Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የወያኔ በሬ ላም ወለደ። ከ-ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

Ketemaበተለያዩ ጽሑፎቼ ለመዳሰስ በተወሰኑ ነጥቦች ሲሆኑ የማብራራት እና ሃሳብን በማሳደግ ዙሪያ እንዲሁም አስተያየትን በመስጠቱ ጉዳይ እንዲሁም የምታውቁትን የማሳወቁ ጉዳይ የአንባቢያን ይሆናል።

አፈ ዲሞክራሲ አፍነህ ግዛሲ የሆነው በኢሕአዲግ ስም የሚንቀሳቀሰው TPLF አውራ አውራ የሚባሉትን የኦሮሞ ህዝብን የሚወክሉ የአማራን ህዝብ የሚወክሉ የደቡብን ህዝብ የሚወክሉ እና የትግራይን ህዝብ  የሚወክሉ ጥምር ስም እንደሆነ እላይ እላዩን ሁሉም ህዝብ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። እላይ እላዩን ያልኩበት ምክንያት ከላይ በጠቀስኳቸው ስም ምክንያት ማሊያ ለብሰው የሚጫወቱ የTPLF ሰዎች ስለሆኑ ኢሕአዲግ የሚለው ስም ከስምነት ያለፈ  እንደሌለው ለማደናገሪያነት ከመዋል ውጪ ምንም ፋይዳ እንደሌለው ስለሚታወቅ የላይ የላዩን የውጪ መንግስታትን እና ህዝብን ለማደናገር በጭቃ ቤት ላይ የአሸዋ ግርፍ ተገርፎ የድንጋይ ቤት ነው ብሎ እንደመዋሸት ያህል ወያኔ ኢሕአዲግ የሁሉ ብሔር ብሔረሰቦች የእኩልነት ድርጅት ነው ብሎ መደስኮር ከጀመረ ሃያ አራት አመት አስቆጠረ።

ልብ በሉ ወያኔ ሃያ አራት አመት ሙሉ የጭቃ ቤትን በአሸዋ ስለተገረፈ ብቻ የድንጋይ ቤት ነው ብሎ እየዋሸ እና እየሰበከን ያለው። አንዱ ነው አሉ ከሚስቱ ጋር ወደ ውጪ ለስራ ጉዳይ ይሄዳሉ ከዛም ይሄ ፓስታ ፒዛ የሰለቸው ባል  እንጀራ አማረኝ ጋግሪና  እንብላ ይላታል። ሚስትም እሺ ትልና ብዙ አመት ውጪ የኖሩትን ጎረቤታቸውን እንዴት እንደሚጋገር ጠይቃ ሁሉን ነገር ገዛዝታ ትመጣለች በኃላም ዛሬ እራት እንጀራ ነው ስትለው ደስ ብሎት የናፈቀውን እንጀራ ለመብላት የራት ሰአትን ይጠባበቅ ጀመረ። እናም እንጀራው ተጋግሮ የራት ሰአትም ደርሶ እራት ይቀርባል። እንጎቻ እንጎቻ የምታክል ነገር ከጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል ዝም ብሎ ሲመለከተው ብላ የውጪ አገር እንጀራ እንደዚ ነው ብላ ኮስተር ስትልበት ባልም ሚስቱን በጣም ይፈራት ስለነበረ ከማነሷ አይን የሚባል የለውም እናም ትኩር ብሎ እያየው ቂጣ ነው ይሄ ነገር ብሎ ሚስቱን ሲጠይቃት አይደለም እንጀራ ነው ብላ ኮስተር አለች አጋገሩን ስላልቻለችበት አይን የሌለው ቂጣ የመሰለ ነገር ነበረ የጋገረችው። እሱም ሁለቱን ሳብ አድርጎ ሰሃኑ ላይ ካስቀመጠ እና ወጥ ካረገበት በኋላ ትኩር ብሎ የምግብ ሰሃኑን  እያየው እንጀራ ነህ እንጀራ ነህ ተብለሃል ብሎ መመገብ ጀመረ ይባላል። ወያኔም እያደረገ ያለው እንዲህ ነው። አሸዋ ግርፍ ቤት የድንጋይ ቤት ነው ብሎ ይናገራል ህዝቡም የድንጋይ ቤት ነህ ድንጋይ ነህ ብሎ መኖር ከጀመረ አመታቶች ነጉደዋል።

እውነትን እንጂ ውሸትን የማይቀበሉ ለህሊናቸው እንጂ ለሆዳቸው ያላደሩ የአሸዋን ግርፍ ቤት የአሸዋ ግርፍ ነው እንጂ  የድንጋይ ቤት አይደለም ብለው የሚናገሩ በእውቀትም በእውነትም የሚሄዱትን ወይ ከአገር በግድ እንዲወጡ ይደረጋሉ አልያም የእውቀት ሃብታም የገንዘብ ደሃ ሆነው ይኖራሉ፣ ወይም ደግሞ ምክንያት ተፈልጎባቸው ወደ እስር ቤት ይወርዳሉ። እነዚህ ሶስት መንገዶች ሲጠቃለሉ ስለእውነት ብለው ባላቸው እውቀት ትክክለኛ ነገር ስለሚናገሩ የሚታሰሩ ናቸው። ዛሬ ይሄ ሰውዬ ይሄ ሰውዬ ይህቺ ሴትዮ ይህቺ ሴትዮ ተብለው በሃብት ሚዛን ላይ የተቀመጡት የኧሸዋን ግርፍ የድንጋይ ቤት ነው ብለው የተቀበሉት እንደሆኑ ይታወቃል ከጥቂት ባለሃብቶች በስተቀር ያለው ሃቅ ይሄው ነው።ስር ሳይኖራቸው መሰረት ሳይጥሉ በአጭር ግዜ እንደ ሸንበቆ ተመዘው የሃብት  አናት ላይ ደርሰው የምናያቸው የኢሕአዴግ ካባ ለብሰው የTPLF ፖሊሲ የሚያራምዱ ናቸው።

ወያኔ ባለእውቀቶችን እና ባለእውነተኞችን የማይፈልግበት ዋናው ምክንያት የወያኔ አሰራርን የአሸዋ ግርፉን ፈልፈል ፈልፈል ቆፈር ቆፈር አድርገው ይሄ እኮ የጭቃ ቤት ነው ከስር መሰረትም የለውም ምሶሶዎችንም ምስጥ በልቶአቸው በስብሰዋል ስለዚህ ይሄ የግርፉን ቤት አፍርሰን በትክክለኛው መሰረት በጠበቀ ብረት ሁሉም ያለስጋት የሚኖርበት የድንጋይ ቤት እንሰራለን ለዚህም ብቃትም እውቀትን እውነትም አገር ወዳድነትም አለን ህዝብን የሚጠቅም አገርን የሚለውጥ እና የሚያሳድግ ችሎታ እንዳላቸው  እና ህዝቡም እንደሚከተላቸው ስለሚያውቁ ባለ  እውቀተኞችን እና ባለ እውነቶችን አየፈልጉም ወይ ያስራሉ ወይ ከአገር እንዲሰደዱ ያደርጋሉ።

ወደፊት አገር ነጻ በምትሆንበት ሰአት ብቁ መምህራን የሚገኙት ከዩንቨርስቲ ሳይሆን ከእስር ቤት ነው። እስር ቤት ስንል አንድም ከነእውቀታጨው ወይኒ የገቡት አንድም እውቀት ኖሯቸው እንዳያስተምሩ የታገዱት አንድም እውቀት ኖሯቸው ከአገር የተሰደዱት ነው። ህዝቡም በእውቀትም በእውነትም በሰላም እጦትም ታስሮ እንዳይኖር የእስር ቤትን ኑሮ አሸንፈው እንዲወጡ ግፈኝነትን ሰብረው ነጻነትን ለብሰው እውቀትና እውነትን ያስተምራሉ። እዚህ ጋር ግን ከዩንቨርስቲ መምህራን አይወጡም እያልኩኝ አይደለም። እውቀት እና እውነት ያላቸው የድንጋይ መሰረቶች እየተባረሩ እና እየታሰሩ የአሸዋ ግርፎች የሆኑት ግን በማስተማሩም በማደናበሩም ለወያኔ ተመራጭ ሆነው የወያኔ ስራ አስፈጻሚ ሆነው ይሾማሉ የሚለውን ሃረግ እንድትመዙልኝ እፈልጋለው።

ስለዚህ የተማረን የሚጠላ እና የሚፈራ እውነትን የማይቀበል እና የማያውቅ ለህዝብና ለአገር ይጠቅማል ተብሎ መጠበቅ በጠራራ ጸሐይ ዝናብ ይዘንባል ብሎ  እንደመጠበቅ ነው። ወያኔን የኢትዮጵያን ህዝብ ንቀውታል ጠልተውታል፣ ገፍተውታል ጥለውታል፣ ዘርፈውታል በልጽገውበታል፣ ሰልጥነውብናል ሰይጥነውብናል፣ ቂም በቀል አብቅለው  ቂም በቀል ዘርተውብናል። የሃያ አራት አመት ፍሬአቸውን የአሸዋ ግርፍ የማስመሰል ስራዎችን አስቃኝተውናል። ታዲያ ዛሬ ግዜው የሰሩትን የክፋት እና የግፍ ስራ ይቀበላሉ። የዘሩትን ማጨጃቸው የሰበሰቡትን መውቂያቸው የወቁትን ማከማቻቸው ግዜው ደርሷል። የአሸዋ ግርፍ ስራችሁ ተገልጦ ሲታይ መሰረት የሌለው ውስጡ ምስጥ የበላው የበሰበሰ ምሶሶዎች ተገልጠው የሚታዩበት የእውነት ግዜው ደርሷል አስመስሎ እና አስፈራርቶ መኖር ከአሁን በኋላ ተቀባይነት የለውም በአሸዋ ገርፋችሁ የውስጥ ማንነታችሁን ደብቃችሁ የተንኮል ስራችሁን ህዝብ ስለተረዳው የበሰበሱት ምሶሶዎችን መሰረት የሌሌው የአሸዋ ግርፍ ቤታችሁን ገፍቶ የሚጥልበት ግዜ እና እውነትን ከባለ እውቀቶች የምንሰማበት ግዜ ቅርብ ነው።

ሃሰት የእውነት ጠላት ነው። አላዋቂ የባለ እውቀት ጠላት ነው። ወንጀለኛ እውነትን ይፈራል። እውቀት የሌለለውም ባለ እውቀቶችን ይሸሻል። ወንጀለኛ ቢደበቅ ለጥቂት ግዜ መሃይምም ቢያዝ ለተወሰነ ግዜ ነውና ፡- እውነት እና እውቀት አሸናፊነታቸው ለሁል ግዜ ነው ነዋሪነታቸው ለዘለቄታ ስለሆነ ይሄንን እንከተላለን ።

ከ-ከተማ ዋቅጅራ

19.03.2015

Email-waqjirak@yahoo.com

 

The post የወያኔ በሬ ላም ወለደ። ከ-ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.


ለብአዴን አባላት ……ከሰማችሁ …….ከሞግዚት አስተዳደር ተፋቱ! –አንበርብር ከአማራ ሳይንት

$
0
0

tplfአፄ ዮሃንስ ንጉስ ተከለ ጊዮርጊስን ድል ነስተዉ ጎጃም ሲገቡ ራስ አዳል አልተደሰቱባቸዉም ነበርና ራስ አዳል ሸሽተዉ በርሃ ገቡ፡፡ አፄዉ ለራስ ደስታ ተድላ ዘመዳቸዉን ድረዉ በጎጃም ላይ ይሾሟቸዋል፡፡ ሆኖም ግን አፄ ዮሃንስ በራስ ደስታ ተድላ ላይ ሙሉ እምነት አልነበራቸዉምና በስራቸዉ ሐጎስ የሚባል አስተዳዳሪ ሾመዋል፡፡ ራስ አዳል ግብር በዛብን ያለዉን ህዝብ አስተባብረዉ የአፄ ዮሃንስ ሰራዊት ሲያጠቁ በዉጊያዉ አፄዉ የሾሟቸዉ ራስ ደስታ እና ሞግዚቱ ሐጎስ ይገደላሉ፡፡

የሟቾችን አስክሬን ወደቀብር ሲወጣ የራስ ደስታን በእንጨት አልጋ፤ የሐጎስን በአጎበር በተከለለ አልጋ ሲወሰዱ ባለቅኔዉ የጎጃም ህዝብ

“እኔስ ምን ቸገረኝ ካንተ አልዋጋ
እስራኤሉን በእንጨት ወታደሩን ባልጋ”

እያለ ሲቀኝ እንደነበር እና የሞግዚት አስተዳደር መጨረሻዉ ዉርድት እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል፡፡(ምንጭ፡- የንግስና ሥርዓት እና የነገስታት የዘር ሃረግ፤በጥላሁን ብርሃነ ስላሴ)

የሞግዚትነት አስተዳደር ሙሉ አስተዳደር አይደለም፡፡ የይስሙላ አስተዳደር ነዉ፡፡ ሲፈለግ የሚፀና ሳይፈለግ የሚነሳ፣ ያልፀና እና መልካም ፈቃድን ያልተከተለ አሰራር ነዉ፡፡ የሞግዚትነት አስተዳደር ህዝብን ካለማመን የሚነሳ ቢሆንም ዋና ዓላማዉ የራስን የበላይነት ጠብቆ ማቆያ ነዉ፡፡

አፄ ዮሃንስ ጎጃሜዉንና ሆነ ራስ ደስታን ስላላመኗቸዉ፣ የሐጎስ ሞግዚትነት አስፈልጓቸዋል፡፡ የሞግዚት አስተዳዳሪነት ህዝብን ካለማመን እና ከመጠራጠር መጥቶ በመጨረሻዉ ሰዓት ክብር የሚሰጠዉ ለሞግዚቱ ነዉ፡፡

ሕወሓት-ኢህአዴግ በየቦታዉ ከሚሾማቸዉ አስተዳደሪዎች ጀርባ አንድ ሞግዚት እንደሚያስቀምጥ ትንሽ እልፍ ወይም ገባ ብሎ ለመመረመረ ከነደስታ ጀርባ ሺህ ሐጎሶችን መመልከት ይችላል፡፡ በሞግዚት አስተዳደር ስር መዉደቅ ሁለት ጊዜ መሞት ነዉ፡፡ አንድ ጊዜ ተንቆ እየተደገፉ መኖር እና ነፃነትን ማጣት ሲሆን ሁለተኛዉ በህዝቡም ሆነ በገዥወቻችሁ ፊት ታማኝነት ማጣት እና በስተመጨረሻ የራስ ደስታን ዕጣ መጋራት ነዉ፡፡

የብአዴን ሰዎች እኔ ከማዉቃችሁ ሰዎች ጨምሮ ኑሯችሁ የቀንድ አዉጣ፣ አስተዳደራችሁ የሞግዚት አስተዳደር እና ከሁለት ያጣ ወገን የሆናችሁ ናችሁ፡፡ በቅርብ እየሰማነዉ እንዳለሁ ጀርባችሁ ሲፋቅ ግንቦት 7 እየተባላችሁ፣ ታማኝነታችሁን አጥታችኋል፡፡ በእነ ሓዱሽ እየገፋችሁት ያለዉ የሞግዚት አስተዳደራችሁ ወደ ሞት የሚወስዳችሁ ከመሆኑ በላይ እናንተን በእንጨት ሞግዚታችሁን በወርቅ ሲጭኗችሁ ሁለተኘዉ ሞት ነዉ፡፡

ጊዜዉ ወደ ወገን የመጠቅለያ ነዉ፡፡ ያረጁትን የብአዴን መሪዎቻችሁን እርሷቸዉ እና ከአዲሱ የአማራዉ ክልል ትዉልድ ጋር ስለህዝባችሁ ተነጋሩ፡፡ በመንግስት ላይ አሻጥር እየሰሩ ስልጣን የያዘዉን አካል ማንኮታኮት እና ማዉረድ ከእናንተ ይጠበቃል፡፡ እኔ የማምናቸዉ ብአዴን ዉስጥ ሰርገዉ የገቡ የቅርብ ሰዎች አሉኝ፡፡ ድርጅቱን በብዙ ነገር እየበከሉት ቀፎዉን ሲያስቀሩትእያየሁ ብዙ ጊዜ አብረን የድርጅቱን መፍረሻ ቀን ቆጥረናል፡፡ አሁንም አስተሳሰብ ለዉጥ ላይ እያተኮርን በየመስሪያ ቤቱ ብአዴን በሚያካሂደዉ አደረጃጀት እና ስብሰባ እየገባን ሌሎችን በአስተሳሰብ ነፃ እያወጣን ጎድጓዱን አርቀን መቆፈር እንችላለን፡፡

እንደ መዉጫ የሞግዚት አስተዳደርነት መነሻዉ ህዝብን መናቅ እና አለማመን ስለሆነ እንደ ራስ ደስታ ሁለተኛ ሞት ሳንሞት ራሳችን ከሞግዚትና ከአሳዳሪዎቻችን ነፃ እናድርግ፡፡ የብአዴን አባሎች ሕወሓት በተደጋጋሚ ጀርባቸዉን ሲፍቀዉ ግንቦት 7 ናቸዉ እያላችሁ ሳትታመኑ አብራችሁ ልትኖሩ አይገባም፡፡ ከድርጅቱ በአስተሳሰብ በልጣችሁ ሄዳችሁም አልሄዳችሁም ከመጠርጠር እና ካለመታመን ስለማትድኑ ዛሬዉን ከሞግዚት አስተዳደር ራሳችሁን አላቃችሁ ተከተሉን፡፡

 

The post ለብአዴን አባላት ……ከሰማችሁ …….ከሞግዚት አስተዳደር ተፋቱ! – አንበርብር ከአማራ ሳይንት appeared first on Zehabesha Amharic.

ትርትር …. –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

 

ከሥርጉተ ሥላሴ 21.03.2015 /ሲወዘርላንድ – ዙሪክ/

እኔ እላላሁ እንዲህ —- ዓለም „ሰው“ ለሚለው ቃል የሚመጥን፣ አቅም ያለው ድርጊትም ትርጉምም የላትም። ፍቅር ግን አለው።

ጠፋብኝ – መንደሩ

የብትንድር  – ግብሩ፤

ንክንኩ – ዛለእግሩ

ንክንፋስ – ምግባሩ

ትርትር ሆነ – በትሩ።

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

እኮ ስለምን ይለፍ እንሰጠዋለን?! እኮ ለምን ይፈቅድለታል? ምን ለማትረፍ? እያዘንኩ ልጀምረው። እኛ በእኛ ላይ ወይነናል። እኛ በእኛ ላይ ሸፍተናል። እኛ በእኛ ላይ ጥቃት እዬፈጸምን – ይመስለኛል። እኮ ለምን? ምን ለማትረፍ? ሃዘኑ እያርመጠመጠኝ ልቀጥለው – እስቲ። ዘሃ ግራው የጠፋበት ዘመን ….

ወያኔ አሸንፎናል ወይንስ አላሸነፈንም? ወያኔ በመንፈሳችን ላይ ጫና መፍጠር ችሏል ወይንስ አልቻለም? እኛስ የመንፈሳችን ስደት ወደ ወያኔያዊ ማንፌስቱ አድርገነዋልን ወይንስ ነፃ ወጥተናል? ዳኛው ህሊናችን ይበይንበት።

አሁን ለእኔ የዲ/ዳንኤል „የአገው ብሄረሰብ አባልነት ወይንም የትዳር አጋሩ ‚ትግሬነት‘“ ምን ይፈይድልኛል ለእኔ ጉዳዬ ነውን?“ በነገራችን ላይ የአገው ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ሥልጣኔ ጉልህና ደማቅ ድርሻ የነበረው፤ ግን አቅም ያለው ዕውቅና ያልተሰጠው፤ ብዙም ያልተባለለት ነው። ሌላው የማንዲጎ ጎንደር ተወልዶ ማደግ ምንስ ዕሴት አለው? እራፊ የቀረች መሬት አንድ አረም በቀለባት ተብሎ መከራ ማዬት። የመጣው ሁሉ እንደ ጥንቸል ቤተ – ሙከራ መሆኑ መፈጸሚያ አልበቃ ብሎ ብተውት ምን አለ ጎንደርን ባዕቱ እኮ ህማማት ላይ ነው። ስለምንስ ብሩኩ ቡቃያ የበቀለበት ዬባለቅኔው! ዬቴዲ እትብት የተቀበረበት አልተጠቀሰም። አስፈላጊ ከሆነ ለንጽጽርም ይረዳ ነበር – አረም አብቃዩና ፍሬ ዘለቁ። ይገርም ነው። የአቶ ኤርምያስ ግማሽ ኦሮሞነትና አማራነት ምን ጠቃሚ ጠረን አለው?“ ወይንም የትናንት በሥርዓትና በሀገር ደረጃ የተከወነ ዛሬም ያለ ኢትዮጵያን የማጥቃት የውጭ ዝንቅ – ገብ ሂደት ከእኛ ጋር ተዋልደው፣ ተጋብተው፣ ተዛምድው ያሉ ወገኖች እዬነቀሱ „የዚህኛው የዛኛው ብሄረሰብ ሃይማኖት ነገድ አባል አይሁድ ምንትስ ማለትስ ምን አመጣው?“ ለዛሬ ወይንስ ለነገ በረከት ይሆናልን? ዛሬም እዬተሰደድን፤ ዛሬም ጥገኝነት እዬጠዬቅን፤ ዛሬም እርዳታ እዬጠዬቅን፤ ዛሬም ከውጭ ሀገር ዜጎች ጋር እዬተጋባን፤ ልጆች እዬወለድን ትናንት እንዲህና እንዲህ ነበሩ በስተጀርባ እከሌ የሚባል ሀገር ነበር ማለቱ ይገባልን? ነገም እኮ ኢትዮጵያ ተለይታ ደሴት ሀገር ልትሆን አትችልም። አስፈላጊው የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመላው ዓለም ጋር ጠንክሮ ቀጣይ ነው።

ህም! ለነገ ደግሞ ስደተኞችን ለይቶ መተንተኑስ … ክቡሩን የሥጋ – ወደሙ ጋብቻ ከማፈናቀል አንፃርስ ይህ ዝንባሌ  ሃይማኖታዊ ነውን? „ትግሬ“ የትዳር አጋሩ የሆነ ሁሉ በሚፈጽመው የራሱ አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ ተግባር ባለቤቱ እያለ ሌላ መንጠላጠያ ሳቢያ መፈለጉ ምን አስፈለገ? ስለምን በምክንያቱ ላይ አናተኩርም? ለዚህም ነው መፍትሄ አመንጭነታችን ታቱ የሚለው። የሚነካካ ነገር ይፈለጋል። የሚወገዝ ነገር ይፈለጋል። ነገ ደግሞ በዚህ ጎሳዊ ማንፌስቶ ተገደው በጠበንጃ ታፍነው የዕለት ኑራቸውን የሚገፉት እዬተነጠሉ ስደት ይታጭላቸዋል። መልካም ነገሮችም አብረው ይናዳሉ – ጥናት አልባ በሆነ ሁኔታ። የሀገር ሃብትነቱ ይዘላል። ለዚህ ከሆነ የነፃነት ራህቡ … ቁርጭምምጭሚቱ ውልቅ ይሆናል። ዛሬም እኮ መስዋዕት የሚከፍሉ ወገኖቻችን አሉበት። በእግር ብረት ሥር ሆነው ስለነፃነት ግንባራቸውን የሚሰጡ – ማገዶዎች አሉበት። በሌላ በኩልም ዬአካላቸውን ካቴና ችለው ኃላፊነት ወስደውም ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳደሩ፤ ዱላውንም – መፈንከቱንም ግልምጫውንም የወያኔን የቻሉ። ዓይን እያዬ ጆሮም እዬሰማ …. ህ!

ብቻ ለእኔ ዜሮ ሲደምር ዜሮ ወይንም ዜሮ ሲባዛ በዜሮ ሆኖ ነው ያገኘሁት። የሚጠቅመው ለምሳሌ፤  ሥርጉተ በተሰማራችበት፤ ወይንም ኃላፊነት ወስዳ በምታራምደው – እምነት ወይንም የፖለቲካ መስመር፤ ያጠፋቸውን ነገር ነቅሶ በማውጣት፤ በትኖ በመተንተን እሷኑ እራሷን ሞግቶ ማሸነፍ፤ ወይንም እድትታረም ማደረግ ነው እንጂ ሥርጉተ ያደገችበት ማህበረሰብ ወይንም ነገድ አብሮ መወቃት – መታጨድ የተገባ አይደለም። እኔ ላጠፋሁት – ለበደልኩት – ላባከንኩት – ለተሻማሁት ጊዜ ተወቃሿ እኔ ብቻ እንጂ ሌላ ቦታ ስደት መሄድ አያስፈልግም።  „ትግሬነት፤ ኦሮሞነት፤ አገውነት፤ አማራነት፤ ጎጃሜነት፤ ጉራጌነት፤ ሃድያነት፣ እስራኤላዊነት ወዘተ – ወዘተ“ የወል መጠሪያ ነው። በዛ ብሄረሰብ ስንት መልካም ሰዎች፤ ስንት ደጎች፤ ስንት አብነቶች ስንትስ የአደራ ናሙና ዜጎች አሉን? እልፍ ናቸው …

በዛ የማህበረሰብ ማዕቀፍ ስንት አንቱዎች፤ ስንት ሊቀ – ሊቃናት፣ ስንት ቅዱሳን አሉ? እልፎች። …. የተጸዎዖ ስም እኮ የወጣበት ምክንያት እኔን እንዲገልጽ ሆኖ ነው። የወል ሥምም እንዲሁ። ….. የወሉን ሥነ – ሞራል፣ ሥነ – ምግባር ሥነ —- ኑሮ፤ ሥነ – ታሪክ እንዲገልጽ ነው። በአንድ ማሳ አረም ይበቅላል። ፍሬ የሚሰጥም እጽዋትም ይበቅላል። አረሙ ከማደጉ በፊት ዘር እንዳያበላሽ ተነጥሎል ይነቀላል። ፍሬ ዘለቁ ደግሞ እድገቱ እንዳይደናቀፍ ተመጣጣኝ አዬርና ህልው የሚያድርጉ ነገሮች ይሟሉለታል። አሁን እኛ እያደረግን ያለው ግን እንደዛ አይደለም። ሁሉንም አረም እያደረግነው ነው። ትውልድን ለማተካካት ድርሻን በዚህ መልክ መከወን ሰባራ መንገድ ነው። ማንዘርዘሪያ ዬት ይገዛ ይሆን?! ይህ ማለት ግን በዳይም – ተባዳይም፤ የበለጠ እጁን ተጠቃሚ የለም ማለት አይደለም። ከጎሳ ፓሊሲ የሚጠበቁት አሳሮች ሁሉ እስከፈለጋቸው ድረስ፤ በረዶው ሁሉ እስኪበቃው አድቅቆናል ወረራውም – ደቁሶናል። ህልማችን በመሰሉ አይጓዝ ነው ብልሃቱ። ተሽሎ መገኘት የሚባል ብሂል አለ ….

የሆነ ሆኖ „ዛሬ የአማራ ወጣቶች እራሳችን መቻል እንችላለን። ስለዚህ እንገንጠል“ የሚል ጥያቄ እንዳነሱ አንብቤያለሁ። ብዕሯ መከፋቷንም አብራ ጨምራ ግልጻለች። እኔም በተደሞ ነበር ያነበብኩት። እንዲሁም በዚህ ዙሪያ ልንሠራበት የሚገባውን ተግባር እያወጣሁ እያወረድኩ እያለ፤ ቀጣይ ጹሑፍ በተከታታይ ወጣ። ዘር ቆጠራው ቀጠለ። ዝንቅንቅ ያለ- ጭብጡም የተቦጫጨረ – ጉድ። „አይሁድ፣ አገው ወዘተ ወዘተ .. ምንትሶ ቅብጥርሶ“ ምን ያድርጉ እነዚህ ወጣቶች!? ወያኔ በፓሊሲ ደረጃ ጎሳዊ ሶሻሊስትን ንድፈ ሃሳብ ፀንሶ – ወልዶ – አሳድጎ – እዬበተነ እኛ ደግሞ በራሳችን መንፈስ የወያኔ ሃርነት ትግራይን ማንፌስቶ ፍለጋ ስደት ፈቃጅ እንሆንለታለን። እያንዳንዷ የዚህ መሰል ስንጥርና ስንጠቅ ሂደት በኢትዮጵያዊነት ላይ ጫና እዬፈጠረ ስለመሆኑ ከልብ ማሰብ ያስፈልጋል። አንዳንድ ወገኖችን ስታወያዩ ተቆርቋሪነታቸው በሁለመናነት ታያላችሁ። ከዛ – ከዛማ ደስ ብሏችሁ አብራችሁ ስትወያዩ መጨረሻ ላይ መዳራሻቸው ከጎሳቸው ላይ ይሆናል። ስለምን? እኛም አብረን በጎጥ፣ በመንደር ዶክተሪን እንዲህ ብልዩነት መስመር ተመስጠን እዬሠራንበት ስለሆነ። ማርክ ቢሰጥ … ውስጣችን ስለ መውደቁ ማወቅ ቀላል ነው። ለዚህም ነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ጥቃት በሰነዘረባቸው ላይ ተባደግ ዕይታ የሚኖረን፤ አርበኛ በላይነሽን የሚያደንቅ ርዕዮትን አይጨምርም፤ ርዕዮትን የሚል ኦልባና ሊሊሳን አያክልም፤ ኦልባና የሚል አንዱአለምን አያካትም፤ አንዱአለም የሚል አቡበከርን ይዘላል፤ አቡበከር የሚለው አብርሃምን ይተዋል፤ አብርሃም የሚለው አንዳርጋቸውን ይሰርዛል ወዘተ .. ወዘተ ። ቃል የማውጣት አቅም ያንሳል። መርምሩት – ወገኖቼ በትህትህና፤ አቅማችን ዋጥ የሚያደርገውን አሳማውን ዝንባሌ ….

ይህም ብቻ አይደለም በተገኘው አጋጣሚ ክፍተት የሚፈጥሩ ነገሮች መደፈን ሲጋባቸው – ይሰፋሉ።  „ሊቃውንተ ቤተክርስትያን እኔን ሲያስተምሩ „ነብዬ መሃመድ“ ብሎ መጥራት ወንጀል ነው ብለው አልነበረም። ይልቁንም ማዕድ ላይ እያሉ „‘አላህ አክብር‘ ሲታወጅ፤ እኛ ማዕድ ላይ ሆነን አነሱ ግን ፈጣሪያችን ያመሰግናሉ ይሉ ነበር – በአድናቆት፤ ዝናብ ሲኮርፍ እባካችሁ ለእነሱ ንገሩ ድዋ – ያድርጉ፤ እኛም ምህላ ለሁለት ሰባት እናደርጋለን ሲሉ‘ የዓለም ሊቃውንት 100 ድንቅ ካሏቸው የሥነጹሑፍ ምርቶች ውስጥ ነብዬ መሐመድ አንዱ ናቸው ሲሉ ነበር ያነበብነው“ እንዲህ ሁሉም ነገር መጫሪያ ፈላጊ ሆኖ ቋፍ ላይ ባለበት፤ ሆድ በባሳው ወቅት፤ በግልም በጋራ ዕንባን አምጦ፤ አልቅሶ ውሎ በሚያድርበት የጨለመ – ምዕራፍ ላይ ሆነን እንዲህ ባሉ ጠመዝማዛ የአረም ቅንጦቶች መጓዙ ዛሬንም አያበረክትም። ነገንም አያሰመርቅም። የትናንት አደራንም አያሰነበትም። ተከታይም – አያገኝም። አንድ መምህር ለትምህርቱ አጋዢ ማነጻጸሪያ ወይንም መንተራሻ ቢያስፈልገው መንቀሳቀስ እንዳይችል እስር እኮ እዬተበዬነበት ነው – ህም! ሥምም ማዕቀብ – ድንበር ተጣለበት። ወዮ ነፃነት! በለስ ቢቀናሽ ሥንት የቤት ሥራ እንዳለብሽ እስኪ መትሪው —-

እኛም እኮ መሃመድ የሚባሉ ብዙ ደሞች አሉን እኮ። መሃመድ በሚል ሥያሜ የሚጠሩ የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆች አሉን። ወገኖቼ „መሃመድ“ የሚባል ጓደኛ፤ የሥራ ባልደረባ፤ ባለ ሱቅ፤ ጎረቤት ወዳጅ ቢኖራችሁ ሥሙን ስትጠሩ በጥቅሻ ሊሆን ይሆን?! ምን አይነት አሲዳዊ ፍሰት እንደሆነ ለእኔ ግራና ወልጋዳ ነው። ግብጽ ላይ እኮ የቅዱስ አባታችን የአቡነ ተ/ሃይማኖት በክብርና በሞገስ መታሰቢያ አለ። http://en.wikipedia.org/wiki/Tekle_Haymanot። በሀገረ ግብጽ በገዳማት ያሉ ደናግል ሆኑ ማህበረ ምዕመናኑ መጠሪያም እንደ ሀገራቸው የአጠራር ዘይቤ ሲሆንም ቋንቋውም እንዲሁ። ዘልቀን ብንገባበት ያነንም እንወነጅል ይሆን? የትኛውም ዓለም ቅዱስ ጊዮርጊስ መታሰቢያ ብቻ ሳይሆን እልፎች ይጠሩበታል። … እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ስለምን ሃጢያተኛ በዛ? ለሚለው ዲያቢሎስ ስለሚያስታቸው ነውና ስለምን ከዲያቢሎስ ጋር እርቅ አታደርግም ብላ አምላኳን ፈጣሪያዋን ስለመጠዬቋ ከታምሯ ላይ አለ። የእሷ ጭንቀት ለኢትዮጵውያን ብቻ አልነበረም፤ ለዓለም እንጂ። … ቅዱሳን ሀገር የላቸውም፤ የትም ቦታ በዬትኛውም ሁኔታ ሊፈጠሩ ሊላኩ ይቻላሉ።

እንዲህ መላ ተቋማት ኢትዮጵያዊነትን የሚያውጁ በመንፈስም በአካልም ጦር በተመዘዘባቸው ወቅት „ወደ ማንነት ማዬት“ አምራጭ የለሽ መፍትሄ ሆኖ ሳለ፤ የቁርሾ ጉድፍ መበተን በፍጹም ሁኔታ ከትውልዱ ድርሻ ውጪ ነው – ለእኔ። እርግጥ የበለጠውን ጉዳት የሚያውቁት የዬአካባቢው ተወላጆች ስለሆኑ፤ ለመረጃ ልውውጥ ካልሆነ በስተቀር ለነገ የኢትዮጵያዊነት አቅም መቅኖ ግን የግልሰቡን ጎሳ ወይንም ባዕት እዬነጠሉ ማቅረብ፤ ተጠያቂም ለማደረግ ማስላት እጥፍ ድርብርብርብ ኪሳራ ነው። የዚህን የእኛ ትውልድ ዋንኛ የተልዕኮም ዕጣም ሆነ አቅጣጫም ቅርጭጭታም፤ ቀጫጫም ያደርገዋል – ባይ ናት ሥርጉተ – ሥላሴ።

ሰው በማንነቱ፣ በእሱነቱ፣ ከውስጡ ነፃነት እንዲሰማው ያስፈልጋል። ሲተችም፣ ሲጽፍም ነፃ ሆኖ መፃፍ የሚችለው በዚህ መንፈስ ሲሆን ብቻ እንጂ ገና ከዚህ አካባቢ እትብቴ ስለተቀበረ፤ ወይንም ሃይማኖቴ ይህ ስለሆነ ወይንም ነገዴ ይህ ስለሆነ፤ ወይንም የትዳር አጋሬ እንዲህ ስለሆነች ብሎ ስጋት ሊኖርበት አይገባም። ቀጥ ብሎ ለመቆም በራሱ የተማመነ፤ ማንነት ካለ እራሱን ገልጦ ውስጡን ማሳዬት ይቻላል። ውስጡን ማዬት ከተቻለ የጎሸውን ለማጥራት፤ እንክርዳድና ግርዱን መለዬት ብቻም ሳይሆን ጤናማና አዎንታዊ መንገድ ለመደልደልም ያስችላል። የተጎዳውንም አይዞህ ከጎንህ ነን ለማለት ይረዳል። ይህን እኛው ከነፈግነው ግን የድብብቆሽ ጨዋታ ይሆናል። የድብብቆሽ ጨዋታ ደግሞ ራዕዩን የድቡሽት ቤት ያደርገዋል፤ ርህራሄ – የለውምና። ከሁሉ በላይ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ በፈቃድ እጃችን ሰጥተናል ማለት ነው። ተወረናል። አቅምም አይኖርም የጎሳ ማንፌስቶን የመተቸት፤ የማውገዝና የመታገል። ነገም ወጮፎው ያዬለበት ዳመናማ ነው።

በአንድ ሥርዓት ውስጥ እልፎች ሠርቶ በማደር መኖር ግድ ይላቸዋል። ሌላም ሃላፊነት አለባቸው። እኛ ትተነው የመጣነውን ትውልድን የመተካት። ከዚህ ውጪ አማራጭ የለም። ስደቱም ቢሆን የአንድ ሀገር ህዝብ እንዳለ ሊሰደድ ከቶውን አይችልም። ጫካ ልግባ ቢልም እንደዚሁ። እኛ ደግሞ አንድ የነፃነት አርበኛ እስረኛ ቤተሰብ አብልተን ለማሳደር የምንችል አይደለንም። እንኳንስ ለእልፍ አለንልህ በማለት ለኑሮው መደጎም። ቀላሏን በወር አንድ ብር በዓመት በነፍስ ወከፍ 12 ብር እንደዬአለንበት ሀገር ማዋጣት እንኳን የምንፈቅድ አይደለንም። በእጃችን አለን የምንላት ቤሳ ሳንቲም የለንም። አቅም ያለው እራሱን በራሱ የሚያስተዳደር ተቋም ለዘር – የለንም። እንኳንስ ከዚህ የላቁ ነገሮችን ለመከወን። ፕሮጀክቱን ለመዘርጋት ቢታሰብም እንኳን፤ ፕሮጀክቱ ከመፈጠሩ በፊት ለራዕዩ ቀብረ – ሥርዓት ይታወጃል። /እራሴ ሞክሬ አይቸዋለሁ/  10 ሺህ ወገን በወር አንድ ብር ቢያወጣ 10 ሺህ ይሆናል በዓመት ደግሞ 120ሺህ …. ይሆን ነበር። ከሁሉ በላይ መንፈስን ወጥ አድርጎ የመግራት፤ አቅሙም አንቱ ነበር ተጨማሪ የኃይል አምንጭነቱም ጉልላት ይሆን ነበር። ሌሎችም ዕምቅ ትርፎች አሉበት ምህረት እርቅ ተስፋ ፍቅር ወዘተ … ለማንኛውም መድረስ አለመቻል ነው መጠነ ሰፊው ህዝብ ተጎጂ ሆኖ ግን ሰጥ ለጥ ብሎ እዬተገዛ ያለው። መድረስ አንችልማ? ቅልብጭ ያለው እውነት ቁምነገርም ይሄው ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ቁልጭ ያለ ባርነት ነው ያለው። ዴሞክራሲ ከባርነት ነፃ ለወጡ ሀገሮች ነው። „ እዬዬም ሲደላ ነው።“ የኛው ግን ከጎጥ አገዛዝ ባርነት ገና አልወጣነም። በዚህ ሁለመናው እራስ ከእግር በሆነ ሁኔታ ላይ ሁነን ተጨማሪ ችግር ለዛውም ጥላቻ- ንቀት – ዘር በጣሽ መስመር ስንቀጣጥል ወይንም ስናመርት ውልን እናድራለን። — ምግለት!

ለመሆኑ አዲስ ሥርዓት ተሳክቶ ቢመሠረት ከሥራአቱ ጋር የሠራህ እዬተባለ ደግሞ ሌላ የስደት መንገድ፣ የመከራ ዘመን ልናጭለት ይሆን – ለዚህ መከረኛ ህዝብ? ህ! ዛሬ ሥልጣን ላይ ያለው የትግራይ ወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ ነው። ነገ ይህ ማንፌስቶ አመድ ቢሆን፤ በዚህ ሥያሜ ሥር የነበሩ በሥርዓቱ ውስጥ ሠርተው ለማደር እንደ ሌሎች ይገደዱ የነበሩ የነገዱ አባሎች ወገኖቻችን ከእነሱ ጋር የተገባ፤ የተዋለደ ወገን አብሮ በነቂስ የበቀል መሻሪያ ሊሆን ነውን?! ሃራም ጋብቻ፤ ሃራም ጉርብትና፤ ሃራም አበልጅነት ሊባል ነውን? የጋራችን ልጆች ደግሞ እኮ አሉ። ለማን ነው ድካሙ?! ለቀጣዩ ትውልድ አይደለንም? ልጅነት እኮ የአንድ ነጠላ ቤተሰብ ብቻ አይደለም። ኃላፊነቱ የማህበረስብ ነው። እርክክብ አለ – የትውልድ። እንዲህ ያለ የተጋጋጠ ወይንም ጠረኑ የተነነ – ብዕር ለእኔ አረም የዘራ፣ አረም የሚያመርት፤ አረም የሆነ መንፈስ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነቱን ወዶ ስደት የላከ ነው። እራሱን አጥቷል በፈቃዱ። „ተቆርቋሪነት“ ትልቅ ተልዕኮ አለው። እጅ – ለእጅ፤ ደም – ለደም፤ ሥጋ – ለሥጋ፤ የሚያያዝባቸው ሊቃናተ – ሁነቶች እረቂቃን ናቸው።

እንጃ! እንዴትና እንዴት ይሆን እምናስበው? ከቱግታ ወጥተን ተግ ላይ እንስከን፤ ኢትዮጵያዊነት በዕውን በውስጣችን ካለ፤ እንዲሁም ያ ክቡር ሰንደቅዓላማ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ህግ ስለታሰረበት ወገን፤ — የለበሰው፣ ሰንደቁን ያፈቀረ ምክንያት ተፈልጎ ግዞት መላኩ እያገላበጠ መንፈሳችን – ከቀቀለው። እባካችሁን እራሳችን ‚እራሳችን‘ እንዲቀማው አንፍቀድለት?!!!

ወደ ራሳችን እንመለስ – በአክብሮት። ወደ ክብራችን እንመለስ – በዘንካታ ትህትና፤ ወደ ውስጣችን እንይ – በጀርጋዳ ቅንነት፤ ወደ ሥነ – ትውፊታዊ ህይወታችን እናስተውል – ከልባችን። የውበታችን ረቂቅነት ከልባችን ይግባ፣ ከደማችን ጋር ይመሳጠር – ያውጋም። ግልቢያ – ለፈረስ ነው፤ ስግረትም – ለወንዝ፤ በረራም – ለወፍ፤ የሰው ልጅ አላምጦ መዋጥ አለበት። „አደራ ለዛውም – የሀገር አደራ፤ አደራ ለዛውም – የዜግነት አደራ፤ አደራ ለዛውም የአኩሪ ታሪክ ባላቤትነት መለያነት – የነፃነት አደራ አለብን፤ አደራ ትውልድን ገንብቶ የመተካት ውድ አደራ አለብን። አደራ በመሆን የከበረ የፍቅር ልዑቅ አደራ አለብን“ ለዚህ እንማስን። የጠላትን ጥቃትን የሚቋቋም ሙሉ አኃታዊ ሥነ ምግባርን አምጠን እንውለደው። የጥቃታችን መሠረተ ፍሬ ነገር የጎጥ ዶክተሪን ነውና።

የትም ሀገር የተሰደደ ወይንም ሊሰደድ ያሰበ፤ ወይንም በትምህርት – በጋብቻ፤ ውጪ የሚወጣ ሁሉ መጀመሪያ ፎርሙን የሚሞላው „ኢትዮጵያዊ“ ብሎ ነው። ወያኔ የፈጠረውም ይሁን እኛ እያመጣን ያለው ልጥፍ ልሙጥ ጉድ ለውጭ ሀገር ዜጎች እራሱ ባዕድ ነው። የሚገርመው በዚህ ማንነት ውስጥ ኑሮ ከተደላደለ በኋላ የተገለበጠ እራስን ያልሰጠ መሽሎክ ይታያል። እሱን ህሊና ይዳኘው። ነገም ቢሆን ኢትዮጵያ የሚለው ሥያሜ ይጠፋል ብሎ ማሰብ መሽቶ አይነጋም ማለት ነው። ወይንም አህጉራት ሁሉም ሰባቱ ውቅያኖስ ይሆናሉ ብሎ ማለም ነው። የዕውነት ፍልቀቱ ዳርቻ የለውም። ኢትዮጵያዊነት ዕድሜውን መገደብ አይቻልም። ዘላቂ ነውና … ። የጎሳ ራዕይ በራሱ ጊዜ በመዳህኒዓለም ጥበብ ከስሟል። በዬትም ዓለም ከእንግዲህ እንደበፊቱ ቁልምጫ የለም።

ለማንኛውም መለመድ ያለበት መንገድ ለዛሬም ለነገም፤ የትኛውም ወገኔ እኔ ባጠፋሁት፣ በፈጸምኩት ስህተት ብቻ ሳይሆን፤ ስህተት ነው ብሎ ባሰበው ወይንም በሚመስለው ወይንም ስህተት ነው በሚለው ቢፈልግ ይክተፈኝ፤ ይተርትረኝ፤ ይፍለጠኝ፤ በመዶሻ ይቀጥቅጠኝ። ከቻልኩ ሙግቴን አቀርባለሁ፤ ከናቅሁት ደግሞ እተወዋለሁ፤ ነገር ግን ዕትብቴ የተቀበረበት ክ/ሀገር ሆነ ነገዴ ወይንም የሃይማኖቴን ዶግማ ግን መንካት የለበትም። በፍጹም። ትዳሬና አካሌም። ደግሞ ነፃነት የዘር ሀረግ ቆጠራ ቀመር አይደለም። ነፃነት ያደገና የሰለጠነ – ሰው የመሆን፤ እንደ ሰው ለመኖር ፈቃዱን ሰው የመስጠትም ሆነ የመንሳት መብት እንዴለለው የሚገልጽ ልዩ ክስተታዊ የእኩልነት አምክንዮ ነው። ነፃነት በጭነት አይተረጎምም። ጓዘ ቀላል ነው።  ….

በመጨረሻ እምለው ኢትዮጵያ ሀገራችን የአድምታ ሚስጢር ልዑላን ዲታ ናት – ተርፎም ይናኛል። ንባቡን፣ ትርጉሙን፤ ማመሳጠሩን ዓራት ዓይናማዎች አሉበት። ክህነተ ሥልጣን የመስጠትም የመነሳትም አቅም ያለው ሃይማኖታዊ ዶግማ በማስፈጸም ከአቨው ነው። ለነገሩ ሥልጣነ ክህነት ሰውኛም አይደለም። „ካልተሠራበት እሳት ሆኖ ያቃጥላል“ ይላሉ – አቨው። ጠያቂውም መዳህኒተአለም ነው፤ እንደ ሥራው ይላል መጸሐፉም። ባለቤቱ „ቅብዕ – ሥልጣኑን“ ቢያረክሰው እንኳን „ተመሥጥሮ ክብሩ አለ“ ይላሉ – አቨው። ስለዚህም „አትዳፈሩት!“ ብለው በአፅኽኖት ይመክራሉ። ለነገሩ እኔ „እኔን“ ሳከብረው ሌላውም እኔን ያከብረኛል። እኔ ሌላውን ሳከብረው ከሌላው ጋር ያሉ መንፈሶች ሁሉ እኔን ያከብሩኛል። ስጥለው ክብሬን የትም ደግሞ ሁሉም የክብረት መንፈስ ይሸሸኛል።

እህ! ሌላስ ያደግነበት ማህበረሰብ እኮ ታላቆችን ወንዶች ጋሼ፣ አይዋ፤ እያያ፤ ጥላዬ፣ ጋሻዬ ብለን አክብርን አቆላምጠን አልበረንም የምንጠራው፤ ሴቶችን እትዬ፣ አቫዬ፣ እቴ-ወለላዬ፣ እታታ፣ እታለም፤ እቴዋ፤ እቴ-አባባ፤ እቴ-አንጀቴ፤ እቴ-ማሬ አልነበረም? ብልህ አዋቂዎችን፤ ማር፣ ቀኝ ጌታ፤ የኔታ፣ ብላቴ፣ ጌታ፣ አለቃ አልነበርንም፤ እንኳንስ ዬሥርዓተ – ቤተክርስትያናት ዓዕማዳተ – ሃውልተ – ሚስጢራት ያለበት „ዲቁና“ ወይንም „ነብይነት“። እንደ ወርዳችን እና ቁመታችን ልክ ቢኖረን መልካም ነው። ልቅነት የእኛ አልነበረም። ጎንደሬም ሲተርት „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላል። ልብ ይስጠን አምላካችን። ከእኛ በመንፈስ በላቀ ጥንካሬና ጽናት ሆነ፤ በማገዶነት የተሻለውን የሚያደርጉት ግን ያልበሉትን ዕዳ እንዲከፍሉ የተገደዱትን አዲስ የትውልዱ – የዘመኑ ባለቤቶች /ግርድ – ድቃቂ – እንክርዳድ/ እዬዛራን አናምሳቸው – እባካችሁን /// //////  መሸቢያ ሳምንት – ለእኔዎቹ። ውዶቼ ዘሃበሻ! እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

ኢትዮጵያዊነት አሸናፊ ቀለማም ማንነት!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

The post ትርትር …. – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

ማነው አሸባሪ የትግሪይ ነጻ አውጪ ግንባር? ወይስ ኢትዮጵያዊው ግንቦት ሰባት? –ከሳሙኤል አሊ

$
0
0

samuelየትግራይ ነጻ አውጪ  ኢትዮጵያን መምራት ከጀመረ 24 አመታትን አስቆጥራል። በዚህ የጭለማ ዘመን ኢትዮጵያዊው በወያኔ  ጭፍን ጥላቻ  እንደ ጭቃ እየተረገጠ መገዛት ከጀመረ አመታቶች ተቆጠሩ። እነዚህ ጨለምተኞች በአፋቸው እውነት የማይናገሩ ልቦናቸው ቂም ያረገዘ፣  አእምሮአቸው በክፋት የተመረዘ፣  የአስተሳሰብ ደሃ፣ ዘረኛ እና ዘረኝነትን በሰው ልቦና የሚዘሩ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ የተጠሉ የደደቢት በቆልቶች ናቸው::

ኢትዮጵያን  ከTPLF  አፓርታይድ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት የሚታገለው ግንቦት 7 አሸባሪ ነውን? እስቲ በከፊል እንመልከት፡-

ወያኔ ያሰመረው መስመር አለ ያም መስመር ኢትዮጵያን የሚያጠፋ መስመር ነው። ህዝብን ከህዝብ ጋር፣ ዘርን ከ ዘር ጋር፣ ጎሳን ከጎሳ ጋር፣ የሚያጋጭ መስመር ነው። ኢትዮጵያኑ  ሀይማኖታቸውን በነጻነት እንዳያምኑ  የሃይማኖት አባቶችን እንዳይመርጡ በነጻነት ፈጣርያቸውን እንዳያመልኩ  የሚያደርግ መስመር ነው።  ዜጎች ሲኖሩበት ከነበረው ቄያቸው ካለበቂ ካሳ የተወሰኑ አካላትን ለመጥቀም ሲባል ብቻ ለልማት በሚል ሰበብ ማፈናቀል እና የጎዳና ተዳዳሪ ተመጽዋች የሚያደርግ መስመር ነው። ነፍስ ጡር እህቶቻችንን አጥንታቸው እስኪሰበር የሚቀጠቅጥ መስመር …መብታቸውን የጠየቁ የነጻነት ታጋዮችን  ወደ ጭለማ ቤት የሚወረውር መስመር… ኸረ ስንቱ ተጠቅሶ ይቻላል…።’

ይሄን የባርነት እና  የሽብርተኝነት አገዛዝ  አይኑን በጥቁር ጨርቅ ሸፍኖ ምንም እንዳልተፈጠረ እራሱን አሳምኖ የሚቀበል ካለ ወያኔ ከደገሰው ድግስ መመገብ ይችላል ወያኔ ከካበው የእንቧይ ካብ መሰቀል ይችላል።

ከመስመሩ  ውጪ የሆኑትን ሁሉ ተለጣፊ ታርጋ እየተስጣቸው አንተ ግንቦት 7 ነህ፣ አንተ ኦነግ ነህ፣ አንት ኦብነግ፣ እያሉ የፖለቲካ እንቅስቃሲያቸውን ለማጥፋት ይጠቀሙበታል። እውን ግን በዚህ በማፈን ስራ እና  በማጠልሽት ድርጊታቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ሊያቆሙት ይችላሉን?

የወያኔው መሪ በአንድ ወቅት  ጠንካራ ተቃዋሚ የለም ብለው በተናገሩ ማግስት መሬት  ያንቀጠቀጠ  ደጋፍ  ያገኙት ቅንጅቶች ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ  በምርጫ በካርድ አሳያቸው ይሄን ያዩ ጊዜ ወደ ሚኒሊክ ቤተመንግስት በታንክ እንጂ በካርድ መች ገባን በማለት የተሰረቀው ድምጻችን ይመለስል ብለው አደባባይ በወጡ ሰላማዊ ዜጎቻችን ላይ  ግንባራቸው ላይ 11 ቁጥር ታፔላ ባስገጠሙ አጋዚ  ወታደሮች በጠራራ ጸሃይ በጥይት ተቆሉ የንጹሃን ደም በየጎዳናው ፈሰሰ  ያን ጌዜ ነበር የኢትዮጵያ ህዝብ በመረጣቸው አካላት ሊመራ  እንደማይችል በመረዳታቸው   ይህን መሰዋትነት ለመክፈል  የተዘጋጁ በጥቂት ግዜ  ውስጥ  ግንቦት 7፣ አርበኞች ግንባር እንዲሁም ሌሎች  ብረት አንስተው ወደ ጫካ ተመሙ። ይሄም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የህዝብ ቁጣ  ሲያዩ ውስጣቸው ተሸበረ ስራቸውንም  ስለሚያውቁ  መርዘኛ ተግባራቸውን  ማሰራጨት ጀምረዋል።

ወያኔ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ግልጽ እና እውቀት ያለው እንዲሁም  ሰለ አገር አሳቢውን በተሰመረላቸው መስመር  ላይ ይገቡ ዘንድ ግድ ይላቸዋል። በዚህ መስመር ያልገቡትን በሙሉ  ስም ይለጥፍላቸዋል አንተ ከኢሳት እና ከ ግንቦት7 ጋር   ግኑኝነት አለህ  የሻብያ ተላላኪ ነህ  አልያም እነዚህ ድርጅቶች ትረዳለህ በሚል ሰበብ ክስ ይቀርብባቸውና   ወደ እስር ቤት ይወረወራሉ።

ወያኔ በፖለቲካና ፖለቲከኞች ዙርያ በወያኔ አዙሪት ውስጥ እንዲዞሩ ይጠየቃሉ  በዚህ አዙሪት ውስጥ ገብተው አራሳቸውን አዙረው የኢትዮጵያን ህዝብ አዙሪት ውስጥ እንዲከቱ ይደረጋሉ የለም የወያኔ ፖለቲካ አዙሪት ኢትዮጵያን አጥፊ ነው ስርዓቱም የበሰበሰ የዘረኝነት ፖለቲካ የሚከተል ነው ይህ የዘር ፖለቲካ ደግሞ እንደ ርዋንዳ  ከመጨራረስ እና ከመተላለቅ ውጭ ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት ነገር የለም። ይህ የዘር ፖለቲካ በአንድ አገር የሁሉንም መብት ባለማክበር እልቂትን የሚያመጣ  እንጂ እድገትና ፍቅርን አይሰጠንም። ይሄ  የዘር ፖለቲካ ለመሰረተውም ለሚከተለውም እንዲሁም ለሁሉም ህብረተሰብ በመጠፋፋት የፀፀት ታሪክ እንጂ የወደፊታን ኢትዮጵያን አይጠቅማትም ብለው የፖለቲካ ፓርቲ መስርተው አቋማቸውን በግልጽ አሳውቀው እየተንቀሳቀሱ ባሉት ፓለቲከኞች ላይ በ 24 አመት ውስጥ ምንም ያልተለወጠውን የወደቀ እና የተናቀ  ስራውን በመስራት የአሸባሪነት ስም ሰጥቶ  እስር ቤቱን የንጹሃን ዜጎች ማሰቃያ ካደረገው አመታቶችን ቆጥሩ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አንድ ሆነን የምንሳበት ጊዜው አሁን ነው። ከአሁን በኋላ ወያኔ እያሰረን እየገደለን እንዲኖር ለደቂቃም ቢሆን መፍቀድ የለብንም። ዘርን ከዘር፣ ሐይማኖትን ከሐይማኖት፣ አጋጭቶ  እራሱ ጥግ ሆኖ ሊስቅ የፈለገን  በኢትዮጵያን ምድር ላይ የበቀለ ወያኔ የተባለውን ባንዳ  ጠላት በጋራ ሆነን እናሰወግድ።  ለነጻነት  እና  ለፍትህ  ለእኩለነት የሚታገለው የግንቦት7  መሪዎችን የምናውቃቸው አብረውን የነበሩ ሰለ ኢትዮጵያ  መጽአኢ ተስፋ  ቀን ከለሊት የሚተጉ  ሰለ  አንዲቷ ኢትዮጵያ ሲሉ መስዋት ለመሆን የተዘጋጁ መሆናቸውን ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው። ስለዚህ   የቻልን ወደዚህ የትግል ጎራ እንቀላል። ሁሉም በያለበት ለነጻነቱ ሲል ይደራጅ።  ገበሬውም ሞፈሩን፣ ተማሪውም ብዕሩን፣ አስተማሪውም ጠሜኔውን፣ ነጋዴውም ብሩን፣ ወታደሩም ብረቱን  ያንሳ።  የሐይማኖት ሰዎችም ጸሎታችሁን  ሰለ   ኢትዮጵያ  ብላቹህ በአንድነት አሰሙ  ኢትዮጵያን እና ህዝቧን የሚታደጋት አምላክ አላትና ። ለ24 አመት ኢትዮጵያን ሲያሸብር   የኖረውን ወያኔን እናጥፋ። ሞት  ለዘረኞች  እና  ለዘርዛሪዎች ይሆናል።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

 

ከሳሙኤል አሊ (ከኖርዌይ)

22.03.2015

samilost89@yahoo.com

 

The post ማነው አሸባሪ የትግሪይ ነጻ አውጪ ግንባር? ወይስ ኢትዮጵያዊው ግንቦት ሰባት? – ከሳሙኤል አሊ appeared first on Zehabesha Amharic.

ምረጫ ክርክር 2፡ “የፌዴራል ስርዓተ በኢትዮጵያ”-የግል ዕይታ –ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0

girmaseifu32@yahoo.com; www.girmaseifu.blogspot.com

ተከራካሪዎች፤

  • ካሳ ተክለብርሃን እና አባዱላ ገመዳ                       ኢህአዴግ
  • በኃይሉ ሸመክት እና ደረጀ ጣሰው                      “ድንኩ አንድነት”
  • ተሾመ ወልደሐዋሪያት እና ሰማቸውን ያልያዝኩት         አዛውንት መኢብን
  • ኤርሚያስ ባልከው እና ሰሙን ያልያዝኩት ወጣት             ኢዴፓ
  • አበባው መሃሪ እና አንድ ሰማቸውን ያልያዝኩት           አዛውንት መኢአድ
(ግርማ ሰይፉ)

(ግርማ ሰይፉ)

የሁለት ሺ ሰባት ምርጫ ክርክር ሁለተኛ ክፍል “የፌዴራል ስርዓተ በኢትዮጵያ” በሚል ነው፡፡ በዚህ ክርክር ዙሪያ ስናወራ አንድ ወዳጄ አንድ ቀልድ ቢጤ ነገረኝ፡፡ በዚሁ ቀልድ ብጀምረው ወደድኩ፡፡ በቅርቡ የእንግሊዝ፣ የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ምርጫ አስፈሚዎች ለልምድ ልውውጥ ተገናኝተው ነበር አሉ፡፡ የአንግሊዙ ተወካይ በቅድሚያ አሁን እኛ ምርጫ በብቃት አካሂደን በዚያው እለት ምርጫ ውጤት መግለፅ ችለናል ብለው የደረሱበትን ደረጃ ሲናገሩ፤ የአሜሪካው ተወካይ ደግሞ እኛ ደግሞ ውጤቱን በቀጥታ ማሰራጨት ችለናል ብለው ይናገራሉ፡፡ የኢትዮጵያ ተወካይ (ፕሮፌሰር መርጊያ በቃና ይሁኑ አቶ ነጋ ዱፊሳ አልተገለፀም) ይህ ምን ያስገርማል ብለው በኩራት በእኛ ሀገር ውጤቱ ከምርጫ በፊት ይታወቃል ብለው አረፉት፡፡ የዘንድሮ ምርጫ የዋንጫው ባለቤት የታወቀበት ውድድር መሆኑ ከግንዛቤ እንዲያዝ እኛም እንደ ህዘብ እንደተረዳን ቀልዱ ያሰረዳል ብዬ አምናለሁ፡፡

በዛሬው ክርክር በእውነቱ ያዘንኩት በክርክሩ ፓርቲያችውን ወክለው ለቀረቡት ለአቶ ካሳ ተክለ ብርሃን እና ለአቶ አባዱላ ገመዳ ነው፡፡ በረጅም ዓመት በትጥቅ ትግል እንዲሁመ 24 ዓመት በመንግሰትነት የፖለቲካ አመራር ሲሰጡ የነበሩ ሰዎች የዚህ ሁሉ “ድካም” እና መስዋዕትነት ውጤት ዛሬ ከጎናቸው ሆነው በደህንነት መስሪያ ቤት ፈቃድ ያገኙ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የደረሰበትን የፖለቲካ ደረጃ የማይመጥኑ የፓርቲ ወኪል ነን የሚሉ ሰዎች ጋር ያደረጉት ክርከር ነው፡፡ ማለት የፈለኩት ኢህአዴግ የዚህን ያህል የፖለቲካ ልምድ አለኝ እያለ ልኩ የዚህን ያህል የወረደ እንዲሆን በአንድነት እና በመኢአድ ፓርቲ ላይ ያደረገው ጣልቃ ገብነት ነው፡፡ እንደ እነርሱ አባባል ለሰማዕታት ክብር ለመስጠት የሚያስችል ደረጃ ዲሞክራሲውን ሊያደርሱት አልተቻላቸውም፡፡ ህወሃት ትግል ከጀመረበት ቢቆጠር ከአርባ ዓመት በላይ ተደክሞ የተደረሰው እዚህ መሆኑ አሳፋሪ ነው የሚል የግል እይታ አለኝ፡፡

ለማነኛውም ወደ ክርክሩ ዝርዝር ስንገባ ካለፈው በተቃራኒ መጥፎውን የክርክር ጀማሪነት የወሰዱት “ድንኩን አንድነት” ወክለው የተገኙት አንድነትን በማፍረስ ቀንደኛ ተዋናይ የነበረው ደረጀ ጣሰው እና በኃይሉ ሽመክት የሚባል አንድነት ውስጥ የማላውቀው ወጣት ነው፡፡ በኃይሉ ሽመክትን በእውነት የት ወረዳ የተደራጃ አባል እንደነበር አላውቅም፡፡ ለማነኛውም ሁሉንም የማወቅ ፍላጎትም ሁኔታም የለኝም፡፡ እርግጡ ግን ለክርክር ካዘጋጀናቸው ሰዎች ውስጥ አልነበረም፡፡ አንድነትን ወክለው እንዲከራከሩ በዝገጅት ላይ የነበሩት የአንድነትን ፕሮግራም ጠንቅቆ ማወቅ የግድ ስለሚል ነው፡፡ ለዚህ ዋነኛው ማሳያ “የኮሚሽነር ጄነራል” ትዕግስቱ አወሉ “ድንኩ አንድነት” ፓርቲ ፕሮግራም ለውጥ ካለደረገ በስተቀር የአንድነት የፌዴራሊዝም አማራጭ “ጂኦግራፊ መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም” የሚል አይደለም፡፡ በኃይሉ ስለ ፌዴራሊዝም ጎግል ሲያደረግ ስራ በዝቶበት የአንድነትን የፌዴራሊዝም ግልፅ አማራጭ ለማቅረብ አልቻላም፡፡ የበሀይሉን ለአንድነት ፓርቲ እንግዳነት የሚያሳብቀው ሌላው አንድነት “ሀብታሙ ሰዩም” የሚባል እሰረኛ የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ደረጀ ጣሰው ከዚህ አንፃር  ጥቁር እንግዳውን በሀይሉ ሸመክትን በመራጃ ማቀበል እንዲረዳው የሚጠበቅ አይመስለኝም፡፡ በክርክር አብሮት ስለተገኘ ምሽት ክለብ ወሰዶ እስክስታ/ዳንስ ሊጋብዘው ይችል ይሆናል፡፡ ሌላው የበሀይሉን እንግዳነት የሚያሳየው “ራዕያችን ዋንጫ ነው” የሚለው የቃላት ግድፈት ዋንጫውን እንደ ምርጫ ምልክት የመረጥን ሰዎች በዋንጫው ዙሪያ ያደረግነውን ዝርዝር ውይይት ስለአላገኙት ዋንጫው ከምርጫ ውድድር ምልክትነት አልፎ “ራዕይ” እሰከመሆን የሚደርስ የቃላት ግድፈት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ ለማነኛም በኃይሉ ከፎረም የመጣ፣ በአንድነት ወጣቶች ውስጥ ራሱን የደበቀ የቀበሮ ባሕታዊ መሰለኝ፤ ለማነኛውም በሀይሉ ሊማር የሚችል ወጣት እንደሆነ ለመገንዘብ አልተቸገርኩም፡፡ አንድነትን ወክሎ ለክርክር ይመጥናል የሚባል ተከራካሪ አይደለም፡፡ ለ”ድንኩ አንድነት” ግን ከበቂ በላይ ነው፡፡ በሀይሉ የአንድነት አባል ከሆነ ወረዳውን እና የወርሃዊ ክፍያ የከፈለበትን ፌስ ቡክ ላይ ቢለጥፈው “ከፎረም” የመጣ ከሚለው ጥርጣሬ እተርፋለሁ፡፡

መኢብን በእርግጥ የመሳፍንት/መስፍን መኢብን ነው ወይ? ያስብላል፡፡ እኔ መሳፍንት/መስፍን የሚባል ግለሰብ የሚመራው ፓርቲ በሀገር ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የኢትዮጵያን ሁኔታ የሚረዱ አባላት አሉ ብዬ አላምንም ነበር፡፡ ይህን ለማለት የሚያስደፍረኝ በግሉ የፈለገውን ከማለትና ከማድረግ አልፎ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በጠራራ ፀሃይ ከገዢዎች ጎን ተሰልፎ ሲዘልፍ ተው የሚለው አባል በፓርቲው ውስጥ መኖር አለበት ብዬ ስለማምን ነው፡፡ ለማነኛውም የመኢብን ተወካዮች በተደራጀ መልክም ባይሆን በዚህች ሀገር ያለውን ፌዴራሊዝም ዕፀፆች ለማሳየት ሙከራ አድርገዋል፡፡ ተከፋፍሎ የተሰጣቸው 19 ደቂቃ አንሶዋል ቢሉም በሁሉም ክፍሎች ግምሻ ላይ ሃሰብ አጥሮዋቸው ፈተና ውስጥ ሲገቡ ታዝበናል፡፡ ለማነኛውም ኢህአዴግ ከ24 ዓመት ወዲህ ያመጣው ኦሮሞ፣ ትግሬም፣ ሀዲያም፣ ወዘተ የሌለ መሆኑን በመግለፅ ይህ የኢህአዴግ የአፋዊ ፌዴራሊዝም ተቀባይነት የለውም ማለታቸው እውነት ነው፡፡ ይህ ግን በምንም መመዘኛ መኢብን የሚባል ፓርቲ ለምርጫ መቅረብ ያለበት ፓርቲ ነው ማለቴ አይደለም፡፡ ህዝብ ወክሎ ለምርጫ ለመቅረብ የሚያስችል የፓርቲ አቋም ያለው ፓርቲ ነው ብዬ ከምር ልወስደው አልችልም፡፡ የመሳፍንት ዓይነት ሰው የሚመራው ፓርቲ የፈለገ ጠንካራ ሰው ውስጡ ቢኖር የትም ሊደርስ አይችልም፡፡ እነዚህም ለክርክር የመጡ ሰዎች መሳፍንትን ያላስታገሱ እንኳን ሀገር፣ ቀበሌ ማስተዳደር የሚችሉ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ መሳፍንት የሚመጥነው ኢህአዴግ ስለሆነ ከተቀበሉት ፎርም ሞልቶ እዚያው ቢገባ የሚል አስተያየት መሰጠት ስህተት አይመሰለኝም፡፡

በዚህ ክርክር እንደ ኢዴፓ ውጤታማ ክርክር ለመከራከር የሚያስችል መረጃ ያለው ፓርቲ በግሌ አልገምትም ነበር፡፡ ለዚህ አስተያየቴ መነሻ  የኢዴፓው ልደቱ አያሌው መፅሃፍ ለማጣቀሸ የሚሆን እንደሆነ ስለማውቅ ነው፡፡ ለክርክሩ የቀረቡት ወጣቶች ግን ከልምድም ሆነ ከዝግጅት ማነስ አዚህ ግባ የሚባል ክርክር ማድረግና ነጥብ ማስቆጠር አልቻሉም፡፡ የልደቱን መፅሃፍ እንደ ማጣቀሻ ሳይሆን እንደ ቅዱስ መፅሃፍ ነው የወዱት፡፡ አሁን በኢዴፓ ውስጥ ፊቱን እየለመድነው የመጣነው ወጣት ኤርሚያስ ባልከው ያባከናቸውን ጊዜዎች ለጓደኛው/ከይቅርታ ጋር ሰሙን አልያዝኩትም/ ቢተውለት የተሻለ ይሆን ነበር ብዬ እገምታለሁ፡፡ ለማነኛውም ኢህአዴጎች ለኢዴፓ ባላቸው ቅን ልቦና እና አሁን ለክርክር የቀረቡት ሰዎች ተናዳፊ ያለመሆን ካልሆነ በስተቀር ኤርሚያስ ባልከው በተደጋጋሚ የኦሮሚያ መገንጠል በሚል በቀጥታ ከልደቱ መፅሃፍ የወሰደውን ሃሰብ እንደወረዳ እያቀረበ ለጥቃት እራሱን ሲያጋልጥ ነበር፡፡ ሰሙን ያልያዝኩት የኢዴፓ ተከራካሪ ህገመንግሰት ለማሻሻል አስቸጋሪ መሆኑ ግልፅ ሆኖ እያለ አሁን ኢዴፓ ባቀረበው ዕጩም ሆነ በሌላ መስመር ሊያሳካው የማይችለውን የህገ መንግሰት ማሻሻል ጉዳይ አንስቶ ጊዜ ሲያባክን ነበር፡፡ የዚህ ክርክር ፋይዳ የሚኖረው ለምርጫ ሳይሆን ለእውቀት በሚደረግ ክርክር ቢሆን ነበር፡፡ የኢዴፓው ተከራካሪ ሊብራል ዲሞክራሲ በሚከተሉ ሀገሮች ያለ ፌዴራሊዝም ተፈትኖ የወደቀ በሚል በኢህአዴግ የቀረበውን መሰረተ ቢስ ክስ ተፈትኖ የወደቀ ሳይሆን ተፈትኖ ያለፈ መሆኑ በደንብ ለማስረዳት ሞክሮዋል፡፡ ፈተና ያላለፈው እንኳን 70 ዓመት 24 ዓመት በቅጡ መቆም ያቃተወ ግራ ዘመም ሀገሮች ውስጥ ያለው ፌዴራሊዝም በተለይም አምሳያ የሌለው አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ለዓለም ያበረከትነው ብለው የተመፃደቁበት ፌዴራሊዝም በእግሩ መቆም ያለመቻሉ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ፌዴራሊዝም ልዩ እያሉ የሚያሞካሹ ምሁር ነን የሚሉ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ አቶ ካሳ ተክለብርሃንም ሆነ ድርጅታቸው ኢሀአዴግ ሁሌም የሚያሰቡትን የሚነግሯቸው ምሁራን ስለሚመርጡ ነው፡፡

በኢዴፓ እምነት አሁን ያሉት ክልሎች ስልጣን ያላቸው ፌዴራል መንግሰት አባላት ሳይሆኑ፣ የሰራ ድልድል የተደረገላቸው ምድብ ሰራተኞች መሆናቸው ትክክለኛ ምልከታ ነው፡፡ በእኔ ዕይታ ለዚህ ማሳያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ርዕስ መስተዳደር ከነበሩት ከአቶ ያረጋል አይሽሹም የተሻለ ማሳያ የሚገኝ አይመስለኝም፡፡ ከእርሳቸውም ሌላ በተፈለገ ጊዜ ከክልል ርዕሰ መሰተዳደርነት ተነሰቶ መጥቶ ወደ ፌዴራል መንግሰት የሚመጡበት ሁኔታ በተደጋጋሚ የታየ ነው፡፡ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒሰትራችን በብቃት ማነስ በሚል ከደቡብ ክልል መምጣታቸው፣ እርሳቸውን በብቃት ይተካሉ የተባሉት አቶ ሸፈራው ሽጉጤ ከመለስ ዜናው ሞት በኋላ ከክልል ርዕሰ መስተዳድረነት መነሳት፣ የጋምቤላው ርዕስ መስተዳድር ተነስተው ፌዴራል መስሪያ ቤት ቢሾሙም አድብተው ስደት መምረጣቸው፣ የድሬዳዋ የዙር አመራር፣ የሀረሪ ሀደሬዎችን ማዕከል ያደረገው የመንግሰት አሰያየም፤ ወዘተ እየተመለከትን በምን መመዛኛ የአንድ ፌዴራል አካል የሆነ የክልል መንግሰታት ናቸው ብለን ተጨፍነን ልንሞኝ አንችልም፡፡ የኢዴፓዎች መፈክር በተሳሳተ መስመርም ሆነው – “ዛሬም ይቻላል” የሚል ነው፡፡

 

በዚህ ክርክር የመኢህአድ ተወካይ አቶ አበባው መሐሪ አንድ ሀቅ ተናግረዋል፡፡ ህዝቡን በዚህ ምርጫ ምረጡን እና እንዲህ እናደርጋለን ብለው እስከመጨረሻው ለማሳሳት አልሞከሩም፡፡ በስተመጨረሻም ቢሆን በግልፅ ያሉተ “ምረጡን እና ምክር ቤት ከገባን ወክለን እንከራከርላችኋለን” ነው፡፡ ለወጉም ቢሆን መንግሰት እንሆናለን አላሉም፡፡ በዚህ አባባላቸው የኢህአዴግን ቀጣይ መንግሰትነትን አምነው ተቀብለውታል፡፡ በክርክሩ ከአንድ ፖለቲከኛ በማይጠበቅ ደረጃ የሰሩት ስህተት እና አቶ አባዱላንም ያሳሳቱት “ህዝቡ በአሰር ብር እንዳይታለል” በሚል የሰጡት አስተያየት ነው፡፡ አቶ አበባው መሃሪ በምድር ላይ ያለውን ሀቅ ገዢው ፓርቲ በኢኮኖሚ ደካማ የሆኑተን ዜጎች በተለያየ መንገድ እንደሚያማልል ለመግለፅ ነው፡፡ ይህን ሀሳብ በቅጡ መግለፅ ካልቻሉ በዚህ ደረጃ ባይሉት ጥሩ ነበር፤ አቶ አባዱላም ይህን በዚሁ መንፈስ ከህዝብ ጋር ለማጋጨት ባይሞክሩ ጥሩ ነበር፡፡ ይህን የአቶ አበባው መሃሪን ስህተት ተከራካሪው አቶ ሬድዋን ሁሴን ወይም ሽመልስ ከማል ቢሆኑ ኖሮ አንድ ዶክመንተሪ የሚወጣው ስድብ ይገጥማቸው ነበር፡፡ አሁንም ኢህአዴግ በቀጣይ በኢቲቪ በሚያቀርበው ዶክመንተሪ ከህዝብ ጋር በሚያጋጭ መልኩ ቅስቀሳ አይደረግባቸውም የሚል እምነት የለኝም፡፡ ለማነኛውም “ከፍትፍት እና ከእሳት” ምርጫ ቀርቦዋል አሰበህ ምረጥ ብለው ክርክሩን አጠናቀዋል፡፡

አቶ አበባው መሃሪ በአማካሪነት ያመጧቸው አዛውንት አስተያየት ካልሰጡ ለምን እንዳደከሟቸው አይገባኝም፡፡ አሁንም እንዚህ ጎምቶ የሀገር አዛውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዋነኛ ተዋናይ ለመሆን የሚያደርጉትን ፍላጎት ለመግታት ካልተቻለ በቀጣይ ዋነኛ ተዋናይ የሚሆነው አዲስ ትውልድ እንዴት እድል እንደሚያገኝ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ አቶ አበባው መሀሪም ቢሆን በዚህ ክርክር ደረጃውን የጠበቀ የቀድሞውን መኢህአድ ወክለው ሊቀርቡ አልቻሉም፣ ወደፊትም አይችሉምና በጊዜ ቢያስቡበት ጥሩ ነው የሚል ምክር መለገስ አለብኝ፡፡ አንተን ብሎ መካሪ የሚልም ቢኖር ማለቴ ነው፡፡

ኢህአዴግ ባለፈው እንዳልኩት አዲስ ሀሳብ ሆነ አዲስ ሰው እንደሌለው አሁንም በድጋሚ አሳይቶናል፡፡ ፌዴራሊዝምን በሚመለከት ኢህአዴግ እየደጋገመ ሲናገረው ለራሱም እውነት እየመሰለው የመጣው አሁን የተዘረጋው ፌዴራሊዝም ስርዓት ባይኖር ይህች ሀገር ትበታተን ነበር የሚለው ነው፡፡ መሳሪያ ይዘው ይህችን ሀገር ሲቆጣጠሩ እነርሱ እንደ ፈለጉ ካላደረጓት ይህችን ሀገር ለመበታተን ፍላጎት ነበራቸው የሚባል ከሆነ እውነት ነው፡፡ እነሱ ስልጣን ሲይዙ እኛ በህይወት ያለን ምስክሮች ሀገራችን ቋንቋን በዋነኝነት መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ካልመጣ እንበታተናለን ብለን ተማምለን አናውቅም፡፡ ልክ ነው ህውሃት ለመገንጠል ሃሳብ ነበረው፣ ኦነግም እንደዚሁ የነፃ ኦሮሚያ ሀሳብ እሰከ አሁን አልተወም፡፡ ኦነግ እንደ ድርጅት ይህን ሀሳብ ባይተወውም መሪዎቹ እነ ሌንጮ ለታ ለአርባ ዓመት በኦነግ ሰም የተከፈለውን መሰዋዕትነት እንዴት እንደሚያወራርዱት ሳናውቅ፤ የመገንጠል ሀሳቡን ትተውት አዲስ አበባ ገብተዋል የሚል ወሬ ነፍስ ዘርቶዋል፡፡

ኢህአዴግ የሚባል ድርጅት ይህችን ሀገር ካልመራ ሀገር ትበተናለች ሰላም የሚባል ነገር የለም የሚባል ቅጥ ያጣ ሟርት ምንጩ ምን እንደሆነ ባይገባኝም፤ ይህን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ደጋግመው ሲያወሩት ለራሳቸውም እውነት እየመሰላቸው መጥቶዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ልዩ በሆነ ሁኔታ ብዙ ቋንቋ እንዳለ አድርገው የሚነግሩን ለምን እንደሆነ እሰከ አሁን ለማንም ግልፅ አይደለም፡፡ በሌሎች የዓለም ሀገራት ብዙ ቋንቋ ብዙ ባሕል እያለም ተፋቅሮ መኖር የሚባል ነገር፣ ሀገር የሚባል የጋራ ቤት መስራት እንደተቻለ በፍፁም እንድናውቅ አይፈልጉም፡፡ በአንድ ቋንቋ እየተናገሩም በሰለምና በፍቅ መኖር አቅቷቸው በጎሳ እየተቧደኑ መገዳደል እንደሚቻል በቅርብ ያለች ሀገር ሶማሌ መፍረስ እንዳለም እንደምናውቅ አያውቁም፡፡ ስለዚህ ኢህአዴጎች ተጨፈኑ ላሞኛችሁ እያሉን ነው የሚገኘው፡፡ ይህንኑ መፈክር ነው አሁን ከ24 ዓመት በኋላ ይዘው ለምርጫ ክርክር የቀረቡት፡፡ ለዚህ ነው አዲስ ነገር የላቸውም የምለው፡፡

ለማነኛውም አስገራሚ ሆኖ ያገኘሁት የመከራከሪያ ነጥብ ከአቶ አባዱላ የቀረበው ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ወደ ትጥቅ ትግለ የገባው በቋነቋ መናገር ሲከለከል፣ ባህሉን ማሳደግ ሲያቅተው ነው የሚለው ነው፡፡ ይህ ክርክር በተለይ አቶ አባዱላ ገመዳ ላይ የሚያምር ሆኖ አላገኘሁትም፡፡  ልክ እንደ ትግራይ ልጆች ይህን ብለው ከአዲስ አበባ የኦሮሞ ልጆችን አደራጅተው ቢሄዱ ይህን ሃሳብ ልናከብረው እንችል ነበር፡፡ ለደርግ ሰራዊት ለመዋጋት ወታደር ሆነው በጦር ሜዳ ተማርከው፤ በምርኮ ወቅት ባገኙት የብሔርተኝነት ምክር በሰማኒያዎች መጀመሪያ ጀምረው ባደረጉት የጠመንጃ ትግል አማርኛ አስጠልቶኝ ነው ጫካ የገባሁት የሚመስል አሰተያየት ውሃ አልቋጥር ብሎኛል፡፡ ኢህአዴግ ፌዴራሊዝምን የመረጠው ብዝዓነትን ለማስተናገድ የቻለ ስርዓት ባለመኖሩ ነው ይሉናል፡፡ ይህ ባይሆን ልንበተን ነበር ሲሉን እኔ የሚገባኝ ግን ሊበትኑን ጫካ የነበሩት ግን እነርሱ ራሳቸው መሆናቸው ነው፡፡

ለማነኛውም ሁሉም የሚስማሙበት እኛም ቤታችን ሆነን ሰምምነታችንን የምንሰጥበት ጉዳይ ኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ሰርዓት ብቸኛውም አማራጭ የሚለውን ትተን ጥሩ አማራጭ ነው በሚለው ሰምምነት ያለበት መሆኑን ነው፡፡  ሰምምነት የሌለበት እና በህዘብ ይሁንታ ሊታረም የሚገባው ደግሞ ምን ዓይነት ፌዴራሊዝም? የሚለው ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአንድ ጊዜ ተሰርቶ የሚያልቅ ሳይሆን ህዝቦች በሂደት እያዳበሩት የሚሄዱት በዓለም ላይ ያለ የአስተዳደር ዘይቤ ነው፡፡ ፌዴራሊዝም በህዘብ ብዛትና በመሬት ሰፋት እኩል የሆኑ የፌዴራል ግዛቶች የሚያዋቅሩትም አይደለም፡፡ አንድ ዓይነት ቋንቋም ሰለሚናገሩ በአንድ የፌዴራል ክልል ውስጥ መሆን አለባቸው የሚል ፎርሙላም አይሰራም፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ያሉት ክልሎች መቼም ቢሆን በራሳቸው መንግሰት ሆነው የራሳቸው የተለየ የአስተዳደር ዘይቤ የመሰረቱበት ሁኔታ ሰለአልነበረ፤ በኢትዮጵያ የሚያስፈልገው ምርጥ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚያመጣ እና በተለይ ደግሞ ዜጎች ባልተማከለ አስተዳደር ፍትህና መልካም አስተዳደር የሚያገኙበት፣ በሀገሪቱ ፖለቲካ በቀጥታ ለመሳተፍ የሚያስችል ብቻ ሳይሆን የአካባቢያቸውን ልዮ ሁኔታ ያገናዘበ የእድገትና የፖለቲካ ተሳትፎ ለማደረግ ነፃነት የሚሰጥ ነው፡፡ ይህን ያገናዘበ የፌዴራል ሰርዓት ቢያንስ፤

  • የተለያዩ ህጎች በፌዴራል ክለሎች በሚገኙ መንግሰታት መካከል ሊኖር ይቸላል፡፡ ለምሳሌ የሞት ፍርድን ቀድመው የሚያስቀሩ ክልሎች ሊኖሩ ይችላሉ፤
  • ኦሮሚያን የመሰሉ ትልልቅ ክልሎች ውስጥ ለምሳሌ ቦረና ጅማ የመሳሰሉት አካባቢዎች የገዳ ስርዓት ሞዴል የክልል አስተዳደር እንዲኖር የሚያደርግ አሰራር፤
  • መሬትን ለኤኮኖሚ ጥቅምና ለክልሉ ፈጣን ልማት ሲሉ በነፃ ለኢንቨስትመንት ማቅረብን ጨምሮ ታክስ ክፍያን በተለያየ ምጣኔ ማስከፈል፤
  • የሰለጠነ የሰው ኃይል ወደ ክልላቸው ለመሳብ ሲባል የሚወሰዱ የተለያዩ እርምጃዎች ለምሳሌ የክፍያ ሰርዓት እና የሰራ ቋንቋን ከአንድ በላይ ማድረግ፤ወዘተ

በግልፅ የሚታዩ ልዩነቶች ሊሆኑ ይቸላሉ፡፡

የሁለት ሺ ሰባት ምርጫ አማራጭ ባይኖርም ወጪን ይዞ ገዢውን ፓርቲ ለማንገስ በሁሉም መስክ እየተውተረተረ ይገኛል፡፡ እኔም ሰራ እንዳልፈታ ያለኝን የግል ዕይታ ወርውሪያለሁ፡፡ ሁሉም ላይስማማ ቢችልም ተመዝግቦ እንዲቀመጥ በሚል ያሰፈርኩትን ሀሳብ ተወያዩበት፤ ኢህአዴግ ለውድድር የተዘጋጀበት ዐውድ ግን በእውነት አሰደማሚ እንደሆነ ይቀጥላል፡፡ ይህም ፍርሃቱን ካልሆነ ምን ሊያሳይ እንደሚችል አልገባኝ ብሎ አለሁኝ፡፡

ቸር ይግጠመን!!!

The post ምረጫ ክርክር 2፡ “የፌዴራል ስርዓተ በኢትዮጵያ”-የግል ዕይታ – ግርማ ሠይፉ ማሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኑሮ በአዲስ አበባ (ነፃነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ)

$
0
0

ትናንት ሲያቀብጠኝ ከአንድ ጓደኛየ ሞባይል እነዚያ አይሲስ የሚባሉ ጉግማንጉጎች እነዚያን 21 ክርስቲያን የግብፅ ዜጎች በሊቢያ አንድ የባሕር ዳርቻ ላይ አንገታቸውን ሲቀሉ የሚያሣይ ቪዲዮ አየሁ – እስከመጨረሻው መዝለቅ አልቻልኩምና ግን ዋናው ባራኪ በግራ እጁ የያዘውን ጩቤ ወደ እኛ ወደተመልካቾቹ ዘርግቶ እያስፈራራ ሲዝት አጠፋሁት፡፡
addis-ababa-realethiopia-141
የሰው ልጅ በሰው ልጅ ላይ እስከዚህ መጨከኑ የሚያመላክተን ዋና ቁም ነገር የዚች ምድር ሰዎች የደረስንበት አጠቃላይ መንፈሣዊና ኅሊናዊ ኪሣራ ሊቀለበስ ወደማይችል ከፍተኛ የመጨረሻ ደረጃ መድረሱን ነው፡፡ ለምግብነት የተፈቀዱልንን እንስሳት እንኳን ስናርድ የሚዘገንነንና በዚህም ምክንያት የማናርድ ብዙ እንስፍስፍ ሰዎች አለን፡፡ ሰውን የሚያህል ክቡር ፍጡር ሊያውም በሚከተለው ሃይማኖት ምክንያት ብቻ በስለት አንገቱን ቀንጥሰው ጀርባው ላይ ሲያስቀምጡ ሊሰቀጥጣቸው ይቅርና በደስታ የሚፈነጥዙ “ሰዎች”ን በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ስናይ በሰዎች ተፈጥሮ መለያየት እጅግ እንገረማለን፡፡

“A Message Signed with Blood, to the Nation of the Cross” ይላል የቪዲዮው መግቢያ፡፡ አስፈሪ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በያዙት የመስፋፋት ሂደት ከቀጠሉ ሌሎቻችንም ይህ አስቀያሚ ዕጣ የሚቀርልን አይመስለኝም፡፡ ነገሩ “የፋሲካው በግ በገናው በግ ይስቃል” እንዳይሆን ያሰጋል – እየሆነም ነው እንጂ፤ ከመካከለኛው ምሥራቅ የተነሣ እሳት አፍሪካ ጫፍ ሊቢያና የመን ሲደርስ አያድርስ ብሎ ከመጸለይ ውጪ እኛስ ምን ዋስትና አለን? ይህን ቪዲዮ ከተመለከትኩ በኋላ ለረጂም ጊዜ ሥራየን በአግባቡ መሥራት አልቻልኩም፡፡ ሰው ሆኖ የመፈጠር ዕዳ የቀሰቀሰብኝ የተስፋ መቁረጥ ስሜት መላ ሰውነቴን ወረረው – በአካልም፣ በመንፈስም፣ በኅሊናም እየኮሰመንኩ ስሄድ በምናቤ ይታየኝ ጀመር፡፡ አለመፈጠሬን የመረጥኩበት አንዱና ትልቁ አጋጣሚ ይህን ዘግናኝ ቪዲዮ በከፊልም ቢሆን ያየሁ ጊዜ ነው፡፡

ይህ በአስቀያሚነቱ ወደር የማይገኝለት ዓለም አቀፍ ክስተት በረድ እያለልኝ ሲመጣ ግን የሀገራችን አይሲስ ነጋዴዎች ታወሱኝና ስለነሱ አብዝቼ መጨነቅን ያዝኩ፤ ሁለቱ ተመሳሰሉብኝ፡፡ ደረጃውና ዓይነቱ ይለያይ እንጂ ጭካኔ ሁሉ መጠሪያውም ሆነ ጎራው ያው ጭካኔ ነው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያጵያውያን ኢይሲሶች የምላቸው በወያኔ የተፈጠሩ የዘመናችን ኅሊና ቢስ ነጋዴዎችንና ኑሯችንን ያመሰቃቀሉትን የሙስና አበጋዞችን ነው፡፡ ከወያኔ ቀጥለው የሀገራችንን የቀብር ሥነ ሥርዓት እያፋጠኑ የሚገኙት እነዚህ የቀን ጅቦች ናቸው፡፡

ወያኔ የዘራው ትልቁና መሠረታዊው ችግር የሀገር ብሔራዊ ስሜትን ማጥፋቱ ነው፡፡ ከዚህ በተያያዘም ሰብዓዊነትን ከሀገር አጥፍቷል፡፡ በምትኩ የተስፋፋው ዘረኝነት በወንዝ ልጅነትና በጎጥ፣ በቋንቋና በቤተሰብ መሳሳብ የጥቅም ትስስርን አንግሦ ጥቂቶች በሀብትና በሥልጣን ሽቅብ ሲመነደጉ አብዛኛው ሕዝብ እንጦርጦስ እየወረደ ነው፡፡ ወያኔ ዘረኝነትን በማስፋፋት ብቻ አልተወሰነም፡፡ ለሰው ልጅ ማኅበራዊ እንስሳነት እንደ አያያዥ ስሚንቶ ይቆጠሩ የነበሩ ሃይማኖትን፣ ባህልን፣ የሞራል ዕሤቶችን፣ መተሳሰብን፣ መፈቃቀርን፣ መቻቻልን፣ አብሮ መብላት መጠጣትን፣ … በጥቅሉ አንድን ሰው ሰው ሊያስብሉት የሚችሉ ሰብኣዊና ተፈጥሯዊ ክሮችን በጣጥሶ አንድያውን ሁላችንንም እንደራሱ ዐውሬ እያደረገን ነው፡፡ ከዚህ በሀገር ደረጃ ከታወጀብን የጥፋት ውርጅብኝ ለማምለጥ የምንውተረተር ዜጎች በጣም ጥቂቶች ነን፡፡ ዛሬ የብዙ ሰው መፈክር “ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ” ሆኗል፡፡ አንድ ማስታወቂያ ነበር – “መጀመሪያ ራስህን አድን ለጫማው በኋላ ይታሰብበታል” የሚል፡፡ እኛም “‹ሀ› ራስህን አድን” በሚለው የራስ ወዳድነት መርህ እየተመራን አንዳችን አንዳችንን በልተን ልንጨረስ የቀረን ጊዜ ኢምንት ነው፡፡ በጩቤ አለመተራረድ ብቻውን ከአይሲስነት ተፈጥሮ ነፃ አያወጣም፡፡ “እሳት ካየው ምን ለየው” ነውና በምንም ይሁን በምን የዘመናችን የጭካኔ መገለጫ አይሲስ ሆኗልና ነጋዴዎቻችንና ጃዝ ባዮቻቸውም የንግዱ ዘርፍ አይሲስ ናቸው – ሥውር አራጆች፡፡

ኑሮ በአዲስ አበባ ምን ይመስላል? ሰዎች ለምንና በምን ብልሃት፣ እንዴትስ ብለው በሀብት ይከብራሉ? ብዙኃኑስ ለምን በሀብት ይደኸያሉ? የሀገራችን የሀብት ክፍፍል ምን ይመስላል?አብሮ መኖር ሲቻል መጠፋፋትን ምን አመጣው?

በአሁኑ ወቅት “ሀገራችን ወዴት እያመራች ነው?” ብሎ መጠየቅ ሞኝነት ይመስለኛል፡፡ ይልቁንስ “በጉዞዋ የት ደርሳለች? በብርሃን ፍጥነት እያስነካችው ያለችውን ጉዞ ጨርሳ ወያኔና ታሪካዊ ጠላቶቿ ወዳቀዱላት የመጨረሻ ግብ ለመድረስ ምን ያህል ጊዜ ይቀራታል?” ብሎ መጠየቅ ይመስለኛል አግባብ የሚሆነው፡፡ እንጂ ዕድሜ ለወያኔ ካሣለፍነው የሃያ አራት ዓመታት የጥፋት ጉዞ በመነሣት ወዴት እያመራን እንደሆነ ቁልጭ ብሎ የሚታይ ጉልህ ክስተት ነው፡፡

በአዲስ አበባ ስል በመላዋ ኢትዮጵያ እንደማለትም ቢቆጠርልኝ ደስ ይለኛል፡፡ ለውጥ ሊኖር ቢችልም እንኳን ያን ያህል የጎላ አይደለምና፡፡ እናም በሀገራችን ኑሮ በአሁኑ ወቅት እጅግ የሚሰቀጥጥ መሆኑን በመጠኑ እንመልከት፡፡

በደመወዝ ብቻ መኖር ከቀረ ብዙ ጊዜ አለፈን፡፡ ደመወዝ ስልህ ደግሞ ይግባህ – የመንግሥትንና በሲፒኤ ደንብ የሚተዳደሩትን ማለቴ ነው፡፡ ትላልቅ ደመወዞችን አይመለከትም፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከፈላቸው አሉና እነሱ የኑሮ ግርፋና ሰቆቃው አይነካቸውም፡፡

በአሁኑ ወቅት የዕቃዎች ዋጋ አይቀመስም፡፡ ሠራተኞች ከወር ወር መድረስ ስለማይችሉ ብዙዎች በተራድዖና በልመና እንዲኖሩ ተገደዋል፡፡ ዕቃዎች ስልህ የመብል ውጤቶችን ለማለት ነው፡፡ አንድ የመንግሥት ወይም የግል ድርጅት ተራ ሠራተኛ በሚያገኘው ደመወዝ ሌላውንና ለዘመኑ እንደቅንጦት የሚቆጠረውን ቤት መሥራትንና ማሳደስን ተውትና የምግብ ፍጆታውን እንኳን መሸፈን አይችልም – ሌላ የጎን ገቢ ካልተጨመረበት፡፡ “ሽምብራ ቆርጥሜ የሠራሁት ቤት” ይባል የነበረው ምሳሌያዊ አነጋገር አሁን የለም – ሽምብራም ከጤፍ በልጦ ተወዷል፡፡ በዚያ ላይ ሽምብራም ቆርጥም ባቄላ ከደመወዝህ ቤሣቤስቲን ተርፎህ ለክፉ ቀን አታስቀምትም፡፡ ሲጀመር ኑሮህ በብድርና በበዕዳ የተወጠረ እንጂ ከሽሮና ከጎመን ያለፈ አታስብም – ለዚህም ከበቃህ ታድለሃል፡፡ ዱሮ በአሥርና በአሥራ አምስት ብር ይገዛ የነበረው ሳልቫጅ ሸሚዝ ራሱ ዛሬ ከብር 130 በላይ ነው – በዚህ ዋጋ በቀደምለት እኔ ራሴ ስለገዛሁ ኅያው ምሥክር ነኝ – ለዚህ መብቃቴም ያስጨበጭብልኛልና እባካችሁን አጨብጭቡልኝ፤ የቢሮ ሠራተኛ – በሙስና ያልተዘፈቀ ማለቴ ነው – ሣልቫጅ ከመግዛት እንኳን አቅም ካነሰው ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ዛሬ ሳልቫጅ ራሱ ለመለስተኛ ሀብታሞች መዘነጫ ሆኗል፡፡ የኔ ቢጤ ሠራተኛ አዲስ ሸሚዝና ጫማ ለመግዛት ዕቁብ መግባት ይኖርበታል፡፡ በሌሎች ያደጉ ሀገራት በአፍሪካም ጭምር አንድ እኔን መሰል ለ20 እና ለ30 ዓመታት ሀገሩን ያገለገለ ባለ ሁለተኛ ዲግሪ ችግሩ ቤትና መኪና ሣይሆን ሌላ ነው፡፡ እኛ ግን ምን ቀምሰን እንደምናድር የምንጨነቅ የነጋዴና የወሮበላ መንግሥት የግዳይ ሰለባዎች ነን፡፡ ቆም ብለው ሲያስቡት ያሣዝናል፡፡ ይህን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ ታዲያ ብዙ ዜጋ አግባብ ባልሆነ መንገድ ገንዘብ ለማግኘት አቅሉን ስቶ ሲራወጥ ታዩታላችሁ፡፡ ድህነት መጥፎ ነው፡፡ ድህነት ከሃይማኖትና ከጨዋ ባህል ያወጣል፡፡ ድህነት ዐውሬ ያደርጋል፡፡ ድህነት ያባልጋል፡፡
ነጋዴው እሳት ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ነጋዴ ዐይንም፣ ጆሮም፣ ልቦናም የለውም፡፡ የለዬለት ዕውር ነው፤ የለየለት ደንቆሮ ነው፡፡ የንግድ ጽንሰ ሃሳብም የለውም፤ ምክንያቱም ወደ ንግድ የሚገባው የፊደል ዘሮች አልገባው እያሉ ሲያስቸግሩት እንጂ በትምህርትና በልምድ ዳብሮ አይደለም፡፡ ብዙው ነጋዴ በአቋራጭ መክበርን እንጂ በህጉ መሠረትና የሕዝቡን ኢኮኖሚያዊ አቅም ባገናዘበ ሁኔታ አይደለም፡፡ የሀገሪቱም ሕግ ሕግ-አልባነት በመሆኑ ማንኛውም ኅሊናቢስ ወንበዴ ወደሀብቱ የሚያደርገው ጉዞ የተቃና ነው፡፡ የመንግሥት ተብዬው ባለሥልጣናትም ከማይማን ነጋዴዎች ጋር እየተመሣጠሩ ሕዝቡን ባልተወለደ አንጀት ይገርፉታል፡፡ ማይም ባለሥልጣናትና ማይም ነጋዴዎች በእከክልኝ ልከክልህ የጥቅም ትስስር ሀገሪቷንና ሕዝቧን ወደ ገደል እየከተቷቸው ነው፡፡ አንድም ሃይ ባይ ሳይኖር ኢትዮጵያን የመሰለች የድንቅ ታሪክ ባለቤት እየጠፋች ነው፡፡ ማን ይድረስላት?

ዱሮ ስንጥቅ ትርፍ ሲባል እንሰማ ነበር፡፡ “እገሌ ስንጥቅ ትርፍ አተረፈ” ይባል ነበር፡፡ ዛሬ ግን እንደዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡ ስንጥቅ ማለት እንግዲህ ግማሽ በግማሽ ለማለት ይመስለኛል – ለምሳሌ መቶ ብር የተገዛን ዕቃ 150 ወይም ግፋ ቢል 200 ብር የመሸጥ ያህል፡፡ አሁን ግን መቶ ብር የተገዛን ዕቃ ጊዜ እየጠበቁና ሆን ብለው እያስወደዱ ከአምስትና ስድስት ሺህ ብር በላይ ካልሸጡ የነገዱ የማይመስላቸው አይሲሶች ተፈጥረዋል፡፡ ስለዚህም አንድ ሰው ንግድ በጀመረ በጥቂት ሣምንታትና ወራት ውስጥ አንቱ የተባለ ዲታ ይሆንና መኪና እንደሸሚዝ ሲለዋውጥ ታየዋለህ፤ በዚያ ላይ ወያኔያዊ የደምና የአጥንት ንክኪ ካለው ሣምንት ቀርቶ ደቂቃዎችም ሳይፈጅበት ቀጭን ጌታ ይሆናል – ትምህርት ዕርሙ በሆነበት ድባብ ውስጥ ለሚኖር አንድ ማይም ዘረኛ ደግሞ ይህ ዓይነቱ በሀብት የመወንጨፍ ዕድል ከባድ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር አእምሮን የማሳመን ጉዳይ ነው፡፡ የሃይማኖትና የግብረገብ ትምህርት የሌለው፣ የይሉኝታና የሀፍረት ስሜት ጨርሶ የሌለው፣ ከአንዲት ትንሽ ጎጥ በዘለለ ማሰብ የማይችል “ሰው” አጭበርብሮና አታልሎ ብቻም ሣይን ገድሎና አሥሮም ቢሆን ቢከብር የሚጠይቀው ኅሊና ወይም ምድራዊ ሕግ የለም፡፡ ሁሉም እርሱን ለመርዳት የቆመ ነውና፡፡ ሰው ደግሞ በተፈጥሮው ከኅሊናው ጋር ከተቆራረጠ የመጨረሻው ዐውሬ ነው የሚሆነው፡፡ በሁሉም መንገዶች ተጉዞ ወደሚፈልገው ማማ መውጣት ነው ጥረቱ፡፡

ትናንት ሰላጣ አማረኝ፡፡ ብዙውን ጊዜ ጥቃቅን የምግብ ፍጆታዎችን ከማንጠግቦሽ በተጓዳኝ እኔም እገዛለሁና ወደጉሊት ወጣ አልኩ፡፡ ገበያው በአንጻራዊ አነጋር ከቀደሙት የጾም ወራት አሁን ደህና ነበር ማለት እችላለሁ – በተለይ በአንዳንድ ዕቃዎች፡፡ ቀይ ሽንኩርት በኪሎ 16 ብር፣ አንዲት የጠወለገች ሙትቻ ሎሚ በአንድ ብር ከሃምሣ፣ ቲማቲም በጣም ቀነሰ ተብሎ ኪሎውን በ8 ብር፣ ቃሪያ (በጣም ጦፏል!) ግማሽ ኪሎ በ23 ብር፣ ሃቱም የተባለውን አንድ ሊትር ዘይት 78 ብር፣ አንዲት እግር ሰላጣ በ8 ብር ገዝቼ ፀጉሬን እየነጨሁ ወደቤቴ ተመለስኩ፡፡ ሰላጣ ለመብላት ስንት እንዳወጣሁ እናንተው አስሉት – ዘይቱ እርግጥ ነው ትንሽ ጊዜ ይቆያል፡፡ ይህን ኑሮ የትኛው የመንግሥት ሠራተኛ ችሎ ይኖራል? ሥጋንና ወተትንማ ጭራሽ አታስቡት፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በሉካንዳ ቤት ስናልፍ የተሰቀለን ሥጋ በሱቲ ጨርቅ እየሸፈኑ ገልጠው ለማሳየት ብቻ ሳያስከፍሉን የሚቀሩ አይመስሉኝም፡፡ ልብ አድርጉ – እኔ ባለደህና ደሞዝተኛ ተብዬው ለልጆቼ ብርቱካንና ሙዝ አንጠልጥዬ መግባት ካቆምኩ ዓመታት አልፈዋል – እንዳልዋሽ እጅግ አልፎ አልፎ በወረት ካልሆነ በስተቀር የምነግራችሁ እውነቴን ነው፡፡ አንዲት ኪሎ ሙዝ 14 ወይ 15 ብር ፣ አንድ ኪሎ ብርቱካን ከብር 22 በላይ ገዝቼ እንዴት እችላለሁ? ደግሞስ አንድና ሁለት ኪሎ መች ይበቃንና ወስፋት ላጩህ? ለመሆኑ ስንቱ ቤተሰብ ነው ሥጋና ወተትን የመሰሉ አልሚ ምግቦችን በቅጡ የሚመገበው? ብዙው ቤተሰብ ሥጋን የሚያውቀው ሃሊዮ ኮሜት በሰባ ስድስት ዓመት አንዴ እንደምትታየው ሁሉ በዓመት ሁለቴና ሦስቴ ብቅ በሚሉ ፋሲካን የመሰሉ ዐውዳመቶች ነው፡፡ ሞተናል እኮ፡፡ ገድለውናል እኮ፡፡ እንዳሰቡት ሆነንላቸዋል እኮ፡፡ ዕቅዳቸው እኛን ማጀታችን ውስጥ ወሽቀው ስለምንቀምሰውና ስለምንልሰው እንድንጨነቅ ማድረግ አልነበረም? ታዲያስ! እናሳ አልተሣካላቸውም? አለመረገማችንን የማናምን ከዚህም ባለፈ እኛ ኢትዮጵያውያን ዕድለኞች መሆናችንን አዘውትረን የምንናገር ብዙዎች ልንሆን እንችላለን – ነገር ግን ሆዱን እንኳን መቻል በሚያቅተው ማኅበረሰብ መካከል መገኘት ከመረገሞችም በላይ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡ የሰው ልጅ በሥልጣኔ የትና የት ደርሶ፣ “አውሮፓውያንና አሜሪካውያን ከማዕዳቸው ተርፎ የሚጣለው የዕለት ምግብ ለአፍሪካውያን የዚህን ያህል ጊዜ ቀለብ ይሆናል” እየተባለ ሲነገር ትንሽም የማይቆጫቸው መሪዎች ያሉን አሳዛኝ ሕዝቦች ነን – አፍሪካውያን በጠቅላላው፡፡ የኛ ደግሞ ከሁሉም በባሰ ቆሎም ባቅሙ አርሮብን፣ ልብሳችን በላያችን ላይ አልቆ፣ አጥንታችን አግጥጦ፣ … እንዲሁ ኑሮ ብለነው እንንጠራወዛለን፡፡ ሞታችንን በቁማችን ጨርሰን በትሽ በሽታ ህቅታችን ስትወጣ መቼም ወግ ነውና ሞቱ ተብለን ድንኳን ተጥሎ ይለቀስልናል፡፡

እርግጥ ነው የፊት ለፊት ስዕላችን አሁን ከምለው ለየት ያለ ሊመስልና እኔንም እንዳጋነንኩ ሊያስቆጥርብኝ ይችል ይሆናል፡፡ እኔ እያወራሁ ያለሁት እውነተኛውን በወያኔ ሚዲያ ግን የተሸፈነውን ሀገራዊ ማንነት ነው፡፡ የኔን ሕይወት፣ የወንድምና እህቶቼን ሕይወት፣ የአብዛኛውን ሕዝብ መሪር ኑሮ ነው እየተናገርኩ ያለሁት፡፡ እንጂ የተመቸው ጥቂት የማይባል ዜጋ መኖሩን አውቃለሁ፡፡ ግን ያም ምክንያት አለው፡፡ የተሻለ ደሞዝ ያላቸው፣ በሥራቸው ምክንያት እጅ መንሻ የሚያገኙ፣ ቤት የሚያከራዩ፣ ቤትና ዕቃ የሚሸጡና የሚለውጡ፣ ከዲያስፖራው ገንዘብ የሚላክላቸው(እኚህኞቹ ቀላል ቁጥር አይደለም ያላቸው)፣ መኖሪያ ቤታቸውን ወደአነስተኛ የንግድ ቤትነት ለውጠው እንደነገሩ የሚውተረተሩ፣ በስርቆት፣ በማጭበርበርና በሙስና ትልቅ ገቢ ያላቸው፣… ወገኖቻችን መሬት ላይ ከሚታየው ህንፃና መንገድ ጋር ተደማምረው እውነተኛውን ሀገራዊ ምስል ለጊዜው ሊደብቁት ቢሞክሩም እስከወዲያኛው ግን ሸፍነው ሊያቆዩት አይችሉም፡፡ ከነዚህ ከጠቃቀስኳቸው የጎን ገቢዎች የራቀው ተራው ገበሬ፣ መምህሩ፣ የመንግሥት (የቢሮ፣የጽዳት፣ የጉልበት፣ የጥበቃ…)ሠራተኛው፣ ተራው ወታደር፣ ከጉቦ ጋር ብዙም የማይወዳጀው የፖሊስና የፀጥታ ሠራተኛ፣ ሥራ አጡ ወገን፣ ህጻኑ፣ ሽማግሌው፣ ለማኙ፣ በረንዳ አዳሪው፣ ሴተኛ አዳሪው፣ ወዘተ. እንዴት እንደሚኖር ብታዩ በኢትዮጵያ ያጡ የነጡ ድሆችን ሣይሆን በምሥኪኖች ላብና ደም የከበሩ ሀብታሞችን ደኅንነት ለመጠበቅ ብቻ ተግቶ የሚሠራ ሥውር ምናልባትም መንፈሣዊ ኃይል መኖሩን እንድታምኑ ትገደዳላችሁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ ሁሉ ተነግሮ በማያልቅ የኑሮ ውጣ ውረድና መሪር አገዛዝ እያረረና እየነደደ የሚገኝ ሕዝብ ርስ በራሱ ተባልቶ እንዳያልቅ ለመርዳት ሲል ፈጣሪ ጓዙን ጠቅልሎ ኢትዮጵያ ውስጥ የከተመ እስኪመስለን ድረስ በፈጣሪ ጥበቃ እንድንገረም የሚያደርግ ሁኔታ እንታዘባለን – የዕንቆቅልሽ ምናውቅልሽ ሀገር፤ ኬንያ ወይም ደቡብ አፍሪቃ እኮ ቀን በቀን ነው ሰው የሚዘረፈው፡፡ እዚህ የምናየው ትግስት ልዩ ነው፡፡ ራሱ እየተራበ የሰው ወርቅ ሲጠብቅ የሚያድር ዜጋ የምታገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ መሆን አለበት፤ ራሱ በጠኔ እየተሰቃዬ ሀብታሞችን አንደላቅቆ የሚያኖር ሕዝብ የምታገኘውም በአፍሪቃ ቀንድ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ይመስለኛል፤ በ“አንተ ታውቃለህ”ና “አንተ ያመጣኸውን አንተው መልሰው” ነባር ጸሎት የሚኖር ብቸኛ ሕዝብ ቢኖር የኛው ሕዝብ መሆን አለበት፡፡ይሁንና ግን ጊዜ የማይወልደው ክስተት የለምና እየተንተከተከ ያለው ማኅበራዊ ቀውስና ፍትህ አልባው የሀብት ክፍፍል አንድ ቦታ ከተነፈሰ መመለሻ የለውም፡፡ “ማን እየኖረ ማን ይሞታል?” ከሚል አሳማኝ መነሻ ሆድ የባሰው ሁሉ ሀገሪቱን የሁከት ማዕከል እንዳያደርጋት ያሰጋል፡፡ ሊቢያና ሦርያም ከብዙ አሠርት ዓመታት ግፍና በደል በኋላ ነው የአሁኑን አስጠሊታ ቅርጽ ሊይዙ የቻሉት፡፡ እናም መፍራት ደግ ነው፡፡ “አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን በያዝሽ” ነው ነገሩ፡፡ የናቁት ማስረገዙ፣ የጠሉት መውረሱ፣ … ከጥንትም ነበር፡፡

የሕዝባችንን ቁስቁልና ለመረዳት እስኪ ለአብነት የአውሮፓን ካምቦሎጆዎችና የሀገራችንን ካምቦሎጆዎች በእግር ኳስ ግጥሚያዎች ጊዜ ተመልከቱ፡፡ የአዲስ አበባ ኳስ ሜዳ በምን ዓይነት ደቃቃ ሰዎች እንደሚሞላ፣ የአውሮፓውያኑ ደግሞ በምን ዓይነት ሰዎች እንደሚሞላ ታዘቡና የደረስንበትን የድቀት ደረጃ አስተውሉ፤ በአለባበስ፣ በሰውነት ይዞታ፣ በቁመት፣ በወርድ … በሁሉም አስተያዩ፡፡ ሰው ምግቡን ይመስላል፡፡ አመጋገብ ብዙ ትርጉም አለው፤ በአስተሳሰብና አመለካከት፣ በፍልስፍና፣ በሥነ ልቦና፣ በአካላዊ ዕድገትና ጤንነት፣ ወዘተ. ምግብ ወሳኝ ነው፡፡ ካለ ተመጣጣኝ ምግብ ጤናማ አእምሯዊ ዕድገት አይገኝም፤ ካለተመጣጣኝ ምግብ ቁንጅናና ውበት የለም፡፡ ካለ ተመጣጣኝ ምግብ ትምህርት መማርም የሚታሰብ አይደለም፡፡ ሆድ ባዶ ሆኖ ወይም አሸርባሸር በልቶ ትምህርት ወደአእምሮ ይገባል ማለት ዘበት ነው፤ የሆዱን ጥያቄ ባግባቡ ያልመለሰ ተማሪ አካሉ ክፍል ውስጥ ይቀመጥ እንደሆነ እንጂ መንፈሱ ወደምናባዊ ኩሽናዎች መሸፈቱ አይቀርም፡፡ ዝም ብለን “ሀበሻ ምቀኛ ነው” ብንል ዋጋ የለውም፡፡ ይልቁንስ ከአመጋገባችን አንጻርም ችግር ይታየኛልና ይህን የተጣመመ የኑሮ ገመናችንን ለማስተካከል ልዩ ኮሚቴ ካሁኑ ተቋቁሞ ይሰብበት፡፡(ይቺ ጤፍ የምትባል ነገር የምቀኝነት መንስኤ ንጥረ ነገር ሳይኖራት እንደማይቀር የሚናፈሰው ወሬም ቢጠና አይከፋም፡፡ ማን ያውቃል?)

በሌላ አቅጣጫ ጥቂቶች መሬትን ተጠይፈው ጮቤ ይረግጣሉ፡፡ ከኛ አላግባብ በሚዘርፉት ገንዘብ አዲስ አበባ ምድር ቃጤ ስትሆን ታመሻለች፤ ታድራለችም፡፡ እኔን እየራበኝና አብዛኞቹ መሠረታዊ ፍላጎቶቼ ታፍነው እነዚህ ጥቂቶች ብሩን ለየምናምኑ ሲረጩት ይታያሉ – ካለድካም የመጣ ገንዘብ ደግሞ እሳት ላይ የወደቀ ቅቤ እንደማለት ነው፡፡ ሀብታሞች ቅጥ አጡ – የኛ ድሀነትም ቅጥ አጣ፡፡ በሀገራችን ሁለት ፍጹም ተቃራኒ ጫፎች ተፈጥረው ለዳኝነት ብቻ ሣይሆን ለታዛቢም ሳይቀር አስቸገሩ፡፡ ሀብታሙ እንዴት እንደሚኖር ስናይ ድሃው ደግሞ ቆሼ ተራ ለፍርፋሪና ለሙዝ ልጣጭ እንዲያ በሺዎች እየተራኮተ ሲታይ የገነትንና የሲዖልን ኅልውና እስክንረሳ ድረስ እንደመማለን – ገነትንም ሲዖልንም በተግባር የምናያቸው ያህል ይሰማናልና፡፡ሙስናው ደግሞ ጣሪያ ያለው አይመስልም፡፡ በደሞዙ ከእኔ ታች የሆነ አንድ የቀበሌ አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ወር እስከወር ከቡና ቤቶች እንደቆርኪ ተጠርጎ ነው ውድቅት አካባቢ ወደቤቱ እየተወላገደ የሚሄደው፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ደሞዛቸውን አያውቁትም፡፡ ከትንሹ እስከ ትልቁ ባለሥልጣን ያለሙስና ቢኖሩ እስትንፋሳቸው ቀጥ የሚል ይመስላቸዋል፤ ይላልም፡፡ ሙስና የሀገራችን የደም ዝውውር ሆናለች፡፡ ካለሙስና የሚኖር የመንግሥት የሥራ ኃላፊ አለ ማለት ያስቸግራል፤ ካለም በድህነት እየተሰቃዬ በመኖር የበይ ተመልካች ለመሆን መርጧል ማለት ነው – ጥሩና አዋጪ ምርጫ፡፡ የአብዛኛው የወቅቱ ምርጫ ግን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መክበር ነው፡፡ ጨረታና ግዢ ደግሞ ዋናዋ የግል ብልጽና ማሳለጫ ናት፡፡ በቡድንም ይሁን በግል ሀገርን መዝረፍና በአቋራጭ መክበር የብዙዎች ምኞትና የዕለት ተለት ድርጊትም ነው፡፡ ምን ይሉኝ የለም፡፡ የሚሠሩ ነገሮች ደግሞ ብዙዎቹ የጥራት ደረጃቸውን አያሟሉም፡፡ የጨረታ አሸናፊዎች ከዘርና ከሙስና ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው – ጥራትና አመክንዮ፣ ሀገርና ሕዝባዊ ወገንተኝነት ዋጋ የላቸውም፡፡ ሥራዎች ተጠናቀው ርክክብ ይፈጸማል፡፡ በሙስና የተሠራ አንድ የግንባታ ዕቅድ ወይ መንገድ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ፍርስርሱ ይወጣና ኪሣራ ብቻ ይሆናል – ያኔ ጠያቂም ተጠያቂም የለም፡፡ ለምን ቢባል ማን ማንን ይጠይቃል? ሁሉም ሌባና ራስ ወዳድ ነው፤ ሁሉም በተመሳሳይ የሙስና ቁስል የነፈረ ነው፤ ቂጥኛም ውርዴን፣ ውርዴም ቂጥኛምን የመጠየቅ ሞራላዊ ብቃትም ሆነ ሕጋዊ መደላድል የለውም – በክት ለበክት እየተጠቃቀሰ ይጠቃቀማል፤ ሀገርና ሕዝብ ግን ያለቅሳሉ፡፡ በመቶ ሺዎች ወጪ ሊሠራ የሚችል አንድ ግንባታ ብዙ ሚሊዮኖች ፈሰውበትም ከሚፈለገውና ከሚጠበቀው የጥራት ደረጃ እጅግ የወረደ ነው፡፡ በእንጨት ባላ የተደጋገፈ አንድ የሕዝብ ትምህርት ቤት አውቃለሁ – ባለ አራት ፎቅ፡፡ እንዲያ ስንጥቅጥቁ የወጣው ደሞ ገና ከርክክቡ ቀደም ብሎ ነው፡፡ ተማሪዎቹ እንዳይወድቁ ወይም ከናካቴው እንዳይደረመስባቸው ያሰጋል – በዚያ ትምህርት ቤት የዘመዴ ልጅ ይማራልና እኔም በዐይኔ አይቼ ተገርሜያለሁ፡፡ ለሀገር ማሰብና መቆርቆር ቀርቷል፡፡ የትም ፍጪው ነው የነገሠው፡፡ ሀገርህ በቁም ሞታለች፡፡ ሀበሻ በያለህበት ዕርምህን አውጣ፡፡ ነገር ግን “ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል” ነውና ተረቱ ያለች ትመስላለች – ሞታ ሳለች፡፡ ሞት ዓይነቱ ብዙ መሆኑን ተረዳ፡፡

ወደሚሰቀጥጠው ኑሯችን ልመልስህ፤ ያንተ ኑሮ የተያዘለት ሊሆን ይችላል – ማለፊያ ኑሮ ማለቴ ነው፡፡ ቢሆንም እኛም ያንተው ወገኖች ነንና እሮሮኣችንን ስማልን፤ እዘንልንም፡፡ ከአንተ በላይ ለኛ ማን ሊያዝንልን ይችላል?፡ እንደዱሮው በተወሰነ ጊዜ ጫማ መግዛት፣ ልብስ መግዛት፣ የቤት ዕቃ መቀየር፣ ወዘተ፣ ዛሬ በተራው ሠራተኛ ዘንድ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ገንዘብ ልታገኝ ትችል ይሆናል፡፡ ዘመድም ሊሰጥህ፣ ጓደኛም ሊለግስህ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሚሰጥህ የገንዘብ መጠን በመቶ ሺዎችና በሚሊዮን የሚገመት ካልሆነ በስተቀር በመቶዎችና በጥቂት ሺዎች የሚገመት ከሆነ ከተወሰኑ ቀናት የምግብ ፍጆታ ውጪ የሚያልፍ አይደለም፡፡ የገንዘቡን የመግዛት አቅም ምች አጠናግሮት ተሽመድምዷል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ብዙዎች በሚያገኙት መጠነኛ ገንዘብ ምንም ዓይነት ሻል ያለ ነገር መሥራት እንደማይችሉ ከመገንዘብ አኳያ እምብርታቸውን ወትፈው ሌት ከቀን ሲጠጡና ሲሰክሩበት የሚታዩት – ይህ ደግሞ እውነተኛ የደስታ ስሜት መገለጫ ሣይሆን የተስፋ መቁረጥ ስሜት የወለደው ጊዜያዊ መጠለያን የመሻት ፍላጎት የፈጠረው ነው፡፡ እና መጠጥ ቤቶች ሞልተው ቢታዩ አገር አማን ነው ማለት አንችልም፡፡ በነገራችን ላይ ይህን መሳይ በሁሉም ረገድ የወደቀና ከሆዱ ባለፈ ምንም ነገር ማሰብ የማይችል ሕዝብ መግዛት ለአምባገነኖች ሠርግና ምላሽ ነው፡፡ የተማረና የሠለጠነ፣ በሀብትም በትውፊትም የዳበረ ማኅበረሰብ ገዢዎቹን ብዙ ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ መብቱን ያስከብራል፡፡ እንደኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች የሚገኙ ማይም ገዢዎች ግን ሕዝቡ እንዳይነቃና ከዕለት ጉርሱ ባለፈም ሀብት እንዳይኖረው በማድረግ እንደእንስሳ እየገረፉ ይገዙታል፡፡ የኛ ግን ባሰና ለዕለት ጉርስና ለዓመት ልብስብም መድረስ አቃተን፡፡ ፈራጁ ኃያል አምላክ በመጨረሻው የድርሻቸውን አይከለክላቸውም፡፡ በዚያ ብቻ እንጽናናለን፡፡

ሰዎች ሀብታም የሚሆኑባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡ አብዛኞቹ ግን ሕገወጥ፣ ኢ-ሞራላዊና ኢ-ሃይማኖታዊ ናቸው፡፡ በነዚህ መንገዶች ለመክበር መሞከር መጨረሻው ባያምርም ብዙዎቹ የሀገራችን ሀብታሞች ይጓዙባቸዋል፡፡

በህጋዊ መንገድ ነግደህ በአሁኑ ሰዓት አትከብርም፡፡ ምክንያቱም ውድድሩ ከባድና ፈታኝም ነው፡፡ ወያኔዎች ደግሞ የዋዛ አይደሉም፡፡ ሌሎችን ለማደኽየት፣ እነሱንና የነሱን ግን ለማክበር አጥብቀው ስለሚሠሩ የውድድሩን መንፈስ ይበልጥ ሕገወጥና አድልዖዊ ያደርጉታል፡፡ በዚህ የተንሸዋረረ ተናግዶት ነግደህ የትም አትደርስም፡፡ ለምሳሌ ቀረጥ ከፍለህ ያስገባኸውን አንድ ዕቃ ከ15000 ሺህ ብር በታች ብትሸጠው ሊያከስርህ ይችላል፡፡ አንዱ የወያኔ ንክኪ ነጋዴ ግን 10000 ሺህ ብር ሲሸጠው ታያለህ፡፡ የተያዘው ጥረት አንዱ ከሌላው ተባብሮ ለማደግ ሣይሆን አንዱ አንዱን ገድሎ በተናጠል የመመንደግ ነው – በተለይ ከዘር አኳያ የሚታየው ዐይን ያወጣ ጠንጋራ አሠራር በኢትዮጵያዊነትህ ብቻ ሣይሆን በሰብኣዊ ፍጡርነትህም እንድታፍር ትገደዳለህ፡፡ ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የለየላት ሲዖል እየሆነችባቸው ብዙዎች የተማሩ ዜጎቿ ወደምዕራቡ ዓለም የሚሰደዱት፡፡ ለዚህም ነው ብዙም ያልተማሩት ዜጎቿ የሚያልሙት እውን ባይንላቸውም እንኳን የበረሀና የባሕር እንስሳት ሲሳይ ወይም የህገወጥ የሰውነት መለዋወጫ ሰለባ ሆኖ የመቅረትን መጥፎ ዕድል እየተረዱም ጭምር በሀገራቸው የሚገኘውን የባንዳዎች መንግሥት አምርረው ከመጥላታቸው የተነሣ ወደውጪ በገፍ የሚፈልሱት፤ በየትኛውም ሚዛን ቢለካ ከዚህ የበለጠ የሀገር ውርደት ሊኖር አይችልም፡፡ ሀገሪቱ ጠማማ ሚዛን ላይ የተቀመጠች ራሷም የተጣመመች ሆናለች፡፡ የጨረባ ተዝካር፡፡ ወደላይ ብትጮኸ የሚሰማህ የለም፤ ወደታች ብትጮኽ የሚሰማህ የለም፡፡ ጩኸትህ ሁሉ የቁራና የምድረ በዳ ጩኸት ሆኖ ይቀራል፡፡ አማራጭ ስታጣ ታዲያ ትሰደዳለህ ወይም ታብዳለህ – ሁለቱም መጥፎ አማራጮች ናቸው፡፡

የወያኔ ሰብኣዊ ንብረት ከሆንክ ቢያንስ እንዳትራብ እነሱው የሚቆጣጠሩት መቁነን ይሠፍሩልሃል – እንዳትሞት እንዳትድን፡፡ በሀብትና በሥልጣን ወደላይ ብቅ ካልክ ለነሱም እንደማትበጃቸው ስለሚገምቱ ይመስላል ያን አይፈቅዱልህም፤ አንተ ግን የማንም ሥጋት እንደማትሆን ቢያንስ ልቦናህ ያውቀዋል፤ ለምን ብለህ? ሀገር ሰፊ ናት፤ ለሁሉም ትበቃለች፡፡፡፡ እነሱ ግን በሀብትም በሥልጣንም ከነሱ አጠገብ እንዳትደርስ አጥብቀው ይከታተሉሃል፤ ይቆጣጠሩሃል፡፡ ወያኔዎች ምድራችን ከፈጠረቻቸው ክፉ ፍጡሮቿ የመጨረሻዎቹ አደገኛ የሲዖል ትሎች ናቸው፡፡ ነግድም፣ የመንግሥትን ደሞዝ አግኝም በርቀት መቆጣጠሪያቸው እየለኩ ዘወትር ስላንተ ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ጥቃቅንና አነስተኛ በሚባሉ የሚያደራጇቸውን ምሥኪን ዜጎችም በዚህ መልክ ነው ለነሱው መሣሪያነት የሚጠቀሙባቸው፡፡ ሲፈልጉ ቸርቺል ጎዳና መሃል ላይ ድንኳን ተክለው እንዲነግዱ ሊያደርጓቸው ይችላሉ፤ ሲፈልጉ አንዱን የመንግሥት አዳራሽ ሰጥተው ለተወሰነ ጊዜ ሊያስነግዷቸው ይችላሉ፡፡ አንተን ግን ጫካ ውስጥ እንኳን ዛፍ ሥር ተቀምጠህ ልነግድ ብትል መጥተው ነግደህ ልታገኝ ከምትችለው አጠቃላይ ገቢ በዕጥፍ ድርብ የሚበልጥ ቀረጥ ይጥሉብሃል፡፡ ወያኔዎች ብልጥም ናቸው – ሂድ አይሉህም እንድትሄድ ግን ያደርጉሃል፡፡ ውጣ ላይሉህ ይችላሉ – እንድትወጣ ግን የማያደርጉብህ ግፊት የለም፤ ያኔ መሮህ እያለቀስክ ትወጣለህ – ካገርህም ጭምር ብን ብለህ ትጠፋላቸዋለህ፡፡ ሌላውና ከወያኔ ጋር የተሞዳሞደው ሀገርንም የሸጠው ወገን ግና መንገዱ ሁሉ ቀኝ በቀኝ ሆኖ በአጭር ጊዜ ይከብራል፡፡

አንዱ የመክበሪያ መንገድ እንግዲህ ወያኔን መጠጋትና በሕገወጥ ንግድ፣ ዐይን በሌለው የዋጋ ንረት በአጭር ጊዜ ቱጃር መሆን ነው፡፡ በዚህ ሂደት ከሕዝቡ አጠቃላይ ቁጥር አንድ መቶኛ የማይሆኑት ጥቂቶች ሽቅብ ሲወነጨፉ ሌሎች በቁማቸው መቀመቅ ይወርዳሉ – በሸፋፋ ጫማ፣ በነተበ ሸሚዝ፣ በቀዳዳ ሱሪ፣ በተጠገነ ፓንትና ካልሲ ወደቢሮ የሚሄዱ ዜጎችን ብታስተውል ሥርዓቱ የፈጠረው ሸፋፋ አካሄድ እንጂ የነሱ ጥፋት እንዳልሆነ ሊገባህ ይገባል፡፡ እንዲያውም እነዚህን የመሰሉ ዜጎች ሊከበሩና ሊወደሱ ይገባቸዋል፡፡ በ”ሀገርህ ስትወረር አብረህ ውረር” ፈሊጥ ተወስደው ከጠላት ጋር በማበር የድርሻቸውን ያልዘረፉና በሚያገኙት እውነተኛ ገቢ ብቻ ለመኖር የሚፍጨረጨሩ ንጹሓን ዜጎች በመሆናቸው በእጅጉ ሊከበሩ ይገባቸዋል፡፡ እነዚያኞቹ ግን ገና በታሪክ ይዋረዳሉ፤ ትውልዳቸውም አንገቱን የሚደፋባቸውና የሚያፍርባቸው ይሆናሉ፡፡

ሌላኛው የመክበሪያ መንገድ ሰይጣናዊ ነው – በለየለት ሁኔታ ማለቴ እንጂ ማንኛውም ኅሊና ቢስ አሠራር ከክፋነቱ አንጻር ሰይጣናዊ መሆኑን ዘንግቼው አይደለም፡፡ በዚህ ሥልት መተት፣ ትብታብ፣ ጥንቆላና የመሳሰሉት ይካተታሉ፡፡ ማመን አለማመን ያንተ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ መንገድ በዓለም ደረጃ ከጥንት ጀምሮ በስፋት የሚታወቅና ብዙዎችም የሚመላለሱበት ሰፊ መንገድ ነው፡፡ በጥንቆላና በመተት -ለጊዜውና ነፍሱን ለሰይጣን ሸጦ – የሚያልፍለት ወገን እጅግ ብዙ ነው፡፡

ከሀብታሞቻችን፣ ከሯጮቻችን፣ ከአርቲስቶቻችን፣ ከባለሥልጣኖቻችን፣ ከታዋቂ ሰዎቻችን፣ ከታዋቂ የሃይማኖት አባቶቻችን … መካከል ስንቶቹ ይሆኑ በሰይጣን ጎታቾች ደጅ፣ በአውሊያና ከራማ ጠሪዎች ክድሚያ ቤት፣ በመጣፍ ገላጮች ቀየ፣ በሞራ አንባቢዎች ጎጆ ያልተንከራተቱና የሀብትና የሥልጣን ጫፍ እንዲደርሱ ያልተጎናበሱ? ገመናችን ብዙና ተቆጥሮም የማይዘለቅ ነው፡፡ ይህ ልማዳዊ ነገር ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻ የተወሰነ ሣይሆን በመላው ዓለም በተለይም በሕንድ፣ በሱዳንና በምዕራብ አፍሪካ በጣም የተለመደ ነው፡፡ ሰይጣን በተለይ በአሁኒቷ ዓለማችን ውስጥ ትልቅ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ኃይል ነው፡፡ ያከብራል፤ ያደኸያል፡፡ ይሰጣል፤ ይነሣል፡፡ እርሱን የፈለጉ ከችሎታና ከሥልጣኑ እንዲቋደሱ ከፈጣሪ ሥልጣን ተሰጥቶታል ይባላል፡፡ በዚህም ምክንያት ለምሳሌ በአሥር ዓመት ከሚመጣ የእግዚአብሔር ፍርድ ይልቅ በደቂቃዎች ለሚመጣ የሰይጣን “በረከት” እየተሸነፉ ብዙዎች ፈጣሪን ችላ ብለው ወደዚህ ቦርቃቃ መንገድ እንደሚገቡ ይነገራል፡፡ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ የመረጠ ይገባበታል፤ የፈራ ይመለሳል፡፡ እንደኔ የፈራ ከነድህነቱ እያከከ ይኑር፡፡ ልከክ፡፡ ሀብት ማናባቱ! (እንዲች ልጽናና አይደል?)

ይህ መንገድ እንዴት ያከብራል እነማን በዚህ ከበሩ ምን ማሟላት ያስፈልጋል … የሚሉት ጥየቄዎች ብዙ ስለሚያናግሩ ወደዚያ መግባት አያስፈልግም፡፡ እንጂ በስንቱ ሕንፃ ሥር ምንና እንዴት እንደተቀበረ፣ ማን በጅብ መንጋ መሀል እያስካካ አድሮ ሊነጋጋ ሲል ሰይጣናዊ ማንነቱን ለዋውጦ ሰው በመምሰል ወደንግድ ቤቱ እንደሚመለስ፣ እነማን በየትኞቹ ጠንቋዮችና አበጋሮች ዘንድ ሲፈናደሱ አድረው ሲወጡ እንደታዬ፣ … ብዙና ብዙ ዝግንትል ነገር ከነምሳሌዎች መናገር ይቻላል፡፡ በጥቅሉ ግን በዘመናችን ሰዎች በኑሮ ከመጨነቃቸው የተነሣ ከኅሊናቸውና ከነፍሳቸው ጋር እየተጣሉ ከጤናማ መስመር በመውጣት ወንድምና እህቶቻቸው ላይ ግፍና በደል እየፈጸሙ መሆናቸውን፤ ይህም ግፍና በደል እየቆዬ ወደራሳቸው ይዞርና በምድርም ሆነ በሰማይ የሚጎዳቸውን መጥፎ ድርጊት እያስቀመጡ መሆናቸውን በመጠቆም ባጭሩ ጽሑፌን ልቋጭ፡፡ ሰላም፡፡

ለጠቃሚ ምክርና ገምቢ አስተያየት የምገኝበት አድራሻ፡- nzeleke35@gmail.com

The post ኑሮ በአዲስ አበባ (ነፃነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ) appeared first on Zehabesha Amharic.

አምባገነኖች ለምን ምርጫ ያካሂዳሉ? –ከአብይ ተክለማርያም

$
0
0

ከአብይ ተክለማርያም (የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጠኛ)

በመጪው ግንቦት ወር በኢትዮጵያ ምርጫ ይካሄዳል። በአምባገነን ሥርዐት ውስጥ የሚደረግ ምርጫ ለገዢም ኾነ ለተገዢ ምጥ ነው። “አምባገነኖች ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል እምነት የሚጣልባቸው እንዳልኾኑ እየታወቀ ምርጫ ላይ ለምን ይሟዘዛሉ?” የሚለው እንቆቅልሽ ለብዙዎች ያልተፈታ ጥያቄ ነው። ዐቢይ ተክለማርያም አምባገነኖች ለምን ምርጫ ያካሂዳሉ የሚለውን እንቆቅልሽ ለመፍታት ስምንት መላምቶችን ይዞ ብቅ ብሏል። በመጀመርያው ክፍል እውን እንደሚባለው አምባገነኖች ምርጫ የሚያደርጉት ሌጂትሜሲ ፈልገው ነውን? ሲል ይጠይቃል።
******

abiye

አምባገነኖች ከሚያካሂዱት ምርጫ ጋራ የሚስተካከል ‘የነፍስ ውጪ-ነፍስ ግቢ’ ፖለቲካ ያለ አይመስልም። ዋንጫውን በልቶ “የርግብ አሞራ” ብሎ የሚጨፍረው ቡድን ማንነት ጫዎታው ሳይጀመር የተረጋገጠ ቢኾንም “ለግጥሚያው ሽር ጉዱ” የሚጀመረው ከአንድ ዓመት በፊት ነው። አምባገነኖች ደግሞ ለሥራ ሲነሱ በጠዋቱ አፋቸውን የሚያብሱት ተቺዎቻቸው ላይ በሚያሳርፉት ዱላ ነው። የዞን ዘጠኞችን ዕጣ ፈንታ ልብ ይሏል።

በምርጫ ሰሞን ተቀናቃኞች መደበቅ እንኳን አይቻላቸውም። ከሁለት እና ሦስት ዓመታት በፊት አፉን ወለም ያለው ሳይቀር በጥርጣሬ ይታያል፣ በዐይነ ቁራኛ ይጠበቃል፣ ከዚያ አልፈው ደፈርፈር ያሉት ደግሞ ለልማት ተብለው ከተቆፈሩ የውኃ ጉድጓዶች ፊት ለፊት በተገነቡ የፖለቲካ እስር ቤቶች ውስጥ ይዶላሉ። ሚዲያው የሥርዐቱን ታላቅነት፣ ልማታዊነት፣ አብዮታዊነት፣ ብሔርተኝት እና ከዓለም አንደኛነት በመለፈፍ ሕዝቡን ሁሉ በዲስኩር ስካር ናላው እስኪዞር ድረስ ይግተዋል። ተቃናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰበብ እየተፈለገ ይዘጋሉ፤ ያልተዘጉት ድርጅቶች አባላት “ምነው የእኛም በተዘጋ” እስኪሉ አካልና ነፍሳቸው የስንግ ይያዛል። ይኼን ሁሉ አንቀጥቃጭ ምት ተቋቁመው የአምባገነኑን መንግሥት ሹማምንት ባገኟት ጥቂት አጋጣሚ በድፍረት የሚሞግቱ ደግሞ “ጉድ ነው – ፖሊሲ የላቸውም” እየተባለ ማፌዣ ይኾናሉ- ዓለማቀፍ ኮንሰልታንቶችን ቀጥሮ ፖሊሲ ማስጻፍ ልዩ ሞያ ይመስል፤ ከዚያ በላይ የሠላማዊ ሰልፉ፣ የይውደም መፈክሩ፣ የልብ አፍስስ ቀበሌ ስብሰባው ጋጋታ። ከዚያ በሁዋላ ምርጫው ይደረግና በአብዛኛው በተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች እስር የሚጠናቀቅ አወዛጋቢ ቆጠራ ይቀጥላል። አምባገነኑ ምርጫውን ከ-እስከ (Landslide) አሸነፈ ተብሎ ይለፈፋል፤ “ታላቅ የሕዝብ ሠላማዊ ሰልፍ” ተደርጎ፤ የሚዛትባቸው ተዝቶባቸው በመጪው ምርጫ በድል እንገናኝ ተባብሎ ቅዠቱ ይጠናቀቃል። እፎይ!!

በአምባገነን ሥርዐት ውስጥ የሚኖሩ በርካታ ሰዎች ይህ ለገዢውም ለተገዢውም ሰላም የሚነፍግ ድራማ ለምን እንደሚካሄድ እንቆቅልሽ ይኾንባቸዋል። ምርጫ ሲቃረብ “እባካችሁ ተውን አርፈን እንኑርበት፤ በተበላ ዕቁብ በሰንበት ባትበጠብጡን . . .” የሚሉ አስተያየቶችን መስማት የተለመደ ነው:: ከአሳዛኙ ድራማ በላይ እንቆቅልሽ የሚኾነው የሐሰት ምርጫ የሚያደርጉ አምባገነን ሥርዐቶች ዕድሜያቸው እንደ ማቱሳላ የተንዘላዘለ መኾኑ። ከግርጌ የተቀመጠውን ቻርት በጥሞና ይመልከቱ።

የፓርቲ አምባገነኖች (party dictatorships) ከሌሎች አምባገነኖች የላቀ ዕድሜ አላቸው። ብዙዎቹ ከኻያ ዓመት በላይ የመቆየት ዕድላቸው ከ50 ፐርሰንት በላይ ነው (ይህን ቻርት ስንመለከት ኢሕአዴግ ለ24 ዓመት በሥልጣን ላይ መቆየቱ ሊያስገርመን አይገባም።) የፓርቲ አምባገነንነትን ሥርዐት ከሚከተሉ አገሮች መካከል የምርጫ ድራማን የሚያካሂዱ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። በርግጥ እነዚህ አምባገነኖች ዕድሜ ጠገብ የመኾናቸው መንስዔ ምርጫ ብቻ አይደለም። ይኹንና የአምባገነን ሥርዐትን የሚመለከቱ ምሁራዊ መጣጥፎች ብናገላብጥ ምርጫ ለዕድሜ ማስረዘሚያ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ እንማራለን። ለምን? የአምባገነንነትን ሥርዐት የሚያጠኑ የፖለቲካ ምሁራን ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሰንጠረዦችን ቧጠዋል፤ ብዙ ምርምር አድርገዋል፤ የሂሳብ ቀመሮችን ፈጥረዋል። በሰባት ኪሎ መጽሔት የመጀርያው ጽሑፌ ውኃ ያነሳሉ ያልኳቸውን ስምንት መላ ምቶች በርብሬ ለማሳየት እሞክራለሁ። የእነዚህን መላምቶች ጨመቅ እንካችሁ።

1) በአምባገነን ሥርዐት ውስጥ የሚደረጉ ምርጫዎች በቀረቡ ቁጥር ማኅበራዊ ሳይንቲስቶች “ዘ ኤል ዎርድ” የሚሉትን ቃል መስማት የተለመደ ነው። ይህ “ዘ ኤል ዎርድ” የሚወክለው ሌጂትሜሲ የሚለውን ቃል ነው። ቃሉን በሙሉ ስሙ የማይጠሩት እንደ ብዙ የፖለቲካ ጽንሰ ሐሳቦች ግልጽና እቅጩን የኾነ ትንተና ሊሰጠው የሚያስቸግር ቃል በመኾኑ “በሩቁ” እንደሚሉት ለመግለጽ ነው። የሌጂትሜሲ ፍልስፍናዊ ትርጉም እጅግ አወዛጋቢ ቢኾንም ከአምባገነኖች ምርጫ ጋራ በተገናኘ ጥቅም ላይ ሲውል ተግባራዊ ትርጉም ይዞ ነው። በፖለቲካ ምሁራን ዘንድ “የሕዝብ ኀልዮት” ተብሎ የሚጠራ አምባገነኖች የሚያደርጉትን ምርጫና ሌጂትሜሲ በሁለት ዐይነት መንገድ የሚያገናኝ ኀልዮት አለ።
abye tekelemariam

፩) የውስጥ ሌጂትሜሲ፦ ብዙ አምባገነኖች ሥርዐታቸው በጥቂቶች የሚሽከረከር ሳይኾን መደበኛ የአካሄድ ሥነ ሥርዐት የሚከተል እና ሉዓላዊ ተቋማት ያሉት እንደኾነ ማሳየት ይፈልጋሉ። “በሕዝብ በተመረጠ” ፓርላማ ሕጎችንና ደንቦችን ተከትሎ አዋጅ ማውጣታቸው ከዚህ ፍላጎት የመነጨ ነው። ምርጫን ማሸነፍ የሕዝብ ድጋፍና የብቃት ማረጋገጫ ማሳያ እንዲኾንላቸው ይመኛሉ። ይህ ዐይነቱ የውስጥ ሌጂትሜሲ ፍጹማዊ ሌጂትሜሲ ተብሎ ይጠራል። ከዚህ የተለየው ሌላኛው የውስጥ ሌጂትሜሲ ሐሳብ ንጽጽራዊ ሌጂትሜሲ ይባላል። የአፈና እና የጭቆና ተጠቂ የኾኑ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ወቅት በቆርኪ-ተሰፍሮ፣ በስንዝር-ተለክቶ በተሰጣቸው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ መላወስ ይሳናቸዋል። አምባገነኖች ወደ እነዚህ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጣታቸውን እየቀሰሩ “እርባና ቢስነታቸውን ተመልከቱ” በማለት የተቃዋሚዎችን ሌጂትሜሲ በመዳመጥ በንጽጽር የራሳቸውን ሊያጎሉ ይሞክራሉ።

፪) ውጫዊ ሌጂትሜሲ፦ አምባገነን መንግሥታት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አካል ለመኾን ከፈለጉ ቢያንስ የይስሙላ ጨዋነት ሊያሳዩ ይገባል። በተለይ እ.ኤ.አ ከ1990ዎቹ መጀመርያ አንስቶ የፖለቲካ ሥርዐቶች ጨዋነት ከሚለካባቸው መስፈርቶች መካከል አንዱ ጊዜውን የጠበቀ ምርጫ ማካሄድ ነው። ለምሳሌ እ.ኤ.አ በ1993 ኢሕአዴግ ባወጣው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ዶክመንት (አብዮታዊ ዲሞክራሲ 1 ) የምዕራብ አገሮችን ድጋፍና ርዳታ ለማግኘት ምርጫ ማድረግ ግዴታ እንደኾነ ያስቀምጣል።

ይህ ኀልዮት ምን ያህል ጠንካራ ነው? በማስረጃዎች የተደገፈ ነውን?

አንዲት አሜሪካዊት የፖለቲካ ምሁር ላስታውሳችሁ። ባርባራ ጌዴስ ይባላሉ። በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ የፖለቲካ ሳይንቲስት ናቸው። ከዕድሜያቸው አብዛኛውን ያሳለፉት አምባገነን መንግሥታትን በማጥናት ነው። የሥራዎቻቸው ፋይዳ በፖለቲካ ሳይንቲስቶች ዘንድ ከፍተኛ እውቅናን አስገኝቶላቸዋል። በባርባራ ጌዴስ ጥናትና ምርምር ላይ ተመርኩዘው የተጻፉ ምሁራዊ መጣጥፎች በርካታ ናቸው። ከፕሮፌሰር ጌዴስ አስተዋጽዖዎች መካከል አንዱ ከላይ የጠቀስኩትን ሌጂትሜሲንና የአምባገነን ምርጫን የሚያገናኝ ሕዝባዊ መላምት በማስረጃዎች ላይ ተመርኩዙ አንኮታኩቶ መጣል ነው። ለምሳሌ፦ አምባገነኖች ያላቸውን የሕዝብ ተቀባይነት በጥንቃቄ የሚመረምሩ ጥናቶች፤ ምርጫ ከሚደረግበት ወቅት ይልቅ ምርጫ በሌለበት ጊዜ የበለጠ ተቀባይነት እንዳላቸው ያሳያሉ። የሥርዐቱ ተገዢዎች በምርጫ ሰሞን በሚጦዘው አፈናና ጭቆና እንዲሁም ከምርጫ ጋራ ተያይዞ በሚመጡ ውዝግቦች ምክንያት በሚፈጠረው አለመረጋጋት ምሬት አሰቃይቷቸው ለአምባገነኑ ያላቸው አስተያየት ቢቀንስ የሚያስገርም አይደለም። ይህን ባርባራ ጌዴስ የሌጂትሜሲ ዕዳ (legitimacy cost) ብለው ይጠሩታል። ይህ ሐሳብ ወደ ውጫዊ ሌጂትሜሲም ይሻገራል። በምርጫ ወቅት አምባገነን መንግሥታት ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሚያገኙት ሽፋን ከአዎንታዊነቱ ይልቅ አሉታዊነቱ ያመዝናል። የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሲቪክ ማኅበራትም ምርጫን ተገን አድርገው አምባገነን ሥርዐቶች የሚፈጽሟቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና አፈናዎች የሚያጋልጡ ዳጎስ ያሉ ሪፖርቶች ያወጣሉ። ይህን የሚያሳዩ በይዘት ብጠራ (content analysis) ላይ ያተኮሩ ጥናቶች አሉ። የአምባገነኖች ወዳጅ መንግሥታት ሳይቀሩ በምርጫ ጊዜ የሚከሰቱ አፈናዎችንና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ፈራ ተባ እያሉ ሲያወግዙ ይታያል። በርግጥ እንደ እ.ኤ.አ በ1990ዎቹና በ2000ዎቹ መጀመርያ ሊበራል ዲሞክራሲ የዓለም ልዑል አይዲዮሎጂ በነበረበት ወቅት እንዲህ ዐይነቱን አሉታዊ ሪፖርቶችና ውግዘቶችን የሚያስከትል ምርጫ አለማካሄድ ይመረጥ ነበር። ይኹንና ከዚያ በኋላና ከዚያ በፊት አምባገነኖች ምርጫ ባለማካሄዳቸው ከሚመጣባቸው ትችት የበለጠ ምርጫ አካሂደው ከምርጫው ጋር ተገናኝቶ በሚነሱ ጉዳዮች የሚከሰትባቸው ውግዘት የበለጠ አሉታዊ ነው። ሌጂትሜሲን የሚሰባብር እንጂ የሚጨምር አይደለም። ታዲያ አምባገነኖች ምርጫ ሲያደርጉ ሌጂትሜሲያቸው የሚቀንስ ከኾነ ለምን አይተውትም?

በጽሑፌ ክፍል ሌሎቹን መላምቶች ይዤ እመለሳለሁ።

ምንጭ 7 ኪሎ ሚድያ

The post አምባገነኖች ለምን ምርጫ ያካሂዳሉ? – ከአብይ ተክለማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.

የዲያቆን ዳንኤል ስሜታዊ ትንታኔና መሬት ላይ ያለው እዉነታ ! የመጨረሻ ክፍል –አብዱላህ

$
0
0

daniel-kibret-300x207ዲ/ዳንኤል አክራሪ ያሉዋቸው ሰለፊስቶች የሃገራችንን ነባር እስልምና ተከታዮች ቅዱሳን የማይቀበሉ ፅንፈኞች ናቸው ሲሉ አውግዘዋቸዋል። እዚህ ላይ የተቆረቆሩላቸው ለማስመሰል የሞከሩትን የቀድሞዎቹን ሙስሊሞች በዚሁ ንግግራቸው ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር አብረው ሃገር ያደሙ በማለት ሲወነጅሏቸው እንደነበር አድማጭ የዘነጋ ይመስል የዛሬዎቹን ሙስሊሞች ዉንጀላ ጎላ ለማድረግ ለቀድሞዎቹ አጋዥ መስለው ቀርበዋል።

ለነገሩ በቀዳሚነት ሊያሳስባቸው ይገባ የነበረው በሃገራችን የተዋህዶ ኦርተዶክስ ቤተክርስቲያን የምታመልካቸውን ቅዱሳን ከማስተባበል  አልፈው የቲዮሎጂ ስነ-ምግባር በጎደለው መልኩ መሳለቂያ እያደረጉ ያሉት አንዳንድ የሃገራችን የፕሮቴስታንት ፓስተሮች ድርጊትና የእርሳቸው እምነት ውስጥ ጉዳዩ ያስከተለው የመከፋፈል ችግርን ነበር ። በዚህም ድርጊታቸው ለአድማጮቻቸው ያላቸን ከፍተኛ ንቀት ይፋ አድርገዋል ።

በንግግራቸው ያነሱት ሌላው ጉዳይ አክራሪዎች የሚሏቸው በአክሱም መስጅድ እንዲገነባ ጥያቄ ማቅረባቸውን ነው።  ከንግግራቸው ለመረዳት የቻልኩት አክሱም ፅላት ያረፈባት ስፍራ በመሆኗ የእስልምና እምነት የአምልኮ ስፍራውን ያረክሰዋል በሚል ህሳቤ ነው። ለዚህ አስተሳሰብ መንስኤው አክሱም ፅድቅነቷ እንዲጠበቅ ከሚያረክሷት ነገሮች የጸዳች ልትሆን ይገባል ከሆነ እስኪ የሚከተሉትን እውነታዎች በሚዛናዊነት ለመዳኘት እንሞክር።

  • ሁላችንም የምንኮራባቸው የአክሱም ስልጣኔ መገለጫ ግዙፎቹ ሃዉልቶች ዛሬም የቀደምት ህዝቦቻችን እምነት የሆነውን የጣኦት አምልኮ አሻራን እንደያዙ በአክሱም ከተማ ይገኛሉ። እንደ ማንኛዉም  ኢትዮጵያዊ እነዚህ ቅርሶቻችን በተገቢው መንገድ እንዲጠበቁ እፈልጋለሁ ። እዚህ ላይ ግልጽ እንዲሆን የፈለኩት ነጥብ አክሱም ፅድቅነቷ እንዲጠበቅ እንፈልጋለን ባዮች አንድን ቅዱስ ስፍራ ከጣኦት አምልኮ መገለጫ ቅርሶችና ድርጊቶች  በላይ  እንዴት ሆኖ አንድ አምላክ የሚመለክበት መስጂድ ሊያረክሰው ይችላል ? የሚለዉን ነዉ ።
  • የአክሱም ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው ቱሪስቶች መዳረሻ መሆኗ ይታወቃል። ከዚህም ጋር በተያያዘ መልኩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዳንኪራ  እና ዝሙት የሚፈፀምባቸው ቤቶች በከተማይቱ ውስጥ ይገኛሉ። ዝሙት ደግሞ በመፅሃፍ ቅዱስ ከተወገዙት ሃጥያቶች አንዱ ነው።  በእውን ለከተማይቷ ቅድስና የምንቆረቆር ከሆነ ከዚህስ የባሰ የሚያረክስ ጉዳይ ይገኛልን ?

ከላይ የጠቀስኳቸውን ነጥቦች በሚዛናዊነት ከዳኘን በአክሱም  የሙስሊሞችን የፀሎት ቦታ መገንባትን የሚቃወሙ ግለሰቦች ለዚህ ሀሳብ ያነሳሳቸው ዋና ምክንያት መንፈሳዊ ገፅታው እንዳልሆነ ለመረዳት አያዳግትም።  ይህ ካልሆነ ደግሞ ተቃውሞው ያነጣጠረው የዜጎችን መብት በመግፈፍ ላይ መሆኑ ግልፅ ነው ።

በሃገራችን ህገ-መንግስት አንቀፅ 27  ዜጎች የአምልኮ ስፍራቸውን በነጻነት የመገንባት መብታቸው የተጠበቀ ሆኖ ሳለ ይህን የጠየቁ የአካባቢው ተወላጆችን እና ነዋሪዎችን እንደ ፅንፈኛ መቁጠር ህገ-መንግስታዊ መብትንና ሃገራችን በፈረመቻቸው ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች የተከበሩ ተመሳሳይ መብቶችን  ማስተባበል ጭምር መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።

ዲያቆኑ የአክራሪዎች ሌላው መገለጫ ያሉት “ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት ነች ”የሚለውን ሃሳብ መቃወማቸው ነው በማለት በሃገራችን   ኢትዮጵያ የእኩል ባለቤትነት መብት እንዳላቸው የሚገልጹ ሙስሊሞችን ለማሸማቀቅ  ሙከራ አድርገዋል ።  ይህን አስተሳሰብ ከታሪክም ሆነ ከዜጎች መብት አኳያ መመርመሩ ግንዛቤ ሊያስጨብጥ ስለሚችል የሚከተሉትን ነጥቦች ማየት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

የዲ/ ዳንኤልን አጠቃላይ ፅሁፉቸው አንኳር ነጥብ ያነጣጠረው ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከሌላ ስፍራ መጥቶ  የሃገር ባለቤት በሆነው የክርስትያን ህዝብ መልካም ፈቃድ በአገሪቱ የሰፈረ ውለታ የተዋለለት ባዕድ ህዝብ አድርጎ መሳልን ነው።  ይህ ህሳቤ መሰረቱ ክርስትናን ሃገር በቀል እስልምና ግን መጤ አድርጎ በመሳል ላይ የተመሰረተ ታሪክን ያዛባ አቀራረብ ነው።  እውነታው ግን ክርስትናም ሆነ እስልምና በመካከለኛው ምስራቅ የበቀሉ እና ወደ ሃገራችን ኢትዮጵያ የገቡ መሆናቸው ነው።  ሁለቱንም እምነቶች የተቀበሏቸው  ሃገር በቀል ህዝቦች ናቸው።  ለዘመናት በግልፅም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ ሲነገር የቆየው እና በህብረተሰብ ውስጥ ለማስረፅ የተሞከረው ህሳቤ ዛሬ ላይ ዲ/ ዳንኤል የደገሙት የተዛበ የታሪክ አቀራረብ ነው። ይህ ህሳቤ ሙስሊሙ እና ክርስትያኑ ማህበረሰብ እኩል የሃገር ባለቤት እና እኩል የሃገር ተቆርቋሪ መሆናቸዉን በማስተባበሉ በጋራ – ለጋራ መብት እንዳይነሳ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል።  ዛሬም ይህንኑ ክፍተት ለማስፋት እና የዜጎችን ለጋራ መብት አብሮ መነሳት ለማኮላሸት በሃይማኖት አባትነት ካባ የተሸፈነ አጀንዳ እያራመዱ መገኘታቸው ነው።

ከዚህ  መረዳት እንደሚቻለው ኢትዮጵያ ሃገራችን ዲ/ዳንኤል እንደሚሉት የአንድ እምነት ተከታይ ህዝቦቻችን ብቻ ሃገር ሳትሆን የሁላችንም ኢትዮጵያውያን ሃገር መሆኗን ነው። ባለንበት በ 21ኛዉ ክፍለ ዘመን ሃገራችን ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ሃገር ነች ለማለት የደፈሩት ዲ/ ዳኒኤል ኢትዮጵያ የጋራ ሃገራችን ነች የሚለዉን ሙስሊም ወገናቸውን አክራሪ ብለው መወንጀላቸው ለምን ይሆን ? አባባላቸው ቀዳማዊ ሃይለስላሴ  እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የማንቆጠርና ይልቁንም የክርስቲያኖች ሃገር በሆነችዉ ኢትዮጵያ የምንኖር መሆናችንን እንዳንዘነጋ በየንግግሮቻቸው “በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሙስሊሞች ” እያሉ ይጠሩን የነበረውን አስታወሰኝ ። ልንዘነጋው በማንችለው መልኩ በልቦናችን ይሰርፅ ዘንድ በተረትና ምሳሌ ሳይቀር “የአሞራ ቤቱ ዋርካ የእስላም አገሩ መካ” ሲሉም እንሰማለን።  ታዲያ ዲ/ ዳንኤል ይህን ከቀደምት ነገስታቶቻችን ካባ ጎን ለጎን በሙዚየም መቀመጥ ያለበትን ዘመን የሚጠየፈውን ህሳቤ የማንቀበል እና በአገራችን ኢትዮጵያ የእኩል ባለቤትነት መብት ይገባናል ባይ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን አክራሪ ሲሉ መወንጀላቸው ምንን ያመላክታል?

ከታሪክ አኳያ፡-

አገራችን ኢትዮጵያ የረዥም ዘመን ታሪክ ያላት አገር ነች።  በተለያዩ  የታሪክ ዘመናትም የተለያዩ የግዛት ክልሎች የነበሯት።  በውስጧ የኖሩባትም ህዝቦች የተለያየ የዘር እና የሃይማኖት ስብጥር ፣  የስልጣኔ ደረጃ ፣ የአስተዳደር ስርዓት ወዘተ  ነበራቸው ።

በሃገራቸን 3000 ዘመን ታሪክ ውስጥ፡-

  • የመጀመርያዎቹ 1300 ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት 900 አመታት እና ከእየሱስ ውልደት በሁዋላ 400 ዓመታት የጣኦት አምልኮ ተከታዮች እና የኋላ ኋላ የተቀላቀሏቸው የይሁድ እምነት ተከታይ ህዝቦቻችን የኖሩባት ሲሆን እነሱም ሁላችንም የምንኮራበትን የአክሱም ስልጣኔን ያስመዘገቡ እና በቅርስነት አስደናቂ ሃውልቶችን ትተውልን አልፈዋል።
  • በመቀጠልም የክርስትና እምነትን የተቀበሉ ህዝቦቻችን በ4ኛው ክፍለ ዘመን ከጣኦት አምልኮ ተከታዮች የወረሱትን ስልጣኔ ለ100 ዓመት ካሳደጉት ቡሃላ በ5ኛው ክፍለ ዘመን ስልጣኔው ማሽቆልቆል የጀመረ ሲሆን በ960 በዮዲት ድል እንደተደረገ በታሪክ ተዘግቧል
  • በማስከተልም የኩሽ ህዝቦች ዝርያ የሆነው የዛጉየ ስረዎ-መንግስት በ1137 -1270 የተተካ ሲሆን እነዚህ የአገው ህዝቦች የላሊበላን ገዳማት እና አብያተ ክርስትያናት በቅርስነት ትተውልን አልፈዋል
  • ከዛጉየ ቀጥሎ የነበረው የንግስና ስርአት ሰለሞናዊው ስርዎ-መንግስት ሲሆን ይህ ስርዎ-መንግስት ከ1270 ጀምሮ የነበረ እና የግዛት ክልሉም በዛሬው ሰሜናዊ የሃገራችን ክልል ላይ ብቻ የተወሰነ ነበር

 

ከላይ የተዳሰሰው በዛሬዋ የሃገራችን ሰሜናዊ ክፍል የነበረውን የታሪክ ገፅታ ሲሆን ።  በዛሬው የመካከለኛው ፣ የምስራቅ እና ደቡባዊ የሃገራችን ክፍሎች ደግሞ ከ7ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተለያዩ የሙስሊም መንግስታት (ሱልጣኔቶች) ነበሩ።

 

  • ከነዚህ ውስጥ የሃረር ሱልጣኔት በ7ኛው እና 11ኛው ክፍለ ዘመን መካከል የተመሰረተ ሲሆን መንግስቷም በንግድ የታወቀና የራሷ ገንዘብም የነበራት ነበረች።  ከተማይቷ በ2006 በዩኔስኮ የአለም ቅርስነት የተመዘገበች ስትሆን ይህንንም ድርሻ ያሰጧት በ10ኛው  ክፍለ ዘመን የተሰሩት ውብ መስጅዶች እና ብዙ የአምልኮ ስፍራዎች ናቸው።  ይህ ማለት ደግሞ ከላሊበላም ሆነ ሌሎች ቆየት ካሉ ታሪካዊ የእምነት ቦታዎች ቀዳሚውን ስፍራ ያስይዛታል።
  • በሁለተኛ ደረጃ የሚቆጠረው የሸዋ ሱልጣኔት ሲሆን ይህም ከ896 እስከ 1283 የኖረ በጉራጌ ህዝቦች የተመሰረተ ስርዎ-መንግስት ነበር። ግዛቱም ከዛሬይቱ አዲስ አበባ 70 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወለላ ተብላ በምትጠራ ሰሜን ሸዋ አካባቢ   ነበር።  ይህ ንግስና ዘጠኝ ሱልጣኖች በተዋረድ የገዙት እና ከ150 ዓመት በላይ የቆየ እንደነበር የታሪክ ሰነዶች ያሳያሉ።  በፈረንሳይ አርኪዮሎጂስቶች የተገኙ ሶስት የከተማ ፍርስራሽ እና የመስጅድ ቅሪቶች የሸዋን ኢስላማዊ መንግስት የእድገት ደረጃውዋናም ማረጋገጥ ችሏል።
  • በሶስተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የሃድያ ሱልጣኔት ነው። ይህ ሱልጣኔት ከ1300 እስከ 1500ኛው ክ.ዘ የዘለቀ ሲሆን ግዛቱም በዛሬዋ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ  ድንበሩም በሰሜን በኩል የአባይን  ወንዝ የሚነካ ነበር
  • የይፋት ሱልጣኔት በመባል የሚታወቀው ደግሞ ከ1285 እስከ 1415 የኖረው ነው። ይህ በአፍሪካ ቀንድ ታላቅ ተብለው ከሚጠሩት የሙስሊም ሱልጣኔቶች ውስጥ አንዱ ነው።  ግዛቱም ከዛሬዋ ሸዋ ጀምሮ ባሌን ያጠቃለለ እስከ ምስራቅ ጅቡቲ እና ሰሜን ሶማልያን የያዘ እንደነበር እና ማዕከሉም ዘይላ እንደነበር ታሪክ ያብራራል። ሱልጣኔቱ ሰባት ዋና ዋና ከተሞች የነበሩትና በአስተዳደር ረገድም የረቀቀ እንደነበር መዛግብት ያሳያሉ። በዚህ ረገድ የተለያዩ ያልተጠቀሱ የሙስሊም መንግስታት እንደነበሩ መታወቅ ይኖርበታል እንደምሳሌ፡- የአዳል ፣ ባሌ እና ወዘተ

ከላይ የተመለከተናቸው አጠር ብለው የቀረቡት ታሪኮች በግልፅ እንደሚያሳዩት ዛሬ የኛ ትውልድ የሚኮራባቸው ታሪኮቻችን በዛሬው የሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የኖሩት የጣኦት አምልኮ ተከታይ ህዝቦች የተዉልን ስልጣኔ 1300 ዓመት እድሜ ያስቆጠረ እንደነበር አይተናል።  ከዛም የክርስትና እምነት ወደ ሃገራችን የሰሜኑ ክፍል ከገባ ቡሃላ የራሱን ድርሻ አበርክቷል።  በተመሳሳይ መልኩ በዛሬው መካከለኛ ፣ ምስራቃዊ እና ደቡባውው የሃገራችን ክፍሎች ደግሞ የእስልምና እምነት የሚከተሉ ህቦቻችን ያበረከቷቸውን ታሪካዊ ስልጣኔዎች እና ቅርሶች ለማየት ሞክረናል። ከዚህ ላይ መረዳት እንደሚቻለው ኢትዮጵያ ሃገራችን ዲ/ዳንኤል እንደሚሉት የአንድ እምነት ተከታይ ህዝቦቻችን ብቻ ሃገር ሳትሆን የሁላችንም ኢትዮጵያውያን ሃገር መሆኗን ነው። ዲያቆኑ ይህን መሰሬታዊ  ነጥብ እንኴ ለመረዳት ያለመቻላቸውን አሳፋሪ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ።

የዲ/ዳንኤል ሌሎች የአክራሪነት ክሶች በጥቅሉ፡-  የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን በሃገራቸው ያላቸውን ዜግነት እና ህገ-መንግስታዊ መብቶች የጣሱ ናቸው እንደምሳሌ፡-

  • እርሳቸው ለአፍሪካ እና ለዓለም ሃዋርያነት እራሳቸውን እና ተከታዮቻቸውን ዝግጁ መሆን እንደሚገባቸው ሲሰብኩ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ በሃገሩ ወገኖቹን ማስተማሩን እንደ ፅንፈኝነት መገለጫ መቁጠራቸው
  • ለራሳቸው ተከታይ ምዕመናን የክርስትና ትምህርትን እንዲያስፋፉ ጥሪ በማቅረብና ህዝበ ኦርቶዶክሱ ሃይማኖቱን በማስፋፋቱ በኩል በንቃት ባለመሳተፋ ወቀሳ ሲያቀርቡ ፥ በሙስሊሞች በኩል ያለዉን በተመለከተ መድረሳዎችን እና የቁርዓን ት/ቤቶችን የሚያስፋፉት አክራሪዎች ናቸው በማለት ወንጅለዋል
  • በመላው የሃገራችን ግዛቶች (ክልሎች) በኢስላማዊ ትምህርት በዲግሪ የሚያስመርቅ አንድም ተቋም የሌለ ሲሆን በዲፕሎም ደረጃ አንድ አወልያ ብቻ እንዳለ እየታወቀ አክራሪ ሙስሊሞች በነዚህ ዘርፎች ብልጫ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ በመሆናቸው ልናጋልጣቸው ይገባል ሲሉ ለምእመኖቻቸው ጥሪ አድርገዋል። ይህ አባባላቸው እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በሃገራችን ያለንን መብት ለመንፈግ የተደረገ የማን አለብኝነት ስሜት ነው።

”ሽብርተኞቹ ንግድ እና ትምህርትን ቀላቅለው የሚያስኬዱ በመሆኑ መረጃ በመሰብሰብ እና በማጋለጥ ለመንግስት ማሳወቅ ይኖርብናል” ብለዋል። ይህም አባባላቸው ተምረው ራሳቸዉን ፣ ሃገራቸውን እና ህዝባቸውን ለማገልገል የሚተጉ ሙስሊም ዜጎችን ለማሸማቀቅ ብሎም ከትምህርት እና ንብረትን ከማፍራት ለመግታት የሚደረግ ኢ-ፍትሃዊ እና ኢ-ህገመንግስታዊ የዜግነት መብት ጥሰት ነው።

ዲያቆን ዳንኤል እንደ  አንድ የሃይማኖት አባት እውነት  በመናገር እና ሚዛናዊ ግምገማ በማድረግ  አርአያ ሊሆኑ  ሲገባ በተቃራኒው የእስልምናን ገጽታ  ለማጠልሸት ባላቸው ስሜት በመነዳት በክርስትናም ሆነ በሌሎች ሃይማኖቶች መሃል ግጭቶች የተነሱና ደም ያፋሰሱ እንደ ነበር በመሸሸግ  በእስልምና ውስጥ ብቻ ተነሱ የተባሉትን በማጋነን እኛ ሙስሊሞችን ለማሸማቅቅ ሞክረዋል ። እስልምና ከጥንት ጀምሮ ነውጥ ያስከተለ  ብቸኛ እምነት ለማስመሰልም

  • ሰለፍይ ብለው የሚጠሯቸውን ሲገልፁ -”ጥንት ከጅምሩ የአስተምሮቱ ተከታዮች እስልምናን ከቁርዓንና ከሃዲስ ውጭ ሌላ ጭማሪ ሳይደረግበት መተግበር አለበት የሚለውን ፅንሰ-ሃሳብ የሚያራምዱ  ናቸው “በማለት የኮነኑ ሲሆን፣ በተመሳሳይ አካሄድ በክርስትና እምነት   ውስጥ የ reformation  መሪና የፕሮቴስታንት ዘርፍ  መስራች የሆኑት ማርቲን ሉተርን  መፅሃፍ ቅዱስ ብቻ (sola scriptura)  ማለትም መፅሃፍ ቅዱስ ብቻ የእምነት መመሪያ ሊሆን ይገባዋል በሚል መርህ የፕሮቴስታንት የእምነት ዘርፍን   የመስረቱ መሆናቸውን ሸሽገዋል።
  • የስለፎች እንቅስቃሴ በአረቢያ እና አካባቢዋ በርካታ ግጭቶችን ያስነሳና ለበርካታ ህይወት መጥፋት ምክኒያት እንደ ነበረ ሲገልጹ እንደ አንድ ታአማኒነት ያለው እዉነት ፈላጊ የሃይማኖት አባት በማነጻጸር ሚዛናው ግንዛቤ እንዲኖረን በሪፎርሜሽን ሳቢያ ተቀስቅሶ  አውሮፓን ለ 124 አመታት (ከ 1524 እስከ 1648) የጦርነት አውድማ ያደረገዉንና የጀርመንን  ፣ የፈረንሳይን ፣የኦስትሪያን ፣የሃንጋሪን፣የጣሊያንን ፣የፖላንድን ፣ የስሎቫኪያ እና የዩክሬንን 30% ህዝቦች ለእልቂት የዳረገዉን አሰቃቂ ሃይማኖታዊ(ክርስትያናዊ)ጦርነትን ግን ለምን ሸሸጉን ? ሰለፎች   ባራመዱት አስተምህሮት ሳቢያ የተፈጠሩትን  የህይወትና የንብረት ውድመትን የምያሳዩ ማስረጃዎችን ቢፈትሹ እርሳቸዉም በስሜት ከመነዳት ድነው ሌሎች ወገኖቻችንንም ከስህተት እንዲድኑ ለማድረግ ይችሉ  ነበር።

ጥንትም ሆነ ዛሬ የጥፋት ሃይሎች በሁሉም ሃይማኖቶች ስም ወንጀል የሚፈጽሙ መሆናቸው እየታወቀ ዲያቆን ዳንኤል  ግን ለጥፋት የተሰማሩ ድርጅቶች በእስልምና ስም ብቻ የሚንቀሳቀሱ ለማስመሰል  እንደ አል ቃእዳ ፣ አል ሸባብ ፣ ቦኮ ሃራም ወዘተ ያሉትን የጥፋት ሃይሎች ብቻ ገልጸው በክርስትና ስም ጥፋት ያደረሱና በማድረስ ላይ ያሉትን  በሰሜን ዩጋንዳ በክርስትና ስም የምንቀሳቀሰዉን ፣ አስርቱን ቃላት በስራ የማዋል አላማ አለኝ የሚለዉን እና  እስከ 150 000 ለሚደርስ ህይዎት መጥፋት ምክኒያት የሆነዉን Lord Resistace Army LRA፣ በኦርቶዶክስ ስም ተንቀሳቅሰው በስረብረኒካ እስ 8 000 የሚደርሱ ሰላማዊ ሙስሊሞችን የፈጁ አክራሪ ኦርቶዶክስ ሰርቦች ፣ በ 2014 Central Africa በብዙ ሺ የምቆጠሩ ሙስልሞችን በግፍ የጨፈጨፉና የጥቂቶቹን ስጋ  የበሉ ራሳቸውን የክርስቲያን ሚሊሺያ ብለው የጠሩትንና ሌሎችንም   ሸሽገዋል።

በጥቅሉ የዲያቆን ዳንኤል ፅሁፍና አዉድዬ የአንድ ሃገር ዜጋ የሆነ ህብረተሰብን የዜግነት መብት የሚያስተባብል በእምነት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እርስ በእርስ በባላንጣነት እንዲተያዩ በማድረግ ለጋራ ጥቅም እና መብት በጋራ እንዳይነሱ ለማድረግ ያለመ ነው።  እንደሃይማኖት አባትነት ወደ ልዩነት ከሚያመሩ ጎዳናዎች ምእመናንን በመከላከል ህዝቦች ተሳስበው ፣ ተከባብረው ፣ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው እንድኖሩ መምከር ስጠበቅባቸው ፣ እሳቸው ግን በተቃራኒው ህዝባችን ተራርቆ ወገኖቻችን የጋራ ሃገራቸውን እንዳይጠብቁ እና እንዳይገነቡ እሳት የመጫር ዓላማ ያነገቡ ናቸው ለማለት እደፍራለሁ።

ጨረስኩ ።

ቸር እንሰንብት!

አብዱላህ

25 March 2015

The post የዲያቆን ዳንኤል ስሜታዊ ትንታኔና መሬት ላይ ያለው እዉነታ ! የመጨረሻ ክፍል – አብዱላህ appeared first on Zehabesha Amharic.


ጊፍት ሪል እስቴት ወደፊት ወይስ ወደ ኋላ

$
0
0

nlmqi6fn76e6fjt0pj5uአንዳንዴ እንዳለመታደል ነው መሰል በሌሎች ሀገሮች ተብለው ተብለው ያለቀላቸው ነገሮች እኛ ሀገር ሲገቡ ልክ በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደምንሠራቸው መስለው ቁጭ ይላሉ፡፡ ሌላ ቦታ ተሠርተው፣ ችግሮቻቸው ታውቀው፣ ልምድ ተቀስሞባቸው፣ አዳዲስ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎች ተፈልስፈውላቸው፣ የኖሩ ጥበቦች እኛ ሀገር ሲገቡ የእናታቸው መቀነት ያደናቅፋቸዋል፡፡ እንዲህ እንድል ከሚያደርጉኝ ነገሮች አንዱ ሪል እስቴት ነው፡፡ ከምዕተ ዓመታት በላይ የዘለቀን የቤቶች ግንባታ ዘዴ እኛ ሀገር ገብቶ መከራውን ሲያይ መታዘቤ ነው እንዲህ ያሰኘኝ፡፡ በሰው መሬት ላይ መገንባት፣ ያልተገባ ውል ከቤት ገዥ ጋር መዋዋል፣ ለአካባቢ ጤናና ውበት አለመጨነቅ፣ በጊዜ ገንብቶ አለማስረከብ፣ ገንዘብን ይዞ ከሀገር መጥፋት፣ ቤት እሠራለሁ ብሎ የወሰዱትን መሬት መሸጥ፣ የፍሳሽ ማስወገጃና የውስጥ ለውስጥ መንገድ የሌለው መንደር መገንባት፣ ኧረ ስቱ ይነገራል፡፡

እኔ ጊፍት ሪል እስቴት ከሚባል ድርጅት የዛሬ ሰባት ዓመት ቤት ገዝቻለሁ፡፡ የቤቱን ዋጋ በመቶ በመቶ ከፍያለሁ፡፡ መቶ በመቶ ብትከፍሉ በፍጥነት ይደርስላችኋል ዋጋም ይቀነስላችኋል ተብሎ ስለነበር፡፡ ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ አሉ፡፡ ነገር ግን ይሄው ሰባት ዓመት ሆነው፤ ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም ሆኗል፡፡ የቤቱ መሠረት ከመውጣት ያለፈ ነገር ጠብ ሊል አልቻለም፡፡ በተደጋጋሚ ከዋና ባለቤቱና ሥራ አስኪያጁ ጋር ተነጋግረናል፣ ከአራት ጊዜ በላይ ተጻጽፈናል፡፡ ውጤት ግን አላመጣም፡፡

ጊፍት ከደንበኞቹ ጋር ውል ሲፈርም በአሥራ ስምንት ወራት ገንብቶ ሊያስረክብ ነበር ግዴታ የገባው፡; እኔ እስከማውቀው ድረስ ግን ከሦስት ዓመት በፊት ገንብቶ ያስረከበው ቤት የለም፡፡ ገንብቶ ያስረከባቸው ቤቶች ቢሆኑም አምስት ችግሮች አሉባቸው፡፡ የመጀመሪያው የባለቤትነት ማረጋገጫ የላቸውም፡፡ ጊፍት ሪል እስቴት ስሙ እንዲነሣበት ከማይፈልጋቸው ነገሮች አንዱ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ነው፡፡  የአዲስ አበባ መስተዳድር እንኳን ሕገ ወጥ ይዞታዎችን ሕጋዊ ለማድረግና ካርታ ለመስጠት በተዘጋጀበት በዚህ ዘመን ጊፍት ግን ቤት ላስረከባቸው ሕጋዊ ገዥዎች እንኳን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተሩን ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም፡፡ ሲጠየቅም የየካ ክፍለ ከተማና የአዲስ አበባ መስተዳድር ካርታውን እንደያዙበትና ለማስለቀቅ እየታገለ መሆኑን ነው የሚናገረው፡፡ ምንጊዜም የሚያመካኘው በመስተዳድሩ ነው፡፡

ሁለተኛው ችግራቸው መንገድ ነው፡፡ ወደ ጊፍት ሪል እስቴት የሚወስደው መንገድ በሁለት ችግሮች ምክንያት አልተሠራም፡፡ አንደኛው ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሲሆን ሌላው በሪል እስቴቱ ድክመት፡፡ ድርጅቱ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር አይጥና ድመት ሆኖ  ነው የሚኖረው፡፡ ለዚህ አንደኛው ምክንያት ደግሞ ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ከመፍታት ይልቅ ማስፈራራትን ስለሚመርጥ ነው፡፡ የክፍለ ከተማው ባለሥልጣናት ባሉበት ችግሩን ለመፍታት የተጠራውን ስብሰባ የጊፍት ኃላፊዎች ባለመገኘታቸው ነው ውጤት አልባ የሆነው፡፡ የድርጅቱ መኪኖችም ሆኑ ነዋሪዎቹ ከዋናው አስፓልት ወደ ግቢው ለመግባት የሚጠቀሙበትና ‹መሪ ቁጥር አንድ› የሚባለው መንገድ ጊፍት ሪል እስቴት የሚደርስበትን መዋጮ ባለመክፈሉ ከሁሉም የአካባቢው መንገዶች ተለይቶ እስካሁን አልተሠራም፡፡ አስፓልት ይሆናል የተባለው መንገድ ኮብል ስቶን እንደናፈቀው ቀርቷል፡፡ የወረዳው መስተዳድር ችግሮቹን ለመፍታት ያደረገው ጥረትም በድርጅቱ እምቢ ባይነት ከሽፏል፡፡ ክፍለ ከተማውም ከዐቅሜ በላይ ነው ብሏል፡፡ ነዋሪዎቹ ግን ይሰቃያሉ፡፡

በሪል እስቴቱ ግቢ ውስጥ መንገድ የለም ማለት ይቻላል፡፡ በተፈጥሮው ሜዳ የሆነ ነገር እንጂ ሆነ ተብሎ የተሠራ መንገድ የለም፡፡ ከቤት ገዥዎቹ ጋር በገባው ውል መሠረት ግን የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ሠርቶ የማስረከብ ግዴታ ነበረበት፡፡ በግቢው ውስጥ ያሉ ኃላፊዎች ድርጅቱ ገንዘብ ስለሌለው ሊሠራው እንደማይችል ይነግሩናል፡፡ ዘወትር የሚሰጡት ምክንያት የነዳጅ ብር ስለጠፋ፣ መካኒኩ ደመወዝ ስላልተከፈለው፣ የሠራተኞች ደመወዝ ስላልደረሰ፣ መኪናው ተበላሽቶ የመለዋወጫ መግዣ ስለሌለ የሚል ነው፡፡ ያ ግን ሕጋዊ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ወይ ባልዘፈንሽ እንደሚባለው አሁን መሐል መንገድ ላይ ዐቅም የለኝም ከማለት መዘጋጀት አስቀድሞ ነበር፡፡ ዝናብ ጣል ካደረገ ጊፍት ግቢ ውስጥ በቦቴ ጫማ እንኳን ለመግባት ከባድ ነው፡፡ መግባት የሚቻለው በሄሊኮፕተር ብቻ ነው፡፡ ለዚያውም ማረፊያ ከተገኘ፡፡

ሦስተኛው ችግር ውኃ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪ ወር ሙሉ ውኃ ጠፋብኝ ብሎ ያማርራል፡፡ ጊፍት ግቢ ውስጥ ግን ላለፉት ሰባት ዓመታት ውኃ የለም፡፡  ውኃ በአህያ እያሸከሙ ቤት የሚሠሩ የሪል እስቴት ባለቤቶች ያሉት ጊፍት ግቢ ነው፡፡ ውኃ የሌላቸው የአራት ሚሊዮን ብር ቤት ሠሪዎች ያሉት ጊፍት ግቢ ነው፡፡ አንዳንዶች ከአካባቢው በጀሪካል እየገዙ፣ ሌሎች በቦቴ እያስመጡ፣ ሌሎች ደግሞ በአህያ እያጓጓዙ ነው ኑሮን የሚገፉት፡፡ ውኃ የሌለው ብቸኛው የሀገራችን ሪል እስቴት ነው ጊፍት፡፡ በዚህ አያበቃም አራተኛ ችግርም አለ፡፡ ጊፍት ውስጥ መብራት የለም፡፡ ለነዋሪዎቹ የታደለቺው መብራት የፍሪጅ መብራት ናት፡፡ ቤቱ ውስጥ መብራት መኖሩን ከመናገር ያለፈ ሌላ ትርጉም የሌላት፡፡ ሰሞኑን የሚደረገውን የምርጫ ክርክር በቴሌቭዥን የማያዩ ነዋሪዎች ያሉት ጊፍት ግቢ ነው፡፡ የኤሌክትሪኩ ኃይል ቴሌ ቭዥን አያንቀሳቅስም፡፡ እንጀራ መጋገርና ስቶቭ መጠቀምማ ጎረቤት ላለው ሥላሴ ተሥለውም አያገኙት፡፡ እንደ ራሽን ጊፍት አንድ ቆጣሪ ለስድስትና ለሰባት አከፋፍሏቸዋል፡፡  አምስተኛው ችግር ደግሞ የፍሳሽ ማስወገጃው ነው፡፡ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት የግቢው የፍሳሽ ማስወገጃ አልተሠራም፡፡ ማጠራቀሚያ ተብሎ ግቢው ውስጥ የተሠራው ዋና ጉድጓድም ከመፋሰሻው ጋር አልተገናኘም፡፡ ለዚያውም የሰዎች ቤት በር ላይ የተሠራ አስገራሚ ዲዛይን ያለው የማጠራቀሚያ ጉድጓድ ነው፡፡

እነዚህን ችግሮች እንዲፈታ፣ መንደሩን ወደ መኖሪያነት እንዲቀይር ድርጅቱ በተደጋጋሚ በደንበኞቹ ተነግሮታል፡፡ የመፍትሔ አቅጣጫዎቹ ግን አስደናቂ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሐሰት ቃል ይሰጣሉ፡፡ የዛሬ ወር፣ የዛሬ ሳምት፣ ከሦስት ወር በኋላ ያልቃል ይላሉ፡፡ ለእነርሱ ሳምንትም፣ ወርም፣ እኩል ናቸው፡፡ አንሠራም ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኞቹ ገዥዎች ውጭ ሀገር ስላሉ ለጊዜው ጩኸው ይሄዳሉ ብለው ያምናሉ፡፤ ስለዚህም ቢሯቸውን ዘግተው ይጠፋሉ፡፡ የሉም፣ ስብሰባ ላይ ናቸው፣ ውጭ ሀገር ሄደዋል የጸሐፊዎቹ መልሶች ናቸው፡፡ ከዚህ የባሰ ከመጣ ደግሞ በክፍለ ከተማውና በከተማው መስተዳድር ያመካኛሉ፡፡ ክፍለ ከተማው አስቸገረን፣ መስተዳድሩ የኛን ጥያቄ አይመልስም፣ ወዘተ የተለመዱ ማመካኛዎች ናቸው፡፡

እንዲህ እየሆነ ግን እስከ መቼ መጓዝ ይቻላል? ባፉት ሰባት ዓመታት ከሰባት በላይ የሥራ ኃላፊዎች ተቀያይረዋል፤መፍትሔ ግን አልመጣም፡፡ እንደ ከበደ ሚካኤል ግጥም የሰማው ሲሄድ ያልሰማው ይመጣል፡፡ ድርጅቱ ኮርፖሬት ኃላፊነቴን እየተወጣሁ ነው ብሎ ለቀይ መስቀል ቤት ሲሰጥ መስቀል አደባባይ ላይ ቢል ቦርድ ለጥፏል፡፡ የኛን ቤት ግን እስካሁን አላስረከበም፡፡ አሁንም በዓል በመጣ ቁጥር ቤት አስረክበናል፣ ሌሎቻችሁ ግዙ ይላል፡፡ በሚገባ ያስረከበው ቤት ግን የለም፡፡ ይኼ ሁኔታ የሚያዛልቅ አይመስለኝም፡፡

  1. ድርጅቱ ዐቅም ከሌለውና ቃሉን የማያሟላ ከሆነ የውሸት ቃል በየጊዜው ከሚገባ ቁርጡን ይንገረን
  2. የሚመካኝባቸው የመንግሥት አካላትም ጠርተው ይጠይቁት
  3. ቃሉን እንዳላሟላ እያወቁ አሁንም ሌሎች ደንበኞችን የሚሸነግሉ አስተዋዋቂ ድርጅቶችም የሞራል ኃላፊነታቸውን ይወጡ
  4. ቤት ገዥዎችም ከመንገብገብና ቢሮ እየሄዱ ከመጨቃጨቅ ይልቅ እንደ አክሰስና በርታ ቤት ገዥዎች ተደራጅተው የጋራ መፍትሔ ይስጡ

 

 

 

 

The post ጊፍት ሪል እስቴት ወደፊት ወይስ ወደ ኋላ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለምወደው እና ለማከብረው ሕዝብ እውነትን የሚገልጽ ውሃን የሚተፋ እንጂ እሳትን የሚተፋ ብዕር የለኝም።

$
0
0

ለአቶ መሃመድ ሙፍታህ -ከተማ ዋቅጅራ

በምስጋና እና በማሳሰቢያ ልጀምር።

Ketemaዘሐበሻ ላመሰግናችሁ እፈልጋለው ምክንያቱም የሚዲያ ተግባርን ስራ በአግባቡ እየተወጣችሁ እንዳለ ይሰማኛል። ከግራ ከቀኝ ያለውን ነገር ያለ አድሎ አቅርባችሁ ህዝብ እንዲያየው እና አስተያየቱን እንዲሰጡ ስላደረጋችሁ ለናንተ ትልቅ ቦታ እንዲኖረኝ አድርጎአል። በሚዲያችሁ የሚሰጠውን ትችት ዋጋ ቢስ እንደሆነ ያሳወቃችሁበት እና ነጻ ሚዲያን ለማይፈልጉት አፋኞች ለሚሰጡት ትችት በሙሉ መልስ የሆናችሁ ስለሆነ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው። በመቀጠልም መሃመድ ሙፍቲህ ስለሰጠኸው የግል አሳብህ ላመሰግንህ እወዳለው። ምክንያቱም ሁሉም ነገር ወደ እውነት ወደሚነገርበት እና ህዝብ ፍርድን ወደሚሰጠው ወደትክክለኛው ሃሳብን በብዕር በመግለጽ ያልተማረው እንዲማር ያላወቀው እንዲያውቀው የማድረጉን ውይይት መምጣቶ ተገቢ ነው። ብዕር ብዙሃኑን የሚያሳውቅ፣ ብዕር ብዙሃኑን የሚያነቃ፣ ብዕር ብዙሃኑን እውቀትን የሚያስጨብጥ፣ የአለማችን የጥበብ ገላጭ ናት። አቶ መሃመድ ሙፍታን ሰለ አስተያየቶት ክብር አለኝ። ነጻነት ማለት ይሄ ነው። የኔም ሃሳብ ወደዚህ ነጻነት  እድንመጣ እና ሃሳባችንን እንድንገልጽ ነው። ሌሎችም የሙስሊም ሙሁሮች በእስላም ስም የሚደረገውን እንቅስቃሴ እስልምናን እንደማይወክሉ እንደዚህ ወተው ማስተማር ከቻሉ ድል ማለት ይሄ ነው።

ማሳሰቢያው ደግሞ አስተያየት ለምትሰጡ ሰዎች። አስተያየት ሰጪ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ

1ኛ. በትክክል ጽሁፉን አንብቦ የራሱን ሃሳብ የድጋፍም ይሁን  የትችታዊ ሃሳብ ያቀርባሉ። እንደነዚህ አይነት አስተያየት ሰጪዎች እራሳቸውን ለውይይት በሰለጠነ መንገድ የሚያቀርቡ መጥፎንም ጥሩንም ተችተው የሚያልፉ ናቸው። እንደነዚህ አይነቱ አስተያየት ሰጪ ጥሩ አመለከካከት ያላቸው ናቸው።

2ኛ.ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት ነው።  እንደነዚህ አይነቱ የራሳቸውን ሃሳብ ብቻ በየትኛውም አቅጣጫ መስማት እና ትክክል እንደሆነ እንዲነገርላቸው አልያም እንድታሰማቸው የሚፈልጉ ናቸው። ወይ ማስረዳት የማይችሉ ወይ መረዳት የማይፈልጉ ሲሆኑ። እንደነዚህ አይነት ሰዎች ለደጋፊም ለተቃዋሚም አይሆኑም።

3ኛ. ወያኔ ሆን ብሎ  ለዚህ አላማ ያሰማራቸው ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ከ3-5 በክርስቲያን ስም ከ3-5 በእስላም ስም ከ3-5 በኦሮሞ ስም ከ3-5 በአማራ ስም ከ3-5 በትግሬ ስም እያለ ይቀጥላል። እንደነዚህ አይነት ሰዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ለዚህ ስራ አንዱ ከአንዱ እንዲጋጭ በመንግስት ከፍተኛ ብር የሚከፈላቸው እና የነጻ ሚዲያን የማንቋሸሽ ስራ የሚሰሩ ካድሬዎች አሉ። እነዚንም የመሳሰሉትን ከግምት ውስጥ በመክተት ነገሮችን ከተለያየ አቅጣጫ እንደሚመጡ መረዳት ተገቢ ነው።

ወደ ቁምነገሩ ስገባ ኢትዮጵያ ክርስቲያን፣ እስላም፣ ዋቄፈና፣ ደብተራውም፣ ጠንቋዩም እምነት የሌለውም በህብረት የሚኖሩባት አገር ናት። እኔ መግለጽ የፈለኩት ግን አቶ መሃመድ የተረዱት አይመስለኝም። ምክንያቱም ለዚህ ጥቃት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚፈጠረው የፖለቲካ እንቅስቃሴ መሃል ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ሊቢያ፣ የመን፣ የመሳሰሉት የአገራቸው ፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት በሚደረገው እንቅስቃሴ የራሱን ሃይል አደራጅተው ታላቅ ጥፋት ያደረሱት እዚህ ጋር አሜሪካ ናት ወይም እስራኤል ናቸው የፈጠሩአቸው  የሚለውን ትንታኔ ውስጥ አልገባሁም መግባትም አልፈልግም እሱ እራሱን የቻለ ሰፊ ጥናት እና ሰፊ ገለጻ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። ዋናው ጉዳይ በነዚህ አገራት ውስጥ የተፈጠረው ችግር በውስጥ የፖለቲካ መቃወስ ምክንያት ነው። የኔም ስጋት እነዚህ ሃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካው እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ  ወደ መለውጡ ሁኔታ እያመራ እና  የተወጣጠረ ነገር ስላለ ለሰላማዊው ህዝብ ለክርስትናውም ለሙስሊሙም ለሁሉም… ከሩቅ ያየነው ቤታችን እንዳይገባ ቀድሞ ለፖለቲከኖች እና ለህዝቡ ግንዛቤን መስጠቴ በኢትዮጵያ ሙስሊም በሙሉ የተደረገ ጥቃት አድርገህ ማቅረብህ ስህተት ነው። የግሎን ሃሳብ የሁሉም ሙስሊም አድርገው ማቅረብ በራሱ ከስህተ ሁሉ የከፋ ስህተት ነው። ጽሁፎን ሊደግፉ የሚችሉትን ያህል ያን ያህል አልያም እጥፍ ሊሆን የሚችሉ አንባቢም ሊቃወሞት እንደሚችሉ መገንዘብ ይኖሩቦታል። የርሶን ጽሁፍ መነሻ አድርጌ በሌሎች አማኒያን ላይ የተቃጣ ጽሁፍ ብዬ ላቀርብ በየትኛውም አቅጣጫ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ እና ኢፍትሃዊ ነው። እዚህ ጋር የተገነዘብኩት እርሶ  መስማት የሚፈልጉት ብቻ መስማት የሚፈልጉ አልያም እንዲነገርሎ የሚፈልጉትን  ብቻ እንዲነገርሎ የሚፈልጉ ሰው መሆኖን ነው።

አቶ መሃመድ ትንሽ ወደኋላ ሄደውም ታሪክን ለመጥቀስ ሞክረው ነበረ። አጼ ዮሐንስ እስላሙን ህብረተሰብን ጨፍጭፈዋል ብለውን ነበረ። ይህ የሚወገዝ ጉዳይ ነው። እኔም አወግዘዋለው። ከፖለቲካው አለም ወጥተው  ሃይማኖታዊ ክርክር  አስመሰለቦት። እዚህ ጋር ግን እርሶ ትክክለኛ ሰው ቢሆኑ ኖሮ ግራኝ መሃመድ በክርስቲያኖች ላይ ያደረሰውንም ጭፍጨፋ  ጠቅሰው ማለፍ ሲኖርብዎ እርሶ ግን የራስህን ስሜት ብቻ እንጂ እውነትን ሊነግሩን ያለመፍቀዶ ለምን ይሆን?። አቶ መሃመድ ሚዛናዊ የሆነ ንግግር እና  እውነተኝነትን የተላበሰ ነገሮችን ማቅረቡ ተገቢ ነው። ተድበስብሶ የሚታለፍ ነገሮች በሙሉ በውስጡ የተደበቁ ነገር እንዳሉ የሚያሳዩ ናቸው።

ጽሁፌንም ከድምጻችን ይሰማ ጋር አገናኝተውታል። ይሄ ደግሞ ሌላው የስህተት እራስ ነው። እኔ ድምጻችን ይሰማ ላይ ምንም ተቃውሞ የለኝም። የኔም አስተያየት ድምጻቸው ይሰማ ነው። ወያኔ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ሃይማኖት ውስጥ ገብቶ ድምጻቸውን አፍኗል። ለዚህ የመብት ጥያቄ የኔም ጥያቄ ነው። በዚህ አጋጣሚ የሙስሊሙን ድምጽ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሰሙ ሃጂ ነጂብ መሃመድ እንዲሁም ዑስታዝ ካሊድ ዑመር እና ጋዜጠኛ ሳዲቅ መሃመድን  ከልቤ የማደንቃቸው እና በመነጋገር የሚያምኑ የሁሉንም ድምጽ የሚሰሙ የራሳቸውንም ድምጽ የሚያሰሙ እና በማስተዋል የሚጓዙ አገላለጻቸውን ጭምር የማከብርላቸው ሙስሊም ወንድሞቼ ናቸው። እዚህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባው ክርስቲያን ሁሉ ቅዱስ ነው ማለት አንችልም ክርስቲያን ሆኖ ክፋትን የሚያራምድ አለና ስለዚህ ይህንን ክፋትን የሚያራምደውን ግለሰብ ክርስቲያን ስለሆነ  ብቻ የሚሰራውን የጥፋት ስራ ልንደብቅለት ወይም ልንደባብስለት አይገባም። ሙስሊሙ  ውስጥም ሁሉም ቅዱስ አይደሉም ከመሃል ክፋትን የሚያራምድ አለና ስለዚህ ይሄንን ክፋትን የሚያራምደውን ግለሰብ እስላም ስለሆነ ብቻ መጥፎ ስራውን ልንደባብስለት አይገባም። ለክፋት አራማጆች የምንደብቅላቸው አልያም የምደባብስላቸው ከሆነ ግን አደጋ አለው ነው የኔ  ሃሳብ። እንደ ዜጋ በቅን ልቦና ያሰብኩትና ያስቀመጥኩት ቁም ነገር ይሄ ሆኖ ሳለ በኢትዮጵያ ሙስሊም ህብረተሰብ የተቃጣ እሳታዊ ብዕር አይደለም። እንዲህም እንዳላሰብኩ  አንባቢው ከጽሁፌ ሊረዳ ይችላል። ለአስረጅነት ከጽሁፌ ጋር አያይዤ የማቀርባቸው ሊንኮችን አይተው መልሶትን እንደሚሰጡኝ ተስፋ አደርጋለው? እኔ ካለመረጃ አይደልም የምናገረው ከመረጃ ጋር ነው እርሶም መረጃዎችን ማቅረብ ቢችሉ ጽሁፎ ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል።በጽሁፎ ርዕስ ላይ እንደገለጹት ፍራቻ እንዳለኝ እና በመሃልም ላይ ዋጋ እንደምከፍል ነግረውኛል። እዚህ ጋር እንዲያውቁት የምፈልገው ስለ እውነት ማንኛውንም ነገር የመቀበል ጉጉት እንጂ ፍራቻ የለኝም። ክርስትና ውስጥ ፍራቻ የሚባል ነገር የለም። ከፈራ እርሱ እምነት የጎደለው ነው። ስጋን የሚገሉትን አትፍሩ ነገር ግን ስጋንም ነፍስንም በአንድ ላያጠፋ የሚችለውን  እግዚአብሔርን ፍሩ ይላ መጽሐፍ ቅዱስ። ስጋን የሚገድሉትን ቅንጣት ያህል እንደማልፈራ እና እውነትን ይዜ የምጓዝ ክርስቲያን ነኝ። በሐይማኖቴ የሚመጣውን መከራ በሙሉ በደስታ ነው የምቀበለው ነገር ግን ክርስትናን በግድ ተቀበሉ ብዬ በሌሎች ላይ  መከራ መጫን ግን አልችልም። እምነት የግል ስለሆነ ክፉም ቢሰራ ደግም ቢያደርግ ዋጋን ከፋዩ እግዚአብሔር  ስለሆነ ፍርድን ለእግዚአብሔር እንተው።

አቶ መሃመድ ISISን እርሶ እንደሚቃወሙት እና እስላምን እንደማይወክል ነግረውናል። ይሄ ያስማማናል የጋራ ጠላታችን ስለሆነ አብረን እንመክተዋለን። ይሄ ትክክለኛ ሃሳብ ነው። ወደፊትም እንደዚህ ISIS ስህተተና እንደሆነ እና አረመኔአዊ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ እያስተማሩ ቢቀጥሉ እና ብንሰማ  ደስተኛ ሆነን ተደጋግፈን እንጓዛለን። ነገር ግን ይህ አልሆነም ዝምታው በዝቷል። ይሄ አደጋው ደግሞ  ለሁሉም ዜጋ ነው። የኢትዮጵያም ፖለቲካ ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ ነው። ትግሉ ስለበረታ በዚህ መሃል አደጋ አገራችን ላይ እንዳይመጣ  ክርስቲያኖችም እስላሞችም ዋቄፈናም ይሁዲዎችም ፖለቲከኞችም ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ማለቴ እስላምን ታርጌት ያደረገ ሊባል ባልተገባ ነበረ። እዚህ ጋር የጸሃፊውን ዝቅ ያለ የአስተሳሰባዊ እይታ እንዳለው እመለከታለው።

በመጨረሻም ላስተላልፈው የምፈልገው ነገር ሁሉም ሃይማኖት ውስጥ ሊታይ የሚገባው ሰው በሰውነቱ ብቻ ሊከበር ይገባዋል። የአንዱን እምነት ካልተቀበልክ ብለን ሊጫንበት የሚገባ ግዴታ  መቀመጥ አምላክ የማይፈቅደው ነው። ነገር ግን ሙስሊም ትክክለኛ እምነት ነው ብሎ ማስተማር ይችላል አስተምሮም  ወደ እስልምና ሊቀይር ይችላል። ነገር ግን የተቀያሪው ቤተ- እምነት እምነቱን በቀየረው ላይ የሞት ፍርድ መፍረድ ግን በምድርም በሰማይም መንግስት ዋጋ ያስከፍላል። ክርስትና ትክክለኛ እምነት ነው ብሎ ማስተማር ይችላል አስተምሮም  ወደ ክርስትና ሊቀይር ይችላል። ነገር ግን የተቀያሪው ቤተ- እምነት እምነቱን በቀየረው ላይ የሞት ፍርድ መፍረድ ግን በምድርም በሰማይም መንግስት ዋጋ ያስከፍላል። ስለዚህ የግለሰቡ ሃሳብ ወደፈለገበት አምኖ  በሚንቀሳቀስበት ግዜ መብቱ ሊከበርለት ይገባል ነጻነት ማለት ይሄ ነው። ሁሉም ሰው እራሱን ይወዳል  በራሱ ውስጥ ደግሞ  የሚያምነው አምላክ አለ። የሰውየውን የግሉን እምነት ልንተች እንችል ይሆናል ትክክልም  አይደለህም ልንለው እንችላለን። ነገር ግን የኛን እምነት ካላመንክ መጥፋት አለብህ ማለት ግን አይቻልም።

ከዚህ ቀጥዬ የምልክሎትን ሊንኮች ተመልክተው ምላሾን እንደሚለግሱኝ ተስፋ አደርጋለው። ጥቂት ሙስሊሞች ለሚያነሱት ጥፋት ፈጥነው ከእስላም ወንድሞቻችን መልስ ቢሰጥባቸው እና ቢያወግዟቸው ብዙ ስራዋችን መስራት ይቻላል። እኔም ያየሁትንና የሰማሁትን የማውቀውን ጽፌአለው።ጽሁፌም ለነጻነት ለፍትህ የሚታገሉትን ሙስሊም ደግፌ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ከእስላም እህት እና ወንድሞች ጋር አብሬ ተጫውቼ በፍቅር ያደኩና አሁንም በፍቅር የምንጫወት እስላም ጓደኞች  አሉኝ። የኔ ፍራቻ እስላም ወጎኖቼ ሳይሆኑ በእስላም ስም ሰይፍ ይዘው የሚነሱትን ነው። አቶ መሃመድ ይህ ደግሞ  ስጋቱ ለእስላሙ ህብረተሰብ ጭምር ነው። ወይንም ደግሞ እርሶ ከዚህ የተለየ የውስጥ አጀንዳ ካሎት ጽሁፌ ላይስማማዎት ይችላል። ይሄንን ሊንክ ይመልከቱት http://www.independent.co.uk/voices/comment/iraq-crisis-how-saudi-arabia-helped-isis-take-over-the-north-of-the-country-9602312.html እነዚህ ጉሩፖች እንኳን ሌላ ሃይማኖት ላለው ይቅርና ለእስላሙ የማይተኙ ደም አፍሳሾች መሆናቸውን እየተመለከትን ነው። ስለዚህ እስላም ክርስቲያን ዋቄፈና ፖለቲከኞችም  አብረን እንታገላቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚመጣው አይቀሬ ለውጥ ምክንያት በሚፈጠረው ክፍተት እነዚህ ግሩፖች ወደአገራችን እንዳይገቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን እንጂ ቸል ብለን ወይም ደባብሰን ለማለፍ መሞከራችን ከአደጋው አያስቀረንም ቅድሚያ ጥንቃቄ ካደረግን ግን በህብረት እንመክተዋለን የሚል ድምዳሜ ያለው ጽሁፌን አቶ መሃመድ  ወደ ሃይማኖታዊ ገጽታ ለውጠውት አጠቃላይ የኢትዮጵያ እስላም ላይ የተቃጣ ብለው ያቀረቡት ግን አንባቢው ብቻ ሳይሆን እርሶም ረጋ ብለው ጽሁፌን ከተረዱት ከኔ ጎን እንደሚሰለፉ ተስፋ አደርጋለው።  ነገር ግን የግሎት ሃሳብ ከሆነ እቀበላለው ።የሁሉም ሰው ሃሳብ የተለያየ ስለሆነ ። እስላሙን ሁሉ ወክለው ግን የተናገሩትን ንግግር ከምን አንጻር እንደሆነ ባይገባኝም ፍርዱን ለአንባቢ ትቼዋለው።

የተወሰኑ ጥያቄዎች ልጠይቆት እና  ሃሳቤን ልቋጭ

1ኛ ISIS የሚደግፉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የሉምን? ወደ አፍጋኒስታን ኢራቅ ቱርክ  የሚሄዱት አንድ አንድ ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞችን  እንዴት ይመለከቷቸዋል? ኢትዮጵያ፣ ኤርትሪያ፣ ሱማሊያ፣ የሆኑ የሌላ አገር ዜግነት ኖሮአቸው ወደነዚህ ጉሩፖች መቀላቀላቸው ምንን ያመለክታል? ላገራቸው ነጻነት ነውን? BBC በቅርቡ የዘገበው ሶስት ከሃያ አመት በታች ያሉ የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው  ይሄንን ግሩፕ መቀላቀላቸውን ዘግቦ  ነበረ ከነዚህ ውስጥ አንዷ የአስራ ሰባት አመት የሆነች ሴት ኢትዮጵያዊ ሙስሊም እንደሆነች አሳይቶን ነበረ  በርሶ እይታ ይሄ ድርጊት ምንድንው? በዚህ አይነት እንቅስቃሴ የተሳተፉትን ዜጎች ህብረተሰቡ እንዲያውቃቸው መደረጉ አቶ  መሃመድ ለርሶ  ጠቅላላ ሙስሊምን ይወክላል ያስብላልን? የነዚህን እንቅስቃሴ ማጋለጥ ለምን ኢትዮጵያ ሙስሊም ላይ ሁሉ እንደተነገር አድርገው ማቅረብ ለምን ፈለጉ? ወይስ ይሄ እናንተን አይመለከትም ዝም በሉ ማለቶት ነው?

http://www.cbc.ca/news/world/shamima-begum-amira-abase-kadiza-sultana-what-we-know-about-isis-bound-teens-1.2967193

2ኛ. አያይዜ ያቀረብኩሎትን ሊንኮች  በኢትዮጵያ ላይ በአንድ አንድ አክራሪ እስላሞች የተደረጉ ድርጊቶች ናቸው። ስለዚህ ምን ይላሉ?  እንደዚህ አይነቱ እንቅስቃሴ ህብረተሰባችን ላይ ያደረሰውን ቀውስ ድርጊቱን ኮንነው እና አውግዘው አስተምረው ይሆን? ከሆነም በመረጃ አስደግፈው ቢያሳዩኝ?                                                                    https://www.youtube.com/watch?v=me1joZHo0Zohttps://www.youtube.com/watch?v=lemvyk5KCp8 ,                                               https://www.youtube.com/watch?v=aVm_AscRaRo

3ኛ. ISIS እስላሚክ ስቴት ብለው ባስቀመጡት አገራት ካርታ ላይ ምን አይነት አስተያየት አሎት?

https://www.google.no/search?q=ISIS+MAP&safe=active&biw=1366&bih=624&tbm=isch&tbo=u&source=univ&sa=X&ei=4R3uVMv-H6b-ygPZhYDYBQ&ved=0CBwQsAQ

አቶ መሃመድ ሙፍታህ ወደ  መድረኩ ስለመጡ እንዘህን ጥያቄ መልሰው ይውረዱ።

መጥፎን ድርጊቶችን ሁላችንም በህብረት እናውግዘውና  እንከላከለው እላለው።

ከተማ ዋቅጅራ                                                                                                                                     25.02.2015                                                                                                                                                            Email- waqjirak@yahoo.com

The post ለምወደው እና ለማከብረው ሕዝብ እውነትን የሚገልጽ ውሃን የሚተፋ እንጂ እሳትን የሚተፋ ብዕር የለኝም። appeared first on Zehabesha Amharic.

“በራስህ ላይ እራስህ ጥላቻን አትፍጠር”–የወጣት ቤዛ ኃይሉ መልዕክት (በድምጽ)

ያልመከተ ተፈነከተ፤ ያልተደራጀ ተፈጀ። –ጌታቸው ኃይሌ

$
0
0
getachew

ጌታቸው ኃይሌ

አንዱን የዘመናችንን ትልቁን ብሔራዊ ችግር ለመፍታት ያስችል የመሰለኝን ሐሳብ ከጥቂት ቀናት በፊት “በኢትዮጵያ ሰላም የሚያመጣ የአማራ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት ያስፈልጋል” በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ በ ethiomedia ለሕዝብ አቅርቤ ነበር። በጽሑፉ ጥቂት ሰዎች የተወያዩበትን ወዳጆች ልከውልኝ አነበብኩት። በስልክ ያወያዩኝም አሉ። ትችቶቹን ሁሉ ስላላየኋቸው ይሆናል እንጂ፥ ያየኋቸውን ሳጠናቸው፥ ከዶክተር ፀሐይ ብርሃነ መስቀል በቀር ፍሬ ነገሩ ላይ ያተኮረ ሐሳብ የሰጠ አላጋጠመኝም።

የተቺዎችን ቀልብ የማረከው “አማራ የሚባል ሕዝብ አለ ወይስ የለም?” የሚለው ነው። ይኸንን መተቸት ደስ ይላል መሰለኝ፥ ተተችቶ ባለቀ በስንት ዓመቱ፥ ትችቱ እንዲያገረሽበት ጽሑፌ ምክንያት ሆነ። እኔ ግን ጽሑፌን የደመደምኩት እንዲህ ብየ ነበር፤

ለዚህ ድርሰት አስፈላጊነቱ ስላልታየኝ፥ “አማራ ማነው?” ከሚል፥ መልሱ ብዙ ገጽ ከሚፈጅ ጥያቄ ውስጥ አልገባሁም። ሁሉም ራሱን ስለሚያውቅ፥ “አማራ ነኝ” የሚል ሁሉ በሙሉ አባልነት፥ በድርጅቱ የዕርቅና የሰላም ዓላማ የሚያምን፥ ግን “አማራ ነኝ” የማይል ኢትዮጵያዊ ደግሞ በደጋፊ አባልነት መመዝገብ ይችላል።

እንዲህ ያልኩት መተቸቱ ተስኖኝ አይደለም። እንዲያውም ካሁን በፊት ማስረጃ እየሰጠሁ በሰፊው እንደተቸሁት የሚያስታውስ አይጠፋም። አሁን እንደገና ያልተቸሁት፥ ታኝኮ የተዋጠን በማመስኳት፥ የኔንም የአንባቢውንም ጊዜ ላለማጥፋት መርጬ ነበር። “አማራ አለ” የሚሉም “አማራ የለም” የሚሉም፥ እንደየመነሻቸው ተቀባይነት ያለው ምክንያት አላቸው። በዘር ከሄድን የዘመን ብዛት ስላዳቀለን፥ ዛሬ አማራ የሚባል ዘር አለ ለማለት አይቻልም፤ የለም። በባህል ከሄድን ግን አለ። አማራ ከማለት አማርኛ ተናጋሪ ማለት የሚመረጠውም ስለዚህ ነው። ይህ የባህል ሕዝብ ለመኖሩ ማስረጃው ቀላል ነው፤

አንደኛ፥ “አማራ ነን” የሚሉ ሰዎች አሉ። “አማራ አይደላችሁም” ብንላቸው ግራ ይጋቡና፥ “ታዲያ ምን ልታደርጉን ነው፤ ዶርዜ፥ ወይስ እስላም?” ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ።

ሁለተኛ፥ ብዙ ሰዎች “አማራ ናችሁ” ተብለው ተገድለዋል፥ ከሀገራቸው ተፈናቅለዋል፥ ንብረታቸው ተዘርፏል። “አማራ አይደላችሁም” የተባሉ ጎረቤቶቻቸው፥ ወይም በአውቶቡስ ላይ አብረዋቸው የተቀመጡ ተሳፋሪዎች ግን አማሮች አይዶሉም ተብለው ድነዋል።

ሦስተኛ፥ በየዘመኑ የሚደረገው የሕዝብ ቈጠራ ሕዝቡን በጎሳ ሲመድብ አማራውን የለህም ብሎ አልዘለለውም። የአማራው ቍጥር መቀነሱን ያወቅነው፥ በቈጠራው አማካይነት ነው። ቈጣሪዎቹ በዚህ መንገድ መሄዳቸው ተሳስተዋል እንዳንል፥ በማንም አገር የሚደረግ ነው። አሜሪካ ረዘም ያለ ጊዜ እየኖረ፥ ይኸንን ልምድ ያልደረሰበት ያለ አይመስለኝም።

አራተኛ፥ አንድ ቋንቋ ለሌለ ነገር ስም አያወጣም፤ “አማራ” የሚል ቃል ወይም መጠሪያ ስም በቋንቋችን ውስጥ ካለ፥ በዚያ ስም ተጠሪ ሕዝብ አለ ማለት ነው።

አምስተኛ፥ “ኢትዮጵያውያንን በዘር መከፋፈል ይሆናል” ተብሎ ቀረ እንጂ፥ የቀድሞ መታወቂያ ደብተር ላይ “ዘር” የሚል መሥመር ነበረበት፤ ያለምክንያት አልነበረም። ምንጮቹ “ቤተ አምሐራ” ይሏቸዋል።

ግን አንድ እውነታ አለ። አማራው (ወይም አማርኛ ተናጋሪው) ራሱን እንዳንድ የተለየ ሕዝብ ቈጥሮ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ራሱን አላገለለም። ማለት፥ አንድነቱ በኢትዮጵያዊነቱ ነው እንጂ በአማራነቱ ላይ አይደለም። በሀገር ጉዳይ ላይ ጎሳ ሳይለይ ከሁሉም ጋር አብሮ ይሠራል። እንዲቀጥልበት ማበረታታት የሁላችን ግዴታ ነው። ግን ጥቃትን ለመከላከል መጠራራትና ዘዴ መፍጠር እንኳን በሰዎች በእንስሳት ዘንድም ያለ ነገር ነው። እንድ ኢትዮጵያዊ፥ “አማራ ነህ” እየተባለ ሲጨፈጨፍና ማንም ሰው ሳይደርስለት ዝም ብሎ ይታይ ወይ? ሌላው ቢቀር “ነግ በኔ” አይደለም ወይ? የሚል ጥያቄ ተነሥቷል። ጥያቄው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? አማርኛ ተናጋሪው እንዳይደርስለት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ተለይቶ የአማራ ወገን መፍጠር ሆነበት። ምን ይሻላል?

ለዚህ መልስ ሳሰላስል ችግሩ በተለይ የአማራው ሕዝብ ሳይሆን የሀገሪቷ ሆኖ ታየኝ። አገሪቷ አማርኛ ተናጋሪውን በጎሳዎች የሚያስጠላ ጠላት (ጸላኤ ሠናያት የሚባለው ሰይጣን) ገብቶባታል። ስለዚህ የጥላቻውን ምንጭና ምንጩን መድፈኛ ዘዴ ወደመፈለግ ሄድኩት። ምንጩ ወያኔ ብዙዎቹን ጎሳዎች በአማራው ላይ በጠላትነት ማስነሣቱ፥ መፍትሔው ደግሞ፥ “በኢትዮጵያ ሰላም የሚያመጣ የአማራ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅት” መሆኑን ለሕዝብ አቀረብኩ። ከአንባቢዎቼ የጠበቅሁት፥ ሐሳቡ የማያዋጣ ከመሰላቸው፥ ምክንያት ሰጥቶ ውድቅ ማድረግ፤ የሚያዋጣ ከሆነ፥ ተከታትለነው ከዚህ ትልቅ ብሔራዊ በሽታ እንፈወስ የሚል ነበር። ሰው ግን የጽሑፌን ቁም ነገር ወደጎን ትቶ፥ የሚያውቀውን ለመናገርና ብሶቱን ለመተንፈሻ አጋጣሚ አደረገብኝ። (1) አማራ አለ፤ (2) አማራ የለም፤ (3) አማራ በዘር መዘጋጀት የለበትም ለማለት ብዕር መዘዛ መጣ። ግን ሦስቱም የጽሑፌ የኅዳግ ነጥቦች እንጂ አስኳሎች አይደሉም።

ዶክተር ፀሐይ ብርሃነ መስቀል ብቻ የዕርቅ ድርጅ የማቋቋሙን ሐሳብ ደግፋ፥ ድርጅቱ በአካባቢ (regional) ቢሆን ይሻላል የሚል አማራጭ አቅርባለች። ግን ሐሳቧ የችግሩን መንሥኤ ይስታል። የተከሰሰው በአንድ አካባቢ ያለ ሕዝብ ሳይሆን፥ አማራው ተለይቶ ነው።

ሌላ ወዳጄ፥ በድርጅቱ ውስጥ አማራ ያልሆኑ ቢገቡበትስ የሚል ሐሳብ አቀረበልኝ። ይኸም የችግሩን መንሥኤ ይስታል። የተከሰሰው አማራው ተለይቶ ነው። ሌሎች እንደ አማራው ተከስሰው እንደ አማራው አልተጨፈጨፉም። ጽሑፌ ያተኮረው ወያኔ በሚያጠቃው ላይ ሳይሆን፥ ወያኔ በሚያስጠቃው ላይ ነው።

ፕሮፌሰር ሀብተ ጊዮርጊስ በዘር መደራጀትን (ከሞተበት) አናስነሣው የሚል ተማፅኖ አቀረበ። ጽሑፌን ባይጠቅስም የተማፀነው የኔ ሐሳብ ተቀባይነት እንዳያገኝ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህን ጽሑፍ ያረቀቅሁት የሱን ጽሑፍ ስላየሁ ነው። የምናካሂደው ውይይት ሀገር የሚጠቅም መፍትሔ ለማግኘት ስለሆነ፥ ስሜትን ገታ አድርገን ከተወያየን፥ ልንግባባ እንዲያውም ከአንዳች ስምምነት ላይ ልንደርስ እንችላለን።

የፕሮፌሰር ሀብተ ጊዮርጊስ ተማፅኖ እንደገባኝ፥ በጎሳ ከመደራጀት በዲሞክራሲ ላይ የተመሠረቱ ሥራዎች እንሥራ የሚል ነው። የዕርቅ ድርጅት ማቋቋምና በዲሞክራሲ ላይ የተመሠረቱ ሥራዎችን መሥራት ሲስማሙ እንጂ ሲጋጩ አይታየኝም። ልብ አላልነውም ይሆናል እንጂ፥ በባህል መደራጀት ከሰው ልጅ ጋር አብሮ የተፈጠረ ነው። ለምሳሌ፥ ክርስቲያኖች በሃይማኖት ተደራጅተው ከፓርትያርክ (ከፖፕ) እስከ ዲያቆን የራሳቸው አስተዳዳሪዎችና አገልጋዮች አሏቸው። ከዚያም አልፎ፥ የዓለም-አቀፍ አብያተ ክርስቲያን ማኅበር አለ። ሙስሊሞችም ተመሳሳይ ድርጅት አላቸው። የአንድ ሰፈር ሰዎች እድር አላቸው። የነጋዴዎች ምክር ቤት አለ። በዓለም ላይ በሚደርስ ድንገተኛ አደጋ ለሚጎዱ ችግረኞች ፈጥነው የሚደርሱላቸው እንደ ቀይ መስቀል ያሉ የክርስቲያኖች የተራድኦ ድርጅቶች ናቸው። ዕርቅና ሰላም ለማምጣት አማሮችን ማደራጀት የሚኮነን ከሆነ፥ መጀመሪያ እነዚህ ድርጅቶች መኮነን፥ ቤተ ጸሎቶችም መዘጋት አለባቸው።

ዲሞክራሲ ያወጀልን ትልቁ ፍልስፍና ሰዎች ዘርንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ የፖለቲካ ፓርቲ እንዳያቋቁሙ በሕግ መከልከልን ነው። ጽሑፌን የደመደምኩትም፥ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚቋቋም የፖለቲካ ፓርቲ መሠረት የሚያደርገው ሁሉን እኩል አብሮ በሚያሳድግ የኢኮኖሚ ፍልስፍና ላይ ነው፤ ሕዝብን በዘርና በባህል የሚከፋፍል ድርጅት ግን “በሕግ መከልከል፥ መኰነንም አለበት። ለመረዳዳት፥ ከዚያም አልፎ ሌሎችን ለመርዳት ከሆነ ግን፥ በሕግ መፈቀድ፥ መደገፍም አለበት” በማለት ነው። እባብ ያየ ልጥ ቢያይ በራየ፤ የጎሳ ድርጅትን ጉዳት ያየ የተራድኦና የዕርቅ ድርጅትን ቢያይ በራየ ሆኖ ነው እንጂ፥ ድርጅቱ ስሕተት ኖሮበት አይደለም። ያልመከተ ተፈነከተ፤ ያልተደራጀ ተፈጀ የምለው ኢትዮጵያን ነው።

 

The post ያልመከተ ተፈነከተ፤ ያልተደራጀ ተፈጀ። – ጌታቸው ኃይሌ appeared first on Zehabesha Amharic.

የእሳት ዲሞክራሲ ፣ የአበባ ሰብአዊነ እና የሰው ነፃነት እንደ ብረቱ ቅላት ነው

$
0
0

ይድነቃቸው ሰለሞን

በገላጣው ዘመን/ ያየ ከጨፈነ በማይተልቅበት

አንድ በሆኑበት/ ግልጡ እና ድብቁ  

ሰሙ ገፅ አይደለም ሸክም ነው ለወርቁ፡፡

(ግጥም፣ በእውቀቱ ስዩም፤ 2001፣127)

 

‹‹ሰው›› ለመኖር ሲታትር፣ ለማሰላሰል ሲጣጣር እና ለማግኘት ሲፈላሰፍ ለነገሮች የሚሰጠው ፍቺ ተስፋን የሰነቀ፣ መኖርን የሚያበረታታ፣ አብሮነትን የሚቀድስ፣ ሃሴትን የሚያላብስ በአጠቃላይ መልካም የሆነ እንጂ እኩይ ያልሆነ ሊሆን እንደሚጋባው እንስማማ፡፡ ካሂሊል ጂብራን በአንድ የግጥም ስንኙ ‹‹ጨለማ ፀሐይን ስትወልድ ተመልክተሃታልን››/ “Have you seen the darkness giving birth to the sun” ይላል፡፡ ጂብራንን ቀምሰን የሃገራችንን ባለቅኔ እናጣጥም፡፡ በህይወት ዑደት የተቋጨውን የብላቴን ጌታ ፀጋዬ ገብረመድህንን ሁሉን አቀፍ ለኢትዮጵያ ባህል እና ስነ-ፅሁፍ አበርክቶት ለማስታወስ ያህል ከሰፌዱ አንዷን ሰንደዶ በመምዘዝ እንጨዋወታለን- ለሙከራ ስለ መከራ፡፡ ዛሬ የምንስባት ሰበዝ በ1973 ታትሞ ለህዝብ ከደረሰው የግጥም መድብሉ ለመታወቂያነት የተመረጠ ነው፡፡ ይህም ባለቅኔው ለግጥሙ የሰጠውን ቦታ ያሳያል፡፡ በግሌ ይህ ግጥም የመድብሉ አቃፊ ግጥም እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ‹‹የገጣሚ ሞቱ ህይወቱ›› (እንዲል ጂብራን) በስራው ሁለገብነት፣ በስብዕናው እነከንየለሽነት፣ በኢትዮጵያዊነት ኩራት ወደር የማይገኝለትን (ክቡር) የዓለም ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህንን እናስበው፣ እናስተውለው፣ እንዘክረው ዘንድ ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል፡፡ በዚህ ትንታኔ በእሳት-ወይ-አበባ የተነሱ ርዕሰ ጉዳዮች ከግጥሙ ጭብጥ ጋር ቀርቧል፡፡

ግጥሙ የሰው ልጅ ለነገሮች ስለሚሰጠው ትርጉም ይበይናል፡፡ ይህውም፣ ሰው ለነገሮች የሚያስቀምጠው ትርጉም መልካምነቱን የሚያጣው የውስጡን እውነት ሲገድሉት፣ ነፃነቱን ሲነፍጉት እና እምነቱን ሲነጥቁት ይሆናል፡፡ በተፈጥሮ የታደለው ‹‹ሰው›› በማህበረሰብ፣ በመንግስት፣ በባለዘመን የግል/የቡድን/የሃገር እውነቱን ሲቀማ ባለመታደል የውበት ዓይን ሲታወር፣ ባህረ-ሃሳብ ሲጨልም፣ እግረ-ህሊና ሲደድር ከግጥሙ እንመለከታለን፡፡ ከግጥሙ፣ ማህበራዊ ወይም/እና ተፈትሮአዊ እንስሳው ‹‹ሰው›› የሚያስቀመጠው ህገ-ደንብ ከተፈጥሮ ሲቃረን ውጤቱን እንገነዘባለን፡፡ ‹‹ሰው›› እምነቱን ሲነጠቅ ነገሮችን በይሁንታ እና በጥሩነታቸው ማስተናገድ እና መረዳት ይሳነዋል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የውስጡን እውነት ሲከለከል ነው፤ በተለይም ተፈጥሮውን ሲሽሩበት፡፡ የማህበረሰብ ህግ ወይም የግለሰብ እይታ ከተፈጥሮ ሲጣላ ‹‹የሰው›› እሳቤ እና እይታ ጭለማ ይሆናል፡፡ ከመገንባት ማፍረስ፣ ከመመረቅ መርገም፣ ከመርዳት መበቀል፣ ከማስታረቅ ማናከስ፣ ከማበረታታት ማናናቅ የሚቀናው ይሆናል፡፡ እናም ብርሃናማነቱን ተነጥቆ ይታወራል፡፡ ተፍጥሮንም ማድነቅ ይሳነዋል፡፡

ባለቅኔው ‹‹ሌሊት›› ጨለማ እንዳይደል በቋንቋ ውበት ከሽኖ፣ በሃሳብ መጥቀት አርቆ፣ አይነኬ ሰማይን አቅርቦ ያስቃኘናል-ውበትን፡፡ የወርሃ መስከረምን ለዓይን ማራኪ ምድራዊ ውበት ከእኩለ ሌሊት ጨረቃ በክዋክብት ታጅባ ከምትፈነጥቀው ሰማያዊ ውበት ጋር ያነፃፅራል፡፡ በሌሊት ክዋክት እንደ ፀደይ ወቅት አበባ ‹‹በቀይ አደይ›› ያጥለቀልቁናል፣ ሰማይ ያማረ ምንጣፍ ተላብሶ ይፈካል፣ ተፈጥሮ በተፈጥሮ ያሸበርቃል፣ ምድር በጨረቃ ብርሃን ይደምቃል፡፡ በወረሃ መስከረም አጋማሽ ማለትም በእለተ መስቀል ከአዝዕርት እና ከአደይ አበባ በሚፈልቀው መአዛ ምድረ-ኢትዮጵያ ይታወዳል፡፡ በዚህ እለት ለደመራ፣ ጨረቃ የሸፈናትን ከል ገፍታ ስትፈልቅ እንደ እንቡጥ ፅጌሬዳ ናት፡፡ በመሆኑም ሰማይ ጨለማ ነው ማለት ውበትን ለማድነቅ አለመታደል፣ የምናብ አለመመጠቅ፣ በህሊናም አለመባረክ ነው፡፡ ይህን ነፀብራቃዊ ውበት ጨለማ አድረጎ መበየን መታወር ነው፡፡ ከብዙ መልካም ነገሮች መካከል ጥቃቅን ጉድፎችን አውጥቶ እንደ ማጉላት ያለ በእኩይነት የተቀነበቡ እውራን ጎራ ያስመድባል፡፡ ያለመታደል ነገር ሆኖ እንጂ ከክዋክብቱ የሚፈነጠቀው ብርሃን ከተለኮሰ ደመራ እንደሚወጣ እሳት ይፋጃል፡፡ የጨለማን ወበት አለመቀበል እቶን እያዩ እሳትነቱን የመካድ ያክል ያስነውራል፡፡

ይህ ገሃድ የወጣ ሃቅ ባለመታደል ካልተገለፀለት ግለሰብ ጋር ከጨራቃና ኮከቦች የፈነጠቀ ጨረረ ውበትን እንዳይመለከቱ የሆኑ አንድ ጉብል እና አንዲት ጉብል እናገኛለን፡፡ ስለዚህ በዚህ ክፍል ውስጥ የጨለማን እሳት የለበሰ አበባነት መካዱን ከላይ ባቀረበው ንፅፅር በሚገባ ጥበብ ካስረዳ በኋል በሚቀጥሉት ክፍሎች የጉብሉን እና የጉብሏን ውበት አለማስተዋል፣ በሃሳብ አለመታደል፣ በህሊና አለመጽዳት እንዴት እንደሆነ ይተነትንልናል፡፡

ጉብል በግለ ወግ ከጉብሉ ጋር ለመነጋገር አለመታደላቸውን፣ በማቀብ ስር እንዳሉም እንረዳለን፡፡ ሁለቱ ለየግላቸው በምኞት፣ በሰመመን፣ እና በጭንቀት ከመብሰልሰል በቀር በአብሮነት መወያየት አይችሉም፡፡ ይልቅስ ሁለቱን የሚገልፃቸው በዝምታ ውስጥ ያለ ዝምታ ይሆናል፡፡ ይህ ዝምታ ግን ሰላም የሰፈነበት ፀጥታ አይደለም፤ ለብየብቻ ሳግ እየተናነቃቸው በእንባ የሚርሱበት፣ በፍርሃት ውስጥ ተሸብበው ነፍስያቸውን የሚዘጉበት፣ የዋህነታቸው ያጎናፀፋቸውን የልጅነት እድሜ የሚያባክኑበት፣ በፍጡርነታቸው ፈጣሪ የቸራቸውን እውነታ የሚዘነጉበት፣ በአጠቃላይ መክሊታቸውን ሊያስጥል የታፈነ የውስጥ ሃሳብ እንደመሆኑ መጠን መስተ-ህልይ በርቅሶ ሊወጣ የሚችል አሰቃቂ ዝምታ ነው፡፡ ይህ ሁለቱን አበባ እንዳይሆኑ እሳትም እንዳይሆኑ ያግዳቸዋል፡፡ ጉዳዩን ከላይ ከተመለከትነው እውነታ ጋር ካናበብነው ውበት ማድነቅ ወይም ውበትን መቋደስ አለመቻላቸውን እንገነዘባለን- ሰማይን ጨለማ ነው ሲል አበባ እና እሳት የተጎናፀፈ ውበትን እንደካደው የምናብ ሰው፡፡

የማይወያዩት ሁለት ነብሶች አንድ ናቸው፡፡ ምስኪኖቹ ገፅ-ለ-ገፅ ተያይተው ልብ-ለ-ልብ ይናበባሉ፡፡ ለይቶ ሳይለያያቸው በእይታ እየገደባቸው፣ በይሉኝታ እንዳጠራቸው፣ በአሉ አሉ እንደለያቸው፣ ለይምሰል እንደከፈላቸው፣ ከብ ለካብ እንዳቆማቸው፣ እሳትም ሆነ አበባ እንዳላረጋቸው በቅፅበታዊ የዓይን ንግግር ሰመመናዊ ተግሳፁን ተረድታ የምር በውስጤ አርግዤሃለው ለማለት ጉብሏ ‹‹ሙት›› ብትለው በአንድነት ውስጥ ያሉ ሁለት ፍጡራን መሆናቸው ይገባዋል፡፡ እይታ ከሙት በላይ ምን ሊል ይችላል፡፡ ይህን ከዓይኗ የተረዳው ገጣሚ ግን ምላሷን በቂ ሆኖ አያገኘውም፤ የልብ ጉዳያቸው በአንዱ ጥጋት መነጋገር፣ መመካከር፣ እንደሚያስፈልገው ግን ደግሞ እንደተከለከሉ ግን ደግሞ አንድ እንደሆኑ … ግራ ቢገባው… በቃ ሁሉም ይቅር፤ ‹‹የወፎቹም ዜማ ይቅር››፣ ጨረቃንም ማድነቅ ይቅር ግን ደግሞ በይቅር ብቻ የሚቀር አይደለምና እንዴት ይቀራል፡፡ የማይያዝ፣ የማየጨበጥ ቢሆንበት፣የማያገኙት የማይተውት ቢሆንበት፣ የማይለዩት አብረው ያሉት ቢሆንበት ግራ ቢገባው … ‹‹ትዝታሽን ማሪኝ›› ሲል ይለምናታል፡፡

በይ ሕመምሽን ታረቂኝ

ሰቀቀንሽን ተማፀኚኝ

ሰመመንሽን ይቅር በይኝ

እምትምሪኝ ከሆነማ፣ ማሪኝ ፣ ትዝታሽን ማሪኝ  …

ጉብል በዓይኗ አልምርህም ብትለው ዘመን ተሻጋሪውን ቅኔ ይለቀዋል፡፡

ነገሩ አያድርስ ነው፡፡ ወይም የደረሰበት ብቻ የሚገባው ግን ሊገልፀው የማይችለው አይነት ነው፡፡ ሆኖም ባለቅኔው ሁላችንም ፅዋው እንዲደርስብን ያደርጋል፡፡ ደርሶኛል፡፡ በተመስጦ ግጥሙን ያነበብኩት ከሁለት አመት በፊት ሲሆን በደገምኩት ቁጥር ነብስያዬ አንደተረበሸች አለች፡፡ በጭንቅ ወልዳ የልጇን መጥፋት እንደገባት እናት ውስጤ በሃዘን ይጥለቀለቃል፡፡ ግን ደግሞ መቼም ግዜ ካለኝ ምናቤን ከልቤ አስታርቄ በመንፈስ የባለቅኔው ታሪክ ተጋርቸዋለው፡፡ የጥበብን የውበት ጥግ በቅኔው መንኮራኩር ተፈናጥጬ እታደማለሁ፡፡ እሳት እና አበባ እሆናለሁ፡፡

በአንድ ውጥን ያሉ ሁለት ነብሶች ቀርበው የጋራ ውጥናቸውን ለብቻ ከማሰላሰል በቀር ቀርበው ማውጋት አልቻሉም፡፡ ግና በአንድ አጋጣሚ በዓይን ስልምልምታ በተነጋገሩበት ቅፅበት ባለቅኔው የጉብሏ ችግሩን መረዳቷ ቢገባው ‹‹ሙት›› ብትለው ግራ ተጋባቶ ትዝታዋን እንድትምረው፣ ናፍቆቷን እንድታክመው፣ ሰቀቀኑን እንድታስታርቀው ቢለምናት ጉብል መልስ ጠፍቷት ዓይኗ ወጓን ቢገታ፣ ግንባሯ መሬት ቢመታ፣ እንባዋ በልውጣ አልውጣ ቢፈትናት … መልሷን ሳይሽት ከውጠ-ውስጠት በፈለቀ ስሜት ይንገበገባል፡፡ ትንታኔዬን ገትቼ …

ምነው ታድያን ድምፅሽ ራቀ?

ምነው ልሳንሽ ረቀቀ?…

የዓይንሽ ብረሃን ቀለስ አለየእንባ ወዝ እንደቋጠረ

ቃትቶ እንደተውተረተረ

የመከራ የጭንቅ የምጥ ስልባቦት እንዳቀረረ

የደም ወዝ እንደነዘረ

እንደተሰቀቀ ቀረ…

ላቀረበላት ‹‹የትዝታሽን ማሪኝ›› ጥያቄ መልሷ እንደፍላጎቱ ምህረት ሳይሆን አንጀት የሚያላውስ ፍርሃት ይሆናል፡፡ በጥያቄው የምትገባበት ያጣች የጉብሏ ነፍስያ ትንፋሽ ያጥራታል፡፡ የመግባቢያቸው በሯ የደረቀ እንባ አርግዞ፣ ሁለመናዋ በሰቆቃ ደንዝዞ ያማትራታል፡፡ የተረበሸ ውስጠቷ በእንባ መልክ የደም እንክብሎችን ለምድር ሲገብር ይታደማል፡፡ ሊያስተዛዝናትም ይሻል፡፡ እንባዋን አያበሰ አይዞሽ ሊላት ይመኛል፡፡ በዛውም ከአይኗ የሚፈልቁትን እሳታዊ ነበልባሎች ሊሞቅ ያስባል፡፡ አበባ የሆነውን እሳት ለውስጥ ህመሙ ፈውስ ሊፀበል፡፡ ቀርቧት የፊቷን ገፅ መዳበስ ባይችል እንኳን መንፈሳዊነትን በተላበሰ እስትንፋሱ ሊፈፅመው ይዳዳዋል፡፡ መለኮታዊ የሆነበትን ውበት በመለኮት ሊያሳካ፤ መንፈሱን ከመንፈሷ ሊያግባባ፤ ወደ ውስጠቷ ሊገባ፤ እሳት ሊሆን ወይ አበባ! ምክንያቱም ያለፍቅሯ በቀር እንባዋ ፍይዳው አይጠቅመኝም ብሎ ያምናል፡፡ እምነቱ ግን እውን አይሆንም፡፡ በዚህም መቃጠላቸው ቢበቃ ሲል ይደመጣል፡፡ ለቃጠሎ የዳረጉትን ፈጣሪውን፣ ማህበረሰቡን እና እድሉን አብዝቶ ያማራል፡፡ በልቡ የተቋጠረው ፍቅረ-ነገር ከሚችለውና ከአቅሙ በላይ ሲሆንበትም እንገኘዋለን፡፡ ቢበቃው ይመኛል፡፡ ፍላጎቱ ባይሳካ፣ ውጥኑ ግቡን ባይመታ፣ ምኞቱ ከምኞት ባያልፍ፣ አለመቻል ቢወርሰው፣ ህመም ቢተርፈው ቢበቃው ይመኛል፡፡ ከምኞት ፈቀቅ አይልም፡፡ የምኞት ምርኮ፣ የይሉኛታ ባሪያ፣ የፍርሃት አሽከር፣ የሰመመን ባላባት ነው፡፡

አረ ይብቃን መቃጠሉ፥ በዓይን ወላፈን መለብለቡ

ያለፈርጁ ያለባሕሉ፥ እሳት አይጭር ሰው በቀልቡ

ፍም አዝሎ ላይዘልቅ ልቡ፥

አጉል ምን አቀጣጠለን

በሰመመን ሟሟን እንጂ፥ በመውደድ ለምልሙ አላለን

ድባብ እንደራቃት ቆሌ

ባህር እንደገባ አሞሌ

እንዲያው በህልም አባይ ገነን፣ ለቅዠት መራወጥ ፎሌ

አረ ወዲያ ይብቃን  ይቅር

የኸ የአይን ብር ትር

ወዝ አይወጣው ድብን እርር…..

ጉብል ‹‹የምትታይ እንጂ የማትበላ›› የገነት ፍሬ ናት፡፡ እጣ ፋንታዋ በማህበረሰቡ እሳቤ ውስጥ የተቀነበበ፡፡ እሷን መንካት አይደለም መቅረብ የሚያስቀጣው፣ እሱን መቅረብ (በሌሎች) የሚያሳጣት  ነው፡፡ ሁለቱም ግን ይፈላለጋሉ፤ አንዳቸው ባንዳቸው ውስጥ ይነዳሉ፤ በአብሮነት ውስጥ ይጋያሉ፡፡ ሕልም አይከለከል፡፡ ምኞት አይታሰር፡፡ ተስፋ አይቀበር፡፡ እውነት አይገደል፡፡ ግን እሳት-ወ-አበባ መሆን አልቻሉምና ብቻቸውን በብቻነት ውስጥ ይጋያሉ፡፡ የከፈላቸውን ጋሬጣ አሽቀንጥረው አንደነታቸው ማሰሪያ ፍቅር መስራት አለመታደላቸው ያመዋል፡፡ በጋብቻ ከሆነ ለፅድቅ፣ በሴሰኝነት ከሆነም ለኀጢያት አለመታደላቸው ያንገበግበዋል፡፡ ይህን በህልም የሚደረግ እሩጫ፣ የሰመመን ውስጥ ፍጥጫ፣ የውስጥ ህመምን አለመናገር ‹‹መረገም›› ይለዋል፡፡ መረገማቸውም እውነትን በውስጣቸው ቀብረው የውሽት ከማስመሰላቸው አንፃር ይሆናል፡፡ እሷን ወግ ነው አጥሯ፤ እሱ ይሉኝታ ነው ከሉ፡፡ በማህበረሰቡ እንዳይታሙ ሲሉ የነፍሳቸውን እውነት ከፍሬነት ደጃፍ እንዳይደርስ ያጨነግፉታል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም የህመማቸው ጥጋት፡፡ መዋደዳቸውን ለሽንገላ ደብቀው፣ መፋቀራቸውን በአደባባይ ክደው የማህበረሰቡ ውቃቢ አምላክ ያይብናል ሲሉ መፍራታቸው ይቆነጥጠዋል፡፡ ለማህበረሰቡ አካሄድ ሲባል ፍቅራቸውን መካዳቸው በመረገማቸው እና ባለመታደላቸው ይሆንበታል፡፡ የስቃያቸው ማብቂያ ግን አይሆንም፡፡ መተጣጣታቸው ማንነታቸውን ሲፈታተን ይዘልቃል፡፡ ያገባሉ፣ ይዳራሉ፣ ይሴሰኛሉ፡፡ የገደሉት መፈላለጋቸው ግን የገቡበት ይገባል፣ ያደሩበት ያድራል፡፡ ይፈትናቸዋል፡፡ የቱን ያህል ቢራራቁ፣ ምንስ ያህል ቢራቀቁ አንዳቸው ካንዳቸው ላይርቁ ነገር፡፡ ብቻ መሳቀቅ ነው፡፡ ሌላዋን እሱ እያቀፈ እሷን ይስላል፤ ሌላውን እሷ እያቀፈች እሱን ታያለች፡፡ ባንዷ አካል ጉብሉን ያግላል፤ ስሟን ከስሟ ያሳክራል፤ በማህፀኗ እሷን ይፀንሳል፤ ታቃፊዋን እቃው ያደርጋታል፤ ከሰውነት ያወርዳታል፤ ኃጢያት ይሰራባታል፡፡ ሁሉም በቁጭት ይለበልበዋል እና ጉብል ቢደርስብሽ ብታይው ይላል፡፡

ምነው ደርሶብሽ አይተሸው

የኔን ግፍ በሰው ውለሽው

የፍትወት ግብር ልትከፍይ የፈፀምኩትን ፈፅመሽ

በሰው አካል እኔን አቅፈሽ

በሰው ጭንቀት እኔን ፀንሰሽ፣

መውደዳቸውን ለወጉ አግዳ፣ ፍቅርን ለቧልት ክዳ፣ ለደስታ ሀዘናቸውን ሰንቃ፣ ለዘርየለሽ ገለባ አስታቅፋ፣ ለፍሬአልባ ወሬ ዳርጋ፣ ላይጠጣ የመነጨ ምንጭ አቅርባ፣ ላይፈጠር በተቀጨ ልጅነት ውስጥ፣ የማይወለድ ፅንስ አስቋጥራ፣ መኖራቸው ተንጉዳለች፡፡ ሕይወት መች ኬላ አላት፡፡ አትቆም ነገር፡፡ በቁዘማ ውስጥ ታልፋለች፡፡ ‹‹በተገማሸረ መስክ ውስጥ እንደሚብሰከሰክ ውሃ›› አለ ደራሲው፡፡ ሕይወት ሹሉክሉክ ትላለች፡፡ ስንቶቻችን ነን የሕይወታችንን ሽሉክሉኪት ለመታደም የሞከርን፡፡ እውነታቸውን በፍርሃት ውስጥ ሽሽገው፣ ፍቅራቸውን ለወግ ገብረው፣ ስሜታቸውን ለይሉኝታ ቸርችረው፣ እሳት ወይም አበባ፣ ፅድቅ ወይም ኩነኔ፣ ሳይደሰቱ ወይም ሳያዝኑ፣ በቁማቸው ሲቆዝሙ እድሜ ይሉት ነገር ድርስ ብሎባቸው እርጅት ቢሉ ምን ይውጣቸው፡፡ ‹‹ሾላ በድፍን›› እንደሆኑ ሳይተነፍሱት፣ ሣይናገሩት፣ እንዳማጡት ባክነውት አረፉት፡፡ ልጅነታቸውን ላይረባቸው እንዳልባሌ ቆሻሻ ደፉት፡፡ እንደተብከነከኑ ባከኑ፡፡ እንዲህ ሆኑ፡፡ ላይሆኑ ሆኑ፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን ‹‹የከንቱ ከንቱ›› እንደለው ሆኑ፡፡

ልጅነትሽን ሳታካብች፥ ዕድሜሽን ምን ሳትሰሪበት

አባከንሽው ባከንሽበት፥

ልጅነቴን ሳላካብት፥ እድሜዬን ምን ሳልሰራበት

አባከንኩት ባከንኩበት፤

እሷን በውስጡ አዝሎ ላይ-ታች እንዳለ፤ ከልጅነት እስከ እውቀት እንደተብከነከነ፣ ምንም ቁምነገረ ሰይፈፅም ከእራሱ እንደተጣላ፣ ማንነቱ እንደተሳከረበት፣ የውስጡን ሰላም እንደ ተቀማ፣ በውበቷ እንደተሸበረ፣ እንዴት እንደሆነ ሳይገባው መባከኑ ግን ገባው፡፡ ልጅነቱን ከጎኑ አጣው፡፡

ተስፋና ምኞት ለፀጋሽ፥ ምዕጥንቱን በቻ ሳውቅበት

ነፍሴን ለነፍስሽ መስዋዕት፥ ግዳይ ስጥል ባደግኩበት

ሳንፈጠር በሞትንበት

ሳናብብ በረገፍንበት

ሳንጠና ባረጀንበት

አበባ ወይንም እሳት፥ መሆን ብቻ አጣንበት፡፡…

እንዳይሆን የለም፣ በመጨረሻ ውበትን ማድነቅ ይሳናቸዋል፡፡ ሕሊናቸው ባዶ ይሆንባቸዋል፡፡ ሁለመናቸው ከሰውነት ጎራ ይለያል፡፡ እናም ሰማይን ጨለማ ነው እንዳለው፣ አይኑ ስር ያለን እውነት እንደካደው፣ ውበትን ማገናዘብ እንደተሳነው፣ እግረ ሕሊናው እንደከረረበት ሰውዬ ይሆናሉ፡፡ ከምድር ሃሴት ይገለላሉ፡፡ አበባ ወይም እሳት መሆን እንደተመኙ፣ ስለመቀራረብ ዘውትር እንደተብሰለሰሉ፣ ስለአብሮነት እንዳለሙ፣ ለፍሬ ለመብቃት እንደታተሩ፣ ሳይሳካላቸው ይቀራሉ፡፡ ይባክናሉ፡፡ ባካናዎች ይሆናሉ፡፡

እናም የግጥሙ ማሰሪያ የሚሆነው የታፈነ እውነት ገዳይነት፣ የተደበቀ ማንነት አጥፊነት፣ ለወግ እና ለይሉኛታ የሚደበቅ ሃቅ እኩይነት፣ የድፍረት ማጣትን እዳነት፣ የአስመሳይነትን ዋጋቢስነት፣ ….ሌላም….ሌላም…ሌላም ሊሆን ይችላል፡፡ ማንነትን ከማጣት ቅጣት፣ እውነትን ካለመፈለግ መዓት፣ በሃሰት ከመሸሸነጋገል ሃጢያት እና ውበትን ካለማድነቅ ክፋት ይሰውረኝ፣ ይሰውራችሁ፡፡ ካልሰወረን ግን ማረፊያችን ወይም እርግማን ነው፣ ወይም አለመታደል ነው፣ ወይም ፍርሃት ነው፡፡

በውልደት እና ሞት መካከል በታጠረች መኖራችን ውሰጥ ተፈጥሮ እኩልነትን እንዳልነፈገን ይሰማኛል፡፡ ተፈጥሮ የመልካምነት ተምሳሌት ትሆናለች፡፡ ለምሳሌ፣ ሰብዓዊነት ውበት አለው፡፡ እንደ አበባ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ዲሞክራሲ ውበት አለው፡፡ እንደ እሳት ነው፡፡ አበባ እሳትም ነው፡፡ ሰብዊነት ዲሞክራሲም ነው፡፡ እሳትም አበባ ነው፡፡ ዲሞክራሲም አበባ ነው፡፡ ሁለቱን አቃፊ ሶስተኛው ነፃነት፣ ነፃነት፣ ነፃነት ነው፡፡ እንደ ብረቱ ቅላት ነው፡፡

Comment

The post የእሳት ዲሞክራሲ ፣ የአበባ ሰብአዊነ እና የሰው ነፃነት እንደ ብረቱ ቅላት ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

“ከትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ለኢትዮጵያ በጎ ነገር ይመጣል ብሎ ማሰብ ከዕባብ ዕንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ ማመን ነው”–ሞረሽ ወገኔ

$
0
0

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
አርብ መጋቢት ፲፰
 ቀን ፪ሺህ፯  ዓ.ም.           ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፲፫

ሠሞኑን በትግሬ-ወያኔ፣ በግብፅ አረብ ሪፑብሊክ እና በሱዳን እስላማዊ አገዛዝ መካከል በአባይ ወንዝ የውኃ አጠቃቀም ላይ የሚያተኩር የጋራ የሥምምነት ሠነድ ተፈርሟል። የሥምምነቱ ሠነድ ለሕዝብ ይፋ የሆነው ማክሰኞ መጋቢት ፲፭ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. (Tuesday March 24, 2015)ነው። ሆኖም የሥምምነት ሠነዱ የወጣበት የካቲት ፳፮ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. (Thursday March 5, 2015) እንደሆነ በሠነዱ ራስጌ ላይ የሠፈረው ጽሑፍ ያመለክታል (ምንጭ፦ http://aigaforum.com/documents/Final-full-text-of-egypt-sudan-ethiopia-agreement-on-nile-use.pdf)። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የሦሥቱ አገዛዞች ገዢዎች እስካሁን ድረስ ዘግይተው ሠነዱን ለሕዝብ ይፋ ያደረጉበት ምክንያት ምናልባት ከሚገዟቸው አገሮች ሕዝብ ሊነሣባቸው የሚችለውን ተቃውሞ ለማለዘብ ታስቦ ይሆናል፣ ወይም ሌላ የተደበቀ አጀንዳ ይኖራቸዋል። ወጣም ወረደ ሠነዱ ለእያንዳንዱ አገር ሕዝብ፣ በተለይም ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የሚያመጣው በረከትም ሆነ የሚያወርደው መቅሠፍት ካለ ያንን በጥልቀት መመርመሩ እና ተገቢውን እርምጃ መውሰዱ የእያንዳንዱ ኃላፊነት የሚሠማው ዜጋ ግዴታ ነው።

Moreshየትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በአባይ ወንዝ የመብት ጥያቄ ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሉዓላዊነት አሣልፎ የሠጠው ገና ወደሥልጣን ከመጣ ሦሥት ዓመት ሣይሞላው ነው። በሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻፹፭ ዓ.ም.  (Thursday July 1, 1993) የያኔው የትግሬ-ወያኔ የሽግግር አገዛዝ ፕሬዘዳንት መለስ ዜናዊ ካይሮ ድረስ ሄዶ ከያኔው የግብፅ አምባገነን ገዢ ሆስኒ ሙባረክ ጋር አንድ ሠነድ ተፈራርሟል (ምንጭ፦ http://ocid.nacse.org/tfdd/tfdddocs/521ENG.pdf)። የዚያ ሥምምነት ዓላማ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ እና በገባር ወንዞቹ ላይ ያላትን ተፈጥሯዊ እና ሉዓላዊ መብት አሣልፎ የሚሠጥ መሆኑን በተለያዩ ባለሙያዎች እና ፖለቲከኞች የተተቸበት ጉዳይ ነው።

ሆኖም ከአራት ዓመታት በፊት ሟቹ የትግሬ-ወያኔዎች መሪ መለስ ዜናዊ በድንገት ተነስቶ «አባይን እንገድባለን» ሲል በኢትዮጵያውያን መካከል ያልተጠበቀ መከፋፈል ተፈጠረ፦ ከፊሉ «የዚህ ግድብ መገንባት ተገቢ ነው፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይጠቅማል፣ ወያኔንም በገንዘብ እና በማናቸውም መንገድ ልንደግፈው ይገባል» ብሎ ተነሣ። ከፊሉ ኢትዮጵያዊ ደግሞ «የትግሬ-ወያኔ ለኢትዮጵያ የሚያስበው መልካም ነገርም ሆነ የሚያመጣው ጠቃሚ ነገር የለውም፤ እንዲያውም ለአሁኑ ብቻ ሣይሆን ለተከታዮቹም ኢትዮጵያውያን ትውልዶች የማይነቀል እና የተወሣሠበ የችግር ነቀርሣ ይተክላል» ብለው አምርረው ተቃወሙ። በዚህ መካከል ገለልተኛ ሆነው ከሁለቱም ወገን የሚወረወረውን የቃላት ጦርነት በትዝብት የሚከታተሉም አይጠፉም። ወጣም ወረደ መለስ ዜናዊ ያንን ያልተጠበቀ ቃሉን ከሠጠ ከዓመት በኋላ ቅዳሜ መጋቢት ፳፬ ቀን ፪ሺህ፫ ዓ.ም. (Saturday April 2, 2011) በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በ15 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የግድቡን ሥራ አስጀመረ።

ሀገር ወዳድ እና ሃቀኛ ኢትዮጵያን አስቀድመው እንዳስጠነቀቁት፣ በግድቡ መገንባት ሥም የትግሬ-ወያኔ ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን አካበተበት፦ በመዋጮ ሥም በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ወደካዝናው አስገባ፣ በፖለቲካው ረገድ «ተቃዋሚ ነን» የሚሉትን ለመከፋፈል እና ለማዳከም ተጠቀመበት። ነገር ግን የግድቡ ሥራ በትክክል ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ሣይታወቅ ይኼው አራት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ቀርቶታል። የግድቡ ሥራ ከመጀመሪያውም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለታሪካዊ ጠላቶቿ አሣልፎ ለመስጠት መሆኑ አያጠራጥርም። ስለዚህ የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን አፈራርሶ፣ ዜጎቿን ከፋፍሎ፣ ግዛቷን ለውጭ ኃይሎች የመቸብቸብ የመጨረሻውን ግቡን ሣያሣካ እንደማያርፍ ማሰብ የማይችል ኢትዮጵያዊ ካለ የአዕምሮው ጤንነት የተቃወሰ ብቻ ነው።

ይህ በዚህ እንዳለ፣ የትግሬ-ወያኔዎች የተፈጥሮ ባሕሪያቸው የሆነውን የአገር ክህደት ድርጊታቸውን በመቀጠል፣ ባለፈው ሰኞ ዕለት መጋቢት ፲፮ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. (Monday March 23, 2015) የሠሞኑን የሥምምነት ሤራቸውን ሠነድ በድረ-ገፃቸው ላይ ይፋ አርገዋል (ምንጭ፦ (http://aigaforum.com/documents/Final-full-text-of-egypt-sudan-ethiopia-agreement-on-nile-use.pdf)። ስለሆነም «በዚህ የሤራ ሠነድ ካሉት አንቀፆች በተለይ የኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያውያንን ኅልውና በእጅጉ የሚፈታተኑት የትኞቹ ናቸው?» ብሎ በጥንቃቄ መመርመሩ ተገቢ ነው። በተለይ፦

·               አንቀፅ 3፦ ፍትኃዊ የውኃ አጠቃቀም መርሆ (III. Principle of Equitable and Reasonable Utilization)

·               አንቀፅ 4 ሌላውን አካል ያለመጉዳት መርሆ (IV. Principle of Not to Cause Significant Harm)

·               አንቀፅ 5 የግድቡን ወኃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሙላት ስለሚያስፈልገው የትብብር ሥራ (V. Principle to Cooperate on the First Filling and Operation of the Dam)

በሚሉት አንቀፆች ላይ ኢትዮጵያውያን በጥልቀት ተወያይተው ብሔራዊ መግባባት እና የጋራ አቋም ላይ መድረስ ይገባቸዋል። እኒህ አንቀፆች እርስ በእርሣቸው በሚቃረኑ፣ በተድበሰበሱ እና የኢትዮጵያንም የወደፊት ኅልውና አደጋ ላይ በሚጥሉ አረፍተተገሮች የታጨቁ ናቸው። ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን በሠከነ መንፈስ፣ ሣንዘላለፍ፣ ነገሮችን በጥልቀት እየመረመርን ለችግሩ መውጫ መንገድ መፍትሔ የሚሆኑ ኃሣቦችን ማፍለቅ ይጠበቅብናል። 

የዚህ የአዲሱ ሥምምነት ዓላማው በግልፅ፦ «እኛ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ ማንም አዛዥ-ናዛዥ የሌለብን ገዢዎች ነን፣ ምን ታመጣላችሁ!» ለማለት ነው። ለነገሩ ከትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን መልካም ነገር ይመጣል ብሎ ማሰብ ከዕባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ የማመን ያህል ቂልነት ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ተገቢውን የተግባር ምላሽ ልንሠጥ ይገባል። ይህንን ማድረግ ካልቻልን ግን የዚህ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከአገር አፍራሹ እና ሻጩ የትግሬ-ወያኔ ባልተለየ ከሃዲዎች በመሆናችን በታሪክ ከተጠያቂነት አናመልጥም። 

ኢትዮጵያ በታማኝ እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

The post “ከትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ለኢትዮጵያ በጎ ነገር ይመጣል ብሎ ማሰብ ከዕባብ ዕንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ ማመን ነው” – ሞረሽ ወገኔ appeared first on Zehabesha Amharic.

እኔ ማን ነኝ? –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

28.03.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

„ቤት በጥበብ ይሠራል። በማስተዋል ይጸናል“ መጸሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 24 ቁጥር 3“

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

እንዴት ናችሁ ክብረቶቼ አንዲት በትርጉም የምትቃና ነገርን አንስቼ ወደ ጉዳዬ አመራለሁኝ። “ያልመከተ ተፈነከተ፤ ያልተደራጀ ተፈጀ። – በተከበሩ ፀሐፊ ጌታቸው ኃይሌ በ25.03.2015 ከተፃፈው ልትቃና የሚጋብትን ብቻ ላንሳ  … “ አማራ ነን” የሚሉ ሰዎች አሉ። “አማራ አይደላችሁም” ብንላቸው ግራ ይጋቡና፥ “ታዲያ ምን ልታደርጉን ነው፤ ዶርዜ፥ ወይስ እስላም?” ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ። ዬክቡር ጸሐፊ ጌታቸው ኃይሌ አገላለፃቸው እኔን እንደገባኝ የአማራ ብሄረሰብ አባላት የት ልትመድቡን ነው? ከዬትኛው ብሄረሰብ ወይንም ነገድ ልታዳብሉን ነው? ለማለት እንጂ ከዬትኛውም ብሄረሰብ እስልምና ሃይማኖት እምነት ተከታይ ወገን የለንም ለማለት አይመስለኝም። የጸሑፉ ጭብጥ ያለፈውና የአሁን ስታያይዙት መንፈሱ በዚህ ፍሰት የሚሄድ ቅንነት – ጠገብ ዝንባሌ ነው፤ እንጂ እስልምና ተከታይ አማራ ወገን የለንም ለማለትም ወይንም ሃይማኖቱንም እንደ አንድ ብሄረሰብ መለያ አድርጎ ለማግለል ወይንም ነውር ሆኖ አይደለም። በዬትኛውም ብሄረሰብ እስልምና የሚከተል ኢትዮጵያዊ ወገን አለን። ስለዚህም የኔዎቹ የእስልምና እምነት ተከታዮች ደሞቼ እንዳይከፋችሁ በዚህ የተቃና ትርጉም ውሰዱት። ኢትዮጵያዊነትን የፈካ ውህድና ውብ የሚያደርገውም ይህን መሰሉ ጌጣማ ፍልቅ ዓምዳዊ ጭብጥ በወጥነት መግለጹ ነው። እንደሚታወቀው ፍጥጥ ያሉ ጭብጦች እያሉ አማራ በነገዱ መጠራቱ ብቻ ሳይሆን ጭራሽም ባለቤትም አድራሻም የሌለው ተደርጎ የመታዬት ዝንባሌ እጅግ ጎልቶ ይታያል። ውለታውንም ገደል። ይህ የታሪክም ራስን የመጋጥም ዝበት ነው። ለዛውም በግራ ቀኝ የቁርሾ ማወራረጃ ሆኖ እዬተፈጨ።

“አማራ” ለማለትም የሚጨንቃቸው ወገኖቼ እንዳሉ በግሌ ተገንዝቤያለሁ። ስለሆነም ነው የመፍትሄ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን እውቅና የማስገኘት ተጨማሪ ሃሳብ ይዘው የቀረቡት። ኢትዮጵያዊነት ሁሉንም ቀለማም መለያዎች ያቀፈና የተዋበ ስለሆነ ለእኔ በግሌ የሚቀለኝ ብቻ ሳይሆን፤ ክብርና ሞገስ የሚሰማኝ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል ብቻ ነው – ለሥርጉተ፤ እንጂ የሚመክት ጉልበታም አቅም ያለው አመክንዮ በማቅረብ ኩሰት ዝንባሌዎችን ሁሉ መግራት መሞረድና መልጋት እንዲሁም ቀጥ አድርጎ ማቆም ይቻላል። መኖር ብቻ ሳይሆን ቀለማም ሁለንታናዊነቱ በሁሉም መስክ አንቱ ነውና። ወያኔ በጥብቆ ውስጥ ተገብቶ መቀርቀር ካለ ታላቁ ዓርማ ኢትዮጵያዊነት ይደብዝዛል፤ ስለሆነም ይህን አብዝቶ ይህን ይሻዋል። ተከታዮችም “ለምን ወጥተው እኛ አማረ ነን አይሉም” ሲሉ ተዘውትረው ይደመጣሉ። መልሱ የበታችነት ስለማይስማው ብቻ ነው። ምን አጥቶ ብድር ይሂድ?! ሌላው በሌላ ክንፍ ያለው ወገን ደግሞ አማራ ምን እንዳለው፤ ምን እንደሚችልና ምን እንደሚፈለግ ዘመን ጠገብ አቅሙን ስለሚያውቁ – ይፈሩታል። ስለዚህም እንዳልተፈጠረ አድርገውም ተረት ይናገራሉ። ወይም ጸጉራቸው ሲቆም ይታያል። ልባቸው ግን ያውቀዋል። ማገርነቱን ባላና ወጋግራነቱን – ረቂቃዊ ጥልቅ መንፈሱን። ነፍሱ ከኢትዮጵያዊነት ጋር የተዋህደ ሰለሆነ ብቻ ሳይሆን ሥልጡኑ ሰብዕናው ጎጥ ላይ ኋላቀርነትን ፍለጋ አይማስንም። የጠራ መስመሩ ኢትዮጵያዊነት ነው።

አሁን ወደ ጉዳዬ „እኔነትን“ የሚገልጸው ሰብዕና ወይንስ ሥም? እንደ ሥርጉተ —- እኔነትን የሚናገረው ውስጥን የማዬት አቅምና ክህሎትን ነው። አቅምና ክህሎት ሊመሳሰሉ ሊወራረሱ ይችላሉም ባይ ነኝ። ክህሎት የአቅም ክምችት ሂደት ሲሆን አቅም ደግሞ ክህሎትን ለመፍጠር፤ ወይንም ክህሎትን ለመወለድ የብቃት የውይይት እርገት ማሳረጊያ ይሆናል።

„እኔ ማን ነኝ?“ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት መቻል በራሱ ትልቅ እርምጃ ነው ብዬ አምናለሁ። „እኔ ማን ነኝ?“ ለሚለው መላሹ „ሥም“ ሊሆን ከቶ ይችላልን? „ሥም“ ተለይቶ መጠሪያ እንጂ የውስጥ ጌጣማ፣ ውበታዊ ሰብዕና አብሳሪ ሊሆን አይችልም እላለሁ። በዛ ሥም ብዙ ሰዎች ይጠራሉና።

ስለሆነም አመልካች ወይንም አቅጣጫ ጠቋሚ ፍሬ ዘር መልክና ቁመና፤ አካላዊ ማንነት ከሚገልጸው ትርጉም አንጻር ሳይሆን ከመንፈስ ፈሎች የእርባታ አጸዳዊ ችሎታ፤ ከሥራ ፍቅር አስተሳሰብ ትንፋሻዊ ጠባይና ውስጣዊ ሰብዕናን ከሚጠይቀው ሥነ ምግባር ጥልቅ – ሰብዕዊነት ማህጸን ይነሳል። በሥራ – በፍቅር – በትዳር እንዲሁም በውስጣዊ ህይወት የውስጠት ሃዲዶች የከተሙ ከዬአቅጣጫው የሚነሱ አምክኖያዊ ጭብጦች „እኔን“ ይተርጉማሉ – ያብራራሉ።

„እኔ ማን ነኝ?“ ለሚለው በኽረ ጥያቄ እራስን ሳያታልሉ ይህን „እኔ ማን ነኝ?“ የመመለስ አቅም – ቁርጠኝነት – መወሰን የመቻል ብቃት ነው። ስለምን? ምላሹ በቀጥታ የፈተናን ድብቅነት ተጋፍቶ ወይንም ረግጦ „እኔን“ ይገልፃልና። ይህን መሰል ወደ ውሰጥ የማዬት እና ውስጣዊ ህይወትን በትኖ ዘርዝሮ በመንፈስ ሰሌዳ ደፍሮ የመገምገም አንጡራ ተግባር መንገዱ የሰላ ነውና፤ የመተርጎም ማዕከል ነው። እዬተዘወተር መንጠር ይኖርበታል። እንደ አጉልቶ የሚሳይ መነጸር ወይንም የሩቁን አቅርቦ እንደ የሚሳይ መሳሪያ ነውና። መፍትሄም!

ስለሆነም ከሚገበዬው እውቀትና ልምድ አኳያ እራስን ፈተና ውስጥ አስቀምጦ መለካት ንጹህ አዬር ሊሆንም ይገባል። ስበቱ ውጪያዊ አዬሩን ሆነ ውስጣዊ ትንፋሹን በማመዛዘን መልክ አስይዞ ሚዛኑን ይጠበቅለታል። ማህበራዊ እውነታዎች የሚፈቅዱትን በባህላዊ ውስጠዊ ሰብዕናን ደረጃ – በደረጃ በመቅረጽ፤ በማሻሻልና የተረጋጋ ውስጣዊ ህይወትን በሰላም ገነት ላይ ባለጉልት ያደርጋል ።

የኑሮው ዘዴ መነሻ ትልሙ ይሁን መድረሻ ግቡ „እኔ ማን ነኝ“ የሚለው ይሆናል። „እኔ“ ማን መሆኑን ካወቀ ከሌላው „እኔ“ ጋር በሰመረ ሰረገላ አብሮ ፍቅር የሚጠይቀውን ተፈጥሯዊ አዎንታዊ ሥነ ምግባር በቀናነት ለመፈጸም ንቁ ወታደር ይሆናል። ለመቅዘፍም „አልጋ ባልጋ ነው መንገዱ አንተን አምነው ሲሄዱ“  ይሆናል። የምር። በእኔ ላይ ሽወዳ እውር ስለመሆኑ ይህ እርምጃ „እኛ“  የሚለውን ቀይሮ „የእኔ“ „በእኔ“ ውስጥ ሁሉንም ሳይቆጠብ የሚለገሰው ገደብ የለሽ ባለመብቱ ዐፄ ፍቅር ይሆናል ማለት ነው። „እኔ ማን ነኝ ?“ እራስን አምጦ የወለደ „የእኔ“ እርካባዊ ሂደት ነው። የውበት አካል የውስጥ አብነት የእኔ ነው። ድርሻውን አስጠግቶ ቤተኛ ማድረግ።

ማለት „እኔን“ „እኔ“ ይወልደዋል። ሂደቱ በስበትና በግጭት ማህል፤ ቢያስፈልግም በጥሰት ውስጥን አውጥቶ ካለይሉኝታ ለተፈቀደለት „እኔ“ በግልጽነት መገበር ይሆናል። እርግጥ ስቃይ አለው – ፈታኝ ነው። ውጤቱ ግን ሰውኛ ጠረን ያለው ስለሚሆን የፍቅርን የአዬር ቧንቧ ከፍቶ ፍሰቱ በተስተካከለ ዝውውር እርካታን ማፍታትን ይተውናል።

መቸቱ ሆነ ገቢሩ ጊዜ የማይገደብለት፤ ደንበር አልበሾ በመሆን ነፃነቱ ሊታወጅለት ይገባል። ነፃነቱን የተቀማ ፍቅር ባይፈጠር ይሻለዋል። ከሁሉም ነገር በላይ ፍቅር በአንክሮ የሚጠይቀው ነገር ልቅ የሆነ የተፈጥሮ ውበቱን የማይጋፋት ንጹህ ነፃነትን ነው። ይህን ብቻ ፍቅር „ከእኔ“ ይፈልጋል። የዚህ ድርጊት ባለሟል ምላሹ „እኔ ማን ነኝ?“ ለሚለው የደፈረ ባለወኔ ብቻ አቅም ይኖረዋል።

ፍቅር ማለት ለሥርጉተ አንድ የላቀ የሙያ ዘርፍ ነው። የተፈጥሮ ባለጸጋ ዲታ የሆነ አለቃ ሩህሩህና ደግ ሙያ ነው። ፍቅር መንፈስ ነው – ቅዱስ።  በሰው እጅ ተንቦልቡሎ ያልተሰራ በደም የቀለመ፤ ፈልቆ የሚያፈልቅ የቀን ተሌት ብርሃን ነው። ዳመና፤ ጉም፤ ጨለማን የሚጥስ ጀግና! ተወዶ የሚያስወድድ፤ ተከብሮ የሚያስከብር – ዐፄ ነው። የፍቅር ባለ ሙያ ማለት መስዋዕትነት ፈቅዶ ሴሉን የገበረ ወይንም የሰጠ፤ እራሱን ያልሸጠ ወይንም ማንነቱን ያልተዋሰ፤ ተፈቅዶና ተወዶ ከውስጥነት በሐሤት የሚቀበሉት የመንፈስ አራሽ – የጸጋዎች ሁሉ እናት ነው – ዓፄ ፍቅር።

እርግጥ ነው ትናንት የአንድ ህብረተሰብ ሞራላዊ ጭብጥ አለ። ይህ ጭብጥ ግን ባለበት ቆሞ አይጠብቅም። ትናንት ያልነበሩ እውነታዎች ዘመን ይፈጥራቸዋል። ወይንም ተከድነው የኖሩትን ዘመን ይገልጣቸዋል – ክንብንባቸውን ያነሳል። አዳዲስ ሥነ ምግባራዊ ጭብጦች „እኔን“ በዬፌርማታው ያፋጥጣል። ስለዚህ የሰው ልጅ ሁልጊዜ ቦታውን ሞልቶ ሳይሆን አዳዲሶችን አዎንታዊ ቀንበጥ ዕሳቤዎችን፤ ዝንባሌዎችንና ዘዴዎችን ሊያዋህድ የሚችል የእንግዳ መቀበያ ክፍል በህሊናው በቋሚነት ሊኖረው ይገባል። (reserved class) ዓለምም ማድረግ ያለባት ይህኑኑ ነው። እርግጥ ልማዳዊ ደንብ በተለይ በረጅም ጊዜ የሚፈጠርና የሚዳብር እንደመሆኑ፤ ይህን በቆይታ ቤቱን የገነባ ደንብ ከአዲሱ ቁሳዊና መንፈሳዊ ባህል ጋር ጎልብቶ በህብርተሰቡ ዘንድ ሥር እስኪሰድ ድረስ ጊዜን ሆነ ትእግስትን ይሻል። በተለይ በማለቅ ላይ ባሉ አሮጌ ልማዶች በሚወገዙበትና በአንጻሩም ደግሞ አዲሱ ሞራሊቲ ገና ለጋ እድገት ዘገባ ላይ እያለ ድብልቅ ቅይጥ ስሜቶች ፈልተው እስኪሰክኑ ድረስ ማስተዋልን ትእግስትን በአጽህኖት ይጠይቃል።

የሽግግር ወቅቱ እንዳለ የሚቀጥሉትና አዲሶችን የሚዋህዱበት አዲስ ምዕራፍ ለመቀበል የሚያንቁ ገመዶች ሁሉ በስክነት መልክ መያዝ አለባቸው። ልዕልት ኢትዮጵያ ሀገራችን በተፃፈ ህግ እንደሚተዳደሩት ሀገሮች በተጻፈ ህግ፤ እንዲሁም ባልተፃፈ ህግ እንደሚተዳደሩት ሀገሮች ባልተፃፈ ህግ በጣምራ ህግ ትተዳደራለች። ይህ የእኔ  ዕይታ ነው። ጭብጦችንም የማቅረብ አቅም አለኝ። እርግጥ ዬህግ ባለሙያዎች ላይስማሙበት ይችላሉ:። እኔ እንደማስበው ግን ከተጸፈው ህግ ይልቅ ያልተጻፈው ህጋችን የበለጠ ተከባሪ፤ አጓጕ፤ ተወዳጅ፣ ስኬታማ፣ ተፈጻሚነት ሆነ ጉልበትም አለው ባይም ነኝ። ስለምን? ቀመሩ በፈቃደ ህዝብ ስለ ሰከነ።

ስለሆነም ሂደቱ በኃይል ሳይሆን መንፈስን አለስልሶና አዋዝቶ መሆን አለበት። የሆነ ሆኖ በሽግግር ወቅት በብዙ ሰዎች ውስጣዊ ሰብዕና መሰረታዊ ማህበራዊ ልማዶች ጊዚያቸውን ጠብቅው እዬተዳከሙ ሲሄዱ፤ የቀደመውን አንለቅም በሚሉ ደግሞ አዲሶቹን የሚቀጭጭ ውስጣዊ ግፊት ሊያነግሡ ይችላሉ። አጠቃላይ ሰብዕና ለመሆን በመፈለግና -በመሆን፤ በማለትና – በማደረግ፤ በማቀድና – በመገኘት መካከል ትልቅ የልዩነት ግንብ አለ። ውስጣዊ ሰብዕናን ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት ፍሪያማ የሚሆነው ከውስጣዊ አካላዊ እና ውጪያዊ እውነታዊ ዛቢያ አኳያ የተመጣጠነ የግንዛቤ ለውጥ ማምጣት ሲቻል ብቻ ነው። ስለዚህ እኔ ዛሬ የጀመርኩት ያልተለመደ ደፋር እርምጃ እንደ መነሻነት ተወስዶ በመሆን ሰቅ ተማክሎ ማዳበር ይቻላል። እርግጥ በዚህ ሃሳብ ዙሪያ የሚጠብቁኝ ጠብሰቅ ያሉ ጉልበታም ትችቶችና ፈለጣ እንደሚኖሩ አስባለሁ። ለመሸከም ስለተሰናዳሁ እቅሜ ሙሉዑ ነው።

ወደድንም ጠላንም ይህ ዬግሎባላይዜሽን አዲስ ዓለም በማህበራዊ ሚዲያ ያመጣው መጠነ ሰፊ ፈጣን የዛሬ ለውጥ ብቻ ሳይሆን ከዛሬው ባደገና በጎለመሰ መልኩ አዲስ ግኝቶች ዳብረው ተሻሽለው ነገ ይፈልቃሉ። ፍቅርንም ሰብዕዊነትንም፤ እንደ ሰው የመሆን ሚስጢርም ከዘመኑ ጋር ይመነደጋሉ። ስለዚህ ለዘመኑ መመቸት ግድ ይላል። ፍቅር የተጠረገ ልብን አብዝቶ ይሻል። ቅይጥ ፍላጎት፤ ታችና ላይ የሚዘል ተራጋጭ ስሜት፤ የዘበጠ ፍላጎት ቁርሾ ተከል ዝንባሌዎች ወንዝ አያሻግርም። ከመብቀሉ በፊት ይፈልሳል – ክው!

ይህን ማዳን የትውልዱ ዕጣ ነው። በቆዬው ባህል ጸንቶ መቆም መልካም ቢሆንም፤ ከዘመን ጋር ግጭት መፍጠር ደግሞ አዳጋው ሰፊ ነው። የተቆጣጠረ ክር ካልተፍታታ ጥቅም አይሰጥም። ጤነኛ የውስጥነት ዓይን ዘመኑን በአጽህኖት ይጠይቃል። ልደግመው አሁንም ሰብዕዊነት፤ እንደ ሰው ማሰብ፤ የሰው ልጅ ለተፈጥሮ የሚሰጠው አክብሮት በፍቅር ፍልስፍና ማደግ አለበት። እድሜ ሲጨምር አዕምሮም ከጣሪያም ከግድግዳውም ማደግና መዳበር ብቻ ሳይሆን  ለም ሆኖ ለስልሶ መጠበቅ ይኖርበታል (fertility)። ሁልጊዜም የሰው ልጅ ለፍቅር ተሸናፊ መሆን አለበት። ለሚወደው ነገር፤ ሥነ ምግባር የማይገዛ በሰው ደረጃ ለማዬት ዳገት ነው። ፍቅር የነጠረ የመኖር ሚስጥር ነውö እርግጥ አለም በቅቡ ነው የሚነጉደው። ግን ጸጋውን አውጥቶ ተጠቃሚ ለመሆን ድምጹን አጉልቶ ማውጣት ያስፈልጋል። ስለ ፍቅር ለሰው ልጅ ከተሰጠው ዕምቅ ሃብት፤ ምንም እንኳን ጥናታዊ መረጃ ማደረግ የሚስችል ሁኔታ ላይ ባልሆንም አንድ አስረኛውን እንኳን አልተጠቀምንበትም። ለዚህ ነው ዓለምና ተስፋዋ እንዲህ እንዳመጠ ተንበርክኮ – የሚታዬው። በአብዛኛው የሚታዬው ፍቅር በተቃራኒ ፆታ ቅንጣት ጉዳይ ወይንም በትናንሽ ግንኙነቶች ዙሪያ ብቻ ነው። ነገር ግን የተፈጥሮ ጭንቅላት ፍቅር ነው።

ስቃዩ ሙቀትን፤ ጭንቀቱ ምህረትን እንዲያድል፤ የፈላ ሰዋዊ ስዋሰዋዊ ትንፋሽ ጠገብ ፍላሎትን እንደ አሻው ማስመቸት ያስፈልጋል። የነፍስን ጨዋታ የምላሻ ጨዋታውን አጉልቶ መግለጥ ይጠይቃል። ፈጣሪ አምላክ የሰጠው የማይገሰስ የውሰጥ ሰላም ተጠቃሚ መሆን ያለመቻላችንም መሰረታዊ ምክንያትም ይህን የመተግበር ክህሎታችን ጠባብ በመሆኑ ይመስለኛል።

የፍቅር ረቂቅነት ልቡን እስከሚያገኙት ድርስ ነው። ምቱን እስኪለኩት ድረስ ነው። በቁጥጥር ሥር እስኪያውሉት ድረስ ነው እንጂ እንደ ፍቅር ለማዳ ቤተኛ እንሰሳ የለም! አዳኝም የምህረት ሐዋርያም። ግን ደፋር ካገኘ ነው፤፡

… ከዚህ በኋላ ቀያሹ እሱ እራሱ ይሆናል። ዋናው የውስጥ ወጥነትን ከጥቃት ለማዳን ለፍቅር ውስጥን በሚገባ መዘርዘር አስፈላጊና መሰረታዊ  ከመሆኑ ላይ ነው። ሁልጊዜም መድገም መሰለስ መመላለስ፣ መለማማድ – መለማመድ ቅንብሩን መከተል ቃናውን ማዋሃድ በአጽህኖት ያስፈልጋል። ጥገና ለሚያስፈልጋቸው የቃና መሳሪያዎቹም ጥንቃቄ፣ ፍጥነትና አድማጭነት ቀልቡ ናቸው። መዘግዬት ግን ዳጥ ነው።

ይህን ለማድረግ ከማንምና ከምንም ስደት ያልጠዬቀውን ንጹሁን „እኔን“ ሳይታክቱ ፈልጎ ማግኘት የመፍትሄው ቁልፍ ነው። ስለዚህም ዘመኑ እራሱ እዬዳጠው ዬሚሄደው ትብትብ አፍታቶ፤ በተፍታታ አቀራረብ — በተብራራ ገለጻ፤ ደረጃውን በጠበቀ የአዬር ሁኔታ ተፈጥሮውን ማድነቅ፤ ማክበር ፋኑስ መሆን ያስፈልጋል። አጉል አቅጣጫ ይዞ አጉል ቦታ ከሚቀረቀር ሰባራ ጎማ፤ ፍቅርን አድኖ ዘመናዊነትን ማስታጠቅ በእጅጉ ያስፈልጋል። እያዋዙ ባህልን – ወግን – ልማድን የዕምነት ዶግማዎችን ሳይጋፉ ጭንቅላቱን ፍቅርን በጠረጴዛ ዙሪያ ማወያዬቱ እጅግ ሥልጡነነት ነው። እንዲያውም ዘግይተናል።

„እኔ“ „እኔን“ ስሰጥለት ቁምነገሩ ለማደግደግ ለመገዛት መሆን አለበት። በልግስና በድርጊት መንቆጥቆጥ አለበት – ፍቅር። ሁለቱ „እኔዎች“ በመንፈስ በድርጊት አኃቲነትን የሚፈጥሩት ሰው – ሰው የሚሸተውን ሰውኛ ጠረን ውስጣቸው ሲያደርጉ ብቻ ነው። ተስፋ ካለተዕቅቦ ሲዋኝ። ዋና የፈለገ ፍቅርን ይዞ ወንዝ ይውረድ ፍቅር ጥሩ የዋና መምህር ነው። ፍቅር ቀለሙ አዲስ ነው። አዲስ ቀለም ይናፍቀን …. ፈቃድ …..

ትልም ምርት – ምርት ግብዕት፤ እርገት – ስክነት፤ – ስክነት ውበት -፤ ውበት ሁነት፤- ሁነት ትፍስት ይሆን ዘንድ የሰማነውን በልቦናችን ያሳድር፤ የኔዎቹ ብርቅ የሐገሬ ልጆች ውድ – አንባቢያን በአብሮነት ቆዬን ሳትሳሱ ፍቅርን በፍቅር አትኩሮት ጠልፋችሁ ሁሉን ሰጣችሁኝ።  ልግስናችሁ እንሆ ቁሞ አስተማረኝ። ስለሆነም እኔ ሎሌያችሁ – ውስጤን በንጽህና ሰጠኋችሁ። ውለታ ሳላጓድል ወይንም ሰላንጋልል በቅንነት – አከበርኳችሁ። የመንፈሴ ጌጥ አድርጌም በመንፈሴ ማህጸን  እንሆ አተምኳችሁ! ኑሩልኝ!  ዘሃበሻ ጌጦቼ – ኑሩልኝ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። በድጋሚ በፍቅር ለጥ ብዬ ሰግጄ – ተሰናበትኩ። መልካም የማስተዋል – የመደማመጥ ክብራዊ ጊዜም ተመኘሁ።

  • ዕይታ በትህትና – የዚህ ጹሑፍ መንፈስ ትንሽ ጠጠር ስለሚል፤ ከቻሉ ደጋግመው ሲያነቡት መልዕክቴን ሊያገኙት ይችላሉ። ግጥም መሰል አመክንዮን ያስተናገደ – ስለሆነ። አመሰግናለሁ – በአክብሮት

ስለ ፍቅር መዋረድ የነፃነት ፍለጋ ጽድቃዊ ጉዞ ነው፤

ፍቅር ለተስፋ አድሮ የሚገኝ ብቸኛ ማተበኛም – ትውልድ።

እኛን ስለሰጠን አምላካችን እናመስግን!

 

The post እኔ ማን ነኝ? – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢትዮጵያና ዐባይ –ግብፅና እስልምና!! –አንተነህ ሽፈራው

$
0
0

መጋቢት 19 ቀን 2007 ዓ.ም (March 28, 2015)

Blue Nile. . . ይኩኑ አምላክ የኢትዮጵያን ማዕከላዊ ሥልጣን ከዛጉኤ ሥረዎ-መንግሥት (ከላስታ) እ.ኤ.አ 1270 ዓ.ም ነጥቀው ወደ ሸዋ ሲወስዱ የመጀመሪያው እቅዳቸው በሁሉም የኢትዮጵያ የግዛት ማዕከሎች ያሉ ክርስቲያኖችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ሃይማኖታዊ ግልጋሎት የሚሰጥ አባት/አቡን/ ይፈልጉ ስለነበር ትኩረታቸውን ወደ ግብጽ አደረጉና የዛን-ግዜውን የግብፅን ፈርሆን/ንጉሥ/ ሱልጣን ባይባርስን እ.ኤ.አ በ1272 በይፋ ቢማጸኑም ሱልጣን ባይባርስ ግን የክርስትና ሃይማኖት መኖርን አለመፈለጉ ብቻ ሳይሆን የክርስቲያን ኑባ ሥረ-ወመንግሥትን ጭራሽኑ ለማውደም በከፍተኛ ዘመቻ ላይ ነበርና የይኩኑ አምላክን ተማጽኖ ሊያስተናግድ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ይኩኑ አምላክም (ከብዙ ቆይታ በኋላ) ፊቱን ወደ ሶሪያ በማዞር አባትነቱን ለሶሪያው ጃአኮቢት ሰጡ. “Baybars, was engaged in the conquest of the Crusaders’ last strongholds in the Holy Land. But he also directed a campaign aimed at destroying the Christian Kingdom of Nubia] …-—[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–

 

The post ኢትዮጵያና ዐባይ – ግብፅና እስልምና!! – አንተነህ ሽፈራው appeared first on Zehabesha Amharic.

ዘመናዊ ባሪያ ፍንገላ በኢትዮጵያ (ነፃነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ)

$
0
0

በታሪክ ትምህርት የሚወሳ “የባሪያ ፈንጋይ ሥርዓት” የሚባል ማኅበረሰብኣዊ ዕድገት የወለደው ጥንታዊ ሥርዓት ነበር፡፡ ያ ሥርዓት በወቅቱ በሰው ዘር መካከል ትልቅ የልዩነት ቋጥኝ ፈጥሮ አንዱን ጌታ ሌላውን ሎሌና ከዚያም አልፎ የጊዜ ማሳለፊያና የመዝናኛ ዕቃ በማድረግ የማይፋቅ ጠባሳ አስቀምጦ ያለፈ ሥርዓት ነው(ሰውን ከአንበሣና ከነብር እያታገሉ በሰው ስቃይ የሚደሰቱ መኳንንትና መሣፍንት ነበሩ)፡፡ ለዚህ ሲያስቡት እንኳን ለሚዘገንን የታሪክ ስብራት አሜሪካ ኅያው ምሥክር ናት – ምንም እንኳ ነገሮች በተወሰነ መልክና ባልተጠበቀ መንገድ ቅርጻቸውን ለውጠው የጉዳቱ ሰለባዎች ለይስሙላም ቢሆን አሁን አሁን መንበረ ሥልጣን የጨበጡ ቢመስሉም የጓዳ ጎድጓዳው ታሪክ አሁንም ብዙ የተለወጠ አይመስልም – በጥቁርና በነጭ የሚታየው የዘር ልዩነት አሁንም ድረስ አልጠፋምና፡፡ አፍሪካውያንና ካሬቢያውያን በተለይም ጋናንና ቤኒንን የመሳሰሉ የባሪያ ንግድ ይጧጧፍባቸው የነበሩ ሀገሮችም ቋሚ ምሥክሮች ናቸው፡፡ የእነኩንታኩንቴ ታሪክ መቼም ቢሆን በኅያውነት ይቆያል፡፡ በኢትዮጵያም እነግንደበረትና እነሰሜን ሸዋ፣ እነቦንጋም ይመስክሩ፡፡ ቋንጃ መቁረጥ፣ የሰውን ልጅ ዛፍ ሥር ኮልኩሎ በወፈረና በከሳ፣ በዕድሜ በገፋና ባልገፋ፣ ባጠረና በረዘመ፣ ከብት ይመስል ጥርሱን በሸረፈና ባልሸረፈ … እየተባለ የሰው ልጅ እንደእንስሳና እንደአሞሌ ጨው በገንዘብ ወይም በዓይነት ይሸጥ ይለወጥ ነበር፡፡ ያ እንግዲህ ዱሮ ነው፡፡ አልፏል፡፡ መልኩን ቀይሮ በኢትዮጵያችን ሊያውም ሰላምን፣ ፍትህን፣ ነፃነትን፣ እኩልነትንና ዴሞክራሲን ከአንደበቱ በማይነጥለው የሕወሓት መንግሥት በዘመናዊ መልኩ አሁንና ዛሬ እውን ሲሆን ግን ምን እንላለን? “ጭቆናና መድሎ አስመርሮኝ ሕዝቤን ነፃ ላወጣ ለትግል በረሃ ወጣሁ” የሚለው ሕወሓት ጥንት የሞተን የባሪያ ፈንጋይ ሥርዓት ነፍስ ዘርቶበትና አቀንቃኝ ሆኖ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ብቅ ሲል በተለይ የድርጊቱ ሰለባዎች ምን ይዋጠን? አሣዛኝ ድርጊት በሀገራችን እየተፈጸመ ነው፡፡ እመለስበታለሁ፡፡

በምሥጋና መጀመር ነበረብኝ፡፡ ይቅርታ፡፡ ብዙም አልረፈደብኝም፡፡

በዚህን ሰሞን “ኑሮ በአዲስ አበባ” በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ ማቅረቤን ተከትሎ ከወትሮው ለዬት ባለና እኔንም ባስገረመኝ ሁኔታ ብዙ አንባቢያን ልባዊ እርካታቸውን በመግለጽ በግል አድራሻየ መይለውልኛል፡፡ ለሁሉም በወቅቱ መልስ ሰጥቻለሁ፡፡ ግን በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም በሁሉም አንባቢያንና በድረገፆቻችን ስም በድጋሚ ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ፡፡ ከውድ ጊዜያቸው ተሻምተው ያን ብሶት-ወለድ ረጂም መጣጥፍ በማንበባቸውና በኑሯችን ከምር አዝነውም ያን የመሰለ ነፍስና ሥጋን የሚያለመልም የሞራል ድጋፍ ከዚያቺው ዕንቁ ጊዜያቸው ሰውተው በመላካቸው አሁንም ምሥጋናየ ድንበር የለውም – ጫት ቤቶችንና መጠጥ ቤቶችን ስታዘብ በኛ ሀገር በኮንቴይነር አሽገን ወደዓለም የጊዜ ገበያ ኢክስፖርት ልናደርገው የምንችለው “ጊዜ” በብዛት እንዳለን ብገነዘብም በውጭ ሀገራት ለሰላምታ እንኳን ጊዜ እጅግ ውድና ብርቅ እንደሆነ እሰማለሁ – ለዚህም ይመስላል ሰዎች በእግር እየተጓዙ በተመሳሳይ ቅጽበት ስልክ የሚያናገሩት፣ ምግብ የሚመገቡት፣ ጽሑፍ የሚያነቡትና… በአካባቢ የሚከናወንን ነገር የሚቃኙት፡፡ አንዲት ደቂቃ ወርቅ ናት፡፡ እንደውነቱ ከሆነ ጽሑፍ መጻፍ ከጀመርኩ ጊዜ አንስቶ ጽሑፌን በማንበብ ይህን ያህል በሀገሩ ጉዳይ ልቡ የተነካ አንባቢ ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ በኔ የጋዜጠኝነት ዕውቀት የአንድ ሰው አጸፋ(feedback) በመቶ ሰው ይመነዘራል፡፡ ስለዚህም እስካሁኒቷ ቅጽበት ብቻ በጎ አስተያየታቸውን የላኩልኝ 15 ሰዎች 1500 ሰዎችን እንደሚወክሉና አጻጻፌንና መልእክቴን ክፉኛ ነቅፎ የወቀሰኝ አንድ ሰው ደግሞ በሌላኛው ጎራ 100 ሰዎችን እንደሚወክል በወያኔያዊ ቋንቋ ግንዛቤ ወስጃለሁ፡፡ የዚህኛውን ሰው አስተያየት ለፍርድ እንዲያመች በመጨረሻው ላይ እንዳለ አስቀምጠዋለሁ፡፡ የሌሎችን ግን ሙያ በልብ ነውና በኔው ይቅር፡፡ ግን ግን አይዞን፤ እንደጨለመብን አንቀርም፡፡ የተበተነው የሚሰበሰብበት፣ የተራበ በልቶ የሚጠግብበት፣ ጠግቦ የሚዘል አደብ የሚገዛበት፣ ፍትህ ርትዕ የሚሠፍንበት፣ ፍቅርና መተማመን የሚናኝበት፣ የእህል በረከት የሚበዛበት፣ … እውነተኛ የመኖሪያ ድባብ በሀገራችን በጣም በቅርቡ ይፈጠራል፡፡ እንዲህ ይታየኛል፡፡ ገደሉን ጨርሰን ጫፍ የደረስንም ይመስለኛል፡፡ መመኪያየ ግን ኢትዮጵያን ፈጥሮ የማይረሣት አምላከ ኢትዮጵያ ወአምላከ ኩሉ ዓለም እንጂ ሰው አይደለም፡፡ተስፋችን እሱ ነው፡፡

ድረ ገፆችን በሚመለከት ሁሉንም ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ እነሱ ባይኖሩ የነፃነት ትግላችን በብዙ ማይሎች ወደኋላ ይቀር ነበር፡፡ ችግራችን እንዲሰማ፣ የሌላው ዓለም ሕዝብም እንዲያውቅልን፣ የነፃነት አርበኞች እንዲጠራሩና እንዲወያዩ … በማድረግ ረገድ እየከፈሉ ያሉት ከፍተኛ መስዋዕትነት በታሪክም በፈጣሪም ዘንድ ትልቅ ዋጋ የሚያሰጣቸው ነው፡፡ አምላክ ይጠብቃቸው፡፡

ይህን ስልም ከነህፀፃቸው ነው፡፡ ዓለማችን ምሉዕ በኩልሄ አይደለችም፡፡ ፍጹምነት የለም፡፡ ማንም በምንም ዓይነት መለኪያ ፍጹም አይደለም፡፡ ከዚህ ፍጹምነትን ከመሻት አኳያ ማናችንም ብንሆን በየሥራችን እንዳንታበይ ወንድማዊ ምክሬን መሰንዘር እወዳለሁ፡፡ ያጠፋን ሳይመስለኝ የምናጠፋበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ ዐውቀን የምናጠፋበት ጊዜም እንደዚሁ አለ፡፡ ቂም የምንቋጥር፣ በቡድን ስሜት በመገፋት በግል ያልበደሉንን የምናሣዝን፣ መቻቻልን የማናውቅ፣ በዱሮ በሬ የምናርስና ከረሜላ እንደከለከሉት ሕጻን በቀላሉ የምናርኮፍ፣ ወዘተ. አለን፡፡ ሰዎች እንደመሆናችን አመንነውም ካድነውም እንሳሳታለን፡፡ እኔ በበኩሌ እንደዚህ ነኝ፡፡ እሳሳታለሁ፤ በስህተቴም እጸጸታለሁ፡፡ ይቅር በሉኝ ብዬም የበደልኳቸውን ሰዎች ከልብ በመነጨ ስሜት እለምናለሁ፡፡ እንዲያ ስንሆን ይመስለኛል የሰው ልጅን የዕድገት መሰላል ወደላይ የምንወጣው፡፡ እንዲህ ካልሆን ታጥቦ ጭቃ እንሆናለን፤ ንግግራችንና ተግባራችንም ለዬቅል እንደሆነ ይቀራል፡፡ በንግግር ብዙዎቻችን እጅግ መሳጭ ነን – በምግባር ግን ያን ያህል አንሆንም፡፡ በጸጸትና በንስሃ፣ በመደማመጥና በመግባባት በተመሠረተ ይቅር መባባል መንፈሣዊ ፈውስን ካላገኘን በመጎሻመጥና በመገፈታተር፣ በትዕቢትና በትምክህት የትም አንደርስም – ምናልባት የነዚህ ነገሮች አባትና የክፋት አበጋዝ ወደሆነው የዲያብሎስ ቤተ መንግሥት ልናመራ እንችል ይሆናል – ያ ደግሞ ብዙ ልፋትና ድካም የለበትም፡፡ ቂምንና በደልን ሠርዞ (ልብ በል – ረስቶ አላልኩም! የተረሣ ይታወሳልና፡፡) በአንተ ትብስ በአንቺ ትብሽ በአዲስ መልክ ፍቅርንና መዋደድን መመሥረት ግን ከባድ ከባድ ቢመስልምና ቢሆንም ይቻላል – ባሕርያዊ እልኸኝነትንና ዕብሪትን ማሸነፍ ከጦርነቶች ሁሉ ከባዱ ይመስለኛል፤ ጽጌረዳ ታምራለች፤ ይቅር ባይነትም ሃሤትን የሚያረብብ ዕፁብ ድንቅ ነገር ነው – ወደአምላክም ያስጠጋል፤ ሁለቱም ግን እሾሃማ ናቸው – በቀላል አይገኙም፤ ጽጌረዳዋ እጅን የሚወጋ ጦረኛ እሾህ፣ ይቅርባይነትም ስሜትን የሚፈታተን መግነጢሳዊ ኃይል አላቸው፡፡ እስከማውቀው ድረስ ትዕቢትና እልኸኝነት ማንንም አዋጥተው አያውቅም፡፡ ስሙን ቄስ ይጥራውና ያን የአዳምና የሔዋንን ቀንደኛ ጠላትም ወደታችኛው ዓለም(the netherworld) ከገነት አውጥቶ ያሽቀነጠረው ይሄው ትዕቢት ነው፡፡
ሳልጠቀስ የማላልፈው ወቀሳ አለኝ፡፡ ይህ ወቀሳየ ደግሞ የኔ ብቻ ሣይሆን የብዙ ጸሐፍት መሆኑን እረዳለሁ፡፡ የችግር ትንሽና ትልቅ የለም ብዬ ስለማምን ይህንንም በመጠኑ ማንቀራበጡ አይከፋም ባይ ነኝ – ተገቢ ትኩረት ያልተሰጠው ትንሹ ችግር ነው አድጎ ትልቅ እሚሆን – “እማዬ፣ ምነው በዕንቁላሌ በቀጣሽኝ!” የሚለውን ሥነ ቃላዊ ብሂል እናስታውስ፡፡ አንድን ችግር ሳይብስበት መግለጡ ለመፍትሔው በግማሽ እንደመቅረብም ይመስለኛል፡፡ ‹ኑ እንዋቀስ‹ አልነበር የሚል ያ አላበሳው ተሰቅሎ የሞተ የዓለም መድሓኒት? ብንዋቀስ ምን ወጪ እናወጣለን? ተዋቅሰን ብንታረቅና የሰይጣንን ቀንድ ብንሰብር ተጠቃሚዎች ነን፡፡ ጥቅምን ደግሞ በግድ ከማቴሪያላዊ ጎኑ ብቻ ማየት የለብንም፡፡ እንደችግር ሁሉ የጠብም ትንሽና ትልቅ የለውም፡፡ ለምሳሌ የኔን ተግባርና ጠባይ ልትንቅ ትችላለህ – እኔን ግን ልትንቀኝ አይገባም፡፡ ነውር ነው፡፡ ኃጢኣትም ነው፡፡ እንዳንተው ሰብኣዊ ፍጡር ነኝና አንተ ባንተ ላይ እንዲያደርጉብህ የማትወደውን ነገር ሁሉ በኔ ላይ ልታደርግ አይገባም – ኮንፊውሸስ ተናገረው፣ አሊጋዝ ደገመው እውነቱ ይሄው ነው፡፡

ዝም ብዬ ሳስበው አንዳንድ ድረገፆች ምን እንደሚፈልጉ የሚያውቁ አይመስሉኝም፡፡ የሚፈልጉትን ነገር እንዳለማወቅ የመሰለ አስከፊ በሽታ ደግሞ የለም፡፡ ጅል ባህል ሆኖባት ሣይሆን አይቀርም ያገሬ ሣዱላ በፍቅር የነሆለለላትን ጉብል ንቃ (ባህሉን ስለሚያውቅ ሆን ብሎ እንድትወደው በማሤር የናቃት መስሎ የሚጀነንባትን ጭምር መሆኑን ልብ ይሏል) የሚንጠባረርባትንና የሚጠላትን እንደምታፈቅር ሁሉ አንዳንድ የድረገፅ አዘጋጆችም በፍቅር የሚንሰፈሰፍላቸውን ወገናቸውን ያለመለየት ችግር አይባቸዋለሁ፡፡ በበኩሌ ምን ስጽፍ በየትኞቹ እንደሚወጣና በየትኞቹ እንደማይወጣ አስቀድሜ ዐውቃለሁ – ባብዛኛው፡፡ ይህ ዓይነቱ መለስተኛ ልዩነት የሚለመድ ነው – በቂ ምክንያት ኖረውም አልኖረውም በበኩሌ ለምጀዋለሁና አንዳንዶች ነሸጥ አድርጓቸው ፊት ሲነሱኝ ማቅ አልለብስም፡፡ ደግሞም – በሚገባ አምናለሁ – የዜጎች ሁሉ አስተሳሰብና አመለካከት በግድ አንድ መሆን የለበትም፤ ልዩነት ይኖራል፡፡ ነገር ግን ልዩነት ይኖራል ሲባል በሁሉም ነገሮች በግድ መለያየት አለብን ማለት አይደለም፡፡ ልዩነትን ተገድደን የምንቀበለውና ለማጥበብም ከልብ የምንጥርበት ሊሆን ይገባዋል እንጂ በ“ማን ምን ያመጣል?” የፈግጠው ፈግጪው ሁከተኛ መንፈስ አነሳሽነት በቤተ ሙከራ ተፀንሶ የሚወለድና የሚያድግ በጥባጭ “in vitro son” ሊሆን አይገባም፡፡ አንድ ሊያደርጉን የሚችሉ ነገሮች መኖር አለባቸው፤ ማወቅ ስለማንፈልግ ይሆናል እንጂ የምንጋራቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ተቃዋሚዎችንና ወያኔን አንድ ሊያደርጉ የሚችሉ ነገሮች አይኖሩም ብዬ በበኩሌ አላምንም፡፡ በዚህኛውም ሆነ በዚያኛው ጎራ እንደአለመታደል ሆኖ ሁሉንም ነገር የመቃወም ባህል ስላዳበርን እንጂ በምንስማማባቸው ነገሮች እየተስማማን በማንስማማባቸው ነገሮች ብቻ ብንነጋገር ኖሮ ትልቅ ሸክም ከትከሻችን በወረደልን ነበር፤ ግን አንዱ ስንጥቅ ሌላውን ሸለቆ እየፈጠረ ነገረ ሥራችን ሁሉ ባቢሎን ሆኖ ቀረ፡፡ ልዩነት ደግሞ በባሕርይው ቶሎ ካላጠበቡትና ከነጭርሱ ካላጠፉት እየተምቦረቀቀ የሚሄድ ክፉ ደዌ ነው፡፡ በአሁኑ ሁኔታችን በአንድ ጎራ ውስጥ አሉ በሚባሉ ወገኖች መካከል እንኳን የልዩነት ቀዳዳዎች ሲሰፉ እንጂ ሲጠቡ አይስተዋሉም፡፡ ይህም መረገም ነው፡፡

ከዚህ አኳያ ያ የበቀደሙ ጽሑፍ በተለይ የዘወትር ደምበኛው በሆንኩት አንድ ድረገፅ ላይ ሳይወጣ ሲቀር ደንግጫለሁ፡፡ በተደጋጋሚ ብጠይቅም እነአያ ሰው ጤፉ ፀጥታን መርጠዋል፡፡ የሕዝብ ነፃነት ተሟጋች ማለት እንግዲህ እንዲህ ነው፡፡ ውሸታም በሏቸው፤ እኔም ብያለሁ፡፡ የአንድን ዜጋህን ጥያቄና ብሶት ለመጋራትና ስሜቱን ለመረዳት፣ ተረድተህም ለማረጋጋት ካልሞከርክ፣ ከዚያም ባለፈ በትዕቢት ተወጥረህ ከተጓደድህበት ውሸታምና የይመስል ታጋይ ነህ – “ፑቲካ!”፡፡ አንድ ዜጋ ክቡር ነው፡፡ ትግላችንም ለዚያ ነው፡፡ እኛ ዘንድ የሌለን መከባበርና መደማመጥ እሌላ ቦታ መፈለግ ላም ባልዋለበት ኩበት ለመልቀም እንደመሞከር ነው፡፡

አንድ ወቅት በጣሊያን ሀገር ለውኃ በተቆፈረ የ36 ሜትር ጥልቀት ጉድጓድ ውስጥ አንድ ሕጻን ይገባና መንደርተኛውና ጠበብቱ ሁሉ እንዴት ሕጻኑን ማውጣት እንደሚቻል በጉድጓዱ ዙሪያ ከብበው ይጨነቃሉ፡፡ በዚህ መሀል ወሬውን በተባራሪ የሰማው የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ይመጣና አብሮ እየተጨነቀና እያዘነ ከሕዝቡ ጋር ሙሾ ያወርድ ገባ፡፡ ሰው ማለት እንዲህ ነው፤ መሪ ማለትም፡፡ ዜጋቸውን እንደትቢያ የሚቆጥሩ ወያኔዎችን የምንታገለው ሌላ የአፈና ሥርዓት አምሮን ሣይሆን የመሰለንንና የምናምንበትን የኛን እውነት በነፃነት መግለጽ እንድንችል ነው፡፡ እርግጥ ነው – አንድ ሰው ወይም አንድ ቡድን የተጻፈው ነገር ትክክል አይደለም ብሎ ሲያምን በዚያው መድረክ በተመሣሣይ መሣሪያ – በብዕር – አጸፋውን በመስጠት የማስተባበልና የማስተማርም ግዴታ አለበት፡፡ ከዚያ ውጪ ወደ አፍ እላፊና እጅ እላፊ እንዲሁም ወደመኮራረፍ መሄድ ከሰውነት ደረጃና ክብር መውጣት ነው፡፡ ሰዎች ወደነዚህ ጅላጅል አማራጮች የሚዞሩት ትግስት በማጣታቸው ብቻ ሣይሆን የእውነት ስንቅ ስለሚያጥራቸው በካፈርኩ አይመልሰኝ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ አዎ፣ እውነት ስታጥረን ሀሰት ከተፍ ትልና የተጓደለውን ነገር በዛቻም፣ በስድብና በጡንቻም ታሟላልናለች፡፡

የኔን ወረቀት ቦጫጭቆ የጣለው ያ ድረ ገፅ ግን አሁንም ድረስ ግራ እንዳጋባኝ አለ፡፡ እንደሰው ድረገፅ ከፍቶ ማስተናገድ ከጀመሩ በኋላ ቀጫጭን ሰበብ እየፈለጉ ተናጋሪን ለማፈን መሞከር ሳቢውን ግረፈው እንዲሉ ነው፡፡ ያበጠው ይፈንዳ – ይህ ዓይነቱ አፈና ከወያኔ ያልተናነሰ ብልግና ነው፡፡ ያ ጽሐፍ በዚያ ድረገፅ የቅርጫት እራት (በኮምቡጠር ቋንቋ የ“Trash” ቀለብ) ሆኖ ይቀራል ብዬ በእውኔ ቀርቶ በህልሜም አላሰብኩትም፡፡ ከናካቴው ያዩትም አልመሰለኝም፤ አይተውት ከሆነና በምንም ምክንት ይን ከተውት ግን በርግጥም የሚዲያ ሥራን አያውቁም፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር ቆሜያለሁ የሚል “የነፃነት ዐርበኛ” ያን የመሰለ ከመስከረም በሉት፣ ከየካቲትም በሉት(በተወሰነ ደረጃም ቢሆን)፤ ከግንቦትም በሉት ከሌላ ማናቸውም ንቅናቄ ምንም ያህል የጠበቀ ግንኑነት የሌለውን ማኅበራዊ ጉዳይ ገሸሽ ሲያደርገው “የሚሠሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” የሚለውን ክርስቶሳዊ ተማጽኖ ከማስታወስ ውጪ ሌላ ቃልም ሆነ አስተያየት የለኝም፡፡ የሚዲያ ሥራ ሆደሰፊነትን፣ ዕውቀትና ችሎታን፣ ሃቀኝነትን፣ አለማድላትን፣ አለማግለልን፣፣ ሙያዊ ትምህርትና ሥልጠናን፣ በጥቅም አለመደለልን … ይፈልጋል፤ ፈራጅና ዳኛው አንባቢ ወይም አድማጭና ተመልካች እንጂ እሱ የመረጠለትን ብቻ የሚያሣልፍ ከሆነ መጥፎ አሣላፊ ሆነ ማለት ነው፡፡ ጋዜጠኛ በሁለት የተራራቁ ጫፎች መሀል የተቀመጠ የሁለቱም ጫፎች የወል አገልጋይ እንጂ ከሁለቱ ወደ አንድኛው የሚሳብ ሊሆን አይገባም – ሰው ነውና አይሳብ አልልም፤ በሥራው ላይ እስካለ ግን አንዱን በመውደድ ሌላውን በመጥላት ሚዛኑን የሚስት ከሆነ የፓርቲ/የድርጅት ልሣን እንጂ የጋዜጠኝነት ሙያዊ ሥነ ምግባር የሚፈቅደው አሠራር አልተከተለም – ኅሊናውንም አቆሸሸ፡፡ ከዚህ መሠራተዊ መርህ አኳያ ድረገፆቻችን ቢፈተሹ … ለነገሩ ማነው ወንዱ ለመፈተሸ የሚነሣ! ማንስ ሊሰማው፡፡ ለማንኛውም ማንም ደመ ሞቃት ካለበቂ ሙያዊ ዕውቀትና ግንዛቤ ከሜዳ እየተነሣ ጋዜጠኛ ልሁን ቢል ኢቲቪን ከሚያስታውሰን በስተቀር ሊታይና ሊጨበጥ የሚችል የረባ ሥራ አይሠራም፡፡ ዐርፎ እቤቱ ቢቀመጥ ወይም ሌላ ነገር ቢሠራ ነው የሚሻለው፡፡ ከልብ ነው ያዘንኩት፡፡ ሰው ደግሞ በወደደው ያዝናል፡፡ አለበለዚያማ ስንትና ስንት ሺህ ድረገፅ ሞልቶ የለም እንዴ? ደግሞ ለድረገፅ! የኮምፒውተር እናት በድባብ ትሂድ፡፡ እኔም እዚህ ሀገር ውስጥ ቀረቀር ውስጥ አጓጉሊት ተሰንቅሬ ባልገኝ ኖሮ አሥሩን ከፍቼ አራውጠው ነበር፡፡(ብዙ ጊዜ የሚያሣዝነኝ ነገር – ብዙ ነገሮች ወደኢትዮጵያ ሲገቡ ተፈጥሯቸውን ይለውጡና amorphous ይሆናሉ – ቅርጽ አልባ፡፡ ጥሎብን ፖለቲካችንም ሸፋፋ፣ ንግዳችንም ሸፋፋ፣ ዕድገታችንም ኳሻርኳራዊ ምች ያጠናገረው ግንጥል ጌጥ፣ የትምህርት ሥርዓቱ ሸፋፋ፣ መንግሥታዊ ተቋማችን ሸፋፋ፣ የግብርና የቀረጥ አተማመን ደንባችን ሸውራራ፣ መሪዎቻችን የአእምሮ መካኖች፣ አንዳችን ለአንዳችን ያለን አመለካከት ሸፋፋ፣… በአሁኑ ወቅት ምን ያልተንሻፈፈ ነገር አለን? በመጪው ዘመን ስንቱን ሸፋፋ አቃንተን እንደምንዘልቀው ፈጣሪ ይወቅ፡፡)

ወደጥንተ ነገራችን እንመለስ፡፡

ባጭር ባጭሩ ልንገራችሁ፡፡ ዘመናዊ ባርነት በኢትዮጵያ ነግሦኣል፡፡ እንዲህ ስላችሁ ባለፈው ጦማሬ እንደገለጸኩት ብዙዎቻችን የምንጠበስበትን የኑሮ ውጣ ውረድና የፖለቲካ እመቃ ማለቴ አይደለም፡፡ ከዚያም የከፋ የለዬለት ዘመናዊ ባርነት አለላችሁ፡፡(በነገራችን ላይ ባለፈው ጽሑፌ የአንድ ኪሎ ብርቱካን ዋጋ 22 ብር ገደማ ያልኳችሁ በጣም ተሳስቻለሁ – 45 ብር ገብቷል አሉ፤ ልብ አድርግ የአንድ ኪሎ ብርቱካን በችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ 45 ብር ብቻ! ጉድ በል ጎንደር ማለት አሁን ነው፡፡)

ሚሚ ስባሃቱን የማያውቅ መቼም አይኖርም፡፡ የማታውቋት ካላችሁ – በቪኦኤ የአማርኛው ክፍል ትሠራ የነበረች፤ ከዚያ ተባርራ ይሁን በራሷ ፈቃድ ወጥታ ወደኢትዮጵያ የገባችና በርሷና በባሏ ስም የመነሻ ፊደላት “ዛሚ” ተብሎ በሚጠራ የኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ በአብዛኛው ወያኔን እያገለገለች የምትገኝ “ጋዜጠኛ” ናት – አንዳንድ ማኅበራዊ ችግሮችን ማንሳቷንም አልክድም፤ ይህንን በጎ ሥራዋን በአወንታዊነት አደንቃለሁ፡፡ … አዜብ መስፍን የምትባለዋን ጉድ ደግሞ የማያውቅ ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡ እንደድንገት የማያውቅ ቢኖር አዜብ መስፍን ወይም አዜብ ጎላ ማለት የቀድሞውንና የዐፅመ-ዕድሜ ልክ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ የብዙዎች ሚስት እንደነበረችና እንደሆነች በብዛት የምትታማና – የአሁን ሁኔታዋን እንጃላት እንጂ – ወንዶችን ብቻ ሣይሆን ንግዱንና የንግዱን ማኅበረሰብ በሞላ እንደፈለገች የምታተረማምስ ሦስተኛዋ ዮዲት ጉዲት እንደሆነች የሚነገርላት ልዩ እስፊንክስ(Sphinx) ናት – ወደመጀመሪያዋ ዮዲት መሄድ ሳያስፈልገን ከሌላኛዋ መበለት ከገነት ዘውዴ ቀጥላ መሆኑ ነው ሦስተኝነቷ፤ ( እንዳለመታደል ሆኖብኝ አንዳንዴ ፈታ ብሎ መናገር ደስ ስለሚለኝ እንጂ ስለዚች ሴትዮ የግል ጠባይ እዚህ መናገሬ ስህተት መሆኑን ዐውቃለሁ፤ ሂሴን ውጫለሁ፡፡) እነዚህ ሁለቱ አዜብና ሚሚ የሚሰኙ ጉዶችና ሌሎች እነሱን የተከተሉ ጥቂት የማይባሉ ባሪያ ፈንጋዮች በሀገራችን የሚሠሩት ተዓምር ልዩ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የዛሬ አሥራ ሦስት ዓመት ገደማ በአንድ ታዋቂ የግል ጋዜጣ አንድ መጣጥፍ ማውጣቴ ትዝ ይለኛል – ሰሚ ግን አልተገኘም፡፡ መጯጯኽ እንጂ መደማመጥ ብሎ ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ጭራሽ የለም፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የነሚሚና አዜብም ሆነ የሌሎቹ በሥራ አስቀጣሪነት ፈቃድ አውጥተው በሕዝብ የሚነግዱ ድርጅቶች ሠራተኞችን “ሥራ እናስቀጥራችኋለን” በሚል በየሙያ ዘርፉ ይመዘግባሉ፤ ይመለምላሉ፡፡ የተወሰነ የአጭር ጊዜ ሥልጠናም ሳይሰጡ አይቀሩም፡፡ በተለይ የጽዳትና የጥበቃ ሠራተኞችን፣ የጉልበት ሥራና መሰል አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞችን የሚፈልጉ መሥሪያ ቤቶች ወደነዚህ ባሪያ ፈንጋዮች ዘንድ በመሄድ የሚፈልጉትን የሠራተኛ ዓይነት እንደፍላጎታቸው መርጠው ይወስዳሉ፡፡ ቀጣሪዎች፣ ደሞዝ ከፋዮች፣ አስጠንቃቂዎች፣ ከሥራ አሰናባቾች፣ … እነዚሁ አስቀጣሪ ድርጅቶች ናቸው፡፡ ሰዎቹን ወስዶ የሚያሠራቸው ድርጅት ግንኙነቱ ከ“ባሪያዎቹ” ጋር ሣይሆን ከአስቀጣዎቹ ድርጅቶች ጋር ነው፡፡ ይህ ዘመናዊ የባሪያ ፍንገላ አሠራር በሀገር ውስጥ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ መንግሥት የፈቀደላቸው የሚባሉ ወደውጪ ሀገራት በተለይም ወደዐረቡ ዓለም የቤትና የጉልበት ሠራተኞችን የሚልኩ አሉ፡፡ የሚያስከፍሉት ገንዘብ አንጀትን ይመዘምዛል አሉ፡፡ የነሱን የመጓጓዣና የደላላ ወጪ ለመክፈል የሚፈጀው ጊዜ የወላጅንና የተደጓሚ ቤተሰብን አንጀት በርሀብ ያነጥፋል፡፡ በዚያ ላይ አንዴ ከላኳቸው በኋላ ቢቀቀሉ ቢገነተሩ መብታቸውን ለማስከበር ዘወር ብለው አያዩዋቸውም ይባላል፡፡ አበሻ እንዲህ ሆዳምና ጨካኝ የሆንነው ግን ከመቼ ጀምሮ ይሆን እባካችሁ? የነሚሚ ጦስ ድንበር ዘለል ነው፡፡ ገንዘብ ባለበት ወያኔ አለ፡፡ ንግድ ባለበት – እዚህ በተጨባጭ እንደምናየው ሰውም ይሸጥ መሬትና ተንቀሣቃሽ ንብረትም ይሸጥ – ወያኔና የሙስና እናት የምትባለዋ አዜብ አይጠፉም፡፡ ይቺ የመርገም ፍሬ ሴትማ የጉልት ሴቶችን ሳይቀር በሽርክና አስገቡኝ ከማለት አትመለስም ይባላል – ፈጣሪን ምን ብንበድለው ይሆን ግን ለዚህ ለወሬ እንኳን ለማይመች መከራና ስቃይ የዳረገን? ይህችን ሴት ባሰብኩ ቁጥር አንዳርጋቸው ጽጌ(አንዱ) የተናገራት cringe የምትል ቃል ትዝ ትለኛለች፤ አዎ፣ ምን የመሰለ ድንቅ ታሪክ ያለን ሕዝብ ይቺን በመሰለች ሴት ስንታመስ በርግጥም መሸማቀቅ ሲያንሰን ነው፡፡ ለማንኛውም በነዚህ ሴቶችና ተባባሪዎቻቸው መሬት መሸከም የሚከብዳት ግዙፍ ግፍና በደል እየተፈጸመ ነው፡፡ ከፍ ሲል የጠቀስኩላችሁ የሀገር ውስጥ ባሪያ ፍንገላ የደመወዝና የጥቅማጥቅም ነገር ሲነሳ ነው ግፉ ቁልጭ ብሎ የሚታየን፡፡ በጥቂቱ እንየው፡-

እኔን የቀጠረኝ የግል ድርጅት ከነዚሁ የድሃን ደም መጣጮች ነው የጽዳትና የጥበቃ ሠራተኞቹን የተኮናተረው፡፡ እነዚህ ምሥኪን ሠራተኞች ደሞዛቸውን የሚያገኙት ከኛ ድርጅት ሣይሆን ከቀጠራቸው አስቀጣሪ ድርጅት ከነሚሚ ወይም ከነአዜብና መሰሎቻቸው ነው – አንዳች ሳይለፉ በድሃው ጉልበት የማይነጥፍ የነዳጅ ጉድጓድ የቆፈሩ ዘራፊዎች፡፡ የኔ መሥሪያ ቤት ለአንድ ጥበቃ ብር 1100(አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር) ለቀጣሪ-አስቀጣሪው ድርጅት ይከፍላል፡፡ አስቀጣው ድርጅት ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ግማሹን ለሥራ ማስኬጃ ይቀነድብለትና ግማሹን ብር 550 ለሠራተኛው በየወሩ ይከፍለዋል – በመረጃ የተደገፈ ወሬ ነው የምነግርህ፡፡ ይህ ሠራተኛ የኛ ድርጅት ቋሚ ቅጥር ቢሆን ኖሮ አንደኛ ደሞዙ ከዚህ አሁን ከሚከፈለው ሻል ሊል ይችል ነበር – የኛ ድርጅት ጭንቅላት የለውም እንጂ ቢኖረው ኖሮ ማለቴ ነው፡፡ ሁለተኛ የሕክምና ዋስትና ይኖረው ነበር፡፡ ሦስተኛ የጡረታ ዋስትና(Provident Fund) ይቆረጥለት ነበር፡፡ አራተኛ የሥራ ዋስትናው አሁን ካለበት ሁኔታ በጣም የተሻለ ይሆንለት ነበር(አሁን እንደ ዕቃ ነው፤መናገር፣ ማጉረምረም፣ መውቀስ፣ ምናምኒት አይችልም – ወዲያውኑ ይባረራል፡፡) እኛ ቢያንስ በግል ስንገናኝ የማጉረምረም መብታችን የተጠበቀ ነው፡፡ እነዚህ በወር 550 ብር የሚከፈላቸው የጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች ባለፈው ጦማሬ የገለጽኩላችሁን የአዲስ አበባ የኑሮ ውድነት እንዴት ሊቋቋሙት እንደሚችሉ እንግዲህ አስቡት፡፡ የዱሮ ባሪያ ደረጃውን የጠበቀ አይሆን እንደሆነ እንጂ ቢያንስ በሕይወት ሊያኖረውና ሥራውን በአግባቡ እንዲሠራ ሊያደርገው የሚችል ምግብ ይሰጠው ነበር፡፡ የዘመናዊ ባርነት ሰለባዎች ግን የላባቸውን ውጤት የሚበላው ሌላ በመሆኑ ለትራንስፖርትም በማይበቃ ገንዘብ ጉልበታቸው ይበዘበዛል፤ ሥራ አላቸው እንዲባሉ ግን ውለው ይገባሉ፡፡ እነዚህ አስቀጣሪ ድርጅቶች በመያዶችና በዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ያስቀጥራሉ፡፡ ከዚያም አካባቢ እንደሰማሁት ባሪያ ፈንጋዮቹ በብዙ ሺዎች ይቀበሉና ለሁለተኛ ዙር ተቀጣሪው ሠራተኛ የሚያቀምሱት በቡና ሥኒ ነው አሉ፡፡ ሰው ሌላ አማራጭ ስለሚያጣ በግዱ ወደነዚህ ድርጅቶች ይሄዳል፡፡ ወደ አሠሪዎቹ ድርጅቶች ሄዶ መቀጠር እንዳይችል እነዚህ የኔን ቀጣሪ ድርጅት መሰል ድርጅቶች ኃላፊነትን ይሸሻሉ፡፡ ከሠራተኛ ቁጥጥር፣ ከጥቅማጥቅም፣ ከሠራተኛና አሠሪ የክስ ውጣ ውረድና ከመሳሰለው የተገላገሉ እየመሰላቸው በእጅ አዙር የሰውን ጉልበት ይበዘብዛሉ፡፡ ግፍ በየዓይነቱ የሚናኝባት ብርቅዬ ሀገር አለችን፡፡

መፍትሔው ምን ይሁን ትላላችሁ? መፍትሔው እንደኔ የአስተሳሰብ ለውጥ ነው፡፡ የወያኔ ዓይነቱ ትውልድን አምካኝ የትምህርት ሥርዓት ሣይሆን ሥጋንና ነፍስን የሚያስታርቅ መንፈሣዊና ዓለማዊ ትምህርት ያስፈልገናል፡፡ በኢትዮጵያችን የሞራል ዕሤቶች ታጥበው ገድል ከገቡ በኋላ ይመስለኛል ይህ ዓይነቱ የጅብ ባሕርይ ወደ ሰዎች የተጋባው፡፡ እንጂ አምስት መቶ ብር ለውሻው የወር ባጀት እንደማይሆን የሚረዳ አንድ ሀብታም “ኢትዮጵያዊ” ዜጋ እንዴት አንድ መሰል ዜጋውን በዚህ ደሞዝ ያሠራል? ምን ዓይነት ደደብነት ነው? በተዘዋዋሪ ቀጥሮ የሚያሠራቸው ድርጅትስ ቢሆን ምናለበት ይህን ችግር ተገንዝቦ ራሱ በቀጥታ ቢቀጥራቸውና ያን አላግባብ የሚመዘበር ገንዘብ ለነሱ ቢያደርገው? ምን ዓይነት ሁልአቀፍ የሆነ የአስተሳሰብ ስንኩልነት ነው እየታዘብን የምንገኘው? አእምሮ ወዴት ገባ? ወዴት ሸፍቶ ይሆን? እዚች ላይ ትንሽ እንጸልይ መሰለኝ፡-“ አቤቱ የሰማዩ አባታችን እግዚአብሔር ሆይ፣ በሞራ የተሸፈነ ኅሊናችንን ግለጥልንና እውነቱን እንድናይ አድርገን! ለሰዎችም እንድናዝን የርህራሄና የመተሳሰብን መንፈስ በላያችን አሳድርልን፡፡ ለይቶልን ሳንጠፋ ጭል ጭል በምትለዋ እስትንፋሳችን ላይ ሞልቶ ከሚፈሰው የማያልቅ ቸርነትህ ላክልንና ወደየልቦናችን ተመልሰን እንድንተዛዘን፣ እንድንፈቃቀድም አድርገን፡፡ ጨርሰን ሳንጠፋብህ በመሀከላችን ገብተው የሚያበጣብጡንን የፍቅረ ንዋይና የአምልኮተ ንዋይን መንፈስ፣ የዘረኝነትና የሙስናን ደዌያት አስወግድልን፡፡ አሜን፡፡”

ችግርን ከማውራት የምገላገልበትን ጊዜ በጣም ናፍቄያለሁ፡፡ ሁልጊዜ ስለችግር ስለማወራ ራሴኑ ጭምር እንደችግር ማየት ከጀመርኩ ቆይቻለሁ፡፡ ከዚህ ቅኝት ለመውጣት ወደፊት ትልቅ ትግል ሳይጠብቀኝ አይቀርም፡፡

ወደ ሌላ ችግር፡፡ ሰሞኑን የወያኔው መንግሥት 37ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በዕጣ ማከፋፈሉ ይታወሳል፡፡ ዕጣ አወጣጡ ራሱ ችግር እንዳለበት ሰምቻለሁ፡፡ እመለስበታለሁ፡፡

ዕጣ ያልወጣላቸው ሰዎች “እንኳንስ ዕጣ አልደረሰኝ!” እያሉ የሚደሰቱበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ምክንያቱም አስቀድሞ የሚከፈለው ገንዘብ ከየት መጥቶ ይከፈል? ዕጣ የደረሳቸው አንዳንድ ጓደኞቼ “ምን ቅብጥ አድርጎኝ ነው የተመዘገብኩት”እያሉ ሲያማርሩ ታዝቤያለሁ፡፡ ምዝገባው የተካሄደው ቀደም ሲል ነው፡፡ ሰው ደግሞ ሲመዘገብ አንዳንዱ ለደራ ነው – ዕድሉን ለማየት፡፡ አንዳንዱ – እንዲያውም ብዙው ከመኖሪያ ቤት ችግሩ አንጻር ነው፡፡ አንዳንዱ ለትርፍ ነው – ቤት እያለው ግን ኮንዶምንየሙን ሸጦ ትርፍ ለማግኘት፡፡ አቤት የመጥፎ ጠባያችን አበዛዙ! ስንትና ስንት ሌላ አማራጭ እያለው ለዚች የአንድና የሁለት ክፍል ጎጆ ከድሃው ጋር ሙሉ ቀን ተሠልፎ የድሃውን ዕድል የሚያሰነካክል ሀብታም ታያለህ፡፡ በሚስቱም በልጁም በዘመዱም ስም ብዙ ቤት እያለው ለዚች ትንሽዬ ነገር የድሆችን ዕድል ሲያጨነግፍ የምታየው ገብጋባ ሰው አለ፡፡ ብዙ ችግር እኮ ነው ጓዙን ጠቅልሎ ወደሀገራችን የገባው፡፡ ለሰው ደግ መመኘትና “ይህ ለኔ በቂ ነው፤ ይህም የሌላቸው አሉና ለነሱ ይሁን” ብሎ ማሰብ ቀርቷል፡፡ እናላችሁ አዳሜ ዕድሏን ለመፈተንና “ከዚህ ወይ ከዚያ በማገኘው ገንዘብ አሟልቼ ቅድሚያ ክፍያውን እከፍላለሁ፣ ከዚያም እኔ በአነስተኛ ገንዘብ እከራይና ቤቱን በትልቅ ዋጋ አከራይቼ ወይ ሸጬ በማገኘው ትርፍ ዕዳየን በቶሎ አጠናቅቃለሁ” ብላ አስባ ስታበቃ አሁን ዕጣው ሲወጣላት ጊዜ ምኑን ከምን ታ’ርገው? ለምሳሌ በምዝገባው ወቅት 60ሺህ ብር ገደማ ተብሎ የተነገረው የባለ ሁለት መኝታ ቤት ኮንዶምንየም የቅድሚያ ክፍያ አሁን በወቅቱ የገንዘብ ምንዛሬ ተሻሽሎ ከ80ሺህ ብር በላይ ሆኗል፡፡ አንዱ ጓደኛየ የዚሁ ቤት ዕጣ ደርሶት ዕጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የሌት እንቅልፉንና የቀን ሰላሙን አጥቷል፡፡ የርሱ ደሞዝ ከዕለታዊ መጠነኛ ኑሮ አያልፍም፡፡ በዕቁብም ሆነ ወደፊት የሚከፈል ተብሎ በብድር መልክ ከሰው ማግኘት የሚታሰብ አይደለም – ከመነሻው ድሃን አምኖ የሚያበድረውም የለም፡፡ ብድርና ቁጠባ ቢል ያጠራቀመው በጣም ጥቂት ነው፡፡ ፒኤፍ ቢጠይቅ እሺ አልተባለም – ቢፈቀድለት እንኳን አይሞላለትም፡፡ ሥራውን ለቅቆ ፒኤፉን እንዳይወስድ በዛሬ ጊዜ በመከራ የሚገኝና በዘመድ አዝማድ በተቆላለፈ ማኅበረሰብ ውስጥ ሌላ ሥራ መፈለጉ መድሓኒት የሌለው ትልቅ ራስ ምታት ነው፡፡ እናም እንዲሁ እየዋተተ አለ፡፡ በዚህ ሁኔታ የሚቸገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህ አጋጣሚ ደስታ ሀዘንን ሲወልድ ያየሁበት ልዩ አጋጣሚ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ይህን የኮንዶምንየም ቅድሚያ ክፍያ በሴከንድ ውስጥ የሚከፍሉ ግን ባለአነስተኛ ደሞዝተኞች አሉ፡፡ እነዚህም የሙስናው ሞተር አሽከርካሪዎችና ልየ ልየ የጎን ገቢ ያላቸው ናቸው፡፡ ሙስና ካለ እንኳንስ ኮንዶምኒየም ኦሮጵላንም ይገዛል፡፡ ይብላኝ ዙሪያ ገባው ለጨለመበት ተራው የመንግሥትና የግል ድርጅቶች ሠራተኛ! ይብላኝ በረንዳዎችን ሙጥኝ ብሎ ለሚገኘው በመቶ ሺዎች ለሚገመተው ዜጋ፡፡ ስለወቅቱ የሥራ አያያዝ ሁኔታ ግን ትንሽ ላውራችሁ፡፡

በዛሬ ጊዜ ይገርማችኋል ወርቅ የሆነ የሥራ ችሎታና ወርቅ የሆነ ጠባይ ቢኖርህ ሰው የሚቀጥርህ ዘርህን ጠይቆ ነው፡፡ የሀገራችን ሠራተኛ ያሣዝናችኋል፡፡ በየጠላና አረቂ ቤቱ ስዘዋወር የምሰማው የዘረኝነት መዘዝ የፈጠረው ብልሹ አሠራር ዕበድ ዕበድ ነው የሚለኝ፡፡ ምን የመሰለ የግምበኝነትና የአናፂነት ሙያ እያለው ትግሬ ወይም ኦሮሞ ባለመሆኑ ብቻ የሚቀጥረው አጥቶ ሲንቀዋለልና በየቁንድፍት ቤቱ ጉበቱን ሲያቃጥል የሚውለውንና የሚያመሸውን ዜጋ በቤቱ ይቁጠረው ብቻ የምንተወው ሣይሆን እኔም ያቅሜን ተዘዋውሬ ተመልክቻለሁና እስክሞት የማይረሳኝ ዕድሉ ከገጠመኝም ምሥክርነቴን በኃያሉ አምላክ ፊት ሣይቀር የምሰጥለት የሀገራችን የወቅቱ ነቀርሣ ነው፡፡ ከዘበኝነት አቅም ዘርህና ጎጥህ ተቆጥሮና ማንነትህ ተጠንቶ ነው የምትቀጠረው – በር እየከፈተ መኪናን ማስወጣትና ማስገባትም ከቁም ነገር ተጥፎ እንዲህ ያለ መድሎ ይታያል፡፡

በዕጣው አወጣጥ ችግሮች እንደነበሩበትም ይነገራል፡፡ ወያኔ ለማስመሰል ድራማው በዕጣው ቤት ይደርሳቸዋል ተብለው ከማይጠበቁ ዜጎች ከዚህም ከዚያም ለአንዳንዶች ጣል ጣል አደረገ እንጂ የአንበሳ ድርሻውን ለራሱ ካድሬዎችና ለሚፈልጋቸው ወገኖች በዕጣ አስመስሎ እንደሸለማቸው በስፋት ይወራል፡፡ ለምሳሌ በአንድ መሥሪያ ቤት ለብዙ የሥራ ሂደት ባለቤቶችና የፖለቲካ ሠራተኞች እንደደረሰና ያን የመሰለ አጋጣሚ እንዴት በዕጣ ሊወጣ እንደቻለ መነጋገሪያ እንደሆነ ከቅርብ ሰው ተረድቻለሁ፡፡ ለነገሩ በህዳሴው ግድብ ሥራ ማስጀመሪያ የመጀመሪያዋ ዕለት እንደተወለደና ስሙም ህዳሴ ለተባለ ሕጻን የህዳሴው የስልክ ሎተሪ ዕጣ የመኪና ሽልማት እንደደረሰ በሚነገርባት ሀገር፣ አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ ወጣት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቷ ባሳየችው የበጎ አድራጎት ሥራ የተመሰጡት ትምህርት ቤቷና ሌላ ድርጅት በጋራ ሆነው የኢትዮጵያን ዓመታዊ አጠቃላይ በጀት ሊሆን የሚዳዳው የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደተቀበለችና ያንንም ገንዘብ – ድምቡሎ ሣታስቀር(እንዴት ያለ ቱጃር ቤተሰብ ነው ያላት ጃል!) ለትምህርት ቤት ግምባታ ልታውለው ለመንግሥት እንዳበረከተች በሚነገርባት የወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ዕጣ ሸር የለበትም ብሎ መቀበል ከየዋህነትም የዘለለ ሞኝነት ነው፡፡

በመጨረሻም አስቀድሜ እንደጠቆምኩት ትዝናኑበት ዘንድ አንድ ወንድም ከቦስተን ማሳሹተስ የላከልኝን ኢሜይል እንዳለ በኮፒ/ፔስት ከሥር አስቀምጣለሁ፡፡ “ያልተነካ ግልግል ያውቃል” ይባላል፡፡ እኔ በመምህር የሚታረም የፈጠራ ድርሰት የጻፍኩ ይመስል ስለ አጻጻፍ ሥልቴ አይረቤነት ያወራል፡፡ ችግራችንን ዘረዘርኩ እንጂ ሥነ ጽሑፍ አልጻፍኩም፡፡ ችግርን ለመናገር ደግሞ አንድ ሰው በልምድም ይሁን በትምህርት የሚያውቀው (አነስተኛም ቢሆን) የንግግርና የጽሑፍ ችሎታ በቂው ነው – መራቀቅና ተቺየ እንደሚለው coherence, cohesive device ቅብጥርስ እንዲያውቅ አይጠበቅበትም፡፡

Comment

 

The post ዘመናዊ ባሪያ ፍንገላ በኢትዮጵያ (ነፃነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ) appeared first on Zehabesha Amharic.

(የሳኡዲ ጉዳይ) “በሁቲ አማጽያን ላይ የተጀመረው ጥቃት አያቆምም!”–የሳውዲው ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ

$
0
0

saudi 1

saudi

የመረጃ ግብአት ( Update )

“በሁቲ አማጽያን ላይ የተጀመረው ጥቃት አያቆምም! ”
የሳውዲው ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ
==============================

* የአረብ ሊግ ሀገራት መራሄ መንግስታት በየመን ጉዳይ ለመመከር ግብጽ ሻርማ ሸክ ተሰብስበዋል ።

* የዘመቻው መሪ ሀገር የሳውዲ ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ ” የመን እስክትረጋጋ በሁቲ አማጽያን ላይ የተጀመረው ጥቃት አያቆምም! ” ሲሉ በመክፈቻ ንግግራቸው አስታውቀዋል ።

* ከሳውዲው ንጉስ ሰልማን በተጨማሪ የየመን ተገፊ መሪ አብድረቡ መንሱር አለሃዲና የተለያዩ አረብ ሀገራት መሪዎች ንግግር በማድረግ ላይ ናቸው !

*** **** ***
“ዘመቻ ማዕበል ” የ3ኛው ቀን አበይት ክንውኖች …
==============================
*በሳውዲ የተመራው የህብረት ጦር በሁቱ አማጽያን እጅ በሰንአ እና በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኘውን የብላስቲክ ሚሳየል ክምችት ballistic missile stockpile ማውደሙን አል አረቢያ ዘግቦታል

* ከየመን ሰንአ የህብረቱ የአየር ኃይል ጦር የደቡብ ከተማዋ በዳሊያ ባደረገው ወታደራዊ ይዞታዎች ኢላማ ያደረገ ድብደባ የሁቲ አማጽያን ጸረ አውሮፕላን በመተኮስ መልስ መስጠታቸውም ተጠቁሟል

* በሳውዲ ባህር ኃይል ሁለት የጦር መርከቦችና ኮማንዶዎችና አየር ኃይልና በልዩ ኮማንዶዎች በታገዘ ዘመቻ 86 የሳውዲ እና የምዕራባውያን ሀገር ዲፕሎማቶች ከወደብ ከተማዋ ከየመን ሁለተኛ ከተማ ከኤደን በተሳካ ዘመቻ መውጣታቸው ተጠቁሟል

* ዛሬ ማለዳ ሰንአ ውስጥ የሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ሰራተኞችን ከሰንአ ለማስዎጣት የሳውዲው መከላከያ ሚኒስትር ሶስት አውሮፕላን መላካቸው ተዘግቧል ። የመንግስታቱ ድርጅት ሰራተኞቹን ለማሰረዎጣት ነጻ የአየር ክልል እንዲሰጥና ከሰንአ ወደ ኢትዮጵያ ለሚደረገው ማሸጋገር ትብብርን ከሁቲ አማጽያን ያቀረበው 140 ሰራተኞች እንዳይንቀሳቀሱ ጋሬጣ ባይጠፋኝ ጥያቄው ተቀባይነት ማግኘቱ ተነግሯል

* በአሜሪካ የሳውዲ አምባሳደር አድል አል ጃብሪ ኢራንና ሂዝቦላህ የሁቲ አማጽያንን ከጀርባ ሆነው እንደሚረዷቸው ከ CNN ጋር ባደረጉት ውይይት አስታውቀዋል

( ከዘመቻው ጋር በተያያዘ ፣ ጅዳ ውስጥ በትልቁ የአየር ማረፊያ ፕሮጀክቶች በህጋዊ መንገድ ይሰሩ ከነበሩት የመናውያን ጋር ኢትዮጵያውያንም “ለደህንነት” በተባለ ምክንያት ወደ አየር ማረፊያው ስራ ፕሮጀክት እንዳይገቡ መከልከላቸውን መረጃ ደርሶኛል )

እስኪ ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 19 2007 ዓም

The post (የሳኡዲ ጉዳይ) “በሁቲ አማጽያን ላይ የተጀመረው ጥቃት አያቆምም!” – የሳውዲው ንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፖለቲካ፣ ሐይማኖት፣ ዘር፣ በሰው ልቦና ውስጥ።

$
0
0

Ketemaፖለቲካ እና ፖለቲከኞችን ስንመለከት ባላደጉ አገሮች ለፖለቲካ ፍጆታቸው ሐይማኖትን እና ዘርን መጠቀሚያ ያደርጋሉ። የወያኔ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማሳያው መንገዱ  ሐይማኖትና ዘርን ለርካሽ ስራው ወደ ሜዳው ያስገባቸዋል። እንደዚህ አይነቱ የፖለቲካ አካሄድ ከአጥፍቶ ጠፊ ቡድን ተለይቶ አይታይም። ሰው የተባለው ክቡር ፍጥረትን በሃይልና በማይፈልገው መንገድ በግድ  ፖለቲካዊ እውቀት ሳይኖራቸው ወደ ሜዳው ማስገባት የወያኔ ስልት ነው። የቀድሞ የወያኔ መሪ የነበሩት እንዲ ብለው ነበረ << ምርጥ ኢሕአዴግ ሁኑ ካልሆናችሁ በናንተ ላይ ሌላ ምርጥ ኢሕአዴግ እሾማለው>> ብለው እንደተናገሩት የሜዳ ውስጥ ጨዋታ ይሄ ነው። ወይ መሆን …አልያም ባንተ ላይ ሌላ መሾም። የትኛውም ሐይማኖት ተከታይ ሁን የትኛውም ዘር ሁን ወደ ሜዳው እንድትገባ ይደረጋል ከምርጥ ውስጥ የሆነ በሜዳው ይቆያል ከምርጥ ውስጥ ያልሆነ ደግሞ ይባረራል።

በስፖርቱ አለም ወደ ሜዳው የሚገቡት ሰውነታቸው  የዳበረ  እና በቂ ችሎታ ያላቸው ናቸው። በተለያየ ግዜ የተለያየ ግጥሚያ ካደረጉ በኋላ በልጦ የሰራ እና በቂ ችሎታ ያለው አሸንፎ ደጋፊውን አስጨብጭቦ የተዘጋጀለትን ዋንጫ እና የተለያዩ ሽልማቶችን ይወስዳል። ባደጉት አገሮች ልክ እንደ ስፖርቱ  ተመሳሳይ ነው። ጠንክሮ የሰራ እና ጥሩ የፖለቲካ ብቃት ያለው አሸንፎ የበላይነትን ያገኛል። የኛ አገር ግን እንደዚህ አይደለም። የአገራችን ፖለቲካ ሐይማኖትና ዘርን ወደ ሜዳው በጥቅም ተብትቦ እና  አስገድዶ  አስገብቷል። ገዢ  የተባለው አካል የራሱ ሜዳ ውስጥ ተገዢ የተባሉ ቡድኖችን ሁሉ በግድም ወይም በማግባባት አልያም በጥቅም እንዲገቡ ተደርጓል። ወደሜዳው የገቡት የፖለቲካ እውቀት፣ የሐይማኖት እውቀት፣ ስለዘር እውቀት የሌላቸውን ባልዳበረ  ችሎታ  ወያኔ ወዳዘጋጀው ሜዳ ገብተው መገኘቱ አደገኛነቱን መናገር አይከብድም። ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ግጥሚያ የሚያስከፍለው መሰዋትነት እንደ ስፖርቱ ላብ ሳይሆን ደምን መሆኑ ከባድ ያደርገዋል። እስቲ በጥቂቱ ስለ ሐይማኖት እና ዘር እንመልከት።

ሐይማኖት፡-

ሐይማኖት ማለት የማይታየውን እግዚአብሔር እንደ  አዩት አድርጎ ማመን ነው። እግዚአብሔር የማያዳላ  ፈራጅ እና ታማኝ አምላክ ነው። አለማትን ፈጥሮ በውስጣቸው የሚኖሩትን በእኩል የሚያስተዳድር ድንቅ አምላክ ነው። ለደጉም ለክፉውም፣ ለጻድቁም ለሃጣኑም፣ ለሚያምነውም ለማያምነውም፣ ለትልቁም ለትንሹም፣ የአምላክነቱን ጸጋ ለሁሉም ሳያዳላ እኩል  ይሰጣል። እግዚአብሔር ፀሐይን ስሙን ለሚጠራውም ለማይጠራውም እኩል ያወጣል፣ እግዚአብሔርን ለሚያምኑም ሰይጣንንም ለሚያምኑ እኩል ዝናብ ያዘንባል፣ የአየር ስጦታንም ለሰውም ለእንስሳም እኩል ይሰጣል፣ እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ እንደሆነ እንረዳለን። ደግ ብቻ ይኑር ክፉው ይጥፋ፣ የሚያምነኝ ብቻ ይቅር ሌላይ ይሙት፣ የሚል ህግ በእግዚአብሔር ዘንድ የለም። እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ የሚችል ሆኖ ሳለ የማንንም እገዛ የማይፈልግ ሆኖ ሳለ በተፈቀደልን እድሜ በነጻነት እንድንኖር ፈቅዶልናል። ውሃም እሳትም ተቀምጦልሃል እጅህን ወደፈለገው  ክተት ብሎ ለሰው ልጆች የነጻ ምርጫ አስቀምቷል።

ውሃ ማለት፡- እምነትና ስራን አዋህደህ መገኘት ሲሆን እንዲህ ይገለጻሉ። ደግነት፣ የዋህነት፣ ፍቅር፣ ራስን መግዛት፣ ታዛዝነት፣ ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ መውደድ። እነዚህ የሰራ መልካም ሰው በማታልፈዋ አለም በደስታ የሚያኖሩ ሲሆን…

እሳት የተባለው ደግሞ ጥል፣ ክርክር፣ መለያየት፣ አድመኝነት፣ ቁጣ፣ ክፋት፣ መግደል፣ ባልንጀራህን አለመውደድ የመሳሰሉት በዚህም አለም በማታልፈውም አለም ደስታን የማናገኝበት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በሐይማኖት ያለን አመለካከት ከፍተኛ ነው። በክርስትናውም በእስላሙም ሐይማኖታቸውም የሚወዱ ያሉባት ህዝብ ናት። ታዲያ ሐይማኖቱን የሚያከብር ማን ነው? እውነት በመናገር በፍቅር በማኖር የእግዚአብሔርን መንግስት እንዲወርሱ ከማድረግ ይልቅ ጥላቻንና ክፋትን እያስተማርን ለሌላው መጥፋትን የምንመኝ ስንቶቻችን ነን? በሐይማኖታችን የሚፈቀደው የታመመን በጸሎት ማዳን፣ የተጣላን ማስታረቅ፣ የተራራቀን ማቀራረብ፣ ስለሰው ሐጥያት መናገር ሳይሆን ስለራስህ ሐጥያት ማሰብ፣ ሰውን ከክፉ ስራው ወደ በጎነት መመለስ እንጂ ውድቀቱንና ጥፋቱን መመኘት በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ የለውም።  ሰው ሆይ እግዚአብሔር ዋጋ ከፋይ ነው። መልካም የሰራ ገነትን ክፉም የሰራ ሲኦልን የሚያስገባ በነፍስም በስጋ ላይ ስልጣን ያለው እግዚአብሔር ስለሆነ በሰራነው ስራ ዋጋችንን ለመቀበል ተዘጋጅተናል ማለት ነው። ዋጋም ከፋዩ እግዚአብሔር ነው።

ዘር፡-

የሰው ዘር በሙሉ ከአዳም እና ከሄዋን እንደተገኘ በሁሉም በተ እምነት አስተምሮ ውስጥ እንዳለ የታወቀ ነው። ይህም እስከ ጥፋት ውሃ ድረስ ማለትም እስከ ኖህ ዘመን ድረስ ከቆየ በኋላ የሰው ልጅ በሰራው ክፋት እግዚአብሔር ተቆጥቶ ከምድር የሚፈልቅ ውያ ከሰማይ የማያባራ  ዝናብ  ምድርን አጥለቅልቆ በውስጧ ያሉትን በሙሉ በሐጥያታቸው ምክንያት ሲጠፉ መልካሙ ሰው የነበረው ኖህና ቤተሰቡ ከእንስሳቱ ሁለት ሁሉት አድርጎ በኖህ መርከብ ከእግዚአብሔር ቁጣ ከመጣው የጥፋት ውሃ በመትረፋቸው የሰው ዘር ሊቀጥል ችሏል። የኖህ ልጆችም ሴም፣ ካምና፣ ያፌት ይባላሉ። ዘፍጥረት 10+1-32

ሴም፡- ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሎድ፣ አራም፣ ቃይናን ስድስት ልጆችን ወለደ።

ካም- ኩሽ፣ ምስራይም፣ ፍጥ፣ ከነዓን አራት ልጆችን ወለደ።

ያፌት፡- ጋሜል፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያህያን፣ ያልሳ፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስ ስምንት ልጆችን ወለደ።

እነዚህ የኖህ ልጆች አሁን ላለው የዘር  መጠሪያ መሰረቶች ናቸው።

በሴም፡- ሴሜቲክስ የተባሉ የኖህ ልጅ ብዙ የምድራችን ግዛትን ላይ በመስፈር መጠሪያ የያዘ የአዳም ዘር ሊጠራበት ችሏል።

በኩሽ፡- ኩሸቲክስ የተባሉ የኖህ የልጅ ልጅ ብዙ የምድራችን ግዛትን ላይ በመስፈር መጠሪያ የያዘ የአዳም ዘር ሊጠራበት ችሏል።

በያፌት፡- ያፌታውያን የተባሉ የኖህ ልጅ ብዙ የምድራችን ግዛትን ላይ በመስፈር መጠሪያ የያዘ  የአዳም ዘር ሊጠራበት ችሏል።

እንዲህ እንዲ እያለ  የሰው ልጅ በሙሉ መጠሪያውን እያበጀ ሊመጣ ችሏል። ወደ ኋላ ከተጓዝን ሁሉም  የኖህ ልጆች ናቸው። ወደ መጀመሪያው ከተመለስን ደግሞ ሁሉም የአዳም ዘር መሆናቸውን እናውቃለን። ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰማኒያ ሁለት ያላነሱ ቋንቋዎች ይነገራል። ሁሉም ቋንቋዎች ግን ገላጪነታቸው እኩል ነው። ቋንቋ ያስፈለገበት ዋናው ቁም ነገር ሰዎች ይግባቡበት ዘንድ ነው። ለምሳሌ ገመቹ፣ ሃጎስ፣ ደስታ የሚሉትን ስሞች ብንወስድ በተለያዩ  ቋንቋዎች አንድ አይነት ትርጉም ያላቸው ገላጭ ስሞች ናቸው።  ለገመቹ፣ ለሃጎስ እና ለደስታ  ልንሰጣቸው የሚገባ ክብር እና ቦታ እኩል መሆን አለበት። እንዲህ ካልሆነ ግን ከላይ በሐይማኖት ትንታኔዬ እንዳስቀመጥኩት ሐጥያት ሆኖብን ከሰው ጋር ብቻ ሳይሆን ከአምላክ ጋር የሚያጣላ ስለሆነ ለሁሉም ተናጋሪዎች እኩል ክብር ልንሰጥ ይገባል። ቋንቋዎች በተናጋሪው ዘንድ ተወዳጅነት ስላላቸው ሁሉም ሊያከብራቸው እና ሊረዳቸው እንዲሁም ክብርም ሊሰጣቸው ያስፈልጋል። ስለ ሌላው ማሰብ ስሌላው መጨነቅ የሌላውን ቋንቋ እና ወገንተኝነትን መውደድ ተገቢ ነው እንዲ ሲሆን ባልንጀራህን መውደድ የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ተፈጻሚነት ያገኛል።

ባጠቃላይ ወያኔ የፈጠረው እና ያዘጋጀው ሜዳ በቀላሉ የሚታይ ጉዳይ አይደለም። ወደዚህ ሜዳ  በሦስት መንገድ ይገባሉ፡-

አንደኛው በግድ ሁለተኛው በጥቅም ሶስተኛው ባለማወቅ። ዛሬ የምንመለከተው ሃቅ ይሄ ነው። ወደ ወያኔአዊ ሜዳ የመግባቱ እና የማስገባቱ ተግባር ክፍተኛ ስራ እየተሰራ ያለው በወያኔዎች ሲሆን  ተጠቃሚዎችም ራሳቸው ናቸው። የሐይማኖት አባቶች በክርስትናውም በእስልምናውም በዋቄ ፈናም በሌላም ያላችሁ እውቀት እና ችሎታው ያላችሁ በሙሉ ምዕመናኖቻቹህን ወደዚህ የጥፋት ሜዳ እንዳይገቡ ንገሯቸው። ስለ ባልንጀራ መውደድ እና ፍቅር አስተምሯቸው። እኛ ክፉ መንግስ እንጂ ክፉ ህዝብ የለንም። ወያኔ በዘረጋው የክፋት ሜዳ ላይ እንዳይገቡ መንጋዎችን ጠብቋቸው።

በዘር ጉዳይ ወያኔ የዘረጋው የጥፋት ሜዳ እንደሆነ ለገመቹም፣ ለሃጎስም፣ ለደስታም ለሌሎችም በቋንቋቸው ንገሯቸው። የኛ ጠላት ገመቹ፣ ሃጎስ፣ ደስታ ሳይሆን… ሐይማኖትን የማይፈራ፣ ዘርን የማያከብር፣ ለወገኑ ግድ የሌለው፣ ወገን ከወገኑ፣ ዘርን ከዘር፣ ለማጫረስ  የሚሰራውን  ወያኔን እንደሆነ አሳውቋቸው። ወደ ወያኔ ሜዳ የምንገባው ወያኔን ለመምታት እንጂ ሌላ እንዳይሆን አሳስቧቸው። ይህንን ስናደርግ ለሐይማኖታችን ለወገኖቻችን በመድረስ በአገር ላይ የተቃጣውን ጥፋት በቀላሉ ማስቆም እንችላለን። ይህ ከራ ረቢ ነው። አዎ መልካምነት የእግዚአብሔር መንገድ ነው።

ከ-ከተማ ዋቅጅራ

29.03.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

The post ፖለቲካ፣ ሐይማኖት፣ ዘር፣ በሰው ልቦና ውስጥ። appeared first on Zehabesha Amharic.

አባይ አባይ። ዳዊት ዳባ

$
0
0

Friday, March 27, 2015

ኬንያ ስደት ካንብ ውስጥ ልጆች ኳስ ተቧድነው ይጫወታሉ። አሊ ለብሩክ አቀበለው። ብሩክ ወደጎል መታት።  ኡመት በቀላሉ ያዛት። ኡመት ለጋ አሁን ኳሷ ጅግሳ ጋር ናት:: ጥሩ አድርጎ ለገብሬ አቀበለው። ገብሬ ደስ በሚል አብዶ ሰርቶ ተከላካዩን ደንፎን አለፈ። አሁን ገብሬና ግብ ጠባቂው ጆሬጌ ብቻ ነው ያሉት። ገብሬ ገብሬ ብቻውን ነው፤ አደገኛ ሁኔታ ነው። ገብሬ መታ ። አይይ ለትንሽ፤ ለትንሽ።  ኳሷ የግቡን እንጨት መታ ወደውጪ ወጣች።

ከተመልካቾቹ መሀል ከድጃ የኔ ነው። የኔ ነው እያለች ወደኳሷ እሮጠች። ሌሎች ተመልካቾችም ተከትለዋት እሮጡ። ከድጃ ከኳሷ ወስጥ የሆነ ነገር ደስ እያላት መዛ አወጣችና ኳሷን ወረወረችላቸው። ከዛም የኔ ነው በቀጣይ ኳሱ ውስጥ የሚገባው ጭቅጭቅ በሌሎቹ ተረኞች መሀል ጠብ ሆነ። ከድጃ የስልኳ ቻርጀሯ አልቆ ስንት ቀኗ  ፍሴ ቡክ ከገባች።ያኔውኑ  ስልኳ ላይ ገጥማ ቻርጅ ማድረግ ጀመረች። ጓደኞቿ ትግስት፤ ፋጡማና ሌንሳም የነሱንም ስልክ ቻርጅ ለማድረግ የሚበቃ የተጠረቃመ ሀይል እንዳለው ስለሚያውቁ አብረዋት ተደሰቱ።

ግድቡን በሚመለከት ሰብሰብ ባለ መንገድ መነሻ ስምምነት ተብሎ በየሜዲያው ላይ የያነው እውነተኛው ስምምነት ነው ወይ?። ወይስ   እንደአየር ጥቃቱ የውሸቱ ነው። ይህን እንድል ያስቻለኝ ጠንካራ ተቃውሞ እየሰማው ስላልሆነ ነው። ስምምነቱ እኔም ልረዳው በምችል ቀላል በሆነ እንግሊዘኛ የተፃፈ ነው።  በእርግጥም የእውሸቱ ቢሆን ይሆናል። አንብቤው የእውሸቱ በሆነ ስል ነው የፀለይኩት። ምክንያቱም  አባይን ውሀ ግብፅ ውስጥ በረዶ አድርገው ቤት ቢሰሩበት፤ ቢመርዙት ፤ ብቻ ያሻቸውን ቢያደርጉት ስምምነት በተባለው ዶሴ ውስጥ በሙሉ እኛ ይህን ማድረጋቸው በዚህ መልክ ጎድቶናል ብለን ልንከስም ሆነ ልንከራከር የምንችልበት መንገድ ባስበው ባስበው አልታየኝ አለ። ስምምነቱ እኛንም ግብፅንም ሱዳንንም በጋራ የምንገዛበትና ተጠያቂ የሚያደርግ ቢመስልም አንድና አንድ በሆነ ሁኔቴ ኢትዬጵያ ማድረግ፤ አለማድረግ፤ መውሰድ ያለባትን ጥንቃቄ በሚመለከት የተጣለባት ግዳጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት።

ግድቡን ለኤሌክትሪክ ማመንጫነት ብቻ ለመጠቀም እንደሆነ እንደተፈራው በስምምነቱ ተካቷል። ከበፊቱም የተገነባው ጠረፍና ለእርሻ የሚሆን መሬት የሌለበት ቦታ ላይ ስለሆነ ለመሰኖ አገልግሎት ለማዋል እስቸጋሪ እንደሚያደርገው አካባቢውን በሚያውቁ ዜጎች  ሲገልጽ ነበር። በእርግጥ ወያኔዎችም ግድቡን ከኤሌክትሪክ ማመንጫነት ውጪ ለሌላ አገልግሎት የማይውል መሆኑን ቀድሞም አልደበቁም። ማንንስ ፈርተው ይደብቃሉ። ይህም ሆኖ ይገደብ እንጂ ወያኔዎች ለዘላለም አይኖሩም። ወደፊት  ወሀውን በቦይ ወደሗላ በመመለስ ለመስኖም ሆነ ለሌላ አገልግሎትም ለመጠቀም እንችላለን ተብሎም ተስፋ ተሰጥቶም አንብቤያለው። አሁን  እድሜ ለወያኔ ግድቡ እንጂ ውሀው የኛ ባልሆነበት ሁሉም ነገር በስምምነቱ እልባት አግኝቷል።

ውሀውን መከልከላችን ሳያንስ ተንከባክበንና አጣርተን ግብፆችን ማጠጣት ተስማምተን የፈረምንበት መሆኑ  እንዳለ “የኤሌክትሪክ ሀይል “ ተብሎ የሚደሰኮርበት እራሱ በቅጡ አልተመረመረም ባይ ነኝ። ወያኔዎቹን ትተናቸው ሁላችንም በይበልጥም  ሙህራኖቻችን ያላዩት ስለዚህም ያለነሱት ወና ችግር ያለ ይመስለኛል። ስብሰለሰልበት ከጀመረ ቆይቷል። ግድቡን በሚመለከት ሲነሳ የነበረው ስጋት በድህነት ከአለም አገሮች ጠርዥ ላይ ያለች አገር ለአንድ ግድብ ብቻ ይህን ያህል የአገር ሀብት አሟጣ ማፍሰስ በብዙ ጎኑ ይጎዳናል። ከተገደበና ሀይል ማመንጨት ከጀመረም በሗላም ይህ ግድብ  ከፍተኛ ወጪ ያለው ነው። ግድቡ መጨቆኛ፤ በዜጎች ዘንድም ለአባይ ካለ ጥልቅ መቆርቆር ፈቅዶ መጨቆኛም ሆኗል  የመሳሰሉ ስጋቶች ነበሩ።

የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨትን በሚመለከት በአለሞያም ባንሆን፤ የጠለቀ እውቀቱም ባይኖረንም ከመረጃ የራቅን ካልሆንና ሜዲያዎችን የምንከታታል ከሆነ በርካሽ ማመንጨትንና  መጠቀምን  በሚመለከት በሚቀጥሉት አስርና ሀያ አመት አለም ምን አይነት ገፅታ እንደሚኖረው መገመት አይከብድም። ተግባር ላይ ውለው ልናያቸው የሚችሉትን የተሻሉ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ አማረጮች ብዙ ናቸው። ኤሌክትሪክ በምን ደረጃ በቀላሉ ሊዳረስ እንደሚችል። ምን አይነት ዋጋ ሊኖረው እንደሚችል መገመትም እንዲሁ ከባድ አይደለም።  በቀላሉ በቀጣይ እንደሞባይል ስልክ የፀሀይ ብርሀንን የሚሰበስበው ፓናል  የአለም ህዘብ ሁሉ ይኖረዋል። አይደለም ህንፃዎች ላይ በየጎጆ ቤቱ ላይ የምናየው ዲሽ የሚሆን ይመስለኛል። አሁን ባለው ገበያ እንኳ በምኖርበት አገር ሰዎች ከ$300 እስከ $1000 ዶላር ባልበለጠ ወጋ  ጣርያቸው ላይ ፓናሉን በመግጠም የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን እየሸፈኑ ነው። እኔ እራሴ $29 በፀሀይ ብርሀን የሚሰራ መብራት ለቤተሰቦቼ አገር ቤት ልኬላው። አንዴ ጨክኜ ፓናሉን ባስገጥም ደግሞ ከገቢያቸው አልመጣጠን ብሎ ከሚማረሩበት ወራዊ የመብራት ክፍያ ይገላገላሉ። በፀሀይ ብረሀን የሚሰራው መብራቱ የ$19 ገበያ ላይ ነበር። የኤሌክትሪክ ሀይል ከንፋስ ከቆሻሻ፤ ከኒኩለር ለዛውም ከመጨረሻው ዝቃዥ መጣያ እየጠፋ ሲቸገሩበት ከነበረው ሳይቀር መጠኑ እጅግ ትልቅ የሆነ ማመንጫነት ተችሏል።

ከፀሀይ ብርሀን የሚገኘው የኤሌክትሪክ ሀይል ይህ በትልቅ እንዱስትሪ ደረጃ የሚሰራም አይደለም። “ ጁአካሊ” በኪሲዋሊ። “በጥቃቅንና አነስተኛ  ሰዎቻችን በሚሉት  በየጎጆ ቤቱ ላይ ሊገጠም የሚችል ነው። ዛሬ ዲሽ የሚገጥሙ ሰዋች ፓናል የሚገጥሙ ይሆናሉ። ኦባማ በቀን ውስጥ ስንት ቤቶች ነበሩ ከፀሃይ ብረሀን ከሚገኝ ኤሌክትሪክ ለማመንጨትና ፍጆታቸውን ለመሸፈን ይቀየሳሉ ያለው?። አሁን አሁን የመንገድ መብራቶች፤ አፓርትመንቶች፤ የንግድ ቦታዎች ፤ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን ከፀሀይ ብርሀን እያገኙ መሆኑን ዞር ዞር ሲሉ ትኩረት ሰጥቶ ማየትን ብቻ ነው የሚፈልገው።

በቅርብ አሜሪካኖች የአፍሪካ መሪዎችን በሙሉ በትእዛዝ ጠርተው  በዋናነት ቃል የገቡላቸው በሉት ያስሟሟቸው ሀይል በማመንጨት አፍሪካ ላይ መዋለንዋይ ሊያፈሱ ነው። ለአፍሪካችን ተጨንቀው ያበረከቱት ቾሮታ።መሪዎቹ በአስቸኳይ የተጠሩበት ዋናው ጉዳይ ይህው ነው። አሜሪካኖች በቀላሉና በርካሽ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት እንደሚቻል አውቀውበታል። ጠቅላላ አፍሪካ ገና ጭለማ ውስጥ ነው ያለው። ከዚህ በላይ ገንዘብ የሚዛቅበት አውድማ መቼም የለም።  መቼም አምስትና አስር ቢሊዬን ብር እያወጡ ግድብ ገድበው አፍሪካን ብረሀን በብረሀን ሊደርጉ ነው ቆርጠው የተነሱት ብለን የምናስብ አንኖርም።

ግድቡ አለቀ እንበል። ለኛ ስንት ዘመን ስንመኘውና ስንዘፍንለት የነበረ  ከአባያችን የተገኘ ስለሆነ በግዳጅም ጭምር ገበሬው ሳይቀር መብላት ትቶ መብራት ይኑረው። ለኬንያ፤ ሱዳንና ጅቡቲ ለሌሎችም አገሮች እንዴት በአለም ገበያ አወዳድረን በቅናሽ እንዲገዙን እንደምናደርግ የሚታይ ይሆናል። አፍሪካዊው አንዴ ሶስት መቶ ዶላር ከፍሎ ለዛውም ላንድ አንፖል ቢበዛ ለፍሪጅ በቀላሉ ኤሌክትሪክ ማግኘት እየቻለ በየወሩ ለመብራት ለምን ይከፍላል። የትኛው አፍሪካዊ መንግስት ለዛውም መንግስት ሳይገባበት ዜጋው እራሱን ችሎ ሊያደርገው ሲችል በየወሩ የውጪ ምንዛሪውን አሟጦ ለኛ እየከፈለ ነው የሚያበለፅገን። በጭራሽ የማይሆን የሞኝ ሀሳብ ነው። ምን አለ በሉኝ ሁሉ ባለ መብራት የሚሆነው ደግሞ እኛ ላባችንና አንጡራችንን ጠብ አድርገን አባይን ገንብተን በምንጨርስበት ጊዜ ጋር እኩል ነው።

ለማንኛው በመጪው አስርና ሀያ አመት በሗላ ኤሌክትሪክ ሳይሆን እራሱ “ውሀው” ነው መዳረሱ አለምን እያስጨነቀ ያለው። በቀጣይ ያአለምን ፀጥታ የሚፈታተነው ነዳጅ ዘይት ሳይሆን ውሀ መሆኑ ብዙ ተብሎበታል። ውሀ የማያልቅ የማይመስለን ተሳስተናል። አላቂ  ሀብት ነው። ይሄ  ስምምነት ደግሞ አይደለም ከግድቡ ከገባር ወንዞችም በጣሳ ቀድተን ስንጠጣ ግብፅና ሱዳን አዩን አላዩን እያልን እንዲሆን የሚያደርግ ነው።  አንዴ ጉዶች ነግሰውብናል። ሊያውም የሚያደባብን። ወገን ለራሳችን እንወቅበት። ምን ማድረግ እንደምንችል ባላውቅም። ዝም ግን አንበል።

comment pic

 

The post አባይ አባይ። ዳዊት ዳባ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live