላይ ሰንደቅ አላማው ሳይቀየር ስለተሰቀለ ነው እንደዛ የተበጣጠሰው፡፡ ለይስሙላ የወጣው አዋጅ ግን ጠዋት 12 ሰዓት ተሰቅሎ ማታ 12 ሰዓት መውረድ አለበት ብሎ ደንግጓል፡፡

በአዋጁ 6/3 የሰንደቅ አላማው ወርድ የቁመቱን እጥፍ ይሆናል ይላል፡፡ በሌላ የአዋጁ ክፍልም ለህንጻዎች መሸፈኛ መሆን የለበትም ይላል፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ካፌዎች፣ ባንኮችና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሰንደቅ አላማው አብዛኛውን የህንጻዎች ክፍል ሸፍኖ ይታያል፡፡ (የፈተናዎች ድርጅት ህንጻ፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ፣ አዋሽ ባንክ ላይ ማየት ይቻላል) ይታያል፡፡ በእነዚህና በሌሎች መስሪያ ቤቶችና ህንጻዎች ሰንደቅ አላማው የህንጻዎቹን አብዛኛ ክፍል ሸፍኖ (ማስጌጫ ሆኖ) ይታያል፡፡

የሰንደቅ አላማው አዋጅ አንቀጽ 10 ሰንደቅ አላማው 6 የተለያዩ መጠኖች እንደሚኖሩት ይገልጻል፡፡ 1ኛ. 210 በ420፣ 2ኛ 150 በ300፣ 3ኛ 135 በ 270፣ 4ኛ 105 በ 210፣ 5ኛ 90 በ180፣ 6ኛ 21 በ 42 ናቸው፡፡ አንደኛው በከፍተኛ አደባባይ ላይ የሚሰቀል ነው፡፡ ሁለተኛው በመካከለኛ አደባባይ ይሰቀላል፡፡ ሶስተኛው በመስሪያ ቤቶች፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ በትልልቅ የመንግስት ህንጻዎችና የድርጅቶች አደባባዮች የሚሰቀል ነው፡፡ አራተኛው በትልልቅ ህንጻዎች ይሰቀላል፡፡ በከፍተኛ መርከቦችና በሰልፍ ጊዜ በክብር ዘብ ይያዛል ይላል፡፡ አምስተኛው የውጭ አገር እንግዶችን ለመቀበልና በበዓላት በየ መንገዱ የሚውለበለብ ነው ይላል፡፡ በስድስተኛ ደረጃ የተቀመጠው ሰንደቅ አላማ መጠን በፕሬዝዳንቱ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በአምባሳደር ጽ/ቤት ጠረጴዛ ላይ እንደሚቀመጥ ይደነግጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በፕሬዝዳንቱና በአምባሳደር መኪና ላይ 20 በ 30 ሴንቲ ሜትር የሆነ ሰንደቅ አላማ ይሰቀላል ይላል፡፡ ከተደነገገው ህግ ውጭ በሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶችም (በተለየ ህግ ካልተከለከለ በስተቀር) ይሰቀላል ይላል፡፡ በካፌ፣ ጸጉር ቤት፣ ስጋ ቤት፣….ይሰቀላል ብሎ የሚደነግግ ነገር የለም፡፡ ለዛሬው በዓል ግን እነዚህ ቤቶች በተለያየ ቁመትና ወርድ ሰንደቅ አላማ ከቀበሌ ታድሏቸው በየ ቦታው አንጠልጥለውታል፡፡

ትልቁ ሰንደቅ አላማ (210 በ420) በአደባባይ የሚሰቀለው ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ትልቁ ከ2 እስከ አራት ሜትር ተኩል ብቻ እንደሚሆን የሚያሳይ ነው፡፡ ሆኖም የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ባንኮች አብዛኛውን ህንጻቸውን ያስዋቡት እንዳለ ሆኖ ለዛሬው በዓል የቀበሌ መዝናኛዎች፣ ካፌዎችና ሌሎች ንግድ ቤቶች ከአንደኛው በረንዳ ጫፍ እስከ ሌላኛው በረንዳ ጫፍ የሰቀሏቸው ሰንደቅ አላማዎች በአንደኛ ደረጃ ከተቀመጠው በብዙ እጥፍ የሚበልጡ (የሚረዝሙ) ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ በተለያዩ ንግድ ቤቶች አንዳንዶች ከግራ ቀደ ቀኝ አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ አሊያም በተገላቢጦሹ ሰቅለውታል፡፡ ካድሬዎቹን ለማስደሰት እንጅ የሚያምኑበት ብዙዎቹ ባለመሆናቸው አንዳንዶቹ ታዛው ላይ፣ ሌሎቹ መስኮት አሊያም ያገኙት ቦታ ላይ መሬት እስኪነካ አንዘላዝለውታል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 16 የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከላይ በተደነገገው መሰረት አንድ አይነት ነው ይላል፡፡ ነገር ግን ለዛሬው በዓል ከተሰቀሉት መካከል በአሁኑ አዋጅ የተቀየረው መሃሉ ላይ ውሃማ ሰማያዊ ያለበትም በስፋት ተሰቅለው ይገኛሉ፡፡ አንቀጽ 17 ሲያረጅ፣ ሲበላሽ ወይንም በሌላ መንገድ በክብር ይቃጠላል፤ ይቀበራል ቢልም ይህ ግን ሲሆን አይታይም፡፡ አንቀጽ 18 ሰንደቅ አላማው ከክልል ሰንደቅ አላማዎች ጋር የሚሰቀልበትን መንገድ የተዘረዘረበት ነው፡፡ ከፍ ብሎ መሰቀል አለበት፡፡ ከሁለት ጋር ቢሆን መሃል ላይ ይሆናል፡፡ ከሁለት በላይ ከሆኑ በስተቀኝ በኩል መጨረሻ ሆኖ ይውለበለባል፡፡ ይህም ቢሆን ሰንደቅ አላማው ውስጣቸው በሌለው ገዥዎች ዘንድ የሚታወስ አይደለም፡፡ ለአብነት ያህል ስድስት ኪሎ አካባቢ የሚገኘው የኦሮሚያ የፍትህ ቢሮ ላይ ሁለት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማዎች ያውም ያሰቃቀሉን ህግ በማያሟላ መልኩ ከክልሉ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ ተሰቅሏል፡፡

አንቀጽ 22 በማኝኛውም ጊዜ ሰንደቅ አላማው ዝቅ ብሎ አይውለበለብም ይላል፡፡ እነሱ ግን በየ ጉራንጎሩ ሲፈልጉ ገልብጠው ያውለበልቡታል፡፡ ምንም እንኳ በፕሬዝዳንቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩና አምባሳደሩ መኪና ብቻ እንደሚውለበለብ ቢደነገግም ለዚህ በዓል ሲባል ታክሲና ባባጆች ሳይቀር እንዲያውለበልቡ ታድሏቸዋል፡፡

አንቀጽ 22 ሰንደቅ አላማ በቀብር ወቅት መሆን ስላለበበት ሁኔታ የሚገለጽበት ነው፡፡ በአንቀጹ ‹‹ቀብሩ ከመፈጸሙ በፊት በአስከሬን ሳጥኑ ላይ ያረፈው ሰንደቅ አላማ በተገቢው ስነ ስርዓት ተጣጥሮ መነሳት ያለበት ሲሆን በማንኛውም መልኩ መሬት መንካት የለበትም›› ይላል፡፡ ነገር ግን በአንድ ወቅት ጨርቅ እንዲመስል ዱቄት የቋጠሩበት፣ ከዛም ጨርቅ ብለው የዘለፉት፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ገልብጠውት የታዩት አቶ መለስ ዜናዊ አስከሬን ላይ ሲቀበር ሁላችንም በቴሊቪዥን ያየነው ኃቅ ነው፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ በሰንደቅ አላማው ላይ ይህን ያህል ኃጢያት ሲሰራ አንድም ቀን ይቅርታ ጠይቆ አያውቅም፡፡ ይህን ሁሉ ሲሰራ ማንም ጠይቆት አሊያም ተቀጥቶ አላየንም፡፡ በተቃራኒው ግን ለሰንደቁ እንደቆመ ለማሳየት ይሞክራል፡፡ የዛሬው በዓልም ለማያምንበትና በውስጡ ለሌለው ሰንደቅ አላማ ክብር እሰጥበታለሁ የሚለው እንዲህ ከራሱ ህግ ጋር እየተቃረነ እና እያዋረደው ነው

በአባላት ቅሬታ እና ነቀፌታ ሃላፊነቱን የለቀቀ የፓርቲ መሪ ቁ.ር 1

$
0
0

ይድነቃቸው ከበደ

“ልዩነት የግድ ጥላቻን ወይም ድብድብን ማስከተል አለበት ብለው የሚያምን እና የሚያስብ በድርጊቱም የሚገፉ ካለ ከባድ ስዕተት ነው፡፡ ፣ልዩነትን በአንድ ጊዜና ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻልም በሰለጠነና በሰከነ አካሄድ በውይይትና በሀሳብ ልውውጥ ማጥበብ ይቻላል፡፡” ለዚህም ይመስላል አንድነት ፓርቲ ውስጣዊ ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ባይባልም መሠረታዊ ችግሩን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት የቻለው፡፡ የዚህም ጥሩ ማመላከቻ የሚሆነው ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው በገዛ ፍቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸው እና በምትካቸው የአብዛኛውን የፓርቲ አባል መልካም ፍቃድ ያገኙት፣ አቶ በላይ በፍቃዱ መመረጣቸው ነው፡፡ይህ ደግሞ ለአመራር ለውጥ የተሄደበትን መንገድ በአብዛኛው ጤናማ ለመሆኑ በቂ መረጃ ነው፡፡

ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ


እርግጥ ነው በሂደቱ እንደ መልካም ተሞክሮ ለመውሰድ የሚቸግሩ፣ ጠቃሚ ያልሆኑ የሃሳብ ልውውጦች ለማየት እና ለመታዘብ ተችሎአል፡፡በተለይ በኢ/ር ግዛቸው የስራ አፈፃፀም ደስተኞች ባልነበሩ በተወሰኑ የፓርቲው አባላት የታዩ ችግሮች መኖራቸው የማይካድ ሃቅ ነው፡፡ይሁን እንጂ በፓርቲው አባላቶች እና አመራሮች እንዲሁም በድጋፍ ሰጪዎች ከባድ ጥረት የተገኘው ውጤት፤ያለፈው ስዕተት በማስታወስ ዋጋውን የሚያስቀንሰው አይደለም ! በመሆኑም አሁን ላይ ለደረሳችሁበት አስደሣች ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ ላለማለት ለውጥ ፈላጊ ለሆነው ሁሉ ለዴሞክራሲ ሃይሎች ምክንያት ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡

ይበልጥ ደግሞ ሂደቱን ለየት የሚያደርገው ኢ/ር ግዛቸው በገዛ ፍቃዳቸው ከስልጣናቸው መልቀቃቸው ሳይሆን የለቀቁበት መንገድ ነው፡፡ ለሁላችንም ግልፅ እንደሆነው ሁሉ አብዛኛው የአንድነት ፓርቲ አባላት በኢ/ር ግዛቸው የስራ አፈፃፀም እና ውሣኔ አሰጣጥ ደስተኞች አልነበሩም ፡፡ሆኖም ግን ምንም ጊዜ ቢወስድም “በእኔ የሰራ አፈፃፀም ደስተኛ ባለመሆናችሁ፣ ከምንም በላይ ደግሞ ፓርቲው ስለሚበልጥ ሃላፊነቴን በገዛ ፍቃዴ ለቂቃለው” ማለታቸው እና ውሳኔቸውን ተግባራዊ ማድረጋቸው ለኢ/ር ግዛቸው አድናቆትን የሚያሰጥ ነው፡፡

ከምንም በላይ ግን በኢትዮጵያ የ23 ዓመት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጉዞ በአባላት ቅሬታ እና ነቀፊታ ከስልጣን ዘመኑ በፊት ሃላፊነቱን የለቀቀ የፓርቲ መሪ ቁጥር አንድ ሊያስብል የሚያስችል ታሪክ ኢ/ር ግዛቸው ለማስመዝግ ችለዋል፡፡ ይህ ማለት ግን የኢ/ሩ የቀድሞ ስዕተቶች ይረሳሉ ማለት አይደለም፡፡ለቁጥር የበዛ በማወቅም ባለማወቅም በኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሰሯቸው ስዕተቶች አሉ፡፡ በተለይ ዛሬ ላይ ሆነው የሰሩት መልካም ስራ ማለትም የአባለት ቅሬታ እና ነቀፌታ የማዳማጥ ልምድ “ያኔ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ያካተተው የ “መርህ ይከበር” ጥያቄ ወቅት አድርገውት ቢሆን ኖሮ አንድነት ፓርቲ ብቻ ሣይሆን የኢትዮጵያ የተቃዋሚ እንቅስቃሴ ከፍ ከማለትም ባለፈ ፤አሁን ካለበት ደረጃ በእርግጠኝነት የወያኔን የአገዛዝ ሥርዓት ጭርሶ ባያጠፋውም የሚያሽመደምደው ነበር፡፡
GizachewShiferaw
በመሆኑም ሰው በገባው ልክ የሚኖር ፉጡር እንደመሆኑ መጠን በገባቸው ቀን የሚገባቸውን በማድረጋቸው እኔም ብሆን አድናቆቴን ለመግለፅ እገደዳለው፡፡ አሁን ላይ በመሆን የባለፈውን በማንሳት ለተጀመረው ሁለንታናዊ የሰላማዊ ትግል ወደፌት ፈቀቅ የማያደርግ፣ ማናቸውን ነገሮች ማንሣት አስፈላጊ እንዳልሆን፤ መገመት ቀላል ነው፡፡ ሆንም ግን ችግሮችን ማስታወስ ክፋት አይኖረውም፡፡ስለዚህም ዛሬ አንድነት የደረሰበት አስደሳች ውጤት ያለፉትን ስዕተቶች ድርጅታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደግባት ከመጠቀም ሊያግደው የሚችል ነገር አይደለም ለማለት ያስደፍራል፡፡

አንድነት ዛሬ ከችግሮች መካከል አንዱን ቀረፍ እንጂ ሙሉ በሙሉ ውስጣዊ የፓርቲ ችግሮችን ፈታ ማለት አይደለም፡፡ከዚህ ቀደም የነበረ፣አሁን ደግሞ የተገኘውን ውጤት መሠረት ያደረገ በራሱ የሚፈጠር ብዙ ችግሮች ይኖራሉ፣ውጫዊ የገዥው ሥርዓት ተፅኖ እንደተጠበቅ ሆኖ ፡፡ ስለዚህም አዲሱ የፓርቲው ሊ/ቀ ወጣቱ በላይ ፍቃዱ ከፍተኛ የሆነ ስራ ይጠብቀዋል፣ በተለይ ደግሞ የእሱ የሃሳብ ተቀናቃኝ የሆኑት የአንድነት ፓርቲ አባለት ከበሆደ ሰፊነት ባለፈ ሃሳባቸውን ሊሰማቸው እና በተግባር ሊያሳትፋቸው ይገባል፡፡በይበልጥ ደግሞ ከሌላ አቻ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር መዋቅራዊ ወይም የስራ ግንንነቶች በይበልጥ እንዲፈጠሩ የማድረግም ሃላፊነት ጭምር አለበት፡፡በአሰራሩም ግልፅነት እና ተጠያቂነት ያለው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያቆቁም ሥራን እንጂ ሌላ የጎንዩሽ ጥቅምን መሠረት ያላደረገ መሆኑ ማረጋገጥ አለበት፡፡ኢ/ር ግዛቸውም በፓርቲያቸው ውስጥ አቅማቸው እና ጊዚያቸው በፈቀደው መልኩ የማገልገልም ሃላፊነታቸውም እንደተጠበቀ ነው፡፡

በመጨረሻም ለአንድነት ፓርቲ አባለት፣አመራሮች ፣ድጋፍ ሰጪዎች እና ለአዲስ ወጣቱ ሊ/ቀ በላይ ፍቃዱ ለደረሳችሁበት ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለው! ይህ የግሌ የሆነው ሃሳብ ከማጠቃለሌ በፊት የጋሽ መስፍን “ሥልጣን ባህልና አገዛዝ ፖለቲካና ምርጫ” ከሚለው መፃፈቸው ገፅ 32 የሚገኘውን ፅሑፍ ሁላችንም ት/ት እንድንወስድበት በመጋበዝ ነው፡፡ “እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወደ ፖለቲካ ሲገባ ከልጅነት እስከ እውቀት በውስጡ የተመረገውን ጌትነትና የሎሌነት ባህል ፍቆ ፈቅፍቆ ማረገፍ አለበት፡፡ በግድ የአስተሳሰብ የጽዳት ዘመቻ ያስፈልገናል፡፡ ዓላማን የማጥራት ዘመቻ ያስፈልገናል፡፡ በግድ የነጻነትና የእኩልነት አራማጆች በቁርጠኝነት መነሳትና ማሳየት ያስፈልገናል፡፡ ብዙዎች የተቀናቃኝ መሪዎች ላይ የሚታየው የድሮው መኳንንትና መሳፍንት ለመምሰል የመሞከር ጠባይና ከዚህም ጋር ተያይዞ ሎሌዎችን በገንዘብ ሆነ በወደፊት ተስፋ እየገዙ የአገዛዝን ባህል ለማራመድ የሚደረገው ሙከራ የፖለቲካውን ሥርዓት አያራምድም፡፡ ጥረቱ ሁሉ በሥልጣን ላይ ያሉትን ሰዎች ለመለወጥ እንጂ ሥርዓትን ለመለወጥ አይመስልም፡፡”

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>