Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ህወሃቶች በደደቢት ለአርቲስቶቹ የነገሯቸው እና ያልነገሯቸው ታሪኮች ሁሉ የሚያሳዩት አሁንም ህወሓት ስለመንደሩ እንጂ ለኢትዮጵያ አለመቆሙን ነው

$
0
0

Agazi+Victim-1
ፎቶ -በ1997 ዓም በአዲስ አበባ በአጋዚ ጦር የተገደሉ ኢትዮጵያውያን

መንደርደርያ

ኢትዮጵያ በታሪክ የእርስ በርስ ጦርነትን እንደ ትልቅ ታሪክ የምትዘክር ሀገር ሆና አታውቅም።እንደዚያ ቢሆን ኖሮማ ዘመነ መሳፍንት የብዙ የእርስ በርስ ጦርነቶች ባለ ታሪክ ነበር።ሆኖም ግን የወቅቱ የሀገራችን መሪ ግዜያዊ ድል ሲያገኝ የእኔን ማሸነፍ የኢትዮጵያ ታሪክ አድርጉልኝ ሲል አልተሰማም።ጉዳዩ የእርስ በርስ ጦርነት ነዋ! በተቃራኒው ግን ኢትዮጵያ ለነፃነቷ እና ለአንድነቷ የሞቱላትን ከህወሓት በፊት የነበሩት የኢትዮጵያ መሪዎች ትልቅ ቦታ ሰጥተውት ኖረዋል።እነኝህ መሪዎች ከጣልያን ጋር የነበረውን ትንቅንቅ ዘከሩ እንጂ ለስልጣን የተደረጉ ውግያዎችን የኢትዮጵያ ትልቁ ታሪክ ነው ብለው አልተሟገቱም።ህወሓት ግን ያለፉትን ለኢትዮጵያ የሞቱትን እየነቀፈ እና እየወቀሰ ሲመቸው ደግሞ ለማደብዘዝ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እየከፈተ ኢትዮጵያ የተፈጠረችው ደደቢት ላይ ነው መሰል ንግግር ሊያሰማን ይዳዳዋል።
ፖለቲከኞችን ማሳመን ያልቻለው ህወሓት ለአርቲስቶች ምን ነገራቸው?

ሰሞኑን አርቲስቶችን አሳፍሮ ደደቢት ላይ የከረመው የወያኔ አመራር ቡድን 150 ሚልዮን ብር ወጪ(ለፀጥታ ጥበቃ፣ትራንስፖርት፣ለሁሉም አርቲስቶች የቀን አበል፣የምሽት እራት እና ዳንስ ወዘተ) መውጣቱን የውስጥ አዋቂ ዘገባዎች ዘግበዋል።አርቲስቶቹም ድራማ ሲሰሩ ከርመዋል።ሰው ለሰው ድራማ በዋና አክተሩ ተወክሏል፣የህወሓት የዛሬ የአዲስ አበባ እና መቀሌ ህንፃ ባለቤቶች ሲደንሱ ታይተዋል።ለአርቲስቶቹ በእርስ በርስ ጦርነት ወቅት እንዴት ድልድይ እንደፈረሰ፣የቱ ጋር ትግራይን ለመገንጠል እንደተዶለተ፣የቱ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ለሻብያ የምፅዋ ጦርነት የትግራይ ልጆች እንዲላኩ እንደተወሰነ፣የቱ ጋር ስለ ብሔር ብሔር በሚል ሽፋን የኢትዮጵያ ጉድ የሆኑትን ጉድ የብሔር ድርጅቶች ለመፈልፈል ህወሓት እንደዶለተች ተነገረ።

ለአርቲስቶቹ ከተናገሩት ውስጥ አቶ ስዩም መስፍን፣አቦይ ስብሐት እና ሳሞራ የኑስ እንዴት ኢህአፓን እና ኢድዮን እንዴት ከትግራይ እንዳስወጡ ተተረከ።አቦይ ስብሃትም በመሃል የሚያስቆማቸውን ሳል እየሳሉ ሲቀጥሉ እንዲህ አሉ ”የቀድሞዎቹ ተቃዋሚዎች ሁሉም የተሰገሰጉት የቀደመውን ስርዓት ለመመለስ የሚፈልጉ ነበሩ” ካሉ በኃላ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግር የብሔር ችግር ነው ካሉ በኃላ የብሔር ችግርን ”የማይታረቅ ቅራኔ” ሲሉ ስደመጡ ተሰብሳቢውን አስደንግጧል።

ቀጥሎ ከተናገሩት ውስጥ አቶ በረከት ነበሩ።አቶ በረከት አቦይን የወረፉበት ንግግር አቦይን ”ድራማቲክ” አቀራረብ ያለው ሲሉ ተደምጠዋል። አቶ በረከት የገለጡበት መንገድ እንዲህ ይነበባል -”የአቦይ ስብሐት አይነት ድራማቲክ አቀራረቦች ስንሰማ ልንዋጥ እንችላለን።በታሪክም ልንጠፋ እንችላለን” በማለት ነበር።የሁሉም ንግግሮች ያጠነጠኑት ትግራይ በሌላው ኢትዮጵያ ላይ የበላይ እንደሆነ ማብራራት ነበር።ደደቢት ላይ ህወሓት ባይመሰረት ኖሮ ኢትዮጵያ ትጠፋ እንደነበር ለመግለፅ መድከም ሌላው ለማስተላለፍ የታሰበው መልዕክት ነበር።

ህወሓት የፖለቲካ ማሳመኛው ፍልስፍናው ሁሉ ተሟጦ የቀረው የደርግ ዘመንን ደጋግሞ ማንሳት ብቻ ሆኗል።አሁን ኢህአዴግን ፖሊሲህ ዘመን ያለፈበት በቂም፣በዘር እና በበቀል የታሸ ነው የሚለው ደግሞ ኢህአዲግ አዲስ አበባ ሲገባ ገና በእግራቸው መቆም ያልቻሉ ሕፃናት የነበሩ ወይንም ገና ያልተወለዱ ናቸው።ህወሓት የኢትዮጵያን ሕዝብ ዲሞክራሲ የነጠቀ፣በጠራራ ፀሐይ ድምፄ ተሰረቀ ያሉ ወጣቶችን በጥይት የቆላ፣ብሔር ከብሄር በማጋጨት ከእራሱ የወጡ አባሎቹ የመሰከሩበት፣አባላቱ በሙስና በሰበሰቡት ገንዘብ መሃል አዲስ አበባ እና መቀሌ ላይ ባለ ሰባት ፎቅ ሲገነቡ እፍረት የማይሰማቸው አባላት ያሉት ወንጀለኛ ድርጅት መሆኑን የሚሞግቱት አሁንም ወያኔ አራት ኪሎ ቤተ መንግስትን ሲቆጣጠር በእናታቸው እቅፍ ሆነው ጡት የሚጠቡቱ ናቸው። በመሆኑም ተከራክሮ የማያሳምነውን ትውልድ ሸሽቶ ስለፖለቲካ ቢናገሩ እናንተን አይመለከትም ለማለት የሚቀሉትን አርቲስቶችን መማፀኑ ካለተከራካሪ የእኔን ብቻ ስሙኝ ስልት መሆኑ ነው።

ህወሓት ለአርቲስቶች ያልነገራቸው

የህወሓት መሪዎች አርቲስቶቹን ፈረንጆቹ ”ዱላ እና ካሮት” በሚሉት አስተያየት እያዩ እና አንዳንዴ ፈገግ መልሰው ኮስተር እያሉ በማሳቀቅ የተረኩት ሁሉ ዛሬ ላለችው ኢትዮጵያ እና ዓለማቀፋዊ ሁኔታ ፋይዳው ምንድነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። የስብሰባው ዋና ዓላማ ህወሓት የተንጠለጠለበት የጎሳ ፖለቲካ እንዳይበጠስ በመስጋት የጎሳውን ታላቅነት የሰበከ መስሎ ብዙዎች አይናቸውን ተክለውባቸዋል ባለው አርቲስቶች በኩል ህዝብን ማስፈራራት፣ተስፋ ማስቆረጥ እና ”መጪውም ገዢዎችህ እኛ ነን።” የሚል መልእክት ለሕዝቡ ማስተላለፍ ነው።”መጪው ምርጫንም ክደደቢት አንፃር ተመልከቱ እና እንዴት ነው በካርድ ስልጣን እንድለቅ የምታስቡት?” የሚልም ቃና አለበት።

እዚህ ላይ ግን አምባገነኖች የራሳቸውን ታሪክ እራሳቸው ከሚተርኩት በዘለለ ነፃ የታሪክ ምሁራን የራሳቸውን ምርምር አድርገው ታሪክ እንዲፅፉ አይፈልጉም እና ተራክዎችም ሆነ ሰሚዎች እራሳቸው እንደሆኑ የመቃብር ጉዞ ይጀምራሉ።እዚህ ላይ ህወሃቶች ለአርቲስቶቹ ያልነገሯቸውን ማንሳት ተገቢ ነው።
አቦይ ስብሐት፣አቶ ስዩም እና አቶ በረከት ቢቢሲ ስላረጋገጠው ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ በ 1977 ዓም እረሃብ የመጣውን የዕርዳታ እህል ሱዳን እየተወሰደ ይሸጥ እንደነበር እና የጦር መሳርያ ይገዛበት እንደነበር አልነገሩትም።
በደርግ ዘመን በአሶሳ የአማራ ተወላጅ ናችሁ ተብለው በአንድ ቤት ተከተው በእሳት ስለተቃተሉት ምንም አላሉም።
ኤርትራ ከኢትዮጵያ ትለይ ብለው እስከ ምፅዋ እና ከረን ድረስ የትግራይ ተወላጆች ደም እንዲገብሩ መላካቸውን አላነሱትም።
ህወሓት እስካሁን ድረስ በአሜሪካ የሽብር መዝገብ ላይ እንደሰፈረ መሆኑን ትንፍሽ አላሉም።
በህወሓት የተሳሳተ ፖሊሲ ሳብያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችንን ለአረብ ሀገር መከራ መዳረጋቸውን ያነሳ የለም።
በህወሓት ውሳኔ በሺህ የሚቆጠሩ ሕፃናት ለጉድፈቻነት መዳረጋቸው እና በለውጡ ህወሓት ብዙ ሚልዮን ዶላር ማትረፉን ትንፍሽ ያለ የለም።
ህወሓት ከተሞች በጎዳና ተዳዳሪዎች፣ወጣቶች ለጫት እና ለሽሻ፣የዩንቨርስቲ ምሩቃን የኮብል ስቶን ሥራ ሰራተኛ እንዲሆኑ የተደረጉት በዘመነ ህወሓት መሆኑን ለመናገር የደፈረ የለም።
በከተሞች የሚኖሩ ብዙ ሺዎች የገዛ ቤታቸው በግሬደር ሲፈርስ እና የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑት በህወሓት ዘመን መሆኑን ህወሀቶች አላነሱትም።
ገበሬው ለዘመናት ከኖረበት ቦታ በጎሳ እና በቋንቋ እየለዩ ለዘመናት ከኖረበት ቦታ የተፈናቀለው በዘመነ ህወሓት መሆኑን ያወሳ የለም።
አስራሶስት የህወሓት አመራሮች በስዊድን ዓለም አቀፍ የጦር ፍርድ ቤት በዓለም አቀፍ ወንጀለኛነት ከተከሰሱ ገና ቀናት እየተቆጠሩ መሆናቸውን ሊያስታውሱ አልፈለጉም።
ከሁሉም የሚገርመው ህወሃቶች ከአርትስቶቹም ሆነ ከትግራይ ሕዝብ የደበቁት ትልቅ ጉዳይም አለ።የሀውዜን እልቂትን ጉዳይ።ይህንን እልቂት አቦይ ስብሐት አዲስ የማስቀየሻ ያሉትን ሃሳብ ይዘው ቀርበዋል።”በጉዳዩ ላይ የእስራኤል እጅ አለበት” ነበር አቦይ ያሉት።መቸው ህወሃቶች ከገደሉ ወይም ከተኮሱ አልያም ከተናገሩ በኃላ ነው ማሰብ የሚጀምሩት።ለእዚህም ነው ነገሩን ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር በማያይዝ ከአረብ ሃገራት ያተረፉ የመሰላቸውን የተናገሩት። ከህወሓት የለቀቁት የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ግን በሃውዜን እልቂት ላይ የህወሓት ቁልፍ ባለስልጣናት እጅ ሆን ተብሎ የተቀናበረ መሆኑን ያብራራል።አቶ ገብረ መድህን አርአያ፣አቶ ግደይ እና አቶ አብርሃም ያየህ በተለያየ ጊዜ በጉዳዩ ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል።ከእዚህ በታች የአቶ ገብረ መድህን የቀድሞው የህወሓት መስራች እና የፋይናንስ ኃላፊ በሃውዜን እልቂት ህወሓት አቀናባሪ እንደነበር እና ምክንያቱንም ጭምር እንዲህ ያብራራሉ።

”“ወይ፡ ሀውዜንም የወያኔ ድራማ ነው።” በዚያን ጊዜ ሕወሀት በምትሰራው ስራ ምክንያት እጅግ በጣም ተጠልታ ነበር። ሰው አጣች። ምልምል ጠፋ። እናስ? ተንኮል አሰቡ። የዚያን ግዜ የትግራይ አስተዳዳሪ ለገሰ አስፋው ነው። ከዚያ ወያኔ ሀውዜን አንድ ክ/ጦር እያስገባች እያስወጣች ወያኔ ሀውዜን ስብሰባ ልታደርግ ነው የሚል ወሬ ለደርግ ደህንነት እንዲደርሰው አደረገች። ሀይሉ ሳንቲም (ሳነቲም ቅጽል ስሙ ነው) የሚባል የወያኔ የጦር ደህንነት፡ የወያኔ ጦር ሀውዜን ሊሰበሰብ ነው የሚለውን መረጃ ለለገሰ አደረሰ። እውነት እንዲመስልም፡ በገበያው ቀን የተወሰኑ ታጋዮች ባካባቢው ውር ውር ሲሉ እንዲታዩ ተደረገ። የሀውዜን ገበያ መቼም እጅግ የታወቀ ነበርና ከብዙ ቦታ ብዙ ሰዎች ለንግድ ይመጣሉ። በእለቱ ስድስተ የደርግ ሚጎች እየተመላለሱ በመስቀልያ ቅርጽ፡ ገበአውን ደበደቡት። ይሄ ሁሉ ሲደረግ ቪዲዮ ይነሳ ነበር። ነገሩ ለረጅም ግዜ የተቀነባበረ መሆኑ የሚታወቅባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው። ወደ አስራ ሁለት ፎቶ አንሺዎች ሱዳን ውስጥ ሄደው እንዲሰለጥኑ ተደርጓል። ገብሬ የዚያን ግዜ ቪዲዮ ካሜራ አያውቅም ነበር። እነ ተክለወይን አስፍሀ፡ እነ ሱራፌል ምህረተአብ፤ እነ እያሱ በርሄ ካሜራ ቀራጭነት ሱዳን ውስጥ ተምረው መጡ። ያ ሁሉ ድብደባ ሲደረግ ተራራ ላይ ቆመው እያንዳንዱን ሚግ ከሁሉም አቅያጫ ቪዲዮ ያነሱ ነበር። ይቀርጹ ነበር። በነጋታው ይሁን ማታውኑ ያ ሁሉ ፊልም ሱዳን ውስጥ በቲቪ ታየ። ገበያ ላይ የሞተው ሰው እንሰሳ፡ ህዝብ፡ ሽማግሌ ሕጻናት በቲቪ በደንብ ተቀርጿል።

የምንስ ለቅሶ መልሶ መልሶ

ባጠቃላይ ህወሓት በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ምንም አይነት አሻራ የለውም የሚል የለም።ሆኖም ግን መታሰብ ያለበት ጉዳይ ዛሬ ላይ በሞቱት አጥንት ላይ ተቀምጠው በሙስና በስብሰው፣ዲሞክራሲን በእግራቸው እረግጠው እና በርካታ ግድያ ፈፅመው የሞቱትን እያነሱ መመፃደቅ አሁንም በሞቱት ላይ መሳለቅም አያጣውም።ለሕወሃቶች የምመክራቸው ሴኮቱሬ ከደደቢት ያስተላልፍ የነበረውን ፕሮፓጋንዳ ዛሬ ላይ ደግመው ማንበብ ቢችሉ የሚል ነው።”ትግላችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ካለምንም ገደብ የመፃፍ፣የመናገር እና ሃሳብን በነፃት የመግለፅ ነፃነትን ለማረጋገጥ ነው።ትግላችን ህዝቦች ካለ አንዳች ፍርሃት ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉበትን በፈለጉት የሀገሪቱ ቦታዎች የመኖር መብታቸው እንዲረጋገጥ ነው” ይል ነበር። ለእዚህ ነዋ ”ህገ መንግስቱ ይከበር” ያሉትን ንፁሃን ወጣቶች እስር ቤት የምታማምቁት? ለእዚህ ነዋ ! ”ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” ብለው የተሰለፉትን የሰማያዊ ፓርቲ እና የዘጠኙን ፓርቲዎች ጥሪ በድብደባ መባረራቸው እና መታሰራቸውን ምን እንበለው። በደደቢት ህወሃቶች ለአርቲስቶቹ የነገሯቸው እና ያልነገሯቸው ታሪኮች ሁሉ የሚያሳዩት አሁንም ህወሓት ስለመንደሩ እንጂ ለኢትዮጵያ አለመቆሙን ነው።

ጉዳያችን ታህሳስ 23/2007 ዓም (ጃንዋሪ 1/2015)


ምክር እስከመቃብር(ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ)- ክፍል ሁለት –በእውቀቱ ሥዩም

$
0
0

እንደምነሽ ሸገር
የከሰመው ወንዝሽ
የከሰመው ወዝሽ
የሚታየው ነጥፎ
እንደምነው ጣፎ
እንዴት ነው ቀበና
እስቲ ድንጋይ ላጥምድ መረብ ልጣልና፡፡
Beweketu Seyoun joke about African leaders summit [Very Funny]
በነገራችን ላይ በኣዲስ ኣበባ የሚገኙ ካፌዎችና ምግብ ቤቶች“ ኒውዮርክ”“ ዴምቨር” “ወዘተረፈ ተብለው የሚጠሩትን ያክል ባውሮፓና በኣሜሪካ ያሉ ሬስቶራንቶች ደግሞ ”ዱከም“ ፤ ኣራትኪሎ ፤ ፒያሳ በሚል ተሰይመዋል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ምንድር ነው ፡፡ ኣዲስ ኣበባ ስትኖር ውጩን ይናፍቅሃል፡፡ ውጭ ስትኖር ደሞ ኣገር ቤት ይናፍቅሃል፡፡ መኖር ማለት የማይበርድ ናፍቆት ማለት ይሆን? መልመድ ይቅደም! ናፍቆት ይውደም!! ያለምንም ደም!!!


ፌንተን መንገድ ዳር ከሚገኙ ያበሻ ሬስቶራንቶች ባንዱ ተኬ ከተባለው የቀድሞው የብሄራዊ ቡድናችን በረኛ ጋር ኣመሸሁ፡፡
ሊጋብዘኝ ዝግጁ እንደሆነ ሲነግረኝ “ኣንድ ሽሮና ኣንድ ያሣ ዱለት ቢመጣልኝ ደስ ይለኛል!“ኣልሁ ራሴን እያከክሁ፡፡
“ይሄ ሁሉ ምግብ ምን ይሰራልሃል? ገና ለገና ኣገርቤት የምግብ እጥረት ስላለ ለወር የሚበቃህን ያህል በልተህ ልትሄድ ነው?“
ምግቡ ሲመጣ ተኬ ከኣሣ ዱለቴ ኣንድ ጉርሻ ጎረሰና ኣላምጦ ግንባሩን ከሰከሰ፡፡
” እንዴት ነው?“ ስል ጠየኩት፡፡


“ምምምም ያባቴን ኣውራጣት፤ ያባቴን ኣውራ ጣት ይላል” ኣለ፡፡
“ጉደኛ ነህ! ያባትህን ኣውራጣት በልተህ ታውቃለህ?”
“ምን መሰለህ!በልጅ እያለሁ ማታማታ የኣባቴን እግር ማጠብ ነበረብኝ፡፡ ትዝ ይለኛል፤ያባቴ እግር በጣም ቀጭን ተመሆኑ በላይ ሲበዛ ጸጉራም ነው፡፡ እግሬን እጠብልኝ ከሚለኝ ይልቅ እግሬን ኣበጥርልኝ ቢለኝ ይሻል ነበር፡፡ ወንድ ልጅ ሲወለድ ከነቃጭሉ ዱብ ኣለ ይባል የለ፡፡ፋዘር ደሞ ከነገምባሌው ነው ዱብ ያለው፡፡እና እግሩን ኣጥቤ ስጨርስ ኣውራጣቱን ያስመኝ ነበር፡፡ያውራ ጣቱ ጣእም እስታሁን ምላሴ ላይ ኣልጠፋም፡፡ኣውራ ጣቱ ይህን ዱለት ይህን ዱለት ይላል፡፡ኣሁን ሳስበው ኣባቴ ምናባቱ ቆርጦት እንደዛ እንደሚያረግ ኣይገባኝም፡፡እግር የሚስም ባርያ የመግዛት ኣቅም ስላልነበረው እኛን ልጆቹን እንዲህ ያስመን ነበር፡ ፡ ኣየህ ልጅ ማለት እግዜር ለወላጅ የፈነገለው ባርያ ማለት ነው፡፡”


በልተን ስንጨርስ ሊመክረኝ ተዘጋጀ፡፡
“ወደ ኢትዮጵያ የሚያስመልስህ ነገር ምንድነው?”
“ያገር ፍቅር!”
“ትያትር ቤቱን ነው ?”
“እረ ስሜቱ!”
ተኬ በመልሴ በጣም ሳቀ፡፡
“ምን ኣሳቀህ?፡፡ ኣገሬ ገብቼ ከልማቱም ከግማቱም ብሳተፍ ኣይሻልም?“ኣልኩት በቁርጠኝነት፡፡
“እንደ ወንድም ልምከርህ፡፡ እዚህ ብትቀር ይሻልሃል፡፡ ደመወዝ ይመስል ውሃ በወር ኣንዴ የሚመጣበት ኣገር ምኑ ይፈቀራል?መብራቱስ የታል? እዚህ ኣሜሪካ በየቤቱ ደጅ ላይ የሚቆመው ክሪስማስ ትሪ ከኣዲስ ኣበባ የተሻለ ያበራል፡፡ ኢትይጵያ ውስጥ ካምፖል ይልቅ ብርሌ ብዙ ስራ ይሰራል፡፡የሰለጠነው ዓለም ጨረቃ ላይ ከተማ ለመገንባት ሲራኮት እኛ በጨረቃ ብርሃን ራት እንበላለን፡፡ በዝያ ላይ የለማኝና የጎዳና ተዳዳሪው ብዛት ኣይዘገንንም?”
“እዚህም እኮ ለማኝ ኣለ” ኣልሁ፡፡


“ያገራችንን መናጢ ለማኝ ካሜሪካ ለማኝ ጋር ስታወዳድረው ሼም ኣይሰማህም? የዚህ ኣገር ለማኝ እንደምታየው ኣለቅጥ ወፍራም ሲሆን የሚለምነውም ለጂም ነው፡ ፡ ባለፈው ቬጋስ ሄጄ ያያየሁት ለማኝ ምን እያለ እንደሚለምን ታውቃለህ?”
“ምን ኣለ?”


‘ወንድሞቼ ለዛሬ ሌሊት ሸሌ የምገዛበት ፍራንክ ስለቸገረኝ ጣልጣል ኣርጉልኝ’
ስስቅለት ጊዜ ቀጠለ፡፡
”በዛ ላይ ኣገሩ ውጥረት ነግሷል፡፡ ኣዲስ ኣበባ ውስጥ የሚታየው መፈክር ይዞ የሚሮጥ ወጣትና ቆመጥ ይዞ የሚያባርር ፖሊስ ብቻ ነው፡፡ኣንተም ገና ኤርፖርት እንደደረስህ ነው መሮጥ የምትጀምረው፡፡ከምርጫ ጋር በተያያዘ ብዙ ጣጣ ይኖራል፡፡ኣደራ ገዥውን ፓርቲም ሆነ ጎምዥውን ፓርቲ እንዳትመርጥ ፡፡ዝምብለህ በኤፍ ኤም ደውለህ ለፍቅረኛህ ዘፈን ምረጥ፡፡ፌር የሆነ ምርጫ ያለው እዛ ይመስለኛል፡፡ I hope የጥላሁንን ገሰሰን ዘፈን ስትመርጥ የጥላሁን ጉግሳን የሚጋብዙ ዲጄዎች እንዳልተቀጠሩ ተስፋ ኣለኝ፡፡“
በፈገግታ ማዳመጥ ቀጠልኩ፡፡


”ያገራችን ብቸኛ ጸጋዋ ኣየሯ ነበረ ፤ ኣሁን እሱም እየተበላሸ ነው ኣሉ፡፡በኛ ጊዜ ጸሃይ ኣመለ ልስልስ ነበረች፡፡ ኣሁን ሙቀቱ ኣይጣል ነው!ጸሃይ በጣም ከማቃጠሏ የተነሳ ያዲሳባ ሴቶች እንጀራ የሚጋግሩት ጃንጥላቸው ላይ ነው ሲባል ሰምቻለሁ ፡፡ እንድያውም ኣንዳንዴ ሳስበው የሰማይ ኮርኔስ የተቀደደው በኢትዮጵያ ኣቅጣጫ ሳይሆን ኣይቀርም፡፡ድሮ ሽማግሌ ኣያትህ እንዲመርቅህ ከፈለግህ የማለዳ ጸሃይ ስር ወስደህ ታሰጣዋለህ፡፡ ዛሬ የማለዳ ጸሃይ ስር ብታሰጣው ይረግምሃል፡፡ምነው ምነው ልጄ ኣልሞት ኣልኩህ? እንዲህ እንደ እንፋሎት ዳቦ በገዛ ላቤ ከምትጥብሰኝ በግልጥ እንደ ደመራ ለምን ባደባባይ ኣታነደኝም?ኣይ ኣይይይ!ርጉም ሁን ፡፡ዘርህ ይማረክ፡፡ቤትህን ቡልዶዘር ያፍርሰው፡፡ርስትህን ህንድ ይረሰው፡፡ሎተሪን ኣንተ ቁረጠው እጣውን ግን ለጠላትህ ይድረሰው ብሎ ይረግምሃል፡፡

“ለኢትዮጵያ አንድነት በጽናት እንቆማለን” –ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

(የፀሐፊው ማስታወሻ — ይህን ፅሁፍ በነጻነት ለሀገሬ ስም ለአማርኛ አንባቢዎቼ አቀርባለሁ። የነፃነት ለሀገሬ ትርጉሞች የረቀቁና የተጣሩ ናቸው። የነፃነት ለሀገሬን ድጋፍ በማግኘቴ ታላቅ ደስታና ክብር ይሰማኛል። ነፃነት ለሀገሬ ያልተዘመረለት/ያልተዘመረላቸው የኢትዮጵያ ጀግና/ጀግኖች ናቸው። ከፍተኛ ክብርና አድናቆቴን ለነፃነት ለሀገሬ አቀርባለሁ/አቀርብላቸዋለሁ !!! ትግሉ ይቀጥላል ለነፃነት ለሀገሬ!!!)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የአፍሪካ አሜሪካዊ ደራሲ፣ ገጣሚ፣ የዳንስ ተወዛዋዥ፣ ተዋናይ እንዲሁም የሙዚቃ አቀንቃኝ የሆነችው ማያ አንጌሉ እንዲህ በማለት አውጃ ነበር፣ “የእኛን ጀግኖች እና ጀግኒቶች ማስታወስ እና መዘከር እንዴት ያለ ጠቃሚ ነገር ነው!“እኛም እነዚህንም የሀገር ጀግኖች እና ጀግኒቶች ተራ በተራ እያነሳን እናክብራቸው፣ እናወድሳቸው ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ሀገሪቱ ከገባችበት ማጥ ውስጥ እንድትወጣ ለማድረግ እና ነጻነት እና ዴሞክራሲ በሀገራችን እንዲሰፍን እራሳቸውን ለመስዋዕትነት ያቀረቡ የሀገር ዕንቁዎች ናቸውና፡፡
Eskinder-Nega
1ኛ) እስክንድር ነጋ፡ የሀገሪቱ መናገሻ ከተማ ከሆነችው ከመሀል አዲስ አበባ በስተደቡብ በኩል ወጣ ብሎ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ከሚገኘው በአስከፊናቱ ከሚታወቀው ከመለስ ዜናዊ የቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት ታስሮ በመሰቃየት ላይ ከሚገኘው ከታዋቂው እና የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል ከሆነው ከእስክንድር ነጋ እጅ በድብቅ በወጣ ደብዳቤው “በጽናት እቆማለሁ” በማለት ጽፏል፡፡

እስክንድር “በጽናት እቆማለሁ!” ሲል ዝም ብሎ ስለእራሱ ለመጻፍ ፈልጎ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በማጎሪያው እስር ቤት በመሰቃየት ላይ ስላሉት የስራ ባልደረባ ጋዜጠኛ ጓደኞቹ፣ ጦማሪያን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ስለሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ዓላማም ጭምር ነው፡፡ ከዚህም በላይ አንድ የህሊና እስረኛ ወይም ደግሞ አንድ የፖለቲካ እስረኛ ብቻውን በጽናት ሊቆም አይችልም፡፡ ብቻውንም በጽናት ቆሞ ብቻውን ውጤት ሊያመጣ እይችልም፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ኢትዮጵያ እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ ከሚጠራው የአምባገነን ወሮበላ ስብስብ መዳፍ ስር ወድቃ በመማቀቅ ላይ እያለች ለዚህ እኩይ ምግባር አራማጅ ዘረኛ ድርጅት የአደባባይ እስረኛ ምርኮኛ ሆኖ በጸጥታ ስለሚገኘው ከ90 ሚሊዮን በላይ ለሆነው ኢትዮጵያዊ/ያት ወገኑ ሁሉ መልዕክት ለማስተላለፍ አስቦ የጻፈው መሆኑን በድፍረት መናገር እችላለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ከወያኔ አምባገነን የወሮበላ ስብስብ ነጻ ለመውጣት እና እውነተኛ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ ለመገንባት በጽናት ትቆማለች፣ እናም ታሸንፋለች!

እ.ኤ.አ በ2014 የተጠናቀቀውን አሮጌ ዓመት ምክንያት በማድረግ የእኔን ጀግና እስክንድር ነጋን እና የእኔን ጀግኒት ርዕዮት ዓለሙን እንደዚሁም በእነርሱም ስም ሁሉንም የፕሬስ ነጻነት የህሊና እስረኛ ጀግኖች እና ጀግኒቶች ኢትዮጵያውያን/ት የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች፣ ለምንም ለማንም ለድርድር ለማይቀርበው ነጻነት ምርኮኛ ለሆኑ ህዝቦች፣ ለነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ለሚታገሉ፣ ለመልካም አስተዳደር እና ለሰብአዊ መብት መከበር ለሚታገሉ ወገኖች ሁሉ ደወል በመደወል ድምጼን ከፍ አድርጌ በመናገር አወድሳቸዋለሁ፡፡ እነርሱን በማወደስ በኩራት እንዲህ እላለሁ፣ “እንደ ፖለቲካ እስረኛነታችሁ በጽናት ቆማችኋል! እኛም በጽናት ቆመናል! ኢትዮጵያ በአምላክ ቸርነት እንደ አንድ ሀገር ብሄር በጽናት ቆማለች፡፡ የእኛን ነጻነት በመግፈፍ በባርነት እና በሁለተኛ ዜጋነት በማስቀመጥ ሲበዘብዙን እና ሲመዘብሩን ለመቆየት ዕቅድ አውጥተው የቆሙት ሆድ አምላኩ ፍጡሮች ጽናት እስከሚሟሽሽ እና ደብዛው እስከሚጠፋ ድረስ በጽናት እንቆማለን፡፡ ድል አድራጊነት ለእውነት በጽናት ለቆሙት ብቻ የተሰጠ ጸጋ ነው!“

ሸክስፒር እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ጥቂቶች ታላቅ ሆነው ተወልደዋል፣ ጥቂቶች ታላቅነትን በሂደት ይጎናጸፋሉ፣ ጥቂቶች ደግሞ ሁኔታዎችና ፈተና ታላቅነትን ያጎናፅፋቸዋል፡፡“ እንደዚሁም በተመሳሳይ መልኩ በእኛ ጀግኖች እና ጀግኒቶች ላይ እምነትን መጣል ይቻላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እንደ እስክንድር እና ርዕዮት ያሉ ዜጎች (ሁሉንም በኢትዮጵያ በማጎሪያው እስር ቤት በመማቀቅ ላይ የሚገኙትን ሌሎችን የህሊና እስረኞች ይወክላሉ) ጀግኖች እና ጀግኒቶች ናቸው ምክንያቱም በሀገሪቱ ላይ ፈታኝ የሆነ አደገኛ ሁኔታ በተፈጠረበት ጊዜ ጀግንነት በእነርሱ ላይ እምነቱን ጥሏልና፡፡ የእነርሱን የህይወት ዕጣ ፈንታ ፈልገው ባገኙበት ጊዜ እንደ አብዛኞቻችን ፊት ለፊት መጋፈጥን እርም ብለው አላስወገዱም ወይም ደግሞ እንደ ግመል ሽንት ወደኋላ አልተስፈነጠሩም፣ እንደዚሁም እንደ ተልባ ስፍር አልተንሸራተቱም፡፡ እነዚህ የጀግንነት ተምሳሌቶች የአሽከርነት ወይም የለማኝነት ባህሪን አልተላበሱም፡፡ እነዚህ የጀግንነት ቀንዲሎች ሌሎች ለከርስ ብቻ የቆሙት ሆዳሞች እንደሚያደርጉት ሁሉ ስብዕናቸውን በቤሳ ሳንቲም አልለወጡም፣ እንደሌሎች ቆርጦ ቀጥሎች አይደሉም፣ በጽናት ከቆሙለት ዓላማ አንዲት ጋት ወደኋላ አላፈገፈጉም፡፡ ላመኑበት ዓላማ በጽናት ቆመዋል፣ ይቆማሉም፡፡ በወሮበላ የጫካ አገዛዝ ነጻነት በሌለው አጥር የሌለው አስርቤት ውስጥ እየሰገዱ እና እየተንገዳወሉ ከመኖር ይልቅ ያመኑበትን ዓላማ በማራመድ ነጻነትን ይዞ በእስር ቤት መኖርን መርጠዋል፡፡

እስክንድር እና ርዕዮት በጉልበታቸው የሚንበረከኩ ቢሆን ኖሮ፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በማጎንበስ ቢለምኑ ኖሮ፣ ወንጀለኛ ተብለው የተፈበረኩባቸውን የሸፍጥ መሰሪ የውንጀላ ክሶች አምነው ይቅርታ ቢጠይቁ ኖሮ፣ የአሳሪዎቻቸውን እግር ቢልሱ እና ይቅርታ እንዲደረግላቸው ቢለምኑ ኖሮ ከማጎሪያው እስር ቤት ይወጡ ነበር፡፡ ከእነዚህ የዓላማ ጽናት ተምሳሌቶች ቀደም ብሎ አሁን በህይወት በሌሉት መለስ ዜናዊ እና ደቀመዝሙሮቻቸው አማካይነት ይቅርታ እየተደረገላቸው እንደወጡት በርካታ ወገኖች ሁሉ ያለምንም ችግር ከማጎሪያው እስር ቤት ይወጡ ነበር፡፡ በሸፍጥ የፍብረካ ወንጀል ክስ አሸባሪ በሚል የገዥው ወሮበላ ስብስብ የማደናገሪያ ታፔላ ተለጥፎባቸው በዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት 11 ዓመታት በእስራት እንዲቀጡ ተበይኖባቸው የነበሩት ጆሀን ፔርሰን እና ማርቲን ሽብዬ በተመሳሳይ መልኩ ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ ነበር የተፈለገው፡፡

መለስ በጥቃት ሰለባዎቻቸው ላይ የውሸት የፍብረካ ውንጀላ የጥፋተኝነት ክስ እንዲመሰረት ካደረገ በኋላ በህዝብ ፊት በአደባባይ አምነው ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ ማድረግ የመጨረሻው የውርደት መቅጫ ወይም ማሸማቀቂያ መሳሪያው ነበር፡፡ ይህንን እኩይ ድርጊት እ.ኤ.አ በ2005 የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ ምክንያት ሰብስበው በማጎሪያው እስር ቤት አጉረዋቸው በነበሩት በደርዘን በሚቆጠሩ የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች ላይ ተግብረውታል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ በሆነችው ሴት የፖለቲካ ፓርቲ መሪ በነበረችው በብርቱካን ሚደቅሳ ላይ ሁለት ጊዜ ተግብረውታል፡፡ አቶ መለስ በማጎሪያው እስር ቤቱ እየተንገዳወሉ እና እየተልፈሰፈሱ ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩትን ንጹሀን ኢትዮጵያውያን/ት እንደ ሀቀኛ ሰው ለምነው በማታለል እያግባቡ እና እያሳመኑ ለአቶ መለስ እብሪተኛ ዓላማ ይቅርታን እንዲጠይቁ እና ከማጎሪያው እስር ቤት በይቅርታ እንዲወጡ የሚያደርጉ ካድሬዎች ነበረው፡፡ አቶ መለስ የራሱን ብልሹ አመራር እና ፖሊሲን የሚቃወሙትን ንጹሀን ዜጎችን ሁሉ በህዝብ ፊት በአደባባይ ማዋረድ ትልቅ እርካታን ይሰጠው ነበር፣ በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙት ይህ እኩይ ድርጊት የእርሳቸውን በሰዎች ስቃይ እና ውርደት ላይ ጮቤ የሚረግጠውን የክፋት ነብሱን በደስታ ባህር ውስጥ እንዲዋኝ ያደርገዋል፡፡ ይቅርታ ጠይቀው የውርደት ካባን ተከናንበው እንዲወጡ የሚያደርገው የገዥው አካል ዲያብሎሳዊ ባህሪ አሁንም ቢሆን ለእስክንድር እና ለርዕዮት ክፍት ሆኖ እየጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ የጽናት ተምሳሌቶች ይጸየፉታል እንጅ አይፈልጉትም፡፡ እነዚህ የጽናት ባለሟሎች ባልሰሩት ጥፋት ላይ የሚቀርብላቸውን የይቅርታ ጥያቄ መሰረተ ቢስ በማለት እንዲህ የሚል መልዕከትን ያስተላልፋሉ፣ “ለአንድ ነጻ ለሆነ ወንድ ወይም ሴት ይቅርታ ልትሰጡ አትችሉም፣ የሞራል ስብዕናውም በፍጹም የላችሁም…የእናንተን ይቅርታ ተሸክማችሁ የትም መሄድ ትችላላችሁ፣ የእናንተ በቅጥፈት እና በሸፍጥ የተሞላ ተራ እና የወረደ የወሮበሎች ይቅርታ በአፍንጫው ይውጣ…!“

በአደጋ ምክንያት አካላቸውን ማንቀሳቀስ የማይችሉት እና ሽባ የሆኑት የሆሊውድ ፊልም ዋና አዘጋጅ የነበሩት ክርስቶፈር ሪቭ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ጀግና በርካታ ውጥንቅጥ መሰናክሎች በበዙበት ወቅት እራሱን ፈልጎ የሚያገኝ እና ለፍትሀዊ ዓላማው በጽናት የሚቆም እና ለተግባራዊነቱ ያለማሰለስ የሚታገል ተራ ግለሰብ ነው፡፡“ እስክንድር፣ ርዕዮት እና ሌሎችም ዜጎች መሰናክሎች እና ችግሮች በበዙበት ወቅት እራሳቸውን ፈልገው ያገኙ እና ለፍትሀዊ ዓላማ በጽናት በመቆም ለስኬታማነታቸው በቆራጥነት ያለማወላወል የሚታገሉ ተራ ዜጎች ናቸው፡፡ ለዚህም ነው እስክንድር፣ ርዕዮት እና ሌሎች የኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ሁሉ ለእኔ ጀግኖች እና ጀግኒቶች የሆኑት፡፡ ሁሉም ለዓላማቸው እና ለዓላማዎቻቸው ስኬታማነት ብቻ በጽናት የሚታገሉ ናቸው፡፡

ድፍረት ጀግናነት እና ጀግኒነት የተዋቀሩበት የሞራል ብቃት ውጤት ነው፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት ሮበርት ኤፍ ኬኔዲ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “የሞራል ድፍረት… በጣም ስቃይ የበዛባትን ወደ መልካም ነገር ለመለወጥ በለውጥ ፈላጊ ሰዎች አማካይነት የሚደረግ አንድ አስፈላጊ እና ዋና የጥራት መለኪያ ነገር ነው፡፡“ በእያንዳንዱ ጊዜ አንድ ሰው ለዓላማ ሲቆም፣ ወይም የሌሎችን ህይወት ለማሻሻል በጽናት ሲታገል ወይም ደግሞ ኢፍትሀዊነትን ሲዋጋ በተለያዩ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ኃይል እና ድፍረት ማዕከል በመሆን የጭቆና እና የብዝበዛ ስርዓትን መንግሎ በመጣል ለተስፋ መለምለም የመሰረት ድንጋይ የሚሆን ማዕበላዊ መልዕክት ሊያስተላልፍ/ልታስተላልፍ ይችላል/ትችላለች፡፡

እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና ሌሎችም ጀግኖች እና ጀግኒቶች የፖለቲካ እስረኞች እውነተኛ የሞራል ድፍረት አላቸው፡፡ እነዚህ የጽናት ቀንዲሎች ለፕሬስ ነጻነት እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት፣ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና ለሰብአዊ መበቶች መከበር በጽናት ቆመዋል፡፡ ለህግ የበላይነት መርሆዎች መከበር በጽናት ቆመዋል፡፡ ከህወሀት የወሮበላ ስብስብ ቡድን በተቃራኒው ቆመዋል፡፡ እነዚህ የነጻነት ቀንዲሎች 90 ሚሊዮን ለሚሆኑት ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖቻቸው ተስፋን የሚያለመልም ሂደትን በመተግበር በጽናት ቆመዋል፡፡

አሮጌውን ዓመት 2014ን ደወል በመደወል ስንሸኝ እና አዲሱን ዓመት 2015ን እየተቀበልን ባለንበት በአሁኑ ወቅት ሁሉም አንባቢዎቼ እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ወብሸት ታዬን፣ አንዷለም አራጌን፣ በቀለ ገርባን፣ አቡባከር አህመድን፣ የዞን 9 ጦማሪያንን ማለትም አጥናፍ ብርሀኔን፣ ዘላለም ክብረትን፣ በፈቃዱ ኃይሉን፣ አቤል ዋቤላን፣ ማህሌት ፋንታሁንን፣ ናትናኤል ፈለቀን፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስን፣ ተስፋለም ወልደየስን እና ኤዶም ካሳዬን ጨምሮ በማክበር እና በማመስገኑ እረገድ ለጀግንነታቸው እውቅና እንድንሰጥ እና እንድንዘክራቸው እንድትቀላቀሉኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡ እነዚህ ጀግኖች እና ጀግኒቶች በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ስም የለሾች፣ የማይታወቁ ትንታጎች፣ ያልተዘመረላቸው እና ያልተሰገደላቸው ጀግኖች እና ጀግኒቶች ለእኩልነት፣ ለፍትህ እና ለክብር ሲባል በዓለም ፍጹም አስቀያሚ በሆኑት በኢትዮጵያ የማጎሪያ እስር ቤቶች በመሰቃዬት ላይ ለሚገኙት ህዝቦች ጥቂት ምሳሌዎች ብቻ ናቸው፡፡ በአስከፊነቱ በሚታወቀው እና ቃሊቲ በመባል በሚጠራው እና በሌሎች በመለስ ዜናዊ የእስረኞች የማጎሪያ ቅርንጫፍ እስር ቤቶች በመላ ኢትዮጵያ በመማቀቅ ላይ ለሚገኙ ጀግኖች እና ጀግኒቶች በሙሉ ታላቅ ክብር እሰጣቸዋለሁ፡፡ ክብር እና ሞገስ ለእነርሱ ይሁኑ!

2ኛ) ርዕዮት ዓለሙ፡ አሁን በህይወት በሌሉት በመለስ ዜናዊ የሸፍጥ ወንጀል ፍብረካ የ14 ዓመታት እስራት የተፈረደባት እና የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል ለሆነችው የ36 ዓመቷ ወጣት ጀግኒት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ታላቅ ክብር አለኝ፡፡ ርዕዮት “የኢትዮጵያ እውነት ተናጋሪዋ እስረኛ” በመባል በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን አግኝታለች፡፡ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ተከራካሪ ኮሚቴ/Committee to Protect Journalists ባቀረበው ዘገባ መሰረት ርዕዮት የታሰረችው የህዳሴው ግድብ እየተባለ ለሚጠራው የግድብ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ እያደረገ ባለው የተሳሳተ አካሄድ በገዥው የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ጠንካራ ትችትን በመሰንዘሯ እና በወቅቱ የሊቢያ መሪ የነበሩት ኮሎኔል ሙአማር ጋዳፊ እና መለስ ዜናዊ አንድ ዓይነት ተመሳስሎ ያላቸው ከአንድ ባህር የተቀዱ አምባገነን መሪዎች ናቸው ብላ እውነትን አፍርጣ በመናገሯ ነበር ብሏል፡፡

3ኛ) ውብሸት ታዬ፡ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይን አጠቃላይ በሙስና መዘፈቅ አስመልክቶ በሚያዘጋጀው ጋዜጣ ትችት በማቅረቡ እና የጋዜጠኝነት የተመልካችነት ሙያውን በመስራቱ ብቻ በአምባገነኑ የወሮበላ ስብስብ ገዥ አካል የፍብረካ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት የ14 ዓመታት እስራት ተፈርዶበት በማጎሪያው እስር ቤት እየተሰቃዬ ያለውን ጀግና ጋዜጠኛ እና አርታኢ ውብሸት ታዬን ከልብ አከብረዋለሁ፡፡ የውብሸት ታዬ የ5 ዓመት ልጅ የፍትህ እንዲህ የሚሉት ጨዋነት የተሞላባቸው ቃላት በአዕምሮዬ ላይ ሁልጊዜ ያቃጭላሉ፣ “በማድግበት ጊዜ እንደ አባቴ ሁሉ እኔም ወደ እስር ቤት ነው የምሄደው ማለት ነው?“

4ኛ) አንዷለም አራጌ፡ ወደ ማሪያው እስር ቤት ከመጋዙ በፊት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ኮከብ የአመራር አባል የነበረውን አንዷለም አራጌን አከብረዋለሁ፡፡ አንዷለም አራጌ ከአዲሱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች እና የሲቪል ማህበረሰብ ወጣት ዝርያ መካከል የሚመደብ ሲሆን በህዝቡ ዘንድ በስፋት የሚከበር እና ተቀባይነት ያለው የጽናት ተምሳሌት ወጣት የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባል ነው፡፡ እ.ኤ.አ እስከ ሜይ 2010 መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ የህዝብ ድምጽ በማግኘት ምርጫውን በድል አድራጊነት አሸንፊያለሁ በማለት ባዶ ዲስኩር እስካሰሙበት የይስሙላ ሀገር አቀፍ ምርጫ ድረስ አንዷለም አራጌ ለዴሞክራሲ መገንባት እና ለህግ የበላይነት መከበር በጽናት በመቆም ሲታገል የቆየ ትንታግ ወጣት ነው፡፡ ግልጽ በሆነ ሀሳብ በመሞላት፣ ፍጹም የሆነ ምሁራዊ አንደበትን በመላበስ፣ ሊታመን ቀርቶ ሊታሰብ በማይችል ድፍረት የተሞላበት አካሄድ፣ በአስደማሚ አንደበተ ርትዑ ንግግር፣ እንደጦር በሚወጋ አመክኗዊ አቀራረቡ፣ ጉብዝና የተመላበት አቀራረብ፣ እውነታዎችን ፈልፍሎ በማውጣት እና ለእውነት በጽናት በመቆም የመለስ ዜናዊን የቴሌቪዥን የቅድመ ምርጫ ክርክር ተሰላፊ አሽከሮች በሚያቀርባቸው በእውነት ላይ የተመሰረቱ አመክኗዊ የክርክር ጭብጦች ባዶ መሆናቸውን ያጋለጠ እና መቅኖ ያሳጣ ጀግና የፖለቲካ ሰው መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ወጣት ነው፡፡ በእርግጠኝነት ይኸ ዓይነት ጽናትን የተላበሰ የትግል መስመር በቀጣይነትም ሊያዝ የሚገባው ጉዳይ ነው!

5ኛ) አብርሃ ደስታ፡ ወጣቱን፣ ፍርኃት የለሹን እና ልዩ ተሰጥኦ ያለውን ኢትዮጵያዊ ጦማሪ አብርሀም ደስታን ከልብ አከብራለሁ፡፡ አሁን በቅርቡ እ.ኤ.አ ጁላይ 7/2014 ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ከመጋዙ በፊት በእራሱ ማህበራዊ ድረገጽ በለቀቀው ጽሁፍ አብርሃ ህወሀት እራሱ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እንዲኖረው ጠንካራ የሆነ የክርክር ጭብጥ ሲያካሂድ ነበር፡፡ “የህወሀትን ካድሬዎች ጠላት ያለማድረግ ወይም ደግሞ በእኔ ድረገጽ እንዳይጠቀሙ ክልከላ የማላደርግበት ምክንያት የህወሀትን ምሁራዊ ክልከላ እና ኪሳራ ማወቅ ጠቃሚ እንደደሆነ ስለማምንበት ነው“ ብሎ ነበር፡፡ ሰዎች ምን ማለት እንደፈለጉ በማዳመጥ የአንድን ሰው የማሰብ እና ምክንያታዊነት ችሎታ መገምገም እንችላለን፡፡ የሚጽፉትን በማንበብ ማወቅ ይቻላል፡፡ ስለሆነም ካድሬዎቹ እንዲጽፉ እንፍቀድ፡፡ እራሳቸው ማን እና ምን እንደሆኑ እራሳቸውን እንዲገልጹ እንፍቀድ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ምን ለማለት እደፈለጉ የሚጽፉትን እናንብብላቸው፡፡ እነርሱንም በሚገባ እንወቃቸው፡፡ እነርሱን ድል ለማድረግ በመጀመሪያ እነርሱን ደህና አድርገን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ የእራስህን ጠላት ማወቅ ጠቃሚነቱ የጎላ ነው፡፡ ለዚህም ነው ይህንን ድርጊት ማድረግ ያለብን!”

6ኛ) የዞን 9 ጦማሪያን፡ የዞን 9 ወጣት ጀግኖች እና ጀግኒቶች ጦማሪያንን አከብራቸዋለሁ፣ አወድሳቸዋለሁ፡፡ እነዚህ ወጣት ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት በኮምፒውተር የመክፈቻ ቁልፎች በመጠቀም እና ለነጻነት ያላቸውን ቀናኢነት በግልጽ በማንጸባረቃቸው እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ በሚጠራው የአሸባሪ የጨለማ ቡድን ስብስብ ልብ ውስጥ ሽብር ለቀቁበት፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ወጣት ጦማሪያኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳ ከእስር እንዲለቀቁ በማሳሰብ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፣ “ስራቸውን በአግባቡ የሚሰሩትን ጦማሪያን እና ጋዜጠኞችን ለማጥቃት በሚል እኩይ ምግባር የጸረ ሽብር ህግ የሚባል የማደናገሪያ ህግ አዋጅ አድርጎ በማውጣት እና እራሳቸውን በዚያ ውስጥ በመወሸቅ በንጹሀን ዜጎች ላይ እያደረሱት ባለው ጥቃት በህገ መንግስቱ እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ዓለም አቀፋዊ መብት ላይ የተደረገ ዘለፋ ነው፡፡ “አጥናፍ ብርሀኔን፣ ዘላለም ክብረትን፣ በፈቃዱ ኃይሉን፣ አቤል ዋቤላን፣ ማህሌት ፋንታሁንን፣ ናትናኤል ፈለቀን፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስን፣ ተስፋዓለም ወልደየስን እና ኤዶም ካሳዬን ምርጥ የኢትዮጵያ ወጣት የነጻነት ታጋይ ቀንዲሎች በመሆናቸው አከብራቸዋለሁ፣ አወድሳቸዋለሁ፡፡

7ኛ) በቀለ ገርባ፣ አቡባከር አህመድ እና ሌሎች የነጻነት ታጋዮች፡ ስለእምነት ነጻነት፣ በሰላማዊ መንገድ ስለመሰብሰብ መደራጀት እንዲሁም ሀሳብን በነጻ ስለመግለጽ መብት በመናገራቸው እና በመጠየቃቸው ብቻ ወንጀል እንደሰሩ ተደርጎ እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ በሚጠራው አምባገነን የወሮበላ ስብስብ የጭቃ ጅራፍ እየተገረፉ እና እየተለበለቡ በመሰቃዬት ላይ የሚገኙትን በቀለ ገርባ፣ አቡባከር አህመድን እና ሌሎችንም ለነጻነት የሚታገሉ ትንታግ ኢትዮጵያውያን/ት ጀግኖች እና ጀግኒቶች ሁሉ ከልብ አከብራቸዋለሁ፣ አወድሳቸዋለሁ፡፡

በቀለ ገርባ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ ንቅናቄ/Oromo Federalist Democratic Movement እየተባለ የሚጠራው የፖለቲካ ድርጅት ምክትል ሊቀመንበር እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር የነበረ ነው፡፡ ለአሸባሪ ድርጅት ጽሁፍ አቅርቧል በሚል በቁጥጥር ስር እንዲውል ከተደረገ በኋላ የሸፍጥ ክስ ተመስርቶበት በዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት የ8 ዓመታት እስራት ተፈርዶበት በአሁኑ ጊዜ በማጎሪያው እስር ቤት በመማቀቅ ላይ የሚገኝ የነጻነት ታጋይ ነው፡፡ በቀለ ወያኔን ወደኋላ የሚንሸራተት እና ለማስተዳደርም አቅም ሳይኖረው በኃይል ለመግዛት ብቻ የተቀመጠ አስከፊ ድርጅት ነው የሚል ትችት ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡ በህወሀት የጭቆና አገዛዝ አራት ዓይነት የዜግነት መደቦች አሉ በሚል የክርክር ጭብጡን እንዲህ አቅርቧል፣ “የመጀመሪያው የዜግነት መደብ በስልጣን ላይ ያሉትን እና መሬትን እንደ ጉልት ሽንኩርት በመቸብቸብ ላይ የሚገኙትን ያጠቃልላል፡፡ የሁለተኛው የዜግነት ምድብ ደግሞ መሬት የሚወስዱትን እና የሚቀበሉትን ያካትታል፡፡ ሶስተኛው የዜጎች ምድብ ደግሞ እነዚህ ህገወጥ ድርጊቶች ሲፈጸሙ በመታዘብ የተመልካችንትን ሚና የሚጫወተው የህብረተሰብ ክፍል ነው ይላል፡፡ የመጨረሻው እና አራተኛው የዜግነት ምድብ ደግሞ ዜጎች በዜግነታቸው ይዘውት የነበረውን አንጡራ ይዞታቸው የሆነውን መሬታቸውን እና ቤቶቻቸውን ኃይልን በመጠቀም የሚወሰዱባቸው ፍትህ ያጡ እና የነጡ ዜጎችን ያካተተ ነው፡፡“ በቀለ ገርባ በቁጥጥር ስር ውሎ ወደማጎሪያው እስር ቤት ከመጋዙ አንድ ቀን በፊት ህወሀት የሸፍጥ የአሸባሪነት ክስ በመመስረት እርሱን ለማጥቃት የጥቃት ዱለታ እያደረገ እንደሆነ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተወካይ ግልጽ አድርጎ ነበር፡፡

አቡባከር አህመድ ጠንካራ የሆነ የእምነት ነጻነት መከበር ተሟጋች ታጋይ ነው፡፡ አቡባከር ጥያቄዎቹን በተቀነባበረ መልክ አዘጋጅቶ የህግ የበላይነት አክባሪ እና አቀንቀቃኛ መሆኑን እንዲህ በማለት ገልጾ ነበር፣ “ማንኛውንም አመራር አልተቃወምንም፡፡ እኛ ጥያቄ አድርገን ያቀረብነው ህገመንግስቱ ይከበር የሚል ብቻ ነው፡፡ ሁላችንም በአንድ ድምጽ እያልን ያለነው ህገመንግስቱን ማክበር አለባቸው የሚሉን አካሎች እራሳቸው በእርግጠኝነት ህገመንግስቱን ማክበር አለባቸው የሚል ነው፡፡“

ከሁሉም በላይ ስም ለሌላቸው፣ እውቅናን ላላገኙት፣ በግልጽ ላልታወቁት እና ላልተዘመረላቸው በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩት በኢትዮጵያ ለነጻነት ልዕልና፣ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር በጽናት በመቆም ለሚታገሉት ጀግኖች እና ጀግኒቶች ኢትዮጵያውያን/ት የፖለቲካ እስረኞች ታላቅ ክብር እሰጣለሁ፣ አወድሳቸዋለሁ፡፡ ለተቀደሰው ዓላማቸው በጽናት በመቆም ጋሬጣውን ሁሉ ችለው በድል አድራጊነት ነጻነትን ያቀዳጃሉ!

እስክንድር ነጋ ድፍረትን በተቀላቀለበት ሁኔታ “በጽናት እቆማለሁ” በማለት አውጇል፣

እ.ኤ.አ ሜይ 2013 ወንድሜ እና የተከበረው ጓደኛዬ እስክንድር ነጋ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፎ ነበር፣ “በጽናት እቆማለሁ!“ ያ ደብዳቤ በአስከፊነቱ ከሚታወቀው ከመለስ ዜናዊ የቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት በድብቅ ወጥቶ ነበር፡፡

“በጽናት እቆማለሁ!“ የሚለው ደብዳቤ 7 ቀላል አንቀጾችን/paragraphs አካትቶ የያዘ ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በውስጡ ይዞት የነበረው መልዕክት ለሰባት እንዲያውም ለሰባት ሰባ ዓመታት የሚያቆይ መልዕክትን አጠቃሎ የያዘ ነበር፡፡ “በጽናት እቆማለሁ!“ የሚለው ደብዳቤ ለፍትህ አልባው አገዛዝ አልታዘዝም፣ አላጎበድድም፣ አልሰግድም፣ ጸጥ ብዬ አልገዛም የሚል ደፋርነትን የተላበሰ ደብዳቤ ነበር፡፡ ይህ ደብዳቤ በተስፋ የተሞላ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ስሜትን የሚኮረኩር እና የነጻነት ትግሉን ሆ ብለን እንድንቀላቀል የሚገፋፋ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ነብያዊ መንፈስን የተላበሰ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ከልብ ውስጥ እጅግ በጣም ዘልቆ የተጻፈ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ በስሜታዊነት ሳይሆን ጥልቀት ባለው ሁኔታ የስነ ልቦናዊ የአስተሳሰብ ሂደቶችን ባካተተ እና ምክንያታዊነትን አጉልቶ በማሳየት የተዘጋጀ የምሁራዊ አንደበት መግለጫ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ለቤተሰቡ፣ ለባለቤቱ እና ለልጁ በቀጥታ እንዲደርስ ሆኖ የተዘጋጀ ደብዳቤ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ እንዲደርስ ተብሎ የተጻፋ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሁሉ እንዲደርስ ተብሎ የተጻፈ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ለመጭዎቹ የኢትዮጵያ ትውልዶች በታሪክ የሚቀመጥ ተብሎ የተጻፈ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ ለነጻነት እና ለሰው ልጆች ክብር ሲባል የተጻፈ ነው፡፡ ይህ ደብዳቤ የአንድን ሰው የነጻነት ጥያቄ ጩኸት፣ አንድ ሰው የወለደውን ልጅ ማሳደግ እንዲችል ነጻ የመሆን መብት እንዲኖረው እንዲሁም አንድ ሰው ከባለቤቱ እና ከቤተሰቡ ጋር ነጻ ሆኖ የመኖር መብት እንዳለው ለማሳወቅ የተጻፈ ነው፡፡ ይህ ድብዳቤ ስለእያንዳንዱ ዜጋ መብት እና እያንዳንዱም ዜጋ በመረጠው ሙያ ሀገሩን የማገልገል መብት እንዳለው ለማሳወቅ የተጻፈ ነው፡፡ በመጨረሻም “በጽናት እቆማለሁ!“ አንድ ነገርን በውል ያመላክታል፡ እውነትን፡፡ በጽናት መቆም ማለት ስለእውነት እና ስለእውነት ብቻ በመቆም አንድን ሰው ነጻ ያወጣል ማለት ነው፡፡

ለጥቂት ጊዜ ፍቀዱልኝ እና የሚሰማኝን የእራሴን እምነት ልግለጽ፡፡ “በጽናት እቆማለሁ!“ የሚለውን ደብዳቤ ደጋግሜ ብዙ ጊዜ አንብቤዋለሁ፡፡ በአዕምሮዬ ላይ ያጫረውን ጥርጣሬ ለማስወገድ እንዲቻል በማለት ይህንን ደብዳቤ አንብቤዋለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ጥርጣሬዎቼ ሁሉ ሙጥጥ ጥርግ ብለው ጠፉ፡፡ ከዚያም በጽናት ቆምኩ፡፡ ወደ ነጻነት የሚወስደው መንገድ ረዥም፣ ብዙ ውጣ ውረድ ያለበት እና እጅግ በጣም አድካሚ እንደሆነ በተሰበረ ልብ ባለሁበት ወቅት ነበር ደብዳቤውን ያነበብኩት፡፡ በእኔ ፍጹም የሆነ እምነት የቱንም ያህል ለነጻነት የሚደረግ ጉዞ ረዥም አይደለም፡፡ ለሰኞ ትችቴ “ርዕስ የሚሆን ቃላትን ባጣሁበት ወቅት“ ነበር የእስክንድርን ደብዳቤ ያነበብኩት

ምንም የምለው ነገር የለም፡፡ ወዲያውኑ ሲኒየ እስከሚሞላ ድረስ በአዲስ ሀሳብ ተጥለቀለቅሁ፡፡ በየጊዜው ስለሁኔታው ባሰብኩ ቁጥር የእስክንድርን ደብዳቤ አነባለሁ እናም ስለሁኔታው አስባለሁ፡፡ የእስክንድር ድምጽ ጆሮ እያላቸው ለመስማት ለማይፈልጉት ወገኖች የጸጥታ ድምጽ ሊሆን ይችላል፡፡ ለእኔ የእርሱ ጸጥታ የሰፈነበት “በጽናት እቆማለሁ!“ የሚለው ድምጽ በየዕለቱ “በጽናት እቆማለሁ!“ “በጽናት እቆማለሁ!“ እያለ ደጋግሞ በህሊናዬ ያቃጭልብኛል፡፡

ለመሆኑ እስክንድር “በጽናት እቆማለሁ!“ ሲል ምን ማለቱ ነው? በቀላል አነጋገር በመለስ ዜናዊ የቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት ቀን በቀን በእስር ላይ ሆኘ እገኛለሁ ለማለት ፈልጎ ነውን? እንደ እስክንድር፣ ርዕዮት እና ሌሎችም የነጻነት ታጋዮች የመሳሰሉ ሰዎች “በጽናት እቆማለሁ!“ ሲሉ በእርግጠኝነት ምን ለማለት ፈልገው ነው?

“በጽናት እቆማለሁ!“ በማለት እስክንድር ሲጽፍ ምን ለማለት እንደፈለገ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ወይም ጠይቆ ለመገንዘብ አስፈላጊ ነው ብዬ አላምንም፡፡ የእርሱ ቃላት ለእኔ ከምንም በላይ ጎላ ብለው የተጻፉ እና ግልጽ መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉ ናቸው፡፡ እስክንድር ማለት የፈለገው ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በአንድ ወቅት “ጽናት” በሚል ርዕስ እንደጻፉት ለማለት ፈልጎ ነው፡፡ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ሰዎች ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግን ለምን ያህል ጊዜ ነው በጽናት የምንቆመው? ነጻነታችንን ለመቀዳጀት ምን ያህል ጊዜ መቆየት አለብን?” በማለት ይጠይቁ ነበር፡፡ (በእርግጥ ህዝቦች ከዚያ የበለጠ እንዲህ የሚል ትርጉም ያለው ጥያቄ መጠየቅ ይችሉ ነበር፣ “እንደዚህ ዓይነቱን ዋጋቢስ የሆነ ስርዓት የምንታገሰው እስከ ምን ያህል ጊዜ ነው?”) ዶ/ር ማርቲን ሉተር “ሩቅ አይሆንም” በማለት ነግረዋቸው ነበር፡፡ ለሌሎችም ጥያቄዎች አጭር እና ተገቢውን መልስ እንዲህ በማለት ሲሰጡ ነበር፡

በአሁኑ ጊዜ “ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?” የሚል ጥያቄ እንደምትጠይቁ በሚገባ እገነዘባለሁ…

በዛሬው ዕለት ከሰዓት በኋላ ልላችሁ እችላለሁ አጋጣሚው ምን ያህል አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ሰዓቱ ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም ጊዜው በጣም ረዥም አይሆንም ምክንያቱም እውነት መሬት ከነካች በኋላ እንደገና ትነሳለችና፡፡

ምን ያህል ጊዜ? ረዥም ጊዜ አይሆንም ምክንያቱም የቱንም ዓይነት ውሸት እና ቅጥፈት ለዘላለም ሊኖር አይችልምና፡፡

እኮ ለምን ያህል ጊዜ? ረዥም ጊዜ አይሆንም ምክንያቱም የዘራኸውን ታጭዳለህና…

እኮ ለምን ያህል ጊዜ እኮ ነው የምንለው? ረዥም ጊዜ አይሆንም ምክንያቱም የሞራል ስብዕና ጠርዙ ረዥም ነውና፣ ሆኖም ግን ወደ ፍትህ ዘንበል ይላል፡፡

እስክንድር፣ ርዕዮት እና ሌሎች የነጻነት ታጋዮች ለምን ያህል ጊዜ ነው በጽናት የሚቆሙት? ኢትዮጵያ ለምን ያህል ጊዜ በጽናት መቆም አለባት? ረዥም ጊዜ አይሆንም፣ ሆኖም ግን ተስፋየለሽ ሰዓት ቢሆንም ቅሉ ረዥም አይሆንም ምክንያቱም ህወሀት የዘራውን ያጭዳልና፡፡ ድልአድራጊነት ጽናቱ ላላቸው ሰዎች ሁሉ የተረጋገጠ ነው፡፡

እስክንድር በደብዳቤው እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር፣ “ግለሰቦች ሊቀጡ ይችላሉ፣ ሊሰቃዩ ይችላሉ (ኦ ልጀን እንዴት እዳጣሁት እና እንደናፈቀኝ) ከዚህም በላይ ሊገደሉ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ዴሞክራሲ ሊወገድ የማይችል የሰብአዊነት ዕጣፈንታ ነው፡፡ ዴሞክራሲን ማዘግየት ይቻል ይሆናል ሆኖም ግን ማሸነፍ አይቻልም፡፡“

ፍትህን ማዘግዬት ይቻላል፣ ሆኖም ግን በፍጹም ማሸነፍ አይቻልም፡፡ በሰብአዊ መብት ላይ ወንጀልን የፈጸሙ ወንጀለኞች በእመቤት በፍህ ላይ ያላግጣሉ፣ አፍንጫቸውን ይነፋሉ፣ አመልካች ጣታቸውንም ይቀስራሉ፣ ሆኖም ግን እመቤት ፍትህ በእጇ ላይ ምን እንዳለ እንጅ ምን ይዛ እንዳለች ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የሰው ልጅ ታሪክ የመጨረሻ መቆሚያ ጠርዙ የሰው ልጆች የሰብአዊ መብት ዕድል የሚከበርበት፣ የነጻነት እና ዴሞክራሲ መኖር፣ ከጭቆና ነጻ የመሆን፣ ከደናቁርት ወሮበላ ዘራፊ አምባገነኖች መላቀቅ፣ አንድ ሰው ከአምላኩ የተሰጡትን ተፈጥሯዊ የማሰብ፣ የመፍጠር እና ነጻ የሆኖ ሰብአዊ መብቶች ማከበር ነው፡፡

እስክንድር ለልጁ ያለውን ሀሳብ እንዲህ በማለት ገልጿል፣ “ኦ ልጀን እዴት እዳጣሁት እና እንደናፈቀኝ“ በማለት የተሰማውን ስቃይ አሳውቋል፡፡ የልጁ ስም ናፍቆት የሚባል ሲሆን ትርጉሙም “አንድን ሰው በመለየት ማጣት” የሚል ነው፡፡ ምን ዓይነት የሚገርም እና ነብያዊ የስም አወጣጥ ዘዴ ነው! ናፍቆት እ.ኤ.አ በ2005 ወላጆቹ በእስር ቤት ያለምንም ወንጀል 16 ወራት ታስረው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጎ ከተፈቱበት በመለስ ዜናዊ የቃሊቲ እስር ቤት ነው የተወለደው፡፡ አረመኔው እና ጨካኙ መለስ ዜናዊ ናፍቆት ገና ያልዳበረ ህጻን በነበረበት ጊዜ የህክምና እገዛ እንዳያገኝ በራሱ ትዕዛዝ እገዳ ጥለው ነበር፡፡ የመለስን ጣልቃገብነት በተመለከተ ያለው ማስረጃ አወዛጋቢ አይደለም፡፡ መለስ እስክንድርን እና ሰርክዓለምን ለመበቀል ሲል የቀናት እድሜ ብቻ የነበረውን ህጻን ልጃቸውን ለመግደል በጽናት ወስኖ ነበር፡፡ መለስ አስክንድርን እና ሰርክዓለምን ህጻን ልጃቸው በእስር ቤት ውስጥ እንዲሞት በማድረግ በሀዘን እንዲገረፉ ለማድረግ ፈልጎ ነበር፡፡ መለስ ጠላቶቸ ናቸው የሚለዉን ሰዎች በአደባባይ በህዝብ ፊት እንዲዋረዱ ማድረግ ብቻ ደስ የሚያሰኘው ሰው ነበር። ሆኖም ግን ከህዝብ እይታ ውጭም ቢሆን ጠላቴ የሚለዉን ንጹሀን ዜጎች ሲሰቃዩ እና መከራ ሲደርስባቸው ማየት ከምንም በላይ ደስ ያሰኘው ነበር ፡፡ እሱን በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች ለዚህ ምስክርነት ይሰጣሉ፡፡ እስክንድር እና ሰርክዓለም በመጨረሻ በጻፉት ደብዳቤ ህጻን ልጃቸው በእግዚአብሄር ታምር ከሞት እንደተረፈ ይፋ አድርገዋል፡፡

አሁን በህይወት የሌሉት መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 2010 በኒዮርክ ከተማ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በመገኘት ንግግር እንዲያደርጉ ፕሮግራም ተይዞላቸው በነበረበት ወቅት እስክንድር እና ባለቤቱ ሰርክዓለም (በእራሷ መብት እና በምታሳየው ደፋር የጋዜጠኝነት ባህሪ እ.ኤ.አ በ2012 ከሴቶች የግንኙነት ተቋም/Women’s Media Foundation የጋዜጠኝነት ሽልማት አሸናፊ የሆነች) ሰውዬው በዩነቨርስቲው ተገኝቶ ንግግር እንዳያደርግ የሚቃወም ደብዳቤ ለዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽፈው ነበር፡፡ የተቃውሟቸውን መሰረትም እንዲህ በማለት ግልጽ አድርገው ነበር፣

ህጻኑ በሚወለድበት ጊዜ ከሚጠበቀው የክብደት መጠን በእጅጉ የቀነሰ መሆኑ ይኸውም ሊሆን የቻለበት ምክንያት ሰርካለም በአፍሪካ በአስከፊነታቸው ከሚታወቁት እስር ቤቶች መካከል ታስራ በመቆየቷ ምክንያት በአካል እና በስነልቦና የተጎዳች በመሆኑ የህጻኑን ህይወት ለማዳን ህይወት አድን የህጻናት ማቆያ የሚሆን ኢንኩቤተር በመጠቀም ኃላፊነት በጎደላቸው እና ምንም ዓይነት ደንታ በማይሰማቸው የበቀል መሪዎች ለሞት ተፈርዶበት የነበረው ህጻን በእስር ቤት ዶክተሮች ጥረት አዲስ የተወለደው ህጻን በእግዚአብሄር ታምር ሊድን ችሏል፡፡ (ክብር ምስጋና ለእግዚአብሄር ይሁን)፡፡

ሸክስፒር እንዲህ በማለት ጽፈዋል፣ “ሰዎች በህይወት ዘመናቸው ይኖሯቸው የነበሩት ጭራቃዊነቶች በህይወት ካለፉ በኋላም ይኖራሉ…“መለስ ከሰራቸው በርካታ ጭራቃዊነት ድርጊቶች መካከል አንዱ በአሁኑ ወቅት መለስ ከሞተ ከሁለት ዓመታት በኋላም በእስክንድር፣ ሰርክዓለም እና በናፍቆት መብት ድፍጠጣ ላይ የሰሯቸው ግፎች አሁንም እንዳሉ ናቸው፡፡ መለስ በሞተ ጊዜ የሱ ጭራቃዊ ድርጊታቸው የመጥፎዎች ሁሉ ተምሳሌት ሆኖ ጣላቴ ናቸው ብለው የሚያስቧቸውን ወገኖች ለማጥፋት እና የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ከእባብ በበለጠ መልኩ በመተጣጠፍ አደገኛ ሁኔታን የሚፈጥር ሆኖ ቀጥሏል፡፡

እስክንድር እና ቤተሰቡ በእግዚአብሄር ኃይል ጽናቱን ሰጥቷቸዋል፡፡ መለስ የአምላክን ቁጣ ሊያመልጡ በፍጹም ሊያመልጡ አልቻሉም፡፡ እርግጠኛ ነኝ እስክንድር እንዲህ ይላል፣ “እራስህ ለመበቀል አታስብ፣ ሁሉንም ነገር ለአምላክ ቁጣ ብቻ ተወው ተብሎ እንደተጻፈው እራሱ ይበቀልልሀል፣ በቀል የእኔ ነው፣ ጌታ የሀጢያት ደመወዝን እኔ እከፍላለሁ ብሏልና፡፡“ የአምላክ ቁጣ በመለስ የበሰበሰው እና እየተፍረከረከ ባለው ስርዓት ላይ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡ እስክንድር አምላክ ሲፈቅድ ቤተሰቡን ሰብስቦ በሰላም እንደሚኖር ጥርጥር የለኝም፡፡

እስክንድር በደብዳቤው ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስፍሮ ይገኛል፣ “የዳኝነት ሂደት ስርዓት በሌለበት፣ መከራ በተንሰራፋበት ዴሞክራሲ ባህሪ እና ጠቃሚነቱን ያጣ ነብስ የሌለው ባዶ ነገር ነው፡፡ እጣፈንታዬን እቀበላለሁ፣ እንዲያውም መልካም ዕድልን እንዳገኘ ሰው እታቀፈዋለሁ፡፡ በቅማሎች መሀከል ቢሆንም በእስር ቤት በሰላም እንቅልፌን እተኛለሁ፡፡ የእኔ አሳሪዎች ግን በሞቀ አልጋ ላይ ሚስቶቻቸውን አቅፈው በቤታቸው የሚተኙ ቢሆንም እንደ እኔ ሰላማቸው የተረጋጋ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም፡፡“

በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው እግንዲህ ኔልሰን ማንዴላ ዕጣ ፈንታቸውን ተቀብለው በአፓርታይድ የዘረኝነት ስርዓት ለ27 ዓመታት በጽናት ታስረው በጽናት ለድል የበቁት፡፡ እንደማንዴላ እስክንድርም በማጎሪያው እስር ቤት ነጻነት ይሰማዋል፣ እናም ሰላሙ የተረጋጋ ነው፡፡ እስክንድር እንደ ማንዴላ የማይበገር ነብስ ያለው መሆኑን አሳይቷል፡፡ እንደ ማንዴላ የእስክንድር እራስ ደምቷል ሆኖም ግን አላጎነበሰም፡፡ እስክንድር በምንም ዓይነት ሁኔታ አልፈራም፡፡ እስክንድር የእራሱ ዕጣፈንታ ጌታ ነው፡፡ እስክንድር ማንዴላ እንዳደረጉት ሁሉ እንዲህ በሚሉት በዊሊያም ኤርነስት ሄንለይ ግጥሞች በመሳሳት አይበገሬነቱን አስመስክሯል፣

እኔን በሚሸፍን በድቅድቅ ጨለማ፣ ጥቁር የተናቀ ወድቆ የገለማ፣

ስብዕናውን ያጣ ከዋልታ እስከ ዋልታ፣ በዘረኛ ወጥመድ ተይዞ እሚፈታ፡፡

ለማይበገረው ደንዳናው ጽናቴ፣ አምላክን ላማስግን ሳለሁ በህይወቴ፡፡

በጭካኔው ማዕበል በአደገኛው ቦታ፣ አልንፈራገጥም አልጮህ በዝምታ፡፡

በእስር ቤት መታጎር ሆኖ ዕጣፈንታዬ፣ ጭንቅላቴ መድማት ቢሆን አበሳዬ፣

ካመንኩበት ጽናት ወይ ፍንክች ወይ ዝንፍ፣ ምድር ቢገለበጥ ሰማይ ቢያወርድ ዶፍ፡፡

ጭካኔ ቢበዛ ስቃይ ቢጠነዛም፣ ከቆምኩበት ጽናት አላጎነብስም፣

እግሮቸም አይርዱ እጀቸም አይዝሉ፣ ዓይኖቸም ፈጠዋል ሳይንቀዋለሉ፣

ጆሮዬም ይሰማል፣ ምላሴም ይቀምሳል፣ አፍንጫዬ ዋናው ነገርን ያሸታል፡፡

ስለዚህ ምን ገዶኝ ከዓላማዬ ጽናት ከቶ ማን አግዶኝ?

ከዚህ ከሰቆቃ ከዋይታ እና ከእንባ፣ ከዚህ ከጭካኔ ከጨለማው አንባ፣

ፍትህ ትፈልቃለች በፍቅር ተውባ፣ ነጻነት ይመጣል ከግፈኞች ጀርባ፣

እናም ለዘመናት የተከማቸው ግፍ፣ እኔን ሳያሸብር ይታየኛል ሲረግፍ፡፡

የማስገቢያው በሩ ይጣመም ይዘርጋ፣

የሸፍጥ ክስ ይምጣ እየተወራጋ፣

ቅጣቱ ይቆለል ይምጣ እየተላጋ፣

ለእኔ ጉዳይ አይደል ከቶ የለው ዋጋ፡፡

እንግዲህ እወቁኝ ከቶም እንዳትንቁኝ፣

ለዓላማዬ ጽናት ነብሴን የሰጠሁ ነኝ፡፡

ለዓላማዬ ጽናት ምንም ሳልረታ፣

ለዕጣ ፈንታ አዛዡ እሆናለሁ ጌታ፣

ከጌታ በመለስ ከፍጥረት ኃያሉ፣

ለነብሴ ዋስትና በምድር ሳር ቅጠሉ፣

አድራጊ ፈጣሪው እኔ ነኝ ሻምበሉ፡፡

ረዥም እድሜ ለእስክንድር፣ ለአይበገሬው አንበሳ!

ቪቫ እስክንድር አይበገሬው!

እስክንድር በደብዳቤው እንዲህ በማለት ጽፏል፣ “መንግስት በሚከተለው የፖለቲካ የሞራል ስብዕና ኪሳራ ምክንያት በተደጋጋሚ እና በማያቋርጥ ሁኔታ ሲዋሽ ቆይቷል፡፡ ሁሉም የታሪክ ታላላቅ ወንጀሎች የምንረሳቸው ካልሆነ በስተቀር በጊዚያቸው በነበረው የሞራል ስብዕና ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡“

እስክንድር ስለምን እየጻፈ እንደሆነ በሚገባ አውቃለሁ፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 “በፖሊስ መንግስት ሸፍጠኞች፣ ዓቃብያነ ህጎች እና ዳኞች የመሰረት ድንጋዮች“ በሚል ርዕስ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀሁት ባለ32 ገጾች ትንታኔ ትችት በወያኔ የዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት ላይ ሸንቋጭ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ ያ ትችት እ.ኤ.አ በ2005 የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት ታስረው ሲማቅቁ በነበሩት ወደ 130 ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ ዋና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ወትዋቾች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ወገኖች ላይ ተመስርቶ በነበረው የክስ ሂደት ላይ ሙያዊ የሆነ ትንታኔ በመስጠት ዓላማ ላይ ያነጣጠረ ነበር፡፡

የወያኔ የታዕይታ የፍርድ ሂደት ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማታለል የተደረገ የመድረክ ተውኔት ከመሆን ዕጣፈንታ የዘለለ አልነበረም፡፡ ያ ፍርድ ቤት ግልጽ በሆነ መልኩ የተዋረደ፣ በስብዕና ጥንካሪያቸው ሳይሆን በታዛዥ እና ሎሌነታቸው እየተመረጡ ለታዕይታ የተቋቋመ ችሎት ነበር፡፡ ያ ፍርድ ቤት የሸፍጥ ክስ እንዲመለከት፣ አጭበርባሪ ዓቃብያነ ህጎች የተመደቡለት፣ ምንም ዓይነት የፍትህ ስርዓት ሂደትን ያልተከተለ እና ውጤቱ ምን እንደሚሆን አስቀድሞ የታወቀ ይኸውም አንድ ነገርን ብቻ ለማድረግ ማለትም ፍትህን በግልጽ በአደባባይ ለማጨናገፍ የተቋቋመ የግፈኞች የይስሙላ የፍርድ ቤት ችሎት ነበር፡፡ የህወሀት የዝንጀሮ የይስሙላ ፍርድ ቤት እስከ አሁንም ድረስ አልተቀየረም:: እንግዲህ እስክንድር “መንግስት በፍትህ አደባባይ በህዝብ ፊት እየዋሸ ነው ያለው” ሲል ሌላ ሳይሆን ይህንን ማለቱ ነው …” የመንግስት ውሸት በዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት ችሎት መድረክ ላይ እውነትን አፈር ድሜ እያስበላ፣ የሰብአዊ መብቶች በመንግስት ስህተቶች እና ቅጥፈቶች እየተደፈጠጡ ያሉበት ሁኔታ ነው ዛሬ በኢትዮጵያ ያለው ቀውስ፡፡ “በአሁኑ ወቅት ያለው ቀውስ” በሚል ርዕስ በጀምስ ሩሴል ሎዌል ግጥሞች ውስጥ እንዲህ የሚሉትን የግጥም ስንኞች እንመልከት፣ “ውሸት ደረቱን ግልብጦ በችሎት ወንበሩ ላይ እና በስህተት እግሩን አንፈራጥጦ በዙፋኑ ላይ ተቀምጧል”:

ለነጻነት ተብሎ ተግባር ሲከናወን፣ በቆራጡ ትግል እውነት እውን ሲሆን፣

ነቢያዊ ደስታ ስናገኝ ሀሴትን፣ በምስራቅ በምዕራብ ስንል ዘብነን ዘብነን፣

ጽናትን ሰንቀን ከመከራው ጽዋ ከግፉ ተላቀን፣ ድል አድራጊ ሆነን በሲቃ ተውጠን፡፡

ደንታቢስ ቢመስለው ታላቁ ተበቃይ፣

ታሪክ ይዘግባል በምድር በሰማይ፣

በጽናት መቆም ነው ለወሳኙ ትግል፣

በበከተው ስርዓት ለመጎናጸፍ ድል

እውነት ለዘላለም በመስቀያ መድረክ፤

ውሸት ለዘላለም በዙፋኑ መድረክ፣

ሆነው አይቀጥሉም አያብልም ታሪክ፡፡

እናም ያ መስቀያ ይጠፋል ይበናል፣

ከጀርባው ባዘለው ጨለማ ማዕበል፡፡

በስውር ከሚያየው ከአምላክ ተነጥሎ፣

ደባን የሚፈጽም እውነት አስመስሎ፣

የአምላክ ሰይፍ ሲመዘዝ ሊሆን አከንባሎ፣

የት ይገባ ይሆን ያ ግም ዘባትሎ?

ወሮበላ ዘራፊዎች ለዘላለም በዙፋን ተኮፍሰው ሊኖሩ ይችላሉን? በፍጹም!

እስክንድር በደብዳቤው እንዲህ በማለት ጽፏል፣ “አሰልችው እና የተለመደው የሸፍጥ የፍርድ ሂደት ምንም ዓይነት ፋይዳ ያለው ለውጥ አያመጣም፡፡ ሆኖም ግን በአንድ ወቅት ክርስቶፎር ሂቸንስ እንደገለጹት የሚያስከትለው ‘የኢምክንያታዊነት ስብስብ እና የንቀት ደረጃን ከማሳየት ያለፈ እርባና የለውም‘“ ለማለት የተፈለገው ይህ ጉዳይ ያለጥፋቱ በግፍ ታስሮ እንደነበረው ንጹህ ፈረንሳያዊ ሻምበል እንደ ድሬይፈስ ያለ የኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ፈታኘኝ ወቅት ብቻ ነው የበከተ እና የበሰበሰውን አምባገነናዊ ስርዓት ገርስሶ መጣል የሚያስፈልገው እንጅ ጥቃቅን ነገሮችን በማከናወን ታጋሽነትን የማራዘም ጨዋታን በመጫወት ከቶውንም ሊሆን አይችልም፡፡

እስክንድር የፈረንሳይ ጦር አዛዥ እንደነበሩት እንደ ሻምበል አልፍሬድ ድሬይፈስ በሀሰት ክስ ተመስርቶባቸው እ.ኤ.አ በ1894 በሚስጥራዊ የጦር ፍርድ ቤት በሀገር ክህደት ወንጀል በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸው እንደነበሩት ንጹህ ዜጋ ማለት ነው፡፡ የፈረንሳይ ዕውቅ ደራሲ የነበሩት ኢሚሌ ዞላ ታዋቂ ደብዳቢያቸውን በብዕራቸው በመጻፍ እንዲህ ብለው ነበር፣ “አይሁዶችን ለማግለል ሲባል እና በሀሰት ወንጅሎ ጥቃት ለመሰንዘር በመገፋፋት በድሬይፈስ ላይ የሀሰት ክስ በመመስረቱ ምክንያት የፈረንሳይን ፕሬዚዳንት እና የፈረንሳይን መንግስት ከስሻለሁ፡፡“ ድሬይፈስ ምንም ሳያቅማሙ እና ሳይሸበሩ በጽናት ቆመው በመከራከራቸው በመጨረሻ ከሀሰት ውንጀላው ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆነው ተሰናብተዋል፡፡

በጊዜ ሂደት እስክንድርም እንደ ሻምበል ድሬይፈስ ነጻ ሆኖ ይወጣል፡፡ እራሱ በሰራቸው በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ጉሮሮውን ታንቆ ባለው አምባገነን እስክንድር በሀሰት የፍብረካ ወንጀል በሀገር መክዳት በሚል የሸፍጥ ውንጀላ ታስሮ በማጎሪያው እስር ቤት ውስጥ በመማቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

እስክንድር የጽናት ተምሳሌት! በግፈኞች ቢከሰስም በጽናት የቆመ ጀግና!

እስክንድር በደብዳቤው እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር፣ “…እ.ኤ.አ በ1930ዎቹ ስታሊኒኒያዊ አምባገነኖች ሚስጥር እንድታወጣ ለማስገደድ አልነበረም የሚገርፉህ እና የሚያሰቃዩህ፣ ሆኖም ግን የሀሰት መግለጫ ለማውጣት እንዲመቻቸው በሚስጥር ህገወጥ ነገር ለመስራት ተባባሪ እንድትሆን ነበር ለማግባባት የሚሞክሩት፡፡ ለዚህም ነው እንግዲህ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ቀውስ ዋና መሰረት ሆኖ የሚታየው፡፡ እንደዚሁም 30 ዓይነት ተደጋጋሚ ድፍረት የተሞላባቸው የፍርድ ሂደቶች ቢካሄዱም ፍትህን ከማዛባት ባለፈ ነጻነትን ሊያጎናጽፍ እንደማይችል ባለስልጣኖች አልተረዱትም፣ በዚህም መሰረት ግፈኞች ከታሪክ ትምህርትን አልቀሰሙም፣ እንዲያውም በታሪክ ተጽፍ ከተያዘው ስሀተት በበለጠ መልኩ ወንጀልን በመስራት በሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀል ባህር ውስጥ እስከ አንገታቸው ድረስ ሰምጠው በመዋኘት ላይ ይገኛሉ፡፡“

ስታሊን በአንድ ወቅት የአንድ ሰው መሞት አሰቃቂ ነው፣ የሚሊዮኖች ሞት ግን የቁጥር ጉዳይ ነው ብለው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ስታሊን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦቻቸውን እራሳቸው አልገደሉም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ጻጥ ካላሉ እና የሀሰት ውንጀላን ለመፈብረክ በሚስጥር የሚተባበሩ ሰዎች እስከሌሉ ድረስ ጭራቃዊነት ድርጊት በንጹሀን ዜጎች ላይ በፍጹም አይፈጸምም፡፡ ጭራቃዊነት ድርጊት ሲፈጸም እየተመለከቱ እና ይኸ ለእኔ ጉዳዬ አይደለም እያሉ በወገኖቻቸው ስቃይ ላይ የሚሳለቁ ህሊናየለሽ ወገኖች ሁሉ ለሸፍጥ ተግባር በሚስጥር ለሚሰሩ መሰሪ ጭራቃዊ ተግባሮች ሁሉ ተባባሪዎች መሆናቸውን መገንዘብ አለባቸው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ቢዝነስ እና የፖለቲካ ተግባራት መጣመር የለባቸውም የሚሉ ወገኖች ሁሉ በሚስጥር ለሚተገበሩ የጭራቃዊነት ተግባራት ተባባሪዎች ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጭራቃዊነት ድርጊት ሲፈጸም እየተመለከቱ አላየሁም ብሎ መካድ ከጭራቃነት ጋር በሚስጥር የሸፍጥ ዱለታ ተባባሪ እንደሆኑ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

እንደዚሁም ደግሞ ጭራቃዊ ድርጊትን ከማውገዝ እና ከመታገል አልፎ ይቅርታ መጠየቅ እና ጭራቃዊነትን ለተፈጻሚነቱ ትክክለኛነት ለመስበክ መሞከር ከጭራቃዊነት ጋር በሚስጥር ተባብሮ በንጹሀን ዜጎች ላይ ደባን የመስራት ተባባሪነት መሆኑን በውል ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ እንደዚሁም ሆን ብለው ያላወቁ መስለው ከጭራቃዊነት ድርጊት ሲፈጸም ዝም ብለው የሚመለከቱ ሁሉ በሚስጥር ጭራቃዊ ድርጊትን ለመፈጸም ተባባሪዎች ሆነው እንደቀረቡ ሊያውቁ ይገባል፡፡ ከዚህም በላይ “ምንም ዓይነት ጭራቃዊነት አላየሁም፣ ምንም ዓይነት ጭራቃዊነት አልሰማሁም፣ ምንም ዓይነት ጭራቃዊነት አልተናገርኩም” የሚሉ መርሆዎችን እያራመዱ ሰው ሳይሆኑ እውነተኛ ሰው መስለው የሚኖሩ አስመሳዮች ሁሉ በሚስጥር ጭራቃዊነት ድርጊትን እየፈጸሙ እንዳሉ በውል ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

እስከንድር በደብዳቤው ላይ እንዲህ በማለት ጽፏል፡ “ ለምንድን ነው የቀረው ዓለም ህዝብ ጉዳዩ የሚሆነው? ይህንን ጉዳይ በማስመልከት ሆራስ በተሻለ መልክ እንዲህ በማለት ገልጸውት ነበር፣ ‘ስሙን ብቻ ቀይር፣ እናም ይህ ታሪክ የአንተም ታሪክ ይሆናል‘ ምን ጊዜም ፍትህ ሲጓደል የእኛ የሰብአዊ ፍጡርነት ስብዕናም አብሮ ይጎድላል፡፡“

እስክንድር ከሮማን ታላላቅ ገጣሚዎች አንዱ የሆኑትን እና በተስፋ በተሞሉ ቃላታቸው ታዋቂ የሆኑትን የሆራስን አባባል ወስዶ ተጠቅሞበታል፡፡ እስክንድር የናዚን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ የጀርመን ምሁራን ዝምታን መምረጣቸውን አስመልክቶ ፓስተር ማርቲን ኒሞለር ፍርሀታቸውን የገለጹበትን በመጥቀስ ጩኸቱን አሰምቷል፡፡ ለምንድን ነው ማንም በሌላው ጉዳይ ላይ የሚያገባው? ምክንያቱም ነገ አንተም ተረኛ ነህ! ባለወር ባላሳምንት ነው ነገሩ፡፡

በመጀመሪያ በኮሙኒስቶች መጡባቸው፣ እናም ዝም አልኩ ምክንያቱም ኮሙኒስት አልነበርኩምና፡፡ በቀጣይነትም በሶሻሊስቶች ላይ መጡባቸው፣ አሁንም ምንም ሳልናገር ዝም አልኩ ምክንያቱም ሶሻሊስት አልነበርኩምና፡፡ ከዚያም በሰራተኛ ማሀበራት ላይ መጡባቸው፣ አሁንም ምንም ሳልተነፍስ ዝም አልኩ ምክንያቱም የሰራተኛ ማህበራት አባል አልነበርኩምና፡፡ በመጨረሻም በእኔ በእራሴ ላይ መጡብኝ፣ ሆኖም ግን ለእኔ የሚጮህልኝ ማንም አልነበረም፡፡

እስክንድር እንዲህ በማለት ጥያቄ ያቀርባል፣ “ሌላው ዓለም ለምንድን ነው የሚያገባው?“ እኔ ደግሞ እንዲህ በማለት እጠይቃለሁ፣ “ኢትዮጵያውያን/ት ስለእስክንድር፣ ስለርዕዮት እና ስለሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ የሚያገባቸው ለምንድን ነው?“ በመለስ ዜናዊ ውስብስብ እስር ቤት ታጉረው በመሰቃየት ላያ ስላሉት ለእስክንድር፣ ለርዕዮት እና ለሌሎች የፖለቲካ እስረኞች የሚናገርላቸው እና የሚጮህላቸው ሰው አለን?

የወያኔ ወሮበላ ስርዓት ወገኖቻችንን አሳር እና ፍዳ እያሳየ ነጻነታቸውን ገፍፎ ሲገዛ እያዩ ዝም በማለታቸው እና ጥቂቶች ሆዳሞች ደግሞ በርካሽ ጥቅመኝነት ህሊናቸውን ለገንዘብ ሸጠው ወሮበላው የወያኔ ስብስብ ወደ ስልጣን እንዲመጣ በመተባበር እና አሁንም በዚሁ አምባገነንነቱ እንዲቀጥል በሚስጥር እየረዱ በመሆናቸው በኢትዮጵያ ምሁራን ላይ ጣቴን ቀስሬባቸዋለሁ፡፡ ከስሻቸዋለሁም!

የጀግኖች እና የጀግኒቶች ረዥም ጉዞ ለነጻነት፣

እስክንድር በደብዳቤው ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስፍሯል፣ “ ከዋሻው ጭፍ ብርሀን ይታየኛል፡፡ ከዚያ ለመድረስ ብዙ ጊዜ ሊወስድም ላይወስድም ይችላል፡፡ በየትኛውም ዓይነት መንገድ ነገሮች ቢፈጸሙ እኔ በጽናት እቆማለሁ!“

“የድብቁ ኃይል/The Power of Myth” እና የሌሎች ወጥ የሆኑ ስራዎች ታዋቂ የሆኑት ደራሲ ፕሮፌሰር ጆሴፍ ካምፕቤል የጀግናን ጉዞ ከብርሀን ወደ ጨለማ ከዚያም ተመልሶ ከጨለማ ወደ ብርሀን የሚያደርገውን ጉዞ ገልጸዋል፡፡ ጉዞው ጽናትን እና እልህ አስጨራሽ የሆነ ታጋሽነትን የሚጠይቅ አድካሚ ጉዞ ነው፡፡ ጀግና ፈታኝ የሆነ ነገር መምጣቱን ምልክት እስከሚያገኝ ድረስ እና በዚህች ብቸኛ እና በውል ባልታወቀች ዓለም ላይ ድብቅ ኃይሎች እና ድርጊቶች እስከሚከሰቱ ድረስ እንደማንኛውም ተራ ሰው ነው የሚኖረው፡፡ ጀግናው ጥሪውን የሚቀበል ከሆነ ሙከራዎችን እና መከራዎችን በድብቁ ዓለም ላይ ብቻውን ወይም ደግሞ ከሌሎች ጋር ሊጋፈጥ ይችላ፡፡ የእርሱን ውስጣዊ ባህሪ ሊፈትኑ የሚችሉ ከፍተኛ የሆኑ ተግዳሮቶች ሊገጥሙት ይችላሉ፡፡ ጀግናው የገጠመውን ፈተና ሊቋቋም ከቻለ የምሁርነት እና የእራስ እውቀት ታላቅ ስጦታን ይሸለማል፡፡ ጀግና ከዚህ ታላቅ ስጦታ ጋር ወደ ተራው ህዝብ ዘንድ ለመመለስ ወይም ላለመመለስ መወሰን አለበት፡፡ በሚመለስበት መንገድ ላይ በጣም በርካታ የሆኑ ፈተናዎችን ይጋፈጣል፡፡ ጀግናው ስኬታማ የሚሆን ከሆነ ታላቁን ስጦታ በመጠቀም ዓለም ለማሻሻል አጋጣሚውን ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ስለሆነም ካምፕቤል እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “የዓለምን ከጥፋት ለማዳን ጉዞ ላይ አይደለንም፣ ሆኖም ግን የእራሳችንን ከጥፋት ለማዳን ነው፡፡ ይህንንም በማድረግ ዓለምን አናድናለን፡፡ የጠንካራ ሰው ተጽዕኖ ጠንካራ ነገርን ይሰራል፡፡ ”

እንግዲህ እንደዚህ ባለ ጉዞ እና አስገራሚ ሁኔታ ነው እስክንድር፣ ርዕዮት እና ሌሎች አይበገሬ የዓላማ ጽናት ሰዎች በወንጀለኛው የመለስ ዜናዊ እስር ቤት ሆነው እየታገሉ ያሉት፡፡ ያላቸውን ታላቅ የጽናት ስጦታ በመጠቀም እና ለቀሪዎቻችንም በማካፈል በጽናት በመቆም ዓለምን ከጨለማው ወደ ብርሀኑ ይመልሳሉ፡፡ ገና ከመለስ ዜናዊ የጭራቅ እስር ቤት ሆድ ውስጥ ከመድረሳቸው በፊት ከታላቁ ገጸ በረከታቸው አንዱ የሆነውን ጽናትን ልከውልናል፡፡

እስክንድር እንዲህ በማለት አወጀ፣ “ከዋሻው መጨረሻ ያለውን ብርሀን ለማየት እኖራለሁ፡፡“ እስክንድር እና የህሊና የእስር ቤት ጓደኞቹ ረዥሙን እና አድካሚውን ጉዟቸውን ከጨለማው ዓለም ወደ ብርሀኑ ዓለም በማድረግ በስኬት ያጠናቅቃሉ፡፡ እንግዲህ ይህ ነው የሁሉም ጀግኖች እና ጀግኒቶች የተቀደሰ ዕድል እና ዓላማ፡፡

ህወሀት በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ላይ የከፈተው የጦርነት ዘመቻ እራሱ በእውነት ላይ የተደረገ የጦርነት ዘመቻ ነው፡፡ ላለፉት 23 ዓመታት ህወሀት በሁሉም ጦርነቶች እና አጫጭር ግጭቶች አሸናፊ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን ጎራዴዎችን እና AK47 ጠብ መንጃዎችን በታጠቁት ወሮበላ አምባገነኖች እና በተማሩ ጋዜጠኞች እና ብዕሮቻቸውን እና የኮምፒውተር መክፈቻ ቆፎቻቸውን ብቻ በሚጠቀሙ ጦማሪያን መካከል የሚደረገው የመጨረሻ እና ወሳኝ ጦርነት ይደረጋል፡፡ ያ ጦርነት በኢትዮጵያ ህዝብ ልብ እና አዕምሮ ውስጥ ነው፣ እንደዚሁም በዚሁ መልኩ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡ ምንም ይሁን ምን የዚያ ጦርነት ውጤቱ የተቀደሰ እንደሚሆን ምንም ዓይነት ጥርጥር የለኝም፡፡ በእርግጥ ያ ጦርነት በአሁኑ ወቅት አሸናፊነትን ተቀዳጅቷል፡፡ ኤድዋርድ ቡለዌር ሊቶን በግጥም ስንኞቻቸው በግልጽ እንዳስቀመጡት በጎራዴ ታጣቂዎች እና በብዕር ተኳሾች መካከል በሚደረግ የጦርነት ፍልሚያ የመጨረሻ ድሉ የሚሄደው ወደ ብዕር ተኳሾች ነው ብለዋል፡፡

እውነት መሰረት ነው እንደዚህ ነው የምል፣

ገዥዎች በጉልበት ሁሉን ለመጠቅለል፣

ምለው ተገዝተው ህዝብን ለመበደል፡፡

መሳሪያ ቢያንጋጉ ላውንቸሩን መውዜር፣

በሰማይ ቢበሩ ቢናውዙ በምድር፣

በባህር ቢቀዝፉ ህዝብን ለማሸበር፡፡

ለጊዜው ድንፋታን በጥቅም ላይ ቢያውል፣

መሳሪያ ኃይል ሆኖ አያበቃም ለድል፣

ብዕር ከጎራዴ ያይላል፣ አስተውል፡፡

ጭራቆች ቢስቁ፣

ወሬን ቢሰልቁ፣

ፍትህን ላያውቁ፣

ህዝብን ለመጨረስ

በምኞት አለቁ፡፡

መሰረቱን ሰርቶ ባዶ ጩኸታቸው፣

ህዝብን ለመበደል ሆኖ ዓላማቸው፣

ሌት ከቀን ቢለፉ በነቀዘ አፋቸው፣

ውድቀትን ካልሆነ ድል አይታያቸው፡፡

ስለዚህ ጭቁኖች ታምርን በመስራት፣

ጭራቅ ቄሳሮችን በወኔ በመርታት፣

የእምብተኝነትን አመጽ በማስነሳት፣

ነጻነትን በሉ የህዝቦች አድርጓት፡፡

ስለዚህ ታላቁ፣

የሀሰት ስላቁ፣

ጀብደኝነት ስንቁ፣

ነጻነት እሩቁ፣

ሸፍጠኝነት ወርቁ፣

ከሀዲነት ብርቁ፣

ከርሳምነት እንቁ፡፡

እንደ ጠዋት ጤዛ በኖ እንደሚጠፋ፣

ቀልቀሎ አቁማዳ ባየር የተነፋ፣

ጠበቅ ሲያደርጉት በራሱ ላይ ከፋ፡፡

ስለዚህ ታላቁን የይስሙላ ስሙን፣

በብዕር ምቱ እና ቀሙት ጎራዴውን፣

በዓለም ህዝቦች ሁሉ ሰላም እንዲሰፍን፡፡

ከዚያማ በዓለም ላይ በሰው ልጆች ሁሉ፣

በጎራዴ ማመን ይቀራል በሁሉ፡፡

ብዕር አሸናፊ የሰው ልጆች ማማ፣

ለአምባገነን እሬት ለጭቁኖች አርማ፣

የስልጣኔ አርማ የምሁራን ጫማ፣

ክላሽንኮብ መውዜር ታንክ ሳይሰማራ፣

በጉልበት ሳያምን ብዕርን ከጠራ፣

መንግስት ይጠበቃል ማንንም ሳይፈራ፡፡

ጽናት ለእኔ ምን ማለት እንደሆነ፣

በርካታ ኢትዮጵያውያን ውንድሞቸ እና አትዮጵያውያት እህቶቸ እራሳቸውን እንዲህ በማለት ይጠይቃሉ፣ “የትግላችንን ፍሬ እስከምናይ ድረስ ምን ያህል ጊዜ መታገል አለብን?” እኔ ደግሞ እራሴን እንዲህ በማለት እጠይቃለሁ፣ “ምን ያህል ጊዜ…?“ ሌሎች ደግሞ እንዲህ በማለት ይጠቁኛል፣ “በስልጣን ላይ ላሉት እና ስልጣናቸውን ከህግባብ ውጭ በሚጠቀሙት አምባገነኖች ላይ እውነቱን በመጻፍ እና በመንገር ለምን ያህል ጊዜ ትቆያለህ? እስከ አሁን አልደከመህምን?“

በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ላይ ትግል የሚያደርጉ ጥቂት ሰዎች የችግሩን አስቸጋሪነት ከግንዛቤ በማስገባት ሽንፈታቸውን አምነው ተቀብለዋል፡፡ ጎማቸውን እያሽከረከሩ እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ ሆኖም ግን እንዲህ በማለት እነግራቸዋለሁ፣ “ጠበቅ አድርጋችሁ ያዙ! ለጥቲት ጊዜ ያህል፡፡“ አምባገነኖችን ለማንበርከክ ለነጻነት እና ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል የ26 ማይል የማራቶን እሩጫ እንጅ የ100 ሜትር የአጭር ርቀት ሩጫ አይደለም በማለት እነግራቸዋለሁ፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 2011 “በኢትዮጵያ ለነጻነት የሚደረግ ታላቁ እሩጫ” በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትችት ላይ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ወትዋቾች፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ሌሎች እልህ አስጨራሽ የሆነውን የማራቶን እሩጫ በጽናት እና በድል አድራጊነት ለማጠናቀቅ ማራቶን ሯጮቻችን በጽናት እና በወኔ መቆም እንዳለባቸው እንዲህ በማለት ተናግሬ ነበር፡፡

…ለነጻነት የሚደረግ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ለረዥሙ እና በጣም አስቸጋሪ ለሆነው የማራቶን ሩጫ የመጀመሪያው ክፍያ እንጅ አጠቃላይ ሙሉ ክፍያ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው እያንዳንዳችን ልዩ የሆነውን ጽናት የሚለውን የማራቶን ሩጫን ማጎልበት ያለብን፡፡

የማራቶን ሯጯ ገና ሩጫዋን ስትጀምር እስከ ሩጫው ማጠናቀቂያው መስመር ድረስ ያለው ርቀት ታላቅ ጥረትን የሚጠይቅ እና በጣም አድካሚ እንደሆነ ታውቃለች፡፡ ሆኖም ግን ረዥሙን የማራቶን ሩጫ እንዴት አድርጋ ሮጣ ማሸነፍ እንዳለባት ቅድመ ዝግጅት ታደርጋለች፡፡ የማራቶን ሯጭ እንዲህ አይልም፣ ‘እጅግ በጣም ረዥም ነው…በጣም አስቸጋሪ ነው…እኔ በፍጹም ላደርገው አልችልም’ የአሸናፊነት ስነልቦናን ሰንቆ ይገባል እንጅ እሸነፋለሁ በማለት ሞራሉን ገድሎ ወደ ሩጫው አይገባም፡፡ ያለውን እምቅ ኃይል እየመጠነ እና እየለካ እርሱን በአንድ ጊዜ እንዲደክም እና ተስፋ እንዲቆርጥ በሚያደርግ መልኩ ሳይሆን ይልቁንም ከዚያ በተለዬ መልኩ እያበረታ እና በተስፋ እየተሞላ ለአጠቃላይ አሸናፊነት የሚያበቃውን የአሯሯጥ ዘዴ መርጦ በተግባር ይተገብራል፡፡ የማራቶን ሯጭ እያንዳንዱን እርምጃ እንዴት አድርጎ በመወንጨፍ ለድል ሊበቃ እንደሚችል አስቀድሞ ዕቅድ ያወጣል፡፡

የርቀት ሯጯ በቀሪዎቹ የማራቶን ርቀቶች ላይ እራሷን አታስጨንቅም ይልቁንም በቀጣይነት ስለምትራመደው፣ ከፊት ለፊቷ ስለሚጠብቃት ተራራ እና በቀጣይነት ስለምትሮጠው ጠመዝማዛ መንገድ እና ሩጫውን እስከምታጠናቅቅበት ድረስ ላለው ዕቅድ ነው እራሷን የምታዘጋጀው እና ኃይሏን እና ሀሳቧን ሁሉ የምታውለው፡፡ ጥቂቶቻችን የማራቶን ሩጫው 10 ኪሎ ሜትሮች እንዲሆኑ እና በአንድ ጊዜ በፍጥነት ሮጠን ከማጠናቀቂያው መስመር ላይ ለመድረስ እንፈልጋለን፡፡ በረዥም ርቀት ሩጫ ላይ ተስፋ የመቁረጥ እና እራሳችንን ዝቅ አድርገን የማየት ሁኔታን እናንጸባርቃለን፡፡ ገና ስናስበው በጣም የድካም ስሜት ይሰማን እና አንዷንም እርምጃ ሳንሰነዝር በዝረራ ሩጫውን ጥለን እንወጣለን፡፡ ሆኖም ግን ለነጻነት የሚደረግ የማራቶን ሩጫ የማጠናቀቂያ መስመር የለውም፡፡ ማንዴላ “አንድን ታላቅ ተራራ ከወጣን በኋላ ሌሎች በርካታ ተራሮችን መውጣት ይጠበቅብናል” እንዳሉት ማለት ነው፡፡

ማራቶንን መሮጥ እና አንድ ተራራ ብቻ በመውጣት ሌሎች ሊወጡ የሚችሉ በርካታ ተራሮች እንዳሉ አስቀድሞ ማወቅ እና በልበሙሉነት በመሮጥ ከማጠናቀቂያው መስመር መድረስ መቻል ነው እንግዲህ ለእኔ ጽናት ማለት! ሌሎች ተራሮች እስካለቁ ድረስ ተራሮችን መውጣት እና ሌሎች ያልተጠናቀቁ ተራሮች የሌሉን መሆናቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል!

ወደኋላ አናፈገፍግም፣ እናም በጽናት እንቆማለን! አይበገሬ እንሆናለን! ድል እናደርጋለን!

በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት ጀግኖች እና ጀግኒቶች ልቤ ይሰበራል፣ የደረት ውጋትም ይሆንብኛል፡፡ እስክንድር በግፍ የ18 ዓመታት እስራት ተፈርዶበት በመለስ ዜናዊ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ የመገኘቱ ሁኔታ ልቤ እንዲሰበር አድርጎኛል፡፡ ሆኖም ግን እስክንድር ምንም የማይፈራ ደፋር መንፈሰ ጠንካራ የማያጎነብስ በመሆኑ ልቤ በደስታ ይሞላል፡፡ ርዕዮት በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ሌት እና ቀን በመማቀቅ ላይ መሆኗን ባስታወስኩ ቁጥር ልቤ ይሰበራል፡፡ ሆኖም ግን ክብሯን እና ነጻነቷን ለመግፈፍ ከሚቋምጡት አሳሪዎቿ እኩይ ሀሳብ ከመንበርከክ እና ቅጣቷን ከመቀበል ይልቅ በዓላማ ጽናቷ በመግፋት የምታሳየውን የአይበገሬነት ጽናት ስመለከት ሞራሌ ከፍ ይላል፡፡

በኢትዮጵያ ያሉትን ጅግኖች እና ጀግኒቶች የፖለቲካ እስረኞችን አከብራቸዋለሁ፣ አወድሳቸዋለሁም፡፡ ለወገኖቻቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ ሲሉ እየከፈሉት ላለው መስዋዕትነት እና እያሳዩት ላለው የዓላማ ጽናት የሚያነቃቃኝ በመሆኑ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ አመሰግናቸዋለሁ፡፡ የዓላማ ጽናቴ የበለጠ እንዲጠነክር አድርገዋል፣ እናም እየከፈሉት ያለውን መስዋዕትነት እንዳስብ እና እንድዘክር የበለጠ የመንፈስ ጥንካሬ እና ስንቅ እንዲሆነኝ አድርገዋል፡፡ የእነርሱን ድፍረት፣ ጠንካራ የሞራል ተስፋ፣ ጽናት፣ የዓላማ ጥንካሬ እና አይበገሬነት ብቻ አደንቃለሁ የእኔ ባህሪም እንዲሆኑ አደርጋለሁ፡፡ የእነርሱን ጽናት ለማግኘት እጓጓለሁ፡፡ እነዚህን ጀግኖች እና ጀግኒቶች ከልብ በመነጨ መልኩ አመሰግናቸዋለሁ፣ አወድሳቸዋለሁ፡፡

እስክንድር ጥልቅ በሆነ ፍልስፍናዊ የአነጋገር አንደበቱ እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር፣ “ በጽናት እቆማለሁ!“ ይህንን ፈላስፋዊ አነጋገር ሁልጊዜ በምንግባባበት የተለመደው የዘወትር ቋንቋ ዘርዘር አድርጌ ስመለከተው እስክንድር በቀጥታ ቶም ፔቲ እና “አላፈገፍግም” የሚሉትን ልብ ሰባሪ ግጥሞቹን ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡

እወቅ አንተ ጭራቅ አላፈገፍግም፣

ከገባሁበት ማጥ አንድ ጋት አልርቅም፡፡

ሳላንበረክክህ ከእነርኩስ መንፈስህ፣

ቃል ለምድር ለሰማይ እውነት ነው እምልህ፣

ተመልሸ አልወጣም ከማጎሪያው ቤትህ፡፡

ማፈግፈግ ማፈግፈግ ፍጹም አታስባት፣

አፈር ትበላለህ በእኔ መስዋዕትነት፡፡

እንጦረጦስ ወርደህ ከነጉግ ማንጉግህ፣

የህዝብ ነጻነት ያበራል በቀብርህ፡፡

ከጋነም ከበሩ ማቆም ትችላለህ፣

መግረፍ ማሰቃዬት መግደል ትችላለህ፣

ሆኖም ግን ከግብሬ ከዓላማዬ ቀርቶ፣

መመለስ ይቅር እና ፊቴ አይዞረም ከቶ፣

አንተን ሳያደባይ ካለህበት ገብቶ፡፡

በዓላማ ጸንቼ፣

ሩቅ ተመልክቼ፣

ለፍትህ ጓጉቼ፣

ጽናትን አንግቼ፣

ለነጻነት ሞቼ፣

ሳልገለባበጥ እንደባህር ዓሳ፣

በጽናት ታግዬ እንደ ጫካ አንበሳ፣

ቁርስ መብላት ሳይሆነ አልሜ ለምሳ፣

ሽንፈት ትጋታለህ ብትወድቅ ብትነሳ፡፡

ዓላማዬ አንድ ነው ዓለምን መጠበቅ፣

ከጭራቅ ድሁሮች ከአምባገነን መብረቅ፣

ከግፈኞች ጉያ ተምዘግዝጋ እንዳትወድቅ፡፡

ስለዚህ በጽናት እቆማለሁ ዳግም፣

ላምባገነን ጨካኝ አላጎብስም፣

ጭራቃዊ መንፈስ ከዓለም እስኪወድም፣

ፍትህ በአደባባይ እስከምትለመልም…

ወደኋላ አናፈገፍግም! ለዓላማችን በአይበገሬነት እንቆማለን! በጽናት እንቆማለን! አይበገሬ እንሆናለን! በመራራው ትግላችን በድል አድራጊነት ድልን እንቀዳጃለን!

በመላው ዓለም የምትገኙ አንባቢዎቼ ሁሉ አዲሱ የፈረንጆች ዓመት የደስታ እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ… በ2015 አዲሱ ዓመት ኃይሉ እና ድሉ ሁሉ ከእናንተ ጋር እንዲሆን እመኛለሁ!

ያለው ኃይል ሁሉ ከድል አድራጊዎቹ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ጋር እንዲሆን እመኛለሁ!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም

ፍትሕ አያረጅም! የኢትዮጵያና የአርሚኒያ ትግል

$
0
0

ኪዳኔ ዓለማየሁ

መግቢያ፤

Justiceኢትዮጵያንና አርሚኒያን ከሚያመሳስሏቸው ጉዳዮች አንደኛው የአንድ ዓይነት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የእምነት መሠረት (ዶግማ) ተከታዮች ያሉባቸው ሐገሮች መሆናቸው ነው። በዚህ ጽሑፍ የማተኩርበት ተመሳሳይነት ግን ሁለቱም ሐገሮች በከባድ የጦር ወንጀሎች ተጠቅተው እያንዳንዳቸው ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ የተጨፈጨፈባቸው መሆኑ ነው። ሌላም እጅግ አስጸያፊ ግፍ የተፈጸመባቸው ሐገሮች ናቸው። በተጨማሪም፤ ሁለቱን ሐገሮች ያቀራረባቸው ሌላው ጉዳይ በኦቶማን ዘመነ መንግሥት፤ ከቱርኮች ግፍ በመሸሽ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት መልካም ፈቃድ ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት 40 አርመኖች ኑሯቸውን በሐገራችን መቀጠላቸው ነው። እነዚህ አርመኖችና ተወላጆቻቸው በኢትዮጵያ ተመቻችተው የኖሩና ብዙዎቹም አማርኛውን ያቀላጥፉ እንደ ነበር የታወቀ ነው። በዚህ አጋጣሚ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት ዱባይ በምሠራበት ጊዜ እዚያ ይኖር የነበረውን፤ ወዳጄን፤አቶ የርቫንትን እያስታወስኩ፤ አርመኖች ያቋቋሟትን ሻርጃ (Sharjah) የምትገኝ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያውያን ምእመናን በማጋራታቸው፤ ውለታቸውን አልረሳውም።

በአርመኖችና በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸሙት እልቂቶችና የጦር ወንጀሎች፤

በአርመኖች ላይ የተፈጸመው የጦር ወንጀል እ.አ.አ በ1915-23 በኦቶማን (Ottoman) (በኋላ ቱርክ) ዘመነ መንግሥት መገባደጃ ጊዜ ነበር። እንደሚታወቀው፤ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመው እልቂት እ.አ.አ በ1935-41 በኢጣልያ ፋሺሽቶችና በቫቲካን ያልተቆጠበ ድጋፍ የተከናወነ ነበር። ከላይ እንደ ተገለጸው፤ ሁለቱም ሐገሮች ቢያንስ አንድ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ተጨፍጭፎባቸዋል። በተጨማሪም እጅግ ብዙ አርመኖች ከሐገራቸው እንዲሰደዱ ተገድደው ለከባድ ችግር ተጋልጠዋል። በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመው ግፍ በብዙ የኢጣልያ አውሮፕላኖች በተነሰነሰው የመርዝ ጋዝ እንዲሁም በሌሎች ልዩ ልዩ መሣሪያዎች የተጨፈጨፈው ሕዝብ፤ (በሶስት ቀኖች አዲስ አበባ የተገደሉት 30 000 ኢትዮጵያውያን ጭምር) ብቻ ሳይሆን የወደሙትን 2 000 ቤተ ክርስቲያኖች፤ 525 000 ቤቶችና 14 ሚሊዮን ያህል እንስሶች ያካትታል። በተጨማሪም እጅግ ብዙ ዝርፊያ የተከናወነ መሆኑ የታወቀ ነው።

የአርመኖች ትግል ለፍትሕ፤

በአርመኖች በኩል፤ ከ100 ዓመት በፊት በቱርኮች ለተፈጸመባቸው ወንጀል ተገቢውን ፍትሕ ለማስገኘት ያላሰለሰ ትግላቸውን እየቀጠሉ ነው። መሠረታዊ ዓላማቸውም ያ ከባድ ጥቃት የዘር ማጥፋት ወንጀል (genocide) መሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅላቸው ለማድረግ ነው። በዚህ በፈረንጆች የዘመን አቆጣጠር በ2015 የእልቂቱ መቶኛ ዓመት የሚደፍን በመሆኑ በሰፊው ለመዘከር እቅድ አላቸው። በዚህ ተግባር ከተሰማሩት ውስጥ፤ የአርመን መንግሥት እንዲሁም በአሜሪካ የሚገኙ፤ (ሀ) የአርመን ብሔራዊ ኮሚቲ በአሜሪካ (Armenian National Committee of America) (www.anca.org) እና (ለ) የአሜሪካ አርመናዊ ሸንጎ (Armenian Assembly of America) (www.aaainc.org) ይገኙበታል።

ሰሞኑን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መማከሪያ (Foreign Affairs Council) በተሰኘው ድርጅት አማካኝነት ታትሞ በወጣው ፎሪን አፌርስ (Foreign Affairs) መጽሔት (January/February 2015)፤ ቶማስ ደ ዋል (Thomas de Waal) የተባለ ዘጋቢ፤(“The G-Word; The Armenian Massacre and the Politics of Genocide”) (ትርጉም፤ የጂ-ቃል፤ ስለ አርመኖች እልቂትና የዘር ማጥፋት ፖለቲካ) በሚል አርእስት የሚከተሉትን ቁም-ነገሮች አቅርቧል፤

 

(ሀ) እ.አ.አ. በ1918 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቲዮዶር ሩዝቬልት (Theodore Roosevelt) በአርመኖች ላይ ስለ ተፈጸመው ስደትና እልቂት አሜሪካ በኦቶማን መንግሥት ላይ ጦርነት ማወጅ አለባት በማለት ሐሳባቸውን በደብዳቤ ገልጸው ነበር።

(ለ) የአርመኖች የፍትሕ ትግል በአሜሪካ መንግሥት መርሆ ላይ ከፍተኛ አጽንኦት አስክትሏል። እ.አ.አ. በ1951 የአሜሪካ መንግሥት ጠበቆች ቱርኮች በአርመኖች ላይ የፈጸሙት እልቂት እንደ የሰው ዘር ማጥፋት ወንጀል (genocide) እንዲታይ ሔግ (The Hague) ለሚገኘው ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (International Criminal Court) አመልክተው ነበር። ነገር ግን የተባበሩት መንግሥታት የዘር ማጥፋት ወንጀል ስምምነት (United Nations Genocide Convention) የታወጀው እ.አ.አ. በ1948 ከአርመኖች እልቂት በኋላ በመሆኑ እስካሁን ጉዳዩን ለፍርድ የማቅረቡ ሒደት አልተሳካም።

(ሐ) እ.አ.አ. በ1975 የአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት (House of Representatives) መሪ፤ ቲፕ ኦኒል (Tip O’Neill) እ.አ.አ. ሚያዚያ 24ን (April 24) የሰውን ልጅ የርስ በርስ ኢሰብአዊነት ብሔራዊ የመዘከሪያ ቀን (National Day of Remembrance of Man’s Inhumanity to Man” ተብሎ እንዲሰየምና በዘር ማጥፋት ወንጀል የተጠቁትን በሙሉ፤ በተለይም እ.አ.አ. በ1915 ለተሰዉት አርመኖች መታሰቢያ እንዲሰየም ሥልጣኑን ለአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሰጠበት የውሳኔ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ነገር ግን በሌላው የአሜሪካ ምክር ቤት፤ በሴኔት (Senate) የአርመኖችን እልቂት እንደ የዘር ማጥፋት ወንጀል የመቁጠር ጉዳይ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።

(መ) ፕሬዚዳንት ሬጋንም (President Reagan) በመጀመሪያ በ እ.አ.አ. በ 1981 ለአርመኖች የዘር እልቂት (genocide) እውቅና በመስጠት ገለጻ አድርገው ነበር። ነገር ግን እ.አ.አ. በ1982 ሁለት አርመናዊ ወጣቶች በሎዛንጀለስ ከተማ የቱርክ ቆንስል መሪ የነበረውን ከማል አሪካንን (Kemal Arikan) በመግደላቸው የፕሬዚዳንት ሬጋን አቋም ተለወጠ።

(ረ) የቱርክ መንግሥት ለአሜሪካ ጠንካራ ድጋፍ ከሚያበረክቱት መንግሥቶች አንዱ በመሆኑ በተለይም የሰሜን አትላንቲክ ሐገሮች ድርጅት (NATO) አባል በመሆኑ በአርመኖች ላይ ስለ ተፈጸመው የኦቶማኖች የጦር ወንጀል አሜሪካ ያላት አቋም ተለዋዋጭ ሆነ።

(ሠ) የአሜሪካና የቱርክ መንግሥቶች ባላቸው የጥቅም ቅድሚያ ለአርመኖች የሚገባውን ፍትሕ ለጊዜው ያመከኑት ቢመስልም የአርመን ታጋይ ድርጅቶች የመቶ ዓመት ጥረታቸውን አጠንክረው እየቀጠሉ ነው። ለዚህም በምርጫ መብታቸው እየተጠቀሙ በአሜሪካ የኮንግሬስ አባሎችና በሐገሩ ፕሬዚዳንት ላይ የማያቋርጥ አጽንኦት እንዲከሰት ለማድረግ እየጣሩ ነው። የዚህም ጥረት ውጤት አንደኛው ምሳሌ፤ እ.አ.አ. በሚያዚያ 24 ቀን 2010፤ ፕሬዚዳንት ኦባማ (President Obama) የሚከተለውን ገለጻ ማድረጋቸው በቶማስ ደ ዋል ጽሑፍ ተዘግቧል፤

“1.5 million Armenians were massacred or marched to their death in the final days of the

Ottoman Empire……..The Meds Yeghern (“Great Catastrophe”) is a devastating chapter in the

History of the Armenian people, and we must keep its memory alive in honor of those who

were murdered and so that we do not repeat the grave mistakes of the past.”

(ትርጉም፤ በኦቶማን መንግሥት የመጨረሻዎቹ ቀናት 1.5 ሚሊዮን አርመኖች ተጨፍጭፈዋል ወይም ለሞት

ወደሚዳርጋቸው እንዲጓዙ ተደርገዋል። ታላቁ ሰቆቃ (መቅሠፍት) በአርመኖች ታሪክ እጅግ አሰቃቂ ምእራፍ

ነበር። ያለፈውን ስሕተት እንዳንደግመው ለተገደሉት ሰዎች ክብር የዚያን ዘመን ትዝታ ሕያው አድርገን

 

ልናስታውሰው ይገባናል።)

ከዚህ በላይ ከተዘረዘረው መገንዘብ የሚቻለው፤ ምንም እንኳ አርመኖች የሚፈልጉት፤ ማለትም በቱርኮች የተፈጸመባቸው ጭፍጨፋ እንደ የዘር እልቂት ወንጀል (genocide) የማሳወቅ ዓላማ እስካሁን ባይሳካላቸውም ጥረታቸው በከፍተኛ ደረጃ እየቀጠለ የአሜሪካ መሪዎች ጭምር ተስፋ አላስቆረጧቸውም። “የአርመን ብሔራዊ ኮሚቲ በአሜሪካ” ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ዲሬክተር የሆነችውን ወ/ሮ ኤሊዛቤት ሹልድጂያንን (Elizabeth Schouldjian) ሰሞኑን በስልክ አነጋግሬያት አርመኖችና የአርመን መንግሥት ትግላቸውን የሚቀጥሉ መሆኑንና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚያከናውኑት እንቅስቃሴ ከአውሮፓ የሰብአዊ መብት ፍርድ ቤት ጋር ጭምር ጉዳዩን እንደሚገፉበት ገልጻልኛለች።

የኢትዮጵያስ ትግል?

ኢትዮጵያ ለተፈጸመባት እጅግ አሰቃቂ ግፍ ተገቢውን ፍትሕ አላገኘችም። ካሣ ተብሎ ለቆቃ ግድብ መሥሪያ የዋለው $25 ሚሊዮን እና ወደ ሐገሩ የተመለሰው የአክሱም ሐውልት በምንም መስፈርት ብቁ ነው ሊባል አይችልም። ኢጣልያ ለሊቢያ $5 ቢሊዮን፤ ለዩጎዝላቪያ $125 ሚሊዮን፤ ለግሪክ ሐገር $105 ሚሊዮን፤ ለሶቪየት ዩኒየን $100 ሚሊዮን፤ ወዘተ ከተስማማችው ጋር ሲመዛዘንና በተለይም በኢትዮጵያ ላይ ከፈጸመችው ክፍተኛ የጦር ወንጀል ጋር ሲነፃፀር በግልፅ የሚታየው የተዛባ ፍትሕ የሚያስቆጭ ነው። “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንደሚባለው፤ ኢጣልያ የፈጸመችው ወንጀል አልበቃ ብሏት፤ በቅርቡ፤ የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት፤ አፊሌ በምትባል የኢጣልያ ከተማ፤ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” በመባል ለሚታወቀው፤ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ አንድ መታሰቢያና መናፈሻ ተመርቆለታል። እንደ ኬንያና ኢንዶኒዚያ ያሉ ሐገሮች ከቀድሞ አጥቂዎቻቸው ከእንግሊዝና ከኔዘርላንድስ ተገቢውን ይቅርታ ተጠይቀው ካሣ ጭምር ሲከፈላቸው ኢትዮጵያ የተሟላ ፍትሕ ሊነፈጋት አይገባም። ስለዚህ፤ ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ (Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause) የተሰኘው ድርጅት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ዓላማዎች እየታገለ ይገኛል፤

(ሀ) የኢጣልያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል፤

(ለ) ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤

(ሐ) የኢጣልያ መንግሥትና ቫቲካን የተዘረፉትን ንብረቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲመልሱ፤

(መ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፋሺሽት ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመችውን የጦር ወንጀል

እንዲመዘግብ፤ እና

(ሠ) በቅርቡ ለፋሺሽቱ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” ለሮዶልፎ ግራዚያኒ ኢጣልያ ውስጥ በአፊሌ ከተማ፤  የተሠራው

መታሰቢያ እንዲወገድ።

አቤቱታውንም ለሚመለክታቸው ሁሉ፤ ለኢጣልያ መንግሥትና ለቫቲካን፤ ለአውሮፓ ምክር ቤት፤ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ ለፕሬዚዳንት ኦባማና ለሌሎች አንዳንድ የዓለም መንግሥታት መሪዎች፤ እንዲሁም በፍትሕ ለሚያምኑ ሰዎች በሙሉ አቅርቧል። በዚህ አጋጣሚ በየዓመቱ የካቲት 12ን ለመዘከር በ30 ከተሞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሐገር ፍትሕና ክብር ለሚንቀሳቀሱ ሁሉ ልባዊ ምሥጋና ይድረሳቸው። የኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበርም የሚያከናውነው ጥረት ሊጠቀስ ይገባል።

በተጨማሪም፤ በድርጅቱ ድረ-ገጽ (www.globalallianceforethiopia.org) የሚገኝ፤ ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ እየተፈረመ ያለ ዓለም አቀፍ አቤቱታ ይገኛል። እስካሁን ክ4200 ሰዎች በላይ ፈርመውታል። ይህንን ጽሑፍ የሚመለከቱ ሁሉ አቤቱታውን እንዲፈርሙት ተጋብዘዋል።

 

ለውድ ሐገራችን ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕና ክብር እስካሁን የተከናወነው ጥረት የሚያበረታታ ቢሆንም በውጤት ደረጃ አመርቂ ደረጃ አልደረሰም። በተለይም አርመኖች ለክብራቸውና ለሐገራቸው ፍትሕ ከሚያከናውኑት ትግል ጋር ሲነፃፀር በኛ በኩል ጥረታቻችንን ማጎልበት እንደሚገባን ግልጽ ነው። ስለዚህ ለሐገርና ለፍትሕ የሚቆጭ ሁሉ በትግሉ እንዲሳተፍና እንዲደግፍ ያስፈልጋል። የአገር ወዳዶች የተባበረ ጥረት የትግሉን ውጤት የተሳካና የተፋጠነ ለማድረግ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

ቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ ለሐገራችን የሚገባው ክብርና ፍትሕ እንዲገኝ የጀመርነውን ጥረት፤ በሁሉም አገር ወዳድ ተሳትፎ፤ አጠናክረን እንድንቀጥል ብርታቱን ይስጠን። አሜን!

የመስቀሉ ደም –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

bahrdar 7

04.01.2014

ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ህማማት – ጸንሶ

ዕንባውን – አፍሶ

መስቀል ረገመ – በደም ተለውሶ

በበላሃሰቦች ኪዳኑ – ተረግጦ።

እህ! – እህህ –ህህህ —ህህህ – ህህህ

ሆይ! አለህን!? – አለህን በቤትህ? – አለህ!?!

እንሆ ——- ዘመን ተገርድሶ

ቀዬውን ተወርሶ – ጢሶ – ጢሶ ——

በትዕቢት – ተጥሶ፤

ፋሽስቱ – ቀስሶ

ዕምነት – ተቆራርሶ

ሽበት – ባት – ተውሶ፤

ቀኑም አለቀሰ – መስቀሉን  – እያዬ

ዘመንም አነባ – ቁም ስቅሉን ስላዬ፤

መርገምትን – አምጦ – እግዚዖታን አዋዬ።

ከልቡ በቅላለች – በላይ እንደ ገና

ዘለቀች ተጣራች መንፈሰ – ገናና

…. ንጥር – ዬአውራ -

ር – ለባንዴራ።

የታሪክ ማህደር – በደም የተቃኘች

ሰንደቁ ናትና ደምቃ –  የታተመች።

አጠናት ከልቡ – የኪዳን ህይወቱን

ይሞቃል ጠረኑ – ድፈረትም ያባቱ፤

የጥንት —– የጥዋቱ

የእናት ሀገር ሃብቱ።

ትናንትን አዳምጦ – በቃኝን አስጊጦ

ነፃነት …. አምጦ – አምጦ – አምጦ -

ዓርነት …… ተጠምቶ – ተጠምቶ – ተጠምቶ -

ተማግዶ – ተማግዶ – ተማግዶ -

ካለ ርህራሄ ተወጋ ——- በዘንዶ፤

ለባዕቱ – ደምቶ – እራሱን ሰጥቶ

ብሩህ ቀን ሰንቆ – ሰላምን ተመኝቶ

እናቱን አላቀ ትውልድ – ታሪክ ሠርቶ።

ሥጦታ – ለቅድስት እናት ለእሙሃይ ይሁንልኝ።

ይህቺ ምልክት አንድ ፊደል „እ“ መዋጧን ታመለክታለች። ከትህትና ጋር፤

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

በተናጥል ሆኖ ፖለቲካውን ማራመድ ጎታች አይደለም –ይልቃል ጌትነት

$
0
0
Hiber Radio Interview with Eng Yilkal Getnet

ይልቃል ጌትነት

የሚሊዮኖች ድምጽ አገር ቤት በአንድነት ፓርቲ ኤዲቶሪያል ቦርድ የምትታተም  ነፃ ጋዜጣ ናት። በሁለተኛ እትሟ የሰማያዊ ሊቀመንበር አቶ ይልቃ ጌትነትን ይዛ ቀርባለች። ሊቀመንበሩ ከሕዝቡ የሚነሱ ፣  አብሮ ከአንድነት ፓርቲ ጋር አብሮ በመስራት ዙሪያ ያጠነጠኑ ጥያቄዎች የቀረበላቸው ሲሆን፣ የአንድነቱ መሪ አቶ በላይ  ፍቃደ በአዲስ ድምጽ ራዲዮ ከሰጡት አስተያየት የተለየ በአብሮ መስራቱ ዙሪያ ተስፋን የሚሰጥ ሳይሆን ተስፋን የሚይጨለም መልሶችን ነበር የመለሱ።

አቶ በላይ ፍቃዱ ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ እና ትብብር ተመሳሳይ የፖለቲካ ፕሮግራም ያላቸው እንደመሆኑ በተናጥል መሆናቸው ትርጉም የማይስጥ ነው የሚል ምላሽ በመስጠት ድርጅታቸው የሕዝብ ጥያቄ  በአክበር ዓብሮ ለመስራት መደረግ ያለበትን ሁልሉ እንደሚያደርግ ማሳወቃቸው ይታወቃል። የሰማያዊ መሪ አቶ ይልቃል ጌትነት ግን፣  በተናጥል ሆኖ ፖለቲካውን ማራመድ ጎታች አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ከቃለ ምልልሱ የተወሰነውን እንደሚክከተለው ያንብቡ

ሚሊዮኖች ድምጽ – ትብብሩ ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች ውጭ ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ አቋም ያለው ፓርቲ አለ ብላችሁ ታስባላችሁ?

አቶ ይልቃል ጌታነት – የሌሎቹ አልጠራም፡፡ ግራ የሚያጋቡና ያልጠራ ነገር አላቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌሎች ፓርቲዎች ላይ አስተያየት ለመስጠት እቸገራለሁ፡፡ የሀገራችን ፖለቲካ ገና ነው፡፡ በጎንዮሽ ለመተቻቸት ቅንጦት የሆነበት ደረጃ ነው ያለው፡፡ ህዝባችንም በተቃዋሚዎች ላይ ተስፋ በሚያደርግበት ጊዜ መተቻቸት ብዙም ጠቃሚ አይደለም፡፡

ሚሊዮኖች ድምጽ – ‹‹ተመሳሳይ ፕሮግራም እና ዓላማ ያላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንድ ሆነው የማይሰሩበት ምክንያት አሳማኝ አይደለም›› የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ፤ እናንተ ደግሞ ‹‹በውህደት ከመሄድ ይልቅ ብቻችንን ሄደን ዓላማችንን እናሳካለን ነው›› የምትሉት፡፡ በዚህም ብዙ ሰዎች ትችት ይሰነዝሩባችኋል፡፡ መልሳችሁ ምንድን ነው?

አቶ ይልቃል ጌታነት – ተቺዎቻች መጀመሪይአ መብታቸው ነው። ሁለተኛ የአደባባይ ሰዎች ስንሆንና በጋራ ጉዳይ ላይ ስንቆም ተቺዎች ሊያወሩ እንደሚችሉ እናምናለን፡፡ ኢትዮጵያ ሰፊ ሀገር ናት፤ ብዙ ውጥንቅጦች ያሉባት ሀገር ናት፡፡ የሃይማኖት መሪዎች ወይም የሃይማኖት ሰዎች አይደለንም፤ ፖለቲከኞች ነን፡፡ በእኛ አመለካከት፣ በእኛ ሃሳብ የማይስማሙም የሚደግፉም አሉ፡፡ ያ በራሱ ጤናማና እንደመልካም የፖለቲካ እድገት ነው የምናየው፡፡ ከተቺዎቻችን የሚመጣው ሀሳብ ዋጋ ያለው ነገር ሆኖ ስናገኘው ደግሞ እንማራለን፡፡

ሚሊዮኖች ድምጽ – በተናጥል ሆኖ ፖለቲካውን ማራመድ ለለውጡ ጎታች አይደለም?

አቶ ይልቃል ጌታነት  – ጎታች አይደለም፡፡ ቢተባበሩ የበለጠ ጥሩ ነው፡፡ በመርህ ደረጃ ችግር የለም፡፡ በተግባራዊነቱ ላይ ነው እንጂ ችግር ያለው፡፡ ያለችህን ኃይል ሁሉ አጠራቅመህ አንድ ላይ ብታደርጋት የተሻለ ጅረት እንደምትሰራ መገንዘብ የማይችል ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡

ሚሊዮኖች ድምጽ – ሰማያዊ እና አንድነት ቢዋሃዱ ሊቀመንበርነቴን ላጣ እችላለሁ የሚል ስጋት አለብህ?

አቶ ይልቃል ጌታነት –  እኔ ስጋት የለኝም፡፡ አንደኛ ስኬትና ውጤት ሊቀመንበር በመሆን ብቻ ነው የሚመጣው ብዬ አላምንም፡፡ ክብርንም፣ ሞገስንም፣ ታሪክንም ሆነ ሰው የሚወዳቸው ነገሮችን በሙሉ ለማግኘት ሊቀመንበር መሆን የግድ አያስፈልግም፡፡ እኔ ሀገሬን ለመጥቀምም ሆነ ራሴ ተከብሬ ለመከበር የሚያስችለኝ ሊቀ-መንበርነቴ ነው ብዬ አላስብም፡፡ 70 ሊቀመንበር ነው እዚህ ሀገር ያለው፡፡ 70ዎቹን ሁሉ እኮ የምታውቀቸው አይመስለኝም፡፡ ምናልባትም አዲስ ጋዜጣ መስርተህ በጋዜጣህ ሁለተኛ ዕትም የመጣኸው እኔ ጋር ነው፡፡ያ የመጣው በተናጥል ሆኖ ፖለቲካውን ማራመድ ለለውጡ ጎታች አይደለም? መብታቸ ው ነው ፡ ፡ ሊቀመንበር በመሆኔ አይደለም፡፡ ስኬትና ውጤት በሥልጣን እርከን አይመጣም፡፡ሌላም አስተያየት አለ፡፡ ‹‹አንድነት እና ሰማያዊ እንዲዋሃዱ የማትፈልገው የመርህ ይከበር አባል ስለነበርክና ከዚያ ጋር በተያያዘ ቂም ነው›› ይባላል፡፡

አቶ ይልቃል ጌታነት –  ይሄ የተሳሳተ መረጃ ነው የሚመስለኝ፡፡ በዛ ደረጃ ከሆነ ከሌሎች ፓርቲ ሰዎች የበለጠ ከአንድነት ሰዎች ጋር ጓደኝነትም ቀረቤታም አለን፡፡ እንዲህ አይነቱ አባባል በመላምት የሚሰጥ አስተያየት ነው፡፡ በጓደኝነት አንድነት ፓርቲ ቤት ካሉ ሰዎች ጋር እንቀራረባለን፡፡ በሥራ አስፈጻሚ ውስጥ ያሉት ሳይቀሩ የቅርብ ጓደኞቼ ናቸው፡፡የምንከባበር ሰዎች ነን፡፡ ቡናም ሻይም አብረን እንጠጣለን፡፡ እዛም ውስጥ እያለን፣ ትግሉ ላይ ባሉ አንዳንድ የመርህ ችግሮች ሳቢያ አብዮት ስናስነሳ ከሰዎቹ ጋር የግል ጠብ እኔ በበኩሌ አልነበረኝም፡፡ ሁሉንም ሰዎች በተለያየ ጊዜ እናገኛቸዋለን፡፡ ከዚያ ከአንድነት ጋር ወደፊት ለመስራትም ሆነ ላለለመስራት የሚወስነን ነገር በሚያራምዳቸው አቋሞች በሚወስዳቸው እርምጃዎችና በያዛቸው የጋራ አስተሳሰቦች መረጃ ነው መታየት ያለበት፡፡ እንደውም ሰማያዊና አንድነት ለመቀራረብ ከሌላው የተለየ ብዙ አጋጣሚዎች ያላቸው ድርጅቶች ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ ሌላም ሰው ብትጠይቅ እንደዛ የሚል ይመስለኛል፡፡በእኛ ሀገር ባህል ‹‹የተጣላ ሰው ተመልሶ አይገናኝም›› ከሚል የሚነሳ መላምት ካልሆነ በቀር እውነታው እንደሚባለው አይደለም፡፡

ሚሊዮኖች ድምጽ  – ሰማያዊና አንድነት ባንተ የሥልጣን ዘመን አንድ የሚሆኑ ይመስልሃል?

አቶ ይልቃል ጌታነት –  ፖለቲካ ተለዋዋጭ ነገር ነው፡፡ዛሬ አይሆንም ያልከው ነገር በአጭር ጊዜ ሆኖ የሚታይበት ጊዜ አለ፡፡ በተግባር ግን ዝብርቅርቅ ያሉ የአስተሳሰብ ርቀቶችና ልዩነቶች እንዳሉ ይታየኛል፡፡ አብረው ሊያደርጓቸው የሚችሉና ሊያከናውኗቸው የሚችሉ ተግባሮችም እንዳሉ ይሰማኛል፡፡በሂደት ደግሞ በሚያገናኟቸው ነገሮች መቀራረብ ሊፈጥሩ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ግን በሐሳብ ደረጃ እኔ ሳየው አሁንም ቢሆን በአንድነት በኩል ያሉት አስተሳሰቦችና ትግሉን የመረዳት ደረጃዎች ከእኔ እይታ ጋር በተወሰኑ ደረጃዎች መራራቆች እንዳሉ ማየት እችላለሁ፡፡ ትግሉን በሚረዱት ደረጃና እንደ ስብስብ በሚወስዷቸው አቋሞች ልዩነት አለ፡፡ አንድነት ከመድረክ ጋር ነበረ፡፡ለምን ከመድረክ ጋር ተለያየ? ወደ መድረክ ሲሄድ ያሻሻላቸው ፕሮግራሞች አሁንስ አሉ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ጥርት ያለ ነገር ካለ አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች የሚፈጠሩ ይመስለኛል፡፡

ሚሊዮኖች ድምጽ – በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ለውጥ ፈላጊዎች፣ “ግራ ተጋባን፤ ማንን እንደግፍ? በአንድነት በሰማያዊና በመኢአድ መሀከል እየዋለልን ነው፡፡” ይላሉ፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ምን ትላቸዋለህ?

አቶ ይልቃል ጌታነት – መዋለሉ በራሱ አንድ የአስተሳሰብ ደረጃ ስለሆነ በቀና ነው የማየው፡፡ በሂደት ወደ አንዱ ይጠቃለላሉ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግልጽ ያልሆኑ ሃሳቦች የሚጠሩበት ጊዜ ሩቅ አይመስለኝም፡፡ ያኔ መልስ ያገኛሉ፡፡

ሚሊዮኖች ድምጽ  – የሰማያዊ ፓርቲን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በአዎንታዊ ጎኑ የሚያዩት ሰዎች እንዳሉ ሁሉ “ጀብደኝነት የሚወዱ ትንንሽ ልጆች ናቸው፡፡ ፖለቲካውን አያውቁትም፡፡ ዝም ብሎ ከፖሊስ ጋር ከመጋፈጥ የራቀ ዓላማ የላቸውም” ብለው የሚተቿችሁም ሰዎች አሉ፡፡ውዳሴውንና ትችቱን እንዴት ታየዋለህ?

አቶ ይልቃል ጌታነት –  ይሄ ለመተቸት ያህል የሚነገር ነገር ነው፡፡ የጠቀሱት ነገር የለም፡፡ ምን በማድረጋችን ነው የምንተቸው? በወሰድነው አቋም ነው? በፕሮግራማችን ነው? እኔ በተናገርኩት ነገር ነው? ወይስ ምንድን ነው? በያዝነው የፖለቲካ አስተሳሰብም ይሁን በአደባባይ በተናገርናቸው ነገሮች ላይ ማንም ሰው አንድ ሁለት ብሎ ነቀፌታ ሰጥቶ አያውቅም፡፡ እኔ ሶስት ዓመት ያህል በሰፊው ተናግሬያለሁ፡፡ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ከተናገርኩት ውስጥ ምናልባት “ተቃዋሚዎችን አጣጣለ” ከሚለው አስተያየት ውጪ በፖለቲካዊ አመለካከቴና በፖለቲካዊ ብስለቴ አሳማኝ ትችት ያቀረበ አንድም ሰው የለም፡፡ ለነገሩ አዲስ ፖለቲካ ውስጥ ነው ያለሁት፡፡ በህይወቴ ብዙ የምማረው ነገር አለኝ፡፡ ትላንት የነበረኝ አስተሳሰብና የዛሬው ይለያያል ፡ ፡

http://www.andinet.org/wpcontent/uploads/2015/01/

የምርጫ 2007 10ቱ ቃላት -ግርማ ሞገስ

$
0
0

ቅዳሜ ታህሳስ 25/2007 (January 3/2015)

Girma Moges

አቶ ግርማ ሞገስ

የዚህ ጽሑፍ ግብ በምርጫ 2007 ቁም ነገር መስራት የሚፈልግ የምርጫ ፓርቲ ማድረግ ከሚገቡት ሌሎች እጅግ በርካታ ዝግጅቶች በተጨማሪ ከግንዛቤ ሊያስገባቸው የሚገቡ 10 ነጥቦች መዘርዘር ነው። ምርጫው ነፃ እና ፍትሃዊ ካልሆነ ከምርጫ መወጣት (ቦይኮት ማድረግ) ጠቃሚ ነው ለሚሉ ወገኖችም መልስ ይሰጣል ይኽ ጽሑፍ። መልካም ንባብ።

 

  • መንግስት በስልጣን መኖር የሚችለው፥ (ሀ) ህጋዊነት የሚለግሰው ህዝብ ሲኖር፣ (ለ) ህዝብ የሙያ ትብብር ሲለግስ፣ (ሐ) ህዝብ የግብር ክፍያ ትብብር ሲያደርግ፣ (መ) የመንግስትን የአገር ተፈጥሮ ሃብት እና አገራዊ ኢኮኖሚ ባለቤትነት ህዝብ እሺ ሲል ብቻ ነው። እነዚህን የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ህዝብ አሳልፎ ለገዢው ቡድን አሳልፎ የሰጠው በፍራቻ ወይንም በፈቃደኛነት ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይህ የእነዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ባለቤት ህዝብ ነው።፡ ስለዚህ ነው የመንግስት ስልጣን ምንጭ ህዝብ ነው የሚባለው። ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት ነው የሚባለውም ስለዚህ ነው። ስለዚህ የመንግስት ስልጣን ባለቤት የሆነው ህዝብ የመንግስት ስልጣን ለመለገስ የተሳተፈባቸው ምርጫዎች ህገወጥ ሊሆኑ አይችሉም። ተቃዋሚ የምርጫ ፓርቲዎች የመንግስት ስልጣን ባለቤት ባለመሆናቸው እራሳቸውን ከምርጫው በማግለል ምርጫውን ህገወጥ አደረግን ማለት አይችሉም። ህዝብ እስከተሳተፈ ምርጫው ህጋዊ ነው። አብላጫ ድምጽ ያገኘውም ፓርቲ ህጋዊ አሸናፊ ፓርቲ ነው። የተባበሩት መንግስታትም ሆነ የምዕራቡ ዓለም መስፈርት የሚለው ይኽንኑ ነው። (ስድስቱ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ሰላማዊ ትግል 101 በሚል ስያሜ በቅርብ ገበያ ላይ በዋለችው መጽሐፍ ውስጥ በሰፊው ቀርቧል።)
  • በምርጫ በስልጣን ላይ ያለን መንግስት ህጋዊነት ማሳጣት የሚቻለው የመንግስት ስልጣን ባለቤት የሆነው ህዝብ እራሱን ከምርጫ ሲያገል ብቻ ነው። አንድ ህዝብ በምርጫ አልሳተፍም ካለ ምርጫ የለም። አሸናፊ ፓርቲ የሚባልም ነገር የለም። ስለዚህ ህዝብ ከሚሳተፍበት ምርጫ እራሳቸውን ብቻ በማግለል (ቦይኮት በማድረግ) ምርጫውን ወይንም አሸነፈ የሚባለውን ፓርቲ ህጋዊነት እናሳጣዋለን ብለው የሚያስቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካሉ የአስተሳሰብ ዝንፈት ወይንም ጨቅላነት አለባቸው። ህዝብን ሊተኩ ወይንም እራሳቸውን ከህዝብ በላይ አድርገዋል ማለት ነው። አምባገነንነትም በልጅነቱ ይኽንኑ ነው የሚመስለው።
  • ዴሞክራሲ በሰረጸባቸው እንደ አሜሪካ እና እንግሊዝ አይነት አገሮች ውስጥ ምርጫ ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት መሆኑ ማረጋገጫ መንገድ ነው። በእነዚህ አገሮች ምርጫ ቦርዱም ሆነ የህዝብ ታዛቢዎች (የምርጫ አስፈጻሚዎች) ገለለተኛ በመሆናቸው የመራጩ ህዝብ ድምጽ ይሰረቃል የሚል ስጋት የለም። የምርጫ ፓርቲዎች ድምጽ ለማስከበር በሚል የሚያደርጉት ስትራተጂያዊ ዝግጅት አይኖርም።
  • ዴሞክራሲ በሰረጸባቸው እንደ አሜሪካ እና እንግሊዝ አይነት አገሮች ውስጥ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝባቸው እንዲመርጣቸው ስለሚጠይቁ ፓርቲዎቹ የመንግስት ስልጣን ባለቤት አለመሆናቸውንም ማረጋገጫ ነው ምርጫ። ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት በመሆኑ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥ የፈለገውን ይቀጥራል (ይመርጣል)። ያልፈለገውን አይመርጥም (አይቀጥርም)። በእነዚህ አገሮች ከሞላ ጎደል ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ ይደረጋል። ስለዚህ በእነዚህ አገሮች ምርጫ የዴሞክራሲ መገለጫ ነው።
  • ዴሞክራስ ባልሰረጸባቸው እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገሮች ውስጥ ምርጫ የህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤትነት ማምጫ መንገድ ነው። በእነዚህ አገሮች ፥ (ሀ) ሶስቱ የመንግስት ዘርፎች የተነጣጠሉ ባለመሆናቸው፣ (ለ) የኢትዮጵያ ህገ መንግስት እንባ ጠባቂ ብሎ ያሚጠራው ተቋም ነፃ ባለመሆኑ፣ (ሐ) በዘልማድ አራተኛው የመንግስት ዘርፍ ተብሎ የሚጠራው ነፃ ፕሬስ እንደልቡ በነጻነት መንቀሳቀስ ባለመቻሉ፣ (መ) በመንግስት እና በፓርቲ መካከል ሊኖር የሚገባው ቀጭን ቀይ መስመር ባለመኖሩ፣ (ረ) ምርጫ ቦርዱም ሆነ የህዝብ ታዛቢዎች (የምርጫ አስፈጻሚዎች) ገለለተኛ ባለመሆናቸው ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ የደረጋል ብሎ ማሰብ ላም ባልዋለበት ኩበት መልቀም ይቻላል ብሎ እንደማመን ነው። በእነዚ አገሮች ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ ይደረግ የሚለው ጥያቄ የሚቀርበው እንደ መታገያ አሳብ መሆኑ ታውቆ የምርጫ ፓርቲዎች ከምርጫ ሳይወጡ ህዝባቸውን የመንግስት ስልጣን ባለቤት ለማድረግ ማለትም ወደ ዴሞክራሲ ለመሸጋገር የጀመሩትን ጉዙ መቀጠል አለባቸው። ስለዚህ ነው በእነዚህ አገሮች በሚደረግ ምርጫ የምርጫ ስትራተጂ ሲቀየት የህዝብ ድምጽ እንዳይሰረቅ ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት በስትራተጂ ውስጥ የሚካተተው።
  • ዴሞክራስ ባልሰረጸባቸው እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገሮች ውስጥ በሚደረግ ምርጫ ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ ካልተደረገ በሚል ምክንያት ከምርጫ መውጣት ለኢህአዴግ (ገዢው ፓርቲ) ጭንቀት መቀነስ ብቻ ሳይሆን ደስታን መለገስ ነው። ባቄላ አለቀ ቢባል ፈስ ቀለለ እንደሚባለው ነው የሚሆንለት ለኢህአዴግ (ገዢው ፓርቲ)። ምክንያቱም የመንግስት ስልጣን ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫ እስከተሳተፈ ድረስ ምርጫው ህጋዊ ነው። ያሸነፈውም ፓርቲ ወዲያው አለም አቀፍ እውቅናን ያገኛል። የገንዘብ እና የቁሳቁስ እርዳታም ይቀጥላል። ይኼን ሃቅ ቀደም ብለው በኢትዮጵያ የተደረጉት አራት አገር አቀፍ ምርጫዎች አስተምረውናል።
  • ዴሞክራስ ባልሰረጸባቸው እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገሮች ውስጥ በሚደረግ ምርጫ በመሳተፍ የህዝብን ድምጽ ማግኘት ግን ለኢህአዴግ (ገዢው ፓርቲ) መከራ እና ጭንቀትን ይፈጥራል። ይኽን ሃቅ በምርጫ 97 ያስተዋልነው ነው። ሽንፈትን አልቀበልም ካለ ድምጽ ይከበር የሚል እንቅስቃሴ ሊፈጠር ይችላል። ይኽንንም ሃቅ በምርጫ 97 አይተናል። አንዴ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከጀመረ ከዚያ ወዴት እንደሚሄድ መገመት አዳጋች ነው። ስለዚህ የምርጫ ፓርቲዎች ለዚህ አይነት አጋጣሚም ቀደም ብለው መዘጋጀት ይበጃቸዋል። አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ጠብቂ በሚለው መመራት ጠቃሚ ነው።
  • ዴሞክራሲ ባልሰረጸባቸው አገሮች ህዝብ ድምጽ የመሰረቅ እድሉ ከፍተኛ ነው። በሰላማዊ ትግል የህዝብ ነፃ አውጭ እራሱ ህዝቡ መሆኑ ታውቆ የምርጫ ፓርቲዎች እምነታቸው በውጭ አገር ድጋፍ ወይንም በምርጫ ቦርድ ሳይሆን በህዝብ ላይ መሆን አለበት። ስለዚህ የምርጫ ፓርቲዎች ህዝብ ድምጹን እንዳይሰረቅ ማድረግ እንዲችል ማሰልጠን እና ማደራጀት አለባቸው። የምርጫ ፓርቲዎች ማድረግ ከሚገቧቸው ስራዎች ውስጥ ጥቂቱ የሚከተሉትን ያካትታል፥ (ሀ) በህዝብ ታዛቢዎች ላይ ገለልተኛ እንዲሆኑ ጫና በማሳደረ፣ (ለ) ለምርጫ እድሜው የደረሰ በሙሉ ለምርጫ እንዲመዘገብ እና የምርጫ ካርድ እንዲወስድ በማድረግ፣ (ሐ) ህዝቡ የምርጫ ካርዱን የሚቀጥሉት አምስት አመቶች በአገሩ አቅጣጫ ላይ ውስኔ መስጫው መብቱ መተግበሪያ አድርጎ እንዲያምን በማድረግ፣ (መ) በምርጫ እለት የምርጫ ካርድ የወሰደ መራጭ በሙሉ በነቂስ ወጥቶ እንዲመርጥ በማሳመን፣ (ሠ) በምርጫው ዕለት በድስፕሊን የታነጹ እና በምርጫ ህግ የሰለጠኑ የእምነት ጽናት ያላቸው የእጩ ታዛቢዎች በየምርጫ ጣቢያው በማሰማራት ታህሳስ 12/2007 ተመረጡ የተባሉት የህዝብ ታዛቢዎች በእድሜ የገፋውን መራጭ ህዝብ ሳያደናግሩ የምርጫ ካርዶችን እና የምርጫ ኮሮጆዎችን በገለልተኛነት እንዲያስተናግዱ በመከታተል፣ (ረ) እጩዎች ህዝቡ እንዲመርጣቸው የሚያደርጉ መልዕክቶች፣ የትምህርት ደረጃ፣ ማራኪ ባህሪ፣ ተወዳጅነትም እንዲኖራቸው በማድረ (ማሰልጠን ይቻላል)፣ (ሰ) ገዢው ፓርቲ ከሽንፈት ማምለጫ መከራከሪያ እንዳይኖረው እና ሽንፈትን ሳያንገራግር እንዲቀበል ለማድረግ ይቻል ዘንድ በሚሸነፍባቸው የምርጫ ጣቢያዎች እና የምርጫ ክልል ወረዳዎች ሽንፈቱ በከፍተኛ ድምጽ (landslide) እንዲሆን ማድረግ (ሸ) የምርጫ ጣቢያዎች ሲዘጉ ድምጽ ተቆጥሮ አሸናፊ እስኪታወቅ መራጩ ህዝብ ከየምርጫ ጣቢያዎች ርቆ እንዳይሄድ ማድረግ። የህዝብ ድምጽ ከተሰረቀ መራጩ ህዝብ ድምጼን ካላከበርክ እኔም የአንተን ገዢነት አላከብርም የሚል እንቅስቃሴ ሊጀምር ይችላል። ስለዚህ በእነዚህ አገሮች የሚደረግ ምርጫ በአግባቡ ከተያዘ እና ከተመራ የህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤትነት ማምጫ መንገድ ነው። ዴሞክራሲን ማምጫ ነው።
  • ዴሞክራስ ባልሰረጸባቸው እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገሮች ውስጥ የሚደረግ ጠብመንጃ-መር ትግል (ለምሳሌ፥ ትጥቅ ትግል፣ የከተማ ግድያ፣ ሽብር፣ በፕላን ያልተመራ ሰላማዊ አመጽ፣ ወ.ዘ.ተ. ) አምባገነን ማምጫ ነው።
  • ዴሞክራስ ባልሰረጸባቸው እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገሮች ውስጥ በሚደረግ ምርጫ የምርጫ ፓርቲዎች በተካሄደው ምርጫ የተገኙ ፖለቲካዊ እና ድርጅታዊ ድሎችን መልቀም የሚያስችሉ ዝግጅቶች ቀደም ብለው ማድረግ አለባቸው። ይኽን ለማድረግ በቅድመ-ምርጫ ዝግጅት፣ በምርጫ እለት እና ከምርጫ ማግስት ሊፈጠሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን (Scenarios) ቀደም ብለው መተንተን እና ቀዳዳዎችን መድፈን የሚያስችሉዋቸው ዝግጅቶች ማድረግ አለባቸው። በምርጫ 2007 የተገኙ ድሎች እንደ ምርጫ 1997 መባከን የለባቸውም። ገዢውን ፓርቲ ሊያስበረግጉ እና ሊያስቆጡ ከሚችሉ ድንፋታዎች፣ ዛቻዎች፣ ፉከራዎች፣ ትንኮሳዎች፣ መፈጸም የለባቸውም ተቃዋሚ የምርጫ ፓርቲዎች። ገዢው ፓርቲ ሽንፈት በደረሱበት አካባቢዎች ሽንፈትን የጀግኖች ሽንፈት አድርጎ መቀበል የተሻለ አማራጭ አድርጎ እንዲዎስድ ማበረታታት ያስፈልጋል።

 

 

ከሰላምታ ጋር

ግርማ ሞገስ

 

የወያኔ ፍሬ መራገፊያው ደርሷል !!!

$
0
0

ከ-ከተማ ዋቅጅራ

rtወያኔ ማለት፡- ወይ ያኔ የሚለውን ፍቺ ይሰጠናል። ወይ ያኔ ደግሞ የቁጭት ቃል ነው። ይሄ የቁጭት ቃል ምስረታቸው ጋር ይወስደናል።ጥቂት ሆነው ወደ መሰረቱት ጋር ያኔ ነበር ስሩን ማድረቅ ያኔ ነበር በአንድ ቦንብ እህ ማለት የሚለውን የቁጭት ቃል ይነግረናል። ወያኔ (ወይ ያኔ) ያኔ ተመሰረቱ ለነሱ አላማ፣ ለነሱ ድብቅ እቅድ፣ ለነሱ የደም ማፍሰ እርካታ፣ ተመሰረቱ። ታዲያ ያንን ድብቅ አላማቸውን ለማሳካት የራሳቸው የቅርብ ሰው የሚባሉትን በአላማቸው ያልሄዱትን የፈጁ እና ያስፈጁ የማፊያ ግሩፕ ናቸው። ምስኪኑን የትግራይ ህዝብ በማያውቀ ለድብቅ አላማቸው ያለምንም ርህራሄ ዳር ቆመው ድብቅ ሴራቸው ለማስፈጸም ወገኑን በማያውቀው እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ሲያደርጉ ልባቸው የደስታ እንጂ የሃዘን ስሜት አልነበራቸውም።

 
ወያኔ መሰረቱ ውሸት፣ ምሶሶው ውሸት፣ ግድግዳው ውሸት፣ ጣራውም ውሸት የሆነ የውሸተኞችና የማፊያ ግሩፕ ነው። አንድ ያነበብኩት ጽሁፍ ትዝ አለኝ፡ <<በኢሕአዲግ ዘምን የሚመረቁ ባለስልጣን እና ካድሬዎች ከአንድ ወፍጮ ቤት ተፈጭተው የወጡ እና እቤት ቁጭ ብለው ሁሉን ነገር በትእዛዝ የሚቀበሉ የወፍጮ ውጤቶች ምሩቆች ናቸው>> የሚለው ።በትክክል ይህ ሃሳብ ይገልጻቸዋል። ባለስልጣኑም ሆነ ካድሬው ወደ ወያኔ (ወይ ያኔ) ወፍጮ ቤት ይገባሉ 1ኛ ድግሪ 2ተኛ ድግሪ ማስተር ዶክተር ፕሮፌሰር እያለ የወፍጮ ውጤቶች የትምህርት ደረጃ ይሰጣቸዋል።ያልሆኑትን መሆን ያልሰሩትን ሰራን ማለት ተንኮል እና ውሸት ከመሰረቱ አይደለ። እናም ገና አፋቸውን ሲከፍቱ ማን ምን እንደሆነ ይታወቃል ወሬአቸው በሙሉ ዱቄት ዱቄት ይላል ምክንያቱም የአንድ ወፍጮ ፍጭት ውጤት ስለሆኑ ነዋ ! ምድረ ዱቄታም ሁሉ። አሁንማ ዱቄት ዱቄት የሚለውን ንግግራቸውን መስማት ህዝቡ ምን ያህል እንደሰለቸውና እንዳንገሸገሸው ቢያውቁት ዱቄት አፋቸውን በየመድረኩ በተገኘው አጋጣሚ አያቦኑብንም ነበረ።

 
ኢሕአዲግ ለህዝቦች እኩልነት የቆመ ድርጅት ነው ይሉናል ዋናዎቹ ካድሬዎች የወያኔ የወፍጮ ውጤቶች። እንዴት በምን አይነት መስፈርት በየትኛው ልኬት ነው ብለህ ስትጠይቃቸው በዱቄት አፋቸው ሳያፍሩ በዝርዝር ያቦኑታል እዚህ ዝርዝር ውስጥ አልገባም እኔም ዱቄት ማቡነን እንዳይሆንብኝ። ግን በትንሹ የህዝቡን ቁጥርና የስራ ድርሻቸውን እንቃኛለን። ለህዝቦች እኩልነት የቆመ ድርጅት ነው ስለሚሉ የቱ ጋር ነው እኩልነቱ ያለው የሚለውን ለማየት…. ኦሮሞ 34.5% አማራ 26.9% ሶማሌ 6.2% ትግሬ6.1% ሲዳማ 4.1% ጉራጌ 2.8% ወላይታ 2.3% ሃድያ 1.7% አፋር 1.7% ይሄንን የቁጥር አሃዝ ያገኘሁት ከgoogle wikipedia ላይ ነው። ታዲያ አሁን ወደ እውነታው ስንመጣ መከላከያ ሚኒስቴር በሃላፊነት ቦታ ያሉት 94% ወያኔ ነው ደህንነት ምንስቴር፣ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ጉምሩክ፣ ኢምግሬሽን፣ አየር መንገድ፣ አየር ሃይል፣ ቴሌኮሙንኬሽን፣ መብራት ኃይል ሌሎችም በሙሉ እድርና እቁብ እራሱ ሳይቀር በወያኔ ካድሬ ነው የተያዘው። ይሄንን ደግሞ አገር ቤትም ሆነ በውጪ ባለው ህዝብ የታወቀ ነው።

 
በዱቄት አፋቸው ኢሕአዲግ ለብሔር ብሔሮች ነጻነት አመጣ ብለው ዱቄታቸውን ያቦኑብናል።የቱጋር ነው የብሔር ብሔረሰቦች መብት የተከበረው ከታች እስከላይ ሃገሪቷን የተቆጣጠራችሁት እናንተ ያውም ያለ መስፈርት ምንም እውቀትና ችሎታ ሳይኖራቸው ሌላው ግን ችሎታ ኖሮት እውቀት ኖሮት አቅም ኖሮት በነጻነት መስራት ያልቻለ ስንት ዜጋ አለ ብለህ በምትናገርበት ግዜ በየቦታው የተቀጠሩት ካድሬዎች የወፍጮ ቤት ወሬአቸውን ይጀምራሉ አድጋለች ተመንድጋለች ይሄ ገባ ይሄ ወጣ ይሄ ሆነ…. ወዘተ ይሉናል መቼስ የወፍጮ ቤታቸውን ወሬአቸውን እንድደግምላችሁ እንደማትፈልጉ አውቃለው የወያኔን ባህሪ የማያውቀው ሰው የለም ያልተረዳቸውም ዜጋ የለም ስለዚህ ዱቄቱን በማቡነን ውድ ህዝቤን አላሰለቸውም።

 
አሁን ግዜው የሰፊው ህዝብ ነው የወያኔ የግፍ ጽዋ ሞልቷል ግፍ የሰሩና የሚሰሩ በአገራችን ምድር የሚነግሱበት ግዜ መቋጫው ደርሷል የሕወሓት ዋና ዋና የማፊያው መሪዎች እርስ በእርስ እየተባሉ ነው አውሬ አውሬን እንደሚበላው። የመከላከያው ሰራዊት ደግሞ ወታደሩ ከነ ሙሉ ትጥቁ እየካደው ነው። ህዝቡ ደግሞ ወያኔን ለመደምሰስ አጋጣሚውን እየጠበቀ ነው። ይሄ ነው ድል ከአሁን በኃላ የወይ ያኔ (ወያኔ) ድምጽ የሚሰማ የለም በፊት እንደ ፈለጉ ሲንሸራሸሩበት የነበረ አገር አሁን እንደፈለጉት መንሸራሸር ቀረ በፊት በውጪ ተዝናንተው ይኖሩ የነበረ አሁን ግን በውጪ የሚኖረው ዜጋ መፈናፈኛ አሳጥቶአቸዋል። በፊት እያሳደዱን እየደበደቡን እያሰሩን እያሰቃዩን እያንገላቱን እየገደሉን ይኖሩ የነበረ። አሁን ግን ነገሮች ሁሉ ተቀይሮ ግጥሚያው ፊት ለፊት ሆኗል። ህዝብን ያሸነፈ ማንም የለም ህዝብ ሁሌም አሸናፊ ነው። ከውስጥ እስከ ውጭ ከመሃል እስከ ዳር ከደቡብ እስከ ሰሜን ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በአንድነት ተነሰተናል ወያኔ ከገባበት ቃሪያ ውስጥ ሰንጥቀን ፍሬአቸውን ለማራገፍ በቆራጥነት ተነስተናል። ወያኔ ሆይ ከአሁን በኋላ ገድሎ መፎከር የለም አቃጥሮ መኖርም የለም አሰቃይቶ መክረምም የለም ጥቂቶችን የሆኑ ወያኔዎች ከነ ወፍጮ በታቸው ለማጥፋት ቆርጠን ተነስተናል። ኦሮሞው ጋር ሂድ ቆርጦ ተነስቷል አማራው ጋር ሂድ ቆርጦ ተነስቷል ሱማሌው ጋር ሂድ ቆርጦ ተነስቷል ደቡቡ ጋር ሂድ ቆርጦ ተነስቷል አፋሩ ጋር ሂድ ቆርጦ ተነስቷል።

 
ወይ ያኔ (ወያኔ) ሆይ አርቀህ የቆፈርከውን የግፍ እና የመከራ ጉድጓድ ከነጭፍሮችህ በመቅበር ለድል ለነጻነት ለዲሞክራሲ ለእኩልነት ለእድገት የምንዘምርበት ግዜ ደርሷል። ህዝቤ ሆይ ወይ ያኔን(ወያኔ) እንደ ቃሪያ ፍሬ አራግፈን እናስወግደው::ነጻነት ፈላጊ ነጻነት ያመጣል።

 
ከ-ከተማ ዋቅጅራ
Email-waqjirak@yahoo.com


ፍትሕ አያረጅም! የኢትዮጵያና የአርሚኒያ ትግል -ኪዳኔ ዓለማየሁ

$
0
0

መግቢያ፤

Justiceኢትዮጵያንና አርሚኒያን ከሚያመሳስሏቸው ጉዳዮች አንደኛው የአንድ ዓይነት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የእምነት መሠረት (ዶግማ) ተከታዮች ያሉባቸው ሐገሮች መሆናቸው ነው። በዚህ ጽሑፍ የማተኩርበት ተመሳሳይነት ግን ሁለቱም ሐገሮች በከባድ የጦር ወንጀሎች ተጠቅተው እያንዳንዳቸው ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ የተጨፈጨፈባቸው መሆኑ ነው። ሌላም እጅግ አስጸያፊ ግፍ የተፈጸመባቸው ሐገሮች ናቸው። በተጨማሪም፤ ሁለቱን ሐገሮች ያቀራረባቸው ሌላው ጉዳይ በኦቶማን ዘመነ መንግሥት፤ ከቱርኮች ግፍ በመሸሽ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት መልካም ፈቃድ ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት 40 አርመኖች ኑሯቸውን በሐገራችን መቀጠላቸው ነው። እነዚህ አርመኖችና ተወላጆቻቸው በኢትዮጵያ ተመቻችተው የኖሩና ብዙዎቹም አማርኛውን ያቀላጥፉ እንደ ነበር የታወቀ ነው። በዚህ አጋጣሚ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት ዱባይ በምሠራበት ጊዜ እዚያ ይኖር የነበረውን፤ ወዳጄን፤አቶ የርቫንትን እያስታወስኩ፤ አርመኖች ያቋቋሟትን ሻርጃ (Sharjah) የምትገኝ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያውያን ምእመናን በማጋራታቸው፤ ውለታቸውን አልረሳውም።

በአርመኖችና በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸሙት እልቂቶችና የጦር ወንጀሎች፤

በአርመኖች ላይ የተፈጸመው የጦር ወንጀል እ.አ.አ በ1915-23 በኦቶማን (Ottoman) (በኋላ ቱርክ) ዘመነ መንግሥት መገባደጃ ጊዜ ነበር። እንደሚታወቀው፤ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመው እልቂት እ.አ.አ በ1935-41 በኢጣልያ ፋሺሽቶችና በቫቲካን ያልተቆጠበ ድጋፍ የተከናወነ ነበር። ከላይ እንደ ተገለጸው፤ ሁለቱም ሐገሮች ቢያንስ አንድ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ተጨፍጭፎባቸዋል። በተጨማሪም እጅግ ብዙ አርመኖች ከሐገራቸው እንዲሰደዱ ተገድደው ለከባድ ችግር ተጋልጠዋል። በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመው ግፍ በብዙ የኢጣልያ አውሮፕላኖች በተነሰነሰው የመርዝ ጋዝ እንዲሁም በሌሎች ልዩ ልዩ መሣሪያዎች የተጨፈጨፈው ሕዝብ፤ (በሶስት ቀኖች አዲስ አበባ የተገደሉት 30 000 ኢትዮጵያውያን ጭምር) ብቻ ሳይሆን የወደሙትን 2 000 ቤተ ክርስቲያኖች፤ 525 000 ቤቶችና 14 ሚሊዮን ያህል እንስሶች ያካትታል። በተጨማሪም እጅግ ብዙ ዝርፊያ የተከናወነ መሆኑ የታወቀ ነው።

የአርመኖች ትግል ለፍትሕ፤

በአርመኖች በኩል፤ ከ100 ዓመት በፊት በቱርኮች ለተፈጸመባቸው ወንጀል ተገቢውን ፍትሕ ለማስገኘት ያላሰለሰ ትግላቸውን እየቀጠሉ ነው። መሠረታዊ ዓላማቸውም ያ ከባድ ጥቃት የዘር ማጥፋት ወንጀል (genocide) መሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅላቸው ለማድረግ ነው። በዚህ በፈረንጆች የዘመን አቆጣጠር በ2015 የእልቂቱ መቶኛ ዓመት የሚደፍን በመሆኑ በሰፊው ለመዘከር እቅድ አላቸው። በዚህ ተግባር ከተሰማሩት ውስጥ፤ የአርመን መንግሥት እንዲሁም በአሜሪካ የሚገኙ፤ (ሀ) የአርመን ብሔራዊ ኮሚቲ በአሜሪካ (Armenian National Committee of America) (www.anca.org) እና (ለ) የአሜሪካ አርመናዊ ሸንጎ (Armenian Assembly of America) (www.aaainc.org) ይገኙበታል።

ሰሞኑን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መማከሪያ (Foreign Affairs Council) በተሰኘው ድርጅት አማካኝነት ታትሞ በወጣው ፎሪን አፌርስ (Foreign Affairs) መጽሔት (January/February 2015)፤ ቶማስ ደ ዋል (Thomas de Waal) የተባለ ዘጋቢ፤(“The G-Word; The Armenian Massacre and the Politics of Genocide”) (ትርጉም፤ የጂ-ቃል፤ ስለ አርመኖች እልቂትና የዘር ማጥፋት ፖለቲካ) በሚል አርእስት የሚከተሉትን ቁም-ነገሮች አቅርቧል፤

(ሀ) እ.አ.አ. በ1918 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቲዮዶር ሩዝቬልት (Theodore Roosevelt) በአርመኖች ላይ ስለ ተፈጸመው ስደትና እልቂት አሜሪካ በኦቶማን መንግሥት ላይ ጦርነት ማወጅ አለባት በማለት ሐሳባቸውን በደብዳቤ ገልጸው ነበር።

(ለ) የአርመኖች የፍትሕ ትግል በአሜሪካ መንግሥት መርሆ ላይ ከፍተኛ አጽንኦት አስክትሏል። እ.አ.አ. በ1951 የአሜሪካ መንግሥት ጠበቆች ቱርኮች በአርመኖች ላይ የፈጸሙት እልቂት እንደ የሰው ዘር ማጥፋት ወንጀል (genocide) እንዲታይ ሔግ (The Hague) ለሚገኘው ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (International Criminal Court) አመልክተው ነበር። ነገር ግን የተባበሩት መንግሥታት የዘር ማጥፋት ወንጀል ስምምነት (United Nations Genocide Convention) የታወጀው እ.አ.አ. በ1948 ከአርመኖች እልቂት በኋላ በመሆኑ እስካሁን ጉዳዩን ለፍርድ የማቅረቡ ሒደት አልተሳካም።

(ሐ) እ.አ.አ. በ1975 የአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት (House of Representatives) መሪ፤ ቲፕ ኦኒል (Tip O’Neill) እ.አ.አ. ሚያዚያ 24ን (April 24) የሰውን ልጅ የርስ በርስ ኢሰብአዊነት ብሔራዊ የመዘከሪያ ቀን (National Day of Remembrance of Man’s Inhumanity to Man” ተብሎ እንዲሰየምና በዘር ማጥፋት ወንጀል የተጠቁትን በሙሉ፤ በተለይም እ.አ.አ. በ1915 ለተሰዉት አርመኖች መታሰቢያ እንዲሰየም ሥልጣኑን ለአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሰጠበት የውሳኔ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ነገር ግን በሌላው የአሜሪካ ምክር ቤት፤ በሴኔት (Senate) የአርመኖችን እልቂት እንደ የዘር ማጥፋት ወንጀል የመቁጠር ጉዳይ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።

(መ) ፕሬዚዳንት ሬጋንም (President Reagan) በመጀመሪያ በ እ.አ.አ. በ 1981 ለአርመኖች የዘር እልቂት (genocide) እውቅና በመስጠት ገለጻ አድርገው ነበር። ነገር ግን እ.አ.አ. በ1982 ሁለት አርመናዊ ወጣቶች በሎዛንጀለስ ከተማ የቱርክ ቆንስል መሪ የነበረውን ከማል አሪካንን (Kemal Arikan) በመግደላቸው የፕሬዚዳንት ሬጋን አቋም ተለወጠ።

(ረ) የቱርክ መንግሥት ለአሜሪካ ጠንካራ ድጋፍ ከሚያበረክቱት መንግሥቶች አንዱ በመሆኑ በተለይም የሰሜን አትላንቲክ ሐገሮች ድርጅት (NATO) አባል በመሆኑ በአርመኖች ላይ ስለ ተፈጸመው የኦቶማኖች የጦር ወንጀል አሜሪካ ያላት አቋም ተለዋዋጭ ሆነ።

(ሠ) የአሜሪካና የቱርክ መንግሥቶች ባላቸው የጥቅም ቅድሚያ ለአርመኖች የሚገባውን ፍትሕ ለጊዜው ያመከኑት ቢመስልም የአርመን ታጋይ ድርጅቶች የመቶ ዓመት ጥረታቸውን አጠንክረው እየቀጠሉ ነው። ለዚህም በምርጫ መብታቸው እየተጠቀሙ በአሜሪካ የኮንግሬስ አባሎችና በሐገሩ ፕሬዚዳንት ላይ የማያቋርጥ አጽንኦት እንዲከሰት ለማድረግ እየጣሩ ነው። የዚህም ጥረት ውጤት አንደኛው ምሳሌ፤ እ.አ.አ. በሚያዚያ 24 ቀን 2010፤ ፕሬዚዳንት ኦባማ (President Obama) የሚከተለውን ገለጻ ማድረጋቸው በቶማስ ደ ዋል ጽሑፍ ተዘግቧል፤

“1.5 million Armenians were massacred or marched to their death in the final days of the

Ottoman Empire……..The Meds Yeghern (“Great Catastrophe”) is a devastating chapter in the

History of the Armenian people, and we must keep its memory alive in honor of those who

were murdered and so that we do not repeat the grave mistakes of the past.”

(ትርጉም፤ በኦቶማን መንግሥት የመጨረሻዎቹ ቀናት 1.5 ሚሊዮን አርመኖች ተጨፍጭፈዋል ወይም ለሞት

ወደሚዳርጋቸው እንዲጓዙ ተደርገዋል። ታላቁ ሰቆቃ (መቅሠፍት) በአርመኖች ታሪክ እጅግ አሰቃቂ ምእራፍ

ነበር። ያለፈውን ስሕተት እንዳንደግመው ለተገደሉት ሰዎች ክብር የዚያን ዘመን ትዝታ ሕያው አድርገን

 

 

ልናስታውሰው ይገባናል።)

ከዚህ በላይ ከተዘረዘረው መገንዘብ የሚቻለው፤ ምንም እንኳ አርመኖች የሚፈልጉት፤ ማለትም በቱርኮች የተፈጸመባቸው ጭፍጨፋ እንደ የዘር እልቂት ወንጀል (genocide) የማሳወቅ ዓላማ እስካሁን ባይሳካላቸውም ጥረታቸው በከፍተኛ ደረጃ እየቀጠለ የአሜሪካ መሪዎች ጭምር ተስፋ አላስቆረጧቸውም። “የአርመን ብሔራዊ ኮሚቲ በአሜሪካ” ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ዲሬክተር የሆነችውን ወ/ሮ ኤሊዛቤት ሹልድጂያንን (Elizabeth Schouldjian) ሰሞኑን በስልክ አነጋግሬያት አርመኖችና የአርመን መንግሥት ትግላቸውን የሚቀጥሉ መሆኑንና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚያከናውኑት እንቅስቃሴ ከአውሮፓ የሰብአዊ መብት ፍርድ ቤት ጋር ጭምር ጉዳዩን እንደሚገፉበት ገልጻልኛለች።

የኢትዮጵያስ ትግል?

ኢትዮጵያ ለተፈጸመባት እጅግ አሰቃቂ ግፍ ተገቢውን ፍትሕ አላገኘችም። ካሣ ተብሎ ለቆቃ ግድብ መሥሪያ የዋለው $25 ሚሊዮን እና ወደ ሐገሩ የተመለሰው የአክሱም ሐውልት በምንም መስፈርት ብቁ ነው ሊባል አይችልም። ኢጣልያ ለሊቢያ $5 ቢሊዮን፤ ለዩጎዝላቪያ $125 ሚሊዮን፤ ለግሪክ ሐገር $105 ሚሊዮን፤ ለሶቪየት ዩኒየን $100 ሚሊዮን፤ ወዘተ ከተስማማችው ጋር ሲመዛዘንና በተለይም በኢትዮጵያ ላይ ከፈጸመችው ክፍተኛ የጦር ወንጀል ጋር ሲነፃፀር በግልፅ የሚታየው የተዛባ ፍትሕ የሚያስቆጭ ነው። “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንደሚባለው፤ ኢጣልያ የፈጸመችው ወንጀል አልበቃ ብሏት፤ በቅርቡ፤ የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት፤ አፊሌ በምትባል የኢጣልያ ከተማ፤ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” በመባል ለሚታወቀው፤ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ አንድ መታሰቢያና መናፈሻ ተመርቆለታል። እንደ ኬንያና ኢንዶኒዚያ ያሉ ሐገሮች ከቀድሞ አጥቂዎቻቸው ከእንግሊዝና ከኔዘርላንድስ ተገቢውን ይቅርታ ተጠይቀው ካሣ ጭምር ሲከፈላቸው ኢትዮጵያ የተሟላ ፍትሕ ሊነፈጋት አይገባም። ስለዚህ፤ ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ (Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause) የተሰኘው ድርጅት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ዓላማዎች እየታገለ ይገኛል፤

(ሀ) የኢጣልያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል፤

(ለ) ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤

(ሐ) የኢጣልያ መንግሥትና ቫቲካን የተዘረፉትን ንብረቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲመልሱ፤

(መ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፋሺሽት ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመችውን የጦር ወንጀል

እንዲመዘግብ፤ እና

(ሠ) በቅርቡ ለፋሺሽቱ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” ለሮዶልፎ ግራዚያኒ ኢጣልያ ውስጥ በአፊሌ ከተማ፤  የተሠራው

መታሰቢያ እንዲወገድ።

አቤቱታውንም ለሚመለክታቸው ሁሉ፤ ለኢጣልያ መንግሥትና ለቫቲካን፤ ለአውሮፓ ምክር ቤት፤ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ ለፕሬዚዳንት ኦባማና ለሌሎች አንዳንድ የዓለም መንግሥታት መሪዎች፤ እንዲሁም በፍትሕ ለሚያምኑ ሰዎች በሙሉ አቅርቧል። በዚህ አጋጣሚ በየዓመቱ የካቲት 12ን ለመዘከር በ30 ከተሞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሐገር ፍትሕና ክብር ለሚንቀሳቀሱ ሁሉ ልባዊ ምሥጋና ይድረሳቸው። የኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበርም የሚያከናውነው ጥረት ሊጠቀስ ይገባል።

በተጨማሪም፤ በድርጅቱ ድረ-ገጽ (www.globalallianceforethiopia.org) የሚገኝ፤ ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ እየተፈረመ ያለ ዓለም አቀፍ አቤቱታ ይገኛል። እስካሁን ክ4200 ሰዎች በላይ ፈርመውታል። ይህንን ጽሑፍ የሚመለከቱ ሁሉ አቤቱታውን እንዲፈርሙት ተጋብዘዋል።

 

 

 

4

ለውድ ሐገራችን ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕና ክብር እስካሁን የተከናወነው ጥረት የሚያበረታታ ቢሆንም በውጤት ደረጃ አመርቂ ደረጃ አልደረሰም። በተለይም አርመኖች ለክብራቸውና ለሐገራቸው ፍትሕ ከሚያከናውኑት ትግል ጋር ሲነፃፀር በኛ በኩል ጥረታቻችንን ማጎልበት እንደሚገባን ግልጽ ነው። ስለዚህ ለሐገርና ለፍትሕ የሚቆጭ ሁሉ በትግሉ እንዲሳተፍና እንዲደግፍ ያስፈልጋል። የአገር ወዳዶች የተባበረ ጥረት የትግሉን ውጤት የተሳካና የተፋጠነ ለማድረግ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

ቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ ለሐገራችን የሚገባው ክብርና ፍትሕ እንዲገኝ የጀመርነውን ጥረት፤ በሁሉም አገር ወዳድ ተሳትፎ፤ አጠናክረን እንድንቀጥል ብርታቱን ይስጠን። አሜን!

 

 

ሰው በላውን ወያኔን እናጠፋዋለን!!! -ከ-አዲስ ብርሃኑ

$
0
0

 ከ-አዲስ ብርሃኑ

andargacew Tsigeአንዳርጋቸውን ሳስበው ውስጤ ያለው የኢትዮጵያዊነት ወኔ ይቀጣጠልብኛል። ብርሃን ካለ  ጨለማ  የለም ብርሃን ከሌለ ግን ጨለማ አለ። አንዳርጋቸው ማለት ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ብርሃን ማለት ነው። የለኮሰው ብርሃን በኢትዮጵያ በሙሉ የሚበራ ብርሃን ነው። አንድአርጋቸው በኢትዮጵያ የለኮሰው ብርሃን የሰላም ብርሃን ነው፣ የፍቅር ብርሃን ነው፣ የቆራጥነት ብርሃን ነው፣ የጀግንነት ብርሃን ነው፣ የአንድነት ብርሃን ነው፣ የትግል ብርሃን ነው። በዚህ ብርሃን ውስጥ የማይጓዝ ማንም ኢትዮጵያዊ የለም። አንድአርጋቸው የኢትዮጵያ ብርሃን!!!የእውነት ብርሃን ጥቅም ያለወጠህ ብርሃን የለኮስከው የነጻነት የትግል ሻማ አንተ ሻማ ሆነህ እየቀለጥክ ብርሃንነትን የለበስክ የኢትዮጵያ ብርሃናዊ ጀግና  አንተ  ነህ።

ወያኔ የፈራው ስራህን ብቻ ሳይሆን ስምህንም ጭምር ነው። አንድነት ለወያኔ አይመቸውም አንድነትን ይፈራል ህብረትን ይጠላል ለያይቶ እና ከፋፍሎ መግዛትን ነው የሚፈልገው። ስለዚህ አንድአርጋቸው ሲባል ያባንነዋል።ወያኔ ለዘረፋው አንድነት አይመቸውም ለተንኮል ስራው አይመቸውም ስለዚህ እንኳን ስራህን ስምህንም አይወዱትም። በኢትዮጵያዊያን ግን ስምህም ተግባርህም ይወደዳል። እዚህ ጋር ነው ቁም ነገሩ በህዝብ መወደድ እና መከበር። የኢትዮጵያ  ህዝብ የሰላም ብርሃን የለኮሱትን እና ወደ ብርሃን የሚወስዱትን ብርቅዬ ታጋይ በማይጠፋው በኢትዮጵያዊ መዝገብ ውስጥ ጽፈው ያስቀምጧቸዋል ። ወያኔ እና ከነግብርአበሮቹ ግን ከነስራቸው ይጠፋሉ።

ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ የተለቀቀውን ቪዲዮ አይቼ በጣም ነውያፈርኩት በቪዲዮ መግቢያው ላይ ምዕራባዊያን የእስር አያያዝ ላይ ትችት ሲያቀርቡ ኢትዮጵያ  ውስጥ ግን የእስረኛ  አያያዝ በሰላም እንደሆነ እጅ እጅ ያለውን ወሬአቸውን በተለመደ የውሸት ቋንቋቸው ዛሬም ሲደግሙት አይናቸውን በጨው አጥበው በመቅረብ አንዳርጋቸው የሚናገረው ንግግር እራሱ ፈልጎ እንደሆነ አድርጋችሁ አቀረባችሁ። ቪዲዮው ስንመለከት ግን 14 ደቂቃ ባልሞላች ንግግር ውስጥ የአንድአርጋቸው የለበሰው ልብስ በየደቂቃው የቀያየራል ቪዲዮው በየደቂቃው ይቆራረጣል ይበጣጠሳል በዛ ላይ የተላለፈው መልእክት ምን እንደሆነ የማይገባ። ይህንን ቪዲዮ እንደ ኢትዮጵያዊ ሆኜ ሳስበው  በጣም አሳፋሪ ነው እንደ  ወያኔ አውሬነት ሳየው ደግሞ የምጠብቀው ስለሆነ አይደንቅም የሚገርመው  የካድሬዎች ጫጫታ ነው ተንጫጩ እኮ ወይ መንጫጫት በዚህ ዘምን የሚታለል ወይም የወያኔን ስራ የማያውቅ ማንም ኢትዮጵያዊ የለም ኢትዮጵያ  ውስጥ የመንግስት አቸባሪ ነው ያስቸገረው። አንዳርጋቸው የለኮሰው የትግል ብርሃን ወያኔን ጥሎ  ካልሆነ  በስተቀር መቆሚያ  የለውም።

ወያኔ የአንድአርጋቸውን  ጽጌ ቪዲዮ የለቀቀው ግራ  ገብቶት ነው ወያኔ ሲጨንቀው ሲጨንቀው ማስተንፈሻ ይፈልጋል ሰሞኑን 3ት የአየር ሃይል አብራሪዎች ከነ ሄልኮፕተር ወደ ኤርትራ መግባታቸው ወያኔን መካዳቸው ያስደነገጠው በተጨማሪም 4ት የአየር ሃይል የተዋጊ አብራሪዎች ወደ ኬኒያ መግባታቸው እና የመከላከያ ሰራዊት ከነ ትጥቁ እየከዳቸው ስለሆነ የመውደቂያው ዋዜማ  ላይ መሆኑን ስላወቀው ስለደነገጠ ማስተንፈሻ ስለፈለገ የህዝቡን ሃሳብ ለመበተን በጣም አሳፋሪ እና የተቆራረጠ በዛ ላይ ሃሳቡ ግልጽ ያልሆነ  ቪዲዮ ለመልቀቅ ተገደዋል። አሁን ወያኔ  በሚደሰኩረው ዲስኩር ዲስኩር ተታሎ ግዜ ሰጥቶ የሚያወራ ቢኖር ወያኔ እና ካድሬዎች ብቻ ናቸው። እኛ ግን አንዳርጋቸው በለኮሰው የብርሃን የትግል ጉዞ ተጉዘን ወያኔን ለመደምሰስ ቆርጠን ተነስተናል። ወያኔ ሆይ አሁን የዘራኽውን ማጨጃህ ሰዓት ላይ ነህ። የኢትዮጵያ ህዝብ የተገደለበት የቆሰለበት የተደበደበበት የተሰደደበት የተረገጠበት የተናቀበት ግዜ አብቅቶ ኢትዮጵያዊው ቁጭቱን ለከፍል ቆርጦ ተነስቷል። ህዝብ ያቸንፋል ወያኔ እና ካድሬዎች ለአንደ እና ለመጨረሻ ግዜ ይጠፋሉ።

ድል ለኢትዮጵያዊያን!!!

ከ-አዲስ ብርያኑ

የማለዳ ወግ … ሰሚ እስኪገኝ እያነባን እንጮሃለን ! – ነቢዩ ሲራክ

$
0
0
የማለዳ ወግ … አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም ?

* የኮንትራት ሰራተኛዋ አይነ ብርሃኗን ማጣትና የስም የለሿ ሟች እህት መጨረሻ   !
*  ሰሚ እስኪገኝ እንጮሃለን  !

saudiwታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም ሰኞ በማለዳው ያገኘኋቸው ሁለት መረጃዎች የወጡት በሁለቱ አንጋፋ የሳውዲ ጋዜጦች በአረብ ኒውስ Arab News  እና በሳውዲ ጋዜት Saudi Gazette  ነው ። በአንዱን አይቸ ቢከፋኝ ፣  መፍትሔ ላይገኝ ይህን መርዶ ከንፈር ለማመስመጠጥ  ብቻ መረጃ ብየ ልለጥፍ ይሆን ?  እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገጥሜ ነፍሴን ሳስጨንቀት በሌላኛው ጋዜጣ የወጣውን ሌላ መረጃ አንድ ወዳጀ በጓዳው የመልዕክት መሰረጫ እንደኔው ማልዶ ያጋጠመውን የወገን መከራ አደረሰኝ ። ሁለቱንም አሳዛኝ መረጃዎች ተመለከትኳቸው ፣ ያማል ብቻ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም  !

     sau-wo-300x213መዲና የተባለች እህት በጽዳት ላይ እያለች አይኗ ላይ ተፈናጥሮ የገባው መርዝ የአይን ብርሃኗን አሳጥቷት በከፋ አደጋ ላይ ወድቃለች  ፣ ሴት አሰሪዋ መዲናን ለማሳከም ደፋ ቀና ቢሉም ለህክምና የተጠየቀው ወጭ ለአቅማ ቸው በላይ በመሆኑ ነገሮች የተወሳሰቡ መሆኑ ተጠቁሟል መረጃው የሳውዲ ጋዜጥ ነው  …. !  መረጃውን በፊስ ቡክ ካሰራጨሁት በኋላ ለማጣራት ሞክሬ እንደተረዳሁት ስትታመም ስትጎዳ ሊያሳክሙ ፣ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ ከለላ በጅዳ ቆንስል የመጣችው እህት ጉዳዩዋን የሚከታተልላት ቀርቶ የመዲናን ለዚህ አደጋ መጋለጥ የሚያውቅ የመንግስት ተወካይ የለም  !
    ሌላዋ እህት የሆነችውን አረብ ኒውስ በአንዲት የጋዜጣው ጠርዝ ካይ እንዲህ ሲል በአጭር አረፍተ ነገር አስፍሮታል ” ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ አል ጀውፍ በተባለ የሃገሪቱ ግዛት በአሰሪዋ ቤት ራሷን በመስቀል ራሷን በራሷ ገድላለች “ይላል  …መረጃው የአረብ ኒውስ ነው  …. !   ስለዚህች እህትም ቢሆን በአቅራቢያው ያለው የሪያድ ኢንባሲ መረጃ የለውም  ፣ መረጃውን ቀድመው ይወቁት አልልም ፣ ቢያንስ ከእኛ እኩል በየጋዜጣው የሚወጣውን እንኳ አለማወቃቸውን እኩለ ቀን ላይ ወደ ሪያድ ኢንባሲ ደውየ ለማወቅ ችያለሁ  ! ሁሉም ያማል  !
ከሳምንት በፊት እኔ ከምኖርበት ጅዳ ከተማ ልጆችን ወደ ት/ቤት በማድረስ ላይ እያለች በተፈጠረ መኪና ግጭት የያዘቻቸውን ህጻናት አትርጋ እሷ መስዋዕትነት የከፈለችን ትጉህ እህት ያዩ አረቦች ተገርመው በምትሰራበት ቢተ ሲጫወቱ የሰማች እህት ታሩኩን በደፈናው ብትነግረኝም ዝርዝር መረጃ አለነበረውምና በዝምታ አልፊው ነበር።  ዛሬ እኩለቀን ላይ ከላይ የጻፍኩትን የሁለቱን ጋዜጦች መረጃ የተመለከተ ወንድም አንዲህ የሚል መልዕክት ደረሰኝ ይህን “ሄሎ ነብዩ ሰላም ነህ ነብዩ በአንድ ጉዳይ ፈልጌህ ነበር
ስልክህን  ልትልክልኝ በትህትና እጠይቃለህ በጣም የማከብሪህ  እና ማደንቅህ …” ይላል ፣ አመስግኘ ስልኬን ሰጠሁት ፣ ምሽቱን ደውሎልኝ ከባድ የመኪና አደጋ ደርሶባት ራሷን የማታውቀውን እህት ጉዳይ አንስቶ በዝርዝር አጫወተኝ ፣ ይህች እህት ያን ሰሞን የአሰሪዎቿን ልጆች አትርፋ መኪናው የዳጣት ለመሆኗ ብዙ መሄድ አላስፈለገኝ። ከወዳጀ ጋር ይህችን ምንዱብ የአልጋ ቁራኛ ለማየት ቀጠሮ ብንይዝም አልስቻለኝምና ወደ ተባለው ሆስፒታል ሄጀ የማትሰማ የማትናገረውን እህት አይቻት ሰላሜን በገዛ እጀ አጥቸ ተመለስኩ  !
    ማለዳ በሰማሁት ባነበብኩት ምሽት  ላይ ባየሁት ውስጤን  ጥሩ ስሜት አልተሰማው ምና ከንዴት በሽታ ውጭ ምንም ላላመጣ በስጨት አልኩ  ፣ ዝም ማለት ግን አልለመደ ብኝምና እናገረዋለሁ  !  … ደግሞ ብስጭቴን ስጽፈው ይቀለኛልና መቸክቸክ ያዝኩ …
ሰሚ ያጣ ጩኸት …
    መረጃ ማቀበሉ በህግ አስፈጻሚ አካላት በኩል ውጤት አለማምጣቱን አሰላስየው የአፈ ጉባኤ አባ ዱላን ሰሞነኛ የሳውዲ ጉብኝትና መፍትሔ እንደማያመጡ እያወቀ እንደኔው ባለመተንፈሱ የተበሳጨውን የጅዳና የሪያድ ነዋሪ አስታወስኩ ! ከምንሰማ ከምናየው የዜጎች አበሳ ጋር ሰሚና ሁነኛ የመብት አስከባሪ የበላይና የበታች ሹማምንት አጥተን በስቃይ ላይ ለመሆናችን ምስክሮች የምናቀርባቸው መረጃዎች ናቸው ። በሳውዲ 350 ሽህ የኮንትራት ሰራተኛ እንዳለ በመንግስት ተረጋግጦ እየተነገረን ፣ የተበተኑት መብት ሳይጠበቅ አዳዲስ መከረኞችን አምጥተን ልንደፋ  ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ይመስላል ።  እኛ ይህ ነገር በተቀናጀ ጥናት፣ በበቂ ዝግጅት ፣ በበሳል አመራር  ካልተመራ ሌላ አደጋ አለው እያልን ነው ።  መከራ ብሶቱን ፣ አሰከፊ ምስሉን እያሳየን ” አረ ያገር ያለህ !”  እያልን እጮህን ነው  ! ሰሚ ህግ አውጭና ህግ አስፈጻሚ ግን የለም  ! ሰሚ ያጣው ጩኸታችን ሰሚ እስኪገኝ ግን ዝም አንልም ፣ እንጮሃለን  !
ግን ለምን አልሰሙንም ?

የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በሳውዲ አረቢያ ጉብኝት አድርገዋል። የሰራተኛ ሚኒስትር አድል ፈቂን ጨምሮ በርካታ የመንግስ ሃላፊዎች አግኝተው እኔና መሰሎቸ ሌት ተቀን ስለምንናገረው በቂ ዝግጅት ሳይደረግ ስለተላኩ የእኛ ዜጎች ለአባ ዱላ ነግረውልናል ።  አፈ ጉባኤ አባ ዱላ በኮንትራት ሰራተኞች ጉዳይ ከሳውዲዎችና መብታችን ካላስጠበቁልን የሪያድ ኢንባሲና የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ፣ በሃላፊዎች  ከተመረጡ  የሪያድ የጅዳ “የተከበሩ ምርጥ” ዜጎች ፣  ከኢህአዴግ የድርጅትና ከተለያዩ ጥሪ ከተደረገላቸው የ ማህበር አባላት ጋር  መክረዋል።

አፈ ጉባኤውና ልዑካኑ በአንጻሩ በማህበራዊ ኑሮው ፣ በመብት ጥበቃው ፣ በኮንትራት ሰራተ ኞች የለት ተለት የመረረ እውነት ተመልካችና ገፋች የሆነውን ነዋሪ ጠርተው ቀርቶ ሊያይ ሊያነጋገራቸው ሄዶ በሆድ አደር አጋፋሪዎች ተከልክሏል። ነዋሪ ዜጋው እንዲህ ተገፍቶ  የሃገሪቱ የበላይ ህግ አውጭ የሆነው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሳያዩትና ሳያነጋግሩት ሔደዋል ። የአፈ ጉባኤ አባ ዱላን ማግኘትና ብሶቱን ማሰማት የፈለገው ነዋሪ ጉጉት ምን ይሆን ? ብየ ጠያይቄም ነበር ። ያገኘሁት የምላሽ እውነታ ነዋሪው ማቆሚያ ስለጠፋው የኮንትራት ሰራተኞች አበሳ ለመናገር መተንፈስ እንጅ መጓጓቱ መፍትሔ ከባለስልጣኑ ይገኛል ብሎ አለመሆኑን ተረድቻለሁ።  እውነት ነው አባቶች  ” ድሃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ… ” እንደሚሉት ሆነና  ነዋሪው ሆየ ብሶቱን ማሰማቱ ህመሙን ያቀልለት መስሎታል  ! ፕሬዚደንትና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ እስካሁን ሳውዲ ለመጡት ከፍተኛ ባለስልጣኖች የአለ የሌለ የተባለውን ጥያቄ አቅርቦ ምልስ እንዳልተገኘ አሳምሮ የሚያውቀው ነዋሪ በዚህና በዚያ ተስፋ  ቆርጧል… ግን ተስፋ ቆርጦም መናገር መተንፈስ ይፈልጋል !

የአስፈሪው ቀን መቅረብ  ምልክቶች …

በሳውዲ መንግስት የተዘጋው የኮንትራት ሰራተኞች ይጀመራል ተብሎ በዋና ዋና ደላሎች ወሬው ከተነዛ ወዲህ በመንግስት በኩል የረቂቅ ደንቡ መውጣቱን ሰምተናል ። ጸድቆ ጉዞው ሊጀመር ተቃረበ ሲሉን ደግሞ አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ ከሳውዲ ባለስልጣነናት ጋር ስለአዲሱ ረቂቅ ህግ መምከራቸውን ሰምተናል ! ከሳውዲዎች ጋር   ስለመከሩ ስለዘከሩበት ህግ በሳውዲ ነዋሪ ከሆነው ኢትዮጵያዊ ጋር አለመምከራቸው ግን ታላቅ ታሪካዊ ስህተት ነው ባይ ብዙ ነን  !  ነዋሪው ብሶቱን ለመናገርም ሆነ ከመምከር መወያየቱ የሚገኝ ፋይዳ አለ ብሎ ሳይሆን እንደ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ ባለ ስልጣን ለምን ዜጎችን እኩል አይተው አላነጋገሩንም ? ሃሳባችን ለምን አያደምጡትም? ለምን አልሰሙንም ?  ለምን የታመቀ ችግራችን ቢያንስ አላዳመጡንም  ? በኦሮሞ ልማት የተመረጡ አባላት ሰብስበው ለቴሌቶን ብር ከመሰብሰብ በስደት ስላለው ስለከፋው ዜጋ መምከር ለምን አለቀደመም?   አፈ ጉባኤ አባ ዱላ  እንደ ኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት ሳውዲን እየጎበኙ ለምን ወደ ዘውግ አድልተው ወርደው ጊዜን ማባከብ አስፈለጋቸው? በጉብኝታቸው ሁሉንም ባንድ የኢትዮጵያ ባንዴራ ማሰተባሰበርና ማመካከር ሲገባ ቅድሚያ ለኦሮሞ ማህበር ከዚያን የኢህአዴግ አደረጃጀት እያሉ ስደተኛውን ከመበታተንና በማዕከላዊነት ያልተማከለ ፣በዘውግ አስተዳደር የከረረ  አካሄድን እንድናይ ለምን አደረጉ?   አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ከምንም በላይ በሁለት ሃገራት የሰራተኛ ውል ማዕቀፍ ውጭ ወደ ሳውዲ የመጡና  እንደ ጨው የተበተኑትን የኦሮሞ ፣የአማራ፣ የትግራይ ፣ የጉራጌ እና የቀሩትን ብሔረሰቦች የአብራክ ክፋዮች ሁኔታ ለመረዳት የጉዳዩ ባለቤትና መከራውን ገፋች ነዋሪውን አላነጋገሩትም።  መፍትሔው  መብታችን ማስከበር ቀርቶ ዜጎች ያለንበትን ሁኔታ መሸፋፈን ከሚቀናቸው ከቆንስልና ከኢንባሲ ተወካዮች እስከ ድርጅትና ማህበራት ያሉትን”ምርጥ ” የተባሉ ነዋሪዎች ማነጋገር መፍትሔ ነውን ?  አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ነዋሪውን በነቂስ ጠርተው በመሰብሰብ ለምን ስለመጡበት ጉዳይ ማብራሪያም ሆነ የነዋሪውን ሃሳብ አልወሰዱም ?  የሚሉ በርካታ ውሃ የሚያነሱ እውነት ያላቸው ጥያቄዎችን ነዋሪው ሲያሰማ አድምጫለሁ ! እኔም ሆንኩ ነዋሪው በእስካሁኑ ሂደት ያየነው ለውጥ ኑሮ ባያስደስተንም ባለስልጣን በመጣ በሄደ ቁጥር ድመጻችን ይሰማ ዘንድ እንሻለን ፣   የለውጥ ተስፋ ባይታየንም የወገናችን አበሳ ግን መናገር አናቆምም  ! አዎ  ! ሰሚ እስክናገኝ እንጮሃለን  !

እስኪ ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም

ያለፈው ሥርዓት “አስማተኛ” ሳይሆን አይቀርም!

$
0
0

tplfእኔ የምላችሁ ግን … ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ ስንት ዓመቱ ነው? ይሄንን ቀላል ጥያቄ የምጠይቃችሁ ወድጄ እንዳይመስላችሁ፡፡ ግራ ቢገባኝ ነው፡፡ ሌላም ጥያቄ አለኝ – ያለፈው ሥርዓት ከተገረሰሰ ምን ያህል ጊዜ ሆነው? (ውዥንብሩ መጥራት አለበት!) አንዳንዴ ያለፈው ሥርዓት “አስማተኛ” ይመስለኛል፡፡ ለምን መሰላችሁ? አንዳንድ ሰዎች አሁንም ከ24 ዓመት በኋላ እንኳን ስለሱ ማውራት አልተዉም፡፡ ለሁሉ ነገር ያለፈውን ሥርዓት ካልጠሩ አይሆንላቸውም – በተለይ የኢህአዴግ ካድሬዎች፡፡ (ፍሬሾቹን ማለቴ ነው!)

ሰሞኑን EBC ባቀረበው የዜና ዘገባ ላይ “…የሴቶች ጥቃት ያለፈው ሥርዓት ችግር ስለሆነ እንታገለዋለን…” (really?!) የሚል ነገር የሰማሁ መሰለኝ፡፡ እውነቱን ልንገራችሁ አይደል … ራሱ ኢህአዴግም እንኳን የሴቶች ጥቃት “ያለፈው ሥርዓት” ችግር ነው አይልም፡፡ እንዲያ ካለማ— ያለፈው ሥርዓት አልተገረሰሰም ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ እንዳልኩት “አስተማኛ” ነው፡፡ (መቃብር እየፈነቀለ የሚወጣ!)
ይሄውላችሁ — በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓይነትም በመጠንም እየጨመሩ ለመምጣታቸው ከፖሊስ ፕሮግራም የበለጠ ማስረጃ የለም፡፡ (የሴቶች መብት ተሟጋቾችም ምስክር ናቸው!) አስገድዶ መድፈር፣ አሲድ መድፋት፣ ከባድ ድብደባና የአካል ማጉደል እንዲሁም አሰቃቂ ግድያዎች…በእጅጉ በርክተዋል፡፡ (ሰብዓዊ ልማት ተዘንግቷል!)

እናም— የሰሞኑ የEBC ዘገባ blame shifting (“የእምዬን ወደ አብዬ”) እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ ሃቁን እንነጋገር ከተባለ — የሴቶች ጥቃት “ያለፈው ሥርዓት” ችግር ሳይሆን የእኛው የራሳችን ችግር ነው፡፡ (የኋላ ቀርነት፣ የትምህርት አለመስፋፋት፣ የግንዛቤ ማነስ፣ የአመለካከት ችግር ወዘተ…) ነገርዬው እምብዛም ከስርዓት ጋር የሚያያዝ አልመሰለኝም (ፖለቲካ እኮ አይደለም!) የግድ የሥርዓት ችግር ነው ከተባለም ባለቤቱ የአሁኑ ሥርዓት ነው፡፡ እናሳ? … እናማ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ወዳለፈው ሥርዓት ለማሻገር ከመታተር ይልቅ እውነታውን ተቀብሎ ለመፍትሄ መትጋት ይሻላል፡፡ (ያለፈው ሥርዓት ከበቂ በላይ የራሱ ኃጢያቶች እንዳሉት አንዘንጋ!!)

ይሄውላችሁ —– እንኳንስ በቅርብ ዓመታት እየተባባሰ የመጣው “የሴቶች ጥቃት” ይቅርና በእርግጥም ካለፈው ሥርዓት የተወረሱ ናቸው የሚባሉት (እነ ድህነት፣ ሙስና፣ የስልጣን ጥመኝነት፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ የነፃነት አፈና፣ የፍትህ መጓደል ወዘተ…) ቢሆኑም እንኳ — 20 ዓመት ስላለፋቸው ውርስነታቸው አብቅቷል፡፡ (ከአባት የተወረሰ ንብረትም እኮ ለዘላለም በውርስነት አይጠራም!) ከምሬ እኮ ነው… ከአሁን በኋላ ችግሮችን ባለፈው ሥርዓት ማሳበብ ራስን ለትዝብት ማጋለጥ ነው፡፡

በመጨረሻ አንድ ሃሳብ ላቅርብ፡ ከፆታዊ ጥቃቶች አንዱ የሆነው አስገድዶ መድፈር፣ ለምን በፀረ ሽብር ህጉ ውስጥ አይካተትም? ይሄ እኮ… ሥርዓቱን ወይም ህገመንግስቱን በኃይል ለመናድ ከመሞከር ፈፅሞ አይተናነስም፡፡ ሴቶች ላይ ጥቃት መፈጸም – ቤተሰብን — ህዝብን — መንግስትን —- አገርን — ማሸበር ነው!!

Politica Befegegta

የግልና የ«ብሄር» ነፃነት በኣቶ ገብሩ ኣስራት እይታ

$
0
0

ኣምሃ ኣስፋው

«ሉኣላዊነትትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ» የተሰኘው የኣቶ ገብሩ መፅሃፍ ከፍተኛ ተቀባይነትና ኣድናቆት እንዳተረፈ በየድረ ገፁ ተወስቷል። መፅሃፉ በኣማርኛው ጥራትም ሆነ በይዘቱ ጥልቀት ሊደነቅ የሚገባው ይመስለኛል። እርግጥ ብዙ የፊደል ግድፈቶች ኣሉበት። ይህ ግን፣ የኣርታኢዎች ስህተት ብቻ ሳይሆን፣ መቀምሮች (Computers) ማንም ሳያዛቸው በራሳቸው ፊደሎችን የመቀያየር ጠባይ ስላላቸውም ጭምር ነው። ይህ መፅሃፍ የደረሰን ከወያኔ/ህወሃት ኣባል እይታ ቢሆንም የዘመኑን ታሪክ ለማወቅ እጅግ ጠቃሚ ይመስለኛል። ሁኔታው ሲፈቅድ፣ ኢትዮጵያዊያን ልጆች ከሚማሩባቸው መፃህፍት ኣንዱ ቢሆን ከተለያዩ ኣቅጣጫዎች በሚመጡ ሃሳቦች የታነፁ ዜጎችን ለማፍራት ይጠቅማል የሚል እምነት ኣለኝ።
የኣቶ ገብሩን መፅሃፍ በኣማርኛው ጥራትና በይዘቱ ጥልቀት ባደንቀውም፣ የኣንድምታውን ትክክለኛነትም ሆነ የጭብጡን እውንነት እቀበላለሁ ማለቴ ኣይደለም። የዛሬው ፅሁፌም ምክንያት ከማይስማሙኝ ኣስተሳሰባቸው ኣንዱን ለመተቸት ነው፤ በንግግር ነፃነት ስለሚያምኑ ትችቴ ቅር እንደማያሰኛቸው በማመን።
Gebru Asrat
ኣቶ ገብሩ ባለማለት፣ የማለትን ጥበብ የተካኑ ፖለቲከኛ ይመስላሉ። የኣፄ ቴዎድሮስን የጀግንነት ኣሟሟት ሲተርኩ፣ ጠላቶቻቸውን፣ እንግሊዞችን፣ እየመሩ ያመጡት ኣፄ ዮሃንስ መሆናቸውን ይዘሉታል። የኣፄ ምኒልክንና የጣሊያኖችን ውል ደጋግመው ሲያትቱ፣ ጣሊያኖች ኤርትራን በኣፄ ዮሃንስ ዘመን ያልያዟት ለማስመሰል ይሞክራሉ። በሻብያና በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል በተደረገው የመጨረሻ ጦርነት፣ ከምእራብ እስከምስራቅ፣ ከሰሜን እስከደቡብ ያለውን ህዝብ ጀግንነት ሲያሞግሱ፣ ሸዋን እንዳልነበረ ሁሉ ይዘሉታል። በምርጫ 97 የቅንጅትን ኣባል ማህበሮች እንቅስቃሴ ሲገልፁ፣ የመኢኣድ ኣስተዋፅኦ እንዳልነበር፣ እነ ኣቶ ሃይሉ ሻውል ደግሞ እንዳልተፈጠሩ ለማድረግ ሞክረዋል። በደፈናው «ነባር ፖለቲከኞች» ይሏቸዋል። ኣድሃሪ፣ ፊውዳል፣ ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛ፣ ምናልባትም እንደ ቀስተ ደመና የምሁራን ሳይሆን የደንቆሮዎች ስብስብ ከሚል ኣስተሳሰብ ብዙም የራቁ ኣይመስለኝም።

እነዚህ የቀድሞ ባለስልጣኖች ስልጣናቸውን ሲነጠቁና ጥቅማቸውን ሲነፈጉ የሚያሰሙት የ«ተሳስተን ነበር» ጩኸት ይገርመኛል። እንዲያውም የጥላሁንን ዘፈን ያስታውሰኛል።

የልብን ሰርቶ ይቅር በሉኝ፣
ምንስ ኣጠፋሁ ምን በደልኩኝ፣

የሚለውን። በስልጣን ላይ እያሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይ ካልታያቸው፣ ስልጣኑን እንደገና ቢያገኙ የህዝቡ በደል ተመልሶ እንደማይሰወርባቸው ምን ዋስትና ኣለን? ኣሁንም ቢሆን፣ የኣቶ ገብሩ ኩራታቸው፣ ጭንቀታቸውም ሆነ ተስፋቸው ለትግሬና ለኤርትራ ህዝብ ብቻ ነው። ይህንን ለመረዳት በመፅሃፉ ሽፋን ላይ ያለውን ካርታ መመልከቱ ብቻ ይበቃል። የመፅሃፉ እኩሌታ የሚነግረን የትግሬን ህዝብ ታላቅነትና ጀግንነት ነው። ካንድ ቦታ፣ ኣንዱን የደርግ መኮንን «ሻብያን ማሸነፍ ለኛ ቀላል ነበር። ሞራላችንን የሰበራችሁትና፣ ድል ያደረጋችሁን እናንተ(ወያኔዎች) ናችሁ።» ብሎ እንዲናገር ያደርጉታል። ከእውነተኛ ሰው ይልቅ የመድረክ ገፀ ባህሪ ነው የመሰለኝ። የትረካቸውን እውነትነት በቦታው ለነበሩና ለታሪክ ኣዋቂዎች ትቼ ወደ ተነሳሁበት ኣላማ ልመለስ። በመፅሃፋቸው ማጠቃለያ ላይ፣ ስለብሄር ነፃነት፣ ስለግል ነፃነትና ስለኢትዮጵያዊነት ያትታሉ።

በመጀመርያ ሌሎችም እንዲያስቡበት ኣንድ ኣንድ ጥያቄዎችን እና የኣቶ ገብሩን ሃሳቦች ላቅርብ።

1. ብሄር ማለት ምን ማለት ነው? ኣቶ ገብሩ ይህንን ጥያቄ ኣይነኩትም፤ ብቻ ትርጉሙ ኣከራካሪ እንዳልሆነ ሁሉ «የብሄር ነፃነት» የሚለውን ሃሳብ እንደልብ ይጠቀሙበታል። መዝገበ ቃላቱ፣ መንደር፣ ኣውራጃ፣ ምድር፣ ኣለም፣ ኩል (Universe) ፣ ባንድ ቋንቋ የሚናገሩ፣ ወገን፣ ነገድ፣ ህዝብ፣ ኣገር፣ ባንድ መንግስት ስር የሚተዳደሩ፣ ባንድ መድበል ስር የተጠቃለሉ ሙሉ መፅሃፎች እያሉ እጅግ ሰፊ የሆነ ትርጉም ይሰጡታል። ሆኖም ኣቶ ገብሩ መፅሃፋቸውን የፃፉት በኣማርኛ ስለሆነ የብሄር ትርጉም ኣማርኛ የተቀበለው ብቻ መሆን ይገባው ነበር። ትርጉሙን በመቀየር ኣዲስ የኣማርኛ ቃል መፍጠራቸው ከሆነም፣ ከመጠቀማቸው በፊት ቃሉን መደንገግ(Define) ነበረባቸው። ዘመናዊ ኣማርኛ የተቀበለው የብሄር ትርጉም «በኣንድ መንግስት ስር የሚተዳደር ህዝብ» የሚለውን ነው። ለዚህም ነው «የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ» እንጂ «የትግሬ ብሄራዊ ቡድን፣ የኣማራ ብሄራዊ ባንክ» የማንለው። ኣቶ ገብሩ ጎሳ የሚለውን ቃል ኣይወዱትም እንጂ የሚፈልጉትን ሃሳብ «ጎሳ» ወይም «ነገድ» የሚሉት ቃሎች የተሻለ ይገልፁላቸው ነበር። ግን፣ ወያኔዎች ሁሌም ድብቅ ኣላማ ስላላቸው «ብሄር» ሲሉ «ኣስፈላጊ በሆነ ጊዜ ነፃነቱን የሚያውጅ የህዝብ ስብስብ» ማለታቸው ይሆናል። ለዛሬው ግን የብሄር ትርጉም ልፅፈው የፈለግሁት ጉዳይ ላይ የሚያመጣው ለውጥ ስለሌ፣ ባላምንበትም የኣማራ ብሄር፣ የትግሬ ብሄር፣ የኦሮሞ ብሄር፣ የደቡብ ብሄር … እየተባሉ የሚጠሩ ህዝቦች ኣሉ፣ የሚለውን ሃሳብ ተቀብየ ልቀጥል።

2. «ፍፁማዊ የግል ነፃነት» በሚል ሃረግ የግል ነፃነት ደጋፊዎችን ለማጣጣል ይሞክራሉ። ፍፁማዊ የሚባል ነገር ኣለ? እንኳንስ በህብረተሰባዊ ስይንስ ይቅርና በሂሳብና በፊዚካ ኣለምም ፍፁማዊነት እንደሌለ ሳያውቁት ቀርተው ኣይመስለኝም። ሆኖም ፍፁማዊነት የለም ተብሎ ኣላስፈላጊ የሆኑ ኣምባገነናዊ ስርኣቶች በህዝብ ላይ ኣይጫኑም።

3. የብሄር ነፃነት ማለት መዝፈንና መጨፈር ብቻ ኣይደለም ብለው ይነግሩናል። የብሄር ነፃነት የሚሰጠን፣ ግን የግል ነፃነት ሊያሟላው የማይችል ምሳሌ ሊሰጡን ይችላሉ? ብየ ጥያቄየን ሳልጨርስ መልሱን ይሰጡናል። የብሄር ነፃነት ልጆችህን በራስህ ቋንቋ ማስተማር፣ ቋንቋህን ማሳደግና ማበልፀግን ያካትታል ብለው።

ሶስተኛዋን ጥያቄ ልውሰድና ሃሳቤን ላጠቃል።
ቋንቋ ሊያድግ የሚችልባቸው መንገዶች ሁለት ናቸው።
1. ሀ. ልጆችን በሚፈልጉት ቋንቋ ማስተማር። ለ. በሚፈልጉት ቋንቋ መፃፍ። መ. በሚፈልጉት ቋንቋ ላይ ምርምር ማካሄድ። ሰ. የሚፈልጉትን ቋንቋ በመገናኛ ብዙሃን ማሰራጨት።

2. ሌሎች ቋንቋዎች እንዳያድጉ በመከልከል የሚፈልጉት ቋንቋ ብቸኛ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ። ኣማርኛ ኣድርጓል ተብሎ እንደሚታማው ማለት ነው።
እውነተኛ ዴሞክራሲ ካለ… ግን፣ እውነተኛ ዴሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው? ለኔ ዴሞክራሲ ማለት የግለ ሰብን መብት የሚያከብር እንጂ የኣብዛኝውን ህዝብ ፍላጎት የሚያስፈፅም ስርኣት ኣይደለም። ኣብዛኛው የኣሜሪካ ህዝብ ባርነትን ይደግፍ ነበር። የባሮቹን የግል መብት ይፃረራልና እንድያ ኣይነቱ ስርኣት እውነተኛ ዴሞክራሲ ሊሆን ኣይችልም።
እውነተኛ ዴሞክራሲ ካለ፡
geberu asrat new book
ማንኛውም ሰው በሚወደው ወይም ያተርፈኛል በሚለው ቋንቋ የሚያስተምር ትምህርት ቤት መክፈት ይችላል። ማንኛውም ሰው ልጁን የፈለገው ትምህርት ቤት ሰዶ ማስተማር ይችላል። የዚህም ምንጩ የግለሰብ ነፃነት እንጂ የብሄር «ነፃነት» ኣይደለም። የራዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ ማቋቋም፣ ጋዜጣና መፃህፍትን ኣትሞ ማሰራጨትም የግል እንጂ የብሄር «ነፃነት» ኣይደለም። እርግጥ ሰዎች ተሰብስበው ከላይ
የተገለፁትን ሁሉ በቡድን ማድረግ ይችላሉ። ይህም ቢሆን ግለሰቦች መብታቸውን ሰብስበው የፈጠሩት ቡድን እንጂ፣ ቡድኑ የቸራቸው ነፃነት ኣይደለም። እነዚህ ተቋሞች በመንግስት ደረጃም ሊመሰረቱ ይችላሉ። ኣሁንም ቢሆን ግለሰቦች ነፃነታቸውን በምርጫ ላቆሙት መንግስት ኣካፍለውት እንጂ መንግስት ለግለሰቦች የሚታደል ነፃነት የለውም።

ታድያ የብሄር ወይም የቡድን «ነፃነት» ጥቅሙ ምን ላይ ነው? ትሉኝ ይሆናል። በመጀመርያ የብሄር ወይም የቡድን ነፃነት የሚሉት ነገር የለም፣ የብሄር ኣምባገነንነት እንጂ። ኮሚኒስቶች እውነቱን ግልፅ ኣድርገው ሲናገሩ «የላብ ኣደሩ ኣምባገነንነት» እንደሚሉት ማለት ነው። የቡድን ወይም የብሄር «ነፃነት» በቁጥር ሁለት የተገለፀውን ኣይነት፣ የሌሎችን የግል ነፃነት መግፈፊያ መሳሪያ ነው። ከኢትዮጵያዊነት ጋርም ጨርሶ ኣይጣጣምም።
ምሳሌ ልስጥ፡፡ የብሄር «ነፃነት» የሚፈጥራቸው ህጎች የሚከተሉትን ይመስላሉ።

• ትግሬ ውስጥ ትግሬ ላልሆነ ሰው የንግድ ፈቃድ ኣይሰጥም።
• ኦሮሞ ክልል ውስጥ ጉራጌኛ መናገርም ሆን መፃፍ ክልክል ነው።
• ሃረር ውስጥ ኣማራ መምረጥም ሆነ መመረጥ ኣይችልም።
የብሄር «ነፃነት» (ትክክለኛው ስሙ ግን የብሄር ኣምባገነንነት ሊሆን ይገባዋል) ጥቅሙ ኢትዮጵያዊነትን መወሰን ብቻ ነው። ስለዚህ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ሊታረቅ የሚችል ባህርይ የለውም።

“እነርሱ ከደደቢት መጥተው የለ፣ እኛም ሸሚዛችንን እንሸጠለንን” የአንድነት አመራር –ኖአሚን በጋሻው

$
0
0

የምርጫ ቦርድ ታህሳስ 28 ቀን  ባደረገው ስብሰባ፣ የሕወሃት አባል ናቸው የሚባሉት የቦርዱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ከአንድ ቀን በፊት በፋና ራዲዮ የተናገርሩትን በማጽደቅ፣ አንድነት ፓርቲ በምርጫው እንዳይወዳደር የምርጫ ምልክት አልሰጥም የሚል ኢሕገ መንግስታዊ የፖለቲካ ዉሳኔ አስተላልፏል። የአንድነት ፓርቲ በሁለት ወራት ጊዜ ዉስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ አመራሩን ካልመረጠ በምርጫዉ መወዳደር እንደማይችልም ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

የአንድነት ፓርቲ ያለፈው ታህሳስ  ወር 2006 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን መምረጡ፣  ኢንጂነሩም ከዘጠኝ ወር አገልግሎት በኋላ፣  ከአባላትና ከደጋፊዎች በተነሳ ግፊት፣ የመሰረቱትን የሥራ አስፈጻሚ በትነው ፣ በመስከረም ወር 2006 ዓ.ም ከሃላፊነታቸው በፍቃዳቸው መልቀቃቸው ይታወቃል።

tigstuበድርጅቱ ደንብ መሰረት ብሄራዊ ምክር ቤቱ፣ ከመካከሉ ሶስት አመራር አባላትን አወዳድሮ፣ አቶ በላይ ፍቃደን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። ከአቶ በላይ ጋር አሁን የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሃላፊ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ፣ አቶ ትእግስቱ አወሉ እና አቶ ደረጀ ለእጩነት ራሳቸውን አቅርበው የነበረ ሲሆን፣ አቶ ነገሰ «እኔን ልትመርጡ ያሰባችሁ፣ አቶ ደረጄን ምረጡ” በሚል ከዉድድሩ ራሳቸዉን በማውጣታቸው ምርጫው በተቀሩት ሶስት እጩዎች መካከል ተከናዉኗል። አቶ በላይ ፍቃደ አብላጫ ድምጽ ሲያገኙ፣ አቶ ደረጄ በሁለተኛ በመሆን ብዙ ድምጽ ያገኛሉ። አቶ ትእግስቱ አወል የርሳቸውን አንድ ድምጽ ብቻ አግኘተው ሶስተኛ ሆኑ። ሁለተኛ የሆኑት አቶ ደረጀ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው እየሰሩ ነው።

አቶ በላይ በደንቡ መሰረት አዲስ የሥራ አስፈጻሚ አዋቅረዉ፣ በምክር ቤቱ ያጸድቃሉ። የምክር ቤቱ ዉሳኔ፣  ሕጉ እንደሚጠይቀው፣ ለምርጫ ቦርድ ይላካል። ምርጫ ቦርድ ለአዲሱ አመራር እውቅና አልሰጥም የሚል ደብዳቤ ይጽፋል። የደብዳቤ ምልልሶች ይጧጧፋሉ። በዚህ ወቅት ብቻ ቢያንስ ወደ ዘጠኝ ደብዳቤዎችን አንድነት ከምርጫ ቦርድ ጋር ተጻጽፏል። አንድነት ምንም አይነት የደንብም ሆነ የህግ ጥሰት እንዳላደረገ ለማስረዳት ተሞከረ። የአመራር አባላቱ ምርጫ ቦርድ ድረስ በመሄድ ሁኔታዉን ለማስረዳት ሞከሩ።  አዉቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም” እንደሚባል ምርጫ ቦርድ በፍትሃዊነት ሁሉንም ድርጅቶች የሚያገለግል ሳይሆን ከሕወሃት መመሪያ ተሰጥቶች ጠንካራ የተባሉ ድርጅቶች ለመኮርከም የተዘጋጀ በመሆኑ፣ ለመስማት ፍቃደኛ አልሆኑም። የአንድነትን ትእግስት፣ የምርጫ ቦርድን አደርባይነት እንግዲህ ተመልከቱ።

የአንድነት ፓርቲ የሰለጠነ ፖለቲካ የሚያራምድ ፓርቲ እንደመሆኑ,  የሚሰራዉን ደባ ታግሶ፣ በመንገዱ ላይ የሚቀመጠዉን መሰናክል ድንጋይ እያለፈ ሕዝቡን ማደራጀቱን እየቀጠለ፣ አላስፈላጊ ጭቅጭቅ ዉስጥ መግባት አያስፈልግም በሚል ምርጫ ቦርድ የጠየቀዉን ለማሟላት ወሰነ። ምርጫ ቦርድ በድርጅቱ ደንብ ላይ የጠቅላላ ጉባኤ የኮረም ቁጥር መጠቀስ አለበት የሚል ጥያቄ በማቅረቡ፣ ምንም እንኳን የኮረም ቁጥር መግባት አለበት የሚል ሕግ ስለሌለ ያንን  የመጠየቅ መብት ምርጫ ቦርድ ባይኖረውም፣ ለአባላቱም ስልጠና ለመስጠት አስቦ ስለነበረ፣ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራል። በጠቅላላ ጉባኤው ምርጫ ቦርዱ  የጠየቀው የደንብ መሻሻል ያደርጋል። የብሄራዊ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሲመርጥ አንድ ድምጽ ብቻ ያገኙት አቶ ትእግስቱ አወል፣  በአቶ በላይ ፍቃደ አመራር ላይ ጥያቄ ያነሳሉ። አቶ በላይ ስልጣኑ የጠቅላላ ጉባኤ እንደመሆኑ፣  የተመረጡት በድርጅቱ ደንብ መሰረት በምክር ቤት እንደሆነ ገልጸው፣ ጠቅላላ ጉባኤው ግን በማናቸውም ጊዜ የምክር ቤቱን ዉሳኔ የመቀልበስ መብት እንዳለው በማስረዳት፣ እንደገና ምርጫ ማድረግ እንደሚቻል ያሳወቃሉ። የድርጅቱ የበላይ አካል የሆነው ከአራት መቶ በላይ ተወካዮች ያሉበት  ጠቅላላ ጉባኤው ፣ የብሄራዊ ምክር ቤቱ በፍቃዳቸው ከሃላፊነታቸው በለቀቁት በኢንጂነር ግዛቸው ምትክ ፣ አዲስ አመራር ማስመረጡ ትክክልና ደንቡን ያልጣሰ መሆኑን ያረጋግጣል። አዲሱን አመራር በድጋሚ ያጸድቃል። አቶ ትእግስቱ አወልን እና አቶ የማነን የተባሉ ግለሰብን ጨምሮ ከአምስት የማይበልጡ ይቃወማሉ። (ቀደምም ብሎ ብዙ ድምጽ ሲያሰሙ የነበሩት አቶ  ዘለቀ ረዲ በጠቅላላ ጉባዔው ወቅትም አልተገኙም ነበር)

አንድ መረሳት የሌለበት፣  የጠቅላላ ጉባኤ በሚደረግበት ጊዜ የምርጫ ቦርድ ተወካይ በስፋራው የተገኙ ሲሆን፣ የጠቅላላ ጉባኤውን ስሜትና የተወካዮችንም አንድነት  በሚገባ ተገንዝበው ሄደዋል።

የጠቅላላ ጉባኤው ቃለ ጉባኤ ፣ የተሻሻለዉን ደንብ በጊዜው ለምርጫ ቦርድ ይላካል። ሆኖም አሁንም ምርጫ ቦርድ አንድነት የምርጫ ዘመቻዉን እንዳያጧጡፍና አባላትን እና ደጋፊዎች ለማዳከምና ለማዘናገት ሲል፣  ሰበብ እየፈጠረ ፣ በኢቲቪም አንድነት ችግር እንዳለበት እየለፈፈ፣ ጸረ-ዴሞክራሲያዊና ጸረ-ሕዝብ ተግባሩን ይቀጥልበታል።

ሕወሃት፣ በጠቅላላ ጉባኤ ያልተገኙት አቶ ዘለቀ ረዲ፣ ለሊቀመነበርነት ተወዳድረው አንድ ድምጽ ብቻ (የራሳቸዉን ድምጽ)  ያገኙት አቶ ትእግስቱ አወሉ ( ሁለቱም አንድነትን በዉህደት ከተቀላቀለው ከብርሃን ለዲሞክራሲ ፓርቲ የመጡ ናቸው)፣ አቶ የማነ የመሳሰሉት በጣት የሚቆጠሩ ሰዎችን በማሰባሰብ፣ ትልቅ የኢቲቪ ሜዲያ ሽፋን በመስጠት፣ የስብሰባ አዳራሾችን በመፍቀድ፣ በገንዘብም በመደገፍ ፣  የአየለ ጫሚሶን አይነት ድራማ ለመስራት መንቀሳቀስ የጀመሩ ይመስላል። እነ ኢንጂነር ዘለቀና ትእግስቱ አወል ከአራት መቶ በላይ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት 10 እንኳን የደገፋቸው ሳይኖር፣ ሕወሃት እነርሱን እያደራጀ ፣ የኢሕአዴግ ካድሬዎችም እንዲቀላቀሏቸው እያደረገ ፣ ስለ እነርሱ እያወራለን ይገኛል።

ሕወሃት “አንድነት እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ አመራሩን ማስመረጥ አለበት። አለበለዚያ በምርጫው አይወዳደርም” የሚል ዉሳኔ ነው በመጨረሻ ሲሰጥ አላማ ምን እንደሆነ በግልጽ አሳይቷል። አንደኛ የአንድነት ደጋፊዎችና አባላት እንዲደናገጡን ተስፋ እንዲቆርጡ ነው። ሁለተኛ አንድነት እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ጊዜዉን እንዲያጠፋ ነው። ሶስተኛ ጠቅላላ ጉባኤው ወጭ የሚጠይቅ እንደመሆኑ አንድነትን በገንዘብ ማዳከም ነው። ቢቻላቸውም ደግሞ አራተኛ በአቶ ዘለቀረ ረዲ ወይም ትእግስቱ አወል የሚመራ የአየለ ጫሚሶ አይነት “አንድነት” ተመስርቶ የአንድነትን ሕጋዊ ሰርተፊኬት ለነርሱ በመስጠት አንድነት ከምርጫው ዉጭ እንዲሆን ማድረግ ነው።

ቅንጅትን  ለአየለ ጫሚሶ ሲሰጡ፣ ያኔ የቅንጅት መሪዎች ከእስር ቤት መዉጣታቸው ነበር። በመካከላቸውም ብዙ አለመስማማቶች ነበር። አሁን ያሉት የአንድነት አመራር አባላት በሥራ አስፈጻሚ ውስጥ ሆነ በምክር ቤቱ፣  የጠነከረ አንድነት ያላቸው ናቸው። ይሄንንም በስራቸው እያሳዩ ነው። በአንድነት ታሪክ አሁን ያለበት አይነት ጥንካሬ አንድነት ኖሮት አያውቅም።

አባላትና እና ደጋፊዎች ተስፋ ለማስቆረጥ ከሆነ ደግሞ፣ ከምርጫ ቦርድ በሚሰዘነዘረው ዱላ እንደዉም አባላት የበለጠ ይጠናከራሉ እንጂ አይዳከሙም። አቶ አዲሱ፣  በፋና ራዲዮ የተናገሩት እንደተሰማ፣ በአገሪቷ ሁሉ ያሉ አባላት ፣ “ይሄ ያህል በራዲዮ ኛ ላይ ዘመቻ ከተጀመረ ጥሩ ሰርተናል ማለት ነው” እያሉ የበለጠ ለመስራት መሯሯጥ ጀምረዋል። አላወቁትም እንጂ ሕወሃት ለአንድነት ትልቅ ማስታወቂያ እየሰራለት ነው። እንኳን የነ አቶ አዲሱና አቶ መርጋ ተራ ደብዳቤ ይቀርና፣  ሞት  ወይም እሥር የማይፈሩ ጀግኖች የበዙበት ፓርቲ ነው የአንድነት ፓርቲ።

አንድነትን በገንዘብ ለማዳከም የታሰበዉን ካየን ደግሞ፣ አንድ የአንድነት አመራር አባል እንደተናገሩት  “እነርሱ ከደደቢት መጥተው የለም እንዴ። ሸሚዛችንን ሽጠን የሚያስፈልገውን እንሸፍናለን” እንዳሉት ፣ ለትግሉ የሚያስፈለገው ወጭ ይሸፈናል። አንድ ጊዜ ሕዝቡ ከጎኑ የሆነ ድርጅት አይወድቅም። የጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ እንደገና አቶ በላይ ሆነ ሌላ ጠንካራ አመራር የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ይመርጣል። ሕወህትቶች ደስ ካልተተሰኙ ጸጉራቸውን ይንጩ እንጂ፣ መሪያችንን  እኛ እንጂ  እነርሱ አይመርጡልንም።

እንግዲህ ዉድ ኢትዮጵያዉያን ይሄ ሁሉ ትግል ነው። ሕወሃት የሚፈልገው ምርጫዉን ከትርኪምርኪ ድርጅቶች ጋር አድርጎ አሸነፍኩ ብሎ ማወጅ ነው። አላማቸው አንድነት ምርጫዉን ቦይኮት እንዲያደረግ ነበር። አንድነት ቦይኮት ማድረጉ ጉዳት እንጂ ጥቅም እንደሌለው በመግልጽ በዉጭም ሆነ በአገር ዉስጥ ያሉት በማሳመን የምርጫ ዘመቻዉን ሲያጋግለው፣ ኦፌሴላዊ የምርጫ ዘመቻ ገና  ሳይጀመር፣ ገና ከወዲሁ ለክልልና ሆነ ለፌደራል ተወዳዳሪዎች አዘጋጅቶ እንደጨረሰ ሲገልጽ፣ በየከተሞችን በሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትሃዊ ምርጫ በሚል ሰልፎችን እና ሕዝባዊ ሰብሰባዎች ሲጠራ፣ ሕውሃት ደነገጠ። ያንን ለማስቆም ብሎ ከህዝብ ካዝና የተገኝ ገንዘብን እየበተነ ነው።

እንግዲህ የአገራችን ፖለቲካ ግለቱ ጨምሯል።  ከዳር የቆምን፣ ተስፋ ቆርጠን የተቀመጥን ትግሉን እንቀላቀል። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን። አንድነትን እንደገፍ። የለዉጥና የነጻንትን ችቦ እናቀጣጥል። እኛ ከተባበረን የሃባትሙ አያሌውን አባባል ልዋስን እመኑኝ ደርግም ወድቋል፤ ወያኔም ትወድቃለች።

 

ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፥ –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፪ሺህ፯ኛ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

moreshነገ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድራችን በአካል የተገለጸበትን ፪ሺህ፯ኛ ዓመት እናከብራለን። እግዚአብሔር ወልድ በምድር በአካል ከእኛ ጋራ በታየበት ዘመን ያስተማረን ትልቁ ቁምነገር ፍቅርን ነው። በተቃራኒው እኛ የዘመኑ ኢትዮጵያውያን በመካከላችን ፍቅር ጠፍቶ እንበጣበጣለን። በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሌላው ቀርቶ በእምነቱ ሥፍራ እንኳን ሰላም ካጣ ቆይቷል። የዚህ ሁሉ ብጥብጥ እና ፍቅር መጥፋት ምንጩ የትግሬ-ወያኔ እና እሱን መሰል ፀረ-ኢትዮጵያ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች እና ልሂቃን ናቸው። ስለዚህ እኒህን የጥፋት ኃይሎች በጋራ ትግላችን ግስጋሴያቸውን ልናቆመው ይገባል። ክርስቲያኖች ከኢየሱስ ክርስቶስ ምሣሌ መማር ካልቻልን እና ካልተፋቀርን መከራችን ይረዝማል፣ ሥቃያችንም አያባራም። የትግሬ-ወያኔ እና መሰል አጋሮቹም እንደሠለጠኑብን ዘመናት ይቆጠራሉ።

ለዚህ መፍትሔው ፈጣሪያችን በፍርድ ቀን ሲመጣ የሚጠይቀንን ጥያቄዎች፥ ማለትም፦ “ስታመም ጠይቃችሁኛል? ስራብ አብልታችሁኛል? ስታረዝ አልብሳችሁኛል? ስታሠር አስፈትታችሁኛል? ስጠማ አጠጥታችሁኛል?” የተባሉትን ሠርክ እናስታውስ፣ በተቻለንም መጠን የሕይዎት መመሪያዎቻችን ለማድረግ እንጣር።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያንን እንኳን ለበዓለ-ልደቱ አደረሣችሁ፣ አደረሰን፣ ይላል። በዚህ አጋጣሚ ድርጅታችን ማስተላለፍ የሚፈልገው ጥሪ፦ ባለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት በትግሬ-ወያኔ ግፈኛ እና ናዚያዊ አገዛዝ ከምድረ-ገፅ የጠፉትን በቁጥር ከ፭(አምሥት) ሚሊዮን የማያንሱ ዐማሮች እናስታውስ። በገዛ አገራቸው ከቅኝ ተገዢዎች በከፋ መልክ ሰብዓዊ መብቶቻቸውን የተነጠቁትን ኢትዮጵያዊ ዐማሮች እንታደግ።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ይባርክ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት


የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ፣ የድሆች አባት ዶ/ር በርናርድ ተለየን ! -ነቢዩ ሲራክ

$
0
0
የማለዳ ወግ …የድሆች አባት ዶ/ር በርናርድ ተለየን !
* የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ
*” ክብር ሞቱ ለሰማዕት ”
(ጸሐፊው ነብዩ ሲራክ)

(ጸሐፊው ነብዩ ሲራክ)

ዛሬ የምናዘክረው ሰው የኢትዮጵያ አፈር ፍቅር ጠርቶት ለጉስቁል ተገፊው ደሃ የሀገሬ ሰው ህይዎት ትንሳኤ ተግቶ ለውጥ ስላመጣ  ጠቢብ ነው። ዝካሬ ታሪኩ ቢያስተምረን ፣ አርአያ ሰብዕናው ግብአት፣ ተሞክሮ ቢሆነን ፣ ህይዎት ንብረቱን በእኛው ቀዬ ስላፈሱሰ ትጉት ሀኪም ነው ! ነፍሳቸውን ይማር ብለን ለሰሩት ስራ ክብር በመስጠት እናዘክራቸዋለን!  ዶክተር በርናርድ አንደርሰን ይባላሉ ! በርናርድ ዛሬ አይሰሙም ፣ አያዩንም …

የዶር በርናርድን እረፍት ያረዳችኝ መነኩሴዋ እናቴ ሀዘኑ ጎድቷት ” ልጀዋ ዋርካችን ተገረሰሰ እኮ ፣ የድሆች አባትና ጠዋሪ መድሃኒታችን አጣንኮ … ” ነበር ያለችኝ … ያልጠበቅኩት ነበርና ድንጋጤው መላ አካሌን ወረረው  ። የእንባ ሳግ እየተናነቃት ሃዘኗን ያጋራችን እናቴን ከማጽናናት ባለፈ ምንም ማለት አልተቻለኝም! እናም ስለ ጠቢቡን የድሆች አባት ዶር በርናርድ አንደርሰን ላዘክር በተጎዳ ስሜት ብዕሬን ሳነሳ ጠቢቡ በሰጡት የኑዛዜ ቃል መሰረት ቀብራቸው በሚወዷት ሀገረ ኢትዮጵያ ምድር ይሆን ዘንድ በተናዘዙት መሰረት ሊፈጸም ተቃርቧል ። ውድ ባለቤታቸው የአርበኛው ደራሲ ገሪማ ታፈረ ልጅ ከሲስተር እማዋይሽ ገሪማም  ከምድረ አሜሪካ የዶር በርናርድን ቃል ለመፈጸም ዛሬ እኩለ ቀን አ.አ ይገባሉ  !  ጥቂት ስለድሆች አባት በርናርድ አንደርሰን ላጫውታችሁ …

ዶር በርናርድን ሳውቃቸው  !

ከአራት አመት በፊት ጠቢቡ ወንድም አግኝቻቸዋለሁ  ።  ስለሚሰሩት በጎ አድታጎት  በቅርብ የሚያውቋቸው ስለደግነት ቸርነታቸው አውርተው የማይጠግቡ ወገኖችን አግኝቸ ብዙ ተነግሮኛል። ከዚህም ተነስቸ ጠቡቡን ወንድም በአንድ የራዲዮ ዝግጅት ከአንጋፋው የረጅም ጊዜ የጀርመን ራዲዮ ጋዜጠኛ ከተክሌ የኋላ ጋር በመሆን በአንድ ዝግጅት ለማቅረብ ጠይቄያቸው ነበር ። ዶር በርናርድ ግን ” ምኑን ሰርቸ ታሪኬ ይነገራል ! ” በማለት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ፋና ወጊና አርአያ ተግባራቸውን ለማስተዋወቅ አልተሳካልኝም ! ያም ሆኖ ጠቢቡ በርናርድ እና ባለቤታቸው ሲስተር እማዋይሽ ገሪማን  በኢትዮጵያ ባህል በተሽቆጠቆጠው ቪላቸውን ሲያስጎበኙኝ እዚህ  ስላደረሳቸው መንገድ አውግተናል ።   “አጴ ቴዊድሮስ በተወለዱበት እና ባቀኑት ሃገር የአህያ ግንባር የምታክል ማስታወሻና መዘከሪያ ቦታ እንዴት አይኖራቸውም?  ” በሚል ለቴዎድሮስ መታሰቢያ ሙዝየም ለማስፈቀድ ሲከላተሙ ያገኘኋቸው ከእውቋ ሀገር ወዳድ  ከወ/ሮ እማዋይሽ ገሪማ ጋር በመሆን የምድረ አሜሪካ የተደላደለ ኑሮ ስላፈናቀላቸው የእናት ኢትዮጵያ ፍቅር ፣ በታሪካዊዋ የጎንደር ከተማ  ስላሰሩት የአዛውኖቶች መጠለያ  ፣ ለህሙማን መርጃ ባቋቋመው የህክምና እርዳታ መስጫ ቦታና ያኔ ጅምር ስለነበረው የሆስፒታል ግንባታ መሰረት በሚጣልበት ማሳ ላይ ቆሜ ህልማቸውን አውገተውኛል ፣ ሃሳባቸውን ተጋርቻለሁ!

ለመሆኑ ዶር በርናርድ አንደርሰን ማናቸው?

በሃገረ ጃማይካ ካትሪን ደብር ተብላ በምትታዎቅ አንዲት መንደር እ.ጎ.አ መስከረም 21 ቀን 1944 ዓም ህጻን በርናንድ አንደርሰን  ከአርሶ አደር ወላጆቹ ተወለደ።  የበርናንድ ህይዎት በጃማይካዋ የካትሪን ትንሽ የገጠር መንደር መጀመሩ እንጅ ከዘር ማንዘሩ ርቆ በሌላ የአለም ጫፍ ካለችው ኢትዮጵያ ጋር በፍቅር ተቆላልፎ ህይወቱን ያሳልፋል ብሎ የሚገምት አልነበረም ። ገና ከልጅነት ህይዎቱ ጀምሮ ብሩህ አዕምሮ የታደለው በርናንድ በካሪቪያን ውስጥ አንጋፋ በሆነው የዎልማር የወንዶች ት/ቤት ተግቶ በመመማር ወደ ተሻለ ደረጃ መሸጋገር ጀመረ ፣ ከዚያም ጉዞውን ቀጠለ … የተሻለ እውቀት ጥም እያንገበገበው ወደ አደገችው ምድረ አሜሪካ አቀና ፣ በትምህርቱ በመግፋት እ.ጎ. አ 1960 ዎቹ መጀመሪያ በዋንሽን ግተን ዲሲ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ሳይንስ የመጀመሪያውን የባችለር ዲግሪ ሲቀዳጅ በከፍተኛ ማዕረግ ነበር ።  ለጎልማሳው በርናንድ በከፍተኛ የህክምና ተቋማት የላቀ ውጤት ማምጣት ተራ ትምክህት ሆኖ ሳይገታው የተሻለና የላቀ ፣ ከፍ ያለ ትምህርት የመቅሰም ህልምን ሰንቆ የማታ ትምህትቱን በመከታተሉን ገፋበት ። ይህንንም ህልም በአጭር ጊዜ ታጥቆ ለስኬት አደረሰው ። እ.ጎ. አ በ1970 ዎቹ በርናንድ በከፍተኛ ማዕረግ የዶክትሬት ማዕረግ ተመረቀ !

የዚያ ደርባባ ጎልማሳ ዶር ማንነት የተገነባው ከመደበ ኛው እውቀት ባለፈ አብሮት ከተቆራኘ ሰብዕና እንደነበር የሚያውቁት ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ ። ዶር በርናርድ አንደርሰን በሙያው ያጡ የነጡ፣ ጉስቁል ፣ምንዱባንን ለመርዳትና ለመደገፍ ቆርጦ ተነሳ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ እንደ ቃል ኪዳን አድርጎ የያዘውን ተተኪ ፍለጋና ተተኪን ማፍራት ነበርና ድሎት ሳያታልለው ያደገ የተመነደገችውን ምድረ አሜሪካ ለቆ ወደሚያውቀው የድሆች ምድር አቀና  !  ወደ ጃማይካ ኪንግስተን …

ጃማይካ ኪንግስተን …

ህልሙን ለማሳካት ወደ ትውልድ ሃገሩ ጃማይካ ተመልሶ በወቅቱ ታዋቂ ከነበረው የኪንግስተን የህዝብ ሆስፒታል ስራውን ጀመረ ። የቀዶ ጥገና ጥበብ ባለሙያው ጎልማሳ ሃኪም ቅድሚያ የሰጠው በድህነት የሚማቅቁ ወገኖቹን መታደግ ነበር ፣ በህክምና ድጋፉ ፣ በተጓዳኝ ጥናትና ምርምሩ አንቱ በሚያሰኘውን ተመክሮ ራሱን እያጎለበተ ጉዞ የጀመረው ሃኪም በህክምና ድጋፍ ከመስጠት ርቆ ሔዶ በመምህርነት ሙያው ተተኪ ትውልድን የማነጽ ህልሙን አሳካ ። በዚህም ጉዞው ዶር በርናርድ አንደርሰን ለሃገሩና ለወገኑ ይህ ነው የማይባል አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ቻለ  !

ከጃማይካ መልስ በዋሽንግተን …

የጃማይካ ኪንግስተን ተልዕኮውን በሚገባ ከውኖ አቅፋ ደግፋ እውቀት ወደ መገበችው ሀገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ተመለሰ ። ዶር በርናርድ ለዚህ ላበቃው ዩኒቨርሲቲ ከእለትጉርሱ ያጠራቀመውን ከ100 ሽህ የአሜሪካ ዶላር የለገሰ ፣ ለሚሰረሰው በጎ ስረሰ ከመደሰተረ ውጭ ፣ መወደስ የማይሻ ሰብአዊም ነበር ።
ዶር በርናርድ ከጃማይካ መልስ እንደ አቻ የሙያው ባልደረቦቹ  ሃብት ንብረት የሚያካብትባቸው ሆስፒታሎ ች በከፍተ ኛ ገንዘብ ሊቀጥሩት ሲሻሙ አሻፈረኝ አለ።   ጥቅም ፍለጋ መማሰኑን ” ወዲያልኝ ” ብሎ ፣  የጤና ከለላና ሽፋን የሌላቸው ፣ በድንገተኛ አደጋ ተጎድተው ህይዎታቸው አጣብቂኝ የገቡትን የስልጡኑ ሀገር ተገፊ ምንዱባን መታደግ ወደ ሚችልበት በዲሲ ጄኔራል ሆስፒታል በአነስተኛ ደመወዝ ተቀጥሮ መስራት ጀመረ ።  በሙያው ተግቶ ፣ በሰብዕናው ጸንቶ ፣ ባሳየው ስኬትም በአጭር ጊዜ አንቱታን በማግኘቱ የሆስፒታሉ ሊቀመንበርና የቀዶ ጥገናው ክፍል ዋና ዳይሬክተር ለመሆን በቃ !  በአስተዳደር እና በሙያው ክህሎት የዲሲ ጀኔራል ሆስፒታል ከፍ ወዳለ ደረጃ ያደገው በዶር በርናርድ አንድሰን አመራር እንደነበር ዝክረ ታሪኩ ያስረዳል። ዶር በርናንድ ሆስፒታሉን ከማስተዳደር ጎን ለጎን የግል ክሊኒክ በድሆቹ መኖሪያ አቅራቢያ በዲሲ ሮድ አይላንድ መንገድ በመክፈት ፣ ለቻሉት በአነስተኛ ክፍያ ፣ ያልቻሉትን በነጻ በማከም ግልጋሎት ይሰጥም ነበር ።

የዶር በርናርድ አፍሪካና ኢትዮጵያ ትስስር …

በቀጣይ ዝካሬ ዶር በርናርድ ስነሳ እንደ አባት አቅርቤ ፣ እንደ ታላቅ ትጉህ ጠቢብ አንቱ እያልኩ መተረኬ ይገባኛል ፣ መልዕክቴ ከገባችሁ ለእኔ ያ በቂ ነው!  ብቻ ያገሬ ሰው ዶር በርናርድን  “የድሆች አባት ” ስላለበት አንድምታ ዘልቀን እናወጋለን …

ታህሳስ 24, 2007  ዓም ይህችን አለም የተለዩን ያልተጨበጨበላቸው ፣ ያልተነገረላቸው የኢትዮጵያ ወዳጅ ጃማይካዊ አሜሪካዊ ዶር በርናርድ የምናዘክረው በታላቅ  ክብር ነው  !  “ዶር በርናርድ ጉስቁል ምንዱባን ን ስትደግፍ ኖረሃልና ሞትህ የክብር ሞት ነው  ! ” ክብር ሞቱ ለሰማዕት ”  በሚል ታህሳስ 29 ቀን 2007 ዓም እኩለ ሌሊት በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገ ሰፊ የጸሎትና የዝክር ስነ ስርአት ቤተሰብ ፣ ወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት የክብር ስንብት አድርገው በርናንድ በድናቸው እንዲያ ርፍ ወደ ፈቀዱባት ቅድስት ሀገረ ኢትዮጵያ በክብር ተሸኝተዋል ! በዚሁ ፕሮግራም ከተሰራጨው ዝክረ ህይዎት ያገኘሁትን መረጃ በቀጣይ እንደሚሆን አድርጌ የምናየው ይሆናል !

ለመላ ቤተሰብ ለወዳጆቻቸውና ለአድናቂዎቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ  !  ለሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪው የድሆችን አባት ፈጣሪ በቀኙ ያሰረቀምጣቸው ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው  ! ነፍስ ይማር  !

ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም

የበደል ድርድር –የቅጥፈት ውድድር። (ከሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

09.01.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

Andargachew 1እንደ ሰው አለመሆንን ፍንትው አድርጎ ባሳዬው የሰሞናቱ የበደል ድርድር አብዛኛው የጭድ ክምር ሆኖ ነው እኔ በግሌ ያገኘሁት። በሌላ በኩል ግን ይህንን እጅግ የወረደ የቴሌቪዥን ቅንብር አይቶ ወያኔ መላእክ ሌላው ዓለም ጭራቅ ብሎ ብይን የሚሰጥ ሰው ይገኛል ብሎ መገመት እራሱ እውርነት ነው። ቀድሞ ነገር ለሰብዕዊ መብት ክብር ህጋዊነትን ለማብሰር የሃሳብ ነፃነት፤ የመደራጀት ነፃነት፤ የዕምነት ነፃነት፤ የመሰብሰብ ነፃነት፤ የመምረጥና የመመረጥ ነፃነት ዕውን መሆን አላባቸው – በጥቂቱ። ይህን ስለአደረጉ አስሮ – ደብድቦ – አፍኖና አሰቃይቶ „ሰብዕዊ መብታቸው ተጥበቆ ተዝናንተው ያልተጠዬቁትን ሳይቀር ተናገሩ¡“ ማለት እጭነት ነው። ለመሆኑ የወንድማቸውን ሁኔታ በአካል ተገኝተው ለማዬት ከሀገረ አሜሪካ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ የሄዱትን እህታቸውንስ ስለምን በ24 ሰዓት ባዕታቸውን ዬእትብት መንደራቸውን ለቀው እንዲወጡ አደረገ ወያኔ? ይህም የወያኔ የነፃነት ገነት ተብሎ ሊወደስ ይሆን¡?
አዎን! የነፃነት አረበኞቻችን ሃሳባቸውን በመግለጻቸው ለምን ታሰሩ? የሚለውን ጥያቄም መመለስ ያስፈልጋል። ሃሳብን መግለጽ እኮ ወንጀል አይደለም። የማይገሰስ ሰማያዊ መብት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። በአንጻሩ ነፃነቱን የተነጠቀ ሰው በማናቸውም ሁኔታ ተደራጅቶ ለነፃነቱ የሚያደርገው ትግልም ቢሆን ህጋዊ ነው። ህገወጥ የሚሆነው ነፃነቱን የቀማው አካል ወንበዴው ወያኔ ሰብዕዊ መብትን እረግጦ፤ የሰው ልጅን ሰብዕዊ መብት ለማስከበር በተጉት ላይ የሚያካሂደው የህሊና ዘረፋ፤ ህሊናን አስገድዶ ድፈረት ነው- ወንጀሉ። አስገድዶ ህሊናን በመዳፈር በታሪክ ወያኔ የመጀመሪያውን ረድፍን ይይዛል።
ወያኔ በቀል ነው መርኹ። በቀል ደግሞ ምህረት የለሽ ነው። ምህረት የለሽ መሆን ደግሞ ከሰው ደረጃ አውርዶ አውሬነትን ያውጃል። ይህ ደግሞ የሚጨበጥ የሃቅ እንክብል ነው። በእያንዳንዷ ቀን፤ በእያንዳንዷ ሰዓት፤ በእዬአንዳንዷ ደቂቃ የዜጎቻችን ደም በህገወጡ ጎጣዊ ድርጅት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በወያኔ ይፈሳል። በወገኖቻችን ላይ ኢ- ፍትሃዊ ተግባር ይፈጸማል። እያንዳንዷ የወያኔ የመኖር ስንቅ ቋሳን ሰንቆ አሪወሳዊ ተግባርን መፈጸም ነው። ይህ ደግሞ በሚታዩ ብቻ ሳይሆን ብዙ በማይታዩ የሰው ልጅ ሊደርስባቸው በማይችሉ ማናቸውም ስለታማ ጦር ጥቃት ይፈጸማል። ወገኖቻችን – ይቀቀላሉ። መፈተኛና መሞከሪያም ይሆናሉ – በገደል ውስጥ እያሉ ተቅብረው አንድ ሜትር በአንድ ሜትር በሆነ ዛኒጋባ ይሰቃያሉ። ወንድ ከሆነ ወያኔ ስለምን ያሉበትን ቦታ ሆነ የተሰወሩበትን ሁኔታ አደባባይ አያውለውም?!
ቀድሞ ነገር እስር ቤት ሆኖ ለዛውም በወያኔ እጅ ተወድቆ „ምቾት ላይ ናቸው¡“ ብሎ ማወጁ የወያኔን የማስተዋል ደረጃ ምን ያህል ቁልቁል እንደሆነ ያሳያል። ለምን? ሰው ሃሳቡን በመግለጹ፤ የተሻለ ሥርዓት እንዲኖር በማለሙ እኮ ለምን ይታሠራል? ለዚህ መልስ አለው ሽፍታው ወያኔ?! ከታሠሩ በኋላ እንኳን ባልተቋረጥ እገዳ ከቤተሰብ – ከጠያቂ ጋር እንዳይገናኙ፤ ስንቅ እንዳይገባላቸው ለምን ያደርጋል?! መልስ አለው ሽፍታው ወያኔ? ለነገሩ ወያኔ በሰብ ተፈጥሮ ማለትም እንደ ሰው በራሱ ተፈጥሮ የሸፈተ አሜኬላ እኮ ነው። እራሱን አያምንም ሌላውንም አያምንም። እራሱን ሆኖ መኖር አይችልም። ስለምን ሰብዕነትን የዘለለ እሾኽ በመሆኑ።
እንሆ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሁለት የግንቦት 7ትን ጥንካሬ ላነሳ ፈልግሁ። የታዘብኩትን – በእኔ ዕይታ። የጹሑፌ ሐዲድ ነውና። የመጀመሪያው የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አካላት የነገን መተንበይ ባልችልም እስከ አሁን ባለው ሁኔታ የመደማመጥ አቅማቸው አንቱ ነው። የሃሳብ ልዩነት በፓርቲ ህይወት ውስጥ እንደሚኖር ግድ ይላል። ነገር ግን ይህን የሀሳብ ልዩነት በበለጸገ የዴሚክራሲ መደማመጥ መምራት መቻል ሥልጡንነት ነው። ከፍተኛ አመራር አካላቱ ሲካሰሱ ወይንም የፈነገጡ ሃሳቦችን አደባባይ አውለው ማስተባበያ ድርጅቱ ሲሰጥባቸው አይታይም። ስለዚህ ግንቦት ጊዜውን በአግባቡ ማስተዳደር የቻለ፤ በጋራ አመራርና በግል ኃላፊነት መመራቱን ዕውነታው ይመሰክራል። ሁለተኛው ብርቱው የብቃት ሚስጢር ደግሞ ግንቦት ህጋዊ በሆነ የህዝብ መድረክ፣ የመገናኛ አውታር ወይንም ማህበራዊ ድህረ ገጽ አቻ የነፃነት ትግል ፓርቲዎችን ሲተች፤ ሲያቃልል፤ ሲያብጠለጥል ተደምጦ አያውቅም። ይህም የጥንካሬው ሌላው የተግባር ህንፃው ነው።
ይህ ደግሞ ለገዢው የጎጥ ድርጅት አይመችም – ፈጽሞ። ከጠጠር ላይ የመተኛት ያህል ይጎረብጠዋል፤ ከረመጥ ላይ የመጋደም ያህል ያርመጠምጠዋል – ከሹል ድንጋይ ላይ የመቆም ያህል ያቆነጠንጠዋል። ስለዚህ የተሰበረ የፍላጎት ድልዱዩን ለመጠገን ሌላ መንገድ ፈለገ። …. ግንቦት ካለተፈጥሮው፤ ከላአደገበት ተመክሮው ከሌሎች ፓርቲዎች ወይንም ድርጅቶች ጋር ማዋጋት ፈለገ። ይህ … ይቀጥላልም። በህልሙ የሚነስተው ነበላባላዊ የነፃነት አርበኛ መጠሪያ ሥም ከህዝብ ፍቅር ለማግለል ብዙ አሳቶች ነገም ይጫራሉ …. ነገር ግን እኛ ሆን የጉዳዩ ባለቤት የነፃነት ትግሉ አባዎራዎች በበሰለ ተምክሮና – ማስተዋል፤ በቀና እና ቀጥ ባለ ህዝባዊ ፍላጎት ትግሉን ሊመሩና ሊያስተዳደሩ ይገባቸዋል። የጠላት ሴራ ጉቶዎች ሆኑ ጉንጉኖች ጅማሯቸው … ይከታተላል። መሆን ያለበት መፈለግና ማሳካት የመቻልን አቅም ይለካልና … ከጫካ ዶክተሪን በልጠው መገኘት ይኖርባቸዋል – እያንዳንዱ የነፃነት ትግሉና መሪው። ። ህዝቡንም ድንቆችን ከነክብራቸው ሊጠበቅቻውና መንፈሱን ሳይሳሳ ሊለግሳቸው ይገባል። የሚቻልን – ለማስቻል ነገን በብቃት ማዬት ይጠይቃል።
ለዚህም ነው በጣም በተከደነ ሁኔታ ሥጋት ያለበት የወያኔ አመራር ኢትዮጵውያንን ቀንዲል ሥም በማስጠራት በዛ ላይ መጥፎ ምስል እንዲኖር ለማድረግ የተጋው። ግን ጥረቱ የበከተ – የበሰበሰና የዛገጠ አተላ ነው የሆነው። ከእሱ በላይ ህዝብ አካሎቹን የነፃነት ትግሉን ተስፋዎች ሆኑ መሪዎችን ልጆቹን ያውቃል – አሳምሮ። ነፍስ አስቶ – ሌላ ሰብዕና ፈጥሮ፤ በመርዝ አደንዝዞ – ይቀዳል። የተናገራችሁት ይህ ነበር ይባላሉ – እስረኞቻችን። በዝብርቅ ፊልም ቅንብር እሱ እንደሚያመቸው ያው በጫካ ተመክሮ ተለብዶ – ተለስኖ – በስሚንቶ ታሽጎ እንዳዬነው ይቀርባል። …. ፍላጎትን ጠንቅቆ የሚያውቀው የአስተዋዩ የኢትዮጵያ ህዝብ አብራክና ማህጸን ክፋይ ወገን ግን ይህን የቅጥፈት ድርድር በሚገባ በልቶ ያውቀዋል። ይልቁንም በምን የብቃት ልክ እዬተመራ መሆኑንም ይመዝንበታል። እንዲህ ማጣፊያ ሲያጥር – ወያኔ ግርድ ያበጥር። ሌላው ደግሞ በጣም ወያኔ ተንጠራራ – እኛ የምናስከፍለው የቋሳ ዋጋ ዝቅ ያለ ነው ይቀረናል —- ዓይነት …. ለሰው ልጆች የስቃይ መጠን ውድድር አሰኘው። – በዴሞክራሲ ትርጎሜና የተግባር ክንውን ከአደጉት ሀገሮች ጋር እራሱን አለካካ። ሽልማትም አሻው —- መካሬ የለሽ፤ ግራጫ የመከነበት ፍልስ ድርጅት – ነገ የሸሸው።
አዎን! የሚገርመው – ወያኔ በእጁ የገባውን ጀግና መንፈስ በጣም ከቀደመው በላይ በሰፋ ሁኔታ ይፈራዋል። በመንፈሱ ብቻ ይርበደበዳል። ያለውን እንኳን በተሰተካከለ ሁኔታ ለማቅረብ አቅም የለሽ እዲሆን ያደረገውም ይሄው ነው። በራሱ ፍርድ ቤት እንኳን ለማቅረብ ድፍረት ከድቶታል። ኮሽታው ሁሉ በድንጋጤ ያደናብረዋል። ስለምን የእኔ የሚለው ከጎኑ የቆመ አንድ ብጣቂ ሃቅ የለምና። በራሱ ድርጊት እፈረቱ በቀለሰለት ጎጆ ተደብቆ ይዳክራል።
ጎጠኛው ወያኔ ሃቅን እንደ ፈራ ኑሮ ከሃቅ ጋር ሳይገናኝ፤ ከሃቅ ጋር ሳይመክር እልፈቱን ያውጃል። ወያኔ ሲከስም ዘር አልባ ሆኖ ነው። ስለምን? የሰብዕነት ፍርፋሬ ተጠግቶት ስለማያውቅ። እውነት ስለ ራቀው። ህዝባዊ ፍቅር ስለ ፈለሰበት – ከባህር የወጣ አሳ ነው። የወያኔ መኖሪያው ዙ ቢሆን መልካም በሆነ ነበር። እንደ እንሰሳ ኑሮ – እንደ እንሰሳ ማለፍ። አዬንለት አዲስ የተባለለትን ቪዲዮ – አንድ የሚጨበጥ ነገር በሌለው ፍሬ ፈርስኪ የፋንድያ ክምር – ዜሮን ደመረ። እኔ እንኳን አዲስ ነው ለማለት በጣም ነው የተቸገርኩት። ምክንያቱም በተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው እጣት ላይ የነበረው ቁስለት ሆነ የጥፍራቸው ደሙ የተመጠጠው ግርጠት አሁንም እንደ አለ ነው። የሰውነት ላሂያቸውን በሚመለከት የፊልም ቅርበትና ርቀት ቀረጻ ካልሆነ በስተቀር እንደ ወቅቱ ተፈሪነት ሁኔታ ያን ጊዜ የተቀረጸውን ቆራርጠው ክፍል አንድ – ሁለት – ሦስት እያሉ ይቀጥላሉ ባይም ነኝ። በሌላ በኩል የዋሁም ደህና ነው የተሻለ ገጽ አለው እንዲል መንፈስ ለማዛል የተጠቀሙበት ነውም ባይ ነኝ። ምክንያቱም በጣም ነው የኖረውን ቁጫን ሁሉ በእሳቸው ላይ የተወጡት። ማንፌስቶውን ጽፎ ወያኔ ድርጅቱን ሲመሰርት የተሰማው ያህል ቁርሾ ነው በሂደቱ ማዬት የተቻለው። ስለዚህም የተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አገግመው ለመወጣት እንዲህ ቀላል አይሆንም ባይ ነኝ። ለዚህም ነው እሳቸውን በሚመለከት ቀዳዳዎች ሁሉ የተወታተፉት። ወያኔ ለፈጸመው ድርብርብ – ዘመን ይቅር ለማይለው ወንጀል አቅርቦ በአካል ለማሳዬት አቅም ያንሰዋል። ነፍስ ያለቀጠሮ ስለማትወጣ እንጂ የክርስቶስን መከራና ስቃይ እንደተቀበሉ መረዳት አያቅትም።
ወሳኝ
ከሰሞናቱ የቪዲዮ ይፋ መረጃ አንድ ዋሳኝ ጉዳይን ዘለግ ባለ ሁኔታ ማዬት ያለብን ይመስለኛል። ከወያኔ ኢንባሲዎች ውጪ የወያኔ ደጋፊ አከርካሪዎች ዘማች እጅ ምን ያህል ለብቅላ ሆነ ለጉርጉራ የመደመጥ አቅም እንዳላቸው እኔ በግሌ ማዬት ችያለሁ። በሌላ በኩል „የታላቋ ትግራይ ህልመኞችንም“ መስመር ተመልክቸበታለሁ። ወያኔ ከቅርቡ ያለውን ጉዳይ እንኳን ከተፈጸመ በኋላ ነው ማዬትና ማስተዋል የሚችለው። እንኳንስ የውጩን የማገናዘብ አቅም ሊኖረው ቀርቶ። ባናኝና ዕብን ነውና። ቀላሉ ምሳሌ የ97 ምርጫ ወያኔ በእጁ ያለውና የሌለውን የተረዳው መቼ ስለመሆኑ ጭብጥ ማስረጃ ነው። ከዚህ በኋላ ነቅቶ ስንት ነገሮችን እንደ ከለሰ ይታወቃል። ስለዚህ በዚህ ስሌት ሲኬድ የአሁኑ ቪዲዮ መንፈስ መነሻው የት እንደሆነ ለማገናዘብ ይቻላል ባይ ነኝ። እርግጥ የጠጠረና ረቂቅ ነው … እንዲህ በበሩ ዘው ተብሎ ተገብቶ የሴራውን ውስጥ ማዬት አይቻልም እንጂ ፍሬ ነገሩ ውጪ ያለው የወያኔ የድጋፍ መስመር የዳንኪራው ሁሉ ማሳረጊያ ሆኖ ነው – እኔ በግሌ ያገኘሁት። ውዶቼ የኔዎቹ ፈትሽቱት – ከልብ ሆናችሁ። ሌላ መልዕክት ያሰተላልፍላችኋል።
መቋጫ
የሆኖ ሆኖ ምንግዜም በጠላት እጅ የወደቀ ወገን ታሪካችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጅ የወደቀ ወገናችን አርበኛችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጅ ጥቃት የተፈጸመበት ህዝብ ሰንደቃችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጄ የተጎሳቆለ ተቋም ዓርማችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጅ የወደቀ መንፈስ ዝክራችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጅ ስቃይ የተፈጸመ ገላ ደማችን ነው። ምንጊዜም በጠላት እጅ የጥቃት ሰለባ የሆነ አካል መርሃችን ነው። ሲጠቃለል ታሪክም ዘመንም የነፃነት ትግሉን መጸሐፍ ይጽፋሉ። መጸሐፎቻችን ውስጦቻችን ናቸው። ታማኞቻችን ማተቦቻችን ናቸው – የወልዮሽ ብሄራዊ ሃይማኖታችንም።
ትናንትም ዛሬም ነገም የተከበሩ አቶ አንደርጋቸው ጽጌ መንፈሳቸው የነፃነት ደወል ነው። የከፈሉት መስዋዕትነት – የሚቀበሉት ስቃይ፤ ያዩት ፈተና የበለጠ እንድናከብራቸው – እንድንወዳቸው – አንድናደንቃቸው ያደርገናል። ሥማቸውን ስናሰብው በደማችን ሃዲድ ያበራል። ተግባራቸውን ስናሰላው በእዝነ ልቦናችን ያፈልቃል – ለምንግዜም። ግርማቸው – አንደበታቸው – ድርሳናችን ነው። የተግባር ሰውነታቸው የትም ይሁኑ የትም መንገዳችን ነው።
አንድ አስተዋይና ሳቂተኛ ንፋስ ይመጣል – አውሬን ለማሰናበት።
ሁሉን ለሰጠ ጀግና ክብራችን የሰንድቕዓላማችን ያክል ነው!
ጀግኖቻችን መርሆቻችንና መንገዶቻችን ናቸው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ወያኔ ኢትዮጵያን አፍርሶ ወደ ጉሬው ለመግባት

$
0
0

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት     ቅዳሜ ጥር ፪ ቀን ፪ሺህ፯  ዓ.ም.                         ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፰

የመጨረሻ መሠናዶውን እያደረገ ነው
· የትግሬ-ወያኔዎች ከተለያዩ ጎሣዎች እና ነገዶች ሰዎችን መልምለው እና አደራጅተው፣ እንዲሁም የወታደራዊ፣ የደህንነት፣ የአደረጃጀት፣ የአመራር እና የቁጥጥር ሥራ የሚሠሩ የትግሬ-ወያኔዎች መድበው በከፍተኛ ሚሥጢር ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሤራ እየተዶለቱ መሆኑን በተጨባጭ መረጃዎች አረጋግጠናል።

moreshየትግሬ-ወያኔ የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያን በመበታተን፣ የትግራይ ረፑብሊክ መመሥረት መሆኑን በ1968 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ፕሮግራሙ መሠረት ላለፉት ፵(አርባ) ዓመታት ያደረገው ጉዞ ያሣያል። በጉዞው የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ታሪክ ክዶ በመቶ ዓመት መገደቡን፣ የትግሬ-ወያኔ መሪዎች እና አባሎች በተደጋጋሚ በጻፉዋቸው መጻሕፍት እና በየአጋጣሚው ባደረጉዋቸው ንግግሮች ለሕዝብ ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። «ኤርትራ በኢትዮጵያ በቅኝ ግዛትነት የተያዘች ናት፤ ስለሆነም ሻዕቢያ የሚያካሂደው የመገንጠል እና የነፃነት ጥያቄ ተገቢ እና ትክክል ነው።» ብለው፣ ከሻዕቢያ በላይ ሻቢያ ሆነው፣ የትግራይን ልጆች የጦር ማገዶ በማድረግ ኤርትራን ማስገንጠላቸው ማንም ሊያስተባብለው የማይችለው ሃቅ ነው። ኢትዮጵያውያንን እንደ አንድ ሕዝብ ያስተሳሰሩ የወል ዕሴቶችን፥ «የኢትዮጵያዊነት አገራዊ እና ብሔራዊ ስሜት የሁሉም በኢትዮጵያ የሚኖሩ ነገዶች እና ጎሣዎች ሳይሆኑ፣ የዐማራው ብቻ የማንነት መገለጫዎች ናቸው፤ ዐማራው ጨቋኝ እና በዝባዥ ነገድ ነው፤ እርሱን ሁሉም ነገዶች እና ጎሣዎች በወያኔ መሪነት ተባብረው ማጥፋት አለባቸው።» በማለት በከፈቱት የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ጦርነት፣ የኢትዮጵያዊነት የወል ዕሴቶችን፣ ተቋሞችን፣ ግንኙነቶችን፣ አሠራሮችን ወዘተርፈ በማጥፋታቸው ዛሬ አገሪቱ እና ሕዝቧ የሚገኙበት ሁኔታ በግልጽ ያሣያል። የአገሪቱ ዘመን-ጠገብ መልከዐ-ምድራዊ መለያ ስሞች እና ወሰኖች ተሽረው በተወሰኑ ነገዶች ማንነት ብቻ ላይ የተመሠረቱ ስሞች በመስጠት፣ የኢትዮጵያውያንን ተዘዋውሮ በፈለጉት ቦታ እና አካባቢ የመኖር እና የመሥራት ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሰብአዊ መብቶቻቸውን ገፍፈው፣ አንድነታቸውን አሣጥተው፣ አብሮነታቸውን ክደው፣ በጠላትነት እንዲተያዩ አድርገዋቸዋል። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከሕዝቡ ስሜት ፈጽሞ እንዲጠፉ መጠነ ሠፊ የሆነ የሥነልቦና ጦርነት ከፍተው አገሪቱን ከመጨረሻው የጥፋት ጠርዝ ላይ አድርሰዋት ይገኛሉ።

የትግሬ-ወያኔ እና ተከታዮቹ በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም፣ እንዲሁም በሕዝቧ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ታሪክ፣ ትውልድ፣ ሕግ እና ማናቸውም ዓይነት ሥነ-ምግባር ይቅር ሊለው የማይችል የክህደት ተግባሮችን የፈጸሙ መሆኑን ከማንም ይበልጥ ራሣቸውም አይክዱም። ይህም በመሆኑ የኢትዮጵያ አንድነት ተጠብቆ ከዘለቀ በየትኛውም ጊዜ በአገር ክህደት ወንጀል ተጠያቂ እንደሚሆኑ ያውቃሉ። ከዚህ ተጠያቂነት ለመዳን እንችላለን ብለው የሚምኑት ሁለት ነገሮችን ጎን ለጎን ማከናወን ሲችሉ ብቻ ነው። እነዚህም፦ አንደኛ የወያኔ ትውልድ ለሚቀጥሉት መቶ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሕይዎት ላይ የወሳኝነቱን ሚና ይዞ የሚቀጥልበት አስተማማኝ ሁኔታ ሲረጋገጥ፤ ይህ የመጀመሪያው ዕቅድ በተለያዩ ምክንያቶች ባይሣካ ሁለተኛው አማራጭ ዕቅድ ትግራይን ከኢትዮጵያ በመገንጠል የትግራይ ረፑብሊክ በመመሥረት ጎጆ መውጣት፤ የሚሉ ናቸው።

ሁለተኛውን ግብ ለማሣካት በኢትዮጵያ ላይ ሥልጣን ከተቆጣጠሩ ጊዜ ጀምሮ ለምትገነጠለው ትግራይ ቁሣዊ፣ ቴክኒካዊ እና ኅሊናዊ ሁኔታዎች እንዲሟሉ የሚያስችሉ ተግባሮችን ማከናወን እንዳለባቸው ታሣቢ አድርገው መንቀሣቀሣቸው ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው ትግራይ ውስጥ አያሌ የመሠረተ ልማት ሥራዎች መሥራታቸው ይታወቃል። በዚህም መሠረት የትግራይ ክልል ከጎንደር እና ከወሎ ክፍለ ሀገሮች መሬት ነጥቀው በታሪክ የትግራይ አካል ሆነው የማያውቁ አካባቢዎችን አጠቃልለው ጥንተ-ነዋሪውን የዐማራ ነገድ አባላት የሚገድሉትን በመግደል፣ ቀሪውን በማሠር እና በማሰደድ ትግሬን አስፍረውበታል። ይህ የያዙት ግዛት ወደፊት ለምትገነጠለው ትግራይ ይጠብባል በማለት ከሰቲት ወደ ደቡብ ምዕራባዊ የጎንደር እና የጎጃምን የሱዳን አዋሳኝ ወረዳዎችን ከቤንሻጉል ጉምዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ጋር በማገናኘት የታላቋ ትግራይን የመሥፋፋት ዓላማ ዕውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ (አባሪ ካርታውን ይመልከቱ)።

በዚህም መሠረት ለወደፊቷ ትግራይ ለምትጠቀልለው ሠፊ ግዛት፣ ከውጭው ዓለም ጋር የሚያገናኙ የመገናኛ መሥመሮችን ዘርግተዋል፣ ተጨማሪ መሥመሮችንም በፍጥነትም በመገንባት ላይ ይገኛሉ። የትግራይን ምርት ወደ ውጭ ለመላክ እና ከውጭ የሚፈለጉ ሸቀጦችን ወደ ውስጥ ለማስገባት፣ ከጅቡቲ እስከ መቀሌ፣ ከሱዳን ጠረፍ እስከ መቀሌ የሚያገኛኙ የባቡር ሐዲድ ግንባታዎች በመፋጠን ላይ ናቸው። ሁለት ታላላቅ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያዎች መቀሌ እና አክሱም ላይ ገንብተዋል። ቀበሌዎችን ከወረዳ ከተሞች፣ ወረዳዎችን ከአውራጃዎች (ዞኖች)፣ አውራጃዎችን ከዋና ከተማዋ ከመቀሌ ጋር የሚያገናኙ፣ ክረምት ከበጋ ያለምንም እንከን አገልግሎት የሚሠጡ መረብ-መሰል አውራ መንገዶች ተገንብተዋል። ድርቅን ለመቋቋም የክረምት ዝናብን ለማቆር የሚያስችሉ በርካታ ግድቦችን ሠርተው አገልግሎት ላይ አውለዋል። የትግራይን አዲሱን ትውልድ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት አውጥቶ የትግራዊነት ስሜት እንዲገነባ የሚያስችሉ፣ በተቀነባበረ ሁኔታ ቅስቀሣ እና ትምህርት በማያቋርጥ መልኩ የሚሰጡ ተቋሞች ተገንብተዋል። በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች፣ የቴክኒክ እና የሙያ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎች ተከፍተዋል። በኢንዱስትሪ ግንባታ ረገድ የነባሮቹን የኢትዮጵያ ፋብሪካዎች ሕልውና የሚያጠፉ የመድኃኒት፣ የጨርቃጨርቅ፣ የስሚንቶ፣ የመጠጥ እና የብረታ ብረት ፋብሪካዎች በሁሉም የትግራይ አውራጃዎች ተቋቁመዋል። ከእነዚህ መካከል፦ የአዲግራት መድኃኒት ፋብሪካ፣ እንዲሁም መቀሌ የተገነቡት የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ፣ የአልሜዳ የጨርቃጨር ፋብሪካ፤ የመሥፍን ኢንጂነሪንግ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ፣ ወዘተርፈ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው። አሽጎዳ አካባቢ በአፍሪቃ በግዙፍነቱ ቀዳሚ የሆነ እና በነፋስ ኃይል ኤሌክትሪክ የሚያመነጩ ተርባይኖች በብዛት ተገንብተዋል።

የአገሪቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መዋቅሮች ያላአንዳች ይሉኝታ በወያኔች የተያዙ ናቸው። የአገሪቱን የአየር እና የምድር ኃይል መከላከያ የማዘዣ ማዕከሎች ከአዲስ አበባ እና ከደብረዘይት በማስወጣት ማዕከላዊ ዕዛቸውን ትግራይ ላይ እንዲሆን በማድረግ ወሣኝ የሆኑት የመከላከያ መሣሪያዎች ትግራይ ውስጥ እንዲከማቹ ተደርጓል። የከባድ ሮኬቶች መተኮሻ መንኮራኩሮች ትግራይ ውስጥ ተገንብተዋል። የአገሪቱ የመከላከያ ኃይል ከጓድ እስከ ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ድረስ ያሉት ቁልፍ የአዛዥነት፣ የመገናኛ፣ የድርጅት፣ የሎጂስቲክ ኃላፊነቶችን በሙሉ በትግሬዎች በማስያዝ የወታደራዊ ተቋሙ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴው የትግራይን መገንጠል ዕውን በሚያደርግ መልኩ ወደፊት እየተባለ ይገኛል።

በአጠቃላይ የትግራይን ግንጠላ ዕውን መሆን ሂደቱ የተመቻቸ እንዲሆን፣ በ«ሽግግር ዘመን» ተብየው «ልማት ቅድሚያ በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች» በሚል ስም የአገሪቱ አጠቃላይ በጀት ለትግራይ ልማት ተመድቦ ለአምስት ዓመታት ከላይ ለተጠቀሱት ተግባሮች እንዲውል መደረጉ ይታወቃል። ከሽግግር መንግሥቱ ፍጻሜ በኋላም የተዘጋጀው «ሕገመንግሥት» ተብየው የሽግግር መንግሥቱ ቻርተር ተከታይ ሆኖ በመዘጋጀቱ፣ አጠቃላይ ያለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ሲሠራ የኖረው ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ሁለት ግቦች ለማሟላት፣ ማለትም፦ የትግሬ-ወያኔ ትውልድ ለመቶ ዓመታት በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ የሚቆይበትን ሁኔታ እያረጋገጡ መጓዝ፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ለምትገነጠለው ትግራይ ቁሣዊ፣ ቴክኒካዊ እና ኅሊናዊ መሠረት ሊሆኑ የሚችሉ የሁለንተናዊ ግንባታ ተግባሮችን በተጓዳኝ ማከናወን የሚለው በተደጋጋፊ መልኩ ሲሠራ መቆየቱ ይታወቃል።

ይህ ሁሉ ሤራ ቢጎነጎንም፣ የትግሬ-ወያኔ ባልጠበቀው መልኩ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከሕዝቡ ኅሊና ውስጥ ከመፋቅ እና ከመደብዘዝ በተቃራኒ፣ የበለጠ እየጠነከረ መሄዱ የአደባባይ ምሥጢር ነው። ለዚህ ማረጋገጫዎች በተከታታይ በሚነሱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች እና በተቃዋሚ ኃይሎች መበራከት ናቸው። ስለዚህ የትግሬ-ወያኔ ቡድን «ለመቶ ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ እቆያለሁ» የሚለው ዓላማው ሊሣካ የማይችል እንደሆነ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በ፲፱፻፺፯ (1997) ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ በማረጋገጡ፣ አጠቃላይ እንቅስቃሴውን «ትግራይን ከቀሪዋ ኢትዮጵያ መገንጠል» በሚለው ሁለተኛ ግቡ ላይ እንዲያተኩር ሁኔታዎች እንዳስገደዱት ይታያል። ለዚህ የግንጠላ ዓላማው ያጸደቀው «ሕገመንግሥት» ተብየው ዋናው መሣሪያው መሆኑ ይታወቃል። አንቀፅ ፴፱(ሰላሣ ዘጠኝ) ለማንም ጥቅም ተብሎ ሣይሆን፣ የትግራይን ግንጠላ ለማሣሳካት የተቀረጸ አንቀፅ እንደሆነ ማንም ይስተዋል አይባልም። ዛሬም ቢሆን የትግሬ-ወያኔ የተመሠረተበትን ዋናውን ስሙን (ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) ያለመቀየሩ የሚያረጋግጠው ሃቅ ትግራይን ከቀሪዋ ኢትዮጵያ መገነጠል በይደር የቆየ የማይቀር አጀንዳው መሆኑን ነው። ይህ ዕውነት እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ አንቀፅ ብቻ ትግራይን ገንጥሎ በሰላም መኖር እንደማይችል የትግሬ-ወያኔ ጠንቅቆ ያውቃል። የትግሬ-ወያኔ መሪዎች ከተጠያቂነት መዳን የሚችሉት፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ንብረት መጠቀም የሚችሉት፣ የትግራይ መገንጠል ለጊዜውም ቢሆን ዕውን ሊሆን የሚመችለው፣ በቀሪዋ ኢትዮጵያ ነገዶች መካከል መበታተን ሲፈጠር፣ ከሁሉም በላይ ዐማራ የተሰኘውን ነገድ ሌሎች ነገዶች በጠላትነት ፈርጀው እርሱን ማዳከም ሲችሉ፣ እንዲሁም «ዐማራ» ሲል የከለለውን ክልል ከውጭ አገር ጋር እንዳይገናኝ ዝግ በማድረግ ብቻውን አቁሞ ኅልውናውን ማጥፋት ሲቻል እንደሆነ ብቻ መሆኑን ይህ ቡድን አቅዶ በተግባር ሲንቀሣቀስ ቆይቷል። ለዚህም ባለፉት ዓመታት ሁሉም በሚባልበት ደረጃ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙት ነገዶች ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጀው የጥፋት እጃቸውን እንዲያነሱበት አድርጓል።

የትግሬ-ወያኔ ምዕራባዊውን «የዐማራውን ክልል» ለም እና ድንግል መሬቶች ለሱዳን በገጸበረከት ሰጥቷል። በቀረው ምዕራባዊ ዳርቻ የትግራይን ግዛት በማስፋት ከቦ፣ ከቤንሻጉል ጉምዝ እና ከጋምቤላ ክልሎች ጋር አገናኝቷል (አባሪ ካርታውን ይመልከቱ)። ከ5 ሚሊዮን የማያንስ ዐማራ ከምድረ ኢትዮጵያ አጥፍቷል። አያሌ ዐማሮች በአገር ውስጥ ሠርቶ የመኖር መብታቸውን በመገፈፋቸው ለስደት ሕይዎት ተዳርገዋል። በስደት በዓለም ዙሪያ ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ መካከል ከመቶ ፷(ስድሣ) እጁ በላይ ዐማራ መሆኑ የሚያመለክተው፣ ዐማራው በገዛ አገሩ ሠርቶ የመኖር መብቱን የተገፈፈ መሆኑን ብቻ ሣይሆን፣ ዐማራው በመጥፋት ሂደት ላይ መሆኑን የሚያሣይ ነው።

ሰሞኑን ለሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ከደረሱት እጅግ አስተማማኝ መረጃዎች መካከል፣ ወያኔ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አናት ላይ የመቆየት ዓላማው የማይሣካ መሆኑን ተገንዝቦ፣ ወደ ሁለተኛው እና የመጨረሻ ግቡ፣ ማለትም፦ ትግራይን ለመገንጠል በከፍተኛ ሚስጢር እየሠራ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው። ይህም የትግራይ ግንጠላ ዕቅድ ለማሣካት እንዲቻል፣ ከአገር ውስጥ ተቃዋሚ ኃይል እንዳይነሣ፣ ኢትዮጵያን በሽግግር ዘመኑ ከፋፍለዋት በነበረው ፲፬(አሥራ አራት) እና ከዚያም በላይ የሆኑ የክልል ወሰኖችን የሚያመለክቱ ካርታዎችን አዘጋጅተው፣ ከየጎሣው ሰዎችን መልምለውና አደራጅተው፣ ለነዚህ ሰዎች የወታደራዊ፣ የደህንነት፣ የአደረጃጀት፣ የአመራር እና የቁጥጥር ሥራ የሚሠሩ የትግሬ-ወያኔዎች ተመድበው በከፍተኛ ሚሥጢር ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ እየተዶለተ መሆኑን አረጋግጠናል። ይህም ከ1997 የምርጫ ሽንፈታቸው ማግሥት ጀምሮ በመከናወን ላይ ያለ ተግባር እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻን ገልፀውልናል። «ይህ አይሆንም፣ አይደረግም፣ አይታሰብም» ሊባል የማይችል እንደሆነ የወያኔ ጉዞ እና ተግባር ከጥርጣሬ ውጭ በሆነ መንገድ ያስረዳናል። ለዚህ ሤራቸው ማረጋገጫዎቹ በነባር ኢትዮጵያዊ እምነቶች መካከል እየሰራ ያለው የማጥፋት ሥራ፤ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ፣ በሶማሌ፣ እየተካሄዱ ያሉት የጥፋት እርምጃዎች የዚህ ዕቅድ አካሎች መሆናቸውን ልብ ሊባል ይገባዋል።

ሌላው የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ተልዕኮው የማይቀር እና የፍጻሜው የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱን ማሣያው፣ የምዕራቡ ዓለም የመረጃ እና የስትራቴጂክ ጥናቶች ተቋም ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት አጋማሽ ላይ በ2030 እ.አ.አ. ከዓለም ካርታ ላይ ከሚጠፉ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ይፋ ማድረጉን እናስታውሳለን። በተመሣሣይ ሁኔታ በኅዳር ወር ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ሞስኮ ውስጥ የተካሄደ የዓለም አቀፍ ቀውሶች ጥናት ተቋም ባዘጋጀው ስብሰባ፣ በምሥራቅ አፍሪካ የሚታየውን ብጥብጥ ለዘለቄታው ለማስወገድ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ኮንፌደሬሽን መመሥረት እንዳለበት ግፊት የሚያደርግ ጥናት ቀርቧል። የኮንፈደሬስሽኑ አባል አገሮች ጥንት እንግሊዝ «ከኢትትዮጵያ ተቆርሶ ወደ ሱዳን ይካተት» ትለው የነበረው የኤርትራ ምዕራባዊ ክፍል ወደ ሱዳን ተካልሎ ሱዳን ከሦስት እንድትከፈል፣ የኤርትራ ደጋማው ክፍል ከትግራይ ጋር ተቀላቅሎ ትግራይ ትግርኝ የተሰኘ ግዛት እንዲፈጠር፣ የአፋርኛ ተናጋሪዎች በአንድ ግዛት ተጠቃለው አንድ ግዛት እንዲሆኑ፣ በአምስቱ ዓመት የአርበኛነት ዘመን ፋሽስት ጣሊያን «ዐማራ» ብሎ ሰይሞት የነበረው ክልል አንድ የዐማራ ግዛት እንዲሆን፣ የቀሩት አካባቢዎች የፋሽስት ጣሊያንን ክፍፍል መሠረት አድርገው የየራሳቸውን ግዛቶች እንዲመሠረቱ እና በነዚህ አገሮች መካከል ኮንፌደሬሽን ይመሥረት የሚል ነው። የእነዚህ ጥናቶች ግብም ከወዲሁ ኢትዮጵያዊው የኢትዮጵያን መፍረስ አይቀሬነት እንዲለማመደውና «ድሮም ተብሎ ነበር» በማለት የአገሩን መፍረስ በፀጋ እንዲቀበል የሥነ- ልቦና ሰለባ ከወዲሁ መሠራቱን የሚያመለክቱ ናቸው።

ካርታ፦ ለወደፊቱ «የትግራይ ሪፑብሊክ» ተብሎ በትግሬ-ወያኔ የሚገነጠለው የኢትዮጵያ አካል በአረንጓዴ ቀለም የተቀለመው ነው።

የትግሬ-ወያኔ እና ዕኩይ ዓላማው ኅልው ሆነው የሚዘልቁት ኢትዮጵያውያን ሠፊውን ለቀን ጠባቡን፣ ኢትዮጵያዊነትን ትተን ጎሣዊ ማንነትን ስንላበስ፣ ዕውነትን ከድተን ከውሸት ጎራ ስንሰለፍ፣ ዘላቂውን ትተን አላቂውን እና ጠፊውን ስንይዝ፣ አኩሪውን ትተን ነገ የሚያሳፍረውን ስንከተል፣ ለኅሊና ሳይሆን ለጥቅም ስንገዛ ነው። እስካሁን የትግሬ-ወያኔ ያለ ልጓም የጋለበን በነዚህ ምክንያቶች ብቻ ነው። አሁን ግን የትግሬ-ወያኔ አጥፍቶን ሊጠፋ ከመጨረሻው ጠርዝ ላይ ቆሟል። የመጥፋቱም ያለመጥፋቱም ጉዳይ የሚወሰነው በእኛ ብቸኛ ምርጫ ነው። ምርጫችን በኢትዮጵያዊነታችን መቀጠል ከሆነ፣ ወያኔ ያጠመደልንን የመነጣጠል መንገድ ትተን በአንድነት በመቆም ኢትዮጵያን ከመጥፋት ለመታደግ ቁርጠኛ አቋም ልንይዝ ይገባል። ቢመሽም፣ እጅግ ብንዘገይም፣ ፈጽሞ ከመቅረት ይሻላል እና እጅ ለጅ ተያይዘን አገራችን እንድናድን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።

ከሁሉም በላይ የትግሬ-ወያኔ ወደ መጨረሻ እርምጃው ሲያመራ አጥፍቶ የሚጓዘው፣ ከጽንሱ ጀምሮ በአውራ ጠላትነት ፈርጆ ላለፉት ፵(አርባ) ዓመታት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲገድለው፣ ሲያስረው፣ ሲያሰቃየው እና ሲያሳድደው የኖረውን ዐማራ እስትንፋስ ሳያቋርቋጥ ከጉሬው እንደማይገባ አውቀን፣ ከተደገሰልን ጥፋት እራሳችን መከላከል እንድንችል ከምንጊዜውም በላይ ነቅተንና ተደራጅተን ኅልውናችን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ ሆነን እንድንቆም ሞረሽ-ወገኔ አደራ ይላል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

ህወሃት/ብአዴን በጨለማ ጐንደርን በታንክ ምን ለማድረግ !!?

$
0
0

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)


ነብሮ ከሰ/አሜሪካ

ኢዲዩ በወገራ፤ጎንደርና ጭልጋ አውራጃዎች ኃይሉን አጠናክሮ ወደ ጎንደር ከተማ እየገሰገሰ ይሄድ በነበረበት ወቅት በጎንደር ክፍለ ሀገር የነበረው የደርግ ወታደራዊ አቅም ደካማ ነበር።በኋላ ግን ከየክፍለ ጦሩ በመሳብ ገስጥ በሚባለው ክፍለ ጦር የተካተተ ከፍተኛ የጦር ክምችት ወደ ጐንደር ዘመተ። ከአዘዞ እስከ ብልኮ ጎንደር በደርግ ብረት ለበስና መድፍ በጫኑ የጦር ኃይል ካሚዮኖች ተጨናነቀች።በዚያች ቀንና ሰአት በሕዝቡ ዘንድ የተለያዩ አመለካከቶች ይንፀባረቁ ነበር። ተማሪው አስተማሪው፤ የከተማ ነዋሪውና የመንግሥት ሠራተኛው፤ነጋዴው በኢዲዩ፤በደርግና ኢህአፓ አመለካከት ውስጥ ተከፋፍሎ ሲመሽግ እንደነበር የአይን እማኝ ሆኜ መናገር እችላለሁ።በወገራና ጭልጋ ያመራውን የደርግ ጦር እንቅስቃሴ ለመከታተል አቅሙና ጊዜው ስለአልነበረኝ ከጐንደር ወደ ሁመራ ያቀናውን እንቅስቃሴ ለመከታተል ሁኔታዎች ረድተውኝ ነበርና የሚከተለው ነበር።

ጦርነቱ ከጐንደር ከተማ ወጣ ብሎ የተጀመረ ሲሆን የደርግ ኃይል ከፍተኛ የጦርነት ልምድ ያለው በትጥቅና ወታደራዊ ሎጅስቲክ የተደራጀ ስለነበር በኢዲዩ በኩል የነበረው ሠራዊቱ የጥቂት ጊዜ የጦርነት ልምድና አብዛኛው ሕዝባዊ ሠራዊት በመሆኑ ደርግ አቅም አግኝቶ የላይ አርማጭሆ ወረዳ ዋና ከተማ ትክል ድንጋይን አልፎ መሄድ ጀመረ።ከዚያ በኋላ ግን ደርግ ያላሰበው ሁኔታ ገጠመው። ገና ቆልማሜ ላይ እንደደረሰ የአርማጭሆ የመሬት ቀማመጥ ራሱ ሌላ ጦር በመሆን ደርግን ይፈታተነው ጀመር። ከቆልማሜ እስከ ሙሴ ባምብ የነበረው የደርግ ጉዞ ደርግን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍለው ሳይወድ በግድ እንዲገነዘብ አደረገው።ደርግ ወደ ሥልጣን ከወጣ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የዚያ አይነት ፈተና ሲገጥመው ቆም ብሎ ማስብና የችግሩን መፍትሄ ማፈላለግ ሲገባው ግፋ በለው በማለት ቀጠለ።

ከትክል ድንጋይ እስከ አሸሬ በቀኝና በግራ በኩል ነዋሪ የሆነው የአርማጭሆ ሕዝብ አካባቢያውን በመልቀቅ ቤተሰቡን ከደርግ ጦርና ተወንጫፊ መድፎች በማራቅ የኢዲዩን ጦር በማናቸውም አይነት መተባበርና ማገዙን ቀጠለ። አንድ የገስጥ ክፍለ ጦር አባል የነበረ ሙሴ ባንምብ በጥይት ተመትቶ የነበረ እኔም ኢህአፓ አባላቱን ሲያሰናብት አንዱ ተሰናባች ስለነበርኩ ሁለታችንም በአንድ ክላስ(ክፍል) አብረን መማር ስንጀምር ከቀናት አንድ ቀን ትንሽ ጥያቄዎች አቀረብኩለትና ብዙ ገጠመኞችን አጫወተኝ። ይኸውም የገስጥ ጦር ያከተመለት ሙሴ ባንምብ ነበር።

ነገር ግን በኢዲዩ በኩል አንድ ወጥ አመራር ስለአልነበረ የገስጥ ጦር ባለበት ሆኖ አቅሙን አጠናክሮ የመከላከል ወይም ወደ ኋላ ማፈግፈግ ከሚል ነጥብ ደረጃ ደርሶ እያለ አንድ የገስጥ ጦር ሻምበል ምልክት አሳየ (ባውዛ )አበራ ያ ማለት ወደፊት ግፋ በለው የሚል መልዕክት ነበረ:- ይሁን እንጅ ከአንገረብ ማዶ ጠገዴ ወልቃይትና ጠለምት በቀኝ አርማጭሆ በግራ የገስጥን ጦር እርሳስ እየቀለቡ በመጓዝ ላይ እንዳለ እኔ ኩፉኛ ቆስየ ስልነበር ወደ ክምና ሄድኩ የገስጥ ጦር ግን የሚከፍለውን መስዋዕትነት እየከፈለ ሁመራ ደረሰ ያ ጊዜ በደርግ ታሪክ መጥፎ ገጠመኝ ነበር ብሎ ነበር በአጭሩ የተረከልኝ።

አንድ በውል ያልተመለከትነውና የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ግራኝ መሀመድ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ኢትዮጵያን ሲወር የገሰገሰው ወደ ጐንደር ነበር፤ድርቡሽ(መሐዲስት) ከሱዳን ተነስቶ ኢትዮጵያን ሊወር ሲመጣ መጀመርያ ያቀናው ወደ ጎንደር ነበር፤የፋሽስት ጣሊያን ወራሪ ጦር ከኤርትራ በመነሳት በሁመራ አድርጎ የገሰገሰውም ወደ ጐንደር ነበር፤ ዘረኛውና ቅጥረኛው ህወሃትም ብረት ለበስ ታንኮቹን አሰልፎ ከመቀሌ የገሰገሰው ወደ ጐንደር ነው።

በሥነ-ምግባር ብልሹ የሆኑ አስተዳዳሪዎች የሚሾሙት ጐንደር ነው። በሀገር ደረጃ አንዳንድ ፖለቲካዊ ውጥረቶች ሲከሰቱ የሚጠረጠረውና ጣት የሚቀሰርበትም ጐንደሬው ነው።የትምህርት እድልና የደረጃ እድገት እንዳያገኝ የሚደረገው ጐንደሬው ነው።በመጥፎ አርአያነት ቆርጦ ቀጥል ስም የሚለጠፈውም ለጐንደሬው ነው።የህወሃት የመሬት ቅርምት ትኩረትም በጐንደር ነው።በደርግ ጨፍጫፊ ሥርዓት የጥይት ሰለባ የሆነው ጐንደሬው ነው።መንግሥት እገለብጣለሁ ያለው ሁሉ የሚመሽገውና አካባቢውን የጦርነት ቀጠና የሚያደርገው በጐንደር አካባቢ ነው።ይህ ሁሉ ደባ ሲፈፀም የጐንደርን ሕዝብ ድምጽ የሚሰማና ቀና ብሎ የተመለከተው የለም።

እኔ እስከማውቀው ድረስ የጐንደር ክፍለ ሐገር ሕዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ቀዳሚውን ቦታ ሊይዝ እንደሚገባውና ዳር ድንበሩን ያለመንግሥት ኃይል በራሱ አስከብሮ የኖረ ሀገር ወዳድና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ሕዝብ ነው።ይህን ስል አእምሯቸው ነገር እንደ ግራምጣ ለመሰንጠቅ የተፈጠሩ አዋቂ ነን የሚሉ ከጠባብነት ጋር ሊያላትሙት እንደሚከጅላቸው ይገባኛል። የኔ መነሻ ግን እሱ አይደለም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይህ የዘረኝነት ወረርሽኝ (ቫይረስ)ከመምጣቱ በፊት ክርስቲያን እስላም፤ ትግሬ ኦሮሞ፤አማራ አፋር፤ሀድያ ጉራጌ….ወዘተ ሳይባባል በጀግንነት፤በጋራና በአንድነት የሀገሩን ዳር ድንበር ሳያስደፍር ሉዓላዊነቷን ጠብቆ ያቆየ ሕዝብ መሆኑን ዘንግቼ አይደለም።የጹሑፌ መነሻ ሰሞኑን ህወሃት የትግራይ ሚሊሻዎችን በማስታጠቅ በአማራ ክልል ከሚኖረው የጎንደር ሕዝብ ጋር ለማጋጨት የሰነዘረውን ጦርነት መሠረት በማድረግ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለአካባቢው ሕዝብ ድምጽ መሆንና ነገሩን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የሁለቱ ክልሎች ሕዝብ አጽዕኖት በመስጠት በተለመደው ባህላዊ የችግር አፈታት ጥበብ የተከሰተውን ችግር እንዲያስወግዱትና ወደ ድሮው አንድነታቸው፤አጋርነታቸው እንዲመለሱና ችግሩን እየገፋ ያመጣውና ጠንሳሹም ህወሃት እንደሆነ እንዲገነዘቡ ለማድረግ ነው።

የድሮዎቹ ደጋግ ወላጆቻችን እንዲህ አይነቱን ጠብ አጫሪነት ሲመለከቱ አትስሙት ** ውሃው ሂያጅ ድንጋዩ ቀሪ ነው ** ይሉት ነበር ሰው(ሕዝብ) ድንጋይ ነው ማለታቸው ሳይሆን በምሳሌያዊ አነጋገር መንግሥት ይሄዳል ሌላ መንግሥት ይመጣል ሕዝብ ግን አይቀያየርም ለማለት ነው። ስለዚህ መንግሥትን ወይንም ማንኛውንም እንደ ህወሃት ያለ ወራሪ እንደ ውሃ ሕዝብን ደግሞ ቀየውን እንደማይለቅ ድንጋይ አስመስለው ይናገሩት ነበር። የአሁኑ ትውልድ በዚያ ምሳሌያዊ ዘዴ የተሞላበት አነጋገር ያምናል አያምንም ብሎ ለመናገር በጣም ይከብዳል።ሆዳምነት ፤አድር ባይነት፤ስግብግብነት የተጠናወተን ዞሮ ማየት የተሳነን የሰውን ሰብአዊነት እንደጨርቅ የምንቦጭቅ፤ተራ በተራ ለግዳይ የምንቀርብ፤ለመተማመን የተቸገርን ትውልዶች ነው በአሁኑ ሰአት ያለነው።

የሠሐራን በርሃ አቋርጦ ወደ ዐረብ አገር በእግር መጓዝ ፤አይከፍሉ ከፍሎ በመርከብ ወደ ዐረብ አገር መንጎድ ሞትን በመፍራት ነው ወይም የኢኮኖሚ ችግርን ለመፍታት ነው። ዳሩ ግን ችግሩን መፍታትም ሆነ ከሞት ማምለጥ እንዳልቻሉ አይተናል። ይህን ጦስ ያስከተለው አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የህወሃት ቅጥረኛ ኃይል ነው።ይባስ ብሎም በነዚህ የኢትዮጵያዊነት ዜግነት ባላቸው አብዛኛዎቹ ገና ሕፃናት ወጣቶች ላይ የደረሰውን አስደንጋጭ የሞት አደጋና ሌላ ለመግለጽ እጅግ የሚዘገንኑ ሁኔታዎች ሲፈጸሙ የዓለም ሕዝብ ሳይቀር ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ሀዘኑን ሲካፈለን የህወሃት/ኢሃዲግ መሪዎችና አባላት አንድም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም በማለት በአራት ነጥብ ደመደሙ።

ወደዚህ ነጥብ እንድገባ የገፋፋኝ ሞት ካልቀረ ለምን የሚገድለንን እየገድለን አንሞትም?ምናልባት እንዴት እንጀምረው የሚለው ሊያስቸግር ይችል ይሆናል ልቡ ለቆረጠና ለወሰነ ግን ቀላል ነው። መድረሻቸው ይህ ነው ለማለት ባልችልም የከፋው ፤ግፍና በደል የተፈፀመበት፤የዜግነት መብቱ የተገፈፈበት፤ፍትህ ያጣ ኢትዮጵያዊ የህወሃትን ሥርዓት ማስወገድ አለብኝ ብሎ ማመን አለበት። በዚህ ከተማመን ዛሬ ነፍጥ አንስተው እየተፋለሙ ያሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ቁጥር የሚናቅ አይደለም ከሚመስለው ጋር ተሰልፎ የጋራ ጠላትን ታግሎ መጣል ይቻላል።

ህወሃቶችና አጋፋሪዎች፦እንድታውቁት የሚያስፈልግ ነገር ቢኖር የአክሱምን ሥርዎ መንግሥት የደመሰሰችው ዩዲት ጉዲት እንጅ የጎንደር ሕዝብ አይደለም። የጎንደር ሕዝብ እንደ ግራኝ መሐመድ፤ጣሊያን፤ድርቡሽና ህወሃት ግፍ አልፈፀመም። የሌላውን አገር ወይም አካባቢ ሊወር አልተነሳም ይልቁንስ በደም በተቦካ አጥንቱ ድንበሩን ጠብቆና አስከብሮ የመንግሥት ግብር ገብሮ የኖረ ጎንደሬ ሆኖ በኢትዮጵያዊነቱ እጅግ የሚኮራ ሕዝብ ነው የጎንደር ሕዝብ ።

አይን ያማረውን ሁሉ የራስ ለማድረግ በሚቋምጥ ስግብግብ አስተሳሰብና ቀሽም ብልጣ-ብልጥነት ጥቂቶች ብዙዎቹን አጭበርብረው ሊሳካላቸው የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።ከዚያ በኋላ ያለው ባለቤቱ እንጉልቻም ካልሆነ ፈላጊው ቢሞክርም በል ተመለስ ድንበሩ እሱ ነው ብሎ ባፍ ጢሙ እንዲደፋ ማድረግ ይቻላል።የወልቃይት ጥገዴ የአርማጭሆ፤የጠለምት ፤ አዳኝ አገር ጫቆ እና የጎንደር ሕዝብ በቅርቡ ያደረገው ይህንኑ ነው። ይህም ተጀመረ እንጅ የመጨረሻው አይደለም። እንዲያ ነው የአገሬ ሕዝብ!! ሽንፋ ፤ቋራ መተማ፤ጭልጋ፤አለፋ ጣቁሳ፤ደምብያ፤ጠዳ፤በለሳ፤ሰሜን፤አምባጊዮርጊስና ዳባት፤አዳርቃይ፤አዲሰላም፤በየዳ ጃናሞራና በለሳ ይዞህ ብቻህን አይደለህም በርታ።ከጎንህ የምንሰለፍበት ቀን ሩቅ አይደለም።

በመጨረሻም ለህወሃት የመከላከያ ሠራዊት ጥብቅ ማሳሰቢያየ ይድረስ፦አሁን እየገደልከው ካለው ሕዝብ አብራክ መፈጠርህን የምትክድ አይመስለኝም። በተግባርህና በአስተሳሰብህ ግን ክህደትህን አጉልቶ የሚያሳይ በርከት ያሉ ማስረጃዎችን ከአራቱም ማዕከል እየመዘዙ ማቅረብ ይቻላል።አለቆችህ ዛሬ ባለፎቅ፤ባለ ዶላርና የተንደላቀቀ ኑሮ እየኖሩ እንዳሉ ታውቃለህ።ይህን አይነት የደላ ኑሮ ለመኖር አንተ ህዝብን በጅምላ መፍጀት ይገባሃል ወይ?የዛሬዎቹ ጌቶችህ ይህ አሁን የመሣሪያህን አፈሙዝ አዙረህ በምትገድለው ህዝብ ከዚህ እንደ ደረሱ በግልጽ ልነግርህ እወዳለሁ።ሰፊ ዘገባ ይዥ እስከምቀርብ ለዛሬ ያለኝ መልእክት ህወሃት ከፊትህ ለህዝብ ነፃነት ከሚፋለሙ ጀግኖች መሣሪያ የሚተፋው እርሳስ ከኋላህ ህወሃት ያሰማራው ገዳይ ኃይል በሚተኩሰው ጥይት ጀርባህንና ግንባርህን እየተመታህ የአሞራ ቀለብ ከመሆን ራስህን በራስህ ልትታደገው ይገባል።እንደ ድሮው ቤት ያፈራውን አካፍሎ የታመመ አስታሞ የቆሰለን እስኪያገግም ሸሽጎና የሞተን እየቀበረ መውጫ መግቢያውን እየመራህ የሚሄድ ሕዝብ የለም።ያለህ አማራጭ የህዝቡን ትግል መቀላቀል ወይም የሰው በላው ሥርዓት ማገዶ በመሆን ማለቅ ብቻ ነው። የአገር መከላከያ ሠራዊት ሳይሆን የህወሃት የእድሜ ዘመን እንዲረዝም የሕዝብን መብት በማፈን ተግባርህ መቀጠል አይገባህም።ዛሬ ብዙ አማራጮች አሉህ።እነዚህ አማራጮች ሳይጠቡ ተጠቀምባቸው ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ከሚዋደቁት ጎን ተሰለፍ፤የሕዝብ ልጅ በመሆን ታሪክ ሥራ ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የማለዳ ወግ …የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ የክብር ጉዞ ፍጻሜ !

$
0
0

መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል …!

image-9d7f88cbdecd3715a84ff1e923f19a265e6c 3ebc9096e18394f23acdc537c8db-V_resized_1አርአያነታቸው ፋና ወጊ ሆኖ እያለ ብዙ ያል ተነገረላቸውን ዶር በርናርድ ብሬድሊ አንደር ሰንን ባዘከርኩበት የማለዳ ወጌ የጠቢቡን ህይዎት ከጃማይካ እሰከ አሜሪካ ለመቃኘት መሞከሬ እውነት ነው ። ዛሬም የምቀጥለው ከዚያ ለጥቆ ያለውን የዶር በርናርድን አፍሪካና ኢትዮጵያ ያደረሰውን መንገድ ሲሆን እንደ መግቢያ በአንድ የጥምቀት ዋዜማ ጎንደር ከዶር በርናርድና ከባለቤታቸው ከሲስተር እማዋይሽ ገሪማ ጋር የነበረንን አጭር ቆይታ በጨረፍታ በመቃኘት መጀመሩን ልቤ ፈቅዷል … የፈቀዳችሁ ተከተሉኝ !

ጎንደር በጥምቀት ዋዜማ …

ባልሳሳት ወርሃ ጥር 2004 ዓም ይመስለኛ ል … ጥምቀትን በጎንደር ለመታደም ሲገሰግስ የሚመጣ አውቶቡስ በአባይ በርሃ ተገልብጦ ተሳፋሪው በማለቁ ጎንደርና ጎንደሬው ማቅ ለብሰው ፣ አዝነው ተክዘዋል … ምክንያት አላቸው ፣ ምክንያቱም ከጎንደር ጥምቀት ክብረ በአል ጋር የቴዎድሮስ ሃውልት ምረቃ ሊከበር በዝግጅት ላይ እያለ ከወደ አባይ በርሃ የተሰማው መርዶ የከፋ ነበርና ነው ። መርዶው በመይሳው ካሳ ሃውልት ምረቃና በጥምቀቱ የደመቀ ዋዜማ ስሜታቱ በደስታ ላይ የነበርነውን በአል አክባሪ ሁሉ ቅስም የሰበረ ነበር። በርሃው ወገኖቹን በልቶታልና ፣ ጎንደሬውን አንገቱን በሃዘን ደፍቶ ማቅ ያለበሰው ቀን ቢኖር ይህ ቀን ነበር። ደስታቸውን ለመግለጽ ሳግ እየተናነቃቸው ለቴዎድሮስና ለሚናፍቋት አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያ ያላቸውን ፍቅር በመግለጽ ላይ የነበረው ኢትዮየጵያዊ ከትንሽ እስከ ትልቅ በርሃው በበላቸው ወገኖቹ በሃዘን ቅስሙ መሰበሩና ስሜቱ መጎዳቱን በእያንዳንዱን ፊት ይነበብ እንደነበር አይረሳኝም …

በአባይ በርሃ ገደል ገብቶ ሰው የጨረሰው አውቶቡስ እኔ ፣ ልጆቸና እህቴ በአንድ ሆነን በተሳፈርንበት አውቶቡስ እኩል ከአዲስ አበባ ነበር የተነሳው። ከአዲስ አበባ እስከ አባይ በርሃ ድረስ ከበስተኋላችን ይጓዝ ነበር ። በአባይ በርሃ ደልደል ባለ መንገድ ዳር በአንድነት ለደቂቃዎች እረፍት አድርገንም ነበር ። እኛ ቀድመን አቀበቱን ወጠን ደጅን እንደደረስን ፣ የማይታመነውን አደጋ መርዶ ሰማን… ይከተለን የነበረው አውቶቡስ ከሃምሳ በላይ አብዛኛው እንደኛ ጥምቀትን በጎንደር ሊያከብር የተሳፈረው ወገን ገደል ገብቶ ሰው አንዳለቀ በቀትር የራዲዮ ዜና እወጃ ሰማን! ያ ቀን ለእኔ የሚረሳ እና የሚዘነጋ አይደለም ! በአባይ አፋፍ አንድ ጫፍ እረፍት ባደረግንባት ደቂቃ ሰላምታ የተለዋወጥኳቸውን ወገኖች በሰአታት ልዩነት የማለቃቸውን አሰቃቂ ዜና የሰማሁባት እለት ሆዳችን ተላውሶ አዝነን ከፍቶን ነበር ጎንደር በጥምቀት ዋዜማ የገባነው …

ሃዘን የጎዳው ጎንደሬ ግን በሃዘን ልቡ ተሰ ብሮም ቢሆን ሽርጉዱ ከጓዳ እስከ አደባባይ አድርቶታል። ጎንደሬው ከዘመድ አዝማዶቹ አልፎ ተርፎ ” ኑ በጥምቀት ኢትዮጵያን ተመል ከቱ ! ” በሚል እንግዳ ተጠርቷልና ሃገሬው እን ግዶቹን ሊቀበል ከጓዳ ጥንስስ እስከ አደባባይ ከተማ ማስዋብ ዝግ ጅት ተጠምዷል … ደግ ሞም ወቅቱ የቋረኛው አጼ ቴወድሮስ ሃውልት የሚመ ረቅበት ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ተገጣጥሟ ልና አጋጣሚው መሪር ሃዘን እያዘኑ መሳቅም ከመሆን ጋር ተደባልቋል …

የዶር በርናርድ ባለቤት ፣ የታዋቂው አርበኛ ደራሲ ገሪማ ታፈረ ልጅ ፣ ወይም የታዋቂው የፊልም ደራሲና የታሪክ ተመራማሪ የፕሮፊሰር ኃይሌ ገሪማ እህት ሀገር ወዳዷ ትጉህ እመቤት ከሲስተር እማዋይሽ ገሪማ ጋር በየተናኘነው በዚህ በጨነቀው የጥምቀቱ ዋዜማ ነበር ። ሲስተር እማዋይሽና ለጀግናው አጴ ቴዎድሮስ መታሰቢያ ቤተ መዘክር ለማቆም ደፋ ቀና የሚሉት የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ባደረጉት ጥረት አንድ እርምጃ የሄዱበት ወቅትም ነበር ፣ ለቴዎድሮስ መታሰቢያ ቤተ መዘክር መስሪያ መሬቱ ተሰጥቷቸው የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል ፣ ከተደረገልኝ ገለጻ አልፎ ተርፎ በቦታው በመገኘት የመሰረት ድንጋዩ ያረፈበትን ቦታ ተመልክቻለሁ … በዚሁ አጋጣሚ ሲስተር እማዋይሽ ገሪማን ጎንደሬው አንስቶ ስለማይጠግባቸው ባለቤታቸው ዶር በርናንር ደጋግሜ ጠየቅኳቸው ፣ እማዋ ግን ስለራሳቸውም ሆነ ስለባለቤታቸው ብዙም አይናገሩም ። ሁኔታው ተመቻችቶ እግሬን ጎንደር ላይ ሳሳርፍ ብዙ ስለሚባልለት ጠቢብ ጥቂት ያወሩኝ ዘንድ መወትወቴ ገፋሁበት ፣ ከሲስተር እማዋ ጋር በአንዱ ቀን አብረን ታሪካዊዋን ከተማ ስንዘዋወር ላላሰለሰው ውትወታየ ጀሮ የሰጡት እማዋ በቁልምጥ ስሜን ጠርተው እንዲህ አሉኝ ” ነብያለም ስለዚህን ቅን ፣ ደግና ቸር ባለቤቴን ማንነት እኔ እንዲህ ነው አልልህም ፣ ደግሞም ስጋየ ነውና እኔ ብናገረው አያምርም ፣ ከምን ም በላይ ግን የሃገሬን አፈር ፣ ባህልና ወጉን እንዲያውቅ አድርጌዋለሁ ፣ ዛሬ ከእኔና ከአንተ በላይ ስለምትወዳት እናት ኢትዮጵያ የሚመሰክር የታሪክ ሊቅ ባይባል ተመራማሪ በመሆኑ ደስታየ ወሰን የለወም ፣ እኔ ለኢትዮጵያ ያደረግኩት ስጦታ በርናርድ ይመስለኛል ፣ የሚገርምህ እኔም ሆንኩ እሱ የምንሰራው ለነፍሳችን ነውና ማንም ይህንን ተመልክቶ እንዲያመሰግነን አንፈልግም ፣ በርናርድም የሚልህ ይህንኑ ነው ፣ አትቸኩል ፣ ሰውየውን ታገኘውና ታወጋላችሁ ” ነበር ያሉኝ ፈገግ እያሉ …

ብዙም ሳይቆይ ከቀናት በኋላ ከሲስተር እማዋይሽ ጋር ተገናኘን ፣ በተያዘልኝ ጠሮ መሰረት ከጎንደር ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘውና አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚታወቀው መናፈሻና የከብት ማድለቢያ መንደር ስናመራ ቀዝቃዛ ንጹህ ነፋሻማ የቸቸላንና የሳሙና በርን አየር እየማግን ነበር ። … ከጎንደር ወደ አየር ማረፊ አቅጣጫ ፣ የአዘዞ መዳረሻ ሳሙና በር ድሮ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ነበር። በዚሁ ትላልቅ የጽድ ዛፎች በሚበዙበት አንድ ጫፍ ጀርባውን ለአንድ ቋጥኝ ሰጥቶ የተገጠገጠ ቤተ መንግስት የሚመስል ቪላ ተገንብቷል። ሲስተር እማዋይሽ መኪናቸውን እንደማብረድ እያደረጉ ወደ ቪላው ሲጠጉ ከውጭ በኩል እያመላከቱ ” አየህው በርናርድ ሃኪም ፣ ታሪክ ተመራማሪ ብቻ አይደለም ፣ ይህንን ቪላ ውስጡን በአስገራሚ የጥንታዊ ኢትዮጵያ ቁሳቁስ አሟልቶ የሰራ ” አርክቴክት ነው ! ” ሲሉ በፈገግታ ጠቁመውኝ ወደ ግቢው ገባን …


ከመኪና ወርደን ወደ እንግዳ መቀበያ አዳ ራሹ ስናመራ በግቢው አጥር ስር የተተከሉ አትክልቶችን ውሃ የሚያጠጣ እድሜው መጠ ጥ ያለ ጸጉረ ልውጥ ሰው ተመለከትኩ ። በአ ግራሞት ስቁለጨለጭ ሲስተር እማዋ በሁኔታ ፈገግ አሉና “ሰውየው ይህውልህ ” አይነት ምልክት በፊታቸው እየተነበበ ሰውየውን አስተዋወቁኝ። ሰውየው ዶር በርናርድ ነበሩ …

ዶር በርናርድ በፍልቅልቅ ፈገግታቸው ተቀብለው ሲኮተኮቱ ነበርና አፈር የነካ እጃቸውን እስኪተጣጠቡ ለሲስተር እማዋይሽ አስረከቡኝ ፣ እማዋይሽም በተንጣለለው የእንግዳ መቀበያ አስገቡኝ ። እግሬን ከግቢው ሳስገባ ጀምሮ ኢትዮጵያዊነትን የሚገለጽባቸው በሚያምር ሸክላ በእውቀት የተሰሩ የአበባ ማስቀመጫ እንስራዎች ፣ ድስቶችና ከመሳሰሉት አልፎ ተርፎ አዳራሹ በደረጃው ከፍ ባለ ቅርሳ ቅርስ ፣ ብሔር ብሔረሰቦችን አጉልቶ የሚያሳየው ቁሳቁስ ያጌጠው ቤት ቀልቤን ሳበው ። የቆመው ልቤ መቀመጥን አልወደደውም ፣ ዙሪያውን ማየት ፈልጓል ! ደግነቱ ብዙም ሳይቆይ ዶር በርናርድ ” ይቅርታ ዘገየሁ አይደል? ” ብለው ከተፍ አሉ! ልነሳ የተቁነጠነጥኩት ጎረምሳ ከሃኪሙ ፣ ከታሪክ ተመራማሪው እና ከስነ ህንጻው ባለሙያ ጋር መቀመጥና አፍ ላፍ ግጥሞ ማውራት አማረኝ … ወጋችን ቀጠልን ፣ ዶር በርናርድንና የእህታቸውን ወንድም ፕሮፎሰር ሃይሌ ገሪማ አንድ ሳይሆን በርካታ የሚያመሳስላቸው ነገር እንዳለ ታዘብኩ … ዶር በርናርድ እንደ ፕሮፎሰር ሃይሌ ገሪማ የሚናገሩት ደረቅ እውነት ጥልቅ ነው ፣ የእኔ ትውልድም ሆነ ያ ትውልፍ ስለሚጎድለውና መሆን ስላለበት የሰላ ሂስ ከነ መፍትሔው ፣ ስለ ኢትዮጵያዊነት ባህል ፣ ስለ ታሪክ አሻራውና ስለይትበሃሉ የቅብብሎሽ ጉድለት ጥልቅ ምክክር ሳይሆን ምክርን ሰጡኝ ! ብዙውን ተደምሜ ግራ ቢገባኝ እርስዎ ዜግነትዎ ከወዴት ነው ? አልኳቸው ፣ ሳቁና አላፊ አግዳሚው ግራ እየተጋባ ስለሚጠይቃቸው መሰል ጥያቄ ሲመልሱ ” እኔ 400 አመት በፊት በአሜሪካና በጃማይካ ከምወዳት ሃገሬ ተለያይቸ የቆየሁ ኢትዮጵያዊ ነኝ ! ” በማለት መለሱልኝ ፣ በርናርድ ስለኢትዮጵያ ቀዳማዊ ታሪክ ፣ በባሪያው ንግድ ዘመን ስለተሰደዱት አፍሪካውያን ታሪክ በአስገራሚ ሁኔታ ተንትነው አስረዱኝ … ዝም ጭጭ ነበር ያልኩት … በህዎታቸው ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ የሰጡኝም በዚህ ወቅት ነበር ! እናም ካጫወቱኝና ከተሰራጨው የህይዎት ታሪክ መካከል የበርናርድን የአፍሪካና የኢትዮጵያ ትስስር እነሆ …

ዶር በርናርድ አፍሪካና ኢትዮጵያ …

ከሁሉ አስቀድሞ አንድ ለዚህ ዝክር ቅኝቴ ምንጭ የሆነኝ መረጃ ያገኘሁት የዶር በርናርድ ሬሳ በምድረ አሜሪካ የመጨረሻ ሽኝት የቀረበው የህይዎት ታሪካቸው መሆኑን መሆኑን ልብ በሉልኝ ፣ ከዚሁ መረጃ ጋር ዶር በርናርድን በአካል አግኝቸ ካጫዎቱኝን የመረጃ ግብአት እያዋሃድኩ ለአንባቢያን በሚመች መልኩ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ ።

የጠቢቡ ሀኪም የህይወት ተልዕኮና የውስጥ ነፍስ ፍላጎት የሚጀምረው ከጃማይካውያን ብርቱ የኢትዮጵያ ወዳጆች ነው ። ከእነ ማርከስ ጋርቬ … በርናርድ ማርከስ ጋርቬ‘ ወደ የስፋዋ የራሳችን መሬት እንመለስ’ ወዳሉባት ጥንታዊ ት ቅድስት የኢትዮጵያ ምድር ሄዶ የማገልገል ፍላጎት በአሜሪካው የተደላደለ ህይዎት ቢወጠንም ምክንያት በባርነት ዘመን የተሰደ ድን የዚያች ሃገር ዜጎች ነን የሚል ብርቱ ምክንያት ነበረው ። ያ ህልሙና ራዕዩን እንዲሳካ ደግሞ የኑሮ አጋሩ የአርበኛው ደራሲ የገሪማ ታፈረ የአብራክ ክፋይ ሀገር ወዳዷ ሲስተር እምዋይሽ ምክንያት ሆነች። እናም ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ከምድረ አሜሪካ የተጸነ ሰው ቅዱስ ሃሳብ አፍሪካን በመጎብኘት አሃዱ ብሎ ተጀመረ … !

ዶር በርናርድ ታንዛኒያን እና ኬንያን ቀዳሚ ጉብኝት ሲያደርግ በአይኑ በብሌሉ የተመለከ ተው ፣ በአካል ያዳመጠውና የዳሰሰው የአፍሪ ካ ልጆች ገና ያልተቀረፈ ችጋር ነፍሱን አደማት ፣ የቀደምቷ “የዳቦ ቅርጫት “የአህጉረ አፍሪካን የኋልዮሽ ጉዞ ታዝቧልና ነፍሱን አስጨነቃት … አፍሪቃ የምትቃትትበትን የሰቆቃ መንገድ ፣ ጫንቃዋን የያዛትን የትላንቱ የቅኝ አገዛዝ ዛር እንዳልለቀቃት አይቶ አዘነ ፣ ተከዘ ! አጭሩን የታንዛንያ እና የኬንያ ጉብኝት አጠናቆ የሃገሩ ልጆች ጃማይካዎች “የተስፋዋ ምድር !” ብለው ወደሚያምኑባት ኢትዮጵያ አቀና …

ዶር በርናንድ ቅድስት ኢትዮጵያ …

የሚሰገመገመው አውሮፕላን የኢትዮጵያን ምድር ነካ ፣ የተቆለፈው የአውሮ ፕላን በር ተከፈተ ፣ በርናርድ እና ነፋሻው ውብ የተፈጥሮ ጣዕም ያለው የተስፋዋ ምድር መዲና የአዱ ገነት ቀዝቃዛ ንጹህ አየር ተገናኙ ፣ አየሩን ሲምገው – ህልሙን አስታወሰው ! … እንዲያ እያለ ጉብኝቱን ጀመረ ! ዶር በርናርድ ሀኪም ነውና በሚያውቀው ሙያ ዳሰሳ ለማድረግ ይመቸው ዘንድ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ቀናት ቆይታው የህክምና ተቋማቱን ጎበኘ ። በየህክምና ተቋማቱ ሕሙማኑ ተኮልኩለው እርዳታ ለማግኘት ሲጠባበቁ ቢመለከት ልቡ ተሰበረ። አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና የህክምና መካነ ጥናት እንዲሁም ቅዱስ ገብርኤል የግል ሆስፒታል ሲጎበኝ፤ ረዠም ራዕዩን ፣ የህክምና ልሂቅ የመ ሆን ዝናውን ያወቁበት ህልሙን የነቁበት ” የእኛ ሁንልን ” ሲሉ ተማጸኑት ! በንዋየ ፍቅር ደንታ ለሌለው ፣ ለሰብዕና ቅድሚያ ለሚሰጠ ው ለዶር በርናርድ ይህ ግብዣ ተቀባይ አልነበረውም ፣ አልተቀበለውም ! የጠቢቡ ጉብኝት ቀጥሏል …

አኩሪ ታሪክ ባህሏን ጠንቅቆ እንዲረዳ ፣ እንዲማርና እንዲመራመር ፣ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ፍቅር እንዲነደፍ ፈር በቀደደ ችው የትዳር አጋሩ በሲስተር እማዋ ገሪማ እየተመራ ኢትዮጵያ አሳምሮ ጎበኛት ። ጠቢቡ ከሰማ ካነበበው የኢትዮጵያ ታሪክና ባህል በላይ ያጣ የነጣው አብዛኛው ህዝብ ሰው አክባሪና እንግዳ ተቀባይነትና ታማኝነት በኩራት ሲያስደምመው ። የድህነቱና የችግሩን መክፋት ግን ህመም ሆኖ አስከፋው ! ዶር በርናርድ አንደርሰን ድህነት ፣ በሽታው መገፋት የሚችል እንደሆነ ከማውጠንጠን መፍትሄ ፈልጎ በእሱ መደገፍ የሚችለውን ድርሻ አውጥቶ መተግበር ጀመረ እንጅ ድህነት ፣ ችግሩ አንገሽግሾት ወደ መጣበት ሽሽትን አልመረጠም ! ከተሜውን ጎብኝቶ ወደ ገጠሮቹ ሊመለከት አዘገመ። የሀኪም እጅ ማየት አይደለም መልኩና ገጹ የናፈቃቸውን ወገኖች አጋጠሙት። በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠው መጥተው ከየሆስፒታሉ ደጃፍ ተኮልኩለው አምላካቸውን እየተማጸኑ፤ ከእለታት አንድ ቀን የሀኪም እጅ እንዲነካቸው ሳምንታትን የሚጠብቁ ምስኪኖች ልቡን አሳዘኑት ፣ መንፈሱን ነኩት …

ጎንደርም በፍቅሯ ነደፈችው ፣ እንግዳዋን በፍቅር ተቀብላ ” የእኔ ሁን ፣ ቅርልኝ! ” አለች ው ። ዶር በርናርድ የእናት ጎንደር ጥሪዋን በጸጋ ተቀበለ ! ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ እድሜን ላስቆጠረው ብቸኛው የጎንደር ሆስፒ ታልን ለማገልገል ለህክምና ኮሌጁ የአሁን ብሩህ ተስፋ እጁን ሰጠ። ከህክምና ድጋፉ ፣ በተጓዳኝ ጥናትና ምርምሩ አንቱ በሚያሰኘ ውን ተመክሮ ራሱን እያጎለበተ ጉዞ የጀመረው ሃኪም ህክምና ድጋፍ ከመስጠት ርቆ ሔዶ በመምህርነት ሙያው ተተኪ ትውልድን የማነጽ ህልሙን ከሞላ ጎደል አሳካ ! በጎ ስራውን የዋሽንግተን ዲሲ በርካታ ኢትዮጵያ ውያንን ጨምሮ የጎንደር ተወላጆች የዶ/ር በርናርድ አንደርሰን ቅን በጎ አድራጎት በመረ ዳት ስህክምናው በሰፊው እጆቻቸው አቀፉት። ዶር በርናርድ ፋታና እረፍት አላስፈለገውም።

ቀድሞውንም እረፍትና ምቾቱ ለህሙማን መድረስ – ለተቸገረ ዋስ መሆን ነበርና ደከመኝ ሰለቸኝ ለዶ/ር በርናርድ ዋጋ አልነበራቸውም። ከአጸደ ስጋ እስከተለየበት ጊዜ ድረስ የስራና ሰውን የማገልገል ቀናት ናቸውና። ከሁሉም የሚያስገርመው ደግሞ “እስመ ትህትና ረከበ ልዕልና” እንዲባል የህክምናው ሊቅ እኔን እዩኝ ሳይል – አለሁ ብሎ ሳይፎክር – እወቁኝ ብሎ ሳያውጅ – ካልተለወደበት ወገን መካከል ከእግር ስር ሆኖ አገለገለ። እንደ ሀገሬው ቋንቋውንና ባህሉን አጥንቶ ፣ እጅ ነስቶ – በባላገሩ ምርቃት ተመርቆ ትሁት እንደሆነ ኖረ። የአሜሪካ ኑሮና ገንዘቡ ሳያሳሳው ይልቁንም ለዘመናት ለፍቶ ያፈራውን – ሰርቶ ያቆመውን ይዞ – ጎንደር ከሆስፒታል ደጃፍ ለሚጠኑት ዋለላቸው ፣ በፍቱን እጁ ዳሰሳቸ ው ፣ ለወሮታው አመሰገኑት !

ከየህክምናው ተቋም ተኮልኩለው የሚያያ ቸው ህሙማን ቢያሳዝኑት – መጠለያ ለማሰራ ት ወጠነ። ሀገር አቆራርጠው ለህክምና የሚ መጡን ለመታደግም ሆስፒታል አስገነባ። በአዘዞ በዶ/ር በርናርድና በባለቤቱ የተገነባው ይህ ሆስፒታልም ለመቶ ህሙማን ማርፊያ መኝታ እንዲኖረው ተደርጎ ተገነባ ፣ ምንም እንኳን ሆስፒታሉን ስራ ጀምሮ ለማየት ዶ/ር በርናርድ በስጋ ቢለይም እንደሙሴ የቃል ኪዳን ሀገር – ስሙን የተከለበትን ራዕይ ለእኛ ትቶልን በክብር ተሸኝቷል !

ዶር በርናርድ አንደርሰን የህክምና ሊቅ ብቻ አልነበረም። ዘርፈ ብዙ ተሰጥኦም ነበረው። በስነ ህክምናው በጣፊያና በጉበት ህመም ለሚሰቃዩ በልዩ ጥበብ ብልቶቹ የሚሰሩበትን ዘዴ በምስል ነድፎ የባለቤትነት (ፓተንት) ያለው ባለሙያ ነበር። ዛሬ መዝገብ የያዛቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ የባለቤትነት ዕውቅና የያዘባቸው ሁለት መሳሪያዎች አሉት። በታሪክ እውቀቱና አስተምህሮ የአፍሪቃን አስተሳሰብ የተከተለ – እውነተኛን ስር ፈልፍሎ በማውጣት በምስል – በጥናታዊ ጽሁፍ ያቀናጀ ፤ በህንጻና በቤት ውስጥ ማስዋብ ጥበብ የተካነ ( ሆስፒ ታሉም – የዶ/ር አንደርሰን ዲዛይን በዶር በርና ርድ የተሰራ ነው) በስነ ግጥም መጽሀፍ የጻፈም ብዕረኛ ነበር። የስነ ግጥሙ ስብስብ መጽሀፍ ርዕስ Limbic glimpses ይሰኛል።
ዶር አንደርሰን ኢትዮጵያን አውቋት ነው የወደዳት። እኛ አልታይ ያለንን ውበቷን አየው ፣ ፣አኛ አልታይ ያለንን ፣ አለያም አይተን መፍትሔ ያጣንለትን የወገን ችግር ተረድቶ በተግባር ችግሩን ለመቅረፍ የተጋ ሰው የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበር ። እኛ ጥለን በምንሸሻትን ሃገር ፣ እኛ የምንለያይበትን ታሪክ አንጠርጥሮ ተረድቶታል ፣ በፍቅሯን እርሱ ሁሉን ተሸከመው። እኛ ጥለናት የሸ ሸናትን እሱ በህይወት በሞትም እንደፈለጋት “ልሁንልሽ፣ በቀሪ ህይዎቴ አገልግልሻለሁ! ” እንዳላት ብቻ አላለፈም ከዚህ ሁሉ ባላይ መንፈሳዊ ህይወቱንም ከጥንታዊው እምነቷ ጋር አዋህዶ – በህልፈተ ህይወቱም አፈሯን ሊለብስ ጸሎተ ፍታት እንዲደረግለት ከእርሷ ማህጸን ሊመለስ ተናዘዘም። እንዳለው ይሆንለት ዘንድ ውድ ባለቤቱ ወዳጆቹና አፍቃሪዎቹ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተጠምቆ – ፍታቱንም በመንፈሳዊ ስርዓት እንዲሆንለት እንተደመኘ ሆነለት !

ከዶ/ር በርናርድ የህክምና ጥበብን ብቻ ሳይሆን ርህራሄን – ሌሎችን የማገልገል መርሀ ጽድቅን – ራስን ከመውደድ የመውጣት ትልቅነትን ተማርን። ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ – ምንምን ሳይንቁ ሰው የመሆንና የመባልንም እውቀት ቀሰምን። ዶ/ር በርናንድ ተናግሮና አውርቶት ሳይሆን ኖሮት አሳየን። በዚህች ቅጽበት መለስ ብለው ሲያስቡት ዶ/ር በርናርድ እኛ ቀረብን – አመለጠን እንጂ እሱማ ክቡር የህይወት ተልዕኮውን አጠናቋል። ሩጫው ለእኛ አጠረብን እንጂ እሱማ ህልሙንና ራዕዩን አከናውኗል። የማገልገልን የቃል ኪዳኑን ምድር አሳይቶናል። ክቡር ሞቱ ለሰማዕቱ ይባልለታል። ዶ/ር በርናርድ ኖሮና ሰርቶ – እኛ ያለወቅናትን ኢትዮጵያ አውቋትና አሳውቆን – የመሆንና የማድረግን ምስጢር አስቃኝቶን ነው ከአጸደ ስጋ የተለየው። ህይወት የእግዚአብሔር ስጦታ ናትና ለአፍታም ቢሆን ዶ/ር በርናርድን ያህል ሰው ሰጥቶና አሳይቶን ወሰደብን።

የህክምና ጠቢቡ ለራሱ አልሆን ብሎ በውስጥ ደዌ ተቀስፏልና በአሜሪካን ዋሽንግተን ለወራት በህክምና ሲረዳ ቢቆይም የተቆረጠችው ቀን ደረሰች ፣ ዶ/ር በርናንድ እድሜውን ድሆችን በመደገፍ ፣ አቅመ ደካሞችን በመንከባከብ ፣ በውስጥ ደዌ የተጎዱትን አክሞ በመፈዎስ የተጋው ዶ/ር በርናንድ አንደርሰን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሸለበ ! ዶ/ር በርናርድ የሁለት ወንድ ልጆች አባት ነበር። ታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓም ወይም እጎአ ጥር 2 ቀን 2015 ዓም በህክምና ለጥቂት ወራት ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት ተለየን … !

ዶር በርናርድ ብራድሊ አንደርሰን “በቀሪ ህይዎቴ ኢትዮጵያን አገለግላለሁ ” ብሎ ቃሉን ፈጽሞ የጉዞው ፍጻሜ ሲቃረብ የሬሳው የመጨረሻ ማረፊያ የተወለደባት ጃማይካ አለያም የተማረ ያደገ ፣ የተሸለመና ዜግነት ሰጥታ ባኖረችው ሀገረ አሜሪካ እንዲያርፍ አላደረገም ። ከጎንደር ታሪካዊ ቦታዎች አንዷ በሆነችው በታሪካዊዋ ቁስቋም ማርያም ደብር እንጅ … ጥር 2 ቀን 2007 ዓም የዶር በርናርድ ብራድሊ አንደርሰን የቀብር ሥነ ሥርዓት ወዳጅ ዘመድ ፣ ተማሪ ዎቹ ፣ የስራ ባልደረቦቹና ሀገሬውና አድናቂዎቹ በነቂስ በመገኘት “ስምህ ህያው! ” ነው ሲሉ በእንባ ተራጭተው በክብር አፈር አልብሰው የመጨ ረሻው ሽኝት በሃዘን በተሰበረ ልብ ተከው ኗል…እነሆ ኑዛዜ ቃሉም ተፈጸመ ! ጠቢቡ ጃማይካዊ ዶር በርናንድ መቀበሪያውን ኢትየጵያ / ጎንደር ውስጥ በአንድ ኮረብታ ማማ ላይ በምትገኘው በታሪካዊዋ የቁስቋም ማርያም ደብር ሆነ !

የዶር በርናርድ ብራድሊ አንደርሰን ! ክብርና ሞገስ ይገባሃል ! እንዎድሃለን እናከብርሃለን !

Dr. Bernard Bradley Anderson we are very proud of you & Thank you !

ነፍስ ይማር !

ነቢዩ ሲራክ
ጥር 3 ቀን 2007 ዓም

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>