Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ኢትዮጵያዊነት ማለት

$
0
0

አንዱዓለም ተፈራ (እስከመቼ) 

“ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው።”

አብዛኛዎቻችን በየጊዜው የምናነሳው ጉዳይ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ ሀቅና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ወይንም አይደለሁም የሚለውን ጥያቄ አይደለም። በየቦታው፣ በተገኘው አጋጣሚ፣ በየዕለቱ በሕዝቡ ላይ የሚደረገውን በደል እናውጠነጥናለን። ኢትዮጵያዊያን ናቸው ወይንም አይደሉም የሚለው ከጥያቄያችን መካከል አይደለም። መቼም አርባ ዓመት ሙሉ፤ በአረመኔው መንግሥቱ ኃይለማርያምና በወገንተኛው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍና በደል ገና ብዙ ፀሐፊዎች ብዙ ይውሉበታል፣ ሊቃውንት ይቀኙበታል፣ አንጎርጓሪዎች ይደረድሩበታል፣ ሰዓሊዎች ያቀልሙታል፣ ገጣሚዎች ይሰነኙበታል፣ መጽሐፎች ይደረሱበታል። ያ ግን፤ ከኛ ቀጥለው የሚመጡት ኢትዮጵያዊያን፤ ስለኛ ስለቀደምናቸው ኢትዮጵያዊያን ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት ውጤት ነው እንጂ፤ ኢትዮጵያዊ ስለመሆናችን ወይም ኢትዮጵያዊ ስላለመሆናችን አይደለም።

እንግዲህ የአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? የሚለውን በደንብ መረዳት አለብን። ይኼን ስናደርግ፤ የሀገራችንን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሀቅ በትክክል እንረዳና፤ በኢትዮጵያዊነታችን፤ ምን ማድረግ እንዳለብንና ማን ኢትዮጵያዊነቷን እየተወጣች እንደሆነች እንገነዘባለን። ትናንትም፣ ዛሬም ነገም ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ሀገርን ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። ወራሪ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ፤ ይህ ግዴታ፤ ወደ መኖር ወይንም አለመኖር የሕይወት ትንቅንቅ ስለሚያመራ፤ አማራጭ የማይሠጥ ጥሪ ይሆናል። ይህ ፖለቲከኛ መሆንን ወይንም አለመሆንን አይጠይቅም። ይህ ታጋይ መሆንን ወይንም አለመሆንን አይጠይቅም። ይህ ሀገራዊ ግዴታን ነው የሚገልጸው። ይህ የኢትዮጵያዊ ሕይወት፣ የትናንት፣ የዛሬና የነገ ሕልውና ጥያቄ ነው። አሁን በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ፤ ኢትዮጵያዊ መንግሥት የለም። ሕግና ሥርዓት የሚያከብር ቡድን አይደልም በሥልጣን ላይ ያለው። ራሱ የሚያወጣቸውን ሕጎች የሚያፈርስ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሳ ክፍል ነው በሥልጣን ላይ የተቀመጠው። ኢትዮጵያዊያንን እየከፋፈለ፣ አንድነት እንዳይኖረን የሚጥር መንግሥት በሥልጣን ላይ አለ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ፤ “ኢትዮጵያዊ ነኝ። አልከፋፈልም። ጠላታችን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ነው።” እያለ ትግል ይዟል። ስለዚህ፤ የአሁኗ ኢትዮጵያዊትና የአሁኑ ኢትዮጵያዊ፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታችን፤ ይኼን ፀረ-ኢትዮጵያዊያን መንግሥት ከታጋዩ ህዝብ ጎን ተሰልፎ ማስወገድ ነው። ሕዝባዊ ንቅናቄ ከፊታችን ተደግኗል። የውዴታ ሳይሆን ግድ ሆኖብን፤ የምርጫ ሳይሆን አማራጭ ሳይኖረን ንቅናቄው አፍጥጦብናል። የዴሞክራሲ ቅንጦት ሳይሆን የሀገር አድን ጥያቄ ቀርቧል።

ባጭሩ ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ወራሪ መንግሥት ማወገድ ነው። ይኼን የኔ ብሎ ያልተነሳ ግለሰብ፤ ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው? በርግጥ ትግሉ ረጅም ነው። ትግሉ የተመሰቃቀለ ነው። በሥልጣን ላይ ተቀምጦ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ፍልስፍናውና መመሪያው የሆነው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብቻ ሳይሆን፤ ይኼኑ ፍልስፍናና መመሪያ የራሳቸው ያደረጉ ሌሎች ክፍሎችም የኢትዮጵያዊነት ትግላችን አንድ ክፍል ናቸው። በትግሉ ውስጥ ያለን ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ይኼን ሀቅ አጥብቀን መያዝ አለብን። ኢትዮጵያ ለዘመናት መንግሥት ኖሯት ስትተዳደር የነበረች ሀገር ለመሆኗ አጥጋቢ መረጃዎች አሉ። እኒህ መንግሥታት በየተከሰቱበት የታሪክ ወቅት፤ በጎም ሆነ በጎነት የጎደለው ተግባር አከናውነው አልፈዋል። በዚህ ረጅም ታሪካችን፤ የመንግሥታዊ ማዕከላቸውን በሰሜን ወይንም በደቡብ፤ በምሥራቅ ወይንም በምዕራብ እንደታሪካዊ ወቅቱም ተንቀሳቃሽ በማድረግ፣ የተለያዩ የጦር አሠላለፍን በማዘጋጀት፣ ጥንካሬያቸው እንደፈቀደላቸው፤ የሀገሪቱንም ደንበር ሲያሠፉና ስትጠብባቸው ነበር። አንዱ ከሌላው ጎጥ፤ ሃይማኖት ሳያግደው፣ የዘር ሐረግ ሳይከለክለው፣ እንደ ጥንካሬያቸውና የፖለቲካ ግኘታ አመቺነታቸው ሲጋቡና ሲዋለዱ ነበር። በኢትዮጵያዊነት ገዝተዋል። እናም በተለያዩ ጊዜያት፤ በተለያዩ መንግሥታት ዘመን፤ የተለያዩ ህዝባዊ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ሕዝባዊ አመፆች ተካሂደዋል። መፈንቅለ መንግሥት ተደርገዋል። በንጉሥ ላይ ንጉሥ ተነስቷል። ንግሥታት ዘውድ ጭነው ገዝተዋል።

የውጭ ሀገር ጉልበተኛ መንግሥታት ሀገራችን ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት እንዳይኖራት የተጫወቱት ሚና ቀላል አይደለም። እንዲያውም ከሞላ ጎደል የሀገራችን የኢትዮጵያ ታሪክ፤ ከውጭ ወራሪዎችና ጣልቃ ገቦች ጋር የመኖርና ያለመኖር ተጋድሎ ነው ብሎ ማስቀመጥ ይቻላል። አሁንም የውጭ ኃይላት ለጥቅማቸው ሲሉ ያላቸው እርጎ ዝምብነት ትልቁ በሽታችን ነው። አሁን በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በጠቅላላው በውጭ ሀገር መንግሥታት ላይ ልናደርግ የምንችለው ጫና ወይንም ቀና አመለካከት እንዲኖራቸው የምናደርገው ጥረት፤ የትም አይደርስም። ይልቁንስ በራሳችን መካከል ያለውን ጥንካሬ በአንድነት በመሰባሰብ ብናጎለብት፤ እኛ ወደነሱ ለአቤቱታ ከመሄድ፤ እነሱ ወደኛ ለጥቅማቸው የሚመጡበትን መንገድ እንፈጥራለን። የሚረዱት ቋንቋ፤ የራሳቸው ጥቅምና የኛ ጥንካሬ ብቻ ነውና! ሆኖም ወደኛ ስንመለስ፤ በዚህ በሀገራችን የታሪክ ጉዞ፤ ኢትዮጵያዊነት በጥያቄ ውስጥ ገብቶ አያውቅም። ለምን?

አንድ ግለሰብ በመንግሥት ውስጥ የያዘው የሥልጣን ደረጃ፣ ያለበት ድርጅት አባልነቱ፣ የተወለደበት አካባቢ፣ የሚናገረው ቋንቋ፣ ያለው የሀብት ብዛት ወይም ማነስ፣ የትውልድ ሐረጉ መሠረት፤ የግለሰቡ ብሶት ወይም ምቾት፤ ይህ ሁሉ አንድን ኢትዮጵያዊ ከሌላዋ ኢትዮጵያዊት ያነሰ ወይንም የተለቀ ኢትዮጵያዊ አያደርግም። ሁላችን ኢትዮጵያዊያን፤ በአንድነት ሙሉ ኢትዮጵያን እንጋራታለን። የጋራ ሀገራችን ናት። የነበሩት፣ ያለነውና የሚመጡት ሁላችን በአንድነት ባለቤቶች ነን። አንድ የተቧደነ ክፍል፤ በመንግሥት ደረጃ ሥልጣን ላይ ወጣም ወይንም በተቃውሞ አፈነገጠ፤ የኢትዮጵያ ግለኛ ባለቤት ወይንም የኢትዮጵያዊነትን ትርጉም ሠጪና ነሽ አይደለም። ይህ ደግሞ ነገሥታትንና ማንኛውንም በሥልጣን ላይ የሚወጣን ክፍል ይጨምራል። ኢትዮጵያዊነት በሥልጣን ላይ የሚወጣው መንግሥት ወይንም አንድ ጅንን ግለሰብ ትርጉም የሚሠጠው ጉዳይ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት ከዚያ በላይ ነው። የታሪክ ትስስር ነው። እትብት ነው።

አይደለሁም ብሎ እስካላፈነገጠ ድረስ፤ አንድ ግለሰብ፤ ኢትዮጵያዊ ሆኖ በመወለዱ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ወይንም የኢትዮጵያ ዜግነት አለው። ኢትዮጵያዊነት የሀገረ ኢትዮጵያ ዜጋ ሆኖ መገኘት ነው። ኢትዮጵያዊነት በዜግነት ላይ የተመሠረተ የግለሰብ ሀገራዊ መብት እንጂ፤ የስብስብ ወይንም የአካባቢ ጥምር መብት አይደለም። “በግል ወይንም በአካባቢ በደል ደርሶብኛልና ኢትዮጵያዊነት ለኔ ምን ያደርግልኛል?” የሚለው አባባል፤ በቀላሉ ሲታይ የየዋህነት አለዚያ ደግሞ የመሠሪነት ገጽታ ነው። መገንዘብ ያለብን፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሠረት አድርጎ የተነሳው፤ በራሳቸው መሥራችና የጦር መሪ አረጋዊ በርሄ እንደተገለጸልን፤ አፄ ሚኒሊክ የጣሊያንን ወራሪ ጦር ለማባረር ትግራይ ሲሄዱ፤ ለወታደሮቻቸው ምግብ እንዲያቀርብ፤ የትግራይን ገበሬ ስላዘዙት ነው። እናም ሀገርን ከወራሪ ለማዳን የዘመተን ጦር መመገብ በደል አድርገው ቆጥረው፤ የዛሬዎቹ ገዝዎቻችን ተስባስበው ደደቢት ገቡ። ኢትዮጵያዊነት ገደል ይግባ አሉ። አሁንም በደደቢቱ ግንዛቤያቸው ኢትዮጵያን ወረዋል። መንግሥታቸው ኢትዮጵያዊ አይደለም። ሌሎችን በሚመለከት፤ እስኪ አስቡ፤ በደል አለብኝ ባይ ኢትዮጵያዊነቱን በጥያቄ ውስጥ ካስገባ፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ምን ለየው?

“ኢትዮጵያዊ አይደለሁም፤ ሌላ ነኝ።” ማለት፤ የግለሰብ መብት ነው። ያ በግል፤ አንድ ግለሰብ፤ ለራሱ ለግለሰቡ የሚሠጠው ዜጋ የመሆን ወይንም ያለመሆን ጉዳይ እንጂ፤ አንዱ ለሌላው ሊሠጠው ወይንም ሊነፍገው የሚችል ዜግነት አይደለም። በመንግሥት ደረጃ፤ ትክክለኛውን የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት በመከተል፤ ለአዲስ አመልካቾች ዜግነት ሊሠጥ ወይንም ሊነፈግ ይቻላል። ኢትዮጵያዊ የሆነውን ዜጋ ግን፤ በምንም መንገድ ኢትዮጵያዊ አይደለህም ሊል የሚችል ማንም የለም። ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ሲያጠፋ በሕግ ይጠየቃል። ፀረ-ኢትዮጵያ ተግባር ሲሠራ ደግሞ፤ በከሃዲነቱ ባንገቱ ላይ ሽምቅቅ ያርፍበታል። ሀገር አስመስጋኝ ተግባር ሲፈፅም፤ የሀገር ታዋቂነትን ያገኛል። ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው። በወራሪ መንግሥት ላይ ማመጽ፤ አርበኝነት እንጂ፤ ወንጀል አይደለም። ይህ ለግለሰብ ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያዊ ለሆኑ ተቋማትም ይሠራል። አስመስጋኝ ተግባር ሲያከናውኑ፤ ሀገራዊ ታዋቂነት ይሠጣቸዋል። ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆኑ ይዘመትባቸዋል። እንደግለሰቡ ሽምቅቅ፤ ለተቋማቱ ደግሞ ፍፃሜያቸውን የሚያገኙበት ክንውን ይደረጋል። መንግሥትም ሀገራዊ ተቋም ነው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ፀረ-ኢትዮጵያ ነው። እናም ፍፃሜውን ማምጣት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታችን ነው።

“እኔ አንድ ግለሰብ ነኝ። ምን ማድረግ እችላለሁ?” በማለት ኢትዮጵያዊ ኃላፊነታችንን ከኛ ማራቅ አንችልም። ኢትዮጵያዊነት አንዴ የሚመጣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚሸሽ ጥላ አይደለም። ሁሌም አብሮን አለ። በደማችን ውስጥ ፈሳሹ፣ በአጥንታችን ውስጥ ጽናቱ፣ በቆዳችን ላይ ሰብሳቢ ክኑ ነው። በድርጅት ተሰባሰብን ወይንም የመንግሥት ሠራተኛ ሆን፤ ኢትዮጵያዊነታችን አይለወጥም። ኢትዮጵያዊነትን ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ሆነን የምንጠይቀው ጉዳይ አይደለም። ነን ወይንም አይደለንም? ብቻ ነው መለኪያው። ግማሽ ኢትዮጵያዊ የለም። ሩብ ኢትዮጵያዊት የለችም። “ቆይቼ እሆናለሁ አሁን ተበድያለሁ።” ብለን በቆይታ የምናስቀምጠው ጉዳይ አይደልም። በደል ሌላ! ማንነት ሌላ!

እኛ አሁን ኢትዮጵያዊያን ነን ብለን፤ በዚህ በዘመናችን የኖርንበትና የምንኖርበት፤ ኢትዮጵያዊ ኃላፊነታችንን አስመልክቶ፤ ምን እያደረግን ነው? የሚለው ደግሞ የዛሬ ጥያቄ ነው። በመካከላችን የተለያየ መልስ የምንሠጥ አለን። ከነዚህ መካከል በዚህ በያዝነው ወቅት ነበርን ለማለት የሚያስችል ምልክታችን ምንድን ነው? የወቅታችን ማመልከቻ ሆኖ የሚታየው፤ አንድም በደሉን በመፈጸም የተሠለፉት ጥቂት የሥልጣን ጥመኞች እና በዝርፊያ በሕዝቡ ገንዘብ ለግላቸው የገነቧቸው ሕንፃዎች ሲሆኑ፤ ሌላ ደግሞ እኒህን ሲታገሉ ሕይወታቸውን ለሕዝቡ ድል የሠጡት ናቸው። በመካከል የሠፈርነው ከሞላ ጎደል ብዙዎቻችን፤ እድሜያችንን ቆጥረን ከማለፍ በላይ የምናስመዘግበው የለንም። በእርግጥ ትግል ተደራጅቶ ነው። ብዙ የሚታገሉ ድርጅቶች አሉ። የድርጅቶቹ ታሪክና የአሁን ሁኔታ ደግሞ አያስመረቃም። ነገር ግን ሌሎቻችን እጅና እግሮቻችንን አጣጥፈን በመቀመጥና “እነሱ” እያልን ተደራጅተው በሚታገሉት ላይ እጣቶቻችንን በመቀሰር፤ ከኢትዮጵያዊ ኃላፊነታችን ነፃ መውጣት አንችልም። ድርጅት መኖሩ ታጋዮች የሚያደርጉትን ጥረት አመልካች ነው። ከነዚህ ጋር መተባበር ካልቻልን፤ ድርጅቶቻቸውን እንደጣዖት የሚያመልኩና ከሀገራቸው ከኢትዮጵያ የሚያስቀድሙ ከሆነ፤ ሌሎችን በማስተባበር እንዲስተካከሉ የማድረጉ ኃላፊነት ከራሳችን አይወርድም። ድርጅት ምክንያት ሆኖ ከኢትዮጵያዊ ኃላፊነታችን ነፃ አያወጣንም። እነ ርዕዩት ዓለሙ፣ እነ አንዱዓለም አራጌ፣ እነ እስክንድር ነጋና የእስልምና እንቅስቃሴው ተወካዮች፤ የድርጅት አባል ስለሆኑ ወይንም ስላልሆኑ አይደለም የታሠሩት። ግለሰቦቹ እንጂ ድርጅት አይደለም የታሠረው። የታሠሩት ኢትዮጵያዊ መብታቸውን ስለጠየቁ፤ በሥልጣን ላይ ያለውን ፀረ-ኢትዮጵያ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በመቃወማቸውና ለገዥው ክፍል ጉቦም ሆነ የገጠጠ እብሪት አንገታቸውን ባለመድፋታቸው ነው። ባጭሩ ኢትዮጵያዊ ሆነውና ኢትዮጵያዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ በመገኘታቸው ነው።

ታዲያ እንዲህ ያሉ ታጋዮች በእስር ቤት በሚማቅቁበት ወቅት፣ አብዛኛው ሕዝብ እንደሁለተኛ ዜጋ በሚንገላታበት ሀገር፣ መሳደዱና መገፋቱ ሀገርን እንደ የእሳተ ጎመራ ግንፍል እየሮጡ ለማምለጥ ብዙዎቹ በሚሽቀዳደሙበት ጊዜ፣ ኢትዮጵያዊ ኃላፊነታችን ምን እንድናደርግ ያስገድደናል? በድርጅት ዙሪያ የልተካተቱ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ከሚሠጧቸው ምክንያቶች አንዳንዶቹ እኒህ ናቸው፤

“ድርጅት ለኔ አይመቼኝም። ሃሳቤን በነፃ የማካፍልበትን መድረክ ብቻ ነው የምፈልገው።

“ድርጅት ለኔ አልጣመኝም። ከዚህ በፊት የነበረኝ ተመክሮ አስቸጋሪ ነበር።”

“እኔ ሌሎች ወደ ተግባር እንዲሄዱ በሃሳብ ልረዳ እችላለሁ።”

“የትግል ማዕከል እኮ የለም። የተያዙት መሥመሮች በሙሉ ትክክል አይደሉም።”

“እኔ በሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ዙሪያ እየሠራሁ ነው።”

“ድርጅቶች እኮ የሚረቡ አይደሉም። እውነተኛ ድርጅት የት አለና!”

“ትንሽ ጊዜ መቆዬት እፈልጋለሁ።”

የሚሉት ናቸው። እኒዚህና የመሳሰሉትን በመደርደር ከኢትዮጵያዊ ግዴታ ለማምለጥ መሞከር ሀቁ ምንድን ነው? በተለይ በአሁኑ ሰዓት! በየጊዜው የሀገራችን የኢትዮጵያንና የህዝቧን ሁኔታ እያነሳን፤ በብዙ የመገናኛ መንገዶች ሁሉ ጽፈናል፣ ተርከናል፣ አንብበናል፣ ተንትነናል። አሁን በያዝነው መንገድ እየተጓዝን የትም አንደርስም። ተባብረን መታገል ያለብን መሆኑ ግልጽ ነው። ዋናው “ሌሎች ይተባበሩ!” “ድርጅቶች ይተባበሩ!” “ህዝቡ ይተባበር!” ማለቱ አይደለም። እኛስ በግለሰብ ደረጃ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ምን ኃላፊነት አለን? እያልን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። ሀገራችን ለሁላችን እኩል ናት። መደራጀታችን ወይንም አለመደራጀታችን ያነስን ኢትዮጵያዊያን አያደርገንም። የሀገራችን ችግር የተደራጁ ኢትዮጵያዊያን ችግር ብቻ አይደለም። ታዲያ ኃላፊነቱን እኩል መካፈል አለብን። እናም እኛስ ምን እንደርግ? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እና እያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ተደራጁም አልተደራጁም እኩል ኃላፊነት አለብን። እናም እያንዳንዳችን መፍትሔ ፍለጋውና የመፍትሔው አካል መሆኑ ላይ፤ እኩል ድርሻ ሊኖረን ይገባል። ይህ የሀገር አድን ወቅት ነው።

ትግሉ የራሱ የሆነ ዕድገት ያለው፤ ሕጉ የማይታወቅበት ሂደት ነው። አሁን በረጋ መንፈስ ባጭር ጊዜ ውስጥ በቀላሉ የምንችለውን የትግል ማዕከል የመፍጠር ሂደት ብናዘገየው፤ ተቀምጠን የተውነውን ቆመን የማናገኝበት ጊዜ ይመጣል። ዛሬ በግልፅ መነጋገር፣ መሰባሰብና ትግሉን በአንድነት ማድረግ ካልቻልን፤ ነገ ይኼ መሰባሰብ ላም አለኝ በሰማይ ይሆንና ቁጭቱ፤ ድሮ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ወጪት ጥዶ ማልቀስ፤ ይሆንብናል።

ለድርጅቶችም ሆነ ለግለሰቦች አሁን ኢትዮጵያዊ ጥሪው፤ አንድነት በኢትዮጵያዊነታችን እንድንሰባሰብ ነው። የምንሰባሰበው ለወገናችን ለመድረስ፣ ሀገራችንን ነፃ ለማውጣት ነው። የምንሰባሰበው በኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ እንዋቀራለን። ይህ የትግሉ ማዕከል ይሆናል። ይህ የነፃነት ንቅናቄ፣ የትግሉን ራዕይና ተልዕኮ በግልፅ አንጥሮ በማውጣት፤ በአደባባይ ሕዝባዊ ንቅናቄውን ይመራል። ይህ ማዕከል፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ በየቦታውና ባመቸው መንገድ፤ የትግሉን ሂደት እያስረዳ ባደባባይ በግልፅ ትግሉን ያካሂዳል። አንድ ማዕከል፣ አንድ ትግል! አንድ ሕዝብ! አንድ ሀገር! ይህ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጠየቀው። አንድ ኢትዮጵያዊ መንግሥት ለማቋቋም። ይህ የኢትዮጵያዊያን የነፃነት ንቅናቄ፤ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት እየከፈለ፤ የትግሉ ሂደት ግፊት በሚፈጥረው የሽክርክሪት ዕድገት መሠረት፤ ወደፊት ይገፋል። ስለዚህ ማስተባበሩ፣ መተባበሩ፣ እና መጥራትና መጠራቱ የኛ የያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ግዴታ ነው። ኢትዮጵያዊነታችን አሁን ተጠይቋል። መልስ እንሥጥ! እኔ በeske.meche@yahoo.comእገኛለሁ።

ኢትዮጵያዊያን እንቆጠር!

eskemeche


ዝም ብለህ አትፍረድ!

$
0
0

ከጌታቸው ሽፈራው

ባለፈው ሶስትና አራት ወር ውስጥ ብቻ 17 ያህል ጋዜጠኞች አገር ጥለው ተሰድደዋል፡፡ በተለይ ባለፈው ሳምንት 12 ያህል ጋዜጠኞች ሲሰደዱ በርካታ ኢትዮጵያውያን ‹‹ለምን ተሰደዱ?›› የሚለውን በደንብ ሳያጤኑ ለመውቀስ ሲጥሩ ተመልክቻለሁ፡፡ በእርግጥ ጋዜጠኞቹ መሰደዳቸውን አልደግፍም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ጋዜጠኞች ለምን ተሰደዱ ብለን ሳናጤን መውቀስም ተገቢ መስሎ ስላልታየኝ ነው፡፡

ከተሰደዱት መካከል ሁለቱን ብቻ ልጥቀስ፡፡ ተሰማ ደሳለኝ ይባላል፡፡ ኢቦኒ የተሰኘች መጽሄት ነበረችው፡፡ ተሰማ ፌስ ቡክና ኢንተርኔት ለቅሞ ከማሳተም ይልቅ ጋዜጠኛ ቀጥሮ ያሰራ ነበር፡፡ መጽሄቷ የሙያውን ስነ ምግባር የጠበቀች እንድትሆንም ጥሯል፡፡ ነገር ግን የመንግስት ስውር እጆች በሚቃኙት ማከፋፈያ (በተለይም ሁለተኛ ደረጃ አከፋፋዮች)፣ የህትመት ዋጋ አንዱ ፈተና ነበር፡፡ ተሰማ ስፖርትና ፋሽን ላይ የሚሰሩ መጽሔቶች ማስታወቂያ እንደሚያገኙ፣ የመንግስት ጫና እንደማይደርስባቸው ያውቃል፡፡ እሱ ግን የመረጠው ለአገሬ ህዝብ ይጠቅማል ያለውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ማንሳት ነው፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች የሚያጠነጥኑት ደግሞ ማስታወቂያ አያገኙም፡፡ ይታፈናሉ፣ ማተሚያ ቤት አያገኙም፡፡ እናም ኢቦኒ ገበያውን መቋቋም አልቻለችም፡፡ እንዲያውም እዳ አለብህ ተባለ፡፡ ተሰማ ልጅና ቤተሰብ አለው፡፡ ተቋሙ ግን ተዘግቷል፡፡ እንዲህም ሆኖ እዳውን ካልከፈለ የሚጠብቀው እስራት ነው፡፡ አሊያም ጎዳና፡፡ በዚህን ወቅት አንድም ሰው ሊያግዘው አልቻለም፡፡ በህትመት ላይ እያለም ለዴሞክራሲያዊ ግንባታ በሚያደርገው አስተዋጽኦ ይህ ነው የሚባል ማስታወቂያ አያገኝም ነበር፡፡ እናም ለአገሩ ሰርቶ መኖር ብቻ ሳይሆን በአገሩ ሰርቶ መኖር ሲያቅተው ከሁለት ወር በፊት አገሩን ጥሎ ተሰደደ፡፡

Lomi-magazine-ሌላኛው አስናቀ ልባዊ ነው፡፡ አስናቀ የጃኖ መጽሄት ባለቤት ነው፡፡ መጻፍ አደገኛ መሆኑን እያወቀም ቢሆን ሲጽፍ ቆይቷል፡፡ ስርዓቱ የማይፈልጋቸውን ጉዳዮች ላይ ዜናዎችን ሲሰራ ‹‹አለቀለት!›› ተብሏል፡፡ ይህን ስራ በድፍረት እየሰራን ቢሆን መሰረታዊ የሆነ የሚዲያው ችግሮች እሱንም አልለቀቁትም፡፡ ማስታወቂያ ማግኘት እጅጉን ፈታኝ ነው፡፡ ከዚህ አለፍ ሲል ደግሞ ተከሰሰ፡፡ በትንሹ 50 ሺህ ብር ቢቀጣ የት አምጥቶ ይከፍላል? እሱም ለአገሩ ሰርቶ መኖር ይቅልና ሰርቶ መኖርም ፈታኝ ሆነብኝ ብሎ ተሰደደ፡፡

የኢትዮ ምህዳሩ ኤፍሬም ያ በደል የደረሰበት ሲሰርቅ ተይዞ አይደለም፡፡ እስክንድር፣ ርዕዮትና ውብሸት የታሰሩት ሲጽፉ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው 90 ሚሊዮን ህዝብ ባላት ኢትዮጵያ 80ና 90 ሺህ ብር ለማውጣት አልተቻለም ነበር፡፡ ውብሸት ታየን በትንሹም ቢሆን ያስታወስነው ፈረንጆቹ ከሸለሙት በኋላ ነው፡፡ የዚህ ትንታግ ጋዜጠኛ ልጅ ትምህርቱን ለማቋረጥ ምንም አልቀረውም ነበር፡፡ ሚስቱ ብዙ ተቸግራለች፡፡ እስክንድር ነጋን የምንጠይቀው ስንቶቻችን ነን? እጅግ በጣም ጥቂቶቹ! ጋዜጠኛ ሲሰደድ ግን አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወቀሳችንን እናዥጎደጉዳለን፡፡ አስናቀና ተሰማ ኤፍሬም ተጎድቶ አብዛኛው ባለሃብት፣ ዲያፖራ፣ ምሁር……ፀጥ ሲል የአይን እማኞች ነበሩ፡፡ የውብሸት ታዬ ልጅና ሚስት መቸገራቸውንና እሱም አስታዋሽ ማጣቱን ከእነሱ በላይ የታዘበ የለም፡፡ ወደድንም ጠላንም ጋዜጠኛም ሰው ነውና አለኝታ ይፈልጋል፡፡ ይህን ሲያጣ ደግሞ ስደትን ሊመርጥ ይችላል፡፡

እነዚህ ሚዲያዎች እየሰሩ በነበረበት ወቅት ማስታወቂያ ሲጠይቋችሁ ‹‹አይ ፖለቲካ ነው የምትጽፈው!›› ብላችሁ ፊታችሁን ያላጠቆራችሁ (ካላችሁ)፣ ስህተት ስታዩበት እንዲሻሻል ደውላችሁ የጠየቃችሁ፣ አንድም መረጃ አገኝበታላሁ ብላችሁ፣ አሊያም በመግዛታችሁ ሚዲያው ይጠናከራል ብላችሁ የገዛችሁ ‹‹ጥለውን ሄዱ!›› ብላችሁ ብታማርሩ ምክንያት ይኖራችኋል፡፡ ይገባችኋልም!

ነገር ግን ለስፖርትና ፋሽን ማስታወቂያ እየሰጠህ እነዚህ መጽሄቶች ማስታወቂያ ሲጠይቁ ‹‹ፖለቲካ ነው የምታሳትሙት!›› ብለህ መልሰህ አሁን ሲሰደዱ ‹‹አይ የእኛ አገር ጋዜጠኞች!›› ያልክ ነጋዴ ለመፍረድ ሞራል የለህምና አትፍረድ! ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ሲደወልልህ ‹‹አይ ይህ መንግስት እኮ…ቅብጥርጥስ›› ብለህ የሸሸህ ‹‹ምሁር›› ጋዜጠኞቹ ተሰደዱ ብለህ እንዳትፈርድ፣ አንተም ድሮም የኢትዮጵያውያን ጉዳይ አያገባኝም ብለሃል አሁን እንዳትፈርድ! ያኔ እነዚህ መጽሄቶችን እንዲሁ አይተህ ያለፍክ ‹‹አንባቢ›› አታውቃቸውምና ተሰደዱ ብለህ እርር ድብን እንዳትል፣ እንዳትፈርድ!

እነዚህ ጋዜጦች አትምልን ሲሉህ ‹‹መንግስት በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ ጫና ያደርስብኛል፣ ለምን ስፖርት አታሳትምም….›› ያልክ የማተሚያ ቤት ባለቤት አሁን ጋዜጠኞች ተሰደዱ ብለህ ከመፍረድህ በፊት የአንተን አስተዋጽኦም መርምር! ኢትዮጵያ ውስጥ ሚዲያዎች በእሳት ላይ መቀመጣቸውን እያወክ፣ ማገዝም እየቻልክ ሲሰደዱ ብቻ በመቆዘም፣ ሲታሰሩ የፌስ ቡክ ፎቶውን በመቀየር ብቻ ለውጥ የሚመጣ የሚመስለህ ዳያስፖራ ‹‹አይ ጋዜጠኛ!›› ከማለት በፊት ‹‹እኔ ምን አደረኩ?›› ብለህ መጠየቅ ይገባሃል፡፡
Lomi-magazine-
የኢትዮጵያውያንን መብት ለማስጠበቅ ተቋቁሞ ጋዜጠኞች ሲታሰሩ፣ ሚዲያዎች ሲዘጉ ሀሳብን በነጻነት ለመግለጽ ነጻነት ያልጮህክ ተቃዋሚና ፖለቲከኛ አሁን ሲወጡ ‹‹አቤት ፍርሃት!›› ከማለት በፊት የራሰህን አስተዋጽኦ መገምገም የግድ ነው፡፡ ለሚዲያውም ሆነ መረጃ አገኝበታለሁ ብለህ ሚዲያዎቹን በመግዛት የራስህን አስተዋጽኦ ያላደረክ ‹‹አንባቢ›› በስሚ ስሚ ‹‹ተሰደዱ!›› አደራህን እብዳትፈርድ!

የትም ሁኑ የት፣ እናንተ! የጋዜጠኞችን መብት ይከበር ዘንድ ያለ ፍርሃት በድፍረት የጮኻችሁ ‹‹ለምን ተሰደዱ?›› ብላችሁ ብትወቅሱ ምክንያት ይኖራችኋል፡፡ ማስታወቂያ ሲጠይቋችሁ የሰጣችሁ፣ አንብባችሁ ገንቢ አስተያየት የለገሳችሁ፣ ያበረታታችሁ ብቻ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጋዜጠኞች ለሚዲያ፣ ሚዲያው ለዴሞክራሲ፣ ዴሞክራሲው ለኢትዮጵያውያን ይጠቅማል ብላችሁ ይብዛም ይነስም የራሳችሁን አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ ‹‹ለምን ተሰደዱ?›› ብትሉ ያምርባችኋል! ያገባናል ብላችሁ የቻላችሁትን ሁሉ አድርጋችኋልና!

“በበዓሉ ግርማ ጉዳይ ላይ ከሕሊና ዕዳ ነጻ ነኝ”

$
0
0

ደራሲና ሐያሲ አስፋው ዳምጤ

ደራሲና ሐያሲ አስፋው ዳምጤ ናደው፣ የተወለዱት መጋቢት 1ዐ ቀን 1927 ዓ.ም. አዲስ አበባ ጊዮርጊስ አካባቢ፣ መርሐ ጥበብ
ማተሚያ ቤት ግቢ ከሚባለው ቦታ ነው፡፡
አቶ አስፋው የቤተ ክህነት ትምህርት ለጥቂት ጊዜ ከተማሩ በኋላ፣ በዘመናዊ ትምህርት፣ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃን፣ በኮከበ
ፅባሕ ቀ.ኃ.ሥ. አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በመጀመሪያ ዲግሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ
በእንግሊዙ ኪምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ተምረው ተመርቀዋል፡፡
ወደሥራ ዓለም ከተቀላቀሉ በኋላ፣አብዛኛውን የሥራ ጊዜያቸው በገንዘብ ሚኒስቴር በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ያገለገሉ ሲሆን፣
ከገንዘብ ሚኒስቴር እንደለቀቁ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ድርጅትና በኩራዝ አሳታሚ ሠርተዋል፡፡
አቶ አስፋው ከኢትዮጵያ ውጭ ካሳለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ፣ በእንግሊዝ ለትምህርት ሶስት ዓመት፣ ቀሪውን አራት ዓመት
ደግሞ በአሜሪካ በሥራ ነበር::
asfaw_damte
በድርሰቱ ዓለምም፣ “አንድ ለአምስት” የተሰኘ ረጅም ልቦለድ ያበረከቱ ሲሆን፣ በደራሲያን ማኀበር ካሳተመው በ“የዘመነ
ቀለማት” መፍሐፍ ላይ በአጫጭር ግጥሞቻቸው፣ በ‹‹እነሆ››መድብል ደግሞ በአጫጭር ታሪኮች ተሳትፈዋል፡፡ከዚህም
በተጨማሪ ከ1970 እስከ 90ዎቹ ዓመታት ድረስ ስለ አማርኛ ጥበበ ቃላት አንዳንድ ነጥቦችን ከስር ጀምረው መጣጥፎችን
አበርክተዋል፡፡

ደራሲና ሐያሲ አቶ አስፋው ዳምጤን የረጅም ጊዜ ጓደኛቸው ከነበረውና የደርግ ጅቦች ሰለባ ከሆነው ታዋቂውና ተወዳጁ ደራሲ
በዓሉ ግርማ ከሚወደው ሕዝብ ጋር የመጨረሻው በነበረችው ምሽት ከአቶ አስፋው ዳምቴ ጋር በሰላም አብረው ከተዝናኑ
በኋላ ፣ተሰነባብተው ሌላ ታሪክ እስኪፈጠር ድረስ፣በአንዲት ግሮሰሪ ደጅ ላይ አብረው አብረው ነበሩ፣
መጽሔታችንም “ማን ያርዳ የቀበረ፣ ማን ይናገር የቀበረ” እንደሚባለው፣ስለበዓሉ ግርማ የመጨረሻዋ ምሽት በዝርዝር
እንዲነግሩን አቶ አስፋው ዳምጤን ጋብዘናቸዋልና እነሆ::

ፍቱን፦- የደራሲ በዓሉ ግርማ ባለቤት፣ ወ/ሮ አልማዝ አበራ፣ ‹‹…የካቲት 24 ቀን 1976 ዓ.ም. ቀን ላይ አስፋው ዳምጤ
እቤት ስልክ ደወለ :: በዓሉ ቤት አልነበረምና፣ ስልኩን አንሥቼ ያነጋገርኩት እኔ ነበርኩ :: የእግዜር ሰላምታ ከተለዋወጥን
በኋላ፣ ‹… በዓሉ እንደመጣ እዚያ እቀጠሯችን ቦታ ባስቸኳይ እንድትመጣ ብሎሃል በዪልኝ …› ብሎ ስልኩን ዘጋ ::››
ብለዋል:: እውነት ነው ?
bealu-girma1
አቶ አስፋው፦ የዚህ አጭር መልሱ ‹ሐሰት ነው› ነው:: ይኸንኑ መልስ ለሚያዚያ 8 ቀን ውንጀላቸው፣ በሚያዝያ 15 ቀን
1989 እፎይታ ጋዜጣ ላይ ከዛሬ 16 ዓመት በፊት ሰጥቼያለሁ ::
በዚያው ወቅት ስለዚያች ዕለት የበዓሉ ከቤት አወጣጥ ፣ Black Lions (ብላክ ላየንስ) የተባለ፣ የበርካታ ኢትዮጳውያን
ደራስያንን የሕይወት ታሪክ እና ሥራዎ ቻቸውን ለማስተዋወቅ የሚጥር መጽሐፍ ደራሲ፣ ሞልቬር፣ እርሳቸዉ ነገሩኝ ብሎ
የጻፈው፣ አንድ ጓደኛው እቤቱ መጥቶ ወደ አንድ ሰዓት ገደማ እርሳቸው አንድ መጥፎ ነገር ይሆናል የሚል ስሜት
ተሰምቷቸው መሔዱን ቢቃወሙም ይዞት ሔደ፤ በዚያውም ቀረ የሚል ነው::
እንግዲህ ስለ እዛች ዕለት ከቤት አወጣጡ የቀረበው መረጃ የተጋጨ ስለሆነ ወይ ስልክ ደውሎ ጠራውና ሔደ ወይም
መጥቶ ይዞት ሔደ ይበሉ፣ አንዱን ይምረጡ የሚል ነበር የኔ የዚያን ወቅት ጥያቄ::
ሐቁ ግን፣ በዚያች ዕለት እንዳጋጣሚ ሆኖ፣ ስልክ አልደወልኩለትም፣ ቤቱም አልሔድኩም ነበር:: ምክንያቱም፣ የአዲስ አበባ
ክልልን የዐሥር ዓመት የአብዮት ታሪክ የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ውስጥ ተሳታፊ በመደረጌ፣ የሥራ ውጥረት ገጥሞኝ አመሽ ስለ
ነበረ ነበር::
በዚያችው ምሽት ግን፣ ስድሰት ኪሎ በሚገኘው በአዲስ አበባ ኢሠፓአኮ በስብሰባ ቢሮ ሌሎቹ ከሔዱም በኋላ አመሻሽቼ
ወደ ቤቴ ስጓዝ ማምሻ ቦታችን አካባቢ ስደርስ፣ ‹ለመንገድ› ለማለት በተለመደችው ቦታችን ለማቆም አዙሬ አቆምኩ:: አንድ
ወጥ ጽሑፍ ለማቀናበር እንድንችል በቀረቡልን የየቀበሌ፣ ከፍተኛ፣ ቃጣና እና የተቋማት የ10 ዓመታት የታሪክ ዘገባ
መረጃዎች ጭንቅላቴ ተሞልቶና ስቆዝም ቆየሁ:: ወደ ሦስት ሰዓት አካባቢ ይመስለኛል ፣ የበዓሉን የመኪና ክላክስ ሰምቼ ዞር
ስል፣ መኪናው ውስጥ አየሁት:: የመጣበት አግጣጫ የቤቱ ስላልነበረ፣ የት እንዳመሸ ገመትኩ:: መኪናዋን ባለችበት ትቶ፣
በእግሩ መንገዱን ረጋ ብሎ አቋርጦ መጣና እኔ መኪና ውስጥ ገባ:: ብዙም የረባ ነገር የምናወራው ስላልነበረን ይሆናል ትዝ
የሚለኝ የለም:: እንደኔው ደከም ያለው መሰለኝ:: ካሰብኩት በላይ በመቆየቴና እሱም የሚሔደው ወደ ቤቱ ስለነበር ብዙ
አልቆየንም:: ሃያ ቢበዛ ሠላሳ ደቂቃ ቢሆን ነው:: መኪናዬን አዙሬ መኪናው ጎን አቁሜለት ሲወርድ እኔ ወደፊቴ ቀጠልኩ::
እየተጠባብቅን አልነበረም የምንሔደው ሁሌም ቢሆን::
ስለዚህ፣ ተቀጣጥረን ሳይሆን በእንደዚያ ዐይነት አጋጣሚ ግን ተገናኝተን ነበር ያችን ዕለት::
አሁን ደግሞ በአበራ ለማ በተበተነው የ16 ገጽ ሐተታ ውስጥ በገጽ 6 ላይ ጓድ ቁጥር ኀምሳ ሦስት ከተሰኘ ባለሥልጣን፣
‹‹…ወደ ማታ በዓሉን የደህንነት ሰዎች ይዘውት እንደሄዱ ከቤተሰቡ ሰማሁ…›› የሚል ባለቤቲቱን ያይን ምስክርነት የሚሰጡ
የሚያስመስላቸው ‹መረጃ› ያስነብበናል:: ምን ማለት ነው; በእርግጥ ባለቤቲቱ ለባለ ሥልጣኑ ይኸን መረጃ ሰጥተዋል ሊለን
ነው ዐላማው; ሞኙ በሬ ሆይ ሣሩን አየህና ገደሉን ሳታይ ሆነበትሳ !
ፍቱን፦ በዓሉ እርሶ ጋ ከመድረሱ በፊት የት ቆየ ብለው ነበር የገመቱት?
አቶ አስፋው፦ ጥቂት ቀደም ብሎ እዚያው አካባቢ ወዳጅ እንደነበረው ተገንዝቤ ነበር ::
ፍቱን፦ የማን ቤት ነው ?
አቶ አስፋው፦ እሱን አላውቅም ::
ፍቱን፦ ወንድ ሴት?
አቶ አስፋው፦ ሴት::
ፍቱን፤ በዚያች ዕለት ምሽት እዚያ ቆይቶ ከተመለሰ በኋላ ነበር ከእርሶ ጋር የተገናኛችሁት?
አቶ አስፋው፦ እንደዚያ ነበር አመጣጡን ሳይ የገመትኩት::
ፍቱን፦ የቅርብ ጓደኛ እንደመሆንዎ ምናልባት ለመምከርም ለመገሠጽም አልሞከሩም?
አቶ አስፋው፦ በአዘቦቱ ከምንወያይባቸው ርእሰ ጉዳዮች ውጭ ነበረ:: የእኔና የርሱ ቁልፍ ጉዳይ ድርሰትንና ተዛማጅ
ጉዳዮችን የሚመለከት እንጂ ሌላውን የሕይወቱን ክፍል የግሉ ብቻ አድርጌ ነበር የማየው:: ከዚያ ያለፈ ነገር እርሱ
በአጋጣሚ በሚያነሣቸው ጉዳዮች ነው የምናተኩረውና ይኸ ተነሥቶ አያውቅም፡፡
ፍቱን ፦ እርሶና በዓሉ በየሳምንቱ ሮብ ካልሆነ ኀሙስ አለዚያ ዐርብ ትገናኙ የነበረበት የተለየ ምክንያት ነበራችሁ?
አቶ አስፋው፦ አዎን፤ እኔንና እርሱን የሚመለከት ትንሽ የግል ጉዳይ ነበረች::
ፍቱን፦ አሁን መግለጽ አይፈልጉም?
አቶ አስፋው፦ ከዋናው ጉዳያችን ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሌለውና ለማንም የሚጠቅም (ወይም የሚጎዳ) መረጃ አይደለም::
ግን የግል ነገር ነው::
ፍቱን ፦በዚያች ምሽት ስንት ሰዓት ላይ ተገናኛችሁ?
አቶ አስፋው፦ ወደ ሦስት ሠዓት ግድም ነው :: በትክክል አላሳተውስም ::
ፍቱን፦ የዚያን ምሽት የበዓሉ አለባበስ እንዴት ነበር?
አስፋው፡- እንደ ሁሌውም ሽቅርቅር ያለ ነበር ማለት ይቻላል:: ቡላ ቀለም የሆነ ሙሉ ልብስ መሰለኝ:: ልብ ብዬ
ያተኩርኩበት አልነበረም:: ዐይኑ ላይ ኦይንትመንት ብጤ ያየሁ መስሎኛል::
ፍቱን፦ ድካም ያዩበት ለምን ይመስልዎታል?
አቶ አስፋው፦ እንደርሱ ንቁ የሆነ ተንቀሳቃሽና በሥራ ውጥረት ውስጥ የቆየ ሰው ያለ ፈታኝ ሥራ ውሎ ሲያመሽ ይህ
ዐይነት ስሜት የሚያድርበት ይመስለኛል:: ጊዜውም እየተማሸ በመሔድ ላይ መሆኑን ማሰብ ይኖርብናል:: የኔም መንፈስ
ብዙ የነቃ መሆኑን እርግጠኛ አይደለሁም:: በውሎዬ ስላጋጠሙኝ አንዳንድ መንፈስ መሳጭ ስሜት ቀስቀሽ ስለሆኑ የቀበሌና
የከፍተኛ የታሪክ ሰነዶችና መረጃዎች እርሱ ከነበረበት ሁኔታ ለመወያያ አመቺ አልነበሩና የሚነሡ አልነበሩም ከርሱ ጋር::
ፍቱን፦ ከበዓሉ ሁኔታ ወይም ከአካባቢው የታዘቡት የተለየ ነገር ነበር?
አቶ አስፋው፦ ምንም የታዘብኩት ነገር አልነበረም:: መኪናዬን ሲያይ ምንም ሳይል ዐልፎኝ መሔድ ስለማይችል መጣ
እንጂ ጊዜው ለተለምዶው ዐይነት
ውይይት አመቺ ሆኖ አልነበረም የመጣው:: እንዳልኩህ ያኔ ሰዓቱ ሁለታችንም ወደየቤታችን ለመሔድ መንፈሳችን
ያዘነበለበት ሁኔታ ነበር::
ፍቱን፦ ስንት ሰዓት አካባቢ ተንቀሳቀሳችሁ?
አቶ አስፋው፦ ከሦስት ሠዓት ቢያልፍም ብዙ አይመስለኝም::
ፍቱን፡- ስትለያዩ፣ በዓሉ ወዴት እንደሚሔድ ያውቁ ነበር?
አቶ አስፋው፦ ወደ ቤቱ ነዋ! የእኔን መኪና አይቶ የቆመው ወደ ቤቱ አግጣጫ እየነዳ ሳለ ነበር:: መኪናው ዘንድ ሳደርሰው
ጉዞውን ነው የሚቀጥለው:: ለእኛ ያቺ ምሽት እንደሌሎቹ ሁሉ አንድ ሌላ ምሽት ነበረች! ከመምጣቱ ዐምስት
ደቂቃዎች ቀደም ብዬ ሔጄ ቢሆን ኖሮ፣ በዚያች ማታ አንተያይም ነበር::
ፍቱን፦ የበዓሉን መሰወር የሰሙት በምን ሁኔታ ላይ ሆነው ነበር?
አቶ አስፋው፦ በማግሥቱ ጧት ወደ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ነበር:: ወደ አዲስ አበባ ኢሠፓአኮ ለመሔድ እየተደራጀሁ
ሳለ፣ ባለቤቱ ደወለችልኝ ::
ፍቱን፦ወ/ሮ አልማዝ፣‹‹በዓሉ የማታ ማታ ወደቤት ይመለሳል ብዬ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ብጠብቅም የውሃ ሽታ
እንደሆነ ቀረ፡፡ ቢቸግረኝ አስፋው ቤት ደወልኩ፡፡ ሚስቱ ስልኩን አነሳች፡፡ ’…አስፋው እቤት ገብቷል?…’ ስል ጠየቅኋት፡፡
’…አዎን ገብቷል…’ አለችኝ፡፡ ይሄኔ ግራ በመጋባት፤ ’…ባሌን ከቤት ጠርቶ ወስዶት የት ጥሎት ነው እሱ ተቤቱ የገባው?…’
እያልኩ አፋጠጥኳት፡፡ ቀጥዬም ’እስኪ አቅርቢልኝና ላናግረው…’ ስላት፤ ’የገባ ምስሎኝ ነበር እንጂ አልገባም’ ብላ
የመጀመሪያ ቃልዋን አጠፈችብኝ፡፡ የስልክ ንግግራችንም በዚሁ ተቋጨ›› ብለዋል እውነት ነው?
አቶ አስፋው፦ ሐሰት ነው
ፍቱን፦ መሥረያ ቤት ነበር የደወሉት?
አቶ አስፋው፦ አዎን፣ ኢትዮጵያ መጻሕፍት ድርጅት እኮ ነው ! እዚያኛውማ ገና ልሔድ ነው ::
ከዚያ፣ ‹‹በዓሉ እኮ ትላንት ማታ አልገባም:: አልተገናችሁም ነበር ወይ;›› ስትለኝ ያመሸበት ትዝ ብሎኝ ነበርና፣ ‹‹አይቸዋለሁ፣
ግን›› ብዬ የምለው ጠፋኝና፣ ‹‹አሁን የምሔደው አንድ ትልቅ ባለሥልጣን ዘንድ ለስብሰባ እንዲህ ዐይነቱን ነገር ለማጣራት
ችሎታ አለው:: በከተማው ውስጥ የሚካሔደው ነገር ሁሉ የሚዘገብለት እርሱ ስለሆነ አነጋግሬ ሁኔታውን አጣራለሁ››
አልኳት:: አዲስ አበባ ኢሠፓአኮ ጽሕፈት ቤት እንደረስኩ በቀጥታ ወደ በላይ ኀላፊው ቢሮ ገብቼ ነገሩን አነሣሁ:: ‹‹አንድ
ቦታ (ጾታን ጠቁሞ) አድሮ ይሆናል ነገ ብቅ ይላል ››አለኝ አቃሎ:: እኔም ይኸ ሊሆን እንደማይችልና ማታ ከዚህ ወደ ቤቴ
ስሔድ እንደተገናኘንና ስንለያይ ወደ ቤቱ እያመራ እንደ ነበር አጠንክሬ ገለጽሁ:: ከዚያ፣ ቆይ ብሎ አንድ ቦታ ደውሎ ጥቂት
ከተነጋገረ በኋላ ምንም መረጃ እንደሌላቸው ገለጸልውልኛል፣ አሁንም ጥቂት አሰብ አደረገና ሌላ ቦታ ደውሎ ተናጋገረ::
ውጤቱ ምንም ለውጥ አልነበረውም:: በዓሉን የሚያህል ሰው ጠፍቶ የአዲስ አበባን አጠቃላይ ሁኔታ የማወቅ ዐቅም ካለው
ከዚህ ቢሮ ተሰውሮ ብዙ እንደማይቆይ ተስፋ ያለኝ መሆኑን ተናግሬ ወደ ስብሰባ ቢሮው ሔድኩ ::
ፍቱን፦ ያ ባለሥልጣን ማን ነበር ?
አቶ አስፋው፦ ኮማንደር ለማ ጉተማ ነበር :: በትምህርት ቤት ዕውቂያ ስለነበረን ነው የሚቻለውን ያህል ሊጥርልኝ ይችላል
የሚል ተስፋ የነበረኝ ::
ፍቱን፦ ኮማንደር ለማ የት እና የት የደወሉ መሰለዎት?
አቶ አስፋው፦ ስለ አዲስ አበባ የየዕለት ሁኔታ የሚያሳውቁት አካላት ዘንድ ነው ብዬ ነበር የገምኩት::
ፍቱን፦ ደህንነት መሥሪያት ቤት ማለት ነው?
አቶ አስፋው፦ ሊሆን ይችላል:: ልዩ ክፍሎችም ሊኖሩት ይችላሉ፣ አላውቅም::
ፍቱን፦ ያንለት ወ/ሮ አልማዝን በድጋሚ አግኝተዋቸው ነበር?
አቶ አስፋው፦ አዎን፣ በስልክ ይሁን በግምባር፣ ምንም ፍንጭ ለጊዜው ባላገኝም፣ ተስፋ እንዳልቆረጥኩ ነግሬያት ነበር ::
ፍቱን፦ የበዓሉን መሰወር ጉዳይ እርስዎ የምር ነበር ያዩት ወይስ …?
አቶ አስፋው፦ አዎን ግን ደግሞ አንዳንድ የገለጻቸውን ሁኔታዎች የሚከርር አይሆን ይሆን የሚል ልብ ከፋይ ስሜት
መነሻው ላይ ልቤን ያሟግት ነበር:: ለምሳሌ፣ ቀደም ብሎ ባንድ ወቅት ታሰረ የሚል ወሬ ተነዝቶ ነበር:: ያን ወቅት ኢትዮጵያ

መጻሕፍት ድርጅት ድረስ ይመጣ በነበረበት ጊዜ፣ ልክ ከእኛ ዘንድ ተመልሶ እንደሔደ፣ አንድ ሰው ደውሎ ስለ መታሰሩ
ነገረኝ:: ግን፣ እኛ ዘንድ መጥቶ እንደነበርና ዝም ብሎ ወሬ ነው ማለቴን አስታውሳለሁ:: ከዚያ በኋላም እርሱው ከቤተ
መንግሥት አካባቢ ቤቱ ተደውሎ ስለ ደህንነቱ የተጠየቀ መሆኑን ነግሮኝ ነበር:: ሆኖም ሙሉ ለሙሉ መተማማን አስቸጋረ
ነበር:: ከኦሮማይ ጋር መያያዙ ታሳቢ ጉዳይ ስለሆነ ስለ ነገሩ ክብደት ማመን ፍጽም አልነበረም::
ፍቱን፦ መንግሥቱ ናቸው የደወሉት?
አቶ አስፋው፦ ማን እንደሆነ ተነግሮት እንደሁ አልነገረኝም:: እኔ ግን ሊሆን ይችላል ብዬ አላሰብኩም፣ አልመሰለኝም::
ፍቱን፦ ስለዚህ የምር ይሆናል ብለው አላሰቡትም ነበር?
አቶ አስፋው፦ አጽናኝነት ያላቸው ምልክቶች ሆነው ቢታዩም ቀላል አድርጎ የሚታይ ነገር አልነበረም :: እርግጥ መንፈስን
አዋዥቋል:: ከዚያ ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ፈልጉ አፋልጉ የሚል ቴሌግራም እንደተበተነ ሰማሁ:: በዚያው ሰሞን
ከበዓሉ ጋር ቅርብ ግንኙነት አላቸው ተብለው ከታሰቡ ውስጥ ይመስለኛል ሦስት ሰዎች በተናጠል ተጠርተው ስለ ጉዳዩ
የሚጠረጥሩት ነገር እንዳለ እንዲጠቁሙ ፍንጭ ካገኙ ደውለው እንዲያሳውቁ ስልክ ቁጥር ተሰጣቸው :: ከሦስቱ ሁለቱ
ባለቤቱና እኔ ነበርን ::
ፍቱን፦ ማን ነበር የጠየቀዎ?
አቶ አስፋው፦ መልኩን እንጂ ስሙን አላውቀውም ::
ፍቱን፦ ወ/ሮ አልማዝ በርስዎ ላይ ቅያሜ ለምን ሊያድርባቸው ቻለ?
አቶ አስፋው፦ በዓሉ ከተሰወረ በርከት ያለ ቀናት ቆይቶ፣ ወ/ሮ አልማዝ ‹‹የበዓሉ መኪና ቃለቲ መንገድ ላይ ቆማለች አሉ፣
ሔደን እናምጣት›› አለችኝ ቤቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ደውላ :: ‹‹ይኸንማ ማድረግ አንችልም:: በተሰጠሸ ስልክ ቁጥር ደውለሽ
አሳውቂ እንጂ ከነረው ሁኔታ እንደፈለገን ማድረግ አንችልም ::››፣
ከዚያ በነገሯ ሁሉ የማላውቃት ሰው ዐይነት ሆነችብኝ:: ከመነሻው ብዙ ትውውቅም አግባብም አልነበረንም:: የኔ ጉዳይ
ከባዓሉና ከድርሰቱ ጋር እና በውጭ ነበር ::
ከሥራ ከታገደ በኋላ ቤቱ መሔድ ግድ ሆነ ፤ እኔና እርሱ መገናኘት የምንችልበት ዋና ቦታ ያ ብቻ ሆና ነው :: እርሱ ሳይኖር
ቤቱ ከማን ለመወያየት ነው እንድሔድ ይጠበቅ የነበረው:: ቀድሞም ቤት ለቤት የመጠያየቅ እና ያን ዐይነት ማኅበራዊ
ግንኙነት አልነበረንም :: ያኛው ለሁለታችንም ሌላ ዐውድ ነበር :: እርሱ የራሱ እኔም የራሴ ነው የነበረን::
ስለዚህ፤ ለዚህ እና ለተለያዩ የእርሷ ውንጀላዎችም ሆኑ ስሞታዎች
ትክክለኛው መልሱ የሚገኘው ከእኔና ከበዓሉ የግንኙነት ዐይነትና መሠረታዊ ባሕርይ ነው :: ነገር በመደጋገም አዲስ እውነት
አይፈልቅም:: ስለ እርሳቸው አመለካከት ትክክሉን ነገር ለማግኘት የምር ለማወቅ በየጊዜው የሰጧቸውን በርካታ ቃለ
መጠይቆች እያገናዘቡ ማንበብ ነው::
አሁን የተበተነውና መጽሔቶችን እያጣበበ ያለው ሰፊ ሐተታ ገሐድ ያወጣው ቁምነገር፣ ሚያዝያ 8 ቀን 1989 በወ/ሮ
አልማዝ ስም ከመነሻ የውንጀላ ጽሑፍ አንሥቶ ሐተታው ውስጥ በስማቸው የወጣው ሐሳብ ሁሉ ከነቃላቱ የእርሳቸው
እንዳልነበረ ነው :: ሰው ትኩረት እንዲሰጠው የበዓሉን ስም ሽፋን አድርጎ የራሱን ቂም፣ በቀልና እና ብሶት ለማሰተላለፊያ
የተጠቀመበት ሆኖ ነው የሚገኘው ጽሑፉን በታኙ :: እውነት ፈላጊ ፈልፍሎ እንደሚደርስበት ጥርጥር የለኝምና፣ ይኸኛውን
በዚህ ጨርሻለሁ::
ፍቱን፦ በዚህ ጉደይ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጠይቀው ያውቃሉ?
አቶ አስፋው፦ አልተጠየቅሁም:: የፍርድ ቤትን ፍጹም አሉቧልታ መች ይቋቋመዋል; ቀደም ሲል አሉቧልታን ይዞ ወደ
መገናኛ ብዙኃን መሔድ ይቀል ነበር:: አሁን ያ በር እየጠበበ ይመስለኛል::
ፍቱን፦ በእርስዎና በበዓሉ መካከል ቅያሜ ወይንም አነሥተኛ ቁርሾ ነበር?
አቶ አስፋው፦ የምን ቁርሾ አመጣህብኝ:: ቀድሞ መች ለበቂ ጊዜስ ተገናኝትን:: በጽሑፉ አድናቂው ነኝ ፤ ሒሳዊ ትችት
የሚጠላ ሰው አልነበረም:: በሙያና በመሥሪያ ቤት የተለያየን ነን:: ስለዚህ፣ ላልከው ነገር ሰበብም አልነበረም::
ፍቱን፦ ኩራዝ እንዲገቡ በዓሉ ከፍተኛ ውትወታ አድርጎ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው፣ ኋላ በምን የተለየ ምክንያት እዚያ
ገቡ?
አቶ አስፋው፦ ወደ ኩራዝ የመግባቱ ጥያቄ ረዘም ያለ የጊዜ ሒደት የነበረውና ከዚህ ቀደም መልስ የሰጠሁበት ነው:: በዚህ
ረገድ በዓሉ ከብዙዎች አንዱ ነበር::
ይሁንና፣ የኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበረው ተስፋዬ አያሌው አንድ የጥበባት ጉዳይ መጽሔት
ለመመሥረት ተነሣሥቶ ከያለበት ጽሑፍ የሚያቀርቡ ሰዎች ሲያፈላልግ በዚያ ሳቢያ ተገናኝተን ተዋወቅን:: ከዚያ፣ ሥነ
ጽሑፍን ለማሳደግ ከልብህ ካሰብክ፣ አሰታሚ ዋና ክፍሉን አጠናክረህ ምራው ብሎ፣ ሊያሠራ የሚችል ሁኔታ
እንደሚያመቻችልኝ አሳመነኝ:: እኔም በኢትዮጵያ መጻሕፍት ድርጅት ላራት ዓመታት ያህል በተግባርም በንባብም
የቀሰምኩትን ዕውቀትና ልምድ ሰፋ ባለ መድረክ ተግባር ላይ ለማዋል አጓጓኝ:: ከባድ ውሳኔ እያደረግሁ መሆኔም እየተሰማኝ
ነበር :: ይሁን እንጂ ስበቱ አየለና፣ ተደራድሬ የአሳታሚ ዋና ክፍሉ ኃላፊ ሆኜ ተቀጥሬ ገባሁ::
ከ1977 እስከ 1983 የነበረውን የኩራዝ አሰታሚ ድርጅት እንቅስቃሴና ተጨባጭ ውጤት ሳሰተውል ያደረግሁት ትክክለኛ
ውሳኔ እንደነበረ እና በውጤቱም እርካታ ይሰማኛል::
ፍቱን፦ ወዳጅዎን የኢትዮጵያ መጻሕፍት ድርጅት ባለቤት እንዴት አሳመኗቸው?
አቶ አስፋው፦ ከእርሱ ጋር ቀደም ሲል ከገንዘብ ሚኒስቴር ዘመኔ ጀምሮ ነበርና የምንተዋወቀው፣ ስለሁኔታዎች የጋራ
መግባባት ነበረን:: በዚያው ተወስኜ እስከ ዘለቄታው እንደማልቆይ አስቀድሞ የታወቀ ነበር:: ስለዚህ ለመልቀቅ ችግር
አልነበረም ::
ፍቱን፦ ለበዓሉ መሰወር ከኦሮማይ ሌላ መንሥኤ ይኖራል?
አቶ አስፋው፦ የግንኙነታችን አግጣጫ ሥነ ጽሑፍ አንድ ጠበብ ያለ ገጽታው ነው:: ከዚያ ውጭ ያለ ገጽታው ነው
የሚበልጠው፣ የሚሰፋው:: በዓሉ የመንግሥት ባለሥልጣን የነበረ በዚያ አግጫም ኃላፈነቶች ነበሩበት :: ስለዚህ ከቁንጽል
እይታ ተነሥቶ ትልቅ ድምዳሜ መድረስ አስቸጋሪ ነው::
ፍቱን፦ በእርሶ ላይ ከሚሰጡ አስተያየቶች መካከል አንዱ፣ አቶ አስፋው ሰኔና ሰኞ የሚባለው ገጥሞባቸው ነው እንጂ ፣
ጓደኛቸውን አሳልፈው የሚሰጥ ሰብእና የላቸውም የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ አቶ አስፋው ጓደኛቸውን የሚሸጡ
ሰው አይደሉም፣ ነገር ግን፣ የዚያች ዕለት ምሽት ያዩትን አይተው ለሕይወታቸው ሠግተው ዝም ብለዋል የሚል ነው?
አቶ አስፋው፦ በኔ ትሑት አስተያየት ከግለሰቡ ሰብእና ተነሥቶ፣ አንድ ሰው ምን ዐይነት ተግባር ለመፈጸም እንሚችል እና
እንደማይችል ለመመዘን ለማየት መነሣት ትክክለኛ የብየና መንገድ ነው ብዬ አስባለሁ:: እኔን በሚመለከት ከነገርከኝ
የሁለተኛው ወገን መላምት እንዳጋጣሚ ሁኖ የተከሰተ ሐቅ አልነበረም:: ያመሸንበት አካባቢ ለዚህ ግብ የሚመረጥ ይሆናል
ብዬ አልገምተውም:: የሆነው ሁኖ፣ ያችን ምሽት በዓሉን የሚመለከት እኔ ያየሁትና ያስፈራኝ ክስተት አልነበረም:: ስለዚህ፣
አይቼ ዝም ያልኩት ወይም የደበቅሁት ነገር እንደሌለ በእርግጠኝነት እናገራለሁ:: ይኸን መቀበል አለመቀበል የእምነት ጉዳይ
ሊሆን ይችላል::
ነገር ግን፣ ከዚህ ዘልዬ አጋጥሞኝ የነበረ ቢሆን ኖሮ የሚለውን ማሰብ አያስልገኝም:: አላጋጠመም በቃ! ብዬ አቆማለሁ::
ፍቱን፦ ሰው በበዓሉ መሰወር እኔን ተጠያቂ አድርጓል የሚል ቅሬታ ወይ ምሬት አድሮቦታል;
አስፋው፦ ፈጽሞ! ኅሊናዬ ንጹህ እና የውስጥ ሰላም ያለኝ ሰው ነው :: ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ፣ በሕግ ፊት ከምኑም ነጻ የሆንኩ
ዜጋ ነኝ:: ከታወቁት ሁለት ወንጃዮቼ ሌላ የማውቀው ሌላ የለም:: የሚጠረጥር ቢኖር መብቱ ነው:: እውነቱን ፈላጊ ከሆነ
ይደርስበታል ብዬ አስባለሁ::
ፍቱን፦በዓሉን በተመለከተ ሕሊናዎ ነጻ ነው?
አቶ አስፋው፦ Absolutely, ምንም:: በበዓሉ ግርማ ጉዳይ ላይ ከሕሊና ዕዳ ነፃ ነኝ:: ለምኑ ብዬ እኮ ነው የምልህ? እንዲህ
አይነት ሁኔታ ውስጥ የሚጨምረኝን ነገር ለምን አደርጋለሁ? እኔ ሰዎች በጥረታቸው ሲሳካላቸው ደስ ይለኛል:: የሆነ
እርካታ ይሰማኛል፣ ይሄ ባህሪዬ ተቃራኒ ስሜትና ዝንባሌ ያላቸውን ሰዎችን ያናድዳቸው ይሆን ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ::
እነሱ ተመኝተውት ያጡትን እኔ ሳልፈልግ አግኝቼ ይሆን?
ፍቱን፦ አቶ አበራ ለማ ጋር ከዚህ በፊት ቅራኔ ነበራችሁ?
አቶ አስፋው፦ እኔ ከእሱ ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብቻለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም:: የተገናኘነው ኢትዮጵያ መጽሐፍ ድርጅት ሆኜ
“ሕይወትና ሞት” የምትለው መጽሐፍ እንዲታተምለት የበኩሌን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ:: የ“ማለዳ ስንቅ” የምትለዋን
ኩራዝ እንድትታተም አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ:: በድርሰት በኩል ግንኙነታችን ይሄ ነው::
አንድ ጊዜ ኩራዝ የጀመርናት መጽሔት የመጀመሪያው ሕትም የመሆኑ ጽሑፎች ሰዎች እዲያመጡልን በአዘጋጁተ በስብሐት
ገ/እግዚአብሔር ጥሪ ተደርጐ ስለነበር ጽሑፋቸውን ካመጡልን ሰዎች መካከል አበራ ለማ አንዱ ነበር::
የሆነ ቀን ስብሐት ቢሮዬ ይመጣና “ይሄንን ነገር አንብበው፣second opinion እፈልጋለሁ” ብሎ የአበራ ለማን ጽሑፍ
ይሰጠኛል:: አነበዋለሁ:: የተጻፈው “ሂስ” ተብሎ ነው:: ሂሱም የሚካሄደው በታዋቂው ገጣሚ በሰይፉ መታፈሪያ “የተስፋ
እግር ብረት” ውስጥ ባለ አንድ ግጥም ላይ ነው:: እንደአጋጣሚ “የተስፋ እግር ብረትን” ሰይፉ መታፈሪያ ሸልሞኝ እጄ ላይ
ስለነበር አውቀዋለሁ:: ሂሱን ሳነበው ትንታው ጥሩ አልነበረም:: ያን ጊዜ አበራ ለማ ገና የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ
መግባቱ ነበር መሰለኝ:: የተማረውን ተግባራዊ ለማድረግ ነው መሰለኝ ያንን ጽፏል:: መደምደሚያውግን ፍጹም ትክክል
ስላልነበረ ይሄንኑ ለስብሐት ነበርኩት:: ስብሐትም የእኔም ሃሣብ ነው ብሎ ተስማማ:: በሁለቱም መጽሐፎቹ ሳቢያ
እንተዋወቃለን በሚል ደውለን አናናግረው ብለን ደውዬ ነበርኩት:: በፍፁም አልተስማማም:: “ተሳስተሃል” አለኝ::
ፍቱን፦ አቶ አበራ ለማ በግጥሙ ላይ የሰጡት ድምዳሜ ምን ነበር?
አቶ አስፋው፦ የግጥሙ መልዕክት ብር ቁፈራ ነው የሚል ነበር የእሱ ድምዳሜ:: በእርግጥ ግጥም ገጣሚ ስለብር መቆፈር
ሊጽፍ ይችላል:: አበራን ወደዚያ ድምዳሜ የመራው ግን የሰይፉ አንዳንድ ፊደሎችን የመደጋገም ስልቱ ነው:: በዚያ ላይ
ተመስርቶ የፈጸመው ስህተት ነው እኔ የመሰለኝ::
(ግጥሙን ቀጥሎ ያለው ነው)
አድካሚ የሕይወትን መልክ ፍለጋ
እፍ እፍ፤ እፍ የጉሽ ገፈት
የጥራት ከለላ
እንትፍትፋት::
..
እፍ እፍ ስልባቦት
የወተት ላይ ውፍረት
እኝካት::
..
እፍ እፍ ግግርት
የውሃ ላይ ቅርፊት
አረንጉዋዴ በቀልት::
..
እንደ ጉሽ ገፈቱ
እንደ ስልባቦቱ
የውሃ ግግርቱ
..
እንደዚያ ደዚያ
እፍልኝ ምሥጢር ከለላ
ሰዋዊ ዐይነ – ጥላ::
..
የሕይወት ምሥጢር
በዘመናት ክምር
ቅበርብርብርብርብር
(እሱን ነው እምቆፍር)::
ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው (መስከረም 1969 ዓ.ም)
ፍቱን፦ ከዚህ ሁሉ በኋላ ልትግባቡ አልቻላችሁም?
አቶ አስፋው፦ ‹‹ተሳስተሃል››አለኝ:: ነገሩ እኔ እኮ የስነ ጽሑፍ ተማሪ ነኝ ነው:: “አይ በአንተ ድምዳሜ ያልተስማማሁት እኔ
ብቻ ሳልሆን የመጽሔቱ አዘጋጅ ስብሐትም ጭምር ነው፣ ስብሐትም እንደዚሁ ነው ያሰበው›› አልኩት:: “ሁለታችሁም
ተሳስታችኋል” ሲለኝ፣ “እኛ ስህተት ነው ብለን የምናስበውን መተው እንችላለን፣ ወይም ደግሞ ከComment ጋር
ልናቀርበው እንችላለን:: ‹‹እንዲህ ብለነው ነበር፣ አንባቢ ራስህ ፍረድ›› ብለን ማውጣት እንችላለን፣”ብዬው በመሐሉ፣‹‹
ገጣሚው ራሱ ስላለ ልደውልለት›› ስለው፣ ‹‹ደውልና ጠይቀው›› አለኝ::
ሰይፉ መታፈሪያን ደውዬ የአበራን ድምዳሜ አነበብኩለትና አስተያየቱን ጠየቅኩት::
“እንዴ ብሩን ከየት አመጣችሁት?” ነው ያለው:: ግጥሙ ውስጥ እኮ ብር የለም፣ ማለቱ ነው::
ይሄንን ነገርኩት::
አበራ ለማ አሁንም፣“እሱም ተሳስቷል” አለኝ:: ‹‹ባለግጥሙ?›› ስለው፣ ‹‹አዎን አያሲው እኮ ደራሲው ያላየውን የግጥሙን
አንድ መልክ ፈልፍሎ ያወጣል›› አለ:: ይሄንን መርህ እንደ መርህ አውቀዋለሁ:: እውነትም ይሆናል፣ ይሄኛው ግጥም ግን
በጣም ግልጽ ነው:: የመጀመሪያው አንጓ፣ የሁለተኛው፣ የሶስተኛው አንጓ በግልጽ ያስቀምጠዋል:: አራተኛው ላይ ሲመጣ
ያንኑ ነው:: ያ የሚቆፈረው የህይ ወትን ሚስጢርን ለማግኘት ነው፣ የሚል ነው:: ግጥሙ ራሱ ግልጽ ነው ››አልኩት:: ይሄ
ነው ያስቀየመው::
የነገሩ መቋጫ ይሄ ብቻ አይደለም:: ለካ ማታ ዩኒቨርሲቲ ሲሄድ ለጓደኞቹ “ሁለት ግጥም የማይገባቸው ሽማግ ሌዎች” እያለ
ወረፍ አድርጐናል:: ሌላው ክፋቱ በዚያን ሰዓት ፣ ስለ ሁለቱ “ግጥም የማይገባቸው ሽማግሌዎች” ማንነትና ስለየትኛው
ግጥም ማለቱ እንደሆነ እየጮኸ ሲያወራ በዚያ በኩል ያልፍ የነበረ አስተማሪው ይሰማዋል ፣አስተማሪው ደግሞ ግጥሙን
ያውቀዋል:: ወዲያውወደ አበራ ቀረብ ብሎ ፣ “የሚያሳፍሪው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ ? አንተ የእኛ ተማሪ ነህ መባሉ
ነው” ብሎት ይሄዳል:: ይኼ መቼም ቅስም የሚሰብር ነው:: ያቺ ትሆን እንዲህ የምታደርገው ብዬ አስባለሁ:: ያ ነው እንግዲህ
በእኔና በእሱ መካከል ተከሰተ የምለው ነገር::

23 ዓመታት እንደ መንግስት ያልመራው ህውሃት (ገብረ ግደይ)

$
0
0

በገብረ ግደይ
ማነው አሸባሪው 。。。 ተማም ? በሚል ርዕስ በአይጋ ፎረም ላይ የወጣ አንድ ፅሁፍ ለማንበብ አጋጣሚውን አግኝቼ ነበር። ታድያ የዚህን ፅሁፍ ሃተታ ተመለከትኩና ምላሽ እንደሚገባው ሳመነታታ ቆይቼ እነሆ ምላሽ ያልኩትን ፅሁፍ ለናንተ ለአንባብያን ጀባ ብያለሁ። ከጅምሩ ፅሁፉን ለማንበብ ስዳዳ አብዱል ከድር የሚለውን ስም ተመለከትኩና ስሙ በራሱ የለበጣ አይነት እና ትክክለኛ ስም እንዳልሆነ አሳባቂ ነው ።  ይህን እንድል ያስቻለኝ አብይ ምክንያት አብዛኛውን ግዜ አብዱል ብሎ ከድር ፣ ጀማል ፣ መሃመድ የሚከተለው ስም የለም። በርግጥ አብዱል ብሎ -ለጢፍ ፣ አብዱል-ከሪም ፣ አብዱል-ፈታህ ፣ አብዱል-ቃድር ወዘተ በሚል የተሰየሙ ቢሆኑ እንጂ። እንደ ስም አብዱል ብቻውን በፅሁፍ ደረጃ ማንም መሰረታዊ የስልምና እውቀት ያለው ሰው አይፅፍም ብዬ ብናገር አልተሳሳትኩም። ብሎም አይሰየምም ይህን ስል ግን በአጭሩ ጎደኞች ወይም ቤተሰብ ሊጠሩን አይችሉምን አያካትትም። ይህ ማለት በቀላል በሃገርኛው የግዕዝ ቋንቋችን ወልደ。。

[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]

 

Comment

ሞረድ ሲደንዝ በቢለዋ ይሳላል የበዓሉ ግርማ ጉዳይ (ሲራክ ዮፍታሄ)

$
0
0

bealu-girma1ዛሬ የምንገኝበት ዲሞክራሲያዊና ቴክኖሎጂካዊ ዘመን ህዝባዊና መንግስታዊ እውቅና ስለነበረው አንድ ሰው የኦሟሟት ምስጢር ጥያቄ ማቅረብ ወንጀል አይደለም። ግርድፍ ማስረጃን አንተርሶ እውነታው እንዲታወቅ መጻፍም አስተዋይ ህሊና ላለው ሰው መጥፎነቱ አይታየውም። ይልቁንም ተጠየቅነቱ ፋይዳ የሚኖረው ለምን የአንድ ሰው አሟሟት ብቻ የሌሎች ወገኖቻችን አሟሟትም ይታወቅ የሚል መሰረታዊ ጥያቄ ከተነሳ ብቻ ነው። ይህም ቢሆን ይቻላል፡፡ እኔ ግን ጥያቄውን ያቀረብኩት በቅርብ ስለማውቀውና ካገኘሁት ማስረጃም ተነስቼ ነው። ሌሎቹ ደግሞ እንውቃለንና ማስረጃም አለን ብለው ቢነሱ መሰረተ ሀሳባቸውን ደጋፊ እንጅ ተቃዋሚ አይደለሁም ቢሉ አጠቃላይ ትኩረቱ ወደ ዋናው የኣቶ በዓሉ ግርማ አሟሟት ተጠየቅነት ያንደረድረናል።[ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]—-

 

በጥፍሩም በጥርሱም ለስልጣን የሚተጋ መንግሰት …… እንዴት እንታገለው!!

$
0
0

ከግርማ ሰይፉ ማሩ

በጥፍሩም በጥርሱም ለስልጣኑ የሚተጋን መንግስት በሁሉን አቀፍ ትግል መጣል አለብን ብለው ጠብ መንጃ ቢያነሱ ክፋቱ ምን ላይ እንደሆነ አልታይህም እያለኝ ነው፡፡ ለምን በጠብ መንጃ ፍልሚያ ስልጣን መያዝ እንዳለብኝ በግሌ ባይገባኝም አሁን ግን የኢህአዴግ ዓይነት መንግሰት ከደርግ እንዴት እንደሚሻል ማሰብ እያቃተኝ ነው፡፡ የሰላማዊ ትግል ሰራዊት እንዴት እንገንባ ለሚለው ጥያቄ አፋጣኝ ምለሽ ካልሰጠን በስተቀር መንግሰት በግልፅ እየደገፈ ያለው በጠብ መንጃ ሊገዳደሩ የፈለጉት ነው፡፡ በሰላም ያልነውን ሰላም እየነሳን ይገኛል፡፡ መንግሰት ሆይ ሰላም እንድትሆን ሰላም ሰላም ለምንል ዜጎች ሰላም ሰጠን የምር የቀረበ ጥያቄ ነው፡፡

(ግርማ ሰይፉ)

(ግርማ ሰይፉ)


በፍትሕ አደባባይ የፈለገውን ማድረግ የወሰነ መንግሰት በእጅ አዙር ደግሞ በየማተሚያ ቤቱ እየሄደ መፅሄትና ጋዜጣ ታትሙና ወዮላችሁ ማለት ተያይዞታል፡፡ ይህ ከህግ ሰርዓት ውጭ በየማተሚያ ቤቱ በግንባር እና በስልክ የሚደረገው ማሰፈራሪያ ከወሮበላነት ውጭ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ መንግሰት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ክስ መስርቻለሁ ብሎዋል፡፡ ህዝቡ የሚለው ግን ሌላ ነው፡፡ መፅሄት መቼ ነው የሚወጣው ነው፡፡ በቃ!!! ፍርድ ቤት በመፅሔትና ጋዜጦች ላይ ቢፊልግ እግድ ቢፈልግ ይዘጉ እሰኪል ድረስ ምን የሚያጣድፍ ነገር መጥቶ እንደሆነ ባናውቅም የመንግሰት አሽከሮች በየጉራንጉሩ ባሉ ማተሚያ ቤቶች ደጃፍ እየዞሩ ማሰፈራራት ተያይዘውታል፡፡ ሹሞቻችን ይህን አላደረግንም ብለው እንደሚክዱ ባውቅም ይህን ዓይነት ወሮበላነት ማስቆም ካልቻሉ ተጠያቂ እንደሚሆኑ መርሳት የለባቸውም፡፡ ስህተታችውን በአደባባይ ተችተን እንዲታረሙ የሚሰጣቸው ምክር ካንገሸገቸው የመጨረሻው ቀን ሲመጣ እንደሚጠየቁ ግን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ የወሮበላ አለቃነት ከወሮበላነት በላይ የሚያስጠይቅ ነው፡፡ እነዚህን ወሮበላዎች አስቁሙልን ግልፅ አቤቱታ ነው፡፡ በየሳምንት ብዙ መቶ ሺ ብር ገቢ ያገኙ የነበሩ ማተሚያ ቤቶች በህጋዊ መስመር ሳይሆን በስልክና በቃል ከወሮበሎች በሚሰጥ ማሰፈራሪያ አጅ መስጠት እና ገበያ ማባረር ደግሞ የሚያስመሰግን ፍርሃት እንዳልሆነ ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ የእያንዳንዳችን ፍርሃት ተደምሮ ነው እነርሱም ያለምንም ይሉኝታ ሊያሰፈራሩን ቤታቸውን ድረስ የሚመጡት፡፡ በወረቀት ትዕዛዝ ይድረሰኝ ለማለት ወኔ የሌለው ማተሚያ ቤት የሙት ዓመትና ተዝካር ወረቀት ሲያትም ይኖራታል፡፡

መንግሰት በሚዲያዎች ላይ በዶክመንተሪ ጀምሮት የነበረውን ወደ ፍትህ አደባባይ ያመጣውን የግል ሚዲያ አሁንም ገና አልበቃውም፡፡ በጥፍርም በጥርስም ሊዘለዝል እየባተተ ይገኛል፡፡ ኢትቪ ቤታችን ድረስ መጥቶ ለሆዳቸው ባደሩ ምሁራን ተብዬዎች እና ሹመኞች ሲሳደብ ያመሻል፡፡ የኮሚኒኬሸን ጉዳዮች መስሪያ ቤት ውስጥ ዳይሬክተር ናቸው የተባሉ ታምራት ደጀኔ የሚባሉ ኃላፊ መሰሪያ ቤቱ የመንግሰት ደሞዝ የሚከፈላቸው እኔ ጭምር በምከፍለው ግብር መሆኑን ዘንግተው የግል ፕሬስ ከተቃዋሚዎች ጋር ወግኖ እየሰራ ነው ብለው ከገዢው ፓርቲ ጎን ቆመው ሲከሱን አምሽተዋል፡፡ እኚህ ግለስብ ከተቃዋሚ ጎን መሰለፍ ማን ሀጥያት ነው እንዳላቸው አላውቅም፡፡ ተቃዋሚዎች በህግ ተመዝግበው የሚሰሩ ተቋማት እንደሆኑ እና የሚደግፋቸውም የሚቃወማቸውም ሰዎቸ መኖራቸው የሚጠበቅ መሆኑን ዘንግተውታል፡፡ ለነገሩ እርሳቸው የሚደግፉት ፓርቲ ነገ ተቃዋሚ የሚባል ወንበር ላይ ሊኖር እንደሚችል በተሰፋ ደረጃ ማሰብ አልቻሉም፡፡ ለነገሩ ኢህአዴግ በጥቅም የተገዙ አባላቶቹ ስልጣን ሲያጣ አብረውት እንደማይቆዩ ይረዳዋል- እርሳቸውንም ጨምሮ ማለቴ ነው፡፡ ለዚህም ነው ኢህአዴግ በጥርስም በጥፍርም ፍልሚያ ውስጥ የሚገባው፡፡ አቶ ታምራት ደጀኔ እንዲረዱ የምፈልገው የግሉ ፕሬስ ተቃዋሚን ቢደግፍ አንድም ነውር እንደሌለው ይልቁንም ገዢውን ፓርቲ ለመደገፍ ገዢው ፓርቲ ብቁ እንዳልሆነ ማሳያ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ በገንዘብ የሚደግፋቸው ነገር ግን ተደግፈው መቆም የማይችሉ “የግል” ተብዬ ሚዲያዎች እንደነበሩ መርሳት የለባቸውም፡፡ ለምሳሌ ኢፍቲን፣ ዛሚ፣ ወዘተ
ሰኞ ነሃሴ 19/2006 በቀረበው ዶክመንተሪ ተብዬ ዘባተሎ ላይ ከለየላቸው የመንግሰት ሹሞኞች እስከ ዩኒቨርሲት መምህራን አልፎ ተርፎም አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴን ያሳተፈ ነበር፡፡ እርገጠኛ ነኝ ሀይሌ በሚዲያ ላይ ስለሚታዩ ግድፈቶች አጠቃላይ ሁኔታ ነበር የሚናገረው እንጂ አሁን ክስ ስለተመሰረተባቸው የግል ሚዲያዎች አልነበረም፡፡ ቆርጦ ቀጥሉ ኢቲቪ ግን ከህዝብ ጋር ሊያጋጨው ፍላጎቱን አሳይቶዋል፡፡ ሌላው ተዋናይ ዶክትረ አሸብር ወልደጊዮርጊስ ነበሩ፡፡ ከብዙ ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ነበር መልስ አሰጣጣቸው፣ የከሰሱትም ሪፖርተርን ነው፡፡ መንግሰት ደግሞ ከሪፖርተር ጋር ጉዳይ የለውም፡፡ እንዲከሱ ሲጠበቅ የነበረው ሌላ ነበር፡፡ ይቅር ብያለሁ ብለው አልፈውታል፡፡ የእርሳቸው ይቅር ባይነት ከመንግሰት ሰፈር ሊገኝ አልቻለም፡፡ ተበቃይ መንግሰት ለስልጣኑ ሲል በጥፍሩም በጥርሱም ከግል ሚዲያው ጋር ግብ ግብ ገጥሞዋል፡፡ ማን ያሸንፋል አና መቼ ወደፊት የሚታይ ነው፡፡
የቀረበውን ዘጋቢ ፊልም ማስታወሻ ይዜ ለሁሉም በስማቸው አንፃር ለመፃፍ ነበር የፈለኩት ይህን ዘባተሎ የበዛበት ድሪቷም ዘጋቢ ተብዬ ከዚህ በላይ ማለት ተገቢ ሆኖ ስለአልተመቸኝ ተውኩት …. ይህ ዘጋቢ ፊልም ተብዬ የተሰራበት ሙሉ ዶክመንት ለታሪክ እንደሚቀር ተሰፋ አለኝ፡፡ የዛን ጊዜ እንወቃቀሳለን፡፡ ምሁራን ተብዬዎች በእናንተ ተሰፋ ቆርጠናል ….. በእናንተ መምህርነት አንድም የተሻለ ጋዜጠኛ እንደማናገኝ፡፡ ለነገሩ ልጆቹ የአስተማሪዎች ብቻ ሳይሆን የእኛም ናቸው እና በቤታችን ይማራሉ፡፡ ሀገር ማለት ልጄ ብለን እናስተምራለን፡፡

የበርማ የስደት መንግስት ለነጻነት ትግል አስኳል በመሆን የመራው የትግል ተሞክሮ

$
0
0

 

entc-logo-5የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጁላይ 27 2014 ባወጣው መግለጫ፤ የወያኔን አፓርታይድ ስርዓት ለማስወገድና በሀሉ አቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግስት ለመተካት ጥንስስ በመሆን መሰረት የሚጥልና የተበታተነውን ትግል በአንድነት ሊመራ የሚችል የአንድነት ሀይል (የስደት መንግስት እንደአማራጭ) እንዲቋቋም ሀገራዊ ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው (ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ  http://goo.gl/KYP32s) ። ምክር ቤቱ ጥሪውን ተከትሎ ከሚመለከታቸው አካላትና ድርጅቶች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል። እስካሁን የተደረጉ ውይይቶች በአብዛኛው አበረታቶች ሲሆኑ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ ምንም አይነት የተለየ አማራጭ ሳያቀርቡና የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በጥልቅ ሳይፈትሹ አግዝፈው በመመልከት  አስቸጋሪና ሊተገበር የማይችል አድርገው ያምናሉ። የኢትዮጲያ ሕዝብ በሰቆቃ ውስጥ ሆኖ ፍዳውን በሚያይበትና ሀገራችን በመንታ መንገድ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት እለታዊ ችግሮችን ከመተንተን ባለፈ የአማራጭ መፍትሔ በማቅረብና ስምምነት ላይ በመድረስ በአንድነት ትግሉን መምራትና ማካሄድ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆኗል።

 

የአንድነት ሀይል (የስደት መንግስት እንደአማራጭ) የማቋቋም አስፈላጊነትን አስመልክቶ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ የነበሩና በጨቋኝና አምባገነናዊ ስርዓቶች ተገፍተው ከአገር ውጭ የስደት መንግስት በማቋቋም ከታገሉና በትግል ላይ ካሉ የሌሎች ሀገራት ህዝቦች የትግል ሂደት በመመርመር ከተሞክሮው ግንዛቤ መውሰድ ለምናደርገው ትግል በጣም አስፈላጊ ነው። በተለይም ምርጫ 97ን ተከትሎ ወያኔ እያካሄደ ካለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ አፈና፤ እስር፤ ግድያ፤ በዘር ከፋፍሎ ማጋጨትና ዘረፋ ጋር በከፊልም ቢሆን ተመሳሳይ ታሪክ ያላት በርማ የምትባለውን አገር በምሳሌነት መውሰድ ጠቃሚ ነው።

 

በርማበደቡብምስራቅእስያየምትገኝበታይላንድናባንግላዴሽየምትዋሰንሀገርናት።በሲ.አይኤየመረጃሰነድመሰረትየበርማየቆዳስፋት 670ሺህካሬኪ/ሜትርይገመታል።ይህማለትየኢትዮጵያግማሽያህልስፋትአላትማለትነው።የህዝቧብዛትምወደ 56 ሚሊዮንይገመታል።በርማበጃፓንቅኝአገዛዝስርየነበረችሲሆንበ1948 ዓ.ምእ.ኤ.አበእንግሊዝእርዳታነጻነቷንአግኝታለች።

በ1962 ዓ.ምእ.ኤ.አጄኔራልነዊንየተሰኙየሰራዊቱአዛዥበመፈንቅለመንግስትስልጣንተቆጣጥረውበሀገሪቱላይየወታደራዊጁንታይመሰርታሉ።ህዝቡንናሀገሪቱንበፍጹምየጭቆናቀንበርውስጥበማስገባታቸውበአለምደረጃበሰብአዊመብትረገጣበቀደምትነትከተመዘገቡትሀገራትውስጥበርማለመገኘትበቃች።ጁንታውየዲሞክራሲሀይሎችንሙሉለሙሉከሀገሪቷአጥፍቶየበርማሶሻሊስትፕሮግራምተብሎየሚጠራው  የአንድፓርቲአምባገነናዊአስተዳደርንአሰፈነ።

ሀገሪቷ ከጎርቤት ሀገራትና ከሌሎች የአለም ሀገራት የተገለለች ብቸኛ እንድትሆን በማድረጉ በአለም ድሀ ከሚባሉት ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። በመንግስት ባለስልጣናት የሚደረገው ዘረፋና የአስተዳደር ብልሹነት በሩዝ ምርት አቅራቢነት ትጠቀስ የነበርችውን የበርማን ኢኮኖሚ አሽመድምዶ ህዝቡን የድህነት ማቅ አለበሰው። የህዝቡ ችግር ከሚሸከመው በላይ በመድረሱ በ1987 ዓ.ም እ.ኤ.አ የበርማ ህዝብ መሪዎቹን በመቃወም በሕዛባዊ እምቢተኝነት ወደ አደባባይ ተመመ።

 

በህዝብ የተቀሰቀሰው አብዮት ምንም እንኳን ለብዙ ሺህ በርማውያን ህይወት መጥፋት ምክንያት ቢሆንም አመጹ እያየለ መጥቶ በ1988 ዓ.ም ፈላጭ ቆራጩ የወታደራዊ ጁንታ ጄኔራል ዊን ከስልጣን ለቀቁ። በህዝባዊ ማእበልና በዘር ፖለቲካ የተናጠችውን ሀገር በማረጋጋት ሰበብ  የወታደሩ ክፍል ስልጣኑን ሳይለቅ፤ የመድበለ ፓርቲ ዲሞክራሲ በመፍቀድ ነጻና ህዝባዊ ምርጫ ለማደረግ ቃል በመግባትና በማዘናጋት አመጹን በተወሰነ መልኩ ለጊዜው አረጋጋው።

በዚህ መሰረት መሰረት በ1990 ዓ.ም እ.ኤ.አ በበርማ ታሪክ የመጀመርያውን ነጻ ምርጫ ለመካሄድ በቃ። በአጭር ጊዜ ተደራጅተው የወታደራዊውን ገዥ ፓርቲ በምርጫ ከገጠሙት በርካታ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ሊግ (National League for Democracy) በመባል የሚታወቀው በከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ በምርጫ አሸናፊ መሆኑ ተረጋገጠ።

በሃገራችን ምርጫ 97ን ተከትሎ ወያኔ እንዳካሄደው ድርጊት፤ የበርማም ወታደራዊ ጁንታም በግፍ የመግዛት ጥም ገና ያልወጣለት የአምባገነኖች ስብስብ በመሆኑ ውጤቱን በጸጋ ሊቀበለው ፈቃደኛ አልሆነም። የህዝብ ድምጽ መነጠቁን ተከትሎ በተነሳው ህዝባዊ ቁጣ ብዙ የበርማ ዜጎች ህይወት በጨካኙ አምባገነናዊ አገዛዝ የጥይት እራት ሆኑ። ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች እየታደኑ ወደ ወህኒ እንዲወርዱ ተደረገ። ገሚሱም ወደየጎርቤት ሀገራት ተሰደደ። የአሸናፊው ፓርቲ የብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ሊግ (National League for Democracy – NLD) መሪና የኖቤል ተሸላሚ የሆኑት ወ/ሮ አን ሳን ሱቺ ከሰው ጋር እንዳይገናኙና በቁም እስር እንዲቆዩ ተደረገ።

ይህንን አይን ያወጣ የህዝብ ድምጽ ንጥቂያ አንቀበልም በማለት ከእስርና ጭፍጨፋው ማእበል ተርፈው ወደ ጎረቤት ሀገር የተሰደዱት የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች በበርማና በታይላንድ የድንበር ከተማ ላይ National Coalition Government Union of Burma (NCGUB) በሚል ስም በስደት የሚንቀሳቀስ መንግስት አቋቋሙ። የተቋቋመው ይህ የስደት መንግስት የአን ሳን ሱቺን NLD ፓርቲ ጨምሮ በርካታ ተቃዋሚ ሀይሎችን ያቀፈ ነበር።

ይህ የበርማ የስደት መንግስት መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በማድረግና ለበርማ የነጻነት ትግል አስኳል በመሆን በተከታዮቹ አመታት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን መርቷል። የስደት መንግስቱ የተቃዋሚዎችን ድምጽና ትግል አንድ አድርጎ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ትግሉን ሲመራና ሲያስተባብር ቆይቷል። በአለም መንግስታትም ከበሬታን እያገኘ በመሄዱ፤ የተለያዩ ሀገር ባለስልጣናትን በማነጋገርና ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራዎችን በመስራት በበርማው ጨቋኝ ስርዓት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ለማስደረግ ችሏል።

በዶ/ር ሴይን ዊን የሚመራው የበርማ የስደት መንግስት በተለያየ ጊዜ ከአሜሪካና ከአውሮፓ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ተወካዮች ጋር ውይይት በማድረግ በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ተጨባጭ የሆኑ ስራዎችን ሰርቷል። በበርማ የነጻነት ትግል ውስጥ በዲፕሎማሲ በኩል ካደረጋቸው አስተዋፅኦዎች ውስጥ፤

በ 1997 ዓ.ም እ አኤአ የአሜሪካው የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የኮሄን-ፋይንስታይን ማሻሻያ Cohen-Fienstein Amendment-Section 569 of the Foreign Operations and Appropriations Act በበርማ መንግስትና በባለስልጣናቱ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የመንቀሳቀስ መብትን የሚገድብ እቀባ ህግ እንዲፀድቅ ትግል አድርጓል።

ለተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት የበርማን ፖለቲካ ቀውስ ሳይታክት በማስገንዘብ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የበርማን ህዝብ ሰብአዊ መብትና ነጻነት መከበር የሚጠይቁ ውሳኔዎችን (resolutions) እንዲያፀድቅ ከፍተኛ ትግል አድርጓል።  UN RESOLUTIONS A/RES/47/144, A/RES/48/150, A/RES/49/197,etc

የስደት መንግስቱ ከውጭ ትግሉን ሲያካሂድና ግፊቱን ሲያደርግ ከውስጥም ከውጭም ያለው ግፊት በመጠንከሩ በ2010 ዓ.ም የወታደራዊው መንግስት በድጋሚ ህዝባዊ ምርጫ ለማካሄድ ተገደደ። በተለመደው የአምባገነኖች ታክቲክ በምርጫው የተቃዋሚ ሀይሎች ተመጣጣኝ የመጫወቻ ሜዳ ካለማግኘታቸውም በላይ ምርጫው ግልጽና ፍትሐዊ ያልነበረ በመሆኑ ብዙዎቹ ድርጅቶች እራሳቸውን ያገለሉ አለበለዚያም ለይስሙላ የተወዳደሩ ነበሩ።

 

ምንም እንኳን ገዥው ፓርቲ ምርጫውን በመንጠቅ በጉልበት አሸናፊነቱን ቢያውጅም የትግሉን አቅጣጫ ሊያስቀይረው ባለመቻሉ የተቃዋሚ ሀይሎች በአንጻራዊ ነጻነት መንቀሳቀስ እንዲችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው ተደረገ። የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት አን ሳን ሱቺን ጨምሮ ከሞላ ጎደል በነጻነት በመንቀሳቀስ በ 2012 ዓ.ም ምርጫ በሀገሪቱ ከሚገኙት ከተሞች በዋና ዋናዎቹ ላይ ተወዳድረው በአሸናፊነት ወደ ፓርላማ ገብተዋል። ሌሎች የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮችም በአሁኑ ሰአት ወደ አገራቸው ተመልሰው በመታገል ላይ ይገኛሉ።

ሀገሪቱ ውስጥ እይታየ ያለውን የፖለቲካ ለውጥ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ለነጻነት ሲንቀሳቀስ የነበረው የስደት መንግስት በ September 2012 ዓ.ም እራሱን ማክሰሙን (dissolve) አስታውቋል። አባል ድርጅቶቹም ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በፖለቲካው ለመሳተፍ የበኩላቸውን እያደረጉ ነው። ምንም እንኳን የሀገርቱ ችግር ገና ብዙ የሚቀረው ቢሆንም በተሻለ ጉዞ ላይ ትገኛለች።

አገራችን ኢትዮጵያ በወያኔ ያፓረታይድ  ስርዓት ስር እየማቀቀች በምትገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት። ተቃዋሚ ሀይሎች በየፊናችን የምናደርገው ሩጫ ወደለውጥ መንገድ ሊመራን ካለመቻሉም አልፎ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ግራ በማጋባትና ተስፋ በማስቆረጥ ለጨቋኙ የወያኔ መንግስት የተመቸ ሁኔታ ፈጥሮለታል። ለዘመናት ተመሳሳይ ነገሮችን በማድረግ የተለየ ውጤት ከመጠበቅ አባዜ በመውጣት ለየት ያሉ አማራጮችን መቀበል ወይም ማቅረብ አራሱን የቻለ የፖለቲካ ጥበብ መሆኑን በመገንዘብና ልዩነታችንን በማጥበብ ከላይ ባጭሩ ለምሳሌነት የቀረበውን የበርማ ህዝብ የትግል ታሪክና የሌሎችንም ተሞክሮ በምሳሌነት በመውሰድ ኢትዮጲያዊነትን መሰረት ያደረገ አንድ ወጥ አመራር ያለው የተባበረ ሀይል (የስደት መንግስት እንደ አማራጭ)  በማቋቋም ስርአቱን ማስወገድ ወይም ማስገደድ የወቀቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው።

 

ትግሉንና ድሉን የጋራ እምናደርገው፤ ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ያንድነትና የአማራጭ ሃይል ነጥሮ ሲወጣ በመሆኑ ዛሬም እንደወትሮው ለሀገር ወዳድና ነጻነት ናፋቂ ወገኖችኖች፤ እንዲሁም ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በዚህ ዙሪያ አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደርጉ ሃገራዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በተመሳሳይ የተለያዩ ድርጅቶች አሉኝ የሚሏቸዉን የአማራጭ መፍትሄዎችን ለህዝብ ለውይይት ይፋ እንዲያደርጉ እንጋብዛለን።

 

የኢትዮጵያ በሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት በመርህ ደረጃ የወያኔ/ኢሕአደግ ስርአትን ማስወገድ መተካት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ገጽታዎች እንደሁኑ በጽኑ ያምናል። ይህንን ጭብጥ በተመለከተ ለመቋጫ ይረዳ ዘንድ  በሃገር ውስጥ ከሚገኙ የፖለቲካ ድረጅት መሪዎች ከተናገሩት ለናሙና ይህንን በመጫን ያድምጡ http://goo.gl/S2g7Ep

 

 

ትግሉንና ድሉን የጋራ እናድርገው!

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት

ያልተገራውን ስርዓት የማዳን ርብርብ

$
0
0

ከጌታቸው ሺፈራው

ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ደቡብ አፍሪካ ያሉ አገራት ነጻነታቸውን አግኝተው የዓለም ቀጣይ ኃያል አገራትን ተቀላቅለዋል፡፡ አብዛኛው የዓለም ማህበረሰብ ዴሞክራሲያዊ በሆኑ ስርዓቶች ለመተዳደር እድል አግኝቷል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ግን ስልጣን ከያዘ ማግስት በህግ ፈቀድኩት ያለውን የሚዲያ ነጻነትን ጨምሮ በማፈን፣ በዛው በርሃ ውስጥ በነበረው ‹‹ውርጋጥነቱ›› ቀጥሏል፡፡ አሁንም ቢሆን ‹‹ሲቪል›› ነኝ ብሎ የሚያስበው በአፈሙዝ ነው፡፡ በአንድ በኩል ዴሞክራትነቱን እያስወራ በተግባር ግን የአምባገነኖች ቁንጮ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በአጠቃላይ በርሃ ከነበረበትም በባሰ አሁንም እንዳፈተተው በኢትዮጵያውያን ላይ ስልጣኑን የሚያስጠብቅለትን እርምጃ መውሰዱን ቀጥሏል፡፡ ኢህአዴግ አልተገራም፡፡
Haile
እንዲያም ሆኖ ግን ሌሎቹን ስለ መግራት ያወራል፡፡ ትናንትና ማታ (ነሐሴ 19/2006) በልሳኑ ያሳየው ‹‹ያልተገሩ ብዕሮች›› የተሰኘ ፊልም የሚያሳየውም ይህንን ከአለ-አቅም መንጠራራትን ነው፡፡ ኃይሌና ገና በጋዜጠኝነት ተመረቁ የተባሉ ወጣቶች የእነ ፕሮፌሰር መስፍንን፣ የእነ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራን፣ የእነ ተመስገን ደሳለኝን፣ የእነ ዓለማየሁ ገላጋይን ብዕር ‹‹ሊገሩ›› ሲፍጨረጨሩ ማየት በእጅጉ የሚያስገርም ነው፡፡

ሲያሸንፍም በስሜት የዘለልንለት፣ ሲሸነፍ የተሸነፍንለት የድሮው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ከስርዓቱ ጋር አብሮ ‹‹ሚዲያ ኑክሊየር ነው!›› ሲል ‹‹አጥፊነቱን›› መስክሯል፡፡ በእርግጥ ኃይሌ በህዝብ ላይ ሲቀልድ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ከአመት በፊት በሰይፉ ፋንታሁን የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ስለ መምህራን የደሞዝ ጭማሬ ተጠይቆ የመምህራኖቹ የደምወዝ ጭማሬ ቅብጠት መሆኑን ተናግሯል፡፡ ከአንድ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ እንዳገኘሁት ከሆነ ኃይሌ ገብረስላሴ ለስርዓቱ አፋኝነትም በግልጽ ድጋፉን እያሳየ እንደሚገኝ ነው፡፡ የመረጃ ምንጩ እንደጠቀሰልኝ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የሚታጎሩበት የካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማስፋፊያ የተሰራው በኃይሌ ገብረስላሴ የገንዘብ እገዛ ነው፡፡ ለዚህ ፖሊስ ጣቢያ ካቴና ከውጭ አገር ያስመጣውም ኃይሌ ገብረስላሴ እንደሆነ ምንጩ ገልጾልኛል፡፡

በርካታ ኢንቨስትመንቶቹ በገዥው ፓርቲ ይሁንታ እንደሚቀጥሉ ያመነ የመሰለው ኃይሌ ትናንትናውም ቢሆን የስርዓቱ መሳሪያ ሆኖ ሚዲያውን ሲተች ያመሸው ከራሱ የኢኮኖሚ ጥቅም አንጻር ነው፡፡ ኃይሌ ከኑክሊየርም በላይ አፍራሽ ነው ያለውን ሚዲያ መተቸት የጀመረው በአንድ ዘገባ ምክንያት አንድ የውሃ ፋብሪካ መዘጋቱን በመግለጽ ነው፡፡ ኃይሌ ይህን ወደ ራሱ አስጠግቶ ሲያጠናክርም ‹‹በእኔ ላይ በመጻፉ ልጆቼ፣ ቤተሰቤ ያያሉ፡፡ በስሬ 1500 ሰራተኛ አለ፡፡ አዋሳ፣ ባህርዳር፣…ያሉት ሰራተኞችም ያዩታል፡፡ ሰራተኞችም ይህ ሰው ምን ነካው ይላሉ፡፡ ቢዝነስ ‹ኮላፕስ› ያደርጋል፡፡›› ሲል ነበር የገለጸው፡፡ እንግዲህ ገና የኃይሌ ልጅ ትሰማለች ተብሎ፣ ሰራተኞቹ ‹‹ምን ነካው!›› ስለሚሉ፣ ‹‹ቢዝነሱ ኮላፕስ›› ስለሚያደርግ ኃይሌ ምንም ያህል ቢያጠፋ ሚዲያው ትንፍሽ ላይል ነው ማለት ነው፡፡ ይህን የኃይሌን ሀሳብ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት ውስጥ መምህር ነች የተባለችውም ‹‹የሰዎች ጓዳ (መቼስ ሚስጥር ማለቷ ነው) ሚዲያ ላይ መውጣት የለበትም፡፡›› ስትል ሀሳባቸውን ተሰብስበው የተስማሙበት አስመስላዋለች፡፡ በቃ ሚዲያ ሚስጥር የማውጣት ሚናውን በእነ ኃይሌ ዳኝነት ተቀማ ማለት ነው፡፡ እነ ኃይሌና ዶክተር አሸብር ለስርዓቱ ክንድ በሆኑበት በዛው ፊልም ላይ ካሳ ተከፍሏቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ‹‹ኃይሌ ገብረስላሴ ሊወዳደር ነው፣ ዶ/ር አሸብር አምባገነን ነው›› የሚሉ ዜናዎችና ትችቶች ሳይቀር በአጥፊነት የተፈረጁላቸው፡፡

ሚዲያ ከሌለው መንግስት ይልቅ መንግስት የሌለው ሚዲያ ይሻላል የሚል መርህ የሚከተሉትን የእንግሊዝና የአሜሪካን ዴሞክራሲ አውቀዋለሁ ያለው ኃይሌ ገብረስላሴ ‹‹ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው›› በሚል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሚዲያ ‹‹ያልተገራ›› በመሆኑ በሚያሳስብ መልኩ ያ ስቅስቅ ብሎ ያለቀሰለትን ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹ራዕይ›› እናስጠብቃለን የሚሉ አካላት እርምጃ እንዲወስዱ ፍርደ-ገምድልነቱን አሳይቷል፡፡

ስርዓቱን የማዳን እርብርብ

በዚህ ፊልም ላይ ስለ ሰራዊት ፍቅሬ የፍቅር ደብዳቤ መጻፍ፣ በሞቅታ ስለሚጨፍሩት አርቲስቶች አስተያየት መስጠት በአውዳሚነት አስፈርጇል፡፡ ይህ የሆነው እነዚህ ‹‹ልማታዊ አርቲስቶች›› ያልተገራው ስርዓቱ ቅቡልነት እንዲያገኝ ሳይታክቱ የሚሰሩ በመሆናቸው ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ‹‹አባይ ለፕሮፖጋንዳ አይዋል›› ማለት ብሄራዊ ደህንነትን ተጻርሮ የቆመ አስመስሏል፡፡ ከምንም በላይ ስርዓቱ ለስልጣኑ መሰረት አድርጎ የሚወስዳቸው አንጓዎች በሚዲያው ሊነኩ የማይገባ ‹‹ቀይ መስመሮች›› ተደርገው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ መቼም አንድ ተቃዋሚ መንግስትን የተቆጣጠረውን ፓርቲ ከስልጣን አውርዶ መንግስት ለመሆነ ነው የሚሰራው፡፡ ያልተገራው ‹‹መንግስት›› መሳሪያ የሆኑትና እነሱም ከስርዓቱ ጋር በጥቅም ከመጋራታቸው ውጭ የተገራ ነገር ያልታየባቸው ነገር ግን የተገሩትን ሲያጣምሙ የታዩት የፊልሙ ሰሪዎች ግን ‹‹ህዝብ ሌላ መንግስት ለማየት ፍላጎት አለው›› የሚለውን ከኑክሊየርም በላይ አጥፊ ነው ብለው ፈርጀውታል፡፡ ጋዜጠኝነት ‹‹በራዲካል ሮል›› ፖሊሲ የማስቀየር ሚና አለው ብለው ሳይጨርሱ ‹‹የብሄር ፌደራሊዝሙ እርምት ያስፈልገዋል›› የሚልን መካሪ ጽሁፍ በአሉታዊነት ለፈውታል፡፡ የ‹‹ብሄር ፖለቲካው›› ላይ ምንም አይነት ትችት መቅረብ የለበትም አይነት ያልተገራ አቋማቸውን ዳግመኛ አሳይተውበታል፡፡ ጠባብ አለመሆናቸውን ማሳመን ሲያቅታቸው ጠባብነታቸውን የሚተቹትን ሚዲያዎች ያልተገሩ ሲሉ ወርፈዋቸዋል፡፡ እነሱ አንዳንድ ተቋማት ስለ ‹‹መንግስት›› ያወጧቸውን መልካም የሚባሉ ነገሮች አመት ሙሉ እንደማይደጋግሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ስለ ድህነት፣ የመፈንቅለ መንግስት ስጋትና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ያወጧቸውን ሪፖርቶች የግል ሚዲያው እንዳያወጣ ቅድመ ክልከላ አውጀዋል፡፡ ማጎሪያ ቤት ውስጥ ያለውን ስቃይ ማስተባበል ሲያቅታቸው ‹‹ማረሚያ የሚያስፈልገው ማረሚያ ቤት›› የተሰኘን መካሪ ጽሁፍ በህገ ወጥነት ፈርጀውታል፡፡

Dr asheber pimping for his own presidency (Video)ኢህአዴግ የውድቀት ዋዜማ፣ ኢትዮጵያ ለምን አሚሶንን ተቀላቀለች? ፍትህ በሌለበት የፍትህ ሳምንት፣ ለአክራሪነት አስተማሪው ማን ነው? ለተሰኙት መልስ መስጠት ሲያቅታቸው፣ እውነት ሆኖ እንቅልፍ ሲነሳቸው በጸረ ሽብር ህጉ አውድ አሸባሪ ብለው ፈርጀዋቸዋል፡፡ በጣም የሚገርመው አብዛኛዎቹ ጽሁፎች በጥያቄ የቀረቡና ኢህአዴግን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርጉ ሲሆኑ ኢህአዴግ ግን ቀድሞ ‹‹እኔን ነው›› ብሎ ለራሱ ወስዷቸዋል፡፡ ሚዲያው ገለልተኝነቱን እያሳየም ቢሆን እነሱ የአንድ አካል አፈ ቀላጤ ይሉታል፡፡ ለዚህ እንደ ማስረጃ ያቀረቡት ደግሞ ‹‹ማንን እንመን?›› በሚል የወጣን አንድ ጽሁፍ ነው፡፡ ይህ ጽሁፍ ዶ/ር ብርሃኑንና በረከት ስምዖንን ያፋጠጠ ጽሁፍ ነው፡፡ ከሁለቱ አካላት ማንንን እንመን ተብሎ በማነጻጸሪያነት የወጣውን ይህን ጽሁፍ ራሱን የማያምነው ኢህአዴግ ‹‹እኔን ነው የማያምኑኝ›› ብሎ ጥፋቱን ቀድሞ ወስዶ ‹‹የአንድ አካል አፈቀላጤ ሆነዋል›› ሲል ይከሳል፡፡

በአጠቃላይ ‹‹ያልተገሩ ብዕሮች›› በሚል የቀረበው ፊልም የኢህአዴግን ፖሊሲ መተቸት ህገ ወጥነት እንደሆነ የታየበት፣ የስርዓቱ ዋና ዋና የስልጣን ማቆያ ፖሊሲዎችን መንካት ስርዓቱን ሊያፈራርሰው እንደሚችል ባልተገራ አንደበት የተነገረበት ፊልም ነው፡፡ በፊልሙ ተዋናይ የሆኑት አካላት እዛው ፊልሙ ላይ ‹‹ፌቨር›› እየተሰራላቸው በትውልዱ ላይ ሲፈርዱ ስርዓቱን ለማዳን እርብርብ ላይ እንደሆኑ በግልጽ ለማየት ተችሏል፡፡ ሁሉንም ነገር ከኢኮኖሚ አንጻር ሲቃኝ ያመሸው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ‹‹ጦርነት ከፈታው ወሬ የፈታው›› በሚል ኃይል በእጁ ለሆነው ያልተገራ ስርዓት በቅኔ እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡ የስፖርት ጋዜጦች ድረስ ተሂዶ የተደረጉበት ጥቃቅን ትችቶች በህገ ወጥነት የተፈረጁለት ዶክተር አሸብር በግልጽ አገልጋይነቱንና ስርዓቱን ለማዳን የቆመ መሆኑን አሳይቷል፡፡ ፓርላማ ላይ ኢትዮጵያ ምንም አይነት ጥቅም ሳታገኝ ለጅቡቲ ውሃ የሚለግሰውን አዋጅ ከተቃወሙት መካከል ዶክተሩ አንዱ እንደነበሩ በሚዲያ ተገልጾ የነበር ቢሆንም ዶክተሩ ግን ስለ አዋጁ ያላቸውን ይሁንታ ሲገልጹ ‹‹ከእኛ ጋር ሳይደርስ ለምን አይጸድቅም?›› የሚል ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የህዝብ ተወካይ ነኝ ብሎ አንድን ህግ ‹‹ፓርላማ ሳይመጣ ለምን ራሱ ኢህአዴግ አያጸድቀውም›› ማለት ስርዓቱን ለማዳን እርብርብ ላይ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

በአጠቃላይ በፊልሙ ላይ በአሉታዊነት የተፈረጁት ጽሁፎች ቢበዛ መካሪ ቢሆኑ እንጂ ይህ ነው የሚባል ‹‹አለመገራት›› አይታይባቸውም፡፡ ነገር ግን ባለመገራቱ ሳይነካ የሚደነብረውን ስርዓት ይበልጡን የሚያስበረግጉ መሆናቸው የሚያስገርም አይሆንም፡፡
እነ ኃይሌ ዴሞክራሲን አይቼባቸዋለሁ ባሏቸው አገራት ሚዲያ አራተኛ የመንግስት አካል ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ሶስቱ የመንግስት አካላትም ሆነ መንግስት ባለመኖሩ አራተኛ መንግስት ሊሆን አልቻለም፡፡ ከዚህ ይልቅ መንግስት በሌለበት፣ ካልተገራ ዘመናዊ የቤተ መንግስት ወንበዴ ጋር ግብ ግብ የሚገጥም ብቸኛው የመንግስት አካል ሆኖ ለማገልገል ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ይህ ደግሞ መንግስትም ሆነ የመንግስት አካላት እንዳይኖሩ የሚፈልገውንና ልጥ ሲያይ እባብ ነው ብሎ የሚደነብር ያልተገራ ስርዓት እጅጉን አስደንብሮታል፡፡ ስለ ተገራና ስላልተገራ ብዕር ይህ ነው የሚባል እውቀት የሌላቸው፣ የማያገባቸው እነ ኃይሌም ያልተገራው ስርዓት ጋር የተጋሩትን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሉ ስርዓቱ በሚዲያው ላይ እርግጫውን በመሰንዘር እራሱን እንዲያድን እርብርብ አድርገዋል፡፡ የእነ ኃይሌ ምክር ስርዓቱ እንደለመደው እንዲራገጥ የሚገፋፋ ቢሆንም ማዳን አለማዳኑንም ሆነ እነሱ በትውልዱ ላይ እየፈጸሙት ያለውን በደል ግን ታሪክ የሚፈርደው ይሆናል፡፡


የማለዳ ወግ …የኢቲቪ ”ያልተገሩ ብዕሮች ”ዘጋቢ ፊልምና ያልተገራው አቀራረብ ….

$
0
0

ነብዪ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

ከሁለት ሰአቱ የኢቲቪ ዜና አወጃ ተከትሎ የቀረበውን ” ያልተገሩ ብዕሮች ” ዶክመንተሪ በደረቁ ሌሊት ድጋሜ ስርጭቱ ተከታትየ ጨረስኩት … ላፍታ እንደተጠናቀቀ ዝም ፣ ጭጭ አልኩና በሃሳቤ በህዝብ ገንዘብ ከፍተኛ ወጭ እየተደረገባቸው የሚሰራጩትን የመንግስት የህትመት ጽሁፍና የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃንን አሰብኳቸው … በምናብ ብዙ ርቄ ሔጀ በዶደመ ፣ ባልተገራ እና በተባውና በተገራው ብዕር ውስጥ ራሴን አትኩሮት ሰጥቸ የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶች በሃሳብ ተመላለስኩባች ! ሰፊ ሽፋን ያለውን ኢቲቪና ራዲዮኑን ፣ በየቀኑ እየታተሙ የሚወጡትን እነ አዲስ ዘመንን ጋዜጣንና የመሳሰሉት እሰብኳቸው …አስቤ አሰላስየ ወደ ደረስኩበት ድምዳሜ ከማቅናቴ በፊት ግን በ”ያልተገሩ ብዕሮች ” ዘጋቢ ፊልም ዙሪያ የታዘብኩትን ቀዳሚ አድርጌ የተሰማኝን ላካፍልዎ ወድጃለሁ…
haile Gebresilase
” ያልተገሩ ብዕሮች ” …

…ስለ ጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ከባለ ሙያዎች የቀረበው መግለጫ ዘጋቢ ፊልሙ የተነሳበትን አላማ በሚያሳካ መልኩ የተጠናቀረ ስለሚሸት ፣ ስለሚመስል አልተመቸኝም። ከሙያው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ወገኖች የሰጡት አስተያየት የግል አመለካከታቸው ነውና ብዘለውም ባዕድ በሆኑት ሙያ የሰጡት ግምገማ አልተዋጠልኝም። “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ” ሆኖብኝ ልቀበለው አልተቻለኝም ፣ አልወደድኩትም ! ምስክርነት ግምገማቸውን ያለወደድኩት “የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶች አያጠፉም !” ከሚል እሳቤ ተንደርድሬ ሳይሆን ላጠፉት ጥፋት ቅጣት መቅጫ ወፈር ያለ ህግ ተቀምጦ በህግ መጠየቅ ሲገባ ጅምላ ነቀፋን ማቅረብ ባልተገባቸውን ነበር በሚል ነው ። የመንግስት ሃላፊዎች የሰጡት ገለጻና ማብራሪያም የተጻፈውን ህገ ደንብ ከማብራራት አልፎ ጥፋት እየተካሔደ በሆደ ሰፊ መታለፉንና አሁን ግን መንግስት ማምረሩን የሚያስረዳ ከመሆን ያለፈ ፍሬ ነገር የለውም ።
ብቻ ….ገና ከጅምሩ ዘገቢ ፊልሙ ድምጻቸው በሚስብ ጋዜጠኞችና በምስል ቅንብር ደምቆ ፣ መልዕክቱ ግን በህግ በተያዙና በሚፈለጉ ተጠርጣሪ የመገናኛ ባለሙያዎች ላይ ከፍርድ በፊት ጥፋተኝነትን የሚለድፍ ሆኖ ታይቶኛል። ሳጠቃልለው የ “ያልተገሩ ብዕሮች ” ዘጋቢ ፊልም ፍርድ ቤት ገና እያየው ባለውና ባልወሰነባቸው በጦማሪ ጸሃፍት ፣ በአምደኞች እና በነጻው መገናኛ ብዙሃን የሚቀርበውን ክስ ለማጠናከር የተሰራ መሆኑ ያሳብቃል ፣ ወንጀሉን ለማጠናከርም ለውንጀላው ምስክሮች በመንግስት ቴሌቪዥን የሰማሁትን ያህል ተሰማኝ !
ከዘመነ ጃንሆይ ፣ ዘመነ ደርግና ዘመነ ኢህአዴግ የመንግስትን አቋም እያራመዱ በጣም በወረደ ዋጋ ለነዋሪው በየቀኑ እየታተሙ ይቀርባሉ ። ዳሩ ግን ትናንትም ሆነ ሃገር ምድሩን በሚሞላ ቁጥር የመታተማቸውን ያህል ቁም ነገር አላቸው የሚባሉት ገጾች የስራ ፈላጊዎችን ቀልብ የሚስቡት ማስታወቂያዎችና የጨረታ ማስታወቂያዎች ብቻ መሆናቸውን ቢያንስ በደርግና በኢህአዴግ ዘመን አውቃለሁ ። ብዙሃኑን ነዋሪ እውነትንና ጠቃሚ መረጃን ቢይዙ አንኳ አጓጉተውት አይገዛቸውም !

ወደ ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ መስኩም ስናመራ የምናየው እውነታ ተመሳሳይ ነው ። ዘመኑ የመረጃ ነው ፣ ዘመነኛ የመገናኛ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ያንጠለጠለው የታደለው ቀርቶ በስማ በለው ከሚነገሩት መስማት የሚናፍቀው የሃገሬ ሰው ቁጥር የትየለሌ ነው። ጭብጥን መረጃ ከሃላፊት ጋር ይዘው ፈርጀ ብዙ በሆነ መንገድ የሚሰራጩ መረጃዎችን በፍቅር የሚከታተለው ወገን መረጃ እንደ እለታዊ ፍጆታው የቆጠረው ይመስላል። ዛሬ ዛሬ ከስልጡን ለውጥ ፈላጊ እስከ መደዴው የኔ ቢጤ ያለ መረጃ መተንፈስ አይቻለውም።
አትኩሮት ሰጥቶ ከሚከታተለው የራዲዮ ፣ ቲቪ መርጦ ጀሮውን ይሰጣል። ለህትመት ውጤት ለሆኑት ጋዜጣና መጽሄቶችን ያለው እየተጋፋ ገዝቶ ፣ የሌላው እየተከራየ መረጃን ይመገባል። ያሻውን ይመርጣል ፣ ያሻውን አንቅሮ የመትፋት ያህል አይቀርባቸውም !
በ ” ባልተገሩ ብዕሮች ” የቀረቡት ባለሙያዎች ያልመረምሩት እውነታ ይህ ነው ። በጥናታዊው ዘገባ የቀረቡት ባለሙያዎች በዋናነት የህዝቡን ነጻ መረጃ የማግኘት መብት አክብረው ሙያዊ ” የተገራ ያልተገራ ብዕር ” ግምገማ አድገው አላሳዩንም ።
ይልቁንም ቀርበው የደሰኮሩበት የህዝብን ገንዘብ መሰረት አድርጎ ከሚንቀሳቀው ኢቲቪ ይልቅ እየፈራ እየተባም ቢሆን ከጽፈኛ ተቃዋሚዎች ልሳንነት የሚደበውን ኢሳትን ይከታተላል ፣ በመንግስት ደጋፊነት የሚፈረጀውን ኢቢኤስን ደረቱን ገልብጦ ማየት ይፈልጋል። የኢትዮጵያ ራዲዮን ትቶ ጀርመን እና አሜሪካን ብሎም በሃገር ቤት የመንግስት እጅ የለባቸውም የሞላቸውን የተመረጡ የኤፍ ኤም አዳዲስ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ያምናል ፣ ማየትና መስማትን ይመርጣል። የዚህ ሁሉ የነዋሪው ግልጽ ሽሽት ምን ይሆን የሚለው ዳሰሳ መላ ምት ውጤት በዘገባ በቀረቡት ባለሙያዎች ቢነገረን ያምር ነበር ። ” ነበር ባይሰበር ” …

ይህ የሆነው ለምን ይሆን ? ብዙሃን ነዋሪ ምርጫ እንዲህ የሆነው ምን ቢሆን ነው ? እውን ውስጣቸው ባልተገራ ብዕር የታጨቁ መረጃዎች ስለተሞላ ነው ማለት ይቻል ይሆን ? አይመስለኝም በሚል የሚሸፈን ሳይሆን ህዝቡ የፈለገውን ማየት መስማት አይሻምና ነው ባይ ነኝ !…”ያልተገሩ ብዕሮች” ምንጭ እያስተዋለ መርጧልና ያለተገራው ብዕር በሰፊው ያለበትን ቦታ አሳምሮ ተረድቶታል … ! እናም የማይፈልገውን አይቀርበውም ኩሩው ህዝብ እንዲህ ነው !
አይ ” ያልተገሩ ብዕሮች !” ? ጊዜ ደጉ ፣ መስናት ፣ ማየት ፣ መናገር መልካም !
ሰላም ለሁላችሁ !
ነቢዩ ሲራክ

ነጻነትን በማሳጣት ዜጎችን ለስቃይ፣ለእስራትና ለስደት የዳረገውን መንግስት ልናስወግደው ይገባል

$
0
0

ገዛኸኝ አበበበ ከኖርዌ ሌና)

BeFunky_BeFunky_CIMG1882.jpg

ወያኔ ኢህአዲግ የስልጣን ወንበሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ በስልጣን በቆየባቸው በሃያ ሶስት አመታቶች በየጊዜው በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና ጭቆና ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱ በአደባባይ የሚታይ እውነታ ሲሆን ከዚህም ጨቋኝና ገዳይ ስርዓት የተነሳ የሀገሪቷ ዚጓች  በሀገራቸው ላይ በሰላም መኖርና የነጻነትን ሀየር መተንፈስ በማይችሉበት ክፉ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ::ለሰው ልጅ ነጻነቱ እየተገፈፈና መብቱ እየተረገጠ እንደ መኖርን የመሰለ አስቀያሚ ህይወት ያለ አይመስለኝም::ስለዚህ ነው በአሁኑ ጊዜ ከማንኛውም ጊዜ በተለየ መልኩ በሀገራችን ኢትዮጵያ  ገበሬው፣  ተማሪው፣  ፣ አስተማሪው ፣ ነጋዲው፣ ጋዜጠኛው ፣ ስፖርተኛው፣ ዘፋኙ፣ አርቲስቱ፣ ወዘተ……በማንኛውም እርከን ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገራቸው ላይ በነጻነት መኖርን ስላልቻሉ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሀገራቸውን ትተው እየወጡ በየጊዜው ለስደት ሲዳረጉ የሚታዩት::

ከሰሞኑ እንኳን እንደተመለከትነው አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ይገኙ የነበሩ ቁጥራቸው አስራ ሁለት የሚሆኑ ጋዜጠኞች የወያኔ መንግስት ስራቸውን እንደ ሚገባ እንዳይሰሩና በነጻነት አላንቀሳቅስ ስላላቸው ሀገራቸውን ጥለው ለስደት እንደተዳረጉ ሁላችንም የተመለከትነው ነገር ነው በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸ ቡዙ የሆኑ ጋዜጠኞች በአንድ ጊዜ ውስጥ ሀገራቸውን ጥለው ለስደት መዳረጋቸው ቡዞዎቻችንን የሚያስገርምና የሚያስደነግጥ ክስተት ሊሆን ይችላል ነገር ግን ለሰዎች ሁሉ የስደት ምንጭ የሆነው የወያኔ መንግስት ከስልጣኑ እስካልተወገደ ድረስ አፈና፣ እስራት፣ግድያው ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ በየትኛውም እርከን ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች መቺም ቢሆን ለስደት መዳረጋቸው የማይቀር እውነታ ነው :.

ሌላው አንድ የታዘብኩት ነገር ሀገራቸውን ጥለው ለስደት ስለተዳረጉ ስለእነዚህ ጋዜጠኞች  በተለያዩ ሰዎች የተጻፉትን ጹሁፉችን ተመልክቻለው  አንዳንድ ሰዎችም የእነዚህ ጋዜጠኞች ከሀገር ለቁ መወጣት ስላልተዋጠላቸው የተለያዩ ትችቱችንና አስተያየቶችን ሲጽፉና ሲሰጡ ተመልክቻለው መቼም ቢሆን ማንኛውም ሰው በሀገሩ ላይ መማርን ፣መስራትንና፣ መኖርን የሚጠላ ሰው ያለ አይመስለኝም :: እነዚህን ጋዜጠኞች ከሌሎች ጋዚጠኞች ጋር እያነጻጸሩ ለምን እንደ እገሌ እዛው ሀገር ቤት ቁጭ ብለው አልታሰሩም ነበር ብሎ መፍረድ አግባብነት ያለው ፍርድ አይመስለኝም :: ማንም ሰው በሀገሩ በነጻነትና በሰላም መኖር ቢሆንለት ስደትን አይፈልግም :: ምክንያቱም ዜጓች በሀገራቸው በተረጋጋ ሁኔታ ለመኑር የሚያስፈልጋቸው  ዋንኛውና ቁልፉ ነገር ሰላም እና ነጻነት ነውና::ማንኛውም ሰው በሚኖርበት ሀገር በሚኖርበት ሰፈር ወይም አካባቢ እና በሚኖርበት ቤት ውስጥ ሳይቀር በሰላምና በነጻነት መኖርን ይፈልጋል:: ነጻነት በምንም ዋጋ ሊተመን የማይችል ትልቅ ጸጋ ነውና:: ሰላም እና ነጻነት በሌለበት ሀገር የሚኖሩ ዜጓች፣   መብታቸው ይረገጣል ፣ ነጻነታቸው ይታፈናል  ዜጓች ለእስር፣ ለሞት፣ እና ለስደት ይደጋሉ::በሀገራችን ኢትዮጵያ የምናየውም በእነዚህ አስራ ሁለት ጋዜጠኞች ላይ የደረሰው ይሄው ነው::

 እንደ አለመታደል ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያም በአለም ላይ ካሉት ሀገራት በግንባር ቀደምነት  የሰው ልጆች ነጻነታቸውን እና መብታቸውን ከሚገፈፉበት ሀገር ተርታ እንደምትገኝና የሀገሪቷ ዜጓች በጨቋኙ ገዥ ስርዓት ነጻነታቸውን ተገፈው ባሪያ ሆነው የሚኖሩበት ሀገር እንደሆነች በየጊዜው ከሚወጡ አለም አቀፍ ሪፖርቶች መረዳት ይቻላል::::

 ዜጓች በከፍተኛ ሁኔታ ለስደት እየተዳረጉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደረገው አፈና፣ እስራት እና ግድያው በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ የሚገኝ ሲሆን ይህም በገሃድ እየታየ ያለ እውነታ ነው :: በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች በፋሺስቱ የወያኔ ቡድን ነጻነቱ እየተገፈፈና መብቱ እየተረገጠ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከእንግዲህ ወዲህ ይሂን የወረበሎች ቡድን እሽሩሩ እያሉ የመኖር አቅም ያለው አይመሰልም :.: በአሁኑ ጊዜ ከየአቅጣጫው ከሚሰሙ ነጻነት ናፋቂ የኢትዮጵያኖቸ ሕዝብ ጩኸት ድምጽ መረዳት እንደሚቻለው ሕዝባችን ለወያኔያዊ አንባገነን ስርዓት መገዛትን የጠላበትና ከመቺውም ጊዜ በተለየ መልኩ እምቢ አሻፈረኝ ብሎ ነጻነቱን ለማስመለስ በአንድነት ለመቋም የተነሳበት ዘመን ላይ የደረሰን በሚያስመስል መልኩ ከየቦታው የሚሰማው የነጻነትና የሰላም ናፋቂዎች የጀግንነት ድምጽ ምስክር ነው::

በቅርቡ እንኳን እንደምናየው የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሀፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን ታግተው በወያኔ እስር ቤት ታስረው በግፍ እየተሰቃዩ እንዳለ ይታወቃል የነጻነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው በወያኔ ሴራ ከየመን ታግተው በወያኔ እጅ ላይ መውደቃቸው ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔን አውሬነት በይበልጥ በመረዳት ከዳር እስከ ዳር በአንድነት መቋሙን እያስመሰከረ ሲገኝ የፖለቲካ ግለቱም ጨምሮ የአረመኔው የወያኔን ቡድን በከፍተኛ ሁኔታ አርበድብዶት እንደሚገኝ ወያኔ ከሚሰራው ስራና ከሚያደርጋቸው ድርጊቷች ማወቅ ይቻላል::የአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ተከትሎ  እየከረረ ያለውን የሕዝብን ቁጭትና ቁጣ ለማጥፋት በሚያስመስል መልኩ ይኼ አረመኔው መንግስት በአሁኑ ጊዜ በሀገር ቤት በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት በህጋዊ መንገድ እንኮን ሳይቀር እየታገሉ ያሉትን ሰዎች ከየመንገዱ እየለቀመ እስር ቤት አስገብቶ እያሰቃያቸው እንዳለ ይታወቃል ::ይህንንም ተከትሎ  ሁላችንም እንደምናውቀው  የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው ምክር ቤት አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና የሕዝብ ግንኙንት ኃላፊ አቶ አብረሃ ደስታና የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ የሸዋስ አሰፋን ጨምሮ ሌሎችም እጅግ ብዙ ለየጻነታቸው የሚታገሉ ኢትዮጵያን ወገኖቻችን  የወያኔ መንግስት በግፍ  አስሯቸው እያሰቃያቸው እንደሚገኝ ይታወቃል::

ይኼ መንግስት እሱን  የሚቃወሙትን ሰዎችንና በድፍረት እየተጋፈጡት ያሉትን የፖለቲካ መሪዎች አአሸባሪ የሚል የታርጋ ስም እየለጠፈላቸው ወደ እስር ቤት መወርወር የተጠናወጠው ክፉ ባህሪው ሆኖል:: የፖለቲካ መሪዎችንና የፖለቲካ ሰዎችን ማፈንና እየያዙ ወደ እስር ቤት መወርወር ይበልጥኑ ትግሉን እያከረረውና የኢትዮጵያን ሕዝብ ይበልጥኑ ለነጻነቱ በመታገል ለድል እያነሳሳው  ነው እንጂ ፈጽሞ ከትግል ወደ ኋላ እይመለሰው እንዳይደለ የወያኔ ባለስልጣኖች ጠንቅቀው ሊያውቁት የሚገባቸው ነገር ይመስለኛል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነትን ተጠምቷል ::Freedom is more than food  በአሁኑ ሰአት በሀገር ቤትም ሆነው በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ይሁኑ ወይም በውጭ ሆነው በሁለገብ ትግል እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች አላማቸውም ሆነ ጥያቄያቸው አንድ ነው የስልጣን ወይም የገንዘብ ሳይሆን የነጻነት ጥያቄ ነው :: የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት ያስፈልገዋል   ::እኛም  ሰላምና ነጻነት የናፈቀን ህዝቦች መብታችንን ለማስከበር ለነጻነት ከሚታገሉ ድርጅቷች ጎን በመቆም ለነጻነታቸው ሲታገሉ  በወያኔ አንባገነን ትህዛዝ ወደ እስር እየተወረወሩ እና በግፍ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖቻችን  ከመንኛውም ጊዜ በተለየ መልኩ ሀገራዊ ስሜት ተሰሞቶን ልንጮህላቸውና የእነሱንም ፈለግ በመከተል ከሁለት አስርት አመታት በላይ የዜግነት መብታችንና እየረገጠና ነጻነታችንን እያፈነ ህዝባችንን ለስደት እያደረገ ያለውን ያለውን ይኼን ሰይጣናዊና አረመናዊ ስርዓት በማንኛውም መንገድ በመታገል፣እውነተኛ ሰላምና ነጻነት በኢትዮጵያ ምድራችን እንዲመጣ ለማድረግ የወያኔን መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዳግም እንዳይነሳ  አከርካሪውን ሰብሮ መጣል  ይጠበቅብናል እላለው::የዜጎች ነጻነት ማጣት ፣መሰቃየት፣ መታሰርና መሰደድ ግድ ብሎን እያንዳንዳችን ትግላችንም ሆነ አላማችን በእውነተኛ የነጻነት ትግል በመነሳት የወያኔን መንግስት ጥሎ ነጻነትን ለመቀናጀት በኢትዮጵያዊ  ስሜትና ተነሳሽነት ከሆነ ድልን የምንቀድጅበት ቀን ሩቅ መስሎ አይታየኝም::

  ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
gezapower@gmail.com

የኢቲቪ “ያልተገሩ ብዕሮች” ዘጋቢ ፊልምና ያልተገራው አቀራረብ (ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0

ነቢዩ ሲራክ

ከሁለት ሰአቱ የኢቲቪ ዜና አወጃ ተከትሎ የቀረበውን ” ያልተገሩ ብዕሮች ” ዶክመንተሪ በደረቁ ሌሊት ድጋሜ ስርጭቱ ተከታትየ ጨረስኩት … ላፍታ እንደተጠናቀቀ ዝም ፣ ጭጭ አልኩና በሃሳቤ በህዝብ ገንዘብ ከፍተኛ ወጭ እየተደረገባቸው የሚሰራጩትን የመንግስት የህትመት ጽሁፍና የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃንን አሰብኳቸው … በምናብ ብዙ ርቄ ሔጀ በዶደመ ፣ ባልተገራ እና በተባውና በተገራው ብዕር ውስጥ ራሴን አትኩሮት ሰጥቸ የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶች በሃሳብ ተመላለስኩባች ! ሰፊ ሽፋን ያለውን ኢቲቪና ራዲዮኑን ፣ በየቀኑ እየታተሙ የሚወጡትን እነ አዲስ ዘመንን ጋዜጣንና የመሳሰሉት እሰብኳቸው …አስቤ አሰላስየ ወደ ደረስኩበት ድምዳሜ ከማቅናቴ በፊት ግን በ”ያልተገሩ ብዕሮች ” ዘጋቢ ፊልም ዙሪያ የታዘብኩትን ቀዳሚ አድርጌ የተሰማኝን ላካፍልዎ ወድጃለሁ…

” ያልተገሩ ብዕሮች ” …

…ስለ ጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ከባለ ሙያዎች የቀረበው መግለጫ ዘጋቢ ፊልሙ የተነሳበትን አላማ በሚያሳካ መልኩ የተጠናቀረ ስለሚሸት ፣ ስለሚመስል አልተመቸኝም። ከሙያው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ወገኖች የሰጡት አስተያየት የግል አመለካከታቸው ነውና ብዘለውም ባዕድ በሆኑት ሙያ የሰጡት ግምገማ አልተዋጠልኝም። “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ” ሆኖብኝ ልቀበለው አልተቻለኝም ፣ አልወደድኩትም ! ምስክርነት ግምገማቸውን ያለወደድኩት “የመገናኛ ብዙሃን ውጤቶች አያጠፉም !” ከሚል እሳቤ ተንደርድሬ ሳይሆን ላጠፉት ጥፋት ቅጣት መቅጫ ወፈር ያለ ህግ ተቀምጦ በህግ መጠየቅ ሲገባ ጅምላ ነቀፋን ማቅረብ ባልተገባቸውን ነበር በሚል ነው ። የመንግስት ሃላፊዎች የሰጡት ገለጻና ማብራሪያም የተጻፈውን ህገ ደንብ ከማብራራት አልፎ ጥፋት እየተካሔደ በሆደ ሰፊ መታለፉንና አሁን ግን መንግስት ማምረሩን የሚያስረዳ ከመሆን ያለፈ ፍሬ ነገር የለውም ።

ብቻ ….ገና ከጅምሩ ዘገቢ ፊልሙ ድምጻቸው በሚስብ ጋዜጠኞችና በምስል ቅንብር ደምቆ ፣ መልዕክቱ ግን በህግ በተያዙና በሚፈለጉ ተጠርጣሪ የመገናኛ ባለሙያዎች ላይ ከፍርድ በፊት ጥፋተኝነትን የሚለድፍ ሆኖ ታይቶኛል። ሳጠቃልለው የ “ያልተገሩ ብዕሮች ” ዘጋቢ ፊልም ፍርድ ቤት ገና እያየው ባለውና ባልወሰነባቸው በጦማሪ ጸሃፍት ፣ በአምደኞች እና በነጻው መገናኛ ብዙሃን የሚቀርበውን ክስ ለማጠናከር የተሰራ መሆኑ ያሳብቃል ፣ ወንጀሉን ለማጠናከርም ለውንጀላው ምስክሮች በመንግስት ቴሌቪዥን የሰማሁትን ያህል ተሰማኝ !

ከዘመነ ጃንሆይ ፣ ዘመነ ደርግና ዘመነ ኢህአዴግ የመንግስትን አቋም እያራመዱ በጣም በወረደ ዋጋ ለነዋሪው በየቀኑ እየታተሙ ይቀርባሉ ። ዳሩ ግን ትናንትም ሆነ ሃገር ምድሩን በሚሞላ ቁጥር የመታተማቸውን ያህል ቁም ነገር አላቸው የሚባሉት ገጾች የስራ ፈላጊዎችን ቀልብ የሚስቡት ማስታወቂያዎችና የጨረታ ማስታወቂያዎች ብቻ መሆናቸውን ቢያንስ በደርግና በኢህአዴግ ዘመን አውቃለሁ ። ብዙሃኑን ነዋሪ እውነትንና ጠቃሚ መረጃን ቢይዙ አንኳ አጓጉተውት አይገዛቸውም !

ወደ ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ መስኩም ስናመራ የምናየው እውነታ ተመሳሳይ ነው ። ዘመኑ የመረጃ ነው ፣ ዘመነኛ የመገናኛ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ያንጠለጠለው የታደለው ቀርቶ በስማ በለው ከሚነገሩት መስማት የሚናፍቀው የሃገሬ ሰው ቁጥር የትየለሌ ነው። ጭብጥን መረጃ ከሃላፊት ጋር ይዘው ፈርጀ ብዙ በሆነ መንገድ የሚሰራጩ መረጃዎችን በፍቅር የሚከታተለው ወገን መረጃ እንደ እለታዊ ፍጆታው የቆጠረው ይመስላል። ዛሬ ዛሬ ከስልጡን ለውጥ ፈላጊ እስከ መደዴው የኔ ቢጤ ያለ መረጃ መተንፈስ አይቻለውም።

አትኩሮት ሰጥቶ ከሚከታተለው የራዲዮ ፣ ቲቪ መርጦ ጀሮውን ይሰጣል። ለህትመት ውጤት ለሆኑት ጋዜጣና መጽሄቶችን ያለው እየተጋፋ ገዝቶ ፣ የሌላው እየተከራየ መረጃን ይመገባል። ያሻውን ይመርጣል ፣ ያሻውን አንቅሮ የመትፋት ያህል አይቀርባቸውም !

በ ” ባልተገሩ ብዕሮች ” የቀረቡት ባለሙያዎች ያልመረምሩት እውነታ ይህ ነው ። በጥናታዊው ዘገባ የቀረቡት ባለሙያዎች በዋናነት የህዝቡን ነጻ መረጃ የማግኘት መብት አክብረው ሙያዊ ” የተገራ ያልተገራ ብዕር ” ግምገማ አድገው አላሳዩንም ።

ይልቁንም ቀርበው የደሰኮሩበት የህዝብን ገንዘብ መሰረት አድርጎ ከሚንቀሳቀው ኢቲቪ ይልቅ እየፈራ እየተባም ቢሆን ከጽፈኛ ተቃዋሚዎች ልሳንነት የሚደበውን ኢሳትን ይከታተላል ፣ በመንግስት ደጋፊነት የሚፈረጀውን ኢቢኤስን ደረቱን ገልብጦ ማየት ይፈልጋል። የኢትዮጵያ ራዲዮን ትቶ ጀርመን እና አሜሪካን ብሎም በሃገር ቤት የመንግስት እጅ የለባቸውም የሞላቸውን የተመረጡ የኤፍ ኤም አዳዲስ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ያምናል ፣ ማየትና መስማትን ይመርጣል። የዚህ ሁሉ የነዋሪው ግልጽ ሽሽት ምን ይሆን የሚለው ዳሰሳ መላ ምት ውጤት በዘገባ በቀረቡት ባለሙያዎች ቢነገረን ያምር ነበር ። ” ነበር ባይሰበር “ …

ይህ የሆነው ለምን ይሆን ? ብዙሃን ነዋሪ ምርጫ እንዲህ የሆነው ምን ቢሆን ነው ? እውን ውስጣቸው ባልተገራ ብዕር የታጨቁ መረጃዎች ስለተሞላ ነው ማለት ይቻል ይሆን ? አይመስለኝም በሚል የሚሸፈን ሳይሆን ህዝቡ የፈለገውን ማየት መስማት አይሻምና ነው ባይ ነኝ !…”ያልተገሩ ብዕሮች” ምንጭ እያስተዋለ መርጧልና ያለተገራው ብዕር በሰፊው ያለበትን ቦታ አሳምሮ ተረድቶታል … ! እናም የማይፈልገውን አይቀርበውም ኩሩው ህዝብ እንዲህ ነው !

አይ ” ያልተገሩ ብዕሮች !” ? ጊዜ ደጉ ፣ መስናት ፣ ማየት ፣ መናገር መልካም !

ሰላም ለሁላችሁ !

Comment

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየወጡ ያሉ ስሞች

$
0
0

1. ልማቱ ፈጠነ
2. ቦንድነህ አባይ
3. ሊግ ይበልጣል
4. አኬልዳማ ታዬ
5. ኑሮ ውድነህ
6. ፌደራል እርገጤ
7. ስልጣኑ በዛብህ
8. ኮንዶሚኒየም ለማ
9. ግምገማ ከበደ
10. ተሳለጭ ሃገሬ
11. መተካካት ተሻለ
12. ባድመ ይበቃል
13. አሰብ ተስፋዬ
14. ቻይና ፍቅሩ
15. መብራት ይታገሱ
16. ቴሌነሽ በዝብዝ
17. አክስዮን ሰብስቤ
18. ቫቱ በዛብህ
19. ግብሩ ጫንያለው
20. ህገመንግስት ጣሴ
21. ነጠፈ ብሩ
22. ፌስቡክ ተመስገን
23. ሀያልነሽ መንግስቴ
24. አምስትለአንድ አደራጀው
25. ግንቦት ሃያ ገብረማርያም

(ምንጭ: Ethio-Sunshine ፌስቡክ)

በአንባቢያን የተጨመሩ:

Gulilat Kasahun የጨመሩት

1. ምርጫዬ ደረሰ
2. ደሞዝ ስሜነህ
3. ይበቃል ገዛኸኝ
4. ብርቅይሁን ምሳዬ
5.ሞላልኝ ጎርፉ
6. ብሩ ባይከዳኝ
http://www.goolgule.com/new-names/

Comment

ዓይናችን ለወቅታችን!  (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 29.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

 

Cry-ethiopiaወርቅ ይቀልጣል። ወርቅ ቀልጦ ከፈሰሰ ደግሞ መልሶ ለማግኘት ይቸግራል፤ አበው „ የፈሰሰ ያልታፈሰ“ ያሉን እኮ ለላንቲካ አይደለም። ብሂሉ ተቋም ነው። መርኹ የምክር አገልግሎትን በተመክሮ ያዘመረ ነው። ይህቺ ወቅት አዎን ይህቺ ወቅት የወያኔ …. ማዕከላዊ አካል ተሰቅዞ የተያዘበት ወርቅ …. ወቅት እንዳትሾልክ እንዳታመልጥ … ጥንቁቅ፤ ብልህ፤ ብልጥ፤ ሥልጡን እንሁን። እንብለጠው የወያኔ ሃርነት ትግራይን ደባና ሸር፤ ቂምና በቀል – እንቅደመው።

ወቅቱን እናዳምጠው። ወቅቱን እናጣጥመው። ወቅቱን እንሁነው። ወቅቱን እናዋህደው – በመስተዋድድ። ይነግረናል … ያውጃል …. ይመሰክራል ….. ይጣራል …. ተጋሩኝ እያለ። ተጠቀሙብኝ እያለ። ወቅቱ የቅምጥል ጊዜ አይደለም። የመከራ ጊዜ ነው፤ የሽርሽር ጊዜ አይደለም። በጽሞና መርምረን ወቅቱ ለጠዬቀን ማናቸውም ሁኔታ ወቅቱን በድርጊት አስመችተን ልናስተናግደው በእጅጉ ይገባል። የወቅት ጽናታዊ ተደሞ እኛን እዬቀደመን ነው። የወቅት በሳል ተመክሮ እኛን እዬበለጠን ነው። የወቅት ጽሞናዊ አርምሞ እኛን እያለፈን ነው። እኮ ምን ምን እንጠብቃለን? „አሻምን በተባ ሥራ ለመሞሸር“ አይበቃም እንዲህ በቋሳ ገጀሞ መከትከት …. ሃላፊነት በማይሰማው ወመኔ መታረስ –

አዎን እኔ እላለሁ … ይህ የዘመናዊነት የእናቴ መቀነት የተጨወትነበት፤ ፍላጎታችን ያሾለክንበት ጊዜን መለስ ብለን በመገመገም ቀዳሚወን ጥያቄ ባሊህ እንበለው። ባሊህ ማለት ብቻ በቂ አይደለም – እንቀበለው የዕንባን የጭንቅ ምጥ ጥሪውን። አለሁልህ እንበለው። ጥሪው የደም ዕንባ ጥሪ ነው። ቀንም ፋታም የማይሰጥ። ላሜ ወልዳ ዬት ትታሰር ግብ ግብ በአስቸኮይ ቆሞ ሁሉም እንደ አንድ – አንዱም እንደ ሁሉ ቀዳዳውን በመድፍን፤ ክፍተቱን በሞሙላት ሰባራውን በመጠገን፤ ወለምታውን ወጌሻ በመሆን በመከራ ጊዜ አብረን ሆነን ህዝብና ሀገርን፤ ታሪክና ትውልድን እናድን ዘንድ ዓይናማው ወቅት እያሳሰብን ነው። አስረግጦ እያሳዬን ነው …. ተንበርክክኮ እዬለመነን ነው፤ መሪ ሆኖ እዬመራን ነው …. በሳል ሆኖ፣ ከእኛም ቀድሞ ተመክሮውን እያቀናልን ነው። ሰነፍ አንሁን —

ገለጥ እናድርገው። በተለያዩ ትብትቦች የተሸበቡ ድቡልቡልና ጠፍጣፋ ሙልሙል ፍላጎቶቻችን እናርቃቸው። ወቅቱ እራሱ መሪውን ያዘጋጃል። ለነገም ሻማ ሁኖ ሊቀልጥ ወቅቱ እራሱን አስቀድሞ እዬተጣራ ነው። አቤት እንበለው። ወይ እንበለው። እሺ እንበለው።

ለዛሬም ለነገም ለነገም ለተወዲያም አዎንታዊ ዘላቂ መስመራችን እንዲሆን እንከብክበው። እንወስን። እንቁረጥ። በራሳችን ላይ የማያዳግም የውስጥ ለውጥ አምጥተን፤ አራሳችን ወቅሰን ከወቅቱ ብሄራዊ ጥሪ ጋር አብረን እንሰለፍ … በፈጠራ – በአዳዲስ የለውጥ አብነቶች ፍላጎታችን እናሳምረው – ራዕያችን እናብራው።

አወን ወቅቱ ዓይናችን ሆኗል። መንፈሳችን አብርተን ካለ ቀጠሮ በማናቸውም የትግል መስመር፤ በማናቸውም የነፃነት እንቅስቃሴ በሁለመናነት በመደጋገፍ፤ በመተባበር፤ በመረዳዳት አብረን – አብርን እንሰለፍ።  በአንድ እግሩ የተጠለለውን እንሰሳዊ ሥርዓት ለማሰወገድ …. ዓይናችን – የሃቅ ዓይን እናድርገው …. ልባም እንሁን። ሥልጡን እንሁን። የ97 ድል እዲደገም …. 12 አካላችን እናሰራው …. ድል – ድል ይሆናል። ናፍቆት እውን ይሆናል …. ከሰባራ ሰንጣራ ስንጥቅ እራስን መታደግ ከተቻለ ….

ይህን ዓይናችን ለወቅታችን!እርእሰ አንቀጽ በድምጽ ማደመጥ ይሻሉን? የ28.09.2014 የጸጋዬ ራዲዮን ዝግጅት በዚህ አድራሻ ያገኙታል። www.tsegaye.ethio.info Aktuell Sendung Radio Lora (Tsegaye Radio)

 

ስንብት – የኔዎቹ አብራችሁኝ ስለቆያችሁ ወደድኳችሁ ፍቅሬንም ሰጠኋችሁ  – አዘናክቼ። መሸቢያ ሰንበት።

 

ድል ለኢትዮጵ ሰፊ ህዝብ! ሞትና ሽንፈት ለወያኔ ሃርነት ትግራይ!

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

“ያልተሄደበት መንገድ” – ሊነበብ የሚገባው ድንቅ መጽሐፍ! (ነፃነት ዘለቀ)

$
0
0

ነፃነት ዘለቀ

ይህን የአንዱአለም አራጌን በራሱ አገላለጽ ከጠባቧ የቃሊቲ እስር ቤት የተጻፈ ግሩም መጽሐፍ ሳነብ የተሰማኝን ስሜት ባጭሩ ለመግለጽ እንጂ ሥነ ጽሑፋዊ ደንብ የተከተለ ሂስ ወይም የመጽሐፍ ግምገማ ለመስጠት አለመነሳቴን መግለጽ እፈልጋለሁ – መሆኑን እንዴት ከረማችሁ?

ከሁሉ በፊት ግን ከሰሞነኛ ጉዳዮች መካከል ቂላቂሉ ወያኔ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የሠራውን አስቂኝ ድራማ ስመለከት እያዘንኩ የታዘብኩትን በዓለም ወደር የማይገኝለት ምርጥ የምርመራ ውጤት በሚመለከት ትንሽ ልበል፡፡

Yeltehedebet-Menged-300x200የኢትዮጵያን ቴሌቪዥን በውነቱ አልመለከትም፤ አለመመልከቴ ስህተት መሆኑ ቢገባኝም ጤንነቴን አጥብቄ ስለምፈልገው ይሁነኝ ብዬና ቁም ነገር አገኝበታለሁ ብዬ ኢቲቪን አላየውም – ብዙዎች እኔን መሰሎች ስላሉ “የዐዋጁን በጆሮ” እንዳትሉኝ እንጂ፡፡ የሆኖ ሆኖ በቀደምለታ ከሰዎች ጋር የሆነ ቦታ ቁጭ ብዬ ቁርስ ቢጤ ስንቀምስ በፖሊስ ፕሮግራም የተከታተልኩት በዓይነቱም ሆነ በይዘቱ ድንቅ የሆነ የወያኔ የወንጀል ምርመራ ቴክኒክና ውጤት ያጫረብኝን ልዩ ስሜት በዚህ አጋጣሚ ሳላነሳው መቅረት አልፈለግሁም፡፡ ከእውነት ሰው መሆኔን ጠላሁ፡፡

“መርማሪው” ወያኔ አይታይም፤ ይህን የለመድነው ነው፡፡ ወያኔዎች ራሳቸውን እንደወንጀለኛ አድርገው ስለሚቆጥሩና ከአልቃኢዳ ጋር የሚያመሳስሏቸውን ድርጊቶች የሚፈጽሙ መሆናቸውን ሕዝቡ የተረዳው መሆኑን ስለለተገነዘቡ ይመስለኛል የመንግሥትን ሥልጣንና ኃይልም የጨበጡ “ምሁራኑ መርማሪዎች” በግልጽ በሚዲያ መታየትን የሚወዱ አይመስሉም ፤ እነዚህ ጭራቅ ገራፊዎችና ሀዘን አምላኪዎች (ሳዲስቶች) በራሳቸውም በመንግሥታቸውም የሚተማመኑ እንዳልሆኑና በሆዳቸውና በዘረኝነት ቁርኝታቸው ብቻ ተለክፈው በስሜት ፈረስ የዕውር ድምብር ግልቢያ ዜጎችን የሚያሰቃዩ ናቸው – ቀናቸው ሲደርስ ምን እንደሚውጣቸው ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፤ አሣር አለባቸው – የቁናው ሥፍር እየተንደረበበ ይጠብቃቸዋል – እዚህ ወይም እዚያ፡፡ ከሞራል ዕሤቶቻችንና ከምርመራ ህግ በወጣ ሁኔታ አቡበከር የሚባለውን የሙስሊም ተቃውሞ አመራር አባል እጆቹን በእጀሙቅ አስረው የሚያካሂዱትን “ምርመራ” በአደባባይ በቲቪ ለዓለም ሕዝብ ሲያሳዩም “መርማሪው ሊቅ” መታየትን አልወደደም – አስጠሊታ ሣቁ ግን ከአንጀቱ ጥርስ ሳይሆን ከማተብ የለሽ አንገቱ ይሰማ ነበር፡፡ ስለዚህ የአንዲ ልዩነት እጆቹ አለመታሰራቸው እንጂ ሂደቱ ልክ እንደአቡቦከር ነው፡፡ ይህ የምርመራ ሂደትና ውጤቱ የሀገራችን የለየለት ውርደትና የወያኔን ማንአለብኝነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ወያኔዎች ከግዑዝ ድንጋይ የማይሻሉ የመጨረሻ ደደቦች መሆናቸውን ምናልባትም ለሚሊዮንኛ ጊዜ የገለጡበት ማፈሪያ ድርጊት ነው፡፡ የሚታዘነው በተመርማሪዎቹ ሳይሆን በመርማሪ ተብዬዎቹ ነው፡፡ ከመነሻው የዘረኝነት ልክፍት ያሽመደመደውና ከዘር ማዕቀፍ ውጭ የማያስብ ደንቆሮ ማይምና ሳዲስት እንዴት አንድን የተማረን ሰው ይመረምራል? እንዲያው ትንሽም ቢሆን የተማረ ዘረኛ ወያኔ ጠፍቶ ነው ወይ? ይህ ዓይነቱ የአደባባይ ግፍ ሄዶ ሄዶ የሚያስከትለውን መዘዝ እንዴት አጡት? ድንቁርና ይህን ያህል በጀብደኝት ያሳውራል?

ወደአስቂኙ ድራማ ልለፍ፡፡ አንዳርጋቸው በ“ነፃ ኅሊናው” የሰጠውና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በደናቁር የወያኔ ወንበዴዎች እሳቤ ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ይህን ይመስላል፤ “የግንቦት ሰባት ኅልውና ከእንግዲህ ግፋ ቢል ለሁለት ወራት ቢዘልቅ ነው፤ ወዲያም አለ ወዲህ ዕድሜው ከሁለት ወር አይበልጥም፡፡ የአውሮፓና አሜሪካ ምቾቱን ትቶ እንደኔ በረሃ ወርዶ የሚያታግል ቆራጥ ሰው አይኖረውም፡፡…”  የግንቦት ሰባት ቀሪ ዕድሜ ሁለት ቀንም ይሁን ሁለት ወር እሱ ሌላ ጉዳይና ወደፊትም የሚታይ ሆኖ ይህን የተናገረው ግን አንዳርጋቸው ጽጌ መሆኑን ልብ ይሏል – አንዲን በሚዲያም ቢሆን ባላውቀው ኖሮ ከአሁን በፊት “የተናገረውን”ና ገና ወደፊት “እንደሚናገረው በጉጉት” የሚጠበቀውን ሁሉ በበኩሌ ሳላንገራግር በሙሉ ልቤ አምኜ በተቀበልኩና ከወያኔ የሸፈተውን ልቤን ወደወያኔ በመለስኩ ነበር – ይህ ሁሉ ድካማቸው ታያ የማንን ቀልብ ለመሳብ ? በመሠረቱ እስካሁን ወያኔ የነበረ በአንዳርጋቸው ንግግር ምክንያት የወያኔነት ደረጃው አይጨምርም – በተቃራኒውም እስካሁን ወያኔ ያልነበረ በዚሁ የአንዲ ንግግር ምክንያት ንዴቱና ቁጭቱ ይጨምርና ወደድርጊት ይገባ እንደሆነ እንጂ ከተቃዋሚነቱ የሚያፈገፍግ አይመስለኝም፤ እናም የወያኔዎች የጅልነት ምጥቀት ያሳዝነኛል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንንና ዓለምን በጠቅላላው እስከዚህን ያህል መናቃቸው ምን ያህል ወራዳዎች – እደግመዋለሁ ምዕመናን – ምን ያህል ወራዳዎች መሆናቸውን ከማሳየት በስተቀር የአንዲ ስቃይና የሙሌት ኑዛዜ የሚጨምርላቸው አንዳችም አወንታዊ ነገር የለም – ይህን ነባራዊ እውነት ለመናገር ደግሞ የክር ወይም የሃቂቃ ጉዳይ እንጂ የግንቦት ሰባት አባልም ሆነ ደጋፊ መሆንን አይጠይቅም፡፡ የወያኔዎችን ውስጠ ምሥጢርና የግፍ ታሪክ በየመድረኮች ሲዘከዘክ ሚሊዮኖችን በዕንባ ሲያራጭና በትካዜ ባህር ሲያሰምጥ የምናውቀው አንዳርጋቸው ጽጌ በምትሃታዊ ፍጥነት ወደማፊያው መንግሥት ተገልብጦ ተናገረው የተባለውን እንዲያ ሲናገር ይታያችሁ፡፡ የምናውቀው አንዳርጋቸው የምናውቅለትን ጽኑ ፀረ-ወያኔ አቋሙን በሻጥርና በብዙ ገንዘብ ክፍያ በየመኖች ተይዞ በወያኔዎች እጅ በገባ በሁለት ሣምንታት ጊዜ ውስጥ ሲለውጥ በዐይነ ኅሊናችሁ ይታያችሁ፡፡

ግሩም የምርመራ ውጤት! ዓለምን የሚያስደምም ሣይንሳዊ የወንጀል ምርመራ ግኝት! በዚህ በአንዳርጋቸው ቃልና የመከራ ኑዛዜ ማፈር ያለበት ቀደም ሲል ለመጠቆም እንደሞከርኩት ወያኔ ብቻ ነው፡፡ ከወያኔ ውጭ ማንንም ሊያሳፍር አይችልም፡፡ እንዲያውም እኔ ብሆን ኖሮ “ግንቦት ሰባት የሚባል ድርጅት ከነአካቴው በሕይወት አለ እንዴ? አሁን እናንተ ስትሉ ሰማሁ፡፡ ማን ተናገር እንዳለኝ አላውቅም ዝም ብዬ ነበር እኮ በኢሳት ያንን ሁሉ ንግግር የምዘባርቀው፡፡ ደግሞ ብርሃኑን ብሎ ግንቦት ሰባት! ከመነሻው ግንቦት ሰባት ብሎ ነገር ሲኖር አይደለም ወርቆቼ! …” ብዬ አስደስታቸው ነበር እንጂ የሌለን ምሥጢር ለመደበቅ በመሞከር ሰውነቴን ለስቃይ አልዳርግም – ሊያውም በዚያ ኑዛዜየም ስቃዩን ቢቀንሱልኝ አይደል? ግን አይቀንሱልኝም – ስለዚህ ብናገርም ባልናገርም ለውጥ የለውም፤ ጠባችን በደም የሚጠራ እንጂ በውሃ ታጥቦ የሚጸዳ አይደለምና፡፡

እንደውነቱ ታዲያ አንዳርጋቸው ሊሰጠው የሚችለው የማይታወቅ የተከደነ አዲስ ምሥጢር ሊኖር ይችላል? ሁሉም ነገር እኮ ግልጽ ነው፤ ወያኔ የሚባል ሀገር አጥፊና ፀረ-ሕዝብ የሆነ የማፊያዎች ቡድን አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ውስጥ መሽጎ አለ – እሱን ለማስወገድ ደግሞ ዜጎች በተበታተነ ሁኔታም ቢሆን በየፊናቸው ጥረታቸውን እያደረጉ ነው፤ ምሥጢር ከተባለ ይህ ነው ምሥጢሩ፡፡  አንዳርጋቸው የትግል መስመሩ ስላበሳጫቸውና እየሠራ ያለው ነገር ለኅልውናቸው አስጊ ሆኖ ክፉኛ የሚያሳስባቸው በመሆኑ እርግጥ ነው እሱን ከመድረክ ገለል እንዲል ማድረግ ቢፈልጉ ያንን መቀበል ይቻላል – ሰይጣናዊ ፍላጎታቸውን ለማርካት የሄዱበት ርቀት ብዙ የሕግና የሞራል ችግር ማስነሳቱ እንዳለ ሆኖ፡፡ ከዚያ ውጪ ምሥጢር አውጣ ብሎ የዓለማችን ቤት ባፈራው የማሰቃያ ዘዴ ሁሉ ሰውን ማሰቃየት፣ በዚያም ሂደት ራስን ለትዝብትና ለስላቅ የሚያጋልጥ ነውረኛ የምርመራ ሂደት ማካሄድና ተመርማሪዎች የማያምኑበትን ነገር እንዲናገሩ ማድረግ በእግረ መንገድም “በሰላም አንገዛም፣ አንገብርምም ያሉንንና ሕዝብን የሚያሳምጹብንን ቀንደኛ ጠላቶቻችንን ‹እንዲህ አሸናናቸው!›፣ የወንዶች ወንዶች መሆናችንን ብልታቸውን እየቆረጥን አሳየናቸው…” በማለት ስብዕናን ለማዋረድ መሞከር ወደራስ የሚዞር አሉታዊ ውጤትን መጋበዝ መሆኑን መረዳት ይገባቸው ነበር፡፡ ለነገሩ ወያኔ ልብሱም ጉርሱም ቅሌትና ውርደት በመሆኑ በዚህ ረገድ የሚሰማው አንድም የሀፍረትም ሆነ የይሉኝታ ስሜት የለም፡፡ ጃዝ ብለው የለቀቁት 13 እና 33 ቁጥሮችም እየሳቁበትና እየተዝናኑበትም ቢሆን ወያኔ ለሚሠራው ግፍና በደል ሁሉ ቡራኬያቸውን አይነፍጉትም፡፡ እነሱስ ቢሆን በጭፍሮቻቸው አማካይነት በጓንታናሞና ኢራቅ ውስጥ አስከሬኖች ላይ እስከመሽናት በሚዘልቅ ኢሰብአዊነት ስንትና ስንት ግፍ ይፈጸሙ የለም? ልጅ ከአባት ቢማርና የጭካኔ ደረጃውን አዘምኖ ምሥኪን ኢትዮጵያውያንን ምድራዊ ገሃነም ውስጥ ቢዘፍቃቸው ዋኖቹ ሀዘን አምላኪዎች ይደሰታሉ እንጂ ከከንፈር ሽንገላ ባለፈ ሕዝቡን ሊታደጉት አይፈልጉም – ይህንንም አሳምረን እናውቃለን፡፡ ጭምብሉን ፖለቲካዊ የተለሳለሰ የሚመስል አካሄድም አንዘነጋም – አገም ጠቀሙን፡፡

በነገራችን ላይ 13 እና 11 ወይም 33 ደግሞ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ለሚያምንበት ሁሉም የትልቁ ቁጥር የአውሬው መገለጫ የ666 ቅንስናሾች ናቸው፡፡ አሥራ አንዶች በ110 የለበጣ ቀመር ቢያላግጡም እውነቱ ቀፎ የመለዋወጥ – የትሮይን ፈረስ ቅርጽ የማሻሻል ጉዳይ እንጂ ሲሙ ያው ነው – አሥራ አንድ፡፡ ለነገሩ ዝናር ባንገቴም ይሁን 11 ወይም ዜሮም ይሁን አንድ ሽንትር ዋናው ነገር ተግባር ነው፡፡ ሌላው ትርፍና ጨዋታን ለማሳመር ያህል በአጃቢነት የገባ ነው፡፡ እናም በሀገራችን ሁኔታ የሰውዬው ማንነት ምንም ይሁን ምን በስቃይና በግድያ የሚያምን ሁሉ እናት ክፍሉና ጥንተ አመጣጡ ከአውሬው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ክፉና ደግ መንፈሶች ኅብረት የላቸውም፡፡ ሩህሩህ መሐሪና አረመኔ/ጨካኝ ገዳይ አንድነት የላቸውም፡፡ መጽሐፉም ጣፋጭ ፍሬ በዛፍ ላይ ሳለ ይታወቃል እንደሚል ማን የማን ወገን መሆኑ በተለይ በዘመናችን በግልጽ ይታወቃል፡፡ ማን ነው የበሽታ ሕዋሳትን በቤተ ሙከራ እየፈለሰፈና እያራባ ለዓለም በተለይም ለኋላቀር ሀገሮች እንደ ዕርዳታ ስንዴ የሚያከፋፍል? ማን ነው የዓለማችንን የአየር ንብረት እያዛባና ዕድሜዋን በብርሃን ፍጥነት እያሳጠረ የሚገኘው? የዓለምን ጠቅላይ ገዢነት በትረ መንግሥት በጉልበት የተቆጣጠረውና “ለኔ ካልሰገዳችሁ ሀብትና ሥልጣን አይኖራችሁም” ብሎ ሁሉን እያስደገደገ የሚገኘውና በትዕምርተ ኅቡኣታዊ ባለአንድ ዐይን ፒራሚዳዊ ቅርጽ ወይም በፔንታጋራማቲን የኮከብ ቅርጽ የሚታወቀው ምሥጢራዊ ኃይል ማን ነው? ማን ነው አሁንም ሆነ ከአሁን በፊት መካከለኛውን ምሥራቅ እያተራመሰ ያለው? መፍለቂያው የሆነችን የአንዲት ትንሽዬ ሀገር ኅልውናና የበላይነት ለማስጠበቅ ሲል ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቱ የዓለምን የመንግሥታት ኅብረት እንደአሽከር ሰጥ ለምበጥ አድርጎ የሚገዛ ማን ነው? አይኤም ኤፍ፣ ዩኤን፣ ወርልድባንክ፣ ኔቶ፣ ሲአርኤፍ፣ … የማን አድቃቂ ክንዶች ናቸው? ለመሆኑ የዚህ ሞገደኛ የወቅቱ የዓለማችን ገዢ ዋና መሥሪያ ቤትና ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ የት የት ናቸው? ጽዮንና ሀማስ የማን ልዑካን ናቸው? የግጭቶች መንስኤና የምክንያታዊነት ሚዛኑ ለማንም ያጋድል ዋናው የሁለቱም ተልእኮ ግና ለአውሬው ግብር የሚሆን ብዙ የደም ባህር ማቆር መሆኑን መዘንጋት የዓለም ነገር አያገባኝም ብሎ እንደመመነን ይቆጠራል፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል – ማን ነው የጦር ኃይሎችን በሁለት ጎራ እየከፈለ በተፃራሪነት በማሰለፍ የሚሊዮኖችን ደም በከንቱ እያፋሰሰ ያለው? ኢራንና አሜሪካ በርግጥም ባላንጣዎች ይሆኑ እንዴ? በፍጹም፡፡ ጠላቶች መስለው ትያትር በመከወን ለአንድ ዓላማ ስኬት የሚተጉ የአንድ ገዢ አንድ አምሳል አንድ አካል ናቸው፡፡  ማን ነው በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከአፍ እስከገደፋቸው በንጹሃን ተሣፋሪዎች ጢም ብለው የሞሉ የሲቪል አውሮፕላኖችን(የማሌዥያን) ባልታወቀ ዕፀ መሠውርና በሚሳኤይል ድራሻቸውን ያጠፋው? ምን ዓይነት ወያኔያዊ ጨካኝ አንጀት ያለው ፍጡር ይሆን ይህን ያደረገ? ለምን ዓላማ? ቫቲካንንና መለስተኛ አውሮፕላን የምታህል የነጭ እርግብ ምስል ለማስመሰል ያህል በሰላም ምልክትነት በዋና የፓትርያርክ ጸ/ቤቱ በር ላይ ያቆመውን የኛኑ ኦርቶዶክስ ሳይቀር ከሞላ ጎደል ሁሉንም የሃይማኖት ተቋማት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተቆጣጥሮ ሁሉንም ሃይማኖት አለኝ ባይ በአውሬው ትዕዛዝ ሥር ያደረገው ማን ነው? ለመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ቅዱስ ሊባል የሚችል ቦታና ሰው አለ ወይ? ፖፕ ጆን ፖል አንደኛ፣ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ፣ ‹አቡነ› ጳውሎስ የኛ… ሌሎችም የማን ወኪል ነበሩ? ፍየሎች በበጎች ጋጣ ውስጥ መሽገዋል፡፡ በጎች እያለቁ ነው፡፡ አውሬው ሆሊውድና ቦሊውድን ብቻ ሳይን ገዳማትንና ካቴድራሎችንም ከተቆጣጠረ ምዕተ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ጭካኔን በሚያስተምሩ ፊልሞች፣ በልቅና ባልተገሩ ኢ-ሞራላዊም በሆኑ ፖርኖግራፊዎች በተለይ የዓለምን ወጣት ትውልድ ጡጦ ከመጣሉ በእንጭጩ ለማምከን  ይህችን ዓለም ማንና ከየትስ ሆኖ እየገዛት እንዳለ መች አጣነው? የዚያ ‹ታላቅ› የጨለማ ንጉሥ የእጅ ሥራዎች የሆኑ ወያኔዎችም ባቅማቸው ቅድስቲቱን ሀገር ድራሽዋን ቢያጠፏት ከድጋፍ በስተቀር ማን ከልካይ አላቸው? በጎችስ ቢጮኹ አለጊዜው ማን ይደርስላቸዋል? ግን ግን አይዞን፤ የፍየሎችና የበጎች የመጨረሻ ዕድል ተለይቶ የሚታወቅበት የፍርድ ቀን በፍጥነት እየመጣ ነው፡፡ ብሎም ቢሆን ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ድል በምኞት ሊገኝ እንደማይችል ልብ ማለት ይገባናል፡፡ ብቻ ይህን መሰሉን ነገር በሆድ ይፍጀው ለሌላ ቀን በይደር ማቆየቱ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ለነገሩ እኛን ምን አገባን? ሁሉም ከልኩ አይዘል፡፡

 

ከሰው ተውሼ እያነበብኩት ነበር – “ያልተሄደበት መንገድ”ን፡፡ በቅርብ ካነበብኳቸው በሀገር ችግር ዙሪያ ከሚያጠነጥኑ የቅርብ ጊዜ መጻሕፍት ውስጥ በኔ ዕይታና ለኔ ፍጆታ ይሄኛውን ወደር አላገኘሁለትም፡፡ አንዱአለም አራጌ ዋለ የተዋጣለት መጽሐፍ በመጻፉ – ሊያውም በዚህ አፍላ የጎልማሳነት ዕድሜውና በመከራ ውስጥ ሆኖ – ባለበት አድናቆቴ ይድረሰው፡፡ ወላድ በድባብ ትሂድ የሚባለው በዚህ ዓይነት አጋጣሚ ነው፡፡ ሚሊዮኖች ፈርተንና ለሥጋችን አድረን በየሽርንቁላው ተወትፈን በፍርሀት ቆፈን ስንርድ ሊያውም በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ ይህን የመሰለ አብሪ መጽሐፍ ካለበቂ ማጣቀሻና ዋቢ መጻሕፍት በአዩኝ አላዩኝ ሰቀቀን ሌሊት ሌሊት እየተደበቁ መጻፍ ልዩ ጀግንነትና ተሰጥዖም ነው፡፡ አንዱአለምና መሰል የብዕርና የፖለቲካ ታጋዮች ለነፃይቱ ኢትዮጵያ በሕይወት እንዲደርሱ እግዚአብሔር ይታደገን፤ ይታደጋቸው፡፡ ቤተሰባቸውንም ይባርክ፡፡ ለእኛም ለባከንነውና ለራሳችን ጥቅምና ፍላጎት ስንል በ‹እስኪያልፍ ያለፋል› ተረት ራሳችንን እያታለልን የወያኔ ባርያ ሆነን ለጠፋነው ዜጎችም ፈጣሪ ረድኤቱንና ወኔውን ይስጠን፡፡ እንደዚህ ያሉ ዜጎች ባይኖሩን ኖሮ ሕይወት በጠቅላላው ለይቶላት ጨለማ በሆነች ነበር፡፡ ከዚህ አንጻር እግዜር የተመሰገነ ይሁን፡፡ እርሱን መሰል ሌሎች ጸሐፊዎችንና ታሳሪዎችንም ጭምር እግዜር ይባርክልን፡፡ ለቤታቸውም ያብቃልን፡፡ የሚሳነው ነገር የሌለው የኢትዮጵያ አምላክ የመከራ ደብዳቤያችንን የሚቀድድና ሃራ የሚያወጣን አንዳች ኃይል ይዘዝልን፡፡ አሜን፡፡

ይህ መጽሐፍ የዋቢ መጻሕፍትን ገጽ ጨምሮ በጠቅላላው 320 ገጾች አሉት፡፡ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ሥር የተካተቱ 18 ርዕሶችንም ይዟል፡፡ ጠቅጠቅ ብሎ የተጻፈ በመሆኑ እንደሌሎች በርካታ መሰል መጻሕፍት በቀላሉ አይገፋም፡፡ የሆኖ ሆኖ በተለይ እስከማገባደጃው ድረስ ስሜትን ቆንጥጦ በመያዝ መነበብ የሚያስችለው ሥነ ጽሑፋዊ ውበትና ይዘታዊ ግርማ ሞገስ አለው፡፡ እናም አንብቡት፡፡ በነገራችን ላይ ይህን መጽሐፍ እያነበብኩ ወደ ገጽ 100 አካባቢ ስደርስ የተዋስኩትን እንደምመልስ ገባኝና ወዲያውኑ ከተማ ወጥቼ ገዛሁት፡፡ ተውሼ ያነበብኩትን ወይም እያነበብኩት ያለሁትን መጽሐፍ ስገዛ ይህ የመጀመሪያ ጊዜየ ነው፡፡ አንጡራ ሀብቴና የመጻሕፍት መደርደሪያየ አንዱ ፈርጥ እንዲሆን ተመኘሁ፡፡ ተመኝቼም አልቀረሁ፡፡ ለልጆቼ ውርስ ይሆናል፡፡ እናንተም አሁኑኑ ግዙና ንብረታችሁ አድርጉት፡፡ መጽሐፉ “ኩሎ አመክሩ ወዘሰናየ አጸንዑ” እንዲል፡፡

አመስጋኝ አማሳኝ እንዳልባል በዚህ መጽሐፍ የታዘብኳቸውን አንዳንድ ግድፈቶችም በዚሁ አጋጣሚ ብጠቁም ደስ ይለኛል፡፡ ጥቂት የማይባሉ የአርትዖት ችግሮች አሉበት፡፡ አሉታዊ መሆን ያለበት በአወንታዊ ወይም የዚህ ተቃራኒ ሆኖ የሚጻፍበት አጋጣሚ አልፎ አልፎ ይስተዋላል፡፡ አማርኛ ላይ ብዙውን ጊዜ የምታስቸግር ነገር አለች – ለምሳሌ “እኔን እንደሚያገባኝ እንዴት ረሳኸው?” በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ “ሚ”ን “ማ” ብናደርጋት ትርጉሙ ሙሉ በሙሉ ይለወጣል፡፡ “ጽንፍ” ለማለት “ቅንፍ” ብንል አንዳንዶችን ግር ሊያሰኝ ይችላል፡፡ የአርትዖት ሥራ ሽንፍላ እንደማጠብ ነው፡፡ በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች በብዙ አዳዲስ ዐይኖች ሊተባበሩበት የሚገባው አስቸጋሪ ሥራ ነው፡፡ እንዲያም ሆኖ የማይጠራበት ጊዜ አለ፡፡ ከዚህ አኳያ ይህን ቆንጆና ለታሪክ የሚቀመጥ መጽሐፍ ዐዋቂ ሰው እንደገና “ኤዲት” ቢያደርገው የበለጠ ማለፊያ ይሆናል፡፡ የግሌ አስተያየት ነው፡፡ (አንድ ወዳጄ የነገረኝ አንድ አርትዖታዊ ስህተት በጭንቅላቴ ብልጭ እያለ ‹እዚህ ላይ ካልጻፍከኝ ሞቼ እገኛለሁ!› ብሎ አስቸገረኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የመሥሪያ ቤቱ የብድር ኮሚቴ ስብሰባ ይጠራል፡፡ ለተሰብሳቢዎችም “ከብድር ኮሚቴ…. ለጠቅላላ አባላት” የሚል ጽሑፍ ተበትኗል፡፡ ሁሉን ያስፈገገው ግን ጸሐፊዋ “ከብድር ኮሚቴ” ከሚለው ሐረግ ውስጥ የአንዱን ቃል የመጨረሻ ፊደል ሳትጽፈው መቅረቷና እስከዚያን የስብሰባ ጊዜ ድረስ ማንም ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ስህተቱን ልብ አለማለቱ  ነበር፡፡ ያቺ “ነገረኛ” ጸሐፊ የትኛዋን ሆሄ እንደዘነጋቻት እኔም አሁን ዘነጋኋት፡፡ )

ከሆሄያት ግድፈትና ሞክሼ ፊደላትን  በነባሩ ሰዋስዋዊ ልማድ ከመጠቀም አኳያ ከሚታዩ አንዳንድ ጥቃቅን “ስህተቶች” በተጓዳኝ ጥቂት የመረጃ መዛባትና የዘይቤና ፈሊጥ አጠቃቀም እጅግ አነስተኛ ችግር ሳይኖር እንደማይቀር እገምታለሁ፡፡ ለምሳሌ “ኢሕአፓ” የሚለው ምሕጻረ ቃል ሲፈታ እኔ የማውቀው “የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ” በሚል ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ግን “የኢትዮጵያ ሕዝብ አደራጅ ፓርቲ” በሚል ከአንዴም ሁለቴ ገደማ ቀርቧል፡፡ ፈሊጥን በተመለከተ “ለያዥ ለገራዥ” ለማለት “ለያዥ ለገናዥ” ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የሃሳብ ድግግሞሽ በስፋት ይታይበታል፡፡ በዚያም ምክንያት አንድ አንባቢ በጀመረበት የስሜት ሞቅታ መጨረስ ባይችል ችግሩ ከዚህ የሃሳቦች መደጋገም የሚመነጭ ይመስለኛል፡፡ የሆኖ ሆኖ የመጽሐፉ አጻጻፍና ለኅትመት መብቃት በብዙ ችግር የታጠረ በመሆኑ የአሁኑ ይዘቱ ራሱ ከሚጠበቀው በላይና በአንጻራዊ ሁኔታ ከሌሎች በርካታ መሰል ጸሑፎች(እኔ ካነበብኳቸው) በጣም የተሻለ መሆኑን በበኩሌ ልገነዘብ ችያለሁ፡፡ በመሆኑም ይህ ጥረቱ ደራሲውን በእጅጉ ያስመሰግነዋል፡፡ እዬዬም ሲደላ ነው ጓዶች፡፡ እነኚህንና መሰል ሌሎች እንከኖችን አስተካክሎ በቀጣይ ኅትመት ለንባብ የሚያበቃው ወገን ከተገኘ መልካም ነው፡፡ ደግሞም የማይቻል አይመስለኝም፡፡

 

አንዱአለምን በዚህ መጽሐፉ ደርቤ እንዳነበብኩት የፕሮፌሰር መስፍን ደቀ መዝሙር ይመስለኛል፡፡ ይህን የምለው ፕሮፌሰሩ አንድ ወቅት እነብርሃኑ ነጋ “ሁለገብ ዘዴን በመጠቀም ወያኔን እንታገላለን” ባሉ ወቅት ክፉኛ ይተቿቸውና “እኛ ወደዚህ ‹የማይረባና ውዳቂ› የአስተሳሰብ ደረጃ አንወርድም”  ማለታቸውን በማስታወስና አንዱአለምም በዚያው ቅኝት አሁንም ድረስ በዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንዝ ቀርቶ የደረቀ ምንጭ በማያሻግር የሰላማዊ ትግል ሥልት ወያኔን እንጥላለን ብሎ የሚያምን በመሆኑ ነው፡፡ እርግጥ ነው አንዱአለም አሁን ባለበት ሁኔታ በኃይል ወይም በጦር መሣሪያ ወያኔን እንታገል ብሎ ቢጽፍ የሚደርስበትን ተጨማሪ መከራና ፍዳ ስለምንገነዘብ ይህን አቋም ያርምድ ብለን በሰው ቁስል እንጨት አንሰድም፡፡ ይሁንና ቢያንስ ዝም ማለት ሲገባ ወያኔ የፈጠረው የኢትዮጵያ ውጥንቅጥ ችግር የሚፈታው ወያኔን በሰላማዊ መንገድ በመታገል ብቻ ነው የሚል እምነት በጭፍን ማራመዱን አልወደድኩለትም፡፡ (በነገራችን ላይ ኤርምያስ ለገሰ ቅድም በኢሳት አንድ ውይይት ላይ ሲናገር እንደሰማሁት የአንዳርጋቸውን በወያኔዎች መያዝ ኔልሰን ማንዴላ በኢዲያሚን ዳዳ እንደተያዘ ያህል እቆጥረዋለሁ ማለቱን እኔም በጣም እደግፋለሁ፡፡) ሰው ከሰው ጋር ቢታገል አሸናፊውና ተሸናፊው ይለያል፡፡ ከአውሬ ጋር ግን እንዴት መታገል ይቻላል? ውሾች በ“አስተሳሰብ” ከሚበልጡት ወያኔ ጋር እንዴት ስለሰላም መወያየት እንደሚቻል አንዱአለም ቢያስረዳኝ ደስ ባለኝ፤ ውሾ ሲሸናነፉ በሚያሳዩት ተፈጥሯዊ ምልክት ይግባቡና ጦርነቱን ያቆማሉ፤ ከዚያም በመካከላቸው ሰላም ይሰፍናል፡፡ ሁኔታዎችም ወደጥንቱ (statusquo ante) ይመለሱና ማኅበረከልባዊ ሕይወት ትቀጥላለች (“ከልብ” ውሻ ማለት ነው – “ል” ጠብቃ አትነበብም)፡፡ ወያኔ ግን ያሸነፈውን ሁሉ በሕይወት ያለውን ብቻም አይደለም የሞተውን ሳይቀር እስከመቃብር ድረስ የፕሮፓጋንዳ ሠራዊት እያዘመተ የቅርብ አጥንቶችንና የሩቅ አፅሞችን የሚፋለም ዶንኪሾት ነው፡፡ ይህን ባሕርዩን ለማወቅ በግድ እንደነአሥራት ወ/የስ መሞትና እንደነእስክንድር ነጋ መታሰር አያስፈልግም፡፡ ዛሬ ላይ ቁጭ ብሎ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ከሥልጣን አስነሳለሁ ብሎ መቃዠት በርግጥም ቅዠትና ሲያንስም የዋህነት እንጂ አንዱአለምን ከመሰለ በሳል የፖለቲካ ሰውነት የሚጠበቅ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ ውሱን ነጥብ አኳያ ምን እንደነካው ሊገባኝ አልቻለም፡፡

አክራሪ ኦርዶቶክሳውያን እንዳይቀየሙኝ እንጂ የአንዱአለም የዋህነት (naivety?) ከ‹ቅድስት› ክርስቶስ ሠምራ ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡ ‹ቅ.› ክርስቶስ ሠምራ – በገድሏ ላይ ተጽፎ እንደሚነበበው – ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ለማስታረቅ ዕቅድ ትነድፋለች አሉ፡፡ … እርሱ ወዳለበት ሲዖል በቀጥታ ትሄዳለች፡፡ “ስፈልግሽ ኖሮ እዚሁ መጣሽልኝ?” ይላትና የክርስቶስ ሠምራን ነፍስ ይዞ ወደግዛቱ ሊያስገባት ሲል መላእክት ደርሰው ወደመጣችበት ወደገነት ይወስዷታል፡፡ በአጋጣሚው ግን 78 ሺህ የተኮነኑ የሲዖል ነፍሳት በቅድስቲቷ መንፈሳዊ አካል ላይ በመጣበቅ ወደገነት ይገባሉ፡፡ እምነት ነው፡፡ በየዘመናቱ በገዢዎችና በሃይማኖት መሪዎች ፈቃድ እንዲካተቱ የተደረጉና እነዚህን አሳሳች ይዘት ያላቸውንና እርስ በርስ የሚቃረኑ፣ “በእግዚአብሔር መንፈስ የተነዱ” ሰዎች ስለመጻፋቸው የሚጠቁም አንዳችም ማስረጃም የሌላቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ የተካተቱ አንዳንድ ጽሑፎችንና ሰይጣናዊ ሳጋዎችን ሳይቀር ላለመቀበል አንድ ሰው መብት ያለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህን ኢትዮጵያዊ ሃይማኖታዊ ድርሰት ማመን አለማመን የማንም ውዴታ እንጂ ግዴታ ሊሆን አይገባም – እዚያው ውስጥ በሚገኙት ዘንድም ቢሆን፡፡ ታርጋ ሳይለጠፍብኝ ስለሃይማኖቴ ልናገር እንዴ? አይ፣ ለማንም አይጠቅምም፡፡ ግን ማንኛውንም ሃይማኖታዊ አክራሪነትና ጽንፈኝነት የምጠላ አማኝ(theist) መሆኔን ብገልጽ ደስ ይለኛል፡፡ አነሳሴ ወዳልሆነ ነገር በመንሸራተቴ ይቅርታ – ምን ላድርግ ሁሉም ነገር አንሸራታች ሆኖ ዐረፈው እኮ፡፡ ብቻ አንዱአለም የዚህችን ቀና ሴት ባሕርይ የተላበሰ ግን በአፀደ ሕይወት የሚገኝ የማይቻልን ነገር ለመሞከር የሚተጋ የወንድ ክርስቶስ ሠምራ ይመስለኛል፡፡  

ሰላማዊ ትግል የራሱ መደላድል አለው፡፡ በቅድሚያ የሀገርህ ሰው ከሆነ ሰው ጋር፣ ዜጋህ ከሆነ ሰው ጋር፣ እንደዜጋው ከሚቆጥርህ ወይም ከሚመለከትህ የአገዛዝ ኃይል ጋር፣ በትንሹ ደግሞ ሰው መሆንህን አምኖ ከሚቀበል ሰው ጋር እንጂ ከአውሬና ከለዬለት የዲያብሎስ መንጋ ጋር በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ብለህ ወርቃማ የመቶዎች ዓመታት ጊዜህን አታባክንም – አንዱአለም የሚለው ግን ዝንታለሙን እየታሰርንና እየተገደልን ነፃነታችንን ከወያኔ በችሮታ እንቀበል ነው – ምናልባትም በወዲያኛው የምፅዓት ዘመን፡፡ ሰዎች ወያኔን መረዳት እንዴት እንዳልቻሉ ወይም እንደማይችሉ ሳስበው ይገርመኛል፤ እንዲያውም ወያኔዎች፣ ሰዎች እንዲህ እንዲሆኑ – ማለትም በሰላማዊ መንገድ ከነሱ ጋር መታገል እንደሚቻል እንዲያምኑና እንዲያሳምኑ – የሚያደርግ ድግምት ቢጤ ሳይኖራቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡ አለበለዚያስ የሰላማዊ ትግልን ገፈት ቀማሽ ከሆነ አንዱአለምን ከመሰለ ብርቅዬ ዜጋ እንዲህ ያለ ተሳስቶ የሚያሳስት አነጋገርና እምነት ሊደመጥ ባልተገባ ነበር፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝና ዝምታ ማንን ገደለ? በከንቱ መነቃቀፍ ከትዝብት በስተቀር ምን አወንታዊ ውጤት ያስገኛል? እንዳለመታደልና እንደርግማንም ሆኖ በኅብረት መታገል ቢያቅት ሁሉም ባመነበት ቢንቀሳቀስ ምን ክፋት አለው? ከአድማስ ማዶ ሊኖር ይችላል ተብሎ በሚታሰብ ሥጋት ከወዲሁ መቆራቆስ አግባብ ነው ወይ? ለዚህማ ወያኔ አለ አይደል? ይህን ስል አንዱአለማውያንና መስፍናውያን – በተወሰነ ደረጃ እኔንም ጨምሮ – ስሜታችን እንደሚጎፈንን ይሰማኛል፡፡ ግን ምርጫ የለኝም፡፡ የሚሰማኝን መናገሬ እንደወንጀል ሊቆጠርብኝ አይገባም፡፡ አውቃለሁ – አንዱአለም እሳት ውስጥ ነው፡፡ አልክድም – እኔም ከርሱ ባልተናነሰ ሁኔታ እሳት ውስጥ አለሁ፡፡ ልዩነታችን እርሱ ባመነበት ገብቷል፡፡ “ደስ”ም ያለው ይመስላል፡፡ የኔ ግን ከሁሉ ያጣ ሆኜ በዕብደትና በስክነት መካከል አንዴ ሰው አንዴ ዐፈር በመሆን እየተቀያየርኩ መረጋጋትና ሰላም የሌለው ሕይወት እገፋለሁ፡፡ ኅሊናህን አፍነህ መኖር ከመታሰር በበለጠ እንደሚጎዳ አውቄያለሁ፡፡ ሰው እንኳን ሳያውቅልህ በአእምሮ ስቃይ ምክንያት ከቤተሰብህም ከጓደኞችህም ‹እየተናጀስክ› ሰላምህን አጥተህ በትልቁ እስር ቤት መኖር በትንሹ እስር ቤት ከመኖር የበለጠ እንደሚያሰቃይ ተረድቻለሁ፡፡ መብላት፣ መጠጣት፣ መዳራትና በሰፊ ጎዳና መመላለስ ትርጉም የሚያጡበትና አንጎልህ ተቀፍድዶ ተይዞ ሰዎችን ሰላም በምትነሳበት ሁኔታ ለመኖር ያህል ብቻ መኖር ከለዬለት ከርቸሌ ያልተሻለ መሆኑን ከተረዳሁ ቆይቻለሁ፡፡ ስለሆነም ከአንዱአለም ባልተናነሰ የኔም እስረኝነት የዋዛ አይደለምና ሁላችንም አንድ ነን፡፡ እንዲህ የምለው ስለኔ ብቻ አይደለም – ስለሌሎች እኔን መሰሎችም እንጂ፡፡ እንዲህ የምለው ግን ለምንድነው? የማንን አንጀት ለማላወስ? ማንስ ነው ሆዴ ላይ ቆሞ ያናዘዘኝ? ሆ!   

በውሸት መከሰሱን፣ በውሸት ምሥክር (አዳፍኔ በሚላቸው) ዘብጥያ መውረዱን፣ በውሸት የግንቦት ሰባት አባልና የሽብር ጥቃት ሊፈጽም ከምንደኞች ጋር እያቀነባበረ ነው መባሉን፣ …. ሁሉንም ዘንግቶ ከእባብ ዕንቁላል እርግብ እንደሚፈለፈል ሊያስረዳን መሞከሩ አንዱአለም ወያኔን ለማወቅ ገና ብዙ ጊዜ የሚፈጅበት መሆኑን አመልክቶኛል – ጠሊቅ ሀገራዊና ታሪካዊ ዕውቀት ያለው መሆኑ ተይዞልኝ፡፡ እናም እላለሁ – ሰማይ ዝቅ መሬት ከፍ ቢሉ ወያኔ በሰላማዊ ትግል ሥልጣን አይለቅም፡፡ ይህን ፀሐይ የሞቀውንና ሀገር ያወቀውን ሃቅ በመካድ ከዚህ የተለዬ ህልም ማለም – እንደአካሄድ ባይከለከልም – ትዝብት ላይ ይጥላል፡፡ በነገራችን ላይ ክርስቶስም ለትግስቱና ለፍቅሩ ገደብ ነበረው፤ ለዚህም ነው በመሳም አሳልፎ የሰጠውን ይሁዳን የረገመው – በአንገቱ የወፍጮ መጅ ታስሮ ወደጥልቅ ባህር ቢወረወር እንደሚሻለው በምሬት በመናገር፡፡

ይቅርታችሁንና በዚህስ አንዱአለምን ተናድጀበታለሁ፡፡ ምን ነካው ግን? እንግዲያውስ ያበጠው ይፈንዳ በኢትዮጵያ እንደእስካሁኑ የስግብግብነትና ራስ ወዳድነት በሽታችንና የሥልጣን አራራችን ከሆነ በሰላማዊ መንገድ እንኳንስ ወያኔ ኢንጂኔር ግዛቸው ሽፈራውም ሥልጣን አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ ኢንጂኔር ኃይሉ ሻውልም አይለቅም (በጤና ምክንያት …ካልሆነ)፤ እንኳንስ ወያኔ ፕሮ. በየነ ጴጥሮስም አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ ዶር. መረራ ጉዲናም አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ ዶር. ፍስሐ እሸቱም አይለቅም፤ እንኳንስ ወያኔ በቁሙ የሞተው ከሃዲው ልደቱ አያሌውም አይለቅም … (ዝርዝሩ ብዙና ብዙ ነው – ስንተዋወቅ? ግን እባብ ልቡን ዐይቶ እግሩን ነሣው ሆነና …)፡፡ የኢትዮጵያ መሬት አዲስ በሚፈልቅ ፍቱን ጠበል ካልተረጨ ይሄ የሥልጣንና የገንዘብ እንዲሁም የሴሰኝነት ጠንቆች በቀላሉ አይለቁንም – በኛ ባሱብን እንጂ እርግጥ ነው እነዚህ መሰናከያዎች የአጠቃላዩ የሰው ዘር መደናቀፊያዎች መሆናቸው የታወቀ ነው (ለምሳሌ የሰሞኑንና የቅርብ ሩቅ ጊዜውን የኢራቁን አልማሊኪንና የግብጹን አልሲሲን የሥልጣን ሱስ ብናይ በሰው ልጅ ራስ ወዳድነት መገረማችን አይቀርም – ይህ ነገር ወደኛ መጥቶ ከማይምነታችን፣ ከሥልጣን ወዳድነታችንና ከቦክሰኛው አስተዳደጋችን ጋር ሲደመርማ ምን ያሳይ፡፡) በኛ ሀገር ለሁሉም ነገር በተለይም ለጥላቻችንና ለራስ ወዳድነታችን ልጓም አጣን፤ ለከት ጠፋ፤ በቃኝን ተጸየፍን፤ ጠገብኩን ጠላን፤ ከይሉኝታና ሀፍረት ተፋታን – ስንገርም፡፡ እናም ለነዚህ ነገሮች ያለን ጥብቅ ቀረቤታ ከሌሎች የጥፋት ሰበዞች ጋር ተደማምሮ እንደሀገርም እንደሕዝብም ከናካቴው ከምድረ ገጽ ልንጠፋ – መለኮታዊ ጣልቃገብነት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ካልተከሰተ –  ዘመኑ ቀረበ፡፡ ውሸት ነው? ውሸት ነው ካልክ እውነት ነው ማለት ነው፡፡ “አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” የሚል መጽሐፍ ዱሮ አነበብኩ ልበል? አዎ፣ ‹ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል› እንዲሉ ካልሆነ ለይቶልን ጠፍናል፡፡ አንወሻሽ፡፡

አንዱአለም ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ሥልጣን እንደማይለቅ አሳምሮ ያውቃል፡፡ መጽሐፉ ላይ በገደምዳሜ ገልጾታል፡፡ እንደመፍትሔ በየገጾቹ የሚያቀርበው ግን ያንኑ የሰላማዊ መንገድ የትግል ሥልት ነው፡፡ “የሰላማዊ መንገዱ ካልሠራ” ይላል አንዱአለም ፈገግ ባደረገኝ ሁኔታ “የሰላማዊ መንገዱ ካልሠራ ሌላ የሰላማዊ መንገድ መሞከር ነው፡፡” ከመሰነባበታችን በፊት በመጽሐፉ መጨረሻ አካባቢ ገጽ 312 ላይ የሚገኘውንና ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ማስወገድ ባይቻል በማስከተል ምን ማድረግ እንደሚገባ አንዱአለም የመጨረሻ መፍትሔ ብሎ የሚሰነዝረውን እንመልከት – ወጣቱ ፖለቲከኛ አይፈረድበትም፡፡ የት ነው ያለውና? አያድርስ ነው – እነዚህ ሰዎች አስጨንቀው ያዙንና እምንለውንም እያሳካሩ ግራ አጋቡን እኮ፡፡ አንዱ ለጓደኛው “ያዋስኩህን ዕቃ ባትመልስ ዋልህ! አሳይሃለሁ!” ይለዋል፡፡ “ምናባህ ልታደርገኝ አንት የውሻ ልጅ!” ብሎ ቢያፈጥበት “አይ፣ ምን አድርግሃለሁ ያው ታዝቤህ እቀራለሁ እንጂ” አለው ይባላል፡፡ እርግጥ ነው መናገር የማድረግን ያህል እንደማይከብድ አውቃለሁ፡፡ “አይ መሬት ያለ ሰው!” ብሏል አሉ የሚጋልበው ፈረስ የደነበረበት አንድ ሰው – “እንዲህ አድርገው፤ እንዲህ ያዘው” ባሉት ጊዜና፡፡ አሁንም እርግጥ ነው – ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ ነው፡፡ እርግጥ ነው – አታሞ በሰው እጅ ስታምር በገዛ እጅግ ግን ልታደናግር ትችላለች፡፡ ቢሆንም የሚሰማኝን ብናገር ቢያንስ ዴሞክራሲያዊ መብቴን “ባልተሸራረፈ” መልኩ እንደተጠቀምኩበት ከመረዳቴም በተጨማሪ የተወሰነ እፎይታን አገኛለሁ፡፡ ለማንኛውም ወደአንዱአለም የመጨረሻ የችግሮቻችን መፍትሔ እናምራና ለአፍታ እንመልከትለት፤

 

ትልቁ ጥያቄ ኢሕአዴግ የብሔራዊ ዕርቁን ጥያቄ አሁንም “የባልና የሚስት ፀብ አይደለም” ብሎ ቢያጣጥለው ምን ማድረግ ይቻላል? የሚለው ነው፡፡ በእኔ እምነት ኢሕአዴግ ከዚህ በኋላም (እስካሁን) ለ21 ዓመታት የዳከረበትን መንገድ የሚመርጥ ከሆነ ተቃዋሚዎች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነው የሚጓዙ(በ)ት የራሳቸው አዲስ መንገድ መፈጠሩ አይቀሬ ይመስለኛል፡፡ ኢትዮጵያን በአስተማማኝ መሠረት ላይ ለመገንባት (የ)ሚያስችለውን የብሔራዊ ዕርቅ መንገድ በመጓዝ ለፍትሃዊ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንገድ መጥረግ የማይፈልግ ኃይል በኢትዮጵያ ሕዝብ ሰቆቃ ላይ የራሱን ግላዊ ወይም ቡድናዊ ጥቅም ብቻ የሚያስቀድም መሆኑን ያመለክታል፡፡ ኢሕአዴግም ይሄን መንገድ እስከመረጠ ድረስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በኃይል ረግጦ የመግዛት ፍላጎቱን አሁንም ለመቀጠል እንደሚፈልግ ያሳያል፡፡ የማንወጣው መንገድ ቢሆንም ከተገደድን ግን ኢትዮጵያውያን በፀና ሰላማዊ ትግል ኢሕአዲግን ልኩን እንዲያውቅ ብሎም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፈቃድ እንዲገዛ ማድረግ አማራጭ የለውም፡፡ … (መስመር የተጨመረ) 

ወያኔ ልኩን የሚያውቀው በሰላማዊ ትግል ነውን? ይህ ነገር እውነት ይሆን? ይህች ነገር አጭር የክበበው ገዳን ቀልድ ትመስለኛለች፡፡

በመሠረቱ ጥሩ መመኘት በራሱ መጥፎ አይደለም፡፡ ነገር ግን የምኞትን ገደብ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ አንዱአለም ከዕድሜ አንጻርም ይሁን ከገጠመኝ ማጠጥ/ማጠር የተነሣ በኢትዮጵያ ምድር አይመኙትን ምኞት በመመኘት እርሱን መሳይ የዋሃንን በተስፋ ዳቦ ለመቀብተትና በከንቱ ለማስገሳት ሲጥር እንመለከታለን፡፡ እዚህም ላይ ወያኔን አለማወቁ ያሳዝነኛል፡፡ ማንበብ ጥሩ ነው፤ ማወቅና መመራመርም ጥሩ ነው፡፡ ተስፈኝነት መልካም ነው፡፡ ተስፋ አለመቁረጥና ሩቅ ማሰብም ደግ ነው፡፡ ይሁንና ጓዳችን ውስጥ እንደመዥገር ተለጥፎ በመርዘኛ ጥርስና ምላሱ እያንገበገበን የሚገኘውን ወያኔ በሰላማዊ ትግል ይወገዳል ብሎ ማሰብና መስበክ አንድም ባለማወቅም ቢሆን የወያኔን ዓላማ የማራመድ ያህል ነው አለዚያም ሞኝነት ነው፡፡ ቢሆን በወደድን፡፡ ግን ፈጽሞ አይሆንም – ተምኔታዊነት (ዩቶፒያን መሆን) ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ለኢትዮጵያ አብነት ሊሆን አይችልም፤ ማኅተመ ጋንዲ ለኢትዮጵያ አብነት ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚህ ምርጥ የዓለማችን ዜጎች የታገሉት ከሰዎች ጋር ነው፡፡ የኛን የሚለየው ትግላችን ከድፍን ቅል ዘረኞችና መቼም በማይበርድ እንዲያዉም እየሰላ በሚሄድ የጥላቻና የቂም በቀል አባዜ ከተሞሉ የባንዳ ልጆች ጋር ነው፡፡ ምናልባት አንዱአለም ያልተገነዘበው ይህንን ሃቅ ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ፡፡ በዚያ ላይ በሰላማዊ ትግል ቀርቶ በመሣሪያም የሚነቀንቃቸው እንዳይኖር ሕዝቡን በማይምነት ጋርደው፣ ፍጹም ከደረጃ በታች በሆነና “A,B,C,D”ን በቅጡ በማያስለይ እንዲሁም ዜጎችን በሚከፋፍል የትምህርት ሥርዓት ትውልድን አደድበው፣ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያንን በማይረባ የጥቅም ፍርፋሪ ከፋፍለው፣ በዘረኛ የፌዴራል ፖሊስ፣ በደንቆሮ ካድሬና መከላከያ አፍነው፣ በቅንድብ ጥቅሻና በስልክ ቀጭን ትዕዛዝ ወንበዴዎቹ የሚፈልጉትን ፍርድ በሚያስተላልፍ ኮንዶም ዳኞችና ፍርድ ቤቶች ሀገር ምድሩን ሞልተውት፣ ዜጎችን በጎጠኛ የፀጥታና ደኅንነት መዋቅር ቀፍድደው፣ በድህነት ኮድኩደው፣ በተለይ ወጣቱን በልዩ ልዩ ሱሶችና በወሲብ የአዶከብሬ ዛር ዳንኪራ አስረግጠው፣ በመርዘኛ የጎሰኝነትና የዘረኝነት በሽታ ሕዝበ አዳምን በክለው፣ … ከጠማማ ጎጆው ባለፈ – የሰኞን ነፍሱን ወደማክሰኞ በማሳደሩ ከመደሰት በዘለለ ለሀገርና ለወገን የሚቆረቆር ዜጋ እንዳይኖር አድርገው የሀገሪቱን ኅልውና ገደል ጫፍ ላይ ጥለውታል፡፡ ይህን ኃይል በሰላማዊ መንገድ እጥላለሁ ብሎ ማሰብ ዕብደት ነው የምለውም ለዚህ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድ ሥርዓት የመጨረሻ ፕሬዝደንት ኤፍ ደብልይው ደክለርክ ጭንቅላቱ ውስጥ ተሸክሞት ይዞር የነበረው ሊማር የሚችል ጤናማ ነጭ አንጎል እንጂ እንደወያኔ በድንቁርና የታጀለ ከመግደልና በሰው ስቃይ ከመደሰት ውጪ ምንም የማያውቅ የገማና የበሸቀጠ ጥቁር ጭቃ አልነበረም፡፡ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ማለት ለወያኔ አዲስና ለራሳቸው ለአባላቱም ቢሆን ግርታን የሚፈጥር ልዩ ተፈጥሮን እንደማላበስ ይቆጠራል፡፡…     

አፄ ኃ/ሥላሴ ለጉብኝት ይሁን ለሥራ ወዳንድ ቦታ ሲሄዱ አንዲት ችግረኛ ሴት ከነልጆቿ መንገድ ዳር ቆማ “ወድቃ በተነሳችው ባንዲራችን፣ በልዑል እግዚአብሔር ይሁንብዎ…” በማለት ባንዴራ ዘርግታ ታስቆማቸዋለች፡፡ ያኔ እንደዛሬው ዘመን መሪ ሲወጣና ሲገባ ግድግዳ እያስደገፉ (የሚገርም እኮ ነው!) ለገዢዎች የኅለውና መሠረት ከመሆናቸው አንጻር ውድና ብርቅ ሊሆኑ የሚገባቸውን ዜጎች በኢሰብአዊነት ማሰቃየት አልነበረምና ጃንሆይ መኪናቸውን አስቁመው በመውረድ “ችግርሽ ምንድነው?” ብለው ይጠይቋታል፡፡ ሴትዮዋም፣ “ጃንሆይ፣ ለምግብ ያላነሱ ለሥራ ያልደረሱ ስድስት ልጆችን ጥሎብኝ ባለቤቴ ሞተ…” ብላ ችግሯን መናገር ስትጀምር በቀልደኛነት የሚታወቁት የቀድሞው ንጉሣችን አጠገባቸው አጅበዋቸው ወደቆሙ መኳንንት ዘወር ብለው “አግባኝ ነው የምትለው?” ብለው እንደዋዛ ጣል ያደረጓት ቀልድ በሴትዮዋ ጆሮ ገብታ ኖሮ ድሃ መቼም ሞኝ ነውና “ጃንሆይ! ሆኖልኝ ነው! አ’ርጎት ነው!” አለች ይባላል፡፡ ቀልድ በአግባቡ ጥሩ ነው፡፡ ኃ/ሥላሴ ሴትዮዋን እንደማያገቧት ግልጽ ነው – ሴትዮዋ ግን ድሃና በዕውቀትም ዝቅተኛ ናትና በጣለችው ተስፋ አንፈርድባትም፡፡ ከወያኔ ጉያ ሕዝባዊ ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ ይገኛል ተብሎ ተስፋ ማድረግ ግን ከሴትዮዋ የበለጠ ጅል መሆንን የሚያመለክት እንጂ የወያኔን ተፈጥሮ ከመገንዘብ የሚመነጭ ገምቢ ዕውቀትና ጥበብ አይመስለኝም፡፡ ይህን የሚመር ቀልድ የሚቀልዱ ሰዎች ራሳቸውን ቢመረምሩ የተሻለ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግል ደግሞም በኢትዮጵያ – ሆ!

በጦርነት የሚገኝ ነገር መልካም ነው እያልኩ እንዳልሆነ ግን ይመዝገብልኝ፡፡ ምርጫ ከጠፋ ግና ምን ይደረጋል? ከሁለት መጥፎዎች የተሻለውን መምረጥ የምንገደድበት ጊዜ ይኖራል፡፡ እናም ሰው ካልሆነ አውሬ ጋር እየታገሉ ከማለቅ ቢያንስ የራሴ ነው ከሚሉት ጨካኝና አምባገነን መሪ ጋር መፋለም ይመረጣል – ለዚያም መብቃት እኮ መታደል ነው፡፡ እንደሚመስለኝ አሁን ሰዎችን እያሳሰባቸው ያለው የማያሳስብ ነገር ነው፡፡ ቀድሞ የመቀመጫየን ያለችው ፍጡር ወድዳ እንዳልሆነ መረዳት ተገቢ ነው፡፡ “ሌላውን እሾህ በመቀመጫየ ተቀምጬ ራሴው እነቅለዋለሁ” ማለቷ ነው፡፡ እና ያልበላንን የሚያኩልን ወገኖች አደብ ቢገዙልን ብዙ እንደረዱን ይቆጠራል፡፡ ለነገሩ ወያኔን ማንም ደገፈው ማን – በማወቅም ይሁን ባለማወቅ -  ወቅቱን ጠብቆ ወረደ መቃብሩን ሳይወድ በግዱ መቀበሉ አይቀርም፡፡ አንድዬ በመንበሩ ካለ – አለም- ይህን ሁሉ ግፍና በደል የፈጸሙ ሰው መሳይ “ሰዎች” የቁናቸውን ሳይከፈሉ ይቀራሉ ብሎ ማሰብ የታሪክንና የፈጣሪን ፍርድ አለመረዳት ነው፡፡ የሞተ ይነሳል፤ የተኛ ይነቃል፤ የቆመ ይቀመጣል፤ የተጋደመ ይቆማል፡፡ ለሁሉም ጊዜ እንዳለው ዛሬ አይደለም የምናውቀው፡፡ ታሪክና እግዜሩ ወያኔ ላይ ሲደርሱ ሥራቸውን ያቆሙ ይሆን? ለጅላጅሎቹ ወያኔዎች እንዲያ ሳይመስላቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ለኔ ግን በፍጹም! ጊዜው ቀርቧል፡፡

አገባቤና አወጣጤ የተምታታ ነገር ያለበት መሆኑ ይሰማኛል፡፡ ለዚህ የተምታታ ነገሬ ማንን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ ግን አላውቅም፡፡ የሆኖ ሆኖ የዚህ ዘመን እውነት ባብዛኛው የተዘበራረቀ በመሆኑ አላግባብ ሊፈርድብኝ የሚቃጣ እንደማይኖር እገምታለሁ፡፡ ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራልና ወደማይቀረው ድል እየተጠጋን ስንመጣ እንጫወታለን፡፡ ማርቲን ሉተር ባይቀድመኝ እኔም “ህልም አለኝ!” ብል በወደድኩ፡፡

“ቀኒቷን ማንም አያውቅም፡፡ ከጥቂቶች በስተቀር ብዙኃኑ ጎጋም እንኳን የምፅዓትን የመጨረሻ ቀን አያውቃትም፡፡ እናንተ የሚገባችሁ ታጥባችሁ ታጥናችሁ መጠበቅ ነው – ከሙስናና ከዕድፍ ርቃችሁ፤ ከዘረኝነት አረንቋና ከሆዳምነት ተቆጥባችሁ፤ አስተዋይነትን ተላብሳችሁ፣ በወረተኛ ወጀባዊ ንፋስ እንዳትወሰዱ ተጠንቅቃችሁ … ፡፡ ይሁንና ምልክቶቹን ስታዩ የቀኒቷን መቅረብ ትረዳላችሁ፡፡ ምልክቶቹን ያዬ ትውልድ ከምፅዓት በፊት የምትገለጠዋን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ቀን ያያታል፡፡ …” (‹መጽሐፈ ትንሣኤ ኢትዮጵያ› ፣ ምዕራፍና ቁጥር የማይነበብ!)  

በየነ

 More on —-http://www.freeandualemaragie.org/?p=359

- See more at: http://www.freeandualemaragie.org/?p=456#sthash.4FvUnrPp.dpuf

ሕወሃት/ኢሕአዴግ ምን ያህል እንዳከረረ (ክፍል 1) – ግርማ ካሳ

$
0
0

የ «ጌታቸውን » የአቶ መለስን ራእይ፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በትጋት እየፈጸሙት እንደሆነ በስፋት እያየን ነው። የአቶ መለስ ራእይ ጭቆና፣ አምባገነንነት፣ ሰላማዊ ዜጎችን ማሰር፣ ሜዲያዉን መጨፍለቅ ነው። የአቶ መለስ ራእይ በእርቅና በፍቅር አገርን ማሳደግ ሳይሆን፣ ማክረር በዜጎችን ላይ መጨከን ነው።


cartoon_691የፍቅርና የሰላም መጽሀፍን (መጽሐፍ ቅዱስን) በየቀኑ አነባለሁ በሚሉት በአቶ ኃይለማሪያም አገዛዝ ግን፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ በመለስ ጊዜ ከነበረው በባሰ ሁኔታ በጣም እያከረረ መጥቷል። በርግጥም አቶ ኀያለማሪያም የአቶ መለስስ ፎቶ እየተሳለሙ ቃል እንደገቡት፣ የአቶ መለስን ራእይ በትጋት እያስፈጸሙ ናቸው።

ምን ያህል አገዛዙ እንዳከረረ የሚያሳይ አንድ ጉልህ ማስረጃ፣ በተለይም በሜዴያዉ አንጻር እንዳቀርብ ይፈቀድለኝ። በምንም አይነት ሕወሃት/ኢሕአዴግ እንዲነገርና እንዲጻፍ ከሚፈለገው ውጭ መጻፍ እንደማይቻል እያየን ነው። ኢቲቪ የመሳሰሉቱ ደግሞ እንደ ሰዉ ለሰው ድራማ ያሉትን ከማየት ዉጭ፣ አስቀያሚ ሜዲያዎች ሆነዋል። በጣም አስቀያሚ !!!!! እነ ሪፖርተር፣ አዲስ ፎርቹን የመሳሰሉቱ፣ የአገዛዙ ቱጃሮች ማስታወቂያ የሚያወጡበት፣ በአገዛዙ እየተደገፉ የሚንቀሳቀሱ፣ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር ኮድን የማይተገብሩ፣ በአጋር ጋዜጠኖች ላይ የሚደርሰው ግፍ የማይሰማቸውና የማይቆረቆሩ፣ ለይስሙላ የሜዱያ ነጻነት አለ ለማስባል ለአገዛዙ የፖለቲካ ፍጆታ የሚዉሉ፣ በአደርባይነት የተሞሉ ፣ ጋዜጠኖች ሊባሉ የማይገባ ጋዜጦች ናቸው።

በአቶ መለስ ጊዜ የታሰሩ ጋዜጠኖች

1. ርዮት አለሙ (የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ)
2. እስክንደር ነጋ
ከ2002 ምርጫ በኋላ በአቶ መለስ ጊዜ የተሰደዱ ጋዜጠኖች
1. አብይ ተከለማሪያም ( አዲስ ነገር)
2. መስፍን ነጋሽ (አዲስ ነገር)
3. ታምራት ነገራ (አዲስ ነገር)
4. አቤ ቶኪቻው (አዉራምባ ታይምስ)
5. ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ተሰዶ ነበር ፣ አሁን ሰላም ነው ብሎ ተመልሷል

ከ2002 ምርጫ በኋላ በአቶ መለስ ጊዜ እንዳይታተሙ ወይም ክስ የተመሰረተባቸው ጋዜጦች
1. አዲስ ነገር

በዳግማዊው መለስ ዜናዊ ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት አመት አገዛዝ፣ ወደ ወህኒ የተወሰዱ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች (ሁሉም በሽብተኘት የተከሰሱ)
1. ተስፋለም ወልደየስ
2. አጥናፉ ብርሃኔ
3. ዘላለም ክብረት
4. ኤዶም ካሳዬ
5. ናትናኤል ፈለቀ
6. ማህሌት ፋንታሁን
7. አቤል ዋበላ
8. በፍቃዱ ኃይሉ
9. አስማማዉ ወልደጊዮርጊስ

በዳግማዊው መለስ ዜናዊ ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት አመት አገዛዝ፣ ከአገር የተሰደዱ ጋዜጠኖችና ብሎገሮች
1. ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ( የሎሚ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
2. ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው (የአፍሮ ታይምስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
3. ጋዜጠኛ ዳንኤል ድርሻ (የሎሚ መጽሔት ሚዲያ ዳይሬክተር)
4. ጋዜጠኛ ሰናይ አባተ (የሎሚ መጽሔት ዋና አዘጋጅ)
5. ጋዜጠኛ ሰብለወርቅ መከተ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)
6. ጋዜጠኛ አቦነሽ አበራ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)
7. ጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ (የጃኖ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
8. አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የሮዝ አሳታሚ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ )
9. አቶ ኢብራሃም ሻፊ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅ)
10. እንዳለ ተሺና (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ከፍተኛ አዘጋጅ )
11. ሀብታሙ ሥዩም (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ዓምደኛ)
12. ዳዊት ሰለሞን (ታዋቂ ብሎገር)
13. ዘሪሁን ሙሉጌታ ( የሰንደቅ ጋዜጣ ረፖርተር)

በዳግማዊው መለስ ዜናዊ ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለት አመት አገዛዝ፣ ሕተመታቸው የተቋረጠ ወይንም ክስ የቀረበባቸው
1. ፍትህ ጋዜጣ
2. ፍኖት ነጻኘት ጋዜጣ
3. የአዲስ ጉዳይ መጽሔት
4. የፋክት መጽሄት
5. የሎሚ መጽሄት
6. የጃኖ መጽሄት
7. የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ

- See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=1504#sthash.XlU4d27X.dpuf


የአቶ ሃ/ማርያም ደህንነት

$
0
0

ከኢየሩሳሌም አረአያ

እያብ ምህረተአብ ይባላል፤ ኤርትራዊው እያብ በ1968 ዓ.ም ሕወሐት እንደተቀላቀለ ከታማኝ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል። ከ6ኛ ክፍል ያቋረጠውን ትምህርት አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ሲቪል ሰርቪስ ተምሮ “ተመረቀ” ተባለ። የሜጋ ፎቶግራፍ ሆኖ ተመደበ። ህንድ አገር ሄዶ ተማረ ከተባለ በኋላ ሲመለስ ስብሃት ነጋ የኤፈርት ሃላፊ በነበሩበት ወቅት አማካሪ ዴክስ ተደርጎ ተሾመ። አቶ ሳሙኤል ገ/ዋህድ የተባለ የጠ/ሚ/ር መለስ አማካሪ በ1996ዓ.ም በኢሮብ ህዝብ በጥይት ተደብድቦ ከተገደለ በኋላ በቦታው እያብ ተሾመ። በ2002 ምርጫ ሃይለማርያም ደሳለኝ ም/ል ጠ/ሚ/ር ተደርገው ሲሾሙ እያብ ደግሞ በመለስ ዜናዊ የጠ/ሚ/ር ረዳት (አማካሪ) በሚል ሽፋን ተመደበ። እያብ የተሾመው የሃ/ማርያምን እንቅስቃሴ እግር በግር እንዲከታተል በመለስ ደህንነት ተደርጐ መመደቡን ምንጮቹ ያመለክታሉ።
Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn walks arrives a day before the G20 Summit, St. Petersburg, Sept. 4, 2013.
የእያብ እህት ወ/ሮ ሂሩት ምህርተአብ ትባላለች፤ ሂሩት የአባዲ ዘሞ ባለቤት ስትሆን የትግራይ ክልል ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ናት። መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ እያብ የጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም ልዩ አማካሪ ተብሎ በነደብረፂዮን የተመደበ ሲሆን ሃ/ማርያምን የሚዘውረው እያብ ነው። ከህወሀት ባለስልጣናት ተወስነው የሚመጡ ማናቸውም ጉዳዮች ሃ/ማርያም እንዲፈርሙ የሚደረገው በእያብ መሆኑን ምንጮቹ ያረጋግጣሉ። የጋምቤላ የቀድሞ ፕ/ትና የአንዳርጋቸው መያዝ እንዲሁም የተቃዋሚ አመራሮችና ጋዜጠኞች ወዘተ..እስርና አፈና ውሳኔ በሕወሐት ሹማምንት ከተወሰነ በኋላ ለፊርማ ሃ/ማርያም ዘንድ የሚመጣው በእያብ በኩል ነው። 12ቱ ወሳኞችን በተመለከተ እመልስበታለሁ።

 

 

ጠበቃ አቶ ተማም እና ማአከላዊ እስር ቤት

$
0
0

ከይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

ጠበቃ አቶ ተማም አባ ቡልጉ በጥብቃና ሙያችው እጅግ በጣም ዝና ያተረፉ ናቸው፡፡በተለይ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በገዥው የወያኔ መንግስት ለእሰር ከተዳረጉበት ጊዜ አንስቶ ጉዳያቸውን በመከታተል ለእነ አብበከር ጠበቃ በመሆን አገራዊ እና ሙያዊ ግዴታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ ይህ በእንዲ እንዳለ የግንቦት ሰባት ዋና ፃሃፊ አቶ አድርጋቸው ፅጌ በህግ ወጥ መንገድ መያዝን ተከትሎ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ፓርቲዎች መካከል የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ም/ት ሰብሳቤ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ከአንድነት አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ከአረና አቶ አብረሃ ደስታ በወያኔ መንግስት በሃይል መያዛቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ጠበቃ አቶ ተማም ከእረዳታቸው ከጠበቃ ከአቶ ገበየሁ ጋር በመሆን በፍርድ ቤት የእነ ሀብታሙን ጉዳዩን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

እነ አብርሃ ደስታ ለእስር ከተዳረጉ ሁለት ወር ሊሞላቸው የተወሰነ ቀናት ይቀራቸዋል፤በነዚህ ቀናት ውጥ ከታሰሩ ለ20 ቀናት ከቤተሰብ፣ከጠበቃ እና ከወዳጅ ዘመድ እንዳይገኛኙ የተደረጉ ሲሆን፡፡ ጠበቃ አቶ ተማም ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል እነ የሺዋስ ከጠበቃቸው ጋር እንዲገኛኙ ማህከላዊ እስር ቤት በወቅቱ ሊፈቅድ የቻለ ሲሆን በዚህም ምክንያት ታሳሪዎች ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ለመገኛኘት ችለዋል፡፡ይሁን እንጂ በተያዙ በ28 እና በ29 ቀናቸው ፍርድ ቤት ቀርበው መንግሰት “በሽብርተኝነት” ከከሰሳቸው በኋላ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀባቸው ሲሆን የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት ከፈቀደበት ቀን አንስቶ ይህ ፁሁፍ እስከቀረበት ወቅት ታሳሪዎች ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ተደርጓአል፡፡

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ


ነሃሴ 21 ቀን 2006 ዓ.ም ጠበቃ አቶ ተማም ወደ ደንበኞቻቸው እነ ዳንኤል ሽበሺ ጋር መአከላዊ እስር ቤት የሄዱ ቢሆንም ለመገናኘት አልቻሉም፡፡በወቅቱ ስለ ገጠማቸው ነገር ከእኔ ጋር ስንወያይ የገለፁልኝ ነገር እጅግ በጣም የሚያስገርም ነገር በመሆኑ ለዚህ ፁሁፍ አንባቢ ሁኔታውን ለማካፈል እውዳለው፡፡ ጠበቃ አቶ ተማም ወደ ማእከላዊ እስር ቤት በመሄድ ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል “ደንበኞቼን ለማነጋገር ነው የመጣሁት” በማለት አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው የጠየቁ ቢሆንም ጉዳዩ የሚመለከተው ፖሊስ “ማናገር አትችልም፣ሂድ ውጣ” ይላቸዋል ፡፡ እሳቸውም “እንዲ ማለት አይገባህም እኔ ለደንበኞቺ ህጋዊ ጠበቃ ነኝ ስለ ደንበኞቼ ማውቅ የሚገባኝ ነገር ስላለ ልተከላከለኝ አይገባም” በማለት ከፖሊሱ ጋር ከፍተኛ የሆነ የቃላት ግብግብ ይፈጠራል፡፡ በዚህን ወቅት ሌሎች ፖሊሶች ገላጋይ ሆነው በመቅረብ ጉዳይ እንዲረግብ ጥረት ያደርጋሉ፡፡በወቅቱም የቀረበው ማስታረቂያ ሃሳብ ጉዳዩ ለበላይ አካል ይቅረብ ፤ይህን ጉዳይ የሚመለከቱት ስብሰባ ላይ ስለሆኑ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ይመለሱ በማለት ማስታረቂያ ሃሳብ ፖሊሶች ያቀርባሉ፡፡የነገሩ ሁኔታ ያላማራቸው እና ጉዳዩን በጥበብ ለማለፍ የፈለጉት ጠበቃ አቶ ተማም ዋና ሃላፊ የተባለው ሰው ከስበሰባ እስኪወጣ ብና ልጠጣ በማለት ከማአከላዊ ጊቢ ይወጣሉ፡፡

የዕለቱ አስገራሚ ነገር ከዚህ ይጀምራል፡፡አቶ ተማም ከማህከላዊ እስር ቤት ፍለፊት ወደሚገኘው ሐረር ብና ወደሚባለው ካፊ በመሄድ በካፊው ውስጥ ከሚገኘው መቀመጫ ወደ አንዱ በማምራት ለመቀመጥ ሲሉ ድንገት ዞር ሲሉ በማአከላዊ እስር ቤት አላስቆም አላስቀምጥ ያላቸው ፖሊስ ፊለፊት ከአጠገባቸው ቆሞ ያገኙታል በዚህወቅት “ እባክህ ብና ጠጣ ና ቁጭ በል በማለት በአክብሮት ይጠይቁታል” ፡፡ይህ ፖሊስ በክፈተኛ ሁኔታ ከእነ የሺዋስ ጋር አቶ ተማም እንዳይገናኙ ሲከላከል የነበረው ነው ፡፡ ለአቶ ተማም አክብሮት ፖሊስ ጠብ ያለሽ በዳቦ አይነት ጨዋታ ያማረው ስለሆነ ምላሹ “እኔን በግቦ አትደልለኝም እከስአለው” በማለት እየተውረገረገ ወደ ማአከላዊ ያመራል ፡፡ለነገሩ ዋናው ተልኮ ይህ ስለሆነ ተላላኪው ፖሊስ የእለቱ ግዳጁን ይወጣል፡፡

አቶ ተማም ለ30 ደቂቃ ያህል ብናቸው እየጠጡ ጊዚያቸውን ካሳለፉ በኋላ ተመልሰው ወደ ማአከላዊ ያመራሉ ፡፡ከበር ሆኖ የሚጠብቃቸው ፖሊስ “ሃላፊው ቢሮ ይፈለጋሉ፤ወደ-ዚያወ ይሂዱ” ብሎ ይነግራቸዋል ፤እሳቸውም ወደ ተጠቀሰው ቢሮ ይሄዳሉ፡፡ወደተጠቀሰው ቢሮ ሲገብ ያልጠበቁት ነገር ይገጥማቸዋል “አቶ ተማም !ከእርሶ ይሄ አይጠበቅም እንዴት ፖሊስን ለመደለል ይሞክራሉ ? እርሶ የህግ ባለሙያ ኖት እንዲ አይነቱ ነገር መፈፀም ወንጅል መሆኑ ያወቃሉ፤በመሆኑም ክስ ተከሰዋል” በማልት ይነግራቸዋል፡፡ እሳቸውም በሁኔታው በመገረም “እኔ ሙያዊ ግዴታዬን ጠንቅቂ የማውቅ ሰው ነኝ! ደግሞም ከደንበኞቼ ጋር መገናኘት መብትም ጭምር ነው፡፡ይህ መሆን እያወኩ አንተ የምትለው አይነት ስእተት አልሰራም፤ይህ ሐሰት የሆነ ነገር ነው” በማለት ይመልሳሉ፡፡ ሃላፊ የተባለው ፖሊስ “ለማንኛውም እዚህ ይቆዩ” በማለት መውጣትም በማይቻልበት ቢሮ ውስጥ ጥሏቸው ይሄዳል፡፡ እዚህ ቆዩ ያላቸው ፖሊስ መጥቶ አንድ ነግር ይለኛል ብለው ቢጠብቁም ለተወሰነ ሰዓታት ያህል ከማንም እንዳይገናኙ ተደርገው በአንድ ቢሮ ውስጥ ታግተው ሊቆዩ ችለዋል፡፡ ከሰዓታት ቆይታ ኋላ ሃላፊ ነው የተባለው ፖሊስ በመምጣት “ ከአንድ ባለሙያ የማይጠበቅ ነገር ነው ያደረከው፤ለማንኛውም ለዛሬ ጉዳዩን ትተነዋል ፡፡ አሁን እስረኛ መጠየቂያ ጊዜ ሰዓቱ ስላለፍ አርብ መጥተ መጠየቅ ትችላለ” በማለት ያስናብታቸዋል፡፡

አቶ ተመማ በገጠማቸው ነገር እጅግ በጣም ቢበሳጩም ሙያዊ እና አገራዊ ግዴታቸውን ቅድሚያ በመስጠት፤ ይህ በሆነ ከአንድ ቀን ቆይታ በኋላ ማለትም ዛሬ ነሃሴ 23 ቀን 2006 ዓ.ም በድጋሚ ወደ ደንበኞቻቸው ማአከላዊ እስር ቤት ይሄዳሉ፡፡ሆኖም ግን ከማአካለዊ እስር ቤት የፊተኛው በር ጀምሮ እስከ ሚመለከተው ቢሮ ድረስ ከፍተኛ የሆነ ውጣ-ውረድ ደርሶባቸዋል፡፡በስተመጨረሻም ዋና አላፊ ነው የተባለው ሰው “እስረኞችን ማግኘት የምትችለው በችሎት ነው፤አሁን ልናገናኝ አንችልም” በማለት አሰናብቷቸዋል፡፡በሆኖም ነገር ጠበቃ አቶ ተማም ከልብ ማዘናቸውን ለመረዳት ችያለው፡፡
የገዥው መንገስት ህግመንግሰት እንደሚለው ከሆነ “በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ መልኩ የመያዝ እና ከህግ አማካሪያቸው፣ ከዘመዶቻቸው እና ከጠያቂዎቻቸው የመገናኘት መብት አላቸው፡፡” በማለት በህገመንግስቱ አንቀፅ 21/ ንዑስ አንቀፅ 1እና2 ተፅፎ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ እስረኞች አያያዛቸው ክብርን ከመንካት አልፎ በህይወታቸው ላይ አደጋ የሚያስከትል ነው፡፡በተጨማሪ ከቤተሰብ፣ከወዳጅ መጠየቅ የማይሞከር ነገር ነው፤ የመጠየቅ እድል ያላቸው እስረኞች እድላቸው በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ነገር ግን እንዲህ አይነቱ የለየለት መንግሰትዊ ውንብድና የአምባገነን መንግሰት ስርዓት የመጨራሽ የውድቀቱ ምልክት እንደሆነ ግልፅ ማሳያ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

እውነት አብርሃ ደስታ አሸባሪ ወይስ ህወሓት? ኢህአዴግ ነው ለሰላማዊ ትግል ፈሪ?

$
0
0

ክብሮም ብርሃነ (መቐለ)

Free Abreha Desta አብርሃ ደስታ ይፈታ

Free Abreha Desta አብርሃ ደስታ ይፈታ

ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም የአረና ትግራይ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር አብርሃ ደስታ በሽብር ተጠርጥሮ በተከሰሰበት ልክ በወሩ ፍ/ቤት እንደሚቀርብ በፌስ ቡክ አይቼ እኔም እንደ ዜጋና እንደ አድናቂው የሚቀርቡለትን የድራማ ክስ ለመስማት ጓጉቼ ፍ/ቤቱ ስደርስ እንደ እኔ አብርሃ ደስታን በአይናቸው ለማየትና የክሱን ድራማ ለማወቅ እንዲሁም ለቆራጡ ወጣት ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ የሞራል ድጋፍ ለመስጠት የተሰባሰቡ የተለያዩ የክልላዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ አባላት፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች እንዲሁም የወጣቱ ፖለቲከኛ አድናቂዎች ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተደማምረው ያልገመትኩት የሕዝብ ብዛት በቡድን በቡድን ሰብሰብ ብለው የአብርሃ ቆራጥነትና የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ሲወያዩ አገኘኋቸው፡፡
የክሱን ሁኔታ ለመመልከት የመጡ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች
*******************************************
1. የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ተክሌ በቀለ
2. የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ም/ፕሩዚዳንት አቶ በላይ ፍቃዱ
3. የሰማያዊ ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ስለሺ ፈይሳ
4. የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው
5. የጌድኦ ሕዝብ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኣቶ ኣለሳ መንገሻ እንዲሁም ጋዜጤኞች፣ ብዙ የታወቁ ሰዎችና ወጣት አድናቂዎቹ ተገኝተዋል፡፡

አብርሃ ደስታ ወደ ፍ/ቤት ሲገባ
**********************************
አብርሃ ወደ ፍ/ቤቱ ግቢ ከመድረሱ በፊት ቁመቱ ትንሽ ረዘም ያለ የፊቱ ቀለም አብርሃን የሚመስል አንድ የትግራይ ተወላጅ ደህንነት (ለራሱ ያልዳነ) ከኋላው ሶስት ጠመንጃ ያነገቡ የፌዴራል ፖሊስ አስከትሎ ሲገባ አብርሃ ደስታን ለማየት ጓጉቶ የነበረ የአዲስ አበባ አድናቂዎቹ ‹‹ መጣ ……. መጣ…….. ›› ማለት ጀመሩ፡፡ ደህንነቱና የፌዴራል ፖሊሶቹ ልክ እንደገቡ ፊታቸውን ከሰል አስመስለው “ገለል በሉ …. ዞር በሉ ……!” እያሉ ትዕዛዝ ስለሰጡ ራቅ ብለን ተሰለፉ ሳንባል ፊታችን ወደ ዋናው መንገድ አድርገን ራሳችን ተሰለፍን
አንድ የፌዴራል ፖሊስ ከፊቱ ሆኖ እየመራው አብርሃ በኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ያለውን የመልካም አስተዳደር እጦት እንዲሁም የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና አፈና ለመግለጽ ቀለም የሚያንጠባጥብ ብዕር መያዝ ብቻ የለመዱ እጆቹ በብረት ሰራሽ ካቴና ክርችም ብሎ እልህ የሚነበብበት ፊቱ ጠቆር ብሎ፣ ሰውነቱ ከሳ ብሎ ሁለት የፌዴራል ፖሊስ አስከትሎ ገባ፡፡ ልክ ሙሽራ ሲመጣ እንደምናደርገው አቀባበል ወደ ፍ/ቤቱ ግቢ እንደገባ ያ ሁሉ ሕዝብ ግቢውን በጭብጨባ ቅውጥ አደረገው ያኔ አብርሃ ደስታ ግራ ገባው፡፡ ያ ሁሉ ሰው በሰልፍ ቆሞ ሙሽራ እንደመጣ ሲያጨበጭብ ይሆናል ብሎ ስላልጠበቀ መሰለኝ ጭብጨባው ለራሱ አልመሰለውም፡፡ አንድ ሁለት እርምጃ እንደሄደ ቀና ብሎ ሲያይ ብዙ የሚያውቃቸው ሰዎች ሲያይና ‹‹ አይዞህ!……. አይዞህ!……. አብርሃ የኛ ጀግና! ከጎንህ ነን! ›› እያሉ እጃቸውን እያወዛወዙ ሰላምታና ሞራል ሲሰጡት ለሱ መሆኑን ሲያውቅ ፊቱን ፈገግ በማድረግ የታሰሩ እጆቹን ከፍ በማድረግና ከወቡ ጎንበስ በማለት በተደረገለት አክብሮትና ሞራል የጨዋ ምላሽ እየሰጠ ወደ ችሎቱ ገባ፡፡
የግቢውን በር ከረገጠበት ጀምሮ ችሎት እስከሚገባ ድረስ ባለማቋረጥ በኃይለኛ ጭብጨባ ታጀበ፡፡ ያኔ ይዞት የመጣው ደህንነት በጣም ስለበሸቀ ‹‹ ስነስርዓት አድርጉ!…. ስነስርዓት አድርጉ!…. ›› ቢልም ሀሳቡ ስነስርዓት የሚያሲዝ ስላልነበረ መሰለኝ ጆሮ የሚሰጠው አልነበረም፡፡ አስከትሎም ምንም እንኳ በግልጽ ለማን መሆኑ ባይታወቅም “ቆይ አሳይሃለሁ!…. ኋላ ይቆጭሃል!…. ” እያለ ማስፈራራት ጀመረ፡፡ ይህን የሚገልጽ አንድ የትግርኛ አባባል አለ፡፡ ምን ይላል መሰላችሁ “ሰበይቱያ ዝለአኸቶስ ደገአፍ ቤተመንግስቲ አይፈርሕን ” በአማርኛም እንደዚህ “ሚስቱ የላከችው ሞት አይፈራም ” ይባላል፡፡ ያ ያልዳነ ድህንነትም ያመነው ነገር ባይኖር ህግ ባለበት ሀገር ደህንነት በመሆኑ ብቻ እንዲህ ብሎ ሰው ማስፈራራት አይችልም ነበር፡፡
“ቆይ አሳይሃለሁ!… ኋላ ይቆጭሃል!….” ማለቱ አንተም በሽብር ከስሼህ አሰቃይሃለሁ ማለቱ ይሆን?
በነገራችን ላይ አብርሃ ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ የተቀጠረው በ8፡00 ሰዓት ነበር፡፡ አብርሃን ለማየት የተሰበሰበ የሕዝብ ቁጥር አላምር ስላላቸው መሰለኝ ምናልባት ተሰላችተው ይሄዱ ይሆናል በሚል ታሳቢ እስከ 10 ሰዓት ከ25 አላቀረቡትም ነበር፡፡ ሕዝቡም ይሄን ተረድቶ እስከ 12 ሰዓትም ቢሆን እንቆያለን ብሎ በመረጋጋቱ እንደማይሆንላቸው አውቆ 10 ሰዓት ከ25 ሲል ነው ያመጡት፡፡ ይህ ግን በአብርሃ ብቻ ሳይሆን በእነ ሀብታሙ አያሌውም እንዲህ ተደርጓል፡፡ የሆነው ሆኖ ከግማሽ ሰዓት የችሎት ቆይታ አብርሃ እንደገና ታጅቦ ከችሎት ወጣ፡፡ ሲወጣም እንደገና ቅልጥ ያለ ጭብጨባና ሞራል ሲሰጠው ፈገግ እያለ አፉ ባይናገርም በታሰሩ እጆቹ አይዟችሁ እያለ እጅ እየነሳ ወጣ፡፡

የአብርሃ ደስታ ክስ በፖሊስ ሲነበብ
********************************

ክብሮም ብርሃነ

ክብሮም ብርሃነ

አብርሃ ችሎት ከገባ በኋላ አጠገቡ የነበረው በሙያውና በስነምግባሩ የታወቀ እንዲሁም ከብር ይልቅ ለፍትህ ቅድሚያ የሚሰጥ ጠበቃው ተማም አባቡልጉ ብቻ ነበር፡፡ ኋላ ግን ሁለት የአረና አመራርና አንድ የአክስቱ ልጅ ገብተው የክሱን ሁኔታ እንዲከታተሉ ስለተፈቀደላቸው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተከታትለዋል፡፡
አጠቃላይ የክሱ ጭብጥ
***********************
1. አረና ትግራይ ሽፋን በማድረግ ከግንቦት 7 አመራሮች እየተገናኘና ገንዘብ እየተቀበለ ሽብርን ለመፍጠር ተንቀሳቅሷል፡፡
2. ሽብር ለመፈጸም 60 ሰዎች መልምሏል፡፡
3. በቤቱ ሽብር ለመፈጸም የሚያስችል ዶክመንት በፍተሻ ተገኝቷል የሚሉ ነበሩ፡፡
መቼም ቢሆን አብርሃ ደስታ ይህን የፈጠራ ክስ ፈጽሞት ይሆን? ብሎ የሚጠራጠር ካለ የዘመኑ በጣም የዋህ ወይም የህወሓት/ኢህአዴግ መሰሪ ሴራና ተንኮል የማያውቅ ብቻ ነው፡፡ አብርሃ ህወሓት የሚፈጽማቸውን አፈናዎችና የህግ ጥሰቶች በየቀኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እያሳወቀ በመሄዱና ሕዝብ በጽናት ታግሎ በሚቀጥለው ምርጫ ከትከሻው አሽቀንጥሮ መጣል እንዳለበት በድህረ ገጾችና በመጽሔቶች እየጻፈ ለብዙ ወጣቶች አርአያ እየሆነ በመሄዱና የትግራይ ሕዝብ የህወሓት ክህደትን አውቆ ለዳግም ሰላማዊ ትግል በሁሉ አቅጣጫ እንዲነሳሳ ማድረጉ ለህወሓት ትልቅ የራስ ምታት ስለሆነበት ነው እንጂ አብርሃ ደስታ የተከሰሰበትን የፈጠራ ክስ እንደማይፈጽምና እንዲህ አይነት ተልካሻ ስራ በሚወዳት ሀገሩና በሚወደው ሕዝብ ላይ ለመስራት የሚያዘው ጭንቅላት እንደሌለው አብርሃን በቅርበት የሚያውቁት ሁሉ ይመሰክሩለታል፡፡

አብርሃ ደስታ ለፍ/ቤቱ ካቀረባቸው አቤቱታዎች
1. በጣም ቀዝቃዛና ጨለማ በሆነ ቤት ብቻውን እየታሰረ እንዳለ
2. ፍ/ቤት እስከቀረበበት ጊዜ 8 የተለያዩ ግለሰቦች ከለሊቱ ከ7 እስከ 8 ሰዓት በየተራ እየመጡ እንደሚደበድቡት
(እንደሚያሰቃዩት)
3. በጭለማ ቤት ሆኖ የማያውቀውንና ያላነበበውን ጽሑፍ (ዶክመንት) እየተደበደበ እንዲፈርም እንደተደረገ
4. የቆየ የጨጓራ ህመም ስላለው እንጀራ ብዙም እንደማይማይበላና ሆኖም ግን አሁን ያለ ፍላጎቱ እያመመው እንዲበላ ስለተገደደ በከፍተኛ የጨጓራ ህመም እየተሰቃየ እንዳለ፣ በማዕከላዊ (ታስሮ ባለበት ቦታ) በሚደረግለትን የህክምና ዕርዳታ ሊያገግም እንዳልቻለ እነዚህና ሌሎች እየደረሱበት ያሉ ስቃዮች ምንም እንኳን ሰሚ ባያገኝም በአቤቱታ መልክ አቅርቧል፡፡
የተከበራችሁ አንባቢዎች እውነት አብርሃና መሰሎቹ ሽብርን ለመፈጸም በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ ተይዞ ከሆነ እመኑ እየተባሉ ያ ሁሉ መደብደብ፣ መሰቃየትና ሳያነቡ ጽሑፍ እንዲፈርሙ መደረጉ ለምን አስፈለገ? የተገኘ እውነተኛ መረጃ ለሕዝብ ግልጽ አይደረግም? ፍርዱን ሕሊና ላለው ሰው ይሁን፡፡

በጠበቃው ተማም አባቡልጉ የቀረበ ክርክር
አንድ ሰው በወንጀል ተጠርጥሮ ሲየዝ በቂ የሆነ መረጃና ማስረጃ መኖር አለበት (ሕገ መንግስት እያጣቀሰ) አለበለዚያ ሰውን አስረህ ፖሊስ መረጃና ማስረጃ ላሰባስብ ጊዜ ይሰጠኝ ስላለ ብቻ ከበቂ በላይ ጊዜ እየተሰጠ ሰው ማሰቃየት ከህግ በላይ መሆን ነው፡፡ ወይም ሰው በእምነቱ እንዳይጓዝ ለመገደብ የሚደረግ ህገ መንግስቱን የጣሰ አካሄድ ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም ፖሊስ ከዚህ ቀደም በቂ ጊዜ ተሰጥቶት እያለ ትርጉም ያለው መረጃና ማስረጃ ሊያቀርብ ስላልቻለ አሁንም እንደገና ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ መጠየቁ ደንበኛዬ ከስራው ለማስተጓጎልና ለማሰቃየት ካልሆነ ሌላ ዓላማ ስለሌለው ደንበኛዬ የዋስ መብቱ እንዲከበርለትና በዋስ ተፈትቶ ክሱን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል ይወሰንልኝ ብሎ ህገ መንግስቱን ተንተርሶ ተከራክሮዋል፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው ከሳሹና ፈራጁ አንድ በሆነበት ሀገር ፍትህ እንዴት ይገኛል? ድሮም እኮ ፍትህ ቢኖር በፈጠራ ክስ ሰው አይከሰስም ነበር፡፡ እንዲህ ስለሆነ እንደገና ከ28 ቀናት በኋላ ነሐሴ 29 ፍርድ ቤት ይቀርባል ተባለ፡፡

በዛን ቀን የታዘብኩት ነገር
ህወሓት/ኢህአዴግ በቋንቋ፣ በብሔርና በጎጥ ከፋፍሎ ሲገዛን የራሱና ለራሱ ብቻ የሚሆን ምክንያት አለው፡፡ ነገር ግን ያን ቀን የታዘብኩት ነገር ካለ በህወሓት/ኢህአዴግ ሴራ ኢትዮጵያዊነታችን አሁንም ጨርሶ እንደማይናድ ነው፡፡ ምክንያቱም ህወሓት/ኢህአዴግ አብርሃን መቐለ ይዘው አዲስ አበባ ፍ/ቤት ሲያቀርቡት የፍርድ ሂደቱን የሚከታተል ብዙ ሰው ስለማይኖር የአብርሃ ሞራል ይጎዳል ብለው ይሆንናል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችን እኩል አይቶ በእኩል የሚቆረቆር፣ ከግላዊ ጥቅምና ክብር የሕዝብ ጥቅምና ክብር የሚያስቀድም እንዲሁም የሀገርና የሕዝብ መብትና አንድነት ይከበር ብሎ በፅናት በአደባባይ የሚከራከር ኢትዮጵየዊ ከየትኛውም ብሔር ወይም ክልል ይምጣ፣ የፈለገውን ቋንቋ ይናገር በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተለየ ክብርና ሞገስ እንዳለውና ሁሌም ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንደሆኑ በደንብ ተረድቻለሁ፡፡ አሳሪዎቹም ጭንቅላት ካላቸው ሳይረዱት አይቀርም፡፡ እንዴት ብትሉኝ አብርሃ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ቢሆንም ህወሓት/ኢህአዴግ እርስ በእርሳችን በጥላቻ አይን ከመተያየት አልፈን እንዳንተባበር የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ሴራዎችን ሰብሮ የአብርሃ ጉዳይ የሁላችን ጉዳይ ስለሆነ ያሳስበናል ብሎ ብሔር፣ ቋንቋ እንዲሁም የህወሓት/ኢህአዴግ የመከፋፈል ሴራ ሳይገድባቸው የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞና የደቡብ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን በአንድነት የግል ስራቸውን ትተው የወጣት ፖለቲከኛና መምህር አብርሃ ደስታ የፍርድ ሂደት ሲከታተሉ መዋላቸውና ከፍተኛ ሞራል መስጠታቸውን ሳይ ኢትዮጵያዊነታችን በህወሓት/ኢህአዴግ ሴራ ጨርሶ እንደማይሸረሸር አረጋግጫለሁ፡፡ በኢትዮጵያዊነቴም ኩራት ይሰማኛል፡፡ አሁንም ገዢዎች በሚያደርጉት ሴራ እኛ ኢትዮጵያዊያን መለያየትና መቀያየም የለብንም፡፡ ለጋራ ዓላማና ጥቅም በጋራ መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ስንተባበር ክንዳችን ይጠነክራል ሞራላችን ከፍ ይላል፡፡
ቸር እንሰንብት!

አንድ ቀን የፍትህና የነፃነት ባለቤቶች እንደምንሆን አልጠራጠርም!

ፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማርያም በዐማራው ቁስል ላይ ጨው ነሰነሱ! የ«ዐማራ የለም» አቋም የክህደት ወይስ የመሣት?

$
0
0

PDF

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት       እሑድ ነሐሴ ፳፭ ቀን ፪ሺህ፮  ዓ.ም.      ቅፅ ፪ ፣ ቁጥር ፳፯

ሰሞኑን ፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማርያም «ሸገር» ከተሰኘ በኤፍ.ኤም. 102.1 (FM 102.1) ከአዲስ አበባ መርኃግብሩን ከሚያሠራጭ የሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ «ዐማራ» የሚባል ነገድ በኢትዮጵያ አለመኖሩን ልባቸውን ነፍተው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ፕሮፌሠር መሥፍን በዚህ ቃላቸው፣ በ፲፱፹፫(1983)ዓ.ም. ከሟቹ የትግሬ-ወያኔዎች መሪ መለስ ዜናዊ ጋር በቴሌቪዥን ቀርበው ስለ ዐማራው ነገድ ያለመኖር ያንጸባrmቁትን አቋም አፅንዖት በመስጠት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ዐማራ የሚባል ነገድ በኢትዮጵያ ውስጥ «አለ» ወይስ «የለም» ብሎ፣ በላ! ልበልሃ! ወደሚል እጅግ የወረደ ክርክር የሚገባ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው የለም። እንዲህ ዓይነት ክርክር ውስጥ የሚገባ ሰው፣ ኃሣቡ ተቀባይነትን እንዲያገኝ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ የማይችል የፕሮፌሠር መሥፍን ዓይነቱ ሰው ብቻ ነው። ለነገሩ በዚህ የቀን ቅዠት አቋም የሚፀና ካለ ከፕሮፌሠር መሥፍን ሌላ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው ይገኛል ተብሎ አይታሰብም። የፕሮፌሠር መሥፍንም ክርክር ጭፍን ክህደት ወይም መሣት (መጃጀት) አልያም ቀቢፀ-ተስፋ የተሞላው ቁጭት ከመሆን አያልፍም። የፕሮፌሠር መሥፍን አቋም የክህደት ከሆነ፣ ወላጅ አባታቸውን ዕውቁን ሊቅ አለቃ አስረስ የኔሰውን ክደዋልና የዐማራ ነገድን ኅልውና ከመካድ የሚያግዳቸው የኅሊና ልጓም ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። ከመሣት(መጃጀት) የመነጨ ከሆነ ግን አያድርስ! እንዲህ እስኪሆንስ ፈጣሪን «አታቆዬን» ከማለት ሌላ ምን ይባላል። ከቁጭት ከሆነ ነገሩ ሌላ ነው። በቁጭት የአንድን ታላቅ ሕዝብ መኖር ኅልውና ክዶ ስለዚያ ሕዝብ መከራከር እና መጮህ አይቻልም። የቁጭት ተገቢ መገለጫው «አሻፈረኝ! በቃኝ! ተነስ! ዱሩ ቤቴ በል!» በማለት እንጂ «የለህም! የሚያጠፉህ ሳትኖር ነው!» በማለት አይደለም። የሌለ፣ ኅልው ያልሆነ፣ ሊያደርገው የሚችለው ምንም ነገር የለምና!

ፕሮፌሰር መሥፍን «ዐማራ የሚባል ነገድ የለም» ከሚል መደምደሚያ የደረሱት፣ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት ከሦሥቱ በአንዱ ወይም በሁሉም ተያያዥነት እንደሆነ ቀደም ካሉት ድርጊቶቻቸው መገንዘብ ይቻላል። የመጀመሪያው በ፲፱፹፫(1983) ዓ.ም. ከሟቹ መለስ ዜናዊ ጋር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባደረጉት ውይይት ዐማራን እና ክርስቲያንን የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን በመዘንጋት፣ ወይም ሆን ብለው «ክርስቲያን እንጂ፣ ዐማራ የሚባል የለም» ብለው ተከራክረው ስለነበር ያ አቋማቸው ያልተለወጠ መሆኑን እና ዛሬም «በዚያው አቋማቸው የጸኑ ናቸው» ለመባል ከማሰብ የመነጨ፣ ከስህተት ወደ ስህተት የመጓዝ አስተሳሰብ ነው። ሁለተኛው ፕሮፌሠር መሥፍን ክህደት የመታወቂያ ባሕሪያቸው ስለሆነ ትናንት የካዱትን ከ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በኋላም በክህደቱ  የቀጠሉ መሆኑ የሚያመለክት ነው። ይህም ሌላው ግትርና «ያለ እኔ ዐዋቂ የለም» የሚለው የገነገነ አስተሳሰባቸው መገለጫ ነው። ሦስተኛው ከክህደት ባሕሪይ በተጨማሪ በዕድሜ መግፋት ምክንያት የመጣ፣ የኋላን ያለማዬት እና የመሣት አባዜ የገጠማቸው መሆኑን የሚያመለክት ነው። አራተኛው በዘመነ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በዐማራው ላይ በተከታታይ እየተፈጸመበት ያለው መገደል፣ መታሠር፣ ከሥራ መፈናቀል፣ ከአገር መባረር፣ መዋረድ እና መጎሳቆል እጅግ በዝቶ የግፉ ጽዋ ሞልቶ የሚፈስበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሆኖም ዐማራው «አሻፈረኝ» ብሎ ወያኔን ግብግብ ከመግጠም ይልቅ የሚሣየውን ሆደ ሠፊነት ከኢዮብ ትዕግሥት በላይ ሆኖ ስላገኙት፥ «ዐማራ የሚባል ነገድ ቢኖር ኖሮ ይህ ሁሉ ጥቃት እና ውርደት ሲፈጸምበት ዝም ብሎ አይመለከትም ነበር! ሌሎቹ እንደሚያደርጉት ኃይሉን አስተባብሮ ጥቃቱን ይቋቋም ነበር! ባለመኖሩ ነው ይኸ ሁሉ ጥፋት የሚፈጸምበት» ከሚል ቁጭት የደረሱበት ድምዳሜ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል።

ይህ ግን ከዐማራው ባህል፣ ዕምነት፣ አኗኗር፤ ማኅበራዊ ግንኙነት እና የኢትዮጵያዊነት ስሜት ጋር አጣምሮ ለሚያይ ሰው፣ ዐማራው በወያኔ የደረሰበትን ሁለንተናዊ ግፍ እና በደል በአርምሞ በመመልከት ላይ ያለው፣ በደሉ ሳይሰማው ቀርቶ አይደለም። እንዲያውም «የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች» እንዳይሆንበት የትግሬ-ወያኔዎችን ግፍ ለመበቀል ሲል በደልን በበደል መመለስ፣ የትልቂቱን አገሩን የኢትዮጵያን ኅልውና እንዳያፈርስ ኅሊናውን ገዝቶት፣ በሆደ ሠፊነት እና በትዕግሥት ማየቱ፥ ብልኅነቱን፣ አስተዋይነቱን፣ «አድሮ እንየው» ማለቱን፣ ውሽንፍርን እና ጥምዝምዝን አጎንብሶ ማሳለፍ ባህሉ መሆኑን፣ እንጂ፤ ጥቃትን እስከ ዝንተ ዓለሙ የሚቀበል አለመሆኑ ታሪኩ ያስረዳል። «ዐማራ ሰንበሌጥ ነው፤» የሚባለውም እኮ ለዚህ ነው። ማንም እንደሚያውቀው ሰንበሌጥ ኃይለኛ ወዠብ (ነፋስ) ሲመጣበት ለጥ ብሎ ያሳልፋል፣ ወዠቡ ሲያልፍ ይነሣል። ዐማራውም በተደጋጋሚ እና በተከታታይ ሊያጠፉት የተሰለፉትን ኃይሎች ሁሉ ተቋቁሞ እስካሁን የዘለቀው በዚህ መንገድ ነው። ጠላቶቹን የሚያሸንፋቸው በመበቀል ሣይሆን በይቅርታ እና በፍቅር መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት አያስፈልግም። የኢትዮጵያዊነት ማገር፣ ዋልታ እና ጭምጭም ሆኖ ለዘመናት የዘለቀውም የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት ስሜቱ የዳበረ በመሆኑ ነው። ይህም በመሆኑ ነው የዐማራው ሥነልቦና በድል ጊዜም ሆነ በጥቃት ላይ እያለ የበላይነቱን  እንደጠበቀ እንዲዘልቅ ያደረገው።

ዛሬ ወያኔን እና መሠል ቡድኖችን ያስጨነቃቸው ይኸው የዐማራው የኢትዮጵያዊነት ሥነልቦና የበላይነት አልሰበር በማለቱ ነው። እኒህን ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ሌት ተቀን የሚያባንናቸው ዐማራው ኢትዮጵያዊነትን ማተቡ፣ ዕምነቱ እና የእሱነቱ መገለጫ፤ ሠንደቅ ዓላማውንም ልብሱ፣ ትራሱ እና መጌጫው አድርጎ በዓለም አደባባይ ስለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት የሚያሰማው ድምፅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያስገመገመ በመጓዙ ነው።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ይህን መግለጫ ለማውጣት የወሰነው በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው። አንደኛው ምክንያት ዛሬ በምንኖርበት የቴክኖሎጂ ዘመን አብዛኛው ሰው የሚያምነው የሚያየውን ብቻ ሣይሆን የሚሰማውንም ጭምር በመሆኑ ነው። እንዲያውም ሰው ከሚያየው ይልቅ የሚሰማውን ይበልጥ አምኖ ይቀበላል። ስለሆነም «ፕሮፌሠር መሥፍን እኮ ዐማራ የሚባል ነገድ የለም ብለዋል» ብሎ የሚቀበለው እና የሚያምነው ሰው ቁጥር ቀላል ስለማይሆን፣ ለዚህ ዓይነቱ አድማጭ ዕውነታውን ማሣወቅ አስፈላጊ ይሆናል። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ፥ ምንም እንኳን ጊዜ እየከዳቸው ያሉ ቢሆንም፣ እስትንፋሳቸው እስካለ ድረስ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሌሎች የክህደት ንግግሮችን ከመናገር ስለማይቆጠቡ፣ ፕሮፌሠር መሥፍን «ዐማራ የለም» ሲሉ የካዱትን ክህደት በተጨባጭ መረጃዎች በማሣዬት ለወደፊት አድማጫቸው እና አንባቢያቸው ከሃዲነታቸውን ከወዲሁ እንዲገነዘብ ለማድረግ ነው። ከዚህ አንፃር የዐማራን ነገድ ከኢትዮጵያ ምድር አልፎ በዓለም ዙሪያ ተሠራጭቶ የሚኖር መሆኑን የሚከተሉት መረጃዎች ያረጋግጣሉ። እነርሱም፦

፩ኛ      አካላዊ (ነባራዊነት)፣

፪ኛ      አማርኛ የተሰኘ ቋንቋ በኢትዮጵያ መኖር እና በስፋት መነገር፣ እንዲሁም

፫ኛ      የጽሑፍ፣ የቃል (ድምፅ) እና የምሥል ማስረጃዎች ናቸው።

፩ኛ.    አካላዊ (ነባራዊነት)

አካላዊ ወይም ነባራዊነት ስንል፥ በእጅ የሚዳሰስ፣ በዐይን የሚታይ፣ ግዙፍ፣ ራሱን «ዐማራ ነኝ» ብሎ የሚገልጽ ሰው የተሰኘ ፍጡር በኢትዮጵያ ምድር በስፋት ተሰራጭቶ የሚኖር ሕዝብ ማለታችን ነው። ይህ ሕዝብ ቀደም ሲል ክርስትና ወደ አገራችን ሲገባ ቀድሞ የተቀበለ በመሆኑ ከክርስትና ኃይማኖት ጋር አያይዞ የራሱን ማንነት የሚጠራ፤ ሌሎችም «ዐማራ» ሲሉ «ክርስቲያን የሆነ» ማለታቸው እንደሆነ አድርገው የሚገልጹት፣ በኋላም በጊዜ ሂደት ወደ አገራችን የገቡ ዕምነቶችን ሳይቃወም፣ መቻቻልን መርሑ አድርጎ የተቀበለ እና ከእርሱም ውስጥ የተወሰነው ክፍል የክርስትና ኃይማኖቱን በመተው ሌሎች ዕምነቶችን በመከተል የኖረ፣ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ነገዶች በቁጥር ከፍተኛውን መጠን የያዘ ማለታችን ነው።

ማንም በግልጽ ሊገነዘበው እንደሚችለው፣ ቋንቋ ከሰው በፊት አልተፈጠረም። ቋንቋ ከሰው ልጅ ኅልውና በኋላ የተከተለ የሰዎች የጋራ የመግባቢያ መሣሪያ ነው። ቋንቋ ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይዳብራል፣ ይሞታል የሚባለውም ከሰዎች መኖር ጋር በጥብቅ የተሳሰረ በመሆኑ ነው። በሌላም በኩል ቋንቋ ባህልም ነው። ከጥንት ጀምሮ የቁጥር መጠኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የሄደ እና ራሣቸውን «ዐማራ ነኝ» በሚሉ ተወላጆች የጋራ ማንነት የተገነባ ነገድ አለ። እኒህ ሰዎች አፋቸውን በአማርኛ ቋንቋ የፈቱ፣ ካለ አማርኛ ቋንቋ ሌላ ቋንቋ መናገር የማይችሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። በመሠረቱም የአማርኛ ቋንቋን መግባቢያ እና መገልገያ ያደረገ ሕዝብ ሣይኖር የአማርኛ ቋንቋ ሊኖር አይችልም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም ነገዶች እና ጎሣዎች አንድ ተብለው መቆጠር ሲጀምሩ በቅድሚያ በማንም ሰው አዕምሮ ውስጥ ድቅን የሚለው ዐማራ ነው። ስለዚህ በማንነቱ ከኢትዮጵያ ኅልውና ጋር በጥብቅ የተሣሰረ «ዐማራ» የሚባለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል ኅልውና መካድ ኢትዮጵያን ከመካድ ተለይቶ አይታይም።

ሌላው አካላዊ ማስረጃ «ዐማራ ሳይንት» የተባለው እና በላኮመልዛ(ወሎ) ክፍለሃገር የሚገኘው የአውራጃ ስም ነው። «ዐማራ» የሚባል ነገድ ሳይኖር፣ በዐማራ ስም የሚጠራ የቦታ ስም ሊኖር አይችልም። በሌላም በኩል ከጥንት ጀምሮ በጌምድርና ስሜን(ጎንደር)፣ ጎጃም፣ ሸዋ እና ላኮመልዛ(ወሎ) የተሰኙ የኢትዮጵያ መልከዐ-ምድር አካል የሆኑ ክፍለ-ሀገሮች አሉ። የነዚህ ክፍለ-ግዛቶች አብዛኛው ነዋሪ ሕዝብ ዐማራ በመሆኑ «ዐማራ የሚኖርባቸው» ተብለው የሚታወቁ ናቸው። ከዚህም አልፎ በዘመነ ትግሬ-ወያኔ «የዐማራ ክልል» በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ክፍል ኅልውናውን ካስቆጠረ ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ሆኗል። ስለዚህ ይህን ሁሉ እንዴት መካድ ይቻላል? ለፕሮፌሠር መሥፍን የክህደት መንገዳቸው ማጠናከሪያ አድርገው የሚያቀርቡት «ስለ ዐማራ አጥንቻለሁ» የሚሉት ፈሊጥ ነው። ይህ አጥንቻለሁ የሚሉት ጥናት ዕውነት ከሆነ፥ ባለፉት ዘመናት «የዐማራ ገዥ መደብ፣ ጨቋኝ የዐማራ ብሔር፣ ነፍጠኛ ዐማራ፣ የኢትዮጵያ ብሔር/ብሔረሰቦች ደመኛ ጠላት፣ ወዘተርፈ» እየተባለ ሲወገዝና የመከራ ዓይነቶችን ሲቆጥር ለምን ዝም አሉ? ኢትዮጵያውያን ዐማሮች ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች፥ «አገራችሁ አይደለም እና ውጡ» ተብለው፣ ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው፤ ከደቡብ፣ ከሐረርጌ፣ ከአርሲ፣ ከባሌ፣ ከወለጋ፣ ከኢሉባቡር፣ ከሶማሌ፣ ከቤንሻንጉል-ጉምዝ እንዲሁም ከሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲባረሩ፣ ፕሮፌሠር መሥፍን «እነዚህ እኮ ዐማራ አይደሉም፣ የሌላ ነገድ አባሎች ናቸው፤» አላሉም? «እንዲያውም ዐማራ የምትሉት ሰው በምድረ-ኢትዮጵያ የለም፤» ብለው ማስተባበል እንዴት ተሣናቸው? እኒህ ሰው የሌሎችን የኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች ኅልው መሆን ሲቀበሉ እንዴት የዐማራ ነገድን ኅልውና ሽምጥጥ አድርገው ለመካድ ዳዳቸው? ማንን ለማስደሰት ይሆን?

በደርግ የአገዛዝ ዘመን ስለኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች በኢትዮጵያ የብሔረሰቦች ጥናት ተቋም በተደረጉት የጥናት ውጤቶች መሠረት፣ የዐማራ ነገድ ከኢትዮጵያ ነገዶች አንጋፋው፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ተሠራጭቶ የሚኖር፣ እንዲሁም በቁጥርም ከፍተኛው እንደሆነ ያሣያሉ።

ሌላው የዐማራን ነገድ ኅልውና የሚያረጋግጠው ደረቅ ማስረጃ በኢትዮጵያ የተደረጉት የሕዝብ ቆጠራ ውጤቶች ናቸው። ለምሣሌም ያህል፦ በ፲፱፻፸፮ (1976) ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት ፵፪(አርባ ሁለት) ሚሊዮን ያህል እንደነበረ ይታወቃል። ከጠቅላላው የአገሪቱ ሕዝብ (42 616 876) ውስጥ የዐማራው ነገድ ተወላጆች ብዛት 12 055 250 (አሥራ ሁለት ሚሊዮን ሃምሣ አምሥት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሣ) ነበር። ይህም ከአጠቃላይ የአሪቱ ሕዝብ 28.288 ከመቶ እንደነበረ ያሣያል። በሥርጭት ረገድም፥ በሸዋ 23.1 በመቶ፣ በአዲስ አበባ 47.86 በመቶ፣ በወሎ 79.86 በመቶ፣ በጎንደር 84.83 በመቶ፣ በጎጃም 87.58 በመቶ፣ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ነበሩ፣ በግለሰብ ደረጃም ሰዎች ማንነታቸውን «ዐማራ ነን» ብለው ማረጋገጣቸው በውል ታይቷል። ዐማራው በሌሎች የአገሪቱ ክፍለ-ሀገሮችም በበቂ መጠን ተሰራጭቶ እንደሚገኝ የቆጠራው ውጤት አሣይቷል። በዚህም መሠረት በሐረርጌ፣ በሲዳሞ፣ በከፋ፣ በወለጋ፣ በጋሞጎፋ፣ በባሌ፣ በአርሲ እና በአሰብ የዐማራው ነገድ ተወላጆች ብዛት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ እንደነበረ መረጃው ያስረዳል። በዚያ የሕዝብ ቆጠራ ውጤት የኦሮሞን ቁጥር ከፍ፣ የዐማራን ቁጥር ግን ዝቅ ለማድረግ ሆን ተብሎ የቁጥሮች ጨዋታ የተሠራ መሆኑ ቢታወቅም፣ ዐማራው በቁጥር በአገሪቱ ከሚገኙ ነገዶች እና ጎሣዎች በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ መሆኑን  ያረጋግጣል (ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለሥልጣን፣ ታኅሣሥ ፲፱፻፹፫ (1983) ዓ.ም.)።

በሁለተኛ ደረጃ በ፲፱፻፹፯(1987) ዓ.ም. በተደረገ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 53 499 248 መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ውስጥ 13 834 297 ያህሉ ዐማሮች መሆናቸውን ያሣያል። በንፅፅር ሲታይ በትግሬ-ወያኔ ዘመን በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት በ፲(አሥር) ዓመታት ውስጥ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ቁጥር የጨመረው በ1,779,047 ብቻ ነው። ይህም የቆጠራው ውጤት የወያኔን ዐማራን የማጥፋት የፖለቲካ ዓላማ በጉልህ የሚያሣይ ነው። ሆኖም የዐማራ ነገድ በቁጥሩ ብቻ ሣይሆን በሥርጭትም ጭምር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በብዛት የሚገኝ መሆኑን የቆጠራው ውጤት አላስተባበለም። በመሆኑም ወያኔ «የዐማራ ክልል» ብሎ በከለለው ውስጥ ከሚኖረው 13 834 297 ሕዝብ መካከል ዐማራው 81.5 ከመቶ መሆኑን፣ በ«ትግራይ ክልል» ከሚኖረው 3 136 267 ሕዝብ መካከል የዐማራው ነገድ 2.6 ከመቶ በመያዝ በክልሉ በሕዝብ ብዛት በሁለተኛ ደረጃ እንደሚገኝ ታውቋል። በ«ኦሮሚያ ክልል» ከሚኖረው 18 732 525 ሕዝብ መካከል 9.1 ከመቶ የሚሆነው የዐማራ ነገድ መሆኑን እና ይህም በ«ክልሉ» ከሚኖሩት ነገዶች መካከል ከኦሮሞው ቀጥሎ በቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ያሣያል። አርባ አምሥት(፵፭) ነገዶች እና ጎሣዎችን ባጠቃለለው የ«ደቡብ ክልል» ዐማራው በቁጥር በስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዚህ «ክልል» 10 377 028 ሕዝብ እንደሚኖር ቆጠራው አሳይቷል። ወያኔ «ሐረሪ» ብሎ የመንግሥትነት ዕውቂያ ከሰጣቸው ክልሎች አንዱ የሆነው የሕዝቡ ቁጥር 131 139 ነው። ከዚህ የ«ሐረሪ ክልል» ነዋሪ ሕዝብ መካከል 52.3 ከመቶው ኦሮሞ ሲሆን፣ 32.6 ከመቶው ዐማራ ነው። ሐረሪዎቹ 7.1 ከመቶ ብቻ ናቸው። እንግዲህ ለእነዚህ አናሣ ቁጥር ለያዙት ነው የአብዛኛውን የኦሮሞ እና የዐማራ ነገዶች ተወላጆች ዕጣ ፋንታ እንዲወስኑ ወያኔ የመንግሥትነት መብት የሰጣቸው። ይህንንም «ዲሞክራሲ ነው» እያሉን ነው። በሶማሌ ክልል 3 439 860 ሕዝብ እንደሚኖር በ፲፱፻፹፱(1989) ዓ.ም. የተደረገው የሕዝብ ቆጠራ ያመለክታል። ከዚህ መካከል በዚያ ክልል ዐማራው 0.69 ከመቶ በመያዝ በሦስተኛነት ደረጃ ላይ ይገኛል። ለሁሉም ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት እንዲቻል የሚከተለውን ሠንጠረዥ እንመልከት።

በ፲፱፻፹፯(1987) እና በ፲፱፻፹፱(1989) ዓ.ም. በተደረጉት የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ ውጤቶች *መሠረት የክልሎችና የአስተዳደሮች ሕዝብ የብሔር /ብሔረሰብ ሥርጭት እና ብዛት

ክልል ወይም አስተዳደር የክልሉ ሕዝብ ብዛት ከአገሪቱ ሕዝብ (በመቶኛ) በክልሉ የሚኖሩ ብሔር/ብሔረሰቦች የየብሔረሰቡ ብዛት ከክልሉ ሕዝብ (በመቶኛ) መግለጫ
ትግራይ 3 136 267 5.6 ትግሬ 2 971 738 94.75 ከ10 ሺህ ሕዝብ በላይ ያላቸው
ዐማራ 81 297 2.59
ሣሆ/ ኢሮብ 22 858 0.73
አፋር 1 060 573 1.99 አፋር 968 018 91.27 ከ2 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው
ዐማራ 46 534 4.39
አርጎባ 9 673 0.91
ትግሬ 8 460 0.8
ኦሮሞ 8 055 0.76
ዐማራ 13 834 297 25.91 ዐማራ 12 615 160 91.19 ከ20ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው
አገው 417 373 3.02
ኦሮሞ 416 883 3.01
ቅማንት 172 291 1.23
ትግሬ 44 609 0.32
አርጎባ 37 626 0.27
ኦሮሞ 18 732 525 35.1 ኦሮሞ 15,709 474 83.86 ከ50 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው
ዐማራ 1 684 128 8.99
ጉራጌ 246 895 1.32
ጌዲኦ 180 215 0.96
ሶማሌ 107 811 0.56
የም 103 823 0.55
ትግሪ-ወርጂ 67 456 0.36
ኩሎ 67489 0.36
ሶማሌ 3 198 514 5.99 ሶማሌ 3 011 453 94.15 ከ3 ሺ በላይ ሕዝብ የያላቸው
ኦሮሞ 70 506 2.21
ዐማራ 20 951 0.66
ጉራጌ 4 085 0.13
ቤንሻንጉል ጉምዝ 464 590 0.86 ጀብላዊ 115 602 25.12 ከ10 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው
ጉምዝ 107 495 23.35
ዐማራ 102 061 22.17
ኦሮሞ 58 833 12.78
ሽናሻ 32 105 6.97
አገው 17 928 3.89
ደቡብ ብሔር/ ብሔረሰቦች 10 377 028 19.43 ሲዳማ 1 820 030 17.539 ከ50 ሺ በላይ ሕዝብ ያላቸው
ጉራጌ 1 646 925 15.871
ወላይታ 1 210 235 11.662
ሐዲያ 874 468 8.427
ጋሞ 679 540 6.549
ከፊቾ 521 223 5.023
ጌዴኦ 549 351 4.423
ከምባታ 459 351 4.423
ዐማራ 443 525 4.274
ኩሎ 312 929 2.631
ጎፋ 273 089 2.320
ኦሮሞ 240 749 1.986
ቤንች 206 244 1.663
ኦሪ 17 ,611 1’488
ኮንሶ 154 381 1.362
አላባ 141 375 1.132
ኮይራ 117 449 1.014
ጠምባሮ 105 244 0.818
የም 84 918 0.586
ጋምቤላ 181 862 0.39 ኑዌር

 

Moresh

ወደፊት ቆሞ ወደ ኋላ መመልከት

$
0
0

ማምሻዬን እጅግ በጣም ከማክበረው ወዳጄ ጋር ሁሌም ስለሚያስጨንቀን ነገር ስናወጋ እረጅም ሰዓት ቆየን፡፡አንዴ ስንስማማ ሣይመስለን ሲቀር በአሳብ ስንለያይ ከቆየን በኋላ ወዳጄ በጃፓን አገር አብዝቶ ስለሚነገር ተረት እንዲህ ሲል ተረከልኝ፡፡ ተረቱ እጅግ በጣም ድንቅ ከመሆኑ ባለፈ የቡዙ ነገር አመላካች ነው፡፡
=====

ይድነቃቸው ከበደ

ይድነቃቸው ከበደ

በአንድ ወቅት ኦሳካ እና ኪዮቶ በተባሉ የጃፓን ከተሞች ውስጥ እርስ በእርሳቸው ሳይተዋወቁ የሚኖሩ ሁለት እንቁራሪቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ እንቁራሪቶች ከሚኖሩባቸው ከተሞች በስተቀር ሌላ ቦታ አያውቁም፡፡ አንድ ቀን በድንገት ሁለቱም የሚኖሩባቸው ቦታ መረራቸው፤ ሰለቻቸው፡፡ በሁለቱም ልቡና ከሚኖሩበት ቦታ ወጥተው በአቅራቢያቸው የሚገኘውን ሌላ የተሻለ ከተማ የመጎብኘት ሃሳብ መጣባቸው፡፡ ሳይመካከሩ እንዲሁ በድንገት ሁለቱም መንገድ ጀመሩ፡፡ አንዱ ከኦሳካ ወደ ኪዮቶ፣ ሌላኛው ደግሞ ከኪዮቶ ወደ ኦሳካ፡፡

መንገዱ እንዲሁ ቀላል አልነበረም፡፡ እጅግ አያሌ ቀናትን የሚፈጅ፣ ተጨማሪ ስንቅ የማይሸመትበት እና እጅግ አድካሚ ነበር፡፡ ከዚሁ ሁሉ በላይ ደግሞ በመካከል እጅግ አስቸጋር እና ረጅም የሆነ ተራራ መገኘቱ ነው፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ተስፋ ባለመቁረጥ ተጓዙ፡፡ እያረፉ እና እየተነሱ ያንን ተራራ ከሁለት አቅጣጫ ተያያዙት፡፡ በድንገት ጫፉ ላይ ሲደርሱ አንደኛው ሌላኛውን ተመለከተ፡፡ አንዱ የሌላኛውን መኖር ፈፅሞ አያውቁም ነበርና ሁለቱም ተገረሙ፤ ደነገጡም፡፡

ወዲያው ተቃቅፈው ከተሳሳሙ በኋላ አንዱ ኦሳካን ሌላኛው ደግሞ ኪዮቶን ለማየት በመጓዝ ላይ መሆናቸውን ተጨዋወቱ፡፡ ከተረፋቸውም ስንቅ አውጥተው አብረው በሉ፡፡ ሳር ላይ ጋደም ብለው ትንሽ እረፍት አደረጉ፡፡

በመካከል የኦሳካው እንቁራሪት ‹‹እንዲህ ትናንሾች መሆናችን ምንኛ መጥፎ እድል ነው›› አለ፡፡ የኪዮቶው እንቁራሪት ደንግጦ ‹‹ምን ተጎዳህ?›› አለው፡፡ የኦሳካውም ‹‹ትልልቆች ብንሆን ኖሮ እዚህ ተራራ ጫፍ ላይ ቁመን የምንሄድባቸውን ከተሞች በሩቅ ማየት እንችል ነበር፡፡ ከዚያም በእውነት እዚያ ድረስ መሄዳችን ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም የሚለውን ሳንለፋ እንወስን ነበር›› አለው፡፡ ያን ጊዜ የኪዮቶው እንቁራሪት ራሱን ከነቀነቀ በኋላ ‹‹ቀላል ነው እኮ፤ ትልልቅ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ ምን መሰለህ ሁለታችንም በኋለኛው እግራችን ብቻ እንቆማለን፡፡ በፊት እግራችን ደግሞ እንያያዛለን፡፡ ከዚያም ፊታችንን ወደ ምንሄድበት ከተማ አዙረን ማየት እንችላለን›› አለ፡፡ በሃሳቡም ሁለቱም ተደሰቱ፡፡

ከዚያም ሁለቱም በኋላ እግራቸው ቆመው አንገታቸውን ቀና አደረጉና በፊት እግራቸው ተያያዙ፡፡ አፍንጫቸውን ወደ ሚሔዱበት አቅጣጫ አዞሩት፡፡ እናም ከተማው ታያቸው፡፡ ‹‹ይገርምሃል፤ አሳካ ከኪዮቶ በምንም አትለይም፡፡ ፎቆቿ፣ መንገዶቿ፣ መብራቶቿ፣ መኪኖቿ ሁሉም ያው ናቸው፡፡ ተመሳሳይ ነገር ለማየትማ እዚያ ድረስ ምን አለፋኝ? ለውጥ ላይመጣ ድካሙ ምንድነው?›› አለ የኪዮቶው እንቁራሪት፡፡ ‹‹ልክ ነህ፡፡ ኪዮቶም እንደ ኦሳካ ናት፡፡ ምንም ለውጥ የላትም፡፡ ለካስ የትም ቦታ ቢሔዱ ተመሳሳይ ነው፡፡ መንገደኞች ዝም ብለው ነው ለካ የሚደክሙት፡፡ ትርፉ ድካም መሆኑን ባውቅ ኖሮ ይህንን ያክል አልደክምም ነበር›› በማለት የኦሳካውም እንቁራሪትም ተመሳሳይ ሃሳብ ነበር የሰነዘረው፡፡

የሁለቱን እንቁራሪቶች ሁኔታ እያየች ትስቅ የነበረች ጉንዳን ‹‹እናንተ እንቁራሪቶች ሞኞች ናችሁ ልበል፤ ወደፊት ብትቆሙም እኮ የምታዩት ወደ ኋላ ነው፡፡ ስለቆማችሁ ብቻ ይታያችኋል ማለትኮ አይደለም፡፡ ዋናው መቆማችሁ ሳይሆን አቋቋማችሁ እንዲሁም ማየታችሁ ሳይሆን አስተያየታችሁ ነው›› አለቻቸው፡፡

እንቁራሪቶቹም ተናደው ‹‹ዞር በይ አንቺ ጉንዳን፤ አንቺ ከኛ በምን በልጠሸ ነው፡፡ ድሮም እናንተ ጉንዳኖች የእንቁራሪቶችን በጎ አትመኙም፡፡ እኛ ያየነውን ለማየት እንቁራሪት መሆን ያስፈልጋል›› አሉና አባረሯት፡፡ ከዚያም ከተያያዙበት ተላቀቁ እና ሳሩ ላይ አረፍ አሉ፡፡
ሁለቱም ያልገባቸው ነገር ቢኖር የኋላ እግራቸውን ዘርግተው የፊት እግራቸውን ወደ ላይ አድርገው ሲቆሙ አፍንጫቸው ወደ ፊት አይናቸው ግን ወደ ኋላ እንደሚያይ ነው፡፡ ሁለቱም ወደ ፊት ያዩ መሰላቸው እንጂ ያዩት የመጡበትን ከተማ ነው፡፡ ሁለቱም የተስማሙት ተመሳሳይ ነገር አይተው አይደለም፡፡ የሚያውቁትን ነገር ስላዩ ብቻ ነው፡፡ ከስንት ትግል በኋላ ተራራው ላይ መድረስ ብቻውን አዲስ ነገር ለማየት አያበቃም፡፡ አዲስ ነገር የማየት ፍላጎት ብቻውንም አዲስ ነገር አያሳይም፡፡ ተደጋግፎ ቀጥ ብሎ መቆም ብቻውን አዲስ ራእይ አያመጣም፡፡ እንዴት እና ወዴት ነው የምናየው? የሚለው ወሳኝ ነው፡፡

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>