መግቢያ
ተወደደም ተጠላም ያለነው በጦርነት ላይ ነው፥፥ የመሣሪያ ድምፅ ኣለመሰማት የሰላም ምልክት!!አይደለም። የሕዋሃት ግፍና በደል ሞልቶ በፈሰሰበት፥ መከራችን በተራዘመበት በዚህ ወቅት፤ እነሱም አዋርደው መግዛትን እንደዋነኛ መገለጫቸው አድርገውታል። እኛም ውርደትን እንደ ኒሻን አጎንብሰን እንድንቀበላቸው፤ እንደውሻ የተፉትን አጎንብሰን እንድንልስላቸው ብቻ አይደለም የሚፈልጉት ከተቻለ ለዘላለም እነሱን ወደማናይበት ወደ ጥልቁ የሞት ሸለቆ ብንወርድላቸው እንጂ ።[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—
ነቀርፉኝት! ነቀርፉኝት ማነው?
ፍርድ ወይስ ፍዳ ! (ይድነቃቸው ከበደ)
በይድነቃቸው ከበደ
Clik here to view.

ይድነቃቸው ከበደ
ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በአናዋር መስጊድ በተነሳው ግጭት ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት፤ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ ኢብራሂም አብዱልሰላም እና ወ/ሪ ወይንሸት ሞላ እንዲሁም የአዲስ ጉዳይ መፅሔት ፎቶ ግራፈር አዚዛ መሐመድ ከህግ አግባብ ውጪ ለተጨማሪ 48 ሰዓት በእሰር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ፡፡
ሚክሲኮ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቂርቆስ ምድብ ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባቀረበው የክስ አቤቱታ መሠረት በተለያየ ቀናት ከሳሽን እና ተከሳሽ መካከል ክርክር ሲደረግ ቆይቶ ሐምሌ 29 እና 30 ተከሳሾች (እነ ወይንሸት) እያንዳንዳቸው 5000 ሺህ ብር የሚገመት የንብረት ዋስ አሲዘው እንዲለቀቁ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ይግባኝ በመጠየቅ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሻር በማድረግ 30 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ7 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት አስደርጓአል፡፡ይህን የህግድ ውሳኔ የሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ነው፡፡ይሁን እንጂ የዚህን ትህዛዝ በክስ መዝግብ ውስጥ ፖሊስ ሳያካት ወይም ቀድሞ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት ሳያሳውቅ እነ ወይንሸትን ፖሊስ በራሱ ፍቃድ ብቻ እስር ቤት ሊያቆያቸው ችሎአል፡፡
በመሆኑም በተሰጠው የህግድ ትህዛዝ መሠረት በ07/12/06 ይግባኝ ባይ ፖሊስ በተሠጠው የጊዜ ቀጠሮ ለፍርድ ቤት ቀርቦ “የሚቀረን ተጨማሪ የሰው ማስረጃ ማሰባሰብ ፣ያልተያዙ አባሪዎችን መያዝ ነው፡፡ሆስፒታል ተኝቶ የነበረው ፖሊሲ የጤናው ሁኔታ ከነበረበት የተሸለ ስለሆነ የህክምና ማስረጃዎችን ጨርሰን ለአቃቢ ሕግ አስታየት ማሰጠት ነው” በማለት ለፍርድ ቤት ያስረዳ ሲሆን ፡፡ፍርድ ቤቱ “ ይግባኝ ባይ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ይሁን እንጂ ቀደም ሲል በተሰጠው የህግድ ትህዛዝ መሠረት የተጎጂዎች የህክምና ማስረጃ በማቅረብ ወይም የምርመራ መዝገቡን በመያዝ በአግባቡ አላስረዳም በመሆኑ የህግድ ትህዛዙን አንስተናል” በማለት በትላንትናው ዕለት ውሳኔ አስተላልፏአል፡፡ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ ቀደም ብሎ ትዕዛዝ ወደተሰጠበት ፍርድ ቤት ታሳራዎችን በዋስ ለማስለቀቅ የተደረገው ጥረት ዳኞች እና የፍርድ ቤት እረዳት ሰራተኞች ስብሰባ ላይ ናቸው በመባሉ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
ይህ በሆነ በማግስቱ ማለትም በዛሬው ዕለት በ8/12/06 ጠዋት 2፡30 ሚክሲኮ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቂርቆስ ምድብ ችሎት በመቅረብ ቀድሞ የተወሰነው ውሳኔ ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት አፅድቆታል በመሆኑም የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ታሳሪዎች እንዲለቀቁ ዋስ በማዘጋጀት ፍ/ቤቱ የማስፈቻ ትህዛዝ እንዲሰጥ ቢጠየቅም ፡፡ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኛ በሰበር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ግልብጭ ያስፈልጋል ይህም በመሆኑ ግልባጭ አምጡ በማለት ትህዛዝ ሰጡ፡፡ ህንዲህ አይነቱ ትህዛዝ በወቅቱ አስፈላጊ ባይሆንም ምን አይነት አማራጭ ባለመኖሩ ወደተጠቀሰው ፍርድ ቤት በመሄድ የውሳኔ ግልባጭ የተጠየቀ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት “እንዲ አይነት ትህዛዝ ከዚህ ቀደም ተሰጥቶ አያቅም በአሰራር ሂደትም ገጥሞን አያውቅም ” በማለት ለተጠየቁት የውሳኔ ግልባጭ ምላሽ ለመስጠት እጅግ በጣም መቸገራቸውን በመግለፅ የሁኔታው አሳሳቢነት ተረድተናል በማለት የተጠየቀውን የውሳኔ ግልባጭ ለመስጠት ችሎአል፡፡
Image may be NSFW.
Clik here to view.
ይውሳኔ ግልባጭ የጠየቀው የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቀውን ትህዛዝ የቀረበለት ሲሆን ቀድሞ ትህዛዙን የሰጡት ዳኛ ምክንያቱ ባልታወቅ ሁኔታ የስራ ገበታቸው ላይ ሊገኙ አልቻሉም፡፡ይህ በመሆኑ የትህዛዝ ችሎት ዳኛ ለሆኑት ለተለዋጭ ዳኛ ጉዳዩን እንዳዲስ በማስረዳት የታሳሪዎች የዋስትና መብታቸው ተከብረሮ ከእስር ቤት እንዲወጡ የማስፈቻ ትህዛዝ እንዲሰጡ የተጠየቁ ሲሆን እሳቸውም በተራቸው “ እኔ ውሳኔ መስጠት የምችለው የሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሠረት ብቻ ሳይሆን ቀድም ብሎ ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት የእኛን ውሳኔ ያገደበት የህግድ ትዛዝ ግልባጭ ሲደርሰን ነው፡፡በመሆኑም ከሰበር ሰሚ ፍ/ቤት የህግድ ትህዛዙን ማምጣት አለባችሁ በማለት ውሳኔ አስተላለፉ፡፡ይህ ሲሆን ጉዳዩን በፍርድ ቤት በመገኘት በቅርበት ስንከታተል ለነበርነው የሰማያዊ ፓርቲ የምክ/ቤት ዋና ሰብሳቢ አቶ ሰኢድ ኢብራሂም፣የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ አቶ እያስፔድ ተስፋዬ እንዲሁም የወይንሸት ሞላ እህት ወ/ሪ መልካም ሞላ እና አቶ አፍወርቅ በደዊ፡፡በተጨማሪም እያንዳንዱን ጉዳይ ፍጥነት በተሞላበት መልኩ በስልክ ልውውጥ ሲከታተሉ ለነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንብር ኢ/ር ይልቀል ጌትነት እና የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ኢ/ር ጌታነህ ባልቻ እጅግ በጣም ከማስገረሙም አልፎ ቁጭት እና በስጭት እንዲሰማን አድርጓአል፡፡ሆኖም ግን ልክ እንደቅድሙ አሁንም ምንም ማድረግ ስለማይቻል ወደተጠቀሰው ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማመልከት ግድ ሆኖአል፡፡
በመሆኑም የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቀውን ትእዛዝ ለመጠየቅ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመቅረብ ከስር ፍርድ ቤት የተጠየቅነውን አስረድተን ሳንጨርስ “ የዛሬው ምን ጉድ ነው ? ምን አይነት ዳኞች ናቸው ፣እንዲ አይነት ትእዛዞችን እየጠየቁ የሚያጉሏሏችሁ ! የቅድሙ ሲገርመን ይሄን ይጠይቃሉ” በማለት በታችኛው ፍ/ቤት ሲገረሙ እና ሲሣሣቁ ለመታዘብ የተቻለ ሲሆን፡፡በሆነው ነገር አብዛኛው የመዝገብ ቤት ሰራተኞች እና የዳኞች ፃፊዎች በማዘና እና በመገረም የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቀውን የህግድ ትህዛዝ በማዘጋጀት በሚደንቅ ትብብር ሊሰጡ ችለዋል፡፡በዚህም መሠረት የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቅውን የህግድ ትህዛዝ በመያዝ የህግድ ትህዛዙ እንዲቀርብላቸው ለጠየቁት ዳኛ በዲጋሚ ለመቅረብ የተቻለ ሲሆን ጉዳይ የተመለከቱት ዳኛ “አሁን ሁሉም ነገር ተሟልቷአል በጉዳዩ ላይ ውሳኔ መስጠት የሚችለው ጉዳዩን በመጀመሪያ ሲያየው የነበረ ዳኛ ነው፤አሁን እሱ ስለሌለ ነገ ጠዋት መጥታችሁ ጉዳያችሁ ማቅረብ ትችላለችሁ” በማለት ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው ውሳኔ አስተላለፉ፡፡
የአገራችን የዳኝነት ስርአት በተለያየ ወቅት እና በተለያየ ተበዳዮች እውነተኛ ፍትህ ሳያገኙ እየቀሩ በእንዲ መልኩ ከስር ከስሩ እየታጨደ ሌጣ ሜዳ ሆኖ መቅረቱ ያስቆጫል፡፡እኔ በሆነው ነገር እጅግ በጣም ነው ያዘንኩት፤ በእንዲህ አይነቱ ግዴለሽነት እና በእጅ አዙር መንግስትን የሚጠቅም ውሳኔ የሚያስተላልፍ ፍርድ ቤት እና የዳኝነት ስርአት መታየቱ የገዥውን የአምባገነን መንግስት ስርአት አደገንኘቱን ከማመላከት ባለፈም ስርአቱ በህዝብ ተሳትፎ ከወደቀም በኋላ ወደፊት ዜጎች በፍትህ ስርአት ላይ አመኔታ እንዲያጡ ሆን ተብሎ የሚቀበር ፈንጂ ስለመሆኑ አርቆ አሳቢነትን አብዝቶ የሚጠይቅ አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
“ውሸታም”!
Image may be NSFW.
Clik here to view.
እመ-ሰብ፣ እምዬ – ደጓ ያልታደሉ፣
ቆንጥጠው ያሳደጉህ – “አትዋሽ” እያሉ፣
የአደይ ምክር፣ ተግሳጽ.. ባክኖ ሲቀር ቃሉ፣
እናትህ ምን ይሉ?!
“ኮትኩቼ ያሳደግሁት፣ ክብሬን የሚጠብቅ..” የሚሉህ ልጃቸው፣ “አሳዳጊ የበደለው..” በሚሉት እርግማን ሲነሳ ስማቸው፣
አባ-ወራ፣ አባትህ – የቤቱ ምሰሶ ምንድን ይሰማቸው?!
ባለቤትህ ምን ትል? – የኑሮህ “ተጋሩ”፣ “ያ! ውሸታም ባልሽ..” – ስትባል በ”ዕድሩ”፤
በብሩህ ተስፋ ስንቅ ጉዞ የጀመሩ – ልጆችህ ምን ይሉ?!
አንገት እሚያስደፋ – አባት ሲታደሉ፤
ባልንጀሮችህስ፣ ወይ አብሮ አደጎችህ፣ ወይ ባልደረቦችህ.. ህሊና ያላቸው፣
ከጎንህ ለመቆም እሚሸማቀቁ – ጊዜ ፈርዶባቸው፤
ህሊናስ ወዴት ነው? – ማተብስ ምን ዋጠው?!
ሲወርድ-ሲወራረድ – ከትውልድ የመጣው፤
ምን ዓይነት “ባህል” ነው? – ከወዴት የመጣ፣
ሰብዕናን ሽሮ – ይሉኝታን ያሳጣ፤
እግዚኦ! ያሰኛል – እኔስ ላነተ አፈርኩ፣
አምላክ ይታረቅህ – ኧረግ! አበስኩ-ገበርኩ!
ጌታቸው አበራ
ነሐሴ 2006 ዓ/ም
(ኦገስት 2014)
——
የሕዝብን መሰረታዊ የነጻነት፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን በቀጥታ መመለስ ሲሳናቸው፣ (ወጣቱ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በመልካም ስነ-ምግባር ታናጾ እንዳያድግ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ እስከሚፈጥር ድረስ) በግልጽ ባደባይ፣ በእጅጉ ዘቅጠው በውሸት ለተዘፈቁ የወያኔ ባለሥልጣኖች እና ለተላላኪዎቻቸው።
ያገር ፍቅር ልክፍት –በዶክተር ኃይሉ አርአያ
Image may be NSFW.
Clik here to view.
ከእናቴ ማህፀን ነው ስፈጠር ከጥንቱ
ከህይወት መስመሩ ካገኘን ከእትብቱ ፡፡
ወይስ ከእናቴ ጡት ካይኖቿ እይታ
ከየት ነው ያገኘኝ ከቶ ከምን ቦታ
ያገር ፍቅር ልክፍት ያገር ፈቅርበሽታ፡፡
ከረገጥኩት መሬት በውስጥ እግሬ ገባ
ወይስ በጠዋት ፀሀይ ተወጋሁ ከጀርባ፡፡
ከበላሁት ቆሎ ጠረሾ አምባሻ
ከእንጀራ ከሽሮው ጥልቅ የእናት ጉርሻ፡፡
ከጠጣሁት ወተት ከጠጣሁት ውሃ
ከእረኝነት ውሎ ከዱር ከበረሀ፡፡
በነሀሴ ምሽት በቡሄ ጨለማ
ሁያሁዬ ስንል አሲዮ ቤሌማ፡፡
እደጉ ልጆቼ ብለው ሲያቀብሉን
የቡሄ በረከት የዳቦ ሙልሙሉን፡፡
ከሙልሙሉ ይሆን ከቃናው ከጣዕሙ
ወይስ ከምረቃው ከቃል ከትርጉሙ፡፡
ከቶ ከየት ይሆን ከምኑ ከስንቱ
ሳላውቀው የነካኝ ያገር ፍቅር ልክፍቱ፡፡
ቄስ ትምህርት ቤት ይሆን ከየንታ ቤት ታዛ
‹‹ሀ ሁ››ስል‹‹ለ ሉ››ስል ፊደልን ሳበዛ፡፡
በቀለም በፊደል በነጥብ ተመስሎ
በውስጤ የገባ ዓይነ ኩሌን ከፍሎ፡፡
ወይስ ውሎ አድሮ ነው ከፊደል በኋላ
የንታን‹‹ሄድኩኝ››ብዬ ስገባ ካአስኳላ፡፡
ገባ በጆሮዬ ተመስሎ ዜማ
‹‹ኢትዮጵያ ሆይ›› ብለው ሲጠሯት ስሰማ፡፡
‹‹ተጠማጅ አርበኛ ባገር መውደድ ቀንበር››
ለሶስቱ ቀለማት በሰልፍ ሲዘመር፡፡
አረንጓዴ ቦጫ ቀይ ቀለም ባንዲራ
ስትወጣና ስትወርድ ስንዘምር በጋራ፡፡
በክፍል ውስጥ ይሆን በእውቀቱ ገበታ
ሳላውቀው ሳላስበው ልቤ የተመታ ፡፡
ከመፅሀፉ ይሆን ከታሪክ ፀሀፊ
ወይስ ከመምህሩ ከዚያ ዕውቀት አስፋፊ
ባገር ፍቅር ልክፍት ተለክፎ አስለካፊ፡፡
ግልፅ ደብዳቤ ለአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አባላት (አሰፋ ዘለቀ)
ከአሰፋ ዘለቀ
አስቸኳይ ጥሪ
በቅድሚያ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ። የአንድነት ፓርቲ ደጋፊ ነኝ። በተለይም ላለፉት አንድ አመት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መርህ፣ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች አንድነት ሲያደርጋቸው የነበሩት ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ እንዲሁም ከሌላው አንጋፋ ድርጅት መኢአድ ጋር ያቀደው ዉህደት በእጁጉ የኢትዮጵያን ህዝብ ያስደሰቱና ቀልብ የሳቡ መሆናቸዉን መቼም እናንተዉ ሳታወቁት አይቀርም።
በአመራሮች መካከል፣ ዉይይቶች ተደርጎ፣ ቅድመ ዉህደት ስምምነት የተፈረመ ሲሆን፣ የውህደት አመቻች ኮሚቴም ተቋቁሞ ሥራዉን በተሳካ ሁኔታ እየከናወነ ይገኛል። የተቃዋሚዎችን መሰባሰብ የማይወደው ወያኔ/ኢሕአዴግ ፣ ምርጫ ቦርድን ተጠቅሞ፣ «ያልተሟላ ነገር አለ» በማለት፣ የዉህደት ሂደቱን ለጊዜው ለማጨናገፍ ሞከሯል።
ምርጫ ቦርድ በእጁ ያለው ወረቀት ነው። የዘነጋው ነገር ቢኖር ግን፣ አገዛዙ እውቅና ሰጠም አልሰጠም፣ መኢአዶች እና አንድነቶች በተግባር መዋሃዳቸዉን ነው። የመኢአድ እና የአንድነት አባላት በዞን እና ወረዳ ደረጃ ተዋህደው አብረው መስራት ከጀመሩ ቆይተዋል። አብረው ነው ድምጻቸውን የሚያሰሙት። አብረው ነው የሚታሰሩትና የሚደበደቡት። በመካከላቸው ልዩለት የለም። የዉህደት እንቅስቃሴ በቅንጅት ጊዜ ሊደረግ እንደነበረው፣ ከላይ ወደ ታች ሳይሆን፣ ከታች ወደ ላይ ነው። ለዚህም ነው ቅንጅትን ማፍረስ እንደተቻለው፣ በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ያለውን ግንኙነት ማፍረስ በቀላሉ የማይቻለው።
ሁኔታው ይህ ሆኖ እያለ፣ የአንድነት ፓርቲ ምክር ቤት፣ አሳፋሪዉ የምርጫ ቦርድ ዉሳኔ በተሰማ በቀናት ዉስጥ፣ ከመኢአድ ጋር በመሆን ምርጫ ቦርድ ላይ ጫና ማሳደር ሲገባው፣ የዉህደት አመቻች ኮሚቴን አፍርሷል። ይሀ በጣም ትልቅ ስህተት ነው ብዬ አምናለሁ።
የዉህደት አመቻች ኮሚቴ ጥሩ ሥራ ከሰሩ ኮሚቴዎች መካከል አንዱ ነው። በመኢአድ እና በምርጫ ቦርድ በኩል ያለውን ችግር መፍታት የሚቻልበትን አማራጭ ሐሳቦችን በማውጣትና በማውረድ ላይ ይገኝ ነበር። ይህ ኮሚቴ እንዲፈርስ ዉሳኔ ሲወሰን፣ ከመኢአዶች ጋር ምክክር አልተደረገም። በመኢአዶች ዘንድ ሊያስከትል የሚችለውን ቅሬታ ከግምት አላስገባም። ዉሳኔው፣ ሊዋሃዱ በተዘጋጁ ወገኖች መካከል ቀዳዳ የሚከፍት ጠቃሚ ያልሆነ ዉሳኔ ነው።
መኢአድ ከወያኔ ጋር እየተፋጠጠ ባለበት ወቅት፣ የዉህደት አመቻች ኮሚቴዉን ማፍረስ፣ በተግባር ምርጫ ቦርድ የጀመረውን ይዞ እንደመሮጥና፣ አገዛዙን እንደማስደስት ተደርጎ በአንዳንዶች ቢወሰድ፣ ተሳስተዋል ብሎ መከራከር ያዳግታል። የምክር ቤቱን፣ በተለይም ደግሞ የሊቀመንበሩን ተቀባይነት በእጁጉ የሚሸረሽር ነው።
የውህደት አመቻች ኮሚቴ መፍረሱ በተጨማሪ፣ ከዚሁ ከአንድነት ጋር በተገናኘ፣ ሌላ ያሳዘነኝ ነገር አለ። ከአንድነት የሥራ አስፈጻሚ አባላት አምስቱ ፣ ምክትል ሊቀመንበር ተክሌ በቀለ፣ ምክትል ሊቀመንበር በላይ ፍቃዱ፣ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ዳንኤል ተፈራ፣ ኢኮኖሚ ጉዳይ ሃላፊ ዳዊት አስራደ፣ የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊው ሰለሞን ስዩም፣ እንዲሁም ገንዘብ ያዡና የዉህደት ኮሚቴው ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ጸጋዬ አላምረው «ከሊቀመንበሩ ጋር መስራት ስለማንችል፣ ሊቀመንበሩ አብረውት ሊሰሩ የሚችሉ አመራሮች መርጦ ስራዉን ይቀጥል። እኛም በምክር ቤቱ አባልነታችን ስራችንን እንቀጥላለን » በማለት ራሳቸውን ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አግለዋል።
እነዚህ አንጋፋ ወጣት የአንድነት አመራሮች ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከወጡ፣ ድርጅቱ ምን አይነት መልእክት ነው የሚያስተላልፈው ? ሊቀመንበሩስ ኢንጂነር ግዛቸው ፣ «የተቃዋሚ ድርጅቶች አሰባስባለሁ። ወጣቶችን ወደ አመራሩ አመጣለሁ» ሲሉ አንዳልነበረ፣ ወጣት አመራሮች «ከርሳቸው ጋር መስራት አንችልም» ብለው ሲለቁ፣ የርሳቸው ተአማኒነት ጥያቄ ምልክት ዉስጥ ሊገባ አይችልምን ? ከርሳቸው ጋር የሚሰሩትን ማቀፍና ማሰባሰብ ካልቻሉ እንዴት መኢአድን ፣ ሰማያዊን የመሳሰሉትን በዉጭ ያሉትን ሊያሰባስቡ ይችላሉ?
ዉድ የአንድነት ምክር ቤት አባላት፣ ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ በቅንጅት ዉስጥ ተፍጠሮ የነበረዉን መከፍፈል ታስታወሳላችሁ ብዬ አስባለሁ። በወቅቱ ለቅንጅት መፍረስ ምክንያት ከሆኑ ወገኖች መካከል ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው አንዱ ነበሩ። በ2000 ዓ.ም የወዳደቀዉን የቅንጅት ፍርስራሽ በማሰባሰብ፣ በወ/ት ብርቱክን ሚደቃሳ የሚመራ ጠንካራ የፖለቲክ እንቅስቃሴ ተጀመረ። በአጭር ጊዜ ዉስጥ አንድነት በሚል ፓርቲ ስም ፣ እንቅስቃሴዉ ሕዝባዊ ድጋፍ አገኘ። ተቃዋሚዎች ሲጠናከሩ የማይወደው ወያኔ/ኢሕአዴግ ብርቱካን ሚደቅሳን አሰረ። ያኔ ኢንጂነር ግዛቸው ድርጅቱን መምራት ጀመሩ። በዚያን ጊዜ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን እና፣ አቶ አመሃ ደስታን ጨምሮ፣ አሁን ሰማያዊ ፓርቲን ከመሰረቱ በርካታ የቀድሞ አንድነት አመራር አባላት ጋር ኢንጂነር ግዛቸው መስማማት አልቻሉም። የሚቋወሟቸውን በዉስጣዊ አሰራር ከድርጅቱ እንዲታገዱ በማድረግ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ትልቅ መከፋፈል እንዲፈጠር አደረጉ። ይህ ደግፊዎችን የሚያደማ ፣ ወያኔዎችን ጮቤ የሚያስረገጥ ክስተት ሲፈጸም እንግዲህ ሁለተኛ መሆኑ ነው። በሁለቱም ጊዜ ኢንጂነር ግዛቸው ዋና ተዋናይ ነበሩ።
አሁን ደግሞ ይኸው ፖለቲካ በቃኝ ብለው ከሶስት አመታት በላይ ከተቀመጡበት ግዞት ወጥተው «ተለውጫለሁ፣ ካለፉት ስህተቶቼ ተምሪያለሁ፣ ከወጣቶች ጋር አብሬ እሰራለሁ። ብቃት ያላቸው ወጣት አመራሮች ከመጡ ደግሞ ሃላፊነቴ እለቃለሁ። ሌሎች ድርጅቶችን አሰባስቤ ጠንካራ ተቃዋሚ ስብስብ እንዲኖር አደርጋለሁ» ብለው ለሊቀመንበርነት ተወዳደሩ። አብዛኛዉ የአንድነት አባል ድጋፉን ሰጣቸው።
ስድስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ እራሳቸው ከመረጧቸው የሥራ አስፈጻሚ ጋር አብረው መስራት አልቻሉም። በድርጅቱ ዉስጥ እንደ ከዚህ በፊቱ የተካኑበትን ዉስጣዊን የሴራ ፖለቲካ ጀመሩ። ቡድን በፍጠር፣ አንዱን ከሌላው በመለየትና በማጋጨት፣ አብረው በጋራ ሲታገሉ የነበሩ ወገኖችን፣ ከሶስት አመታት በላይ ዶር ነጋሶ መሪ የነበሩ ጊዜ ሰላም የነበሩትን፣ ለስልጣናቸው ሲሉ መከፋፈል ጀመሩ።
እንግዲህ ክቡራን የአንድነት ምክር ቤት አባላት፣ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ዉስጥ በማስገባት፣ በኢንጂነር ግዛቸው እየተደረገ ያለዉን ጎጂ እንቅስቅሴ መገደብ አያስፈልግም ብላችሁ ታምናላችሁን ? ለሁለት ጊዜ ኢንጂነር ግዛቸው የታጋዮችን ልብ አቁስለዋል። ለሶስተኛ ጊዜ ተመሳሳይና ከፋፋይ ሥራ እንዲሰሩ ስለምንም ይፈቀድላቸዋል? የአንድነት ፓርቲ ላለፉት አንድ አመት ተኩል እጅግ በጣም ጉም ስራዎችን እየሰራ ነበር። ይኸው ኢንጂነር ሽፈራው ወለድ በሆኑ ችግሮች ነገሮች ቆመዋል። ሰኔ መጨረሻ ላይ ይገባደዳል የተባለው የሚሊዮኖች ንቅናቄ ተረስቷል።
እንግዲህ ምክር ቤት ቆም ብሎ ራሱን እና ድርጅቱ ያለበትን እንዲመረምር እጠይቃለሁ። የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት አመቻች ኮሚቴ እንዲፈርስ የተደረገው ዉሳኔ እንዲቀለብሱና ከሥራ አስፈጻሚ የለቀቁ አንጋፋ ወጣት የአመራር አባላት ያቀረቡትን፣ መልቀቂያ ዉድቅ በማድረግ፣ ሊቀመንበሩ ኢንጂነር ግዛቸው ቡድናዊ የሴራ ፖለቲካቸው ትተው፣ በቅንነት ከነርሱ ጋር እንዲሰሩ መመሪያ እንዲሰጥ፣ ወይንም ሊቀመንበሩን ከሃላፊነታቸው እንዲያነሳ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
አንድነት የአንድ ሰው ተክለ ሰዉነት የሚገነባበት ሳይሆን ተቋማዊ ጥንካሬ እንዳለው መታየት አለበት። ከ4፣ 5 አመታት በፊት ወጣት አመራሮች እንደተገለሉት፣ አሁን ወጣት አመራሮችን በማግለል፣ የስድሳዎቹ ፖለቲከኞች የትግሉን ግለት ወደ ታች እንዲያወርዱት ሊፈቀድላቸው አይገባም። ምክር ቤቱ፣ በታሪክ እና በትዉልድ የሚያስጠይቀው ትልቅ ሃላፊነት ስላለበት፣ ለግለሰቦች ታማኝነቱን ለማሳየት ይልቅ፣ የአገርን እና የሕዝብ ጥቅም እንዲያስቀድም እመክራለሁ።
አንድነት የዉህደት ኮሚቴዉን አፍርሶ፣ ሲሰሩ የነበሩ ወጣት አመራሮች ገፍቶ ፣ በሕዝብ ተቀባይነት ያለው ድርጅት ሆኖ ሊቀጥል አይችልም። ያለ ምንም ማገነን የነኢዴፓ እጣ ፋንታ ይደርሰዋል። ትልቅ ትኩረት ይሰጠበት እያልኩ፣ መልካም ዜናን እንደምታሰሙን ተስፋ አደርጋለሁ።
Image may be NSFW.
Clik here to view.
ኧረ ተው ኢህአዴግ ተረጋጋ!! “ዴዣ ቩ” –በአምስት አመቱ የተደገመ ታሪክ የጋዜጠኞችን ማሰርና ማሳደድ፤ ንግድ ቤቶችን ማሸግና ማዋከብ
የ2001 ዓ.ም ዘመቻ – ለ2002 ምርጫ?
ዘመቻው የተጀመረው በአዲስ ዘመን ላይ በወጡ ፅሁፎች ነበር። “የውጭ ሃይሎች በአገራችን ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ ነው” በሚል ውግዘት ዩኤስአይዲ ላይ ጣት ከመቀሰር ቢነሳም፤ ብዙም ሳይቆይ ነው ነፃ የግል ጋዜጦች ላይ በማነጣጠር ዘመቻ የተካሄደው። ከዚያ ኢቴቪ “ጥናታዊ ዘገባ” ሰርቻለሁ ብሎ በወቅቱ ሲታተሙ የነበሩ ጋዜጦችን የኩነኔ መዓት አወረደባቸው – በአብዛኛው ከሕትመት የወጡ የድሮ ጋዜጦችን እያሳየ። ብዙም ሳይቆይ ወከባና እስር መጣ። የቪኦኤ ጋዜጠኛ ለበርካታ ቀናት እንደታሰረና የኤፒ ጋዜጠኛ እንዳይታሰር በመስጋት ከአገር እንደወጣ የሚያስታውሱ የሙያ ባልደረቦች እንደሚሉት፤ ወከባው የበረታው ግን በግል ጋዜጦች ላይ እንደነበር ይገልፃሉ – የአዲስ ነገር ጋዜጣ መዘጋትንና የጋዜጠኞቹ መሰደድን በመጥቀስ።
ከመነሻው ዩኤስአይዲ ላይ የተጀመረው ውግዘት ብዙ ባይዘልቅም፣ ወደ ሌሎች አለማቀፍ ድርጅቶች ተሸጋገረ እንጂ አልከሰመም። ውግዘቱ ብዙ አለማቀፍ ድርጅቶችን ቢያዳርስም፤ ዋናው ኢላማ ግን ሂዩማን ራይት ዎች ነበር። የኋላ ኋላም በአለም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ፤ በሂዩማን ራይት ዎች ላይ ሰለማዊ ሰልፍ እስከመውጣት ተደርሷል።
የመንግስት ዘመቻ በፖለቲካ መስክ ላይ ብቻ ያተኮረ አልነበረም – በኢኮኖሚ መስክም ጭምር እንጂ። ከልክ ባለፈ የብር ህትመት ሳቢያ በመንግስት የተፈጠረው ከፍተኛ የዋጋ ንረት፣ በወቅቱ ከተከሰተው የዝናብ እጥረት ጋር ተዳምሮ በጣም አሳሳቢ ሆኖ ነበር። አሳዛኙ ነገር፤ ሁሉም ችግር በነጋዴዎች ላይ ተሳበበ። እናም፤ ነጋዴዎች አበሳቸውን እስኪያዩ ድረስ ዘመቻ ተካሂዶባቸዋል።
Image may be NSFW.
Clik here to view.
እነዚህ የ2001 ዓ.ም ዘመቻዎች ተገቢ ባይሆኑም፣ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ቢበዛም፤ “ምንም መነሻ አልነበራቸውም” ማለት አይደለም። አንደኛ፣ የ97 የምርጫ ቀውስ ገና መንፈሱ አልደበዘዘም ነበር። በዚያ ላይ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር መንግስት ላይ ቀላል የማይባሉ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫናዎች ወይም ፈተናዎች ተጋርጠው እንደነበር አይካድም። ከአገር ውስጥ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፈተናዎች በተጨማሪ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘመቻ ራሱ ቀላል አልነበርም – በተለይ የኢትዮጵያ ጦር የሶማሊያ አክራሪዎችን ለመዋጋት ከተሰማራ በኋላ።
የኢትዮጵያ ጦር ስምሪት ከአሜሪካ ድጋፍ አግኝቷል የሚለው ስሜት ለኢህአዴግ እንዲያ ፈታኝ ይሆንበታል ብሎ ማን ገመተ? ከአሜሪካ መንግስት ጋር የሚተባበር አገር ላይ ክፉኛ ጥርሳቸውን የሚነክሱት ሂዩማን ራይትስ ዎች እና ኒው ዮርክ ታይምስ ናቸው፤ ኢህአዴግን ከግራና ከቀኝ ወጥረው የያዙት። በዚያው ልክ፤ የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት ጫናም የሚናቅ አልነበረም። ከዳያስፖራ ፖለቲካው ጋር በአገር ውስጥ የ”መድረክ” ተቀናቃኝነት፣ የዋጋ ንረት፣ የረሃብ አደጋ … ኢህአዴግ፤ በእነዚህ ተደራራቢ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፈተናዎች ምክንያት ስለተጨናነቀ ሊሆን ይችላል ወደ አላስፈላጊ ዘመቻ ያመራው።
አሳዛኙ ነገር ምን መሰላችሁ? የያኔዎቹ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፈተናዎች ዛሬ ቢደበዝዙም፣ ልክ እንደያኔው፣ በነፃ ፕሬስ ላይ የእስር እና የስደት፤ እንዲሁም በቢዝነስ መስክ የእሸጋና የወከባ ታሪክ ዛሬም እየተደገመ ነው።
የ2006 ዓ.ም ዘመቻ – ለ2007 ምርጫ?
አለማቀፉን የፕሬስ ነፃነት ተቋም (አርቲክል 19ን) በማውገዝ የተለኮሰው የዘንድሮ ዘመቻ፤ አዲስ ዘመን የግል መፅሔቶችን በመወንጀል ባሰራጨው “ጥናታዊ ሪፖርት” ነው ጎልቶ የወጣው። በኢቴቪ የተሰራጩትንም ዘገባዎች ተመልክታችኋል። ዘጠኝ ፀሐፊዎችና ጋዜጠኞች ሲታሰሩም ታዝበናል። ሰሞኑን ደግሞ ጋዜጠኞች ሲሰደዱና ሕትመቶች ሲቋረጡ እያየን ነው።
ከላይ እንደጠቀስኩት፤ ያኔ በ2001 ኢህአዴግ ብርድ ብርድ ቢለው አይገርምም። የ97ቱ ትዝታ ገና አልደበዘዘም። 2001 ላይ በሶማሌ ክልል ከፍተኛ ግጭት ነበር። የጎዳና ላይ አመፅ፣ በወቅቱ ገና ፋሽኑ አላለፈበትም። በአገር ውስጥ ቅጥ ባጣ የብር ህትመት ከተፈጠረው የዋጋ ንረት በተጨማሪ፣ የረሃብ አደጋው ታክሎበት፤ በዚያ ላይ አለማቀፍ የኢኮኖሚ ቀውስ ተደምሮበት፤ የአገሬው ኢኮኖሚ ከፍተኛ አደጋ ላይ ነበር።
ዘንድሮ ግን ያን ያህልም የሚያሰጋ የዋጋ ንረት አልተከሰተም። የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ስለተደረገ የዋጋ ንረት ይከሰታል በሚል ሰፊ የፕሮፓጋንዳና የማስፈራሪያ ዘመቻ ቢካሄድም፤ እንደተለመደው የቢዝነስ ስራን በማውገዝ የንግድ ቤቶችን በገፍ የማሸግ ዘመቻ ቢካሄድም፤ ለዚህ መነሻ የሚሆን ሰበብ እንኳ የለም። የማዕከላዊ ስታትስቲክስ የሐምሌ ወር ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ ከሰኔ ወር የሚያንስ እንጂ የሚበልጥ የዋጋ ንረት አልተፈጠረም። ደግሞም አይገርምም። መንግስት አለቅጥ የብር ኖት ከማተም እስከተቆጠበ ድረስ፤ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ሊከሰት አይችልም።
ዘንድሮ ከ2001 ዓ.ም የሚለየው፣ አስደንጋጭ የዋጋ ንረት ባለመፈጠሩ ብቻ አይደለም። ትልቅ የረሃብ አደጋም አልተፈጠረም። በእርግጥ የኑሮ ችግር እንደያኔው ዛሬም አለ። ሰባት ሚሊዮን ገደማ የሴፍቲ ኔት ተረጂዎችና ደራሽ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አሉ። እንደምንም ብለው ኑሯቸውን የሚገፉ ችግረኞችም ቁጥራቸው ጥቂት አይደለም። ነገር ግን፤ የዘንድሮው ረሃብ፣ ችግርና ድህነት ካለፉት አመታት ይሻል እንደሆነ እንጂ አይብስም።
የፖለቲካ ጫና እና ፈተናስ – ድሮና ዘንድሮ
በ2001 ዓ.ም፤ ምንም እንኳ ከምርጫ 97 ፉክክር ጋር የሚስተካከል ባይሆንም፤ በስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተመሰረተው “መድረክ”፤ ጠንካራ እንቅስቃሴ ያካሂድ ነበር። ከመድረክ በተጨማሪ፤ የዜጎችን ትኩረት ለመሳብ የሚጣጣሩ አዳዲስ ፓርቲዎች ብቅ ብቅ ይሉ ነበር። ከያኔው ጋር ሲነፃፀር፤ ዘንድሮ ኢህአዴግን ክፉኛ የሚቀናቀን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የለም። አዳዲስ ፓርቲዎችንም እያየን አይደለም።
Image may be NSFW.
Clik here to view.
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ነፃ ማህበራትና ነፃ ጋዜጦች ለመንግስት እንደ ፈተና የሚቆጠሩ ከሆነም፤ ከ2001 ወዲህ ቁጥራቸው በእጅጉ ቀንሷል፤ ህልውናቸውን ያላጡትም ተዳክመዋል። በአጭሩ፤ በአገር ውስጥ ኢህአዴግን ለስጋት የሚዳርግ ከባድ የፖለቲካ ጫና ወይም ፈተና አይታይም።
ከአገር ውጭም ያን ያህል የጎላ ስጋት የለም። በሶማሊያ በኩል የነበረው የአልሸባብ ስጋት ረግቧል። በኤርትራ በኩል፤ ብዙም እንቅስቃሴ አይስተዋልም። በእርግጥ በአሜሪካ፣ በአውሮፓና በደቡብ አፍሪካ የዳያስፖራ ፖለቲካው የተለወጠና የተጠናከረ ይመስላል። ግን ብዙም አልተለወጠም። በ1996 ዓ.ም “ህብረት” ለመፍጠር ሲሰባሰቡ የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ብዛትና እንቅስቃሴ ምን ያህል ከፍተኛ እንደነበር ማስታወስ እንችላለን። የቅንጅት መሪዎች ከእስር ከተፈቱ በኋላ፣ እነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎች ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ በውጭ አገራት ያካሄዱት እንቅስቃሴም ከፍተኛ ነበር። የዳያስፖራ ፖለቲካ እንደወትሮው፣ ለገዢው ፓርቲ የሚመች ባይሆንም፣ ዛሬ ከድሮው የባሰ ፈታኝ ሆኗል የሚባልለት አይደለም።
የውጭ መንግስታትና አለማቀፍ ተቋማትማ፤ በአብዛኛው ድምፃቸው ጠፍቷል ማለት ይቻላል። አንዳንዶቹ ድምፃቸውን ለማሰማት ቢሞክሩም ያን ያህልም ብዙ ጆሮ እያገኙ አይደለም። በ2001 ዓ.ም ላይ ታች እያሉ ድምፃቸውን አጉልተው ሲያሰሙ የነበሩ አለማቀፍ ተቋማትን በጥቂቱ እናስታውሳቸው።
የውጭ መንግስታትና አለማቀፍ ተቋማት – ድሮና ዘንድሮ
“በሶማሌ ክልል መንግስት ጭፍጨፋ አካሂዷል” ከሚለው የሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ጀምሮ፤ የኒውዮርክ ታይምስ ተከታታይ የትችት ዘገባዎችን ጨምሮ በ2001 ዓ.ም የውጭ መንግስታትና የአለማቀፍ ተቋማት ጫና ለኢህአዴግ እጅግ ከባድ ሆኖበት ነበር።
“መንግስት የአገሬውን ረሃብ ደብቋል” የሚሉ የረድኤት ድርጅቶች የሚያሰራጩት ተከታታይ መግለጫ ታክሎበት፤ “ገዢው ፓርቲ በ77ቱ ረሃብ ለእርዳታ የመጣ ገንዘብ ለመሳሪያ መግዣ አውሎታል” የሚል የቢቢሲ ሰፊ ዘገባ፣ “በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ተስፋ ጨልሟል” የሚል የኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ሪፖርት፣ ከዚያም “የሰብአዊ መብት ረገጣ ተባብሷል” የሚል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ሪፖርት… የያኔው ጫና ቀላል አልነበረም። የአሜሪካ ኮንግረስ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ያወጣውና በእንጥልጥል የነበረው ኤች.አር 2003 የተሰኘው ህግም ለኢህአዴግ እጅግ ፈታኝ መሆኑ አልቀረም።
የዚያ ሁሉ ርብርብ መነሻ፤ “ለውጥ ማምጣት እንችላለን” የሚል ተስፋ ነው። “መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና በማሳደር ወይም ተቃውሞ በማበረታታት፤ ገዢው ፓርቲ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በድርድር ተቻችሎ እንዲሰራ መገፋፋትና ለውጥ ማምጣት ይቻላል” የሚል አስተሳሰብ በስፋት ይታይ ነበር – በውጭ መንግስታትና በአለማቀፍ ተቋማት ዘንድ።
ይህ አስተሳሰብ ግን፤ ባለፉት አምስት አመታት ተሸርሽሯል። አንደኛ፣ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአፍሪካም ሆነ በሌሎች አገራት ላይ ጫና የማሳደር ፍላጎት የላቸውም። ሁለተኛ፣ የአሜሪካና የአውሮፓ አገራት በኢኮኖሚ ቀውስ ስለተመቱ፣ አብዛኞቹ መንግስታት በራሳቸው ውስብስብ ችግር ውስጥ ተጠምደዋል። በመጨረሻ ደግሞ፣ በኪሳራ የተደመደመው የአረብ አገራት አብዮት መጣ።
በእርግጥ፤ “በአረብ አገራት ውስጥ የነፃነት ለውጥ ማምጣት ይቻላል” የሚለው የምዕራብ መንግስታት አስተሳሰብ እየተሸረሸረ የመጣው፣ በአፍጋኒስታን እና በኢራቅ ጦርነት ማግስት ነው። በአፍጋኒስታን የአክራሪው የታሊባን አገዛዝ ቢወገድም፤ በኢራቅ የሳዳም ሁሴን አምባገነንነት ቢወገድም፣ የነፃነት መንፈስ አልሰፈነም። በሃይማኖት ወይም በጎሳ እየተቧደኑ ስልጣን ለመያዝ ሲጨፋጨፉ፣ በአንዳች አጋጣሚ ስልጣን ላይ የወጣ ቡድን አምባገነንነትንና ግጭትን ለማስፈን ሲጣጣር ነው የታየው። በሁለተኛው የአለም ጦርነት ማግስት፣ በጃፓን እና በምዕራብ ጀርመን ላይ የተፈጠረው የነፃነት ለውጥ በአፍጋኒስታንና በኢራቅ አልተደገመም።
ምናልባት ጥሩ ለውጥ የሚመጣው፣ በውጭ ሃይል ጣልቃ ገብነት ሳይሆን፣ በፖላንድ እና በቼክ እንደታየው፣ የአገሬው ህዝብ በሚያካሂደው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ይሆን እንዴ? በግብፅ፣ በሊቢያ፣ በቱኒዚያ፣ በሶሪያ የተቀሰቀሰው የህዝብ ተቃውሞ፣ “የፀደይ አብዮት” በሚል ስያሜ ተስፋ የተጣለበትም በዚህ ምክንያት ነበር – ለውጥ ያመጣል በሚል። ደግሞስ፣ እንደ ሙዓመር ጋዳፊ የመሳሰሉ አምባገነኖች ከስልጣን ሲወገዱ፣ ብዙዎች ቢደሰቱ የተስፋ ብርሃን ቢታያቸው ምን ይገርማል?
ነገር ግን በፓላንድ እና በቼክ እውን ለመሆን የበቃው የነፃነት ለውጥ፣ በእነ ግብፅ እና በእነ ሶሪያ አልተደገመም። ሊቢያና ሶሪያ፣ በደርዘን በሚቆጠሩ ታጣቂ ቡድኖችና ጎራዎች አማካኝነት የጦርነትና የግጭት ማጥ ውስጥ ገብተዋል። በቱኒዚያና በግብፅ፤ ለወጉ ያህል የፖለቲካ ምርጫዎች ተካሂደዋል። ነገር ግን፤ “ለውጥ” እና “ምርጫ”፣ በቀጥታ “የነፃነት ለውጥ” እና “የነፃነት ምርጫ” ይሆናሉ ማለት አይደለም። በግብፅ፣ ምርጫውን ያሸነፉት የሃይማኖት አክራሪዎች ናቸው። የጦር ሃይል ኮሎኔል በነበሩት በሁስኒ ሙባረክ ከሚመራው መንግስት ይልቅ፤ በመሃመድ ሙርሲ የሚመራው የአክራሪዎች መንግስት፣ በአምባገነንነት የባሰ ሆኖ አረፈው። አሁን የመንግስት ስልጣን ወደ ጦር ሃይል ተመልሷል – በጄኔራል አልሲሲ።
Image may be NSFW.
Clik here to view.
በሊቢያም እንዲሁ፤ የነፃነት ተስፋ አይታይም። ተቀናቃኞቹ ቡድኖች፣ አንድም አክራሪዎች ናቸው፤ አልያም በቀድሞ የጦር ጄኔራል ስር የተሰለፉ የስልጣን ጥመኛ ቡድኖች ናቸው፤ ወይም ደግሞ በጎሳ የተቧደኑ ታጣቂዎች። የሶሪያም ተመሳሳይ ነው። የኢራቅም እንዲሁ። በአጭሩ፣ መልካም የነፃነት ለውጥ አልመጣም። በዚህም ምክንያት፤ “መልካም ለውጥ እንዲመጣ መገፋፋትና ጫና ማሳደር እንችላለን” የሚለው የምዕራብ መንግስታት የቀድሞ ዝንባሌ ዛሬ ተሸርሽሯል።
እናም፣ ጋዜጠኞች በገፍ ሲታሰሩ ወይም ሲሰደዱ፣ በተቃውሞ ሰልፍ ላይ ሰዎች ሲገደሉ ወይም የፓርቲዎች ፉክክር የማይታይበት ምርጫ ሲካሄድ፣ አለማቀፍ ተቋማትና የምዕራብ መንግስታት ዛሬ ዛሬ፣ ብዙም ድምፃቸውን አያሰሙም። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ስለ ጋዜጠኞችና ፀሐፊዎች መታሰር ሲጠየቁ የሰጡትን ምላሽ ማየት ይቻላል።
እንደ ድሮ ቢሆን፤ ጆን ኬሪ እስኪጠየቁ ድረስ ባልጠበቁ ነበር። የጋዜጠኞችን እስር እንደሚያወግዙ በመግለፅ ከእስር እንዲለቀቁ ጥሪ ያቀርቡ ነበር። ዛሬ ግን እንደ ድሮ አይደለም። ጆን ኬሪ እዚሁ አገር መጥተው ስለ ጋዜጠኞች መታሰር አልተናገሩም። ትንፍሽ አላሉም። ጥያቄ ሲቀርብላቸውም፤ “የጋዜጠኞቹና የፀሐፊዎቹ መታሰር ያሳስበናል…” የሚል ምላሽ ነው የሰጡት። በቃ? “ያሳስበናል” በሚል ነው ጉዳዩን ያለፉት።
ከአገር ውጭ የሚመጣ ጫና ተመናምኗል። እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች የመሳሰሉ አለማቀፍ ተቋማት፣ በየጊዜው እንደተለመደው መግለጫና ሪፖርት ማውጣት አቁመዋል ማለት አይደለም። ነገር ግን፤ የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታትን ወደ እርምጃ የማነሳሳት አቅማቸው ተዳክሟል። ምናለፋችሁ? ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግስታት እንዲሁም ከአለማቀፍ ተቋማት ይሰነዘር የነበረው ግፊትና ጫና፣ ዛሬ ከሞላ ጎደል ከስሟል ማለት ይቻላል። “ያሳስበናል” ከሚል የአንድ ደቂቃ መግለጫ ያለፈ ጫና እየጠፋ መጥቷል።
በአጭሩ፤ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር በ2001 ዓ.ም ኢህአዴግን ሲያስጨንቁ የነበሩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፈተናዎች፣ ዛሬ በአብዛኛው ጠፍተዋል፤ ወይም ደብዝዘዋል። እና ለምድነው የያኔው የወከባ ታሪክ ዛሬ የሚደገመው? ኧረ ተው ኢህአዴግ ተረጋጋ!
* ይህ ጽሁፍ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ወጥቷል።
ትክክል! (ሥርጉተ ሥላሴ)
ከሥርጉተ ሥላሴ 17.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
ዛሬ ዕለተ ሰንበት እ.ኤ.አ 17.08.2014 ጀግና አበራ ሃይለመድህን ሲዊዘርላንድ ጄኔባ የገባበት 7ኛ ወሩ ነው። ቤቴ ውስጥም ሰባት ሻማዎች እዬበሩ ነው። ይገባል አይደል?! ፎቶው ደግሞ ፊት ለፊቴ አለ -አይቼም አልጠግበውም!
Image may be NSFW.
Clik here to view.ወገኖቼ የኔዎቹ ልክ የስድስተኛ ወሩ ስናከበር እኛ ማለትም በ17.07.2014 ከሰዓት በኋላ ዘንድሮ ወፉ ያላወጣቸው የማልዥያ አዬር መንገድ ዩክሬን ላይ ዳግም ሃዘን አደጋ የገጠማቸው ዜና ተደመጠ። አንድም የሰው ዘር ቁራጭ ምልክት ሳይገኝ አመድ ዶቄት ሆኖ መላ ዓለም በሃዘን ሰቆቃ የተደመመበት የጨለመው ዕለት ነበር። እንደ ሰው ለተፈጠረ፤ ብቁ ህሊና ላለው ፍጡር ይህ ድንገተኛ አደጋ ቀለምም፣ ወሰንም፣ ደንበርም ሳይኖረው የሰው ልጅ በሙሉ ሃዘኑን በተለያዬ መልኩ ተጋርቶታል።
የዚህ መከራ ቀን ፊርማ ሳይደርቅ ነበር በዕንባ ተሰቅዛ አሳሯን በምታዬው እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘረኛው የወያኔ አስተዳደር የጀግና ካፒቴን አበራ ሃይለመድህን ክስ በአምሳሉ በፈጠረው ፍትህ አልቦሽ ተቋም ምስክር አዳመጥን ብሎ የባዶነት ሙጣጭ ሂደቱን የገለጠልን።
ህሊና ቢኖር 202 ፍጡራንና ነፍስ የታደገውን ወጣት ተግባር ዩክሬን ከደረሰው ሰቅጣጭ አደጋ፤ አስደንጋጭ ዜና ጋር አነጻጽሮ – በማስተዋልም ፈትሾ፤ ቆም ብሎ ማሰብ በቻለ ነበር። አቅልም ህሊናም መግዛት ወይንም መሸመት አይቻል ነገር ሆኖ ነው እንጂ፤ „ተፈጥሮን ተመክሮ አያድነውም“ ይላሉ ቀደምቶቹ … ባልተራራቀ ቀንም እንደ ማልዢያውም ባይሆን የአውሮፕላን አደጋ ተከስቷል። ሰው ማለት ታላቅ የፍጡርና የፍጥረታት አውራ ነው። ፍጥረቱም – ጽንሰቱም – ውልደቱም ሆነ ዕድገቱ ረቂቅ ነው። የሰው ልጅን የነገረ ፍጥረት ረቂቅነት በሰው ልጅ ህሊናዊ ቀመር ወይንም ፍለስፍና ሳይንስ ሊደፍረው ከቶውንም አይችልም። ለወያኔ ደግሞ ሰው ማለት ሸቀጥ ነው። እሚገዛ – እሚለወጥ – እሚሸቀጥ እንዳወጣ በጉልት ገብያ የሚቸበቸብ። ባለፈም እንደ አውዳመት ዶሮ ባገኘበት አርዶ ባሰኘው ቦታ የሚጥለው የበቀል ማስከኛው፣ የደም ጥማቱ እርካታ ማወራራጃ – መፈተኛ – መሞከሪያ ….
ስለሆነም አረሙ ወያኔ የበለጠበት ሰው ሰራሹ ቆርቆሮ በሰላም አርፎ እስከ ዓይን ጥርሱ ተረከቦ ግን በጥቃቅን ወጪዎች ስሌት እንዲህ ይዳክራል። ይህ ነው የወያኔ የስብዕዊነት፤ የዕንባ ተቆርቋሪ ድርጅት በሚር/ ማዕረግ አደራጀሁ እያለ የሚያላግጠው። ሰው ለወያኔ ከእንሰሳትም፤ ከማሽን መሳሪያም እጅግ ያነሰ ፍጡር …..
አይደለም ሰው ከነህይወቱ ተርፎ። አውሮፕላኑ ብቻውን አደጋ ቢድርስበት እንኳን ሰው ተረፈ ተመስገን ይባላል። በሌላ በኩልም ዬትልቁ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ሞተሩ መንፈሱ ነው። በዚህም ዘርፍ እጅግ በጥንቃቄ ነበር ትክክል የከወነው። አደጋ ሲደርስ ለዛውም ሰማይ ላይ ያቺ የግቢ ውጪ ነፍስ ቆይታ እራሱ በምንም ምንዛሬ ሊሰላ ከቶውንም አይችለም። ግን ለአድናቆት ቀርቶ እንደ ሰው ለማሰብ ለተሳነው የዘረኛው አፓርታይድ የወያኔ ከፋፋይ ሥርዓት ለፍጡራን ደንታ ቢስ በመሆኑ ስሌቱን በጎጥና በሂሳብ እንዲሁም በጭካኔ መንፈስ እንዲህ ያወራርደዋል። እንጠብቃለን …. አዬር አልባው ፉኛ ችሎት የሚሰጠውን ብይን ….
ካፒቴን አበራ ሃይለመድህን ከመጠን የዘለለውን ረገጣና ግፍን መክቶ – ጥቃትን ለማውጣት ትክክል ሆኖ የተፈጠረ ብቁ ዜጋ ነው። „አሻምን“ የገለጠበት መንገዱ በስክነት ከእጁ በገባ ዕድል ለትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ሁኔታ፤ ለትክክለኛው አቅም ትክክለኛውን የኃላፊነት ደረጃ፤ ለትክለኛው ውሳኔ ትክክለኛውን ችሎታ መግቦ ትክክልን አቅም መግቦ፤ በትክክል ንጹህ አዬርን አስማምቶ ሰጥቶ ካለ ብክነት ንጥርነትን በስኬት አወራርዶ ዕውነት – ትክክል ሆነ ከደባባዩ ላይም ዋለ። ፍትህ – ርትህ – ፍርድ ይሏችኋል ይህ ነው። የተገፋ -የተገለለ መንፈስ በዚህ መልክ የጠላቱን ዕላቂ መንፈስ ያወላልቃል።
ሲፈጠር ተስተካክሎ ስለነበረ በዝምታ የከወነው ድንቅ ተግባር አቋሙን፤ ውሳኔውን፤ ድርጊቱን፤ ችሎታውን፤ ለትክክል ውስጥ ሸልሞ ለዘመኑ ትክክሉን የጀግንነት ጥሪት ባለቤት ለመሆን እንሆ ቻለ። አረሙ ወያኔ እንዲህ ተቆፍሮ ተቀብሮ እንደ ኖረ አውሬ ያዬውን ሁሉ በሽብር ሴራ ፈርጆ መቆሚያ መቀመጫ ላሳጣው ግዑፋን ትውልድ የደም መላሹ ወጣት አንዳዊነትን በአሃታዊ ፍላጎት ቀምሮ ድልን ያበለገ እራስ እግሩ ፍሬ ዘር እርምጃ ነበር የወሰደው።
ጀግናዬ አበራ ሃይለመድህን ይህን ዬታሪክ ዕለት እዚህ ሲዊዘርላንድ ካስመዘገበ ጀምሮ እኔ በግሌ አድርጌ የማላውቃቸውን ነገሮች እፈጽማለሁ። እንዴት ቢሉ …. ሁልጊዜ ጉግል ገብቼ ምን የአውሮፕላን ክስተት እንደተፈጠረ አያለሁ። በሰማይ ላይ አውሮፕላን ሲበርም ቀና ብዬ አይና በሰላም ያግባችሁ እላለሁ። ከአደጋዎች ሁሉ የከፋው ሰማይ ላይ አመድ – ዱቄት ሆኖ ለወሬ ነጋሪ እንኳን ሳይበቁ መቅረት ነውና ለህይወቴ በዚህ ዙሪያ አዲስ ምዕራፍ ነው ማለት እችላለሁ። ማለት ልክ ከቤተሰቤ አንድ ሰው በዚህ ሙያ እንደተሰማራ ያህል ነው ውስጤ እያዳመጠ ያለው።
ዓይን ያለው ህሊና፤ መንፈስ ያለው ፍላጎት፤ ተስፋ ያለው ችሎታ እንዲህ ካለምንም ግድፈት ሲከውን መምህርነቱ፤ አብነቱ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ዓለምአቀፋዊ ነው። ያኮራል ወንድም ጋሼ – ተባረክልኝ!
አንድ ሰው ብዙ ነው። ሰው መኖርን አስቦ መኖር ሳያማክረው ወይንም መኖርን ሳይወስንበት በእንዲህ ዓይነት አጋጣሚ ማለፍ ዘላለማዊ ጸጸት ነው። ጀግና አበራ ሃይለመድህን በዞግ የከረፋ አስተዳደር መከራውን – መከፋቱን – ቅሬታውን – መሸከም አለመቻሉን የገለጸበት መንገዱ ሆነ ከማናቸውም ጉዳት ያዳነውን የሰው ልጅ ሆነ ንብረት ስሌቱን በሂሳብ መተመን ዕብንነት ይመስለኛል።
ጀግናዬ – ለተፈጠረበት መክሊቱ – የልጅነት ምኞቱ፤ የወጣትነቱ ተስፋው አፈጻጸሙና ሂደቱ እንከን የማይወጣለት ትክክሉ ልኩ ነው። የኔው ጀግና አበራ ሃይለመድህን እንኳንም ተፈጠረ። ደመ ከልብ ሆኖ ለቀረ ወገን ፊት ላይ ሆኖ እንዲህ መከተ።
ዛሬ እንዲህ በአንድ የመንደር አስተዳደር ሀገር ተከትፋ እየታመሰች ባለችበት ወቅት፤ ልጆቿ በዬሄዱበት እዬታደኑ በመርዝ ጋዝ መሞከሪያ በሆኑበት ወቅት፤ አልፎ ተርፎ ውጪ ያለነውን ብዕርና አንደበት ለመዝጋት፤ አብሶ የነገ ተረካቢ ወጣቶቻን ግንባር ቀደም፣ ትንታግ፣ ሀገር ወዳድ የነፃነት ትግሉን ቤተኞችን ከእንቅስቃሴያቸው ለመገደብ ከፍተኛ የሥነ – ልቦና ጦርነት በታወጀበት ዘመን እንዲህ ሞግድ ግጣሙን ሲያገኝ የሰማይ ታምር ነው። ጀግንነትና አደራ ተጋቡ። ቃላቶች ሁሉ ሰልፍ ቢወጡ መተርጎም የማይችሉት ብሄራዊ የሀገር ፍቅር እንዲህ ፈክቶ በተባ ድፍረት በትክክል ተከውኖ አዬን።
የኔዎቹ ታስታውሱ እንደሆን ቱቦው የዘር አስተዳደር ቀለብ ተሰፋሪዎች ልዑክ ሆነው እዚህ ሲዊዘርላንድ መጥተው በነበረቡት ጊዜ „ታሟል“ ይሰጠን ነበር ጥያቄያቸው። አሁን ደግሞ „ጤነኛ ነው“ በወንጀል ይጠዬቃል። አያችሁት የበቀል ብቅሉ ወያኔ ጥልቅ ሴራና የቋሳ ጉድጓድ። ፍርዱም ባለጉዳዩ በሌለበት ይታያል። የሥነ -ልቦናውም ጦርነት ይቀጥላል። ግን በማያውቁት ተፈጥሮ ላይ ስለሆነ ይሄን አጅሬ ሃይልዬ መንፈሱን ከቀለሙ ጋር አስተጋብቶ የሀገሬውን ቋንቋ ጥናቱን አስከንድቶት ይሆናል – ትክክል ነዋ! ጠፈፍ ብሎ የተፈጠረ የህሊና ዓይንና ጆሮ።
አይደለም እነሱ እነ – የዘር ብልቂያጦች፤ የዘር በሽተኞች ቀርቶ የወለዱት አጅግ በሚደንቅ እንክብካቤና ሥነ – ምግባር ኮትኩተው ያሳደጉት ክብርት እናቱ ወ/ሮ የህዝብአለም ሥዩምና የተከበሩ አባቱ አቶ አበራ ተገኜ አያውቁትም – በፍጹም። የማያውቁትን ልጅ ነው ወልደው ያሳደጉት። እርምጃውና ዕቅዱ፤ ዕቅዱና ውጤቱ፤ ብልህነቱና ላቂያነቱ በዚህ ዘመን ከቶ የማይተሰብ ነው። ደሙን ሲመልስ ኮሽ ሳያደርግ በእጥፍ ድርብ፤ እራሱንም ጠብቆ – ክብሩንም ጠብቆ – የሙያውን ክህሎት ጠብቆ – የሙያውን ሥነ ምግባር ሳያጓድል እንግዶቹን እንዳከበረ፤ የኢትዮጵያዊነትን ጠንቃቃነት በናሙናነት ጠብቆ ታሪክንም አልምቶ ነው። ቀበቶውንስ እሱ ይታጠቀው …. ትክክሉ ነውና። ወንድነቱን እሱ ይነገር ትክክሉ ነውና። ተግባርም ይናገር ትክክሉን አግኝቷልና። ተመስገን – ተስፋዬ!
ካፒቴን አበራ ሃይለመድህን መሰደድን ሲተረጉመው በጠላቱ ጦር ሰፈር ላይ የመንፈስ ትቅማጥ አውጆ፤ ጥቃቱን አስገድዶ ግቶ -፤ ለጎጠኛው ወያኔ – ቁርስ – ምሳ እራቱን ሽንፈትን – አስጎንጭቶ። የሴራ – የሸር – ዬኢጎ – የምቀኝነትን ትብትቦችን በተከደነ መንገድ አፈር አስግጦ። መገለልን – በተግባሩ አሸንፎ፤ እንደ ወያኔ ላለ ሙጃ አስተዳደር ትክክሉ እንዲህ ዓይነት የዝምታ ገድል ነው። ጠላት ባለሰበው – ባለወጠነው – ባላተኮረበት መንገድ ሆድ ዕቃውን እንዳልነበር አድርጎ ማስማጥ – ማስመጥ። ማጥቃት እኮ መልኩም ዘርፉም ረቂቅ ነው። ረቂቅነቱን እንዲህ በትክክል ኢትዮጵያዊነት መሸነፍ አለመሆኑ ይተረጎማል። ለመክሊቱ ያደረ ፍጥረት ትክክልነቱን በድርጊት እንዲህ ያበሥራል። የኔ ጌታ – የእኔ አባት – የእኔ ውድ – ዬእኔ ብርቅ እግዚአብሄር አምላክ የልቦናህን አሟልቶ ያሳዬኝ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ውድድድድ ….
ክብረቶቼ የምትችሉ በፌስ ቡካችሁ – በቲዩተር አካውንታችሁ ጀግናችሁን ከፍ አድርጋችሁ ሰንደቃችሁ አድርጋችሁ ብተውሉ ቤታችን አውዳችን ጠረኑ ጀግና – ጀግና ….. ይመቻችሁ። መሸቢያ – ጊዜ።
ጀግኖቻችን የመንገዳችን መብራቶች ናቸው!
ደሜን ሳዳምጠው ውስጤን አገኘዋለሁ!
ለእኔስ ሰው ሆኜ መፈጠሬ ብቻ ይበቃኛል!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
የውጭ ምንዛሪ ንዋየ-ኩብለላ ከሃገረ ኢትዩጵያ ወደ ባህር ማዶ ሃገራት (ሚሊዬን ዘአማኑኤል)
Image may be NSFW.
Clik here to view.ከሚሊዬን ዘአማኑኤል በአለፉት 40 አመታት ውስጥ፣ከኢትዬጵያ የውጭ ምንዛሪ ንዋየ-ኩብለላ በብዙ ቢሊዬን ዶላር በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሃገራቶች እንደወጣ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ ኢትዬጵያ ከአለማችን ከሚገኙ ደሃ አገራቶች ውስጥ ከመጨረሻዎቹ ጠርዝ ላይ የምትገኝ ስትሆን ይሄን የሚያህል የውጭ ምንዛሪ ከሃገር ውስጥ ወደ ውጭ ሲኮበልል የሃገሪቶን ድገት በማቀጨጭ ስርAቱ ምን ያህል በሙስና የተጨማለቀ፣ግልፅነት የጎደለው መንግስታዊ Aደረጃጀትና Aሰራር በሃገሪቱ ኢንደሰፈነ ያሳያል —-[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]———
የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ –ከኤፍሬም ማዴቦ (የግንቦት 7 አመራር)
ባለፈዉ ሰሞን ቻይና አፍሪካ ዉስጥ ሰላሳ አመት በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ያደረገችዉ የኤኮኖሚና የፖለቲካ መስፋፋት ያሳሰባቸዉ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምነዉ ምን አድረግናችሁና ነዉ ፊታችሁን ያዞራችሁብን ብለዉ ለመጠየቅ በርከት ያሉ የአፍሪካ መሪዎችን ቤተ መንግስታቸዉ ድረስ ጋብዘዋቸዉ ነበር። በዚህ የሃሳብ ልዉዉጥ፤ ምክር፤ የእራት ግብዣና የዋሺንግተን ዲሲን ጉብኝት ባጠቃለለዉ የፕሬዚዳንት ኦባማ ድግስ ላይ በመልካም የዲሞክራሲ ጅምራቸዉ የሚወደሱት የጋናና የደቡብ አፍሪካን መሪዎች ጨምሮ እንመራሀለን የሚሉትን ህዝብ በየቀኑ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት የወያኔ መሪዎችም ተገኝተዋል። በዚህ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ጠ/ሚ ደሳለኝ ኃ/ማሪያምን አጅበዉ ከመጡት የወያኔ ሹማምንት አንዱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ./ር ቴድሮስ አድሃኖም ነበሩ። ዶ/ር ቴድሮስ በዋሽንግተን ዲሲ ቆይታቸዉ ብዙዎቻችንን እየዋለ ሲያድር ደግሞ እራሳቸዉንም ግራ ያጋባ የሬድዮ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዉ ነበር።
Image may be NSFW.
Clik here to view.
“በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ” የአገራችን ባለቅኔዎች አፉ እንዳመጣለትና እንዳሻዉ የሚናገርን ሰዉ . . . ዋ ተጠንቀቅ በአፍ የሚነገር ነገር ዋጋ ያስከፍላል ለማለት የተረቱት ተረት ነዉ። አዎ! ባለቅኔዎቹ እዉነታቸዉን ነዉ። የሚያዳምጡንን ሰዎች ለማስደሰት ስንል ብቻ አፋችን እንዳመጣ የባጥ የቆጡን የምንዘባርቅ ሰዎች የምንላቸዉ ነገሮች እኛዉ ዘንድ ዞረዉ መጥተዉ መጥፊያችን ሊሆኑ ይችላሉ። በቅርቡ ዋሺንግተን ዲሲ ብቅ ብለዉ የነበሩትን የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ያጋጠማቸዉ ይሄዉ በጋዛ አፍ ተናግሮ የመጥፋት ቅሌት ነበር። ዶ/ር ቴድሮስ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ መንግስታቸዉ የሰራተኛ ደሞዝና የአየር ላይ ወጪ እየከፈለ በሚያስተዳድረዉ ሬድዮ አፋቸዉን ሞልተዉ የተናገሩትን ነገር አዲስ አበባ ተመልሰዉ በፌስ ቡካቸዉ በለቀቁት መልዕክት ለማስተባበል ቢሞክሩም ነገሩ “ከአፍ ከወጣ አፋፍ” ሆኖባቸዉ በስህተት ላይ ስህተት እየፈጸሙ ይገኛሉ።
ሬድዮ አገር ፍቅር በመባል ከሚታወቀዉ ሳምንታዊ ሬድዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ መሪዎች የአሜሪካ መንግስት ጓንታናሞ ዉስጥ ካሰራቸዉ የአልቃይዳ አባላት ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ ማረጋገጫ አግኝተናል ካሉ በኋላ የአሜሪካ መንግስት ይህንን ግኑኝነት አስመልክቶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን ኢትዮጵያ ድረስ ሄዶ ለማነጋገር ለመንግስታቸዉ ጥያቄ እንዳቀረበ ተናግረዋል። ያልነገሩን ነገር ቢኖር የአሜሪካ መንግስት ባቀረበዉ ጥያቄ መሰረት ቃሊቲ ድረስ ሄዶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን ማነጋገሩንና አለማነጋገሩን ብቻ ነዉ።
ዶ/ር ቴዎድሮስ ብቻ ሳይሆኑ እሳቸዉ በአባልነት የሚገኙበት ህወሃት የሚባዉ ድርጅት ሃያ ሦስት አመት ሙሉ እየዋሸ የዘለቀ ድርጅት ነዉና የዶ/ር ቴድሮስ ዉሸት ብዙም ላይገርመን ይችላል። ሆኖም ግን ዶ/ር ቴድሮስ ግማሽ ደቂቃ በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ሁለት ቱባ ቱባ ዉሸቶችን ሲዋሹ “ከማንም ጋር አንወግንም፤ የቆምነዉ ለእዉነት ብቻ ነዉ” የሚለዉ የአገር ፍቅር ሬድዮ ጣቢያ አዘጋጅ ካለምንም ተከታይ የማብራሪያ ጥያቄ የዶ/ር ቴድሮስን ቆሞ የሚሄድ ዉሸት እንዳለ ተቀብሎ ጭራሽ ዶ/ር ቴድሮስን ማመስገኑ የወያኔ ስርዐት ዉሸትና ቅጥፈት አገር ዉስጥ ብቻ ሳይሆን በዉጭ አገሮችም ምን ያክል ህብረተሰባችንን አንደበከለ ያሳያል።
የኢትዮጵያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ከአልቃይዳ ጋር ማገናኘት እነዚህ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ያነሱትን ህጋዊ የመብትና የነጻነት ጥያቄ ላለመመለስ የሚደረግ አጉል ዉጣ ዉረድ ከመሆኑ አልፎ ማንም ማየትና ማሰብ የሚችል ሰዉ የማይቀበለዉ ከንቱ ቅጥፈት ነዉ። ደግሞም ይብላኝ ለዶ/ር ቴድሮስ አፋቸዉን ላዳለጣቸዉ እንጂ ወጣቶቹ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችኮ የጓንታናሞ አስር ቤት ሲከፈት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት መፍጠር ቀርቶ አልቃይዳ የሚባል ነገር መኖሩን እንኳን ሰምተዉ የማያዉቁ አንድ ፍሬ ልጆች ነበሩ።
ሌላዉ የዶ/ር ቴድሮስ ትልቁ ዉሸት የአሜሪካ መንግስት ከአልቃይዳ ጋር የነበራቸዉን ግንኙነት አስመልክቶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን የታሰሩበት ቦታ ድረስ ሄዶ ላናግራቸዉ ብሎ ጠየቀን ማለታቸዉ ነዉ። እኔ እንደሚመስለኝ ዶ/ር ቴድሮስ አደስ አበባ ከገቡ በኋላ “ምን ነካኝ” ብለዉ ዉሸታቸዉን በፌስ ቡክ ገጻቸዉ ለማስተባበል የቸኮሉት ደጋግመዉ ወዳጃችን ነዉ ብለዉ በተናገሩት በአሜሪካ መንግስት ስም የዋሹት ዉሸት ከንክኗቸዉ ይመስለኛል፤ አለዚያማ ወያኔም ሆነ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ዶ/ር ቴድሮስ በዋሹ ቁጥር ዉሸታቸዉን የሚያስተባብሉ ቢሆን ኖሮ የወያኔ አገዛዝ መሪዎች ስራቸዉ እየዋሹ ማስተባበል ብቻ ይሆን ነበር።
የሚገርመዉ ዶ/ር ቴድሮስ ከአሜሪካ ተመልሰዉ አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ የመጀመሪያዉን አንድ ሳምንት ያሳለፉት አንድም አሜሪካ ዉስጥ የዋሹትን ዉሸት በማስተባበል ሌላ ግዜ ደግሞ ሌሎች አዳዲስ ዉሸቶችን በመዋሸት ነበር። በእርግጥም ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በየአገሩ የሚገኙትን አምባሳደሮቻቸዉን ሰብስበዉ የኢትዮጵያን ህዝብ ከት አድርጎ ያሳቀ ነጭ ዉሸት ዋሽተዋል። ለምሳሌ አሜሪካ ዉስጥ የህዳሴዉ ግድብ ቦንድ ሽያጭ እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ከተናገሩ በኋላ ምክንያቱን ሲገልጹ የአሜሪካ ህግ ለቦንድ ሽያጩ አመቺ አለመሆኑን ገልጸዉ ይህንን ለማሻሻል መንግስታቸዉ ከአሜሪካ መንግስት ጋር አብሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። መቼም ለራሱ አገር ይህ ነዉ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ህግ አዉጥቶ የማያወቀዉ እንቅልፋሙ የኢትዮጵያ ፓርላማ የአሜሪካንን መንግስት የሚገዛ ህግ ካላወጣ በቀር ዶ/ር ቴድሮስ አደራ የተጣለባቸዉን የቦንድ ሽያጭ እንዴት አሜሪካ ዉስጥ እንደሚወጡት ባላዉቅም መንግስታቸዉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባለበት ቦታ ሁሉ ሁሉ ቦንድ መሸጥ ያልቸለዉ የየአገሮቹ ህግ ችግር ፈጥሮበት ሳይሆን ለወገኖቹ መብትና ነጻነት የሚታገለዉ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቼንና እህቶቼን እየገደላችሁ የምትሸጡልኝ ቦንድ ባፍንጫዬ ይዉጣ ብሎ እምቢ ስላላቸዉ ነዉ። ይህንን ደግሞ መዋሸት እንጂ እዉነትን ሸፍኖ ማስቀረት ያልቻሉት ዶ/ር ቴድሮስም ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በስተቀር የሁሉም አገሮች የቦንድ ሽያጭ እጅግ በጣም ደካማ እንደነበር ለሰበሰቧቸዉ አምባሳደሮች ተናግረዋል፡፡
ከዶ/ር ቴድሮስ በፊትም ሆነ እሳቸዉ እያሉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከትዉልድ አገሩ ርቆ የሚኖረዉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በጥቅማ ጥቅም እየደለለ ከአገዛዙ ጎን ለማሰለፍ ተደጋጋሚ ጥረቶችን አድርጓል። በተለይ የህዳሴዉን ግድብ ቦንድ ሽያጭና የዕድገትና ትራንስፎርሜሺኑን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ዳያስፖራዉን አንደ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ ተመልክቶት ነበር፤ ሆኖም አብዛኛዉ ዳያስፖራ ከአገዛዙ ጎን ተሰልፎ ከሚያገኘዉ ግዜያዊ ጥቅም ይልቅ ዘላቂ የሆነዉን የእናት አገሩን አንድነትና የወገኖቹን ፍትህ፤ ነጻነትና እኩልነት በመምረጡ የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ከዳያስፖራዉ እዝቃለሁ ብሎ የተመኘዉ የዉጭ ምንዛሬ ህልም ሆኖ ቀርቷል።
ሌላዉ የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝ ከፍተኛ በጀትና የሰዉ ኃይል መድቦ ዳያስፖራዉን ለማማለል በሙሉ ሀይሉ የተንቀሳቀሰበት አካባቢ ቢኖር የከተማ ቦታና ቤት ሽያጭ ዘመቻ ነዉ። በእርግጥ አንዳንድ ከህዝብና ከአገር ጥቅም ይልቅ የራሳቸዉን ጥቅም ያስቀደሙ የዳያስፖራዉ አባላት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚካሄደዉን የመሬት ቅርምት በይፋ እየተቃወሙ የቅርምቱ ድግስ የእነሱን ቤት ሲያንኳኳ ግን በራቸዉን ወለል አድርገዉ ከፍተዉ የድግሱ ተሳታፊዎች ሆነዋል። አብዛኛዉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ግን እናትና አባቴን እያፈናቀላችሁ የምትሰጡኝን መሬትም ሆነ ቤት አልፈልግም ብሎ በቦንድ ሽያጩ ላይ የወሰደዉን ጠንካራ አቋም በከተማ መሬትና ቤት ሽያጭ ላይም ደግሞታል። የወገኖቹን ነጻነትና ፍትህ ለማስከበር በህይወቱ የተወራረደዉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የማያወላዉል አቋም ያልተረዱት ዶ/ር ቴድሮስ ግን ያንን የለመዱትን በጥቅማ ጥቅም የመደለል ሴራቸዉን አሁንም እንደቀጠሉበት ነዉ። ለምሳሌ ዳያስፖራዉ በመጪዉ አመት በሚደረገዉ የምርጫ ድራማ ላይ ያለዉን እይታ እንዲለዉጥ ለማድረግ ሲባል ብቻ 40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት የከፈሉበት ቤት የ2007ቱ ምርጫ ከመጀመሩ በፊት በአስቸኳይ ተጠናቅቆ እንዲሰጣቸዉ ትዕዛዝ ተላልፏል። እዚህ ላይ አንድ እጅግ በጣም የገረመኝም ያሳዘነኝም ነገር ቢኖር በአንድ በኩል ግብር ከፋይ በሌላ በኩል ደግሞ ቤት አልባ የሆነዉና እነ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም 99.6% መረጠን የሚሉት አገር ዉስጥ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ ተረስቶ ትርፍ ቤት ፈላጊዉ ዳያስፖራ ቅድሚያ እንዲሰጠዉ መደረጉ ነዉ።
ለመሆኑ ዶ/ር ቴድሮስና መንግስታቸዉ ሁሌም አክራሪዉ ዳያስፖራ እያሉ የሚያሙትን ማህበረስብ ወድደዉ ሊስሙት ነዉ ወይን ተጠግተዉ ሊያልቡት እንዲህ የተንሰፈሰፉለት? የዳያስፖራዉን አባት፤ እናት፤ ወንድምና እህት እያሰሩ፤ እየገደሉና የመብትና የነጻነት ጥያቄ የሚያነሳባቸዉን የዳያስፖራ አባል ደግሞ አገርህ አትገባም ብለዉ አገር እየነሱት እነሱ ግን የልመና ኮሮጇቸዉን ተሽክመዉ አሜሪካና አዉሮፓ እየመጡ አገርህን እናሳድግልሃለን ገንዘብ ስጠን ብለዉ የሚጠይቁት በማን አገር ማን ለሚጠቀምበት ልማት ነዉ? እነ ዶ/ር ቴድሮስ እነሱን ከመሰለ ፀረ ህዝብ አገዛዝ ጋር ተመሳጥረዉ የዳያስፖራዉን አባል በህገ ወጥ መንገድ አግተዉ እየደበደቡና መታሰሩን ሰምታ ልትጠይቀዉ የሄደችዉን እህቱን ተወልዳ ካደገችበትና እትብቷ ከተቀበረበት አገር በ24 ሰዐት ዉስጥ ዉጪ ብለዉ እያስገደዱ እንዴት ቢገምቱንና እንዴት ቢመለከቱን ነዉ ዞር ብለዉ እኛኑ ገንዘብ ስጡን ብለዉ የሚጠይቁን?
ዶ/ር ቴድሮስ ከአገር ፍቅር ሬድዮ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ከማጠቃለላቸዉ በፊት ደጋግመዉ የተናገሩት ኢትዮጵያን ምን ያክል እንደሚወዱና ይህ የሚወዱት አገር ህዝብ በእድገት ወደ ፊት ከገፉ አገሮች ተርታ ተሰልፎ ማየት አንደሚቸኩሉ ነዉ። መልካም ምኞት ነዉ። ሆኖም ይህ ምኞት የዚያችን የሚወዷትን አገር ህዝብ ሲናገር አፉን እየዘጉ፤ ሲጽፍ እጁን እያሰሩ፤ ሃሳቡን ሲገልጽ ማዕከላዊ ወስደዉ ሰቅለዉ እየገረፉና ሰላማዊ ሠልፍ ተሰልፎ መብቴንና ነጻነቴን አክብሩልኝ ብሎ የጠየቃቸዉን ደግሞ ደረቱንና ጭንቅላቱን በጥይት እያፈረሱ የሚሳካ ምኞት አይደለም። ዶ/ር ቴድሮስ በአፋቸዉ ብቻ የሚናገሩት ምኞት ዳያስፖራዉ በአፉም በልቡም ዉስጥ ያለ፤ የነበረና ለወደፊትም የሚኖር ምኞት ነዉ። ምኞታችንና ምኞታቸዉ ገጥሞ ኢትዮጵያ አድጋና በልጽጋ የምናያት ግን ዶ/ር ቴድሮስ እኛም እንደሳቸዉ በአገራችን ጉዳይ እንደሚያገባን በዉል ሲረዱና ይህንን ሃያ ሦስት አመት ሙሉ በችንካር ቀርቅረዉ የዘጉብንን በር ወለል አድርገዉ ሲከፍቱ ብቻ ነዉ።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ በልጆቿ መስዋዕትነት ይረጋገጣል!!!!
አቶ ኤፍሬምን በኢሜይል ለማግኘት ebini23@yahoo.com ይጠቀሙ።
የኢቦላን ቫይረስ በአስተማማኝ ዝግጅት መከላከል የግድ ነው!
በጋዜጣው ሪፖርተር
በምዕራብ አፍሪካ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ መላውን አፍሪካ ብሎም ዓለምን እንዳያዳርስ ሥጋት አለ፡፡ ይህ ሥጋት የሁላችንም ነው፡፡
Image may be NSFW.
Clik here to view.ከዚህ ጎን ለጎን ግን በከፍተኛ ደረጃ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮች አሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በጎረቤት አገር በደቡብ ሱዳን በተከሰተ ግጭት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ በየቀኑም በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ይገባሉ፡፡ ከኤርትራም በኩል እንዲሁ፡፡ በድንበሮች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር በጤና ባለሙያዎችና አስፈላጊ ናቸው በሚባሉ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ካልታገዘ ችግር ይኖራል፡፡
ከተለያዩ የጎረቤት አገሮች ጋር የሚዋሰኑ ክልሎች ከፌዴራል መንግሥት ጋር ጥብቅ የሆነ ትብብር ፈጥረው የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል አቅማቸውን ማጠናከር አለባቸው፡፡ የአገሪቱ የጤና ፖሊሲ መከላከል ላይ እንደማተኮሩ መጠን በየትኛውም ጊዜ ሊከሰት የሚችለውን ይህንን ገዳይ ቫይረስ ተጠናክሮ መከላከል የግድ ይላል፡፡ ለጊዜው በአገራችን ወይም በጎረቤት አገሮች አልተከሰተም በሚል ከመዘናጋት፣ የችግሩን አስከፊነትና መዘዝ በመረዳት አስፈላጊው ሁሉ ቅድመ ዝግጅት መደረግ ይኖርበታል፡፡
Image may be NSFW.
Clik here to view.የአገሪቱ ዋነኛ መግቢያና መውጫ በሆነው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን፣ የብሔራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታውቀዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከኅብረተሰቡ ጤና በላይ ትልቅ አጀንዳ አለመኖሩንም ገልጸዋል፡፡ መንግሥት በዚህ ደረጃ መተማመኛ ሲሰጥ ደስ ይላል፡፡ ነገር ግን ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ሲባል የቁጥጥሩ ጥራትና ደረጃ ምን ያህል ነው? ከቁጥጥሩ በላይ በሩቅ ርቀት የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ምን ታስቧል? ድንገት ቫይረሱ ቢከሰት ዜጎችን በምን ዓይነት ሕክምና ማከም ይቻላል? የኢቦላ ቫይረስን በተመለከተ ለሚመለከታቸው የጤና ባለሙያዎች ሥልጠና እየተሰጠ ነው ወይ? የመሳሰሉትን ማሰብ ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ የመንገደኞች፣ የአየር መንገዱ ሠራተኞች፣ የፀጥታ አስከባሪዎች፣ የኢሚግሬሽንና የአውሮፕላን ማረፊያው ሠራተኞች ደኅንነት ታሳቢ መደረግ አለበት፡፡
በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እየተደረገ ያለው ቁጥጥርና ደኅንነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳይም ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ምንም እንኳ አየር መንገዱ ወደ ላይቤሪያ፣ ጊኒና ሴራሊዮን ከበፊትም ቢሆን በረራዎች ባይኖሩትም፣ በተነፃፃሪ አነስተኛ የኢቦላ ቫይረስ ታይቶበታል ወደሚባለው ናይጄሪያ ግን መደበኛ በረራ ያደርጋል፡፡ አየር መንገዱ ለሠራተኞቹና ለመንገደኞቹ ደኅንነት ሲል አስፈላጊውን ተግባር እያከናወነ መሆኑን ቢገልጽም፣ በሚመለከታቸው አካላት ተጨማሪ ዕርምጃዎች እንዲወስድ የመፍትሔ ሐሳብ ከቀረበለት ተግባራዊ እንደሚያደርግ ቢያስታውቅም፣ የኢቦላ ቫይረስ ዓለም አቀፍ ሥጋት ከመሆኑ አንፃር የበረራውን ጉዳይ ሊያስብበት ይገባል እንላለን፡፡
በናይጄሪያ 13 ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ ተጠቅተው አራት መሞታቸው ሲረጋገጥ፣ በ189 ሰዎች ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑን የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳ የአየር መንገዱ የገበያ ተፎካካሪ የሆኑ ሌሎች አየር መንገዶች የናይጄሪያ በረራቸውን ባያቋርጡም፣ የዓለም የጤና ድርጅትና የዓለም አቀፍ አየር ትራንስፖርት ማኅበር አየር መንገዶች ወደ ምዕራብ አፍሪካ የሚያደርጉትን በረራዎች እንዳያቋርጡ ቢወተውቱም፣ የኢቦላ ቫይረስ ፍቱን መድኃኒት ሳይገኝለት በድፍረት የሚደረግ እንቅስቃሴ ውጤቱ የከፋ ሊሆን ይችላል፡፡ ናይጄሪያ ውስጥ ከሞቱ ግለሰቦች መሀል አንዱ ሴራሊዮን ውስጥ የኢቦላ ተጠቂዎችን ሲያክም የነበረና ናይጄሪያ ገብቶ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱን ያጣ ሒኪም ነው፡፡ ስለዚህ የአየር መንገዱ ባለሥልጣናት ይህንን ታሳቢ ቢያደርጉ መልካም ነው፡፡ ከገበያ በላይ የሕዝብ ጤና ጉዳይ አሳሳቢ ነውና፡፡
መንግሥት ከሕዝቡ ጤና በላይ ሌላ ትልቅ አጀንዳ የለም ማለቱ ጥሩ ነው፡፡ ለሕዝብ ጤና ጥበቃ ሲታሰብ ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት፣ እንዲሁም በተገቢው መንገድ ምላሽ መስጠት የሚችል ተቋም መቋቋም አለበት፡፡ ለብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ የሕዝብ ጤና መናጋት ወይም ቀውስ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ለሚፈጠር ወረርሽኝ ብቻ ሳይሆን ዘላቂነት ያለውና ድንገተኛ አደጋን መመከት የሚያስችል ማዕቀፍ ሊኖር ይገባል፡፡ በአንድ አገር ላይ ከፍተኛ ወረርሽኝ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጎርፍ፣ የሰደድ እሳትና የመሳሰሉ ጥፋቶች ቢደርሱ ብቁና የተደራጀ አካል ሊኖር የግድ ይላል፡፡ በወረርሽኝ ለሚከሰቱ በሽታዎች ደግሞ እንዲህ ዓይነቱን ተቋም በቋሚነት ማቋቋም ሊታለፍ አይገባውም፡፡ ድንገት ለሚፈጠሩ ቀውሶች እስከ መቼ ኮሚቴ ወይም ግብረ ኃይል ይቋቋማል?
በጤናው ዘርፍ የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ያሳካሉ ተብለው ከሚጠበቁ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ይህ ማለት ከምሥራቅ አፍሪካ አልፎ በመላው አኅጉር የኢቦላን ቫይረስ ሥርጭት ለመግታት አማራጭ ሐሳቦችን የማቅረብ ኃላፊነት አለባት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከአፍሪካ ኅብረት መቀመጫነቷም በላይ በአፍሪካ ያላትን ተደማጭነት የምታሳይበት በመሆኑ መንግሥት በከፍተኛ ትኩረት ይህንን የማስፈጸም ኃላፊነት አለበት፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት መረጃዎች እንደሚያሳዩት በኢቦላ ቫይረስ ተይዘዋል ከተባሉ 2,240 ተጠርጣሪዎች ውስጥ ከ1,200 በላይ ሞተዋል፡፡ የእዚህን ገዳይ ቫይረስ ሥርጭት ለመግታትና ሊከሰት የሚችለውን የጤና ቀውስ ለመግታት አገሮች ድንበር ዘለል የሆነ የተቀናጀ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ እየቀረበ ነው፡፡ መረጃዎችን ከመለዋወጥ አልፎ ዘርፈ ብዙ የሆኑ የጋራ ጥረቶች እንዲደረጉ እየተጠየቀ ነው፡፡ ለዚህም ፈጣን ምላሽ ሊኖር ይገባል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ትሁን፡፡
በብሔራዊ ደረጃ በምንም ዓይነት መንገድ የኢቦላ ቫይረስ እንዳይገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ ሕዝቡን ከዚህ ገዳይ በሽታ ለመታደግ አስፈላጊው ሁሉ መስዋዕትነት መከፈል ይኖርበታል፡፡ ኤችአይቪ/ኤድስ በአገራችን ያደረሰውን ከፍተኛ ሰብዓዊና ማኅበራዊ ቀውስ በማስታወስ፣ የኢቦላ ቫይረስን በተደራጀ ዝግጅትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ መከላከል የመንግሥትና የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነት ቢሆንም፣ ሕዝባችንም በከፍተኛ ጥንቃቄ ራሱን መጠበቅ አለበት፡፡ ‹‹ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ›› የሚለውን ዕድሜ ጠገብ ብሂል እያስታወስን፣ ይህንን ገዳይ በሽታ በአስተማማኝ ዝግጅት መከላከል የግድ ይለናል!
ዳኞች ካድሬ ሲሆኑ እንደማየት የመሰለ የአገር ዉድቀት የለም – (ግርማ ካሳ)
Image may be NSFW.
Clik here to view.አገሩን እና ሕዝቡን የሚወድ ። እንደ ሌሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን፣ ኢትዮጵያ ከግፍ አገዛዝ ተላቃ ዜጎች መብታቸዉና ነጻነታቸው ተጠበቆ፣ ተከባብረዉ በስላም የሚኖሩባት አገር እንድትሆን፣ የሚያደርጉትን ትግል የተቀላቀለ ነው። ወጣት ነው። ጉልበትና አቅም አለው። እንደ አንዳንዶች በጥቅም ተታሎ አደርባይነትን መምረጥ ይችል ነበር። ነገር ግን አላደረገዉም። «ሰዉ ያለ ነጻነቱ ምንድን ነው ? » ብሎ ለነጻነቱ ቆመ። የባለ ራእዩ ወጣቶች ማህብርን ከዚያም የአንድነት ፓርቲን ተቀላቀለ። በአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ መዋቅር የቦሌ ወረዳ አመራር አባል ሆኖ ይሰራ ነበር። በሶሻል ሜዲያዉም ብዙ ጊዜ ድምጹን ያሰማል። አይፈራም። ወኔ አለው።
በቅርቡ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ እየተደረገ በነበረዉ፣ ዉህዱን ፓርቲ ለመምራት በተደረገው የምርጫ ፉክክር «አዲስ አመራር ያስፈልጋል» በሚል ለአቶ በላይ ፍቃደ ይቀሰቅስ ነበር። ለዉጥ ፈላጊ ነው።
ነሐሴ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ፣ ዜጎችን ማሰርና ማሰቃየት የለመደባቸው የአገዛዙ ታጣቂዎች ከየአቅጣጫው ተረባረቡበት። ምክንያቱ ለጊዘው ባልታወቀ ሁኔታ ወደ ወህኒ ወረወሩት። ይህ ወጣት ፣ ብዙዎች የማያወቁት፣ የማደንቀዉን የማከብረው ጥላዬ ታረቀኝ ይባላል።
ፖሊሲ ፍርድ ቤት ይዞት በቀረበ ጊዜ፣ «በሰው ላይ ጉዳት አድርሷል» የሚል ክስ ነበር ያቀረበበት። ፖሊሲ በሰው ላይ ጉዳት አደረሰ የሚል ክስ አቅርቦ ጉዳት ደረሰበትን የተባለው ግለሰብ ግን ለማቅረብ አልቻለም። «ጉዳይ ደረሰበት የተባለውን ሰው ማግኘት አልቻልኩም» ብሎ መረጃዎችን ለማሰባሰብ ጊዜ እንዲሰጠው ጠየቀ። ወጣት ጥላዬ ግን ለፍርድ ቤቱ ፣ «የያዙኝ ደህንነቶች እየመጡ ከእኛ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ እስካልሆንክና የምንሰጥህን ተልዕኮ እስካልፈፀምክ እዚህ ትበሰብሳለህ እንጂ አትወጣም» እያሉ እንደሚዝቱበት አስረዳ። ዳኛው ግን መረጃ ባልቀረበበት እና በወጣት ጥላዬ ላይ በፖሊሶች ዛቻና ማስፈራሪያ እየተሰጠ ባለበት ሁኔታ፣ በዋስ እንዲፈታ ሳይፈቅ ቀረ። ለነሐሴ 12 ፖሊሲ መረጃዎቹን አጠናቆ እንዲያቀርብ ትእዛዝ ሰጠ።
ጉዳት ደረሰ የተባለው ከሁለት ወራት በፊት፣ በሰኔ 12 ቀን 2006 ዓ.ም ነው። በቀጠሮዉ ቀን፣ ፍርድ ቤቱ «ሁለት ወራት ሙሉ የት ነበራችሁ? ለምንስ ጉዳት የደረሰበት ሰው አላቀረባችሁም ? » ሲል ጠየቀ። ፖሊሶች «ጉዳይ የደረሰበትን ሰው ልናገኘው አልቻልንም። የሕክምና ማስረጃ እንድናቀርብ ይፈቀድልን» ብለው ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጣቸው ጠየቁ። ወጣት ጥላዬ «የአንድነት ፓርቲ አባል በመሆኔ፣ ባለኝ የፖለቲካ አመለካከት ጫና ለማሳደር የተወጠነ ውጥን» ነው ሲል ከፍርድ ቤቱ ፍትህን ጠየቀ።ፍርድ ቤቱ ግን አሁን ለሰላማዊ ዜጎች ፍትህን ነፈገ። ወጣት ጥላዬ በወህኒ እንዲቆይ ተደርጎ ተለዋጭ ቀጠሮ ለነሐሴ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ተሰጠ።
አስቡት፣ የሕክምና መረጃ ያለ ባሌበቱ ሆስፒታሎች መስጠት የለባቸውም። (የአገር ደህንነትን የሚነካ ካልሆነ በቀር)። አሁን፣ ፖሊስ እያለ ያለው፣ ታከመ የተባለው ሰው ፍቃድ ሳይጠየቅ፣ የህክማን ማስረጃ ከሃኪም ቤቶች እንደሚያቀርብ ነው። ለነገሩማ የሆስፒታል አስተዳዳሪዎች ዉሸትን ጨማምረው፣ ያለዉን እንደሌለ፣ የሌለዉን እንዳለ አድርገው መረጃ መስጠታቸው አይቀርም። በተለያዩ ጊዜያት በሌሊት የሚገደሉ፣ በረሃብና በጠኔ የሚሞቱ ብዙ ናቸው። በአገር ቤት ችግር እንደሌለ የዉሸት ገጽታ ለማቅረብ የሚፈልገው አገዛዙ፣ ሆስፒታሎች የዉሸት አታብሲ (የሞት ይሕክምና ማረጋገጫ) እንዲጽፉ እንደሚያደርጓቸውም ያው አገር ሁሉ የሚያወቀው ሐቅ ነው።
እንግዲህ ይሄ ሁሉ የሚያሳየው ሁለት ትላልቅ ነጥቦች አሉ።
1. ብዙዎቻችን በጣም የሚታወቁ ግለሰቦች ሲታሰሩ ነው የአገዛዙ ዜጎችን የማሸበርና የማወክ ተግባር የሚታየን። ነገር ግን በአገራችን እየተደረገ ላለው እልህ አስጨራሽ ትግል፣ ብዙ የማናውቃቸው ወገኖቻችን ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ከነዚህም አንዱ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ ነው።
2. በኢትዮጵያ አገራችን ባሉ ፍርድ ቤቶች እየታየ ያለው፣ ፍትህን የማስከበር ሥራ ሳይሆን፣ ፍጹም አሳፋሪ፣ ኋላ ቀርና አሳዛኝ የፍርድ መዛባት እንደሆነ ነው። ፖሊስ ዜጎችን እንደፈለገ ሲያስርና ሲያሸብር፣ በፈለገ ጊዜ ተጨማሪ ቀጠሮ ሲጠይቅ፣ ዳኞች ቅንጣት እንኳን የሕግ ባለሞያዎች የስነ-ምግባር ኮድ (ኤቲክስ) ሕሊናቸውን ወቅሷቸው፣ ትክክለኛ ነገር ሲሰሩ እንደማይታዩ ነው። ዳኞች ካድሬ ሲሆኑ ደግሞ ከዚህ የበለጠ ለአገር ዉድቀት የለም።
ገዢዎች ይኸው ስልጣን ከያዙ ጀመሮ እንደገደሉና እንዳሰሩ ናቸው። ሕግን መቀለጃ እያደረጉ ናቸው። ነገር ግን በዱላ፣ በጠመንጃ፣ በማስፈራራት፣ በዛቻ ኢትዮጵያዉያን ለመብታቸው፣ ለነጻነታቸውና ለአንድነታቸው የሚያደርጉት ትግል ሊገቱ አይችሉም። እሳት የለበሱ፣ በወኔ የተሞሉ፣ የስለጠነ ፖለቲካ የሚያራምዱ፣ በአንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን በመላ አገሪቷ የሚኖሩ፣ አገዛዙ ከዘረጋዉን የጎሳ ድንበር አልፈው በሰብእናና በኢትዮጵያዊነት የተሳሰሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንደ ጥላዬ ታረቀኝ ኢትዮጵያ አፍርታለች።
እንግዲህ ይሄ ሁሉ የሚያሳየው ሁለት ትላልቅ ነጥቦች አሉ።
ገዢዎች ይኸው ስልጣን ከያዙ ጀመሮ እንደገደሉና እንዳሰሩ ናቸው። ሕግን መቀለጃ እያደረጉ ናቸው። ነገር ግን በዱላ፣ በጠመንጃ፣ በማስፈራራት፣ በዛቻ ኢትዮጵያዉያን ለመብታቸው፣ ለነጻነታቸውና ለአንድነታቸው የሚያደርጉት ትግል ሊገቱ አይችሉም። እሳት የለበሱ፣ በወኔ የተሞሉ፣ የስለጠነ ፖለቲካ የሚያራምዱ፣ በአንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን በመላ አገሪቷ የሚኖሩ፣ አገዛዙ ከዘረጋዉን የጎሳ ድንበር አልፈው በሰብእናና በኢትዮጵያዊነት የተሳሰሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንደ ጥላዬ ታረቀኝ ኢትዮጵያ አፍርታለች።
ከቤተ ክርስቲያኑም በላይ ‹‹ቤተ ክርስቲያን››
ከጌታቸው ሽፈራው
ባለፈው ሰኞ ዕልት ነው፡፡ ምን አልባትም ከአንድ ሰዓት በላይ ሊያስጠብቀን የሚችለውን የታክሲ ሰልፍ ትተን ከቤተ መንግስቱ በስተ ቀኝ ያለውን መንገድ ይዘን ወደ አራት ኪሎ አቀናን፡፡ በስተመጨረሻም ስላሴ በተክርስቲያን ደረሰን፡፡ በወቅቱ ማን የት ጋ እንደተቀበረ የተሻለ መረጃ የነበረው ብርሃኑ ተክለያሬድ የአስጎብኝነቱን ሚና እየተወጣ ነው፡፡ ‹‹እዚህ ጋር 60ዎቹ የተቀበሩበትን ነው፣ እዚህ ጋር አብዲሳጋ፣ እዚህ ጋ ጥላሁን ገሰሰ፣ ይህኛውን አዳራሽ ደግሞ ለሰርግ ያከራዩታል…..››፡፡
Image may be NSFW.
Clik here to view.ብርሃኑ ቀጥሏል! ‹‹‹ስብሃት ገብረግዚያብሄርም እዚህ ነው የተቀበረው፡፡››
አሁን ስማቸውን የማላስታውሳቸውን የዘመኑን በርካታ ካድሬዎች የተቀበሩበትን ካሳየን በኋላ (አለማየሁ አቶምሳን አስታወስኩት) ከስላሴ ወደታች እያሳየ ‹‹በዛ ታች ባለው ቤተክርስቲያን ደግሞ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ቀብር ታገኛላችሁ››፡፡ ያሳዝናል ስንት ካድሬ ስላሴ ተቀብሮ ስንቶቼ ደግሞ ‹‹ስላሴ አይመጥናችሁም!›› ተብለዋል፡፡
ትንሽ አለፍ ስንል አንድ በየ አቅጣጫው መብራት የሚንቦገቦግበት ቦታ ይታያል፡፡ ለካስ የመለስ ዜናዊ ቀብር ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ አጥር ግቢ ውስጥ ከሚታየው ሁሉ ደመቅ ያለው ቦታ ይህ መቃብር ብቻ ነው፡፡ በየ ቦታው ሻማዎች ይበራሉ፡፡ በርካታ መብራት አንፖሎች ይንቦገቦጋሉ፡፡ በርካታ አበቦች ዙሪያውን ተኮልኩለዋል፡፡ ቦታው ከመጠን በላይ ከበራው መብራት ጋር ተዳምሮ ያንጸባርቃል፡፡ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወዲህና ወዲያ ይንጎራደዳሉ፡፡
ወታሮች ከሚንጎራደዱበት ቀበር ፊት ለፊት የሚታየው ቤተክርስቲያን በር ላይ በርከት ያሉ አማኞች መሬት ላይ ተደፍተው አምላካቸውን ይለምናሉ፡፡ ወታሮቹ ደግሞ የድሮ ገዥያቸውን አስክሬን በመሳሪያ እየጠበቁ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያኑ ላይ ብዙም ደመቅ ያለ ነገር (መብራት) አይታኝም፡፡ ምን አልባትም የቀብሩ መብራት ደመቅ ብሎ ስለበራ ይሆናል፡፡ ምዕመናኑ ከሚሰግዱበት በማይመጣጠን መልኩ ቀብሩ ዙሪያ የተነጠደው እብነ በረድ ያዳልጣል፡፡ ዙሪያውን የዕለት ደማቅ አበቦች ተደርድረዋል፡፡ ቀብሩና አካባቢው የሚገኙ አትክልቶችና ሳር በየ ቀኑ ብቻ ሳይሆን በየ ሰዓቱ እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው በቀላሉ መገመት ይቻላል፡፡ ቀሪው የቤተ ክርስቲያኑ ክፍል ላይ እንዲህ አይነት ልምላሜም ሆነ እንክብካቤ አይታይም፡፡ እንዲያውም ምእመናን የሚሰግዱበት አብዛኛው የቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ወለሎቹ የተራቆቱ ናቸው፡፡
ለአቶ መለስ ቀብር ከፍተኛ እንክብካቤ ይደረግለታል፡፡ ቀን ላይ የዋሉ ሁለት የሰራዊት አባላት አሉ፡፡ መቼም ማታም ላይ ይቀየራሉ ማለት ነውና ሁለትና ከዚያ በላይ ጠባቂዎች ሊመደቡ ነው፡፡ በ6 ሰዓት ከሆነ የሚቀያየሩት ደግሞ ቢያነስ ከ10 በላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ያስፈልጋሉ፡፡ አትክልት የሚያጠጣ፣ ጽዳት የሚያጸዳና እነዚህን ሁሉ የሚያዝ አካል ያስፈልጋል፡፡ ሌሎች የቀብሩ ተቀጣሪዎችም ይኖራሉ፡፡ ያ ‹‹ቤተ ክርስቲያን (ቀብር)›› ከ10 እስከ 20 ሰው ሰራተኛ አለው ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ቀበሌዎች 10 ፖሊስ የላቸውም፡፡ አብዛኛዎቹ የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች 20 ሰራተኛ የላቸውም፡፡ ሌሎች ተቋማትን እንዲሁ! ቤተ ክርስቲያኗ ራሷ ይህን ያህል ቋሚ ሰራተኛ ይኑራት አይኑራት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡
አዎ! ከዛ አጥር ግቢ ውስጥ ከቤተ ክርስቲያኑ በላይ ‹‹ቤተ ክርስቲያን›› ሆኖ ከፍተኛ እንክብካቤ የሚደረግለት የአቶ መለስ ቀብር ነው፡፡ ከታቦቱ በላይ ጥበቃ የሚደረግለት የአቶ መለስ አስከሬን ነው፡፡ በአጠቃላይ ከስላሴ ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ከቤተ ክርስቲያኗም በልጦ ክብር እየተሰጠው የሚገኘው የአቶ መለስ ዜናዊ ቀብር ነው፡፡ ይገርማል! ለእነዚህ ሰዎች አቶ መለስ ከስላሴም በላይ ናቸው ማለት ነው?
መለስን ቅበሩት! –ተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)
ከኢትዮጵያ ሀገሬ የደቀቀ ኢኮኖሚ ላይ በማን አህሎኝነት ወጪ ተደርጎ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ በመላ አገሪቱ እየተከበረ ስላለው የቀድሞ አምባገነን ጠ/ሚኒስትር ሁለተኛ ሙት ዓመት ዝክርም ሆነ ሰውየውን ዛሬም በአፀደ-ህይወት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ላሉት ጓዶቹ አንዲት ምክር ብጤ ጣል ማድረጉ ተገቢ ነው ብዬ ስለማስብ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፡-
Image may be NSFW.
Clik here to view.አብዮታዊው ገዥ-ግንባር ግንቦት ሃያ፣ የህወሓት ምስረታ፣ የብአዴን አፈጣጠር፣ የኦህዴድና የደኢህዴን ውልደት፣ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል፣ የባንዲራ ቀን፣ የመከላከያ ሳምንት፣ የፍትሕ ሳምንት፣ የሕዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት… ጅኒ-ቁልቋል እያለ ዓመቱን ሙሉ በማይጨበጥ ተራ ፕሮፓጋንዳ ማሰልቸትን መንግስታዊ ኃላፊነት አድርጎታል፡፡ ይህ እንግዲህ ለቁጥር የሚያታክቱ፣ በነጭ ውሸት የታጨቁ እና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቅኝት የተንሸዋረሩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞቹ›ን ረስተንለት ነው፡፡
ይህ ሁሉ ያልበቃው ‹‹ጀግናው›› ኢህአዴግ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ወዲህ፣ ወርሃ-ነሐሴንም እንደ ግንቦት ሃያው ሁሉ የሟቹን ታጋይነትና አብዮታዊነት፤ ሕዝባዊነትና አርቆ አስተዋይነት፤ የርዕዮተ-ዓለም ተራቃቂነትና የአየር ንብረት ተካራካሪነት፤ በፖለቲካ ቢሉ በኢኮኖሚ ቁጥር አንድ ጠቢብነትና ባለራዕይነት፤ ፍፁም ፃድቅነትና ሰማዕትነት…. የሚተረክበት ሲያደርገው ቅንጣት ታህል ሀፍረት አልተሰማውም፡፡ ሰሞኑን በ‹‹ኢትዮጵያ›› ቴሌቪዥን ግድ ሆኖብን ተመልክተንና ሰምተን በትዝብት ካሳለፍናቸው ‹‹መለስ፣ መለስ›› ከሚሉ የከንቱ ውዳሴ አደንቋሪ ድምፆች በተጨማሪ፣ የኦሮሞን ባሕላዊ ልብስ ሲያለብሱት፣ ሐረሪዎች ጋቢ ሲደርቡለት፤ በደቡብ የሚገኙ ብሔሮች የየራሳቸውን ባሕል የሚወክሉ አልባሳት ሲሸልሙት፣ ስለወላይታነቱ ሲመሰክሩለት… ደጋግመን ለመመልከት ተገደናል፤ ይሁንና ድርጅቱ ስለ ቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አልፋና ኦሜጋነት ለመስበክ ዙሪያ ጥምዝ ከዳከረለት ከእንዲህ አይነቱ የተንዛዛ ፕሮፓጋንዳ ይልቅ፣ በዚሁ የቴሌቪዥን መስኮት የቀረበ አንድ ጎልማሳ ‹‹መለስ ሁሉም ማለት ነው›› ሲል የሰጠው አስተያየት፣ ቅልብጭ አድርጎ ይገልፅለት ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የዚህ አይነቱ ምጥን አስተያየትም በጥራዝ ነጠቅነት ዘላብዶ የኋላ ኋላ በሀፍረት ከማቀርቀር ያድናል፡፡ ለምሳሌ እናንተ የግንባሩ ካድሬዎች ስለመለስ ምሁርነት ለመናገር ስትዳዱ ሁሌ የምትደጋግሙት፣ ያንኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አርቃቂነቱ እና የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ኀልዮት አዋቃሪነቱ ነው፡፡ ግና፣ ይህ ‹‹ንድፈ-ሃሳብ›› ተብዬ ራሱ በርዕዮተ-ዓለምነት ለመጠራት የማይበቃ የተውሸለሸለ ጭብጥ ስለመሆኑ በርካታ ምሁራን በጥናቶቻቸው ከማስረገጣቸው ባሻገር፣ አገሪቷን ለከባድ ኢኮኖሚያዊ ድቀት፣ ሕዝቧን ደግሞ ለጥልቅ ድህነት መዳረጉን ብቻ ማስታወሱ በቂ ይሆናል፡፡ ስለልማታዊ መንግስት አዋጭነት በብቸኝነት እንደተከራከረ ተደርጎ የሚለፈፈውን እንኳን ንቆ መተው ሳይሻል አይቀርም፡፡ ከታንዲካ ማካንደዋሬና መሰል የፅንሰ-ሃሳቡ አበጂዎች የዘረፋቸውን መከራከሪያዎች ማን ዘርዝሮ ይዘልቀውና፡፡ ‹መለስን ቅበሩት› የምለውም፣ እንዲህ ያሉ አስነዋሪ ማንነቶቹን ማስታወስ ስለሚያም ነው፡፡
Clik here to view.

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
እናም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- ስለሰውዬው የምትነግሩን እና የምታስቀጥሉት ‹ሌጋሲ›ም ሆነ የምትተገብሩት ረብ ያለው አንድም ራዕይ የለምና ዝም፣ ፀጥ ብላችሁ የምራችሁን ቅበሩት፡፡ እስቲ! ኦጋዴንን ተመልከቱ፤ ካሻችሁም ወደ አኝዋኮች ተሻገሩ፤ ያን ጊዜ እናንተ በአርያም የሰቀላችሁት ሰው፣ ለነዚህ ሁለት ብሔሮች የቀትር ደም የጠማው ጨካኝ መሪ እንደነበር፣ በክፋት ትዕዛዞቹ ጥፋት ከተረፈ ጠባሳ ትረዱታላችሁ፡፡ ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ህፃናት በሰልፍ የሚደፈሩባት፣ ወጣቶች እንጀራ ፍለጋ በተስፋ-ቢስነት ጥልቁን ውቅያኖስ ሰንጥቀው ለመሰደድ የማያመነቱባት፣ የጤና ኬላ ማግኘት ተስኗቸው በልምሻ የሚባትቱ ብላቴኖችን በአቅም-የለሽነትና በቁጭት የምናስተውልባት ደካማ አገር አስረክቦን እንዳለፈ ከወዴት ተሰወረባችሁ? ከቀዬዎቻቸው በጉልበት ለተፈናቀሉ ወገኖች በመቆርቆር ‹‹ሕግ ይከበር!›› ባሉ በየጉራንጉሩ ወድቀው እንዲቀሩ የተፈረደባቸው ጎበዛዝትን ሬሳ እንድንቆጠር ያደረገን ደመ-ቀዝቃዛ ‹መሪ› እንደነበረስ ስንት ጊዜ እያስታወስን እንቆዝም? ቀደምት አባቶች ወራሪውን ፋሽስት ለማንበርከክ የተዋደቁባቸው ጢሻና ኮረብቶች በዚህ ዘመን የዜጎች ወደሞት አገራት መሸጋገሪያ ጽልማሞቶች የሆኑት በማን ሆነና ነው? ከሕግ ተጠያቂነት ቢያመልጥ፣ ከታሪክ ተወቃሽነት ልትታደጉት የምትችሉ ይመስላችኋልን?
…ይልቅ እመኑኝ! ፀጥ ብላችሁ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍራችሁ ቅበሩት! ላይመለስ በመሄዱም እንደ ግልግል ቆጥራችሁት እርሱት!! መቼም በገዛ ራሱ ሕዝብ ላይ ትውልዶች ይቅር ሊሉት የሚሳናቸውን ይህን መሰሉ መከራ ላዘነበ ሰው በአፀደ-ስጋ ሳለም ሆነ በበድን የሙት መንፈሱ ስር በየዓመቱ ለአምላኪነት መንበርከክ፣ የናንተን አልቦ ማንነት እንጂ ሌላ አንዳች የሚነገረን ቁም ነገር ጠብ ሊለው አይችልም፡፡ ይህም ሆኖ ለመለስ አምልኮ እጅ መስጠት አሳፋሪነቱ፣ ለካዳሚዎቹ ብቻ መሆኑን መስክሮ ማለፉ የቀሪዎቻችን ዕዳ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡
“የመለስ ትሩፋቶች” –ኤርምያስ ለገሰን በጨረፍታ
ከሆረቶ ቶላ
Image may be NSFW.
Clik here to view.
ኢሳት ቲቪ ከአቶ ኤርምያስ ለገሰ ጋራ ያደረገውን ተከታታይ ቃለ-መጠይቅ ከሰማሁ በኋላ የአቶ ኤርምያስን መፅሃፍ የማንበብ ጉጉት አደረብኝ :: በሁለት ምክንያቶች ፤
1) አቶ ኤርምያስ ስለ ወያኔ ስርዓት ብዙ መረጃ ያለው መሆኑና መረጃውን የማስረዳት ችሎታ ያለው ሆኖ ስለ ታየኝ::
2) ቃለ-መጠይቁ ላይ ብዙ ነገሮችን ከማብራራት ይቆጠብና ሙሉ መረጃውን በመፅሃፍ እንደሚያወጣ ስለነገረን:: መፅሃፉን ለማግኘት ሩጫ ተያያዝኩኝ::
በአንድነት ሃይሎችና በህወሃት ሥር ያለች ‘ስዊንግ ስቴት’ኮሎራዶ!
Image may be NSFW.
Clik here to view.በሮቤል ኦገስት 18, 2014
“ወይን ለኑሮ” ተቀባይነት ያለው የኑሮ ዘይቤ እየተባለች የምትጠራዋ ኮሎራዶ በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚኖሩባት ከተማ ብትሆንም ቅሉ ሁሉም ግን የህወሃት ደጋፊዎች ናቸው ማለት በጣም አስቸጋሪ ነው። ለዚህ ዋቢ ማስረጃ ከትግራይ የወጡ ጠንካራ የአረና ፓርቲ የኮሎራዶ ቻፕተር ተጠቃሽ ነው። አረና በኮሎራዶ ከአንድነት ሃይሎች ጋር ብዙ ጊዜ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ይታያል።
ስለዚህ የጽሁፌ መነሻ በህወሃትና በተቃዋሚዎች መካከል መፈራረቅ የበዛባት ኮሎራዶ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ እንቅስቃሴዎችን በተቃዋሚው ጎራ እየታየባት ነው። ኮሎራዶ እንኳን ለአበሾቹ፣ ለነጮቹም በዴሞክራቶችና በሪፐብሊካን ያለች ስዊንግ ስቴት(swing state) ነች። ልዩነቱ ለሆዳቸው ባደሩ፣ ለስምና ለዝና ሲሉ ለሃገራቸው ውድቀት ሌት ተቀን በሚሰሩና ሃይሎችና፤ ለእውነተኛ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ በሚታገሉ ነው።
ኮሎራዶ የወያኔ መሪዎች በሰላም ገብተው የሚወጡባት ከተማ ነች። በኮሎራዶ ያለው የህወሃት ስልት በተቃዋሚ ጎራ ያሉትን በ 40/60 እና በሌሎች ጥቅማ ጥቅም በመደለል የገለልተኛ ካርድ በመስጠት ቢያንስ እንቅፋት ለህወሃት እንዳይሆኑ ከፍተኛ መዋእለ ነዋይ በማፍሰስ ቢያንስ (undecided voters) እንዲሆኑ ይሰራል።
ከእነዚህ ውስጥ ተጠቃሾች የእምነት ተቋማትን እርስ በርስ ማጋጨት፣ የኮሚውኒቲ ማህበራትን በየጎራው በመክፈል ለምሳሌ በብሄር የተደራጁ፣ የትግራይ ተወላጆች ኮሚውኒቲ፣ የአፍሪካ ኮሚውኒቲ ሴንተር እና ዋነኛውና ሌላው የገለልተኛ ካርድ በመምዘዝ ደግሞ የኢትዮጵያ ኮሚውኒቲ በኮሎራዶ በሚል ተቋማትን ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በዝርዝር እመለስበታለሁ።
ኮሎራዶ በርካታ ኢትዮጵያኖች የሚገኙባት ተራራማ ከተማ ስትሆን፣ ህወሃት ወያኔ የተመሰረተባት ከተማ በመባልም ትጠቀሳለች፡፡ ከተማዋም አክሱም ሲስተር ሲቲ በሚል የህወሃት ባለስልጣኖች በአክሱም ስም ፓርክ እንዲሰየምላቸውም አድርገዋል። ምንም እንኮን አክሱም የሁላችን ቢሆንም ትልቅ መዋእለ ነዋይ አፍሰዋል። እንግዲህ ይህ በሚሆንባት ከተማ የተቃዋሚ ሃይሉ በጋራ በመሆን ለኢትዮጵያ አንድነት ልዩነትን በማቻቻል እየሰራ ቢሆንም ቅሉ ገና በርካታ ስራዎችን በመስራት ኮሎራዶ እንደ ተቀረው የአሜሪካን ስቴት ወያኔዎች የሚዋረዱባት እና የሚሰቀቁባት ከተማ ለመሆን ግን ሰፊ ስራዎች ያስፈልጋሉ። ኮሚውኒቶችን ማጠናከር፣ እድሮችንና፣ ማህበራዊ ስብሰባዎችን ማደራጀት ያስፈልጋል። በቤተክርሰቲያን ያሉ ልዩነቶችን በሰከነ መፍታትም ተገቢ ነው።
በርግጥ ነው ኢትዮጵያን የገጠማት ፈተና አድረባይነትና “ወይን ለኑሮ” ተቀባይነት የሌለው የዘመኑ የኑሮ ዘይቤ ሲሆን፣ ኮሎራዶም የተቃዋሚ ሃይል ደጋፊ ነው የሚባለው ከህወሃት አባላት ይልቅ የሌላው ብሄር ተወላጅ እራሱን አናሳ በማድረግ ተላላኪነትን ወይም አዲስ አበባ ስገባ በሚል ወያኔዎች ያዘጋጁትን የገለልተኛ መታወቂያ በመውሰድ ከደሙ ንጹህ ለመምሰል ሙከራዎች ሲያደርግ ይታያል። በኮሎራዶ የህወሃት አስተባባሪ የሆኑት ወርቁ፣ ፈጸመ፣ ሰመረ፣ ወንዶሰን፣ ይሳቅ የጎንደር እና የደቡብ ልጆች ናቸው፤ ማለትም ታማኝ የህወሃት አገልጋዮች ሲሆኑ በየጊዜው በይፋ የህወሃት ስብሰባዎችን የሚያዘጋጁ ሲሆኑ እነዚህን ከበስተጀርባ ሆኖ የሚነዳቸው ግን የህወሃት አባል የትግራይ ተወላጆች ናቸው።
ይህ በንዲህ እንዳለ ነው ኮሎራዶ በተቃዋሚዎች ከፍተኛ ጥረት እና ትብብር የኮሎራዶ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ለሃገርና ለሕዝብ የቆሙ ግለሰቦችና ኢትዮጵያውያን ድርጅትና፤ ተቋማት የሚያደርጉት ያላሳለሰ የአንድነት ጥረት ይበረታታል። ይሁን እንጂ ከላይ እንደገለጽኩት በባንዳ ተላላኪ እና ለሆዳቸው ባደሩ ለማን እንደሚሰሩ በማያውቁ ሰዎች በመደገፍ ህወሃት/ወያኔ አሰልጥኖ ያሰማራቸው ቅጥረኞች ሕዝብን ሳይፈሩና ሳያፍሩ የባንዳነት ተግባራቸውን ቀጥለውበት ይገኛሉ።
ጥሩ ምሳሌ፡- በኮሚውኒቲ ደረጃ ሁለት አይነት ኮሚውኒቲ አለ። አንደኛው በግልጽ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰበአዊ መብት የሚከራከር ከ20 አመት በላይ ያስቆጠረ በኢትዮጵያኖች እጅ ተይዞ የሚገኝ ሁሌም በሀገራዊ ጉዳዮች ያገባኛል የሚል ኮሚውኒቲ በአቶ ሽፈራው የሚመራ ሲሆን፤
ሌላኛው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባለመስማማት የተፈጠረ ነገር ግን የወያኔ ሰዎች የወረሩት እና ተቃዋሚዎችም የነበሩትና ግለሰቦች በጥቅማ ጥቅምና በፍርሃት አገልጋይ የሆኑበት በአቶ መለሰ ወርቅነህ የሚመራው ኮሚውኒቲ ነው።
የሁለቱ ኮሚውኒቲ ልዩነቶችና የሚመራው አካል፡-
በእነ አቶ ሽፈራው የሚመራው፡- የኢትዮጵያ ባንዲራ አርንጎዴ ቢጫ ቀይ ነው፣ የሰበአዊ መብት ጥሰቶች ካሉ በኮሚውኒቲያችን ላይ የደረሰ በደል ስለሆነ ማውገዝ ግዴታችን መሆን አለበት፣ ከመንግስት የሚደረጉ ድጋፎችን አንቀበልም፣ ለዝና ብለን አንሰራም የሚል ነው። እነ አቶ አስቻለው ከእኛ ተገንጥለው የወጡ ናቸው ህጋዊ ኮሚውኒቲ አይደሉም የአንድ መንግስት ደጋፊ ናቸው። ኢትዮጵያውያን በአርብ ሀገራት ለደረሰባቸው እንግልትና ሞት ተጠያቂው መንግስት አይደለም፣ መንግስትን አትቃወሙብን በማለት በአደባባይ በጠሩት ሰልፍ የወያኔን ባንዲራ ይዘው ማንነታቸውን ያስመሰከሩ ናቸው ይሁን እንጂ በአማካሪ ቦርድ ስም ደግሞ ‘ተቃዋሚ” ቢኖሩም ንጹህ በሚል ሽፋን ለወያኔ ጥቃት ተጋልጠናል የሚባሉ ግለሰቦች አሉበት የሚሉ ናቸው።
በአቶ መለሰ (የህወሃት አባል እና የትግራያን ኮሚውኒቲ መስራች) ኦፊሻል ባንዲራችን በዩናይትድ ኔሽን የጸደቀው የኮኮብ ምልክት ያለበት ነው፣ (ይህ በዚህ ቡደን አማካሪ ቦርድ በሆኑት በእነ ፕ/ር ሚንጋ ተቃውሞ ውድቅ ተደርጎል) በኢትዮጵያ ሰበአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ አያገባንም እኛ ውጪ ነን ያለነው፣ መንግስት የሚያወጣቸውን እንደ 40/60 ጥቅማጥቅሞች ለህዝብ ማድረስ ይገባናል፣ ያኛው ኮሚውኒቲ በኢሃፓ እና በግንቦት 7 የሚመራ ነው፣ እነ አቶ ሽፈራው ግትሮች ናቸው፣ ኮሚውኒቲውን እየከፋፈሉብን ነው የሚሉ የክስ መላምቶች አሉበት።
ድህረ ገጽ http://ethiopiancommunityofcolorado.org/announcment
በህወሃት ይመራል የሚባለውን ኮሚውኒቲ አመራሮችና እና ጀርባ ያሉ ግለሰቦችን ዝርዝር በሚቀጥለው ጽሁፌ ይዤ እወጣለሁ።
እንግዲህ በዚህ ፍትጊያ ህወሃት የሚሰራውን የውስጥ ስራ አጠናክሮ እየሰራ ነው። ተቃዋሚውን በመክፈል ተቃዋሚ የነበሩትን ገለልተኛ በማድረግ ከትግሉ እንዲወጡ እያደረገ ነው። ለዚህ ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ በወያኔነት የማይጠረጠሩትን ግለሰቦች በመያዝ ክፍፍልን መፍጠር ሁነኛ ስራው አድርጎታል። ለዚህ ደግሞ ኮሎራዶ ምቹ ነች! የወያኔን ሞፈር መሸከም የሚችሉ ያሉባት፣ ዝና ፈላጊዎች የሚታዩባት፣ የኔ ሃሳብ ብቻ የሚል ያለባት፣ የህወሃት እህት ከተማ የሆነች ስትሆን በቀላሉ ባንዳዎችን በብልጭልጭ መፍጠር የሚቻልባት ውጣ ውረድ ያለባት ተራራማ ከተማ።
የኢሳት ኮሎራዶ ቻፕተር የዛሬ አመት ይህንኑ ኮሚውኒቲ እንዲረዳው በድበዳቤ ሲጠይቅ በእነ አቶ አስቻለው አማካኝነት ይህ የተቃዋሚ ድርጅት ሚዲያ ስለሆነ አንረዳም መተዳደሪያ ደንባችን ፓለቲካ ውስጥ እንደንገባ አይፈቅድም ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በአንጻሩ ደግሞ በእነ አቶ ሽፈራው የሚመራው ኮሚውኒቲ ለኢሳት በላከው ደብዳቤ ኢሳት የኢትዮጵያኖች CNN እንዲሆን ተመኝተው ነጻ የሚዲያ አውታር ሆኖ እንዲቀጥል መደገፍ አለበት በሚል ከገንዘብ እስከ ጊዜ መሰዋእት አደርገዋል። እዚህ ላይ ሳይጠቀሱ የማይታለፉ ጉዳይ ቢኖር የኢሳት ኮሎራዶ አስተባባሪ በወቅቱ ከፍተኛ በሆነ ሀገራዊ ሞራልና ብርታት ደከመኝ ሳይሉ ሁሉንም ወገኖች እንዲሳተፉ ያደረጉት ጥረት ይደነቃል።
በአሁኑ ሰአት ደግሞ ይሔው ኮሚውኒቲ በመከፋፈል ላይ ነው ቢባልም በእነ አቶ አስቻለው አማካኝነት ኮሚውኒቲውን ከፖለቲካ አናሰገባም፣ ይሁን እንጂ መንግስትን ግን እንደ አንድ ሀገር መንግስት በመንግስትነቱ እንቀበለዋለን። ተቃዋሚው እኮ ራሱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፎ የሰጠው ግንቦት 7 ነው። ስለዚህ እኛን ለምን ፖለቲከኛ ሁኑ ትሉናላችሁ በሚል የካድሬ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ። እንግዲህ የሚባሉትን የሚናገሩ እንጂ ከእራሳቸው ጋር ኖረው የማያውቁ ጥርቅም ጉጅሌዎች ያሉበት ቡድን መሆኑን ለማየት ይህ በቂ ነው።
ዞሮ ዞሮ ኮሎራዶ ተቃዋሚው ሲጠነክር ወደ ተቃዋሚው የምታጋድል፤ ህወሃት ሲጠነክር ደግሞ ወደ ህወሃት የምትሄድ ከተማ ነችና የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ ተኩላዎች በመጠንቀቅ ኮሚውኒቲው ለወያኔ አገልጋይና አደርባይ እንዳይሆን እነሱ በሚጠሩት ማናቸውም ስብሰባ ባለመገኘት ነዋሪው አንድነታችንን ማሳየትና መጠበቅ አለበት። በአለም አቀፍ ደረጃ የወያኔ ሰዎችን የሚተባበሩ፣ የጥቅሙ አገልጋዮች የሆኑትን ግለሰቦች፣ ድርጅቶች በየከተማችን በማውጣት ህወሃትን በተመባበራቸው የታሪክ ተጠያቂ እንደሆኑ መንገር ተገቢ ነው። በገለልተኛ ስም “ወይን ለኑሮ” ተቀባይነት የሌለው የኑሮ ዘይቤ መሆኑን በግልጽ ማሳየት ይኖርብናል። ዛሬ በወያኔ ወህኒ ቤቶች ተወርውረው የሚገኙት ሰመአታት ኮሚውኒቲው እንደሚለው ሳይሆን ለእናት ሀገራቸው ከበርሃ በርሃ ሲንከራተቱ መሰዋእት የሆኑ የቁርጥ ልጆች እንጂ፤ አእምሮ የሌላቸው ትንንሽ ሽፍን ሆዳሞች እንደሚሉት እንዳልሆነ የሚረዱበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።
ለዚህ ተምሳሌት ኦገስት 9 በኮሎራዶ እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል የተዘጋጀው ስብሰባ ማህበረሰቡ ያሳየው ድጋፍ የሚበረታታ ነው። ምናልባትም አንዳርጋቸው እሱ መሰዋእት ሆኖ ያስተሳሰረን ይመስላል።
በመጨረሻም የህወሃት አባላት የሆናችሁ በተለይም በኮሚውኒቲው ስም የምትገኙ ፡- አሁንም በኮሎራዶ የምታደርጉትን የድርጅት ድጋፍ እስከአላቆማችሁ ድረስ የምታደርጉትን እየተከታተልን ለህዝብ የምናሳወቅ መሆኑን እንገልጻለን።
ጨረስኩ
ያላችሁን አስተያየት በ loveethio777@gmail.com ይላኩልኝ
የዘንዶ ሱባዔ? –ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
Image may be NSFW.
Clik here to view.nigatuasteraye@gmail.com
ነሐሴ ፳፻፮ ዓ.ም.
ማሳሰቢያ:- የዚህን አመት የፍልሰታን ሱባዔ በመጨረስ ላይ ነን። ይሁን እንጅ በዘንድሮዋ ሱባዔ በቨርጅንያ የተከሰተው ነገር የዘንዶን ሰባዊዔ የሚያንጸባርቅ ነው። ስለዚህ ይህች ጦማር የዚህን አመት ሱባዔ ለማስታወስ ተዘጋጅታ የቀረበች ናት።
አብርሃ ደስታ ሃብታሙ አያሌዉና እና ኤርትራ ( ግርማ ካሳ)
Image may be NSFW.
Clik here to view.ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር እና ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በመገናኘት ፤ እንዲሁም ከባንክ በትዕዛዝ ብር በመቀበል የግንቦት 7 ተልዕኮና አላማ ለመፈፀም፤ ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ግለሰቦችን ለዚህ ጥፋት እንዲሰማሩ በማድረግ» የሚል ክስ ነው በወዲ ሃዉዜን/ትግራይ በሆነው አንጋፋ ፖለቲከኛ እና ብሎገር ላይ ክስ የቀረበው። ሌላው አንጋፋና አንደበተ ርትኡ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ፣ ሃብታሙ አያሌውም፣ «የግንቦት ሰባት ተባባሪ ነው» በሚል ነው ለመክሰስ ነው ዝግጅት እየተደረገ ያለው።
አብርሃ ደስታ እና ሃብታሙ አያሌው ፣ «ግንቦት ሰባትን ይደግፋሉ» የሚል ክስ ከቀረበባቸው፣ በተዘዋዋሪ መንገድ «ከሻእቢያ ጋር ወዳጆች ናቸው» ማለት ነው። ታዲያ የሻእቢያ ወዳጅ የሆነ ሰው፣ የኤርትራን መገንጠል ተቃዉሞ፣ ወይንም የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤት መከበር እንዳለበት በማስመር ይናገራል ወይ ? እስቲ የጸረ-ሽብርና የአገር ደህንነት ተብዬው ምላሽ ይስጠን !!!
ሁላችንም እንደምናውቀው፣ በኤርትራ በኩል ትግል እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች፣ ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት ሊናገሩ አይችሉም። በሻእቢያ ሥር እስካሉ ድረስ ቀይ መስመር ተሰምሮላቸዋል። እነ ግንቦት ሰባቶች፣ ኦነጎች …፣ እርዳታ የሚያገኙጥ ከሻእቢያ ማእከላቼ ደግሞ አስመራ እስከሆነ ድረስ፣ «ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል» ብለው የመናገራቸው ነገር ጭራሽ የማይታሰብ ነው።
ዶር ብርሃኑ ነጋ ከቃሊት እሥር ቤት ሆነው የጻፉት አንድ መጽሃፍ ነበር። መጽሀፍ ላይ ባለው የ ኤርትራ ካርታ ፣ ኤርትራ ተቆርጣለች። ሃብታሙ አያሌው የጻፈው መጽሃፍ ላይ በሚታየው የ ኤርትር ካርታ ኤርትራ አልተቆረጠችም። ሃብታሙ አያሌው፣ ምንም እንኳን ሻእቢያና ሕወሃት/ኢሕአዴግ ከመረብ በስተሰሜን እና በስተደቡብ ያለዉን ሕዝብ ከፋፍለው፣ በደም ቢያቃቡትም፣ «ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ ሁለቱም ወገኖች አሸናፊ በሆኑበት መልኩ፣ ወንድማማቾችን አንድ ማድረግ ይቻላል» የሚል እምነት ስላለው ነው፣ ኤርትራ ከተቀረው የኢትዮጵያ አካል ጋር የቀላቀላት። ከ23 አመታት በፊት ያለው አስቦ ሳይሆን ፣ ወደፊት የሚሆነው ታይቶት ነው። ታዲያ ይህ አይነት ፖለቲከኛ ነው የሻእቢያ አሽከር ነው ተብሎ የሚከሰሰው ?
ወደ አብርሃ ደስታ ልውሰዳችሁ። በቅርብ ጊዜ ስለ አሰብ የጻፈው አስደናቂ ጽሁፍ ነበር። «ጦርነት ፈርተን ግን ሐገራችንን አሳልፈን አንሰጥም» በሚል ርእስ፣ በአደብ ጉዳይ ላይ፣ አብርሃ ደስታ ሲጸፍ « እኛ ጦርነት አንፈልግም። ሕጋዊ ንብረታችን (ወደባችን) በሰለማዊ መንገድ እንዲሰጠን ነው የምንጠይቀው። አዎ! ጦርነት አንፈልግም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ግን ጦርነት ከፍተን በሃይል የሌላ ሀገርና ህዝብ ንብረት አንወርም ማለት እንጂ ጦርነት ፈርተን ልአላዊ ግዛታችን (ሃብታችን) ለሌሎች ሃይሎች አሳልፈን እንሰጣለን ማለት አይደለም። ጦርነት አንፈልግም ማለት ጦርነት እንፈራለን ማለት አይደለም። አዎ! ጦርነት ስለማንፈልግ ሌሎች ህዝቦችን አንወርም። ጦርነት ፈርተን ግን እናት ሀገራችን አናስደፍርም» ነበር ያለው።
ታዲያ በምን መሰፍርትና ሚዛን ነው አቶ ሃብታሙ አያሌው እና አቶ አብርሃ ደስታ የ«ሻእቢያ ተላላኪ» የሚሆኑት ? በምን መስፈርት ነው ግንቦት ሰባቶች ሊባሉ የቻሉት ?
«ህወሓት በራሱ ኮ የሻዕቢያ ተልእኮ ለማስፈፀም በሻዕቢያ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ህወሓት የመሰረተው ማነው? ሻዕቢያ ነው። ሻዕቢያ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) የተባለ ኤርትራዊ የሻዕቢያ አባል በትግራይ ለሻዕቢያ ሊያግዝ የሚችል ድርጅት እንዲያቋቁም ወደ ኢትዮዽያ ላከ። እነዚህ ህወሓት የመሰረቱ የሚባሉ ሰባት ሰዎች አሰባስቦ እንዲደራጁ አደረገ» ብሎ አብርሃ ደስታ እንደጻፈው፣ ለሻእቢያ ዉስጥ ዉስጡን የሚቆረቀረዉስ ሕወሃት አይደለችንም ? ያ ባይሆን ኖሮ ተሽቀዳድሞ የአልጀርስ ስምምነት ይፈረም ነበርን? ያ ባይሆን ኖሮ አገር ቤት ካሉ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ጋር አልነጋገርም እያሉ፣ የሕወሃት/ኢሕአዴጉ ዳግማዊ መለስ ዜናዊ፣ ኃይለማሪያም ደሳለኝ «ካስፈለገም አስመራ ድረስ እሄዳለሁ» ይሉ ነበርን ?
እርግጥ ነው እነዚህ ሁለቱ አንጋፋ ወጣት ፖለቲከኞች፣ ኢሳት በተሰኘው ሜዲያ ቀርበው ቃለ ምልልስ አድርገዋል። አቦይ ስብሐት ነጋ፣ አምባሳደር ቪኪ ሃደልሰን፣ ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን፣ ወንጌላዊ ዳንኤል ጣሰው ..የመሳሰሉትም በኢሳት ቀርበዋል። ታዲያ እነ አባይ ስብሐት ፣ «ኢሳት ላይ ቀረባችሁ» ተብለው ወደ ወህኒ የወረዱበት ሁኔታስ የታለ ?
በአንድ ሜዲያ መቅረብ አንድን ሰው ጥፋተኛ አያሰኘዉም። አንድ ሰው መከሰስ ካለበት፣ ሊከሰስ የሚገባው በቃለ መጠይቆቹ ዉስጥ ባለው ይዘት ነው። አቶ ሃብታሙና አቶ አብርሃ፣ ሲጽፉም ሲናገሩም በግልጽና በአደባባይ እንደመሆኑ «ይሄን ተናገረዋል.. » ተብለው የሚከሰሱበት ነጥብ ይኖራል ብዬ አላስብም። በመሆኑም አገዛዙ ፣ እነዚህ ሰላማዊ ዜጎችን ሽብርተኞች ናቸው ብሎ ማሰሩ የትም አያደርሰውም። ይህ አይነቱ ፍርድ ገምድልነትና ዜጎችን ያለ ከልካይ ማሰርና ማንገላታት መቆም አለበት።
‹‹ይድረስ ላንቺ›› ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ –በዘላለም ክብረት
‹‹ይድረስ ላንቺ››
ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ
በዘላለም ክብረት
ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡
‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣
እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››
Image may be NSFW.
Clik here to view.
የደላው! ቢያሻው በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም ቅንጦት ነው (ወይ ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ ሊገደብ ይችላል)፡፡ ቆይ ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡
እመቤት ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ (Ethiopian by choice) ዱቼ ሞሶሎኒ እትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡ በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›… እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ› ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ? ፤ በፍፁም! ጌቶች እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi
ቧልቱ ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡ ‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡ ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን እያነሳሁ እነግርሻለሁ፡፡ወይ ትስቂያለሽ (ሳቅሽ እንዴት ያምራል?) ወይ ደግሞ ታዝኛለሽ (እኔን!)
ይህንን ደብዳቤ የመፃፍ መብት
እነሆ ላንቺ ስለሆነው ሁሉ ላጫውትሽ ስጀምር፤ በመነሻው ያሰብኩት ነገር ይሄን ደብዳቤ የመፃፍ ሕጋዊ መብት አለኝን? የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም መነሻዬ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ በመጀመሪያ “ሕገ-መንግስታዊ ስርአቱንና ሕገ-መንግስቱን በሀይል ፣በዛቻና በአድማ ለመናድ በመምከር/ በመናድ” ወንጀል ተጠርጥሬ የታሰርኩ ቢሆንም፤ በታሰርኩ በ23ኛው ቀን ወንጀል ወንጀልን፤ ጥርጣሬ ሌላ ጥርጣሬን እየወለደ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ለማሴርና ለማነሳሳት ወንጀል ተጨማሪ ጥርጣሬ በፓሊስ ዘንድ በማሳደሬ የክፋት ልኬ ከፍ ያለ ሲሆን፤ በመጨረሻም ሕገ-መንግስቱን እንደ እያሪኮ ግንብ ለመናድ በመሞከር፤ ሕብረተሰቡን ደግሞ ከሚተነፍሱት የሰላም አየር ለማቆራረጥ ከማሰብ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ ተይዟል በሚል ወንጀሎች ተከስሼ በማረፊያ ቤት እገኛለሁ፡፡ ይሄን ሁሉ የምነግርሽ ‹ለ አንቺ› አዲስ ነገር ነው በማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ያለሁበት የእስር ሁኔታ ደብዳቤ ካንቺ ጋር እንዳልፃፃፍ ይከለክለኛልን? የሚለውን ለማስረዳት በማሰብ ነው፡፡
መቼም አሁን ያለሁበት ሁኔታ ተገቢ ነው ብዬ ባላምንም ‹ ዋስ ጠበቃዬ ነውና› ስለመብቴ ስናገር ያን የፈረደበት ህግ መጥቀሴ አልቀረም፡፡ ታዲያስ በእስር ላይ ያለ ሰው ከወዳጁና በሕይወቱ ጋር ደብዳቤ ሊፃፃፍ ምን ገደብ አለበት? ይላል ስል፤ ስለፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 138/1999 በአንቀፅ 18 ላይ “ታራሚዎች (ተጠርጣሪዎች) ከማረሚያ ቤቱ (ከማረፊያ ቤቱ) ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር መፃፃፍ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ሆኖም ለጥበቃ ስራ ተቃራኒ የሆነ ተግባር እንዳይፈፀም በፅሁፎቹ ላይ ቁጥጥር ይደረጋል” በማለት የኔና አንቺ ደብዳቤ መፃፃፍ በሕግ የተፈቀደ ነገር እንደሆነ ደንግጎልናል፡፡ አሜን! (እንዲያው ይሄ ልጅ አሁንስ ተስፋዬ.. ማነው ? ሕጉ አይደለምን… የሚል የጅል ዘፈኑን አላቆምም እንዴ? ብለሽ እንደማታሾፊብኝ እምነቴ ነው) ጓድ ሌኒን በዛች የፒተርስበርግ እስር ቤት ውስጥ ደብዳቤ መፃፃፍ አትችልም ተብሎ ተከለከለ እርሱ ግን የ Russia Social Democratic Party ን ፕሮግራም መፅሀፍ ውስጥ በየመስመሮቹ መሀል በ Invisible Ink በመፃፍ ታሪክ ስራ፡፡ እነሆ እኔ ግን በትናንት ሌኒኒስቶች (ፋና)፤ በዛሬ አሳሪዎቻችን መልካም ፈቃድ ደብዳቤ የመፃፃፍ ሕጋዊ መብቴ ተከብሮልኝ ይሔው በነጩ ወረቀት ላይ እንደ ሕዳሴው ባቡር እፈነጭበታለሁ፡፡
እንዲህ ሆነልሽ
አበባዬ- አፄ ሀይለስላሴ ከማንኛውም ባለስልጣን በሕይወት ዘመናቸው የበለጠ የቀረቧቸው የነበሩት ከ1934-1948 ድረስ ለ14 ዓመታት በፅህፈት ሚንስትርነት ያገለገሏቸውን ፀሀፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዎርጊስ ወልደ ዮሀንስን እንደ ነበር ነግሬሻለሁ? ወዳጅነትና ፍቅር ያልፋልና ሀይለስላሴና ወልደ ጊዎርጊስ ተጣሉ፡፡ የአፄ ሀይለስላሴ መንግስት መፅሀፍ ፀሀፊ አቶ ዘውዴ ረታ የወልደጊዎርጊስን መጨረሻ ሲተርኩ፡፡
‹‹ ፀሃያማው ሚያዚያ 17/1948 ቀን ለ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሀንስ እንደ ሌሎቹ ቀናት ብሩህ ሁና ነበር የነጋችው፡፡ ብሩህ ሁና እንደምታመሽም አልተጠራጠሩም ነበር፡፡ ምን ያደርጋል! ያች ክፉ ሰኞ የወልደጊዎርጊስ ከፍተኛ ስልጣን መጨረሻ ሆነች፡፡ በእኩለ ቀን ገደማ ቤተ መንግስት ተጠርተው ከፅህፈት ሚንስተርነታቸው ተነስተው የአሪሲ ጠቅላይግዛት ደረሳቸው››
(መፅሀፉ አጠገቤ ስለሌለ ቃል በቃል አልጠቀስኩም)
ወልደጊዮርጊስ ተሽረው ከቤተ-መንግስት እንዲርቁ የተደረገበት ምክንያት የሀይለስላሴን ወንበር በሰዒረ መንግስት ለመገልበጥ አስበዋል በሚል ምክንያት ነበር፡፡ወልደጊዎርጊስን እዚህ ጋር ማንሳቴ የሚያዚያ 17 ስለት እኔም ጋር በመድረሷ ነው፡፡ ውዴ! የእኔዋን ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ውሎ እንደ ዘውዴ ረታ ስተርክልሽ ይሔን መሳይ ይሆናል፡፡
‹‹ ፀሃያማዋ ዓርብ ሜያዚያ 17/2006 ዓ.ም አጀማመር እንደ ወትሮው አልነበረም፡፡የጠዋት ትምህርት ክፍለ ጊዜ እንዳይረፍድብኝ እየተቻኮልኩ ወደማስተምርበት (የመጨረሻ ክላስ ነበር) አምቦ ዩንቨርሲቲ ስሄድ፤ ተማሪዎች አዲስ የተዘጋጀውን የአዲስ አበባ ከተማ መሪ እቅድ ‹ሕገ-መንግስታዊ አይደለም በሚል መነሻ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር፡፡ ሰልፉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ በሰልፍ ምክንያት የቀረውን የመጨረሻ ክላስ ሚያዚያ 18/2006 ዓ.ም ለማካሄድ ተማሪዎቼ ጋር ቀጠሮ ይዤ ብለይም ‹ሰው ያቅዳል ፣ እግዜር ይስቃል› እንደሚባለው ሆነና በዛች ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ማምሻ ላይ እንደ ወልደጊዎርጊስ ወልደ ዮሃንስ ‹የመንግስትን ዙፋን በሕዝባዊ አመፅ ልትነጥቅ አሲረሀል› በሚል ክስ በቁጥጥር ስር እንደዋልኩ የደህንነት ግሪሳዎች (8 ወይም 9 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ) አበሰሩኝ፡፡
ነገሩ ብዙም አልገረመኝም፡፡ ትንሽ ያበሳጨኝ አቶ ዘላለም ለጥያቄ ስለምንፈልጎት አዲስ አበባ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማእከላዊ) ነገ ጠዋት 3 ሰዓት እንዲገኙ ብለው በስልክ ቢጠሩኝ ‹እሺ ነገ ሶስት ሰአት ላይ ክላስ አለኝ ከክላስ ወደ 9 ሰዓት አካባቢ አመጣለሁ › ብዬ የምቀርበውን ሰው ይሔን ሁሉ ሀይል ከሁለት መኪና ጋር በመመደብ ላከበረኝ መንግስቴ ‹ጉዳት› ባሰብኩ ግዜ ነው፡፡ ላክባሪዬ ውለታ መላሽ ያርገኝ i
ዓለሜ- ደብዳቤዬን እያነበብሽው እንደሆነ ተስፋ አለኝ፡፡ በቁጥጥር ስር ውሏል የምትለው ሀረግ ድሮም ትንሽ ፈገግ ታደርገኝ ነበር፤ አሁን ደሞ እኔን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከአዲስ አበባ የመጣው የደህንነት ቡድን መሪ የመሰለኝ እድሜው ትንሽ ገፋ ያለ ሰው አንድ ሶስቴ ስልክ እየደወለ (ለማን ይሆን) ‹በቁጥጥር ስር አውለነዋል› እያለ መልክት ሲያስተላልፍ ስሰማ ፈገግ ማለቴ አልቀረም፡፡ ሀሳቤ ልቤ ፣ ይሄውልሽ ከስራ ቦታዬ ‹ሀገር ሰላም› ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አስበሃል በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋልኩት እንዲህ እንደገለፅኩት ነበር፡፡ ከሚያዚያ 17/2006 -ሀምሌ 11/2006 ዓ.ም ያሉት 84 ቀናት የተደጋገሙና ሕይወት አልባ በመሆናቸው እንዲሁ ከማሰለችሽ 5 ሁነቶችን ልፃፍልሽና ዘና በይ፡፡ ከሁነቶቹ በፊት ግን ስለ 84 ቀናቱ አጭር መግለጫ ልስጥሽ፡፡
የመጀመሪያዎቹን 75 ቀናት በፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ጥብቅ ጥበቃ ክፍል (Siberia) ውስጥ 5 ቁጥር የተባለ 4 ሜትር በ5 ሜትር የሆነችና 5 ፍራሾችን በምትይዝ ክፍል ውስጥ ከረምኩ፡፡ ክፍሉ የተፈጥሮ ብርሀን በምንም አይነት መንገድ (ቀንን ጨምሮ) የማይገባበት ሲሆን፣ ለ24 ሰዓታት የመብራት ብርሀን ይበራበታል፣ መብራት ሲጠፋ በጄኔሬተር ሀይል ይተካል፡፡ ጄኔሬተሩ ነዳጅ ሲጨርስ ደግሞ ቀንም ሆነ ማታ ጨለማ ነው ባትሪ፣ ሻማ፣ ማንኛውንም አይነት ሰዓት መያዝ አይቻልም፡፡ ጠዋት 12 ላይ ለ10 ደቂቃ ፤ ማታ ከ10 ሰዓት አስከ 12 ሰዓት ለ 10 ደቂቃ ሽንት ቤት ለመጠቀም የክፍላችን በር የሚከፈት ሲሆን፤ በቀን ውስጥ ከ15 – 20 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ደግሞ ከክፍላችን በየተራ ወጥተን ነፋስ/ፀሀይ እናየለን፡፡ ከዛ ውጭ በቀን ውስጥ ከ23 ለሚበልጠው ሰዓት የክፍሉ በር ዝግ ሲሆን ጮክ ብሎ ማውራትና መዝፈንም ቅጣት ያስከትላል፡፡
ወዳጄ በነዚህ 75 ቀናት ስንት ‹አሸባሪ› ወዳጆችን አፈራሁ መሰለሽ፡፡ መንግስቴ የ 15 እና የ14 ዓመት ልጆችን በአሸባሪነት ጠርጥሮ እንደሚያስርም ለመረዳት ችያለሁ፡፡ አብረውኝ በእስር የነበሩት ወዳጆቼ ጥርጣሬ አጅግ የተለየ ነው፡፡ ከአል-ሸባብ አስከ ኦብነግ እስከ ኦነግ እስከ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች ነፃ እውጭ ግንባር እስከ አቂዳ(አዲስ የሽብር ቡድን)… ስቃይን መማር ጥሩ ነውና ሁለት ለሚሆኑ ቀናት ብቻዬን በመታሰሬም solitary confinement ን experience ለማድረግ ‹ታድያለሁ›፡፡ በርግጥ ብቻዬን ታስሬ ነበር ከምል ካንቺ ሀሳብ ጋር ታሰርኩ ብል ይቀለኛል፡፡
አምስቱን ሁነቶች ዘንግቼ ስለ ስቃዬ ተንዛዛሁብሽ ይሆን? ለዚህ ተግባሬ በእስረኛ ቋንቋ ‹ተፀፅቻለሁ›፡፡ በቃ ወደ ጉዳዮቹ፡፡ ከዚህ በታች የምገልፃቸው ሁነቶች የ84 ቀናቱ የእስር ወቅት (የምርመራ) ጊዜ ምን እንደሚመስል እንደነበር ያስረዱሻል ብዬ አስባለሁ፡፡ (ሁሉም በእውነት እኔ ላይ የደረሱ ጉዳዮች ናቸው)፡
1. ተማሪዎቼን እንዳላበላሻቸው በማሰብ በቁጥጥር ስር ስላዋለኝ አመሰግናለሁ
ሚያዝያ 17/2006 ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ከምኖርበት አምቦ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከደህንነቶች ጋር በቤት አውቶሞቢል እየተጓዝኩ ነው፡፡ አንድ ልጅ እግር ደህንነት ጠየቀኝ
‹‹ዘላለም የህግ መምሕር ነህ አይደል..››
እኔ፡ አዎ
ደህንነቱ፡ “ስንት ጠበቆች ዳኞች ማፍራት ሲጠበቅብህ አንተ ‹ልማቱን ካላደናቀፍኩ› ማለትህ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ለማንኛውም እንኳን ተማሪዎቹን ሳታበላሻቸው በጊዜ በቁጥጥር ስር ዋልክ፡፡ ኧረ ለመሆኑ ከውጭ ስንት ሽህ ደላዮችን አግኝተሻል? Any way በልማታችን ቀልድ የለም” አለኝ፡፡ (እኔም ባስተማርኩባቸው 4 አመታት ስንት ተማሪዎችን ‹እንዳበላሸሁ › እያሰብኩና ልማታችን በወለደው የአስፋልት መንገድ ፏ ብዬ ከምሽቱ 3፡50 ላይ ማዕከላዊ ከቸች፡፡
2. አላማችሁ ምንድን ነው?
እመቤቴ – መንግስት ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አሲራችኋል፤ ለዚህም በቂ ማስረጃ አለኝ በማለት ያሰረን ቢሆንም መንግስት ሀሳቡ እውነት ይሆንለት ዘንድ የእኛን ‹አዎ አሲረናል› የሚል መልስ በማባበልና በሀይል ለማግኘት ከመሞከር ውጭ ሌላ ያቀረበው አንዳችም ማስረጃም ሆነ መረጃ(በጠ/ሚንስትሮች ቋንቋ) አልነበረም/የለምም፡፡ ለዚህም ይመስላል በማእከላዊ የቆየሁባቸው ቀናት ምርመራው በሙሉ ‹አላማችሁ ምንድን ነው?› በሚል ሕይወት አልባና አሰልቺ ጥያቄ የተሞላው፡፡ እኔም የዚህ ጥያቄ ሰለባ ሁኜ ከረምኩልሽ፡፡ እንዲህ ላጫውትሽ፣
መርማሪ ፖሊስ (በተደጋጋሚ) – እንደ ዞን 9 አላማችሁ ምንድን ነው?
እኔ፡ ዓላማችን ግልፅ ነው፡፡ ማንም ብሎጋችንን የተመለከተ ሰው በቀላሉ ሊረዳው ይችላል፡፡ባጭሩ የተለያዩ ተረኮችን የሚያስተናግድ እና ሕብረተሰባዊ ተዋጾን የሚያሳድግ ፕሮፋይል ነው፡፡
መርማሪ ፖሊስ፡ እሱ ሽፋን ነው፤ እውነተኛ ዓላማችሁን ተናገር?
እኔ፡ ከዚህ የተለየ አላማ የለንም!
መርማሪ ፖሊሱ እንድንመልስለት የሚፈልገው ‹ከበላይ አካል› ይዞ እንዲመጣ የታዘዘውን መልስ፤ “አላማችን እንደ ጭቃ ተረግጦ፤ እንደ ገል ተቀጥቅጦ የሚገኘውን ጭቁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተጫነበት ቀንበር ነፃ ማውጣት ነው፡፡ ለዚህም መሳካት ሕዝባዊ አመፅ ማደራጀትን እንደ ዋነኛ ዓላማ አድርገን ነው የተቋቋምነው፡፡”
ሲሆን ይህ ደግሞ ከአላማችን ጋር የማይገናኝ መንግስታዊ ፍላጎት በመሆኑ እንዲህ አይነት መልስ ከእኔ ማግኘት እንደማይችል የተረዳው መርማሪ በተደጋጋሚ አስብበት በማለት ይሰናበተኝ ነበር፡
3. ከመርማሪዎች ጋር የነበረኝ ቆይታ
የእኔ ፅጌሬዳ አላማችን እንደ ቡድን ባይጠይቁኝ ኑሮና የግል ዓላማዬን ቢጠይቁኝ አላማዬ ‹አንቺ› እንደሆንሽ ከመናገር ወደኋላ እንደማልል ታውቂያለሽ አይደል? የሆንሽ ‹አሸባሪ› ነገር፡፡ Any way ምርመራዬ ቀጥሎልኛል፡፡ ሁለት መርማሪዎች እየተፈራረቁ ገራሚ ገራሚ ጥያቄዎችን እየጠየቁኝ ነው፡፡ እነሆ ፡
መርማሪ ፖሊስ፡ ከአለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተህ ታውቃለህ?
እኔ፡ ማንንም
መርማሪ ፖሊስ፡ እኛ እኮ ያለመረጃ አይደለም እየጠየቅን ያለነው፡፡ ጉድ ሳይመጣብህ ብትናገር ይሻላል፡፡
እኔ፡ እስኪ አስታውሱኝና ምን እንደተነጋገርን ልናገር፡፡ በርግጥ ባለፈው የኔልሰን ማንዴላ ማስታወሻ ፕሮግራም በ አፍሪካ ህብረት በተከበረበት ወቅት ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ሌላ የማስታውሰው የለም፡፡
መርማሪ ፖሊስ፡ ህም! እሺ ዘንድሮ ኦባማ ፊት ንግግር ለማድረግ ከተመረጡ 3 ኢትዮጵያውያን አንዱ አንተ አይደለህም? አሜሪካ በ አፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት ነው፡፡ ወጣት አመራሮች ምናምን እያለች የምታሰለጥነው?
እኔ፡ ‹‹እንዴ ኦባማ ፊት ንግግር ነው ያልከኝ? ድንገት ከታሰርኩ በኋላ ተመርጬ (በማሾፍ ድምፀት) ከሆነ አላውቅም፡፡ወይ በስም መመሳሰል ሊሆን ይችላል፡፡ አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት ነው? ላልከኝ ግን ወጣቶችን Empower ማድረግ ችግር ያለው አይመስለኝም ፤ ደግሞ በረሀቡም በድርቁም ጊዜ ርዳታ የምታደርገው እኮ አሜሪካ ነች፡፡ ምን አግብቷት ነው የምትረዳው አይባልም መቼም?!››
መርማሪ ፖሊስ፡ አሁን ዘመኑ የልማት ነው፤የምን ረሀብ ነው የምታወራው? በል ተወው፡፡
(‹ፈሪ ውሃ ውስጥ ያልበዋል› ሰምተሻል ውቤ? መንግስቴ ብቻውን እየሮጠም ፍርሃቱና ስጋቱ ብዛቱ፡፡ የሚቆጨኝ ነገር ከዓለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተሃል? ‹ስባል› ከሲሪላንካ ፕሬዜዳንት ጋር ተገናኝቼ ወደ ደቡብ አሜሪካ ፔሩ በመጓዝ ማቹፒቹን ጎብኝቻለሁ ብዬ ብናገር ኑሮ፤ ክሳችን ላይ ‹ከሲሪላንካ መንግስት ባገኘው የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ ወደ ፔሩ በመጓዝ ሕገ-መንግስት እንዴት እንደሚናድ በማቹፒቹ ኮረብታ ስልጠና ወስዶ ተመልሷል፡፡ ለዚህ እንደ ማስረጃ ይሆን ዘንድ ላፕቶፔ ውስጥ የተገኙት ከ300 በላይ የቼጉቬራ ምስሎችና Machu Pichu: The Mecca of Hippies” የሚል ባለ 22 ገጽ ‹ሰነድ› አብሮ ይያዝልኝ ነበር፡፡ ሲያበሳጭ
4. ‹አሸባሪው› ገብረሕይወት ባይከዳኝና ሀገሪቱን በሀራጅ የመሸጥ ጉዳይ
ፍቅር አደከምኩሽ አይደል?! ልጨርስ ስለሆነ ትንሽ ታገሺኝ፡ በዛውም ‹ፍቅር ታጋሽ ነው› የሚለውን Paulian ወንዴነት፤ ‹ፍቅር ታጋሽ ናት› በሚል ማስተካከያ እንድናርመው፡፡ የዚህ የምርመራ ነገር እኮ አላልቅልኝ አለ፡፡ በእስሬ ወቅት ሌላው በተደጋጋሚ እንዳስረዳ ስጨቀጨቅበት የነበረው ጉዳይ ‹ኒዮ-ሊብራልነቴና ልማትና ዲሞክራሲ ጎን ለጎን አብረው ይሄዳሉ ማለቴ ነበር፡፡
መርማሪ ፖሊሶቹ እየተቀያየሩ ስለኢህአዴግ የፖሊሲ ትክክለኛነት ‹ያስረዱኝ› ነበር፡፡ “አንተ ምን ጎደለብኝ ብለህ ነው ነጭ አምላኪ የሆንከው ? ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ስናይ አንተና ጓደኞችህ አይናችሁ ለምን እንደሚቀላ እስኪ ንገረን ? ይህች አባቶቻችን ‹በደምና በጾም› ያቆዩልንን አገር አንተና ያንተ ትውልድ ግን ውበቷ እና ድንቅነቷ ላስጎመጃቸው ነጮች ለመሸጥ መደራደር ጀመራችሁ….” እያሉ ‹በባንዳነት› ሲከሱኝ ከረሙ፡፡ የሀገሪቱ ውበትና የነጮች በውበቷ መጎምጀት ነገር ሲነሳ ጊዜ ‹አንቺ› ትስቂ ዘንድ የሚከተለውን አንቀፅ አሻግሬ ታደሰ የተባሉ ፀሐፊ ከ 50 ዓመት በፊት ‹እኔና አንተ› ካሉት ጽሁፋቸው ላይ እጠቅስልሻለሁ
“ኢትዮጵያ እጅግ ያማረች፤ የተዋበች ፤የተደነቀች፤ላያት ሁሉ የምታማልል፤የምታዘናጋ…….ናት፡፡ ዓይኗ የብር አሎሎ መለሎ ከአጥቢያ ኮከብ የተፎካከረ….. ነው፤ አገራችን ኢትዮጵያ ፅጌረዳ መስላ የሰኔን ቡቃያ ትመስላለች፡፡ የመስከረም አበባ ሆና በሩቅ ትስባለች፤የመስህቧ ኃይል ማግኔት ምስጋን ይንሳው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ጥርሷ እንደ በረዶ ሆና ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልፀው እንኳንስ ለሰው ግብዙ መልዓክ ያብዳል፡፡ ኢትዮጵያ ፀጉሯ የሀር ነዶ ነው፤ኢትዮጵያ አጠረች ፤ረዘመች፤ወፈረች፤ብሎ ስለአካሏ መናገር አይቻልም፡፡ እንዲያው ዝም ይሻላል፡፡ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውበቷ ሰነፉን ይገድላል፡፡ ብርቱውን አነሁልሎ ያሳብዳል፡፡ እግዚአብሔር፤ኢትዮጵያን ሲፈጥር በብዙ ተራቋል፤ተጠቧል፤ ውበቷ በሩቅ ይስባል፤ አጥንትም ይሰብራል፤አዕምሮን ይሰውራል፡፡ ይገርማል!” ይላሉ፡፡
ምንም እንኳን ውበት እንደተመልካቹ ነው ቢባልም፤ መርማሪዎቹ በዚህ ዓይነት Vulgar Natioanlism ሰክረው እኔና የእኔ ትውልድ ሀገሪቱን ‹በውበቷ ለሰከሩ› ነጮች ልንሸጣት እንደተዋዋልን እየነገሩኝ ነው፡፡ ይገርማል! ዲሞክራሲን ከልማት እኩል ማስኬድ ነውር የለበትም፤ ተገቢም ነው ማለት እንደ አገር ሽያጭ ውል የሚቆጠርበት ብሎም ‹ሩቅ አስባ ሩቅ ለማደር እየተጋች ያለችን አገር› መንገድ ላይ በጠረባ ለመጣል የተደረገ ሙከራ ተደርጎ የሚወለድባትና ‹አሸባሪ› የምንሰኝባት፣ ‹ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልጠው እንኳን ሰውን ግብዙን መልዓክ የምታሳብደው ኢትዮጵያ!
ሊቁ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ‹ልማትን ሲተች› “እውቀት በሌለው ሕዝብ አገር መንገድና የምድር ባቡር ቢሰራ ሕዝቡ እንዲደኸይ ያፋጥናል እንጂ አይጠቅመውም፡፡ ጥቅሙ ከርሱ ጋር የሚገበያዩ አዋቂ ሕዝቦች ነው” በማለት ‹ልማት ብቻውን ዋጋ የለውም› ሲል ይበይናል፡፡ ገብረሕይወት የእኛው ትውልድ አባል ቢሆን ኖሮ “የኢኮኖሚ እድገቱን በመካድ፤ ሕዝቡ በአዕምሮ መናወጥ ምክንያት የዘረጋነውን የባቡር ሀዲድ ፈነቃቅሎ እንዲጥልና ሌሎች የሽብር ተግባራትን እንዲፈፀም በማነሳሳት ‹ወንጀል›” መመርመሩና መከሰሱ አይቀሬ ነበር፡፡
ውዴ! ያን ‹አሸባሪ› ሳቅሽን ሳስብ በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት ጉዳይሽ ሊታይ ይችላል የሚል ስጋቴ የበዛ ነው፡
5. ናፍቆቴ ሆይ!
እንዲያው ለዚህ 84 ቀናት ውስጥ የሆንኩትን ሁሉ እንዳልፅፍልሽ እንዳትሰለችብኝ ፈራሁ፡፡ እያንዳንዱን ሁነት በ Diary መልክ ከትቤ እንዳልክልሽ በነዛ ቀናት ውስጥ ብዕርም ሆነ ነጭ ወረቀት ይዞ መገኘት ‹ከፍ ብሎ አንገትን፣ ዝቅ ብሎ ባትን› ባያስቆርጥም ዛቻና ዱላን ማስከተሉ አይቀርም ነበርና ልከትብ አልቻልኩም፡፡ እንዲሁ በደፈናው ግን አንዳንድ ጉዳዮችን ብዘረዝርልሽ፡
በነዛ ክፉ ቀናት ከምሽቱ 12 ሰዓት እንቅልፍ መተኛትን ለመድኩ፡፡ ይሔም ነገር መልካም እንደሆነ አየሁ፡፡ ምክንያቱም ሌሊት ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው ራቁታቸውን ሲደበደቡ አድረው ከ 3 እና 4 ሰዓታት ቆይታ በኋላ በነፍስ ወደ መኝታ ክፍላችን የሚመጡ የእስር ጓደኞቼን (Cellmates) ስቃይና ሰቆቃ ላለመስማት፡፡
በ2004 ዓ.ም የፌዴራል ፖሊስ ‘Cyber crime Laboratory’ ተቋቁሟል መባሉን ሰምቼ ‹እንግዲህ cyber criminal ሁሉ የት ትገቢ? አለቀልሽ!› ብዬ ነበር፡፡ በጊዜ ቀጠሮ ጊዜ እንደተረዳሁት ደግሞ ‹ያለችን አንዲት ኮምፒውተር ናት የእነዚህ ልጆች ዳታ በአንድ ኮምፒውተር መርምረን መጨረስ ስላልቻልን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን› ሲባል ነው፡፡ አረ እንዲያውም ‹እስኪ Anti-virus ካለህ ኮምፒውተሬ ላይ ጫንልኝ› ተብዩ ሁሉ ነበር፡፡ ‹ለሽብር ተግባራት› መመርመሪያ ያልሆነ ‘Cyber crime laboratory’ ለመች ሊሆን ነው?
አንድ ቀኑንና ወሩን በማላስታውሰው ቀን አንድ ጎልማሳ የታሰርንበትን ክፍል አስከፍተው ገቡና እያንዳንዳችን መጠየቅ ጀመሩ፡
- ‹አንተ ከየት ነው የመጣኸው?› (አንድ ተማሪ ወዳጄን)
- ‹ከሀሮማያ ዩኒቨርስቲ›
- ‹አሀ እናንተ ናችኋ…..›
****
- ‹አንተኛውስ ከየት ነው የመጣኸው?!›
- ‹ከወለጋ ዩኒቨርስቲ›
- ‹አሁን ኦሮሚያ ብትለማ ምን የሚያስከፋ ነገር አለው?!….›
*****
- ‹አንተስ ከየት ነው የመጣኸው› (እኔን ነው)
- ‹ከአምቦ ዩኒቨርስቲ›
- ‹ሕዝቡን እርስ በርስ አጋጭታችሁ ከተማዋን በደም ያጠባችኋት እናንተ….›
- ‹አረ እኔ ከግጭቱ በፊት ነው የታሰርኩት›
- ‹በእውነት ነው የምልክ እድለኛ ነህ፡፡ የኦሮሚያን ልማት ተቃወመ ተብለህ በታሪክ አለመስፈርህ በጣም እድለኛ አድርጎሀል፡፡›
(ለመሳቅ ሁላችንም የጎልማሳውን ከክፍል መውጣት እየተጠባበቅን እኮ ነው ውዴ) – ሁሉ ቧልት የሆነበት ሀገር!
በነዚህ ሁሉ የጉድ ቀናት ለምን እንደታሰርኩ ትክክለኛውን ምክንያት የሚነግረኝ አካል ፍለጋ ሁሌም አስብ ነበር፡፡ መታሰሬ ግን አያስገርመኝም፤ አያስከፋኝም! ደስታን በሔድኩበት ሁሉ እፈልጋለሁ፤ የእድል ነገር ሆኖ ደስታም ከእኔ አይርቅም፡፡ ፍቅሬ ለረጅም ዘመናት ‹የሰው የመኖር አላማ ማወቅ ነው› የሚለውን Aristotlian (አሪስቶትሊያን) አስተምህሮ በልቤ ይዤ እኖር ነበር፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ‹የመኖር ዓላማ መደሰት ነው› የሚለው አስተምህሮ በአርስቶትሉ ‹የማወቅ ዓላማ› ደባልቄ ይሔው እየተደሰትኩልሽና እያወቅሁልሽ እገኛለሁ፡፡ ‹አንች› የደስታዬ ምንጭ፡
‘‘Thanks to you….For you exist’
Clézio
ስለክሴና ስለተስፋዬ ሌላ ደብዳቤ እፅፍልሻለሁ፡፡
P.S አሳሪዬ ሆይ ልብ ይስጥህ!
ያንችው ዘላለም
ከብዙ ፍቅር ጋር!
ከውጭ የተላከ ያልተመዘገበ ገንዘብ /የሐዋላ ቅሸባ
Image may be NSFW.
Clik here to view.ከሚሊዬን ዘአማኑኤል እንደ ዓለም ባንክ መረጃ መሠረት በግምት 30 ሚሊዩን አፍሪካዊያን በAለም ላይ ተሰደው ይገኛሉ፡፡ የአፍሪካውያን ስደተኞች ቁጥር በሚቀጥሉት Aስርት ዓመታት ውስጥ እንደሚጨምር ህዝበ ፅንፍ ተመራማሪዎች ይተነብያሉ፡፡ በአፍሪካ በሚሊዩን የሚቆጠሩ ቤተስቦች ባህር ማዶ ከሚኖሩ ዘመዶቻቸው በሚላክ የውጭ ሐዋላ ወይም ገንዘብ Eየተዳደሩ እንደሚኖሩ ይታመናል፡፡ በ2010 እኤአ በክፍለ አህጉሩ የውጭ ሐዋላ ፍሰት በአለፉት ሃያ አመታት ውስጥ አራት እጥፍ Eንደአደገ Aጥኝዎች ይገምታሉ ማለትም 40 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ይገመታል ይህም (ከብሔራዊ ዓመታዊ ጠቅላላ ምርት 2.5 በመቶ) ድርሻ እንዳለው ጠበብት ይገልፃሉ፡፡ለአፍሪካ አህጉር የውጭ ቀጥተኛ Iንቨስትመንት አንደኛ ደረጃ የገቢ ምንጭ ሲሆን ማለትም ከአጠቃላይ የውጭ መዋለ ንዋይ ፍስት ዋነኛ ድርሻ አለው፡፡ቀጥሎ የዓለም ዓቀፍ የውጭ ሐዋላ ፍሰት በክፍለ አህጉሩ ሁለተኛ ደረጃ የገቢ ምንጭ ድርሻ አስመዝግቦ ይገኛል፡፡በንፅፅር ሲታይ የውጭ ሐዋላ የገቢ ምንጭነት ከውጭ እርዳታ እንደሚበልጥ የዓለም ባንክ መረጃ ያረጋግጣል፡፡በክፍለ አህጉሩ ሦስተኛ ደረጃ የገቢ ምንጭ ድርሻ ያለው የውጭ እርዳታ ነው፡፡ –- ––[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]———
የጎረና ጉርና –ነዳላ (ሥርጉተ ሥላሴ)
ልብ አምላክ ዳዊት „ህግ ተላላፊዎችን ጠላሁ“ አለ።
ሱባኤውም ተጠናቀቀ – መልስ ይሰጥበት።
ከሥርጉተ ሥላሴ 25.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
ይድርስ ለጸሐፊ ጌታቸው ረዳ ካሉበት። እንደምን አሉ? ደህናነዎት ወይ። ደስ ሊለዎት የሚገባ ሊያሰተላልፉት የሚፈልጉትን መልዕክት በማስተላለፈዎት ሳይሆን እራሰዎትን ፈልገው ከመሸ በማግኘተዎት ነው። እንኳን ለዚህ አበቃዎት! አሻቅቦ መናገር ከመንፈሴ ዕድገት ውጪ ቢሆንም ልክን ማወቅ ከልክ የሚያድርስ ስለመሆኑ ተምሬ ስላደኩ አቻውን ዬፍላጎተዎትን እንሆ – ይረከቡኝ!
„ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል“ ወይ ዘመን ምኑን ጉድ ነው እዬዘለዘለ ያለው? እግዚአብሄር ይይልህ አይዋ ዘመን ምን አለበት ጉግልን ባትጋፋው?
የኔዎቹ እንዴት አላችሁልኝ። ጥያቄ ተጠዬቁ እስቲ። ደግሞ ብለው ብለው ላልጠፋው እህል እውሃ በነጭ ሀገር ብዕርና ብራና ስንቃቸው አብሾ ሆነ እንዴ?
አልኳችሁ ወዳጆቼ አጣደፉኝ። ስሄድ ካላሆነ ቦታ ገባሁ። ከዛንላችሁ ቀጥ ብዬ እርእሱን ይዤ ኤዲተር ካላው ወዳጄና ረጃጅም ትንተናዊ ጹሑፍ በማወጣት ወደ ዬሚታወቀው ኢትዮ ሚዲያ ጎራ ስል ተዛም ዝክንትሉ ብራና የለም። ያው እንደፈረደብኝ ተመልሼ እንደ ነገሩ ከብትክትኩ ጋር በባዕቱ መተያዬት አይቀር – ተያዬን። እርእሱና ፎቶው በቂ ነበር „የናዚ ኔት ወርክ“ ዘመናይ ነዎት — ዖዬ!
ከዛ ደግሞ አነበብሽው? ምንስ ተሰማሽ መጣ? ስለ ወጣቶች „ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ“ በመሆኑ ሰቀጠጠኝ። እኔ ለወጣት የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች ስስታም ነኝ። እንዲሁም ቀጥ ያለ አቋም ብቻ ላላቸው የመወያያ መድረኮችና ሙሁራንም እጅግ ቀናተኛ ነኝ።
በተረፈ እኔን በሚመለከት አደራ አበደች እንዳትሉኝ። ደስ አለኝ። እዬሳቅኩኝ ነበር የተያዬነው። በቃ የጠላት ጎራ መንፈስ እንዲህ በአንድ ጹሑፍ ትቅማጥ ሲይዘው ማዬት የምር ምኞቴ ነበር። ሆድ ዕቃው ወስፋቱ የተንጫጫ ሲገኝ አጋጠመ ነው። ለዚህ ነበር እኮ እኔ የጻፍኩት። በቃ! ሁልጊዜ ፋሲካ የለምና እንደ ወትሮው መንፈስን ከአንድነት ኃይሉ ማፈናቀል ያልቸል ደካማ መሆኑ ደግሞ ተከታታይ መረጃ ወገኖቼ ሲሰጠኙ የበለጠ ሐሴት አገኘሁበት። አዎና! እኔ እኮ ስጽፍ በውስጤ ሁኜ ነው። የፓርቲ አባል ዬማልሆነውም ለዚህ ነው። በዲስፕሊን መታሰር አልሻም። ፓርቲዬንም ማስነቀስ አልፈልግም። እንዲህ በልቅ ዓለም መኖር፤ በምንም ነገር ያላታሰረ ነፃነት እሻለሁ። ባሩዱ ተነጣጠረ ዓላማውን ሳይስት ጦሮዎ በጠላት ሰፈር ልኮ እንዲህ ቆርቆሮውን ቢና ጢናውን አወጣው። ዓይነተኛ የውስጥ ተቆርቋሪ ይሄው እንዲህ ከእንቅልፍ ጋር ተጣልቶ ጎልቶ አውሎ ያሳድራል ጌታውን ሲያስጨር። ተመስገን – አነቃነቀ – ናጠም።
በግራ ቀኝ ስውርና ረቂቅ ሴራ በጠላት እጅ ለወደቀ – ስለ ራሱ ቆሞ ሊናገር ለማይችል፤ በጠላት እጅ በመንፈስ ማደንዘዣ የበቀል መርዝ ሙከራ የሚሠራበት ታላቅ ወገኔ በሌለበት ቦታ ስለ እሱ ተናግሬ ወንጀለኛ መሆን ክብር ነው – ለሥርጉትዬ። ይልቅ ያልተገባኝን ክብር ባልተገባኝ ወቅት ሰጡኝና ከነፃነት አባት ጋር አንጠለጠሉኝ። ከአንድ የነፃነት ሙሴ – ሰማዕት ጋር ደረጃዬ አይፈቅድም። ይህ ባይሆን ጥሩ ነበር። ይሄ ወቅትን ጊዜን ያልጠበቀ ከፍ ማለት አልወደወም። አጉል መንጠራራትን ፈጥሮ እሸት ቅመሱ ሳይባል ዘጭ ያደርጋልና። ለዚህም ነው በብዕር ሥሜ እምጽፈው። እንጂ እኔ እህታችሁ በተፈጥሮዬ ደስታ ላይ አልገኝም። ከተሸነፈ ወይንም ከተጠቃ ጋር ግን ማን ይዞኝ። ባለፈው ዓመት የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እዚህ መጥተው አባላቱን ካነጋገሩ በኋላ እንዲሁም በተለዬ ሁኔታ ለሚያግዙ የነፃነት ትግሉን ግንባር ቀደም „አክቲቢስቶች“ ነው የሚባለው ከእነሱ ጋር እንደተወያዩም አዳምጬ ነበር። አሁን ደግሞ ፎቶም አይቻለሁ። ለእኔ ይህ ጉዳዬ አይደለም። ድንበር አለው ኑሮዬም – ተፈጥሮዬም።
አንድ ነገር – እንዲህ ሆነላችሁ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ታስራ በነበረች ወቅት በዬሳምነቱ እደውል ነበር ለቤተሰብ። እምችለውን የመንፈስ ደጋፍ አድርጌያለሁ ብዬ አስባለሁ። ስትፈታ ግን አልደወልኩም። ኢሜሏም አድራሻውም አላስፈለገኝም። አላገኘኋትም።
ለእኔ ቁም ነገሩ ጠላት እንዲህ ጥቃት ሲፈጽም፤ ሰብዕዊነትን ሲዳፈር፤ የዜግነት መንፈስ ሲጨፈለቅ፤ ህግ በጠራራ ፀሐይ በጉልበተኛው ወያኔ ሲረሸን የእኔ ብዬ መቀበል – በግንባር በባለቤትን በዕውነታዊ ውስጥ መገኘት ነው። እንዲያውም ጀግናዬ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የግል ህይወታቸውን ከተከበሩ ወንድማቸው ከሰማሁ በኋላ የበለጠ ነው እኔን ዬመረመረኝ። እንዲህ በአደገ ሀገር በአንዲት ክፍል ቤት ሁሉንም ዓይነት አማራጭ ደፍሮ ለመሞከር እራስን ረስቶ ታጥቆ መጠበቅ ልዩ ጸጋ ነው። መታደል – የእውነት። እና መከራን ለፈቀደ ወገን መሰከራችሁ ነው „ናዚነቱ ሆነ ጉዲትነቱ“። ወቅትንና ጊዜን ማድመጥ በሚመለከት ለሽበት መንገር ወንዝን አሻቅበህ ተጓዝ እንደማለት ከቶ ይሆንብኝን? ግድፈቱ ዘመን ይቅር አይለውም – ጌታው። ግራጫ አለቀሰ – እዬተቀነሰ – እዬተበጠሰ …. ከቶ ይህቺ ስንኝ ተመቼዎትን?!
ሌላው ከትክት ብዬ በፈንጠርጣራ ጥርሶቼ የሳቅኩት ደግሞ በነፃነት ሀገር ፈቃድ ጥዬቃ መዝመት ነበረብን ወደ ዘመን ሰጡ ጌታው። ወይ አቅምን አለማወቅ?! „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላል ጎንደሬ ሲተርት። ሃሳብን በሃሳብ መታገል የአባት። ድንበር ዘለል የጎጥ አገዛዝ ለዛውም ነጭ ሀገር ግን እማይቻል ልግጫ ነው። ዝለት – በፍዘት ይሉታል ዕብኑን ህልም። ለነገሩ የጎጥ በሽታ ከዚህ በላይ መሄድ አይችልም … በጣም ረጅም ጊዜ እኮ ነው፤ 23 ዓመት መስሎ – ተመሳስሎ መኖር መርግ ነው አቅልን የሚፈትል።
መኖር ማለት መኖር የለገሰውን ተፈጥሯዊ ጸጋና ክህሎት በጊዜ አውቆ ተጠቃሚ መሆን መቻል ነው። መቻል ደግሞ እራስን ሆኖ እንደ ራስ ሆኖ በመጤ እንደራሴ ሳይጠቀለሉ እንዲህ አደባባይ ላይ ወጥቶ ውስጥን ማስጎብኘት ነው። ይህ መሸቢያ መንገድ ነው። ስለምን? ድርጀቶችን ተጠልሎ ጥቃት መፈጸም ሆነ ወቅትን አስታኮ ማመስ ከምድር በታች ይቀበራሉና። ብዙ ድርጅቶች ታሪካዊ ስህተት የሚፈጽሙት በእንዲህ ዓይነት ዝበትና ግብዝነት በጎበኛቸው መንፈሶች የዋህ ወገኖች በቅንነትና በአዎንታዊ ተመልክተው ይጥቅማል በማለት ሃሳብን ስለሚያስተናግዱ ነው። ስንሰበሰብ ሲበተን፤ አፍሰን ስንለቅም ወይንም ለቅመን ስናፈስ የኖርነው … በዚህ ጆሮ አልቦሽ መንገድ ነበር።
ከእንግዲህ ያ ይናፈቅ የነበረ ዬናሙናዊነት መለዮ ልዑቅ ክብር፤ ተወዶና ተፈቅዶ የተለገሰው ንጡር ፍቅር፤ በብዙኃኑ የተጫነለወት ልዩ ዘውድ ተምልሶ ዳግም አይገኝም። ቁርጠዎትን ይወቁ – ጌታው። ዬትኛው ጌታቸው ረዳ? የኛው ወይንስ የወያኔው? ….. መለያወት ላቂያ ፍቅር ነበረው። ጌጥማ አቅርቦትና ልዩ ዜማዊ አክብሮት – ቅርበትም በነኑ – ስለፈቀዱላቸው። የአብነት ት/ቤት – ነትወትንም ለዘለዓለም ከረቸሙት – ምነው እንዲህ – የጤና?! ከብዙኃኑ ቤተኝነት መውጣትስ ይመች ይሆን? ይህ ግንፍል ግንፍል ማለቱስ — ?
ማንም ሰው እንደ ሰው በምድር ላይ ብዙ ነገር ሊኖረው ይችላል። ከሁሉ የሚልቀው ግን የህዝብ ፍቅር ሃብት ነው። ፍቅር የተጠረገ ልብና ብቁ አስተዳዳሪን ይሻል። ፍቅር አድማጭና ተናጋሪም ነው። ስለፍቅር መሸነፍም ውስጥን እንደ ተፈጥሮው እንዲኖር መፍቀድ ነው። ይህን ሁሉ ዘመን በነፃነት የኖረ አባወራ በመዳፉ ላይ ያለውን የህዝብን ፍቅርን በአግባቡ ለማስተዳደር አቅቶት ወይንም ግራጫዊ ዘመን ዘለቅ ተመከሮው መተርጎም ተስኖት እንዲህ እናት ሀገር ማቅ ለብሳ በማህጸኗ የደም ዕንባ በምታለቅስበት እጅግ በጠቆረ ዘመኗ፤ በከፋት ዘመኗ፤ ሾልኮ መቅረት ….. ብልሃት የሌለው ቅላት ነው ለእኔ።
እኔ ሰው ነኝ። ከዚህ በላይ ስለ እኔ የሚተረጉም ምንም አልፈልግም። እርስዎ ግን አስፈለገዎት። በአደገው ሀገር ተቀመጠው ዘመን የሰጠውን፤ የፈቀደውን ፍትህና ነፃነት አግኝተው እዬኖሩ በጣም ታች ወረዱ። ጎሳ ላይ -
ዘመነዎትና ተመክሮዎት ውስጥዎትን ለማሸነፍ አቅልም - አቅም አነሰው። ምነው ቸኮሉ?! ኩታረነቱን* ለልጅ መስጠት ይገባ ነበር። ምን ቆጠቆጠዎት? ምን እንዲህ አንተከተከዎት? ምን አበሳጨዎት? ምን አቅለዎትን ነስቶ በነፈሰበት መረጃ አካልዎትን የገዛ ቤተሰቦወትን ለመወንጀል ምን አስነሳዎት? የምን ጥድፊያ ነው ትቅማጥ እንደያዘው ሰው?
እኔ ልመልሰው። እስከ ዛሬ ድርስ እራስዎትን አሸንፈው አልኖሩም ነበር። ፍላጎቶዎትና እርስዎ አብራችሁ አልነበራችሁም። ወይንም ውስጥወትን አያውቁትም ነበር። ከዚህ የከፋ ነገርም እኮ ሊመጣ ይችላል። በደለኛ እስካለ ድረስ። ሰው እራሱን ሳያውቅ ወይንም እራሱን ሳያዳምጥ ሲኖር አንድ ቀን እንዲህ እራሱን ፈልጎ ያገኛዋል። እሱን ያገኘው ዕለት እንዲህ ይቧርቃል። ሜዳውም ሸንተረሩም አይበቁትም። ይጠበዋል። ታፍኖ እንደ ኖረ ስለሚቆጥረውም ይተነፍሰውና እንዲህ ይወጣለታል። እንኳን ለዚህ አበቃዎት – ጌታው። እንጡሩብ አዘለለዎት …. ነዘረዎት – ሰረሰረዎት።
መመካት ቢኖር አብነት ላለው – ትንሽ ብጣቂ የመንፈስ ማረፊያ ዬብትን አፈር ተቆርቋሪነት ቢኖር ነበር። አንድ የመንደር ወመኔ ስብስብ የፈጸመው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚል ጣዕም ቢኖረው፤ ወይንም ሰውኛ ያለው ጠረኑ ቋት የሚሞላ ተግባር ላይ የሚታይ ተጨባጭ ነገር ቢኖር በነበር። ዕድሉን ቢጠቀምበት በነበረ። ጭብጦ አኮ የለም። የፈለሰ = የመከነ – የተፋቀ፤ የፈሰሰበት ዘመን ጥልማሞተ ነው የወያኔ ያረገዘው ዘመኑ። ምን ተነስቶ ምንስ ተጥሎ? …. በወያኔ ያልተበከለ ወይንም ያልተጠቃ – ያልተቃጠለ ተቋም ምን አለና? መርዝ!
ጸሐፊ ጌታቸው እረዳ እንደ እርስዎ ያለ ታላቅ የዕድሜም ባለጸጋ፤ በፖለቲካ ልምድ የበለጸገ አባወራ፤ በቀለም ትምህርትም ሙሑርነቱ ታክሎበት „ከትግራይ የወጣ፤ ከትግራይ የተፈለፈለ እጭ’፤ ትግራይን ነፃ እናወጣለን ብለው የተነሱ ጎጠኞች፤ ሀገርና ትውልድን የገደሉ፤ ትውፊትና ማንነትን የቀበሩ፤ የሀገራችን አካል የጎረዱ፤ ዜግነታችን የጠቀጠቁ፤ በዘር እዬነጠሉ ያጠቁ፤ እረቂቅ ዛሬ የማናያቸው ነገ ግን እዬፈነዱ ሀገር አልባ የሚያደርጉን ደባ የፈጸሙ፤ ሰንድቅዓላማን የተዳፈሩ – የተጸዬፉም፤ ባህልን ካለርህራሄ የጠቀጠቁ፤ ግብረ ሰዶምን ያበረታቱ፤ የዕምነት ምኩራቦችን በትዕቢት የረገጡ፤ በወገኖቻችን ላይ አራዊታዊ ተግባር የሚፈጽሙ፤ ሀገራቸውን በጠላትነት ፈርጀው ተቋማቷን ሁሉ ያከሰሉ፤ ጥርጣሬን ያነገሡ፤ ምቀኝነትን ያፋፉ፤ አብሮነትን በተባይ ያስወረሩ….“ ምኑ ያልቃል እንዲህ አውሎ ጎልቶ በሚያሳደር የብዕር እልልታ ጎሽ ያሰኝ ነበርን? ህሊና ቢኖርስ አንገት ያስደፋል። ያሳፍራል?
ብዕረኛው ቢያውቁትና ቢገነዘቡት ዛሬ ወያኔ በሚፈጽመው በደል የተፈጠረበት መሬት ያለው ንክኪ ሁሉ ቁስል ነው። መግልን ፈቅዶ ያዘለ። አጋጣሚው ቢሾልክ እንዴት እልቂትን በቀለን ታግሶ ምህረት ማውረድ እንደሚቻል በዚህ መስመር ነበር ምርምር ሊያደርጉበት የሚገባ። እኛ አንቅልፍ የነሳን ይህ ነው። …. ጀግና አንዳርጋቸው ጽጌን የማድንቅበት ትልቁ መስፈርቴ ይህን የተፈራ አምክንዮ ሁሉን ችለው – ዘለፋውን ሁሉ ተሸክመው፤ ወጨፈውን ሁሉ ተቋቁመው ደፈረው መግባታቸው ነው። ጤናማ የመተንፈሻ ቧንቧ ለመዘርጋት አብነቱ ነበሩ – ቀንዲል።
እንደ እርስዎ ያለ በልምድና በተመክሮ ከለማ ወገን እምንጠብቀው የነበረ የበቀል ተጠቂ ተቋማትና ወገን ለማዳን የትግራይን ዬኢትዮጵያዊነት ጉልተኝነት ለማስከበር ፊተኛው ረድፍ ላይ ቆመው እሳቱን ቋያውን እንዲቀበሉ ነበር። ተዉ! በቃ! በዛ! እንዲሉ ነበር። እንጂ እንዲህ አይጥ የበላው ጨርቅ የመሰለ ብትክትክ ያለ፤ በዬቦታው የተቦጫጨቀ፤ ዘሎ ፈርጦ ዪሚወራጭ የነገር ጅምናስቲክ አስተሳሰብ ይዘው ብዕርና ብራናን ሲያገናኙ አንገትን ቀና አድርጎ ለመሄድ ከእንግዲህ ጋዳ ነው የሚሆነው። ፍሰኃና ሰናይ ከሆነወት —— ስ
እውነቱን ብነግረዎት ለትግራይና ለትግራይ ህዝብም የእርስዎ መስመር መዳህኒቱ አይሆንም። በፍጹም። …. ደግሞስ ወጪውንስ ጉዞውንስ እንዴት ቻሉት? – የቀረዎት ሀገር፤ የቀረዎት ሰው፤ የቀረዎት የነፃነት መንፈስ የለም። አዳረሱት። ግን ብዕሮዎት እንዲህ ዟሪ ናት? … ኧረ እንዲህ ስድ አደግማ አያድረጓት!…. የጠብ ተጠማኝም አያድርጓት። እ! መንጠራራቷም ልክ ቢኖረው መልካም ነው። ምን አልባት እርስዎን እረስታ በራሷ ኢጎ መጪ ብላ ይሆን? ኧረ በፈጠረዎ ልጓም ቢጤ ይፈልጉላት …. እዘጭ ያደረገችው እኮ ትልቁን ዳቦ …. እም! አቤት ያንት ያለህ! ከስንቱ ረገጠች? ደግሞ ጠላት ማብዛት ግጥሟ ሆኖ አረፈ — አፈርም ላይ ፈርፈር አለች …. ተጋግጣ – ህም!
አሁን ባለው ሁኔታ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጎሽ እንኳንም የኛ ሆናችሁ የሚያስብልበት ጊዜ አይደለም። የትግራይን ክብርና ዝና የፈገፈገ የጎጥ ስብስብ ከረፋህን ብሎ ትግራይን ማዳን ማለት ለእኔ ኢትዮጵያን ማዳን ስለሆነ፤ በዚህ በጣም የተጋ ተግባር በተከታታይነት በተከወነበት ነበር። መሬት ያያዘ፤ ጭብጥን የተንተራሰ፤ ሥልጡን – እርጋታ የከበከበው የምርምር ድርጊት ያስፈልግ ነበር። የማዳን ዘመቻ እራስን አቅልጦ …..
የብዕረዎት ጠብታ ግን ጦርነት ነው ያወጀች ….. ይገባልን? በመገዳደል፤ በመጨፋጨፍ፤ በጥላቻ በተከዘነ ጎጣዊ ጉዞ ሀገርና ህዝብ ይድናሉን? ለመሆኑ ሽበተዎት በውስጥ ወይንስ ውጪ ላይ ነው ያለው ይሆን? ለሰው አይደለም ለታሪክ – ለትውፊት – ለሀገር – ለሰንድቅአላማ – ለአደራ -ሽምግልና በሚያስፈልጉበት ጊዜ እንዲህ ያለ መላቅጡ የጠፋ የጎረና ጉርና ነዳላ አስተሳሰብ ይዞ መቅረብ ከቶ ወደ ዬትኛው ዕድሜዎት ላይ ተመልሰው ይሆን?
አሁንም አልጠገቡም ይጽፋሉ። ስህተቶችን አነባብረው እዬካቡ ነው። ቃላቶቹ አምጸው – ተንደው ቢደርምሰዎትስ? ሞትንም እርሰዎም ብዕረዎት እረሱ መሰል። ሰው ያዘነበትም ሰው ….. የበቀል አምላክ አለና ይበቀላል። „ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ“ አድርገው ጭንግፍ ያደረጓችን የነገ ወጣቶች እኛ ህይወቱ ባይኖረን ወላጆቻቸው ያነባሉ — ሀገርም ….. ታነባላች። ጊዜያቸውን – ጉልበታቸውን – ገንዘባቸውን – እያፈሰሱ፤ ደፍረው ቅራኔ ውስጥ እዬገቡ፤ ሌትና ቀን በሚተጉ የነፃነት አርበኞች፤ ወጣትነታቸው ሳያውቁት አልፎ ሲሄድ እያዬዩት ኑሮን ንቀው ነገን በተግባር በሚያደምቁት ላይ …. እነዚህ ፎቷቸውን በማናለብኝነት የለጠፏቸው ወጣቶች አንድ ነገር በህይወታቸው ቢደርስ – ተጠያቂ መሆነዎትን ግን ልብ ብለውታልን? …. ከልበዎት ሆነው ይስቡት። ጹሑፎዎትንም ደግሞው ያንብቡት። ተኝተውም ይሰቡ። ግን ግን እርሰዎ ነው የጻፉት ወይንስ ኮበሌው ጌታቸው ይሆን የጻፈለዎት …..? ኦ አምላኬ! ተሳህለነ!
„ኢትዮጵያዊነትን ሃይማኖታቸው“ ስላደረጉ ብቻ ፎቷቸውን የለጠፉት ወጣቶች ወያኔ አፍኖ ወስዶ ምን እንዲያደርጋቸው ይሆን የፈለጉት? ወይንም ሽፍታው ወያኔ የሞት ቅጣት ወይንም ዕድሜ ልክ እስራት ፈርዶባቸው በዛ ተደናግጠው ምን እንዲሆኑ ይሆን ምኞተዎትና ዓላማዎት? ወይንም አንዱ እንዲህ እራሱ የሾለከበት የዘር በሽተኛ ባገኘው አጋጣሚ አነጣጥሮ እንዲገድላቸው ይሆን? ለምንስ መሳሪያውን ገዝተው አይሰጡትም ለአንዱ የዘር ብኩን?! ….. ገድለዋቸዋል እኮ እርስዎ። ሞት እኮ ነው የፈረዱባቸው።
እኔ እኮ እበቃዎት ነበር – ጌታው። የጻፍኩት እኔ። ስለምንድነው ሳቢያ ዬሚፈልጉት። „አንዳርጋቸው ስለምን ጀግና ተባለ?“ ነው አይደል። ጸሐፊዋ እኮ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ነኝ። ፎቶዬ ከናፈቀዎት ከፈለጉት ላይ ይለብዱት። በፈሉጉት ዘይቤ ይሰልቁኝ። እንዳሻዎ ይቀጥቅጡኝ። እኔ እመመኘው ነፃነት የማይመቸኘን ሃሳብ ለማስመቸት ነው። ሃሳብን በሃሳብና በፋክት አፋጭቶ በነጠረው ሃሳብ በብዙሃን ድምጽ የሚመራ ነፃነት ነው ናፍቆቴ። ስለሆነም በፈለጉት ዓይነት አቀራረብ ዱላዎት ይደላው ነበር። እችለዋለሁ። ምንም እንኳን ጹሑፎ ብናኝ ጭብጥ ባይኖረውም – እንኩቶ ቢሆንም።
ከእነዚህ ወጣቶች እራስ ግን መውረድ አለበዎት። ፎቷቸውንም ማንሳት። ትእዛዝ አይደለም – አስተያዬት እንጂ። እኔና እርስዎ አንደራረስም እርስዎ ከፍ ያሉ እኔ ደግሞ ትቢያ። በሁሉም ነገር እንደሚበልጡኝ አሳምሬ አውቃለሁ። ለዚህም ነበር በጭምትነት ዝም ብዬ የሰነበትኩት። እርስዎ ግን የከተቡት ሁሉ የተሰባባረ – አቅጣጫው የጠፋበት – የወለላለቀ – ወለምታው የሰቀዘው የቃላት ድርደር ሁሉ ቁጭተዎትን፤ ለወያኔ ያለዎትን መጠነ ሰፊ ተቆርቋሪነተዎትን ሁሉ ሊመክትለውት አልቻለም። መደረት – መደረት በላይ በላይ – ከሽበተዎት ጋር ይምከሩ።
እኔ ልንገርዎት ዓላማው የሥነ – ልቦና ጦርነት በውጪ የነፃነት ታጋይ ቤተሰብ ለመሰንዘር ነው። ችግሩ አንተዋወቅም። ከብረት ቁርጥራጭ ዬተሰራው መንፈሳችን ግን ከቶውንም ለአፍታ አያንቀላፋም። ጠላታችን ወያኔ ፋሽስታዊ ማኒፌስቶው እስኪነቀል ድረስ የነፃነት ትግሉ በበቃን መሪነት ይቀጥላል። ለሰማዕትነት የቆረጠ ጀግና በጠላት እጅ ነው። ውስጡን ጎርጉራችሁ ምን እንዳደረጋችሁት አይተናል። ይህ ደግሞ ሃይልና አቅም እንደ አዲስ እዬፋፋ እንዲሄድ ያደርገዋል። አንፈራም! አንገታታችንም አንደፋም – በፍጹም።
በስሜት ጋልበንም ከህዝብ ፍቅር ማሳ አንወጣም። ይህ ይመረወታል – ይወረወታልም። ይህ ተቆስቁሶ „ትግራይን“ እንደናብጠለጥል ነበር የፈለጉት። ጓደኛ ፍለጋም እዬባዘኑ ነው። በዓይናችን በተከበሩ አቶ ገ/ድህን አርያማ አይምጡ። አዩ ቅናት! እኔ ስነግረዎት – የተጠለሉበት ጥግ ቀን ዋቢ የለውም። ቀን ወዳጅ የለውም – አውላላ ሜዳ ላይ ጥሎዎት እንዲህ እብስ -
የፈሩት – እንዲህ ያባከነዎት የተከበሩ የአቶ አንዳርጋቸው ዝክረ ጀግንነት በቋሚነት ጽላታችን ይሆናል – ለአብዛኞቻችን። ተከፍሎን ወይንም ባውንድ ተሸልመን አይደለም። እንዲያውም እንዲህ አቅም ሆነን ማገር እንዳንሆን የራሳችን ቅንቅኖችን እዬተጋፋን – እዬገፈተርን ነው ዕውነትና ሃቅን ለማድመጥ የፈቀድነው። በገንዘብ ተገዝቶ ዕንባና ጥቁር ልብስ ሄሮድስ መለስን ቀበረ። እኛ ግን ለአርበኞቻችን – ለሰማዕቶቻችን ፈቅደንና ወደን ደስ ብሎን የምናደርገው ድርጊት ነው …. ለህሊና መኖር ማለት ተፈጥሮን የመተርጎም አቅምና ብቃት ማለት ነው።
መላሾ አሞሌ እኔ ሳውቀው ለከብት እንጂ ለሰው ልጅ አይታሰብም። የወያኔ ሥር ለማረግረግ ጥሎሹ ወይንም እጅ መንሻው እንደልቡሻ ማይጨውና መተማን እንዲሁም ሌሎች ሀገር ወዳድ ወገኖቼን ታሪካቸውን አቃጥለው፤ ሞት ፈርደው ሲባትሉ ሰነበቱ። መጥኔ ለእርስዎና ለአውቆ አበድ ብዕርዎ። እኔ ልንገረዎ እንደ እግር እሳት ያንገበገበዎት ለወያኔ ሽፋን ለመስጠት በሰላማዊ ትግሉ ስም ጠንከር ብለው የሚወጡትን የነፃነት ድርጅቶችን በውስጥ ለውስጥ መንገድ ስትንዱ፤ ስታናክሱ፤ አንጃ ስታስፈጥሩ በዚህ ለሰው በማይታይ ደባ እሳካሁን አረሙ ወያኔ ትንፋሹን እዬሰበሰባ የተፈጠረበትን የጥፋትና የባንዳነት ተልዕኮውን ሲከውን ኖረ።
ከዛም በፊት አልተሳካም እንጂ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በሚያመክኑ ሥውር ሴራ ረቂቅ በሆነ – ሰልጠን ባለ መንገድ ፍርሻ -ህውክት – ሲፈጠር ማገዶዎች ሌሎች ነበሩ። አሁን ጥግ ጠፋ …. በጠራራ ጸሐይ መሸፈኛ አልባ ገመና መውጣቱ ግድ ሆነ። የወገን የበዛ ሰቃይ የምትፈሩትን አቅም በመንፈስ ጽዑም ለዛ አጋባና ፋሽስቱን ወያኔ ፊት ለፊት ወጥቶ አወገዘ። ይህ ሲቀጠል ደግሞ ተከታዩ ምን ሊሆን እንደሚችል ታውቁታላችሁ …. አጃቢ ጠፋ … አቆላማጭ ጠፋ …. ሸፋኝ ጠፋ …. ቅኖች ዛሬን አነበቡ ….. ሚስጥር ተግልጦ እንዲህ በጉባኤ ሥጋና ደምን አዋህደ፤ የሀገራችን ውርዴት ውርዴታችን ነው አሉ ዬእትብት የቁርጥ ቀን አላማና ራዕይ ያላቸው ልጆቿ እንሆ ፊት ላይ ተገኙ። የወገናችን ስቃዩ ስቃያችን ነው አሉ የትውፊት አንበሶች። የወገናችን መከራው መከራችን ብለው ሆ! ብለው እንደ ትሩፋታቸው ተነሱ። ሌሎችም በዚህ በመከራ ቀን መታቀብ አለብን ብለው ሰብሰብ ብለው ተቀመጡ። ወቀሳ የለ ነቀሳ የለ። መነገድ በቃ ….. እዬተጣቡ መጣባት ማብቃት አለበት አሉ። ወሰኑ - ቆረጡ – ተንቀሳቀሱ። ይህ ደግሞ መሽጎ ብቅ እያለ ቤንዚን ለሚያርከፈክፈው አልማጭ አልተመቸም።
ጭድ ከማቀበሉ በፊት ሃሳቡና እልሙ ጭድ ሆኖ አረፈ። ራሱን ገልብጦ አቃጠለው። እኔ እንደማስበው ወቅቱን በአግባቡ አድምጦ ማስተዳደር ከተቻለ አሁን የነፃነት ትግሉ ከጠራ መስመር ላይ ይገኛል። በእጣት የምትቆጠሩ ወገኖች በሰላማዊ ትግል ሥም፤ ወይንም በሉዕላዊነት ተቆርቋሪነት ሥም፤ ወይንም ሊዋህዱ ባልቻሉ የአንድነቱ ቤተሰቦች ሥም ወይንም በሃይማኖት ሥም፤ ወይንም በብሄርና ብሄረሰቦች ሥም ስሱን ቦታ እያዩ ካቫውን ደረብ አድርጎ ጠቅ እያደረጉ አጋግሞ ዞር፤ ወይንም እኔም አለሁ እያሉ እዬገቡ ማመስና ማተራመስ አይቻልም። ቀኑ እንደ ክብረዎት ሾለከ …. አዬ ቀን! …. እርግጥ ሲያስቡት ጎሽ መሸቢያ የሚባሉ መስሎዎት ነበር። በጣም ብዙ ሰው ነው ያዘነቦዎት።
እጅግ የምትናፍቁኝ የሀገሬ ልጆች በዚህ ዓመት ብቻ ሁለት ነገር ተከሰተ። ጀግና ካፒቴን አበራ ሃይለመድህን በሚመለከት በተፈጠሩ ክስተቶች በዬቦታው እጅግ በጣም ብዙ ነገር ነው የተዝረከረከው፤ የነፃነት ትግሉ አካል ተብለው ባለወርቅ ተክሊል ባለቤት የነበሩትን ሁሉ ነው የዛ ጀግና ድል ያንዘረዘረው – ካልጎሽ አይጣራ፤
ከዚህ ቀጥሎ ጀግናዬ አንዳርጋቸው ጽጌን በማፍያ ትብብር ከወያኔ እጅ መግባት በሚመለከት ደማችን የተቆጣ ሃይሎች የሀገራችን ክብር መደፈር ያነገበገበን ወገኖች፤ በገፍ ሰላማዊ ቀንበጥ አርበኞቻችን ወደ እስር እዬተጣሉ በሚወሰድባቸው ፋሽስታዊ ህገ ወጥ እርምጃ ይግርመዎታል ብዕረኛው አቶ ጌታቸው እረዳ ጉዳያችን ነው ብለን አካላችን እንዳይመስለዎት መንፈሳችን በፈቃድ አጋባን። በቃ! ተሰደንም ሰላም እንዴት እናጣለን ብለን ለይ አልን። ….. ለስላሳዊ ተፈጥሯዊ ባህሪያችን ጎርበጥባጣ ሆነ … ልንመች አልቻልነም። እኔ እንዲያውም ቆርጫለሁ የፈለገ ህዝባዊ ስበሰባ ይሁን አቋሙ ባለዬ፤ በተወዛወዘ ቦታ አልገኝም። ብዕሬም ብራናዬም መደከም የለባትም። በሃይማኖት፤ በማህበራዊ ግንኙነት ሁሉ ጥርት ባለ መስመር መድከም – ለትርፍ፤ በስተቀር ለኪሳራ ቆራጣ ነገር አይባክንም ከእንግዲህ።
ኢትዮጵያዊነት ሃይማኖታችን፤ ኢትዮጵያዊነት ቀለበታችን፤ ኢትዮጵያዊነት ድምጻችን፤ ኢትዮጵያዊነት ቀለማችን፤ ኢትዮጵያዊነት ህገ – መንግሥታችን፤ ኢትዮጵያዊነት ቅኔያችን፤ ኢትዮጵያዊነት ውስጣችን ብለን እነሆ ተነሳን። የሃይላችን ምንጩ – የሃይላችን ጭንቅላቱ – የሃይላችን ጉልበቱ – ብንዘገይም እግዚአብሄር ምክንያት ሰጥቶ ከቀስት እናመልጥበት ዘንድ አጥቢያ ኮከብ አበራልን።
ይህ ነው ፋታ ነስቶ – እረፍት ነስቶ አምክንዮው የፈለሰበት፤ ጠረኑ የተበተነ፤ መግቢያና መውጫው የተተበተበ፤ ፍላጎቱ እንጡሩብ የሚዘል፣ አንድም መረጃ ሊቀርብበት ያልቻለ ብትክ – ብትክትክ ያለ የቃላት ድርድር ያሰነበቡን። …. ድጋሚ እንኳን ደስ አለዎት እራስዎትን ስላገኙ። ከመሼ ቢሆንም። ከቻሉ በመጪው ምርጫ ለጠ/ሚር ውድር ወይንም ለከዘራ ደጋፊነት ይወዳደሩ …. ምን ሻታ ያዞረዎታል? … ከዘራ ስል እርጅና ማለቴ አይደለም። አልወጣኝም እንዲያውም ብዕረዎት በሬ ወለደ ናት እንኳንስ እኔ ብዬ። ለማለት የፈለግኩት ስንት ናቸው የሽፍታው ዬወያኔ ም/ጠ ሚር …. ለነገሩ በመጪው ምርጫ ያው ዘሬን ዘሬን እያለ የሚዳጭረው አቶ ወንበር ከቦታው ወርቃማውን ካገኘ ከዘራ ላያስፈልገው ይችል ይሆናል …. ከዛ በፊት ግን ነፍሳችን በመቋጠሪያ አልያዝናትም ሁላችንም …. ማን ያውቃል የሁለት ቢላዋ ባላቤቶች …. ሽኝት ቢጤ ይኖር ይሆን? ወፏን ጥያቄ መሄድ ….. አሰኘኝ …. እንደ ማለት —-
ሌላው እንዲያውቁት ዬምፈልገው ነገር ኢትዮጵዊ ተቋማቱ የመወያያ መድረኮች ስለምን እንዲህ „የናዚ ኔት ወርክ“ እስከማለት አደረስዎት ቢባል። ለዘር – ለመንደር በሽተኞች „ኢትዮጵያ“ የምትል ሥም ሁሉ ዛር ታስወርዳላች …. የወያኔ ተልዕኮ ይህቺን ምድር በተፈለገው መልክ ማጥፋት ነው። ይመኟት የነበሩት ባእድ ሀገሮችም እነሱ ስላልቻሉ ከማህጸኗ በፈሉ ተውሳኮች ፍላጎታቸውን በማስፈጸም ላይ ይገኛሉ።….ሽፍታው ወ ያኔ መሰረተ ጥንስሱ በአንድ ዘር የበላይነት ኢትዮጵያዊነትን ለማጠፋት፤ ለመደምሰስ በተከታታይነተትና በትጋት መሥራቱ ፍጥረተ ነገሩ ነው። ሲከስም ግን ከሥሩ ዘር አልባ ሆኖ ይሆናል። እኔ እምሻው እንደዚህ ነው … መርዝ መነቀል አለበት።!
ሌላው ቀርቶ ወያኔን የተገባውን ያህል „ለትግራይ“ አላደረገም ወይንም በደሉ መረን ለቀቀ እቃወመዋለሁ ብሎ የሚነሳ አንድም ድርጅት ወይንም አንድም የመወያያ ክፍል „ኢትዮጵያ“ የምትለውን አስቀድሞ አያውቅም። አይደፍሯትም። ቀዳሚው …. ለምን ይህ አልጎረበጠወትም? ይመቸወት ይሆን - የሸረፋ ሸጎሬ?
አቶ ጌታቸው ረዳ ጹሑፎዎት በጣም ቁንጥንጥ ያበዛ ቁንጣን ያያዘው ነበር። እጅግ አብዝቶ የዕድሜዎትን ተፈጥሯዊ ጸጋ ሁሉ ድጦታል ልበልን? ጥንቃቄ ፈጽሞ አልጎበኘውም። ማገናዘቢያው ሆነ ማመሳካሪያው የእንቧይ ካብ ነበር። እንዲህ የሚጋልብ ስሜታዊነት ኢትዮጵያንም ሆነ ኢትዮጵያዊነትን አያድንም። የሳሙና አረፋ ያውቃሉ? ወይንም ፈረሰኛ ውሃ ሙላት የሚባል እንደዛ ነው ልበልን? ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የሚያድነው ከበቀል የጸዳ ከቂም የነፃ እራስን በፍጹም ሁኔታ ያሸነፈ፤ ውስጥን በሚገባ መቆጣጠር የቻለ፤ ዬባህላዊ ትውፊታችን ህግጋት በስክነት ያወያዬ መንገድ ብቻ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ኢትዮጵያዊነት እንደማንነት መግለጫ ያድነዋል። በዚህ ሃዲድ ብቻ ትውልዱ ከአፍር ለማኝነት ይድናል። በስተቀር ግን ዛሬ ስንዴ ነገ ደግሞ ከበለጸጉ ሀገሮች አፈር ለማኝ መሆናችን አይቀሬ ነው። የአንድነቱ ዋቢ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ አቅም ብቻ አይደለም ለዚህ የበቁት። ዬኢትዮጵያ ዬአፍሪካ ቀንድነት፤ የመካከለኛው አፍሪካ እራስነት መናድ በጥረታቸው የማይቻል መሆኑን ሲያውቁ ከውስጧ ባንዳ አመረቱላት። ይህ ዕውን እንዳይሆን ነው የሴራው ድርና ማግ። ለማንኛውም በዚህ ሳይሞቅ እንደ ጉድ በሚፈላ ኮበሌ ብዕርና ብራና የተበዳይን – የመከራን – የግፉዕንን ሰዉ ትእግስቱን ያሸፍታል። አይገባም። እልህና ቁጭት ሌላም እሳት ያቀጣላል። የከረፋ በደል አለ። የሚያንገሸግሽ አድሎ አለ። የሚያንገፈግፍ መገፋት አለ።
በከረፋው በደል ውስጥ ወያኔ እንዲሸፈን ሽፋን ፈልጎ የትግራይን ህዝብ ምሽጉ አድርጓል። ይህን ሚስጥር ተፈልፍሎ እንዲገኝ ማስተዋል ተንበርክኮ ይጠይቃል። ማስተዋል ሱባኤ ላይ ነው። ዕንባም ህማማት ላይ። ስለሆነም መርዛማ እጩን ለይቶ ነቅሎ ዬማውጣት ሥራ ነው መሠራት ያለበት። እርስዎ እያሉን ያሉት ደግሞ ሌላ በበቀል የጨቀዬ – ጨቀጨቅ ከሃሞት ጋር አንድንጎርስ ነው። ቢያዳምጡኝ ምልዕትን አግልሎ ኢትዮጵያን ማዳን ከቶ አይቻልም። ስለዚህ ወቅቱ አብዝቶ ከእያንዳንዳችን እላፊ አለመሄድን ይጠይቃል። በተጨማሪም እራስን አሸንፎ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል። እርስው እኮ እራስዎት አመለጠወት። ሰው መሆን በቂ ነው – ለዛሬም – ለነገም – ለነገ ተወዲያም። በበቀል ብቅል እዬታረሰ ያለውን የምልዕት መንፈስ መፈወስ የሚቻለው እርስው በመረጡት መንገድ አይደደለም። የድህንቱ መንፈስ እንዲህ ሲል ይቃኙታል http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33615
ህዝባችን ጎጥ አስተዳደር እጅ እጅ ብሎታል። እጅ እጅ ያለውን አስተዳደር የበቀል ብቅል ሚዛን ላይ አስቀምጦ ፍትሃትንት ማወጅ …. ቢደለዝ – ቢቀባባ – ቢሸፋፈን አይሆንም። ኢትዮጵያ ከትግራይ በወጡ ፈለፈሎች እዬተደበደበች ነው ያለችው። ልጆቿ መጠጊያ አልባ በቀን ብርሃን ጨለማ ተውጠው ነው ያሉት። በዜግነታቸው ለመኖር አልተፈቀደላቸውም። አልሰሙም ማለት ነው። የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት እኮ በ24 ሰዓት ሀገር ለቀው እንዲወጡ ነው የተበዬነባቸው … ምን ማለት ነው ይሄ …. የቀለም ጥልቅ ዕውቀተዎት ይህንን አምክንዮ እንዴት ይተረጉመዋል? እውነትና ሃቅን አይሸሹት! … ይድፈሩት! ….. ማነው የዜግነት ፈቃድ ሰጪው?! …. ሀገሬ ሰንድቅዓለማዬ ብሎ የማያውቅ የጎጥ አስተዳደር ….? ብዕረዎት ማጅራቷ ላይ ይሆን ዓይኗ ያለው? የጥበብ ሰው እኮ መከራን አብዝቶ መጋራት አለበት። መረመጥ አለበት። አልቻለችም ብዕረዎት …. ወንዝ መሻገር አቃታት …. ቃተተችም። የጥበብ ቋንቋ እኮ ሰውነት ብቻ ነው። የፍቅር መግለጫው ደግሞ ህግን አለመዳፍር ነበረ። ወደቀች አንዘላልጦትም። ወያኔ ማለት በግልጽ ቋንቋ ከባህር የወጣ አሳ ማለት ነው።
የኔዎቹ ወገኖቼ። እንደዚህ ዓይነት ክብሪት ብዕሮችና አንደበቶች አብረው የኖሩ ናቸው። በሰላሙ ጊዜ የተረጋጋ ተግባር ሲከውን ከቀፏቸው ውስጥ ተሰብስበው አድብተው ይቆያሉ። ወያኔ በወሰደው ጨካኝ እርምጃ ቁጣ ሲነሳ ግን አዲስ ተለጣፊ ነገር ፈብርከው ብቅ ይላሉ። መጠለያ አላቸው ድርጅት። ይህንንም መፈተሽ ያስፈልጋል። ማንዘርዘሪያ ማዘጋጀት በእጅጉ ያስፈልጋል።
እርግጥ ነው አንድ የፖለቲካ ድርጅት አባላቱ የሚተዳደሩበት ደንብ ለአባላቱ የህይወታቸው መተዳደሪያቸው ነው። ከዚህ ማዕቀፍ ከወጡ በድርጅቱ ሥርዓት ቅጣት ይፈጸምባቸዋል። እንደዚህ ዓይነት ሀገር የሚንድ ውጪ ያለነውን ሳይቀር ህግን ጥሶ ነፃነት የሚቀማ፤ ክብርን የሚዳፍር ተግባር አባላት ሲፈጽሙ ድርጅቶች ሃግ ማለት አለባቸው። በስተቀር ግን ተስማምተውበታል ማለት ነው።
በሌላ በኩል ድርጅቱን አትንኩ፤ የግል አስተያዬት ነው ለማለት የሚቻል አይመስለኝም። የፓርቲ አባል ትንፋሹ ከፓርቲው ማልያ ጋር የተሳሰረ ነው። በፓርቲ ህይወት ውስጥ ዬግል ዕይታ የሚባል ነገር የለም። በቀኝም – በግራም – በፊትም ሆነ በኋላም ቢመዘን – ቢፈተሽ በስተጀርባ ካላው የፓርቲውን አቋም ጋር እንደዚህ መሰል የአባላት ግድፈቶች ነፃ ሊሆኑ ከቶውንም አይችሉም። ነፃ ሊሆን የሚችሉት ፓርቲው በአባሉ ላይ ፈጣን እርምጃ ሲወስድ ወይንም ግልጽ የሆነ አቋሙን በአደባባይ ሲገልጽ ብቻ ነው። በስተቀር ድርጅቱ አብሮ መድቀቁ የግድ ነው። አኔ ከፓርቲዬ – ፓርቲም ከእኔ ፈጽሞ መለዬት አይችልም። ምክንያቱም አንድ የፓርቲ አባልን ከፓርቲው ነጥሎ ለማዬት ፈጽሞ አይቻልም። ሰርገኛ ጤፍ ላይ ነጭ ጤፍን ለቅሞ የማውጣት ያህል ከባድ ነው። ስለዚህ የእስካሁኑ ጉዞ በዚህ በተደባለቀ ዝንቅ ጉዙ ጊዜው መቃጠሉ አይደለም በጣም ብዙ ሀገራዊ ጉዳዮች ተጎድተዋል። ተመስገን! ሱማሌን መመከት በይቻል ዛሬ እንደ ህዝብና እንደ ሀገር ለመጠራት ባልቻልንም ርፍራፊ ነገር አለችን።
ከዚህ ባለፈ በዚህ መሰል የሀገር ጠላትንት ነቀዝነት ማጋዶዎቹ – ቅኖች – ደጎች – የእውነት አርበኞች – የግንባር ሥጋዎቹ አለፉ፤ ቤት ንብረት ፈረሰ፤ ልጆች ወላጅ አልባ ሆኑ፤ የሰው ልጅ እንደ እንሰሳ በመርዝ መሞከሪያ ሆነ …. በቤንዝንም ተቃጠለ … በጠራራ ጸሀይም በመዲናዋ የባሩድ እራት ሆኑ … በርካቶች ታፈኑ …. ከእንግዲህ ግን ዬሚከፈለው መስዋዕትና የትግሉ የጥራት ጉዙ መመጣጠን አለበት። ይህ የማግለል ዘመቻና ፖሊሲ የወያኔ ብቻ አይደለም አዲስ ነገር በቅሎ ለማዬት አይናቸው የማይችሉትም አቅም ቢሶች መገለጫ ነው። የሆነ ሆኖ የሾለከው ነጥሎ ሌላው ሾላኪውን እዬቀደሙ በጥንቃቄና በማስተዋል መጓዝን ይጠይቃል። ወቅቱ የመቆላማጫ የመላላሻ የጥሎሽ ጊዜ አይደለም።
…. ግን እንዲያው ለነገሩ ለእርሰዎ የተከበሩ ዬአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመያዛቸው እንደዛ ሆነው በጎጥ አራዊቶች ማዬታችን፤ ወጣት ጀግኖቻችን የሃብታሙን፣ የዳንኤልን፤ የሽዋስን፤ የአብርሽን የጣር ድምጽ መሰማት እንዲህ ያስጨፍራል? ለእኔ አቶ አንዳርጋቸውን ጀግናዬም ሽልማቴም ብዬ መጻፌ ይህን ያህል ዛር ያስነሳል? ጎሽ ወያኔ ደግ አደረክ መልካም ሰራህ – የምትፈራውን ሰማዕት በእጅህ ስለገባልህ ሻማ ይብራልህ ልንል ነበር የተፈለገው …. ደግሞስ እኔ እኮ ነፃ ሴት ነኝ። የፈለግኩትን ድርጅት የመቀላቀል፤ የፈለኩትን ድርጅት ዬማድነቅና ዬማክበር፤ ውስጤ የሚያምንበትን አውጥቼ መጻፍ እንድችል እኮ ነው የተሰደድኩት። የእሶዎ አጋዚ ብዕር ተፈርቶ ጭጭ ረጭ እንዲባል ነበር የሚፈልጉት። እንዴት ተቀለደ?!
…. እጅግ የማከብራቸው ሙሴን ነው ወያኔ ያፈነው – የማድመጥ ሊቅም ነበሩ። ይውጣለዎት። ወያኔ ባንዳው ጠላቴ ነው። አሁንም ይደገም እስከ ማንፌስቶው መነቀል አለበት። www.tsegaye.ethio.info በዚህ ገባ ብለው „ተስፋ“ ላይ የድህረ ገጹን ዓላማ ያንብቡት ካስፈለገዎም በድምጽም ያገኙታል። በተጨማሪም እኔ ስላለኝ አቋም በዬ15 ቀኑ በዚህ በድምጽ ያገኙኛል እርግጥ አሁን የበጋ እረፍት ላይ ነን ግን አርኬቡ ላይ ያለውንም Radio Tsegaye Aktuell Sendung ገባ እያሉ ይኮምኩሙ።
ትናንት የተፈጠረች አይደለችም ሥርጉተ። እንዲህ ገባ ተብሎ የሚዘለልባትም አይደለችም። ነዳያንን ስንት ፍሪዳ አርደው ድንኳን ጥለው የልደት ፆምን አደግድግዎ ጉንብስ ቀና ብለው ከሚያስተናግዱ ሊቀ ሊቃውንታት የተፈጠረች ናት። መንገድና መርህ ራይና ተስፋዋ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። በምንም ንቅዘትና ጸያፍ ተግባራትም ፈጽሞ የማትታሰብ ክውን ናት። እንዴት የምትደነግጣውን ሴት አግኝተዋል? እሷን አፍ ለማዘጋት – አይችሉም! – ህልም ነው! — ለመሆኑ ይህ ግራ በሚባለወስ ታላቁ መርህ „የሴቶች የእኩልነት የአርነት ትግል አልነበረንም? ምነው ግፊያ አሰኘዎት? አንዲት ሴት እንኳን ለማስተናገድ ታዬ አቅመዎት …. ትንሽ እራፊ ቦታ የለዎትም ለሴቶች ተሳትፎ …. እግዚኦ! አዬ አቅል – አዬ አቅል — አይገዛ ነገር ———–
በተረፈ የሀገሬ ጫካ ሆነ እስር ቤቱንም የማውቀው ነው። ለእኔ አዲስ ዬሆነ ነገር የለም። ምነው ወጣት በሆንኩ በነበረ እንዲህ የዘር ዛርን በብዕር ሳይሆን በባሩድ ነበር የማሰተነፍሰው በለመድኩት ጫካ።
የኢትዮጵያ ወቅታዊ የመወያያ ክፍል መድረክን በሚመለከት በእኔ ሥም አይወርፉት። እኔ አድሚንም ቦርድም አባል አይደለሁም። በህግ ዕውቅና ያለው የተደራጀ ስለሆነ ዕውቅና የሰጠው አካል ቢጠይቀዎት መልስዎት ምን ይሆን? በቃ ቱግ – ቱጉ ብቻ … ማህከነ!
ከረንትን ያህል ኢትዮጵያዊ ተቋም በቦርድ አባልነት ለመምራት አቅሙ የለኝም። ቢሆን ግን ደስታውን አልችለውም። እርግጥ ነው ከዬካቲት 2009 አስከ የከቲት 8 . 2010 ቋሚ አባል ነበርኩኝ። አሁን አባል ባልሆንም እናት ቤቴነቱ ግን እንደተጠበቀ ሆኖ የድህረ ገጹ ደግሞ ዘበኛው ነኝ። የማይመቸኝ ላይ ሚዛን ለመጠበቅ ብዙ ጊዜ ከሥር እጽፋለሁ። አላምነውም በቀን እስከ ስድስት ጊዜ አዬዋለሁ። ይገርመወታል ሌሊት ሁሉ ክፈት አድርጌ አዬዋለሁ። እንደ ጦር የምትፈሩት የተግባር ቤት ስለሆነ ነው። ከረንት አቅሙን የሚገልጸው በሥራ ነው። አቋሙ ደግሞ ከጊዜ ጋር እንደ ወጀብ እንደነካው ዛፍ አይዘፍንም። ቀጥ ያለ የአደራ ማውጫ ቤት ነው። ኢትዮጵያዊነትን ሰንደቁ ስላደረገ ትቢያ ለበሳችሁ አፈር ቆረጠማችሁ ብትረግሙትም ከተግባሩ አንድ ጋት ፈቅ እንደማይል አስባለሁ። ግልጽና ጽኑ አቋም ነው ያለው። አቋሙ ወያኔ ከነጉቱ ከነ ዘረኛ ማኒፌስቶው መነቀል አለበት ባይ ነው። ይህ ደግሞ የእኔም የህይወቴ መርህ ነው ተግባባን ጌታው?!።
ማይጨውን ሳዬው ደግሞ … ዬሽበት ትርጉሙ ሽሽጉኝ ብሎ ጆንያ ውስጥ ሲቀረቀር አዬሁት። ታዬኝ እኮ ማይጮ የግንቦት 7 አባል ሲሆን? በመንፈሱ የጉልማ መሬት ታህል ለትጥቅ ትግል ቦታ እንዳልነበረው ነበር እኔ ሳውቀው። ሰላማዊ ትግል ደጋፊ ሆኖ ነው እኔ የማውቀው። ኢሳትን ሊደግፍ ይችላል – የነፃነት ትግሉ መተንፈሻ ንጹህ ቧንቧ ስለሆነ። ይህ ደግሞ ለወያኔ ስርዎ ስውርም ደጋፊዎች ረመጥ ነው። ቅጥል – ድብን - ፍርክርክ አድርጎ ብርክ ያስይዛችኋል። እኔ እንደማስበው ያው እርስዎም ተደብቀው ያጣጥሙታል ብዬ አስባለሁ። ያው ቅናት ናት እንዲህ ፈርፈር የምታደረግዎ እንጂ። በልበዎ ያደንቁታል አይደል ኢሳትን? ማንም የአፍሪካ ሀገር ያልደረሰበት የእድገት ደረጃ ላይ ስደት ላይ ሆኖ ተግባሩ አንቱ ነው።
ሳረሳው ደግሞ አንድ ነገር – አልኮዎት ጌታው አሁን እኔ ሌላ የወመኔውን ድራማ እዬጠበኩ ነው። … ኢሳትን የሚረዱት ጥንታዊ ጠላቶችችን ናቸው የሚል …. ይህ አይቀሬ ነው። ለነገሩ እርሰዎም እኔም ተሰደን የምንኖርባቸው ሐገሮች አንድም ቀን ለአፍሪካ የነፃነት ትግል ቀን ያወጣቸው ዬሀገረ – ኢትዮጵያ ወዳጆች አይደሉም። ማንስ ወዳጅ ኖሯት ሲያውቅ ነውና? ስለዚህ እርስዎም እኔም ጓዛችን ጠቅለላ ነዋ ከእነሱ ዘንድ አይደለን ያለነው? በፈለገው ቅርጽና ይዘት ብቅ ይበል ዬእንኮሸሽሊቱን* የበቀል ብቅሉ ድራማ እንኩቶ እናዳርገዋለን። አይገርመንም – አይደንቀንም። አሁንስ ተግባባን?! … ያው ያችን አንጠልጥሎ ማቀጣጠያ የባህር ዛፍ ቅጠል ለቀማ ቢወጣ ባዶ እጁን ተመላሽ ይሆናል – ግፋፎው – ወያኔ። ሌላው እርስዎም አንደሚያውቁት ዘረኛው ወያኔ የሚተነፍስው በልምና ስንዴ ነው እንኳንስ የስደቱ ሚዲያ …. ስለዚህ ገና ወያኔ አፉን ሲከፍት ቆረቆንዳ በልኩ ተሰርቶለት ይደፈናል – እሺ!
ሲገርሙ! ምነው ይህቺ ሚዛኗ ላይ አስኳላዋን ገፋ አላደረጉ ይሆን? ሰው በነፃነት በሚኖርበት ሀገር ካላፈቃድ ፎቶ በወንጀለኛ ሥንኝ … መለጠፍ፤ እንደ ተቋም ሶስቱም ሩሞች ህግ በመተላለፍ ክስ ቢመሰርቱ ዋጋወን ያገኙ ነበር። ታዳሚውን ሁሉ እኮ ነው አብረው ያረሱት። ኦኦ! በግለሰብ ደረጃም ቢሆን ፎቶና ከሥሩ የጨነቆሩት ሐረግ በራሱ ገመድ ነበር አዙሮ የሚያንቅዎት። በጣም ተዳፈሩ፤ በጣም እራስዎትን ውድና ዬትግራይ ህዝብ ተቆርቋሪ አደረጉ፤ ቆርጠውና ቀደው የሚያሳድሩን ያህል ነው የተጋፉት፤ ግን ህግ እዬተላለፉ – እዬዘለፉ – እያዋራዱ …. እንዴት እንቅልፍ ወሰዶዎት?
ለመሆኑ „ናዚ“ ማለት ምን ማለት ነው? እንዴትስ በምንስ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል? አስፈጻሚ ተቋማቱ ምንድን ናቸው? ዬዶክተሪኑ ሥነ ህይወት ገጽታ ሆነ ፍለስፍናው በምን ይገለጻል? በዚህ እድሜ - በዚህ የዘመናት ተመክሮ በስሜት የተከዘነ ጆንያ ሙሉ የጭድ ትንፋሽ የኢትዮጵያን የነፃነት ራህብ አይታደግም። ዙሪያ ገባው ነዳላ – መወተፊያ ወይንም መጥቀሚያ መርፌ ወይንም ለማያያዝ ሙጫ ነገር የማይደፈረው የተቆራረጠ ሙጣጭ – ግብና መቋጠሪያ አልቦሽ ኩረት ነው ሲደረደሩ እንቅልፍ አልባ ሆነው የሰነበቱት ….
ጌታው አንሰነባበት – ስንብቱ ለዳርቻ ነው። ከዚህ በኋላ የገደሉትን ገድለው – የወቁትን ወቅተው – ቀረኝ የሚሉት ማሳ ካለዎት ያስኬዱት። የፈራን እንዳይመስለዎት። ከትጋታችን አንዲት ጋት ፈቅ የማንል እንደሆነ እንዲያውቁት ነው የተጣፈለዎት። ቀጣዩ ህይወትዎትን – ዘርዎትን ፍለጋ መማሰን ሽበትዎትን – ዝልቅ ተመክሮዎት አንገቱን ደፍቶ እዬጠበቀዎት ነውና ይታረቁት። የሽንፍላ ጹሑፎወትን የመረጃ ማያያዣ ሊንከዎትን አለጠፍኩትም ተጸዬፍኩት – ገዳይ ገዳይ ወይንም አስገዳይ አስገዳይ ይሸታል – ይከረፋል። እኔ አብቅቻለሁ። መልካም የምንም ጊዜ …..
ውዶቼ የእኔዎቹ አሻቅቦ በሁሉ ነገር የሚበልጥን ወገን መናገር እንዴት ይከብድ ይመስላችኋል። ያልኖርኩበትና ያላደኩበት ሆኖ ውስጤን አብዝቶ አስጨነኩት። ግን መሆን ነበረበት። የኔዎቹ ደህና ሰንብቱልኝ። መሸቢያ ጊዜ! ውድድድ.
- ጉርና – የቅል ዕድገት ማብቂያ – ቅርጽ የለሽ ዕድገቱ አንገቱን ውጦ ሽንጡን ያሰፋዋል። በባለሙያ ውስጡ በሚገባ ይዘጋጅና ማንገቻ ይሠራለታል። ከባላ መንታ እንጨት ላይ ሆኖ እርጎ ይገፋበታል ወይንም እርጎው ተንጦ ቅቤ እንዲወጣ የሚረዳ ባህላዊ ዕቃ ነው። ትንሽ የምትሉት ብዙ ስለሚይዝ ጉርና ይመስል ሆድ አታብዛ ይባላል። ከተሰጠው ጸጋ ወጥቶ እሳት ላይ ቢጣድ ግን ከማረርም አልፎ ከእርጎ ጋር ጎርንቶ ተነዳድሎ እራሱ ህልፈቱን ያውጃል።
- ኩታራ - የልጅነት ጊዜ። ምራቁን ለዋጠ የእድገት ደረጃ ገና ጮርቃ የሆነ እንደ ማለት።
- እንኮሸሸሊት - ቅጠሉም ግንዱም ፍሬውም እሾህ የሆነ በወይና ደጋ የሚበቅል የዕጽዋት ዓይነት
ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል!
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር ነው!
ደሜን ሳደምጠው ውስጤን አገኘዋለሁ!