Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

እሪ በይ ሃገሬ

$
0
0

ethiopian flag

ከአብርሃም ያየህ

ይህች  “እሪ በይ ኣገሬ” የተሰኘች ኣጭር ስንኝ፤ በኣሰብ ወደብ ያንድ የውጭ ባለሃብቶች የመርከብ ወኪልና የግምሩክ ኣስተላላፊ ትራንዚት ኩባንያ ቅርንጫፍ ስራ ኣስካያጅ በነበርኩበት ወቅት ታሪካቸውን በቅርበት ለማውቅላቸው፤

  • ለኣንጋፋው ኢትዮጵያዊ ስራ ፈጣሪና፥ ታላቅ ኣገር ኣልሚ ለሆኑት፤ 
  • ከትቢያ ኣፈር ተነስተው ዝነኛውን  የኢትዮጵያ ኣማልጋሜትድ ኩባንያ በመመስረት፥ ውድ ዋጋ በማስከፈል ህዝብ ሲበዘብዙ የነበሩትን የውጭ ኣገር ኩባንያዎችን በህጋዊ የዋጋ ውድድር ከገበያ ለማስወጣት ለቻሉት፤ 
  • በዚህ ኩባንያቸው ኣማካኝነትም በብዙ መከራ ያሳደጋቸውን የኢትዮጵያ ድሃ ገበሬን ህይወት ለመለወጥ ሲያኮበክቡ የ66ቱ “ኣብዮት” ደርሶ በሚያሳዝን ሆኔታ ላደናቀፋቸው፤ 
  • “ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ ኣብረህ ተወቀጥ” እንዲሉ፥ እኒህ ያንድ ድሃ ጭሰኛ ገበሬ ልጅ የሆኑትና፥ ምንም እንከን ሳይኖርባቸው በደርግ ማጎሪያ ቤት ለረጅም ዓመታት ለተሰቃዩት በኋላም ለስደት ለተዳረጉት፤ 
  • የማሌሊት/ወያነ ትውልደ ኤርትራዊያን መሪዎችና ግብረ-በላዎቻቸው ኣምርረው የሚጠሏትን ኢትዮጵያ እንደተቆጣጠሩ፥ የወራሪዎቹን ማንነት በውል ሳያወቁ በየዋህነት ወዳገራቸው ተመልሰው ባላቸው ከፍተኛ የስራ ልምድና እውቀት ኣማካኝነት ላገራችንና ለዝባችንን ከፍተኛ ጥቅም ለማበርከት ታጥቀው ቢነሱም፥ በደርግ እግር በተተኩት የህዝብ ጠላቶች፥ ኣገር ኣስገንጣዮችና ዳር-ድንበር ኣስደፋሪ ወያኔ/ማሌሊቶች እብሪት፥ የሚወዷትን ኣገራቸው ጥለው ለዳግም ስደት ለተዳረጉት፤ 
  • በቀ. ኃይለ-ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ገበሬዎችና በቅርብ በሚያውቋቸው የወቅቱ ፖለቲካ እቀንቃኞች “ተራማጅ ነጋድራስ” የሚል እውቅና ለተሰጣቸው ለክቡር እምክቡራን ላቶ ገብረየስ ቤኛ የክብር ማስታወሻ ትሁንልኝ! 

እሪ በይ ኣገሬ

እሪ በይ ኢትዮጵያ ፥ ቅል ድንጋይ ሰበረ፤

ውሃ ሽቅብ ወጣ ፥ ዘመን ተቀየረ፤

ሌባ እየከበረ ፥ ነጋዴው ከሰረ፤

ኣገር ፈራረሰች ፥ ድንበር ተደፈረ፤

እንደ ቅርጫ ስጋ ፥ እየተመተረ፤

ላረብ ለድርቡሹ ፥ ይታደል ጀመረ፤

ጀግና ኣንገቱን ደፋ ፥ ባንዳ ተወጠረ።

(ግጥም፤ ከኢየሩሳሌም ጀማል Facebook የተወሰደ።)

ኣንጀት የሚያሳርረውና የሚያበግነው፥ ኣቶ ገብረየስ ቤኛ ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ጋር ያደረጉት፥ በኣምስት ክፍል የቀረበ፥ ሰፊ የምስል (የቪዲዮ) ቃለ-መጠይቅ በትዕግስት በመመልከት፥ ኣሁን በኢትዮጵያ ቤተመንግስት የሰፈሩትና ፍፁም ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑት ኣደገኛ የዲያብሎስ ልጆች ምንነትና ኣጥፊ ዓላማ በትክክል ለመረዳት ያስችላል። በወያነ/ማሌሊት ኣመራር ምንነት ኣሁን ያለዎትን መረጃ በማዳበር ቢሆንም ተጨማሪ ኣቅም ይገነባል።  

  

Part-1: http://ethsat.com/video/esat-yesamintu-engeda-gebreyes-begna-august-2014-part-1/


ቅኔና አዘማሪ –ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

$
0
0

ቀሲስ አስተርዕየ

ቀሲስ አስተርዕየ

nigatuasteraye@gmail.com
መስከረም ፳፻፯ ዓ.ም.

http://www.medhanialemeotcks.org/

መግቢያ

ለአዘማሪ ሙያ ተስማሚ የግብር መግለጫ መሆን ያለበት የቱ ነው? አዘማሪ ወይስ አርቲስት? በሚል በአቶ ዓለም ነጻነት ሬድዮ የቀረበው ውይይት ለዚህች ጦማር መነሻ ሆኖኛል።ከቀደሙ አባቶች እንደሰማሁት አዘማሪ ብቻውን የቆመ አይደለም። ከብዙ ነገሮች ጋራ ከቅኔያችን፣ ከዜማችንና ከስሜታችን ጋራ የተያያዘ ነው። አዘማሪ የሚለውን ቃል ከነዚህ ነጥሎ ለማቅረብ መሞከር ያዘማሪን ክብርና ቦታ ዝቅ ያደርገዋል የሚል ስጋት አለኝ።

ስለዚህ አዘማሪ ወደሚለው ቃል ዘው ብለን ከመግባታችን በፊት የአዘማሪን ተልእኮ መዳሰስ ሊኖርብን ነው። አዘማሪ የሚለው ቃል የግብሩ (የተልእኮው) መግለጫ ነው። ተልእኮውም ራሱ አዘማሪ ተቀኝቶም ሆነ ገጥሞ ወይም ሌላ የተቀኘውን በዝማሬው ቅላጼ ከጉሮሮውና ከመሳሪያ ጋራ አስማምቶ፣ ቀምሞና አስወድዶ አስውቦ ለህዝብ ማቅረብ ነው። ህዝቡንም ከባህሉ ከታሪኩ ከኢትዮጵያዊነቱ ከስሜቱ ጋራ እርስ በርሱ የበለጠ ያጣብቃል። እርስ በርሱ ያቀራርባል። ያዋህዳል። ያስተባብራል። እንደ ኢትዮጵያ ከመሰለ በቅኝ ግዛት ሳይወረር የራሱን ጠብቆ ከሚኖር አገር የሚፈልቅ አዘማሪ የሚያስተላልፈው ቅኔ፦ ኅብር፤ ሰምና ወርቅ፤ ሰረዝ፤ ጎዳና፤ ውስጠ ወይራና ሌላም ዓይነቶች አሉ። ያዘማሪን ክብርና ቦታ ዝቅ ላለማድረግ ስለአዘማሪ ከመናገሬ በፊት ስለኢትዮጵያዊ ቅኔ ትንሽ ማብራሪያ መስጠት ፈለኩ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በኦጋዴን ክልል የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተደረገውን የጅምላ ጭፍጨፋ እናወግዛለን

$
0
0

entc-logo-5አገር በቀል የሆነው፤ የቅኝ አገዛዝና ዘረኛው የወያኔ ሰርአት በኦጋዴን ክልል የሚኖሩ ወገኖቻችንን ከተቃዋሚ ድርጅት ጋር ግንኙነት  አላቸው በሚል ሽፋን ያደረገውን የጅምላ ጭፍጨፋና ጭፍጨፋውን ተከትሎ አስከሬን መሬት ለመሬት እየተጎተተ እንዲከማች  መደረጉን በመስከረም 5 ቀን 2007 ዓም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን በመረጃነት የቀረበውን ዘግናኝ ድርጊት ተመልክተናል። የዚህ  ዘግኛኝ ወንጀል አስፈጻሚ የሆኑ ግለሰቦችም የወገኖቻችን አስከሬን እነደእንስሳ እያስጎተቱ ባንድ ቦታ እንዲከማች ትዛዝ  በሚያስተላልፉበት ወቅት ሲናገሩት የነበረውን ማድመጥ ልብ የሚሰብረና አይምሮን የሚሰቀጥጥ ነው። የኢትዮጵያዊ ብሔራዊ የሽግግር  ምክር ቤት ይህን ፋሽስታዊ ድርጊት በጽኑ ያወግዛል።—  ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

ኢህአዴግ የሰራው ቤት! ግድግዳው ሰንበሌጥ!

$
0
0

ገለታው ዘለቀ

እንደ መግቢያ
ፌደራሊዝም የመንግስት ኣወቃቀር ሰፊ የቆዳ ስፋትና ብዙ ህዝብ ላላቸው ኣገሮች፣ በዛ ያሉ የተለያየ ቋንቋና ባህል ያላቸው ቡድኖች ላላቸው ሃገሮች፣ ተመራጭ ኣስተዳደራዊ መዋቅር እንደሆነ እጅግ ብዙ ሰው በዓለም ላይ ይስማማል። ፌደራሊዝም የተመረጠበት ዋናው ምክንያት ስልጣን እና ፍትህ ከህዝቡ እንዳይርቅ ነው። እንዳይርቅ ስንል ከመልክዓ ምድርም ከወረፋም ኣንጻር ነው። ትላልቅ የሆኑ ኣገሮች ስልጣንን ቢያማክሉ ዜጎች ለኣንዳንድ ጉዳዮች ስልጣን ወደተጠራቀመበት ለመሄድ ስለሚርቃቸው ብዙ ከሆኑ ደግሞ ሰልፉ ስለሚበዛ ወረፋው መጉላላትን ስለሚፈጥር ነው። ዜጎች ስልጣን ወርዶ ከፍተኛ የሆኑ ጉዳዮቻቸውን ሳይቀር በክልሎቻቸው እንዲታይላቸው መደረጉ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ፍትህንና ኣገልግሎትን ለማደል በጣም ይረዳል። ስልጣን ተማክሎ የመካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ ባለስልጣናት እንደ ቧንቧ ማስተላለፍ ብቻ ከሆነ ስራቸው መንግስትና ህዝብ ልብ ለልብ ከመራራቃቸውም በላይ በውሳኔና በእቅድ ላይ ተሳትፎኣቸው ዝቅተኛ ይሆናል ኣገልግሎት ኣሰጣጡም ብዙ ችግር ይገጥመዋል።። ሌላው ደግሞ የተለያየ ባህልና ቋንቋ ያላቸው ቡድኖች በተለያየ መልክዓ ምድር ለብቻ ለብቻ ሰፍረው ነገር ግን ደግሞ ኣንድ ኣገር መስርተው እየኖሩ ከሆነ እንዲሁ ባንድ በኩል ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ጠብቀው በኣንድ ሃገር ጥላ ስር እንዲኖሩ የሚረዳ መሆኑንም ሁሉም ይረዳል። ኢትዮጵያ ካላት የቆዳ ስፋትና ካላት የህዝብ ብዛት እንዲሁም ካላት የቡድኖች ብዛት ኣንጻር ፌደራሊዝም ተመራጭ ኣስተዳደር መሆኑን እጅግ ብዙ ሰው ያምናልና በዚህ ላይ ውይይት ኣስፈላጊ ኣይደለም።

eprdfበዚህች በዛሬዋ መጣጥፌ የማስተላልፈው መልእክት ፌደራሊዝም ጠቃሚነቱን ለመግለጽ ሳይሆን ኣቶ መለስ ዲዛይን ኣደረጉት ወይም በሳቸው ምህንድስና ተዋቀረ የተባለውን የዛሬይቱን ኢትዮጵያን የፌደራል ኣወቃቀር ትንሽ መተቸት እፈልጋለሁ። መተቸትም ብቻ ሳይሆን ምን ኣልባት ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሊጠቀሙበት ይችሉ ይሆናል በሚል ተስፋ ኣማራጭ የፌደራል ኣወቃቀር ኣሳብ ለማቀበል እሞክራለሁ።

የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት

የኢትዮጵያ ፌደራል ሲስተም ተፈጥሮ በሚገባ ከሚገለጽባቸው ጉዳዮች መካከል ኣንዱ የክልሎች መንግስታት ኣወቃቀር ነው። እነዚህ መንግስታት ሲዋቀሩ መስፈርቱ ምን ምን እንደሆነ ማወቅ የኢትዮጵያን ፌዴራል ስርዓት ለመረዳትና ለመገምገም ይጠቅማል። ኣቶ መለስ ዲዛይን ያደረጉትን ይህንን የክልል ኣፈጻጸም ብዙ ሰው የሚገልጸው በብሄር ፌደራሊዝም(Ethnic federalism) ነው። በርግጥም የፖለቲካውን ኣወቃቀር ስናይ ማለትም የፖለቲካው እግሮች(radicals) በብሄር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ፌደራሊዝም ካለ የብሄር ፌደራሊዝም ነው ያለው ለማለት ያስችለናል። ይሁን እንጂ የክልል መንግስታቱ ኣመሰራረት በምን ላይ እንደቆመ ማየት ደግሞ የመንግስትን ተፈጥሮና ፍላጎት ለማየት ይረዳናል። ስለዚህ የነዚህ የዘጠኝ ክልሎች መንግስታት ምስረታ ይህንን የብሄር ፌደራሊዝም የተባለውን መርህ ተከትሎ ነው ወይ የተፈጸመው ብለን ማየት ተገቢ ነው። የገዢው መንግስት ኣካላትና ደጋፊዎቻቸው እንደሚገልጹት የክልል መንግስታት ምስረታው ራስን በራስ ማስተዳደርን መሰረት ያደረገ፣ ማንነትን ያገናዘበ፣ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ያገናዘበ እንደሆነ በኣጠቃላይም በብሄር ፌደራሊዝም(Ethnic federalism) ሊገለጽ እንደሚችል ይስማማሉ።

የብሄር ፌደራሊዝም በምሁራንና በኣብዛኛው ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ነቀፌታ ያለበት ቢሆንም መንግስት ግን በተለይ የብሄር ብሄረሰቦችን “ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን” እንዳጎናጸፈለት ደጋግሞ ይገልጻል። ኣጥብቀው ለሚቃወሙት ወገኖች ደግሞ የብሄር ፌደራሊዝም እኛ ጋር ብቻ ኣይደለም ያለው ስዊዘርላንድን፣ ህንድን፣ ቤልጂየምን ተመልከቱ እነሱም በብሄር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ነው ያላቸው ይላል። በመሰረቱ ግን የነዚህን ኣገሮች ኣወቃቀር በሚገባ ማየት ያስፈልግ ይመስለኛል። ርግጥ ነው ስዊዘርላንድ ምንም እንኳን የህዝብ ብዛቱዋ ትንሽ ቢሆንም ጀርመንኛ ተናጋሪዎችን፣ ጣሊያንኛ ተናጋሪዎችን፣ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎችንና ሪሂቶ ሮማንስን በሃያ ስድስት ካንቶኖች ከፋፍላ በባህላዊ ኣስተዳደር እያስተዳደረች ያለች ኣገር ናት። ። ስዊዘርላንድ ውስጥ ያለው ይህ ቋንቋን የተከተለ ኣከላለል ባንድ በኩል ባህልን እየጠበቁ በሌላ በኩል ለኣስተዳደር ኣመቺነቱን በማየት ነው። የስዊዘርላንድ ኣከላለል ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ሳይሆን ኣስተዳደራዊ ኣመቺነትን በማየት ነው። በብሄር በፖለቲካ መደራጀትን የስዊዘርላንድ ህግ ይከለክላል። ከኢትዮጵያ የሚለየው በዚህ ነው። የኢትዮጵያ የክልሎች ኣወቃቀር በብሄር ፖለቲካ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝሙም የሚመነጨው ከዚህ ኣስተሳሰብ ነው።ዋናው ፍልስፍናቸውም “ብሄሮች ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድሩ” የሚል ፖለቲካዊ ኣስተዳደርን የሚመለከት በመሆኑ ነው ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ነው የሚያሰኘን። የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ከዚሁ ከብሄር ፖለቲካ ኣስተሳሰብ የመነጨ ሲሆን የስዊዝ ደግሞ በኣንድ ብሄራዊ ፖለቲካዊ ማንነት ጥላ ስር ያደረ ባህላዊ ኣስተዳደር ተደርጎ ነው ሊወሰድ የሚችለው። ስዊዘርላንድ ከላይ እንደ ጥላ የረበበ ኣንድያ ጠንካራ ማንነት ያላት ሲሆን ኢትዮጵያ በኣሁኑ ጊዜ ብሄራዊ ማንነቷ የት እንዳለ የት እንደተጠለለ በሚገባ ኣይታይም። ለዚህም ነው ብዙ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያዊነታችንስ? የት ጣላችሁት? ….ወዘተ. እያሉ የሚያጉረመርሙትና ፍለጋ የገቡት:: በኢሕ ኣዴግ ዘመን ኢትዮጵያዊነት የት ኣደረ? የት ነው ያለው? ብለን ኣጥብቀን ከጠየቅን ኢትዮጵያዊነትን ኣድሮ የምናገኘውና ብሄራዊ ማንነት የሚገለጸው በብሄር ፓርቲዎች ግንባር ደረጃ ነው። ኢሕ ኣዴግ ኣይዲዮሎጂ በሌላቸው የብሄር ፓርቲዎች የተገነባ ግንባር ሲሆን የግንባር ተፈጥሮ ደግሞ ለኣንድ ለተወሰነ ዓላማ የሚሰባሰቡበት ድርጅት ነው። በርግጥ ኢሕዓዴግ የሚባለው ራሱ በዓለም ላይ ኣለ ወይ? የሚለውን ፍልስፍናዊ ጥያቄ ለጊዜው ቁጭ ኣርገነው ግንባር የሚመሰረተው ለኣንድ ለተወሰነ ዓላማ ነው። ግንባር የመሰረቱ ድርጅቶች መንግስት የመጣል ተፈጥሮ ካላቸው እስኪጥሉ ኣብረው ይታገሉና ከዚያ በሁዋላ ወይ ይዋሃዳሉ ወይ በየፊናቸው ይቀጥላሉ። ግንባር በተፈጥሮው ኣድራሽ ነው። ዘላለማዊ ኣይደለም። ትልቁ ችግር ግንባር መሆኑ ብቻ ሳይሆን በብሄር ድርጅቶች የተፈጠረ ግንባር መሆኑ ነው። ኢሕ ኣዴግ ስልጣን ሲይዝ ወይም መንግስት ሲመሰርት ይሄው የግንባር ተፈጥሮው ይንጸባረቃል። ኣንቅጽ ሰላሳ ዘጠኝም የዚህ ተፈጥሮ ውጤት ይመስላል። እስከ ተወሰነ ኣብረን ግንባር ፈጥረን እንሄዳለን ካልሆነ እንለያያለን ኣይነት ነው ነገሩ። ብዙ ጊዜ የመንግስት ተወካዮች ኢህዓዴግ ስልጣን ከለቀቀ ኣገሪቱ ትበታተናለች ብለው የሚናገሩትና የሚያምኑት እነሱ የፈጠሩዋት ኢትዮጵያ ብሄራዊ ማንነት በግንባር ደረጃ ተውሸልሽሎ ያለ በመሆኑ ይሄው እየታያቸው ሊሆን ይችላል። ስዊዘርላንድ ምንም እንኳን ክልል የሰራችው በቋንቋና በባህል ላይ ቢሆንም ፖለቲካዊ ጨዋታዋ ግን በኣንድ ጠንካራ የፖለቲካ ማንነት ጥላ ስር ነው። ይህን ብሄራዊ ማንነት ትቶ በብሄር ማንነት ላይ የፖለቲካ ቤት መስራትና የጀርመንኛ ተናጋሪዎች የፖለቲካ ድርጅት የፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች ድርጅት የሚባል ነገር በህግ ክልክል ነው።ግንባር ነኝ የሚለው ኢህዓዴግ ኢትዮጵያን በግንባር የፖለቲካ ኣስተሳሰብ የሚያስተዳደር ሲሆን እስከ መቼ ለሚለው ጥያቄ መልሱ ኣይታወቅም።ይህ ኣንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ ለማስፈራሪያ ተቀምጦም ከሆነ ማንን ለማስፈራራት እንደተቀመጠም ኣይታወቅም። ጉዳዩ በማስፈራራት ወይም ካልሆነ እንለያያለን ብለን ሰለጻፍን ዋስትና ኣይሆነንም።
EPRDF
የዚህ ዘመን ኣስተዳደራዊ ችግር የሚመነጨው ከፖለቲካው የመጀመሪያ የእምነት ምንጭ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ የብሄር ፖለቲካ እምነት ዋናው መነሻ ስነ -ህይወታዊ (DNA and genealogy)ጉዳይን ኣጥብቆ የያዘ መሆኑ ነው። በዚህ ኣሳብ ልብ ውስጥ ያለው ጉዳይ ኣንድ ሰው ኣገር ለሚለው ጽንሰ ሃሳብ ማሰብ ሲጀምር ከታች እንዲጀምር ነው የሚበረታታው። ቤተሰብ፣ ዘመድ ኣዝማድ፣ ጎሳ፣ ብሄር ከዚያ ኣገር እያለ ከታች ወደ ላይ የሚሄድ እምነት ነው። የህወሃት ሰዎች የደም ጉዳይ ነው…… ተፈጥሮ ነው…… ምን እናድርገው? ይላሉ።እርግጥ ነው ስነ-ተፈጥሮኣዊ እውነት ኣለ። ኣንድ ሰው ለቤተሰቡ ማለትም ለወንድሙ፣ ለእህቱ፣ ለናቱ፣ ላባቱ ወዘተ. የሚራራና የሚታመን ቅርብ ልብ ኣለው። ከዚያም ከፍ ሲል ለዘመዶቹ ከዚያም ባህል ኣቋራጭ (cross cultural) ጉዳይ ሲመጣ ለባህላዊ ቡድኑ ተቆርቋሪ መሆኑ ተፈጥሮኣዊና ስነ-ተፈጥሮኣዊ ሊሆን ይችላል።ይሄ ኣይካድም። የብሄር ፖለቲካ ይህንን ስነ ህይወታዊ ትንታኔ ይዞ ነው ፖለቲካዊ ይዘት ያለበሰው። ከዚህ ጽኑ የጄነቲክ እምነቱ የተነሳም ብሄሮች በራሳቸው ባህላዊ ቡድን ኣባል ኣስተዳደራዊ መዋቅር ቢዘረጉ ኣስተዳደሩ ርህራሄ ይሞላዋል፣ ችግርን መረዳት ይኖራል፣ ከፍተኛ ተግባቦት ይኖራል፣ ስለዚህ በተወላጁ መተዳደሩ ተፈጥሮኣዊ መሰረት ያለው ነው የሚል እምነት ያለ ይመስላል።ይሄ መሰረታዊ የብሄር ፖለቲካ ፍልስፍና በርግጥ ገዢውን መንግስት ኣብከንክኖታል ወይ? የሚለውን እንተወውና በኣጠቃላይ የብሄር ፖለቲካ እምነት ምንጩ እንደዚያ ነው። የዚህ የብሄር ፖለቲካ መሰረታዊ እምነት ግን ትልቅ ችግር ያለበት ነው። ችግሩ ምንድነው? ካልን የዴሞክራሲና የፍትህ ተፈጥሮ ከዚህ መሰረታዊ እምነት ጋር ኣብሮ ኣለመሄዱ ነው። ዴሞክራሲና ፍትህ ከላይ ሆነው ነው የምናያቸው። ፍትህና ዴሞክራሲ መርህ ነው ወገናቸው። ጀነቲክ ወይም የደም ሃረግ ጉዳይ ዓይደለም። ዴሞክራሲ ኣስተዳደሩን ሲዘረጋ በብዙሃን ድምጽ ከላይ ይነሳና ወደ ታች እስከ ግለሰብ ድረስ ወርዶ፣ የልዩነት የመጨረሻው ቅንጣት እስከ ሆነው የግለሰቦች የተለያየ ተሰጥዖ፣ችሎታና ምርጫ ድረስ ወርዶ እንክብካቤ የሚያደርግ ስርዓት ነው። እነዚህ ሁለት የሃገር ዋልታና ማገሮች ማለትም ፍትህና ዴሞክራሲ ከዚያ ከብሄር ፖለቲካ ጋር የሚጻረሩት በዚህ ነው። ኣንዳንዴ ወንድምህና ኣንድ የማታውቀው ሰው በፍትህ ፊት በዴሞክራሲ ፊት ቆመው ሳለ ወንድምህ ካጠፋ በወንድምህ ላይ ትፈርድ ዘንድ ያስገድድህና የባዮሎጂውን የርህራሄ የምናምኑን ጉዳይ ይሰብረዋል። የጀነቲኩን ጉዳይ ኣደባባይ ላይ ሳያወጣ ግለሰባዊ ኣድርጎት ቁጭ ይላል። በመሆኑም ዴሞክራት መሪዎች በኣስተዳደር ጊዜ ከላይ ይሆኑና የተፈጥሮ ሃላፊነታቸውን ከዘመዶቻቸው ጋር የሚወጡት በጓዳ ነው። ንስር በተፈጥሮው ከፍ ብሎ ይበራል። ከፍ ብሎ እየበረረ ወደ መሬት ጥቃቅን የሆኑ ነገሮችን ነጥሎ የማየት ችሎታ ኣለው። ዴሞክራት መሪዎች የዴሞክራሲንና የፍትህን መርሆዎች ከላይ ይዘው ታች የግለሰቦችን ህይወት የሚነካ ስራ ይሰራሉ። የብሄር ፖለቲካ መሪዎች ደግሞ ጄነቲክ የሆነውን ተፈጥሮኣዊ የጓዳ ግንኙነት የፖለቲካ ቤት ሰርተው ኣደባባይ ኣውጥተው ደግሞ በሌላ በኩል ዴሞክራሲን በሌላ እጃቸው ለመጎተት ሲሞክሩ ይታያል። በኢትዮጵያ ውስጥ ኣሁን ያለው ግጭት ይሄ ነው። የዚህ የብሄር ፖለቲካ ኤነርጂ ለዴሞክራሲ ያልተመቸውም በዚህ ነው። በእንዲህ ዓይነት መሬት ላይ ዴሞክራሲ ቢዘራ ኣይበቅልም። የዴሞክራሲና የብሄር ፖለቲካ ተፈጥሮ ኣብሮ ባለመሄዱ ነው ዛሬ ዴሞክራሲ በሃገራችን የጠፋው። ከፍ ሲል እንዳልኩት የህወሓትና የሌሎች ብሄር ተኮር ድርጅቶች ችግር የእምነት ችግር ነው። ይህ እምነት ደግሞ ባዮሎጂካዊ እውነት ቢኖረውም ኣስተዳደራዊና ፖለቲካዊ መልክ ሲይዝ ጥሩ ኣይደለም። የብሄር ፖለቲካ በዓለም ታሪክ ውስጥ ብዙ ኪሳራ ኣምጥቱዋል።የብሄር ፖለቲካ ኣራማጆች ካደጉበት መንደር ወጥተው ኢትዮጵያን በሙሉ ዓይን ማየት መጀመር ካልቻሉ የኢትዮጵያን ኣንድነት መረዳት ያዳግታቸዋል። ታላቋ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የተባበሩት ህዝቦች የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) መልካም ፈቃድ ኣምባሳደርና የፊልም ተዋናይ ኣንጀሊና ጆሊ በኣንድ ወቅት የተናገረችውን ቁምነገር እዚህ ጋር መጥቀስ ኣስፈላጊ ይመስለኛል።

“If you don’t get out of the box you’ve been raised in, you won’t understand how much bigger the world is” Angelina Jolie

eprdf_meetingሌላው የዚህ የፌደራሊዝም ምህንድስና ጉዳይ ሲነሳ የኢትዮጵያን ኢሜጅ የማስተካከልም ስራ ነው። የኢትዮጵያን ብዙነትና ኣንድነት ማሳየት የሚችል የፌደራል ስርዓት ያስፈልጋል። የኣሁኑን ስርዓት ስናይ ኢትዮጵያን የሚገዛት የብሄር ፖለቲካ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የሚያሳዝነው የብሄር ፖለቲካው ኣምባገነን መሆኑ ነው። በዚያው በብሄር ከተደራጁት መካከል ኣንዱ ሲበዛ ሃይለኛ ሆኖ በኣምባገነንነት ይኖራል። ለስሙ የብሄር ጉዳይ ይግነን እንጂ ኣንድ ሃይለኛ ፓርቲ በየቡድኑ የተወከሉትን ኣስተዳዳሪዎች የሚቆጣጠርበት እንደፈለገ የሚያደርግበት ሁኔታ በመሆኑ ስልጣን በተግባር ያለ ልክ ተማክሎ ነው የሚታየው። ይሄ ችግርም የዚሁ የብሄር ፖለቲካ ተጽእኖ መገለጫ ነው። እንደዚህ ዓይነቱ ፖለቲካ ባለበት ምድር ዳይቨርስ የሆኑ ከተሞች እንደ ኣዲስ ኣበባና ሌሎች ከተሞች ችግር ውስጥ ይገባሉ። ኣጠቃላይ የሆነው ኣስተሳሰብ ቢያንስ ወደ ማንነት ድምጽ(Identity Voting) ሊመራቸው ይችላልና በምርጫዎች ላይ ጥላ መጣሉ ኣይቀርም።ኣንድ ሰው ኣዲስ ኣበባ እየኖረ በመታወቂያው ላይ ኣማራ… ትግሬ…. እየተባለ መጻፉ የዚህ ኣስተሳሰብ ውጤት ነው። ፓለቲካው ኣስተዳደራዊ ጉዳይን ከማንነት ጋር ስለጨፈለቀው የፖለቲካ ሰዎች ለምርጫ ሲቀርቡ የብሄር ዳራቸውን የማወቅ ፍላጎት በዜጎች ዘንድ ከማደሩም በላይ ከተመራጩ ታለንትና ፖለቲካዊ ብቃት ይልቅ ለጄነቲክ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ስለሚገፋ ዜጎች ለማንነት ድምጽ(identity voting) መጋለጣቸው ኣይቀርም ከዚያም ጋር ተያይዞ ለሚመጣ ሃሜትና ጉምጉምታ መጋለጣቸውም ኣይቀርም በውጤቱም ኣጠቃላይ የዴሞክራሲን ባህል እያጠፋ ይሄዳል።የህዝቡን ስነ ልቦናም ያበላሻል።ኣክቲቪስቶች ሳናውቀው የዚህ ፖለቲካ ሰለባ እንዳንሆን መጠንቀቅ ኣለብን። ሳናውቀው ሰለባ ከሆንን ኣዲስ ኣበባ ኣካባቢ ሁለት ሰው ሲሞት የምንጮኸውን ያህል ኦጋዴን ወይም ጋምቤላ በጅምላ ሲጨፈጨፉ ኣዘናችን ያን ያህል ላይሆን ይችላል።
የብሄር ፖለቲካ ችግሩ የመነሻው እምነት ነው ብለናል።ዴሞክራሲስ እምነት ኣይደለም ወይ? የሚል ጥያቄ ይነሳል።በርግጥ ዴሞክራሲ ይልቃል ስንልም በእምነት ነው። በዴሞክራሲ ላይ ስንቆምም በዴሞክራሲ ላይ ታምነን ነው። ልዩነቱ ዴሞክራሲ በተፈጥሮው የቆመበት መሰረት ከጄነቲክ፣ ከባህልና ቋንቋ መሰረት በላይ በሰው ግለሰባዊ ስብእናና ታለንት ላይ በመታመን ፍትህን ማደል ሲሆን በጋራ ምርጫ ጊዜ ደግሞ ኣንድ ሰው ለኣንድ ድምጽን መሰረት ያደረገ ነጻ ምርጫ ኣድርጎ በድምሩ ኣብላጫ ያለውን ድምጽ ኣሸናፊ በማድረግ ተሸናፊው የኣሸናፊውን ድምጽ ኣክብሮ በጋራ እስከ ቀጣዩ ምርጫ መስራት ነው። ዴሞክራሲ ከላይ ሆኖ የሚያይ በመሆኑ በዚህ ጥላ ስር ዜጎች ቢያርፉ እረፍትና መተማመን ሊያመጣላቸው ይችላል የሚል እምነት ነው ያለው። ይህ እምነት ደግሞ በተግባር ተፈትኖ የወጣለት በመሆኑ ነው የምንመርጠው። ከሁሉም በላይ ከዘመኑ የሰው ልጆች ኣስተሳሰብ ደረጃ ጋር ኣብሮ መጓዝ የቻለ የኣስተዳደር ጥበብ ሆኖ በመገኘቱ ነው ይህን እምነት የበለጠ እንድናምነው የሚያደርገን። ሌላው ከፍ ሲል እንዳልነው የዚህ የብሄር ፖለቲካ እምነት የፍትህ ኣሳላፊዎቹን ብሄራዊ ማንነት ለማወቅ በፍትህና ኣገልግሎት ፈላጊዎች ዘንድ ፍላጎት እንዲሰርጽ ማድረጉ ነው። በዴሞክራሲ ጊዜ ይህ ስሜት ጨርሶ ይጠፋል ማለት ኣይደለም። ይሁን እንጂ ከላይ ያለው የዴሞክራሲ መርህ ለዜጎች መተማመኛ ስለሆነ በኣንዳንድ ሰዎች ስሜት ላይ ሊጎላ የሚችለውን ችግር ተጠያቂነት የሚባለው ነገር ስላለ ይህንን ስሜት ያደበዝዘዋል፣ ቀስ እያለ ዴሞክራሲ ባህል እየሆነ ሲመጣ ደግሞ ይህ ስሜት እየከሰመ ይሄዳል።የኢትዮጵያን ኢሜጅ ስናስብ የኣንድ ብሄር የበላይነት የነበረባት ኣገር ከነበረች ኣሁን ደግሞ የበለጠ ስም ኣውጥቶ የሌላ ኣንድ ብሄር የበላይነት ካለ ለውጥ የለም። የኢትዮጵያ ኢሜጅ የሚስተካከለው በዴሞክራሲና በፍትህ ነው። ዜጎች እንደ ዜጋ ቡድኖች እንደ ቡድን እኩል ሲሆኑ የቡድኖች ትንሽና ትልቅነት ሲጠፋ ፍትህ ሲበየን የሃገሪቱ ኢሜጅ ይስተካከላል። መቶ የፖለቲካ ፓርቲ በየስማችን ማቋቋሙ የኢትዮጵያን ኢሜጅ ኣያሳይም። ካሳየም የተበታተነች ኣገር መሆኑዋን ነው። ባህላዊ ማንነትንና ፖለቲካዊ ማንነትን መለየት ያስፈልጋል ። ብዙ ኣገሮች እምነትንና ኣስተዳደርን ለይተው ይታያል። በኢትዮጵያ ህገ መንግስትም ኣንቀጽ ኣስራ ኣንድ ላይ ሃይማኖትና መንግስት መለያየታቸውን ይገልጻል። ልክ እንደዚህ ኢትዮጵያ ባህላዊ ማንነትንና ፖለቲካዊ ማንነትን መለየት ኣለባት ለዚህም ኣንቀጽ ኣስራ ሁለት ብላ እነዚህ ጉዳዮች መለያየታቸውን ማስመር ኣለባት።

መጀመሪያ ወደ ኣነሳነው ጉዳይ እንመለስና ለዛሬው የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ሌላዋ የኢህዓዴግ ምሳሌ ደግሞ ህንድ ናት:: እውነት ነው በርግጥ ህንድ ውስጥ የክልል ፓርቲዎች ኣሉ:: ኢትዮጵያ ውስጥ ህወሃት ብዓዴን ወዘተ. እንደሚባለው ህንድም ውስጥ የክልል ወይም(state or local parties) የሚሉዋቸው ፓርቲዎች ኣሉ።። ይሁን እንጂ ስልጣኑን የያዘውና እጅግ ኣብዛኛውን መቀመጫ የተቆጣጠረው ብሄራዊ ኣጀንዳ ያለው በዚህ ኣመት ለጠቅላይ ሚንስትርነት በተመረጡት ናረንድራ ሞዲ የሚመራው BJP የተሰኘው ብሄራዊ ፓርቲ ሲሆን የክልል ፓርቲዎች ተሰሚነታቸው በጣም ዝቅተኛ ነው።በያዝነው ኣመት ህንድ ውስጥ በነበረው ምርጫ ቀደም ባሉት ጊዚያት ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር ውህደት ፈጽሞ ተጠናክሮ የወጣው BJP ፓርቲ ኣምሳ ኣንድ ነጥብ ዘጥኝ በመቶ የሚሆነውን ኣጠቃላይ ምርጫ ያሸነፈ ሲሆን ሌሎች ከፍተኛ መቀመጫ የያዙትም ብሄራዊ ፓርቲዎች ናቸው። የክልል ፓርቲዎች እዚህ ግባ የማይባል ውጤት ነው ያላቸው። በኣጠቃላይ ህንድ በብሄራዊ ፓርቲዎች የመንፈስ ልእልና የምትመራ ኣገር ስትሆን ብሄራዊ ፓርቲ ቢዳከምና የክልል ፓርቲ ቢያብብ በርግጥ ህንድም ኣደጋ ላይ መውደቋ ኣይቀርም። ነገር ግን የሚመስለው ህንዶች የክልል ፓርቲዎችን ለጊዜው ዝም ያሉዋቸው ሲሆን በምርጫ እየቀለሉ ቀስ እያሉ ይጠፋሉ ከሚል ዘዴም ሊሆን ይችላል እንጂ ህንድም ብትሆን የማንነት ፖለቲካን የምታበረታታ ኣገር ኣይደለችም።ማሌዢያን ብናይ በርግጥም በዘር ላይ የተመሰረቱ ወይም ስያሜያቸው ከዘር ጋር የተያያዘ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኣሉ። ጠንካራ የሆነ ፓርቲ ቢኖራቸውም በብሄር ላይ የቆሙት ፓርቲዎች የኣድቫንቴጅ ጥያቄዎችን በየጊዜው እንዲያነሱ ያደርጋቸዋል። በህንድና በማሌዢያ የዚህ የብሄር ፖለቲካ ክፉ ውጤት ጎልቶ ካልታየባቸው ጉዳዮች መካከል ኣንዱ የኢኮኖሚው እድገትም ይመስላል። ዜጎች የኢኮኖሚ ሁኔታቸው ሻል ሲል ዘንጋ ቢሉም የኢኮኖሚው ሁኔታ መናጋት ሲጀምር እንደ እምቅ ችግር ሆኖ መነሳቱ ዓይቀርም። በቅርቡ የእስያ ሪቪው እንደዘገበው የማሌዢያ ኢኮኖሚ መውደቅ ሲጀምር ዘረኝነት ብድግ ማለቱን ገልጹዋል። በዘር ላይ የቆመ ፖለቲካ ሲኖርና የሪሶርስ ማነስ ሲሰማን ያ በዘር ላይ የቆመው ፖለቲካ ድርጅት ስልጣኑን ተጠቅሞ ወገኑን ይረዳል ብለን መጠርጠር የመጀመሪያ የዓመጽ መነሻችን እንዲሆን ሊያደርግ ይችላል። የትም ሃገር በብሄር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምዱ ሁሉ መውጫ ፍለጋ እየጣሩ እንጂ ተደስተው ኣይኖሩም። ብሄራዊ ማንነታቸው ተናግቶ፣ ፍትህ ቀጭጮ ተቸግረው ነው ያሉት።

ቤልጂየምም ብትሆን ከኢትዮጵያ የተለየች ናት። በዘውዳዊ ህገመንግስት (constitutional monarchy) ስር ያሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢኖሩም ኣንድ ከላይ የረበበ ብሄራዊ ኣንድነት ይዙዋቸው ይታያል። ስለ ህገመንግስታዊ ሞናርኪ ሳስብ ለእኔ የሚመስለኝ፣ ያልተጻፈ ቢሆንም፣ ምንም እንኳን ከዘውዳዊ ኣገዛዝ ወደ ዘመናዊነት መሸጋገር ያማራቸው ኣገሮች ኣዲሱ ትውልድ በኣንድ ወቅት ዘውዳዊ ኣባቱን ኣሁን እኔ ኣዲስ ኣስተዳደር ተገልጦልኛል፣ ዴሞክራሲ በተባለ ጥበብ ኣገሪቱን ላስተዳድር ነው ብሎ ለውጥ ሲጀምር ዘውዳዊ ኣገዛዙን በስምምነት ኣስተዳደራዊ ጉዳዮችን እንዲሰጠው ጠየቀ ማለት ኣዲስ የሚመጣው ኣስተዳደራዊ ስርዓት፣ ዳይናሚክ የሆነው ጥበብ ፣ ሉዓላዊነትን ከዘውዱ ይነጥቃል ማለት ኣይመስለኝም። ዘውዱ ኣሁንም የኣገሪቱን ሰማይና የብስ የሚገዛ ይመስለኛል። ኣልገባኝ እንደሆን ኣላውቅም። ለማናቸውም ግን ዘውዳዊ ኣገዛዙን ያልገደሉ ዘመናዊነት ሲመጣ ወደ ህገ መንግስታዊ ዘውዳዊ ኣገዛዝ ሲመጡ በህገ መንግስት ብዙውን ኣስተዳደራዊ ስልጣን ኣዲስ ነገር ተገልጦልኛል ላለው ትውልድ ቢሰጠውም ልእልናው ግን ኣለና ያ ልእልና የኣንድ ሃገር ብሄራዊ ማንነትን ሊገልጽ የሚችል ከላይ የረበበ ጥላ ሊሆንላቸው ይችላል:: የዳር ድንበርን (territorial integrity) ጉዳይ በህይወት ሆኖ ታሪክን የሚያስታውስ ይመስለኛል። የቤልጂየም ንጉስ ፊሊፕ ኣንድነትን ሲያበረታቱ ነው የምናየው። ይህም የቤልጂየም ዘውድ ለኣንድነታቸው መገለጫ መሆኑን ያሳያል። ኢትዮጵያ በ1960ዎቹ ጊዜ የሆነ ኣዲስ ነገር በራልኝ ያለው ትውልድ ዘውዱን በድንጋይ ስቶ ሲያበቃ ወታደር ሲመጣ በጥይት ብሎ ስለገደለ ብሄራዊ ኣንድነታችንን የምንገልጽበት ምልክት (symbol) በብሄር ፖለቲካ ጊዜ የለንም።

ኔፓል እንደሚታወቀው እንደ ኢትዮጵያ ብዙ የተለያየ ቋንቋና ባህል ያላቸው ቡድኖች የሚኖሩባት ኣገር ናት። ይህቺ ኣገር በ 2008 ዓ.ም ከፍጹም ዘውዳዊ ኣገዛዝ ከተላቀቀች በሁዋላ ኣዲሲቱዋን ኔፓልን በምን መንገድ ኣዋቅረን እንቀጥል የሚለው ጉዳይ እስካሁን ያልተቋጨ የኔፓሊስ ሌሂቃን የቤት ስራ ሆኖ ይታያል። የማኦይስቶች እምነትና ግፊት ኔፓል በብሄር ፌደራሊዝም እንድትተዳደር ሲሆን የኔፓል ኮንግረስ ፓርቲ መሪና የኣሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሶሺል ኮይራላ ግን ይህን ኣሳብ በጥብቅ እየተቃወሙ ነው። የኔፓል ኮንግረስ ፓርቲ በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የፖለቲካ መሰረት(constituency) ያለው ሲሆን ይህ ፓርቲ የብሄር ፌደራሊዝም በዓለም ላይ ግጭትን ያመጣ በመሆኑ ኣዲስ ሊፈጥሩት ባሰቡት ህገ መንግስት እንዳይካተት እየወተወቱ ነው።

እንዲህ ዓይነት በማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ብዙህ በሆኑ ሃገሮች ቀርቶ ሆሞ ጂኒየስ በሆኑ ኣገሮችም እንኳን ጥሩ ኣይደለም። በዓለማችን ላይ እንደምናየው በሃይማኖት ማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ በሚያራምዱ ኣገሮች ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በሰፊው ከመስተዋላቸውም በላይ በኣንዳንድ ኣካባቢዎች ጽንፈኞችን እያፈራ እንደነ ኣልቃይዳ፣ ኣይ ኤስ ኣይ ኤስ (ISIS)፣ ኣልሽባብ፣ህዝቦላ፣ሃማስ የመሳሰሉትን ለዓለም ህዝብ ስጋት የሆኑ ድርጅቶችን ፈጥሮኣል። በዚህ በሃይማኖት ማንነት ላይ የሚመሰረትን ፖለቲካና በሃይማኖት ማንነት ላይ የሚገነባ ብሄራዊነትን በተመለከተ በዓለም ላይ ትኩረት ያገኘ ሲሆን በባህላዊ ማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ኣደገኛነቱ ብዙም ትኩረት ያገኘ ኣይመስልም። የማንነት ፖለቲካ ሃይማኖታዊም ይሁን በብሄር ላይ የተመሰረተ በዓለማችን የሁዋላ ታሪክ ውስጥ ጥሩ ምስክርነት የለው። የዓለምን የዘር ማጥፋት ታሪክ ብንመረምር በዓለም ላይ ከተፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መካከል ኣብዛኛዎቹ በኣንድም በሌላም መንገድ ወይ ሃይማኖታዊ ወይ ደግሞ ከብሄር ፖለቲካ ጋር በተያያዘ የመጣ ጥፋት ነው። በኣርመን፣ በሩዋንዳ፣ በናይጄሪያ፣ በቦስኒያ፣የተፈጸሙትን ወንጀሎች መጥቀስ ይቻላል። በጣም የታወቀው የሆልኮስት የዘር ማጥፋት ወንጀል መነሻም እነ ሂትለር ያመጡት ዘረኝነትን ሳይንሳዊ ለማድረግ በመሞከር (Scientific racism) ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው ስላደረጉ ነው። እነ ሂትለር ብሄራዊ ስሜትን ሊገነቡበት የፈለጉበት ፍልስፍና ኣደገኘ ነበር። የማንነት ፖለቲካ ብዙህ ለሆኑ ኣገሮች ቀርቶ ሆሞ ጂኒየስ ለሆኑ ኣገሮችም የሚጠቅም ኣይደለም። ሆሞ ጂኒየስ የሆኑ ኣገሮች ብሄራዊነትን ለመገንባት ብለው ባህላዊ ማንነታቸውን በጣም ካራገቡት ውጪያዊ ሶሺያል ካፒታላቸውን(External social capital) ይጎዳል።ብዙህነትን (Multiculturalism) ወይም ዓለማቀፋዊነት ላይ የሚኖራቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት እድገታቸውን ይገታዋል። ብሄራዊ ኩራትን(national pride) ኣገራቸው ለሰባዊና ለዴሞክራሲ እድገት በምታደርገው ጥረት፣ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት ባላቸው ኣስተዋጾ፣ ዓለማቀፋዊ ተቋማትን ለማገዝ በሚያደርጉት ጥረት ዜጎች እንዲኮሩ ማድረግ በጣም ጥሩ ይመስላል። በቅርቡ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስዊድን ፍርድ ቤት ሊከሰሱ እንደሆነ ስሰማ ሁለት ነገር ኣሰብኩ። ኣንደኛው ለውጥ ፈላጊው ኢትዮጵያዊ ምን ይሰማዋል? የሚል ነው። ይህንን ሳስብ ኣንደኛ ደስታ ሁለተኛ ሃዘን ነው። ደስታው የሚመነጨው የሚያዝንባቸውን መሪዎች ሊጠይቅ የሚችልበት ፍርድ ቤት ከባህር ማዶ መኖሩን ሲሰማ ሲሆን የሚያሳዝነው ደግሞ በሃገሩ ሰማይ ስር የራሱ ፍርድ ቤት ጉዳቱን ሳይፈርድለት በመቅረቱ ፍትህ ፍለጋ ባህር ማዶ በማለሙ ነው። በሌላ በኩል ያሰብኩት ኣሁን እኔ ስዊድናዊ ብሆን ይህን ዜና ስሰማ ምን ይሰማኛል? ብየ ነው። ስዊድናዊ ብሆን ኖሮ ደስ ይለኝ ነበር፣ በሃገሬ እኮራ ነበር። የምኮራውም በሃገራቸው ፍትህ ያጡ ህዝቦች እኔ በገነባሁት ነጻ ፍርድ ቤት ፍትህ በመፈለጋቸው ነው። ጥላ በመሆኔ የሌሎች ህዝቦች ፍትህ ማጣት ለእኔም እንደሚሰማኝ በማሳየቴ ደስታ ይሰማኛል እኮራለሁ ብየ ኣሰብኩ። ዜጎች በነጻ ተቋማት ላይ የተመሰረተ ብሄራዊ ኩራት እንዲያዳብሩ ማድረግ ጥሩ ይመስለኛል ለማለት ነው ይህን ያመጣሁት።

ኣገሮች ባህላዊ ማንነትን በኣንድ በኩል እየተንከባከቡ በሌላ በኩል ለመልቲ ካልቸራሊዝም ክፍት መሆን ካልቻሉ እየመጣች ያለችዋ ኣለም ታስቸግራቸዋለች። ብዙህ የሆኑ ኣገሮች ደግሞ ለየብቻ ሆሞ ጂኒየስ መሆን ፍትህ ሊያመጣ ይችላል የሚል እምነታቸው መሰረቱ ከዴሞክራሲ ጋር የማይሄድ መሆኑን መገንዘብ ካልቻሉ የብዙ ሰውን ህይወት እየጎዱ ሊኖሩ ይችላሉ።ስለ መልቲ ካልቸራሊዝም ሳስብ የሚሰማኝ ነገር ኣለ። ብዙ ጊዜ የምእራቡ ዓለም ባህል ተጫነን ሲባል እሰማለሁ። የምእራብ ዓለም ባህል ምን እንደሆነ በሚገባ ኣልገባኝም። የምእራብ ኣገራት ብዙ ናቸው። ስለ ባህል ካወራን እነዚህ ሃጋራት በጣም የተለያየ የየራሳቸው ባህል ያላቸው ናቸው። የምእራቡ ባህል ሲባል ምን ኣልባት የምእራብ ስልጣኔ ከሆነ ስልጣኔን መከላከል ኣስፈላጊ ዓይደለም።ስልጣኔ በራሱ መጥፎ ባህልን ኣይፈጥርም ነገር ግን ስልጣኔ ስናስገባ ወይም ስንፈጥር ማህበራዊ ለውጥ ውስጥ እንገባለንና በዚህ ለውጥ ጊዜ ለህብረተሰብ እድገት የማይጠቅሙ ክስተቶች ብቅ ብቅ ማለታቸው ኣይቀርም።ይሄ የማህበራዊ ለውጥ ኣንዱ ክስተት ነው። በዚህ ጊዜ እነዚህን ኣላስፈላጊ ክስተቶች ዳብረው ባህል ከመሆናቸው በፊት የመቅጨት ስራ በመንግስትና በህዝቡ በኩል መሰራት ኣለበት። ከዚህ ውጭ ስለ ምእራባዊያን መረዳት ያለብን ኣሁን ለምናያት የሰለጠነች ኣለም ያደረጉት ኣስተዋጾ እጅግ ከፍተኛ ነው። ለእኔ ከክርስቶስ በታች የዚህ ዓለም ብርሃን ናቸው። የምእራቡ ዓለም የስልጣኔ ባህል ዓለማችንን ከጎጂ ባህሎችና ልምዶች በማላቀቅ ላይ ይገኛል። ዓለም ስለ ሰብዓዊ መብት ያላትን ግንዛቤ እንድታሰፋ፣ ዴሞክራሲን እንድትለማመድ፣መልካም ኣስተዳደር እንዲሰፍን፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እዚህ እንዲደርስ የደከሙት ድካም ኣይዘነጋም። የዓለም ህዝቦች በሰብዓዊ መብት ዙሪያ እንዲነቁ፣ ገዢዎቻቸውን ስለ መብታቸው እንዲጠይቁ፣ ሰብዓዊ መብት የዓለም ህዝቦች ባህል እንዲሆን ከፍተኛ ኣስተዋጽዖ ኣድርገዋል። ታላላቅ የሰብዓዊ መብት ተሙዋጋች ድርጅቶችን በማቋቋም ታላቅ ኣስተዋጾ ኣድርገዋል። በኣፍሪካ በላቲን ኣሜሪካና በእስያ ኣገሮች የሚታዩትን ብዙ ጎጂ ልማዶች ለማስቀረት የወሰዱት እርምጃ ብዙ ለውጥን ኣምጥቱዋል። የምእራብ ኣገሮችና ኣሜሪካ ሌላው በዓለም ህዝቦች ዘንድ ሊረሳ የማይችለው ኣስተዋጾ ሴቶች መብታቸው እንዲከበር ማድረጋቸው ነው። ከባህል ጋር እየተያያዘ ሴቶች በብዙ ኣገራት ከፍተኛ በደል የሚፈጸምባቸው ሲሆን ይህንን ለማስቀረት የተጫወቱት ሚና በዓለም ሴቶች ዘንድ ተደናቂ ያደርጋቸዋል። ኣንድ ጊዜ ኣንድ ህንዳዊ ኣገኝቼ ስለ ህንድ ባህል ጠየኩት። የሰማሁት ነገር ስለነበረ ነው የጠየኩት። እንዴት ነው ሴቶችን በእሳት የማቃጠሉ ባህል እየጠፋ ነው ወይ? ብየ ጠየኩት። ኣዎ የሰባዊ መብት ተሙዋጋች ድርጅቶች እየለፉ ነው እየቀነሰ የመጣ ይመስለኛል ኣለኝ። ህንድ፣ ባንግላዴሽ፣ ፓኪስታን ኣካባቢ ሙሽራን ማቃጠል(bride burning) የሚባል ባህል ኣለ። በዚህ ባህል መሰረት ሴቲቱ ኣግብታ ባሉዋን ካላረካችና የምትሰጠው ጥሎሽ ህይወቱን ካልለወጠው በሚነድ እሳት ያቃጥላት ዘንድ የሚፈቅድ ባህል ኣለ። ይህንን የመሳሰሉ ጎጂና ኣስደንጋጭ ባህሎች ለማስቀረት የዓለምን ግማሽ የሚሆነውን ህዝብ ማለትም ሴቶችን ነጻ ለማውጣት ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ የሚታዩት የምእራብ ኣገሮች ህዝቦችና መንግስታት ናቸውና ሊመሰገኑ ይገባቸዋል።ከነሱ የምንማረው እጅግ ብዙ ነው። በኣፍሪካ ኣህጉራችን ውስጥ ብዙ ብሄሮች ሰውነታቸውን በስለት ሲዘለዝሉ ይታያል፣ ጠለፋ፣ ኣስገድዶ መድፈር፣ የሴት ልጅ ግርዛት፣ ስንቱ ተቆጥሮ። ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ ስለ ሴት ልጅ የሰማሁት ኣስደንግጦኝ ነበር። በዚያ ብሄረሰብ ባህል መሰረት ሴት ልጅ የወር ኣበባዋ ሲመጣ ከቤት ትወጣና ጫካ ውስጥ ትደበቃለች። ለተውሰኑ ቀናት ብቻዋን ተገልላ ከቆየች በሁዋላ እንደገና ወደ ቤቱዋ ትመለሳለች።እንዲህ የመሳሰሉ ጎጂ ልማዶችን ለማስቀረት ህዝብን ማስተማር ስልጣኔን ማስረጽ ብቻ ሳይሆን የሚያስቀጣ መሆን ኣለበት። ከምስራቁ ዓለምም የምንማረው ኣለ። ሰራተኛነትን ከቻይናዊያንና ከኮርያዊያን እንማራለን። ማቴሪያል ካልቸራችንን ለማሻሻል ከኮርያና ከጃፓን የምናደርገው ግንኙነት በጣም ጠቃሚ ነው። በሌላ በኩል እኛ ኢትዮጵያዊያን በባህልም፣በታሪክም ብዙ የምናካፍለው ኣለንና ክፍት በመሆን ከዓለም ህዝቦች ጋር እውቀትን መከፋፈል ያስፈልጋል። በዓሁኑ ሰዓት ቴክኖሎጂ፣ ትራንስፖርት የሰው ልጅ እውቀት ዓለምን በጣም እያቀራረባት ስለሆነ የዓለም ህዝቦች እያዋጡ የጋራ ባህልን ሲመሰርቱ ነው እያየን ያለነው። ይሄ ደግሞ መልካም ነው። ዋናው ጉዳይ ኣንዳንድ ኣደገኛ የሆኑ ባህሎች ጎልተው ሲታዩ እነዚህን ባህሎች የራሳችንም ይሁኑ ማህበራዊ ለውጥን ተከትለው የመጡ ይሁኑ ቶሎ ብሎ የመቅጨት ስራ መስራት ነው።

የተነሳንበትን መሰረታዊ ጉዳይ እንዳንስት ወደ ፌደራሊዝሙ ጉዳይ እንመለስና የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ወይም የክልሎች መንግስታት ኣመሰራረት ብዙዎቻችን በብሄር ፌደራሊዝም እንግለጸው እንጂ እውነቱን ለመናገር ስም የለውም። የሶሲዮሎጂና የፖለቲካ ምሁራን ያልመከሩበት በነሲብ የተደረገ የክልልሎች መንግስታት ምስረታ የተካሄደ ነው የሚመስለው። ከሁሉም በላይ ትግራይን ለመከለል የተጨነቀውን ያህል ራሱ ፓለቲካው በሚያምነው “ራስን በራስ የማስተዳደር” መርህ ሌሎቹ ተከልለው ኣይታይም። ትግራይ ክልል ከተመሰረተ በሁዋላ ውሎ ኣድሮ እንዴውም ራያ ውስጥ ብዙ ትግርኛ ተናጋሪ ኣገኘን ብለው ወደ ትግራይ ከልለዋል ወልቃይትንም እንደዚሁ።ይህ ዓይነቱ ድርጊት የትግራይን ህዝብ ጠቅሞታል ለማለት ሳይሆን የመንግስትን ኣሰራር ለማሳየት ነው። በተለይ …በተለይ ….የደቡብ ህዝቦች ኣንድ ክልል የመሆኑ ነገር መነሻው ምን እንደሆነ ኣይታወቅም። እንደሚታወቀው ደቡብ ውስጥ ወደ 56 የሚጠጉ ብሄሮች ያሉ ሲሖን እነዚህን ብሄሮች በሙሉ ሰብስቦ ኣንድ ክልል ሊያደርጋቸው የሚችል ምን መመዘኛ ነበር ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ለምን የደቡብ ክልል ኣንድ ክልል ተባለ ኣይደለም ጥያቄው። ጥያቄው የደቡብ ክልል የሚባል ክልል ከተፈጠረ ለምን የሰሜን ክልል፣ የምስራቅ ክልል፣ የምእራብ ክልል እያለ ኣልቀጠለም የሚል ነው።ጥያቄው የህወሃትን መርህ ኣልባነት ለማሳየት ነው። በደቡብ ውስጥ ያሉ እነዚህ ብዙ ብሄሮች ኣንድ መንግስት ብቻ እንዲመሰርቱ የተደረጉበት ምክንያት ኣንዳንድ የወያኔ ሰዎች ሲናገሩ የደቡብ ብሄሮች በስነ ልቡና የተቀራረቡ እንደሆኑ ይገልጻሉ። ይሄ ምን ማለት እንደሆነ ኣይታወቅም። ለምሳሌ ያህል ጉራጌንና ኮንሶን ብንወስድ ሁለቱም ብሄሮች በቋንቋም ሆነ በባህል በጣም የተራራቁ ናቸው። ጉራጌ የሴም ቋንቋ ተናጋሪ ኮንሶ ደግሞ የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪ ነው። በጉራጌና በኮንሶ መካከል ካለው የባህልና የቋንቋ ዝምድና ይልቅ የኣማራና የትግራይ የባህልና የቋንቋ ዝምድና ይቀራረባል። ይህንን የምለው ምን ያህል መርህ ኣልባ የሆነ ኣንድን ክልል ብቻ ለመጥቀም የተደረገ የክልል ኣመሰራረት እንደሆነ ለማሳየት እንጂ የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ይሄ ኣይደለም እንዴውም ባህልና ቋንቋ ኣንድ መንግስት መስርተን ለመኖር እንቅፋቶቻችን ኣይደሉም ከዚህ በፊት ለዘመናት ኖረናል እያሉ ነው።

የደቡብ ህዝብ በኣንድ መንግስት ስር ሲተዳደር “ራስን በራስ የማስተዳደር መብት” የሚባለው የኢህዓዴግ መርህ ትግራይ ላይ የሰራውን ያህል ኣይሰራም ማለት ነው። ክልል ኣመሰራረቱ በህዝብ ብዛት ነው እንዳይባል የትግራይ ክልል ከሲዳማ ህዝብ ጋር ተመጣጣኝ ነበር። ለዚህ ነው የሲዳማ ህዝብ እኛስ ለምንድነው በዞን ደረጃ የምንታየው ለምን መንግስት ኣንሆንም ብለው እየጠየቁ ያሉት። መንግስት ራሱ ባወጣው መስፈርት መሰረት ነው እየጠየቁ ያሉት። ያም ሆኖ ግን ትግራይ ላይ የሰራው “ራስን በራስ የማስተዳደር” መብት ሲዳማ ላይ ኣይሰራም። በመሰረቱ የብሄርን ፖለቲካ ተከትሎ የመጣው የፌደራል ኣወቃቀሩ ዝም ብሎ የተዋገረ ስለሆነ ጥርት ያለ ምላሽ ኣይገኝበትም። የደቡብ ህዝብ ደስ የሚለው ወያኔ ያንን ኣለ ያንን ብዙም ከቁብ ሳይቆጥር ኣንድነቱን ጠብቆ ይኖራል። ጥያቄው ግን የመርህ ጥያቄ ነው። የደቡብ ህዝብ ኢህዓዴግ ከገባ በሁዋላ የፖለቲካ ተሳትፎው ጥያቄ ለማኝ ነበር። እንደሚታወቀው ይህንን የብሄር ፖለቲካ ተከትሎ ኢህዓዴግ እንደገባ ሁሉም የደቡብ ብሄሮች የፖለቲካ ድርጅት ኣቋቁመው ነበር። እነዚህ የየብሄሩ የፖለቲካ ድርጅቶጅ ቁጥራችሁ ትንሽ ስለሆነ ለመንግስትነት ኣትበቁም ኣይነት ተባሉና የደቡብ ህዝቦች የሚባል መንግስት ሲመሰርቱ ደህዴግ የሚባል የክልል ፓርቲ ተጠናክሮ ወጣ ተባለ። ይህ ድርጅት በነዚያ ከየብሄሩ በመጡ ፓርቲዎች የተዋቀረ ግንባር ነው። የሚገርመው ይህ ግንባር ወደ ፌደራል ሲመጣ እንደገና ኢህዓዴግ ከተባለው ኣስገራሚ ድርጅት ጋር ሌላ ግንባር ይፈጥራል ይህ ማለት እነዚያ በየብሄሩ የተመሰረቱት ድርጅቶች የኢህዓዴግ የልጅ ልጆች ይሆናሉ ማለት ነው። ወይም ኢህዓዴግ ኣያት ነው ማለት ነው። ኢህዓዴግ ለህወሃት ኣባት እንደሆነው ሁሉ ለነዚያ ለደቡብ ብሄሮች ድርጅቶች ኣባት መሆን ኣልቻለም ማለት ነው። በቁጥራቸው ምክንያት የልጅ ልጅ ሆነው ሲኖሩ ሲኖሩ ቆዩና ከብዙ ኣመታት በሁዋላ በኣስራ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ኣምስት የየብሄሩን ፓርቲ እያፈረሱ ያን ደህዴግ የተሰኘውን ኣንድ ክልላዊ ፓርቲ ኣድርገው እነሱ ከሰሙ። ይህ የሚሻል ቢሆንም ኣሁንም ግን ከመንግስት ኣጠቃላይ የፖለቲካ ኣወቃቀር ጋር ሲታይ የደቡብ የፖለቲካ ተሳትፎ ጉዳይ ጥያቄ ያለበት ነው። የሎጂክ ጥያቄዎችን የሚለምን ሁኔታ የከበበው ነው። የኣሁኑን ጠቅላይ ሚንስትር ኣቶ ሃይለማርያምን ከብሄራቸው ኣንጻር ራሳቸውን የሚገልጹበት የፖለቲካ ድርጅት የላቸውም ማለት ነው። እንደ ህወሃት፣ ብዓዴን፣ ኦህዴድ ጓዶቻቸው ራሳቸውን ፖለቲካዊ በሆነ መንገድ የሚገልጹበት ድርጅት ሳይሆን ያላቸው ከመልክዓ ምድር ኣንጻር የሚገልጹበትን ድርጅት ነው የሚመሩት። ደቡብ ቢሄዱ ደግሞ የመጡበት ብሄር የፖለቲካ ድርጅት ባይኖራቸውም ኣጠቃላይ የፖለቲካው ስሜት የሚገፋቸው ሰዎች የወላይታ ተወካይ ነው የሚያደርጓቸው። ጨዋታው በየቤትህ እደር ከሆነ እንዲህ ዓይነት ብዙ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ፌደራሊዝም ነው ያለው ኣገራችን ውስጥ።

የኢትዮጵያ የፌደራሊዝም ጉዳይ ሰሜኑን በቋንቋ ደቡቡን በጂኦግራፊ የሸነሸነ ሲሆን የክልል መንግስት ኣመሰራረቱ የኢህዓዴግን መርህ ኣልባነት ምህንድስናው ኣንድ ኣካባቢን ብቻ እንዳሰቡት ለማድረግ የተሰራ እንጂ ወጥነት የሌለው ነው። ዋናው የኢትዮጵያ መንግስት መገለጫ በብሄር ፖለቲካ ሲሆን ቡድኖች በባህላዊ ማንነታቸው ራሳቸውን ፖለቲካዊ በሆነ መንገድ እንዲገልጹ የሚያደርግ ሲሆን የደቡብ ብሄሮች ግን ራሳቸውን ከፖለቲካ ኣንጻር የሚገልጹት በብሄር ማንነታቸው ሳይሆን በጂኦግራፊ በመገናኘታቸው ነው። ከፍ ሲል እንዳልኩት ኮንሶ ከጉራጌ ይልቅ በባህልም በሃይማኖትም ለኦሮሞ ነው የሚቀርበው። የኮንሶ ህዝብ ዋቃ የተሰኘ ኣምላክ የሚያመልክ ሲሆን ከኦሮሞ ጋር የተወራረሰ ነው። በቡርጂና በሱርና ብሄረሰብ መካከል ካለው የባህልና የቋንቋ ግንኙንነት ይልቅ ቡርጂዎች ለጉጂ ኦሮሞዎች የቀረበ ነገር ኣላቸው። ብዙዎቹ የቡርጂ ማህበረሰብ ኣባላት ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ናቸው። ደቡብ ውስጥ የሴም፣ የኩሽ፣ የኦሞና የናይሎ ሳሃራ ቋንቋ ተናጋሪዎች ያሉበት የኢትዮጵያ ተምሳሊት የሆነ ክልል ነው።

እንግዲህ ደቡብ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ከሃገሪቱ የምንነት ፖለቲካ (Identity politics) ኣንጻር ራሳቸውን የሚገልጹት ከደቡብ ኣንጻር ነው ማለት ነው። እንዴው ወያኔ ራሱ የሚለውን ተከትለን በራሱ ሎጂክ እንጠይቀው ብለን እንጂ የብሄር ፖለቲካው ምን ሊጠቅማቸው።
ለስራ ጉዳይ ለተወሰነ ጊዜ ደቡብ ኣካባቢ ነበርኩና የታዘብኩት ነገር የመገንጠል ጥያቄ ሲነሳ ለደቡብ ህዝቦች የሚመች ጥያቄ ኣይደልም። ሌሎች ብሄሮች ሰሜን ምስራቅ ምእራብ ሳይባሉ እነሱን በጂኦግራፊ ብቻ ደቡብ ብሎ መሰየሙ ግራ እንደሚያጋባቸው ተረድቻለሁ። ያም ሆኖ ግን የኢትዮጵያን ኣንድነት ስለሚናፍቁ ኣንድ ቀን የዚህ የብሄር ፖለቲካ ሲቀር ጥያቄያቸው እንደሚፈታ ያስባሉ።

በኣጠቃላይ በብሄር ላይ የቆመ ፖለቲካ የምታራምድ ኣገር፣ ራስን በራስ ማስተዳደር ከዳቦና ከእንጀራ በላይ ሆኖ ኣግኝቸዋለሁ ለሚለው መንግስት ኣንዳንዶቹን ብሄሮች መስፈርቱ ባልታወቀ መልኩ ለመንግስትነት ማእረግ ኣትበቁም ወይ በልዩ ወረዳ ወይ በዞን ደረጃ ተሰየሙ መባሉ ኢፍትሃዊ እኮ ነው። ቡድንን ቡድን የሚያሰኘው የህዝቡ ብዛት ሳይሆን ቋንቋውና ባህሉ ሲሆን የማንም ቋንቋ ከማንም ኣይበልጥም ኣያንስምና እነዚህ ቡድኖች ሁሉ የክልል መንግስትነት ጥያቄ ቢያነሱ ምን ጥፋት ኣላቸው?

ሰማኒያ የሚሆኑ ቡድኖች ባሉበት ኣገር ቁጥራቸው ኣነስ ያለውን “ኣናሳ” እያሉ ወደ ኣንዱ ለጠፍ እያደረጉ ዘጠኝ ክልል መስራት ምን ይባላል? ፍትህ የጎደለው እንዲሆን ያደረገው ራሱ መንግስት ይዞት የተነሳው እምነት ነው። ኣድካሚ የሆነ እምነት:: የኢትዮጵያን የቡድንም ሆነ የግለሰብ ጥያቄ የማይመልስ እምነት። በጣም ያሳዝናል።

በኣጠቃላይ የኢትዮጵያ ክልል ኣመሰራረት ከራሱ ከኢህኣዴግ ፖለቲካ ጋር የተጋጨ፣ ከሁሉም በላይ ከኢትዩጵያ ተፈጥሮ ጋር የተጋጨ፣ ሳይንሳዊ ያልሆነና መርህ የጎደለው በመሆኑ ይህ ነገር የሚመጣ መንግስት ሲመጣ በተሻለ ክልል ማሰዳደር ይቻል ዘንድ ኢትዮጵያዊያን ከወዲሁ ልናስብበት ይገባል።
በኣጠቃላይ ይህን ሁሉ የማወራው የኣቶ መለስ ምህንድስና ምን ያህል እንዳሻው የተዋቀረ እንደሆነ ለመግለጽ ነው። ከዚህ በላይ የኢትዮጵያን የኣርባ ኣመት የማንነት ጥያቄ በተሻለ የሚመልስና ወጥነት ያለውና በመርህ ላይ የተመሰረት ፌደራሊዝም ስርዓት ለመመስረት ጥቂት ኣሳብ ለማቀበል እፈልጋለሁ።
የኣዲሲቱ ኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት እንዲህ ቢሆንስ?

በዚህ በወያኔ ብሄርተኛ ኣስተዳደር የተቆጣን ሰዎች ለለውጥ ስንታገል የምንፈልጋት ኢትዮጵያ ምን ዓይነት እንደሆነች በሚገባ ስለን ማሳየት ኣለብን።ምን ዓይነት የፌደራል ስርዓት ነው የምንፈልገው። ያለፈውን የኣርባ ኣመት ጥያቄ እንዴት ነው የምንፈታው ብለን ቀድመን ጥንቅቅ ኣድርገን ልናስብበት ይገባል።የወደፊቱዋን የፈለግናትን ኢትዮጵያን በጸዳ ሁኔታ ኣሰተዳደራዊ ቅርጹዋን ማሳየት ይጠበቃል። ኣንዳንድ ሰዎች የኣሁነ ዘመን ትግላችን ከፍትህና ከዴሞክራሲ ጥያቄም በላይ ሃገርን የማዳን ስራ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባዋል ይላሉ። ይህን ጉዳይ የምጋራው ሆኖ ኣገርን የሚያድን ጥርት ያለ ኣማራጭ የፖለቲካ ስርዓት ለኢትዮጵያ ህዝብ ማሳየት ይጠበቃል። በዚህ ረገድ ባለፈው ጊዜ ደጋግሜ በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ካልኩት ኣሳብ የሚቀዳ ኣንድ የመንግስት ኣወቃቀር ጠቆም ለማድረግ ነው ፍላጎቴ።
የክልል ኣመሰራረቱ የሚመነጨው ኢትዮጵያን ከምናይበት እይታ ነው። በዚህ ኣገባብ ኢትዮጵያን የምናየው በስምምነት ላይ ከተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ኣሳብ ኣንጻር ነው።ከሁሉ የሚቀድመው በብሄራዊ እርቅ መንገድም ይሁን በሽግግር መንግስት ስም ቡድኖችን የሚያወያይ ከፍተኛ ኣገራዊ ኣጀንዳ ይዞ ወደ ስምምነት መምጣት ነው። ለውይይት ከምናቀርበው ኣሳብ ውስጥ ኢትዮጵያን በተሻለ ሊያስተዳድር የሚችል ጥበብ ማሳየት ከቻልን ቡድኖች የማይስማሙበት ጉዳይ የለም። ይህ ወይይትና ስምምነት የፓርቲዎች ጉዳይ ኣይደለም። ባለፉት ኣርባ ኣመታት ህዝባዊ ውክልና የሌላቸው ፓርቲዎች ልክ ህዝብ የመረጣቸው ይመስል ኣንዴ የማንነት ፖለቲካ ይሻላል፣ ኣንዴ ሶሻሊዝም ኣንዴ ምን እያሉ ቆይተዋል። ይህ ጉዳይ ተለውጦ ኣሁን ኣንድ ኢትዮጵያን ኣጠናክሮ ሊገነባ የሚችል የስምምነት ኣሳብ ይዞ ቡድኖችን በቀጥታ ማነጋገር ያስፈልጋል። ህዝቡ በቀጥታ ተሳታፊ የሆነበት ከፍተኛ ውይይት ተደርጎ ኣንድ ኪዳን ሊፈርም ያስፈልጋል። ከዚያ በሁዋላ ፓርቲዎች እየተነሱ ህገ መንግስት ኣርቅቀው እያስጸደቁ መንግስት እየተቀያየረ መኖር ይቻላል። ኢትዮጵያዊያን ልንወያይበት ከሚገባው ጉዳይ መካከል ኣንዱ የዚህ የፌደራሊዝም ጉዳይ በመሆኑ ፌደራሊዝሙ ብዙ የሆነችውን ኢትዮጵያን ባህላዊና ፖለቲካዊ ማንነቱዋን ለይቶ የሚያስተዳደር ቅርጽ ሊይዝ ይገባዋል። በዚህ መሰረት በሁለት ፌደሬሽን የምትመራ ሁለት መንግስታት ያሉዋት ኣገር ኣድርገን ብንሰራት የተሻ ይሆናል። ይህ ሁለት መንግስት ማለት ኣንደኛው ባህላዊ መንግስት ሲሆን ይህ መንግስት በህገ መንግስት ሃላፊነት የተሰጠው ባህላዊ ጉዳዮችን ለይቶ የሚንከባከብ ሲሆን ሌላው መንግስት ደግሞ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የሚመራ ነው። እነዚህ ሁለት መንግስታት ቢመሰረቱ ኣንደኛ የማንነት ፖለቲካ ጥያቄያችንን ያቃልላል። ሁለተኛ ብዙህነታችንን ኣደባባይ ኣውጥቶ መልካችንን ያሳያል። ከዚህም በላይ ሰላምና ልማትን ለማፋጠን የማትከፋፈል ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማሳለፍ ይረዳናል።

ኢትዮጵያ ኣንድ ናት ስንልም ከነዚህ ከሁለት ዋልታና ማገር የተሰራች መሆኑዋን እያሰብን ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያ ሁለቱንም ማንነቶቹዋን ሳያደባልቅ የሚያስተዳድር ፌደራሊዝም ልትመሰርትና በሁለት መንግስታት ልትተዳደር ትችላለች። እነዚህ ሁለት መንግስታት ኣንዱ የባህል መንግስት ሲሆን ሁለተኛው ፓለቲካዊና ዴሞክራሲያዊ የሆነ መንግስት ነው። ሁለቱም መንግስታት በመሰረታዊ ህግ በሚገባ የተለየ ስልጣንና ተግባር ኖሩዋቸው ይኖራሉ። ፖለቲካዊው መንግስት ዳይናሚክ ሲሆን በየጊዜው ዴሞክራሲን እያሳደገ ዘመናዊ ኣሰራርን እያዳበረ ኣገሪቱን ወደተሻለ ህይወት ይመራል። ባህላዊው መንግስትም ባህሎቻችንን እየጠበቀ በመሰረታዊ ህጉ ላይ ያለውን ሃላፊነት እየተወጣ ይኖራል። ባህላዊ መንግስትን ስንመሰርት ዘመናዊነት መጣ ብለን ጥለን የነበርነውን ጠቃሚ ባህል ሁሉ እንድናነሳ ያደርገናል። የየቡድኖች ነገስታት ወደ ኣደባባይ በማውጣት በምንመሰርተው ህብረ ብሄር ቤተ መንግስት ይመጡና ከፍ ብለው ይታያሉ። ኮሚንዝም ያስጣለንን ባህል ሪስቶር እያደረግን ታሪካዊ ሃገራችንን የቀድሞ የፈጠራ ውጤቶቹዋን ኣክብረን ካዲሱ ትውልድ ፈጠራ ጋር ጎን ሎጎን ማስኬድ እንችላለን። ለኣርባ ኣመት የቆየውን የማንነት ጥያቄ በማቃለል ፣ ማንነትን ሳናወዳዽር የምንፈጥረው ስርዓት የረጋና ሰላም የሰፈነበት ይሆናል። በተለይ እኛ ኢትዮጵያዊያን ከኛ ሁኔታና የህይወት ልምድ፣ ካለፍንበት ረጅም ጎዳና ኣንጻር ፖለቲካዊና ባህላዊ ማንነቶችን ማደባለቅም ሆነ ኣንዱን ከኣንዱ የማበላለጡ ስሜት ጎድቶን ኣጨቃጭቆን ይታያልና ውድ ድር ውስጥ ሳናስገባ ባለንበት ቡድን ስም ራሳችንን ብንገልጽ ክፋት የለውም። ኣንድ ዜጋ ክርስቲያን ነኝ ብሎ ራሱን በዚህ ሃይማኖታዊ ማንነት ሲገልጽ ከኢትዮጵያዊነትህና ከክርስትናህ የቱን ታስቀድማለህ ወይም የቱ ይበልጣል እያሉ መፈተን ጠቀሜታ የለውም። ባህላዊ ማንነቶቻንንም እንደዚያ ማየት ነው። ኣንድ ዜጋ በባህላዊ ማንነትም ሆነ በፖለቲካዊ ማንነቱ ራሱን የሚገልጽበት ሁኔታ መኖር ኣለበት። በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በፊት ብዙ ብያለሁና ይብቃ። ይህንን ማንነቶቻችንን መለያየታችንን የሚያሳየው የሁለቱ መንግስታት ምስረታችን ነው። የምንመሰርታቸው መንግስታት ሌሎች ኣካባቢዎች ባህላዊ ኣስተዳደር ኣለ እንደሚባለው ሳይሆን በሚገባ በመሰረታዊ ህጉ የስልጣን ክፍፍል ያደረገ ቤተመንግስት የመሰረቱ መንግስታት ናቸው የሚኖሩን። ከህገ መንግስት ወይም መሰረታዊ ህጉ በላይ በሚውለው ኣዲስ ኪዳን ስር የሚመሩን ሁለት መንግስታት ማበጀታችን ኣንድ የመጀመሪያ ርምጃ ይሆንና ከዚህ በሁዋላ የክልሎችን ኣመሰራረት ወይም የፌደራሉን ኣወቃቀር በተመለከተም ሁለቱም መንግስታት የየራሳቸው ኣስተዳደራዊ ክልል ይኖራቸዋል። የፖለቲካው መንግስት ክልሎችን ሲገናባ ኣስተዳደራዊ ኣመቺነትን እያየ የሚከፋፍል ሲሆን በመሬት ላይ የሚነበብ ክልል ይኖረዋል። ስልጣንና ፍትህ ወደ ህዝቡ በተቻለ መጠን የሚቀርብበትን ክልሎች ማቆም የፖለቲካው መንግስት ስራ ነው። ፌደራሊዝም ለትላልቅ ሃገራት ተመራጭ ይሁን እንጅ ውድነት(expensiveness) ስላለው ይህንንም ከግንዛቤ ያስገባ ፌደራሊዝም ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ ካላት የቆዳ ስፋት ኣንጻር ከኣራት የማይበልጥ ስቴቶች ቢኖሩዋትና ኣራቱም ሰሜን፣ደቡብ፣ ምስራቅና ምእራብ ኢትዮጵያ ተብለው ቢሰየሙ ጥሩ ሊሆን ይችላል። ስልጣንን ከስቴት መንግስታት ቀጥለው የሚፈጠሩ የመንግስት ሃየር ኣርኪዎች ማውረድ ኣስፈላጊ ነው።

ሌላው መንግስት ማለትም ባህላዊ መንግስት ያልነው ደግሞ በመሬት ላይ የሚነበብ ክልል ወይም ስቴት ኣይኖረውም። የኣንድ ባህላዊ በድን ኣባላት በመላው ሃገሪቱ ተሰራጭተው የሚኖሩ ከሆነ እነዚህ ኣባላት በያሉበት ባህላቸውን የሚጠብቁበት የሚንከባከቡበት ሁኔታ ነው የሚኖረው። የኦሮሞ ስቴት፣ የኣማራ ስቴት፣ የሙርሲ ስቴት ወዘተ ስንል ባህሉና ቋንቋው ነው ሊታየን የሚገባው። እነዚህ ስቴቶች ኣሳባዊ ይሆኑና ኣባላት በያሉበት የዚያ ኣሳባዊ ስቴት ኣባል ይሆናሉ የሚጠበቅባቸውንም ያደርጋሉ። ኣንዳንድ ጊዜ ባህላዊ መንግስቱ ኣስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የመንግስትን መዋቅር ሊጠቀምበት ይችል ይሆናል።
ይህ ባህላዊ መንግስት ባለፈው ግዜ እንዳነሳነው የኣርበኞች ቤት የሚባል ካውንስል የሚያቋቁም ሲሆን ይህ ቤት የሚመሰረተው በቡድኖች ነገስታት ይሆናል። ከዚያ ስር የሚያዋቅራቸው 3 ቤቶች ይኖሩታል። ኣንደኛው የባህልና ቋንቋ ጠባቂና ተንከባካቢ ቤት፣ ሁለተኛው የኬር ቴከር ቤት፣ ሶስተኛው የሰላምና የእርቅ ግጭት ኣስወጋጅ ቤት ይሆናሉ። በባህልና ቋንቋ ጥበቃ ስር ተጨባጭና ተጨባጭ ያልሆኑ ባህሎችን የሚንከባከብ ክፍልና የብሄራዊ ሙዚየም ይኖረዋል።በኣጠቃላይ የባህላዊው መንግስት የራሱ የሆነ ሲስተም ሲኖረው ፖለቲካውም እንዲሁ በፊናው የራሱን ሲስተም ዘርግቶ በየተወሰነ ጊዜው ምርጫዎችን እያደረገ ይኖራል።

በዚህ ኣርቲክል ውስጥ በነዚህ ንኡስ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትንታኔ ኣንሰጥም። ዋናው ኣላማ ኣጠቃላይ መዋቅሩን ማሳየት ሲሆን በዚህ ዓይነት ኣወቃቀር ሰላምን፣ ፍትህን ለማሳለጥ በኢትዮጵያ ይመረጣል ለማለት ነው። ኣጠቃላይ ቅርጹ በሚከተለው ቻርት የተገለጸ ነው።
የCCU የመንግስት ኣወቃቀር
ኣንዳንድ ፓርቲዎች ይህ ኣንገብጋቢ ጉዳይ ኣይደለም ወያኔን መጣል ነው ኣንገብጋቢው ጉዳይ የሚሉ ከሆነ ትክክል ኣይመስለኝም። የሆነ የጠራ ኣማራጭ በኣንድ እጃችን ይዘን ነው ለለውጥ መታገል ያለብን ብየ ኣምናለሁ። በመሆኑም ኣንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ሊለውጡዋት ያሰቡዋትን ኢትዮጵያ እንዲህ የሚያዩዋት ከሆነ ፕሮግራማቸው ውስጥ ኣስገብተው ለህዝብ ቢያስተዋውቁ ጥሩ ነበር።

ለማናቸውም እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ኣስተያየት ካለ እነሆ ኣድራሻየ
geletawzeleke@gmail.com

የኮብላዩ ሚኒስትር ወጎች –ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

በዚህ ተጠየቅ ጨርፈን የምንመለከተው በኮሙኑዮኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረውና ዛሬ በስደት የሚገኘው የአቶ ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ትሩፋቶች፣ ባለቤት አልባ ከተማ” የተሰኘው መጽሐፍን ነው፡፡ የመድብሉ ጻሐፊ ኤርሚያስን በግል አላውቀውም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት አቶ በረከት ስምዖን እርሱን እና ሽመልስ ከማልን ምክትሎቹ አድርጐ በሚኒስቴር ዲኤታ ማዕረግ መሾሙን በግዮን ሆቴል ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረገበት ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህ ለጥቆ፣ በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ በኤምባሲው ግቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ባዘጋጁት የዕራት ግብዣ ላይ (ግንቦት 19/2001 ዓ.ም) ድንገት ተገናኝተን እጅ ለእጅ ተጨባብጠን ሰላምታ ተለዋውጠናል፤ ለመጨረሻ ጊዜ የተያየነው፣ በኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ግንቦት 7 እና እነጀነራል ተፈራ ማሞን በተመለከተ መግለጫ በተሰጠበት ዕለት እንደ አፄ ኃይለሥላሴ የክብር ዘብ፣ ከሽመልስ ከማል ጋር በረከት ስምዖንን ግራና ቀኝ አጅቦ በተገኘበት ወቅት ነው፡፡ በተቀረ በመንግስት ሥልጣን ሲገለጥ ብዙም አላስተዋልኩም፡፡ ከዚህ ይልቅም ኢህአዴግነቱን ለማሳየት የሞከረበትን አንድ ገጠመኝ አስታውሳለሁ፤ ይኸውም “የፍትሕ” ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የነበረው እና አሁን በስደት ሀገር የሚገኘው ባልደረባዬ ማስተዋል ብርሃኑን ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ባለው ቢሮው ድረስ በመጥራት ከባድ ዛቻና ማስፈራሪያ ከሰነዘረበት በኋላ፣ ዛሬ የቀድሞ ጓዶቹ ሥራዬ ብለው እንደቀጠሉበት አይነት በጋዜጣው ላይ የሀሰት ውንጀላ ደርድሮ ሲያበቃ፣ ከኃላፊነቱ ራሱን እንዲያገል አስጠንቅቆት እንደነበር ከራሱ ከባልደረባዬ ማስተዋል አንደበት ሰምቻለሁ፡፡
temesgen-desalegn
የሆነው ሆኖ አቶ ኤርሚያስ ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፉ በተመላኪው ሰው አመራር “ሁሉን አዋቂነት” ላይ የቆመው መንግስት ምን ያህል በጠባብ የወንዝ ልጅነት የተተበተበ እና በዘራፊ ባለሥልጣናት የተዋቀረ እንደሆነ በስፋት ተርኮልናል፡፡ በተለይም ሙስና እና የህወሓት ካድሬዎች የበላይነትን በተመለከተ በማስረጃ አስደግፎ በተዋበ ስነ-ጽሑፋዊ ቋንቋ ዘርዝሮልናል (በርግጥ “የጋዜጠኛው” አሊያም “የደራሲው ማስታወሻ” የሚያነቡ እስኪመስልዎ ድረስ የመጽሐፉን አርትኦት ተስፋዬ ገ/አብ ወይም የተስፋዬ ብዕር ተፅእኖ ያለበት ደራሲ ብዙ እንደለፋበት በግልፅ ማስታወቁን መካድ አይቻልም)፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም ዛሬም ከአገዛዙ ጋር የተሰለፉ የቀድሞ ጓዶቹ ለህሊናቸው ሲሉ በድብቅ የሚፈፀሙ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ደፍረው እንዲያጋልጡ በጠየቀበት ብዕሩ፣ የራሱንም ጥፋቶች እና በትዕዛዝም ይሁን በግል ተነሳሽነት በደል ያደረሰባቸውን ንፁሃን በይፋ ይቅርታ ቢጠይቅ መልካም ነበር፤ አሁንም ቢሆን ለዚህ አይነቱ ቅንነትና በጎ አርአያነት ገና አልረፈደም፡፡ ርግጥ ነው የስደት ምርጫው ባደረጋት ሀገረ-አሜሪካ ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ ድርጅቱ ኢህአዴግ ይሰራው በነበረው ሕገ-ወጥ ድርጊትና የጭካኔ እርምጃ አልፎ አልፎ ቢሮውን ዘግቶ እንደሚያለቅስ፣ ባስ ሲልም ህሊናውን ቆጥቁጦት ታምሞ አልጋ ላይ እንደሚውል በመግለፅ የራሱን ጲላጦሳዊነት ለመስበክ መልፋቱን ስናስተውል፤ ጸሐፊው የሥርዓቱ ጋሻ-ጃግሪ በነበረበት ወቅት የበደለውን ሕዝብ ይቅርታ የመጠየቅ ዝግጁነትም ሆነ ፍላጎት (ቢያንስ በዚህ ሰዓት) የለውም ብለን ማዘናችን አይቀርም፡፡

እንዲሁም ከሀገር እንዲወጣ የተገደደበት ምክንያት ተብሎ ስለተናፈሰው ወሬ ትንፍሽ አለማለቱ በበኩሌ አስተዛዛቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፤ በወቅቱ የስደቱ መነሾ ተደርጎ በከተማዋ በስፋት የተናኘው፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖቹ እና “የግንቦት 7 አባላት ናችሁ” የተባሉ ግለሰቦች ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ ለአንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያ “ሙከራው መፈንቅለ መንግስት ነው” የሚል መግለጫ በመስጠቱ እንደነበረ ነው፤ በዚህም እጅግ የተበሳጨው ጠ/ሚኒስትሩ፣ አለቃው በረከት ስምዖን ላይ ጭምር የጭቃ-ጅራፉን ከማወናጨፉም በላይ፣ ኤርሚያስን ያለ ሥራ እንዳንሳፈፈው መወራቱን አስታውሳለሁ፤ ይህንን መረጃ አምኖ ወደመቀበሉ የሚገፋን ደግሞ በዚያው ሰሞን መለስ ዜናዊ ራሱ በቴሌቪዥን ቀርቦ ‘…የተደረገው ነገር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፣ ከአልቃይዳና አልሸባብ ጋር ሲነፃፀሩ የእኛዎቹ አማተሪሽ (ልምድ አልባ) ናቸው’ እያለ የሚኒስትር ዴኤታውን ንግግር ለማስተባበል ሲዳክር የመስተዋሉ እውነታ
ነው፡፡ እርሱም ቢሆን ከዚህ ግልፅ ሹክሹክታ በኋላ በትምህርት ሰበብ ሀገር ለቅቆ መሰደዱ የአንድ ሰሞን የከተማ ወሬ ሆኖ ነበር፡፡ እነሆም ወንድም ኤርሚያስ ለገሰ ይህንን ጉዳይ ዳጉስ ባለው መጽሐፉ ውስጥ ሽራፊ ገፅ ሊሰጠው አለመቻሉ እዚህ ጋ በትዝብት እንዳነሳው መገደዴን በትህትና እገልፃለሁ፡፡ አሸንፈሀልና በዝብዘህ ብላ!

ህወሓት-ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ በግርማ ብሩ አነጋገር “ደሀ-ዘመም” (በመጽሐፉ የተጠቀሰ) እንደሆነ ለማሳመን የሚሞክርበት ብልጠት፣ ራሱን ለሙስና ፅዩፍ አስመስሎ በማቅረብ ነው፤ ይህን አይነቱን ስሁት አመለካከት በሕዝብ ውስጥ ለማስረፅ ጥቂት የፖለቲካ መታመን-ጉድለት ጥርስ ያስነከሰባቸውን ጉምቱ ጓዶቹን “ሙሰኛ” በሚል ወንጅሎ በወህኒ የቃየል መስዋዕት ሲያደርጋቸው ተስተውሏል፤ እርምጃውንም በፓርላማው መድረክ ሳይቀር ሲኩራራበትና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲያውለው ተመልክተናል (ከሩቁ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ እና መከላከያ ሚኒስትሩ ስዬ አብርሃ፤ ከቅርቡ ደግሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ዳይሬክተር መላኩ ፈንቴ፣ የደህንነት ኃላፊው ወ/ስላሴ እና መሰል ባለሥልጣናትን እስር ልብ ይሏል)፡፡ የሚኒስትር ዴኤታው መጽሐፍ፣ መለስ እና ጓዶቹ ካደነቆሩን በግልባጩ ‘የዘረፋ መሪዎች’ የሚላቸው ሁለት የህወሓት ሰዎች፣ በባላንጣነት ተሰልፈው እንዴት የሀገር ሀብት ለመቀራመት ይሽቀዳደሙ እንደነበር አጋልጧል፤ አዜብ መስፍንን እና አርከበ እቁባይን፡፡

“እነ አርከበ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው ጥቂት ወራት በፊት በህወሓት ውስጥ መደናገጥ ተፈጥሮ ነበር፡፡ የህወሓት ዳግም መከፋፈል ምክንያት ደግሞ በወ/ሮ አዜብ እና አርከብ ቡድኖች መካከል አለመግባባቶች መፈጠራቸው ነበር፡፡ መነሻው መረን የለቀቀ የጥቅም ግጭት ሲሆን ዓላማው የህወሓት ኢንዶመንቶችን መቆጣጠር ታሳቢ ያደረገ ነበር፡፡” (ገፅ 25) ከዕለት ተዕለትም ይህ ሁኔታ የተካረረ ልዩነት ፈጥሮ፣ ፖለቲካዊ ቁመና በመላበሱ፤ አርከበ እቁባይ፣ ህወሓት መገፋቱን እና መለስ በበረከት በኩል የድርጅቱን ካድሬዎች እያስጠቃ ነው የሚል ክስ ከማጎኑም ባሻገር፤ ወደኋላ ተጉዞ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተጠናቀቀበትን መዛግብት አቧራ በማራገፍ፣ ተጠያቂነቱን ከፍ ሲል ወደ መለስ ዜናዊ፣ ዝቅ ሲል ደግሞ ወደ በረከት ስምዖን በመወርወር ማጠቋቆሩ ያመጣውን ውጤት እንዲህ ሲል ገልፆታል፡- “በሂደት አቶ አርከበ ይዞ ብቅ ያለው መቀስቀሻ የካድሬውን እና አባሉን ቁስል የነካ በመሆኑ ተቀባይነት አገኘ፡፡ በትግራይ ፕሮፓጋንዳ እና ድርጅት ተመድበው የሚሰሩ ቁልፍ ካድሬዎች ተቀላቀሉት፡፡” (ገፅ 26)

ይህንን ተከትሎ ወትሮም በደፋር ንግግሯ የምትታወቀውና አንጋፋ ታጋዮችን ሳይቀር በቁጣ የምታስረግደው ቀዳማዊት እመቤት የሰነዘረችው የመልስ ምት በመጽሐፉ ላይ እንደሚከተለው ሰፍሯል፡- “ወ/ሮ አዜብ በበኩሏ አርከበና ቡድኖቹ በሙስና ተዘፍቀዋል የሚል ክስ ይዛ ብቅ አለች፡፡ አርከበ በሚስቱና ቤተሰቦቹ የያዘውን ንብረት በመረጃ አስደግፋ አራገበች፡፡ ላውንደሪ ቤት፣ ፋርማሲ፣ ክሊኒክ፣ ሱፐር ማርኬት፣ መስታወት ማስመጣትና መሸጥ…፡፡ በትግራይና አዲስ አበባ የተፈጠሩት አዳዲስ ባለሀብቶች የአርከበና ቡድኖቹ እንደሆኑ በስም ዘርዝራ አሳወቀች፡፡ ስዬ በታሰረበት የሌብነት ወንጀል አርከበ እጁ እንደነበረ፣ በተለይም የስዬ ወንድም ለገዛቸው በርካታ መኪናዎች ቅናሽ እንዲያገኝ ማግባባቱን የፈፀመው አርከበ መሆኑን አጋለጠች፡፡” (ገፅ 26)

እዚህ ጋ አቶ ኤርሚያስ ‹‹አርከበ በሚስቱና በቤተሰቦቹ…›› ስለያዛቸውና አዜብ መስፍን በስም እየጠራች አጋለጠች ስላላቸው የንግድ ድርጅቶች በስም አንድ በአንድ እየጠቀሰ ይፋ ቢያደርግልን ኖሮ መረጃው ምሉዕ (ከ‹ኮሪደር ሀሜት› የዘለለ) ይሆን ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ ከሁሉም ቁጭታችንን የሚያንረው፣ ደራሲው የንግድ ተቋማቱን ባለቤቶች በስም መጥቀስ እየቻለ (አቀራረቡ ለይቶ እንደሚያውቅ ያሳብቃልና) በደፈናው ያለፈው ወንጀል (ሕገ-ወጥ ዘረፋ) ይህ ብቻ አለመሆኑ ሲገባን ነው፤ በዚሁ ገፅ ዝቅ ብሎ የሰፈረው እንዲህ ይላልና፡- “በወቅቱ ሁለቱም ቡድኖች ‹ያለ ኢኮኖሚ የበላይነት፣ የፖለቲካ የበላይነት አይመጣም› የሚል ፖሊሲ ቀርፀው የህወሓት ባለሀብቶችን ለመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በዚህ ፖሊሲ ምክንያት በአንድ ሌሊት ከሹፌርነት ወደ አስመጪና ላኪነት፣ ከጋራዥ ሰራተኛነት ወደ መኪና ዕቃ መለዋወጫ አስመጪነት፣ ከታጋይነት ወደ ሪል እስቴት ባለቤትነት፣ ከወታደርነት ወደ ፋብሪካ ባለቤትነት፣ ከህወሓት ምድብተኛ ካድሬ ወደግል ባንክ ከፍተኛ አክሲዮን ባለድርሻነት የተቀየሩ ሰዎችን መስማት የተለመደ ነበር፡፡” (ገፅ 26) እነዚህ ‹‹ተላላኪ›› እና ‹‹ሹፌር›› ባለሀብቶችን በስም አለመጥቀሱ ያስቆጫል፤ በተለይም ለመረጃው ከነበረው ቅርበት አኳያ ይሄ ጉዳይ እንደተራ ነገር በደፈናው ባይታለፍ ኖሮ፣ ለተቃውሞው ስብስብ በዋናነት ሁለት ታላላቅ የፖለቲካ ትርፍ ማስገኘቱ አይቀሬ ነበር፡፡

የመጀመሪያው በጅምላ ህወሓት፣ መላው ትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪን ተጠቃሚ ያደረገ የሚመስለው ኢትዮጵያዊ ስህተቱን እንዲያጠራ ስለሚያስችለው፣ በድርጅቱ እና በብሔሩ መሀከል ያለውን ነጭና ጥቁር ልዩነት እንዲያስተውል ይረዳው ነበር፤ ሌላው ደግሞ እነዚህን በፖለቲካ ውሳኔ ወደሀብት ማማ የወጡትን ግለሰቦች የትላንት ማንነት አብጠርጥሮ የሚያውቀው ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ ዘመድ አዝማድ… የዘረፋ ወንጀላቸውን ተፀይፎ በኢኮኖሚያዊ ማግለል (ሸቀጦቻቸውን ባለመግዛትም ሆነ አገልግሎታቸውን ባለመጠቀም) በተቃውሞ ጎራ እንዲሰለፍ ገፊ-ምክንያት ይሆነው ነበር የሚለው ጭብጥ ነው፡፡ ‹‹የመለስ ትሩፋቶች›› መጽሐፍ በሀገሪቱ ውስጥ ከመጋረጃው ጀርባ ስለተፈፅሙ ህልቆ-መሳፍርት ያሌላቸው አሳፋሪ የህወሓት ሕገ-ወጥ ድርጊቶች እና እብሪቶችን ተንትኖ አስነብቦናል፡፡ ከእነዚህ መሀልም የስምንቱ ኮሎኔሎች ‹‹ጀብድ››ን እዚህ ጋ መጥቀሱ አግባብነት አለው ብዬ አምናለሁ፤ ከ268-269 ባሉ ገፆች እንደተተረከው፣ በምርጫ 97 ማግስት በአንዱ ዕለት በወታደራዊ የደንብ ልብስ የተንቆጠቆጡ ስምንት ከፍተኛ መኮንኖች በሶስት ሄሌኮፕተር ተሳፍረው አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ፤ በቀጥታም የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከንቲባ ወደነበረው አባተ ስጦታው ቢሮ በማምራት፣ መሬት እንደሚሰጥ መረጃ ደርሷቸው ከጦር ግንባር እንደመጡ ይነግሩታል፤ እያንዳንዳቸውም ‹‹ዘመቻ ፀሀይ ግባት የቤት ማሕበር››፣ ‹‹ኃየሎም አርአያ የቤት ማሕበር››፣ ‹‹ዛላአንበሳ የቤት ማሕበር››… የሚል እና መሰል የማህደር ስያሜ ያላቸው የአስራ ሁለት መኮንኖች ስም ዝርዝርና ፊርማ የያዘ ወረቀት ይሰጡታል፤ እንደ ብራ መብረቅ ድንገት ባጋጠመው ክስተት ክፉኛ የተረበሸው ከንቲባም እንዲህ ያለ መመሪያ እንዳልወረደ ለማስረዳት ሲሞክር፣ ለዚህ ዓይነቱ እሰጥ-ገባ ጊዜ ያልነበራቸው የጦር አበጋዞቹ አብረቅራቂ ሽጉጦቻቸውን በመምዘዝ ግንባሩ ላይ ደቅነው በወቅቱ ፋሽን በነበረው ኢህአዴጋዊ ፍረጃ ‹‹የቅንጅት ተላላኪ መሆንህን ደርሰንበታል››፣ ‹‹ኢህአዴግ እንዲሸነፍ ያደረጋችሁት እንዳንተ ያሉ ሰርጎ-ገቦች ናቸው››፣ ‹‹እዚሁ ደፍተንህ እንሄዳለን››… የሚሉ ማስፈራሪያዎችን አዥጎድጉደው በማስጠንቀቅ ነፍስ-ውጪ፣ ነፍስ ግቢ ወጥረው ይይዙታል፤ ይህን ጊዜ የህወሓት አባል የሆነው ምክትል ከንቲባው ነጋ በርሔ፣ የአባተን ቢሮ በርግዶ ሳይታሰብ ዘው በማለቱ፣ አንደኛው ኮሎኔል ያነጣጠረውን መሳሪያ ከአይን በፈጠነ ቅፅበት አዙሮ ይደቅንበታል፡፡ ሁኔታውን ከጉዳይ ያልጣፈው ነጋ በርሔም ባለሽጉጦቹን የጦር አበጋዞች በባዶ እጁ እንዲህ ሲል ተጋፈጣቸው፡-
“ነፍጥ ከእናንተ በፊት አንግበን ተራራ ደርምሰናል፡፡ የምታስፈራሩትን ሂዱና ሌላ ቦታ አስፈራሩ!”

ከፍተኛ መኮንኖቹም በድንጋጤ መሳሪያዎቻቸውን በመዘዙበት ፍጥነት ወደአፎቱ መልሰውና የምክትል ከንቲባውን የስድብ ውርጅብኝ በፀጥታ አዳምጠው ሲያበቁ፣ አባተን ይቅርታ እንዲጠይቁት ይታዘዛሉ፤ እንዲያ በጥንካሬያቸው ለማንም የሰው ልጅ የማይበገሩ መስለው ሲንጎማለሉ የነበሩት ቆፍጣናዎቹ ኮሎኔሎች ባንዴ እንደፊኛ ተንፍሰው በፍርሃት የታዘዙትን ይፈፅማሉ፤ ከዚህ በኋላም ህወሓቱ ነጋ በርሔ በተረጋጋ አንደበት ዋናው ከንቲባውም ጭምር እንዲሰማ ድምፁን አጉልቶ የሚከተለውን ‹‹ምርጥ›› ምክር ለገሳቸው፡ –
“ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ጥያቄያችሁን ብታቀርቡ ኖሮ አባተ እንኳን ቤተሰባችሁን ጥላችሁ ግንባራችሁን ለጥይት ለምትሰጡት ቀርቶ ለሌላውም አይጨክንም፡፡ ያውም ከቀናት በኋላ ጠላት (ቅንጅት) ተረክቦ ለሚዘርፋት አዲስ አበባ!” (ገፅ 255) ከንቲባውም መሬቱን ፈቀደ፤ ነጋም ወደ መቀሌ እንዲዘዋወር ተደርጎ፣ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴን እና የትግራይ ክልል ካቢኔን ተቀላቀለ፤ ከጊዜ በኋላም በበረከት ስምዖን በተመራ ግምገማ ላይ በአስቸኳይ አዲስ አበባ መጥቶ ይህንን ጉዳይ እንዲያስረዳ ቢጠየቅ አሻፈረኝ ብሎ ይቀራል፡፡ ደራሲውም ‹‹ዘመን አለፈና አዲሱ ለገሰን ለማገዝ ኢህአዴግ ቢሮ የሥልጠና ማዕከል በምክትል ሚኒስትርነት ማዕርግ ተመደበ›› ሲል የሆሊውድ ፊልምን የሚያስንቀውን ታሪክ ይደመድማል፡፡ በርግጥ አባተም ቢሆን ይህ አስፈሪ ገጠመኙ እንደድንቅ ቃለ-ተውኔት ሁሉ፣ በህወሓት መሪዎች ተደርሶ በኮሎኔሎቹ እና በነጋ የተተወነ መሆኑን ለመረዳት በርካታ ወራት እንደፈጀበት
ተጠቅሷል፡፡

በሌላ ምዕራፍ ደግሞ፤ በምርጫው ቀን እኩለ ሌሊት ተቋቁሞ፣ በአርከበ እቁባይ እና በጄነራል ታደሰ ወረደ እንዲመራ የተደረገው ‹‹የፖለቲካ ፀጥታ ጥምር ኮሚቴ››፣ ከ1978 ዓ.ም በፊት ወደ ትግል የገቡና ማዕረጋቸው ከኮሎኔል በላይ የሆነ የህወሓት መኮንኖች ቦሌ ላይ መሬት እንዲያገኙ ማመቻቸቱን አስነብቦናል፡፡ በአናቱም፣ ከኮሎኔል በታች ያሉ የህወሓት ታጋዮች በሌሎች ማስፋፊያ ከተሞች መሬት ማግኘታቸውን ተከትሎ የተፈጠረውን ሁኔታ ሚኒስትር ዴኤታው እንዲህ ያወጋናል፡- “…ወሬው ባድመና ጾረና ጦር ግንባር ድረስ ተዳረሰ፡፡ ወታደራዊ መኮንኖቹ ምሽጋቸውን እየለቀቁ በጦር ሂሊኮፕተሮች ጭምር እየተሳፈሩ አዲሳባን ወረሯት፡፡ የክፍለ ከተሞች ግቢ አቧራ በጠጣ የኮከብ ጋሻና ጦር ክምር የተሸከመ ካኪ ተጥለቀለቀ፡፡” (ገፅ 255-256) ዘመነኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ‹‹…አንዳንድ እንሰሳት ይበልጥ እኩል ናቸው›› በሚል ያልተፃፈ ሕግ ማደሩን ከውስጥ-አወቅ ምስክርነት የምንረዳው ከህወሓት ውጪ ያሉት ኢህአዴግን የመሰረቱ ድርጅቶች የአመራር አባላት ብቻ የወሰዷትን መሬት በግምገማ እንዲመልሱ መገደዳቸው በዚሁ መጽሐፍ መስፈሩን ስናስተውል ነው፡፡ በወቅቱም በግምገማው ፊት-አውራሪ በረከት ስምዖን የተዘጋጀ ‹‹ከምርጫው በኋላ የድርጅታችንን ስም ያጎደፉና የሕዝቡን ቅሬታ ያባባሱ ተግባራት›› የሚል ሃያ ገፅ ሰነድ የመነሻ ሃሳብ ሆኖ ቀርቦ ነበር፤ የግምገማው ውጤትም የተዘረፈ መሬት ማስመለሻ ፎርምን ህወሓት ያልሆኑ ከ600 በላይ የኢህአዴግ ካድሬዎች እንዲሞሉ አስገድዶ ተጠናቅቋል፡፡

ለአብነትም ደራሲው ‹‹ለታሪክ የተቀመጠው የይቅርታ ፎርም›› ብሎ በመጽሐፉ ያሰፈረውንና በአንድ የብአዴን አመራር የተሞላውን እንደወረደ ልጥቀሰው፡- “ለቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር እኔ ህላዊ ዮሴፍ ድርጅቴ ኢህአዴግና መንግስት የጣለብኝን አደራና ኃላፊነት ወደጎን በመተው ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ የመሬት ወረራ ላይ በመሰማራት አንድ መሬት ወስጃለሁ፡፡ በመሆኑም ይህን ያለአግባብ የወሰድኩትን መሬት አስተዳደሩ እንዲረከበኝ በማክበር እጠይቃለሁ፡፡ ድርጅቴ ኢህአዴግና በእሱ የሚመራው መንግስትም ይቅርታ እንዲያደርግልኝና ከእንግዲህ ወዲያ በየትኛውም የድርጅቴንና የመንግስት ስም በሚያጎድፍ ተግባራት ላለመሰማራት ቃል እገባለሁ፡፡
ከሰላምታ ጋር ህላዊ ዮሴፍ
ግልባጭ
ለአዲስ አበባ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር
ለቦሌ ክፍለ ከተማ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር
ለኢህአዴግ ጽ/ቤት” (ገፅ 257)
የሆነው ሆነ ኤርሚያስ ለገሰ በዚህ መጽሔት ላይ እንዲህ በቀላሉ ጠቅሰን የማንጨርሳቸውን በርካታ አይን ያወጡ ድርጅታዊ እና ግለሰባዊ ዘረፋዎችን ልባችን ቀጥ እስኪል ድረስ አስነብቦናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ዛሬ በየመድረኩ ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው!›፣ ‹መለስ መሲህ ነው!›… አይነት ፕሮፓጋንዳ በማድመቅ ግንባር-ቀደም እየሆነ የመጣው ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ራሱ የዘረፋው ተቋዳሽእንደነበረ እንዲህ ሲል ነግሮናል፡-

“ከሁሉም የሚያሳዝነው ሀገራችንን በዓለም መድረክ በማስጠራቱ የምንወደው ኃይሌ፣ በአስታራቂ ሽማግሌነቱ የምናመሰግነው ኃይሌ፣ በዓለም አደባባይ አልቅሶ ያስለቀሰን ኃይሌ ‹ኃይሌና አለም ሪል ስቴት› በሚል የድርጅት ስም በመስከረም 7/1998 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 18 ውስጥ 50,000 ካሬ ሜትር ሕጋዊ ሰውነት በነዋሪው ድምፅ ከተገፈፈው አርከበ እቁባይ እጅ ወስዷል፡፡ መቼም ታላቁ ሯጭ እየተካሄደ ያለው ውንብድና አዲስ አበባን ማጥፋት እንደሆነ ሳይገባው ቀርቶ አይመስለኝም፡፡” (ገፅ 400-401)

…የወዶ ተሳዳጁ የኦህዴድ ካድሬ፣ ከሁለት ዓስርታት በላይ ሲነገርና ሲፃፍ የነበረውን ርዕሰ-ጉዳይ ለማጠናከር በርካታ የመጽሐፉን ገጾች ሰውቷል፡፡ ይህ የህወሓት ብቸኛ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጠቅላይነት ትርክት፣ ገዢ የተቃውሞው መከራከሪያ መሆኑን በሚገባ የሚያውቀው ኤርሚያስ፣ በተለይም ባገለገለበት አዲስ አበባ ዙሪያ ያልተገለጡ የሚመስሉ ሁነቶችን አስተሳስሮ ለመተረክ ጥሯል፡፡ በርግጥ ለእግረ-መንገድ ያህል አንድ ጥርጣሬ ጥለን እንለፍ፤ ይህን መስመር አብዝቶ ማብራራት፣ ተደማጭነትን እና የፖለቲካ ሁለተኛ ዕድልን እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ከመረዳቱ አኳያ፤ የተባሉትን በምልዐት መቀበሉ ጥቂትም ቢሆን አስቸጋሪ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ አልፎም፣ የትግሪኛ ተናጋሪውን እና ህወሓትን ቀላቅሎ ወደመመልከት እንዳያሻግረን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረጉም ሊታወስ ይገባል፡፡

(በሚቀጥለው ሳምንት ይህንኑ መጽሐፍ በማጣቀሻነት እያወሳን፣ የህወሓትን የፖለቲካ የበላይነት እና ጠቅላይነት የሚያሳዩ ወጎችን እንዳስሳለን)

የህወሓት ትውልድ ገዳይ ስውር መርዝ

$
0
0

አሁን እጅግ በላቀ የዕድገት ደረጃ ሆኖው የሚናያቸው የአለም አገራት መሰረታቸው እውቀት ነው::ያለ እውቀት ፈጠራና ምርምር÷ጥበብና ክህሎት÷ዕድገትና ልማት ሊኖሩ አይችሉም::
ትምህርት የእውቀት ቤት ነው:: እውቀት ካለ ደግሞ ምክንያትነት አለ:: ምክንያትነት ካለ ደግሞ ምርምርና ጥናት አለ::ምርምር ካለ ደግሞ መጠየቅ አለ:: መጠየቅ ካለ ደግሞ መከራከርና መወያየት አለ:: መከራከር ካለ ደግሞ የለውጥ መንገድ አለ:: የለውጥ መንገድ ካለ ደግሞ ዕድገት አለ!!!!
ህወሓት ገና በረኻ ደደቢት እያለች 1973 “የወደፊት የኔ ጠላት ሙሁሩ ክፍል ነው” ማለቷም “የኔ ጠላት ዕውቀት ነው” ከሚል ሐሳብ ጥልቅ የሆነ ግንኙነት አለው::በአሁኑ ዘመን ትምህርት ምላሷ እንጂ ተክለ ሰውነቷ(ቁመናዋ) የለም ማለት ይቻላል:: ይህ ማለት ደግሞ የዕውቀት ግንብ ፈርሷል ማለት ነው::ይህ ማለት ደግሞ የጥበብና የምርምር ቤት ተንዷል ማለት ነው::ይህ ማለትም ምክንያታዊ አስተሳሰብና ግንዛቤ ቀብሮ አገርን ያለ ጠያቂና ተጠያቂ በማስቀረት የለውጥ ድልድይ እንዳይሰራ ያደርጋል::አሁን እያየነው ያለነውም ይህ ነው::
በህወሓት ዘመነ ስልጣን ብዙ ሙሁራን ደብዛቸውን ጠፍቷል::ወህኒ ቤት(ጓንታናሞ) ወርዷል::አገራቸውን ለቀው በባዕድ አገር ሰፍሯል::ይህ ማለት ደግሞ የህወሓት/ኢህአዴግ የዕቀት ጠላትነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መስታዎት ነው::

ህወሓት በእውነት ለኢትዮጵያ ዕድገት ከልብ የሚቆረቆር ቢሆን ኖሮ አሁን ያለው እጅግ የሞተ የትምህርት ጥራት አስተካክሎ ትውልድን የዕውቀት ባለቤት አድርጎ የምርምር ማዕበል በመክፈት ለውጣዊ የዕድገት መንገድ መስራት በቻለ ነበር:: ዳሩ ግን ይህ አይደለም::
የህወሓት ዋና አለማ ከጅምሩ የትምህርት ጥራትን በማበላሸት የትውልድ የእውቀት ጥይትን በመቅበር አገር ያለ ምንም ጠያቂና ተጠያቂ በማስቀረት ዘላለማዊ አምባገነናዊ ስልጣን መቆናጠጥ ነው::ይህ እባባዊ ጥቁር ሴራ “ለህዝብ ኑሮ ለህዝብ የሞተ አገራዊ÷አህጉራዊና አለማዊ ምጡቅ መሪ”እየተባሉ የተሞካሹ የአቶ መለስ ዜናዊ ነው:: አቶ መለስ ዜናዊ የትውልድ የእውቀት ጥይት ለመቅበር የእውቀት አባት የሆኖውን ‘መምህር’ ክብሩን ዝቅ አድርገው በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማያቅ አኳሃን አድቅቀውና አመንምነው አረከሱት::የእኝህ ሰው ታላቁ ጥቁር አስተሳሰብም መነሻው ይህ ነው::ትውልድ ገዳይ ስውር መርዝም ይህ የእውቀት ጠላትነት ነው!!
በአሁኑ ዘመን መምህርና ትውልድ ላይገናኙ አብረው እየተራመዱ ነው::እውቀትና ትውልድም በጣም ተራርቋል::የዕውቀት ድልድይ ተንዳለች::የትውልድ አስተሳሰብም በእጅጉ ወርዷል::የለውጥ ሻማም ጠፍታለች::

ኢትዮጵያ የትምህርት አብዮት ያስፈልጋታል::የዕውቀት አብዮት ያስፈልጋታል::የጥበብና የምርምር አብዮት ያስፈልጋታል::የባህል አብዮት ያስፈልጋታል::ይህን ሳታደርግ ዕድገት ልታመጣ አትችልም::ኢትዮጵያ በድንጋይ ሳይሆን በእውቀት መገንባት አለባት::በምላስ ሳይሆን በተግባር መገንባት አለባት::በዘፈቀደ ሳይሆን በምርምርና በጥበብ መገንባት አለባት::
ህወሓት በአሁኑ ጊዜ የት እንደነበረ÷አሁን የት እንዳለ÷ለወደፊት ወዴት እየሄደ እንዳለ በእውን ለይቶ የማያቅ የምክንያታዊ አስተሳሰብ መኸን ትውልድ እያፈራ ይገኛል:: ይህም ዛሬ ኢትዮጵያ በካድሬው÷ ነገ ደግሞ በካድሬው ልጆች መመራቷ የማይቀር ነው ማለት ነው::
ይህ የህወሓት ጥቁርና የማይረባ አጉል አስተሳሰብ(የእውቀት ጠላትነት) እስካልተወገደ ድረስ “ኢትዮጵያ መካክለኛ ዕድገት ካላቸው አገራት ትቀላቀላለች” ማለትም ከንቱ ምኞት(ቅዠት) ከመሆን የሚያልፍ አይደለም::………..

tplf

ትግል ለምንና ለማን ! ዓላማውስ ምንድነው ? ትግል ሲባል ሳይንሳዊ ሊሆን ይችላል ወይ ?

$
0
0

ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ

እንደምናየውና እንደምንከታተለው የዓለም ሁኔታ እጅግ እየተወሳሰበ መጥቷል። በተለይም የጥቢው አብዮት በመባል ከሶስትና ከአራት ዐመታት በፊት በሰሜን አፍሪካ በአንዳንድ አገሮች የተካሂዱት እንቅስቃሴዎችና የለውጥ ፍላጎቶች የመጨረሻ መጨረሻ የተጠበቀውን ውጤት አላመጡም። ከዛሬ ሶስት ዐመት ጀምሮ የፕሬዚደንት አሳድን መንግስት ለመጣል የተካሄደውና የሚካሄደው እልክ አስጨራሽ ትግል ለብዙ መቶ ሺህ ሰዎች መገደል፣ መሰደድና መንገላታት፣ እንዲሁም ለጥንታዊ የታሪክ ቦታዎች መውደም ምክንያት ሆኗል። ––[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

 

Comment

ማስታወሻ ለኢሣይያስ፣ ለኤልያስ፣ ለብርሃኑና መሰል ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ!!!!

$
0
0

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ (ከአዲስ አበባ)

ኧኸ …. ዴዴዴዴዴዴዴ …. ነይ ነይ ያገሬ ልጅ፣ ነይ ነይ የወንዜ ልጅ … (2)

መለሎ ቁመናሽ ሸምበቆ አንገትሽ (2)
ከቶ ወዴት ገባ ያ ሰውነትሽ (2)

አይ አንቺ ገራገር አይ አንቺ ሞኝ አድባር (2)
በቁመናሽ ፈቱት ያሰርሽውን አምባር (2)

እምዬ ቀሚስሽን በጠባቡ አሰፊው (2)
ዛሬ በሙሉ አካል የለሽም በሰፊው (2)

እንግዲህ እናቴ ቁራጭ ልበሽልኝ (2)
ወጪም አላበዛ እንዲህ ካነስሽልኝ (2)

ጠበቃሽ ማን ይሆን? ዋስሽስ ማን ይሆን? እማኝሽ ማን ይሆን? ጠበቃሽ ማን ይሆን?
የነበረሽ ሁሉ እንዳልነበር ሲሆን፡፡ (2)

ኧኸ… ኤዴዴዴ… ዴዴዴዴ ….ዴዴዴ… ያገሬ ልጅዬ፣ የወንዜ ልጅዬ … ነይ ነይ ያሬ ልጅ … ነይ ነይ የወንዜ ልጅ

እትብቴ ከወዲያ መቃብሬ ወዲህ (2)
በተወለድኩበት አልኖርኩም ከእንግዲህ (2)
ምንድነው ውዳሴ ከእንግዲህ ለጠላ (2)
የደረቡት ሁሉ ከሆነ ነጠላ (2)

ጠበቃሽ ማን ይሆን … (አዝማች)

ከሌሎች ያነሰነ ምንስ ብንሆን ድሃ (2)
እንዴት እናጣለን ከቤታችን ውሃ (2)
አንዲቷ ጎረቤት ያለውን ስትቀዳው (2)
እኛ ብዙ ሆነን ተጠማን ከጓዳው (2)

የቤቱን ስባሪ ሸክም የሚያግዝ (2)
ማን አይዞህ ይለዋል ቢያዝን ቢተክዝ (2)
ሲጠፋ እማያየው እልፍኝ አዳራሽ (2)
አይጨነቅም ወይ ለነገው ወራሽ (2)

ጠበቃሽ ማን ይሆን? ዋስሽስ ማን ይሆን? እማኝሽ ማን ይሆን? ጠበቃሽ ማን ይሆን …
የነበረሽ ሁሉ እንዳልነበር ሲሆን፡፡ (2)

ድምፃዊ ቻላቸው ከበደ ካቀነቀናቸው ግሩም ሀገራዊ ዜማዎች ውስጥ የአንደኛው ግጥም (ነፍሱን ይማር)



በኢትዮጵያዊነታችሁ የምታምኑም ሆናችሁ የማታምኑ ከፍ ሲል በርዕሴ የጠቀስኳችሁ ውድ ኢትየጵያውያን ወገኖቼ፣ እንደምን አላችሁልኝ? የአዲሱን ዓመት ዋዜማና መባቻ እንዴት አያችሁት? መጪውን ዘመንስ ለእናንተም ሆነ ለእናት ሀገራችሁ ምን እንደሚሆን ትጠብቃላችሁ? ለማንኛውም አንድ ወንድማችሁ በግል ተነሣሽነትና በነፃ ፍላጎቱ ይህችን ማስታወሻ ልኮላችኋልና የእርኩሳን መናፍስት ጠባይ ከሆኑት ትዕቢትና ዕብሪት ታቅባችሁ እንድትመለከቷት አደራ ይላችኋል፡፡ መልካም አዲስ ዓመት፡፡ አዲሱ ዓመት ሁላችንም ልብ ገዝተን ወደዬኅሊናችን የምንመለስበት እንዲሆን የወቅቱ ምኞትና ጸሎቴ ነው፡፡
Eliask4513697854126548
ግልጽ ለመሆን ያህል በርዕሴ የተጠቀሱት ኢትዮጵያውያን ኢሣይያስ አፈወርቂ፣ ኤሊያስ ክፍሌና ብርሃኑ ነጋ መሆናቸውን መጠቆም እወዳለሁ፡፡ እነዚህ ወገኖች በየራሳቸው ከአንድ ግለሰብነት የማይዘሉ ተራና ብናኝ ሰብኣዊ ፍጡራን መሆናቸውን አምናለሁ፡፡ ነገር ግን እንደዬፖለቲካ አቋማቸው የተለያዬ ውክልና ያላቸው በመሆናቸውና በአንድ ወይ በሌላ መንገድ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆናቸው ስለሚታወቅ ግምታቸው ከፍ ሲል ከገለጽኩት የአንድ ግለሰብነት ይዞታ ይበልጣል፡፡ ይህም ማለት ብዙ ኢሣይያሶች፣ ብዙ ኤሊያሶችና ብዙ ብርሃኑዎች መኖራቸው የአደባባይ መሥጢር ነው ለማለት ፈልጌ ነው፡፡ አነሳሴ ከወቅቱ የፖለቲካ ሙቀት ጋር የሚቀጣጭ ነው፡፡ አንዴ ሞቅ ደመቅ አንዴ ደግሞ ፈዘዝ ቀዝቀዝ እያለ ሲሻው ደንገላሣ ሳያሻው ሶምሶማ የሚጋልበው የወቅቱ ፖለቲካችን በአብዛኛው ከነዚህ ሦስት ግለሰቦች ዙሪያ አይወጣም – በሒሣባዊ የ“set and subset” ቀመር አኳያ ብንመለከተውም በሺህ ጎራ ተሰልፎ የሚደናቆረው የፖለቲካ ተቃዋሚ ነኝ ባይ ግሪሣ ሁሉ በነዚህ ሦስት ሰዎች ሊወከል ይችላል፡፡ የምናገረው ለኔ እንደመሰለኝ እቅጭ እቅጯን ነው፡፡


ሎራን ካቢላ በአሥራ አንድ ወራት የአመፅ ትግል ሞቡቱን ገልብጦ ሥልጣን ያዘና “ዴሞክራሲያዊት ሪፑብሊክ ኮንጎ”ን መሠረተ – በሥልጣን ብዙ ጊዜ ባይቆይም፡፡ ኢሣይያስ አፈወርቂ የመራው ጦር በመለስ ዜናዊ ትብብርና ሁለንተናዊ ድጋፍ ኢትዮጵያን እንደደሮ ገነጣጥሎ በጥቂት ስኬታማ ዓመታት ውስጥ ለማንም የማትሆን ባለቤት አልባ ሀገር አስገኘ፡፡ የመለስ ዜናዊ የመንፈስ ወንድም የሩዋንዳው ፖል ካጋሜም በጥቂት ወራት ውጊያ መንግሥት ጥሎ በሩዋንዳ “ዴሞክራሲ”ን ገነባ፡፡ ለሤራ ፖለቲካ ማራመጃነት በኃያላኑ መንግሥታት ተጠፍጥፈው እንደተሠሩ የሚነገርላቸውና እንደአለቆቻቸው ሁሉ እነሱም በአምልኮታዊ የሰው ነፍስ ግብር (ጭዳ – death cult) የሚያምኑት ክፉዎቹ የኢስላሚክ እስቴት ወያኔዎችም በጥቂት ወራትና ዓመታት ዝግጅትና ፍልሚያ ምዕራባውያንን የሚያርበደብድ ዘመቻቸውን በማጧጧፍ ዓለምን ጉድ እያሰኙ ነው፤ የኡክሬን አማጽያንም በጣት በሚቆጠሩ ወራትና ሣምንታት ውስጥ ባደረጉት ዘመቻ ከመገንጠል ጀምሮ የራስን መንግሥት እስከመመሥረት ደርሰዋል፤ መነሻውም መድረሻውም የሰውን ዘር በእምነቱ አሳብቦ ከምድር ማጥፋት የሆነው የናይጄሪያው ቦኮሃራም በጥቂት ወራት ትግል ዓለምን “እያስጨነቀ” ናይጄሪያንም እያመሳት ነው፤ … በነዚህ ሁለት ቀናት እንኳን የየመኖቹ ኅዳጣን ሁቲዎች በጥቂት ሣምንታት ውስጥ – ለ‹አንዳርጋቸው ጽጌና ለብዙዎች ኢትዮጵያውያን ዕንባና ጸሎት ምሥጋና ይድረስና› – የሀገሪቱን ቆሾቆምበሬ መንግሥት ዋና ከተማዋ ሰንዓ ድረስ ገብተው ስሊውን በማነቅ ለድርድር እንዲቀመጥ አስገድደውታል፡፡ ስንክሣሩ ቀጣይና እስከዓለም ፍጻሜም የማያባራ ነው፡፡ የዓለም የነማን መፈንጪያ ሆችና …..


በኢትዮጵያ ውስጥ ከወያኔና ከሻዕቢያ በኋላ የተሣካ ዐመፅ ማካሄድና የመንግሥት ሥልጣን መያዝ ያልተቻለው ለምንድን ነው? ከተቋቋሙ ዐርባና ሃምሣ ዓመት የሞላቸው ንቅናቄዎችና የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴዎች ለምንድን ነው – ዘወትር እንደሚባለው ሁሉ – አንዲትም ትንሽዬ መንደር ሊይዙና በ“ጉጉት የሚጠብቃቸውን” ሕዝብ በደስታ ማስፈንደቅ ያልቻሉት? “አታምር ወይ አታፍር” ይባላል፡፡ ንቅናቄዎች ተብዬዎቹ እንዳልሆነላቸው ሲረዱ – መሆንና አለመሆንን መረዳት የሚያስችላቸው አእምሮ ካላቸው ማለቴ ነው – የማያዋጣ የለበጣ መንገድ እየተከተሉ በሕዝብ ላይ ከሚያላግጡ – የወያኔንም ጅራፍ ከሚያባብሱበት – የፖለቲካ ትግሉንም እንደሃይማኖቱና ንግዱ ሁሉ የመተዳደሪያ ቀፈት መሙሊያ ከሚያደርጉት ለምን በጊዜው ጥግ አይዙምና በሕዝብና በሀገር ስቃይ ከመቀለድ አይቆጠቡም? ለምሳሌ ከድርጅት ኦነግ፣ መኤሶን፣ ኢሕአፓ፣ … ከግለሰብ መረራ፣ በየነ፣ ግዛቸው፣ ነገደ፣ ኢያሱ፣ … ሌሎችም የዓዞ ዕንባ አንቢዎች ሁሉ ለምን ከሕዝቡ ጫንቃ ወርደው ራሳቸውን አይችሉም? ወጣቱስ ለምን ተኛ? ለነገሩ ቦታውን ማን ሰጠውና፡፡ አለቃ ገ/ሃና ያቺን ቤታቸው ውስጥ ያሰለቻቸውን ጎመን ጠልተው ጓደኛቸው ቤት ቢሄዱ ያቺው ጎመን ቀረበችላቸውና “በየት ዞረሽ መጣሽ?” አሏት አሉ፡፡ ንቅናቄዎችና እንቅስቃሴዎች እንዲሁም -ዲዶችና ታዋቂ ግለሰቦች ሁሉ ሕዝቡ “ነቄ” ብሏልና በሩ ሳይዘጋ ራሳችሁን እንድትመረምሩ ሃሳብ አቀርባለሁ፡፡


isayas afewerkiኢሣይያስ አፈወርቂ – በቃህ፡፡ ታሪክ ሥራና ሙት፤ የልጅነት ዕድሜህን መስዋዕት ያደረግህበትን የዚያን ዘመን ሁሉ የትግል ውጠየት አየኸው፤ ለአንተ ምን ተረፈህ? መብላት መጠጣትና መስከር? ርሀብን ሊያስታግስ ከማይችል ባዶና አንተው የፈጠርከው ብሔራዊ ስሜት በስተቀር ለኤርትራና ዜጎቿስ ምን አተረፍክላቸው? እውነቱን ብቻ እንነጋገር ካልን በትግልህ ከተጠቀሙት ይልቅ የተጎዱት ይበልጣሉ፡፡ የእልህ ፖለቲካ ከምን ተነስቶ ምን ላይ እንደሚደርስም በራስህ ተሞክሮ ተረዳኸው፡፡ እንዴት እንደምትኖር ከውስጥ ዐዋቂዎች እንሰማለን፡፡ እንዲያ የተቅበዘበዘና አደብ ያጣ ሕይወት የምትመራው ወደህና ፈቅደህ ባይሆንም በሕዝብ ዕንባና ልቅሶ ምክንያት መሆኑን እኔ ትንሹ ወንድምህ ላስታውስህ እወዳለሁ፡፡ ተለያይተው የማይለያዩ የአንዲት እናት ልጆችን በማለያየት ሁለቱንም የቁም ስቅል ስታሳይ ላለፉት 23 ዓመታት ዘለቅህ፡፡ ወደድክም ጠላህም አሁን ሰዓቱ መሽቷል – “ምን እሆናለሁ? ማንስ ምናባቱ ያደርገኛል?” በሚል የቀድሞ ትዕቢትና ዕብሪት የምትመራ ከሆነ የጊዜንና የታሪክን ፍርድ በትግስት ጠብቅ ከማት ውጪ የምልህ የለኝም – አየህ፣ ጠብ-መንጃና ወኔ የሚሠሩበትና የማይሠሩበት ጊዜ መኖሩን አንተም ታውቃለህ ብዬ እገምታለሁ፡፡ የሆነው ሁሉ ሆኖ በዚህ የምሽት ወቅት ግን የአፍሪካ ሲንጋፖር ልትታይ አልቻለችም፡፡ ሕዝብህንም ከስደትና በስደት ከሚገኝ መዋጮ አላዳንከውም፤ ተያይዘን እየጠፋን እንደምንገኝ አታውቅም አልልም፡፡

በአንተ፣ በመለስና በመንግሥቱ የሦስትዮሽ ውጋት ምክንያት ኢትዮጵያ ያጣችው የተማረ የሰው ኃይልና አምራች ገበሬ ለግምት ያስቸግራል፡፡ በዚያም ላይ የዓመታት ጦርነቱን ለማካሄድ የወጣው በመቶ ቢሊዮን ዶላሮች የሚገመተው ገንዘብ ሀገራችንን በአሁኑ ወቅት ከነቻይናና ማሌዥያ ባልተናነሰ በከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ባስቀመጣት ነበር፡፡ ወጪውም ለጦርነት ማካሄጃ በሁለቱም ወገን የተከሰከሰውን ሀብትና ንብረት ብቻ ሣይሆን በጦርነቱ የወደመውን መንግሥታዊና ሕዝባዊ ታህታይ መዋቅርና የዜጎችን በቀላሉ የማይተካ ውሱን አንጡራ ንብረት ሁሉ የሚያካትት ነው፡፡ ድሆች ጦርነትን ሊሠሩ ቢችሉም የመኖር ኅልውናን ግን ሊያረጋግጡ እንደማይችሉ ከነስዬ ዲስኩርና የዲስኩር ባዶነት ተገንዝበናል፡፡ ያ ሁሉ ውድመት የተከናወነው መሠረት በሌለው ጥላቻና ቂም በቀል ተነሳስታችሁ በተለይ አንተና ወንድምህ መለስ ዜናዊ ባካሄዳችሁት እልህ አስጨራሽ አፍራሽ የብረት ትግል ነው፤ እርግጥ ነው አንተና መሰሎችህ ባታምኑበትም ትንቢቱንና የትንቢቱን የአፈጻጸም ቅደም ተከተል ከመነሻው እስከመድረሻው ሳናውቀው ቀርተን አይደለም፤ እናም ታዲያ የጥፋቱ ማሽን ዘዋሪ አንተና ወንድምህ መሆናችሁ ባይካድም መንስኤው ግን ኃጢኣታችንና ክፉ ተግባራችን እንደሆነ ልጠቁምህ እፈልጋለሁ፡፡ ታውቃለህ – “እግዜር ሲቆጣ ሽመል አይቆርጥም፤ ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም” የሚል ብሂል እንዳለን፡፡ አሁንም የምታውቀው ይመስለኛል “ፈጣሪ አንድን ሕዝብ ሊቀጣ ሲፈልግ ጨካኝ ንጉሥን ይሾማል” የሚል ጥቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ተቀምጦ እንደሚገኝ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያንተና የፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ጀምበር እያዘቀዘቀች፣ ገሚስ አካሏም እየገባች መሆንዋን በድፍረት መናገር የተቻለበት ምክንያትም የኢትዮጵያ ታሪካዊ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ተቀስፈው የተያዙበትን ምችና ዋግ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያን የነካ ሁሉ በአሁኑ ወቅት ብጉንጅ በብጉብጅ ሆኖ እያቃሰተ እንደሚገኝ አንተም ከያዘህ ብጉንጅ በመነሳት የምታውቅ ይመስለኛልና በዚያ በኩል ብዙ አልናገርም፡፡

ይልቁንስ ወደልቦናህ ብትመለስ የመልካም ታሪክ ተሻሚ ከመሆን የሚያግድህ ነገር የለም፡፡ በምከተለው ሃይማኖት፣ በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ በመባል የሚታወቀው የክርስቶስ አገልጋይ በፊተኛው ሕይወቱ ልክ እንዳንተው ወንበዴና ፀረ-ክርስቶስ ነበር – ፀረ- ኢትዮጵያዊትህን በውል ሳውቅ ፀረ-ክርስቶስነትህን ከግምት ውጪ አላውቅምና ምስስሉን በዚህ ማሻሻያ አስተካክልልኝ፡፡ ንስሃና ጸጸት ግን አዲስ ስብዕና ያላብሳሉና ከአንጀቱ በማልቀስ ሳዖል ተመለሰ፤ በሩ ሳይዘጋበትም ወደ ጠባቡ አዳራሽ ገብቶ አንገቱን ለሠይፍ እስከመስጠት በሚደርስ ጽናት ክርስቶስን አገለገለ፡፡ ሁሉም ባይሆን ብዙ ነገር ይቻላል፤ አዲስ ስብዕናም መላበስ ይቻላል፤ ባንታደል እንጂ ችኮነትና ካፈርኩ አይመልሰኝ ባይነት የሰውኛ ባሕርይ መገለጫ አይደለም፤ እንደዚያ ከሆን የአእምሮ ባለቤቶች አይደለንም ማለት ነው፡፡ ትልቁ ነገር ራስን መመርመር ነው፡፡ በ11ኛው ሠዓትም ቢሆን የኢትዮጵያ አምላክ የልብ መሰበርን ይቀበላል፡፡ የአንተ ልብ ቢሰበርና አንተን እንደሰው ትታይ ዘንድ የመልካም ሰውነት ባሕርይ ቢያሰጥህ አንተን በጭፍን የሚከተሉና ግደሉ ስትላቸው የሚገድሉ፣ እሠሩ ስትላቸው የሚያስሩ፣ አሰቃዩ ስትላቸው የሚያሰቃዩ አገልጋዮችህ ሁሉ ንጹሓን ዜጎችን ወደምድራዊ ሲዖል ከመክተት ይታቀቡ ነበር፡፡ ለነሱም የጽድቅ መንገድን በከፈትክላቸውና ለምትጨነቅ ነፍሳቸው ዕረፍትን በሰጠሃት ነበር፡፡ በተረፈ ሃሳብ አይግባህ – ኢትዮጵያን ከማንም የዓለም ሀገር ባልተናነሰ ሁሌ የሚያስታውሳት ፈጣሪዋ ነፃነቷን በቅርብ ያቀዳጃታል፡፡ ከቻልህ ምክሬን ስማ፤ ካልቻልክ እንድትቸገርብኝ አልፈልግም፤ ባለህበት ሰላሙን ይስጥህ፡፡


ኤሊያስ ክፍሌ፤ በጣም ከምወዳቸው ጋዜጠኞች አንዱ ነህ፡፡ ልፋትህንና ድካምህን ሰዎች ሲያጣጥሉ ስመለከት እናደዳለሁ፡፡ ዛሬ ለምሳሌ ድረ-ገጽህን ሳነብ ከነብርሃኑ ጂ-7 በተያያዘ ባለህ አቋም የተነሣ ብዙዎች አስተያየቶች ሊያውም በራስህ ሚዲያ ሲያብጠለጥሉህ ሳይ ከፍቶኛል፡፡ ተፃራሪህን ማስናገድህን ግን በጣም ወደድኩልህ፡፡ እንዲህ መለመድ አለበት፡፡ ስለራስ ከሚነገሩ ደግ ደጉን ብቻ እየመረጡ መስማትማ ማን ይጠላል? ይህ በከንቱ የመነቃቀፍና ጫፍ እየያዙ መናቆር እንዲቀር በበኩሌ እየጸለይኩበት መሆኔ በታሳቢነት ተይዞልኝ በጻፍካቸው አንዳንድ ነጥቦች ላይ ግን እኔም የተሰማኝን ቅሬታ መጠቆም ፈለግሁ፡፡ ትፈቅድልኛለህ አይደል?

ብዙዎቹ የምትላቸው ነገሮች በጥንቃቄ ሊታዩና ጆሮ ሊነፈጋቸው የማይገባ መሆናቸውን በበኩሌ አምናለሁ፤ ጭፍን አማኝ መሆንም አልፈልግም – ይጎዳልና፡፡ ግን ግን ለምሳሌ ግንቦት ሰባት ያለው የተዋጊ ኃይል ከአሥር አይበልጥም ስትል ምን ማለት እንደሆነ ደጋግሜ አስተንትኜው ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ አንተም በቅጡ ያሰብክበት አልመሰለኝም፡፡ የምትለውን ሁሉ ለማመን የማላመነታ ቅንና የዋህ አንባቢ ነኝ ልበልና ራሴን ላሳምን፡፡ ግንቦት ሰባት ታዲያ ለማስመሰልም ቢሆን ከአሥር የሚበልጡ ወታደሮች አይኖሩትም ብለህ ትገምታለህ? እንደሰማሁት ወደ ሰባት ይሁን ዘጠኝ ዙር ያህል ተዋጊ ወታደሮቹን እንዳስመረቀ ተዘግቧል፡፡ በአንድ ዙር ሁለት ወታደሮችን አሠልጥኖ ቢያስመርቅ እንኳን ቢያንስ አሥራ አራት ወይም አሥራ ስምንት ወታደሮች አይኖሩትምን? ታዲያ በዚህ ረገድ ኤሊያስ ምን ትለኛለህ? ይህ ግነት መንስኤው ምን ሊሆን ይችላል? ይህን ያህል ዝቅ ብለህ – መረጃው እውነትም እንኳን ቢሆን – የወዳጅን ምሥጢር ለጠላቶች መስጠት ተገቢስ ነው ወይ? የጦር ኃይል መጠንና የሥልጠና ሁኔታ፣ የመሣሪያ ዓይነትና ብዛት፣ የስንቅና ትጥቅ ምንጭና አቅርቦት፣ ወዘተ. የአንድ ድርጅት ምሥጢሮች መሆናቸው ይታወቃል – አንተ ደግሞ ምድብህ በተቃውሞው ጎራ መሆኑን ስለማውቅ – እንደእስካሁኑ ከሆነ ማለቴ ነው – ቢያንስ ከወታደራዊ ምሥጢሮች ወጣ ያሉ ተቃውሞችህን በንቅንቄው ላይ ብታሰማ የወግ ነው፡፡ ለምሳሌ የኤርትራ መንግሥት ሊታመን የማይችል በመሆኑ ሌላ አማራጭ መፈለግ ይሻላችኋል ዓይነት ሃሳብ ብትሰነዝር በበኩሌ አይከፋኝም ብቻ ሣይሆን ደጋፊህም ልሆን እችል ነበር፡፡ ያ የጂ -7 ተዋጊዎች ከአሥር አይበልጡም የሚለውና መሰል ውኃ የማያነሱ ቃላተ-ቅዋሜዎች ግን ምን ዓላማ ሊያራምዱልህ እንደሚችሉ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ እንዲያ በማለትህ በአንተና በንቅናቄው መካከል ያለውን ግንኙነት በጣሙን እንድጠራጠር አድርጎኛል፡፡ ምሳሌ ነው ይህን ያልኩህ፡፡ በተረፈ “ሽልም ከሆነ ይገፋል፤ ቂጣም ከሆነ ይጠፋል” እንዲሉ ነውና የምትወራከቡበትን ማዕከላዊ የቅራኔ ነጥብ እውነትነት ለማረጋገጥ ትንሽ ጊዜ ሳያስፈልገን የሚቀር አይመስለኝም፡፡ እስከዚያው ግን ለትዝብት በማይዳርግ ሁኔታ ብንተቻች ቢኖረን ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ሁሉም ጥንቅር ብሎ ለሚቀረው ነገር በከንቱ መጠላለፉ ለማንም አይጠቅምም፡፡

እስኪ ዐይናችንን እንጨፍንና ከመቶ ዓመት በፊት ወደነበረው ጊዜ በምናብ እንሂድ፡፡ እስኪ አሁንም ዐይናችንን እንጨፍንና ከአንድ መቶ ዓመት በኋላ ያለውን ጊዜ በምናባችን ለማየት እንሞክር፡፡፡ ይህ ሁሉ መራኮት ከነዚህ ሁለት መቶ ዓመታት ውስጥ በየትኞቹ አሠርት ዓመታት ውስጥ ነው ተዘርቶ፣በቅሎ፣ አሽቶና ተመርቶ ወደታሪክ ጎተራ የሚከተተው ብለን ደግሞ እናስብ፡፡ አያችሁ – ነቢዩ ሶሎሞን በመጽሐፈ መክብብ “ሁሉም ከንቱና የከንቱ ከንቱ ነው” ማለቱ ለዚህ ነው፡፡ ይህ ሁሉ መጠላላታችን፣ ይህ ሁሉ ጠብና ግጭታችን፣ ይህ ሁሉ መገዳደላችን፣ ይህ ሁሉ ለገንዘብና ለሥልጣን መጓጓታችንና መስገብገባችን፣ ይህ ሁሉ ትርምስ … እንግዲህ ለዚህች ብቅ ብላ ለምትጠፋ እንደጤዛም ለምትመሰል አጥበርባሪ ሕይወት ነው ማለት ነው፡፡ እውነትን እያስታወስኩ እንጂ ሃይማኖትን እየሰበክሁ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡ ሴትዮዋ ምን ነበር ያለችው ? “እንዲህ ልጠግብ በሬየን አረድኩ”፡፡ ኋላ የምንቆጭባቸው ነገር ግን ደስ እያለን የምንገባባቸው ጉዳዮች ብዙ ናቸው፤ ዲያብሎሳዊ ምርቃና ደግሞ ክፉና የክፉ ክፉ ነው፡፡ ሦስተኛውን ዐይናችንን እንዲከፍትልን አምላክን እንጠይቅ፡፡ (በነገራችን ላይ የቪኦኤው ሄኖክ ሰማእግዜር ፈንቴን ምን ነካውና እንዲያ በቁሙ የተበለሻሸው? ምን ጎደለብኝ በሎ ነው ቆሻሻ ቱቦ ውስጥ ወድቆ እየተግማማ ቪኦኤንም ሊያበክተው የፈለገው? ለገንዘብ ነው ለዓላማ ወይንስ ለእውነት ጥብቅና የቆመው? ወዳጅ ካለው ይምከረው፡፡)


Dr. Berhanu Nega and Dr. Beyan Assoba on ESAT TVዶክተር ብርሃኑ ነጋ፡፡ ሀገር ቤት ውስጥ ስላለሁ ለናንተ ንቅናቄ ሕዝቡ ያለውን ደግና በርህራሄ የተሞላ አመለካከት ለመገንዘብ ችያለሁ – ስሜታዊ ቅኝት እንጂ ሣይንሳዊ ጥናት ግን አላደረግሁም፡፡ ዕድል እንዲገጥማችሁ ፈጣሪን የሚለምነው ብዙ ነው፡፡ በተለይ አንዳርጋቸው ጽጌ ታሪክ በቅርቡ ሊያወጣው በሚችለው አሁን ግን ሥውር በሆነ ምሥጢር የተነሣ ለወያኔው የምሥራቅ አፍሪካ ካሊፌቶች ተላልፎ ከተሰጠ ወዲህ የሕዝቡ ስሜት ክፉኛ ተለውጧል፤ በግልጽ አይናገረው እጅ ውስጥ ውስጡን እየተብሰከሰከ ነው – የሚፈልገው ማስተንፈሻ ቀዳዳ ነው፡፡ ሕዝብ ስል በሆዳምነትና በዘረኝነት አረንቋ ገብቶ የሚዳክረውን በሰው ቅርፅ የሚንቀሳቀስ አጋሰስና አድርባይ ሣይሆን ጭቁኑንና የኢትዮጵያን ትንሣኤ አንጋጦ በጉጉት የሚጠባበቀውን ማለቴ ነው፡፡ ሕዝብ ሕዝብ ሲባል ሁሉም እየተነሣ ይህን መከረኛ ቃል ስለሚናገር ሕዝብ ሲባል ምንና ከማን አንጻር እንደሆነ መለየት አስፈላጊ ነው፡፡ ዘምቦለል አርቲስቱም፣ መዥገር ፖለቲከኛውም፣ ሐሳዩ መሲህ ‹የሃይማኖት አባቱ›ም፣ … ብቻ ሁሉም እየተነሣ “ሕዝብ፣ ሕዝቡ፣ ሕዝቤ፣ ሕዝባችን፣ ለሕዝባችን፣ በሕዝባችን፣ ከሕዝባችን…” ሲል ሁልጊዜ ይገርመኛል፡፡ ዓለም ለይቶላት የውሸት መናኸሪያ መሆንዋን ከምረዳባቸው አመላካች ነጥቦች ውስጥ አንዱ ይሄው ነው፡፡
ወያኔን መጣል የተፈቀደለት አካል ይህን ዕኩይ የአፍሪካ ካሊፌት በቀላሉና ካለብዙ ወጪ እንደሞጄሌ ከነሰንኮፉ መንግሎ እንደሚጥለው በበኩሌ ቁልጭ ብሎ ይታየኛል፡፡ … ሌሊን የዛሩን መንግሥት ለመጣል በሚታገልበት ወቅት መካሪዎች “አንተ ምን ቅብጥ አድርጎህ ነው ይህን ግምብ መንግሥት ለመጣል ካለአቅምህ የምትፍጨረጨረው?” አሉት አሉ፡፡ እሱም አላቸው – “የምትሉት ነገር እውነት ነው፣ የዛሩ መንግሥት ትልቅ ግምብ ነው፤ ነገር ግን ግምቡ የበሰበሰ በመሆኑ በቀላል ግፊ ይወድቃል፡፡” ሌኒን እውነቱን ነበር፡፡

የወያኔ ግምብም ሰው አጥቶ እንጂ ከበሰበሰ ቆይቷል፡፡ ደፋሪ አጣ፤ ጀግና አጣ፡፡ በኅብረት የሚበላ እንጂ በኅብረት አታግሎ ለድል የሚያበቃ የነፃነት አርበኛ አጣ(ን)፡፡ ይህን እውነት የሚናገሩ ዜጎችን ቀንድ ቀንዳቸውን ማለት የተለመደ ቢሆንም የበሰበሰ ዝናብ ስለማይፈራ እኔ የሚሰማኝን እናገራለሁ፤ አሃ፣ መፍራት ደግ ነው ጎበዝ! ሥነ ልቦናችንን ሁሉም ከየአቅጣጫው አደቀቁትና ልምጥምጥ ሆነን ቀረን አይደል?

ለኢትዮጵያ ነፃነት በጦር እታገላለሁ ብሎ ማንም ኢትዮጵያዊ መነሣት ይችላል ብዬ በበኩሌ ካመን ቆይቻለሁ፡፡ ምክንያቱም ወያኔ ካለጦር በምንም መንገድ አራት ኪሎን እንደማይለቅ ግልጽ ነውና፡፡ ውሻን ከአጥንት፣ ጅብን ከአህያ በድን ማላቀቅ የሚቻለው በኃይልና በጉልበት እንጂ በጩኸት የማይሞከር ነው፡፡ በግሌ የማላምንበት ግን ከአሁን ወዲያ የዚህ ወይም የዚያ ጎሣ ጦር የሚባል ነገር ዳግም ሊጠቀስ የማይገባው መሆኑን ነው፡፡ እሱ ነውር ነው፡፡ በዘጠና ነገድ መሀል የአንድን ነገድ ወይም ዘውግ መብት ለማስከበር ዘጠና ጦር ሠራዊት ማቋቋም ማለት እንደወያኔ ሀገርን በኳስ አበደች ለማተራመስ ማቆብቆብ ማለት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር አሁን የምናያቸው ዴምሃትን የመሳሰሉ የትጥቅ ኃይሎች ለሕዝብ የሚያስቡና ሕዝብን ማዕከላቸው የሚያደርጉ ከሆነ ብዙ ሳይረፍድባቸው ስማቸውንና የፖለቲካ አመለካከታቸውን ወደ ኅብረ ብሔራዊነት ይቀይሩ፡፡ ስም ብቻም አይደለም – ሕዝብ በሚወዳት ሰንደቅ ዓላማ ላይ የለጠፉትን ሀውልት በአፋጣኝ ያንሱ፡፡ እንዲህ የምለው “የአክሱም ሀውልት ለደቡቡ ምኑ ነው?” ያለው የዚያ ጋጠወጥ ልጅ ንግግር ትዝ ብሎኝ አይደለም፤ የጎሣ ወይም የቡድን ፖለቲካ አንዱ ችግር ባንዴራንና ሕገ መንግሥትን በመሳሰሉ ታላላቅ ጉዳዮች ላይ ኃይል የሚሰማቸው ጥቂቶች በዝግ ስብሰባቸው እየወሰኑ ሕዝብ ላይ መጫናቸው ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንገሽግሾናል፤ ቋቅ እስኪለን ባለፉት በስባሳ ማኅበራዊ ሥርዓቶቻችን አለውድ በግዳችን እንድንጋታቸው ተደርገናል፡፡ ማንም ግን አልተጠቀመም፤ ስንረጋገም ይሄውና እነሱም እኛም መቅኖ አጥተን በምናብም ይሁን በአካል ከመንከራተት አልወጣንም፡፡ ድንጋይ ራሷ ሰምሃል መለስ አምስት ቢሊዮን ዶላር በስሟ መቀመጡን እንደመታደል ከቆጠርነው ስህተት ነው፡፡ ዶክተር አርከበ ዕቁባይ በተንጣለለ ግቢ በብዙ ሀብት እየተዝመነመነ መኖሩን ከጤና ከቆጠርነው ተሳስተናል – ለዚህም ነው ሁላችንም በሽተኞችና ሰላም የሌለን ተንከራታቾች ነን የምለው፡፡ አሁንም ልድገመው – በኢትዮጵያ ምድር ገዢዎችም ተገዢዎችም አልታደልንም፡፡

እነብርሃኑ የነፃነታችን ምክንያቶች መሆናችሁ እውነት ከሆነ በበኩሌ እንዲህ ብታደርጉ ደስ ይለኛል፡፡ እንዴት ብሎ መጠየቅ ከጨዋ ሰው ይጠበቃል፡፡ በግል ካልጠየቃችሁኝ ደግሞ እዚህ አልናገርም፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡ ኧረ ቆይማ አንድ ነገር ትዝ አለኝ – በሀገራዊ ወኔው በጣም የምወደውና የማከብረው እንትናዬ አንድም ቀን በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ ስለፈጣሪ (ስለእግዚአብሔር አላልኩም) ትንፍሽ ብሎ የማያውቀው ለምን ይሆን? ለነገሩ ማመን አለማመን የግል ጣጣ እንጂ እኔን ምን አገባኝ?…)

ለመሰነባበቻ፤
“የታሪክ አጤሬራ”

አጤሬራ ማለት የዘመኑ ትምህርት ቤታዊ ልክፍት ነው – ተማሮች በእጃቸውም በወረቀትም ለፈተና መልስ ይሆናሉ ብለው የሚገምቷቸውን ነጥቦች ባጭር ባጭሩ ጽፈው ወደፈተና አዳራሽ የሚያስገቡት የባዶ ጭንቅላት ማሳያ ጽሑፍ አጤሬራ ይባላል፡፡ ቀጣዩን አጤሬራ አንብበህ የማትናደድ ከሆንክ መናደድ ብሎ ነገር አልፈጠረብህም፡፡ ስለዚህ ያለህበት ሁኔታ እንደሚገባህ ወስነሃል ማለት ነው፡፡

ሀ. ተፈሪ መኮንን፤ ጅብ፣ ዓሣማ፣ ምሥጥ፣ መሠሪ፣ ተንኮለኛ፣ አስመሳይ፣ ራስ ወዳድ፣ የሁለት ጌቶች ተገዢ፣ ‹አነር›፣ ስግብግብ፣ሥልታዊ፣ …
ለ. መንግሥቱ ኃ/ማርያም፤ አህያ(ከደደብነት አንጻር ብቻ!)፣ ቆቅ፣ ግልብ፣ ደንቆሮ፣ ግትር፣ እልኸኛ፣ ሥልጣን ወዳድ፣ ሰይጣን፣ ጭራቅ፣ ዕብሪተኛ፣ ኢ-ሥልታዊ፣ ግልፍተኛ፣ አርቆ የማያይ፣ የአንድ ጀምበር ሰው፣ …
ሐ. መለስ ዜናዊ፤ (ከ“ሀ” እና ከ“ለ” ብዙ የሚጋራቸው ባሕርያተ ሰውና ባሕርጣተ አጋንንት አሉት)፣ ውሻ፣ ፍየል፣ እባብ፣ እስስት፣ ከሃዲ፣ ዘረኛ፣ አግቦኛ፣ አሽሙረኛ፣ ሥራየ ቤታዊ፣ ሊቀ ሣጥናኤል፣ ግብዝ፣ …
መ. ምዕራባውያን፤ ፍየሎች፣ ሰይጣን አምላኪዎች፣ ባፎሜታውያን፣ ሸፍጠኞች፣ አስመሳዮች፣ ገሃነማውያን፣ መሠሪዎች፣ ሆዳሞች፣ አስመሳዮች፣ የታሪክ ቀበኞች፣ ዘረኞች፣ ፀረ-ሕዝቦች፣…

የኤርትራን ካርታ ለአፍታ አስብ፡፡ ከሱዳን ተነስቶ የሣህል በረሃንና ቀይ ባሕርን ይዞ ሺዎች ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ የት እንደገጠመ ልብ በል፡፡ የኮንጎን ካርታ ደግሞ ለአፍታ አስብ፡፡ እንዴት በመሰለ ቀጭን መስመር ኮንጎን ወደባሕር እንዳቆራኛት አስተውል፡፡ የሰዎችን ተንኮልና ቀናነትም በዚህ ተረዳ፡፡ አንዲትን ሀገር ሆን ብሎ የራሷን ግዛት በመቀስ እንደዶሮ በልቶና ቆርጦ ቆራርጦ የባሕር መውጫ ለማሳጣት የተሤረውን ሤራና ያን ሰይጣናዊ ሤራ እውን ለማድረግ የተሄደውን ርቀት ልብ በል፡፡ በአዲስ አበባ ውስጥ ዜጎች ለዓመታት ደጅ ጠንተውና ከፍተኛ እጅ መንሻ ጉቦ ከፍለው 72 ሜትር ካሬ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ እየተሰጣቸው ባለበት ሁኔታ፣ የውጪ ኤምባሲዎቻችን በየሽንቁላው በአነስተኛ ክፍሎች ተወትፈው በሚገኙበት ሁኔታ፣ … የአሜሪካንን፣ የፈረንሣይንና የእንግሊዝን ኤምባሲዎች የግቢ ስፋት ልብ በል፡፡ እያንዳንዳቸው እነዚህ ሀገሮች የያዙት ቦታ ጂቡቲ፣ ጂቡቲን ያካክላል – ፈረስ ያስጋልባል የሚለው ሥነ ቃልም አይገልጸውም፡፡ ምክንያቱም ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣላ፡፡ ደግሞም ምክንያቱም “ሞኝ የለቱን ብልህ ያመቱን” ይባላላ፡፡ እናሳ መሪዎች ነበሩን? አሁንስ አሉን? የአሁኖቹን ግዴለም ተዋቸው፡፡ ዱሮስ ነበሩን? ከነበሩንስ ከአንድ ወር በላይ ሊራመድ የሚችል ርዕይ(ቪዥን) ነበራቸውን? እንዲያ ገምድለው ገምድለው ለየኤምባሲው ያን ያህል ኹዳድ የሰጧቸው ምን ነክቷቸው ይሆን? ከመግረም አልፎ በሞኝነት ያስቀኛል፡፡

ለ1600 ዓመታት ጳጳስ ከግብጽ እናስመጣ ነበር አሉ፡፡ ሙስሊሞቹ ግብፆች ቢቸግራቸው ቁመተ ዠርጋዳውን ሙስሊም ሰላይ የጳጳስ ልብስ እያለበሱ በስመ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ወደኛ ይልኩልን ነበር አሉ – በሣይቸግር ጤፍ ብድር የገባንበትን ዕዳ በወርቅና በእምነት ሊያስከፍሉን፡፡ በማከያው ከኛ ሰው የጠፋ ይመስል ምሥጢሩ እስካሁን ባልታወቀ ሁኔታ ኢትዮጵያ በግብጽ ተፅዕኖ ምክንያት የዓለም ሬሞርኬ (ተጎታች) ሆና ቀረች፡፡ ለምን ቢሉ – እሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣልና፡፡ ሀፍረትን አናውቅም እንጂ ይህም ነገር እጅግ በሀፍረት ሸማቅቀን በተገባ ነበር፡፡ የክርስቲያን ደሴት የሆነችው ኢትዮጵያ ከሕዝቧ 90 በመቶው ሙስሊም ከሆነና መንገሥታዊ ሃይማኖቷ እስልምና ከሆነ የጥቅም ተጋሪ ሀገር – ለሸፍጥ ሥራ ቀጭን ሰበብ በሚያስፈልጋት ግብጽ ጳጳስ “ኢምፖርት” እናደርግ ነበር፡፡ ዕንቆቅልሽ፡፡ ተናደድ!

ያገርህን የዘመኑን ደናቁርት ባለሥልጣናት ተመልከት፡፡ ከዋሽንግተን ቀርቶ ከመንግሥተ ሰማይ ሳይቀር ስልክ ደዋይ ጋዜጠኛ “ወንጀለኛ”ን ካለበት ሊያስር የሚችል ሊያውም ነቃ ባለው የቦሌ ወረዳ የተመደበ የፖሊስ ኮሚሽነር የምታገኘው በሀገርህ ብቻ ነው፡፡ ሀፍረት ሞታ ተቀብራለች፡፡ ያሣፍራል፡፡ እንደሀገር ብቻ አይደለም ይህ ሁኔታ ሊያሣፍር የሚገባ – እንደሰው ፍጡርነትም በሀፍረት ሰውነትን ሊያሳንስ የሚገባው መራር እውነት ነው፡፡ ሰው ጠፍቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን የመሰለ በወሣንሳ የሚነሣ ባዶ ቀፎ ሀገርህን በፕሬዝደንትነት “እንዲመራልህ” ተሹሞልህ በዚህ ቶርቶራ ሰውዬ “ወርቃማ አመራር” ዓለምህን ቀጭተሃል – ዕድገትህም ሰማይ ደርሶ ስደትህንና ጠኔህን አስፋፍተህ ቀጥለሃል፡፡ ሰው ጠፍቶ በስመ የፖለቲካ ታማኝነት ራሱንና አካባቢውን እንኳን አስተካክሎ ሊገልጽ የማይችል የምሁር ማይም ደሳለኝ የሚባል ጠቅላይ ሚኒስትር ተጎልቶልሃል፡፡ በየዓለም ሀገራቱ ኤምባሲዎቻችንን ለብቻ ተቆጣጥረው የሚገኙት ወያኔ ወንድም እህቶቻችን ከፊደል መቁጠር እምብዝም ያለፉ አይደሉም – ማይም አጋሰስ ደግሞ ከ24 ሰዓት ውስጥ ወደ 30 የሚጠጋውን ስለሆዱ ሲጨነቅ ይውል ያድራል እንጂ ለሀገር ሥራ አንዲት ሴከንድም አያውልም፡፡ ሦስተኛና አራተኛ ክፍል “ግራጁየት”(ምሩቅ) ጄኔራልና ከርኔል የሆኑባት ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ ምርጫ በሌለበት ሁኔታ በምርጫ ስም እጅግ ብዙ ገንዘብ በይስሙላው ምርጫ ሰበብ የሚከሰከስባት ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ናት – በዚህስ ኤርትራ ተሻለች – ወዲ አፈወርቂ እውነቱን ነው በትያትር ለምን ገንዘብ ይባክናል? ከቀበሌ እስከ ታላቁ ቤተ መንግሥት ሥልጣን ላይ የተቀመጡ ሰዎች በአንድ ዘውግ የሚዘወሩና በአብዛኛው የአንድ መከረኛ ዘውግ አባላት የሆኑ ከነዚሁም ብዙዎቹ ፍጹም ዘረኛና ትምህርት ዕርማቸው የሆኑ ማይማን ሆዳሞች ናቸው – ይህም በግልጽ የሚታየው በሀገርህ ውስጥ ነው፡፡ በአንድ ዘውግ ላይ በፈረንጅኛው አጠራር ጄኖሣይድ የሚባለው ዕልቂት ታውጆ ያ ዘር በየሚገኝበት ሥፍራ ሁሉ እንደዐይጥ እንዲጨፈጨፍ፣ ዘሩም እንዲመክን፣ ከሀብትና ከመንግሥታዊ ሥልጣንም እስከወዲያኛው እንዲወገድ የሚደረገው በኢትዮጵያ ሊያውም በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሰው ልጆች ሥልጣኔ ላይ ነው፡፡ በአንድ የታሪክ አንጓ ላይ በሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ነዋሪ የነበሩ ሕዝቦችን በመሪር አገዛዝ ያንቀጠቅጥ የነበረውን የቀድሞ ንጉሠ ነገሥት ዓርማ በማንሣት እነዚህ አሁን ሥልጣን ያሉ በላኤሰቦች በ“የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ” አረመኔያዊ አገዛዛቸው ተሻሽሎ የተቀመረን ስቃይ ሕዝብ ላይ ቀጥለው የሚገኙት በዚሁ ዘመን ነው፡፡ እሊህ የእፉኚት ልጆች የባንዳ አባቶቻቸውን ቂም በቀል አንግበው ከየአካባቢው የሚገኘውን ለምና ምርጥ ቦታ የኛ ክልል ነው ወደሚሉት ነዋሪን እያፈናቀሉና አልነሳም ብሎ የሚያንገራግርንም አለርህራሄ እየጨፈጨፉ የሚገኙት በዚህ ዘመን ነው፡፡ በኦጋዴን፣ በሶማሌ፣ በጋምቤላ፣ በሸዋ፣ በጎጃም፣ በሐረር… ሰዎቻቸውን እያዘመቱ መሬት የሚቀሙና ለጥሪ እንኳን በማይበቃ ርካሽ ዋጋ ለባዕዳን የሚሸጡ፣ ባለይዞታዎችን በመትረየስ እየረፈረፉ አስከሬኖችንም ከጭፍጨፋ ለጥቂት በተረፉ ምሥኪን ወገኖቻችን ከየወደቁበት እያሰበሰቡ “ደርድር፤ እዚያ ጋ በብዛት አለ አይደል እንዴ” የሚሉ ጉዶች የተፈጠሩብን በዚህ ዘመን ነው፡፡ የአሜሪካን ወታደሮች በአልቃኢዳዎች ሬሣ ላይ ሽንታቸውን ቢሸኑ የሥልጣኔያቸው ጉዳይ ውሃ እንደበላው ተቆጥሮ በሀገር ልጅነትና በሌሎች ነገሮች ስለሚለያዩ ነው ሊባል ይችል ይሆናል – ሰብኣዊነትንም ለጊዜው ዘንግተንላቸው፡፡ የኞች ግን ምን እንደነካቸውና ልባቸው ለምን እንደዚያ እንደደነደነ፣ በሬሣ ላይ ሣይቀር ለምን እንደዚያ የሰውነት ባሕርያቻው ወደ ጭራቅነት እንደተለወጠ ቀን ሲመጣ መጠናት ያለበት አስደንጋጭ ጉዳይ እንጂ አሁን በቀላሉ ልንመልሰው የሚቻለን አይደለም፡፡ አጤሬራየን እዚህ ካልቋጨሁት- ስዶጎዱግ ውዬ ስዶፎዱግ ማደሬ ነው፡፡ ለማንኛውም መልካም አዲስ ዓመትና መልካል የመስቀል በዓል በዓል፡፡ መስከረም 13 ቀን 2007፡፡ ይቺን 13ትን እንኳን አልወዳትም ነበር …


ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ኤርምያስ ለገሰ)

$
0
0

ኤርምያስ ለገሰ

temesgen-desalegnበቅድሚያ መጵሀፉን ጊዜ ሰጥተህ በማንበብ አስደማሚ ምልከታ በመስጠትህ ከልብ አመሰግናለሁ ። የተጳፈበትም አንዱ አላማ ይህ ስለሆነ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በእይታህ ላይ እነዚህ ጉድለት ይታይባቸዋል ብለህ ያነሳኸው እና የወደፊት ግምቶችህ ላይ የተወሰነ አስተያየት ለመስጠት የሚጋብዙ ስለሆነ ትንሽ ማለት ፈለኩ። በዚህ አጋጣሚ ሌሎች በመጵሀፉ ይዘት ላይ ዝርዝር ግምገማ ላደረጉ ሰዎች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለእያንዳንዱ አስተያየት መስጠት ከጊዜ አኳያ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ የማልዘልቅበትን መንገድ ልጀምረው አልፈለኩም ። የጋዜጠኛ ተመስገንን በልዩ ሁኔታ መመልከት የፈለኩበት የራሱ ምክንያቶች አሉት። ተመስገን ሀገር ቤት ባለ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በድፍረት መጵሀፉን ማንበቡን በአደባባይ ገልጶ በመጵሄት ሳይቀር መክተቡ ልዩ ያደርገዋል ። አንዳንድ የቀድሞ ” የትግል ጓዶቼ! ” በሚስጥር ቢሮ እየቆለፉና እቤታቸው እየደበቁ ባነበቡበት ሁኔታ የተመስገን ፊትለፊት ማውራት ምንያህል የህሊና ራስ ምታት እንደለቀቀባቸው ማሰቤ ሁለተኛ ምክንያት ነው( ቢያንስ ሁለት “ሚኒስቴር ደረጃ ያሉ ሰዎች ” የተፃፈው ሐቅ ስለሆነ ማስተባበል አይቻልም ” የሚል አስተያየት መስጠታቸውን እርግጠኛ ከሆነ ምንጭ ሰምቻለሁ ። ማረጋገጥ ለምትፈልጉ ” የዲሞክራሲ ሐይሎች” በውስጥ በኩል ጠይቁኝ) ከዚህም በተጨማሪ ከወደ ካሊፎርኒያ የደረሰኝ ዜና የስርአቱ ደጋፊ የሆኑ ሰዎች መጵሀፉን ሲያዙ በአንድ ጊዜ እስከ ሀምሳ ኮፒ መጠየቃቸውን ነበር( መረጃውን ያደረሰኝ የዘወትር ተባባሪዬ ሔኖክ የሺጥላ ” እነዚህ ሰዎች ሊያነቡት ነው ወይስ ሊያቃጥሉት?” የሚል ጥያቄ ቢጠይቀኝም መልስ መስጠት አልቻልኩም ። መልስ ካላችሁ ተባበሩኝ።)

ሦስተኛው ምክንያት የተመስገን ፅሁፍ ሐገር ቤት በመጵሄት መልኩ ቢሰራጭም የመለስ ” ትሩፉቶች” ግን ህጋዊ በሆነ መንገድ እንድትባዛ ብትጠየቅም ሐገር ቤት ያሉ (ጥያቄው የቀረበላቸው) አሳታሚዎች ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል ። በዚህም ምክንያት ወደ ህዝቡ በሰፊው መሰራጨት አልቻለም። ( በዚህ አጋጣሚ ነጳነት አሳታሚ ኢትዮጵያ ለሚያሳትም ሰው ስክሪፕቱን በነፃ ለመስጠት ፍላጐት እንዳለው ገልጶልኛል።)
ይህን እንደ መንደርደሪያ ካነሳሁ ዘንዳ የጋዜጠኛ ተመስገን ምልከታዎች ላይ ያሉኝን አስተያየቶች ላስቀምጥ።
1• “መፈንቅለ መንግሥት”

ተመስገን ከሐገር የወጣሁበት ዋነኛ ምክንያት በአንድ ወቅት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተደርጓል ብዬ መናገሬ አቶ መለስን እንዳስቆጣው እና አቶ በረከት ይህን ተከትሎ ያለስራ እንዳንሳፈፈኝ፣ በዚህም ምክንያት ቅሬታ ቋጥሬ በትምህርት ሰበብ ከሐገር መኮብለሌን ገልፆአል ። ይህን ክስተት በመጵሀፉ ላይ መገለጵ እንደነበረበት አመላክቷል ።ይህ የተዛባ መረጃ ነው። ኢንፎርሜሽኑ ከውስጥ ወደ ውጭ ስለሆነ መዛባቱ ብዙም አልገረመኝም።

ጋዜጠኛ ተመስገን በመጵሀፉ የመጀመሪያ ገፅ ላይ ” የአሳታሚው ማስታወሻ” የሚለውን ክፍል ያነበበው አልመሰለኝም ። አሳታሚዎቹ ግልፅ በሆነ ሁኔታ በመጀመሪያው መፅሐፍ ትኩረት የተደረገባቸውን የአዲሳአባና ተያያዥ ጉዳዬች ብቻ እንደሚያሳትሙ ፣ በቀጣይ በሌሎች ጉዳዬች ( መፈንቅለ መንግስቱን ጨምሮ) እንደሚመለሱ ገልፀዋል።

በማሰከተል ” የመንግሥት ግልበጣ” የምትለው ማእከላዊ መልእክት ጣጣ እንዳመጣችብኝ መገለጱ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ውሸት የመናገር ፍላጐት ቢኖረኝ ኖሮ ይህን የተመስገን አስተያየት ልክነው እል ነበር። ይህን የሚያክል ሀገርና አለም የሚያናውጥ መልእክት ቀርጬ የማስተላለፍ ስልጣን ቢኖረኝ ኖሮ ፣ የሃገሪቷን ስልጣን ” ከትግራይ የፈለቀው ገዥ መደብ” ጠቅልሎ ይዞታል የሚል አንደበት አይኖረኝም ነበር። እንደዚህ አይነት ማእከላዊ መልእክት የመቅረጵ ሚና ትላንትናም ሆነ ዛሬ እኔ፣ ሽመልስ ከማል፣ሬድዋን ሁሴን የለንም ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማሪያምም የላቸውም / አይኖራቸውም ። በመሆኑም ከ ” መፈንቅለ መንግስት” ወደ ” ባለሥልጣናት ግድያ” ከዛም ወደ ” ቀቢፀ ተስፉ ” የሚል መልእክት የተቀረፀው ከአንድ ግለሰብ ነበር። መቼም ለምን? እንዴት? ምን ለማትረፍ የሚለው ጥያቄ አሁን እንደማይነሳ ተስፉ አደርጋለሁ ።

በማስከተል የአሜሪካ ጉዞዬን በተመለከተ ትምህርት የሚባለው መንግሥት ተደናግጦ በመጀመሪያው ሰሞን ያስተላለፈው ነበር ( በቅርብ ቀን ደግሞ ሌላ ነገር ብለዋል።) ሲጀመር ወደ አሜሪካ እንደምመጣ የተነገረኝ ኮሙዩኒኬሽን ጵ/ ቤት ከመቋቋሙ በፊት አደረጃጀቱን ለማስተካከል ስለ “Situation Room” አሰራር ለመመልከት አስቀድሞ የተያዘ ፕሮግራም ነበር። እኔ ብቻ ሳልሆን ከውጭ ጉዳይም ሌላ ሐላፊ አብሮኝ ነበር። በታህሳስ የታቀደው ጉዞ በአጣዳፊ ስራዎች ምክንያት ተላልፎ ሰኔ መጨረሻ ተቆረጠ።በርግጥ እንደ ማስታወሻ ፀሐፊ እስከ ሰኔ መቆየቴ አልከፉኝም( ድርጊቶቹ የግድ መፈፀማቸውና ሰለባዎች መኖራቸው እስካልቀረ ድረስ።) ወንድም ተሜ! መቼስ እንደራስህ የምትወዳቸውን እስክንድርና ሲሳይ አጌና ከውስጥ ወደ ውጭ ምን አይነት ሴራ ሲጠነሰስባቸው እንደነበር መስማት ትፈልጋለህ፣ መቼስ! የክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ የቀብር ስርአት ላይ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት አታካራ መስማት ትፈልጋለህ( አንተም ቢሆን በፍትህ ጋዜጣ ላይ ” ለምን አባረህ በለው ያንን አመጸኛ… ” ብለህ የጳፍከውን የፀቡ አንድ ክፉይ መሆኑን ቀብድ ያዝልኝ ፣ መቼስ! የአልበሽር ፣ የብርቱካን ሚደቅሳ፣የቴዲ አፍሮ፣… ወዘተ ጉዳዬች የወቅቱን የፓለቲካ ምህዳር አጣበውት እንደነበር አይዘነጋም። እናም ስለእነዚህ እና ሌሎች ጉዳዬች ለማውጋት እድሉን በማግኘቴ ጊዜውን እንደባከንኩ ይቆጠር ይሆን?

2• የፍትህ ጋዜጣ ባልደረባ ስለነበረው ማስተዋል ብርሐኑ በተመለከተ፣

ጋዜጠኛ ማስተዋል እንደገለፀው ቢሮ ጠርቼ አናግሬዋለሁ። እንደ ማስፈራራትም ከተመለከተው የስርአቱ ባህሪና እኔም የዛ ስርአት ውላጅ ስለነበርኩ ከዛ ውጭ ልሆን አልችልም። ለደረሰበት የስነ ልቦና ጫና ይቅርታዬን አድርስልኝ።( በነገራችን ላይ ስርአቱ ውስጥ በነበረኝ አስተዋጽኦ ይቅርታ መጠየቁ ችግር ያለብኝ ሰው አይደለሁም ።በተለይ በግለሰብ ደረጃ ከይቅርታም አልፌ በመጵሀፉ ምእራፎች መታሰቢያ ያደረኩት አለ። ” እውን ታሪክ ራሱን ደገመ? ” የሚለውን ምእራፍ ልብ ይሏል።)

ነገር ግን ከሃላፊነት ራሱን እንዲያገል ጠይቆኝ ነበር የሚለው ትክክል አይደለም ። እንደውም በወቅቱ የነበረው አቅጣጫ ጋዜጠኛን ወደ ኢህአዴግ መሳብ ስለነበር በተቃራኒው ሊሆን ይችላል ። መቼስ ወንድም ተሜ!ከፍትህ ጋዜጣ ጋር ኢሕአዴግ ለምን ተጣላ? ጋዜጠኛ ማስተዋልን በምን ጉዳይ አናገርኩት? ጋዜጣው ላይ ለምን እርምጃ ተወሰደ ( የነበርኩት ጥንስሱ ላይ ነበር)የሚለውን ቁምነገር አሁን እንደማትጠብቅ ተስፉ አደርጋለሁ። በነገራችን ላይ በጋዜጣህ ላይ እኔና ጋዜጠኛ ሳምሶን ( ካልጠፉ ሰው!!) አጃምላችሁ ” ሚኒስትር ዴኤታውና ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ሊከሰሱ ነው!” ብላችሁ በፊት ገፅ ያወጣችኃት በሀገረ አሜሪካ ኢምግሬሽን ጵ/ ቤት የጥያቄ መአት አዥጐድጉዳለች። ሂሳብ ማወራረድ ሳይጠይቅ አይቀርም!! እውነት እውነት እልሃለሁ የበግ ለምድ ከለበሰው ተኩላና ከጅምሩ ከምጠየፈው ሰው ጋር ማጃመላችሁ አሳዝኖኛል ። ጋዜጣዋ የወጣች እለት ለእሱ የወገንተኝነት ማረጋገጫ ብስራት፣ ለእኔ ደግሞ ሐዘን ነበር።እውነቴን ነው የምልህ ጋዜጠኛ (?) ሳምሶንን ኢህአዴግ ቢሮ ጀምሮ እጠየፈዋለው። ታዲያ እኔ ብቻ እንዳልመስልህ?…

3• የፓለቲካ ሁለተኛ እድል

ይህቺ አስተያየት የአንተ አይደለችምና ጣላት ። ነው ካልከኝም በድፍረት እነግርሀለሁ ። ተሳስተሀል። ይህ አጀንዳ ሆን ተብሎ በኢህአዴግ እና እጅግ በጣም ጥቂት የራሳቸው ሚና ያነሰ የመሰላቸው ( self ego) ባላቸው ሰዎች የሚቀነቀን ነው። አልፎ አልፎም ” የማንነት ሰርተፍኬት ሰጪና ነፉጊ ” አድርገው ራሳቸውን ከቆጠሩ ግለሰቦች የሚመነጭ ነው። ከኢህአዴግ ውጭ ያሉት የተዛባም ቢሆን ምክንያትና ተጨባጭ ተሞክሮ ስላላቸው የሚጣል አይደለም ። ተገቢ የማይሆነው ኢህአዴግ ይህን እንደ መደላድል እንዲጠቀም ለም መሬት ሆነው ማገልገላቸው ነው።
ወንድም ተሜ! ወጋችን ካንተ ጋር ስለሆነ ወደዛው ልመለስ ። እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅ? ከዚህ በፊት ከኢህአዴግ ጋር ከሰሩ እና ጥለው በመውጣት ተቃዋሚን ከተቀላቀሉ ግባብዳ ካድሬዎች ላይ ይህን እኔ ላይ ያነሳኸውን ጥያቄ አንስተሀል?

ግራም ነፈሰ ቀኝ እኔን በተመለከተ የየትኛውም ፓለቲካ ፓርቲ አባል አይደለሁም። አባል ያልሆንኩት ለጊዜው የድርጅት ተልእኮ የመሸከም አቅም ስለሌለኝ ነው ።ከዚህ በተጨማሪም ለተወሰነ ጊዜ ( ቢያንስ የጀመርኳቸውን መፅሐፍት እስክጨርስ) ያለድርጅት ተጵእኖ ነፃነቴን ጠብቄ መኖር ስለምፈልግ ነው። የድርጅት አባል መሆን ( በተለይ የተቃዋሚ) ቁርጠኝነት ፣ የአላማ ጵናት፣ ጊዜን መስዋዕት ማድረግ፣ ግለኛ አለመሆን… ወዘተ ይጠይቃል ። ለእንደዚህ አይነት ሰዎች( የትኛውንም የትግል ስልት ለሚጠቀሙ ) ልዩ አክብሮት አለኝ። መደገፍ አለባቸው የሚል እምነት አለኝ።
እንግዲህ በመጀመሪያው ምልከታህ ላይ ያሉኝ አስተያየቶች ከሞላ ጐደል እነዚህ ናቸው። ሁልግዜም የተላበስከውን የቁርጠኝነት ፀጋ አብሮህ እንደሚዘልቅ እምነቴ ነው።

የትዉልድ አተላዎች ከመሆን ይሰዉረን –  ናኦሚን በጋሻው

$
0
0

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የሟቹ የመለስ ዜናዊ ሰላባ ከሆኑት ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች መካከል አንዱ ነበሩ። ከ19 ዘጠኝ አመታት በፊት፣ በኩወቤክ ካናዳ የቀድሞ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስተር ጆን ክሬቲየን፣ ባለፈው ሳምንት ደግሞ በስክቶላንድ የአሁኑ የእንግሊዘ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዴቪድ ካሜሮን ፣ የአገራቸውን አንድነት ለማስጠበቅ፣ ክዌቤክና ስኮትላንድ እንዳይገነጠሉ ብዙ የደከሙ፣ የድካማቸውን ፍሬ ያዩ አገራቸዉን እና ህዝባቸውን  የሚወዱ መሪዎች መሆናቸውን ያስመሰከሩ ናቸው።

 

ሟቹ መለስ ዜናዊ ግን ፣ ከጉዳዩ ባለቤቶች  ከኤርትራዊያን በላይ የኤርትራ መገንጠል ዋና አዝማች ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ፣ ኢትዮጵያን ባህር አልባ ያደረጉ፣ ወንድምን ከወንድም የለያዩ ሰው ነበሩ።

 

ከዚያም የተነሳ ለጅቡቲ ኢትዮጵያ 700 ሚሊዮን ዶላር በአመት  ለወደቡ መጠቀሚያ እንድትከፍል ተደርጋለች። 700 ሚሊዮን  ዶላር፣  የአዲስ አበባ የመለስተኛ ባቡር እንዲሁም ከሰበታ ሜኤሶን ያለውን የባብሩ መስመር ለመገንባት የሚያሰፈልገው ሙሉ ወጭን ይሸፍን ነበር (ከማንም ብድር ሳንበደር) ። ለጅቡቲ በየአመቱ የሚከፈለው ፣ በስድስት አመት ዉስጥ የአባይን ግድብ ወጭ ሙሉ ለሙሉ ይዘጋ ነበር።

 

በወቅቱ፣   መለስ ዜናዊ «ስዊዘርላንድም ያለ ወደብ አድጋለች። ሶማሊያ ደግሞ ወደብ ሞልቷት አላደገችም።  ለእድገት ወደብ አያስፈልግም»  እያሉ ሲፎክሩ ፣ ፕሮፌሰር አስራት ፣ በዋናነት ኢትዮጵያ ባህር አልባ መሆን እንደሌለባት፣ የኤርትራ ህዝብ ወንድም ህዝብ እንደሆነ በማረጋገጥ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲከራከሩና ሲሟገቱ የነበሩ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ። አገራችንንም ለምንወድ  ኢትዮጵያዊ ሁሉ አባት ! (በነገራችን ላይ ያኔ ከመለስ ጎን የነበሩ እንደ አቶ ገብሩ አስራት ያሉ በርካታ የቀድሞ የሕወሃት ባለስልጣናት የፕሮፌሰር አስራትን አቋም ይዘው፣ አሁን ለኢትዮጵያ ወደብ እንደሚያስፈልጋት መከራከራቸው፣ የፕሮፌሰሩ ሐሳብ በሕወሃቶችም ዘንድ እያሸነፈ መምጣቱን አመላካች ነው)

 

መለስ ዜናዊ በአካል ቢሞቱም ፣ አሁንም ዳግማዊ መለስ ዜናዊው ኅያለማርያም ፣ ሕሊናቸዉን፣  ክብራቸውን፣ ማስትሬት ያገኙበትን እውቀታቸዉን ፣ የክርስትና እምነታቸዉን ጥለው፣ የጥቂት ሕውሃት ማፊያዎች ሮቦት በመሆን፣ የመለስ ጸረ-ኢትዮጵያዊ፣ ጸረ-ሕዝብ፣ ጸረ-ዲሞክራሲያዊ አሰራሮችና ጎጂ ፖሊሲዎች እያስቀጠሉ ነው።  መለስ ቢሞቱም የመለስ መንፈስ በሃይለማሪያም ዉስጥ አድሮ ሕዝብን እያሸበረ ነው።

 

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ለአገራቸው ኢትዮጵያ ደማቸውን ያፈሰሱ፣  ሰማእት ሆነው ያለፉ ትልቅና የተከበሩ ሰው ነበሩ። መለስ ዜናዊ አሰቃይተው ነው የገደሏቸው። ፕሮፌሰር አስራት ያኔ እንደሞቱት አሁንም ብዙዎች እንደ ቅጠል እየረገፉ ነው። ብዙዎች እየታሰሩ ነው። ብዙዎች እየተሰደዱ ነው። ብዙዎች የሚኖሩበት አካባቢ በጥቂት ከአገዛዙ ጋር ግንኙነት ባላቸው  ኢንቨስተሮች ስለተፈለገ ብቻ በጭካኔ ከቅያቸው እየተፈናቀሉ ነው። ሰቆቃና መከራ በዛ። በርግጥ ይህን የመለስን መንፈስ ከመዋጋትና ከመታገል ዉጭ ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም።

 

አንዳንዶች በሌላው ላይ የሚደርሰው ግፍ ሳይሰማቸው፣ ከአገዛዙ ትናንሽ ፍርፋሪ ጥቅም ስላገኙ ብቻ፣ ዝምታን የመረጡ ወይንም የአገዛዙ አቀንቃኝ ሆነው የሚሯሯጡ እንዳሉ እናያለን። «የተሰሩ ብዙ የልማት ስራዎች አሉ» ይሉናል። «እንዴት ይሄ ሁሉ ፎቅ፣ ይሄ ሁን መንገድ ተሰርቶ ኢሕአዴግን ትቃወማላችሁ ? » ይሉናል።  «መንገዱን፣ ልማቱን እንደግፋለን። ግን የልማቱ ተጠቃሚ ጥቂቶች ሳይሆኑ ሁሉም ይሁን። በሚሰሩ ፎቆች ደስ ብሎናል፤ ግን የጀነራሎች ፎቅ ብቻ ሳይሆን ሌላውም የሚኖርበት ይሁን» እንላቸዋለን። ስናክልም « ሰው ያለነጻነቱ ምንድን ነው? እንደተባለው፣ መንገድ ተሰርቶ፣ ፎቅ ተገንብቶ፣  የኛ መኖሪያ ወህኒ ከሆነ ፣ ነጻነታችንና ልእልናችን ከተደፈረ፣ ፎቁና ሰገነቱ ለኛ ምናችን ነው ? » ብለን እንጠይቃቸዋለን።

 

ፕሮፌሰር አስራት ከ22 አመታት በፊት በደብረ ብርሃን  አደባባይ ካደረጉት ንግግር የሚከተለውን ቀንጭብ አድርጌ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ፡

 

«የአባቶቻችንን የሚያኮራ ታሪክ በማስደፈርም ሆነ ባለማስደፈር በውርደትም ሆነ በኩራት ለማስረከብ ባለብን የዜግነት ግዴታ አንፃር በአሁኑ ጊዜ በታሪክ ፊት ተጋልጠን የምንገኝበትን እንደገና ላስታውሳችሁ እገደዳለሁ፡፡ በጠላት ወረራ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ3 ተከፍሎ እንደነበር አስታውሱ። አንደኛው ወገን ውርደትን በመጥላት በነፃነቱና ለክብሩ ሲል ቤት ንብረቱን ትቶ ወደ አርበኝነቱ በመግባት፣ የዱር ገደሉን ኑሮ በመጀመር፣ ታሪክ ሠርቶ ያለፈና የኖረ፣ ሁለተኛው አገር ሲረጋ እመለሳለሁ ብሎ ሕይወቱን ለማዳን ሲል የተሰደደ፣ ሦስተኛው ለሆዱ አድሮ የጠላት መሳሪያ በመሆን ወገኑን ከሚጨፈጭፈው የኢጣሊያ ጦር ጋር ያበረ ነበር፡፡
ሆዱን ለመሙላትና የማይቀረውን ሞት ለጊዜው ለማዘግየት ሲል የውርደትን መንገድ የመረጠው በትዝብት ውስጥ ወደቀ እንጂ የኢትዮጵያ አርበኞች ድል አድራጊነት አልቀረም፡፡
ለሀገሩና ለወገኑ ክብርና ደህንነት ደረቱን ለጥይት በመስጠት የቆረጠው አርበኛም ያለቀኑ አልወደቀም፣ አልሞተም እንዲያውም ከተፈጥሮ ሞቱ በኋላም ቢሆን በታሪክ ውሰጥ እየኖረና ኢትዮጵያንም በታሪክ እያኖረ ነው፡፡
ወገኑን የከዳውና ለሆዱ ያደረው ባንዳም ከውርደት በቀር ትረፍ ሕይወትና ትርፍ ኑሮ አልኖረም፡፡ ዛሬም እንደነዚህ ያሉ የሕዝብ ጠላቶች ለማንም የማይበጁ ማንኛውንም የሀገርና የወገን ጉዳይ ለጥቃቅን ጥቅማቸው የሚሸጡ፣ የትውልድ አተላ ስለሆኑ እግዚአብሔር በቸርነቱና በኃይሉ ቀናውን አስተሳሰብ እንዲሰጣቸው እየተመኘን ይህን ከመሰለው የትውልድና የታሪክ አተላነት የሚላቀቁበትን ልብ ለማግኘት በቂ ጊዜ ስላላቸው ማሰብና ደጋግመው ማሰላሰል ከዚያም ስለአቋማቸው መወሰን የኖርባቸዋል፡»

 

ፕሮፌሰሩ  እንዳሉት ለመብታችን እና ለነጻነታችን የምንቆም ያድርገን። የትዉልድ አተላዎች ከመሆንም ይሰዉረን !

 

Comment

 

 

ኢትዮጵያዊያንና ትግላችን፤ (ትግሉ ወደፊት እንዲሄድ ምን ማድረግ አለብን? )

$
0
0

እስከመቼ ቅፅ ፲፯ ቁጥር ፲፯

አንዱ ዓለም ተፈራ

መስከረም ፲፭ ቀን ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት  ( 9/25/2014 )

በስታቲስቲክስ የተደገፈ የጥናትና ምርምር ዘገባ ማቅረብ ባልችልም፤ ባካባቢዬ ያለውን ሀቅ ተከታትዬ የሚኖረኝ ግንዛቤ፤ መንገዱኝ ይከፍትልኛል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት ሰብስቤ፤ ይሄ ነው ብዬ የማቀርበው የጥናት ዘገባ የለኝም። ውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ስለሚፈልጉት ወይንም ስለሚያደርጉት ተጨባጭ ማስረጃ ያጠራቀምኩት ዝርዝር የለኝም። ነገር ግን፤ በመጀመሪያ እኔ ራሴ የውጪሰው ኢትዮጵያዊያን አካል በመሆኔ፤ በዙሪያዬ ከምገናኛቸው እንደኔው የውጪሰው ኢትዮጵያዊያን ጋር ስለሀገራችን ሁኔታ እወያያለሁ። ለጥቆም በየድረ ገጹ የሚጻፈውን አነባለሁ። ባጠቃላይ በማንኛውም የዜና መለዋወጫ መንገዶች ሁሉ የሚካሄደውን የሀገሬ ጉዳይ ሳላሰልስ በቀን ሳይሆን በየሰዓቱ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ እከታተላለሁ። ከሞላ ጎደል ሁላችን በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሀቅ መለወጥ እንዳለበት እናምናለን። ከዚያ አልፎ እያንዳንዳችን ለዚህ ለውጥ ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት እንዳለብን እናምናለን። እናም ዝግጁ ነን። ታዲያ እንዴት አድርገን ነው ይኼን ኃላፊነት፣ ፍላጎትና ዝግጁነት፤ በትክክለኛና በተሰባሰበ የአንድነት መንገድ ለትግሉ እንዲሠለፍ የምናደርገው?

በተከታታይ፤ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ በሀገራችን ያለው ምን ዓይነት መንግሥት እንደሆነና ምን ዓይነት ትግል እንደሚያስፈልገን በዚሁ ድረገጽ አስፍሬያለሁ። ( የጎደለና ያላነበቡ ካሉ፤ nigatu. wordpress.com  በመሄድ ሙሉ ጽሑፎችን መመልከት ይቻላል። ) በዚህ ጽሑፍ ደግሞ የሚከተሉትን በቅደም ተከተል የማቀርባቸው ነጥቦች፤ ሀ) ይህ የወራሪ መንግሥት ሀገራችንንና ሥልጣኑን ወዶ እንደማይለቅ፤ ለ) ከዚህ መንግሥት ጋር የሚደረገውን ትግል፤ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ለስኬት እንደሚያበቃው፤ ሐ) ትግሉ በአንድ ማዕከል መመራት እንዳለበት፤ መ) ትግሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ የነፃነት ንቅናቄ እንደሆነ፤ ሠ) ትግሉ የግድ የሰላም ትግል እንደሆነ እና ረ) አሁን የተያዘው አወቃቀሩ የተሣሣተ የድርጅቶች መንገድ መሰረዝ እንዳለበት በመዘርዘር፤ ምን ማድረግ እንዳለብን አመላክታለሁ።

Tensaye

ሀ)      ይህ የወራሪ መንግሥት ሀገራችን እና ሥልጣኑን ወዶ አይለቅም።

አንዳንዶች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወራሪውን መንግሥት ስለማይወደው፤ “በምርጫ አቸንፈነው ሥልጣኑን ይለቃል”፤ ብለው ያምናሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ወራሪውን መንግሥት ስለማይወደው የሚለው፤ ትክክል ነው። ቀጥሎ ያሉት ሁለት ነጥቦች ግን አጠያያቂ ናቸው። በመጀመሪያ በምርጫ አቸንፈነው! የሚለውን እንመልከት። ምርጫን ማቸነፍ የሚቻለው፤ ትክክለኛ የሕዝብ ወኪልነትን ለማግኘት ትክክለኛ መፍትሔ መያዝ ቅድሚያ ያለው ሆኖ፤ ትክክለኛ የምርጫ ቅንብርና አስተማማኝ የአመራረጥ ሂደት ሲኖር ነው። የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በምንም መንገድ ትክክለኛ የምርጫ ቅንብር እንዲኖር አይፈልግም። እንዳልነው ሕዝቡ አይወደውምና! ምርጫ የሰላም የፖለቲካ ትግልን መሠረት ያደረገ ነው። ለዚህ ደግሞ፤ መንግሥቱ የኢትዮጵያ ሆኖ፤ የሚያስተማምን ሕጋዊ መንገድ ሲኖር ነው። ይኼ የለም።

ሰላማዊ ትግልን በተመለከተ፣ ያልተስተካከሉ ሁለት አፅናፋዊ አመለካከቶች አሉ። የመጀመሪያው “ሰላማዊ ትግል አይሠራም!” ብሎ አጠቃሎ የሚኮንነው ክፍል ነው። ሌላው ደግሞ “ሰላማዊ ትግሉን እንደ እንቁላል ተሽቆጥቁጦ አቅፎ መጓዙ!”ን ያመነበት ክፍል ነው። ሰላማዊ ትግል፤ በነዚህ መካከል ነው በተግባር የሚካሄደው። ሰላማዊ ትግሉን የሚያምኑ ታጋዮች፤ ባለው ሕገ መንግሥት ተገዝተው ማጌጫ፤ ያንገት ጌጥ የሚሆኑ አይደሉም። ማኀተማ ጋንዲ ወራሪ እንግሊዞችን፤ ፓርላማ እንዲያስገቡት ከምርጫቸው ውድድር አልገባም። በጥቅማቸው ላይ ተነስቶ አመጽ ነው ያካሄደው። እሰሩን እንጂ አናደርግም ብሎ ነው ያመጸው። “የናንተን ጨው ከምንቀበል፤ በእግራችን ረጂም መንገድ ተጉዘን የራሳችን እናገኛለን!” ነው ያሉት። ማርቲን ሉተን ኪንግና አፍሪቃዊ አሜሪካዊያን ሰላማዊ ታጋዮች ለሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ፤ ፕሬዘዳንቱና አቃቤው “እባካችሁ ታገሱን፤ እስካሁን ያገኘነውን ድል ያስተጓጉልብናል!” ሲሉ፤ “ያ የናንተ ጉዳይ ነው። ለኛ ከነፃነታችን የበለጠ የናንተን አቋም አክብደን ቦታ አንሠጠውም!” በማለት ሰልፋቸውን ቀጠሉ።

ሰላማዊ ታጋዮች እንግዲህ ዋና ዓላማቸውን ለማግኘት፤ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እያወቁ፤ እምቢታን ማስቀደማቸው ነው ትግሉ። ይህ ወራሪ መንግሥት ነው። በሱ ፓርላማ መግባትና አለመግባት፣ በዚህ ምርጫ ቁጥር ማግኘትና አለማግኘት፤ ዋጋ እንደሌለው ታሪኩ አስተምሮናል። ይህ ወራሪ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ ምንም ዓይነት የመግባባትና አብሮ ነገሮችን የመመልከት አእምሮ የለውም። ስለዚህ የምርጫ ጉዳይ ለሱ ጌጥ ከመሆን ሌላ ምንም ትርጉም የለውም።

ወራሪው መንግሥት የፈለገውን ገደብ ቢያደርግም፤ የሕዝቡ ታጋይ ክፍል ባንድነት የሚነሳበትን መንገድ ማበጀት አለብን። ለሕዝቡ የሚቀርቡት ምርጫዎች፤ ወራሪው በሚያዘጋጃቸው የሱ መደነቂያ መድረኮች ሳይሆኑ፤ ታጋዩ ክፍል በሚያዘጋጃቸው የራሱ መድረኮች መሆን አለባቸው። የራሱ መድረኮች በሙሉ ለራሱ የተዘጋጁ ናቸው። እኒህን ማስወገድና ከኒህ መራቅ አለብን። በታጋዩ ክፍል ለሕዝቡ የሚቀርቡት፤ ኢትዮጵያዊነት ወይንም የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆን አለባቸው። በዚህ ታጋዩ ራሱ በሚያዘጋጀው ምርጫ፤ ወገን ይለያል። አንድም ከሕዝቡ ጋር መቆምን፤ አለያም ከወራሪው ጋር መቆምን። ትግሉ በኢትዮጵያዊነት ላይ ብቻ ያተኮረ መሆን አለበት። ይህ እንዳይሆን ወራሪው መንግሥት ሰማይ ይቧጥጣል፣ ይለምናል፣ ያስፈራራል፣ ጦር ይቀስራል፣ የማያደርገው ነገር የለም። እኛም ተመችተንለታል። ስለዚህ ራሳችንን ካላስተካከልን፤ ወደፊት መሄድ አይቻለንም። እናም በምርጫው ለሱ ጃኖ አልባሽ ከመሆን ይልቅ፤ የመውደቂያው አለት ድንጋይ እንዲሆን ማድረግ አለብን። በሱ ድግስ እናቸንፋለን የሚለው ተቀይሮ፤ የምርጫውን ምንነት በማሳወቅ በራሱ ድግስ መውደቂያዉን ለማዘጋጀት እንጣር።

በሌላ በኩል ደግሞ ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሥልጣኑን ስለመልቀቁ ነው። ይህ እኮ ወራሪ ነው። ወራሪ በየትኛው ታሪክና ቦታ ነው ወዶ ሥልጣኑን የለቀቀው? ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግምባር እኮ ሥልጣኑን የሚለቀው፤ መቃብሩ ላይ ሲደርስ ብቻ ነው። እናም በአንድነት እንግፋው። ወዶ ይለቃል ማለታችንን ትተን፤ አስገድደን ለማስለቀቅ ወስነን በተግባሩ እንሰማራ። የምናስገድደው ጦር መዘን ሳይሆን በሕዝብ የአንድነት እምቢታ ነው። ጠመንጃችን እምቢታችን ነው። ይህ ወራሪ ሕግ ያወጣል መልሶ ያፈርሰዋል። የሚያውቀው ቢኖር እሱ ዘለዓለም ገዥ ሆኖ መቀመጥ እንዳለበት ብቻ ነው። ስለዚህ ምንም መያዣ መጨበጫ ስነ ሥርዓት የለውም። እናም በዚህ ወይንም በዚያ የሚለው መንገድ አይሠራም። ራሱ የገነባቸውን ሕጎች የሚያፈርስ መንግሥት፤ ለማናቸውም የሕዝቡ አቤቱታ ፈቱን ሠጥቶ ያስተናግደዋል የሚል፤ ራሱን መመርመር አለበት። የራሱን ሕጎች በማፍረሱ፤ ሕጎችን ማፍረስ ትክክል ነው! እያለ እኮ ነው። ሕዝቡ ለምን የሱን ሕጎች መከተልና ማከበር ይገደዳል? ይህ መንግሥት በምንም መንገድ ሥልጣኑን ወዶ አይለቅም።

አንዶንዶች በውጭ መንግሥታት ተገፍቶ ትክክለኛ ምርጫ ያደርጋል ብለው ያምናሉ። የውጭ መንግሥታት እኮ የቆሙት ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ነው። ለኢትዮጵያዊያን የተመሠረተና የቆመ የውጭ መንግሥት የለም። ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሎሌያቸው ሆኖ፤ የነሱን ጥቅም እስካስጠበቀላቸው ድረስ፤ በምንም መንገድ እንዲወግድባቸው አይፈልጉም። እኛኮ ዳር ደንበራችንን እናስከብራለን፣ ለሙን የሀገራችን መሬት ለራሳችን አራሾችና የመሬቱ ባለቤቶች እናስመልሳለን፣ ይህ ወራሪ መንግሥት ያለእውቅናው ያደረጋቸውን ሀገር የማስገንጠል፤ ወደብ የማሳጣት፣ የአባይን ዕድል በሌሎች እጅ የማስገባትና የመሳሰሉትን ዓለም አቀፍ ውሎች ልናፈርስ የተነሳን ነን! ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያዊያን ብለን የተነሳን ነን! እንዴት ብለው እኛን ይደግፉ? ወይንስ የዋህነት ውጦናል? ስለዚህ፤ ለውጭ መንግሥታት አቤቱታ ማቅረባችንን ትተን፤ በአንድነት በመሰባሰብ፤ ጠንካራ ሆነን በመገኘት፤ ወደኛ እንዲመጡና እንዲለምኑን እናደርግ።

አንዳንዶች ዴሞክራሲያዊ አሠራር ሊከተል ይችል ይሆናል ብለው ያምናሉ። ከእባብ እንቁላል እርግብ እንዲፈለፈል እንጠብቃለን ወይ? ምንነቱና የሕልውናው ምሰሶ የሆነውን ፀረ-ኢትዮጵያዊነት እንዴት አድርጎ ይገፈዋል? ምኞት ጥሩ ነው። ምኞት ገሃድ ሆኖ በራሱ ይቆማል ብሎ መጠበቅ ግን የዋኅነት ነው። ወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በምንም ተዓምር ዴሞክራሲያዊ አሠራርን ይጎራበታል ማለት ቅዠት ነው። በታሪኩም ሆነ ዛሬ፤ በዛሬው ዕለት በሚያደርገው ተግባር፤ ዴሞክራሲያዊነትን ከአጥሩ ወዲያ በጎሪጥ በጠላትነት የሚያይ ነው። የአዲስ አበባን መሬት እንዳሻው ከሕዝቡ እየነጠቀ ለራሱ ጄኔራሎችና ደጋፊዎች የሠጠ ድርጅት፤ ምን ይከተላል ብሎ ነው ዴሞክራሲያዊ አሠራርን የሚቀበል? ዴሞክራሲን ሊማረውም የማይችለው ጉዳይ ስለሆነ፤ በፀረ-ዴሞክራሲያነቱ እንደዳቆነ በዚያው ቀስሶ ይቀበርበት።

ለ)      ይህን ትግል፤ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው ለስኬት የሚያበቃው።

የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመከፋፈልና ይሄንን ክፍፍል ዘለዓለማዊ ለማድረግ፤ የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ያልፈነቀለው ደንጋይ፤ ያልገባበት ጉድጓድ የለም። የዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን እምነቱ፤ “ደጋግሜ ካሰቃየኋቸውና ጊዜ ከወሰደ፤ የኔ ፍላጎትና ተግባር ዘለዓለማዊ ሆኖ ይቀመጣል።” ነው። “ኢትዮጵያዊነትን አጥብቀው የሚሟገቱለትን ግለሰቦች በማሰቃየትና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠብቁ ድርጅቶችን መፈናፈኛ በማሣጣት፤ ደፍረው ወደ ኢትዮጵያዊነት የሚመጡትን ቁጥራቸውን እቀንስና፤ ያለትክ የሚያልፉት ሲያልቁ፤ ለኢትዮጵያዊነት ቋሚ አይኖርም።” ብሎ ነው። ይህ መንግሥት ምንም ዓይነት ጠንካራ እምነት በዚህ ላይ ቢኖረውም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነቱን በነጠላው ጫፍ ቋጥሮ የያዛት ዕቃ ሳትሆን፤ በልቡ ውስጥ ያለ የደሙ ቀለም፣ የእምነቱ ማሠሪያ ስለሆነ፤ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊነቱን ይዞ፤ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ሕዝቡን ይዞ ይኖራሉ። የሚጠፋው፤ ጊዜ ያበቀለው የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ከነመንግሥቱ ነው።

አሁን በሀገራችን በኢትዮጵያ ያለው የወራሪና የተወራሪ ግዛት ነው። ይህ የዴሞክራሲ ጥያቄ አይደለም። ይህ እኔ በዚህ ተበድያለሁ ብሎ የራስን በደል የሚቆጥሩበት አይደለም። ይህ ርስ በርስ የምንወዳደርበት የቁንጅና ምርጫ ዝግጅት አይደለም። ይህ የወገን ደራሽ የሀገር አዳኝ ትግል ነው። ይህ ትግል እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊና እያንዳንዷን ኢትዮጵያዊት በአንድነት የሚያሰልፍ ትግል ነው። እናም ኢትዮጵያዊነት ነው። ስለዚህ ትግሉ ለድል የሚበቃው መላ ኢትዮጵያዊያን የኔ ብለን አብረን ስንነሳ ነው። ለዚህ ደግሞ የሁላችን ፍላጎትና እምነት የያዘ የትግል ራዕይ መቀመር አለበት። ባሁኑ ሰዓት ይህ ራዕይ አራት የትግሉ ዕሴቶችን ያካተተ ይሆናል።

አንደኛ፤           የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ መሆኑንና ሉዓላዊነቱን መቀበል ነው።

ሁለተኛ፤                  የኢትዮጵያን አንድ ሀገር እና አንድ ብሔር መሆን መቀበል ነው።

ሶስተኛ፤           የየአንዳንዱ/ዷ/ን ኢትዮጵያዊ/ት/ የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር መቀበል ነው።

አራተኛ፤                    በሀገራችን በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን መስፈን መቀበል ነው።

እኒህ ናቸው ሁላችን የምንጋራቸው አሁን የኢትዮጵያ መታገያ ዕሴቶቻችን።

ሐ)     ይህ ትግል በአንድ ማዕከል መመራት አለበት።

አሁን በፊታችን የተዘረጋው አንድ ትግል ነው። አሁን ሀገራችን ኢትዮጵያን ወጥሮ የያዛት፤ ወራሪው መንግሥት በሕዝቡ ላይ የሚያደርገው በደል ነው። በዚህ በደል የሚማቅቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በትግል ላይ ነው። ይህ ትግል በኢትዮጵያ ሕዝብና በወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መካከል ያለ ትንቅንቅ ነው። ትግሉ፤ ሕዝቡ ነፃ ለመውጣት፤ ወራሪው የፈለገውን በሕዝቡና በሀገሩ፣ በሕዝቡ ነፃነትና በሕዝቡ እምነት ላይ የሚያላግጥበትን ሁኔታ ለመቀጠል፤ እያደርጉ ያሉት ግብግብ ነው። ስለዚህ ያለው የትግል ሠፈር፤ ሁለት ብቻ ነው። አንዱ የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሠፈር ሲሆን፤ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሠፈር ነው። እናም ትግሉ አንድና አንድ አጥር ብቻ ነው ያለው። የሚቻለው አንድም ከአጥሩ ወዲህ ሆኖ ከሕዝቡ ጋር መቆም ነው፤ አለያም ከአጥሩ ወዲያ ሆኖ ከወራሪው ጋር መቆም ነው።

ይህ በግልፅ የሚያሳየው የዚህ የወራሪ መንግሥት ጠላትና ድራሹን አጥፊ፤ ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሣሪያ ነው። ለዚህ የሚያስፈልገው ደግሞ አንድ ማዕከል ነው። ኢትዮጵያዊ ማዕከል። የትግሉ ማጠንጠኛ በሆነው ኢትዮጵያዊነት ዙሪያ አንድ ማዕከል ማበጀት ነው። ይህ ሕዝባዊ ንቅናቄ ብቻ ነው፤ ሕዝቡን ለድል የሚያበቃው። ይህ ማዕከል ነው ትግሉን መምራት ያለበት።

መ)     ይህ ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ንቅናቄ ነው።

የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር ለማጥፋት፤ ድርጅት መመሥረትና መታገሉ አንድ ነገር ነው። መዋቅርና በዚህና በዚያ ማስፋፋቱ አንድ ነገር ነው። ቆም ብሎ፤ እያንዳንዱ የድርጅት አባል፤ ድርጅታችን ከተመሠረተ አንስቶ ምን ሠራን? ከጀመርንበት ነጥብ እስካሁን ምን ያህል ፎቀቅ አልን? ተሳክቶልናል? ወይንስ አልተሳካልንም? አደግን? ወይንስ ደከምን? የዚህ ሂደት ዕድገታችን መመዘኛው ምንድን ነው? ባገኘነው ስኬትስ ጠግበናል ወይ? እያልን መለካት አለብን። በዚህ ምርምራችን ደስተኞች ከሆን መቀጠሉ ተገቢ ነው። ካልተደሰትን ደግሞ፤ አንድም ድርጅቶቻችንን መቀየር አለያም ግባችንን መቀየር ይኖርብናል። አለያ ትግሉን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ተዘጋጅተናል ድርጅታችንም ጌጣችን ነው፤ ማለት ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ጊዜም በሚደርስበት በደል አንገቱን ደፍቶ አልተቀመጠም። በየወቅቱ በደሉን በመቃወም የተለያዩ ትግሎችን አድርጓል። ከነመንግሥቱ፣ ግርማሜ ንዋይና ወርቅነህ ገበየሁ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጀምሮ፤ በተማሪዎች እንቅስቃሴ፤ በየክፍለ ሀገሮች የገበሬዎች መነሳሳትና በየካቲት ፷ ፮ቱ የታየው ሕዝባዊ እምቢታ የዚህ ምስከር ነው። በየጊዜው የተደረጉት መነሳሳቶች በተለያዩ ምክንያቶች ለስኬት አልበቁም። ይኼንን መርምረን ትምህርት መውሰድ አለብን። ሀገራዊ ውይይቶች የተደረጉባቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ያማረ ውጤት ያስከትላሉ። ይሄን ለማድረግ ግን ጥረቶች አልታዩም። ለምን?

አሁንም ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች አሉ። ችግራቸው ምንድን ነው? ብለን አልጠየቅንም። ለምን? ለምሳሌ፤ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችን ለረጅም ጊዜ እየታጋሉ ነው። ይህ እንቅስቃሴያቸው በአብዛኛው የሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ ተቀባይነት አለው። ታዲያ ለምን ግቡን አልመታም? በተጨማሪ፤ በኤርትራ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ እናደርጋለን ብለው የተነሱ ብዙ አሉ። እኒህም ለረጅም ጊዜ መግለጫዎችን ሲያወጡ ስምተናል። ለምን ከፍተኛ ደረጃ ላይ አልደረሱም? እንቀጥል። በውጭ ሀገር ያለን ኢትዮጵያዊያን ነፃነት፣ ጊዜ፣ ንብረት፣ ሀገር ወዳድነት፣ ለወገን ተቆርቋሪነት ሞልቶናል። ታዲያ ለምን በአንድነት ተሰልፈን አልተነሳንም? ልጨምርበት። በሀገር ቤት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ። ለምን እንቅስቃሴያቸው ወደፊት አልተራመደም? በማዕከላዊነት ደግሞ፤ የየድርጅቶቹ መሪዎችና የትግሉ ልሂቃን፤ ለምን ይሄን ማድረግ እንዳልቻልን ጥናት አድርገን መፍትሔ ለምን አላቀረብም? ይሄ በተደጋጋሚ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው።

ለዚህ ሁሉ ጥያቄ መልስ የግድ መኖር አለበት። እንግዲህ ሁሉም በያሉበት ያነሱት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄዎችን ነው። አንዱ ከሌላው የሚለየው፤ በራሳቸው ዙሪያ ብቻ ያለው ላይ ማተኮራቸው ነው። ቁም ነገሩ ግን የያዳንዳቸው ጥያቄዎች የሁሉም ጥያቄዎች ናቸው። የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የጠየቁት የመብት ጥያቄ ነው። መምህራንና ተማሪዎች የጠየቁት ይኼኑ ነው። ነጋዴዎች የጠየቁት መብትና እኩልነትን ነው። ይህ የሁሉም ጥያቄ ነው። ቤት ተከራዮችና ቤት ለመሥራት የተዘጋጁት የጠየቁት መብታቸውን ነው። ይሄ የሁሉ ጥያቄ ነው። በደቡብ የተፈናቀሉት ኢትዮጵያዊያንና በኦጋዴን የሚሰቃዩት ኢትዮጵያዊያን የጠየቁት ኢትዮጵያዊ መብታቸውን ነው። ይህ የሁሉ ጥያቄ ነው። ስለዚህ የጎደለው እኒህን ጥያቄዎች በማያያዝ የሁሉም ማድረግና ሁሉም በአንድ ላይ የሚነሱበትን ማዘጋጀቱ ነው። ሁሉም የመብት፣ የነፃነት፣ የሕግ፣ የእኩልነት ጥያቄዎችን ነው ያነሷቸው። ሁሉም የሁሉም ጥያቄዎች ናቸው። ስለዚህ ሁሉም በአንድ ላይ ሁሉንም ማንገብ ያለባቸው ጥያቄዎች ናቸው። የድርጅት ሚና ይሄን ማድረግ ነው። ድርጅት የራሱን መርኀ-ግብር ብቻ አንግቦ ለራሱ ሥልጣን ማግኛ መንገድ ማስላት ሲይዝ፤ ፉክክር ይነግሳል። በርግጥ ነግሷል። እናም ቁጥር ለማብዣ ያለው እሽቅድድም፤ ዋናው ቁም ነገር ሆኗል። ከዚህ መውጣት አለብን። ይህ ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳሳት ነው። የሕዝቡ ንቅናቄ ነው።

ሠ)     ይህ ትግል የሰላም ትግል ነው።

አሁን ያለንበትን የደበዘዘ የትግል እንቅስቃሴ ሕይወት ሠጥተን ወደፊት ለመጓዝ፤ ማመንና መከተል ያለበን የትግል ቅደም ተከተል ዝርዝር፤ በግልፅ መስፈር አለበት። ነፃነት የመጀመሪያው ነው። ወራሪውን፤ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ማስወገድ አለብን። የተለያዩ ክፍሎች በተለያየ መንገድ በትግሉ ተጠምደዋል። የተለያዩ ድርጅቶች በመድረኩ ተጋግረዋል። በትጥቅ ትግል ላይ “ተሰማርተናል” የሚሉም አሉ። እንግዲህ ማን ከማን ጋር እንደሚታገልና ድሉ በምን እንደሚተረጎም ግራ የተጋባበት ሀቅ በመካከላችን ሰፍኗል። ይህ ትግል ወራሪውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ማስወገድ ብቻ ሳይሆን፤ ከዚያ ቀጥሎ ለሚመጣው ሥርዓትም ጭምር ነው። ወራሪውን ማስወገድ ብቻ የትግሉ ዋና ማውጠንጠኛ ማድረግ አጓጉል ነው። ከዚያ ቀጥሎ የሚመጣው ሥርዓትም በእኩል ደረጃ መቀመጥ አለበት። አንድን ትግል በሌላ ትግል የመተካት አባዜ በሺታ ነው። ይህ ለኔ ብቻ ብለው በራሳቸው ድርጅት ተጎናንፈው የተቀመጡ ክፍሎች አጀንዳ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ አጀንዳ አይደለም። ስለዚህ የዚህ ትግል ባለጉዳዮች መላ ኢትዮጵያዊያን ነን። እናም ትግሉ አሁን ባለበት ደረጃ፤ ሰላማዊ ነው። የትግሉን ተሳታፊዎች መሰባሰብ እና አንድነትን መፍጠር፤ ዋና የቅድሚያ ተግባሩ ነው። ሕዝቡ የትግሉ ባለቤት ነው፣ ሕዝቡ ሉዓላዊነቱ መጠበቅ አለበት፣ ሕዝቡ ትግሉን ይምራ ስንል፤ በአንድነት ሆነን ትግሉን ሁላችን እንቀላቀልበትና የሕዝቡን መብት እናስከብር ማለት ነው። “የኔ ድርጅት ሲያቸንፍ መብቱን ለሕዝቡ እሠጣለሁ።” የሚለው የቁጮ አባባል፤ ትናንት አልፎበታል። የዛሬ ሰዎች ነን። የዚህ ትርጉም፤ በቀጥታ ሲቀመጥ፤ “እኔ ገዥ መሆን እፈልጋለሁን በኔ ሥር ሆናችሁ እኔን ለማንገሥ ታገሉ።” ማለት ነው።

ረ)      አወቃቀሩ የተሣሣተው የድርጅቶች መንገድ መሰረዝ አለበት፤

አዎ! ሳይደራጁ ትግል የለም። ጣሊያን ፋሽስቱን የተጋተሩት ጀግኖች አርበኞቻችን፤ በየጎጡና በየመሪያቸው ከመንደር እስከወረዳ፣ ከወረዳ እስከ አውራጃ፣ ከአውራጃ እስከ ንጉሣቸውና ከንጉሣቸው እስከ ንጉሠ ነገሥታቸው ባንድ ሀገር፤ ባንድ መንግሥት ስም ተደራጅተው ነው። በየግሉ የሚደረግ እንቅስቃሴ ለድል አያበቃም። ከራሳችን ከዚህ ታሪክ የምንወስደው ትምህርት፤ ድርጅት ለወቅታዊ ጥያቄው መልስ የሚሆን መሣሪያ ነው። አሁን ደግሞ የሚያስፈልገን መሣሪያ፤ መላ ኢትዮጵያዊያንን በኢትዮጵያዊነት አሰብስቦ፤ በወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ላይ የሚያስነሣና፤ ለድል አብቅቶ የሽግግር መንግሥት የሚያቋቁም ነው። ይህ የሀገር ነፃነትን ለማስገኘት የሚደረግ መደራጀት ነው። ይህ መደራጀት የሚያስከትለው የሽግግር መንግሥት፤ ሕገ መንግሥት ተረቆ የሚጸድቅበት፤ ሕገወጥ በሆነ መንገድ የተደረጉት የወራሪው መንግሥት ዓለም አቀፍም ሆነ የሀገር ውስጥ ውሎችና ሕጎች የሚሰረዙበት፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ምዝገባ ተደርጎ፤ እኒህ ድርጅቶች የሚወዳደሩበትና ተቀባይነት የሚያገኘው ወገን ሥልጣኑን የሚያስረክብበት ወቅት ነው።

ለዚህ ሂደት የሚያስፈልገን ኢትዮጵያዊ የሆነ አንድ ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ክፍት ነው። “ጉዳዬ ነው” ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በግሉ ገብቶ የሚሳተፍበት ንቅናቄ ነው። መደራጀት ለሆነ ተግባር የሚደረግ የሰዎች መሰባሰብ ነው። አሁን በኢትዮጵያ የትግል ምኅዳር፤ ለዚህ ንቅናቄ ተወዳዳሪ ሌላ ድርጅት አይኖርም። ያሁኑ ሰዓት መደራጀት ሀገርን ነፃ አውጥቶ የሕዝቡን የበላይነት ለማስከበር ብቻ ካልሆነ፤ ኢትዮጵያዊም ሕዝባዊም አይደለም። ከዚህ ይልቅ የራሴን ድርጅት ነው የማጠናክረው ብሎ የሚሯሯጥ ድርጅት፤ ከወራሪው የትግሬዎች ነፃ ወጪ ግንባር የተለዬ አጀንዳ የለውም። አሁን ቅድሚያ ቦታ ያዥነት ኖሮኝ፤ ሌሎችን ዘግይተው ሲመጡ አቸንፋለሁ የሚል ድርጅት፤ ከመርኀ ግብሩና ከቆመለት ዓላማ ይልቅ ብልጣ ብልጥነትን የተካነ፤ ድርጅቱን ከሀገሩ ያስቀደመ፤ ግለኛ ድርጅት ነው። ይህ የሕዝብ ወገን አይደለም። ይህ ኢትዮጵያዊ አይደለም። እናም ይኼን የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነት ንቅናቄ በአንድነት እንመሥርተው። ሃሳብ ላለው በ eske.meche@yahoo.com እገኛለሁ።

“ሀገርን እግዚአብሄር ካልጠበቀ ሰራዊቱ በከንቱ ይደክማል”

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 27.09.2014 / ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ይህ ቃል አካል የሌለው ዬህዝብ አገለጋይ የሆነው ቃለ ወንጌል ነው። እንዴት ናችሁ የእኔዎቹ? እንኳን ለአዲሱ ዘመን እንዲሁም ለተዋህዶ አማንያን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ – አደረሰን። ጠፍቼ ከረምኩ ባለመቻል። ንፍቅ አላችሁኝ።

ብዙ ሰው በጣም የሚጨነቅበት – የሚጠበብት መሰረታዊ ጉዳይ የሠራዊት መኖርና አለመኖር። የመሳሪያ – መጠንና ጥራት እንዲሁም የሎጅስቲክ ብቃት ታክሎ ስሌት ውስጥ ይገባል። ስለሆነም የነፃነት ትግሉ ውጤታማነትም ሆነ የድርጅቶች የብቃት ተልዕኮ በዚህው ይመትሩታል። ለእኔ ደግሞ ይህ ምንም ነው። ስለምን?

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

መሣሪያ ከአለመንፈስ ደጋፊነት ባዶ ነው። ሎጅስቲክም ቢሆን የፈቀደ መንፈስ ከሌለው ባዶ ነው። ባዶ + ባዶ  ውጤቱ ባዶ ነው። ሰው ብቻውን ሆነ መሳሪያ ብቻውን፤ በተጨማሪም ሎጅክስቲክስ ብቻውን ባዶ ነው። የመጀመሪያው ነገር ፈቃደ እግዚአብሄር ወሳኝ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ውስጡ ዬነፃነት ራህብ የፈጀው የምልዕት ህዝብ የለማ መንፈስ አስፈላጊ ነው። አብሶ ለነፃነት ትግል ፍሪያማነት ነፃነቱን የፈለገ፣ የለውጥ አስፈላጊነት ከውስጡ ያመነ፣ ለለውጡ ሂደት መንፈሱን በገፍ ለመቀለብ የተሰናዳ፣ ለውጡን ለማዬት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመቀበል የቆረጠ – የወሰነ፤ ግን ያልነፈሰበት መንፈስ ያስፈልጋል።

“የለማ መንፈስ” ይህ ማለት የጠላትን ፍሬ ነገር፣ ፍላጎተ – ግብ፣ መርምሮ ህዝብ ከነፃነት ትግሉ ጎን እንዲሰለፍ መንፈሱን ሊያነሳሱ፤ ሊያዳብሩ፤ ሊያንቀሳቅሱ የሚችሉ የህሊና ሥራዎች በስፋትና በተከታታይነት የመከወን አስፈላጊነትን ያጠይቃል። ሁሉ ሰው የሚያስበው ሁሉን ያወቀ ሆኖ እንደተገኘ አድርጎ ይገምታል። ይህ ስህተት ይመስለኛል። ለምሳሌ “ድርጅት ማለት” በፅንሰ ሃሳብ ደረጀ ሆነ በተግባር ሂደት፤ በፈተናዎቹ ዙሪያ፤ በተግባር ስንቅና ትጥቁ ዙሪያ፤ በመብትና በግዴታዎቹ አካባቢ ምን ያህሉ በቂ ግንዛቤ ወይንም ዕውቀት አለው? በጥናት ቢሰራ መረጃዊ ዳታው ከገመትነው በታች ቁልቁል ይወርዳል። ይህ ለናሙና ያነሳሁት ጉዳይ ነው እንጂ መንፈስን በጥንቁቅ አጥቂነት፤ ደጀንነት ወይንም አብሪነት ለማሰለፍ መጠነ ሰፊ ያልሰራንባቸው ጉዳዮች አሉን እንጂ ከብረቱ ቆጠራ ይልቅ ለድሉ ቅርብ የሆነው ጠላትን በለማ ህሊናና መንፈስ መርታት መስዋዕትነቱም ሆነ ጊዜው በጣም ቅርብ ያደርገዋል። እርግጥ ኃይል በጎጥ ያለተደራጀ ወጥ ኢትዮጵያዊ ሠራዊት ደጀን አያስፈልግም ማለቴ ግን አይደለም። የሆነ ሆኖ ላነሳሁት ነጥብ መነሻወችን ትንሽ ልበል።

ይቻላል። አዎን ይቻላል። ትልቁ መሳሪያ የህዝብን መንፈስን ልማት ለማስበል … “ራዲዮ” ፕሮግራም ሰፊውን ድርሻ ሊወጣ ይችላል። ሚሊዮወን የመሳሪያ ጋጋታ፤ የትጥቅና ስንቅ ሆነ ዬሎጅስቲክስ ድርጅት የሚሠራውን ፋይዳ ያህል የመከወን አቅሙ ራዲዮን አለው። እኔ እንደማስበው ዘለግ ባለ ብልጫ ራዲዮ ፕሮግራሞች ሊሠሩት ይችላሉ። ራዲዮ ፕሮግራሞችን በሁለት አቅጣጫ ከፍለን ማዬት እንችላለን።

  1. የኮምኒቲ ራዲዮ ፕሮግራሞች /በደጀንነት/ ለነፃነት ትግሉ የቀረቡና ጠላታቸውን ጠንቅቀው ያወቁትን ማለቴ ነው። እነዚህን ራዲዮ ፕሮግራሞች ውጪ ያለውን የነፃነት ደጋፊ፣ ማህል ሠፋሪ፤ ዝመተኛ ወገን፤ አልፍ ሲልም በጎጥ አስተዳደር ደጋፊነት የተሰለፈውንም አክሎ በአንድ ማዕድ ዙሪያ ሊያመጡ የሚችሉ መሰመሮችን እንዲከተሉ ማድረግ ይቻላሉ። ነገር ግን አብዛኞቹ በዚህ ዙሪያ ከሚሠሩት ይልቅ ለተደጋገመ መረጃ የሚሰጡት የአዬር ጊዜ ሰፊ ነው። ብዙዎቹ በጣም የተደጋጋመ ጉዳዮችን በተወራራሽነት ነው የሚነሱት። አንድ ሰው ቃለ ምልልስ ከተደረገለት ያው ደግሞ በሌላው ይደገማል ይሰለሳል። ይህ ለእኔ ጊዜን የሚበላ ዕዳ ይመሰለኛል። በዚህ ዙሪያ ሌላ ማንሳት የምሻው ጉዳይ ሁሉ ሰው የተስተካከለ ግንዘቤ እንዳለው – እንዳወቀ አደርጎ ይገምታል። እእ! በጣም በብዙ እርቀት ላይ እንደምንገኝ ሃቁን ብንቀበል መልካም ነው። መንፈሳችን አለመደራጀቱ የሚረጋገጠው ለተመሳሳይ ጉዳይ ምን ያህል አቅምን እያሾለኩ – አቅምን የሚሰልቡ አቅለ ቢስ ጉዳዮችን እንደምንከበክብ ሁላችንም እናውቀዋለን። ስለዚህ ሁላችንም ገና ነን። ስለዚህ መንፈሳችን በመስኖ መልማት አለበት …. ቢቻል ቢቻል የኮሚኒቲ ራዲዮ ፕሮግራሞችን በአህጉር ደረጃ እንኳን አቅጣጫቸውን ማዕከላዊ ለማድረግ ቢሞከር አንድ መንገድ ነው። ካልተቻለ ግን የኮሚኒቲ ራዲዮ ፕሮግራሞች “በመንፈስ ልማት” ላይ ሰፊውን የአዬር ጊዜ ቢሰጡ መልካም ይስለኛል። በተደራጀ ሁኔታ የመንፈስ ፈሎች ተከታታይ በሆኖ እንደ አልሚ ምግቦች መስጠት፤ በታቀደና በተሰናዳ ሁኔታ የማስተማር፣ የማሰናደት ተግባር መከወን ያለበት ይመስለኛል። ጊዜም ሆነ አቅም መባከኑ ካልቀረ ዒላማው ወደ ጎሎ ማነጣጠር አለበት። ይህ መስክ የተዘለለ ነው ማለት እችላለሁ።
  2. ሀገር ቤት የሚደርሱ የራዲዮ ፕሮግራሞች /በአጥቂነት/ እኔ እንደማዬው ሀገር ቤት በሚደርሱ ራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ የጥራት – የብቃት የዝግጅት አቅም ሙሉ ነው። አብሶ የድምጽ ጉዳይ ለራዲዮ ፕሮግራም ወሳኙ ክፍል ነው። በዚህ በኩል ብዙም ችግር አላዬሁም። የመረጃው ዕውነትነትም እንዲሁ። እንደ ሥርጉተ መንፈስ የነፃነት ትግል ራዲዮ ፕሮግራሞች ከቤት መከራና ችግር የሚነሱ ተከታታይ መስኖችን በመንፈስ ሥር በመቀዬስ መስኩን ማልማት በሚመለከት ሰፊ ጊዜ ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ። ለእኔ እራህብ ላይ ለሆነ ወገን መዝናኛ ፕሮግራም ወይንም ትረካ ምኑ ነው? የወያኔ ዜና የተንተራሰ መረጃ ከሆነ ሃቁን ሳይሸፋፍን የገለጠና የደፈረ የመሆንም አለበት ባይ ነኝ። የወያኔን የሚዲያ ቅጥፈት በሚገባ ማገለጥ በእጅጉ ያስፈልጋል።

ከዚህም ሌላ ዜናዎች ይሰማሉ ዜናዎችን መነሻ ያደረጉ የጠላትን የጎን አጥንት እንኩት ዬሚያደርጉ የህሊና ሥራዎች ግን እንብዛም ነው። ለምሳሌ አቶ ኤርምያስ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሰጡት መልስ ላይ “ማስፈራራት የሥርአቱ ባህሪ ስለሆነ እኔም ከዚህ ልወጣ አልችልም ነበር በማለት የእምነት ቃላቸውን ሰጥተውናል” ወሸኔ ነው። ይህ አገላለጽ የወያኔን ሆድ ዕቃ ቁልጭ አድርጎ ያሳዬ፤ ተረት ተረት ያልሆነ ተጨባጭ አምክንዮ ነው። በዚህ ዙሪያ ማገናዘቢያ ስለተገኘ ለዓለም ዓቀፍ የሰባዕዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች በሚጻፉ ደብዳቤዎች ላይ መረጃውን በትክክል ማቀበል። ሀገር ውስጥ ለሚቀጠቀጠው ወገንም አጫጭር ጹሑፎችን በማዘጋጀት በዚህ ዙሪያ ተከታታይ፤ ጠንካራና ጫሪ አቀጣጣይ ስሜቶችን አባብሎ ወደ ግንባሩ ማምጣት ይቻላል። ሰራዊት እምለው እኔ ይሄን ነው። ፈንጅም በሉት አዬር መቃወሚያም ሆነ ተዋጊ ጀትም እምለው ይሄን ነው። ለዛውም ቋፍ ላይ ላለ ምልዕትማ ከሚሊዮን ሠራዊት ወይንም የብረት ኳኳቴ በላይ በአጭር ጊዜ ምልዕትን መንፈሱን አሸፍቶ ለድሉ ማብቃት ይቻላል። አንጋጦ ሰማይ ከማዬት መሬት ላይ ያለውን ዕድል በቅጡ አደራጅቶ የመምራት አቅምን ይጠይቃል። ብዕርና ብራና እንዲሁም ሸበላ ድምጽ ብዙ ያተርፋሉ። በጎጥ የተጠቀሙ /የተሰፉ/  ዲሪቶዎችን ሁሉ አመድ የማደረግ አቅማቸውም አንቱ ነው። ከሁሉ በላይ ሰፊው ህዝብ በፋፋ መንፈስ የሚያገኘው ድል የራሱ ነው። የማንም – የምንም ጥገኛ አይሆንም። ተስፋው መዳፉ ላይ አሱን ብቻ ይጠበቃል።

እኔ እላለሁ – ከጠላት የሚመጡ ማናቸውም መረጃዎች ሁሉ ከዜናቸው ቀጥሎ መረጃውን ተንተርሶ የጠላትን አቅም የሚቀጠቅጥ፤ አከርካሪውን እንኩትኩት አድርጎ የሚሳባብር በጉልበታም ድምጽ አጫጭር ጹሑፎች የአዬር ላይ የትምህርት ዜግነት ት/ ቤቶች ናቸውና የዘመኑ ቅኝት በዚህ ላይ ቢያተኩር መልካም ነው።

ጹሑፎቹ ግልጽ፣ አጭር፤ በቀላል አማርኛ የተቀነባበሩ፤ ራህብን ጠረጴዛ ላይ ቁጭ አድርገው የሚያወያዩ መሆን ይኖርባቸዋል። ደቂቃው ቢበዛ አምስት ቢያንስ 3 ደቂቃ መሆን አለበት። ለነገሩ በራዲዮ ፕሮግራም እኮ ከአምስት ደቂቃ በላይ ህጉም አይፈቀድም። አጃቢ ሙዚቃው በሚመለከት ውስጥን የሚያቆላምጥ ግን የሚያስቆርጥ መሆን ይገበዋል ባይም ነኝ።  ብሄራዊነት ወንጀል በሆነበት ሁኔታ ላይ ህዝብን ሆ! ብሎ እንዲነሳ ለማደረግ ከሻንበል፤ ከሻለቃ፤ ከብርጌድ፤ ወይ ከክፍለጦር በላይ አዛዥም ኮከብም ሳይኖር አቶ ራዲዮ መከውን ይችላል። ዜግነታችን ተጠቅጥቋል – ለነገም እንዲጠፋ ተዶልቶበታል፤ ማንነታችን ተረግጧል – ለነገም ስደት ታውጆበታል፤ ክብራችን ተፍቋል ለነገም መቃብር ተቆፍሮለታል። ከዚህ በላይ ሊመጣ የሚችል ነገር የለም – በፍጹም።

መሳሪያ ለሚቆጥሩ፤ የሠራዊትን አቅም ለሚያገኑ ወይንም ለሚያንኳስሱ ወገኖች እኔ የምላቸው መሣሪያ ዬሰው ልጅ ያለው በእጁ ነው። እሱም አንጎሉ ነው። አንጎሉን በሚገባ መምራት ከተቻለ ድሉ በእጅ ነው። የወያኔ ሽንፈቱም አይቀሬ ነው። አለኝ ለሚለው ሠራዊት እሱ ከሚነዛው የጎጥ ፕሮፖጋንዳ ይልቅ ተጨባጩን እንዲተረጉም መንፈሱን ማልማት ከተቻለ አረሙ ወያኔ ባደራጀው  ዬእኔ ባለው ሠራዊት ይቀባራል። ነገር ግን ይህ ከግብታዊነት ሆነ ከበቀል የጸዳን የመምራት አቅምን ሆነ ብቃትን ይጠይቃል። አብዝቶ ማሰብን – ማብሰልንም።

ከዚህ ላይ እንደ ህልም – እንደ ታምር የማዬው አንድ ሀቅ አለ። “የድምጻችን ይሰማ” የአመራር – የክህሎት ተመክሮ – የእውቀት መብለጥ – ብቃት ለእኔ የዘመኑ ፊኖሚናል ነው። እንደ ማንኛውም እንቅስቃሴ በውስጣቸው ፈታኝ ሁኔታወች ገጥሟቸዋል። የወጣት ጆዋር ጉዳይ ብቻም ሳይሆን እሱን ተከትለው የተመዘዙ ህፃፆች። ለንቅናቄው እጅግ ፈታኝ ነበር። መሪዎቻቸው ደጋፊዎቻቸው ተሰቃይተዋል፤ ታስረዋል፤ ተገድለዋል። ግን ተዘናጉ? ተረቱ? ወይንስ ፈረሱ? በፍጹም። በአዲስ መንፈስና ሃይል፤ በብቁ ስልትና በስልጡን አመራር ደምቀው አሉ። የለማ የመንፈስ ሀብታት ባለቤቶች ስለሆኑም በአኃታዊነት ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም ትጉሃን ናቸው። አቅም አይባክንም ወይንም ሲሾልክ አይታይም። የሚገርመው ነገ ሰላማዊ ሰልፍ ከኖራቸው እንዲቀር ሰልፉ ሌሊት ቢወሰን በተቆረጠው ሰዓት አንድም ሰው በሰልፉ ቦታ ዝር አይልም። በምን ታምር ይህን እንደሚከውኑት ጥበቡ ልቅናው ዘሊቅ ነው። መሪና ተመሪ በትክክል በእትብት የተገናኙበት ከድንቅ በላይ አመክንዮ ነው – ለእኔ። ለእኔ ይህ ንቅናቄ ተስፋዬን የሚያለምልም ንጹህ አዬሬ ነው። ልንማርበት የሚገባ የተግባር ተቋም። ዘመኑ መማሰን ያለበት ተመክሮውን እንደ አንድ የልምድ ማዕከል ማደረግን ነው።

እኔ በግሌ እምመኘው እንዲህ ዓይነቱ፣ ፍጹም የላቀ አዎንታው የአዛዥና የታዛዥ የፍላጎት አዎንታዊ ጋብቻን ነው። ወይንም የመሪና የተመሪ አዎንታዊ የራዕይ ጋብቻን ነው። ይህን ለማምጣት ደግሜ – ደጋሜ እምገልጸው ነገር እራሰን አሸንፎ ለማደር መቁረጥና መወሰንን ነው። ስልቶቻችን – ሂደቶቻችን በመመርምር ወቅቱን ያዳመጠ፣ ከዘመኑ ጋር ሊሄዱ የሚችሉ ፈጠራዎችን አክሎ አዲስ መስመርን መከተል የነፃነት ትግሉ ያለበት ይመስለኛል።

የሠራዊት ሆነ የመሳሪያ ብቃት መለኪያው ለእኔ መንፈስን የማልማትና ለማብቀል ዝግጁ የማደረግ በእንግሊዘኛው /ፈርታይል/ መሆኑን ነው። ይቅርታ ፎንቱን ቀይሬ በእንግሊዘኛ አልፋቤት ለመፃፍ ለጊዜው አልችልም። /ፈርታይል/ መደረስ … ሴት ልጅ ልትጸንስ የምትችልበት ጊዜ አላት። የነፃነት ትግሉም ጊዜና ወቅት እንዲሁም ፈቃደ እግዚአብሄርና ቀን ያስፈልጋቸዋል። ቅድመ ሁኔታውን ማሟላት ደግሞ የሁላችንም ግዴታ ነው። ወቃሽም ሆነ ተወቃሽ ሊኖር አይገባም። የጎደለውን መሞላት የሁላችንም ነው። እንደ እኔ ፊት ለፊት ወጥተው ከጠላት ጋር በማናቸውም ዘርፍ ለመታገል የቆረጡ ሁሉ ሊደገፉ፤ ሊበረታቱ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል። ተከፍሎት የሚሰራ የለም። አብዛኛው ነፃ አገልግሎት ነው የሚሠጠው። ካላ ቋሚ የፖለቲካ ሠራተኛ ወይንም ፋንክሽነሪ የነፃነት ትግል ጉዙ ረጅም መሆኑንም መቀበል ያለብን ይመስለኛል።  ይህም ቢሟላ እንኳን በጎጥ የተደራጀን መንፈስ አሸንፎ ህዝባዊነትን ለማምጣት የሰከነ ትዕግስት – በማስተዋል የተቀመመ ተግባር ይጠይቃል።

በተረፈ የኔዎቹ አብርሽ በዘሃበሻ የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢሳት ምርጥ ሰውነታቸው ድምጽ ስላገኘ ደስ ብሎኛል። ጀግና አልጋነሽ ገብሩ ደግሞ ልጆች ት/ቤት ከመጀመራቸው በፊት መፈታቷ ሰላም ሰጥቶኛል። በተረፈ ሳይታክቱ ሌትና ቀን የአራዊትን ግፊያና ግልማጫ ችለው የሚሰቃዩትን የእስረኛ ቤተሰቦች፤ የትዳር አጋሮች፤ ልጆች፤ ደጋፊዎች፤ ጠያቂዎች ሁሉ ላደረጋችሁት መልካም ነገር ሁሉ ምስጋናዬን ሆነ አክብሮቴን ሸልሜ የልቤን የሚያደርስልኝን ዘሃበሻ ዝቅ ብዬ አመስግኜ ልሰናበት። መሸቢያ – ሰንበት።

 

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

አዲስ አበባ የሚታተመው ”አዲስ አድማስ ጋዜጣ” ቅዳሜ መስከረም 17፣2007ዓም የሰሞኑን የኢህአዲግ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ስልጠና የዳሰሰበት ሊነበብ የሚገባ ፅሁፍ።

$
0
0

Addis_Abeba_University_(Sam_Effron)በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የህግ ተማሪ የሆነው አቤል ስሜ መንግስት ካለፈው ነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባዘጋጀው የ15 ቀናት ሥልጠና ላይ ተሳትፏል፡፡ በቴሌቪዥን የተላለፈው ማስታወቂያ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ ዩኒቨርስቲ ተመዝገቡ የሚል ስለነበረ በሚኖርበት ከተማ በሚገኘው አምቦ ዩኒቨርሲቲ መመዝገቡን የገለፀው አቤል፤ ለ15 ቀናት የሚዘልቅ ሥልጠና ላይ እሳተፋለሁ ብሎ እንዳልጠበቀ ይናገራል፡፡ አቤል ለስልጠና የተመደበው አቃቂ በሚገኘው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን አልጋና ቀለብ እንዲሁም ትራንስፖርት በዩኒቨርሲቲው እንደተሸፈነላቸው ለአንዳንድ ወጪዎች ተብሎም 400 ብር እንደተሰጣቸው ጠቁሟል፡፡ የመጀመሪያዎቹ በርካታ ቀናት ስልጠና በኒዮሊበራሊዝም ርዕዮተ – ዓለም ላይ ያተኮረ እንደነበረ ያስታወሰው ተማሪው፤ የኒዮሊበራሊዝም ውድቀት በተለያዩ አገራት ማሳያነት በስፋት እንደተብራራላቸው ይናገራል፡፡

እኔን ጨምሮ በርካታ ተማሪዎች ስለጉዳዩ ምንም ግንዛቤ አልነበረንም ያለው አቤል፤ ከስልጠናው በኋላ በገባን መጠን ጥያቄዎችና አስተያየቶች አቅርበናል ብሏል፡፡ በስልጠናው የተነሳው ሌላ አጀንዳ ልማታዊ መንግስትና አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚል ነበር ያለው ተማሪው፤ በዚህ ስልጠና ከአፄዎቹ ስርአት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ሃገሪቱ የተጓዘችበት ውጣ ውረድ መዳሰሱን ጠቁሟል፡፡ በዚህ ርዕሰጉዳይ መነሻነት በርካታ ፈታኝ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተማሪዎች መነሳታቸውን አቤል ይገልፃል፡፡ ከተነሱት ጠንካራ ጥያቄዎችና አስተያየቶች መካከልም “ልማቱ ስራ አጥነትን በመቅረፍ ረገድ ምን ውጤት አመጣ?” “የተማረው ኃይል ስራ አጥ ሆኗል፣ ሃገሪቷም ጥቅም ማግኘት አልቻለችም፤ ይሄም በአጠቃላይ ሃገሪቱ የምትመራበት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ችግር ያመጣው ነው” የሚሉ ይጠቀሳሉ ብሏል – አስተያየት ሰጪው፡፡ በተለይ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች በስራ አጥነት እንደሚንገላቱ በመጥቀስ መንግስት ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት የተጓዘባቸውን መንገዶች አምርረው እንደተቹ አቤል ይናገራል፡፡ ዲግሪ ይዘው ድንጋይ ጠራቢ የሆኑ ተማሪዎች እንዳሉ በመጥቀስም ሃገሪቱ በቂ የተማረ ሰው ኃይል በማፍራቷ ነው ወይ የተማረው ረክሶ በእውቀቱ ሳይሆን እውቀት በማይጠይቅ ሙያ ላይ እንዲሰማራ የተገደደው? የሚሉ ጥያቄዎች መሰንዘራቸውንም አስታውሷል፡፡

ከተማሪዎቹ ከቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ አሰልጣኞች ለአንዳንዶቹ ተገቢ ማብራሪያና ምላሽ እንደሰጡ የተናገረው አቤል፤ ጥቂት የማይባሉ በቸልታ የታለፉ ጥያቄዎች እንደነበሩም አልሸሸገም፡፡ በተለይ ሰፊ የመወያያ አጀንዳ በነበረው በፌደራሊዝም ጉዳይ ላይ ለቀረቡ አንኳር ጥያቄዎች መልስ አልተሰጠም ብሏል፡፡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛው ዙር የተሰጠውን ስልጠና የዲላ ዩኒቨርሲቲ የ1ኛ ዓመት የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ተማሪ ሄለን ጉርሜሳ፣ ስልጠናው በአመዛኙ በጥያቄና አጨቃጫቂ ውይይቶች የተሞላ እንደነበር ትገልፃለች፡፡ በተለይ ያለፉት ስርአቶች ታሪክ እየተመዘዘ በንፅፅር መልክ ሲቀርብ፤ ተማሪዎች ንፅፅሩ ምን ጠቀሜታ አለው? የሃገሪቱን ታሪክ ማበላሸት አይሆንም ወይ? እንዲህ ያለው ጉዳይ የብሄርና ጎሳ እንዲሁም የሃይማኖት ግጭት ሊቀሰቅስ ይችላል፣ ቂም በቀልንስ አይቀሰቅስም ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በስፋት እንደቀረቡ ታስታውሳለች፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከሰቱ ብሄርንና ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች፤ በተማሪዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል የምትለው አስተያየት ሰጪዋ፤ በተለይ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተነስቶ በነበረው ግጭት የሞቱ ተማሪዎችና ሰዎች ጉዳይ መጣራትና ወንጀለኞችም ፍርድ ማግኘት እንዳለባቸው ተማሪዎቹ አጥብቀው ጠይቀዋል ብላለች፡፡ አንዳንድ ተማሪዎችም በመምህራን የትምህርት አሰጣጥ ዘይቤና የፈተና ውጤት አያያዝ ላይ ያላቸውን ቅሬታም እንዳቀረቡ ታስታውሳለች፡፡

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት ተማሪ የሆነው አስቻለው ብርሃኔ በበኩሉ፤ ስልጠናው ሙሉ ለሙሉ ከፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር የተገናኘ መሆኑን ባይወደውም በየመሃሉ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት አሰጣጥና ከተማሪ ውጤት ነጥብ አያያዝ ጋር በተገናኘ በተማሪዎች የተነሱት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ባይሰጥባቸውም ጠቃሚ እንደነበሩ ይነገራል፡፡ በአንዳንድ የስልጠና መድረኮችም አሰልጣኞች ያልጠበቋቸውና ፈታኝ የሆኑ ጥያቄዎች ከተማሪዎች መቅረባቸውን ምንጮቻችን ጠቁመውናል፡፡ “የፀረ ሽብር አዋጁ ተቃዋሚዎችን ለማፈን ነው የወጣው ይባላል…” “ኢህአዴግ ከስልጣን የሚወርደው መቼ ነው?” የሚሉና ሌሎችም እንደተነሱ ለማወቅ ችለናል፡፡ በአለማያ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ስልጠና በአዲስ አበባ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የቆመውን የምኒልክ ሃውልት በተመለከተ ከተማሪዎች ጥያቄ መነሳቱን የጠቀሱት ምንጮች፤ ምኒልክ የኦሮሞን ህዝብ ጨፍጭፈው ሃውልታቸው መቆሙ ተገቢ አይደለም የሚል አስተያየት ተሰንዝሯል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል መንግስት ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያዘጋጀውን ሥልጠና በተመለከተ ተቃዋሚዎች በሰጡት አስተያየት የአንድ ፓርቲን አመለካከት ለማስረፅ የተዘጋጀ ነው ሲሉ ተቃውመውታል፡፡ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፤ ስልጠናው በግዴታ መሆኑ የሰዎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲዊ መብት የሚጥስ ነው ብሏል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ጉዳዩን አስመልክቶ ለአዲስ አድማስ አስተያየታቸውን ሲሰጡ፤ “ስልጠናው ታቅዶበት የተከናወነ ሳይሆን ድንገት ደራሽ ነው፣ በስልጠናው ያልተሳተፉ ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርት እንደማይቀጥሉ የሚያስጠነቅቅ፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብትን የሚደፈጥጥ ነው” ብለዋል፡፡ ወደ ከፍተኛ ትምህርት የሚገባው በትምህርት ብቃት እንጂ በዚህ መልኩ ተጣርቶ መሆን የለበትም የሚሉት ኢ/ር ግዛቸው፤ ተማሪዎች ያላቸውን አስተሳሰብና አመለካከት የመያዝ መብታቸው ሊጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ለዚህ መሰሉ ስልጠና የመንግስትን መዋቅርና ንብረት መጠቀም እንደማይገባ የሚናገሩት ኢ/ሩ፤ ይሄ የመንግስትና የህዝብ ሃብት ብክነት ነው ባይ ናቸው፡፡ ስልጠናው ውጤታማ አለመሆኑን ካሰባሰብናቸው መረጃዎች ለመረዳት ችለናል ያሉት ኢ/ር ግዛቸው፤ ስልጠናው ይበልጥ ኢህአዴግን ያስገመገመ እንደነበር ጠቅሰው የግምገማው ውጤትም አስከፊ እንደሆነ ተረድተናል ብለዋል፡፡ የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ በበኩላቸው፤ የስልጠናው መንስኤ “በገዥው ፓርቲ በኩል ያለው ፍርሃትና ጭንቀት ነው” ይላሉ፡፡ ስልጠናው ተማሪዎቹ እንዴት ማጥናትና መማር እንዳለባቸው ቢሆን ኖሮ ሁሉም የሚደግፈው ሰናይ ተግባር ይሆን ነበር የሚሉት አቶ አበባው፤ ከዚህ ይልቅ የአንድን ፓርቲ አመለካከትና አስተሳሰብ አዳምጠው እንዲወጡ ነው የተደረገው፤ ይህ ደግሞ ለሃገር የሚጠቅም አይደለም ሲሉ ተችተዋል፡፡

በስልጠናው ወቅት የሚወጣው ወጪም ህግን የጣሰ ነው የሚሉት አቶ አበባው፤ ህጉ “የመንግስት ንብረትና ሃብት ለምርጫ ቅስቀሳ ወይም ለፖለቲካ ስራ አይውልም” እንደሚል ጠቁመዋል፡፡ ገዥው ፓርቲ ይህን ድንጋጌ ጥሶ የመንግስት ሃብትን ለግል ጥቅሙ እያዋለ ነው ሲሉም ከሰዋል፡፡ “ስልጠናው በተማሪዎች ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን ዜጎችን በአጠቃላይ አፍኖ ለመያዝ የሚደረግ ጥረት በመሆኑ ወደ ሌሎች ዜጎችም እየወረደ ነው” ብለዋል አቶ አበባው፡፡ በየስልጠና መድረኩ ያለፉ ታሪኮች እየተመዘዙ ትችት ማቅረቡና ታሪክ ማዛባቱ ተገቢ አይደለም የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፤ እነዚህ ጉዳዮች በየስልጠና መድረኮቹ አከራካሪ ሆነው ጎልተው መውጣታቸውን ካሰባሰቡት መረጃ መረዳታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ተማሪዎቹ ባነሷቸው ጠንካራ ጥያቄዎች ምክንያት ከአሰልጣኞቹ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብተው እንደነበረም አቶ አበባው ይገልፃሉ፡፡

ለተማሪዎቹም ሆነ ለመምህራኑ የተዘጋጀው ስልጠና ሃገሪቱን የሚያስተዳድሩ ሰዎች ለሃገሪቱ በሚገባ የማያስቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው የሚሉት የመድረክ አመራር አቶ ገብሩ ገ/ማርያም፤ ለዚህ ጉዳይ በይፋ የተመደበ በጀት ሳይኖር በስልጠና ስም የህዝብ ሃብት ማባከንና የአንድ ወገን አስተሳሰብ ለማስተላለፍ መጠቀም ነውር ነው ብለዋል፡፡ የአንድን ወገን የፖለቲካ አመለካከት በወጣቶች አዕምሮ ውስጥ ለማስረፅ የሚሰጥ ስልጠና ትውልድንም ሃገርንም አጥፊ ነው ያሉት አቶ ገብሩ፤ “እኛ ለዚህች ሃገር እንዲፈጠር የምንፈልገው በራሱ የሚተማመን፣ ራሱ የሚያስብ፣ ራሱ ጠይቆና አንብቦ የሚረዳ፣ ለጠየቀው ጥያቄ ተገቢ መልስ ማግኘቱን የሚያረጋግጥና ሀገር መምራት የሚችል ወጣት ነው፡፡” ሲሉም አስረድተዋል፡፡ “ስልጠናው የታለመለትን ግብ አልመታም” ብለው እንደሚያምኑ የገለፁት አመራሩ፤ በአንዳንድ መድረኮች ባለስልጣናት መልስ መስጠት እስኪያቅታቸው ድረስ በጥያቄ የተፋጠጡበት፣ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መርህ ይበልጥ የተፈተሸበት፣ መንግስት ከጠበቀው ውጤት የተለየ ተቃራኒ ውጤት የተመዘገበበት የስልጠና ሂደት መሆኑን እንደተረዱ ጠቁመዋል፡፡

በአጠቃላይም ስልጠናው አስቀድሞ የታቀደበት አለመሆኑንና ምርጫውን ታሳቢ ያደረገ፣ የግራ መጋባት ውጤት እንደሆነ አቶ ገብሩ ተናግረዋል፡፡ በአሠልጣኝነት ተሣታፊ የነበሩት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እውነቱ ብላታ በበኩላቸው፤ ስልጠናው ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ምርጫን ታሳቢ ያደረገ ሳይሆን ታቅዶና ታስቦበት የተካሄደ ነው፡፡ በስልጠናው ሂደትም መንግስት የመልካም አስተዳደር ችግሮች መኖራቸውን የተረዳበትና ለቀጣይ የእርምት እርምጃዎች አጋዥ የሆኑ ግብአቶችን ያገኘበት እጅግ ስኬታማ ስልጠና እየተከናወነ ነው ብለዋል – አቶ እውነቱ፡፡ አክለውም ስልጠናው በግዴታ ነው የተካሄደው የሚለው ሃሰት መሆኑንና በሠልጣኞች ውዴታና ፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ መስከረም 17፣2007ዓም (27 September, 2014)

Source:: gudayachn

መነገር ያለበት ቁጥር 7 የክፍፍላችን ገጽታ

$
0
0

በልጅግ ዓሊ

ባለፈው ዓመት ሃገራችንንም በሚመለከት አስደሳችም፣ አስከፊም፣ አስደናቂም፣ አናዳጅም ተግባሮች ተፈፅመዋል። አሮጌው ዓመት ለአዲሱ ዓመት ቦታውን ሲለቅ ፈጣሪ አምላክ አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የፍቅር፣ የመግባቢያና ችግሮቻችንን ሁሉ የምንፈታበት ዓመት ይሁን ማለታችን አልቀረም። ግን የዚህ ምኞታችን ፍፃሜ ከቅርብነቱ ሩቅነቱ በክፍፍላችን ምክንያት የጎላ ነው። አንዳንዶቹ ቅራኔዎቻችንን መፍትሔ ለማግኘት ስናጠናቸው የችግሩን መንስዔ ለማግኘት እንኳን የተጠላለፉ በመሆናቸው በጣም የሚያስቸግሩ መሆናቸውን እንረዳለን። በትልቁ ፆም አጋማሽ ዕለት ጀርመን ፍራንክፈርት ላይ የተመለከትኩት ሁኔታ በእኔ ዘንድ በዓመቱ ከታዘብኩት ክስተቶች ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ ይዟል። ይህ የክፍፍላችን አንዱ ገጽታ ነው።

ደብረ ዘይት . . . ግማሽ ፆም

ይህ የተፈጸመው የግማሽ ፆም ዕለት ነው። የዐብይ ጾም አጋማሽ። ዘወትር በዕለተ እሁድ የምናስቀድስባቸው ቤተ ክርስቲያኖች ፍራንክፈርት አካባቢ ይገኛሉ። ወደ ቤተ ክርስቲያኖቹ ለመሄድ ከየቦታው በባቡር የመጣው ሕዝብ ፍራንክፈርት ባቡር ጣቢያ በተመሳሳይ ሰዓት ይገናኛል። ከዚያም ሁሉም በአንድነት ከባቡር ጣቢያው ፊት ለፊት ከሚገኘው የከተማ ውስጥ የመንገድ ባቡሮችን(ትራም ወይም በጀርመን ስታራሰን ባን) ለመሳፈር እንሰባሰባለን። የተለመደው የዜጎቻችንን የፍቅር ሰላምታ ይቀጥላል።

ደህና ነሽ ፣ ደህና ነህ ? . . . ምነው ጠፋሽ ? ምነው ጠፋህ ? ትከሻ ለትከሻ መጋጨት . . . አምሮብኻል ምን ተገኘ ? . . . አምሮብሻል ? . . . እንዴ ልጅሽ አደገ አይደለም እንዴ? . . . ጎረመሰ እኮ ? . . . ትልቋ ልጅሽ? አልመጣችም እንዴ ? እንቅልፍ ይዞት አልመጣ አለች . . . የዘንድሮ ልጆች መች እሺ ይላሉ . . . ሥራ እንዴት ነው? ሃገርቤት ሄደህ ነበር እንዴ ? . . አዎ ሰሞኑን ነው የተመለስኩት . . እንዴት ፋሲካን ሳትውል? . . . ፍቃድ አልነበረኝም ፣ ቶሎ ተመለስኩ ። ሃገር ቤት እንዴት ነው?. . . ፆም ሃገር ቤት ነው እንጂ ፣ በዚያ ዓይነት ልዩ ልዩ የፆም ወጥ እየተፆመ፣ ፆም አይባልም.። እንደሱ ከሆነ ዘላለም በፆምኩ . . . ባክሽ አትስጎምዢኝ . . . ሰላም ነው ? . . ሰላም ነው ። .

ባቡሩን የምንጠብቅባት ትንሽ ደቂቃ ነች።“ፍቅር“ በጣም የበዛባት ትመስላለች። አንዱ ሌላውን አቋርጦ ሰላም ይላል፣ ጥድፊያም አለ፣ አንጠፋፋ እንገናኛ . . . የውሸት ቀጠሮም ብዙ ነው። ስልክ ቁጥር ሳይሰጣጡ እንደዋወል መባባሉም አለ. . . ። አንዳንዱ የድሮ ጓደኝነትን በማሰብ መፎጋገር ይመስላል። መቼን ያልጨመረው እንገናኛ የሚለው ቀጠሮ ለመገናኘትን ያለመፈለግን ያሳብቃል።

በዛች ትንሽ ደቂቃ ሁሉም ለሁሉም “ፍቅሩን“ ያሳያል። በአሁኑ ወቅት ዜጎቻችን ሳይነጣጠሉ በአንድነት የሚገናኙበት ቦታ ይህቺ ባቡር ጣቢያ ብቻ ትመስላለች ። ምንአልባት ከለቅሶ በስተቀር። ያውም አስከሬን ከቤት ከወጣ። ሠርግ እንኳን እንደ ድሮው አይደለም። የተወሰኑ የሚስማሙ ብቻ ናቸው የሚጠራሩት። ጎረቤት ስለሆንኩ ሠርግ እጠራለሁ ማለት አይቻልም። ለምሳሌ የወያኔ ተቃዋሚ ከሆንክና የኤምባሲ ሰዎች ከተጠሩ የመጋበዝህ ጉዳይ የመነመነ ነው። የወያኔ የዘር ፖለቲካ የሠርግ ግብዣ ላይ ብዙ ችግር ፈጥሯል። ለስደተኛነት የሰጠኸውን ምክንያትም ለሠርግ ጋባዥነትም ሆነ ተጋባዥነት ምክንያት ሊሆን ይችላል። ልደት፣ ክርስትና ሌሎችም ድግሶች ለዜጎቻችን መገናኛነታቸው ካከተመ ሰንብቷል። ለምሳሌ የዲያስፖራ “ኢንቬስተር“ መሰሉን ነው የሚፈልገው። “ከኢንቬስተርነቱ“ በፊት የነበሩትን ጓደኞቹን የረሳ ብዙ ነው።

የባቡር መምጣት የመለያየቱን ጊዜ እንደ ደረሰ አበሰረ። የሰላምታው ጥድፊያ በባቡሩ መምጣት ተቋረጠ። መጀመሪያ የመጣው 16 ቁጥር ባቡር ነበረ ። የተወሰኑት ዜጎቻችን ወደ ባቡሩ ገቡ ። ያ ደስ የሚል አንድነት ተበጠበጠ። በዚህኛው ባቡር የተጓዙት ወደ ማርያም ቤተክርስቲያን የሚሄዱት ነበሩ ። የፍራንክፈርቱ ማርያም . . . ከአዲስ አበባው ሲኖዶስ ጋር የተያያዘ ሲሆን አብዛኛው ተሳፋሪ ምንም እንኳን ወያኔን የሚቃወሙ የማርያም ወዳጆች ቢገኙበትም በመንግሥት ደጋፊነት የሚጠረጡሩ ናቸው። የታየው “ፍቅር“ ግን አልጠናም። እነርሱ ከሄዱ በኋላ ሐሜት ተጀመረ. . . ። ቀሪዎቹ ባንድነት ሆነን ቀጠለን። ጭውውቱ እንደገና ጦፈ።
– ዛሬ ማሪያም አትሄጂም እንዴ? . . .
– አይ ዛሬ ገብርኤል ነው የምሄደው።
– አንቺሽ ? እኔ መድኃኔዓለም ነው እኮ ሁል ጊዜ የምሄደው።
– ምን ልዩነት አለው ሁሉም ጋር ከልብ መፀለዩ ነው።
– አለው እንጂ አሁን ማርያም የሄዱት አታይም እንዴ ?
– ብዙዎቹ እኮ ሃገርቤት ቤት የሠሩ ናቸው ይባላል። ካለ ማርያም ሌላ ቤተክርስቲያን ከሄዱ ቤታችን ይወረሳል ብለው ይፈራሉ።
– ማነው ደግሞ የሚወርሳቸው? ይህ መንግሥት ተደራጅተሽ አትቃወሚ እንጂ ምን እንዳያደርግሽ ?
– ብዙዎቹ የሰሜን ሰዎች አይደሉም እንዴ ወደ ማርያም የሚሄዱት?
– እሱማ የታወቀ ነው ።
– ቄሱ ከሰሜን ናቸው እኮ።
– ለመሆኑ አሁን ሰላም ነው እንዴ ማርያም?
– የሙኒኩ (የሙንሽኑ) ቄስ መስፍን 150 ሽህ ኤሮ ከቦደሰ በኋላ እኚህኛውን ማን ተናግሯቸው። ይባስ ብለው ይህንን ሁሉ ገንዘብ የሰረቀውን ቄስ ታቦት አሽከሙት አይደለም እንዴ ባለፈው ጊዜ?
– እኛ ምን አገባን ፈጣሪ አምላክ ሁሉንም የሚመለከት ይፍረድባቸው እንጂ . . . ። ፈራጅ አንድ ፈጣሪ ነው። በእሱ ሥራ ገብተን መፈትፈት የለብንም። እኔ እንደሆንኩ የማራያም ቀን ማርያም፣ የገብርኤል ዕለት ገብርኤል፣ የመድኃኔዓለም ቀን መድኃኔዓለም እሄዳለሁ።

የማርያምን ቤተክርስቲያን ጉድ ስንሰማ ቆየን ። ሌላ ባቡር ደግሞ መጣ። የሚቀጥለው 11 ቁጥር ባቡር ነበረ። የተወሰኑ ዜጎቻችንን ተሳፈሩ። አሁን ደግሞ ሃሜቱ ተቀየረ። የማሪያሙ ቀርቶ የገብርኤሉ ተጀመረ።

– ድሮ እኮ ከእኛ ጋር ነበሩ። ከመድኃኔዓለም ተገንጥለው እኮ ነው ገብርኤልን ያቋቋሙት።
– እኚህ ወጣቱ መነኩሴ ለራሳቸው ሲሉ ነው እኮ የከፋፈሉን፣ እንጂ ሕዝቡማ አንድ ነው።
– ልክ ነሽ ።ብዙዎቹ እኮ አሁንም መድኃኔዓለም ይመጣሉ።
– ለመሆኑ ለምንድነው የተከፈሉት ?
– ለነገሩማ ገብርኤሎች ከሁለቱም ሲኖዶስ አንሆንም ብለው ነው ይባላል። ገለልተኛ ነን ባይ ናቸው። ግን ሕዝቡ ነው እንጂ ገለልተኝነትን የፈለገ፣ ወጣቱ መነኩሴ እንኳን እንጃ።
– አንድ ቀንማ እንደባለቃለን። ሕዝቡ አንድ ዓይነት አመለካከት ነው ያለው።
– የረባ ሽማግሌ ጠፍቶ ነው እንጂ ሊታረቁ የሚችሉ ነበሩ። ምንም ልዩነት የለንም።
– እግዜር የፈቀደ ቀን ይሆናል። መቼም እንዲህ ሆነን አንቀር።

ይህንን ስንባባል የእኛም 17 ቁጥር መጣና ተሳፈርን እና ወደ መድኃኔዓለም ጉዞ ጀመርን። በሌሎቹ ባቡሮች ስለኛ ምን እንደተባለ ባልሰማም፤ መባሉ ግን እንደማይቀር መገመት ይቻላል። ያው ወያኔዎች እንዳስወሩት ፖለቲከኞች ናቸው መባሉ አይቀርም። ምክንያቱም ወያኔን በቆራጥነት የሚታገሉ በዚህ ቤተክርስቲያን በብዛት ይገኛሉና ነው።

ገና አንድ የባቡር ማቆሚያ እንደ ሄድን አንድ የኛ ዜጋ ንብረት ከሆነው ቡና ቤት ፊትለፊት ደረስን። ቁጥራቸው በዛ ያሉ ዜጎቻችንን ቡና ቤቱ አድረው ሲወጡ በቡጢ እንካ ቅመስ ይባባላሉ። ጠርሙስ ከአንዱ ወደ ሌላው ይወረወራል ። ከቡና ቤቱ ውስጥ የሚወጡ ወጣት ሴቶች ይታያሉ ። እነርሱን የከበቡ ወጣት ወንዶችም አሉ። ልቀቁኝ፣ ልቀቀኝ ግልግሉ ብዙ ነው። ጃኬቱን ጥሎ ለጠብ የሚከንፍም አለበት። ጫማዋን አውልቃ በእጇ የያዘች ሴትም ትታያለች። አካባቢው ድብልቅልቅ ብሏል። ባቡሩ መብራት ይዞት ቆመ። እኛም የሚያሳዝነውን ትዕይንት ማየት ቀጠልን።

የፖሊስ መኪና ጩኸት በሩቅ ሲሰማ ጎረምሳው ተበታተነ።

ባቡር ውስጥ ያለነው ተሳፋሪዎች ጨዋታ ተቀየረ ።
– ፍራንክፈርት በጣም ተበላሸ እኮ ።
– ድሮኮ አበሻ እንደዚህ ዓይነት አሳፋሪ ተግባር አያደረግም ነበር ።
– ቆይ ታያላችሁ አሁን የጀርመን መንግሥት መቀበል ያቆማል።
– እነዚህ እኮ በሰሃራ በኩል የመጡት ናቸው ። እዚያ ያዩት መከራ ጨካኝ አድርጓቸዋል እኮ!
– ጥሩ ኮሞኒቲ ቢኖረን እነዚህ ልጆች መምከር ያስፈልጋል።
– ኮሚኒቲው እማ የወያኔ ሰው ነው የሚመራው ይባል የለም እንዴ?
– እኛ ጥለን ስለሄድንለት ነዋ ? ደግሞም አሁንም ደህና ደህና ሰዎች ኮምኒቲው ውስጥ አሉበት እኮ። ለወያኔ ጥለን አንሄድም ብለው የሚታገሉ።
– ሊቀመንበሩ ከወያኔ ኤምባሲ አይወጣም ነው የሚባለው።
– የስደተኛው ኮሚኒቲ መሪ ከወያኔ ጋር ምን ይሰራል?
– እረ ዝም በይ፣ ሃገር ቤት ትሄጂ የለም እንዴ?
– ብሄድስ ለእሱ ብዬ ልፈራ ነው እንዴ? አፍሽን ዝጊ።
– በይ ተይው ጎመን በጤና አለ አሉ ፀሐዬ። አሁን ደግሞ እዚያ ውስጥ ማን ገብቶ ይጨቃጨቃል። እንደፈለጉ ያድርጉት ።
– ከእነዚህ ከሚረብሹት መሸሽ ነው። አሉ አንድ ሸምገል ያሉ አዛውንት። አገላለፃቸው እውጭ ሆነው ጠቡን ሊገላግሉ ቢገቡ ግፍትሪያው የፈሩ ይመስል።
– እነዚህ የሚደባደቡት እኮ ድራግ (ዕጽ)ሽያጭ ውስጥ አሉበት እኮ ።
– ውይ በሞትኩት አበሻ ድራግ ውስጥ ገባ እንዴ ? አበሻ አለቀላት ማለት ነው ። አለች አንዷ አፏን በማጣመም ፣ እንደ ማሽሟጠጥ።
– ቆይ ታያላችሁ! ጀርመኖች ቀላል አይደሉም እየለቀሙ ነው የሚያስወጧቸው ። አለ አንዱ ።
– እኔ መቼም እነዚህ የጀርመን መንግሥት ሊያስወጣቸው ነው ቢባል እንደ ሳውዲ ጊዜ ሰልፍ አልወጣም። እነዚያ እኮ ምስኪኖች ናቸው።

በዚህ በዚያ ስናማም ስንታማም መድኃኔዓለም ደርሰን ልባችንን ለእግዚአብሔር ሰጠን። ቅዳሴው ላይ ምንድነው እንዚህ ወጣቶች እንዲህ ጨካኝ ያደረጋቸው ብዬ አሰብኩ።

ለነገሩ ሱዳንን ፣ሰሃራ በርሃን ፣ ሜዲትራንያንን ፣ የመጡበትን ጀልባ ፣ ከመስመጥ እንዴት እደተረፉ ላየ ሰው እነዚህ ወጣቶች እንዲዚህ ዓይነት ሁኔታ ላይ ቢገኙ ላይፈርድ ይችላል። ግን ሁኔታው ደግሞ የተለየ ነው። ሮማ ኮለንቲናና አነኒና የሚባሉ ሕንጻዎች ውስጥ ስለሚነሳው ጠብ የነገረኝ አንድ ወንድም ታናሽ ብዬ የምጠራው በሳህራ አቆርጦ ጣሊያን የደረሰ ወጣት ነበር። ምንድነው ዜጎቻችንን እንዲህ ጨካኝ ያደረጋቸው? ብዬ ለጠየቅሁት እንዲህ ብሎ አጫወተኝ።

“ወንድም ታላቅ አትሳሳት እዚህ የሚቧቀሱት ምን ዓይነት ፈሪ እንደሆኑ ልንገርህ አልችልም። እኔ ሱዳንም ሊቢያም አውቃቸዋለሁ። አንተም ቱኒዚያ፣ ጣሊያንና ጀርመን አይተሃቸዋል። ለመሆኑ ቱኒዚያ ውስጥ ሲጣሉ አይተሃል? ምን ያህል ተለዋዋጭ እንደሆንን መናገር ይከብዳል። ፈሪዎች ነን። እዚህ እንደ ጀግና ስንጣለዝ የምታየን ሊቢያና ሱዳን፣ በተለይ ሰሃራ ውስጥ ምን ያህል ቦቅቧቃ እንደሆንን ታውቀዋለህ። አንድ ዐረብ ሊቢያዊ መንገድ ላይ ሲደበድበን ችለን ነው የምንመጣው። የሴት ጓደኛችንን ዓይናችን እያየ ሲነጥቁን ዝም ነው የምንለው። ናይጀሪያዊው፣ ሱማሌው፣ ሌላው አፍሪካ ለመብቱ ሲታገል እኛ ግን ያ ሁሉ በደል ሲደርስብን ዝም ነው የምንለው። የኛ ጀግንነት የሚጀምረው ጣሊያን ላምባዱሳ ላይ ነው። ሕግ መኖሩን ስናውቅ ሕግ ለመጣስ አንደኞች ነው። ድብድባችን ደግሞ የሚጀምረው እርስ በራሳችን ነው። የምናሳዝን ሰዎች ነን። ለመተባበር አልፈጠረንም፣ ለመከፋፋል እንቸኩላለን ። አለኝ።

ይህ ሲጽፉት የሚከብድ እውነት ነው። በዚህ ዓመት ከፍራንክፈርት ከተማ ውስጥ በዜጎቻችን በሃያ ዓመት ከተሰራው ወንጀል በላይ ተሰርቷል። በሆላንድ ፣ በቅርብ በሙኒክ እና በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የጦፈ ድብድቦች ታይተዋል። በኢጣሊያን በስደተኞች መኖሪያ አካባቢ በየቀኑ ድብድብ ይታያል።

በተለይ በአስቸኳይ ሃብታም ለመሆን ወጣቶቹ ካደረባቸው ፍላጎት አንጻር ብዙ ብዙ ወንጀሎችን እየተፈጸሙ ነው። ይህ ከዕጽ ጋር የተያያዘ ወንጀል ወጣቶቹ ከሃገር ቤት ጀምሮ የተማሩት እንደሆነም ይነገራል። ስለ ትምህርት ያላቸው አመለካከት የደከመ ነው። ሠርቶ ራስን ማሳደግ በአንዳንዶቹ መሃል ጥያቄ ውስጥ አይገባም። ዛሬ ወያኔ ከፈጠረብን ትልቁ ችግር አንዱ ይህ ነው።

እነዚህ በጣም ጥቂት የሆኑ ጋጠ ወጥ ወጣቶች ሕግ አክባሪዎች ናቸው ተብሎ ለእኛ የተሰጠንን ጥሩ ስም እያጠፉት ነው። ይህ ደግሞ የሃገሩ መንግስት በእኛ ላይ እንዲጨክን ሊያደርግ ይችላል። በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ ንፁሃን እንደሚጎዳ ግልጽ ነው። ችግሩ ንጹሁን ከመጥፎው ከመለየቱ በፊት ኢትዮጰያውያን እንዲህ አደረጉ መባሉ ብቻ በጀርመኑ ሕብረተሰብ መካከል ጥላቻን ይፈጥራል። እነዚህ ሕግን ጥሰው ሃገርን የሚያውኩ ከስደተኛው መሃል በጣም ትንሽ ናቸው።

ይህ ነገር እየገፋ መጥቶ በዜጎቻችን ላይ ጉዳት ሲደርስ መቼም ዝም ብለን ላናይ እንችላለን። ምክንያቱም ንጹሃንም አብረው ስለሚጎዱ። ግን የምንከራከረው ለማን ነው? በፖለቲካ ምክንያት መጥተው ዕጽ ለሚሸጡ? ጠግበው በስካር በቡጢ ለሚዣለጡ? ወደፊት ክፉ ዘመን ሲመጣ ሰላማዊ ሰልፍ ውጡ እንዳንባል ፍራቻዬ ነው። ለምንስ ነው ሰልፉ? እነዚህ አንባጓሮ ፍለጋ ከሃገር የተሰደዱ ጋጠ ወጦችን በመደገፍ። ደግሞ በዚሁ ማሀል ስንት ሐቀኞች ደግሞ ይጎዳሉ። ከአሁኑ መምከር ፣ ሕግን መጣስ አስፈላጊ እንዳልሆነ ማስረዳት ያስፈልጋል። ይህ ከመድረሱ በፊት ሁላችንም በየአካባቢያችን እነዚህ ወጣቶች መምከር ይኖርብናል። በተለይ ድጋፍ የሚጽፉ የፖለቲካ ድርጅቶች ለማን ድጋፍ እንደሚጽፉ ማወቅ ይኖርባቸዋል። ችግራችን ነውና ዝም ብለን ማየት አይኖርብንም። የሚቀጥለው ዓመት የተሻለ ይሁንልን ብለን ስንመኝ የክፍፍላችንን ገጽታዎችን ወደ ውስጥ ተመልክተን ራሳችን መፍትሄ መሻት ያስፈልጋል።

ስለ አንድነታችን የሚያስቡ ሁሉ በሰላም ይክረሙ!

beljig.ali@gmail.com

በልጅግ ዓሊ ፣
ፍራንክፈርት ፣
መስከረም 2007

አቶ ኃይለማሪያም እንዳሉት የዲሞክራሲ እጦት አብዮትን ያመጣል (ግርማ ካሳ)

$
0
0

አገር ቤት የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ፣ በረእቡ መስከረም 7 እትሙ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከቱርክ የዜና አገልግሎት ኤጀንሲ አናዶሉ ጋር በቅርቡ ያደረጉት ቃለ ምልልስ ለአንባቢያኑ አቅርቧልል። ከቃለ መጠይቁ፣ በተለይም በምርጫውና በፖለቲካ እስረኞች ረገድ ጠቅላይ ሚኒስተሩ የመለሱትን ቀንጭቤ ለማቅረብ እወዳለሁ።

“ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ዓመት በአገር አቀፍ ምርጫ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ምርጫውን የሥርዓቱ አካላት በሕግና በደንብ እንዲሠሩ በማድረግ ለማካሄድ ምን ዓይነት ዝግጅት እየተደረገ ነው? በኢትዮጵያ ስላለው የመድበለ ፓርቲ ዲሞክራሲ ያለዎት አጠቃላይ ግምገማ ምንድነው? “ ለሚለው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሲመለሱ   “ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ እንደሆነ ነው፡፡ ያለዲሞክራሲ ሰላማዊና ጠንካራ ኢትዮጵያን ማሰብ አንችልም፡፡ ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ ከመሆኗ አኳያ የሁሉንም ብሔሮች ፍላጎት ለማካተት የግድ ዲሞክራሲያዊ ሒደት ያስፈልጋል፡፡ ያለዲሞክራሲ እንሂድ ብንል ብጥብጥ ነው የምንጋብዘው፡፡ ኢትዮጵያ ባለብዙ ሃይማኖቶች ናት፡፡ በዓለም ላይ ያሉት ሁለቱ ትላልቅ ሃይማኖቶች ክርስትናና እስልምና ለዘመናት ተቻችለው የሚኖሩባት አገር ናት፡

ተቻችለው መኖራቸው የሚቀጥለው ዲሞክራሲያዊ ከሆንን ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያ 80 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ዕድሜው ከ30 ዓመት በታች በመሆኑ ወጣቶች የሚበዙባት አገር ናት፡፡ ወጣቶች ደግሞ ንቁና ለውጥ ፈላጊዎች ናቸው፡፡ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ከመራሃቸው ለልማት እሴቶች ናቸው፡፡ ዲሞክራሲ ከሌለ ግን ለሥርዓቱ አደጋ ይሆናሉ፡፡ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወጣቶች እያመጡት ያሉት አብዮት በዲሞክራሲ እጦት የመጣ ነው፡፡ ጎረቤት አገሮቻችን በቀላሉ ተሰባሪ ናቸው፡፡ ይህንን ተፅዕኖ ለመቋቋም ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ግድ ይለናል፡፡ ሌላው አሁን ባለው ተጨባጭ የዓለም ሁኔታ ያለዲሞክራሲ ሕይወትን መምራት አስቸጋሪ ነው፡፡ በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ያስፈልገናል” ሲሉ እርሳቸውና ድርጅታቸው ኢሓዴግ ለዲሞክራሲ ግንባታ ቁርጠኝነት  እንዳለው ነበር ለማሳየት የሞከሩት።

“ ምርጫዎች ደግሞ የእዚህ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አንዱ መገለጫዎች ናቸው፡፡ ፍትሐዊ፣ ነፃና ተቀባይነት ያለው ምርጫ ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ፡፡ በሕጋዊ መንገድ የተመዘገቡና በምርጫው ለመሳተፍ የሚችሉ ከ90 በላይ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ “ ሲሉም የሚደረገው ምርጫ ፍትሐዊ፣ ነጻና ተቀባይነት ያለው ምርጫ መሆን እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ይናገራሉ።

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ መድረክ፣ አረና ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በመርጫ ቦርድ የተመዘገቡ፣ አዲስ ከተቋቋመው ከሰማያዊ በስትቀር ባለፉት ምርጫዎች  የተሳተፉ ፣ ከ ”ዘጠና በላይ” ካሏቸው ድርጅቶ መካከል ያሉ ናቸው።  “ምርጫ የማይፈልጉ፣ መንግሥትን በጦርነት ለመጣል የሚፈልጉ አማፂ ቡድኖችም አሉ፡፡ እነሱን ለመዋጋትና ራሱን ለመከላከል መንግሥት በዲሞክራሲያዊ መንገድ ሳይሆን ወታደራዊ መንገድ ነው የሚከተለው” እንዳሏቸው ድርጅቶች አይደሉም።

ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች የመሰባሰብ፣ ጋዜጣዎች የማተም፣  ሰላማዊ ሰልፎች የመጥራት ፣ ዉህደት የመፍጠር መብታቸው እየተገፈፈ ነው። በገዢው ፓርቲ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል። ከፍተኛ አመራሮቻቸው በፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ እየታሰሩ ነው። ከአንድነት አንዱዋለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳን ኤል ሺበሺ፣ አንዱዋለም አየለ፣ አበበ ቀስቶ፣ ሻምበል የሺዋስ  ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ የሺዋስ አሰፋ፣ በፍቃዱ አበባ፣ ጌታሁን አያለ፣  ከመድረክ በቀለ ገርባ፣ አብርሃ ደሳታ ፣ ኦልባና ለሌሳ  ታስረዋል።

ታዲያ ይሄ፣ በሕግ በተመዘገቡ ሰላማዊ ፓርቲዎች ላይ፣  በግልጽ የተከፈተ ጦርነት እና ወከባ ካልተባለ ምን ሊባል ነው የሚችለው ? ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማሪያም እንደው ደረታቸውን ነፍተው ይህን አይነት መለስ ሲመልሱ፣ እኛ በተቃዋሚው ጎራ ለምንለው ግድየልም አይጨነቁ፣  አብረዋቸው ያሉ ጓደኞቻቸው ምን ይሉኝ ይሆን ብለው እንኳን አይፈሩም?

“የፖለቲካ እስረኞችን በተመለከተ ምን ይላሉ?” ተብለው ሲጠየቁ ደግሞ የመለሱት መልስ ከማስገረም አልፎ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው። “ የፖለቲካ እስረኞች የሉንም፡፡ የታሰሩት የአማፂ ቡድኖች አባላት የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህ የፖለቲካ ‹‹አክቲቪስቶች›› ሳይሆኑ ጦር ያነሱ ኃይሎች ናቸው፡፡ የሚፈልጉትን ነገር በትጥቅ ትግል ለማሳካት የመረጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ሽብርተኞች ናቸው “ የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት። የሚሰቀጥጥ መልስ !!!!!!!

ያሳያችሁ የመቀሌው መምህርና ብሎገር አብርሃ ደስታን  ነው ጦር አነሳ የሚባለው ? ሃብታሙ አያሌው፣ አንዱውዋለም አራጌ ፣ የተከበሩ አቶ በቀለ ገርባ ናቸው ጦር አነሱ የሚባሉት ? እነዚህ ወገኖች ቤታቸው፣ ቢሯቸው፣ ኮምፒተራቸውና  ያላቸው ንብርት በሙሉ  ተበርብሯል። ፈንጂ፣ ቦምብ፣ የኮሚኒኬሽን መሳሪያዎች አልተገኘባቸውም። በድበቅ ፣ በሚስጠር የጻፉት፣ የተናገሩት ነገር የለም። ወንጀላቸው አገራቸውን  መዉደዳቸው ነው። ጥፋታቸው እነ አቶ ኃይለማሪያም ጓዶቻቸው እንዲነገርና እንዲጻፍ የማይፈልጉትን በመጻፋቸውና በመናገራቸው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም በርግጥ ሐቀኛ  ነኝ የሚሉ ከሆነ፣ በርግጥ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲደረግ ቁርጠኝነት ካላቸው፣ “ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ የሕልዉና ጉዳይ ነው” ያሉትን ከልብ የሚያምኑበት ከሆነ ፣ እንግዲህ እርሳቸውና ድርጅታቸው የዘጉትን በር በመከፈት በተግባር ያሳዩን። የታሰሩ እስረኞችን በሙሉ ይፍቱ። ተቃዋሚዎች በነጻነት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሕዝቡን እንዲያደራጁና እንዲቀሰቅሱ፣ አማራጭ ፖሊሲዎቻቸዉን እንዲያቀርቡ ይፈቀድላቸው። በፖሊስ፣ በደህንነት በካድሬ መዋከባቸው ይቁም።

አለበለዚያ  “ዲሞክራሲ ከሌለ ግን ለሥርዓቱ አደጋ ይሆናሉ፡፡ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወጣቶች እያመጡት ያሉት አብዮት በዲሞክራሲ እጦት የመጣ ነው፡ “ እንዳሉት እርሳቸው ቁንጮ የሆኑበት ስርዓት አደጋ ላይ ነው የሚወደቀው። በሚሊዮንኖች የሚቆጠሩ ወጣቶችም፣ ሰሞኑን በየ ዩኒቨርሲኦቲና ትምህርርት ተቋማት እያደረጉት እንዳለው መነሳታችቸውና አብዮት መምጣቱ አይቀሬ ነው።

 

Comment

 

 

 

 

 

 


ልማት ያለ ነፃነትና ፍትሕ ፋይዳ የለውም

$
0
0

ከይኩኖ መስፍን (ቦስቶን ሰሜን አሜሪካ )

ሙሱና! አፈና እና አድልዎ ከማንም ግዜ በላይ በሰፈነበት ሀገር ዘላቂ ፍትሕ! ዴሞክራሲ! ዕድገትና የህግ የበላይነት ይመጣል ብሎ ማሰብ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይወለዳል ብሎ መጠበቅ ነው:: ዛሬ በኢትዮያ ሙሱና እና ዓይን ያወጣ ያገር ሀብት ዘረፋ የስርዓቱን ሁለንትናዊ መገለጫ ባህሪይ ከመሆኑም በላይ የህዝባችንን ንሮና ህይወት እየገደለና እያቀጨጨ ያለው ከኤይድስ በላይ ስር የሰደደ ተላላፊ በሽታ እየሆነ መጥቷል:: ዘረፋውም ሆነ አፈናው ከግለ ሰብ አልፎ ወደ ተቋማዊና የተደራጀ ሌብነት በመሸጋገሩ ኢትዮያ ሕገ መንግስታዊ ዋስትና የሌላት” ፍትሕ አልባ የሆነች ሀገር አድርጓታል::

እኔ የምኖረው በውጭ ዓለም በሰሜን አሜሪካ ቢሆንም በቅርቡ ለግል ጉዳይና ቤተሰቦቼን ለመጠየቅ ወደ ኢትዮያ ሂጄ ስለነበር ለሶስት ወር ያህል አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሬ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በወሬ የምሰማውን ነገር ሁሉ በአካል ተገኝቼ በቀጥታ በሕብረተሰቡ ዘንድ በመሬት ላይ ያለው እውነታ ምን እንደሚመስል በማየቴ ብዙ ነገሮችን ለመገንዘብና ለመማር ጥሩ ዕድል አጋጥሞኛል::
እኔም “ማየት ማመን ነውና” በቅርብ ተገኝቼ ባንድ በኩል ከህዝቡ አንደበት የሰማሁትንና ያየሁትን እሮሮ በሌላው ገጽ ደግሞ በመንግስት በኩል ያለው ተግባራዊ ምላሽና እንቅስቃሴ ምን እንደሆነ ሰፊው ሕብረተሰብ በተለይም ከሁኔታው ርቆ በውጭ ዓለም በዲያስፓራ የሚኖረው ኢትዮያዊ ወገን ሁሉ ማወቅ አለበት ብዬ ያሰብኩዋቸውን አንገብጋቢ ጉዳዮች በማንሳት አቅሜ የፈቀደውንና አእምሮየን የዘገበውን ያህል በማካተት የተሰማኝን ስሜትና ተሞክሮ ለማካፈል ከዚህ ቀጥሎ ያለው ጠቅለል ያለ ሃሳብ ለማቅረብ ሞክሬያለሁ::

ክፍል አንድ:-
የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ፍትሕ ጥያቄ

በስልጣን ላይ ያለው የህወሓት/ኢሕአዴግ ሞኖፓላዊ ፓርቲ በተለያዩ የዜና አውታሮች አማካይነት ለኢትዮያውያን ከዚያም አልፎ ለዓለም ማሕበረሰብ ነጋ ጠባ አሸብራቂ በሆኑት ቃላት እንደሚገልፀው “በልማታዊ መንግስታችን አመራር ስር ኢትዮያ በፈጣን ዕድገት ጎዳና ላይ ነች:: በቅርቡም መካከለኛ ገቢ ካላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገሮች ተርታ ትሰለፋለች:: ህዝቡም የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ስርዓት የልማት ተጠቃሚ ሆነዋል:: በአቶ መለስ ዜናዊ የልማት ራዕይ ድሕነት በቅርቡ ነበር ሆኖ ይቀራል” ወዘተ ወዘተ ሲሉ ይደመጣሉ::
በየደረጃው የተኰለኰሉ ካድሬዎችና የፓርቲው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አፍቃሪዎችም የሚነግሩን ይህንን ነው:: በአብያተ ትምህርትም ከመዋእለ ህፃናት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉት መምህራንና ርእሳነ መምህራን የሚሰብኩትና ለለጋ ወጣቱ የሚያስተምሩት ይህንን ነው::
በህዝብ አንጡራ ገንዘብ የሚተዳደሩ የብዙሃን መገናኛ ጋዜጠኞችና አንዳንድ አፈ ቀላጤ ምሁራንም ሆኑ ከላይ ያሉት ባለስልጣናት የሚያስተጋቡትና የሚሰሩት ተውኔት “በሀገራችን ልማት ተረጋግጧል የሚል ነው:: ከርእሰ ብሄሩ ጀምሮ እስከ ታች ቀበሌና ጎጥ ድረስ ያሉት የአስተዳዳር አካላትም ረሃብተኛውን ህዝብ የሕልም እንጀራ ለማብላት ሲባል ዋና ስራቸው “ኢትዮያ ለምታለች” የሚል ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨትና ማስተማር ነው፡፡
ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ በቢሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ሀብት ወጪ እየተደረገበት የሚተላለፈው የፕሮፖጋንዳ ክምር እና በልማት ስም የሚሰራው ስንክሳር ድራማ በመሬት ላይ ያለው ሓቅ ሊሸፍነውና ሊለውጠው አልቻለም:: እርግጥ ነው በአዲስ አበባና በሌሎች አንዳንድ የክፍላተ ሀገር ከተሞች መጠነኛ ትላልቅ ፎቆች፣ መንገዶች፣ ትምህርት ቤቶች! የጤና ተቋማት፣ እንዲሁም አንዳንድ ግድቦች አልተሰሩም አልልም:: ማንኛውም መንግስት መጠኑን ይለያል ይሆናል እንጂ በጊዜው አንዳንድ ነገር ሰርቶ ያልፋልና:: ነገር ግን ዋናው እና መሰረታዊ ጥያቄው ስንት ፎቅ ተሰራ፣ ስንት ግድብ ተገነባ፣ ስንት ተማሪ ወደ ትምህርት ቤት ሄደ! ሳይሆን በሀገሪትዋ የዜጎች ሰብኣዊ መብትና ነፃነት፣ የሕግ የበላይነት! ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ ሳይረጋገጥ ዘላቂ ልማትና ዕድገት ሊኖር ይችላል ወይ? የዕድገቱንና የልማቱን ባለቤት ማን ነው? በህወሓት ኢሕአዴግ የልማት ፓሊሲ ማን ነው እየለማ ያለው? አሁን ያለው የትምህርት ፓሊሲ ምን ዓይነት ትውልድ ነው እያፈራ ያለው? በአጠቃላይ መሰረቱ የተናደ ቤትና ስርዓት ዘላቂነት ያለው ልማትና ዕድገት ሊያመጣ ይችላል ወይ? የሚሉትንና ሌሎች የህዝቡን የልብ ትርታ የሚነኩ ጥያቄዎች በቅድሚያ መመለስ ያለባቸው ይመስለኛል::
የስርዓቱን የልማት ፓሊሲና አመራር ምን ያህል ትውልድ ገዳይና ሀገር አውዳሚ መሆኑን ለመገንዘብም ሆነ ለማወቅ የግድ የተወሳሰበ ቲኦሪ መተንተን ወይም የፓለቲካ ፈላስፋ መሆን የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም:: ሀገርንና ህዝብን ማእከል አድረገው ካዩት በያንዳንዱ ቤት ያለው የንሮ ችግር! በየልማት ዘርፉ የሚታየው ዝርፊያ! በወጣቱ ትውልድ ዘንድ የሚታየው ተስፋ መቁረጥና ፍልሰት! በማሕበራዊ ንሮ የሚታየው ምስቅልቅል! በየመንግስት መሥሪያ ቤቱ በየደረጃው የሚታየው አስተዳዳራዊ አድልዎ! በሕብረተሰቡ ውስጥ የሚታየው ፍርሃትና ስጋት ሁሉም ተደማምረው የስርዓቱን አስከፊ ባሕሪይ አፍ አውጥተው የሚናገሩ የህዝቡ እሮሮዎች ናቸው:: አብዛኛውን በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መብላት የተሳነው ህዝብ ይዞ ስለ ልማት ማውራት በሕብረተሰቡ ላይ ከመቀለድ በስተቀር ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም:: ችግሩ በዚሁ ፅሑፍ ብቻ ተወርቶ የሚያልቅ ባይሆንም ሁኔታውን ለማወቅ ብዬ በተለያዩ የስራ ቦታዎች ተንቀሳቅሼ ከተመለከትኩዋችው ችግሮች ውስጥ የሚከተሉትን አብነቶች መጥቀሱ ብቻ በቂ ይመስለኛል::
በትምህርት
ትምህርት ላንድ ሀገር የእውቀት ማፍለቂያ መሳሪያ ብቻ ሳይሆን የልማትና የእድገት አንቀሳቃሽ ሞተርም ጭምር ነው:: አብዛኞቹ ያደጉና በፈጣን እድገት ላይ ያሉት ሀገሮች የእድገታቸው ሞሰሶና መነሻ የሆነው ከሁሉም በላይ ነፃ አስተሳሰብ ካለው ሕብረተሰብ የሚመነጭ የሰብኣዊ ዓቅም ግንባታ ላይ ቅድሚያ በመስጠት በቀጣይነት ስለተረባረቡ ነው:: በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ኢኮኖሚ የሚሸከምና የሚያንቀሳቅስ ሕብረተሰብ (ክህሎት) ለመገንባት ደግሞ ቢያንስ የሞያ ነፃነት፣ ደረጃውን የጠበቀና ከአንድ ፓርቲ ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ስርዓተ ትምህርት! በነፃነትና በጤናማ ውድድር ላይ የተመሰረተ የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ወሳኝነት አለው::
ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የትምህርት ስርዓት ግን በተገላቢጦሽ ነው:: ላንድ ሰራተኛ ለመቅጠር መመዘኛው የሞያ ጥራትና ክህሎት ሳይሆን ለድርጅት ያለው ቅርበትና የፖለቲካ ታማኝነት ነው:: የሀገሪትዋ ስርዓተ ትምህርትና ፓሊሲም የሚመነጨው ከዓለም አቀፍ የእውቀት ስታንዳርድ እና ከሀገሪትዋ ነባራዊ ሁኔታ ሳይሆን ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ የጥቂት ሰዎች ሞኖፓላዊ አስተሳሰብ እና እምነት ነው:: ለምሳሌ የትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ሁሉም የፓርቲ አባላት ወይም ካድሬዎች ናቸው፡፡ አስተማሪዎች ከ95 በመቶ በላይ የፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ አባል ያልሆኑና በነፃ ህሊና ማገልገል የሚፈልጉ ብቃት ያላቸው ባለሞያዎች ምንም የስራ እድገት እንዲያገኙ አይፈቀድላቸውም ብቻ ሳይሆን በስራ ገበታቸው የመቆየት እድላቸውም በጣም ትንሽ ነው፡፡ በሰበብ አስባቡ እንዲባረሩ እና እንዲጎሳቆሉ ይደረጋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በስራቸው የሚተማመኑ እና ብቃት ያላቸው ቢሆኑም ሆን ተብሎ ከህብረተሰቡ እንዲገለሉ እና እንዲሸማቀቁ ይደረጋሉ፡፡ ትምህርት ከጨረሱ በሗላም የተሻለ የስራ ዕድል ለማግኘት! ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመግባት! ወደ ውጭ ሀገር እስኮላርፕ ለመላክ! የመሳሰሉ ዕድሎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው የፓርቲ አባላት! ታማኝና ደጋፊዎቻቸው ናቸው:: ሌሎች ብዙሃኑ ዜጎች ግን በገዛ ሀገራቸው ባይተዋር እና የበዪ ተመልካች ሆነው ከመቅረት ሌላ አማራጭ የላቸውም::
ከትምህርት ጋር ተያይዞ ሌላው በጣም አሳሳቢና አስደንጋጭ ችግር ደግሞ አሁን የድርጅቱን አባላት! ታማኞች የሆኑ ሰዎች! እንዲሁም በየወረዳው የትምህርት ቢሮ የሚሰሩ ካድሬዎች እና ባለስልጣናት ከዛው ከወረዳው ትምህርት ቢሮ ውስጥ የሚቀናጀው የዲግሪ ፕሮገራም ፅሁፍ በመቸብቸብ የሐሰት ዲግሪ እየተሸከሙ የሕብረተሰቡን ሸክም የመሆን አባዜ ነው፡፡ ለአንድ የዲግሪ ፅሁፍ እስከ 500 ብር እንደሚሸጥ አረጋግጬለሁ:: በአንድ የወረዳ ትምህርት ቢሮ የሚሸጠው የዲገሪ ማዘጋጃ ሰነድም ለማስረጃነት ያህል በእጄ ይገኛል፡፡ ስም እና አድራሻ እያቀያየሩና እያባዙ በተሰማሩበት ሁሉ ይቸበቸባል:: ልብ በሉ!! በዚሁ ዓይነት የሐሰት ዲግሪ በተሸከሙ ሰዎች የሚመራው ሕብረተሰብ! የሚማረው ወጣት ትውልድ! የሚቀየሰው የልማት ስተራተጂና ፓሊሲ ምን ያህል ውጤታማ እና ዘላቂነት ይኖረዋል ብላችሁ ትገምታላችሁ?
አዎ!! የዚህ ሁሉ ድምር ዉጤትም በካድሬ ቁጥጥር ስር የተማሩ ወጣቶች ለውጥ ማምጣት ካልቻሉ” አስረኛ ክፍል ጨርሶ ስማቸውን በደንብ መፃፍ ካልቻሉ” ወደ 80 በመቶ አስረኛ ክፍል ማለፍ ካልቻሉ” 20 በመቶው 11 እና 12 ተምሮ እንደገና 50 በመቶ ከወደቀ” በመጨረሻ ሁሉንም መሰናክል አልፎ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብቶ ከተማረ በውሗላም ያንድ ፓርቲ አገልጋይ እንዲሆን የሚፈረድበት ከሆነና ተመልሶ ወደ አላስፈላጊ ብክነትና ማሕበራዊ ቀውስ በመግባት የሕብረተሰቡን ሸከም ሆኖ የሚቀር ከሆነ ትምህርት ቤት መመላለሱ ፋይዳ ምንድን ነው?
በጤና እና በሌሎች የመሰረተ ልማት ዘርፎች
ህዝቡ በጤና ዙርያ ያለበት ችግርም በጣም ብዙ ነው፡፡ በአማካይ በየወረዳው ያለው የህዝብ ብዛት ከ150 ሺ እስከ 200ሺ ይደርሳል፡፡ ልክ ከላይ በትምህርት ዘርፍ እንዳየነው ሁሉ የጤና ቢሮ ሃላፊ በሞያው ተመጣጣኝ እውቀት የሌለው የፓርቲ እና የመንግስት ታማኝ ነው፡፡ የሚሰራው ስራም የፖለቲካ ነው፡፡ በጥቂቱ ለ200 ሺ ህዝብ አንድ ዶክተር ማግኘት ወይም መመደብ አልተቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት ህዝቡ ወደ ሌላ ቦታ ሻል ያሉ ትላልቅ ከተሞች ሄዶ ለመታከም ደግሞ ከተለያዩ የኢኮኖሚ ችግሮች ባሻገር እዛ ሂዶም ትክክለኛ ህክምና አያገኝም፡፡ በሞያው ማነስ ምክንያትም ለተለያዩ ችግሮች ይዳረጋል:: ለምሳሌ ለበሽታው የተሳሳተ መድሃኒት መስጠት! ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት መስጠት! ከአቅም በላይ ገንዘብ መጠየቅ! ለሰሩት ስህተት ተጠያቂ አለመሆን! መንግስት የመደበው መድሓኒት በመንገድ ላይ መሰወር የመሳሰሉ ችግሮች የተለመዱ ሆኗል:: መንግስት በብዙሃን መገናኛ በኩል የሚለው እና በመሬት ላይ ያለው ሃቅ በጣም የተለያዩ ናቸው፡፡
በሌሎች የአገልግሎትና የልማት ዘርፎች የሚታየው እንቅስቃሴም ተመሳሳይ ነው:: ለምሳሌ የኤለክቲሪክ መብራት አላቸው በሚባሉ ከተሞች ቢያንስ በቀን ወደ አራት ገዜ እንደሚጠፋ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ ችግሩ መብራት መጥፋቱ ብቻ ሳይሆን መቼ ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል እና ህዝቡም ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያውቅበት አሰራር የለም፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ የተጀመሩ ስራዎች ይስተጓጎላሉ:: አንዳንድ ምርቶችም ተበላሽተው የሚጣሉበት ጊዜ እንዳለ ይታያል:: አንድ ቀን በዓይኔ ያየሁት ቀላል ገጠመኝ ላንሳ፡፡ የፀጉር አስተካካይ ቤት ነው፡፡ በርካታ ሰዎች ፀጉራቸውን ለመስተካከል ተራ ይዟል:: በዚህ ማሃል መብራቱ ጠፋ እና ሰዎቹ የተወሰነ ጊዜ ከጠበቁ በሗላ ወደየቤታቸው ሄዱ፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ደግሞ በጅምር ላይ ስለነበሩ ግማሽ ፀጉር ይዘው እንዴት ቤት መሄድ እንደሚችሉ ተቸግረው እነሱም ሳይቀር ራሳቸው በራሳቸው እየሳቁ ሄዱ፡፡ ይህንን ቀላል ነገር ለአብነት ያህል ጠቀስኩ እንጂ በዚሁ ብልሹ አስተዳደር ምክንያት ተጠያቂነት በሌለበት አኳሃን የሚጉላላው የሰው ብዛት እና የሚባክነው የህዝብና ያገር ሀብት ቤቱ ይቁጠረው፡፡
ሌላው በኢትዮያ ትልቁ የመዝረፊያ ቦታ በመንገድ ስራ! በውሃ ሀብት ልማት! በመሬት ድልድል! በቤቶች ኮንስትራክሽን! በሰፋፊ የግልና የመንግስት እርሻዎች ያለው የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ነው:: እነዚህ ፕሮጀክቶች አንዳንዴም “የባለስልጣኖች የሚታለቡ ላሞች” እየተባሉ እንደሚጠሩ በዘርፉ የሚሰሩ ጓደኞቼ ነግረውኛል:: በነዚህ ፕሮጀክቶች ከውጭ በእርዳታና በብድር የሚገኘው ዕዳን ጨምሮ በየዓመቱ በብዙ ቢሊዮን የሚፈሰው መዋእለ ንዋይና በጀት ቁጥር ስፍር የለውም:: በነዚህ የስራ ዘርፎች ቀጥተኛ እጅና ተሳታፊነት ያላቸው ግዙፍ ባለድርሻዎች በዋናነት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ተቋራጮች (ኮንትራክቶሮች)! ዲዛይኖሮች! ኮንሳልታንቶችና እንዲሁም የመንግስት ተቆጣጣሪዎችና ተጠሪዎች ናቸው::
በነዚህ የልማት ዘርፎችና ፕሮጀክቶች አካባቢ ጎልተው ከሚታዩ መሰረታዊ ችግሮች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ማነቆ የባለ ሙያዎች (ብቁ የሰለጠነ የሰው ሓይል) እጥረትና ፍልሰት ነው:: በሌላ አነጋገር ለስርዓቱ ታማኝ ያልሆኑ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን ከስራው እየገፈተሩ በማባረር በምትካቸው ታማኝና ታዛዝ በሆኑ ካድሬዎች ስለሚተካ በሞያቸው ብቁ የሆኑ ሰዎች ያላቸው ዕድል ሥራ አጥ ሆኖ እየተንሳፈፉ መኖር አሊያም ሳይወዱ ወደ ስደት መፍለስ ነው::
ሁለተኛው ትልቁ ችግር ጥራት ነው:: ጥራት የሌለው ፕሪጀክት ደግሞ የወደፊቱ የትውልድ ዕዳ እንጂ ልማት አይባልም:: ለምሳሌ መንገዶች! ድልድዮች እና የውሃ ቧምባዎች ከተሰሩ ከጥቂት ወራት በሗላ እንደሚፈራርሱ እና መተላለፍያ መሰመሮችን እየተዘጉ ሕብረተሰቡ ለአደጋ እና ለኪሳራ እንደሚዳረግ በግልፅ የሚታይ ነገር ነው:: ለዚህም ነው ሕብረተሰቡ በፌዴራል የሚሰሩ እንደ መንገድ የመሳሰሉ የመንግስት ፕሮጀክቶች የራሱ የሆነ መጠሪያ በመስጠት ሽሮ ፈሰስ ዛሬ ተሰርቶ ነገ የሚፈርስ በሚል የህዝቡ መነጋገሪያ ሆኖ ሲታይ በጣም የሚገርምና የሚቆጭ ነው::
ሶስተኛው ትልቁ ችግር ሙሱና እና ዓይን ያወጣ የሀገር ሀብት ዘረፋ ነው:: ዘረፋው ደግሞ ተራ ዝርፊያ አይደለም:: ዘረፋው አጠቃላይ የስርዓቱን መገለጫ ባህርይ የሆነ ተቋማዊ! ሰንሰለታዊና ድርጅታዊ ይዘት ያለው ሌብነት ነው:: በዚሁ ቀጥተኛ ዝርፊያ የተሰማሩ ደግሞ ከላይ የተጠቀሱት አካላት ናቸው:: ሁሉም በተናጠልም ሆነ በቅንጅት በዝርፊያ የተሳተፉ ስለሆነ አንዱ አንዱን ደፍሮ መቆጣጠርና ስርዓት ማስጠበቅ ወይም በሕግ መክሰስ አይችልም:: ለምሳሌ አብዛኞቹ የውጭ ኮንትራክተሮች የመንግስትን ፕሮጀክቶች ለመስራት ሲቀጠሩ ተወዳድረው በብቃታቸውና በጥራታቸው ተመርጠው ሳይሆን በተለያየ መልኩ የባለስልጣናትን አፍ አጉረሰውና እጅ ጨብጠው ነው ኩንትራቱን የሚያገኙት:: እንደነ ሳሊኒ! ሚድሮክ! የቻይና እና ሌሎች ኮንትራክተሮች በአብነት የሚጠቀሱ ናችው:: የኢትዮያ አንጡራ ሀብት የሆነው ለውጭ ባለሀብቶች እየተቸበቸበ ያለው መሬትም ትልቁ የሙሱና ምንጭ ሆኗል::
ይህ ሁሉ ቅጥ ያጣ ዝርፊያ እየተካሄደ መንግስት ለምን አይቆጣጠርም? ለምን ዝም ይላል? የሚል ጥያቄ እንደሚነሳ እርግጠኛ ነኝ:: ይህ ጉዳይ የራሴም ጥያቄ ስለነበረ መልስ ለማግኘት በተለያየ የሃላፊነት ደረጃ ያሉትንና እንዲሁም እስከ ታች የቀበሌ ነዋሪዎች ድረስ ብዙ ሰዎችን ለማነጋገር ዕድል አጋጥሞኛል:: ከዚህ ሁሉ የተረዳሁትና የተነገረኝ ሙሱና እንደ ክፉኛ ተላላፊ በሽታ ልክፍት መድሃኒት የማይገኝለት ወረርሽኝ በሽታ ሆኗል የሚል ነው:: ይህ ማለት ሙሱና የአገዛዙን ሁለንትናዊ መገለጫና ባሕርይ (ደመ ነብስ) ሆኗል የሚል ነው::
ሙሱናን መቆጣጠር የሚቻለው ደግሞ ሃላፊነት የሚሰማውና ለሕግ ተገዥ የሆነ” ተጠያቂነትና ግልፅነት ያለው መንግስትና የአሰራር መካኒዝም ሲኖር ነው:: በሌላ አነጋገር ህዝቡ ራሱ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በህዝብና በሀገር ሀብት ላይ የሚቀልዱ! የሚዘርፉና የሚባልጉትን ባለስልጣናት ለመቆጣጠር የሚችልበት ብሎም ወደ ፍርድ የሚያቀርብበትን ነፃ የሚድያ! የፍትሕ! የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት ሲኖሩና ሲከበሩ ብቻ ነው::
ነገር ግን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ራሱን ለመቆጣጠር ቀርቶ የህዝቡን እሮሮና ጥያቄ ለማዳመጥና ለመመለስ የሚያስችል ባህርይ! ብቃት! ጆሮና ዓይን የለውም:: አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ መንግስት ሙሱናን መቆጣጠር ማለት እንደ ራስህን በራስ የመግደል (ሱሳይዳል) ዓይነት አድርጎ ነው የሚያየው:: ዛሬ በሀገራችን ስልጣናቸውን ተገን አድርገው የሚዘርፉ ብዙ ጎበዝ አለቆችና ብድኖች ተፈጠሯል:: ባጠቃላይ ሲታይ ማን ለማን መቆጣጠርና መክሰስ በማይችልበት ሁኔታ ላይ እርስ በርስ በተፋጠጥ ላይ የቆሙ ናቸው:: አልፎ አልፎ ሙሱናን እንቆጣጠራለን በሚል ሽፋን የሚያደርጉት እንቅስቃሴም ተቀናቃኝና ለስርዓቱ ታማኝ ያልሆኑ ዜጎችን ለመምታት የሚጠቀሙበት ስልት እንጂ ስርዓቱን ከስረ መሰረቱ ለማፅዳት እንዳልሆነ ህዝቡ በነቂስ ያውቃል::
ሁላችንም እንደሰማነው ከጥቂት ወራት በፊት ሙሱናን ለመቆጣጠር ተብሎ የተጀመረውን የአንድ ሳምንት ሞቅ ሞቅታ እንደ ነበር ይታወሳል:: ህዝቡም በጉጉት ይጠብቅ ነበር:: ነገር ግን የሚፈልጉዋቸውን ጥቂት ሰዎች ካሰሩና ከመቱ በሗላ እርምጃው ባልታወቀ ሁኔታ ወዲያውኑ እንዲቆም እንደተደረገ የሚታወቅ ነው:: እንዲቆም የተደረገበት ዋናው ምክንያት ደግሞ ጉዳዩ እስከ ላይ ድረስ ሰንሰለታዊ! ድርጅታዊ ይዘትና ግንኙነት ስላለውና በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ የህወሓት/ኢሕአዴግን ህልውና አደጋ ላይ ስለሚጥል” የአቶ መለስ ዜናዊንና ተከታዮቻቸውን ስምና ታሪክ ስለሚያጎድፍ” እንዲሁም በብዙ ባለስልጣናት ዘንድ ተጠያቂነትን ሊያስከትል ይችላል በሚል ስጋት ለህዝቡ ያዳባባይ ሚስጢር ሆኖ እንዲቀር ተደርጓል::

ማጠቃሊያ
የሞያ ነፃነት በተገደበበት” ነፃ የፍትሕ” የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት በሌሉበት! የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት በጠፋበት” ባጠቃላይ አንድ ፈላጭ ቆራጭ ፓርቲ የሀገሪትዋን ሁለንትናዊ ሰብኣዊ” ማተሪያላዊና አእምራዊ ሀብት ተቆጣጥሮና ገድቦ ራሱ ሕግ አውጪ! ራሱ ሕግ ተርጓሚ! ራሱ ሕግ ፈፃሚና አስፈፃሚ በሆነበት ድሃ ሀገር ምን ያህል ለዝርፊያ የተጋለጠ ሕብረተሰብ እንደሆነ እንኳን ለዜጎችዋ ለዓለም ማሕበርም የሚዘገንን ተግባር መሆኑን መገመቱ አያዳግትም::
ይህንንም ተደጋግሞ የተነገረ ስለሆነ አሁን ባነሳው ምናልባት ለሰሚው የሚሰለች ወይም ለቀባሪ ማርዳት ሊሆን ይችላል የሚል ሃሳብ ነበረኝ:: ነገር ግን የሀገርና የህዝብ ጉዳይ እያዳረ የሚቆረቁር ስለሆነ እንደ ግል ጉዳይ ሰልችቶህ የምትተው ነገር አይደለም:: እኔም ላለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ወደ ሀገር ቤት በሄድኩ ቁጥር መሰረታዊ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል ብዬ በማምንባቸው ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተደጋጋሚ የእርምት ፅሑፍ አቅርቤ እንደነበር አስታዉሳለሁ:: ይሁን እንጂ በተመላለስክ ቁጥር የሚያሳዝን እንጂ የተሻለ ነገር አታይም:: በተለይም ከአቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት በሗላም ምናልባት ካለፈው ስህተታቸው ተምረው የተወሰነ ለውጥ ይመጣ ይሆናል የሚል ግምት ቢኖረኝም አሁን ያለው ሁኔታ ሲታይ ግን የባሰ እንጂ የተሻለ አይደለም:: እንዲያውም በሀገርና በወገን ላይ ለሚደርሰው ጥፋትና ጉዳት ለማን አቤት እንደሚባል አውራ እንደሌለው ንብ መንገዱ የጠፋበት ሁኔታ ሆኖ ነው ያገኘሁት::
ትእዝብቴ በዚህ ብቻ አላበቃም:: በተለይም በመልካም አስተዳደር! በፓለቲካ ምሕዳር! በሀገር ድህንነትና አንድነት ዙሪያ መንግስት እየወሰደ ያለው የቂቢፀ ተስፋና አፍራሽ እርምጃ ምን ያህል መረኑ የለቀቀና የከፋ መሆኑን ተጨባጭ ማስረጃዎችን በማስደገፍ በክፍል ሁለት ፅሑፌ ለማቅረብ እሞክራለሁ

ኢትዮያ ሀገራችን ለዘላለም ትኑር
sgbtsait@gmail.com

የዋሽግተኑ ጉዳይ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንፃር ሲታይ

$
0
0

ከጌታቸው በቀለ

”ዓለም አቀፍ ሕግ፣ዓለም አቀፍ ሕግ” የምትል ቃል በእየቦታው ትሰማ ጀመር።እሰይ! እንዴት ደስ ይላል።ይህንን ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ-ገፅ ላይ የሚጠቅሱት ደግሞ የስርዓቱ አድናቂዎች ናቸው።ጉዳዩን የሚያነሱትደግሞ በዋሽግተን ኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በተደረገው ተቃውሞ ሳብያ ነው።እስኪ ለህሊናችን መጀመርያ በሀገር ውስጥ እራሱ ላወጣው ሕግ መገዛት ቢያቅተው ለዓለም አቀፍ ሕግ እንዲገዛ ስርዓቱን እንምከረው።እንዲህም እንጠይቅ-

ለመሆኑ ዓለም አቀፍ ሕግን እንደ ዓለም ዋንጫ ቅሪላ በእግሩ የሚያጦዛት ማን ነው?
embassy shooter
ማን ነው የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውን የጋምቤላ አስተዳዳሪ ከደቡብ ሱዳን ጠልፎ ወስዶ ያሰረው? ዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ቁጥር ስንት እንበለው?
ማን ነው የእንግሊዝ ፓስፖርት የያዙትን አቶ አንዳርጋቸውን ከየመን ጠልፎ ያሰረው? ዓለም አቀፍ ሕግ ቁጥር ስንት እንበለው?
ዓለም አቀፍ ሕግ የአፍ ማሟሻ አደለም! በተግባር ለእራስ ሲሉ የሚያከብሩት ነው።ዛሬ የዋሽግተን ኤምባሲ ሲደናገጥ ”ሕግ ምናምን” አትበሉ።የዋሽግተኑን ጉዳይ በዓለም አቀፍ ሕግ አንፃር ካየነው የኤምባሲው የሕግ ከለላ ከባዕዳን ነው እንጂ ከሀገሩ ተወላጆች አይደለም! አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በሀገሩ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ውስጥ ገብቶ የመቃወምም ሆነ ዋሽግተን ላይ ባለው በሀገሩ ኢምባሲ ውስጥ ገብቶ የመቃወም መብቱን ዓለም ዓቀፍ ሕግ አይገድበውም።የሰንደቅ አላማው ጉዳይም ሰንደቅ አላማው በሌላ ሰንደቅ አላማ ተተክቶ ቢሆን ነበር የሚያሳዝነው።ይህ ቢሆን ኖሮ በሕግም አከራካሪ ይሆን ነበር።የሉዓላዊነት ጥያቄም አብሮ ሊነሳ ይችል ነበር።የሆነው ግን ለሕግ ወቀሳም አይበቃም። ተቃዋሚዎቹ የተኩት ቀድሞ የኢህአዲግ አርማ ያለበትን በእራሷ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ነው።

አንድ ሀገር የውጭ ቆንስላ ወይንም ኤምባሲን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት።ይህ የሚያደርገው ግን ከእዛ ሀገር ዜጎች የበለጠ ኃላፊ ሆኖ አይደለም።የኤምባሲው ሀገር ተወላጅን ወደ ኤምባሲው ‘ግባ አትግባ’ ማለት ሌላ ሳይሆን አንድን ኢትዮጵያዊ ወደ እራሱ ሀገር ‘ግባ አትግባ’ ንትርክ ውስጥ መግባት ማለት ነው።የዋሽግተኑ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ጉዳይ ይሄው ነው።ኢትዮጵያውያን በኤምባሲያቸው ቅጥር ግቢ ሆነው የሚያደርጉት ሁሉ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንዳደርጉ ነው የሚቆጠረው።የኢምባሲ ግቢ ማለት የታፈረ የተከበረ ኢምባሲው የተጠራበት ሀገር ምድር ማለት ነው።ለእዚህ ነው አንድ ስደተኛ ወደ አንዱ ሀገር ኤምባሲ ገብቶ ጥገኘነት ቢጠይቅ ኤምባሲው ሀገር እንደገባ የሚቆጠረው እና ኤምባሲው ያለበት ሀገር ፖሊስ ዘሎ ሊገባ የማይችለው።ኢህአዲግ አዲስ አበባ ሲገባ ጣልያን ኤምባሲ እጃቸውን የሰጡ ባለስልጣን የፌድራል ፖሊስ መያዝ ያልቻለው ለእዚህ ነው።ግቢው ሃገሩ ነው።ተቃዋሚዎችም ዋሽግተን ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግቢ ሀገራቸው ነው።የመቃውም መብታቸው ላይ አሜሪካን አይመለከታትም።ጉዳዩ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ነው።አሜሪካ የሚመለከታት በምድሯ ላይ የማይፈቀደው የመግደል ሙከራ፣ማስፈራራት እና ድምፁ በግቢው ውስጥ መወሰን ያልቻለው አካብቢውን ያሸበረው የተኩስ ድምፅ ነው።

ባጭሩ አሜሪካ ኃላፊነት ያለባት የጦር መሳርያ ይዘው ወይንም የሚያሸብር ነገር ይዘው ወደ ኢምባሲ የመጡትን የመጠበቅ እንጂ በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ለመቃወም ሰንደቅ ዓላማ እና የታሰሩ እስረኞች ፎቶ ይዘው ለመጡ አይደለም። እንዲያውም አሜሪካ በእንዲህ አይነቱ ጉዳይ ከገባች አሁንምበኢትዮጵያ የሀገር የውስጥ ጉዳይ እንደገባች ነው የሚቆጠረው።በነገራችን ላይ ከእዚህ በፊት ለአመታት ኢትዮጵያውያን በዋሽግተንም ሆነ ሌሎች ኢምባሲዎች ፊት ሰልፍ ካደረጉ በኃላ የሰልፋቸውን ጥያቄ የያዘ ደብዳቤ ለአምባሳደሩ ለመስጠት ሲጠይቁ የኢህአዲግ የኤምባሲ ሰራተኞች ከፎቅ ላይ ሆነው ቪድዮ ማንሳት እንጂ ደብዳቤ አይቀበሉም።እናም ዜጎች እንዴት ሃሳባቸውን ይግለፁ? ተቃዋሚዎቹ ሌላ አማራጭ ነበራቸው ወይ? የሚለውን የአሜሪካ መንግስትም የሚመለከተው ነው። በሰልፍ ሲወጡ ፖሊስ እንዲጠራ ይደረጋል።በፅሁፍ ሲያቀርቡ ኤምባሲው ለፎርማልቲም ቢሆን አይቀበልም።ልክ ‘ምናምን’ እንደነካው እንጨት ይጠየፋል።

ይህ ትልቅ የኢምባሲዎቹ የትዕቢት መገለጫ ነው።አንድ ዜጋ የፈለገው ጉዳይ ላይ የመቃወም ሃሳቡን በቃልም ሆነ በፅሁፍ የማቅረብ መብት አለው።ኢምባሲው እዝያ በተሰለፈው ሕዝብ እና በቤተሰቡ ገንዘብ ደሞዙን እንደሚያገኝ ዘንግቶ የተቃውሞ ደብዳቤ አለመቀበሉን በምን እንግለፀው? አዲስ አበባ ላይ ሆኖ ”እሰይ ደግ አደረካቸው” እያሉ መፎከር አይደለም።አሰራርን መፈተሽ፣ትዕቢትን መቀነስ ነው የሚያስፈልገው። መጨረሻ ምን ሆነ ዜጎች ”ስሙን!!! ኡ ኡ ኡ !!” እያሉ ወደ ኤምባስያቸው ገቡ።አሳፋሪው ድርጊት ግን የሀገራቸው ኤምባሲ ተኮሰባቸው።ይህ ነው አሳፋሪ ተግባር የሚባለው።ዓለም የገረመው ይህ ነው።ኢትዮጵያውያን ምን አይነት አሳፋሪ አገዛዝ ስር እንደወደቁ የተረዳው እዚህ ላይ ነው።በሀገራቸው የፖለቲካ ጉዳይ የተናደዱ፣ያዘኑ ዜጎች ዋሽግተን ላይ ሃሳባቸውን መግለፅ ካልቻሉ በሃገራቸውማ ቢሆን በታንክ ነው የሚሏቸው ብሎ የደመደመው ለእዚህ ነው።የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ቶሎ መግለጫ አላወጣም።ጉዳዩን የሚመለከተው ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች አንፃር እንደሚሆን ይታወቃል።የውጭ መገነኛ ብዙሃን በተቃዋሚዎች ላይ የመተኮሱን ጉዳዩን ከገለፁበት ቃላት ውስጥ ”በካሜራ የተያዘ ድራማዊ እንቅስቃሴ” ብሎ የዘገበው የእንግሊዝን ”ዴይሊ ሜይል” ይጠቀሳል።

ከሰሞኑ ዋሽግተን ላይ ከተከሰተው ክስተት አንፃር ኢትዮጵያውያንም ለሁሉም ወገን ማስረዳት ያለባቸው ከላይ ከተጠቀሱት የአፈና ደረጃዎች አንፃር መሆን ይገባዋል።ፀሐፊዎች፣ጋዜጠኞች፣በውጭ ሀገር በልዩ ልዩ ኃላፊነት ላይ ያሉ ሁሉ ለዓለም (ለአሜርካኖችም ጭምር) ማስረዳት በእንግሊዝኛም መፃፍ ይጠበቅባቸዋል።የኢህአዲግ አድናቂዎችም ከህሊናችሁ ጋር ኑሩ! እውነታውን መርምሩ።መንግስታችሁ እንዴት ወዴት እየሄደ እንዳለ እና በውስጡ የተሰገሰጉት የትዕቢት አባቶች አደብ እስካልገዙ ድረስ ከትርፍ ይልቅ ኪሳራው እየበዛ መሄዱ አይቀርም።ዓለም አቀፍ ሕግን ግን ለቀቅ አድርጉት።

ጉዳያችን
መስከረም 21/2007 ዓም (ኦክቶበር 1/2014)

አማራው የራሱ ሚዲያ ኖሮት ቃል በቃል ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ፥ ምላሽ ለጀዋር መሃመድ የቃለ ምልልስ ቅጥፈት

$
0
0

Download (PDF, Unknown)

በአበበ ተድላ፣ እሑድ መስከረም 18 ቀን 2007 ዓም

አማራው የራሱ ሚዲያ ኖሮት ቃል በቃል ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ ምላሽ ለጀዋር መሃመድ የቃለ ምልልስ ቅጥፈት
በትክክለኛው መሆን የነበረበት በሚዲያዎች ይህ ሰው የሰጠው ቃለመጠይቅ እየተደመጠ ቃል በቃል ምላሽ መሰጠት ነበረበት። ነገር ግን አማራው በሁሉም ዘርፍ ሊከላከልለት የሚችል አካል ስለሌለው እና ሚዲያውንም ጨምሮ መሳ ለመሳ የሆነ የተጠናከረ ሃይል ለጊዜው ስለሌለው በግሌ ለግለሰቡና ለሱ ሃሳብ አራማጆች መልስ ልሰጥ ተገድጃለው። እዚህ ጋር ቃለመጠይቁን ፖስት ማድረጌ መርዝ ንግግሩን ማሰራጨት ቢሆንም አዲስ ሃሳብ ሳይሆን ሁሌ የሰማነው ስለሆነ እና ባግባቡ መልስ እስከተሰጠበት ችግር የለውም ብዬ ነው ለመረጃነት አብሬ ያቀረብኩት። መልሱም ቃል በቃል ሳይሆን ጠቅለል ባለ መልኩ በሁለት ክፍሎች ከቀረቡት የተወሰኑ የከፉ ወሸቶችን/ግነቶችን ነው።

1. “በአንድነት ስም ያሉ ፓርቲዎች (ባንተ አገላለፅ አማራዎች) እኔ ኦሮሞነቴን እንኳን ሊቀበሉ አይፈልጉም ኦሮሞ ነኝ ስል ዘረኛ ይሉኛል” ጀዋር መሃመድ
እንግዲህ ከዚህ የበለጠ ውሸት ምን ሊኖር ይችላል። ማን ኦሮሞ ነኝ ብለህ ኦሮሞ አይደለህም ያለህ አለ? ይልቅስ አስበህው ታውቃለህ ኢትዮጵያዊያን በጣም የተቀላቀልን ስለሆንን የተለያየ ብሄር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የለም አንዱ ወገኔን መካድ አልፈልግም እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲሉ መብታቸውን እንደተከለከሉ እና አንዱን ክደው አንዱን እንዲመርጡ እንደተገደዱ? ከኦሮሞ ይልቅ አማራ ማንነቱን እንዲያጣ እንደተካደ ልብ ብለህ ታውቃለህ? ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሄር መቁጠር አልፈልግም ሲል አማራ የለም እንዲህ የሚሉት የድሮው ስርአት ናፋቂዎች ናቸው እየተባለ ኢትዮጵያዊ ነኝ እንዳይል ጥረት ይደረጋል አፉን ያዘጉታል። እሺ እንግዲህ የቸገረ ከሆነ እና ወደኃላ ተመልሰን ብሄር መቁጠር ግድ ከሆነ ልቁጠር አማራ ነኝ ሲል የለም አማርኛ ተናጋሪ እንጂ አማራ የሚባል ብሄር የለም ይሉታል። ሰዎች አማራ ብሄር ብለው እያሳደዱት እየገደሉት እነሱ አይደለም አማርኛ ቓንቓ ተናጋሪዎች ተሰደዱ ይላሉ አስሰዳጆቹም አማርኛ ቓንቓ እየተናገሩ። አሁን ሰሞኑን ደግሞ ከመሃል አገር የመጡ ከሰሜን የመጡ መባል ተጀምርዋል አማራው ተለይቶ ሲጠቃ እያየን አማራው ተጠቃ ላለማለት። እንግዲህ ኢትዮጵያዊም መሆን አማራም መሆን የተነፈገው አማራ እያለ አንተ እሹሩሩ ለተባልክ ምን ተብለህ ነው ኦሮሞ ነኝ ስል ኦሮሞነቴን አልተቀበሉኝም የምትለው? የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ ማለት ይሄ ነው። አዎን ምንም ስለ ብሄር እኩልነት ብናወራ ብሄር ከሃገር አይበልጥም ስለዚህ “Oromo first” and “Ethiopia out of Oromia” ማለትህ እንዳሳፋሪነት ቢጠቀስ ኦሮሞነትህን መካድ አይደለም። አንተ ያለህበት አገር አሜሪካ በሃገር ጉዳይ/ጥቅም ምንም ድርድር የለም እና በሃገር መደራደር አትችልም ነው የተሰጠህ መልስ እንጂ ማን ኦሮሞ ነኝ አትበል ቓንቓህን አትናገር ባህልህን አትጠብቅ አለህ? ግልፅ ነው መጀመሪያ ሰው ስለራሱ ከዛ ስቤተሰቡን ከዛ ስለቤተዘመድ ከዛ ስለአካባቢው ሰው (ባንተ አስተሳሰብ ስለብሄርህ በለው) ያስባል። ነገር ግን ስላራስህም ሆነ ስለሌላው ለማሰብ የሚቻለው መሬት ላይ ቆመህ አገር ላይ ቆመህ ነው እንጂ አየር ላይ ቆመህ ስላልሆነ ቅድሚያ ስለሃገር ማለት ነበረበት ተብለህ ብትወቀስ አይገርምም። ለነገሩ አንተና መሰሎችህ እንደ ኤህነግ (ሻቢያ) ከኢትዮጵያ መሬት ላይ ቆርሳቹ አዲስ አገር ስለማቓቓም እንጂ (ያውም በሸሪያ የሚተዳደር አገር) ስለእኩልነት ስለማታስቡ አገር የምትሉት ማንን እንደሆነ ይታወቃል።በሚቀጥለው ነጥብ ላይ መልስ ሰጥበታለው።

2. “የአንድነት ፓርቲዎች (በተለይም አማራዎች) ትንሿን የፌደራሊዝም መብታችንን እንኳን ሊቀበሉ ዝግጁ አይደሉም” ጀዋር መሃመድ
ብሄርተኝነት አይንን እንደሚከልል ቢታወቅም ይሄን ያህል ግን እንደሚያሳውር እና አንድ የማሰቢያ አእምሮን ቆርጦ እንደሚያወጣ በጀዋር እና መሰሎቹ መረዳት ችያለው። እንዴት ነው ነገሩ እነሱ (ትህነግ፤ኦነግ ወዘተ) ያሉትን የብሄር ፌደራሊዝም (ያውም የአማራውን ብሄር መብት ያላካተተ የብሄር ፌደራሊዝም) አለመቀበል ማለት አጠቃላይ የፌደራሊዝምን ስርአት አለመቀበል ነው ያለው ማነው? በድሮው ስርአት አልተወከልንም ድምፃችን አልተሰማም የሚል ወገን እንዴት ነው 1/3 የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ አማራው ባልተወከለበት የተካሄደ የመሬት ሽንሸና ያለማመንታት ተቀበሉ የሚሉን? ሲጀመር ድሮም አሁንም እኮ አማራው ደሃ ነው ጥቂት የአማራ ልሂቃን ናቸው አገሪቱን ከሌላው ብሄር ልሂቃን ጋር ሆነው የጨቆኑት ያደሞ የኦሮሞ ልሂቃንንም ይጨምራል ሲባሉ የለም እነኛ ኦሮሞዎች ኦሮሞን አይወክሉም ይሉናል። እኔምለው መቼ ነበር አማራው ታዲያ ይወክሉኝ ብሎ ልሂቃኑን ልኮ የተወከለው በቃ የተደራጀ ጉልበት ያለው ያሻውን አድርጎ አለፈ እንጂ። ከቀደሙት መሪዎች መልካም ነገራቸውን ተምረን ጥፋታቸውን እንዳይደገም አድርገን እንለፍ ሲባሉ የለም መጀመሪያ ይሄንን ተቀበሉ ይላሉ አለበለዚያ በደፈናው ስም ይሰጥሃል። ስታስቡት በሰሜን ትግራይ በምስራቅ አፋር በምዕራብ ቤኒሻጉል በደቡብ ደሞ ኦሮሚያ እያላቹ አጎቶችህ ኦነግ ከትህነግ ጋር ተስማምቶ አማራንም ሆነ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ህዝበ ውሳኔ ሳይጠይቅ የተፈጠረ የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ባንቱስታን ስታይል አከላለል ተቀበሉ ስትሉ አታፍሩም? አዲስ አበባን ጨምሮ ቁጥራቹ ያነሰበት ቦታ የለም በታሪክ የኛ ነበር ትላላቹ ልክ ምድር ስትፈጠር ጀምሮ እዛ ቦታ የኖራቹ ይመስል (ታሪክ የ 200 አመት ብቻ ሳይሆን 500 ከዛም 1000 ከዛም 3000 እያለ ይቀጥላል ቅንጭብ አድርጋቹ አትውሰዱ)። ያውም እንደኢትዮጵያ ባለ ብዙ ሲቪል ዋር ውስጥ ባለፈች ህዝብ ከቦታ ቦታ በጦርነት በረሃብ በተለያየ ምክንያት በሚሰደድባት በሚቀላቀልባት ሃገር ይሄ ቦታ የኛ ብቻ ነው ሲባል እንዴት ሰው አያፍርም። እህ በአማራ መካከል በዛ ያለ ኦሮሞ ሲኖር ደሞ አማራ ብላቹ ቁራጭ ከሰጣቹት መሬት ላይ ልዩ ዞን ምናምን ተብሎ ለብቻ ይከለላል። ምነው ኦሮሚያ የተባለው ክልል ውስጥ በርካታ አማራ ያለበት ቦታ ልዩ ዞን አልተፈቀደም? አማራው የመምረጥ የመመረጥ መብት አለው ኦሮሚያ በተባለው ቦታ ሁሉ ነው ያልከው ሳታፍር በዛውም የትህነግን የምርጫ ድራማ እያፀደክላቸው ማለት ነው? እስቲ ሃረር ድሬዳዋን እንመልከት አማራም ኦሮሞም ሃረሪም ሶማሌም ሌላውም አለ ነገር ግን ተለይቶ አማራው መብቱ እንዳይከበር እና በሌሎች መልካም ፍቃድ እንዲኖር የተደረገበትን ስርአት ነው እንግዲህ ልክፍተኞቹ ያለድርድር ተቀበሉ የምትሉት? አሳፋሪ ነው። የሁሉንም መብት የሚያከብር ሁሉን አቀፍ የሆነ ስርአት ማሰብ አትፈልጉም። አገሪቱ ብሄራዊ ቓንቓ ሳይኖራት የተለያየ አገር ከምትሆን (አሁን አማርኛ ፌደራል ቓንቓ ብቻ ነው) ቢሆን ህዝቡ ከመረጠ ሁለት ብሄራዊ ቓንቓ ይኑራት እና አንድ ሰው ሌላ የሃገሪቱ አካባቢ ሲሄድ ሌላ ሃገር የሄደ ይመስል አዲስ ቓንቓ ያውም ብሄራዊ ቓንቓ ያልሆነ ማጥናት ሊገደድ አይገባም ቓንቓ ማወቅ መልካም ቢሆንም ሲባል የድሮ ስርአት ናፋቂዎች ትላላቹ እንዲህ ያለ ቢቻል ሁለት ብሄራዊ ቓንቓ ይኑረን የሚል ሃሳብ ድሮ ያለ ይመስል።

አንድ አማራ የተባለ ክልል ውስጥ ተወልዶ አማርኛ ብቻ የሚናገር ወይንም የሌላ ክልል የተባለ ግን ከተማ ስለሆነ አማርኛ በብዛት ስለሚነገር አማርኛ ብቻ እየተናገረ ያደገ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አማርኛ ስለሆነ የሚናገረው ትግራይ ተብሎ የተከለለው ልሂድ ቢል ትግርኛ ማጥናት አለበት ወይ ደሞ ኦሮሚያ ተብሎ ወደተከለለው ቢሄድ ኦሮምኛ ማጥናት አለበት ወደ ሶማሌ ወደተባለውም ከሄደ እንዲሁ ማለት ነው። ታዲያ ስንት ቓንቓ ያጥና ያ/ያቺ ሰዉ በገዛ አገሩ ለመኖር? ሌሎቹ ብሄሮች ግን አማርኛን በተለያየ አጋጣሚ ስለሚማሩ የትም ሄደው ይሰራሉ። ከዚህ በላይ አፓርታይድ ስርአት አለ? አገሪቱ ሁለትም በሉ ከዛ በላይ ብሄራዊ ቓንቓ ህዝቡ እስከመረጠ ድረስ ማለት ነው እና ሁሉም ህዝብ ከብሄራዊ ቓንቓ በተጨማሪ አካባቢያዊ ቓንቓ ይጠቀሙ ቢያንስ ሁሉንም የሚያግባባ ነገር ስለሚያስፈልግ እንደሃገር እስከቆየን ሲባል የለም አካኪ ዘራፍ ከኦሮምኛ ውጪ እዚህ አይነገርም ትላላቹ ትህነጎቹ ደሞ ከትግርና ውጪ እዚህ አይነገርም እንደሚሉት ወዘተ። አማራም ሆኖ ከአማርኛ ውጪ እዚህ አካባቢ እንዳይነገር የሚል ካለ ከናንተ አይለይም። በግሌ አማርኛና ኦሮምኛ ብዙ ተናጋሪ ስላላቸው የሀገሪቱ ብሄራዊ ቓንቓ ቢሆኑና ሁሉም በየአካባቢው ከራሱ ቓንቓ በተጨማሪ በብሄራዊም ቓንቓ ቢጠቀም አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ያስማማል ባይ ነኝ ግን ውሳኔው የህዝብ ነው። ያኔ ውድድሩ ለሁሉም እኩል ይሆናል አገሪቱ የሁሉም ትሆናለች ማለት ነው። አለበለዚያ ወይ ቁርጥ ባለው ፓስፖርት መጠየቅ እኮ ነው የቀረው ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ በገዛ አገራችን። ያደሞ አይሆንም አንቀበልም ምክንያቱም አከላለሉ አማራን ግምት ውስጥ ያስገባ አልነበረምና እንዲሁም ደሞ በብሄር ክልል ድንበር መቼም ልንስማማ አንችልም ተቀላቅለን ስለኖርን ጉልበት ያለው ድንበር ያስምር ካልሆነ በስተቀር ጨዋታው። ለነገሩ ህገመንግስት የተባለው የኢትዮጵያ ድንበር ሳይሆን የሚጠቅስ ክልል ያላቸውን ድንበር ነው ና ኢትዮጵያ የምትባል ሀጋር ራሱ በህገመንግሱቱም የለችም። ይቺ ዘዴ ትህነጎች (ወያኔዎች) ትግራይን ለግል ሌላውን የኢትዮጵያ ክፍል በጋራ ለመጠቀም ብለው ኤርትራዎች ያደረጉትን ኤርትራን ለግል ሌላውን ኢትዮጵያ በጋራ ብለው መጀመሪያ እንዳሰቡት ማለት ነው። ለመሆኑ ሌላ ቦታ ተውና አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ በሆነችው አርከበ የሆነች ሰአት ከመሾሙ በስተቀር ለምን ኦሮሞ ከንቲባ ብቻ ሁሌ ይሾማል በትህነግ ዘመን? ሌላ የሚመጥን ሰው የለም? ይሄንን ነው ዋና ከተማ መብት ሳይኖር ሁሉም ቦታ አማራም ማንም የመመረጥ መብት አላቸው የምትለው? ለነገሩ የትስ ማንም ይሾም ማን ትህነግ ነው የሚያስተዳድረው ጉልቻ ማለዋወጥ ካልሆነ እንዲያው ለነገሩ አነሳሁት እንጂ። ችግሩ ምን መሰለህ የአንድነት ፓርቲ የሚባሉትም ኦሮሞውን እንዳይከፋው በሚል ይሄንን አሳፋሪ የአከላለል ሸፍጥ ሲያነሱ እና ሲከራከሩ አማራ ያኔ አለመወከሉን ሲናገሩ አይሰሙም አማራውን ሲፈልገው ይከርፋው ኢትዮጵያ የምትባለው ስም እስከጠራን የትም አይሄድም በሚል የተሳሳተ ግምት። አልፎ አልፎ የወልቃይት ጠገዴ ከዚህ በፊት ትግራይ ሆኖ አያውቅም አሁን ነው ወደ ትግራይ የተከለለው ከማለት በስተቀር ፕ/ር አስራት ወልደየስ የተቃወሙትን እና ህይወታቸው ያለፉበትን ምክንያት አማራው 1/3 የኢትዮጵያ ህዝብ ሆኖ ሳለ አንድም አማራ ሳይወከል ህገመንግስት ተብዬው ጭምር እንደፀደቀ የአንድነት ፓርቲዎችን ጨምሮ ማንም ሲቃወም አይሰማም። ስለዚህም የልብ ልብ ተሰማቹ እና by default ሁሉም ሰው ይሄ ብዙ ሚሊዮን አማራም ሆነ ሌላውን ኢትዮጵያዊ በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዜጋ የሚያደርግ ሲስተም የአለም ምርጥ ፌደራሊዝም እንደሆነ የትህነግ (ወያኔ) አፈቀላጤ ሆነህ እየተናገርክ ከዚህ ውጪ አይታሰብም ትላላቹ።

የሚገርመው ደግሞ በኦነግም ቻርተር ላይም ይሁን አሁን ኦሮሚያ ተብሎ በተከለለው ውስጥ ያለው ሌላው ኢትዮጵያዊ እኩል የመምረጥ የመመረጥ መብት አለው መብታቸው እየተከበረ ነው ያልከው? አሳፋሪ ሰው ነህ የትህነግ ምርጫ የውሸት ነው እንዳላልክ አሁን ደሞ የኢትዮጵያ ህዝብን ንቀህ አያስተውልም ብለህ ይሀው ሌላ ውሸት ታወራለህ። በመጀመሪያ ትህነግ ህገመንግስት ተብዬው ወረቀት ላይ ስለ እኩልነት ያልፃፈው ህግ አለ? ስለሰብአዊ መብት አከባበር ምን ያልፈረመው ወረቀት አለ ትህነግ አይተገበርም እንጂ? እኛ ህግ ወረቀት ላይ መፃፍ መቼ ቸገረን መተግበሩ እንጂ? ሀገሪቱ እንደሃገር የራሷ ብሄራዊ ቓንቓ ባይኖራትም እኮ ህገመንግስት ተብዬው ሁሉም ሰው በመላ ሃገሪቱ ተዟዙሮ መኖር ይችላል እያለ እኮ ነው ትህነግ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያላቆመው የአማራውን የዘር ማፅዳት ዘመቻ የሚካሄደው ያውም ሰዎች ለዘመናት ከኖሩበት አገር አማራ ናቹ ብቻ በሚል (ልብ በል አማርኛ ተናጋሪ አላልኩም አማራ እንጂ)። ግን አስበህው ታውቃለህ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ትተህ አማራው ብቻ በገዛ ሃገሩ ሀገር እንዳይኖረው የተደረገው ህዝብ ቁጥሩ ከትግራይ ወይንም ከሶማሌ ህዝብ ተብሎ ክልል ተከልሎ ከተሰጠው በላይ እንደሆነ? ማሰብ ተሳነህ ጠባብ ብሄርተኝነት ስንት ነገር ያነበበን ሰው የተለያየ አገር በማየት እንኳን ልምድ የቀሰመውን ፖለቲከኛ ሰው በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዚጋ ሲሆን የሚፈጠረውን ይቺን እንዳያስብ አሳወረው መሰል ያውም ተበድለን ነበር ከሚል ወገን ማለት ነው።
ሌላው በቀደመው ዘመን ንጉስ የሚናገረው ቓንቓ እና ንጉስ የሚከተለው ሃይማኖት እንዲከተል ማድረግ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የትም የነበረ ነው። በዚህ ዘመን ይሄ ቀርቷል ከተወሰኑ የእስላም ሃገሮች በስተቀር ሁሉም በእስልምና እንዲተዳደር ከሚደረግበት ሁኔታ በስተቀር። አንተም የነሱ ግርፍ ስለሆንክ ይሀው አንተ ያልከው ካልሆነ ሞቼ እገኛለው ትላለህ የቀደሙትን የራሳቸውን አላማ ብቻ አካሄዱ እያልክ እየወቀስክ። አትርሳ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን አንተ አትጫኑብኝ ስትል ሌሎች ላይ አለመጫንህን አስብ አንደ IS (ISIS) የማታስብ ካልሆነ በስተቀር። ለነገሩ የ OMN ሎጎም የየመን ወይን የግብፅ ባንዲራ ሲመስል እያየን የእስላም አክራሪዎች ሚዲያ እንደሆነ አይጠፋንም። የኦነግ ባንዲራ ሌላ ነው ኦነግ ይሄንን የአረብ ሃገሮች ባንዲራ የመሰለውን ጥቁር ፤ቀይ፤ ነጭ አያውቀውም ነበር እንዳትሉኝ ኦነግ ሲመሰረት ይሄንን ባንዲራው ያላደረገበት። የኦሮሞን እኩልነት ጥያቄ የእስላም አክራሪዎች ጠምዘው የእስላም ሃገር ለመመስረት እየሰሩ እንደሆነ ጸሃይ ያወቀው አደባባይ የሞቀው ስለሆነ ብዙም ስለዛ እዚህ አላወራም።

3. “ኦሮሞ ራስን መቻል ለአማራ ስጋት አይደለም በኦሮሚያ ገንዘብና ሃብት አማራዎችንም ሆነ ሌሎችን በአማርኛ እያስተማርናቸው ነው።” ጀዋር መሃመድ
በጣም ከሚያሳፍሩ ንግግሮቹ አንዱ ይሄ ነው። የሆነ ሰዉ ግብፅ ወይንም የመን እየኖረ ለህዝቡ በመልካም ፈቃደኝነት በአንተ ችሮታ ስጦታ የሰጠህና የፅድቅ ስራ አስመሰልከውእኮ። እኔምለው ጀዋር ይሄ ትናንት ትህነግና ኦነግ ኦሮሚያ ብለው ያሰመሩትም ሆነ ሌላ የተከለለው ነገር ሁሉ በኢትዮጵያዊያን የተገነባ ትናንት ወረቀት ላይ ከመሰመሩ በፊት በኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቀረጥ በከፈለው የተገነባ ሃገር መሆኑን ረሳህው? ቀረጥ ከፍዬ እንደዜጋ ያለኝን መብት ደግነት አደረከው ትንሽነትህን ሲያሳይ። እነኚህ ሰዎች እኮ አገሬ ብለው እየኖሩ ሳለ በድንገት ይሄ ኦሮሚያ ሌላ ሌላ እየተባለ በጎጠኞች ተሸነሸነ እንጂ እኮ አገራቸው እየኖሩ ያሉ ሰዎች እኮ ናቸው በናንተ ችሮታ እያስተማራቹሃቸው ያሉ ያስመሰልካቸው። ያውም ትምህርት ሲጨርሱ ሌላ ክልል ሄደው ሊሰሩ እንጂ የኛ ባላቹትማ የግድ ኦሮምኛ መማር አለባቸው። እንደመብት ሁሉም አፉን በፈታበት ቓንቓ ይማር ትክክል ሆኖ አንተ ግን ውለታ ለሌላው የዋልክ አስመሰልከው። መሆን የነበረበት ሁለት ቓንቓ የስራ ቓንቓም የትምህርት ቓንቓም ሆኖ ሰው በፈቀደው መማር ሲሆን እናንተ ግን ልክ እንደደግነት አማርኛን እንዲማሩ እንደፈቀዳቹ ስታደርጉ አያንቅህም? ከዛም ደሞ ይሄን የመሰለ ፌደራሊዝም ስለሌላ ይሄንን ተቀብላቹ ነው የምንደራደር ስትልም አታፍርም። የምታብጠለጥሉዋቸው በተለይ ከአፄ ምኒሊክ ጀምሮ የቀደሙት መሪዎች እኮ የሁላችንም አገር በሚል ሁሉም መሃል ሀገራ አካባቢ ነው በኢትዮጵያዊያን ገንዘብ (በኦሮሞ ብቻ ሳይሆን) ልማት የሰራው እንጂ የብሄር አገር መርጠው አልሰሩም። አጼ ምኒሊክ አንኮበር ለብቻ ምንም አልሰሩም። ደረቆቹ በሁሉም ኢትዮጵያዊ የተገነባ ሃገር (ልማቱ እንዳቂሚቲ ቢሆንም ማለቴ ነው) በሁሉም ኢትዮጵያዊ ደም በምእራብ ከደርቡሽ፤ በምስራቅ ከቱርክ እና ዚአ,ድባሬ እንዲሁም በሰሜን ከብዙ ጠላት በኦሮሞ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ደም የተጠበቀን አገር ድንገት ተነስታቹ የኛ ብቻ ነው ስትሉ ሌላውን በናንተ መልካም ፈቃድ እንደሚኖር ስታደርጉ ትንሽ አያንቃቹም። ለነገሩ አማራው አዚም የፈሰሰበት ይመስል ተኛላቹ ፈነጫቹ። እርግጥ አማራው እንዴት አይተኛ ከደርግ ጀምሮ ሲቀጠቀጥ እንደብሄርም እንዳይኖር ያልተቃጣበት ሴራ የለምና። እኩልነት መብታችን ባህላችን ይከበር ሌላ እኛ የበላይ ሆነን እኛ የፈቀድነው ብቻ ይሁን ሌላ! አየው ሌላ ወየው ሌላ አሉ!
4. “የኦሮሞ ተማሪዎች በጠራራ ፀሃይ በትህነግ ወታደሮች መገደል በቂ ሽፋን አላገኘም አብረውን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አልጮሁም በተለይም በአማራ ልሂቃን ሚዲያዎች ለዞን 9 ብሎገርስ ከተሰጠው ትኩረት አኳያ” ጀዋር መሃመድ

መቼስ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ። እኔ እንግዲህ እስካየሁት ድረስ ጀዋርን ካገነኑት ሚዲያዎች አንዱ የሆነው እነ ኢሳትን ጨምሮ ይሄንን ሲዘግቡ ነበር። ምስጋና ቢስ ቢሆኑም ያውም ኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን ሰልፈኞቹ ሰልፍ ላይ ምን ይዘው እንደወጡ እያየን ስንት ሰው አብሮአቸው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ስለሆኑ ተሰልፍዋል። እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን ይደረግ? አማራው ይሀው 23 አመት በትህነግና አጋሮቹ ሲጨረስ መቼ ነበር ኢትዮጵያዊ ለአማራ ሲሰልፍ ያየሀው ባሁኑ ሰአት ጭምር አማራው እየተጨፈጨፈ ማለት ነው? ሌላም ብዙ ኢትዮጵያዊ እያለቀ ያልተጮሀላቸው ብዙ አሉ ምን ስለ ኦሮሞ ብቻ ታወራለህ? እንዲያውም ኢትዮጵያዊ ናቹ ይሉናል ስንሞት ግን ኢትዮጵያዊ ናቹ ብለው ኢይጮሁልንም ነው ያልከው ደሞ? ካንተ የበለጠ ሚዲያዎች ሁሉ ሲያራግቡት ነበር ምናልባት አንተ በጠባብነት ስለታወርክ ሌላው የሚያደርገውን ሁሉ አልታይህ ብሎህ ይሆናል። እኔምለው ልጆቹ ወያኔ እና እናንተ አስተምራቹሃቸው ይዘው የወጡትን መፈክር ረሳህው እንዴ? ኦሮሚያ ለኦሮሚያ ብቻ አማራ ትግሬ ኦሮሚያ ከተባለው ይውጣ እኮ ነው ያሉት መፈክራቸውን ባይናችን እያየን? የቱጋር ነው ያሳደጋቹሃቸው ልጆች ስለኢትዮጵያ ያነሱት እና ኢትዮጵያዊያን ያልጮሁላቸው የምትል? ሌላው ቢቀር ደብረማርቆስ ጭምር እኮ አማራው የኦሮሞን ወገኖቻችንን አትግደሉ ብለው ሰልፍ ወጥተውላቸው ነበር ምኑ ከሃዲ ነህ። እንደዚህም ሆኖ ነበር እንግዲህ ህዝቡ የወያኔን ያልታጠቁ ወጣቶችን ግድያ ያወገዘ በምንም ሁኔታ ትክክል አይደለምና። ዝም ያለ የለም ምንም ይሁን ጥያቄያቸው የትህነግ ደህነኖቶችና ወታደሮች የወሰዱት እርምጃ ግፍ ጥጋብ ነውና። በጣም የሚያሳዝነው የጠገበ የትህነግ ወታደር ኦሮሞ ኢትዮጵያዊያንን ለገደለ የትህነግ አሻንጉሊት ኦህዴድ ኦሮሞዎችን አደራጅቶ ከርታታ የአማራ ደሃዎችን እየገደለ እያሰደደ ነበር። ኢሳት እርሙን ያንን እውነታ ከጊምቢ ዘግቦ መልሶ ይቅርታ አለ ስትጮሁ ስለተደራጃቹ ያልተደራጀው አማራ አፈር ለምን አይግጥም ብሎ? እንግዲህ የቱጋር ነው ታዲያ የኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን በግፍ መገደል አትኩሮት አላገኘም የምትለው? የወጣቶቹም ሆነ የሌሎች እስረኞች ጉዳይ ሁሌም ያለ የወያኔ ግፍ ሲሆን እስካሁንም የሚዲያዊችን ትኩረት እንደሳበ ነው ምንድነው ከኦሮሞነት ጋር የምታቆራኘው ለመሆኑ የልጆቹ ብሄር ምን እንደሆነ ማን ያውቃል? የሚያሳዝነው የምትለው ለዚህም አንተ ለታየህ ነገር ተጠያቂው አማራው ነው ማለትህ ነው። መቼ ነው ከአማራው ራስ ወርዳቹ እየገደላቹ ያለውን ትህነግ የምትቃወሙ? ለነገሩ አንተ ንግግርህ ሁሉ በተቃዋሚ ስም የወያኔ አፈቀላጤ ሆነህ ሰራህ እንጂ ምንም ወያኔን የሚቃወም ነገር አልወጣህም ስልጣን ለብቻ ቶሎ ይስጠን ከማለትህ ውጪ።

ጀምረህ እስክትጨርስ አንገቱን እንዲዲፋ የተደረገውን አማራ እንዲያውም እንዳያቆጠቁጥ አድርገን እናጥፋው ብለህ የወያኔን ቃል ነው የደገምከው። በነገራችን ላይ ኦህዴድ እና ኦነግ ልዩነታቸው አንድ ብቻ ነው። ኦህዴድ ትህነግ እስኪጠግብ በስሩ ተለጥፌ ኦሮሚያ የምትባል አገር ቀስ እያልኩ ሰራለው ሲሆን ኦነግ ደግሞ የለም ያኔ ስንገናኝ መስመር ያሰመርንባትን ኦሮሚያ የምትባለዋን ሙሉ በሙሉ ዛሬ ይሰጠኝና እንዳሻኝ ካሁን ጀምሮ ልዘዝበት ሲል ገና ከርሱ ያልሞላው ትህነግ የለም ገና ብዙ የኢትዮጵያን ንብረት ስለምዘርፍ ብሎ ኦነግን አሁን የፈለከውን ስልጣን አልሰጥህም ብሎ አባረረው። እኔምለው ግን አማራው ባሁኑ ሰአትም ጨምሮ ላለፉት 23 አመታት ተራ በተራ ክልል ተብለው ድንበር ከተበጀላቸው በኢትዮጵያ መሬት በትህነግ እና አጋሮቹ ባሁኑ ሰአት ጭምር ሲጸዳ (ስለ ጋንቤላ ተብሎ ስለተከለለው አካባቢ መስማት ባትፈልግም ስለአማራው እልቂት ሳትሰማ አትቀርም ብዬ ነው) ምንም ሰልፍ አላየንም እኮ እንዴት አየሀው ታዲያ ኢትዮጵያዊያኖቹን አትወቅሳቸውም ታዲያ ለዚስ ወይስ እሰየው እያልክ ነው። ታዲያ አማራው ኢትዮጵያዊ ሆኜ ሰልፍ ሳይወጡልኝ መች አለ? የአማራ ነፍስ የዶሮ ነፍስ ይመስልሃል? ለነገሩ ቀና ቀና የሚል ክርስቲያን በሜጫ አንገቱን ነው የሚባል ያለ የአማራ ነፍስን አሳንሶ ቢቆጥር እና ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ቢል አይደንቀኝም። እርግጥ አንተ ና መሰሎችህ ብቻ ሳይሆን ብዙ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተቓማት በመቶዎች የሚቆጠር ህይወት ሲጠፋ እንኳን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፀመ የሚሉ አማራው በሚሊዮን የሚቆጠር ሰው ሲጠፋም ዝም ስላሉ አይገርመኝም። አማራው ስለተኛ ለሱ ታዲያ ማን ይከራከርለት? አንድ ነገር ግን እስማማለው። አንድ የትህነግ አባል የሆነች የሆነ ሰሞን እንደተለመደው አማራውን ሲጨርሱ ሰዉ ሲንጫጫ ተዉት የዲያስፖራ ፖለቲካ እንደ ፈንዲሻ አንድ ሰሞን ቻቻ ብሎ ፀጥ ይላላ ያለችው ውስጤ እውነት ነው እንዴ ብሎ ሁሌ ያቃጭላል። ምክንያቱም አንድ ነገር አንድ ሰሞን ሲሰማ ሃይ ሃይ ይባላል ከዛ ይረሳል አዲስ ሲመጣ ደሞ እንደገና ሃይ ሃይ እንጂ የተቀናጀ ነገር የለም። የኦሮሞውም እልቂት እንዲሁ ተዘንግታል ከሆነ ለብቻቸው ባይሆንም ልክ ነው የመርሳት ችግር በደንብ አለ። አጠቃላይ የ ኢትዮጵያዊው የ memory span እንደገና መታየት አለበት ብዙ ነገር ትተን የፊት የፊት ብቻ ስንጮህ ይሰማልና።

5. ድምዳሜ።
አንደኛ ጀዋር መሃመድ በግልፅ ወያኔ መሆኑን አረጋገጠልን። ከወያኔ ይልቅ ሙሉ ጊዜውን አቅም የሌለውን አንገቱን እንዲደፋ የተደረገውን አማራን በማውገዝ ያሳለፈ ሲሆን የሚገርመው እዚህ ሆኖም ኢትዮጵያን አሁንም እንደሚያስተዳድር ነው የሚዘባርቀው ምናልባት ውስጥ ለውስጥ ግንኙነት ስላለው ሊሆን ይችላል።

ሁለተኛ ደጋግሞ ሲናገር እንደሰማቹት ተንቀን ተንቀን ይላል። ማን ማንን እንዴት እንደናቀ ባይናገርም እንግዲህ ካንዱ ጋር ሲከራከር ምንዳለው እኔንጃ ደሃው አማራ ህዝብ ምንም በማያውቀው ተንቀን ይላል። እርግጥነው አለማችን በግለሰቦች ወይንም ቡድኖች እልህ መያያዝ ምክንያት ስንቱ ሰላማዊ ህዝብ እንዳለቀ እናውቃለን ዝሆኖች ሲጣሉ የሚጎዳው ሳሩ ነው እንደሚባለው ማለት ነው። ሌላም ሳንሄድ በመለስና ኢሳያስ ወይንም በትህነግ (ወያኔ) እና ኤህነግ( ሻቢያ) እልህ መያያዝ ያለቀውን ሰው ቤቱ ይቁጠረው። ስለዚህ ይህ ሰው እና መሰሎቹ ከየትኛውቹ ግለሰብ ይሁን ቡድኖች ከፍተኛ የሆነ እልህ እንደተጋባ ባናውቅም ለእልህ ሲባል ምን አይነት አደገኛ ጉዞ እየሄደ እንደሆነ ልብ በሉ። የዚህ አይነት ሃሳብ ብዙ ጊዜ የዝቅተኝነት ስሜት በሚሰማው የሚታይ ሲሆን ከዚህ ህመሙ እግዚአብሄር ይማረው ከማለት በስተቀር ምንም ማለት አይቻልም። ግን ደሞ እንቅስቃሴው ተንቆ የሚተው አይደለም። ጠላቱን የሚንቅ ፖለቲካ ያልገባው ነው። እነ ትህነግ (ወያኔ) እና ኤህነግ (ሻቢያ) ተንቀው ነው ይሀው ዛሬ ያለንበት ጥፋት ላይ ያደረሱን። መለስ የባንዳ ልጅ እየተባለ አንገቱን ሲደፋ ስላደገ የዝቅተኝነት ስሜት ያሳደረበትን ኢትዮጵያዊነት የሚባለውን ለማዋረድ የቻለውን ሁሉ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ የምትባል አገር አምርሮ እነደጠላ፤ሃገሪቱ እንጂ ኢትዮጵያ ብሎ ሳይጠራ ሊበታትናት የቻለውን ሁሉ አድርጎ ሞተ።

ሶስተኛ ጠባባብ ብሄርተኝነት መቼስ በቀላሉ የማይለቅ አደገኛ በሽታ ስለሆነ እና አመለካከትን ሁሉ አሳውሮ እኛ ከሚለው አውጥቶ እኔ ወደሚለው ያመጣል እና ከጀዋር ሃሳብ ላይ ልክ ትህነጎቹ (ወያኔዎች) ላይ እንደታየው የሱ ወገን የሆነው ቅዱስ ደሙ ንፁህ ሌላው ደሞ ወንጀለኛ ይሆናል (ሂትለርን አስቡ እዚህጋ)። አንተስ እዚያው ገባህ አይደል ስለአማራ አተኮርክ እንዳትሉኝ። አልታመምኩም ባይ ነኝ ምክንያቱም አንደኛ አማራን ለይቶ ስላጠቃ ምላሽ ብቻ የሰጠው ሲሆን ሌላው ምክንያት ደሞ ቢያንስ ስለህመሙ insight አለኝ። በተጨማሪም አማራውን ከሰው በታች አታድርጉት ከሰው እኩል አድርጉት ከማለት ውጪ የአማራ ድንበር እዚህ ጋር ነው ይሄ ክልል የአንድ ብሄር ነው ብዬ አላምንም ይልቅስ ሁሉም ሰው በጋራ በእኩልነት ስለመኖር እንመካከር ባይነኝ።

በመጨረሻም ከማስተባበር ችሎታው ተምረን ራሳችንን ለማዳን እኛም ተባብረን እንስራ። ግባችን የተለያየ ቢሆንም ከጠላት አካሄዶች መማር ጥሩ ነው አትርሱ። እንደሰማቹት ኦሮሞን በኢኮኖሚ በትምህርት በሌላም እናጠናክር ነው ያለው እየሰሩም ነው። የትግሬዎቹ ጉዳይ ፀሃይ የሞቀው ስለሆነ ብዙም ስለዛ አላወራም። ስለዚህ አማራው ለሰው ብሎ ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ በልና ትምህርት ወስደህ ወገንህን አደራጅ። ያለጠያቂ በራሳቸው ሚዲያ የማይሆን ነገር ሲናገሩ የራስህ ሚዲያ ቢኖርህ ኖሮ ቃል በቃል መልስ መስጠት ይቻል እንደነበር አትርሱ። አማርኛን እንኳን መናገር መስማት አይፈልጉም የጥላቻ ፖለቲካቸውን ለማስፋፋት ስለሚፈልጉ ብቻ ነው በአማርኛ ፕሮግራም የጀመሩት እንጂ የኦሮሚያ ቲቪ በሚል አማርኛን ምን አመጣው? ትህነግ እንዳደረገው አማራውን ለማወናበድ የጀመሩት ዘዴ ነው። ምንም እንኳን እንደኢሳት ያሉ በአብዛኛው በጀት የሚያዋጣው አማራው እንደሆነ ብናውቅም ኢሳት የኢትዮጵያ እስከተባለ እያንዳንዱን የአማራ ጥቃት አንስቶ እንዲከራከር አንጠብቅ። የኢትዮጵያ ከተባለ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ በደል መናገር ስላለባቸው በጥልቀት ገብተው ስላንድ ብሄር መናገር ይቸገሩ ይሆናል። በኢትዮጵያዊነታችን እስካመንን ኢሳትን መቃወም ሳይሆን ኢሳት ያልሸፈነውን የአማራ በደሎች አማራው በደሉን የሚያስረዳበት የራሱ ሚዲያ መኖር አስፈላጊ ነው ባይ ነኝ በዚህ ላይ ቢሰራ ይሻላል።

አማራው ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ አለበለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል የተባለው እየሰራ እንደሆነ ልብ በል።
ኢትዮጵያን ሁሉም ባህሉና ቓንቓው ተከብሮ እንዲሁም አነስተኛ ቁጥር ያላቸውም መብታቸው ተከብሮ ብዙሃን የሚመሩበት የሰላም አገር አድርጎ ያሳየን።

Moresh

 

 

 

ቡዳ ምንድነው? በቡዳ የሚበሉት እነማን ናቸው? * ‹‹ተበላች አትበሉኝ ያንክተኝ ዓለሜ፤ ቢጥመው ይሆናል ያበሻነት ደሜ››

$
0
0

ቅንብር በኢሳያስ ከበደ

‹‹ቡዳ›› በባህልና እምነት ውስጥ ለረዥም ዘመን ማህበራዊ አስተሳሰብና እምነት ይዞ የዘለቀ ትርጓሜ አለው፡፡ በአውሮፓና ኤዥያ ሀገራትም የዚህ የቡዳ አስተሳሰብን በሰፊው የሚያራምዱት የማህበረሰብ ክፍሎች አሉ፡፡ በሀገራችን በአውሮፓውያን ዘንድ ያለውን ይሄን አመለካከት የተሰሩ ጥናቶችን ዋቢ አድርገን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
Buda
…ህጻኗ ቤቲ ከእኩዮቿ ጋር ትጓተታለች- ትጫወታለች፡፡ የልጅነት ጨቅላ ዘመን… የእምቦቀቅላ አሻራዋ መጫወት ነው- አፈር መፍጨት- ውሃ መራጨት፡፡ አራት ዓመት… እያለችም ነፍሷ የጨዋታ ነው- የቡረቃ፡፡
የፀሎት መፅሐፉን ከማህደሩ አኑሮ አንገቱ ላይ እንዳጠለጠለ ደብተራ፣… እሷ አንገት ላይም በአራት መአዘን ክብ የተዘጋጀና በቆዳ የተሰፋ ትንሽዬ የቡዳ መከላከያ እንደ መስቀል አንገቷ ላይ አንጠልጥላለች፡፡ ‹‹ቡዳ እንዳይበላት›› ተብሎ ነው፡፡ ከፍ እያለች ስትመጣ ነው አንገቷ ላይ የታሰረላት የቡዳ መድኃኒት መሆኑን ያወቀችው፡፡ ቡዳ ማለት ምን እንደሆነ እየተረዳች የመጣችውም አምስተኛ ዓመቷን በተሻገረች ማግስት ነበር፡፡

…ቤቲ እያደገች መጣች፡፡ እየበሰለች ሄደች፡፡ ያን ጊዜ ግን አንገቷ ላይ ተንጠልጥሎ የቆየው የቡዳ መድኃኒት አልነበረም፡፡ ለምን? ብዙ ጊዜ የቡዳ መድኃኒት ተቀምሞና በቆዳ ተሰፍቶ አንገታቸው ላይ የሚታሰርላቸው ነፍስ የማያውቁ ህፃናት ናቸው፡፡ ስለምን? እነሱ ከቡዳ መጠንቀቅ አይችሉም… ይደነገጥባቸዋል… በቅናት አይን ይታያሉ፡፡ ቡዳ ህፃናት ስለሚቆነጁ… አይጠነቀቁም ይበሏቸዋል- ነፍስ አያውቁምና፡፡ ነፍስ ቢያውቁ ይጠነቀቃሉ፡፡ መንገድ ላይም እየበሉ ሊሄዱ ይችላሉ… ያን ጊዜ ቡዳ ያያቸዋል… ስለሚባል በተለይ ለነሱ መከላከያው ይታሰርላቸዋል፡፡ የቡዳ መከላከያው ከቅጠላ ቅጠሎችና ቡዳን ሊያርቁ ይችላሉ ተብለው ከሚታሰቡ ነገሮች ስብስብ ተዘጋጅቶ እንደሚታሰርም እየበሰለች ስትሄድ አወቀች፡፡

ቤቲ ስለ ቡዳ ትኩረት መስጠት የጀመረችውና ግን በቡዳ ተበሉ የተባሉ ሰዎች ‹‹ሲቀባጥሩ… ጭሳጭስ እየታጠኑ ሲያስቀባጥሯቸው ፀበል እየተጠመቁ ሲያጓሩና ሲለፈልፉ… ኋላም ሲሻላቸው ነው፡፡ ‹‹በዚህ መልኩ ተጨባጭ ነገሮችን እያየሁ ሰዎችም ስም እየጠሩ እየለፈለፉ እከሌ በሉኝ እያሉ ሲጮሁ ሲሻላቸው ማየት የልጅነት ዘመን ትውስታዬ ነው›› የምትለው የዛሬዋ ወጣት ቤቲ፣ ‹‹ቡዳ በላው…›› የሚሉት ነገሮች ተጨባጭ መሆኑን በዚያ ዘመን አረጋገጥኩ›› ትላለች፡፡ በቡዳ መበላት… ለፍልፎ የማስወጣት ትዕይንት መኖሩን አሁንም ታምናለች- ቤቲ፡፡
ነገር ግን ቤቲ ደቡብን ለቅቃ አዲስ አበባ ስትገባ ‹‹ቡዳ›› የሚለው ነገር ትዝ ያላት እኔ ለዚህ ፊቸር ጥንቅር ግብአት እንዲሆን ጥያቄ ብቅ ሳደርግላት ነው፡፡ አዲስ አበባ ለእንደዚህ አይነት ባህላዊ ወይም ልማዳዊ አስተሳሰብ ‹‹ክብር›› ስለማትሰጥ ይሁን… በቴክኖሎጂ ውጥንቅጧን ያጣች ከተማ ስለሆነች ይሁን… ጥሞና ስላጣ- መረጋጋት ስለሌላት ይሁን እሷ አልገጠማትም፡፡ ቢገጥማት የምትተማመንበትን ቁንጅናዋን እንደ ኤግዚቢሽን ከማሳየት ትቆጠባለች እንደሷ አነጋገር፡፡ በዚህ ጉዳይ አዲስ አበቤ እንደ ክፍለ ሀገሩ ሲያወራና ሲሰጋ ቢገጥማት ዛሬ ከቤት ወደ ካምፓስ አይስክሬም እየላሰች ባልሄደች ነበር፡፡ ግን ዝም ብላ እየኖረች ነው፡፡

…የዚህ ፊቸር ፀሐፊም ወደ ኋላ መለስ አለ- መለስ አለና የስብ ስቴውን ዘመን አገኘ- ጨቅላ ጊዜውን… ከዚያ የታዳጊነት ዘመን ጀምሮ ወተትና የወተት ተዋፆ ምግቦችን አይወስድም፡፡ ወላጆቹ ምክንያቱን የገለፁት ‹‹ቡዳ በልቶት› ነው የሚል ነው፡፡ ወተት የሚባል ነገር በዓይኑ ሊያይ ያንገፈግፈዋል፡፡ ‹‹ውይ ቡዳ በልቶት ነው!›› ይላል – የአካባቢው ማህበረሰብም፡፡ በዚህ አሰተሳሰብ ውስጥ ቅንጣት ጥርጣሬ ስለሌለ ‹‹ቡዳ ስለበላኝ ወተት አልጠጣም!›› የሚል ድምዳሜ ላይ ደረስኩ- ከጠጣሁ የምሞት ያህል ነው የሚሰማኝ፡፡ ግን ወተትና የወተት ተዋፅኦ ምን ያህል ለጤንነት ጠቃሚ እንደሆኑ እያወቅሁ ስመጣ ‹‹መበደሌ›› አሳዘነኝ፡፡ ‹‹የጠጣሁ ቢሆን እላለሁ!…›› ግን አልጠጣም፡፡ ምክንያቱም ቡዳ በልቶኛል- ወተት ስጠጣ፡፡

የትውልድ አገሬን ለቅቄ ከወጣሁ ዘመናት ነጎዱ፡፡ አሁንም ወተት አልጠጣም፡፡ ቡዳ በልቶኛል፡፡ ሃያ አምስት ዓመቴ ተጠግቶ ነበር- አሁን በቅርብ ወዳጆቼ አንድ ወተት ቤት ይዘውኝ ገቡ፡፡ መኖሪያ ቤት ነው፡፡ በጣም እርቦኝ ነበር- እነሱ እርጎ እኔ ደግሞ ከወተት ውጪ ሌላ ቁርስ ባገኝ ብዬ ነበር፡፡ በኩባያ ከመጣው እርጎ እጅግ ጽዱና ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከመርጋቱ የተነሳ እንደማዘቅዘቅ ቢሉትም አይደፋም- እርጋታው! ይሄንን ዳቦ እየገመጡ ሲጠጡ ለምን እንደሆነ አላውቅም በጉጉት አያቸው ነበር- አለመታደሌ እያልኩኝ፡፡ አለመጠጣቴ ግራ ያጋባው ወዳጄ ‹‹አትጠጣም እንዴ?›› አለኝ፡፡ የአገሬ ልጅ አብሮአደጌ (የይርጋ ጨፌው ጎታ እንግድነት መጥቶ) ከኔ ፈጥኖ ‹‹ቡዳ በልቶታል!›› አለና- መለሰለት፡፡ ‹‹ዝም ብለህ ጠጣ ምንም አያደርግህም!›› አለኝ- ወዳጄ፡፡ እኔም አብሯደጌም ተሳሳቅን፡፡
‹‹እየውልህ ሚጥሚጣ አብዛበትና ግጥም አድርግ ስነ ልቦና ነው!›› አለኝ፡፡ ስነልቦና ሲል ራሴን ጠየቅሁ፡፡ እርግጥ ሞክሬ ባየውስ? አይገለኝ! ደፍሬ ብገባበትስ? ብዬ ራሴን ሞገትሁ፡፡ የጥፋት ነገር ስላልሆነ መጣልኝ፡፡ ወዳጄ እንዳለኝ በርበሬ አበዛሁበትና የወተቱ ጣዕም እንዲጠፋ አደረግሁ፡፡ ከዚያም ግጥም አድርጌ ጠጣሁት፡፡ እውነቱን ለመናገር በጣም ተመቸኝ፡፡ ነፃነት ተሰማኝ፡፡ በሁለተኛ ጊዜ በሶስተኛ ጊዜ የፍርሃት ደመናውን ለመግለጥ በበርበሬ ብዛት ተወጣሁት! እነሆ ዛሬ እርጎ ያለበርበሬ እጠጣለሁ፡፡ (መጀመሪያም አልተበላው ይሆን? አላውቅም) ወዳጄ ምስጋና ይግባው! (የሳሪሱ ይሄይስ ታሪክ ሰርተኻልኮ) ትኩስ ወተት ለመጠጣት አሁን የምፈልገው እንደ ይሄይስ አይነት ቀስቃሽ ወዳጅ ይመስለኛል፡፡

በሀገራችን በቡዳ መበላት ላይ ያለው ባህልና እምነት ረዥም ዘመን ያስቆጠረ እምነት ነው፡፡ በቡዳ የተበሉ ሰዎች በቡዳ የበሏቸውን ሰዎች እንደሚለፈልፉም ይታመናል፡፡ ሰለሞን ገ/ጊዮርጊስ በአንድ ወቅት የገጠመውን ይናገራል፡፡
‹‹አንድ ወቅት ላይ ከአዲስ አበባ ወጣ ባለ አካባቢ በእንግድነት ሄድን፡፡ እህታችን እጅግ በጣም ቆንጆ ናት፡፡ ከተማ ውስጥ ረፋድ ላይ ገብተው ሌሊት ላይ ኡኡ… ማለት ጀመረች›› ‹‹ምን አድርጌህ ነው!…›› ትላለች፡፡ ታለቅሳለች ትስቃለች- በጣም ትለፈልፋለች፡፡ ሁላችንም ተደናግጠን ተሰባሰብን፡፡ መለፍለፏን ግን ቀጠለች፡፡ በኋላ ቡዳ መሆኑን አወቅን- ቡዳ እንደበላት አረጋገጥን፡፡ ወዲያውኑ በጭሳጭስ እንድትታጠን አደረግን፡፡ መለፍለፍ ጀመረች፡፡ ቄሱ ‹‹ማነህ ውጣ!… ውጣ!!!…›› እያሉ እየታጠነች በመስቀል አናቷን ይደባብሱታል…
‹‹የት ነው የያዝካት! አንተ ማነህ!››
‹‹እያስተናገድኳት እያለ ነው ደስ ብላኝ ነው የበላኋት!›› ማለት ጀመረ፡፡ ስሙንም ጠቀሰ፡፡
‹‹እሺ አሁን ትወጣለህ አትወጣም! ውጣ!… ውጣ!!…››
‹‹እሺ እወጣለሁ! እወጣለሁ…››
‹‹እኮ ውጣ!… ውጣ…›› ቄሱ አቀርቅራ እየታጠነች አናቷን በመስቀል ይመቱታል፡፡
‹‹በቃ ወጥቻለሁ!›› መስከረም ይሄን ጊዜ በላብ ተጠምቃ-ሰውነቷ ዝሎ ነበር፡፡ ወደ ማንነቷ የመመለስ ሁኔታ ውስጥ መግባቷን እየተረዱ የሄዱት ቄሱና ቤተሰቡ አረፍ አሉ፡፡
‹‹የሚገርምህ ነገር›› ይላል- ሰለሞን ገ/ጊዮርጊስ፤

‹‹…ሌሊቱን ሻል ብሏት አደረችና ጠዋት ወደ ከተማ ወጣ እንዳለን የበላትን ሰውዬ አየነው፡፡ ሲያየን በጣም ነው ድንግጥ ያለው…›› ይላል፡፡
በተለምዶ ቡዳ (evil eye) እየተባለ የሚጠራው በማህበራዊ ህይወታችን ውስጥ የራሱ የሆነ ቦታና መልክ የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ በቡዳ የሚመሰሉ ሰዎች አይናቸው ከፍተኛ ሀይል (power) ስላለው ነው… በጣም በሚስባቸውና በሚወዱት ነገር ላይ በተለየ ሁኔታ ስለሚደነግጡ ያን ጊዜ ነው በግለሰቡ ውስጥ የሚያድሩት…›› የሚሉት አስተሳሰቦች ከመላምትም በላይ በአብዛኛው አካባቢ ዘንድ የሚታመንባቸው ናቸው፡፡
የተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ብቻ ‹‹ቡዳ›› ተብለው እንደሚፈረጅም የሚናገሩ አሉ፡፡ ለዚህም በዚህ መልኩ በማህበረሰቡ ‹‹ቡዳ›› ናቸው ተብለው የተፈረጁ የማህበረሰብ ክፍሎች ህብረተሰቡ በተለየ ሁኔታ ስለሚመለከታቸው ስለሚያማቸው… ስለሚሸሻቸው… ስለሚያገላቸው ቤተሰባዊ ህይወታቸው በስነ ልቦና የተሸነቆጠና ሰላማቸው የጠፋባቸው እንደሆኑ ይታሰባል፡፡ ሌላው ቀርቶ በዚህ መልኩ ይታወቃሉ የሚባሉት የማህበረሰብ ክፍሎች ተሰብስበው በሚኖሩበት ወይንም ባለበት መንደር ውስጥ ለመኖር ጥርጣሬና ፍራቻ የሚፈጠርባቸው ሰዎች እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ቡዳ ቅናትና ጥላቻ?
በአማርኛ ቋንቋ ‹‹ቡዳ›› ተብሎ የሚጠራውና የሚታወቀው ከዓይን የሚመነጭ ኃይል (evil eye) በተለያዩና በብዙ ባህሎች (ህዝቦች) እንደሚታመንበት ከሆነ ይህ ጎጂ የማየት ኃይል የታለመበት ሆነም የተሰነዘረበት ሰው (ሰለባ) ላይ አንድ አይነት ጉዳትን ወይንም መጥፎ ዕድልን ያስከትልበታል፡፡ በአብዛኛው እንደሚታመንበት ከሆነ ይህን ጎጂ የእይታ ኃይል የሚያመነጨው ‹‹ቡዳ›› ከቅናትና ከጥላቻ የመነጨ የዕይታ ኃይሉን ሌላው ሰው ላይ በሚያሳርፍበት ጊዜ መጥፎ ጉዳትን ያስከትልበታል፡፡
ቢያንስ ከአንድ ሚሊኒየም (አንድ ሺህ ዓመት) በላይ የሚያልፈው ይህ አመለካከትና እምነትም አያሌ ባህሎች (የተለያዩ ማህረበሰቦችና ህዝቦች) የየራሳቸውን የቡዳ መከላከያ ዘዴዎች እንዲሹ መነሻ ሆኗቸዋል፡፡
ስለ ቡዳ ዓይን ካሉት እምነቶች ውስጥ አንዱ ‹‹አንዳንድ የቡዳነት ኃይል ያላቸው ሰዎች ምትሃታዊ ከሆኑት ዐይኖቸው የሚያመነጩት ከጥላቻ የመነጨው የማየት ኃይላቸው በሰለባዎቻቸው (ተጠቂዎቻቸው) ላይ ጎጂ የሆነ እርግማን እና አሉታዊ ተፅዕኖን (ህመም፣ ስቃይና ሞትን) የመሳሰሉ ጉዳቶችን ያስከትላሉ›› (some people can bestow a course on victims by the malevolent goze of thiren magical eye) የሚል ነው፡፡ ከዚህ እምነት ውስጥ በስፋት ተቀባይነት ያለው አመለካከት እንደሚለው ከሆነ ቡዳው በሰለባው ላይ ጎጂ የሆነ አደጋን በማየት ኃይሉ የሚያደርስበትን ሳያውቀው፤ ሳይፈልግ ወይንም ሆን ብሎ እንዳልሆነ ይነገራል፤ ይታመናል፡፡ በተጠቂዎች ወይንም በቡዳ ዓይን ጥቃት የሚደርስባቸው ሰዎችም የተለያዩ ‹‹ጉዳት›› እንደሚያደርስባቸው ይታመናል፡፡ አንዳንድ ማህበረሰቦች አስረግጠው እንደሚዘግቡት የቡዳ ዓይን መጥፎ እድልን (ክፉ ነገርን) ያስከትላል፡፡ ሌሎች ባህሎች እንደሚሉት ደግሞ የቡዳ ዓይን (መጥፎ የማየት ኃይል) ህመምን መክሳትና መመንመንን ብሎም ሞትን ያስከትላል፡፡ በብዙ ማህበረሰቦች ውስጥ ያለው እምነት ደግሞ በአብዛኛው የቡዳ ዓይን ተጠቂዎች የሚሆኑት ጨቅላዎች እና ህፃናቶች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ህፃናቶች በተለያዩ እንግዳ ‹‹ፀጉረ ልውጥ›› ሰዎችና ልጅ አልባ (መሃን) በሆኑ ሴቶች ስለሚደነቁና በቅናት አይን ስለሚታዩ በቀላሉ ለጉዳት ይጋለጣሉ፡፡ የበርክሌይ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ፕሮፌሰር አለን ደንዴስ በበርካታ ባህሎች ውስጥ ስለ ቡዳ ያሉትን እምነቶች አስሰውና አበጥረው በማጥናት እንዳረጋገጡት ከሆነ ጥብቅ የሆነው የ‹‹ቡዳ ዓይን›› የማየት ኃይል የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች የሚገልፁት ምልክቶች (symptoms) ውስጥ ድርቀት፣ መክሳትና መመንመን በስፋት የሚታዩት የህመም ምልክቶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ በብዙ የአውሮፓ ማህበረሰቦች ውስጥ ዓሳ የቡዳ መከላከያ ሆኖ የሚታመነው እርጥብ (ውሃ ውስጥ ነዋሪ) ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ነው፡፡
‹‹እርጥብና ደረቅ የቡዳ ዓይን›› በሚል ርዕስ ፕሮፌሰሩ ያወጡት የምርምር ፅሑፍም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የተዘጋጀ ጥናታዊ ዘገባ ነው፡፡ እኛም የሌሎችን ሀገራት እምነትና አመለካከት የምናስነካባችሁ ጥናት ላይ ተመስርተን ነው፡፡ የቡዳ ዓይን አዋቂዎች ህፃናት፣ የቤት እንስሳት እና ሌሎችም ንብረቶች ላይ ሁሉ የቅናት አስተያየት በማየት ብቻ አደገኛና የተለየዩ ጉዳቶችን የጥናት ዘገባ ያሳያል፡፡

ታሪክ
በቡዳ ዓይን ላይ የተመሰረቱ ትውፊታዊ፣ ስነ ፅሑፋዊና አርኬኦሎጂያዊ መረጃዎች መነሻቸው ወይንም ምንጫቸው ከምስራቃዊው የሜድትራኒያን ባህር ክልሎች አካባቢ ከሺህ ዓመት በፊት የተፃፉት የፕላቶ፣ ዲዮዶርስ ሲክለስ፣ ቴዎክራተስ፣ ፕሉታሮች እና የፕሉኒ ሰነዶች ናቸው፡፡ ፒተር ዋልኮት ‹‹ቅናት እና ግሪኮች›› በተባለው መፅሐፍ (1978) እነዚህንና ሌሎችም ከመቶ የበለጡ ጥንታዊ የታሪክ ፀሐፊዎች ስለ ቡዳ ዓይን የፃፉትን መረጃ ጠቅሷቸዋል፡፡

የሶቅራጠስ የቡዳ ዓይን
በጥንቱ ዘመን ስለ ቡዳ ዓይን የነበሩት እምነቶችን በተመለከተ ምንጮቹ የአሪስቶ ፌነስ፣ አቴኒየስ፣ ፕሉተሮችና የሄሉ ኦዲረስ ጽሑፎች ሲሆኑ የዘመኑ ፈላስፋ ሶቅራጠስ ራሱ የቡዳ ዓይን (evil eye) ኃይል እንደነበረውና ደቀመዛሙርቱም በሶቅራጠስ ዓይኖች የፈጠጠና ሰርሳሪ (glaring) የሆነ የማየት ኃይል ይደነቁ እንደነበረ ተዘግቧል፡፡ የሶቅራጠስ ተከታዮችና ተማሪዎች በግሪክኛው ‹‹ብለፔዳይመንስ›› ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡ ትርጉሙም ‹‹እርኩስ፣ አመለካከት›› ማለት ሲሆን ደቀመዛሙርቱ ቡዳነታቸውን ሳይሆን በመምህራቸው ሶቅራጠስ የቡዳ አይኖች ተፅዕኖ ስር መውደቃቸውን ለማመልከት የተሰጠ አጠራር ነው፡፡
ስለ ቡዳ ዓይን የተቀመሩ ሳይንሳዊ ማብራሪያዎች ለምሳሌ ፐሉታሮች ያቀረበው ሳይንሳዊ ማብራሪያ…
‹‹የቡዳ ዓይን›› ያለው ሰው ከውስጡ የሚያፈልቀውን እና እንደ መርዛማ መርፌዎች አደገኛና ጎጂ የሆኑ ጨረሮችን የሚረጭባቸው ዋነኛ መሳሪያዎቹ ዓይኖቹ ናቸው!›› ብሏል፡፡ ይህንን የቡዳ ዓይን ‹‹ክስተትን›› ፐሉታርች የሚያቀርበው ማብራሪያ የለሽና አስደናቂ ክስተት አድርጎ ነው፡፡

የቡዳ ዓይን እምነት ታሪክ
ስለ ቡዳ ዓይን (evil eye) በርካታ መጽሐፍትና ድርሳናት ተጽፈዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ፍሬደሪክ ቶማስ አልዎርዙ የፃፈው ‹‹የቡዳ ዓይን የአል እምነቶች ምንጭና ተግባር›› (Terrors of the evil eye exposed) የተሰኘው መፅሐፍ አንዱ ነው፡፡ በዚህ የቡዳ ዓይን እምነት ላይ እኔ ካገኘኋቸውና ከሁሉም በላይ ለምርምር የሚጋብዘው አካዳሚያዊ ጽሑፍ ‹‹እርጥብና ደረቅ የቡዳ ዓይን›› (wet and dry) የተሰኘው የፕሮፌሰር አለን ዱንዴስ መጽሐፍ ዋነኛው ነው እላለሁ፡፡ አለን ዱንዴስ በካሊፎርኒያው በርክሌይ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መምህር ነው፡፡
ስለ ቡዳ ዓይን ፕሮፌሰር ቡንዴስ የሚያቀርበው ንድፈ ሀሳብ (Logic) የተመሰረተው በምስራቅ ሜዲትራኒያን፤ በአሜሪካ በፓሲፊክ ደሴቶች፣ በኢሲያና በአውስታራሊያ የተስፋፋና የአውሮፓውያን ባህል እስከመጣበት ዘመን ድረስ የዘለቀ እምነት መሆኑን ያብራራል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ባህሎች ውስጥ የተንሰራፋው እምነት መሰረቱ ወይንም ምንጭ ያደረገው መርህ ‹‹ውሃ የህይወት ምንጭ-ድርቀት የሞት ምንጭ›› (water equating to life and dimes equating to death) በሚል እሳቤ ላይ የተመሰረተ ነው ይልና ‹‹በቡዳ ዓይን (evil eye) የሚደርሰው ክፉ፣ እርኩስ ጉዳት ህይወት ያላቸውን ነገሮች ያደርቃል፣ በተለይም ህፃናት፣ የሚጠቡ እንስሳት፣ የደረሱ የፍራፍሬ ዛፎች እና የሚያጠቡ እናቶች ዋነኛዎቹ ተጠቂዎች ናቸው›› ይላል፡፡
በቡዳ ዓይን የሚደርሱ ጉዳቶችና አሉታዊ ህመሞች ምልክቶቻቸውም (symptoms) በህፃናት ላይ የሚከሰቱ ድንገተኛ ትውኪያዎችና ተቅማጥ፣ የአጥቢ እናቶችና እንስሳት ጡት (ወተት) መንጠፍ መድረቅ፣ የፍራፍሬ ዛፎች መጠውለግና መድረቅ እና በወንዶች ላይ የሚከሰት ስንፈተ ወሲብ ናቸው፡፡ ባጭሩ ፕሮፌሰር ዱንዴስ ስለ ቡዳ ዓይን ያቀረበው ምርምሩ ‹‹የቡዳ ዓይን እርጥበትን ወይንም ፈሳሽ ነገሮችን ያደርቃል!›› የሚል ነው፡፡
ዱንዴስ ይህንኑ ንድፈ ሀሳቡን የበለጠ ማጠናከሪያ አድርጎ የሚያቀርበው መረጃው እንደሚለው ከሆነ… ‹‹የቡዳ ዓይን እምነት የመነሻ ስፍራው የሆነውን ጥንታዊውን የሱሜር ምድር (ግዛት) ማዕከል ባደረገ ጂኦግራፊያዊ ቀለበት የተሰራጨ ነው›› (Evil eye belief is geographically spread out in a reediting from ancient summer) ይላል፡፡ (የማጅራት ገትር፣ ማኔንጃይትስ ቀለበት ወይንም ለበሽታው የተጋለጡ አገሮች ክልል እንደሚባለው አይነት መሆኑን ልብ ይሏል)
የቡዳ ዓይን በእርግጠኝነት ስለመኖሩ በብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ከመጠቀሱም ሌላ በዘመናዊ (የወቅታችን) አይሁዶች፣ አረቦችና ክርስቲያኖችም እውቅና የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ (በዚህ ጉዳይ ምሁራን ጥናትና ምርምር ያድርጉ እንጂ ሳይንሳዊ እውቅና አልተገኘለትም) ይህ እምነት ከመካከለኛው ምስራቅ በመነሳት በስተ ምስራቅ እስከ ህንድ፣ በስተምዕራብ ስፔይን፣ ፖርቹጋል፣ በስተሰሜን እሰከ ስካን ዲኔቪያን እና እንግሊዝ እና ወደ ደቡብ እስከ ሰሜናዊ አፍሪካ ግዛቶች ድረስ ተሰራጭቷል፡፡
የቡዳ ዓይን እምነት በተንሰራፋባቸው ስፍራዎች ሁሉ ‹‹ከመደበኛው የበለጠ ወይንም የጋለ የቅናት ወይንም የአድናቆ ስሜትና አመለካከት ጎጂ ተፅዕኖ ያሳድራል›› ተብሎ ይታመናል፡፡

ሃራ-ሃራ!
በጣም የተለመደ ‹‹የቡዳ ዓይን›› መገለጫ (በብዙ አገሮችና ባህሎች ማለት ነው) ‹‹ልጄን አዲስ ልብስ አልብሼው ወደ ከተማ ወሰድኩትና አንዲት ልጅ የሌላት ሴት አይታው አቤት! እንዴት የሚያምር ህፃን ነው! ስትል አደነቀችው፡፡ እቤት ተመልሰን እንደገባን ወዲያውኑ ማስመለስ ጀመረ!›› የሚለው ትረካ በጣም የተለመደ ነው፡፡
ከዚህ አባባል የምንረዳውም ‹‹የቡዳ ዓይን (evil eye)›› ቅናትን መቆጣጠር ካለመቻል የሚመነጭ ጎጂ ተፈጥሯዊ ክስተት መሆኑን ነው፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቡዳን ዓይንን ‹‹ዓይን eyin ሃራ ሃራ hara›› ሲል ይጠራውና መንስኤውም ቅናትና ምቀኝነት እንደሆነ ያብራራል የሚለው የፕሮፌሰሩ የጥናት ፅሑፍ በአይሁዶች አካባቢ ህፃናትና ከቡዳ ዓይን ወይንም በቡዳ ‹‹ከመበላት›› ለመከላከል ሲባል ፀጉራቸው ላይ የተለያዩ ጨሌዎችን እና ዶቃዎችን ያስሩላቸዋል፡፡ በብዙ ባህሎች ውስጥ የቡዳ ዓይን (ኃይል) ያለው ሰው በሌላው ሰው ላይ ጉዳት የሚያደርሰው ሆን ብሎ ወይንም ለመጉዳት ፈልጎ ሳይሆን ሳያውቀው ወይንም ከፍላጎቱ ውጪ ነው ተብሎ ቢታመንም ከዚህ በተለየ መልኩ በደቡብ ኢጣሊያና በሲሲሊ ግዛቶች ብቻ አንዳንድ ሰዎች ሆነ ብለው በሌሎች ላይ የቡዳ አይናቸውን ይጥላሉ (በሀገራችን አባባል በቡዳ ይበሏቸዋል!) ተብሎ ይታመናል፡፡ በእነዚህ ግዛቶች ዙሪያ የሰፈነው እምነት እንደሚለው ከሆነ ‹‹አንዳንድ ሰዎች፣ የቡዳ ዓይን ኃይልን ይዘው ይወለዳሉ፡፡ ሳያውቁትም በሌሎች ላይ ያንፀባርቁታል (ያሳርፉታል) ወይንም በእንግሊዝኛው ‹‹ፕሮጀክት›› ያደርጉታል ይባላል፡፡ ከዚህም በመነሳት ነው ቡዳዎች ወይንም የቡዳ ዓይን ኃይል ያላቸው ሰዎች ‹‹ፕሮጀክተሮች›› ተብለው የሚጠሩት፡፡

የቡዳ ዓይንን በቃል እና በአካል መከላከል
የቡዳ ዓይን በግልፅ እና በዝርዝር የተገለፁ ጉዳይ በመሆኑ ቡዳን መከላከያ የሆኑ ድምግምቶችና ክትባቶች የመከላከያ መሳሪያዎችም በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡ በአንዳንድ አገሮች አንድ ሰው ወደ ህንድ ህፃን የፍሬ ዛፍ ወይንም የወተት እንስሳ ላይ የአድናቆት ስሜትና አስተያየት ከሰጡ አድናቆቱን ወይንም ሙገሳውን ተከትሎ ወዲያውኑ በአደነቀው ነገር ላይ ምራቁን እንትፍ እንትፍ ይልበታል፡፡ (በአገራችንም ይህ በጣም የተለመደ ነው) በሌሎች ባህሎች ውስጥ ደግሞ ከአድናቆት በኋላ ወዲያውኑ የህፃኑን ራስ ወይንም የተደነቀውን ነገር በእጅ በመንካት ‹‹የቡዳ ዓይንን መልሶ መውሰድ›› ወይንም መከላከል ከተመልካቹ ይጠበቅበታል፡፡ አድናቂው ሰው ይህንን የማክሸፊያ ተግባር ሳያደርግ ከቀረ ግን የህፃኑ እናት በልጇ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ‹‹ቡዳ የመበላት አደጋ›› ለማክሸፍ ወይንም ለማርከስ ወዲያውኑ ኃይማኖታዊ የሆኑ ድግምቶችና መነባንቦችን በአዋቂች በማስደገም ትታደገዋለች፡፡ በአንዳንድ ባህሎች ደግሞ አንድ ህፃን በሌላ ሰው ሲደነቅና ሲታይ ወዲያውኑ ልጁ ላይ ምራቅን እንትፍትፍ ይሉበታል ድርቀትን ለመከላከል፡፡ መምህር አስፋው ይልማ ደምሴ በአንድ ወቅት ለዘፈን ግጥም ቢሆን ብለው የሰጡኝ ስንኝ ይሄኔ ነው ብቅ የሚልብኝ፡፡
‹‹ዓይኔ ሲንከራተት በድንገት ታምሜ
ቡዳ በላት በቃ ይለኛል አዳሜ
ተበላች አትበሉ ንክተኝ ዓለሜ
ቢጥመው ይሆናል ያበሻነት ደሜ…››

ልማት ያለ ነፃነትና ፍትሕ ፋይዳ የለውም – (የኔ ትዝብት ከኢትዮጵያ ቆይታዬ መልስ)

$
0
0

ሙሱና! አፈና እና አድልዎ ከማንም ግዜ በላይ በሰፈነበት ሀገር ዘላቂ ፍትሕ! ዴሞክራሲ! ዕድገትና የህግ የበላይነት ይመጣል ብሎ ማሰብ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይወለዳል ብሎ መጠበቅ ነው:: ዛሬ በኢትዮያ ሙሱና እና ዓይን ያወጣ ያገር ሀብት ዘረፋ የስርዓቱን ሁለንትናዊ መገለጫ ባህሪይ ከመሆኑም በላይ የህዝባችንን ንሮና ህይወት እየገደለና እያቀጨጨ ያለው ከኤይድስ በላይ ስር የሰደደ ተላላፊ በሽታ እየሆነ መጥቷል:: ዘረፋውም ሆነ አፈናው ከግለ ሰብ አልፎ ወደ ተቋማዊና የተደራጀ ሌብነት በመሸጋገሩ ኢትዮያ ሕገ መንግስታዊ ዋስትና የሌላት” ፍትሕ አልባ የሆነች ሀገር አድርጓታል::
ከ ይኩኖ መስፍን
ቦስቶን ሰሜን አሜሪካ

እኔ የምኖረው በውጭ ዓለም በሰሜን አሜሪካ ቢሆንም በቅርቡ ለግል ጉዳይና ቤተሰቦቼን ለመጠየቅ ወደ ኢትዮያ ሂጄ ስለነበር ለሶስት ወር ያህል አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሬ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በወሬ የምሰማውን ነገር ሁሉ በአካል ተገኝቼ በቀጥታ በሕብረተሰቡ ዘንድ በመሬት ላይ ያለው እውነታ ምን እንደሚመስል በማየቴ ብዙ ነገሮችን ለመገንዘብና ለመማር ጥሩ ዕድል አጋጥሞኛል::
እኔም “ማየት ማመን ነውና” በቅርብ ተገኝቼ ባንድ በኩል ከህዝቡ አንደበት የሰማሁትንና ያየሁትን እሮሮ በሌላው ገጽ ደግሞ በመንግስት በኩል ያለው ተግባራዊ ምላሽና እንቅስቃሴ ምን እንደሆነ ሰፊው ሕብረተሰብ በተለይም ከሁኔታው ርቆ በውጭ ዓለም በዲያስፓራ የሚኖረው ኢትዮያዊ ወገን ሁሉ ማወቅ አለበት ብዬ ያሰብኩዋቸውን አንገብጋቢ ጉዳዮች በማንሳት አቅሜ የፈቀደውንና አእምሮየን የዘገበውን ያህል በማካተት የተሰማኝን ስሜትና ተሞክሮ ለማካፈል ከዚህ ቀጥሎ ያለው ጠቅለል ያለ ሃሳብ ለማቅረብ ሞክሬያለሁ::
addis-ababa-realethiopia-141
ክፍል አንድ:-
የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ፍትሕ ጥያቄ

Semawi Party Demonstration in Addis Ababa
በስልጣን ላይ ያለው የህወሓት/ኢሕአዴግ ሞኖፓላዊ ፓርቲ በተለያዩ የዜና አውታሮች አማካይነት ለኢትዮያውያን ከዚያም አልፎ ለዓለም ማሕበረሰብ ነጋ ጠባ አሸብራቂ በሆኑት ቃላት እንደሚገልፀው “በልማታዊ መንግስታችን አመራር ስር ኢትዮያ በፈጣን ዕድገት ጎዳና ላይ ነች:: በቅርቡም መካከለኛ ገቢ ካላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገሮች ተርታ ትሰለፋለች:: ህዝቡም የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ስርዓት የልማት ተጠቃሚ ሆነዋል:: በአቶ መለስ ዜናዊ የልማት ራዕይ ድሕነት በቅርቡ ነበር ሆኖ ይቀራል” ወዘተ ወዘተ ሲሉ ይደመጣሉ::

በየደረጃው የተኰለኰሉ ካድሬዎችና የፓርቲው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አፍቃሪዎችም የሚነግሩን ይህንን ነው:: በአብያተ ትምህርትም ከመዋእለ ህፃናት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉት መምህራንና ርእሳነ መምህራን የሚሰብኩትና ለለጋ ወጣቱ የሚያስተምሩት ይህንን ነው::
በህዝብ አንጡራ ገንዘብ የሚተዳደሩ የብዙሃን መገናኛ ጋዜጠኞችና አንዳንድ አፈ ቀላጤ ምሁራንም ሆኑ ከላይ ያሉት ባለስልጣናት የሚያስተጋቡትና የሚሰሩት ተውኔት “በሀገራችን ልማት ተረጋግጧል የሚል ነው:: ከርእሰ ብሄሩ ጀምሮ እስከ ታች ቀበሌና ጎጥ ድረስ ያሉት የአስተዳዳር አካላትም ረሃብተኛውን ህዝብ የሕልም እንጀራ ለማብላት ሲባል ዋና ስራቸው “ኢትዮያ ለምታለች” የሚል ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨትና ማስተማር ነው፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ በቢሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ሀብት ወጪ እየተደረገበት የሚተላለፈው የፕሮፖጋንዳ ክምር እና በልማት ስም የሚሰራው ስንክሳር ድራማ በመሬት ላይ ያለው ሓቅ ሊሸፍነውና ሊለውጠው አልቻለም:: እርግጥ ነው በአዲስ አበባና በሌሎች አንዳንድ የክፍላተ ሀገር ከተሞች መጠነኛ ትላልቅ ፎቆች፣ መንገዶች፣ ትምህርት ቤቶች! የጤና ተቋማት፣ እንዲሁም አንዳንድ ግድቦች አልተሰሩም አልልም:: ማንኛውም መንግስት መጠኑን ይለያል ይሆናል እንጂ በጊዜው አንዳንድ ነገር ሰርቶ ያልፋልና:: ነገር ግን ዋናው እና መሰረታዊ ጥያቄው ስንት ፎቅ ተሰራ፣ ስንት ግድብ ተገነባ፣ ስንት ተማሪ ወደ ትምህርት ቤት ሄደ! ሳይሆን በሀገሪትዋ የዜጎች ሰብኣዊ መብትና ነፃነት፣ የሕግ የበላይነት! ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ ሳይረጋገጥ ዘላቂ ልማትና ዕድገት ሊኖር ይችላል ወይ? የዕድገቱንና የልማቱን ባለቤት ማን ነው? በህወሓት ኢሕአዴግ የልማት ፓሊሲ ማን ነው እየለማ ያለው? አሁን ያለው የትምህርት ፓሊሲ ምን ዓይነት ትውልድ ነው እያፈራ ያለው? በአጠቃላይ መሰረቱ የተናደ ቤትና ስርዓት ዘላቂነት ያለው ልማትና ዕድገት ሊያመጣ ይችላል ወይ? የሚሉትንና ሌሎች የህዝቡን የልብ ትርታ የሚነኩ ጥያቄዎች በቅድሚያ መመለስ ያለባቸው ይመስለኛል::
የስርዓቱን የልማት ፓሊሲና አመራር ምን ያህል ትውልድ ገዳይና ሀገር አውዳሚ መሆኑን ለመገንዘብም ሆነ ለማወቅ የግድ የተወሳሰበ ቲኦሪ መተንተን ወይም የፓለቲካ ፈላስፋ መሆን የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም:: ሀገርንና ህዝብን ማእከል አድረገው ካዩት በያንዳንዱ ቤት ያለው የንሮ ችግር! በየልማት ዘርፉ የሚታየው ዝርፊያ! በወጣቱ ትውልድ ዘንድ የሚታየው ተስፋ መቁረጥና ፍልሰት! በማሕበራዊ ንሮ የሚታየው ምስቅልቅል! በየመንግስት መሥሪያ ቤቱ በየደረጃው የሚታየው አስተዳዳራዊ አድልዎ! በሕብረተሰቡ ውስጥ የሚታየው ፍርሃትና ስጋት ሁሉም ተደማምረው የስርዓቱን አስከፊ ባሕሪይ አፍ አውጥተው የሚናገሩ የህዝቡ እሮሮዎች ናቸው:: አብዛኛውን በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መብላት የተሳነው ህዝብ ይዞ ስለ ልማት ማውራት በሕብረተሰቡ ላይ ከመቀለድ በስተቀር ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም:: ችግሩ በዚሁ ፅሑፍ ብቻ ተወርቶ የሚያልቅ ባይሆንም ሁኔታውን ለማወቅ ብዬ በተለያዩ የስራ ቦታዎች ተንቀሳቅሼ ከተመለከትኩዋችው ችግሮች ውስጥ የሚከተሉትን አብነቶች መጥቀሱ ብቻ በቂ ይመስለኛል::

በትምህርት

Addis-Ababa-University-337x200ትምህርት ላንድ ሀገር የእውቀት ማፍለቂያ መሳሪያ ብቻ ሳይሆን የልማትና የእድገት አንቀሳቃሽ ሞተርም ጭምር ነው:: አብዛኞቹ ያደጉና በፈጣን እድገት ላይ ያሉት ሀገሮች የእድገታቸው ሞሰሶና መነሻ የሆነው ከሁሉም በላይ ነፃ አስተሳሰብ ካለው ሕብረተሰብ የሚመነጭ የሰብኣዊ ዓቅም ግንባታ ላይ ቅድሚያ በመስጠት በቀጣይነት ስለተረባረቡ ነው:: በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ኢኮኖሚ የሚሸከምና የሚያንቀሳቅስ ሕብረተሰብ (ክህሎት) ለመገንባት ደግሞ ቢያንስ የሞያ ነፃነት፣ ደረጃውን የጠበቀና ከአንድ ፓርቲ ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ስርዓተ ትምህርት! በነፃነትና በጤናማ ውድድር ላይ የተመሰረተ የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ወሳኝነት አለው::

ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የትምህርት ስርዓት ግን በተገላቢጦሽ ነው:: ላንድ ሰራተኛ ለመቅጠር መመዘኛው የሞያ ጥራትና ክህሎት ሳይሆን ለድርጅት ያለው ቅርበትና የፖለቲካ ታማኝነት ነው:: የሀገሪትዋ ስርዓተ ትምህርትና ፓሊሲም የሚመነጨው ከዓለም አቀፍ የእውቀት ስታንዳርድ እና ከሀገሪትዋ ነባራዊ ሁኔታ ሳይሆን ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ የጥቂት ሰዎች ሞኖፓላዊ አስተሳሰብ እና እምነት ነው:: ለምሳሌ የትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ሁሉም የፓርቲ አባላት ወይም ካድሬዎች ናቸው፡፡ አስተማሪዎች ከ95 በመቶ በላይ የፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ አባል ያልሆኑና በነፃ ህሊና ማገልገል የሚፈልጉ ብቃት ያላቸው ባለሞያዎች ምንም የስራ እድገት እንዲያገኙ አይፈቀድላቸውም ብቻ ሳይሆን በስራ ገበታቸው የመቆየት እድላቸውም በጣም ትንሽ ነው፡፡ በሰበብ አስባቡ እንዲባረሩ እና እንዲጎሳቆሉ ይደረጋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በስራቸው የሚተማመኑ እና ብቃት ያላቸው ቢሆኑም ሆን ተብሎ ከህብረተሰቡ እንዲገለሉ እና እንዲሸማቀቁ ይደረጋሉ፡፡ ትምህርት ከጨረሱ በሗላም የተሻለ የስራ ዕድል ለማግኘት! ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመግባት! ወደ ውጭ ሀገር እስኮላርፕ ለመላክ! የመሳሰሉ ዕድሎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው የፓርቲ አባላት! ታማኝና ደጋፊዎቻቸው ናቸው:: ሌሎች ብዙሃኑ ዜጎች ግን በገዛ ሀገራቸው ባይተዋር እና የበዪ ተመልካች ሆነው ከመቅረት ሌላ አማራጭ የላቸውም::

ከትምህርት ጋር ተያይዞ ሌላው በጣም አሳሳቢና አስደንጋጭ ችግር ደግሞ አሁን የድርጅቱን አባላት! ታማኞች የሆኑ ሰዎች! እንዲሁም በየወረዳው የትምህርት ቢሮ የሚሰሩ ካድሬዎች እና ባለስልጣናት ከዛው ከወረዳው ትምህርት ቢሮ ውስጥ የሚቀናጀው የዲግሪ ፕሮገራም ፅሁፍ በመቸብቸብ የሐሰት ዲግሪ እየተሸከሙ የሕብረተሰቡን ሸክም የመሆን አባዜ ነው፡፡ ለአንድ የዲግሪ ፅሁፍ እስከ 500 ብር እንደሚሸጥ አረጋግጬለሁ:: በአንድ የወረዳ ትምህርት ቢሮ የሚሸጠው የዲገሪ ማዘጋጃ ሰነድም ለማስረጃነት ያህል በእጄ ይገኛል፡፡ ስም እና አድራሻ እያቀያየሩና እያባዙ በተሰማሩበት ሁሉ ይቸበቸባል:: ልብ በሉ!! በዚሁ ዓይነት የሐሰት ዲግሪ በተሸከሙ ሰዎች የሚመራው ሕብረተሰብ! የሚማረው ወጣት ትውልድ! የሚቀየሰው የልማት ስተራተጂና ፓሊሲ ምን ያህል ውጤታማ እና ዘላቂነት ይኖረዋል ብላችሁ ትገምታላችሁ?
አዎ!! የዚህ ሁሉ ድምር ዉጤትም በካድሬ ቁጥጥር ስር የተማሩ ወጣቶች ለውጥ ማምጣት ካልቻሉ” አስረኛ ክፍል ጨርሶ ስማቸውን በደንብ መፃፍ ካልቻሉ” ወደ 80 በመቶ አስረኛ ክፍል ማለፍ ካልቻሉ” 20 በመቶው 11 እና 12 ተምሮ እንደገና 50 በመቶ ከወደቀ” በመጨረሻ ሁሉንም መሰናክል አልፎ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብቶ ከተማረ በውሗላም ያንድ ፓርቲ አገልጋይ እንዲሆን የሚፈረድበት ከሆነና ተመልሶ ወደ አላስፈላጊ ብክነትና ማሕበራዊ ቀውስ በመግባት የሕብረተሰቡን ሸከም ሆኖ የሚቀር ከሆነ ትምህርት ቤት መመላለሱ ፋይዳ ምንድን ነው?

በጤና እና በሌሎች የመሰረተ ልማት ዘርፎች

tuberculosisህዝቡ በጤና ዙርያ ያለበት ችግርም በጣም ብዙ ነው፡፡ በአማካይ በየወረዳው ያለው የህዝብ ብዛት ከ150 ሺ እስከ 200ሺ ይደርሳል፡፡ ልክ ከላይ በትምህርት ዘርፍ እንዳየነው ሁሉ የጤና ቢሮ ሃላፊ በሞያው ተመጣጣኝ እውቀት የሌለው የፓርቲ እና የመንግስት ታማኝ ነው፡፡ የሚሰራው ስራም የፖለቲካ ነው፡፡ በጥቂቱ ለ200 ሺ ህዝብ አንድ ዶክተር ማግኘት ወይም መመደብ አልተቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት ህዝቡ ወደ ሌላ ቦታ ሻል ያሉ ትላልቅ ከተሞች ሄዶ ለመታከም ደግሞ ከተለያዩ የኢኮኖሚ ችግሮች ባሻገር እዛ ሂዶም ትክክለኛ ህክምና አያገኝም፡፡ በሞያው ማነስ ምክንያትም ለተለያዩ ችግሮች ይዳረጋል:: ለምሳሌ ለበሽታው የተሳሳተ መድሃኒት መስጠት! ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት መስጠት! ከአቅም በላይ ገንዘብ መጠየቅ! ለሰሩት ስህተት ተጠያቂ አለመሆን! መንግስት የመደበው መድሓኒት በመንገድ ላይ መሰወር የመሳሰሉ ችግሮች የተለመዱ ሆኗል:: መንግስት በብዙሃን መገናኛ በኩል የሚለው እና በመሬት ላይ ያለው ሃቅ በጣም የተለያዩ ናቸው፡፡

በሌሎች የአገልግሎትና የልማት ዘርፎች የሚታየው እንቅስቃሴም ተመሳሳይ ነው:: ለምሳሌ የኤለክቲሪክ መብራት አላቸው በሚባሉ ከተሞች ቢያንስ በቀን ወደ አራት ገዜ እንደሚጠፋ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ ችግሩ መብራት መጥፋቱ ብቻ ሳይሆን መቼ ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል እና ህዝቡም ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያውቅበት አሰራር የለም፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ የተጀመሩ ስራዎች ይስተጓጎላሉ:: አንዳንድ ምርቶችም ተበላሽተው የሚጣሉበት ጊዜ እንዳለ ይታያል:: አንድ ቀን በዓይኔ ያየሁት ቀላል ገጠመኝ ላንሳ፡፡ የፀጉር አስተካካይ ቤት ነው፡፡ በርካታ ሰዎች ፀጉራቸውን ለመስተካከል ተራ ይዟል:: በዚህ ማሃል መብራቱ ጠፋ እና ሰዎቹ የተወሰነ ጊዜ ከጠበቁ በሗላ ወደየቤታቸው ሄዱ፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ደግሞ በጅምር ላይ ስለነበሩ ግማሽ ፀጉር ይዘው እንዴት ቤት መሄድ እንደሚችሉ ተቸግረው እነሱም ሳይቀር ራሳቸው በራሳቸው እየሳቁ ሄዱ፡፡ ይህንን ቀላል ነገር ለአብነት ያህል ጠቀስኩ እንጂ በዚሁ ብልሹ አስተዳደር ምክንያት ተጠያቂነት በሌለበት አኳሃን የሚጉላላው የሰው ብዛት እና የሚባክነው የህዝብና ያገር ሀብት ቤቱ ይቁጠረው፡፡

ሌላው በኢትዮያ ትልቁ የመዝረፊያ ቦታ በመንገድ ስራ! በውሃ ሀብት ልማት! በመሬት ድልድል! በቤቶች ኮንስትራክሽን! በሰፋፊ የግልና የመንግስት እርሻዎች ያለው የፕሮጀክት እንቅስቃሴ ነው:: እነዚህ ፕሮጀክቶች አንዳንዴም “የባለስልጣኖች የሚታለቡ ላሞች” እየተባሉ እንደሚጠሩ በዘርፉ የሚሰሩ ጓደኞቼ ነግረውኛል:: በነዚህ ፕሮጀክቶች ከውጭ በእርዳታና በብድር የሚገኘው ዕዳን ጨምሮ በየዓመቱ በብዙ ቢሊዮን የሚፈሰው መዋእለ ንዋይና በጀት ቁጥር ስፍር የለውም:: በነዚህ የስራ ዘርፎች ቀጥተኛ እጅና ተሳታፊነት ያላቸው ግዙፍ ባለድርሻዎች በዋናነት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ተቋራጮች (ኮንትራክቶሮች)! ዲዛይኖሮች! ኮንሳልታንቶችና እንዲሁም የመንግስት ተቆጣጣሪዎችና ተጠሪዎች ናቸው::

በነዚህ የልማት ዘርፎችና ፕሮጀክቶች አካባቢ ጎልተው ከሚታዩ መሰረታዊ ችግሮች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ማነቆ የባለ ሙያዎች (ብቁ የሰለጠነ የሰው ሓይል) እጥረትና ፍልሰት ነው:: በሌላ አነጋገር ለስርዓቱ ታማኝ ያልሆኑ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን ከስራው እየገፈተሩ በማባረር በምትካቸው ታማኝና ታዛዝ በሆኑ ካድሬዎች ስለሚተካ በሞያቸው ብቁ የሆኑ ሰዎች ያላቸው ዕድል ሥራ አጥ ሆኖ እየተንሳፈፉ መኖር አሊያም ሳይወዱ ወደ ስደት መፍለስ ነው::

ሁለተኛው ትልቁ ችግር ጥራት ነው:: ጥራት የሌለው ፕሪጀክት ደግሞ የወደፊቱ የትውልድ ዕዳ እንጂ ልማት አይባልም:: ለምሳሌ መንገዶች! ድልድዮች እና የውሃ ቧምባዎች ከተሰሩ ከጥቂት ወራት በሗላ እንደሚፈራርሱ እና መተላለፍያ መሰመሮችን እየተዘጉ ሕብረተሰቡ ለአደጋ እና ለኪሳራ እንደሚዳረግ በግልፅ የሚታይ ነገር ነው:: ለዚህም ነው ሕብረተሰቡ በፌዴራል የሚሰሩ እንደ መንገድ የመሳሰሉ የመንግስት ፕሮጀክቶች የራሱ የሆነ መጠሪያ በመስጠት ሽሮ ፈሰስ ዛሬ ተሰርቶ ነገ የሚፈርስ በሚል የህዝቡ መነጋገሪያ ሆኖ ሲታይ በጣም የሚገርምና የሚቆጭ ነው::
ሶስተኛው ትልቁ ችግር ሙሱና እና ዓይን ያወጣ የሀገር ሀብት ዘረፋ ነው:: ዘረፋው ደግሞ ተራ ዝርፊያ አይደለም:: ዘረፋው አጠቃላይ የስርዓቱን መገለጫ ባህርይ የሆነ ተቋማዊ! ሰንሰለታዊና ድርጅታዊ ይዘት ያለው ሌብነት ነው:: በዚሁ ቀጥተኛ ዝርፊያ የተሰማሩ ደግሞ ከላይ የተጠቀሱት አካላት ናቸው:: ሁሉም በተናጠልም ሆነ በቅንጅት በዝርፊያ የተሳተፉ ስለሆነ አንዱ አንዱን ደፍሮ መቆጣጠርና ስርዓት ማስጠበቅ ወይም በሕግ መክሰስ አይችልም:: ለምሳሌ አብዛኞቹ የውጭ ኮንትራክተሮች የመንግስትን ፕሮጀክቶች ለመስራት ሲቀጠሩ ተወዳድረው በብቃታቸውና በጥራታቸው ተመርጠው ሳይሆን በተለያየ መልኩ የባለስልጣናትን አፍ አጉረሰውና እጅ ጨብጠው ነው ኩንትራቱን የሚያገኙት:: እንደነ ሳሊኒ! ሚድሮክ! የቻይና እና ሌሎች ኮንትራክተሮች በአብነት የሚጠቀሱ ናችው:: የኢትዮያ አንጡራ ሀብት የሆነው ለውጭ ባለሀብቶች እየተቸበቸበ ያለው መሬትም ትልቁ የሙሱና ምንጭ ሆኗል::
ይህ ሁሉ ቅጥ ያጣ ዝርፊያ እየተካሄደ መንግስት ለምን አይቆጣጠርም? ለምን ዝም ይላል? የሚል ጥያቄ እንደሚነሳ እርግጠኛ ነኝ:: ይህ ጉዳይ የራሴም ጥያቄ ስለነበረ መልስ ለማግኘት በተለያየ የሃላፊነት ደረጃ ያሉትንና እንዲሁም እስከ ታች የቀበሌ ነዋሪዎች ድረስ ብዙ ሰዎችን ለማነጋገር ዕድል አጋጥሞኛል:: ከዚህ ሁሉ የተረዳሁትና የተነገረኝ ሙሱና እንደ ክፉኛ ተላላፊ በሽታ ልክፍት መድሃኒት የማይገኝለት ወረርሽኝ በሽታ ሆኗል የሚል ነው:: ይህ ማለት ሙሱና የአገዛዙን ሁለንትናዊ መገለጫና ባሕርይ (ደመ ነብስ) ሆኗል የሚል ነው::
ሙሱናን መቆጣጠር የሚቻለው ደግሞ ሃላፊነት የሚሰማውና ለሕግ ተገዥ የሆነ” ተጠያቂነትና ግልፅነት ያለው መንግስትና የአሰራር መካኒዝም ሲኖር ነው:: በሌላ አነጋገር ህዝቡ ራሱ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በህዝብና በሀገር ሀብት ላይ የሚቀልዱ! የሚዘርፉና የሚባልጉትን ባለስልጣናት ለመቆጣጠር የሚችልበት ብሎም ወደ ፍርድ የሚያቀርብበትን ነፃ የሚድያ! የፍትሕ! የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት ሲኖሩና ሲከበሩ ብቻ ነው::

ነገር ግን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ራሱን ለመቆጣጠር ቀርቶ የህዝቡን እሮሮና ጥያቄ ለማዳመጥና ለመመለስ የሚያስችል ባህርይ! ብቃት! ጆሮና ዓይን የለውም:: አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ መንግስት ሙሱናን መቆጣጠር ማለት እንደ ራስህን በራስ የመግደል (ሱሳይዳል) ዓይነት አድርጎ ነው የሚያየው:: ዛሬ በሀገራችን ስልጣናቸውን ተገን አድርገው የሚዘርፉ ብዙ ጎበዝ አለቆችና ብድኖች ተፈጠሯል:: ባጠቃላይ ሲታይ ማን ለማን መቆጣጠርና መክሰስ በማይችልበት ሁኔታ ላይ እርስ በርስ በተፋጠጥ ላይ የቆሙ ናቸው:: አልፎ አልፎ ሙሱናን እንቆጣጠራለን በሚል ሽፋን የሚያደርጉት እንቅስቃሴም ተቀናቃኝና ለስርዓቱ ታማኝ ያልሆኑ ዜጎችን ለመምታት የሚጠቀሙበት ስልት እንጂ ስርዓቱን ከስረ መሰረቱ ለማፅዳት እንዳልሆነ ህዝቡ በነቂስ ያውቃል::
ሁላችንም እንደሰማነው ከጥቂት ወራት በፊት ሙሱናን ለመቆጣጠር ተብሎ የተጀመረውን የአንድ ሳምንት ሞቅ ሞቅታ እንደ ነበር ይታወሳል:: ህዝቡም በጉጉት ይጠብቅ ነበር:: ነገር ግን የሚፈልጉዋቸውን ጥቂት ሰዎች ካሰሩና ከመቱ በሗላ እርምጃው ባልታወቀ ሁኔታ ወዲያውኑ እንዲቆም እንደተደረገ የሚታወቅ ነው:: እንዲቆም የተደረገበት ዋናው ምክንያት ደግሞ ጉዳዩ እስከ ላይ ድረስ ሰንሰለታዊ! ድርጅታዊ ይዘትና ግንኙነት ስላለውና በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ የህወሓት/ኢሕአዴግን ህልውና አደጋ ላይ ስለሚጥል” የአቶ መለስ ዜናዊንና ተከታዮቻቸውን ስምና ታሪክ ስለሚያጎድፍ” እንዲሁም በብዙ ባለስልጣናት ዘንድ ተጠያቂነትን ሊያስከትል ይችላል በሚል ስጋት ለህዝቡ ያዳባባይ ሚስጢር ሆኖ እንዲቀር ተደርጓል::

Addis abab Demoማጠቃሊያ
የሞያ ነፃነት በተገደበበት” ነፃ የፍትሕ” የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት በሌሉበት! የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት በጠፋበት” ባጠቃላይ አንድ ፈላጭ ቆራጭ ፓርቲ የሀገሪትዋን ሁለንትናዊ ሰብኣዊ” ማተሪያላዊና አእምራዊ ሀብት ተቆጣጥሮና ገድቦ ራሱ ሕግ አውጪ! ራሱ ሕግ ተርጓሚ! ራሱ ሕግ ፈፃሚና አስፈፃሚ በሆነበት ድሃ ሀገር ምን ያህል ለዝርፊያ የተጋለጠ ሕብረተሰብ እንደሆነ እንኳን ለዜጎችዋ ለዓለም ማሕበርም የሚዘገንን ተግባር መሆኑን መገመቱ አያዳግትም::
ይህንንም ተደጋግሞ የተነገረ ስለሆነ አሁን ባነሳው ምናልባት ለሰሚው የሚሰለች ወይም ለቀባሪ ማርዳት ሊሆን ይችላል የሚል ሃሳብ ነበረኝ:: ነገር ግን የሀገርና የህዝብ ጉዳይ እያዳረ የሚቆረቁር ስለሆነ እንደ ግል ጉዳይ ሰልችቶህ የምትተው ነገር አይደለም:: እኔም ላለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ወደ ሀገር ቤት በሄድኩ ቁጥር መሰረታዊ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል ብዬ በማምንባቸው ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተደጋጋሚ የእርምት ፅሑፍ አቅርቤ እንደነበር አስታዉሳለሁ:: ይሁን እንጂ በተመላለስክ ቁጥር የሚያሳዝን እንጂ የተሻለ ነገር አታይም:: በተለይም ከአቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት በሗላም ምናልባት ካለፈው ስህተታቸው ተምረው የተወሰነ ለውጥ ይመጣ ይሆናል የሚል ግምት ቢኖረኝም አሁን ያለው ሁኔታ ሲታይ ግን የባሰ እንጂ የተሻለ አይደለም:: እንዲያውም በሀገርና በወገን ላይ ለሚደርሰው ጥፋትና ጉዳት ለማን አቤት እንደሚባል አውራ እንደሌለው ንብ መንገዱ የጠፋበት ሁኔታ ሆኖ ነው ያገኘሁት::
ትእዝብቴ በዚህ ብቻ አላበቃም:: በተለይም በመልካም አስተዳደር! በፓለቲካ ምሕዳር! በሀገር ድህንነትና አንድነት ዙሪያ መንግስት እየወሰደ ያለው የቂቢፀ ተስፋና አፍራሽ እርምጃ ምን ያህል መረኑ የለቀቀና የከፋ መሆኑን ተጨባጭ ማስረጃዎችን በማስደገፍ በክፍል ሁለት ፅሑፌ ለማቅረብ እሞክራለሁ

ኢትዮያ ሀገራችን ለዘላለም ትኑር
sgbtsait@gmail.com

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live