Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ይህም አልፎ እናየው ይሆናል

$
0
0

ከደቂቃዎች በፊት ሠንጋተራ አካባቢ ነበርኩ፡፡ አንድ ቦታ ላይ ችምችም ብለው የተሠሩና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ሦስት ትላልቅ ሕንጻዎችን አየሁ፡፡ ለቀድሞው ቁጭራ ሠንጋራ ከፍተኛ ግርማ ሞገስ አላብሰውታል፡፡ ከአንድ ሰው ጋር ስለነበርኩ ወሬ ለማጧጧፍ ፈለግሁና በቀልድ መልክ “እርግጠኛ ነኝ እነዚህ ሕንጻዎች የትግሬ መሆን አለባቸው” አልኩ፡፡ ያ አብሮኝ የነበረ ሰው ለካንስ ዝርሩን ያውቅ ኖሮ ቀጣዩን ታሪክ አጫወተኝ፡፡ እኔም ይህ ዓይነቱ ነገር ቢያስጠላኝም ታሪክን እየመዘገቡ ላሉ ሰዎች አንዳች ግባት ይሆናል በሚል እሳቤ ባጭሩ ልነግራችሁ ወደድኩ፡፡ ለነገሩ ሳይመዘገብ የቀረ ወያኔዊ ቅሌት ሲኖር አይደል! ለማንኛውም ምድረ አበሻ በምቀኝነት ተንጨርጨሪ እንጂ ይህችን የሰማሁዋትን ነገር አሁኑኑ እዘረግፋታለሁ፡፡

የዚህ ሕንጻ ባለቤት ብርሃኔ ግደይ ይባላል፡፡ አበባ ግደይ የምትባል እህቱ መገናኛ ሚ/ር ከፍተኛ ባለሥልጣን ናት አሉ፡፡ ሚስቱም የሥዩም መስፍን እህት ናት፡፡ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ እዚሁ ሠንጋራ ላይ “ዮቤክ ኤሌክትሮኒክስ” የምትል አንዲት ትንሽዬ ሱቅ ነበረችው፡፡ በዚያች እየተዳደረ  እንደማንኛውም የአካባቢው አነስተኛ ነጋዴ ራሱንና ቤተሰቡን በዝቅተኛ ኑሮ ያስተዳድር ነበር፡፡ ነገር ግን ወዳለው ተጠጋ ነውና በዘሩ ከእብቁና ከንፋሹ የመሀል አገር ሣይሆን ከ“ወርቁ” ዘውግ የተገኘ ቀብራራ ወያኔ ከመሆኑም በተጨማሪ ከቱባው ወያኔ ከሥዩም መስፍን ደም ጋር ደሙን በጋብቻ በመቀላቀሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ሀብትና ንብረት  ባለቤት ሊሆን በቅቱዋል፡፡ መታደል ነው፡፡ የምን ኅሊና – የምን ማሰብና አንጎልን መጠቀም ነው፡፡ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ያለችው ፍጡር ዱሮ ለወንድሞቼና እህቶቼ የተሰጠች ልዩ መጠሪያ ነበረች፤ አሁን ደግሞ ዘመን ተገለበጠና እኔ ለወያኔዎች መጠሪያነት አዋልኳት፡፡ ይህም ሲያንሳቸው ነው፡፡ በማሰር፣ በመግደል፣ በሸርና በተንኮል ዜጎችን በማጣላትና በማናጨት፣ በጥቅም በመደለል፤ እስከ‹ጥግ›  በመጨከን … ሥልጣንንና ሀብትን እስከወዲያኛው ማቆየት ቢቻል ኖሮ ከወያኔ በብዙ ነገር ይሻሉ የነበሩት ብልጡ ራስ ተፈሪ እና/ወይም አረመኔው መንግሥቱ ኃ/ማርያም ከሁለት አንድኛቸው እሰካሁን አራት ኪሎን የሙጥኝ ብለው ባልለቀቁ ነበር – እንደዚያ ያለ ቀመር አይሠራም፤ የለምም፡፡ ግን ሰዎች ስንባል በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት የታደሉ በስተቀር ብዙዎቻችን በተፈጥሯችን የለየልን ደናቁርት ስለሆንን ይመስላል አንዳችን ከሌላኛችን አንማርም፡፡ የነዚህ የወያኔዎች ድንቁርናና አህያነት ደግሞ ለከት አጣ – ግን እኮ ልማድ ሆኖብን እንጂ አህያ ለመልካም ተምሣሌትነት ነበር መጠቀስ የነበረባት – በለፋችና በቅንነት ባገለገለች ለምን መሳደቢያ ትሁን፡፡ ይህም አንዱና ሌላው ሞኝነት ነው፡፡

ለነገሩ ወያኔዎች ቢ…ሩ ቢቀ…ብን እውነታቸውን ነው፡፡ ለቅጣት መምጣታቸውን ለሃይማኖታውያኑ የስብከት ፍጆታ እንተወውና – እነሱም እንደሌሎቻችን ሁሉ በሕይወት አሉ ብዬ በበኩሌ ባላምንም  – እኛም ከነሱ ከወያኔዎቹ የባስን አህዮች ነን – ከአራት ሚሊዮን የተውጣጡ የጠራራ ወንበዴዎች ዘጠና ምናምን ሚሊዮን ሕዝብ ካነሆለሉና ከፋፍለው ከገዙ “ይደልዎሙ” (ይገባቸዋል) ከማለት ውጪ ምን ሊባል ይችላል? “ወደሽ ከተደፋሽ …” ነው ነገሩ ወንድሜ፡፡ ቀኒቱ ግን አትቀርም፡፡ ሰማይ ዝቅ፣ ምድር ከፍ ብትል የፈጣሪን ፍርድ ሊያስቀር የሚችል ወያኔዊ “ጥበብ”ና ኃይል የለም፡፡ ሃያ አራት ዓመት ደግሞ በሀገር ደረጃ ሲታይ በጣም ኢምንት ዘመን ነው – ከወያኔዎች የተለዬ ጭራቃዊ አገዛዝ አንጻር እንደ 2400 ዓመታት ቢቆጠርም፡፡ ሦስት ሺህ ዘመንስ በከንቱ ነጉዶ የለም እንዴ፡፡ በነገራችን ላይ ወያኔዎች አይዟችሁ – በያዛችሁት መንገድ እንደልባችሁ ፈንጩ፡፡ ግደሉ፤ እሰሩ፤ ጠጡ ፤ ብሉ፤ ጨፍሩ፤ ተዋሰቡም፡፡ የምትኖሩት ዕድሜም ከሺ በላይ በመሆኑ ስለዕድሜ ዘመናችሁ አትጨነቁ፡፡ ብትሞቱም ትተካካላችሁ – እስከዚያው፡፡ ያቺ ክፉ ሰዓት ስትመጣ ግን …

ብርሃኔ በቀሰቀሰብኝ ቁጭት አዲስ አበባን ለቅጽበት ያህል ቃኘሁዋት፡፡ እናም እላለሁ – በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ አሥር አዳዲስ ዘመናዊ ሕንጻዎችን ካያችሁ ካለማጋነን ዘጠኙ የወያኔ ትግሬ ናቸው፡፡ አሥር ዘመናዊ አውቶሞበሎችን አስፋልት ላይ ሲፈሱ (“ሱ”ን አጥብቁልኝ ‹ፕሊዝ›) ካያችሁ አሁንም ካለማጋነን ስምንት ያህሉ የወያኔ ትግሬዎች ንብረቶች ናቸው፡፡ አሥር ሱቆችን ካያችሁ በጣም ዝቅተኛ በሆነ ግምት ሰባቱ የወያኔ ትግሬዎች ለመሆናቸው አትጠራጠሩ፡፡ አሥር የዩኒቨርስቲ ምሩቃንን ብታዩ እጅግ ሲያንስ ስድስቱ የወያኔ ትግሬዎች ናቸው፡፡ አሥር ለማኞችን ብታዩ ከዘጠኙ ውስጥ ትግሬ ላታገኙ ትችላላችሁ፡፡ በኔ ይሁንባችና “ሠነፍ” ወይም ብልጣብልጥነት የጎደለው ‹እንከፍ› ወይም ነገን ማስተዋል የቻለ አስተዋይ ወይም ህመምተኛ ካልሆነ በስተቀር የትግሬ ለማኝ አሁን የለም ወይም ቢያንስ ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ አሃ! የሁሉ ነገር አዛዥ ናዛዥ ማን ሆነና! ትንግርት ነው ምዕመናን፡፡ በዓለም ታሪክ ቀርቶ በሲዖል እንኳ እንዲህ ያለ መድሎና ጎጠኝነት ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አያውቅም፡፡ ያዝልቅላቸው፡፡ ግን ወዮ ለቀኑ፤ ወዮ የፈጣሪ ፍርድ ወደ ምድር በወረደ ጊዜ! ወዮ ለኢትዮጵያዊው የምፅዓት ቀን! እንዲህ ያለው ጭፍን ጉዞ ምን ሊያስትከል እንደሚችል የማያውቅ እንደብርሃኔ ግደይና እንደ‹ሐጎስ ጎይቶም› ያለ ድፍን ቅል ዜጋ ጭንቅላቱ ውስጥ ጭቃ እንጂ አንጎል የሚባል ነገር የለውም፡፡ ትንሽነት ለካንስ መድሓኒት የሌለው ክፉ ደዌ ነው፡፡ ትንሽነት ለካንስ በሰው አምሳል እንደሚንቀሳቀስ አውሬና ጭራቅ ማለት ነው፡፡ ከትንሽ አስተሳሰብ ይሰውራችሁ፡፡ በቃኝ፡፡

ግን ግን ቢበቃም ቅሉ ለነአብርሃ ደስታ፣ ለነፀጋዬ ገ/መድኅን፣ ለነጌታቸው ረዳ (የኢትዮሰማይ ድረገፅ አዘጋጅና ባለቤት)… ስንት ቆጠርኩ ይሆን? አይ፣ ደከመኝ ይቅርብኝ፤ እናም ከምር በቃኝ፡፡

አንዱ ነኝ ከአዲስ አበባ – ስም ዱሮ ቀረ!

Comment


ድንቄም ጠቅላይ ሚኒሴቴር!

$
0
0

ወንድሙ መኰንን፣ ከብሪታኒያ 19 December 2014

ብዙ ተብሏል። እኔም አንድ ነገር ልጨምርና ልገላገለው። “የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይኖራል” ነው የሚባለው? ተናግሮ ከሚያናግር ይሰውራችሁ! ውሀን ምን ነበር የሚያናግረው? ድንጋይ! የሰውም ድንጋይ እራስ አለ! ይቅርታ አንጀቴ አርሮ ነው!
prime minister
ሦስት መንግስታትን የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ተወልጄ፣ አድጌ፣ ተምሬ ለዩኒበርሲቲ የበቃኹት በንጉሠ ነገሥቱ ዘመነ መንግሥት ነበር። ዕውነቱን እንናገር ከተባለ፣ ንጉሡ ሲናገሩም ሆነ ሲራመዱ፣ የርዕሰ ብሔርነት ግርማ ሞገስ ነበራቸው። “በንጉሥ መገዛቱ ጊዜ ያለፈበት፣ ያረጀ ያፈጀ፣ ገበሬውን በገባርነት ጠፍንጎ የያዘ፣ አገሪቱ በዕድገት ወደፊት እንዳትራመድ ያገዳት፣ ኋላ ቀር የፊውዳል ሥርዓት ነውና ወደሶሻሊዝም እንለውጣት” የሚሉ ድምጾች ከተማረው ክፍል አካባቢ እያየሉ መጡና እኛንም እንደጎርፍ ይዘውን ነጎዱ። ተከተልናቸው። “መሬት ለአራሹ እያልን” ተማሪዎች በጠበጥን። እንዳጋጣሚ ሆኖ በ፲’፱፷፮ ዓ/ም የጠና ረሀብ በወሎ በመከሰቱ ሕዝብ በረሀብ እየረገፈ ፹ ዓመታቸውን “ድል” ባለ ድግስ አከበሩ የሚል በተማሪዎች የተጀመረው ርብሻ በመምሕራን (ሴክተር ርቬው)፣ በታክሲዎች እና በሠራተኞች ሥራ ማቆም አድማ ተቀጣጥሎ ለወታደሩ “መንግሥት የመገልበጥ” እድል ተፈተለት። የሥርዓቱ ጠባቂ የነበረው የወታደሩ ክፍል አመጸና የንጉሡን መንግሥት አፈረሰው። አዝጋሚ ዕድገት ላይ የነበረች ኢትዮጵያ የባሰውኑ በወታደራዊ ደርግ ተጠፈነገችና ወደ ኋል ተወረወረች። የንጉሡ ሥርዓት በአምባገነን ወታደሮች ሲተካ፣ ሶስት መኰንኖች ተፈራረቁባት። ርዕሰ ብሔርነቱም መጀመሪያ ለጥቂት ወራትም ቢሆን (ከመስከረም እስከ ኅዳር ፲፱፻፷፯) ሌፍትናንት ጀኔራል አማን አንዶም፣ ቀጥሎም ትንሽ ውረድ ብሎ ለጥቂት ዓመታት (ከኅዳር ፲፱፻፮፯ – ጥር ፲፱፷፱) ብርጋዴር ጄኔራል ተፈሪ በንቲ፣ ቀጥሎ በጣም ወርዶ-ወርዶ፣ ለብዙ ዓመታት (ጥር ፲፱፻፷፱ – ግንቦት ፲፱፻፹፫) ሻለቃ መንግሥቱ ኃይለማርያም (በኋላ ኮሎኔል) በመጨራረስ ተተካኩ። ሲምሩ በሰደፍ፣ ከፈለጉም በእሥራት፣ ከጨከኑም በጥይት ሕዝቡን በጅምላ እየረሸኑ፣ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በወታደር ፌሮ ጭንቅላታችን ላይ ቁመው ወታደሮቹና ጀሌዎቻቸው ቀጠቀጡን።  ግድያው እሥራቱ ያደነዘዘው ሕዝብ፣ “የባሰ አይመጣም” በማለት፣ ገንጣይ አስገንጣይ ዘረኞች ወደ አዲስ አበባ ሲገሰግሱ፣ ዝም ብሎ አያችው። እንዲያውም አንዳንዱ መንገድ እየመራ ወደ አዲስ አበባ አደረሳቸው። ይኸውና በወያኔ የሚመራው የዘረኞች ቡድን ከዚያች ከተረገመች ከግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓ/ም ጀምሮ፣ ያላንዳች ርኅራሔ፣ ቀጥቅጦ እየገዛን ነው። ያም ብቻ አይደለም። መሬታችንን እየሸነሸነ፣ ነዋሪውን እየፈነቀለ በርካሽ እየቸበቸበው ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ንጉሡ ለደርግ ከአስረከቧት እጅግ አንሳ ትገኛለች። መሪዎቹም፣ ከበፊተኞችም እጅግ ወርደው የወረዱ ቀትረ ቀላሎች ሆኖብን። መጀመሪያ መለስ ዜናዊ ለሀያ አንድ ዓመታት (ከግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፹፫ – ከግንቦት ፳ ቀን ፳፻፬)፣ ፏልለውብን ሞት ገላገለን። መለስ ዜናዊን የተኩት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ድቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር ናቸው።

 

እንግዲህ እኔ እስካሁን የኖርኩት ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እስከ ኃይለማርያም ደሳለኝ መሆኑን ተገንዘቡልኝ። ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በሊግ ኦፍ ኔሺን ላይ ያደረጉትን ንግግር፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ፣ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ/ም ካደረጉት አሳፋሪ ንግግር እና የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ሰሞኑን የስልጤ ዞን ዋና ከተማ፣ ወራቤ የተመሠረተችበትን አሥረኛ ዓመት ለማክበር ተግኝተው ከተናገሩት አሳፋሪ ንግግር ብናወዳድር፣ “እንዴት ወርደን እዚህ ደረሰን” ያስብላል።

መለስ ዜናዊ ለሰው ስሜት የማይጨነቁ፣ በአራዳ አነጋገር ሁሉንም የሚዘረጥጡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ስቃይ ነበሩ። ሙት ወቃሽ ላለመባል፣ ያሉትን አስነዋሪ አባባሎች “ሾላ ብድፍን” ብለን እናልፈዋለን። አሽቃባጮችም ነበሯቸው። ብልግና በተናገሩ ቁጥር፣ መላው የፓርላማ አባላቸው፣ የሚያቅለሸልሽ ታሪክ እንኳን ቢሆን፣ ከት ብሎ የሚስቅላቸው ሞልቷቸው ነበር። እሳቸውን የተኩት ጉድ እንደሳቸው መሆን ቢያምራቸውም፣ የተለዩ ፍጡር ናቸው። ወላጆቻቸው፣ “ኃይለ ማርያም”ብለው ስም ሲያወጡላቸው፣ ለመሆኑ ምን ታይቶአቸው ነው? በዚህ ስማቸው መጨረሻ ላይ እደምደማለሁ መልካም ንባብ።

ኃይለማርያም፣ ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሳይሆኑ፣ የወያኔ ባለአደራ ሁነው የጠቅላይ ሚኒስቴርነቱ ቦታ ጠባቂ ናቸው። አልጋ ጠባቂ እንበል?! አልመሆናቸውን ገና በጠዋቱ፣ የሟቹ የመለስ ሚስት፣ ደፋሯ አዜብ ጎላ (መስፍን) አስመስክራለች። “የምኒልክን ቤተ መንግሥት አልለቅለትም” ብላ ጎዳና ተዳዳሪ ልታደርጋቸው ምንም አልቀራትም ነበር። ደንቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር!

ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የራሳቸው ሰው ባለመሆናቸው፣ የወያኔ መሣሪያ መሆናቸውን ለማስመስከር፣ አራዳው መለስ የተናገሩትን አነጋገር ቃል በቃል፣ አንዲት ቃል ሳይጨምሩ – ሳይቀንሱ፣ እንደበቀቀን ሲደግሙት ተሰምተዋል። የእነ አቤ ቶኪቻው መሳቂያ መሳለቂያም ሁነዋል። ከኦሪጂናሌው መለስ ላለማነስ፣ ብዙ ነውሮችን ካፋቸው ዘርግፈዋል። አዪዪ! ምናለ በተማሩት የውሀ ማጣራት ሙያ ቢሰማሩ ኑሮ! ከሰውም ሞገስን፣ ከእግዚአብሔርም በረከቱን ባገኙ ነበር። ለጠማው ንጹሕ ውሀ ማቅረብ በሰማይም ባጸደቃቸው በምድርም ባስከበራቸው!

“ያለቦታው ገብቶ፣ ያለ ሰገባው

አሳዛኙ ልቤ፣ የተንገላታው”

ነበር ያለው ያ አፍቃሪ! ያለቦታቸው ገብተው፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አገር የመምራቱን ኃላፊነት አምቦጫረቁት። የቢቢስን እና የሲኤንኤንን ገዜጠኞች በሽብርተኝነት ሊያስሯቸው እንደሚችሉ አስፈራርተዋል። አራዳ ሳይሆኑ፣ እንደመለስ ጮጋ ለመሆን የሚያደርጉት መፍጨርጨር የመጨረሻው ፋራ መሆናቸውን፣ አጋልጦባቸዋል። አይ የኛ ነገር። ወርደን ወርደን እዚህ ደረስን? እንዲያው ኢትዮጵያውያን ፈጣሪን ምን ያኽል ብንበድለው ነው፣ ለእንደነዚህ ዓይነቶቹ ጉዶች አሳልፎ የሰጠን? ነገራችን ሁሉ፣ “ከድጡ ወደ ማጡ” ሆኖብናል። ሕዝባችን መገድሉ፣ መታሰሩ፣ መሰደዱ፣ መራቡ፣ መጠማቱ፣ መታረዙ ሳያንስ፣ እነዚህ መዥገሮች በየቀኑ እየተነሱ የሚመርጉበት ስድብ፣ የባሰ የሚያስመርር ደረጃ ላይ አድርሶታል። “ጠቅላይ ሚኒስቴር” ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር!

የታኅሣሥ ፪ቱን (11 December 2014) የኢሳት ሬዲዮ ፕሮግራም እንደኔ ያደመጠ ሁሉ መቼም ሆዱ በንዴት ድብን እንደሚልበት አልጠራጠርም። ጨጓራ የሚልጥ የአልሰርን በሽታ ያስንቃል። ከአንደ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቀርቶ፣ አንድ እራሱን ከሚያከብር፣ አባትና የቤተሰብ ኃላፊ ነኝ የሚል ሰው፣ እንዲህ የወረደ ንግግር አያደርግም። ምን አለ አሁን እንዲህ ዓይነት ቅሌት ቢቀርባቸው? እዲያ! እዲያልን ወዲያ! ምን ዓይነቱ ለዛው ሙጥጥ ናቸው? እኔ ስለሳቸው አፈርኩ። ሰውዬው ያልበላቸውን ነበር የሚያኩት። ወራቤ፣ የስልጤዋ ዋና ከተማ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር መስለዋት አሥረኛ ዓመቷን ልታከበር፣ የወያኔ ባላደራውን ጠርታ፣ መከበሯ ቀርቶ ተዋረደች። ጠቅላይ ሚኒስቴር ተብዬው፣ እንዲህ ነበር ያሉት፣ ዲንቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር!

፩ኛ፡ አሜሪካ ተሰደው ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

“አንዳንድ ጌዜ አሜሪካን አገር ውስጥ የሆነ መርቸዲስ፣ ማለት፣ መኪና ተደርድሮ ባለበት ፎቶግራፍ ይነሱና ከዚያ በኋላ ወደቤተሰብ ይልኩና፣ ይኼ የኔ መኪና ነው ይላሉ። ማንን እንድሚያታልሉ ግን አይገባም።”

ያጣ ወሬ! እንዴ! ጠቅላይ ሚኒስቴር ተበዬው እኮ በሥፍራው የተገኙት የወራቤን ከተማን አሥረኛ ዓመት ምስረታ ለማክበር ነበር። አሜሪካ የሚኖሩት ስደተኞችናና የወራቤ ከተማ ምን አገናኛቸው? ከተደረደሩት መኪናዎች ጋር ተደግፈው የተነሱትን ፎቶ የት ቁመው ያዩት? ሰውዬ ለምን ያልበላቸው ቦታ ያካሉ? ለመሆኑ፣ አሜርካን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንቱ የተባሉ ስንት ኢትዮጵያውያን ምሑራን እንዳሉ ያውቁ ይሆን? አሜሪካን ሆስፒታሎች ውስጥ ስንት እውቅ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች እንዳሉ ማን በነገራቸው። አሜሪካ የምርምር ማዕከላት ውስጥ፣ ናሳ ሳይቀር፣ ስንት ኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶች እንዳሉ የሚያስብ ጭንቅላት አላቸው ልበል? ኢትዮጵያን ለማንቋሸሽ እራሳቸው ቆሽሸው አረፉት! ይሁን! ይህቺ ቀን እኮ ታልፋለች። ማርቸዲስ ለኃይለማርያም ብርቅ ይሆን ይሆናል እንጂ፣ ወጪ አገር ማርቸዲስ ታክሲ ነው። ፈራሪም፣ ሎተስም፣ ቤንትሌይም፣ ሮልስ ሮይም ማለት እኮ አንድ ነገር ነበር። ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር!

፪ኛ፤ በጀርመን ተሰደው ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ

“… ለልጆቼ ዶሮ ይዘህ ሂድ አሉኝ። እሺ ብዬ ጀርመን አገር ዶሮ ወጥ ተሸክሜ ሄድኩኝ። ከሄድኩ በኋላ፣ በተሰጠኝ ስልክ ብደውል፣ ብደውል፣ ልጆቹን ማግኘት አቃተኝ። ምንድነው ሲባል፣ ስልኩን ለጓደኞቼ፣ ለጀርመናዊ ለጓደኞቼ አሳየኹዋችወ፣ ኧረ! ይኸማ ሀይም(?) ውስጥ እኮ ነው አሉኝ። ምንድነው ሀይም አልኳቸው። ሰው የሚሰቃይበት እስር ቤት ዓይነት ነገር ነው አሉኝ። ዶሮ ወጡን ይዤ እዚያ ሀይም ሄድኩ። ስደርስ ኮንቴነር ውስጥ ነው ያሉት። እዚያ ዱቄት ይሰጣሉ፣ ዱቄቱን እያቦኩ፣ ዱቄት ብቻ ነው የሚበሉት። እቃውን አስረከብኩላቸውና፥ “ታዲያ ያ ሁሉ ፎቶግራፍ የላካችሁት፣ ከየት የመጣ ነው?” አልኳቸው። ብዙዎቻችን እናውቃለን፣ ውጭ አገር ሰው እንዴት እንደሚኖር።“

ደግሞ “ጀርምናዊ ጉደኞቼ ይላሉ! አያፍሩም? ለመሆኑ፣ የማን ደፋር እናት ናት፣ እንደተራ ሰው፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒቴራችንን ዶሮ አሸከማ ጀርመን አገር ድረስ የምትልክ? “የማይመስል ወሬ፣ ለሚስትህ አትንገር” ነው የሚባለው? እንዴ! የወራቤ ነዋሪ ላለፉት አሥር ዓመታት ያደረገውን ጉዞ እንዲገመግሙለት እንጂ፣ ጀርመን ውስጥ ስለሚኖር ስደተኛ ወሬ ጠምቶአቸው ነው እንዴ የጋበዟቸው? በነገራችን ላይ፣ ጀርመን አገር አዲስ የመጡት ስደተኞቹ፣ ምናልባት ጉዳያቸው እስከሚጠናቀቅ በዚያ ዓይነት አኗኗር ለጊዜው ይኖሩ ይሆናል፣ ለመሆኑ፣ አዲስ አባባ ስንት የጎዳና ተዳዳሪዎች እንዳሉ የሚያይ አይን ተተክሎላቸው ይሆን?

፫ኛ፣ በአረብ አገር ተሰደው ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ

“እኛ እህቶቻችንን ለማየት አልቻልንም። ሳውዲ ሂደን፣ ማየት አልቻልንም።… ይኸ የዚያ አካባቢ የሀይማኖትዊ ሥነ ሥርአት ሊኖር ይችላል። ነገር ግን ሂጄ ማየት ስላልተቻለኝ፣ የፈቀዱልኝስ እንድሄድ ነበር። ለምንድነው፣ ማየት የማይፈቀድልኝ፣ የሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ሊሆን ይችል ይሆናል ግን፣ በእዚያ ደግሞ ቦታ ስንሄድ፣ መንገድ ላይ እንደአበደ ውሻ የሚኖሩ እህቶቻችን አየን። ከዚያ ቦታ ስንሄድ፤ በኤምባሲ በራፍ፣ ወደ ሺ የሚጥጉ፣ አንድ ላይ ተኰልኵለው  በዚያ ሙቀት ውስጥ ኤር ኮንዲሺነር በሌለበት ታጭቀው ሲሰቃዩ አየሁ። ከዚያ በኋል ግን፣ ምን ትዝ ይለኛል፣ ቢያንስ እዚህ ገጠር ውስጥ በእግራቸው ተጉዘው በልተው ጠግበው እኮ ይኖራሉ።

ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር! ወያኔ አገሪቱን መቀመቅ ውስጥ በመጨመሩ፣ ኢኮኖሚዋን ማድቀቁ፣ እና እንደ ኃይለማርያም ደሳለኝ ያሉ አሽከሮቻቸው በልተው በልተው ሆዳቸው ተወጥሮ ሲነፋፋ፣ ቤተሰቦች የሚበላ የሚቀመስ ሲያጡ፣ ወጣት ሴቶቻችን ገና በሎጋ ዕድሜአቸው፣ትምሕርታቸውን አቋርጠው፣ ሴተኛ አዳሪ ከመሆን፣ በጉልበታቸው ሠርተው ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት የሚያደርጉትን መፍጨርጨር፣ ከእብድ ውሾች ቆጥረዋቸው አረፉ? ደግሞ ሰለ አረቦች ግርድና አፋቸውን ሞልተው ተናግረዋል። ለመሆኑ የግርድና ንግዱን የሚያካሄዱት የሕወሀት አባላት መሆናቸውን የሚረዳ ጭንቅልታ ማን ባዋሳቸው! አፋቸው ተበላሽቷል። ታዲያ ምን ያደርጋል! በቅቤ አሽተው አይመልሱት ነገር። ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር!

ድንጋይ ይወረውራሉ ስለሚሏቸው የስልጤ ወጣቶች

“አንድ እኛ እዚህ ግድም የሚያሳዝነን፣ አብዛኛው እዚያ መርካቶ አካባቢ ደንጋይ የሚወረውረው ወጣት የዚህ ዞን ወጣት መሆኑ ነው። በሙስሊምነት ከሆነ፣ ትልቁ ሙስሊም፣ ኦሮሞ ነው፣ ኦሮሚያ ነው። ነገር ግን ድንጋይ የሚወረውረው ግን የሥልጤ ወጣት ነው። ምን ማለት ነው ይኼ? ምን ማለት ነው? አባቶች በተለይ እስቲ ይታያችሁ የናንተ ልጆች ድንጋይ ሲወረውሩ፣ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መስኮት ሲሰብሩ፣ መኪና ሲሰብሩ፣ እናንተ እዚህ ሁናችሁ ሲታዩ እንዲያው በአጠቃላይ፣ ይኸ ምን ማለት ነው? ይኸ አደብ መግዛት አለበት። ትላንት ከዚህ ሞባይል ገዝቶ፣ መርካቶ የገባ ሰው ድንጋይ እያነሳ ንብረትና ኃብት ማውደም ማለት፣ ይኽ ንቀት ነው። በምንም ምልኩ! ድንጋይ ወርውሮ መስኮት ሰበረና መኪና ከሰበረ በኋላ ሲታሰር ደግሞ በኃይማኖት ምክንያት ታሰርኩ ካለ፣ ድንጋይ የሚያስወረውር ሀይማኖት የለም። እንደዚያ ነገር ድንጋይ የሚያስወረውር ሀይማኖት የለም …።”

ለዛው ሙጥጥ! ወይ ጉድ! ከክብር እንግዳ ተሳዳቢ እግዚአብሔር ይሰውራችሁ። የሥልጤ ሕዝብ የጋበዛቸው፣ የወራቤን ከተማ መቆርቆር አሥራኛ ዓመት ሲያከብሩ፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴራቸው ጋር አብረው በክብር ተደስተው ቀኑን ለማሳለፍ ነበር እንጂ፣ ሊሰደቡ፣ ሊዋረዱ፣ ልጆቻቸው ላይ የሚቃጣውን ማስፈራሪያ ሊያዳምጡ ነበር እንዴ! የስልጤን ሕዝብ አዋረዱት! ምንኛ ሕዝቡ ልቡ ይቁሰል! ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር!

ስለሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሞቴ

አፋጣኝ የፍርድ ውሳኔ ለምን አይሰጥም ተብሎ የተጥየቁ ግለሰቦችን በተመለከተ በመጀመሪያ ደረጃ እኛ ሰዎቹ የሙስሊሙ ኮሚቴ ተወካዮች ነን ሊሉ ይችላሉ። ይኸ መብታቸው ነው። ማንም አይከለክላቸውም።  ግን መንግሥት ተወካይ ለመሆናቸው ምንም ማስረጃ የለውም። ሙስሊሙን እነሱን እንዴት እንደወከለ አናውቅም። ስለዚህ ስለማናውቅ ጉሕጋዊ ወኪሎች ስለመሆናቸው ማስረጃ የለንም ነው የምንለው። ሕጋዊ ወኪሎች አይደሉም። እነዚህ ግለሰቦች ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው በሀማኖታቸው ምክንያት ወይም ዕምነታቸው ምክንያት ወይም በሚያራምዱበት ዕምነት ምክንያት አይደለም የታሰሩት። የታሠሩት ሀይማኖታቸውን እና እምነታቸውን ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት ከማካሄድ አልፈው ሂደው ከምንግሥትና ከሕዝብ ጉዳዮች ላይ ወንጀል በመፈጸማቸው ነው የታሰሩት።

ምን ወንጀል? ሰው ገደሉ? ዕቃ ሰበሩ? በቃ ወያኔ አስተዳዳሪአቸው “ወንጀለኞች” ናቸው ካለ እንደበቀቀን ተከትለው፣ የኛ “ጠቅላይ ሚኒስቴር” ፍረዱባቸው ማለት ነው። ወያኔ ከሳሽም፣ ምስክርም፣ ዳኛም ነው። አገሪቱን ጠፍንጎ ይዞአል። ምን ዓይነት ጭንቅላት ቢኖራቸው ነው፣ ወያኔ እንዲህ የሚጫወትባቸው። አይ ሆድ! ለሆዱ ያደረ አንጎሉ አይሠራም። ይህቺን አጥብቃችሁ ያዙልኝ! ሕግ የሚሠራው ሁሉም ሲገዛለት ነው። ወያኔ ሕግን የሚጠቀመው ሌላውን ጠፍንጎ ለመያዝ ነው። ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዕውቀታቸው ወሀ ማጣራት ነው አንጂ ሕግ አይደልምና የተማሩት፣ የሕጉን ነገር ባያጨማልቁት ጥሩ ነበር።  ከዚያ አልፈው ተርፈው፣ እስካሁ ፍርድ ያልተሰጠበትንም ምክኒያት ሲደረድሩ፣ የተከሳሾቹ ጥፋት እንደሆነ ሊነግሩን ከጅሎአቸዋል። ኧረ ምን ከጀላቸው፣ ወነጀሏቸው እንጂ! ጥፋተኛ ላለመሆናቸው፣ አራት መቶ ገደማ ምስክሮች በማቅረባቸው፣ ያንን ለማዳመጥ የዘገየ ፍርድ ነው ብለውን አርፍዋል። ድንቁርና አንዳንዴ ጡሩ ነው። ከሒሊና ቀሳ ያድናል።በድፍኑ፣ ወያኔ ወንጀለኛ ነው ብሎየፈረጀው ሁሉ ወንጀለኛመሆን ስላለበት፣ እራሱን መከላከል የለበትም ሊሉን ምንም አልቀራቸውም! በቃ! ወያኔ ከእግዚአብሔር በታች ትልቁ አማላካቸው ነው። ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር።

የወላይታን ሕዝብ በጅምላ ሰድቡ

“እኔ የተወለድኩበት ብሔር፣ ብዙ ሰው ነው እዚህ ጋ የሚያሰፋው። ያኛውን ለመምሰል ሲል ነ። ትንሽ ቀላ ካለ፣ ያኛውን እመስላለሁ ለማለት ይኸንን አሰፍቶ፣ እራሱን ለውጦ፣ እራሱን ለመሸት የምንሸቃቀጥበት ነው የኛ ትውልድ።

ኧረ በሕግ አምላክ! እኚህን ሰው አንድ በሉልን! የወላይታ ሕዝብስ እራሱን እንደሸቀጥ አልሸጠም። ይልቁንስ ከኩሩውና ከርህሩሁ የወለይታ ሕብረተሰብ ተፈጥሮ ሒሊናውን ለቁራሽ እንጀራ የሸጠ ማን እንደሆነ እናውቃለን። የሥነ አዕምሮ ሐኪም ጋ የሚወስዳቸው ዘምድ የላቸውም? ወያኔ ምንኛ ጭንቅላታቸውን ብታዞራቸው ነው ጃል፣ እራሳቸውን እንዲሰድቡ የለወጠቻቸው? ደግሞ የወላይታን ባሕላዊ ጠባሳ ለመሸፈን መሰፋትን፣ ከወራቤ አሥረኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ጋር ምን አገናኛቸው? ስድብ ርቦአቸዋል? ስድብ ጠምቶአቸዋል? የእሳቸውን አዕምሮ ነው ወያኔ ግጥም አድርጋ የሰፋችባቸው እንጂ፣ እኔ የማውቀው የወላይታስ ሕዝብ ባሕሉን አክባሪ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነው። ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር!

በመጨረሻ፣ ጠቃላይ ሚኒስትሩ፣ ለምንድነው ዲያስፖራውን የሚጠሉት? ምክንያት አላቸው! በፈረጆቹ አቆጣጠር፣ 2011 ላይ ወያኔ ገንዘብ ከዲያስፖራው ለመለምን ወሰነች። እሳቸው የአሜርካውን ልዑክ እንዲመሩ ተላኩ። ሁሉም በሄዱበት ተመሳሳይ ዕድል ገጠማቸው። ከሄዱበት ሁሉ ዲያስፖራው ምድረ ወያኔን ባዶ እጃቸውን ስደዳቸው። ለንደን ላይ ለምሳሌ፣ ከኢምፔሪያል ኮሎጅ አሳደናቸው አባረን፣ እምባሲ ከተናቸው፣ አንዲት ሳንቲም ሳይሰበስቡ ተመለሱ። አሜርካ ላይ እንዲሁ አዳራሻቸው ተረብሾባቸው፣ ኪሳራ በኪሳራ ሆነው፣ ቤሳ ቤሲትን ሳይሰብበሰቡ የተመለሱ። ታዲያ በዚህ የበሸቁት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፳፻፫ (23 April 2011) በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ፣ እንዲህ እያሉ ነበር የተሳደቡት!

“ከሁለት ሺ በላይ ሕዝብ በሚሰበሰብበት አካባቢ፣ ከ20 እስከ 150 ሰዎች፣ የተቃውሞ ሰልፍ ቢወጡ፣ ምንም የሚገርም አይደለም። እነሱም፣ የቀደሞ የደርግ ሥርዓት ርዝርዦችና፣ በሽብር ተግባር ላይ የተሰማሩ የአማጺ ቡድኖች አባላት ናቸው። እነዚህ ሰዎች፣ በበርካታ ዓመታት ሲጮሁ ኑረዋል። ኢትዮጵያ ግን ወደፊት እየገሰገሰች ትገኛለች። እንሱ እየጮሁ ይኖራሉ፣ ምናልባትም፣ አርጅተው እስኪሞቱ ድረስ የሚጮሁ ይኖራሉ። ሬሳቸው አገር ቤት ሊቀበር ይመጣል… እኛም እንቀጥላለን። ይልቁንስ፣ በዚህ ታሪካዊ ወቅት እራሳቸውን በእሳት ባያስለበልቡ የሚሻል ይሆናል”።

“አርጅተው እስኪሞቱ ድረስ የሚጮሁ ይኖራሉ። ሬሳቸው አገር ቤት ሊቀበር ይመጣል” ነበር ያሉት? ይኸንን የተናገሩት ሚያዚያ ፲፭ ነበር ያሉት። ከነዚያ ሰላማዊ ሰልፈኞች እስከአሁን ሙቶ ወደ አገር ቤት የተመለሰ ሬሳ የለም። እግዚአብሔር ይመስገን። ዳሩ ግን እንደ ጣዖት የሚያመልኳቸው አሳዳሪ ጌታቸው፣ መለስ ዜናዊ፣ ነሐሴ ፲፭ ቀን 2004 ዓ/ም ብራሴልስ ሆስፒታል ሙተው ወራት ከከረሙ በኋላ ለቀበር፣ አዲስ አበባ ሬሳቸው ገብተውላቸዋል። በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው ግፍ አይናገርም። አንዳንዴ እግዚአብሔር ቅርብ ነው። ስሙ የተመሰገነ ይሁን!

ሰውዬው የዞረባቸው ናቸው። ጠቅላላ ሰብዕናቸው፣ ውጥንቅጡ የወጣባቸው የሚናገሩትንም ሆነ የሚያደርጉትን የማያውቁ ጉድ ናቸው። ወይ አያምሩ ወይ አያፍሩ! እንኳን ለጠቅላይ ሚኒስቴርነት፣ የአንድ መስሪያ ቤት ዴፓርትመንት እንኳን ለመምራት ብቃት ያንሳቸዋል። እንኳን ሠርተው፣ ተናግረው ስሜት የማይሰጡ አሳፋሪ ሰው ናቸው። ለወያኔ መሣሪያነት ያበቃቸው ይኸው ቅደመ ሁኔታ ነው።

አንድ ለብዙ ጊዜ አምቄው እስከዛሬ ያቆየሁትን ልበልና ልሰናበታችሁ።

ደንታ-ቢስ ከሀዲ፣ አድር-ባይ ሆድ-አደር

ወገኑን የሸጠ፣ የወያኔ አሽከር፣

ስብዕናውን ገድሎ፣ ከሒሊናው የራቀ

ስሙ ኃይለ-ማርያም፣ እሱ ጸረ-ማርያም፣ የተዘባርቀ

ግርማ ሠይፉ፣ ሠራዊት ፍቅሬና ቴዎድሮስ አድሐኖም ያልመረጥናቸው የህዝብ ልዑካን (ሁኔ አበሲኒያ)

$
0
0

ከሠሞኑ ወደግብፅ የሚያቀና ህወሀታዊ የልዑካን ቡድን ሲቋቋም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊጠብቀው በማይችለው መልኩ የልኡካን ቡድኑ ውስጥ የአንድ ሠው ስም ተሠማ “ግርማ ሠይፉ” የሚል በርካቶች ተገረሙ ወይ አንቺ ሐገር ሲሉም አዘኑ፡፡ ከዚህ ቀደም ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በፓርላማ ተብለው በተቀመጡባቸው ያለፉት 4 ዓመታት ለሐገራችን ፖለቲካ ያንን ያህል ለውጥ ባያመጡም፤ የህሊና እስረኞቹ ይፈቱ ዘንድ አሁንም ያንን ያህል ጠንከር ያለ ስረ ባይሠሩም አቶ ግርማ ሠይፉን ሌሎች አካላት ሲተቿቸው ግርማ ሠይፉን ደግፈው ከሚቆሙ አካላት መካከል አንዱ እኔ ነበርኩኝ ብዬ አስባለው፤ አስባለው ያልኩት ስለግርማ ሠይፉ ከኔ በላይም የሚያስብ ሌላ ህወሀት የተሠኘ የሠዎች ስብስብ መኖሩን ስላልተረዳሁና በቅርቡ እየታዩ ያሉትን የግርማን መንሸራተቶች ባለመመልከቴ ነበር፡፡

Renaissance-Dam-Contentበሐገራችን ፖለቲካ ማየት ከማንፈልጋቸው ነገሮች የከዳተኝነት ፖለቲካ አንዱ እና ዋነኛው ነው፤ ይህ ህዝብ ለፍቶ ከሚያገኘው የወር ገቢው ላይ ግብር ተወስዶበት ፓርላማ ለሚገኙ የህዝብ ተወካዮች በአበል እና በደመወዝ መልክ ይሠጣል ህዝቡ ይህንን የሚያደርገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተሠኘው የሚገኙ አባላት መብቴን የሚያስከብር ህግ ያወጡልኛል፤ ስለእኔ መብት ስለቆሙ የታሠሩ የህሊና እስረኞችን የበላይ አካል እንደመሆኑ ያስፈታልኛል ብሎ አለመሆኑ እሙን ነው ምክንያቱም በህወሀት ፓርላማ ውሳኔ ችግሬ ይፈታልኛል ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ እርሱ የህወሀት አባል መሆን አለበት ሆኖም ተባራሪ ሆነው ፓርላማ ውስጥ የሚታዩ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የህዝብ ችግር ያሏቸውን ጉዳዮች ነቅሰው አውጥተው ለፓርላማው ሲያቀርቡ እንመለከት ነበር እነዚህ ሠዎችም ሲከዱ ተመልክተናል እውን ግርማ ሠይፉ ካዳ? ግርማ ሠይፉ ካዳ ወይስ አሁንም ለህዝቡ እንደቆመ ነው የሚሉትን ጉዳዮች ከማንሳታችን በፊት ከግርማ ሠይፉ ጋር የልዑካን ቡድኑ አባላት ውስጥ የሚገኙ አባላት እነማን ናቸው የሚሉትን መመልከት ተገቢ ይመስለኛል፡፡

የህዝብ ልዑካን ቡድን ሲቋቋም መታሠብ ካለበት መካከል አንደኛው እና ዋናው ነገር የልዑካን ቡድኑ አባላት በህዝብ የታመኑ፣ በመልካም ስነምግባራቸው አርዓያ የሆኑ እና ለሌሎች ምሳሌ የሚሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል ወደግብፅ ባቀናው የልዑካን ቡድን ውስጥ የተካተቱት ግን በየትኛውም መለኪያ የህወሀት ጉዳይ አስፈፃሚ ከመሆን ውጪ የህዝብ አመኔታ ያላቸው ግለሠቦች አይደሉም፡፡ ከልዑካን ቡድኑ ውስጥ መካከል አንዱ ሠራዊት ፍቅሬ የተሠኘው ግለሠብ ነው፡፡ ይህ ግለሠብ ልክ እንደሌሎቹ የህወሀት አባላት እና አመራሮች ከወታደር ቤት ወጥቶ ሚሊየነር የሆነ ግለሠብ ነው፡፡ ሠራዊት ፍቅሬ የህዝብ ተወካይ መሆን የማይችልባቸውን ምክንያች ለማንሳት ያህል ከዛሬ ሁለት አመት በፊት በአንድ ተማሪ ላይ በማን አለብኝነት የፈፀመውን የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ ሠራዊት ፍቅሬ አስገድዶ ሊደፍረኝ ሲል አመለጥኩኝ ያለችውን ግለሠብ አዲስ አድማስ የተሠኘው ሐገር ቤት የሚታተም ጋዜጣ አነጋግሯት እንደነበረና ከጥቂት ቀናት በኋላ በሠራዊት ፍቅሬ የመድፈር ሙከራ የተደረገባት ተማሪ ሁኔታ ተደባብሶ ቀረ ወጣቷ አሁን የት እንዳለች እንኳን አይታወቅም አዲስ አድማስም ከህወሀት ሠዎች ሊደርስበት የሚችለውን ዛቻ በማሠብ ተወው ይህንን ድርጊት የፈፀመው ሰራዊት ፍቅሬ ነው አንዱ የዚህ ልዑክ አባል፡፡ ሌላኛው የልዑካኑ ቡድን አባል ቴዎድሮስ አድሐኖም ወይም እንደሱ አጠራር ቴድሮስ አድሐኖም ነው፡፡ ይህ ግለሠብ አምና በዚህ ሠዓት ሣውዲ አረቢያ ይገኙ ለነበሩ ሠዎች ሞት እና እንግልት ተጠያቂ ሊሆን የሚችል ሠው ነው፡፡ ቴዎድሮስ አድሐኖም የውጪ ጉዳይ ሚኒስተሩነቱን እና የህወሀት አባልነቱን ተጠቅሞ ለሳውዲአረቢያ የንጉሳውያን ቤተሠቦች በላከው ደብዳቤ ኢትዮጵያውያኑ ከሳውዲ ኢሠብዓዊ ድርጊት ተፈፅሞባቸው እንዲወጡ ማድረጉ ይታወሳል ይህ ግለሠብ ስለእውነት እና ስለህዝብ የቆመ ቢሆን ኖሮ የሳውዲ ንጉሶችን አሳምኖ የኢትዮጵያውያን መውጫ ቀን በማስረዘም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ከእልቂት እና ከግፍ ያድን ነበር ሆኖም ዛሬ ይህ ግለሠብ የሠራቸው ወንጀሎች ተደብቀውለት ዛሬ የህዝብ ልዑካን ተብሎ ተሠይሞ ይገኛል፡፡ ግርማ ሠይፉም ከእነዚህ ሠዎች መካከል ይገኛል የህዝብ ልዑካን ቡድን ተብሎ፡፡ ከሠራዊት ፍቅሬ እና ከቴዎድሮስ አድሐኖም ጋር አብሮ መስራትን የመሠለ ምን ከዳተኝነት ይኖር ይሆን?

ግርማ ሠይፉ የልዑካን ቡድኑ ውስጥ መካተቱን ሳይነግረን ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ “ይህ የአሁኑ ሠንደቅ ዓላማ ለእኔ ከበፊቶቹ ይሻለኛል፤ ሁሉም የታሠሩት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ንፁህ ናቸው ብዬ አላምንም” ምናምን የሚሉ በህዝብ ላይ የተቀለዱ መጥፎ ንግግሮችን በኢንተርቪው እና በብሎጉ ላይ አሰምቶናል በተጨማሪም አምና አንድነት ጠርቶት በነበረው ሠላማዊ ሰልፍ ላይ ሠልፈኛው ሲግናል አካባቢ ሲደርስ ሲግናል ለአንድ ጎሳ አባላት ብቻ የተሠሩትን ህንፃዎች ተመልክቶ ዝም ብሎ ማለፍ ያልቻለው ሠልፈኛ ሌባ ሙሰኛ እያለ ሲጮህ ዝም በሉ እያለ ሠልፈኛውን ከሀብታሙ አያሌው ለመነጠል ሲሞክር እንኳን በግርማ ላይ ተስፋ አልቆረጥኩም ነበር አሁን ግን ከኢትዮጵያ የምንም ጊዜ ጠላቶች ጋር አበረ፡፡ የልዑካን ቡድኑ ውስጥ ያሉት ሠዎች እኮ በበደኖ እና በአርባጉ የአማራውን ጎሳ የጨፈጨፉ፤ በአምቦ ንፁሐን የኦሮሞ ተማሪዎችን የገደሉ፤ ፤ በጋምቤላ ንፁሀንን ያስፈጁ፤ ፕ/ር አስራትን እና አሠፋ ማሩን የመሳሰሉ ድንቅ የሐገራንን ምሁራን ያስገደሉ፤ እስክንድርን፤ ርዕዮትን፤ በቀለ ገርባን፤ ኤርባና ሌሊሳን፤ የሺዋስ አሠፋን፤ አብርሐ ደስታን፤ ዳንኤል ሺበሺን፤ አበበ ቀስቶን፤ ናትናኤልን፤ ሐብታሙን፤ እና ሌሎችንም ያሠሩ፤ ከጥቂት ቀናት በፊት እንኳን የሠማያዊ ፓርቲን እና የትብብሩ አባላትን ቶርች ያደረጉ፤ በትላንትናው እለት ባህርዳር ላይ ህዝብን ያስፈጁ ሠዎች ጥርቅም ውስጥ ግርማ ዘው ብሎ የገባው፡፡

ግርማ ቆም ብሎ አስቦ ህዝቡን ይቅርታ ብሎ ጠይቆ እራሱን ከፖለቲካ ከማግለል ውጪ ሌላ አማራጭ ይኖረዋል ብዬ አላስብም ፓርቲው አንድነትም ቢሆን እንደግርማ ሠይፉ ያሉ አባላትን ይዞ መቀጠሉ ለፓርቲው አደጋ መሆኑን ተገንዝቦ ህዝቡን ይቅርታ ሊጠይቅ እና ግርማ ሠይፉን ሊቀጣው ይገባል ይህ ካልሆነ ግን ለወትሮውም በሐገራችን ፖለቲካ ተስፋ ለቆረጠው ህዝባችን ጭራሹኑ ፊቱን እንዲያዞር የሚያደርግ ታሪክ ሲወቅሠው የሚኖር ተግባር ከዛም አልፎ ሌሎች እየለፉ ያሉ ፓርቲዎች ላይ ህዝቡ እምነት እንዳይኖረው የሚያደርግ አስወቃሽ ስራ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ በፊት ከግርማ እና ከፓርቲው መልስ ያስፈልጋል

የፍረጃ ፖለቲካ አይጠቅመንም!  መልስ ለሁኔ አቢሲኒያ ( ግሬስ አባተ)

$
0
0

በመጀመሪያ ይህን ፅሁፍ የምፅፍልህ ሌላውን ወገን ወግኜ ሳይሆን ይህ አካሄድ በመሰረታዊነት ትግሉን የሚጎዳ ስለሚመስለኝ ነው፡፡ በምንም ጉዳይ ትግሉን አንድ ኢንች በሚጎዳ ነገር ዝምታን አልመርጥም፡፡ ሲጀመር ሰራዊት ፍቅሬንና የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን በአንድ ሚዛን ላይ የሚቀመጡ ግለሰቦች አንዳይደሉ በደንብ የምታውቅ ይመስለኛል፡፡ የቆሙለት አላማ በራሱ ይህንን አስረግጦ ስለሚነግረን በዚህ ላይ ጊዜ ማባከኑ ትርጉም የለውም፡፡ የመረጥከው ርዕስ በራሱ ሶስቱን ለይተህ ማቅረብህ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ያልመረጥናቸው ስትል ቀሪዎቹን ወይ መርጠሃቸዋል ወይ ይሁንታ ሰጥተሃቸዋል ማለት ነው፡፡

(ግርማ ሰይፉ)

(ግርማ ሰይፉ)

ያልመረጥናቸው ከምትል ይልቅ በምን መስፈርት ተመረጡ ብትል ጥሩ ይሆን ነበር፡፡ መብትህም ስለሆነ ! እንደምታውቀው የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ የተቋውሞው ፖለቲካ ብቸኛ የፓርላማ ተወካይ ናቸው፡፡ እንደምታውቀው የተቃውሞ ጎራው የግድቡን ጉዳይ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ መዋሉ በተለይም የአረቡ አብዮት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመጣ ለማስቀየሻ የተመዘዘ እና በቂ ጥናት ሳይደረግበት ወደ ስራ በመገባቱ እንጂ የሚቃወሙት ግድቡ ለምን ተገነባ በሚል አይደለም፡፡ ስለዚህ አቶ ግርማ የፓርላማ አባል በመሆናቸው ብቻ የዚህ ልዑክ አካል መሆን ቢችሉ ብዙም የሚገርም አይደለም፡፡

ግድቡን አስመልክቶ የስርዐቱ አንዱ ችግር እንደውም ሌላውን ወገን አግልሎ የራሱን ፕሮፓጋንዳ መጫወቻ ማድረጉ ነው ትልቁ ችግር፡፡ ስለዚህም ይህን ግብዣ ማድረጋቸው እንደ ጥሩ ጅማሬ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡ ሁኔታው ይህ ሆኖ እያለ በተለይም ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር ተጨባብጠው ፎቶ መነሳታቸውን አስመልክቶ ‹‹የልኡካን ቡድኑ ውስጥ አቶ ግርማ ሰይፉ የሚል ስም ተሰማ…፤ በዚህ በርካቶች ተገረሙ ወይ እቺ አገር ሲሉም አዘኑ›› ይህ የተጋነነ ነው፡፡ ከዚህ ግድብ ጋር ተያይዞ ስርዐቱ በሚፈጥረው ፕሮፓጋንዳ ስንቶች በተቃውሞ ፖለቲከኞች እንዳዘኑ ብነግርህ እንዳይገርምህ፡፡ አንተ እንዳልከው ማዘን መገረም ሳሆን ህዝቡ ጋር ያለው ከዚህ በተቃራኒ እንደሚሆን እምነቴ የፀና ነው፡፡

547 የስርዐቱ አባላት ባሉበት ፓርላማ የሚቻለውን ማድረግ የቻለ ግለሰብ ነው፡፡ ሰው የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ አንድ ድምፅ ይዞ የጎላ ለውጥ የሚያመጣበትን ምክንያት ከቻልክ ንገረኝ? እንዲሁ ሌላው ለሰራ ክሬዲት መንፈግ ካልሆነ በቀር ይህ አንድ ድምፅ ይዞ እንደሌሎች ለወከላቸው ህዝብ ሳይሆን ለፓርቲቸው ተጠሪ የሆኑ 545 ሰዎች ባሉበት ፓርላማ ያንን ያህል ጠንካራ ስራ አልሰሩም ተብሎ ሊወቀሱ አይገባም ባይ ነኝ፡፡ ከቻልክ ፖለቲካውን ከስሜትና ከጥላቻ በዘለለ ለማየት ሞክር፡፡ ፍረጃ ላለፉት ምናምን አመታት የሄድንበት ስለሆነ ያንን መድገም ካልሆነ በቀር የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡

ወደ ፍረጃ መሮጥህ ተገቢ ያልሆነ ነው፡፡ ቆይ አንተ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን እንዴት አድርገህ ነው ምታያቸው? እስከሚገባኝ ግለሰቡ በሰላማዊ ትግል ለውጥ አመጣለሁ ብለው እየታገሉ ያሉ ግለሰብ ናቸው፡፡ አንተ ሰላማዊ ትግል ለውጥ ኤመጣም ልትል ትችላለህ፡፡ መብትህም ነው፡፡ ይህ ከሆነ እውነታው አቶ ግርማን ጨምሮ ሰማያዊ ሆነ አንድነት ውስጥ ያሉ የፓርቲ አባላትን ሕወሃት/ኢህአዴግ ጠላታችሁ ነው ወይ ብትላቸው? የምን ጠላት ነው፡፡ በሰላማዊ ትግል ጠላት የሚባል ነገር የለም ይሉሃል፡፡ባለው የህግ ማእቀፍ ውስጥ ሆኖ በሰላማዊ ትግል እየታገለ እንዴት እንደጠላት እንዲተያይ ወይም ግብዣ ሲቀርብለት ከጠላቶቼ ጋር እንዲል ትጠብቃለህ? የሚታገለው እኮ በሰላማዊ መንገድ ያለውን ስርዐት ለመቀየር ነው፡፡

ግለሰቦች የሚሉትን አስመልክቶ ፖለቲካው ላይ አቧራ ባናስነሳ ይሻለናል፡፡ አሁን መሬት ላይ ያለውን እውነት ይዤ ለመሞገት እንጂ ስለ አቶ ግርማ ጥብቅና ለመቆም አይደለም፡፡ ስለግለሰቦች መቶ ሺ ጊዜ ብንከራከር ለውጥ አናመጣም፡፡ አሉት የተባለው በራሱ ያን ያህል ለውንጀላ የሚቀርብ አይደለም፡፡ አንተ ራስህ ያቀረብከውን ልጥቀሰው ‹‹ይህ የአሁኑ ሰንደ ቃላማ ለእኔ ከበፊቶቹ ይሻለኛል፤ ሁሉም የታሰሩት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ንፁህ ናቸው ብዬ አላምንም›› ያለውን ጠቅሰሃል በናትህ ፖለቲካውን ከስሜት በዘለለ ተመልከተው፡፡ በዚህ ሁኔታ ከቀጠልን አንድም ኢንች ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡ ቀደም ብዬ አንዳልኩት ይህን አለ እከሌ እከሊት ይህን አለች የሚባል ፖለቲካም የለም፡፡

አሁን አሉት የተባለውን ከዚህ ቀደም አቧራ ተነስቶ ብዙ ሲባል አስተውያለሁ ነገሩን በቅንነት ማየት ነው የሚሻለው፡፡ የግለሰብ መብት በቅድሚያ እንዲከበር የሚታገል ድርጅት እንዴት ይህን ተናገርክ ብሎ ሊከሰው ይችላል፡፡ እንዳንተ ቢሆን ይህ ሰው ሂስ ማውረድ አለበት፡፡ በአንድነት ቤት ግን ይህ አይሆንም፡፡ ቃሉ በራሱ የሚለው እኮ ‹‹ይህ የአሁኑ ሰንደ ቃላማ ለእኔ ከበፊቶቹ ይሻለኛል›› እናስተውል! ለአንድነት አይደለም ያለው ‹‹ለእኔ›› ነው፡፡ ይህ መብቱን ታድያ ማን ሊከለክለው ይችላል? ለምሳሌ እኔን ብትጠይቀኝ ምንም ሌለበትን አረንጓዴ፣ቢጫ ፣ቀዩን ነው ምልህ! ግርማ እንዲህ ስላለ ግን ምንም ልል አልችልም መብቱ ነው፡፡ ለምን እኔ የመረጥኩትን ካልመረጥክ እንዴት ልለው እችላለሁ? ይህን ከቻልክ ብታስረዳኝ?

የታሰሩትን አስመልክቶ የሠጠው ለኔ ምንም የሚያስከፋ ነገር የለውም፡፡ ምንድነው ያለው ‹‹ሁሉም የታሰሩት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ንፁህ ናቸው ብዬ አላምንም›› አሁንም እዚህ ጋር ሲገልፅ አንድነት ምናም ሳይሆን እራሱን ወክሎ ነው ሚናገረው፡፡ ይህ ማለት ግን የታሰሩት ሁሉ ወንጀለኞች ናቸው ማለት አይደለም፡፡ አልያም የታሰሩት በሙሉ ንፁሃን ናቸው ማለት አይደልም፡፡ ለምሳሌ ሁሉም ነፃ ናቸው ለማለት ቃሊቲን ጨምሮ በአገሪቷ ውስጥ ያሉ ሁሉም እስር ቤቶች ውስጥ ያሉ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን በሙሉ ማወቅ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አንተኑ ልጠይቅህ በዝዋይ ምን ያህል ፖለተከኛና ጋዜጠኛ ታስሮ ይገኛል? ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ… እያልክ የምታውቃቸውን ብቻ ትጠራለህ እንጂ የማታውቃቸውን ከየት አምጥተህ ትጠራልኛለህ? ስለማታውቃቸውስ ጥብቅና ልትቆም ትችላለህ? ስለዚህ ‹‹ሁሉም›› ያሉበት ሁኔታ ስህተት ሊሆን አይችልም፡፡ ለምሳሌ እኔን ብትጠይቀኝ ብዙ የፖለቲካ እስረኞች እንዳሉ ልገምት እችላለሁ ተናገር ብባል ግን አሁንም እንዳንተው እስክንድር፣ ርዕዮት ነው ልል የምችለው እንጂ የታሰሩት ሁሉ ንፁሃን ናቸው ለማለት በአገሪቷ ውስጥ ያሉ እስረኞችን ሁሉ ማወቅ ይጠበቅብኛል፡፡ ይህ ደግሞ የማይቻል ነው፡፡ ይህ ከሆነ እውነታው የሰጡት አስተያየት እንዴት ስህተት ሊሆን ይችላል?

እንዳልከው የልዑካን ቡድኑ ውስጥ ስለተካተቱ ግለሰቦች ይመጥናሉ አይመጥኑም በሚለው መነጋገር እንችላልን፡፡ ብንነጋገር እንኳ የመምረጥ እድሉ አልሰጡንም፡፡ ወይንም ህዝቡ እንዲመርጥ እድል አልተሰጠውም፡፡ ይህ ማለት ግን በጭፍኑ እዛ ውስጥ ያሉ ሁላ ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ናቸው ማለት ጅምላ ፍረጃ ከመሆን ውጪ አያልፍም፡፡ እንዳልከው በዚህ ልኡካን የተካተቱ ግለሰቦች በስልጣን ዘመናቸው አንተ የጠቀስካቸውን ጨምሮ በርካታ ወንጀሎችን ሰርተዋል፡፡ እየሰሩም ይገኛሉ፡፡ የተከበሩ አቶ ግርማ ከዚህ ልዑክ ጋር አብረው መሄዳቸው እንዴት ሆኖ ነው ከነዚህ አምባገነኖች ጋር መተባበር ተደርጎ የሚወሰደው? የልዑኩ አላማስ ምንድን ነው? የሚለውን ጨምረህ ብትመልስልኝ አወዳለሁ፡፡

ቀደም ብዬ ያልኩትን መድገም ነው የሚሆነው፡፡ ግርማ ወደ እዚህ ልዑክ ሲሄድ እንዳልኩት በፓርላማ አባልነቱ እንጂ አንድነት ፓርቲን ወክሎም አይደልም፡፡ ይቅርታ የሚጠይቀውስ ምን አድርጌያለሁ ብሎ ነው? አንድነት ፓርቲስ ግለሰቡን የሚቀጣው በምን መስፈርት ነው? ፓርቲውስ መግለጫ የሚሰጠው በምን ምክንያት እንደሆነ አብራራልኝ፡፡ አሁን የመጣች ፋሽን አለች ግለሰቡ ይህን ተናገረ ይህን አሉ ያም በአመራር ደረጃ ያለ ስለሆነ የፓርቲው አቋም አድርገን እንወስዳለን የምትል ቀልድ፡፡ ለጊዜው አትመጥንምና ተዋት፡፡ ስለጉዞው ለምን አልነገረንም ለሚለው ከፈለገ የሚለን ይኖራል ሊገደድ የሚችልበት አመክንዮ የለም፡፡ ማንም እንደሚረዳው ብቸኛ መቀመጫ እንዳለው አባል መካተቱ ብዙም የሚገርም አይደለምና፡፡ አትሳሳት ፓርቲው ግን መልስ እንዲሰጥ አትጠብቅ፡፡ እዚህም እዚያም ለሚነሳ አቧራ ፓርቲው መግለጫ በመስጠት ጊዜ ሚያባክንበት ሁኔታ ተገቢነቱ አይታየኝም፡፡

ጥሩ ጊዜ ተመኘሁ!♡

https://www.facebook.com/gracet.sewoch/posts/9048768128693

የአንድነት መንገድ! (አስራት አብርሃም)

$
0
0
አስራት አብርሃም

አስራት አብርሃም

አንድነት ለዴሞከራሲና ለፍትህ ፓርቲ በ2007 ምርጫ ከሁሉም ፓርቲዎች በተለየ ሁኔታ በጣም ግልፅና የማያሻማ የምርጫ እስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ያለ ፓርቲ ነው። በዚህ ስሌትም የተዘጋውን የፖለቲካ ምህደር ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር ማስከፈት እንደሚችል አምኖ በምርጫው በሙሉ ልብ ለመሳተፍ ወስኗል። በዚህ ምክንያትም የያዘውን የምርጫና የሰላማዊ ትግል መስመር አስቀድሞ በይፋ በማወጅ የመርህ ፓርቲ መሆኑ አስመስክሯል። ይሄ አቋሙ በምርጫው እንደሚሳተፉ እርግጠኛ ሳይሆኑ የምርጫ ምልክት ከወሰዱ ፓርቲዎችና በሂደቱ ዝም ብለው በደመነፍስ ከገቡ ፓርቲዎች በእርግጠኝነት የተሻለ አቅጣጫ ያስቀመጠ ፓርቲ እንዲሆን አድርጎታል። ይህ ሊሆን የቻለው አንድነት የፖለቲካ ምህዳሩ እንዴት እንደሚሰፋ፤ ገዥውን ፓርቲ በምን ሁኔታ አስገድዶ ወደ ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ መምጣት እንደሚችልና እንዴት አምባገነናዊ በሆነ ስርዓት ውስጥ በምርጫ አሸናፊ ሆኖ መውጣት እንደሚቻል ተረድቶ የመታጊያ እስትራቴጂውን በአግባቡ የነደፈ ፓርቲ በመሆኑ ነው። -—[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——-

 

 

ግፍና አፈና ዐመጽን ይወልዳሉ! (ያሬድ ኃይለማርያም)

$
0
0

የዐመጸኛ አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው (መ. ምሳሌ ም. 22፣  ቁ. 14)

ከያሬድ ኃይለማርያም

ብራስልስ፣ ቤልጂየም

ታኅሣሥ 10፣ 2007

ethiopia_flagሰብአዊ መበቶችን በመጣስ፣ ግፍ በመፈጸምና አፈናን በማጠናከር እደሜ የሚሸምት የአገዛዝ ሥርዓት የእያንዳንዱን ሰው መንፈሳዊና አካላዉ ጥንካሬ የማዳከም፣ ቅስምን የመስበርና ፍርሃትን የማንገስ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ሁሉ በብሶት የሚወለዱ፣ እምቢኝ ለግፈኞች፣ እምቢኝ ለአንባገነኖች፣ እምቢኝ ለነጻነቴ የሚሉ መንፈሰ ጠንካራ ጀግኖችንና ታጋዮችንም ይወልዳል:: የአለማችን ስመ ጥርና ዘመን የማይረሳቸው የነጻነት ታጋዮች እነ ማህተመ ጋንዲ፣ ማርቲን ሉተር ኪነግ፣ ማንዴላ፣ ኡንግ ሳን ሱ ኪ እና ሌሎችም ብዙዎች የፈለቁት በብሶት ከተሞላ፣ ጭቆና ካንገሸገሸውና በአፋኝ ሥርዓት ከታመቀ ማኅበረሰቡ ጉያ ነው:: አንድን ማኅበረሰብ በአፈሙዝ፣ በሕግና በገንዘብ ኃይል ጭፍሎቆና አፍኖ ማቆየት የሚቻለውም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ መሆኑን የእነዚህ ታጋዮች ገድልና የአለም ታሪክም ይመሰክራል:: አንድ ሕዝብ በላዩ ላይ ገዢዎች እየተፈራረቁበት ረዘም ላለ ጊዜ በአገዛዝ ሥርዓት ሥር ሊቆይ ይችል:: ይሁንና እድሜ ልክ የገዛ አፋኛ ሥርዓት ግን የለም:: ሥርዓቱም እንደ ድርጅት፣ ሹማምንቱም እንደ ሰው የጉብዝና እድሜያቸው የተወሰነ ነው:: የአፈናን ስልት በመለዋወጥና ሸምቀቆውን በማጥበቅም እድሜን ማራዘም የሚቻል ቢመስልም በተቃራኒዉ ውድቀትንም ያፋጥናል:: ግፉ እየበረታና የመብት ጥሰቱም መረን እየለቀቀ በሄደ ቁጥር የሕዝብ ትእግስት ይሟጠጣል:: ሕዝብ መቆጣት ከጀመረና ቁጣውም ወደ አደባባይ አመጽ በተቀየረ ጊዜ የግፍ አገዛዝ ወደ መቃብር፣ ግፈኞቹም ወደ ዘብጥያ እንደሚወርዱ እርቀን ሳንሄድ ባለፉት አምስትና አሥርት አመታት ውስጥ በአለም የታዩ ሕዝባዊ ነውጦችንና ያስከተሉትን መዘዝ ማጤን በቂ ነው::

ትልቁ ጥያቄ በግፍ አገዛዝ ውስጥ ያለ ሕዝብ መቼ እና ብሶቱስ ምን ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው የሚቆጣው? መቼ ነው ቁጣውንስ በየመንደሩ ከማጉረምረም አልፎ ባደባባይ የሚገልጸው? ቁጣውስ ወደ አመጽ ሊያመራው የሚችለው በምን ሁኔታ ነው? የሚለው ነው:: የሕዝብ ቁጣ ወደ አመጽ የሚለወጥበት ጊዜና ደረጃው የሚለካው በተለየ ሳይንሳዊ ቀመር ስላልሆነ መቼና በምን ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቸግራል:: ይህ አይነቱ ሁኔታ በእያንዳንዱ ማኅበረሰቡ ባህላዊ፣ ኃይማኖታዊና ማኅበራዊ አመለካከቶችና የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ላይ ይወሰናል:: በትንሽ በትልቁ አደባባ እየወጣና በሚሊዮን የሚገመት የመንግሥትና የሕዝብ ንብረትን እያወደመ ተቃውሞውን የሚገልጽ ሕዝብ አለ:: በሌላ መልኩም አገሩን ቢሸጡበት፣ መሬቱን ቢነጥቁት፣ ሚስቱን ቢያስጥሉት፣ ልጆቹን ቢደፍሩበት፣ ቢገድሉበት፣ ቢያስሩበትና ቢያፍኑበት፣ ቤቱን በላዩ ላይ ቢያፈርሱበት፣ ቀየውን ለቱጃሮች ሰጥተው ቢያፈናቅሉት፣ ግብር እየከፈለ ያስተማራቸውን ልጆቹንና አመራቹን ኃይል እያዋከቡ ከአገር ቢያሰድዱበትና ለባርነት ቢዳርጉት፣ ከሰው ተራ አውርደው በየጎዳናው ቢጥሉትም ‘አዬ ጉድ፣ አዬ ጉድ’ ከማለት ባለፈ ቁጣውን የማያሳይም ሕዝብ አለ:: በከፋ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ታዋቂ የነበሩት ሟቹ ጠ/ሚ መለስ ያረፉ ወቅት አስከሬናቸውን ይሳለሙ ከነበሩ ሰዎች በኑሮው እጅግ የተጎዳና የተጎሳቆለ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በመንግሥት የቴሌቪዥን ማሰራጫ ሃዘኑን የገለጸበት መንገድ ጥሩ ማሳያ ሊሆን ይችላል:: የአዞ እንባውን እያነባ “እኔ እኮ እሳቸውን ተማምኜ ነው ጎዳና ላይ የማድረው” ነበር ያለው::

በሳንቲም ደረጃ የዋጋ ጭማሪ ተደረገብኝ ብሎ ወደ አደባባይ እየደጋገመ የሚወጣውን የኬኒያን ሕዝብ ቁጣ ለማየት በሚያዚያ ወር 2011 (እ.ኤ.አ) የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብን ተከትሎ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት በመቃወም በናይኖቢ የተካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ማየት ይቻላል:: እኛ ዘንድ የነዳጅ ዋጋ ስንት ጊዜ አሻቀበ? በእያንዳንዱ የእለት ተዕለት መገልገያ ቁሳቁሶች ላይ በምን ያህል መጠንና ስንት ጊዜ የዋጋ ንረት ታየ? የቤት ኪራይ፣ የትራንስፖርት፣ የጤና አገልግሎት፣ የመድሃኒቶች እና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ዋጋስ በስንት እጥፍ ናረ? እኛስ ስንት ጊዜ ቁጣችንን ገለጽን? በኑሮ መማረራችንንስ በምን መልኩ ለገዢዎቻችን አሳየን? ከኑሮ ዋስትና ማጣት ባሻግር የሹመኞች ከሕግ በላይ መሆን የዜጎችን በሕገ-መንግሥቱ የተደነገጉ መሰረታዊ የፖለቲካና የሲቪል መብቶችንና ነጻነቶችንም ትርጉም አልባ ሲያደርጋቸው እያየን ምን አደረግን? ለዚህም ነው የሕዝብ ብሶትና ምሬት የት ደረጃ ላይ ሲደርስ ቁጣ ወደተቀላቀለበት ተቃውሞ ሊያመራ እንደሚችል ሳይንሳዊ በሆነ ቀመር ማረጋገጥ ወይም መገመት የማይቻለው:: ምክንያቱም ግፍና በደሉን የተሸከመው ሕዝብ ያለው የታጋሽነት ልክ፣ ሆደ ሰፊነቱ፣ አርቆ አሰተዋይነቱ፣ የተዋጠበት የፍርሃት ጥልቀት ወይም ሌሎች ስነ-ልቦናዊ ሁኔታዎች ናቸው ይህን የሚወስኑት:: በዛሬዎቹም ሆነ በትላንት ገዢዎቹ ጭካኔና የማስተዳደር ብቃት ማነስ የተነሳ ለከፋ ድህነት የተጋለጠውና በልቶ ማደር ፈተና የሆነበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ምሬቱንም ሆነ ተማጽኖውን የሚያሰማው ለፈጣሪው ብቻ ነው:: ሲመረውም ‘ምነው ዝም አልክ? ወይ ፍረድ ወይ ውረደ’ እያለ ካምላኩ ጋር መሟገት ይቀለዋል:: ትንሽ ሲደሰትም ‘ተመስጌን ይችን አትንሳኝ’ እያለ የነገን እጣፈንታውን እያሰላሰለ ፈጣሪውን ያመሰግናል:: ስለዚህ መንግሥት በሕዝብ ላይ ያሻውን ቢያደርግም ሕዝብ የልቡን የሚወያየውም ሆነ ይግባኝ የሚለውም ከመንግስት ዘንድ ሳይሆን ከፈጣሪው ጋር ነው:: ይህ አይነቱ የኅብረተሰብ ምላሽ ገዢዎችን ያማግጣል፣ ያሻቸውን እንዲያደርጉም ያበረታታል፣ ሕዝብን እንዲንቁና እራሳቸውንም ከሕግ በላይ አድርገው እንዲያስቡ ያደርጋል::

በዚህ አይነት ማኅበረሰብ ውስጥ ትልቁ ቀውስና ፖለቲካዊ ነውጥ የሚጀምረው የገዢዎቹ መረን መልቀቅ እየበረታ፣ የሕዝቡም ክፌት እየገነፈለ ሕዝብ የሚጠብቀው የፈጣሪው ምላሽ ግን የዘገየ ዕለት ነው:: ያኔ የሕዝብ ትግስት ይሟጠጣል፣ ሰፊውም ሆድም በቂም፣ በክፌትና በጥላቻ ይሞላል፣ አርቆ አሰተዋይነቱም ወደ ግብታዊነትና ንዴት ይለወጣል፣ ፍርሃቱም ተስፋ መቁረጥ ወደሚያሰከትለው ጨለምተኝነትና ጀብደኝነት ይቀየራል:: እዛ ደረጃ ከተደረሰ በኋላ የሚሆነውን መገመት አይከብድም:: በቅርቡ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በተለይም በቱኒዚያ፣ በግበጽ፣ በሊቢያ፣ በዩክሬንና ሌሎች አገሮች የተከሰቱት የሕዝብ ቁጣዎች ለዚህ ጥሩ ማሳያዎች ናቸው:: ባለፉት አራት አመታት ውስጥ በሕዝብ ቁጣና አመጽ ሲናወጡ የከረሙትን፣ በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመቶችን ያሰተናገዱትንና የመንግሥታትም ለዉጥ የታየባቸውን የአረብ አገራት መለስ ብለን የተመለከትን እንደሆነ አብዛኛዎቹ በቡዙ መልኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚገኝበት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሁኔታዎች እጅግ በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው:: ጥሩ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው፣ ሕዝብ በምግብ አጦት የተነሳ በርሃብ የማይሰቃየባቸውና የማይሞትባቸው፣ እጅግ የተሻለ የእሌክትሪክ፣ የውሃ፣ የነዳጅ፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የኢንተርኔትና ልሎችም መሰረታዊ አቀርቦቶች የተሟሉባቸው አገሮች ናቸው:: ከፖለቲካ ነጻነቱም አንጻር ብዙዎቹ ከኢትዮጵያ በተሻለ ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት፣ ባደባባይ የመሰብሰብና ተቃውሞንም የመግለጽ ነጻነትም የሚታይባቸው ናቸው:: ይሁንና በእነዚህ አገራት ውስጥ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ የሥልጣን ባለቤት ባለመሆኑና ብለሹ በሆኑት የፖለቲካ ሥርዓቶች እጅግ ተከፍቶ የቆየ ስለነበር በቀላሉ ወደ አመጽ ሊያመራ ችሏል:: አንዳንዶቹም ዘላቂ ለሆነ ቀውስ መዳረጋቸው ይታወቃል::

በእነዚህ አገራት የሕዝብ የነጻነትና የመብት ጥያቄ የሥርዓት ለውጥን ለማምጣት ወደሚችልበት ሕዝባዊ አመጽና ኃይል ወደታከለበት ግጭት እንዲያመራ የውጪው አለም ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ አይካድም:: ቢሆንም ዋነኛው ምክንያት ግን የተጠራቀመው የሕዝብ ክፌትና ብሶት ነው:: በእነዚህ አገሮች በተነሱት የሕዝብ አመጾችና በተከሰቱት የፖለቲካ ቀውሶች ማን አተረፈ የሚለው እራሱን የቻለ ሰፊ የመወያያ ርዕስ ነው:: ነገር ግን በግልጽ እንደሚስተዋለው የመጀመሪያዎቹ ተጠቂዎች ሕዝብን ሲያሰቃዩ፣ ሲያፍኑ፣ ሲገደሉና ሲያስገደሉ፣ ሚሊዮኖችን እያደኸዩ ሃብት ሲያካብቱ የነበሩ ሹማምንትና ዙሪያቸውን የከበቡዋቸው ባለሃብቶች ለመሆናቸው በጋዳፊና በሙባረክ እንዲሁም በዙሪያቸው የነበሩ ሰዎችን እጣ ፈንታ ማየት በቂ ነው:: ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሕዝብ ክፌትና ብሶት፣ የአፈናው ደረጃ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመሰረታዊ አቅርቦቶች መጓደል፣ የባለሥልጣናቱ ሙሰኝነትና ከሕግ በላይ መሆን፣ የሥራ አጡ ቁጥር፣ የድኅነቱ ደረጃ፣ ተሰፋ ማጣትና ጨለምተኝነት በምንም መልኩ ቢሆን ከሌሎች በአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ ከሚገኙ አገሮች ጋር የሚወዳደር አይደለም:: የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ከገጠሙት ክፉና አንባገነናዊ ሥርአቶች ውስጥ የወያኔን አገዛዝ የተለየና የከፋ የሚያደርገው የዘረኝነት ፖሊሲው ብቻ ሳይሆን በአገር ሃብትና ንብረት የከበሩ የንግድ ድርጀቶች ባለቤትና ከታጋይነት ወደ ሚሊየነርነት የተቀየሩ ቱጃር ባለሥልጣናትንና የጦረ አዛዦችን የያዘ ድርጅት መሆኑ ነው:: ብሶት የወለዳቸው የወያኔ ባለሥልጣናት ዛሬ በተራቸው ሕዝብን ሆድ ከማስባስ አልፈው ማቆሚያ ወደማይኖረው የእርስ በርስ ግጭት፣ አመጽ፣ ቀውስና የዘር ቁርሾ ውስጥ እንዲገባ እየጋበዙት ነው::

የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔ ሥርዓት አራሱን እንዲያርቅና አገሪቱንም ከተንጠለጠለችበት የገደል አፋፍ እንዲታደግ ከሃያ ዓመታት በላይ እድል ሰጥቶታል:: ፍጹም ሰላማዊና ስልጡን በሆነ መልኩም በ1997ቱ ምርጫ የማስጠንቀቂያ ደውሉን አቃጭሏል:: ይሁንና ይህን ማስጠንቀቂያ የወያኔ ባለሥልጣናት የተረጎሙበት መንገድ ሕዝብ ማስተላለፍ ከፈለገው መልዕክት እጅቅ የራቀና በተሳሳተ መልኩ መሆኑን ለመረዳት ምርጫውን ተከትሎ የወሰዱትን የኃይል እርምጃና ከዛም ወዲህ ያሳዩትን አፈናውን በሕጎች አጠናክሮ የመቀጠል ፍላጎት ማጤን በቂ ነው:: ለሕዝብ ያላቸውን ንቀትና እብሪትም በደንብ ያመላክታል:: ከዚህ በመነሳት ከፊታችን የሚጠብቀን ምርጫ ሊኖሩት የሚችሉትን ሁለት ገጽታች መገመት ይቻላል::

  • የመጀመሪያው ወያኔ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት ምርጫዎች ብቻውን ተወዳደሮ ወይም አጃቢ ተቃዋሚዎችን አስከትሎ ያለምንም ችግር 99% ወይም ተቀራራቢ በሆን አሃዝ ጠቅልሎ ይቀጥላል:: አለያም የተወሰኑ ግጭቶችን ባስከተሉ ተቃዉሞዎች ውስጥ አልፎ ከ 10% እስከ 20% መቀመጫን ለተወሰኑ ተቃዋሚዎች ለቆ የፖለቲካ መዘውሩን እንደያዘ ተደላድሎ ይቀጥላል::
  • ሁለተኛው ግምት ደግሞ በተቃዋሚዎች አበሮ መስራት ላይ በተመሰረት ጥንካሬና ከሕዝብ በሚገኝ ድጋፍ ምርጫው ለምክር ቤት ወንበር ሽሚያ ሳይሆን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከአንባገነናዊ ሥርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማላቀቅ፣ ሕዝብንም የሥልጣን ባለቤት ለማድረግና እና አገሪቱንም ካንዣበበባት አደጋ ለመታደግ የሚደረግ የነጻነት ወይም ሞት ትግል ይሆናል::

በመጀመሪያው ሂደት ውስጥ የሚከሰቱት ነገሮች መሰረታዊ ለውጦችን ለማምጣት የታለሙ ሳይሆን የአገዛዝ ሥርዓቱ ያስቀመጠውን የጨዋታ ሕግ በማክበር ተቃዋሚ የሆነው የፖለቲካ ኃይልም ሆነ ሕዝቡ ሥርዓቱን በረዥም ጊዜ ሂደት እንለውጠዋለን ወይም በራሱ ጊዜ ይከስማል ወይም አራሱን በሂደት ያርቃል የሚል ተስፋ ሰንቀው እድሜውን እንዲያራዝም የሚፈቅዱበት ሁኔታ ነው:: ባጭሩ “ያለ ምንም ደም ወያኔ ይቅደም” ነው:: በዚህ አካሄድ አትራፊዎቹ ወያኔ እና በወያኔ መቆየታ ላይ ተማምነው በኢኮኖሚም፣ በጸጥታ ዘርፍም እና ሆነ በአካባቢው የፖለቲካ መረጋጋት ለማትረፍ ከሥርዓቱ ቃር የተወዳጁ የውጪ ኃይሎችና የዘመኑ ባለሃብቶች ብቻ ናቸው:: ሰፊውና ድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ አገሩን ለቀማኞች አስረክቦ የስቃይ ዘመኑን በየአምስት አመቱ በሚደረጉ የማደናገሪያ ምርጫውዎች እያደሰ የግፍ እንቆቆውን መጋቱን ይቀጥላል::

ይህ አይነቱ በምርጫ ስም የሚደረግ ማደናገሪያ ከቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ወዲህ በበርካታ የሦስተኛው አለም አገሮች ተደጋግሞ የሚታይ ክስተት ሆኗል:: ባለፉት አስርት አመታት እንደተስተዋለው ምርጫ አንድ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባትና የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚረዳ መንገድ የመሆኑን ያህል ድሃ ሕዝብን አፍኖ ለመግዛትና የአንባገነኖችንም እድሜ ለማራዘም እያገለገለ መሆኑን ነው:: በዚህ ሂደት ውስጥ ዋነኛ ተዋናዮቹ የአገዛዝ ሥርዓቶቹ ብቻ ሳይሆኑ የምዕራቡ አለም እና የአለም ከበርቴዎችም ናቸው:: የቅኝ ግዛት ታሪክ ካከተመ በርካታ አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም አገሮችን በቅኝ ለመግዛት የምዕራቡ አለም ቆርጦ የተነሳባቸው ዋነኛ የኢኮኖሚና የፖለቲካ መንስዔዎች ዛርም እጅግ በከፋና ባፈጠጠ መልኩ ይታያሉ::

የምዕራቡ አለምና ከበርቴዎቹ የቅኝ ግዛት ፖሊሲዎቻቸውን ለማስቀጠልና ጥቅሞቻቸውንም በእነዚህ ድሃ አገሮች ላይ፣ በተለይም በአፍሪቃ አገሮች ውስጥ እንደተጠበቀ ለማቆየት እንደ አማራጭ ከወሰዱት መንገድ አንዱ ከትቢያ እያነሱ ወደ ስልጣን እንዲመጡ የረዷቸውን የጫካ ሽፍቶች በስልጣን ለማቆየት በገንዘብና በጦር መሳሪያ ከሚያደርጉላቸው ድጋፍ ባሻገር አንጻራዊ የሆነ የፖለቲካ መረጋጋትም እንዲኖር የእነዚህን አፋኝ ቡድኖች እድሜ በይስሙላ ምርጫ እንዲታጀብ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ማድረግ ነው:: ይህ አካሄድ ሁለት ግቦች አሉት:: አንዱ እነዚህ አንባገነኖች ሙሉ በሙሉ በምዕራቡ አለም ድጋፍ ነው የቆሙት ወደሚል ድምዳሜ ከተደረሰ የዳግም ቅኝ ግዛት እቅዳቸውን ከማጋለጡም በላይ የምዕራቡ አለም ከአንባገነኖችና የሰብአዊ መብቶችን በገፍ ከሚጥሱ ቡድኖች ጎን አብሮ በመቆም የደሃ አገር ሕዝቦችን በማሰቃየትና ሃብታቸውንም በመዝረፍ ተግባር ውስጥ መጠመዳቸው ፈጦ እንዳይታይ ይጋርዳል:: ሌላው ምርጫው የተጭበረበረ ቢሆንም የሕዝብ ተሳትፎ እስከታየበት ድረስ ገዢዎቹ እራሳቸውን ትክክለኛና ተቀባይነት (legitimate) ያላቸው አድርገው እንዲቆጥሩና ሕዝብም ይህን አምኖ እንዲቀበል ለማስገደድ ይረዳል:: በምርጫ ወቅት የሚታዩ ግድፈቶችም ሆኑ ያፈጠቱ ውንብድናዎች በእነዚህ ድሃ አገሮች ውስጥ እስከሆነ ድረስ የተከሰቱትና በሥልጣን ላይ ያሉት ቡድኖችም የምዕራቡ አለም ወዳጆች እስከሆኑ ድረስ ችግሮቹ የዲሞክራሲያዊ ግንባታው ሂደት አካል ተደርገው እንዲወሰዱ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረትና የሚዲያዎች ቅስቀሳም ይደረግበታል::

ሁለተኛው ሂደት ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ማካሄድ የሚቻለው ነጻ የፖለቲካ መድረክ፣ ነጻነት የሚሰማውና የሌሎችንም ነጻነት የሚያከብር መንግሥት፣ በነጻነት ማሰብና ሃሳቡንም በነጻነት መግለጽ የሚችል ሕዝብ፣ በነጻነት መደራጀትና መንቀሳቀስ የሚችሉ ጠንካራና ተፎካካሪ የፖለቲካ ኃይሎች እና ነጻ ተቋማት በተለይም ገለልተኛ የሆኑ ምርጫ አስፈጻሚዎችና የፍትሕ ተቋማት ሲኖሩ ብቻ ነው ከሚል እምነት ይመነጫል:: ይህ ደግሞ በወያኔ ዘመን እስካሁን ያልታየና ወደፊትም እነዚህ ነገሮች በሂደት ሊሟሉ ስለመቻላቸው ምንም አይነት የሚታዩ ምልክቶች፣ ዋስትና ወይም መተማመኛ ሊሆን የሚችል ነገር የለም:: እንዚህ ፖለቲካዊና ተቋማዊ አደረጃጀቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች ጭርሱኑ በሌሉበት ሁኔታ ነጻ ምርጫ ሊካሄድ አይችልም:: ያለፉት አይነት ምርጫዎች ቢካሄዱም ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ቀላል ነው:: ሰለዚህ ምርጫው ሊሆን የሚገባው በቅድሚያ የሕዝብን ነጻነት ማረጋገጥ ወይም በግዞት ውስጥ ሆነን ወያኔ የመረጠልንን ሕይወት መቀጠል ነው:: የእነሱን ቋንቋ ልጠቀምና ባጭሩ “ሃርነት ወይስ ባርነት”::

ይህ የሁለተኛው ሂደት በሕዝብ እምቢተኝነት ላይ የተመሰረተና ፍጹም ሰላማዊ በሆነ የትግል ሂደት ሊመጣ የሚችል ስኬት ነው:: ብዙዎች በሕዝብ እምቢተኝነት ላይ የተመሰረተን ሰላማዊ ትግል ከምርጫ ውድድር ጋር ሲያምታቱት ይሰታዋል::  በአገሪቱ ውስጥ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች አለመሟላት ወይም በነጻነት የመደራጀት፣ የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመግለጽና ተቃውሞ የማድረግ መብቶችና ነጻነቶች አለመኖርን ለሰላማዊው ትግል ማክተም እንደ አስረጂነት ያቀርቡታል:: ይህ እጅግ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው:: የእነዚህ ሁኔታዎች አለመሟላት የሚያሳየው በምርጫ ሂደት ተወዳድሮ ሥልጣን መያዝ የሚቻልበት እድል አለመኖሩን በቻ ነው:: እነዚህ ነጻነቶች በተከበሩበትና ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ የተወሰኑ ነገሮች እንኳን ከተሟሉ ሂደቱ ሰላማዊ ትግል መሆኑ ቀርቶ በፓርቲዎች መካከል የሚደረግ ውድድር ነው የሚሆነው:: በአሜሪካም ሆነ በሌሎች ዲሞከራሲያዊ ሥርዓት በጎለበተባቸው አገሮች ፓርቲዎች ለሥልጣን ይወዳደራሉ እንጂ ሰላማዊ ትግል ውጥስ አይደለም ያሉት:: ብዙዎቹ ይህን የትግል ምዕራፍ ከዘጉ ዘመናቶች ተቆጥረዋል:: ሰላማዊ ትግል የሚካሄደው እነዚህ ነጻነቶች ፈጽሞ በሌሉበት፣ አፈና እና ጭቆና በተንሰራፋበት የአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ ነው:: ትግሉም ጠመንጃ ያነገበና በኃይል ሕዝብን በሚደፈጥጥ አካል እና በልበ ሙሉነትና ከፍ ባለ የመንፈስ ልዕልና ተሰባስበው ሕዝብንና አገራዊ ዕራእያቸውን ጋሻ በማድረግ ያለ ነፍጥ ሥርዓቱን በሚያርበደቡዱ የሰላም መልዕክተኞች መካከል ነው:: አንደኛው ወገን ይገድላል፣ ያስራል፣ ያሰቃያል:: ሌላኛው ወገን እየሞተ፣ እየታሰረ፣ እየተደበደበና እየተዋከበም ስለ ነጻነት፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ እኩልነት፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ ሰላምና ስለ ሕግ የበላይነት በአደባባይ ይዘምራል፣ ይሰብካል፣ ሕዝብን ያደራጃል፣ ይታገላል::

ከወያኔ የአገዛዝ ሥርዓት ለመላቀቅ በ1997ቱ ምርጫ ወቅት ታይቶ የነበረው የሕዝብ ተነሳሽነትና የተጀመረው ሰላማዊ ትግል ሥርዓቱ በወሰደው የጭቃኔ እርምጃ ቢቀለበስም በአገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትቶት ያለፋቸው በርካታ ነገሮች አሉ:: ከዚህ ሂደት ትምህርት በመውሰድ የተጀመረውን ሰላማዊ ትግል ለመቀጠል በአገር ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ባርቲዎች እየከፈሉት ያሉት መስዋትነት ሊበረታታና ሊደገፍ የሚገባው ነው:: በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ ደጋፊዎችና አመራሮች እንዲሁም የዘጠኙ ፓርቲዎች ጥምረት በመባል የሚጠሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያሳዩ ያሉት እንቅስቃሴና ከሥርዓቱ ጋር የገጠሙት የእምቢተኝነት ግብግብ ሰላማዊ ትግልን በኢትዮጵያ ውስጥ ማካሄድ እንደሚቻል ብቻ ሳይሆን መጀመሩንም ያረጋግጣል:: ሕግን ማክበርና በሕግ የበላይነት ማመን ከእያንዳንዱ ዜጋ ይጠበቃል:: ግድታም ነው:: ይሁንና ዜጎች በዚህ ግዴታ የሚወሰኑት እያንዳንዱ ሕግ የሕገ-መንግሥቱን የበላይነት እስካልጣሰና በውስጡም የተደነገጉትን መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ባረጋገጠ መልኩ እስከ ተደነገገና በአግባቡም እስከ ተተገበረ ድረስ ብቻ ነው:: ልክ እንደ ደቡብ አፍሪቃው አፓርታይድ ሕግን የማፈኛ መሳሪያ አድርጎ በሚጠቀም ሥርዓት ውስጥ የሚደረግ ሰላማዊ ትግልና ሕዝባዊ እምቢተኝነት የዜጎችን መሰረታዊ ነጻነቶችን ለሚያጠቡ ወይም ጭርሱኑ ለሚያግዱ ሕጎች፣ ደንቦችንና መመሪያውችን አለመገዛትንም ይጨምራል:: በአገር ውስጥ ያለውም ሆነ ከአግር ውጭ ያለው የአገሩ ጉዳይ የሚያሳስበው ኢትዮጵያዊ ለእነዚህ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ብዙ መከራዎችን እየተቀበሉ አንባገነናዊ ሥርዓትን ታሪክ አድርገው ለማስቀረት ከሚታገሉ መንፈሰ ጠንካራ ኢትዮጰያዊያን ጎን በመቆም ትግሉ እንዳይደናቀፍና አገሪቱም አሰከፊ ወደ ሆነ ደም አፋሳሽ ሁኔታ እንዳታመራ ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል::

 

አንባገነናዊ ሥርዓትን ታሪክ አድርገን ለማስቀረት ከሰላማዊ ታጋዮቹ ጎን እንቁም!

በቸር እንሰንብት!

ያሬድ ኃይለማርያም

 

እየተደረገ ያለዉን በዘርኝነት ላይ የተመሠረተ የጥፋት ቃለ መሃላ ማክሸፍ የእያንዳንዱ እትዮጵያዊ ነኝ ባይ ሁሉ ግዴታ ነው ፤

$
0
0

ከአየነው ብርሃኑ

ኢትዮጵያዉያን የዉጭ ጠላት ሲነሳባቸዉ የዉስጥ ልዩነታቸዉን ወደ ጎን በመተዉ ጠላትን ድባቅ የመምታት አቅሙ እንዳላቸዉ የሩቅም ሆነ የቅርብ ታሪካችን ነዉ።

ከቅርቡ እንኳን ብንነሳ በሻቢያና ወያኔ የጥቅም ግጭት ምክንያት በተነሳ ጦርነት ሮጠዉ ያልጠገቡ ወጣቶች የፈንጅ ማምከኛ እየሆኑ ዉድ ህይወታቸዉን አሳልፈዋል።

ወያኔ ለራሱ ህልዉና ማጠናከሪያ ቢጠቀምበትም የጦርነቱ የመጨረሻ ዉጤት ለኢትዮጵያ ያደላዉ  ከኢትዮያዊነት ስሜት በመነጨ ወኔ መሆኑ አይዘነጋም።

አዎ ወያኔ እና ጀሌዎቹ ከኋላ ፤ በሺህዎች  የተቆጠሩ ወጣቶች ግን በግንባር ቅደምትነት ተሰልፈዉ የቦንብ ማምከኛ በመሆናቸዉ የጦርነቱ አቅጣጫ ተቀየረ። በዚህ እልቂት ኢትዮጵያዉያን እናቶች የሃዘን ማቅ ለበሱ። ወያኔም በሥልጣን መንበሩ ላይ መቆየቱን አረጋገጠ።

ጭር ሲል አልወድም የሚለዉ ወያኔ ዛሬም የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ነው። የማይደፈር ሃይል መሆኑን ለማሳየትም በርጥባን ከጌቶቹ ያገኘዉን የጦር መሳሪያ ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ህዝብን በማሸበር ላይ ነዉ።

በጦር ሃይሉ ዉስጥ ያሉ የሌላ ብሄር የጦር መሪዎችን በማባረር በአንድ ዘር ላይ የተመሠረተ የግድያ እና የጥፋት ሃይሉን በማዘጋጀት ላይ ዪገኛል።

ለዚህ ተግባር የሚዉል  አዲስ ወታደራዊ ቅጥር  ጥሪ እያደረገ መሆኑ ዪታወቃል።

የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጠላት ከሆነችዉ ሱዳን ጋር ወታደርዊ ስምምነት አደረኩ የጋራ ጦርም መሠረትኩ በሚል ለጥቂት ቀናት አደነቆረን።

 

ተጠቅሞ የጣላቸዉን የቀድሞ ሰራዊት አባላት ተመልሰዉ እንዲቀላቀሉት በተለያየ መንገድ ጥሪ እያደረገ ነው። ሁሌ እኔ ብቻ ላሞኛችሁ የሚል የደንቆሮዎች ዘይቤ። መልሱ ግን ሞኚህን ፈልግ ሆነ  !!

ለመሆኑ ይኸ ሁሉ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም ከምን መጣ ? ይህ የድረሱልኝ ጥሪ መነሻዉ ምንድን ነዉ፡የዉጭ ጠላት አልወረረን!!!!!

የወንድ ልጅ ሞቱ የሚጀምረዉ ያደረገዉን የረሳ ጊዜ ነው ይላሉ አበዉ ሲተርቱ።

ሃብት አደንቁሮአቸዋልና !! ወያኔን ለማጥፋት አዲስ አበባም ጫካ መሆኑን ለመገንዘብ የዕዉቀት አድማሳቸዉ አልፈቀደላቸዉም ።

ያም ሆነ ይህ ግን ምኞታቸዉ የተሳካ ጥያቂያቸዉም በአግባቡ እየተመለሰላቸዉ ባለበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል። የስብሃት ነጋ የዘር ጥላቻ፡ የአባይ ጸሃየ የዕምነት ተቋማትን የማፈራርረስ ሴራ፤የአዲሱ ለገሰ ከጡረታ መመለስ ከውዲያ ወዲህ መፈራገጥ፤ የበረከት በስብሰባ ላይ ራሱን ጥሎ ከመዉድቅ  ዉጭ ፋይዳ ያለዉ ሥራ ለመከወን  ከማይችልበት ደረጃ ላይ መድረስ  ወይም ደግሞ ብአዴን በግንቦት ሰባት  ኦህዴድንም በኦነግነት መፈረጅ ከዉድቀት አያድናቸዉም ።

የእነ ደብረጽዮን እና ጌታቸዉ አሰፋ ድንበር ዘለል የዉንብድና ተግባር አልፈየደም ። የህዝብ ወገኖችን እያደኑ መያዝ፡ በአለም ላይ አለ የተባለ የማሰቃያ መንገድ ሁሉ በታጋዮች ላይ እንዲፈጸም ማድረግ በተጠናወታቸዉ የዘር ጥላቻ  እየተወጠሩ ለመኖር እና ያለ አግባብ በተካበተ  የሀገር ሃብት እየተንደላቀቁ ለመኖር  መፍትሄ አልሆነም።

በሌላ መልኩ  የመሃል አገር ህዝብ የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ ዘይቤ በመበጣጣስ አንድነቱን አጠናክሮ ወያኔን ጥግ ማስያዝ ከጀመረ ሰነባበተ ። የህዝብ ጉልበትም መጎልበትና መፈርጠም ጀምሮአል ።

ሰላሙና ተቻችሎ መኖሩ ይበጃል በሚል እንጂ ለሌላዉማ ከእናንተ በተሻለ  እኛም እናዉቅበታለን የሚሉ አንበሶች ብቅ ብቅ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል።  አንድነታቸዉንም  አጠናክርው ለመጨረሻዉ ፍልሚያ በትጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ ።

ለዚህም  የትግራይ ረመጦች በአንድ በኩል የግንቦት 7 ፤ የአርበኖች ግንባርና ሌሎችም አንበሶች በሌላ በኩል ለዎያኔ እኩይ ተግባር ምላሽ ለመስጠት ዝግጅታችንን ጨርሰናል በሚል የድል ችቦ እየለኮሱ ያሉት ህያዉ ምስክር ነው።

ወያኔ አንድ አርጋቸዉንና ሌሎችንም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ያዘ፤ አሰቃየ ፤ የአካልም የመንፈስም ጉዳት አደረሰ ይህን ሲያደርግ ግን ያለኪሳራ አይደለም። መቃብሩን እየቆፈረ መሆኑን  ራሱ ወያኔም ያዉቀዋል ።

ለትግራይ ረመጦችና  ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል መጠናከር መሠረት የሆነዉን  አንዳርጋቸዉ ነዉና ። አንዳርጋቸዉን መያዝና ማሰቃየት ዉድቀቱን እያፋጠነለት መሆኑን ወያኔ ራሱ ከተረዳዉ ቆይቶአል።

በሌላ በኩል እስኪ የዘርኝነት መሃንዲሶቹን አንድ አንድ ጥያቄዎች እንጠይቅ፡

ይኸ የህዝብ ትግል  የጦርነት ነጋሪት በመጎሰምና የድረሱልኝ ለቅሶ በማላዘን ወደ ኋላ ይቀለበስ ይሆን እንዴ አቶ ስብሃት?

የስንት ቀን ፋታ የምታገኙ ይመስልሃል አቶ አባይ?

በርግጥ የአንተና የስዩም መስፍን ማገገም፡ ወደ ሥራ መመለስና  መንፈራገጥ መፍትሄ  ይሆን እንዴ አቶ አዲሱ ለገሠ?

ሃዉልትህ  ምትሃታዊ ሃይል ኖሮት የልቀቁኝ በቃኝ ጥያቄህን  ወደ ኋላ እንድትል ይረዳህ ይሆን ጀኔራል ሳሞራ?

በአፈናና በስቃይ ተግባራችሁ ግለሰቦችን ከማሰቃየት በዘለለ የህዝብን ትግል አፍናችሁ  ከዛሬ  ነገ ምን ይከሰት ይሆን ከሚለዉ የፍርሃት ቆፈናችሁ የምትላቀቁ ይመስላችኋል እነ ደብረ ጽዮን ፤ ጌታቸዉ በላይ እና የአፈና ቡድናችሁ?

በጭራሺ ከንቱ ድካም። ከንቱ ልፋት። የኢትዮጵያ ህዳሴ መቃረቡን የህዝብ የነጻነት ጮራ እየፈነጠቀ መሆኑን ምነዉ ያኔ የሱዳኑ አባታችሁና የአምልኮት ጣኦታችሁ ሲሞት በቀብር የተገኙት እነስዩም መስፍን አልነገሯችሁም ነበር እንዴ?

ኢትዮጵያዉያንን እርስ በርስ ለማገዳደል እያሰባችሁ ያላችሁት የጥፋት ድግስ የማይሳካ ጊዜዉ ያለፈበት ዘዴ ነው። የተበላ እቁብ !!!

በሀገራዊ ስሜትም ሆነ በግል የኢኮኖሚ ችግርህ አሁን ያለዉን የመከላከያ ሠራዊት የተቀላቀልክ ጭቁን የኢትዮጵያ ሠራዊት አባል ቆም ብለህ አስብ። እነዚህ የቀን ጅቦች ለጥፋት እያዘጋጁህ መሆኑን ለአንዲት ደቂቃም ቢሆን መዘንጋት የለብህም።

የባህር በር እጠብቃለሁ እንዳትል ወያኔ አገርህን የባህር በር አልባ አድርጎልሃል። ድንበር አስከብራለሁ እንዳትል ወያኔ የአገርህን ድንበር እየቆራረጠ ለአገራችን ጠላቶች ለገጸ በረከትነት እያቀረበልህ ነው።

ወያኔ ወኔህን ሰልቦ ብሄራዊ ወኔህን ገፎታል። እንድ ለአምስት እንድትደራጅ ፡መሪህ ከወርቁ ዘር የወጣዉ  ብቻ እንዲሆንና አንተ አንድ ካርታ ጥይት ብቻ እንዲኖርህ መሪህ ግን እስካፍንጫዉ እንዲታጠቅ እየተደረገ ያለዉ ለምን ይመስልሃል። በዚህ አይነት ጥርነፋ ከወገኖችህ ጋር እንድትዋጋ ከኋላ ሆነው ሊነዱህ እንደሆነ ግን ተገንዝበኸዋል?

ይኸን ከንቱ የወያኔ ምኞት ለማክሸፍ ከነጻነት ታጋዮች ወገኖችህ ጋር ጊዜ ሳትሰጥ ተቀላቀል።

ይህን በማድረግህ አገርህን ከነዚህ የባንዳ ዉላጆች ነጻ ታወጣለህ ። በስቃይ ላይ የለዉን ወገንህን እንባ ትጠርጋለህ።

በዘር ማንነት ፖለቲካ ተሰብካችሁ ከሌላዉ በበለጠ ጀግንነት የእናንተ ብቻ እንደሆነ እየተሰበካችሁ ያደጋችሁ የመሪነት ቦታዉን የያዛችሁና እኛ ከኋላ ሆነን ሌላዉን ኢትዮጵያዊ ከፊት በማሰለፍ የጌቶቻችንን የስልጣን ዕድሜ እናራዝማለን ብላችሁ  በዘር ላይ የተመሠረተ  ቃለ መሃላ የፈጸማችሁ ። ይህ መሃላ ግን መፈራረሱን ወደ ህዝብና ወደ ህሊናቸዉ ተመልሰዉ ወደ ዕዉነታዉ ዓለም በተቀላቀሉት ሻምበል ግደይ ሳሙእል እና ቴክኒሺያን ፀጋብርሃን ግደይ ላይ ያዎረዳችሁት የከሃዲነት ዉንጀላ አብይ ምስክር ነው።

በከንቱ ዉዳሴ ተወጥራችሁ ህዝብን አሸንፈን በሥልጣናችን እንቀጥላለን ብላችሁ የምታስቡ የጦር መሪ ነን ባዮች ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ። የኢትዮጵያ ህዝብ ከእናንተ ጋር ምንም ችግር የለበትም። ታሪኩ፡ ባህሉ ወጉና ልምዱ በአብሮ መኖር በኩል ችግር እንደሌለበት ምስክሮች ናቸዉና!!!

በሌላ በኩል ግን የትግራይ ረመጦችም ሆኑ የግንቦት ሰባት አንበሶች ለአንድ አላማ  ለኢትዮጵያዊነት እና በሰላም ተቻችሎ ለመኖር ነዉ እየዘመሩ ያሉት።

ይህ ሲባል ግን ስብሃት ነጋ ከዘር ጥላቻዉ እንዲላቀቅ ሱባኤ እንዲገባ አይደረግም ማለት አይደለም።

አባይ ጽሃይም ላለበት ሃይማኖትን የማፍረስ አባዜ በአርባ ቀን ጥምቀት ለመንጻት ቄስ አያጠምቀም ወይም ሼህ እይጎበኘዉም ማለት አይደለም። የትኛዉ እንደሚፈዉሰዉ ምርጫዉ የራሱ ነው።

የነ ደብረጽዮን ፤ ጌታቸዉ አሰፋና አምስቱ የአፈና ቡድናችዉ  የመሰረቷቸዉን ድብቅ ያማሰቃያ ቦታዎች ይፋ እንዲያደርጉ ፤ ያጠፏችዉን ኢትዮጵያዉያን  ዝርዝር እንዲያቀርቡ  ህዝብ አይጠይቃቸዉም ማለትም አይደለም።

ሳሞራ የኑስ ምን ኣልባት ለዚያ ከደረሰ የጀኔራልነት ሃዉልቱን ተሸክሞ በአደባባይ በመዞር ለዚህ ያበቃዉን ገድል እንዲተርክለት ህዝብ ይጠቅ ይሆናል ።

የብአዴን፤ ኦህዴድና ኦህዴድ ፈረሶችም ቢሆኑ በሀገር ላይ ክህደት ከፈጸመዉ ደመቀ መኮነንና በንጹሃን ደም እጁ ከተጨማለቀዉ ሃይለ ማርያም ደሳለኝ እና ከመሳሰሉት በስተቀር ሌሎቹ የማስመሰያ የዘር ጭምብላቸዉን አዉልቀዉ ለአጠፉትም ጥፋት ይቅርታ ጠይቀዉ ወደ እዉነተኛ ማንነታቸዉ እንዲመለሱና የ 24 ዓመት ድራማዉን እንዲተርኩለት የኢትዮጵያ ህዝብ መጠየቁ የሚቀር አይመስለኝም።

የትናት ሺፍቶች የዛሬ ሚሊዮነር ጀኔራሎች የሃብት ምንጫቸዉን እንዲነግሩን መጠየቅ የኢትዮጵያዊነት መብታችን  መሆኑም መዘንጋት ያለበት አይመስለኝም።

ዕዉነት ዕዉነት እላችኋለሁ ። ዛሬ ወገኖቻችን እየታደኑ በተገኙበት እርምጃ የሚወሰድባቸዉ ፤ ወደ ወህኒ የሚወረወሩት  እና ሁሉም ስቃይ በህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለዉ ወያኔ በጣዕር ላይ በመሆኑ እርምጃዎቹ ሁሉ የደመነፍስ በመሆናቸዉና  በዚያዉ ከዘር ጥላቻ በመነጨዉ ጥላቻዉ  ነው።

እናም እላችኋለሁ ግንቦት ወር  የወያኔ የምርጫ ድራማ  የምናደምቅበት አይሆንም። በሌላ በኩል ግን ወያኔን አሽቀንጥረን ጥለን ለመቻቻል አብሮ ለመኖርና  ያገራችንን የወደፊት አካሄድ የምወስንባት ወር ነው መሆን ያለባት ግንቦት ወር።

ይህን ዕዉን ለማድረግ በጥቅማ ጥቅም ተገዝተህ ለዘረኛዉ ቡድን ሰግደህ ያደርክ ሁሉ  ወደ ህሊናህ ተመልሰህ ከህዝብ ተቀላቀል።

ለግል  ጥቅምህ ተገዥ በመሆን ከዚህም ከዚያም አይደለሁም እያልክ ሌላዉ ሳይሆን ራስህን እያታለልክ የምትኖር  የወገንህን ብሶት አስብ ከጎኑም ለመሰለፍ ጊዜ አትዉሰድ።

ባጋጠማችሁ መልካም አጋጣሚ ሥልጣን ላይ ተኮፍሳችሁ ያካበታችሁት ያገር ሃብት የማሰብ ህሊናችሁን ለሸፈነው ዘረኞች የእስካሁኑ ይበቅል ። የያዛችሁትን ለመብላት ከበቃችሁ ከበቂም በላይ ሁሉንም አድርጋችኋል። ይህ ግን እንዳይቀጥል ህዝብ በቃ ብሎአል እና ለሁሉም አይንት ጥፋት ብላችሁ ከምርጥ ዘራችሁ ዉስጥ ያዘጋጃችሁት የጥፋይ ሃይል አያድናችሁምና ለንስኃ ሞት የምትበቁበትን መንገድ ፈልጉ የምነት ድሃዎች ። ህዝብ  በቃ ብሎአልና!!!

የጥፋቱን መጠን መቀነስ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለሚል   የሆነ ሁሉ ሃላፊነት ነዉ።

ከዚህ በተረፈ  ግን ሁሉንም ሥራዉ  ያዉጣዉ !!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

 

comment pic

የናቁት ያስቀራል ራቁት! የትግሬ ወያኔ ዐማራን ከመጨፍጨፍ እና ከመጥላት አልፎ ንቆታል –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

የትግሬ ወያኔ ዐማራን ከመጨፍጨፍ እና ከመጥላት አልፎ ንቆታል፤  ይህ ደግሞ ነገ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል!

Moreshአንድ ሰው ወይም ቡድን ሌላን ሰው ወይም ቡድን በጅምላ መጥላት ከጀመረ፣ የጠላውን ሰው ወይም ቡድን በቀጥተኛ እና በተዘዋዋሪ መንገድ ለማጥፋት ይጥራል። አልፎ ተርፎ ይህ ሰው ወይም ቡድን የጠላውን ሰው ወይም ቡድን መናቅ ሲጀምር እርሱን ለማጥፋት ሰበብ አይፈልግም። ንቀት ያሳደረበትን ሰው ወይም ቡድን «ምን ያመጣል? ምንስ ያደርገኛል? ከየትስ ይደርሳል?» በሚል ትዕቢት «ጠላሁት፣ ጠላቴ ነው፤» ያለውን ግለሰብ እና ቡድን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ጥቃት ይሰነዝርበታል፣ ይገድለዋል፣ ያዋርደዋልም።

ሰሞኑን የትግሬ-ወያኔ በባሕርዳር ከተማ «የእምነታችን ሥርዓት መፈጸሚያ ቦታ ለባለሀብት ሊሰጥብን አይገባም!» ብለው ለራሱ ለአገዛዙ ባለሥልጣኖች አቤት ለማለት በተሰለፉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ምዕመናን ላይ የወሰደው የግድያ፣ የድብደባ እና የእስራት እርምጃ፣ ዐማራውን እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖትን ከመጥላት አልፎ የናቃቸው መሆኑን ዓይነተኛ ማሣያ ነው። የትግሬ-ወያኔ ዐማራውን ከጥላቻ አልፎ ንቆታል የምንለውም ባለፉት ፵(አርባ) ዓመታት በዐማራው ላይ በፈጸማቸው ተከታታይ  የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት እርምጃዎች፣ ከዐማራው ወገን ተመጣጣኝ የመልስ ምት ባለማግኘቱ፣ ጥላቻው ወደ ንቀት እና ማንአህሎኝነት የተሸጋገረ እንደሆነ ድርጊቶቹ  አፍ አውጥተው እየተናገሩ ነው።

ገና ከጥንስሱ የትግሬ-ወያኔ በዐማራው ላይ የገነባው ጥላቻ ሥር የሰደደ እና የደነደነ በመሆኑ፣ ዐማራው የትግሬ ደመኛ ጠላት እንደሆነ በመስበክ የትግሬ ነገድ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ዐማራን እንዲያጠፋ ሰበከ። የተሰበከውን የነገዱን አባል አደራጅቶ እና አስታጥቆ ያገኘውን ዐማራ ሁሉ ባሻው መንገድ እንዲገድለው አዘዘ። በዚህም ምክንያት በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሰቲት፣ በራያ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲ፣ በወለጋ፣ በኢሉባቡር፤ በሲዳሞ፣ በከፋ፣ በአሶሳ፣ በመተከል፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ወዘተርፈ በ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ጌዜ ውስጥ ብቻ ከ5 ሚሊዮን  በላይ ዐማራ  ከምድረ ገጽ አጠፋ።

በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ መነኮሳት እንኳን ርኅራሄ አይደረግላቸውም

bahrdar 7የትግሬ-ወያኔ በዐማራው ላይ የገነባው የጥላቻ መጠን እጅግ የከፋና የከረረ መሆኑን ማሣያው ዐማሮች ናቸው ባላቸው ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው የአገዳደል ሁኔታ እስካሁን በዓለም ላይ የነበሩ ጨካኝ እና አረመኔ የተባሉ አምባገነኖች ያልፈጸሙት ዓይነት የአገዳደል ሥልት ወይም ዘዴ መጠቀሙ ነው። እርጉዞች ሆዳቸው በሳንጃ ተቀዶ ሽል እንዲሰለብ ሆኗል። መነኮሳት ከነሕይዎታቸው ወደ ጥልቅ ገደል ተወርውረው ተሰቃይተው እንዲሞቱ ተደርጓል።  በቤት ውስጥ ተዘግተው  በእሳት ነደው እንዲሞቱ ሆኗል። የራሳቸውን መቃብር ራሳቸው በቁመታቸው ልክ ቁልቁል ቆፍረው እስከ አገጫቸው በመክተት መልሶ አፈር በመሙላት አጓዳ ነድተው አሰቃይተው የገደሏቸው አያሌዎች ናቸው። እንደ ጋማ ከብት ቁስል ማዳኛ በፈላ ብረት(ጉባ) የተተኮሱ ብዙዎች ናቸው። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ያነገቡትን «ዓርማ» ከሰዎች ጀርባ ላይ በፍላት አትመዋል። በአደባባይ በአርኣያ ሥላሴ የተፈጠረን ሰው ርቃኑን  በማቆም ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ሚስት የባለቤቷን የመራቢያ አካል በገመድ አሥራ እንድትጎትት አድርገዋል።  ይህ ሁሉ የትግሬ-ወያኔ ድርጊት ከጥላቻ አልፎ በዐማራው ላይ ያለውን ንቀት የሚያሣይ ለመሆኑ መጠራጠር አይቻልም።

bahrdar 3

የትግሬ-ወያኔ ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ከመፈረጅ አልፎ፥ ዐማራን፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖትን እና የአማርኛ ቋንቋን ሣያጠፋ ለአፍታም እረፍት እንደማይኖረው በፕሮግራሙ ቀርጾ የሚንቀሣቀስ ድርጅት ነው። ለዚህም ተግባራዊነት «የእኔ ነገድ ነው» የሚለውን ሕዝብ በነቂስ አንቅቶ፣ አደራጅቶ እና አስታጥቆ በዐማራው ሕዝብ ላይ በማዝመት ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት  ብቻ ከ5 ሚሊዮን የማያንስ ዐማራ ከምድር ገጽ አጥፍቷል፤ አያሌዎችን አሰድዷል፤ አሥሯል፤ አሰቃይቷል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዐማሮችን በሰውነታቸው እና በኢትዮጵያዊነታቸው የሚገባቸውን እና በፈለጉበት አካባቢ የመኖር እንዲሁም በመረጡት የሥራ መስክ የመሰማራት የዜግነት መብታቸውን ገፎ ለተመጽዋችነት እና ለአገር አልባነት ዳረጓቸዋል። ስለሆነም ሰሞኑን የትግሬ-ወያኔ በባሕርዳር ከተማ ሰላማዊ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ምዕመናን ሰልፈኞች ላይ የወሰደው «የፈሪ በትር እና የላም አሸናፊነት» ድርጊት በዐማራው ላይ ያለውን ጥላቻ እና ጥላቻውም ወደ ከፍተኛ ንቀት መሸጋገሩን በተጨባጭ ያሣያል።

bahr dar 2

በዚህ የጅምላ ግድያ እና አፈና ላጠፋው ዐማራ፣ ከወገኑ  ከዐማራው «ለምን?»  ብሎ ጥያቄ ባለማነሣቱ ይኸውና «ጉድጓዳቸው የተማሰ፣ ልጣቸው የተራሰ» መነኩሲት እናት ልጅ እንዳልወለዱ፣ ተቆርቋሪ ወገን እንደሌላቸው ተቆጥረው መደብደባቸው እና እጃቸው መሰበሩ የሚሰጠን ቀጥተኛ ትርጉም «ዐማራው ከዚህ በኋላ ምን ያመጣል?» የሚል ንቀት የወለደው ትዕቢት መሆኑን ማንም አይስተውም። የትግሬ-ወያኔ በሰላማዊ ሰልፈኞቹ ላይ ያደረሰው ግድያ እና ድብደባ የንቀቱ መጠን የቱን ያህል የናረ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

«ጎጃም ተቃጠለ ዐባይ እስከ ዐባይ፣በታሪክ ንፅፅር ሲታይ በባሕርዳር ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታዮች ላይ የተወሰደው ጥላቻ እና ንቀትን የቀላቀለ እርምጃ፤ ዐፄ ዮሐንስ ፬ኛ በተከታታይ ጊዜ በጎጃም ሕዝብ ላይ ያደረሱትን ጥፋት ያስታውሰናል። ዐፄ ዮሐንስ ፬ኛ ጎጃምን ከአባይ እስከ አባይ ሲያቃጥሉ፣ እንኳን ሰውን የቤተክርስቲያን ጽላትም አልማሩም ነበር። አፄው በደብረማርቆስ (የያኔዋ መንቆረር) ዙሪያ በጎዛምን እና ማቻከል ወረዳዎች ጦራቸውን አስፍረው ቤተክርስቲያን ሲያቃጥሉ እና ጽላት ሜዳ ላይ ሲጥሉ የተመለከቱት አቡነ ሉቃስ፦ «ደርቡሽን አጠፋለሁ ብዬ መጣሁ ያልከው ለጎጃም አንተ ደርቡሽን ሆንክበት፤» ብለዋቸዋል። አፄው በሁለት ተከታታይ የጥፋት ዘመቻቸው በጎጃም ሕዝብ ላይ ባወረዱት የጅምላ ጭፍጨፋ አስለቃሾች፦

ትግሬ ቅጠል ይዞ ሊያጠፋው ነዎይ፤

በላይኛው ጌታ በባልንጀራዎ፣

በቅዱስ ሚካኤል በጋሻ ጃግሬዎ፣

በጽላተ-ሙሴ በነጭ አበዛዎ፣

ጎጃምን ይማሩት ፈሪም አንልዎ፤»

ብለው እንደነበር ታሪካችን ያወሳል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የትግሬ-ወያኔ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ በጎጃም ሕዝብ ላይ ባደረሰው ግድያ እና እንግልት፣ «ታሪክ ራሱን ይደግማል» እንደሚባለው  ሆኖ፣ የዐፄ ዮሐንስ ፬ኛ የልጅ ልጆች ተመሳሳይ ግፍ በመፈጸማቸው እንዲህ ተባለ፣

« ጦማችን ባይሰምር፣ ጸሎታችን ባይደርስ፣

በልጅ ልጅ መጡብ ዐፄ ዮሐንስ፤»

የዐማራው ትውልድ በተከታታይ ታሪክ እና በዛሬውም ነባራዊ ሁኔታ ከትግሬ በሚወለዱ ሰዎች ተጠቂ መሆኑ እየታወቀ፣ ለተፈጸመበት እና እየተፈጸመበት ባለው ግፍ ኢትዮጵያዊነትን በማስቀደም «ሁሉም ይቅር፣ ለትናንት ሳይሆን ለነገ እንኑር» በማለቱ፣ ይኸውና ከጥላቻ አልፈው በመናቅ መነኮሳት እናቶቻችን፣ አዛውንት አባቶቻችን፣ በእኛ ልጆቻቸው በመከበሪያቸው ጊዜ ለውርደት እና ለመከራ ተዳርገዋል። እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን ለሞት እና ለስደት፣ ለተዋራጅነት ተጋልጠዋል። ይህ ሁላ የሚሆነው ዐማራው ዝምታን እና ትዕግሥትን አለቅጥ በማብዛቱ፣ ወይም የማይቀረውን ሞት በክብር ከመሞት ተዋርዶ ለመሞት በፍርሃት ቆፈን ተጨምዶ በመያዙ ነው።

በትግሬ-ወያኔ ታጣቂዎች የተገደለ የባህር ዳር ነዋሪ አስከሬን

 

ስለሆነም እኒህን እናት መነኩሲት ያየህ፣ እናታችን እማማ ኢትዮጵያ እንደደማች፣ የእያንዳንዳችን እናት እንደተመታች ቆጥረን ኅሊናችንን ልናስቆጣው ይገባል። የአባቶቻችንን፣ የእናቶቻችንን ፣የወንድሞቻችንን እና የእህቶቻችንን ደም ተሸክመን መጓዙን ከዚህ በኋላ ልንገታው ይገባል። የዐማራውን ሕዝብ የቆየ ክብር እና ዝና፣ መልካም ስም እና ጀግንነት፣ በእኛም በልጆቹ ደም እና ኅሊና ውስጥ ያለ መሆኑን ለማሳየት ጊዜ ልንወስድ አይገባም። ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታ እጅግ ብዙ ጊዜ ነው። ከእንግዲህ  ወዲያ «ከእኛም ቤት እሳት አለ፣ የእኛም እጅ የብረት አለሎ ነው፣ ማንም ሊጨብጠው አይችልም፤» በማለት የተዋረደ ክብራችንን፣ የጎደፈ ስማችንን፣ የፈሰሰ ደማችንን ለመመለስ ቁርጠኝነቱ ካለን፣ የመጨረሻ ምዕራፍ  ላይ የደረስን ስለሆነ፣ እያንዳንዱ ዐማራ፣ ለወሳኙ ትግል ራሱን ማዘጋጀት ይጠበቅበታል። በተለይ ደግሞ በዐማራው ላይ ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን ማንነት መዝግቦ መያዙ እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ፣ እያንዳንዱ የዐማራ ልጅ በሚኖርበት አካባቢ የወንጀለኞቹን ሙሉ ስም፣ የወንጀሉ ዓይነት፣ ወንጀሉ የተፈጸመበትን ቦታ፣ ቀን እና መሰል  መረጃዎችን በድምፅ፣ በምስል፣ በሰነድ ድጋፍ አጠናቅሮ በመያዝ ለትውልድ የማስተላለፍ ግዴታውን እንዲወጣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል። የትግሬ-ወያኔ ከመጠን በላይ ጠልቶናል። በዐማራው ላይ ለገነባው ጥላቻ፣ ከዐማራው ወገን ተመጣጣኝ የመልስ ጡጫ ባለማግኘቱ፣ ጥላቻው ንቀትን ወልዷል። ከእንግዲህ «የናቁት ያስቀራል ራቁት» ነውና፣ አንተ የተናቅህና የተጠላህ የዐማራ ወጣት፣ ሴት ወንድ፣ አዛውንት፣ ሽማግሌ ሣትል፣ የናቁህ መልሰው እንዲያከብሩህ ክንድህን ማንሳት ይጠበቅብሃል። መከበር የሚገኘው ለራስ ክብር በመስጠት፣ ራስንን በመጠበቅ፣ ራስን በመከላከል፣ «መጡብን» ከማለት ይልቅ «መጣንባችሁ» ሲባል፣ ለሁሉም ነገር «እሺ» ሣይሆን፣ «የለም፣ አይሆንም፣ እምቢ» ማለት ሲቻል ስለሆነ፣ ውርደቱ እና ንቀቱ ከአንድ ቦታ ሊቆም ይገባዋል።

ከሁሉም በላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታዮች ወያኔ ገና «ሀ» ብሎ ደደቢት ሲገባ «መጥፋት አለባቸው» ብሎ የወሰነባቸው ዐማራ፣ የአማርኛ ቋንቋ እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ናቸው። ስለሆነም በባሕርዳር ከተማ የጥምቀተ-ባሕር የታቦታት ማደሪያ ላይ ያሳለፈው ውሣኔ፣ ከዚህ በፊትም በዋልድባ፣ በዝቋላ አቦ እና በሌሎች ገዳማት እና አብያት ክርስቲያናት ላይ የሚያደርሰው ጥፋት ቤተክርስቲያኗን የማጥፋቱ ሌላው ተጨማሪ ርምጃ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል። ስለዚህ እንደአቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል ለኃይማኖታችን ለመሞት መዘጋጀት ውዴታችን ሣይሆን ግዴታችን መሆኑን ተገንዝበን፣ ለማተባችን ቆመን ሰውነታችንን የምናረጋግጥበት ወቅት ላይ የደረስን መሆኑን አውቀን ለተገቢው መስዋዕትነት ዝግጁ መሆን አለብን። በዚህ ረገድ የኃይማኖቱ አባቶች የአርአያነቱን ሚና ሊጫዎቱ የሚገባቸው መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን። በመጨረሻም ለኃይማኖታቸው ቀናዒ ሆነው ሰማዕት ለሆኑት ኃያሉ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በጻድቃን እና ሰማዕታት ጎን በአጸደ-ገነት እንዲያስቀምጣቸው የዘወትር ጸሎታችን ነው። ለሟች ቤተሰቦችም አምላክ  መጽናናቱን እንዲሰጥልን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መሪር ሐዘኑን ይገልጻል።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!


 ህወአት የቆመበት መሬት እየከዳው ነው

$
0
0

ዳዊት መላኩ

እንደሁልጊዜው እያሰረ እና እየገደለ  ለዘላለም ስልጣን ላይ በአንባገነንነት መኖር የሚፈልገው ዘረኛ  ነፍሰ ገዳይ ቡድን በተለመደው መልኩ  የባህርዳር ነዋሪዎችን አካል ጉዳተኞች እና በእድሜ የገፉ አሮጊት እናቶችን ጨምሮ አሰቃቂ  ድብደባ ሲፈጽም አምስት ንጹሀን ዜጎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡መቼም ለመዘርዘር እስኪታክተን ድረስ በዚህ ህዝብ ላይ ያልተፈጸመ የወንጀል አይነት የለም፡፡ በጅምላ  በሶማሌ ክልል የተፈጸመውን ግድያ እና የአሰከሬን ሁኔታ በዘር ልክፍት የተጠመዱት ነፍሰ-ገዳዮች በግፍ ለተገደሉት  አሰከሬን  እንዴት በእግራቸው ይረጋግጡት እንደነበር በኢሳት ቴሌቭዥን ያየነው ሁሌም ከአይናችን የማይጠፋ ምስል እና የስርዓቱን  ሰይጣናዊነት ቁልጪ አድርጎ አሳይቶናል፡፡በጋምቤላ ፣ በአፋር  በኦሮሚያ፣ በደቡብ እንዲሁም  በእስልምና እምነት ተከታዮች የተወሰደው የግፍ ግድያ እና የጀምላ እስራት  በስርዓቱ  ምሬት ምን ያህል የታመቀ ብሶት  እንዳለ የሚያሳይ ነው፡፡

በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ስብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ የተከለከሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮቻቸው በጅምላ እየታሰሩ እና እየተደበደቡ ባለበት ሁኔታ የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች በሀይል ለመጨፍለቅ የሚደረገውን ጥረት ሕዝቡ በራሱ ብሶቱን መቆጣጠር ከማይችልበት ደረጃ አድርሶታል፡፡ታህሳስ 19 ቀን 2014 እ.ኤ.አ የእስልምና እምነት ተከታዮች  በአዲስአበባ  በኑር መስጊድ እና የክርስትና እምነት ተከታዮች በባህርዳር በተመሳሳይ ቀን ያለማንም አነሳሸነት ያካሄዱት ተቀውሞ ለዚህ ማሳያ ከበቂ በላይ ናቸው፡፡አባቶች ሲተርቱ “ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ” ይላሉ፡፡ካለፈው መማር ያልቻለው የወያኔ አገዛዝ በግድያ እና በእስራት እንባገነንነትን ለማስቀጠል ይፈልጋል፡፡የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ  እንኩዋን  ለጊዜው  ወደጎን ትተን የሀገራችንን ያለፉት አራት አስር አመታት ወደ ኋላ ዘወር ብሎ መቃኘት በቂ ነው፡፡በንጉሱ ጊዜ የታየውን የለውጥ ነፋስ ዘውዳዊ አገዛዙ በማናኛውም መልኩ ማስቆም አልቻለም፡፡በደርግ ጊዜ የነፈሰውም የለውጥ ነፋስ በአንድ ቀን 12 ከፍተኛ የጦር መኮነኖችን እና የበታች አመራሮችን በመረሸን ለውጡን ማስቆም እንዳልተቻለ በቂ ማስረጃዎች ቢሆኑም አይናቸውን የሸፈነው ግብዝነታቸው እና የዘር ልክፍታቸው ከዚህ ወጣ ብለው እንዲያስቡ እና ቆም በለው አካሄዳቸውን እንዲመረምሩ አላደረጋቸውም፡፡ዛሬም በእብሪት እና በማንአለብኝነት ተወጥረዋል፡፡

ህወአት ያጠለቀው የሀሰት ካባ እየተቀደደ ገመናውን ፍንትው አድርጎ እያሳየን ነው፡፡ቀደም ሲል  በነ ገብረ-መድህን አርኣያ ፣አብረሃ ደስታ እንዲሁም በሌሎች የተጀመረው ስርዓቱን የመተቸት እና ትግሬነትን ከህወአታዊነት በመነጠል በኢትዮጵያዊነት ከሌሎች ጋር አብሮ ለመታገል የተጀመሩ ለውጦች የሚበረታቱ ናቸው፡፡ በ19/12/2014 ለልምምድ  የተሰጣቸውን MI-35 የውጊያ ሄሊኮፕተርን ይዘው ስርዓቱን ከዱት የአየር ሀይል አባላት  የዘር ግድግዳን ጥሰው ከፍተኛ ሚስጢር የሚጠይቀውን  አኩሪ ገድል ፈጽመዋል፡፡እነዚህ ጀግኖች ባስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲህ ያለ ውሳኔ መወሰናቸው  ሰራዊቱ ምን ያህል በስርዓቱ እንደተማረሩ ያሳያል፡፡ህወአት የተንጠለጠለባቸው ሁለቱ ባላዎች  ሰራዊቱ እና የትግራይ ህዝብን ስውር ደባውን ሲያስፈጽማበው የነበሩት ዛሬ ከጎኑ እየተለዩ ነው፡፡ ህወአት የቆመበት መሬት እንደከዳው በየጊዝው ስርዓቱን ትተው የሚጠፉት የሰራዊ አባላት እና ከተቀዋሚ ጎራ የሚሰለፉት የትግራይ ተወላጆች  ቁጥር መበራከት እንደማሳያ ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡

ህወአቶች እንዲህ በታመቀ እሳተ-ገሞራ ላይ ቆመው እንደዚህ ቀደሙ የህዝቡን ትኩረት ለማስቀየር ዛሬም በተለመደው መልኩ ለማታለል ይሞክራሉ፡፡በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ታሪክ የማይረሳው ግድያ ፈጽሞ የህዝቡን ትኩረት ለማስቀየር ጊምቢ በሚገኙ አማራዎች ላይ ዘራፊዎችን አሰማርቶ ቤታቸው እንዲቃጠል እና በርካቶች እንዲገደሉ አድርገው የዘር ግጭት ለማሰነሳት እና እነሱም አስታራቂ ለመምሰል ሲሞክሩ አይተናቸዋል ፡፡ጋምቤል ውስጥ ከ500 በላይ አማራዎች ተገድለው የሌሎችም ህይወት በስጋት ተውጦ ባለበት ሰዓት በ12 የሰዊድን ዜጎች ላይ የግድያ ሙከራ ተካሄደባቸው ሚል አስቂኝ የለማጅ ተውኔት ለመድረክ አብቅቷል፡፡በተመሳሳይ መልኩ ስርዓቱን ከድተው ስለተሰወሩት የአየር ሃይል አባላት እና በባህዳር ስለተገደሉት ንጹሀን ዜጎች የተለያዩ አለም አቀፍ ሜዲያዎች እየዘገቡ ባለበት ሰዓት  አለምአፉን ማህበረሰብ ለማወናበድ ያለመ የተለመደውን ትርዓት ሰርቶ በ23/12/2014 የአንድ እንግሊዛዊን ነፍስ በመቅተፍ   ለመድረክ አብቅቷል፡፡ከወያኔ ተፈጥፘዊ ባህሪ በመረዳት በዚህ እንግሊዛዊ ጎብኚ ላይ የተወሰደውን ግድያ ለመገመት አያዳግትም፡፡ ቀደም ሲል በአፋር ክልክ ላይ የነበሩ ጎብኚዎች በተመሳሳይ ሁኔታ በዚህ መልኩ የተቀነባበረ ድራማ ሰለባ መሆናቸው እና የቀሩትን በሀገር ሽማግሌዎች  አደራዳሪነት  አሰመልስኩላችሁ ሲል ገመናውን ለመሸፈን ሲሞክር ተስተውላል፡፡ እዚህ ላይ ኦጋዴን ክልል ሲዘግቡ በነበሩ ሁለት ሰዊድናዊ ጋዜጠኞች ላይ  የተወሰደውን እርምጃ ማስታወሱ ግድ ይሏል፡፡

ለምን ወያኔ የውጪ ዜጎችን ታርጌት ያድርጋል ?በሽበርተኝነት ስም ከአሜሪካ እና ከምዕራብ ሀገራት የሚሰጠውን እርዳታ እና ብድር ዘላቂነት ለማስጠበቅ እና በሀገሪቱ የሽብር አደጋ እንደተጋረጠ ለማስመሰል እንዲረዳው ያለመ ነው፡፡ሰሞኑን እንግሊዛዊው ላይ የተወሰደውም እርምጃ ከዚህ የዘለለ አይሆም፡፡አንድም የነጻነት ታጋዩ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን እስራት አስመልክቶ እንግሊዝ ዜጋዋን እንድታስፈታ የሚደረገውን ጥረት ጥላ ለማጥላት ምናልባትም ግድያው በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ የተናደዱ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች የወሰዱት እርምጃ ሊሆን ይችላል የሚል የማደናገሪ ፈጠራ ማሰራጨት እና እሱን ተከትሎ እንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸውን  በተመለከተ የያዘችውን አቋም ማስቀየር ፤ቀደም ብላ ስትሰጥ የነበረውን ድጋፍ እና ብድር ማስቀጠል፡፡ሌላውን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሀሰት ፕሮፖጋናዳ ለቀጣዩ ምርጫ የገንዘብ ድጋፍ የለማግኘት ለልመና በር ለማናኩኳት አፍ መክፈቻ  ተጨባጭ  የሚመስል ምክንያት ለመፍጠር  ያለመ  ሊሆን ይችላል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ እና በግድያ የማያምን መሆኑን ማንም ያውቀዋል፡፡በቂም በቀል ቢያምን በሚያዝያ ወር አንቦ ላይ የኦሮሞ ተማሪዎን  በጠራራ ጸሀይ ሲገደሉ፤ሶማሌ ክልል ንጽሀንን እንደቄጠማ አስከሬናበውን ሜዳ ላይ ሲነሰንሱት፤ጅማ ላይ  ወጣቱን መኖሪያ ቤቱ ገብተው በግፍ ገድለውት ሲሄዱ፤በ1997ዓ.ም  200 የሚጠጉ ዜጎች በግፍ ሲገደሉ፤አኙዋኮች ጭዳ ሲሆኑ፤ዛሬም በባህርዳር የነገ ተስፋ የሆኑ ህጻነት ባዶ እጃቸውን ወጥተው ግንባራቸውን በጥይት ሲነደሉ ባለደማቸውን  ገድለው ያሳዩት ነበር፡፡መግደል እንኩዋን ባይችሉ የድመትን ያክል ሳይጭሩት አይቀሩም ነበር፡፡ግን ሰላምን ህዝብ ስለፈለገው ብቻ ሰላም የማያውቁት ወያኔዎች የህዝቡን አስተዋይነት ከፍራት ከመቁጠር ያለፈ ፋይዳ አለው ብለው አያስቡም፡፡ሞት በመጣ ቁጥር መጮህ መፍትሄ አደለም፡፡ከዚህ ላይ አንድ የለቅሶ እንጉርጉሮ ማስታወስ ግድ ይሏል፡፡

ወይ ሰውና ጫጩት አሞራ እና ሞት፣

ሲመጣ መንጫጫት ሲሄድ መረሳት፡፡

መሞት ካለቀረልን በተናጠል ከምንጠቃ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሊገድለን የመጣ ጠላታችንን መከላከል እና ከተቻለም ወደ አጻፋዊ እርምጃ ካለተሸጋገርን ወያኔ ነገም ሌላ የሞት ድግስ ከመደገስ አይቆጠብም ፡፡በዚህ ገዳይ ስርኣት ስር ሁናችሁ ህዝባችሁን እየገደላችሁ ያላችሁ የመከላከያ ፣የደህንነት እና የፖሊስ አባላት ከከበባቸሁ የፍርሀት ካባ ወጥታችሁ ከሚገደለው፤ ከሚሞተው ወገናችሁ ጎን በመቆም ሊመጣ ከሚችለው  ህዝባዊ እልቂት  ካልታደጋችሁት በስተቀር ህዝቡ ከሚችለው በላይ ታግሷችኋል፡፡በዚህ አጋጣሚ ከስርዓቱ እየተለዩ ራሳቸውን ነጻ በማውጣት ከነጻነት ሀይሎች ጎን የተቀላቀሉትን እና በቅርቡ ኤም.አይ.35 ሄሊኮፐተርን ይዘው ስርዓቱን የከዱት የአየር አባላት እውነተኛ ጀግኖች ናቸው፡፡ተገቢውን  እርምጃ   በተገቢው ሰዓት ወስደዋል፡፡ ሌላውም የሰራዊቱ፣የፖሊስ፣የደህንነት እንዲሁም በተለያዩ እርከን ያላችሁ ዜጎች የጀግኖችን  አርአያቸውን በመከተል የጀመርነው ትግል በማፋጠን ተስፋችንን እውን እናድርገው፡፡ወያኔ የቆመበት መሬት እየከዳው በመንገዳገድ ላይ በመሆኑ ወደ ገደሉ አፋፍ እንዳይመለስ አድርጎ ለመጣል ሁላችንም በተቻለ መጠን ልዩነታችንን ወደጎን ትትን በዋናው ጠላታችንን ላይ እናተኩር፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

tplf

 

 

የስርዓቱ ቡድን መሪዎች እና ጀሌዎቻቸውን ፋሽሽታዊ ባህሪ የሚያሳይ ተግባር

$
0
0

ጉዳያችን

በባህር ዳር የአንድ እንግሊዛዊን ድንገተኛ ሞት እየመረመርኩ ነው ያለው ወያኔ/ኢህአዲግ ”በታህሳስ 9/2007 ዓም የአምስት ሰዎችን ሞት እና የአንድ መነኮሳይትን ጨምሮ የሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ደም መፍሰስ ትክክል ነበር” የሚል ሰልፍ እያዘጋጀ ነው።

bahr dar 2ፎቶ -ታህሳስ 9/2007 ዓም የቤተ ክርስቲያን ይዞታን መንግስት ያክብር ብለው ከምዕመናን ጋር ከተሰለፉት ውስጥ በጥይት የተመቱ መነኮሳይት
ወንበዴ መሪ በሆነበት ሀገር ፍትህ መቀለጃ ትሆናለች።ሕግ፣ስርዓት እና ምክንያታዊነትን ዜጎች ቢናፍቁም ህገወጦች ስልጣን ከተቆናጠጡ ዙርያቸውን በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶም ጭምር የሚኮለኩሏቸው ለሆዳቸው እና ለጥቅማቸው ብቻ የሚሰለፉቱን ነውና ብዙ ጆሮ የሚጠልዙ ነገሮችን መስማት ይለመዳል።
ታህሳስ 9/2007 ዓም በባህር ዳር ከተማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ይዞታነት የመስቀል ደመራ እና የጥምቀት በዓል የሚከበርበት ቦታ ለግል ባለ ሀብት የሚተላለፍ መሆኑ እና ከቀሪው ቦታ ላይ ደግሞ ተቆርጦ ለመንገድ ሥራ የሚውል መሆኑ እንደተሰማ የባህር ዳር ነዋሪ የእምነቱ ተከታይ በከፍተኛ ቁጣ ወጥቶ ተቃውሞውን መግለፁ ይታወሳል።
በወቅቱ የስርዓቱ ታማኝ ወታደራዊ ፖሊሶች በሰላማዊ ሰልፈኛው ላይ በወሰዱት ጨካኝ እና አረመኔያዊ ተግባር 5 ሰዎች ሲሞቱ አንድ ደካማ መነኮሳይት እና በርካቶች በዱላ እና በጥይት ጉዳት እንዲደርስባቸው ሆኗል።ጉዳዩን አስመልክቶ በዕለቱ በምሽቱ 2 ሰዓት የስርዓቱ ልሳን በሆነው በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተላለፈው ዜና ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ”ከሽብርተኛ ወገኖች ጋር የወገኑ፣”ወዘተ የሚል አሳፋሪ ዜና ከመለቀቁም በላይ ምንም አይነት ይቅርታ ከመንግስት አለመጠየቁ እና ይልቁንም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታት ቤተ ክህነት አንዳችም አይነት መግለጫም ሆነ አሁን በመንበሩ ላይ የተሰየሙት ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ አንዳችም የሚያፅናና ቃል ለምእመናን በቦታው ተገኝተው አለማስተላለፋቸው ይታወቃል።
የእዚህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር ምዕመናንን በእጅጉ አስቆጥቶ ሳለ ነው እንግዲህ ሌላ አሳፋሪ አረመኔያዊ ተግባር በሕዝቡ ላይ ሊፈፀም መሆኑ የተሰማው።በባህር ዳር የአንድ እንግሊዛዊን ድንገተኛ ሞት እየመረመርኩ ነው ያለው ወያኔ/ኢህአዲግ ”በታህሳስ 9/2007 ዓም የአምስት ሰዎችን ሞት እና የአንድ መነኮሳይትን ጨምሮ የሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ደም መፍሰስ ትክክል ነበር” የሚል ሰልፍ እያዘጋጀ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ዜናውን ”ነገረ ኢትዮጵያ” በማኅበራዊ ድረ-ገፁ ለቆታል።ጉዳዩ ከፍፁም የለየለት ዘረኛ እና አረመኔያዊ ድርጊት ከመሆኑም በላይ የስርዓቱ ቡድን መሪዎች እና ጀሌዎቻቸውን ፋሽሽታዊ ባህሪ በትክክል የሚያሳይ ነው።

የነገረ ኢትዮጵያን የዛሬ ታህሳስ 17/2007 ዓም ዜና ከእዚህ በታች ያንብቡት።

ገዥው ፓርቲ ባህርዳር ላይ የተደረገውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ሊጠራ ነው በሰልፉ የማይገኝ ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል።

ገዥው ፓርቲ በአማራ ክልል አስተዳደር ባህር ዳር ከተማ የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በባህር ዳር ቀደም ሲል የተካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ሊጠራ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
መንግስት ታህሳስ 9/2007 ዓ.ም የተደረገውን ህዝባዊ ተቃውሞ የ‹‹ፀረ ሰላም ኃይሎች እጅ እንዳለበት›› በመግለጽ ‹‹ህገ-ወጥ ሰልፍ›› ማለቱ የሚታወስ ሲሆን ባህር ዳር ከተማ የሚገኙት የቀበሌ ካድሬዎች የተደረገውን ህዝባዊ ተቃውሞ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ እያስተባበሩ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የቀበሌ ካድሬዎች በየ ቤቱ እየሄዱ የነዋሪዎችን ስም በመመዝገብ በሰልፉ የማይሳተፍ ሰው ቅጣት እንደሚጠብቀው እያስጠነቀቁ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ የድጋፍ ሰልፉ ታህሳስ 21 ወይንም 22 ቀን 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡

ጉዳያችን
ታህሳስ 17/2007 ዓም

ብልጽግናና ባሕል

$
0
0

በዳንኤልክብረት

መንገድ አቋርጣለሁ፡፡ በእግሬ፡፡ ሁለት ጎልማሶች በመንገዱ ማቋረጫ ላይ ተገናኙ፡፡ ከሁለት አንዳቸው ቀድመው ወይም ተከትለው ማለፍ አለባቸው፡፡ ሁለቱም ቆሙ፡፡ ከዚያም አንዱ ሌላኛው ቀድሞ ያልፍ ዘንድ ጋበዘ፤ የተጋበዘውም ጋባዡ እንዲያልፍ ለመነ፡፡ ግብዣው ጥቂት ደቂቃዎች ፈጀ፡፡ እኛም ከኋላ ያለነው ትኅትናቸውን አድንቀን በትዕግሥት ቆምን፡፡ በመጨረሻ አንደኛው እያመሰገነ አለፈ፡፡ ሌላኛውም ‹ምን አይደል›› እያለ አሳልፎ አለፈ፡፡
daniel-kibret-300x207
ደግሞ ሄድኩኝ፤ እነሆም በአንድ መስቀለኛ የአስፋልት መንገድ ላይ ደረስኩ፡፡ መኪኖቹ ከአራቱም አቅጣጫ ይመጣሉ፡፡ ሁሉም ወደ መስቀለኛው መጋጠሚያ ይገባሉ፡፡ አራቱም በአንድ ጊዜ ለማለፍ ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን አይችሉምና የመኪኖቹ አፍንጫዎቻቸው ተፋጥጠው ይቆማሉ፡፡ ለማለፍ እንጂ ለማሳለፍ የሚጥር አላይም፡፡ አራቱም በመስኮት ብቅ ብለው ‹ወደ ኋላ በልልኝ ልለፍ› ይላሉ፡፡ እነርሱ ሲከራከሩ ሌሎች ባለመኪኖችም ይመጣሉ፡፡ እንደ ዘንዶ ተጣጥፈው በአራቱ መኪኖች መካከል ለማለፍ ይሞክራሉ፡፡ እነዚያ ቀድመው የመጡትም ይናደዱና ወደ ፊት ገፍተው መንገዱን ያጠባሉ፡፡ በዚህ የተነሣም እነዚያም ከኋላ የመጡት በተራቸው ይቆማሉ፡፡ ሁሉም ቀድሞ ለማለፍ በሚያደርገው ፍትጊያ ሁሉም ይቆማሉ፡፡ እለፍ፣ እለፍ ተባብሎ መገባበዝ የለም፡፡

እየገረመኝ አልፋለሁ፡፡
አልፌም አንድ ያረጀ የዕድር ድንኳን የተጣለበት ጋ እደርሳለሁ፡፡ ድንኳኑ ለሁሉም አይበቃምና ከድንኳኑ ውጭ አግዳሚ ወንበር ላይ ሰዎች ተቀምጠዋል፡፡ ሌሎች ልቅሶ ደራሾ ሲመጡ ቀድመው ተቀምጠው የነበሩት ግር ብለው ይነሡና ወንበር ይለቃሉ፡፡ ‹ይቀመጡ አልቀመጥም› የግብዣ ግብግብ ይፈጠራል፡፡ በመካከል ገላጋይ ገብቶ እንግዳ ይቀመጣል፡፡ ‹ኖር› መባባል መልቶ ሰፍቶ ይከናወናል፡፡ ሰውን በአግዳሚዎቹ መካከል ለማሳለፍ ሁሉም እግሩን ያነሣል፣ ወይ ራሱ ይነሣል፡፡

እያደነቅኩ አለፍኩ፡፡
የማልፍበት መንገድ በግራ በቀኝ ቤት ሠሪዎች አሸዋና ጠጠር፣ ድንጋይና ብረት አውርደውበታል፡፡ እዚህም እዚያም ተጀምረው ያላለቁ፣ አልቀው ደግሞ ሰው የገባባቸው ቤቶች አሉ፡፡ አሸዋውና ድንጋዩ፣ ጠጠሩና ብረቱ መሐል መንገድ ላይ ይቆለላል፡፡ ሰው በምን ይተላለፋል? መኪና በምን ያልፋል? ብሎ ነገር የለም፡፡ ሁሉም በቤቱ ፊት ለፊት ይደፋል፡፡ ሲብሰው ደግሞ መሐል መንገድ ላይ ሲሚንቶ ያቦካል፣ ድንጋይ ይፈልጣል፡፡ እዚያ ድንኳን ውስጥ የነበረው ‹ኖር› መባባል፣ በአግዳሚዎች መካከል ሰው ለማሳለፍ መከራ መቀበል፣ እንግዳ ሲመጣ ከመቀመጫ ተነሥቶ ክብር መስጠት በቤት ሠሪዎቹ ዘንድ የለም፡፡

ይህንንም አለፍኩት፡፡
እነሆም በኑሮ ደከም ያሉ ሰዎች ወደሚኖሩበት መንደር ደረስኩ፤ የቆርቆሮ ጣራና የቆርቆሮ ግድግዳ ወደሚበዛባቸው፡፡ አቡኪዎቻቸው በእድሜ ገፍተው በሞቱ የጭቃ ግድግዳዎች ወደተሠሩ፤ ተቃቅፈው እንደሚሄዱ የሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ትከሻ ለትከሻ የተደጋገፉ ግድግዳዎች ወዳሏቸው ቤቶች መንደር፡፡ በዚያም ሳቋርጥ ‹‹ወ/ሮ እንትና ደኅና አደሩ፤ ምነው ሰሞኑን አላየሁዎትም› የሚል የጎረቤት ድምጽ ሰማሁ፡፡ ወ/ሮ እንትናም አብራሩ፡፡ እልፍ ስል ደግሞ ‹‹እ-ን-ት-ና፣ ቡ-ና-ው ፈ-ል-ቷ-ል› የሚል ዘለግ ያለ የግብዣ ጥሪ አዳመጥኩ፡፡ ደግሞ ልጆቹም ሰብሰብ ብለው በመንደሩ መካከል ከምትገኘው የእጣቢ መድፊያ መስክ ላይ አፈር ልሰው አፈር መስለው ይጫወታሉ፡፡ ውሾም ከልጆቹ ጋ ይዘላሉ፡፡
እነሆ ያንንም መንደር አለፍኩትና ከመንገዱ ማዶ ተሻገርኩ፡፡
ይኼ ደግሞ የባዕለ ጸጎች ሠፈር ነው፡፡ እያንዳንዱ ግን በአጥር ተከልሏል፡፡ ወደዚያ መንደር ለማለፍም እንደ መንግሥት መሥሪያ ቤት መታወቂያ ይጠየቃል፤ ወደ ውስጥ ስትዘልቁ እንደ ሙታን መንደር ጭር ያለ ነው፡፡ መስክ ላይ ተሰባስበው የሚጫወቱ ልጆች አታዩም፤ ሁሉም ወይ ጌም ላይ ናቸው ወይም ቲቪ እያዩ ነው፡፡ አለያም ግቢያቸው ውስጥ ናቸው፡፡ ወላጆቻቸውም ግቢ ግቢያቸውን ዘግተው አይጠያየቁም፡፡ እንዲያውም ጎረቤታቸው ማን እንደሆነ የማያውቁም አሉ፤ ከግቢያቸው ሲወጡ ‹‹ወ/ሮ እገሊት ደኅና አደሩ፤ ምነው ሰሞኑን አይታዩምሳ›› ብለው አይጠይቁም፡፡

በዚህም ተገረምኩ፤ አለፍኩም፡፡
እነሆም ሰዎች ታክሲ ለመሣፈር ወረፋ የያዙበት ቦታ ደረስኩ፡፡ ረዥም ሰልፍ፡፡ ልጆች፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን፣ በከዘራ የሚሄዱ፣ ጎንበስ ብለው መሬት መሬት የሚያዩ፣ ጥላ የያዙ፣ በወረቀት ፀሐይን የሚከልሉ፣ ሁሉም ተሰልፈው የታክሲውን መምጣት ይጠባበቃሉ፡፡ ቆምኩና አየኋቸው፡፡ ታክሲዎቹ በመጡ ቁጥር የቻሉትን ሰው ይጭናሉ፡፡ በዚያ ፀሐይ ጨዋነታቸው ይነበባል፡፡ ራሳቸው ተራ አስከባሪዎች ከሚፈጥሩት ግርግር በቀር ግርግር ለመፍጠር የሚቻኮል ያንን ያህል ሰው የለም፡፡

ይህንንም አይቼ አለፍኩ፡፡
አለፍኩና ወደ አንድ ማደያ ዘንድ ደረስኩ፡፡ የነዳጅ ወረፋው የመንገዱን ጥግ የመኪና መሸጫ አስመስሎታል፡፡ ወደ ማደያው አካባቢ ሸውደው ለማለፍ የሚሞክሩ፤ አልፈው የሚሄዱ መስለው በሰው ሰልፍ የሚገቡ፣ ያንን ረዥም ሰልፍ እያዩ ሌላ ሰልፍ የሚፈጥሩ፣ መኪናቸውን አቁመው ጓደኛቸውን የሚያስገቡ ባለመኪኖች ይታያሉ፡፡ ከመኪኖቻቸው ውስጥ የብልግና ስድቦች ይወጣሉ፤ ይወራረፋሉ፤ ታክሲ እንደሚጠብቁት ሰዎች ፀሐይና አቧራ አያገኛቸውም፤ ከታክሲ ጠባቂዎቹ በላይ ግን ትዕግሥት የለሾች ናቸው፡፡ በመካከል ነዳጅ አልቋል ሊባል እንደሚችል ያውቃሉ፤ ነገር ግን ከኋላቸው የተሰለፉት ሰዎች ድካም ምንም ሳይመስላቸው ከነዳጅ ታንከራቸው በተጨማሪ በጀሪካቻኖቸው ይሞላሉ፡፡

እነሆ ይህንንም ታዝቤ አለፍኩ፡፡
አሁን ግን ዝም ብዬ አላለፍኩም፤ ያሳስበኝ ጀመር፡፡ እንዴው የኛ በጎ በጎ ባሕላችን በድህነት ላይ ነው እንዴ የተመሠረተው? አልኩ፡፡ በድሃው ማኅበረሰብ አካባቢ የምናያቸው የመከባበር፣ የመተባበር፣ የመጠያየቅ፣ የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ ባሕሎች የተሻለ ገቢ ያለው ማኅበረሰባችን ላይ ሲታዩ ወይ ጠፍተዋል ወይም ቀንሰዋል፡፡ የዘመዶቻቸውን ልጆች እንደራሳቸው አድርገው የሚያሳድጉ ክቡራን ወላጆችን በብዛት የምናየው ድሃው ወገናችን ዘንድ ነው፡፡ የአንድ ሰው ጉዳይ አሳስቦት የት ነበርክ? ብሎ የሚየጠይቀው፣ ያለውን ተካፍሎ ለመብላት የሚተጋው፣ ጉርብትናው የሚያምረው፣ መከባበሩ ሞልቶ የሚፈሰው እዚህ ደሃው ወገናችን ላይ ነው፡፡

የተሻለ ኑሮና ዕውቀት ያለው ጋ ስትሄዱ ግለሰባዊነት፣ ብቸኛነትና ድንበርተኛነት ሠፍኖ ታዩታላችሁ፡፡ የማይለብሳቸው ብዙ ልብሶች አሉት፣ ግን አይሰጥም፤ የማይመገበው ትርፍ ምግብ አለው ግን፤ ግን አይመጸውተውም፡፡ ታላላቅ ግቢ አለ፤ ነገር ግን ተረት የሚያወሩ፣ ባሕል የሚያስተምሩ አክስቶች፣ አጎቶችና አያቶች አይኖሩበትም፡፡

እነዚያን የመንደር ሐኪሞች፣ እነዚያን እጆቻችንን አሽተው ያዳኑን ወጌሾች፣ እነዚያን ሐረግሬሳ በጥሰው፣ ስሚዛ ጨምቀው ያዳኑንን የመንደር እናቶችን አስቡና የአሁኑን የሕክምና ሥነ ምግባር አስቡት፡፡ ጠዋት ከዕንቅልፍ ብንቀሰቅሳቸው፣ በምሳ ሰዓት ብንሄድባቸው፣ በእኩለ ሌሊት ብንጠራቸው ለመንደሩ ሰዎች የነበራቸው ትጋት፤ ዛሬ ከዘመናዊ የሕክምና ተቋማት ለምን ተወሰደ? ይበልጥ ባወቅንና ይበልጥ ባገኘን ቁጥር ይበልጥ ጨዋነት ይጠፋብናል ማለት ነው? ከጉልት ሻጮች ይልቅ በሱፐር ማርኬቶች፣ ከመንደር ሱቆች ይልቅ በገበያ አዳራሾች ለምን ማጭበርበሩ በዛ?

ከተለያየ ጎሳና ነገድ ይበልጥ ተዋሕዶ፣ ተጋብቶና ተዛምዶ የምናገኘው የትኛውን ኅብረተሰብ ነው? ከውስኪ ቤትና ከጠጅ ቤት ኢትዮጵያን የሚያሳየን የትኛው ነው? በሀገር ቤት ከሚኖረውና በውጭ ከሚኖረው የትኛው ነው ጠባቡ? በአውቶቡስ ከሚሄድና በአውሮፕላን ከሚሄደው የትኛው ነው የሚገባበዘው? የትኛውስ ነው የሚጨዋወተው?

ባደግንና በተለወጥን ቁጥር፣ ዕውቀትና ሀብትም ባፈራን ቁጥር፣ የኑሮ መደባችንም በተቀየረ ቁጥር እነዚያን የኛ ናቸው የምንላቸውን ወጎች፣ ልማዶች፣ ሥነ ምግባሮችና ባሕሎች እየተውናቸው እንሄዳለን ማለት ነው? ሥልጣኔና ብልጽግና የበጎ ባሕል ማጥፊያ ናቸው እንዴ? ኢትዮጵያዊ የምላቸው ባሕሎች፣ ወጎችና ልማዶች ካልተማረው ይልቅ በተማረው፣ ከሀብታሙ ይልቅ በደሃው ማኅረሰብ ዘንድ ይበልጥ የሚከበሩትና የሚጠበቁት ለምንድን ነው? ይበልጥ በበለጸግን ቁጥር፣ ይበልጥስ በተማርን ቁጥር ይበልጥ ኢትዮጵያዊነታችንን እንለቃለን ወይስ?

የ“ምርጫ” ወግ እና የውይይት ማስታወቂያ –ተክለሚካኤል አበበ

$
0
0

ስለሂደት፤ ስለትእግስት፤

  • Election2007የዚህ ጽሁፍ ዓላማ፤ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መሪዎች፤ አሁድ ድሴምበር 28 ቀን ከሰአት በኋላ 2pm ላይ፤ በውጭ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ያዘጋጁትን የስልክ ውይይት ማስተዋወቅ ነው። ይሁን እንጂ ማስታወቂያውን እርቃኑን ባሰፍረው፤ አይማርክም በሚል፤ አንዳንድ ተያያዥ ነገሮችን ላለብሰው ፈቀድኩ። መለመላውን ከሚቀርብ የስልክ ጉባኤ ማስታወቂያ ይልቅ፤ ትንሽ ውዝግብ የለበሰ ማስታወቂያ ቀልብ ይስባል፡፡
  • አንደኛው ልብስ፡ ሂደት የሚሉት ነገር ነው፡፡ ስለምርጫና ሰላማዊ ትግል ሳስብ አሁን አሁን የሚታየኝ ነገር፤ ሂደት የሚለው ሀሳብ ነው፡፡ ውዝግብ አንድ፤ ለኔ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ሰላማዊ ትግል የድሮውን የልደቱ አያሌውን መንገድ ተከትሎ ቢሆን ኖር፤ እስካሁን አሸንፈን ነበር፡፡ የዛሬ አስራ አምስት አመት አካባቢ፤ የኢዴፓ መሪዎች ይመስለኛል ሲናገሩ ያደመጥኩት፡፡ በየምርጫው አስር አስራአምስት፤ ሰላሳ አርባ ወንበሮች ብንይዝ፤ በሂደት፤ ባራት ባምስት ምርጫዎች አሸንፈን የመንግስት ስልጣን እንይዛለን የሚል ስሌትና ስልት ነበር፡፡ ያኔ በአንድ ምርጫ አሸንፈን ስልጣን እንይዛለን የሚል ቅዠት አልነበረም፡፡ አሁን አሁን ሳስበው ያንን መንገድ ተከትለን ቢሆን ኖሮ በ2012ቱ ምርጫ ስልጣን ልንይዝ እንችል ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ፤ እነብርሀኑ የልደቱን ትተው፤ የሀይሉ ሻውልን መንገድ ተከተሉ፤ አይወድቁ አወዳደቅ ወደቅን፡፡
  • በሂደትና በትእግስት ማመን አለብን፡፡ በተለይ እድሜያችን ሲገፋና ሽንፈት ሲደጋገምብን፤ የበለጠ በሂደትና በትእግስት ማመን አለብን፡፡ ይሄንን ትእግስትና ሂደት የሚል ቃል ለምን አነሳሁ? ምርጫ ምርጫ የሚሉ ሀይሎች የእምነታቸው መግፊያ ሀይል ሂደት የሚለው ቃል ይመስለኛልና ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች አሁን ባለው ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሀዊና ነጻ ምርጫ ለማድረግ እንደማይሞከርና፤ ኢህአዴግ በምርጫ ስልጣን እንደማይለቅ ለማሳየት የኤርምያስ ለገሰን ኤክስፐርቲዝ ሁሉ ሲጠቅሱ ተስተውለዋል፡፡ አሁን በማርያም፤ አንድነት መጪው ምርጫ ነጻ ምርጫ እንደማይሆን ያጣዋል? ጥያቄው፤ እንዲህ ያለ ፍትህ የጎደለው ምርጫ ውስጥ መሳተፍ ፋይዳው ምንድርነው? አንድነትንም ይሁን ሌሎች ፓርቲዎችን፤ የዚህ ሀሰተኛ ምርጫ ተባባሪ፤ የስርአቱም አዳማቂ አያደርጋቸውም ወይ፤ የሚለው ይመስለኛል፡፡
  • ጥያቄውን በማያዳግም መልኩ መመለስ ይከብዳል፡፡ አንዳንድ ነገሮች ጭራሹኑ መልስም ላይኖራቸው ይችላል፡፡ ወይም ጊዜ ይመልሳቸዋል፡፡ እኔ እንደተረዳሁት ግን፤ አንድነትም ይሁን ሌሎች ያገርቤት ድርጅቶች፤ ምርጫውን እንደአንድ የትግል ግንባር የወሰዱት ይመስለኛል፡፡ እንደአንድ የትግል ግንባርም፤ አስቀድመን እጅ ከምንሰጥ፤ ትንሽ እንፋለምበት አይነት ነገር፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ቀላሉን መንገድ ይመርጣሉ፡፡ ምርጫ እንሳተፍም ብሎ አኩርፎ መውጣት ቀላሉ መንገድ ነው፡፡ አንድነት ግን ያንን ቀላሉን እጅ አጣጥፎ የሚቀመጡበትን መንገድ አልመረጠም፡፡ በራሳቸው በኢህአዲጎች ሜዳ ትንሽ እንሞግታቸው ያለ ይመስለኛል፡፡ አንድነቶች ወደምርጫ የሚገቡት የምርጫውን ምርጫ አለመሆን ለማሳየት ይመስለኛል፡፡ ትግል ደግሞ ሂደት ነው፡፡ ተከታታይ ነው፡፡ አምና አይተነዋል ተብሎ ቁጭ አይባልም፡፡
  • የለም ምርጫው የተበላ እቁብ ነው፤ በዚህ ሂደት ውስጥ ገብተን አናጃኩምም ብለው የሚከራከሩትም ቢሆን መከራከሪያቸው ስሜት ይሰጣል፡፡ ችግር የሚፈጥረው፤ ሁሉም የራሱን መከራከሪያ እንደብቸኛው የተቀደሰ ሀሳብ፤ አንዱ አንዱን እንደእንቅፋት ቆጥሮ ጠለፋ የተጀመረ እንደሆነ ነው፡፡ በአንድነት በኩል እንደድርጅት ምርጫው ውስጥ መሳተፍ የለባችሁም የሚለውን ክርክር የሚመለከቱት በበጎ ነው፡፡ መሪዎቹ፤ በተቻለ መጠን ወደምርጫ የሚገቡበትን ምክንያት ለማስረዳት ይተጋሉ፡፡ በቅርበት እንደተረዳሁት፤ ይሄ በዚህ እሁድ ድሴምበር 28 ከሰዓት የተዘጋጀው የስልክ ውይይትም የዚሁ ሂደት አካል ነው፡፡
  • አንዳንድ በውች የሚኖሩ የአንድነት ደጋፊዎች ግን ምርጫ መግባትን እንደብልሀት የሚጠይቁትን ሁሉ የአንድነት ጠላት፤ የግንቦት ሰባት ወኪሎች አድርጎ የመፈረጅ አዝማሚያ ያሳያሉ፡፡ ለምሳሌ፤ ወዳጄ መሳይ መኮንን በዚህ ሳምንት፤ ምክንቶቹን ዘርዝሮ፤ ምርጫ መሳተፍ ሞኝነት ነው ብሎ ስለተሟገተ፤ አንዳንዶች የመሳይን አቋም የኢሳት አቋም፤ ኢሳትን ደግሞ የአንድነት ጠላት አድርገው ለመፈረጅ ሲጣደፉ አስተውያለሁ፡፡ ይሄ ስህተት ነው፡፡
  • አንደኛ፤ ያለፈው ልምድ፤ የአሁኑም የመንግስት አቋም እንደሚያሳየን ከሆነ፤ ምርጫው ፍትሀዊ እንደማይሆን ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ፤ ምርጫ መግባት ያዋጣል ብሎ የማሳመን ሸክም ያለው ምርጫ እንግባ የሚለው ወገን ላይ ነው፡፡ ሁለተኛ፤ በዚህ መገናኛ ብዙሀን ሁሉ በታፈኑበት ሰዓት ለአንድነት ደጋፊዎች ከኢሳት ጸብ መግጠም ብልህነት አይደለም፡፡ ከሚዲያ ጸብ ገጥሞ ያሸነፈ ማግኘትም ይከብዳል፡፡ የቀድሞ የቶሮንቶ ከንቲባ፤ ሮብ ፎርድ እና ወንድሙ ከሚዲያ ጸብ ገጠሙ፡፡ በመጨረሻም ከሚዲያ የገጠሙት ጸብ ለሽንፈታቸው ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ስለዚህ አንዳንድ የአንድነት ደጋፊዎች አንድነትን ከኢሳት ባያላትሙት መልካም ነው፡፡
  • ኢሳት የአንድነትን የምርጫ ማስታወቂያ ያለምንም ጥያቄ አንጠልጥሎ እንዲሄድ መጠበቅም ደካማነት ነው፡፡ በርግጥም ምርጫ መግባት የሚለው ሀሳብ በደንብ መፈተሽ፤ መተንተን፤ በክርክርም መዳበር አለበት፡፡ ያለቀለት መልካም ሀሳብ አድርገው የሚያስቡ የአንድነት ደጋፊዎች ካሉ ተሳስተዋል፡፡ የምርጫ መግባትን ትክክለኛነት የሚጠይቁትን ሁሉ የአንድነት ተቃዋሚዎች፤ የግንቦት ሰባት ደጋፊዎች አድርጎ ማየት ሰንካላ አተያይ ነው፡፡ አንዳንድ ደጋፊዎች ጠንቀኞች ናቸው፡፡ ከትርፋቸው ኪሳራቸው ይበዛል፡፡ ስለዚህ አንድነትና አመራሩ ከጠንቀኛ ደጋፊዎች መጠንቀቅ አለባቸው፡፡
  • ከልምድ እንዳየነው፤ አንድነትም ይሁን ሌሎች አገርቤት ያሉ ድርጅቶች በርትተው ስራቸውን ከሰሩ፤ ኢሳት ይዘግባል፡፡ የኢሳት ጉልበት አገርቤት ነው፡፡ የኢሳት ቅመም፤ አገርቤት የሚካሄድና የሚከሰት ክስተት ነው፡፡ የአንድነቶች ሃላፊነት ያንን ክስተት መፍጠር ነው፡፡ ለኢሳት ፍጆታ ሳይሆን ለራሳቸው አላማ መፈጸም፡፡ ለምሳሌ፤ አሁን በዚህ ሰዓት፤ አንድነቶች እንደሚሉትም ለምርጫው ዝግጁ ከሆኑ፤ ቢያንስ በዋና ዋና ከተሞቻቸው በእጩነት ያሰለፏቸውን ሰዎች ምስል፤ የትምህርት ደረጃ፤ ልምድ፤ ራእይ፤ በስብሰባ፤ በሰለልፍ፤ በኢሳትም ይሁን በሌላ ሚዲያ እያቀረቡ ትግሉንና ፕሮፓጋንዳውን ማጡዋጡዋፍ እንጂ፤ ከሚዲያ ጋር ጸብ መግጠም የለባቸውም፡፡ አንድነት የምርጫ አጀንዳውን ሁሉ ዛሬ ካላሳወቀ፤ ምን ይዞ ምርጫ ውስጥ እንደሚገባ አልገባንም፡፡ የጸረ ሽብር ህጉን እንቃወማለን የሚለው መፈክር የምርጫ አጀንዳ አይሆንም፡፡ የሆነ ሆኖ፤ የምርጫውም ይሁን የትግሉ ስልት ውይይት ይቀጥላል፡፡ እስከዚያው ግን፤ ሰዎች ባመኑበት እንዲጓዙ ነጻነታቸውን እንቀበል፡፡
  • በዚህ ዙር፤ የኔ አሰላለፍ ከአንድነት ሆኗል፡፡ ምክንያት፤ አንደኛ የዛሬ አምስት አመት፤ አረጋሽ አዳነ አድዋ ላይ እንድትሰለፍና ሟቹን አቶ መለስን እንድትፋለም ከጓደኞቼ ጋር ሆነን ትንሽ ገንዘብ ልከንላት ነበር፡፡ በምርጫው ባናሸንፍም፤ አቶ መለስ በህወት ተሸነፉና አድዋን በአካል ለቀቁልን፡፡ መንፈሳቸውና ውርሳቸው ግን አራትኪሎን አልለቀቀልንም፡፡ እስካሁን ባለውም ሁኔታ፤ በንጽጽር አንድነት ተጠናክሮ የሚወጣና የሳቸውን ውርስ ሊያጸዳ የሚችል ተፎካካሪ ድርጅት ይመስላል፡፡
  • በርግጥ የአንድነት አመራር ከሰማያዊ ሰዎች ጋር የሚያደርገውን እንካሰላንቲያ ማቆም አለበት፡፡ ይሄ ጠቅላላ ጉባኤን በሳምንት ዝግጅት ማካሄድን እንደስኬት የሚቆጥሩትን ነገርም መተው አለባቸው፡፡ ጠቅላላ ጉባኤን ያህል ነገር አስቀድሞ ታልሞ መካሄድ ሲገባው፤ ድንገት መደረጉ፤ ስልጣን ቢይዙም እንዲህ በድንገተኛ ስበሰባ ነው እንዴ የሚመሩን የሚለውን ጥያቄ ይፈጥራል፡፡ አንድነት፤ ከኢህአዴግ የተሸለ እንጂ፤ እንደኢህአዴግ መሆን የለበትም፡፡ የ250 ሚሊዮን ብር መንገድ ባስመረቀ ባመቱ፤ ለባቡር ስራ የሚያፈርሱ አይነት መንግስት አንፈልግም፡፡ የሆነ ሆኖ ግን፤ ሰማያዊንና ሌሎች እህት ድርጅቶችን አስተባብሮ መጓዝ ከቻለ፤ አንድነት በመጪዎቹ ወራት ጠንካራ ሆኖ የማይወጣበትና፤ በዚህኛው ዙር ባይሆን፤ በ2012ቱ ምርጫ አሸናፊ የማይሆንበት ምክንት የለም፡፡
  • ይሄ ጭላንጭል ተስፋም ስላለ አንድነትን እንደግፋለን፡፡ እንጂ የግንቦት ሰባትንና የአርበኞች ግንባርን ውህደት ስንጠብቅ አናረጅም፡፡ ከላይ ከመግቢያዬ እንደገለጽኩት፤ የአንድነት ሊቀመንበርና ካቢኔው፤ ከአንድነት የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጪ ማህበር ጋር በመተባበር፤ በፓርቲው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የስልክ ጉባኤ አዘጋጅቷል፡፡ ውይይቱ የሚካሄደው፤ እሁድ ዲሴምበር 28, 2ዐ14 በ 2:00 PM Eastern ሲሆን፤ እርስዎም ተገኝተው የአንድነትን መልእክት እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል፡፡ የመገናኛ/ውይይት መስመሩ 1 857 216 6700 ሲሆን Access code 478975፡፡ እንዲሁም፤ 712 775 7085 Access code 767490 ነው፡፡

ተክለሚካኤል አበበ፤ ቶሮንቶ፤ ካናዳ፤ ትህሳስ፤ 2007 (2014)

እሺ አሁንስ ባህር ዳር ላይ ደግሞ ወገኖቼን ለምን ገደላችሗቸው? –ለዚህ ደርግ ኢሰፓ ዜጎችን አይደለም ዝናብ አይገልም

$
0
0

Friday, December 26, 2014

ዳዊት ዳባ።

የባህር ዳር ህዝብ ይህን ቦታ እጅግ ለረጅም አመታት ለአምልኮ ስንጠቀምበት የነበረ ነው። ለባለ ሀብት መሰጠቱና ለሌላ አገልግሎት እንዲውል መወሰኑ ትክክል አይደለም ብሎ ቅሬታውን ሊያሰማ አደባባይ ወጣ። ይህ ለእምነቱ የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ቀናዊ የሆነ በአገሬ ጉዳይና በኑሮዬ እሚንት የምታህል መብት አለኝ ብሉ የሚያስብ የየትም አገር ዜጋ ሊያደረገው የሚችል  ነው። በእውን ይህን  ማድረግ የሚከለከል ወይ ማድረጉስ ወንጀል የሚደረግበት ህዘብ በአለም ላይ አለ ወይ?። እኔ እይመስለኝም።

4bahrdar 7በዋናነት ቅሬታቸውን ሰልፍ ወጥተው ማሰማታቸው የህግ አግባብ ያለው ነው። ህዝብ ይህን ማድረጉ ተፈጥራዊም ህገ መንግስታዊም እምነታዊም መብት መሆኑ ደምቆ ይሰመረብት። ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ቅሬታቸውን ማቅረባቸውንም እንዲሁ።

ይህም ሆና በባህር ዳር ላይ የሆነው እጅግ እጅግ በጣም ቀላል ነገር ነበር።  መገድል መደብደብ ማዋከብ ውስጥ ሳይገባ ይህን የህዝብ ቅሬታ ማስተናገድ በቀላሉ የሚቻልባቸው መንገዶች ነበሩ።የሚያዳምጥ አካል በመላክ ቅሬታውን  ማዳመጥን ብቻ ነበር  እኮ የሚፈልገው። የህዝቡ ቅሬታ እውነታ ከሌለው  እውነታውን ማስረዳት። የህዝቡ ቅሬታ እውነትነት ኖሮት ቦታው  ለሌላ አገልግሎት ተሰጥቶ ከሆነ ውሳኔው የተላለፈበትን አግባብና በልዋጭ ህዝብ አምልኮውን የሚፈፅምበት ቦታ ተዘጋጅቶ ከሆነ ይህንን መንገርና በቀላሉ ሰላማዊ ፍፃሜ መስራት ይቻል ነበር። ሌላ ሶስተኛ አካል ከጀርባ ህዝብን አሳስቷል። ነጭ የገዳዬች ምክንያት ነው። ካልሆነ ከጨፈጨፍክ በሗላ ሳይሆን እዛው ሰልፉ ላይ አሳስተዋችሁ ነው። የምታቀርቡት ቅሬታ ምንም መሰረት የሌለው ነው። በማለት  የተፈጠረውን አለመግባባት ማጥራት አይቻልም ነበር ወይ?። ቅሬታው አግባብ ኖሮት ውሳኔው የተላለፈበትን አግባብ እዛው መንገሩ ጥሩ አይሆንም ተብሎ ከታሰበም። ቅሬታውን አድምጠናል። መልሳችንን በዚህ ቀን በዚህ መንገድ እንሰጣለን ማለትንስ ማንን ገደለ። አዎ ይህን በማድረግ በሰለጠነው መንገድ መጨረስ ስትችሉ ፈጇችሗቸው።

ሁላችንም ማወቅ ያለብን እንደሁሌው ይህ እጅግ ቀላል ነግር  በዚህ አይነት  አሳዛኝ ሁኔታ የተፈፀመው አምጠንም ሰበብ ልንወልድልት በማይቻለን ስልጣን ላይ ያሉት የትግሬ  ወያኔዎች በመሆናቸው ነው።  አንድነት፤ ሰማያዊ፤ አዎ ኢሰፓም ብቻ  የትኛውም አካል ስልጣን ላይ ቢሆን ኖሮ የሚያደርገው ካላይ ያልኩትን ነበር። በእርግጠኛነት የምናገረው ለዚህ ቀላል ነግር  የሰው ልጅ ለዛውም ዜጋ አይደለም ዝንብ አይሞትም ነበር። እናንተ ግን በምታውቁትና ሁሌም የዚህ አይነት የህዝብ ቅሬታን በምታስተናግዱበት መፍጀት በእድሜ የጠገቡ አሮጊቶችንና ለአካለ ስንኩላን እንኳ ሳትራሩ ዘግናኝ ወንጀል በድጋሚ ፈፀማችሁ። ግን ለምን?። ለምን ለሰው ለጅ ለዛውም ለወገናችሁ ሂወት የምትሰጡት ክብር እዚህ ደረጃ ወረደ?። ህዝብን ማሸበር እንዴት ነው እንደዚህ ደስታን እየሰጣችሁ ያለው?። ጎበዝ ግርም የሚል ነገር እኮ ነው የገጠመን።

ይህ በመፍጀት የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችንና ቀላል ቅሬታዎችን ሁሉ መፍታት ለሀያ ሶስት አመት ሙሉ በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ የነበረ መሆኑን ልብ እንበል። ሚሊዬኖችን ቀጥቅጠውበታል። በመቶ ሺዎች ገድለውበታል። በመቶ ሺ ዎች በየማጎርያው የመከራ ሂወት እንዲገፉበት አድርገዋል። ሚሊዬኖችን አሰድደዋል። ብዙዎችን ያለወላጅ አስቀርተዋል። ይህ ግፍ የተፈፀመባቸው ብዙዎቹ ይህን አይነቱን  በሽታ ዝም ስለተባለ ማቆሚያ የሌለው መሆኑን በጠዋቱ አውቀው አቁሙ ስላሉ መሆኑን ደግሞ አንዘንጋ።

ዛሬም የሆነ አይነት “መንግስት” አድራጋችሗቸው ህግና ስርአትን ከማስከበር አኳያ፤ እንዲሁም በአደባባይ ስሜትን ለመግለፅ ከማሳወቅ በሉት ከማስፈቀድ  የህግ አግባብ አኳያ እያያችሁ ትርጉም እንዲሰጣችሁ እየጣራችሁ ያላችሁ ትኖራላችሁ። እውነት እውነት እላችሗለው በጣሙን ተሳስታችሗል። እሩቅ ቦታ ሳልሄድ ሀዘን ደስታ ንዴት የስሜት ጉዳዬች ናቸው። ሁሌ በቀጠሮ የምናደርጋቸው አይደሉም። የሄን ደግሞ እኔ ስላልኩ አይደለም። ወያኔዎችም ያውቃሉ። ብሄራዊ ቡድናች ሌላ ጊዜ ደግሞ እሯጮቻችን አሸነፉ ብሎ ይህው  ህዝብ በብዙ ቁጥር በደስታ ስሜት ብዙ ጊዜ ሳያስፈቅድ አደባባይ ወጥቷል። ገደሉት?። አልገደሉትም። ጦርነት አሸነፍን ባድሜ ለኛ ተወሰነ ብሎ ደስታውን ለመግለፅ ህዝብ አደባባይ በብዙ ቁጥር ወጥቶ ነበር። ፈጅት ፈፀሙበት?። አልፈፅሙም። መለስ ሞተ ብለው ሀዘኑን ሊገለፅ ነው ብለው ያለ ምንም ፍቃድ አሁንም አደባባይ ያወጡትን ህዝብ ፈጁት?። አልፈጁትም። እነሱ ደስታቸውን፤ ዝክራቸውንና ስኬታቸውን ሊነግሩን የበዛውን ጊዜ አደባባዩን የሚጠቀሙና ሲሰበሰቡ የሚውሉ  ናቸው። እያስፈቀዱ ስለመሆኑ የምታውቁት ነገር አለ?። አስፈቀዱ ወይ ተከለከሉስ ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?። ወይ እዚህ ቦታ መሰብሰብ ወይ መሰለፍ አትችሉም ተባሉስ ሲባልስ?። ሲቀሰቅሱ አባላት ታሰሩባቸውስ ሲባል ሰምታችሗል?። አውቃለው ጥያቄዬ የሞኝ እንደሚመስል። የማነሳው ግን ህጋዊነት ላይ ጠንካራ እምነት አለችሁና እነሱ ከህግ በላይ ናቸው እንደማትሉ ገምቼ ነው።

ወያኔንና ወንጀሎቹንና ጥፋቶቹን በሚመለከት ተሳስታችሗል ስላልኩ አይክፋችሁ። ይህን ለጉድ የገነነብንን ድርጅት በሚመለከት  ማንም ሁሌ በሁሉ ነገር ትክክል ሆኖ አያውቅም። ሁሌ ትክክል መሆንም ለማንም ቀላል አልሆነም። በዙ ጊዜ የህዝብ ስህተተኛነት ከጨዋነትና አርቆ ከማሰብም እንደሚመጣም አሳምሬ አውቃለው። ደጋፊዎቹን እንተዋቸውና ወያኔዎችን በብዙ ድምር ምክንያቶች መሰረት አድርጎ  በጭራሽ የማይፈይድና ጎጂ ቡድን ነው። ለመልካም በቶሎ መጥፋት አለበት ብለን ያሰመርን ብዙዎች አለን። በሌላ ወገን ደግሞ በእምነቱ ለመቆየት የሚያያቸውንና የሚሰማቸውን አስገራሚ፤ዘግናኝ ጥፋቶችና ወንጀሎችን በሙሉ በሚቻለው ሁሉ አመክንዮ ሊሰራባቸው፤ትርጉም እንዲሰጡት ሲጥር ሲጥር የሚኖር አለ። ምክንያታዊ ለመሆን ከእለት እለት እየከበደውና እጅጉኑ እየተቸገረ  ያለ  ቢሆንም  ተስፋው ፈፅሞ ያለተሟጠጠ ወይ እንዳይሟጠጥ እየጣረ ነው። ይህ ክፍል ብዛቱ ቀላል የማይባል እንደሆነም ይታወቃል። ወያኔዎችን በሚመለከት ሁላችንም በሁሉ ነገር ሁሌ ትክክል ለመሆን ይከብደናል ስል ግን በሁሉም ወገን ያለነው ስህተት ስለምንሰራ ነው። የኔን በሰሞኑ የተገለፀልኝን ደደብ የነበረ ስህተት ልንገራችሁ።

በጠኔ ለሚሰቃይና ልጆቹን መመገብ ለቸገረው ብዙ ሚሊዬን ህዝብ እርቦናል ሲላቸው ጠግበሀል ብለው ሲከራከሩት እሰማለው።  አንዷለም እስክንድርና፤ ዞን ዘጠኞችን አሸባሪ ስለሆኑ ነው ብለው   ሲከራከሩ እሰማለው። ቦንብ አፈንድተው ገድለው እነንትና ናቸው  ብለው ሲከራከሩን እሰማለው። ቤተሰቦቻችንን ሰብስበው ልጆቻችሁን አሁን እንገላለን ወይ ልንገላቸው አምሮናል ሲሉና ሲደነፉ እሰማለው። እነዚህ እንደው ለምሳሌ ነው ያቀረብኳቸው። ሁሌና ሁሉ ነገራቸው አስገራሚ ድርቅና ያለበት፤ አሳማኝና አግባብ ያለው እንዲመስል እንኳ ቅንጣት ታክል የማይጨነቁበት እንደሆነ አውቃለው። የበዛ ድፍረትም አይባልም ጥጋብ ያለበቻው መሆኑን አውቃለው። በዚህ ደረጃ  ነው እየተረዳሗቸው ነው እንግዲህ።  እንደዚህ የሚያደርጉት ለምንድን ነው?። ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ስሞክር  የተሳሳትኩት።

የሚመስለኝ የነበረው ከጠቅላላ የመሀበረባችን ግንዛቤ፤ የድህነቱ ደረጃ፤ የበዛው ዜጋ ከነሱ ወገን የሚቀርበውን መረጃ ብቻ ስለሚያገኝ፤ ያልቆረጠለትና እንዲቆርጥለት የማይፈልገው ዜጋ ገና ብዙ ቁጥር ያለው ስለሆነ። ምንም ብንለው ሀሳቡን የገዛዋል ከሚል ነው አይነት  ምክንያቶችን እደረድር ነበር። የሚመስለኝ የነበረው እነዚህንና የመሳሰሉ ነገሮች በጥልቅ አስበው፤ አይተውትና አስልተው፤ ሌሎች መንገዶች መኖራቸውን ቢያውቁም ላሁን መፍጀቱ መቀጥቀጡና ማሰሩ ይሻላል፤ ያዋጣልም፤ ሰርቷልም ብለው በማወቅ የሚያደርጉት ነበር የሚመስለኝ። ስህተቴን ያሳየኝ በሰሞኑ በስዊድን ዜጎች ላይ ያደረጉት የመግደል ሙከራና እንግሊዛዊ ዜግነት ያለውን ግለሰብ መግደላቸው ነው። ለምን የነዚህ አገር ዜጎች እንደተመረጡ ማወቁ አልከበደኝም። ለምን መግደሉን መረጡ ለሚለው ጥያቄ ግን ከዚህ በፊት የምደረደርው ምክንያቶች አንዳቸውም በጭራሽ  እንደማይሆኑ ተረዳው። እስከዛሬም  ስህተቴ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን  እውነቱን ለማመን አለመፈለግ [Denial]  እንደነበረበትም አወኩ። ምን ላድርግ ስልጣን ላይ ያለን አካል በዚህ ደረጃ ለማወቅ የሚያስፈራ ነገር አለው።

ለማንኛውም ይህን በሽታ ዝም ብለን እንዲቀጥል አናድርገው። በጭራሽ አይቆምም። በአንክሮ ላጤነው በፈጠነ ሁኔታ እየጨመረ እየባሰበት እየሄደ ነው። ብዙ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ነገሮች አሉ። ልናደርግ የምንችለውን የምር አድርገን ልናስብበት ግን እንጀምር። ላሁኑ የተቃውሞ ሰልፎች ታቅደዋል እንቀላቀል። ሁላችንም ልናደረገው የምንችላቸው ቀላል የሆኑ ነገሮች ደግሞ ብዙ አሉ። እነዚህን አንዳኗም ሳናስቀር ሁላችንም ዛሬ ማድረግ እንጀምር። አሁን ለምሳሌ እድሜያችሁ ለመምረጥ የደረሳችሁ በሙሉ ማድረግ የምንችለው ስለሆነ እባካችሁ ሄደን የመምርጫ ካርዳችንን አሁኑኑ እንውሰድ። የተለያየ አመለካካት ምርጫው ላይ ሊኖረን ይችላል። ቅንጦት ቢኖርበትም ይህ ችግር አይደለም።  ልዩነቱ ላይ መጨቃጨቁ ይቀጥል። ማወቅ ያለብን አገዛዙ  ምርጫ አለ፡፤ ውጡና ምረጡ ብሎን ይህን ማድረጋችን ደግሞ የሚረብሸውና የሚያስጨንቀው መሆኑን ነው። ደግሞ ፍራቻው ምክንያታዊም ትክክልም ነው። ሁላችንም ከተመዘገብን ምርጫ የሚባለው ነገር እራሱ ቀርቷል ሊሉ ወይ ካርድ ሊያወጣ የተሰለፈ ህዘብ ላይ ደግሞ ልተወው። ብቻ ትግል ብለን ካደረግነው ትግል የማይሆን ምንም እስከጭራሹ ምንም ነገር የለም። እስቲ ነገ ፖሊሱንም፤ ወታደሩንም፤ ደህንነቱንና ካድሬዎችን በተለየ ሁኔታ ሞቅ አድረገን ፈገግታ መስጠትና ሰላም ማለት ሁላችንም እንጀምር። ድርጊታችንን ትግል ነው እንበለው። በእርግጠኛነት በነጋታው መሳቅ ከአሸባሪነት ጋር ተያይዞ በኢቲሺ ሲተነትኑበት ትሰማላችሁ። ቆያይቶ ደግሞ ማግጠጥ ይባልና ህገ መንግስትን በመናድ የሚል ህግ ተጠቅሶበት እስር ቤት የሚገባ ይኖራል። ብቻ ዝም አንበል። በሆነ መንገድ በግፍ ለገደሏቸው ወገኖቻችን መቆርቆራችንን እናሳይ። ላሁኑ እንጠራራ፤ እንሰባሰብ፤እንቀሳቀስ  ሄደን ከርዳችንን በእጃችን እናስገባ። የተቃውሞ ሰልፎችን በገፍ ወጥተን እንቀላቀል።

የሞቱትን ነብስ ይማር። መፅናናቱንና ጥንካሬውን ለሁላችንም ይስጠን።

የህወሃት በዓል ሳሞራ፣ አባዱላ፣ ንዋይ ደበበና ሰራዊት ክፍል1

$
0
0

የህወሃት በዓል ሳሞራ፣ አባዱላ፣ ንዋይ ደበበና ሰራዊት ክፍል 1
ሰሞኑን የ40ኛውን አመት የህውሃት ምስረታን በማስመልከት ብዙ የኪነጥበብ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ወደ ትግራይ ክልል በማምራት የወያኔን የትግል ታሪካዊ ስፍራዎችን ሲጎበኙ ከርመዋል:: ከጉብኝቱም በኋላ ብዙ የተለያዩ አስተያየቶችንም ሰጥተዋል ተብሎ አንብቤያለሁ:: እስቲ አንዳንዶቹ ያሉትን እንይ
-“የትግራይ ሕዝብ በፍቅር ሊገድለን ነው” ያለው አርቲስት አበበ ባልቻ ነው፡፡
-የደራሲያን ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው በለጠ በበኩላቸው “ያየነው ነገር ከነገራችሁንና ከጻፋችሁት በላይ ነው፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊመለከታቸው የሚገቡ ብርቅዬ ፍፃሜ የያዙ ዋሻዎች ናቸው:: ይኼ ታሪክ የትግራይ ሕዝብ ታሪክ ነው አላችሁት? እንኳን የትግራይ ሕዝብ ታሪክ ማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ማለትም ያንሰዋል፡፡ የመላ አፍሪካ ታሪክ ነው፡፡ መቀመጥም ያለበት እዚሁ ተወሽቆ ሳይሆን የአፍሪካ ኅብረት በሚገኝበት ሥፍራ ከኔልሰን ማንዴላ ጎን ነው፡፡ ይኼ ታሪክ ከእሱም በላይ ነው” ብለዋል፡፡
– አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ በተሳታፊዎች ከፍተኛ የድጋፍ ጭብጨባ የተደረገለት ይሄን ሲል ነበር “እስካሁን የምንሰማው ትግራይ ለምታለች፣ ተለውጣለች ሲባል ነው፡፡ ስንሰማው የኖርነውና አሁን በዓይናችን ያየነው ግን ለየቅል ነው፡፡ ሰው ሠራሽ ሐይቅ ያየነው ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ሕዝብ የተሠራ ነው፡፡ ተራራ እየፈነቀለ የሚሠራውን ተመልክተናል፡፡ የኑሮው ሁኔታ ግን ድሮ እንደነበረ ነው አልተሻሻለም፡፡ ይህንን በእውነት ልታስቡበት ይገባል፡፡ ይህንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለ ሕዝብ ልጆቹን ለመስዋዕትነት መርቆ የሸኘ ሕዝብ አልተካሰም፡፡ አሁንም እኔ የምለው አስቡበት ነው” በማለት አላበቃም፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የተመለከተው የልማት አማራጭ መንገዶች በዚህ ክልል ተግባራዊ የማይሆኑበት ምክንያት “ምንድነው?” ሲል ጠይቋል፡፡ ደጋግሞ ባለሥልጣናቱ እንዲያስቡበትም ተማፅኗል፡፡ የሚወራው ሌላ እየሆነ ያለው ሌላ”
ይህ ሰው ረሳው የትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም እንዳላገኘ ረሳው እንዴ?
-በመጨረሻም “የወያኔ ህወሃት ታጋዮች ምርጥ የኢትዮጵያ ጀግኖች መሆናቸውን አይተን አረጋግጠናል” በማለት፣ ሰማዕታቱ ትተውት ያለፉት ንፁህ ታሪክ ሳይበረዝና ሳይከለስ ለሕዝብ ለማሳወቅ በየሙያቸው እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል::
ይህንን ሲናገሩና ለተከታታይ ቀናት ጉብኝቱን ሲያደርጉ በነባር የሕውሓት መሥራቾችና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ታጅበው ነበር:: እነዚህ የኪነጥበብ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ኑሮ እጅግ በጣም ተወዶ ህይወት አንገብጋቢና ተስፋ አስቆራጭ በሆነበት በዚህ ጊዜ እንዲህ አይነት አድርባይነትን ከየትኛው የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ አስተዳደግ እንደተማሩት ማወቅ ተስኖኛል::
እነዚህ የኪነጥበብ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ዋናዎችን ባለስልጣናትን በመፍራትና በመሽቆጥቆጥ እናንተ ምንም አላጠፋችሁም የበታቾቻችሁ ናቸው ያስቸገሩት “እናንተን የማይመስሉ ባለሥልጣናት ሾማችሁብናል፡፡ ሕዝቡን ከታች እስከ ላይ እያማረሩ ነው፡፡ ትናንት የደማችሁለት ቅዱስ ዓላማ ዛሬ እየተበላሸና እየረከሰ ነው፡፡ አርሟቸው፡፡ እኛም ጦር ይዘን ከጎናችሁ እንቆማለን” ማለት እንዴት ነው የቻሉት?
የኢትዮጵያ ህዝብ ባሁኑ ሰአት እንኳን የፈለገውን መናገርና መጻፍ ቀርቶ ህወሃት እና ኢህአዴግን ካማና ስለመንግስት ክፉ ከተናገረ ግፍ እንደሚደርስበት ከነሱ በላይ የሚያውቅ ማን አለ? እውነት ግን የኪነ ጥበብ ሰው እንደዚህ ሞራሉን ገድሎ እና ስብእናውን አሳንሶ መኖር ይችላል? ጥበብ በእንደዚህ ያለ ደረጃ ሃገሬ ላይ መውረዷና መዋረዷ በጣም እጅግ በጣም አሳዝኖኛል:: የጥበብ ሰው እንደዚህ ረክሶ የህዝብን ችግር ከመናገር የመንግስትን ባለስልጣናትን መታዘዝንና ጥቂት ፍርፋሪ ለማግኘት እንደ ውሻ መኖርን እንዴት ይመርጣል? (አንዳንድ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆች እንዳሉ እንዳንረሳው)
የነበሩት ባለስልጣናት እኮ አቦይ ስብሐት ነጋ፣ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ አቶ አዲሱ ለገሠ፣ አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ካሱ ኢላላ፣ አቶ አባዱላ ገመዳ ታጋይ አቶ ቴድሮስ ሐጎስና ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ናቸው:: እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የሰሯቸውን ግፎች እነዚህ አርቲስት ተብዬዎቹ አያውቁት ይሆን? ጋዜጠኞቹስ?
መንገድ ላይ በጥይት ላለቁ ወገኖች፣ በየወህኒው የሚሰቃዩ ኦሮሞ ወገኖች፣ ከየቦታቸው ሚፈናቀሉ አማሮች፣ በግፍ የታሰሩ ሙስሊም ወገኖች፣ የክርስቲያን አባቶች፣ ጋዜጠኞች… ማን የሚሰራው ግፍ ነው?? እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ባለስልጣናት አይደሉም እንዴ?
ድሮም ቢሆን ሰው ለሆዱ መኖር ከጀመረ ምን ሰው ነው? ህሊና የሚባል ነገር የሌለው ሰው ምኑን ሰው ይባላል? በጣም ያሳፈርኝና እጅግ በጣም ከባድ የሞራል ዝቅጠት ነው ብዬ ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ያስገደደኝ ደግሞም በጣም ማመን ካለመቻሌ የተነሳ ያሳቀኝ ነገር ሁለት ነው::
– የመጀመሪያው ይህ የሰራዊት ፍቅሬ ፎቶ ነው:: ይህ ሰው የደርግ ወታደር ነበር ብዬ ለማመን ሁላ ከብዶኛል:: የደርግ የሽሬ ሽንፈትን ሲጎበኝ የህወሃት ታንክ ላይ የተነሳው ነው:: የራሱን ሽንፈት ሰላምታ እየሰጠ ያንቆለጳጰሰ ወራዳ ወታደር በአለም ላይ አለ ብዬም አላምንም::

hg

– ሌላው ደግሞ ነዋይ ደበበ አገሬን አልረሳም እያለ ከሳሞራ የኑስ እና ከ አባ ዱላ ገመዳ ጋር እየተቃቀፈ የሚዘፍነውን ሳይ ነው:: የዛሬ አስር አመት 1997 ላይ ይህ ድምጻዊ ከአሜሪካን አገር አንድ ፎቶ ልኮ ነበር በዛ ፎቶ ላይ ጣቶቹን የ‘V’ ቅርጽ ሰርቶ የቅንጅት ደጋፊ መሆኑን እና ወያኔ ነብሰ ገዳይ ነው ብሎ ስንት ሰው እንዳነሳሳ ትዝ ይለኛል:: እሱን ተከትሎ የሞተውን ወጣት እንዲረሸን ካደረገው ከሳሞራ ጋር እየተቃቀፉ መደነሱን ሳይ በጣም ልቤ ተረበሸ:: ንዋይ ደበበ ምንም ቢሆን ይህን ያረጋል ብዬ ስላላሰብኩ
እንግዲህ ይህን ካልኩ በኋላ ሌሎች የኪነጥበብ ሰዎች ደግሞ አላማቸው እና ህልማቸው እስኪሳካ በቻሉት አቅም ትክክለኛ ስነምግባር ለማነጽ ጥበብን ይጠቀሙበታል:: አሸርግዶና ተሞዳምዶ ተዋርዶና ክብርን ሸጦ መኖርን እጅግ ይጠየፉታል ሁልጊዜም ጥበብን እንደ ታላቅ ጸጋ ተቀብለው ከህዝባቸው ጎን እንደተሰለፉ በድህነትና በስደት ይኖራሉ እንጂ ክብራቸውንና ህሊናቸውን ሸጠው መኖር ስለማይመርጡም እንኮራባቸዋለን:: ለዛሬው በዚህ ላብቃና ለመሰነባበቻ

ስለ ኢትዮጵያ ብለህ ተነስ!!! –ከ- ሳሙኤል አሊ (ኖርዌይ)

$
0
0

የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል መሸከም ከምንችለው በላይ ሆኗል። ከጫንቃችን በላይ ሸክም፣ ከአእምሮአችን በላይ መከራ የሚደርስብን እየሆነ ከመጣ ዘመናቶች አልፈዋል። አሁን በዚህ በ21 ክፍለ ዘምን ላይ ዓለም በሰለጠነችበት እና እንደ ኔት ዎርክ በቀላሉ የዓለም ህዝብ በሚገናኝበት ዘመን ይህ ሁሉ በደልና አንባ ገነንነት ስርዓት አልበኝነት አገዛዝ በኢትዮጵያ መኖሩ ያሳዝናል። -—[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–

Download (PDF, Unknown)

 

samuel


ምክር እስከመቃብር  – (ከኣልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) –በእውቀቱ ሥዩም

$
0
0

እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)
የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር እየመጣሁ ነው፡፡ ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው፡፡እናቶች ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን እንዳትጀምሩት ኣደራ፡፡ ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ፡፡የጥይት መከላከያ ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ፡፡ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ እቆጣጠራለሁ፡፡ በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ፡፡ ባሩድ ኣገነፋለሁ፡፡ የታንክ ጎማ እነፋለሁ፡፡በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤ በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ፡፡
ይሄም ኣላዋጣ ካለ የኤፍሬም ይሳቅን ቡድን የሚፎካከር ኣስታራቂ ቡድን ኣቋቁሜ” ኣንተም ተው ኣንተም ተው፤ ያስታረቅሁበትን ኪሴ ውስጥ ክተተው” የሚል ኣገልግሎት እሰጣለሁ፡፡ቃሌ ነው፡፡የተናገርኩት ከሚጠፋ በቅርቡ የገዛሁት ጋላክሲ ሙባይል ይጥፋ(በዝች ንግግር ውስጥ የተደበቀ ጉራ እንዳለ እናንተ ሳትሉኝ ኣውቀዋለሁ)
ገና ለገና ካሜሪካ ሊመጣነው በማለት ማጅራቴን ለመመታት እያሟሟቃችሁ ያላችሁ ዱርየዎች እንዲሁም ከዱላ የተረፈች ማጅራቴን በማሸት ትርፍ ለማጋበስ የተሰናዳችሁ ወጌሻዎች ተስፋ ቁረጡ ፡፡ ቤሳቢስትን የለኝም፡፡(ማጅራት መምታት ሲነሳ ፋሲል ደመወዝ ትዝ ኣለኝ፡፡እንኳን እግዜር ማረህ ልለው ብደውል ከዲሲ በርሮ ኣትላንታ እንደገባ ነገረኝ፡፡ለኮንሰርት ይሁን ለስልታዊ ማፈግፈግ ኣልነገረኝም፡፡ ወይ ኣበሳ!እኛ ኢትዮጵያውያንኮ ምስኪን ነን ፤ ኣገር በቀል- ዱላ ሸሽተን ስንሄድ የውጭ ኣገር ዱላ ይጠብቀናል፡፡
ኣሜሪካ ሁለት ወር ስቆይ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ግብዣና ምክር ነው፡፡ዲታው ቢራ ጋብዞ ወደ ኣገርቤት ይዣት የምመለስ ቦርጭ ያወጣልኛል፡፡ቺስታው ቦርጬ እንዴት እንደምቀንስ ይመክረኛል፡፡ኣሜሪካ ፍሪሽ የሆነ ሰው ኑሮው ምክር እስከመቃብር ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ወደ ኣሜሪካ ገንዘብ የተላከለት የመጀመርያው ሰው ሳልሆን እቀራለሁ?
ለምሳሌ ጺም ለመቆረጥ ኣስር ዶላር መከስከስ ነበረብኝ፡፡ ፈርዶብኝ ኣሜሪካ ስገባ ጺሜ ያለወትሮው ቶሎቶሎ ማደግ ጀመረ፡፡ኣዲኣበባ እያለሁ ጺም ኣልነበረኝም፡፡እንዲያውም” ይሄ ልጅ ጺሚ የሚባል ነገር የለውም ስልብ ነው እንዴ?” የሚል ኣሜት በመንደራችን ይናፈስ ነበር፡፡ስልብ ኣለመሆኔን ለማሳየት ኣንድ ሁለት ቀን መንገድ ዳር ሸንቻለሁ፡፡

እንደልማዴ ከቀናኝ የሚጋብዘኝ ከፈረደብኝ የሚመክረኝ ኣላጣም በማለት Fenton መንገድ ላይ ወደሚገኝ ያበሻ ምግብ ቤት ጎራ ኣልኩ፡፡ ኣንዱ መድረክ ላይ የሱዳን ዘፈን ይዘፍናል፡፡ከተስተናጋጆች ውስጥ ኣንድም የሚያዳምጠው የለም፡፡ሁሉም ሙባይሉ ላይ ኣቀርቅሯል፡፡የታደለው ከፍቅረኛው በቫይበር የተላከለትን የክንፈር ምስል እያየ በደስታ ይዋኛል ፡፡ያልታደለው”የትምርት ቤት ክፍያ እየደረሰብኝ ስለሆነ ቶሎ ላክልኝ እንጅ”የሚል ካገር ቤት የተላከ መልክት እያነበበ ተክዟል፡፡ ሌላው ግድግዳው ላይ በተንጠለጠለው ቲቪ ላይ የሚተላለፈውን ያሜሪካ እግርኳስ እየተመለከተ ምድር ጠቦታል፡፡ ያሜሪካ እግርኳስ ቢሏችሁ እንደ ዋናው እግርኳስ እንዳይ መስላችሁ፡፡ ኣንዱ ጠብደል ጥቁር ሙልሙል ኳስ ይዞ ይሮጣል፡፡ሌላው ኣሳድዶ ይደርስበትና ዘርጥጦ ይጥለዋል፡፡ ለኔ ይህ ጨዋታ ሳይሆን ህጋዊ እውቅና ያለው ኣምባጓሮ ነው፡፡በዚህ መሃል ዘፋኙ “ከ እኔ ጋ ናችሁ?” እያለ ኣስሬ ቢጣራም ማንም ተጉዳይ ኣልጣፈውም፡፡ ልምምድ ላይ ያለ ይመስል ለራሱ ዘፍኖ ወረደ ፡፡ስላሳዘነኝ ባንኮኒውን እንደመቋሚያ ተደግፌ በጥሞና ኣዳመጥሁት፡፡ድምጹ ከዛፍ ላይ ኣምፖል ያረግፋል፡፡ቢሆንም ዘፈኑን ኣለቅጥ ያስረዝመዋል፡፡የሱን የሱዳን ዘፈን ታግሶ መጨረስ ሱዳንን በእግር እንደማቋረጥ ነው፡፡

ጥግ ላይ ክበበው ገዳ ተቀምጧል፡፡ ወንበር ስቤ ኣጠገቡ ተሰየምሁ፡፡ ራት ይጋብዘኛል ብየ ስጠብቅ ከራት ጋር የተያያዘ ገጠመኝ ጋበዘኝ፡፡
ክበበው ገዳ ጎረምሳ እያለ የለቅሶ ቤት እራት ኣያመልጠው ነበር፡፡ እንድያውም እንዲያባላኝ እያለ ቃሪያ በኪሱ ይዞ መዞር ጀምሮ ነበር፡፡ ኣንድ ለቅሶ ላይ ታድያ እራት ሲቀርብ ክበበው ከቤቱ ይዞት የመጣውን ቃርያ ከኪሱ ኣውጥቶ ኮርሸም ሲያደርግ የተመለከተ የሰፈር ልጅ ወደ ኣስተናጋጆች እያጨበጨበ “እዚህ ጋ ቃርያ ኣልደረሰኝም” ብሎ ጮከ፡፡

ኣለፍ ብሎ፤ የጃንሆይ ኣምባሳደር ዘውዴ ረታና ያሬድ ጥበቡ ቁጭ ብለዋል፡፡ያሬድ ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ሲሆን ዘውዴ የተንቀጠቀጠው ተራራ ነው፡፡ኣሁን ዲማሚቱና ተራራውም ባንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምው ሳያቸው ገረመኝ፡፡

ከማጅራቴ ኣካባቢ “ልትጽፍ ነው የመጣህ ኣይደል”የሚል ሹክሽክታ ሰማሁ፡፡ወይንሸት ናት፡፡ ባለፈው ኣመት ከባህል ቡድናችን ጋር ስትመጣ ኮከብ ድምጻዊ ነበረች፡፡ኣሁን እዚሁ ቀርታ ኮከብ ኣስተናጋጅ ሆናለች፡፡ኣፍንጫዋ ላይ የወርቅ ቡግር የመሰለ ሎቲ ለጥፋለች፡፡እዚህ ኣገር ሴቶች ሎቲ የሚያንጠለጥሉት ጆሮኣቸው ላይ ሳይሆን ኣፍንጫቸው ላይ ነው፡፡ ስለወይንሸት በሌላ ምእራፍ እተርካለሁ፡፡

በሩ ኣጠገብ ተኬን ኣየሁት፡፡ ተኬ በደርግ ዘመን ካይሮ ላይ ከጠፋው የብሄራዊ ቡድናችን ገንዘብ- ያዥ ነበር፡፡ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ባደረገችው በግጥምያ ዋዜማ ላይ በረኛውን ጨምሮ ብዙ ተጫዋቾች ስለኮበለሉ እሱ የበረኛውን ቦታ ተክቶ ተሰልፏል፡፡ ከተቃራኒ ቡድን የተለጋች ኳስ ወደእሱ ኣቅጣጫ ስትመጣ በገንዘብ ቆጠራው ለምዶበት ጣቱን በምላሱ እያጣቀሰ ሲርበደበድ ፤ ኣስራ ሰባት ጎል ገበቶበታል፡፡ (ምንጭ፡ የይድነቃቸው ተሰማ ሪፖርት)ተኬ ጉዳዩ ሲነሳበት ያማርራል፤“ይሄ ውለታ ቢስ ህዝብ የገባብኝን ኣስራ ሰባት ጎል እንጂ ያዳንሁትን ሰባት መቶ ጎል ኣላሰበልኝም” ይላል፡፡ካገሩ ወጥቶ መቅረት ኣሳብ ፈጽሞ ኣልነበረውም፡፡ይሁን እንጅ ይህን ሽንፈት ይዞ ጓድ መንግስቱ ፊት መቆም የሚያመጣውን ነገር ኣስቦ በዛው” ነካው“፡፡

ኣሁን በሩ ኣጠገብ ቁጭ ብሎ ”ብሉ ሙን“ ቢራ ይጠጣል፡፡ የቢራ ጠርሙሱን በጥርሱ ከፍቶ ቆርኪውን ጠረጴዛ ልይ ተፋው፡፡ቢራ መክፈቻ ቢቀርብለትም ተጠቅሞበት ኣያውቅም፡፡እግዜር መንጋጋን የፈጠረው ሲርብህ ኣጥንት እንድትቆረጥምበት ሲጠማህ የቢራ ጠርሙስ እንድትከፍትበት ነው ይላል፡፡

አቶ በረከት እሱን መች ጠየቅንህ?

$
0
0

January 1, 2015

Bereket በረከትህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) የተመሠረተበትን አርባኛ ዓመት ለማክበር ሽር ጉድ እየተባለ ባለበትና በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ የሀገሪቱ የገንዘብ ወጭ ተደርጎBereket-Simon አስረሽ ምችው የሚደለቅበት ሰአት ላይ ያለን ሲሆን የዘድሮው በዓል አከባበር ደግሞ የተለየ ሆኗል አስቀድመው ነው የጀመሩት ያም ሆነ ይህ በዓሉ ለምን ይከበራል? የሚያከብረውስ ማን ነው? ብለን ስንጠይቅ ድርጅቱ በጫካ አሥራ ሰባት ዓመት በትረ ሥልጣኑን ከጨበጠ በኋላ በከተሞች ለሃያ ሦሥት ዓመታት ያህል የምሥረታ በዓሉን በከፍተ የገንዘብ ወጭ እያከበረ ዘልቋል።በዓሉ የሚከበርበት ምክንያት፦ ህወሃት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሳበት ዓላማ ግቡን እየመታ በመምጣቱ፤ ከዚህ ግቡ የማይባሉ ሰዎችን ለሀገር ሥልጣን በማብቃቱ፤ጥቂቶቹን ሚሊየነር በማድረጉ፤የድርጅቱን ዓላማ የሚቃወሙትን እያወደመና እየበላ በመምጣቱ፤ ከሀገር እንዲሰደዱ በማድረጉ እንዲሁም አሰቃቂና ጭካኔ በተሞላበት ድብደባና እንግልት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ፤ጋዜጠኞች፤ ጦማርያን፤ የሃይማኖት መሪዎች፤ ተማሪዎች፤አስተማሪዎች፤ ነጋዴዎች፤አርሶ አደሮች ወህኒ ቤት ወርደው እንደ ብረት እየተቀጠቀጡ የሚገኙበት፤የሀገር ሀብት ተንጠፍጥፎ ካዝናው ባዶ እስኪሆን ድረስ ተጠርጎ ወደ ውጭ አገር ተልኮ በጥቂት ባለሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸው የግል ባንክ አካውንት በመቀመጡ፤ ከአጎራባች አገሮች ጋር የሚዋሰነው የኢትዮጵያ ለም መሬት በገፀ-በረከትነት የኢትዮጵያ ጠላት ለሆኑ አገሮች በመሰጠቱ፤በኢንቭስት-መንት ስም ነዋሪው ኢትዮጵያዊ ዜጋ እየተፈናቀለ መሬት ለውጭ ባለሀብት ያለምንም ክፍያ በመሰጠቱ፤ የንግዱም ሆነ የግብርናው ዘርፍ ሕዝብ የማይሳተፍበትና በባለሥልጣናት እጅ የገባበት፤አገሪቱ ወደብ አልባ የሆነችበት፤ አንድነት የጠፋበትና ለዘመናት አብረው በሰላምና በፍቅር በአንድነት የኖሩ ነገደ ኢትዮጵያውያን በጥርጣሬና በጥላቻ የሚተያዩበት ሁኔታ በመፈጠሩ፤ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ የተረገጠበት ላይ በመድረሱ ህወሃትና ጋሻ ጃጌዎችን የሚያስደስት ተግባር ከዚህ በላይ ስለማይኖር በዓሉ ይከበራል።

ይህን የህወሃት በዓል የሚያከብረው ማን ነው? የህወሃት አባላት፤ አመራርና ጋሻ-ጃግሬዎች ምስኪኑን ሕዝብ በቀጭን ትዕዛዝ በኃይል ተገዶ እንዲወጣ በማድረግ ሲሆን እምብኝ አልወጣም በዓሉ የኔ በዓል አይደለም ያለውን ደግሞ በታጠቀ ኃይል በመሣሪያ ጀርባውን፤ ግንባሩን በጠመንጃ አፈሙዝ እየተገጨ እንዲወጣ በማስገደድ ነው በዓሉን የሚያከብሩት። ከህወሃት አምባገነናዊ ባህርይ መልካም ነገር የማይታሰብ ቢሆንም ህወሃት ለተነሳበት እኩይ ዓላማ ፀንቶ የቆመ በመሆኑ በዓሉን አታክብር ማለት የዋህ የሚያስብል ይሆናል።ነገር ግን ይህን ጠባብና ዘረኛ ሥርዓት ማስወገድ አለብኝ የሚሉ ኃይሎች በዓላማቸው ፀንተው አንድነት ፈጥረው ትግል አለማካሄዳቸው ህወሃትን ለዚህ ያበቃው መሆኑን ግልጽ አድርጌ ማለፍ እወዳለሁ።ሕዝቡ በቃኝ ካለ ሰንብቷል፤ አመጽ ያረገዘ ሕዝብ ከየአቅጣጫው እየሰነዘረ ያለው ርምጃ የተቃዋሚ ኃይሎችን የሕዝቡ ትግልና አመጽ ጭራ አድርጓቸው እየታየ ነው።ስለዚህ የተቃዋሚ ኃይሎች (ድርጅቶች)ሕዝብ እየሄደበት ባለው ፍጥነት በመሄድ የማደራጀት ተግባር መቅደም አለበት ብየ አምናለሁ ወይም ይጠበቅባቸዋል።ይህ የሚያግባባን ከሆነ መነሻ ወደ አደረኩት ርእሴ ተመልሸ ከበረከት ህብረ-ብሄራዊ ድርጅት መቆም አልቻለም።ውሎ አድሮ ደግሞ ኢህአዲግ በሚል የጋራ ግንባር ሥር ገብቶ ወደቀ መጥፎ ቀን የኢህዲን ታጋይ ባመናቸው መሮዎቹ ሊወጣ ከማይችልበት እሥር ቤት ገብቶ የህወሃት ጥቅም አስጠባቂ ሆነ።እነዚህ ከላይ ስማቸውን የጠቀስኳቸው ግለሰቦች የታገሉት የአማራው ነገድ ሕዝብ በሚኖርበት አካባቢ ሲሆን አማራ ስለአልሆኑ ኃላፊነት በጎደለው መንፈስ የአማራውን ነገድ ሕዝብና አብሯቸው ይታገል የነበረውን ትውልደ አማራ እየበሉና እያስበሉ የመጡ የእናት ጡት ነካሾች ናቸው። ይህ አይነት የግድያ ተግባር በደርግ ጊዜ የተጀመረ ብቻ ሳይሆን ደርግ ከወደቀ በኋላም ተጠናክሮ ቀጥሏል። የመጀመርያው ዘመቻ አማራውን ማስወገድ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ደግሞ በኦሮሞው ላይ ይሆናል። የዚህን ጅማሮ እየተመለከትነው ነው።

4ኛ/ ህወሃት አንድ የሚመፃደቅበት አንድ ትራጀዲ አለ እሱም የብሄር ብሄረስቦችን መብት አረጋግጫለሁ የብሄር ብሄረሰቦች ምክር ቤት አቋቁሜ ያለሁ የሚለው ፈሊጥ ነው።እያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብና ጐሣ ወይም ነገድ ሕዝብ በሰላም ውሎ እንዳያድር የዲሞክራሲና የፍትህ፤የእድገት፤ የእምነት ጥያቄዎችን እንዳያነሳ እርስ በርስ እያናከሳቸው ይገኛል።በአጭሩ ለማሳየትም ሁለት ምሳሌዎችን ልጥቀስ በኢትዮጵያ ሶማሌና አፋር ክልል ግጭት ተፈጠረ የግጭቱ ፈጣሪ ራሱ ህወሃት ሲሆን የተሰጠው መፍትሄ ደግሞ በጣሙን የሚገርምና በሁለቱ ሕዝቦች መሀከል ያለውን ግንኙነት ለማሻከርና ተባብሶ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው። ሶሞኑን በአማራና በትግራይ አጎራባች ክልሎች የተፈጥረው ግጭት ሆነ ተብሎ በህወሃት የተፈበረከ ሲሆን ከሁለቱም ወገኖች ደም እንዲፈስ ንብረት እንዲወድም እስከወዲያኛው የማያገናኝ ተግባር እየተፈፀመ ይገኛል። ድርጊቱን የሚያስፈጽሙት እንደ እባብ ገላ ማንነታቸውን አውልቀው የጣሉ የለየላቸው ሆዳም የህወሃት ጀሌዎች አማራዎችና የወረራው ፊታውራሪ ህወሃት መሆናቸው ቢታወቅም ሰፊው የትግራይና የአማራ ነገድ ሕዝብ እንደ ድሮው እንደ ጥንቱ በአገራችን ባህል መሠረት የተጫረውን እሳት ሊያበርዱት ይገባል።በተለይ የትግራይ ሕዝብ ህወሃት ለአርባ ዓመታት ያህል መጠቀሚያ አድርጐ የተጠቀመበት ሲሆ ዛሬም ባድማው ባዶ እንዲሆን ከኤርትራ ሕዝብና ከአማራ ሕዝብ ጋር በማጋጨት ሰላምህን እያደፈረሱ ስለሆነ በቃችሁ በላቸው።

በመጨረሻም አቶ በረከት እሱን መች ጠየቅንህ በሚል የጀመርኩት ብእዴንም ወያኔዎች (ወየንቲ) ነን ብሎ የተናገረውን ሰምቼ ነው። ህወሃትን ከሚገባው በላይ ሲያወድስ ብእዴን እንዴት ይንከባከቡት እንደነበር ሲደርት ብእዴን የመጣ አሁን በዚያ ወቅት የነበረው ኢህዲን ይህንም መለየት ከማይችልበት የደረሰ ይመስለኛል ታናንት **ህወሃት የታገለው የአክሱማዊ ዳይናስቲን ለመመለስ አይደለም ** ያለው ጀግና ዛሬ ድመት እጅ እንደገባች አይጥ በጣም አንሶና አድርባይነቱን ሊሸፍን በማይችል መልኩ ሲዘላብድ ደደቢት ላይ ሆኖ የተወራ ወሬ ወይም ድስኩር አይሰማም ብሎ አስቦ ወይንስ አንዳች ነገር ወርዶበት? ህወሃት በዓሉን የሚያከብረው በየካቲት ነው ዘንድሮ አስቀድሞ ወደ ደደቢት ሄዶ ያን ያህል ውሽከታ ሲደረግ ግርምት ጥሎብኝ ነበር።

በረከት፦ ላንተ የሚቀርብህ ሻእብያ እንጅ ህወሃት አይደለም ብአዴን ልትሆንም አትችልም ምክንያቱም አንተ የሞቱት እማ ብሬና የአባ ገብረእግዚአብሔር ልጅ ነህ እነሱ ደግሞ ጥርት ያሉ ጨዋ ኤርትራዊ ናቸው ታዲያ አንተ ብሔረ አማራ ሆነህ እንዴት ነው አማራውን የምትወክለው? ይህን ነው መመለስ የሚገባህና የምንጠይቅህ ስለህወሃት ጀግንነት ስለደርግ ጨቋኝነት አንተ አትነግረንም ይልቁንስ አንተን ጨምሮ ከጌቶችህ ጋር የምታራምዱት ሥርዓት ምን እንደሚመስል ለማሰብ ሞክር። ወጣት ሴቶችና ወንዶች በዘመናዊ ባርነት ሥር እንዲወድቁ የሚያደርግ ህጋዊ የደላላ ጽ/ቤት ከፍቶ ስደትን የሚጠራ መንግሥት፤ በተለያየ ሱስ ተለክፈው መደበኛ ተግባራቸውን እንዳይፈጽሙ የሚያደርግ መንግሥት፤ በዓረብ አገር ያሁሉ ግፍ ሲፈጸም፤ ወደ ዓረብ አገር ለመሄድ በሽዎች የሚቆጠሩ ባህር ላይ ሰምጠው የአሳ ቀለብ ሲሆኑ ከየአቅጣጫው በኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት ሲደርስ ያንተ መንግሥት አንድም የደረሰ ጉዳት የለም፤ የሞተ፤የታሰረ የለም ብሎ ሞግቶናል የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን ጋዜጠኞችን፤ ጦማርያንን፤ ተማሪዎች አስተማሪዎችን ነጋዴውን፤አርሶ አደሩን የሃይማኖት መሪዎችን ማሰር መግደል አስሮ ማሰቃየት የሚል መርህ የሚያራምድና የዘረጋ ጭፍን አስተሳሰብ ከሚያስቡትና በቀልተኝነትን ከሚገፉት አንዱ አንተ ነህ ምናልባት ባንተ አመለካከት እንደ ኤርትራዊነትህ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ጥቃትም ሆነ ጉዳት ላይሰማህ ይችል ይሆናል ደግሞም ትክክል ነው። እኛ ግን እንጠይቅሃለን ማተብህን ከፈታህ ወዲህ በአስፈጃቸው አማራዎች ሁሉ እንጠይቅሃለን፤የመንግሥት ሥልጣንን መከታ በማድረግ በአባቶቻችን ደምና አጥንት ተከብሮ የኖረውን ዳር ድንበራችን በማስደፈርህ እንጠይቅሃለን፤አንዱን ጐሣ ከሌላኛው ጐሣ ጋር በማጋጨት ደም በማፋሰስህ እንጠይቅሃለን፤ ምስኪን አብሮ አደጐችህን የትግል ጓዶችህን ጊዜ ጠብቀህ ስለበላሃቸው እንጠይቅሃለን። ብአዴን እንዲፈርስ አንተም ከአማራ ሕዝብ ትካሻ እንድትወርድ ሌሎችንም እንዲወርዱ እንጠይቃችኋለን ፤የአማራ ዘር እንዲመክን በማድረግህ እንጠይቅሃለን።ለዛሬው ይህ ይበቃሃል ደጋግመህ አንብበው አያ በረከት።

ነብሮ ነኝ ከሰ/አሜሪካ

 የግቢዬ ዛፎች –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

አንድ በእድሜ ባለጸጋ የሆኑ አባት በግቢያቸው 14ት አይነት ዛፍ እየተንከባከቡ ያሳድጉ ነበረ። እነዚህ ዛፎችን አባዝተው ግቢያቸውን ሞልተውታል። የግቢያቸው ስፋት የዛፎቹ ልምላሜና የከለር ድምቀት ላየ ልብን ይማርካሉ። ህይወት ማለት እጽዋት እጽዋት ማለት ህይወት እንድሆነ በግቢው ያሉት ዛፎች ይናገራሉ። የዛፎቹ ልምላሜ ንጹ አየር የሚተነፍሱበት ከፀሐይ የሚጠለሉበት ከፍሬአቸው ምግብ የሚመገቡበት ባጠቃላይ ህይወታቸው ናቸው። በማለዳ  ጠዋት ተነስተው ከዘራቸውን  ይዘው ግቢውን ቃኘት ቃኘት እያደረጉ የደረቁ ቅጠሎችን በከዘራቸው እያራገፉ መሬት የወደቁትን እየሰበሰቡ ግቢያቸውን ከቃኑ በኃላ ነው ወደ ጉዳያቸው የሚሄዱት።

ለመሆኑ አልኳቸው አሁን ግቢዎትን እንደዚ የሞሉት 14ት የዛፍ ፍሬዎት ናቸው ? አልኳቸው።

አዎ አሉኝ ልባቸውን ሞልተው …ወዲያው ግን ክፍት ብሎአቸው ከ14ቱ አንዷ  በለሊት የመጣ ሽፍታ ቆረጣት በእጃቸው እያመለከቱኝ ያችትልህ ስር አላት ግንድና  ፍሬዎቻ ግን የሉም። የቀሩት 13ት ነበሩ በግቢየ የገባው ሽፍታ 9ኝ አስቀርቶ 4ቱን አጠፋው። ይሁን 9ኙ ዋና ዋና ናቸው ብዬም ዝም ብለው የ9ኙን ዛፍ ያለኔ ፈቃድ ማንም እንዳይነካ ፍሬአቸውንም ያለኔ ፈቃድ ማንም እንዳይመገብ ብሎ የሽፍታ ህግ አውጥቶ  ግቢዬን  በመሳሪያ  አጠረው። ግቢዬም በሽፍታ ተወረረ ፍሬዎችንም ያለግዜው ሳይደረሱ በላቸው የዛፎቼን ውበት አጠፋቸው በፊት እንደ ልቤ ተዘዋውሬ የምንከባከባቸው እንደልቤ ከፍሬአቸው የምመገብባቸው በፍቅር የማያቸው ተክሎቼን ድንበር አበጅቶላቸው እንዳልጎበኛቸው አጠራቸው። ድንበሩም ባልከፋ ግን ሽፍታን ማን ያምናል? የሽፍታ  በኅሪ ያው ሽፍታነት ነው ዘረፎ መብላት ገድሎ መኖር። ለዛፎቹ 1,2,3,4,5,6,7,8,9 ቁጥር ሰጣቸው አንድ ላይ አንድ ይኑር ሁለት ለይ ሁለት ይኑር እያለ ለዘጠኙም ተናገረ። የአንድን ሁለት እስከ ዘጠኝ ያሉት እንዲነኩ አይፈቀድላቸውም የሁለትንም እንደዚሁ እያለ እስከ ዘጠኝ ይቀጥላል ለምን ሲባል ሁሉም በራሱ  እንዲኖር ነው ይላል። አንድ ለአንድ ሁለትም ለሁለት ሶስት ለሶስት አራትም ለአራት እያለ ዘጠኙም ስለራሳቸው የመብት ጥያቄ ሲያነሱ ሽፍታነቱ ይመጣና ብረቱን አንስቶ መፍጀት ይጀምራል ምን አገባችሁ ከ1-9 ያሉት የዛፎቹ ባለቤት እኔ ነኝ በኔ ስር እስካላችሁ ድረስ ከኔ ሃሳብ ውጪ ማሰብም መጠየቅም አትችሉም ሃሳባችሁን በኔ ሃሳብ ልክ ስፉት እያለ  ሽፍታነቱን ያሳያል። አንድ በሁለት ለይ ሁለት በሶስት ላይ ሶስት በአራት ለይ ሲነሱ ግን ቁጭ ብሎ  ይስቃል የእርስ በራስ ፍጭቱ ሽፍታው የሚኖርበትን ዘመን ስለሚያራዝመው እንደዚህ አይነቱን ግጭት ይናፍቀዋል የናፈቀው ነገር አልሰራ  አለው እንጂ። ዛሬ 9 ያደረጋቸውን ነገ 19 ሊያደረጋቸው ይችላላ 9ኙ በ9ኝነታቸው እንዲቆዩ አልያም ወደሚፈልጉት ኃሳብ መድረስ እንዲችሉ ሽፍታን ከስሩ ነቅሎ ዳግም እንዳይመጣ ማድረግ ያስፈልጋል። ሽፍታ  በራሱ ህግ በየግዜው አንድ ነገር ብልጭ ስትል ለብልጭታ አዲስ ህግ እያወጣ ግቢውን አመሰው ወይ ግቢውን መምራት አልቻለ ወይ ፍሬውን በአግባቡ መመገብ አልቻለ ብቻ ዘይት እና  ውሃን ለመቀላቀል ይሞክራል  ደግሞም ይላል በኔ ዘመን(በሽፍታው ዘመን) ዘይት እና  ውሃ ሲቀላቀል ታያላችሁ በግቢው ለሚኖረው ነዋሪ በሙሉ የኔን ቃል የመቀበል ግዴታ አለበት የማይቀበል ቢኖር ግን ዘይት እና  ውያ መቀላቀላቸውን ሳያይ ይወገዳል። የሚል የሽፍታ ህግ አጽንቶ ግቢውን አምሶታል። እኔም መልእክቴን ላስተላልፍና  ወደ ተከለለው ግቢዬ ልግባ። በግቢ ውስጥ አንቱ የተባሉ የተከበሩ ሽማግሌዎች አሉ። እግዚአብሔርን ሲያመልኩ በእድሜ የሸመገሉ፣ አላህን ሲያመልኩ በእድሜ የሸመገሉ፣ ዋቄፈናን ሲያመልኩ በእድሜ የሸመገሉ እናንተ በእውቀት የበሰላችሁ ብዙ ፍሬ  ያፈራችሁ አባቶች ስለ  ግቢያችሁ የምታስቡ ስለ ዛፎቻችሁ የምትጨነቁ ስለ ፍሬዎቻችሁ የምትጓጉ አባቶች ስለ  ግቢያችሁ አስቡ ስለ ዛፎቻችሁ አስቡ ስለ  ፍሬዎቻችሁ አስቡ። ግቢ የተባለችው አገር ናት። ስትደሰቱ የምትደሰቱባት ስታዝኑ የምታዝኑባት አርሳችሁ የምታበቅሉባት ነግዳችሁ የምታተረፉባት ተምራችሁ የምታስተምሩባት ደምቃችሁ የምትታዩባት ከደምና ከአጥንታችሁ የተሳሰረች ይህቺ ናት አገርህ።  ዛፎች የተባሉት 9ኙ ክልሎች ናቸው። በእድሜ ከፍ ከፍ የምትሉበት ከራሳቸው ሽበት ከአእምሮአቸውም በሳል እውቀት ከአንደበታቸውም ጠጋኝ ቃላት የሚናገሩባት የሚኖሩበት። አባት.. አባት እናት.. እናት ብለን የምንጠራቸው መኖሪያ፣ ቄዬ.. ቄዬ አድባር.. አድባር የምልበት፣ ሰፈር.. ሰፈር መንደር.. መንደር የምንልበት፣ ጎሳ ..ጎሳ ብሔር.. ብሔር የምንልበት፣ እሷ ናት ክልልህ። ፍሬ የተባሉት ደግሞ ሮጠው ያልጠገቡ፣ ቁልቁለት ዳገቱን ሜዳው ላይ የሚቧርቁ፣ ነገ አባት እናት የሚሆኑ፣ ነገ የሰፈር መሪ፣ የመንደር መሪ፣ የጎሳ መሪ፣ የክልል መሪ፣ የአገር መሪ የሚሆኑ፣ ነገ  ጳጳስ፣ ሼህ፣ አባ ገዳ፣ የሚሆኑ እነሱ ናቸው ፍሬዎች።

ሽፍታ  ግቢህን ወሮታልና የፈለከውን ላማድረግ የፈለከውንም ለመስራት አትችልም። ምክንያቱም የሽፍታ  ባህሪ ከራሱ ውጪ የሚሰማው ነገር ስለሌለ። ትላንትና 14 ዛፍ የነበርክ የአገሬ ዛፍ ሆይ ዛሬ 9ኝ ሆነኻል ይህ ጥሩ ባልከፋ ነገር ግን ሽፍታ  ነግሶ ባለበት ግቢ ውስጥ ነገ ምን እንደሚልና ምን እንደሚሰራ አይታወቅም እና የግቢ ነዋሪዎች ግቢ ማለት አገር እንደሆነ ጠቅሻለው የማን ግቤ ያልተደፈረ የማን ፍሬ ሳይደርስ ካለግዜው ያልተቀጠፈ የማን ዛፍ ያልተለመለመ የለም ከአንድ እስከ ዘጠኝ ብንሄድ ዘጠኙም ዛፍች  ሃዘን ላይ ናቸው። እህህ…. የማይል የለም። ሽፍታ እስካለ ሃዘን ለቅሶ ችግር ስደት ድህነት ፍቅር ማጣት የደስታ ህይወት ባጠቃላይ ሰላም በግቢህ ውስጥ አይኖርም። ደስታ ሰላም ፍቅር ነጻነት እድገት የምንፈልግ ከሆነ ሽፍታን መጣልና  ማጥፋት አለብን። ሽፍታ  የሚጠፋው በልመና ሳይሆን በሽፍታነት ነው። ሽፍታ  የሚፈራው ሽፍታን ብቻ ነው። እናንተ  ዘጠኙ ዛፎች የናንተ  ሽፍታነት ሽፍታን እስከሚጠፋ  ብቻ  ነው እንጂ ነገ ሽፍታው ከጠፋ  በኃላ እናንተም ሌላ ሽፍታ  እዳትሆኑ አጥብቄ እነግራችኃለው።

 

በዚህ አባባል መልእክቴን ልጨርስ <<<የማትረባ  ፍየል ዘጠኝ ትወልድና

እርሷም ትሞታለች ልጆቿም ያልቁና>>>

እንዳይሆንብን ስለ አገርህ ስትል፣ ስለ አባት እናትህ ስትል፣ ስለ ባል ሚስት ስትል፣ ስለ ልጆችህ ስትል፣ ሽፍታውን በማስወገድ ከፊታችን የተጋረጠውን ጨለማ ገፈን ሰላም የነገሰበት አገር እንመስርት።

 

rtከ-ከተማ ዋቅጅራ 31.12.2014

Email-waqjirak@yahoo.com

ሃገራችን ኢትዮጵያ በፈረንጆች ኣዲስ ዓመትስ? -ገብረየሱስ!

$
0
0

በደርግም ይሁን ላለፉት 23 ዓመታት፤ በኛ በኢትዮጵያውያን የኣዲስ ኣመት መለዋወጫ ግዜ የኣመለካከት እና የተግባር ስራ መሻሻል ስለማናደርግ እስቲ በኣውሮፓውያን ኣዲስ ዓመት መለዋወጫ እንመኩረው ብየ ኣሰብኩኝ። ምን ነው የሌሎች መዋስ መረጥክ የሚል ኣይጠፋም። የውጭ ስልጣኔ ያልተማጸነ ኣልነበረም መጥፎውን እየተውን። ኣሁንማ በውጭ ያለነው በሚልየን ስለሆን ኣንድ ሊያደርገንም ይችላልና ኣይጠላም።

ስለዚህ ላለፉት 23 ዓመታት ወያኔ/ኢህኣዴግ እና ተባባሪያቸው እንደደላቸው፤ ሌላው ወገን ደግሞ ሲሰቃይ እንዳለ ግልጽ ነው። የሃይማኖት፣ የስርዓት፣ የባህል፣ ኣትንኹኝ ባይነት የነበረች ሃገር፤ ለወያኔ/ኢህኣዴግ መስገድ ኣልያም ቤት ኣልባ እንደመሆን ተደርሶ መሬት ላራሹ እንዳልተባለ መሬት ለባእዳን እንዲሰጥ ህዝብ መሬት ኣልባ ሁነዋል። ፍጥጫው በወያኔ/ኢህኣዴግ እና በተቃዋሚ ደጋፊዎች ተፋጥቶ፣ የመለያየት እንጂ የመደማመጥ ባህል ጠፋ። ኣውሮፓውያን እየተደማመጡ ኣንድ ሁነው በሰላም ይኖራሉ። ኣክራሪነትና ጠባብነት መለያችን ኣድርገን ክርቢትና እሳት ሁኖ እየተቀጣጠለ የባሰ ኣስከፊ ክስተት የምናይበት ሁነታ እየገባን ነው። ቂም በቅል እንጂ ሰው መሆናችን ኣልታነጸም።

 

ኣሁን ችግሮቻችን ተገዝበን እንዴት ወደ ኣብሮ የመስራት ባህል እንሸጋገር ነው ጥያቄው???  

ግልጽ እንሁንና የሚሰማንን ኣውጥተን፣ የሚያዳምጥ ልቦናም ሰጥቶ፣ ይቅር ይቅር ተባብለን ወደ ተሻለ ደረጃ መሸጋገር ኣለብን። ካልሆን እንዳለፉት 44 ኣመታት መጠላለፍ፣ መገዳደል፣ መበታተን እና ፍዳችን ማየት ነው። ሰለዚህ፤

፩ ኦሮሞዎች ኣጼ ሚነሊክ በድለውናል ይላሉ፣ ትክክል ነው እንቀበለው።

፪ ትግሬዎች ኣጼ ሚነሊክ ኣደሀዩን ይላሉ፤ ትክክል ነው እንቀበለው።

፫ ኤሬትርያኖች ኣጼ ሚነሊክ ለጣልያን ሸጡን ይላሉ፣ ትክክል ነው እንቀበለው።

፬ በኣጼ ሚነሊክ መሪነት ኢትዮጵያውያን ኣንድ ሁነው ወደ ዓድዋ ዘምተው፣ የሰለጠነውና ሃያሉን ጣልያን

ኣሸንፈዋል፤ ትክክል ነው እንቀበለው። እምየ ለሚሉዋቸውም መብታቸው ነው። የተበደለው ዓማራ ትተን።

፭ ዘውዳዊው መንግስት እና ባልደሮቦቻቸው (ከኣማራ፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሞ፣ ከሃድያ፣ ወዘተ) ሲደላቸው ሌላው

ተበድለዋል፣ ትክክል ነው እንቀበለው።

፮ በደርግ የምንለያይ ኣይመስለኝም።

፯ መኢሶን እና ኢህኣፓ ከኣመራር ኣለመስማማት ተጨራረሱ ትክክል፣ ፍርዱ በምስክርነት በፍርድ ቤት ይፈጸማል።

፰ የርስ በርስ ኣለመስማማት ወደ ጦርነት ገብተው መጨረሻው ህወሓት ኣሸንፎ ኣዲስ ኣበባ ገባ። ወያኔ ስልጣን

ኣላካፈልም ብሎ ሌላውን እያባረረ፣ እያሰረ፣ እየገደለ፣ ንግድ እያካሄደ ሙሱና ነግሶ፣ የሌላውን መብት በኔ መስፈርት

ካልሆነ ወየላቹህ ብሎ፣ ሃገሪትዋ የሶማሌ እጣ ሊደርስባት ወደሚችል መንገድ እየመራት ነው።

የፈረንጆች 2015:

ብርቅየው ኒልሰን ማንዴላ ለበዳዮቹን ይቅር ብሎ በህግ እንዲጠየቁ እንዳደረገ ሁሉ፤ እኛም ሌላውን ኣልተበደልክም ከማለት፣ ሰምተን በጥናት ቀርቦ እንድንማርበት እንቀበለው። የብሄሮችና የብሄረሰቦች መብትና ኣደገጃጀት የደረሰበት ተገንዝበን፣ ባንዲት ኢትዮጵያ ስር እንዴት እንደሚተዳደር ረጋ ብለን ማገናዘብ ኣለብን። ለስልጣን የሚደረገው ሩጫ ተስፋ የለውም። ኣብረን ሁላችን ህገ መንግስት ማጽደቅ ነው ያለብን። ከዛ ነጻ ማህበራት ማደራጀትና ነጻ ምርጫ ማካሄድ። ውጤቱን ያለ ምንም መቀባጠር መቀበል፣ ለተግባራዊነቱ በትጋት መስራት። የዘርና የክልል የፖለቲካ መደራጀት የትም ኣያደርስም፣ የማይፈታ ህልም ነው። ስለዚህ ያመለካከት ለውጥ ከራሳችን ይጀምር። ሌላውን እናክብር። ኣብረን እንስራ። ሃገርና ህዝብ በህግ የመላይነት ይተዳደሩ። የፈረንጆች ዓዲስ ዓመት ለሁላችሁም መልካምን እመኝላቹሃለሁ። ወገኖቼ ያባረሩኝ ፈረኝጆች ተቀብለው በሰላም ኣኑረውኛልና እግዝኣብሔር ይባርካቸው። እነሱን የደረሰቡት ማልካሙን ያድለን።

 

comment picገብረየሱስ!

ለምን ወለድናቸው?። –ዳዊት ዳባ።  

$
0
0

ፖሊስ የደብረ ማርቆስ ተማሪዎችን እየደበደበ ነው፡፡ የትናንትናው ተቃውሞ በኢሳትና በሌሎች ሚዲያዎች መተላለፉን ተከትሎ ‹‹ማን ነው ከኢሳትና ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር እየተደዋወለ መረጃ የሚሰጠው?›› እንዲሁም ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ካለ ተናገሩ›› በሚል ተማሪዎቹን አሳልፈው እንዲሰጡ ከፍተኛ ደብደባ እየፈጸመ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡ ፖሊስ አሁንም ተማሪዎችን እየፈለገ እያሰረ መሆኑም ተገልጾአል ይላል የዛሬ ዋና ዜና።

deberemarcos-7ለምን ለሚልና ላልሰማ። ወያኔዎች አንድ ቀን ቀደም ብሎ ‹‹የአብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና በደብረማርቆስ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (መሰናዶ) ተማሪዎች መስጠት ጀመሩ። ክርክሩን በኢሳት ራዲዬ የሰማን በሙሉ ምስክር ልንሆን በምንችልበት  ህፃናቱ  በሀሳብ  ሞግተው ግልፅ ሆኖ በሚታይ ሁኔታ የስርአቱን ካድሬዎች አሸነፏቸው። ያነሷቸው ጥያቄዎችና መከራከሪያዎች ፍፁም እውነትነት ያላቸው፤ ብስለት የተሞላባቸውና ስክን ባለ ሁኔታ የሚቀርቡ ነበሩ። አይደለም ተራ ካድሬዎች አውራዎቹም ቢመጡም የሚቋቋሟቸው እንዳልሆነ ላዳመጠው ሁሉ ግልፅ ነበረ።  ካድሬዎቹ  ለጊዜው   እንደ መፍትሄ አድርገው በተለመደው የመከፋፈል ዘይቤ ህፃናቱ ይሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ ወጥተው 20፣ 20 ሆነው በጠባብ ክፍል እንዲሰለጥኑ በማድረግና ጥያቄ የሚያነሱትን በማስፈራራት ሊወጡት ሞከሩ። ህፃናቱ  በዚህም የሚሸነፉ አልሆኑም ማለት ነው። ይህው በሚቀጥለው ቀን ወያኔዎች ወደሀይል እርምጃ መግባታቸውን የሚያሳይ ከላይ የተቀመጠውን አሳፈሪም አሳፋሪም ዜና ሰማን።

እነዚህ ልጆች ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ታዳጊ ህጻናት ናቸው። ወዲያም አደረግነው ወዲህ ደህንነታቸው በዋናነት በቤተሰብና በማህበረሰቡ ሀላፊነት ላይ ነው ገና ያለው። ጥቃት እየፈፀመባቸው ያለው አካል ስራው ደህንነታቸውን መጠበቅ ይገባቸው ከነበሩት አንዱ  “መንግስት” ተብዬው ነው። ይህ አካል ሁላችንንም እየቀጠቀጠ እየገዛ ያለና አሁንም ቤተሰብ ለምን ቢል ጥቃት ከመሰንዘር የማይመለስ መሆኑ ቢታወቅም።  በአጠቃላይ እጅግ ግዙፍ የሆነ ባላንጣ  ቢሆንም። እነዚህ ልጆች ለብቻቸው መተው ግን በጭራሽ የለባቸውም።ቤተሰብም ማህበረሰቡም ዝም ብሎ ይህንን ህፃናት ልጆቹ ላይ የሚፈፀም ወንጀል መመልከት የለበትም።  እጅጉኑ  ዝም ልንለው ከሚገባው በላይ ያለፈም ነው።

ህፃናቱን ምን አድርጉ ነው የሚላቸው። 90%የሚሆኑት ለመምረጥ ገና እድሜያቸው አልደረሰም። ምረጡኝን ምን አመጣው። በጣም ከጥቂቶች በቀር አስራ ስምንት አመት ገና ያልሞላቸው አማካኝ እድሜያቸው አስራ ስድስት አመት አካባቢ የሆኑ ታዳጊ ህፃናት ናቸው። የትኛውንስ ርእዬት አለም  ለማጥመቅም ሆነ ተከታዬ ሁኑ ለማለት ቤተሰቦቻቸውን አስፈቅዷል ወይ?። ተጠይቀንስ ፈቅደናል ወይ?። ይህም ሆኖ መታወቅ ያለበት ለአቅመ አዳም ለደረስነውም   ማስገደድ ከባድ  ወንጀል ነው።  ህፃናትን አስገድዶ ተከታዬ ሁኑ፤ አስገድዶ ምረጡኝ ማለት አስገድዶ ከመድፈር በምንድን ነው የሚለየው?። ይህ አላንስ ብሎ መደብደብ፤ ማሰር፤ ትምህርታቸውን ማስተጓጎል፤ ማሸበርንስ ምን የሚሉት?፤ ማን አለብኝነትስ ነው?። እንዴትስ ነው ይህ ዝም ተብሎ የሚታየው?። ለልጆቹስ ይወጡት ተብሎ የሚተወው።

ልጅ እያለው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲለቀቁ እየጠበቅን ቾክ እንለምን ነበር። ልጅ ስለነበርኩም ይሆናል ተማሪዎቹ ጠብደል ጠብደል ያሉ፤ በስርአቱ የለበሱና ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚሄዱ ጎልማሶች ነበሩ።  እኔ ሁለተኛ ደረጃ ስደርስ እንደጠበኩት አልነበረም። ገና ፔፕሲ፤ ሱዚና ሌባና ፖሊስ እረፍት ላይ ቅልጥ አድርገው የሚጫወቱ ነበሩ። አሁን ደግሞ ልጆቼ ናቸው። አውቃለው በእርግጠኛነት በጣም በለጋ እድሜ ያሉ ታዳጊ ህፃናት ናቸው። በዛ ላይ ገና አስረኛ ክፍል ያልደረሱ።

 

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>