Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

አሳዛኙ ብሔራዊ ውርደታችን

$
0
0

ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? የአሜሪካ አምባሳደር ለኢትዮጵያ መንግስት በቀይ ባህር ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ ላኩ።ኢህአዲግ/ወያኔ እስካሁን አንዳች አልተነፈሰም።Statement by Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ላይ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች በየመን የባህር ዳርቻ፣ በቀይ ባህር ውስጥ ከሰባ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መስመጣቸው መሰማቱ ይታወቃል።ጉዳዩ በሀገር ቤት እና በመላው ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ሃዘን አስከትሏል።

ከእዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያውያንን ልብ ያደማው ጉዳይ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የዜና አውታሮች የተቀባበሉትን ጉዳይ ላይ አንዳች የሃዘን መግለጫ አለማሰማቱ ነው።በትናንሽ አደጋ ለሞቱ ለሌላ ሀገር ዜጎች የሃዘን መግለጫ በማውጣት እና በመላክ የሚታወቀው ኢህአዲግ/ወያኔ ለኢትዮጵያውያን ሞት አንዳች አልመተንፈሱ ሌላው የብሔራዊ ውርደታችን መገለጫ ነው።በሳውዲ ጉዳይ መንግስት እንደሌለን አውቀን ነበር።ዘንድሮም በቀይ ባህሩ አደጋ አረጋገጥን።በፌስቡክ ገፃቸው የእየእለቱን ውሎ የሚለጥፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሰሞኑን ከ 300 ሚልዮን ብር በላይ ወጣበት ስለተባለው በአሶሳ ስለነበረው ብሔር ብሄርሰቦች በዓል ማውሳታቸው ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? ብለው ብዙዎች እንዲጠይቁ ማስገደዱ አልቀረም።

ከእዚህ በታች በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ከሰባ በላይ ለሚሆኑት በቀይ ባህር ሕይወታቸው ላለፈው ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ አወጣ።የኢትዮጵያ መንግስት ስለጉዳዩ እስካሁን ድረስ ምንም አላለም።

”ትናንት በየመን የባህር ዳርቻ ቀይ ባህር ውስጥ በሰጠመችው ጀልባ ሕይወታቸው ባለፈው ኢትዮጵያውያን የተሰማኝን ትልቅ ሃዘን ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለሟቾች ቤተሰብ እገልፃለሁ።ልባችን ከሟቾች ቤተሰቦች እና ወዳጆች ጋር ሁሉ ነው” በኢትዮያ የአሜሪካ አምባሳደር ወ/ሮ ፓትሪሽያ ሃስላች

Source – US EMBASSY ADDIS ABABA

http://ethiopia.usembassy.gov/latest_embassy_news.html

”I would like to offer my condolences to the government of Ethiopia and the families of the many victims, including Ethiopian citizens, who drowned in the tragic sinking of a boat off the coast of Yemen in the Red Sea yesterday. Our thoughts are with the families and friends of those who died.” Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

ከእዚህ በታች ያለው ቢቢሲ አደጋውን አስመልክቶ የዘገበው ነው።

Yemen migrant boat carrying Ethiopians sinks killing 70

Source - BBC
A boat carrying African migrants has sunk off Yemen’s western coast, killing 70 people, Yemeni officials say.
The boat, carrying mostly Ethiopian migrants, sank off Yemen’s al-Makha port due to strong winds and rough waves, security officials said.
Tens of thousands attempt to cross the Red Sea into Yemen every year, often in rickety, overcrowded vessels. Hundreds have died making the journey.
Yemen is viewed by many migrants as a gateway to the Middle East or Europe.
The latest sinking occurred on Saturday, with reports of the incident emerging on Sunday.
The Red Sea crossing between the Horn of Africa and Yemen is one of the world’s major migration routes, BBC Arab affairs editor Alan Johnston says.
Migrants dream of finding jobs and better lives in rich places like Saudi Arabia – but they are in the hands of unscrupulous people smugglers and, too often, never reach the Yemeni shore, our correspondent adds.

 

In October, the UN refugee agency said that more than 200 people had died at sea in 2014 while attempting to reach Yemen.
“There have been frequent reports of mistreatment, abuse, rape and torture, and the increasingly cruel measures being adopted by smuggling rings seem to account for the increase in deaths at sea,” the UN said at the time.

 

 

Source:: gudayachn


ግንቦት ሰባት ሆይ…. ከሄኖክ የሺጥላ

$
0
0

Henok Yeshitila

Henok Yeshitila


ውድ ወዳጆቼ ሆይ ፣ ዛሬ ተክሌን መሆን አምሮኛል ( ተክሌ ይሻውን ሳይሆን ተክለሚካዔል ሳህለ ማርያምን )። ልጅ ተክሌ መቼም እኔ’ነቴን ለምን ወሰድክብኝ እንደማትለኝ ነው ። እንኩዋን እኔነት ፣ የእኔነት መፈጠሪያ የሆነችውን ሀገርህን ወስደዋትስ የለ ።

የዛሬ ጽሁፌ የሚያጠነጥነው ትልቁንና እና ጠንካራውን ድርጅት ግንቦት ሰባትን ላይ ነው ። እንደውም ጽሁፌን ከማውጠንጠን ማነጣጠር ሳይሻል አይቀርም ( የታጠቀን እንዲያ ነው እንጂ !) ። እና የምወደውን ግንቦት ሰባት ፣ ባልሞትለት እንክዋ የምደማለት ግንቦት ሰባትን ፣ የኔ የምለውን ግንቦት ሰባት ፣ የ አንዳርጋቸውን ግንቦት ሰባት ፣ የብርሃኑ ነጋን ግንቦት ሰባት ፣ የዔፍሬም ማዴቦን ግንቦት ሰባት ፣ የአበበ ገላውን ግንቦት ሰባት ፣ አዎ ስለሱ ነው ።
andargachew
አንተ ግንቦት ሰባት ሆይ ፣ አንተን ካወቅኩበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ትቢት ትቢት ይለኛል ፣ ወያኔ ምን ለማስፈራራት ቢሞክር ፣ ነገራቸው ሁሉ ድንፋታ እንጂ አንዳች ፍርሃት ልቤን ይሁን ሆዴን ቅም አይለውም ፣ ስላንተ ሳስብ አባቱን ከሩቅ እንዳየ ህጻን እፈነድቅአለሁ ፣ ስምህ በክፉ ሲነሳ ፊቴ ደም ይለብሳል ፣ የባንክ ደብተሬ እንኩዋ ዜሮ እያሳየ ስላንተ ስሰማ ምን እንደሆነ ባላውቅም መንዝር መንዝር ይለኛል ፣ ዘርዝር ዘርዝር ይለኛል ፣ ያም ሆኖ አንዳርጋቸው ከታሰረ ወዲያ ላንተ ያለኝ ፍቅር ወደ ንዴት እየሄደ ነው ። ይሄም የሆነው አንዳርጋቸው በመያዙ ሳይሆን ፣ የአንዳርጋቸውን መያዝ ተከትሎ ይህ ነው የሚባል አጸፋዊ እርምጃ ባለመውሰድህ ነው ። ሰማያዊ እንኩዋ ነጭ እርግብ ጭንቅላቱ ላይ አድርጎ ሰላም ሰላም እያለም ፣ እየተገፈተርም ቢሆን ሰልፍ ወጥቶዋል ፣ “የምንገለው ባይኖረንም የምንሞትለት ሕዝብ ግን አለን” ብሎ ይሄው እሳት ከጨበጠ ጋ በ እስክርቢቶ ትግሉን ሀ ብሎ ከጀመረ ቆየ ፣ አረ እንደውም እስክርቢቶ መግዣውን እኔም ተባብሬያለሁ ( በሱም በጣም ደስተኛ ነኝ ) ። ኢንጂነር ይልቃልን ሳስብ ማህታማ ጋንዲ ወይም ማርቲን ሉተር ኪንግ ትዝ አይሉኝም ፣ ምክንያቱ ደሞ፣ ወዳጄ ይልቃል እንደነሱ ጠንካራ አይሆን ይሆን ብዬ ስለማስብ ሳይሆን ፣ መሃተማ ጋንዲና ማርቲን ሉተር ኪንግ መስዋት የሆኑላቸው አይነት ሕዝብ ከጎኑ ስለሌለ ብቻ ። ይልቃል እና ጉዋደኞቹ እንደውም ከማህታማ ጋንዲም ሆነ ከ ማርቲን ሉተር ኪንግም ይበልጣሉ ፣ ለምን ቢባል ፣ የሚታገሉት ስርዓት ምን ያህል ጨካኝ እንደሆነ እያወቁት ትግሉ ውስጥ በአስር ጣታቸው እንደገቡበት ሳስብ ። የብረት ትግል የሚል ነገር ባያነሱም ግን ከብረት ትግል እኩል የሕይወት መስዋትነት እየከፈሉ እንደሆነ ስገነዘብ እውነት እውነት እልሀለው ደግሜ ደጋግሜ አከብራቸዋለሁ ። እንደውም አንዳንዴ ግር የሚለኝ ፣ እነሱ ለተገረፉት ፣ እነሱ ለተሰቃዩት ፣ ” በሰላማዊ ትግል ወያኔ ይወድቃል ብሎ ማስብ ዘበት ነው !” እያልኩ እኔ ራሴ አወራ ነበር ። ግን ቆይቶም ቢሆን የገባኝ ለካ ለሀገር ሲሉ መሞቱን ነው ” ሰላም ” ያሉት እንጂ ትግሉማ መች ሰላም አለው ብለህ ነው ። መቼም በደንብ እንደምታውቀው እኔ ” ወያኔ ባሩድ አሽትተን እንጂ ፣ እርግብ አሳይተን እናሸንፈዋለን ማለት ዘበት የሚመስለኝ ሰው ነኝ ” እንዴት ሸለምጥማጥን እርግብ ሆነህ ትቀርበዋለህ ?

ወደ አብይ ጥያቄዬ ስመጣ ስለ ትግሉ ሳስብ ሆድ ይብሰኛል ፣ መቼ ይሆን ጦርነቱ የሚጀመረው እያልኩ ከራሴ ጋ አወራለሁ ፣ በይበልጥ በግንቦት ሰባት ስም የተገደሉ ፣ የታሰሩ ፣ ከስራ የተፈናቀሉትን ሰዎች ሳስብ ፣ በጣም የዘገየህ ይመስለኛል ፣ ይሄ የኔ ብቻ ጥያቄ እና መብሰልሰል እንዳይመስልህ ፣ ያው እኔ ስለማልፈራ ነው ጥያቄውን የጠየቅኩት እንጂ አሁን አሁን የብዙ ወዳጆቼ ጥያቄ እየሆነ ነው ። መቼ ነው አዲስ አበባ ላይ የወያኔ ባለስልጣን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ ሲባል የምንሰማው ? መቼ ነው የወያኔ ባለስልጣኖች ሲንማ-ራስ መቃም የሚያቆሙት ፣ መቼ ነው ከህዝብ ጋ መተራመስ የሚያቆሙት ፣ መቼ ነው ቀን የግንቦት ሰባትን አባላት እና ሌሎች ንጹሃን ሰዎችን ማዕከላዊ ወፌ ላላ ሲገርፍ የዋለ የ ወያኔ ባለስልጣን ማታ አንገቱ ተቆርጦ የምናየው ? መቼ ነው ? የክርስቶስ ዳግም መምጣት እንኩዋ እንዳንተ ውጊያ መጀመር በዙም አልጉዋ-ጉዋ-ንኝም !

መልሱን በድርጊት ትመልሱልኝ ዘንድ ከወገቤ ዝቅ ብዬ እጠይቃለሁ ።

ስምንት ጠቃሚ ነጥቦች ከእስራኤላውያን -ክፍል 6 (ዮፍታሔ)

$
0
0

ከዚህ ቀደም በነበሩት 5 ክፍሎች የእስራኤልን ታሪክ በአጭር በመቃኘት ስለአንድ ማዕከላዊ ድርጅትና ስለተቋማት አስፈላጊነት፣ ትግሉን ዓለምአቀፋዊ ስለማድረግ፣ ስለዳያስፖራው ወሳኝ ሚና፣ የጋራ ቋንቋ ለአንድ አገር ያለውን ጥቅም በሚመለከትና በአገር ጉዳይ የሀይማኖት መሪዎችና አገልጋዮች ሊኖራቸው ስለሚገባው የመሪነትና የማስተባበር ሚና ተገልጿል። ቀጣዩ ክፍል 6 ስለማስረጃና ስለማስረጃ ተቋም አስፈላጊነት ያብራራል።

  1. ሁሉንም መዝግቦ መያዝ (Documentation & Archaiving)

Jewish+Ethiopians+Reunited+Families+Israel+o1h5oGhsf2Vlበእስራኤላውያን የትግል ጊዜም ሆነ እስራኤልን ከመሠረቱበት እ.ኤ.አ 1948 በኋላ ሕዝብን ለማሳወቅ፣ ወንጀለኞችን ወደፍትሕ ለማቅረብ፣ ችግሩ እንዳይደገም ዓለምን ለማስጠንቀቅና ለማስገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ የጠቀሙት በራሳቸው በእስራኤላውያን እና እስራኤላዊ ባልሆኑ ሌሎች ሰዎች በጊዜው ይደርስ ስለነበረው ግፍና ሰቆቃ በጽሑፍ፣ በፎቶግራፍ፣ በቪዲዮና በድምፅ ተመዝግበውና ተቀርጸው የተያዙ ማስረጃዎች ናቸው።

ይልቁንም እስራኤላውያን ለዚህ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም ካቋቋሙ በኋላ ይህ ተቋም በሕፃናት ከተሣሉ ሥዕሎች ጀምሮ ከ25 ሺህ በላይ የተለያዩ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ በማጥናትና ለማስረጃ፣ ለምርምርና ለሙዚየም እንዲመቹ አድርጎ በማዘጋጀት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በጀርመኖች የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የነበረችው አነ ፍራንክ (Anne Frank) የተባለች ትንሽ ልጅ ከመሞቷ በፊት በየቀኑ ስትመዘግበው የነበረው የግሏ ገጠመኝ (Diary) እና ሌሎችም ተመሳሳይ ስብስቦች ከነዚህ መካከል ተጠቃሽ ናሙናዎች ናቸው።  እነዚህ ማስረጃዎች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ለ6 ሚሊዮን አይሁድ ሕይወት መጥፋት ተጠያቂ የሆኑት የናዚ ወንጀለኞች ወደፍርድ ቤት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ በእጅጉ ጠቅመዋል። ለመማሪያ፣ ለምርምርና በሕዝብ እንዲጎበኙ በሚዚየም ተቀምጠው እስከዛሬም በጥቅም ላይ እየዋሉ ነው። እነዚህ ተቋማትና ድርጅቶች በእስራኤል ብቻ የተወሰኑም አይደሉም። በመላው ዓለም በተለያዩ ከተሞች ይህን የሚሠሩ በርካታ የአይሁድ ተቋማት፣ ላይበራሪዎች፣ ሙዚየሞች፣ የማስረጃ ክምችት (Archivals) እና የምርምር ተቋማት ዛሬም ይገኛሉ። በአሜሪካን አገር ብቻ United States Haloucast Memorial Museum በሚል በሚታወቀው ተቋም ሥር ይህን ሥራ የሚሠሩ አያሌ ድርጅቶች በበርካታ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ይገኛሉ።

እነዚህን ማስረጃዎች በመንተራስ የተዘጋጁ መጻሕፍት፣ ፊልሞች፣ ትያትሮችና ትእይንቶች (Exhibitions) ቁጥራቸው አያሌ ነው። ይህ በእስራኤላውያን የደረሰውን ዓለም እንዲገነዘበው፣ እንዲማርበትና ይህን መሰል ነገር በድጋሚ በማንም እንዳይደርስ ካለው አስተዋጽኦ በላይ ለእስራኤላውያን ጥንክሮ መሥራት፣ ብልጽግና፣ አይበገሬነትና የመንፈስ ኩራት አጎናጽፏል። ከወደቁበት መነሳትና አገራቸውን መልሰው ማቋቋም ብቻ ሳይሆን እንደ እንስሳት እያዩ የገደሏቸውን ጀርመኖች ይቅርታ ለማስጠየቅና እስራኤላውያን በዓለም ፊት አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሄዱና እንዲከበሩ እነዚህ ማስረጃዎች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም።

ከዚህ ምን እንማራለን? በመጀመሪያ ማስረጃና መረጃን የሚያሰባስብ፣ የማያቋርጥ የመረጃ ዳሰሳ የሚያደርግ፣ ለሥራ እንዲመች አድርጎ የሚያከማች/የሚያደራጅ፣ ሳይበላሹ ተጠብቀው እንዲቆዩ የሚንከባከብ፣ የሚቆጣጠር፣ ማስረጃዎቹ ለሌሎች የሚደርሱበትን የሚያመቻች፣ የሚያጠናና የሚተነትን ጠንካራ ተቋም ያስፈልገናል። ይህ ተቋም ከአገዛዙ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በጠቅላላ እና በግእዝ በአማርኛና በሌሎችም የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና የተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች ስለኢትዮጵያ የተጻፉትን ማንኛውም መጻሕፍት፣ የተዘጋጁትን የፎቶግራፍ፣ የድምፅና የቪዲዮ ሥራዎች ከአገር ውስጥም ከውጭም በስጦታ፣ በግዢ እና ኮፒ በማድረግ የሚሰበስብ መሆን ይኖርበታል። በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ጥረት በማይክሮፊልም የተሰባሰቡት ሥራዎች ቋሚ ምስክር ናቸው። በአርቲስት ታማኝ በየነ አስተባባሪነት ይህ ተቋም በቅርቡ መቋቋሙ ደግሞ የቡድኑን አርቆ አስተዋይነት የሚያመለክትና እጅግ የሚያስደስት ነው። በሰው ኃይል፣ በእውቀት፣ በአደረጃጀትና በገንዘብ አቅም እንዲጠነክርና ሥራውን በብቃት እዲወጣ የመላው ኢትዮጵያዊ ድጋፍ ያስፈልገዋል።  ይህ ተቋም ትንሽ ቀደም ብሎ ቢሆን ኖሮ በቅርቡ በአዲስ አበባ በኪሎ እየተሸጡ በነበሩት ታሪካዊ መዛግብት ላይ ሊደርስባቸው ይችል እንደነበረ መገመት ይቻላል። አሁንም በየሰው እጅ ያሉትን በስጦታና በግዢ ለመሰብሰብ ጥረት ቢያደርግ ለአገርና ለወገን ባለውለታ ይሆናል።

መረጃዎች ዕለት በዕለት እየሰበሰቡ ለዚህ ተቋም ማስተላለፍ ደግሞ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ኃላፊነት ነው። ይህ ሁለተኛው አስፈላጊ ተግባር ነው። ማንም ነፃነት ወዳድ ኢትዮጵያዊ በእጁ የገባውን መረጃና ማስረጃ ከቻለ ዋናውን ካልቻለ ኮፒ አድርጎ፣ ያጋጠመውን በጽሑፍ፣ በፎቶና በቪዲዮ መዝግቦ የማስቀረት ኃላፊነት አለበት። ሕፃናት ሳይቀር በገጠርና በከተማ በዚህ አገዛዝ ሲፈጸሙ ያዩትንና ስለአገዛዙና ስለኑሮአቸው የሚሰማቸውንና በቤተሰባቸው የደረሰውን በሥዕልና በጽሑፍ እንዲገልጹት መምህራንና ወላጆች ማበረታታት ብሎም ማስረጃውን በጥንቃቄ ቀን መዝግበው ማስቀመጥና በጊዜው ለተቋሙ ማስተላለፍ ይኖርባቸዋል።

ዛሬ በየሰው እጅ ያለው ተንቀሳቃሽ ስልክ ካሜራ አለው። ይህን ካሜራ በመጠቀም ብዙ መረጃዎች ወጥተዋል፤ አሁንም እየወጡ ነው። ነገር ግን ከዚህም በበለጠ እያንዳንዱ ዜጋ ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ በካሜራው ቀርጾ የማስቀረት ኃላፊነት ሲወስድ ከፍተኛ ሥራ ይሠራል። መሻሻል የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር የምስሎቹን ጥራት በሚመለከት ነው። ለዚህ መፍትሔው በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትኩረት ሰጥተው የካሜራ ባለሙያዎችን ከመቅጠር ጀምሮ ለአንዳንድ የድርጅት አባላቶቻቸው በቂ የፎቶግራፍና የቪዲዮ ቀረጻ ስልጠና በመስጠትና ከካሜራ ጋራ በማሰማራት ከፍተኛ ሥራ ሊሠሩ ይችላሉ። አባላቶቻቸው አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ሚስጥራዊ ጥቃቅን ካሜራዎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ ይቻላል።  እዚህ ላይ ጠንካራ የሆኑት በውጭ የሚገኙ የኢራን አክቲቪስቶች በኢራን 2009 (እ. ኤ. አ) ምርጫ የተነሣ መንግስታቸው የወሰደውን ጭካኔ የተሞላበት ርምጃ ለማጋለጥ የተጠቀሙበትን ዘዴ መጥቀስ ይጠቅማል። በዳያስፖራ የሚገኙት አክቲቪስቶች ከምርጫው በፊት በርካታ ሚስጥራዊ ካሜራዎችን ገዝተው ወደአገር ውስጥ ማስገባት ችለው ስለነበረ ከምርጫው በኋላ በምርጫው ውጤት ያፈረው የኢራን መንግሥት የወሰደው ርምጃ በዓለም የቴለቪዥን መስኮት ሊናኝና ከፍተኛ ውግዘት ሊያደርስበት በቅቷል። በገንዘብ የተሻለ አቅም ያለውና ለቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነው ኢትዮጵያዊው ዳያስፖራ በዚህ በኩል ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርበታል።

(ይቀጥላል)

 

ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ሥራ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

 

  „ከአዞ ዕንባ –ከዝንብ ማር አይጠበቅም“ (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 11.12.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ውዶቼ – የእኔዎቹ አንድ ነገር ከተሳራ በኋላ ተከፍቶ ቢያድር ተወሳክ ይገባበታል። ለጤናም ይበክላል። ጹሑፉ ቅናዊ ቢሆንም ትንሽ ማነፃጸሪያዎችን በማቅረብ ሃስብን መሰብስብ የዘበኝነት ተግባሬ ግድ ስለሚለው ተፃፈ።

de
መቼም ቅጥል – እርር – ካሉ ቅን ወገኔ የተጻፈ „ አሳዛኙ ውርዴታችን“ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/37001 በሚል እርስ አንድ አጠር ያለ ጹሁፍ ከዘሃበሻ አሁን አነበብኩኝ። ወንድምዓለም / እህትአለም/ „ከአዞ ዕንባ – ከዝንብ ማር“ እኔ አልጠብቅም። ሃውዚ ላይ ዕልፎች ሲያልቁ ካሜራውን ደቅኖ ለፖለቲካ ትርፍ ወገኑን ከጨረሰ አረመኔ ተስፈኛ እኔይቱ አልሆንም። በራህብ ለሚያልቁት ወገኖቼ ብሎ ላገኘው ገንዘብ ወያኔ፤ ማወራራጃው አሽዋ ነበር። ለደምና ለሥጋዎቹ ብጣቂ ሳይራራላቸው ለእናንተ ነው እያለ፤ እዬማለና እተገዘተ አሸዋ ሰፍሮ ነው ሞታቸውን ያወጀው። በልግ፣ መህር ሲደርስ እልፎች ከቀያቸው ሲነቀሉ – ባለቤት የላቸውም። ከእርሻ ማሳቸው የሚነቀሉት እኮ ህይወታቸው ሞት ነው።

እስኪ አንድ ነገር ልጠይቅ ጸሐፊውን … ወያኔ እነዚህ ወጎኖቻችን ማለቃቸውን ምክንያት አድርጎ የሀዘን ቀን ቢያውጅ፤ ጥቁር ለብሶ ቢውል ከቶ ሆድ ይሆነዎት ይሆን?

የሚገርመዎት አደጋውን ያደረሰችው ጀልባ ብቻውን ብትመለስ ሞቱን የሰሙ ወጣቶች እኔ እቀድም እኔ እቀድም ብለው ተሳፍረው ወደ ቀጣይ መዋዕቲነት መሄዳቸው አይቀሬ ነው። ከዚህ ጋርም ሌላ ነገር ማንሳት እሻለሁ። እሰረኞችን ወያኔ ቢፈታ፤ ሌላ ባለተራ ግበቶ ደግሞ ይማቅቃል። የአረብ ሀገሩ ትዕይንት በሚመለከት በቅብ ወያኔ ሲያረገርግ የመሰላቸው ወገኖች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን ያን ሁሉ መከራ ተቀብለው ሀገራቸው ገቡ ተብሎ ከተደመጠው ዲስኩር ጀርባ እኛ ያላዬነውና ያልሰማነው፤ ያልደረስንበትም ስንት የበቀል እርምጃ ተወስዶ ይሆን?! ፊት ለፊት በወጡት ላይ …. ሆነ መጠጊያ ባጡት ላይ። ዋናው ልናተኩርበት የሚገባው መሰረታዊ አውራ ተግባር የችግሩ ምንጭ ምን እንደሆን ከጋራ ስምምነት መድረስን ነው። መርዛማ ምንጭ ከምንጩ ነው ሊደርቅ የሚገባው። በስተቀር ተፋሰሱ ሁሉ ብክል ስለሆነ – አይምሬ ነው። ይህ ማለት የችግሩን ምንጭ ማውቅ እስካልተቻለ ድረስ መፍትሄ ሊገኝ ከቶውንም አይቻልም። እንግሊዘች „የችግሩን ምንጭ ማወቅ ለችግሩ ግማሹ መፍትሄ እንደ ተገኘ ይቆጠራል“ ማለታቸው፤ የችግሩ ጥልቀት – ስፋትና መጠን፤ ልኩን መፍትሄውን ሆነ ጉልበታምና የማያዳግም መፍትሄ አምንጪ ያደርገዋል ለማለት ነው። በእኛም ሀገር „በሽታውን ያልተናገረ መዳህኒት አያገኝም“ ይባል የለ። እንደዛ ነው።

ሌላው የተነሳው „መንግሥት“ በሚመለከት ነው። ጎሳ ላይ የጎሳ አለቃ እንጂ መንግሥት እድገቱ አይፈቅድለትም። ከቤተሰብ ቀጥሎ ባለው ጎሳ ውስጥ መንግሥት አለ ከተባለ፤ ቤተሰብ ላይ የመንግሥት besement አለ ማለት ነው። ስለዚህ ትንሽ ወደ ውስጥ ዘልቀን እንመርምረው። እርግጥ ነው ከቀደሙ ሥርዓቶች የተወረሱት ኢትዮጵያዊ ተቋማትን አፍልሶ ከኢትዮጵያዊነት ጋር አይገናኙም ያላቸው መዋቅሮች ወያኔ አሉት። ቀድመው የተደራጁ ስለነበር። ነገር ግን ባዶ ግድግዳ ጣሬያ የሚሆነውን ቆርቆሮ ወይንም እሳር ካለበሰ – ቤት ሊሆን አይችልም። „ቤት“ የቤትነት መስፈርቱን ካላሟላ ህይወትን ሊያቆይ አይችልም። የወያኔም መዋቅራዊ ቅራቅንቦው ይሄው ነው። ግጭትና ስበቱም እኮ የማይገናኙ ነገሮች በግድ ተሳበቁ ተብለው ነው እኮ?!

d2በተያያዥነት የተነሳው ጉዳይ „አሳዛኝ“ መቼ አባርቶ አውቆ። መርዶ ነው ደመር* ነው ዕጣ ፈንታችን።  „ውርደት“ ለሚለው ግን አልተመቸኝም። እኛ ምን ሆነን እንዋረዳለን?! ፈጻሚው አንገቱን ይድፋበት፤ ቀልብ ተሰፋሪው አንገቱን ያቀርቅርበት? ይልቅ እኛ እንዲህ የነገ ተስፋ እዬተዳፋ ባህር ውስጥ የሚደፋበትን ሳቢያውን ሳይሆን፤ የአምክንዮውን ምክንያታዊ መቅኖ በማወቅ …. የዓለም ዕድገት ደረጃና ዘመኑ የፈቀደለት ሥርዓት በኢትዮጵያ እንዲሰፍን መንፈሳችን መሞረድ ነው – መፍትሄው። ሞቱ ይቀጥላል …. ግፉም ይቀጥላል ወያኔ አስካለ ድረስ። ተጠግኖም አይድንም – ነዳላው ብዙ ነውና። ስለዚህ ሊገፋ የሚገባው ነገር፤ የህዝብ ፈቃድ የሚገዛው፤ የሚያስተዳድረው  አዲስ ሥራዓትን ለመፍጠር „በቃንን!“ ወደ አደገ ደረጃ ማድረስ ነው ቁም ነገሩ።

በተጨማሪነት የተነሳው የአሜሪካ አንባሳደር ሃዘናቸው መግለጻቸው ነው። ይህ በሁለት መልክ ሊታይ ይችላል። አንደኛው ከሰብዕዊነት አንፃር ቀኑም የሰብዕዊ መብት ቀን መሆኑ፤ ሁለተኛው ደግሞ ባሉበት ሀገር ለሚፈጸመው ግፍ ቸል ቢሉ የዓለም – ዐቀፉን ማህበረሰብ ወቀሳ ሽሽትም ጭምር ነው። ወቀሳውን አይችሉትም። እንዲሁም በቀጣይ ምርጫውም ላይ የሥልጣን ሚዛኑ ላደላው ዲሞክራት ፓርቲ ከፍ ያለ ተጽዕኖም አለው – በስፋት ሲታይ ጉዳዩ። በተረፈ ቅርበታቸውና ሀዘናችን ሃዘናቸው መሆኑ ያስመስግናቸዋል። ነገር ግን  ዬአሜሪካ መንግሥት የነፃነት ቀማኛ ሥርዓትን ከማንቆለባበስ ተቆጥቦ እኛም ሰውነን እና አዲስ ዕይታ እንዲኖረው ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር፤ ይሄ በቅብ የተሽቆጠቆጠው የወያኔ ምስል ቀርቶ ሃዘኑ ሃቁን የመግለጥና የማጋላጥ አቅም አንዲኖረው ከማደረጉ ላይ ነው ብልሃቱ ያለው። ለዚህ ተግተው ከቀጠሉበት – ማለፊያ ነው። በስተቀር ግን …..

ወያኔ እስከ አለ ድረስ የነገ ኢትዮጵያ ተስፋም እንዲህ አመድ ተላብሶ፤ አመድ ቅሞ፤ የተፈጥሮ ገላ ወዙ በጉስቁልና የሚኖሩበት ሥርዓት  ለአፍታ ለድርደር የሚቀርብ ሊሆን አይገባም። እንደ ህዝብ እረኛም ሊታይ አይገባም። ዛሬ እኮ እኛ ትተነዋል። መሰረታዊ የሰው ልጆች አስፈላጊ ጉዳዮችን። መጠለያ፤ ከፈን፤ ምግብ፤ ንጹህ ውሃ ት/ቤት …. እንደ ቅንጦት ከተቆጠሩ ዓመታት ተቆጠሩ። ስለምን? ወገን በባዕቱ ድህነቱን ችሎ መኖር አልቻለም። ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ እስረኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ የጭንቀት በሽታም ተጠቂም ነው። ከሥጋት፣ ከፍርሃት ቀጥሎ የመንፈስ ጫና ያለው በሽታ በዬጓዳው እንዳሻው እዬተወራኘ ነው። ለመሆኑ ለ90 ሚሊዮን ስንት የሥነ – ልቦና ባለሙያዎች ከቶ ይኖሩን?!

ክውና – የነገ ተስፋ እንዲህ ነው …. አሮ – ጠውልጎ  – አፈር …. ለብሶ፤ አይመስሉ መስሎ፤ አይሆኑቱን ሆኖ – አፈር ቅሞ፤ ትቢያ ተንተርሶ፤ ትቢያን ተማምኖ፤ ትቢያን መጠለያ አድርጎ፤ ትቢያን ጉርሱ አድርጎ፤ ትቢያን ከፈኑ አድርጎ፤ ልጆቻችን በዚህ ሁኔታ ላይ ነው የሚገኙት – እ! እም!

  • ደመር … ጠብቆ ነው የሚበበው። ደመረ ከሚለው ቃል የተራባ ነው። ደረበ- ጨመረ – ሰበሰበ ይሆንና በገጠር የጋራ የለቅሶ ቀን ተቀጥሮ በወል ዕንባ የሚፈስበት የዕንባ ምጥ ቀለበት ቀን ማለት ነው።

እልፍ ነን እና እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

11ዱ የማዕከላዊ ገራፊዎችን እወቋቸው

$
0
0

ከዳዊት ሰለሞን

በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ጋዜጠኞችን፣ፖለቲከኞችን፣የሀይማኖት ምሁራንና ያለ ምንም ተሳትፎ ኦሮሞዎች በመሆናቸው ብቻ በኦነግነት ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ መተኪያ አልባ ዜጎችን በማሰር ቃላት ሊገልጸውና የሰው ልጅ ሊሸከመው አይችልም ተብሎ የሚታሰብን ሰቅጣጭ ድርጊት በመፈጸም ረገድ ወደር የሌላቸው ገራፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ተደርጓል፡፡እነዚህ ሰዎች አሁንም በዚሁ ድርጊታቸው ጸንተው ወንድሞቻችንን እያሰቃዩ የሚገኙ በመሆናቸው ህዝብ ሊያውቃቸውና ቀን ሲወጣም ፍትህ ሊጠይቅባቸው ይገባዋል፡፡
ethiopia-torture-620
ስማቸው የተጠቀሱትን ሰዎች የምታውቁ አልያም በእነዚህ ሰዎች በማዕከላዊ ምርመራ ወቅት ስቃይ የደረሰባችሁ ዜጎች መረጃውን ልታዳብሩት ወይም ሊጨመሩ የሚገባቸውን ገራፊዎች ልታጋልጡ ትችላላችሁ፡፡

ገራፊዎቹ ነጭ ወረቀት በማቅረብ ተጠርጣሪዎች ፊርማቸውን እንዲያኖሩ የሚያስገድዱ፣ገልብጠው የሚገርፉ፣በወንድ ብልት ላይ ውሃ የተሞላ ላስቲክ በማንጠልጠል የሚያሰቃዩ፣ሴት እስረኞችን ጡታቸውን በበትር የሚደበድቡ፣ሰውን ካልደበደቡ ስራ ያልሰሩ የሚመስላቸው ቃሉ ከገለጻቸው ‹‹አረመኔዎች››ናቸው፡፡ምናልባት የፍትህ ጸሀይ ወጥታ ህዝብ አሸናፊ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ይፈጽሙ የነበሩትን ግፍ በአደባባይ እንዲመሰክሩ ይደረጉ ይሆናል፡፡

ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ወዳጆቻቸውም ስማቸውን ተመልክተው የህሊና ዕዳ ይፈጥሩባቸው ይሆናልና ስማቸውን ይፋ ማድረጉ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል ባይ ነኝ፡፡

1. ታደሰ መሰረት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ
2. ዩሀንስ ኢንስፔክተር
3. ተዘራ ቦጋለ ኢንስፔክተር
4. ብርሃነ ኢንስፔክተር
5. ከተማ ኢንስፔክተር
6. ሰይድ አሊ ኢንስፔክተር
7. ገብረመድህን ኑር ኢንስፔክተር
8. ሙልጌታ ኢንስፔክተር
9. አሰፋ ትኩት ምክትል ኢንስፔክተር
10. ታደሰ አያሌው ኢንስፔክተር
11. በለጠ ኢንስፔክተር

‹‹የኢትዮጵያና የጂቡቲ ሕዝቦች ፍላጎት ከሆነ ውህደትን ተግባራዊ ማድረግ አለብን›› የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ

$
0
0

 

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ

ረፖርተር

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ፣ ጥንታዊና ታሪካዊ የሆነው የኢትዮጵያና የጂቡቲ ግንኙነት በአሁኑ ጊዜ ጥልቅ እየሆነ መምጣቱንና አንዱ አገር ለአንዱ አስፈላጊ የሆነበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገለጹ፡፡

የሁለቱ አገሮች ሕዝቦች የውህደት ፍላጎት ካላቸውም ይህንኑ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የተወጣጡ ባለሙያዎች ባለፈው ሳምንት  ጂቡቲን በጎበኙበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንቱ ከጋዜጠኞቹ ጋር አጭር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡

በጂቡቲ መንግሥት ግብዣ ወደ አገሪቱ የተጓዙት ጋዜጠኞች ለአምስት ቀናት በነበራቸው ቆይታ ከተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች የተገነዘቡትን የጂቡቲና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቁርኝት ፕሬዚዳንቱ በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

‹‹የባቡር መስመር ሳይዘረጋ በፊት የኢትዮጵያና የጂቡቲ ሕዝቦች የተቆራኙ ናቸው፤›› ያሉት ፕሬዚዳንት ጌሌ፣ ከኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጂቡቲን ለመጎብኘት የመጣ ሰው ይህንን ቁርኝት ማንም ሳይነግረው መረዳት እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡

‹‹ሁለቱ አገሮች ሽርክ ናቸው፡፡ ያልተባበሩበት ዘርፍ የለም፤›› የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹በኢትዮጵያና በጂቡቲ መካከል ልዩነት አይሰማንም፤›› ብለዋል፡፡

አሁን በየደረጃው የሚታየው ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር መጨረሻው ምን ይሆናል? ሁለቱ አገሮች ተዋህደው አንድ አገር የመሆን ዕድል አላቸው ወይ? ይኼንንስ እርስዎ እውን ሆኖ ማየት ይፈልጋሉ ወይ? በሚል ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹የኢትዮጵያና የጂቡቲ ሕዝቦች ፍላጎት ከሆነ ውህደትን ተግባራዊ ማድረግ አለብን፤›› ብለዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ዓመት ባፀቀደው አዋጅ የጂቡቲ መንግሥት 103,000 ሜትር ኪዮብ ውኃ ከኢትዮጵያ በየቀኑ በነፃ እንዲያገኝ መፍቀዱ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ኃይል በዝቅተኛ ታሪፍ ለጂቡቲ መንግሥት መቅረቡና አሁን እየተሸጠ ካለው የኤሌክትሪክ አቅርቦት በተጨማሪ፣ በአፋር በኩል ተጨማሪ ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት የመጨረሻው ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሁለቱን አገሮች በባቡር ለማገናኘት በጂቡቲ በኩል 98 ኪሎ ሜትር የባቡር ሐዲዱ የመዘርጋቱ ሥራ 60 በመቶ መድረሱን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

በጂቡቲ በኩል ደግሞ ለአፋር ክልል ቅርብ በሆነ ታጁራ በሚባል አካባቢ ለኢትዮጵያ የፖታሽ ማዕድን ኤክስፖርት ማድረጊያ ወደብ በ160 ሚሊዮን ዶላር እየተገነባ ነው፡፡ ይኼንን ወደብ ምክንያት በማድረግም ከመቐለ ታጁራ የሚደርስ የባቡር መስመር ለመዘርጋት በኢትዮጵያ በኩል እየተሠራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ጂቡቲ በወደብ ግንባታ ረገድ ለኢትዮጵያ የኤክስፖርት ዓይነቶች ልዩ ወደቦችን በመገንባት ቅድሚያ ሰጥታ እየሠራች እንደሆነ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ከላይ እንደተገለጸው ለፖታሽ ኤክስፖርት ግንባታው ከተጀመረው የታጁራ ወደብ በተጨማሪ የኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ኤክስፖርት ማድረጊያ ወደብ በዕቅድ ተይዟል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በረዥም ጊዜ ዕቅድ ግሬት ሆርንስ የተባለ የመርከብ ድርጅትና ወደብ ለማቋቋምና ለደቡብ ሱዳን፣ ለኢትዮጵያና አካባቢው አማራጭ ወደብ የመፍጠር ዕቅድ ተይዟል፡፡

‹‹ለመድረስ ከምንፈልግበት በጣም ብዙ ሩቅ ነን፤›› የሚሉት ደግሞ የአገሪቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ኤልያስ ሞሳ ዳዋሌ ናቸው፡፡ ሚኒስትሩ አክለውም፣ ‹‹ያለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት የጂቡቲ እንቅስቃሴ ጣዕም የለውም፤›› ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ለጂቡቲ የኃይል አቅርቦት በርካሽ ዋጋ በማቅረቡም 30 በመቶ የኃይል ግዥ ዋጋ መቀነሱን ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት ለመንግሥት ግንኙነት ከሞላ ጎደል በየቀኑ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ግን ክፍተት መኖሩን ተናግረዋል፡፡ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በበኩላቸው፣ ‹‹የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ከዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ባለፈ የሚገለጽ ነው፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ሁለቱ አገሮች እየፈጠሩ ያሉት የኢኮኖሚ ውህደት ነው፤›› ያሉት አምባሳደሩ፣ የኢኮኖሚ ውህደት ካለ ደግሞ የፖለቲካ ውህደት እንደሚመጣ ዕምነታቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ጀግኖችን እያሰብን የበኩላችንን እንወጣ!! በመስዋዕትነት ነፃነት ይረጋገጣል፤ ሰላም ይሰፍናል። (በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ)

$
0
0

teachers associationመምሀር የኔሰው ገብሬ በዳውሮ ከተማ ነዋሪና ትጉህ መምህር ነበር። እንደማንኛውም አገር ወዳድና የወገን ተቆርቋሪ እርሱም የወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዓተ መንግሥት በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ገደብ የለሽ ሰቆቃ መቀበል ባለመቻሉ ፣ በአንፃሩ በተቃውሞ አቋሙን በአደባባይ የሚገልጽና ይህ እኩይ ድርጊት እንዲቆም ታግሎ ለማታገል በጽናት ስለቆመ የሥርዓቱ ሰለባ ሆነ። እስራቱና እንግልቱ አልበቃ ብሎ ከሥራ መደቡም ተገለለ ። በዚያው ላይ ፍትህ ለማግኘት የሚያስብ ሕሊናና የሚሰማ ጆሮ እንደሌለ ተረድቶ ለአሰቃዩትም ለአጠቃላይ ሕዝቡም መራር መልእክት ያስታላልፋል ብሎ ያሰበውን መስዋዕትነት መርጦ ራሱን በጋዝ አንድዶ ሕዳር 1 ቀን 2004 ዓ.ም መስዋዕት ሆነ። ይህ ተግባሩ ቀደም ሲል ለአገር አንድነትና ለሕዝብ ሉዓላዊነት ፣ ለመምህሩ መብትና ጥቅም መከበር ሲታገሉ መስዋዕት የሆኑትን፣ በእስራት የማቀቁትን፣ ከእናት አገራቸው ተሰድደው በባዕድ አገር ያለውዴታቸው የእንግልትና የናፍቆት ኑሮ የሚገፉትን መምህራን፣ የሙያ ማህበሩ የኢመማ መሪዎችን፣ ደጋፊዎቻቸውንና ተባባሪዎቻቸውንም የሚያስመካ አንጸባራቂ መስዋዕትነት ሆኖ አልፏል። መቼም ቢሆን ነፃነት ያለመስዋዕትነት ተገኝቶ አያውቅም። በሕዝቡ ጫንቃ ላይ ተፈናጦ የሚገኘውን ጨካኙን፣ ዘረኛውን፣ ግፈኛውን፣ —-  [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–

 

 

ናሚቢያ፤ ሌላዋ የፍትሕ ጀግና! ኢትዮጵያስ? –ኪዳኔ ዓለማየሁ

$
0
0

“ዘ ጋርዲያን” (The Guardian) በተሰኘው ታዋቂ ጋዜጣ እ.አ.አ ነሐሴ 15 ቀን 2006 እንደ ተዘገበው፤ የጀርመን መንግሥትን በመወከል፤ ወ/ሮ ሔይደማሪ ዊዞረክ-ዜዩል (Mrs. Heidemarie Wieczorek-Zeul)፤ የጀርመን የልማት ሚኒስትር፤ ሐገራቸው እ.አ.አ. በ1904 በናሚቢያ ነዋሪዎች (ሔሬሮዎች) ላይ ስለ ፈጸመችው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቅርታ ጠይቀዋል። ለዚህም ወንጀል፤ ናሚቢያውያን (ሔሬሮዎች) ከይቅርታ መጠየቁ በተጨማሪ $4 ቢሊዮን ካሣ እንዲከፈል የጀርመን መንግሥትን መጠየቃቸው ተገልጿል። ከዚህ ቀጥሎ በቀረበው ምንጭ ላይ በመጠቆም ዝርዝር ሐተታውን መመልከት ይቻላል፤

http://www.theguardian.com/world/2004/aug/16/germany.andrewmeldrum

ከላይ በተጠቀሰው ዜና እንደ ተገለጸው፤ ጀርመኖች በፈጸሙት ወንጀል 65 000 ሔሬሮዎች (በኋላ ናሚቢያን) እንደ ተጨፈጨፉ ታውቋል። በጊዜው የነበረው የጀርመኑ የጦር መሪ፤ ጀኔራል ሎታር ቮን ትሮዛ፤ የናሚቢያን ጎሳ (ሔሬሮዎችን) ጥርግርግ አድርገው እንዲጨርሱ ትእዛዝ ማስተላለፉ ተገልጿል። የዚህ የጀርመን ጄኔራልና “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” በመባል የሚታወቀው የሮዶልፎ ግራዚያኒ አስተሳሰብና ተግባሮች ተመሳሳይነት የሚያስገርም ነው። ለማንኛውም፤ የናሚቢያ መንግሥትና ናሚቢያውያን በሐገራቸው ላይ ለተፈጸመው ወንጀል በመቆርቆር ፍትሕ እንዲገኝ በመታገል ላስገኙት የመጀመሪያ ተጨባጭ ውጤት ሊደነቁ ይገባል። ምንም እንኳ፤ ለጊዜው የጀርመን መንግሥት የሚፈለግበትን ካሣ ለመክፈል ፈቃደኛ ባይሆንም በናሚቢያ ሕዝብና መንግሥት በኩል በቀጣይ የሚከናወነው ጥረት ተገቢውን የፍትሕ ውጤት እንደሚያስገኝ ይታመናል። ለማስታወስ ያህል፤ ናሚቢያ፤ በኢትዮጵያ ድጋፍ ጭምር ከቅኝ ግዛት ቀምበር የተላቀቀችው በቅርብ ጊዜ መሆኑ የታወቀ ነው።

ከናሚቢያ በተጨማሪ፤ ተመሳሳይ የፍትሕ ጀግንነት ካስገኙት ሐገሮች ውስጥ፤ እሥራኤል፤ ሊቢያ፤ ኬንያና ኢንዶኔዚያ ይገኙበታል። ከነዚህ ውስጥ በተለይ እሥራኤል ይቅርታ በመጠየቋም ሆነ በተከፈላት እጅግ ከፍ ያለ ካሣ በኩል ተምሳሌት የሆነች ሐገር ናት። ሌላዋ ለሐገሯ ክብርና ፍትሕ በመቆም ተጨባጭ ውጤት ያስገኘች ሐገር ሊቢያ ናት። በነግራዚያኒ መሪነት ሊቢያ የኢጣልያ ቅኝ ግዛት በነበረችበት ጊዜ ለተፈጸመው የ30 000 ዜጎች ጭፍጨፋ ኢጣልያ ለሊቢያ $5 ቢሊዮን ለመክፈል መስማማቷ ተረጋግጧል። ኬንያም፤ በእንግሊዝ መንግሥት፤ እንዲሁም ኢንዶኔዚያ በኔዘርላንድስ መንግሥት በቅርቡ ይቅርታ ተጠይቀው ካሣ እንዲከፈላቸው ተደርጓል። እነሱም ለሐገራቸው ክብርና ፍትሕ ታግለው መብታቸውን በማስከበራቸው ሊደነቁ ይገባል።

ትልቁ ጉዳይ፤ ኢትዮጵያ ለደረሰባት እጅግ መራርና አሰቃቂ የፋሺሽት ኢጣልያ የጦር ወንጀል ምን ጥረት እየተከናወነ መሆኑን የሚያጠይቀው ነው። እንደሚታወቀው፤ እ.አ.አ. በ1935-41 ፋሺሽት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ዘመን፤ አንድ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ተሰውተዋል። ከነዚሁ ውስጥ፤ በሶስት ቀኖች ብቻ (የካቲት 12-14 ቀኖች 1929 ዓ/ም)፤ በአዲስ አበባ ከተማ፤ 30 000 ኢትዮጵያውያን ተጨፍጭፈዋል። በተጨማሪም፤ 2000 ቤተ ክርስቲያኖች፤ 525 000 ቤቶችና 14 ሚሊዮን እንስሶች ወድመዋል። እንዲሁም መጠነ-ሰፊ የሆነ የኢትዮጵያ ንብረት በፋሺሽቶች ተዘርፎ አሁንም በቫቲካንና በኢጣልያ መንግሥቶች ይዞታ የሚገኝ አለ።

በኢትዮጵያ ላይ፤ በመርዝ ጪስ በመጠቀም ጭምር፤ ለተፈጸመው የጦር ወንጀል፤ ኢጣልያ እስካሁን ድረስ የከፈለችው ኢምንት የሆነ፤ ቆቃ ግድብ የተሠራበት $25 ሚሊዮን ብቻ ነው። ኢንዲያውም፤ የጦር ወንጀሉ አልበቃ ብሏት፤ “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንደሚባለው፤ በቅርቡ፤ የኢጣልያ መንግሥት ለግፈኛው የጦር ወንጀለኛ ለግራዚያኒ ልዩ መታሰቢያና መናፈሻ አስመርቃለታለች። በነገራችን ላይ፤ በምረቃው ሥነሥርዓት ላይ የቫቲካን ተወካይ ተገኝተው እንደ ነበር ቢ.ቢ.ሲ ዘግቧል።

ባቲካንም በጊዜው የነበሩት ፖፕ ፓየስ 11ኛና የፋሺሽቱ መሪ፤ ሙሶሊኒ፤ እጅና ጓንት ሆነው በኢትዮጵያ ላይ ለተፈጸመው የጦር ወንጀል፤ እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ አልጠየቀችም። አይሑዶችን ግን፤ በናዚ ጀርመኒ ስለ ደረሰባቸው ጭፍጨፋ በጊዜው የተቃውሞ ድምፅ ባለማሰማቷ ብቻ በመደጋገም ይቅርታ ጠይቃለች።

በአጠቃላይ፤ ኢትዮጵያ ለተፈጸመባት የጦር ወንጀል የሚገባት ፍትሕ፤

1ኛ/ የኢጣልያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል ማድረግ፤ ይኸውም መከናወን ያለበት

ለኢትዮጵያ ሕዝብ በተጨባጭና ለዘለቄታው በሚጠቅም መንገድ፤ ለምሳሌ አስፈላጊ በሆኑ ፕሮጀክቶች

ሊፈጸም ይገባል።

2ኛ/ ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ልትጠይቅ ይገባል።

3ኛ/ ከኢትዮጵያ የተዘረፉት ንብረቶች ለባለቤቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲመለሱ ማድረግ ያስፈልጋል። አመላለሱ

ግን አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለመጪው ትውልድ ሁሉ ታሪካዊ ማስረጃነቱ ተጠብቆ እንዲቆይ ማረጋገጥ

ያስፈልጋል።

4ኛ/ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመውን ወንጀል መዝግቦ ተገቢው ፍትሕ እንዲገኝ

አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይገባዋል።

5ኛ/ ለግፈኛውና ወንጀለኛው ፋሺሽት፤ ለግራዚያኒ፤ አፊሌ ከተማ (ኢጣልያ) የተቋቋመው መታሰቢያና መናፈሻ

መወገድ ይገባዋል።

በተጨማሪ፤ ሰሞኑን የቫቲካን ከፍተኛ መልእክተኞች ቡድን ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ በመሆኑ ከቫቲካን ስለሚያስፈልገው ፍትሕ ጉዳይ ለመነጋገር ጥሩ አጋጣሚ ሊያስገኝ ይችላል። የሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣኖች፤ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ሌሎችም በኢትዮጵያ ለሐገር ፍትሕ የሚታገሉ ሰዎችና ድርጅቶች በዚህ አጋጣሚ ቢጠቀሙ መልካም ይሆናል።

ዓለም-አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ (Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause) www.globalallianceforethiopia.org ከላይ ለተዘረዘሩት አምስት ዓላማዎች እየተንቀሳቀስ መሆኑንና በሚቀጥለውም የየካቲት 12 የሰማእታት ክብረ-በዓል ቀን፤ ከኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር በመተባበር በዓለም ዙሪያ ከ30 ከተሞች በላይ ለሐገር ፍትሕ ጥረቱን ይቀጥላል። በዚህ አጋጣሚም፤ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ድር-ገጽ ውስጥ የሚገኘውን ዓለም-አቀፍ አቤቱታ አንባቢዎች እንዲፈርሙት ይጋብዛል።

ውድ ሐገራችን የሚገባትን ክብርና ፍትሕ እንድትጎናጸፍ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተባብረን እንድንታገልና ተፈላጊውን ውጤት እንድናስገኝ ቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳን። አሜን።

 

Comment

 

 

 


የአንድነቱን ጉባዔ በወፍ በረር (ዳንኤል ተፈራ)

$
0
0

እንደ መነሻ

ዳንኤል ተፈራ

ዳንኤል ተፈራ

ከሁለት ወር በፊት አንድነትን እንዲመሩ በጠቅላላ ጉባዔ የተመረጡት ኢ/ር ግዛቸው ሺፈራው ጥቅምት ሁለት ቀን 2007 ዓ.ም ካቢኔያቸውን በትነው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለብሔራዊ ምክር ቤቱ አስረከቡ፡፡ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ኢ/ር ግዛቸው ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር በአመራራቸው ያልተደሰቱ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎችን የ‹‹ልቀቅ›› ጫና መቋቋም እንዳልቻሉና ከህሊናቸው ጋር ተማክረው ለፓርቲው ጥቅም ሲባል በፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ እንደወሰኑ ተናገሩ፡፡

ምክርቤቱም በጥሞና አድምጧቸው ሲያበቃ ውሳኔያቸውን በአድናቆትና አክብሮት በመቀበል በክብር ሸኛቸው፡፡ በጉዳዩ ላይም ጊዜ ወስዶ መከረ፡፡ አንድነትን ያለመሪ ለአንድ ቀንም ቢሆን ማሳደር አደገኛ እንደሆነና የፕሬዘዳንት ምርጫውን ማከናወን እንደሚገባም ወሰነ፡፡ ይህንን ለመወሰን የሚያስችል ስልጣን እንዳለው ከደንቡ ተጠቀሰ፡፡ ‹‹ብሔራዊ ም/ቤቱ ደንብ ከማሻሻል ውጭ ጠቅላላ ጉባዔውን ወክሎ እንዲንቀሳቀስ ውክልና ተሰጥቶታል›› ይላል፡፡ በዚህ የጠቅላላ ጉባዔ ውክልናው መሰረት ሦስት ዕጩ ፕሬዘዳንቶችን በጠቅላላ ጉባዔው የማወዳደሪያ መስፈርት መሰረት አወዳድሮ አቶ በላይ ፈቃዱን የፓቲው ፕሬዘዳንት አደርጎ ሾመ፡፡ ካቢኔያቸውን በአስቸኳይ አዋቅረው ወደ ስራ እንዲገቡ መመሪያ አስተላለፈ፡፡

ትንሽዋ ግርግር

በዚህ ሂደትም ‹‹አልተደሰትንም፣ ኢ/ር ግዛቸው ለምን ሄደብን!›› ያሉ ጥቂት ግለሰቦች ምክር ቤቱ ባካሄደው ምርጫ አምነው ከተሳተፉ በኋላ ሌላ የጎንዮሽ እንቅስቃሴ ያዙ፡፡ ይሄ እንቅስቃሴያቸውም መኢቲቪ፣ ምርጫ ቦርድና በትርፍ ፈላጊ ሃይሎች መታጀብ ጀመረ፡፡ እውነት መጥራቷ ላይቀር መንሻፈፍ ጀመረች፡፡ መግለጫዎች ተዥጎደጎዱ፡፡ የገዥው ፓርቲ ቀኝ እጅ ኢቲቪም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በየቀኑ ከስድስት ጊዜ በላይ በማስተላለፍ ትንሽዋ ግርግር ህይወት እንዲኖራት ጣረ፡፡ ነገርግን እውነቱ እንደዚያ አልነበረምና ግርግርዋ የአንድ ሳምንት ከመሆን አልዘለለችም፡፡ አዲሱ አመራር በስራ በመጠመዱ እና ለጓዳ ወሬዎች ምላሽ ባለመስጠቱ የአባላትን ትኩረትና ድጋፍ ለማግኘት ቻለ፡፡ ግርግሯም ከምሱሩ እንከሸፈ ጥይት ቱሽሽሽሽ አለች፡፡

ምርጫ ቦርድ ግን ምክርቤቱ የመረጠውን አመራር ዕውቅና ለመንፈግ አንገራገረ፡፡ በተደረጉ የደብዳቤ ልውውጦችም ምርጫ ቦርድ ሁሉንም ነገር ተቀብሎ ሲያበቃ አንዲት ትንሽ ቀዳዳ አመጣ፡፡ እሷም፡- ‹‹የጠቅላላ ጉባዔተኛ ኮረም ቁጥር በደንቡ ይካተት›› የምትል ናት፡፡ በተፈለገ ጊዜ ለመምዘዝ የታሰበች ቀይ ካርድ ናት፡፡ ደንብ ሊያሻሽል የሚችለው ደግሞ ጠቅላላ ጉባዔው ነው፡፡ ወደ ተሟሟቀ ህዝባዊ ንቅናቄ ስንገባ ይችን ካርድ ለመጠቀም እንዳሰቡ ግልፅ ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ በተወሰኑ ፓርቲዎች ላይ እንደሚያደርገው ጥብቅ ቁጥጥር 60 እና 70 በሚላቸው ፓርቲዎች ላይ ማድረግ ቢችል የፓርቲዎቻችን ቁጥር ከ5 ሊዘል እንደማይችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ ስለዚህ አንድነት የምርጫ ቦርድን የመጫወቻ ካርድ ማስጣል እንደሚገባ አመነ፡፡ ጠቅላላ ጉባዔውን መጥራት ለእንደ አንድነት ያለ ሀገራቀፍ መዋቅር ላለው ፓርቲ ብዙ ከባድ አይደለም፡፡ ሆኖም አያውቅም፡፡ እንዴውም በዚህ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ያሉ አመራሮችን ማግኘት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይሉት አይነት ነው፡፡

ጉባዔው

ጉባዔ ለማካሄድ ቀን ተቆረጠ፡፡ ያለችው አንድ ሳምንት ብቻ ነበረች፡፡ በሀገር ውስጥ ያለው አመራርና አባላት እንዲሁም በውጭ ያሉ ብርቱ ደጋፊዎቻችን ተረባረቡ፡፡ ለጠቅላላ ጉባዔ አባላት ጥሪ ተላለፈ፡፡ የዞንና የወረዳ አመራሮች ጉዳዩን በንቃት ይከታተሉት ነበርና ሆ ብለው አዲስ አበባ ገቡ፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግን ያስደነገጠ ጉባዔ ነበር፡፡ በአንድ ሳምንት እንደዚህ የደመቀ ጉባዔ ማካሄድ ብር ለሚነሰንሰው ገዥ ፓርቲ እንጅ ለተቃዋሚዎች የሚቻል አይመስልም፡፡ ለዚህም ‹‹ጉባዔ ጥሩ!›› እንደማስፈራሪያ ያገለግላል፡፡ አንድነት ግን በሀገራቀፍ ደረጃ ያለውን አቅም አሳየ፡፡

አርብ በማለዳው ከ400 በላይ የሚሆነው የጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊ በኢትዮጵያችን ባንዲራ በተመሰለ አለባበስ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ለብሶ አዳራሹን ሞልቶታል፡፡ ሁሉም ላይ እልህና ወኔ ይነበባል፡፡ ስብሰባው የተጠራበት አጀንዳ ለውይይት ክፍት ሆነ፡፡ ትንሽዋን ግርግር ለመፍጠር የሞከሩ ግለሰቦች ጉባዔተኛው ፊት እንዲከራከሩ ወይም ሂሳቸውን እንዲሰለቅጡ ጥሪ ቢደረግላቸውም ሳይመጡ ቀሩ፡፡ የተገኙ ግለሰቦችም እንደ አሮጌ ቴፕ እየተንተፋተፉ ለምን ወደ ኢቲቪ እንደሄዱ ለማቅረብ ቢሞክሩም ከውግዘት በስተቀር ምላሽ አጡ፡፡ ምክንያቱም ኢቲቪ ለተቃዋሚው ያለው ምልከታ ይታወቅ ነበርና አኮረፍን ብለው ወደ ኢቲቪ መሄዳቸው ክስረት ነበር፡፡

እነሆ ጠቅላላ ጉባዔው ምክር ቤቱ የወሰደው ርምጃ ጠቅላላ ጉባዔው በሰጠው ውክልና መሰረት በመሆኑ ደንባዊም ተገቢም ነው ሲል ወሰነ፡፡ በላይ ፈቃዱም ፓርቲውን እስከ ቀጣይ ጉባኤ ድረስ የፓርቲው ፕሬዘዳንት በመሆን እንዲመራ በማለት በከፍተኛ ድምፅ ወሰነ፡፡ የሚገርመው ከራሱ ከበላይ የቀረበውንና ሌሎች አመራሮች የደገፉትን ዕጩዎች ቀርበው ፕሬዘዳንት ይመረጥ የሚል ሃሳብ ጠቅላላ ጉባኤው ውድቅ በማድረግ የም/ቤቱ ውሳኔ ትክክል ነው በማለት በሙሉ ድምፅ መወሰኑ ነው፡፡

ይሄው ግዙፍ የአንድነት የፖለቲካ ሃይል ደንቡንም አሻሽሏል፡፡ ሌሎች የፖለቲካ ውሳኔዎችንም አሳልፏል፡፡ አንድነት በ2007 ዓ.ም ሀገራቀፍ ምርጫ አሸናፊ ሃይል ሆኖ እንዲወጣ በሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ ጥናቶች ቀርበው ውይይት አድርጓል፡፡ ህዝቡን ያሳተፈ ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲደረግ እና ምርጫውን ነፃና ፍትሃዊ ለማድረግ ትግሉ ተፋፍሞ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

ተደራጅ፣ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ተከታተል፤ አምባገነኖችን የምትቀጣበትን የምርጫ ካርድ ያዝ፤ ድምፅህ እንዳይዘረፍ ጠብቅ፤ ይህን ሁሉ አልፈው ከዘረፉህ በህዝባዊ እምቢተኝነት አምበርክካቸው የሚለውን ጉባዔተኛው በአንድ ድምፅ በመናገርና ቃልኪዳን በመግባት ታላቁ የአንድነት ጉባዔ በድል ተጠናቀቀ፡፡

2007 ለለውጥ!!

 

 

ሕዝባዊ ዕንቢተኝነት ለኢትዮጵያ ትንሳኤ!

$
0
0

ነብዩ ኃይሉ

ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ዘጠኝ ፓርቲዎች ያቋቋሙት ትብብር የጠራው የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ፣ በገዢው ቡድን ውንብድና ከተስተጓጎለ በኋላ ስለሰላማዊ ትግል አይረቤነት የተለያዩ አስተያየቶች በመሰጠት ላይ ናቸው፡፡ የተወኑት አስተያየቶች “ትግሉ አልጋ በአልጋ መሆን አለበት” ከሚል የዋህ ልቡና የመነጩ የተስፋ መቁረጥ ስሜቶች ቢሆኑም፤ ጥቂት የማይባሉት ግን የህብረተሰቡን ቀልብ ከሰላማዊ ትግል አውድ ለማፋለስ ታቅደው የሚሰነዘሩ ይመስላሉ፡፡
Tensaye
በመሰረተ-ሀሳብ ደረጃ የትኛውንም የአገዛዝ ስርዓት ለመጣል የሚደረግ ትግል በአንድ ወጥ ቀኖናዊ የትግል ስልት ላይ ብቻ መመስረት ይገባዋል የሚል ድምዳሜ መስጠት አይቻልም፡፡ ሆኖም ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የትኛው የትግል ስልት ያዋጣል የሚለውን በኃላፊነት ስሜት የመምረጡ ተግባር ለታጋዩ የሚሰጥ ነው፡፡ በየትኛውም መለኪያ በትግል ላይ የሚፈጠር እንቅፋት ሁሉ ስልቱን ጥያቄ ምልክት ውስጥ ሊከት ግን አይችልም፡፡

ዓለም-አቀፍ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት የአገዛዝ ስርዓት የሚወገድባቸው በርካታ መንገዶች አሉ፡፡ከሚያስከፍሉት መስዋዕትነት አንፃርም በደረጃ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው የትጥቅ ትግል ነው፡፡ የትጥቅ ትግል መጠነ-ሰፊ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት የሚያስከትል ከመሆኑም በላይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማንበር እጅግ ፈታኝ ነው፡፡ በሰላማዊ ትግል ላይ የረጅም አመታት ጥናት ያደረጉትና በቅርቡ “ሰላማዊ ትግል 101” በሚል ርዕስ መጽሀፋቸውን ያሳተሙት አቶ ግርማ ሞገስ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ከጦርነት ጋር የተጋመደ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ “ሀገራችን በስልጣኔ እንዳትገሰግስ ደንቃራ የሆነባት አገዛዞችን በጦር ሀይል ለማስወገድ የሚደረጉ የእርስ በርስ ጦርነቶች ናቸው” ሲሉም ይሞግታሉ፡፡

“ለዘጠኝ መቶ አመታት ላላነሰ ጊዜ ኢትዮጵያ በዘመናዊ (Secular) ትምህርት፤ ትምህርቱን ተከትሎ ለሚመጣ ዘመናዊነት እና ስልጣኔ ጀርባዋን መስጠቷ ለኋላ መቅረቷ አንዱ አውራ ምክንያት እንደነበር ከላይ ለመግለፅ ተሞክሯል፡ ፡በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ደግሞ ቢያንስ ቢያንስ ከአክሱም ስልጣኔ መውደቅ በኋላ አምባገነኑ ህወሓት/ ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም ስልጣን እስከጨበጠበት 1983 ዓ.ም ድረስ የእርስ በርስ ጦርነት (ትጥቅ ትግል) አካሂዶ ስልጣን መያዝ ጀግና የሚያሰኝ ባህል ነበር/ነው፡፡ ነፍጥንና ጉልበትን መሰረት ያደረገው የመንግስት ሽግግር ባህሏ ኢትዮጵያን እጅ እና እግሯን ተብትቦ ስለስልጣኔ የምታስብበት መተንፈሻ ጊዜ እንኳን እንዳይኖራት
አድርጓት
ሞገስ፡ ትግል101”
ነበር።
ግርማ “ሰላማዊ 2006፡33-34

ሌላው የትጥቅ ትግል ደካማ ጐን፣ ትግሉ በሶስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት ጭምር የሚወሰን መሆኑ ነው፡ ፡ በዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ እንደተመለከትነው ከሀገራችን ጋር መሠረታዊ የጥቅም ባላንጣነት ያላቸው ጐረቤት ሀገራት ለደፈጣ ተዋጊዎች ድጋፍ እንደሚሰጡ ተመልክተናል፡፡ አገራቱ የደፈጣ ተዋጊዎቹን የሚረዱት ኢትዮጵያን ከአገዛዝ ስርዓት ለማላቀቅ ሳይሆን፣ አማፅያኑ የመንግስትነት መንበር ሲይዙ የመንግስታቸውን ጥቅም ማስከበር ነው፡፡

ሌላው የአገዛዝ ስርዓቶች የሚወገዱበት መንገድ መፈንቅለ-መንግስት ነው፡ ፡ መፈንቅለ መንግስት፣ የጥቂት ባለስልጣናትና የጦር መሪዎችን ለስልጣን ከማብቃት ባለፈ ህዝብን የስልጣን ባለቤት በማድረግ አገዛዝን ሲያስወግድ አይታይም፡፡ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት ሲተገበር እንዳስተዋልነውም፤ መፈንቅለ መንግስት የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ነው፡፡ በቅርቡ ነፃነቷን ያገኘችው ደቡብ ሱዳን አሁን ያለችበትን ምስቅልቅል መመልከቱ የመፈንቅ ለመንግስትን አደገኝነት የሚያመላክት ነው፡፡ በውጤቱም ሆነ በሂደቱ አምባገነንን በሌላ አምባገነን ከመተካት አንፃርም ከትጥቅ ትግል የተለየ አይደለም፡፡ የበርካታ ሀገራት ዜጐች የስልጣናቸው ባለቤት የሆኑት ከላይ በተጠቀሱት ሁለት መንገዶች ሳይሆን በሀይል አልባ ህዝባዊ እንቢተኝነት ነው፡፡

የህዝባዊ እንቢተኝነት የትግል ስልት፣ ከክርስቶስ ልደት በፊት በጥንታዊያኑ ግሪክና ቻይና እንደተተገበረ የዘገቡ የታሪክ ድርሳናት ቢኖሩም፣ በይበልጥ ያስተዋወቀው ግን ህንዳዊው የነፃነት ታጋይ ማህተማ ጋንዲ ነው፡ ፡ የጋንዲ የህዝባዊ እንቢተኝነት አስተምህሮ፣ በሂንዱ ቋንቋ Sanskrit ahimṣṣ በመባል ይታወቃል፤ አስተምህሮው በትግል ሂደት ውስጥ በራስም ሆነ በሌሎች ላይ በየትኛውም ሁኔታ ጉዳት እንዳይደርስ የሚያስችል ነው፡፡ የትግል ስልቱ ሰላማዊነት የሚንፀባረቀው ሞራላዊ፣ ሀይማኖታዊና መንፈሳዊ ዕሴቶችን የያዘና አንድን ውጤት ለማምጣት በሰው፣ በእንስሳትም ሆነ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ የሚያደርስ መሆን እንደሌለበት ያስተምራል፡፡ ህዝባዊ እንቢተኝነት ሀይል አልባ መሆኑም የአገዛዝ ስርአትን ለማስወገድ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ውሱን ያደርገዋል፡፡ ህዝባዊ እንቢተኝነት በጥናትና በዕቅድ የሚከወን ነው፡፡ ባልተቀናጀና ግብታዊ በሆነ መንገድ የሚደረግ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ግን ህዝብን ሽንፈት ከማለማመድ ባለፈ ህዝባዊ እንቢተኝነትን ይወልዳል ብሎ መጠበቅ አላዋቂት ነው፡፡

ያልተጠኑ፣ በግብታዊነትና በተናጥል የሚደረጉ ያልተሳኩ የተቃውሞ ትዕይንቶች በህዝቡ ውስጥ ሽንፈትን የሚጠሩ ናቸው፡፡ ህዝባዊ እንቢተኝነት፣ ከአነስተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ወደ “ምድር አንቀጥቅጥ” የተቃውሞ ትዕይንትነት የሚያድግ እንደመሆኑ መጠን ከጅምሩ የሚደረጉ ተቃውሞዎች የተጠኑና ታቅደው የሚደረጉ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ለራስ የሚሰጡ የተጋነኑ ወይም የተንኳሰሱ ግምቶችም ሆነ ለተቀናቃኝ የሚሰጡ የተጋነኑ አሊያም የተንኳሰሱ ግምቶች የሚፈጠሩት ጥናትና እቅድ ላይ የተመሰረቱ እንቅስቃሴዎች ባለመደረጋቸው ሳቢያ ነው፡፡ ባሳለፍናቸው ጥቂት አመታት እንኳን የተደረጉ የተቃውሞ ትዕይንቶችን ብንፈትሽ፣ የምናገኘው ውጤት አብዛኞቹ በተጠና እና በታቀደ ሁናቴ የተከወኑ እንዳልሆኑ እንረዳለን፡፡ ማንኛውም ተግባር አመቺ ጊዜ ይፈልጋል፤ ጥሩ የሚባል ጥናት የተሰራለትን አንድን ተግባር ውጤታማ እንቅስቃሴዎች ውሱኑንት ታይቶባቸዋል፡ ፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎቹ ውጤትን ሊያመጡ እንዲችሉ ተደርገው ያተጠኑና አመቺ ጊዜ ተመርጦላቸው ያልታቀዱ በመሆናቸው ግብታዊነት የሚስተዋልባቸው ሆነዋል፡፡

ሌላው ሊነቀፍ የሚገባውና ህዝቡን ሽንፈት የሚያለማምደው የተቃውሞ እንቅስቃሴዎቹ የተናጠል መሆናቸው ነው፡፡ ህዝባዊ እንቢተኝነትን ያመጡ፣ በሂደትም ለውጥን ያበሰሩ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የህዝቡን ትኩረት ያገኙት፣ ሁሉንም ህዝብ በአንድ የጋራ ተተኳሪ ነጥብ ላይ ያሰባሰቡ በመሆናቸው ነው፡፡ በሀገራችን የተደረጉና እየተደረጉ ያሉት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ግን የህዝቡን የለውጥ ፍላጐት እውን እንዲሆን፣ ወደአንድ የትኩረት ነጥብ የሚስቡ ለመሆን አልቻሉም፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት የተናጠል የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆኑ ይፋዊ ያልሆኑት የቡድን መብት አራማጅ ስብስቦች፤ እንቅስቃሴያቸውን ወደአንድ የትኩረት ነጥብ እንዲወስዱ ይጠበቅባቸዋል፡፡ይህ መደረጉ በተቃውሞ ትዕይንቶቹ ላይ የሚገኘውን ተሳታፊ ቁጥር ከፍ እንዲል የሚያደርግ በመሆኑ፣ አገዛዙን የሚያንበረክክ ይሆናል፡፡ በየትኛውም መለኪያ ተፅዕኖ ከቁጥር ጋር ያለውን ትስስር ማስቀረት ስለማይቻል፣ የተናጥል እንቅስቃሴዎችን ማሰባሰብ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ግዙፍ ውሱንነቶች፣ የነፃነት ትግሉን እጅ ከወርች ያሰሩ ከመሆናቸውም በላይ በህዝቡ ውስጥ የሽንፈት ስሜትን የሚዘሩ ናቸው፡፡ በተቃውሞ ትዕይንቶች ላይ የሚታየው አነስተኛ የሰው ቁጥር ለውጥን ሊያመጣ የሚችል የሀይል ሚዛን ተቃዋሚዎች ጋር እንዳለ ዋስትና ስለማይሰጥ፤ ህዝቡን ለተስፋ መቁረጥ አሳልፎ እንደሚሰጥ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

የያዝነው አመት ምርጫ የሚካሄድበት እንደመሆኑ ዘጠኙ ፓርቲዎች ምርጫው ፍትሀዊ እንዲሆን በመጠየቅ ሊያካሂዱት የነበረውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፣ ጭካኔን በቀላቀለ ሁኔታ እንዲደናቀፍ መደረጉ ገዢው ቡድን ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር አሁንም አለመዘጋጀቱን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህን በዕብሪት የተወጠረ፣ በመሳሪያውና በሰራዊቱ ብዛት የሚመካ ቡድንን ለማስወገድ ተመጣጣኝ አቅም መገንባት የግድ ይላል፡፡ ገዢው ቡድን የያዘው መሳሪያና የሰራዊት ብዛት ከኢትዮጵያ ህዝብ አቅም ጋር ሊወዳደር አይችልም፤ ይህን የግብፅ፣ የቱኒዝያ፣ የዩክሬንና ሌሎች በህዝባዊ ዕምቢተኝነት ግብአተ-መሬታቸው የተፈፀሙ አንባገነኖች ታሪክ ይመሰክራል፡፡

በማንነት ፍለጋዉ ጉዞ –የአፋሩን ቅኔ፤ በእኔ ቅኝት

$
0
0

ከ ኆኅተበርሃን ጌጡ /ጀርመን

አጠገቡ ሆኖ ሲያወሩት ጨዋታዉ ለዛለው። ተፈጥሮዉ ሆኖ የ…….. ጠንጋራ ሳይቀር ለይቶ ያዉቃል። በጨዋታ መካከልም ሁለት አይነት ሳቆች አሉት። የዘወትርና  የክት። ወደ ደም ስር ዘልቆ የሚገባ ቀልድና ቁምነገር ከገጠመዉ  ደግሞ ከልቡ ይፍነቀነቃል። ካልጣመዉም በዘወትሩ የለበጣ ሳቅ ያልፈዋል። የሳቁ ዓይነት ሲነግረንም  በረዥሙ ልንቀድ ያሰብነዉን ጉዳይ ባጭሩ  እንቀጨዋለን። ሳቁ ለእኛ ምልከታ ወይም ርችት ነዉ። ለጨዋታዉ ዉበት የሚሰጠዉ ደግሞ አማርኛ የአፍ መፍቻ ቑንቑዉ አለመሆኑ ነዉ። ለምንም ለማንም ሳይል ደፋር ተናጋሪነቱ ደግሞ የብዙዎቻችንን ቀልብ ለመሳብ አስቸሎታል። በእርግጥ ለዚሀ አይነቱ አቑሙ ሰዎች የተለያየ ትርጉም ይሰጡታል። ግራና ቀኝ ተሽክመነዉ  የምንዞረዉ ጆሮ ባእዳቸን ስለሆነ እሱም እራሱ እስካሁን ጉዳዩን ያልሰማዉ ሊሆን ይችላል። የሚባለዉን እኔም ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ አደባባይ ማዉጣቴ ነዉ። የእሱ ደፋርነት ከሌሎች የተለየ ወንድ ሆኖ አይደለም። ደሙም እንደ የሁላችንም ደም ቀይ ነዉ። ልዩነቱ ከአፋር ክልል ዉጭ በከተማ የሚኑሩ ዘላኖች ስላሉ የዚያ አይነቱ ዘላኔያዊ ባሕርይ ብልጭ እያለበት ነዉ በማለት፤ ሊሞግቱን ይሞክራሉ። ነገርን ነገር እያነሳዉ ተወራጨሁ ወይም ዙሪያ ጥምጥም እየሄድኩ ለአንባቢ አስቸገርኩ መሰል እንጅ፣ ዓላማዬ የሰዉየዉን ባሕርይ ማተት አይደለም። እኔን በግል የሚያስደስተኝና የምመካበት ምንጊዜም የማይበገር ኢትዮዽያዊነት አቁኣሙ እንጅ ግላዊ ባሕርዩ ስላልሆነ፣ ይህን ይህን ለባለቤቱ ለሓዋ ሙሳ ትቼ ወደ ተነሳሁበት ነጥብ ባመራ ከአንባቢም ጋር የምስማማ ይመስለኛል።

አሰባሳቢ ማንነት ባንድ ሃገር ልጅነት፣ የኢትዮጵያ ዕጣ ፋንታ በሚል ርዕስ የተከተበ መጽሓፍ ሰሞኑን ለንባብ መብቃቱን የተለያዩ ድረ ገጾች አብሥረዉናል። ደራሲዉ በሚኖርበት የኖርዌይ መዲና ኦስሎ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንም በደመቀ ሥነ ሥርዓት ኖቬምበር 22 ቀን 2014 መፅሐፉን በይፋ መርቀዉታል፤ ከመፅሃፉ የዉጭ ሽፋን እስከ ጀርባ ድጉሥ፤ ከአርትኦት ሥራ እስከ ሥርአተ ነቁጥ (ነጥብ)፣ ከጎላ ግምገማም አልፈዉ ቀመረ ሰዋስዉ የተከተለ መሆኑንና አለመሆኑንም ጭምር አበራይተዉታል። ደራሲዉንም በጥያቄ አፋጠዉታል። እታዲያ ከዚህ የመፅሃፍ ግምገማ ነክ ምረቃ ሥነ ሥርዓት በዓል፤ ወደ ጀርመን ይዤዉ የተመለስኩት ትዝታ ቢኖር፤ የኖርዌይን ብርድና ስሙን የማላስታዉሰው የዋሽራዉ ተወላጅ፣ የሉሲዉ (ድንቅነሽ) አገር የአፋሩ  ተወላጅ መፅሃፍ የአማርኛ ቑንቑ አጠቃቀም እንደከበደዉ ጥያቄ ማቅረቡና እንደዚህ ዓይነት ችግር ላለባቸዉ ሌሎችም ተመሳሳዮች፤ በኦስሎ ከተማ በቅርቡ  የአማርኛ መማሪያ ጣቢያ እንደሚከፈት የደራሲዉ ባለቤት ስላቅን ያዘለ፤ ፈጣን መልስ መስጠታቸዉና ቃል መግባታቸዉ ተስብሳቢዉን በእጁጉ ማስደመሙ ነዉ። በእርግጥ መፅሃፉና የደራሲዉ የተጸዉኦ ሥም አደባባይ ወጣ እንጅ፤ ሰዉየዉ ለብዙ ኢትዮጵያዉያን አዲስ አይደለም። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ልሳን፣ አይንና ጆሮ ሆና ስትታገል የነበረችዋ ጦቢያ መፅሄት ቑሚ አምደኛ በመሆን መጽሃቷን በእግሯ ካቆሙዋትና ተነባቢ እንድትሆን ካበቁአት ጸሐፍት መካከል (እንደነ ጸጋዪ ገብረመድሕን አርአያ፣ ስንሻው ተገኝ…….ወዘተ) በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንደኛዉ ነዉ። ሐሰን ኡመር አብደላ በሚለዉ ተናዳፊ የብዕር ሥሙ። ለአራት አመት ያህል ነጻዉን ፕሬስ ተቀላቅላ በአቅም እጥረት ምክንያት የከሰመችዉ የራዕይ መፅሄትም (ፍራንክፈርት ጀርመን ትታም የነበረችዉ) መሥራች የቦርድ አባልና አምደኛም ነበረ። ካረሳሁት በወቅቱ የመፅሄቷ የሥራ መርሆ ምን መሆን እንዳለበት የተለያዩ ሃሳቦች ቀርበዉ ስንነጋገር፣ <ለሁሉም መድረክ ነን፣ የማንም ልሳን ግን አይደለንም>፣ የሚል እንዲሆን፤ ሁሉንም የቦርድ አባላት በአንድ ድምፅ ያሳመነ ሀሳብ አፍላቂዉ እሱ ነበረ። ይህ ብቻም አይደለም፤ ተዘዉትሮ በጀርመን ድምፅ ራዲዮ የምሥራቅ አፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ ተንታኝነቱም የሬዲዮ ጣቢያዉ አድማጮች ጆሯቸዉን ቀስረው የሚያዳምጡት ነዉ። ዛሬም የቀድሞ የጦቢያ ደንበኞች በተለያዩ አጋጣሚዎች በአካል ስንገናኝ ያ፣ አፋሩ የጦቢያ መጽሄት የነፍስ አባት ደኅና  ነዉ? ሳንባባል  አናልፍም። ይኽዉ አሁን ደግሞ በእዉነተኛ ሥሙ ሁላችን ስንጠብቀዉ የነበረዉን እምቅ ችሎታዉን ያሳየበትን፣ የወደፊቷን ኢትዮጵያን ዕጣ ፋንታ እንደ መስታወት ወለል አድርጎ  የሚያሳየዉን  መጽሃፍ ይዞ ብቅ ብሏል።

ኮብላዩ ሚኒስትር ኤርምያስ ለገሰ ስለባለቤት አልባዋ ከተማ አዲስ አበባ በወዶ ገብ የኢሕአዴግ ካድሬነቱ ለአሥራ ሁለት አመታት ያለፈበትን ጉዞ፣ ሥርአቱ ምን ያህል የተግማማ እንደሆነና ከቀዳማዊት እመቤት ጀምሮ እስከ አዉራ ካድሬዎቹ በከተማ ቦታ ዝርፊያና በሙስና የነቀዙ መሆናችዉን የጆሮ ሳይሆን የአይን ምሥክርነቱን ሰጥቶበታል። <አሰባሳቢ ማንነት ባንድ ሃገር ልጅነት> የተሰኘዉ ይህ መጽሃፍ ደግሞ ስለባለቤት አልባዋ፣ የእነሱ? ወይንስ የእኛ የሁላችን የዜጎቿ? መሆኗ ገና በዉል ስላልታወቀችዉ ኢትዮጵያ ስለምትባለዋ ሀገራችን ነዉ። እስኪ እራሳችሁን ጠይቁ፣ በአሁኑ ጊዜ ማነዉ የኢትዮጵያ ባለቤትዋ? እነሱና እኛ ተባብለን ሳንቧደን እኛ ኢትዮጵያዉያን የምንላት የሁላችን የሆነች፤ እኛም ዜጎቿ የእሷ የሆንላት፤ የጋራ ሀገር እንዴት መፍጠር እንደሚቻል በአመክንዮ አስረግጦ፣ የአብሮነት ቀመርን አስፈላጊነት ከነመፍትሄዉ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጧል። ከማንነቶች መራኮት ይልቅ ወደ ኢትዮጵያዊነት አሰባሳቢ ማንነት፤ ፍለጋ የመኹተን አስፈላጊነትን በአጽንኦት ለማሳዬት ደክሞበታል። አዎ፤ ሁላችን የምንነጋገረዉ፤ ኢትዮጵያ ስለምትባለው ሃገር ከሆነ፣ ኢትዮጵያዊነት ግን ግለሰቡ በምርጫዉና በገዛ ፈቃዱ የሚላበሰዉ ወገንተኝነት በመሆኑ፣ ይህን አሰባሳቢነት ኢትዮጵያዊነት በእያንዳንዱ ተወለድሽኝ ዜጋ ሥነ አዕምሮ እንዴት ማስረጽ እንደሚቻል፣ አትቷል። የመጽሃፉ ምሥጢርና ሰምና ወርቅም በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥን ሆኖ እናገኝዋለን። የመጽሃፉ መዘዉረ ሃሳብ በዚህ ዙሪያ ያቀንቅን እንጅ፣ ደራሲዉ ወደዚህ የማሳረጊያ ነጥቡ ለመድረስ ብዙ የማንነት ፍለጋ ጉዞ እንዳደረገ፣ ያገላበጣቸዉ ዋቢ መረጃዎቹ ያስረዳሉ። ዋቢዎቹም ሀገርኛና የዉጭ ቑንቑዎችን አካተዋል። ከመጽሃፉ ይዘት ጋር ቁርኝት ያላቸዉ የኅብረተሰቡን ገሃድ አለም አቀንቃኞች የሚገልጹባቸዉ የዘፈን ስንኞችም ልብ መሳጭነት ባለዉ መንገድ ሰፍረዋል። የመጽሃፉ ዘይቤያዊ አገላለጽና የአጻጻፍ ሥልት ሲፈተሽ፤ በመንዝኛም፤ በጎንደርኛም፤ በሸበል በረንታም ቅላጼ ባለዉ አማርኛ ሳይሆን፤ እራሱን ዩሱፍ ዩሱፍን በሚሸት የራሱ ዩሱፋዊ ዘይቤና ቃና ባለዉ መንገድ ተክሸኖ የቀረበ ነዉ። የመልዕክቱን ይዘት ለተረዳዉ ደግሞ አፋሩ ለኢትዮጵያዉያን የተቀኘዉ ይበል የሚሰኝ ቅኔ የተቀኘበት መጽሃፍ ነዉ። ብዙአዪሁ የሚባል ዘፋኝ ቅርብ ጊዜ ባወጣዉ አልበሙ፣ አንዷን ኮረዳ ይህ ቀረሽ በማይባል ዉበት መላበሷን ሲግልፅ፣ ፈጣሪ ተራቆብሻል፤ ጥበቡን ማሳያ አርጎሻል። እንዳለዉ፣ የኢትዮጵያዉያንን የአብሮነት የመኖር ጥበብን አስፈላጊነት ጆሮ ያለዉ ከሰማ፣ልብ ያለዉ ካስተዋለ ለአሰባሳቢ ማንነታችን እንደ ፍቱን መሳሪያነት ልንጠቀምበት የሚገባ ሰነዳችን ነዉ።

ከማንነቶች መራኮት ይልቅ ወደ አሰባሳቢ ማንነት ፍለጋ ጉዟችንን እንድናሳምር፣ ጸሐፊዉ የማሳረጊያ ቡራኬ ከመስጠቱ በፊት፤ ለመጽሃፉ አላማ ግብ መምቻ የሚዉሉና በቀጥታ ለመፅሃፉ መደረስም አዉራ አመክንዮነት ያላቸዉን መድበለ ሃሳቦች በአሥራ ሦስት ሞእራፎች (መሪ ርዕሶች) እና በሰማንያ አራት ንኡሳን ክፍሎች (መዘርዝረ ሐተታ) በመፈረጅ፤ ለእያንዳንዱ ተጟዳኝ ርዕስ ጥልቅ ትንተና ሰጥቶባቸዋል። ስለማንነት፤ ማንነትን ስለመለዬት ሂደት፤ በምን፣ በምን፣ እንደምንኮራ፤ ከምን፣ ከምንስ፣ እንደምንሰጋ፤ያለን የመንግሥትነት ታሪክ? ወይንስ ረዥም የሥልጣኔ ታሪክ? በማለት ከራሱና ካለፈ ታሪካችን ጋር ይሟገትና ከዚሁ ርዕስ ጋር ተቆራኝቶ፤ ያለን የረዥም ጊዜ የሥልጣኔ ታሪክ ነዉ ወደሚል መደምደሚያ የምናመራም ከሆነ፤ ሌሎቹ ለምን ጥለዉን ሄዱ? ለምን እኛ ጭራ ሆነን ቀረን? ብለን እራሳችንን በቁጭት እንድንጠይቅ ያደርግና፤ በቁስላችን ላይ እንጨት ሰድዶ ሆዳችንን ያባብሰዋል። የመንግሥት ጣልቃ ገብነትንና የሃይማኖት ተቑማትን ነጻነት ስለመለዬት አስፍላጊነት፤ በታሪካችን ስለተከናወነዉ የግዛተ አፄን የማስፋፋትና የማዕከላዊ መንግሥትን መደላደል ዘመቻ፤ ይህ የጥንት ዘመቻም በአሁኑ አብሮነታችን ላይ ያሳረፈዉ አሉታዊና አወንታዊ ገጽታዉ ምን እንደሆነ፤ ይህን ርዕስም ያጎዳኝና፤ የኦሮሞ ብሔረተኛነት፣ የማንነት ፖለቲካና ተፈታታኝ ተግዳሮቶቹን አስመልክቶ ድንቅ ትንተና አድርጎባቸዋል። እንኝህንና መሰል ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮችን በየምዕራፉ ካብጠለጠላቸዉ በኁላ ነዉ፤ አብዛሔነትን አስተዳድሮ ለዜግነታዊ መንግሥት መሠረት መጣል፤  ወደሚለዉ አዉደ ሐሳብ የተሸጋገረዉ። ከፊታችን ተደቅኖ ከሚታዬዉ ከዉስብስቡ ግዙፍ ሀገራዊ የፖለቲካ ችግር አንፃር፤ ይህ ነዉ፣ እያንዳንዳችንንም ኢትዮጵያዉያን ዜጎች የሚመለከተዉና ወቅታዊዉም የመፅሃፉ ምሥጢርና የአፋሩ ቅኔ።

እስኪ መጽሐፉ ካዘላቸዉ  ቁምነገሮች ጥቂቱን ቀንጨብ አድርጌ ላቃምሳችሁ። “<….ሁላችን የተሳፈርንባትን፣ እየተወዛወዘች ለመስመጥ የቀረበችዉን ጀልባ ላይ፣ እሳት ማቀጣጠሉንም ሆነ ሽንቁር መሸንቆሩን አቁመን፣ ሃገራችን ባሁኗ ሰአት የምትገኝበትን አሳሳቢ ሁኔታ ተገንዝበን፣ ወደ ልበ ልቦናችን ተመልሰን በሃገራዊ የሃላፊነት ስሜት እያንዳንዱ ድርሻዉን ለመሸከም ዝግጁነቱን ማረጋጥ ይኖርበታል። …..የተቁኣማት፣ የሕግ ልዕልና ሲቪል፤ ዜግነታዊዉ መንግሥት ምሥረታም ሆነ ማደላደል ረዥም  ጉዞ ቢሆንም ቅሉ የሀገሬ ልጆች፣ የተለያዩ የብሔረስብና የእምነት አባላት፣ የተለያዩ የመደብና የሙያ ማሕበራት፣ ሴቶችና ወንዶች እጅ ለእጅ ተያይዘዉ የዜግነታዊ መንግሥት ዳገቷ ላይ ሲደርሱ ይታዩኛል። አጣልቶ የሚያፋቅር ትዳር ይስጣችሁ ተብሎ ሲመረቅ ሰምተናል፣ ያጣላንም ይበልጥ እንድንፋቀር ከሆነም አጣልቶናልና ያፋቅረን!! አንዱ በሌላኛዉ ወንድሙ ባደረሰዉ በደል ምክንያት የቑጠረዉን የቅሬታ ስሜትና የታሪክ ቁርሾ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሽሮ፣ የሚያፋቃር በተደላደሉ መሠረቶች የቆመ ብሔራዊ አንድነትም ይስጠን! የሁሉንም የሕብረተሰባችን ተካይ ነቃይ ብዛሔሰብዕ ባንድነት በሚያቅፍ አቃፊ ደጋፊዉና አጣሪው አሰባሳቢና ሃገራዊ ማንነት በሆነዉ፣ ዜግነታዊ መንግሥትና ተቑማቱ ሥር ሁላችን ያስጠልለን!! ያሰባስበን!! በዚችዉ ሃገር፣ ባንድ ሃገር ልጅነት በእኩልነት ያኑረን! ያኗኑረን!! አ..ሜ..ን! ይለናል በሐገራዊ ቡራኬዉ።

ግን በተደላደሉ መሠረቶች ላይ የቆመ ብሔራዊ አንድነት እንዴት እንፍጠር? እንዴትስ ነዉ መምጣት የሚችለዉ? ነዉ ጥያቄዉ። ምን ዓይነት አንድነት ነዉ የነበረን? አብሮ ያኖረንን አንድነት አሁን ለምን ጠላነዉ? ችለናቸዉ እንጅ አብረን የኖርነዉ ተቻችለን ስላልነበር፣ እስኪ እንሞክረዉ ደግሞ ተለያይተን የሚል እንጉርጉሮዉን እያሰማ፣ ነፍጥ አንስቶ ዱር ቤቴ ያለ ክፍል አለ። ለዘመናት በደረሰብኝ በደል ከበሽታዬም ገና ስላልተፈወስኩ፣ አንድም ከእግሬ ጫማ ሥር ወድቀዉ፣ እንደገናም ላይለምዳቸዉ ቃል ገብተዉ፣ ይቅርታ ይጠይቁኝ፣ ይህ ካልሆነ፣ ከእነርሱ ጋር አብሮ የመኖሩ ጉዳይ አይታሰቤ ነዉ በማለት የበቀል ፖለቲካ ሲያካሂድ እየተስተዋለ ነዉ። እዚህ ላይ መረሳት የሌለበት ነጥብ ግን ከፊደሉ ጋር መርዙን አብሮ የተጎነጨዉ የኤሊቱ ጥያቄ ነዉ የብሔርትኝነት ጥያቄዉን ያጎላዉ? ወይንስ የአብዛኛዉ የአሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ሆኖ አብሮነትን ተፈታትኗል? በዚህ ረገድ የተደረገ ጥናትስ አለ ወይ? በእርግጥም የሕዝብ ጥያቄ ሆኖ እስከቀረበ ድረስ ግን ያንድ ሀገር ዜጎች መሆናችንን የሚያበሥር፤ የዜግነት ሕገ መንግሥታዊ መብትን በተግባር ያጎናፀፈ መልስ ማግኘት የግድ ይኖርበታል። የጥያቄዉ ግንባር ቀደም አስተጋቢዎችም፤ ጣራ የነካ የቂም በቀል ፖለቲካቸዉን ወደ ጎን በመተዉ፣ በኢትዮጵያ ሥም ይቅር ለእግኣብሔር የምንባባልበትን መንገድ ቢቀይሱ በዕዉንም የፖለቲካ ጠበብት መሆናቸዉን አስመሰከሩ ማለት ነዉ። ያ ሳይሆን ቀርቶ ግን የመጠፋፋትን መንገድ ከመረጥን ተጎጅዎቹ ሁላችንም ነን። ያለፈ ቂምና በደልን ከአዕምሯችን ፍቀን ስለነገዉ ብቻ እንሰብ!!  የፅድቅ መንገዱም ይህ ነዉና። ይህን ማድረግ ካልቻልን ግን አቀንቃኙ፤ ቂማችን ተራራ፣ መንገዳችን ግራ፤ አልተገናኘንም ከፈጣሪ ጋራ። እንዳለዉ፣ እንዴት ነዉ ከፈጣሪም፣ ከኢትዮጵያም ጋር የምንገናኘዉና አብረንስ የምንኖረው ነዉ ጥያቄዉ?

በሌላዉ ጫፍ ደግሞ የተፈፀመ የታሪክ ስህተት ኖረም አልኖረም፣ በተለባበሰ የአረም እርሻ ላይ ቆሞ፤ የጭፍን አንድነት መዝሙር እያስተጋባ፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ የአንድነት ወይም ሞት ቀረርቶና ፉከራዉን የሚያድለቀልቅ ፅንፈኛ አቑም አራማጅ አለ። ጭራሽ ጥያቄዉን መስማትና እንዲነሳም የማይፈልግ። የእምቧይ ካብ አንድነት ሳይሆን ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ማዕበል የማያናዉፀዉ፤ በኢትዮጵያዊነት ማገርና ምሰሶ ተለብዶ የቆመ፤ ብሔራዊ አንድነት የግድ ያስፈልገናል።  ይህም ሲባል፤ ምንም ይሁን ምን ያለፈ ታሪካችን ኅፀፅ አልነበረበትም ብለን አንሟገትም። ለመቀበል ገታራ አቁኣም ተያዘ እንጅ፣ አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንሄድ የሚያደርገን አኩሪ ታሪካችንንም፤ አንገት የሚያስደፋ የወል የሰቆቃ ግፋችንንም በጋራ ተቀብለነዉ ወደ አዲስ የመኖር ምዕራፍ እንሸጋገር ነዉ የምንለዉ። በእንደነዚህ ዓይነት መሠረተ ሀሳቦች መስማማት የማንችል ከሆነ፣ ምን ዓይነት አንድነት ብንመሠርት እነኝህን ጫፍና ጫፍ የተለጠጡ ገታራ ፅንፎች ወደ ኢትዮጵያዊነት አሰባሳቢ ማንነት ማዕቀፍ ሥር ማጠቃለል የምንችለዉ? ስለቂም በቀል ጉዳይ ካነሳሁ በቅርቡ የሰማሁትንና ለማመን የሚያስቸግረዉን ተምሳሌት ከቶዉኑ ለአንባቢ ሳልጠቅስ ማለፍ ግድ ይለኛል። ተወዛዋዡ ወጣት አብዮት (ካሣነሽ) ደመቀ በእሳት ቴሌቪዥን ጣቢያ በታማኝ በየነ የጥበብ ቃና ሾዉ ቀርቦ ባደረገዉ ጭዉዉት፤ በ 1993 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ሲረበሽ ብቸኛ ልጃቸዉን ፍለጋ ከቤት ወጥተዉ፣ ከፖሊሶች በተተኮሰ ጥይት እየተዝለፈለፉ በደቂቃ ዉስጥ ልጃቸዉንም ያገኙትና ለራሳቸዉ ሳይሆን ለእሱ የኖሩት እናቱ ካሣነሽ፣ በእጁ እንደደገፋቸዉ እጁ ላይ እንዳሉ ሕይወታቸዉ ታልፋለች። ከቤታቸዉ ላይመለሱ ለአንዴና ለመጨረሻ እንደወጡ ቀሩ። በመላ ሕይወቱ የማይረሳዉ ገጠመኙ ቢሆንም፤ ገዳዮቹን ለመበቀል ግን እንደማያስብ፣ የሚከተለዉ ሃይማኖቱም የቂም በቀል መንገድ በር መክፈትን እንደማይፈቅድለት ሲገልፅ፤ በቴሌቪዥኑ መስኮት  የማዬዉን ሰዉ ማመን፤ የገዛ ጆሮዬንም መጠራጠር ጀመርኩ። እስኪ ማን ይሙት በዓፄ ምኒልክ ሠራዊት በተተኮሰ ጥይት በቅድመ ዘር ቆጠራ ደርሶበት የቅድም፣ የቅድም አያቱ እጁ ላይ ሕይወቱ ያለፉበት ዜጋ በመካከላችን ካለ፣ የዚህን ወጣት ታሪክ ሲሰማ የቂም በቀልን ሥርዓተ ቀብር ፈፅሞ ከራሱም፣ ከሌላዉም ጋር ታርቆ፤ አዲስ የመኖር ምዕራፍ አይጀምር ይሆን ትላላችሁ? እስኪ ልቦና ይስጠን!!

ሦስተኛዉና በጣም አደገኛዉ የትርምስ አካሄድ ደግሞ፣ ተጠቃሾቹን ሁለት ፅንፈኛ አቁም አራማጆችን የማን አባቱ ገደል ገባ እያለና በችግራቸዉ ክብሪት እየጫረ፣ ችግሩንም የፈታ እያስመስለና በችግሩም እያፌዘ፣ ዓላማዉም እራሱን ከሥልጣን ላይ አደላድሎ ማቆዬት ብቻ ይሆናል። ምክንያቱ ደግሞ በተደላደሉ መሠረቶች ላይ የቆመ ብሔራዊ አንድነት መመሥረት ከመጀመሪያዉም አጀንዳዉ አይደለምና። ወጋ ወጉ ተይዟል፣ ችግር አንቆ ይዟል እንደሚባለዉ ዓይነት ሆነ እንጅ፤ ባለጊዜዉ ቡድን በችግሩ መፍቻ የማኀበራዊ ሳይንስ መድኃኒትነት ተጠቅሞ ሳይሆን፣ ለራሱ በሚያመቸዉ መንገድ ብቻ የብሔረሰቦችን ችግር ፈትቻለሁ ባይ ነዉ። የነበረንን የአሐዳዊ የመንግሥትነት አወቃቀር አፍርሶ በሐዉርታዊ (ብሔር-በሐዉርት) ፌዴራል መንግሥት መሥርቼ፣ ሁሉም እራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር አድርጌያለሁ ይለናል። ይህ ብቻም አይደለም። ብሔረሰቦቻችን ልዩነታችን ዉበታችን እያሉ እየዘመሩ፣ በየዓመቱም የብሔረሰቦችና የሰንደቅ ዓላማ ቀን እያከበሩ እንዲፈነጥዙ በማድረግ አግኝተዉት የማያዉቁትን ድል እንዲጎናፀፉ በማብቃት ተወዳዳሪ የማይገኝልኝ ለብሔረስቦች እኩልነት የቆምኩ ብቸኛ መንግሥት እኔ ነኝ ባይ ነዉ፤ የእኔ መስታወት በሆነዉ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መስኮት ስመለከታቸዉና የግል ጥሩንባዬ በሆነዉ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጣቢያ ወደ ላይ፣ ወደ ላይ እየዘለዘሉ ልዩ ልዩ ኅብረ ቀለማት ባላቸዉ አልባሳት አሸብርቀዉና ደምቀዉ ስመለከታቸዉ፣ የቆምኩለት ዓላማ ምን ያህል ግቡን እንደመታ እርካታን ይሰጠኛል ባይ ነዉ፤ የሕዝብ ብሶት ወለደኝ የሚለዉ ጀግናዉ  ኢሕዲአግ። የአሃዳዊ መንግሥት  አለመኖር በመርኀ ደረጃ አያጣላንም። ፌዴራሉ የፌዝና የቧልት ፌዴራል መሆኑ ነዉ፣ የማያስማማን።

ከቀድሞዉ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ አሁንም ገና ዕልባት ያላገኘዉና አብሮ የመኖርና ያለመኖር ተግዳሮታችንም ይኽዉ የብሔር-ብሔረሰብ ፈታኝ ጥያቄ መሆኑ ለሁሉም ገሃድ ዕዉነት ነዉ። በደራሲዉ መፅሃፍ እንደተገጸዉ፣ አንድ አናሳ ቡድን በራሱ ስብስብ ሥም  የተቆጣጠረዉን ሥልጣንና የሃብት ምንጭ እንዳያጣ፤ ነባሩን ችግር ይበልጥ እንዲወሳሰብ አደረገዉ እንጅ፣ መፍትሄ አልሻተለትም። መፍትሄዉን አጥቶት አይደለም። ለችግሩ በትክክል መፍትሄ ከተገኘለት አናሳዉ ቡድን ቦታ የለዉም። ሥልጣን ከሌለ ደግሞ፣ በሃያ አራት ሰዓት የናጠጠ ሐብታም የሚያደርግ የሀገር ዘረፋ ሎተሪ የለም። ተመልሶ ወደ ጫካ የማይታሰብ ነዉ። የቃታ እጆች ለስልሰዋል። ጫንቃዎች አብጠዋል። ቦርጮች ወጥተዋል። በከተማዎች ብዙዉን ጊዘ የስኩኣር መጥፋት የሚያጋጥመዉ ገበሬዉ ስኩኣር መቃም ስለለመደ ነዉ፣ እየተባለ እንደሚፌዝበት፣ ተጋዳላዮቹ ዛሬ የቢራ ደንበኞች መሆናቸዉን ግን መካድ አስቸጋሪ ነዉ። ባጭሩ ብዙ ዳገት ሳንወጣና ሳንወርድ ፍላጎቶች ከመበርከት አልፈዉ  ቅጥ አጥተዋል ነዉ። ሥሜቶች ገደብ አልፈዋል። ኀሊና ተጋርዷል። ለሕዝቦች የተገባዉ የጫካዉ ቃል ኪዳን አዲስ አበባ ሲገቡ ፈርሷል። ለዲሞክራሲ ማበብ የተዘመረዉ መዝሙር የቁራ ጩኸት ሆኖ ቀርቷል። በብሶት አዋለደን ለሚሉት ሕዝብ መኖር ተረስቶ ለእራስና ለቤተስብ መኖር ተመርጧል።

ስለዚህ መፍትሔዉ፣ ሥልጣን ከእጅ እንዳያፈተልክ፣ ሕዝቡ አንድ ሆኖ ጣቶቹን ወደ እኛ እንዳይቀስር፣ እርስ በርሱ ማናከስ፤ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸዉ ዕሴቶችን ድኩማን በማድረግ፣ ብሔራዊ ሥሜቱን ማኮሰስ፣ ከመንደርና ከቀዬዉ አርቆ እንዳያስብ ማድረግ፣ አስተሳስብ አድማሱን በዘር ልጟም መሸበብ፣ እርስ በርሱ ሲባላም፣ እኛ የማታለል ሥራችንን ተቀባይነት ያለዉ በሚያስመስል መንገድ ማካሄድ፡ ለዚህ ደግሞ እኛን ገና ሳያስነጥሰን ይማራችሁ የሚሉ ካድሬዎችን በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጂያችን የአብዮታዊ ዲሞክራሲን ድጟ እንዲያስመሰክሩ  በማድረግ ለሥርዓቱ ዘብ በመቆም ሥልጣን ከእጅ አፈትልኮ እንዳይወጣ የሞት የሸረት ትግል ማካሄድ ለአንዳፍታም ቸል የማይባል ዓላማችን መሆን ይኖርበታል ይላሉ ኢሕዲጋዉያን። አካፋዉን አካፋ፤ ዶማዉን ዶማ ብለን ከተነጋገርን ግን እነሱ በሃገር ሃብት የኑሮን ጣዕም እያጣጣሙ ሲኖሩ፣ ድምፅ አልባዉና እነሱን አኗኗሪው ሕዝብ ግን (ከተሜዉም ገጠሬዉም) በድምፆቹ፣ በልሳኖቹ፣ ጆሮዎቹ በሆኑት የኪነጥበብ ሰዎች እንዴት ነዉ ብሶቱን የሚያሰማው ብለን እስኪ እራሳችንን እንጠይቅ? አለ ነገር፣ አለ ነገር፣ ዘንዶሮ አለ ነገር፤ አለ ነገር፣ ከርሞም አለ ነገር፤ መቼም ታመን፣ ታመን አንገት ደፍተን አንቀር። ይላል፤ ይህ የገጠሬዉ እንጉርጉሮም ሆነ፣ የከተሜዉ እሮሮ ዉስጠ ወይራም፤ ሠም ለበስ ቅኔም አይደለም። ምን ያህል ሕይወት እንደመረረዉና ወቅት ጠብቆ የሚፈነዳ ቦምብም በጉያዉ አቅፎ እንደሚኖር ጠቑሚ የሆነ ፅድቅ ቅኔ እንጅ።

ይቺ ቂም የቑጠረች አባባል ጊዜዋ ሲደርስ እንደ የካቲት 66ቱ፣ እንደ ግንቦቱ 83ቱ፣ ሌላ ብሶት የሚወልደዉ፣ ገና ሥሙ የማይታወቅ ሊመጣ ይችልና ተሰዳጁ አሰዳጅ፣ አሳሪዉ ታሳሪ፣ ፈራጁ ተፈራጅ፣ አዛዥ ናዛዡ ባላሥልጣን ከሰዉነት ወርዶ ምስኪን ዜጋ ሆኖ ሲንገዋለል የሚታይበትን ቀን ከማቃረብ፤ አስቀድሞ ቢታወቅበት ግን ሀገርንም እራስንም ማዳን አይቻልም ትላላችሁ? ያለጥርጥር ይቻላል ነዉ መልሱ። ግን ከፀሐዩ ንጉሣችንም፣ ከአብዮታዊዉ መሪያችንም ትምሕርት ማግኘት አልተፈለገም። የመፅሃፉን ርዕስና ደራሲ ለጊዜዉ በዘነጋሁት ግን ደግሞ ካነበብኩት የማስታዉሰዉ፤ ፕሬዚደንት ኮሎኔል መንግሥቱ ባንድ ወቅት የጦር አበጋዞቻቸዉን ይሰበስቡና ስለስሜኑ የሀገራችን ሁኔታ ዉይይት ያደርጋሉ። ከጦር አዝማቾቻዉ መካከል አንደኛዉ (ጄኔራል ታሪኩ ያይኔ ይመስሉኛል) ይነሱና ጟድ ፕሬዚዴንት፤ ችግራችን ሻቢያ ወይንም ጀብሃ አይደለም፣ የትግራዩ ነፃ አዉጪ ከተመታ እነኛን ይተዋቸዉ ብቻቸዉን የትም አይደርሱም፣ ዋናዎቹ ፍልፈሎች እነኘህ ናቸዉ ይሉና ሃሳባቸዉን ያቀርባሉ። ዘወር በል አንተ የምታዉቀዉ ጉዳይ የለህም ይባሉና ቀልባቸዉ ይገፈፋል። ብዙም ሳይቆይ ሁላችን በዓይናችን በብሌኑ ያየነዉን ዕዉነት በመናገራቸዉ ብቻ፤ ቀልባቸዉ ብቻም ሳይሆን፣ ዘግይቶም ማዕረጋቸዉም ጭምር ይገፈፍና የአብዮቱ ሠይፍ አርፎባቸዉ ይችን ዓለም ተሰናብተዋል።  እዉነት እንነጋገር ከተባለ፣ መቀሌን እስከተቆጣጠሩ ድረስ መንግሥት የእነሱን ሥም አንስቶና ዕዉቅና ስጥቶ ለመነጋገርና ብሔራዊ ዕርቅም ለማዉረድ ፍላጎቱም አልነበረም። ከዚህ ነጥብ ጋር የሚሄድ፣ እስኪ አንድ ስንኝ ከመዝሙረ ዳዊት ላቃምሳችሁ። ዕብን ዘመነንዋ ነደቅት ወይዕቲ ኮነት ዉስተ ርዕሰ ማእዘንት (የተናቀች ድንጋይ እርሷ የማዕዘን ጭንቅላት-ራስ ትሆናለች እንደ ማለት) ሆነና የተናቀችዋ የደደቢት ፅንስ ለዚህ በቅታ፤ የደርግን መንግሥት በዚህ መንገድ ተሰናብተን አሁን እምንገኝበት ደረጃ ደርሰናል። አሁን ጥያቄዉ በደርግ መቃብር ላይ ሥልጣኑ ያበበዉ ኢሕአዲግ ለሕዝብ የገባዉን ቃል ፈፅሟል ወይ? የሚፈለገዉ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትስ በሀገራችን ሰፍኗል ወይ? ያለጠብ መንጃ አስገዳጅነት በሕዝብ ይሁንታ የተመረጠ መንግሥትስ አለን ወይ? እነዚህ ሁሉ የሚገዙብት፤ በሕዝብ ይሁንታ የረቀቀና የፀደቀ ሕገ መንግሥት አለን ወይ? በእነዚህ መሠረታዊ ጥያቄዎች አለመመለስ ልቡ ለሸፈተ ሕዝብና ፋኖ ተሠማራ ላለ ቡድን፣ የማስተናገጃ መልሱ አሁንም እንደ ትናንቱ እኛ በመጣንበት ኑና ሞክሩን ነዉ ሽለላው? ወይንስ……..? እስከ መቼስ ነዉ ወንድም ወንድሙን እየገደለ ጀግና የምንባባልበትን አሳፋሪ ብቻም ሳይሆን አንገት አስደፊ የሆነዉን፣ የታሪክ ምዕራፍ ለአንዴዬና ለመጨረሻ ጊዜ የምንዘጋዉ?

ለመሆኑ የአሰባሳቢ ማንነት፣ ባንድ ሀገር ልጅነት-የኢትዮጵያ ፋንታ ደራሲ ምን የሚለን አለ? ልዩነታችን ዉበታችን ነዉ ለማለት የምንደፍረዉ ወይም የደራሲዉን አገላለፅ ልዋስና …ከአብዛኄነታችን ጋር መኗኗር ችለናል ማለት የምንደፍረዉ፤ ስለመንግሥት አስተዳደር፤ የሥርዓቱ ባሕርይና ምንነት ዙሪያና ሳቢያ የተለያዩ ዕይታ አመለካከቶች መኖራቸዉንና ጉራማይሌነታቸዉን በተግባር ተቀብለን ማስተናገድ መቻላቸዉን ማረጋገጥ ስንችል ብቻ ነዉ። ለሁሉም በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ቀዳሚዉ ብሔራዊ መግባባት ነዉ። ከሁሉም በፊት አንዱ ከሌላዉ ጋር የሚኖረዉ መስተጋብር፣ ግንኙነት፤ ተዛምዶ ነዉና ወሳኙ መቀሰም ያለበት ትምህርት ቢኖር፣ የዚህን ዓላማ ተግባር አስፈላጊነትንና ቀዳሚነትን መገንዘቡ ላይ ነዉ ቅድሚያ የምንሰጠዉም።…. ከብሔረተኛ መፈክርነት ባሻገርና በመለስ፣ ኢትዮጵያዊነት እንደ አንድ ሐገራዊ የኢድዮሎጂ ትክክለኛዉ ይዘቱ መፈታት አለበት ነዉ በሌላ መልኩ። ማለትም ከሌሎች ከእሱ ጋር ከሚፎካከሩ ኢድዮሎጂዎች አሸንፎ ወይንም የእሱን ተፃራሪዎች በአመክንዮ አምክኖ፣ አሰባሳቢ የበላይነቱን ማረጋገጥ ካልቻለ፣ ኢትዮጵያዊነት እንደ ኢድዮሎጂ የትሕተ ሀገራዊ ማንንትን ካባ ከደረቡ ቅርንጫፍ ማንነትቾች ጋር ግብግቡን ሳያሸንፍ ይቀርና ይሽመደምዳል። ይህ ግን አይታሰቤ ነዉ።…. በሀገሪቷ የዲሞክራሲ ልደት ወይም የመበታተን ዋዜማ ላይ ቆመን፣ ማንም ይግዛ ማን ገዢዉ አካል የዜጎቹ መብት ሳይገሰሥ፣ በተፍጥሮ የተጎናፀፉት ሰብዓዊ መብታችዉ ሳይገፈፍ፣ ሕገ መንግሥታቸዉን በራሳቸዉ ወኪሎች አርቅቀዉና አፀድቀዉ፤ ባጭሩ ሌሎችን የማኗኗር ሕይወት የሚገፉባት ሳትሆን፤ እነርሱ እራሳቸዉም የሕይወትን ጣዕም የሚቀምሱባት ሀገር ኢትዮጵያዊነት አሰባሳቢ ማንነት አሸንፎ እንዲወጣ፤ እንዚህን ሁሉ ተግባራት በዋስትናነት የሚመክቱ ተቑማትን በማረጋገጥ፣በተደላደሉ መሠረቶች ላይ የቆመ ብሔራዊ አንድነትን መፍጠር ይኖርብናል ነዉ የመልዕክቱ አስኹል። ደራሲዉ በመጨረሻም የመፅሃፉን ዋንኛ የመዳረሻ ግብ ሲያጠቃልለዉ፣ ለዜግነታዊ መንግሥት መሠረት የመጣል ክንዉን የሩቅ ተግባር እንጅ፣ ባንድ ጀንበር የሚከናወን የይድረስ፣ የይድረስ ተግባር አለመሆኑን አፅንኦት ይሰጠዋል። …. አሰባሳቢ የሆነ ሀገራዊ ማንነት ለመቅረፅ የምናደርገዉ ረዥም ጉዞም በሀገራችን  ከምንመኘው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ጋር ተዳብሎ የሚታይ ብቻ ሳይሆን፤ በዋንኛነት ነጥሮ መዉጣት ያለበት ብሔራዊ አጀንዳችን መሆኑንም ያሠምርበታል። ይህንን ሀገራዊ ራዕይም ወደ ተግባር ለመመንዘር፤

በሥልጣን ላይ ያለዉን መንግሥት ማስገደድ፣ ካልሆነም ማስወገድ፣

የብዙዎች ስምምነት የታከለበት ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ፤

የሸግግር ጊዜ ተግባራትን በመግባባት መንደፍ፤

እነኝህ ቅድመ ሁኔታዎችም ለምንፈልገዉ የለዉጥ እንቅስቃሴ ወሳኞች በመሆናቸዉ፤ ስለሌላዉ ማዉራቱን አቆመን እርስ በራሳችን ስለወደፊቱ መነጋገር ማስፈለጉን አስረግጧል፤ ዜጋዉ እርስ በርሱ ሳይተማመን ኢትዮጵያዊነት አይሰበክም ይላል። ከዚሁ ጋር አያይዞም፣ በአካል ስንነጋገር፣ የብዙ ዓመት ጟደኛቸዉ በመፅሃፉ ጀርባ ባስመዘገቡት መወድስ፣ < የልቡን እንደ ልቡ፣ ለነገ ሳይል የሚናገረዉ ጟደኛዬ> የሚለዉን የዶክተር ደረጀ ዓለማዬሁን አባባል ጋሼ የሱፍ ሲያጫዉተኝ  ከዚህ ይልቅ <ለነገ ብሎ የልቡን እንደ ልቡ የሚናገረዉ ቢባል እኔን በሚገባ ይገልፀኛል። ይህንንም የምለዉ ዝምብዬ ከምድር በመነሳት ሳይሆን፣ የወደፊቱ የአብሮነታችን ጉዳይ፣ ወይም የነገዉ ዕጣ ፋንታችን ስለሚያሳስበኝ ነዉ ይላል። በቅርቡም ዋሸንግተን ላይ በተካሄደ ሕዝባዊ ስብሰባ የአማርኛው ቃና የሚጥመዉ የጊዜያችን ጥቁሩ ሰዉ የአኝዋኩ  ኢትዮጵያዊ ኦባንግ ሜቶ ስለነገዉ ካሰብን፣ ለመተማመን እንነጋገር በማለት እንደደገመዉ፣ ድሉን እንድናቃርብና ኢትዮጵያዊነት አሰባሳቢ ማንነት እንዲያብብ፣ እንዲፈካና  በአሸናፊነትም ተመንጥቆ እንዲወጣ ማድረግ አለብን ባይ ነዉ ጋሼ ዩሱፍ። እኔ በማንነት ፍለጋዉ ጉዟችን የአፋሩን ቅኔ፣ ቅኝት በተገለጸዉ መልክ  ተረድቼዋለሁ። እናንተስ? ለማንኛዉም ገና መፅሃፉን አግኘታችሁ ላላነበባችሁ መልካም ንባብ።

Comment

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የስቃይ ድምጾች በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ

$
0
0

addis ababa semayawi party 1
በላይ ማናዬ

ካዛንቺስ በተለምዶ እንደራሴ በተባለው ቦታ ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ረፋድ ላይ የሆነው እንዲህ ነው….

በቅርቡ በሰማያዊ ፓርቲ እና በሌሎች 8 ፓርቲዎች ስምምነት የተመሰረተው የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የትግል መርሃ-ግብር ማሳረጊያ ሊደረግ በነበረው የ24 ሰዓት የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ ያሉ ሁኔታዎችን ለመዘገብ የሰልፉ መነሻ በሆነው የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሰልፉ ይጀምርበታል ከተባለው ጊዜ መዘግየቱን አስመልክቶ ከቢሮ ወጣ ብዬ ሁኔታውን ለመቃኘት እየሞከርኩ ነበር፡፡ ድባቡ ፍጹም ዝብርቅርቁ የወጣ ነበር፡፡ ሰልፍ ለመውጣት የወሰኑት ሰዎች በቢሮው ውስጥ መሰናዷቸውን እያደረጉ በነበረበት ሰዓት ከቢሮ ውጭ ያሉ ፖሊሶችና ሲቪል የለበሱ የደህንነት ኃይሎች ደግሞ ቁጥራቸው በየደቂቃው እየጨመረ አካባቢውን መክበብ ተያይዘውት ነበር፡፡

ሁኔታውን በአንክሮ ለተመለከተው በደቂቃዎች ውስጥ ‹ፍጥጫ› ሊጀመር እንደሚችል አመላካች ነበር፡፡ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የእውቅና ደብዳቤ ለአስተዳደሩ አስገብቻለሁ፣ ስለሆነም ሰልፉን ለማድረግ ወስኛለሁ ሲል መንግስት በበኩሉ ሰልፉን ‹ፈቃድ አልሰጠሁትም› ሲል አስታውቆ ነበር፡፡ ዳሩ ግን ትብብሩ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ‹ማሳወቅ› እንጂ ‹ማስፈቀድ› አይጠበቅብኝም ሲል አዋጅ ጠቅሶ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ አስገብቶ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

በዚህ አለመግባባት ውስጥ ተሁኖ ነበር የአዳር ሰልፉ ሊካሄድ ሽርጉድ ይባል የነበረው፡፡ በእንዲህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ሰልፉ ከሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ውስጥ ተጀመረ፡፡ የሰልፉ አጀማመር በራሱ የሚገርሙ ነገሮች ነበሩት፡፡ ባላሰብኩት ፍጥነት ቢሮ ውስጥ የነበሩት ሰዎች በአንዴ ሰብሰብ ብለው ቀጥታ ከበር እንደወጡ መፈክሮችን እያሰሙ በፈጣን እርምጃ ወደፊት ተስፈነጠሩ፡፡ እርምጃየን በእነሱው ፍጥነት ልክ አስተካክየ መቅረጸ-ድምጼን አበራኋት፡፡ ‹‹ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት!….›› እያሉ መፈክሩን አስተጋቡት፡፡

ፖሊሶች በሰልፈኞች ፍጥነት ግር የተሰኙ መሰሉ፡፡ ሰልፈኞቹ በጣም ብዙ ፖሊሶች በተሰደሩበት መንገድ ፊት ለፊት ቀጥታ ገሰገሱ፡፡ ይህኔ ፖሊሶች እርምጃ ለመውሰድ ተቁነጠነጡ፡፡ ሰልፈኞች መፈክራቸውን ለወጡ፤ ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው! ፖሊስ የህዝብ ነው! ፖሊስ የህዝብ ነው!›› እያሉ ለፖሊሶች መልዕክት ለማስተላለፍ ሞከሩ፡፡ ይህኔ ሁኔታዎች ከመቅጽበት ተለዋወጡ፡፡ እዛ የነበረው የ‹ፀጥታ ሰራተኛ› በሙሉ እንደንብ ሰልፈኞች ላይ ሰፈረ፡፡ እንደደነበረ ፈረስ ያገኙትን መርገጥ ጀመሩ፡፡ በሰልፈኞች ላይ የሆነው ሁሉ በእኔም ላይ ሆነ፡፡ የመጀመሪያው ዱላ ካረፈብኝ በኋላ ያለውን የዱላ ብዛት አሁን አላስታውስም፡፡ ብቻ ዘግናኝ ነበር!

በእርግጠኝነት በሂደቱ ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ አንዳንድ ደስ የማይሉ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ቀድሜ ብገምትም፣ የሆነው ግን ከግምቴም በላይ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ነበር፡፡ ሴቶች እና እድሜያቸው ከ70 በላይ የሆኑ አዛውንቶች ርህራሄ አልተደረገላቸውም፡፡ እንዲያውም በእነሱ ላይ ሳይበረታ አልቀረም፡፡ ያ ሁሉ ፖሊስና ‹ሌሎች የፀጥታ ሰራተኞች› እንደአሸን የፈሉ ነበሩ፡፡ አንድም ዱላ ሳይሰነዝሩ ሰልፉን ማገት በተቻላቸውም ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ትዕዛዝ ይመስላል፤ ዜጎችን ደብድብ የሚል ትዕዛዝ! ያሳፍራል፣ ያሸማቅቃል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አቧራ ላይ ተጥለው ተደበደቡ፡፡ ሴቶች ሆዳቸውን ተረገጡ፡፡ አዛውንቶች ዘለፋ ከተሞላበት ኃይለ-ቃል ጋር ድብደባ ተፈጸመባቸው፡፡ ጋዜጠኛ ሰልፍ ላይ ተገኝተህ መዘገብ አትችልም ተብሎ ተቀጠቀጠ፡፡ አቶ ኤርጫፎ ኤርደሎ እና አቶ ቀኖ አባጆቭር (አባዬ) ተይዘው ከእኛው ጋር ሲንገላቱ ሳይ በእኔ ላይ የደረሰውን ሁሉ ረሳሁት፡፡ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው በሚሆኑ ‹የጸጥታ ሰራተኞች› የአሳፋሪው እርምጃ ሰለባዎች ሆኑ፡፡ በእርግጥ እነ አባዬ ስለእኛ እንጂ ስለራሳቸው አልተሰማቸውም፡፡ እኛ ደግሞ በእነሱ ላይ ስለሆነም የበለጠ እናዝን ነበር፡፡

ይህ ሁሉ ድርጊት በካዛንቺስ እንደራሴ አካባቢ ከመሆኑ ከደቂቃዎች በፊት ብዙ ዜጎች በመስቀል አደባባይ እና በሌሎች ስፍራዎች እየተያዙ እንደነበር አውቃለሁ፡፡ መንግስት የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ ዜጎችን ለማፈን ቆርጦ እንደተነሳ ተገነዘብኩ፡፡ በዕለቱ የሆነው ተራ እስር አልነበረም፤ አፈሳ ነበር የተደረገው፡፡ ጅምላ እስር ነበር የተፈጸመው፡፡ ካዛንቺስ እንደራሴ አካባቢ የሆነው ግን በኃይልና በድብደባ የታጀበ ነበር፡፡ በድብደባ እራሱን ስቶ የቆየው ወጣት አቤል ኤፍሬምን ጨምሮ ብዙዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን በመኪና እንደእቃ እንድንጫን ተደርገን ካዛንቺስ አካበቢ ወደሚገኘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተጋዝን፡፡ ጣቢያ እንደደረስን በአንድ ቦታ እንድንሰበሰብ ተደርገን በፎቶ እና ቪዲዮ ካሜራ ቀረጻ ተደረገብን፡፡ የሚገርመው ራሱን ስቶ ወድቆ የነበረው አቤል ሳይቀር በዚያ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ህክምና ሳያገኝ ቀረጻው ይደረግበት ነበር፡፡ ግራ ቀኜን ዞር ዞር ብዬ የተያዙ ሰዎችን አስተዋልኩ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃልን ጨምሮ የተለያዩ የፓርቲ አመራሮች ተይዘዋል፡፡ አንዳንድ በዚያ ሲያልፉ የተገኙ፣ ስለጉዳዩ ምንም የማያውቁ ሰዎችም አብረው ተጀምለው ተይዘዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል በሁኔታው ተደናግጠው የሚያለቅሱ ሰዎች ይገኙበት ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ሰልፍ ይሁን ሌላ የሚያውቁት ጉዳይ አልነበረም፡፡ እንዲሁ በቦታው ስለተገኙ ብቻ የተያዙ ነበሩ፡፡

ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እያለን ከመስቀል አደባባይ የተያዙ ሰዎችም በጣቢያው እንደሚገኙ ተገነዘብኩ፡፡ በጣም ብዙ ፖሊሶች ግቢውን ሞልተውታል፡፡ ብዙዎች ሰልፈኞችን ይሳደባሉ፤ አንዳንዶች አሁንም ለመደባደብ ሲቋምጡ አስተዋልኩ፡፡ ገረመኝ! ከመደብደብ የሚገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ቀደም ብሎ በተያዝንበት ቦታ ላይ ብዙ ከተደበደብን በኋላም ቢሆን ድብደባው እንዲቆም ትዕዛዝ የሰጡት የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዘውዴን በዓይኔ ፈለኳቸው፡፡ ግን ላገኛቸው አልቻልኩም፤ የእውነት ከድብደባው የሚገኘውን ትርፍ ማወቅ እፈልግ ነበር፡፡ ፍርሃቴ ልበለው አልያ ድንጋጤዬ ብን ብሎ ጠፍቶ ስለነበር ማናቸውንም አይነት ጥያቄ ልጠይቃቸው እፈልግ ነበር፡፡ የእውነት በወገኖቼ መካከል መገኘቴን እንኳ እጠራጠር ነበር፡፡ እንዴት ሰው አንዲት ጠጠር እንኳ በእጁ ሳይዝ፣ በሰላም ድምጹን ስላሰማ ብቻ ይህን ያህል ድብደባ በራሱ ወገኖች፣ በመንግስት ኃይሎች ይደርስበታል?

ስድስተኛ ብዙም አልቆየንም፤ የቪዲዮ እና የፎቶ ቀረጻው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ወደሌላ ፖሊስ ጣቢያ እንድንዛወር ተደረግን፡፡ የደረስንበት ፖሊስ ጣቢያ ፖፖላሬ ፖሊስ ጣቢያ ነበር፡፡ በዚህ ፖሊስ ጣቢያ ደርሰን ትንሽ ጊዜ እንደቆየን ቃላችንን እንድንሰጥ ተደረግን፤ ድጋሜ ፎቶ እንድንነሳ ሆነ፣ አሻራም ተነሳን፡፡ ይህን አድርገው ወደተለያዩ ክፍሎች ካጨቁን በኋላ ምሽት ላይ እንድንወጣ ታዘዝን፡፡ በዚህ ጊዜ በታሳሪዎች መካከል የተለያዩ አስተያየቶች ይሰጡ ጀመር፡፡ አንዳንዱ ልንፈታ ነው ሲል ሌላው ደግሞ ወደ ካምፕ ሊወስዱን ነው ይል ነበር፡፡ ቀሪዎች ደግሞ ወደሦስተኛ ፖሊስ ልንወሰድ እንደሆነ ግምታቸውን ሰነዘሩ፡፡ እነዚህኛዎቹ ልክ ነበሩ፡፡ ጉዙው ወደ ሦስተኛ ነበር፡፡ በፖለስ መኪና እና ሞተር ሳይክል ታጅበን፣ የሳይረን ድምጽ በሚያሰማ ሞተረኛ መሪነት ሦስተኛ ፖሊስ (የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት) ተወሰድን፡፡

ወደሦስተኛ ፖሊስ እንድንዛወር የተደረግነው ታሳሪዎች ከመስቀል አደባባይ የተያዙትን አይጨምርም፤ ቁጥራችንም 44 ነበርን፡፡ ሌሎቹ እስከተፈቱበት ዕለት ድረስ እዚያው ፖፖላሬ ጣቢያ ቆይተዋል፡፡ ሦስተኛ ፖሊስ እንደደረስን በሁለት እንድንከፈል ግድ ሆነ፡፡ በአመራር ደረጃ ላይ ያሉት ወደቀዝቃዛ ክፍል (በረዶ ቤት) እንዲገቡ ሲደረጉ፣ ሌሎቹ ደግሞ በተለያዩ ክፍሎች (ጨለማ ክፍልን ጨምሮ) እንድንገባ ተደረግን፡፡ በዚያው በህዳር 27/2007 ዓ.ም ዕለት የሦስተኛ ፖሊስ ቆይታችን አሃዱ ተባለ፡፡ (በነገራችን ላይ አብዛኞቻችን ታሳሪዎች ለ24 ሰዓታት ያህል ምግብና ውሃ በአፋችን አልዞረም ነበር፡፡)

የስቃይ ድምጾች በሦስተኛ ፖሊስ

ሦስተኛ ፖሊስ አሁን ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት የሚገኝበት ስፍራ ነው፡፡ ቦታው ድሮ በሚታወቅበት ገጽታው ሳይሆን በቅርቡ በተገነባው ዘመናዊ ህንጻው ተጀቡኖ በግርማ ሞገስ የሚታይ ነው፡፡ ይህ ቦታ በፌደራል ፖሊስ የማዕከላዊ ምርመራ ጣቢያን ተጎራብቶ የሚገኝ ነው፤ (አንዳንዶች ከማዕከላዊ ጋር በምድር ዋሻ ይገናኛል ይላሉ፤ ይህን በተመለከተ እንደ ቀልድ ከእስር በወጣንበት ቀጣይ ቀን ሞባይል ስልኬን ልወስድ ወደጣቢያው ባመራሁበት ወቅት ለመርማሪዬ ፖሊስ በቀልድ መልኩ ጥያቄ አንስቼለት ነበር፡፡ መርማሪው ‹‹ማዕከላዊ እና እኛ አንገናኝም!›› ነበር ያለኝ በጥያቄየ ግር በመሰኘት አተያይ እያየኝ)፡፡ ሦስተኛ ፖሊስ በህንጻው ዘመናዊ ይሁን እንጂ በአሰራር ግን ብዙ ገራሚና አሰቃቂ ድርጊቶችን የሚያስተናግድ ቦታ መሆኑን በቆይታየ ለመታዘብ ችያለሁ፡፡

ወደ ጉዳዬ ስመለስ፣ ሦስተኛ የገባን ዕለት (ህዳር 27) በሌሊት ምርመራ ሲደረግብን ነበር ያደርነው፡፡ በፖፖላሬ ፖሊስ ጣቢያ የሰጠነውን ቃል በመድገም ሙሉ ማንነታችን ከመዘገቡ በኋላ ሌሎች ምርመራዎችም ተደረጉምብን፡፡ በምርመራው ወቅት ከሞላ ጎደል ድብደባ አልደረሰብንም፡፡ ምናልባትም በተያዙበት ወቅት የተደበደቡት ይበቃቸዋል ተብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ በቀጣዩ ቀን ሁላችንም ፍርድ ቤት እንድንቀርብ የተደረግን ሲሆን ፖሊስ ፍርድ ቤቱን 14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠየቀ፤ የትብብሩ አመራሮች በበኩላቸው በሰልፈኞቹ በኩል የተፈጸመ አንዳችም ህገ-ወጥ ተግባር አለመኖሩን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ በነጻ እንዲያሰናብተን ጠየቁ፡፡ በተለይ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ኢህአዴግ በዘንድሮው ምርጫ ሙሉ ለሙሉ እንደምናሸንፈው ስላወቀ ነው ያሰረን፤ ይህም ህገ-መንግስቱን የጣሰ ነው›› ሲሉ አስረድተው ነበር፡፡

በዚሁ ፍርድ ቤት በቀረብን ጊዜ ብዙ አስገራሚ ነገሮችን ታዝቤያለሁ፡፡ በተለይ በታሳሪዎች በኩል የደረሰባቸውን ድብደባ ተከትሎ ህክምና አለማግኘታቸውን፣ እንዲሁም አመራሮቹ በበረዶ ቤት ስለሚገኙ ለጤናቸው አስጊ ስለሆነ የተሻለ አያያዝና ህክምና እንዲደረግላቸው ለፍርድ ቤቱ ባስረዱ ጊዜ የዕለቷ ዳኛ ያሉትን አልረሳም፤ ወደ ፖሊሶች ዞር ብላ ‹‹የጠየቁትን ህክምና እንዲያገኙ አድርጉ፣ ለእናንተም ለመቅጣት እንድትችሉ በህይወት ይቆዩላችሁ›› ነበር ያለችው፡፡ ጆሮዎቼን ማመን ነበር ያቃተኝ! ሁኔታው ሰው ቅጣት እንዲቀበል ብቻ ነው በህይወት መቆየት ያለበት ማለት ነው ብዬ ራሴን እንድጠይቅ አድርጎኛል፡፡

ፍርድ ቤት የነበረን ቆይታ አብቅቶ ወደ ሦስተኛ ተመለስን፡፡ ምርመራውም ቀጠለ፡፡ በምርመራ ወቅት ተመሳሳይና አሰልቺ ጥያቄዎች ነበር በተደጋጋሚ የሚቀርቡልን፡፡ በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ መርማሪዎቹ የኢሜልና ፌስ ቡክ አካውንት እስከ ይለፍ ቃል (password) ድረስ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ነበር፡፡

ኢሜልና ፌስቡክ ይኖረኝ እንደሆን ጠየቀኝ፡፡ እንዳለኝ ነገርኩት፡፡ አስከትሎ አካውንቱንና ፓስወርዱን እንድነግረው ጠየቀኝ፡፡ ‹እንዴት ይሆናል፣ ይሄኮ የግል ጉዳይ ነው፤ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዴት ስጠኝ ትላለህ?› ስል መልሼ ጠየቅኩት፡፡ ፈቃደኛ ባለመሆኔ አንዴ በንዴት ሌላ ጊዜ በማባበል አይነት የጠየቀውን እንድነግረው ሞከረ፡፡ በአቋሜ መጽናቴን ሲያይ፣ ‹‹ይሄኮ የመንግስት አሰራር ስለሆነ ነው፤ ባትናገርም እኮ መንግስት ያውቀዋል›› አለኝ፡፡ አልመለስኩለትም፡፡ እሱም ‹‹ኢሜልና ፌስቡክ አካውንት አለው፣ ግን ለመናገር ፈቃደኛ አይደለም›› ብሎ የምርመራ መዝገቡ ላይ ሲያሰፍር አነበብኩ፡፡

ከምርመራ ክፍል ወጥቼ ሌሎች ታሳሪዎች ጋር ስንገናኝ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን እንዳስተናገዱ ነገሩኝ፡፡ ለመሆኑ ይሄ ምን አይነት የመንግስት አሰራር ይሆን?

የሦስተኛ የስድስት ቀናት ቆይታዬ ለእኔ ብዙ ነገሮችን እንድቃኝ ያስቻለኝ ስለነበር መታሰሬን በግድም ቢሆን ሳልወደው አልቀረሁም፡፡ ምናልባት ባልታሰር ኖሮ እኒያን ሁሉ ባለብዙ ታሪክ እስረኞች አላውቃቸውም ይሆናል፡፡ በታዳጊ ሃና ላላንጎ አስገድዶ መደፈር ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙት አምስት ተጠርጣሪዎች እስከ በነፍስ ግድያና ሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው እስከገቡት ወንድሞች ጋር ብዙ ታሪኮችን አደመጥኩ፡፡ በምርመራ ወቅት የደረሰባቸውን እና እየደረሰባቸው ያለውን ሰቆቃም ለመገንዘብ ቻልኩ፡፡

ሦስተኛ ፖሊስ በዘመናዊ ህንጻ ውስጥ ኋላቀር የምርመራ ዘዴ የሚተገበርበት ስፍራ መሆኑንም ከብዙ ሰዎች ላይ በደረሰው በደል አየሁ፡፡ በምርመራ ወቅት በተፈጸመባቸው ድብደባና ሌሎች የማሰቃያ ዘዴዎች ምክንያት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እዛ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በረዶ ቤት (የትብብሩ አመራሮች ታስረውበት የነበረው ቤት) አንዱ የምርመራ ወቅት ማቆያ አሰቃቂ ስፍራ ነው፡፡ ሌላው ‹ቆመህ እደር› የሚባል ሲሆን ተጠርጣሪዎች ለቀናት በዚህ ስፍራ ቆመው ውለው ቆመው እንዲያድሩ የሚደረግበት እንደሆነ በዚህ ሁኔታ ላይ ያለፉ ታሳሪዎች አጫውተውኛል፡፡ ብዙዎች በ‹ቆመህ እደር› ያለፉ ሰዎች የተለያዩ የአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ሰለባ ይሆናሉ፡፡

እውነትም በሦስተኛ ፖሊስ ያለው የምርመራ ስልት እጅግ ኋላቀር ብቻ ሳይሆን ኢ-ህገ-መንግስታዊም ጭምር ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ተጠርጣሪዎች ሰውነታቸው በስፒል ይጠቀጠቃል፣ ትልቅ ሃይላንድ ውሃ ተሞልቶ ብልታቸው ላይ ይንጠለጠላል፣ እግራቸውን ከፍተው ቆመው እንዲያድሩ ይደረጋል፣ ከፍተኛ ድብደባ ይፈጸማል፣ ከብዙዎቹ እስረኞች አፍ እንደሰማሁትና በአካላቸው ላይ የደረሰውን ጉዳት በዓይኔ እንዳየሁት፡፡ በዚህ አይነት ምርመራ የሚያልፉ ሰዎች ምርመራቸው እስኪያልቅ (ለሳምንታት) ከቤተሰብ ጋር መገናኘት አይፈቀድላቸውም፡፡ በነገራችን ላይ በሰልፉ ወቅት የተያዝን እና በሦስተኛ የነበርን ወንድ እስረኞች በሙሉ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እንድንገናኝ አይፈቀድልንም ነበር፡፡

በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ባለው ከባድ የማሰቃየት የምርመራ ዘዴ የተሰቃዩ ተጠርጣሪዎች አንዳንዶቹ ራሳቸውንም ለማጥፋት ሙከራ አድርገው ያልተሳካላቸውን አግኝቼ አናግሬያቸው ነበር፡፡ አንድ ተጠርጣሪ ራሱን ለማጥፋት የገፋፋውን ምክንያት እንዲህ ሲል አስረዳኝ፣

‹‹ምርመራው እጅግ ኢሰብዓዊ ነው፡፡ ራስህን ትጠላለህ፡፡ በቃ በግድ እመን ነው የሚሉት፡፡ ወንጀሉን ሳትፈጽም እዚህ ተጠርጥረህ ብትገባ በግድ ወንጀለኛ ነኝ በል ትባላለህ፡፡ ድብደባው ፋታ የለውም፡፡ በየዕለቱ ማታ ማታ እየወሰዱ ሶስተኛ ፎቅ ላይ ይቀጠቅጡሃል፡፡ ሰው አትመስላቸውም፡፡ በሀሰት የጠየቁህን አንድ ወንጀል ብታምንላቸው ሌላ ወንጀል ፈጥረው እመን ይሉሃል፡፡ በቃ መዝገቡ ክፍት ነው፤ አንተን ይጠብቃል እመን ይሉሃል፡፡ ከነገ ዛሬ ማሰቃየቱ ያበቃል ስትል ማብቂያ የለውም፡፡ ስለሆነም ከዚህ ሁሉ ስቃይ ለምን አልገላገልም ብለህ ታስባለህ፡፡ በዚህ ጊዜ ትዝ የሚልህ ደግሞ ራስን ማጥፋት ነው፡፡››

ይህ የብዙ ሰዎች አንደበት የተናገረው እውነታ ነው፡፡ ድርጊቱ በህግ ያልተፈቀደ ቢሆንም ምርመራው ግን በዚህ መልኩ እንደሚከናወን ብዙዎች አስረዱኝ፡፡ የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 19 (5) ስለተያዙ ሰዎች እንዲህ ይላል፣ ‹‹የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የእምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም፡፡ በማስገደድ የተገኘ ማስረጃም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡››

ሌላ ተጠርጣሪ በምርመራ ወቅት ያጋጠመውን ገጠመኝ የግዱን እየሳቀ አወጋኝ፡፡ ‹‹ለምርመራ በገባሁበት ክፍል ውስጥ መርማሪዎቼ በዱላ ተቀበሉኝ፡፡ ከጥያቄ በፊት ዱላ ይቀድማቸዋል፡፡ ደብድበው ደብድበው ሲደክማቸው እኔን እግሬን ከፍቼ እንድቆም በማዘዝ እነሱ ኮምፒተር ላይ ፊልም እያዩ መዝናናት ጀመሩ፡፡ ከሰዓታት በኋላ ሽንት ቤት እንዲወስዱኝ ለመንኳቸው፡፡ ተሳለቁብኝ፡፡ እየቆየሁ እየቆየሁ ስሄድ ሽንቴን መቆጣጠር እንዳልቻልኩ በመግለጽ ‹ስለወንድ ልጅ አምላክ› ስል በድጋሜ ተማጸንኳቸው፡፡ ሊሰሙኝ አልቻሉም፡፡ ከዚያ ‹በቃ እዚሁ እሸናለሁ› ብዬ ሽንቴን ለቀቅኩት፡፡ በጣም ታፍኜ ስለነበር ሽንቴ እጅግ መጥፎ ጠረን ፈጠረ፡፡ ይገርምሃል ለእኔ ሳይሆን ለቢሯቸው አዝነው እንደውሻ አባርረው ከቢሮ አስወጡኝ፡፡››

ለመሆኑ እነዚህን የስቃይ ድምጾች ሰሚያቸው ማን ይሆን?

የኢትዮጵያን ዲሞክራሲ ለመዉለድ ስንት ዘመን ይፈጃል? (ከ ቶፋ ቆርቾ)

$
0
0

ከ ቶፋ ቆርቾ

የምርጫ ወግ

electionምርጫ ደርሷል አይደል? ለዛ መሆን አለበት በአንድ በኩል EBC ‘ምርጫ ቦርድ ለምርጫ አስፈፃሚዎች ስልጠና ሰጠ … ኮሮጆ አሰራጨ’… ሌሎች መገናኛ ብዙሃን ደግሞ ‘ምናምን የሚባል ፓርቲ ሰልፍ ጠራ’ … ‘የነእከሌ ፓርቲ ትየንተ ህዝብ በፖሊስ ሃይል በሃል ተበተነ’ ….. ዱዱዱዳ…እንዲያም እንዲህም የሚሉ ወሬዎች መስማት ከመሰንበቻዉ የተለመደ ሆኗል፡፡

እኛ ሃገር ስለምርጫ አምስት ዓመት እየጠበቁ ማዉራት የተለመደ ተከታታይ ድራማ (series TV show) ይመስላል… የመጪዉ ግንቦት አምተኛዉ ምእራፍ (Season 5) መሆኑ ነዉ ማለት ነዉ? ቂቂቂቂ….! እኔ የምለዉ ግን ለይመሰል ብቻ ምርጫ ማድረግ ምን ይጠቅማል? መጨረሻዉን ቀድመዉ ያወቁትን ፊልም ማየት ወይ ‘ልብ አንጠልጣይ’ የተባለ ልብ ወለድ መፃፍ ማንበብ ጊዜ ማሳለፊያ አልያም የደራሲዉን ችሎታ ለመገምገም ካለሆነ በቀር ምኑ ይነሽጣል? እሺ አንድ ሁለቴ እያወቁ መሸወድ ያለ ነዉና ምን አይደል እንበል…. አመስቴ ስሆንስ? አራዶቹ  ቢሰሙ ‘አይከይፈፍም’ ይሉናል ከምር ኩሸት ይሆናል! ልጆች ሆነን ‘ክስክስ’ የምንለዉ አይነት አክሽን ፊልም ስናይ ‘አክተሩ’ አይሞትም ምናመን ብለንና አምነን አሳምነን ፊል ማየት እንጀምራለን እዉነትም ፊልሙ ሲገባደድ አክተሩ ጠላቶቹን ያሸንፋል በቃ አይሞትም…. የኛም ሃገር ምርጫም ልክ እንደዛዉ ነዉ….. መሪ ተዋናዩ የማይሸነፍበት አክሽን ፊልም! ልየነቱ በሚሊዮነች የሚቆጠሩ መሪ እና አጃቢ ተዋንያን የሚሳተፉበት መሆኑና ለወራት የሚወራለት መሆኑ ብቻ ነዉ! የሆነዉ ሆኖ አሸናፊዉና አጃቢዎቹ ቀድሞ ዉጤቱ የታወቀበትን ምርጫ የሚባል ድራማ መሰል ነገር ማካሄድ ለምን አስፈለጋቸዉ? ቃለ ተዉኔቱን… ዝግጅቱን… ቀረፃዉን…. ዳኝነቱን አንድ አካል ብቻዉን በተቆጣጠረበት ቲያትር ዉስጥ መግባት የሚያስገኘዉ ትርፍ ይኖረዉ ይሆን? ይመሰለኛል አለዉ…. ባይሆን ኖሮ አጃቢዎቹ ስለምን ይሄን ያህል መፈራገጥ ያስፈለጋቸዉ ነበር? ብዬ እጠይቀለሁ… በርግጥ መልሱን እነሱ ያዉቁታል!  የትወና ብቃትን ለማሳደግ ብቻ የሚያደረጉት ከሆነም ከልብ ያስገርማል …. ይቺ ይቺ በጣም አደገኛ ‘አድቬንቼር’ ነች!  የምሬን ነዉ ያለገባኝ ነገር እንዳለ አላዉቅም ግን ደግሞ እንደዉ አጉል ጉንጭ ከማልፋት… ሰዉም ከማስቸገር ምርጫ የምንለዉ ጉዳይ እዉነተኛ የፉክክር መድረክ እስኪሆን ተወት ብናደርገዉስ? ባይሆን መሰራት ያለባቸዉን መሰረታዊ ጉዳዮችን በርትተን እንስራ….፡፡

የዲሞክራሲ ሂደት?

የሆነዉ ሆነና እቺ ዲሞክራሲ የሚሏት “ዛር” ኢትዮጵያ ዉስጥ ምች ሆን ሞልቶላት የምትቆመዉ? ብትለመን ብትለምን አልወርድ አለች አይደል? ለነገሩ ብቅ ስትል ገና አስደንብረዉ እያባረሯት በየት በኩል ትምጣ? ይልቅዬ ‘ዲሞከራሲዊነት ሂደት ነዉ’ የሚባለዉ ተረት ተረት አብሮን ሊያረጅ ነዉ አይደል? ከምር 10 ዓመት ሆነዉ እኮ….! እናማ መቶ አመት እስኪሞላዉ ልንጠብቅ ነዉ ማለት ነዉ?

በነገራችን ላይ የዚህ ‘ሂደት ነዉ’ የሚሉት ማሳበቢያን ፅንሰ-ሃሳብ ከየት ይሆን ያገኟት ብዬ ሳስብ ድንገት እንግሊዝያዊዉ የኢኮኖሚክስ ሊቅ አዳም ስሚዝ ‘The Wealth of Nations’ የሚለዉ መፃሃፉ ዉስጥ ቶሸንቅሮት ኖሮ አገኘሁትና ‘እነኚ እንግሊዞች ተኮለኞች ናቸዉ….’ የሚሉት ስንኝ ወዲያዉ ትዉስ አለኝ፡፡ ለነገሩ ስሚዝ ስለዲሞክራሲ አስቦ የተናገረዉ ሳይሆን ስለእድገት ሲያወራ ያነሳዉ ሃሳብ ነዉ፡፡ እንደ ሰዉየዉ አባባል የሃገራት የኢኮኖሚ እድገት ተፈጥሮላዊ ሂደቱን ጠብቆ የሚመጣ ዝግመታዊ ለዉጥ (the natural progress of opulence) የሚለዉ አይነት ነዉ፡፡ እንዲህ ማለት ደግሞ ዛሬ የበለፀጉት ሃገራት የደረሱበት የእድገት ደረጃ ላይ ለመድረስ ዕዉደቱ ይተበቅ ከተባለ ለታዳጊ ሃገራት ከመቶ አመት በላይ ሊፈጅ ነዉ፡፡ ሃሳቡን ብዙ ሙሁራን ፉርሽ ያደረጉት ጉዳይ ቢሆንም እኛ ቤት ሲመጣ ታዲያ ዲሞክራሲዊ ለዉጥ በሂደት የሚገኝ ነዉ ከሚባለዉ ማስመሰያ ጋር መሳ ለመሳ የሆነ ይመስላል፡፡ ለምን ቢባል ይሄዉ ሃያ አራት አመታትን አስቆጠርን ያየነዉ መሻሻል የለም … እናም መቶዋን ልነደፍን ነዉ ማለት ነዉ?

ነገሩማ የሚመስለዉ ወደኋላ መመለስ የጀመርን እንጂ ወደፊት መንቀሳቀሱ ሲያምራችሁ ይቀር የተባልን ነዉ፡፡ ወደ ኋላ መንሸራተት እንደ ሃገርና እንደ ስርዓት ትልቅ ኪሳራ ነዉ… ‘የዲሞክራሲ ውርጃ’ አይነት ነገርም ይመስላል፡፡ …. ከምር እንዴት ቁልቁል እንወርዳለን? እዚህ ላይ ፖላንዳዊዉ የምጣኔ ሃብት ሙሁሩ ፖል የተናገረዉን መጥቀስ የተገባ የሆናል…. ‘ሰዉ ከሆንን ምን እንደ ዉሻ ወደ ትፋታችን ይመልሰናል ይልቁንስ የተሻለ ሁኔታን እንፈጥራለን እነጂ’… ያላትን አይነት ሽንቆጣዉን ያስታዉሷል (if we were to emerge alive, we should not return to previous status quo but … form a better world)….. እናማ በዚህ ሁኔታ ከቀጠልን ተስፋችን ምን ይሆን? ይሄ መከረኛ ትወልድ ያሰበዉን ሳይናገር… የፈቀደዉን ሳይመርጥ… አቛሙን እዳሻዉ ሳይገልፅ ዘመናትን ጠብቆ ያሰበዉ ሳይሳካ ሊያለፍ መሆኑ አሳዛኝ ነዉ፡፡

‘እና ምን ይሁን?’ የሚሉ ጠያቂዎች አይጠፉምና ለማለት የተፈለገዉን ማስረዳት ይገባል፡፡ ጉዳዩ እንግዲህ ኢንዲህ ነዉ….. ዲሞክራሲያዊ ሂደቱን የጠበቀ ለዉጥ ለማየት የግድ ዘመናትን በናፍቆት መጠበቅ የለብንም…. ሂደት ነዉ እያሉ መቀለዱን አቁመን ዛሬዉኑ መደረግ ያለበትን ማደረግ የሁሉም ወገን ሃለፊነት መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡ምርጫ ማካሄድ በራሱ ግብ አይደለም! ይልቁን ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት ከሚጠበቁ  ግብዐቶች መካከል አንዱ ብቻ ነዉ:: ኢትዮጵያ ዉስጥ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓትን እንገነባለን የሚባለዉ ለተፈላጊዉ ስርዓት መታጣት ተግዳሮት የሆኑ ነገሮችን ምንነትን ከስር መሰረቱ አጥርቶ ሳይለዩ ከላይ ከላይ በመጋለብ ነዉ:: ዋናዉን የስርዓቱን በሽታ መርምሮ ከለዩ በኌላ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ የተያዘዉ ምልክቶችን ማስታመምና ግባዐቶች ላይ መረባረብ ነዉ:: እንደ ሚታወቀዉ ሃገሪቱ ሊፈቱ የማይችሉ የሚመስሉ ቅራኔ ዉስጥ ሰምጣ ገብታለች…. ታፍና ከመሞቷ በፊት የነፍስ አድን ስራዎች መሰራት አለባቸዉ፡፡

መድሃኒቱ

ቀዳሚዉና ዋንኛዉ ጉዳይ፡- ለታሪክ ቅራኒዎቻችን መፍትሄ ማበጀቱ ነዉ፡፡ በአንድ ወቅት… በወዲኛዉ ዘመን በበርካታ ቤሔርና ቤሔረሰቦች ላይ የደረሰ በደል አለ ይባላል፡፡ ይህም የመታገያ አጀንዳ ከሆነ ከአራት አስርት ዓመታት አለፉ:: እርግጥ ነዉ ኢትዮጲያ ዉስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ሁሉ እከሌ ከከሌ ሰይባል በጭቆና ዉስጥ ነበሩ… (ምናልባት ዛሬም ያ ሁኔታ የተለወጠ አይመስልም)፡፡ እናም በተለየ መንግድ የበደል ገፈት ቀማሽ የነበሩ ቤሔሮች፣ ቛንቛ ተናጋሪዎችና የእምነት ተከታዮች ነበሩ፡፡ የዝሆን ጆሮ ይሰጠኝ አልሰማሁም ወይም አይኔን ግንባር ያደርገዉ አላየሁም ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ለመካድ ካልሆነ በቀር ታሪክ የመዘገባቸዉ እዉነታዎች አሉ::  በሚኖሩበት ስፍራና ቀየ ስንክሳር ያዩ… በማንነታቸዉ እንዲያፍሩና እንዲሸማቀቁ ተደርገዉ የነበሩ የህበረተሰብ አካላት ነበሩ ምናልባተም ዛሬም ቅርፁን ይለወጥ እንጂ በዚህ ሁኔታ ዉስጥ የሚያለፉ ህዝቦች አሉ፡፡ በሌለላ አነጋገር የአማራና የትግራይ ተወላጅ ያለሆኑ እንዲሁም የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታይ ያልነበሩ ህዝቦች ላይ በተለየ መልኩ የደረሰ በደልና ስቃይ ነበር፡፡ የአፄ ሚንሊክ የግዛት ማስፋፋትና ትልቛን ኢትዮጲያን በመፍጠር ሂደት ዉስጥ የፈጠረዉ ጠባሳ ያለተፈቀ ሃቅ ነዉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ሁኔታ ሆን ተብሎ በተፈጠረ የማጋጋያና የማጋነኛ የፈጠራ ንግርቶች ታጅቦ በህዝቦች ማካከል በጋህድ የሚታይ ቅራኔን ፈጥሯል፡፡ በዉጤቱም ግልፅ የሆኑ መናናቆችና መጠላለፎች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በአሁኑ ወቅት እየታዩ ነዉ፡፡ ዛሬ በርካታ አስደንጋጭ  ሁነቶች እየተሰተዋሉ ነዉ …. በፊዉዳሉ ዘመን ለጋብቻ አጥንት ይቆጠር እንደነበረዉ ሁሉ በኛም ዘመን ለሁለት ጥንዶች መጋባት መፈላለጋቸዉና ማፋቀራቸዉ ብቻ በቂ አልሆነም ዘርን ማስተካከልም ተቀዳሚ ጉዳይ ሆኗል ፡፡ ይሄ ደግሞ በከተሞች ጭምር የሚያጋጥም ጉዳይ ነዉ፡፡ በግለሰቦች ደረጃ ያለዉን ማንሳቱ በህዝቦች ማካከል የቱን ያህል ስር የሰደደ የመጠፋፋትና የበቀል ስሜት እያደገ እንደሆነ የሚያመላክት አይነተኛ ሁነት በመሆኑ ነዉ፡፡ ቁምነገሩ ይህን እያወራን እና እያራገብን እስከ መቼ እንዘልቃለን የሚለዉ ነዉ፡፡ እዉነተኛዉ አደጋ አይኑን አፍጥጦና ጥርሱን አግጦ እኪመጣ ከዚያም እኪያጠፋን እተጠባበቅን ያለን ነዉ የምንመስለዉ፡፡ አሳዛኙ ጉዳይ ታድያ ይህ ሁሉ ዐደጋ በዚህና በመጪዉ ትዉልድ ላይ የተደቀነዉ ትዉልዱ በግል ላልፈፀመዉና ላልደረሰበት በደል ነገር ግን ያለፈዉ ትዉልድ ያወረሰዉ ስንክሳር መሆኑ ነዉ፡፡ የዚህን ማለቂያ የሌለዉን የመካሰስ ወጥመድ ሰብሮ መዉጣት የሁሉም ወገን ሃላፊነት መሆን ይኖርበታል:: ለዚህ ደግሞ  ድፍረት ይጠይቃል… እዉነተኛ እርቅና የወገናዊነትን መንፈስ ለመፍጠር ከበዳይም ከተበዳይም ወገን ተወላጅ የሆንን ሁሉ ደፍረን ልንቀበለዉ ጨክነን ልንጋተዉ የሚገባ እዉነታ አለ፡፡

ተወደደም ተጠላ በአንድ ሃገርና አከባቢ እንድንኖር ተፈጠሮ ግድ ብላናለች…ምንም ባንፈላለግ እንኴን ልንነጣጠል አንችልም… ይህ ቀዳሚዉ ሃቅ ነዉ፡፡ ሌላኛዉ ትላነት ለደረሰዉ ጥፋትና በደል የዚህ ትዉልድ ሰዎች ቀጥተኛ ተሰታፊዎች አይደለንም፡፡ ይሄን ታሳቢ አድርግን ቀጣዩን እርምጃ መዉሰድ ተገቢ ይሆናል:: ስለሆነም ለዚህ የዉርስ ፀብ መፍትሔ ማበጀት አለብን፡፡ ሃቁ ይህ ነዉ… አፄ ሚኒሊክና ጦራቸዉ አደዋ ላይ ወራሪዉን ጠላትን አሳፈሮ በመመለስ በሰሩት ገድል የኢትዮጲያ ብቻ ሳይሆኑ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ጀግና እደነበሩት ሁሉ በሌላዉ ገፅታቸዉ ደግሞ ግዛት ለመስፋፋት በደረጉት ዘመቻና በተከቱሉት ፖሊሲ ኢሰባዉነት የተሞሉ ጨፍጫፊ ነበሩ፡፡ በተለይ በአርሲ፣ በባሌ፣ በሐረር፣ በቦረና፣ በወላይታ፣ በከፋና በሌሎችም አከባቢዎች የደረሱ ዘግናኝ ጥፋቶች የማይረሱ የሃያኛዉ ክፍለ-ዘመን የታሪካችን መጥፎ ገፅታ አንዱ አካል ነዉ፡፡ ለዚህ ጥፋት የኦሮሞ ህዝብ እና ሌሎችም ቤሔሮች ብቻ የሚቆጩበት… የአማራ ህዝቦች ብቻ ለዘመናት የሚወቀሱበት ጉዳይ ሊያቆም ይገበዋል፡፡ የድርጊቱ ፈፃማዎች በዚያ ዘመን የነበሩ የስርዓቱ ጠበቂዎች ሲሆኑ በደሉ የደረሰዉ ግን በሁሉም ኢትዮጵያዉያን ላይ እንደሆነ ሊታሰብ ይገባዋል፡፡ ስለሆነም ሚኒሊክ መወገዝ ካለባቸዉ በጋራ እናዉግዝ … ለችግሩ ሰለባ ለሆኑ ሰዎች መታሰቢያ ማድረግ ካለብን በጋራ ስንዘክራቸዉ እንኑር…! ይህን ጉዳይ መቛጨት የሚቻለዉ ሃያት ቅደመ ሃያቶችህ በድለዋል የሚባሉት የአማራ ተወላጆች ሃያት ቅድመ ሃያቶቻችን መከራን ተቀብለዋል ለሚሉ ለሌሎቹ ቢሔሮች ሃዘናችሁ ሃዘናችን ነዉ … ያለፈዉ ትዉልድ ስራ ተገቢ አይደለም ብሎ በደፈናዉ ይቅር በመባባል ብቻ ከሆነ ማድረግ ነዉ፡፡ ተበድለናል የሚሉ ወገኖችም ይቅር ለማለት ዝግጁ መሆን ይኖርባቸዋል:: ይሄ ጉዳይ መፍትሄ ሳይበጅለት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንገነባለን ብሎ መነሳቱ አለያም ለዉጥ እናመጣለን ማለት የህልም እሩጫ ከመሆን አያልፍም::

ሁለተኛዉ ጉዳይ፡- ከመጀመርያዉ ሃሳብ ጋር የተያያዘና ተቀዋሚ ነን ብለዉ የቆሙ ሃይሎችን ይመለከታል:: ከትዉልድ ትዉልድ የተሸጋገረዉ ተቃርኖ መፍትሄ ሊበጀለት ባለመቻሉና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መስማማት ባለመፈለግ አንድ ኢህዲግን ለመገዳደር ዘጠና ምናምን ፓርቲዎች ተፈጥረዋል:: ብዙዎች ስለምን በሃገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ ያሉ የፖለቲካ ሃይሎች የጋራ ተቀናቃኝ የሚሉትን ሃይልን ለመታገል ሲሉ መስማማት እንኳን ይሳናቸዋል የሚለዉ ጥያቄ መልስ የሚያጡበት ጉዳይ ነዉ:: መልሱ ግን ቀላል ግልጽ ነዉ::አንደኛዉ ያለፈዉ ታሪካዊ ተቃርኖ የጋራ ግብ እንዳይኖራቸዉ አድርጔቸዋል…. የጋራ ግብ ቢኖራቸዉ እንኳን ተቀራርበዉ ለመወያየትና ከልብ የሆነ ጥምረትም ይበሉት ጅኒ ቁልቋል ለመፍጠር አልተቻላቸዉም:: ትልቁ የሙግት መከፈቻና የስጋት ምንጭ ሊሆን የሚችለውም እነዚህ ገዢዉን ግንባር እንቃወማለን የሚሉ ሃይሎች እርስ በርስ መቀዋወማቸዉ ብቻ ሳይሆን በጠላትነት ስሜት መተያየታቸዉ ጭምር ነዉ::ስለተመሳሳይ ጉዳይ በተለያየ መድረክ በተመሳሳይ ቌንቌ እየተናገሩ በህብረት ግን መስራት ሲሳናቸዉ ሲታይ የሚገርም ትይንት የሚሆነዉ ያኔ ነዉ::  ሌላኛዉ ጉዳይ ስለመጪ ጊዜ ያላቸዉ አተያይ ጉራማይሌ መሆኑ ነዉ:: አይበለዉና ይህ የከፋዉና የመረረዉ ህዝቡ ነግ በግብታዊነት ተነስቶ ለዉጥ እንፈልጋለን ብሎ በሌሎች ሃገራት እንደታየዉ ስልጣን ላይ ያለዉን ሃይል ቢያባርረዉ ተቃዋሚ ነን የሚሉት ሃገሪቷን በየትኛዉ ፍኖተ ካርታና ፕሮግራም ሊመሯት ይሆን? ይህን የመሰለለዉን ተቃርኖ መፍታት ሳይቻላቸዉ በሰላማዊዉ መድረክም ሆነ በሌላ ዘዴ የስርዓት ለዉጥ እናመጣለን ብለዉ የተነሱ ሃይሎች ሃገሪቱን እና ህዝቡን ወደሌላኛዉ አዙሪት ዉስጥ ያስገቧታል የሚለዉ ስጋትን የምንጋራ ጥቂቶች አይደለንም:: ዋናዉ ጉዳይ ተቃዋሚዎች ላለመስማማት የተስማሙበትን ባህል ቀይረዉ መቀራረብና በጋራ መስራት ካልተቻላቸዉ  ስልጣንን እደንደተመኛት ሳይወርሷት እኛም ዲማክራሲን እንደናፈቅናት ሳናገኛት በምድረ በዳ መቅረታችን የምር ይመስላል::

ሦወስተኛዉ ጉዳይ ከላይ ከተጠቀሱት አበይት ሃሳቦች ጋር በቀጥታ የሚያያዝና መዳረሻ ሊሆን የሚገባዉ ነዉ::ይሄዉም ለዘመናት የተቆለሉ ፖለቲካዊ ቅራኔዎችን በሰከነና በሰለጠነ መንግድ መፍትሄ እዲያገኙ የማደረግ ሂደት ነዉ፡፡ በሌላ አነጋገር ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ስለ ቤሔራዊ እርቅና ስለ ሃገራዊ መግባባት መሰራቱ የተሸለ መሆኑን መረዳት የተገባ ነዉ፡፡ በርግጥ ይህን ሃሳብ ብዙዎች ያዝ ለቀቅ ሲያደርጉት ይስተዋላል፡፡ የሆነዉ ሆኖ ሁሉም መንታ ልብ መሳይ ናቸዉ፡፡ ለምን ቢባል ሲገፉበት አይታይም…. ዛሬ ስለ እርቅ በተናገሩበት አንደበት ነገ ሲያወግዙና ሲፈርጁ ይታያሉ፡፡ እረቀ ሰላምን ለማስፈን ቀዳሚዉ ጉዳይ እዉቅና መስጠትና መከባበር ነዉ፡፡ እዉቅና መስጠት እዉነታን ከመቀበል ይጀምራል፡፡ያለፈን ታሪክ ተቀብለን መፍትሄ እንደምንሻለት ሁሉ የዛሬዉንም ነባራዊ ሁኔታ በቅጡ መረዳት የተገባ ይሆናል:: ተወደደም ተጠላም ባለንበት ዘምንም ሆነ በመጪዎቹ አመታት አሁን ስልጣን ላይ ያለዉ ሃይል ባሻዉና በፈቀደዉ ምንገድ ሃገሪቱን እየመራ የመቀጠሉ ነገር  እዉን ይመስላል፡፡ ይህን ሃይል ያገለለ የእርቅ ሃሳብም ሆነ ሌላ አይነት እንቅስቃሴ መድረሻዉ የትም ነዉ፡፡ ስለሆነም ለማዉገዝና ለማጥላለት የሚያስንፈዉ ሃሳበችን ስልጣን ላይ ያለዉን ሃይል እንደ መንግሰት ተቀብሎ ያስገኛቸዉን ዉስን ነገር ግን ነባራዊና አዉንታዊ ለዉጦች ወይም እድገቶች አክብሮ እዉቅና መስጠት ተቀዳሚዉ እርምጃ ሊሆን ይገባዋል፡፡ የዚህ አይነቱ አቀራረብ ተንበረካኪ.. ተለጣፊ… ሌላለም ሌላም ነገሮችን ሊያስብል እንደሚችል ይገመታል፡፡ ይሁን እንጂ እዉነት ስለሆነ በዚህ መንገድ መጔዙ ግድ ይለናል፡፡ ፈረንጆቹ walk the talk እንደሚሉት የምናወራዉን ልንተገብረዉ ይገባል፡፡ እዚህ ላይ ለማለት የተፈለገዉ ጠላትነትን ብቻ ግብ ያደረገ ዘለቄታ የሌለዉ አካሄድ ስለሚሆን መደረግ ያለበትን ሁሉ አድርጎ እርቅና ድርድር ለመፍጠር የሚቻለባትን በር ክፍት አርጎ ቢያንስ መጠባበቁ የተገባ ነዉ::

እንደ መዉጫ

ከላይ የተዘረዘሩት ቅድመ ሁኔታዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ ዲሞክራሲ … መብት… ለዉጥ …ትግል ቢባል እመኑኝ የትም አንደርስም፡፡ ቢሞከር እንኴን ከዚህ ቀደም እደታዩት የታሪክ አጋጣሚዎች ታጥቦ ጭቃ ከመሆን ፈቅ እንደማንል ለመተንበይ ነብይ ሞን አያሻም፡፡ ስልጣን ላይ ያለዉ ሃይል በታዓምር ዲሞክራያዊ ሊሆን እንደማይፈልግ እየታወቀ… ሰልፍ ቢወጣ… ባምርጫ ላይ ምርጫ ቢደረደር እንደዉ አጉል መፈራገጥ ለመላላጥ የሚሉት አይነት ካልሆነ በቀር ጠብ የሚል ነገር ይኖራል ማልት ቂልነት ከመሆን የሚያለፍ ነገር የለዉም፡፡ ዲሞክራሲያዊነት ደግሞ ለድርድር መቅረብ የለለበት የለዉጥ መንገድ መሆን ይኖርበታል፡፡ ሌላ ዙር ጦርነትና ወይም ሌላ ምዕራፍ አብዮት ለሃገሪቱም ሆነ ለህዝቡ የሚበጅ አይሆንም፡፡ ስለሆነም የምንፈልገዉን አይነት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እዉን ለማድረግ የሚቻለዉ የዘመናት የታሪክ ቅራኔዎችን በቅንነት አይቶ መፍትሄ እንዲያገኙ በማድረግ፣ ተቃዋሚዎች እርስ በእርስ ከመቀዋወም ሲዎጡና በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ተግባብተዉ ለለዉጥ አብረዉ መስራት ሲችሉ ነዉ::የነኝህ ሁለት መሰራታዊ ጉዳዮች እዉን መሆን ወደ ሶስተኛዉ ግብ የሚያንደረድረን ይሆናል:: ይኄዉም ከገዢዉ ሃይል ጋር ለመደራደርና መገባባት ላይ ለመድረስ የሚያስችል አቅም የሚፈጥር ሁነኛ መንገድ ተደርጎ ሊወሰድ ይቻላል:: ያኔ ሁሉንም ወገን ያሳተፈ ስርዓት መመስረት ሲቻል የምንፈልገዉ የሰዎች መብት መከበር፣ ሰላም፣ እኩልነት፣ ነፃነት፣ እድገት ብልፅግና በምንወዳት ሃገራችን እዉን ማድረግ እንችላለን:: ይሁንና ይህን ህልም የሚመስል ምኞት እዉን ለማድረግ ስንት ዘመን ይፈጅብን ይሆን? ተምኔቱን ተጨባጭ ማደረግ የሁሉም ዜጎች ሃላፊነት ሊወሆን ይገበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

 

 

 

የማለዳ ወግ …አስገራሚው ትዕይንት “በተስፋዋ”የአረብ ምድር በሳውዲ   !

$
0
0

ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 8 ቀን 2007 ዓም

* የገቡት ይወጣሉ ፣ የወጡት ተመልሰው ይመጣሉ
* የሳውዲ መንግስት “ህገ ወጦችን” የማጽዳቱ ዘመቻ ቀጥሏል
* ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዜጎች ከሞት ጋር ተፋጠው እየተሰደዱ ነው
* የሳውዲ መንግስት ማስጠንቀቂያና እርምጃ …

unnamed (1)
  የሳውዲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውንና ህጉ በማይፈቅደው መንገድ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ካለው ሙያ ውጭ የሚሰሩ የማናቸውንም ሀገር ዜጎች በመላ ሀገሪቱ ለማጽዳት የተደራጀ ዘመቻ ከተጀመረ ወር ደፍኗል። በየቀኑ በመንግስትና በግል መገናኛ ብዙሃን የሚለቀቁት የማስጠንቀቂያ መረጃዎች ከበድ ከበድ ያሉ ናቸው ።

ዛሬ ማለዳ   ” ህገ ወጦችን ጠራርገን እናስዎጣለን ” ያሉትን የሰራተኛ ሚኒስቴር አድል ፈቂን ይዞ የወጣው አረብ ኒውስ ሚኒስትሩ ሃገራቸው ለህገ ወጥ ሰራተኞች ቦታ እንደሌላት በአጽንኦት መጠቆማቸውን ያስረዳል። የሰራተኛ ሚኒስትሩ በማከልም መንግስት ህገ ወጦችን እግር በእግር እየተከታተለ በመያዝ የማስወጣቱን ስራ እንደሚገፋበት ሲያስታውቁ 150 የሚደርሱ ተጨማሪ የሴት ተቆጣጣሪዎች ስልጠና ተሰጥቷቸው ህገ ወጦችን በማጣራቱ ስራ መሰማራታቸውን አስረድተዋል። ተቆጣጣሪዎች ስራቸው ሲከውኑ በተአማኒነት  ፣ በሃላፊት ፍትሃዊ በሆነ አግባብ ባለው መንገድና ስርአት መሆን እንደሚገባው ሚኒስትር አድል ፈቂ አሳስበዋል። የሰራተኛ ሚኒስቴር አድል ፈቂ በቤት ሰራተኛ አቀጣጣጠር ዙሪያ ያለውን ችግር ለመፍታታ ከ200 የተለያዩ ሃገር ዜጎች ጋር መምከራቸውንና በጠቃሚው ምክክር የተገኙትን መፍትሄ ሃሳቦች በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ አሳስበዋል።

ዘመቻው …

unnamed (2) ወር በደፈነው በዚህ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ኢላማዎች ፈርጀ ብዙ በሆነ ምክንያት ሳውዲ ገብተው በህገ ወጥነት የሚኖሩትን ጨምሮ በኮንትራት ቪዛ መጥተው ከአሰሪዎቻቸው የጠፉትን ያጠቃልላል። ዘመቻው ጅዳ ደርሶ በተለያዩ አካባቢዎች በየመኖሪያ ቤቱ አሰሳው ተጠናክሮ መቀጠሉን የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡት ነው ። እስካሁን በቀጠለው በዚህ ዘመቻ በኢትዮጵያን ላይ ሲያዙ ማንገላታትም ሆነ የተለየ ጥቃት መስተዋሉን አልሰማሁም። መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ቢያዙም እየተጣራ ተለቀዋል። ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውና ለአሰሪያቸው የጠፉት ግን እየተያዙ ተወስደዋል። ዘመቻው ግን አሁንም ቀጥሏል … በዘመቻው የተያዙት በርካታ ዜጎችን ስልክ እየደወሉ እንደገለጹልኝ ከሆነ  ” በፍተሻው ስንያዝ የረባ ልብስ እንኳ አልለበስንም ፣ ለአመታት ያፈራነው ንብረታችን አልሰበሰብንም ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ቢያንስ ሻንጣችን ይዘን የምንገባበትን መንገድ ያዘጋጅልን  ” ሲሉ ተደጋጋሚ ምሬታቸውን ገልጸውልኛል !

ወደ ” ተስፋዋ ምድር ” ያላባራው ጉዞ …

ወደ “ተስፋዋ” የአረብ ሃገር ምድር ወደ ሳውዲ የሚደረገው ጉዞ አላቆመምም። የእኛ ደላሎች ከሳውዲ እስከ ሀገር ቤት ትላልቅ ከተሞች፣  ገጠርና የወረዳ ከተሞች በዘለቀ የእዝ ሰንሰለት ተደራጅተው በወገናቸው ስደት ተጠቃሚ ሆነዋልና በማን አለብኝነት ሰውን እያጋዙት ይገኛሉ ። አምና ካቻምናና ዘንድሮ በአሳር በመከራ ሀገር ቤት የገቡት ኢትዮጵያውያን እነሱ ” የተስፋ ምድር ” ወደ ሚሏት ሳውዲ እየጎረፉ ነው። ባሳለፍነው ወር በተደጋጋሚ የየመን የቀይ ባህር ዳርቻ የቅርብ ርቀት ባህር ከበላቸው ወገኖች ባልተናነሰ በየበርሃው በአሸጋጋሪ ደላሎች ታግተው አሳር መከራቸውን የሚያዩትን ወገኖች የከፋ የስቃይ ስደት ህይዎት ያማል ።

እነ ሞት አይፈሬዎች የእኛ ዜጎች አሳምረው የሚያውቁትን የሞት ጉዞ ተከትለው ፣ ሞትን ዳግም ለመፋጠጥ ቆርጠው ፣ ከቀያቸው ነቅለው  የመጡ ይመስላል። እነሱን በአደጋ አስከብቦ እዚህ ስላደረዳቸው ምክንያት አብዛኞችን ስንጠይቃቸው ጣራ የነካው የኑሮ ውድነት ፣  ድህነት ፣ የተሻለ ኑሮ ፍለጋውን አማረው ይነግሩናል። አንዳንዶች ከተጠቀሰው ምክንያት አዳምረው በሀገር ቤት የፖለቲካው ትኩሳት ሙቀት የመለብለቡ ፍርሃቻን እንደ ምክንያት ያቀርቡታል። ያን ሰሞን ሃገር ቤት ለእረፍት የሄዱ የቤተሰብ አባሎቸንና ወዳጆቸን ሀገር ቤት ስላለው የኑሮ ውድነትና ኑሮ ጠይቄያቸው የእድገት ምጥቀቱን ፣ ገንዘብ ላለው ሀገር ቤት የመመቸቱንና አንገቱን ደፍቶ ልስራ ላለ ስራ ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል አጫውተውኛል። ታዲያ ሰው ለምን ይሰደዳል?  ለሚለው ጥያቄየ ግን መልሱ ” እሱ ግራ የሚያጋባ ነው! ” የሚል ነው ። እርግጥ ነው ይህ ምላሽ አጥጋቢ ሆኖ አላገኘሁትም … የሀገር ቤቱ እውነታ እድገት ምጥቀቱ ፣ ገንዘብ ላለው ሀገር ቤት የመመቸቱንና አንገቱን ደፍቶ ልስራ ላለ ስራ ሰርቶ መለወጥ እየተቻለ አስከፊውን ስደት የማያውቁትን ቢያጓጓም ከሞት ጋር ተፋጠው ተሰደውና ወደ ሀገር ቤት በዘመቻ ተመልሰው የገቡት እንዴት የመከራ ሰቀቀኑን የአረብ ሀገር ስደት መረጡት?  ብሎ መጠየቅ ግድ ይላል ፣ ለዚህም ሁነኛ የሆነ መልስ ሰጭ አካል አልተገኘም !  ይህ ምላሽ እስኪያገኝ ግን ወደ “ተስፋዋ የአረብ ምድር ”  የሚደረገው ስደት ተጠናክሮ ቀጥሏል …
ላለፉት ሶስትና አራት ተከታታይ አመታት የሁለት ሃገራት ውል ባልተዋዋሉበት ፣ ቅድመ ዝግጅት ባልተደረገበት ሁኔታ በኮንትራት ስራ ስም ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ አብዛኛው ሴት እህቶቻችን ወደ ሳውዲ ገብተዋል። ምንም እንኳን የተሳካላቸው በተወሰነ መንገድ እራሳቸውን ረድተው ቤተሰቦቻቸውን እየረዱ መሆናቸው ባይካድም መብት ጥበቃ የጎደለባቸው ፣  ያለተሳካላቸው ከአሰሪዎቻቸው ጠፍተው ህገ ወጥ ነዋሪነቱን ተቀላቅለው የሰቀቀን ኑሮን እየገፉ ነው። በአንጻሩ በአሰሪዎቻቸው ተቀፍድደው ተይዘው መላወሻ ያጡት የተጨነቁት ምንም ማድረግ ያልቻሉት ከጨለማው ኑሮ ከእገታው ለመላቀቅ በለየለት ወንጀል ተዘፍቀው ስማችን አክፍተውታል። የቀሩት አሁን ድረስ የገሃነም ኑሮን እየኖሩ ነው። የዚህ ሁሉ ክስተት ምክንያት ህጋዊ ውል በሌለበት ፣ የመብት ጥበቃው ባልተጠናከረበት ሁኔታ የኮንትራት ስራ መጀመሩ መሆኑን ገና ኮንትራት ሊጀመር ነው ሲባል እኔም ሆንኩ ” ያገነባናል ” ያልን ባቀረብናቸው ጭብጥ መረጃዎች እንደ ዜጋ ከነ ነባሬ መፍትሄ ሃሳቡ ጥቁመ ነበር ።  ያ ሰሚ ሳያገኝ ቀርቶ እዚህ ደርሰናል። ይህ በመሆኑ ትልቅ ስህተት ተሰርቷል ባይ ነኝ።

ዛሬም ” ከስህተቱ ተምረናል ” ብለን እያቀነቀንን ፣ ግን ከስህተቱ ያለመማራችን ጠቋሚ መረጃ እየሰማን ነው ። ከአመት በፊት የተዘጋው የኮንትራት ስራ ሊከፈት “ረቂቅ ደንብ ” ወጥቷል ተብሏል። ያን ሰሞን ኤጀንሲዎች በረቂቁ ዙሪያ ሲመክሩ በዜጎች መብት ማስጠበቅ ዙሪያ ያሉት ነገር ባይሰማም ስለሚያስይዙት ገንዘብ አማረው ሲናገሩ ሰምተናል። በውይይቱ የገንዘቡ ከፍ ማለት “ህገ ወጥ ስደቱን ያባብሰዋል” ያሉት ኤጀንሲዎች ስለየትኞቹ ህገ ወጥ ስደተኞች እንደሚያወሩ ግራ እየገባን መመጻደቁን ሰምተነዋል ። ይህን ማለቴ ህገ ወጥነትን ያባብሳል ያሉት አይገባምና ነው ፣ ለመሆኑ ባህር ቆርጠው በየመን እየገቡ ያሉት አብዛኛው ወንድ ወንድሞቻችን የገጠር ልጆች የኮንትራት ስራ ቪዛው ተጠቃሚ አድርጎ መውሰዱና አግባብ ነውን?  ይህ ማስመሰያ ምክንያት ሊታረም ይገባል ።   ያም ሆኖ በኤጀንሲዎችና በደላሎች አማካኝነት በየመን ፣  በሱዳንና በዱባይ የጉብኝት ቪዛዎች ሽፋን እየተሰጣቸው አሁን ድረስ ለሚሰደዱትን መላ አልተገኘለትምና ጉዞው አላቆመም ። የኤጀንሲዎች “ህገ ወጥ ጉዞን ያበረታታል ” ለማለት የሰጡት ምክንያት እኒህኞቹን ለመታደግ ከሆነ ደግሞ እንደ ዜጋ ኤጀንሲዎች አዲሱ ረቂቅ ከገንዘብ ማስያዙ በላይ ቀድሞውንም ባላስጠበቁት መብት ላይ መነጋገር እንጅ በየጣለባቸው ግዴታ ላለማሟላት ጉንጭ አልፋ ምክክር ማድረጋቸው አያስደስትም ።

ማጠቃለያ

የኢትዮጵያ መንግስት በአረብ ሃገሩ ስደት ጉዳይ ላይ ከፕሮፖጋንዳ ያለፈ ጥልቅ ጥናት ባላደረገበት ሁኔታ የሚሰራውን ስራ ቆሞ ሊመረምር ግድ ይለዋል !

ወገኔ ሆይ  ፣ በሃገር ቤት ወደ አረብ ሃገራት ለመሰደድ የቋመጠው ወገንም ከፊት ለፊቱ ያለውን አደጋ ሊያስተውልና ሊመረምረው ይገባል !  በባህር እና በበርሃው በባዕድ ምድር ደመ ከልብ ሆኖ ከማለፍ በወገን መካከል በሃገር የመጣውን ችሎ ማለፉ ይበጃል ባይ ነኝ  !

ባለ ጊዜ ባለጸጋዎች ደላሎች ሆይ  ፣ ላንድ አፍታ ወደ ነፍሳችሁ ተመልሳችሁ በወገኖቻችሁ በተለይል ለአቅመ አዳም በደረሱና ባልደረሱ እህቶችን ላይ ቅቤ እያነጎታችሁ በማማለል እየፈጸማችሁት ያለውን ዘመን የማይሽረው  ግፍና በደል ተረጋግታችሁ አስቡት !  ጊዜው ቢያልፍም ፣ በሰራችሁት በደል ጠያቄ እንኳ ቢታጣ ውሎ አድሮ ከማይተዋችሁ የህሊና ጸጸት ለመዳን ስትሉ ከክፉው ምግባራችሁ ራሳችሁን ለመግታት ሞክሩ  ! ሌላ ምን እላለሁ  !

ቸር ያሰማን   !

አክራሪ … አሸባሪ … የሰለቸን መንግስታዊ መዝሙር … የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አክራሪነት/አሸባሪነት የህዝቦች ስጋት ነው፡፡

$
0
0

ምንሊክ ሳልሳዊ

ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት/አሸባሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: ጥላችሁን እንዳታምኑ እየተባለ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡

Ethiopian soldiers ride on an army truck on the road to Afgooye, south of Mogadishu«መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»…የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ የሚፈረጀው የሚራመዱ የፖለቲካ ጡዘቶች በሰዎች ላይ ሌላ እምነትን በመጫን በግዳጅ እና በሃይል ሊያስገድዱ ሲሞክሩ ይህ ማለት አህበሽን እና ተሃድሶን በጥንታውያኑ እስልምና እና ተዋህዶ ላይ በኢትዮጵያ እንደተሞከረው ማለት ነው::

አክራሪነት አሉታዊ ትርጉም ሲኖረው የራስን እምነትና አመለካከት በሌሎች ላይለመጫን መሞከር ነው፡፡ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር ራሱ አክራሪነት ነው፡፡ አክራሪነት የፖሊቲካ ገጽታ ያለው ነው፡፡ ኾኖም ግን ሃይማኖትን ማጥበቅ አክራሪነት አይደለም፡፡ሃይማኖት ፍጹም እውነታን በፍጹም እምነት ስለሚቀበል ከሌሎች ግላዊ አስተሳሰቦች የተለየ ነው፡፡ የሃይማኖት መገለጫዎችን መጠቀም የዚያን ሃይማኖት ጥልቀት የሚያሳይ እንጂ እንደ ችግርም የሚወሰድ ወይም አክራሪነት ሊኾን አይችልም፡፡ «መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተአምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባልአይችልም፤» ይላሉ የዘርፉ ምሁራን፡፡

የአክራሪነትና የአጥባቂነት ፅንሰ ሐሶቦች በጥሩ ኹኔታ ተለይተው ተገልጸዋል፡፡ አንዳንድ ሰነዶች ወያኔም ለይስሙላ የገለበጣቸው ሰነዶቹ አክራሪነትንና አጥባቂነትን በአግባቡ ለይተውና ተንትነው ያስቀምጣሉ፡፡ በዚሁ መሠረት አጥባቂነትን፣ ‹‹የግል ሃይማኖትን ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ሳይንጠባጠብ ሁሉንም ትእዛዛት መፈጸም ነው፤» በማለት ሲፈታው አክራሪነትን ደግሞ፣ «ከራስ እምነት ወጥቶ ሌላውን መተንኮስና የሌሎችን ሃይማኖት መኖር አለማመንና አለመፍቀድወይም ሌሎቹን አስገድዶ የራስ እምነት ተከታዮች ለማድረግ መጣር ነው፤» ይላል፡፡ በተግባር ላይ አለመዋሉ እና በጣልቃ ገብነት መተርጎሙ ጉዳት አመጣ እንጂ::

ከዚህ ብያኔ ስንነሣ ክርስቲያንም ሆነ ሙስሊም ከርሱ ውጭ የኾኑትን የሌሎቹን መኖር የማይቀበልና ከግለሰቦቹ ፈቃድ ውጭ አስገዳጅ እስከኾነ ድረስ እርሱን አክራሪ ማለት ይቻላል፡፡መብትን መጠየቅ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መሸሽ አክራሪነት አይደለም:: በዚህ መልኩ አክራሪው ይህንኑ ድርጊት ሊፈጽም የተነሣውን ቡድን ብቻ እንጂ «አክራሪው ቡድን» የወጣበትን/የተገኘበትን ቤተ እምነት ሊወክል አይችልም፡፡ ስለዚህ በአለማቀፍ ደረጃ የአክራሪ ክርስትና እና እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም፤ ለሌላው ቤተ እምነትም እንዲሁ፡፡ ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው::

#ምንሊክሳልሳዊ


ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ ብቻ ሳይሆን የሰላማዊ ትግል ስልት አካል ጭምር ነው!

$
0
0

ተሾመ ዳባ

ምርጫ በአንባገነን መንግስት ውስጥ?
2007 electionምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ የሚሆነው ነጻ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ (free, fair and contested) ባህሪያትን የተላበሰ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ በኢ-ዴሞክራሲዊ መንግስት ውስጥ የሚደረጉ ምርጫዎች በምንም መመዘኛ የዴሞክራሲ ስርዓት መገለጫዎች አይሆኑም፡፡ በሀገራችን በአጼው፣ በደርግ እና በኢህአዴግ ዘመነ-መንግስታት ተደርገው የነበሩ ምርጫዎች የአጼውን፣ የደርጉንና የኢህአዴግን የአገዛዝ ስርዓቶች የስልጣን ዘመን ለማራዛም የተደረጉ (“mechanism of regime maintenance”) ምርጫዎች እንጂ አንዳቸውም የዴሞክራሲዊ ምርጫ ባህሪያትን የተላበሱ አይደሉም፡፡ በእርግጥ በባለፉት ሁለት የመንግስት ስርአቶችም ሆነ በኢህአዴግ ዘመነ-መንግስት የተደረጉ ምርጫዎች በተለያዩ የፖለቲካ አገዛዝ ስርአቶች ውስጥ እንደመደረጋቸውና በወቅቱ ካለው የሀገራችን የፖለቲካ ዕድገት አንጻር የተለያዩ ባህሪያትን የተላበሱ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የታየ ሳይሆን በማንኛው ኢ-ዴሞክራሲያዊ መንግስት ውስጥ የሚደረጉ ምርጫዎች አጠቃላይ ገጽታ ነው፡፡

ምርጫ እንደ ሰላማዊ ትግል ስልት?

በአንባገነን ስርአት ውስጥ የሚደረጉ የነጻነት፣ የፍትህ እና የዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች የአንባገነን ስርአቱን ጥቅምና ፋላጎት ባስከበረ መልኩ ሊመለሱ አይችሉም፡፡ ይህ የሚወልደው ፖለቲካዊ ግጭቶችም እልባት የሚያገኙት አንድም እጅን አጣጥፎ በመቀመጥ የአምባገነን ስርአት የፍርሃት እስረኛ በመሆን (passive submission)፣ አሌያ በትጥቅ ትግል(violent)፣ ወይም ደግሞ በሰላማዊ ትግል (non-violent) ነው፡፡ ሰላማዊ ትግልን ከትጥቅ ትግል የሚለየው የጭቆና መጠን ጉልህ ወይም ቀላል የመሆን አለመሆን ፣ ወይም ደግሞ የሰብአዊና ፖለቲካዊ መብቶች ጥሰት አናሳ መሆንና ያለመሆን ሳይሆን ልዩነቱ የሚመጣው በምንክተለው የፖለቲካ ትግል ስልት ላይ ነው፡፡ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል አባት የሚባለው ጄን ሻርፕ፣ የሰላማዊ ትግል ትርጓሜ ሲስቀመጥ፡- “the exercise power depends on the consents of the ruled who, by withdrawing that consent, can control and even destroy the power of their opponents” ብሎ ነው፡፡ ከዚህ የምንረዳው፣ ሰላማዊ ትግል አንደኛ፣ መሰረቱ ተገዢውና ተጨቋኙ ህዝብ ነው፡፡ ሁለተኛ፣ የትግል ስልቱ ህዝቡ ለገዢዎቹ የሰጠውን ይሁንታን በማንሳት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሶስተኛ፣ ህዝቡ ገዢው ፓርቲ ስልጣኑን መኪያስጠብቅበት ጉልበት ያልተናነሰ ጉልበት ለገዢዎቹ በማሳየት (by means of wielding power) ገዢዎቹን መቆጣጠር፣ ከዚህም ከላፈ የመሪዎቹን ጉልበት በማፍራረስ ነጻነቱንና ዴሞክራሲያዊ መብቱን የሚያስጠብቅበት ነው፡፡

ከሰላማዊ ትግል ዘዴዎች አንዱ የፖለቲካ ትብብርን መንፈግ (the method of political noncooperation) ነው፡፡ ከዚህ ዘዴ ውስጥም፣ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በአምባገነኑ ስርአት ውስጥ የሚደረጉ ምርጫዎች ውስጥ እራሳቸውን ማግልለ አንዱ ስልት ነው፡፡ ሆኖም ግን፣ በተደጋጋሚ እንደታየው ከምርጫ እራስን ማግለል ውጤታማ የሆነ የሰላማዊ ትግል ስልት አይደለም፡፡ ከ1990 እስከ 2009 እ.ኤ.አ ከተደረጉ 171 ከምርጫ እራስን የማግለል ማስፈራራት እና ከምርጫው እራስን በማግለል የተገኙ ውጤቶች ሲታዩ ከምርጫ እራስን ማግልለ ሳይሆን ከምርጫ እራስን አገላለው የሚል የማስፈራራት ስልት ውጤታማ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታከሉ፡፡ ከምርጫ እራስን የማግለል ስልት ደካማ ጎኑ በራሱ ቁሞ ውጤት የሚስገኝ ስልት አለመሆኑ ነው፡፡ በሀገራችንም በ1985 ዓ.ም እና በ2005ዓ.ም ተሞክሮ ውጤት አልባ መሆኑን አይተንዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ ይህን ክፍተት የተረዱ የፖለቲካ ሳይንቲስቶች ምርጫን እንደ ሰላማዊ ትግል ስልት መጠቀም የሚቻልበትን ዘዴ ቀይሰዋል፡፡ ይህን ዘዴ Democratization by Elections በሚል የሰየሙት ሲሆን፣ ዋና ዋና ሃሳቡም፡-

• ምርጫዎ ለአንባገነኑ መንግስት መጨቆንን በጣም ከባድ እና መዘዘ-ብዙ እንዲሆን ያደርጋሉ፣
• ምርጫን ማካሄድ ለአንባገነኑ መንግስት ከውጭ መንግስታት ጋር ለሚያካሂደው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥቅም መስጠቱ፣
• ዜጎች አንባገነናዊ መንግስትን ከሚታገሉበት ስልት አንዱ መብቶቻቸውን ለማስከበር የሚያደርጉት ትግል አንዱ ነው፡፡ በምርጫ መሳተፍ (እንደ መራጭም ተመራጭም) ደግሞ የዜጎች ፖለቲካዊ መብት ነው፡፡ ይህን መብት መጠይቅ፣ ለመብታቸውም መታገል፣ ድምጻቸውን በምርጫ መስጠት፣ ድምጻቸውን እንዳይሰረቅ ማስጠበቅ አንዱና ወነኛው ስልት መሆኑ፣
• በሌላ ጊዜ አምባገነኑ መንግስት የሚዘጋቸውን በሮች ለምርጫ ሲባል ብቻ የሚከፍታቸው በሮች መኖራቸው፣
• ምርጫዎች ተቋዋሚ ፓርቲዎችን በጋራ በትብብር እንዲሰሩና ወደህዝቡ እንዲቀርቡ እንድል ስለሚፈጥሩ፣ እና
• ምርጫዎች ሰብአዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፖለቲካዊ መብቱን የሚጠይቅ ዜጋን ለመፍጠርር መነቃቂያ መድኮች በመሆናቸው (bargaining power) ነው፡፡
በመጪው ምርጫ በመሳተፍ ይህን ዘዴ ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር በመቃኘት ተግባራዊ ማድረግ ይቻል ይሆን?

መነሻ ሃሳብ
1. በመጪው ምርጫ መሳተፍ ማለት ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ነው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሂደት አለ ማለት አይደለም፡፡ ኢ-ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መሆኑን ማንም የሚገነዘበው ነው፡፡ አለምአቀፉ ማህበረሰብም የሚረዳው ነው፡፡
2. ኢህአዴግ የኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡ ምን አይነት መንግስት ነው? ኢ-ዴሞክራሲያዊ፣ አምባገነናዊ መንግስት ነው፡፡
3. በምርጫው እራስን በማግለል ተቋዋሚ ፓርቲዎች ሊያገኟቸው የሚችሉ ውጤቶች አናሳ (እሱም ካለ) ናቸው፡፡
4. ገዢው ፓርቲ የሚከፍታቸውን በሮችና የተገኙ እድሎችን በአግባቡ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡
5. ባለፉት 23 ዓመታት ስለገዢው መንግስት ጨቋኝነት፣ አምባገነንነት ተወርቷል፡፡ ይሄ ምንም ውጤት አላመጣም፡፡ አሁን ደግሞ የዕይታ ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ የተቋዋሚ ፓርቲዎች ላይ ማተኮር ተገቢ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግል መሰረቱ የአምባገነን የጨቋኝነት አቅም ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የተጨቋኙ አቅም ላይ የተመሰረተ ነውና፡፡
6. ማንም ተቋዋሚ ፓርቲ ብቻውን በመሮጡ ሊያሳካው የሚችለው ውጤት አናሳ ነው፣ በጋራ ሊገኝ ከሚችለው ውጤት አንጻር፡፡
7. በዚህ ምርጫ ሊገኝ የሚችለው ውጤት መንግስትን መቀየር የሚያስችል ውጤት ሳይሆን፣ ሊገኝ የሚችለው ውጤት መመዘን ያለበት ዴሞክራሲያዊ ስርአት የተገነባባት፣ ፍትህ የነገሰባት፣ እኩልነት የሰፈነባት ሃገር ለመፍጠር ምን ያህል ወደፊት ያራምደናል ከሚል መሆን አለበት፡፡

ይህን ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ዘዴዎች
ገዢው ፓርቲ በሚከፍተው በር ሁሉ ለመጠቀም ውስጣዊ አቅም መገንባትና ዝግጁ፡- የሬዲዮ ክርክር፣ የቴሌቭዥን ክርክር፣ በህትመት ሚዲያዎች የሚሠጡ ዕድሎችን በአግባቡ በመጠቀም በግል ሚዲያ አለመኖር የሚፈጥረውን ክፈተት ማጥበብ እንዲሁም ገዢው ፓርቲ ላይ ስራ ማብዛት፣

ተቋዋሚ ፓርቲዎች ተናቦ የመስራት ዘዴ መከተል፡- ተቋማዊ ፓርቲዎቻችን በአንድነት መስራት ከብዷቸዋል፡፡ እርስ በእርስ የሚያረጉትን ትርጉም የለሽ የፖለቲካ ሽኩቻ በማስወገድ፣ ከተቻለም በምርጫው ጊዜ የእርስ በእርስ ውድድር እንዳይኖር የዕጩዎቻቸውን የመወዳደሪያ ክልል አወሳሰን ላይ በጋራ በመስራት ከገዢው ፓርቲ ጋር በአብዛኛው የምርጫ ክልሎች ላይ መወዳደር፡፡ እንዲህ በማድረግ የገዢውን ፓርቲ ጉልበት መሳሳትና መበተን ይቻላል፣ የጭቆና ወጪውም ከፍተኛ ይሆናል፣

የምርጫ ስትራተጂ፡- የተቋማዊ ፓርቲዎች የምርጫ ስትራተጂ ህዝባዊ መሰረት ለመፍጠር፣ ከዚህ ምርጫ ባሻገር የፖለቲካ መሰረት በመጣል ለቀጣይ ስራዎች ግብዓት የሚሆኑ አደረጃጀቶች መፍጠርንም ማካተት ይሆናል፡፡ የሚፈጠሩት አደረጃጀቶች ለቀጣይ ሰላማዊ ትግል መሰረት ይሆናሉ፡፡

በምርጫው ሂደት ንቁ ተሳታፊ መሆን፡- የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫ ላይ፣ የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ እና በሁሉም የምርጫው ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፎ ማድረግ፡፡ እንዲህ በማድረግም በተቻለ አቅም ለገዢው ፓርቲ ምርጫ ለማጭበርበር የማያመች ሁኔታ መፍጠር

ሰነዶችን የመያዝ አካሄድ፡- በምርጫው ወቅት የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን፣ የምርጫ ማጭበርበርን፣ ህገወጥ የሆነ የገዢውን ፓርቲ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰነዶችና መረጃዎች በአግባቡ በማሰናዳት የምርጫዉን ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ማሳየት ይቻላል፡፡

ሊጠበቁ የሚችሉ ውጤቶች
የአጭር ጊዜ ውጤቶች
ተቋማዊ ፓርቲዎች ያላቸውን አነስተኛ የፋይናንስ፣ የሰው ኃይል እና ድርጅታዊ አቅም በአግባቡ መጠቅም ያስችላቸዋል፡፡
በህግ ማውጫው ምክር ቤት ውስጥ በመሳተፍ አማራጭ ፖሊሲዎቻቸውንና የመፍትሄ ሃሳቦቻቸውን ለማቅረብ የሚችሉ ይሆናል፡፡ የህዝቡን ብሶት፣ የመብት ጥሰት የሚያሰሙበት መድረክ ይኖራቸዋል፡፡

የረጅም ጊዜ ውጤቶች
በጋራ አምባገነኑን መንግስት መገዳደር ይችላሉ፡፡ ከአምባገነኑ ስርአት መውደቅ በኃላ ለሚፈጠረው ስርአት ግብዓት የሚሆን በመተባበር ላይ የተመሰረተ ተቋዋሚ ፓርቲዎች ግንኙነት ይፈጠራል፡፡
ሊደርስባቸው ከሚችልው የገዢው ጭቆና በጋራ የመከላከልና የመደጋገፍ ባህል ያጎለብታሉ፡፡
ትግሉን ከዲያስፖራ ወደ ሀገር-ቤት ወዳለው ህዝብ ይመለሳል፡፡ ይህም ለተቋዋሚዎች የበለጠ የመንቀሳቀሻ እድልና የስራ ነጻነት ይሰጣቸዋል፡፡ ይህም የድል ቀኑን ያቀርበዋል፡፡ “ድል ሁል ጊዜም የህዝብ ነው” እንዲሉ አበው፡:

እስማኤል አሊ ስሮ ለረዥም ጊዜ በክልል ፕረዝድንትነት የቆዩ ብቸኛ የኢህአዴግ አገልጋይ የሆኑበት ምክንያት ምንድነው ?

$
0
0

አኩ ኢብን ከአፋር

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕረዝደንት የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት በ 2006 ዓ.ም በጻፉት ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጲያ በተሰኘው መጽሀፍ ላይ ሰለ እስማእል ዓሊ ሲሮ ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ….

(አፋር ክልልን ፍልሥሥ ብሎ የሚመራው ኢስማኤል አሊስሮ ይህ ነው)

(አፋር ክልልን ፍልሥሥ ብሎ የሚመራው ኢስማኤል አሊስሮ ይህ ነው)


በ1993 በኢህአዴግ ውስጥ ቀውስ በተፈጠረበት ወቅት የአፋር ብሔራዊ ዴሞራሲ ፓርቲ ሊቀመንበርና የክልሉ ፕረዝድነት የነበሩ ዓሊ ሲሮ አፈንጋጮችን ደግፎ ለተወሰኑ ቀናት የመለስን ቡዱን ተቃውሞ ነበር።

መለስ ድል አድረግያለሁ የባለንጣዎች ጃኬትም አውልቀያለሁ ካለ በኃላም ዓሊ ሲሮ ደስተኛ አልነበረም።
ሰለሆነም ከክፊፊሉ በኃላ ዓሊ ሲሮ መገምገም ነበረበት ከመገምገምም አልፎ ላሳየው ተቃውሞ መቆንጠጥ ነበረበትና በወቅቱ የፈዴራል ሚኒስትር የነበረው አባይ ፀሐዬና የክልሎች ዴስክ ኃላፊ የነበረው ዘርኣይ አሰገዶም የአፋር ዴሞክራሲ ፓርቲን አመራር ዓሊ ሰሮን ጠርተው ቁም ስቅሉን አሳይተውት ነበር።

ዓሊ ሲሮም ከአፈንጋጮች ጎን ተሰልፈው እንደነበረ እንዲያምን ብዙ አስለፍልፈውታል።
ሁለት አወያዮች ይህን ካደረጉ በኃላ ዓሊ ሲሮ ከስልጣን እንዲወርድ ለመለስ ሀሳብ ቢያቀርቡም አለቃ ፀጋይ በአቆራጭ መለስን ተማጽኖ ከመባረር አድኖታል።

የአለቃ ፀጋይ ዓሊ ሲሮ በስልጣን እንድቆይ መማጸን ከማናውቀው ማላእክ የሚናውቀው ሰይጧን (ሸይጣን) ይሻለናል ከሚል እንደነበረ ምንጮቻችን ነግሮናል።

እውነትም ሁኔታዎች በተለዋወጡበት ሁኔታ እንኳን አብዴፓና መሪው ሌላም አፋር ለውጥ ለማምጣት የሚቸገር ነበረና ዓሊ ሲሮ ባለበት እንድቆይ ተወስኖ ኢህአዴግን ከአስራ ሁለት አመታት በላይ ሊያገለግል ችሏል ይላል መጽሀፉ።

እዚህ ለይ እኔም የራሴ ትንሽ ልጨምረበትና በእርግጥ የእስማእል ዓሊ ሲሮ የአገልግሎት ላይ መቆየት ምክንያት አለቃ ፀጋይ ነው።
ይህም በ1993 ባደረገለት ተማጽኖ ብቻ ሳይሆን መለስ ከሞተ በኃላም ያልተቆረጠ ድጋፍ ከአለቃ ፀጋይ አላቸው።
ይሁን እንጂ መለስ ከሞተ በኃላ አለቃ ፀጋይ እራሱ ይህ የሚባል ስልጣን ባይኖረውም አቆያህለሁ እያለ ከአቶ እስማእል ብዙ ሚሊዮን ብሮች እንደሚያገኝ ይነገራል።

አለቃ ፀጋይ የትግራይ ክልል ፕረዝደንት በነበሩበት ጊዜ ዓሊ ሲሮ መቀለ ሳይዘይሩ (ሳይሳለሙ) ሳምንት አያሳልፉም ነበር።
አሁን ግን ሁለቱም መሀይሞች የሚገናኙት አዲስ አባባ ወይም ሰመራ ቢሆንም አቶ ሲሮ ስልጣን ላይ ለመቆየት ከአለቃ ፀጋይ ሌላ አዲስ ሽማግሌ የቀጠሩ የመስላሉ።

እርሱም የጀቡት ፕረዝደንት የሆኑት እስማእል ኡማር ገሌ ስሆኑ ካለፉት ሦስት ሳምንታት በፊት አቶ እስማእል አሊ ስሮ በማያገባቸው የሁለት አገር ድምበር ከተሞች የፀጥታ ኃላፊዎች በተጠሩበት ሰብሰባ ምክንያት በማድረግ ወደ ጀቡቲ ሄደው ነበር።
በዛን ጊዜ ሁለት እሰማእሎች ተገናኝተው የበሩ መሆኑን ኦና ኢህአዴግ ከእስማእል ኡመር ገሌ የሚፈለገው ብዙ ነገሮች ሰላለው ኢህአዴግን እንዲማጸኑለት እስማእል ዓሊ ሲሮ ጠይቀው ነበር።

ያነ የኢትዮጲያ ኢሳ ጎሳ ተወላጅ የሆኑት ገሌ እስማኤል ዓሊ ሲሮ ለኢሳዎች ልዩ ቀበለዎች እንዲሰጡ ወይም የኢሳ ጎሳ በአፋር ክልል በሰላም እንዲኖሩ እንዲያመቻቹ ጠይቀው አቶ ሲሮ የሁለቱም ጥያቀዎች መልስ ያለው በኢህአዴግ እጅ ውስጥ እንደሆነና እርሰዎ እንድጠይቁ በማለት በሚስጥር ከተሰማሙ በኃላ ወደ ሰመራ ተመልሷል።

ከሳምንት በኃላ የጀቡቲ ፕረዝደንት በአሶሳ በተከበረው የበሔር በሔረሰቦች ቀን ላይ ተግኝተው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
ከዛም ከሳምንት በኃላ የፈደራል ሚኒረስትር በአፋር ክልል በአዋሽ ከተማ በሁለት ክልሎች ጣልቃ ገብተው የአፋር መሬት ለኢሳ አሳልፈው ስጥተዋል።

ድንበር ዘለሉ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች አፈና እና የጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እጣፈንታ !

$
0
0

nebyu sirak

ነብዩ ሲራክ ላለፉት አስርት አመታት በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድምጽ በመሆን በአረቡ ዓለም ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን መረን የለቀቀ ስቃይ እና በደል መቋጫ እንዲበጅለት በድህረ ገጹ በማስተጋባት ላይ የሚገኝ ጋዜጠኛ ነው ። ይህ ጋዜጠኛ በተለይ ያለምንም ቅድመዝግጀት እና ሁለትዮሽ፡ስምምነት በቤት ሰራተኝነት በደላሎች ተወናብደው ቁም ስቅላቸውን እያዩ ሰለሚገኙ እህቶቻችን አሰቃቂ ተእይንት በማለዳ ወጎቹ በማስቃኘት በአጭር ግዜ ውስጥ የአያሌ ወገኖችን ትኩረት መሳብ የቻለና የጉዳዩ ባለቤት በሆነው ህዝብ ዘንድ አንድናቆትና ክበርን ያተረፈ መሆኑም ይነገራል።

በሌላ አቅጣጫ በጋዜጠኛው ዘገባዎች ያልተደሰቱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ካድሬዎች እና አንዳንድ የሰራተኛ እና አስሪ ኤጀንሲ ባለቤቶች አይን የሚደረግበት ክትትል የጋዜጠኛው ን የስደት አለም ህይወት ውስብሰብ እና የከፋ አድርጎታል ። ጋዜጠኛው በስደት አለም ከሚገኝበት ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ በግሉ ተከራይቶ ከሚኖርበት የመኖሪያ ቤቱ በተለያዩ ምክንያቶች እንዲፈናቀል ከሚሸረብበት ሴራ እና ኮሚኒቲ አካባቢ እንዳይደርስ እይተደረገበት ካለው ተጸኖ ባሻገር የመንግስት ካድሬዎች እና ፡ደላሎች በህይወቱ ላይ የሚሰነዘረውን ዱላ በመጋፈጥ መራራውን ጽዋ በአደባባይ ለመቀበል ተገዷል። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን ለማጥፋት በተለያየ አቅጣጫ መልኩን እየለዋወጠ የሚሰነዘረው ጥቃት ፍጹም ወገናዊ ርህራሄ የጎደለው በመሆኑ የጋዜጠኛው ደህንነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ፡ መግባቱን ብዙዎች ይናገራሉ። በተለይ ጋዜጠኛው የሚከተለውን ሃይማኖት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የአባራኩ ክፋይ ከሆነው ሙስሊም ወገኑ ጋር ለማጋጨት እነዚህ ወገኖች በድህረ ገጻቻቸው ከሚያሰሙት ሴጣናዊ ጩሀት ባሻገር ከአመት በፊት ነብዩ ሲራክ የሳውዲ አረቢያን ህግ በመተላለፍ በጥብቅ የተከለከሉ የአልኮል መጠጦች እና መስል አይምሮ አደንዛዥ እጽ ንግድ ላይ የተሰማራ አስመስለው በሃሰት ወንጀላ ለወህኒ በመዳረግ ጋዜጠኛው የስይፍ ሰለባ እንዲሆን በጋዜጠኛው ህይወት ላይ የተቃጣው ሙከራ ድፍን የኢትዮጵያን ህዝብ አስደንግጧል በጅጉም አሳዝኗል ።

የዚህ ጋዜጠኛ የብዕር ጩሀት እንቀልፍ የነሳቸው የመንግስት ካድሬዎች እና ደላሎች ጋዜጠኛው ለረእፍት ወደ ሃገር ሲያቀና ለማፈን የነበራቸው እቀድ ይዚሁ እርኩስ ተግባራቸው አንዱ አካል እንደነበረም ይነገራል። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ በአረቡ ዓለም እንደ ጨው ተበትነው በሚገኙ ወገኖቻችን ዙሪያ በሚያቀርበው መረጃ በዲፕሎማቶቻችን ስራ ላይ ተጸኖ ፈጥሯል በሚል ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ከጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ካድሬዎች በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢደርሰውም ጋዜጠኛ ነብዩ ግን በወገኖቹ ላይ የሚደርሰውን አሰቃቂ ትዕይንት እያየማለፉ ሊከፍለው የማይችለው እዳ ሆኖበት ከህሊና ጸጸት ለመዳን በሙያው ያስተማረውን ህዝብ ውለታ ለመክፈል ዛሬም የሚመጣውን ሁሉ ለመጋፈጥ እውነታዎችን መዘገቡን ቀጥሎሏ ።

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሰሞኑንን ለፓስፖርት እድሳት ወደ ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት አቅንቶ እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች ጋዜጠኛው የነዚህ ካድሬዎች እና ምስለኔዎች ሰለባ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ ። ጋዜጠኛው ቀደም ሲል በወገኖቹ ዙሪያ በድሀረ ገጹ ሲያቀርባቸው በነበሩ መረጃዎች ያልተደሰቱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.መንግስት ካድሬዎች እና ደላሎች ነብዩ ሲራክ በጃችን ገባ ሲሉ መደመጣቸውን የሚገልጹ ምንጮች የጋዜጠኛው ፓስፖርት እድሳት በ ድርጅታዊ ውሳኔ በገወጥ ሊታገድ እንደሚችል ስጋታቸውን አክለው ገልጸዋል።

በዚህ ዙሪያ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን በአካል አጊቷ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም ይህ ጋዜጠኛ ከተለመደው የእንገለሃልን እና በጃችን ትገባለህ ተራ የስልክ ማስፋራሪያ ባሻገር እስካሁን ምንም አይነት ችገር እንዳልገጠመው የሚገልጹ ምንጮች ፡ ጋዜጠኛው በጀመረው በጎ ተግባር እንደሚቀጥል እና እስከ ዛሬ ሲያቀርባቸው በነበሩ ዘገባዎቹ በየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣውን መከራ እና ስቃይ በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ይናገራሉ።

Ethiopian Hagere Jed Bewad

ተስፋዬ ገ/አብ ገዳ              ከሰመረ አለሙ      

$
0
0

 

ተስፋዬ ገ/አብ ለኤርትራ ነጻነት ታግሎ አገሬ የሚለዉን አገር ነጻ ከወጣ በሗላ በየጊዜዉ ኢትዮጵያን ሰፈር የሚያደርገዉን ቅሌት አስመለክተዉ ብዙዎች ዘግበዉታል በተለይም የተከበሩ የኢትዮጵያ ልጂ ኢንጂነር ዘዉገ አስፋዉ ተስፋዬ ስለሰዬ የማላዉቀዉ የለም ብሎ ሲቀባጥር በምሁር ብእራቸዉ ቢያበራዩትም ግለሰቡ ለእዉቀት ያልታደለ በመሆኑ አሁንም ኢትዮጵዉያን ሰፈር መተናኮሱን አላቆመም። ኤርትራ ዛሬ ምድር ላይ ያለ ችግር ተጠራቅሞ እሷ ላይ እንዳላረፈ ሁሉ ተስፋዬ ግን ለዉጊያ የመረጠዉ ሀገር ይችኑ ኢትዮጵያችንን ነዉ።

Tesfaye Gebreabተስፋዬ ገ/አብ በወጣትነት ዘመኑ በዘመኑ ሀገሪቱ ዉስጥ እንዳሉት ወጣቶች ተምሮ ወይ ተቀጥሮ ሊሰራ ባለመቻሉ በችሎታ ማነሰ ምክንያት ማለቴ ነዉ በወቅቱ በገፍ ልዩ ችሎታ ሳይጠይቅ ሁሉንም ያስተናግድ በነበረዉ በዉትድርና ዘርፍ ዉስጥ ተቀጥሮ ደርግን ሲያገልግል የቆየ ነበር። ችግሩ ዉትድርናዉንም በሀሞተ ቆራጥነት ሊወጣዉ ባለመቻሉ አንዴ በካድሬነት አንዴ በግጥም አንባቢነት የወቅቱን ጌቶቹን ሲያገለግል ቆይቶ የደርግ ዉድቀት አይቀሬ በመሆኑ ዘር አቋጥሮ ወደ ጠላት ጎራ ተቀላቅሎ ለመቀላቀሉ ግን የራሱን የሆን አንካሳ ምከንያት እየሰጠ በየጊዜዉ በመገለባበጥ የሚኖር ኤርትራዊ ነዉ።

ተስፋዬ ገ/አብ ህዋአትን ከተቀላቀለ በሗላ ነብስና ስጋዬ ከህዋአት የተሰራ ነዉ በማለት ከዋናዉ መስራቾቹ በላይ ፊታዉራሪ ሲሆን ገድላቸዉን ሲጽፍም እነሱ በህልም ያልታያቸዉን ገድል እና ጀብድ ቀጥሎ ቀጣጥሎ ጌቶቹን በሚገባ ያስደሰተ ካድሬ ሲሆን ለዚህም ስራዉ ለሱ የማይገባዉን ቦታ በአቶ በረከት እና በአቶ መለስ አማካይነት ተችሮት ያንን የመሰለ ትልቅ ተቋም ምን ያህል እንዳራከሰዉ ከራሱ ከጋዜጠኛዉ ማስታወሻ ኑዛዜዉና አልፎ አልፎ ከሚሰጠዉ ቃለ ምልልስ መገንዘብ ይቻላል። ተስፋዬ ገ/አብ ጠላቶቼ  የሚላቸዉ እነሱ የማያዉቁት እሱ ግን ያቄመባቸዉን በዘመነ ሹመቱ ቁም ስቅል አሳየ፤ቀጣ፤ሞራል ጣለ፤ ከስራ አባረረ ሌላም ሌላም።

በወቅቱ የዚህ ሰዉ ጣራ መንካት መጨረሻዉ ያልተመቻቸዉ ካቅሙ እና ችሎታዉ በላይ የተሸከመዉ ስልጣን ለእሱ የሚመጥን ባለመሆኑ ነገሩን ሁሉ  የልጂ ጨዋታ አደረገዉ መላ ይበጂለት በማለት ረጋ ሊያደርጉት ሲሞክሩ፤ የተለቀቀለት ጥቅማ ጥቅምም ልጓም ሲበጅለት፤ ኤርትራ ጋርም ያለዉ ንክኪ ሲደረስበት እጁ በካቴና ከመግባቱ በፊት ከእሱ ጋር በተለያየ ነገር ትስስር ያላቸዉ ግለሰቦች ነብሰህን አድን ጥቆማ በማድረጋቸዉ ወደ ባህር ማዶ ከእፍኝ ብር ጋር ተሰዶ እስከ ለከፈዉ ልክፍት ጋር አብሮ ይኖራል። እንደዉም አንዳንዶቹ የሻቢያ ሰላይ ነዉ ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ የወያኔ ሰላይ ነዉ የሚሉም አሉ።

ተስፋዬ እንደማንኛዉም ስደተኛ እራሱን እንደማኖር የለከፈዉ ልክፍት አለቅ ብሎት አንዴ ኢትዮጵያዊ አንዴ ወያኒያዊ አንዴ ኤርትራዊ አሁን አሁን ደግሞ ኦሮማዊ ቀጥሎ ደግሞ ምስራቅ አፍሪካዉ ሊሆን ተዘጋጂቷል። ከጂምሩ የዚህ ግለሰብ መላ ማጣት ቀደም ብሎ የተገለጠላቸዉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ “ተስፋዬ ምነዉ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ሆነ መላዉን አጣ” ብለዉ የተናገሩት ለጊዜዉ የሚያስቅ ቢመስልም እሳቸዉ ግን ከንግግራቸዉ ጀርባ ብዙ ነገር በመታዘብ የወረወሩት አስተያየት በመሆኑ በጊዜዉ ሳይሰተዋል እዚህ ላይ ተደርሷል። ተስፋዬ ገ/አብም በዚህ ቂም ይዞ ደጂ በሚጠናበት በኦሮሞ ስብስባ ሁሉ እሳቸዉንና አቶ ቡልቻ ደመቅሳን ከተቀረዉ ኦሮሞ ለማለያየት ሳያጣጥል ያለፈበት ጊዜ የለም።

ብቻ አሁን አሁን ሚዛኑ ቀንሶ የኢትዮጵያ የድር ገጾችም የተስፋዬን ጽሁፍ ወደ ቅርጫት በመጣል ትምህርት እዉቀት ልምድ ያላቸዉ ኢትዮጵያንን በማስተናገድ ላይ በመሆናቸዉ የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ሳያመስግን አያልፍም ። ለወደፊትም አምዳቸዉ ላይ የሚያወጡት ጽሁፎች ሁሉ ኢትዮጵያዊ መስፈርትን የጠበቁ ይሆናሉ የሚል እምነትም ይኖረናል።  እዚህ ላይ የኢትዮጵያ መጽሀፍ አሳታሚዎች ትርፍን ባማከለ መልኩ ብቻ ጸረ ኢትዮጵያ ጽሁፍ ባታስተናግዱ መልካም መሆኑን እየጠቆምን ነገር ግን ከትርፍ በላይ ሀገር የለም በሚል እምነት የተስፋዬን እና መሰሉን  መጽሀፎች ብታሳትሙ በሀገር ፍቅር ስሜት ልባቸዉ የነደደ ዜጎች በድር ገጹ አማካይነት የራሳቸዉን እርምጃ ስለሚወስዱ ትርፋችሁን ቀርቶ ዋናዉን ከማጣታችሁም በላይ በሀገር ክህደት መዝገብ ዉስጥ እንደምትቀመጡ ከወዲሁ ማስገንዘብ እንወዳለን። ቀደም ሲል የደረሰዉ ችግርም ሊደርስባችሁ ስለሚችል ጥንቃቄ ማደረጉ ተገቢ ነዉ እላለሁ። ተስፋዬና መሰሎቹ ታሪክ የሚያጠፋበት ዜጋ የሚያጠባብጡበት መሳሪያዎች እናንተ ከሆናችሁ ታሪክ ይቅርታ እንደማያደርግላችሁ በአጽንኦት ልናስገነዘብ እንወዳለን።

ብዙ ጊዜ ደጋግሞ እንደሚናገረዉ አድአ ተወልጄ አድአ አደኩ የሚለዉ ተስፋዬ ገ/አብ ኦሮሞዎች ከገበያ ሲመጡ ለእናቴ ቅቤ ይሰጡ ነበር ይላል እናቴም ቡና አፍልታ ትጠብቃቸዉ ነበር ይለናል ተስፋዬ (ገዳ)። ማንኛችንም እንደምናዉቀዉ ኤርትራዉያን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተሳተፉባቸዉ የመተዳደሪያ ዘርፎች ወይ ሜካኒክ ወይ ንግድ ወይ ዳቦ መጋገሪያ የመሳሰዉ ሁኔታ ሁኖ ሳለ የጣሊያን ስልጣኔ የተጣበቀባቸዉ የተስፋዬ እናት ከኦሮሞ ጋር ያን ያህል የጠበቀ ግንኙነት እንዴት ሊኖራቸዉ ቻሉ? ምናልባት ተስፋዬ አሁን ለሚያከናዉነዉ የኦሮሞ እና አማራን ማጋጨት ስራ መሰረቱን የጣሉት እናቱ ሊሆኑ ይችላሉ ብንል ከምክንያት አንጻር ብዙም የሚያሳማን አይመስለኝም። ምክንያቱም ደብረ ዘይት ከመላዉ ኢትዮጵያ ካሁኗ ኤርትራ ጨምሮ ተደባልቀዉ የሚኖሩባት አገር ሁና እሳቸዉ ግን ከኦሮሞዎች ጋር ብቻ ግንኙነት በመፍጠራቸዉ ነዉ (የመረጃ ምንጭ እራሱ ተስፋዬ ገ/አብ)። እንግዲህ ይህ ሁኔታ በጥልቀት ሲታይ ተስፋዬም የሳቸዉ የስጋ የመንፈስ እና የእምነት ተቀጣይ በመሆ

ኦሮሞና አማራዉን የማፋጀት ኤርትራዊና ወያኔያዊ  ተልእኮዉ የተጠነሰሰዉ በናቱ መምህርነት ሊሆን ይችላል ማለት ነዉ።  በስራቸዉና በኑሯቸዉ ሰልጥነናል በሚል አባዜያቸዉ  ምክንያት ኤርትራዉያን ከኦሮሞች ሲርቁ የተስፋዬ እናት ግን ተስፋዬ እንዳለዉ እንዲህ ያለ መጣበቅ የደረጉበት ምክንያቱ ከዚህ ዉጭ ሊሆን አይገባም።

 

የእናቱን ጉዳይ ስላነሳ ከምክንያት አንጻር ተወያየንበት እንጂ አስፈላጊነቱ እምብዛም አልነበረም። የአባቱ ጉዳይማ በፍጹም ተነስቶ አያዉቅም ከናት ብቻ እንደ ተፈጠረ ሁሉ። እዚህ ላይ ጸሀፊዉ ተስፋዬ ማንኛዉንም የኢትዮጵያ አይኮኖችን( በእድሜ ከአባትነት አልፈዉ አያቱ የሚሆኑትን እንደ ጽሁፉ ባልተገታዉ አንደበቱ አንተ ወይም አንች እየለ ማብጠልጠሉን ያልታዘበ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም እኔ ግን የተስፋዬ እናቴ ተስፋዬን የመሰለ ለስብእና ጠንቅ የሆነ ፍጥረት በተፈጥሮ አስገዳጂነት ቢፈጥሩብንም በኢትዮጵያዊነቴ የሚገባኝን ኢትዮጵያዊ ክብር በአንቱታ መስጠቴ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ ልጃቸዉም ለወደፊቱ ከዚህ ትምህርት ያገኛል የሚል ተስፋ ይኖረኛል። መብቱ የእሱ ነዉ ያደቆነ ሰይጣን ግን ሳያቀስ አይገልም የሚባል አባባል አለ።

በሌላዉ ከተስፋዬ ጽሁፍ እና አንደበት ተደጋግሞ እንደተሰማዉ  እናትየዉ በኦሮሞ ቋንቋ እጂግ የተካኑ ከመሆናቸዉም በላይ ተረትና ምሳሌያቸዉም በኦሮምኛ መሆኑን አልፎ አልፎ ሁኔታና አካባቢዉን እያየ ይናገራል። ይህን አባባልም በመሳብ የልጅነት ጊዜዉን ደብረ ዘይት ዉስጥ ከኦሮሞ ልጆች ብቻ እየተጫወተ እንዳደገ እንደ ሰመመን ትላንት እንደሆነ ሁሉ በትዝታ ለኦሮሞ ተሰብሳቢዎች እምባ እየተናነቀዉ ያወራዋል። ዉድ አንባቢ ሆይ እናቱ ኦሮምኛ ተናጋሪ ከሆኑ በልጂነቱ ዉሎዉ ጨዋታዉ ትምህርቱ እድገቱ ከኦሮሞ ልጆች ጋር ብቻ ከሆነ ይህ ሰዉ አማርኛ ተናጋሪዉን እነዲገድልላቸዉ ሌት ተቀን ለሚሰብክላቸዉ ለኦሮሞ ተወላጆች መልእክቱን ለማስተላለፍ የመረጠዉ ቋንቋ እንዴት አማርኛ ሊሆን ቻለ? እሱስ ኦሮምኛ መናገር እንዴት ተሳነዉ? እንግዲህ የታብሎይዱ ተስፋዬ ገ/አብን ተመልከቱልን ነብሱ ወደ ገደል ተጥላ ለመዉጣት ስትጥር ካቡ እንደገና እየተናደባት መልሶ ወደ እንጦሮጦስ ሲልካት።  ተስፋዬ ገ/አብ ደብረ ዘይት ተወልዶ እድገቱ ከኦሮሞ ልጆች ጋር ሁኖ እናቱ ኦሮምኛን አቀላጥፈዉ ተናግረዉ እሱ ግን ኦሮምኛን ካልተናገርከዉ ኦሮሞንና ቋንቋዉን ከእሱ በላይ የሚጠላ እንደሌለ በአጽኖት መግለጽ ያስፈልጋል። ቋንቋ በልጅነት ዘመን በቀላሉ ሊለመድ ይችላል ተስፋዬ ግን ለህዝቡና ለቋንቋዉ ንቀት ስለነበረዉ ሳይለምደዉ ተላልፎታል ከዚሀ ዉጭ ግን ሊሆን አይችልም። የሚያዉቀኝ ሰዉ የለም ወይም ደግሞ ሊደረስብኝ አይችልም  ቅቤ ሰጡኝ እያሉ መወሻከት ተስፋዬን ትዝብት ዉስጥ ከመጣል በስተቀር የሚያመጣዉ ፋይዳ አይኖርም። ተስፋዬ ስለ ኦሮሞ መጻፉም ከኦሮሞ ጋር ባለዉ ፍቅርና ትስስር ሳይሆን በኤርትራ እና አስመሮም ለገሰ በሚሰጡት የዉሸት መረጃ እና ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚቻለዉ ሁለቱን ትልቅ ጎሳዎች በማናከስ ነዉ በሚል ሂሳብ ተመስርቶ መሆኑን ማስገነዘብ ያስፈልጋል። እዚህ ላይ ጊዜዉ ረዘመ እንጂ ጀግናዉ አለማየዉ መለስ ከእጁ ፈልቅቆ  ያወጣዉን ሰነድ አያይዞ ማየት ጠቃሚነት ይኖረዋል። በነገራችን ላይ 40000 የኦሮሞ ተዋጊ መሳሪያዉን ሲያስፈቱት ተስፋዬ ከበረከት ስምኦን ጋር ዉስኪ እየጨለጠ ሲያንጓጥጥ ነበር።

ተስፋዬ ደብረዘይት ከተማ ዉስጥ ከደብረ ዘይት ልጆች ጋር ነዉ የኖረዉም የተማረዉም ደብረ ዘይት ደግሞ የወታደር ከተማ ሁና ይህን ተከትሎ በስፋት ቡናቤቶች እና ተጓዳኝ ንግዶችን ለመነገድ ከተለያየ ቦታ የመጡ ነዋሪዎች የሚኖሩባት እንጂ ተስፋዬ ገ/አብ እንደሚለዉ ኦሮሞዎች ብቻ ተመርጠዉ ኢትዮጵያዊነትን የሚጠሉባት የጎሳ ስብስብ አልነበረችም እኔም የደብረዘይት ሰዉ ነኝ ቤተሰቦችም የተለያዩ ጎሳዎች ቅይጦች ናቸዉ። የደብረዘይት፤ የናዝሬት፤ የሻሸመኔ፤ የዝዋይ ነዋሪዎች ተመሳሳይነት አላቸዉ አንድ ዘር የበላይነት ጎልቶ የሚታይባትም ከተማ አልነበረችም። ተስፋዬ  ግን እንዲመቸዉ በዛ መልኩ አቅርቧታል። እሱ ከኤርትራ መጥቶ ለደብረ ዘይት ኦሮሞዎች ቅርበት ሲኖረዉ ከኦሮም ጋር ሲጋቡ ሲዋለዱ ኢትዬጵያን የመሰረቱት አማሮችን ግን እንዲገደሉ ቀጭን ትእዛዝ ይሰጣል ይህ ነዉ ተስፋዬ ገ/

አብ አሙቼ።

ተስፋየ ገ/አብ የኦሮሞ ኔት ዎርክ በተባለዉ ቴሌቭዢን ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት “ከቲፒለፍ ጋር ምን አጣላህ” ለሚለዉ ጥያቄ የቀለጠፈዉ መልሱ ጠያቂዉን ለማስደሰት “ከቡርቃ ዝምታ መጽፈህ በሗላ ህወአት ጤና አልሰጠኝም በዚሁ ካገር ጥዬ ወጣሁ” ይላል። እስቲ ይህን አባባል ታአማኒነቱን ከምክንያት  እና ከእዉነት ማእዘን እንመርምረዉ። ያለመታደል ሆነና በደርግ መላ ባጣ አሰራር  ኢትዮጵያ በሁለት ክፉ ጠላቶቿ እጂ ወደቀች (ሻቢያ እና ወያኔ) ብዙም ሳይኬድ ሻቢያ ተበልጦ ሙሉ ቁጥጥሩን ህዋቶች ወሰዱት። እነዚህ ድርጅቶች  የፍልስፍናቸዉ መሰረት የሆነዉ ኢትዮጵያን በዘር መከፋፈል ፤አማራዉን ማዳከም፤ ማጥፋት፤ሀገሪቱን በጎሳ መከፋፈል፤የኦርቶዶክስ  ሀይማኖት የስርአቱ አካል በመሆኑ ማፈራረስ ዋናዉ ሲሆን የዚህ ዘርፍ ደግሞ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ይንጸባረቃል። እነዚህ የስርአቱ መመሪያዎች ዛሬም ድረስ በመተገበር ላይ ይገኛሉ ተስፋዬም ካድሬ በመሆኑ ዋናዉ ስራዉ ይህን ማስፈጸም ነዉ። ተስፋዬ ግን ህወአትን የአማራ ድርጅት በማስመሰል  ጠያቂዉን ሲያጃጂል ከቡርቃ ዝምታ በሗላ ነዉ ይለዋል በጣም ቀላላ መልስ የጭንቀት መልስ። ይህ መልስ ተስፋዬ  አቅጣጫ ማሳያዉ እንደተወናበደበት ከማሳየቱም በላይ የአእምሮዉ ሚዛን ምን ያህል እንደ ተዛባ ለማመላከት አዳጋች አይሆንም።   የቡርቃ ዝምታም ወገንን ከወገን ማናከስ የስራ ድልድሉ እና የተመሰገነበት ስራዉ በመሆኑ በህወአት ቤት በርታ ያሰኘዋል እንጂ  የሚያጣላዉ ነገር በፍጹም ሊኖር አይችልም። ተስፋዬ ግን ትርፍ አገኝበታለሁ ኦሮሞዎችን አጃጂልበታለሁ በማለት ይህን ከሚዛን የቀለለ ምክንያት ሰጥቷል። እዚህ ላይ ጠያቂዉ ብዙ ነገር የሚያዉቅ ሁኖ ሳለ በተስፋዬ ከሳሽነትም ወደ እስር የተወረወረ  ሁኖ እያለ  የተስፋዬም ምክንያት ተረት መሆኑን እያወቀ የተስፋየ መልስ ለእሱ ፖለቲካ ጠቃሚነት አለዉ ብሎ በመገመቱ ሲያልፈዉ የተስፋዬ መልስ ግን  ከአንድ ህፃን ልጂ የማይጠበቅ እንዳልሆነ ከጠያቂዉ የፌዝ አስተያየት መገንዘብ ይቻላል።  ተስፋዬ በኦሮሞ ስብሰባ  ዜግነቱን ለመቀየር በተደረገዉ ስነስርአት ላይ አስተዋዋቂዉ እንዳለዉ ተስፋዬ “በእዉቀት የተጎዳ ቢሆንም ጥሩ ጸሀፊ ነዉ” ብሎ ደረጃዉን መድቦት አልፏል።  አስተዋዋቂዉ እንዳለዉ ተስፋዬ የሚያስበዉን ከመናገሩና ከመጻፉ በስተቀር ከእሱ ከወጣ በሗላ በሌሎች ንግግሩ ወይም ጽሁፉ መመዘኑ ብዙም የሚያሳስበዉ ሰዉ አይደለም መታደል ነዉ በእዉነት።

መልካም ገና እና አዲሰ አመት

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

እንግዲህ ደጋፊዎቹ ለጥቃትም ሆነ ለእርማት በዚህ ድረሱኝ መልካም ገና እና አዲሰ አመት።semere.alemu@yahoo.com

 

 

 

ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ ቁ. 3

$
0
0

ጎንደር ተወልደን ያደግን ሁሉ እንደምናዉቀዉ ህዝባችን እንግዳ ተቀባይ፤ ሽራፊ እንጀራውን ተካፍሎ አዳሪ፤ እንዲሁም በደስታም ሆነ በመከራ አብሮ ከመቆም ባህሪው በመለስ፤ በየዘመኑ ሊያጠቁን እና እናት አገራችን ሊወሩ የመጡብንን ጠላቶቻችን፤ መሪ ሲኖረው ከመሪው ጋር። መሪ ሳይኖረው ጀግኖቹን የጎበዝ አለቃ አድርጎ በመምረጥ እራሱን በራሱ አደራጅቶ እሴት ወንድ፤ ትንሽ ትልቅ ሳይል እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ የነጻነት አርበኛ ሆኖ፤ የብዙ ጀግኖችን ህይወት ሰውቶ ትልቅ ታሪክ ሰርቷል። በዚህ በፈሰሰው ደሙ እና በተከሰከሰው አጥንቱ ለዛሬ መመኪያ የሆነችንን ጎንደርንም፤ ኢትዮጵያንም አዉርሶናል። ለሶስት መቶ አመታት 27 ነገስታት ያገለገሉበትን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ኩራት የሆነውን የመጀመሪያዉን የጎንደር ቤተ መንግስት የገነባዉም ይኽው በአንድነቱ ሲወደስ የኖረው አማራዉ፤ ቅማንቱ፤ አገዉ፤ ቤተ እስራኤሉ፤ ክርስቲያኑ፣ እስላሙ እና ሃይማኖት የሌለዉም ጎንደሬ ጭምር ነዉ።
Fasil , Gonder
ስለ ኋላ ታሪካችን ከአሁን በፊት በወጡት መግለጫዎቻችን ላይ ብዙ ስላልን፤ ለዛሬ ከ“አብዮት” በኋላ የደረሱብንን ማንነታችን አንድነታችን ፈታኝ የሆኑ አሥቀያሚ ገጽታዎችን ማንሳቱ በቂ ነው። ከስልሳ ስድስት አብዮት በኋላ፤ በተፈጠረው የመሥመር ልዩነት፤ ወደ ትጥቅ ትግሉ ለመግባት ከተመረጡት ቦታዎች አንዱ በዚሁ በጎንደር ክ/ሀገር ነበር። በመሆኑም፤ ወደ ትጥቅ ትግሉ ለመግባት የወሰኑትን ከመላ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዜጎቻችን ያሥተናገደው እና በዚሁም ሰበብ ከፍተኛውን የደርግ ቀይ ሽብር ጭፈጨፋ መራራ ጽዋ ከተጎነጩት ክፍለ ሀገራት አንዱ የጎንደር ክ/ሀገር ህዝብ ነው። የማይረሳው የቅርብ ጊዜ አሥከፊው ትዝታችን ደግሞ፤ የትግራይ ክ/ሀገሩ ተወላጅ ገብርህይወት ገ/እግዚአብሔር በፊት የወገራ፤ ሰሜን እና ጭልጋ አውራጃ የጦር አበጋዝ፤ በመጨረሻም የጎንደር ክፍለ ሃገር የደህነት ሃላፊ፤ ግን የወያኔ ሰርጎ ገብ የዉስጥ ነጻ አዉጭ፤ የደርግ ተወካይ በመምሰል ከነመላኩ ተፈራ ጋር ተባብሮ በከተማም ሆነ በገጠር እጅግ ብዛት ያላቸው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መጨረሱ ነው። ይህን ሁሉ የቅጣት ዋጋ ያስከፈለን፤ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ወንድማችን እህታችን ብለን ማስተናገዳችን ብቻ ነዉ። ጎንደር ሌላ ጥፋት የለዉም፤ በዘር ሳይደራጅ ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ! በማለቱ እንጂ። አሁን ግን በዛብን፤ ባበላን ተነከስን፤ ባስተናገድን ተወረርን። ፍቅራችን እና ትብብራችን ያሥደነገጣቸው ከፋፋዮች ሊያለያዩን ጎሳ ሥለታቸውን ሰነዘሩበን።

በ1991 ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ ዉስጥ ዉስጡንም ሆነ በይፋ ሰርቶ ባዘጋጀዉ ካርታ መሰረት የጎንደር ክልል የነበረውን የሁመራን፤ ወልቃይት ጠገዴን እና የጠለምት መሬታችንን በጉልበት በመውረር ወሰደ። ከቦታዉ የነበረዉን ለዘመናት የኖረ ህዝብ አፈናቀለ። የዘር ማጥፋት ዘመቻዉ አሁንም ቀጥሏል። በአብደራፊ፤ በመተማ እና በቋራ ዘይትና ወርቅ ብሎም የርሻ ልማት ያለበትን የጎንደር መሬት ለመዉሰድ በኢንቬስተር (INVESTOR) ስም ለወያኔ ካድሬዎች በገፍ እዬቸበቸበ ነዉ። ተወላጁ የጎንደር አራሹ ገበሬ እየተፈናቀለ፤ እየታሰረ፤ እየተገደለ፤ እየተሰደደ፤ አንዴ የትግራይ መሬት ነዉ፤ ሲያሰኛቸዉ በመተማ በኩል ያለውን ደግሞ የቤኒሻንጉል ነዉ፤ እያሉ ግማሹን ለራሳቸዉ የቀረዉን ለሱዳን ቆርሰዉ እያስረከቡ ደካማ እና ታሪክ የሌላት ጎንደርን በፈለጉት መንገድ ሊሥሏት እየተዘጋጁ ነዉ። አሁን ያመጡት የመጨረሻዉ ጥቃት ደግሞ ግማሹን የጎንደር መሬት ሲነጥቁ የቀረዉን ጎንደሬ ቅማት እና አማራ በሚል ማለያየት የጠነሰሱት እኩይ የጥፋት ሴራ ነዉ። አማራዉን በኢትዮጵያ በአራቱ ማዕዘን አዳክሞ አገር የማጥቃት እስትራቴጂ ዋንኛው አካል ነዉ። ላለፉት 23 ዓመታት መላዉ የጎንደር ህዝብ ጎንድር አንድ ነዉ፤ ጎንደር የቅማንት የአማራ፤ የቤኒሻንጉል፤ የአገዉ፤ የቤተ እስራኤል አገር ነዉ ብሎ በዘር መከፋፈልን በጽኑ ተቃዉሞ ቆይቷል። በወቅቱ ወያኔ የመለመላቸዉ በጣት የሚቆጠሩ የቅማት ተወላጆች በዋና ከተማዋ ጎንደር ሲኒማ አዳራሽ ስብሰባ ሲጠሩ ሁሉም የከተማዉ ህዝብ ቅማንት ነን ብሎ ከአዳራሹ ገብቶ ግራ እንዳጋባቸዉ ሁላችሁም ታዉቃላችሁ።

አሁን ግን እነሱ ከገቡ የተወለዱና ሲገቡ ወጣት እድሜ የነበራቸው የተወሰኑ ወጣቶችን፤ እንዲሁም ጥቂት አዛዉንት እና ምሁራንን ለሂደቱ አዳማቂ እንዲሆኑ በዘረኛነት አጥምቀዉ ጎንደርን፣ አማራ እና ቅማንት በሚል ካርታ ለይተዉ የጎሳ እሳት መለኮስ ጀምረዋል። ለበለጠ ጥፋትም ተዘጋጅተዋል። ይህን እሳት ማጥፋት አለብን። የሥራአቱ መራሽ የሆኑት ወያኔወችከጀርባ እዬሰሩት ያለዉ ሃቅ ግን እኛን እያዋጉ መሬት ለመንጠቅ እንድሆነ ግልጽና በተግባር የታየ ነዉ። እዉነተኛዉ እኛ የምናዉቀዉ ጎንደሬ የቅማንት ተወላጅ፤ ሁመራን ወልቃይት ጠገዴን ጠለምት እራስ ዳሸንን ወያኔ ወሮ ዘመቻ በከፈተበት የጥፋት ዘመን ላይ መሆናችንን እያዬ፤ ለቅማንት ጎሳ ሌላ ክልል ልፍጠር ብሎ ለአዲስ ካርታ ጦርነት ይገባል ብለን ፍጹም አናምንም። ወያኔ መራሹ መንግሥት ግን ይህን ለማስፈጸም እየሰራ እንደሆነ አንጠራጠርም። እኛ የጎንደር ተወላጆች የገንደርን አብሮነት የጎንድርን ዳር ድንበርና አንድነት ለማስከበር ሃይማኖት ጎሳ ወይም ቋንቋ ሳይለያየን እስከመጨረሻዉ መታገል የግድ ይላል። ከዚህ ያነሰ አማራጭ ጎንደርን የሚያዳክም ብሎም የሚያጠፋ ነዉ ሊሆን የሚችለው። የታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን ወያኔወችንም ተከታዮቻቸዉንም አምርረን ቁርጡን እንገራቸዉ። ሁሉም ጎንደሬ አማራ፤ ቅማንት፤ ቤተ እስራኤል፤ አገዉ፤ ክርስቲያን ወይም እስላም ሆኖ የመኖር ማንነት ማንም የመንፈግም ወይም የመስጠት መብት የለዉም። ይህ አብዛኛዉ የአማረኛ ተናጋሪ ህብረተሰብ ጠንካራ አይበገሬ የኢትዮጵያዊነት አቋም በመያዙ የጥፋት ማዕበል የአገራችን እምብርት በሆነችው ጎንደር ላይ የመከፋፈል ዘመቻ ከፍተዋል። የክፍፍል ማዕበሉ የወያኔን ጎጠኞች እና የዘረኛነት ማቃቸዉን ጠራርጎ እንዲወስድ የጎንደር ህዝብ ተባብሮ መነሳት አለበት።
ወያኔ ቅማንት የሚለዉን የነገድ ስም ከኢትዮጵያ ማህደር ከወረቀት እንዲፋቅ ያደረገዉ፤ ዘረኝነትን ያልተቀበለዉ ጎንደሬዉ ቅማት ዘራፍ ብሎ አምጾ አንቀጽ 39 እንዲቀበል የተጠነሰሰ ሴራ ነዉ ብለን እናምናለን። የቅማንት ምንነት ቋንቋ ወይም የስነ ልቦና ባህላዊ አኗኗር የጎንደር ታሪክ ነዉ ብሎም ተቀብሎ የቆየበት ዘመን እጅግ እረጅም ነዉ ከ፪፬፻፲ (2410) ዓመተ ዓለም ጀምሮ የኢትዮጵያ ነገዶች ቅርስ ሁኖ ቆይቷል። ይህም ኩሽ በተባለዉ ንጉስ የኢትዮጵስ አባት ዘመነ መንግስትም እረዘም ያለ ወደ አራት ሺህ ዓመታት ገደማ ያስቆጠረ ነዉ። አንዳዶች በቅርብ ቀን አንዴ ከኢሽያ፤ ሌላ ጊዜ ከግብጽ መጣ ይላሉ። ግን ኢትዮጵያ 200 ዓመታት 2335 ዓ. ዓ ግብጽን ማስተዳደራን ጠቅሰዉ አይጽፉም።

የጎንደር ህዝብ፤ በተለይም ይህ ትዉልድ የቅማንትን የምንነት መልካም ታሪክ የራሴ ነዉ ብሎ እዉነተኛ ጎንደሬነቱን ይቀበላል። የዘመኑ ዘረኛ ጎጠኞች ግዛታቸዉን ለማራዘም አንዱን ትንሽ ሌላዉን ትልቅ እያደረጉ ያለስም ስም የመስጠት አጉል እና ኋላ ቀር ባህል ፍጹም የዚህ ትዉልድ አቋም አይደለም፤ አይቀበለዉም። ይልቁንም ያለፉትም ሆነ፤ አሁን በግፍ ላይ ግፈ ሞልቶ እስኪፈሥ እየተደራረበ ያለው የመጥፎ አስተዳደር ዉጤት ነዉ ብለን ሁላችንም እናምናለን። የወያኔን የመሬት ወረራ የመስፋፋት ፖሊሲን ለማሳካት ቅማንት እና አማራ ብሎ የጎንደር ክፍለ ሃገርን ሕዝብ ከሁለት ግዛት ለመክፈል የሚካሄደዉን ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን። “ጎንደር አንድ ነዉ” በሚል ተንቀሳቅሰን እና ተደራጅተን የጎንደርን መሬት ለማስመለስ እና አንድነታችን ለማስከበር በጎንደር አንድነት (አብሮነት) ጥላ ስር ተሰባስበን ከመታገል ሌላ ምርጫ የለንም። ጎንድር እንደነበረዉ ያልተሸራረፈ ጎንደር ይሆናል። አገራችን ኢትዮጵያም እንደነበረች ለዘለዓለም በአንድነቷ ተከብራ ትኖራለች።

ይህን ዕራያችን እዉን ለማድረግ ለአንድ ዓመት ጠንክረው በኮሚቴ ደረጃ ሲንቀሳቅውሱ የቆዩት የጎንደር የቅማት ብሔረሰብ ተወላጆች እ. ኢ. አ በ 11/23/14 ዓ. ም በጠሩት የህብረት ጥሪ ተሰባሥበን እጅግ መሳጭ እና የጎንደርንም ሆነ የኢትዮጵያን ታሪክ ጠንቅቀው በሚያውቁ እውቅ ምሁራንና እድሜ ጠገብ ተወላጆችን ያካተተ ውይይቶት አድርገን እንደገና ለበለጠ መጠናከር ለሁለተኛ ጊዜ ሁሉን ጎንደሬ አቀፍ ኮሚቴ ከመሰረትን በኋላ በ12/07/14 እጅግ ብዛት ያላቸውን የጎንደር ተወላጆች ቴሌፎን ሰብሰባ (Tele conference) በመጥራት አራት ሰዓት የፈጀ ጥልቅ ውይይት አደረግን።

በነዚህ ሁለት ቀናት የሥልክ ሥብሰባዎች የተገኙት የጎንደር ተወላጆች የመነጋገሪያ አጀንዳቸው የነበረው ከወልቃይት እና ከራስ ዳሸን ወደ ትግራይ መከለል በኋላ ሌላ የጎንደርን አንጀት እንደመዘርገፍ የሚያስቆጥረውን የቅማንትን ብሔረሰብ ከሌላው ወገኑ ለይቶ ለማዋቀር የሚደረገውን አደገኛ እና ወደ ተግባር ሊቀዬር ሲሞከር ሊያመጣ የሚችለውን የሕብረተሰብ ቀውሥ በተመለከተ ነበር።
በነዚህ ሥብሰባዎች፤ የታየው ብሔራዊ ስሜት የተጠበቀም ቢሆን፤ በየአንዳንዱ ተናጋሪ አንደበት ይወጣ የነበረው ፍቅር የተላበሰ፤ ከአንድነት እና ከአብሮነት የተወረሰ ወኔ ቀሥቃሽ ሐሳብ በሲቃ እና በሃዘን የተቀላቀለ ነበር። በተለይም፤ ከታች አርማጭሆ እና ከላይ አርማጭሆ የቅማንት ተወላጅ ካልሆኑ የእድሜ ብቃት ካላቸው አዛውንቶች የተሰማው ልብ የሚበላ ሃሳብ እንዲህ የሚል ነበር፤ “እነ ፊታውራሪ አየለ አባ ጓዴ፤ እነ ደጃዝማች ጣሹ፤ አገራቸው ሲደፈር አሻፈረኝ ብለው፤ ሰላቶን ለረዥም አመታት የተዋጉት የቅማንትን ተወላጅ ብቻ ይዘው አልነበረም። አገሬን ለሰላቶ አላሥደፈርም፤ ለነጭም አልገዛም ያለውን ኩሩ ኢትዮጵያዊ በመምራት እንጂ። በዘመነ ኃይለሥላሴም ዘመነ መንግሥት፤ እነ ሹምዬ በቀለ፤ እንደሻው ቦጋለ፤ ግራዝማች ካሰኝ አለማዬሁ፤ ልጅ ደምረው ጣሹ፤ ተፈሪ ንጉሴ እና የመሳሰሉት ለፓርላማ አባልነት በጎንደር ከተማ እና የተለያዩ አውራጃዎች ተወዳድረው ሲያሸንፉ የነበሩት፤ በቅማንትነታቸው ፤ በቅማንቱ ሕዝብ ብቻ ተመርጠው ሳይሆን፤ ሁሉም የጎንደር ሕዝብ የዘር ሃረጋቸውን ሳይመዝ በእውቀታቸው እና በችሎታቸው ይወክሉኛል፤ ጉዳዬን ያሥፈጽሙልኛል በሚል መርጧቸው እንጂ” በማለት የአንድነት ኩራታችን የሆነውን የሩቅ ጊዜ ትዝታ ታሪክ በመጥቀሥ፤ በዚያን ዘመን የነበሩትን ታሪክ ሰሪዎች በማወደሥ፤ አንድነታችን ዛሬም በሚያልፍ መንግሥት፤ የማያልፍ ሥም እንዳንፅፍ፤ በሚል ለዚህ ትውልድ አደራነታቸውን አሥተላልፈዋል።

በአጠቃልይ፤ በነዚይ ሁለት ቀናቶች በተደረገው የሥልክ ስብሰባ (Teleconference) በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ በመሥማማት፤ አገር ውሥጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን እንደሚከተለው የውሳኔ ሃሳባቸውንን አሥተላልፈናል።

1. በአገራችን ኢትዮጵያ ለሃያ ሦስት ዓመት የአገሪቱን ሰላም እያመሰ ያለው የጎሳ ክልል፤ ወደ ጎንደር ሲመጣ ደግሞ እጅግ የከፋ እንደሚያደርገው ተገንዝበው፤ የቅማንት ማንነትን ከማሥከበር በመለሥ፤ ራሥን በራሥ የማሥተዳደር ጥያቄን ያነሱ ወገኖች፤ እንደገና ዓላማችውን እንዲመረምሩ።

2. በሰሜን አሜሪካ የደላ ኑሮአቸውን እየኖሩ፤ ከዬትም ዓለም የተሰባሰቡ ህዝቦች፤ ያለ ልዩነት ሲኖሩ፤ የሰው ልጅ በዘሩ ሳይሆን፤ በሰባዊነቱ መከበሩን መረዳት አቅቷቸው፤ ተግባር ላይ ሊውል የማይችለውን የወገኖቻችን የወሰን ጥያቄ እንቅሥቃሴ በገንዘብ የሚያግዙ ሰሜን አሜሪካ ያሉ፤ የቅማንት ተወላጅ ወገኖቻችን፤ የአገር ቤቱ እንቅሥቃሴ ወደ ፈራነው አቅጣጫ ሄዶ የደም መፋሰሥ ችግር ቢፈጥር፤ በታሪክ እንደሚያሥጠይቃቸው አውቀው፤ የያዙትን አቋም እንደገና እንዲመረምሩ እና ከእኛ ጋርም ተቀራርበው እንድንመካከር በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናደርጋልን።

3. የቅማንት እና የአማራ ብሔረሰብ በልማድ በየጎሳቸው ተዋውቀው ቢኖሩም፤ በእምነት፤ በባህል፤ በቋንቋ፤ በታሪክ እንዲሁም በቦታ የተሳሰሩ በመሆናቸው፤ ለያይቶ ለማሥቀመጥ የማይቻል ከምሆኑም በላይ ሙከራው ራሱ የከፋ ታሪክ ጽፎ ከማለፍ በሥተቀር፤ በተግባር ላይ ሊውል የማይቻል መሁኑን የሁለቱ አካባቢዎች ተረድተው አሥቸኳይ መፍትሔ እንዲፈልጉለት።
4. የኢትዮጵያ ገዥው መንግሥትም ሆነ የክልል መሪዎች፤ ይህን ራሥን በራሥ የማሥተዳደርን ጥያቄ ያሥነሳውን የቅማንት ብሔረሰቦች ብሶት በቀናነት ከመፍታት አልፈው፤ ብሶቱን እውነት የክልል ጥያቄ አሥመሥሎ ማሥተናገድ፤ እጅግ ለአካባቢው
4 አለመረጋጋት ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ተገንዝበው በሁለንተናዊ መልኩ የተዋህደውን ህብረተሰብ ሰላም፤ በራሥ አሥተዳደር ሥም ከማደፈረሥ እንዲቆጠቡ።

5. መላው የጎደር ህዝብ፤ በቅማንት ብሔረሰብ ወገኖቻችን የተነሳውን፤ የራሥን በራሥ የማሥተዳደር ጥያቄ አደገኛነት ተገንዝቦ፤ ለዚህ ጥያቄ ያነሳሳቸውን በደል በጋራ እንዲመረምር እና ችግሩን በጋራ ለመፍታት በጋራ እንዲቆም።

6. ሁለቱም የቅማንት እና የአማራ ቤተሰቦች፤ በዚህ በሰለጠነው ዘመን፤ ኋላ ቀር የሆኑ፤ የሰውን ልጅ እንደ ሰው የማያስቆጥሩ አፈ ታሪኮች አሥወግደው፤ የመናናቅ እና ያለመከባበር አጉል ባህል ተላቀው፤ ሥድብ እና ዛቻ፤ ጠብ እና ጥላቻን፤ ብሎም እስከ መገዳደል ከሚያደርሱ ፉክክሮች ተቆጥበው፤ ይህ ሥራዓቱ ያመጣባቸውን የዘር ጣጣ፤ በብልሃት ይዘው ጊዜውን እንዲሻገሩ።

7. ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው በሰላም ያለ ወሰን ለረዥም ምዕተ ዓመታት የኖሩትን ህብረተሰቦች እሥከ ወዲያኛው እንዲለያዩ ከሁሉም አቅጣጫ የውጡልኝ ጥያቄ ያነሱ ቡድኖች፤ እየሰሩ ያሉትን እጅግ ትርጉም የሌለው እንቅሥቃሴ አቁመው፤ በዚህ ምክንያት በአካልም ሆነ በህሊና የበደሏችውን ወንድሞቻቸውን፤ በአካባቢው በተመረጡ ሽማግሌዎች አማካኝነት ይቅርታ ጠይቀው፤ የአካባቢውን ሰላም እንዲያረጋጉ።

8. እጅግ አሳዛኝ እና ከሰባዊ ተፈጥሮ ውጭ በሆነ መልኩ፤ ዛሬ የሰው ህይዎት ቀርቶ፤ የእንሰሳት ህይዎት ክብር እያገኘ በመጣበት ዘመን፤ በኮምፒተር ጀርባ፤ በፌሥ ቡክ፤ “የማን አባት ጎበጠ” አይነት ፉክክር የሳይበር ጦርነት የከፈቱ የቅማንት ተወላጆች ነን የሚሉ ጥቂት ግለሰቦች፤ ወደ ህሊናቸው ተመልሰው፤ ጦርነት ጥፋትን እንጂ ልማትን እንደ ማያመጣ ተረድተው፤ ወደ ሰላማዊ ህሊናቸው እንዲመለሱ።
የሚሉትን እና የመሳሰሉትን የውሳኔ ሃሳቦች ከተሰነዘሩ በኋላ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን በመላ አገሪቱ እያመሰ ያለውን ጊዜው ያለፈበት የጎሳ ፖለቲካ ፋሽን በመተባበር አውልቆ እንዲጥል እና ሁሉም በጎሳ በረት ሳይዘጋ፤ በመላው የኢትዮጵያችን ክልል ተከባብሮ እና ተፋቅሮ በፈለገበት ቦታ በኩራት የሚኖርበትን ሥርአት እንዲፈጥር የትግል ጥሪያችን እናሥተላልፋለን።
እንዲሁም መላ የጎንደር ተወላጆች፤ ይህን የሕዝባችን አንድነት የመጠበቅ ቅዱሥ ዓላማ፤ ያላችሁን የአገርቤት ግንኙነት መሰመር በመጠቀም፤ የበኩላችሁን ድርሻ በመወጣት እንድትተባበሩ አደራ እንላለን።

በጎንደር ክ/ሀገር እየተለኮሰ ያለው የጎሰኝነት እሳት ያሳሰበን በውጭ አገር የምንተኝ የጎንደር ክ/ሀገር ተወላጆች ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ።
Gondar-Unity-forum+noreply@googlegroups.com

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live