Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የባህር ማዶ ልማት ትብብር እርዳታ በIትዩጵያ (ከሚሊዬን ዘAማኑኤል)

$
0
0

Official Development Assistance in Ethiopia፡ (ODA)
ddየባህር ማዶ ልማት ትብብር (ODA፡ Official Development Assistance) እርዳታ ሰጭ አገራቶች ከ1991 እኤA  እስከ 2012  እኤA  ለህወሃት/አህAዴግ መንግስት አርባ ቢሊዩን ዶላር የልማት እርዳታ ሰጥተዋል፡፡ በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በአማካኝ በAመት ሁለት ቢሊዩን ዶላር እርዳታ ሃገሪቱ እንዳገኘች ያስረዳል፡፡ በይፋ የተለያዩ ለጋሽ ሃገራት የሰጡትን ገንዘብ ብዛትን ለማስላት ያህል በትንሹ ስምንት ታላቁን የህዳሴ ግድብ ኤሌትሪክ ማመንጫን ሜጋ ፕሮጀክቶች በእርዳታ ገንዘቡ ለመስራት የሚያስችል ነበር፡፡ወይም የቻይና መንግስት በ200 ሚሊዩን ዶለር ያሰራውን የአፍሪካ ህብረት Aዳራሽ ህንፃን ዓይነት ሁለት መቶ ህንፃዎች ሊገነባ የሚችል ገንዘብ ነበር፡፡አጠቃላይ  ዝርዝሩን ከሰንጠረዡ ላይ ያስተውሉ፡፡ –-[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—-


የወገኔ ዓማራ ነገር! ከ ቦጋለ ካሳዬ

$
0
0

የወገኔ ዓማራ ነገር!

በወልቃይትም ሆነ በተቀረው ኢትዮጵያ ወያኔ ካለማቁዋረጥ ላለፉት 23 ዓመታት የሚያካሄደው አማራን የማጽዳት ዘመቻ በኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ በሌላ አገር የሚወዳደረው እንዳለ አላውቅም። ህዝብን ማጽዳት ግን እጅግ የቆየ፤ ምናልባት በአሳርያን የተጀመረ ድርጊት እንደሆነ ጻሕፍት ያስረዳሉ።

amaraኢትዮጵያውያን ደጎችም ቂሎችም ስለሆንን፤ ወያኔ የሚያደርገውን ጭካኔ ስንሰማ፤ ኸረ ይኼ እንዴት ተድርጎ! ብለን የሆነውንና እየሆነ ያለውን ነገር ለመቀበል እንቸገራለን። ውይ! ውይ! እምጽ! የሰይጣን ጆሮ አይስማ ብለንም በደሉን እንደ ቀላል ነገር የምናረግብ አድርባይ የህሊና ዱልዱሞችና የውሸት ቤተክርስቲያን ተሳላሚዎችም ብዙዎች ነን። 
የወገናቸውን በደል እውነት መሆኑን አጣርተው፤ ግፉ ነገ በራሳቸው ላይ ሊደርሰም እንደሚችል አስበው፤ ለችግሩ የማያዳግም መፍትሄ ለመስጠት ጥቂቶች ቁርጠኝነት ማሳየት ቢጀምሩም ለእስር፣ስደትና ግድያ እየተዳረጉ ነው። ብዙሃኑ በተለይ መረጃ በቀላሉ የሚያገኘው ከተሜ፤ መቼ የራሱም ሆነ የወገኑ በደል አንገፍግፎት ይኼን ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ በሕብረት ከትከሻው ላይ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል አምላክ ብቻ ነው የሚያውቀው ማለት ሳይሻል ይቀራል?

ኽረ ለመሆኑ የሕዝብ ጽዳት ምንድን ነው? ነገሩ በእቅድ ተይዞ፤ ሆን ብሎ በጎሳ/ነገድ/ብሄር፣በሃይማኖት፣በዘር፣በመደብ፣ ወይም በጾታ የሚለይና የማይፈለግ ሕዝብን ከአንድ አካባቢ ማስወገድ ነው። አተገባበሩም፤ ሰፋ ያለና የማያቁዋርጥ፣ በአንድ ጽንፍ የዘር ማጥፋት(ለምሳሌ፤ እንደ በደኖና አርባጉጉ) በሌላው ጽንፍ ደግሞ ተጽእኖ እያሳደሩ ሕዝብ የሚኖርበትን አካባቢ ለቅቆ(ለምሳሌ፤ ጉራ ፈርዳ፣ቤነሻንጉል) እንዲሰደድ ማድረግ ነው።

ዓማራ

ዛሬ በዓማራ ላይ እየተካሄደ ያለውን የሕዝብ ጽዳትን ለማስቆም እሪ ከማለት ይልቅ፤ ዓማራ አለ የለም በሚል ጉንጭ አልፋ ትንተና ውስጥ የተጠመዱም ሞልተዋል። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም የተናገሩትን እንዳሻቸው የሚመነዝሩ የዓማራ ነጉላዎችና ጠላቶቹ ሳያውቁም ሆነ አውቀው መደናበራቸው በዓማራ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ አይናቸውን ካልጨፈኑ በስተቀር ሊክዱት አይችሉም።

ዓማራ የለም የሚለው የፕሮፌሰሩ አባባል ልብ ብሎ ላዳመጠው፤ ዓማራ የሚባል የጎሳ ስሜት የለም ነው። ፕሮፌሰሩ ዓማራ እንደ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እንዳለ አልካዱም። ይኸ ደግሞ እንደ ክርስቲያንነቱ ከጎሳ በላይ የሚያስብ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብን የሚመለከት ነው። ፕሮፌሰሩ በአርባጉጉ ከተገደሉት ውስጥ ክርስቲያኖች የሆኑ ጎሳቸው ኦሮሞችም የሆኑ አሉ ብለዋል። ኢሰመጉ ያወጣው የስም ዝርዝር አጠገቤ የለም። በእርግጠኝነት የማውቀው ግን በአርባጉጉ የተካሄደውን እልቂት ዘግበው ለአዲስ አበባ ዩኒቬርስቲ ያስረከቡት ሰዎች፤ የጻፉት አማርኛ የአፍ መፍቻ ቁዋንቁዋቸው እንዳልሆነ ነው። ዘገባቸውም በተለይ እልቂቱ በክርስቲያኑ ሕዝብ ላይ ማነጣጠሩን አጽእኖት ስጥቶበታል። በተከታታይም እልቂቱን የሰሙት ከሸዋ የተነሱ ተቆርቁዋሪዎች የአጸፋ እርምጃ እንደወሰዱም በወቅቱ ይሰራጩ በነበሩ የነጻው ፕሬስ መጽሄቶች ተዘግቡዋል። ዞሮ ዞሮ ዓማራ እንደ ጎሳ ስሜት የለም ቢባል እንኩዋን፤ እንደ ክርስቲያን ተለይቶ መገደሉ በሃይማኖት ሰበብ እየተካሄደ ያለ ጽዳት ከመሆን አይለውጠውም። ፕሮፌሰሩ በዓማራ የለም ጉዳይ ላይ በተለያየ ጊዜ የሰጡት አስተያየት ይለያያል። ከመለስ ዜናዊ ጋር በቴሌቪዝን ቀርበው ከትነጋገሩ በሁዋላ፣ “ዓማራ የለም ያልኩት፤ አለ ተብሎ የታሰበው የለም ሲባል ኢላማ ያስታል ከሚል ነው”ማለታቸውን እርስተውት ወይም ወቅታዊ አልሆነም ብለው ትተውት ሊሆንም ይችል ይሆናል።

ዞሮ ዞሮ ዓማራ ማለት ክርስቲያን ማለት ብቻ እንኩዋን ቢሆንም፤ መሬት ይቅለላቸውና ፕሮፌሰር ዓሥራት ወልደየስ እንዳሉት፤ የወያኔ ትግሬዎች ዓማራ ብለው የሚያድኑትን ጠላት መለየተ ሲቸገሩ አናይም። ፕሮፌሰር መስፍን ዓማራ እንደ ሕዝብ የለም የሚል አባባላቸውን ለማጠናከር ከተጠቀሙበት ዋቢ አንዱ የሰምና ወርቅ መጻህፍ ነው።ይኽ እንዳለ ሆኖ፤ የደራሲውን የአማርኛ ችሎታ ማድነቃቸው እጅግ አስገርሞኛል። የሌቫይን/ሊበን የአማርኛ ቈዋንቁዋ ችሎታ እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ ራሱም በኢሳት ላይ ነግሮናል። ከፕሮፌሰሩ የበለጠ ስለ ሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ መሆን ጣር ነው አሳር ካልሆነ። ይሁን እንጂ የእርሳቸው ፕሮፌሰራዊ ትንተና የሚፈጥረው ውዥንብር ዓማራን ከጥፍት ለመታደግ የሚደረገውን ትግል አያቆመውም። ዓማራ ምንም ይሁን ምን፤ ፍሺስት ኢታሊያ፣ወያኔ/ሻእቢያና ሌሎች ጎሰኞች ሊያጠፉት ሲፈልጉ አላጡትም። ዛሬ እንዳይጠፋ በቀንደኛ ጠላቱ በወያኔ ላይ ተቆጥቶ መነሳት አለበት። ደጉ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከጎኑ እንደቆመና እንደሚቆም ምንም ጥርጥር የለውም።

Source:: Moreshinfo

ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ –ግልጽ ደበዳቤ ለብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ክፍል ሁለት)

$
0
0

በስመ አብ፣ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን። ብፁዕ አባታችን እንደምን ሰንብተኋል። ባለፈው ደብዳቤዬ የደብረፂዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ካህናት እና መእመናን አባ ጳውሎስን ብፁዕ ወ ቅዱስ ብለን አንጠራም ብለው በመወሰናቸው የተነሳ ይደርስባቸው የነበረዉን  ዉግዘት፣ እንዲሁም በአንፃሩ ዛሬ አባ ግርማ ከበደ ክብራቸዉን በመጣል በአባ ጳውሎስ ደጋፊዎች ፊት ተደፍተው  ያልበደሉትን በድያለሁ እያሉ ይቅርታን ሲማፀኑ ሳይ እንደ ቤተክርስቲያን አባልነቴ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያዊነቴም  የተሰማኝን ሃፍረት በትንሹም ቢሆን ለመግለጽ ሞክሬያለሁ። ይህንን የመኖክሴዉን አድራጎት ከመዘምራኑም መካከል  አንዳንዶቹ ቀድሞዉንም ቢሆን የማይደግፉት መሆኑን እየገልፁ ሰለሆነ፣ የርስዎ የራዲዮ ቃለ ምልልስ የተለያየ  አመለካከት ባላቸዉን ክርስቲያኖች መካከል የሃሳብ መለዋወጥን ባህል በማስፈን ረገድ በር ቀዳጅ ይሆናል በዬ  እገምታለሁ። መዘምራን ልጆቻችንም ሰዉን በማገልገልና እመቤታችንን በማገልገል መካከል ያለዉን ልዩነት መርምረው  አግባብ ያለው ዉሳኔ ላይ ለመድረስ እንዲችሉ መድረክ ቢዘጋጅ በጣሙን ጠቃሚ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። አንድ ወዳጄ “እነርሱ [መዘምራኑ] የቤተክርስቲያኗ ገንዘብ ተከፋይ ስላልሆኑ የሚያካሂዱት እንቅስቃሴ ሁሉ  ለቤተክርስቲያናችን ይጠቅማል ከሚል የመነጨ እንጂ እነ አባ ግርማ ለስልጣን እና ገንዘብ ለማካበት ሲሉ የሚያደርጉት  ትግል አካል አይደለም” ብሎ ካለው ጋር ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ። ስለዚህ በዚህ ደብዳቤ ላይ የማቀርባቸዉን ሃሳቦች  በጥሞና ተመልክተው ትክክል ነው ብለው የሚያምኑበትን፣ ዓይናቸው ያየዉን እና ጆሯቸው የሰማውን መዝነው ለሰው  ሳይሆን ለዕውነት ይመሰክሩ ዘንድ የደብዳቤዉን ቅጂ ሁኔታ እንደፈቀደ ላደርሳቸው እሞክራለሁ  -—[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—-

 

 

Comment

ነገ ለወያኔ –ምኑ ነው? መልስ –ደመኛው። (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 05.09.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

 

Ethio flag„እንሆ፣ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ  ሁሉ ገላባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፣ ሥርናንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር። ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣለች፤ ፈውስም በክንፎቿ ውስጥ ይሆናል። እናንትም ትወጣላችሁ እንደ ሰባም እንቦሳ ትፈነጫላችሁ፤ በምሠራበት ቀን በደሎኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና፤ እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፡፤ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር“ (ትንቢተ ሚልክያስ ምዕራፍ 9 ከቁ. 1 እስከ 3)

የባንዳ አመድነት ጊዜው ቢረዝምም አይቀሬ ነው። የህዝብ ከመጠን ያለፈ ዕንባ ማዕትን ያወርዳል። ቀን የተዘጋባቸው የነፃነት ሰዎች ደግሞ አንገታቸውን ቀና አድርገው ጸሐይን ያያሉ – ይህ በኢትዮጵያ ምድር አይቀሬ ነው። ውስጣችን ጠርገን ዕንባችን እዬረጨን አቤት ካልን —- ግን የአዎንታዊነት አርበኝነትን ይጠይቃል። በፍላጎታችን ውስጥ በርግጠኝነት ስለመኖራችን ማንነት ፊረመኞች ከሆን። ግን እርግጠኞች ነን? ፍላጎታችን – እንፈልገዋለን? የማዬው ብስልና ጥሬ ስለሆነ። ዝንቅ ፍላጎት – የጎሽ መስመር – የተበረዘ ሥህነ – ስርክራኪ ጠረን ይሸተኛልና። የእኛ ጥንካሬ ምንጩ መከራ ሆኖ ግን አቅም እያለን ያንሰናል። ጠላትንም እጅግ አቃለን በማዬት ቀኑም አጭር እንደሆነ እናስባለን። ግነቱም ኩሰቱም ለነፃነት ትግሉ የሚበጅ አይመስለኝም። ቀኑን የሚያሳጥረው የተግባር ሥልጡንነት – የተባ ስልት፤ የማድረግ ፈቃደኝነትና የውስጥ ተቀባይነት፤ ዕድሎችን በመተርጎም ቅልጥፍና ጥራትን በሚገባ አደራጅቶ ስምሪቱ በፍላጎት ልክ መመጣጠን ሲቻል ብቻ ነው። ብዙ ምቹ ሁኔታዎች አሉ። ሁኔታዎችን አድምጦ ከተግባር ጋር ማጣመር ከተቻለ አቅምን መምራት ይቻል ይመስለኛል።

ወደ ርዕሰ ጉዳዬ ስዘልቅ – ነገ ለወያኔ ምኑ ነው? ብዬ መልሱን ደግሞ እኔው እራሴ ልመልሰው ደመኛው ነው አልኩኝ። ትክከለኛ መልስ ነው። ወያኔ ስለ ነገ የሀገር ቀጣይነት፤ የሀገር መኖር ሆነ የቀጣዩ ትውልድ ግንባታና ጥንቃቄ በሚመለከት ባዕዱ ነው። ነገ ስለሚባል ነገር ወያኔ አስታውሶት አያውቅም። እንዲያውም ነገ ለወያኔ የሚፈራው ጦሩ ዕዳውም ነው። ስለምን?

ዛሬ አመርትኩ ያለውን የዞግ ኩረት ነገ ፍርከስክስ ብሎ ስለሚያገኘው ወያኔ ነገን ሲያስብ ወባ ይይዘዋል። እንዳሰበው እንዳለመው አልሄደለትም። ማለት መንፈስን በማማረት ብሄራዊነትን ማክሰል የነገ መሰረተ አስትምኽሮቶ ነበር። ግን አልሆነለትም። አመድ ለብሶ አኮፋዳውን ተሸክሞ አሸዋ እያመረተ ስለመሆኑ፤ አበቀልኩ ያለው የአረም ችግኝ ሁሉ አፈር ለብሶ ትቢያ ተንተርሶ ፍግ ሲሆን እያዬ እንዴት አይንዘፍዘፍ።

ተግቶ ታጥቆ የተናሳበት „ብሄርተኝነት“ እያለ እያደነ „በአሸባሪነት“ የሚፈርጃቸው ወጣቶች „ዬሽብርተኝነት“ ወንጀላቸው ሀገራዊነትን ኢትዮጵያዊነትን መርሃቸው ስላደረጉ ብቻ ነው። ሳልጠግበው እንደወደድኩት መዳራሻውን ለማዬት እጅግ እጓጓለት የነበረውን የአንድነቱ አቶ ሃብታሙ አሸባሪው ወያኔ ካሰናዳለት የወየኔ ቁሮ ዬወጣት ሊግ ዬመሪነት እድገት ደረጃ መስፈርቱ አለማሟላቱን የነገሩን አቶ ኤርምያስ ለገሰ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ „ብሄርተኛ“ በሚል ስለመሆኑ ነበር።

አሁን ይህ አመክንዮ እጅግ በጽሞና ላስተዋለው፤ በጥልቀት በነገረ ጉዳዩ ሥረዎ ግንድ ውስጥ እራስን አስቀምጦ ማለትም ይህችን ነጥብ ብቻ ይዞ እያንዳንዱ ዜጋ ቢፈትሽ የወያኔ ሃርነት ትግራይን የነገን ህልም ቁልጭ አድርጎ ያሳዬናል። አንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት፤ በላቀ ብቃት እጅግ ሊታመን በማይችል የህሊና ጥሪት ሁሉንም አሟልቶ „አጥባቂ ብሄርተኝነት“ በሚል መሥፈርት ለብቃቱ ሌላ ተለጣፊ መመዘኛ ተሰርቶ – ተገለለ።

አክብሮተ – ኢትዮጵያዊነት ሊያስከብርና ሊያስመርጥ ሲገባ እንዲህ ከደረጃ የሚያስገልል – የሚያስገፋ ከሆነ የነገይቱ ኢትዮጵያ ለወያኔ በትክክልም ደመኛው ናት ማለት ነው። ወያኔን ብዙ ምላጭ አለው። ምላጩ ወይንም ቅርፊቱ የቁጥር ድንበር የለውም። አስኪደክማችሁና እስኪያሰለቻችሁ ድረስ ብትልጡት – ብትልጡት – ብትልጡት ተደጋግሞ የምታገኙት የአምክንዮ እንብርት ኢትዮጵያን በጠላትነት በጥርሱ መያዙን ነው።

ኢትዮጵያ ሀገራችን ቅጽል ወይንም ተወላጠ ሥም ሳይሆን ልዩ የሆነ ገናና ሥም መጠሪያ አላት። ይህ ሥሟ በሚመራት – በሚያስተዳድራት – በሚገዛት ቡድን ተደፍሮ አይጠራም። „ሀገሪቱ – በሀገሪቱ፤ በእሷ፤“ በቃ በተወላጠ ሥም ነው የምትጠራው። ሄሮድስ መለስ አፋቸውን ከፍተው „እናት ሀገሬ ኢትዮጵያ“ ዜግነቴ፤ የእኔነቴ መገለጫ ኢትዮጵያዊነት የነፃነቴ ዓርማ ሰንድቅዓላማዬ ሳይሉ“ ቀን እንጦርጦስ ላካቸው። ባዶ ሳጥናቸው ነው የተቀበረው። እሬሳው እራሱ አልተመለሰም እንደ እኔ። ከሰመጠበት ጉድጓድ እንደተከረቸመ – ተከረቸመ።

ዛሬ የሚታሠሩት – ለመረጃ ሳይበቁ ሳንሰማው የሚሰወሩት – የሚገለሉት – የሚገደሉት – የሚታፈኑት  ሃጢያታቸው ነገን ሊያሳድር የሚችለውን ሀገራዊ ፍቅር በውስጣቸው ጽላታቸው ስላደረጉ ብቻ ነው። ለሰንድቅዓላማ ክብር ምላሹ እስር ነው። ብሄራዊነት አርበኝነት መታፈን መገረፍ ነው። ስለምን የኢትዮጵያ ሰንድቅ ዓላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ለወያኔ የደም ግፊቱን ያስነሳበታል። ነገ መቆዬት የሚችለው ደግሞ በዚህ የደም ዋጋ በተከፈለበት አርማ ሥር ብቻ ነው።

ወያኔ በባላንጣነት እንደ ቀረመት ሥጋ የሸነሸነው አካል ድልዝ አርማ ሳይሆን የልባችን ጌታ በህብረ ቀለማት አንድነት ያፀና፤ ግርማ ሞገስ ያለው ብሄራዊነት ከምንጩ ከሰንደቅአላማችን ነው። ይህ ደግሞ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ውጋቱ ነው። ወያኔ ሲገባ እኮ እኔ በዓይኔ ያዬሁት የእግሩ ገንቤላ አድርጎት ነበር የገባው ሰንድቅዓላማችን፤ በወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪ „የተራከሰው“ ስለ ቃሉ ሎቱ ስብሃት ጉልላታችን፣ አፍሪካን ከደሟ ጋር ያገናኘው አብነታዊ ምልክታችን፣ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ዜግነታችን እንደ ማንነት መግለጫነት ጠብቆ ያቆዬ ልዩ ሰማያዊ ባለውለታችን ስለመሆኑ በሚገባ ስለሚረዳ ወያኔ ትውልዱ በዚህ ሥር እንዲሰባሰብ አይሻም። የአረሙ ወያኔ ፍላጎት – ትውልዱ ከስንት ሞቶ ሺህ ዓመት ወደ ኋላ ተመልሶ ጎጥ ላይ እንዲቸክል ነው የሚሻው። በዚህ ስሌት ነገን አርመጥምጦ የዶግ አመድ ማደረግ ነው የወያኔ ሠርጉ። የወያኔ አንጡራ ፍላጎት ይሄ ነው። ትውልዱ ደግሞ እስርን – ስደትን – መገለልን – ረሃብን ፈቅዶ ከደሙ ጋር ሙጭጭ ብሎ ሞትም ድህነትም ከአንተ ጋር ብሏል። ….. ያረሙ ወያኔ እንብርት ገልብጦ ከበሮውን የሚያስደልቀው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ዓርማ ለመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ምኑም አይደለም።

ከዚህ ሰንድቅዓላማ ጋር የሚጣላ ማናቸውም ድርጅት በሉት ንቅናቄ ወይንም ግንባር በሉት የተቀባይነት መንፈሳዊ ሃብቱ እሳተ ጎመራ ይበለዋል። ሰንደቅአላማችን መንፈስ አለው የሚያስጠጋ – የሚያጽናና – ተስፋ የሚሆን – አፍቅሮትም። የተለዬ መክሊትና ጸጋ ያለው የተመረቀ ዓርማ ነው። ምህረትም ነው። እንዲህ በሰው ሰራሽ እሳቤ መሰረዝ ቀርቶ መነቅነቅ አይቻልም። ልብ ውስጥ ልብ ሆኖ መኖር ዬቻለ ትንግርተኛ ነው። ቅዱስ መጸሐፋችን ነው – ሰንደቅአለማችን። ፍቅር ሰጥቶ ፍቅርን በገፍ የተቀለበ የፍቅር እጬጌ ነው ሰንድቅአላማችን።

ሌላም ነገር ማንሳት ይቻላል በርካሽ እዬቸበቸበ ያለው የደም ዋጋ መሬታችን ነገ ምርት ስለማብቀሉ ደንታ የለውም ወያኔ፤ ገዢዎች ቢፈልጉ በመርዝ ቢፈልጉ በኬሚካል ቢያነዱት ጉዳዩ አይደለም ወያኔ። ዬነገ የኢትዮጵያዊ ትውልድ ፍልሰት ምኞቱ ስለሆነ ዛሬ በሥልጣኑ በመጠቀም የነገን ውድመት ሌትና ቀን በርትቶ እዬሠራበት ነው ያለው። በእዳም ማግሥት እንዲቧጥጥ አብዝቶ እዬባተለ ነው።

በትምህርቱ ዘርፍም ስንመጣ የዛቀጠ ደረጃ ላይ ይገኝበታል። እርግጥ የተለዬ እንክብካቤና ትኩረት ያልተነፋጋቸው አሉ። እድገቱ ሆነ የሚያስገኘው ዕሴት እርግጥ አሁን አይታይም፤ የዕውቀት ዕድገትና የግንባታ ፍሬ የሚታዬው በተደራረቡ ዓመታት ነው። በሂደት ልክ የደቡብ አፍሪካን ስልት የተከተለ ግንባት ከሥር ተስተካክሎ በፈለገው ቦታ ላይ እንደ ተጀመረ ይታያል። ይህ ያልተመጣጠነ የአትኩሮት ዝንባሌ በሰፊው ህዝብ ልጆች የበቀል ቂም ልኩን ወይንም መጠኑን ያሳያል። ስለምን? የተሻለ ኢትዮጵያዊ ትውልድ – የበለጠ ትውልድ – የቀደመ ትውልድ ለወያኔ የህልሙ መቃብር ቆፋሪ ስለሚያደርገው በዚህ መልክ እያላሰላሰ ትውልዱን አስተኝቶ መገደሉን ተያይዞታል።

የእነሱማ ልጆች አይደለም የምርጥ ዘር ቤተሰቦች ማናቸውም የቀረቤታ ግንኙነት ያለው ሁሉ በሚሊዮን ዶላር ውጪ ሀገር ይማራሉ። በዓመት በተደጋጋሚ እረፍት ጊዜያቸውን እዬተመላለሱ ያሳልፋሉ። ልጆቹም የሚወለዱት አሜሪካ ሲሆን የቀጥታ ዜግነታቸውን እንዲያገኙ …. ይደረጋል። ሌላም ሌላም —- ይህን አድላዊ ጭቆና ሰፊው ህዝብ ከነገን ጋር አስልቶ  ከልቡ ሆኖ ሊመረምረው ይገባል።

ይህ የድብብቆሽ ጨዋታ መፈታት አለበት። ሰንድቅአላማችን የኢትዮጵያን ነፃነት ያቆዬ፤ ያዋጋ፤ ያደራጀ፤ በመከራችን ቀን ሁሉ ያልተለዬን፣ አንባሳደራችን ሲሆን፤ በዚህ ማዕቀፍ ሥር የሚመሩ አምክንዮዎች ብቻ ናቸው የእኛ ሊሆን የሚችሉት እንጂ „ለታላቋ ትግራይ“ ህልም አልሞ ተነሰቶ – ተሳክቶለትም በጠላትነት በሚከተክታት አርማ ሥር ማደገደግ ውርዴትውርዴም ነው። ለነገሩ ጭቆናው ሆነ መጋፋቱ ብሄራዊነታችን ሆነ ሰንደቀችንም ይጨምራል።

ስለሆነም በንጹሁ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንድቅዓላማ ሥር ማናቸውም መስዋዕትነት ጥሞ ሊከወን ይቻላል። „በታላቋ ትግራይ“ ህልም ግን ከንቱነት ነው። ሞቱም ሆነ መሰዋዕትነቱ ዋጋ ቢስ ነው። በጠላትነት የተፈረጀ ሰንድቅዓላማ ባለቤቶች ሆነን ሥጋና ደማችን ተረግጦ፤ የአደራ መክሊታችን ተጠቅጥቆ ይህን ተላልፎ በዬትኛውም መስፈርት አንዲት ጋት ለወያኔ ደጋፍ የሚያሰጥ አቅም ቢኖር ብክነት ነው። ሊሆንም አይገባም።

የናቀው – ያንቋሸሸው – የተጸዬፈው – የረገጠው፤ ማሰሪያ ህግ የሰራለት እኮ ሚሊዮኖች ለብሰነው ስንወጣ ስለሚያርመጠምጠው ነው እኮ። አይኑ እኮ የወያኔ ጉርሽጥ ነው የሚሆነው መግለጫችን – ኩራታችን – ፍቅራችንን ሰንድቅአላማችን ስናጌጥበት። እንዴት የዚህ ሚስጢር ድንቡልቡል ይሆንብናል። በምንም ነገር ሊጠቀለል የማይችል ሃቅ እኮ ነው፤ እኛ ስንዋበት ዓይነት የወጣላቸው ደጋፊዎቹ ሳይቀሩ ነው ከእሳት እንደ ገባ ፕላስቲክ ኩምትርትር – ኩፍትርትር የሚሉት። ይህን አምክንዮ ለማዘከር አቅምን በአግባቡ አደራጅቶ የጠሉትን፤ የፈሩትን ነገር ማስጎንጨት ደግሞ መስፈርቱ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።

እንቆቅልሹን የወያኔ ሃርነት ትግራይን የለበጣ ንድፍ በሆድ አደርንት የተሰለፈው ሃይል ቢሆን ሊያሰተውለው የሚገባው ቁም ነገር —- የሚሠራው፣ የሚደክመው፣ የሚጥረው፣ የሚረገርገው ለራሱ መጥፊያ – ለራሱ ሰብዕና መደርመሻ መሆኑን በሚገባ ክልቡ ሆኖ ሊመረምረው ይገባል። እንደገና አዎን እንደገና ይመርምረው። ይህንን ነው ኢትዮጵያዊው ሁሉ ዓይኑ ተገልጦ ሊያስተውለው የሚገባ ፍሬ ነገር። አንጡራ የነገ ጠላት ጋር በምን ሂሳብ ቅንጣት መንፈስ ይቸርለታል? ዕብንነት ነው። እያሉ መሳት እራስን።

እርግጥ ነው አንድ እውነት አለ። ገዢ በሆነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥር ምልዕቱ ሥራ መሥራቱ ላም ጣም ያጣውን ኑሮውን መግፋቱ  ግድ ነው። 90 ሚሊዮን ህዝብ ልሰደድም ወይንም ልሸፍትም ቢል የማይሆን ነው። ነገር ግን እኛ የአንተ ነን የሚለውን የሙጃውን ቧልት ግን አፈረጥርጦ ሊያውቀው – ሊገነዘበው ይገባል። ስንዴ እንክርዳድ አይሆንም እንክርዳድም ስንዴ አይሆንም። ወያኔ ከበቀለበበት ዓላማው አንዲት ስንዝር ፈቅ አይልም። ማሳው ዘርኝነት ነው። ድልዝ የለው ስንጥር የለው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ መላያ ፍጥረቱ በዞግ ፍልስፍና አፈናና ረጋጣ ማካሄድ።

ሃቁ ይህ ነው። አሁን በቅንነት ያሉ ወገኖች ኢትዮጵያ አደገች እያሉ የሚላግጡትን የወያኔን ጭንብሉን ገለጥ ቢያደርጉት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ „ለታላቋ ትግራይ“ ሴራ እዬሰራ እዬተባበረ መሆኑን መገንዘብ ያስችለዋል። ማለት ትውልድና ሀገርን ከሚገድል ዶክተሪን ጋር ፈቅዶ ግን ሳይገባው ወይንም በግድዬለሽነት ተጋብቷል ማለት ነው። ይሄ ነው እውነቱ። ውጪ ያለውም ቢሆን የወያኔ ደጋፊነቱ ቁልጭ ባለ መልኩ ነገ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እንዳይኖር አብሮ ከትሟል ማለት ነው። ለማን ሲባል? „ለታላቋ ትግራይ ልዕልና“ ሲባል።

ይህ ነገን ያበረክታልን? ፈጽሞ! ታላቅነታችን፤ ኃይላችን ሆነ ተፈሪነታችን ያለው ከኢትዮጵያዊነታችን ብቻ ነው። „የታላቋ ትግራይ ምሥረታ“ ህልም ሆኖ የሚቀር ብናኝ ነው። የልተባረከ የረከሰ መንገድ። ቀንና ብቃት፤ ፈቃድና መሆን ሲጋቡ ተኖ ሚቀር ግልብ ጭድ ህልም ነው።

አያችሁ ልብ ቢኖር አሁን ፍዳውን የሚያው ውዴ ልበለው እንዴት ብዕሩ እንደ ናፈቀኝ እኮ፤ ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ እንኳን ይሄን ስቃይ የመቀበሉ አመክንዮ ይሄ ነው። ታናሼ አብርሽ ነገ እንዲኖር ይፈልጋል። ዬሀገሩ ዬኢትዮጵያ ሉዕላዊነቷ ተከብሮ እንዲቀጥል ይፈልጋል። እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ወደብ እንዲኖራት ይሻል። ጦርነትን ባይፈቅደውም ግን ግድ ከሆነ ማደረግ እንደሚገባ አበክሮ ገልፆል። ወጣቱ መምህሩ ጸሐፊው ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ የለበጣ ሳይሆን „ግድ ከሆነ“ ብሏል። የእውነት መርህና የሃቅ ፍላጎት እርገትን በጽኑ ይሻል። የሚሰማውን ከውስጡ ሆኖ ፍርፋሪ ሳያስቀር እራሱን ውስጡን እንደ ህፃን ልጅ አሳይቶናል። ታዲያ  ሰው እንዴት ከእሱ መማር አይችልም?!

„የታላቋ ትግራይ ራዕይ“ እኮ ለዚህ ጀግና ይቀርበው ነበር። ያ የሁላችንም ታናሽ ከዛ ረግረጋማ የጎሳ ዝልቦ እራሱን አውጥቶ እንሆ ለታላቋ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ቀለጠ። …. አብርሽ እንዲህ ሲያደርግ እኛ እንዴት በጥፋትና በምክነት ከበከተ የጎጥ ዶክተሪን ጋር እንሰለፍ?! …. ያሳፍራል ….

እያንዳንዱን የወያኔ ሃርነት ትግራይን ትልምና ጉዞ ስትበትኗት መርዝ አለው። እኛነትን፣ ማንነትን፣ ውስጥነትን፣ ወጥነትን አብሮነትን፤ ቤተሰባዊነትን፤ አርበኝነትን፤ ብሄራዊነትን፤ የኢትዮጵያዊነት፣ ፍቅራዊነት፣ ህይወታዊነትን የሚያጠፋ ማላታይን። ወያኔ እኮ ዲዲቲ ነው …..

ህሊና ቢኖር በማናቸውም ዘርፍ ጠላትን አውቆ ቆርጦ መለዬት የተገባ በሆነ ነበር። ነገ እንዳይመጣ አጥበቆ በሚሠራ የትውልድ መንጣሪ የፊት ለፊት ጠላት ቅርጥምጣሚ – ቅንጥብጣቢ ዬሆነ የመንፈስ እርሾ መለገስ ሰንድቅዓላማን መርገጥ ነው – ለእኔ። ይህ ጥቁር ዘመን ያልፋል። የማያልፈው ግን ለአደራ ሁነኛ መሆን ብቻ ነው። እንደ አርበኞቻችን የነፃነት ማገዶዎች። ሃቅን ፈልጎ፣ እውነትን ታጥቆ ነገን ከሚያጠፋ ጉያ ተለይቶ ለህሊና ማደር የቁም ጽድቅ ነው። ፓለቲከኛው ወጣት አቶ ሃብታሙ አያሌው ከዚህ የረድኤት እርከን ላይ ያለ ድንቅ ፍጡር ነው። ማዬት አይከፋም። አይቶ ግን ከረፋህኝ ብሎ በጊዜ መለዬት የሰውን ደረጃነት ያሰጣል። አብነትም ነው።

እኔ እንደማስበው ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት የለም ማለት አይቻልም። በሚገባ አለ ጦርነት። ጦርነቱ ዬሥነ -ልቦና ጦርነት ነው። ኢትዮጵያን እንደ ሀገር የማስቀጠልና ኢትዮጵያን ከዓለም ካርታ ዬማሰወገድ። ብሄራዊነትን የመደርመስና ጎሰኝነትን የማንገሥ። ይህ እንግዲህ 40 ዓመት ሁሉ የተሠራበት፣ የተደከመበት ደቂቃ ያልባከነበት የአጥፊው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማኒፌስቶ ቁልጭ ያለው አስፓልቱ ነው። ይህ መንገድ የጎረበጣቸው - ዕፀጹ ከተፈጠረበት ጀምሮ ይታገሉታል። ገዢ ሆኖም አልቀረለትም ጦርነቱ ቀጥሏል። ወራሪውም ባዶ እንስራውን አሸኮኮ አድርጎ አለ። ነገን እንዳይመጣ የሠራው ዳጥ እሱን ላጥ አድርጎ ያሰምጠውና ዘር አልባ አድርጎ አምክኖት ይቀራል። ምክንያቱም ፍልሚያው ከደም ጋር ነው። ደም – ቀለሙም ተግባሩም ተልዕኮውም ደም ነው። የደሙ መልክ ደግሞ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው።

ደምን ከእያንዳንዱ ዜጋ አውጥቶ የረከሰ ደም ማስገባት ፈጽሞ አይቻልም። እራሱ ሙከራው የማይቻል ከንቱነት ነው። በዚህ መንገድ መቀጠል አይቻልም።

እኔ አንድ ነገር አስባለሁኝ። ምንአልባትም ቀኑ እያለቀበት ሲመጣ፤ ወያኔ ማጣፊያው ሲያጥረው ከመሸ ከውስጥ እዬተጸዬፈ ግን እንደለመደበት ለማባጨል ንጹሑን ቅዱስ ሰንደቅዓላማችን ለብሶ ይመጣል እያለች ወፊቱ ሽክ እያለችኝ ነው። ሞላጫ ነው ስላችሁ። ግን ቢመጣ እንኳን በጽናት ፍላጎትን በውስጥ ጽላት አድርጎ፤ እናት ሀገር ኢትዮጵያ የአሳር መሞከሪያ የሆነውን የመፈተኛ ዘመኗ እንዲከትም ተግቶ ጠላትን ከነሥሩ ለመንቀል መሥራት አቅጣጫችን ሊሆን ይገባል – እላለሁ እኔው። ጎሳዊ አስተዳደር ታዬ አኮ – ከተከተን።

ዛሬ አንዲት ሳር ለኪስ አውላቂው ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ያቀበለ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ የራሱን ውስጡን መፍረሱን ፈርሞቦታል። ሰው እንዴት ቤቱን – ቤተ መቅደሱን እንዴት ያፈርሳል – ፈቅዶ?! ለዛውም ከባንዳ ጋር ዶልቶ። የዚህ ሰላባ የሆነ ፍጡር የማንነቱም ጠላት ወያኔ ሳይሆን እራሱ ነው። ይህ ደግሞ ጭንጋፍነት ነው። በድኑን ቆሟል ማለት ነው። ውስጡ ሾልኮበታል። ስለምን? የሚሠራው አንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ አባል ለማይሆንበት ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ድርጅት ነውና። ይህ ደግሞ ነገን አምካኝ ነው። ሰብዕናንም ያፋድሳል – ያሳድፋል። የነገ ማህጸን በወያኔ ሃርነት ትግራይ ዶክተሪን እንዲቃጠል ነው ዬሚፈለገው። ዘሃ ግራው ጠፍቶብን ከሆነ ንጥር ያለው ዕውነት ይሄ ነው …. ስለዚህ ቢያንስ መንፈስን ማሸፈት …. የወቅቱ መስመር ….. ሊሆን ይገባል። ለማን? ለምን? ግን እንዴት? – ውስጥን በመፈተሽ ከወርቅ እንክብሉ አመክንዮ ጋር መኖርን መምረጥ። ምርጫ ለራስ ነው ….

ክውና – የኔዎቹ እንሥራ – ለነገሩ በተለያዬ ጥፍጥፍ የወያኔ አፍራሽ ተግባር የሰለጠኑ የኛው ጉዶች እያሉ እንዴት መሥራት ይቻላል? ሁለት ሆኖ መሥራት አይደለም መታዬት እንኳን ችግር ነው እዬነው ነው ያለው ጉድ። ተያይዞ በመተኛት ያርፋሉ የእኛ ጉዶች ትንሽ ተግባር ሊያፈራ መነቃነቅ ሲጀመር ይባንኑና የወያኔውን ግልባጭ መርህ ተከትለው የተርትር ዘመቻቸውን በስልት ያሰነኩታል። ችግር ሆነ የማንነት መንፈስ እዬተገፋ – እዬተገፈተረ። ታማኝት እራሱ እዬተቃጠለ። የሆነ ሆኖ ከህሊና ጋር ኖሮ ማለፍ መኖር ነው። ከፊቱ ላይ ሆነው እኮ ነው የሰላም ትግል አርበኞች በድፍረት እዬታገሉ – እዬተቀቀሉ ያሉት …. ግን እኛ …. እምምምም …..////……

አብሶ ድርጅቶች ወኪሎቻቸውን የሚቆነጥጡበት ሥርኣት ያላቸውአይመስለኝም። ለእኔ ከአቅም ጋር የሚታገል የነፃነት ትግሉ ተወካይ የአረም ሾርባ ነው።  ፈጠራ – ማደግ – መሻል ቀርቶ ሌላው ዬሚያንገበግበውን የተቃጠለበትን ዕንቡጥ ፍሬ ዘር በጋለ ማረሻ …. አዝናለሁ። የሚቻለውና ለውጤት የሚበቃው ለፍርሻም የማይደፈረው ብቻ ተሁኖ የሚሠራ ነገር ብቻ — በቃ! ሰዎ እኮ ተሰርቋል ልበል ይሆን? በነፃነት ሀገር እንደ ቃል ለመኖር እንኳን ፈተናውን መውደቅ – አዚም ይሆን? ወይንስ ምትኃት … እምታውቀውን አውሬ ስንት ቀን ሥጋ ታቀርበለታለህ – ሥጋውን ነጥቀህ ከባህር የወጣ አሳ ማደረግ እያለ። …. በሠለጠነ ዕሳቤ – በሰከነ ማስተዋል እንጂ በፉክክር ቤት አይሠራም። ደም ነፍስ ነውና!

ግን ጥቁር ለባሿ ኢትዮጵያ እሰከነ ምጧና እንባዋ በውስጥ አለችን? ወይንስ ዘብ ጠባቂ አደረግናት ይሆን? ይህ ማተብ የሚባለውስ የወያኔ መጋዝ በሞፈር ዘመት አቅም ኖሮት በጠሰውን? አይገባኝም? ያ የስቃይ መኖርን የሚያፋጥጥ የመከራ የወገን የቶርች ድምጽ ማህተሙ ተፋቀን? ከመቼው? እም!

ጨርስኩ – ኑሩልኝ የኔዎቹ። መሸቢያ ሰንበት!

 

ኢትዮጵያዊነት እዬነጠረ የሚሄድ ዬማንነት ዕንቁ ነው።

ደሜን ሳዳምጠው ውስጤን አገኘዋለሁ።

ለእኔ ስለፈቀድኩለት የባንዳ ቲወሪ አልጨፈረብኝም!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

የአረብ ሃገሩ ክፉ ስደት! እንደ እቃ እንጣላለን፣ መደጋገፍ ጠፋ! (ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0

ነቢዩ ሲራክ

eth-arabia-300x265ገና ረፋዱ ላይ ጸሃዩ ናላን ያዞራል … የቢሮ የቤት ማቀዝቀዣዎች እንኳ ሙቀቱን ተቋቁመው የማብረድ ስራቸውን እንዳይከውኑ የሳውዲ ጅዳ በጋ ሃሩር ጸሃይ ፈተና ሆኖባቸዋል! … በዚህ የቀለጠ የበርሃ ሃሩር ጤነኛ መቋቋም ያልቻለው  ሙቀት በአንዲት ሰውነቷ የደቀቀ እህት ይወርድባታል … ቦታውም ከጅዳ ቆንስል ግቢ የቅርብ ርቀት በሚገኝ የአንድ አረብ ግቢ በር ላይ ነው  …. ስለዛሬው የማለዳ አሳዛኝ አጋጣሚ ላጫውታችሁ…! ያሻችሁ ተከተሉኝ!

የኩባንያ ስራየን በመከዎን ላይ እንዳለሁ እግረ መንገዴን ቀዝቃዛ ውሃና ማኪያቶዋን ለመነቃቂያ ፉት ልበል ለማለት በጅዳ ቆንስል ቅጽር ግቢ ውስጥ ወደሚገኘው የኮሚኒቲ ካፍቴርያ ብቅ ብየ ያችኑ ማኪያቶ አዘዝኩ … ማኪያቶየን እየቀማመስኩ እንደኔው የካፍቴሪያ ታዋቂ ደንበኞች ከሆኑ ወዳጆቸ ጋር ስንጨዋወት አንድ ሌላው ወዳጃችን ግዙፍ ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ ገባ ! … ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ በቆመበት “አንዲት እህት በር ላይ ወድቃለች ፣ ማን ይሆን የሚረዳኝ?” እያለ እኛን ትቶ ሌላ ሰው በአይኑ መፈለግ ያዘ፣ ብዙም ሳይቆይ ወጥቶ ሄደ። የካፍቴሪያው ደንበኞች እኛ ከደቂቃዎች በፊት አድምቀን ስንረባረብበት የነበረውን ያህል ወሬ ወንድማችን ስለሰጠን መረጃ ግድ የሰጠን አንመስልም ለማለት ደረቅ ቢልም ችግሩን ለምደነው ጉዳያችን ብለን ማንሳት ሳይገደን ቀረና ዝም ብለን ተፋጠጥን …

ብዙም ሳልቆይ ወደ ወደቀችው እህት አመራሁ! ብዙ ኢትዮጵያንውያን ለጉዳይ በሚመላለሱበት የቅርብ ርቀት የወደቀችውን እህት ጠጋ ብለው የሚጠይቃት አይስተዋልም። ይልቁንም እያየን ከንፈር እየመጠጥን ከምናልፈው የነገ ተረኞች ይልቅ አረቦች ቀረብ ብለው “ምነው?  ምን ሆና ነው? ለምን ወደ ቆንስላው አታስጠጓትም? ለምን አንቡላንስ አትጠሩላትም?” እያሉ ወድቃ ባዩዋት የእኛ እህት ሲጨነቁ ተመልክቻለሁ! እኛ ይህን ቀርቦ መጠየቅና መርዳት ባይቻለን ይህች እህት ቢያንስ ቀዝቃዛ ውሃ የምታገኝበትንም ሆነ ማቀዝቀዣ ወዳለው የቆንስሉ መጠለያ የአፍታ እረፍት እንድታገኝ ሙከራ ማድረግ አልቻልንም። እኔና ያ ወዳጀ ሰብሰብ እያሉ ለመጡትና ጉዳዩን በቅርብ ላዩ ለቆንስሉ ባለሟሎች ሳይቀር “ለምን ወደ መጠለያው አናስገባትም?” አልናቸው ባለሟሎቹም  “መጀመሪያ ፍቃድ ማግኘት ያስፈልጋል” ሲሉ መለሱልን ፣ “ታዲያ እናንተው ግቡና እንደ ቀረቤታችሁ የቆንስሉን ሃላፊዎች አስፈቅዱልን” የሚል ጎታጉታችን አቀረብን፣ ሃሳባችን ተቀብለው ሊያስፈቅዱ ወደ ቆንስሉ ሃላፊዎች ቢሮ ሄዱ። ተሎ አስፈቅደው ይመጣሉ ብለን በተስፋ ጠበቅናቸው፣ አልመጡም፣ ለምን ወደ ኃላፊዎች አልደውልም የሚል ሃሳብ መጥቶልኝ ወደ ቆንስል ሸሪፍና ቆንስል ሙንትሃ ደወልኩ፣ ስልኩ ይጠራል ግን አያነሱም!…

እኔና ወዳጀ እኛው ራሳችን መጠየቁ ሳይሻለን አይቀርም በሚል ስንንቀሳቀስ ፈቃድ ሊጠይቁ የላክናቸው ወንድሞች የቁራ መልዕክተኛ ሆነዋልና  በላይኛው በር ገብተው በታችኛው በር ሲወጡ በማያርፈው አይኔ አሳዛኙን ሂደት ታዘብኩ! …ቢገርመኝ በንዴት ተቁለጭልጨ ቀረሁ! ወዳጀን በአይኔ በላይኛው ገብተው በታችኛው ወደ ሾለኩት ወንድሞች አቅጣጫ እያመላከትኩ ራሴን በመነቅነቅ “ይህን ጉድ እያየህ ነው!” አይነት ጠቆምኩት፣  እሱም አይኑን ፈጠጥ ራሱን በአንድ በኩል ሽቅብ ነቅነቅ እያደረገ “እነሱ ድሮውንም እንዲህ ናቸው!” የሚል የሚመስለውን ምላሽ መለሰልኝ…

ወደ ቆንስሉ ሃላፊዎች ቢሮ አቀናሁ፣ ሰው የቢሮውን በር ግጥም አድርጎታል። ቆንስሉን እናነጋግር ስንላቸው “ማን ይሰማናል ብለህ ነው?” የሚል ድፍን ያለ ምላሽ የሰጡኝ አንዳንዶች በቦታው የነበሩ ወገኖች ጉዳያቸውን ሊያስፈጽሙ ወረፋ ይዘው ተመለከትኩ። የሚያውቁትን ጉዳይ ደግሜ አስረድቸ በወረፋው እንዲያስቀድሙኝ ብማጸናቸውም ምን ሲባል አሉኝ፣ ግራ ተጋብቸ ተንደርድሬ የሃላፊዋን ቢሮ ከፍቸ ገባሁ! ሃላፊዋ የሉም፣ ተፈናቃዮችና የመጠለያው ጉዳይ የሚያገባቸውን ወንድም አገኘሁና ጉዳዩን በማስረዳት ይህች እህት ወደ መጠለያው ወይም የጸሃይ ከለላ ወደምታገኝበት የቆንስል ወይም የኮሚኒቲው ግቢ እንድትገባ ይተባበሩን ዘንድ ተማጸንኩት! ከሁሉ በማስቀደም ልጅቱን ለመርዳት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በስብሰባ ላይ  ከነበሩት ከቆንስል ሙንትሃ ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ጉዳይ ፈጻሚው አሰረዱኝ። እኔ፣ ወዳጀና የቀረነው ያገባናል ያልን ይህች ምስኪን የተጣለች እህት ከሙቀት ላይ እስካሁን የቆየችውን ያህል ከአሁን በኋላ ብትቆይ እንደማትተርፍ ተረድተናልና አፋጣኝ እርምጃ ይገኝ ዘንድ ወደ ቆንሰሉ ሃላፊ ወደ ቆንስል ሸሪፍ ከይሩ ቢሮ አመራሁ።

ቆንስሉ ሃላፊ ሞቅ ባለ ሰላምታ ተቀብለውኝ ሰላምታ ተለዋወጥን።  ከምጣቴ አስቀድሜ ስልክ ደውየ ምላሽ ሳጣ ወደ ቢሯቸው ለመምጣት መገደዴን አስረድቸ የወደቀቸውን እህት ጉዳይ ለቆንስል ሸሪፍ አስረዳኋቸው። ቆንስል ሃላፊው አቶ ሸሪፍ ስብሰባ ላይ ስለነበሩ ስልኬን በጊዜው  አለማንሳታቸውን ገልጸውልኝ ከታችኛው ቢሮ “ፈቃድ ላግኝ ” ወዳሉኝ ጉዳይ ፈጻሚ ሰራተኛ ደውለው የወደቀችውን እህት ከወደቀችበት ወደ መጠለያ እንዲያስገቡ ጠየቋቸው።  አሁንም ጉዳይ ፈጻሚው ወንድም ቆንስል ሙንተሃን ለማስፈቀድ እየጠበቋቸው መሆኑን ለሃላፊው ገለጹላቸው። ሃላፊው “መጀመሪያ እያትና የሚረዳ ነገር ካለ ትረዳ ፣ ወደ ግቢ አስገቧት፣ ይህን ለማድረግ ምንም ፈቃድ አያስፈልገውም!” ብለው ትዕዛዝ ሰጥተው ስልኩን ዘጉት፣ እኔንም ስለመረጃው አመስግነውኝ፣ እኔም ለትብብራቸው አመስግኛቸው ተለያየን…

ትዕዛዝ የተቀበሉትን ጉዳይ ፈጻሚ ይዠ ወደ ወደቀችው እህት ስንደርስ ከተጣለችበት ወደ ተሻለው የቆንስሉ ግቢ ፊት ለፊት ካለ አንድ ግቢ ታዛ አምጥተዋት ተመለከትን! በቦታው ቆንስል ሙንትሃ ሰውነቷ በውስጥ ደዌ የረገፈውን አህት ውሃ እያጠጡና እያነጋገሯት ደረስን! ቆየት ብየም ከዚህ ቀደም ቆንስሉ በትብብር ሆስፒታል አስገብቷት እንደነበር ለመረዳት ችያለሁ። ያም ሆኖ ውሃ በአፏ ላይ ስታደርግ መናገር የጀመረችው እህት ከሆስፒታል አውጥተው እንደጣሏት ተናግራለች ….

ወደ ዝርዝሩ አንገባም … ከሁሉም በላይ “አይ የሰው ነገር፣ አይ ቁንጅናና ረጋፊው የሰው ገላ! ለይላ! አንች እንዲህ ሆንሽ?!” በማለት በአይኑ አንባ ግጥም እያለ የሚያደርገው የጠፋው “ሃገር ቤት አውቃታለሁ!” ያለን ወንድም ለይላ ለ15 ዓመታት ሳውዲ እንደቆየች አጫውቶኛል …ተሰባስበን “አንቡላንስ አዘናል!” ያሉንን የቆንስል ሃላፊና ምስኪኗን እህት ከበናል …ትክዝ ብየ የአረብ ሃገር ስደት መጨረሻ አሰብኩት …መጨረሻችን ይህው መሆኑ ቢያመኝ “የአረቡ ሃገር ክፉ ስደት … ስደት ክፉ ነገር ነው!” አልኩ ለራሴ በውስጤ በማልጎምጎም ዝም አልኩ! … ድንገት “ኤሽ እንደክ?” “ምን አላችሁ?” ሲል ቆንስሉን ከሚጠብቁት የሳውዲ ልዩ ኮማንዶዎች አንዱ ወደየስራችን እንድንሰማራ አዘዘን  …  ወታደሩ አዞናልና ተበታተንን… !

“ያገባናል!” ብላችሁ ለደከማችሁ ፈጣሪ ዋጋውን ይክፈላችሁ! ዝምታን ለመረጣችሁ፣ ለሸሻችሁ፣ አይታችሁ ላላያችሁ፣ ሰምታችሁ “የዝሆን ጀሮ ይስጠን” ላላችሁ ልቦና ይስጣችሁ! ሌላ የምለው የለም!

ብቻ …  እውነት እላችኋለሁ ወደ አረብ ሃገር አትሰደዱ! ክፉው የአረብ ሃገር ስደት መጨረሻው አያምርም፣ ስንቱን ወገኔን በላው?

እስኪ ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአረቡ አለም….(2)

$
0
0

በግሩም ተ/ሀይማኖት ‹‹..እኛስ በስደት ሀገር ምን እየሰራን ነው? ወገን ወገኑን አሳልፎ የሚሸጥበት፣  ለአደጋ የሚያጋልጥበት፣  ጥቂቶችበሚሰሩት  መጥፎ  ተግባር  ሁሉም  የሚወቀስበት፣  የሚታሰርበት  ሁኔታ የለም? አለ፡፡  ይህንንም  ለማየትእንሞክራለን፡፡ በተያያዥነት እንዲረዳይ ወይም መገለጽ አለበት የምትሉት ሀሳብ/መረጃ/ ካለ ላኩልኝ፡፡..››ብዬ ነ በር ባለፈው  ጽሁፌ  የዘጋሁት፡፡ ‹‹…በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ማየት የሚገባ ነገር አለ፡፡….. በተለይ በአረቡ አለም ላይ ሽርሙጥናን ስራ አድርገው ገላቸውን መቸርቸር ብቻ ሳይሆን ሀገር የሚያሰድቡ ሞልተዋል……በሌብነትም ቢሆን ተሰማርተው ሰርተን እንዳንበላ ስማችንን እያተፉ ያሉ በርካታዎች አሉ…›› የመሳሰለ አስተያየት የሰነዘራችሁ አላችሁ፡፡

yemenብዙ እህቶችም ሆኑ ወንድሞች የተለያየ ሀሳብ ሰንዝረዋል፡፡ የሁላችሁንም ሀሳብ እንደ ሀሳብነቱ እቀበላለሁ፡፡ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ የሚታፈነው ወያኔ ጋር እንጂ እኔ ጋር አይደለም፡፡ ጥቃቅን ስድቦች ለወረወራችሁ ከአነስተኛ እና ጥቃን ስድብ አምራችነት አውጥቶ በሰፊው የብልግናውን ካባ ያልብሳችሁ ስል እመርቃችኋለሁ፡፡ የአምስቱ አመት ትራንስፎርሜሽን እቅዳችሁ በስድቡም መስክ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግም ሳይሆን አይቀርምና ካሰባችሁበት ያድርሳችሁ፡፡  ከሁሉም በላይ ግን አንድ ወዳጄ ያለውን አስፍሬ ወደ ሀሳቤ እግባለሁ፡፡ ፍሬሰናይ ከበደ ይባላል፡፡ የሰጠው አስተያየት….በነገራችን ላይ በቅንፍ ውስጥ የማደርገው የራሴን ሀሳብ እና ምላሽ ነው፡፡

‹‹….ግሩምተክለሃይማኖት በጻፈው   ሙሉ በሙሉ  እስማማለሁ። የስም ማጥፋት  ያስመስላል ላልከውግለሰብ፡ ነቃ  በል ነው  የምልህ?? (ወዳጄ ምነ ው ስም ማጥፋት  ምንድን ነው?  ምንስ አገናኘው? ያልተሰራ ይሆን የተናገርኩት? እስኪ  በመረጃ እንነጋገር?)  ግብረገብ  ባለው  ቃልስለጻፍክ  ትክክለኝ የሆንክ እንዳይመስልህ! በሃገር ውስጥ እያለን

ውርደት ውስጥየከተተንን ፋሽስት ወያኔና ሻቢያን ታግለን ወይም ተዋግተን እናሰወግድ ጥሪ ላንተም ሆነ ለሌላው ተጠራ፤ ከዚያም  በኋላ  በነጻው  ፕሬስም ተባለ፡  አረብ ሃገር አማራጭ ሆነና፡  ግሩምየጻፈው ሆነ፤ በግልጽ እየታየ ያለ ነገር ሆነ። በስደቱ ዓለም ተሁኖ ያሰደደውን   ፋሽስትወያኔ  ዱርዬ ወንበዴ  ቡድን መታገል ይሻላል? ወይስ ሽርሙጥና ?????  ነጻነት  ይሻላልወይስ ጊዜያዊ  ሽርሙጥና  አላስፈላጊ  የንዋይ  እርካታ???  መስማት ብቻ አይደለም ፡ያሳፍራልም።   በስደት  ዓለም  ሆነን  ሃገራችንን  አልረሳንም ስንል፡ ስለነጻነታችን በምናምነውተቃዋሚ ድርጅት ውስጥ ሆነን ስለሃገራችን ነጻነት እንታገላለን እንጂ፡ ሃገራችንን ነጻነትካሳጧት  የጎረቤት ሃገር  ዱርዬዎች ጋር እንኳንስ ልጅ ወልዶ መኖር፡ እያንድናዷ ቀንስለነጻነታችን እናውራ.. ሃገራችንን ሳናሳፍር ወገናችንን ከመጦር ወደ ኋላ ሳንል ወይፍንክች የሚሉም አሉ። እነዚህ  ዓላማ የለሽ ለሱዳን ወንድ የሚታገሉት፡ የወለዷቸውልጆቻቸው ሃገራቸው የት እንደሆን አውቀው ሃገራቸውንና ወገናቸውን አውቀውኢትዮጵያዊ ነን ብለው፡ ወይስ ሱዳናዊ ነን ብለው እንደሚምታታባቸውና አድገውእንደሚጠሏቸው ባወቁ። የራስን ሆድ ለመሙላት  ልጅ ካላሰቡት ቦታ ፈጥረው ትውልድንየሚያሰቃዩ ወንጀለኞች ናቸው። ካደጉትና ዜግነት ከተምትታባቸው አድምጠናል፤አንብበናል። ወንድማችን ግሩም፡ አላስፈላጊ ኮሜንቶችን ማጥፋት አዲሱን ትውልድማዳን ነውና እግዚአብሄር ይስጥልን።…..›› ይላል ፍሬ ሰናይ ከበደ፡፡  ከልብ አመሰግናለሁ፡፡   በዚህ  ርዕስ   የመጀመሪያውን  ፅሁፍ   እንደለቀኩ  ኢ-ሜሌም   ሆነ  ስልኬ የግል መልዕክቶች በመቀበልተወጠሩ፡፡ ከ142 በላይ ሰዎች ቻት ያደርጉኝ ነበር፡፡ የሚገርመው ግን አብዛኛዎቹ ያስተላለፍኩትን መልዕክትበትክክል ካለመረዳት  የመነጨ  ጭንቀት  ነበር  ያማከሩኝ፣ የወቀሱኝ፡፡ ካስተላለፍኩት መልዕክት ባፈነገጠመልኩ የተረዱኝ የተረጎሙብኝ አሉ፡፡ ከዛም ተነስተው የሰደቡኝ  ሞልተዋል፡፡ ስድብ ለብስልት   መገለጫአይሆንም፡፡ እውነታ የያ ሰው ይሄ ይሄ ነው እውነታው ቢለኝ  የማልቀበልበት መንገድ የለም፡፡ አስተውላችሁበማንበብ ወገን ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ግፍ፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚሰሩ ስህተቶችን  ብንነጋገር እናመፍትሄ ካገኘንም፣ መርዳት የምንችለውን  ብንረዳ ቀና ወገናዊነት ነው፡፡ ‹‹..ሴቶቹ በሴትኛ አዳሪነት ተሰልፈው  አሰደቡን፣ አዋረዱን የምንለውን ያህል ወንዶችም  በዚሁ  መስክተሰማርተው መገኘታቸው ያሳፈራል፡፡ ኩሉን ተኩሎ ሊፒስቲክ  ተቀብቶ ታይት አድረጎ ለገበያ የሚቆም፣ ተደውሎለት ፒክ የሚደረግ ኢትዮጵያዊ አለ መባሉ ምን  አይነት ስሜት ይጭርባችኋል? ዱባይ ካሉኢትዮጵያዊያኖች ጋር በዚህ ዙሪያም አውርቻለሁ፡፡ እመለስበታለሁ፡፡ …›› ነው ያልኩት፡፡ በዚህ ሀሳብ ላይ ተነስታ የሰደበችኝ ልጅ አለች፡

ይሄ ማለት ዱባይ ያሉ ሴቶች በሙሉ ይሸረሙጣሉ ማለት ነው? በየትኛውስሌት  እና አባባል እንደተተረጎመ  ዲክሽነሪ ላይ ቢፈለግ አይገኝም፡፡ ስለ ወንዶቹ ድርጊት ተወያይቻለሁ   ነው ያ ልኩት፡፡ ቢሆንእንኳን  ዱባይ ያሉ  ጥቂት ሴቶቻችን የሚሰሩት ነገርየለም? ወገኖቻችን ላይስ ግፍ አልተፈጸመም? በቅርቡ ተጫውተውባት ዛፍ ላይ አንጠልጥለው   ራሷን ሰቀለችየተባለች የለችም?  በደረሰባቸው ግፍ አብደው ኮሚኒቲ ውስጥ የነበሩ የሉም? አሁንስ አይኖሩ ይሆን? ለሶስትተጫውተውባት  የፌስቱላ ችግር ገጥሟት አዋጡላት ተብሎ  የታከመች የለችም? በስም ብቻ ሳይሆን በፎቶጭምር የ ማውቃቸው ወንዲኛ አዳሪዎች የሉም? /ለሴቶች ሴተኛ አዳሪ ከተባለ ለወንዶች ወንዲኛ አዳሪየሚለውን ልጠቀም እንጂ እስከዛሬ ስላልተለመደ ቃል ያለው አልመሰለኝም፡፡/  ጥቂት በጣም ጥቂትእህቶቻችን ለሚያገኟት ሳንቲም ብለው በቪዲዬ ተቀርጸው መጠቀሚያ አልሆኑም?   እንዲያውም እዚህ ጋር አንድ ገጠመኜን ላሰፍር ወደድኩ፡፡ አንድ ፈረንሳያዊ ተጓዥ ጋዜጠኛ ነው፡፡ በአንድወቅት የመን የጋዜጠኞች ማህበር ስብሰባ ላይ እንድገኝ ተጋበዝኩና ስሄድ አገኘሁት፡፡ እሱም ተጋብዞ ስለነበርሁለታችንም የተጋባዥ ወንበር ላይ ነው ያለነው፡፡ ከየት እንደመጣሁ የጠቀኝ እና  ወሬ ተጀመረ፡፡  በወሬያችንመካከል እዚሁ እ ንደምኖር ተነፈስኩ፡፡ የመን ትንሽ ጊዜ ስለሚቆይ አብራው የምትዝናና ሀበሻ ሴትእንዳስተዋውቀው ጠየቀኝ፡፡ አንደኛ እኔ አቃጣሪ ደላላ አለመሆኔን ሁለተኛ ማንኛዋም ሀበሻ የእንደዛ አይነትፍላጎት እንደሌላት እና ለስራ እንደመጣች ነገርኩት፡፡ የዛሬ ወር ዱባይ ነበርኩ ብሎ የያዛትን ዲጂታል ካሜራከነካካ በኋላ ፊልሙን ዝግጁ አድርጎ እንዳየው አቀበለኝ፡፡ አፍ እና ጭን ተጋጥመው /…/ በስሜት ጥድፊያይዋከባሉ፡፡ ፊልሙን ለማየት እንዳቀረቀርኩ ደረኩ፡፡ አንገቴን ቀና እንዳላደርግ ሀፍረት በግሩፕ ሰፍሮብኝ ሸብቦያዘኝ፡፡ ካሜራውን ስመልስለት መቅረጽህን ታውቃለች? ለነገሩ ይህቺ ልጅ ሀበሻ አይደለችም አልኩት፡፡ለማምለጫ እንጂ ልጅቷን ኢትዮ ስፖት ዌብ ሳይት ላይ ተደጋጋሚ እርቃን ገላ በሚያጋልጥ ሁኔታ ፎቶ ተነስታስትለቅ ነው የማውቃት፡፡ በደንብ እንደምታውቅ እና ክፍያውን ጨምሮ እንዳደረገው ነገረኝ፡፡ የፈለገውን ያህልቢከፍላት ከ1000 ዶላር በላይ አይከፍላትም፡፡ እሱ ግን የሚያፍሰውን ያፍሳል፡፡ እህቶቻችን ባለማወቅከወሲብ ውጭ ሌላም ንግድ መጠቀሚያ እየሆኑ ነው፡፡ እዚህ የመን ውስጥ አሁን ሳዑዲ ያሉ  ሁለትእህትማማቾች  አውቅ ነበር፡፡   ትልቅየዋ ጀርመናው  ጓደኛ አላት፡ ፡ ከእሱ  ጋር  የምታደርገውን   ነገር በህገ-ወጥሁኔታ ስትፈጽም ታናሽዬው ቪዲዮ ካሜራ ይዛ መቅረጽዋን ከራሷ አንደበት ሰምቻለሁ፡፡ እንደጀብዱበተሰበሰብንበት ያወሩልን 500  ዶላር  ሰጥቷቸው ነበር፡፡ እነዚህ አይነት ነገሮች በመጀመሪያ የራስን ሰብዓዊክብር፣ ሞራል ከማዝቀጥ አንጻር  ቀጥሎ የወገንን  ብሎም የሀገርን ስም….እያልን እንድናስብ  ነውየሚያስፈልገው፡፡ እንዳሰው ችግራችንን እንነጋገር ነው አላማዬ፡፡ ባለማወቅም የሚሰራ ነገር መኖሩንምመገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ሌላው በሞባይል ስልኬ ከደረሰኝ መልዕክት ውስጥ ስሟን ካስተዋወቀችኝ በኋላ ‹‹….እግዚአብሄርይመስገን አለኝ፡፡ /አይ እታለም ቢኖርሽ ለምን ተሰደድሽ?/ ለራሴ እና ለቤተሰቦቼ እንጂ ጎረምሳ ልቀልብአልወጣሁም፡፡/ቱ..ቱ..ቱ.. ያሳድግሽ፡፡ እኔም እኮ እያልኩ ያለሁት ለራሳችን ምን ያህል አውቀናል? ቤተሰብበችግር ሲማቅቅ እኛ ለምን ስራ  ጠልቶ እንደ ውሻ እጅ እጅ የሚያይ ሰው እንቀልባለን ነው፡፡/ እና አረብ ሀገርያሉ በተለይ ዱባይ አያልክ ሰውን  ባታጎሳቁል ደስ ይለኛል፡፡  ሌሎችን ወክዬ መናገሬ ግን አይደለም፡፡ ያለከውንየሚሰሩ አሉ፡፡ የሉም አልልም፡፡ እናንተ ጋርም እንዳሉ እህቶቼ ይነግሩኛል፡፡ እዚህ ዱባይ የብዙ ሴቶችን ትዳርእና ጓደኝነት  እንደምትበጠብጥ   ልብ ያልክ አልመሰለኝም፡፡..›› ይላል፡፡ ልብ እንዲባልልኝ የምፈልገው በተለይዱባይ ያልኩበት ቦታ የት ነው? እኔ ያልኩት ‹‹..ጥቂቶች ደግሞ በሉብናን /ቤይሩት/፣ ዱባይ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ባህሬን.. ኩዌት ያሉ ሴቶቻችን የሱዳን ወንዶች ሲሻሙ እና የለፉበትን አባክነው  ቤት ተከራይተውላቸውማስቀመጣቸው…›› ነው፡፡ ያውም ጥቂቶች እንጂ ሁሉም አላልኩም፡፡ እህቴ ቅድሚያ አስተውሎ ማንበብቢቀድምስ? ሌላው ደግሞ ሱዳን ውስጥ ራሱ የተወሰኑ ሴቶች  የሰሩበትን  ማብላት ብቻ ሳይሆን ተደባድበው ፖሊስ ጣቢያ እንደደረሱ ካርቱም ነዋሪ የሆንን የምናውቀው ነው በማለት አንድ ወዳጄ ነግሮኛል፡፡ አሁን ጠለቅ ያለ መረጃ እጄ እየገባ ነው እምለስበታልሁ፡፡

የግብረሰዶማዊነት አደጋ – (የአቡነ ሳሙኤል ወቅታዊ ጽሑፍ)

$
0
0

(አባ ሳሙኤል)

(አባ ሳሙኤል)

ግብረሰዶማዊነት ማለት በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወይም ተራክቧዊ መማለል ነው። ግብረሰዶማዊነት /Homosexuality/ ተፈጥሯዊ ከሆነው ግንኙነት የተለየ ሲሆን ይህም ወንድ ከወንድ /Gay/፣ ሴት ከሴት /Lesbian/ ጋር የሚፈጸመው ነው። እንዲሁም አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ከተመሳሳይ እና ተቃራኒ ጾታ ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት /Bisexuality/ ይሉታል። ይሁንና በሥነተፈጥሮም ሆነ በሳይንስ እንዲሁም በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮ፣ ጤናማና ተቀባይነት ያለው ወንድ ከሴት፣ ሴት ከወንድ ጋር የሚፈጽሙት ግብረሥጋ ወይም ሩካቤ ብቻ እንደሆነ ነው።

የግብረሰዶማዊነት አደጋ እንዴት ይገለጻል?
ይህን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ለግብረሰዶማዊነት የሚያበቁ ምክንያቶችንና የሚያስከትሉትን አስከፊ ጉዳቶች እናያለን። ምክንያቶቹን ስንጠይቅ የዕጾችና ሱሶች ተገዢ መሆን፣ ተገድዶ መደፈር፣ መጠለፍ፣ ተቃራኒ ጾታዎችን መጥላት፣ ለተመሳሳይ ጾታ መማረክ ወዘተ.. ሲሆን የሚያስከትላቸው አደጋዎችም ድብርት፣ ጭንቀት፣ ራስን መውቀስ፣ የህሊና ጸጸት፣ በከባድ በሽታ መለከፍ፣ ፊስቱላ፣ ራስን ማጥፋት፣ የኢኮኖሚ ውድቀት ወዘተ… ናቸው።ስለግብረሰዶማዊነትና ፀያፍ ልምምዱ በተመለከተ የመጀመሪያውን መረጃ የምናገኘው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው። ከታሪኩ መረዳት እንደምንችለው ከ5000 ዓ.ዓ በፊት የነበሩት የሎጥ ዘመን ሰዎች በዚህ አስከፊና አሳዛኝ ድርጊት ውስጥ በመገኘታቸው፣ ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሣ በወረደው የእሳት ዲን ሰዶምና ጎሞራ የተባሉ ከተሞች መጥፋታቸውን ነው። አሁን ባለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመንም አደጉ ከሚባሉት ምዕራባውያን እስከ ደሀ አገራት ድረስ ርኵስ ተግባሩ ቀጥሎ ይገኛል። በተለይም ምዕራባውያኑ ይህን ርኵስ ተግባር እንደ ሥልጣኔ በመቁጠርና በሰባዊ መብት ስም /በቀጣዩ ጽሑፌ የምናየው ይሆናል/ የሕጋቸው አካል አድርገው በመደንገጋቸው፣ ድርጊቱ ተቀባይነት አግኝቷል። ታዳጊ ሀገራትም ብድርና ዕርዳታ ማግኘት ይችሉ ዘንድ የግብረሰዶማዊነትን ሰነድ እንዲፈርሙ የማባበልና የማስገደድ ዲፕሎማሲያቸውን ተያይዘውታል።

ከሀገራቱ ሁኔታ ለመረዳት እንደሚቻለው የተጽዕኖ ዲፕሎማሲውን በመቀበልና ባለመቀበል የቆሙ እንዳሉ ሁሉ የተንበረከኩም አልጠፉም። ለምሳሌ የዑጋንዳ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ጠንካራ አቋሙን ሲገልጽ ከቆየ በኋላ መጨረሻ ላይ ሊንሸራተት ችሏል። አትዮጵያም በተለያየ ወቅት በዚህ ጫና ውስጥ ያለፈች ስትሆን በዋናነት ግን ግብረሰዶምን በተመለከተ በወንጀል ሕጓ የሚያስቀጣ ድርጊት አድርጋ መደንገጓ ውጫዊዉን ተጽዕኖ በብርቱ እንድትከላከል አስችሏታል። ለዚህ ታላቅ ውሳኔ የሀገሪቱ መሪዎች ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽዖ ምሥጋና ሊቸራቸው ይገባል። የመሪዎቹ ማሳመኛና የመከላከያ ሐሳባቸውም፡-
ሀ/ ሕዝቡ በሚገኝበት የክርስትና እና እስልምና ሃይማኖቶች መጻሕፍት ግብረሰዶማዊነት የተወገዘ መሆኑ፣
ለ/ ለረዥም ዘመናት ከአንዱ ትውልድ ወደ ቀጣዩ ትውልድ በቅብብሎሽ ተጠብቆ የቆየውና አሁንም የሚገኝበት ባህልና ሞራል ግብረሰዶምን ጸያፍና ርኵስ አድርጎ ስለሚያምን ነው። በሌላ በኩል ሕዝብ መንግሥት ነው፤ መንግሥትም ሕዝብ ስለሆነ የሕዝብን ዕሴት ሕዝብ ራሱ ያስከብረዋል።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች የምናየውና የምንሰማው ሁኔታ፣ እኒህ ለዘመናት ተጠብቀው የቆዩት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ሞራላዊ እሴቶቻችን አደጋ ላይ መውደቃቸውን ነው። ጭፈራ ቤቶች፣ የጫትና ደባል ሱስ ማዘውተሪያ ሥፍራዎች፣ ምሽት ክለቦች፣ አንዳንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሳይቀሩ በዚህ የዐመጽ ተግባር መጠለፋቸውን የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ። ከዚህ አኳያ እንደ ሀገር የተደቀነብን ሥጋት ምን ያህል አሰቃቂ እንደሆነ በቃላት መግለጥ ያስቸግራል። ስለሆነም ወላጆች ልጆቻቸውን፣ የሀገር መሪዎች በየተዋረድ ያሉ አመራሮቻቸውን፣ የሃይማኖት
አባቶች ምዕመናኖቻቸውን፣ እንዲሁም በየዘርፉ የሚገኙ ምሑራን ሀገርንና ትውልድን ለማዳን በአንድነት የሚቆሙበት ግዜ አሁን ነው።ከላይ እንደጠቀስኩት ምዕራባውያን ለጸያፍ ድርጊታቸው ዕውቅና ይስጡት እንጂ የተጋፈጡትን ማኅበራዊ ቀውስ ከቶውኑ ሊቋቋሙ አልቻሉም። ቀላል ቁጥር የማይሰጣቸው ዜጎቻቸው ራሳቸውንና ሌላውን በማጥፋት ተግባር ውስጥ መሆናቸውን ከብዙኀን መገናኛዎቻቸው እያየን እየሰማንላቸው ነው። ይህም ሰዶማውያኑ ራሳቸውን በመውቀስና በሚሰማቸው ጸጸት የተነሣ እንደሆነ የሥነልቡና ምሑራን ይናገራሉ።
እንደ CDC /Center for Disease Control/ ያሉ ዓለማቀፍ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል፣ ግብረሰዶማዊነት ከሚያስከትላቸው አያሌ ጉዳቶች ውስጥ ስድስቱን በሳይንሳዊ ጥናታቸው ይፋ ያደረጉ ሲሆን ለግንዛቤ እንዲረዳን በአጭር በአጭሩ እንያቸው፡-

ተላላፊ በሽታ
ሰዶማዊነት በግብረሥጋ ለሚተላለፉ በሽታዎች በተለይም ለባክቴሪያና ቫይረስ ተጋላጭ ያደርጋል። እነዚህ ተላላፊ በሽታ አምጭ ረቂቅ ተዋህሲያን ከአንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው በቀላሉ የሚተላለፉ ሲሆን፣ የበሽታ ተቀባዩ ሰው በተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅም /Immunity system/ ሊቋቋመውና ሊከላከለው የማይችለው ይሆንበታል። እንደ ሲዲሲ መረጃ ከሆነ በአሜሪካ ከጠቅላላው ሕዝብ ሁለት በመቶ ያህሉ ግብረሰዶማዊያን እና ሌዝቢያን ሲሆኑ፣ ከእነዚህም ውስጥ ስልሳ አንድ በመቶዎቹ በደማቸው ውስጥ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ያለባቸውና ከቫይረሱ ጋር መኖራቸውን እንኳ የማያውቁ ናቸው። ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሣ የደም ምርመራ አያደርጉም። ይህ ማለት ለሕይወታቸው ዋጋና ትርጉም አይሰጡም እንደ ማለት ነው።

የኢኮኖሚ ድቀት

በአንድ ሀገር አምራችና የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ የሚባለው ከ15 እስከ 64 ዕድሜ ድረስ ያለው የሰው ኃይል ሲሆን፣ ከ65 ዓመት በላይ የሚገኙ አረጋውያንና ለሥራ ያልደረሱ ሕፃናት ደግሞ ጥገኛ ወይም በኢኮኖሚ መዋቅር ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የሌላቸው እንደሆኑ የሥነ-ምጣኔ ባለሞያዎች ይናገራሉ። ስለዚህ የአንድ ሀገር አምራች ኃይል ሲታመምና በሞት ሲለይ፣ የምርት መጠን የሚቀንስና ተተኪ የሰው ኃይል እስኪዘጋጅ ድረስ ኢኮኖሚው እንደሚናጋ ነው እነዚሁ ባለሙያዎች የሚገልጹት።ከላይ የተጠቀሰው ድርጅት ባካኼደው ጥናት የአሜሪካ መንግሥት፣ ለ40 ሺ ያህል ታማሚዎች ወይም በሥራ ገበታቸው ላይ ላልተገኙ ሠራተኞቹ ማስታመሚያ በዓመት 12 ነጥብ 1 (አሥራ ሁለት ነጥብ አንድ) ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በአመዛኙ የሚሞቱ ናቸው ብሏል። እንግዲህ የበለጸገችዋን አሜሪካን ችግሩ ይህን ያህል ከነቀነቃት ኢትዮጵያንና ሌሎች ደሀ ሀገራትንማ
እንዴታ! እንዴታ!

የአዕምሮ ሕመም

ግብረሰዶማዊነት በርኵሳን መናፍስት ግፊት የሚፈጸም ሰይጣናዊ ተግባር በመሆኑ በመልካምና ቅዱስ መንፈስ ሥራቸውን ከሚያከናውኑ ሰዎች አዕምሮና አስተሳሰብ የተለየ የአዕምሮ ሕመም ያጋጥማቸዋል። ስለዐመፃ ተግባራቸው በቤተሰዎቻቸውና ኅብረተሰቡ ስለሚገለሉ በታናሽነትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ከባድ ለሆነ የአዕምሮ ሕመም ይዳረጋሉ። የጥፋተኝነት መንፈስ፣ ፍርሃት፣ ድብርት፣ ብስጭት፣ ራስን ለማጥፋት መነሣሣት ወዘተ… ዓይነቶቹ ስሜት በግብረሰዶማዊነት የሚመጡ ናቸው። ከጠቅላላው ግብረሰዶማዊ ሃምሣ በመቶ ያህሉ በጭንቀትና ድብርት እንዲሁም ለአደንዛዥ ዕጾች የተጋለጡ ናቸው።
በጥፋተኝነት ስሜት ደግሞ ሁሉም ማለት ይቻላል ራስን በራስ እስከማጥፋት ግዴለሾች ናቸው። የአንድ ግብረሰዶማዊ ዕድሜ ከአንድ ጤነኛ ሰው በ24 ዓመት ያህል ያነሰ እንደሚሆን ጥናቶች ያሳያሉ። በሚያድርባቸው ክፉ መንፈስ የተነሣ ሰዎችን የመጥላት፣ የመተናኮል፣ የመበቀልና ለማናቸውም ግጭቶች በቀላሉ ተጋላጭ ያደርጋቸዋል።

ጠለፋ

ብዙዎቻችን ጠለፋ የሚፈጸምባቸው ለጋብቻ የደረሱ ሴቶች እንደሆኑ እናውቃለን። አሁን ግን ግብረሰዶማዊነት በመስፋፋቱ ምክንያት ጠለፋ የሚፈጸምባቸው ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንድ ሕፃናትም የድርጊቱ ሰለባ ሆነዋል። በንጽጽር ሲታይ በአሜሪካ ከተፈጸሙት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል 24 በመቶው
በግብረሰዶማውያን እና 9 ነጥብ 6 በመቶ ያህሉ በተቃራኒ ጾታዎች ‘Heterosexuals’ እንደሆነ ነው። በእርግጠኝነት ሁሉም ወላጅ በልጁም ሆነ በወገኑ ጠለፋና የአስገድዶ መደፈር ጥቃት እንዲገጥመው አይሻም። ይሁንና በአሁኑ ወቅት ወንጀሉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ሕፃናቱን በተገቢው ሁኔታ ሊቆጣጠር ይገባል። ለሱስ ተጋላጭ በሆኑ ነገሮች እንዳይጠመዱና የርኵሰቱን ዓላማ ከሚያስፋፉ ሰዎች እንዲርቁ መምከርና ማስተማር ያስፈልጋል።

ብዙ የወሲብ ጓደኞችን ማጥመድ
ግብረሰዶማውያን እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ የወሲብ ጓደኞችን ይቀያይራሉ። ይህም እርስ በራሳቸው በሚያድርባቸው አለመተማመንና በጨለምተኝነት ሕይወት መኖራቸውን ያመለክታል። ተመራማሪዎቹ ቤልና ዌንበርግ ስለዚሁ ጉዳይ ባደረጉት ጥናት “83በመቶ ያህሉ ግብረሰዶም አሜሪካውያን 50 ያህል የወሲብ ጓደኛ፣ 43በመቶ ያህሉ 500 የወሲብ ጓደኛ፣ 28በመቶ ያህሉ ደግሞ ከ1000 ወይም ከዚያ በላይ የወሲብ ጓደኞች ይኖራቸዋል” ብለዋል። ሉማን የሚባል ሌላ ተመራማሪ ደግሞ “85በመቶ ያህል ሴቶች፣ 75በመቶ ያህል ወንዶች ለወሲብ ጓደኞቻቸው ታማኝ አይደሉም፤ 4 ነጥብ 5 ያህሉ ግብረሰዶማውያን ለወሲብ ጓደኞቻቸው ይታመናሉ” ይላል። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግብረሰዶማውያን እንደ ዓለማቀፉ ምሥጢራዊ ቡድን /Member of secret society of the world/ ጋር ግንኙነት እንዳላቸውና ይህም ትስስርን በመፍጠር አባላትን ለማብዛት ሚንቀሳቀሱበት ስትራቴጂ መሆኑ ነው።

የኅብረተሰብ እልቂት
ምንም እንኳ በተጠላ ተግባራቸው ቢገለሉም ግብረሰዶማውያን የማኅበረሰብ አባል፣ የሀገር ዜጎችና የዓለም ሕዝብ አካል ናቸው። እናም በሚፈጽሙት ውጉዝ ተግባር የተነሣ ለተለያዩ ሕመሞችና ራስን በራስ ማጥፋት ወዘተ… ተጋልጠው ካለቁ ግለሰብ ሳይሆን ቤተሰብ፣ ቤተሰብ ሳይሆን ኅብረተሰብ ብሎም የሀገር ሞትና ጥፋት ይከተላል። ጋብቻ ተመሥርቶ ዘር ካልተተካ፣ ሥራ ተሠርቶ ምርት ካልጨመረ፣ ሰው ታምሞ ካልዳነ በርግጥም የኅብረተሰብና የሀገር ሞት መሆኑ የማይታበል ነው።እንግዲህ ስለግብረሰዶማዊነት ጠንቅና የሚያስከትለው መዘዝ ይህን ያህል ከተመለከትን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት
እስከ ራዕይ ድረስ ደግሞ ፍጹም የተጠላ እና ሞት የሚገባው ኃጢአት ተደርጎ መጠቀሱን ባለመዘንጋት ነው። ለአብነት ያህል ግን ተከታዮቹን ማየት እንችላለን። ዘፍ ፲፱. ፩- ፴፰ ‹‹ሁለቱ መላእክቶች በመሸ ግዜ ወደ ሰዶም ገቡ። ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ግዜ ሊቀበላቸው ተነሣ። በፊቱንም ተደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፤ አላቸውም ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ፤ ከዚያም እደሩ። እግራችሁንም ታጠቡ። ነገ ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትኼዳላችሁ። ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየሥፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ ቤቱን ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፡-
በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው አሉት። ሎጥም ወንድሞቼ ሆይ! ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ እነርሱን ላውጣላችሁ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ እነርሱ በጣሪያዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና። እነርሱም ወዲያ ሂድ አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ፤ ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል፤ አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን፤ ሎጥንም እጅግ ተጋፉ፤ የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ። ሁለቱም ሰዎች ሎጥን ወደ ቤት አገቡት፤ መዝጊያውንም ዘጉት። በቤቱ ደጃፍ የነበሩትም ሰዎች ከታናሾች ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው። ደጃፉንም ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ። ሮሜ ፩፤፳፮-፳፰ ‹‹ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው።
ሴቶቻቸውም ለባህሪያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕሪያቸውን በማይገባ ለወጡ። እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕሪያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በራሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ። ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስህተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ።››

ማጠቃለያ

ግብረሰዶማዊነት በሃይማኖትም በሳይንስም ጎጂ እና የተጠላ ድርጊት መሆኑን ለማሳየት ሞክሬያለሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲያውም ሰውን ከመግደል በተካከለ ሁኔታ ኃጢአት መሆኑን ተናግሮ ሲያበቃ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ከእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደሌላቸው ገልጿል። አንዳንዶቹ ግን መጽሐፉ አላወገዘንም ሲሉ ይደመጣሉ። ይህ ፍጹም ክህደት ነው። መጽሐፉን ቢክዱ እንኳ ይህች ዓለም በመረጃና በብዙ የተፈጥሮ ምስክርነት የጸናች ናት። ስለዚህ ካላወቁ መማር፣ ከተማሩ የተማሩትን መተግበርና በሥራ ማሳየት ይልቁንም ከዚህ አጸያፊ ተግባር መውጣት አለባቸው። መጽሐፉማ እንኳንስ ግብረሰዶማዊነትን የሚያህል አስከፊ ተግባር ይቅርና ለትንንሽ በደልና ኃጢአት ሥርዓትና ሕግን የሚሠራ መጽሐፍ ነው። ለምሳሌ ከግብረሰዶማዊነት ውጭ ያለው ራስን በራስ የማርካት /Masturbation/ እና መሳሳም ወዘተ… ሁሉ ትክክል እንዳልሆኑ የሚያስተምር መጽሐፍ ነው። ይልቁንም እንደዚህ ሚያደርጉ ሁሉ ሕግን ተላልፈዋልና ንስሐ ካልገቡ፣ ደግመው ወደ ኃጢአት እንዳይመለሱ ቃል ገብተው ለእግዚአብሔር ካልታመኑ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

(አባ ሣሙኤል፤የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ናቸው።)¾ *ይህ ጽሁፍ በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወትቷል።

“ጉድ በል ጎጃም አለ ያገሬ ሰው!” የወያኔኢሕአዴግ ተላላኪው የዳላሱ ወጣት ኢብራሂም ሲራጅ ማን ነው?

$
0
0

በሚሊዮን ኢትዮጵያ(ከዳላስ)

dallas1ወያኔ/ኢሕአዴግ በውጭ ሃገር የሚኖሩት ኢትዮጵያውያንን ለማደራጀት የሚያስችላቸውን የጥፋት ውጥን በመወጠን ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል ተወልደውያደጉ ለሆዳቸው ያደሩ አደርባዮችን በመመልመል የቤት ስራውን እየሰራ ይገኛል። አያሌ ኢትዮጵያውያን የስርአቱን አስከፊነት በመገንዘብ ሳይወዱ በግድ የሚወዱት ሃደራቸውና ሕዝባቸውን ትተው ቢሰደዱም እንኳን  እስካሉበት የስደት  ሃገር በመከተል የከፋፍለህ ግዛ መሰሪ ፖሊሲያቸውን ለማስፈጸም በፖሊሲ ደረጃ በመንደፍ የጥፋት ተግባራቸውን ገፍተውበታል። በዚህም መሰረት ምንም እንኳን እዚህ ገቡ የሚባሉ ቁጥር ያላቸው አባላት ማፍራት ባይችሉም ጥቂት ርካሽ ተውዳጅነት ለማትረፍና የግል ንዋይ ፈላጎታቸውን ለማሟላት ከመራሹ መንግስት ጋር በመተባበር ህዝብን ለማወናበድና ለማታለል የሚተጉ ግን አልጠፉም።  ኢብራሂም ሲራጅ ከእነዚህ በጥቅም ከተደለሉትና የመሰሪው የወያኔ መንግስት ተልእኮ ለመወጣት ሌት ተቀን ደፋ ቀና ከሚሉት አንዱ ነው።

ዳላስ በወያኔ መሰሪ ተባባሪዎች እጅ ወድቃለች ማለት ባይቻልም እነዚህ ጥቂት ርዝራዦት በኮሚኒቲ፣ በቤተክረስቲያንና በሌሎችም ኢትይጵያዊ በሆኑት ተቓማት እጃቸውን በማስገባት ቀላል የማይባል የጥፋት ተልዕኮአቸውን ለመወጣት ሌት ተቀን ደፋ ቀና እያሉ ለቱባ የወያኔ አለቆቻቸው ታማኝ ለመሆን ተግተው ይሰራሉ። ምንም እንኳን በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አላማቸውን ማሳካት ባይችሉም። የጥፋቱ ሰለባ ከሆኑት ኢትዮጵያዊ ተቓማት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያንና (http://www.stmichaeleoc.org/) በዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የጋራ መረዳጃ ማህበር (http://maaecdallas.org/) ዋና ተጠቃሽ ናቸው። በእነ አቶ ተፈራወርቅ (ጋሻው ኢንሹራንስ) የሚመራው የጥፋት ቡድን አማካኝነት ቤተክርቲያኒቷን ፍርድ ቤት ሶስት ጊዜ በመክሰስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮች ወጪ ዳርገዋል። ኮሚኒቲውም ምርጫ በመጣ ቁጥር የወያኔ ጀሌዎቻቸውን ለማስረጽ ህዝብን በማወናበድ ላይ ይገኛሉ። ከወራት በኳላ የሚደረገውን የመራዳጃው ማህበር የቦርድ አባላት ምርጫ ላይ የወያኔ አባላትን ለማስገባት ተጽዕኖ ለመፍጠር የቤት ስራቸውን እየሰሩ ናቸው። ይህ እውነታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሁሉም የኮሚኒቲው አባላት ኮሚኒቲው በወያኔ እጅ እንዳይወድቅ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ሊታደገው ይገባል።

እነዚህ የጥፋት ሃይሎች እራሳቸውን “ሰበቡ” የሚል ስያሜ በመስጠት በእነ ተኮላ፣ ደምመላሽ፣ ተፈራወርቅና ሌሎችም መሪ ተዋናይነት የሚመራ ሲሆን ሁሌም ምክንያት እየፈጠሩ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮ በተነጠቀ በወያኔ በተመደበላቸው ባጀት ስጋዊ ፍላጎታቸውን የሚያስደስቱ ለሌላው ግድ የሌላቸው ህሊናቸው የሸጡ አገርና ሕዝብን የካዱ የግል ጥቅማቸውን ብቻ የሚያዩ ስንስቦች ናቸው። የማህበሩ አባላት ለሚሰሩት የጥፋት ተልዕኮ ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በትውልድ ቀዬያቸው በህገ ወጥ መንገድ ከድሃው ምስኪን የሃገሬ ገበሬ መሬት እየተነጠቀ ለውለታቸው የመኖሪያና የንግድ ቦታ መስሪያ ይሰጣቸዋል። ኢብራሂም ሲራጅ የዚህ ማህበር ተላላኪ እንደመሆኑ መጠን የጽዋው ተቓዳሽ በመሆን በባህር ዳር ከተማ ሲኒማ ቤት መስሪያ ቦታ ለውለታው ተችሮታል። እነዚህ የጥፋት ሃይሎች ኢትዮጵያውያን በሚሳተፉበትና የገቢ ማሰባሰቢያ ቦታዎችን በመገኘት ወያኔኢሕአዴግ ለዚህ ተግባር በተመደበውብ ባጀት በመለገስ ሕዝብን ለማወናበድና የኮሚኒቲው ተቆርቓሪ ለመምሰል ይጥራሉ።

የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ፕላን(GTP) በተመለከተ የወያኔ/ኢሕአዴግ ቱባ ባለስልጣናት ወደ ሰሜን አሜሪካ በመጡበት ወቅት ምንም እንኳን ጥሪው ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚመለከት ቢሆንም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለመታደም ግን አልታደሉም። ስብሰባው ለመታደም የተዘጋጀበት ስፍራ ብሄድም ውይይቱን ለመካፈል ከተነፈጉት አንዱ ነኝ። የኢትዮጵያ ጉዳይ የሁሉም እንጂ የወያኔ አባላት ብቻ አለመሆኑን እይርታወቅ ስብሰባውን ለጥቂት አባሎቻቸው ብቻ በደብዳቤ በመጥራት ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደብዳቤ የላች ሁም በማለት ወደ ስብሰባ አዳራሹ እንዳይገቡ ተደርገው በፖሊስ እንዲባረሩ ተደርገዋል። በዚህ ወቅት እንዳይገቡ የተደረጉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሲያሰሙ ለወያኔ የደህንነት አባላት የሚላክ ቪዲዮ በመቅረጽና ተቃውሞ እያሰሙ በነበሩት በመሳለቅ ኢብራኢም ሲራጅ ለወያኔ ታማኝነቱን አሳይቷል። ይህ ደግሞ ከሃገርና ህዝብ ክህደት በተጨማሪ ለዲያፖራው ማህበራሰብ ያለው ንቀት ምን ያህል እንደ ሆነ ያሳያል።

ኢብራሂም ሲራጅ በሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌደሬሽን(ESFNA) ዳላስን ወክለው ከሚጫወቱት ሁለት የስፖርት ክለቦች አንዱ በሆነው ኢትዮ ዳላስ ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ላለፉት 11 አመታት ስጫወት ነበር ብሎ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጠው ቃለ መጠየቅ በፍጹም ከውነት የራቀ መሆኑን ቡድኑ ውስጥ ከሚጫወቱት አባላት ለመረዳት ችያለሁ። ለነገሩ መች ኢቲቪ እውነት አውርቶ ያውቅና። ወያኔ ማለት የውሸት ከረጢት መሆኑን ከታወቀ ውሎ ሰንብቷል። ነገር ግን ቡድኑ አባላት ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባት እጁን በማስገባት ከጀርባ በመሆን ለሁለት እንዲከፈሉና ልዩነታቸው በሰላም እንዳይፈቱ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል። ወጣቶቹ ችግራቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከማድረግ ይልቅ ከዋናው ቡድን እራሳቸውን ላገለሉት አባላት የቅርብ ጓደኞቹና ዘመዶቹ በመመልመል የጥፋት ሴራውን ሲሸርብ ነበር። ምንም እንኳን ያሰበው አላማ ባይሳካለትም የመጨረሻ ግቡ ግን ወጣቶቹን በጥቅም በመደለል የዛሬ ሁለት አመት ገደማ በአብነት ገመስቀል መሪ ተዋናይነትና በሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ ለተቓቓመው የስፖርት ማህበር ለማስረከብ ነበር።

ኢብራሂም ሲራጅ በአሁን ሰአት ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ ቴሌቪሽን በእንግዳ ፓሮግራም በተደረገለት ቃለመጠየቅ ኢትዮጵያ ውስጥ የማይካድ ለውጥ አለ፣ በውጭ ኃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስለ ልማቱ የሚናገሩትን አልሰማም፣ ወያኔኢሕአዴግ በሚያደርጋቸው ሁሉም ስብሰባዎች መሪ ተዋናይ ነኝ፣ የፖንድ ሽያጭና በቅርብ የማውቃቸው አቅም ያላቸው ኌደኞቼን በማስተባበር ላይ ግንባር ቀደም ነኝ ይለናል። በዚህም አንባገኑ የወያኔ ስርአትን ቀንደኛ ደጋፊ መሆኑና መራሹ ወያኔ ልማታዊነት ምስክርነት ይሰጣል። ውሸታሙን ኢቲቪንና ወያኔን እውነትነት አስረግጦ በመናገር የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ውሸታም መሆኑን ይነግረናል። ይህ ደግሞ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ያለው ንቀት ያሳያል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንባገነኑ ስርአት ለእስራት፣ ለስደት፣ ለሞት፣ ለረሃብ፣ ለእንግልትና ለስቃይ እየተዳረገ ባለበት ሁኔታ ወያኔን ማሞካሸትና ልማታዊነት መመስከር የህሊና ዳኝነት የጎደለው ከመሆን ውጪ ምን ይሉታል። ለመሆኑ ወያኔ የሚለውን የሚያስተጋባለትን እንጂ መች ሕሊና ያለው ሰው ይፈልግና።

ጀግናው በላይ ዘለቀ ያፈለቀችው ጎጃም ኢብራሂም ሲራጅ አሳድጋለች የናት ሆድ ዥንጉርጉር ይሉታል ይህ ነው። አንዱ የባህርዳር አንድ ክለብ የሚያሰነጥለው አብሮ አደጉ ስለ ኢብራሂም ሲራጅ ሲናገር ይህ ትልቅ ሃብታችን ነው ልንጠቀምበት ይገባል ብሎናል። ጀግናው በላይ ዘለቀ በተወለደበት ሃገር ሃገሩን ሽጦ ለሆዱ ያደረውን እንደ ሃብት ሲቆጠር ጉድ በል ጎጃም ማለት ይሄኔ ነው።

ውድ የሐገሬ ልጆች ሆይ ኢትዮጵያ ሃገራችን አንድነቷና ዳርድንበሯ ጠብቃ ልትቆይ የቻለችው ብዙ የደም መስዋዕትነት ተከፍሎባት እንድሆነ ሁሉም ጠንቀቆ የሚያውቀው ስለሆነ እኔ ልነግራች ሁ አልሻም ለቀባሪ ማርዳት እንዳይሆንብኝ። ዛሬ ግን ወያኔና ግብራበሮቹ ይህን ታሪክ ለማጥፋት የዘር ፖለቲካ በመከተል ህዝቡን አንድነቱን እንዳይጠብቅ በማድረግ፣ የገዛ መሬታችን ለጎረቤት ሀገራት አሳለፎ በመስጠት፣ ምስኪን ገበሬ በማፈናቀል ለውጭ ባለሃብት በመሽጥና ሌሎችም አያሌ መሰሪ ተግባራቸውን ገፍተውበታል። ወያኔ/ኢሕአዴግ ያለ ሕዝብ መልካም ፍቃድ ስልጣን በአፈሙዝ በማስፈራራት ቢቆናጠጥም ሕዝብ ያለመረጠው መንድስት ዘላቂነት ሊኖረው ስለማይችል ሰርጎገብ ከሆኑት የወያኔ ተላላኪዎች ሰላባ እንዳንሆን ነቅተን በመጠበቅ ማጋለጥ ይኖርብናል። የዚህ ጽሁፍም ዋናው አላማም ይህ ነው።

ኢብራሂም ሲራጅ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግዳ ፕሮግራም ያደረገው ቃለመጠይቅ እዚህ በመጫን ይመልከቱ! http://www.diretube.com/engeda/ebrahim-serag

አንድ ሕዝብ!!!

አንድ ኢትዮጵያ!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም አንድነቷን ጠብቃ ትኑር!!!


ጅራፍ ራሷ ገርፋ ራሷ ትጮሃለች (አስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል)

$
0
0

‹‹ብርሃኑ በርሄ የህወሓት አባል ነው›› 
አስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል (ከመቀሌ)

 

አስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል

አስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል

የአረና ሊቀ መንበርና ሌሎች አመራሮች ባለፈው ሃምሌ 18-20/2006 ዓ.ም በተካሄደው መደበኛ የማ/ኮሚቴ ስብሰባ በጠንካራ አባላቱና አመራሮች በተወሰደው ህገ- ወጥ እርምጃ ጥፋታቸውን ለመሸፈን በተለያዩ ጋዜጦች፣ መፅሄቶችና ማህበራዊ ድረ-ገፆች የስም ማጥፋት ዘመቻ ተዘምቶብን እንደሰነበተ የሚታወስ ነው። እኛም ግብረ መልስ ስንሰጥ ቆይተናል። አሁን ደግሞ የስም ማጥፋትና ውሸታም ተግባራቸው ቀይረው በሌላ መልክ ወንጀላቸውን ለመሸፈን እየሞከሩ ነው። 

መነሻየ በነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ነሃሴ 2/2006 የአረና ሊቀመንበር ብርሃኑ በርሄ በሰጠው ቃለ ምልልስ እኛን በተመለከተና አጠቃላይ የትግል ሂደቱን መሰረታዊ ስህተት በመሆኑ ዋና ዋና ነጥቦችን በመለየት መልስ ለመስጠት ተገድጄለሁ። 

ብርሃኑ በርሄ ‹‹ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ ገዢው ፓርቲ በሰላማዊ መንገድ በምርጫ ውድድር ከስልጣኑ እንዲወርድ ማድረግ አልያም የመንግስት ስልጣን ባንይዝም የህዝብ ጥያቄና አጀንዳ የፖለቲካ ስራችን ማእከል በማድረግ ተገዶም ቢሆን መሻሻል እንዲያደርግ በመታገል ለውጥ እናመጣለን ብለን ነው የምናምነው›› ይላል። ብርሃኑ በርሄ የተወላዋይ ሃይሎች አስተሳሰብ እዚህ ሲጋለጥ፤ እኛ አረናዎች የምንታገለው አምባገነኑ የህወሃት ስርአት እናስወግዳለን ስንል በአይዶሎጂ በሁሉም አንድ አይነት ፖሊሲዎች በሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት አጠባበቅ ባለን መሰረታዊ ልዩነት ህወሓት ኢህአደግን በምርጫ በማስወገድ የስርአት ለውጥ ለማምጣት ነው። ብርሃኑ በርሄ ግን የህወሓት መሪዎች በሚፈልጉት አቅጣጫ እየተራመደ ‹‹እኛ ስህተት ካለን በውስጣችን ሁናችሁ አስተካክሉን ለጠባቦችና ትምክህተኞች አሳልፋችሁ አትስጡን›› የሚሉት አቋም የሚያራምድና ሁለተኛ ልደቱ ሁኖ በስመ ተቃውሞ እየሸወደን ይገኛል። 

ብርሃኑ: ‹‹አፈናው እጅግ መጠናከሩና የፋይናንስ አቅማችን ውስኑነት የሚፈጥሩት ጫና ካልሆነ በስተቀር ከህዝብ ድጋፍና ፖሊሲያችን ከማስተዋወቅ አንፃር በመጪው ምርጫ ሰፊ ሽፋን ሊኖረን ይችላል›› ይላል። ሙሽራ ሳይዙ ሚዜን ይቀጥራሉ እንደሚባለው የብርሃኑ መጪው ምርጫ ለማሸነፍ ወይስ ለመሸፈን? የህወሓት ተግባራት በማጋለጥ የራስህን ሃሳብ በግልፅ ለህዝብ በማሳመንና የህዝብን ማዕበል በመፍጠር ነው ማሸነፍ የሚቻለው። ብርሃኑ በርሄና ጓደኞችህ ግን በዘንድሮ አመት በ8 ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባ ተጠርቶ በ6 ከተሞች ሲከሽፍ በቀሩት ከተሞች ጥቂት ከተሞች ነው ያገኘነው። የተሰራጩ የቅስቀሳ ፅሁፎችም የህዝቡ ችግር ነቅሰው የሚያወጡ ሳይሆኑ ለህወሓት መሪዎች ተገዢነትና የተለሳለሱ እንደውም የሚያሞካሹም ጭምር ነበሩ። በነዚህ እንቅስቃሴዎች ጥቂት አመራሮች እንደ አብርሃ ደስታና እኔ የመሳሰልን በጋዜጣ በፌስቡክ በሬድዮ የምናደርጋቸው ቅስቀሳዎችም በብርሃኑ በርሄና በአቶ ገብሩ አስራት ተቀባይነት አልነበራቸውም። ለዚሁ እንደ ማረጋገጫ ብርሃኑ በርሄ እኔ በነበርኩበት ለ5 ስራ አስፈፃሚ አባላት ሰብስቦ በሚዲያ የምትፅፉትና በሬድዮ የምትናገሩት ለህወሐት መሪዎችና ካድሬዎች የሚያናድድ መሆን የለበትም፡፡: ተናደው በኛ ላይ እርምጃ ሊወስዱብን ነው ብሎ በተለይ በኔና አብርሃ ደስታ በማነጣጠር ነው ሽብር የፈጠረብን። አቶ ገብሩ አስራትም ከ8 ወር በፊት አዲስ አበባ ላይ በተደረገው የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ በጥያቄ መልክ ያነሳው ‹‹አብርሃ ደስታና ሌሎች የሚፅፉትና የሚናገሩት ከፖሊሳችንና ከመስመራችን ጋር አብሮ ይሄዳል ወይ እነዚሀ ሰዎች ቢቆጠቡ?›› ብሎ ተናግረዋል። በዛን ወቅት አብርሃ ደስታ ተናዶ ‹‹ይህ አባባል የግለሰቡን ነፃነት ይነጥቃል›› ብሎ መልስ ሰጥቶታል። 

በሌላ በኩልም የፋይናንስ እጥረት ካልወሰነን ብዙ ስራ እንሰራለን የሚለው የነበረው ገንዘብ መቸ አነሰና እድሜ ለደጋፊዎቻችንና‼ ግን ያ ገንዘብ በጥቂት የቡድን አመራሮች በብርሃኑና ሶስት ስላሴዎች ቁልፍ በመሆኑ የፋይናንስ ስርአታችን በጣም የተበላሸ ከመሆኑ በላይ ለሙስና የተጋለጠ ሁኖ ይገኛል። 

አረና በምርጫ ሰፊ ሽፋን እንዲኖረው ከተፈለገ ብርሃኑ በርሄም ሊቀ መንበር ሁኖ ከተደበቀ፤ እነ ገብሩ አስራትም አዲስ አበባ ምሽግ ከሰሩ፤ አባሉና ህዝቡ ማን ያንቀሳቅሰዋል? ብርሃኑ በርሄና የአረና ህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ተብየው አምዶም ገ/ስላሴ’ኮ ሌላው ቀርቶ ሚዲያዎች ስለ አብረሃ ደስታ መረጃ እንድትሰጧቸው ፈልገው በተደጋጋሚ ስትጠየቁ ፍቃደኞች አይደላችሁም፡፡ ለምሳሌ እንደ ማስረጃ ኢሳትን መጥቀስ ይቻላል። በምርጫ ብዙ ቦታዎች መሸፈን ይቻላል የምትለው የትኛው አባል ይዘህ ነው ምትሸፍነው? ከአለቆችህ በተሰጠህ ትእዛዝ’ኮ አባሉን በትነኸዋል። በየትኛው አቋምህ ጠባብ ፀረ-አንድነትና ውህደት የሆነ ጠባብ የህወሓት አስተሳሰብ ወርሰህ ሰፊ የኢትዮጵያን መሬት ምትሸፍነው? አሁንም ዜጎችን ባትሸውዱ‼

ብርሃኑ በርሄ፡ ‹‹በፓርቲው ችግር የለም ነገር ግን የሰዎች አቋም ባህሪም ጭምር በእንቅስቃሴው ፈተና ውስጥ ስለሚገቡ አንዱ ጠንከሮ ሲወጣ ሌላው አዳናቃፊ የሚሆንበት አጋጣሚ ይስተዋላል፤ እንቅስቃሴው ሲበረታና እንቅስቃሴውን ለማኮላሸት የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሲበዙና ሲከብዱ ተስፋ መቁረጥም የሚጠበቅ ነው፤ ሌላው ደግሞ እንቅስቃሴው የሚወልዳቸው ፈተናዎች ከብደውት ወይ ብዥታ አድሮበት የመቀዛቀዝና ግራ የመጋባት ባህሪ ይስተዋላል›› ይላል። 


በአረና ውስጥ ዋናው ችግር ፈጣሪዎች አንተና አለቆችህ ናችሁ፤ በ2002 እኮ አንተና እነ ገብሩ አስራት እንቅስቃሴያችን ከመቀሌና አከባቢዋ መራቅ የለብንም፤ ለሪስክ (አደጋ) እንጋለጣለን አላችሁን፤ እኛ ገፍተን እኮ ነው ትግራይን ከጫፍ እስከ ጫፍ ተንቀሳቅሰን 138 ጠንካራ አባላት ለውድድር ያቀረብነው፤ እነ አረጋዊ ገ/ዮሃንስ’ኮ እንደ ሰንጋ በሬ የታረደው በበረሃ ሲቀሰቅስ ነው፤ ትግሉ የከበደህ’ኮ አንተ ነህ፤ ከባድ ነው በምትለው አከባቢ’ኮ ተደብቀሃል፤ ሌላው እንተወውና ዘንድሮ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ህዝባዊ ስብሰባዎች’ኮ በብዙ ቦታዎች ተደብቀሃል፤ የአኒማል ፋርም የአመራር ስልትህ በመከተል ችግር እየፈጠርክ ያለኸው’ኮ አንተ ነህ፤ ታድያ በየትኛው ሞራልህና ብቃትህ ነው አንተ “ተስፋ ቆርጠው የሚሸሹ አሉ” ማለት የምትችለው? ቁጥር አንድ ተስፋ አስቆራጭ አንተ መሆንህ እነዚህ በየግዜው ከፓርቲው የለቀቁ በሺ የሚቆጠሩና አሁን በፓርቲው ውስጥ ያሉም እየገለፁት የሚገኝ። ብርሃኑ ማን መሆንህ የትግራይ ህዝብ በተለይ የመቀሌ ህዝብ ያውቅሃል፤ የአድዋ፣ የአላማጣ፣ የአዲጉዶም፣ የውቅሮ፣ የማይጨውና ሌሎች አከባቢዎች’ኮ አቋምህ ከህወሓት ምንም ልዩነት እንደሌለህ ነግሮሃል።

ብርሃኑ በርሄ፡ ‹‹የአረና ከፍተኛ አመራር እነ አስራት አብርሃም ቡድናዊነት አለ ብለው ከፓርቲው መሸሻቸው በኔ እምነት ሃላፊነትን አለመወጣት ነው›› ይላል። እነ አስራት አብርሃም በፓርቲው ውስጥ የነበሩ ችግሮች አለመታገላቸው ከብርሃኑ እስማማለሁ። ነገር ግን ያሁኑ ወጣቶች ከዚያ ያረጀና ያፋጀ ፀረ-ዲሞክራሲ ትውልድ በቋንቋም በባህልና አስተሳሰብ አይግባቡም። እነ አስራት ብዙ ታግለዋል፤ በውስጣችን የነበሩ ችግሮችም ለመታገል ሞክረዋል፤ አንተ ስብሰባ ረግጠህ እስከምትወጣ፤ ምክንያት እየፈጠርክ ከስብሰባ ወጥተህ በግል ስራህ ትውል እንደነበርክ እናቃለን፤ ባንተና በ3ት ስላሴዎች ባህሪ ምክንያት እስካሁን እነ አስራትን ጨምሮ 18 ማ/ኮሚቴ፣ ስራ አስፈፃሚና ቁጥጥር ኮሚሽን ከፓርቲው አግልለዋል፤ ችግሩም አሳታፊነት የለም፣ አባታዊነት ነግሰዋል፣ የፋይናንስ ስርአታችን ግልፅነት የለም ወዘተ.በማለት ነው። እንድያው አንዳንዶቹ “የአረና አመራር በስም ካልሆነ ከህወሓት በምንም አይለይም” ብለው ላንተ የነገሩህ የአረና መስራች አባላት የነበሩ እጅግ ብዙ ናቸው። 

እነ አስራት አብርሃም በነበሩበት እኮ ቡድናዊነት እጅጉን የጠነከረ ነበር፤ ያ ቡድናዊነት በስራ አስፈፃሚ ውስጥ ከላይ እንደገለፅኩት አራታችሁ በድብቅ የጨረሳችሁት ጉዳይ ወደ ስራ አስፈፃሚና ማ/ኮሚቴ የሚቀርበው ለይስሙላ ነበር፤ ማ/ኮሚቴ ለስሙ የተቀመጠ እንጂ አምስት አመት ሙሉ የሰራውና የሚያውቀው አልነበረም፤ ያ ቡድናዊነት አሁንም ተባብሰዋል።
ብርሃኑ በርሄ፡- ‹‹እነ አስራት በለቀቁት ማግስት በተካሄደው 3ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ቡድናዊነት እንዳለ አስመስለው ሲናገሩ የነበሩ ግለሰዎችም አላሳመኑም ብቻ ሳይሆን ለስሙም አላነሱም፤ ስለዚህ እነ አስራትም ሆነ አስገደ የሚያማርሩት ቡድናዊነት አረና ውስጥ አልነበረም›› ይላል፡፡ ሀሰት ተደጋግሞ ሲነገር ሃቅ ይሆናል የሚል የነ ሂትለር፣ መንግስቱና ህወሓት ብሂል ይዘህ የትም አትደርስም። ከ3ኛ ጉባኤ በፊት በ3ት የስራ አስፈፃሚና በ2ት ማ/ኮሚቴ መደበኛ አመታዊ ስብሰባ ተነስተዋል፤ የፋይናንስ ስርአታችን በም/ሊቀመንበርና በ3ት ስላሴዎች በሚስጥርና በቡድናዊነት መሆን የለበትም፤ ወደ ስብሰባ የሚቀርብ አጀንዳ በህገ ደንብ መሰረት ሳይሆን በጥቂት ስራ አስፈፃሚ በቡድናዊነት መሆን የለበትም፤ የዲፕሎማሲ ስራዎች ለወጣት አመራሮች እድሉን አለመስጠት ወዘተ የሚሉ ወሳኝ ጥያቄዎች ተነስተዋል። የዚህ ቡድናዊነት እንደ ማስረጃ ደግሞ በ3ኛ ጉባኤ ታይቷል፤ የጉባኤው ተሳታፊዎች አባላት መሆናቸውና አለመሆናቸው ማይታወቁ፤ በጉባኤው ጠንካራ ነባር አባላት ወደ አመራር እንዳይመጡ አስቀድሞ በህዝብ ግኑኝነትና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች የማያውቁት ባወቁ ጊዜም የተቃወሙት አቶ ብርሃኑና 3ት ስላሴዎች ያወጡት ካሪክለም የውሸት ስልጠና የሰጥቷቸው ለጉባኤ የቀረቡ መሆናቸው ሁሉም አባል ያውቃል። ሌላው ቀርቶ በጉባኤ ብርሃኑና 3ት ስላሴዎች በየ6ት ሰአት በድብቅ እየተሰበሰቡ ይወስኑት እንደነበር ፤ከዚያም አልፈው የፕሮዚዴሙ ለቀመንበር አብርሃ ደስታም ወደ ቡድኑ በማስገባት በማስፈራራት ጉባኤው በድፈን ድፈን እንዲታለፍ ተደርጓል። በተለይ ደግሞ በውህደት ጉዳይ፣በፌደራሊዝም፣ በመሬት ጉዳይ፣ ህገ-ደንብን ማሻሻል በተመለከተ ጊዜ ስሌለለን የሚመረጠው ማ/ኮሚቴ አይቶ እንዲወስን አድርግ ብለው ጉባኤተኛ እንዲታፈን እንዳደረጉ አብርሃ ደስታና ስልጣኑ ሕሸ የሚመሰክሩት ነው። በተለይ ገብሩ አስራትና አረጋሽ አዳነ የፕሮዚዴም አባላት ስለነበሩ አብርሃ ደስታን ያስፈራሩት ነበር። ብርሃኑ በርሄ በአረና ቡድናዊነት አልነበረም፣ አሁን ደግሞ ቡድናዊነት የሚል ሃሜት ወደ አባታዊነት ተሸጋገረ። 

በአረና አባታዊነትና አምባገነንነትን በሚመለከት በየካቲት 2005 መደበኛ ማ/ኮሚቴ ስብሰባ እኔ አንስቼው ተሰብሳቢው ጠንከር ብሎ ለብርሃኑ በርሄ ሂስ በመሰነዘሩ ብርሃኑ አባታዊ በሆነ ትእቢት በተሞላበት በንቀት መድረክ ረግጦ ወጥቶ በኋላ ተለምኖ ነበር የተመለሰው። ሌላ የአባታዊነት መገለጫ በአረና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ የፋይናንስ አቅማችንና አሰራራችን ለሁሉም ስራ አስፈጻሚ ግልፅ ይሁን የሚል ጥያቄ ቀርቦ በአቶ አውዓሎም ወልዱ የፋይናንስ አቅማችን ሁሉ የስራ አስፈጻሚ አባል ሊያውቀው ግዴታ አይደለም የሚል ሃሳብ ሲሰነዝር ገብሩ አስራት ተቀብሎት አረጋሽም ጨምራበት በዛው አለፈ፤ ታዲያ ከዚህ በላይ አባታዊነት ምን አለ? ከፓርቲዎች የሚደረገው ግንኙነት በቡድንነት እንደሆነ ሲነገራቸው ያኮርፋሉ፤ ሁሉም ነገር እኛ እንጨርሰው በማለት አያሳትፉም ሌላ አባል ከሰራ እንደሚያበላሽ አድርገው ነው የሚያዩት፤ ሌላው ቀርቶ ግለ ሰዎች ገዢው ፓርቲን በማጋለጥ በሚዲያ የምንሰነዝረው ሃሳብ መጀመርያ ኢዲት እናድርገው ብለውናል ተቀባይነት ባያገኙም፤ ታዲያ የግለሰብ መብት መጣስ የለበትም የሚለው የአረና እምነት አይፃረርም?

በሌላ በኩል ወደ ውጭ የዲፕሎማሲያዊ ስራ ከወጣቶች እንላክ ስንል በነዚህ 4ቱ ሰዎች ተቀባይነት አላገኘም፤ ወጣቱ ምንም አይሰራም ያበላሻል’ጂ የሚል አመለካከት ነበር፤ በሃገር ውስጥም ስለ ውህደት የት ደረሰ ተብለው ሲጠየቁ ለሁሉም ነገር በሚስጥር ይዘውት ነበር፤ በመጨረሻ ከአንድነትና ሌሎች የአማራ ፓርቲዎች አንዋሃድም ሊውጡን ነው ብለውናል፤ እንደውም በዚህ በሃምሌ 19ና 20/2006 የማ/ኮሚቴ ስብሰባ በ3ት አቅጣጫ ጦርነት ተከፍቶብናል፤ 

1. በህወሓት 2. በበተቃዋሚ ፓርቲዎች 3. በውስጣችን ባሉ በጥባጮች በማለት እኛን ካባረሩ በኋላ ያወጡት መግለጫ ያሳያል። ይህንን ደግሞ ለምን ተነካን ብለው ያላቸው አባታዊነት አሳይተዋል። 

ብርሃኑ በርሄ ‹‹በአረና የመብት ጥያቄ አንስቶ የታፈነ አንድም የለም፤ ታፍነናል በማለት ለሃገር ውስጥና ለውጭ ሚዲያዎች ብቻ ሳይሆን ለማይመለከታቸው ፓርቲዎች ሳይቀር የዚህ አመት አስገራሚ ሊባል የሚችል ምርጥ ውሸት በመደርደር የፓርቲያችንና አመራሩ መልካም ስም ለማጥፋት የዘመቱ›› ይላል፡፡ ደግ ብርሃኑ ለማያውቀው ሰው ሲናገር ሃቅ መስሎ ሊሰማው ይችላል። ሃቁን ለመናገር ግን ካሁን በፊት ለመግለፅ እንደሞከርኩት በአረና ትግራይ ዲሞክራሲያውነት መስፈርት ብለን የምናምንበት ከግለሰው መብት እስከ ቡድንና የህዝቦች መብት መከበር ነው፤ በብርሃኑና ጓደኞቹ አመለካከት ግን የግለሰው መብት አያከብሩም ብቻ ሳይሆን በግልም ሆነ በቡድን ማንኛውም አይነት ጥያቄ ማስነሳት ወንጀል ነው፤ ለዚሁ ምስክር በተለያዩ ጊዝያት ጥያቄ በማንሳታቸው በመታፈኑ ከፓርቲው ራሳቸው ያገለሉ ግን ደግሞ በህወሓትነት የተፈረጁ ግን እስካሁን ከህወሓት ምንም ግንኙነት የሌላቸው አሉ፡፡

አሁን የተባረርን አባላትና አመራርም በፓርቲው ያሉ ነባራዊ ችግሮች ለማስተካከል ብለን በመድረክ፣ በፅሁፍ፣ በክስ መልክ ደረጃውን ጠብቆ ህገ ደንብን መሰረት በማድረግ ለ9 ወራት ጠይቀናል። ሌሎች በራሳቸው ይገልፁት ይሆናል። እኔ የሄድኩበት መንገድ ልግለፅ ፤ከ2003 እስከ 2005 በማ/ኮሚቴና ስራ አስፈፃሚ በፓርቲያችን መጥፎ ሁኔታ እንዳለ አንድ በአንድ ዘርዝሬ አቅርቤ ነበር። በተለይ ደግሞ በ2005 በአረና ውስጥ ስል አንድነትና ውህደት የላላ አቋም እንዳለ፤ አባታዊነትና አምባገነንነት ባህርያት እንዳለ፤ ከማ/ኮሚቴ እስከ ታች የተዘረጋ ቡድናዊነት ወዘተ. እንዳለ በአጠቃላይ ከላይ የገለፅኳቸው የፓርቲው ችግር እንዲስተካከሉ አንስቼ ነበር፤ በ3ኛ ጉባኤም በመድረክ አንስቼዋለሁ፤ ከጉባኤ በኋላም ከጥቅምት ወር 2006 ጀምሮ በማ/ኮሚቴ በተለይ በሊቀመንበሩ ስለ ሃገራዊ አንድነትና ውህደት የሚታዩ ችግሮች፤ ቡድናዊነት በማስፋፋት አባላቱ እንዲፈርሱ ሚደረገው መጥፎ ስራ፤ ከህወሓት ካድሬዎችና አመራሮች የጠበቀ ግንኙነት መኖር እስከ በህብረት ሲሚንቶ መንገድ ወዘተ. ብየ አጀንዳ በመያዝ መቀሌ ካሉ 5 ስራ አስፈፃሚዎች እንዲያወያዩን ጠይቄ ብርሃኑ አፍኖ ለ2 ወር ቆየ፤ እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ ብርሃኑ ግብረገብነት የጎደለውና ህገ-ደንብን በመጣስ ህገ ወጥ ስራ እየሰራ ነው ይታይልኝ በማለት ለጠቅላላ ማ/ኮሚቴ አመለከትኩ፡፡ ለ32 ቀናት ታፈነ፡፡ ቀጥሎ 13 አጀንዳዎች የያዘ አቀረብኩ፡፡ አልተቀበሉትም፡፡ ቀጥሎ ሊቀመንበሩ ማኸል ያደረገ 4 ጊዜ ለቁ/ኮሚሽን ክስ አቀረብኩ፡፡ ቁጥጥር ኮሚሽንም ለ2 ወራት ዘጋው፡፡ በቃ አፈናው በረታ፡፡ መጨረሻ አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቼ አሁንም ተዘጋሁ፡፡ መጨረሻ በአረና ስራ አስፈፃሚ የታፈነው ጥያቄ 15 ነጥቦች የያዘ 5 ገፅ ሰነድ ለአረና አባላትና ደጋፊዎች ብቻ አሰራጨሁ፡፡ ሁሉም በፅሁፍ ያቀረብኳቸው ጥያቄዎች የአረና ፅ/ቤት ፈርሞ ተቀብሎታል፡፡ በመዝገብ ቤቱ ይገኛል።
ለ9 ወራት ያመለከትኩት ጥያቄዎች ከአረና አመራር ውስጥ በግልም ይሁን በቡድን ያነጋገረኝ ሰው የለም፡፡ አንፃሩ ብርሃኑ በርሄና ጥቂት አጃቢዎቹ በጥላቻ አይን እያዩ በሃሜት ስሜን እያጠፉ ቆይተዋል። በእኔ እምነት አንድ ዲሞክራሲያዊ መሪ ይቅርና ከአባላቱ ለሚነሱ ጥያቄዎች ከማንም ሰው ለሚነሳ ጥያቄ በማዳመጥ መፍትሄ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ከዚያ አልፎ በቅርብ ርቀትና በርቀት እየተከታተለ ምን አይነት ሁኔታ እንዳለ በመከታተልና ኢንፎርሜሽን በማሰባሰብ ጥያቄዎቹ እሱ ላይ ከመድረሳቸው በፊት መፍትሄ ማስቀመጥ ይገባ ነበር፡፡ ብርሃኑ በርሄ፣ 3ቱ ጓደኞቹና አጃቢዎቹ ግን ለዚህ አይነት መልካም አመራር አልታደሉም፡፡ ይኸ ደግሞ ሆን ተብሎ አረናን ለማዳከምና እነሱን የሚፈታተን መሪ እንዳይወጣ አባላቱን በማመናመን እነሱ ደግሞ በዚህ ምሽግ እድሜ ልካቸው እንዲኖሩበት እኩይ ተግባር ነው። 

የተከበራችሁ ወገኖች የአረና ማ/ኮሚቴ ለ9 ወራት ሙሉ ሲያፍነኝ እኔ ግን ምንም ቂም ሳልይዝ አንድ ቀን ይፈታል ብየ ተስፋ በማድረግ ለአፋኙና አምባገነኑ የህወሓት ኢህአደግ ስርአት ለማጋለጥ ከአረና ማ/ኮሚቴ ሆነ ስ/አስፈፃሚ በላይ ግምባር ቀደም በመሆን በህወሓት ባንዳዎች እየተደበደብኩ በጎዳና ደሜን እየነዘረ እየታሰርኩ እልህ አስጨራሽ ትግል ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡ እነ ብርሃኑና አጃቢዎቹ ለመናገር የሚፈሩት እኔ፣ አብርሃ ደስታና መ/ር ታደሰ ቢተውልኝ ነበር፡፡ ህዝቡን ማሳመን የቻልነው ህዝቡም የነ ብርሃኑ ተወላዋይነትና የኛ ጥንካሬ ነግሮናል፡፡ በሌላ በኩል በሃገር ውስጥና በውጭ ሚዲያዎች አምባገነኑ ስርአት ስናጋልጥ ብርሃኑ በርሄ ሚዲያዎች መረጃ ፈልገው እንደ ሊቀመንበር ሲጠየቅ እምቢተኝነቱን ነው ያሳየው፡፡ አስፈላጊ ከሆነ ወደፊት እገልፀዋለሁ፡፡ ብርሃኑ በርሄ ግን አፉን ሞልቶ በአረና አፈና የለም ማለቱ ምን ያህል ሞራል አልባ መሆኑ ያሳያል። ብርሃኑ በርሄ እስካሁን ከአባይ ወልዱ የማይተናነስ አረናን እያፈነ ይገኛል፡፡ ጭራሹም ወደ ህወሓት ለመቀላቀል በበር መዝግያ ከፍቶ ለመግባት በፍጥነት የሚያጋልጠው ስለሆነ በምርጫ አማካኝነት በጓዳ በመግባት በፓርላማ የህወሓት አፈና ሟሟያ እንዲሆን አዘጋጅቶ የተቀመጠ ነው የሚመስለው።
ይህ ካልኩ በኋላ እኔና ሌሎች ጥያቄ ያነሱ ወገኖች ባለፈው ሀምሌ 19ና 20/2006 ዓ.ም የማ/ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ጥያቄያችን መልስ ያገኛል ብለን ነበር፡፡ በተለይ አቶ ገብሩ አስራት ከአሜሪካ በሮ መምጣቱ ችግሩ በሰላማዊና በበሰለ መንገድ ይፈተዋል ብለን ነበር፡፡ ውጤቱ ግን የባሰ አፍራሽና የገብሩ ማንነት በማያጠራጥር ያጋለጠው ሁኖ ነው የተገኘው፡፡ እንደውም አቶ ገብሩና ጓዶቹ በጓሮ ወደ ህወሓት ለመግባት ፈልገው ይሆናል? የሚል ሃሜት እየተናፈሰ ሰንብተዋል፡፡ ምክንያቱም ጠንካራ አባላት ማባረር ለህወሓት እንደ መጠናከር ለአረና እንደመፍረስ ማለት ነው የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው። 

ብርሃኑ በርሄ፡- ‹‹በፓርቲ የምንወስደው ቅጣት ደረጃ በደረጃ ነው›› ይላል፡፡ በኔ ላይ የተወሰደ እርምጃ 1ኛ የከሰሰኝ ማነው? 2ኛ ያ ቁጥጥር ኮሚሽንስ አይቶታል ወይ? 3ኛ ያጠፋሁት ጥፋትስ አይነገረኝምን? 4ኛ የተጣለብኝ ውሳኔስ በወሰነልኝ ኣካል በስርአት በደብዳቤ ሊሰጠኝ አይገባምን?
ብርሃኑ በርሄ፡- ‹‹አስገደ 2005 ከባድ የስነ ምግባር ጉድለት በማሳየቱ በቁጥጥር ኮሚሽን ማስጠንቀቅያ ተሰጥቶት ነበር፤ አሁንም ሊያሻሻል ስላልቻለ ተባረዋል›› ይላል፡፡ ለመሆኑ የተፈፀመው የስነ ምግባር ጉድለት ምንድ ነው? የተሰጠኝ ማስጠንቀቅያስ ለማ/ኮሚቴ ወይ በጠቅላላ 3ኛ ጉባኤ መገለፅ አልነበረበትምን? ለመሆኑ ቁጥጥር ኮሚሽን ለአንድ ስራ አስፈፃሚ ማስጠንቀቅያ የመስጠት ወይ የመቅጣት ስልጣንስ አለዉን? ለመሆኑ አሁን ያባረሩኝ የመቀሌ ዞን መሰረታዊ ድርጅት የሚባሉ አዛውንትስ እነማን ናቸው? ማነው ጠፍጥፎ ያቋቋማቸው? መቀሌ’ኮ አባል የሚባል የለም፡፡ ስለዚህ የብርሃኑ ማጭበርበር ካልሆነ በስተቀር እኔ በአረና በነበርኩበት 6 አመታት በሁሉም ዞኖች ያሉ አባሎቻችን አንድም ቀን ሂስ አድርጎልኝ አያውቅም። በአንፃሩ ብርሃኑ ያባረራቸውና ያበሳጫቸው አባሎቻችን ለማግባባትና ለማበረታታት ተጠምጄ ነው የኖርኩት፡፡›› በነገራችን ላይ የአረና ስራ አስፈፃሚ እንዳባረረኝ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ተናግረዋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ይግባኝ ማለት ይችላል ብለዋል፤ በአንድ መሰረታዊ ድርጅት የተወሰነ ስህተት በስራ አስፈፃሚና ማ/ኮሚቴ ሊቀየር ይችላል፡፡ ነገር ግን ይግባኝ ከማለቴ በፊት ያየመጨረሻ ብይን ይሰጣል የሚባል የፓርቲው አካል በራሱ አባርሮኛል፡፡ በመሰረታዊ ድርጅት ይሁን በስራ አስፈፃሚ የተወሰነው የውሳኔ ደብዳቤ 4 ጊዜ ብለምናቸውም ሊሰጡኝ አልቻሉም፡፡ በአንዳንድ የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባላት ለምሳሌ እንደ ሃፍታይ ወልደሩፋኤል እንዲያሰጡኝ ብለምናቸውም ሊሰጡኝ አልቻሉም፡፡ ታዲያ በየትኛው የስንብት ደብዳቤ ለየትኛው አካል ነው ይግባኝ የምለው? የብርሃኑ የውሸት ሰደድ አድርጌ ነው የምመለከተው።
ብርሃኑ በርሄ: ‹‹በአረና የውስጥ ችግር የለም፡፡ ፓርቲው በፕሮግራም በእስትራተጂ አልተለያየም፡፡ እንደ አንድ አካል ሁነን ተስማምተን እንሰራለን፡፡ በአንድ ሁነን ሁሉም የፓርቲ እቅዶችን እያወጣን እንሰራለን፡፡ አንድ ሁለት ሰዎች ከራሳቸው ምክንያት ተነሳስተው ስማችን እያጠፉን ያሉት ውሸት ነው›› ይላል፡፡ በአረና እስካሁን የተደረጉ ስብሰባዎች፣ የአባላት ስልጠና ተብየዎች፣ የማ/ኮሚቴ ስብሰባዎች፤ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባዎችና ጉባኤዎች በህገ ደንቡ መሰረት የሚመለከታቸው አካለት አጀንዳ ይዘው ተወያይቶበትና ተግባብተው ሳይሆን ብርሃኑና 3ት ስላሴዎች በፈለጉትና ባቀዱት ብቻ እየተካሄዱ ቆይተዋል። ህገ ደንቡ ግን የማ/ኮሚቴ ስብሰባ ሲደረግ ስራ አስፈፃሚ አጀንዳ አዘጋጅቶ ከስብሰባ በፊት ለኩሉም ማ/ኮሚቴ ከ7 ቀናት በፊት ያሰራጫል።

እስካሁን ሲሰራ የነበረ ግን የሚቀርቡ አጀንዳዎች በብጣሽ ወረቀት በሊቀመናብርቱ ይቀርባል፡፡ ይህ ተግባር በ2004፣ በ2005 በ3ኛ ጉባኤ ህገ-ደንብ ተጥሰዋል እየተባለ በተደጋጋሚ ሲነሳ ንሯል፡፡ አቶ ገብሩ አስራት ግን በጣም ያበሳጨው ነበር፡፡ በአረና ትግራይ እስካሁን ድርጅታዊ አሰራር ተግባራዊ ተደርጎ አያውቅም፡፡ ኮሚቴአዊ አሰራር የሚያስፈልገው በኮሚቴ ተወስኖ አያውቅም፡፡ አሁንማ እቺ ፓርቲ የብርሃኑ በርሄ፣ 3ት ስላሴዎችና ጥቂት ባንዳዎች የግል ድርጅት ነው ቢባል ይቀላል። ሌላ ውህደትን በተመለከተ የህወሓት ሌጋሲ በመከተል አረና ክልላዊ ፓርቲ መሆኑ ቀርቶ ራሱ ሃገራዊ አውራ ፓርቲ ሊሆን ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ የትምክህተኛ አማራ ፓርቲዎች መሰባሰብ ሊውጠን ነው የሚል ጠባብ አስተሳሰብ ራሱ ትልቅ የስተራተጂና የፕሮግራም ልዩነት ነው። በነገራችን ላይ አረና በቃል ካልሆነ በስተቀር የቅርብና የሩቅ እስትራተጂ በሰነድ የተነደፈ የለም። ሌላ በውስጥ መከፋፈል የለም የሚለው እነ ሰለሞን ገ/አረጋዊ፣ ብርሃኑ መለሰ (ብርሃኑ ሞርታር)፣ አስራት አብርሃም፣ ጉዕሽ ገ/ፃዲቅ፣ ስልጣኑ ሕሸ፣ ይልማ ይኩኖ ወዘተ. ፓርቲው ውስጥ ባለው ችግር አይደለምን የወጡት? አሁን ደግሞ ታደሰ ቢተውልኝ፣ ገብሩ ሳሙኤል፣ ሽሻይ አዘናውና እኔ ራሴ ያነሳነው መሰረታዊ ጥያቄዎች ማለት የህገ-ደንብ አለማክበር፣ የተጠያቂነትና ኮሚቴአዊ አሰራር ግድፈት ስንቃወም አንድነትን ያመላክታል። አረና ትግራይ በመጋቢት 20/2000 የትግላችን የሩቅ አላማ በሃገራችን ከሚገኙ ማናቸውም ሃገራዊና ክልላዊ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ከቅንጅት እስከ ውህደት በመጓዝ አንድነቷና ሉአላዊነቷ የተረጋገጠ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮፕያን ለመመስረት ነው ብለን በሃሳብ ከተስማማን በኋላ በዛ መሰረት ተጉዘን እስከ ግንባር ተጉዘናል፡፡

ውህደትን በተመለከተ ግን ያ ሃገርን ያበላሸ የህወሓት ጠባብ አስተሳሰብ አገረሸባቸውና ብርሃኑ በርሄና 3ት ስላሴዎች የአንድነትና መኢአድ መሰባሰብ አማራን አጠናክረው የበላይነታቸው ለማረጋገጥ ስለሆነ ከአንድነትና ሌሎች የትምክህት ሃይሎች አናብርም ብለው የህወሓት የ1968 አቋም ይዘው ቁጭ ማለታቸው የእስትራተጂ ስህተት ከመሆኑ አልፎ ሃገርን የማስገንጠል አቅጣጫ የሚከተሉ ይመስላሉ። የአንድ ብሄር ፓርቲ የኢትዮጵያ አውራ ፓርቲ እንሆናለን ካላችሁ ከህወሓት በምን ትለያላችሁ? ለምን ፊትለፊት የህወሓት በር ከፍታችሁ ህወሓትን አትቀላቀሉም? ለምን በስመ ተቃውሞ በጓዳ መግባት አስፈለገ? ስለሆነ አሁንም ብርሃኑ በርሄ አታጭበርብር! ጠበቃ ስለሆንክ አልሸነፍም ብለህ እየተሟገትክ ከሆነም አሁን አይደለህም የተሸነፍከው ከተሸነፍክና ከተነቃብህ ቆይቷል። 

ፕሮግራማችን የግለሰው መብት የሚያስቀድም ነው፡፡ በነብርሃኑ ግን ጥያቄ ላነሳ ግለሰብ ይቅር በማ/ኮሚቴ በቡድንና በተናጠል የሚቀርቡ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በአንፃሩ የአረና ፈላጭ ቆራጭነት የነገሰበት ሁኔታ ነው ያለው፤ ግለሰዎች ነፃ ሁነው ሃሳባቸውን መግለፅ አልቻሉም። 

ብርሃኑ በርሄ ‹‹የነዚህ ሰዎች አቀራረብ እነሱ ራሳቸው ለነበራቸው ሃላፊነት የሚያበቃ እውቀትም ሆነ ስነ ምግባር እንደሌላቸው ለአንባቢ ያስረገጡበት ሁኖ ነው የተሰማኝ›› ይላል። የአንድ ሰው እውቀት መመዘኛ የህወሓት ጠባብ አስተሳሰብ በማራመድ ሃገርን ለመገነጣጠል ማቀድ፣ ከህገ-ደንብ በላይ ሁነህ መገኘት፣ አባላትን በማባረር፣ ስርአትና ግብረገብ አልቦ ወዘተ. ከሆነ ብርሃኑ እውነት አዋቂ ነህ፡፡ አለበለዚያ የአንድ መሪ እውቀት ዲሞክራሲያውነት፣ ተጠያቂነት፣ ግልፅነት፣ የሰዎችን ሃሳብ ማዳመጥና በብቃት መመለስ፣ በሀገ-ደንብ መገዛት፣ መሪዎችን በማፍራት የድርጅቱን ራኢይ ብሩህ የሚያደርግ በአጠቃላይ ለህዝብና ሃገር ጥቅም መቆምና መስዋእት መሆን ከሆነ ብርሃኑ መሃይም ነው ማለት ይቀላል። እኛ’ኮ ህገ ደንባችን ይከበር፣ ለህዝብና ሀገር ጥቅምና ክብር መስዋእት እንሁን፣ ከጠባብ አስተሳሰብ ወጥተን ለተዋሃደች ኢትዮጵያ እንቁም፣ ለሆዳችን መገዛት ትተን የገባነው ቃል እንፈፅም፡፡ በአጠቃላይ ህገ ደንባችን ፕሮግራማችንና አላማችን ተንዷል ነው እያልን ያለነው። ይኸ አለማወቅና ሃላፊነትን አለመወጣት ከሆነ አንባቢ ይፍረደን፡፡ ብርሃኑ ግን ካሁን በፊትም አህያ ግብሯን አይቶ ቀንድ ከለከላት ብሎ በኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ከአህያ ጋር አመሳስሎናል፡፡ የአህያ አስተሳሰብ የታደለ ማን እንደሆነ ፍርዱ ለአንባቢ ትቼዋለሁ። 

ብርሃኑ በርሄ፡- ‹‹ … ሽሬን በጎጠኝነት ካነሱ ሽሬ የብቻቸው እንዳልሆነች መከራከሩ ብዙ ባያስፈልግም የሽሬ አረና አባላት እነዚህ አሁን በጎጠኝነት ተባረርን አሉ ያልከኝ ወደ ሽሬ እንዳትልኩልን እንዳሉ በማ/ኮሚቴው ስብሰባ ከፈጠሩት ችግር ተያይዞ ተነግሮአቸዋል….. አቶ አስገደ የጎጥ ፕሮጀክት ሽሬን ተንተርሶ በጎጥ መክሰስ መጀመራቸው የህወሓትን አርማ ደግመው ማንሳታቸው ካልሆነ አንዳች እውነታም ሆነ ምክንያት የለውም›› ይላል። መጀመርያ ከላይ የዋሸኸው በሽሬ ያሉ አባላት እነዚህ ሰዎች እንዳትልኩልን ብለውናል የምትለው በነሱ ፊት አትደግመውም፡፡ እጅጉን ሰነፍና ውሸታም ተከራካሪ ስለሆንክ፡፡ ሁለተኛ እኔ አስገደ በጎጠኝነት አልታማም፡፡ አረና ከተመሰረተ በሁሉም የትግራይ ዞኖችና ወረዳዎች እስከ ቀበሌ ድረስ ተንቀሳቅሼ ለዚህ ፓርቲ ብዙ አባልና ደጋፊ አፍርቼአለሁ፡፡ በትግራይ ያለው ሙሁሩ፣ ገበሬው፣ ነጋዴው ወዘተ. ያውቀኛል፡፡ አንተ ደግሞ በአንፃሩ መለያህ ጎጠኛነትህ ነው፡፡ እጅጉን የወረድክና ውሸታም መሆንህ ደግሞ ሽሻይ አዘናው የእህቱ ልጅ ማለትህ ሀቀኛ እንቅስቃሴ ወደ ዘረኝነት አቅጣጫ ለማስቀየር መሞከርህ ነው፡፡ የራያ ትውልድ መኖሬንም ብታውቅ ኑሮ ገብሩ ራያንም የወንድሙ ልጅ ትለው ነበር፡፡ ይህ ተግባርህ ደግሞ የጌታህ ህወሓት ጠባብ አስተሳሰብና የጎጥ አርማ እያነሳህ ያለኸው አንተ ራስህ ነህ፤ በተግባርም ለአረና ጎድትሃታል፡፡ ባዶዋን አስቀርሃታል፡፡ ከህወሓት እጅና ጓንት ሁነህ እየሰራህ ያለኸው አንተ ነህ፡፡ እስኪ አንድ ነገር ልጠይቅህ፡፡ እንኳን የአረና አባል ደጋፊ ነው ተብሎ የተጠረጠረ እንኳን መሳርያው እየተነጠቀ ባለበት ሁኔታ አንተ በምን መስፈርት ነው በምልሻነት ነፍጥ የታጠቅከው? እኔና ሌሎች ንፁሃን አባላትማ እንኳን መሳርያ ሊፈቀድልን ልጆቻችንና ዘርመንዘራችን የ3ኛ ዜጋ መብትም የለንም። 

ብርሃኑ በርሄ፡- ‹‹አብርሃ ደስታ የአረና የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል ስለነበረ ሃላፊነቱ በአግባቡ ተወጥተዋል ብቻ ሳይሆን ብቁ የፖለቲካ መሪ ሁኖ ሊወጣ ተስፋ የሚጣልበት መሆኑ ደጋግሜ ስለው የነበረ ነው›› ይላል። አብርሃ ደስታ ወደ አረና ከመቀላቀሉ በፊት 2 አመት አስቀድሞ ከኔ ጋር ነበር የተገናኘው፡፡ ከአብርሃ ደስታ በሳምንት ቢያንስ 2 ጊዜ እንገናኝ ነበር፡፡ በኋላ ግን በየቀኑ እስከ ሁለት ጊዜ እንገናኝ ነበር ስለ አብርሃ ደስታ ብዙ ጊዜ እነግርህ ነበር፡፡ ደስ ግን አይልህም ነበር፡፡ አባል ይሁን ፎርም ይሙላ ስልህ ይቆይ እናጥናው ነው ያልከኝ፡፡ ሰውየው በማህበራዊ ድረ-ገፅ እየታወቀ ሲመጣ አንተ ደስ አይልህም ነበር፡፡ ነገር ግን በኔ ተፅእኖ ወደ ፓርቲው ተቀላቀለ፡፡ እነ ስልጣኑም በጥሩ ሁኔታ ስለያዙት በአጭር ጊዜ ውስጥ በአባላት ታዋቂ ሆነ፤ በ3ኛ ጉባኤም ለፕረዚዴም ሲመረጥ አልተደሰትክም፡፡ በኋላም ለአረና ህዝብ ግኑኝነት ሲጠቆምም አቶ ገብሩ አስራት በፀረ-ዲሞክራሲ ያለጥቆማና ድምፅ አምዶም መሆን አለበት ብሎ ያለድምፅ አፀደቀለት፤ ለህዝብ ግንኙነት ምክትልም አብርሃ የተጠቆመ እያለ ባንተ ጥቆማ ፍፁም ግሩም ሆነ፤ ስለሆነ አብርሃ ደስታ ጥሩ መሪ እንዲሆን ፍላጎት አልነበራችሁም፡፡

አብርሃ ደስታ በማህበራዊ ድህረ ገፆችና ሚዲያዎች በሚያደርገው እንቅስቃሴ ትእግስት አድርግ እያልክ ተፅእኖ ታደርግለት ነበር፡፡ እሱ ግን እኔ የግለሰብ ነፃነቴ ካላከበርኩ እንዴት ነው የህዝብ ነፃነት ማከብረው ብሎ ተቃውሞሃል፤ አቶ ገብሩ አስራትም የአብርሃ ደስታ እንቅስቃሴ ከፓርቲያችን አቋም ይሄዳል ወይ ብሎ ሲጠይቅ አሁንም ተቃውሞታል፤ እኔጋ በነበረው ግንኙነትም እንደ ቡድን ትቆጥረው ነበር እሱ ግን አልተቀበለህም፤ በአጠቃላይ በአብርሃ ደስታ ያለህ አመለካከት የቅናት እንጂ የፍቅር አይደለም፡፡ ለዚሁ እንደ ማስረጃነት አብርሃ ደስታ በጠራራ ፀሃይ ሲታፈን እኛ በየፖሊስ ጣቢያ ስናፈላልግ አንተ ግን በጥብቅና ቢሮህ ሁነህ ራፖልህ ነበር የምትሰራውና ገንዘብ የምትለቅመው፤ ደብዳቤ ፅፈን ፈርምልን ስንልህም ደስተኛ አልነበርክም፡፡
አብርሃ ደስታ ሲታሰር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበሃል፤ እኔ በኢሳትና ሌሎች ሚዲያዎች ስለ አብርሃ ስፅፍ አንተና አምዶም በውጭ ሚዲያ ተጠይቃችሁ ፍቃደኞች አልሆናችሁም፡፡ ስለ አብርሃ መታሰርም ለአባላት አልተናገራችሁም፤ ብዙ አባላት ጠበቃ እናቁምለት ብለው ሲጠይቁም ይቅርና ጠበቃ ለማቆም ሂዳችሁ’ኳን ለማየት አልሞከራችሁም፡፡ መጨረሻም ጠበቃ ልታቁምለት የተገደዳችሁበት ምክንያት አንድ ወገን በራሱ ሊጣበቅለት ሲወስን እንዳትታሙ እንከፍላለን ብላችሁት፡፡ ታዲያ የቱ ጋ ነው አድናቆቱ? የት ነው ፍቅሩ? መልሱ ላንተ። 

ብርሃኑ በርሄ፡- ‹‹በአብርሃ ደስታ አሳብበው የራሳቸው ፍላጎት ማስተንፈሻ ለማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች መኖራቸው እናውቃለን ግን ያላወቁት ሁነው ነው’ጂ አብርሃ ደስታ ባለፉት 9 ወራት ስራ አስፈጻሚ ሁኖ የአረና ባህሪና አመራር ያውቀዋል፡፡›› ይላል። በመሰረቱ በአብርሃ ደስታ ምናስተነፍሰው ነገር የለም፤ ያንተ ጨካኝነትና ከዳተኝነት አብጠርጥረን እናውቃለን፤ አብርሃ ደስታ በናንተ እጅጉን አዝኖ እንደ ነበረ ታውቃለህ፤ የህወሓት ካድሬዎች የሚያስቆጣ ነገር እንዳትናገሩ ስትለው አልነበርክም፤ አብርሃ በደንብ ሚያውቃችሁ በፀረ-ዲሞክራሲ አስተሳሰባችሁ፤ አባታዊነታችሁ፤ በአምባገነናዊነታችሁና ቡድናዊነታችሁ ነው፤ በናንተ በጣም ተስፋ ቆርጦ እንደነበር ይነግረኝ ነበር፤ እንደውም አስገደና አብርሃ ደስታ እኛን ከድተው አንድነትን የሚቀላቀሉ በግምባር ቀደምትነት እንደምንጠቀስ አጃቢዎችህ ያሙን ነበር፤ አሁን በውጭም በውስጥም ደጋፊ ስለበዛ ቀንተህ ነው። አብርሃ ደስታ’ኮ ባሳየው ጠንካራ ተቃውሞ አሸባሪ ተብሎ ነው የታሰረው፤ አንተ ግን አሸባሪ እንዳትባል ከህወሓት ተለማምጠህ ትኖራለህ። 

ብርሃኑ በርሄ፡- ‹‹ክላሽ የለኝም ሽጉጥ ግን አለኝ ባለ ፍቃድ ነው፤ ሽጉጡ በትጥቅ ጊዜ እኔጋ የነበረ ነው፤ በትጥቅ ትግል ታጋይ በመሆን ትጥቁ የያዙ ፓርቲው ጋር ቢቀጥሉም ባይቀጥሉም አልተነጠቁም፤ ሊነጠቁም አይገባም፤ አቶ አስገደ ገ/ስላሴም ሽጉጥና ክላሽ ነበረው አሳበው ችግር እንዳይፈጥሩብኝ ትጥቄን አስረክቤያለሁ ብሎ በ2000 ነግሮኛል…››
አሁንም ብርሃኑ እየሸፈጥክ ነው፤ በኢትዮጵያ የፓርቲዎች ማቋቋምያ አዋጅ ማንም ፓርቲ ነፍጥና ሰውን የሚጎዳ መሳርያ አይታጠቅም፤ መንግስት ካቋቋማቸው ፖሊስ፣ መከላከያ ፣ ደህንነት ብቻ ይታጠቃሉ፤ የህወሓት አባልም ከነዛ የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ውጪ የሆኑ ትጥቃቸው ያራግፋሉ ይላል፤ በዚህ መሰረት ሁሉም ተቃዋሚ ሃይሎች ማንም ነፍጥ የታጠቀ የለም፤ ህወሓት እንደ ሆነ ራሱ ዳኛ ልጁ ቀመኛ ዳኛ የለውምና በትግራይ ክልል ብቻ በምልሻ ስም ካድሬ አመራሮች በአንድ ቀበሌ ከ72-90 ታጣቂዎች አሉ፡፡ እነዛ ሁሉ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ስጋት ናቸው፡፡ ይህ የሆነበት ህወሓት ፀረ-ህገ መንግስት ስለ ሆነ ብቻ ነው። ታዲያ ብርሃኑ የፓርቲ ሊቀመንበር ሁኖ ነፍጥ መታጠቁ የህወሓት ልጅ አይደለምን? ምልሻ ታጋይ የነበሩ አሁን የአረና አባላት የሆኑ ነፍጣቸው ተቀምተው በሁሉም መልኩ መብታቸው ተነጥቀው እየተሰቃዩ ነው፡፡ ይቅርና አባል ዘመድ አዝማድ እየተቆጠረ ተፍጓቸዋል። ታዲያ ብርሃኑ እንዴት አድርገህ ታታልለናለህ? እኔ በተደጋጋሚ ትጥቃችን እናስረክብ፤ ለራሳችን ነፃ አድርገን ለህወሓት ሲቪል ታጣቂዎች እንዲያስረክቡ እናድርግ ብየው እምቢ ብሎኛል።

አሁን ብርሃኑ ፍቃድ አለኝ ብሎናል፤ ፍቃድ የሚሰጠው በደህንነት ወይ በፀጥታና ፍትህ ነው። በመሆኑ ብርሃኑ ደህንነት ወይ ሚሊሻ ካልሆነ ፍፁም አይፈቀድለትም፤ ስለዚህ ብርሃኑ ደህንነት ወይ ሚሊሻ መሆኑ እያረጋገጠልን ነው። ደህንነትና ሚሊሻ ደግሞ የህወሓት ካድሬዎች ናቸው። ስለዚህ ብርሃኑ በርሄ የህወሓት አባል ነው፤ በኛ ላይ የተወሰደ እርምጃም አረናን ለማዳከም ተብሎ ነው።
ማሳሰቢያ:
1.የአረና አባላትና ደጋፊዎች በአረና ውስጥ ያለ ልዩነት በኔና በብርሃኑ የግል ንትርክ አድርገው የሚመለከቱ አባላት አሉ፤ ይኸ ፍፁም ስህተት ነው፤ የግል ቂምም የለኝም፤ ልዩነታችን በብርሃኑና በ3ት ስላሴዎችና በኛ ያለው ከላይ በተዘረዘሩ ችግሮች ምክንያት ነው፤ እነሱ ተሸፍነው ለመሄድ ሲሞክሩ እኛ ችግሩ መታገላችን ብቻ ነው ልዩነታችን፤

2.ውህደትን በተመለከተ እኛ ለመላው የኢትዮጵያ በእኩል የሚያስተናግድ፤ ህዝቡን ከዘር ፖለቲካ አውጥቶ በህዝቦች ጠንካራ መተማመን እንዲሰፍን፤ ክብሯና ሉአላዊነቷ የተረጋገጠች ኢትዮጵያን ለመገንባት ከማንኛውም ኢትዮፕያዊ ያለ ጥርጥርና ስጋት መወሃሃድ ስንፈልግ እነሱ ደግሞ ልክ የህወሓት አቋም እያራመዱ ስለሆነ ነው፤ በተለይ ብርሃኑ አባላት ሰብስቦ ከነ አንድነት ለውህደት ብየ አልደራደርም፤ አንድነትና ሌሎች ፓርቲዎች በመወሃሃድ የትግራይን ስነ ልቦናዊ ፍላጎት አያከብሩም ወዘተ. በማለቱ ነው፤

3. በዲያስፖራ የአረና ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ አመራርና አባላት እኛ ያነሳነው ጥያቄ ረጋ ብለው ምን እየተባለ እንደሆነ አስበውና አጣርተው አቋም እንደመውሰድ የነ ብርሃኑ የአንድ ወገን ሃሳብ ብቻ በማዳመጥ ጥያቄያችሁ በውስጥ እንደ መፍታት የትምክህተኛ አማራ መሳቂያ አደረጋችሁን ብላችሁ ፅሁፍን ማሰራጨታችሁ ከህወሓት ጠባብ አስተሳሰብ እጅጉን የወረደ ነበር፡፡ በእርግጥ ፅሁፉ የሁሉም ዲያስፖራ ደጋፊያችን እንደማይወክልና የጥቂት የነብርሃኑ አጃቢዎች አስተሳሰብ ብቻ ብለን ነው የምናምነው። እኛ ግን ከዚህ ሁሉ ጠባብ አስተሳሰብ ነፃ ነን።

4. በኔ እምነት ለህወሓት ተሸክመን መጥተን ሃገር አጠፋን፤ እንደገና ሁለተኛ ህወሓት የሚሸከም ትክሻ የለንም። አሁንም እኔ ለአምባገነኑ የህወሓት ስርአት በሰላማዊ መንገድ ከመታገል ወደኋላ አልልም፤ ለኢትዮጵያ አንድነት፤ ሉአላዊነት በአጠቃላይ የኢትጵያ ችግር ለመፍታት ቆርጦ ከተነሳ ሃይል በመሰለፍ ትግሌን እቀጥላለሁ፤ ለህወሓትና ለተበላሸው የአረና አመራር እኩል እታገለዋለሁ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ‼

ሕወሃት/ኢሓዴግ ምን ያህል እንዳከረረ (ክፍል 2) – ግርማ ካሳ

$
0
0

አገር ውስጥ በሰላም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አመራር አባላት ናቸው። አብርሃ ደስታ ከአረና፣ ዳንኤል ሺበሺና ሃብታሙ አያሌው ከአንድነት፣ የሺዋስ አሰፋ ከሰማያዊ። ሐምሌ 1 ቀን 2006 ሽብርተኞች ናችሁ ተብለው ተያዙ። ጠበቃዎቻቸው በሌሉበት በድብቅ ፍርድ ቤት ቀረቡ ተባለ። ፖሊስ ዜጎችን ከመያዙ በፊት በእጁ መረጃ ሊኖረው ሲገባ፣ መረጃ ለማሰባሰብ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሎ ለ28 ቀናት ቀጠሮ ይጠይቃል። ፍርድ ቤቱ፣ ያለምንም ማቅማማት፣ ምን መረጃ በሌለበት ሁኔታ፣ የታሳሪዎችን የዋስትና መብት ከልክሎ 28 ቀናትም እንዲታሰሩ ያዛል።

tplfከ28 ቀናት በኋላ ሃብታሙ፣ ዳንኤል እና የሺዋስ ነሐሴ 27 ቀን እንደገና ፍርድ ቤት ቀረቡ። አሁንም ፖሊስ ማስረጃ ሳያቀርብ ለ28 ቀን ሁለተኛ ቀጠሮ ጠየቀ። ፍርድ ቤቱ አሁንም፣ ምንም መረጃ ሳይመለከት፣ ፖሊስ ስለጠየቀ ብቻ፣ ዜጎች በወህኒ እንዲቆዩ አዘዘ። አምሣ ስድስት ቀናት መረጃ ሳይቀርብ ዜጎች ሕግ ያስከብራል በሚባለው አካል የሰብአዊ መብታቸው ተረገጠ። እንደገና ለመስከረም 22 ቀን ተቀጠሩ። ነሐሴ 29 ቀን ደግሞ አብርሃ ደስታ ፍርድ ቤት ሲቀርብ የተለየ ነገር አልነበረም። «ተጨማሪ ሰነድ ለማሰባሰብና ምስክሮች ለማቅረብ ጊዜ ያስፈልገኛል» ብሎ ፖሊስ በመጠየቁ ተጨማሪ 27 ቀን ይሰጠዋል።

እነዚህ የታሰሩ ወጣት ፖለቲከኞች የሰሩት አንዲት ወንጀል የለም። ወንጀላቸው ለፍትህ፣ ለሰላም፣ ለዲሞክራሲ መቆማቸው ነዉ። ወንጀላቸው አገራችውን መዉደዳቸው ነው። የሕወሃት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ግን፣ ሕግን እንደ በተር በመጥቀም፣ ጠንካራ የሚባሉ፣ ተሰሚነት ያላቸውን ወጣት የፖለቲካ አመራሮች በማሰር፣ ሆን ብሎ የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ ለማሽመድመድ እየሞከረ እንደሆነ ግን ግልጽ ነው።

ከዘጠና ሰባት በኋላ በተፈጠረው ሁኔታ «ቅንጅት ሞቷል፤ የተቃዉሞ እንቅስቃሴውም አልቆለታል» በሚል ሕወሃት/ኢሕአዴጎች ዳንኪራ ሲመቱ እንደነበረ ይታወቃል። ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የተበታተነዉን አሰባስባ አንድነት በሚል ስም ጠንካራ ፓርቲ እንዲወጣ አደረገች። የአገዛዙ ባለስልጣናት 50 ሰው አይገኝም ያሉት፣ በሜክሲኮ አደባባይ መብራት ኃይል አዳራሽ ያኔ በተደረገው፣ የመጀመሪያው የአንድነት ሕዝባዊ ስብሰባ፣ ከ5 ሺህ ሰው በላይ በመግባቱ አዳራሹ ሞላ። የአዳራሹ በር ተዘግቶ ብዙ ህዝብ እንዲመለስ ተደረገ። በአራት ኪሎ ያሉ ባለስልጣናት ደነገጡ። ሰበብ ፈልገው ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን አሰሯት። ኢንጂነር ግዛቸው ሃላፊነቱን ያዙ። ነገር ግን የፓርቲው እንቅስቃሴ ተዳከመ። አንድነት ተከፋፈለ። በድጋሚ በሕወሃት/ኢሕአዴጎች ዘንድ ፌሽታ ሆነ።

አንድነት ዉስጥ እንደ አንድዋለም አራጌ ያሉ ወጣት አመራሮች መጡ። መጠነ ሰፊ ድርጅታዊ ሥራ መስራት ጀመሩ። ትንሽም ብትሆን አንድነት በአገሪቷ ሁሉ ድርጅታዊ መዋቅሩን መዘርጋት ጀመረ። የአንድነት ጥንካሬ ያሳሰበው ሕወሃት/ኢሕአዴግ እንደገና በትሩን አነሳ። አንድዋለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን የመሳሰሉ ጠንካራ አመራሮች ታሰሩ።

ብዙም አልቆየም ተወዳጁ እና ተስፍ ሰጪው የሚሊየነሞች ንቅናቄ ተጀመረ። በሌላ በኩል ከመኢአድ ጋር አንድነት የሚያደርገው የውህደት እንቅስቃሴ ትልቅ መነቃቃትን ፈጠረ። የአንድነት ፓርቲ ገዢዎች ከጠበቁት እና ከገመቱት በላይ ገፍቶ ስለሄደባቸው በድጋሚ በትራቸውን አነሱ። በሚሊዮኖች ንቅናቄና በመኢአድ አንድነት ዉህደት ዙሪያ፣ ትልቅ ሚና የነበረው፣ የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ወጣት ፖለቲከኛው ሃብታሙ አያሌውን አሰሩት። በተለይም በደቡብ ክልል ትልቅ ድርጅታዊ ሥራ ሲሰራ የነበረዉን የፓርትቲው ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ዳንኤል ሺበሺንም እንደዚሁ። የአንድነት መሪ የሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ፣ ሃብታሙ ከታሰረ በኋላ የሚሊየነኖምችን ንቅናቄ ማስኬድ አልቻሉም። እንቅስቃሴው ባለበት ቆመ። ወደፊትም ቆሞ የሚቀር ይመስላል፣ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ግፊት አድርገው ፓርቲው ከቢሮ ወደ ሜዳ እንዲወጣ ካላደረጉት በቀር።

በአብዛኛዉ የአገዛዙን በትር የቀመሰው የአንድነት ፓርቲ ቢሆንም፣ ሰማያዊ፣ አረና እንዲሁም ሌሎችም አላመለጡም። የሰማያዊ እና የአንድነት አብሮ መስራት ፣ ብሎም መዋሃድ ፣ የአንድነት እና የመኢአድ መዋሃድ የአገዛዙ ራስ ምታቶች ነበሩ። በተቻለ መጠን ሰማያዊን እና አንድነትን ማራራቅ፣ አንድነት እና መኢአድ እንዳይዋሃዱ ማድረጉን ትልቁ ግባቸው አድርገው ነበር ሲሰሩ የነበሩት። በመሆኑም የሚቆጣጠሩትን ምርጫ ቦርድ ተጠቅመው፣ የመኢአድ እና የአንድነት ዉህደትን ለጊዜው አደናቀፉ። በሰማያዊና በአንድነት መካከል መቀራረብ እንዲኖር ይተጋ የነበረዉን የሰማያዊ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ የሺዋስ አሰፋንም ወደ ወህኒ ወሰዱት።


በሰሜን የሕወሃት እምብርት በሆነችዋ ትግራይ፣ የፍትህና የዲሞክራሲ ድምጽ ሆኖ ሲጽፍ የነበረው፣ የአረና አመራር አባል አብርሃ ደስታ፣ ለሕወሃቶች ትልቅ ራስ ምታት ነበር የሆነባቸው። እነርሱ ጠመንጃ ይዘዋል። እርሱ ግን ብእር ብቻ ነበረች በእጁ። በትግራይ ዉስጥ ትልቅ ንቅናቄ መፈጠሩን፣ የትግራይ ሕዝብ ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር አብሮ ለትግል እጅ ለእጅ መያያዙ አስደነገጣቸው። ሕወሃቶች ሊኖሩ የሚችሉት ህዝቡን ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ እያሉ ሲከፋፍሉት ብቻ ስልሆነ፣ ኢትዮጵያዉያንንን የማሰባሰብ ፖለቲካን ይጸየፉታል። በተለይም በአብርሃ ደስታ ግፊት መቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠራ፣ ሰልፉ እንዳይደረግ መከልከል ሳይበቃቸው፣ የሰልፍ ጥያቄ እንደገና እንዳይነሳ በሚል ነው መሰለኝ አብርሐ ደስታን ከነሃብታሙ ጋር ወደ ማእከላዊ አስገቡት።

እንግዲህ ከላይ የጠቀስኳቸው በሙሉ የሚያሳዩት ሕወሃት/ኢሕአዴጎች ምን ያህል የተጨበጠ ሥራ የሚሰሩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ማየት እንደማይፈልጉ ነው። እነርሱ የሚፈልጉት ዝም ብሎ መግለጫ የሚያወጡ፣ ዝም ብለው የሚያወሩ፣ ዝም ብለው ስብሰባ ማድረግ የሚቀናቸው፣ ከቢሯቸው የማይወጡ፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የማያደርጉ፣ ትግሉን ወደ ሜዳ የማይወስዱ መሪዎችን እና ድርጅቶችን ነው። እንደነዚህ አይነት ድርጅቶች እየጠቀሱ የዉሸት መድበለ ፓርቲ እንዳለ ለማሳየት የሚጠቀሙባቸው ድርጅቶች ናቸው።

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ «የዲሞክራሲ ስርዓት መገንባት ለኛ አማራጭ ሳይሆን ሕልዉናችን ነው» ሲሉ ብዙ ጊዜ ሰምቻቸዋለሁ። ዶር ቴዎድሮስም አዳኖምም አንድ ወቅት ከጆን ኬሪ ጎን ለጎን ቆመው፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዲሞክራሲ እንደሚያብብ ነበር የነገሩን። ነገር ግን እያየን ያለው፣ ከመለስ ዘመን በባሰ ሁኔታ ሕወሃት/ኢሕአዴግ እንዳከረረ ነው። አቶ ኃይለማሪያም፣ መለስን አውት ሻይን ለማድረግ ነው መሰለኝ፣ ብዙዎችን በማሰር፣ በማስገደል፣ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በመጨፍለቅ በጣም እየተጉ ናቸው።

አንድ ሕወሃት/ኢሕአዴጎች የዘነጉት ነገር ቢኖር ግን ትግሉ፣ የፖለቲክ ድርጅት መሪዎች ብቻ ሳይሆን የሕዝብ መሆኑን ነው። የሕዝብን ኃይል ደግሞ አፍነው ሊቆዩ አይችሉም። ሕዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው።

ወያኔና ይሉኝታ አይተዋወቁም (አንተነህ መርዕድ)

$
0
0

ጋዜጠኛ አንተነህ መርዕድ

tplf-rotten-apple-245x300ህወሃት በሻዕብያ ታዝሎ* ምኒልክ ቤተመንግስት ከገባና ኦነግንም ሆነ ሌሎቹን ጠፍጥፎ የሰራቸውን መናኛ ድርጅቶች እንኳ ሳያስቀርብ በብቻው የተያያዘው ዘረፋ፣ ሁሉን ለእኔ ብቻ ያለ ሂደቱ ያላስደነገጠው ኢትዮጵያዊ አልነበረም። ያለፉትን ስርዓቶች የተሻገሩ ሁለት አንጋፋ ጓደኛም ጋዜጠኞች ሲጨዋወቱ በቦታው ነበርሁ። አንደኛው ወያኔ ነፃ አወጣዋለሁ ከሚለው ከኩሩው ኢትዮጵያዊ ከትግራይ ህዝብ አብራክ የተገኘ ነበርና “ወንድሜ ይሉኝታ በትግርኛ ምንድን ነው የሚባለው?” ሲል ጠየቀው። “ይሉኝታ..ይሉኝታ…” እያለ ቃሉን ማፈላለግ ሲጀምርና ፈጥኖም ቃሉን ማግኘት ሲሳነው “ተወው ወንድሜ የሌለውን ነው የጠየቅሁህ ቃሉ ከሌለ ወያኔዎች ከየት ይማሩታል ብዬ ልጠብቅ” በማለት ሁላችንንም አሳቀን።

ለነገር ማሳመርያነት አነሳሁት እንጂ ይሉኝታማ ኢትዮጵያዊ ባህል ነው። ወያኔ ከመፈጠሩ በፊት ሆነ ስልጣን ከያዘም በሁዋላ በርካታ የሰሜን ወንድሞቼና እህቶቼ ጋር ኑሬአለሁ። የሚታወቁበት ትልቁ ኢትዮጵያዊ ባህላቸው ይሉኝታቸው ነው። የወያኔ መሪዎች ካባቶቻቸው ያልወረሱት ኢትዮጵያዊነታቸውንና ይሉኝታቸውን ነው። የትግራይ ህዝብ የሚታወቀው ከቀሪው ወንድሙ ኢትዮጵያዊ ጋር ተባብሮ አገሩን ሲያስጠብቅ፣ የመከራን ጊዜ በመደጋገፍ ሲያሳልፍ እንጂ ራሱን ከሌሎች አብልጦም ሆነ አሳንሶ ሲመለከት አይደለም። ከአብራኩ ወጣን ያሉት ጥቂት የህወሃት መሪዎች ግን ትናንት ተንቆ እንደነበር ከመስበክ አልፎ ከሌሎች የሚበልጥ መሆኑን በመንገር በፈጠሩለት ማንነቱ ዙርያ ለዘላለማዊ ስልጣናቸው ጭፍን ድጋፍ እንዲሰጣቸው ያዘጋጁታል። ከተቃወማቸውም ራስን ዝቅ በማድረግ እንደተሳተፈ በመወንጀል እንዲያፍርበት ሊያደርጉ ይሞክራሉ። ለዚህም ነው በርካታ የትግራይ ምሁራን አንድም በፍርሃት ያለዚያም እነመለስ ያስቀመጡትን የማይጠቅም ይበላይነት ምናብ መዳፈር አቀበት የሆነባቸው። የተያዘው መርዘኛ አካሄድ ልጆቻቸው ነገ ቀና ብለው እንዳይሄዱ እንደሚያደርግ ሳያጡት ቀርተው አይደለም።

ሂትለር የአርያንን ዘር ንፁህና ከማንም በላይ ነው ሲል እውነት ለጀርመኖች ትልቅነት አስቦ አልነበረም። ጠቅልሎ የያዘውን ስልጣን ለማቆየት የዋህ ጀርመኖች በጭፍን እንዲደግፉትና እንዲታወሩ፣ በፈጠረላቸው የምዕናብ ዓለም እየማለሉ እውነቱን እንዳያዩ በመሆኑ ይህንን ያልደገፉትን የበላይነታቸውን የሰበካቸውን ጀርመኖች ሳይቀር አይቀጡ ቅጣት አድርሶባቸዋል። ጀርመኖች ከውድቀታቸው በኋላ በዓለም ፊት አንገታቸውን ቀና እንዳያደርጉ፣ አባቶቻቸው በሠሩት ስህተት ልጆቻቸው እንዲያፍሩበትና ይቅርታ እንዲጠይቁ ተደርገዋል። በጊዜው “ኸረ ይህ ነገር ትክክል አይደለም፣ ሰው ሁሉ እኩል ነው፣ ጀርመኖች ከሌላው አንበልጥም፣ ሌላውም ከኛ አያንስም፣ በሌሎች ላይ የሚሰራውን ግፍ አንቀበልም” የሚል እውነት ገኖ እንዳይወጣ በዚህ መርዘኛ የዘር ልክፍት የተበከሉ ውርጋጦች ጩኸት ሰማየ ሰማያትን ሞልቶ፣ ሰይፋቸው ማንንም ተቃዋሚያቸውን ለመቅላት ሲወናጨፍ በፍርሃትና ባርምሞ የተቀመጡ ብዙ የሆኑትን ያህል ታላላቅ የተባሉ ምሁራን ሂትለርን ለመሰለ መሃይም በአገልጋይነት ተንበርክከዋል። እነዚያ አገልጋዮች እስከ ዛሬ ከየተደበቁበት እየታደኑ በዘጠና ዓመታቸው ሳይቀር ፍርዳቸውን ሲያገኙ የዛሬ ጀርመኖች ዓለምን ተባበሩ እንጂ ትክክል ናቸው ብለው ከጎናቸው አልቆሙም።

ወያኔዎች ስልጣን በያዙ ማግስት ጎንደር ከተማ ጣልያን የተከለውን የበሰበሰ አሮጌ ጄኔሬተር ነቅለው ወደ ትግራይ ሲወስዱ ለትግራይ ህዝብ ይጠቅማል ብለው አልነበረም። ገና ሲነቀልና ሲጫን ፍርስርሱ የሚወጣ መሆኑን ያውቁታል። ዋናው ዓላማቸው ዮሃንስ አንገታቸውን ሰጥተው ያጸኑትን የጎንደርና የትግራይ ህዝብ የቆየ አንድነት ለመበጠስ ነው። ስልጣን ላይ ያሉትን ወያኔዎች እንተውና በጊዜው የዚህ እኩይ ተግባር ተዋናይ የነበረውን ስዬ አብርሃን “ለምን ጥቅም ነበር የወሰዳችሁት?” ብሎ በመጠየቅ እውነቱን የሚናገር ከሆነ መስማት በተቻለ ነበር።

ሰሞኑን ኢሳት የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ተወካዮች ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ናቸው ሲል ዜና አቅርቧል። ዜና የሆነው ለኢሳት ነው? ወይስ ለኢትዮጵያ ህዝብ? ብሎ መጠየቅ የተገባ ነው። በውጭ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ እንኳ ዜና መሆን አይችልም። ምክንያቱም በየትኛውም ውጭ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን ለማስፈፀም የሄደ ሁሉ ኤምባሲው በማን እንደተሞላ በቀላሉ ያየዋልና። አውሮፓና አሜሪካ ቤት የሚገዙት፣ ቢዝነስ የሚከፍቱት አዳዲስ ስደተኞች እነማን እንደሆኑ ያውቀዋልና። አባዱላ ገመዳና ጥቂት ኦህዴዶች የተወረወረችላቸውን ፍርፋሪ ሲሻሙና ሲሻኮቱ ቀልባችን ተስቦ ሳለ ድፍን ኦሮምያን መሬት ቱባ ህወሃቶች ወስደውት ብታገኙ፣ የጋምቤላን ደን ከነነዋሪው ጨፍጭፈው ዐይናችንን ካራቱሪ ላይ ተክለን ሳለ በነጋታው ባንድ ቋንቋ ተናጋሪ ህወሃቶች ሁሉም መሬት ተይዞ ብናገኘው፣ የአዲስ አበባ ክፍት ቦታ ሆነ ነዋሪው ያለበት ለልማት ነው ተብሎ በማፈናቀል ጄኔራሎቹና ትልልቅ ካድሬዎች የሰማይ ጠቀስ ፎቅ ባለቤት ቢሆኑና አዲስ አበባ ጠብባቸው ከኦሮምያ ዞን ገበሬ ማፈናቀል ቢያምራቸው የተቃወማቸውን አምቦ ላይ ቢጨፈጭፉ ለምን አዲስ ይሆንብናል? የመለስን ቦታ ማን ይይዘው ይሆን በሚል እሳቤ ሰው ሁሉ ስራ ሲፈታ ያለ ጠቅላይ ሚኒስትር አቅራቢነት ከትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ ጄኔራሎች ሲሾሙ ለምን እንደነግጣለን? ሃያ ሶስት ዓመት ሙሉ የሚደረገው አንድ ዓይነት ነገር ሆኖ በየቀኑ ለምን ዜና ይሆናል? የተያዘው ነገር የትግራይ ህዝብ ከቀሪው ኢትዮጵያዊ የተለየ ተጠቃሚ በማስመሰል መለያየትና ያለነሱ ስልጣን ላይ መቆየት የትግራይ ህዝብ ህልውናው እንደማይጠበቅ በማስፈራትና በማሳመን ሙሉ ድጋፉን እንዲሰጣቸው ነው። ልክ ሂትለርና ጓዶቹ እንዳደረጉት። ከትግራይ ህዝብ መካከል ለህሊናው፤ ለእውነት የቆመ ብቅ ሲል ይቀጠፋል። አብርሃ ደስታን ያዩአል። ለሌሎቹ ለህሊናቸው የተገዙ ትግርኛ ተናጋሪዎች ሊተላለፍ የተፈለገ መልዕክት ነው።

ከአስራ አምስት ዓመት በፊት ከከርቸሌ ፍርድ ቤት ከሚያመላልሱን ህወሃቶች አንዱ ጠጋ ብሎ ያዋራኝ ነበር። የምንጽፈው ሁሉ የትግራይ ህዝብ የበለጠ ተጠቃሚ እንደሆነ አድርገን መሆኑን ሊነግረኝ ሞከረ። እኛ የምንጽፈው ሆነ የምንናገረው ከዚያ በተቃራኒ እንደሆነ አስረዳሁት። የተወያየነው ብዙ ቢሆንም ጭብጡ እንዲህ ነበር። እያንዳንዱ የትግራይ ቤተሰብ አንድና ሁለት ልጆቹን ለዚህ ትግል ገብሯል፣ የጋገራትን ቂጣ፣ የቆላትን ጥሬ አካፍሏችሁ ለዚህ በቅታችኋል። ከበርካታ ሺህ ወያኔዎች የጥቂቶች ህይወት ብቻ ተቀይሯል። እንኳን ጠቅላላው የትግራይ ህዝብ ይቅርና አንተና መሰሎችህ እንኳ ይዛችኋቸው የመጣችሁልንን መኳንንትና እነሱ የሚያስሩንን ከመጠበቅ የምትገላገሉ አይመስለኝም። አይደለም ያንን ሁሉ በወጣህ በወረድህበት ገደላገደል የሚኖሩ ትግራዋይን፤ የቅርብ ቤተሰብህን የሚያረካ ነገር የማድረግ አቅም የለህም። አንተና አለቆችህ በሌሎች ኢትዮጵያውያን በምትፈጽሙት ግፍ የትግራይ ህዝብ ርሃብ ቢጠናበት እንኳ ተሰድዶ ነፍሱን ማትረፍን እንዲፈራ፣ ሌሎችም በጥርጣሬ እንዲያዩት አደረጋችሁ። የወንድማማችነት ገመዱን በጠሳችሁ። በማለት ስሞግተው አንገቱን ከደፋበት ማቅናት ተሳነው። እውነቱ በርግጥ ገዝፎ ታይቶት ይሆን? ያ አጃቢዬ ዛሬ አንድም እንዳልሁት አሁንም የጌቶቹና የእስረኞች ጠባቂ ነው። ቀንቶት ሚሊየነር ከሆነም የሱ ኑሮ ጥርሾና ቆሎ እያካፈሉ ነፍሱን ላሳደሩት የትግራይ ገበሬዎች አይተርፍም፤ አስር የሚሆኑ ቤተሰቦቹን ረድቶ ከሆነም ትልቅ ነገር ነው። አዲስ በለመደው ኑሮ ተውተብትቦ ሲኳትን የቀሪውን ትግራይ ህዝብ መከራ ያከብደዋል። ሃውዜንና በሌላም የትግራይ አካባቢዎች ላይ የተጨፈጨፉ ሰዎችን አፅም ከርሻው እየለቀመ ወደ ጎን አድርጎ ዝናብ ጠብቆ በደንጋዮች መካከል በምትበቅል እፍኝ የማትሞላ እህል የሚንጠራወዝ የትግራይ ብዙሃን ከርሃብ አሁንም አልተገላገለም። ከዚችውም ኑሮው የአካባቢ የህወሃት ካድሬዎች ስቃይ ይታከልባታል።

ይህ ይሉኝታ ያጣ የወያኔዎች ዘረፋ ይዋል ይደር እንጂ ራሳቸውን መልሶ ይውጣቸዋል። ስግብግብ ፍላጎታቸው ዳርቻ ስለሌለው መከራው የበዛበት ህዝብ አሁንስ በቃኝ የሚልበት ምልክቱ እየታየ ከመሆኑም በላይ ዳር ለዳር ፍርፋሪ በመልቀም የደለቡ የኦህዴድ፣ የብአዴን፣ የደህዴን፣ የሶማሌ፣ የአፋር፣ የጋምቤላ ወዘተ ካድሬዎች ፍርፋሪው እጅ እጅ ብሏቸው ከዋናው ሞሰብ ወያኔዎች ጋር በእኩልነት መቋደሱ ስለሚያምራቸው መገፋፋቱ መናናቁ እየተከሰተ ነው። የትግራይ ህዝብም ሆነ ልሂቃኑ አዳጋው ማንጃበቡን ለማየት የሚሳናቸው አይመስልም። በተለይ ምሁራኑ ሳይማር ያስተማራቸውን ህዝብ ከወንድሞቹ እንዳይቆራረጥ በማስተማርና ድምፃቸውን በማሰማት መታደግ ያለባቸው ጊዜ አሁን ነው።

በረሃ ላይ በርካታ የትግራይ ልጆችን ሲጨፈጭፉ ምንም ያልተሰማቸው ወያኔዎች ባለፉት ሃያሶስት ዓመታት በቀሪው ኢትዮጵያዊ ደም የጨቀየ እጃቸውን በትግራይ ህዝብ ላይ ሊያብሱ ሲሚክሩ ዝም ሊባሉ አይገባም። ሰሞኑን በኢሳት እንደተከታተልነው ያንን ሁሉ ግፍ የሰሩት በጣት የሚቆጠሩት የህወሃት ባለስልጣናት በስዊድን ዓለም አቀፍ ጦር ፍርድ ቤት ክሳቸው ሊመሰረት እንድሆነ ሰምተናል። አርከበ እቁባይ፣በረከት ስምዖን፣አባዱላ ገመዳ፣ ሳሞራ የኑስ፣ አባይ ፀሃዬ፣ጌታቸው አሰፋ፣ ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ፣ ሃሰን ሺፋ፣ ሙሉጌታ በረሄ፣ ነጋ በረሄ፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ ኮማንደር ሰመረ…ስማቸው ይፋ ሆኗል። እነዚህና ሌላ ጥቂት የህወሃት ከፍተኛ ወንጀለኞች ዓልም አቀፍ በሆነ መልኩ ተጠያቂ እንዲሆኑ መቅረቡ ብቻ አይደለም ትልቁ ድል። ከአሁኗ ሰዓት ጀምሮ ህዝቡ ዐይኑን ገልጦ የሰሩትን ሁሉ ወንጀል በመከታተል ለፍርድ ሊያቀርባቸው ቆርጦ መነሳት መጀመሩም ነው። ከህዝብ በግፍ የጋፈፉት ገንዘብ የሰሩትን ሃጢያት ሊሸፍንላቸው ካለመቻሉም በላይ በየትኛውም የዓለም ክፍል ቢሄዱ ከተጠያቂነት አያመልጡም። የሂትለር ናዚዎችም ከሰባ ዓመት በፊት በሰሩት ወንጀል ፍርዳቸውን ለማግኘት እስካሁኗ ሰዓት እየተለቀሙ ነው። በስሙ የተነገደበት የትግራይ ህዝብ እነሱን ደግፎ የራሱን ታሪክ አያበላሽም። ለልጆቹም ሃፍረትን አያወርስም።

በፍርሃትና በጥቅም ወያኔን የተጠጋ ሁሉ ከሚወድቅ ስርዓት ጋር አብሮ መውደቅ እንደሌለበት ማገናዘብና ወደ ህዝብ መቀላቀል ያለበት ጊዜ አሁን ነው። አምባገነኖች በተለይም ወያኔዎች ይሉኝታ የሚባል ነገር የላቸውም። ነገሮች ሲከፉ ቆይተው ለመስዋዕት የሚያቀርቡት ቢኖር በአድርባይነት የተጠጋቸውን ነው። ከራሱ በላይ ለሚያገለግለው እቃ ክብር የሚሰጥ ማን አለ? ኦህዴዶች፣ ብ አዴኖች፣ ደህዴዶች፣ አፋሮች፣ ሶማሌዎች፣ ጋምቤላዎች ወዘተ እየተባላችሁ ለፍርፋሪ የተጥጋችሁ የሞሰቡ ዋና ተቋዳሽ አለመሆናችሁን አውቃችሁ ከዘመናዊ ባርነት ራሳችሁን አውጡ።

ቀሪው ኢትዮጵያዊ እነሱ በፈጠሩልን መከፋፈል ሆነ በራሳችን ድክመት ያሳለፍነው መከራ ተጠያቂዎች ነን። ሁሉም በተደራጀ መልኩ ሆነ በግሉ ጠጠሩን ወደ አንድ አቅጣጫ ይወርውር። ወደ ዘረኛው ወያኔ። ያ ጠጠር ናዳ ሆኖ የማይገደብ ሃይል ይሆናል። ከአሁን በኋላ ከወያኔ ውጭ በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ ጠጠር በመወርወር ጊዜና አቅሙን የሚያባክን ካለ ከውያኔ አረመኔዎች አካል እንደሆነ ይቆጠራልና።

የኢትዮጵያ ህዝብ በልጆቹ ትግል ነፃነቱን ይጎናጸፋል!

ጸሃፊውን በ amerid2000@gmail.com ማግኘት ይችላሉ

በወያኔ ስር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት፣ የወያኔ አገልጋይ ኢሕአዴግ፣የአፋኞችና የነፍሰ ገዳዮች ምሽግ- የወያኔ ደህንነት

$
0
0

ነዓምን ዘለቀ

ዋና ጸሃፊያችንና  የትግል ዳችን  አንዳርጋቸው ጽጌ

neamen zeleke

ነዓምን ዘለቀ

የንቅናቄአችን ዋና ጸሃፊና የትግል ጓዳችን  አንዳርጋቸው ጽጌ  በየመን ትብብር በፋሽስታዊ ወያኔ አፋኞች  እጅ መውደቅ ያስቆጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባሳየው ወገናዊነት ልባችን ተነክቷል። የአንዳርጋቸው መታሰር ይቆጨናል፤ እየደረሰበት ያለው ስቃይ ያንገበግበናል፤ የሱን አይነት ብርቱ፣ ቆራጥ፣ አስተዋይና ብቃት ያለው ታጋይ ትግሉ ማጣቱ ይጎዳናል:: አንዳርጋቸው በሳል የፖለቲካ ሰውና ቆራጥ የተግባር ታጋይ ብቻ አይደለም። በግል ለማታውቁት በበርካታ የእውቀት ዘርፎች በጥልቀት ያነበበ፤ ፍልስፍና፣ ሊትሬቸር፣ ሲኒማ የሚወድና ህሊናው በዕውቀት በከፍተኛ ደረጃ የበለፀገ ነው። የሰው ልጅ መከራ፣ በደልና ስቃይ እስከ አጥንቱ ይሰማዋል። ዱባይ ላይ ከአመት በፊት ስላገኛት ኢትዮያዊት የነገረኝ ሲቃ እየተናነቀው ነበር።ልጅቷ ሲያገኛት ያለማቋረጥ ታለቅሳለች፤ ምን እንደሆነች ቢጠይቃት ለመናገር ባትፈቅድም አጥበቆ ሲይዛት እንደተናገረችው፤ ተቀጥራ በምትሰራበት  የቤቱ ባለቤት ሽማግሌ አረብና አራት ወንድ ልጆቹ በየገዜው ተራ በተራ ደፍረዋታል። የሚያስነባት ይህ ነበር። አንዳርጋቸው “የኢትዮጵያውያን መከራና ውርደት መቼ ነው የሚያበቃው” በሚል ነበር ሲቃ እየተናነቀው ያጫወተኝ።

አንዳርጋቸው የንዋይና የስልጣን ፍቅር የለበትም። ፍላጎቱ ያ ቢሆን ኖሮ ዛሬ  ወያኔ ከሰበሰባቸውና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የወያኔ ሎሌዎች የተሻለ ደረጃ ላይ ባገኘነው ነበር። በምንም መለኪያ በሱ ደረጃ ብቃት፣ ምሁራዊ ብስለትና ስብዕና  የተላበሡ እንደሌሉባቸው ግልጽ ነው። አንዳርጋቸው የመረጠው የፍትሕ፣ የነጻነትና የእውነትን መንገድ ሲሆን እሱ የመረጠው ከህሊናው ጋር መኖርን ነው።  ለዚህም ነው ስልጣን እና ገንዘብን ገፍቶ፣ የአውሮፓን ምቾት ትቶ፣ በርሃ ወርዶ አፈር ላይ እየተኛ በርካታ ታጋዮችን አስተምሮ ትግሉን ጠንካራ መሰረት ላይ የተከለው – ትግሉን መስመር አስይዞ ዛሬ በፋሺስቶች እጅ ቢወድቅም።

ፋሽስቶቹ ወያኔዎች በተለመደው ድንቁርናቸው ያቀዱትና የአለም አቀፍ ህግን ጥሰው የሄዱበት የብልግናና የውንብድና  መንገድ እሱን በማፈን ነጻነትና  ፍትህ የጠማውን የኢትዮጵያ ህዝብ አንገት እናስደፋለን፣ ቅስም እንሰብራለን፣ ታጋዮችና ትግሉን እናዳክማለን፣እናመክነዋለን ከሚል ስሌት  ነበር። በተቃራኒው ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥም በውጭው አለም ከዳር ዳር በከፍተኛ ቁጣና ቁጭት እንዲንቀሳቀሱ እያደረገ፤ ለመራራ ትግል እንዲዘጋጁና ለመስዕዋትነት እንዲቆርጡ እያነሳሳ ይገኛል። <<እኔም አንዳርጋርጋቸው ጽጌ ነኝ>> በሚል በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ትግሉንም ንቅናቄአችንንም እንዲቀላቀሉ እያደረገ ነው።  ዛሬ ብዙ ሺዎች የአንዳርጋቸው ጽጌን ፈለግ ተከትለዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሚሊዮኖች የነጻነት፣ የእኩልነት፣ የፍትህ ጠበቆችና ታጋዮች ሆነው የፋሽስታዊውን የወያኔን ስርዓት በሁሉም መንገዶች እንደሚፋለሙ አፍታም ጥርጥር የለንም። በግንቦት 7 በኩል  እልሃችን፣ ቁጭታችን፣ ጽናታችን፣ ቁርጠኝነታችን እጥፍ ድርብ እንዲሆን አድርጎናል። እኛም ግንባራችችንን ሳናጥፍ የተጀመረውን ትግል ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት ተነስተናል። በዛሬው እለትና በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ንቅናቄያችን በመላው ዓለም በ27 ከተሞች ከሚያደርገው ህዝባዊ ስብስባዎች አንዱ በሆነው በአትላንታ ከተማ በመካከላችሁ የተገኘሁት ኢትዮጵያ ሀገራችንንና ህዝባችን የሚገኙበትን የምታውቁትን እጅግ አስከፊ ሁኔታ  ለመደጋገም አይደለም።

የዛሬው ስብሰባ ዋና አላማና ትኩረት ትግሉ ወደ አንድ ሌላ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን በተመለከተ የጋራ ግንዛቤና የትግል አቅጣጫ እንዲኖረን ለመመካከር ነው ሲሆን፤ ሁሉም የዚህ ትግል ንቁ ተሳታፊና አባል እንዲሁም ደጋፊ በመሆን ምን አይነት ተግባራዊ የትግል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንደሚገባን ሁላችሁም ወስናችሁ እንድትንቀሳቀሱ ለማስገንዘብና ለልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም የንቅናቄአችንን ጥሪ ለማቅረብ ነው።

ዘረኛውና ዘራፊው የወያኔ አርነት ትግራይ ስርዓት

የኢሕአዴግ/ኦህዴድ ከፍተኛ ካድሬና የካድሬዎች አሰልጣኝ የነበረውና በልዩ ልዩ ከፍተኛ መንግስታዊ ሃላፊነቶች  ስርአቱን  ያገለገለው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር በኢሳት ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ያደርገውን ሰፊ ቃለ-ምልልስ  የተከታተላችሁ ይመስለኛል። አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በርካታ ሃቆች፣ መረጃዎችና ቁም ነገሮችን በአካተተበት “የመለስ ትሩፋቶች” በሚል ርእስ ያሳተመው የመጀመሪያ መጽሐፉ በቨርጂንያ በተመረቀበት ወቅት በስፍራው ተገኝቼ  ኤርሚያስ ሲናገር የሰማሁዋቸውና ለዚህ ስብሰባ ፋይዳ አላቸው ብዬ የወስድኳቸውን እዚህ ለመጥቀስ እወዳለሁ፡፡

“ስርዓቱ የኔ ነው እንድትል፤ የኔነት ስሜት (Sense of Belongingness) እንዲሰማህ አያደርግም።  የወያኔ/ህወሃት ዋና ተግባሩ ዘረፋ ነው”።  “ኢህአዴግ  በጥራትም፣ በጽናትም፣ በብቃትም እዚህ ግባ የሚባል ድርጅት አይደለም” የሚሉ አስተያየቶችን ሰንዝሮ ነበር

የወያኔን አገዛዝ ምንነት አሁንም ድረስ በአግባቡ ላልተረዱ ብዙ መረጃዎችና ሃቆች ያካተተ መጽሀፍ ነው። ባለራዕይ ከሚሉት ከቀድሞ የወያኔ ቁንጮ ጀምሮ በቀለኞች፣ ቂመኞችና ዘረኞች መሆናቸውን ይበልጥ ተረድተንብታል። የአብዛኞቹን የወያኔ መሪዎችና አባላት እኩይነት፣ ዘራፊነት፣ አጭበርባሪነት፣ የስርዓቱን እጅግ የወረደና የዘቀጠ ምንነት፣የመሪዎቹን ርካሽነት፣ ጭካኔአቸውን፣ ለከት የሌለው ስግብግብነታቸውን፣ በስርዓቱ ውስጥ የነገሰውን አድርባይነት ገላልጦ አሳይቶናል። እጅግ የወረደ ስብዕና ባላቸው ጨካኝና ርካሽ ሰዎች እጅ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደወደቀችም ተገንዝበናል። ስርዓቱን ጥለው ከወጡት የቀድሞ ባለስልጣናት ያልሰማነውን በርካታ ውስጠ ድርጅታዊ ምስጢሮችን ያካተተ ትልቅ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ታሪካዊ ሰነድ ጭምር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው የሚል እምነት አለኝ።

እነዚህን  ላለፉት በርካታ የትግል አመታት ካጠራቀምናቸው መረጃዎችና ሃቆች ጋር ስንደምራቸው የዚህ ዘረኛና  ለከት የለሽ ስግብግብ የወያኔ አገዛዝ ማንነት መፈተሽ የሚገባው በይፋ (officialy)  ባስቀመጠውና በብልጣ ብልጥነት በሚነግድባቸው – አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ ልማታዊ መንግስት፣ የትራንስፎርሜሽን እድገት ወዘተ – ርዕዮቱ ሳይሆን በተግባር በሚሰራበት (Operating) ርዕዮት ሊሆን ይገባዋል፤ ይህም ተግባራዊ ርዕዮት ዘረኝነትን መሰረት ያደረገ ወያኔዎች የተያያዙት መንግስታዊ ዘረፋ ነው። ወደ ስልጣን እስኪመጡ ከደርግ/ኢሰፓ ጋር በሚታገሉበት ወቅት በጠባብ ብሄረተኝነትና በዘረኝነት የታጀለ ቢሆንም፣ ቢያንስ በወቅቱ አንግበውት የነበረው ፍትህ፣ እኩልነት፣ የብሄር ብሄረሰቦች መብት ወዘተ የሚሉ ነበሩት። ዛሬ ግን ትርጉም አልባ መፈክሮች መሆናቸውን የወያኔዎች 23 ዓመታት ተግባሮቻቸውና አድራጎቶቻቸው በይፋ ይመሰክሩባቸዋል።

የፋሽስቱ ወያኔ ዘረኝነት ከህመም ወደ ነቀርሳ (Cancer) የተለወጠ መሆኑ ግልጽ ነው። ከ23 ዓመታት በኋላም የመከላከያ ሰራዊቱን ዕዝ ወሳኝና ቁልፍ ቦታዎች ከላይ እስከታች 95 በመቶ፤ የደህንነቱ መዋቅሩም 90 በመቶ እንዲሁም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ 50 በመቶ ኤፌርት የሚባለው የህወሃት ግዙፍ ኩባንያዎች ስብስብ (Conglomerate) ተቆጣጥሯል። የህወሃት አባላትም በቤተሰብ፣ በዘመድ-አዝማድ የተያያዙ  በሰፊው የትግራይ ህዝብ ስም የሚነግዱ የትግቋንቋ ተናጋሪዎች ሁሉንም በበላይይዘዋል። ይህ አዲስ ዘረናና ዘርራፊ ገዥ ቡድን (oligarchy)  የዳበረበት፣ ፍጹም የሆንር ኢፍትሃዊ  የስልጣን፣ የጥቅም፣ የስራ፣ የትምህርት፤ የኢኮኖሚ ወዘተ የነገሱበት፤  አድሎ  የተንሰራፋበት  መሆኑን  የምታውቁትና  የኢትዮጵያ ህዝብም  የሚኖርበት ሃቅ ነው ።

አሸባሪው የወያኔ አገዛዝ በመጠነ ሰፊ ቅራኔዎች ተቀስፎ የተያዘ፣ ደካማና ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የገባ ስርዓት ነው። መሪዎች እርስ በርስ የማይተማመኑ፣ የጎሪጥ የሚተያዩ፣ የሚናናቁ ስለመሆናቸው ንቅናቄያችን በርካታ መረጃዎች አሉት። ለስልጣን ያላቸው ስግብግብነትና ዘራፊነታቸው ስላስተሳሰራቸውና ስላያያዛቸው ብቻ በጉልበት፣ በአፈና በሽብር የሚገዙ ናቸው። ራሱ ባወጣው ህገ መንግስት ውስጥ የደነገጋቸውን ዩንቨርሳል ዲክላሬችን ኦፍ ሁማን ራይትስና ሌሎች ህጎችን ሁሉ በየእለቱ እየረገጠ የቀጠለ ስርዓት ነው። በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት (Legitimacy) የሌለው መሆኑን የስርዓቱ መሪዎች ያውቁታል። የዚህን ስርዓት ደካማነትና የፈጠራቸውን ዘርፈ ብዙ ቅራኔዎች የሚመሰክሩት ስርዓቱን ጥለው የሚወጡት  ብቻ አይደሉም፤ በቅርብ ጊዜ አዲሱ ለገሰ የሚባለው መሪ ካድሬ የፃፈውንና በኢሳት የቀረበውን ብዙዎቻችሁ የሰማችሁ ይመስለኛል። ስርዓቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደወደቀ ከፍተኛ የሆነ የአመራር እጦትና በርካታ ሌሎች ችግሮች እንዳሉበት፤ ከግንቦት 7ና ከኦነግ ጋር የሚሰሩ የብአዴንና የኦህዴድ አመራሮች እንዳሉ ወዘተ አዲሱ ለገሰ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪዎች ባቀረበው ሪፖርት ዘርዝሯል። ይህን ተከትሎም በመላው አገሪቱ የሚገኙ 350ሺህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ኢህአዴግ  የሚባለው የወያኔ መገልገያ ድርጅት አባል ለማድረግ አስገዳጅ ስልጠና መጀመሩን ታውቃላችሁ፡፡

የወያኔ/ህወአት አገልጋይና መሳሪያ የሆነው  ኢሕአዴግ

ወያኔዎች ኢህአዴግ በሚባለው ጭንብላቸውና መሳሪያቸው ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት አሁንም ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አስገድዶ የፓርቲ አባል የማድረጉ ሂደት  እድሜያቸውን የሚያራዝም የሚያድን እንደማይሆን እነሱን ከተኩት ከደርግ/ኢሰፓ ስርዓት ትምህርት ለመወስድ ያልቻሉ የአዕምሮ ስንኩላን ስብስብ መሆኑን ዳግም እያረጋገጡ ነው። እነሱ የተኩት ኢሰፓ ሁሉም የህብረተስብ  ክፍል ሁሉም ዜጋ  በግድ አባል ለማድረግ የሞከረ፣ በግለስብና በህዝብ ላይ ፍጹማዊ አገዛዝ (Totalitarian)  ለመዘርጋት ሞክሮ ያልተሳካለት፡ ለውድቀቱም አንዱ መንስኤ አሁን ወያኔ በማድረግ ላይ ያለውን በዜጎችና በህዝብ ላይ ፍላጎቱን በማስገደድ፤ በጉልበት መጫኑ ነበር። በኢሰፓ ርዕዮት አምነው ከልብም ተቀብለው ለፓርቲው ህልውና የታገሉና መስዋዕት የሆኑት ስንቶቹ እንደሆኑ በዚያች ቀውጢ ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብም ራሳቸው ወያኔዎችም የሚያውቁት ነው፡፡

ዜጎችን  በማስገደድ የስልጣናቸውን እድሜ ለማራዘም የስርዓቱ አገልጋይና የአፈና  መሳሪያ ለማድረግ የሚደረገው ይህ ሂደት የፋሽስቱን የወያኔን ስርዓት እድሜ የሚያራዝም አይሆንም። ታሪክ አንዳንዴ ራሱን ስለሚደግም የዚህንም ሂደት ውጤት የምናየው ይሆናል፡፡ ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ ከመሆን እንደማያልፍ ጥርጥር የለንም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፓርቲ አባላት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰላዮችና አፋኞች አምባገነናዊ ስርዓቶችን – ከሆስኒሙባርክ እስከ ሙአመር ጋዳፊ – ሊያድኗቸው እንዳልቻሉ  የቅርብ ጊዜ ምሳሌዎች ናቸው።

በስርዓቱ ውስጥ የሚገኙ ኢህአዴግ የሚባለው  የህወሃት መሳሪያ የሆነው ድርጅት አባላት አብዛኞቹ ለኑሮ ዋስትና፣ለእለት ጉርስ፣ የስራና የትምህርት እድል ለማግኘት ወዘተ ሲሉ አባል እንደሆኑ እናውቃለን። በኢትዮጵያዊነታቸው በዜግነታቸው ማግኘትና መጎናጸፍ የሚገባቸውን መብቶቻቸውን ለማግኘት ባለመቻላቸውና በመገደዳቸው እንደሆነ  ግልጽ ነው። ለሆዳቸው ሳይሆን ለህሊናቸው ጭምር ተጨንቆ ማሰቢያው ግዜው አሁን ነው፤ ጊዜው ሳይመሽ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መወገን እንላለን ።

ይህን ስርአት ከውስጡ እንዲታገሉት፤ የስርአቱ መናጆና ባይተዋር ለሆኑት ብዙሃኑ የኢሃአዴግ አባላት ጥሪያችንን እናቀርብላቸዋለን። የወያኔ ስርአት ዘረኛና ዘራፊ፤ የህዝብን መብቶች አፋኝ ስርዓት መሆኑን ከእነሱ በላይ እማኝ እንደሌለ ያውቁታል። ጥቂት ሺዎች የሚመዘብሯትና የሚንደላቀቁባት በአፈና በሽብር የሚገዟት ኢትዮጵያ እንደሆነች እነዚሁ ብዙሃን የኢህአዴግ አባላት ያዉቁታል። የፋሽስቱ ወያኔ ግብዓተ መሬት ሁሉንም ጠራርጎ ወደ ክፉኛ ወድቀትና አይቀሬው ግብዓተ መሬቱ ከመሄዱ በፊት ከህሊና  ጋር ተነጋግሮ ከአፋኞች፣ ገዳዮችና ዘራፊዎች ጋር አብሮ መቆም ሳይሆን በልዩ ልዩ መንገዶች የዚህን አሸባሪና የዘርኝነት ነቀርሳ የተጠናወተው ስርአት ወድቀት እንድታፋጥኑ፤ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንድትቆሙ ጥሪ እናቀርባለን። በታሪክ ሆነ በህግም ፊት ከተጠያቂነት ለመዳን የሚቻለው ለዚህ ስርዓት እድሜ የማራዘም ተግባራትን በመፈጸም ሳይሆን የስርዓቱን እድሜ የሚያሳጥር ተግባራትን በማድረግ ብቻ ነው እንላለን።

የኢህአዴግ የሚባለው የህወሃት መጠቀሚያ ድርጅትም ሆነ የራሱ የፋሽስቱ የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣኖችና ከፍተኛ ጄነራሎች ዛሬ የዘረፉትን የህዝብ ገንዘብ በምዕራብ ሀገሮች ንብረት እየገዙበትና ወደ ውጭ ባንኮች ገንዘብ እያሸሹ እንደሆነ በየጊዜው የሚደርሱን በርካታ መረጃዎች አሉ። ቤተስቦቻቸውንም ወደ ውጭ የሚልኩ ጥቂቶች አይደሉም። እንድ እግራቸው አገር ውስጥ ሌላው ወደ ውጭ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ብዙሃኑ የስርአቱ ተከታዮችና ደጋፊዎች ሊያውቁት ይገባል።

የአፋኞችና የገዳዮች ምሽግ -የወያኔ ደህንነት

የፋሽስቱ አገዝዝ ያለፈውን የደርግ/ኢሰፓ መንግስትና በታሪክም  ያለፉትን የኢትዮጵያ አገዛዞችን ኢ-ፍትሃዊ፣ጨቋኝ፣ ሰው በላ፣ ወዘተ እያለ ሲከስ፣ ሲያወግዝ፣ ሲያሳጣ የነበረው ሰቆቃ ፈጻሚ ኢ-ሰብአዊ እያለ እንደነበር ሲታወስ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የማይገኝለት በሰብዓዊ ፍጡር ላይ ግፍ የሚሰራ፣ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ሰቆቃ ፈጻሚ፣ አፋኝና ገዳይ ራሱ ወያኔ ህወሃት ነው::

ዛሬ ማዕከላዊ ምርመራ ሌሎችም የወያኔ የደህንነትና የፓሊስ ምርመራ ቦታዎች የምድር ሲኦል ሆነዋል። ሰው ከሰው መፈጠሩን የሚያማርርባቸው ስፍራዎች ናቸው። “ሞት ምርጫ ሆና ለሚሰቃዩት የማይቀርብበት” ከስቃይ ብዛት አዕምሮአቸውን የሚስቱበት ሲሆን፣ እጅግ ዘግናኝና አረመኔያዊ ሰቆቃዎች ሳቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን እዚያው በሰቆቃው ወቅት ህይወታቸው ያልፋል፤ ወንድ፣ ሴት፣ ሽማግሌ፣ ለጋ ወጣት ላይ ልዩነት አይደረግም፤ሁሉም ስቃይ ይቀበላል፤ በፍርድ ስም ይሸፈጣል። ዳኛው ከሰቆቃ ፈጻሚው ጋር አብሮ ንጹሁን ዜጋ ያጠቃል:: በወያኔ፤ ኢትዮጵያ ሰብዕናተዋርዷል፣ ሰብዓዊ ፍጡር ረክሷል:: የግፍ ጽዋ ሞልቶ ፈሷል!!

ዛሬ በየለቱ በማዕከላዊና በደህንነቱ መስራያ ቤት የአፈና ቪላ ቤቶች፣ በየክፍለ ሀገር እስር ቤቶች ለመስማት እንኳን የሚዘገንኑ ሰቆቃዎች በኢትዮጵያውያን ላይ ይፈጸማሉ። አካላቶቻቸው ይተለተላሉ፣ ይጎድላ፣ ይደማሉ፣ ይጮሃሉ። የትውልድ ብሄራቸው እየተጠቀሰ ይሰደባሉ፣ ሰብእናቸው በህወሃት መርማሪዎች ደጋግሞ ይዋረዳል፣ ፍርድቤት ሳይደርሱ ዓመታት ይማቅቃሉ፣ ለፍርድ ቤት ተብየው የወያኔ ቧልት ቢቀርቡም ባላመኑበት ባልሰጡት ቃል ይቀጣሉ።

ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ “ሞቶ መነሳት” በሚል ርዕስ የጻፈውን ብዙ ኢትዮጵያዊያን እንዳነበቡ እገምታለሁ። ይህንኑ አስመልክቶ በአየር ሃይል በተመደቡ የወያኔ ደህንነቶች ተወስዶ በጨለማ ቤት ተወርውሮ ለሁለት ዓመት ያህል  የደረሰበትን ስቃይና ግፍ አስመልክቶ ለኢሳትና ለሌሎች ሚዲያዎች የሰጠውን ቃለ ምልልስ ብዙ ኢትዮጵያውያን ተከታትለውታል የሚል እምነት አለኝ።

የወያኔ ታጣቂዎች በህዝባችን ላይ የሚፈጽሙትን ግድያ፣ ሰቆቃ፣ ግፍና፣ ዜጎችን የማዋረድ ተግባራት ከዜጎች አንደበት እጅግ ጥቂቱን ለማቅረብ እወዳለሁ። ጥቂቶቹን እንስማ፡-

  1. አቶ ጋስ – የአፋር ሰባዓዊ መብት በአፋር ውስጥ የስምንት ልጆች አባት የሆኑ ግለሰብ፣< -SOBE&feature=youtu.be”>https://www.youtube.com/watch?v=0IYVtJ-SOBE&feature=youtu.be
  2. ድምጻችን ይሰማ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በመብት እንቅስቃሴ ወቅት በቅርብ ሳምንት የወያኔ ፖሊሶችና ደህንነቶች ድብደባ፤ ስቃይና ውርደት ከደረሰባቸው ሴቶች አንዱዋ የምትለውን እንስማ፣http://youtu.be/PCktoq2htcY
  3. በራሱ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ወያኔዎች በተለመደ ጭካኔያቸው በምርጫ 97 ያደረሱበትን የጻፈውንና ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በኢሳት ያቀረበውን በአጭሩ እናድምጥ፣
  4. በቅርብ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚባለው የፋሽስቱ የወያኔ አገልጋይ ለአንድ ሚዲያ ነኝ ለሚል ግለሰብ በሰጠው ቃለ ምልልስ እናድምጥhttp://youtu.be/aL1RyvCTyms

    ይህን አሳዛኝ  ሰቆቃ በመአከላዊና በሌሎች ሰቆቃ መፈጸሚያ ቤቶች ወያኒዎች ዘግናኝና አሰቃቂ ሰቆቃ ከፈጸሙባቸው መካከል ለምሳሌነት ስለበደሎቻቸው ያልዋቸውን ደግሞ ቀጥሎ እንመልከት፡

    -“ዓይን ተሸፍኖ፣ እጅ በካቴና ታስሮ መደብደብ፣ ውስጥ እግርን ረፍ፣ የአውራጣት ጥፍር ማውለቅ፣ ቁስሉን መርገጥ፣ ጆሮን በጥፊ መምታት፤ አንዱ ፊት ሌላው ኋላ ሆኖ ጀርባንታፋንመቀመጫንወገብትከሻን መደብደብ። ደክም ግድግዳ አስደግፈው ብደብ፣ ስደክም በላውሃ እያፈሰሱ መደብደብ፤ ሰውነት ኪቆስል ድረስ መቀመጥ መነሳት ፤እስኪዝለፈለፍ ስፖርት መስራት፣ ሲያቅተው፣ ሲወድቅ መርገጥ፤መጫሚያ፣ ታፋን፣ የእጅ ጣቶችን፣ እራስን መቀጥቀጥ፤ የውስጥ ሱሬ ሳይቀር አስወልቀው ብልት መቀጥቀጥ፤ መሬት ሲዘረር አንገት ላይ በጫማ ቆሞ ማሰቃየት፤ ጡት ሳይቀር በኤለትሪክ ገመድ መግረፍ፤ ውስጥ እግር፣ መቀመጫ፣ ጀርባ መግረፍ፤ እጅ በካቴና አስረው በዚያ ግድግዳ ላይ መስቀል፤ በአካል ላይ ከፍተኛ ድብደባ፣ ለረጅም ሰዓት ዘቅዝቆ መሰቀል፣ ሲጮህ አፍ በጨርቅ መጠቅጠቅ፤ ክብር የሚነካ ስድብ፣ 45 ቀናት ማታ ማታ ድብደባ ለረጅም ሰዓት፤ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ሲታሰር ፍርድ ቤት አልቀረበም፤ ለስድስት ወር እጅና እግሩ በእግር ብረት ማሰር፤ በድብደባ የግራ የዘር ፍሬው (ብልቱ) ሟሙቶ ጠፍቷል፤ በኤሌትሪክ ሰውነቱ ተጠብሷል፤ ለ48 ሰዓታት ምግብና ውሃ መከልከል፤  ለቀናት እንቅልፍ መከልከል፤  በአንድ እግር ለረጅም ሰዓታት ማስቆም” ።  በቅርብ ሳምንታት የሙስሊም ሴቶች ይህ ነው በማይባል ጭካኔና አረመኔያዊ መንገድ መገረፋቸው፣ልብሳቸው ወልቆ እርቃናቸውን እንዲሆኑ መደረጉ፣ የቁርዓን እና የመሳሰሉት እምነት ተኮር መገለጫዎች በታሰሩባቸው የፖሊስ ጣቢያዎች በሙሉ እንዲቃጠሉ ተደርገዋል።ሲለቀቁም እራቁታቸውን ሌሊት ሰው በማያያቸው ሰዓት ተፈትተው ወደሚሄዱበት እንዲሄዱ መደረጉ እውነታ ነው።

    ከላይ የተዘረዘሩን አሰቃቂ ጭካኔዊ ተግባራትን፣ ሰቆቃን፣ አፈናን ግድያን እንመራዋለን በሚሉት ህዝብ ላይ የሚፈጽሙ “ሰውን አንደበድብም፣ አናሰቃይም፣ አንገርፍም” በማለት እንደለመዱት ይክዳሉ።  ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚባለው የፋሽስቱ የወያኔ አገልጋይ  ግለሰብ በሰጠው ቃለ ምልልስ፣ የወያኔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም በሌላ ቃለ ምልልስ የደገመው ይህንኑ አይናችንን ግንባር ያድርገው የሚል ክህደትና የተለምዶ ሽፍጦችን ነው።

    ከሶስት ሳምንታት በፊት በዋሽንግተን ዲሲ በአንዳንዶቹ የፋሽስቱ ወያኔ ሎሌዎችና ተላላኪዎች ላይ በተቆጡ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የደረሰባቸውን ማሸማቀቅ፣ ውግዘትና፣ ማስነወር “ብልግና” ተደረገ “ነውር” ተፈጸመ በማለት በዚያ ሰሞን እነሱና የስርዓቱ ተጠቃሚዎች በሆኑ ሚዲያዎች ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ተደምጠዋል። ሰዎች የሚከበሩት ሌላውን ሰው ሲያከብሩ፣ በጎ ሲሰሩ፣ መልካም ሲሰሩ፣ አርአያዊ ስነ ምግባር ሲኖራቸው ነው። ጨዋነት ያልተጻፈ ማህበራዊ ፕሮቶኮል ነው። የሚሰራው ጨዋዎች ባሉበት ማህበረስብ ሁሉ አብዛኛው ማህበረሰብ በጋራ የሚገዛበት የሚመራበት ማህበራዊ (Social Norm and etiquette ) ሲሆን ነው። ያለ መቀባበል (Reciprocity) ጨዋነት  የሚሰራ ሊሆን አይችልም።

    የወያኔ ጉዶች በአንጻሩ ምንም ሃፍረት ያልተፈጠረባቸው ይሉኝታና ሞራል የማያውቁ ኢትዮጵያና ህዝቡዋን ያዋረዱ፣ ቤተ ክርስትያንና መስጊዶችን ሳይቀር የሚያረክሱ ተግባራትን የሚፈጽሙ፣ ቅዱሳን መጽሃፍትን የሚያዋርዱ የሚያረክሱ፣የውንብድና የሽብር ተግባራት የሚፈጽሙ፣ በንጹሃን ዜጎች ላይ ሰቆቃ እየፈጸሙ የዜጎችን ቅስም መስበር ምንም የማይመስላቸው (Saddists) እጃቸው በደም ተጨማልቆ በጉልበት እየገዙ ያለምንም ይሉኛታ፤ በለየለት አይናአውጣነት ስለ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ሊሰብኩ ይዳዳቸዋል። የወያኔ ፋሽስቶችና ሎሌዎቻቸው በዘረኝነት፣ በዘረፋ፣ በአፈና ቅስም እየስበሩና እያዋረዱ፤ ፍርሃትን በህብረተስቡ ውስጥ  ስላነገሱ፣ በህዝብ እንዲከበሩ እንዲታፈሩ የሚከጅሉ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ አድርቅ የሚለው ብሂል ፈጽሞ የማይገልጻቸው እንደሆኑ በድጋሚ አረጋግጠውልናል።

    በዋሽንግተን ዲሲ ወጣት ታጋዮች እንደተደረገው በመላው አለም የወያኔ አገዛዝ መሪዎች የነሱ ሎሌ ባለስልጣኖቻቸው በተገኙበት ሀገር ከተማና ቦታ ሁሉ ማስነወር ማሸማቀቅ፤ ስላምና እረፍት መንሳት፣ የእግር ረመጥ መሆን በመላው ዓለም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት የትግላችን አካል ነው። ይህ ስልት የህዝባዊ እምቢተኝነት አካል ነው። የአልገዛም፣ አናከብርህም፣ አንቀበልህም፣ ወግድ የማለት የሰላማዊ አመጽ አካል ነው። በዴሞክራሲያዊ ሃገሮች በህግ የበላይነት ማቀፍ ውስጥ ለምንገኝ ሁሉ የመታገያ መሳሪያ በመሆኑ ይህን የትግል ስልት ተግባራዊ እንድናደርግ በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥሪያችንን እናድሳለን ።

    እነዚህ ወደ ምእራብ ሀገሮች የሚመጡ  ባልስልጣኖቹም ሆኑ በእነሱ መሪነትና ውሳኔ ሰጪነት ባለፉት 23 ዓመታት በህዝብ ላይ ወንጀል የፈጸሙ፤ ስቆቃ፤ ግድያ፤ አፈና ጭካኔያዊ ተግባራትን በንጹሃን ዜጎች ላይ ያስፈጸሙና የፈጸሙ የደህንነት፣የፌደራል ፖሊስ፣ የልዩ ህይል፣ የክልል ፖሊስና በተዋረድ ያሉ የዚህ ስርአት የአፈና መዋቅሮች የወያኔ የስልጣን ምሰሶዎች በመሆናቸው በሁሉም መንገድ መታገልና ለፈጸሙት መጠነ ሰፊ ወንጀሎች በህግ ፊት እንዲቀርቡ ዝግጅቶችን ማድረግ ሌላው አንገብጋቢ የትግል ዘርፍ ነው።

    የወያኔ የብሄራዊ ደህንነት የሚባለው የአፋኞች፣ የሰቆቃ ፈጻሚዎችና፣ የገዳዮች ምሽግ በሚመለከት በደርግ ዘመን በደህንነትና በፓሊስ ውስጥ  ያገለግሉ የትግርኛ ተናጋሪዎች ተመርጠው እስካሁን በቁልፍ ቦታዎች ላይ እንደሚገኙበትማ እነማን እንደሆኑ እናውቃለን፤ ባዶ ስድስት በሚባለው የወያኔ እስር ቤት ጀምሮ ግፍ፣ ግድያና ሰቆቃ የፈጸሙ የወያኔ ህወሃት አባላት ፈላጭ ቆራጭ እንደሆኑበት በማእከላዊ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ በሚገኙ ሰቆቃ መፈጸሚያ ቪላ ቤቶች (Safe Houses) የት የት እንደሚገኙ፤ ምን ዓይነት ወንጀልች ሲፈጸሙ እንደነበር፤ በልዩ ልዩ የሀገራችን  አካባቢዎች ትግራይን ጨምሮ ተመሳሳይ ድብቅ የአፈና ቦታዎች በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን የገደሉ፣ ያስገደሉ፣ ያሳፈኑ፣ ያፈኑ፤ ሰቆቃ የፈጸሙ እነማን እንደሆኑ  ንቅናቄያችን መረጃዎች አሉት።  በጎረቤት  ሀገሮች  በኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ እንዲሁም በቅርቡ የመን ድረስ ድንበር ዘለውና ባህር አቋርጠው ግድያ አፈና ያቀነባበሩ የፈጸሙት እነማን እንደሆኑ ከተለያዩ አቅጣጫዎች በርካታ መረጃዎች ለንቅናቄያችን እየደረሱ ናቸው።

    እነዚህን አፋኞችና ገዳዮች እንዲሁም ውሳኔ ሰጪ አለቆቻቸውን ለፍርድ ለማቅረብ የሚቻልበትን መንገዶች በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና የህግ ባለሙያዎች ነዋሪ የሆኑባቸውን ሀገሮች  ህጎች በመፈተሽ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጸሙ የጦር ወንጀሎች፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ የጅምላ ግድያ፣ ከፍርድ ቤት ውጭ የተደረጉ ግዳያዎች፣ አፈናዎች፣ ሰቆቃዎች ተጠያቂ የሚሆኑ የወያኔ ውሳኔ ሰጪዎች፣ ውሳኔ አስፈጻሚና ፈጻሚዎችን ፍርድ ፊት እንዲቀርቡ በተደራጀ መንገድ መንቀሳቀስ አንዱ የወቅቱ ዓብይ የትግል ተግባር ነው። በስዊድን የተጀመራውን የወያኔን ወንጀለኞች ወደ ፍርድ የማቅረብ ሂደት በሌሎችም የአውሮፓ ሀገሮች እንዲሁም በአሜሪካና በካናዳ መጀመር የትግሉ አንዱ ዘርፍ ነው።

    በኢትዮጵያ ውስጥ ቤተሰብ ዘመድ በወያኔ የታፈኑባችሁ፣ የደረሱበትን የማታውቁ፣ በወያኔ አፋኞች መገደላቸው ማስረጃ ያላችሁ፣ የደህንነትና የፖሊስ አፋኞች፣ ሰቆቃ ፈጻሚዎች፣ ገዳዮችን ማንነት መረጃዎችን የምታውቁ፣ ለዚሁ ተግባር ለሚቋቋሙ ግበረ ሀይሎች ስለወንጀለኞቹ ዝርዝር መረጃ በመሰብሰብ እንድትልኩ ጥሪ እናቀርባለን። ወንጀለኞች በተለይም በዴሞክራሲያዊ ምዕራብ ሀገሮች መሽሸጊያ እንዳያገኙ በውጭ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ስለእነዚህ ወንጀለኞች የምታገኙትን መረጃዎች ሁሉ እንድታቀብሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

    ቀደም ሲል ፋሽስታዊው የወያኔ ዘረኛ  ስርአት ደካማና በቅራኔዎች ተቀስፎ የተያዘ ፤ ውስጡ የበሰበሰ፤ የነተበ ነው ብለናል። ካልገፋነው ግን ሊወድቅ አይችልም። እየተንፏቀቀና እየተንገዳገደ እንዳይቀጥል ገፍቶ መጣል ያስፈልጋል። ወያኔን በሥልጣን ላይ ያቆየውን የመከላከያና የስለላ ተቋማቱን ማዳከም አለብን። መስዋትነት ለመክፈል የተዘጋጁ ሃይሎችን መቀላቀል የሚችል ዜጋ ሁሉ እንዲቀላቀል ንቅናቄያችን ጥሪ ያቀርባል። በደጀን የተሰለፈው ኃይል ደግሞ የዘማቹን ስንቅ በማዘጋጀት በገንዘቡ፣ በጉልበቱ፣ በመረጃ ይተባበር። የተቆጣ፣ ጥቃት፣ ውርደት፣ ግፍ የመረረው ሁሉ ለነፃነቱ ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የስነ ልቦና ዝግጅት ያድርግ። ከወያኔ ሰላዮች ራሱን ተከላክሎ በያለበት በጥብቅ ከሚያምናቸው ጋር በመሆን በየአካባቢው በቡድን በቡድን ይደራጅ፤ የወያኔ ቀንደኛ ሹሞችና ወንጀለኞችን ይሰልል፤ መረጃዎችን ለንቅናቄችን በዘዴ እንዲልክ ጥሪ እናደርጋለን።

    በወያኔ ስር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት

    ዘረኛውና እና ፋሽስቱ ወያኔ አርነት ትግራይ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚያደርሰው በደል፣ ግፍና ዘረኝነት ሌላው ገፈት ቀማሽ በፋሽስቱ ወያኔአባል በሆኑ የጦር መኮንኖች እዝና ቁጥጥር (Command and Control)  ተወጥሮ የተያዘው ከኢትዮጵያ ህዝብ አብራክ የወጣው ከአማራ፣ ከኦሮሞ፣ ከደቡብ ህዝቦች፣ ከአፋር፣ ከጋምቤላ፣ ከሌሎች ብሄር ቤሄረሰቦች የተመለመለው በታችኛው እርከን ላይ የሚገኘው ሰራዊት ነው።

    ይህ 5ኛና 6ኛ ክፍል ባልጨረሱ የወያኔ መኮንኖች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተሰንጎ የተያዘ ሰራዊት ዘርፈ ብዙ በሆኑ ችግሮችና ቅራኔዎች እንደተወጠረ ከበቂ በላይ መረጃዎች አሉ። ኢትዮጵያ ስትዘረፍ፣ ወገኖቹ  ሲፈናቀሉ፣ ወንድምና እህቶችህ ሲሰደዱ ይህ ስራዊት የሚመለከት ነው።  ከላይ ከዋናው ኤታማጆር ጀምሮ ዕዞች፣ ክፍለ ጦሮች፣ ብርጌዶች፣ ሬጅመንቶች፣ ሻለቃ፣  ሻምበል እስከ ጋንታና እስከ ታች ጓድ ድረስ የፋሽስቱ ህወሃት አባላት በበላይነት የያዙት ይህን ያገጠጠ ዘረኝነት በየእለቱ የሚኖርበት በመሆኑ ሰራዊቱ ያውቀዋል። በችሎታ በአገልግሎትና በብቃት ሳይሆን በዘረኝነት የተጫኑበት እንደሆነ ይህ ሰራዊት በሚገባ ያውቃል። ይህ ሰራዊት ከስንቁ፣ ከአልባሳቱ፣ ከትጥቁ ጭምር እየዘረፉና እያጭበረበሩ በመነገድ እነዚህ የወያኔ አርነት ትግራይ አባላት በሆኑ አዛዦችና ጥቂት ተባባሪ ሎሌዎቻቸው እንዲከብሩም ያውቀዋል፡፡ 90 ከመቶ የሚደርሱት ከፍተኛዎቹ የህወሃት ጀነራሎች የዋና መምሪያ፣ የዕዝ፣ የልዩ ልዩ መምሪያዎች፣ የክፍለ ጦርና ከዚያም ዝቅ ብለው በተዋረድ የሚገኙ ቈልፍና ወሳኝ ቦታዎች ላይ በኃላፊነት የተቀመጡት የወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት፣ እውቀት፣ የአመራር ብቃት፣ ልምድ ለ21ኛ ክፍለ ዘመን ዘመናዊ መደበኛ (የሽምቅ ተዋጊ ሃይል ያልሆነ ማለት ነው) ሰራዊት  እዝና ቁጥጥር (Command and Control) በምንም መለኪያ የማይመጥኑ ምናልባትም ለዚህ እጅግ አሳፋሪ ሁኔታ ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ሀገር እንድሆነች ከታች ያለው ከታች የሚገኘው ብዙሃኑ የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ሊገነዘቡ ይገባል።

    የፋሽስቱ ወያኔ ታማኝ ጀነራል መኮንኖች አብዛኞቹ ነጋዴዎች፤ ሙሰኞች፤ ዘራፊዎች እንደሆኑ፤ ባለብዙ ፎቅ ህንጻዎች ባለንብረቶች እንደሆኑ፤ ልዩ ልዩ ሃብቶችን እንዳጋበሱ፤ ወደ ወጭ ሀገሮችም ገንዘብ እንደሚያሸሹ፤ ቤተስቦቻቸውንም እንደሚያሸሹ ይህ ሰራዊት በሚገባ ያውቀዋል። በአንጻሩ የተበላሸ ስንቅ እየመገቡት፤ በሰበብ  አስባቡደሞዙን እየቆረጡ በችግር ይቀጡታል። የደሞዝ፣ የአልባሳት፣ የምግብ አስከፊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ጥያቄ  ያነሱ የጦሩ አባላት ከልዩ ልዩ ግንባሮች ታፍነው የጠፉ፤ እስከአሁንም ድረስ የደረሱበት እንደማይታወቅ ሰራዊቱ  ስለሚኖርበት የሚታዘበው፤ በልዩ ልዩ ወቅቶች ሰራዊቱን እየጣሉ የኮበለሉ የስራዊቱ መኮንኖች፣ የበታች ሹሞችና ወታደሮች  በይፋ እንዳጋለጡ ይሰማል፤ እርሱም በየግንባሩ ይሰማል።  በግምገማና በልዩ ልዩ ስልቶች  እርስ በእርሱ እምነት እንዳይኖር፣በጥርጣሬ እንዲተያይ፣  ለአንድ ሰራዊት የውጊያ ብቃት ወሳኝ ከሆኑት መስፈርቶች አንዱ የጋራ የውጊያ መንፈስ (Esprit de corps) የሌለው መሆኑን እናውቃለን፡፡ እርስ በእርስ መተማንን (Cohesion) እንዳይኖረው፤ በፖለቲካና በብሄር ተከፋፍሎ ተንፈራቆ እንዲቆም፣ የጎሪጥ እንዲተያይ፣ በራሱም እንዳይተማመን የተደረገ በዚህም ምክንያት ሞራሉ እንዲላሽቅ መደረጉ የሚኖርበት ሃቅ መሆኑን የታችኛው የመከላከያ ስራዊት አባላት ያውቁታል እየኖሩበትም ነው።

    ወያኔ ጦርነት ባወጀ ቁጥር፤ ጠብ በጫረባቸው ወቅቶች ሁሉ  መቶ በመቶ ከፊት እንዲጋፈጥ፤ የጥይት እራት እንዲሆን፤ፈንጂ ረጋጭ የሚያደርጉዋቸው የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የደቡብ የጋምቤላ እንዲሁም የሌሎች ብሄር ብሄረስብ አባላትን እንጂ በዘረኝት በላዩ ላይ በአዛዥነት የተጫኑበት የወያኔ አርነት ትግራይ ወታደራዊ ሹሞች እንዳልሁኑ ያውቃል፤ ኖሮበታልም። በ 1990 –1992 (እ.ኤ.አ. 1998-2000) ከኤርትራ ጋር ወያኔ ባደረገው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ለጋ ወጣት ወንድሞቹን ፈንጂ ረጋጭ አድርገው ለእልቂት እንደዳርጉዋቸው ያውቀዋል። በመጨረሻው በ2000 ዓ.ም. በተደረገው ውጊያ የጦርነቱን ሁኔታ ለመለወጥ የተቻለው በወታደራዊ ሳይንስ በልምድ በብቃት ምርጥና ከፍተኛ ዝና የነበራቸውን ብ/ጄነራል ተስፋይ ሀብተማርያም አየር ወለድ (ከብ/ጄነራል ለገሰ ተፈራ ጋር የህብረተሰባዊት ኢትዮጵያ የላቀ ጀግና ሜዳልያ ተሸላሚ)  ብ/ጄነራል በሀይሉ ክንዴ ታንከኛ፣ ብ/ጄነራል ንጉሴ አዱኛ መድፈኛ፣ ብ/ጄነራል ተጫኔ መስፍን ከአየር ሃይል፣ እንዲሁም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በደርግ ኢሰፓ ስር በነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥ ያገለገሉ ወያኔ ከደርግ ውድቀት በኋላ እነሱና ቤተሰቦቻቸውን ለውርደትና ለችግር የዳረጋቸው የቀድሞ ሰራዊት የመስመር መኮንኖች፤ ባለሌላ ማዕረግተኞችና ወታደሮችን መልሶ በማስገባት ነበር። ከተጠቀሙባቸው በኋላም መልሰው ነው ያባረሯቸው። ይህን የዘረኝነት በቀጽሞ ሰራዊት አባላት ላይ የተፈጸመ ዳግመኛ የግፍ  ታሪክ ብዙው የኢትዮጵያ ህዝብ አያውቀውም። ወያኔዎች በእነዚህ ሙያዊ ብቃትና ክፍተኛ አስተዋጽዖ የጦርነቱን ሁኔታ ለመለወጥ መቻላቸውን ህዝብ እንዲያውቅ ማድረግ ዘረኝነታቸውና የበታችነት ስሜታችው  አልፈቀደምና። እ.ኤ.አ. በ2006 ወያኔ ሶማሊያን ሲወርር ማን ከፊት ሆነው እንደተማገዱ ፈንጂ ረጋጮች እነማን እንደነበሩ ይህ ሰራዊት አይቶአል፤ ያውቀዋል። ኖሮበታል።

    በወታደራዊ ሳይንስ ትምህርታቸው በአለም ታዋቂ ከሆኑ የጦር ኮሌጆች፣ ወታደራዊ አካዳሚዎች፣ ስታፍና ኮማንድ ተቋማት የተመረቁ የምድር ፣ የአየርና የባህር ምርጥ የበላይ አዛዦችና የመስመር መኮንንኖች በብዛት ነበሩበት።  የሶማሊያ ወራሪን ጦር ሃይል መክቶ ከማባረር እስከ ሰሜን የጦር ግንባሮችን ይህ ነው በማይባል ጀግንነት የተዋጋ  ሰራዊት የነበረበት።  ይህ ግምሽ ሚሊዮን የሚገመትና ከአፍሪካ ውስጥ ከነበሩት የመከላከያ ሰራዊቶች ትልቅ ከሚባሉት ፤ እስከ አፍጢሙ በዘመናዊ መሳሪያዎች ታጥቆ የነበረው በደርግ ኢስፓ አመራር ስር የነበው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ውድቀት በዋነኝነት የሚቀርቡት ምክንያቶች ለ23 ዓመታት ወያኔዎች ህዝብን ለማንበርከክና አይበገሬዎች ነን የሚል የውሸት ታሪክ ለመጻፍ እንደሞከሩት፣ እንደሚፎክሩት አይደለም። ወያኔዎች   ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተለየ ጀግንነት የወያኔዎች የወታደራዊ ብቃትና ስትራቴጄካዊ ብስለትና እወቅት ስለነበራቸው ሳይሆን  የኢትዮጵያ ህዝብና  በወቅቱ የነበረው የደርግ/ኢሰፓ መንግስት ሆድና ጀርባ ስለነበሩ ነው። የነበረው አገዛዝ  ፖሊሲዎችና ብዙዎቹ ተግባራቱ የህዝብን ልብ ስላሸፈቱ፤ ቅራኒዎቹም  የህዝብ ድጋፍ ስላሳጡት፤ ስራዊቱም የህዝቡ ነጸብራቅ ስለነበረ በዘርፈ ብዙ ቅራኔዎች ሰለባ ሰለተደረገ እንደነበር  የዛሬው የመከላከያ ሰራዊት ከዚህ ከራሱ ታሪክና ከሌሎችም ሃገራት የወታደራዊ ውድቀት ታሪኮች ማወቅ ይገባዋል።

    ዘመናዊ መሳሪያ እስከአፍንጫ ቢታጠቅ ፤ ሰራዊቱን በሚሊዮን ቢያደራጅ፤ ስርዓቱ በህዝብ የተተፋ፤ በቅራኒዎች የተዋጠ–በተለይም እንደወያኔ ዘረኛና ዘራፊ አገዛዝ፤ ሀገራዊ ራእይ ባላቸው ግፍና በደል አንገሽግሾዋቸው ፍትህና ነጻነት የተራቡና የተጠሙ የህይወት መስዋትነት ለመክፈል በቆረጡ፤ የህዝብ ልጆችና በኢትዮጵያ ህዝብ ደጀንነት በአቸናፊነት እንደሚጠናቀቅ ከአገራችንም ሆነ ከሌሎች አምባገነናዊ ስርዓቶች ውድቀት መማር የግድ ነው።  ከላይ እንደገለጽነው ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ የሚለው የሰራዊቱ ዓላማ በራሱ በወያኔ የተደፈረ፤ የተረገጠ ህገ መንግስት በመሆኑ  የሞተ ሰነድ ባዶና ቀፎ በመሆኑ ህይወቱን የሚገብርበት ምክንያት የዛሬው የመከላከያ ሰራዊት ሊኖረው አይችልም። የሁሉም ብሄረሰቦች እኩልነትና የተመጣጠነ ሰራዊት በሚል የተቀመጠውም የወያኔዎች ቡዋልት ከመሆን ያላለፈ መጭበርበሪያ እንጂ ዛሬ ይህ ስራዊት በአንድ ብሄር በአንድ ቋንቋ የበላይነት በፋስሽቱ የወያኔ አርነት ትግራይ ጀነራሎችና መኮንኖች  ፈላጭ ቆራጭነት ከላይ እስከ ታች ስር እንዳለ ከታች ያለው የመከላከያ  ሰራዊት ያውቀዋል። በወያኔ ስር የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት ዘርፈ ብዙ ችግሮችና ቅራኔዎች እንዲሁም ደካማነት በሚመለከት በወታደራዊ ሳይንስ የላቀ እውቀት፤ ልምድና በህወአት ስር ስለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት  ወቅታዊ መረጃ ባላቸው የአየርና የምድር መኮንኖች የተደረጉ ጥናቶችን ንቅናቄያችን በቅርቡ ይፋ ያደርጋል።

    የፋሽስቱ የወያኔ አርነት ትግራይ ጀነራሎችና ወታደራዊ መኮንኖች እንደ ሲቪል የወያኔ ዘመዶቻቸው፤ በጎሬጥ የሚተያዩ፣ የሚናናቁ፣ በጥቅምና በስልጣን የሚሻኮቱ፤ የተቋሰሉ እንደሆነ ከታች ያለው ሰራዊት ያውቀዋል። አንዳንዶቹ ልባቸው የሸፈተና አጋጣሚና ጊዜ ቢያገኙ እርምጃ ለመውሰድ የሚያደቡ እንዳሉ በልዩ ልዩ ጊዜዎች ንቅናቄችን መረጃዎች ደርሰውታል። በ3ኛ ሀገሮች ከንቅናቄው ተወካዮች ጋር ለመገናኘት መልዕክት የላኩም አሉባቸው። አላማቸው፣ ራዕይያቸውና ግባቸው ህዝባዊ ስላልሆነ በንቅናቄው በኩል የእነዚህ የህወሀት መኮንንኖች ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም።

    በዘራፊ፣ ሙሰኛና ዘረኛ የወያኔ ወታደራዊ አዛዦች ለሚመራው ከህዝብ አባራክ ለወጣው ሰራዊት የምናቀርብለት ጥሬ መሣሪያውን በግፈኞችና በፋሽስቶች ላይ እንዲያዞር ነው። የነፃነት ታጋዮችን እንዲቀላቀል ጥሪ እናደርጋለን። ነገ ጥለውትና አጋልጠውት ለሚፈረጥጡ የዚህ የዘረኛና ዘራፊ ስርዓት ግፈኛ መሪዎች መሳሪያ ሳይሆን የህዝብ ወገን መሆን መርጦ ራሱን ኢትዮጵያንም፤ ከአብራኩ የወጣበትን የኢትዮጵያ ህዝብ ከውርደት እንዲያወጣ ንቅናቄያችን ጥሪ ያቀርብለታል!

    የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ፦ይህን ትግል ዳር ለማድረስና  በድል ለማጠናቀቅ ዋና መሰረቱ ጠንካራ ድርጅት ነው።

    • ግንቦት 7፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስተባብሮ ወደ ድል ለመምራት ዝግጁ ነው፤ ድርጅታዊ አቅሙን እንድናጠናክር ለሁሉም አትዮጵያዊ ጥሪ እናደርጋለን፤
    • ግንቦት 7 ሁለገብ ትግልን – ሕዝባዊ ተቃውሞን፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነትን እና ሕዝባዊ አመጽን – አስተባብሮ መምራት ወደሚችልበት ደረጃ ለማድረስ በጋራ ቆርጠን እንድነሳ ጥሪ እናደርጋለን፤
    • ትግሉ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በአጎራባች አገሮችና ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩባቸው ሌሎች አገራት ውስጥ በመሆኑ በሁሉም ቦታዎች ድርጅቱን በማስፋት እንድናጠናክር ጥሪያችንን እናቅርባለን፤
    • ትግሉ በከተማም በገጠርም፤ በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም በመሆኑ እነዚህን  አስተባብሮ  የሚመራ ድርጅት ያስፈልጋል።

    በፀረ-ወያኔ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የፓለቲካ ድርጅቶች የሚዋሃዱበትና የሚቀናጁበት ወቅት አሁን ነው። ከሁሉም በላይ ከወያኔ በኋላ የተዋሃደችና የጠነከረች ኢትዮጵያ እንድትኖረን ካሁኑ አገር አድን ኃይል ማደራጀት አስፈላጊነቱን ንቅናቄያችን ከምንም በላይ ይገነዘባል። በዚህም መሠረት ግንቦት 7 በተግባራዊ ትግል ውስጥ ካሉ ድርጅቶች ጋር በየጊዜው እየዳበረ መጥቶ የአገር አድን ኃይል ምሥረታን ያለሙ ኅብረቶችን ለመፍጠር ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህም መሠረት:

    በዓላማ፣ በአደረጃጀትና በስልት ከሚመስሉን ለመዋሃድ ጥረት እናደርጋለን። በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እና ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ጋር

    ለመዋሀድ ተስማምተን እየሰራን እንገኛለን። በዓላማ የምንስማማ ሆኖ አደረጃጀታችንን የማቀራረብ ሥራ የሚጠይቅ በሚሆንበት ጊዜ በጥምረት ለመሥራት ጥረት እናደርጋለን። በዚህ ረገድ የሚጠቀሱት  ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን)፣ በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ እና ከአፋር ሕዝብ ፓርቲ ጋር የመሠረትናቸው ጥምረቶች  አብይ ምሳሌ  ናቸው። በተለይ ከትሕዴን (ደሚት) ጋር የምንሠራቸው የጋራ ሥራዎች እየጎለበቱ መጥተዋል። ከሌሎች የኢትዮጵያ ድርጅቶች ጋር ለጋራ ሥራ የምናደርጋቸው ትብብሮች፣ በዚህ ረገድ የሚጠቀሱት የቤኒንሻጉል ሕዝቦች ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ንቅናቄ፣ ኦነግ፣ አብነግ በአርአያነት ይጠቀሳሉ።

    ዛሬ ለሁሉም ለነፃነቱ፣ ለሰብዓዊ ክብሩና መብቶች ለሚቆረቆሩ ኢትዮጵያዊያን  የቀረቡትአማራጮች ሁለት ብቻ ናቸው።

    • በዜጎች ላይ ጭካኔዎች የሚፈጸሙባት፤ የሰው ልጆች ሰብዓዊ ፍጡራን ለአርመኔያዊ ግፍና ስቆቃ በሚዳረጉባት ሀገር፤ በውርደትና በደል የሚማቅቁባት፤ ዘራፊና ዘረኛጥቂት ፋሽስቶች  እንዳሻቸው የሚፈነጩባት፣ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ባይተዋርና የበይ ተመልካች፣ መብትና ሀገር አልባ የሆነ በሶስተኛ ዜግነት፤ እንዲያውም በባርነት አንድ ጊዜ ብቻ የሚኖርበት፣ የምትኖርበት በዚህ አለም  ውድ ህይወቱን በሲኦል የሚገፋበት አንዱ አማራጭ ነው፡፡
    • በሌላና በተጻጻሪው የሚገኘው አማራጭ ደግሞ የሰው ልጅ፤ ሰብዓዊ ፍጡር፣ ማንም ኢትዮጵዊ ዜጋ ምንም ያድርግ ወይም ታድርግ ወንጀል ቢፈጽም እንኳን በህግ የበላይነት — በግፍ ሰቆቃና ቅስም ሳይሰብር፣ ውርደት ጭካኔያዊ ተግባራት ሳይፈጸምበት– ቅጣቱን የሚቀበልበት የህግ የበላይነትና ነጻ ዳኝነት የነገሠባት ኢትዮጵያ ናት። እያንዳንዱ ዜጋ፣ እያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብ አሮሞው፣ አማራው፣ የደቡብ ህዝቦች፣አፋሩ፣ ኦጋዴኑ፣ ጋምቤላው፣ ህይወታቸው፤ እድላቸው  በእንደአሁኑ በጥቂት ዘረኞችና በእነሱ ሎሌዎች ሞግዜትነት፤ ፈላጭ ቆራጭነት የሚወሰንበት፣ በላያቸው  ላይ የሚሾሙበት፣ በግድ የሚጫኑበት ሳይሆን ብሄር፤ ብሄረሰቦች ፤ እያንዳንዱ ህዝብ በየአካባቢው ነጻና ርዕታዊ በሆነ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ራሱ በሚመርጧቸው መሪዎች/ተወካዮች  ብቻ የሚተዳደርበት ስርዓት በትግላችን እወን ማድረግ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡
    • ምርጫችን ሙስሊም ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን፣ ሁሉም የእምነትቶች፣ መብቶቻቸው የሚረጋገጥበት፤ ስብዕናቸው፣ ድምጻቸው የሚከበርበት፣ እምነቶቻቸው በሚፈቅዱት መስረት የራሳቸውን ጉዳዮች በራሳቸው መንገድ በነጻ የሚወስኑበት፣ በመንግስት ጣልቃ ገብነት ሳይሆን በህግ የበላይነት ብቻ የሚወስኑበት፣ በምንም መልኩ የማይደፈሩበት፣ የማይዋረዱባት፣ የማይረገጡባት፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ለስደት ባርነት ተዳርገው ለስቃይ ለበደል፣ ለወርደትና ጥቃት በየአረብ አገሩ የማይሸጡባት ኢትዮጵያ በትግላችን እውን ማድረገ ብቸኛው አማራጭ ነው።
    • ምርጫችን ስልጣን የተገደበባት፣ አንዱ ስልጣን ሌላውን ስልጣን የሚቆጣጠርባት፣ ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እንጂ ለመንግስታዊ ዘረፋ የማይውልበት፣ ህዝብን ለማገልገል እንዲ ህዝብን መገልገያ የማይደረግበት፣ ስልጣንና ባለስልጣናት ለህዝብ ተጠያቂ የሚሆኑባት፣ ትክክለኛ የህዝብ ወሳኝነት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚረጋገጥበት ፤ ሰብዓዊት የሰፈነባት ፤ የዜጎችዋ ሰቆቃና ስቃይ፣ ወርደትና ስደት፣ ድቀት የሚያከትምባት፣የነጻነት አየርን ሁሉም ዜጎች የሚተነፍሱባት፣ ትክክለኛ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርዓት የነገስባት ኢትዩጵያን በትግላችንና በሁለንተናዊ በመስዋእትነት እውን ማድረግ የቀረበልን ብቸኛ አማራጭ ነው።
    • ምርጫዎችን የመወስን ወስኖም ለተግባራዊ የትግል እንቅስቃሴዎች ዝግጁ መሆን ጊዜው አሁን ነው!! ንቅናቂያችን ለኢትዮጵያ ወጣቶች፤ የዩኒቨርሲቲና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ለሁሉም ብሄር ብሔረሰቦች፣ የልዩ ልዩ እምነት ተክታዮች፣ ለኢትዮጵያ ሴቶች አልገዛም ባይነት፣ የህዝብ እምቢተነት፣እንዲሁም አመጽ እንዲያቀጣጥሉ ንቅናቂያችን ጥሪውን ያቀርባል!! የመንግስት ሰራተኞች ስራ በመጎተት ስራ በማቀዝቅ ስርዓቱን የበለጠ እንዲያዳክሙት ጥሪያችንን እናቀባለን።

    የተዋበች፣ ሰብዓዊትነት የሰፈንባት፣ የገዢዎ ሳይሆን፣ የዘረኞች ሳይሆን የህግ የበላይነት ብቻ የነገሱባት የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ፍትሃዊ የሆነ የሃብት፣ የስልጣን፣ የጥቅም ክፍፍል የሚረጋገጥባት ፤ የእያንዳዱ ዜጋ ነጻነት የተረጋገጠባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን  በትግላችን በመስዋዕትነት እውን ለማድረግ ሁላችንም ቆርጠን እንነሳ! የምንችለውን አይነት መስዋዕትነት በእጥፍ ድርብ ለመክፈል በጋራ ተነስተናል!! ሁሉም የሚችለውን የትግል ዘርፍ መርጠን ያለውን ጠጠር ሁሉ እንወረውራለን!! ለዚህም ቃል ኪዳን እንገባለን።

    አትላንታ ፤ ኦገስት 31፡ 2014

    Etfreedom.2015@gmail.com

የድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ ታሪካዊ አጀማመር

$
0
0

*ጦርነት፣በሽታ፣ድህነት– ለድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ መስፋፋት አስተዋጽኦ አበርክተዋል

“ድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ”የሚለውን አጠራር የተባበሩት መንግስታት ዓለምአቀፍ የህፃናት ፈንድ(ዩኒሴፍ)፤ ልጆች ከትውልድ አገራቸው ድንበር ተሻግረው ወደ ሌላ አገር በመግባትበጉዲፈቻ የሌላ ቤተሰብ አባል የሚሆኑበት ሁኔታ ነው ሲል ይተረጉመዋል

BAD392AE-8998-410B-986B-F186C0C498E5_w640_r1_sበተለያዩ አገራት ዜጐች መካከል የሚፈፀም ጉዲፈቻ እየጨመረ የመጣው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ ነው፡፡ በዚህ ጦርነት የተነሳ አያሌ ህፃናት ወላጆቻቸውን በማጣታቸው፤በማሳደጊያዎች ውስጥበአሰቃቂ ሁኔታ ተይዘው ለማደግ ይገደዱ ነበር፡፡ከዚያ የተሻለ ሌላ አማራጭም አልነበራቸውም፡፡

ድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ የተጀመረው የተለያዩ አገራት ወታደሮች የጦርነት ቀጠና በሆኑ የዓለም አገራት መስፈራቸውን ተከትሎ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ በኋላ በበርካታ የአለም ክፍሎች የተነሱ ግጭቶች ለወታደሮች በየአገሩ መስፈር ምክንያት ሆኗል፡፡ በተለይ የተባበሩት መንግስታት ወታደሮች በኮሪያ ጦርነት እንዲሁም የአሜሪካ ወታደሮች በቬትናም ውጊያ ወቅት በርካታ ልጆችን እንደወለዱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በአብዛኛው ጉዲፈቻ የተደረገው ወደ አሜሪካ እና አውሮፓ አገራት ሲሆን የጉዲፈቻ ልጆች ምንጭ አገሮችም ደቡብ ኮሪያ፣ ቬትናም እና የመሳሰሉት ነበሩ፡፡ ከጦርነትና ግጭቶች በተጨማሪም ድርቅ፣ በሽታና ድህነትም ለድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ መስፋፋት ምክንያት ሆነዋል፡፡

ለዚህም ሩሲያ፣ ጉዋቲማላ፣ ቻይና እና የአፍሪካ አገራት ይጠቀሳሉ፡፡
በተለይ ከደቡብ ኮሪያ በርካታ ቁጥር ያላቸው ህፃናት በጉዲፈቻ የተወሰዱ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ በሰሜኑና ደቡብ መካከል በተደረገው በርካታ አገሮች የተሳተፉበት ጦርነት፣ ልጆች ቤተሰባቸውን በማጣታቸው ነው፡፡ ከዚህም ሌላ በወቅቱ በደቡብ ኮሪያ ሰፍረው ከነበሩ የአሜሪካ ወታደሮች የተወለዱ ህጻናት በመልክ ከአካባቢው ማህበረተሰብ የተለዩ ስለነበሩ፣ለማህበራዊና ስነልቦናዊ ችግሮች ተጋልጠዋል፡፡እነሱ ብቻ ሳይሆኑ እናቶቻቸውም በሕብረተሰቡ ዘንድ መገለል ይፈጸምባቸው ነበር፡፡በጦርነት ሰበብ የተወለዱ ህፃናት በአብዛኛው በጉዲፈቻ የሚወሰዱት ወደ አባቶቻቸው አገር ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ በአባታቸው የዜግነት መብት ስላላቸው ነው፡፡ ይሔም ለድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ መጨመር አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ከዚህም ባሻገር“በጦርነት ምክንያት የተወለዱ ልጆች በመሆናቸው ልንታደጋቸው ይገባል”የሚለው አስተሳሰብ ድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻን ያስፋፋ ሲሆን “ጉዲፈቻ በአገሮች መካከል መልካም ግንኙነት ለመፍጠርም ይረዳል”የሚለው አመለካከት ስር መስደዱ ሌላው ምክንያት ነው ሊባል ይችላል፡፡

በአሜሪካ ድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ ተቋማዊ በሆነ መልኩ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ1956 ዓ.ም ሆልት በሚባል በጎ አድራጊ ግለሰብ ሲሆን በአሁኑ ወቅት “ሆልት ችልድረንስ ሰርቪስ” በበርካታ አገራትየሚንቀሳቀስና ብዙ ቅርንጫፎች ያሉት የጉዲፈቻ አገልግሎት ኤጀንሲ ለመሆን በቅቷል፡፡ ኤጀንሲው ኢትዮጵያ ውስጥ መስራት ከጀመረም ከሰባት ዓመት በላይ አስቆጥሯል፡፡
በተለያዩ አገራት የተከሰቱ ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችምለድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

በሮማኒያ የቻችስኩ መንግስት ፖሊሲ /Ceausescu’s Policy/ እያንዳንዷ ሩማንያዊት ሴት፣ቢያንስ አምስት ልጅ የመውለድ ግዴታ ተጥሎባት ነበር፡፡ አንዳንድ ቤተሰቦች ታዲያበድህነት የተነሳ የወለዷቸውን ልጆች ማሳደግ ስለማይችሉ ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ ለማስገባት ይገደዱ ነበር፡፡ የቻችስኩ መንግስት እ.ኤ.አ. በ1989 ዓ.ም በወደቀ ማግስት፣በአገሪቷ ውስጥ ከስድስት እስከ ስምንት መቶ የሚደርሱ የህፃናት ማሳደጊያዎች ነበሩ፡፡በእያንዳንዱ ማሳደጊያም ከ100ሺ እስከ 300ሺ የሚገመቱ ህፃናትእንደነበሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በማሳደጊያዎች ውስጥ ያሉ ህፃናት ሁኔታበመገናኛ ብዙሃንበሰፊውይነገር ስለነበር፣ አሁንም “ልጆችን ልንታደጋቸው ይገባል” በሚል ዓላማ፣የምእራቡ አለም ድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻን ማድረጉን ቀጠለበት። በተመሳሳይ ሁኔታ በሩሲያ በነበረው ከፍተኛ የሆነ ድህነት የተነሳም ከ300ሺ በላይ ህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡ ይሄን ተከትሎም የድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ ሊጨምር ችሏል፡፡

በቻይና አሁንም ድረስ የሚተገበረውና የህዝብ ብዛትን ለመቀነስ በመንግስት የወጣው አንድ ልጅ ብቻ የመውለድ ፖሊሲ፣ ዜጎች ጉዲፈቻ እንዳያደርጉ ከተቀመጠው ክልከላ እንዲሁም ህብረተሰቡ “ወንድ ልጅ ቤተሰቡን ይጦራል” በሚል ለሴት ህፃናት ባለው አሉታዊ አመለካከት የተነሳ፣ ብዙ ልጆች በተለይም ሴት ልጆች ማሳደጊያ ውስጥ እንዲገቡ ተገደዋል፡፡

የኤችአይቪ/ ኤድስ መስፋፋትምለድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ መጨመር ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ ከሰሃራ በታች ባሉ የምስራቅ አፍሪካ አገራት 12.3 ሚሊዮን ህፃናት በኤድስ ምክንያት ወላጆቻቸውን እንዳጡ ይገመታል፡፡ ሆኖም በአፍሪካ ድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ እንደሌሎች የዓለም አገራት በብዛት አልተለመደም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአህጉሪቱ ልጆችን በቤተዘመድ የማሳደግባህል መኖሩ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ግንወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት በቤተዘመድ የማሳደግ ሁኔታ መቀጠሉ በእጅጉ የሚያጠራጥር ነው፡፡ እናም በአፍሪካ ድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ እየተስፋፋ እንደሚመጣ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

ድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ፤ ዝምድና በሌላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ የጉዲፈቻ ዓይነት በሚለው ዘርፍ የሚመደብ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ጉዲፈቻ ልጁ የተፈጥሮ ልጅ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን በጉዲፈቻ አድራጊዎችናበጉዲፈቻ ተደራጊ መካከል የድንበር፤ የቀለም፣ የባህል፣ የዘር፣የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልዩነትምየሚስተዋልበት መሆኑ ነው፡፡

የድንበር ተሻጋሪ ጉዲፈቻ፤ መንግስት ወላጅ ለሌላቸው ህጻናት ከሚያቀርበው አማራጭ የእንክብካቤ መንገዶችአንዱ ሲሆን ጉዲፈቻው ፐብሊክ /public adoption/ በሚለው ዘርፍ ይመደባል፡፡ ይህም ለጉዲፈቻ የሚቀርቡት ልጆች ዕጣ ፈንታየሚወሰነው በሚመለከተው የመንግስት አካል መሆኑንያመላክታል።

ምንጭ፡ አዲስ አድማስ

የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከአውሮፓውያን ጋር ያለው ልዩነት መንስኤ እና ትክክለኛ መሰረቱ (የጉዳያችን ጡመራ ልዩ ጥንቅር)

$
0
0

የዘመን መስፈሪያዎች

 

Adeyabebaእግዚአብሔር «ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ፣ ለዕለታት፣ ለዘመናትና ለዓመታት ምልክት ይሆኑ ዘንድ» / ዘፍ.1. 14- 15/ የፈጠራቸውን የፀሐይንና የጨረቃን እንቅስቃሴ መሠረት ያደረጉት መስፈሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህም፤

 

ሀ. ዕለት-

አንድ ዕለት አንድ ቀንን /የብርሃን ክፍለ ጊዜን / እና አንድ ሌሊትን /የጨለማ ክፍለ ጊዜን/ ያካተተ ፀሐይ አንድ ጊዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ የያዘ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን አንድ ዕለት ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ የምትሸከረከርበት ጊዜ ነው፡፡

ለ. ውርኅ-

 

ወርኅ ማለት በግእዝ ጨረቃ ማለት ነው፡፡ አንድ ወርኅ የሚባለው ጊዜ ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን / በጥንቱም ጨምሮ/ ይህ ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዙራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ አንድ ወር ሃያ   ዘጠኝ ተኩል ዕለታትን ይፈጃል፡፡

 

ሐ. ዓመት-

አንድ ዓመት ማለት መሬት አንድ ጊዜ በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ ይህም 365 ከ1/4 / ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ከሩብ/ ዕለታት ይፈጃል፡፡ይህ ከመታወቁ በፊትም ግን የዓመት ጽንሰ ሓሳብ ነበር፡፡ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኃይሌ የፅንሰ ሐሳቡን አመጣጥ እንዲህ ያስረዳሉ፡፡

 

ሰዎች ርዝመታቸው እኩል የሆኑ ሁለት  ሻማዎችን ሠሩና ልክ ፀሐይ ስትወጣ /ቀኑ ሲያልቅና ሌሊቱ ሲጀምር/  አንዱን ሻማ አበሩት፡፡ልክ ፀሐይ ስትወጣ እሱን አጠፋና ሌላውን / ሁለተኛውን/ ሻማ አበሩት፤ ጧት ፀሐይ እንደገና ስትወጣ / ሌሊቱ አልቆ ሌላ ቀን ሲጀምር/ ሻማውን አጠፉት፡፡ አሁን እንግዲህ ከየሻማዎቹ /ከሁለቱ ሻማዎች/ ምን ያህል እንደተቃጠለላቸው ሲያስተያዩት ከሁለቱ ሻማዎች የተቃጠለው እኩል አለመሆኑን ተመለከቱ በዚህም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ እኩል አለመሆኑን ተረዱ፡፡

 

ቀደም ብለውም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ በተለያዩ ወቅቶች የተለያየ መሆኑን ልብ ብለው ነበርና ይህንን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ በቀኑና በሌሊቱ ርዘማኔ / በሚቃጠለው የሻማዎቹ መጠን/ መካከል ያለው ልዩነት ከወቅት ወቅት የተለያየ እንደሆነ ተመለከቱ ይህን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ ግን በየ182 /ተኩል/ ዕለቱ ቀኑና ሌሊቱ እኩል የሚሆኑባቸው ሁለት ዕለታት በዓመት ውስጥ እንዳሉ ተገነዘቡ፡፡ እነዚህ ዕለታት አንዱ የሙቀት ወራት ከመጀመሩ በፊት የሌላው ደግሞ የቅዝቃዜው ወራት ከመጀመሩ በፊት የሚመጡ ናቸው፡፡ ስለዚህ የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት አንድ ጊዜ እኩል ሁኖ ደግሞ በዚያው ወቅት እኩል እስከሚሆን ድረስ ያለውን ጊዜ ማለትም / 182 ተኩል + 182 = 365/ ዕለት አንድ ዓመት አሉት፡፡ አሁን ባለን ግንዛቤ ምድር በራሷ ዛቢያ እንደተሽከረከረች በፀሐይ ዙሪያ ትዞራለች፡፡ ምድር በፀሐይ ዙሪያ የምትዞረው ወደ ጎን 23 ተኩል ዲግሪ ያህል አጋድላ ነው፡፡ ይህ የቀንና የሌሊት ርዝመት መለያየትም የሚከሰተው በዚህ ማጋደል ምክንያት ነው፡፡

 

እንግዲህ በአጠቃላይ ዋናዎቹ የጊዜ / የዘመን/ መስፊሪያዎች ዕለት፣ ወር እና ዓመት ናቸው፡፡ ሦስትቱም ተመላላሽ ክስተቶችን / ለምሳሌ የፀሐይን መውጣት/ መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ እነዚሀ ተመላላሽ ክስተቶች አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪከሰቱ የሚፈጁት ዘመን ወይም ጊዜ  ዓውድ ይባላል፡፡ ዓውድ ማለት ዙሪያ፣ ክብ፣ እንደ ቀለበት ዙሮ የሚገጥም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዓውድ ማለት ክስተቶቹ አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪመጡ ድረስ ያለው ጊዜ ማለት ነው፡፡

 

በዚህ መሠረት ከላይ ያየናቸው ሦስት መስፈሪያዎች / ዕለት፣ ወርኀ፣ ዓመት/ ዓዕዋዳት / ዓውዶች/ የሚወጡበት ጊዜ ዓውደ ዕለት፣ ዓውደ ወርኀ፣ ዓውደ ዓመት ይባላሉ፡፡

 

መጀመሪያ ላይ ሰዎች እነዚህን ሦስቱን መስፈሪያዎች /ዓዕዋዳት/ /በተለይም ቀንና እና ወርን/ ለየብቻቸው ይጠቀሙባቸው ነበር፡፡ ከዚህን ያህል ቀን፣ ከዚህን ያህል ወር በኋላ /በፊት/ እያሉ ጊዜን ይለኩ ነበር፡፡

 

እነዚህ ሦስቱን በቅንብር /በቅንጅት/ ለመጠቀም ሲፈለግ ግን የዘመን አቆጣጠር ስሌት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም አንድ ወር 29 ከግማሽ ቀን ነው፡፡

 

እንዲሁ እንዳለ ለመቁጠር ቢፈለግ የመጀመሪያው ወር ጠዋት ላይ ቢጀመር ሁለተኛው ወር ምሽት ላይ ይጀምራል፣ ሦስተኛው ደግሞ ድጋሚ ጠዋት ላይ ይጀምራል፤ ይህን ለመቅረፍ ወሩን ሙሉ  ሰላሳ ቀን ቢያደርጉት ከትክክለኛው ወር /የጨረቃ ዐውድ/ ግማሽ ቀን ይተርፋል፤ 29 ቀን ብቻ ቢያደርጉት ደግሞ ግማሸ ቀን ይጎድላል፡፡ አንድ ዓመት 365 ከሩብ ዕለታት አሉት፡፡

 

ዓመትን በወራት ለመቁጠር ቢፈለግ፤ ዓመቱን 12 ወር ቢያደርጉት የዓመቱ /የዕለታት ቁጥር /29.5X12=354/ ብቻ ይሆናል፡፡ ይህም ከትክክለኛው ዓመት /365-354=11/ ዕለታት ያህል ያንሳል፡፡ 13 ወር ቢያደርጉት ዓመቱ /365X13=385.5/ ቀናት ይሆናል ይህም ከትክክለኛው ዓመት /383.5-365=19/ ቀናት ያህል ይበልጣል፡፡

 

ስለዚህ እነዚህን መስፈሪያዎች በቅንጅት ለመጠቀም ይህንን አለመጣጣም የሚፈታ ቀመር /የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት/ ያስፈልጋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የዘመን አቆጣጠሮች ተዘጋጅተዋል፡፡

 

የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር

አይሁድ ዘመን አቆጣጠር እያንዳንዳቸው 29 እና 30 ዕለታት ያሏቸው 12 ወራት አሏቸው፤

ተ.ቁ የአይሁድ ወራት የዕለታት ብዛት ወራቱ በእኛ
1 ኒሳን 30 መጋቢት/ ሚያዝያ
2 ኢያር 29 ሚያዝያ/ ግንቦት
3 ሲዋን 30 ግንቦት/ ሰኔ
4 ታሙዝ 29 ሰኔ/ ሐምሌ
5 አቭ 30 ሐምሌ/ ነሐሴ
6 አሉል 29 ነሐሴ/ መስከረም
7 ኤታኒም 30 መስከረም/ ጥቅምት
8 ቡል 29/30 ጥቀምት/ ኅዳር
9 ከሴሉ 30/29 ኅዳር/ ታህሳስ
10 ጤቤት 29 ታህሳስ/ ጥር
11 ሳባጥ 30 ጥር/ የካቲት
12 አዳር 1 29 የካቲት/ መጋቢት

እነዚህ የዓመቱ 12 ወራት በአጠቃላይ 354 ያህል ብቻ ዕለታት ይኖሯቸዋል፡፡ ይህም በትክክለኛው ዓመት በ11 ዕለታት ያህል ቢያንስም አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ልዩነቱ በሁለት ዓመታት 22 ዕለታት፣ በሦስት ዓመት ደግሞ 33 ዕለታት ያህል ይሆናል፡፡ ስለዚህ በየሦስት ዓመቱ ከአስራ ሁለተኛው ወር ጳጉሜን በፊት አንድ ሌላ ወር ይጨምሩና ጨምረው የዓመቱን የወራት ቁጥር ዐሥራ ሦስት ያደርጉና ልዩነቱን ያስተካክሉታል፡፡

 

የኢትዮጵያውያንና የግብጻውያን ዘመን አቆጣጠር

የሀገራችን ኢትዮጵያ እና የጥንት ግብጻውያን /ዛሬም ድረስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት/ የዘመን አቆጣጠር ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለታችንም እኩል ሰላሳ ቀናት ያሏቸው 12 ወራት አሉን፡፡ እነዚህ 12 ወራት / 12X30=360/ ቀናት አሏቸው እነዚህ ቀናት በትክክለኛው ዓመት በ/365.25-360=5.25/ ቀናት ያንሳሉ፡፡ ይህንንም 5 ቀናት / በ4 ዓመት አንድ ጊዜ 6 ቀናት/ ያሏትን 13ኛ ወር በመጨመር ያስተካክሉታል፡፡ የኢትዮጵያውያን እና የግብጻውያን ወሮች ስም እንደሚከተለው ነው፡፡

 

ተ.ቁ የግብጽ ወሮች የኢትዮጵያ ወሮች
1 ቱት/ዩት መስከረም
2 ባባ/ፓከር ጥቅምት
3 ሀቱር ኅዳር
4 ኪሃክ/ከያክ ታኅሣሥ
5 ጡባ/ቶቢር ጥር
6 አምሺር/ሜሺር የካቲት
7 በረምሃት መጋቢት
8 በርሙዳ ሚያዝያ
9 በሸንስ ግንቦት
10 ቦኩሩ ሰኔ
11 አቢብ ሐምሌ
12 መስሪ ነሐሴ
13 ኒሳ/አፓጎሜኔ ጳጉሜን

/ባሕረ ሐሳብ፣ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ፣ገጽ.65/

የኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር

የኢትዮጵያ እምነታዊ ባህል የሚወረሰው በሦስት ዐይነት ጠባይ ነው። አንዱ ሕገ ልቡና ይባላል። ከመጽሐፍ በፊት የነበረ ነው።ከአበው ቃል በቃል የተወረሰ ነው። ሁለተኛው በሕገ ኦሪት ከኦሪት የተቀዳ ነው። ሦስተኛው በሕገ ወንጌል ከወንጌል የተማርነው ነው።እና በሦስት ዐይነት ጠባይ የሚመራ ነው። በዚህ ዐይነት ከወረስናቸው በዓላት ማለት በሦስቱም ጠባያት ከወረስናቸው በዓላትየየራሳቸው መልክ ያላቸው አሉ። ለምሳሌ ልደት፥ ጥምቀት፥ ዕርገት፥ ደብረ ታቦር እነዚህን የመሳሰሉት ከወንጌል የተማርናቸውናቸው፤ በብሉይ የሉም። ፋሲካ፥ በዓለ ጰራቅሊጦስ ደግሞ ከኦሪት የተማርናቸው ናቸው። የዘመን መለወጫ በዓል ግን ከሕገ ልቡናቃል በቃል ተምረን፥ በኦሪት የመጽሐፍ መሠረት አግኝተንለት በወንጌልም አጽንተን ይዘነው የኖርነው ሦስት የሥራ ዘመን ክፍልየተላለፈና እዚህ የደረሰ ነው። እኛ የዘመን መለወጫ ብለን በሀገራችን ባህል የምናከብረው ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር የተገኘበት፥ብርሃን፥ ጊዜ፥ ዕለት፥ ሰዓት የተፈጠሩበት፤ ለብርሃን፥ ለጊዜ፥ ለዕለት፥ ለወር ለዓመት ጥንት መሠረት የሆነ ቀን ነው። ይህንን ሁሉበማስገኘት እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት፥ ዓለምን በመፍጠር ከሃሊነቱን ያረጋገጠበት ቀን ነው ብለን ነው የምናከብረው። ስለዚህምጥንተ ብርሃን፥ ጥንተ ዕለት፥ ጥንተ ጊዜ፥ ጥንተ ፍጥረት ርእሰ ዐውደ ዓመት ብለን ነው የምናከብረው። በዚህ ስያሜ በዓሉ ርእሰ ዐውደዓመት፥ ቅዱስ ዮሐንስ፥ የዘመን መለወጫ ብለን እናከብረዋለን።

 

ቅዱስ ዮሐንስ

የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ በዓል ሌላው ስሙ ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል። ቅዱስ ዮሐንስ የሚባልበትም ሁለት ጠባይ አለው። አንዱ፤መጥምቁ ዮሐንስ በሄሮድስ አንቲጳስ ጊዜ ከጳጉሜን ፩ ቀን ጀምሮ ታስሮ ሰንብቶ በመስከረም ፩ ቀን ዐሳብ ስለ ተቆረጠበትናበመስከረም ፪ ቀን እንዲሞት ውሳኔ ስለ ተሰጠበት አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ስለ ሞተ ሊቃውንት ይህንን በዓል እሱ ራሱ ለኦሪትናለወንጌል መገናኛ መምህር ስለ ነበረ ይህም በዓል ላለፈው ዘመን መሸኛ፥ ለሚመጣው ዘመን መቀበያ እንዲሆን ብለው በመስከረም ፩ቀን እንዲከበር ስላደረጉ በሱ ስም ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል። በሁለተኛው ግን ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱ ወንጌላዊ ዮሐንስየተሰየመበት ስለ ሆነ በአቆጣጠርም ተራ ወደ ኋላ ተመልሶ ቢቈጠር ዓለም የተፈጠረበት ዘመን በዘመነ ዮሐንስ እንዳጋጣሚ ሆኖስለሚገኝ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎ ይጠራል።

 

ዕንቍጣጣሽ

በዚያም ጊዜ የነበሩ ኖኅና ልጆቹ ሰማዩ በደመና በመክበዱ ምክንያት ማየ አይኅ እንደገና ይመጣ ይሆን፥ የጥፋት ውሃ እንደገና ይዘንምይሆን እያሉ ሲደነግጡ ከርመው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ሙሉ የፀሓይ ብርሃን ስላዩ፥ ምድር በአበባ አሸብርቃ ስለ ተገለጠችናበዚህም የእግዚአብሔርን ቸርነት፥ የቃል ኪዳኑን መጽናት ስለ ተረዱ ይህንን በዓል ቀድሞ ከአባቶቻቸው እንደ ወረሱት ያው ጥንተብርሃን፥ ጥንተ ዓመት፥ ጥንተ ዕለት አድርገው አክብረውታል። ሲያከብሩትም እንግጫ ነቅለው፥ አበባ ጐንጕነው መጀመሪያ መሥዋዕትይሠዉነት ከነበረው ቦታ ሄደው ለእግዚአብሔር ገጸ በረከት አቅርበው ከዚያ በኋላ ግን እርስ በርሳቸው የአበባ ስጦታ በመለዋወጥአክብረውታል። ሲያከብሩትም ዕንቍጣጣሽ በሚል ቃል እውነት የመልካም ሞኞታቸውን ይገላለጡበት ነበር። ዕንቍጣጣሽ ማለትንምብዙ ታሪክ ጸሓፊዎች በልዩ ልዩ መልክ ተርጕመውታል። እንዲያውም ንጉሡ ሰሎሞን ለሳባ ንግሥት የዕንቍ ቀለበት ሰጥቷት ነበርና«ዕንቍ ለጣትሽ» ማለት ነው ብለው የጻፉ ብዙ ሰዎችም አሉ፤ የሚናገሩም አሉ። ነገሩ ግን እንዲህ አይደለም። ዕንቍጣጣሽ ማለትተንቈጠቈጠ፥ አንቈጠቈጠ ከሚለው ቃል ተወስዶ ምድር በአበባ አጌጠች፥ ሰማይም በከዋክብት አሸበረቀ እንደ ማለት ሰማይንበከዋክብት ያስጌጠ አምላክ ምድርንም በአበቦች አጎናጸፋት ለማለት የተሰጠ ቃል ነው እንጂ ስለ ሳባ ንግሥት የተሰጠ አይደለም።ሁለተኛም አባቶቻችን ኢትዮጵያን በሙሉ ሀብት ተረክበዋት ነበርና፤ «ዕንቍ ዕጣ ወጣሽ፤» ሲሉ ወደ አገራቸው ሲገቡ ለአገራቸውመታሰቢያ አድርገው የተጠቀሙበት ቃል ነው ይባላል። በመሠረቱ ግን ያ የጥፋት ውሃ ቀርቶ ምድር ጸንታ፥ አበባ ቋጥራ፥ ፍሬለመስጠት ተዘጋጅታ መገኘቷን የሚያበሥር ቃል ነው።

 

መስከረም

መስከረም የሚባለው ወርም ኖኅ በመርከብ ውሥጥ በነበረ ጊዜ እንደ ዕብራውያን አቈጣጠር ሰባተኛ በሆነው በመስከረም ወርመጀመሪያ ላይ መርከቢቱ አራራት ከሚባለው ተራራ ላይ ዐርፋ ምድር ጨብጣለች። በግእዝ ቋንቋ መርከብ መስቀር ይባላል። ከዘመንብዛት በኋላ «ቀ» ወደ «ከ» ተለውጦ መስከረም ተባለ እንጂ መስቀርም ምድር አገኘች፥ መርከብም ምድር ነካች ለማለት የተሰጠ የወሩስያሜ ነው።

 

ርእሰ ዐውደ ዓመት

የምንለው፤ ዐውድ ማለት በግእዙ ቋንቋ ዙሪያ፥ ክብ የሆነ ነገር ማለት ነው። የዓመት ጠቅላላ ቀኖች መሠረታውያን ቀኖች የሚባሉትሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀኖች ናቸው። እነዚህም በኀምሳ ሁለት ሱባዔ ተከፍለው ለእያንዳንዱ ቀን በዓመት ውስጥ ለሰባቱ ዕለታትኀምሳ ሁለት ኀምሳ ሁለት ቀን ይደርሳቸዋል። ከነዚህ ቀኖች የተሳሳበ የሴኮንድ፥ የደቂቃ፥ የሰዓት ዕላፊ ተጠራቅሞ ሦስት መቶ ስድሳዐምስተኛዋን የዘመን ማገጣጠሚያ ቀን ያስገኛል። ይህቺ ቀን እንግዲህ ዙሪያ፥ ክብ መግጠሚያ ናት ማለት ነው። በዚህች ቀንአማካይነት ወደ ዐዲሱ ዘመን መጀመሪያ እንተላለፋለን። ይህቺ ቀን ዕለት አዕዋዲት፥ ዕለተ ምርያ የመዘዋወሪያ ቀን ወይም የመጨረሻቀን ተብላ ትጠራለች። በአራት ዓመት ደግሞ ከዚህች መሳሳብ የምትገኝ አንዲት ቀን ትመጣለች። ሦስት መቶ ስድሳ ስድስተኛ። ይህቺቀን ዕለተ ሰግር ትባላለች። መረማመጃ ማለት ነው። አንድ ቀን ታስተላልፋለች። እንግዲህ እነዚህን ሁለቱን ቀኖች ተከትሎየሚመጣው ቀን የዘመን መጀመሪያ፥ የዘመን ክብ መነሻና መድረሻ ተብሎ ርእሰ ዐውደ ዓመት ተብሎ በግእዙ ይጠራል። እነዚህ ቀኖችበኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ተጠቃለው አንድ ጊዜ የሚገኙ ናቸው።

 

የኢትዮጵያ ቍጥር መሠረቱ መጽሐፈ ሔኖክ የሚባለው ነው። መጽሐፈ ሔኖክ በ፲፱፥ ፳፥ ፳፩ እና ፳፪ ምዕራፎች የሚሰጠን የፀሐይን፥የጨረቃን ጉዞ መነሻ አድርጎ የወሮችን፥ የዕለታትን፥ የዓመታትን መነሻ፥ መድረሻ፥ መዘዋወሪያ ብተታቸውን፥ ጥንታቸውን ነውየሚያሳየው። ስለዚህም በሔኖክ ቍጥር የወር ቀኖች ቍጥር ሠላሳ ናቸው። በሦስት በሦስት ወር ግን አንድ ቀን ትከተላቸዋለች። እናዓመቱ ለአራት ይከፈላል። በዘጠና አንድ በዘጠና አንድ ቀን። ጠቅላላው ይሄ ድምር ሦስት መቶ ስድሳ ስድስት ቀን ይመጣል። ይህካለቀ በኋላ አንዲት ቀን ለዘመን ማገጣጠሚያ ዕለተ ምርያ የምትባለው ትመጣለች። እንግዲህ በኢትዮጵያውያን ቍጥር ወሩ ከሠላሳአያንስም፤ ከሠላሳ አይተርፍም። ለዓመቱም ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ቀን መደበኛው አቆጣጠር ነው ማለት ነው። ይህ ነገርበአውሮፓውያን ቍጥርም አለ። ግን እነሱ ከዓመት ወሮች ሰባቱን ሠላሳ አንድ ሠላሳ አንድ አድርገው አራቱን ደግሞ ሠላሳ ሠላሳአድርገው አንዷን ወር ሦስቱን ዓመት ሃያ ስምንት፥ በአራተኛው ዓመት ሃያ ዘጠኝአድርገው ያጣጧታል።

 

እንግዲህ የአቀማመጡ ለውጥ ካልሆነ በስተቀር በቍጥር አካሄድ ዞሮ ዞሮ የዓመት ቀኖች ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ወይም ሦስት መቶስድሳ ስድስት በመሆን አንድ ሆነዋል ማለት ነው። ልዩነቱ ግን የአቀማመጥ ለውጥ ነው። በኢትዮጵያ አቈጣጠር ግን ጠቅላላውን ፲፪ወሮች መደባቸው ሠላሳ ብቻ ነው። እነዚያ በሔኖክ መጽሐፍ በጣልቃ ገብነት የነበሩት አራት ቀኖች ተጠቅለው ጳጉሜን በሚባልበዓመቱ መጨረሻ ላይ ተገኝተዋል። ዐምስተኛዪቱ ቀንም ከእነሱ ጋር ተገኝታለች። ይህም ለቍጥር ተራ ቅምር መቅናት የተደረገ እንጂቀኑን የሚለውጥ ምንም ነገር የለበትም። እና ከእነዚህ ቀኖች በኋላ የምናገኘው ቀን ርእሰ ዐውደ ዓመት ይባላል። ይህንን በዓል ከአዳምጀምሮ እስከ ኖኅ ድረስ የነበሩ ዐሥሩም አበው በዐሥሩ ትውልድ እስከ ማየ አይኅ ድረስ ሲያከብሩት እንደ ቆዩና ኋላም የኖኅ ልጆችከአባታቸው ተቀብለው ሲያከብሩት እንደ ነበረ ኩፋሌ የተባለው መጽሐፍ በምዕራፍ ፯ ያስረዳናል። እንግዲህ ኢትዮጵያ ይህንን ቀንየወረሰችው ከአበው ነው የምንለው በዚህ ምክንያት ነው።

 

  

  የዘመን ቁጥር ልዩነት

ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ የዘመን አቆጣጠር መለያየትን መነሻ እንዲህ በማለት ያብራራሉ፤ «ክብ የሆነ ነገር ሲከብ ከየትኛውም ቦታ መጀመር ይቻላል፤ የዘመን አቆጣጠር /ዓውደ ዓመትም/ ይኸው ነው፡፡ ዋናው ነገር አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ ነው፤ የዘመን አቆጣጠሮቹም ልዩነት መንስኤው ይኸው ነው» ይላሉ፡፡ ባሕረ ሐሳብ፣ ጌታቸው ኃይሌ፣ ገጽ.65/ ለምሳሌነትም ሮማውያን የሮም ከተማ የተቆረቆረችበትን ጊዜ መነሻ ማድረጋቸውን/ በኋላም ታላቁ እስክንድር የነገሠበት ዘመን የዘመን ቆጠራ መነሻ ሆነው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ መሐመድና ተከታዮች ከመካ ወደ መዲና ያደረጉትን ስደት መነሻ የሚያደርገው ኢስላማዊ  የዘመን አቆጣጠርም ሌላው ተጠቃሽ ነው፡፡

 

የአይሁድን አቆጣጠር ትተን ከላይ ያየናቸው ሁለቱ የዘመን አቆጣጠሮች /የምዕራባውያኑ የጁልየስ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠርና የኢትዮጵያና የግብጽ አቆጣጠር/ ሁለቱም ዘመንን የሚቆጥሩት ከክርስቶስ ልደት መነሻ አድርገው ነው፡፡ ይሁን እንጂ እኛ ዛሬ 2006ዓ.ም ነው ስንል እነርሱ ደግሞ 2014 ዓ.ም ነው ይላሉ፡፡ በመካከሉ የ7/8 ዓመታት ልዩነት አለ፡፡ እንግዲህ ጥያቄው ትክክለኛው የትኛው ነው? የሚለው ነው፡፡

 

ጉዳዩ መጻሕፍትን ሊያጽፍ የሚችልና በእርግጥም የተጻፉበት ቢሆንም ለማሳያ ያክል ሁለት ነገሮች እንመልከት፤

  1. አሁን ባለው የምዕራባውያን አቆጣጠር ሄሮድስ የሞተው 4 ዓመት ቅ.ል.ክ ነው፡፡ ሄሮድስ የሞተው ጌታ ተወልዶ በስደት ሦስት ዓመት ያህል በግብጽ ከቆየ በኋላ ነው፡፡ ይህ ማለት በእርሱ አቆጣጠር ጌታ የተወለደው በ7 ዓመት ቅ.ል.ክ ነው ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ጌታ በትክክል በተወለደበት በአንድ ዓ.ም እነርሱ ጌታ ሰባት ዓመት ሆኖታል ይላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛውን ቁጥር ለማግኘት አሁን ካላቸው ቁጥር ላይ ሰባት ዓመት መቀነስ አለባቸው፡፡
  1. ፍላቪየስ ጆሴፈስ የተባለው የአይሁድን ታሪክ የጻፈው ሊቅ እንደመሰከረው ጌታ የተወለደበት ዓመት ነው ተብሎ በወንጌል ላይ የተጻፈው የቆጠራ ዓመት /ሕዝቡ ሁሉ የተቆጠረበትን ዘመን /ሉቃ.2.1/ በጎርጎሪያን ዘመን አቆጣጠር «7 ዓመተ እግዚአ /A.D/ ላይ ነው፡፡» በማለት መረጃ ትቶልናል ይህ ማለት ደግሞ ከምዕራባውያኑ ዘመን አቆጣጠር ላይ 7 ዓመቶች የግድ መቀነስ አለበት ማለት ነው፡፡ ያ ሲደረግ ደግሞ የኛን ዘመን አቆጣጠር ያመጣል፡፡

የዘመን መለወጫ ቀን ልዩነት

ሁለተኛው ጉዳይ የዘመን መለወጫ ወርና ዕለት ልዩነት ነው፡፡ እኛ መስከረም  1 አዲስ ዓመት ስንጀምር እነርሱ በ January 1 / በእኛ ታኅሣሥ 23/ አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ይህ ከየት የመጣ ልዩነት ነው?

የእኛ እና የግብጻውያን አቆጣጠር እዚህ ጉዳይ ላይ ከአይሁድ አቆጣጠር ጋር ይስማማል፡፡ በአይሁድ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ኒሳን የሚባለው /በእኛ መጋቢት/ ሚያዝያ/ ነው፡፡

«ይህ ወር የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፣ በዚህም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የአንድ ዓመት ተባዕት ላይ ወስደው ይረዱ፡፡ . . .»/ዘፀ.12.1-14/ ተብሎ የተሰጣቸውን የፋሲካ በዓል የሚያከብሩት በዚህ ወር ነው፡፡

ይሁን እንጂ አዲስ የዓመት በዓል አድርገው የሚያከብሩት «የሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ዕረፍት ይሁናችሁ፡፡ በዚሁ በመለከት ድምጽ የሚከበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ መስዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የተለመደ ተግባራችሁን አታከናውኑበት» /ዘሌ.13.23-25/ ተብሎ የተሰጣቸው የሮሽ ሆሻና፣/የመለከት በዓል ወይም በዓለ መጥቅዕ/ ተብሎ የሚጠራው በዓል ነው፡፡ ይህም ማለት አዲስ ዓመት የሚያከብሩት በሰባተኛው ወር በኢታኒም ወር /በእኛ መስከረም ጥቅምት/ ነው፡፡

በቤተክርስቲያናችንም ትምህርት ዓለም የተፈጠረው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ መስከረም ደግሞ ከመጋቢት ጀምሮ ሲቆጠር ሰባተኛው ወር ነው፡፡ ይህም ከአይሁድ ዘመን አቆጣጠር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

አይሁድስ ቢሆኑ የመጀመሪያው ወር እያለ አዲስ ዓመትን ለምን በሰባተኛው ወር ያከብራሉ ለሚለው ጥያቄ ሁለት ዓይነት ምላሾች /ምክንያቶች/ ይሰጣሉ፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት «ሰባተኛው ወር ኖኅ ከመርከብ የወጣበት ወር በመሆኑ ይህ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ተደርጎ መከበር በመጀመሩ ነው» የሚል ነው፡፡ በዘመን መለወጫ ዕለት ልጃገረዶች አበባ እና ለምለም ሣር መያዛቸው ርግቢቱ ለኖኅ ካመጣችው ለምለም ወይራ /ቄጠማ/ ጋር ተያይዞ የተጀመረ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ሁለተኛው ደግሞ መስከረም የቀንና የዕለቱ ርዝመት እኩል የሚሆኑበት ወር በመሆኑ ነው የሚል ነው፡፡ የመስከረም 1 ቀን ስንክሳር «የተባረከ የመስከረም ወር የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመታት ወሮች ርእስ ነው፤ የቀኑ ሰዓትም ከሌሊቱ ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው» ይላል፡፡

እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባው ሌላው ጉዳይ በቤተክርስቲያናችን ትምህርት እመቤታችን ጌታን የጸነሰችው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ጳዉሎስ ፣የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት ተወለደ» /ገላ.4.4/ እንዳለው የ5500 ዘመኑ ፍጻሜ /ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ/ ነው፡፡

ጽንሰትን መጋቢት 29 ካልን በኋላ ልደትን ታህሣሥ 29 ቀን እናከብራለን፡፡ ከመጋቢት 29 እስከ ታህሣሥ 29 ድረስ 9 ወር ከ5 ቀን ነው፡፡ /ጳጉሜን ጨምሮ/፡፡ ጳጉሜ 6 በምትሆንበት ጊዜ ደግሞ ታህሣሥ 28 ቀን ልደት ስለሚከበር አሁንም በመሐሉ ያለው ጊዜ 9 ወር ከአምስት ቀን ይሆናል፡፡

ማጠቃለያ

በመጨረሻም የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ፍፁም መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የሚቆጥር መሆኑን እንጂ እንደ ዘመኑ ነገስታት ፍላጎት በታሪክ ክስተትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን ከተረዳን ይህንን ሃሳባችንን የሚያጠናክርልን የሳምንታንት እና የወራት ስያሜዎቻችንን እንዲሁም የልሎቹ የቀን አቆጣጠር ምንጭን ከ እዚህ በታች ባሉት ሰንጠረዦች እንመልከት።ለምሳሌ እነኚህ የሳምንታንት ልዩነቶች አውሮፓውያን ከጥንት ከነበረ አምልኮት ጋር የትዛመደ ሲሆን የእኛ ግን እግዚአብሔር አለምን መፍጠር ከጀመረ የመጀመርያ ቀን ስንል እሁድ ማለታችንን ሁለተኛ ቀን ስንል ሰኑይ (ሰኞ) ማለታችንን ወዘተ እንረዳለን።

ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም

ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም

ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም

አሮጌው ዘመን 2006 ዓም ተጠናቆ አዲሱን 2007 ዓም ልንቀበል ሰዓታት ቀርተውናል። የሮማ ካቶሊክ ፓፓ ቤኔዲክት 16ኛ ”የናዝሬቱ እየሱስ” በተሰኘ መፅሐፋቸው አሁን አውሮፓውያን የሚጠቀሙበት የክርስቶስ የልደት ዘመን ትክክለኛ እንዳልሆነ ሲገልጡ እንዲህ ብለዋል-“The calculation of the beginning of our calendar—based on the birth of Jesus—was made by Dionysius Exiguus, who made a mistake in his calculations by several years,”  ”ከጅምሩ የቀን አቆጣጠራችን ክርስቶስን ተወለደ ያለበት ዘመን መሰረት (በእክስጉሥ የተቀመረው) የብዙ አመታት የስሌት ስህተት አለው” ብለዋል።

(http://www.charismanews.com/world/34714-pope-says-jesus-birth-date-is-wrong)

ይህ ከአንድሚልዮን ኮፒ በላይ እንደተሸጠ የተነገረው መፅሐፍ ላይ ፓፓው ይህንን ይበሉ እንጂ ስህተቱን

 ለማረም እና ወደ ትክክለኛው ወደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ለመምጣት የደፈረ እስካሁን አልታየም።ወደፊት

 ግን ይጠበቃል። 

 

ጉዳያችን ጳጉሜን 2/2006 ዓም

ምንጮች  -

1/ መስከረም 2004 አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም
2/ አለቃ አያሌው ታምሩ ትምህርት http://www.aleqayalewtamiru.org/new_year_2003.html

3/ ማኅበረ ቅዱሳን ድህረገፅ http://www.eotc-mkidusan.org/site/-mainmenu-24/–mainmenu-26/30—-

 4/ደጀ ሰላም መስከረም 11/ 2011 http://www.dejeselam.org/2011/09/blog-post_11.html#more

  5/ማኅበረ ቅዱሳን 2000 ዓም አውደ ርዕይ

 

 

Source:: gudayachn

የ 2007ዓ/ም አዲሰ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጫ (ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት )

$
0
0

Arena-Tigray-logoዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት የ 2006 ዓ/ም ዘመነ ማርቆስ ተገባዶ ወደ 2007 ዓ/ም ዘመነ ሉቃስ እንካን በሰላም አሸጋገረን በማለት አዲሱ ዘመን የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት እንዲሆንል በማለት ለመላ የኢትዮåያ ህዝቦች የመልካም ምኞት መግለጫውን ያቀርባል ፡፡

ኣዲሱ ኣመት የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት እንዲሆንልን ማደረግ በኛው ኢትዮåያውያን ዜጎች እጅ ነው፡፡ አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት እንዲሆንልን መመኘት የመጀመርያው እርምጃ ቢሆንም ምኞቱ ክውን ሆኖ ለማየት ግን በግልም ሆነ በቡድን ከእያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የሚጠበቅ ሃገራዊ ግዴታ አለብን፣፣ ስለሆነም መጪው ኣዲስ ኣመት የሰላም ‘የደስታና የብልፅግና ኣመት ይሆንልን ዘንድ ከመመኘት ወደ እውነታ ለመብቃት ከገ¸ው ፓርቲ ‘ከመንግስትና’ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሁም ከሲቪል ማሕበራትና ከእያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቀው ሚና ወሳኝነት ኣለው፡፡
የፍላጎት’የሃሳብና የእምነት ልዩነት መኖር የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ባህሪ ሆኖ ለየተለያየ ፖሊሲ የሚያራምዱ ፓርቲዎችን መፈጠር ምክንያት ሆኖ ብሎም የህዝቦች የሰላም ፍላጎትና የህዝቦች ፍላጎት የበላይነት መከበር ሲባል የሰላማዊ ‘ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ ውድድር መኖር የግድ ማለቱ፣ ይህ ባልተቻለበት ወይም የሚቻል እያለ ባልተጠቀምንበት ደግሞ ለ የእርስ በርስ ጦርነቶች ማቆጥቆጥ ምክንያት እንደሚሆንና ይህን ለሃገር ሰብኣዊና ቁሳዊ ሃብት ውድመት ዓይነተኛ ምክንያት እንደሆነ ከታሪክ የምንማረው ብቻ ሳይሆን በህይወታችን ያየነው እውነታ ነው፡፡

ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት ፓርቲ /ዓረና / መጪው አዲሱ ዓመተ 2007 የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት እንዲሆንልን የሚያግዙት የ 3 ዓመት የሰላማዊ ውድድር ስትራተጂ ረቂቅ ሰነድ በማፅደቅና የ2007 ዓ/ም ምርጫን ማእከል ያደረግ የተግባር እቅድ ነድፎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ለመላ የኢትዮጵያ ህዝብና ለነፃነትና እኩልነት ወዳጁ የትግራይ ክልል ህዝብ ሲያበስር ደስታ ይሰማዋል ፡፡

እናም ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት ስንሸጋገር በአሮጌው አመት ያየናቸውና ያጋጠሙን ችግሮች ወደ አዲሱ አመት እንዳይሸጋገሩና አዲሱ ዐመት የሰላም ፣የደስታና የብልፅግና አመት እንዳይሆን የሚያውኩ መልከ ብዙ ችግሮቻችን ይወገዱ ዘንድ በግልም ሆነ በቡድን የዜግነት ሃላፊነታችን መወጣት የገድ የሚሉን አሉ፡፡
1. መላው ኢትዮጵያዊ ዜጎች ፣ ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ችግር ያለ ልዩነት መላው ኢትዮጵያዊያንን ያቆሰለ እንጂ አንዱን ሸልሞ ሌላው የጎዳ ባለ መሆኑና የችግሩ መፍትሄም በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ አsምና የጋራ መስዋእትነት ብቻ መሆኑን መገንዘብና ፣ እንዲሁም የአገራችን እጣ ፈንታ ለማስዋብና የሃገራችን ፖለቲካ ለማዘመን ከማናቸውም መልኩ ከዘር ፖለቲካ መራቅ የሚጠበቅብን መሆኑን፣

2. ሰላማዊ የትግል አማራጭን የመረጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘመቻ ማሳደድ ፣የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በግድ አባልነታቸው እንዲሰርዙ ማስገደድ/ ለምሳሌ ፣በራያ ፣ አፅቢ ፣ ወልቃይት፣ አኩሱም / ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህዝብ የሚገናኙበት እንደ ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ ማፈን / መቐለ/፣ ከሁሉም ጥፋች የከፋ ጥፋትና የሰላም ጠንቅ በመሆኑ በተለይ በተለይ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የሃገር እጣ ፈንታ ከፖለቲካ ፍላጎት እንደሚቀድም ተገንዝበው የበኩላቸውን ሃገራዊ ሃላፊነት እንዲወጡ ፣

3. ሰብአዊ መብትና ነፃነት በገዛ ትግልና ጥረት የምታመጣው እንጂ በገፀ በረከት የሚሰጥ ፀጋ ባለመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ የገዛ ራሱ መብትና ነፃነት ለማስከበር የሚያሳየው ድፍረትና ቆራጥ አsም መጪው አዲሱ አመት የሳላም ፣የደስታና የብልፅግና ሆኖ እነዲከወን የማድረግ ወሳኝ ሃላፊነት ያለው መሆንና ይህንኑ ሃላፊነቱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በመተው በገዛ መብቱ ባይተዋር ለመሆን መፍቀድ እንደማይጋበው፣ፍርሃት በማናቸውም መስፈርት ሰብአዊ መብትና ነፃነት አሳልፎ ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል መሆኑንና እንዲያውም መፍራት ያስፈልጋል ከተባለ ከሁሉም ባላይ መፍራት ያለብን እየፈሩ መኖር መሆኑን መገንዘብ ፍርሃትን በማስወገድ አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት ማድረግ የሚጠበቅብን መሆኑን፣

4. በፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ ልዩነት እንዳለ ሆኖ በሃገራችን የሰላም ፣የደስታና የብልፅግናና ራኢ ሊተገበር የሚቻለው የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩልነት በመቀበልና በመተግበር ፣ብሄርነትና ብሄረሰብነት እንዲሁም የተለያዩ ባህላዊና ማንነታዊ ማሕበረሰብነት ተፈጥሮአዊ ፀጋና የሃገሪቱ ውበት አድርጎ መቀበልና የሁሉንም ፍላጎት ያካተተ የፖሊሲ አቅጣጫ ብቻ የሃገራችን የሰላምና የብልፅግና መነሻና መድረሻ አድርጎ መቀበልና መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ፣

መገንዘብና ለጉዳዩ ቁርጠኛ አsም መሳየት እንደሚጠበቅብንና በጋራ እንድንቆም ዓረና ጥሪውን እንሆ አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታና የብልፅግና ዓመት እንዲሆንልን ምኞቱን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ያቀርባል፡፡

ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉእላዊነት /ዓረና /
ጳጉሜን 2/2006 ዓ/ም
መቐለ


አዲሱ የዳያስፖራ የትግል ስልት (ጌታቸው ሺፈራው )

$
0
0

ጌታቸው ሺፈራው

105አምባገነኖችን በሰላማዊ መንገድ ለማንበርከክ ይውላሉ የሚባሉ ከ180 በላይ የትግል ስልቶች እንዳሉ ይጠቀሳል፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ በተለያዩ መንገዶች ግለሰብ ላይ ጫና ማሳደር ነው፡፡ በዚህ የትግል ስልት ውስጥ የሚጠቀሰው ደግሞ መሪዎች በስራቸው እንዲሸማቀቁ ማጋለጥ ይገኝበታል፡፡ አንዳንዶቹ ባለስልጣናትን ማሸማቀቅ፣ ማጋለጥ ባለፉት አስርት አመታት እንዳልተጀመረ ያስረዳሉ፡፡ ሮማውያንና ቻይናውያን ስር የነበሩ ተገዥ ህዝቦች የድሮዎቹ ገዥዎችን ንግግር በማቋረጥ፣ የእነዚህ አገዛዞች ወረራ፣ ፖሊሲ አላግባብ የሆነ ግብር አሊያም በግለሰብ ደረጃ ለመሪዎቻቸው ያላቸውን ተቃውሞ በመጮህ ይገልጹ እንደነበር ይገለጻል፡፡ ይህ መሪዎችን የማሸማቀቅ የሰላማዊ ትግል ስልት ከድሮዎቹ በበለጠ ባለፉት በተለይም የሶቬትን መፈረካከስ ተከትሎ የሰላማዊ ትግል ስልቶች ይበልጡን የህዝብ መሳሪያ በሆኑበትና አምባገነኖች ስልጣናቸውን በመልቀቅና ባለመልቀቅ መሃል ሲወዛገቡ በነበሩበት ዘመን ጀምሮ በስፋት እየተሰራበት ይገኛል፡፡

የሙታድሃር አልዛይዲ መንገድ

ሙንታድሃር አል ዛይዲ የኢራቅ የመንግስት ቴሊቪዥን ውስጥ የሚሰራ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ይህ ጋዜጠኛ ኢራቅ ውስጥ የነበረው የአሜሪካ ሰራዊት በኢራቃውያን ህጻናት፣ እናቶችና ወጣቶች ያደርሰው የነበረውን ግፍ በቀዳሚነት ተመልክቷል፡፡ ኢራቃውያን በአሜሪካ ሰራዊት ፍዳቸውን ማየታቸውን ይፋ ለማውጣት የተቀጠረበት የመንግስት ሚዲያ ባያመቸውም በግሉ ግን የቡሽ አስተዳደር የሚፈጽመውን ግፍ በሰላማዊ መንገድ ማጋለጥ ችሏል፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥር 14/2008 ላይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሎው ቡሽ በኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤተ መንግስት ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጡ በመሆኑ ሁኔታውን እንዲዘግብ ሲላክ ይህን ትግሉን የሚያካሂድበት አመች ሜዳ አግኝቷል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ሆነው የአሜሪካ መንግስትና ህዝብ ኢራቅን ለመታደግ የወሰዱትን ፖሊሲ፣ የአሜሪካ ሰራዊት ለኢራቃውያን የሚያሳየውን ርህራሄና ደጀን አስመልክተው ድስኩር እያሰሙ በነበረበት ወቅት አንድ በአሜሪካ ፕሬዝንት ላይ፣ ያውም በኢራቅ ቤተ-መንግስት ውስጥ ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ፣ አንድ የመንግስት ሚዲያ ውስጥ የሚሰራ ጋዜጠኛ ይፈጽመዋል የማይባል አስደንጋጭ ነገር ተከሰተ፡፡ ከቡሽ ዲስኩር ይልቅ ‹‹ይህ ከኢራቅ ህዝብ የተላከ የመሸኛ ሰላምታ ነው!›› የሙንታድሃር አል ዛይዲ ድምጽ አስተጋባ፡፡ ድምጹን አጅቦት የጋዜጠኛው ጫማ የአሜሪካኑን ፕሬዝዳንት ለጥቂት ሳተው፡፡ ለጋዜጠኛው ይህ ሌላ ጊዜ የማያገኘው ጦር ሜዳው ነውና ‹‹ይህኛው ደግሞ ኢራቅ ውስጥ ለሞቱት፣ ባል አልባና አባት አልባ ለቀሩት ኢራቃውያን ማስታወሻ›› ይሁን በሚል ሁለቱንም ጫማዎች ወደ ቡሽ በመወርወር የኃያሏን አገር አሜሪካ ፕሬዝደንት በጫማ አስጨነቃቸው፡፡ ቡሽ በሚያዙት የአሜሪካ ሰራዊትና ይሁንታ ስልጣን ላይ የነበሩት የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹እኔን ይምታኝ›› ብለው ለተደናገጠው ቡሽ ሲደረቡ ታዩ፡፡

የዚህ ጋዜጠኛ ተግባር ሰላማዊ ለመሆኑ ቡሽ በወቅቱ የሰጡት አስተያየት በግልጽ አሳይቷል፡፡ ከስድብ ጋር በጫማ ባራወጣቸው ጋዜጠኛ ተግባት ተበሳጭተው ‹‹ተደፍረናል፣…›› አላሉም፡፡ ይልቁንስ ‹‹ይህ ጉዳይ ምንም አያስጨንቀኝም፡፡ ሰዎች ትኩረት ለማግኘት የሚወስዱት ስልት ነው›› በማለት ሰላማዊ እንደሆነ ተገንዝበው አልፈውታል፡፡

በእርግጥ የኢራቁ ጋዜጠኛ የወሰደውን እርምጃ ቡሽ ‹‹ይህ ጉዳይ ምንም አያስጨንቀኝም›› ቢሉም በቡሽ ይሁንታ ስልጣን ላይ የነበሩት የአገሪቱ ገዥዎች እንዲሁ ሊያልፉት አልቻሉም፡፡ በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠባቂዎች ጋዜጠኛውን እየደበደቡ ለስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት አሳልፈው ሰጥተውታል፡፡ ከፍተኛ ደብደባ እንደደረሰበትም ታውቋል፡፡ በዛች የወደቀች አገር የስርዓቱ እጅ የሆነ ፍርድ ቤት የሶስት አመት እስር ወስኖበታል፡፡ በተቃራኒው ህዝብ ጋዜጠኛው ጀግና መሆኑን በመግለጽ እንዲለቀቅ ጎዳና ላይ ወጥቶ ጭምር ጠይቋል፡፡ ተወሰደበት የተባለውን እርምጃ ተቃውሟል፡፡ የኋላ ኋላ ጋዜጠኛው ከ9 ወር በኋላ መልካም ጸባይ ያለው ሰው ነው ተብሎ ተለቅቋል፡፡ በዛች በፈራረሰችውና በአሜሪካ ስር በምትተዳደር ኢራቅ ውስጥ ያውም በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ላይ ጫማ የወረወረ ኢራቃዊ ጋዜጠኛ የወሰደው እርምጃ ሰላማዊ በመሆኑ ሰላማዊ ነው ተብሎ ተለቋል፡፡ አገሪቱ ያለችበት ሁኔታ እንጂ ለአንድም ቀን የሚያሳስት አልነበረም፡፡ በኋላ ላይ የወረወረውን ጫማ ቅርጽ የሚያሳይ ሀውልት የተቀረጸለትም ትግሉ ሰላማዊና አርዕያ የሚሆን ስለነበር ነው፡፡

የዚህ ኢራቃዊ ጋዜጠኛ ስምና ዝና እንዲሁም የትግል ስልት ኢራቅ ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡፡ ጫማ መወርወር አንድን ሰው ምን ያህል እንደሚጠሉት ለማሳየት በአረቡ ዓለም የተለመደ ባህል ነው፡፡ ከዓረቡ ዓለም ውጭም በመላው ዓለም አዲስ አምባገነኖችን የማሸማቀቂያ ስልት ሆኖ የታየ ሲሆን ሙንታድሃር በፕሬዝዳንት ቡሽ ላይ ጫማ ከወረወረ በኋላ በፖለቲከኞችና በሌሎች ታዋቂ ሰዎች ላይ ቢያንስ 44 ያህል ጊዜ ጫማ ተወርውሮባቸዋል፡፡

ቡሽ ከተወረወረባቸው በኋላ ጦርነቱን የተቃወሙ የአሜሪካ ዜጎች በሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ወደ ዋይት ሃወስ ጫማቸውን በመወርወር የኢራቁን ጋዜጠኛ ተግባር አሜሪካ ውስጥ ደግፈውታል፡፡ በተመሳሳይ ካናዳ ውስጥም ሰላማዊ ሰልፈኞች ከአሜሪካ ቆንጽላ ፊት ለፊት በርካታ ጫማዎችን በመወርወር ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ እ.ኤ.አ 2008 ጥር ወር መጨረሻ ላይ የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ወይንጃባው ካምብሪጅ ዩኒቨርሰቲ ውስጥ ከጎርደን ብራውን ጋር ስለ ኢኮኖሚ ትብብር እያወሩ በነበረበት ወቅት ከአንድ ጀርመናዊ ተሳታፊ ወጣት ጫማ ተወርውሮባቸዋል፡፡ በወቅቱ ስለ ቻይና እድገት ሲደሰኩሩ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ አምባገነንነታቸውና ውሸታቸው ተቃውሞውን ካቀረበው ወጣት ውርጅብኝ ተርፈዋል፡፡ ጀርመናዊው ወጣት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቻይናውያን ላይ የሚያደርሱትን በደል በመቃወም ጫማ መወርወርን ዓለም አቀፋዊ የሰላማዊ ትግል ስልት አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡

የቻይና ባለስልጣናት ወጣቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩንና የሁለቱን አገር ግንኙነት ለመጉዳት ነው በሚል ቅጣት እንዲጣልበት ጫና ቢያደርጉም ወጣቱ ግን ይህን ለማድረግ የሚያሳይ መረጃ በመታጣቱ ተለቅቋል፡፡ በተመሳሳይ አመት ስዊድን ውስጥ ይገኙ የነበሩ የእስራኤል አምባሳደር ስለ ጋዛ በሚያወሩበት ወቅት ‹‹ገዳይ›› በሚል ድምጽ ንግግራቸውን በማቋረጥ ጫማ ተወርውሮባቸዋል፡፡ ሄላሪ ክሊንተን ግብጽን እየጎበኙ በነበሩበት ወቅት ‹‹ሞኒካ›› ከሚል የማሸማቀቂያ መዝሙር ጋር ግብጾች ጫማቸውን ወርውረውባቸዋል፡፡ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር በሌላ ቀንም እየተናገሩ በነበረበት ወቅት አንድ ተማሪ ‹‹ዘረኛ›› ከሚል ማሸማቀቂያ ጋር በጫማ ተስተዋል፡፡ አህመዲን ኒጃድ ግብጽና አገራቸው ውስጥም ጫማ ተውርውሮባቸዋል፡፡

ከእነዚህ በተጨማሪ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞናህ ሲንህ፣ የዓለም ገንዘብ ድርጅት ዳይሬክተር ዶሚኒኩ ስትራውስ ካህን፣ በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር (ካርቱም ውስጥ)፣ የቱርኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርዶጋን፣ የፓኪስታኑ ፕሬዝዳንት አሲፍ አሊ ዛርዳሪ፣ ቶኒ ብሊየር (ጫማና እንቁላል)፣ የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔርቬዝ ሙሻራፍና ሌሎችም የጫማ ውርወራ ተቃውሞ ሰለባና የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ መነጋገሪያ ሆነው ተሸማቅቀዋል፡፡

ይህ ጫማ በመወርወር ባለስልጣናትን ማሸማቀቅ አንዳንዶች ሰላማዊ አይደለም ቢሉትም የተወረወረባቸው አካላት ሳይቀሩ እንዲሁ ሲያልፉት ተስተውሏል፡፡ በባለስልጣናት ጫማ ከወረወሩት መካከል ከበድ ያለ ቅጣት የተጣለበት ሰው እምብዛም አይነገርም፡፡ የኢራቁ ጋዜጠኛ ጫማ በወረወረበት ወቅት እውቅ የሆኑ የሰላማዊ ትግል ጠበብቶች ‹‹ጋዜጠኛው ቡሽን ለመጉዳት ሳይሆን ጫማ መወርወር በዓለቡ ህዝብ ዘንድ ለሚጠላ ሰው የሚደረግ ተግባር በመሆኑ ነው›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ጋዜጠኛው ለ9 ወር ከታሰረ በኋላም መልካም ስነ ምግባር ያለው ሰው ነው ተብሎ ከመለቀቁም ባሻገር በአሁኑ ወቅት ለኢራቃዊያን ሰብአዊ እርዳታ በመስጠት ላይ የሚገኝ መሆኑ ይህን ሰላማዊነቱን የሚያሳይ ነው፡፡ በቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ ጫማ የወረወረው ጀርመናዊ ወጣት ‹‹የወረወርኩት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመምታት ብዬ አይደለም፡፡ ጫማውን መድረኩ ላይ ስጥለው የጋራ መግባባት እንደሚፈጥር አውቃለሁ፡፡ ይህ አንድ የተቃውሞ ምልክት ለመሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ሰው ለመጉዳት ፍላጎት የለኝም›› በሚል የተቃውሞውን ሰላማዊነት ገልጾ ነበር፡፡

የአበበ ገላው (የዲያስፖራው መንገድ)

የባለስልጣናትን ንግግር በማቋረጥ የሚፈጽሙትን በደል ለሚዲያና ለዓለም ማህበረሰብ ማሰማት አንዱ የሰላማዊ ትግል ስልት ነው፡፡ በህዝብ ላይ በደል በፈጸሙ ባለስልጣናት፣ የኩባንያ ባለሃብቶች፣ ግለሰቦች ለሚዲያ በቀረቡበት ወቅት አሊያም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አሜሪካ ውስጥም ጮኸት እንደተደረገባቸው ይነገራል፡፡ ለአብነት ያህል በምርጫ ክርክሮች መሃከል በመናር ላይ የነበሩ ባለስልጣናት በፖሊሲያቸው የማይስማሙ ዜጎች ንግግራቸውን በማቋረጥ መቃወም፣ ማሸማቀቅ ተደርጎባቸዋል፡፡

በግንቦት ወር 2004 ዓ.ም በባራክ ኦባማ ግብዣ ወደ አሜሪካ ያቀኑት የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊም በሌሎች የአፍሪካ መሪዎች፣ የአሜሪካ ተወካዮችና የዓለም ሚዲያ ፊት ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ገጥሟቸዋል፡፡ ልክ እንደ ኢራቁ ጋዜጠኛ የውይይት መድረኩን እንደ ሰላማዊ የጦር ሜዳ የተጠቀመው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ‹‹መለስ ዜናዊ አምባገነን ነው፣ ነጻነት እንፈልጋለን፣ እስክንድርና ሌሎች የህሊና እስረኞች ይፈቱ›› የመሳሰሉትን መፈክሮች ሲያስተጋባ መለስ ዜናዊ አቀርቅረው ታይተዋል፡፡ ጋዜጠኛው ያደረገው ነገር ሰላማዊ በመሆኑ የውይይቱ አስተባባሪዎች አበበ ገላው መፈክሩን እንዲያቆም ‹‹ሰምተናል፣ እናመሰግናለን›› ከማለት ውጭ ሌላ እርምጃ አልተወሰደበትም፡፡

የኢራቁ ጋዜጠኛ ካደረገውም በበለጠ እጅግ ሰላማዊ በሆነና የዓለም ማህበረሰብ በሰፊው በሚሰማበት አጋጣሚ በኢትዮጵያ ዲያስፖራ የተጀመረው ተቃውሞ በአንድ ወቅት መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ምንም እንኳ ሰላማዊ ትግልን ይህን ያህል ለውጥ እንደማያመጣ በሚያምነው ማህበረሰብ ውስጥ የአንድን ባለስልጣን ንግግር ማቋረጥ ባንዳንዶቹ ከዚህ ግባ የማይባል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ብልግና ተደርጎ ቢወሰድም በስርዓቱ ደጋፊዎችና ባለስልጣናት ላይ ከፍተኛ መደናገጥን መፍጠሩ የሚታወስ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግል ለውጥ ያመጣል ብለው በሚያምኑት ዘንድም እንደ ድል የተቆጠረ ሲሆን ሌሎች መንገዱን እንዲመርጡት አድርጓል፡፡ አበበ አቶ መለስ ‹‹አምባገነን ነው!›› ከተባሉ ከሁለት አመት በኋላ አርብ ሜይ 9/2014 እ.ኤ.አ በፕሬዝዳንት ኦባማ ላይ ዳግመኛ ተግብሮታል፡፡

‹‹ሚስተር ኦባማ እኛ ኢትዮጵያውያን እንወድወታለን፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻነት እንፈልጋለን›› በማለት የጀመረው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጨቋኝ ስርዓት መደገፍ አቁመው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ አሳስቧል፡፡ ከጋዜጠኛ አበበ ገላው ጋር እንደሚስማሙ የተናገሩት ፕሬዝደንት ኦባማ ስለ ጉዳዩ ከአበበ ጋረ እንደሚያወሩበት በዓለም ሚዲያ ፊት ቃል ገብተውለታል፡፡ በስተመጨረሻ አበበ ለፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል፡፡ የአበበ ገላው ተቃውሞ ሰላማዊ በመሆኑ ፕሬዝዳንት ኦባማ ከመበሳጨትና እንደ አቶ መለስ አንገታቸውን ከመድፋት ይልቅ ‹‹እኔም እወድሃለሁ!›› ብለው ሰላማዊነቱን ገልጸውለታል፡፡

አበበ ገላው የአቶ መለስን ንግግር ካቋረጠ ከሁለት አመት እንዲሁም ፕሬዝዳንት ኦባማን ካቋረጠ ከሁለት ወር በኋላ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት በተመሳሳይ የትግል ስልት የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ማሸማቀቅ፣ ጉዳዩን የሚዲያ መነጋገሪያ ማድረግና ሌሎችም በተመሳሳይ ሰላማዊ ትግል ስልት እንዲሳተፉ ማነቃቃት ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ያህል ከአንድ ወር በፊት ወደ አሜሪካ አቅንተው የነበሩት የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ዋሽንግተን ውስጥ በሚገኝ አንድ የኢትዮጵያ ሪስቶራንት ውስጥ በነበሩበት ወቅት በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ እንዳሰሙባቸው ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ የአሜሪካ መንግስት የአፍሪካን መሪዎች በጋበዘበት ወቅት በአሜሪካ የተገኙ የኢትዮጵያ ባለስልጣናትም ከዳያፖራው ቀላል የማይባል ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡ ለአብነት ያህል የኮሚኒኬሽ ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን በአንድ የገበያ ማዕከል ውስጥ በነበሩበት ወቅት ‹‹ገዳይ ነህ! ተላላኪ!›› የሚሉትን ጨምሮ ስድብና ተቃውሞ ሲደርስባቸው ተመልክተናል፡፡ ምንም እንኳ በአቶ ሬድዋን ላይ ከተቃውሞም ባለፈ ተራ ስድብ ጭምር የተሰነዘረባቸው ቢሆንም ምንም ቢሆንም እንቁላልና ጫማም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን መግለጫ በሚያገለግሉበት በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ አይደለም ለማለት አይቻልም፡፡ ከቪዲዮው ማየት እንደተቻለው ተቃውሞውን ያቀረቡት ኢትዮጵያውያን አቶ ሬድዋን ጋር ከነበራቸው የአካል ቅርርብ አንጻር ከሰላማዊ መንገድ በሆነ መልኩ እርምጃ ሊወስዱ የሚያስችል አጋጣሚ ነበራቸው፡፡ በመሆኑም ተቃዋሚዎቹ ሰላማዊ የሆነውን መንገድ መምረጣቸውን ያሳያል፡፡

ሱቅ ውስጥ ሲዋከቡ አቶ ሬድዋን ሁሴን የመጀመሪያው ፖለቲከኛ አይደሉም፡፡ የሰለጠኑት አገራት ባለስልጣና ያውም አገራቸው ውስጥ ጭምር ተመሳሳይ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል እ.ኤ.አ በ2012 የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አገራቸው ላይ ተመሳሳይ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል፡፡ በአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ደስተኛ ያልሆኑ ዜጎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገቡበት ሱቅ ውስጥ ጩኸታቸውንና ተቃውመዋቸውን አሰምተዋል፡፡ ይህ አውስትራሊያ ውስጥ ተገለልን በሚሉ ህዝቦች የተደረገ ጮኸት አሜሪካንና አውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከአውስትራሊያ ውጭ ያለውን የዓለም ህዝብ አነጋግሯል፡፡ ከዚህ በኋላም በእነዚህ ህዝቦች ላይ ተፈጸመ በተባለው ወንጀል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቅርታ እስከመጠየቅ ደርሰዋል፡፡ አቶ ምንም እንኳ አቶ ሬድዋን ሁሴን በገጠማቸው ተቃውሞ ሲሸማቀቁ ቢታዩም እንዲህ እንዲሸማቀቁ ላደረጋቸው ተግባር ግን ይቅርታ ይጠይቃሉ ብሎ መጠየቅ የዋህነት ይሆናል፡፡

ከአቶ ሬድዋን በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ያረፉበት ሆቴል በመሄድ ተቃውሞ ለማሰማት ጥረት እንዳደረጉና ዶክተር ቴዎድሮስን ደብቀዋል ያሏቸውን ሰዎች ለይ ጫና ሲያደርጉ የሚያሳይ ቪዲዮም ተለቅቋል፡፡ በተመሳሳይ ዳያስፖራው ተቃውሞ እንደሚያቀርብባቸው አውቀዋል የተባሉት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እነ አበበ ገላውና ‹‹Global Alliance for the Rights of Ethiopians›› የተባለ አካል እያደራጁት በነበረ ተቃውሞ ምክንያት አዙሳ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በሌሎች በተያዘላቸው ፕሮግራም መገኘት አለመቻለቸው የዳያስፖራው አዲስ መንገድ ምን ያህል ባለስልጣናቱን እያሸማቀቀ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

የሌሎች የአፍሪካ አገራት በመኪናቸውና በአረፉበት ሆቴል ላይ የየአገራቸውን ሰንደቅ አላማ ሲያውለበልቡ አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በመኪናቸውም ሆነ ባረፉበት ሆቴል ላይ ሰንደቅ አላማ አለማድጋቸውንና ዳያስፖራው በተጠናከረ መንገድ ከሚያደርግባቸው ተቃውሞ ለመደበቅ ያደረጉት መሆኑን የዳያስፖራው ሚዲያዎች ‹‹Ethiopia: Prime Minster Hailemariam in Hiding›› ሲሉ ተቀባብለውታል፡፡ በአቶ ሬድዋን ሁሴን ላይ ተቃውሞ ያደረሱት ኢትዮጵያውያን ከተናገሩት መረዳት እንደሚቻለው ዳያስፖራው ስለ ባለስልጣናቱ መረጃ በመስጠትና በየግሉ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ መደራጀቱን ነው፡፡ ይህ የዳያስፖራ ተቃውሞ በሰላማዊነቱና በተጠናከረ መልኩ ከቀጠለ አሜሪካ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሊያቀኑባት የሚፈሯት አገር እንድትሆን ያደርጋታል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አፈና፣ የባለስልጣኑ ተደራሽነትና በመሳሰሉት ምክንያቶች ይህ የትግል ስልት እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ነው የሚባል ሚና ባይኖረውም የዳያስፖራው የትግል ስልት አገር ቤት መለመድ አለመለመዱ ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡

የዘ-ሐበሻ አንባቢያን የዓመቱ ምርጥ ሰው ይፋ ሆነ

$
0
0

ነጻነት፣ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ሁሉ በነጻ የሰጠን ገጸ በረከት ነው። ነገር ግን በአገራችን ኢትዮጵያ፣ ጥቂቶች፣ የያዙትን መሳሪያና ያላቸዉን ጡንቻ በመጠቀም፣ ነጻነታችንን ሰርቀዉን፣ በባርነትና በፍርሃት እንድንኖር አድርገዉናል። ከፍርሃት የተነሳ ብዙዎቻችን ከአገር ተሰደናል። ብዙዎቻችን በአገራችን እንደ ሁለተኛና ሶስተኝ ዜጎች ተቆጠረን፣ አንገታችንን ደፍተን፣ በሉ የምናብለውን እያልን፣ ሰልፍ ዉጥ ስንባል ሰልፍ እየወጣን፣ ከፍቃዳችን ዉጭ የጥቂቶችን ፍላጎት ብቻ እየፈጸምን የምንኖር አለን። በፍርሃት ተተብትበንና በጥቅም ታስረን።
person of the year
በሌሎች ትግልና መስዋእትነት ነጻነታችንን ማግኘት የምንፈልግ ጥቂቶች አይደለንም። ነጻነትን ፈልገናት፣ ግን ለነጻነት የሚከፈለዉን ዋጋ ለመከፈል ፍቃደኝነት አይታይብንም። ከታሰርንበት ፍርሃት ለመላቀቅ አልቻልንም።
ነገር ግን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ፣ የፍርሃትን ቀንበር በመስበር፣ ለራሳቸው ነጻነትን አዉጀው፣ ለሌሎች መብት የተሰለፉ ብዙ አኩሩ ልጆችን ኢትዮጵያ እያፈራች ነው። እስራትን፣ እንግልትን የማይፈሩ፣ ለአገራቸዉን ለሕዝባቸው መስዋእትነት ለመክፈል የተዘጋጁ፣ ጠመንጃና ጥይት ሳይዙ ጀግንነት ምን ማለት እንደሆነ ያስመሰከሩ ልጆች !

ከነዚህ አኩሪ የኢትዮጵያ ልጆች መካከል፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆነው፣ ታዋቂው ጦማሪ፣ ወጣት አብርሃ ደስታ ይገኝበታል። ወጣት አብርሃ ፣ ከሕወሃት አፍንጫ ሥር ሆኖ ፣ ብዙዎች ያላወቁትንና ያላዩትን፣ በትግራይ ባሉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍና ጭቆና ሲታግልና ሲያጋልጥ የነበረ ወጣት ነው። ብዙ ጊዜ በሕወሃት ካድሬዎች ተደብድቧል። ተሰድቧል። ዛቻና ማስፈራራት ደርሶበታል። ነገር ግን አብርሃ አልተበገረም። አንዳንዶች እንደሚያደርጉት፣ የሕወሃት አባልና ካድሬ ሆኖ በግሉ የተለየ ጥቅም ሊያገኝ ይችል ነበር። በጥቅም ሊደልሉት ሞክረዋል። ነገር ግን ራስ ወዳድ አልሆነም። ከግል ጥቅም ይልቅ የአገርን እና የሕዝብን ጥቅም አስቀደመ። የህዝቡን ብሶት እያነሳ ጮኸ።

አገራችን ኢትዮጵያን ትልቅ ስጋት ላይ ከጣሉት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ በሕወሃት/ኢሕአዴግ የተዘረጋው የዘር ፖለቲካ ነው። አገዛዙ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ … እያለ ዜጎችን በመከፋፈል ፣ አንዱን ከአንዱ ጋር በማጣላት፣ ለብዙ ወገኖች እልቂትና መፍናቀል ምክንያት ሆኗል። አብርሃ ደስታ « ብሄሬ(ዘሬ) ኢትዮጵያዊነት ነው» በሚል ዜጎችን በዘራቸው ሳይሆን በስራቸው ብቻ መመዘን እንዳለባቸው የሰበከ፣ በነአጼ ዮሐንስ እና ራስ አሉላ አባ ነጋ መንፈስ፣ የኢትዮጵያዊነትን ደውል ያቃጨለ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ነው።

ሐሳብ፣ ጽሁፍን መመከት የማይችሉ፣ የጫካ ፖለቲካ የሚያራምዱ ሕወሃቶች ግን ፣ ትችቶችን ተቀብለው ማሻሻያዎችን ከማድረግና የሕዝብ ጥያቄ ከማዳመጥ ይልቅ፣ እንደለመዱት የሚቃወሟቸውን መጨፍለቅ መረጡ። ሐምሌ አንድ ቀን 2006፣ አብርሃ ደሳታን እየደበደቡ አሰሩት። ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ ወሰዱት። በሽብርተኝነት ክስ ከሰሱት። ፖሊስ «መረጃ እስካሰባሰብ» ብሎ የ28 ቀን ቀጠሮ ጠየቀ። «ፍርድ ቤቱ» ግን መረጃ ሳያይ፣ የፖሊስን ጥያቄ ተቀበሎ፣ የአብርሃን የዋስታና መብት ረግጦ፣ ለነሐሴ 29 ቀጠሮ ሰጠ። በቀጠሮ ቀን፣ አሁንም ፖሊስ ማስረጃ ያቀርባል ተብሎ ሲጠብቅ እንደገና ተጨማሪ 28 ቀን መረጃ ለማሰባሰ ጠየቀ። ፍርድ ቤቱ እንደገና ሁለተኛ ቀጠሮ ለመስከረም 22 ሰጠ። አብርሃ ደሳታ፣ ምንም አይነት መረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ይኸው ፣ በማእከላዊ እሥር ቤት እየማቀቀ ይገኛል።

አብርሃ ደስታ ሊታሰር እንደሚችል ያውቅ ነበር። ነገር ግን የዜጎችን የነጻነት ጥያቄ፣ ጥቂቶች አፍነው ማቆየት እንደማይችሉ በመረዳቱና፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች፣ ምሳሌ አግኝተው፣ ይበረታቱ የዘንድ፣ የትግል ቁርጠኝነትን ያሳየው።
የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማየት፣ እንደ አብርሃ ደስታ ያሉ በየክልሉና በየቦታው በብዛት መነሳታቸው አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፣ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በያለንብት የአብርሃ ደስታን ፈለግ ተከትለን፣ ለሕግ የበላይነት ፣ ለሰብአዊ መብት መከበር፣ ለነጻነት፣ ለኢትዮጵያነት እንቆም ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን። ላባረከተው ትልቅ አስተዋጾ፣ ላሳየው ቁርጠኝነት፣ ከአንባቢያኖቻችንም ብዙ ባገኘው ብዙ ድምጽ መሰረት፣ አብርሃ ደስታን የ2007 የዘ-ሐበሻ አንባቢያን የዓመቱ ሰው መሆኑን ስናሳወቅ በታላቅ አክብሮት ነው።

በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያዉያን ሁሉ መልካን እንቁጣጣሽ እየተመኘን ፣ 2007 የለወጥ፣ የሰላም፣ የነጻነት አመት እንዲሆንልን ምኞታችንን እንገልጻለን።

አዲሱን ዓመት በማስመልከት ከነጻነት ታጋዮች ጋር በቂሊንጦ እስር ቤት

$
0
0

ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ‹‹ጥቁር ሳምንት›› (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት ‹አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር› በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል፡፡ ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል፡፡
kiliminto jail

ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ

‹‹ሀገሬ ላይ እርግጠኛ የሆንሁበት ጉዳይ ቢኖር እኔን እንደ ዜጋ የሚጠብቀኝ መንግስት የሌለኝ መሆኑን ነው፡፡ ህገ-መንግስቱ አልጠበቀኝም፡፡ ህገ-መንግስቱ ጥሩ ቢሆንም አልተከበረም፡፡ ይህ ሁሌም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ነው፡፡

ታስሬ ባለሁባቸው ቀናት ሁሉ የታዘብኩት ነገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት በሁሉም ዘርፍ መኖሩን ነው፡፡ አቅም ያላቸው ዜጎች ከስርዓቱ በመገፋታቸው ክፍተቱ እንዲሰፋ ሆኗል፡፡ በጣም ነው የሚያሳዝነው፤ የሚሰሩ ሰዎች በተገቢው ቦታ ላይ አለመኖራቸውን አይቻለሁ፡፡ የሚያሰራ ስርዓት ስለሌለ ብዙዎች ህሊናቸውን መርጠው በመራቃቸው ይመስለኛል አቅም ያላቸው ሰዎች የራቁት፡፡ ይህ ለሀገር አሳሳቢ ነው፡፡

የሚቆጨኝ ነገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ተቋማት በእንግሊዝኛ የተሰሩ የጥናት ስራዎችን በመምረጥ አሰባስበን በአማርኛ ቋንቋ በጆርናል መልክ ለመስራት አስበን ያን ሳንሰራ በመታሰራችን ነው፡፡

አሁን በተለያዩ ሁኔታዎችና ጉዳዮች ላይ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያው በኩል የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ እኛን አስረው ሌላው ዝም እንዲል ፈልገው ኖሮ ከሆነ እንዳልተሳካላቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ለሀገር የሚያስቡ ብዙ ወጣቶች በየጊዜው ማበባቸው አይቀሬ ነው፡፡ እየታየ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ምንግዜም የሚበረቱ ሰዎች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አምናለሁ፡፡››

አይመዲን ጀበል፣ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል

ልትጠይቁን ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ በተለይ ወጣቶቹ እያደረጋችሁ ያለው እንቅስቃሴ እንሰማለን፡፡ በጣም ደስ ይላል፡፡ እስካሁን በአገር ጉዳይ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የቆዩት የ1960ው ትውልድ አባላት ናቸው፡፡ አሁን ወጣቶች እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡ ይህ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ነገር ግን በቂ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስለሆነም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡

ያሲን ኑሩ፣ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል

‹‹እስር፣ እንግልትና ሌሎችም በደሎች የአምባገነኖች እርምጃ መለያ ባህሪያት ናቸው፡፡ አምባገነኖችን አንድ የሚያደርጓቸው እነዚህ ባህሪያት ናቸው፡፡ አምባገነኖች ከታሪክ አይማሩም፡፡ የዛሬ 20 አመትም ሆነ 50 አመት ወደ ስልጣን የሚወጣ አምባገነን ይህን ነው የሚደግመው፡፡

መንግስት በኃይማኖቶች መካከል ልዩነት መፍጠር ይፈልጋል፡፡ እናንተ ክርስቲያኖች የኃይማኖት ድንበር ጥሳችሁ ከእኛ ከሙስሊም ወንድሞቻችሁ ጋር መቆማችሁን እናደንቃለን፡፡ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ መብት በመቆም የሚያደርገውን ጥረት እናደንቃለን፡፡ እኛን ለመጠየቅ እስር ቤት ድረስ ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ ትግሉ ከዚህም በላይ መስዋዕትነት ያስከፍላልና በርቱ፡፡››

ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ

‹‹ማዕከላዊ የገባነውን የመጀመሪያ ሰሞን ለእኛ አስቸጋሪ ነበር፡፡ በማንኛውም ጊዜ እስር ሊኖር ይችላል በሚል ማዕከላዊ የሚደረጉትን ነገሮች ለማሳወቅ እንጥራለን፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የጻፍናቸው ጽሁፎች ለዚህ ያግዛሉ ብየ አምናለሁ፡፡ በመሆኑም በእኛ ላይ ከደረሱብን ነገሮች ሌሎች ይማሩባቸዋለን ብለን እናምናለን፡፡ ይህ ሲሆን የሚታሰሩ ሰዎች የሚደርስበት ችግር አዲስ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ ወደ ቂሊንጦ ከመጣን በኋላ የተሻለ ነገር ቢኖርም አሁንም ድረስ መጽሃፍና ጋዜጣ አይባልንም፡፡

በጥቁሩ ሳምንት ዘመቻ ያደረጋችሁትን ነገር ሰምተናል፡፡ በጣም ደስ የሚል ስራ ሰርታችኋል፡፡ መጥታችሁ ስለጠየቃችሁን ደስ ብሎናል፡፡ እስሩ ቀጣይነት እንደሚኖረው ቢታወቅም፣ በየትኛውም ሁኔታ በርታትችሁ እንድትቀጥሉ እፈልጋለሁ፡፡

በየቀኑ ጋዜጠኞች በሚደርስባቸው ጫና አገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን እንሰማለን፡፡ ይህ በጣም ያሳዝናል፡፡››

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ

‹‹ከመታሰሬ በፊት ማዕከላዊ ውስጥ ስለሚፈጸሙ በደሎች በተለያዩ ሪፖርቶች ላይ ማንበብ ችዬ ነበር፡፡ ማዕከላዊ ከገባሁ በኋላ ያየሁት ግን ሰፊና ከጠበኩት በላይ ነው፡፡ በተለይ ትጥቅ ትግልን የመረጡ ተቃዋሚዎች አባላት ናቸው የተባሉ አሊያም በሚዲያው የማይታወቁና ጠያቂ የሌላቸው አካላት ላይ የሚደርሰው በደል ዘግናኝ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ተመሳሳይ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡ ድሮ ማዕከላዊ ውስጥ ይደረጉ እንደነበር ሰምቼ ነገር ግን ይሆናሉ ብዬ የማላምናቸውን ነገሮች ሁሉ እንደሚፈጸሙ ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡

የማዕከላዊ መርማሪዎች አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ ምርመራ ማድረግ ሳይሆን ጥፋተኛ መሆናችንን እንድናምንላቸው ነው ሁሌም ተመሳሳይ ጥያቄ የሚያነሱልን፡፡ አንዳንዶቹ ጥያቄዎች በጣም የሚገርሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል በምርመራ ወቅት ‹‹እከሌ ጋር ሻይ እየጠጣን›› ብለን የተናገርነውን ነገር እነሱ ‹‹ስብሰባ አድርገን›› ብለው ይጽፉታል፡፡ ሻይ መጠጣት በእነሱ ስብሰባ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ አንድ ጋዜጠኛ የሚሰራው ህጋዊ ስራ ህገወጥ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለአብነት ያህል ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25/2004 ዓ.ም ባደረገው ሰልፍ ተገኝቼ ፎቶ አንስቼ ነበር፡፡ ይህ ፎቶ ግራፍ በክስ ቀርቦብኛል፡፡ አስቡት በዚህ ሰልፍ ኢቲቪና ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎችም ፎቶ አንስተዋል፣ ቪዲዮ ቀርጸዋል፡፡ መርማሪዎቹን ‹‹ይህ ስራዬ ነው፡፡ አያስወነጅለኝም›› ብትል አያምኑልህም፡፡ ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስም ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ ተገኝተሃል የሚል ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡

በተመሳሳይ ዩጋንዳ እያለሁ ባቋቋምኩት ጋዜጣ ላይ ሙሃመድ ሰልማን ‹‹ፒያሳ ሙሃመድ ጋ ጠብቂኝ›› በሚል ከጻፈው መጽሃፍ ላይ ያሉ ጽሁፎችን ጋዜጣው ላይ አውጥቻቸው ነበር፡፡ ሆኖም ይህም በክስ ቀርቦብኛል፡፡ ‹‹መጽሃፍ ላይ ነው የወሰድኩት፡፡ መጽሃፉ ህጋዊ ሆኖ አገር ውስጥ ይሸጣል›› ብትል ማንም አይሰማህም፡፡ ፖሊስ ህዝብን ለመጠበቅ የቆመ አካል ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡ ነገር ግን ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ ገና ሳይፈረድብን ‹‹እናንተስ ለምን ሽብር ትፈጥራላችሁ?›› ያሉን ፖሊሶች አጋጥመውናል፡፡ ቀድመው ፈረዱብን ማለት ነው፡፡

በምርመራ ወቅት በጣም የሚያስገርሙ ነገሮች ተነስተዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጆን ኬሪ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ወቅት መርማሪዎቹ የሚገርም ጥያቄ አንስተውልን ነበር፡፡ ‹‹ጆን ኬሪ ጓደኛችሁ ነው?›› ብለው ጠይቀውናል፡፡ በጣም የሚገርም ነው፡፡ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን የእኛ ጓደኛ እንደሆነ አድርገው አቅርበውታል፡፡ ደግሞም ይህንንም ህገወጥ አድርገው ነው የሚያቀርቡት፡፡ በሌላ በኩል አንዴ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር፣ ሌላ ጊዜ ከግንቦት ሰባት ሌላ ጊዜ ደግሞ ከኦነግ ጋር ግንኙነት እንዳለን ይገልጹልናል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች በምንም መልኩ የሚገናኙ አይደሉም፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ጋዜጠኛ የሚከሰሰው በመጻፉ አይደለም፡፡ በጋዜጠኝነት ብትከሰስ አንድ ነገር ነው፡፡ እነሱ ግን የሚያነሱብህ ክስ ሌላ ነው፡፡

ፌስቡክና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ የነበርን ሰዎች ያለመረጃ ስንቀመጥ ከባድ ነው፡፡ በተለይ በመጀመሪያዎቹ 75 ቀናት ነገሮች አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ ከዛ በኋላ ግን ቢያንስ ኢቲቪን መመልከት ችለናል፡፡ ኢቲቪ በሚያቀርባቸው ጉዳዮች ላይ የየራሳችን ትርጉም እየሰጠን አገራችን ውስጥ በጥቂቱም ቢሆን ምን እየተካሄደ እንዳለ መረዳት እንችላለን፡፡ ወደ ቂሊንጦ ከመጣን በኋላ ነገሮች የተሻሉ ናቸው፡፡ ከጠያቂዎቻችን መረጃዎችን ማግኘት እንችላለን፡፡››

ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

አንድነት ኃይል ነው፤ መበታተን ጥቃት ነው (ዶ/ር. አክሎግ ቢራራ)

$
0
0

 አስተያየት

 ዶ/ር. አክሎግ ቢራራ 

unityበመሳሪያ ኃይልና በውጭ መንግሥታት ድጋፍ የስልጣን እርካብ የተቆናነጠጠው፤ በጠባብ ብሄርተኛው በህወሓት ፍጹም የበላይነት የሚመራው፤ የኢህአዴግ መንግሥት ከተመሰረተበት ጀምሮ የኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ ደህንነትና ነጻነት፤ የዘጠና አራት ሚሊዮን ሕዝቧ ሉአላዊዊነት፤ እውነተኛ እኩልነት፤ ማህበራዊ ጥቅም፤ መሰረታዊ ትብብር፤ ነጻነትና ዲሞክራሳዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ተናግተዋል፤ ተገፈዋል። በማንኛውም የዘመናዊነት መስፈርት ቢፈረጅ፤ ኢትዮጵያን ከባሰ አደጋ፤ ሕዝቧን ከከፋ ድህነት እና የእርስ በርስ ግጭት፤ ወጣቱን ትውልድ ለሁላችንም ከሚያሳፍር ስደተኛነትና ውርደት ሊያድነው የሚችለው ተተኪ የአገዛዝ ስርአት (አማራጭ) በሕግ የበላይነት፤ በእውነተኛ የኢትዮጵይያውያን እኩልነት፤ በሕዝብ ስልጣን የተመሰረተ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ብቻ ነው። ሰፊ ለም መሬት፤ ዝናብ፤ ወንዝ፤ ተስማሚ አየር፤ ከመሬት በታች ገና የማይታወቅ ሃብት ያላት አገር ለሁሉም አስተናጋጅ ለመሆን እንደምትችል አልጠራጠርም። ፍትህ-ርትእ ከሌለ ይኼን የማይገኝ ሃብት የሚጠቀሙበት የውጭ ኢንቬስተሮችና አጋር የሆኑ የውስጥ ሃብታሞች ሆነው ይቆያሉ። ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች የሚስማሙበት አንድ አበይት ጉዳይ አለ። ይኼውም ዲሞክራሳዊ አማራጭ አስፈላጊ ነው የሚል። ከጽንሰ ሃሳብ ባሻገር ግን ሁለቱም ወገኖች ዲሞክራሳዊ አሰራርን በተግባር አላሳዩም፤ ለማሳየትም የተዘጋጁ አይመስልም። አንዱ በሌላው እያመኻኘ ሃያ ሶስት ዓመታት አልፈዋል። የሚቀጥለው ምርጫ ዘጠኝ ወሮች ቀርተውታል። ሑኔታው ከቀጠለ የሚቀጥለው ምርጫ ከአሁኑ ተወስኗል ለማለት እንችላለን፤ የገዢው ፓርቲ የበላይነት ብቻ ይሆናል። መቶ በመቶ አሸነፍኩ ቢል አንገረም። የሚወዳደረው ከራሱ ጋር ይሆናል።

ገዢው ፓርቲ መከፋፈልን ወደ ሳይንስ ለውጦታል። ተቃዋሚው ይኼን ሳይንስ አልቀበም በማለት ፋንታ እርስ በርሱ መናከሱን ቀጥሎበታል። በተደጋጋሚ የሚታየው የራእይ፤ የግብ፤ የአደረጃጀትና የአመራር ደሃነት በቀላሉ አለመፈታቱ ተቃዋሚውን ፍሬ ቢስ አድርጎታል። በአገር ውስጥ ብቻ ያለው ሳይሆን በውጭም ያለው፤ በነጻነት ለመወያየትና አብሮ ለመስራት ገዢው ፓርቲ ሊቆጣጠረው የማይችለው። ቢቀበለውም ባይቀበለውም ተቃዋሚው የገዢው ፓርቲ አገልጋይ ሆኗል ለማለት ያስችላል። የምናውቀው የሃገሪቱን አስተዳደር በቋንቋ የቀየሰው አምባገነን መንግሥት ቆይታውንና የኢኮኖሚ ጥቅሙን ለማጠናከር ህዝብን እርስ በርሱ እንዲጋጭ፤ ተቃዋሚዎች እርስ በርሳቸው እንዲናከሱ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይኼ የመከፋፈልና ስልጣንና ሃብትን የማስተማመኛ ስልት ከታወቀ፤ በአገር ቤትም ሆነ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በሰከነ መንገድ አስበው፤ ተፈላልገው፤ ተከባብረው፤ “ተናበው”፤ በዋናው ዓላማ ላይ ተስማምተው ለመስራት የገዢው ፓርቲ ፈቃድ አያስፈልጋቸውም ነበር። ችግሩ ጥበባዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ የማደራጀትና የመምራት ድክመትና ክፍተት መኖሩ ነው። ስርዓቱ  የራሱን መቆያ ያጠናከረውና የሚያጠናክረው የሃገሪቱን ባጀት፤ የተፈጥሮ ሃብትና ሌላ ጥሪት ለጥቂቶች አገልጋይ የሆነ ተከታታይ የብልጭልጭ እድገት በማሳየት፤ “እኔ እስካለሁ የእድገቱ ተጠቃሚዎች ትሆናላችሁ፤ እኔ ከሌለሁ፤ ትበላላችሁ” በሚል ዘዴ ነው።

ስርዓቱ የሚሰራውን ያውቃል ማለት ነው። የሚሰራውን የማያውቀው ተቃዋሚው ሆኗል። የተበታተነው ተቃዋሚ የሚለው በኢትዮጵያ እድገት የለም አይደለም። ፍትህ የለም። የአብዛኛው ሕዝብ ኑሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ታች በመሄድ ላይ ይገኛል፤ የኑሮ ውድነት የተራውን ዜጋ የመግዛት አቅም አስጊ በሆነ ደረጃ ቀንሶበታል። የወጣቱ ትውልድ እድል ተምሮ መሰደድ ሆኗል። በዘመነ ኢህአዴግ የሃገሪቱ ለም መሬትና ወንዝ ለውጭ ኢንቬስተሮች በእርካሽ ዋጋ ሲሰጥ ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ አላሙዲ ብቻ የሚያመርተው በዓመት አንድ ሚሊዮን ቶን ሩዝ ለሳውዲ ገበያ ይቀርባል። እንደ ካሩቱሪ ያሉ የህንድ ኢኒቨስተሮችም የጋምቤላን ለም መሬት ተረክበው ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ያቀርባሉ። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እየተነገደባት ነው። ሳውዲዎች እየተመገቡ  ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ይራባሉ፤ አገሪቱ በዓመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለምግብ ግዢ ታወጣለች። ህይወቱ የተናጋው አብዛኛው ሕዝብ መብቱ ሰለታፈነ፤ ድምፁን ለማሰማት ስላልቻለ መከራውን ተቀብሎ ይኖራል ወዘተ የሚሉ ናቸው።

ስለሆነም፤ ተቃዋሚው የጠራ አማራጭ ለማቅረብ ነባራዊው ሁኔታ ይፈቅድለታል። የሚጎድለው የዓላማ አንድነትና የአመራር ብልሃት ነው። እርግጥ ነው፤ የገዢው ፓርቲ አቅም ከፍተኛ ነው። መንግሥትን ከተቆጣጠረ ባጀትንም እንደፈለገው ፈሰስ ለማድረግ ይችላል።

 

ስንቅ ብቻውን አቅም አይሆንም

የተቃዋሚው ክፍል አቅም ጠንካራ ሊሆን የሚችለው ከሕዝብ ከሚያገኘው ድጋፍ፤ ከመተባበሩ፤ ያለውን የቁሳቁስ አቅም በጋራ ከመጠቀሙ፤ በብልሃት ከመስራቱ፤ በአንድ ድምፅ ከመነሳቱ፤ ለዓላማው ጠንክሮ፤ በውስጥ አመራር ሳይበከል መስዋት ለመክፈል ፈቃደኛ ከመሆኑ ላይ ነው። በውጭ ያለው አገር ወዳድ፤ ዲሞክራትና የሰብአዊ መብቶች ጠበቃ ኃይል ያልተቆጠበ ድጋፍ ለማድረግ አቅምና ፍላጎት አለው። “ተባበሩ ወይንም ተሰባበሩ” እያለ ሲመክር ቆይቷል። ገንዘቡን፤ እውቀቱን፤ ድጋፉን ችሯል። ወደፊትም ይችራል የሚል እምነት አለኝ። ሆኖም፤ ስንቅ አቀባይነት ያለ ድርጅትና አመራር ብቃት ኢትዮጵያን አይለውጥም። ለዚህ ነው፤ ደጋፊዎች ተስፋ እየቆረጡ “ተቃዋሚ ነኝ” ማለቱን ቀልድ አታድርጉት፤ “ጩኸቱን ወደ ተግባር ለውጡት፤ በፍርሃትና በመጠላለፍ ዓለም መኖራችሁን አቁሙ፤ ነጻነት፤ ፍትህና ዲሞክራሳዊ ስርአት ያለ መስዋእትነት ስኬታማ ሊሆኑ አይችሉም። የእርስ በርስ ጦርነቱን አቁሙ። በውጭ ኃይሎች ማምለኩን አቁሙ። ድርጅት አፍርሳችሁ በድርጂት መተካቱን ተውት። አትጠላለፉ። መገናኛ ብዙሃኖችን ለእርስ በርስ ጦርነት አትጠቀሙ፤ አትወነጃጀሉ፡  የራሳችሁን የውስጥ አመራር ሳታጠናክሩ ሁሉን ነገር በገዢው ፓርቲና በሌላው ላይ አታመኻኙ፤ ተቃውሞ ብቻውን የማህበራዊ ጥቅም አይኖረውም” ወዘተ፤ ወዘተ የሚሉት።

በጀ፤ ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው?

ይኼ አጭር የፖለቲካ ኢኮኖሚ ስእል በተደጋጋሚ ያሳየው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን ትተው ለሃገሪቱ ዘላቂነት እና ለመላው ሕዝቧ ደህንነት ሲባል መተባበር፤ ቢቻል መዋሃድ አለባቸው የሚለውን ባለፉት አስር አመታት በተደጋጋሚ ሁሉን በሚመለከት ያቀርብኩትን ምክርና ጥሪ ነው። ምክር እንጅ ትእዛዝ አይደለም። ማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን ከውጭ ሆኖ ትእዛዝ ለመስጠት አይችልም። ትግሉ በአገር ቤት ካልተጠናከረ፤ አገር አቀፍና አሳታፊ ካልሆነ የፈለገው ጥረት ቢደረግ ዲሞክራሳዊ መሰረት ለመጣል አይቻልም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው አብሮና ተሳስቦ መኖርን ነው። ቂም በቀልነትን አይፈልግም። አንዱን አምባገነን በሌላ አምባገነን መተካት አይደፈልግም። ይኼማ ከሆነ ኢህአዴግ ምን አደረገ፤ የተካው ደርግ ምን አደረገ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴስ ምን አደረጉ? የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱ የስልጣኑ፤ የመንግሥቱ፤ የመሪዎቹ ባለቤት ለመሆን ይፈልጋል። ለዚህ ብዙ መስ ዋት ከፍሏል። ስለሆነም፤ ሁሉም ተቃዋሚ ኃይሎች በዓላማ እንድነት በመንቀሳቀስ ታሪክ የሚጠይቀውን ሃላፊነት መወጣት አለባቸው። ሕዝብን ካጎለመሱ ተመጣጣኝ አቅም ይኖራቸዋል። ወሳኙ ሕዝብ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫ ዘጠና ሰባት ለቅንጅትና ለህብረት የሰጠው ያልተቆጠበ ድጋፍና የከፈለው መስዋእት እንዲያንሰራራ ከተፈለገ በአገር ቤትና ከአገር ውጭ የሚገኙ የፖሌቲካና የማህበረሰብ ድርጅቶች፤ የሞያ ስብስቦች፤ ግለሰሶብችና ሌሎች ከቡድን፤ ከፓርቲ፤ ከግል ዝናና ጥቅም በላይ ለኢትዮጵያ ዘላቂነትና ለመላው ስብጥር ሕዝቧ ደህንነት አብረው መነሳትና አምባገነኑን መንግሥት ማንበርከክ፤ ቢያንስ ለድርድር እንዲስማማ ማድረግ ይኖርብናል። ከሁሉም በላይ የተቀነባበረ የሕዝብ አመፅ አገር አቀፍና ዘላቂነት ባለው ደረጃ ከተካሄደ ገዢው ፓርቲ ለመደራደር ይገደዳል።

ይኼን ትንተና ለማዘጋጀት የተገደድኩበት ዋና ምክንያት የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የለመደውን መንገድ እየተጠቀመ፤ ከመጭው ምርጫ በፊት በሰላማዊ መንገድና በሁለገብ ትግል የሚንቀሳቀሱና ተባብረው ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑትን ተቃዋሚዎች ሁሉ ተባብረው እንዳይሰሩ በማሰብ በመከፋፈል ላይ ይገኛል። ይኼ አዲስ ነገር አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ ጥሎበት የነበረው የመኢአድና የአንድነት ውህደት ሂደት አሳዛኝና ተስፋ በሚያስቆርጥ መልክ ስኬታማ አለመሆኑ ለገዢው ፓርቲ ቆይታ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርጓል። ይኼ ችግር የገዢው ፓርቲ ሳይሆን የተቃዋሚው ነው። በቅርቡ የተከሰተም ሌላ የተቃዋሚውን ክፍል ከጥያቄ ውስጥ ያስገባ አከራካሪ ጉዳይ አለ።

እንደማንኛውም አገር ወዳድ በ August 28, 2014 ሶስት በውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች በዜናና በድህረገጾች ያሰራጩትን፤ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ትኩረት የሰጡትን የጋራ መግለጫ በሰከነ መንገድ ተመልክቻለሁ።  መግለጫው እንዲህ ይላል። “ኢትዮጵዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋእትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ መድረሳችንን፤ የወያኔን ቡድን በሁለገብ ትግል እየተፋለምን ያለን ድርጅቶች ተጣምሮና አንድ ሆኖ መታገል እንዳለብን ካመንን ዓመታት አስቆጥረናል። ስለሆነም፤ ወደፊት ለመዋሃድ የተሰማማነው ድርጅቶች፤

  1. የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
  2. የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
  3. የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች ንቅናቄ ነን” የሚል መግለጫ ወጥቶ ሲያነጋግር ቆይቷል።

ከአንድ ሳምንት በኋላ በ September 6, 2014, በኮሎኔል አለበል የሚመራው የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች ንቅናቄ ማስተባበያ አውጥቶ “ከግንቦት 7 ጋር አልተዋሃድኩም” ብሏል።

በእኔ ግምትና እምነት ምንም እንኳን የጋራ ስምምነቱ በምን አጀንዳ ላይ እንደተቀረጸ ባላውቅም፤ አሰራሩ በግልፅነት፤ በሃላፊነት፤ በዲሞክራሳዊነት፤ በዘላቂነትና ሌሎችን በሚያበረታታ መንገድ የውህደቱ ድርድር እንዲካሄድ ያለኝን ተስፋና ምኞት ለማቅረብ እፈልጋለሁ። በተመሳሳይ፤ በአንድነትና በመኢአድም በውስጥና በመካከላቸው መካከል የተከሰቱ ልዩነቶችም በውይይት፤ በግልፅነት፤ በሃቀኝነት፤ በብልሃት፤ በዲሞክራሳዊ ስልት እንዲፈቱ የታሪክ አደራ እሰነዝራለሁ። ዛሬ ለፍትህ- ርትእ፤ ለህግ የበላይነት፤ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፤ አገርን ከአደጋ ለመከካለክ፤ ለእውነተኛ እኩልነትና ለዲሞክራሲ የሚታገሉ ኃይሎች “ኢህአፓ፤ መኤሶን፤ እሴፓ፤ ፓሪስ አንድ፤ ፓሪስ ሁለት፤ ኢዲዩ፤ እዴፓ፤ ቅንጅት፤ ህብረት፤ ታንድ፤ ኦነግ፤ መድረክ፤ አሬና፤ ግንቦት 7፤ አርበኞች፤ የአማራ ዲሞክራሳዊ ኃይሎች፤ አንድነት፤ ሰማያዊ፤ መኢአድ፤ አንድ ሁለትና ሶስት ወዘተ የሚሉበትና እርስ በርስ የሚወቃቀሱበት ዘመን አልፏል ለማለት የሚያስችሉ ብዙ ክስተቶች አሉ። የኼን ስል፤ ሁላችሁም ተዋሃዱ ማለቴ አይደለም፤ ብዙ ተሞክሮ አለተቻለም። ዲሞክራሳዊ ለውጥ ከተፈለገ ለመተባበርና ለመደጋገፍ ይቻላል። ይኼም ፈቃደኛነት ካለ ብቻ ነው። “አገር ትሸጥ ሲባል ስንት ታወጣለች” የሚል አዲስ ባህልና አዲስ ባለሃብት መደብ መፈጠሩን እያየን እርስ በርሳችን የምንናከስ ከሆነ ከትግሉ ዓለም መውጣት አለብን። አዲሱ ትውልድ ለራሱ ህይወት ሲል ይታገልበት ለማለት መድፈር አለብን። በምትካችን አዲስ ትውልድና አዲስ ዓመራር እየታገለ አመራሩን እንዲይዝ ቦታውን እንልቀቅለት። መሰናክል አንሁን። መቀበል ያለብን፤ እኛ ራሳችን ለመምከር ወይንም ለመመከር ስለማንፈልግ ሌሎች፤ በተለይ ፈረንጆች ለእኛ ተናጋሪ ሆነዋል። ለምሳሌ፤ ለኢትዮጵያ የሚለግሱ መንግሥታትና ድርጅቶች ደጋግመው የሚነግሩን በአንድ ላይ፤ በአንድ ድምፅ ለመናገርና አግባብ ያለው አማራጭ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማቅረብ እስካልቻላችሁ ድረስ ማንም አያዳምጣችሁም ነው። ሃቁ፤ ያለውን መንግሥት እንደግፋለን ነው የሚሉት። የተበታተነ ተቃዋሚ ውጤቱ ይኼው ነው። አንፈረድባቸው። የሚያኮራ ታሪክ እያለን የራሳችን ህብረተሰብ ለመታገድ ካልቻልን ሌሎች ያዙብናል። እያዘዙብን ነው። ከዚህ የበለጠ የጠነከረ ምክር መጠበቅ ራስን ማታለል ነው።

ለማጠቃለ፤ በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች እንዲያስቡበት የምመኘውና አደራ የምለው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት እድሜውን ለማራዘም ለሚያደርገው ያልተቆጠበ ሴራና ሰለባ ምርኮኛ መሆን የለባችሁም/የለብነም የሚል ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገውና የሚመኘው የእርስ በርስ መጠላለፍና ለስልጣን መሻማትን አይደለም፤ አብሮና ተባብሮ አምባገነኑን ስርዓት በዲሞክራሳዊ ስርዓት መተካትና ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው የእድገት በርና መሰረት እንዲከፈትለት ነው። ስለሆነም፤ የተቃዋሚዎች ሙሉ እምነት በኢትዮጵያ ሕዝብ አቅም ላይ ይሁን አላለሁ።

9/10/2014

 

በሃገራችን እውነት እና የሚሰራ ሰው አይወደድም፤ መፈራረጅ የትግል ስልት አይደለም

$
0
0

ናትናኤል መኮንን ( NATI MAN ) ስዊዘርላንድ

ኢትዮጵያውያን በያዝነው አምባገነንነትን የማውደም ትግል ውስጥ እያንዳንዱ ዜጋ የራሱ ድርሻ እንዳለው የማይካድ ሃቅ ነው ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በእኛ ሰዎች ዘንድ አንድ ችግር አለ ፡ አንድ ሰው በራሱ አስተሳሰብ የሚሄድ ከሆነ እውነታን ይዞ አንገቱን ሰብሮ የሚታገል ከሆነ አንዱ ለአንዱ ለምን አላጎበደደም እንደኛ ለምን አላሰበም ለምን አስተሳሰቡን ጻፈ በሚል በከፍተኛ ፍጥነት ጥላቻ ይንጸባረቅበታል ይፈረጃል። እያንዳንዳችን ሰዎች የራሳችን አስተሳሰቦች እና አመለካከቶች አሉን፡፤ አስተሳሰቦቻችንን እና አመለካከቶቻችንን ደሞ የማንጸባረቅ መብት አለን፡፤ የግዴታ ለማንም ተገዢ አንሆንም አሁን እየታገልን ያለነው በ እምቢተኝነት ጭቆናን ነው። ሌላ ጭቆና በነጻው የማህበራዊ ድህረገጽ ላይ እንዲግውጥመን አንፈልግም፡፤ ሌላው ደም ሰዎች ከኛ በመረጃም ይሁን በአጻጻፍ ዘይቤ በልጠውን ሲገኙ አይናችን ደም የሚለብስበት ምክንያት አይገባኝም ። መከባበር ሲገባን የሰውን አስተሳሰብ ማክበር እና መተራረም ሲገባን ብድግ እያልን ሰውም መጠራጠር መፈረጅ መሳደብ መዝለፍ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት አሊያም የትግል ስልት አይደለም።
Tensaye
በየድህረገጹ የሚጽፉ ሰዎችን ቃላት እየሰነጠቁ ነገር እየፈለፈሉ ለማሳጣት መሞከር እና መታገል ለየቅል የሆነ እና የማይገናኝ ነገር ሆኖ ሳለ የፖለቲካ እውቀቱ እና ብስለቱ የሚያጥራቸው ጥቂት ሰዎች የማይታወቅ ጅራፋቸውን ታግለው በሚያታግሉ ሰዎች ላይ ሊሰነዝሩ ሲንደፋደፉ ይታያሉ። ሰዎች ሁሉ እንደ ተቃዋሚ ድርጅት አሊያም እንደ ተቃውሚ ግለሰብ ሆነን ስንሽከረከር እንደና ካላሰበ እኛን ካልተከተለ የኛን ካለጠፈ እሱ ተቀብሮ እኛ ካልታየን የሚሉ ከሆነ ይህ ትግል ለሃገር እና ለህዝብ ሳሆን ለስም እና ለዝና የሚደረግ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። ሰዎች የራሳቸውን መረጃም ይሁን ጽሁፍ ይዘው ሲመጡ ልናከብርላቸው ሲገባ ባንቀበለውን ባንስማማበትም መፈረጅ እና ማሳጣት አሊያም ትግሉን ሽፋን በማድረግ መዝለፍ አያዛልቅም። በአሁን ሰአት የሚደረጉ ዝባዝብንኪ የዘለፋ እና የትችት ተግባራት የትም የማያደርሱ እና ጭራሽ ትግሉን የሚገሉ መሆኑን ልናውቅ ይገባል። በተጨማሪም ሰዎች በጃቸው ያለውን የፖለቲካ መረጃ ደራርበው የሚያወጡት ከሆነ ትግሉን እንደሚገል እና እንደሚያጠፋ በግልጽ ለመመስከር የምንገደድበት ወቅት ላይ መድረሳችን በማይረቡ ሰዎች ትግሉን የማኮላሸት ሂደትን መጋበዝ አንዱ ስህተት ሆኖ ይሰማኛል። ፖለቲካ ማለት ጥንቃቄ የሚፈልግ እና የትግል ስልትን የማያዳከም ታላቅ ድል የሚሻ ጉዳይ ነው።

ይህንን ከግንዛቤ የማያስገቡ ሰዎች የግለሰቦችን ዱካ እና አረፍተ ነገር እየተከተሉ በቃላት ስንጠራ ላይ ከተሰማሩ ትግሉን ማን ይታገል ? ዘለፋ ላይ ካተኮርን ትግሉን ማን ይታገል ? በቂ ማስረጃ እና መረጃ ሳንይዝ እከሌ ላይ እንዲህ ይሁን እከሌ እንዲህ ነው ምናምን እየተባለ በስም ማጥፋት ላይ የምንሰማራ ከሆነ ህዝቡ በነቃ ጊዜ መግቢያ ቀዳዳ እንድሚጠፋን ካሁኑ ማሰብ ያስፈልጋል። ተቃዋሚ ነን የሚሉ ሁሉ በአጋር ተቃዋሚዎች ላይ የከፈቱት ዘመቻ እስካሁን ምን ያህሉ እንደተሳካ በተቃዋሚ ግለሰቦች ላይ የከፈቱት ስም ማጥፋት ምን ያህሉ እውነት እንደሆነ በቂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እውነተኛ ሰው የለም። ያሌለ ነገር ከመዘባረቅ እና የግለሰብ ማንነትን በሃሰት ከመበከል እንዲሁም ባልበሰለ የፖለቲካ ግምት ሰዎችን ከማሳጣት ውጪ ለትግሉ ምንም አልፈየደም። ምንም እድገት አላመጣም።

ትግሉን እንዴን ማሳካት እንችላለን? አሁን ካለበት እንዴት ልናሳድገው እንችላለን ? ምን መርዳት አለብን ? ምን መተባበር አለብን ወዘተ የሚሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ይዘን ህዝብን ማነቃቃት ህዝብን ማስተማር ለለውጥ ማነሳሳት ሲገባን የግለሰቦችን ዱካ እየተከተልን ስም ማጥፋት እና መነካከስ መፈራረጅ በህዝቡ ዘንድ ያለውን ተቃዋሚዎች አይረቡም ተነካካሾች ናቸው እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ እኛን እንዴት ይመሩናል የሚለውን አስተሳሰብ እያሰፋ እንጂ እያጠበብ አይሄድም። ስለዚህ የግለሰቦችን ስም ማጥፋት እና መዘርጠጥ የማይሆን ስም መስጠት ታፔላ መለጠፍ ለትግሉ ምንም አይፈይድም።የሚሰደቡት ሰዎች በጥንካሬ በርትተው እያየናቸው እንጂ እንድ ተስአድቢዎች ሲከስሙ አላየንም ፡፤ የሚሰደቡ ሰዎች መረጃዎቻቸው እውነት ሆነው ሲገኙ እንጂ ሲያፍሩ አላየንም። ስለዚህ ይህ መፈራረጅ እና መዘላለፍ ቆሞ በጋራ ለትግሉ አስታውጾ ማበርከት አለብን ። ሊታሰብበት የሚገባ አቢይ ጉዳይ ነው።

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>