Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የማይዝሉ ጀግኖች! (በላይ ማናዬ)

$
0
0

ጫማ ማውለቅን ጨምሮ እጅግ አሰልቺና አሳቃቂ የሆነውን ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ዘለቅን፡፡ በጋራ ሰብሰብ ብለን ወደ ስፍራው ካቀናነው ወጣቶች መካከል ግማሻችን በዞን አንድ ሌሎቻችን በሌላኛው ዞን ተከፋፍለን ወደ ወዳጆቻችን ገሰገስን፡፡

አሁን ያለነው በፌደራል መንግስቱ ስር ከሚተዳደሩት እስር ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው ቂሊንጦ ውስጥ ነው፡፡ እዚህ እስር ቤት ውስጥ ልናያቸው የናፈቅናቸው የአርነት ታጋዮች፣ የብዙሃን ድምጾች አሉ፡፡ ከሁለቱ ቡድኖች ከአንደኛው ጋር በመቀላቀል ወደጀግኖቹ አመራሁ፡፡ ከፊት ያሉት ቀድመው አስጠርተዋቸው ኖሯል፡፡ ሁሉም በፈገግታ ታጅበው ከአጥሩ ማዶ ሰላምታ ሰጡን፡፡ ውብ በሆነ ፈገግታና የናፍቆት ስሜት ውስጥ መሆናችን ከጠያቂዎችም ከተጠያቂዎችም በኩል በጉልህ ይታያል፡፡

10616558_581452168647112_4041948437710460738_n

በቀጭን ሰውነቱ ላይ ስስ ነጭ ቲሸርት ለብሶ ሲታይ በእድሜ በጣም ለጋ አስመስሎታል፡፡ ረጂም ቁመቱ ደግሞ ቅጥነቱን አጉልቶታል፡፡ ፍልቅልቅ ነው፤ ሙሉ ደስተኛ ገጽታው ማንንም ቢሆን በፍጥነት የሚያላምድ ይመስላል፡፡ ሲናገር የሚደመጥ፣ ሲናገሩ የሚያደምጥ ግሩም ወጣት ነው፡፡ ይህ ወጣት የዞን 9 ጦማሪያን ቡድን አባልና በ2006 ዓ.ም የቡድኑ አስተባባሪ የሆነው ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ነው፡፡ ሌሎች አብረውኝ የነበሩት ወጣቶች ከሌሎች ሁለት ታሳሪ ጋዜጠኞች ጋር እያወሩ ሳሉ እኔ ከናቲ ጋር አንዳንድ ጉዳዮችን እያነሳን እያለ ስለወቅታዊ አያያዛቸውና ስላለፈው ሁኔታ ወደ ኋላ መለስ ብዬ ጥያቄዎችን አነሳሁለት፡፡ ‹‹ሀገሬ ላይ እርግጠኛ የሆንሁበት ጉዳይ ቢኖር እኔን እንደ ዜጋ የሚጠብቀኝ መንግስት የሌለኝ መሆኑን ነው፡፡ ህገ-መንግስቱ አልጠበቀኝም፡፡ ህገ-መንግስቱ ጥሩ ቢሆንም አልተከበረም›› አለኝ ወጣቱ ጦማሪ፡፡

በ2006 ዓ.ም ሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይ ነበር መንግስት የዞን 9 አባላትን ለቃቅሞ ወደ ማዕከላዊ ማጎሪያ ያጋዛቸው፡፡ የጡመራ ቡድኑ አባላት በሽበር ወንጀል ተጠርጥረው እንደታሰሩ ተገልጾላቸው ለረጂም ጊዜያት በምርመራ ላይ መደበኛ ክስ ሳይመሰረትባቸው ከቆዩ በኋላ፣ መደበኛ ክሱ ሲመሰረት ‹ከሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ ህገ-መንግስቱን በኃይል ለመናድ…› በሚሉ ‹ወንጀሎች› ተከሰው በቂሊንጦ እስር ቤት ሆነው የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ ከቡድኑ አባላት መካከል ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና ዘላለም ክብረት እንዲሁም አብረው በተመሳሳይ ክስ የተያዙት ሁለቱ ጋዜጠኞች ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ በዚሁ በቂሊንጦ ሲገኙ ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ ደግሞ ቃሊቲ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህን እና ሌሎች ቀደም ብለው በእስር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኞች፣ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኪሚቴ አባላትን፣ ፖለቲከኞችን እና ሌሎችንም ታሳሪዎች 2007 ዓ.ም አዲስ አመት መባቻን አስመልክተን ወጣቶች ሰብሰብ ብለን በዋዜማውና በበዓሉ ዕለት ጠይቀናቸው ነበር፡፡ በተለይ ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ‹‹ጥቁር ሳምንት›› (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) በተካሄደ ጊዜ በዘመቻ መጨረሻው ቀን የዘመቻው አስተባባሪዎች አዲስ አመትን በማስመልከት ‹አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር› በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮችን እንድንጠይቅ ጥሪ ማስተላለፋቸውና ጥሪውን የተቀበሉ ወጣቶች መበርከት የእስረኞችን የጥየቃ ፕሮግራም ልዩ አድርጎት ነበር፡፡

እስር ቤት ታጉረው የሚገኙ የነጻነት ታጋዮችም በወጣቶቹ ድርጊት እጅግ መደሰታቸውን በመግለጽ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ እኒያ የማይዝሉ ጀግኖች እስክንድር ነጋና አንዱዓለም አራጌ በቃሊቲ በተገኘንበት ወቅት በወጣቶቹ ድርጊት እንደኮሩና ትግሉ እንዳልቆመም ማሳያ መሆኑን ከመግለጽ አልተቆጠቡም፡፡ ‹‹እኛ ገና በሰላማዊ ትግሉ ጅማሮ ላይ ነው የታሰርነው፡፡ ትግሉ ገና መጀመሩ ነው፡፡ ትግሉ በተግባር የሚፈትናቸው በርካታ ጀግኖች አሉ›› ሲል ነበር ትንታጉ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ወጣቶችን ያበረታታው፡፡

እስክንድር የታሰረ አይመስልም፡፡ አልታሰረምም! በእስር ቤቱ ፖሊሶችና በአንድ ሲቪል በለበሰ ጆሮ ጠቢ ታጅቦ ወደ እኛ ቢቀርብም እስክንድር ፍጹም ነጻ ሆኖ ነበር የሚያወራን፡፡ እስክንድር ነጋን ይፈሩታል እንጂ እሱ አይፈራቸውም፡፡ ይህንን ደግሞ በተግባር ያሳየ ጀግና ነው፡፡ ‹‹አንተ እኮ የምንግዜም ጀግናችን ነህ፤ እንኮራብሃለን!›› አለው ከመካከላችን አንዱ፡፡ እስክንድር መለሰ፤ ‹‹ለእኔ ደግሞ እናንተ ከውጭ ያላችሁ ወጣቶች ናችሁ ጀግኖቼ!››

የእስክንድር መንፈስ ወደ ሌሎች የመጋባት ኃይል አለው፡፡ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላት የጥንካሬ ምንጭ ይህ የማይዝል ጀግና እስክንድር ነጋ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ቂሊንጦ በነበርንበት ወቅት ፍልቅልቁ ወጣት ናትናኤል የሚያረጋግጠውም ይህንኑ ነው፡፡ ‹‹ያኔ ወደ እስር ቤት ሳንገባ በፊት እስክንድር ነጋን ልንጠይቅ ቃሊቲ ስንሄድ እስክንድር ሁሌም ይገርመን ነበር፡፡ ሁሌም ጠንካራ፣ ደስተኛና አስተዋይ ሆኖ ነበር የምናገኘው፡፡ እና፣ እሱን እያየን መታሰር፣ መስዋዕትነት መክፈል ሌላውስ ለምን ይፈራል ታዲያ ስንል ራሳችንን እንጠይቅ ነበር፡፡ እስክንድር ልዩ ሰው ነው፤ የሚጋባ መንፈስ ያለው ጀግና!››

ተስፋለም፣ ናትናኤል፣ አስማማው እና ሌሎችንም ወጣቶች ‹‹እስክንድር አክብሮቱን ገልጾላችኋል እኮ፤ ሰምታችኋል?›› ሲባሉ በደስታ አወንታዊ ምላሽ ሰጡ፡፡ እስክንድር ጀግኖችን የሚያፈራ ጀግና ነው፡፡ ዛሬ ሌሎች ወጣት የአርነት ንቅናቄው የማይዝሉ ጀግኖች የአርዓያቸው እስክንድርን ቃል ለሌሎች ሲናገሩ ይደግሙታን፡፡ ወጣቱ ጦማሪ ናትናኤል ከቂሊንጦ ተናገረ፣ ‹‹ለሀገር የሚያስቡ ብዙ ወጣቶች በየጊዜው ማበባቸው አይቀሬ ነው፡፡ እየታየ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ምንግዜም የሚበረቱ ሰዎች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አምናለሁ፡፡››

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆነው ያሲን ኑሩ ደግሞ እዛ ቂሊንጦ እስር ቤት ልንጠይቅ ለሄድነው ወጣቶች እንዲህ አለን፤ ‹‹መንግስት በኃይማኖቶች መካከል ልዩነት መፍጠር ይፈልጋል፡፡ እናንተ ክርስቲያኖች የኃይማኖት ድንበር ጥሳችሁ ከእኛ ከሙስሊም ወንድሞቻችሁ ጋር መቆማችሁን እናደንቃለን፡፡ እኛን ለመጠየቅ እስር ቤት ድረስ ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ ትግሉ ከዚህም በላይ መስዋዕትነት ያስከፍላልና በርቱ፡፡››

ከሁሉም ታሳሪዎች አንደበት የሚወጣው መልዕክት አስገራሚ ነው፤ ሊያበረታቸው ወደ እነሱ የሚሄደውን ጠያቂ ሁሉ መልሰው አበርትተው ይልኩታል፡፡ እነሱ የማይዝሉ ጀግኖች ሆነው የዛለውን የሀገሬ ወጣት ‹‹በርታ!›› ይሉታል፡፡ አጠር ቀጠን ያለ ቆፍጣና ወጣት ነው፤ ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ፡፡ ‹‹በጥቁሩ ሳምንት ዘመቻ ያደረጋችሁትን ነገር ሰምተናል፡፡ በጣም ደስ የሚል ስራ ሰርታችኋል፡፡ መጥታችሁ ስለጠየቃችሁን ደስ ብሎናል፡፡ እስሩ ቀጣይነት እንደሚኖረው ቢታወቅም፣ በየትኛውም ሁኔታ በርታትችሁ እንድትቀጥሉ እፈልጋለሁ›› ሲል እሱም የማበረታቻ ቃሉን ተናገረ፡፡

ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ በበኩሉ የማሃተመ ጋንዲን የሰላማዊ ትግል አስተምሮ በምሳሌነት ሲያነሳ ከቆየ በኋላ፣ እሱን አብነት አድርገን በሰላማዊ ትግላችን እንድንበረታ አሳሰበን፡፡ ‹‹የሁላችንም ተስፋ ያለው እዚህ እስር ቤት አይደለም፡፡ ከዚህ ውጭ ካላችሁት ነው ሁሉም ነገር ያለው፡፡ በርቱ! ኢትዮጵያ እንደ እናንተ ያሉ እጅግ ብዙዎችን ትፈልጋለች፡፡ ደግሞም አሉ! በበዓል ቀን ስለመጣችሁና ስለጠየቃችሁን ኮርተንባችኋል፡፡››

ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የባለሙያ እጥረት እጅጉን እንደሚያሳስበው ይናገራል፡፡ በእስር ላይ ካለ ጀምሮ የሚያየው የባለሙያ እጥረት ሳይታሰር በፊት ከሚያውቀው በላይ ሳይሆንበት አልቀረም፡፡ ‹‹ታስሬ ባለሁባቸው ቀናት ሁሉ የታዘብኩት ነገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት በሁሉም ዘርፍ መኖሩን ነው፡፡ አቅም ያላቸው ዜጎች ከስርዓቱ በመገፋታቸው ክፍተቱ እንዲሰፋ ሆኗል፡፡ በጣም ነው የሚያሳዝነው፤ የሚሰሩ ሰዎች በተገቢው ቦታ ላይ አለመኖራቸውን አይቻለሁ፡፡ የሚያሰራ ስርዓት ስለሌለ ብዙዎች ህሊናቸውን መርጠው በመራቃቸው ይመስለኛል አቅም ያላቸው ሰዎች የራቁት፡፡ ይህ ለሀገር አሳሳቢ ነው፡፡››

ለመሆኑ በተለየ ሳላከናውነው (ወይም እንደ ቡድን ሳናከናውነው) በመታሰሬ እቆጫለሁ የምትለው ነገር ይኖር ይሆን ስል ጥያቄ አነሳሁለት፡፡ ‹‹የሚቆጨኝ ነገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ተቋማት በእንግሊዝኛ የተሰሩ የጥናት ስራዎችን በመምረጥ አሰባስበን በአማርኛ ቋንቋ በጆርናል መልክ ለመስራት አስበን ያን ሳንሰራ በመታሰራችን ነው›› አለኝ ትክዝ ባለ ስሜት፡፡ ሆኖም አለ ናትናኤል፣ ሆኖም ‹‹አሁን በተለያዩ ሁኔታዎችና ጉዳዮች ላይ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያው በኩል የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ እኛን አስረው ሌላው ዝም እንዲል ፈልገው ኖሮ ከሆነ እንዳልተሳካላቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ለሀገር የሚያስቡ ብዙ ወጣቶች በየጊዜው ማበባቸው አይቀሬ ነው፡፡ እየታየ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ምንግዜም የሚበረቱ ሰዎች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አምናለሁ›› አለ ቀጭኑ ቁምነገረኛ ወጣት፡፡

በግሌ እንደዘንድሮ አይነት አዲስ ዓመት በማይረሳ መልኩ ያሳለፍኩ አይመስለኝም፡፡ ከእነዚህ ባለብሩህ አዕምሮ ባለቤቶች፣ ሰላማዊ ታጋዮች፣ ሀገር ወዳዶች ጋር በዓልን ከማሳለፍ የበለጠ ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር ይኖራል!

እናንተ የማትዝሉ ጀግኖች…የእናንተን ፈር በሚከተሉ እልፍ ኢትዮጵያውያን ነገ ብሩህ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊና የዘመነ አስተዳደር ይገባታል!


የዩክሬይን ክራሚያና የሩስያ ጉዳይ ስለኢትዮጵያና ኤርትራ ያልተዘጋ አጀንዳ ምን ያሰተምረናል?

$
0
0

(አክሊሉ ወንድአፈረው – የግል አስተያየት)

መስከረም 2, 2007 (ስፕተምበር 12 2014  )

 

ukrባለፉት ጥቂት ወራት በዩክሬንና ክራሚያ ውስጥ የተቀሰቀሰው ሁኔታ እና አሁን የደረሰበት ደረጃ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር አንጻር ብዙ ዕድምታዎች አሉት፡፡ እነዚህን ዕድምታዎች መመርመር  በሀገራችን ውስጥ ያለፉና የወደፊት ጉዞ ላይ የተከሰቱ፤ እና ሊከሰቱም የሚችሉ ጉዳዮችን  ከወዲሁ በግምት ውስጥ በማስገባት  ሀገራዊ ራዕያችንን ፣ የትግል አቅጣጫችንን አና አጋርና ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን ሃይሎች ለይቶ ለማወቅ ያግዛል ብዩ አሰባለሁ።  ይህን ማወቁ ደግሞ በሀገራችን እና በብሑራዊ  ጥቅማችን ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ተግባሮች እንድንቆጠብ ዕድል ይሰጠናል። የዚሀ ጽሁፍ ዓላማም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ለመጫር ነው።

 

ለመንደርደሪያ ያህል፦ ለመሆኑ በታሪክ ክራሚያ ዩክሬን ወይስ ሩሲያ ነበረች?

ጠቅለል ባለ ሁኔታ የክራሚያን ያለፉት 200 ዓመታት ታሪክ ስንመለከት በዋናነት የሩሲያ አካል ሆና መቆየቷን እናያለን። በሌኒን የሚመራው የሶሻሊስት አብዮት ከተቀጣጠለ ከ 1917 በሁዋላም ቢሆን ክራሚያ በሶቭየት ህብረት ዕቅፍ ውስጥ አንድ ራስ-ገዝ አስተዳደር ሆና ቆይታለች።

 

ክሬሚያ የዩክሬን አካል የሆነችው ባውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1954 በወቅቱ የራሽያ ኮሚኒስት ፓርቲና ያገሪቱ መሪ በነበሩት በኒኪታ ክሩስቼቭ ሲሆን፤ እኘህም ሰው የትውልድ ቦታቸውና የፖለቲካ አጋራቸው ለሆነችው ዩክሬን በስጦታ መልክ ከሰጡ በሁዋላ ነበር፡፡ በወቅቱ ይህ ጉዳይ ለሶቭየት ፖለቲካ መሪዎችም ሆነ ለክራሚያ ነዋሪዎች አስጨናቂ ጉዳይ አልነበረም፡ ለምን ቢሉ ዩክሬን የሶቭየት ህብረት አንድ ክፍለ ሀገር (ሪፐብሊክ) የነበረች ሲሆን የክራሚያ ዩክሬን ውስጥ መግባት ለአስተዳደር አመቺነት ካልሆነ በስተቀር በጊዜው ሌላ ሰፊ የፖለቲካ እንደምታ አልነበረውምና ነው። ከዚያም አልፎ በተለይ በምስራቅ አውሮፓ ይገኙ የነበሩት ሁሉም ሶሻሊሰት ሀገሮች  በሶቭዬት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ የበላይነት ጥላ ስር  እንዳንድ ሀገር ሆነው  (በሶሻሊስት ዓለማቀፋዊነት መርህ) ይመሩ ስለነበርም እንኳንስ በአንድ ሀገር ስር ያሉ ያስተዳደር ክልሎች በተለያዩ ሶሻሊስት ሀገሮችም መካከል ቢሆን ድንበርና ድንበርተኘነት ታላቅ ቁምነገር ያለው ተደርጎም ይወሰድ እንዳልነበር ማሰታወስ ያስፈልጋል።

 

የክራሚያ ነዋሪዎች በማንነት አንጻር ራሳቸውን እንዴት ይመለከታሉ?

ይህ ጉዳይ አጅግ አወዛጋቢና በዪከሬን ግጭት ውስጥ ተፋላሚ የሆኑ ክፍሎችም የግል አቌማቸውን የብዙሃኑን ፍላጎት እንደሚንጸባርቅ አድርገው የሚሟገቱበት ዕውነታ ነው::

 

በዩክሬይን ስልጣኑን የጨበጡት ክፍሎች እና ደጋፊዎቻቸው “የክራሚያ ነዋሪዎች ራሳቸውን የሚያዩት ከሁሉም በላይ  ከራሽያ የተለዩና ዩከሬንያዊ አድርገው ነው የሚቆጥሩት”  የሚለውን አመለካከት ሁሉም ስው እንዲቀበለው ይፈልጋሉ:: ክራሚያ የዩክሬን አካል ሆና የቆየችበትን ጊዜ በማጣቀሰም በተለይም አዲሱ ትውልድ የተማረውም፤ ያደገውም ስለዩክሬን እየተነገረው ስለሆነ ስለ ራሽያዊነት የሚሰማውም የሚያውቀውም  ቅንጣት ያህል ነገር እንደሌለና ይህም በመሆኑ  ከራሽያ ጋር  የሚያገናኝው ስንሰለት እንደተበጣጠስ ደጋግመው ሲናገሩ ይደመጣሉ::

 

በክራሚያ ውስጥ የሚታየውና የሚጨበጠው  እውነታ ግን ሌላ ነው:: ከ 60 ዓመታት የዩክሬን አካልነት እና ከ23 አመታት ሙሉ ለሙሉ መለያየት በሁዏላም የከሬሜያም ሆነ ሌላው የምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ ዩክሬን ነዋሪዎች የሚሰማችው ስሜት ግን ከሩሲያ ጋር ያላችው የቀደመ ትስስር አንጅ የዩክሬን አካልነት ሆኖ አልተገኘም:::

 

ከዚህ በታቸ የሚታየውና በቅርቡ የተካሄደ  አንድ ጥናት  እንደሚያሳየው  ከ 70%  (ሰባ ከመቶ) የማያንሱ ክራሚያዎች ራሳቸውን የሚቆጥሩት ብቻ ሳይሆን ትስስርንም ቢሆን የሚሹት ከሩሲያ ጋር እንደሆነ ያመለክታል::

 

Data: Razumkov Center; Figure: Grigore Pop-Eleches and Graeme Robertson/The Monkey Cage

 

ይሀ ሁኔታ የሚያሳየው ከአቅመቢሷ ዩክሬን ጋር ከመዳበል ይልቅ ሰፋና ጠንከር ካለችው ሩሲያ ጋር መሆኑ ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው መገንዘብን ብቻ ሳይሆን የረጅሙ ጊዜ ትስስር የፈጠረውን ማንነትንም በቀላሉ መበጣጠስም  እንደማይቻል ነው::

 

በዚህም ምክንያት ይመስላል ክራሚያዎች በተለያየ ሁኔታ በዩክሬን ውስጥ ማንነታቸውን ሊያሰከብሩ ሲጥሩ ቆይተውና ሳይሳካላቸው ባሉበት ሁኔታ ዩክሬን ጓዟን ጠቅልላ በአውሮፓ ማህበረሰብ ዕቅፍ ስር ለመግባት ርምጃ መውሰድ ስትጀምር ሁኔታው ስላልጣማቸው ከገቡበት ፈተናና አጣብቂኝ እንድትታደጋቸው ሩሲያን የተማጸኑት።

ቀደም ሲል በምዕራቡ ዓለም ፖለቲካ ተንታኞች  ክራሚያወች ወደ ራሽያ መዋሀድን አይፈልጉም፤  ፍላጎታቸው ከሌላው አውሮፓ ጋር ይበልጥ መተሳሰር ነው በማለት ደግመው ደጋግመው ይናገሩ ወይም ያስተጋቡ እንጂ በማርች 2014  ሬፈረንደም ሲካሄድ ግን  97%  የሆነው ህዝብ ነበር ዩክሬንን ትቶ ወደ ራሽያ መቀላቀልን የመረጠው። ይህ ሁኔታ የክራሚያ ተወላጆች ከሩሲያ ጋር  ለረጅም ዘመናት ከነበራቸው የታሪክ፣ የፖለቲካ፤ የቤተሰብ፣ የባህል፣ የስነ ልቦናና፣የማሕበራዊ ግንኙነት   ሙሉ በሙሉ  መለያየት ችለናል፤  በራሸያና በክራሚያወች  መካከል የነበረውን የአንድነትና የትስስር ስሜት አጥፍተነዋል፤  ብለው ሲያስቡ ለነበሩ ሁሉ መርዶና የራስ ምታት ነው የሆነባቸው::

ክራሚያውያን ከሩስያ ጋር መልሶ ለመቀላቀል ከ 90 በመቶ በላያ በሆነ ድምጽ  ፍላጎታቸውን ገልጸው ደስታቸውን ሲገልጹ )  Mike Collett-White and Ronald Popeski SIMFEROPOL/KIEV Sun Mar 16, 2014 SIMFEROPOL/KIEV (Reuters) – Russian)

ባሁኑ ሰአት በክሬሚያ የሚታየው ሁኔታ በሻቢያ ስር የወደቀውን ህዝብ የማንነት ጥያቄ በተመለከተ ብዙ ጉዳዮችን እንድናገናዝብ ያስገድዳል። ላለፉት 23 አመታት “የኛ ሀገር ነች; የማንነታችን  መግለጫ ነች”; ብለው ከሚመለከቷት እና ከሚወዷት ኢትዮጰያ ተነጥለውና በኤርትራ ውስጥ ከነመሬታቸው ተገደው ከሚገዙት የአፋር፤ ኩናማ፤ ኢሮብ፤ የሀማሴን፣አካለጉዛይ እና ሌሎችም ወገኖቻችን ሁኔታ ጋር እጅግ ይመሳሰላል። ታላቁ የአፋር ተወላጅ የተከበሩት ቢትወደድ ዓሊ ሚራህ፣ “እንኳንስ ህዝቡ ግመሎቻችንም ቢሆኑ የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውቃሉ” ሲሉ የተናገሩት ታላቅ መሪ ቃል  ስለአፋር ህዝብ የማይናጋ ጥልቅ ኢትዮጽያዊነት በቂ ማስረጃ ነው። ከዚህም ሌላ ቅድመ ሻቢያ/ወያኔ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ምንም አናውቅም ብለው ስለቆሙ በሻቢያ ሰራዊት በተደጋጋሚ የተደበደቡት የኩናማ፤ የሳሆ ወዘተ ወገኖች ታሪክ  ኢትዮጰያዊነትንና የትዮጵያዊነትን ስሜት ከነዚህ ህዝቦች መለየት እንደማይቻል ወይም እጅግ ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ያመላክታል።

በመሀል ብዙ ቅሬታ እንደተከሰተ አጠያያቂ ባይሆንም ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ለማሰተሳሰር ስለታገሉትና ስለወደቁት አርበኞች፣በልጆቻችውና በልጅ ልጆቻቸው አዕምሮ ውስጥ በአሁኑ ሰአት ምን አይነት ስሜት እንደሚመላለስ  የክራሚያ ተመክሮ ፍንጭ ሊሰጥ ይችላል:: በተለይም ደግሞ የክሬሚያ አዲስ ትውልድ አሁንም ከአማሪጮች ሁሉ ወደ ራሸያ ማዘንበሉን እንደመረጠ ስንመለከት አበረታች ሁኔታ ቢፈጠር በሻቢያ ስር በምትገኘው ኤርትራ ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን ዕውነታ መገመት አይከብድም::

 

የክራሚያን ሁኔታና ዕውነታ ስንመለከት፤ የህወሀት መሪወች ሲሰብኩት የቆየውና አሁን ደግሞ ባንዳንድ  ተቃዋሚወች ውስጥም እየሰረጸ ያለው “የኤርትራ ጉዳይ ያለቀለት ጉዳይ ነው” የሚለው  አመለካከት የህዝብን ሰነልቦናዊ ጥንካሬ ወደሚቦረቡር እና ብሄራዊ ጥቅምንም ወደሚጎዳ ተግባር እንዳያነጉደን ያሰጋል። የሀገር ጥቅም የሚጠበቀው ጽናት እና ጥራት ባለው ራዕይ ላይ በተመሰረተ ትግል እንጂ  ጊዚያዊ ጥቅምን ለማሳደድ ሳያላምጡ በመዋጥ ወይም ደግሞ መሰረታዊ የሀገር ጥቅምን “እሱን አሁን እርሱት”  በሚል  ራእይ የለሽ አካሄድ ከቶውንም ሊሆን አይችልም::

 

ሩሲያ ስለ ክራሚያ ምን ያስጨንቃታል?

ሩሲያ በኢኮኖሚም ሆን በወታደራዊ ሃይል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊነትና ተደማጭነት ያላት ታላቅ ሀገር እንደመሆኑዋ በቆዳ ስፋቱዋም ቢሆን አሁንም ባንደኘነት ደረጃ ላይ ትገኛለችል። ባንጻሩ ደግሞ ክራምያ በህዝብ ቁጥርም ሆነ በኢኮኖሚ ለሩስያ እዚህ ግባ የማይባል አስተዋጽኦ ነው የሚኖራት። በኢኮኖሚ አንጻር ብቻ ካየነው በዋናነት ተጠቃሚዋ ከራሚያ እንጂ ሩሲያ አትሆንም፡፡ ሆኖም ግን የዘር ሓረግና ታሪክን የሚገዛው ገንዘብ ብቻ አደለምና  ክራሚያ በሩስያ  (ሩስያም በክሬምያ) በታሪክም ሆነ በህዝቡ ሥነ-ልቦና ላይ እጅግ ቁልፍ ቦታ አላቸው፡፡ይህ ሁኔታ ምን ያህል መሰረት ያለው እንደሆነ ለመገንዘብ የሚቀጥሉትን ታሪካዊ ሁኔታዎች እንመልከት፡

 

  • በጊዜው በመዳከም ላይ የነበረው የኦቶማን ኢምፓየር እና ራሸያ በኦክቶበር 1853 ውጊያ ውስጥ የገቡት በክሬምያ ጉዳይ ነበር፡፡ ውጊያው የተቀሰቀሰው ሩሲያ በክራሚያ የነበሩ የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮችን ከጥቃት ለማዳን በወሰደችው እርምጃ ነው ።
  • ይህን ተከትሎ ከ 1853–1856 ባንድ በኩል በራሸያ በሌላ በኩል ደግሞ በፈረንሳይና እንግሊዝ ጥምር ጦር መሀል የተካሄደው ጦርነት በክሬምያ ውስጥ ነበር፡፡
  • የቦልሽቪኮችን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ነጩ ሰራዊት ( the white army) እየተባለ የሚጠራውና ሶሻሊዝምን በሚቃወሙ የምዕራብ ሃይሎች ይደገፍ የነበረው የተቃዋሚዎች ሀይል በ1920 የመጨረሻውንና ወሳኙን ውጊያ ያካሄዱትም በዚሁ በክሬሚያ ነበር።
  • በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ደም የፈሰሰበት ጦርነት ከተካሄደባቸው ቦታዎች ውስጥ ክራሚያ አንዷና በዋናነት የምትጠቀስ ነች።
  • የጀርመን ናዚዎች ክራሚያን ለመያዝ ባደረጉት ወረራ ከ 170 ሽህ በላይ የሶቭየት ጦር የተሰዋ ሲሆን በወቅቱ ፋሽስቶችን እስከመጨረሻ የመከተችው ኣና የጀግኖች ከተማ በመባል ልዩ ሽልማት የተሰጣት የክራሚያ ዋና መናገሻ የሆነችው ሴቫስቶፖል ነበረች። በወቅቱ ምዕራብ ዩክሬን የፋሽስቱ ሂትለር ተባባሪ በመሆን በሽዎች የሚቆጠሩትን ጸረ-ፋሽስት ሃይሎች እንደገደሉና እንዲሰደዱ እንዳደረጉ ታሪክ መዝግቦታል።
  • በሁለተኛው ያለም ጦርነት ማጠቃለያ በሦስቱ ተባባሪ ሐያላን ሀገሮች (Allied Forces) መሪዎች ያሜሪካው ፍራንክሊን ሩዝቬልት፣ የሩሲያው ጆሴፍ ስታሊን እና የኢንግሊዙ ዊንስተን ቸርችል መካከል የተደረገው ስብሰባ የተካሄደው በያልታ ፣ ክራሚያ ውስጥ ነበር።

 

ይህ ሁሉ በራሽያውያንና ክራሚያ መካከል ያለውን ከፍተኛ የታሪክና  የሰነልቦና ትሰሰር  አንዱ ሌላውን ለምን እንደሚፈልግ ያሳያል::

 

ይህ ብቻ ሳይሆን ክራሚያ ለሩሲያ የምታስገኘው  ጂኦ-ፖለቲካዊና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታም እጅግ ትልቅ ነው። ክራሚያ ቀደም ሲል የሶቭየት ህብረት በሁዋላም የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ሀይል የሆነው ብላክ ሲ ፍሊት የጦር ሠፈር ነች። በዩክሬን ውስጥ የራሽያ ፍቅር የሌለው መንግስት ሥልጣን ቢይዝ የሩሲያን ደህንነት ዛሬም ባይሆን ነገና ከነገ ወዲያ አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል ራሸያ ጠንቅቃ ታውቃለች። ይህ አደጋም አፍንጫዋ ስር ሲከሰት እጅ አጣጥፎና ምንም እንዳልተፈጠረ በማስመሰል ማለፍን የራሸያ መሪወችም አልፈለጉም። ስለዚህም ቀልጠፍና ፈርጠም  ያለ እርምጃ መውስድን አስፈላጊ ሆኖ አግኝተውታል። የራሽያው ፕሬዚደንት ፑትን በቅርቡ ለሀገሪቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ክራሚያ ለሩሲያ ምን ያህል ስትራተጂያዊ አስፈላጊነት እንዳላት ሲገልጹ “ ወደ ሜዴትራንያንና ወደ ጥቁር ባህር መሽጋገሪያችን የሆነችው ሶቫስቶፖል በባዕዳን ቁጥጥር ስር ሆና ማየት ከቶውንመ ተቀባይነት የለውም “ ነበር ያሉት።

 

ከላይ ስንደረደርበት የቆየሁት አመለካከት ወዳገራችን ሁኔታ ሲመለስ፤ ኢትዮጵያሰ ስለ ኤርትራ ምን ያስጨንቃታል የሚለውን ጥያቄ ማጫሩ አይቀሬ ነው። ከዚህ አኳያ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ምርምር አድርጎ መደምደሚያ ላይ እንዲደርስ ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ። ሆኖም ግን ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በኢኮኖሚ፣ በሀገር ደህንነት ወዘተ አንጻር እጅግ ብዙ ጉዳት እንደደረሰባት  እና ወደፊትም መገመት የሚከብድ አደጋ እንደተጋረጠባት ብዙወች በመረጃ አስደግፈው ጽፈውበታል። በኢኮኖሚ አንፃር ብቻ ሲታይ እንኴ የራሷን ወደብ እንድታጣ የሆነችው ኢትዮጵያ ለጂቡቲ መንግስት ለወደብ ኪራይ የምትክፍለው ገንዘብ በየቀኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠር እንደሆነ ይታወቃል:: ይሀ ገንዘብ ለሀገር ልማት ቢውል ኖሮ የምን ያክል ህጻናትን ህይወት ማዳን እንደሚቻል ምን ያህል ተጨማሪ ትምርት ቤት ጤና ጣቢያ ማቌቌም እና ህይወት ማዳን እንደሚቻል ስናስብ የሁኔታውን አንገብጋቢነት ለመገንዘብ ይረዳል::

 

አሁን ካለው አሀዝ ስንነሳ ኢትዮጵያ የራሷን ወደብ አጥታ ለጅቢቲ የምትከፍለው ወጪ  በያመቱ ለአንዳንዱ ወረዳ በሚሊዮኞች የሚቆጠር ተጨማሪ በጀት ለመመደብ የሚያሰችል ነው። ይህ ታዲያ ድህነትን ለመቀነስ፣ ለልማት ወዘተ ምን ያህል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ማንናውም ጤነኛ አእምሮ የሚገነዘበው ነው።

 

በዚህ አንጻር ሰፋ ያለ ግንዛቤ ለማግኘት ለሚፈልግ ሁሉ የዶ/ር ያዕቆብ ሐይለማርያም “አሰብ የማን ናት”፤ የአምባሳደር ዘውዴ ረታን “የኤርትራ ጉዳይ”፤ ባዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የታተመውን “የአክሊሉ ማስታወሻ” ጥሩ ግንዛቤና መረጃ ሊሰጡ የሚችሉ መጻህፍት መሆናቸውን መጥቀስ እወዳለሁ።

 

የሶቭየት ህብረት መፈራረስ ክራሚያና ኤርትራ

የሲቭየት ህብረት መፈራረስን ተከትሎ በነበረው ያልተረጋጋ ወቅት ክራሚያም በግርግር ከዩክሬን ጋር ተደባልቃ ከራሸያ ተገንጥላ እንድትሄድ አድርገዋል የሚባሉት እንኳንስ ለሀገር ለራሳቸውም ማሰብ ይሳናቸው ነበር እየተባለ የሚነገርላቸው ፕሬዚደንት ቦሪስ ዬልሰን ናቸው:: ግለሰቡ የዚሀ አይነት ውሳኔ ሲወስኑ የክሬሚያን ታሪክ፣ ስትራተጂክ ጠቀሜታ ወዘተ ከቁብ አላስገቡትም፣ የህዝቡንም ስሜት ቦታ አልሰጡትም ነበር። የሳቸው ሩጫ ከምን እንደመነጨ በግልጽ በማይታወቅ መልኩ ጎርባቾቭ የቀደዱትን የለውጥ መንገድ በመለጠጥ ሶቭየት ህብረትን በማፈራረስ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ክራሚያን በተመለከተም የሶቭየት ህብረት ታላቅ የባህር ሀይል የሆነው ብላክ ሲ ፍሊት ንብረት ሽያጭና ገንዘብ መሰብሰብ ላይ ነበር ትኩረታቸው። ያም ሆኖ  በንግድ አንጻር እንኳ እዚህ ግባ የሚባል ገንዘብ አላገኙበትም።

 

የክራምያን ጉዳይ መደምደሚያ ለመስጠት የተሞከረው በሶቭይት ሕብረት ባጠቃላይ እንዲሁም በራሽያና በተቀሩት  ሶሻሊስት ሀገሮች ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ እና አለመረጋጋት በሰፈነበት ወቅት ነበር። በዚያ የቀውስ ወቅት በቂ የሆነ አማራጭና ረጋ ብሎ ለማሰብ ጊዜ ሳይኖር ሬፈረንደም ተካሄደና 58% የሚሆን ህዝብ ደገፈው በማለት ክራሚያ ከሩሲያ ተለይታ የዩክሬን ግዛት ሆና እንድትሄድ ተወሰነ።

 

ይህ ጉዳይ ግን በብዙ ዜጎች ልብ ውስጥ ቁርሾ አስከተለ፤ ጠባሳም ጣለ። የጊዜው ሁኔታ ባይመችና በወቅቱ ማድረግ ስለሚገባቸው ነገር ግራ ቢጋቡም፤ እጅግ ብዙ የክራሚያ ኑዋሪዎች ልባቸው መሸፈቱ አልቀረም፡፡ በዘሩም በታሪኩም ራሽያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነው የክሬምያ ሀዝብ የለም ዩክሬናዊ ነህ ሲባል ጥርሱን ነከሰ። ሆኖም ግን በወቅቱ የሚያዳምጠው አላገኝም። ያ ታምቆ የቆየ  ቅሬታ  አሁን በቅርቡ አመጽ ወልዶ እነሆ እየሆነ ያለውንና የሆነውን ዓለም እየመሠከረ ነው።

 

የኤርትራ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ዕውነታ ከሶቭየት ህብረት መፈራረስ እና ከቀዝቃዛው ጦርነት “መገባደድ” ጋር በቅርብ የተቆራኘ ነበር፡ “ህዝበ ውሳኔ” (ሬፈራንደም ) የተባለው ሂደትም በሀሪቱ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ በነበረችበት፣ ገና ቋሚ መንግስት እንኳን ሳይኖራት ነበር። በ“ህዝበ ውሳኔ” ሂደት ውስጥም የኢዮጵያዊነት አማራጭ በታፈነበት ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነውና የሆነውን የአፋርና ኩናማ፣ የሳሆ፤ ወ.ዘ.ተ ህዝብንም ፍላጎት ለማክበር ምንም ጥረት ሳይደረግና ውጤቱም ሳይታይ በግድ ያልሆነውንና ያላመነበትን ማንነት  ተቀበል ተብሎ የተጠናቀቀ የግርግር ሁኔታ ነው። ይህ ስለሆነም እነሆ እስካሁን የቀጠለው ቅሬታ የመሳሪያ ግጭትን ወልዶ ካንድ ቀውስ ወደሌላ በመሽጋገር ላይ ይገኛል።

 

የሚገርመው ከስልሳ አመት በሓላ ሩሲያ በክሩስቼቭ ጊዜ የተጀመረውን ያስተዳደር ክልል ማሸጋሸግ እና በቦረስ ዬልሲን ዘመን የተወሰደውን የረጅም ጊዜ ዕይታ የጎደለውን የፖለቲካ ርምጃ ለማረም የተዘጋጀ ድርጅትና መሪ አግኝታለች። ኢትዮጵያችን ግን በሁሉም መልኩ ሀላፊነት የጎደለውን የመለስ ዜናዊ ለሀገር ደንታ ቢስ የሆነ ውሳኔ ለማረም እና ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ጥቅም በድፍረት የቆመ የመንግስት መሪ ገና አልታደለችም። ያም በመሆኑ መከራውም ቀጥሏል መፍትሄውም እየተወሳሰበ መሄዱ አይቀሬ ሆኗል።

 

የተባበሩት መንግሥታትየዩክሬንን ሀገራዊ አንድነት ስለማሰከበርያካሄደው የድምጽ አሰጣጥ

የክሬሚያ ነዋሪወች በዩክሬን ስር መተዳደርን አንፈልግም ብለው ማጉረምረም ሲጀምሩ ነው ታላላቆቹ የምእራብ መንግስታት ሁኔታውን ለማዳፈን መሯሯጥ የጀመሩት። የክሬምያን ህዝብ ታሪክ፣ ፍላጎትና ማንነት ጠንቅቀው የሚያውቁት ምዕራባውያን ጭንቀታቸው ያነጣጠረው በክሬምያ ላይ ሳይሆን ሩሲያ እንደገና ተጠናክራ በመውጣት ጉዳይ ላይ ስለሆነ ይህንን ለማከሽፍ፣ ባለፈው የካቲት መጨረሻ ገደማ ዩክሬን ውስጥ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው መንግስት ባመጽ ሲፈነቀል ቃል ያልተነፈሱት ምዕራባውያን፤ በክራሚያ የተደረገውን ሬፈረንደም ተከትሎ ዩክሬን ተወረረ፣ ወዘተ፤ የሚለውን ከበሮ መደለቅ ጀመሩ። ከሁካታው በስተጀርባ ግን አሁን ባለው ሁኔታ ምዕራባውያኑም ሆኑ ራሱ የዩክሬይን መንግስት የክራሚያ ጉዳይ ያለቀለት እንደሆነ የተቀበሉት ይመስላል። ሩጫው ሊፈጠር የሚችለውን ሌላም ምስቅልቅል ሁኔታ ለመቀነስ ምናልባትም ራሱ የዩክሬን እንደሀገር የመቀጠል ጉዳይ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የመጨነቅ፣ ሰፋ ያለ የርስ በርስ ጦርነት ባውሮፓ ውስጥ እንዳይቀሰቀስ የመፍራት ጉዳይ እንጂ ክራሚያን የማስመለስ ፍላጎት አይመስልም።

 

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃው ምከር ቤት (ድምጽን በድምጽ ሽሮ ጥርስ-አልባ የሆነው) እና ጠቅላላ ጉባኤውም በዚህ ጉዳይ ያስተላለፈውና ከፍተኛ ክፍፍል የነበረበት ውሳኔ “ይህን ብለን ነበር “ ከማለት የማያልፍ ነው። ጠንከር ያለ የማዕቀብ እርምጃ ወሰዱ የተባሉት አሜሪካና የአውሮፓ ማህበረሰብም ቢሆኑ ርምጃቸው ጥቂት ባለስልጣኖችን የሚነካ ከመሆን አላለፈም።

 

ቀረብ ብሎ ሲታይ ደግሞ ያፍሪካ መንግስታት በተለይም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስታት የወሰዱት አቋም ትኩረትን የሚስብ ነው፡፡ የሁለቱም ወኪሎች  በተባበሩት መንግስታት ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የክሬምያን ከዩክሬን መገንጠል ሳያወግዙም ሳይደግፉም ድምጽ ተአቅቦ (አብስቴን) በማድረግ ማለፉቸውን እንገነዘባላን።

 

ይህ የድምጽ አሰጣጥ ከብዙሀኑ ያፍሪካ ሀገሮች የተለየ አይደለም፤ በተባበሩት መንግሰታት ምክር ቤት ”የዩክሬንን ሀገራዊ አንድነት ማሰከበር “ በሚል ርእስ የክራሚያን መገንጠል ለመቃወም የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ የደገፉ ያፍሪካ ሀገሮች 19 ብቻ ሲሆኑ የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙ ሁለት (ሱዳንና ዚምባብዌ ) ድምጸ ተአቅቦ ያደረጉ ደግሞ ወደ 22 ያፍሪካ ሀገሮች ነበሩ። ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጰያና ኤርትራ ይገኙበታል። ይህ በሶሰት ቦታ የተከፈለ የድምጵ አሰጣጥ  የሚያሳየው የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ ያፍሪካ አንድነት ማህበር በተመሳሳይ ሁኔታዎች ላይ የሚወስዷቸው አቋሞች ከሀገራቸው ፖለቲካ፣ እና ከሚያስገኝላቸው ጥቅም አንጻር እንጂ ከቋሚ መተክልና ዕምነት በመነሳት እንዳልሆነ ነው፡፡

 

ከዚህ ሁኔታ መገንዘብ እንደሚቻለው ለተመሳሳይ ሁኔታወች እያንዳንዱ ሀገር ስለሚወስደው እርምጃ ወሳኙ ጉዳይ “የተባበሩት መንግስታት ወይም ያፍሪካ አንድነት ህግ” ሳይሆን እያንዳንዱ ሀገር የሚያገኘው ጥቅማ ጥቅም እንደሆነ ነው። ባጭሩ የሀይል አሰላለፉን  የሚገዛው መተክል (ፐሪንስፕል) ሳይሆን በጊዜው ሀገራት የሚያገኙት ጥቅም እና የሀይል ሚዛን ይመስላል።

 

ጠቃለያ

ከዩክሬይን ክራሚያና የሩስያ ጉዳይ የሚገኘውን ትምህርት በከፊል እንደሚከተለው ላጠቃል፡

 

  1. ሀገራዊ ራዕይና አርቆ አሳቢነት ከፖለቲካ መሪዎች (ገዠዎችም ተቃዋሚም ) የሚጠበቅ ተግባር ነው፣

 

  1. ለአጭር ጊዜ ፖለቲካዊ ጥቅም ሲባል የሚወሰዱ ርምጃወች ጦሳቸው እጅግ የተወሳሰበ ይሆናል። ክሬሚያና ዩክሬንን በተመለከተ ፕሬዚደንት ያልሰን የወሰዱት ይህን ያመለክታል፡

 

  1. የህዝብ ታሪክ እንደፈለጉ የሚጽፉት፤ የሚፍቁት ወይም የሚቀያይሩት ኣደለም፡፡ ክራሚያውያን ባገኙት የመጀመሪያ አጋጣሚ ወደ ራሽያ ልመለስ ማለታቸው የሚያሳየውም ይህንኑ ነው፡፡ የክራሚያ ዓይነቱ ጥያቄ በክራሚያ ብቻ አልተወሰነም። አሁን በምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ ዩከሬን 10 ያህል ከተሞች ውስጥ እየተካሄደ ያለውም አመጽና ጥያቄ ባብዛኛው የክራሚያ ነዋሪዎችን ጥያቄ የሚያሰተጋባ ነው።

 

  1. የሀገር መሪዎች ሀገራዊ እና ስትራተጂያዊ ጠቀሜታን ማረጋገጥ ከሁሉም በላይ ግዴታቸው ሊሆን ይገባል። ይህን ሲያደርጉ ደግሞ ዋናው መሠረት የህዝባቸው ፍላጉት፣ ታሪክና እውነታ እንጂ የባዕዳንን ጥቅምና ትዕዛዝ ከማስጠበቅ አኳያ ሊሆን አይገባውም።

 

  1. የሀገሩን ታሪካዊና ስትራተጂያዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚቆም መሪ ደግሞ የህዝብን ድጋፍ የሚያገኝ ለመሆኑ የክሬምያ ሁኔታና የፑቲን ተወዳጅነት ያረጋግጣል። ካውሮፓ፤ ካናዳና አሜሪካ የሚሰማው ተቃውሞ ቢቀጥልም የፕሬዚደንት ፑቲን የህዝብ ድጋፉ እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡ተጻርረው የቆሙ ደግሞ የተወገዙ ከመሆን እና “የታሪክ ጠባሳ” ተሸክመው ከመጓዝ ሊድኑ አይቸሉም። በቅርብ የተካሄደ አንድ ጥናት እንደሚያሳዪው 85% የራሽያ ህዝብ ፕሬዚደንት ፑቲንን ይደግፋል  http://www.levada.ru/06-08-2014/avgustovskie-reitingi-odobreniya:: በነገራችን ላይ ጥናቱን ያካሄደው ለፑቲን ፍቅር እንደሌለው የሚታወቀው ሊቪዳ የተሰኝው የጥናት ተቌም ነው

 

  1. ባለራዕይ መሪዎች የተለያዩ ታሪካዊ ሁኔታዎች የሚፈጥሩላቸውን አጋጣሚዎች በመጠቀም የትናንት ስህተቶችን ለማረም ቆራጥ እና ፈጣን ርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ይህም ከፖለቲካ ቀኖናና ከአይዲዮሎጂ እሥረኛነት መላቀቅን እና ድፍረትን ይጠይቃል።

 

7.ድርጅቶች ኤርትራን በተመለከተ ያልተዘጋውን አጀንዳ  በጥልቀት በመረዳት የህዝብን ወኔ ከሚሰልብ በሽንፈትና በጨለምተኛነት ከተተበተበ አመለካከትና አካሄድ ራሳቸውን ሊያጸዱ ይገባል እላለሁ:: ወላጆቻችን አያቶቻችንና ቀደምት ትውልዶች  ጠላት የጫነባቸውን ሁሉ “ያለቀለት ነው” ብለው በመንበርከክ ሳይሆን ሀገራዊ ጥቅምን በተመለከተ በጠራ ራእይ ላይ ተመርኩዘው በጽናት በመቆማቸው ነው ያችን ሀገር ለኛ ያወረሱን። እኛስ?

 

አስተያየት ቢኖርወት በሚከተለው ኢሜል አድራሻ ሊልኩልኝ ይችላሉ  ethioandenet@bell.net

 

 

 

ወያኔ፣ ሽብር እና እኛ (ያሬድ ኃይለማርያም)

$
0
0

ያሬድ ኃይለማርያም

ከብራስልስ

መስከረም 3 ቀን 2007 ዓ.ም.

 

Woyanes shoud face justiceበአለም አቀፍ ደረጃ ስለ ሽብርተኝነት ያለው አረዳድ እና ወያኔ ሽብርተኝነትን የሚተረጉምበት መንገድ ለየቅል ናቸው። በአለም አቀፍ ደረጃ የሽብርተኝነት ጉዳይ እንደ ዋና አጀንዳ ተይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ መነጋገሪያ የሆነው በ1934 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ነው። በዛሬው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተተካው የሊግ ኦፍ ኔሽን በሽብርተኝነት ዙሪያ ሲመክር ቆይቶ በ1937  ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና ለመቅጣት የሚያስችል አንድ ድንጋጌ (Convention for the prevention and punishment of terrorism) አጽድቋል። ከዚህ ድንጋጌም በኋላ ከ14 የሚበልጡ አለም አቀፍ ድንጋጌዎችና ስምምነቶች በተባበሩት መንግስታት ጸድቀዋል። የእነዚህ ሕጎች ዋነኛ አላማም መንግሥታት ሽብርተኝነትን በተናጠልም ሆነ በጋራ እንዲዋጉ ለማስተባበር ብቻ ሳይሆን  ሽብርተኝነትን እንዋጋለን በሚል ሽፋን በዜጎቻቸውም ሆነ በተቀረው የሰው ዘር ላይ መድልዎን፣ ግፍና በደሎችን በመፈጸም ሰብአዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር የተጣለባቸውን አለም አቀፋዊ ግዴታ እንዳይዘነጉም ለማሳሰብ ነው። ምንም እንኳን ኃያላኖቹ አገራት ሳይቀሩ የጸረ-ሽብር ዘመቻን ለፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቻቸው ማስገኛ ሲያውሉትና ሲመነዝሩት በግልጽ ቢስተዋልም በሽብርተኝነት ላይ ያላቸው ምልከታና አቋም ግን በአለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጡት መመዘኛዎች የራቁ አይደሉም።

በወያኔ መንደር ሽብርተኝነት ለየት ያለ መልክ ነው ያለው። የወያኔ የሽብርተኝነት መስፈርትም ሆነ ትርጓሜ ብዙ ሃገሮች፤ አንባገነን የተባሉት ሳይቀሩ ስለሽብርተኝነት ካላቸው ግንዛቤም ሆነ ከአለም አቀፉ መመዘኛዎች የተለየ ነው። የሽብርተኝነት ተግባር እየተተረጎመ ያለው በወያኔ ባልሥልጣናት የመሸበር መንፈስና ሰለራሳቸው ሥልጣን ብቻ በማሰብ ከጭንቀት በመነጨ የፍርሃት ስሜት ላይ የተመሰረተ ነው:: ባለሥልጣናቱን ጭንቅት ወስጥ የሚጥል፣ የሚያስደነብር፣ የሚያስቀይም፣ የሚያስቆጣ ወይም የሚያሰፈራራና እንቅልፍ አጥተው እንዲያድሩ የሚያደርግ ተግባራትን የፈጸመ ሁሉ በሽብርተኛነት ይፈረጃል:: ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀይ መስመር አስምረውና አዋቅረውት የሄዱትን የወያኔን አጥር የሚነቀንቅ ብቻ ሳይሆን ጠጋ የሚልም ሁሉ በአሸባሪነተ ሊፈረጅ፣ ሊታሰርና ሊከሰስ እንዲሁም ሊፈረድበት እንደሚችል እየታየ ነው:: ለአገዛዝ ሥርዓቱ የሥልጣን ዘመን መራዘም ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉዋቸውን አካላትና ግልሰቦች ሁሉ አሸባሪ አያሉ መክሰስ የተለመደ ሆኗል። ብዕራቸውን አንስተው በመንግሥት ላይ የሰሉ ትችቶችን በመጻፍ ተቃውሟቸውን የገለጹ፣ የሃይማኖትና የተለያዩ ማህበራዊ ተቋማትን በመወከል የመብት ጥያቄዎችን አንስተው የተሟገቱ የሕዝብ ወኪሎች፣ በወያኔ በባለሥልጣናት የተፈጸሙ ወንጀሎችን፣ ሙስናዎችን፣ አገርና ሕዝብን ያዋረዱ ተግባራትን ያጋለጡና ባደባባይ ሥርዓቱን የሞገቱ ጋዜጠኞች፣ የማህብራዊ ድረ-ገጽ ገተሳታፊዎች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ጭምር የሽብርተኝነት ካባ እያከናነቡ ማጎርና መወንጀል የሥርዓቱ ዋና ስልት ሆኗል። ይህም ወያኔ አለም በሚሸበርበት ጉዳይ ሳይሆን ራሱ በፍርሃት በፈጠረው የሽብር ዓለም ወሰጥ መሆኑን ያሳያል::

ከግለሰብ (ከሟቹ ጠ/ሚ መለስ) አንባገነናዊነት ወደ ቡድን አንባገነናዊነት የተሸጋገረው የወያኔ-ኢሕአዴግ ሥርዓት ከመቼው ጊዜ በከፋ ሁኔታ በፍርሃት መዋጡን የሚያመላክቱ በርካታ ክስተቶችንም እያስተዋልን ነው። ፍጹም አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ የነበሩትን አቶ መለስ በብዙ ትናንሽ መለሶች ለመተካት ተጥሯል። ምንም እንኳን በበቂ ማስረጃ ማረጋገጥ ባይቻልም የሥርዓቱ ተዋናይ ከነበሩ እና አሁንም በሥልጣን ላይ ካሉ የአመራር አባላት እየሾለኩ የሚወጡት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በድርጅቱ ውስጥ ባሉት ጎሣን መሰረት ያደረጉት ክፍልፋዮች መካከል ከሚስተዋለው ጤናማ ያልሆነ የፖለቲካ ፉክክር እና ሽኩቻ ባሻገር በግለሰቦች ዙሪያ የመቧደን ስሜት እየጎላ በመምጣቱም ድርጅቱ ውስጥ ፍርሃት እንዲነግስ አድርጓል። ይህንን ክፍተት በመጠቀም በሰላማዊም ሆነ በነፍጥ ኃይል የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት የተደራጁ የፖለቲካ ኃይሎችና ቡድኖች መነቃቃትም በፍርሃት ውስጥ ያለውን የወያኔን ሥርዓት የበለጠ እንዲደነብር አድርጎታል።

በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰላማዊ ትግል አምነው ከተደራጁት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የተወሰኑት  በተከታታይ ያካሄዷቸው የተቃውሞ ሰልፎችና የሕዝብ ምላሽ፣ አፈና እና ስቃዩን ተቋቁሞ ለአመታት የዘለቀው የሙስሊሙ ማኅበረሰብ እንቅስቃሴ፣ ልማትን ሽፋን አድርጎ ሥር እየሰደደ ያለው የኑሮ ዋስትና መታጣትና የከፋ ድህነት፣ በሃያ አመት ውስጥ የተዘራው የዘር ፖለቲካና በአዲሱ ትውልድ አእምሮ ውስጥ ፍሬውን አፍርቶ በሥርዓቱ ላይ ጭምር የዘር ጥላቸቻን ማሳየቱ እና ሌሎችም ውጫዊ ምክንያቶች ተደማምረው ገዢውን ኃይል እንዲፈራና የፈሪ ዱላውንም እንዲያነሳ አስገድደውታል። ዛሬ የወያኔ አመራሮች ሕዝብን ብቻ ሳይሆን የሚፈሩት እራሳቸውንም ጭምር ነው። ድርጅቱ አባላቱን ይፈራል፣ በአወራውና አጃቢ ድርጅቶች መካከል መፈራራት አለ፣ አባላቱ እርስ በርስ ይፈራራሉ፣ አባላቱ መሪዎቻቸውን ይፈራሉ፣ መሪዎች ተከታዮቻቸውን (ተራ ካድሬውን) ይፈራሉ፣ በአመራር ላይ ያሉት ሰዎችም እርስ በርስ ይፈራራሉ። የአንድ ላምስት የስለላ መዋቅር ምንጩም ይህ ነው። አንድ ሥርዓት ጭልጥ ወዳለ አንባገነናዊነት (totalitarianism) ሲገባ ሕዝብን ብቻ ሳይሆን እራሱንም ይፈራል:: በደርግ ዘመንም የሆነው የሄው ነበር:: ለዚህም ነው በእንዲህ ያሉ ሥርዓቶች ውስጥ አባላቱና ደጋፊዎች ከሚሰሩበት ይልቅ እርስ በርስ የሚገማገሙበት ጊዜ ሳይበልጥ አይቀርም የሚባለው።  ሕዝብን እና ራስን መፍራት የሽብር መንፈስ ውስጥ ይከታል።

የፖለቲካ ተቀናቃኞችንና የሰላ ትችት የሚሰነዝሩበትን ሁሉ አሸባሪ እያሉ የጥቃት ዒላማ ማድረጉም ዋነኛ አላማው አነሱን ከትግሉ ሜዳ ለማሸሽ ብቻ ሳይሆን የቀረውንም ሕዝብ ለማሸማቀቅና በፍርሃተ ውስጥ ሆኖ ጸጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛም ለማድረግ ነው::  ሥርዓቱ የሕዝብ ስላልሆነ ሕዝብን ይፈራል። ለነገሩ ሕዝብን ብቻ ሳይሆን ለጥቅም ሲሉ በዙሪያው የተኮለኮሉትን ሹማምንት፣ አባላቱን እና ‘የአባቴ ቤት ሲዘረፍ አብሬ ልዝረፍ’ በሚል ሕሊና ማጣት ወይም አይን ያወጣ ሌብነት የከበቡትን ‘መሁራን’ና ባለሃበቶች ጭምር ይፈራል:: በመሆኑም የሥርዓቱ ደጋፊዎችና አባላቱ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል በከፋ ሁኔታ የአፈና መዋቀሩ ዋነኛ ሰለቦች ናቸው:: አንድ የወያኔ-ኢህአዴግ አባል የሆነ ሰው በአባልነቱ የተለያዩ ቁሳዊ ጥቅሞችን በብቸኝነት ወይም በቅድሚያ ከሌላው ሰው ተለይቶ የማግኘት እድል ይኖረዋል:: ይሁን እንጂ ይህ እድል በነጻነት ማሰብን፣ ሃሳቡን በነጻነት መግለጽን፣ ያመነበትን የፖለቲካም ሆነ ሌሎች አስተሳሰቦቹን ባደባባይ ማንጸባረቅን ወይም ባመነበት ጉዳይ አቋም የመያዝን፣ በመንግሥት ፖሊሲዎችና አፈጻጸሞች ላይ የሰሉ ትችቶችን የመሰንዘር ባጠቃላይ የፖለቲካና የሲቪል መብቶቹንና ነጻነቶቹን አያጎናጽፈውም:: በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ ሰዎች የነጻነትን ጣእም አያቁትም።

ጥልቅ በሆነ ፍርሃት ወስጥ ሆኖና ውሉ በማይታወቅ የሸብር ስጋት ተሸብሮ ሕዝብን ማሸበር፣ በጎሣ ፖለቲካ የሰበጣጠሩትን ሕዝብ የቡና ማህበር ድረስ ሥር የሰደደ የአፈና መዋቅር ዘርግቶ በመጠርነፍ የልቡን እንኳን ቡና እየጠጣ እንዳይተነፍስና በሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቹም እንዳይተዛዘንና እንዳይረዳዳ ማድረግ ሥርዓቱ አገሪቱን እና ሕዝቡን ይዞ ሊገባ እየተንደረደረ ያለበትን ጥልቅ ገደል ያመላከታል:: በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ያነሱዋቸው ጥያቄዎች ባህሪያት እና የሥርዓቱ ምላሽ የዚህን አደጋ ቅርበት ጥሩ አድርጎ ያሳያል:: እንግዲህ የሁሉም ሰው ጥያቄ እንዲህ ፈርቶ እያስፈራራ፣ ተሸብሮ እያሸበረ፣ ሕዝብንም አገልጋዮቹንም አፍኖ አገሬውን ሁሉ የቁም እስረኛ፤ ቀሪውንም በየማጎሪያው ካምፑ ከርችሞ እያሰቃየ ያለውን ክፉና በአጉል ቀን የተጣባንን ሥርዓት በምን መላና ዘዴ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከትከሻችን ላይ አውርደን እንገላገለው የሚል ይመስለኛል:: ለዚህ ጥያቄ መልስ ማግኘት እንዲህ ቀላል ባይሆንም ወደ መልሱ የሚያመሩ መንገዶችን ግን መጠቆም ይቻል ይሆናል::

 

እኛስ?

ሥርዓቱ ዕለት ተዕለት በአገርና በሕዝብ ላይ የሚፈጽማቸውን ወንጀሎችና ደባዎች፤ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እየተከታተሉ በማጋለጥና ሕዝብ እንዲያውቀው በማደረግ ረገድ የግል ሚዲያውና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ትልቁን ሚና ተጫውተዋል:: ይሁንና ጥረታቸውን የሚያግዝና ሥርዓቱን ሊያርቅ የሚችል ሌላ የተጠናከራና አገራዊ ዕራይ ያነገበ ኃይል ሊፈጠር ወይም ከተፈጠረም በዘላቂነት ሊቆይ ባለመቻሉ የተቆለሉት ወንጀሎችና ጥፋቶች የወያኔን ገጽታ ወደ አስፈሪ ጭራቅነት አግዝፈውታል:: በተቃዋሚ ጎራ ውስጥ ያሉ ቡዙዎቹ የውይይት መድረኮችና ሚዲያዎች ወያኔን ለማዋረድ በማሰብ ብቻ በየቀኑ የሚያዥጎደጉዱት ፕሮፓጋንዳ ብዙዎች ወያኔን የማይደፈር ኃይል አድርገው እንዲያስቡት እስተዋጾ አድርጓል:: ከዚያም በላይ ከጥላቻ ያልዘለለው የአንዳንድ ሚዲያዎች ያላቋረጠ የጸረ-ወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተደማምሮ ደርግ አላሸቆት የሄደውን የሕዝብ ወኔና የመንፈስ ጥንካሬ እንዳያገግምና የፖለቲካ ምህዳሩን እንደ ፈንጂ ቀጠና እንዲያየው አድርጎታል:: ወያኔ ባያወቀው ነው እንጂ እነዚህን ሚዲያዎች ለማፈንና ከሕዝብ ዘንድ እንዳይደርሱ ለማድረግ የሚጥረው እነዚህ ሚዲያዎች ባለውለተኞቹ ናቸው:: በግምት 95% በሚሆነው ዘገባቸው የወያኔን ወንጀል የመፈጸም ችሎታ፣ አቅምና የአፈጻጸም ሥልቱን፣ ስለ ተደራጀው የአፈና መዋቀሩ፣ ወደር ስለሌለው ጭካኔው፣ ከሕግ በላይ ሰለመሆኑ እና ያሻውን ቢያደርግ የሚመልሰው አንዳችም ኃይል አለመኖሩን ነው ነጋ ጠባ የሚዘከዝኩት:: ወያኔ እነኚህን መድረኮች ከሚያፍናቸው ይልቅ ሕዝብን የማስፈራራቱን ሥራ እየሰሩለት ስለሆነ በእጅ አዙርም ቢሆን ገንዘብ እየደጎመ ቢያጠናክራቸው አድሜውን ለማራዘም ይረዱታል::

በእነዚህ መድረኮች እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ስላለው እምቅ ኃይል፣ በሰውነቱ ሰለተጎናጸፋቸው መበቶችና ነጻነቶች፣ ከሌሎች ጋር በጋራ አብሮ ሲቆም ሊፈጥር ስለሚችለው ኃያል ጉልበትና ተአምር፣ ሕዝብ እንዴት የሥልጣን ባለቤትነቱን ማረጋገጥ እንደሚችል፣ የሰላማዊ እመቢተኝነት ኃያልነትን ማወራትና ማሰተማር የተለመደ አይደለም:: ወያኔን ለመታገል በተቃራኒው ተደራጅቶ ሰለቆመውም የፖለቲካ ኃይል ከሚናገሩት ውስጥ አመዛኙ መርዶ ነው:: አንጃ ተፈጠረ፣ ኅብረት ፈረሰ፣ ውህደቱ መከነ፣ እገሌ ከዳ፣ እገሌ የተባለው ፓርቲ ‘እገሌ-ዲ’ የተባላ ደባል አፈራ የሚሉና አዳዲስ ግንባሮችና ውጥኖች መጠንሰሳቸውን ሰምቶ የሚቦርቀው ሰው ላቡን ሳያደርቅ ደም እንባ የሚያስለቅሱ የክሸፈት መርዶዎችን ያበስሩናል:: እንደ እኔ እምነት እነዚህ ሚዲያዎችም ሆኑ የሚዲያዎቹ ተሳታፊዎች የሳቱት ትልቁ ነገር የኢትዮጵያ ሕዝብ ዝምታ የወያኔን ደባና ወንጀል በደንብ ካለማወቅ ነው ከሚል መነሻ ላይ ሆነው ሥራቸውን መጀመራቸው ይመስለኛል:: ተደበደብክ፣ ታሰርክ፣ ታፈንክ፣ በላይህ ላይ ሞሰኑብህ እያሉ ለተደበዳቢው፣ ለታፋኙ፣ ለታሳሪው፣ ሌት ከቀን የግፍ እንቆቆውን ለሚጋተው ሰው ለራሱ ‘ሰበር’ ዜና እያሉ ማደንቆር ተበዳዩን አያጀግነውም፣ ለትግልም አያነሳሳውም፣ ብርታትም ሊሆነው አይችልም:: የማይካደው ቁምነገር ግን ቢያንስ በደሌን ሕዝብ አውቆልኛል ብሎ አንዲጽናና እና አሱም የሌሎችን በደል እያደመጠ በደልን እንዲላመድ ይረዳው ይሆናል::  ለዛም የምስለኛል ይህ ሁሉ መከራ ቢሚወርድበት አገር ከ90 ሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ብቻ ለራሳቸውና ለሕዝብ ነጻነትና ከብር ባደባባይ ወጥተው የሚታገሉት:: ለዚህም ይመስለኛል ሃዲዱን የሳተውን የአገሪቱን የፖለቲካ አቅጣጫ ለማስተካከልና መረን የለቀቀውን የወያኔን ባህሪ ለማረቅ ዕዳው በጣት በሚቆጠሩ ግለሰቦችና ደርጅቶች ላይ የተጫነው:: እዚህ ላይ ለማሳሰብ የምወደው ሥርዓቱ የሚፈጽማቸው ወንጀሎችና ጠፋቶች አይነገሩ፣ ሕዝብ እንዳይሸበር ተሸፋፍነው ይቅሩ እያልኩ አይደለም::

ሕዝቡ የሚደርስበትን በደል ጠንቅቆ ሰለሚያወቅ እሱኑ ነጋ ጠባ አያወጡና እያወረዱ ማብጠልጠል መፍትሄ አይሆንም:: ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ጋዜጠኞችም ሆኑ ሌሎች የለውጥ ኃይሎች በሕዝቡ ውስጥ የሰረጸውን ጨለምተኝነት ለመግፈፍና ሕዝቡም የትግሉ አካል እንዲሆን፤ እንዲሁም የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል፣ ባለድርሻም ነኝ፣ ኃላፊነትም አለብኝ፣ ለውጥ ለማምጣትም የሚያስችል አቅም አለኝ በሎ ማሰብ እንዲጀምር ሊያስተምሩትና አቅሙን አጉልተው ሊያሳዩት ይገባል:: መልካም ዜጋን የመገንባት ሥራ ላይ ልናተኩር ይገባል:: የአገዛዝ ሥርዓቱን አያገዘፉ ሕዝብን ማኮሰስና ማስፈራራት ወያኔ እንደተፈራ ሌሎች አስርት ዓመታትን እንዲቆይ ይረዳዋል:: ሸነጥ ሲያደርገን በቻ እየተነሳን ሥርዓቱን የገለባ ክምር አድርጎ በማቅለል በስድስት ወር እንንደዋለን፣ የመሪዎቹን ጉሮሮ አንቀን ከምድረ ገጽ እናጠፋለን አያሉ መፎከርና ለአመታት ይህንኑ እየደጋገሙ መማልና መገዘት በጭንቅ ውስጥ ያለውን ሕዝብ በቀቢጸ ተሰፋ እንዲቆይና በአገር ላይ የተጋረጠውንም አደጋ በቅጡ እንዳያይ በማድረግ መዘናጋትን ይፈጥራል እንጂ ግዴታውን እንዲወጣ አያነሳሳውም:: ፉከራና ቀረርቶውም እየተስተዋለ ይሁን::

በቸር እንሰንብት!

ከያሬድ ኃይለማርያም

የቪኦኤ አማርኛ ሪፖርተር የሆነውና አወዛጋቢና የተዛባ መረጃ በማቅረብ በስፋት የሚታወቀው ሄኖክ ሰማእግዜር

$
0
0

በአበበ ገላው

የዛሬ ወር ገደማ የቪኦኤ አማርኛ ሪፖርተር የሆነውና አወዛጋቢና የተዛባ መረጃ በማቅረብ በስፋት የሚታወቀው ሄኖክ ሰማእግዜር ሙሉ በሙሉ ሃሰት የሆነ ዘገባ በአሜሪካን ሬድዎ አማካኝነት አሰራጨ። የዘገባው አላማ በካሊፎርኒያ የሚገኘው አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰጥቶ የነበረውን የክብር ሽልማት መልሶ መንጠቁንና ዝግጅቱ መሰረዙን በማስመልከት የቀረበው ዘገባ ሃሰት ነው ብሎ ለማስተባበል እና እኔን፣ አለማቀፉን የኢትዮጵያዊያን መብት የጋራ ህብረት እንዲሁም ኢሳትን በሃሰተኝነት ለመወንጀል የታለመ ነበር።Peter-Heinlein-Henok-Semaezer-Fente

ይሁንና ለእርምጃው ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዩኒቨርሲቲው እንዲመረምርና ሽልማቱን መልሶ እንዲያጤን ስለተደረገ መሆኑ በግልጽ የተነገረ እውነታ ነበር። ዩኒቨርሲቲውም ለክብሩ ስነ ስርአት መሰረዝ የሰጠው ዋነኛ ምክንያት ይሄው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጉዳይ መሆኑን በይፋ ደጋግሞ ገልጿል።

አልተሳካም እንጂ ሄኖክ በተለይ በእኔ ላይ ያነጣጠረ በተንኮል የተሞላ ጎጂና የተዛባ ዘገባ ሲያቀርብ ይሄኛው ሶስተኛው ነው። በግንቦት 10, 2004 (May 18, 2012) በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ የተቃውሞ ድሞጽ ሳሰማ ሄኖክ በአይኑ ያየው በጆሮው የሰማው ሃቅ ቢሆንም ድምጼን ሳንሱር አርጎ ዘገባውን አዛብቶ ለስርጭት አበቃው። በዚህም ምክንያት ቪኦኤ ከአድማጮቹ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለቀረበበት በሳምንቱ ዘጋባውን እንደገና በሌላ ሰው አስተካክሎ ተቆርጦ የቀረውን ድምጼን አስገብቶ ሌላ ዘገባ ለማስተላለፍ ሞከረ። ይሄን በጋዜጠኝነት ስም የተሰራ እርካሽ የፖለቲካ ቁማር ታዝበን አለፍነው።

ከዛም ግኡሽ አበራ የሚባል አንድ የቦስተን ነዋሪ በእኔ ላይ የግድያ ወንጀል ለመፈጸም ሲዶልት ገና ከጥንስሱ በFBI ተደርሶበት ምርመራ እንደተደረገበት ተዘገበ። በዚህ ላይ ወያኔ የተቀናጀ ስራ በመስራት፣ አንዳንድ ድህረ ገጾችን፣ ፓልቶኮችን እና ቪኦኤን በመጠቀም እኔ ግኡሽ አበራን ልክ በሃሰት የወነጀልኩት ለማስመሰል ሌላ ያልተሳካ ጥረት ተደረገ። እንደተለመደው ሄኖክ አሳፋሪ የካድሬ ስራውን በመቀጠል ከፍተኛ መዛባት ለመፍጠር ሞከረ። ትንሽ ብዥታ ቢፈጥሩም ያሰቡትን ያህል ግን አልተሳካም። ፈጽሞ ያላናገረውን የFBI ቃል አቀባይ ጠቅሶ እንደለመደው ድምጽ ሳያስገባ “የጥቅሱ መጀመሪያ፣ የጥቅሱ መጨረሻ” በማለት አድማጭን ግራ የሚያጋባ ዘገባ ለቀቀ። እኔ እንደ ጋዜጠኛ ባይሆንም እንደ ጉዳዩ ባለቤት ከቦስተን FBI ቃል አቀባይ ግሬግ ኮምኮዊች ጋር ያደረኩት ንግግር የድምጽ መረጃ እስካሁን በእጄ ላይ አለ። በተጨማሪም እንደነ ግኡሽ ስራ ቦታው ድረስ ሄደው የFBI መርማሪዎች ካፋጠጡት ግን በሴራው አለመሳተፉ ከተረጋገጠው ቤዛ ጥላሁን ያገኘሁት ዝርዝር መረጃ ጭምር በእጄ ይገኛል።

 http://youtu.be/Zv1LtuLEFIU

ዘፋኝና የግኡሽ ደባል የነበረችው አበራሽ የማነ በግዜው የቤዛ ወዳጅ የነበረች ሲሆን አሁን ትዳር መስርተዋል። በወቅቱ ለአበራሽ የማነ መርማሪዎቹ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምንም አይነት ውንጀላ ማንም ባያቀርብባትም ፓልቶክ ላይ ብቅ ብላ በሃሰት አበበ ገላው ወነጀለኝ እንድትል ተደረገ። እነ አውራምባ ታምስም ወገንተኛ የሆነና የሚያስተዛዝብ ስራ ሰሩ። ይህንንም በወቅቱ ታዝበን አለፍነው።

FBI በዋነኛነት ትኩረት ያደረገው ግኡሽ ላይ ነበር። ለዚህም ምክንያት ደግሞ እንዳወሩት በፌስቡክ ስለተሳደበ ወይንም ስለዛተ ሳይሆን በግድያ ወንጀል ዱለታ ሊያስጠይቅ የሚችል መረጃ መርማሪዎች እጅ በመግባቱ ነበር። በቀጣይነት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ እርምጃ የመውሰድና ያለመውሰድ መብት የመርማሪዎቹ ሲሆን የዘገባው እውነታ ግን ከላይ የተጠቀሰው ነው።

በግልጽ አፍቃሪ ወያኔ የሆነው ሄኖክ ሰማእግዜር ግን ጥቅስ ብሎ ያነበበውን ብዥታ የሚፈጥርና ከዋናው ጭብጥ ውጭ የሆነና አዛብቶ ያቀረበውን ሃተታ በተውሶ የወሰደው ከሶስተኛ ወገን፣ እንደውም እንደሰማሁት ከሆነ፣ ከትግሪኛ ዝግጅት ክፍል ነበር። ይሁንና ጥረቱ እውነቱን አልቀየረውም። ግኡሽ አበራ እኔን በስም ማጥፋት በፍርድ ቤት እንደሚከስ ወያኔዎች ደጋግመው ከመናገር አልፈው ከፍትኛ ገንዘብ ቢያዋጡም እስካሁን የተሰማ ክስ የለም።

እኔ በወቅቱ ወንጀል ሲዶልት የተደረሰበት ሰው ማንንም በስም ማጥፋት መክሰስ አይቻለውም ያልኩት እውነትን በመተማመን ነበር። አሁንም ፍርድ ቤቶች ክፍት ስለሆኑ ግኡሽ ብቻ ሳይሆን የውሸት ዘገባ በማሰራጨት እጅ ከፍንጅ በመያዝ አደባባይ ያወጣሁት ሄኖክ ሰማእግዜር (እስከ እረዳቶቹ) ዶሴውን ጠርዞ ፍርድ ቤት መሄድ ይችላል። ይሁንና ውሸት ታጥቆ አየር ላይ መውጣትም ይሁን የውሸት ዶሴ ጠርዞ ፍርድ ቤት መሮጥ ፈጽሞ እንደማያዋጣ ከወዲሁ መጠቆም እወዳለሁ።

የአሁኑ ይባስ እንዲሉ ሄኖክ አቶ ሃይለማሪያም አሜሪካ ሳይደርሱ ላስቸኳይ ስራ ተመለሱ፣ ያልደወሉትን ስልክ ደውለው ክብሩ ይቅርብኝ አሉ፣ እኔ ያልጻፍኩትን ደብዳቤ እያነበበና እያጠቀሰ፣ ያልተናገርኩትን ተናገረ፣ ያልዘገብኩትን ዘገበ እያለ ፈጽሞ ያላናገራቸውን ቃል አቀባይ ያላሉትን አሉ እያለ፣ አደባባይ ወጣ። በሁዋላ ስናጠያይቅ እንደውም የተረዳነው አሳፋሪው የቪኦኤ የሃሰት ዘገባ የተሰራው በቡድን ለሶስት መሆኑን ነው።

ታዲያ ምነው ይሄ ሁሉ የቪኦኤ ሰራዊት አንዲት ቅንጣቢ መረጃ ማውጣት ተሰናው? ከሁሉ የሚገርመው ደግሙ ውሸታችን “ቢቢጂ” የተባለ ቦርድ አጸደቀልን ብለው አይናቸውን በጨው አጥበው አደባባይ መውጣታቸው ነው። በእውነቱ በጣም ያሳዝናል። ቢቢጂም ቢሆን በመረጃ የተደገፈ ማስተባበያ ይዞ እስካልመጣ ድረስ አድማጭም አክባሪም በቀላሉ ማግኘት ይችላል ብዬ አላምንም። የተራዳሁት አንድ ጉዳይ ቪኦኤ ውስጡን ለቄስ ነው። ማንንም የመውደድም ይሁን የመጥላት ግላዊ መብታቸውን ብናከብርም ውሸት ታጥቀው አየር ላይ ከወጡ ግን ችላ ሳንል ደግመን በእውነት ሚሳኤል አናወርዳቸዋለን።

እኛ ለህዝባችን ነጻነትና መብት ከመከራከርና ከመታገል አንቆጠብም። ለዚህም ደግሞ ከማንም ፍቃድ አንጠይቅም። አንዳንድ የቪኦኤ አማርኛ ክፍል ባልደረቦች የእነ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ክብር ተነካ ብለው እኛን ለማጥቃት መነሳታቸው ባያስገርምም ያሳዝናል። በከንቱ ይደክማሉ እንጂ አቶ ሃይለማርያምም ሆኑ አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ በዙ ተቀጣሪዎች አሏቸው። ሁለቱም ወገኖች ቪኦኤን በቃል አቀባይነትይሁን በጥብቅና አለመቅጠራቸውን በርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

እንኳን በሜድያ ስራ የተሰማራ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ይቅርና ማንም እንደሚያውቀው አንድ ሚድያ ስተት ሲሰራ ባግባቡ እርማት እንዲያደርግ ይጠየቃል። ስህትት ተሰርቶ ከተገኝም አግባብ ባለው መንገድ እርምት አድርጎ ይቅርታ ይጠይቃል።። ቪኦኤን የሚያህል ግዙፍ ተቋም የሌሎችን ስራ ከማኮሰስ አልፎ በውሸት ጭብጦ የእውነትን ተራራ ለመናድ ጥረት ማድረጉ በጣም ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ከመሆን አልፎ የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ የሚለውን አባባል ያስታውሰናል።

ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ በዚህ የሀሰት ዘገባ ቁልፍ ሚና የተጫወተው ፒተር ሃይንላይን በአጠያያቂ መስፈርት ባለፈው ሳምንት ለሄኖክ ሰማ እግዜር “ሽልማት” ማቀበሉ ነው። ሄኖክም ይህንኑ ሽልማት ከአፍሪካ ክፍል ሃላፊው ከአቶ ንጉሴ መንገሻ እጅ ተቀብሏል። በርግጥ ሄኖክ ለማዛባትና ሃሰትን በይፋ በማሰራጨት ተወዳዳሪ ስላልተገኘለት ታላቅ ሽልማት ይገባው ይሆናል። ለጋዜጠኛነቱ ሽልማት መስጠት ግን ጋዜጠኝነትን መስደብ ነው።

በዚህ አይን ከፋች በሆነ አጋጣሚ ከእነ ሄኖክና ፒተር ሃይህላይን ይልቅ የአማርኛው እና የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ የሆኑ ሁለት አንጋፋ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችን በጣም ታዘብኩ።። ክብር ወደ ትዝብት ያለ ምክንያት እንደማይቀየር ለማንም ግልጽ ነው። ለምን ታዘብከን ብለው ከጠየቁኝ ምላሹን በዝርዝር በአደባባይ ላስረዳቸው ዝግጁ ነኝ። እስከዛው ሆድ ይፍጀው በማለት ለዛሬው የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የቪኦኤን ከድጡ ወደ ማጡ የሆነውን የሰሞኑን ጉዞ አስመልክቶ ያዘጋጀውን ምርጥ ዝግጅት ካልሰሙት አያምልጥዎ።

መልካም አዲስ አመት ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!

የቀጣዩ መንግሥታችን ሸክም (ይሄይስ አእምሮ)

$
0
0

ይሄይስ አእምሮ

 

(ይህ ጽሑፍ የተጻፈው ግንቦት ውስጥ 2006 ዓ.ም ነው፤ ትቼው ከርሜ ሳበቃ አሁን ምን በል እንዳለኝ አላውቅም ደግሜ ቃኘሁትና ላክሁት፡፡)

 

“እሳቸው በመጡና ድንጋይ በበሉ” አለች አሉ አንዷ የዳግም ዘማች ባለቤትና የቤት ሙሉ ልጆች እናት፡፡ በደርግ ጊዜ ነው፤ ወጣት-ሽማግሌ ባሏ ለዳግመኛ ሀገራዊ ወታደራዊ ግዳጅ ተጠርተው ሄደዋል፡፡ “አባታችን ናፈቀን” የሚሉ ብዙ ልጆች አሏት፡፡ ከልጆቿ ጋር የሚኖሩት በድህነትና በጠባብ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ሰው ሊጠይቃት በመጣ ቁጥር የባለቤቷን ከዘመቻ መመለስ አጥብቃ እንደምትሻ ትናገራለች፡፡ አንዱ ጠያቂ ታዲያ “ይምጡ፣ ይምጡ፣ የምትይው ቢመጡ ምን ልታበያቸው ነው?” ሲል ይጠይቃታል፡፡ እሷም በወቅቱ ያጣቻቸው ባለቤቷ መመለስ እንጂ ቀጣዩ ነገር የሚያሳስባት እንዳልሆነ ለመግለጽ “በመጡና ድንጋይ በበሉ!” የሚል መልስ ሰጠች ይባላል፡፡

አዎ፣ የኛ የምንለው መንግሥት ይምጣ እንጂ የሸክሙ ነገር ሊያሳስበን አይገባም እያልኩ መሆኔን መጠርጠር ከነገር ዐዋቂ አንባቢ ይጠበቃል፡፡ ግን ግን እውነት ለመናገር በእጅጉ ፈራሁ! የፍርሀቴ መሠረትም የቀጣዩ መንግሥታችን ታሪካዊ ኃላፊነት መክበድ ነው፡፡ ወያኔ ሀገራችንን በቁሟ እንጦርጦስ ያወረዳት በመሆኑ መልሶ የመገንባቱ ነገር ሲታሰብ ከምንም ነገር በላይ ያስጨንቃል፡፡ እንዲያውም አለማሰቡም ሳይሻል አይቀርም፤ ቢሆንም ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም – እንዲሁም እስላም – ይባላልና ሁሉን ነገር ማድረግ የማይሳነው ታላቁ የሰማይና የምድር ፈጣሪ በቅርቡ መልካም ነገርን እንደሚያደርግልን፣ እነዚህን መዥገሮችም በኪነ ጥበቡ እንደሚነቅልልን መጠበቁ በተለይ የትንቢቱን ፍጻሜ ከሥር መሠረቱ ስንከታተል ለነበርንና በዳግም ትንሣኤያችን የብሥራት ጫፍ ላይ እንደምንገኝ ለምናምን ጥቂት ወገኖች አግባብነት አለው፤ ይገባናልናም ያደርግልናል፡፡ እንግሊዝኛ አማረኝ – So I shall sincerely suggest that we deserve both independence and freedom; as a nation, we are not independent and as people we are not free. Understandably, Ethiopia is under colonial apartheid system, a system led by few Tigrian mercenaries who are clandestinely supervised by anti-Ethiopian foreign forces who crave to see the over-all downfall of Ethiopia and her historic people. In light of this, it is quite right to say that the country is neither independent nor the people are free from oppression and ethnic segregation run and sponsored by TPLF and its international. For instance, the Amharas have been exposed to genocide and ethnic cleansing since the time TPLF came to existence some 40 years back, first in Tigray and later in all parts of the country, while other ethnics are stifled or even victimizedif they don’t obey this crooked ruling junta.

ከአእምሮየ ሰሌዳ ሳትሰወርብኝ አሁን ትዝ ያለችኝን አንዲት በጣም የምታውቋትን ነገር ላስታውሳችሁ፡፡ በአፄው ዘመን አንዷ ትንሽዬ የቤተ መንግሥት ልዕልት ፣ የአሁኑን አያድርገውና “የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እኮ በአስደንጋጭ ሁኔታ 20 ሚሊዮን ደረሰ፡፡” እያሉ መኳንንት መሣፍንቱ ሲያወሩ ብትሰማ ጊዜ “ለመሆኑ 500 እንሆናለን እንዴ?” ብላ በአግራሞት ጠየቀች አሉ፡፡ እኔም አሁን ማንም ሊመልስልኝ የማይችል ከባድ ጥያቄ – እንዲያው ለላንቲካው ያህል – ልጠይቅ “በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ስንት ይሆን?” 90 ሚሊዮን? 70 ሚሊዮን? 50 ሚሊዮን? 30 ሚሊዮን? አንድ ሚሊዮን? ወደ ዜሮ የሚጠጋ ሚሊዮን? ስንት ነን በውነቱ? አካላዊ ዐይናችሁን ለአፍታ ዝጉና በኅሊናዊ ዐይናችሁ ራሳችሁን ጠይቁ፤ መልስ ለማግኘትም ሞክሩ፡፡ አንድ ሕዝብ፣ በሕዝብነት ታውቆ ሊመዘገብ የሚችለውስ ብዛቱ ስንት ሲሆን ነው? አንድ ማኅበረሰብ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በአስተሳሰብ፣ በሃይማኖት፣ በባህል፣ … ምን ዓይነት የልኬት ደረጃ ላይ ሲደርስ ይሆን “ሕዝብ” የሚባለውን ዓለማቀፍ መጠሪያ የሚያገኘው? በእውነቱ አሁን እኛ ‹ሕዝብ› ነን? የአንድ ሀገር ሕዝብ ሲባል ምን ማለት ነው? ቀጣዩ መንግሥት ሕዝብ የመፍጠር ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት አለበት – ሀገርና ሕዝብ የመፍጠር ግዴታና ኃላፊነት ደግሞ እጅግ ፈታኝና እልህ አስጨራሽ ነው፡፡

በመሠረቱ መልካም አስተዳደርና ለሀገርና ለሕዝብ የሚቆረቆር መንግሥት ካለ፣ እንደወያኔ ለጥቂቶች የሚያደገድግና በብዙኃን ሥቃይ የሚደሰት መንግሥት ሣይሆን እውነተኛ የመንግሥት መዋቅር ቢኖር ሕዝብ አንደኛውና ትልቁ የሀገር ሀብት ነው፡፡ የሕዝብ ብዛት እንደችግር የሚቆጠረው ጥቂት አምራችና ብዙ በላተኛ ሲኖር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሁሉንም ዜጋ እንደችሎታውና እንደዬአቅሙ በአግባቡ በማስተማርና በማሰልጠን ለሥራ ካሰማሩት መጽዋችም ተመጽዋችም አይኖሩም፡፡ ልመናና ስርቆት፣ ሙስናና ንቅዘት ይቀንሳሉ ወይም ከነአካቴውም ሊጠፉ ይችላሉ እንጂ መንገዶችና የአምልኮት ሥፍራዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ በለማኞችና ባጡ በነጡ ድሆች አይሞሉም፡፡ የማጭበርበርንና በአቋራጭ የመክበርን ጎጂ ልማድ ሣይሆን በሥራና በመልካም ሥነ ምግባር የታነፀ ትውልድን የመገንባት ባህል የሚያዳብር የሕዝብ ወገን የሆነ አምባገነንም ይሁን በሕዝብ የሚመረጥ መንግሥት በአንድ ሀገር ውስጥ ካለ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ፈጥጦ ያለው ችግር አይኖርም ነበር፡፡(በነገራችን ላይ አምባገነን መንግሥት በህዝብ ምርጫም ሊመጣ እንደሚችል ያሜሪካውን ትንሹን ጆርጅ ቡሽና የግብጹን ሞሀመድ ሙርሲን ማስታወስ በቂ ነው)፡፡  ሕዝብና ሀገር ሲባል ደግሞ ተጨባጩ የሀገር ሁኔታና ተጨባጩ የሕዝብ ኑሮ እንጂ በታሪክ ካባ ተጀቡኖ የአሁን ስቃይንና ኋላቀርነትን ለመርሳት መሞከር አይደለም፡፡ ወንዞችና ተራሮች፣ ሸለቆዎችና ዋሻዎች፣ ባህሮችና ኩሬዎች እንዲሁም በቱሪስት መስህብነት የሚያገለግሉ የታሪክ አሻራዎችም ወቅታዊ የሕዝብ ኑሮ መገለጫዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ “በቅሎ አባትሽ ማን ነው?” ቢሏት “እናቴ ፈረስ ነች” አለች እንደተባለው እንዳይሆን መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ እዚህ ላይ ለኢሳቷ እሳት ለመታሰቢያ ቀፀላ አክብሮቴን መግለጥ እፈልጋለሁ፡፡ በቅርብ በተከታተልኩት አንድ ውይይት እውነቱን አፍረጥርጣ በመናገር ይህን ቆሎ የማያበላንን የቀድሞ ብሔራዊ የኢትዮጵያዊነት ኩራት አላግባብ እንዳንለጥጠውና በከንቱ እንዳንኮፈስ ወይም በከንቱ መኮፈሳችንን እንድንቀንስ በመረጃና በማስረጃ በተደገፈ ገለጻዋ በልጅነት አንደበቷ መክራናለች፡፡ እውነትን ብትመርም ብትጎመዝዝም መቀበል ይኖርብናል፡፡ ዘፈንንና ሽለላን ለተወሰነ ጊዜና ለተወሰነ ዓላማ ይጠቀሟል እንጂ ራስን ለማነሁለልና ምንም ያልተነኩ መስሎ ምናባዊ መቼት ውስጥ በሥነ ልቦናዊ የተደላደለ ጉዝጓዝ ላይ ለመዘርፈጥ ልናቀነቅን አይገባም፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ምን አለ? የአስፋልቱና የመንገዱ ግንባታ፣ የኤልክትሪኩና የስልኩ ዝርጋታ፣ የሕንፃና ኢንዱስትሪው ጋጋታ፣ የትምህርትና ጤና ኬላዎች ‹ተደራሽነት›፣ … በጥቅሉ ይህ የምናየው የዕድገትና ብልጽና ምልክት ሁሉ እሰዬው የሚያስብል ነው፡፡ ግን “ሰው አለ ወይ?” ብለን ከመጠየቅ የሚያግደን ነገር የለም፡፡ ለዚህም ነው ታዋቂው መንግሥቱ ለማ ቀጣዩን ዘመን የማይሽረው ሥነ ግጥም የቋጠረው፤

 

ምን ሕንፃው ቢረዝም ቢንጣለል አስፋልቱ፤

ሰው ሰው ካልሸተተ የታለ ውበቱ፡፡

 

በተለይ ለዚህ ዘመን ተለክቶ የተሰፋ ልጨኛ ሥነ ግጥም ነው፡፡

 

ወጣም ወረደ፣ ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ የኛ የምንለው መንግሥት ሊያውም በቅርቡ ይኖረናል፡፡ ቆሜም ተኝቼም የሚያስጨንቀኝ ግን የመንግሥታችን ሸክም ነው፡፡ እንደኔ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዲት ሽርንቁላ ውስጥ ተወትፎ ኢትዮጵያን ከነአጠፋፏ ጭምር እየታዘበ ለሚገኝ ዜጋ ኢትዮጵያን ከነዚህ መዥገሮች ነፃ ለማውጣት ከሚደረገው ትግል ይልቅ ከሙታን ሀገራት ተርታ ፈልቅቆ ለማውጣትና ትንሣኤዋን ለማብሠር የሚደረገው ግብግብ ይበልጥ ያስጨንቀዋል፡፡ በቁማችን እኮ ሞተናል!

ወጣቱም በለው ጎልማሳው ከየኅሊናው ጋር ተኮራርፎ ለሥጋው ብቻም አድሮ ሌት ከቀን ሲባዝን የምታየው በባሌም ይሁን በ”ቦሌ” እንዴት አድርጎ ገንዘብ እንደሚያጋብስና በአንድ አዳር እንደሚከብር ነው፡፡ “ቦሌ”ን ያላገጥኩባት በአሁኑ ሰዓት በባሌ እንጂ በቦሌ መክበር እንደብርቅና እንዲያውም ከነአካቴው የሌለ መሆኑን ለመጠቆም ፈልጌ ነው፡፡ ባሌን እንደህገ ወጥ፣ ቦሌን እንደህገኛ መንገድ ካሰብነው ዛሬ ዛሬ በህገኛ መንገድ የሚያልፍለት ዜጋ የለም ቢባል ከእውነቱ አልራቅንም፡፡ ሕግ በጉልበተኞች መዳፍ ሥር ወድቃ እያቃሰተችና ለይቶላት እየሞተች ናት፡፡ በህጋዊ መንገድ መነገድ፣ በህጋዊ መንገድ ተሟግቶ ፍትህን ማግኘት፣ በህጋዊ መንገድ ሥራ ማግኘት፣ በህጋዊ መንገድ ተምሮ ሥራ መያዝ፣ በህጋዊ መንገድ ተከራክሮ መርታት፣ በህጋዊ መንገድ ጉዳይህን ማስፈጸም፣ በህጋዊ መንገድ የዜግነትና የሰብኣዊ መብቶችህን ማስከበር፣ በህጋዊ መንገድ የንብረትህ ባለቤት መሆን፣ ወዘተ. ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ፈጽሞ አይታሰብም፡፡ የሁሉም ነገር መሠረት ዘርህና እንዲያም ሲል አድርባይነትህ ወይም ሆዳምነትህና ኅሊናቢስነትህ ነው፡፡ የወደፊቱ መንግሥታችን – የኛ የምንለው መንግሥታችን – ሸክሙ እንደሚበዛ የምንረዳው ይህን የተንሸዋረረ የአሁን አካሄዳችንን ለማስተካከል የሚጠበቅበትን ከፍተኛ ትግል ስናስብ ነው፡፡

አሁንና ዛሬ ወያኔና አጫፋሪዎቹ የሀገሪቱን ቁልፍ ለብቻቸው ይዘውና ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው ሁሉን ነገር ማድረግ ይችላሉ፡፡ ለቃሉ አጠራር ይቅርታ ይደረግልኝና ኮንዶሙ ደሳለኝ ኃ/ማርያም በሰሞኑ የግንቦት 20 (2006ዓ.ም) ንግግሩ – ያን ንግግርም ጌቶቹ አዘጋጅተው የሰጡት መሆኑን ማስታወስ አያስፈልግም ብዬ ነው – አንሻፍፌም ቢሆን እጠቅሳለሁ – “በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ‹ኢትዮጵያውያን› ዜጎች ሚሊዮኔሮችና ቢሊዮኔሮች መሆን የቻሉት በኢሕአዴግ አመራር ነው” ብሎ የተናገረው ማንን እንደሚያካትት ግልጽ ነውና ወደዚያ መግባት አይገባም፡፡ ለነገሩ ቢገባስ ምን ክፋት አለው? የዐዋጁን በጆሮ፡፡

ሀብታሞቹ በኔ ግርድፍ ግምት 95 ከመቶው በላይ ወያኔ ትግሬዎች ናቸው፡፡ የትም ይኑሩ የትም ከነሱ ውጪ ሀብታም ወይም እነሱ ሀብቱን የማይቆጣጠሩትና በፈለጉ ጊዜ ሊያደኸዩት የማይቻላቸው ኢትዮጵያዊ ሀብታም የለም፡፡ በቀላሉ ላስታውስ – የአማልጋሜትዱ ገ/የስ ቤኛ፣ የአያት ቤቶች ኮንስትራክሽን ባለቤት አያሌው (ተሰማ?)፣ ኤርምያስ አመርጋ፣ ብርሃነ መዋ፣ ያለምዘውድ (ጎጃሜው ሀብታም) … ስንቱን ዘርዝሬው … በዚህች ጠባብ ቅንጭላቴስ ስንቱን አስታውሼው … እነዚህ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከሀብትም ከሀገርም ሣይሆኑ የቀሩት ሌላ ወንጀል ፈጽመው ሣይሆን “ኢኮኖሚውን የማይቆጣጠር ዘውግ ፖለቲካውንም ሊቆጣጠር አይችልም፤ ስለሆነም ከኛ ሌላ ሀብታምና ከኛ ሌላ ተፅዕኖ ፈጣሪ ነጋዴ መኖር የለበትም ” በሚል ያረጀና ያፈጀ የአገዛዝ ፈሊጥ እስከዕለተ ሞቱ ድረስ በዕውር ድንብር የሚነዳው ወያኔ ባሳረፈባቸው ዱላ ነው፤ መላው ኢ-ትግራዋይ በወያኔ የቁጥጥር ራዳር ውስጥ ነው የሚገኘው፡፡ ስለዚህ የተጋቦት ወያኔ ሆንክም አልሆንክም ወደሀብትና ሥልጣን ማማዎች ልትወጣ ካሰብክ እንደመናጆ ሊጠቀሙብህ እንጂ የእውነት ከመሰለህ ጊዜህን ጠብቀህ ቁልቁል ስትፈጠፈጥ ያኔ የእንሥራ ጆሮነትህ – ባዳነትህና ለኮንዶምነት አገልግሎት መዋልህ ይታወቅሃል፡፡ ይህን እውነት ለመረዳት የቅርብ ጊዜ መረጃ ልጠቁምህ – ኤርምያስ ለገሠ የተባለ ወጣት የቀድሞ የተጋቦት ወያኔ  በቅርብ ለኢሳት የሰጠውን ቃለ ምልልስ አድምጥና ዕርምህን አውጣ፡፡ ሀገሪቱ አልቆላታል ወደሚል አሳዛኝ ደረጃ ትደርሳለህ – እስካሁን ተስፋ አለኝ የምትል ከሆንክ ነው ሊያውም፡፡ የኤርምያስን ቃለ ምልልስ ያዳመጠ ሰው፣ ወያኔ – ትግሬ ምን ያህል ቅሌታም፣ ምን ያህል ዐይኑን በጨው ያጠበ ዘረኛ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይችላል፡፡ ይህ ለቅጣት የመጣ የአንበጣ መንጋ የሰንበት ጽንስ ጥርቅም ኢትዮጵያን እንዴት እንዳዋረዳትና ዜጎቿን ከመጤፍ ባለመቁጠር እንዴቱን ያህል እላያቸው ላይ እንደሚጸዳዳ ማንም መገንዘብ አይከብደውም፡፡ አሣሪዎቹ እነሱ፣ ገራፊዎቹ እነሱ፣ መርማሪዎቹ እነሱ፣ ደብዳቢዎቹ እነሱ፣… አንድም ቅልቅል ሳይኖርባቸው ኢትዮጵያውያን ላይ የሰለጠኑ አልቃኢዳዎችና የአዲሶቹ የእስላሚክ ስቴት ካሊፌቶች እነሱ ናቸው፡፡ ሙስሊሞቹ ፀረ-ምዕራባውያን አሸባሪዎች በተቆጣጠሩት ነፃ ግዛት በምዕራባውያን ጋዜጠኞችና የረድኤት ሠራተኛ ላይ ሲፈጽሙ በቅርቡ እንደታዘብነው፣ ወያኔዎች አንድን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቢላዎ ጭንቅላቱን ከአንገቱ ቆርጠው ጀርባው ላይ ሲያስቀምጡ በበኩሌ አላየሁም እንጂ የነዚህ ትግሬ ወያኔዎች የጭካኔ ደረጃ ከነዚህ አረመኔ ፍጡራን ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ የሚገርመኝ ይህን ሁሉ አረመኔያዊ ባህርይ ከየት እንዳገኙት ነው፡፡ በውነቱ ሰዎች ናቸው? ማታ ማታ ቤታቸው ሲገቡ ከቤተሰብ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት እንዴት ይሆን? ለመሆኑ እንቅልፍስ ይይዛቸዋል? … ይህንን መሰሉን የተበላሸ ስብዕና መለወጥም የወደፊቱ መንግሥታችን የኃላፊነት ሸክም ነው፡፡

በነገራችን ላይ “ዘባራቂ” አትበሉኝና በብርሃኑ ነጋ ቃለ ምልልስ ላይ ብርሽ ሸፋፍኖ ያለፋትን አንዲት ጥያቄ “እኔ ብሆን” እንዲህ አድርጌ እመልሳት እንደነበር በዚህ አጋጣሚ ልጠቁም፡፡ ጥያቄውን ለማስታወስ ያህል – “ወያኔ ሲወርድ በወያኔያውያን የተዘረፈው የሀገር ሀብትና ሥልጣን እንዴት ወደ ሕዝብ ይመለሳል? በትግሬዎች የተያዘው ቢሮክራሲና ቤትና ቦታ ሁሉ ለሕዝብ የሚሆነው በምን ዓይነት አግባብ ነው? አሁን እንደሚታየው የኢትዮጵያውያን ቤት ስደትና ከርቸሌ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ጊዜ ሲገለበጥ አሁን የሚታየው ሀገርንና ሕዝብን እያስለቀሰ ያለ የዝርፊያና የውንብድና ጎርፍ አመጣሽ ዐይን ያወጣ የዘመን ክስተት እንዴት ይስተካከላል?” (የሲሳይ አጌናን ጨዋነት በኔ ግልጽነት ለማካካስ መሞከሬን ልብ ብትሉልኝ ደስ ይለኛል – ለማለት የፈለገ የመሰለኝን ግን ያላለውን ብያለሁና!) የኔ መልስ ባጭሩ – “ያንተ ያልነበረ ያንተ አይሆንም፤ ከአፈር ነውና የተፈጠርከው ወዳፈር ትመለሳለህ” የሚል ነው፡፡ ቀኑ መምጣቱ አይቀርም፤ ቀኑም ቀርቧል፡፡ ያኔ የተዘረፈው ሁሉ ወደየቦታው ይሄዳል እንጂ አለበለዚያማ ትግል ለምን አስፈለገ? ሰው ሀኪም ቤት የሚሄደው ታክሞ ለመዳን አይደለምን? ነቀርሣ ያለበት ሰው ሀኪም ቤት ሄዶ “ነቀርሣየን በጣም እወደዋለሁ፤ እሱንና ያደረሰብኝን ጉዳት አትንኩብኝ፡፡ ነገር ግን ከአሁን በኋላ እንዳይጎዳኝ ምከሩልኝ፡፡” ሊል ይችላልን? እንዴት ተድርጎ! አዎ፣ ፍትህ ለተጎዱ ይበየናል እንጂ ማለባበስ የሚነግሥበት ነፃነት አይኖርም፡፡ ሁሉም እንደዬሥራው፡፡

ሊሆን የሚችለው – ያድርሰንና በቻልነው ሁሉ የምንጥረውም ፍትህ እንድትገኝ ነው፡፡ የቀማ የቀማውን ነገር ለተቀማው ወገን ይመልሳል – መመለስ ብቻም አይደለም፤ ከነኪሣራውና ከነሞራል ካሣው እንዲከፍል በህግ አግባብ ሊበየንበት ይገባል፡፡ ከየትኛው ጊዜ ጀምሮ ምን በነማን እንደተደረገ ይታወቃል፡፡ ሕዝብ ደግሞ መዝገብ ነው፡፡ ሐጎስ የቀማኝን ንብረት ለማስመለስ የሚያስፈልገኝ ነገር የሕዝብ ውሳኔ የደገፈው የመብት ማስከበሪያ ቀላጤ እንጂ ይሉኝታ አይሆንም፡፡ እንደዚያ ከሆነ ነፃነትም የነፃነት ትግልም አያስፈልግም፡፡ አምባቸው በተላላኪነትና በሙስና ያካበተው መቶ ሚሊዮን ብር የሕዝብ ገንዘብ ወደመጣበት ካዝና የማይመለስ ከሆነ በጥፊ አቀርንቶ ይቅርታ እንደመጠየቅ ነው፡፡ ጥፋትን ማስተካከልና ይቅርታ ለዬቅል ናቸው፡፡ የተዘረፈ ወደተዘረፈበት ቦታ ይመለሳል እንጂ አንዴ ተዘርፏልና በዘረፈው ገንዘብ እየተንፈላሰሰ ይኑር ብሎ በፍርደ ገምድልነት መበየን ዝርፊያን ቅድስና መስጠት ነው፡፡ ይህ ሁሉ ግን የወደፊቱ መንግሥታችን ሸክም ነው፡፡

አሁን ገንዘቡንም በባንክ በፈለጉት ስም ያከማቹ፡፡ ሕንፃውንም የትም ይገንቡት – በማንምም ስም ይገንቡት፡፡ ግን ግን ነገ ይህ ሀብትና ንብረት የሀገርና የቀጣዩ መንግሥት ሀብትና ንብረት ይሆናል፡፡ የህግ ዐዋቂዎች አንድ ጥፋት  በሁለት መንገድ ይታያል ይላሉ – በፍትሐ ብሔርና በወንጀል፡፡ ስለዚህ ወያኔም ይሁን ግብረ በላው ሁላ በሚሠራው የፍትሐ ብሔር ነክም ይሁን የወንጀል ድርጊት ይጠየቅበታል እንጂ ዝም ብሎ የሚታለፍ ሊሆን አይገባም፡፡ ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ከሕዝብ ዐይን የሚሠወር ደግሞ ምንም ነገር የለም፡፡

የቀጣዩ መንግሥት ሸክም ብዙ ነው፡፡ አንደኛው እየመረረውም ቢሆን ከዚህ ከፍ ሲል የጠቀስኩትን የሕዝብ ብሶት በፍትህ አደባባይ ቆሞ በደለኞች ተበዳዮችን እንዲክሱ የማድረጉ ጣጣ ነው፡፡ ጥፋት እንዳይደገም ማድረግ የሚቻለው አጥፊነት የሚያሳድግ ሳይሆን የሚያቀጭጭ፣ የሚያለማ ሳይሆን የሚያኮስስ መሆኑን በገሃድ በማሳየት ነው፡፡ አለበለዚያ “እንዲህ ባደርግም ምንም አልሆንም” የሚል ስሜት በአጥፊዎች ዘንድ እየፈጠረ ጥፋት መሥራት ባህል እንደሆነ ይቀጥላል፡፡

አንድ ችግር ግን አለ፡፡ ፍትህን ለማስፈን ማን ነው የሞራል ብቃት የሚኖረው? የክርስቶስን ቃል እዚህ ላይ ያስታውሷል፡፡ የዚያችን በአመንዝራነት የተከሰሰች ሴት ታሪክ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ኃጢኣት ያልሠራ የመጀመሪያውን ድንጋይ እንዲወረውርባት ክርስቶስ ሲናገር ሁሉም ሹልክ ሹልክ እያሉ ጠፉና ተከሳሹዋ ብቻ ቀረች፡፡ ማን ይድፈር? … ለመሆኑ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ስንት ነን? ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ ማን ነው በማን ላይ መፍረድ የሚችል? ማን ነው ንጹሕ? ማን ነው ዕድፋም? በሰው ዐይን ውስጥ የሚገኝን ስንጥር የሚያህል ጉድፍ ለማውጣት ከመሞከራችን በፊት በራሳችን ዐይን ውስጥ እርፍ እሚያህል ጉድፍ ላለመገኘቱ እርግጠኞች ልንሆን ይጠበቅብናል፡፡ ትግል ከራስ ብላለች ዘፋኟ፡፡

የነገዎቹ መሪዎቻችን አሁን የት ነው ያሉት? ምን እያደረጉ ነው? ከደሙ ንጹሕ ናቸውን? እየተጠላለፉ ነው ወይንስ ምቹ ሁኔታ እስኪፈጠር በአርምሞ እየተጠባበቁ ናቸው? ራሳቸውን ከወንጀልና ከሙስና አጽድተው በጥሩ ድህነት እየኖሩ ነው ወይንስ በ“ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ” ዓይነት እንደአየሩ ጠባይ ድርጊታቸውንም አነጋገራቸውንም እያስተካከሉ በእስስታዊ ባሕርይ ቀን ይጠብቃሉ? አሮጌው ወይን በአዲስ አቅማዳ ይገለበጥና ከአንዱ የመከራና የሥቃይ አዙሪት ወደሌላው እንዛወር ይሆን ወይንስ ፈጣሪ በቃችሁ ይለናል? የአዲሱ መንግሥታችን ሰብኣዊና መዋቅራዊ ቅርጽና ይዘት ከአሁኑ ያስጨንቀኛል፡፡ ለምን ቢሉ እባብን ያዬ በልጥ ይበረያልና፡፡ ስንቱ ቂጣ ይረረብን? ምጣዱስ፣ ማገዶ እንጨቱስ፣ ጊዜውስ፣ ትውልዱስ … አያሳዝኑምን? ኧረ ወደቀልባችን እንመለስ!

ስለሆነም ቀጣዩ መንግሥት ብዙ ዕዳ አለበት ነው ባጭሩ፡፡ ቀዳሚው ዕዳው ራሱን የማወቅና ካለፉት በርካታ እንቶ ፈንቶ ሰይጣናዊ አገዛዞች የተለዬ መሆኑን በተግባር የማሳየት ኃላፊነት ነው፡፡ ጨካኝ መሆን ሩህሩህ ከመሆን ያነሰ ወጪ እንዳለው ግልጽ ነው – የዞረ ድምሩ ግን ብዙ ኮተት አለው፡፡ ከሞላ ጎደል የሁሉም ጨካኝ ገዢዎች የመጨረሻ ዕድል ተመሳሳይ ነው፤ ቢያንስ በታሪክ ስማቸው ሲወቀስ ይኖራል፡፡ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው በሀፍረት እየተሸማቀቁ አንገታቸውን ደፍተው ለመኖር ይገደዳሉ፡፡

በተረፈ የቀጣዩ መንግሥታችንን ሸክም የሚያበዙ ሀገራዊ ጉዶችን ዘርዝረን አንጨርሳቸውም፡፡ በትምህርት ረገድ “ A,B,C,D” ን በቅጡ ያልለዩና ስማቸውን እንኳንስ በእንግሊዝኛ በሀገርኛ ቋንቋም መጻፍ የማይችሉ ወይም የሚከብዳቸው የቢኤና ኤምኤ ዲግሪ ተመራቂዎችን እንደገና ለማስተማር ራሱ ትልቅ ሥራ ይጠብቀዋል፡፡ በዜግነትህና በሰውነትህ ብቻ ተንቀባርረህና “ጎይታይ እምበይተይ” ተብለህ ሊፈጸምልህ ለሚገባ አንድ ጉዳይ እጅ እጅህን  የሚመለከት ሲቪል ሰርቫንት የሚዋኝበትን የመንግሥት ቢሮክራሲ ለማጽዳት የፈጣሪ ተዓምር ካልታከለበት በስተቀር መቶ ዓመትም የሚበቃ አይመስለኝም፡፡ ወደ ሆድ ወርዶ የተሸጎጠውን የሚሊዮኖች ጭንቅላት ከቦርጭ አውጥቶ ወደ ትክክለኛ ሥፍራው ለመመለስና በአንጻራዊ አነጋገር እንደቀድሞው ያለ የመተሳሰብና የመተዛዘን ዘመን ለማምጣት 90 ሚሊዮን ሕዝብን እንደገና የመፍጠር ያህል ከባድ ሥራ ነው፡፡ ግን ግን ኢትዮጵያውያን ስንት እንሆን ይሆን?(እኔ በበኩሌ ከቁጥር የማልገባ ቦቅቧቃ መሆኔን ከአሁኑ እቅጩን መናገር እፈልጋለሁ – ለከንቱ ውዳሤ እንዳይመስላችሁ!! ከእውነት ፈሪና ሀገሬ የኔን አስተዋፅዖ በምትፈልግበት ወቅት ተደብቄ የምኖር ወሬ ጠራቂ ነኝ፡፡)

በአንድ ወይ በሌላ ነገር ያልጠፋን ዜጎችን ለማግኘት አይቻልም፤ እንዲያ ባንሆን ኖሮ ቢያንስ ሀገር በኖረን ነበር፡፡ ትልቁ የመጥፋታችን ምልክት በጥቂት ወንበዴዎች መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ መቅኖ አጥቶ መቅረቱ ነው፡፡ የሎጥን ታሪክ አስታውስ፡፡ “ጌታ ሆይ አምሳ ሰው እንኳን ባገኝ ቁጣህን አትመልስልኝምን?” – ከተሳካልህ እሺ ይሁንልህ፡፡ ፈለገ፡፡ አጣም፡፡ … “ጌታ ሆይ! አምስት ባገኝስ?” – ከተሳካልህ እሺ ይሁንልህ፡፡ አሁንም ፈለገ፤ ግን አጣ፡፡ ታሪኩን ራስህ ጨርሰው፡፡ የሆነውንም አስብ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ደረጃውን የጠበቀ ጥሩ ዜጋ ለማግኘት እግርህ እስኪነቃ ብትሄድ የምታገኝ አይመስለኝም፡፡

ነጋዴው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር እየተመሣጠረ በየቀኑ በሚቆልለው የሸቀጦች ዋጋ ኑሮው የሰማየ ሰማያትን ድምበር ጥሷል፡፡ ለጠቅላላ ዕውቀትህ ያህል የቀዳማዊ ኃ. ሥላሴ ዘመን አንድ ብር በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ ዕቃዎች 30 እና 40 ብር ሲሆን በአንዳንድ ውድ ዕቃዎች ደግሞ ከ500 ብር የሚበልጥባቸው ምንዛሬዎችም አሉ፡፡ ሆድ ተምቦርቅቆ ጤናማ ኅሊና ቁልቁል በመውረድ ቦርጭ ውስጥ ተወሽቆ ሕዝብ ደም እያለቀሰ ነው፡፡ በሕዝቡ መካከልም ፍቅርና መተሳሰብ ጠፍቶ፣ መተዛዘንና መከባበር ተረት ሆነው፣ ሃይማኖት በፍቅረ ንዋይ ተለውጦ፣ ቄሱና ጳጳሱ ሳይቀሩ ከዓለማውያን በበለጠ ሥጋውያን ሆነው የደም ግብር ለለመደውና ካለደም ግብር እስትንፋሱ ለማትቀጥለው የደራጎን መንግሥት አድረው ለዲያብሎስ መንግሥት እየሰገዱ፣ ሞራልና ትውፊት ባህልና ወግ ልማድ አጥራው ተደረማምሶ ዜጎች ወደ አውሬነትና ወደ እንስሳነት እየተለወጡ፣ መስጊድና ቤተ ክርስቲያናት ለግብር ይውጣ ካልሆነ በሃቅ አምልኮት የማይካሄድባቸው የአጋንንት መፈንጪያ ሆነው፣ ከህገ አምላክና ከህገ ተፈጥሮ ባፈነገጠ ሁኔታ ልቅ ወሲባዊነትና አመንዝራነት እንዲሁም አፈንጋጭ የሴሰኝነት ልማዶች ሀገር ምድሩን ሞልተውትና ይህንን ሰይጣናዊ አፈንጋጭነትም በህግ ለማስረገጥ በሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ለማቅረብ የማያፍሩ ዜጎች እየበዙ፣ ቅድስቲቷን ሀገር ለማርከስ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ተከፍቶ ለብልግና ሥራዎች ማስፋፊያ የውጭ የገንዘብ ድጎማና በክፋት ሥራ የሰለጠነ የሰው ኃይል ድጋፍ እየተደረገ፣ ዘረኝነት ሀገሪቱን እንደብል እምሽክ አድርጓት ሁሉም ነገር በወያኔዎች ቁጥጥር ገብቶ… ባለበት ሁኔታ አዲሱ መንግሥታችን ቢመጣ የሚገጥመውን ሁለንተናዊ እንቅፋትና የሥራ ብዛት ከአሁኑ አስቡት፡፡ ጓዶች – የአዲሱ መንግሥታችን ሸክም እጅግ ከባድና ካለፈጣሪ ዕርዳታም የማይሞከር ነው፡፡ በሰው አምሳል የሚንቀሳቀስን አገር ሙሉ አውሬና ነቀዝ ወደሰውነት ለመለወጥ ብዙ ትግስት፣ ብዙ መንፈሣዊና ሥጋዊ መልካም ዕውቀት፣ ብዙ ጥበብ፣ ብዙ ልምድና የአስተዳደር ችሎታ፣ ብዙ ትምህርት፣ ብዙ ተሞክሮ፣ ብዙ መለኮታዊ እገዛና ብዙ የእምነት ጥንካሬ … ያስፈልጋል፡፡ ማይማኑና ደናቁርቱ ወኔያዎች ከ23 ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ያበለሻሹትን የመንግሥት ቅርጽና ይዘት ለማስተካከል ሌት ከቀን የሚሠሩ ሀገር ወዳድና ለሆዳቸው የማያድሩ ቆራጥ ዜጎች ያስፈልጉናል፡፡ እንዲሁ ስለማይገኙ በየምነታችን ወደዬምናመልከው እንጸልይ ምዕመናን፡፡

ግን ግን ካንጀቴ ልጠይቃችሁና በአሁኑ ወቅት እኛ ኢትዮጵያውያን ስንት እንሆን ይሆን? ጥያቄዬ የሚመለከተው በትልቁ እሥር ቤት ማለትም በዞን ዘጠኝ ውስጥ የምንገኘውን እንጂ በጠባቡ የቃሊቲና መሰል ኢትዮጵያውያን የወያኔ ኦሽቲዊዞች ውስጥ እየተሰቃዩ የሚገኙትን እንዲጨምርብኝ አልፈልግም፡፡ በነዚህ እሥር ቤቶች ውስጥ የሚማቅቁ ዜጎች የኔን ፍርሀት በነሱ ወኔና ጀግንነት አሸንፈው የኔንም የነሱንም ስቃይ እየተሰቃዩ የሚገኙ ዳግማዊ ክርስቶሶች ናቸውና በነገይቱ ኢትዮጵያ የድል አክሊል የሚቀዳጁ የነፃነት አርበኞች ናቸው፡፡

(ዲባቶዎች መሣይ ከበደ፣ ብርሃኑ ነጋና ተስፋዬ ደምመላሽ በግዛው ለገሰ የኢሳት ቲቪ ውይይት ላይ ስከታተላቸው ከመሣይ አስተሳሰብ የፈለቀ አንድ አመለካከት ገረመኝ፡፡ ሌላ ቦታ ስለማላገኝ አሁኑኑ ባጭሩ ልተች፡፡ መሣይ የሚለው  “ወያኔዎች ጋር ሰላምና ዕርቅ ለመፍጠር መከላከያውንና ፀጥታውን በነሱው ቁጥጥር ሥር እንደሆኑ ትተን በሌሎች የፖለቲካ መስኮች አብረን መካፈል እንድንችል ለድርድር እንጋብዛቸው” የሚል ነው፡፡ መሣይ ውስጥ በእንግሊዝኛው የቃላት አጠቃቀም naivety ቁልጭ ብሎ ይታየኛል፡፡ ዋናዎቹ የወያኔ መሣሪያዎች ምን ምን ሆኑና ነው? እነዚህን ጡንቻዎች የያዘ አካል ምን ዓይነት መብት ነው ለሕዝብ የሚሰጥ? ዋናው የተቃዋሚም ሆነ የህዝብ ትግልስ እነዚህን የወያኔ እንደልብ መፈንጠዣ ተቋማት ለመቀማትና ለሕዝባዊና ሀገራዊ ዓላማ ለማዋል አይደለምን? ለዚህ ለዚህማ ምን ድርድር ያስፈልጋል? ልክ እንደነልደቱ አያሌውና አሁን አሁን ደግሞ እንደግዛቸው ሽፈራው መሰል የወያኔ አጫፋሪዎች ከወያኔ ጋር አብሮና ተባብሮ የሕዝብን ሰቆቃ ማራዘም ይቻላል፡፡ ብርሃኑ እንዳለው አምባገነኖች በምንም ዓይነት መንገድና ሁኔታ ለድርድር አይቀርቡም፡፡ ሞተውም ሞታቸውን የማያምኑ ገልቱዎች ናቸው፡፡ ጋዳፊ በሰደፍ እየተወገረና ሣንጃ በእንትኑ እየገባበት የሀገሩ መሪ እርሱ እንደሆነና እስከዚያን ቅጽበት እንኳን በሊቢያ እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ አመፅ ለማመን ባለመፈለግ እንዲያውም ምን እንደተፈጠረም ለማወቅ በሚመስል የልብ መደፈን “ጠባቂዎቼ የት አሉ? ምን ሆናችኋል? ግርግሩ ምንድንነው?…” ይል ነበር አሉ፡፡ አምባገነኖች እስከዚህን ድፍን ቅል ናቸው፡፡ እናም የመሣይ የቀቢፀ ተስፋ ንግግር አስገርሞኛል፤ አስቆኛልም፡፡ “ራስዋ ሄዳ ጣፊያ የከለከሏት ‹ምላስ ሰምበር ላኩልኝ› አለች” ይባላል፡፡ ወያኔ እንዴትና መቼ እንደሚወድቅ ለምንገምት ወገኖች የመሣይ ሃሳብ ምን ያህል ሞኝነት እንዳለበት መረዳት አይከብደንም፡፡)

ለማንኛውም እንኳን ለ2007 ዓመተ ፍዳ በሰላም አደረሳችሁ፡፡ እንዳይመስልህ – ይህም ያልፋል ደግሞ፡፡

Comment

 

አረንጓዴ ኢኮኖሚና መለስን ምን አገናኛቸው? (ጌታቸው ሺፈራው)

$
0
0

ጌታቸው ሺፈራው

10የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተጣጣመ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ይህ የኢኮኖሚክስ መርህ በበርካታ ምሁራን የተነሳ ቢሆንም መንግስታት ለጊዜያዊ ጥቅማቸው ሲያምታቱት ይስተዋላል፡፡ በአብዛኛው አረንጓዴ ኢኮኖሚ ሲባል እንደ ጸሃይ ብርሃንና ባዮ ጋዝን እንዲሁም የአየር ንብረትን ለመከላከል የሚያስችሉ (ለምሳሌ በኤሌክትሪክ መኪናዎችን) ቴክኖሎጅ መጠቀም ያካትታል፡፡ የውሃ ንጽህናን መጠናከርና ብከላን ማስወገድ፤ የፍሳሽ አገልግሎትን በማዘመንና ቆሻሻን እንደገና በመጠቀም አካባቢን ከብክለት መከላከል የዢሁ ስልት አንድ አካል ነው፡፡ ደንን ማልማት፣ መሬትን ከመከላት መከላከልና የመሳሰሉትን ከባቢ አየርን ለመከላከል የሚያስችሉ ዘዴዎችን መጠቀም ላይ የሚያተኩር ፖሊሲም ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጋር ሲያያዝ ይታያል፡፡

በእርግጥ ምሁራንም ቢሆን አረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚለውን ትርጉም እንደ የራሳቸው የሚተሩሙት መሆኑን ተከትሎ እስካሁን ግልጽ ትርጉም እንዳልተሰጠው የሚናገሩት በርካቶች ናቸው፡፡ ከዚህም አለፍ ሲል አረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚባል ነገር የለም ከሚሉት ጀምሮ ከአፈጻጸሙ፣ ለመጠቀሚያነት ብቻ የሚውል መሆኑ፣ በትርጉም ልዩነትና በመሳሰሉት ተቃውሞዎች ይገጥሙታል፡፡

አረንጓዴ ኢኮኖሚ እንደ መለስ ራዕይ

ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ኢህአዴግ አዲስ አባዜ የተጠናወተው ይመስላል፡፡ ሁሉም የአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስኬቶች በአቶ መለስ የተወጠኑ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ሲያወራ ይደመጣል፡፡ ተቋማት፣ ምሁራንና ሰራተኞች የሌሉ ያህል አቶ መለስ የሁሉም የአገሪቱ ፖሊሲና ስትራቴጅዎች ቀያሽና የመጽሐፎች ሁሉ ደራሲ ተደርገዋል፡፡ ልማታዊ መንግስትና አብዮታዊ ዴሞክራሲ የተባሉት በውል ያልተተረጎሙ እና በመልካም ተሞክሮነት ከሌሎች የተለበጡ የስልጣን መወጣጫ መርሆች ሳይቀር አቶ መለስ የፈጠሯቸው ተደርገው እየተወሩ ነው፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲም ሆነ ልማታዊ መንግስት አቶ መለስ ስልጣን ከመያዛቸው በፊት ሌሎች ስርዓቶች ተግባራዊ ያደረጓቸው ቢሆንም በኢህአዴግ መንደር ግን የአቶ መለስ ግኝቶች ተደርገው እየቀረቡ ነው፡፡

በቅርቡ ደግሞ ኢህአዴግ አቶ መለስ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን መርህ ለዓለም አማራጭ ማቅረባቸውን እየነገረን ነው፡፡ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ባዮ ጋዝና የጸሀይ ብርሃን መጠቀም፣ ቆሻሻን እንደገና መጠቀም፣ ደን እንክብካቤ፣ የአካባቢ ጥበቃ ጋር ምቹ የሆኑ ምርቶች (አረንጓዴ ምርቶች) ማምረትና የመሳሰሉትን የሚያጠቃልል በመሆኑ ስሙ ተሰጥቶትም ሆነ ሳይሰጠው በርካታ የዓለም አገራት አቶ መለስ ከመወለዳቸው በፊት ጀምሮ ተጠቅመውበታል፡፡ ለአብነት ያህል የጸሃይ ብርሃንን በታዳሽ ምንጭነት ለመጠቀም የሚያስችለው የመጀመሪያው የዘርፉ (የአረንጓዴ) ቴክኖሎጅ የተሰራው እ.ኤአ በ1883 ቻርለስ ፍሪት በተባለ ግለሰብ ነው፡፡ ምንም እንኳ ይህ ቴክኖሎጅ በተለይ ኤሌክትሪክ ማመንጨት የቻለው ዘግይቶ ቢሆንም ይህም ቢሆን አቶ መለስ ስልጣን ከመያዛቸው 6 አመት ቀድሞ እ.ኤ.አ በ1985 ነው፡፡ ምዕራባዊያን አገራት ይህን ታዳሽ ሀይል አቶ መለስ ምኒልክ ቤተ-መንግስት ከመግባታቸው በፊት ወደ ሀይል ቀይረው ተጠቅመውበታል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሀሳቡ ከመነሳቱ በፊት የሰሜን አፍሪካ አገራትና ጎረቤታችን ኬንያን ጨምሮ በርካቶቹ አገራት ተጠቅመውበታል፡፡

ለአረንጓዴ ቴክኖሎጂ እንደ አንድ ግብዓት የሚጠቀሰው ኢታኖል ነው፡፡ የኢታኖል ሳይንሳዊ ቀመር የተገኘው እ.ኤ.አ በ1840 ዎቹ ነው፡፡ አሜሪካውያን ይህ የኢታኖል ሳይንሳዊ ቀመር ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለመብራትነት ሲገለገሉበት ኖረዋል፡፡ እንግዲህ አቶ መለስ ከመወለዳቸው ከሁለት መቶ አመት በፊት መሆኑ ነው፡፡ አረንጓዴ ቴክኖሎጂ የአሁኑ ትርጉም ተሰጥቶት ተግባራዊ መሆን በጀመረበት ወቅትም ቢሆን ለአቶ መለስና ኢህአዴግ ሩቅ ነው፡፡ አረንጓዴ ኢኮኖሚ በተደራጀ መልኩ በተለይም በተቋማት አነሳሽነት የጀመረው እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ለአብነት ያህል እ.ኤ.አ በ1980 ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ህብረት አገራት ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ እንዲችሉ ለማድረግ በሚል ይህን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው በጥናቱ ላይ እስቀምጧል፡፡

ከ12 አመት በኋላ እ.ኤ.አ በ1992 (አቶ መለስ ስልጣን በያዙ ከአንድ አመት በኋላ ሲሆን በስብሰባው አልነበሩም) በብራዚሏ ሪዮ ዲጀኔሮ በተካሄደው ስብሰባ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመሆኑም ኢህአዴግ አቶ መለስ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለዓለም በአማራጭነት ያቀረቡ በሚል የሚያቀርበው ሙገሳ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ አቶ መለስ በቅርብ አመታት አፍሪካን ወክለው በተለያዩ መድረኮች ስለ አየር ንብረት ድርድር አድርገዋል፡፡ ይህም ቢሆን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ያላት መቀመጫና ተደማጭነትንም ጭምር ያገናዘበ ነው፡፡

አቶ መለስ በዓለም አቀፍ መድረክ የማሳመን ብቃት ስላላቸው ነው ቢባል እንኳ በድርድሩ ወቅት የሚያቀርቡት ማሳመኛ የአፍሪካ አገራት ባለሙያዎች፣ መሪዎችና ሌሎች አካላት ተወያይተው የተስማሙበትን ሀሳብ ነው፡፡ በአንድ ወቅት አቶ መለስ በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ መድረክ አፍሪካ ልታገኝ ይገባት የነበረውን 30 ቢሊዮን በላይ ዶላር ጥቅም 10 ቢሊዮን እንዲሆን አድርገዋል በሚል ከሱዳንና ከሌሎች ልዑካን ተቃውሞ እንደደረሰባቸው ስናስታውስ ደግሞ አዲስ ፈጠራ ማበርከት ብቻ ሳይሆን አፍሪካውያን የተስማሙበትንም እንዳላስፈጸሙ እንመለከታለን፡፡ በ2005 ዓ/ም አፍሪካን የወከለችው ኢትዮጵያ ስለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለተባበሩት መንግስታት አቅርባ ተቀባይነት ማግኘቷ ተዘግቧል፡፡ ይህም ቢሆን ጥቃቅን ማሻሻያ ረቂቅ እንጂ የአጠቃላይ አረንጓዴ ኢኮኖሚው ጠንሳሽ ሊያደርጋት አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን በርካታ አገራት አጀንዳና ሃሳብ ያቀርባሉ፡፡ ማሻሻያና የመሳሰሉትን በማቅረባቸው ግን ራሳቸውን የዋናው ሀሳብ አመንጭ አድርገው ሲያቀርቡ አይታዩም፡፡

በነገራችን ላይ ህወሓት በርሃ በወጣባቸው በመጀመሪያ አመታት ደርግ ‹‹አረንጓዴ ልማት›› በሚል ሰፋፊ እርሻዎች ልማት ጀምሮ እንደነበር ይነገራል፡፡ በወቅቱ አሁን ለአቶ መለስ መታሰቢያ የየመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ አትክልት ከሚተክለውም በላይ ኢትዮጵያውያን በግድ ምግባቸው ብቻ እየተቻላቸው ያለሙ ነበር፡፡ ይህ ኢትዮጵያውያን ተገደው ያሉሙት የነበረው ልማት ለደርግ ‹‹አረንጓዴ ኢኮኖሚ›› መሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ ኢህአዴግም ይህን ያህል ተግባር ቢፈጽም ከደርግ ያልተናነሰ ራዕይ ጨምሮበት ለፕሮፖጋንዳ ሊጠቀምበት እንደሚችል የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ይህን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተግባዊ እያደረጉ ከሚገኙ አገራት መካከል በመጨረሻዎቹ ረድፍ የተመደበች አገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ ባለፈው 40ና 50 አመት ከ40 በመቶ በላይ የደን ሽፍን እንደነበራት ይነገራል፡፡ በህዝብ ብዛትም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች ከ20 አመት በፊት ይህ የደን ሽፋን ከ3-4 በመቶ ይሆን እንደነበር በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ አሁን ከዚህም በታች ወርዷል፡፡ ለ99 አመት ለአረብ፣ ህንድና ቻይና ባለሀብቶች እየተሰጠ ያለው በደን የተሸፈነ መሬት ሲመነጠር ድግሞ ይህን የደን ሀብታችን በእጅጉ እንደሚያመናምነው አያጠራጥርም፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመርህ ደረጃ እፈጽማለሁ ቢልም ተግባራዊነቱ ግን ገና በእንጭጭ ላይ ነው፡፡ ከተቋማቱ ጀምሮ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዝግጁ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ አለብነት ያህል፣ አብዛኛዎቹ ክልሎች የደን ልማት በግብርና ሚንስትር ስር የሚገኝ ነው፡፡ በመሆኑም የግብርና ሚንስተር በተቻለ መጠን አገሪቱን መሬት እንዲታረስ ማድረግ ነው፡፡ የደን ጥበቃ ደግሞ ደንን ማሰጠበቅ፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሚጋጩ ለጥዕኮዎች አላቻው ናቸው፡፡ በተለይ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት በሚል ለኢንቨስተሮች ሰፋፊ መሬቶችን የሚሰጡት የክልል ቢሮዎች ለደን ልማትና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ምንም ዝግጅት የላቸውም፡፡ ለምሳሌ ያህል ጋምቤላ ብንወስድ፤ ለውጭ ባለሀብቶች እየተሰጠ ያለው መሬት ታርሶ የማያውቅና በደን የተሸፈነ እንደሆነ ይነገራል፡፡ እስካሁን በጋምቤላ ብቻ ከሲውዘርላንድ የሚበልጥ የቆዳ ስፋት ያለው መሬት ለውጭ ባለሀብቶች ተሰጥቷል፡፡ እነዚህ የውጭ ባለሀብቶች የሚጠቀሙበት ኬሚካል የአካባቢውንና የአገሪቱን የአየር ንብረት ይበክላል፡፡ ይህ ሰፊ ደንን እያስመነጠሩ መሬትን በሲጋራ ዋጋ መሸጥ፣ በኬሚካል ማስበከል አቶ መለስ ጀምረውት ሌሎቹ በ‹‹ራዕይ›› እያስቀጠሉት ነው፡፡ እንዲህ ደን እየወደመ፣ የአየር ንብረት እየተበከለ፣ አፍሪካውያን ለተበከለው ይከፈለን የሚሉትን ሰያስፈጽሙ አቶ መለስና ኢህአዴግ ከአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ጋር ምን እንደሚያገናኛቸው አይገባኝም፡፡

ከጠባቡ እስር ቤት ሰፊውን መርጠናል –ጋዜጠኛ መልካም ሰላም ሞላ

$
0
0

ጋዜጠኛ መልካም ሰላም ሞላ

ጋዜጠኛ መልካም ሰላም ሞላ

ጋዜጠኛ መልካም ሰላም ሞላ

..እነሆ በስደት ስሜት ውስጥ ሆነን፣ ከሃገር መውጣት ከሞት የመረረ ጽዋ እንደሆነ እያወቅነው፤ ህሊናችንን ሽጠን ለሆዳችን ማደር ቢያቅተን ፣ ከህዝብ በተሰበሰበ ብር ተንደላቀን የህዝብን እውነት ቀብረን ህዝብ ለእኛ ባደራ ያስረከበንን እምነት ረግጠን እያጭበረበርን እየዋሸን እየቀጠፍን እንድንኖር የቀረበውን ጥያቄ ንቀን፣ እንደአለቆቻቸው እንደገደል ማሚቶ በሉ የተባሉትን እያስተጋቡ ከህሊናቸው ተጣልተው እንደሚያድሩት “የቁጩ በጎች”፤ በጋዜጠኛ ስም ተሸፍነን በአንድ ወቅት አብረናቸው ከበላን እና ከጠጣን በማህበራዊ ህይወታችን ብዙ መልካም ነገሮችን አብረን ከተቋደስናቸው ሰዎች /ኧረ ባጋጣሚም ቢሆን አንድ ቤት ውስጥ ከ20 በላይ ሰዎች ሆነን ካደርን/ ከወያኔ መዶሻ ተርፈው ጥቂት መራመድ ከቻሉ እና የነገ የሃገር ተስፋ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁትን ሰዎች ጀርባ እንድንሰልል፣ስማቸውን እንድናጠፋ እና ለነደፉት የመበታተን እቅድ ተባባሪ እንድሆን ስንጠይቅ በፍጹም! ብለን የቀረበልንን የጉቦ ማታለያ ቤት እና ገንዘብ ረግጠን፣ እኛ የጀግኖች ኢትዮጰያዊያን ልጆች እንጂ የባንዳ ውላጆች አለመሆናችን አስረድተን፤ በተጨማለቀ ስርአት ውስጥ ህዝብን ለማታለል ከሚገነቡ ጥቂት ህንጻዎች ይልቅ በየጉራንጉሩ የሚጠፋው የሰው ህይወት የሚረገጠው የዜጎች መብት የሚካሄደው ኢ-ሰብአዊ ጥሰት አይተን እንዳላየን ሰምተን እንዳልሰማን ከማለፍ የሚመጣብን መቀበል ይሻላል ብለን እሾህና አሜኬላ በበዛበት የኢትዮጵያ የፕሬስ ስርአት አመታት አስቆጥርን፡፡

በጥቂት የገዥው መደብ ባለስልጣናት የሚካሄደውን ምዝበራ እና ዝርፊያ እያወቁ ጸጥ ማለት ከአእምሯችን በላይ ቢሆንብን፤ ገንዘብ የኢትዮጵያን ህግ ሲገዛ፤ ጥቂት የገዥው መደብ አቀንቃኞች ተመችቷቸው አብዛኛውን ሲጨቁኑ በዲሞክራሲ ስም አምባገነንነት አስፍነው እንደፈለጋቸው ታሪክ እያበላሹ፤ በፌዴራሊዝም ስም በጎሳ እና በዘር ኢትዮጵያን ለመበታተን ቆርጠው መነሳታቸውን እኛ እወቅን እነርሱ እየዋሹ እድሚያቸውን ለማረዘም የሚያደርጉትን ሂደት ለማክሸፍ ህይወታችን አደጋ ላይ ጥለን፤ እንደአህያ በዱላ የሚያምነው ጭንቅታቸው ሌት ከቀን አንዴ ከቤታችን አንዴ ከቢሯችን አንዴ በስልካችን አንዴ በቤተሰባችንን …. እየመጡ ችለን ብዙ መንገድ ለመጓዝ ጥረናል፡፡

የኢትዮጵያን ህዝብ ብሶት ማሰማት ለሙያ መታመን ነው ብለን፤ በሙያችን በቆየንባቸው ጊዜያት ዛሬም ከጫካ አስተሳሰብ ያልተላቀቀው የደህንነቶች የጉልበት ማስፈራሪያና መደለያ ሳያሸንፈን ለሙያችን ተገዝተን የኢትዮጵያ ህዝብ የናፈቀውን እውነትን ፍለጋ፣ ሰላምን ፍለጋ፣ ፍትህን ፍለጋ፣ ከሞቀው ቤታችን፣ ከደመቀው መንደራችን፣ በስስት ከሚያዩን ቤተሰቦቻችን፣ ሌት ከቀን ስለኛ ከሚያስቡ እና ከሚጨነቁ ጓደኞቻችን ርቀን፤ የነበረንን ሜዳ ላይ በትነን የምንወዳትን ሃገራችንን ትተን ከሃገር ተሰደንም ቢሆን ፤በዓሉ ቢያልፍም አልዘገየንም እና እንኳን ለዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ አልን፤ ከዚሁ ከስደት መንደራችን ከሌባ እና ፖሊስ ሩጫ ባስተረፍናት ጊዜ ተጠቅመን፡፡ ኮካዎች ሲንጫጩ (በልቶ ዝም የለምና) እኛም እዚህ ሆነን ከመከራችን ባስተረፍነው ፈገግታችን ሂሂሂ አልንባቸው፡፡ የራሳቸውን ማንነት ክደው የሙት መንፈስ ቅዠት የማስጠበቅና የማስቀጠል ቋሚ ስራቸው ስለሆነ ከእነርሱ የሚጠበቅ ነውና “የመለስ ራእይ” እየተሳካ ስለሆነ ደስታቸውን እንዲያከብሩ ፈቀድንላቸው፤ ባንፈቅድም ፈቅደዋልና ሳቅንባቸው፡፡ እድሜ ለወያኔ በዚህ 23 አመት የተወለድን ልጆች ራሳችንን እንድንችል የሚያደርግ ስርአት ባይፈጠርልንም ቤተሰቦቻችን ከእኛ አልፎ ለሌላው የሚርፍ ስራ እንደሚሰሩ እና መሰደዳችን እንዳመማቸው ግልጽ ነው፡፡

በተለይ ልክ እንደማንኛውም ሰው ከሃገር ተሰደዱ የሚለውን ዜና አይሉት ሰቆቃ በአዲስ አመት መግቢያ በአውዳመት መዳረሻ ሲሰሙ በጳጉሜ ያሳለፍነው ጥቁር ሳምንት ለእነርሱ አዲስ አመት አዲስ ሰቆቃ ይዞ በአደይ አበባ ሳይፈካ እንደጨለመ 2007 እያሉ ቀን መቁጠር ጀመሩ፤ ጥቁራቸውን እንደለበሱ፤ በርቀት የብርሃን ፍንጣቂ ጮራ እየናፈቁ እንደልባቸው ሰላም ተመለሱ ብለው መልካም ምኞታቸውን ለመናገር እንኳን ሲቃ አንቋቸው ሳይተነፈሱ ሰማይ ሰማዩን እያዩ ከፈጣሪያቸው ጋር እያወሩ ቤተሰቦቻችን አስቧቸው፡፡ አብዛኞች ስደተኛ ጋዜጠኞች የወያኔ ትውልድ ስላልሆኑ አብዛኛውን የእድሜ ዘመናቸውን የኖሩለት ሙያ የከፈላቸውን “ዉለታ”፣ ንብረታቸውን ሜዳ ላይ በትነው ግማሹን በማይረባ ዋጋ በነጻ መስጠት ከማይተናነስ አውጥተው ጥለው፤ አይደለም በዓል ደርሶ እንዲሁም በአዘቦት መምጣታቸውን በጉጉት ከሚጠብቁት ልጆቻቸው በስስት ከሚያዩዋቸው ቤተሰባቸው ከሚያስተዳድሩዋቸው ቤተዘመዶቻቸው ተነጥለው ቢሰደዱም፤ ቅሉ አንድ ሁለቱ እዚህ ያለውን ሁኔታ እንዲሰልሉ በወያኔ ተልከው የመጡም አልጠፉም፡፡ ለነገሩ ይሄ አይገርምም፡፡ እንኳን ተሰደን፤ ሀገር ቤት በጋዜጠኛ ሽፋን፤ በጓደኛ ሽፋን፤ በጉርብትና ሽፋን ተደብቀው አብረውን እየበሉ አብረውን እየጠጡ ክፉ ደጉን እያሳለፉ አብረውን እየሰሩ የገዥው መንግስት ተላላኪ ሆነው እያንዳንዷን እንቅስቃሴያችንን የሚያቃጥሩ “ጓደኞቻችን” እያወቅን እንዳለወቅን ሆነን ብዙ ኮካዎችን ስቀን አልፈናቸዋል፡፡ ጥያቄው የነጻነት እንጂ የዳቦ ቢሆን ኖሮማ ከተሰደደው አብዛኛው ጋዜጠኛ ተንደላቆ ለመንግስት አሸርግዶ በኖረ ነበር፡፡

ጥያቄው ኢኮኖሚ ቢሆን ኖሮማ ገና ድሮ እባካችሁ አትጻፉብን ምን እንዳርግላችሁ የየት ሃገር ቪዛ እንምታላችሁ ስንባል ዘንጠን በመረጥነው ሃገር በሄድን ነበር፡፡ ምን እስክንከሰስ አስቆየን? ጥያቄው የህሊና ሆነ እንጂ የሆድ ቢሆን ኖሮማ ባመጡልን መደለያ ተጠቅመን ለኛም ለቤተሰቦቻችን ህይወት የሚቀይር ብር በተቀበልንና የኢትዮጵያን ህዝብ ሮሮ እንዳልሰማን ባለፍን፡፡ መንገዳችን ሃገር ለመልቀቅ ቢሆን ኖሮ አብዛኛው ጋዜጠኛ ፓስፖርት በእጁ ያስምጣል እንጂ በተከሰሰ ማግስት ስለፓስፖርት ማውጣት ባልተጨነቀ ነበር፡፡ ጥያቄው የፍትህ እና የነጻነት ሆነ እንጂ ቪዛ ማግኛ ቢሆን ኖሮማ የተደራጀ ኑሮ እና ቤተሰብ ሃገር ቤት ውስጥ ባልመሰረተ ነበር፤ ባሳለፍነው ጥቁር ሳምንት አንዳንዱን ሰው ታዘብነው ብዙውን አከበርነው፡፡ ኮካዎችን…. አይ እነርሱማ ኮካ ናቸው፡፡ እኔን የገረመኝ ግን የባለቀለሞች ነው ፤ የባለ ቀለም ምልክቶች አስተሳሰብ፡፡ ወያኔ ለራሱ እንኳን በቅጡ የማይገባውን ፖሊሲውን በሰዎች ላይ ለመጫን እንዴ በስብሰባ አንዴ በስልጠና አንዴ በአበል ብዙ ጊዜ በግድ ለማስረጽ ሌት ተቀን ሲለፋ አካኪ ዘራፍ ያልነው፤ “የመለስን ራእይ በማጣጣል” ተብለን ስንወነጀል የመለስ ራእይ የዮሃንስ ራእይ አይደለም ያለመቀበል መብት አለን ብለን ስንከራከር እኮ አቋማችንን እየገለጽን እንጂ የመቃወም ሱስ ኖሮብን አይደለም፡፡ ዛሬም እናንተ አንዳንድ የባለቀለም አባላቶች ለምን ተሰደዱ ብላችሁ የራሳችሁን አስተሳሰብ እኛ ጋር ለመጫን ማሰባችሁ ያስቃል፡፡ ሰው የሚኖረው በገባው ልክ ነው፡፡ እኛ አስበን እንጂ አስበውልን አንኖርም፡፡ (በተለይ አንቺ የ10 ቀን መታሰር “ጀግና” ያደረገሽ ባለቀለም ሳሞራ የኑስ ከ11ኛ ክፍል አቋርጦ የኢትዮጵያን መከላከያ ልምራ ብሎ “ታሪክ” አበላሸ፤ ታሪክ እንዳይደገም እስኪ እልፍ ….እልፍ በይ… ) ለነገሩ እናንተ ባለቀለሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ከአንድ ጋዜጠኛ ውጭ ያለ አይመስላችሁም ፤ እርሱ እናንተ ያላችሁ ባይመስለውም፡፡

ቢሆንም በጥቂቶች ብዙሃንን አንፈርጅም “ለምጣዱ ስንል አይጧን ትተናል” እና አፉ ብለን አሁንም ተስፋ ጥለናል፡፡ ቅር ብሎንም መልካም ምኞታችን አንነፍግም እና እንኳን አደረሳችሁ ብለናል፡፡ እናም ከዚህ ሁሉ ሃተታ በኋላ ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ በመሰደዳችን ከማንም እና ከምንም በላይ ላዘናችሁ ፈጣሪ እንዲከተለን ለጸለያችሁ ቤተሰቦቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ ሳትነግሩን ብላችሁ የተቀየማችሁን ወያኔ ራሳችንን እንዳናምን አድርጎን በስልክ ማውራት ባንደፍርም፣ ከሃገርም ውስጥም ሆነ ውጭ ሰምታችሁ ደንግጣችሁ መልእክት የላካችሁ፣ ተናዳችሁ እላፊ ስድብ ላወረዳችሁብን ባለቀለሞችና ኮካዎች ፣ ካላችሁበት እኛን ለመርዳት እየተንቀሳቀሳችሁ ላላችሁት በሙሉ ለሁላችሁም መጭው ዘመን የሰላም እና የእርቅ እንዲሆን ተመኘን፡፡ ከጠባቡ እስር ቤት ሰፊው ይሻላል ብለን መርጠናል እና ሃገራችንን ኢትዮጵያ እግዚአብሄር ሰላሙን ያምጣላት፡፡

አረንጓዴ ኢኮኖሚና መለስን ምን አገናኛቸው?

$
0
0

ጌታቸው ሺፈራው

የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተጣጣመ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ይህ የኢኮኖሚክስ መርህ በበርካታ ምሁራን የተነሳ ቢሆንም መንግስታት ለጊዜያዊ ጥቅማቸው ሲያምታቱት ይስተዋላል፡፡ በአብዛኛው አረንጓዴ ኢኮኖሚ ሲባል እንደ ጸሃይ ብርሃንና ባዮ ጋዝን እንዲሁም የአየር ንብረትን ለመከላከል የሚያስችሉ (ለምሳሌ በኤሌክትሪክ መኪናዎችን) ቴክኖሎጅ መጠቀም ያካትታል፡፡ የውሃ ንጽህናን መጠናከርና ብከላን ማስወገድ፤ የፍሳሽ አገልግሎትን በማዘመንና ቆሻሻን እንደገና በመጠቀም አካባቢን ከብክለት መከላከል የዢሁ ስልት አንድ አካል ነው፡፡ ደንን ማልማት፣ መሬትን ከመከላት መከላከልና የመሳሰሉትን ከባቢ አየርን ለመከላከል የሚያስችሉ ዘዴዎችን መጠቀም ላይ የሚያተኩር ፖሊሲም ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጋር ሲያያዝ ይታያል፡፡
በእርግጥ ምሁራንም ቢሆን አረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚለውን ትርጉም እንደ የራሳቸው የሚተሩሙት መሆኑን ተከትሎ እስካሁን ግልጽ ትርጉም እንዳልተሰጠው የሚናገሩት በርካቶች ናቸው፡፡ ከዚህም አለፍ ሲል አረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚባል ነገር የለም ከሚሉት ጀምሮ ከአፈጻጸሙ፣ ለመጠቀሚያነት ብቻ የሚውል መሆኑ፣ በትርጉም ልዩነትና በመሳሰሉት ተቃውሞዎች ይገጥሙታል፡፡

  Meles Zenawi

Meles Zenawi


አረንጓዴ ኢኮኖሚ እንደ መለስ ራዕይ

ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ኢህአዴግ አዲስ አባዜ የተጠናወተው ይመስላል፡፡ ሁሉም የአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስኬቶች በአቶ መለስ የተወጠኑ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ሲያወራ ይደመጣል፡፡ ተቋማት፣ ምሁራንና ሰራተኞች የሌሉ ያህል አቶ መለስ የሁሉም የአገሪቱ ፖሊሲና ስትራቴጅዎች ቀያሽና የመጽሐፎች ሁሉ ደራሲ ተደርገዋል፡፡ ልማታዊ መንግስትና አብዮታዊ ዴሞክራሲ የተባሉት በውል ያልተተረጎሙ እና በመልካም ተሞክሮነት ከሌሎች የተለበጡ የስልጣን መወጣጫ መርሆች ሳይቀር አቶ መለስ የፈጠሯቸው ተደርገው እየተወሩ ነው፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲም ሆነ ልማታዊ መንግስት አቶ መለስ ስልጣን ከመያዛቸው በፊት ሌሎች ስርዓቶች ተግባራዊ ያደረጓቸው ቢሆንም በኢህአዴግ መንደር ግን የአቶ መለስ ግኝቶች ተደርገው እየቀረቡ ነው፡፡

በቅርቡ ደግሞ ኢህአዴግ አቶ መለስ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን መርህ ለዓለም አማራጭ ማቅረባቸውን እየነገረን ነው፡፡ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ባዮ ጋዝና የጸሀይ ብርሃን መጠቀም፣ ቆሻሻን እንደገና መጠቀም፣ ደን እንክብካቤ፣ የአካባቢ ጥበቃ ጋር ምቹ የሆኑ ምርቶች (አረንጓዴ ምርቶች) ማምረትና የመሳሰሉትን የሚያጠቃልል በመሆኑ ስሙ ተሰጥቶትም ሆነ ሳይሰጠው በርካታ የዓለም አገራት አቶ መለስ ከመወለዳቸው በፊት ጀምሮ ተጠቅመውበታል፡፡ ለአብነት ያህል የጸሃይ ብርሃንን በታዳሽ ምንጭነት ለመጠቀም የሚያስችለው የመጀመሪያው የዘርፉ (የአረንጓዴ) ቴክኖሎጅ የተሰራው እ.ኤአ በ1883 ቻርለስ ፍሪት በተባለ ግለሰብ ነው፡፡ ምንም እንኳ ይህ ቴክኖሎጅ በተለይ ኤሌክትሪክ ማመንጨት የቻለው ዘግይቶ ቢሆንም ይህም ቢሆን አቶ መለስ ስልጣን ከመያዛቸው 6 አመት ቀድሞ እ.ኤ.አ በ1985 ነው፡፡ ምዕራባዊያን አገራት ይህን ታዳሽ ሀይል አቶ መለስ ምኒልክ ቤተ-መንግስት ከመግባታቸው በፊት ወደ ሀይል ቀይረው ተጠቅመውበታል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሀሳቡ ከመነሳቱ በፊት የሰሜን አፍሪካ አገራትና ጎረቤታችን ኬንያን ጨምሮ በርካቶቹ አገራት ተጠቅመውበታል፡፡

ለአረንጓዴ ቴክኖሎጂ እንደ አንድ ግብዓት የሚጠቀሰው ኢታኖል ነው፡፡ የኢታኖል ሳይንሳዊ ቀመር የተገኘው እ.ኤ.አ በ1840 ዎቹ ነው፡፡ አሜሪካውያን ይህ የኢታኖል ሳይንሳዊ ቀመር ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለመብራትነት ሲገለገሉበት ኖረዋል፡፡ እንግዲህ አቶ መለስ ከመወለዳቸው ከሁለት መቶ አመት በፊት መሆኑ ነው፡፡ አረንጓዴ ቴክኖሎጂ የአሁኑ ትርጉም ተሰጥቶት ተግባራዊ መሆን በጀመረበት ወቅትም ቢሆን ለአቶ መለስና ኢህአዴግ ሩቅ ነው፡፡ አረንጓዴ ኢኮኖሚ በተደራጀ መልኩ በተለይም በተቋማት አነሳሽነት የጀመረው እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ለአብነት ያህል እ.ኤ.አ በ1980 ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ህብረት አገራት ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ እንዲችሉ ለማድረግ በሚል ይህን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው በጥናቱ ላይ እስቀምጧል፡፡

ከ12 አመት በኋላ እ.ኤ.አ በ1992 (አቶ መለስ ስልጣን በያዙ ከአንድ አመት በኋላ ሲሆን በስብሰባው አልነበሩም) በብራዚሏ ሪዮ ዲጀኔሮ በተካሄደው ስብሰባ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመሆኑም ኢህአዴግ አቶ መለስ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለዓለም በአማራጭነት ያቀረቡ በሚል የሚያቀርበው ሙገሳ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ አቶ መለስ በቅርብ አመታት አፍሪካን ወክለው በተለያዩ መድረኮች ስለ አየር ንብረት ድርድር አድርገዋል፡፡ ይህም ቢሆን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ያላት መቀመጫና ተደማጭነትንም ጭምር ያገናዘበ ነው፡፡
አቶ መለስ በዓለም አቀፍ መድረክ የማሳመን ብቃት ስላላቸው ነው ቢባል እንኳ በድርድሩ ወቅት የሚያቀርቡት ማሳመኛ የአፍሪካ አገራት ባለሙያዎች፣ መሪዎችና ሌሎች አካላት ተወያይተው የተስማሙበትን ሀሳብ ነው፡፡ በአንድ ወቅት አቶ መለስ በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ መድረክ አፍሪካ ልታገኝ ይገባት የነበረውን 30 ቢሊዮን በላይ ዶላር ጥቅም 10 ቢሊዮን እንዲሆን አድርገዋል በሚል ከሱዳንና ከሌሎች ልዑካን ተቃውሞ እንደደረሰባቸው ስናስታውስ ደግሞ አዲስ ፈጠራ ማበርከት ብቻ ሳይሆን አፍሪካውያን የተስማሙበትንም እንዳላስፈጸሙ እንመለከታለን፡፡ በ2005 ዓ/ም አፍሪካን የወከለችው ኢትዮጵያ ስለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለተባበሩት መንግስታት አቅርባ ተቀባይነት ማግኘቷ ተዘግቧል፡፡ ይህም ቢሆን ጥቃቅን ማሻሻያ ረቂቅ እንጂ የአጠቃላይ አረንጓዴ ኢኮኖሚው ጠንሳሽ ሊያደርጋት አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን በርካታ አገራት አጀንዳና ሃሳብ ያቀርባሉ፡፡ ማሻሻያና የመሳሰሉትን በማቅረባቸው ግን ራሳቸውን የዋናው ሀሳብ አመንጭ አድርገው ሲያቀርቡ አይታዩም፡፡

በነገራችን ላይ ህወሓት በርሃ በወጣባቸው በመጀመሪያ አመታት ደርግ ‹‹አረንጓዴ ልማት›› በሚል ሰፋፊ እርሻዎች ልማት ጀምሮ እንደነበር ይነገራል፡፡ በወቅቱ አሁን ለአቶ መለስ መታሰቢያ የየመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ አትክልት ከሚተክለውም በላይ ኢትዮጵያውያን በግድ ምግባቸው ብቻ እየተቻላቸው ያለሙ ነበር፡፡ ይህ ኢትዮጵያውያን ተገደው ያሉሙት የነበረው ልማት ለደርግ ‹‹አረንጓዴ ኢኮኖሚ›› መሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ ኢህአዴግም ይህን ያህል ተግባር ቢፈጽም ከደርግ ያልተናነሰ ራዕይ ጨምሮበት ለፕሮፖጋንዳ ሊጠቀምበት እንደሚችል የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ይህን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተግባዊ እያደረጉ ከሚገኙ አገራት መካከል በመጨረሻዎቹ ረድፍ የተመደበች አገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ ባለፈው 40ና 50 አመት ከ40 በመቶ በላይ የደን ሽፍን እንደነበራት ይነገራል፡፡ በህዝብ ብዛትም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች ከ20 አመት በፊት ይህ የደን ሽፋን ከ3-4 በመቶ ይሆን እንደነበር በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ አሁን ከዚህም በታች ወርዷል፡፡ ለ99 አመት ለአረብ፣ ህንድና ቻይና ባለሀብቶች እየተሰጠ ያለው በደን የተሸፈነ መሬት ሲመነጠር ድግሞ ይህን የደን ሀብታችን በእጅጉ እንደሚያመናምነው አያጠራጥርም፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመርህ ደረጃ እፈጽማለሁ ቢልም ተግባራዊነቱ ግን ገና በእንጭጭ ላይ ነው፡፡ ከተቋማቱ ጀምሮ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዝግጁ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ አለብነት ያህል፣ አብዛኛዎቹ ክልሎች የደን ልማት በግብርና ሚንስትር ስር የሚገኝ ነው፡፡ በመሆኑም የግብርና ሚንስተር በተቻለ መጠን አገሪቱን መሬት እንዲታረስ ማድረግ ነው፡፡ የደን ጥበቃ ደግሞ ደንን ማሰጠበቅ፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሚጋጩ ለጥዕኮዎች አላቻው ናቸው፡፡ በተለይ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት በሚል ለኢንቨስተሮች ሰፋፊ መሬቶችን የሚሰጡት የክልል ቢሮዎች ለደን ልማትና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ምንም ዝግጅት የላቸውም፡፡ ለምሳሌ ያህል ጋምቤላ ብንወስድ፤ ለውጭ ባለሀብቶች እየተሰጠ ያለው መሬት ታርሶ የማያውቅና በደን የተሸፈነ እንደሆነ ይነገራል፡፡ እስካሁን በጋምቤላ ብቻ ከሲውዘርላንድ የሚበልጥ የቆዳ ስፋት ያለው መሬት ለውጭ ባለሀብቶች ተሰጥቷል፡፡ እነዚህ የውጭ ባለሀብቶች የሚጠቀሙበት ኬሚካል የአካባቢውንና የአገሪቱን የአየር ንብረት ይበክላል፡፡ ይህ ሰፊ ደንን እያስመነጠሩ መሬትን በሲጋራ ዋጋ መሸጥ፣ በኬሚካል ማስበከል አቶ መለስ ጀምረውት ሌሎቹ በ‹‹ራዕይ›› እያስቀጠሉት ነው፡፡ እንዲህ ደን እየወደመ፣ የአየር ንብረት እየተበከለ፣ አፍሪካውያን ለተበከለው ይከፈለን የሚሉትን ሰያስፈጽሙ አቶ መለስና ኢህአዴግ ከአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ጋር ምን እንደሚያገናኛቸው አይገባኝም፡፡


“ወያኔ ጠላቶቹ ሕብረት ሲፈጥሩ እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም፤…ድክመቱ የኛው ነው”–አቶ ኢያሱ ዓለማየሁ (የኢሕአፓ ከፍተኛ አመራር)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ባለፉት 2 ሳምንታት ውስጥ በተከበረው የኢሕአፓ 42ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አቶ ኢያሱ ዓለማየሁ ቃለ ምልልስ ሰጡ። የኢሕአፓ ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት አቶ ኢያሱ ከፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በተቃዋሚዎች ሕብረት ዙሪያ “ወያኔ ሊከፋፍለን በመቀመጡ ጠላቶቹ ሕብረት ሲፈጥሩ እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም፤ ወያኔ ከፋፈለን ከማለት ይልቅ ወደውስጥ ማየት ያስፈልጋል” አሉ። “ተቃዋሚዎች ከተባበሩ የወያኔን ስልጣን ዶግ አመድ ስለሚያደርጉት ወያኔ ስልጣኑን ለመጠበቅ ሕብረቱን ማደናቀፉ የሚጠበቅ በመሆኑ ወያኔ ከፋፈለን ማለቱን ማቆም ያስፈልጋል” ያሉት አቶ ኢያሱ ተቃዋሚዎች ህብረት ሲፈጥሩ ከመሰረቱ መስማማት እንዳለባቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ቃለ- ምልልሱን ያድምጡት።

“ወያኔ ጠላቶቹ ሕብረት ሲፈጥሩ እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም፤… ድክመቱ የኛው ነው” – አቶ ኢያሱ ዓለማየሁ (የኢሕአፓ ከፍተኛ አመራር)

በመለስ “ትሩፋቶች” ዙርያ የሕዳሴው ግድብ የማን ፕሮጀክት ነው?

$
0
0

meles bookዳኛቸው ቢያድግልኝ
‘የመለስ ትሩፋቶች ባለቤት አልባ ከተማ’ን አነበብኩት ግሩም ሥራ ነው ብዬ አድናቆቴን ቸርኩ። ቀላል አቀራረብና ብዙ የትየባ ግድፈትም የሌለው በመሆኑ ለማንበብ አይታክትም። ያነበብኩት ውስጥ ሊነሱ የሚገቡ ቁርጥራጭ ሃሳቦችን በማንሳት የሰዎችን ትኩረት መሳብና በጉዳዩ ዙርያም ተጨማሪ መረጃዎች ካሉ በሚል አንዳንድ ነገሮችን መነካካት ፈለኩኝ። ይህ የመጽሃፍ ግምገማም ቅኝትም አይደለም በዚያ ጉዳይ አንዳንድ ወገኖች የሚሉትን ብለዋል። የኔ ሳር እንደ መምዘዝ ተብሎ ይወሰድና ለዛሬ አንዷን ሳር አብረን እንምዘዝ። ኤርምያስ ገና ብትንትናቸውን እያወጣ የሚነግረን አለና ይህ ምናልባትም ሰልፍ ላስያዛቸው ድርሳኖቹ ያግዘውም ይሆናል። የበርካቶቻችን ልምድ የነበረን ስህተት ለመሸፈን ደጋግሞ መሳሳት ነውና ሰዎች ለምን ተሳሳቱ ሳይሆን ስህተታቸውን ተገንዝበው ወደ እውነቱ ጎዳና መምጣት መቻላቸውን በማድነቅ ኤርምያስን እንኳንም ወደ ህሊናህ ተመለስክ እንደ በደልህ መጠን ሳይሆን ከዚያም በላይ ሀገርህ ካንተ የምትሻው አለና በሙሉ ልብና በቆራጥነት የድርሻህን አበርክት እስካሁን ላደረከውም እያደረግህ ላለውም አክብሮት አለኝ ብለው እወዳለሁ። ይህንን የሚጋሩም በርካቶች ናቸው።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ከአቶ ገብሩ አስራት አዲስ መጽሐፍ የተገኙ 9 ነጥቦች

$
0
0

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕ/ት አይተ ገብሩ አስራት “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” የሚል አዲስ መጽሐፍ ማሳተማቸውና በዋሽንግተን ዲሲ ሴፕቴምበር 1 ቀን 2014 እንዳስመረቁ ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል። በዚህም መሥረት ከመጽሐፉ ውስጥ የተገኙ 9 ነጥቦችን ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ አስነብቦናል፤ ሙሉ መጽሐፉን እስክታነቡት ድረስ ነጥቦቹን እነሆ፦
ከመጽሐፉ የተወሰዱ
gebru asrat
1ኛ. ህወሃት በ17ቱ የትግል ዓመታቱ 54ሺ ሰዎች መሞታቸውንና ከነዚህ 90 ከመቶ የሚሆኑት የገጠር ወጣቶች ናቸው። በገጽ 165 ።
2ኛ. “የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች በሚሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ እያፈሰሱ ህዝቡ ትግላቸውን እንደገድለ ሰማዕታት እንዲቀበለው አድርገው በሥልጣን ለመቆየትና ከሞቱም በኋላ ዘለዓላማዊ ክብርና ዝና ለማግኘት መሞክሩን ተያዘውታል። ይህን የህዝብና የሰማዕታት የተጋድሎ ታሪክ ጠቅልለው ለአንድ ሰው ለማሸከም ይሞክራሉ። ሰውየው ከሰውነት አልፎ እንዲመለክ ለማድረግ ይሞክራሉ። ይህን ሁሉ የሚያደርጉትም በአሁኑና በወደፊቱ ተግባሮቻቸው ከመኖር ይልቅ ባለፈው ታሪክ መኖሩ ለሥልጣናቸው ህልውና ጠቃሚ ሆኖ ስላገኙት ነው።(ገጽ 4)
3ኛ. እጅግ የሚያናድደኝ ይህ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የዘመነ ምኒልክ የጎፌሬዎች ቀረቶና ሸለላ ነው።- ስብሀት ነጋ ገጽ 303
4ኛ. የደርግ ሠራዊት አባላት በግለሰብ ደረጃ እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በጥቅም ላይ የሚያውሉበትና አዲስ በተደራጀው ሠራዊት ውስጥ በአባልነት የሚቀጥሉበት ሁኔታ ቢመቻች ኖሮ ከፖለቲካው አንጻር ይፈለግ የነበረውን የብሔር ብሄረሰብ ስብጥር ከማሟላትም ሌላ የረጅም ጊዜ ልምዳቸውንና እውቀታቸውን አገራዊ ሠራዊት ለመገንባት ባዋሉት ነበር።222
5ኛ. አሁን ሳጤነው በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነታችን ምክንያት የመረጃ ፍሰትን ገድበን የአገራችንን የአስተሳሰብ እድገት በመጎተታችንና በማጫጨታችን እጸጸታለሁ። ገጽ 249
6ኛ .. ኢህ አዴግ ተቃዋሚዎችን ለመድፈቅና ለማጥፋት ከሚጠቀምባቸው ስልቶች የአመራር አባላቱንና ከፍተኛ ኃላፊዎችን መቆጣጠር። በጥቅም መግዛትና መደለለል ነው። በክፍያ መዝገብ ስማቸው የሠፈረ አሁን ድረስ ተቃዋሚዎች ነን እያሉ የሚንቀሳቀሱ የማውቃቸው አሉ። የነዚህ ሰዎች ተቀጣሪነት ያወቅኹት በኢሕአዴግ አመራር አባልነቴ ሳይሆን ቅርበት ከነበረኝ የደሐኀንነት አባላት ነውና አሁንም የነዚህን የማውቃቸውን ሰዎች ስም ላለመጥቀስ መርጫለሁ። 251
7ኛ. ኢሕአዴግ አማራው ክልል ውስጥ ሲንቀሳቀስ ጠባቦች መጥተው ሊውጡህ ስለሆነ ከ እነርሱ የሚያድንህ ከኢህ አዴግ ጎን ተሰለፍ ብሎ ይቀሰቅሳል። በኦሮሚያ በትግራይና በሌሎች ክልሎች ደግሞ ትምክህተኞች ዳግም አንሰራርተው ሊውጡህ ነው ኢሕ አዴግን ካልተቀበልክና ካልደገፍክ መቀመቅ ትገባለህ እያለ በማስፈራራት ይቀሰቅሳል። ገጽ 199
8ኛ. የሓየሎም ሞት ገዳዩ ኤርትራዊ መሆኑን እያወሱ ከኤርትራ ከነበረው አለመግባባት ጋር ያያዙታል። ይህ ፍጹም ሊሆን አይችልም ብሎ ለማለትም ያዳግታል። 265
9ኛ. (ስለተባረሩ ኤርትራውያን) ጉቦ እየተሰጣቸው መባረር ያለባቸውን እያስቀሩና መባረር የሌለባቸውን ያባርሩ እንደነበር የሚባረሩት ንብረታቸውን ሲሸጡ ተደራጅተው ንብረቱን በርካሽ ይገዙ እንደነበር ኋላ ላይ ተጋልጧል።…እኛን ፀረ- ኤርትራውያንና ፀረ- ዴሞክራሲያዊ ናቸው እያሉ ሲከሱን የነበሩ ቱባ ባለሥልጣኖች ሳይቀሩ ኤርትራውያን ሲባረሩ ቪላዎቻቸውንና የንግድ ድርጅቶቻቸውን ገዝተው እንደነበር ተራው ዜጋ ሳይቀር ያውቀዋል። ሆኖም የህወሃት/ኢህአዴግ አመራር በአንዱ ወይም በሌላው ከኤርትራውያን ጋር በተያያዘ ወንጀል ተዘፍቀው ስለነበር “በመስተዋት በተሠራ ቤት የሚኖር ሰው በድንጋይ አይጫወትም” እንዲሉ ምንም ማድረግ አልቻሉም። 281

ምንጭ፡ ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ

የአቶ ገብሩ አስራት መጽሐፍ ቅኝት –ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ (ሊያነቡት የሚገባ ትንታኔ)

$
0
0

በዋሽንግተን ዲስና አካባቢዋ ከሚታተመው ከዘኢትዮጵያ ጋዜጣ የተገኘ

Gebru Asrat

አቶ ገብሩ አስራት

ታሪክ የሚታወቀው ሲጻፍ ወይ ሲነገር ነው። መታመን አለመታመኑም የሚያከራክረው ተጽፎ ወይም በሌላ ቅርጹ ተመዝግቦ ሲገኝ ብቻ ነው። የታሪክ ታሪክነቱ ስነ ጽሑፉነቱ ሳይሆን ሁነቱ ክስተቱ በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ መደረግ መፈጸሙ ነው። ካልሆነ ግን ልብወለድ ድርሰት መሆኑ አይቀርም። ሆነም ቀረ ግን ተፈጽሟል እንዲህ ሆኗል እንዲያ ነበር እያሉ ከነማረጋገጫው የሚነግሩን ታሪክ ዘጋቢዎች አሉ። ለተአማኒነቱ ሲባል ከስሜታዊ ወገንተኝነቱ እንዲጸዳ ታሪክ በታሪክ ሠሪዎች ባይጻፍም፣ እነሱ የሚተዉት ማስታወሻ ግን ለታሪክ ፀሐፊዎች ግሩም ስጦታ መሆኑ የታመነ ነው። አቶ ገብሩ አስራት በዚህ ረገድ ለታሪክ ፀሐፊዎች አንድ ማስታወሻ ትተዋል። መጽሐፉ ሰፕቴምበር 1/2014 በዋሽግንተን ዲሲ በተደረገ አንድ ሥነ ሥርዓት ተመርቋል። ዶ/ር ካሳ አያሌው በመሩት በዚህ የመጽሀፍ ምርቃት ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መጽሐፉን የቃኙት አቶ ፈቃደ ሸዋቀናም መጽሐፉ ለሌሎች ፀሐፊዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ፓለቲከኞችና አንባቢዎች እርሾ ሊሆን የሚችል ፈር ቀዳጅና አከራካሪ መጽሐፍ ሆኖ አግኝቸዋለሁ” ብለዋል።

እንደተባለውም ማከራከሩ አይቀርምና ታሪክ ፀሐፊዎች ወደፊት ፍሬውን ከገለባ ለይተው እውነቱን ከሐሰት አበራይተው ይህን ያለንበትን ዘመን ይገልጹታል። የታሪክ ማስታወሻ መተው እየተበራከተ ባለበት በዚህ ዘመን ዘመኑን አሳምሮና ወክሎ የሚገልጸው ታሪክ የትኛው እንደሆነ ማወቁ ይቸግረን ይሆናል።
ቢሆንም ነገሮች በፍጥነት መደበላለቅ በያዙበት በዚህ ዘመን የተደበላለቀ ስሜት የሚፈጥረው የአቶ ገብሩ መጽሐፍ ለታሪክ የሚተወው ማስታወሻ ምን ሊሆን እንደሚችል መቃኘቱ አይከፋም። ዘመኑን ያልተረጋጋ፣ የአፈና፣ የስደት፣ የመከፋፈል፣ የመከራ፣ የእስርና የጭቆና በማድረግ ግንባር ቀደም ተዋናይ ከሆኑት ሰዎች መካከል እግዜር አንዳንዱን እየመዘዘ ቶሎ ሳይዘነጉት፣ እያደረጉ ያሉትን ነገር ቆም ብለው አስተውለው እንዲጽፉት ሲያደርግ ደስ ያሰኛል። አቶ ገብሩም በመጽሀፋቸው ደጋግመው የሚጠቀሙባት “ አሁን ቆም ብዬ ሳዬው፣ አሁን መለስ ብዬ ሳየው፣ አሁን ሳጤነው” የምትል አገላለጽ አለች። ይክፋም ይልማም ቆም ብለው የሚቆጩበት ነገር አለ ማለት ነው። ለምሳሌ በመጽሀፋቸው ገጽ 249 ላይ “አሁን ሳጤነው በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነታችን ምክንያት የመረጃ ፍሰትን ገድበን የአገራችንን የአስተሳሰብ እድገት በመጎተታችንና በማጫጨታችን እጸጸታለሁ።” ብለዋል።

ይህን ያጫጩትን የአስተሳሰብ እድገት ለማምጣት ከህሊናቸው ጋር ተማምለው ፋይዳ ያለው መጽሀፍ ለማዘጋጀት መነሳታቸውን በመግቢያቸው ጽፈዋል። “ ስለሆነም ለኀሊናዬ ትክክል የመሰለኝን ሁሉ ለማስፈር ሞክሬም፣ ሰማዕታቱ የተሰውለትን ዓላማ ለማክበር ሞክሬያለሁ” (ገጽ4) በማለት ከደጋፊዎቻቸውና ተቃዋሚዎቻቸው የሚመጣባቸውን ነቀፌታ የገመቱ መስለዋል። ሚዛናዊ ነኝና ልብ አድርጉልኝ ነው ነገሩ። ቢሆንም ነቀፌታውና ውርጅብኙን ያቆሙት ዘንድ ግን አይችሉም። የሚችሉትና ችለው ያሳዩት ነገር ለታሪክ የሚሆን ማስታወሻ መተው ነው። እሱን ትተውልናል! ጥያቄው የተውልን ነገር ምንድነው? የሚለው ነው። በዚህ ዘገባ “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” ከሚለው ባለ 516 ገጽ መጽሐፋቸው የተውልንን ማስታወሻ ከመጠነኛ አስተያየት ጋር መቃኘት ሞክረናል። መቸም የዘንድሮ መጽሐፍ ከድንጋይ ዳቦ ዘመን ካልጀመረ፣ ታሪክ ካላስተማረ አይሆንለትም። መጀመሪያ ረጀሙና ገናናው ታሪካችንን አንስተን እንጸልይበት ካለለ ወደ ፍሬ ነገሩ መምጣት ያስቀስፋል። ስለዚህ አንዴ ሺ ዘመን አንዴ መቶ ዓመት እየሆነ እንደ ስቶክ ማርኬት ገበያ የሚወጣ የሚወርደውን ዘመን እንለፈውና ወደ አቶ ገብሩ ዘመን ቀረብ ብሎ ያለውን የመጽሐፋቸውን ገጽ ገለጥ ገለጥ እናድርገው። መጽሐፉ በስድስት ም ዕራፎች በበርካታ ን ዑስ ም ዕራፎች የተከፋፈለ በቁመቱም ዘለግ ያለ ባለ 516 ገጽ ነው። አክሱምን የድርጅታቸውን የትጥቅ ትግል ዘመን ህወሓት ለሥልጣን የበቃበትንና ከኤርትራ ጋር በመንግሥት አብሮ የኖረበትን እንዲሁም ጦርነቱንን ከጦርነቱ በኋላ ያለውን ሁኔታ ሁሉ በዝርዝር ይዳ ስ ሳል። ሰለኢትዮጵያ የዴሞክራሲና ሰብ አዊ መብቶች አያያዝ ስለምርጫን የፖለቲካ ምህዳር መስፋት መጥበብ ያነሳል። መፍትሔ ሀሳቦች ናቸው የሚላቸውንም ሰንዝሯል። እጅግ የተደከመበት መጽሐፍ መሆኑ ያስታውቃል። ከመጽሐፉ ፍሬ ነገሮች ጥቂቶቹን ለመጋራት ያህል የሚከተለው ቅኝት ተደርጋል።

ፖለቲካ ፓርቲ ተጀመረ!
geberu asrat new book
እንደ አቶ ገብሩ መጽሐፍ – ከ1930ዎቹ ቀደም ብሎ በኤርትራና በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ትጥቅ አንግበው ከሥርዓት ጋር መፋለም የጀመሩ ግንባሮች ነበር። እነዚህ ከማዕከሉ ርቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ቢሆንም ወደኋላው ላይ በአዲስ አበባ ጭምር እየተጧጧፉ ለመጡት አገር አቀፍና ብሔር ተኮር ድርጅቶች እንዲሁም የተማሪ ቤት የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ሆነዋል። በመሆኑም ከኤርትራና ከሶማልያ ድርጅቶች ቀጥሎ በ1960 በጀርመን ሃምቡርግ ከተማ በእነ ኃይሌ ፊዳ የተመሠረተው “የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ” /መኢሶን/ አንጋፋው ፓርቲ ነው። ይሁን እንጂ አቶ ገብሩ ይህን ያገኙት ተስፋዬ መኮንን በ1985 ይድረስ ለባለ ታሪኩ በሚል ርዕስ ካሳተሙት መጽሐፍ ገጽ 119 ላይ መሆኑን ጠቅሰው “አንዳንዶች መኢሶን በ1960 መመስረቱን እንደሚጠራጠሩ” ገልጸዋል። ለታሪክ በተውት መጽሐፋቸው የዘገቡት ግን “መረጃው ትክክል ነው ብለን ከተቀበልነው” (ገጽ35) በሚል ጥርጣሬ ነው። የ66 አብዮቱ ከመፈንዳቱ 10 ዓመት በፊት መሆኑ ነው።

በ1964 በጀርመን በርሊን በእነ አቶ ብረሃነ መስቀል ረዳ፣ ኢያሱ ዓለማየሁ ዘርኡ ክሸን ተስፋይ ደበሳይ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አርነት ድርጅት / ኢሕአድ/ ኋላም አገር ቤት ከነበሩት እንደ አብዮት የመሳሰሉ ቅድመ ፓርቲ ድርጅቶች ጋር አብሮ ሲሰራ ቆይቶ መዋሃዱንና የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ/ ኢሕአፓ ተብሎ መሰየሙን ተመሳሳይ ምንጭ ጠቅሰው ጽፈዋል። ከእነዚህ የህብረ ብሔር ከሆኑት የመኢሶንና የኢሕአፓ ፓርቲዎች ቀጥሎ ምናልባትም ቀደም ብለው ሌሎች የብሔር ድርጅቶች እየተቋቋሙ መምጣታቸውን ጽፈዋል። ቀደም ሲል በሜጫና ቱለማ የመረዳጃ እድር እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ በ1966 በይፋ መቋቋሙን ዘግበዋል። ከእነዚህ ሁሉ የቀደመውና እንደ ሌሎቹ በኤርትራ ተጠልሎ ይንቀሳቀስ የነበረው የብሔር ድርጅት በ1962 በትግራይ ተወላጆች የተቋቋመውና በመምህር ዮሐንስ ተክለ ኃይማኖት “ማህበር ፖለቲካ” ተብሎ የሚጠራው ነው። የትጥቅ ትግል በማንሳት ከኤርትራ ድርጅቶች ቀጥሎ በሰሜን ኢትዮያ የተቋቋመው ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ /ግገሓት/ የትግራይ ትግሪኝ ወይም ኤር-ትግራይ በሚል ኤርትራና ትግራይን አቀናጅቶ አንድ አገር ለመፍጠር የተነሳ መሆኑ በመጽሐፉ ተጽፏል። ለማንኛውም እነዚህኞቹን ጀብሃ ኢሕአደንን ደግሞ ሻዕቢያ እየደገፉት ለትጥቅ ትግል ዝጅግት ሲያደርጉ እስከ 1967 በኤርትራ ቆይተዋል። የትጥቅ ትግል ለማድረግ በኤርትራ እየተደገፉ ከተቋቋሙ የትግራይ ብሔር ድርጅቶች መካከል ሌላኛው መጀመሪያ ማህበረ ገስገስቲ ብሔረ ትግራይ ቀጥሎም ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ /ተሓህት/ እያደርም ህወሓት ሆኖ የወጣው ድርጅት መሆኑን ከገብሩ መጽሐፍ መረዳት ይቻላል። የትግራይ ተማሪዎች ገና ዩኒቨስቲ መግባት ሳይደርሱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያሉ ይቀሰቀሱ እንደነበር ገብሩ የራሳቸውን ታሪክ እያመሳከሩ እንዲህ ጽፈዋል፟-
“ገና ዘጠነኛ ክፍል እያለሁ አንዳንድ ከቀዳማዊ ኃለሥላሴ ዩኒቨርስቲ የመጡ ስለአገሪቱ ፖለቲካ ችግሮች እያነሱ ይቀሰቅሱ ነበር..በ1960ዎቹ መጀመሪያ የክልሉ ተወላጆች የሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ክረምት ለዕረፍት እየመጡ ፖለቲካዊ ቅስቀሳዎችን ያካሂዱ ነበር።” (ገጽ 40) “የትግራይ ተወላጅ የሆኑት
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለእረፍት ሲመጡ የክረምት አካዴሚያዊ ትምህርት እንሰጣለን በሚል ሽፋን የፖለቲካ ትምህርት መስጠት ጀምረው ነበር። እነዚህ አስተማሪዎች የሚሰጡን ትምህርት አብዛኛውን ጊዜ የቀዳማይ ወያኔ እንቅስቃሴን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ይሰጡን ነበር” (ገጽ 41” ብለዋል። የትግራይ ብሔርተኞች የተለያየ ስያሜና የፖለቲካ አስተሳሰብ ቢኖራቸውም ዞሮ መግቢያ መደምደሚያቸው ያቺው ትግራይነታቸው መሆኑን ለማስተዋል የአቶ ገብሩ መጽሐፍ ጥሩ የማመሳከሪያ ሰነድ ነው። ከትግራይም ደግሞ እንዲሁ ወደ ጎጥ እየወረዱ ይሄዳሉ። እነሆ የገብሩ ቃል!“በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች
ተሓትን ጨምሮ እጅግ ወግ አጥባቂ ባህል የተጠናወታቸው ነበሩ። የድርጅቶቹ አመራሮቹም ቢሆኑ ከዚህ የጸዱ አልነበሩም። እንዲያውም አንዳንዶቹ ሥር የሰደደ ኋላ ቀርነትና ጎጠኝነት የተጠናወታቸው ነበሩ።(ገጽ 82)ከፍ ሲል ያየነውና አቶ ገብሩ በመጽሀፋቸው በአንጋፋነታቸው ከጠቀሷቸው ህብረ ብሄር የፖለቲካ ድርጅቶች መኢሶን አንዱ ነበር። የዚሁ ድርጅት አመራር የነበሩት ዶ/ር ነገደ ጎበዜ ሰሞኑን “ይድረስ ከየካቲት ለግንቦት” ብለው በወቅቱ ይዋደቁ የነበሩት የኢትዮጵያ ተማሪዎች ዓላማና አደረጃጀት ምን እንደነበር ባወሱበት በዚህ መጽሐፋቸው እንዲህ ብለዋል “ በዛሬው ግርግርና የብሄር /ብሄረሰብ ድርጅቶች ማየል የተነሳ ብዙ ሰው ልብ የማይለው ቁም ነገርና እኛ መኢሶኖች የቀሰምነው ትምህርት አለ፡፡ መሬት ለአራሹ ብለን ያኔ ስንዋደቅ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ደህንነት በአንድ ላይ ታግለን ነው፡፡ የደርግ መንግስት የመኢሶን መሪዎች በማለት በአንድ ቀን አምስት ታጋዮችንን ማለትም፤ ሀይሌ ፊዳን፤ ዶክተር ንግስት አዳነን፤ ቆንጂት ከበደን፤ ደስታ ታደሰንና ሃይሉ ገርባባን ወስዶ ሲረሽን እነዚህ መሪዎቻችን ከኦሮሞ፤ ከትግራይ፤ ከአማራና ከጉራጌ ብሄሮች የተውጣጡ ዜጎች ነበሩ፡፡ ለዚህ ወይም ለዚያ ብሄር ሳንል በአንድ መንፈስ በአንድ አላማ በወንድማማችነት መንፈስ ታግለናል፡፡”እነ አቶ ገብሩ የሞቱለት ድርጅት በራሳቸው መጽሐፍ ገጽ 43 ላይ እንደምናስተውለው ገና ከማለዳው በትግራዮቹ ታጋዮች ዘንድ “የታላቋ የኢትዮጵያ አስተሳሰብ አራማጅ” ተብለው መወጀንልና መፈራረጅ የነበረ መሆኑን ነው። የካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት ላይ ትጥቅ ትግል የጀመረው ተሓህት ጠመንጃ ማጮህ ጀመረው ወዴት እንደሚሄድ ምን እንደሚፈልግ አጥርቶ ሳያውቅ፣ በገብሩ አነጋገር “በሰነድ የሰፈረ የፖለቲካ ፕግራም” ሳይኖረው ነው። “ተሓህት ውስጥ እስከ 1968 ዓም ድረስ የዚህ ዓይነቱ ክፍተት ስለነበር አባላቱ የተሓህትን ዓላማ በመሰላቸው መንገድ ይገልጹት ነበር። አንዳንዶቹ የተሓህት ዓላማ የትግራይን ሕዝብ ነጻ ማውጣት ነው ሲሉ” ሌሎች ደግሞ የመደብ ትግል በማካሂያድ ጭቁኖችን ነጻ ለማውጥት ነው ይሉ ነበር። የብሔር ጥያቄና የመደብ ትልግ የተዘባረቁበትና አቅጣጫም ያጡበት ሁኔታ ነበር።”45

ከመጽሐፉ የተወሰዱ
gebru asrat
1ኛ. ህወሃት በ17ቱ የትግል ዓመታቱ 54ሺ ሰዎች መሞታቸውንና ከነዚህ 90 ከመቶ የሚሆኑት የገጠር ወጣቶች ናቸው። በገጽ 165 ።
2ኛ. “የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች በሚሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ እያፈሰሱ ህዝቡ ትግላቸውን እንደገድለ ሰማዕታት እንዲቀበለው አድርገው በሥልጣን ለመቆየትና ከሞቱም በኋላ ዘለዓላማዊ ክብርና ዝና ለማግኘት መሞክሩን ተያዘውታል። ይህን የህዝብና የሰማዕታት የተጋድሎ ታሪክ ጠቅልለው ለአንድ ሰው ለማሸከም ይሞክራሉ። ሰውየው ከሰውነት አልፎ እንዲመለክ ለማድረግ ይሞክራሉ። ይህን ሁሉ የሚያደርጉትም በአሁኑና በወደፊቱ ተግባሮቻቸው ከመኖር ይልቅ ባለፈው ታሪክ መኖሩ ለሥልጣናቸው ህልውና ጠቃሚ ሆኖ ስላገኙት ነው።(ገጽ 4)
3ኛ. እጅግ የሚያናድደኝ ይህ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የዘመነ ምኒልክ የጎፌሬዎች ቀረቶና ሸለላ ነው።- ስብሀት ነጋ ገጽ 303
4ኛ. የደርግ ሠራዊት አባላት በግለሰብ ደረጃ እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በጥቅም ላይ የሚያውሉበትና አዲስ በተደራጀው ሠራዊት ውስጥ በአባልነት የሚቀጥሉበት ሁኔታ ቢመቻች ኖሮ ከፖለቲካው አንጻር ይፈለግ የነበረውን የብሔር ብሄረሰብ ስብጥር ከማሟላትም ሌላ የረጅም ጊዜ ልምዳቸውንና እውቀታቸውን አገራዊ ሠራዊት ለመገንባት ባዋሉት ነበር።222
5ኛ. አሁን ሳጤነው በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነታችን ምክንያት የመረጃ ፍሰትን ገድበን የአገራችንን የአስተሳሰብ እድገት በመጎተታችንና በማጫጨታችን እጸጸታለሁ። ገጽ 249
6ኛ .. ኢህ አዴግ ተቃዋሚዎችን ለመድፈቅና ለማጥፋት ከሚጠቀምባቸው ስልቶች የአመራር አባላቱንና ከፍተኛ ኃላፊዎችን መቆጣጠር። በጥቅም መግዛትና መደለለል ነው። በክፍያ መዝገብ ስማቸው የሠፈረ አሁን ድረስ ተቃዋሚዎች ነን እያሉ የሚንቀሳቀሱ የማውቃቸው አሉ። የነዚህ ሰዎች ተቀጣሪነት ያወቅኹት በኢሕአዴግ አመራር አባልነቴ ሳይሆን ቅርበት ከነበረኝ የደሐኀንነት አባላት ነውና አሁንም የነዚህን የማውቃቸውን ሰዎች ስም ላለመጥቀስ መርጫለሁ። 251
7ኛ. ኢሕአዴግ አማራው ክልል ውስጥ ሲንቀሳቀስ ጠባቦች መጥተው ሊውጡህ ስለሆነ ከ እነርሱ የሚያድንህ ከኢህ አዴግ ጎን ተሰለፍ ብሎ ይቀሰቅሳል። በኦሮሚያ በትግራይና በሌሎች ክልሎች ደግሞ ትምክህተኞች ዳግም አንሰራርተው ሊውጡህ ነው ኢሕ አዴግን ካልተቀበልክና ካልደገፍክ መቀመቅ ትገባለህ እያለ በማስፈራራት ይቀሰቅሳል። ገጽ 199
8ኛ. የሓየሎም ሞት ገዳዩ ኤርትራዊ መሆኑን እያወሱ ከኤርትራ ከነበረው አለመግባባት ጋር ያያዙታል። ይህ ፍጹም ሊሆን አይችልም ብሎ ለማለትም ያዳግታል። 265
9ኛ. (ስለተባረሩ ኤርትራውያን) ጉቦ እየተሰጣቸው መባረር ያለባቸውን እያስቀሩና መባረር የሌለባቸውን ያባርሩ እንደነበር የሚባረሩት ንብረታቸውን ሲሸጡ ተደራጅተው ንብረቱን በርካሽ ይገዙ እንደነበር ኋላ ላይ ተጋልጧል።…እኛን ፀረ- ኤርትራውያንና ፀረ- ዴሞክራሲያዊ ናቸው እያሉ ሲከሱን የነበሩ ቱባ ባለሥልጣኖች ሳይቀሩ ኤርትራውያን ሲባረሩ ቪላዎቻቸውንና የንግድ ድርጅቶቻቸውን ገዝተው እንደነበር ተራው ዜጋ ሳይቀር ያውቀዋል። ሆኖም የህወሃት/ኢህአዴግ አመራር በአንዱ ወይም በሌላው ከኤርትራውያን ጋር በተያያዘ ወንጀል ተዘፍቀው ስለነበር “በመስተዋት በተሠራ ቤት የሚኖር ሰው በድንጋይ አይጫወትም” እንዲሉ ምንም ማድረግ አልቻሉም። 281

እዚህ ላይ ይህን የአቶ ገብሩን አባባል ለመፈተሽ ያህል፣ የመደብ ትግልና ጭቆናን ለመቃወም ማልደው የተነሱ እንደ ኢሕአፓና መኢሶን የመሳሰሉት ሌሎች ድርጅቶች ቀድመው በተቋቋሙበት፣ በመላው ኢትዮጵያ ተማሪዎች ለለውጥ በተነሳሱበት ሁኔታ፣ የትግራይ ልጆች ለብቻቸው ተነጥለው በረሃ ግባታቸው፣
የመደብ ትግል ሳይሆን የብሔር ፖለቲካን ማራመዳቸውን ያመለክታል። ሁለቱን ማጣመር የሚቻል እንኳ ቢሆን ሁለቱንም ያጣመረ ፕሮግራም መቅረጽ አያቅታቸውም ነበር። ግን ጨወታው ወዲህ ይመስላል። ለማንኛውም ገብሩ ራሳቸው ድርጅቱ ከተቋቋመ አንድ ዓመት በኋላ የካቲት 1968 በአመራሩ ተረቆ የጸደቀውን ማኒፊስቶ ወይም መርሐ ግብር ሲጠቅሱት እንዲህ ብለዋል “ …የአብዮታዊው ትግል ዓላማ ከባላባታዊው ሥርዓትና ከኤምፔሪያሊዝም ነጻ የሆነ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ማቋቋም ይሆናል” (ገጽ 51) እዚህ ጋር ምንም እንኳ ይህ ትግራይን ለመገንጠል ያቀደ ማኒፌስቶ በአባላቱ ዘንድ ውዝግብ ፈጥሮ ከ6 ወራት በኋላ ቢለወጥም ይህን በአረቀቁት የአመራር አባላት ውስጥ የተቋጠረውን ችግር መገንዘብና መታዘብ ይቻላል። ይህን እንኳን ሌላው ሰው ገብሩ ራሳቸው በገጽ 98 እንደሚከተለው ታዝበውታል።“በዚሁ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ድርጅቱን ይመራ የነበረው ማዕከላዊ ኮሚቴ ባሰራጨው የፖለቲካ ፕሮግራም ያካተተውን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የማቋቋም ዓላማ አንስቶ አልተቸም።…ማን በፕሮግራሙ እንደካተተው የመለየትና ኃላፊነት የመውሰድ ድፍረቱም አልነበራቸውም….ሁሉም እኔ አልነበርኩበትም የሚል መግለጫ ሲሰጡ ይደመጣሉ።” ረቂቅ ፕሮግራሙን እንዲያዘጋጁ ድርጅቱ በወቅቱ መድቧቸው የነበሩት ሁለት ሰዎች ግን መለስ ዜናዊና አባይ ፀሐዬ መሆናቸውን ገብሩ ጽፈዋል። ይህን የማስተዋል ጥቅሙ፣ ነገር መደበቅ፣ መቅጠ ሽምጥጥ አድርጎ በግልም ሆነ በቡድን መካድ ገና ከማለዳው አብሯቸው ተወልዶ ያደገ ልማድ መሆኑን ነው። እንጂማ በፕሮግራም የተጻፈን ነገር ማን እንደጻፈው ማን እንዳዘጋጀው ሳያታወቅ ቀርቶ አይደለም። ከዚህ መጽሐፍና ከሌሎችም መረጃዎች በመነሳት ሕወሓት ማለት አመራሩ ዐይኑን በጨው አጥቦ የሚቀጥፍበት፣ አባላቱም ያዩትን እንዳላዩ ሆነው ማለፉን የተካኑበት ብሔርተኝነት ብቻ አቆራኝቷቸው ተቻችለው የሚኖሩበት
ድርጅት ነው ማለትም የሚቻልበት ሁኔታ ይታያል።

ትግራይ ባንዲራ ነበራት እንዴ?

አቶ ገብሩ ብዙ የተዋደቁለትን ድርጅት አመራሩንና ጓደኞቻቸውን ሲተቹ አንዳንዱን ማፍረጥ እንደፈሩት ቁስል ቀስ ብለው የሚነካኩት መሆኑ ቢያስታውቅም አንዳንዱን ግን ያለምህረት ይሉታል። ለምሳሌ ይህንን በመጽሐፋቸው ገጽ 100 ላይ የታዘቡትን የድርጅታቸውን ጉድና ትዝብት እንመልከት፣ “መጀመሪያ ባንዲራው ከመቀየሩ በፊት የህወሓት ባንዲራ ጥቁርና ቀይ ነበር። “ቀይ መስዋአትነት ቢጫ ተስፋ ኮከብ ዓለም አቀፋዊነት በመጀመሪያ ባንዲራው ለምን ጥቁር ቀለም ተካተተ የሚል ጥያቄ ሲቀርብም በደፈናው የድሮው ትግራይ ባንዲራ ያን ይመስል ስለነበር ነው። የሚል መልስ ይሰጥ ነበር። ኖም ተሓህት/ህወሓት ይል ከነበረው ውጭ በታሪክ ትግራይ የራሷ ባንዲራ ነበራት የሚል ማረጋገጫ አላገኘሁም።” ብለዋል። መቸም አቶ ገብሩ ያላገኙትን አንባቢዎችስ ብንሆን ከየት እናመጣዋለን!ሉዓላዊነት በሶማልያም በኩል ነበር! አቶ ገብሩ ትሑት መሆናቸው ንግግራቸውንም ትችታቸውንም በወጉ ማድረጋቸው ያስመሰግናቸዋል። አንዳንዴ አፍታተው ወይም ጠበቅ አድርገው ሀሰቱን ሀሰት እውነቱን እውነት ቢሉ ከዚያም ርቀው ምነው አንዳንድ ነገሮች ማለት በቻሉ ያሰኛል ። ብዙ ማስረጃ እየደረደሩ የሞገቱትን ሐቅ እንኳ ደፍረው እንዲህ ነው ብለው አይቋጩትም። እያደር ህብረ ብሄራዊና ለሉዓላዊነቱ የሚቆረቆር ድርጅት እየመሰለ መምጣቱን መግለጽ የሚፈለገው ድርጅታቸው በሶማልያ ወረራ ጊዜ እንደሌሎቹ ወረራውን ማውገዝ ብቻ ይሆን ከደርግ መንግሥት ጋር ተሰልፎ ለእናት አገሩ ለመዋጋት ሀሳብ የነበረው መሆኑ እንዲመዘገብለትና የክህደት ታሪኩ እንዲፋቅለት ሲጥር መኖሩ ይታወቃል። ይህን በጨርፍታ አንስተው የተቹት አቶ ገብሩ የአቶ ስብሐት ነጋን አንዲት አብነት አንስተው እንደሚከለተው ጽፈዋል፦

“የድርጅቱ ሊቀመንበር ስብሐት ነጋ ሶማልያ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ስትሰነዝር ከደርግ ጋር በመሆን ጥቃቱን ለመመከት ሓሳብ አድርገን ነበር ቢልም በድርጅቱ ታቅፎ የነበረው አባል ሁሉ ይህን ዓይነት ጥሪ እንደተደረገ ፍጹም አያስታውስም። አባባሉም በሰነድ ሊደገፍ የሚችል አይደለም። ያ ቢሆን ኖሮ የተቃወሙትንና የመስፋፋት ፖሊሲውን ያደናቅፋሉ ያላቸውን የኦሮሞ ተወላጆች ያሰረውና የገደለው ዚያድ ባሬ ተሓህት/ህወሓት በሞቃዲሾ ተወካይ ኖሮት እንዲንቀሳቀስ ባልፈቀደ ነበር። የሶማልያ የይለፍ ፓስፖርት ለተሓህት/ህወሃት ባለሥልጣናት አባላት ባልሰጠ ነበር። ለተሓህት/ህወሃትን በጦር መሣሪያ ባላስታጠቀ ነበር። 93 እንዲያውም ገብሩ ይህኑ የሚያጠናክር መረጃ በሌላኛው ገጽ 117 ላይ ሰጥተዋል። “ የህወሃት ፖለቲ ቢሮው እኔና አው አውሎም ወደ ኤርትራ ሳህል ሄደን ..የሶማልያ መንግሥት የሰጠንንና በሻዕቢያ በኩል ተጓጉዞ እንዲደርሰን የተስማማንበትን ከ3ሺ በላይ ክላሺንኮቭና ሲሞኖቭ ጠመንጃዎች ከነመሰል ጥይቶቻቸው የመረከብ…ተልእኮም ሰጥቶን ነበር” እያሉ ጽፈዋል። ስለዚህ ድርጅታቸው የአገር ሉዓላዊነት ሊያሳስበው ቀርቶ ከወራሪው ኃይል ጋር ተስማምቶ መሣሪያ እስከመታጠቅ መድረሱን አጋልጠዋል። ይሁን እንጂ ሉዓላዊነትን በኤርትራ ብቻ ሳይሆን በሶማልያም በኩል አያይዘው ቢያነሱትና ቢያሰፉት መልካም ነበር። ለወረራውም ቢሆንኮ ኤርትራ እናት አገሯን ከእናት አገሯም ትግራይን ነው የወረረችው ሶማሌን ግን ጎረቤቷን ነው የወረረችው ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ። ወይንም አለን።

ኤርትራን እናስተኛት!?

ከገብሩ መጽሀፍ የሉዓላዊነት ፍሬነገሮች ሁለቱን ዋና ዋና ነገሮች አውጥተን ብንመለከት አንደኛው ቁጭታቸው ሌላኛው ስጋታቸው ነው። ስለተቆጩበት እንዲህ ይላሉ-፤ “ከሁሉም በላይ የሚከነክነው በወቅቱ ኢትዮጵያ በዓሰብ ላይ የነበራትን የባለቤትነት መብት ያመለምንም ድርድር ለሻዕቢያ አሳልፋ መስጠቷና በታሪክ ትልቅ ጥቁር ነጥብ መጣሉ ነው። ከ30 ዓመት በላይ የህዝቦችን ደም ያፋሳሰሰው ጦርነት በሰላም መፈታቱ ተገቢ ቢሆንም የኢትዮጵያ ጥቅሞች ሳይከበሩ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአንድ ኮንፈረንስ ለኤርትራ ነጻነት ሕጋዊ እውቅና መስጠቱ ግን ከፍተኛ ስህተት ነበር። የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች
ከዚህ ስህተት ተጠያቂነት ሊያመልጡ ባይችሉም ዋናው ተጠያቂ ግን ውሳኔውን የቀየሰውና ተቀብይነት እንዲያገኝ ቁልፍ ሚና የተጫወተው የህወሓት/ኢሕአዴግ አመራር ነው። (ገጽ 184)ስጋታቸው ደግሞ የኤርትራ መንግሥት መቸም አይተኛልንም የሚል ነው። “ ..እንደኔ አመለካከት በኢሳያስ የሚመራው
የሻዕቢያ መንግሥት ኢትዮጵያን ለመውረር ያነሳሳውን በአካባቢው የኢኮኖሚ፣ የወታደራዊና የዲፕሎማስያዊ የበላይነት የመጎናጸፍ ፍላጎት እስካሁና አልጠፋም።..ኢትዮጵያን በማዳከምና በመበታተን በአካባቢው የበላይ የሚሆንበትን ስትራቴጂ ቀይሶ በመንቀሳቀስ ከትግራይ ጀምሮ እስከ ኦጋዴን ትግል እያካሄድን ነው ብለው ለሚያምኑ….መጠጊያ ሆኖ ሥልጠናና ትጥቅ በመስጠት ኢትዮጵያን ለማተራመስ እየሠራ ነው፡፡ (ገጽ 427)
geberu asrat new book
እነዚህን የአቶ ገብሩ ሁለት ቁጭትና ስጋት ፈጣሪ ነገሮችን ብንመለከት። አንደኛ የፈሰሰ የቀይ ባህር ውሃ አይታፈስም። ጥፋተኞችን ለፍርድ ማቅረብም ቢሆን አገርና ዘመን ላይ አይፈረድም። በታሪክ ተጠያቂ የሚባለውም ነገር ታሪክ ማንን ጠይቆ እንዳፋጠጠ ስላማናውቅ ብዙ አንራቀቅበትም። እንኳን ሊያፋጥጣቸው ይኸው ታሪክ ሰሪዎቹ በቁማቸው መጽሀፍ እየጻፉ በቁማችን ያስነበቡናል። ኤርትራ ትወረናለች አትተኛልንም ማለቱም ጥሩ ስጋት ነው። ታዲያ እንድትተኛልን ምን ማድረግ ይበጃል? ኤርትራ ኢትዮጵያን መጥላት ትታ ራሷን ብቻ ብትወድ ኖሮ ይኼኔ የት በደረሰች ብሎ መምከር ይቻል ይሆናል። ግን ትግሬ ለአማራው፣ አማራው ለትግሬ፣ ኦሮሞው ለአማራ፣ አማራው ለኦሮሞው፣ እስካልተኙ ድረስ እኛም ለኤርትራ ኤርትራም ለኛ ትተኛለች ብሎ መጠበቅ አይሆንልንም። መቸም በዚሁ ገመድ ሲጠላለፉና ሲገዳደሉ የኖሩት ምሁራኑ ፖለቲከኞቻችን ይህን አፍታተው የሚያውቁት ጉዳይ ሊሆን
ይችላል። ይልቁንስ መበላላት የትም ካልቀረ ኤርትራውያን ተመልሰው መጥተው እዚሁ ከኛው ጋር እየተበላሉ ቢኖሩ ይሻላቸዋል ብሎ ከመቀለድ ጋር ቁጭት የሚፈውሰውን ስጋት የሚያስቀረውን ዘለቄታዊ መፍትሔ ማሰቡና ስለሱ መጻፉ ይበጃል።

የአቶ ገብሩ መጽሀፍ ጉልበቱ አንባቢን እስከዚህ ድረስ በሀሳብ መንዳቱ ነው። የሚያሳስበው ትልቁ ነገር የኤርትራ ጉዳይ የውስጥ ጉዳይ ሆኖ ይዝለቅ ወይስ እዚያው እየተገፋ ከባህር ይጥለቅ የሚለው ጥያቄ ነው። ቀኝ እጁ ኢትዮጵያዊ ግራ እጁ ኤርትራዊ እየሆነበት ግራ የተጋባ ትውልድ፣ አንዴ እንጣበቅ አንዴ እንላቀቅ፣ ከሚል ማለቂያ አልባ ፍልሚያ የሚገላገልበት መካሪ መጽሀፍ ማስፈለጉን የገብሩ መጽሐፍ ሹክ ይላል። ካለበለዚያ መሬት ወንበር የሆነ ይመስል እስኪ እሱን የተቀመጥክበትን መሬት አቀበልኝ አይባልም። ስለዚህ ይህን ችግር አሰብ፣ ወደብ፣ ባድመ፣ ሉዓላዊነት፣ የሚል ጥያቄ ብቻውን አይፈታውም። ከወንድማማቾች ጋር ዘላቂ ሰላም የሚመጣው፣ መሬት በመተሳሰብ ሳይሆን፣ እርስ በርስ በመተሳሰብ ነው። እሱን ደግሞ ስላቃተን ነው ወንድም ወንድሙን ወግቶ ድል ሊነሳ በረሃ የሚወርደው። በእነ አቶ ገብሩ መጽሐፍ የሚታየውም ይኸው ነው። ማንኛቸው ኢትዮጵያዊ ማንኛቸው ኤርትራዊ መሆናቸውን መለየት እስኪያቅታቸው ድረስ እንደቆቅ ሲጠባበቁና ሲተናነቁ ኖረው መጨረሻቸውና መጨረሻችን እንዲህ ሆኖ ቀርቷል። አቶ ገብሩ እንደሚነግሩን በድርጅታቸው ህወሃት የትግል ዘመን የሞቱት የትግራይ ልጆች ብዛት ወደ 54ሺ ይጠጋል። ይሄ ቁጥር ባንድ ሰሞኑ የባድመ ጦርነት ብቻ ካለቁት 70 እና 80ሺ ሰዎች ቁጥር ጋር ሲተያይ በራሱ የሚናገረው ነገር ይኖረዋል። የሚሰማው ከተገኘ! ለማንኛውም አቶ ገበሩ የድንበር ማካለልንና የአልጀርስ ስምምነትን አለመቀበልንና ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነቷን የምታረጋግጥበትን መንገድ የመሻት አስፈላጊነትን በመፍትሔነት ከዘረዘሯቸው ሀሳቦች ውስጥ ይካተታሉ። ይህ ሁሉ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በዚሁ ይቀራል ኤርትራም እንደወጣች ትቀራለች፣ ወይም እንደ አንዳንዶቹም የታባቷንስና በዚያው መቅረት አለባት ከሚል ስጋትና ፍላጎት የመነጨ ይመስላል። ያም ሆኖ ግን ገብሩ ምንም እንኳ ትልቁ ተስፋ ሰጪ ነገር አድርገው ባያጎሉትም በገጽ 478 ላይ በመፍትሄነት ከዘረዘሯቸውና በመጨረሻውና በ4ኛ ደረጃ ባሰፈሩት ላይ፣ “ሁለቱ አገሮች የላቀ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትስስር ለማድረግ ከተስማሙ፣ ህዝቡን በስፋት ያሳተፈና የቆየውን ባላንጣነት የሚያስወግድ ግንኙነት እንዲመሠርቱ ህዝቦቻቸው በነጻ የሚገናኙበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት” ብለዋል። የህዝብ ለህዝቡ ግኑኝነት መሻሻል (ኖርማይላዜሽን) በሰከነ መርሃ ግብር ተደግፎ ወደላቀ ትስስር ለማምራት በር ከፋች መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። በአቶ መለስ ወገኖችና በእነ አቶ ገብሩ ወገኖች በኩል የነበረው አንዱ ፈተና ይሄን የህዝብ ለህዝብ ሚዛን የመጠበቅ ችግር መሆኑንም ከጠቅላላው የአቶ ገብሩ መጽሀፍ ይዘት መረዳት ይቻላል። ሻዕቢያና ወያኔ ተብለው ትግራይ ትግሪኝ ሆነው አብረው ለአንድ ዓላማ ለሞቱት ሰዎች ቀላል ያልሆነው ኖርማላይዜሽን ለሌላው ሊከብድ መቻሉንም ከመመርመር ጋር፣ ይህን ሀሳብ ከመደገፍ የተሻለ ሌላ አማራጭ ያለ አይመስልም። በመጽሐፍ የተዘረዘሩት ሌሉቹ የአቶ ገበሩ አማራጮችም ከዚህኛው ጋር ባይሻሙ ይሻላቸው ነበር።

ወያኔን አትናገሩ ህወሓትን ግን እንደፈለጋችሁ!

ማለት የፈለጉትን አይበሉት ወይም ካሉት በላይ አይግለጹት እንጂ አቶ ገብሩ አስራት በተዋቃሚው ጎራ የሚታመሙበት አባባል ያላቸው ይመስላል። የምርጫ 97ን ወቅት እያሰቡ እንዲህ ጽፈዋል “የወቅቱ ተቃዋሚዎች የትግራይን ህዝብና ህወሓትን ያለመየት ችግር የሚጀምረው ከህወሓት ስያሜያቸው ነበር። ምንም እንኳን ህወሃት “ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ተብሎ ቢጠራም ተቃዋሚዎች ህወሃትን የሚጠሩት ወያኔ ብለው ነበር። ወያኔና ህወሃት አንድ አይደሉም። ወያኔ በትግራይ ህዝብ ሥነ-ልቦና ከፍተኛ ቦታ ያለው የአልገዛምና የእምቢተኝነት መገለጫ ነው። ህወሓትም ይህን ስያሜ የመረጠው የህዝቡን የቆየ ሥነ-ልቦና ለማጋራት ነው።” ወረድ ብለውም “ኢህአዴግ ራሱ በፈጠረውና አንዳንድ ተቃዋሚዎችም ባስተጋቡት የፍርሃት ድባብ ምክንያት ብዙ የትግራይ ተወላጆች በገዛ አገራቸው በስጋት እንዲኖሩና አማራጭ አጥተው የኢህአዴግን ከለላ እንዲሹ አድርጓቸዋል። ለህወሓት/ኢህአዴግ አንዱ የሥልጣን መሠረት
የሆነውም የእነዚህ በስጋት የተዋጡ ዜጎች ሥነ-ልቦና ነው።” (ገጽ 436)አቶ ገብሩ ይህን ይበሉ እንጂ በድርጅታቸውም በኩል ያለውንም የተጠያቂነት ችግርና ድርሻ አልዘነጉትም። ምክንያቱም ቀደም ሲል በመጽሐፋቸው በገጽ 140 ላይ የሚከተለውን ጽፈዋል “ የጠባብነት ጥያቄ ከተነሳ መጠየቅ የነበረበት
ከጅምሩ ብሔራዊ (ትግራዊነት?) ስሜትን ከአገራዊ አንድነትና ስሜት በላይ በማስጮኽ ይቀሰቀስ የነበረው አመራሩ ነበር። ድርጅቱ (ህወሃት) ከሌሎች አገር አቀፍና ብሔር ተኮር ድርጅቶችጋ ያደረገው ትስስር ደካማ ነበር። እንዲያውም ከመሸ በኋላ ከኢሕዴን ጋር ከፈጠረው ግንባር ውጪ፣ ለአስራ ሶስት ዓመታት ያህል በብሄር ተደራጅቶ በተናጠል የተጓዘበት ሁኔታ ነበር። የላብ አደሩ ፓርቲ ሲመሰረት እንኳን ብሔር ተኮር መልክ ይዞ (ትግራይ ብቻ ሆኖ?) እንዲደራጅ ተደርጓል፡፤ እነዚህ በአመራሩ የተቀየሱ ዓላማዎች አደረጃጀቶችና የትግል ስልቶች በታጋዩ ሥነ-ልቦናና አስተሳሰብ ላይ ተጽእኖ ነበራቸው። የታጋዩ አስተሳሰብ ቅድሚያ ተሰጥቶት የተገነባበት አቅጣጫ በብሔራዊ ወይም ክልላዊ ማንነቱ እንጂ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ዙሪያ አልነበረም። በአጠቃላይ የተከተልነው የትግል ስልት ዋና ማጠንጠኛም ብሄራዊ እንጂ አገራዊ ወይም መደባዊ አልነበረም” በወዲያና ወዲህኞቻችን ምህረት አልባ ነቀፋ አጣብቂኝ ውስጥ ያሉት ገብሩ ይህን ሲሉ በፍጹም ቅንነት የተናገሩት መሆኑን ያለጥርጥር መገመት ይቻላል። አቶ ገብሩ በዚህ መጽሐፋቸው ያወቁትን ሁሉ ተናግረዋል ማለቱ ጨርሶ የማይታሰብ ቢሆንም ሆን ብለው ያጣመሙት ነገር አለ ብሎ ለማሰብም ይቸግራል። የሚያግባባ ነገር ላይጽፉ ይችላሉ የጻፉት ግን ያመኑበትን ነው ብሎ ማሰቡን መጽሐፋቸው አይከለክልም።

ሉዓላዊነት እና ባለማህተቡ ኢህአፓ

ምንም እንኳ የድርሻቸውን ያህል ስህተትና ተጠያቂነትን የሚጋሩ ቢሆንም፣ ምንም እንኳ አብረዋቸው በእምነት ተሳፍረው እንድ ዓለም ሰፍተው እንደመንደር ጠበው፣ በክህደት የተንጠባጠቡ ቢኖሩባቸውም፣ ምንም እንኳ የእድሜና የርዕዮተ ዓለም ለጋነት እናም የዋህነት ለቅጽበት አሳስቶ የፈጃቸው ቢመስልም፣ በእናት አገር ኢትዮጵያ ፍቅር ግን ስተው ያልተገኙት የኢህአፓ ልጆች ታሪክ እያደር ይፈካል። እንደ ስልባቦት ከላያቸው የሚገፈፈው ስህተታቸው ሲነሳ እንደ ወተት የነጣው የልጅነት ልባቸው ወከክ ብሎ ይታያል። ያን ጊዜ ገድላቸው እንኳን በወዳጆቻቸው የኛ ልጆች አይደላችሁም ብለው በፈጇቸው ጠላቶቻቸው አንደበት ጭምር ይመሰከርላቸዋል። ኢህአፓዎች ሥርዓትን እንጂ አገራቸውን አለመክሰሳቸው ለሌሎች ሁሉ እንጂ ለራሳቸው ወገን ብቻ ያልሞቱ የማንነት ስግብግቦች አለመሆናቸውን እነሆ ታሪክ ይናገርላቸዋል። በገዛ ግዛቱ እንደ ውጭ ጠላት እያሳደደ በወጋቸው፣ በቀድሞው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ድርጅት፣ ፖሊት ቢሮ አባልና አንጋፋ ታጋይ አቶ ገበሩ አስራት ብዕር ሳይቀር እንደሚከተለው ተመስክሮላቸዋል!“ኢህአፓ በአብዛኛው የመኻል አገር ከተሞች በምሁራንና በወጣቶች ከፍተኛ ድጋፍ የነበረው ፓርቲ ቢሆንም በብሔር ድርጅቶች ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም። በተለይ ተሓትና ኦነግ የብሔር ብሔረሰብ አቋሞቹን በተመለከት በጥርጣሬ ይመለከቱት ነበር። …..ኢህአፓ በመርህ በደረጃ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት እስከመገንጠል ተቀብሎ ከብሔሮች ትግል ይልቅ ለመደባዊ ትግል ቅድሚያ መስጠት ይኖርበታል በማለቱና በኤርትራ ጥያቄ ቁርጥ ያለ አቋም ባለመውሰዱ በአንዳንድ ብሔር ተኮር ድርጅቶች በተለይ ደግሞ በተሓትና በሻዕቢያ የታላቋ ኢትዮጵያ (ግሬተር ኢትዮጵያ) አቀንቃኝ ወይም የንኡስ ከበርቴ ትምክህተኛ ፓርቲ የሚል ስም አሰጥቶታል። (አረጋዊ በርሔም በመጽሐፋቸው ገጽ 119 ያሉትን መጥቀሳቸውን ጠቅሰዋል)ገጽ 53። “ኢህአፓ በፕሮግራሙ ውስጥ የኤርትራ ጥያቄ በሰለማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት ከመግለጹም በላይ በዲሞክራሲያ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ከሰላማዊ ድርድር ውጭ ሌላ መፍትሔ ማፈላለግ እልቂት እንጂ ሌላ ውጤት እንደማይኖረው በተደጋጋሚ ይገልጽ ነበር። ይህ የኢህአፓ አቋም የኤርትራን ድርጅቶች የሚያረካ አልነበረም። የኤርትራ ድርጅቶች
ኢሕአፓ በሁለት ጉዳዩች ላይ ጠንከር ያለ አቋም እንዲኖረው ይፈልጉ ነበር። አንደኛው አቋም የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት መሆኑንና ቅኝ ገዢዋም ኢትዮጵያ እንደሆነች መቀበል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጥያቄው በኤርትራ ነጻነት መፈታት እንዳለበት መቀበል ነበር። እነዚህ ሁለት አቋሞች ከኢህአፓ ሊገኙ ባለመቻላቸው የኤርትራ ድርጅቶች በኢሕአፓ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬና ጥላቻ ነበራቸው። የኢህአፓ አቋም ባይዋጥላቸውም ኢህአፓ ደርግን ከማዳከም አንጻር ሊኖረው ከሚችለው አስተዋጽ ኦንጻር ድጋፋቸውን ይሰጡት ነበር። (ገጽ 54)
ሻእቢያዎቹ ይሰጡ ነበር የተባለውም ድጋፍ ወዲያ ተቋርጦ እንዲያውም ህወሃት ኢሕአፓን ወግቶ ሲያጠፋው እንደ ገብሩ አገላለጽ “ ሻዕቢያ አስተያየት ባለመስጠት የዝምታ ድጋፉን ሰጥትቶታል። ኢሕአፓ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ነው አፈታቱም በነጻነት መሆን አለበት፣ ብሎ ቁርጥ ያለ አቋም ባለመውሰዱ እሳት ሲጎርስ በአንጻሩ የሚፈልገውን አቋም ለወሰደው ህወሓት በመሪዎቹ በእነ ሮመዳን መሐመድ ኑርና በኢሳያስ አፈወርቂ አማካይነት ከፍተኛ ምስጋና ችረውታል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከኢሕአፓ ይልቅ ከህወሓት ጋር የተሻለ ግንኙነት ነበራቸው። (ገጽ 105) የኢህአፓ የወቅቱ ተቀናቃኝና የፖለቲካ ባላንጣ እንደነበረ የሚነገረው መኢሶን አመራር የነበሩት ዶ/ር ነገደ ጎበዜም በበኩላቸው በአዲሱ መጽሐፋቸው “ኢህአፓን ጨምሮ የየካቲት ሃይሎች እንደንጉሱ ዘመን አንዱን ወገን ብቻ እያወገዙ ከመቀጠልይልቅ የሁለቱምተጠያቂነትብቻ ሳይሆን የኤርትራ ግንባሮች በጠባብ አጀንዳ ተሰማርተው ከኤርትራም ከኢትዮጵያም ህዝቦች የጋራ ጠላቶች ጎን መሰለፋቸውን” ወደ ማውገዝ ተሸጋግረዋል ሲሉ የወቅቱን ሁኔታ ጽፈዋል። ኢትዮጵያውያን ሁልጊዜም መንግስታቸውንና ሥርዓቱን ለመቃወም ሲሉ የውጭ መንግሥታትን እርዳታ ይሹ ይሆናል። በ ኢትዮጵያዊነታቸው ግን አይደራደሩም። ሉዓላዊነት ማለት
እሱ ማለት ከሆነ በጣልያንም በሶማሌም በሻዕቢያም ዘመን ኢትዮጵያውያን ሲያከብሩትና ሲሞቱለት የኖሩት ጉዳይ ነው።

አሳሩ ገና ነው! መቸም እኛ ከገብሩ አናውቅም
የህወሃት ሰዎችም ደጋፊዎችም በኤርትራ ጥያቄና ወዳጅነት ላይ ሌላውን ሲከሱም ሆነ ሲወቅሱ ሲደመጥ መኖራቸው ይታወቃል። እሱስ ይቅር መቸም ፖለቲካቸው እንደሱ ነው። ወቀሳቸው ግን ኤርትራውያንን በፀረ ኤርትራዊነት እስከመክሰስ ከሄደ ምን ይባላል? ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ የሚለው የአቶ ገብሩ አስራት መጽሐፍ ከገጽ 125 እስከ 126 ያስፈረውን አንዲት አንቀጽ ቀንጭበን እንመልከት! በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የኤርትራ ድርጅቶች ከደርግ ጋር ሊደራደሩ ነው የሚል ጭምጭምታ በተሰማበት ወቅት ህወሃቶች እጅግ ተናደን ነበር። በአንድ በኩል ሻዕቢያ ተስፋ ቆርጦ ትግሉን አቋርጦ
እጁን ለደርግ ሊሰጥ ነው የሚል ስጋት ነበር፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሻዕቢያ በኤርትራ ነጻነት ጉዳይ ላይ ከደርግ ጋር ሊደራደር ነው የሚል ስጋት ነበር። ሁለተኛው ስጋት አግባብ አልነበረም፡፡ …ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እንዲሉ ባለቤቶቹ ችግራችንን በአንድነት ማዕቀፍ እንፈታለን ሲሉ፣ እኛ የለም ይህን መሆን የለበትም ብንል፣ የድርጅቶቹን ነጻነት ከመጻረራችን ባሻገር፣ የኢትዮጵያን ጥቅም እየጎዳን እንደነበር አልተገነዘብነውም ነበር። ከዚህ በመነሳት ሻዕቢያ ከደርግ ጋር ሊደራደር ነው የሚለውን ወሬ ስንሰማ ሻዕቢያን በተምበርካኪነት ፈርጀን መክሰስ ጀመርን። የኤርትራ ነጻነት እርግፍ አድርጎ ትቶ ከደርግ ጋር ሊታረቅ እንደሚችል ገመትን። የደርግና የሻዕቢያ ጌቶችም ሶቭዬቶች ስለሆኑ ሊያስታርቋቸው ይችላሉ የሚል ግምት ስለነበረንም ስለ ኤርትራ የምንጽፋቸው ጽሑፎችና የምናወጣቸው መግለጫዎች ሁሉ የኤርትራ ህዝብ ከነጻነት ባሻገር ሌላ መፍትሔው እንዳይቀበል የሚሰብኩ ነበሩ። እንዲያውም አንዳንድ የምናወጣቸው ጽሑፎች ከኢትዮጵያ ሳይሆን ከኤርትራ ድርጅት የመነጩ ይመስሉ ነበር።

ህወሓት ኤርትራን በተመለከት ካቀረባቸው ጽሑፎች አንዱ “ብረት ህዝቢ ኤርትራ ቁልቁል አፉ አይድፋእን!” “የኤርትራ ጠመንጃ አፈሙዝ ቁልቁል አይዘቀዘቅም!” በሚል ርዕስ የተጻፈው ነበር። ይህ በመለስ ዜናዊ የተጻፈው ጽሑፍ ምሁሩና አርቆ አሳቢው ኤርትራዊው ተስፋ ጽዮን መድኃኔ ለጻፈው የተሰጠ ምላሽ ነበር፡፡…ባለቤቶቹ ጉዳዩ ሳያሳስባቸው ህወሃት ተቆርቋሪ ሆኖ መቅረቡ ያስገርማል። ኤርትራዊ ስለ አንድነትን ሲጽፍ አንድነትም ለሁለቱም ህዝቦች የሚጠቅም ሆኖ ሳለ፤ መገንጠልን ደግፈን ያን ያህል ርቀን መሄድ ባልንበረብን ጉዳዩም ይበልጥ ለኤርትራውያን መተው ነበረብን። 126 አቶ ገብሩ በመጽሀፋቸው ከቀድሞ የትግል ጓዶቻቸው ያለ ይቅርታ የሚወቅሷቸውና አውራ ተጠያቂ የሚያደርጓቸው ሟቹን አቶ መለስ ዜናዊና አቶ ስብሐት ነጋን ነው። በተለይ እጅጉን በተማረሩበትና የመጽሐፋቸውም ርዕስና ማጠንጠኛ ያደረጉት የኤርትራ ጥያቄና የሉዓላዊነት ጉዳይ ዋነኛ ተጠያቂዎቹ እነዚህ ሁለት ሰዎች
ናቸው። አቶ ሥዩም መስፍን፣ ብረሃነ ገ/ክርስቶስ ኤታማዦር ሹሙ ሳሞራ የኑስ፣ ሟቹ የቀድሞ ደህንነት ሹሙ አቶ ክንፈ ገመድህንና የአሁኑ ደህንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ እንዲሁም የአቶ መለስ አማካሪ የነበሩ አቶ ሙልጌታ ዓለምሰገድን በተለያዩ ጊዜያት ኤርትራን አስመልክቶ በወሰዷቸው አቋሞቻቸውና ባሳዩት ተባባሪነት ታሪክ እንዲወቅሳቸው ያጠቆሯቸው ይመስላል። የስብሀትና የአቶ መለስ ግን የተለየ ነው።

ሻዕቢያዎቹ ከህወሓቶች ሁሉ አጥብቀው የሚወዷቸውና የሚያምኗቸው አቶ ስብሐት ነጋን መሆኑን ገብሩ ጽፈዋል። እንዲያውም ባንድ ወቅት ኢሳያስ ሞቅ ብሏቸው “ ስብሐት ነጋ ስልጣኑን ሳይለቅ አጥብቆ ቢሄድ ኖሮ የሻዕቢያና በሕወሃት መካከል አለመግባባት እንደማይፈጠር “መናገራቸውን በገጽ 223 ጽፈዋል። ስብሐት “ ከድርጅቱ የጸጥታ ክፍል /ሐለዋ ወያነ/ ጋር በመሆን ቀውስ ፈጣሪዎች በተባሉት ላይ የምርመራና የማጣራት ሥራ ሲያካሂድና አብዛኛውን ጊዜ የቅጣት ውሳኔ ሲሰጥ የነበረ የአመራር አባል ነበር።101” ያሉት ገብሩ ስብሐት በዚያ ልምዳቸው የተነሳ የራሳቸውን ሥልጣን ሲክቡና ሰዎቻቸውን ቦታ ቦታ ሲያዙ መኖራቸውን ይገልጻሉ። የኤርትራን ጉዳይን በሚመለከትም ስብሐት በገዛ ፍቃዳቸው መሬት አሳልፎ ይሰጡ እንደነበር እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል። “በ1990 ዓም ግጭቶች የተኪያዱባቸውን አንዳንድ የምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች ስብሐት ነጋ በሊቀመንበርነት ሥልጣኑ ከህዝቡ ፍላጎት ውጭ ከ1974 እስከ 1976 ባለው ጊዜ ለሻዕቢያ የሸለማቸው ነበሩ። ስብሓት መንደሮቹን ለሻዕቢያ አሳልፎ ሲሰጥ ከህወሃት የህዝብ አደረጃጀት አባላት ከፍተኛ ተቃውሞ ቢገጥመውም ማዕከላዊ ኮሚቴው ግን ለጉዳዩ እምብዛም ትኩረት አልሰጠውም ነበር።” 109አይ መለስ ዜናዊአቶ ገብሩ በጣም ሚወቅሷቸውን አቶ መለስ ዜናዊን ደግሞ እንዲህ ገልጸዋቸዋል “መለስ በወታደራዊና በሕዝብ አደረጃጀት እንቅስቃሴዎች ይህ ነው የሚባል ሚና ባይጫወትም ታጋዮችን በመቀስቀስና በመስበክ ጽሑፎችን ቶሎ በማንበብና በመጻፍ ረገድ ከፍተኛ ችሎታ ነበረው። ዐልፎ ዐልፎም ድንጋይ ዳቦ ነው ብሎ እስከማሳመን ይደርስ ነበር። አብዛኛው ገበሬና ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ የነበረው የድርጅቱ አባል በመለስ የስብከት ችሎታ እጅግ ይገረም ነበር። ይህ በአብዛኛው የድርጅቱ አባላት ተሰሚነት እንዲያገኝ ረድቶታትል፡፤ በ1969 ዓም ከጦርነት አፈግፍጓል ተብሎ በደረሰበት ብርቱ ሂስ ሞራሉ ዝቅ ብሎ የነበረውም መለስ ከሁለተኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በኋላ ሲያንሰራራና የሐሳብ መሪነት ለመጨበጥ ሙከራ ሲያደርግ ታይቷል።113ሌሎች አቶ መለስን እንዴት እንደሚያይዋቸው ሲጽፉም “አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘርአ ፅዮን መለስን ጽናት እንደሌለው ከመጠን በላይ ተናጋሪና ተግባር ላይ እንደማይገኝ ታጋይ ያዩት ነበር114” ብለዋል። ይሁን እንጂ አቶ መለስ ዜናዊ ገና ከጧቱ በሥራ አጋጣሚ ከተቀራረቧቸው “እነ ተወልደ ወ/ማርያምን ስዬ አብርሃን፣ ክንፈ ገ/መድህን ሳሞራ የኑስ ጋር የጠበቀ ዝምድና መስረታቸውንና ወደ ሥልጣን መፈናጠጣቸውን ጽፈዋል።

በመለስ ተወጥረው በተያዙበት የኢትዮ-ኤርትራ አንድ ስብሰባ ላይ የቀድሞ አቋማቸውን ሽምጥጥ አድርገው ሲክዱ አቶ ስዬ ንዴታቸውን መቆጣጠር ያቅታቸዋል ። በቃለ ጉባኤ የተያዘ ነገር እንዴት ይክዳሉ? መለስ ይቺን አጥተዋት አይደለም። ገብሩ እንዲህ ጽፈውታል- ስዬ “መለስ የቀድሞ ሐሳቡን
ለውጦ ሌላ ሐሳብ እያቀረበ እያጭበረበረ ነው፣ ይህ አኪያሄዱ ትክክል አይደለም፣ የአቋም መንሸራተቱን ለማረጋገጥ በቃለ ጉባኤው የሰፈረው ይታይልኝ ብሎ አለ። ….ቃለ ጉባኤው ቢታይ በአግባቡ ያልተመዘገበ ሆኖ ተገኘ። ምክንያቱም ቃለ ጉባኤ ያዡ በረከት ስለነበር አልመዘገበውም።” (ገጽ 340) መለስ ምናቸው ሞኝ ነው። እነ በረከትን ቃለ ጉባኤ እያስያዙ ካልሆነ እነዚህን ሰዎች የት ይችሏቸዋል። መቸም ተንኮለኛ ናቸው ። ተቃናቃኛቸው ስዬን በልማት ስም ከመከላከያ ሚኒስትርነት አንስተው የኤፍረት ስራ አስኪያጅ ሲያደርጓቸው ማዕከላዊ ኮሚቴ ብዙም ያላስታውለው ጉዳይ ነበር ይላል
የገብሩ መጽሐፍ። ለነገሩ ስመ ገናና የመሰሉት ስዬም ከዚህ ተነስተህ እዚያ ሂድ ከዚያ ወደዚህ ና ሲባሉ ዝምብለው የሚሽከርከሩ ኖረዋል እንዴ ያስብላል።መለስ ግምገማና ስብሰባ የሚወዱትን ጓደኞቻቸውን በስብሰባ እያጠመዱ እሳቸው በጎን ሥራቸውን ይሠሩ ነበር። ይህም ሌላው ጮሌነታቸው ነበር “ የሥራ አስፈጻሚውንና ማዕከላዊ ኮሚቴውን በማያባራ ውይይት ጠምዶ ዋነኛ የሥልጣን ማስጠበቂያ መሣሪያዎች የሆኑትን የጸጥታና የመከላከያ ኃይሎችን እያባባለ ድጋፋቸውን ለማሰባሰብ እየተቀንሳቀሰ እንደነበር መገንዘቡም ከባድ አልነበረም። (ገጽ 340)

መለስ ጮሌ ብቻ ሳይሆኑ ለሥልጣናቸው ሲሉ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይክዱት ነገር የለም። ሌላው ቀርቶ ለሥልጣን ያበቃቸውን የትግራይ ህዝብና ጓደኞቻቸውን እንኳ አሳልፈው ከመስጠት አልተመለሱም። አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ከሥልጣናቸው ሊባረሩ በደረሱበት አንድ ወቅት ድርጅታቸውን ህወሃትን ትተው የአማራው ወኪሎች ነን የሚሉ ብአዴኖችን ተቀላቅለው እንዴት ከጎናቸው እንዳሰለፏቸውና ህወሓቶችን ክስ እንደመሰረቱባቸው ይታያል። ነገሩ ሲወራ የቆየ ቢሆንም ገብሩም በዚህ መጽሐፋቸው አረጋግጠውታል። አዲሱ ለገሠ እነዚህ ሰዎች (እኛን) ጠባቦችና የበሰበሱ ናቸው- ብሎ ተናግሮ ነበር። 391 ….በተለይ አዲሱ አፈንጋጮች የበሰበሱና ጠባቦች ነበሩ እያለ የትግራይ ህዝብ በተለየ ሁኔታ ተጠቃሚ ሆኗል የሚለውን የመለስን የፕሮፖጋንዳ ጨዋታ ከመጠን በላይ ያራግበው ነበር። (ገጽ 392) ። በአቶ መለስ እርዳታ ከጀኔራሎችም እነ ባጫ ደበሌ ሳይቀሩ የትግራይ ገበሬዎች
የበለጠ ተጠቃሚ ሆነዋል ሁሉ ነገር ትግራይ ትግራይ ብቻ መሆን የለበትም ብለው እስከመናገር መድረሳቸውና ሥርዓቱን በጠባብ ብሔርተኝነት መክሰሳቸው ታይቷል።

አቶ መለስ የፓርቲ አባሎቻቸው ድጋፍና ድምጽ በጎደላቸው ወቅትም ባለቤታቸውና ማሰማራታቸውን ገብሩ ጽፈዋል። “አዜብ ለመለስ ድጋፍ ለመሰብሰብ በቤተ መንግሥት ቅልጥ ያለ ግብዣ እያዘጋጀች ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ታምበሸብሽ ነበር” ገጽ 351 ብለዋል። ከአቶ ገብሩ አጻጻፍ የዘወትር አቶ
መለስ አቋማቸውን በፍጥነት በመገለባበጥ የሚታወቁ የልባቸውን ካደረጉ በኋላ ፈጥነው ይቅርታ ተሳስቻለሁ ብለው አ ም ታ ተ ው እ ን ደ ሚ ያ ል ፉ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እየጠቀሱ ጽፈዋል። ከሁሉም የእግር እሳት ሆኖ የሚያቃጥላቸው ኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ዋስትና ሊሰጥ በሚችል መልኩ ሊጠናቀቅ ይችል ነበር ያሉት የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ባልፈለጉት መንገድ ድንገት መጨናገፉ ነው። እንደገብሩ ገለጻ ለዚህ ዋነኛ ተጠያቂው አቶ መለስ ናቸው እንዲህ ጽፈዋል፦መለሰ በዚህ ዓይነት የተወሳሰበና ተንኮል የተሞላበት አግባብ ብቻውን ያደረገውን የጦርነቱን ሂደት የማስቆም ውሳኔ ተገቢ እንዳልነበረና ይህን ለመወሰንና ለማወጅ የሚያስችል ሥልጣን እንዳልነበረው ኋላ ላይ ሂስ ሲቀርብለት “አዎን ስህተት ፈጽሜያለሁ ሆኖም ከጦር ግንባር ሳገኘው የነበረው መረጃ ጦርነቱን ለማስቀጠል ያስችላል የሚል ስላልነበረ ከዚህ ተነስቼ ጦርነቱን በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲቆም አውጃለሁ። የሥራ ባልደረቦቼን ማማከር ነበረብኝ ይህን ባለማድረጌ ተሳስቻለሁ።” አብዛኛዎቹ የማዕከላዊ ኮሚቴ ወታደራዊ እዝ አባላትና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አዋጁን የሰማነው እንደተራው ዜጋ በመገናኛ ብዙኃን ስለነበር አዋጁ የተጣደፈው ምናልባት በግንባር የነበሩት አዛዦች ግምገማቸውን አስተላልፈው መቀጠል እንደማይችሉ ስለገለጹ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ነበረን። ነገር ግን የግንባር አዛዦቹ ግምገማ ለማዕከላዊ እዙና ለሥራ አስፈጻሚው አባላት የደረሰው መለስ ጦርነቱ እንዳበቃ ካወጀ ከቀናት በኋላ ነበር። ይህ በመሆኑ የግንባር አዛዦቹ ግምገማ እርሱ ከሚፈለገው ውጭ እንደማይሆን አስቀድሞ በደጋፊዎቹ ተነግሮታል የሚል ግምት አለኝ። ሳሞራና ተከታዮቹ ከነዚህ ህወሓት ውስጥ ቴክኒካል አሬንጅመቱን ተቀብለን እንፈርም ከሚሉ ወገኖች ጋር ጥብቅ ግንኙነት ነበራቸው። 314-315

በተቃዋሚዎች ምሽግ ላይ እልል በል!- አብ ዱፋዖም አልል!

በአጠቃላይ የመንግሥት ሥልጣን ከመቆጣጠራችን በፊት ስንጠቀምባቸው የነበሩትን ጠላትና ወዳጅ የሚለዩ ፅንሰ ሐሳቦች መንግሥት ካቋቋምን በኋላም አላስወገድናቸውም ነበር። 186 አብ ዱፋዖም አልል- በምሽጋቸው ላይ እልል በል! በ002 ምርጫ ወቅት ኢህአዴግ ያልተገበረው የአፈና ስልትና ያላካሄደው ከባ አልነበረም። ወቅቱ ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ የተካሄደበት ሳሆን በተቃዋሚዎች ላይ ግልጽ ጦርነት የታወጀበት እንበር። ለነገሩ በዚህ የምርጫ ዋዜማ ህወሓት/ኢህ አዴግ አብአብ ዱፋዖም አልል- በምሽጋቸው ላይ እልል በል! የሚለውን የትጥቅ ትግል የድል ዘፈን በተደጋጋሚ ያስዘፍን ነበር። ይህ የዋዛ ቢመስልም መልዕክቱን በጥልቀት ለተመለከተው በተቃዋሚዎች ላይ እንደ ደርግ ጦርነት መታወጁ ግልጽ ነበር።463

ትግራይና ኤርትራ – አንቺው
ታመጪው አንቺው ታሮጪው

አቶ ገብሩ ስለ ህወሓትና ሻዕቢያ ግንኙነት አንድነትና ልዩነት ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል ” እውነቱን ለመናገር ግን ግኙነታችን ሞቅ ሲል ልክ እንደ አንድ ድርጅት በጋራ የምንሠራበት ግንኙነቱ ሲቀዘቅዝ ደግሞ በዓይነ ቁራኛ የምንተያይበት ሁኔታ ነበር እንጂ ግንኙነታችን ስትራቴጂያዊ አይደለም የሚለው አቋማችን ግንኙነትቻን ላይ ስለሚኖረ ተጽ እኖ በግልጽ ተዘርዝሮ አልተቀመጠም ነበር። ስለዚህ ከሻ ዕቢያ ጋር አሉን ያልናቸው የፖለቲካ ልዩነቶቻም የይዘት ሳይሆን የስም ብቻ እንደነበሩ እነዚህ ያደረግናቸው የፖለቲካ ለውጦች ያሳያሉ…በመሆኑም ሁለቱም ድርጅቶች በተጨባጭ ከቃላት ያለፈ የር ዕዮት ዓለምም የስትራቴጂም ልዩነት አልነበራቸውም ማለት ይቻላል። (ገጽ 236)ስለዚህ በሁለቱ መካከል የዓላማም ሆነ የስትራቴጂም ልዩነት ከሌለ ወደ ግጭት የወሰዳቸው ወይም ህመማቸው ታዲያ ምንድነው የሚል ጥያቄ ያጭራል። አቶ ገብሩንና መሰሎቻቸውን ሁሌም የሚያበግናቸው ነገር ከበረሃ ጀምሮ የሻዕቢያ ባለሥልጣናት ለህወሓት ባለሥልጣናት የሚያሳዩት ንቀትና የሚፈጽሙት የትዕቢት ድርጊት ነው። እንደገብሩ መጽሐፍ ያኔ ሁለቱ ሻዕቢያና ህወሓት ወዳጅ መንግሥታት በነበሩ ጊዜ ኢሳያስ ምንም የፕሮቶኮል አግባብ ሳይጠብቁ መኪናቸውን አስነስተው መቀሌ ይገቡ ነበር። ከካርቱም አልበሽርን ከአዲስ አበባ አቶ መለስን ይዘው መቀሌ ላይ ስብሰባ ይቀምጡ ነበር። ሌላው ቢቀር ፕሮቶኮል አለመጠበቁን ያማርሩ የነበሩት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶም ስለ ጉዳዩ ቅሬታቸውን መግለጻቸውን እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል”

“የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ነጋሶ በሽርና ኢሳያስ አፈወርቂ ያለ እርሱ እውቅና በበርካታ አጋጣሚዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡና ….365 ሲያሰኘን እንደ መንግሥት ሲያሰኘን እንደታጋይ ሆነን የፈለግነውን እንግዳ ወደ ኢትዮጵያ ስናስገባና ስናስወጣስ ነጋሶ ከፕሮቶኮልና ከአሠራር አንጻር ላነሳው ጥያቄ ክብደት ልንሰጠው በተገባ ነበር። በሽርና ኢሳያስ አዲስ አበባ ሳይደርሱ በቀጥታ ወደ መቀሌ መጥተው በወቅቱ ርዕሰ ብሔር ካልነበረው ከመለስጋ ሶስቱን አገሮች በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ብዙ ጊዜ ይነጋገሩ ነበር። 365ይህ የሚሆነው እንግዲህ አቶ ገብሩ ፕሬዚዳንት ሆነው በሚያስተዳድሯት የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ ውስጥ ነው። ይህም ሳይበቃ ለኤርትራ አዋሳኝ በሆነቸው የትግራይ ክልልና ድንበር ውስጥ በሚፈጸሙ አንዳንድ ቅሬታዎች የተቆጡት አቶ ኢሳያስ በአስመራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለነበሩት አቶ አውአሎም ዛሬ ሄጄ ገብሩን ሰድቤ እመጣለሁ ብለው እየነዱ እንደሚመጡ ገብሩ ጽፈዋል።
ዋነኛው ችግርና ለግጭት ያበቃቸው ምክንያት ግን የኢኮኖሚ ግኙነት መሆኑን አቶ ገብሩ በመጽሐፋቸው ለማሳየት ሞክረዋል። ይህም ቢሆን ኤርትራን አምራች ኢትዮጵያን ሸማች ከማድረግ ኤርትራን መሪ ኢትዮጵያን ተከታይ የማድረግ አዝማሚያ መታየቱ ዋነኛው ሰበብ ይመስላል። መጽሐፉ “ ሻዕቢያዎች ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ስለነበራችው ህልምና ነጻነታቸውን ባወጁ ሁለተኛው ወር ላይ ሐምሌ 1983 ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኮንፈረንስ ማዘጋጀታቸውን፣ በኮንፈረንሱም የኢትዮጵያን አየር መንገድ እንደገና አዋቅሮ ከኤርትራውያን ጋር የጋራ አክስዮን ኩባንያ እንዲፈጠር፣ ትግራይ ውስጥ የሚሠራውን የመንገድ ፕሮጀክት ሁሉ ኤርትራውያን እንዲገነቡት፣ ቀይ ባህር የንግድ ድርጅት በሚል አንድ የንግድ ኩባንያ እንዲቋቋም ማንኛውም ኤርትራዊ 500 ብር አውጥቶ አክስዮን እንዲገዛ የመሳሰሉት ውጥኖች መኖራቸው በመጽሀፉ ተመልክቷል፡፡ አስመራና መቀሌ ላይ ብዙ ምክክሮች ቢደረጉም ጨርሶ ሊስማሙ የሚችሉበት ሁኔታ ግን አልነበረም።ከዚያም አልፎ ወደ በጥቃቅን ጉዳዮች ሁሉ ወደ መጨቃጨቅና የንግድ ልውውጥና የገንዘብ ዝውውርን እስከ መገደብ ተደረሰ። ሁኔታው ከባለሥልጣናቱ እጅ ወጥቶ ወደ ህዝብና ሚዲያ ጆሮ መድረስ ጀመረ። ኤርትራን የሚከሱት አቶ ገብሩ አንዱን ምናልባትም የግንኙነት
መበጠሻ የሆነውን የመጨረሻ አጋጣሚ እንደሚከተለው ገልጸውታል፦

በሻዕቢያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከፍተኛ የፀረ- ትግራይ ቅስቀሳ ይደረግ ነበር።“በአንድ ወቅት ከትግራይ ወደ ኤርትራ የሚገባውን ማንኛውንም ሸቀጥ በመከልከል ጉሮሮአችንን ለማነቅ እየተንቀሳቀሱ ነው ነው የሚል የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ይደመጥ ነበር። ይህን የሰሙ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያንና የተወሰኑ የሻ ዕቢያ አባላትት እጅግ ተደናግጠው ምን እየተደረገ እንው? ይህ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻስ ወዴት እያመራ ነው?” የሚል ስጋት አድሮባቸው ነበር። ኢሳያስ የመጨረሻውን ስብሰባ ከኛ ጋር ሲያደርግም “የዚህ ዓይነት ዘመቻ እየተኪያሄደ ያለው ለምንድነው? ብለን ስንጠይቀው ለጥያቄያችን ያህን ያህል ክብደት
ሳይሰጠው “የምታነሱት ነገር በሚዲያ ሲተላለፍ ባልሰማም ሰዎች ሲንጫጩ ሰምቼ እስቲ በቴሌቪዥን የተላለፈውን አሳዩኝ ብዬ ምጽዋ ላይ ተመልክቼው ነበር። የተላለፈው መልዕክት ትንሽ የተጋነነ ቢሆንም መሠረታዊ ስህተት ግን አላየሁበት። አሁንም ትግራይ ጉሮሮአችንን ለማነቅ እየተንቀሳቀች ነው።
ብሎ አረፈው። 256ይህን ካለ በኋላም ኢትዮጵያ ኤርትራ ያቀረበቻቸውን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጥያቄዎች ብትመልስ እንድሚሻላት ደጋግሞ አሳሰበን። በኛ በኩል ደግሞ እየቀረበ ያለው ጥያቄ አግባብነት እንደሌለው ደጋግመን መለስንለት። “መልሳችሁ ይህ ከሆነ ከ እንግዲህ በሁለት አገሮች መካከል ግንኙነት ልሊኖር አይችልም አለ። እንዲያውም ድንበራችንን የሚያካልል ኮሚቴ(በአስቸኳይ) ይቋቋም የሚላ አሳብ አቀረበ። 256ወደ አዲስ አበባ ከተመለስን በኋላ አስመራ ላይ የሆነውም ሁሉ ለመግለጽ አስችኳይ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ እንዲጠራልን መለስን ጠየቅነው። ሻዕቢያ ወረራ ያካሂዳል ብለን እናምናለን አናምን ተብሎ በተሰጠ የፖሊት ቢሮው ድምጽ መለስ ዜናዊ ስዩም መስፍን ስዬ አብርሃ ስብሐት ነጋ ክንፈ ገ/መድህን ሲሆኑ ወረራ ያካሂዳል ብለን እናምናለን ያሉት ዓባይ ተወልደ ወልደ ማርያም፣ ዓለምሰገድ ገ/አምላክ ዓባይ ፀሐዬ እና ገብሩ አስራት ነበሩ። (ገጽ 258) በፀረ ሻዕቢያ አቋማቸው ይታወቃሉ የተባሉት አቶ ስዬ አብርሃ እስከዚያ ድረስ ታውረው ነበር ማለት ይሆን? እስከ ህወሓት አምስተኛው ጉባኤ ድረስ አልነቁም ነበር።

ከዚያ በኋላ የአቶ ገብሩ መጽሀፍ እንደሚያትተው አይቀሬው ጦርነት ተካሄደ። በጦርነቱ ዙሪያ በተያዘው አቅዋምና እሱን ተከትሎ በተነሳ ክፍፍል አቶ መለስ ተቀናቃኞቻቸውን በሙሉ እንዴት አድርገው ከፓርቲው እንዳባረሩ መጽሀፉ ይተረካል። መለስ የኢህአዴግ ጽ/ቤት እንዲታሸግና እንዲፈተሽ ማድረጋቸውን ለዚህም ደህነቱ አቶ ክንፈ ታዘው መፈጸማቸውን ያትታል። ከዚያ በኋላማ በቃ ከአቶ መለስ በስተቀር ሌላው የአመራር አባል ከራስ ጠጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ እየተፈተሸ ወደ ስብሰባ አዳራሾች መግባት ጀመረ ብለዋል ከአፈንጋጮች አንዱ የተባሉት አቶ ገብሩ አስራት፡፡ አቶ መለስ በብቸኝነት ወጡ!እሱ በህይወት ኖሮ ይህን መጽሀፍ ባሳተምኩ ኖሮ ደስ ይለኝ ነበር ያሉት አቶ ገብሩ ይህን መጽሐፍ ለማሳተፍ ያሰብኩት ከመለስ ዜናዊ እልፈት በፊት ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አልተሳካልኝም ብለዋል። እሱ በሕይወት ኖሮ መልስ ቢሰጥበት ደስ ባለኝ” በማለት ይህ ባለመሆኑ ቅሬታ ንደሚሰማቸው
ገልጸዋል። አቶ መለስን በህይወት ያሉትንም ሰዎች የሚተቹት በቂም በቀል ሳይሆን ሥርዓቱን ለመተችት እንደሆነም ጽፈዋል። መልካም ንባብ! (ዘኢትዮጵያ)

ይድረስ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ: ሕገ-መንገስቱ ተጣሰ፣ ሻለቃ መላኩ ተፈራ ታገተ

$
0
0

ለክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

ጉዳዩ፡- በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37(1) መሠረት ፍትሕ ለማግኘት ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበ አቤቱታ፤

1. በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 51(1) ሕገ-መንግሥቱን መጠበቅና መከላከል የፌዴራል መንግሥት ሥልጣንና ተግባር በመሆኑ፤

2. በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 74(13) ሕገ-መንግሥቱን ማክበርና ማስከበር የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣንና ተግባር በመሆኑ፤ አቤቱታዬን እነሆ ለሁለተኛ ጊዜ ለክቡርነትዎ ለማቅረብ ተገድጃለሁ፡-

ጅቡቲ በስደተኞች ሰፈር በምኖርበት ቤት ውስጥ ታሕሣሥ 26 ቀን 1985 ዓ.ም. ከምሽቱ 3 ሰዓት በቅጥር ነፍሰ ገዳዮች በተፈጸመብኝ የመግደል ሙከራ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኝ፣ በጅቡቲ ሆስፒታል ለ1 ዓመት ከ3 ወራት በሕክምና ስረዳ ቆይቼ በእግዚአብሔር ቸርነት ከሞት ልተርፍ ችያለሁ፡፡ በወቅቱ በጭካኔ ከተደበደብኩባቸው 9 ጥይቶች መካከል አንዱ ጥይት አሁንም በሰውነቴ ውስጥ ስለሚገኝ ከሳምባዬ ጋር በሚያደርግው ንክኪ በየጊዜው ለከባድ የሳል ሕመም የሚዳርገኝ መሆኑን በሐኪም ተረጋግጦ ተነግሮኛል፡፡ ለዚህ የወንጀል ድርጊት ተጠያቂ የሆኑት ሰዎች ግን ዛሬም የመንግሥት ሥልጣናቸውን መከታ አድርገው ከእሥር እንዳልፈታ የተለመደ የበቀል እርምጃ በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡ አልፎ ተርፎም ከማረሚያ ቤት ብወጣም ሕይወቴ በእነሱ እጅ እንደሆነና የሚፈልጉትን ማድረግ እንደሚችሉ ዛቻዎቻቸው እየደረሰኝ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ደምን በደም ቢያጥቡት ተመልሶ ደም ነው፡፡
pen
የሆነው ሆነ ይህንን ማመልከቻ ልጽፍልዎ የተነሳሁበት ዋና ምክንያት፣ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 25 እና በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 4 ‹‹ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው›› የሚለውን ድንጋጌ በሚቃረን መልኩ በዜግነቱ በዕኩልነት የመታየትና የመዳኘት ሕገ-መንግሥታዊ መብቴ በመጣሱ የተነሳ ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰብኝ፤ ፍትሐዊ ውሳኔ ይሰጡኛል በሚል እምነት ሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም አቤቱታዬን በጽሑፍ ለክቡርነትዎ ማቅረቤን ያስታውሱታል ብዬ አምናለሁ፡፡ እንደሚታወቀው በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 202(1) ማንኛውም ተቀጪ ፍርዱ የዕድሜ ልክ እስራት ከሆነና ታሳሪው ሃያ ዓመት ከታሰረ፣ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው በአመክሮ እንዲፈታ እንደሚወስን ተደንግጓል፡፡ በዚህ መሰረት እኔም በተከሰስኩበት ጉዳይ እጄ ከተያዘበት ከ22/8/1986 ዓ.ም. አንስቶ የተፈረደብኝን የእድሜ ልክ እሥራት (20 ዓመት) በ22/8/2006 ዓ.ም. ጨርሻለሁ፡፡ ሆኖም ከ23/8/2006 ዓ.ም ጀምሮ በማላውቀው ጉዳይ ሕገ-መንግስታዊ መታግቼ አሁንም በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት /ቃሊቲ/ ዞን አራት ውስጥ በእሥር ላይ እገኛለሁ፡፡ ማረሚያ ቤቱ የአመክሮ መብትን ለማክብር ታራሚው በእስር ቤት ቆይታው ያለውን ባሕሪ መገምገም እንዳለበት አውቃለሁ፤ በዚህ መሰረትም እኔ 20 ዓመት በእሥር በቆየሁበት ጊዜ የነበረኝ ጠባይ ተገምግሞ ያገኘሁት ውጤት እጅግ የሚያስመሰግነውን ዘጠና አምስት ከመቶ (95%) ነው፡፡ ይህም በማረሚያ ቤቱ ኃላፊ በአቶ አብርሃም ወልደአረጋይ ፊርማ ተረጋግጦ፣ ለፍቺ ከሌሎች ታራሚዎች ሠነዶች ጋር በ9/8/2006 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት ተልኮ የነበረ ቢሆንም፤ በ17/8/2006 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት ከተላኩት ሠነዶች መካከል የእኔን ብቻ ነጥለው መለሰው በማስመጣ ራሳቸው አቶ አብርሃም ወልደአጋይ በእጃቸው እንደያዙት በማረሚያ ቤቱና በፍርድ ቤቱ ሠራተኞች ተረጋግጦ ተነግሮኛል፡፡ ይህን የሚያስረዳ የፍርድ ቤቱ ማረጋገጫ ሠነድም ከዚህ ጋር ተያይዟል፡፡ እኔም ሆንኩ ቤተሰቤ፣ አቶ አብርሃም ወልደአረጋይን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ሊያነጋግሩን ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሊሳካልን አልቻለም፡፡

በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 19(3) በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት እንዳላቸው የተደነገገ ቢሆንም፤ እኔ ግን የተፈረደብኝን ቅጣት ጨርሼ ያለአንዳች ምክንያት ሕገ-መንግሥቱን በመጣስ እስከ ዛሬ (ነሐሴ 17 ቀን 2006ዓ.ም) ድረስ 115 ቀናት ወይም 2760 ሰዓታት ታግቼ እገኛለሁ፡፡

ክብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 365/1999 አንቀጽ 39(1) መሠረት በወጣው የፌዴራል ታራሚዎች አያያዝ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 138/1999 አንቀጽ 44(1) ስለማረሚያ ቤቱ ግዴታ እንደሚከተለው ተደንግጓል፡፡
‹‹ማንኛውም ታራሚ የእሥራት ጊዜውን ሲጨርስ፣ ይቅርታ ወይም ምሕረት ሲያገኝ ወይም ፍርድ ቤት በአመክሮ እንዲፈታ ትእዛዝ ሲሰጥ ማረሚያ ቤቱ ታራሚውን ወዲያው የመፍታት ግዴታ አለበት››፡፡
ነገር ግን እኔን ለመጉዳት ሲባል ብቻ ይህ ደንብ ሊጣስ መቻሉን ክብሩነቶ እንዲያውቁት ነው፡፡

እንዲሁም በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 9(1) የሕገ-መንግሥቱ የበላይነት እንደሚከተለው ታውጇል፡-
‹‹ሕገ-መንግሥቱ የበላይ ሕግ ነው፡፡ ማንኛውም ሕግ፣ ልማዳዊ አሠራር፣ እንዲሁም የመንግሥት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግሥት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም›› ተብሎ የተደነገገ ቢሆንም አሁንም እኔን ለመጉዳት ሲባል ብቻ ይህ የሀገሪቱ ሕገ-መንግሥት ተጥሷል፡፡
ስለዚህም እስከ ዛሬ ድረስ ከነቤተሰቤ የደረሰብኝን የረዥም ጊዜ ተደራራቢ ችግር በጥሞና ተረድተውልኝ በሕገ-መንግሥቱ የበላይነት ከእስር እንድፈታ ክቡርነትዎ ለማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ለአቶ አብርሃም ወልደአረጋይ ትእዛዝ እንዲሰጡልኝ በማክበር አመለክታለሁ፡፡
ሻለቃ መላኩ ተፈራ ይመር

እኛ ኢትዮጵያውያን ለውጥ እንፈልጋለን ስንል ሌላ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረስ ለውጥ እንፈልጋለን ማለታችን ነው

$
0
0

ስብሃት አማረ

Justiceእንደሚታወቀው ላለፉት 23 አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተቀምጠውን ዘራፊውን እና ጨቋኙን የወያኔ ጁንታ በጀመርነውና በተያያዝነው አዲስ አመት ለመቅበር የአንድነት እና የለውጥ ሃይሎች ልዩነቶቻችንን በማቻቻል በጋራ ልንታገል የሚገባና ለህዝባችንና ለሃገራችን ስር ነቀል ለውጥ ልናመጣ የሚያስችለንን ምዕራፍ  የምንጀምርበት አመት መሆን አለበት። ባሳለፍናቸው በርካታ  የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በእርስ መፈራረጅና መወነጃጀል  የወያኔን እድሜ ከማራዘም ውጪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያተረፈው  አንዳችም ነገር የለም። የአንድነት የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተቻቻለ የሃሳብ መግባባት ተቻችሎ እና ተግባብቶ ሁለገብ የትግል ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ ጠንክሮ መስራት ይጠበቅብናል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ኢትዮጵያውያን ለውጥ እንፈልጋለን ስንል እውነተኛና ዴሞክራስያዊ የሆነ ለውጥ እንፈልጋለን ማለታችን ነው ። ለለውጥ፣ ለፍትህና ለእኩልነት ነገ የምንጠብቀውንና የምንናፍቀውን የማይቀረውን ዴሞክራሲያዊ የመንግስት ለውጥ እስከምናገኝ ድረስ እንደትናንቱ ዛሬም አሁንም ድምጻችን እንዲሰማ እንጮሃለን።

በሃገሪቱ ያለውን ሁኔታ በትክክለኛው መንገድ የማያስቀምጡ የወያኔ ሚዲያዎች እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ዘገባዎችን በመስራት እና እውነትን ለመሸፋፈን በመትጋት የሕዝቦችን የማወቅ መብት ያለርሕራሄ እየተጋፉት/እየገፈፉት ይገኛል። ይህ በወያኔ የፕሮፓጋንዳ አካላት የሚፈጸም ማጭበርበር እና ማደናገር የገዢውን ፓርቲ ውስጣዊ ዝርክርክነት በይፋ ያሳብቃል። የሌለውን እንዳለ፤ ያልተሰራውን እንደተሰራ፤ ሕዝቡ የማያገኘውን አገልግሎት እንደሚያገኝ፤ ወዘተ በማድረግ በተጋነነ ሁኔታ ባልሆነ ስሌት በማባዛት በመቶኛ በማስላት በመደመር በማባዛት የሌለ ምስልን በመፍጠር ሕዝቡንና እርዳታ ሰጪ መንግስታትን ለማደናገር  ይሞክራሉ።

ፍትሕ  አጣን፣ ፍትሕ ዘገየብን፣ ፍትሕ ተነፈግን የሚሉ በርካታ ዜጎች ባሉበት አገር ውስጥ የፍትሕ ሥርዓቱ ተደራሽነት ወደር እንደሌለው የሚደሰኩሩ  የመንግስት ሪፖርቶችና መግለጫዎች የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ሕዝቡ በየፍርድ ቤቱ በተጓደለ ወይም በተነፈገ ፍትሕ ምክንያት ከላይ ታች ሲባዝን/ሲንከራተት እየታየ የማይመስልና የሌለ ነገር  ይነገራል፡፡ ከሰሞኑእንኳን ጋዜጠኞችና ጦማሪያኑ መንግስት ያወጣውን ህግ እንዲያከብር ስለጠየቁና በአደባባይ ስለጻፉ ግፍ እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ የአለም ህዝብ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ያወገዙት የወያኔ ተግባር ነው። በየእስር ቤቱ የሚማቅቁትንና የግፍ ግፍ እየተፈጸመባቸው ያሉት በነርዕዮት፣ ውብሸት፣ አንዷለም፣ እስክንድርና በሌሎችም ላይ እየተደረገ ያለው ስቃይና እንግልት ሳያንስ ሰሞኑን ደግሞ የሚወዱትን ህዝብ፣ የሚወዱትን ሃገርና የሚወዱትን ሞያቸውን በመተው የተሰደዱትን ጋዜጠኞች ማስታወስና እየከፈሉ ያሉትን መስዋእትነት መዘከር ያስፈልጋል። እኚህ የተሰደዱትና የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ያሸበሩት ሀገርና ህዝብ የለም፥ መንግስት ያወጣውን ህግ እንዲያከብር ለህግም ተገዢ እንዲሆን ጠየቁ እንጂ ።

ሌላው በየአካባቢው ‘ቀና ብለህ ባለስልጣን ተናገርክ፣ አግባብነት የሌለው ጥያቄ ጠየቅህ፣ ባለስልጣን ተዳፈርክ፣ ከሁለት በላይ ተሰብስበህ አየንህ’ ወዘተ እየተባለ የሚገረፈው፣ እንደ እንስሳ እየተገደለ የሚጣለው ኢትዮጵያዊ የሰራው ወንጀል የለም። በፍጹም አሸባሪም አይደለም! በየቦታው ቦንብ እየቀበረ ወይንም እያስቀመጠ አፈንድቶ ንጹሃንን ገድሎ ሲያበቃ ‘ሊያፈነዱ ሲሉ ተደረሰባቸው’፣ ወይንም ‘ፈንድቶባቸው ራሳቸውን ገደሉ’ ብሎ ውዥንብር የሚነዛው አሸባሪው ህወሃት እንጂ ንጹሃኑ ኢትዮጵያዊ እንደአይደለ የታወቀ ነው።

ተደጋግሞ ከተለያዩ የህግ ባለሙያዎች እንደተገለጸው አለምዓቀፍ ህግን በተጻረረ መልኩ ኦኬሎ አኳይንና አንዳርጋቸው ጽጌን ከመንገድ ያውም ከሰው አገር በጉቦ አስጠልፈውና አፍነው በመውሰድ ያው የተለመደ  ግፋቸውን እየፈጸሙ ይገኛሉ፣ ይህ የሚያሳየው ወያኔ እጁ ምን ያህል ረጅም እንደሆነ ነው። እነዚህ ሁለት የፍትህና የእኩልነት ታጋዮች ኦኬሎ አኳይንና አንዳርጋቸው ጽጌ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው እንደ ሌሎች የተቃዋሚ መሪዎች የበኩላቸውን ለማበርከት ደፋ ቀና ሲሉ በወያኔ መረብ ውስጥ ቢገቡም ለፍትህና ለእኩልነት እንዲሁም ለሃገር ነጻነት የከፈሉት አስተዋጽኦ መቼም የማይረሳ ታላቅ መስዋእትነት ያበረከቱ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው።

በአጠቃላይ ሲታይ ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢና አስጊ  የመሆኑን ያህል የወያኔ አባልና ደጋፊ  ‘ጤነኛ’ ለሃገር አንድነትና ለፍትህ የሚከራከረው ተቃዋሚው ወገን ደግሞ ‘አሸባሪ’  የሚል አጸያፊ ተቀጥላ በማበጀት ንጹሃኑን በየእስር ቤቱ በማጎር ህዝባዊውን ትግል ለማኮላሸት በመፍጨርጨ ላይ ይገኛል፡፡

ትግልን በጋራና በውህደት ማቀናጀት ወቅቱ የሚጠይቀው ሁኔታ እንደሆነ እየታዩ  ያሉት አንዳንድ ምልክቶች አሉ፣ በመሆኑም ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚል ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ የወያኔን ቡድን በሁለገብ ትግል በመፋለም በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ድርጅቶች ተጣምሮና አንድ ሆኖ መታገል እንዳለባቸው ከሰሞኑ የተወሰዱት የ3 ድርጅቶች የውህደት ንግግርና ስምምነት ያሳያል።

ወቅቱ ለጠየቀው የሀገር አድን ጥሪ ምላሽ በመስጠት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የአርበኝነት ትግል ችቦውን በመለኮስ እንደ ሻማ በመቅለጥ ብርሃን እየሰጠ ያለ ግንባር እንደመሆኑ መጠን የተለኮሰውም የትግል ችቦ ሳይጠፋ የታለመለትንና ለታቀደለን አላማ እስከግብ ድረስ እንዲዘልቅ የወያኔን አገዛዝ እድሜ ለማሳጠር ትግሉን በማጠናከር በአሁኑ ሰዓት ግንባሩ ከግንቦት 7 የፍትሕ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ጋር ውህደት ለማድረግ መስማማታቸው የሚያስመሰግንና ለሌሎችም የአንድነት ሃይሎች ተባብሮ የመስራትን ነገር ማሳያ በመሆን አስፈላጊ የሆነ ጥርጊያ መንገድ ይከፍታል/ከፍቷል። ውህደቱ ተጠናቆ የድሉን ፍሬ ተቋዳሽ የምንሆነበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን አምናለሁ።

ስለዚህ ኢትዮጵያውያን የአንድነት ሃይሎች በመተባበር፣ በመጣመርና በመዋሃድ ሃይልን፣ እውቀትን፣ ህብረትን እንዲሁም ገንዘብን በማቀናጀት የወያኔን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ምድር ወደ ከርሰ መቃብር ለአንዴና ለመጨረሻ አሸቀንጥሮ ወርውሮ ሃገርንና ህዝብን ለነጻነት ለማብቃት በጋራ መታገል ግዴታችን መሆኑን አውቀን በአንድነት ስርዓቱን ማስወገድ ማንኛውም ሃገሬንና ህዝቤን እወዳለሁ የሚል ዜጋ ሊነሳለት እና ሊተገብረው የሚገባ መሆኑን በመግለጽ የበኩሌን ሃሳብ ለማቅረብ እወዳለሁ::

አንድነት ኃይል ነው !!

ድል ለሰፊው ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!

 

 

 

“ነጻነትነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም!”

$
0
0

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች ያስተላለፈው ግልጽ መልዕክት

የተወደዳችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤

smneበቅድሚያ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የአክብሮት ሰላምታ በማቅረብ በትግሉ መስክ የምትከፍሉትን መስዋዕትነት የሚያደንቅ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ምህዳሩ እጅግ ጠብቦ የለም የሚባልበት ደረጃ በደረሰበት ወቅት በምታገኙት ስንጥቅ ሁሉ እየተጠቀማችሁ ለህዝባችሁ የብርሃን ጭላንጭል ስለምትፈነጥቁ አኢጋን ሥራችሁን ያደንቃል፤ ያከብራል፡፡ እኛ በሥራችሁ ስኬት የምንመኘው ለቆማችሁለት የፖለቲካ ዓላማ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት አቅቷቸው መፈናፈኛ ላጡትም የመወሰን ኃይል እንደምትሰጧቸው በማመን ነው፡፡

አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ የበርካታዎች ጥያቄ “ህወሃት/ኢህአዴግን በምን ዓይነት የተሻለ አስተዳደር እንዴት መለወጥ ይቻላል የሚለው ነው?” ይህ ጥያቄ “እኛ ኢትዮጵያውያን የዘርና የጎሣ ትንንሽ አጥሮቻንን አፍርሰን ሁሉን አቀፍ ትግል ለማድረግ ተዘጋጅተናል ወይ?” ብለን ራሳችንን መልሰን አንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ እንዲሁም ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠት ሁሉም ነጻ ሳይወጣ ራሳችንን ነጻ ለማውጣት እንችላለን ወይ? ብለንም እንድንጠይቅ የሚያስገድደን ነው፡፡ …

ሽንፈት ላይ እያተኮሩና የጠላትን ኃይለኛነት እየሰበኩ ድል አይገኝም፡፡ ልዩነትን እያራመዱ ኅብረትና አንድነት ተግባራዊ መሆን አይችልም፡፡ ለአገራዊ ዕርቅ እንሰራለን እያሉ በፓርቲ መካከል ከዚያም በታች በግለሰብ ደረጃ መተራረቅ ካልተቻለ ብሔራዊ ዕርቅ ከቀን ቅዠት አያልፍም፡፡ እያንዳንዳችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ፣ መኢአድ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ ኦህኮ፣ አረና፣ እና ሌሎች እጅግ በርካታ ፓርቲዎች የተቋቋማችሁትና ዓላማ ያደረጋችሁት ኢህአዴግን እየተቃወማችሁ ለመኖር እንዳልሆነ የፓርቲ ፕሮግራማችሁ ይመሰክራል፡፡ ወይም ዓላማችሁ የራሳችሁን የፓርቲ ምርጫ የማድረግና ፕሬዚዳንት (ሊቀመንበር)፣ ምክትል፣ ሥራ አስፈጻሚ፣ … በመምረጥ አዙሪት ውስጥ ራሳችሁን ላለማሽከርከር እንደሆነ ከማንም በላይ ራሳችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ከዚህ አንጻር በጥንቃቄና በብዙ ጥናት የተቀመጠው የፓርቲያችሁ ፕሮግራምና ዓላማ ለአገራችን አንዳች ለውጥ ሳያመጣ እንደዚሁ እንዳማረበት ቢቀመጥ ለሕዝብ የሚያመጣው ትርፍ ምንድርነው? እናንተንስ ለመቃወም ብቻ የምትሰሩ አያደርጋችሁምን? …… (ሙሉውን መልዕክት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)


“የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ እና የማዕከላዊ መንግስታት ምላሽ ከአፄ ዮሐንስ IV እስከ ኢህአዴግ”–የመጽሐፍ ግምገማ

$
0
0

የመጽሐፍ ግምገማ
ደራሲ፡- አለሙ ካሳ ረታ እና ሲሳይ መንግስቴ አዲሱ
ገምጋሚ፡- መንገሻ ረቴ እንዳለው
የግምገማ ቦታ፡- አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መኮንን አዳራሽ
ቀን፡- ጳጉሜን 2፣ 2005 ዓ.ም
የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ እና የማዕከላዊ መንግስታት ምላሽ ከአፄ ዮሐንስ IV እስከ ኢህአዴግ
እንደ መጽሐፍ ገምጋሚ በአዎንታዊነት የታዩኝን እና መካሪ ወይም ማስተካከያ የምላቸውን ጉዳዮች ለመግለጽ እሞክራለሁ :: መጽሐፉ መልዕክት ያዘሉ ዓረፍተ ነገሮችንና ገላጭ የሆኑ ፎቶግራፎችን በሽፋኑ የያዘ ሲሆን በአጠቃላይ በስድስት ምዕራፎች የተከፈለ ነው:: የመጀመሪው ምዕራፍ ታሪካዊ ዳራው ላይ ያተኮረ ሲሆን አሁን ራያ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ይኖሩ የነበሩ ቀደምት ህዝቦች ከቀደምት ነገስታቶች ጋር የነበራቸው ትስስርና ተጽዕኖ እንዲሁም ከአጎራባች ህዝቦች ጋር የነበራቸውን ግጭትና የአብሮነት ኩኔታ ያሳያል:: በዚህ ምዕራፍ በቀጣዮቹ ምዕራፎች የተንጸባረቁት የራስን በራስ ላስተዳድር ጥያቄያዊ መልዕክቶችም ተነስተዋል:: አምስቱ ምዕራፎች ከአፄ ዮሐንስ IV አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያን የመሩ ገዥዋች ለራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ የነበራቸው ምላሽ ምን እንደሚመስል ያተኮሩ ናቸው::
1. የመጽሐፉ አዎንታዊ ጎኖች
Raya Book
የመጽሐፉን ጭብጥ በመረዳት የተገነዘብኩት ጉዳይ የጸሐፊዎቹ ዓላማ የዘውግ/የብሔር ፖለቲካ – ethnocentric politics or ethno-nationalism የሚንጸባረቅበት የራያን የፖለቲካ ታሪክ መተረክ ነው :: ጽሁፉ ሲገመገም አንድ የታሪክ መጽሐፍ ሊያሟላቸው የሚገቡ የጥናት ስልቶችን በተለይም የመረጃ አጠቃቀምን ከሞላ ጎደል ይዞ ይታያል :: የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ የታሪክ መረጃዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በትግርኛ፣ በጣሊያንኛና በእንግሊዝኛ የተጻፉ ጽሁፎችን እንዲሁም ቃለ መጠይቆችን በሰፊው በመጠቀም ልፋት የሚታይበት ፍሬ ያለው ስራ እንዳከናወኑ መረዳት ተችሏል:: አለፍ ሲልም መረጃዎቻቸውን በግርጌ ማስታወሻዎች በማስደገፍ የጽሁፉን ተዓማኒነት ለማሳየት ጥረዋል::

ከታሪክ አጻጻፍ የሚጠበቀውን የክስተቶችን ምክኒያታዊ መንስኤና ውጤት በደንብ ማብራራት የተቻለበት በመሆኑ ቁምነገር ያዘሉ መልዕክቶች በመጽሐፉ ይገኛሉ:: ለምሳሌ በአፄ ዮሐንስ IV፣ በዳግማዊ አፄ ምንሊክና በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ አልገዛም የሚል አመጽ በራያዎች ሊነሳ የቻለው ራያዎች በራሳቸው ወግና ባህል መሰረት በሚመርጧቸው መሪዎች መመራት በሚሹበት ወቅት ነገስታቶቹ ያለምንም ስልት ከሌላ አካባቢ በሚመጡ ፊውዳላዊ ገዥዎች በሀይል እንዲተዳደሩ ስለሚደረጉ መሆኑን በበርካታ የታሪክ መረጃዎች በማስደገፍ በአሳማኝ ሁኔታ ተገልጧል:: መንስኤን ከውጤት ጋር በማገናኘት በኩል ስኬቱ የላቀ መሆኑን ካሳዩበት ክፍል ለማንሳት ያክል የራያ ህዝብ ወራሪው ጣሊያንን መደገፉንና በሌላ በኩል ደግሞ ጣሊያንን መውጋቱ ታሪካዊ ክስተቱን ከማሳየት በላይ ለምን ይህ ሊሆን እንደቻለም በመረጃ አስደግፈው ለታሪክ አንባቢያን በሚያረካ መንገድ ተርከዋል::

የክስተቶች ምክኒያታዊ መንስኤና ውጤት በሚገባ ከተገለጸበት የመጽሐፉ ክፍሎች ውስጥ ከሶስቱ አፄዎች ጋር የነበሩትን ግጭቶች በምሳሌነት በማንሳት በሚከተሉት አንቀጾች ማብራራት ይቻላል::

አፄ ዮሐንስ እ.አ.አ በ1879 ዓ.ም በቁጥጥራቸው አድርገው በተወካያቸውና በአካባቢው ባህላዊ መሪዎች ያስተዳድሩት በነበረው የራያ መሬትና ህዝብ አንድ ባለሟላቸውን ወደ ተወካያቸው ደጃች ገ/ኪዳን ዘሞ ሲልኩ የቆቦና የአካባቢዋ አስተዳዳሪ የነበሩት አባ ቦና ኩቢ ከአንድ ሸኝ ጋር የንጉሱን ባለሟል በሸኙበት ወቅት ባለሟሉ በመገደላቸው ምክኒያት አፄ ዮሐንስ አባ ቦና ኩቢንና ሰራዊታቸውን ለእርቅና ለደስታ ጨዋታ እንደሚፈልጓቸው በማታለል ሶስት ሺ የራያ ታጣቂ ገበሬዎችን በግፍና ተመጣጣኝ ባልሆነ መንገድ ጨፍጭፈዋል:: በዚሁ ምክኒያት ራያዎች የሚከተሉትን የግጥም ስንኝ መደርደራቸው በመጽሐፉ ተገጧል::

አትመኑት ትግሬን ቢምል ቢገዘት፣
ክርስትና አግብተው ኩቢን አረዱት፣
ያበሉታል እንጂ ያጠጡታል እንጂ
እንዴት ይገደላል ለሆነለት ልጅ::

ልብ ይበሉ አባ ቦና ኩቢ አንገቱ ከመቀላቱ በፊት ክርስቲያን እንዲሆን ያደረጉት እንዲሁም ክርስትና አባቱም ራሳቸው አፄ ዮሐንስ IV እንደነበሩ ፀሀፊዎቹ አስረድተዋል::

በዳግማዊ አፄ ምንሊክ ዘመንም ቢሆን ራያዎችን ረግጦ የመግዛቱ ሂደት በመቀጠሉ የማዕከላዊ መንግስቱ ሰራዊት በአንፃራዊነት ዘመናዊ መሳሪያ ከመያዙም ባለፈ በእጅጉ የተደራጀ በመሆኑ ራያዎች ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተዳደር የሚሞክሩት ሙከራ ግፍ በተሞላበት ጭፍጨፋ በመጨናገፉ በንዴትና በዕልህ ብቀላ ለማካሄድ መላ እየፈለጉ ባለበት ወቅት ከንጉሱ ጋር ቅራኔ ያላቸውን የህ/ሰብ ክፍሎች በማጥናት ኢትዮጵያዊያንን ከፋፍሎ ለመግዛት ሲያጠና የነበረውና ለወረራ ሲዘጋጅ የነበረው ጣሊያን ፐሪስኮ የተባለ ጣሊናዊ ሰላይ ወደ ራያዎች ላከ፡፡ ሰላዩም በእስልምና ሀይማኖት ረገጣ ምክኒያት በነገስታቶቹ ላይ ተቃውሞ የነበረውን የወሎውን ሸህ ጣላህ ከራያዎች ጋር በማገናኘት በሚስጢር ራያዎች በርካታ መሳሪያዎች ከጣሊያን እንዲያገኙ አደረጓቸው እና በሸህ ጣላህ መሪነት አሸንጌ ላይ የመንግስትን ጦር ለመውጋት ጦርነት ተካሄዶ ራያዎች በምኒልክ ሰራዊት ተሸነፉ፡፡ ከዚሁ በመቀጠልም የምኒልክ ሰራዊት ወደ አድዋ በዘመቱበት ወቅት የራያን ህዝብ በጥላትነት በማየት በአሰቃቂ ሁኔታ ጨፈጨፉት፤ ቤቱን አቃጠሉት፤ ሴቶችንም ደፈሯቸው፡፡ የግፉ መጠን የበዛባቸው ራያዎች በምላሹ የምኒልክ ሰራዊት ከአድዋ ጦርነት ሲመለስ በየዛፉና በየቋጥኙ ሆነው እያነጣጠሩ ከባድ እልቂት አወረዱበት፡፡ የምኒልክ ሰራዊት በአድዋ ጦርነት ላይ ካለቀው በላቀ በራያ መሬት እንደላቀ እንደነ ፍራንኬቲ የመሳሰሉ ፀሐፍት ተናግረዋል፡፡

የማዕከላዊ መንግስት እና የራያዎች ፍጥጫ በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመንም እንደቀጠለ በመጽሐፉ የተብራራ ሲሆን ራያዎች ከሌሎች አካባቢዎች ጋር የሚያደርጉትን ዉጊያ (በተለይም ከአፋር ጋር) ለማስቆም በሚል ሰበብ እነሱ የሚፈልጉትን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በራስ ጉግሳ አራያ፣ በደጃች አያሌው ብሩ እና በራስ ሙሉጌታ የተመሩ የመንግስት ወታደሮች በራያ ላይ አሰቃቂ ግፍ እንደፈጸሙ ተተርኳል፡፡

ይሁንና የደረሰባቸውን ግፍ ወደ ጎን በመተው ተንቤን ላይ ከጣሊያን ጋር በተደረጉት ሁለት ዙር ጦርነቶች ራያዎች የኃይለስላሴን ሰራዊት ደግፈው በቆራጥነት መዋጋታቸውን ኮሎኔል አሌሳንድሮ ዴልቫዬ የተባሉ የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ የጦር አማካሪ መኮንን የሚከተለውን የአይን ምስክር እንደጻፉ ተተርኳል፡፡
« ….. እነዚህ ራያዎች ያለማቋረጥ ትንፋሻቸውን ዋጥ አድርገው ይዋጋሉ፡፡ ደከመኝን፣ እንቅልፍንና ራበኝን አያውቁም፤ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሀይል አላቸው፡፡ ጠላታቸውን ከአካባቢያቸው ለማስወገድ፣ ህይወታቸውን ለመስጠት በፍጹም አይሳሱም፤ ፈጣንና ጠንካሮች እንዲሁም ቀልጣፎች ናቸው፤ የሰው ልጅ ያልፍበታል ተብሎ በማይገመተው ቦታ ሁሉ ተሸለክልከው ያልፋሉ፡፡ »

የሚያሳዝነው ግን እንደዚህ የመሰለ ጀብድ እየፈጸሙና ህይወታቸውን እየሰጡ ራያዎች በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ የጦር መሪዎች በደል ይደርስባቸው እንደነበር ፀሀፊዎቹ በመረጃ አስደግፈው እንዲህ ሲሉ ያወሩናል፡- « እንደ ሌሎቹ የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ወታደሮች በቂ ምግብ፣ ውሃ እና ለውጊያው አስፈላጊ የሆኑ ትጥቅና ስንቅም በበቂ ሁኔታ ከሌሎቹ ጋር እኩል [አይቀርብላቸውም ነበር]፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በራስ ሙሉጌታ የሚመራው በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ሰራዊት የሚከተለውን አሰቃቂ ግፍ በራያዎች መፈጸሙን ቀይ አንበሳ በሚል ርዕስ በታተመው መጽሐፍ ላይ የሰፈረውን ትረካ ጸሐፊዎቹ በሚከተለው ሁኔታ አንጸባርቀዋል፡፡

“ቆቦን በምናቋርጥበት ወቅት የጦር አለቃው ደጃዝማች መሸሻ ክብራቸው ተደፍሮ ነበር፣ ከመንደሩ ነዋሪዎች አንዱ በአደባባይ ከጓደኞቻቸው አንዱን ገድሎባቸዋል፡፡ የሰፈርንበት ቦታ ከቆቦ 3 ማይል ርቀት ላይ ወጣ ብሎ ነው የሚገኘው፡፡ መሸሻም ቁጭታቸውን ለመወጣት የነኳቸውን ሰዎች አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት በልባቸው ወስነዋል፡፡ በጧት ድምጽ ሳያሰሙ 5000 ሰዎችን አሰባስበው ወደ ቆቦ ጉዞ ቀጠሉ፡፡ ከተማዋንም እንዳልነበረች አድርገዋት ተመለሱ፡፡ ያጠቋቸውንና የደፈራቸውን በሙሉ በጎራዴ ቀነጠሱ፡፡ ሽማግሌዎች፣ ልጆች፣ ወንድ ሴት፣ ሳይለዩ ገድለዋል፡፡ እነኝህ ሊወድቁ የደረሱ ቤቶች በውስጣቸው ከ1200 በላይ ሬሳ ታቅፈው ቀርተዋል፡፡”

ይህን ከነገሩን በኋላ ጸሐፊዎቹ በመቀጠልም ሰባት የራያ ሽፍቶች በመያዛቸው በራስ ሙሉጌታ የሚመራው ሰራዊት የሚከተለውን አጸያፊ ድርጊት እንደፈጸመ ከላይ የተጠቀሰው መጽሐፍ ውስጥ ሰፍሮ እንደሚገኝ በሚከተለውን አስቀምጠው እናገኛለን፡፡

«በመጀመሪያ ጆሯቸውን፣ቀጥሎ እጆቻቸውን፣ ቆየት ብሎ ምላሳቸውን፣ ቅጣት ፈጻሚዎቹ የእነዚህ ያልታደሉ ጥፋተኞች እያንዳንዷን የሰውነት አካል በፍጥነት ሲቆራርጡ ማየት በጣም ይዘገንን ነበር፡፡ ያለ እግር ያለ እጅ በደም የተለወሰ መሬት ላይ የተቀመጠ ጭንቅላት፣ወገብና ደረት ብቻ ከአይናቸው በስተቀር ምንም የሚንቀሳቀስ ክፍል የሌላቸው የተቆራረጡ ገላዎች፣አሳዛኝ ፍጡሮች፡፡ አይኖቻቸውም ቢሆኑ ከዚያ ከፊታቸው ክብ ቦታ በጦር ተቦርቡረው እንዲወጡ ተወሰነ፡፡ ዙሪያውን የከበበው ሰራዊትም የበቀል ምኞቱን ለመወጣት እየጮኸ ድርጊቱ ሲፈጠም ያደምቃል፡፡”

ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ራያዎች ከጣሊያን ጋር ወግነው አረመኔውን የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴን ጦር ለመውጋት ቆርጦ የተነሳው፡፡ በዚህ ምክኒያት አምባራዶም ላይ በጣሊያን ወታደሮች ሽንፈት የደረሰበት የራስ ሙሉጌታ ሰራዊት በራያ በኩል ሲሸሽ ራያዎች ብቀላ እንዳካሄዱ የሀበሻ ጀብዱ በሚል ርዕስ መጽሐፍ ላይ ፀሀፊው አዶልፍ ፓርለሳክ እውነታውን በሚከተለው ሁኔታ እንዳስቀመጠ የአለሙ ካሳ ረታ እና የሲሳይ መንግስቴ መጽሐፍ የሚያበስረን፡፡

“[ራስ ሙሉጌታ] ከፈረንሳይ አገር የወታደራዊ ትምህርቱን አቋርጦ በመጣው ልጃቸው ታጅበው የአሸንጌን ሀይቅ በፈረሳቸው ላይ ተቀምጠው በመሻገር ላይ እንዳሉ ታልመው በተተኮሱ ሁለት የራያና የአዘቦ ሽፍቶች ጥይት ተመትተው ወደቁ፡፡ ከፊት ለፊቱ ከፈረሳቸው ላይ ዘንበል እያሉ የወደቁትን አባቱን ለመርዳት ከፈረሱ ላይ ዘሎ በመውረድ አባቱን ለመደገፍ ጎንበስ ያለውንም ልጃቸውን ታልመው ተደጋግመው የተተኮሱ ጥይቶች በአባቱ ሬሳ ላይ ጣሉት::”

በዚሁ በመቀጠል ወሳኝ የነበረውን የማይጨውን ጦርነት የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ሰራዊት ለማሸነፍ ሲቃረብ ከጣሊያን ጋር ሆነው ጉዳት በማድረስ ለጦርነቱ መሸነፍ ራያዎች ዋነኛ ምክኒያት እንደሆኑ የተተረከ ሲሆን ከዚህ በኋላ ግን የተወሰነው የራያ ጦር ከአርበኞች ጋር በሚስጢር በመገናኘት የጣሊያንን ሰራዊት ሲጨፈጭፍ እንደነበርና እንደማናኛውም ኢትዮጵያዊ አርበኛ እስከመጨረሻው እነደተዋጋ ተገልጧል፡፡ በዚህም ምክኒያት ወራሪው ጣሊያን ከአገር ከተባረረ በኋላ ሹመትና ሽልማት ያገኙ ራያዎች እንዳሉ ጸሀፊዎች የተሸላሚዎቹን ስም ሳይቀር ዘርርረው እስረድተዋል፡፡

መንስኤና ውጤትን በጥሩ የታሪክ መረጃ አስደግፈው ማቅረባቸውን ከጠቆምኩ በኋላ ፀሐፊዎቹ አንዳንድ የተደበቁ ጣሪካዊ ክስተቶችንም በጽሁፋቸው ማካተታቸው መጽሐፉን ይበልጥ ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡ ራያዎች በብዙ መንገድ በዘር ሐረግ ትስስር ካላቸው የወሎና የየጁ ህዝቦች ጋር እንዴት በፍቅር ይተያዩ እነደ ነበር እርስ በእራሳቸው ሲያደርጉት የነበረውን ግጭት እንደሚፈቱትና አልፎም በመረዳዳት ያሳዩትን ትብብር ለማተት ተሞክሯል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የራያዎችና የልጅ እያሱ ግንኙነት የሚስብ ታሪክ ነው፡፡ ለምሳሌ “የሸዋ መሳፍንቶችና ራስ ተፈሪ መኮነን (ኋላ ላይ አጼ ኃይለስላሴ የተባሉት) ልጅ እያሱን የቤተክርስቲያን ነገር ትቶ መስጊድ ድረስ በመሄድ እየሰገደ ነው፤ የተለያዬ ሀይማኖት ከሚከተሉ ወይዛዝርት ጋር አብሮ እየወጣ ነው በማለት በእሱ ላይ አመጽ ንዲነሳሳ ሴራ አሲረው” በልጅ እያሱ ላይ መፈንቅለ መንግስት ሲያደረጉበት ራያዎች ጋር ተደብቆ በመቆየቱና የልጅ እያሱን ልጅ ማለትም አንድ ጊዜ ወርቀልዑልሰገድ እያሱ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሸህ ሰይድ አህመድ እያሱ በመባል የሚታወቀውን ወደ አፋር አካባቢ ወስደው በመደበቃቸው ኋላ ላይ ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ የብቀላ እርምጃ በራያዎች ላይ እንደወሰዱ ጸሐፊዎቹ ሲያወሱ በሌላ በኩል ደግሞ ራያዎች የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴን ስልጣን አንቀበልም ብለው የልጅ እያሱን ልጅ ለማንገስ ከመሞከር አልፈው ንጉሳችን የልጅ እያሱ ልጅ ነው ብለው ማወጃቸውን ገልጠዋል፡፡

በመጨረሻም የወያኔ እንቅስቃሴ የተጸነሰውም ሆነ ከህዝባዊ አመጽነት ወደ ትግል የተሸጋገረበት በራያ መሆኑን በማስረዳት አትተዋል፡፡ የወያኔ ህዝባዊ አመጽ በራያዎችና በዋጀራቶች ትብብር የተካሄደ ሲሆን ከዚህ ህዝባዊ አመጽ እንቅስቃሴ በፊት በራያ ህዝቦች መካከል ሲከናወን የነበረ ዘመን ጠገብ የራያ ባህላዊ ፍልሚያ መሆኑን ተርከዋል፡፡ እንደ ፀሐፊዎቹ በወያኔ አባባል ህዝባዊ አመጽ ምክኒያት የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ሰራዊት ከብዙ ተጋድሎ በኋላ በለስ እነደ ቀናው እና የተለመደውን የብቀላ እርምጃ እንደወሰደ ተርከዋል፡፡ በጦርነቱ መጨረሻ ገደማ ከሰሜን የመጡ ትግሬዎች ህዝባዊ አመጹን እንደተቀላቀሉ እና የመሪነት ሚናውን እኛ እንውሰድ ማለታቸውንም አውስተዋል፡፡

ለማጠቃለል ያክል ጽሁፉ በርካታ ቁም ነገሮችን ያዘለ ከመሆኑም አልፎ አሁን ያለው ትውልድ ካለፈው ስህተት መማር የሚችልበትን እውነታ ፀሐፊዎቹ አለሙ ካሳ ረታና ሲሳይ መንግስቴ አዲሱ የበኩላቸውን ሚና ሲያበረክቱ የወደፊቱ የራያ ህዝብ እጣ ፈንታስ ምን መሆን አለበት ለሚለው የግል አስተያየታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

2. አሉታዊ ጎኖች

– በተወሰኑ ምዕራፎችና ገጾች ጸሐፊዎቹ የተጠቀሙት ትረካ በምናባዊ ልብወለድ እንደሚታወቀው ሁሉን አዋቂ(Omniscient) ባህሪ ማላበሱና የግል ገጠመኞች (Personal anecdots) መስለው መቅረባቸው የታሪክ ምርምርነቱን ልፋታቸውን አደብዝዞታል፡፡ ለምሳሌ በገጽ 140 ጸሐፊዎቹ እንዲህ ይላሉ፡- «ራያዎች ግን ይህንን የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው አይነት ፓሊሲ በፍጹም አይቀበሉትም ነበር ብቻ ሳይሆን አጥብቀውም ይቃወሙት ነበር፡፡ ኩሩና ታማኝ የአገር አንድነት ጠበቃ ለመሆንም የግድ አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሐይማኖት ወይም አንድ ወጥ የሆነ ታሪክና ባህል ሊኖረን የግድ አይደለም የሚል የጸና እምነት ነበራቸው፡፡ እንዲያውም ራያዎች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህች አገር የብዙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም የበርካታ ሀይማኖቶች አገር መሆኗን ጠንቅቀው የሚያውቁና በአግባቡም የተገነዘቡ ህዝቦች ነበሩ ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡”

ታሪክ የተደረገን ነገር በማስረጃ አስደግፎ ማቅረብ እንጂ በዘመነኛ ቃላት ራያዎች እንዲህ ያስቡ ነበር ብሎ መጻፍ ከታሪክ አጻጻፍ የወጣ አተራረክ ከማድረጉም በላይ የምርምር ውጤትነቱን ያቀጭጨዋል፡፡
– 15 ገጽ ያለው የተንዛዛ መግቢያ ከማዘጋጅትም ባለፈ የጸሐፊዎቹን እምነት የሚያንቀባርቅ ሀሳብ አስቀድሞ ማቅረቡ ከፈረሱ ጋሪው እንዲሉ ውጤትን አስቀድሞ መወሰን እና ማሳየት ስለሆነ አንባቢን አስቀድሞ ከመዝጋቱ ባለፈ መጽሐፉ የምርምር ስራ መሆኑን አስቀድሞ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ያስገባዋል፡፡
– በመካከለኛው ዘመን አማራ ተብሎ ከሚታወቀው ህዝብ ጋር የአስተዳደርና የባህል ተቀራራቢነት እንዲሁም የቋንቋ አንድነት የነበራቸውና አሁን ራያ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ይኖሩ የነበሩ የአንጎትና የቀዳ ህዝቦች እንዲሁም የበዕደማሪያም ሰሪዊትና የዘር ሐረጋቸውን ከጎንደር ከሚመዙት የዘወልድ ህዝቦች ከዶባዎችና ከራያ ኦሮሞዎች ጋር የነበራቸውን ውህደት በማመልከት በኩል የተነሳ ጉዳይ ስለሌለ የቅጽ ሁለት ህትመት በቀጣይ የማያካትተው ካልሆነ በስተቀር መጽሐፉ የራያን ታሪክ ጎደሎ ያደርገዋል፡፡
– በመጽሐፉ አነዳንድ ክፍሎች ከታሪክ ጽሁፍ የማይጠበቁ ጸሐፊዎቹ ጀማሪ መሆናቸውን የሚያሳዩ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ በገጽ 71 እንዲህ ተብሏል፡- «በዚህ መድብል ፀሐፊዎች እምነት ይህ ከአገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚካተት ስለሆነ “እውነተኛ የቅኝ ግዛት” ቦታዎች የሚለውን ሐረግና ተከትሎት የሚመጣውን ሐሳብ በፍጹም አይቀበሉትም፡፡”

የታሪክ ምርምር እውነትን ፈልፍሎ አውጥቶ በመረጃ አስደግፎ መተረክ ነው፡፡ ታሪካዊ ትንታኔም ካስፈለገ ከሀቁ ተመርኩዞ ነው የሚተነተነው፡፡ አገር ግንባታን እዚህ ላይ ምን አመጣው ? አገር ግንባታ ወይም ማፍረስ የተመራማሪ ሳይሆኑ የፖለቲከኛ ማጭበርበሪያ ቃላት ናቸው ፡፡

– ከገጽ 83 – 94 ያሉት 12 ገጾች የራያ ህዝብ በራስ ወሌ ሲተዳደር ከነበረበት ወደ ራስ ሚካኤል አስተዳደር እንዲሆን መደረጉንና ራያዎች በየጁ፣ በላስታ፣ በዋግና በትግራይ ተከፋፍለው እንዲተዳደሩ መደረጉን ለማስረዳት የተሄደበት አተራረክ ለአንባቢ አሰልቺ በሆነ መንገድ ስለቀረበ በ2 ገጽ ጨምቆ ማቅረብ የሚቻል ነው፡፡

– ለአካዳሚክ ማህበረሰብ ብቻ ቀላል የሆኑ የእንግሊዝኛ ቃላት እነደወረዱ ማስቀመጥ ከአካዳሚክ ውጭ የሆነውን አንባቢ ስለሚያደናግር ለምሳሌ በገጽ 128 ወታደራዊ ጁንታ የሚለውን ደርግ/ወታደራዊ ሸንጎ ብሎ መተካቱ ይመረጣል፡፡

– በገጽ 148 የራያ ህዝብ ከጣሊያኖች ጋር ጥብብር ያደረገባቸውን ወቅቶች ባንዳ እንደማያሰኝ ለማስረዳት ፀሐፊዎቹ ያደረጉት ሙግት የሚከተለውን ይመስላል፡- « … እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሀገር እየመሩ የሚገኙ ፖለቲካኞች ሳይቀር የጠባብነት አሊያም የባንዳነት ስሜት እያንጸባረቁ ባለበት ሁኔታ ያውም አብዛኛው የራያ አካባቢ ህዝብ እንደሌሎቹ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ሁሉ ማድረግ ያለበትን ነገር ሁሉ አድርጎ በማለፉና ጥቂት የሚባሉ የራያ ተወላጆች ከጣሊያን ጋር ወግነው ቢገኙ ምኑ ነው የሚያስገርመው? ከሌላው ኢትዮጵያዊ ባንዳስ በምን ስለሚለይ ነው ይኸን ያህል ተጋኖ እንዲቀርብ የሚደረገው? እያለ ይቀጥልና በግርጌ ማስታወሻ ደግሞ “የግንቦት 7 ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቀደም ሲል ከወራሪው የኤርትራ መንግስት መሪዎች በቅርቡ ደግሞ ከግብጽ ፖለቲከኛች የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸው በመገናኛ ብዙሃን ሰዎች ሲገለጽ የሰነበተ ጉዳይ ነው” …. አሁንም በመቀጠል ኦብነግ፣ ኦነግ እየተባለ በተመሳሳይ ተጠቅሰዋል፡፡

ይህ አንድ ገጽ የማይሞላ ክፍል የመጽሐፉን በርካት ኩምነገሮች ወደታች እዘጭ አድርጎ የጣለበት የኢህአድግ የፖለቲካ ጠመቃ/political brainwashing/ የፈጠረው ክፉ ተጽዕኖ ነው፡፡

በመጀመሪያ ነገር ራያዎች ለምን ጣሊያንን ሊተባበሩ እንደቻሉ በጥሩ መረጃ በማስደገፍ በምክኒያታዊነት የተረዳንበት የጽሑፍ ክፍል አለ፡፡ ሲቀጥል ግለሰብ ወይም በቁጥር ብዙ ያልሆኑ የተወሰኑ ግለሰቦች ከጥቅም ጋር በተያያዘ ከጠላት ጋር የሚያደርጉት ትብብር ነው አንጂ ባንዳ የሚያስብለው እንደ ህዝብ የሚዋጋ ከሆነ የሚዋጋበትን ምክኒያት መግለጽ እንጂ ህዝቡን በሞላ ባንዳ ልትለው አትችልም፡፡ ይህም ሆኖ ህዝቡን ባንዳ ብሎ የሚጠራ ካለ ጣሊያን በወረረ ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ ከጣሊያን ጋር ወግነው የነበሩ ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን በትይዩ በመጥቀስ የኢትዮጵያ ገዥዎች ቱርፋት እንጂ ጣሊያንን የወገኑት ያልተማሩት ህዝቦች የባንዳነት አባዜ አለመሆኑን ለማስረዳት በተቻለ ነበር፡፡ የኢህአዴግ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ መንዣ የሆኑ ሚዲያዎችን ዋቢ አድርጎ ግንቦት 7፣ ኦነግና ኦብነግን ከራያ ታሪክ ጋር አገናኝቶ ማቅረብ ግን ፈጽሞ የማይገናኝና የታሪክ ምርምርነቱን ክብደት የሚያቀለው ነው፡፡ ድርጅቶቹ ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዴሞክራሲ ብለን ነው የምንታገለው ስለሚሉ ስለነሱ መጻፍ ካስፈለገ ከራያ ታሪክ ጋር ሳያዘበራርቁ ለብቻው መጻፍ ይቻል ይሆናል፡፡ ስለሆነም በራያ ህዝብ ስም የመጽሐፉን ገጽ 148 በቀጣይ እትም ላለማካተት ቃል ቢገባ መልካም ነው፡፡

– በገጽ 186 እና 187 “የሰሜን ትግራይ ሰዎች የወያኔን አመጽ የተቀላቀሉት የቀረችባቸውን የስልጣን ፍርፋሪ ለማስመለስ ሲሆን ራያዎች ግን መሰረታዊ የሆነውን መብታቸዉን ለማስከበር ነበር” የሚለው ለአንዱ ህዝብ ወገንታዊነትን ስለሚያሳይ የተመራማሪነትን ብቃት ስለሚያጎድፍ በተገቢ ቃላት አስተካክሎ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡

– በምዕራፍ ስድስት «የኢህአዴግ ስልጣን መያዝና የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ» በሚለው ክፍል የግል አስተያየት በዝቶበት ይታያል፡፡ ይህ ከሚሆን የተለያዩ ወገኖችን በህወሐት ትግል የተሳተፉ የራያ ልጆችንና ትግሬዎችን ጭምር በሰፊው ቃለ-መጠይቅ አድርጎ ማብራራት ቢቻል ጥሩ ነበር፡፡ በርካታ የራያ ሰዎች ልጆቻቸውን ኃየሎም እያሉ እስከመጥራትና በጥግሉም እስከመሳተፍ ለድርጅቱ ፍቅራቸውን ያሳዩበትን እና በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቱ መልኩን ቀይሮ ተግባራዊ ሂደቱ ሌላ የሆነበትን ክስተት በማስረጃ አስደግፎ ማቅረብ ላይ ውስንነት ይታይበታል የሚል እይታ አለኝ፡፡

– በመጨረሻም ራያ እንደነ ስልጤ የራሱ አስተዳደር ሊያገኝ ይገባዋል የሚል አስተያቶች መንጸባረቃቸው ሁለት አይነት ችግሮችን እንዳዘለ ይታየኛል፡፡ በመጀመሪያ እንደ ምርምር ስራ እውነትን አስቀምጦ ማለፍ ብቻ ተመራጭ ስለነበር በሌላ ፖለቲካዊ ነክ ጽሁፎች ማንሳት ሲቻል ታሪክንም፣ ፖለቲካንም ጥያቄንም አንድ ላይ ማቅረቡ ስራዉን የምርምር ጽሁፍ ነው ለማለት አስቸጋሪ ያደርጋል፡፡ ሁለተኛውና ወሳኙ ግን የራያ ህዝብ አሁን ያለበት ችግር በአንድ ቡድን ፍጹም የላይነት ተጨንፍሮ የተያዘው አስተዳደር ተቀይሮ ፍትሃዊ አስተዳደር ሲይዝ ከአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ጋር የሚፈታ እንጂ እየተደረገ እንደምንመለከተው ተላላኪ ለመፍጠር ተብሎ በዚሁ ጠባብ ቡድን « ራስህን በራስህ አስተዳድር » ተብሎ ምላሽ እንዲሰጥ ማሰብ ያው የኢህአዴግ የፖለቲካ ጠመቃ ተጽእኖ የፈጠረው ጥያቅ ከመሆን ለራያ ህዝብ የሚፈይደው ጥቅም የለም የሚል አስተያየት አለኝ፡፡

ማሳሰቢያ፡- መጽሐፉን ከደረሱት አነዱ፣ ሲሳይ መንግስቴ አዲሱ፣ ከልጅነት እድሜው ጀምሮ ከብአዴን ጋር ሆኖ ደርግን ለመጣል የተዋጋና ኃላ ላይም በአማራ ክልል በቢሮ ሃላፊነት ደረጃ ስርዓቱን ሲያገለግል ቆይቶ የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የነፃነት ጥያቄዎችን በተለያዩ መድረኮች በማቅረቡ ምክኒያት በተለይም የህወሐት አመራሮች ብአዴንን እንደ ፈለጉ ማሽከርከራቸው ተገቢ እንዳልሆነ በግልጽ መናገሩ ተጽእኖ እንዲደርስበት ስላደረገው በራሱ ፈቃድ ስልጣኑን ትቶ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር ሆኖ መስራትን መርጦ እየሰራ ይገኛል፡፡ የሚያሳዝነው ይህን መጽሐፍ አሳትሞ እንዳወጣ አቻው ባልሆኑ ሆድ አድር ካድሬዎች በእጂ አዙር ከድርጅቱ እንዲባረር ከመደረጉም በላይ በህወሐት ካድሬዎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ በተለያዩ ወቅቶች እየደረሰበት ይገኛል፡፡

ሕወሐቶች መረዳት ያለባቸው ጉዳይ ሲሳይ ከአካዳሚክ አንጻር ምንም ይሁን ምን ዓየነት ጽሁፍ ቢጽፍ ጽሁፉን የመውደድ ወይም የመተቸት የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ሆኖ በሲሳይ መንግስቴ ላይ በሚቃጣ ማናቸውም ዓይነት እርምጃ ግን የራያ ህዝብ ከሲሳይ መንግስቴ በስከጀርባ መሆኑን መዘንጋት የለባቸውም፡፡ ባጭሩ ሢሳይ ጋር መጣላት ከራያ ህዝብ ጋር መጣላት ነው፡፡

“ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ” –የለንደኖቹ ልማታዊ “ካኅናት” ወያኔያዊ ዘጋቢ ፊልም አቀናበሩብን!

$
0
0

ወንድሙ መኰንን፡ ኢንግላንድ መከረም ፯ ቀን ፪፲፻፯ ዓ.ም
መግቢያ
london Churchእንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ። መባል ስላለበት ነው። ያለፈውማ ዓመት አንደኛውን ጥቁር ዓመት ተብሏል። ሲያንሰው ነው። ወያኔ ከመቼው በበለጠ ጥቃቷን በኢትዮጵያ ልጆች ላይ በሁሉም አቅጣጫ ያጧጧፈችበት ዓመት ነበር። ነጻውን መገናኛ ብዙሀን ከጨዋታ ውጪ አድርጋለች። ብዙ ጋዜጠኞች በማሠሯ ወህኔ ቤቱ ጠቧል መሰለኝ፣ አሁን አሁን የያዘችው ዜዴ፣ በቁጥጥሯ ሥር ከሌሉ፣የፋሺን ጋዜጠኞችም ሳይቀሩ ማዘዣ ሳይደርሳቸው፣ በሬዲዮዋና በጋዜጦቿ “ከስሼአቸዋለሁ!” በማለት ፣ ነጭ ሽብር እየነዛችባቸው በርግገው ከአገር እንዲጠፉ ማሳደዷን በሰፊው ተያይዛቸዋለች። በዓመቱ መጨረሻ ወር ብቻ 21 ጋዜጠኞች ተደናብረው አገር ጥለው እግሬ አውጪኝ ብለዋል።ሲሸሹም እያየች አታስቆማቸውም። ብቻ ሲወጡላት፣ “እስየው ተሰደዱልኝ!” ብላ “ደቁሴ ንሬ፣ ተባራብሬ!”ዋን ትደልቃልች! ወንድማችን እስክንድር ነጋ፣ እህታችን ርዕዮት ዓለሙና ሌሎች ጋዜጠኞች ብዕር ስላነሱባት ተሸብራ “ሽብርተኞች” ብላ ወህኒ አጉራቸዋለች። አንዷለም አራጌ፣ በአንደበቱ፣ “ወያኔ የሰው ልጅ መብት ረጋጭ ነው” ብሎ ጮክ ብሎ በመናገሩ ተሸብራ፣ 14 ዓመት ፈርዳበት ቃሊቲ ወርዶ ፍዳውን እያየ ነው። ነፍጥ አንስቶ አንድ ሁለቱን ቢደፋማ ኑሮ፣ “እንደራደር” እያለች አፏን ታሞጠሙጥ ነበር። አሁን በቅርብ ቀን ወያኔ እያዳፋች የወሰደቻቸው እነ ኃብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳኒኤል ሺበሺ፣ አብርሀ ደስታ በቃላት ካለሆነ በጥየት የት ቦታ ነክተዋት! ዕውነትም ዓመቱ የጨለማ ዓመት ነበር። የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ግን፣ ወንድማችንን፣ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ አለማቀፍ የአየር ትራንስፖርት የመንገደኞችን ደኅንነት በጣሰ ሁኔታ መጥለፏ ነው። ይኸ ወንጀል ብዙዎቻችንን ቆሽታችንን አድብኖታል። ለንደን ደብርጽዮን ቅድስት ማርያምን ከሕዝቡ ቀምተው ለወያኔ ሊያስረክቡ ለሁለት ዓመታት ጎልተው የሚሞግቱን ልማታዊ ካኅናቶቿ ግን በደስታ እያሸበሸቡ ነው። እንዲያም ዘጋቢ ፊልም ሠሩብን!

ካኅን ማነው?

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

እኔም አንዳርጋቸው ነኝ

$
0
0

Andargachew Tsige.jpg2አቶ አንዳርጋቸውን በሕይወት ያገኘሗቸው አንድ ቀን ብቻ ነው። ይኸውም የቅንጅት አመራሮች ታስረው በነበረበት  ጊዜ ይፈቱ እያልን በዓለም ዙሪያ ሰላማዊ ሰልፍ በምናደርግበት ጊዜ ባንዱ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ነበር። ከዚያ በተረፈ  የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ እሳቸውንም አካትቶ ከተቋቋመ በዃላ፤ በተለያዩ መድረኮች እየተገኙ  የሚያደርጓቸውን የውይይት ቪዲዎዎች፤ በተለያዩ ሚዲያዎች በሚሰጣቸው ቃለ ምልልሶችና እንዲሁም ካንዳንድ ሰዎች  ጋር የሚያደርጉትን ክርክር በማዳመጥና በመሳሰሉት ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜም ድምጻቸውን በዚህ መልክ የሰማሁት   መስከረም ወር 2006 ዓ.ም. ገደማ በዲያስፖራው አካባቢ ባጠቃላይና እንዲሁም ባንዳንድ ለየት ባሉ አቀራረቦች  ወያኔን ለቀቅ፤ ግንቦት 7ትን ጠበቅ የሚያስብል ዓይነት ጠረን ያለው ተቃውሞን ያስከተለ ከኢሳት ቴሌቪን ጋር  ባደረጉት ቃለ ምልለሳቸው ነው። ከዚህ የተለየ ስለሳቸው የማውቀው ነገር የለኝም።

ከላይ የአቶ አንዳርጋቸውን ስም ማዕከል አድርገው የተቋጠሩትና ለዚህ ጽሁፌ ርዕስ አድርጌ ያስቀመጥኳቸውን ሶስት  ቅኝቶች ስንሰማቸው ወራቶችን መሸኘታችን አከራካሪ እንዳልሆነ በሁላችን በኩል ግንዛቤ እንዳለ እምነት አለኝ። በበኩሌ  ግን ከስማ በለው ባለፈ አቶ አንዳርጋቸውንና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም አያይዘው በተዘጋጁ አጋጣሚዎች ላይ  ተገኝቼ ደጋግሜ አዳምጫቸዋለሁ።

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

የቀድሞው “የአብዮት አድናቂ” ኑዛዜ (“Confession of the Ex-Revo” )

$
0
0

በፍቃዱ ዘ ኃይሉ

ርዕሱን አላስታውሰውም ‘ንጂ እ.ኤ.አ በ2011 Arab Uprising በመባል የሚታወሰውን አብዮትተከትሎ፣ ኢትዮጵያውያን ፌስቡከኞችም (በተለይ ዲያስፖራ የሚገኙ) ግንቦት 20 ላይ (ልክ በኢሕአዴግ የ20ኛ አገዛዝ ዕድሜ) “Anger day” በሚል በፌስቡክ አብዮትመጥራታቸውን ተቃውሜ አንዲት ጽሑፍ ጽፌ ነበር፡፡ በዓመቱ ደግሞ ‹‹ አብዮት ወረት ነው›› በሚል ርዕስ በፌስቡክ አብዮት ለማስነሳት ፍላጎት ያላቸው በርካቶች እንዳሉ ገልጬ ነገር ግን ይጎድላቸዋል የሚባሉትንነገሮች ዘርዝሬ ጽፌ ነበር፡፡ በነዚህ ሁለት ጽሑፎች ላይ፣ ላዩን አብዮትን የተቃወምኩ ቢመስልም እውነታው ግን ጽሑፎቹ በተጻፉበትወቅት ሕዝቡም፣ ተቃዋሚ ልሂቃኑም፣ ሁኔታዎቹም ለአብዮት ዝግጁ አይደሉም የሚል ዝንባሌ ማሳየቱ ነበር፡፡
ከሌላ ዓመት በኋላደግሞ ‹‹ስለለውጥ›› በሚል ርዕስ ተከታታይ ጽሑፎችን በ‹‹ዞን 9›› ላይ በግል ተነሳሽነት ማስፈር ጀምሬ ነበር፡፡ ጽሑፉን የጀመርኩት ‹‹ኢሕአዴግ ሥልጣኑን በምርጫ ይለቃል?›› በሚል ጥያቄ ነበር፡፡ ‹‹አይለቅም›› የምልባቸውን ምክንያቶች ካስቀመጥኩ በኋላ የለውጥ አማራጭ የምላቸውን (አብዮት፣ሰላማዊ አለመታዘዝ /civil disobedience/ የመሳሰሉትን) በየዘርፉ እየቀነጫጨብኩ ለማሳየት ነበር ዓላማዬ ከዚያም ‹‹የለውጥ ፍርሃት››፣ ‹‹የሥርዓት ለውጥ እና ሃይማኖት››፣ ‹‹የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት እና የማኅበራት ሚና›› የሚሉ ርዕሶችን በማንሳት በሐሳቦቹ ላይ በሐቀኝነት ለመከራከር ጥረት አድርጌያለሁ (ከዚህ በላይ አልገፋሁበትም እንጂ)፡፡ በበኩሌ ስለአብዮት በደንብ ያነበብኩትም፣ ያሰብኩትም፣ የጻፍኩትም፣ የተረዳሁትም ያኔ ነበር፡፡ ያኔ በአብዮት ላይ የነበረኝ እምነት ተሸርሽሮ ግማሽ ደርሶ ነበር፡፡ ተንጠፍጥፎ ያለቀው ግን አሁንም በዓመቱ (በ2006 አጋማሽ) ነው፡፡ አንባቢ ከአብዮት አድናቂነት ወደ ዝግመተ ለውጥ አራማጅነት (በ ‹‹ያ ትውልድ›› ሰዎች አጠራር ከRevo ወደ Sabo) የተሸጋገርኩበትን የሐሳብ ዳገት (ከፈለጋችሁ ቁልቁለት በሉት) ይረዳ ዘንድ በመጠኑ ዘርዘርአድርጌ ማስረዳት አለብኝ፡፡ (ታዲያ አብዮት አድናቆቱም ቢሆን ከወረቀት እንዳላለፈ ልብ በሉልኝ)፡፡

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)


እነዚያን ተከታታይጽሑፎች በጻፍኩበት ሰሞን ‹አብዮት ‹‹እቆጣጠረዋለሁ›› ብለው ያሰቡትንነገር ግን ድንገት ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን የሚችል እሳትን መለኮስ› እንደሆነ እያሰብኩ ባለሁበት ሰሞን ግብጻውያን ሙርሲን ለመጣል ያምጹ ጀመር፡፡ የግብጹ ድጋሚ አመጽ (አብዮት) በጣም የተዘበራረቀ ስሜት ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ሙርሲ እኔ በግሌ ከማምንባቸውና ቋሚም ከሆኑ የዲሞክራሲ መርሆች እያፈነገጠ ነበር፡፡ ስለዚህ የግብጾች ማበይ ምክንያታዊ ነው ብዬ አምኛለሁ፤ እንዲያውም ሕዝብ አንዴ ‹ከነቃ አይሆንም ዕቃ› ብዬ ነበር፡፡ የግብጽ ሕዝብ የሚፈልገውን ዓይነት ሥርዓት እስከሚያገኝ እያበየ ይቀጥላል የሚል ግምት ነበረኝ- ልክ እንደ ፈረንሳዮቹ ተከታታይ አብዮቶች፡፡ ነገር ግን የግብጽ ሕዝብ እያበየ ቢቀጥልም እንኳን የፈለገውን ላያገኝ እንደሚችል የተረዳሁት ወታደራዊ ክንፍ ቀስ በቀስ አገሪቱን በአብዮቱ ተከልሎ ሲጠቀልላት ስመለከት ነበር ፡፡ ከአገራችን የደርግ አመጣጥ አልለይ ብሎኝ ‹አብዮቶች ሁሉ አንድ ናቸው እንዴ?› እስከሚያስብል ድረስ ተመሳስሎብኝም ነበር፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሚዲያ እና ፕሬሶች በአንዳች ተዋስኦ ይናጡ ጀመር፡፡ ተዋስኦው የተጀመረው የጃዋር መሐመድን ‹ኦሮሞ ቅድሚያ›(Oromo First) የአልጄዚራ ምላሹን ተከትሎ ነበር፡፡ ብዙዎች ይሄን ወቅት የሚያስታውሱት እንደአላስፈላጊ የንትርክ ወቅት ቢሆንም፣በበኩሌ ብዙዎች ቆም ብለው አቋማቸውን እና የአቋማቸውን መሠረት እንዲፈትሹ፣ በታሪካዊ እና ፖለቲካዊ ኩነቶች ላይ ንባባቸውን እንዲቀጥሉ ያስታወሰ መልካም አጋጣሚ ነው ባይ ነኝ፡፡ ይህ አጋጣሚ በስመ ተቃዋሚ (dissent) የአንድ ኢሕአዴግን ከሥልጣን መውረድ ብቻ እንደ ለውጥ ግብ አድርገን በጋራ ስንንቀሳቀስ የነበርን ተቃዋሚ ግለሰቦች እና ቡድኖች እርስ በርስ ያሉትን ልዩነቶች እና ልዩነቶቻችንን የምናቻችልባቸውን መንገዶች እንድናስተውል መንገድ ፈጥሯል፡፡ ብዙዎቻችን የማንፈልገውን እንጂ የምንፈልገው ምን እንደሆነ በቅጡ እንደማናውቅ፣ትግላችን ከመርሕ ይልቅ በእልሕ እንደሚመራ ያጋለጠ፣ ራሳችንን እንድንገመግም ያስገደደ አጋጣሚ ነበር፡፡

ከዚህ ድንጋጤ ውስጥነው ‹አምባገነን መሪዎቻችን ከሕዝብ ጉያ የወጡ› የአስተሳሰብ ችግር የወለዳቸው የመሆናቸው ሐቅ ዘልቆ የገባኝ (ወይም genuinely comprehend ማድረግ የተቻለኝ) ስለዚህ አብዮት ሲፀነስ ዓላማው ባልተለወጠ ሕዝብ ላይ የተለወጠ መሪ ማስቀመጥ ቢሆንም ሲወለድ ግን አንድም ያልተለወጠ ሕዝብ የተለወጠ መሪ መውለድ ስለማይችል፣ አንድም ደግሞ የተለወጠ መሪ እና ያልተለወጠ ሕዝብ መዋሐድ ስለማይችሉ፣ አብዮቱ (ዓላማው) ይጨናገፋል፡፡
በዚሁ ጊዜ ነበር የቅርብጊዜ ምሳሌያችንን የአረብ አብዮትን መልሼ በወፍ በረር ለመገምገም የተገደድኩት፡፡ ቱኒዚያ፣ ግብጽ፣ ሊቢያ፣ ሶሪያ…. ከተሳካው የከሸፈው፣ከለማው የወደመው ይበዛል፡፡ የአምባገነን መገርሰስ ብቻውን ለውጥ አያመጣም፤ ከነዚህኞቹ ለውጦች ይልቅ የእኛው ፊውዳሊዝምን ገርስሶ- ወታደራዊ አምባገነንነትን ያመጣው አብዮት የተሻለ ኪሳራ ነበረው ማለት ይቻላል፡፡ (እዚህጋ በኢሕአፓ፣ መኢሶን እና ሌሎችም የደርግ ፓርቲዎች መካከል የተደረገው የድኅረ አብዮት የሥልጣን ሽኩቻ ሳቢያ የጠፋውን ሕይወት ሳንቆጥር መሆኑ ነው፡፡) ከትንሽ ጊዜ በኋላ ደግሞ በብርቱካናማ አብዮቷ የምትደነቀው ዩክሬን አበየች፡፡(‹“የተውኩትን ነገር ተነግሬ፣ ተመክሬ ባገር ምን ጎትቶ አመጣብኝ፣ የአብዮትን ነገር?” Another revolution? ብዬ ትዊት አድርጌም› ነበር) አብዮቷ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ የአካሏ ክፋይ የሆነችው ክሬሚያን በማሳጣት ይጀምራል፡፡ ምዕራብ ዩክሬናውያን ሲያብዩ ‹የአገራችን መንግሥት ከምዕብራባውያን ይልቅ ምስራቃውያን (ራሺያ….) አደላ› ብለው ቢሆንም በውጤቱ ግን ጭራሽ ራሺያ ክሬሚያን ጠቅልላ አረፈችው፡፡ልብ በሉ! አብዮቱ ከተነሳበት 360 ዲግሪ ዞሮ ተጠናቀቀ፡፡ ለነገሩ አልተጠናቀቀም፤ አሁን ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ተሸጋግሯል፡፡
ይኼኔ ነበር በግል ጦማሬ ላይ ጥር 2006 ‹‹Are revolutions meant to be betrayed?›› ብዬ በመጠየቅ የጻፍኩት፡፡ ዜጎች አብዮትን ሲጀምሩት የማይታዩ ችግሮች ሲጨርሱት የሚስተዋለው ‹ሌባ ሲካፈል እንጂ ሲሰርቅ አይጣላም› ነበር የጽሑፌ አንኳር ሐሳብ፡፡ ‹‹ሌባ›› ያልኳቸው በሕዝባዊ አብዮት ስም የግል ሕልማቸውን የሚያሳኩ አጀንዳ ያላቸውን ቡድኖች (interest groups) ነው፡፡ በኢትዮጵያ ነባራዊ የፖለቲካ እውነታ ደግሞ እነዚህ ዓይነቶቹ interest groups ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ በአብዮት ለውጥ አማጭነት ተስፋ ስቆርጥ የመጀመሪያ ጥያቄዬ ‹‹ሳያብዩ ለውጥ ማምጣት ይቻላል?›› የሚል ነበር፡፡ የመጀመሪያ መልሴ ‹‹እንግሊዝ›› ነበረች፡፡ የእንግሊዝ ሕዝብና መንግሥት በሕግ የበላይነት ላይ ለማንም ምሳሌ መሆን የሚችል ነው፡፡ የዓለምን ግማሽ በገዙበት ጊዜም አሁንም አብየው አያውቁም- እንግሊዛውያን፡፡ ምክንያቱም ተወያይተው ችግራቸውን መፍታት ይችላሉ፡፡ ሕዝብና መንግሥት ሲለወጡ ሁሉም በሰላም ይካሄዳል፡፡

ይህንን የመጨረሻ አቋሜን ያውቅ የነበረ ወዳጄ፣ ‹‹እህ አሁንስ?›› አለኝ ‹አብዮት ልታስነሳ አሲረሃል› ተብዬ ተጠርጥሬ ከታሰርኩ በኋላ ሊጎበኘኝ መጥቶ፡፡ ‹‹አየኸው አይደል፣ ያለአብዮት ለውጥ እንደማይመጣ?›› የሚገርመው፣ የኔና የጓደኞቼ በሕገ-ወጣዊ ማንአለብኝነት መታሰርና፣ የመንግሥት (ፖሊስ) ተጠያቂነት ማጣት ውስጥም ሕዝባዊ አለመለወጥ ነው የሚታየኝ፡፡ መንግሥት አሁንም ቢሆን የሚያስጨንቀው ‹‹የውጭ ኃይሎች ጫጫታ›› እንጂ የውስጥ ሰዎች ጥያቄ አይደለም፡፡ በእኛ ላይ የደረሰው (ሐሳብን በመግለጽ ጦስ መታሰር) በሌሎች ላይ ሲደርስ የነበረ፣ እየደረሰ ያለ ፣ ወደፊትም የሚደርስ መሆኑ ቢታወቀውም ሕዝባችን ግን ‹‹መብቴን ማስጠበቅ አለብኝ›› ከማለት ይልቅ ‹‹ዝም ብል ይሻለኛል›› (ጎመን በጤና) mode ውስጥ ነው፡፡ ሕዝብ ገና አልተለወጠም፤ የለውጥ ጣዕሙም የገባው አይመስልም፡፡ ሌሎች ሰላማዊ የትግል አማራጮችም ገና በኢትዮጵያ አልተሞከሩም፡፡ ሕዝቡ ጣዕሙን የማያውቀውን ለውጥ ከመስጠት በፊት ደግሞ የለውጡን ጣዕም አውቆ ለውጡን ራሱ ጠይቆ፣ ራሱ እንዲያመጣው ማንቃት ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ እንግሊዛውያኑ እንደሚሉት ‹ጋሪው ከፈረሱ ቀድሞ› አይሆንም! ለወዳጄም ይህንኑ ሃሳቤን ነበር የነገርኩት፡፡
ለነገሩ ይህንን ሁሉአልኩ እንጂ ክፍሉ ታደሰ በ‹‹ያ ትውልድ›› (ቅጽ 1) ላይ ‹ኃይሌፊዳ በ1965 በኢትዮጵያ በ25 ዓመት ጊዜ ውስጥ አብዮት ይነሳል ብዬ አልገምትም ብሎ ነበር› እንዳለው ካልሆንኩ በቀር እኔም በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ አብዮት ይነሳል የሚል ምንም ግምት የለኝም፤ በመጨረሻም በአቤ ቶክቻው ዋዘኛ አባባል ‹‹ካጠፋሁ፣ልጥፋ!››

ተጠያቂነት የማያረጋግጥ የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ (ግርማ ሠይፉ ማሩ)

$
0
0

ግርማ ሠይፉ ማሩ

Girma Seifu

ግርማ ሠይፉ ማሩ

ባለፈው ሳምንት ማጠናቀቂያ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሰብሳቢነት የመንግሰት ከፍተኛ ባለስልጣኖች የ2006 የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ ሁሉም ሪፖርት አቅራቢዎች “ፖወር ፖይንት” በሚባል የማይክሮ ሶፍት ፕሮግራም የተጠቀሙ ሲሆን አብዛኞቹ ይህን ፕሮግራም በቅጡ ለመጠቀም በግል ያላቸውን ዝቅተኛ ችሎታ ያሳየ ብቻ ሳይሆን በየመስሪያ ቤታቸው ሞያ ያላቸውን ሰዎች መጠቀም ያለመቻልና ያለመፈለግን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር፡፡ የተፈቀደላቸውን አጭር ጊዜ ያመጣጠነ ዝግጅት ማድረግ ሳይችሉ ቀርተው ያዘጋጁትን የፅሁፍ ሪፖርት ሲያነቡ ጊዜ አለቀ እየተባሉ ማስተላለፍ የሚፈልጉትን ቁም ነገር (ካለቸው ማለቴ ነው) ትተው በመግቢያና በሪፖርት ይዘት ጊዜ ሲያባክኑ መታዘብ አሰገራሚ ነበር፡፡ ከዚህ አንፃር የውሃ መስኖ ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ በንፅፅር የተሻሉ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ ቴክኖሎጂ የመጠቀም አስፈላጊነቱም ሰዓትን በአግባቡ በመጠቅም ተገቢውን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው፡፡ ረፖርት አቅራቢዎች ስዓት በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላቸው ሊያቀርቡ ያሰቡትን በሙሉ ካለማቅረባቸው በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሰዓት ቁጥጥር ስራ ጨምረውባቸው ነው የዋሉት፡፡ እርግጠኛ ነኝ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሆኑ ኖሮ እንዴት ሊበሳጩባቸው እንደሚችሉ፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰቴር ሚኒስትሯ ወ/ሮ አስቴር ማሞ ድርጅታቸው ኢህአዴግ ንቅናቄውን እንደ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ግብዓት ለመጠቀም መወሰኑን በሚያሳብቅ ሁኔታ መሪ ድርጅታችን ኢህአዴግ አና መንግስታችን በሰጡት ትኩረት በሚል ነበር ንግግራቸውን የጀመሩት፡፡ የመሪ ድርጅታችን ኢህአዴግ በንግግሩ መግባት መልዕክት ለተሰበሰቡት የመንግስት ሹሞች ሳይሆን ጥሪ ለተደረገላቸው እና በአዳራሹ በብዛት ለታደሙት በኢህአዴግ አጣራር “የህዝብ አደረጃጀት” በመባል ለሚታወቁት የኢህአዴግ አፍቃሪዎች ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቢሆን የስብሰባ ታዳሚዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት “ውድ” የሚል ተቀፅላ ያገኙት እነዚሁ የህዝብ አደረጃጀቶች ናቸው፡፡ እርግጥ ነው በቀጣዩ ምርጫ በአሸናፊነት ለመውጣት የእነዚህ የህዝብ አደረጃጀቶች ሚና የላቀ ነው፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ተቃዋሚዎች ተጠናክረው ታዛቢ ካስቀመጡ ምርጫ ቦርድ ያለነዚህ የህዝብ አደረጃጀት ንቁ ተሳትፎ ቢሮ ቁጭ ብሎ ኢህአዴግን ብዙ ሊረዳው አይችልም፡፡ ጠቅላይ ሚኒሰትሩም ሆነ ፓርቲያቸው ይህ በቅጡ የገባቸው ይመስለኛል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመልካም አስተዳደር ጉዳይ እዚህና እዚያ የጎደሉ አግልግሎቶችን በማስተካከል ብቻ የሚያበቃ እንዳልሆነ ይልቁንም የመልካም አስተዳደር ችግር በቀጣይ የሚያመጣው “መዘዝ” ብዙ መሆኑን አበክረው ገልፀዋል፡፡ እርሳቸው “መዘዝ” ያሉትን እኛ አብዮት ስንለው የመንግሰት ሚዲያዎች ደግሞ ተቀብለው “የቀለምና የፍራፍሬ አብዮት” ይሉታል፡፡ ተመስገን ደሳለኝ አብዮት ብቻውን የማይጥም ከሆነ ብሎ ይመስለኛል “የህዳሴው አብዮት” ብሎታል፡፡ ለማነኛውም በዚህች ሀገር የተንሰራፋው የመልካም አስተዳደር ችግር መዘዙ ብዙ መሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ከታመነ ይህ መዘዝ የተባለው ነገር ስሙ ብዙ አያስጨንቀንም፡፡ የሚያስጨንቀን ይህ መዘዝ እንዳይከተል ምን ማድረግ ይኖርብናል ነው፡፡ በተለይ መንግሰት ይህን መዘዝ ለመከላከል ብሎ ለናይጄሪያ ሽብርተኝነትን ለመከላከል ልምድ ይሆናል ተብሎ የተነገረለትን “የፀረ ሽብር” ህግ እንደመፍትሔ አሰቦት ከሆነ ከመዘዙ እየራቀ ሳይሆን ወደ መዘዙ በፍጥነት እየተጠጋ መሆኑን መረዳት ይኖርበታል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኖ ሌሎች ሚኒሰትሮች በተደጋጋሚ ያነሱት ሌላ አብይ ነገር የኪራይ ሰብሳቢነት የሚመለከት ሲሆን ይህን የኪራይ ሰብሳቢነት የገለፁት የኪራይ ስብሳቢነት መረብ በሚል ነበር፡፡ በዕለቱ ያነበብኩት ጋዜጣ ደግሞ በኮንትሮባንድ ሊገባ የነበረ ወተት በኬላ መያዙን የሚገልፅ ክፍል ነበረው፡፡ ታዲያስ ስብሰባ ላይ ቁጭ ብዬ “የሰው ለሰው ድራማ” አስናቀ እና ኢህአዴግ ቁልጭ ብለው ይታዩኝ ጀመር፡፡ ይህን መረብ ለመበጠስ እሰከ አሁን እንዳልተቻለ እና ከፍተኛ ትግል እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒሰትሩን ጨምሮ ሚኒስትሮቹ  እየገለፁ ኢቲቪ ደግሞ አሰናቀ ለፍርድ ሳይቀርብ ለምን ሞተ ብሎ ዶክመንተሪ ይሰራል፡፡ የኪራይ ስብሳቢነት መረብ እስኪበጣጠስ ድረስ አስናቀ መኖር እና ማጋለጥ ነበረበት የሚል አቋም አለኝ፡፡ እናንተስ ምን ትላላችሁ ጎበዝ? አሁን አንድ የቴሌቪዥን ድራማ አጨራረስ እንዴት መሆን እንዳለበት ዶክመንተሪ ያስፈልገዋል? ለማንኛውም የሰው ለሰው ድራማ ደራሲና አዘጋጆች የህዝቡን እንጂ “ባለሞያ” ተብዬዎች በኢቲቪ ያቀረቡትን አስተያየት እንደማትሰሙ እርግጠኛ ነኝ፡፡

ዶክተር ደብረፅዮን በዕለቱ ሪፖርት ከሚያቀርቡት ሚኒስተሮች ቀዳሚውን ቦታ ያገኙ ነበሩ፡፡ ሪፖርት ያቀረቡት በዋነኝነት የቴሌኮሚኒኬሽን ሴክተሩን  በሚመለከትነው፡፡ ከሚመሩት መስሪያ ቤት አንፃር ሲታይም ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተሻለ መሆን ሲጠበቅባቸው ማድረግ አልቻሉም፡፡ የቀረበው ሪፖርትም በፍፁም በመሬት ላይ ካላው የቴሌ ችግር ጋር የሚጣጣም አይደለም፡፡ በሪፖርቱ መስረት ሁሉም ችግሮች በእቅድ ከተያዘው ጊዜ ቀደም ብሎ የተተገበረ ሲሆን በአሁኑ ስዓት በተለይ በአዲስ አበባ ይህ ነው የሚባል ችግር እንደሌለ ነው ያበሰሩን፡፡ ይህ ግን በምንም መመዘኛ ተቀባይነት እንደሌለው ለመረዳት ከሪፖርታቸው በኋላ በሻይ እረፍት የተሰበሰቡት ሹመኞች ሳይቀሩ ሲያፌዙ እንደነበር ልነግራቸው እወዳለሁ፡፡ ዶክትር ደብረፅዩን ከአቀረቡት ሪፖርቱ ውስጥ የቴሌን ሰራ ለመስራት የፈጠሩት አደረጃጀት አንድ ጥሩ ነገር ጠቆም አድርጎን አልፏል፡፡ ይህም ፓርላማው ማፅደቅ የማያስፈልገው የቴሌን አገልግሎት በአሰራ ሦስት ክበቦች ወይም ክልሎች መከፋፈላቸው ነው፡፡ ይህም የተደረገው ለአሰራር ቅልጥፍና ሲባል እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ተቀባይነት ያለው በጎ ጅምር ነው፡፡ በዚህ አደረጃጀት ሀረሪ ወይም ድሬዳዋ በምንም መለኪያ አንድ ክልል ሊሆን አይችሉም፡፡ አዲስ አበባ እንኳን አንድ ክልል ሊሆን አልቻለም፡፡ ሌሎችም በተመሳሳይ እንዲሁ፡፡ ይህ ለቴሌ አገልግሎት ምቹ የሆነ አደረጃጀት ለሌሎች የመልካም አስተዳደር እንዲሁም ማህበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ በሚመች መልኩ የፌዴራል ስርዓቱ ይዋቀር ለምንል ሰዎች እንደ ጥሩ መግቢያ ሊያገለግል ይችላል የሚል እምነት አለኝ፡፡የፌዴሬሽን ምክር ቤት ይህን ሀሳብ ከዶክተር ደብረፅዮን ወስዶ የህዝቦችን ቋንቋ እና ስነ ልቦና መሰረት ባደረገ ሁኔታ ቢየጠናው ጥሩ ሀሳብ ይመስለኛል፡፡ እሰኪ አንዴ ከያዝነው አስተሳሰብ ወጣ ብለን በተለየ መንገድ ለማሰብ እንሞክር፡፡ ዶክተር ደብረፅዩን ያቀረቡት ሀሳብ በሌሎች ፌዴራል መስሪያ ቤቶችም ሊሞከር ይችላል፡፡ ይህ የምክር ቤት ውሳኔ አይጠይቀም ብለዋልና፡፡

የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ባለፈው ዓመት ሰኳር እና ስንዴ እጥረት እንደነበረ በይፋ አምነዋል፡፡ ያቀረቡት ምክንያትም ሰኳር ይደርሳል ተብሎ ተገምቶ በፊንጫ እና ተንዳሆ ሰኳር ፋብሪካ በእቅዱ መሰረት ባለመድረሱ ችግር መከሰቱን ነው፡፡ እኛም ሰንል የነበረው ችግር አለ በእቅድ መስራት አልቻላችሁም እንዲሁም አትችሉም ነው፡፡ የሰንዴም የሰኳርም እጥረት የለም ሲሉን እንዳልነበር አሁን ችግር መኖሩን አምነው ከውጭ ግዥ እየተፈፀመ እንደሆነ ነግረውናል፡፡ ይህች ሀገር በሌላት የውጭ ምንዛሪ በሀገር ውስጥ ሊመረት የሚችልን ምርት ከውጭ እንድታሰገባ እያደረገ ያለን ፖሊሲና ፈፃሚዎቹ ተጠያቂ ሊያደርግ አልቻለም፡፡ ሰኳርና ስንዴ ማቅረብ ያልቻለ የሃያ ዓመት አገዛዝ መዘዝ ሊመጣበት እንደሚችል ቢፈራ ተገቢ ነው፡፡ አንድ በግብርና ላይ የተሰማሩ ባለሀብት ፈራ ተባ አያሉ “ስንዴ ከውጭ ታዞ የሚመጣበት ገዜ እና በሀገር ውስጥ ቢመረት የሚወሰደው ጊዜ ተቀራራቢ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ አስከትለውም “ኢትዮጵያ ሰንዴና ሰኳር ኤክስፖርት የምታደርግ ሀገር እንጂ ከውጭ የምታስገባ መሆን የላባትም፡፡” በማለት ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡ ግብርና ግን መሬት ይፈልጋል መሬት ደግሞ በመንግሰት እጅ ሆኖ እንደልብ የሚገኝ አይደለም፡፡ የመሬት ፖሊሲያችን ይፈተሸ ስንል ለምን ጫጫታ ይበዛል?

የፍትሕ ሚኒሰትር ሪፖርት በጥቅምት ወር ባቀረቡት እቅድ በግርፊያ ምርመራ ያደርጋሉ ያሉዋቸውን ፖሊሶች እንዴት እንደተቆጣጠሩ ሳይነግሩን ቢጫ ታክሲ ማህበራት ጋር ስብሰባ አድርገናል እና የመሳሰሉትን ሪፖርት ማድረግ ምን ፋይዳ እንዳለው መረዳት ከባድ ነው፡፡ አስገራሚው ደግሞ ፍትህ ሚኒስትር የሚያዘጋጀው የዜጎች ቻርተር ነው፡፡ በእኔ እምነት ፍትህ ሚኒስትር ከህገ መንግሰቱ የተሻለ ሌላ የዜጎች ቻርተር የሚያስፈልገው አይመስለኝም፡፡ በፍትህ ሰርዓቱ እምነት እንዲኖረን ህገ መንግሰቱን ማስከበር ላይ ትኩረት መስጠት ይኖርበታል ብዬ አምናለሁ፡፡ ከሌሎች የመንግሰት አካላት ጋር ተባብሮ የህገ መንግስቱን መስረታዊ ድንጋጌዎች መናድ ማቆም አለበት፡፡ ለዚህም ማሳያው በቅርቡ በመፅሔቶች እና ጋዜጦች ላይ በመንግሰት ሚዲያ የተጀመረውን ስም ማጥፋት ተከትሎ በፍትህ ሚኒስትር መሪነት ወደ ፍርድ ቤት ማምራቱ ነው፡፡ ዘጠና ሚሊዮን ለሚሆን ህዝብ ቢበዛ 20 ሺ ኮፒ ለሚያትም  አንድ መፅሔት ሀገር ሊያጠፉ ነው የሚል መዓት ማውራት ምን አመጣው? ለነገሩ የፈሪ ዱላ የሚባለው ብዒል አንደሆነ መገመት አያሰቸግረም፡፡ ግለሰቦችን እያሳደዱ በማሰር እና አሰሮ ማሰረጃ እያፈላለኩ ነው ከሚል ፌዝ  መውጣት ይኖርብናል፡፡ መንግሰት “የፀረ ሸብር ህግ” ያሰፈልገናል ሲል የነበረው ሰዎችን ሳይዝ በቂ ማሰረጃ ለመሰብሰብ ይጠቅመኛል በሚል እንደነበር እናስታውሳለን፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ ይህ ነው የሚባል ነገር ሳያቀርቡ ሰዓት ሰዓት አልቋል ቢባሉም በከተማው የተንሰራፈውን የቤት ችግር ለመቅረፍ በተለይ በማሕበር ለመገንባት ገንዘባቸውን ባንክ ላስገቡ፣ ቅድሚያ ታገኛላችሁ ተግለው ከሚፈለገው 40 ከመቶ በላይ ባንክ ያስገቡ በ40/60 የተመዘገቡ እና በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊየን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የቤት አቅርቦት ማሳካት አለመቻል አንድም ነጥብ ሊያነሱ አልቻሉም፡፡ ዜጎች ቤት እናገኛለኝ ብለው ተብደረው ባንክ ያሰቀመጡትን ገንዘብ የመንግሰት ባንክ እየነገደበት ትርፍ በትርፍ ሲሆን ዜጎች ቀጣይ ተሰፋቸው ምን እንደሆነ እንኳን ማሰረዳት አልቻሉም፡፡ አዲሱ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ምዝገባ የተጀመረ ሰሞን አንድ ፅሁፍ አቅርቤ እንደ ነበር ይታወሳል፡፡ በሚቀጥለው ዓመት የቤቶች ግንባታን አስመልክቶ ሂሳብ ማውራረድ ስለሚኖር ለዛሬው በዚሁ ማለፍ ይሻላል፡፡ ዜጎች ግን አሁንም ተሰፋ እያደረጉ ነው?

በመጨረሻ ሁሉም ሪፖርት አድራጊ መስሪያ ቤቶች እንደ ችግር ያነሱት “የከፍተኛ አመራር እና ፈፃሚዎች የአመለካከት ችግር መኖር” የሚለው ይገኘበታል፡፡ ይህ ችግር ሁሌም በኢህአዴግ ሰፈር እንዳለ የምንረዳው ስለሆነ መፍትሔው በየአዳራሹ እየመሸጉ ሰልጣና፣ ስልጣና እየተባለ የሀገር ሀብትና ንብረት ከማባከን ተጠያቂነት የሚያሰፍን ሰርዓት በመዘርጋት ኃላፊነቱን ብቃት ላለው ዜጋ ማስረከብ ነው፡፡ አሁን በኢህአዴግ አባልነት በመንግሰት ስልጣን ላይ የሚገኙት በአብዛኛው ከዝቅተኛ ደረጃ እስከ ማስተርስ እና ከዚያም በላይ በርቀትም ሆነ በመደበኛ ይህች ሀገር አስተምራለች፡፡ እነዚህ ኃለፊዎች ባለፉት ሃያ ዓመታት የሰለጠኑ ቢሆንም ለህዝብ መልካም አስተዳደር ለማስፈን የሚያስችል አመለካከትና ክዕሎት ማደበር አልቻሉም፡፡ ስለዚህ ቦታውን መልቀቅ ግድ ይላቸዋል ብንል ድፍረት ሊሆን አይችልም፡፡ ቦታውን የማስለቀቅ ኃለፊነት ደግሞ የህዝብ ነው፡፡ የህዝብ ድምፅ ይከበር ዘንድ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት፡፡ ማንም የማንም ነፃ አውጪ አይደለም፡፡

 

ቸር ይግጠመን!!!

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>