Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

  **ድንቄም ምርጫ** –ነብሮ

$
0
0

ፍትሕ በተረገጠበትና የዴሞክራሲታዊ ሥርዓት በኃይል በታፈነበት አገር ሕዝብ መሪውን መምረጥ አይችልም።

              EPRDF Election1የምርጫ ጉዳይ ሲነሳ ወደ ኋላ ሄደን የዘመነ ኃይለሥላሴን፤የደርግን የምርጫ ሂደቶች ብናስብ ከዚህ በሰለጠነው ዓለም ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በምንም ሁኔታ ሊመሳሰል እንደማይችል ሁላችንም ግልጽ የምንሆን ይመስለኛል።አድሎአዊና ሕዝብን ያላሳተፈ የገዥው መደብ የሚፈልጋቸውን እጩዎች መልምሎ በማቅረብ ሕዝቡን አስገድዶ እንዲመርጣቸው ማድረግ አይነተኛ ባሕሪው መሆኑን መጠራጠር አይኖርብንም።

የባሰ አለ እንዲሉ ከአንድ መንደር የተሰባሰቡና በዘረኝነት በሽታ የተመረዙት (ጎሰኞች) የአሁኖቹ ገዥዎቻችን ከ1997 ምርጫ በፊት ከምርጫው በፊትና በምርጫ ወቅት ሲፈጸም የነበረውን ሤራ በሚገባ የማውቀው ሲሆን የተቃዋሚ ኃይሎች(ድርጅቶች)ውስብስቡን የካድሬ መሰናክል አልፈው በፓርላማው ውስጥ ጥቂት አባሎቻቸውን በፓርላማ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጉ ነበር።በፓርላማው ውስጥ ሃሳባቸውን የመግለጽና የማራመድ እድላቸው የጠበበ ቢሆንም የፓርላማውን ውሳኔ የሚነቅፍ የተቃውሞ ድምጽና የተአቅቦ ድምጽ ማስቆጠር ችለው ነበር።ከ1997 ምርጫ በኋላ ግን ዘረኝነት መራሹ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ(ህወሃት)ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተነጥሎ እንደቆመ ተንሳፎ የሚገኝ መሆኑን ሕዝብ በምርጫ ካርዱ ፍርዱን ሲሰጥ የበረገገው ገዥ ቡድን ረጅም እጁን የምርጫ ኮሮጆ ዘረፋ ውስጥ አስገባ ያልተመረጠውን ተመርጫለሁ አለ።ሰርቀሃል ድምጻችን መልስ ሲባል ደግሞ ግድያ፤እስራት፤ስብሰባ መከልከል፤ሰላማዊ ሰልፍ የማይደረግ መሆኑን አወጀ በግብርም ውሎ አየነው።ከዚያ በኋላ የዚህን ትውልድ አምክን ዘረኛ አገዛዝ እድሜ ለማስረዘም የደህንነት፤የመከላከያ፤የፖሊስና የልዩ ፖሊስ የክልል ፈጥኖ ደራሽ፤የካድሬው መዋቅር ትኩረት ተሰጥቶ እንዲጠናከር ተደረገ።አፈናው ግድያው ተስፋፍቶ ኢትዮጵያውያን በየጎዳናው ወድቀው የሚገኙበት ሁኔታ ተፈጠረ።

woyaneይህ የምታዩት የህወሃት መለያ ሲሆን ከብጫው ላይ የተቀመጠው ዓርማ የጀርመን ናዚ ልዩ ምልክት የነበረ ሲሆን ዛሬ ኢትዮጵያውያን ህወሃትን ሲያነሱ የጀርመን ናዚን የጀርመን ናዚን ሲያነሱ ህወሃትን የሚያስታውሱበት ምክንያት ህወሃትና የጀርመን ናዚ በቆዳ ቀለም ቢለያዩም በተግባር አንድ ናቸው ብለው ስለሚያምኑ ነው። እኔ የዚህ ጹሑፍ አቅራቢም ህወሃትን ከጣሊያንና ጀርመን ፋሽስቶች ለይቸ አይደለም የምመለከተው።ለዚህ ጹሑፌ መነሻ የሆነኝ የፊታችን ግንቦት ለሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ የህወሃትን ሥርአት በሰላማዊ መንገድ ታግለን በምርጫ አቸንፈን ሥልጣን እንጨብጣለን ብለው በተነሱ ኃይሎች ላይ የህወሃት የምርጫ ቦርድ የፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊት ተመልክቸ ሲሆን በምንም አይነት መስፈርያ ይሁን የተቃዋሚ ኃይሎች ለምርጫ ውድድር የሚያቀርቡትን እጩ ራሳቸው ወስነው ያቀርባሉ እንጅ የምርጫ ቦርድ ይህ ይመረጥ ይኸኛው አይመረጥ ብሎ የመወሰን ሞራሉም ሆነ ብቃት የለውም።ለዚያውም በእጣ! የምርጫ ኮሮጆ ገልብጦ ያልተመረጠውንና ሕዝብ አንቅሮ የተፈውን ተመርጠሃል ሕዝብ ይሆነኛል ያለውን በምርጫ ያቸነፈውን አልተመረጥክም ብሎ የሚቀጥፍ የአንድ ሥርአት አገልጋይና ተቋም አምኖ ምን አይነት ምርጫ እንደሚካሄድ ከወዲሁ መተንበዩ ነብይ የሚያሰኝ አይደለም።ለሥርአቱ አስጊ የሆኑ የተቃዋሚ ድርጅቶችን አንድነትና መኢአድን በኃይል አፍርሶ የየድርጅችን ንብረት ዘርፎ በሌሎቹ የተቃዋሚ ኃይሎች ጉያም ለመግባት ረጅሙን ዘራፊ እጁን ለማስገባት እያሴረ ያለው ህወሃትና ጉዳይ አስፈጻሚው የምርጫ ቦርድ ሕገ-መንግሥቱን እየናዱ መሆኑን ሊያጤኑ ይገባቸዋል።

ህወሃት መሠረታዊ ችግሩ ድህነት ከሆነ በትግራይ ሕዝብም ይህ ችግር እንደ ዋነኛ ተደርጎ ከተወሰደ ሌሎችስ ብሎ ማሰብ የሚችል ተፈጥሮ በህወሃት ቤት እንዳማይኖር ቢታወቅም በትግራይ ለተፈጠረው የኢኮኖሚ መዳከምም ሆነ የንዋይ ጥማት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠየቅበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይገባውም የህወሃት መራሹ ቡድን በፈጠራ ውሸት የቆጥ የባጡን በመቀባጠር የሕዝብ እልቂት እንዲፈጠር በማድረግ በውንድብድና የካሄደው ዘረፋ፤ዜጎችን በተለይም ምሁሩንና አምራቹን ኃይል ከሀገር መንቀልና የመራሹ ቡድን እንባ ጠባቂዎችና ቤተሰቦች አገሪቱን ተስፋፍተው እንዲይዙና ሌላው ዜጋ በዘመናዊ ባርነት መቀጠል ወይም በሌሎች ላይ የደረሰው ጽዋ ሞልቶ እንዲፈስበት ማድረጉ የሚያስከትለውን መዘዝ መገንዘብ ባለመቻል የተፈፀመ ስለሆነ የዛሬው እዩኝ እዩኝ ነገ ሸሽጉኝ ሸሽጉኝን እንደሚያስከትል በድፍረት መናገር ይቻላል።

በአንድ ወቅት የህወሃቱ ፊታውራሪ ስብሃት ነጋ ከጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ፡) እንዲህ ብሎ ነበር-ጋዜጠኛ አቶ ስብሃት ድሮ የሃብታምና የባለሥልጣን ልጅ ነበር ስኮላር ሽፕና የውጭ ትምህርት እድል ያገኝ የነበረው ዛሬ ደግሞ የእናንተ ልጆች የሚማሩት ወደ ውጭ አገር ሄደው ነው ሲባል(፡ አቶ ስብሃት ታዲያ እነሱ ያደረጉትን እኛ ብናደርገው ነውሩ ከምኑ ላይ ነው ብሎ ነበር በአራት ነጥብ የዘጋው።እንግዲህ ህወሃት እንዲህ ያሉትን ውዳቂዎችንና ፀረ-ሕዝቦችን አቅፎ ነው ኢትዮጵያን በኃይል አንበርክከን እንገዛታለን ካልሆነልን ደግሞ እናፈራርሳታልን የሚሉን።ከዚህ ወዲያ እብደት የለም እንዲህ ያሉት እብዶች የተሰባሰቡበት ህወሃት ነው ዛሬ በትረ ሥልጣኑን ጨብጦ እየገዛ ያለው።

አንዱ በአንዱ ላይ እምነት እንዳያሳድርና በጥርጣሬ እንዲተያይ ጦርነት ውስጥ እንዲገባ፤አንተ የዚህ አንተኛው ደግሞ የዚህኛው ዘር ነህ በማለት በዘር በማናከስ የሕዝብ ሰላም እንዲደፈርስ ያደረገው ህወሃት ነው። ሰሞኑን ደግሞ አንድ አስገራሚ ድርጊት ተፈፀመ ይህኸውም(ጥቂት ህወሃት የመለመላቸው የቅማንት  ተወላጆች ) በአማራ ገዥ መደብ እስከ ዛሬ ተገዝተናል አሁን በቃን ጐንደር የቅማንት አገር ስለሆነ ራሳችን በራሳችን ለማስተዳደር እንድንችል የራስ ገዝ አስተዳደር ይገባናል በሚል ሲንቀሳቀሱ ቆይተው አሁን የነአቶ በረከትና አዲሱ ለገሠን ይሁንታ አግኝተው ያልተጻፈ የታሪክ ድሪቶ አንግበው በደምና በስጋ የተቀላቀላቸው ወገናቸው ጋር ደም የሚያፋሥስ መንገድ መጀመራቸው ቀልጥፈው ተግባራቸው እኩይ ተግባር መሆኑን አውቀው እንዲያቆሙት ለማስገንዘብ ነው ይህን ጹሑፍ ያዘጋጀሁት። በዚህ ተግባር ግንባር ቀደም ሆነው የሚያራምዱትን በአካል ስለማውቃቸውም ጭምር ወንድማዊ ምክሬን ሊሰሙ እንደሚችሉ በማመን ነው። ህወሃትና የአማራውን ህዝብ ጋንጃ እየመታ የሚገኘውን ብ.አ.ዴ.ንን አምኖ ወደዚህ አጣብቂኝ ጉዳይ መግባት በፍጹም ስህተት ነው።የቅማንት ተወላጅ ለህወሃት የምርጫ ፍጆታ መዋል የለበትም፦የህወሃት ሥርዓትና የሥርአቱ አራማጆች መቀበሪያቸውን ቆፍረው ከመቃብር አፋፍ ላይ በሚገኙበት ወቅት መልካም ታሪክን ማጉደፍ አይገባም።ይህ ስርዓት ወዳቂ ነው በሀገር ጥፋትና እጁን በደም የነከረ ሁሉ በሰፈረው እንደሚሰፈርም ግልጽ ነው።ነገ የዛሬዎቹ ዳኞችና እኛ ፊት ለፊት እንገናኛለን፤ ነገ እኛና ይህወሃት ካድሬ እንገናኛለን፤ነገ የምርጫ ቦርድና እኛ እንገናኛለን፤ነገ የፌደራል ፖሊስና እኛ እንገናኛለን፤ነገ እኛና ፖሊስ እንገናኛለን፤ነገ የአጋዚ ሠራዊትና እኛ እንገናኛለን፤ነገ እኛና የክልል ፈጥኖ ደራሽ እንገናኛለን፤ለዘመናዊ ባርነት ወደ ዐረብ አገር የተላኩ እምቦቃቅላ ሴትና ወንድ ወጣቶችን መዝግበናል፤አገር ጥለው እንዲወጡ የተገደዱ ሙራንና ጋዜጠኞችን ዝርዝር ይዘናል፤ወህኒ ቤት ወርደው ሌትና ቀን እንደ እባብ እየተቀጠቀጡ የሚገኙትን ወጣት ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችን እናውቃቸዋለን፤በመላ ኢትዮጵያ የመኖርና ሠርቶ የመብላት መብት የተነፈገው ዘሩ በመድሃኒት እንዲመክን የተደረገውን የአማራ ነገድ ሕዝብ ጉዳይ በሚገባ ተመዝግቦ እንዲቀመጥ ተደርጓል፤ከወሎና ጎንደር ተነጥቆ ወደ ትግራይ የሄደውን መሬት በሚገባ እናውቀዋለን ይህን ሁሉ ህወሃትና መንገድ መሪዎቹ የሚከፍሉት እዳ እንደሆነ ሊያውቁት ይገባል። በዚህ አጋጣሚ አቶ በየነ አስማረና አበበ ንጋቱን አመስግኘ ማለፍ እወዳለሁ።« በወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ » ጣሊያን ጎንደር ሲገባ የተጠቀመበትን ፕሮፓጋንዳ ያነገበው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለመበታተን ሲል የሚያራምደውን የጎሳ ፖለቲካ የተጋቱ አውቆ አጥፊ የቅማንት ተወላጆችንና ሌሎች የተለያዩ በአማራው ነገድ ህዝብ ክልል የሚኖሩ ጎሳዎችን በማነሳሳት በጎሳ መራሹ ቡድን ጣቱን የቀሰረውን ሕዝብ አስተሳሰብና አመለካከት አቅጣጫውን እንዲስት ለማድረግ የሚጠቀምበትን ሕዝብን በሕዝብ የማናከስ ሤራ እያራመዱ ይገኛሉ።

24 ዓመት በመድፈን ላይ የሚገኘው የህወሃት አገዛዝ በሚያካሂዳቸው ምርጫዎች አንድም ቀን ፍትሃዊነት ያልታየበትና የተጭበረበረ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በምርጫ ወቅት ለሕዝብ የሚገባቸውን ቃሎች ከመካዱ አልፎ በተቃራኒው እንደሚተገብራቸው ይታወቃል።የዘንድሮ ደግሞ በጣም የለየለትና አውሬነቱን በግልጽ የሳየበት ሁኔታ ላይ ደርሷል ሁላችንም የምግባባበት አንድ መሠረታዊ ጉዳይ ህወሃት ለአፍታም ቢሆን ሥልጣን ከእጁ ካፈተለከ የሚደርስበትንና የሚከፍለውን ዋጋ ስለሚያውቅ በሰላማዊ መንገድ ሥልጣን ያስረክባል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ዋናው አነጋጋሪ ጉዳይ ሕዝብ ካለፈው ተመክሮ የማያገኘውና አልመርጥም የማይልበት ምክንያት ምንድን ነው የሚለው ይሆናል።የሚያሰድድን፤የሚገድልን፤አስሮ የሚያሰቃይን፤ዘር በማጥፋት ላይ የተሰማራን ነብሰ-ገዳይ ቡድንን መርጦ በሥልጣን ላይ ማስቀመጥ አገርን ከመገደል የከፋ ወንጀል ነው።ስለዚህ ሕዝቡ የዘንድሮውን ምርጫ በእምብይታ ሊያስተናግደው ይገባል።

ነብሮ ነኝ ከሰ/አሜሪካ

The post   **ድንቄም ምርጫ** – ነብሮ appeared first on Zehabesha Amharic.


የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ

$
0
0

በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሃዱ አምላክ አሜን!!
ባህረ ሐሰቱን የምንሻገርበትን የእውነት መርከብ ማን ይሰጠናል? ወዳጄ ሆይ፡- አትፍራ! እውነት አባትህ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዮሐ. 14÷6)፡፡ እርሱ ‹‹ መንገድም ፣ እውነትም ፣ ሕይወትም ›› ነው፡፡ መንገድ ነው፡- ትሰማራበታለህ፣ እውነት ነው ፡-ትይዘዋለህ፣ ሕይወት ነው፡- ትኖረዋለህ !!!

debre-tsion-kidiste-mariam-church-london
የርዕሰ አድራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ።
በእንግሊዝ ሃገር የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ገንዘብና ጉልበቱን አስተባብሮ በእግዚአብሔር ተራዳዒነት የገዛውን ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ለወያኔ ሹማምንት አሳልፈው በመስጠት ሥልጣንና ንዋይን የሚያጋብሱ የመሰላቸው የለንደኑ ዳያብሎስ አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው፤ የቤተ ክርስቲያኑን አባላት መብት የሚነፍግ ተግባር ፈጽመው አባላቱ በቤተ ክርስቲያኗ ንብረት እኩል የመገልገል መብታቸው እንዲከበርላቸው ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው በ13/02/2013 በዋለው የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ችሎት ተፈረደላቸው።

More…

The post የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ appeared first on Zehabesha Amharic.

የምርጫ ክርክር ሶስት- ግብርና እና ገጠር ልማት (ከግርማ ሰይፉ ማሩ)

$
0
0

“በ24 ዓመት አሁንም በአዝማሚያ ላይ ነኝ የሚለው ኢህአዴግ ……”
“የ1997 የምርጫ ክርክር ይደገም ……”
ግርማ ሠይፉ ማሩ
girmaseifu32@yahoo.com; girmaseifu.blogspot.com
ተከራካሪዎች፤
አቶ ተፈራ ደርቤ እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
አቶ ግርማይ አደራ እና ዐዐዐዐዐ
አቶ ትዕግሰቱ አወሉ እና አቶ ዮሃንስ አሰፋ
አቶ ግዑሽ ገብረሰላሴ እና ትዕግሰቱ ዱባለ
አቶ ጥላሁን እንዳሻው እና ሙላቱ ገመቹ

(ግርማ ሰይፉ)

(ግርማ ሰይፉ)

በመጋቢት 18 እና 19 2007 ለግንቦት ምርጫ የተደረገው “የምረጡኝ ክርክር” የተጀመረው በአቶ ተፈራ ደርበው በተመራው የኢህአዴግ ቡድን በግንባሩ ውስጥ በከባድ ሚዛኑ ህወሃት ተወካዮ ዶክተር አብርሃም ተከሰተ በመታገዝ ነበር የተገኘው፡፡ ተከራካሪዎቹ በኢህአዴግ በተተኪ መስመር የሚገኙ ቢሆኑም እንደ ወትሮ ሁሉ ኢህአዴግ የሚያቀርበው አዲስ ሀሳብ ለሚቀጥለው የስልጣን ዘመን ሊያቀርብ አልቻለም፡፡ እነዚህ የኢህአዴግን ሹሞች ልብ አውልቅ የሆነውን በእውሸት የተሞላውን የቁጥር ጫወታ ይዘው ብቅ ያሉ ሲሆን በዚህ ደረጃ ሊሞግታቸው የሚችል፤ አንድም ተቃዋሚ ነኝ የሚል ለማየት አልቻልንም፡፡ ኢህአዴጎች ከታቃዋሚዎች በላቀ ደረጃ ጎላ ያደረጋቸው የለበሱት ሱፍና የተጫሙት ጫማ ማብቅረቅ ሲሆን ተቃዋሚዎች አሁንም ከጀርባቸው ያስቀመጧቸው አማካሪ ተብዬዎች ምንም ያለመፈየድ ሳይሆን እንቅልፍ ሲያንጎላጃቸው ማየት ኢህአዴግ በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ምን ዓይነት ሰዎችን ወደፊት እያመጣ እና ወደፊትም እንደሚያመጣ አመላካች ነው፡፡ ከተቃዋሚ ጀርባ ለተቀመጡትም ሆነ በፊት መስመር ላሉት ደካማ ተቃዋሚዎች ተጠያቂው ኢህአዴግ እና የዘረጋው ስርዓት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡
ኢህአደግ ለቀጣይ አምስት ዓምት በስልጣን እንደሚቆይ ቢያውቅም ይህን በትህትና ለገጠሩ ህብረተሰብ ያስተላለፉት ዶክተር አብርሃም ተከሰተ እና ቆጣ ቆጣ ሲሉ የነበሩት አቶ ተፈራ ደርቤ ናቸው፡፡ ለዚህም እንደማስረጃ ያቀረቡልን
· 60 ሺ በላይ የገጠር ልማት ሰራተኞች እና የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች(በተቃዋሚዎች በትክክል ካድሬዎች ተብለው የተፈረጁት)፤
· ድህነትን በ1988 ከነበረበት 48 ከመቶ ወደ 24 ከመቶ ዝቅ ማድረጋቸው፤ (በመቶኛ ቀነሰ ቢባልም በቁጥር ግን በ1988 ከነበረው ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡)
· መስኖ እና ሰፈራ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ማስፋፋቱ፤
· 2.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በግል ባለሀብት እየለማ መሆኑ (ይህ መረጃ በቅርቡ እየተነገረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን በዚህ መስክ የሚያደርጉት ተሳትፎ በግልፅ የሚታይ አይደለም)
· የመሰረተ ትምህርት እና ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት መስፋፋቱ፤ ወዘተ ሲሆን

በዚህ መነሻ አርሶ አደሩ ሀብት እያከባተ በመሆኑ ወደ ማንፋክቸሪንግ ዘርፍ እንሚገባ አሰረድተውናል፡፡ አህአዴጎች በዛሬው ክርክር የቀደሞ ሰርዓት መክስስ ዘዴያቸውን የገቱ ቢሆንም ተቃዋሚዎችን ማጣጣል በተለይ መድረክ ላይ ለመዝመት ተዘጋጅተው እንደመጡ አቀራረባቸው ያሳብቅ ነበር፡፡ አቶ ተፈራ ደርቤ በተደጋጋሚ ተቃዋሚዎች ከላይ የተዘረዘሩትን የኢህአዴግ ሰኬት በመቃወም መሬት ይሸጥ ይለወጥ በማለት አርሶ አደሩን በማፈናቀል ለጥቂት ባለሀብቶ የቆሙ መሆናቸውን ያረጋገጡበት ክርክር ነበር፡፡ አቶ ተፈራ ደርበው ከመድረክ ጋር ተከራከሩ ተብለው መመሪያ እንደተሰጣቸው በሚያሳብቅ ሁኔታ መድረክን መሬት ይሽጥ? ነው የምትሉት ወይስ ሌላ አማራጭ አላችሁ? እያሉ በተደጋጋሚ አንስተውታል፡፡ አቶ ጥላሁን እንሻውም እንዳሻቸው መልሰውላቸዋል፡፡

ከኢህአዴጉ ተወካይ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ያነሱት ሀሳብ ግን ወደ 1997 ክርክር መልሶኛል፡፡ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ አቶ አዲሱ “ግብርና ሴክተር የእድገት ፍንጭ” እያሳየ ነው ሲሉ ለሰጡት አሰተያየት “ከ14 ዓመት በኋላ ፍንጭ እየታየ ነው አትበሉን” በሚል የሰጣቸውን ምላሽ አሰታውሶኛል፤ በ2007 ክርክር ዶክተር አብርሃም ተከስተ የግብርና ፖሊሲው “የስራ አጥ ቁጥርን የመቀነስ አዝማሚያ” እያሳየ ነው ብለውን ከ24 ዓመት በኋላ አዝማሚያ ላይ እንደሆኑ ነግረውናል፡፡ በእኔ እምነት የግብርና ዘርፉ ይህን ሁሉ ጉልበት ይዞ መቀመጥ አይጠበቅበትም፡፡ በግብርና ዘርፍ ያለው ትርፍ ጉልበት ሊቀበል የሚችል ግብርና ያልሆነ ዘርፍ መፍጠር ያልቻለው ኢህአዴግ ሊከሰስበት የሚገባው ዋና ነጥብ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ 24 ዓመት ያልበቃው ኢህአዴግ ምን ሲሰራ ነበር ተብሎ አይጠየቅም፡፡ ብዙዎቹ ሚኒሰትሮች ከሁለተኛ ደረጃ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም ድህረ ምረቃ ትምህርት ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡ አንድ አንዶች ለሶሰተኛ ዲግሪ የሚሆን ጊዜ ነበራቸው፡፡ አበበ ገላው እየገዙ ነው የሚለውን ወደጎን እንተወው ከተባለ ማለት ነው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ያሉትም ማሰታወስ ያሰፈልጋል “እነዚህ ሰዎች ሀገር እየመሩ/እያሰተዳደሩ ሶሰተኛ ዲግሪ መያዛቸው ወይ ሰራቸውን እየሰሩ አይለም፣ ካልሆነም ትምህርቱ ቀሎዋል ማለት ነው” አሰተያየት ሰምቻለሁ፡፡ ቃል በቃል ባይሆንም፡፡

ለማነኛውም ኢህአዴግ መነሻ ሀሳቡንም፣ ማብራሪያውንም ማጠቃለያውን “በሚመጥነው” ደረጃ አቅርቦ ክርክሩን አጠናቆዋል፡፡ ከዚህ የጠነከረ ክርክር ቢያቀርብ ማን ከቁብ ሊቆጥርለት ነው፡፡ በእኔ ግምት ዶክተር አብርሃም ተከስተ በዚህ ክርክር ላይ ባልመጣው ሳይል የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ጠንከር ያለ ቁጥርና ቁጥር ነክ ጥያቄዎች በተለይ ደግሞ የመዋቅራዊ ሽግግር ጥያቄዎች እና ማክሮ ኤኮኖሚክ ነክ የሆኑ ለምሳሌ በውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ በግብርና ሴክተር የመሪነት ሚና ላይ ዝርዝር ሀሳቦች ለመመለስ በክርክሩ ላይ የተገኘ ይመስል ነበር፡፡ ዶክተር አብርሃም ተከስተ የክርክር ጊዜውን ለመግደል ዘና ብሎ ሲመልስ ላስተዋለ በእግር ኳስ ጫወታ እየመራ ያለ ቡድን ጎል ጠባቂ ጊዜ ሲያባክን የሚያሳየውን ባህሪ የሚያሰታውስ ነው፡፡

ለማነኛውም አቶ ተፈራ ደርቤ ያቀረቡት የመሬት ጉዳይ በህገ መንግሰት ውስጥ መግባቱ እና አሁን የሚከተሉት የመሬት ፖሊሲ መሰረቱ ኤኮኖሚያዊ ነው ብለው ቢዋሹም፣ ኢህአዴግ መሰረቴ ነው የሚለውን አርሶ አደር ለመቆጣጠር እንዲችል የተቀመጠ ፖለቲካዊ መሰረትነቱ መቼም ክዶት የማያወቅው ታውቆ ያደረ ጉዳይ መሆኑን የሚያስታውሳቸው አላገኙም፡፡ የዶክተር አብርሃም ተከሰተ ትህትና የተሞላበት የምረጡን ጥያቄም አማላይ ነበር፡፡

ኢህአዴግ በአቶ ግርማይ አደራ በሚባሉ ሰው የተወከለ ሲሆን በረዳትነት የተገኘውን ለማወቅ እድል አላገኘንም፡፡ አቶ ግርማይ ጊዜው አይበቃም ቢሉም ሲጀምሩ ቀስ ብለው ተዝናንተው ሲጨርሱም ሁለት ደቂቃ አሰቀርተው ሲያጣቃልሉም ለጊዜ አጠቃቀም ምንም ግድ ሳይሰጣቸው ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ከእኝ ግለሰብ ልይዝላቸው የቻልኩት ነጥብ መሬት ለኢትዮጵያን የዜግነት፣ የሀገር ባለቤትነት፣ የነፃነት መገለጫ ነው የሚሉት እና የማዳበሪያ ዕዳ ለመክፈል አዲስ አባባ ለልመና የሚመጡ አርሶ አደሮች መኖራቸውን ያስታወሱን መሆኑን ነው፡፡ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ በፅሁፍ የያዘውን በቅጡ የማያነብ፣ በቂ አይደለም ብሎ ካለው ጊዜ ውስጥ በመግቢያና በመውጫ ሠዓት ማባከን ምን ግምት እንደሚያሰጥ ተከራካሪው ያሰቡበት አይመስለም፡፡ ለማነኛውም ኢህአዴግ አቻውን አግኝቶዋል ማለት ይቻላል፡፡ በቃ ኢህአዴግ የሚመጥነው እንደ አቶ ግርማይ አደራ ያሉ ፖለቲከኞች ናቸው፡፡ ምርጫቸው ነው እና ማክበር አለብን፡፡ አቶ ግርማይ አርማው ጋሻና ጦር የሆነ እድር ቢኖራቸው ችግር የለኝም ነገር ግን እርሳቸውም ሆነ የእርሳቸው ፓርቲ በሚሰጡት አመራር በማጠቃለያ እንደነገሩን በምግብ እህል ራሷን የቻለች ኢትዮጵጰያ ሊዚያውም ተርፎዋት ኤክስፖርት የምታደርግ ሀገር አይሰሩልንም፡፡ ለኢትዮጵያዊ የቀረበለት ከዝንጀሮ ቆንጆ መረጣ ነው፡፡

“ድንኩ አንድነት” እንደ ተለመደው በትዕግስቱ አወሉ የተወከለ ሲሆን በረዳትነት የተመደበለት ደግሞ አቶ ዮሐንስ አሰፋ ነው፡፡ አቶ ትዕግሰቱ በቴሌቪዥን በክርክር የሰንብት ክርክሩን አድርጎ ሄዶዋል፡፡ እኛም ተገላገልን፡፡ ባለፈው ድንኩ አንድነት የአንድነት ፓርቲ ውስጥ አባል ያልሆነ ሰው ለክርክር ቀረበ ብለን ትንሽ ተንጫጭተን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በረዳትነት የመጣው አቶ ዮሃንስ አሰፋው ለጫጫታ መነሻ የሚሆን አወዛጋቢ ግለሰብ ነው፡፡ ዮሐንስ በወረዳ 24 ውስጥ፣ ገዢውን ፓርቲ ወክሎ ወረዳውን ሲያምሰ የነበረ ነው፡፡ የሴራው ማጠንጠኛም አስራት አብርሃም ነበር፡፡ ፓርቲው አምኖበት በከፍተኛ ሃላፊነት ላይ ያስቀመጠውን ሰው የወያኔ ተላላኪ ነው እያለ ውንጀላ ሲያደርግ፣ በአስራት አብርሃም ደረጃ አሰተዋጽኦ የሚያደርግ ከየትም ቢመጣ ችግር እንደሌለብን አሰርደቼው ነበር፡፡ ለነገሩ ፓርቲውን ለመፍረስ ከሚያሴሩት ጋር በግልፅ እንደሚሰራ እያወቅን በዝምታ ያለፍነው የውስጥ አርበኛ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በአሰራት አብርሃም ቦታ ወረዳ 24 ዕጩ ሆኖ የቀረበ ሲሆን ለትዕግሱቱ አወሉ ቡድን በቂ አማካሪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ከዚህ የተሻለ ከትዕግሱቱ ጎን ማግኘት አጉል ነው የሚሆነው፡፡ ትዕግስቱም የልኩን አማካሪ ኢህአዴግም የሚመጥነውን ተቃዋሚ አግኝተዋል፡፡

ትዕግሰቱ የአንድነትን የፖሊሲ አማራጭም ሆነ ዝርዝር የኢህአዴግን የአፈፃፀም ክፍተት በተሟላ ይዞ ሊቀርብ እንደማይችል ማንም ያውቃል፡፡ በድፍረት ግን “የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ በአሰቸጋሪ ሁኔታም ቢሆን አንድነትን ምረጡ” የሚል ቃል እንዴት ሊወጣው እንደቻለ አልገባኝም፡፡ ከሁሉም ያስገረመኝ ደግሞ “ኢህአዴግ የመሬት ፖሊሲ የምቀይረው በመቃብሬ ላይ ነው” ይላል በሚል የሰጠው አስተያየት ነው፡፡ ኢህአዴግ ለስልጣኑ ዋልታና ማገር ያደረገውን የመሬት ፖሊሲ በመቃብሬ አለ የሚለው ትዕግሰቱ አወሉ እልህ ምላጭ ያስውጣል በሚል መፈክር ከራሱ ሌላ አንድ ሌላ ድምፅ ለማግኘት ያልቻለበትን አንድነት ፓርቲን ከምርጫ ቦርድ እና ከገዢው ፓርቲ ጋር እርሱ በሚያውቀው መስመር ተመሳጥሮ ድንክ ያደረገ ግለሰብ፣ ታንክና ባንክ ለማዘዝ የሚያሰችል ስልጣን የሚያስገኝን የመሬት ፖሊሲ በመቃብሬ ላይ ቢባል ምን እንደሚያስገርም አልገባኝም፡፡ ትዕግሰቱ አወሉ ታንክና ባንክ የሚያዝ መንግስት ቢሆን ብዬ ሳሰበው ዘገነነኝ፡፡

አቶ ትዕግሰቱ አወለ በክርክሮች ሁሉ ቀና ብሎ የቴሌቪዥን ካሜራ ለማየት ማፈሩ ተገቢ ሆኖ ባገኘውም የሚያፍር ከሆነ ለምን ቴሌቪዥን ላይ እንደሚመጣ ነው የማይገባኝ፡፡ አንድነት አማራጭ እንዳለው ሰንድ ማሳየት ይቻላል ያለው ትዕግሰቱ የአንድነትን ፕሮግራመ በቅጡ ማንበብና መዘጋጀት ሳይችል (የምርጫ ማኒፌስቶ እርሱ ሊያገኘው አይችልም፣ ቢሮ ዕቃ በጉልበት ሲዘርፍ በአባላት ጭንቅላት የሚገኝ እውቀት ግን በእርሱ እጅ አልገባም) የዛሬ አምስት ዓመት የተዘጋጀውን ሰትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ለዚያውም በመግቢያ ላይ የተፃፈውን ሰለ ዜጎች ሰደት የሚያወራውን ክፍል ለግብርና ክርክር ይዞ ሲቀርብ፣ “የድንኩ አንድነት” ተወካይ መሪ አቶ ትዕግሰቱ ለመዘጋጀት ፈተና የሆነበት ምን ያህል የውስጥ ሰላም አጥቶ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው፡፡ አንድነት በየትም ቦታ ዜጎች ወደ ከተማ መምጣት ችግር ነው ብሎ አያውቅም፡፡ ይልቁንም ችግር ከሆነ እንደ ችግር የሚያየው ዜጎች ከመሬት ጋር ተጣብቀው በገጠር እንዲኖሩ መደረጋቸወ ነው፡፡

ሌላው ያስገረመኝ የጥርሶቹ ማለቅ ሲሆን (መለስ መላጣ ማለት ይቻላል፣ መንካት ግን አይቻልም ባለው መሰረት)፣ እንዴት ነው አሁን ያለው የገንዘብ ፍሰት ለዚህ የሚሆን እንጥፍጣፊ የለውም ወይ? የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል፡፡ ከዚህ በፊት ጥርሳቸውን ያስተከሉ መሪዎች በፓርቲው ገንዘብ ነው እያለ እርሱ ሲያወራ ስለነበር ነው፡፡ ለማነኛውም “ሞያ በልብ ነው አንድነትን ምረጡ” ያለው ትዕግሰቱ በግሌ የወረዳ 8 ነዋሪ ከራሱ በስተቀር አንድም ድምፅ እንዳያገኝ በማድረግ እንዲያዋርደው በማክበር ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ በሰፈሩ ያሉት እድሮችና የትዕግሱ የማሪያም ፅዋ ማህበርም ይህን እንዲያስተባብሩ እና ትዕግሰቱ ከራሱ በስተቀር አንድም ድምፅ እንዳያገኝ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን የኢህአዴግ ኮካዎች ማህበራዊ ማግለል ወንጀል ነው ይሉታል፡፡ በትዕግስቱ ላይ ማህበራዊ ማግለል ወንጀል የሚሆንበት ህግ ካለ ለመማር ዝግጁ ነኝ፡፡ መቼም ትዕግሰቱን በመወከል ታዛቢ ይኖራል ብዬም አላምንም፡፡ በተጨማሪ የአንድነት ደጋፊዎችም ትዕግሰቱ ከራሱ ሌላ አንድም ሌላ ድምፅ እንዳያገኝ ጠንክረው መስራት ይኖርባቸኋል፡፡ ይህን ሳናደርግ ብንቀር ሌሎች ትዕግሰቱዎች ለዚህች ሀገር እየጋበዝን መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ አንድነት ዋንጫ የሚያነሳው ትዕግሰቱና የትዕግሰቱ ቡድን ድምፅ ሲያገኝ ሳይሆን እነርሱ ተገቢውን ውርደት ሲከናነቡ ነው፡፡

ኢድአን አቶ ግዑሽ ገ/ሥለሴ እና ትዕግስቱ ዱባለ በተባሉ አባላቱ ተወክሎ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ አቶ ግዑሽ ገ/ሰላሴ በ2002 ምርጫ ወቅት መድረክ ሞቅ ያለ የምርጫ ስራ ላይ እያለ “ኢድአን ከምርጫ ወጥቶዋል” በሚል መድረክን ያመሱ ግለሰብ ናቸው፡፡ በምርጫ ወቅት የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎችን የሚያዳክምበት መሳሪያ ናቸው፡፡ ከምርጫ በኋላ እዚህ ግባ በሚባል ፖለቲካ ውስጥ ጉልዕ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይታዩም፡፡ አቶ ግዑሽ ካቀረቡት ክርክር ነጥብ አድርጌ የያዝኩላቸው “ … እሰከ መገንጠል መብት የሰጠ መንግሰት፣ ለአርሶ አደሩ መሬትን እሰከ መሸጥ ለምን መስጠት ፈራ” የሚለው ነው፡፡ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት እሰከ መገንጠል ስለተሰጠ የተገነጠለ የለም በሚል የሚከራከረው ኢህአዴግ አርሶ አደሩ እሰከ መሸጥ የሚደርስ መብት ቢያገኝ በመሬቱ ተጠቃሚ ከሆነ አይሸጠውም የሚል መርዕ እንዴት ሊገባው አልቻለም የሚል ነው፡፡ ተዋዋሚዎች ትንሽ ከሚሏት የክርክር ደቂቃ ሁለት ደቂቃ ያገኘው የአቶ ግዑሽ ረዳት አቶ ትዕግሰቱ ዱባለ ያገኛትን ሁለት ደቂቃ በቅጡ የሚረባ ነገር ሳይናገር ላብ በላብ ሆኖ ወጥቶዋል፡፡ ከእንቅልፉ ድባብ ተቀስቅሶ በመናገሩ የተቸገረ ነው የሚመስለው፡፡ ኢህአዴግ የመጨሻውን ማጠቃለያ መስጠቱን ዘንግቶ ለኢህአዴግ ጥያቄም አቅርቧል፡፡ ለማነኛውም በማጭድ ምልክት ዘመናዊ የግብርና መሳሪያ በድጎማ ማቅረብ አማራጭ አድርጎ ያቀረበልን ኢድአን ከቁም ነገር የሚቆጠር አማራጭ ነው ብለን ልንወሰደው እንቸገራለን፡፡ እንኳን ሌሎች እንዲመርጧቸው ልንደግፋቸው አይደለም የራሳቸው “ከተመረጥን” የሚለው ድምፅ ለመመረጥ እንዳልተዘጋጁ የሚያሳጣ ነው፡፡

መድረክ ተወክሎ የገባው በአቶ ጥላሁን እንዳሻው እና በአቶ ሙላቱ ገመቹ በሚባሉ አባላት ሲሆን፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን በዋነኝነት ሊከራከረው የገባው ከላይ እንደገለፅኩት ከመድረክ ጋር ብቻ እንደሆነ ያስታውቅ ነበር፡፡ መድረክ በመጀመሪያ ሰድስት ደቂቃ አንዱን ደቂቃ ጊዜው ትንሽ ነው በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ጊዜ ያባከነ ሲሆን፤ በተጨማሪ መልስ በሌላቸው ህገመንግሰታዊ ድንጋጌዎችና ትርጉም ጊዜውን እንዳባከኑት ይሰማኛል፡፡ በእኔ ግምት በመሃል የተቆረጠ በሚመስል ሁኔታ አምሰት ደቂቃ የሚሞላ ሀሳብ አልሰማንም፡፡ ኢቲቪ ኢህአዴግን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ የቆረጠው ሃሳብ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ መድረክ በቀጣዩ በነበረውን ዘጠኝ ደቂቃም ቢሆን ኢህአዴግ ላቀረበለት ጥያቄ መልስ በመስጠት፣ ለምሳሌ በሚል የአቶ ጥላሁን እንዳሻው ትውልድ አቅራቢያ ቦታዎች ላይ የሚገኙ የመሬት መፈናቀልና የመሰረተ ልማት እጥረትን በመዘርዘር ለክርክሩ የሚመጥን ነበር ለማለት የሚያስቸገር ሃሳብ ሲያቀርቡ ነበር፡፡ በ2002 አቶ ጥላሁን እንዳሻው በተመሳሳይ ርዕስ ተከራካሪ የነበሩ ሲሆን ይህን ልምድ ይዘው በተሻለ የመቅረብ እድሉ ቢኖራቸውም ሊጠቀሙበት አልቻሉም፡፡ ከመድረክ ክርክር ነጥብ የሚወሰድ ከሆነ በልማት ሰራተኛ ስም የተሰገሰጉት ካድሬዎች ጉዳይ ሲሆን ኢህአዴጎች ይህን ከሰራተኞቹ ጋር ለማጋጨት ሊጠቀሙበት የሞከሩ ቢሆንም በልማት ሰራተኛ ሰም በገጠር የሚንከራተቱት ሰራተኞች ይህን ተጨማሪ ያለፍላጎታቸው የሚሰጣቸው ሰራ እንደማይወዱት ለሚያውቅ የኢህአዴግ መንገድ የሚሳካ አይመስለኝም፡፡ በክርክሩ የመጨረሻ ተከራካሪ መሆን ያለውን ከፍተኛ የማጥቃት እድል በማያሰፈልግ ሁኔታ ከረዳታቸው ጋር የተካፈሉት አቶ ጥላሁን ረዳታቸውም ምንም አዲስ ነገር ሳይነግሩን ክርክሩም እንዲያበቃ አደርገውታል፡፡

በእኔ እምነት ኢህአዴግ አሁንም ቢሆን መንግሰት ሆኖ ያከናወናቸውን ስራዎች ይህን ማድረግ የማይችሉትን ተቃዋሚዎች መክሰሻ አድርጎ ለማቅረብ ሲሞክር ከመስማት የበለጠ አሳፋሪ ነገር የለም፡፡ ይህ ማለት ግን ተቃዋሚዎች በያዘው ስልጣን ሊያከናውን ያልቻለውን፣ በተለይ ደግሞ ባለፈው አምስት ዓመት በግብርና ዘርፍ አሳካዋለሁ ብሎ ያላሳካቸውን ነጥቦች አንሰተው ደካማ መሆኑን ማሳየት አይችሉም ማለት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አሁን የሚሞግተን የግብርና ፖሊሲና ስትራቴጂ፤

· ባለፉት 24 ዓመታት ይህችን ሀገር በምግብ እራሷን እንድትችል ባለማድረጉ የሚከሰሰበት ዋነኛ ነጥብ ነው፡፡ በሃያ አራት ዓመት አሁንም አዝማሚየ በሚባል ሁኔታ መሆናችን ተቀባይነት የለውም፤

· በኢትዮጵያ ሀገራችን በገጠር የሚኖረው ህዝብ ባለፉት 24 ዓመታት ከነበረበት 85 ከመቶ ወደ 83 በመቶ ብቻ ነው ዝቅ ሊል የቻለው፡፡ ይህ ደግሞ በአፍሪካ ደረጃ ከተሜነት 50 ከመቶ በላይ በደረሰበት ወቅት እጅግ አሳፋሪ ሲሆን፤ ይህን እንደ ነጥብ አንሰቶ የሚሞግት ያለመኖሩ ከዚያ ይልቅ የገጠሩ ህዝብ ወደ ከተማ እየፈለሰ ነው የሚል ቅሬታ የሚያሰሙ ተቃዋሚዎች መኖራቸው የሚያሳዝን ነው፤

· የከተሜነት ያለመስፋፋት፣ ዜጎች በገጠር ከመሬት ጋር ተጣብቀው እንዲኖሩ እያደረገ ያለው ደግሞ፤ ኢህአዴግ በውሸት ኤኮኖሚያዊ ምክንያት የሚለው ነገር ግን ፖለቲካው ምክንያት የሆነው መሬትን ህገመንግሰት ውስጥ መደንቀሩ ነው፤ ይህን ፖለቲካዊ የሆነ ጉዳይ ኤኮኖሚያዊ ነው ብለው ምንአልባት ከፓርቲው አቋም ውጭ የግብርና ሚኒሰትሩ ሃሳብ ሲሰነዝሩ የሚሞግታቸው አላገኙም፤

· ኢህአዴግ መሬት መሸጥ መለወጥ የሚለውን ሃሳብ ሲያነሳ መሬት የሚገዙ ጥቂት የሚላቸው ዜጎች መሬቱን የሚገዙት ምርት ለማምረትና ለማትረፍ በዚህም ሀገራችንን በምግብ እህል ራሰን ከመቻል አልፎ ኤክሰፖርት ለማድረግ መሆኑ ቀርቶ ለቀብራቸው መሬት የሚገዙ ያሰመስለዋል፡፡ መሬቱን ሸጦ የሚፈናቀል አርሶ አደር ደግሞ በሌሎች አገልግሎት ዘርፍ የማይገባ፣ ከመሬት ጋር ብቻ ተጣብቆ እንዲኖር የተፈረደበት ያሰመስልብናል፡፡
ባጠቃላይ በእኔ እምነት የ1997 የግብር እና የገጠር ልማት ስትራቴጂ ክርክር በድጋሚ ይቅረብልን ብዬ ማጠቃለል መርጫለሁ!!!

ቸር ይግጠመን!!!!!!!

The post የምርጫ ክርክር ሶስት- ግብርና እና ገጠር ልማት (ከግርማ ሰይፉ ማሩ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያ አንድነት ፈተናዎች –ከአበበ ከበደ

$
0
0

የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሃገር ኢትዮጵያ በቀደሙት ዘመናት ክፉ ነገሮችን የምትከላከል፣ የደጋጎችና የቅን ሰዎች መኖርያ እንደነበረች ታሪክ ያስረዳናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃገሬን አትንኩ” ይል እንደሆን እንጂ ከማንም ጋር በልቶ፣ ጠጥቶ ከመሸበት የሚያድር የዋህ ፈሪሃ አምላክን የተላበሰ ሕዝብ ነው። ኢትዮጵያ ሕዝቡን በፍትህና በጥበብ የሚያስተዳድር ጀግና መሪንም የምታገኘው ከእግዚአብሄር ነበር። ኢትዮጵያ ሃገሯና ሊወር የመጣን ጠላት ድባቅ የምትመታው እግዚአብሄር ከፊት ቀድሞ ስለሚዋጋላት እንጂ ከሌሎች የበለጠ የፈረጠመ ጡንቻ ኖሯትም አልነበረም። ይህ ሁሉ ታሪክ ምስቅልቅሉ የወጣው ኢጣልያ ዳግም ኢትዮጵያን ከወረረች በኋላ ነው። ራሷ ኢጣልያ በኤርትራ የቆየችበት ዓመታትም ዋናውን የአንድነቱን ማብከኝያ መርዝ በቅርብ ሆና ለመቀመም የቻለችበት ኢትዮጵያን የጎዳ ዘመን ነበር። የኤርትራ ጉዳይ እንደመዥገር ሆኖ ከኢትዮጵያ ገላ ላይ አልላቀቅ ያለውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው። የኤርትራ ከእናት ሀገሯ ጋር የተደበላቀችበት ጥበባዊ ሥራ በምእራብያውያኖች፣ በመካከለኝው ምሥራቅ ፖለቲካ መዘዝ፣ በግራ ክንፉ የሥልጣን ትንቅንቅ ሳብያና በፖለቲካ መሪዎቹ አናሳ ብስለት ምክንያት ተጨናገፈ። የግራው ክንፍ ፖለቲካም ከኢጣልያ መሠሪ አሰራር ልምዱን ባገኙ ኤርትራዉያን ፖለቲከኞች ሲመራ ቆይቷል። ሻዕቢያ የፊትና የኋላውን መመርመር ያልቻሉትን ግለሰቦች በመደለል፣ የነቁትን በማግለል፣ ላንዳንዱ ደግሞ ሥልጣን መዳረሻ የሚሏቸውን የሃሰት ሥልቶች አስታቅፈው፣ ሲቻል እያፋጇቸው ሳይቻል እያነታረኳቸው፣ ዓላማቸውን ከንቱ ለሆነውና እርባና ቢሱ የኤርትራ ግንጠላ አዋሉት። ኤርትራም በከንቱ ተገንጥላ ለመከራና ስደት ስትዳረግ ኢትዮጵያና የዋህ ሕዝቧ በቆሸሸው ፖለቲካ ውስጥ ተነከሩ።

የኢትዮጵያ ችግር በአብዛኛው መንፈሳዊ ነው። ፀሎት ሥጋዊ ሆኗል፣ ፖለቲካው አስመሳይ ሆኗል። ድህነቱ አዋራጅ ሆኗል። አብዛኛው ሰው ከደረሰበት ችግር ለመላቀቅ የእግዚአብሄርን መንገድ ትቶ ለምእራቡ ዓለም ሰግዷል። ለንዋይ መምበርከኩ ታቦትና ጽላት እስከመሸጥ ድረስ ደፋር አድርጓል። ስደቱ ማንነቱን ከመለወጡ አንስቶ ወደ ሌላ አሳፋሪ ድርጊት ተሸጋግሯል። አሁን ግን አምላክ በቃ እንዲለን ከዚህ በታች የምዘረዝራቸውን የመፍትሄ ሃሳቦች ሳላንዛዛ ባጭሩ ለማቅረብ እሞክራለሁ። ይህ ከዚህ ቀደም ብዙ ቢባልለትም እኔ ለማስታወስ ያህል እንደገና እንዲህ አድርጌ አቀርበዋለሁና በጥሞና አስተውሉት።

ኢትዮጵያ ማነችኢትዮጵያዊስ

ኢትዮጵያ ከሰባት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በኅልውና የቆየች እግዚአብሄር አላማውን ለመፈጸም ሲል ከሚታይና ከማይታይ መከራ እየከለለ ያቆያት የዋህና ጀግኖች ሕዝቦችን ያቀፈች በአፍሪካ ቀንድ አሕጉር የምትገኝ ሃገር ነች። ኢትዮጵያ የጽላቱና የታቦቱ ምስጢር የተገለጠባት፣ ጥንታዊ የሆነ የራሷ ጽሑፍ ያላት፣ ከእግዚአብሄር ምልክቷ ይሆን ዘንድ ልዩ ባንዲራን የለበሰች በአምላክ ልዩ ጸጋ የምትደዳደር ሃገር ነች። ነብር ዥንጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን መቀየር አይቻለውም። ኢትዮጵያዊ ድህነት፣ ችግርና መከራ ተንበርካኪ የማያደርጉት ጀግና ነው።

ቅናት ምንድነው?

ከእግዚአብሄር ልዩ ጸጋን የታደለ ሃገርም ይሁን ግለሰብ አርፎ አይተኛም። ቀናተኛው ዲያቢሎስ ይግደራደራቸዋል። የቃል ኪዳኑ ታቦት ቤት የሆነችው ኢትዮጵያም ከቀናተኞች ዓይነጥላ አትሰወርም። የእግዚአብሄር ቃል ኪዳን መፈጸምያዋ እስራዔልም ብትሆን ችግሮች ተፈራርቀውባታል። ዲያቢሎስ እስራኤልንም ኢትዮጵያንም ፋታ አይሰጣቸውም። እናንተ እሥራኤሎች ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ አይደላችሁም” የሚለው የእግዚአብሄር ቃልም እሥራኤል በኢትዮጵያ ላይ ፊቷን እንድታዞር ያደርጋታል። መንፈሳዊ ቅናት ተፈጥሯዊ ነው፣ መጠኑ የበዛ ሥጋዊ ቅናት ግን የሰይጣን ነው። ያእቆብ በልጆቹ መካከል ያደረገው ልዩነት ነው ቅናትን አሳድጎ ታናሽ ወንድማቸውን ዮሴፍን ወደ ጉድጓድ እንዲወረውሩ የገፋፋቸው። ኢትዮጵያውያኖች ቀድሞ በግዕዝ ቋንቋ ይጠቀሙ ነበር። የኋላ ኋላ እስከዛሬ ድረስ የመንግሥቱ መጠቀምያ የሆነው ቃንቋ አማርኛ ግዕዙን ተካ። በአማርኛ ቋንቋ ላይም ቅናት ተበራከተ። ኢትዮጵያ ሁሉንም ታላላቅ ኃይማኖቶች ማለትም ክርስትናን፣ እስልምናንና የአይሁድ ኃይማኖትን አካታለች። ሶስቱ ኃይማኖቶች በመሃላቸው የቀኖና ልዩነት አላቸው። ልዩነት ውበት መሆኑ ቀርቶ ውዝግብ የሚያደርገው ቅናት ነው። ዮዲት ጉዲት በአይሁድ ኃይማኖት ሥር ለማካተት እልቂትን ስታመጣ ግራኝ መሃመድም ወደ እስልምናው ለመጠቅለል ለአስራ ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ላይ አውዳሚ ዘመቻ አወጀባት። ቅናት ከብልሹ ስሜት ይመነጫል። አንዳንድ ጊዜ ከፍርሃት አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የፍላጎት መጠን መንዛዛት የቅናትን ስሜቶች ያሳድጋሉ። ኢትዮጵያ ዙርያዋን በከበቧት ቅናቶች ሳብያ ዘወትር ትመሰቃቀላለች፣ ትቦረቦራለች፣ ትከሳለች። ከእጇ የጎረሱት፣ ውሃዋን የተጎነጩት እንኳን ተረከዛቸውን ያነሱባታል። በገዳማቱ ባሉ እውነተኞች አባቶችና እናቶች ጸሎት ይኸው በኅልውና አለች።

ቅናት በዘመናዊ ፖለቲካ ሲቀመም

ከኢጣልያ ዳግም ወረራ በኋላ ኢትዮጵያን የሚያጠፋው መርዘኛው ፖለቲካ በቅኝ ግዛት በተያዘችው በኤርትራ ውስጥ ይቀመም ጀመር። ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የሚጨቆኑባት ሃገር ነች አሉ። አማርኛ ቋንቋን መጨቆና መሣርያ አድርጎ ለማሳየት ከቅኝ ግዛት አስተዳደሩ ውክልናን ያገኙ ሰዎች ከማርክሲዝም ሌኒኒዝም ቀኖና ጋር ለውሰው የቀድሞ ቅናታቸውን አነባብረው አማራው ሌሎች ብሔረሰቦችን በጭቆና ይገዛል” የሚል አጥፊ ሃሳብ ፈበረኩ። ተከታታይ የነበረውን የኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር ላንዴና ለመጨረሻ ለመናድ ከ ሀ እስከ ፐ ያለውን አማርኛ ፊደልንና አማራ ሕዝብን ጨቋን ጭራቅ አድርጎ የመሳሉ ተልዕኮ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማህበራዊ አኗኗርንና የዋህነቱን በሚገባ ለሚረዱት ሠርጎ ገብ አጥፊዎች የቤት ሥራ ተደርጎ ተሰጠ። በዚሁ መሠረት የሻዕቢያ ተላላኪዎች በተማሪው እንቅስቃሴ ኋላም በተለያዩ ጊዜዓት በተመሰረቱት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በደርግም ጭምር፣ ሠርገው በመግባት ሌሎች ኢትዮጵያ በሚጠሉ ሃገሮች እየታገዙ ለኤርትራ ግንጠላና አዋሉት። ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ስለተባለ ይህን ብቻ ባጭሩ አስቀምታለሁኝ። ሻዕቢያ በዲያቢሎስ ቅናት ተገፋፍቶ አማራን ጭራቅ አድርጎ ስሎ ሲያበቃ ጥቂት ግለሰቦችን በማሰባሰን ፀረ አማራውን ኦነግን መሠረተ። ይህ ትልቁ መሠርያዊ ተግባር ለጊዜው ተሳክቶለት ራሱ ሻዕቢያ ኤርትራን ሲያስገነጥል፣ ማለሊት ኋላም ሕወሃት ለስልጣን በቅቶ ሻዕቢያ ሠራሹን ኦነግን እንደ ጉም በተነ። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ስለሚጠብቅ ቋንቋቸውን አደበላልቆ በሻዕቢያና ሕወሃት መካከል ያለውን ስምምነት በብረት መጋረጃ ጋረደው። ሆኖም ግን ሕወሃት ከወንድሙ ሻዕቢያ በተማረው መሠረት አማራን ይበልጥ ጭራቅ አድርጎ ስሎ በርካታ ዘርን ማዕከል ያደረጉ ድርጅቶችን ፈጠረ። አማራ ሊመጣባችሁ ነው ራሳችሁን ጠብቁ” እያለ እያሞኛቸው በስልጣን ወንበሩ ላይ ለረዥም ዓመታት ተቀመጠ።

መፍትሄ ያመጣሉ ብዬ የገመትኳቸው ሃሳቦች

አንደኛ፣ እኛ ኢትዮጵያውያኖች ዘመናዊው ዘመነ መሳፍንት ውስጥ ሳናውቀው ድንገት ተዘፍቀናል። በመሆኑም በአጼ ቴዎድሮስ፣ አጼ ዮሃንስና አጼ ሚኒልክ ዘመን የነበረውን የቀደመውን ፍቅርና አንድነትና ጀግንነት ዳግም መመለስ ይገባቸዋል። ሶስቱም ነገሥታት አማርኛ ቋንቋን የመንግሥት ቋንቋ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር እንጂ አማራን ጨቋኝ አድርገው አልሳሉም። ራዕያቸውም ሆነ የነጋ ጠባ ምኞታቸው ኢትዮጵያን አንድ ማድረግና ከውጭ ጠላቶቿ መጠበቅ ነበር። አጼ ቴዎድሮስ ራዕያቸው አንድነት በመሆኑ ነው ሃሳባቸውን የተቃወሟዋቸውን የራሳቸውን ዘመዶች ሳይቀር ያስወገዱት። አጼ ዮሃንስ አማራን ቢጠሉ ኖሮ አማርኛን አስወግደው በትግሬኛ ቋንቋ ለመተካት ሙከራ ያደርጉ ነበር። አጼ ሚኒልክ በዘር ቢያስቡ ኖሮ ራስ ጎበናን፣ ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ወይም ደጃዝማች ባልቻን ለትልቅ ሥልጣን አያበቋቸውም ነበር። እኛ ኢትዮጵያውያኖች ይህን መልካም መንፈስ ዳግም እንድንላበስ ማስተዋላችንን ዳግም ማደስና ለመሆኑ ወዴት እየተጓዝን ነው?” ስንል መጠየቅ እንዲሁም መፍትሄ ማፈላለግ ይኖርብናል።

ሁለተኛ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አባቶች በቤተ ክርስትያኗ መሃከል የተፈጠረውን ክፍፍል ለመቅረፍ መንፈሳዊ መላ ማፈላለግ የሚኖርባቸው ይመስለኛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ኃያል የነበረውን የቅኝ ግዛት ወረራርን ለመቋቋም ከጀግኖች አባቶቻችን ጋር አብራ መዝመቷን ከታሪክ ተምረናል። በግራኝም ሆነ በኢጣልያ ፋሺስት ወረራ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በዱር በገደሉ ተሰዳ እየጸለየች እስከዛሬ ገድላቸው ምሳሌና ጥንካሬ የሆነልንን እንደነ አቡነ ተክለሃይማኖትንና አቡነ ጴጥሮስን የመሳሰሉ መስዋዕቶችን አፍርታለች። ዛሬ በስደት የሚኖሩት ወገኖች ለሁለት ተከፈለው ከፖለቲካ ጉዳይ በባሰ ሁኔተ የሚነታረኩትና አንዱ ባንደኛው ላይ እጁን የሚቀስረው በሃገር ቤትና በውጭ ሁለት ሲኖዶሶች በመኖራቸው ሳብያ ነው። ተሳስቼ ከሆነ እርማቱን ለመቀበልና ለመማር ዝግጁ ነኝ። ቤተ ክርስትያኗ ለሁለት መከፈሏ ለጠላት እንዲሁም ኢትዮጵያን ለሚጠሉት ሁሉ አመቺ ሆኗል። እውነትን ደፍሮ የሚናገር ራሱን በንሥሃ አድሶ በቅዱስ ቁርባን አጽድቆ የሚተጋ፣ ለሌሎች ምስክርነቱን በተግባር የሚያሳይ፣ ግዳጁ በሥራ የሚታይ ጠፋ። ስነምግባር ተወላግዶ ግብረገብነት ተሰውሮ፣ ኃይማኖት ተንቃ፣ የሚፈራ የሚከበር ተዉ የሚል ዳኛ ጠፍቶ ሁሉም አንደኛውን ተገን አድርጎ እንዳሻው ይናገራል። ዲያቆኑ ቄስ፣ አስመሳዩ ዳኛ፣ ጉልበተኛው አገልጋይ፣ አዝማሪው ዘማሪ፣ ባለገንዘቡ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው እስኪቀርቡ ድረስ ታሪካዊዋ ቤተክርስትያናችን ህልውናዋ ደበዘዘ። ስለዚህ ጉዳይ በጥልቀት ለመናገር በቂ እውቀት የለኝም ነገር ግን የቤተክርስትያኗ ዋናው ሲኖዶስ መንበረ ፓትርያርክ ሃገር ውስጥ እግዚአብሄር እመረጣት ቅድስት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲቆይ በሃገርም በውጭም የሚገኙ መንፈሳዊ አባቶች እርቀ ሠላምን ፈጥረው፣ እግዚአብሄርን በጽኑ ተመርኩዘው በመጾም፣ በመጸለይና በእምነተ ተግባር በመንደርደር መንፈሳዊው ትግሉን በማጎልበት ኅያውን ቅርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲያስተላልፉ ስል ተንበርክኬ ልመናዬን አቀርባለሁ። ማንም ለእግዚአብሄር ሲል ቢሸነፍ በሰማዩ አባታችን እግዚአብሄር ዘንድ ትልቅ ሥፍራን ይጎናጸፋል። የምድር ነገሥታት ወይም ተጻራሪ አቋም ያላቸው ድርጅቶች እንኳን በዲፕልማሲው ስልት እየተግባቡ ጦርነትንና መናቆርን ያስቀራሉ እንኳንስ የእግዚአብሄርን አደራ የተሸከሙ ታላላቆቹ አባቶች ይቅርና። ቤተክርስትያናችን አንድነቷ ሲመለስ የሃገሪቱ መንፈሳው ችግር ይቀረፋል።

ሶስተኛ፣ ቢቻል የተማረው፣ የተመራመረው በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወደ ሃገሩ መመለስ ይገባዋል። ለሃገሪቱ ሙያዊ አስተዋጾ ማቅረብ የሚችሉት ሃኪሞች፣ ማምህራን፣ መተርጉማን፣ ደራስያን፣ መሃንዲሶች፣ የተግባረ ዕድ ባለሙያዎችና የማህበራዊ ሣይንስና ወታደራዊ ጠበብት ባጠቃላይም በችግሯ ጊዜ አብረዋት ሆነው አይዞሽ ሊሏት የሚገባቸውና በሰላማዊ ትግሉ የሚሳተፉ ደፋሮች ሁሉ ቢመለሱ ሃገሪቱ አሁን ከተዘፈቀችበት መከራ ትገላገላለች የሚል እምነት አለኝ። የተማረው ሁሉ ከተሰደደ የሥራ ዕድል እንዴት ይፈጠርሠብሎችንና ንጥረነገሮች ተቀምመው ለምርት ውጤት እንዴት ይብቁሃገሪቱን ከውጭ ጠላት ማን ይጠብቅበአሜሪካና አውሮፓ ላሉት ስደት ትልቅ የገቢ ምንጭ ወይም የድሎት ቤት መሆኑ ቢታወቅም እንኳን በሌላ በኩል ደግሞ ስደት የቅድስቲቱ ኢትዮጵያን ስም ማጉደፉን ልንገነዘብ ይገባናል። ስደት ኢትዮጵያዊና እስራኤላዊ ላይ አያምርም። ዜግነት በመለወጡ ከኢትዮጵያዊነት ቀለም ማምለጥ አይቻልም። ሠበባ ሠበብን ከምረው ራሳቸውን በማታለሉ ስልት የሚኖሩ ሁሉ እርካታ በሌለበት ሕይወት የሰባውን፣ የላመውን፣ የጣመውን እየበሉ መኖር ብቻ ነው ትርፋቸው። ኢትዮጵያዊነትን ለመለወጥ የሚያበቃ ኅሊና የማይታዘበው እውነተኛ ሠበብ ከቶም የለም።

አራተኛ፣ አማራው ጭራቅ አለመሆኑን የሚያሳይ አዲስ በቅን መንፈስ ላይ የተመሠረተ የቃል ኪዳን ማህበር ሊመሰረት ይገባል። የዚህ ማህበር አባል ሊሆኑ የሚገባቸው እውነተኞችና ራሳቸውን ለሃገሪቱ ሲሉ መሰዋዕት ለማድረግ የተዘጋጁ ከበቀልና ጥላቻ የራቁ ማስተዋልን የተላበሱ እንዲሁም ራስን በንሥሃ አንጸው ለኢትዮጵያዊነት የሚበቁ ደጋጎች ሊሆኑ ይገባል። አባላቱ ኢትዮጵያዊ የሆኑ፣ በውጭ ሲኖሩ ዜግነታቸውን ያለወጡ፣ በማንነቱ ቀውስ (identity crisis) ያልተበከሉ ወይም የለወጡትን ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን ሊያስመልሱ የተዘጋጁ ሊሆኑ ይገባል። አታክልትን ውሃ እንጂ ማር ቢያጠጡት አይበቅልም። ሃቀኛና ለመስዋትነት ያልተዘጋጁ ሰዎችን አባል ማድረግ ድርጅትን በቁጥር ብዛት ማሳደግ እንጂ በዓላማ፣ ተግባርና ጥራት አያጸናም። እውነተኞችና ደፋሮች ጥቂት ሊሆኑ ይችላሉ። ጥቂት እውነተኞች ግን ኃይላቸው ጠንካራ ነው። ቆራጥ ዓላማ የጽናት ድምር እንጂ የሰዎች ብዛት ብቻውን ቁጥር ነው። ዛሬ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት በዘፈቀድ ወደ ቤተክርስትያን የሚመላለሱትንም ሆነ ለማህበራዊ ጥቅም ሲሉ ልዩ ልዩ ድርጅቶችን የተቀላቀሉትን ወገኖች በማስተማር ወደ ትክክለኛ አስተሳሰብና እውነት እንዲመለሱ ለማድረግ የተማሩት፣ የተመራመሩት ሁሉ የማስተማር ግዴታ ቢኖርባቸውም የኃይማኖት አባቶች ደግሞ ከእግዚአብሄር የተቀበሉት ልዩ አደራ አለባቸው። 

አምስተኛ፣ እንደ ግንቦት ሰባት ያሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ከሻዕቢያ ጋር ያሰሩትን የቃል ኪዳን ቀለበት እንዲያወልቁ በቅጡ መገሰጽ ያስፈልጋል። ሻዕቢያ እንኳንስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርና አቅፈው ደግፈው፣ ገንዘብ አዋጥተው ሰልለውና አሰልለው ለስልጣን ላበቁት ወገኖቹም እንኳን በጎ አልሆነም። ሻዕቢያን መፍትሄ ያመጣልናል” ብለው ያሰቡት ትላልቆቹ ሰዎች ቀድሞ በትምህርት ቤት ሲማሩ አይጥ ሞቷን ስትሻ ስታበዛ ሩጫ፣ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ” የተባለውን የታሪክና ምሳሌ መጽሔትን ምሳሌያዊ አነጋገር አላነበቡም አይባልም። ህወሐትን ለመጣል ሻዕቢያን የመጠጋቱ ስልት እማዬ፣ ድመት የኛን የመሰለ ለስላሳ ቆዳ አለው የቀይ ስጋ ቁንጮ ራሱ ላይ ያለው ዶሮ ነው የሚያስጠላው” በማለት እናቷን ልታደናግር እንደሞከረችው የትንሽቱ አይጥን ተላላ ሃሳብ የመከተል ዓይነት ስልት ነው። ሻዕቢያን የጋረደው ራሱ እግዚአብሄር ነው። ይህ ሊገባን እንዲችል አድርጎ አምላክ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን ፈጽሟል። መገንጠሉ ባዶ ፖለቲካ ከመሆኑ አንስቶ ኢትዮጵያን መጠበቁ ራሱ ዋነኛ ምልክቶች ናቸው። አቶ ኢሳያስ ይህን እውነት አልተረዱም አይባልም ግን ሕዝቡን ይቅርታ ለመጠየቅ ባህርያቸው ገና አልፈቀደላቸውም። ኢሳት ባቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ ላይ በግራው ፖለቲካ ላይ ያካበቱት ችሎታቸውን በእብሪት መልክ እንደገና ሊያስረዱን ሞክረዋል። አቶ ኢሳያስ ብዙ ምልክቶችን አይተዋል፣ ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር የቃል ኪዳን ሃገር መሆኗንም ተረድተዋል ነገር ግን የኢትዮጵያን ቅድስትነትና የታሪኳን ገናናነት ገና አልተቀበሉም። ሻዕቢያ ቀድሞውንም ቢሆን እንደነ ፕሮፌሰር ጌታቸው፣ዶክተር ታዬ ወልደሠማያት፣ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ የመሳሰሉት ደፋሮቹንና ሃቀኞችን የፖለቲካና ታሪክ አዋቂዎች እንዲገለሉ የሚያስደርገው ኢትዮጵያን የማዳከሙ ዓላማ እንዲመቻችለት ነው። ሻዕቢያ እውነተኛ ኢትዮጵያዉያን ድርጅቶችንና ማህበሮችን እንዳይጠጉ ለማድረግ እንደ ፈረስ በሚጋልብባቸው ተላሎች፣ ወረተኞችና ጥቅመኞች ይታገዛል።

ስድስተኛ፣ ቀድሞ እሽቅድምድሙ የኢትዮጵያ አንድነትን ማጎልበትና ልዕልናዋን ማስጠበቁ ላይ እንጂ ለስልጣን መራወጡ እንዲህ እንዳሁኑ አሳፋሪ አልነበረም። የቀደመውን እንኳን ትተን የቅርቡን አንስተን ብንወያይ በንጉሡም በድርግም ዘመንችሎታ” እንጂ ዘር” ለስልጣን ክህሎቱ የሚያበቃ መስፈርት አልነበረም። ይህ የተበላሸው በግራው ፖለቲካ አስተሳሰብ ከአልቤንያ ኮሙኒስቶች ካባ የለበሰው ህወሐት ስልጣኑን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ሥልጣን የአንድነቱ ማስጠበቅያ መሳርያ መሆኑ ቀረ። ህወሐት በአናሳ ብሄረሰቦች ስም ሳይቀር የዘር ድርጅት መስርቶ መሳለቅያ አደረጋቸው። በመሆኑም ይህን የተሳሳተ ምግባር ለመቀየር ሁሉም ዘሩ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ማስረዳት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያዊነት ኃይማኖት፣ ጀግንነትና አንድነት ነው። ዛሬ አስፈሪ ሆኖ የሚታየውን በሻዕቢያ የሚታገዙትን የአልሻባብንና ኦነግን የሽብር ዛቻ ለመቋቋም ኢትዮጵያዊነትን ይበልጥ ማጎልበት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ የታላላቆቹ ኃይማኖቶች እስልምናና ክርስትና የጋራ መሰባሰብያ ቤት ነች። ይህ ሃገራዊ ጉዳይ ልል እንዲሆን የሚያደናግሩትን እውስጣችን የተሸሸጉትን የሻዕቢያ ጉዳይ ፈጻሚ ተላላኪዎችን ልንነቃባቸው ይገባል። ሌላው ቀርቶ ትግራይዋን ወገኖችን በማስጠላትና በማስገለል ድርጊቶቻቸውና ቅስቀሳቸው ላይም ቢሆን መተባበር የለብንም። ትግራይ የሚኖረው ወገናችንም ቢሆን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በደሎች የሚፈራረቁበት ሕዝብ ነው።

ሰባተኛ፣ ባዶ ስሜት ሊወገድ ይገባል። ባዶ ስሜት ሙያን ገደል። ባዶ ስሜት ጋዜጠኛ ሆነ። ባዶ ስሜት ፖለቲከኛ ሆነ። ባዶ ስሜት ጦረኛ ሆነ። ባዶ ስሜት ፓስተር፣ ቄስ ሼህ ሆነ። ከንቱ ስሜት እንደስካር ነው፣ እመስዋትነቱ መንደር ጫፍ ላይ ሳያደርስ ድንገት ይበናል። ልበ ደንዳናነት፤ ለጥቅመ ጥቅሞች ማነፍነፍ ወይም ፍርሃት ባዶ ስሜትን ያመነጫል። ልባቸው ያልተለወጠውን፣ ድፍረት ያለበሱትን፣ ሃቅን ያልተመረኮዙትንና ያልተማሩትን ያልተመራመሩትን ማሰለፉ ሽንፈትን ይጋብዛል። ለጥቅም በተሰለፉ ሰዎች ብዛት ድርጅት ቢፈላ ጠብ የሚላ ነገር የለም። ባዶ ስሜተኞች በዝተው እውነተኞች ካህናት የተናቁባትና ኃይማኖታዊ ምግባርን የማይተገብሩ ሰዎች የበዙባት ቤተክርስትያን መንፈሳዊነቷ ደካማ ነው፣ አታስተምርም፣ በቅዱስ ኪዳኑ ኃይማኖት አታፀናም፣ ፍቅር አታላብስም፣ ይቅር ባይ ልብ አትፈጥርም፣ ፍሪ አታፈራም፣ ቅንነት አታጎለብትም፣ ምዕመናን ያልተንዛዛ የኑሮ ሥርዓት እንዲከተሉ ወይም ሕይወትን በመልካምነት እንዲመሩ አታደርግም። ባዶ ስሜተኞች የበዙባት የፖለቲካ ድርጅትም መካን ነች። ለሥጋዊ ጥቅሙ የሚያደላና ለዕለት ኑሮው የሚጨነቅ ግለሰብ ለኃይማኖቱ፣ ለኢትዮጵያዊነቱም ሆነ ለወገኑ ደንታም የለውም። ደንታ ያለው እንዲመስል በባዶ ስሜት ይወራጫል፣ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል። ሲለቁት ደግሞ ተግባር የለም።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃል።

Comment

The post ኢትዮጵያ አንድነት ፈተናዎች – ከአበበ ከበደ appeared first on Zehabesha Amharic.

በቀልድ የታጀበው ምስክሮችን የመስማት ውሎ -የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ

$
0
0

ከዞን 9 ብሎግ የተገኘ የፍርድ ቤት ውሎ ዘገባ

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው የማስረጃ መስማት ውሎ ዛሬ ምስክሮችን በማስማት ተጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት አቃቤ ህግ ጉዳዬን ያስረዱልኛል ያላቸውን 17 ምስክሮች ያስመዘገበ ሲሆን 15ቱ በፍርድ ቤቱ ተገኝተው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ አቃቤ ህግ ችሎቱ በዝግ ችሎት አንዲሆን የጠየቀ ሲሆን ምስክሮቼ እና የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ችሎቱ በዝግ ሊሆን ይገባል የሚለውን አቤቱታውን ጠበቆች በከፍተኛ ደረጃ ተቃውመውታል፡፡ ምስክሮቹ የጭብጥ ምስክሮች ሳይሆኑ ፍተሻን የታዘቡ የደረጃ ምስክሮች በመሆናቸው እና ስማቸውም በግልጽ ተከሳሾች ጋር ስለደረሰ ምንም አይነት የደህንነተ ስጋት የለባቸውም ከሚለው የጠበቆች ክርክር በኋላ ፍርድ ቤቱ በጉዳዬ ላይ ተወያይቶ ለመወሰን ረፍት ወስዷል፡፡ በዚህም መሰረት የአቃቤህግን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ችሎቱ በግልጽ ሆኖ መስክሮች ምስክርነታቸውን እነዲያሰሙ ታዟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አቃቤ ህግ ያቀረባቸው ምስክሮች አነማን ላይ አንደሚመሰክሩ እና ምን አንደሚመሰክሩ በተጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱም በጠበቆቹ ስለተነሱት ነጥቦች የአቃቤ ህግን ምላሽ ጠይቋል፡፡ አቃቤ ህግም በዛሬው ዕለት የቀረቡት ምስክሮች በ2ኛ፣ በ3ኛ፣ በ5ኛ፣ በ6ኛ፣ በ7ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ( በስድስቱ የዞን9 ጦማርያን ላይ እና በጋዜጠኛ አስማማው ላይ ) ላይ እንደሚመሰክሩ ገልጾ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቡድን በብርበራ ያገኛቸው ማስረጃዎች ከተከሳሾች የተገኙ ስለመሆናቸው ያስረዱልኛል ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
zone 9 bloggers
በምላሹም መሰረት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ምስክርነታቸው ሰጥተዋል፡፡ ምስክርነታቸው ሲሰጡ በነበረበት ወቅት የተከሳሾችን ስም አለማወቅ አንዲሁም የተከሳሾችን መልክ አለመለየት የመሳሰሉት ጉዳዬች የተስተዋሉ ሲሆን ምስክርነታቸውን የሰጡት ሰዎች ስም ዝርዝር እና የምስክርነታቸው ጭብጥ በአጭሩ አንደሚከተለው ነው ፡፡

1.ሙሉጌታ መዝገቡ ለማ – ናዝሬት ነዋሪ ነኝ መአከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄጄ ፓሊስ ታዛቢ ምስክር አንድሆን ጠይቆኝ በዚያ መሰረት ምስክር ሆኜ ተገኝቻለሁ፡፡ ከአቤል ከኮምፒውተሩ ላይ ጽሁፍ ሲወጣ እና ሲፈርም አይቼ እኔም ፈርሜያለሁ ፡፡ የጽሁፉን ይዘት አላነበብኩም አንዳንድ ቦታ አፍሪካ ሪቪው ኬንያ የሚል ቃል አይቻለሁ የሚል ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡

2.በለጡ አበበ ዮሴፍ ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 32 ሲሆን ከፍተኛው ፍርድ ቤት የካ ምድብ ሰራተኛ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ በማን ላይ ለመመስከር እንደመጡ ሲጠየቁ በስም እንደማያስታውሱት ገልጸው በአካል ግን ለይተው አሳይተዋል፡፡ መስካሪዋ በ6ኛ ተከሳሽ ዘላለም ክብረት ላይ የሚመሰክሩ ሲሆን በተለየ ስም ሲጠሩት ተስተውለዋል:-
“የሽብርተኝነት ጉዳይ የሚያመለክት ይመስለኛል፡፡ ወደ 70 ገጽ አማርኛና 10 ገጽ እንግሊዝኛ ጽሁፍ ተገኝቷል፡፡ ያየሁትን አይቼ ፈርሜያለሁ፡፡” ካሉ በኋላ ተከሳሹስ ፈርሟል ተብለው ሲጠየቁ መጀመሪያ አላስታውስም ቢሉም እንደገና ሲጠየቁ ግን አዎ ፈርሟል ብለዋል፡፡

3.እታፈራሁ ጌታቸው ወልዴ የሚባሉ ሲሆን እድሜያቸው 36 ነው፡፡ በመንግስት ት/ቤት በአስተዳደር ሰራተኛነት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ማን ላይ እንደሚመሰክሩ ሲጠየቁ ፍቃዱ እና…..(ስሙ ጠፍቶባቸው ቆይተው) እ…አጥናፉ ብለዋል፡፡ በአካል ደግሞ በፍቃዱን አሳዩ ሲባሉ አጥናፍን አሳይተዋል፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ማእከላዊ ምርመራ ለግል ጉዳይ ሄደው ጽሁፎች ሲታተሙ ማየታቸውንና በፍቃዱ በፍቃደኛነት ሲፈርም ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ስለጽሁፎቹ ሲጠየቁ “የአማርኛ ጽሑፎች ናቸው፡፡ 60 ገጽ የሚሆን ‹ወያኔ ይውደም› ምናምን የሚል ጽሑፍ አይቻለሁ፡፡ እንግሊዝኛም አለው 10 ገጽ ይሆናል፡፡ በምስል ከውጭ ሰው ጋር ሆነው የሚነጋገሩትም አይቻለሁ፡፡ ይዘቱ ግን ግር ይለኛል፡፡” ብለዋል፡፡ አጥናፍን አስመልክቶ ደግሞ ‹‹የእሱንም በዚያው መልኩ ነው ያየነው፡፡ ዕለቱም ግንቦት 16/2006 ነው፡፡ ኮምፒውተሩ ላይ የነበሩትን ጽሁፎች እዚያ ለነበሩት ሲያሳይ ነበር፡፡ ጽሑፎችን አይቻቸዋለሁ….‹የጨለማው ቀን….የጨለማው ንጉስ› የሚል አይቻለሁ፡፡ ‹ኢትዮጵያ አንድ ናት› የሚልም አይቻለሁ፡፡ ወደ 30 ገጽ ይሆናል፡፡ ሁሉም ፕሪንት ተደርጎ ሁላችንም ፈርመንበታል፡፡››ብለዋል::
zone 9 ethioia1
ሶስቱ ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ጠበቆች በሂደቱ ላይ አስተያየት አለን በማለት፣ ዶክመንቶቹ ፕብሊክ ዶክመንት ናቸው በአደባባይ የተጻፉ ጽሁፎቻቸው እና በማንኛውም ቦታ የሚገኙ ስለሆኑ ዶክመንቶቹን ክደን አልተከራከርንም የእኛ ክርክር ዶክመንቶቹ ለወንጀል ስራ የሚበቁ አይደሉም ነውና በዚህ ጭብጥ ዙሪያ ምስክር መስማቱ ያብቃልን የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡አቃቤ ህግ በበኩሉ ሁሉም ምስክሮች አንዲሰሙልኝ እፈልጋለሁ በማለቱ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ያስረዱልኛል ካለ ይቀጥል በማለቱ ምስክሮቹ ቀጥለዋል፡፡ ጠበቆች መስቀለኛ ጥያቄ ሳይጠይቁ ተከታዬቹ ምስክሮች መሰማታቸው ቀጥሏል፡፡

4.አራተኛው ምስክር አፈወርቅ ካሳ ይባላሉ፡፡ የግል ሰራተኛ ሲሆኑ እድሜያቸው 46 ነው፡፡‹‹ቀኑ ሚያዝያ 18/2006 ነው፡፡ የተከሳሹ አስማማው ቤት ጠዋት 3፡00 አካባቢ ሲፈተሸ ታዛቢ ነበርኩ፡፡ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ ፓስፖርት…ብዙ ወረቀቶች ላይ ‹‹አዎ የእኔ ናቸው›› እያለ ሲፈርም አይቻለሁ፡፡ እኔም ፈርሜያለሁ፡፡ ቤተሰቦቹም ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ አብዛኛው ያየሁት የግል መጽሄቶችን ነው፡፡ ማህተምም አይቻለሁ፡፡ ደሞ ቢሮው ሄደን ላፕቶፕ፣ ፍላሽ፣ ሲዲ፣ መጽሔቶች አይቻለሁ፡፡ ፖሊስ የሚፈልገውን እየለየ ፈርመናል፡፡ ወደቢሮው የሄድነው በመኪና ነበር፡፡ ከዛ ደግሞ አድራሻችንን ይዘው ስለነበር ሰኔ 4….አይ 14/2006 ነው መሰለኝ ከማዕከላዊ ተጠርተን ላፕቶፕ ላይ የነበረውን ስዕሎችና የእንግሊዝኛ ንግግሮች ሲወጡ አይቻለሁ፡፡ የእኔ ነው ብሎ ሲፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡›› ብለው ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

5.አምስተኛ ምስክር አጌና አንከና ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 48 ሲሆን ነዋሪነታቸው አ.አ ነው፡፡ የሚመሰክሩት ደግሞ በ3ኛ ተከሳሽ ናትናኤል ላይ ነው፡፡ የምስክርነት ቃላቸው፣ ‹‹ሰኔ 17/2006 ለግል ጉዳይ ማዕከላዊ ነበርኩ፡፡ ከቀኑ 8፡00 ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ፖሊስ ጠይቆኝ ታዝቤያለሁ፡፡ ላፕቶፑ ላይ አማርኛ ጽሑፎች አይቻለሁ፡፡ ጽሑፎቹ የተከሳሹ ስለመሆናቸው አምኖ ሲፈርምባቸው ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡ ይዘቱን ግን አላነበብኩትም፤ አልተረዳሁትም፡፡ የገጹን ብዛትም አላስታውስም፡፡›› የሚል የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
36884-zone9-bloggers4
6.ስድስተኛ ምስክር ገብረጨርቆስ ገብረመስቀል ይባላሉ፡፡ የ50 ዓመት የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ ምስክሩ በአስማማው ላይ ለመመስከር እንደመጡ ቢናገሩም በአካል ግን ለይተው አላወቁትም፡፡ እንዲያውም አስማማውን አሳዩ ሲባሉ አቤልን አሳይተዋል፡፡

ከፍርድ ቤቱ ውሎ በኋላ አስተያየታቸው የሰጡት የተከሳሾች ጠበቆች አቃቤ ሀግ ያቀረባቸው ምስክሮች ወረቀት ሲፈረም አየን ከማለት ውጪ ምንም አይነት ለሂደቱ ቁም ነገር ያለው ምስክርነት የሚሰጡ አይደሉም ፡፡ ተከሳሾች ተገኘባቸው የተባለው ጽሁፍ የአደባባይ ዶክመንት ከመሆኑም በላይ አልተገኘብንም ብለን ክደን አልተከራከርንም በይዘቱ ላይ ክርክር ስላልተደረገ መስቀለኛ ጥያቄ ለማቅረብም ብዙ አልጨነቅንም ብለዋል፡፡አቃቤ ሀግ የወንጀሉን የመጀመሪያ ደረጃ ጭብጥ የሚያሳዬ ምስክሮችን ያቅርብ አይቅርብ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ የማስረጃ ማሰማት ሂደቱ ነገ ይቀጥላል፡፡

በተቃራኒው ምሳቸውን ችሎት ውስጥ የተመገቡት ሁሉም እስረኞች በጠንካራ መንፈስ ሆነው ሲጨዋወቱ እና ሲነጋገሩ ተስተውለዋል፡፡ የችሎቱ ተሳታፌዎች በምስክሮች መደናበር እየሳቁ ነበረ ሲሆን የዞን9 ወዳጆች አጋሮች ቤተሰብና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል፡፡

የዞን 9 ማስታወሻ

የዛሬውን አስቂኝ የፍርድ ቤት ውሎ ባልተካደ ነገር ላይ ወርቃማውን የተከሳሾች ሰአትም ሆነ የፍርድ ቤቱን የስራ ሰአት ማባከኑ የሚገርም ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ችሎቱ በግልጽ አንዲካሄድ መፍቀዱን በበጉ መልኩ ተመልክተነዋል፡፡ አቃቤ ህግ ለምስክሮቹ ደህንነት ሳይሆን የራሱን መዋረድ ለመቀነስ ሲል ችሎቱን በዝግ ለማድረግ መሞከሩ ተከትሎ የመጣውም የምስክሮች መወዛገብ ግልጽ የሚያደርገው ነው ፡፡ የዞን9 ጦማርያን አና ጋዜጠኞች ላይ የቀረበባቸው ማስረጃ በተለያየ ቦታ የጻፏቸው የራሳቸው እና የሎሎች የአደባባይ ምሁራን ጽሁፎች በመሆናቸው ጽሁፉ የእኛ መሆኑ ምስክር አያሻውም ፡፡ በተደጋጋሚ እንዳልነው ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው የታሰሩት ወጣቶች ክስ የጸፉት ጽሁፍ ይዘት ላይ ነው፡፡ የታሰሩ ወዳጆቻችንን ለመፍታት አሁንም አልረፈደም ፡፡

በዚህ አጋጣሚ ፍርድ ቤት ተገኝተው አጋርነታቸውን ለሚያሳዬ የዞን9 ወዳጆች ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ህገ-መንግስታዊ መብት ይከበር ፡፡

Source: ዞን9

The post በቀልድ የታጀበው ምስክሮችን የመስማት ውሎ -የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከፍትፍቱ አጉሩሱኝ ከመረቁ ፃመኛ ነኝ –ቢንያም ግዛው (ከኖርዌይ ኦስሎ)

$
0
0

Biniamየብዙሀኑ  የጣት ሽታ  እንደገደፈ ያሳብቃል። በጥቂትም ሆነ በብዙ ያልተነካካ ቢፈለግ በግራም ሆነ በቀኝ ቢነፍስ ፃሙን ያላፈረሰ ማግኘት አልተቻለም።ከፍትፍቱ አጉሩሡኝ ከመረቁ ፃመኛ ነኝ ብሎ እንክት አድርጎ ከሰለቀጠ ወዲያ ምንም  እንዳልገደፈ አፉን ጠረግ ጠረግ አድርጎ ባላየ ባልሰማ የሚጓዘው ተበራክቷል።  በዕንዶድም የማይነፃ ጣት! ከምን አይነት መረቅ ውስጥ ቢዘፈቅ ይሆን ? . . . ጠቢቡ ሠሎሞን በምሳሌው . . .  ስጦታ በስውር ቍጣን ታጠፋለች፥ የብብትም ውስጥ ጉቦ ጽኑ ቍጣን ታበርዳለች ያለው ትዝ አለኝ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያን የባለስልጣን ቢሮዎችን ሳስባቸው ምን ቢያምራቸው እንኳን  ምራቃቸውን ገርገጭ አርገው ውጥው ስርዓቱ እና ህጉን በማክበር ቢፃሙ ምን አለ?  ሁሉም ቢሮ ስጋ ስጋ ደም ደም ነው የሚሸተው። በፃሙ!

 

ትምህርት ሚኒስቴር፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ፍትህ ሚኒስቴር፣ ፌዴራል ፖሊስ ፣ ወህኒ ቤት፣ ሆስፒታል፣ ባንክ ቤቶች፣ ወ ዘ ተ . . . መጥቀስ እስኪታክት ድረስ ሁሉም በዋና ዋና  የሀጢያት አበጋዞች ተዘፍቀዋል። በተለይም በወያኔ ዘመን ያለቅጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘው  ብዙ በደለኞችን ፃድቅ አድርጎ ፍርድን እና ፍትህን በማጣመም አይን የሚያስውረው በሽታ   ምድሪቷን ጠፍንጎ ከመግቢያው የግሙሩክ መስሪያቤት ጀምሮ እስከመውጫው ኢሚግሬሽን ድረስ በጉቦኝነት ጠፍንጓታል። በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ እስካለ ድረስ ሀቀኛ ነኝ አልነካካም  ብትል እንኳን ብዙም ሳትሔድ በቀላሉ በጥንቃቄ እያሽከረከርክ በምትነዳበት መንገድህ ላይ የሸሚዙ ቁልፍ እስኪፈናጠር በላይ በላይ የሚበላው ትራፊክ ፖሊሱ እቁብ ስለደረሰበት ብቻ ፊሽካውን ነፍቶ ሲያስቆምህ ከመንጃ ፈቃድህ ይልቅ የመቶ ብር ኖቶችን ማዘጋጀቱ ብቻ ነው መገላገያ መንገዱ።በቃ ፃምህን ያስገድፉሐል።  በዚህ ውስጥ ያልተነከረ እና ያልተዘፈቀ  እጁን ያሳይ? . . . የተነከረበት ከሩቅ የሚሰነፍጠው መረቁ ምስክር ነው ። በጉቦ መረቅና  በሙስና የተዋዛ ጣት !

 

እጅ የሚስቆረጥም የፍትፍት ጉርሻ ፅኑ ቁጣን እንደምታበርድ ፥ የንፁሐንን ቃል እና ፍርድ በጉቦ ተጣሞ  ለማይገባቸው ሲፈረድላቸው ማየት አዲስ ነገር አይደለም። በተለይም ድንገት አዲስ እንደተወለደ ህፃን ከዚህ በፊት ሳይታዩ ከባዶ ካፒታል ላይ ተንደርድረው ከናጠጠ ሀብት ጋር ብቅ የሚሉት ቱጃሮች የሀብታቸው ምንጭ ከየት እንደፈለቀ ለማወቅ ግልፅ ሆኖ ሳለ ከባለስልጣናቱ ጋር በመሞሳመስ የሚያደራጁያቸው የተለያዩ የንግድ ሂደቶችም በፌደራሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምንም አይነት ክትትል  ሊደረግባቸው የማይችልበት  ዋናው ምክንያት ባለስልጣናቱ ከላይ እስከታች እያንዳንዱን ተጠያቂ ስለሚያደርጋቸው እና ክትትል አድራጊውም ሆነ ድርጊቱን ፈፃሚው ከአንድ ወንዝ የተቀዱ ስለሆኑ ነው። ቢሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣኑ ባለቤት ሆኖ ይህ አገዛዝ ለፍርድ እስከሚቀርብበት ጊዜ  ድረስ  አንድነትን በመጠበቅ በፅናት እና  በትዕግስት ለሐገሪቷ ነፃነት እየታገሉ መቆየት የእያንዳዳችን ድርሻ ሊሆን የተገባ ግዳጃችም ነው።

 

እያልኩ ያለሁት ለምን ሰው ባለጠጋ ሆነ አይደለም። ይልቁንም የፖለቲካን የበላይነት እና ባለስልጣን መሆንን ተገን አድርጎ የሚደረግ  የሀገርን  ሀብት የመዝረፍ ወንጀል ከአውራነቱ የተነሳ  በምድሩም ሆነ በሰማይ  በሚሰየመው ችሎት እንደሚያስጠይቅም ለማሳሰብ ጭምር እንጂ። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ከተከሰቱት ታላላቅ መፍትሔያቸው የራቁ የኑሮ ቀውሶች መካከል ለሰው ልጅ መኖር መሰረታዊ  የሆኑትን ብቻ    ለመገብየት ከዋጋው ግሽበት የተነሳ የሀገሪቱ የገንዘብ ጉልበት  እጅግ ደቃቃ  ሆኖ አቅም የለሽ በሆነበት፣ ስራ አጥነት ተበራክቶ ብዙሀን የወጣቱ ክፍል ህይወቱን ያጣበት የበረሀ ጉዞ እና በባህር ሰጥሞ አስከመቅረት  ዋጋ የሚይስከፍሉ የስደት አይነቶች ህዝብ እንዲጋለጥ፣ ወላጅ እየተጦረ እፎይ ብሎ በሚያርፍበት የሽምግልና ዘመኑ ለልመና ሰው ፊት የቆመበት እንዲሁም በብዙ ምሬት ውስጥ በመሆን ለተጎነበሰበት እና በምድሪቷ ላይ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሙስና ባህል እስኪመስል ድረስ በእጅጉ ተንሰራፍቶ ጥላውን እንዲያጠላ እና እንዲባባስ ገዢው ብድን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። እየተጫወተም ይገኛል። አምባገነናዊነት፤ እብሪት፤

ግትረኛነትና ትምክህተኛነት በከባድ የተጠናወተው ቡድንተኛ መሪ የሃገሪቱንም ሆነ የህብረተሰቡን አንጋፋ ችግሮች በጋራ ተመካክሮ፤ የፖለቲካ ስልጣንን በመካፈል ፤ የሕዝቡን ድምጽ አክብሮ፤ በተለይ ሀገር ተረካቢውን ወጣቱን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ  በእኩልነት ለመስራት የተዘጋጀ አይደለም። አቅሙም ልቡም የለውም። ይልቁንም የአብዛኛው ህብረተሰብ የኑሮ ሁኔታ ወደ ማጡ አባብሶታል። ይህ የአንድ ብሔር ብቻ ወገንተኛ  የፖለቲካ ብድን ፤ የኢትዮጵያን ህብረተሰብ እና የተለያዩ ብሔሮችን ግልፅ በሆነ አሰራር ሳያካትት የሀገሪቷን አንድነት  ባልጠበቀ ዘመቻው በአደገኛ ሁኔታ በሙስና እና በተለያዩ ጤናማ ባልሆኑ አካሄዶቹ የህዝቡን ኑሮ ከስሩ አናግቶታል። የጉቦኛነት ተስቦ ሳያንሰው ከሁሉም በላይ አዲሱ ትውልድ በኢትዮጵያዊነት ሳይሆን በጠባብ ጎሰኛነት  እንዲያምን በሚያደርገው ርብርብ ኢትዮጵያዊነት ከቶውንም ተሽሮ ብሔርተኝነት እንዲያብብ  የማያቋርጥ ተጋድሎ እያደረገም ጭምር ነው።

 

የሙስናው እንቅስቃሴ እና  ተግዳሮት  ለሀገርና ለህዝብ ጠንቅ መሆኑ አለም ሁሉ የሚስማማበት ስለሆነም በተለይም ደግሞ ሰላም በሰፈነባቸው  ሀገሮች ይህ ድርጊት እንደ ትልቅ ውርደት የሚታይ እና በአንዳንዶች ዘንድ ፈፅሞ የማይታወቅ ተልካሻ ስርዓት ነው። ዛሬ የስቃይ ኑሮ ገፈት ቀማሽ ያደረገን ወያኔ ከፅንሰቱ ጀምሮ እጁ ከሙስና ሳይፆም የረከሰ በመሆኑ ምክንያት አባላቱን እንኳን ሲመለምል ቀድሞውንም ስለ ኢትዮጵያ በመቆም ለትግሉ በእውነተኛነት አሳምኖ ሳይሆን በፍቅረ ንዋይ የተቃጠሉትን በማማለል ከድል ማግስት የሚገኘውን ሀብት በማለም ብቻ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ በሀገራችን የተማረው  ክፍል በሙያቸው፣ በዲግሪያቸውም ሆነ በልምድ እውቀታቸው ሰርተው ሀገር የሚያለሙበት  መንገዱ ሁሉ ቢዘጋጋባቸው ለመኖር ሲሉ የግዳቸውን ከባለስልጣናቱ ጋር የተለያየ አይነት የሙስና መንገዶችን ለማጠቀም የሚገደዱት።

 

በኢትዮጵያ ከኖርክ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ለመኖር ስትል ጉቦ ትሰጣለ ወይም ታበላለህ። በዕጅ ማለት ብርቅ አይደለም። ከዘበኛው ጀምረህ ባለስልጣኑን እስክታገኘው ድረስ ሁሉን እያጉረስክ ማለፍ የግድ ነው። ለምሳሌ የገንዘብ ተመን ከወጣላቸው ጉቦኝነት መሀከል የመኪና መንጃ ፈቃድ ለማውጣት የሚከፈለው ክፍያ ነው። ካልሰጠህ መንጃፍቃድ የምይታሰብ ጉዳይ ነው ፥ ሊያውም ዳጎስ ያለ እንደሆነ ደግሞ ያሉበት ድረስ ይመጣልዎታል። ይህም ሂደት ሀገሪቷን ለከፍተኛ የመኪና አደጋ አጋልጦ ሰጥቷታል። በመሬት ንግዱ ዙሪያ እና የፃድቁን ውሳኔ ለማጣመም በፍርድ ቤቶች   የሚከፈሉት የዳጎሱ ጉርሻዎች ሐገር ሁሉ የሚያውቀው ራቁትነት ነው። የተማረው፥ፊደል የቆጠረው በደጅ ሆና ተስፋ ቆርጦ ሲማረር እና ፀሀይ ሲበላው ሌላው ዘሩን ጠርቶ የግንባሩን ምልክት አሳይቶ ለምሁሩ የተዘጋበትን በር አስከፍቶ ዘው ይልበታል። ለዚህ ሁሉ ውድቀት ዋናው  ምክንያቱ  ባለቤት እና እውነተኛ መሪ በሌላት ሀገር ላይ  የመንግስት ተቋማት ከፍትፍቱ አጉሩሱኝ ከመረቁ ፃመኛ ነኝ በማለት ሳይነክሱ መኖር አቅቷቸው ለሙስና በመዘፈቃቸው ብቻ ነው፡፡

 

ጉቦኝነት ሁሉን ዳሶታል ። ፈተናውን ሁሉ ለመለፍ ወይ ገንዘብ አሊያም እንደ ባለስልጣናቱ  ጥያቄ መሰረት ፍላጎታቸውን ማርካት የተለመደ ቢሆንም ይህን ሀገርን ወደኋላ የሚጎትት አሰራር ከስሩ ለማድረቅ ኢትዮጵያውያን የሆንን ሁሉ ለሀገራችን ነፃ መውጣት የምንከፍለው ሌላ ክፍያ አለ። በሁሉ አቅጣጫ አንድነታችንን በማጉልበት ለወያኔ አገዛዝ በእንቢተኛነት መጋፈጥ! ብሔር ከሀገር አይበልጥምና  የጎሰኝነትን እና የብሔርተኝነትን የመለያየት መርዝ አርክሰን በአንድነት መቆም!

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

ቢንያም ግዛው (ከኖርዌይ ኦስሎ)

 

 

 

 

The post ከፍትፍቱ አጉሩሱኝ ከመረቁ ፃመኛ ነኝ – ቢንያም ግዛው (ከኖርዌይ ኦስሎ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል!!

$
0
0
ተክሌ በቀለ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት

ተክሌ በቀለ

ለኔ እዉነተኛዉ የአንድነት ፓርቲ ትናንት በፍ/ቤት ዉሳኔ ተቀብሯል፡፡ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንደሆን ቀድም ሲል አዉቀናል፡፡ዳኛ ብርቱኳንም ፍርህይወትም ዳግም አልተከሰቱም፡፡እንደ ኢህአዴጉ የምርጫ ዉጤት 99.6 ከመቶዉ አመራሩና አባላቱ በምርጫ ቦርድ እንዲበተኑ የተበየነበት እንዲሁም በደጋፊዎች የተገዛ ንብረት ያለፍ/ቤት ትእዛዝ በመንግስት ታጣቂ ፖሊሶች የተዘረፈበት አንድነት የፍትህ ተቋሙን ለመፈተሸ ም/ቦርዱን መክሰሱ ይታወቃል፡፡

ም/ቦርድን መክሰሳችን አግባብ እንዳልሆነ አንቀጽ ተጠቅሶ ከማስፈራሪያ ጋር ክሱ ዉድቅ ተደርጓል፡፡ መፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል፡፡ቀጣዩን በቀጣይ ሂደት የምናየዉ ይሆናል፤እንደሚፈልጉት ተበትነን አንቀርም፡፡አንድነቶች በያለንበት እንረጋጋ!!
ታላቋ ምእራብ አፍሪካዊት ሃገር ናይጀሪያ እዚህ የደረሰችዉ ዉድ ዋጋ ከፍላ ነዉ፡፡ከናይጀሪያም በላይ ዋጋ ብንከፈልም በልተዉ በማይጠግቡ በሎች ትግሉ እየተነጠቀ ዛሬም እዛዉ ላይ ነን፡፡ታላቅዋ የምስራቅ አፍሪካ ኮከብ ሀገረ ኢትዮጵያ በልማት ስም ክብሯ እንዲወርድ እየተደረገች ትገኛለች፡፡እናም በዲፕሎማሲ፤በዲሞክራሲ፤በኢኮኖሚም ይሁን በሁለንተናዊ ልማት የአለም ማህበረሰብ በአፍሪካ ትኩረት ናይጀሪያ ሆናለች፡፡ኢትዮጵያ የምትፈለገዉ ለክፍለአሁጉሩ የደህንነት አጋርነት ብቻ ነዉ፡፡

የናይጀሪያ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና(የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ትብብርና ዉህደት ያስከተለዉን ዉጤትም ልብ ይሏል) የተወዳዳሪ ግለሰቦች ሚና ቀላል ባይሆንም ለናይጀሪያ ተስፋ የሆናት ግን ህዝቡ ነዉ፡፡የኢትዮጵያችንም የለዉጥ ተስፋ ህዝቡ ነዉ፡፡በዚህ ወቅት የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች አሰላለፍም የጎላ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

The post ፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል!! appeared first on Zehabesha Amharic.

እራት ሳይኖር መብራት ምን ይሠራል?

$
0
0

grand-renaissance-dam-1የታላቁ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ሕዳሴ ግድብ ብዙዎች እንደተለመደው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እያሉ ይጠሩታል፡፡ ውስጥ አወቅ የሆኑ ጋዜጠኞች ግን በታላቁ እና ሕዳሴ መካከል ኤሌክትሪክ ማመንጫ የሚል ሀረግ በመጨመር ላይ ናቸው፡፡

‘ድሮ ውኃ ይጠጣ ነበር፤ አሁን ግን ልንበላው ነው፡፡’ የሚለው ተስፋ በተስፋነት ቀረ ማለት ነው፡፡ መቸም ኤሌክትሪክ አይበላም፡፡

አባቶቻችን ሲመርቁም ‘እራት እና መብራት አይንሳችሁ!’ ነበር የሚሉት፡፡ እኛም . . . . መብራቱስ ግድ የለም፣ ከጨረቃ ጋራ ይገፋል ሌሊቱ እኛን የከበደን፣ ያልበላ አንጀት ሲጮህ ማዳመጥ-መስማቱ፡፡

በማለት የአባቶቻችን ምርቃት እራትን ከመብራት እንዲያስቀድም አሳሰብነ፡፡ ከሰሞኑ የመርሁ ስምምነት ላይ የግብፁ መሪ( Al SISI የፕሬዜዳንቱ ስም ሲገለበጥ ISIS ይሆናል) እና ምን አሉ . . . ‘የኢትዮጵያ ልጆች በብርሃን የሚማሩበት፤ የግብፅ ልጆችም በልተው የሚያድሩበት . . .’ ዓይነት ንግግር ተናግረዋል፡፡ እኛ ኤሌክትሪክ እነሱ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሆነ ነገሩ፡፡ . . . . . የአባይን ውኃ ልንበላው ነው ስንል ልታዩት ነው/ኤሌክትሪክ ነው/ ተባልነ፡፡ እራት ሳይኖር መብራት ምን ይሠራል? እሳቱ

The post እራት ሳይኖር መብራት ምን ይሠራል? appeared first on Zehabesha Amharic.


የጊፍት ሪል እስቴት ጉዞ በስም ማጥፋት ዘመቻ ወደኋላ አይመለስም

$
0
0

ከጊፍት ግሩፕ ኩባንያ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ

nlmqi6fn76e6fjt0pj5uይህ ጽሁፍ “ጊፍት ሪል እስቴት  ወደፊት ወይስ ወደኋላ” በሚል ርዕስ ‘አበበ ወርዶፋ’ በተባሉ ግለሰብ  ለተጻፈውና ጸሃፊው ‘ሪል እስቴቱ ጉዳት ያደረሰብኝ ደንበኛ ነኝ’ በሚል ሽፋን የኩባንያውን መልካም ስም ያለአግባብ ለመጉዳት በማሰብ እ.ኤ.አ ማርች  24 እና 25 ቀን 2015 ze-habesha.com እና satenaw.com ድረገጾች ላይ ለንባብ ላበቁት ሃተታ  የተሰጠ ምላሽ ነው።

ጸሃፊው በቂ ማስረጃ ሳይኖራቸው ግነት የተሞሉና ከሃቅ የራቁ መረጃዎችን በመደርደር በስሜት ብቻ ተነሳስተው ላቀረቡት ትችት መልስ ከመስጠት በፊት “ጊፍት ሪል እስቴት ማነው?” የሚለውን ጥያቄ መመለስ ተገቢ ይሆናል። ይህን ማድረግ የሚያስፈልገው በብዙዎች ዘንድ የታወቀ መልካም ስምና ዝና ያለውን ጊፍት ሪልእስቴትን እንደአዲስ ኩባንያ ለማስተዋወቅ ሳይሆን አንባቢ የሁለቱንም ወገን ጽሁፎች ሲያነብ በጉዳዩ ላይ ሙሉ ስዕል እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ በመሆኑ ጭምር ነው።

በኢትዮጵያ የግል የሪል እስቴት ዘርፍ ለመሰማራት ቀዳሚ ከሆኑት ኩባንያዎች አንዱ ጊፍት ሪል እስቴት ነው፡፡ ጊፍት ሪል እስቴት ሲኤም ሲ እና ሃያት አካባቢ በተረከበው 16.3 ሄክታር መሬት ላይ በሶስት ፌዞች የተለያየ ዲዛይን ያላቸው ከ300 በላይ ዘመናዊ ቪላዎችንና ታውን ሃውሶችን እንዲሁም 44 ብሎክ         አፓርትመንቶችን በአጠቃላይ እስከ አንድ ሺህ የሚደርሱ አባወራዎችን መያዝ የሚችሉ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በተለያየ ደረጃ ለተጠቃሚዎች እያስተላለፈ ሲሆን አሁንም በመጠናቀቅ ላይ ያሉትን ጨምሮ አዳዲስ ግንባታዎችን በማካሄድ ላይ የሚገኝ ኩባንያ ነው።

ጊፍት ሪል እስቴት የሚያከናውነው የቤቶች ግንባታ ስራ ሰፊና በካፒታል ደረጃ ሲሰላም 2 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ኢንቨስትመንት ነው። በግንባታው ሂደት እስከ 2ሺህ የሚደርሱ በተለያየ የሙያ ደረጃ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞችን በማሳተፍም ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር የቻለ ሃገርበቀል ኩባንያ ነው።

ጊፍት እንደ ቢዝነስ ግሩፕ ኩባንያ በሪል እስቴት ልማት ዘርፍ ላይ ለመሰማራት እቅድ ሲነድፍና ምክረሃሳቡን ለአዲስ አበባ አስተደደር አቅርቦ መሬት ሲረከብ ዓላማው ቢዝነሱን ማስፋት ብቻ አልነበረም።  ኩባንያው በመመስረቻ ሰነዱ ላይ ካስቀመጣቸው ተቀዳሚ አላማዎች (core objectives) ዋናው በሃገር ውስጥ እየኖሩ ደረጃውን የጠበቀ ምቹና ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን ለሚፈልጉ እንዲሁም በውጭ ሃገራት እየኖሩ በሃገራቸው ውስጥ ማረፊያ የሚሆናቸውና ከሰለጠነው ዓለም ጋር ተመጣጣኝ ደረጃ ያለው መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸው ለሚመኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፍላጎታቸውን የሚያረካ አገልግሎት የሚሰጥ ሃገር በቀል ሪልእስቴት አልሚ መሆን ነው። ጊፍት ሪል እስቴት እስካሁን እያከናወነ ያለው ስራ ይህንኑ ዓላማ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ያተኮረ ነው።

ሪል እስቴቱ ግንባታ የሚያካሂድባቸው ሲኤምሲና ሃያት አካባቢዎች ለመኖሪያነት አንደኛ ደረጃ ተመራጭ  ከሆኑት የአዲስ አበባ አካባቢዎች በቀዳሚዎቹ ተርታ ላይ የሚገኙ መሆናቸውና የቦታውና የቤቶቹ ኢንቨስትመንት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሄዱ በደንበኞች ዘንድ የጊፍትን ቤቶች ቀዳሚ ተመራጭ ሊያደርጓቸው ከቻሉት ምክንያቶች ዋናው ነው።ይህንን ሃቅ በሃገር ውስጥም ይሁን  በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ኩባንያው ቤት የገነባላቸው ደንበኞች በተደጋጋሚ የሚናገሩት ነው።

ጊፍት ሪልእስቴትን በተመለከተ  እንደመረጃ ከላይ የሰፈሩትን ነጥቦች ካነሳን ከዚህ በመቀጠል  ጸሃፊው በሰነዘሯቸው ትችቶች ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ብቻ በማትኮር አንባቢ ሃቁን አገናዝቦ ይረዳ ዘንድ እውነታውን ለማሳየት እንሞክራለን።

ጸሃፊው የሪል እስቴቱ ደንበኛ አይደሉም

ጊፍት ሪል እስቴት ካሉት ከ300 የሚበልጡ ቤት የገዙት ደንበኞች ዝርዝር ውስጥ አበበ ወርዶፋ የሚባሉ ግለሰብ የሉም።ጸሃፊው ‘አበበ ወርዶፋ’ በሚል ስም የሪል እስቴቱ ደንበኛ እንደሆኑ በመግለጽ ሃተታ የመጻፋቸው ዋነኛ ዓላማ በአንባቢያን ዘንድ እምነት በማግኘት የስም ማጥፋት እቅዳቸው እንዲሳካ ከማድረግ የዘለለ አይሆንም። ሪል እስቴቱ ካልገለጸ በቀር አንባቢያን የኩባንያውን ደንበኞች ዝርዝር ለማወቅ አጋጣሚው እንደማይኖራቸው የሚገነዘቡት ጸሃፊው ይህንን ክፍተት በመጠቀም ራሳቸውን ጉዳት እንደደረሰበት ደንበኛ አድርገው ማቅረባቸው ትችታቸው በቀላሉ ተዓማኒነትን እንዲያገኝ መንገድ ይከፍታል። ነገር ግን ጸሃፊው አሳንሰው እንዳዩት ሳይሆን አንባቢ ይጠይቃል፣ያገናዝባል፤ይፈርዳልም።

በሌላ በኩል ጸሃፊው ጊፍት ሪልእስቴት ቤት የሚገነባላቸው ደንበኛ መሆናቸው እንዳይታወቅባቸው ሲሉ ወይም በራሳቸው የተለየ ምክንያት (መቼም ሪልእስቴቱ ለደህንነቴ ያሰጋኛል እንደማይሉ ተስፋ እናድርግና )  በብዕር ስም ተጠቅሜያለሁ ቢሉ እንኳን  ለሃቀኝነታቸው ጥቂት ማሳያዎችን ብቻ ማቅረብ ዳገት አይሆንባቸውም ነበር።

ለምሳሌ ከሪልእስቴቱ ገዝቻለሁ ያሉት መኖሪያ ቤት ጊፍት ከሚገነባቸው የተለያየ ዓይነትና ዋጋ ካላቸው ቤቶች ውስጥ የትኛው መሆኑ፣ለግንባታው ምን ያህል ዋጋ እንደከፈሉ ፣ቤቱ ከሶስቱ የጊፍት ሳይቶች የትኛው ሳይት ላይ እንደሚገኝና ከመሰል ተያያዠ መረጃዎች አንዱን እንኳን  ሳይገልጹ በደፈናው ‘ደንበኛ ነኝ’ ብለው ማለፋቸው ትችታቸው ገንቢ ሳይሆን አፍራሽ ዓላማ ያለው መሆኑን በግልጽ ያሳያል።ይህም በደንበኛ ስም አንባቢንና የጊፍትን ደንበኞች በማሳሳት ስም የማጥፋት አጀንዳ እንደያዙ ይመሰክራል። ይህን ሁሉ መረጃ መግለጽ አያስፈልገኝም ቢሉ እንኳን ኩባንያው ደንበኝነታቸውን ለማወቅና ያቀረቧቸውን ትችቶች ለመመዘን የሚችልበትን አንድም ተጨባጭ እውነት አለማስቀመጣቸው ግን ፍላጎታቸው መፍትሄ ማግኘት ሳይሆን ድርጅቱን በመልካም ዝናው የሚያውቁትን በውጭ ሃገራትና በሃገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማሳሳትና የተዛባ ግንዛቤ እንዲይዙ የማድረግ ዓላማ ይዘው መነሳታቸውን ይመሰክራል።

 

የተዛቡና የሚጋጩ መረጃዎች

ይህንን እንዳለ ብንቀበለው እንኳን  የዛሬ 7ዓመት ከጊፍት ሪል እስቴት ቤት ገዝቻለሁ ያሉት እኚሁ ጸሃፊ “መቶ በመቶ ብትከፍሉ በፍጥነት ይደርስላችኋል ተብለን ስለነበር የቤቱን ዋጋ 100% ከፍያለሁ” ብለዋል። እውነቱ ግን የዛሬ 7 ዓመት 100% ከፍሎ ከሪል እስቴቱ ቤት የገዛ ደንበኛ የሌለ መሆኑ ነው። ከ 3 ዓመት ወዲህ ባሉት ጊዜያት ቅድሚያ 100% ክፍያ ከፍለው ቤት ለገዙ ደንበኞቹም ሪል እስቴቱ 6 በመቶ ቅናሽ አድርጎላቸው ቤታቸውንም ገንብቶ አጠናቆ አስረክቧቸዋል።

ጸሃፊው “ቤታችሁ በፍጥነት ይደርስላችኋል ተብለን 100% ከፈልን” ያሉትም ቢሆን ከእውነት የራቀ ነው።ሪልእስቴቱ ቅድሚያ ሙሉ ክፍያ ለሚፈጽሙ ደንበኞች  6% የዋጋ ቅናሽ ከማድረግ  ውጪ ቤታችሁን  ከ18 ወራት በታች በሆነ ጊዜ በፍጥነት ሰርቼ አስረክባለሁ የሚል ስምምነት ከየትኛውም ደንበኛ ጋር አልገባም። እኚህ ጸሃፊ በየትኛውም የጊፍት ደንበኛ እጅ ውስጥ የሚገኘውን ውል በማየት በቀላሉ መረጋገጥ ከሚችለው ከዚህ እውነት ተቃራኒ የሆነ ቃል እንደተገባላቸው በማስመሰል በተዛባና እርስ በርሱ በሚጋጭ መረጃ አንባቢን ለማሳሳት ሞክረዋል።

የጸሃፊው ሌላ ግድፈት የዛሬ 7 ዓመት 100% ከፍያ ፈጽመው ነገር ግን የቤታቸው ግንባታ መሰረት ከማውጣት አለማለፉን መግለጻቸው ነው። ጊፍት ሪል እስቴት ውል ገብቶ የቤታቸውን ግንባታ ከሚያከናውንላቸው ደንበኞች መካከል ብዙዎቹ ቤታቸውን በተለያየ የግንባታ ደረጃ ተረክበዋል። በቅርብ ጊዜ ከኩባንያው ቤት ለገዙ ደንበኞች እየተገነባ የሚገኘው መኖሪያ ቤት የደረሰበት ደረጃ የተለያየ ቢሆንም ቅሉ ጊፍት ሪልእስቴት በራሱ ወጪ ገንብቶ ሊሸጣቸው እየገነባቸው ከሚገኙ ቤቶች በቀር ደንበኛ ክፍያ ፈጽሞበት ሳይገነባ የቀረ አንድም ቤት የለም። በጽሁፉ ውስጥ  ይህንን ፍጹም የተጋነነና ከተዓማኒነት የራቀ ትችት ለማስፈር የተፈለገበትን ዓላማ የሚያውቁት ራሳቸው ጸሃፊው ብቻ ናቸው።

የባለቤትነት ማረጋገጫ ያለው ማን ጋር ነው!

ጸሃፊው በሃተታቸው ውስጥ “ጊፍት  ቤት ላስረከባቸው ህጋዊ ገዠዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለም” የሚል ጭፍን ትችት አስፍረዋል።ከዚህ በተጨማሪም “የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ሲጠየቅ የሚያመካኘው በመስተዳድሩ ላይ ነው” ብለዋል። ጸሃፊው በርግጥም የጊፍት ደንበኞችን አነጋግረው ከሆነ (እርሳቸው የጊፍት ደንበኛ ስላልሆኑ) የባለቤትነት ማረጋገጫ የመስጠት ሃላፊነት የማን እንደሆነና እስካሁን የዘገየውም በምን ምከንያት እንደሆነ በሚገባ ይገነዘቡ ነበር።

ጊፍት ለገነባቸውና ለደንበኞቹ ላስረከባቸው ቤቶች የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር እንዲሰጠው በአሰራሩ መሰረት የየካ ክፍለከተማንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽህፈት ቤቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ ጠይቋል። በአፈጻጸሙ መዘግየት ሳቢያም እስከላይኛው የአስተደደሩ የስልጣን እርከን የደረሱ ተደጋጋሚ አቤቱታዎችን አቅርቧል። ድርጅቱ በክፍለከተማው በኩል የገጠመውን የአገልግሎት መዘግየት ችግር ለመፍታትና የጀመረውን የቤቶች ልማት በውሉ መሰረት አጠናቅቆ ለደንበኞቹ ለማስረከብ ያደረጋቸው ጥረቶች ተገቢ ባልሆኑ አሰራሮች ተጓተዋል። ይህንንም ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቋል።ጊፍት ምን ያህል ጊዜ በጉዳዩ ላይ ከአስተዳደር አካላቱ ጋር ውይይት እንዳደረገ ከተጻጻፋቸው ደብዳቤዎች ጭምር ጉዳዩን መረዳት ለሚፈልግ አካል ማሳየት ይችላል።

ያም ሆኖ እስካሁን ኩባንያው ጉዳዩ ሲጓተትበት ቢቆይም በቅርቡ በተደረጉ ጥረቶች ግን ችግሩ እልባት ለማግኘት ወደሚችልበት መስመር ገብቷል።በአሁኑ ወቅት ከኩባንያውና ከክፍለከተማው የህግ ክፍል ጋር በመሆን  በጋራ የማጣራት ስራዎች እየተሰሩ ነው።ጊፍት ይህ ችግር በቅርብ ጊዜ አልባት እንደሚያገኝ ያምናል።

ጸሃፊው እንዳሉት ጊፍት ለደንበኞቹ ካርታ ባለመስጠት ተጠቃሚ አይደለም። በተቃራኒው በቅርቡ መፍትሄ የሚያገኝ ቢሆንም ካርታው ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች በመዘግየቱ ምክንያት የተወሰኑ ቤታቸውን የተረከቡ ደንበኞች የመጨረሻውን ክፍያ እንዳይፈጽሙ እንቅፋት ሆኗል። በዚህም ኩባንያው  ከተወሰኑ ደንበኞች ገቢ መሰብሰብ አልቻለም። ይህም የኢንቨስትመንቱን ወጪ ሸፍኖ ስራውን ለማቀላጠፍ በገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ ላይ ጫና አሳድሯል። በሌላ አነጋገር አስተዳደሩ  የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ አለመልቀቁ ለኩባንያውም ጉዳት ነው።

እውነቱ የህ ሆኖ ሳለ ጸሃፊው  ጊፍት የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተሩን በእጁ ይዞ ለደንበኞቹ መስጠት እንዳልፈለገ አስመስለው ተችተዋል። ዓላማቸው የኩባንያውን ስም ማጥፋት ባይሆን ኖሮ “ጊፍት የደንበኞቹን ካርታ መያዙ የራሱን ገቢ ከማስቀረት የዘለለ ምን ይጠቅመዋል?” የሚል ቀላል ጥያቄ በመጠየቅ ብቻ መልሱን ከራሳቸው ማግኘት ይችሉ ነበር።

የመንገዱ ጉዳይ

ጸሃፊው ወደጊፍት ሪልእስቴት ፌዝ ሁለት ሳይት የሚወስደው መንገድ አለመሰራቱን በተመለከተ ኩባንያውን ተጠያቂ ለማድረግ የግራውን ከቀኝ እያጋጩ ማስረጃ አልባ ክስ ዘርዝረዋል። እንደእውነቱ ከሆነ “ቤቴ መሰረቱ ብቻ ነው የወጣው” በሚል አቤቱታ ትችታቸውን የጀመሩት ግለሰብ ‘ወደቤቴ የሚወሰድ መንገድ አልተሰራልኝም’ የሚል ክስ መጨመራቸው ራሳቸውን በራሳቸው አቃርኗቸዋል።

ጊፍት አሁን ሙሉ በሙሉ ቤት ወደገነባበት ፌዝ ሁለት ሳይት የሚወስደው መንገድ በሪልእስቴት ፕላኑ ላይ በግልጽ ተለይቶ የተቀመጠና የተፈቀደ ነው። ነገር ግን በመንገዱ ላይ ጥቂት ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ ቤት የገነቡ በመሆኑ አስተዳደሩ ወይ ህገወጥ ግንባታውን እንዲያስነሳ ካልሆነም ተለዋጭ መንገድ እንዲያዘጋጅ ከበላይ አካላት ጭምር በደብዳቤ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል። እስካሁን ድረስ ግን ትዕዛዙን ተፈጻሚ አላደረገም። ይህም የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናትን ጨምሮ የከተማ ስራ አመራርና ማኔጅመንት ኢኒስቲቲዩት ባለሙያዎች ጭምር ያጠኑትና ችግሩ የአስፈጻሚው አካል በመሆኑ ላይ መግባባት ላይ የተደረሰበት ፣በፍጥነት መስተካከል  እንደሚገባውውም ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ ነው። ጊፍት በዚያ ሳይት ያሉትን ቤቶች ለደንበኞቹ ሙሉ በሙሉ አስረክቦ እስኪያጠናቅቅ የመንገዱ ጉዳይም እልባት እንደሚያገኝ ተስፋ ተሰጥቶታል።

ጸሃፊው ወደዚሁ ሳይት በጊዜያዊነት የሚገባበት መንገድ ኮብልስቶን ያልተነጠፈው ጊፍት መዋጮ ባለመክፈሉ ነው የሚል ትችት አስፍረዋል።አስተዳደሩ ወደሪልእስቴቱ የሚገባውን በማስተርፕላን ተለይቶ የተቀመጠ መንገድ አስከብሮ ነጻ ማድረግ ባለመቻሉ ሳቢያ ግለሰቦች ለህገወጥ ተግባራቸው መጠቀሚያነት ቢያውሉትም ሪልእስቴቱ ግን ውሳኔው ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ለግንባታ ስራው በጊዜያዊነት የሚጠቀምበትን መንገድ አልምቷል። ይህንን መንገድ በበጋና በክረምት ለመጠቀም በሚያስችል ሁኔታ በኮብል ስቶን ለማሰራትም ከአስተደደሩና በሳይቱ አካባቢ ከሚኖሩት ግለሰቦች ጋር በተደረገ ውይይት ጊፍት ለልማት ከተጠየቀው ገንዘብ ውስጥ 150ሺህ ብር ያለምንም ማቅማማት አዋጥቷል። ከአካባቢው ነዋሪዎች የተሰበሰበው ገንዘብ 40ሺህ ብር ብቻ ስለነበር በቂ ገንዘብ እስኪሰበሰብ ድረስ ኮብልስቶኑ ሳይነጠፍ ዘግይቷል። ከአንድ ወር በፊት ኩባንያው የመንገዱ ስራ ያልተጀመረበትን ምክንያት በተመለከተ የሚያስተባብረውን የአካባቢውን  አስተዳደር ማብራሪያ ሲጠይቅም የልማት ኮሚቴው ላይ በነበሩት  ክፍተቶች ሳቢያ ስራው መዘግየቱ ተነግሮታል።ጊፍት ስራው ከተጀመረ ለአካባቢ ልማት ማንኛውንም ድጋፍ ከማድረግ የማይቆጠብ መሆኑን አሳውቋል።የባለሙያና የማሽን እገዛ ካስፈለገም ድጋፍ እንደሚያደርግ በቅርቡ ከክፍለከተማው ስራ አስፈጻሚ ጋር በጉዳዩ ላይ ባደረገው ውይይት ቃል ገብቷል። ከብዙ ጊዜያት መባከን በኋላ በቅርቡ የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦ የመቅበር ስራ እየተሰራ ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ጸሃፊው ግን ሁሉንም ችግሩን ወደጊፍት ሪልእስቴት በመግፋት ደንበኞች በኩባንያው ላይ እምነት እንዲያጡና የአካባቢው ነዋሪዎችንም ከሪልእስቴቱ ጋር በማቃቃር  እንደህልውናቸው ጠላት እንዲያዩት ሆን ተብሎ የታቀደ ማስረጃ አልባ ሃተታ አቅርበዋል። ይባስ ብለው “ለወረዳው አስተዳደርና ለክፍለከተማው  ሪልእስቴቱ እምቢ ባይ በመሆኑ ከአቅማቸው በላይ ሆኗል” የሚል ኢተዓማኒ መረጃ ተጠቅመዋል።አካባቢውን ለማስተዳደር፣ ህግና ደንብ ለማስከበርና ለማስፈጸም ሃላፊነት የተሰጠው አስተደደር ለሚመራው ህዝብ አንድን ኩባንያ “ከአቅሜ በላይ ነው” ብሎ አቤቱታ ሲያቀርብ ምናልባት ከእኚህ ጸሃፊ በቀር ማንም ሰምቶ አያውቅም።

ጸሃፊው በአላዋቂ አተያይ የቃኙት የአካባቢ ልማት ለኩባንያዎች የኮርፖሬት ማህበራዊ ሃላፊነትን የመወጣት የሞራል ሃላፊነት እንጂ በውልና በአስተደደራዊ ጫና የሚተገበር ስራ አይደለም። ጊፍት በውዴታ አስተዋጽዖ አደርጋለሁ ብሎ የገባበት ይህ የአካባቢ ልማት በጋራ ርብርብ ተፈጻሚ ሆኖ ህብረተሰቡ ሲጠቀም ማየት ከአላማዎቹ አንዱ ነው።ጊፍት በአካባቢያዊና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሁሌም ቀዳሚ ተሰላፊ የሆነ ፣ ማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት በኩል የተከበረ ስም ያለው ተቋም ነው። ለቀይመስቀል ህንጻ ማሰሪያ የለገሰውን ከ6መቶ ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ቤት ጸሃፊው ራሳቸው በጽሁፋቸው ማጠናቀቂያ ለአሉታዊ ሃሳባቸው ማጠናከሪያ ምሳሌ ቢያደርጉትም አልካዱትም። ጊፍት  ማህበረሰቡን አግልሎ ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ ያለመ ኩባንያ ቢሆን ኖሮ አንጋፋ ሆኖ የሚሳተፍበትን የሪልእስቴት ኢንቨስትመንት ዛሬ ድረስ ማቆየት ባልቻለ ነበር።

የመሰረተ ልማት ጥያቄ  የጊፍት ጥያቄ ብቻ ነውን?

ጸሃፊው በመጨረሻ ላይ በግልጽ በሚያስታውቅ ግነት ያነሱት የውሃ፣የመብራትና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ጉዳይ የጊፍት ሪልእስቴት ብቻ ሳይሆን የመላው አዲስ አበባ ችግር መሆኑ ጠፍቷቸው አይደለም። በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የትኞቹም የሪልእስቴት አልሚዎች ከገጠሟቸው ዋና ዋና ችግሮች ተጠቃሾቹ እነዚህ ጸሃፊው ከላይ የጊፍት ስህተቶች አስመስለው ሊያቀርቧቸው የሞከሯቸው የመሰረተ ልማት ችግሮች ናቸው።ዛሬ እንኳን በከተማ ማስፋፊያ አካባቢ አዲስ የሚመሰረት መንደር ቀርቶ በመሃል ከተማ የሚገኝና ከ50 ዓመት በላይ የቆየ ነባር መንደር ጭምር የውሃ መጥፋትና የመብራት ሃይል መቆራረጥ ችግር ያጋጥመዋል።ይህ ከከተማው መስፋት፣ከህዝብ ቁጥር መጨመርና ከውሃና ከሃይል ፍላጎት ማደግ ጋር በተያያዘ የተከሰተ የጋራ ችግር ነው። መንግስት ለሪልእስቴት አልሚዎች መሬት ሲሰጥ የውሃና የመብራት መስመር የመዘርጋት ሃላፊነት እንዳለበት ቢያውቅም በአቅም ማነስና በሃብት ውስንነት ሳቢያ በተፈለገው ጊዜ አገልግሎቱን ማድረስ አልቻለም። ማንኛውም አካል ይህ ችግር ተፈትቶ ከተማዋ ለኑሮና ለነዋሪዎቿ ምቹ ሆና ማየት ይናፍቃል።

ጊፍት ሪልእስቴትም ቤት የገነባው አዲስ አበባ ውስጥ አንደመሆኑ በከተማው ቤት ልማት ላይ የተሰማሩ  አቻ ኩባንያዎች ከገጠማቸው የተለየ ችግር አልገጠመውም። የጊፍት ሪልእስቴት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ይህን ጊፍትን ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱ ሪልእስቴት ዘርፍ በሚፈለገው ሁኔታ ላለማደጉ እንቅፋት የሆኑበትን መሰረታዊ ችግሮች በተመለከተ በአዲስአድማስ ጋዜጣ ለቀረበላቸው መሰል ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በግልጽ ያስቀመጧቸውን ነጥቦች መጋቢት 5 ቀን 2007 ዓ.ም ከወጣው የጋዜጣው እትም ገጽ 14 በንግድና ኢኮኖሚ አምድ ላይ በማንበብ እውነቱን መረዳት በዚያውም አዕምሯቸው ውስጥ ላለው ጥያቄ መልስ ማግኘት ይችላሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፉት ዓመታት ጊፍት ግንባታ ወዳካሄደበት ፌዝ ሁለት ሳይት የውሃና የመብራት መስመር እንዲዘረጋለት በተደጋጋሚ ጊዜ ጠይቋል። የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ዛሬ ነገ ከሚሉ ተስፋዎች የዘለለ አጥጋቢ  ምላሽ መስጠት ባይችሉም።ያም ሆኖ ኩባንያው ሳያሰልስ ጉዳዩን በመከታተሉ  ከዓመታት ጥረት በኋላ ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ ወደሚቻልበት ምዕራፍ አድርሶታል። በአስፈጻሚ መስሪያቤቶቹ የተጀመሩት ስራዎች ሲጠናቀቁ የደንበኞች ጥያቄ ምላሽ ያገኛል የሚል ዕምነትም አለ።

እንዲያም ሆኖ ቤታቸውን ተረክበው የገቡ ነዋሪዎች በውሃና በመብራት እጦት እንዳይቸገሩ ኩባንያው ተጨማሪ ወጪ በማውጣት ጊዜያዊ መስመር በመዘርጋት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ለማድረግ ሞክሯል። ለስራ የሚጠቀምበትን የኤሌክትሪክ ሃይል ለነዋሪዎች በማከፋፈል ችግራቸውን በጊዜያዊነት ለመፍታትም ጥሯል። ይህ ችግር የጋራ ችግር መሆኑን ደንበኞቹ ይገነዘባሉ። ጸሃፊው የግራውን ከቀኝ እየቀላቀሉ ‘የምርጫ ክርክር ማየት አልቻልንም’ ብለው እንዳጋነኑትና ፍሪጅ አስነስቶ ቴሌቪዠን የማያሰራ ሃይል  እንዳሉት ሳይሆን ሊጠቀሙበት የሚችሉትን ሃይል ነው ያከፋፈላቸው። ጸሃፊው ለወቀሳቸው ማጠናከሪያ አጋንነው ቢያቀርቡትም ይህንን ማድረግ የኩባንያው ሃላፊነትም ጭምር ነውና ምስጋና የሚሻበት ጉዳይም አይደለም ።

ጸሃፊው በመጨረሻ “የኩባንያው ሃላፊዎች ደንበኞችን አያነጋግሩም” የሚል ጭብጥ ለአንባቢ ለማስያዝ “ሃላፊዎቹ ቢሮ  ዘግተው ይጠፋሉ” የሚል ቃል ተጠቅመዋል። እሳቸው በጽሁፋቸው መግቢያ ላይ “በተደጋጋሚ ጊዜ አነጋግሬያቸዋለሁ” ያሏቸውን የድርጅቱን ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ ከቢሮ ውጪ የት አግኝተው አነጋግረዋቸው እንደሆን ቢጠቅሱት የራሳቸውን ሃሳብ በራሳቸው ከማፍረስ ያድናቸው ነበር። በመሰረቱ የሪልእስቴቱ ሃላፊዎችም ሆኑ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ከስራ ሰዓት ውጪም ቢሆን ሁልጊዜ በቢሯቸው ደንበኞችን እንደሚያስተናግዱ ራሳቸው ደንበኞች ምስክር ናቸው። በጊፍት ሪል እስቴት ደንበኞች ቀን ሳይወሰንባቸው ስድስቱንም የስራ ቀናት መጠቀም ይችላሉ፣እየተጠቀሙበትም  ነው። ጸሃፊው በይመስላል ከመጻፍ ይልቅ የአዲስ አበባ ነዋሪ ከሆኑ ቢሮ መጥተው የሚያነጋግራቸው አጥተው ከሆነ በግልጽ ቢናገሩት መልካም ነበር። ማስረጃ አልባ ክስ ክፋቱ ከስም ማጥፋት አለመዝለሉ ነው።

እንደማጠቃለያ

አንባቢ ይህንን ለጸሃፊው የተሰጠ ምላሽ ሲያነብ “ጊፍት ሪልእስቴት ከማንኛውም ችግር የጸዳ ነው” የሚል መልዕክት ለማስጨበጥ ታልሞ የተጻፈ አድርጎ እንዲገነዘበው ኩባንያው ፍላጎቱ አይደለም። ከላይ ለመግለጽ እንደተፈለገውና ጸሃፊው ራሳቸው በመንደርደሪያቸው እንዳስቀመጡት በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ከጀማሪነት ደረጃው ከፍ ባለ እርከን ላይ እንዳይቀመጥ ባደረጉት በብዙ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ውስጥ ያለ ዘርፍ ነው። እነዚህ ችግሮች በኩባንያዎቹ ላይ ሲጫኑ ደንበኞችም ችግሩ የሚያስከትለውን ጫና በከፊልም ቢሆን መሸከማቸው እውነት ነው።ያም ሆኖ ጊፍት ሪል እስቴት በተቻለ መጠን ደንበኞች ለከፈሉት ገንዘብ እርካታ አግኝተው የሚወጡበት ሰርዓት እንዲፈጠር ጥረት እያደረገ ነው።ቅሬታዎች ቢኖሩም ቅሬታዎቹን “ደንበኛ ሁሌም ትክክል ነው” በሚለው የኩባንያው መርህ መሰረት በማስተናገድ  በጋራ መግባባት የተጀመሩትን ስራዎች ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ ፍላጎትና አቋም አለው። ነገር ግን ሆን ተብሎ የኩባንያውን መልካም ስምና ዝና በሃሰት መረጃዎች ለመጉዳትና በደንበኞቹ ዘንድ እምነት እንዲያጣ ለማድረግ እንደ ‘አበበ ወርዶፋ’ ባሉ ግለሰቦች የሚፈጸሙትን ደባዎችን ኩባንያው በዝምታ ሊያልፈው አይችልም። አንድን በህግ የህግ ሰውነት የተሰጠው ኩባንያ ስም ማጥፋት በህግም በሞራልም ተቀባይነት የሚኖረው አይሆንም።

ጸሃፊው በውጭ ሃገራት ሰፊ ጎብኚዎች ባሏቸው ze-habesha.com እና satenaw.com ድረገጾች ላይ ጽሁፋቸው እንዲታተም ያደረጉት ሆን ብለው የሪልእስቴቱን ደንበኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አመለካከት ለመበረዝና ድርጅቱን ለማጣጣል እንዲሁም ኩባንያው ላይ እምነት እንዳይኖራቸው ለማድረግ መሆኑን ጊፍት ሪል እስቴት ይገነዘባል። ጸሃፊው “የኩባንያው ብዙ ደንበኞች በውጭ ሃገራት ስለሚኖሩ ቢበዛ ጮኸው ይሄዳሉ በማለት ሃላፊዎቹ ምላሽ አይሰጡም” ላሉት በርግጠኝነት የድርጅቱ ደንበኛ አለመሆናቸውን ያመለክታል። ምክንያቱም ኩባንያው በዘረጋው የመረጃ ግልጽነት ስርዓት እያንዳንዱ ደንበኛ በኩባንያው ኦፊሺያል ዌብሳይት ላይ በተከፈተለት አካውንት የቤቱ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ በፎቶግራፍ ጭምር እንዲያይ የሚደረግ ከመሆኑ በተጨማሪ የተለያዩ መረጃዎችን እንዲሁም ደንበኛው ያለውን ማንኛውንም አስተያየትና ቅሬታ በኢሜይል መልዕክቶች በመለዋወጥ የየዕለት ክትትልና ግንኙነት ያደርጋል።

እነዚህ ሁሉም የጊፍት ሪልእስቴት ደንበኛ የሚያውቃቸው ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች የጸሃፊውን መረጃ ትክክለኛ አለመሆን ያሳያሉ። ከዚህ በተጨማሪም ዌብሳይቱ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ የሁሉም የጊፍት ደንበኞች እምነት አለመሆኑን ቢያንስ ይህ ጽሁፍ ለድረገጹ እስከተላከበት ቀን ድረስ የጸሃፊውን ሃሳብ ደግፎ አስተያየት የሰጠ አንድም ሰው አለመኖሩ  ቀላል ማሳያ ነው። በመጨረሻም  ጸሃፊው በርዕስነት ለተጠቀሙበት “ጊፍት ሪል እስቴት ወደፊት ወይስ ወደኋላ?” የሚል ጥያቄ ኩባንያው አጭር ምላሽ ሊሰጣቸው ይወዳል። “የጊፍት ሪል እስቴት ጉዞ በስም ማጥፋት ዘመቻ ወደኋላ አይመለስም !”

በዚህ አጋጣሚ ጊፍት ሪል እስቴት ስሙ ተጠቅሶ ለወጣበት ጽሁፍ ተገቢ ነው ያለውን ምላሽ ሲልክ ze-habesha.com እና satenaw.com ድረገጽ ሃላፊነት እንደሚሰማቸው ሚዲያዎች ተቀብለው ለንባብ በማብቃታቸው ኩባንያችን ከፍ ያለ ምስጋናውን ሊያቀርብላቸው ይወዳል።

 

The post የጊፍት ሪል እስቴት ጉዞ በስም ማጥፋት ዘመቻ ወደኋላ አይመለስም appeared first on Zehabesha Amharic.

የጦርነት ድባብ ያቀዘቀዘው ምርጫ! –አምዶም ገብረሥላሴ ከመቀሌ

$
0
0

የዘንድሮ ምርጫ ኣሸንፎ ለመውጣት የህወሓት መንግስት ኣርባው ሲያስወጣ “…ከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጥሬ ድጋፍ ኣገኛለው…” ብሎ ኣስቦ ነበር። ይሁን እንጂ ከድጋፍ በላይ ተቃውሞ በመውለድ ያሁሉ ጥረቱ መና ሁኖ መቅረቱ ህወሓት ተረድተዋል። ድሮም በወከባ የሚገኝ ህዝባዊ ድጋፍ እንደሌለ የሚታወቅ ነው።
Ethiopian soldiers ride on an army truck on the road to Afgooye, south of Mogadishu
ህወሓት ጥረቱ ከንቱ ሲቀር የዘየደው መላ በትግራይና የሚያዋስኑት የኢትዮ ኤርትራ ድንበር ኤርትራ የጦርነት ድባብ በመፍጠር የምርጫው ኣቅጣጫ ለማስቀየስ እየሞከረ ነው። የዚህ ማሳያ “..የኢትዮዽያ ኣየር ሃይል የወርቅ መዓድንና የትጥቅ መጋዘን ደብድበው ጉዳት ኣድርሰዋል..” የሚል በፌስቡክ ካድሬዎቹና በድህንነት ኣካላት በሰፊ እንዲወራ ኣድርገዋል።

የዚህ ምላሽ ተብሎ የተገለፀው ደግሞ “..ሻእብያ ሶሎዳ ተራራን(ኣድዋ ከተማ ኣጠገብ የሚገኝ) በሚሳይል እንደደበደበ..” እነ ዳኒኤል ብርሃነ ኣበሰሩን። ምድረ ካድሬም “..ኣሸው..” እያሉ ለኣየር ሃይላችን ኣንቆለዻዸሱት።

ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለይም ስለ የኣየር ጥቃቱ ሲጠየቁ “..ተደበደብኩ የሚል ኣካል ሲኖር መልስ እንሰጣለን…” የሚል ኣመላካች የእምነት ቃል ገለፁ።

“…በኣንዳንድ የኢትዮ-አርትራ ድንበር የተወሰነ ወተሃደራዊ እንቅስቃሴ መኖሩና ይህንን ተከትሎ የህብ መፈናቀል እንደተስተዋል..” የፌስቡክና ምንጭቻቸው በግልፅ የማይታወቁ ወሬዎች በትግራይ ክልል እንዲወሩ ተደረገ።

የመቐለ መስተዳደርም የዚህ ወሬ ከሚያራግቡ ኣካላት ኣንዱና ዋነኛው ነበር። በከተማዋ የሚገኙ የባጃጆችና የታክሲ ሹፌሮች በማዘጋጃ ቤት ኣዳራሽ በመሰብሰብ “..ፀጉረ ለወጥ ሰው ስታስተናግዱ መታወቅያ ጠይቁ፣ መኪኖቻቹና ባጃጆቻቹ ፈንጅና ሌላ ተቀጣጣይ ነገር እንዳይጠመድባቸው በንቃት ጠብቁ..” የሚል ማስጠንቀቅያ ሰጣቸው።

በማስቀጠልም “..በመከላከያችን ጥቃት ደረሰ፣ ይህን ያክል ሰው ሞተ፣ ቆሰለ የሚል ኣሉባልታ እንዳታምኑ፣ እንዳታወሩ..” ወዘተ የሚሉና የውትድርና ምልመላ ማስታወቅያዎች በማስተዋወቅ ህዝቡ የጦርነት ስጋት እንዲያድረው እየተደረገ ነው።

እነዚህ ወሬዎች የትግራይ ክልል ህዝብ ትኩረቱ ከምርጫው ይልቅ በሚናፈሱ ወሬዎች እንዲያደርግና የጦርነት ድባብ እንዲሰማው እየተደረገ ነው።
ይህ ህዝቡ በጦርነት፣ ወተሃደራዊ ጥቃት፣ የሽብር መንፈስ እንዱያድረውና የነዚህ ክፉ ወሬዎች ውጤት የሆኑት መልኣከ ሞት፣ ስደትና ችጋር ወደ ህሊናው እንዲመጡና የምርጫው ትኩረቱ እንዲቀይር እየተደረገ ነው።

በዚህ ኣካሄድ በትግራይ ክልል ምርጫ ማካሄድ በማይቻልበት ሁኔታ ላይ ነው ያለው። ህዝቡ በተረጋጋ ሁኔታ መብቱን መጠቀም እንዲችል የምርጫው የግዜ ሰሌዳ ለሌላ ግዜ ማራዘም ግድ ይላል።

በተለያዩ ኣካላት እየታነፈሰ ያለው ወሬ ሃቅነት ይኑረው ኣይኑረው ህዝቡን በተረጋጋ ሁኔታ ይበጀኛል የሚለው እጩ ተወዳዳሪና ድርጅት መምረጥ ካልቻለ ለኣገራችን ሰላምና እድገት ኣሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ግድ ይሆናል።

የህወሓት መንግስት ከምርጫ ይልቅ የጦርነት ድባብ ማስፈኑ ምክንያት ከትግራይ ህዝብ ያጣው ድጋፍ ተረድቶ ምርጫው ኣጨናግፎ ለማለፍ ነው።

ምርጫው ሊጨናገፍ ኣይገባም።

ነፃነታችን በእጃችን ነው..!

IT IS SO..!

The post የጦርነት ድባብ ያቀዘቀዘው ምርጫ! – አምዶም ገብረሥላሴ ከመቀሌ appeared first on Zehabesha Amharic.

በዚህ ሳምንት የተማርናቸው አምስት ነገሮች

$
0
0

ከ7 ኪሎ መጽሔት

1ኛ) ፖለቲካ ለብዙሃን “ውስጡን ለቄስ ነው”
ከሰባት ዓመታት በፊት የቅንጅት እስረኛ የነበሩት አቶ አንተነህ ሙሉጌታ “የሁለት ዓለም ሰዎች” በሚል ርእስ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞችን የሚመለከቱ የፍርድ ቤት ድራማዎች ላይ ያነጣጠረ መጽሐፍ ጽፈው ነበር። መጽሐፉን ያነበበ በዚህ ሳምንት በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የፍርድ ሂደት ላይ የታየው ትዕይንት አይገርመውም። ችሎታ የሌላቸው አቃቤ ሕጎች፣ የመንግሥት ታዛዥ ዳኞች፣ ግራ የተጋቡ እና ያልተዘጋጁ የአቃቤ ሕግ ምስክሮች ላለፉት ኻያ ሦስት ዓመታት የፖለቲካ ችሎቶች ቋሚ ንብረቶች ኾነው ቆይተዋል። ታዲያ ከእነዚህ የፍርድ ቤት ሂደቶች ጋራ ተያይዞ በተደጋጋሚ የሚነሳው ጥያቄ “መንግሥት ራሱን በዚህ ደረጃ ከሚያዋርድ፤ እንዲሁም የማይረባ አማተር የደረሰው እና ያዘጋጀው የሚመስለውን ቴአትር ትቶ፤ ለምን ማሰር የሚፈልጋቸውን ያለ ፍርድ ቤት ሂደት ዘብጥያ አውርዶ አይገላገልም?” የሚል ነው። ጥያቄው ከሕጸጽ (fallacy) የመነጨ ነው። ይህ ሕጸጽ በእንግሊዝኛ ኢ-መደበኛ ስሙ Ubiquitous Political Junkie Fallacy ይባላል። ሕጸጹ አብዛኛውን ሰው የፖለቲካ ሱሰኛ አድርጎ የማየት አባዜ ነው። የዚህ ሐሳብ ተጠቂዎች በአብዛኛው ፖለቲካን በቅርቡ የሚከታተሉ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች ናቸው።

እንደዚህ ዐይነት ግለሰቦች ሌሎች ሰዎች ልክ እንደ እነርሱ ፖለቲካን ቀን ከሌት የሚያመነዥኩ ይመስላቸዋል፤ ሐቁ ግን ከዚህ የተለየ ነው። የማሕበራዊ ሳይንስ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አብዛኞቻችን ፖለቲካን በቅጡ አንከታተልም፤ ከተከታተልንም ላይ ላዩን ነው። አምባገነን መንግሥታት ይህን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ፖለቲካን ከላይ ከላይ ለሚከታተሉ ብዙሃን ማሳየት የሚፈልጉት መንግሥታቱ ሥርዐት እና ሂደት የሚያከብሩ፤ ውሳኔዎቻቸውን በመደበኛ ተቋማት የሚያስወስኑ እና በዘፈቀደ የማይመሩ መኾናቸውን ነው። ይህን ለማሳየት ማስመሰል ይበቃቸዋል። ሥርዐት እንዳለ ማስመሰል የዐይነተኝት መንፈስ (aura of legitimacy) ያላብሳቸዋል። የፍርድ ቤት ትዕይነቱ በጥልቅ ሲመረመር ለመንግሥት አሳፋሪ ነው። ይኹንና ይህን ጥልቅ ምርመራ የሚያደርጉ ጥቂቶች ናቸው። የእነርሱ ድምጽ ብዙሃኑ ጋር የሚደርስበት መንገድ ከተዘጋ ንጉሡ ራቁቱን ቢኾን እንኳ ልብስ እንደለበሰ እያስመሰለ መቆየት ይቻለዋል።
Nile Countries
2ኛ) አቴናዊው ቱስይዲዴስ በአባይ ጉዳይ ልክ ነው
እ.እ.ኤ ከ460 እስከ 395 ዓ.ዓ የኖረው አቴናዊው የፖለቲካ ፈላስፋና ጄነራል ቱስይዲዴስ የጌም ቲዎሪ አባት ተደርጎ ይወሰዳል። ከቱስይዲዴስ ታላላቅ ሐሳቦች መካከል አንዱ የሐይል ልዩነትን አንጻራዊነት የሚያትት ነው። ጊዜና አውድን በሚገባ የሚያጤን እና የሚጠቀም ደካማ ባለጋራ በረዥም ጊዜ በብልሃት ጠንካራ ባላጋራን ሊገዳደር ይችላል። የአባይ ፖለቲካ ለዚህ ተምሳሌት ነው። የግብጽንና የኢትዮጵያን ፍጹማዊ ሐይል በግልጽ መለኪያዎች ብንገመግም ልዩነቱ በጣም ሰፊ ነው። ይህ ልዩነትም በአባይ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ ለረዥም ጊዜ ሲንጸባረቅ ቆይቷል። እ.ኤ.አ. በ1959 ግብጽ ኢትዮጵያን ወደ ጎን አድርጋ ከሱዳን ጋር አባይን ለሁለት ለመጠቀም ስትስማማ ኢትዮጵያ ስምምነቱን አጥብቃ ብትቃወምም ከጩኸት አልፋ ጠጠር ልትገፋ አልተቻላትም። ዐፄ ሐይለሥላሴና ደርግ ግድብ ለመገንባት ቢነሱ ግብጽ የተለያዩ መንገዶችን (እርዳታ ማስከልከል፣ አማጽያንን መርዳት ወዘተ) ተጠቅማ ፈቅ እንኳ ሳይሉ እንዲያቆሙ አድርጋቸዋለች።

እ.ኤ.አ. በ2011 በግብፅ የሕዝብ አመጽ ተቀስቅሶ የመንግሥት አለመረጋጋት ማስከተሉ ለኢትዮጵያ ያልታሰበ ዕድል ፈጠረላት። ብርታኒያዊው አድሚራል ዊልያም ሄልሲ ለደካሞች እንዲህ ዐይነት ዕድል ሲፈጠር “strike fast, strike hard” ሲሉ እንደመከሩት ኢትዮጵያ ዕድሉን ለመጠቀም በፍጥነት ተንቀሳቀሰች፤ የግድቡ ግንባታ ተጀመረ፤ የአባይ ተፋሰስ አገሮችን ከግብጽ በተቃራኒ ማስተባበር ቀጠለ። በውስጥ ችግር ተወጥሮ ያልተረጋጋው የግብጽ መንግሥት ለዚህ እንቅስቃሴ ፈጣን አጸፋ ለመስጠት የሚያስችል ትንፋሽ አልነበረውም። ጀነራል ሲሲ ሥልጣን ላይ ወጥተው መንግሥትን ሲያረጋጉ ደግሞ መሬት ላይ ያሉት ኹኔታዎች ተቀይረዋል። ለ2014 ኹኔታዎች እንጂ ለ2010 ኹኔታዎች መልስ መስጠት እንደማይቻላቸው አውቀው ወደ ድርድር መጡ። የድርድሩ ውጤት የኾነው የፖለቲካ ስምምነት ግብጽ ሳታወላውልና ሳታመነታ ስትከላከለው የነበረውን የ1959 ኪዳን በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል። 2010 ላይ ኾነን ከአምስት ዓመት በሁዋላ ኢትዮጵያ እና ግብጽ የ1959ን ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥል የፖለቲካ ውል ይገባሉ ተብሎ ቢነገረን ለማመን እንቸገር ነበር። የቱስይዲዴስን ነፍስ ይማር።
ali birra
3ኛ) ዐሊ ቢራ ብረት ነው
ለፖለቲካ ዘፋኞች ክብርና ተምሳሌትነትን እንደተጎናጸፉ ዘመንን መሻገር እጅግ አስቸጋሪ ነው። መጠነኛ የሐሳብ ለውጥ ካሳዩ ወይም ያሳዩ ከመሰሉ አድናቂዎቻቸው በድንገት ይገለበጡባቸዋል። ፖለቲካ የጋለ ስሜት የሚቀሰቅስ ጉዳይ በመኾኑ ከቀድሞ ተከታዮቻቸው የሚደርስባቸው ነቀፌታ ምሬት ያዘለ ነው። አንዳንዴ አደጋው የሚመነጨው ሐሳብን ከመቀየር ብቻ ሳይኾን ካለመቀየርም ነው። ዘመን ሲቀየርና ደጋፊዎቻቸው ሐሳባቸውን ሲለውጡ የፖለቲካ ዘፋኞች የቀድሞ አቋማቸውን ይዘው የሚቀጥሉ ከኾነ ዕጣ ፈንታቸው በሐሳብ ለውጥ ችግር ውስጥ ከሚገቡቱ የተለየ አይደለም። ተጠንቅቆ መጓዝም ዕድሜን በመጠኑ ያራዝም እንደኾን እንጂ ዘመን አያሻግርም። ዝናቸውንና ክብራቸውን ጠብቀው ዘመን የሚሻገሩ የፖለቲካ ዘፋኞች በአብዛኛው አጠቃላይ እና ዕቡይ በኾኑ ሐሳቦች ላይ የሚያተኩሩቱ እንጂ መሬት የሚነካ ጭብጥ የሚያነሱቱ አይደሉም። መዝፈን የጀመረበት ኢዮቤልዩ እየተከበረለት ያለው ታላቁ ዐሊ ቢራ የኦሮሞ ብሔርተኝነትን እና ጸረ ጭቆናን ያነገቡ መሬት የወረዱ ዘፈኖችን በማቀንቀን ይታወቃል። ሃምሳኛ ዓመቱን እያከበሩ ያሉት በተለያዩ ተቀናቃኝ ድርጅቶችና ጎራዎች ውስጥ የተሰለፉ እና ያልተሰለፉ ኦሮሞዎች ናቸው። የኦፕራይዱ ጸሐፊ መሐመድ አዴሞ እንዳስቀመጠው “ብሔራዊ ተምሳሌት፣ ጀግና፣ ፈር ቀዳጅ፣ የኦሮሞ ሙዚቃ ንጉስ” እያሉ የሚያንቆለጳጵሱት የአንድ ወይም የጥቂት የፖለቲካ ቡድን/ቡድኖች አባላት ብቻ ሳይኾኑ በፖለቲካዊ አቋማቸው እዚያና እዚህ የቆሙት ጭምር ናቸው። የኦሮሞ ብሔርተኛ ፖለቲካ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት በነውጥና በውዝግብ ውስጥ እያለፈ ነው። ዐሊ በዚህ ታሪክ ውስጥ ቢያልፍም የተጎናጸፈው ሕየንተ ክብር ሳይፈርስ ለወርቅ ኢዮቤልዩ መብቃቱ ከድንቆች ያስመድበዋል።
bob geldof ethiopia
4ኛ) ቦብ ጌልዶፍ በጎ አድራጎትና ኢንቨስትመንትን እያምታታ አስቸግሯል

አየርላንዳዊው አቀንቃኝ ቦብ ጌልዶፍና ኢትዮጵያ የጋብቻ ቀለበት ካሰሩ ድፍን ሰላሳ ዓመት ሞልቷል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጋብቻው የተመሠረተው በጌልዶፍ ደግ ሳምራዊነት ላይ ነበር። አሁን ግን ጌልዶፍ በኢትዮጵያ ስም ርዳታ መሰብሰብ እና ርዳታ ሰጪዎችን ሎቢ ማድረግ ትቶ ምዕራባውያን ባለ ሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ኢንቨስት እንዲያደርጉ መወትወት ጀምሯል። በዚህ ሳምንት በተለያዩ ዓለማቀፍ ሚዲያዎች ቀርቦ ሐሳቡን አስረድቷል። ነገር ግን ጌልዶፍ “ኢትዮጵያ ሄዳችሁ ኢንቨስት አድርጉ” ሲል ፈላስፋውና ኢኮኖሚስቱ አዳም ስሚዝ ባስቀመጠው የኢንቨስትመንት ጽንሰ ሐሳብ መንፈስ አይደለም። ስሚዝ እንደሚለው ኢንቨስትመንት ኢንቨስተሩ ለራሱ ጥቅም ሲል የሚገባባት ከግል ፍላጎት (private interest) የሕዝብ ጥቅም (public virtue) የሚገኝበት ነው። ጌልዶፍ የሚቀሰቅሰው ግን እንዲህ ሲል ነው። “ትኩረት ሳትሰጣቸው ቀርተህ በርካቶች መሞት የለባቸውም፤ አፍሪካ ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ ሊያስገኝ የሚችለው ጥቅም ሌላ ቦታ ከሚገኘው የላቀ ነው።” ይህ ሐሳብ ኢንቨስትመንትንና ደግ ሳምራዊነትን የሚቀላቅል ነው። ‘ድመት መንኩሳ ዐመሏን አትረሳ” ብለን እንለፈው።

abay Tsehaye
5ኛ) የቃላት ዕብሪተኝነት ያለመረጋጋት ውጤት ነው

ውስጣዊ ጽናት የማጣት (insecurity) ስሜት ችግር ያለባቸው መሪዎችና ፖለቲከኞች ችግራቸውን ለመሸፈን ከሚጠቀሙባቸው ማካካሻ ጠባያት መካከል አንዱ የቃላት ዕብሪተኝት እንደኾነ ሳይኮሎጂስቶች ይነግሩናል። ሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፤ በመግለጫቸው ሲደነፉና ዕብሪት የተቀላቀላበቸውን ቃላቶች በተደጋጋሚ ሲጠቀሙ አስተውለናል። እነዚህንም መልሶች የሰጡት መፈናፈኛ ለሚያሳጡ ብቻ ሳይኾን ለገራገር የማብራርያ ጥያቄዎችም ነበር። ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እንዲህ ዐይነት መረን የለቀቀ ዛቻና ስድብ መጠቀም፣ ማንጓጠጥ እና ንቀት መደርደር ያልተለመደ አይደለም። አቶ መለስ ዜናዊ በዚህ የተካኑ ነበሩ። ሬድዋን ሁሴን፣ አባይ ጸሐዬ፣ ሽመልስ ከማልና በረከት ስምዖን ካላሽሟጠጡና ካልዛቱ የቦተለኩ አይመስላቸውም። ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ 24 ዓመት ኾኖታል። በእነዚህ ዓመታት ከ1997 በስተቀር በትረ ሥልጣኑን የሚነቀንቅ ከውጪ የመጣ ጠንካራ ግፊትና ጥቃት አልደረሰበትም። እንደብዙ የአንድ ፓርቲ አምባገነኖች የኢሕአዴግ መንግሥትም የተረጋጋ ረዥም ዕድሜ አሳልፏል። ነገር ግን የባልሥልጣነቱ የማይለወጥ ዕብሪተኝነት በስጋትና ባለመጽናት ስሜት እንደተዘፈቁ ጠቋሚ ነው። ናሲም ታሌብ የተባሉ ምሁር በአምባገነን ሥርዐቶች ዝግ መኾን ምክንያት የሚፈጠሩ የኢንፎርሜሽን ችግሮች (information problems) ተጠቂዎች ተገዢዎች ብቻ ሳይኾኑ የአገዛዙ መሥራችና አንቀሳቃሾችም ጭምር እንደኾኑ ያስረዱናል። እንደ ምሑሩ ከኾነ አምባገነኖች ስለ ራሳቸው ያላቸው እውቀት ከምናስበው በታች ደካማ ነው። የኢትዮጵያ ባለ ሥልጣናት የማያባራ የቃላት ዕብሪት ራስን ካለማወቅ የመነጨ አለመረጋጋት የፈጠረው ይኾን?

The post በዚህ ሳምንት የተማርናቸው አምስት ነገሮች appeared first on Zehabesha Amharic.

የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው!”–የጐንቻው

$
0
0

yengochaw

ማስታወሻነቱ፡-

አባይ ከብሄራዊ ስነ- ልቦናችን፤ ማንነታችን፤ ከታሪካችን፤ መልካ ምድራዊ አሰፋፈራችን፤ተፈጥሯዊ ትሥሥራችን ጋር ተቆራኝቶ ሺህ ዘመን አብሮን የነጐደ ከወንዝ የበለጠ ትርጉም፤ስላለውም እንደየዘመኑ የኑራችንን ፈተና ልንሻገርበት ምኞትና ሕልም ቋጥረን የምንፈታበት፤የእድገትና የልማታችንን ቁጭት የምንገልጽበት ሚስጥራዊ ኃይል መሆኑን የተረዱ የዘመኑ ‘ብልጣብልጥ ገዥዎች’ በቀውጢው ሰዓት፤በፊታውራሪነት ከሚስጥር ኪሳቸው ሳይታሰብ ‘ህዳሴ ግድብ’ ብለው የመዘዙት ካርድ፤ነበርና አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ከኪስ ባለፈ፤በገዘፈ ብዙ፤ብዙ አስወጥቶታል።

[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

 

 

 

The post የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው!” – የጐንቻው appeared first on Zehabesha Amharic.

ድምጽ ከመስጠት ደም መስጠት   (አብርሃም Hታዬ)

$
0
0

በቅድሚያ ይሄን አስተማሪ ቀልድ ጀባ ልበላችሁ

electionአንድ ግለሰብ ይሞትና ነፍሱ ዳኞች ፊት ቀረበ።እንደ አጋጣሚ ለወደፊት የሚኖርበትን ገነትን ወይም ሲኦልን ገብኝቶ የመምረጥ እድል ተሰጠው።በመርሐ-ግብሩ መሰረትም በመጀመሪያ ሲኦልን እንዲጎበኝ ይጋበዝና ገና ከበሩ ላይ በመልካም አለባበስ የተሸቆጠቆጠው ሳጥናኤል በሞቀ ሰላምታ ተቀብሎት ወደ ውስጥ ይዞት ይገባል።ገሃነም ውስጥ የሟች የድሮ ወዳጆች ሁሉ ተሰብስበው እየጠጡ፣ ከረንቦላ እየተጫወቱ፣ ዲኤስ ቲቪ እያዩ እና በሙዚቃ እየጨፈሩ አስደሳች ጊዜ ሲያሳልፉ ተመለከተ።

ከዚያም ወደ ገነት ተወሰደ። ገነት እንደ ገባ አንድም የድሮ ጓደኛውን ሊያገኝ አልቻለም። ከዚያም በላይ ሲያስበው ያስመረረው ግን በገነት ያሉ ሰዎች ነጫጭ ለብሰው ስራቸው  ማሸብሸብ፣መጸለይና መስገድ ብቻ መሆኑ ነው ።

ሟች ሁለቱንም ሁኔታዎች አመዛዝኖ ሲያበቃ ገሃነም ከወዳጆቹ ጋር ለመቀላቀል ወስኖ ፊርማውን አኖረ። በማግስቱ ወደ ገሃነም ሲወሰድ ግን የጠበቀው ነገር ሌላ ነበር። ሳጥናኤል በአስፈሪ ዕርቃኑ ቆሞ እህል-ውሃ የማያሰኝ ጅራፍ ይዞ እየዠለጠ ወደ ውስጥ አስገባው። ውስጥ የነበሩት ጓደኞቹም ግማሽ ሰውነታቸው በእሳት ተዘፍቆ ሲሰቃዩ ተመለከተ።  ወደ አንድ ጓደኛው ጠጋ አለና ‹‹ትላንትና ያየሁት ደስታ የት ሄደ?›› ብሎ  ቢጠይቀው። ‹‹አይ እሱማ የምርጫ ቅስቀሳ ነው›› ብሎት እርፍ!

በሃገራችንም ምርጫ ሲደርስ ገዢው ፓርቲ የኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ ደርሷችኋል ይለናል ቤቱ ግን ኣልተሰራም ወይ አላለቀም።የገባንባቸው ቤቶችም ፍሳሽ ከላይ ወደታች ሰው ላይ ይንጠባጠባል:: ምርጫ ሲደርስ ሰላማዊ ሰልፍ ይፈቅድልናል ስንወጣ ግን መንገድ ይዘጋብናል፥ የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተሮች ይቀዱብናል፤ያስሩናል፤ ይደበድቡናል። እስከምርጫው ዋዜማ በየቀበሌው በየሰፈሩ እየዞሩ ድጎማ ይሰጡናል ይደልሉናል በምርጫው ማግስት አይናችንንም ማየት ይቀፋቸዋል።

ባለፉት አመታት ሊሰሩ ታቅደው የመሰረት ድንጋይ የተጣለባቸውን ቦታዎች እስካሁንም ሳይሰራ ተጎልቶ ምርጫ ሲደርስ ተጠቅላይ ምኒስተር ሃይለ ማርያም ደሳለኝ በወሎ መሰረት ድንጋይ ጣሉ ወይም ባላፈው የተመረቀ የዉሃ ማቆሪያ መረቁ ይሉናል በድጋሚ።ሃገር አቀፍ ምርጫ በደረሰ ቁጥር ወተት እንደ ዉሃ በቧንቧ አስገባለው እያለ የሚለፈልፈው መንግስታችን የተዋጣለት ፎጋሪ መሆኑን የሚያንጸባርቀውን የቀላል ባቡር ምርቃ እንመልከት።  አዲስ አበባን የበርሊን ግንብ ኣስመስሎ ለሁለት የከፈላት  የባቡር መንገድ ግንባታ አንድ ሰው ከሳሎን ቤቱ ወደመኝታ ቤቱ ለመሄድ የአንድ ሰአት ታክሲ መንገድ ርቀት ሆኖበታል። ሃዲዱ  ተመርቋል ተብሎ የካቲት ላይ ተነግሮን አገልግሎት የሚጀምረው ግን  ከሶስት ወር ኋላ ምርጫ ሲቃረብ  ነው ያሉን ያው ለምርጫው ማሟሟቂያ ዘገባ ካንድም ሁለቴ ሲመረቅም ሲጀመርም በመተረክ ህዝቡን በወሬ ለማጥገብ ነው። በተግባር ግን መንገዱ ከመሰራቱ ከ 6 ጊዜ በላይ ከባባድ የመኪና ግጭቶች ደርሰውበታል። አሰራሩ የይድረስ ይድረስ ስለሆነ የብረት አጥሩም የባቡሩ ሃዲድም ገና በድምጽ ይደረመሳል። የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ የሚለው አባባል ለፎጋሪው ወያኔ የተጠቀሰ እስኪመስል ድረስ ቻይና ሰራሽ መንገዶች ድልድዮች ሲልም ህንጻዎች ገና አመት ሳያገለግሉ ይሰነጣጠቃሉ ከጥቅም ውጭ ይሆናሉ።የቀለበት መንገድም ሆነ ቀላል ባቡር  የእግረኛ መንገድ ስለሌለው  በታጠረው የባቡር እና የመኪና   መንገድ እግረኞች  ሲዘሉ ሲሻገሩ ለአደጋ ይጋለጣሉ።

ገና ከመሰራታቸው ከተቆፈሩት መንገዶች አንዱ ዛሬ ባቡር መንገድ ተብሎ የታጠረው ከመስቀል አደባባይ ወደ ሳሪስ የሚወስደው ሰፊ የአስፋልት መንገድ መሆኑ መረሳት የለበትም። ከ2005 አም በፊት ለመኪና ብቻ ተብሎ የመስቀል አደባባይ ሳሪስ መንገድ ሲሰፋ በርካታ ሰዎች ካካባቢው ተነስተዋል ከቁፋሮ ጀምሮ  እስከ  አስፋልት የማልበስ ድረስ ከፍተኛ የዉጪ ብድር ገንዘብ ተከስክሶበታል። ይሁንእና  ስንት ወጪ ፈሶበት በተሰራው ባለሶስት መስመር መንገድ መኪኖች ሸር ማለት እንደጀመሩ ለባቡር መሆን አለበት የሚል ሃስብ በደንገት ብልጭ ባለበት የመለስ  የትራንስፎርሜሽን ቅዠት ምክንያት  ያው አስፋልት በድጋሚ ለባቡር ተብሎ ታጠረ ተቆፈረ አሁን ደሞ ተመረቀ ሲባል  አንድም ባቡር ሳይሄድበት ተሰባበረ።እንግዲህ ወያኔዎች ለ አዲስ አበባ ህዝብ በአምስት አመቱ የ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት ሰራንልህ የሚሉት  ፉከራ ፉገራ ሲሆን እያየነው ነው። እውነታው ግን ድንጋይ መንገድ ላይ ከምሮ ሰውን ሁሉ ቃሊቲ አስሮ ማሰቃየት ነው::

በድፍረት ምርጫ ዲሞክራሲያዊ የሚያሰኘው ሂደቱ ነው እንጂ ውጤቱ አይደለም የሚለን የመንግስት የኮሚኒኬሽን ሃላፊ የእስካሁኑ ሂደት ዲሞክራሲያዊ ነው ብሎ መግለጫ ይሰጣል። ለመሆኑ  ጽሁፍን ሳንሱር ማድረግ ህገመንግስቱን የሚጻረር አይደለምን? ይሄው እስካሁን እንኳ ሰማያዊ ፓርቲ ከ10 ጊዜ በላይ የምረጡኝ ቅስቀሳውን በአንድዬዋ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ እንዳያቀርብ ተከልክሏል። ተለጣፊ የሚባለው መ ኢ ኣ ድ እና የተቃዋሚ ካባ ለብሶ የሚጫወተው ኢህአዴጉ ኢዴፓም የቅስቀሳ መልክቶቼ ሳንሱር እየተደረጉብኝ ነው ሲሉ ስንሰማ ወያኔ የራሱ የሆኑት እንኳ ለዘብተኛ ተቃውሞ ወይ ውዳሴ  ላለማዳመጥ መቁረጡ አምባገነንነቱ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን ያረጋግጣል።

ህወሃት ኢህኣዴግ ሙሉ ሃያ አራት አመት ሙሉ ሃያ አራት ሰዓት እየደሰኮረ  በአምስት አመት አንዴ ለዛውም አንዲት ሰዓት  ለማይሞላ የተፎካካሪ ፓርቲ የሚሰጥ የአየር ሰዓት  ከተከለከለ  ህዝቡ ተፎካካሪ ፓርቲን መኖሩን ካልሰማ ቀጣይ አመታትን በድህነት፥ በ ኢ-ፍትሃዊነት፥በዘረኛው  ስርዓት ወስጥ መክረሙ አሌ ኣይባልም።

ምንም የግል ሚዲያ በሌለበት ሁኔታ በብቸኛው የመንግስት ቲቪ እና ራዲዮ ካመት ኣመት የሚሰለቸውን ወሬ መስማት ብዙ ኢትዮጵያውያንን አስመርራል ። ተፎካካሪ ፓርቲዎች ኣላማቸውን ባላስተዋወቁበት ሁኔታ ህዝቡን ንብን ይምረጡ ሲል ግራ ያጋባል። ሌሎቹን ከልክሎ ኣፍኖ እና አስሮ ብቻውን ምረጡኝ እያለ የህዝቡን የመዝናኛ ፕሮግራሞች የማየት ፍላጎቱን ገድቧል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫ ዘጠና ሰባት ተመሳሳይ የኮንዶሚኒየም ቤት ምርጫ ሲደርስ የተሰጠው እና  በገንዘብም የተደለለ ቢመስልም በነበረችው ትንሽ ቅስቀሳ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን መርጦ ነበረ።ይሁንእና በማግስቱ ለምን ቅንጅትን መረጣቹ ብሎ ለምርጫ ቅስቀሳ ያሳየንን ፊት ነስቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታስረዋል ተገድለዋል አሁንም የበቀል ሰለባ ሆነዋል::  ያኔ የተሰለፍነው የሚመረጥ ስለነበረ ሲሆን አሁን ግን ደም መጣጩን ከምንመርጥ ብንታቀብ ይበጃል::ሃሳብን የመግለጽ መብት በይፋ በተዘጋበት በዚህ ወቅት መከራከር ራስ ላይ ሰበብ መጠምጠም ነው::

በ አሁኑ ኣለም ቀፍ ታዛቢዎች በማይገኙበት የኣውሮጳ ህብረት ምርጫውን እንዳይታዘብ በተከለከለበት በዚህ ወቅት ከምንም በላይ ታዛቢው ህዝብ  የወያኔን እንጂ የሌላን ፓርቲ ኣላማ እንዳይሰማ ገድበው፥ የምርጫ ቆጣሪዎች ሳይቀሩ ከወያኔ ሴት ሊግ ወጣት ሊግ ያለህዝብ ይሁንታ ተመርጠው የምርጫ ድምጽ ለመስረቅ ለማዛባት ኣቆብቁበው፥ የሰማያዊን ከሁለት መቶ በላይ ዕጩዎች መወዳደር ኣትችሉም ብለው ያለህግ አግደው፥ በአጠቃላይ በዘንድሮው ምርጫ የመወዳደሪያ ሜዳው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጠበበ መምጣቱን የሚያሳይ ተግባራት ተከምረውብን የሚቆሰቁሱን ድምጽ ለመስጠት ሳይሆን ደም ለመስጠት  ነው።

ከገባን የምርጫ አጃቢ አድርጎን በሗላ ጅብ ሆኖ ከሚበላን ለወንበዴ ወያኔ ድምጽ ከመስጠት ለነጻነት ደም ብንሰጥ ይቀላል።

የቀድሞው የ አሜሪካ ፕረዚዳንት እብርሃም ሊንከን Ballot is stronger than bullet የምርጫ ካርድ ከጥይት የጠነከረ ነው ቢልም በሃገራችን የምርጫ ሳጥኖች በጠበንጃ ሲቀየሩ ስላየን  We are forced to use bullet instead of ballot የሃይል አማራጭ እንድንጠቀም እንገደዳለን።

እነ እስክንድር ነጋ ወይ ርእዮት አለሙ ብቻ ሳይሆን መላ ኢትዮጵያውያን ስለታሰርን በቅድሚያ ልንፈታ ይገባል።

ከአብርሃም ታዬ

The post ድምጽ ከመስጠት ደም መስጠት   (አብርሃም Hታዬ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የመረጃ ግብአት…የ”ወሳኙ ማዕበል”ዘመቻ 9ኛ ቀን ውሎ አበይት ክንውኖች –ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓም

የመረጃ ግብአት…

የ” ወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ 9ኛ ቀን ውሎ አበይት ክንውኖች

Nebiyu Sirak* በ9ኛ  ቀን በሳውዲ መራሹ  ” ወሳኙ ማዕበል !” የአየር ማጥቃት ዘመቻ በየመን  ሰማይ በተጠኑ ወታደራዊ የሁቲ አማጽያን ይዞታዎች ላይ አየር ድብደባው መቀጠሉን የዘመቻው መምሪያ ቃል አቀባይ ብ.ጀኔራል አህመድ አሲሪ ናቸው ፣ ጀኔራሉ በዚሁ መግለጫች በወደብ ከተማዋ በኤደንም የሁቲ አማጽያ አልበገርላቸው ካለው የአካባቢ ሚኒሽያ ጋር ውጊያ መግጠማቸውን አስረድተዋል

* ከሁቲ አማጽያንን ኤደንን እንዳይቆጣጠሩ በአካባቢው ሚኒሽያ በመሬት ቃታ እየሳበ እንቅስቃቀሴያቸውን ሲያሽመደምደው በሰማይ የህብረቱን ጦር በተጠኑ  ኢላማዎች ላይ እንዲያተኩር በማድረግ በሚከወነው ድብደባ አማጽያኑን አቅመ ቢስ አድርጎ እንዳዳከማቸው ቃል አቀባዩ ተናግረዋል

*  ቃል አቀባዩ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሰርጎ የሚገባባትን በሚዮን ደሴት Meon Island የሚገኙ የባህርና ሃይሉና የእግረኛው  ጦር መሳሪያዊች በሳውዲ መራሹ የአየር ድብደባ ኢላማ ገብተው ተደምስሰዋልም ብለዋል

* በአየር ድብደባው ተስፋ የቆረጡና የተዳከሙት የሁቲ አማጽያን በመገናኛ ብዙሃንን ከእውነት የራቁ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን በማሳሳት ላይ ናቸውም ብለዋል ብ.ጀኔራል አህመድ አሲሪ

* በሌላ በኩል እየተካሔደ ስላለው ዘመቻ ማብራሪያ የሰጡት በአሜሪካ የሳውዲ አንባሳደር አድል አልጃብሪ  ዘመቻው በጥሩና በመጥፎ መካከል እንጅ በሱኒና በሸአ የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ሚካሔድ ጦርነት አለመሆኑን ተናግርዋል።  አምባሳደሩ በማከልም የሳውዲ መራሹ አረብ ሃገራት ዋና አላማ በኢራን በሂዝቦላህ የሚመራውን የሁቲ አማጽያን ከስልጣን አስወግዶ ፣  ህጋዊው የፕሬዚ አብድልረቡ መንግስት ወደ ቦታው መመለስ ነው ብለዋል ። አንባሳደሩ የቀድሞው የየመን ፕሬዚ አሊ አብደላህ ሳላህን በሚመለከት ሲናገሩ አሊ አብደላ ሳላህ ከሁቲዎች ጎን መሰለፋቸው  የተሳሳተ አካሄድ ነው ሲሉ ነቅፈውታል

በሳውዲ የመን ደንበር ድንበር መገዳደል …

* በሳውዲ የመን ድንበር ባሳለፍነው ረቡዕ አንድ ድንበር ጠባቂ በሳውዲ የመን ድንበር ሁለት የድንበር ጠባቂ መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ትናንት አርብ ተጨማሪ ሁለት ወታደሮች መሞታቸውን ተጠቅሷል ። መረጃውን የድንበር ጦሩ ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል  አዎል ቢን ኢድ አል በላዊ አረጋግጠውታል

* የሳውዲው ንጉስ  ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ የሟች የድንበር ወታደር ቤተሰቦችን ልዩ የሀዘን መልዕክተኞች በመላክ  አጽናንተዋል

ከዘመቻው ድጋፍ እስከ የመንን መልሶ መገንባት  ….

* በሳውዲ ታላላቅ ምሁራንና ታላላቅ የሐይማኖት አባቶች በሳውዲ መራሹን የየመን አየር ድብደባ ድጋፋቸውን እየሰጡ ነው

* የመን ከሁቴ አማጽያን ጠርታ የፕሬዚደንት አብድል ረቡ መንሱር ሃዲ መንግስት በሁቲ አማጽያን የተቀማውን ስልጣን ተቀብሎ የመን ስትረጋጋ የባህረ ሰላጤው ባለ ሃብቶች 150 በላይ ፕሮጀክቶችን በመክፈት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ እቅድ መያዛቸው ተጠቅሷል
( መቸ ይመጣ ይሆን?  ብቻ ለዚያ ቀን ያድርሰን …)

በየመን የኢትዮ ይዞታና  የ” እውነት ፣ ውሸቱ”  እሰጣ ገባ

* በየመን የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጥቃት እንደደረሰበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖምና መስሪያ ቤታቸው ከቀናት በፊት ፣ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ቢያስታውቁም የተላለፈው መረጃ አነጋጋሪ ሆኗል።  በተባራሪ ጥይት በኢንባሲው የሚገኝን አንድ መኪና ጎማ መታ ተብሎ ጥቀሰት ብሎ ማቅረቡ የተጋነነ መሆኑን ከየመን ሰንአ የደረሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ

* በየመን ሰንአ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ዲፕሎማቶች ሳይሆኑ የኮሚኒቲ  ሰራተኞች ለመመለስ ፍላጎት ያላቸውን ተመላሽ ዜጋዎች በመመዝገብ ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል ። የኢንባሲውን መደብደብ ዜና የሰሙት በቦታው ያሉትን የኮሚኒቲ ተወካዮች ሳይቀር በሚኒስትሩ ኢንባሲው ተጠቃ በሚል በቀረበው መረጃ ግራ የተጋቡ እንደነበር የአይን እማኞች ጠቁመዋል

*  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም ” በየመን ሰነአ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጥቃት ደረሰበት!”  ያሉትን ሰሞኛ ዝርዝር መረጃ ያልቀረበበት አነጋጋሪ መረጃቸውን  ተከትሎ ” ከአውስትራልያ የመጣች ታዳጊ 20 ሚሊዮን… ለገሰች !” እንደተባለችው ታዳጊ ወጣት ስጦታ ገንዘብ ምንጭ ዙሪያ የተደረገውን ያህል ሙግት እሰጣ ገባ የየመኑ ጥቀሰት ባይገንም  ” እውነት ፣ ውሸቱ ”  ግን ቀጥሏል
( አሜሪካ ቢሆን ይህ ይደምቅ ነበር ያሉኝ አሉ: )  )

* ከቀናት በፊት በኤደን የመን አድርገው ጅቡቲ የገቡት 30  ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት መግባታቸው ተጠቁሟል ፣ ”  ወደ ሃገር ቤት መግባቱ ለደህንነታችን ያሰጋናል !”  ያሉት ግን ወደ ሶስተኛ ሃገር የሚሻገሩበትን መንገድ በመላ አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ድምጻቸውን እናሰማላቸው ዘንድ በመማጸን ላይ ናቸው   !

እስኪ ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓም

The post የመረጃ ግብአት… የ” ወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ 9ኛ ቀን ውሎ አበይት ክንውኖች – ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.

ጋዜጠኝነት የማሰብ ጥበብ ልቅና ነው! –ሥርጉተ –ሥላሴ

$
0
0

ሥርጉተ – ሥላሴ 4.04.2015 /ዙሪክ ሲዊዘርላንድ/

„እንቅልፍ ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም“ – ከአቨው ብሂል

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

እንዴት ናችሁ የኔዎቹ  ሐገር ሰላም ነውን? ዬዛሬ መነሻዬ “ኢትዮጵያዊቷ የISIS ሙሽራ እና “ጽንፈኛ” ሆነው የተገኙት አባቷ” ይህ እርእሱ ሲሆን በውስጡ ብንሄድበትም እርገቱ እንዲህ ይላል “ድምጻችን ይሰማ በዚህ ውዥንብር „ሳይደናገር” ላለፉት 3 ዓመታት ያሳየንን ሰላማዊ እና ስልጡን ተቃውሞ እንደሚቀጥል ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለኝም።” ዬፁሑፉን ምንጭ ፌስ ቡክ ላይ ከካሳሁን ይልማ(የኢሳት ጋዜጠኛ) ሲል ዘሀበሻ ባጠናቀቅነው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት ጹሑፉን ለጥፎታል።http://www.zehabesha.com/amharic/archives/40100 እኔ የፌስ ቡክ ተሳታፊ ባለመሆኔ መልካም ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ለምን? ሚሊዮን አድናቂ አለና ብዙ ሰው አንብቦታል፤ በውስጡም አስቀምጦታል ብዬ ስለማስብ ብቻም ሳይሆን የዋህ ወገኖች ባልሆነ መልክ ሊተርጉሙትም ስለሚችሉ “ህልም እንደፈቺው” አይደል የሚባለው እንዲሁ ተንጠልጥሎ ከሚቀር ቅርጥምጣሚ ስጋቶች መሬት ላይ ወርደው በቅጡ መያዝ ስላለባቸው ልንሸራሸርበት እንዲህ አሰኜኝ። በቅድሚያ ግን ላመስግነው ዘሃበሻን – እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

እኔ የፌስ ቡክ ተሳታፊ ባለመሆኔ መልካም ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ለምን? ሚሊዮን አድናቂ አለና ብዙ ሰው አንብቦታል፤ በውስጡም አስቀምጦታል ብዬ ስለማስብ ብቻም ሳይሆን የዋህ ወገኖች ባልሆነ መልክ ሊተርጉሙትም ስለሚችሉ “ህልም እንደፈቺው” አይደል የሚባለው እንዲሁ ተንጠልጥሎ ከሚቀር ቅርጥምጣሚ ስጋቶች መሬት ላይ ወርደው በቅጡ መያዝ ስላለባቸው ልንሸራሸርበት እንዲህ አሰኜኝ። በቅድሚያ ግን ላመስግነው ዘሃበሻን – እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ጹሑፉ „ድምጻችን ይሰማን” አክብሯል። ለዚህም ለታናሼ ምስጋና ይድረሰው እላለሁ። ያልተመቸኝ ነገር ግን አለ። ለዚህም ነው ከእሜቴዋ ጋር ተመካክረን የምንለውን ልንል የተሰናዳን። እንዲህ ዓይነት ጉዳዮች በተፈጠሩ ቁጥር ከሌሎች ነገሮች ጋር ዬምናያይዘው ነገር ፈጽሞ አይገባኝም። ባለቤቶች እኮ አሉ። በተጠያቂነት የሚቀርቡ። እኔ ሥርጉተ በእንደነዚህ ዓይነት ጉዳዮች ጋር አብሬ አልቆዝምም። ለወያኔ የፈጠራ ክስ አጨብጫቢነት የሰናፍጭ ታክል ክፍተት – ድንኳን ሰብርነትንም አልፈቅደውም። እኔ በግሌ ንቅናቄ፤ ድርጀት፣ ግንባር በአጠቃላይ ተልዕኮውና በውላዊ ሂደቱ ብቻ ነው የምለካው። “ሳይደናገር” ምን ያደናግረዋል? የተነሳበት ንፁህና ቀጥ ያለ ግልጽ የነፃነት ዓላማ አለው። ለማንኛውም ….

  1. ድምጻችን ይሰማ ለእንደዚህ መሰል ነገሮች በዬሰከንዱ ለሚፈጠር ግሎባል ግድፈት ጋራንቲ ዋስትና ሊሰጠን ፈጽሞ አይችልም። አይጠበቅበትም-ም። ስለምን የሚለውን እመጣበታለሁ።
  2. በፍጹም ሁኔታ እንዲህ አይነቶች ነጠላዊ ጉዳዩች ወይንም ቀንጣዊ ክስተቶችን ዬሚሊዮን ወላዊ ድምጽ ኃላፊነት ወስደው ከሚሸከሙ እንደ “ድምጻችን ይሰማ” ካለው ጋር ሆነ ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ማነካካት አይገባም ባይም ነኝ። ፈጽሞ በዚህ ዕይታ ውስጥ “ድምፃችን ይሰማ” መጠቀስ ሥሙ መነሳት አልበረበትም። ስለምን? የነጠረውን እውነት ፈላጊነታችነን ዳመናማ ያደርገዋልና። ለሰብዕዊ መብት ተሟጋችነታችነንም በአረም ያስውጠዋል። ወያኔ ሃርነት ትግራይ “አሸባሪ” ያላለው ምን አለና። ሳር ቅጠሉ ንፋሱ ሳይቀር ለወያኔ “አሸባሪ” ነው፤
  3. በሌላ በኩል የነፃነት ረሃብተኛነት ቋሚ ፍላጎትን ስንጥር ሊነቀንቅው አይገባም። ሶስት ዓመት እኮ ልጅ ተጸንሶ ተወልዶ በእግሩ የሚሄድበት ብቻም ሳይሆን አፍም የሚፈታበት ወቅት ነው። ንቅናቄው በዚህ ቆይታው ከመምህርነቱ በስተቀር የታዬበት ግድፈት የለም። ፈተናዎቹንም በስልትና በጥበብ በመያዝ ትብትቦቹን እዬረገጠ ወደ ፊት መገስገሱን ነው ያዬነው።

ወጀቡ ሊያል ይችላል። ጦሩም ሊመዘዝ። አውሎም ሊንጥ። እኔ እላለሁ ጋዜጠኝነት የማሰብ ጥበብ ልቅና የሚታይበት የህማማት ሙያ ነው። ጋዜጠኝነት የምቾት፣ የድሎት ወይንም የዕውቅና ፍለጋ፣ ወይንም የቅልጣን ሙያ  አይደለም። ይልቁንም ሁሉንም መከራ ተቀብሎ ለዕውነት ጥንግና ድርብ በመሆን ሚዛን ጠብቆ ዘብ መቆም ነው። ስለሆነም ፈተናውን ሁሉ በመቀበል ሂደት ውስጥ አጋዢ ወይንም ጥግ ወይንም አይዞህ /ሽ/ የሚል ላይኖር ይችላል። ግን ዕውነት በጠባቂነት ስለሚሰለፍ፤ የእውነት አቅም ኃይልን እያመረተ ወደ ውስጥ የማዬትን ጸጋ ያፈልቀዋል – መጎናጸፊያውም ትጋትን አበረታቶ ፊት ለፊት ወጥቶ በማገዶነት መጓዝን ይመርቅለታል። ስለዚህ ለጋዜጠኛ ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል – ይመራዋል። የሙያው ሥነ – ምግባር ሃይማኖቱም ይሄው ነው። ፈጣሪ አምላክ በአምሳሉ ለፈጠረው „ሰው“ ልዩ የአክብሮት አቅምና ጉልበት በውስጡ የመገንባት ጥበብ – ጋዜጠኝነት። ደንበር የለሽ ሙያ – ጋዜጠኝነት። ከተከፉ ጋር የሚሰለፍ መከራን የደፈረ ሙያ – ጋዜጠኝነት።

አብሶ ነፃነት ተጋድሞ እንደ ግንድ በአንባገነኖች በሚፈለጥበት ወቅት „ነፃነትን“ ነፃ ሊያወጡ የሚተጉ ከሌላ ሙያ ያሉ ወገኖች ሳይቀር ወደ ሙያው አዘንብለው የእውነት፣ የሰብዕዊ መብት ጥሰት፣ የህግ ረገጣን በመቃወም ፊት ለፊት ወጥተው አንባገነኖችን ሆነ አንባገነኖችን የሚደግፉትን ዲታ ሀገሮች ሳይቀር ይሟገታሉ። ለዚህ ሩቅ ሳንሄድ መምህርና ጋዜጠኛ ርዕዮትን አለሙን፤ መምህርና ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታን እንደ ናሙና መውሰድ እንችላለን። በሌላም በኩል የዞን ዘጠኝ በመባል የሚታወቁትን ወጣት ትንታግ የብሎግ አርበኞች ዕጣ ፈንታ በማስተዋል መመርመር እንችላለን። የጠራቸው፤ ያሰባሰባቸው፣ ያነሳሳቸው አንድ ነገር ብቻ ነው። ማህበራቸውም አንድ ነው። የሰብዕዊ መብት ጥበቃ በአረም መዋጥ። ነፃነትነትን ከነደራጎን መንጋጋ ለማውጣት ከህዝብ ጎን ቆሞ „ሰብዕነትን“ ሁሉን መከራ መቀበል ነፃ ማውጣት። ይህ ነው የጋዜጠኝነት ተልዕኮ። በአጋጣሚ በእሳት ላይ ሁነው በዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች የቀጠሮ ቀን ሳይታክቱ፤ በራስ በመተማመን ፍጹማዊ መንፈስ በፍርድ ሂደቱ ቦታ በመገኘት እራሳቸውን ለመስጠት የተዘጋጁትን ወገኖቼን በማድነቅ – አመሰግናቸዋለሁ። በወራሪ ወታደር ታጅበው ይህን ያህል ጥንካሬ ማሳዬት፤ በመከራ ቀን ለዕንባ ዘብ መቆም የኢትዮጵያን ተስፋ ያሰፋዋል – ኑሩልን። እናንተ እራሳችሁ የጀግንነት ድሪ ናችሁና።

አሁን ወደ ነጥቤ። ሙያውን ከነፍሳቸው ጋር አዋህደው ወደውትም የጀመሩትም ቢሆን፤ መፍቅድ የቻሉት አንድ ነገርን ብቻ ነው። ዝናን አይደለም። ስለ እውነት ጧፍ መሆንን ብቻ ነው። ለዚህም አባ ትርጉም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን፤ አብነቱን በጥልቀት በመስተዋል መመርምር ይቻላል። ታታሪዎችን ጋዜጠኛ ውበሸት ታዬ እና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝምም ፈለጉን አጠንከረው ራሳቸውን የሰጡበት ሚስጢር የህሊናቸው የማስብ ደረጃ ልቅናው ከፍ ያለ በመሆኑ፤ እነኝህ የዘመን አባ እና እማ ወራዎች ማገዶነቱን በመምረጥ በመከራው ዘመን ቀንዲል መሆን ችለዋል። በርካቶችም ሳይወዱ ተገደው ተሰደዋል። ይህ እንግዲህ በእኛዋ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ያዬነው ጭብጥ ንጡር የሙያው ባላቤቶች ተግባር ነው። በውጪውም ቢሆን ከሞቀውና ቅልጥ ካለው ስልጡኑ ሀገራቸው ወጥተው ለሙያው ክብርና ሥነ – ምግባር ሲሉ ባልተወለዱበት ሀገር በጦርነት ውስጥ ያለፉ፤ የሃቅ ፈርጦች፤  ዬእውነት ኮከቦች የሙያው ዘውዶች ዓለማችን በዬዘመኑ በእጅጉ አስተናግዳለች።

በዘመነ አዶልፍ ሂትለር ያን ያክል እሳት ውስጥ ገብቶ የተርመጠመጠው አርበኛ ፍራንስ ለሆዱ አላደረም ነበር። ባለቤቱ ወ/ሮ ሶፊ በሚደርስባት ተጽዕኖ ተጨንቃ „ትዳራችን እይ ስትለው „እጃችን ተመልከችው የእኔና የአንቺ አንድ አይደለም አስተሳሰባችንም“ በማለት ነፍሱን ለናዚ በለሃሰብ ወታደሮች ሰጥቷል፤ አጋሩ ወ/ሮ ሶፊም ከልቧ በገባው ዕውነት ተማርካ እስከ መጨረሻው አብራው እንድትሆን አድርጓታል። አዶልፍ ሂትለር ጀርመንን ከሌላው የለዩበት ዶክተሪንና ያን ያህል ነፍስ ያጠፋበት፤ ያቃጠሉበት ኢ-ሰብዕዊነት ድርጊትና የሄሮድስ መለስ ዜናዊ „እንኳንም ከእናንተ ተፈጥርኩ፤“ ጠፍ መንገድ ሚሊዮኖች እንዲከፉ፤ አንዲገለሉ እንዲሞቱ እንዲሰደዱ ያደረገው ሁለቱም አንድ መንገድ ነው የተከተሉት። አዶልፍ ጀርመናዊነት ዝርያን ማንጠራራታቸው፤ ሄሮድስ ደግሞ ትግራዊነት ዝርያን ማንጠራራታቸው ወጥ የናዚዝም ጸረ ሰብዕ ፍላጎት በዬዘመኑ እንድናይ አድርጎናል። ለዚህም አውራንባ ታይምስን ከሁለት በከፈለው ግድግዳ የሰውን ልጅ ተፈጥሮ በቅጡ የመተርጎም አቅም ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ነጥሮ ወጣበት፤ በሌላም በኩል የኢትዮጵያ ቴሊቪዥንና ራዲዮ አገልጋዮችና የኛው ውድ ጋዜጠኛ አብርሃም ደስታ ደምቆ የወጣበት ሃቅ ማገርና ግድግዳው ሆነ ባላና ወጋግረው „ሰብዕዊነትን“ በእኩልነት ከማዬት፤ የተፈጥሮን ሚስጢሩን ከማግኘት ያደገ አስተሳሰብ መንጭቶ ነው። ዛሬም እሳት ከሚተፋው ቦንብ ሥር መስዋዕትነቱን እዬከፈሉ የሚገኙ አሉ።

ጋዜጠኝነት — እውነትን የመግለጽ ብቻ ሳይሆን እውነትን የማመን፤ እውነትን የማመን ብቻ ሳይሆን እውነትን የመቀበል፤ እውነትን የመቀብል ብቻ ሳይሆን ስለ እውነት ውስጥን ገዝቶ የእውነት ብራ መሆን የክቡሩ ጋዜጠኛ ምግባሩም ህይወቱም ነው። ጋዜጠኛ ውስጡ የሚቃጠለው እውነት ተዘቅዝቃ ስትንጠለጠል ነው። ጋዜጠኛ መንፈሱ የሚርመጠመጠው „ሰው“ የሚለው አባወራ / እማወራ ፍጡር ክብሩ ትቢያ ሲለብስ ነው። ተፈጥሮ ሲደፈር ማዬት ለጋዜጠኛ ህመሙ ነው።

በዬትኛውም መስፈርት ቢሆን አንድ ጋዜጠኛ በቋሚ የዕውነት ማገሩ ላይ ጽኑ የሆነ አቋም ሊኖረው ይገባል። ኢትዮጵያ የዓለም አካል ናት። ስለሆነችም ነው እኛ መኖራችን የዓለም አቅምና ጉልበት መሆናችን አትዘንጉ። ስለዚህም በሀገራችን ባለው የመብት ረጋጣና የመብት ድፍጠጣ አንባገነናዊ ጎጣዊ አፓርታይድ ሥርዓት ለማስወገድ በምናደርገው የነፃነት ትግላዊ ሂደት ከጎናችን ልትቆሙ ይገባል፤ በማለት በመላ ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵውያን ሲችሉ በጋራ፤ ሳይችሉ ደግሞ በግል የሚችሉትን ሁሉ በማደረግ ላይ የሚገኙት።

በአንፃሩም እንደ ዓለም አካልነታችን ከዬትኛውም ሃይማኖት ወይንም ማህበራዊ ተቋም በዓለም በሚከሰቱ አሉታዊ ሁነቶችም ሆነ መሰል ጥፋቶች ሊሳተፉ የወደዱና የፈቀዱ መኖራቸው ደግሞ ግድ ነው። ዓለም በሽታን የሚያውቅ መሳሪያ አላት። ነገር ግን የሰውን ልጅ አሉታዊና አዎንታዊ ረቂቅ አስተሳሰቡን የምታይበት ወይንም የምታነብበት ወይንም የምትመዘግብበት መስታውት ዘመን አመጣሽ ዲጂታል መሳሪያ እስካሁን አልፈለሰፈችም። ቢሆንማ ዕድሜ፣ ፆታ፣ ሃይማኖት ሳይለይ ይህ በዬሰከንዱ የሚታዬው እጅግ ዘግናኝ፣ አሰቃቂና አስፈሪ አደጋን መቆጣጠር በቻለች ነበር። ዛሬ በእያንዳንዱ ፍጥረት ዙሪያ ስጋት ገዝፎ አለ። ሰው ወጥቶ ስለመመለሱ ስለማያውቅ የስንብት ደብዳቤ ጽፎ መውጣት እዬተለመደ መጥቷል። እርግጥ አንድ የሚያድን ነገር ነበር። ይህን የሚያድን ነገር እሰከ አሁን ዓለም እራሷ አልተጠቀመችበትም። ሚስጢሩንም የደረሰችበት አይመስለኝም። ብትደረስበትም በአንድ ጀንበር ውጤት የሚታይበት አይደለም። የረጅም ጊዜ የጥረት ውጤት ነውና።

የሆነ ሆኖ ዓለም ያልቻለችውን ኢትዮጵያዊው „ድምጻችን ይሰማ“ ከዬትና በምን አቅሙ ያመጣዋል። ሚሊዮኖች የታደሙበት እንቅስቃሴ ውስጥ በምን ስሌትና በምን ሁኔታ፤ በምንስ አቅሙ ዬእንክርዳድ ከስንዴ የውስጥን ስሜትና አቅጣጫ መመርመር ያስችለዋል? ዳኝነት ለራስ ነው። ፁሑፉ ተጠያቂ እንዳለደረገው አውቃለሁ። ነገር ግን የዝንባሌው መንፈስና ጠረን „ድምፃችን ይሰማ“ አቅጣጫውን እንዳይቀር የሚነካኩ ኩነቶች አሉበት። እንደገናም ከውስጡ አረም ቢበቅል የሚል ቅርጥምጣሚ ስጋትም ሸቶኛል። በማህበራዊ ኑሯችንም ስንለካው „በሬ ካራጁ ጋር“ የሆኑ ገጠመኞች እንዳሉንም መዘንጋት የለብንም። ገጹን ታያላችሁ ይመቻችኋል። አብራችሁ መልካሙንም መልካም ያልሆነውን ትጋራላችሁ። ቀጥሎ ደግሞ አጋጣሚ ቀን የሰጣችሁ ቀን  የምታውቁት ያ ሩህሩህ – አስተዋይ – ደግ – አለኝ ብላችሁ ያስጠጋችሁት እምነት የሰጣችሁት፤ በውስጣችሁ ያነገሳችሁት ገፅ ሌላ የማታውቁት ገፅ ሆኖ ያፋጣችኋል። እንደዚህ መሰሉ ረቂቅ ውስጣዊ መንፈስን የማንበብ ሆነ ቀድሞ የመተንበይ ብልሃት „ድምጻችን ይሰማ“ ከአቅሙ በላይ ስለሆነ ተጠያቂ ሊያደርገው ፈጽሞ አይችልም። የሆነ ሆኖ ….

ደግሞስ ምንስ አዲስ ነገር አለው። ከዬትም ቦታ ከዬትኛውም ሀገር እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸው ጋድሞች፣ ሲዖሎች፣ ጸረ ተፈጥሮዎች ይፈጠራሉ። በዬቀኑ አውሮፓ ላይ በግል አባል ሆነው የሚገኙ የሚታሰሩ፤ ሄደው የሚቀላቀሉ እንደ አሉ ዜናዎች ያመልክታሉ። ነገም ከነገም ወዲያ ኢትዮጵያ የዓለም አካል እንደመሆኗ ኢትዮጵያዊ የሆነ ወይንም የሆነች ይህን ጸረ ሰብዕ፤ ጸረ እድገት፤ ጸረ ነፃነት የሆነውን አጥፊ ድርጅት ሊቀላቀሉ የሚችሉ የጥፋት አቀንቃኝ ብቻ ሳይሆን መሪ ሆነው ሊገኙም የሚችሉ ይኖራሉ። ይህን መጠበቅ ይገባል። ለዚህ „ድምጻችን ይሰማ“ ጋራንቲ ወይንም ጥብቅ የዋስትና ኪዳን እንዲሰጥ አይጠበቅበትም – በፍጹም። ክፍል ከፍተው እኮ በይፋ „ጀሃዲስትነትን“ በአደባባይ ሲያውጁ ነበር። ይህን በዛ „ጆኖሳይድ“ በሚባል ክፍል ውስጥ የበቁት ዬኢንተርኔት ባለሙያ ኢትዮጵውያን ወገኖቼ አድራሻቸውን እንደሚይዙት ተስፋ አደርጋለሁ። ያው ኢትዮጵያዊነት ዬይሉኝታ ማርዳ በመሆኑ አሳልፈው ሳይሰጧቸው በመረጃነት አስቀምጠውት ይሆናል ብዬም አስባለሁ።

„ድምፃችን ይሰማ“ እንቅስቃሴ ነው። እንቅስቃሴው አንድ የነፃነት ትግል ፕሮጀክት አለው። ፕሮጀክቱ የዕምነቱን ነፃነት በነበረው አቮዊና ትውፊታዊ መልክ ማስመለስ ነው። ይህ ከተመለሰለት ዬፕሮጀክቱ ተልዕኮው ያበቃል ማለት ነው። በቃ! ግልጽ ጥያቄ ነው። „መሪዎቻችነን በመስጊዳችን እንመርጥ። ምርጫው የሃይማኖታችን ሥርዓት በሚፈቅደው መሰረት ስለመሆኑ ለእኛ ተውልን። መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን፤ ካለአግባብ የታሰሩ መሪዎቻችን ይፈቱልን፤ ከታሰሩበት ቦታ ኢ – ሞራላዊ ጭካኔ አይፈጸምባቸው፤ መሪዎቻችን የሃይማኖት መሪ እንጂ አሸባሪዎች አይደሉም፤ በሃይማኖታችን በምታደርሱት በደል ከፍቶናልና ድምፃችን ስሙ“ ይሄ ነው። ከተሳሳትኩኝ ልታረም ዝግጁ ነኝ። ይህን ቀላል ጥያቄ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መመለስ አልቻለም። ለምን?

እስትንፋሱ የሚቆዬው በዚህ ዙሪያ በሚሰራቸው የጣልቃ ገብነት ተግባር ስለሆነ ሽፋን አይገኝም – ከዲታ ሀገሮች። በኢትዮጵያም „አሸባሪዎቸ አሉ እነሱን እዬገላገልኩላችሁ ነው። ሰብስቤ አስሬላችሁአለሁ፤ ማለት እንዲችል „ፈጥሮ የአሸባሪ ሥም ለጥፎላቸዋል“ ይህም ብቻ አይደለም። ይህን በማደረጉ „የድምጻችን ይሰማ“ በእልህና በቁጭት ተነሳስቶ ወደ ጥፋት ተግባር እንዲሰማራ፤ የሌሎችን የሃማኖት ተቋማትን በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ክብር በግብታዊነት እንዲያወድም – እንዲያዋርድ፤  ዬእርስ በእርስ ሃይማኖታዊ ግጭት ጠብ እንዲጭር፤ እሳት እንዲነድ ለማድረግ ብዙ ጥሯል። ግን አልተሳካለትም። „ድምፃችን ይሰማ“ የብልህነት ጥንካሬው ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ነውና።

„ድምፃችን ይሰማን ፍላጎትና ተልዕኮ“ የቁጣ፣ የእልህ እርምጃ አድርገውት ቢሆን ኖሮ፤ ለወያኔ ሰፊ የሆነ የቅጠፈቱ ቋት ይሆን በነበር። ዓለምም „ትክክል ነህ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በማለት ጎሽ! ደግ አደረከህ ብሎ ይሸልመው በነበር።“ ሌላው ወያኔ የማይተኛበት ነገር በመሃላቸው አስርጎ የማስገባቱ ጉዳይ ነው። ይህም ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባዋል። አንድነት ለኢትዮጵያን የመሰለ ብሄራዊና መጠነ ሰፊ ትልም የነበረውን የተስፋ ፓርቲን ያፈረሰው በዚህ በሰለጠነበት የሸር ሙያው ነው። የሆኖ ሆኖ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንዳሰበው አልተሳካለትም የከሸፈ ባዶ ቀላሃ ነው የሆነው።

እንቅስቃሴው ትእግስቱን ዋጥ አድርጎ፤ መከራውን ችሎ በስልትና በጥበብ እርምጃዎችን ሳይመራ ለወያኔ ሴራ ቀለብ ቢሆን ኖሮ፤  እኛም ብዕራችን ሰብሰብ አድርገን፤ መንፈሳችን ቁጥብ አድርገን እንቀመጥ ነበር። ስለምን? ወጥቶ መቅረትን የሚመኝ አንድም ዜጋ ሊኖር አይችልምና። ሰቀቀን የሚደግፍና የሚበረታታ ነፍስ አይኖርምና። ጭካኔን የሚያባብል አንድም መንፈስ አይኖርምና። ከሁሉ በላይ የሃይማኖት ነፃነቱን ለመቀማት ማንም ሊተባበር አይችልምና። ነገር ግን በሁሉንም መሥፈርት የቀደመ፣ ብልህና ሥልጡን አመራሩ ተልዕኮውን በአረም አላስዋጠውም። ይልቁንም በጠራ መስመር መራው እንጂ ….። ከዚህ ጋር ተያይዞ መታዬት ያለበት ቁም ነገር በሰላማዊ ትግል ውስጥ ምላሽ ያለማግኘት ጉዳይ ዕድሜ ጠገብ ሲሆን፤ ከፍ እያሉና እያደጉ የሚሄዱ ማዕቀቦች መኖራቸውን መዘንጋት የለብንም። መብቱን የተቀማ ግን ህግን የጠበቀ፤ ብስጩነትን የተቆጣጠረ ግን ሙት መሬት ላይ ሆኖ ድልን ያለመ ብርቱ ሰላማዊ ተጋድሎ ከዚህ ጠንከር ብሎ ሊሄድ እንደሚችል ልብ ሊባልም ይገባዋል። እኔ በዕድሜዬ እንዲህ ያለ ምራቁን የወጣ ብርቱ፤ ተከታታይነት ያለው፤ ትጉህ፤ ንቁ፤ የመሪና የተመሪ ግንኙነት የሰመረበት ጤናማ ሂደት አይቼ አላወቅም። ከድንቅ በላይ ነው። ለታሪክ ሥጦታ ነው! በራስ የመተማማን ብቃቱ ከተነሳበት የእውነት ማህደር ይቀዳል። ስለዚህም – አይወዛወዝም።

ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ለቃቅሞ መሪዎችን ከማሰሩ በፊት ጉዝጓዝ ሰርቶለት ነበር። የክርስትና እምነትን ለማስነሳት። ይህን በድንገት የመሠረተው ጉዳይ አልነበረም። የረጅም ጊዜ ዕቅዱ ነበር። ባዶ ቦታ ላይ፤ ምንም ሰው በሌለበት ቦታ ላይ፤ መስጊድ ሲያሰራ ሲያበረታታ የነበረው – ለስውር ፍላጎት ማመሳከሪያነት ነበር። ስለምን? እሱ ለፈጠረው – ለፈበረከው ክስ ቅድሚያ ቬሎ ያስፈልገው ስለነበር። ይሄው ቀድሞውንም ኢትዮጵያን የእስልምና እምነት ተከታይ ሀገር ለማደረግ የታሰበ እርምጃ ሲወሰድ ነበር ለማለት። ግን ወያኔ የሠራው የድቡሽት ትዕይንት ሁሉ አሞራው በረረ ቅሉም ተሰበረ ነው የሆነበት።

ሥነ ጥበብ የመንፈስ ሃብትነቱ እያዋዛ ወደሚፈልገው በጎ አቅጣጫ የመግራት ረቂቅ ልዩ ክህሎቱ ነው። እኔ የማዬው „የድምጻችን ይሰማ“ የሶስት ዓመት ታሪካዊ መምህር አንቅስቃሴም የዚህን ያህል ለእኔ ከልቤ የገባ መሆኑን በድፍረት እናገረዋለሁ። እኔን ኮትኩቶ ከጎኑ ያሰለፈ፤ የአቅም ጥሪትን በአግባቡ የመምራትና የማስተዳደር ልቅና ያለው ሆኖ ነው ያገኘሁት። አንድ እንቅስቃሴ እኮ በተግባሩ ነው የሌላውን ቀልብ መግዛት የሚችለው። የሚወደደውም በተግባሩ ነው። እንዲህ ዓይነት በጨዋነት – የሰከነ፤ ዘመኑን – ያዳመጠ፤ የአብሮነት ሥነ ምግባርን – ያልጣሰ፤ የኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ብልጹግ ቀለማም መንፈስን ያልተፃረረ፤ ልዑቅ – በተግባር የከበረ፤ በእድገት የጎለመሰ ረጅም ቆይታ ያለው ሰላማዊ እንቅስቃሴ በታሪኳ ኢትዮጵያ ኖሯት አያውቅም። የታደለ!

ስለሆነም መለኪያችን ሆነ መመተሪያችን እንዳአለ የአካሉን አጠቃላይ እንቅስቃሴና ወላዊ ትልም ተግባራዊነት ላይ ሊሆን ይገባዋል የግድፈት መለኪያችንም እንጂ በእስልምና ዕምንት ዙሪያ በዬሰከንዱ አንድ ሁለት ከዚህም የበረከቱ ቀንጣና ተናጠላዊ የግለሰቦች ከመስመር የወጣ ግድፈት በተፈጸመ ቁጥር፤ ዜናዎችን ባደመጥን ቁጥር ያን እዬመዘዙ ከዚህ ግዙፍ የነፃነት እንቅስቃሴ ጋር ስጋትን መቋጨት ወይንም ጥቂትም ቢሆን ማነካካት የተገባ አይደለም። ዛሬ እናቴ እንኳን ይህን መሰል መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ያለው አካል የአንድ ማህጸን ልጆችንም አወቀዋለሁ ለማለት ገደብ አለው። ስለዚህ ከሚጠበቀው በላይ የሠራና ያለዬነውን ደመ ግቡ ሥነ ምግባር ያሳዬን ውድ ብሩኽ የነፃነት ተጋድሎ  እንቅስቃሴ አካላችን ስለሆነ ክብሩን ልንጠብቅለት፤ ለመንፈሱ ልንጠነቀቅለት ይገባል ባይ ነኝ። ዕሴቱ ከፍ ያለ ነውና። በሚመለከተው ጉዳይ ብቻ እንጥቀሰው … በሚያይዘው ኩሁነት ብቻ እንጥራው …

ፍላጎታችና ድጋፋችን መሰረት ይኑረው! ተጎድተዋል ወይ!? ጥያቄያቸው ትክክለኛ ነው ወይ? ይህን የነፃነት ትግሉ አካል ነኝ የሚል ወገን መመለስ ይኖርበታል። መልሱ አዎን ተጉድተዋል ነው። እንዲያውም የወያኔ ሃርነት ትግራይ በስውር በሚሰራው ሴራ ሀገርና ህዝብ የመበደሉ ገመና እንዳይጋለጥበት ካሳ ነው ያደረጋቸው። ይህን ልብ ልንለው ይገባል። ዬብዙ ሀገር ዲክታተሮች እዬተጠቀሙበት ያለውም በዚህ ስበብ ነው። ሁሉም እጣቱን የሚጠነቁለው ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ ነው። የበለጸጉ ሀገሮች የሰብዕዊ መብት ረገጣ ለዛውም በ21ኛው ምዕተ ዓመት እዬተመለኩቱ ዓይናቸውን በዓይነ እርግብ ሸፍነው ዲክታተሮችን ከጎናቸው ቁጭ አድርገው የሚያበረታቷቸውም በዚህ ምክንያት ነው። በተለይም ጋዜጠኞች የነፃነት ፍለጋ ጉዞና ሌላውን ደባል አጥፊ ፍላጎት መቀላቀል አይገባቸውም። ስለምን? ጋዜጠኝነት የማሰብ ጥበብ ልቅና ነውና። ማለት የሰው ልጅ የማሰብ ልቅናው መለኪያ አፍቅሮተ ሰው ነውና። አፍቅሮተ ሰው ደግሞ የሰውን ልጅ ተፈጥሮ ከማክበር ይነሳል።

ፍላጎታች ሥር አለው። ሥሩ አንድ ግንድን ፈጥሯል። ነፃነት የመፈለግ ጉዞና ራዕይ። ነፃነት የመፈልግ ጉዞ ዬሥሩ ሴል የሴቶች እኩልነትን፤ የህፃናት ጥበቃና ፍትህን፤ የሙያ ክብራዊ ዕውቅና፤ የአዛውንታት ክብርና ሞገስነት፤ የወጣቶች የተተኪነት መብት፤ የዘመኑ ሥልጣኔ እኩል ነፃነታዊ ማህበራዊ ተጠቃሚነት፤ የቤተሰብ አክብሮትና ጥበቃ፤ ሙያን የመምረጥና በፈለጉት ሙያ የመሰማራት ያልተሸራረፈ ነፃነት፤ በፈለጉት አካባቢ ሰርቶ የመኖር ነፃነት፤ ሃብት የማፍራትና የማስተዳደር እንዲሁም ባፈሩት ሃብት የመጠቀም ነፃነት፤ የመንፈስ ሃብት የማስፋፋት፤ የማሰራጨትና የማሳደግ ነፃነት፤ የዕምነት እኩልነት ነፃነት፤ ዕምነትን በዕምነቱ ዶግማና ቀኖና የማስተዳደር ነፃነት፤ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ ብቻ ሳይሆን በሃሳቡ ዙሪያ የመወያዬት፣ የመምከር የመተቸት ነፃነት፤ በሀገር ጉዳይ ላይ የመወስን ነፃነት፤  የመደራጀት – የመሰብሰብ – መሪዎችን የመመረጥና እራስም የመመረጥ የማስተዳደር ነፃነት፤ ድጋፍና ተቃውሞ የማቅረብ ነፃነት፤ ብሄራዊ ሰንድቅዓላማን የፈለጉትን ያህል ያልተገደበ የመውደድ ነፃነት፤ የሀገርና የክ/ሀገራት የወሰን ድንበር ውርሳዊና ተፈጥሯዊነት የመጠበቅ ነፃነት፤ በሀገር ንብረትና ሀብት እኩል ተጠቃሚ የመሆን ነፃነት፤ ትክክለኛ መረጃ የማግኘት ነፃነት፤ የሃብት ድልድና ሥርጭት የእኩልነት ነፃነት፤ የባህል ነፃነት፤ የፍልስፍና የሳይንስና የምርምር ነፃነት፤ የህግ የበላይነት ነጻነት ወዘተ ወዘተ …. ወዘተ …

ስለዚህ አንዱን ሥር ስንነካው ሌላው ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ብቻ ሳይሆን፤ ያሰምመዋል፤ ያቆስለዋል፤ ያጠወልገዋል። በተዘዋዋሪ አይደለም በቀጥታ – በእያንዳንዱ የፍላጎታችን ሥር ሴል ላይ ጥቃት ይፈጽማል።

ህም! „ለሚያራግቡት ደህና አጋጣሚ አገኙ“ ለሚባለው ከእውነት ያልተነሳ ቀልብ ሳቢያ ፍለጋ እንደማሰነ ነው ኑሮው የሚጠናቀቀው። ሳቢያ ደግሞ መንገዱ አጭር ነው። ወርዱም – ጥብቆ። በራሱ ጊዜ ይከሽፋል። በራሱ ጊዜ አጀንዳው ይሟሟል። ሳቢያ ቆይታው ለቅጽበት ነው። ለማደግ – ድፍረት የለውም። በዬትኛው አደባባይ ነው የሚታዩት?!  አንገታቸውን ደፍተው ውስጥ – ለውስጥ አዩኝ – አላዩኝ ብለው ተሽሎክሉከው ነው እንደ እባብ መሬት ለመሬት ሲሄዱ የሚታዩት። ስለምን? የሚያቀርቡት አንዲት ሽራፊ የሃቅ ብናኝ የላቸውም። 30 ሺህ ፍትህ ጋዜጣ ሲቃጠልና ቁርሾው አገርሽቶ ለእስር የበቃባት ተሜ አፈር በሆኑት ሄሮድሳቸው ነው። ይህ እውነት አይደለም ለእነሱ። እሬሳ ታቅፈው ዜናውን ኢሳት ሲያቀርብ የተሳሰተ ማሰረጃ ሰጠ ብለው ሲከሱ ነበር። ከዚህ የበለጠ የተገለበ ጉዳይ ምን አለና?! በአደባባይ „ከአዲስ ዓመት በፊት ሥራ ይጀምራል መሪያችን“ አይደለም ያሉት? ግን ሆነ? አፈር ነው የጋጠው ቅጥፈታቸው። እነሱ በአስተሳሰብ ድህነት የተሸፈኑ ናቸው – ሠረገላቸውም ድንብስ። በጎጠኞች የህሊና ሰሌዳ ላይ ያለው ባዶ ቀለሃ … በቻ —–

ነገር ግን ምክንያታዊ የሆኑ አምክንዮች ጭብጣቸው ሆነ ዘላለማዊነታቸው ታሪክን በማብቀል – ነገን አሳምሮ በመስመቸት የበለጸገና የዳበረ ተመክሮን አዝምረው እውነትን በዓምድነት ያበራሉ። እውነት ቀጥ ያለ ደፋር ጧፍ ነው። ስለዚህ የአንድ ሰሞን አታሞ ዘላቂ ፍላጎትን ሊነቀንቀው አይገባም። እንዲያውም እንደ አሮጌ ቆርቆሮ ሲጮሑ ገዢ መሬት ላይ ያለው አሸናፊው ሥነ ልቦና ይደላደላል። ማንነት አለውና! ኢትዮጵያዊነት!

ለማንኛውም „የድምጻችን ይሰማ“ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት አንድ የነፃነት ማሰከበሪያ ፕሮጀክት ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ አቅም ኑሮት ለጥያቄው መልስ ቢሰጥ፤ ከጀርባ ሆኖ የሚጎትተው አንዳችም ስውር ፍላጎት ስሌለው ታሪክን በተግባር አቅልሞ በምስራች ይሰናበታል። ይህ ማለት ግን ነፃነት በመከነባት ሀገር የሚኖሩ ዜጎች ለነፃነታቸው በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ከሚፈልጉት የፖለቲካ ድርጅት ጋር ሆነው ትግላቸውን አያደርጉም ማለት አይደለም። የራህቡ – የመገለሉ – የመታረዙ – የሞቱ ሲሳይነታቸው እንደ ዜጋ የእስልምና እምነት ተከታዮችንም ታዳሚ የደርጋቸዋልና። ከዚህም ባለፈ የእስልምና እምነት አባላት የሆኑ ሴቶች – በፆታቸው፤ ወጣቶች – በዕድሚያቸው፤ የሙያ ሰዎች – በሙያቸው፤ የሥነ- ጥበብ ሰዎች – በጸጋቸው፤ የከተማ ነዋሪዎች በከተማ – የገጠር ነዋሪዎች በገጠር ነዋሪዎች ተደራጅተው እንደ ማንኛውም ዜጋ የቡኩላቸውን ድርሻ ይወጣሉ። ይህ ቀጣይ ነው። ከዚህም ባለፈ በተለምዶ በሚታወቁት በወበራ በሥራ ህብረት ወይንም በደቦ፤ በእድር፤ በቁቤ መሰሉን ተግባር በማህበራዊ ኑሯቸው ይከውናሉ። ነገም ቢሆን በማናቸውም የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ የተሳትፎ ጎራዎች ሁሉ እኩል የመሳተፍ መብትም ግዴታም ይኖርባቸዋል። ይህን ኃላፊነት በብቃት የመወጣት አቅማቸው ሆነ ሥልጡኑ ሥነ ምግባራቸው  በአደባባይ ታይቷል -ምስክር ነው። ያደርጉታል። ያኮራሉና።

መጠነ ሰፊውን የነፃነት ጥያቄ የእኔነት አቅም እንስጠው። በቅንነት ወደ ውስጥ እንዬው። በስጋት ቅንጥብጣቢ ጉዳዮች ፍሬያማ ተልዕኮው እንዳይጎዳ እንጠንቀቅለት። ወያኔ ሃርነት ትግራይ መጫሪያ መለማማጃ ማድረጉ ላይበቃ፤ እኛም ጥግ ከነሳናቸው ሁለት ያጣ የሁለት ሀገር ስደተኛ ይሆናሉ። በወያኔ ሃርነት ትግራይ ጥቃት የሚፈጸምበት ተቋም ወገን ትንፋሻችን ሊሆን ይገባል። እናስጠጋው! ጠረኑ እኛን – እኛን ስለሚል። አቅምም ነው በቅጡ መያዝም ማስተዳደርም ከቻልን።

ኢትዮጵውያን እጅግ ታላቅ ግዙፍ የወል ኪዳናዊ አምክንዮ አለን። „ሰው የመሆን፣ ኢትዮጵያዊነታችን ከጎጣዊ የበታችነት ወረራ የማስመለስ ፣ ነፃነትን – የመናፈቅ፣ ባለሀገር የመሆን፣ ዬወጥ ሰንድቅዓላማችን ብሄራዊ ክብር የማስመለስ፤ የጋራ የሆነ የሚያስማማ ብሄራዊ መዝመሩ ባለቤት የመሆን፤ በህዝብ በጸደቀ ህገ መንግሥት ድምጽ የሚመራት የእኩልነት የተስፋ ሀገር የማግኘት፤ ተናፋቂዋን ሀገራችን የርትህ ባዕት የማደረግ፣ የተጣሱ ደንበሮችን ተፈጣሯዊነት የማስጠበቅ፤ ፍቅር ወተታችን ምህረት ማራችን፣ አብሮነት ተክሊላችን የማደረግ ራዕይ የወልዮሽ አቅጣጫችን ነው። ግን እንዲህ ዓይነትን ችግሮች ሲያፋጥጡን በጋራ የመቀበል አቅም፤ መራራውን ዘመን አብሮ የመሆን ውስጣዊ ፈቃድ ከኖረን ብቻ። የማይናወጽ ዘላቂ ፍላጎት ከኖርን ብቻ። በመሰረታዊ የችግሩ ምንጭ መስማማት ከቻልን – ብቻ። ለተጎዳ – ለተገለለ ውስጣችን መገበር እስከፈቀድን ድረስ ብቻ።

እጅግ የማከብራችሁ ወገኖቼ  ቆዳችን የውስጥ አካላችን መሸፈኛ ብቻ ነው። ጸጉራችንም የአንጎላችን መሸፈኛ። የውስጡ ልባችን፣ ኩላሊታችን፣ ደማችን፣ ሳንባችን፣ ትንፋሻችን ጠረኑ ሰውኛና ወጥ ነው። ሰውኛነት ደግሞ ሰብዕነትን ያዳምጣል። „የድምጻችን ይሰማ“ መሪዎች ኢ – ሞራላዊ ግፍ ከውስጣችን እናስገባው። የውስጣችን ማተብ እናድርገው። ከሂደቱ፤ ከተግባሩ፤ ከስልቱ፤ ከሥልጣኔው፤ ከብልህነቱ፤ ከስተዋይነቱም ለመማርም እንፍቀድ። ግምገማችን፣ እድምታችን ሆነ ዕይታችን በወላዊ ፍላጎቱና ግብዕቱ ላይ እንጂ በተነጠላዊ ግለሰባዊ ቅንጣቶች አይሁን እላለሁ – እኔ። …. በምንም ሁኔታ የትም ሀገር ቀርቶ ኢትዮጵያው ውስጥም በግልሰብ ደረጃ ይህ ነገር ቢከሰት ከጽኑው አቋማችን ፈቅ አንበል።

ናይጀሪያ ላይ እኮ የቦኮ ሃራም ቡድን የተወሰነው ክፍል ተቆጣጥሮ እዬጨፈረ ነው ያለው። ነገር ግን የናይጀሪያ ተወላጆች የእስልማና እምነት ተከታዮች የሆኑት በዚህ አልተፈረጁም። የሚደግፉት ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ቢቻልም ማንኛውም ናይጀሪያዊ የእምነቱ ተከታይን ግን በጎሪጥ አይታይም። …. እንኳንስ አንዲት ጋት መሬት ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለው። እንዲያውም ጋት መሬት እንዲኖረው ይህ አሸባሪ ቡድን ወያኔ ይፈልጋል።  ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚቀርበው እኮ የህዝብ ኃላፊነት አይደለም እእ! ቅዠቱን ማስፈጽም ነው “ የታላቋ ትግራይ ህልመኛነት“ አሽዋ ሞልቶ እህል ያለ፤ ዬሃውዚን ህፃናትን – ነፍሱጥር – እናቶችን፤ አዛውንታትን አስደብድቦ ድጋፍ ያፈሰ አረመኔ እኮ ነው ወያኔ ማለት። ወያኔና አሸባሪነት፤ ወያኔና ስጋትን መፈብርክ መቼ ተፋተው ሲውቁ ነውና። ኢትዮጵያዊ እስልምና እምነት ተከታዮችን ሰላም የነሳቸውና ሰላማቸውን ያሳጣቸው እሱ እራሱ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ አንድ የአልሸባብ ጉድብ ቢደረምስ „የድምጻችን ይሰማ“ አካላዊ ቅስም አይሰበረም። ስለምን? ግንኙነት – ስሌለው።  ይልቁንም እንደ ሰው ዬዓለምን ሰላም የነሳው፣ መኖርን በስጋት ያስዋጠው፤ ሃይማኖታቸውን ተገን አድርጎ ዬትውልድን ተስፋ ጥቁር ለማልበስ በሚተጋው፤ የሃይማኖታቸውን ክብር በማጥቆር በጥርጣሬ በጠቀለለው „የአሸባሪ ቡድን“ ክንፉ ሲሰበር፤ ሲደመሰስ ደስታውና የምሥራቹ  ከእኛ ጋራ ነው የሚሆነው። እምነት ተወዶና ተፈቅዶ የሚቀበሉት የመልካም ነገሮች ሁሉ የነፃነት ፍሬ ነው። ሃይማኖት ሰብዕዊነት የፈጠረ ነው፤ ተፈጥሯዊነትን ያረቀቀ – ያጸደቀ ነው ነው እንጂ፤ የሰው እርድ ናፋቂ አይደለምና።

ክወና „ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም“ ይላሉ አቨው ቀደምቶች። ገና ዓለምን በሽብርተኛ ተግባሩ እዬናጠው ያለው ISIS  ዬእስልማና እምነት ጽንፈኝትን የዓለም የስጋት ምንጭ ነው ተብሎ፤  የእምነት ነፃነታቸውን በግፍና በማንአለብኝነት የተቀሙት የነፃነት ራህብተኛ ወገኖቻችን የጠራ ጥያቄያ ቀጣይ እንቅስቃሴ ላይ እኛ እራሳችን ስጋት ማከል አይገባንም። እነሱም  ከዚህ ጋር ሊያያዝ ይችላል ብለው፤ ወይንም የዚህ ድርጅት ኢትዮጵያዊ አባላት ተገኙ ወደፊትም ሊኖሩ ይችላሉ ብለው “ድምጻችን ይሰማ” አንድ ጋት ወደ ኋላ ከተልዕኮው ሊያፈግፍግ አይገባውም ባይ ነኝ። አይደለም ይሄ የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ዛሬ “ድምፃችን ይሰማ” ከሚመሩት መሃከል የዚህ ድርጅት አባል አለ ብሎ ዓለም ዓቀፍ የስለላ ድርጅት ቢያረጋግጥ እንኳን “የድምጻችን ይሰማ” የሚልዮኖች ድምጽ ለእምነት ነፃነት ትግል ሊቋረጥ አይገባም። በዬደቂቃው እስር ሳይሆን ያን መራራ ስቃይ የተቀበሉ፤ የተደፈሩም መሪዎችን ማሰብ በአጽህኖት ይገባዋል። ንቅናቄው በህይወቱ እኮ የተከሰቱ በርካታ ፈታኝ ነገሮች አሉ። ጽንፈኛ መንፈሶች ነበሩ “ድምጻችን ይሰማ” ግን ክብር ነስቶ ጥሏቸው ነው የተጓዘው። ለደቂቃም ቀልቡን አልሰጣቸውም። ዞር ብሎም አላያቸውም። ቂጡ እንደ ወለቀ እንሰራ አውልቆ ሲያስቀራቸው ተመልክተናል። ትቢያ ነው ያለበሳቸው። ይህ ጥንካሬው በቀጣዩ ተስፋ ላይ ማዕቀብ እንዳይኖር ያደርገዋል።

እኔ በግሌ ሁልጊዜም ከድምጻችን ይሰማ መንፈስ ጋር መንፈሴ ውል አስሯል። ጥያቄያቸው በአግባቡ መልስ ሊያገኝ ይገባዋል ባይ ነኝ። ስጋትም የለብኝም። ነገም ከነገ ወዲያም ዘለግ አድርጌ በግለሰብ ደረጃ የሚፈጠሩ ግድፈቶች እንደሚኖሩ አስባለሁ፤  ነገር ግን ከ„ድምፃችን ይሰማ“ ተልዕኮ ጋር ግን አይደባለቅብኝም። ግልጽ ጥያቄ ነው ጥያቄው። ለዛውም በአንድ ስብሰባ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባ የነበረ፤ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ግን ያሾለከው ብርቅዬ ዕድል። „ድምጻችን ይሰማ“ ድምጹ ሊደመጥ የሚገባው ብቁና የነፃነት ትግሉ በኸረ ጉልበታችን ነው! የዕምነት ነፃነት የራበው ማስታገሻው ጥያቄው መልስ ሲያገኝ ብቻ ሲሆን „ድምፃችን ይሰማ“ ትግሉን አጠንክሮ በሚያደርገው ጉዞ እኛም በአጋርነት መሰለፍ ይገባናል። በተለይም ጋዜጠኞች፣ የጥበብ ሰዎች፣ የሰብዕዊ መብት ረገጣ የሚጎረበጥው ዜጋ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል። ኢትዮጵያዊነትን የሚጠይቀው በኽረ ጥያቄ የመመለስ አቅም „ሰው“ መሆንን ብቻ ነው። ቅመሙ የተሠራው ከእኔም ከእርሰዎ ነውና – ኢትዮጵያዊነት!

ለነበረን ውብ ጊዜ አመስግኜ መሸቢያ ህልም ተመኝቼ ልሰናበት። ደህና ሁኑልኝ – የኔዎቹ።

ዓራት ዓይናማው መንገዳችን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

 

 

The post ጋዜጠኝነት የማሰብ ጥበብ ልቅና ነው! – ሥርጉተ – ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.


ታሪክ ይፋረደናል! –አንዱዓለም ተፈራ –የእስከመቼ አዘጋጅ

$
0
0

አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ
ቅዳሜ፤ መጋቢት ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓመተ ምህረት – 04/04/2015

እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ ቡድን በእብሪት ተወጥሮ ሀገራችንን ሲጫወትባት፤ እኛ “የኔ ድርጅት! የለም የኔ ድርጅት!” “እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ! የለም እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ!” “እኔ እበልጣለሁ! የለም እኔ እበልጣለሁ!” እየተባባልን፤ በሌለ ሥልጣን ሽሚያ ልባችን አብጦ፤ ዛሬ ትናንት፤ ነገ ደግሞ ዛሬ እየሆነ ዓመታትን አስቆጠርን። ለምን? የሀገር ጉዳይ እያንዳንዳችንን የሀገሯ ተወላጆች እኩል አይሸነቅጠንም? ምን እስኪሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው? በየድረገጹ የማነበው፣ በየፓልቶኩ ክፍል የማዳምጠው፣ በየሬዲዮኖች የሚተላለፈው፤ በአንድነት እስካልተነሳን ድረስ፤ ትግሉ አይሳካም! የነገውም ሂደት አያስተማምንም! ነው። ለምን በዚህ አውቶቡስ ሁላችን አንሳፈርም? ኧረ ተው! ታሪክ ይፋረደናል!

አሜሪካ ፈልጌውና ጓጉቼለት የመጣሁበት ሀገር አይደለም። የዴሞክራሲ ሥርዓቱ ናፍቆኝም አይደለም የመጣሁት። የተሰማራሁበት ትግል ሂደት ተሰናክሎ፣ ቀኑ ጨልሞብኝ፣ በሰደት ከነበርኩበት የኑሮ ዝግመት ማምለጫ ስለሆነልኝ ነበር። መጥቼ ደግሞ በአድናቆት ተውጬ ማንነቴን ረስቼ አልቧረቅሁበትም። ያገኘሁትን ዕድል በመጠቀም ኑሮዬን ገፍቻለሁ። ይኼው ከመጣሁ ሰላሳ ዓመታት አልፈዉኛል። የሀገሬ የፖለቲካ ሀቅና በስደት ነዋሪ መሆኔ፤ የፖለቲካ ጥንዚዛ አድርጎኛል። የአሜሪካን የዴሞክራሲ ሥርዓት አካሄድ ስገነዘብ፤ ያላቸውን ድክመት ደግሞ በዚያው ጎን ለጎን አጤናለሁ። ለሀገሬ ከማደርገው መሯሯጥ ጋር፤ በአሜሪካ ሀገር ያለሁበትን ሀገር የፖለቲካ ሀቅ ለማስተካከል፤ እንዲህ መሆን ሲገባው ለምን አልሆነም? እያልኩ ከማንጠርጠር አልቦዘንኩም። አሜሪካኖች የራሳቸውን የዴሞክራሲ አካሄድ “ፍጹም ወደ መሆን እያዘገምን ነው።” ብለው ነው የሚያምኑት። “ፍጹም ነው!” አይሉም። በምችለውና ባጋጠመኝ መንገድ ሁሉ፤ ይኼን ፍጹም ወደመሆን የሚጓዘውን ሂደታቸውን፤ በንቃት በመሳተፍ እየረዳሁ ነው።

አሁን በሀገራችን የኑሮ ሀቅ፤ የወሃ ጥማት፣ የምግብ ማጣት፣ የሰላም የገበያ አገልግሎት፣ የመንገድ አለመሠራት፣ የትምህርትና ሕክምና አለመስፋፋት፣ የመናገርና የመጻፍ፣ የመሰባሰብና ተቃውሞን የመግለጽ፣ የአድልዖና ሙስና መንገሥ፤ መሠረታዊ የኅብረተሰቡ ጥያቄዎች፤ የፖለቲካውን መድረክ ማዕከላዊ ቦታ አልያዙም። ለዚህ ተጠያቂ የሆነውን መንግሥት በመወንጀል ባንድነት የመነሳት ግዴታችንን በውል አልጨበጥነውም። በርግጥ ከአሜሪካ ጋር የኛን ሀገርና የኛን ሁኔታ እያወዳደርኩ አይደለም። አዎ እንደነሱ በሀብት የበለጸግን አይደለንም። ግን ይኼ ላለንበት ሁኔታ ወሳኝነት የለውም።

የሀብት ጉዳይ ከተነሳ፤ በሀብት ያልበለጸግን መሆናችን አዲስ አይደለም። ከሕዝቡ ጥቅምና ከሀገሪቱ ዕድገት ይልቅ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ቅድሚያ የሠጡ ገዥዎች በነበሩበት ዘመን፤ አጠቃላይ የሀገሪቱን እውነታ ፈትሸው፤ ለረጅሙ የወደፊት ብልጽግና በማቀድ እርምጃ ስላልወሰዱ፤ ድኅነቱ አብሮን ኖሯል። እዚህ ላይ አንዳንዶቹ ያደረጉትን ከልብ የመነጨ አስተዋፅዖ በምንም መንገድ ልስት አልችልም። በታሪካችን፤ ባገኘሁት ዕድል ሁሉ፤ መጽሐፍትን በማገላበጥ ለማወቅ ጥረት ከማደርጋቸው መሪዎች መካከል፤ አፄ ዘርዓ ያዕቆብንና አፄ ቴዎድሮስን እጠቅሳለሁ። በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ምን ነበር? ያሁኑስ ዘመን ከዚያ ዘመን በምን ይለያል?

ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመን የአሁኑ ዘመን የሚለየው፤ ያኔ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ትልቅ ክብር የነበራቸው ሲሆን፤ አፈሩ እንኳ ሳይቀር የተከበረበት ዘመን ነበር። አፄ ቴዎድሮስ፤ ከሕዝቡ በመጠቀ ደረጃ፤ ከራሳቸው የወቅቱ ክብር ይልቅ፤ የሀገራቸው እድገትና በአካባቢያቸው የተኮለኮሉት የውጭ ጠላቶች እንቅስቃሴ፤ የዕለት ተዕለት ጭንቀታቸው ነበር። የተበታተነች ኢትዮጵያን ለመመለስና የቀድሞ ቦታዋን ለማስያዝ የሕይወታቸው ዋና ማዕከላዊ ትርጉም አድርገው ጣሩ። ለራሳቸው የስም ማስጠሪያ ግንብ ወይንም ቤተክርስትያን ከማሠራት ይልቅ፤ ለሀገራቸው መጠበቂያ የጦር መሣሪያ እንዲያበጁላቸው ነበር የውጭ ሀገር ሰዎችን የጠየቋቸው። ምንም እንኳ አሁን ምሁር ነን ባዮች፤ የአፄ ቴዎድሮስ ጠላቶች በውጭም ሆነ በውስጥ የነበሩት የጻፉትንና ያሉትን ተሸክመው ቢያጥላሏቸውም፤ እኒህ መሪ በተወለዱበት ዘመንና በቦታው የነበራቸውን የፖለቲካ ድርሻ አጢነው ቢመረምሩ፤ ከማንም መሪ የበለጠ ሊያደንቋቸው በተገባ ነበር።

የበዕደ ማርያም መምህሬ ዶክተር ገብሩ ታረቀኝ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሠጡት መልስ እጅግ በጣም አርክቶኛል። ከነበሩት መሪዎች ሁሉ አንደኛ አድርገው የሚያደንቁትን ቃለ መጠይቅ አቅራቢዋ እንድትነግራቸው ስትጠይቃቸው፤ ያለምንም ማመናታት “አፄ ቴዎድሮስ ናቸው!” በማለት በኩራት አስቀምጠውላታል። ልክ ድሮ ሲያስተምሩኝ እንዳደነቅኋቸው ሁሉ፤ አሁንም የማደንቃቸው መምህሬ ሆነው አገኘኋቸው። ከመሬት ተነስተው፤ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ሀገራዊ ሕልውና፤ የመሠረቱን ደንጋይ ያስቀመጡ አፄ ቴዎድሮስ ናቸው። ከግለሰብ ማንነታቸው ይልቅ፤ የሀገራቸው መሪነታቸው ነበር ልባቸውን የሞላው። ያኔ በሕዝቡም መካከል፤ ከግለሰብ ምንነታችን ይልቅ የስብስብ ማንነታችን ማዕከላዊ ቦታውን የያዘ ነበር። ዛሬ በኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያዊነት አፈር የተንከባለለበት፤ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ኢትዮጵያዊ አለመሆን የተወደደበት፣ ከኢትዮጵያዊያን ስም ይልቅ የውጪ ሀገር ስሞች የተመረጡበት፣ ከራሳችን ቋንቋ ይልቅ የውጪ ቋንቋ፣ ከራሳችን እምነት ይልቅ የውጪ እምነት፣ ከራሳችን ምግብ ይልቅ የውጪ፤ ባጠቃላይም ከራሳችን ማንነት ይልቅ የውጪውን መቅዳትና መስሎ መገኘት የጎላበት ክስተት፤ ሀቅ ሆኖ ይታያል። ለምን? ዋናውን ማዕከላዊ ቦታ ይዞ በተጠያቂነት የቆመው ያለው ገዥ ቡድን ነው። ይህ ገዢ ቡድን ዋና ሥራዬ ብሎ የያዘው፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው። ይኼንንም በትውልድ ማንነት ተክቶታል። እናም “ከራሱ የገማን አሣ! . . .” እንደሚባለው ተቆርጦ መጣል ያለበት፤ ይኼው ገዥ ክፍል ነው።

አሁንም ያኔም ኢትዮጵያዊነት፤ ኢትዮጵያዊነት ነው። አሁን ግንዛቤያችን ፈሩን ለቋል። የብሔር ብሔረሰብ ጥያቄ የፖለቲካውን ማኅደር አጥለቅልቆታል። ምኑም ሆነ ምኑ የሀገራችን ሀቅ፤ ከዚህና ከዚህ ብቻ እንዲታይ ተደርጓል። ይህ ደግሞ በገዥው ክፍል ብቻ ሳይሆን በታጋዩም ወገን ያለ እውነታ ነው። በዚህ ተለጉመን፤ መሠረታዊ የመኖርና ያለመኖር የሕልውና አምዶች፤ ቦታ ተነፍገዋል። የፍትኅ መጓደል፣ የትምህርት ጥራትና ዕድገት ወደ ታች ማሽቆልቆል፣ የሕክምና አለመሟላት፣ የምግብ እጥረትና ረሃብን የመቋቋም ዕቅዶች አለመኖር፣ የሴቶችን እኩልነት አለመቀበልና ተሳትፏቸውን አለማሳደግ፣ አድልዖና ሙስና፤ እነዚህ መሠረታዊ የሕልውና ጥያቄ ተጎትተዋል። መስመሩ የተዘጋበት የውሃ ፈሰስ፤ ዙሪያውን ይቃኛል። የተገደበበትን መዝጊያ መጋፋቱን፤ በጎን መፋሰሻ ከመፈለግ ጋር በእኩል ይዳስሳል። ተገድቤያለሁ ብሎ ተስፋ በመቁረጥ አይረካም። ከግድቡ ጋር ብቻም አይታገልም። ዙሪያውን በሙሉ ነው ጥረት የሚያደርገው። በግድቡ አናት፣ በግድቡ ሥር፣ ከታቆረበት ክብ ዙሪያ ይውዘገዘጋል። የታፈነ በመሆኑ ቦርቅቆ ለመውጣት ይፍጨረጨራል።

ወገኖቻችን በየበረሃው መንገላታታቸው፣ እህቶቻችን በአረብ ሀገሮች መጎሳቆላቸው፣ በገዛ ሀገራቸው ወገኖቻችን መፈናቀላቸው፣ በገዛ ሀገራቸው ወንድምና እህቶቻችን በረሃብ ተጠምደው ለማኝና፤ ሀገሪቱ በሞላ የውጭ ሀገር ምጽዋተኛ መሆናቸው፤ አእምሯችንን በማስጨነቅ የፖለቲካ ምኅዳሩን ሊያናጉት ይገባል። በርግጥ በአሁኑ ሰዓት የፖለቲካ ውይይቱ ተጧጡፏል። ይህ ውጥረት ላይ መሆናችንን አመልካች ነው። ነገር ግን መፍትሔ አፈላለጉ ላይ ለየብቻ እየሮጥን ነው። ለየብቻ ሮጦ፤ የግብ መሰመሩ ላይ ለየብቻ ነው የሚደረሰው። ታዲያ ምን ዋጋ አለው? ግቡ የማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን የግል መኖሪያ አይደለም። የሁላችንም ነው። ባንድ ላይ መሯሯጥ አለብን። የተጎተቱ ካሉ፤ አብረን መሳብና መሳሳብ እንጂ፤ እኔ ቀድሜ ሄጄ እሸለማለሁ ወይንም ሌሎችን እጎትታለሁ የሚባልበት አይደለም። አብረን ስንነሳ፤ ቀዳሚ ሆነው የቆሙት ሲመሩ፤ የተጎተቱት ደግሞ ሲከተሉ፤ ባንድነት ከግባችን እንደርሳለን። ታሪክ ደግሞ ከኛ ጋር አብሮ ይኖራል። ታሪክ ተወቃሽ አያደርገንም። ከታሪክ ተወቃሽነት መዳን አለብን። በሕይወት እስካለን ድረስ፤ ሆዳችን መሙላቱን ብቻ ሳይሆን፤ በሕይወት የኖርንበትን ወቅትም ትርጉም መሥጠቱ ላይ ማተኮርና መጣር የኛ ኃላፊነት ነው። ቆመን እንቆጠር። አብረን በአንድ እንሰለፍ። eske.meche@yahoo.com https://nigatu.wordpress.com/

The post ታሪክ ይፋረደናል! – አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ appeared first on Zehabesha Amharic.

‹‹አስተማሪነት የተከበረ ሞያ በመኾኑ፣ በልመና እና በፍርድ ቤት ውሳኔ መምህር ለመኾን መሞከሩ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም፡፡›› ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

$
0
0

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

dr dagnachew Assefaኢ.ም፡- የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ዓርብ መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የእርስዎን እና የዶ/ር መረራ ጉዲናን የቅጥር ውዝግብ በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል፡- ‹‹ዩኒቨርስቲው በየትኛውም የትምህርት ክፍል በቂ መምህራን አሉኝ ብሎ ካመነ፣ ለጡረታ የደረሱ መምህራንን ኮንትራት ላያራዝም የሚችልበት የቆየ አሠራር አለው፤›› ብለዋል፡፡ በዚህ ዙሪያ ምን የሚሰጡት አስተያየት አለ?
ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፡- ለዚህ አባባል መልስ ከመስጠቴ በፊት፣ ከትምህርቴም ኾነ ከአስተዳደጌ የተማርኹትና አብሮኝ የኖረ ቁልፍ የሞራል አስተምህሮ አለ፡፡ ይኸውም፣ በማናቸውም ጊዜ ግጭት፣ ፍልሚያ ወይም ክርክር በምንገጥምበት ጊዜ፣ በተቻለን መጠን እውነትን ጨብጠን መሔዱ በጣም አስፈላጊ ነው የሚል ግንዛቤ አለኝ፡፡ እውነትን ሰለባ በማድረግ ጊዜያዊ ድልን ለመጎናጸፍ መሞከር በራሱ ለምንቃወማቸው ድርጊቶች እና ሰዎች ተላልፎ በመሰጠት ተሸናፊ ስለሚያደርገን፣ በሐሰት ድልን ለመጎናጸፍ መሞከርን የመሰለ ሽንፈት የለም ብዬ ስለማምን ነው፡፡
ዶ/ር አድማሱ፣ ‹‹የትምህርት ክፍሉ በቂ መምህራን አሉኝ ካለ ግለሰቡ ኮንትራቱ አይታደስለትም›› ያሉት እውነት ነው፡፡ ኾኖም ዋናው ጥያቄ፣ የትምህርት ክፍሉ እኔን በሚመለከት አገልግሎቴን አልፈልግም ብሏል ወይ፤ የሚለው ነው፡፡ ይህን ጥያቄ በተመለከተ እኔ እንዲህ ነው ወይም እንዲያ ነው ከምል፣ የትምህርት ክፍሌ የእኔን አገልግሎት በጥብቅ እንደሚፈልግና ኮሌጁም (የሶሻል ሳይንስ) እንደተስማማበት ለፕሬዝዳንቱ የቀረበውን ደብዳቤ በማረጋገጫነት ልታቀርቡት ትችላላችኹ፡፡ የፕሬዝዳንቱን አቀራረብ የቱን ያህል ከእውነት የራቀ መኾኑን አንባቢ አይቶ ፍርዱን እንዲሰጥ እጋብዛለኹ፡፡
ኢ.ም፡- ሰሞኑን ‹‹ተወይኖብኛል›› ብለው ባስነበቡት ቃለ መጠይቅ ላይ ‹‹ብጣሽ ወረቀት ስጠብቅ አልኖርም›› ብለዋል፡፡ እስኪ ስለዚህ ወረቀት ትንሽ ያብራሩልኝ፡፡

ዶ/ር ዳኛቸው፡- ከዚኽ ቀደም እንደገለጽኩት፣ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል የእኔን ተጨማሪ የሥራ ዘመን አገልግሎት እንደሚፈልግ ለሶሻል ሳይንስ ኮሌጁ ዲን እና በበላይነት ለሚሰበስበው አካዳሚክ ኮሚሽን የፍልስፍና ትምህርት ክፍል ሊቀ መንበር በአካል ተገኝተው ከማስረዳታቸውም በተጨማሪ በደብዳቤም ጠይቀዋል፡፡ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጁም ቢኾን የፍልስፍና ትምህርት ክፍልን ጥያቄ ተቀብሎ የሥራ ውሌ እንዲታደስ፣ በፕሮፌሰር ወልደ አምላክ በዕውቀት (የኮሌጁ ዲን) በኩል ለዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ እንዲያጸድቁት በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
ኾኖም ፕሬዝዳንቱ አራት ወር ሙሉ ይኾናልም – አይኾንምም ሳይሉ ለደብዳቤው መልስ ሳይሰጡ በእጅጉ በመዘግየታቸው የእርሳቸውን ቅን ልቡና የጎደለው እና ተንኮል ያዘለ አካሔድ ለመግለጽ ‹‹ብጣሽ ወረቀት አልጠብቅም›› የሚለውን ሐረግ ተጠቅሜአለኹ፡፡ ፕሬዝዳንቱ መልስ አለመስጠታቸው ከሕግ እና ከሞራል አገባብ ውጭ እንደኾኑ ቀደም ሲልም ለማብራራት ሞክሬያለኹ፡፡
ነገሩን ለማጠቃለል ያኽል፣ የእናንተ አንባቢዎች በጉዳዩ ላይ የራሳቸውን ግንዛቤ እና ፍርድ እንዲሰጡ ለፕሬዝዳንቱ የተላከውን ደብዳቤ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚኽ ቃለ ምልልስ አጋጣሚ ላቅርብ፡፡ ከማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲኑ በእንግሊዝኛ የተጻፈው የደብዳቤው ይዘት የአማርኛ አቀራረቡ በአጭሩ የሚከተለውን ነው፡-
ጉዳዩ፡- የዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን የኮንትራት ውል እደሳ ይመለከታል፤
የፍልስፍና ዲፓርትመንት፣ ለዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የኹለት ዓመት ኮንትራት እድሳት እንዲያገኙ ጠይቋል፡፡ ስለ ኮንትራት እድሳቱ አስፈላጊነት ዲፓርትመንቱ ያቀረባቸው ምክንያቶች፡-
– ዶ/ር ዳኛቸው ሦስት የድኅረ ምረቃ ትምህርቶች (ኮርሶች) እና የቅድመ ምረቃ ዲግሪ ኮርሶችንም ስለሚያስተምሩ፤
– በርካታ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎችን (ከ12-15 ተማሪዎች) የመመረቂያ ጽሑፎችን ስለሚያማክሩ፤
– ከፍልስፍና ዲፓርትመንት ውጭ በርከት ያሉ ኮርሶችን በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት፣ በሰብአዊ መብቶች ተቋም የትምህርት ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ኢንቲትዩት እና የሕግ ትምህርት ቤት ስለሚያስተምሩ፤
– በቅርቡ ለሚጀመረው የሦስተኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) መርሐ ግብር የዶክተር ዳኛቸው አገልግሎት በእጅጉ አስፈላጊ ነው ብሎ ዲፓርትመንቱ ስለሚያምን፣
የሚሉት ናቸው፡፡
የአካዳሚክ ኮሚሽኑ በህዳር 24 ስብስባው ወቅት በዚኽ የዲፓርትመንቱ ጥያቄ ላይ ተወያይቶ የዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የኮንትራት ቅጥር ውል ከታኅሣሥ 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ለኹለት ዓመት እንዲራዘም ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በመኾኑም የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ቢሮው፣ ለውሉ መራዘም የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝዳንት ይኹንታ በማረጋጥ የውል እድሳት ሒደቱን እንዲያስፈጽምልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ደብዳቤው በአድራሻ የተላከው ለዩኒቨርስቲው ለሰው ሀብትና ልማት አስተዳደር ቢሮ ሲኾን፣ ላኪው ደግሞ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ ነው፡፡ ይኸው ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ቢሮ፣ ለአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ቢሮ፣ ለአካዳሚክ ጉዳዮች ቢሮ፣ ለፍልስፍና ትምህርት ክፍል እና ለማኔጂንግ ዳይሬክተሩ በግልባጭ እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡
ኢ.ም፡- እርስዎ እንዳሉት፣ ጥያቄዎ ሕግና ደንብን ጠብቆ ከቀረበ፣ ችግር ፈቺ እንዲኾን ከሚጠበቅ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ምላሽ የተሰጠበት አግባብ ስለ አገራችን ኹኔታ ምን አንድምታ እና ማሳያ ሊሰጠን ይችላል?

ዶ/ር ዳኛቸው፡- ከኹሉ አስቀድሞ የአንድ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ለኹለት ዓበይት ጉዳዮች ተጠሪ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ አንደኛና ተቀዳሚው ተጠሪነቱ ዩኒቨርስቲው ለቆመለት ተቋማዊ መርኆ (አይዲያል) ነው፡፡ በኹለተኛው ደረጃ ደግሞ ለዩኒቨርስቲው አጠቃላይ ማኅበረሰብ (ኮሚዩኒቲ) ተጠሪ መኾን አለበት፡፡
እኔ፣ ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ከኾኑ ጀምሮ የታዘብኩትና ያየኹት፣ እንደ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ተጠሪነታቸው ለዩኒቨርስቲው ርእይ ሳይኾን መንግሥት ለሚያወጣው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዕቅዶች (social and political policy) መኾኑን አያለኹ፡፡ ከዚኽም ባሻገር ለዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ በጎነት ከመቆም እና የአካዳሚክ ነፃነት እንዲከበር ከመጣር ይልቅ ለሾሟቸው የፖለቲካ ኃይሎች በተደጋጋሚ ተጠሪነታቸውን በጉልሕ አሳይተዋል፡፡
በእርሳቸው አመራር አንድ ትጉህ አስተማሪ የሚዳኘው በአካዳሚያዊ መሥፈርት ሳይኾን፣ በብሔር ተዋፅኦ፣ በፓርቲ ተሳትፎ እና የመንግሥት ፖሊሲን ለማስፈጸም በሚያሳየው ተነሳሽነት ነው፡፡ ለማጠቃለል ያኽል፣ ዶ/ር አድማሱ ከሚዘነጓቸው ነገሮች መካከል፣ አንድ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የመንግሥት ተከፋይ ቢኾንም ቅሉ፣ የመንግሥት ሠራተኛ (ሲቭል ሰርቫንት) እንዳልኾነ ነው፡፡

ኢ.ም፡- በዩኒቨርስቲው ውስጥ እርስዎ የሚሉት ዓይነት ድባብ እንዴት ሊሰፍን ቻለ? በዚኽ አኳኋንስ የዩኒቨርስቲ ምሁራን ለመጠየቅ እና እውነት ላይ ለመድረስ የሚጥሩ ወጣት ዜጎችን እንደምን ሊያፈሩ ይችላሉ?

ዶ/ር ዳኛቸው፡- ጥያቄው ኹለት ጉዳዮችን የያዘ ይመስለኛል፤ ተራ በተራ ለመመልከት እሞክራለኹ፡፡ አንደኛ፣ እንዲኽ ዓይነት የማይጠይቅ፣ ተቀባይነት እና የፖሊሲ አስፈጻሚነት መንፈስ ከዬት መነጨ ብለን በምንፈትሽበት ጊዜ፣ ጉዳዩ በማወቅና ባለማወቅ፣ ግንዛቤ በማግኘትና በማጣት (Epistmic) ምክንያት ብቻ ሳይኾን ከግል ጥቅምና ከፍቅረ ንዋይ ጋር የተሳሰረ ስለኾነ ነው፡፡ እንዲኽ ዓይነት ፖሊሲ አስፈጽሙ ሲባል፣ ትእዛዙ የሚመጣው ብቻውን ሳይኾን ከብዙ ዓይነት ዳረጎት (ኮሚሽን) ጋር ስለኾነ፣ ሳያቅማሙ እና ሳይፈትሹ ወደ መቀበልና መተግበር ይገባሉ፡፡
በዩኒቨርስቲው ውስጥ ያሉትን መምህራን በሙሉ ሳይተቹ ተቀባይ እና ፖሊሲ አስፈጻሚ አድርጎ መመልከቱ አግባብነት አይኖረውም፤ እንዲያውም በዩኒቨርስቲው ለሰባት ዓመታት በቆየኹባቸው ጊዜያት ከአገኘኋቸውና ከተዋወቅኋቸው የግቢው ሊቃውንት ብዙ ትምህርት እንደቀሰምኹ ለመግለጽ እወዳለኹ፡፡
ነገር ግን፣ ጠያቂና ተቺ የኾኑ ዓይናማ ሊቃውንት በግቢው ውስጥ እንዳሉ ኹሉ፣ በርከት ያሉ ካድሬዎችም በምሁራን ስም ተቀጥረው ግቢውን እያጣበቡት እንደኾነ ማንም አይስተውም፤ ፕሬዝዳንቱም አንድ ለአምስት በሚል የጥርነፋ ፕሮግራም መምህራኑን እያስቸገሩ አትኩሮታቸውን ለመማር ማስተማር ሒደቱ በቅጡ እንዳያውሉ እና የትምህርት ድባቡን እያስተጓጎለ እንደሆነ በግቢው ውስጥ በሰፊው እየተወራ ነው፡፡
በጥያቄህ ላይ በእንዲህ ዓይነት ድባብ ውስጥ የሚወጡት ተማሪዎች ምን መልክ ይይዛሉ ብለኽ ለጠየቅኸኝ፣ ኹኔታው ጥሩ ተማሪ ለማፍራት ተግዳሮት ቢኾንም፣ ጥቂት የማይባሉት መምህራን በግላቸው ሞያዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በእጅጉ እየጣሩ ይገኛሉ፡፡
ኢ.ም፡- እኔ እንደሰማኹት፣ በመስከረም 2007 ዓ.ም መንግሥት ለዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ ለዐሥር ቀናት የዘለቀ ሥልጠና በሰጠበት ወቅት፣ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ መምህራንን የመቅጠር ሒደትና ሌሎችንም ዋና ዋና ሥልጣኖች ከዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ይልቅ ወደ ዩኒቨርስቲ ኮሌጆችና ዲፓርትመንቶች ተሰጥቷል ሲሉ ተደምጠዋል፤ እንዲያውም ኮሌጆችና ዲፓርትመንቶች መምህራንን ለመቅጠር ፈቃደኛ ባለመኾናቸው ከፍተኛ በጀት ለመንግሥት ተመላሽ እየተደረገ ነው በማለት አማርረው ነበር፡፡ በአንጻሩ እርስዎንና ዶ/ር መረራን ዲፓርትመንቱና ኮሌጆቹ እንፈልጋቸዋለን እያሉ ፕሬዝዳንቱ ግን ቅጥራችኹ የሚራዘምበት ይኹንታን ፈቃደኛ አልኾኑም፡፡

ዶ/ር ዳኛቸው፡- በመሠረቱ በወቅቱ እኔ በሥልጠናው ላይ ለመገኘት ስላልፈለግኹ በስብሰባው አልተሳተፍኩም፤ ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ከቀድሞው የዩኒቨርስቲው አስተዳደር በተለየ መልኩ ለኮሌጆችና ለዲፓርትመንቶች ሥልጣን አውርጃለኹ በማለት እየተኩራሩ ሲናገሩ በሌላ አጋጣሚ ሰምቻለኹ፡፡ ይኹንና ወደ ተጨባጭ እውነታው ስንመጣ፣ ከነቢብ አልፎ በገቢር ባለመተርጎማቸው፣ ፕሬዝዳንቱ ተቀዳሚ የሚያደርጉት የዩኒቨርስቲውን ጥቅምና ፍላጎት ሳይኾን፣ የራሳቸውን የግል ፍላጎት ለመኾኑ ከዚህ የበለጠ ማረጋገጫ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡
ኢ.ም፡- በደብዳቤው እንደተገለጸው፣ ኮሌጁና ዲፓርትመንቱ አጥብቆ በሚፈልግዎት በእርስዎ ላይ ፕሬዝዳንቱ እንዲኽ ዓይነት ርምጃ ለመውሰድ ያበቃቸው ምን ሊኾን ይችላል ብለው ያስባሉ?
ዶ/ር ዳኛቸው፡- ይኸውልህ ነገሩ የተጀመረው ፕሬዝዳንቱ ተሹመው በመጡ ማግሥት ነው፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ማኅበረሰብ በጠቅላላ ሰብስበው ለዓባይ ግድብ ምን አስተዋፅኦ ማድረግ እንችላለን ብለው ከመድረክ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አንድ- አራት- አምስት ሰዎች ተነሡና እኔ እንዲኽ አደርጋለኹ፤ እኔም እንዲኽ አደርጋለኹ ብለው ተናግረው ሲያበቁ፣ የተሰበሰብነው ሰዎች በሺሕዎች ብንቆጠርም ፕሬዝዳንት አድማሱ፣ ‹‹የምትሉት ገብቶኛል፤ የወር ደሞዝ እንሰጣለን ነው የምትሉት፤›› በማለት ቀድሞ የተጻፈ የአቅዋም መግለጫ አስነብበው ስብሰባውን በዚኹ ቋጩት፡፡
እኔም በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ፣ አራትና አምስት ሰው ብቻ በተናገረው እንደምን የብዙኃኑን ሰዎች ፍላጎት አገኙት በማለት ግልጽ ሒሳዊ ደብዳቤ ጻፍኹላቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ መተቻቸት በአካዳሚያዊ ተቋማት የተለመደ ቢኾንም፣ እርሳቸው ግን፣ እኔ ባቀረብኹላቸው አስተያየት አቂመው ቆይተዋል፡፡ ይህን የሚያስረግጥ ሌላም ጉዳይ ልጠቀስልኽ፤
የቀድሞው የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ በነበሩበት ጊዜ፣ 19ኛው የዓለም አቀፍ የትምህርት ፍልስፍና ጉባኤ (International Network of Philosophers of Education Conference) ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኾን ተወሰነ፡፡ ጉባኤውን የዩኒቨርስቲው የትምህርት ክፍል ለብቻው ማዘጋጀት ቢፈልግም፣ ፈረንጆቹ የፍልስፍና ዲፓርትመንትም መካፈል አለበት ስላሉ፣ በዚያን ጊዜ ፕሮፌሰር አንድርያስ የትምህርት ክፍሉን በመወከል በዝግጅቱ እንድሳተፍ ጋበዙኝ፡፡
ጉባኤውን ለማዘጋጀት በተቋቋመው ኮሚቴ፥ ፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ፣ ዶ/ር ጄሉ ዑመር፣ ዶ/ር አማረ አስገዶም እና እኔ በጋራ መሥራት ጀመርን፡፡ ከዚያም ዶ/ር አማረ አስገዶም ለጉባኤው ዝግጅት ከአራት ሚልዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ነገረኝ፤ አዲስ የተሾሙት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬም ብሩን እንደሚፈቅዱም በርግጠኝነት ገለጸልኝ፡፡ ወጪው በጣም ከፍ ያለ መስሎ ስለታየኝ፣ ይህን ያኽል ብር ለምን ያስፈልገናል ብዬ ጠየቅኹት፡፡ ዶ/ር አማረ ሲመልስልኝ፣ ከተለያየ የዓለም ክፍል የሚመጡትና ከሀገር ውስጥ የጉባኤው ተሳታፊዎች ከፍለው ስለሚገቡ ወደ ሰባት ሚልዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ተገኝቶ የኒቨርስቲው ሦስት ሚልዮን ብር እንደሚያተርፍ ነገረኝ፡፡ በመቀጠልም ፕሬዝዳንቱን ስለ ጉዳዩ ለማሳወቅ ቀጠሮ እንደተያዘ ነገረኝ፡፡
ኾኖም ኹለት ጊዜ ባካሔድነው ስብሰባ ላይ ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ሳይመጡ ቀሩ፡፡ በጊዜው ሳይመቻቸው ቀርቶ ነው በማለት ነገሩን ብዙም ትኩረት አልሰጠኹትም ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ ዶ/ር አማረን ስለ ጉባኤው ዝግጅት ኹኔታ ስጠይቀው፣ አንተ ከኮሚቴው እንድትወጣ አድርገናል፡፡ በአንተ ምትክ ከፍልስፍና ትምህርት ክፍል ዶ/ር በቀለ ጉተማን አካትተናል አለኝ፡፡ ይኸውም የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አንተን ስለማይወድኽ ነው አለኝ፤ አክሎም ‹‹እርሱ ከኮሚቴው ካልወጣ በስተቀር ስብሰባው ላይ አልገኝም›› ስላሉና አማራጭ ስለሌን አንተን ከኮሚቴው አስወጥተን በሌላ ለመተካት ተገደናል፡፡ ነገሩ ቢገርመኝ፣ አካዳሚያ ውስጥ መውደድና መጥላት የሚባል ነገር ምን አመጣው በማለት ትዝብቴን ገለጽኹለት፡፡
የሚያሳዝነው ግን፣ በዚህ ታላቅ ጉባኤ የጥናት ወረቀት የሚያቀርቡ ኢትዮጵያውያን፣ የጥናትና ምርምር ግኝታችኹን ለማቅረብ ገንዘብ በ‹‹ዩሮ›› ከፍላችሁ ነው በመባላቸው ጉባኤው የታለመለትን ዓላማ ስቶ መክሸፉ ነው፤ ፈረንጆቹም በዓለም ላይ በፍልስፍና ሥነ ትምህርት ከተዘጋጁ ጉባኤዎች ኹሉ እንዲኽ ዓይነቱ ሥምረት የሌለበት ጉባኤ እንዳልገጠማቸው አምርረው በመናገራቸው፣ ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም ኾኖ ክንዋኔው በብዙኃን መገናኛ ሳይዘገብ እንደተዳፈነ ቀረ፡፡
በፕሬዝዳንቱ በኩል በእኔ ላይ ቅሬታ ማሳደር የተጀመረበት አጋጣሚ ይህ ኾኖ፣ በዋናነት ግን በተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች መንግሥት የሚሠራቸውን ተገቢ ያልኾኑ ድርጊቶች በዐደባባይ መተቸቴንና ሒስ ማድረጌን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንትም ይኹኑ የውጭ የፖለቲካ ኃይሎች እንዳልወደዱት ግልጽ ነው፡፡
ኢ.ም፡- ይህን ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ሊወስዱት አስበዋል?
ዶ/ር ዳኛቸው፡- የሥራ ውሌ አልተራዘመም ብዬ ወደ ፍርድ ቤት የመሔድ ሐሳብ የለኝም፡፡ በእኔ እምነት፣ አስተማሪነት የተከበረ ሞያ በመኾኑ፣ በልመና እና በፍርድ ቤት ውሳኔ መምህር ለመኾን መሞከሩ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም፡፡ በተጨማሪም፣ የኔ ከሥራ መሰናበት በተቀዳሚነት የአካዳሚያው ውሳኔ ሳይሆን፣ በውጭ ባሉት ፖለቲካዊ ኃይሎች የተገፋ ብያኔ እንደኾነና የፕሬዝዳንቱ ሚና ደግሞ ያን የማስፈጸም ጉዳይ እንደኾነ ስለምረዳም ጭምር ነው፡፡ የሳባቲካሉን ጉዳይ ግን ወደሚመለከተው ፍርድ ቤት እወስደዋለሁ፡፡
ኢ.ም፡- በኮንትራት ቅጥር ውልዎ እና በሴኔት ሕጉ ላይ የጥናትና ምርምር ዕረፍት (ሳባቲካል) እንደሚሰጥዎ ሰፍሯል፡፡ ኾኖም በስድስት ዓመት የማስተማር አገልግሎት የሚገኘውን ይህን መብትዎን እንደተነፈጉ እርስዎ ቀደም ሲል ለተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ሲመልሱ፣ ‹‹የጠየቁት ጡረታ ከወጡ በኋላ ነው›› ብለዋልና ለዚኽ ምን ይላሉ?
ዶ/ር ዳኛቸው፡- ከኹሉ አስቀድሞ ይህ ጉዳይ በፍርድ ቤት ሒደት ላይ ነው፡፡ ስድሳ ዓመት (የጡረታ ዕድሜ) ሳይሞላኝ ከሦስት ዓመት በፊት ነው ሳባቲካል ዕረፍት እንዲፈቀድልኝ የጠየቅኹት፡፡ የጠየቅኩበት ሰነድም በእጄ ይገኛል፡፡ ዋናው ቁም ነገር ፕሬዝዳንቱ በኹለት ጉዳዮች ላይ ከእውነት የራቀ መልስ መስጠታቸው በጣም አስገርሞኛል፡፡ አንደኛው፣ ከላይ የጠቀስኹት ስድሳ ዓመት ሳይሞላኝ የዕረፍት ጊዜው እንዲፈቀድልኝ ማመልከቴ ነው፡፡ ኹለተኛው ደግሞ ጡረታ ከወጡ በኋላ ሳባቲካል የተሰጣቸው ሌሎች መምህራን እንዳሉና እርሳቸው እንደሚሉት ከጡረታ በኋላ ሳባቲካል ዕረፍት አይሰጥም ያሉት ነጭ ውሸት መኾኑ ነው፡፡ ይህንም ለፍርድ ቤቱ እንደማቀርበው ስም ጠቅሼ ልነግራችኹ እችላለኹ፡፡
ኢ.ም፡- ወደ አገራዊ ጉዳዮች ልውሰድዎና የቅድመ ምርጫ ሒደቱን እንዴት ገመገሙት?
ዶ/ር ዳኛቸው፡- ብዙ ጊዜ ምርጫውን በሚመለከት ወደ አእምሮዬ የሚመጣው ለጥቂት ጊዜም ቢኾን በእነ አቶ በላይ ፍቃዱ ይመራ የነበረው የአንድነት ፓርቲ መፍረስ ነው፡፡ ይህንንም የምልበት ምክንያት፣ ከወጣት አመራሩ መካከል አቶ በላይ ፍቃዱ፣ አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ዐሥራት ኣብርሃ እና ሌሎችም በዚያ አመራር ውስጥ የተሰባሰቡ ሳተናዎች ከጨዋታ ውጪ መደረጋቸው የሐቀኛ ፉክክሩን ጎዳና በመዝጋት የናፈቅንለትን እውነተኛ የምርጫ ውድድር መንፈስ አደንብሾታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ስለምርጫው ውጤትም፣ ብዙ ሰው ከሚለው የተለየ ሐሳብ የለኝም፡፡ ይኸውም ገዢው ግንባር ያለጠንካራ ተፎካካሪ ያንኑ የተለመደውን ከፍተኛ መቀመጫ ይይዛል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ኢ.ም፡- ላለፉት ኻያ አራት ዓመታት ኢትዮጵያን በመምራት ላይ የሚገኘው ህወሓት/ኢሕአዴግ አገሪቱን እና ሕዝቦቿን ወዴት አቅጣጫ እየወሰደ ይገኛል ብለው ያስባሉ?
እኔ እስከሚገባኝ ድረስ በኢሕአዴግ የፖለቲካ ፍልስፍና ወሳኝ የኾነው ቃል ‹‹ብሔር›› የሚለው ነው፡፡ በመሠረቱ የብሔሮች እኩልነት፣ የብሔሮች ራስን በራስ ማስተዳደር የሚለው ጥሪ በራሱ ክፉ አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ስናየው ግን ዜጋ እና የዜግነት ብሂልም ተገቢውን አትኩሮትና ቦታ ሊሰጠው ይገባል እላለኹ፡፡ ከዚኽ በፊት በአንድ ስብሰባ ላይ እንዳቀረብኩት፣ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንደሚከበረው ኹሉ ወደፊት በቅርብ ጊዜ የዜጋ-ዜጎችንም ቀን እንድናከብር ቢፈቀድልን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀልብ እና የልብ ትርታ የትኛው ላይ እንደሚያርፍ ይታይ ነበር፡፡
በመጨረሻም፣ ዩኒቨርስቲውንም ኾነ የአገራችንን የፖለቲካ ድባብ በተወሰነ ደረጃ ይገልጽልኛል ብዬ ከምለው ከዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ‹‹እውነት ማለት የኔ ልጅ›› ከሚለው የግጥም ስብስብ የሚከተሉትን ስንኞች አቅርቤ እንድጭርስ ብትፈቅድልኝ፡-
የኔ ልጅ፣
እውነት ጽድቅ እንዳይመስልሽ፣ ኲነኔ ነው እውነት ያማል፤
አይታከሙት ደዌ፣ ያከሳል ያጎሳቁላል
ኹሌ አያስከብርሽም፣ አንዳንዴ ሕይወት ያስከፍላል፡፡
እውነቱ ነው ጀግንነቱ፣ ቴዎድሮስ ራሱን ቢያጠፋ፤
ከዙሪያ ገባው እውነት፣ የራሱ ሐቅ ቢገዝፍ፣ የራስ እምነቱ ቢሰፋ፤
ቊርባኑን አላፈርስ ብሎ፣ ከእውነቱ አልተጣላ፤
ማተቡን አልበጥስ ብሎ ነው፣ የወደቀው ከመቅደላ፡፡ …
አቡነ ጴጥሮስ በዐደባበይ፣ በጥይት የተደበደበ፣
ደብር እንደፈታ ሽፍታ
እውነቱና ሕይወቱ፣ ሕይወቱና እምነቱ፣ ብሎት ነው አልፋታ፡፡ …
አጥተውት መሰለሽ ልጄ፣
በላይ ዘለቀ አድር ቢል፣ እጅ ቢነሣ አስመስሎ፣
ጴጥሮስ ለፋሽስት ቢሰብክ፣ የአገር ወገን እውነቱን፤
የአካል የመንፈስ፣ እምነቱን ጥሎ፤
ጊዜ አጨብጭቦ፣ ወርቅ ተሸልመው፤
እንበለ ኃጢአት፣ ቅዱሳን ተብለው፤
በሕይወት እንደሚኖሩ፤
እውነትን ሽረው እንደሚከብሩ፤…
ልጄ፣ እውነት ከሕይወት ይከብዳል፤
በመኖር ከሕይወት ተገኝቶ መልሶ ሕይወትን ይበላል፡፡
(ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ ቅጽ 03፣ ቁጥር 101፣ ረቡዕ መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም)

'- ‹‹አስተማሪነት የተከበረ ሞያ በመኾኑ፣ በልመና እና በፍርድ ቤት ውሳኔ መምህር ለመኾን መሞከሩ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም፡፡››<br />
                                                             ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ</p>
<p>ኢ.ም፡- የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ዓርብ መጋቢት 18 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የእርስዎን እና የዶ/ር መረራ ጉዲናን የቅጥር ውዝግብ በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል፡- ‹‹ዩኒቨርስቲው በየትኛውም የትምህርት ክፍል በቂ መምህራን አሉኝ ብሎ ካመነ፣ ለጡረታ የደረሱ መምህራንን ኮንትራት ላያራዝም የሚችልበት የቆየ አሠራር አለው፤›› ብለዋል፡፡ በዚህ ዙሪያ ምን የሚሰጡት አስተያየት አለ?<br />
ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፡- ለዚህ አባባል መልስ ከመስጠቴ በፊት፣ ከትምህርቴም ኾነ ከአስተዳደጌ የተማርኹትና አብሮኝ የኖረ ቁልፍ የሞራል አስተምህሮ አለ፡፡ ይኸውም፣ በማናቸውም ጊዜ ግጭት፣ ፍልሚያ ወይም ክርክር በምንገጥምበት ጊዜ፣ በተቻለን መጠን እውነትን ጨብጠን መሔዱ በጣም አስፈላጊ ነው የሚል ግንዛቤ አለኝ፡፡ እውነትን ሰለባ በማድረግ ጊዜያዊ ድልን ለመጎናጸፍ መሞከር በራሱ ለምንቃወማቸው ድርጊቶች እና ሰዎች ተላልፎ በመሰጠት ተሸናፊ ስለሚያደርገን፣ በሐሰት ድልን ለመጎናጸፍ መሞከርን የመሰለ ሽንፈት የለም ብዬ ስለማምን ነው፡፡<br />
ዶ/ር አድማሱ፣ ‹‹የትምህርት ክፍሉ በቂ መምህራን አሉኝ ካለ ግለሰቡ ኮንትራቱ አይታደስለትም›› ያሉት እውነት ነው፡፡ ኾኖም ዋናው ጥያቄ፣ የትምህርት ክፍሉ እኔን በሚመለከት አገልግሎቴን አልፈልግም ብሏል ወይ፤ የሚለው ነው፡፡ ይህን ጥያቄ በተመለከተ እኔ እንዲህ ነው ወይም እንዲያ ነው ከምል፣ የትምህርት ክፍሌ የእኔን አገልግሎት በጥብቅ እንደሚፈልግና ኮሌጁም (የሶሻል ሳይንስ) እንደተስማማበት ለፕሬዝዳንቱ የቀረበውን ደብዳቤ በማረጋገጫነት ልታቀርቡት ትችላላችኹ፡፡ የፕሬዝዳንቱን አቀራረብ የቱን ያህል ከእውነት የራቀ መኾኑን አንባቢ አይቶ ፍርዱን እንዲሰጥ እጋብዛለኹ፡፡<br />
ኢ.ም፡- ሰሞኑን ‹‹ተወይኖብኛል›› ብለው ባስነበቡት ቃለ መጠይቅ ላይ ‹‹ብጣሽ ወረቀት ስጠብቅ አልኖርም›› ብለዋል፡፡ እስኪ ስለዚህ ወረቀት ትንሽ ያብራሩልኝ፡፡</p>
<p>ዶ/ር ዳኛቸው፡- ከዚኽ ቀደም እንደገለጽኩት፣ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል የእኔን ተጨማሪ የሥራ ዘመን አገልግሎት እንደሚፈልግ ለሶሻል ሳይንስ ኮሌጁ ዲን እና በበላይነት ለሚሰበስበው አካዳሚክ ኮሚሽን የፍልስፍና ትምህርት ክፍል ሊቀ መንበር በአካል ተገኝተው ከማስረዳታቸውም በተጨማሪ በደብዳቤም ጠይቀዋል፡፡ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጁም ቢኾን የፍልስፍና ትምህርት ክፍልን ጥያቄ ተቀብሎ የሥራ ውሌ እንዲታደስ፣ በፕሮፌሰር ወልደ አምላክ በዕውቀት (የኮሌጁ ዲን) በኩል ለዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ እንዲያጸድቁት በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡<br />
ኾኖም ፕሬዝዳንቱ አራት ወር ሙሉ ይኾናልም - አይኾንምም ሳይሉ ለደብዳቤው መልስ ሳይሰጡ በእጅጉ በመዘግየታቸው የእርሳቸውን ቅን ልቡና የጎደለው እና ተንኮል ያዘለ አካሔድ ለመግለጽ ‹‹ብጣሽ ወረቀት አልጠብቅም›› የሚለውን ሐረግ ተጠቅሜአለኹ፡፡ ፕሬዝዳንቱ መልስ አለመስጠታቸው ከሕግ እና ከሞራል አገባብ ውጭ እንደኾኑ ቀደም ሲልም ለማብራራት ሞክሬያለኹ፡፡<br />
ነገሩን ለማጠቃለል ያኽል፣ የእናንተ አንባቢዎች በጉዳዩ ላይ የራሳቸውን ግንዛቤ እና ፍርድ እንዲሰጡ ለፕሬዝዳንቱ የተላከውን ደብዳቤ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚኽ ቃለ ምልልስ አጋጣሚ ላቅርብ፡፡ ከማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲኑ በእንግሊዝኛ የተጻፈው የደብዳቤው ይዘት የአማርኛ አቀራረቡ በአጭሩ የሚከተለውን ነው፡-<br />
ጉዳዩ፡- የዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን የኮንትራት ውል እደሳ ይመለከታል፤<br />
የፍልስፍና ዲፓርትመንት፣ ለዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የኹለት ዓመት ኮንትራት እድሳት እንዲያገኙ ጠይቋል፡፡ ስለ ኮንትራት እድሳቱ አስፈላጊነት ዲፓርትመንቱ ያቀረባቸው ምክንያቶች፡-<br />
- ዶ/ር ዳኛቸው ሦስት የድኅረ ምረቃ ትምህርቶች (ኮርሶች) እና የቅድመ ምረቃ ዲግሪ ኮርሶችንም ስለሚያስተምሩ፤<br />
- በርካታ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎችን (ከ12-15 ተማሪዎች) የመመረቂያ ጽሑፎችን ስለሚያማክሩ፤<br />
- ከፍልስፍና ዲፓርትመንት ውጭ በርከት ያሉ ኮርሶችን በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት፣ በሰብአዊ መብቶች ተቋም የትምህርት ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ኢንቲትዩት እና የሕግ ትምህርት ቤት ስለሚያስተምሩ፤<br />
- በቅርቡ ለሚጀመረው የሦስተኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) መርሐ ግብር የዶክተር ዳኛቸው አገልግሎት በእጅጉ አስፈላጊ ነው ብሎ ዲፓርትመንቱ ስለሚያምን፣<br />
የሚሉት ናቸው፡፡<br />
የአካዳሚክ ኮሚሽኑ በህዳር 24 ስብስባው ወቅት በዚኽ የዲፓርትመንቱ ጥያቄ ላይ ተወያይቶ የዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የኮንትራት ቅጥር ውል ከታኅሣሥ 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ለኹለት ዓመት እንዲራዘም ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በመኾኑም የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ቢሮው፣ ለውሉ መራዘም የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝዳንት ይኹንታ በማረጋጥ የውል እድሳት ሒደቱን እንዲያስፈጽምልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡<br />
ደብዳቤው በአድራሻ የተላከው ለዩኒቨርስቲው ለሰው ሀብትና ልማት አስተዳደር ቢሮ ሲኾን፣ ላኪው ደግሞ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ ነው፡፡ ይኸው ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ  ቢሮ፣ ለአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ቢሮ፣ ለአካዳሚክ ጉዳዮች ቢሮ፣ ለፍልስፍና ትምህርት ክፍል እና ለማኔጂንግ ዳይሬክተሩ በግልባጭ እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡<br />
ኢ.ም፡- እርስዎ እንዳሉት፣ ጥያቄዎ ሕግና ደንብን ጠብቆ ከቀረበ፣ ችግር ፈቺ እንዲኾን ከሚጠበቅ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ምላሽ የተሰጠበት አግባብ ስለ አገራችን ኹኔታ ምን አንድምታ እና ማሳያ ሊሰጠን ይችላል?</p>
<p>ዶ/ር ዳኛቸው፡- ከኹሉ አስቀድሞ የአንድ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ለኹለት ዓበይት ጉዳዮች ተጠሪ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ አንደኛና ተቀዳሚው ተጠሪነቱ ዩኒቨርስቲው ለቆመለት ተቋማዊ መርኆ (አይዲያል) ነው፡፡ በኹለተኛው ደረጃ ደግሞ ለዩኒቨርስቲው አጠቃላይ ማኅበረሰብ (ኮሚዩኒቲ) ተጠሪ መኾን አለበት፡፡<br />
እኔ፣ ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ከኾኑ ጀምሮ የታዘብኩትና ያየኹት፣ እንደ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ተጠሪነታቸው ለዩኒቨርስቲው ርእይ ሳይኾን መንግሥት ለሚያወጣው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዕቅዶች (social and political policy) መኾኑን አያለኹ፡፡ ከዚኽም ባሻገር ለዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ በጎነት ከመቆም እና የአካዳሚክ ነፃነት እንዲከበር ከመጣር ይልቅ ለሾሟቸው የፖለቲካ ኃይሎች በተደጋጋሚ ተጠሪነታቸውን በጉልሕ አሳይተዋል፡፡<br />
በእርሳቸው አመራር አንድ ትጉህ አስተማሪ የሚዳኘው በአካዳሚያዊ መሥፈርት ሳይኾን፣ በብሔር ተዋፅኦ፣ በፓርቲ ተሳትፎ እና የመንግሥት ፖሊሲን ለማስፈጸም በሚያሳየው ተነሳሽነት ነው፡፡ ለማጠቃለል ያኽል፣ ዶ/ር አድማሱ ከሚዘነጓቸው ነገሮች መካከል፣ አንድ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የመንግሥት ተከፋይ ቢኾንም ቅሉ፣ የመንግሥት ሠራተኛ (ሲቭል ሰርቫንት) እንዳልኾነ ነው፡፡</p>
<p>ኢ.ም፡- በዩኒቨርስቲው ውስጥ እርስዎ የሚሉት ዓይነት ድባብ እንዴት ሊሰፍን ቻለ? በዚኽ አኳኋንስ የዩኒቨርስቲ ምሁራን ለመጠየቅ እና እውነት ላይ ለመድረስ የሚጥሩ ወጣት ዜጎችን እንደምን ሊያፈሩ ይችላሉ?  </p>
<p>ዶ/ር ዳኛቸው፡- ጥያቄው ኹለት ጉዳዮችን የያዘ ይመስለኛል፤ ተራ በተራ ለመመልከት እሞክራለኹ፡፡ አንደኛ፣ እንዲኽ ዓይነት የማይጠይቅ፣ ተቀባይነት እና የፖሊሲ አስፈጻሚነት መንፈስ ከዬት መነጨ ብለን በምንፈትሽበት ጊዜ፣ ጉዳዩ በማወቅና ባለማወቅ፣ ግንዛቤ በማግኘትና በማጣት (Epistmic) ምክንያት ብቻ ሳይኾን ከግል ጥቅምና ከፍቅረ ንዋይ ጋር የተሳሰረ ስለኾነ ነው፡፡ እንዲኽ ዓይነት ፖሊሲ አስፈጽሙ ሲባል፣ ትእዛዙ የሚመጣው ብቻውን ሳይኾን ከብዙ ዓይነት ዳረጎት (ኮሚሽን) ጋር ስለኾነ፣ ሳያቅማሙ እና ሳይፈትሹ ወደ መቀበልና መተግበር ይገባሉ፡፡<br />
በዩኒቨርስቲው ውስጥ ያሉትን መምህራን በሙሉ ሳይተቹ ተቀባይ እና ፖሊሲ አስፈጻሚ አድርጎ መመልከቱ አግባብነት አይኖረውም፤ እንዲያውም በዩኒቨርስቲው ለሰባት ዓመታት በቆየኹባቸው ጊዜያት ከአገኘኋቸውና ከተዋወቅኋቸው የግቢው ሊቃውንት ብዙ ትምህርት እንደቀሰምኹ ለመግለጽ እወዳለኹ፡፡<br />
ነገር ግን፣ ጠያቂና ተቺ የኾኑ ዓይናማ ሊቃውንት በግቢው ውስጥ እንዳሉ ኹሉ፣ በርከት ያሉ ካድሬዎችም በምሁራን ስም ተቀጥረው ግቢውን እያጣበቡት እንደኾነ ማንም አይስተውም፤ ፕሬዝዳንቱም አንድ ለአምስት በሚል የጥርነፋ ፕሮግራም መምህራኑን እያስቸገሩ አትኩሮታቸውን ለመማር ማስተማር ሒደቱ በቅጡ እንዳያውሉ እና የትምህርት ድባቡን እያስተጓጎለ እንደሆነ በግቢው ውስጥ በሰፊው እየተወራ ነው፡፡<br />
በጥያቄህ ላይ በእንዲህ ዓይነት ድባብ ውስጥ የሚወጡት ተማሪዎች ምን መልክ ይይዛሉ ብለኽ ለጠየቅኸኝ፣ ኹኔታው ጥሩ ተማሪ ለማፍራት ተግዳሮት ቢኾንም፣ ጥቂት የማይባሉት መምህራን በግላቸው ሞያዊ ግዴታቸውን ለመወጣት በእጅጉ እየጣሩ ይገኛሉ፡፡<br />
ኢ.ም፡- እኔ እንደሰማኹት፣ በመስከረም 2007 ዓ.ም መንግሥት ለዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ ለዐሥር ቀናት የዘለቀ ሥልጠና በሰጠበት ወቅት፣ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ መምህራንን የመቅጠር ሒደትና ሌሎችንም ዋና ዋና ሥልጣኖች ከዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ይልቅ ወደ ዩኒቨርስቲ ኮሌጆችና ዲፓርትመንቶች ተሰጥቷል ሲሉ ተደምጠዋል፤ እንዲያውም ኮሌጆችና ዲፓርትመንቶች መምህራንን ለመቅጠር ፈቃደኛ ባለመኾናቸው ከፍተኛ በጀት ለመንግሥት ተመላሽ እየተደረገ ነው በማለት አማርረው ነበር፡፡ በአንጻሩ እርስዎንና ዶ/ር መረራን ዲፓርትመንቱና ኮሌጆቹ እንፈልጋቸዋለን እያሉ ፕሬዝዳንቱ ግን ቅጥራችኹ የሚራዘምበት ይኹንታን ፈቃደኛ አልኾኑም፡፡</p>
<p>ዶ/ር ዳኛቸው፡- በመሠረቱ በወቅቱ እኔ በሥልጠናው ላይ ለመገኘት ስላልፈለግኹ በስብሰባው አልተሳተፍኩም፤ ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ከቀድሞው የዩኒቨርስቲው አስተዳደር በተለየ መልኩ ለኮሌጆችና ለዲፓርትመንቶች ሥልጣን አውርጃለኹ በማለት እየተኩራሩ ሲናገሩ በሌላ አጋጣሚ ሰምቻለኹ፡፡ ይኹንና ወደ ተጨባጭ እውነታው ስንመጣ፣ ከነቢብ አልፎ በገቢር ባለመተርጎማቸው፣ ፕሬዝዳንቱ ተቀዳሚ የሚያደርጉት የዩኒቨርስቲውን ጥቅምና ፍላጎት ሳይኾን፣ የራሳቸውን የግል ፍላጎት ለመኾኑ ከዚህ የበለጠ ማረጋገጫ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡<br />
ኢ.ም፡- በደብዳቤው እንደተገለጸው፣ ኮሌጁና ዲፓርትመንቱ አጥብቆ በሚፈልግዎት በእርስዎ ላይ ፕሬዝዳንቱ እንዲኽ ዓይነት ርምጃ ለመውሰድ ያበቃቸው ምን ሊኾን ይችላል ብለው ያስባሉ?<br />
ዶ/ር ዳኛቸው፡- ይኸውልህ ነገሩ የተጀመረው ፕሬዝዳንቱ ተሹመው በመጡ ማግሥት ነው፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ማኅበረሰብ በጠቅላላ ሰብስበው ለዓባይ ግድብ ምን አስተዋፅኦ ማድረግ እንችላለን ብለው ከመድረክ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አንድ- አራት- አምስት ሰዎች ተነሡና እኔ እንዲኽ አደርጋለኹ፤ እኔም እንዲኽ አደርጋለኹ ብለው ተናግረው ሲያበቁ፣ የተሰበሰብነው ሰዎች በሺሕዎች ብንቆጠርም ፕሬዝዳንት አድማሱ፣ ‹‹የምትሉት ገብቶኛል፤ የወር ደሞዝ እንሰጣለን ነው የምትሉት፤›› በማለት ቀድሞ የተጻፈ የአቅዋም መግለጫ አስነብበው ስብሰባውን በዚኹ ቋጩት፡፡<br />
እኔም በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ፣ አራትና አምስት ሰው ብቻ በተናገረው እንደምን የብዙኃኑን ሰዎች ፍላጎት አገኙት በማለት ግልጽ ሒሳዊ ደብዳቤ ጻፍኹላቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ መተቻቸት በአካዳሚያዊ ተቋማት የተለመደ ቢኾንም፣ እርሳቸው ግን፣ እኔ ባቀረብኹላቸው አስተያየት አቂመው ቆይተዋል፡፡ ይህን የሚያስረግጥ ሌላም ጉዳይ ልጠቀስልኽ፤<br />
የቀድሞው የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ በነበሩበት ጊዜ፣ 19ኛው የዓለም አቀፍ የትምህርት ፍልስፍና ጉባኤ (International Network of Philosophers of Education Conference) ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኾን ተወሰነ፡፡ ጉባኤውን የዩኒቨርስቲው የትምህርት ክፍል ለብቻው ማዘጋጀት ቢፈልግም፣ ፈረንጆቹ የፍልስፍና ዲፓርትመንትም መካፈል አለበት ስላሉ፣ በዚያን ጊዜ ፕሮፌሰር አንድርያስ የትምህርት ክፍሉን በመወከል በዝግጅቱ እንድሳተፍ ጋበዙኝ፡፡<br />
ጉባኤውን ለማዘጋጀት በተቋቋመው ኮሚቴ፥ ፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ፣ ዶ/ር ጄሉ ዑመር፣ ዶ/ር አማረ አስገዶም እና እኔ በጋራ መሥራት ጀመርን፡፡ ከዚያም ዶ/ር አማረ አስገዶም ለጉባኤው ዝግጅት ከአራት ሚልዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ነገረኝ፤ አዲስ የተሾሙት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬም ብሩን እንደሚፈቅዱም በርግጠኝነት ገለጸልኝ፡፡ ወጪው በጣም ከፍ ያለ መስሎ ስለታየኝ፣ ይህን ያኽል ብር ለምን ያስፈልገናል ብዬ ጠየቅኹት፡፡ ዶ/ር አማረ ሲመልስልኝ፣ ከተለያየ የዓለም ክፍል የሚመጡትና ከሀገር ውስጥ የጉባኤው ተሳታፊዎች ከፍለው ስለሚገቡ ወደ ሰባት ሚልዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ተገኝቶ የኒቨርስቲው ሦስት ሚልዮን ብር እንደሚያተርፍ ነገረኝ፡፡ በመቀጠልም ፕሬዝዳንቱን ስለ ጉዳዩ ለማሳወቅ ቀጠሮ እንደተያዘ ነገረኝ፡፡<br />
ኾኖም ኹለት ጊዜ ባካሔድነው ስብሰባ ላይ ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ሳይመጡ ቀሩ፡፡ በጊዜው ሳይመቻቸው ቀርቶ ነው በማለት ነገሩን ብዙም ትኩረት አልሰጠኹትም ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ ዶ/ር አማረን ስለ ጉባኤው ዝግጅት ኹኔታ ስጠይቀው፣ አንተ ከኮሚቴው እንድትወጣ አድርገናል፡፡ በአንተ ምትክ ከፍልስፍና ትምህርት ክፍል ዶ/ር በቀለ ጉተማን አካትተናል አለኝ፡፡ ይኸውም የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አንተን ስለማይወድኽ ነው አለኝ፤ አክሎም ‹‹እርሱ ከኮሚቴው ካልወጣ በስተቀር ስብሰባው ላይ አልገኝም›› ስላሉና አማራጭ ስለሌን አንተን ከኮሚቴው አስወጥተን በሌላ ለመተካት ተገደናል፡፡ ነገሩ ቢገርመኝ፣ አካዳሚያ ውስጥ መውደድና መጥላት የሚባል ነገር ምን አመጣው በማለት ትዝብቴን ገለጽኹለት፡፡<br />
የሚያሳዝነው ግን፣ በዚህ ታላቅ ጉባኤ የጥናት ወረቀት የሚያቀርቡ ኢትዮጵያውያን፣ የጥናትና ምርምር ግኝታችኹን ለማቅረብ ገንዘብ በ‹‹ዩሮ›› ከፍላችሁ ነው በመባላቸው ጉባኤው የታለመለትን ዓላማ ስቶ መክሸፉ ነው፤ ፈረንጆቹም በዓለም ላይ በፍልስፍና ሥነ ትምህርት ከተዘጋጁ ጉባኤዎች ኹሉ እንዲኽ ዓይነቱ ሥምረት የሌለበት ጉባኤ እንዳልገጠማቸው አምርረው በመናገራቸው፣ ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም ኾኖ ክንዋኔው በብዙኃን መገናኛ ሳይዘገብ እንደተዳፈነ ቀረ፡፡<br />
በፕሬዝዳንቱ በኩል በእኔ ላይ ቅሬታ ማሳደር የተጀመረበት አጋጣሚ ይህ ኾኖ፣ በዋናነት ግን በተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች መንግሥት የሚሠራቸውን ተገቢ ያልኾኑ ድርጊቶች በዐደባባይ መተቸቴንና ሒስ ማድረጌን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንትም ይኹኑ የውጭ የፖለቲካ ኃይሎች እንዳልወደዱት ግልጽ ነው፡፡<br />
ኢ.ም፡- ይህን ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ሊወስዱት አስበዋል?<br />
ዶ/ር ዳኛቸው፡- የሥራ ውሌ አልተራዘመም ብዬ ወደ ፍርድ ቤት የመሔድ ሐሳብ የለኝም፡፡ በእኔ እምነት፣ አስተማሪነት የተከበረ ሞያ በመኾኑ፣ በልመና እና በፍርድ ቤት ውሳኔ መምህር ለመኾን መሞከሩ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም፡፡ በተጨማሪም፣ የኔ ከሥራ መሰናበት በተቀዳሚነት የአካዳሚያው ውሳኔ ሳይሆን፣ በውጭ ባሉት ፖለቲካዊ ኃይሎች የተገፋ ብያኔ እንደኾነና የፕሬዝዳንቱ ሚና ደግሞ ያን የማስፈጸም ጉዳይ እንደኾነ ስለምረዳም ጭምር ነው፡፡ የሳባቲካሉን ጉዳይ ግን ወደሚመለከተው ፍርድ ቤት እወስደዋለሁ፡፡<br />
ኢ.ም፡- በኮንትራት ቅጥር ውልዎ እና በሴኔት ሕጉ ላይ የጥናትና ምርምር ዕረፍት (ሳባቲካል) እንደሚሰጥዎ ሰፍሯል፡፡ ኾኖም በስድስት ዓመት የማስተማር አገልግሎት የሚገኘውን ይህን መብትዎን እንደተነፈጉ እርስዎ ቀደም ሲል ለተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ሲመልሱ፣ ‹‹የጠየቁት ጡረታ ከወጡ በኋላ ነው›› ብለዋልና ለዚኽ ምን ይላሉ?<br />
ዶ/ር ዳኛቸው፡- ከኹሉ አስቀድሞ ይህ ጉዳይ በፍርድ ቤት ሒደት ላይ ነው፡፡ ስድሳ ዓመት (የጡረታ ዕድሜ) ሳይሞላኝ ከሦስት ዓመት በፊት ነው ሳባቲካል ዕረፍት እንዲፈቀድልኝ የጠየቅኹት፡፡ የጠየቅኩበት ሰነድም በእጄ ይገኛል፡፡ ዋናው ቁም ነገር ፕሬዝዳንቱ በኹለት ጉዳዮች ላይ ከእውነት የራቀ መልስ መስጠታቸው በጣም አስገርሞኛል፡፡ አንደኛው፣ ከላይ የጠቀስኹት ስድሳ ዓመት ሳይሞላኝ የዕረፍት ጊዜው እንዲፈቀድልኝ ማመልከቴ ነው፡፡ ኹለተኛው ደግሞ ጡረታ ከወጡ በኋላ ሳባቲካል የተሰጣቸው ሌሎች መምህራን እንዳሉና እርሳቸው እንደሚሉት ከጡረታ በኋላ ሳባቲካል ዕረፍት አይሰጥም ያሉት ነጭ ውሸት መኾኑ ነው፡፡ ይህንም ለፍርድ ቤቱ እንደማቀርበው ስም ጠቅሼ ልነግራችኹ እችላለኹ፡፡<br />
ኢ.ም፡- ወደ አገራዊ ጉዳዮች ልውሰድዎና የቅድመ ምርጫ ሒደቱን እንዴት ገመገሙት?<br />
 ዶ/ር ዳኛቸው፡- ብዙ ጊዜ ምርጫውን በሚመለከት ወደ አእምሮዬ የሚመጣው ለጥቂት ጊዜም ቢኾን በእነ አቶ በላይ ፍቃዱ ይመራ የነበረው የአንድነት ፓርቲ መፍረስ ነው፡፡ ይህንንም የምልበት ምክንያት፣ ከወጣት አመራሩ መካከል አቶ በላይ ፍቃዱ፣ አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ዐሥራት ኣብርሃ እና ሌሎችም በዚያ አመራር ውስጥ የተሰባሰቡ ሳተናዎች ከጨዋታ ውጪ መደረጋቸው የሐቀኛ ፉክክሩን ጎዳና በመዝጋት የናፈቅንለትን እውነተኛ የምርጫ ውድድር መንፈስ አደንብሾታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ስለምርጫው ውጤትም፣ ብዙ ሰው ከሚለው የተለየ ሐሳብ የለኝም፡፡ ይኸውም ገዢው ግንባር ያለጠንካራ ተፎካካሪ ያንኑ የተለመደውን ከፍተኛ መቀመጫ ይይዛል የሚል እምነት አለኝ፡፡<br />
ኢ.ም፡- ላለፉት ኻያ አራት ዓመታት ኢትዮጵያን በመምራት ላይ የሚገኘው ህወሓት/ኢሕአዴግ አገሪቱን እና ሕዝቦቿን ወዴት አቅጣጫ እየወሰደ ይገኛል ብለው ያስባሉ?<br />
እኔ እስከሚገባኝ ድረስ በኢሕአዴግ የፖለቲካ ፍልስፍና ወሳኝ የኾነው ቃል ‹‹ብሔር›› የሚለው ነው፡፡ በመሠረቱ የብሔሮች እኩልነት፣ የብሔሮች ራስን በራስ ማስተዳደር የሚለው ጥሪ በራሱ ክፉ አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ስናየው ግን ዜጋ እና የዜግነት ብሂልም ተገቢውን አትኩሮትና ቦታ ሊሰጠው ይገባል እላለኹ፡፡ ከዚኽ በፊት በአንድ ስብሰባ ላይ እንዳቀረብኩት፣ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንደሚከበረው ኹሉ ወደፊት በቅርብ ጊዜ የዜጋ-ዜጎችንም ቀን እንድናከብር ቢፈቀድልን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀልብ እና የልብ ትርታ የትኛው ላይ እንደሚያርፍ ይታይ ነበር፡፡<br />
በመጨረሻም፣ ዩኒቨርስቲውንም ኾነ የአገራችንን የፖለቲካ ድባብ በተወሰነ ደረጃ ይገልጽልኛል ብዬ ከምለው ከዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ‹‹እውነት ማለት የኔ ልጅ›› ከሚለው የግጥም ስብስብ የሚከተሉትን ስንኞች አቅርቤ እንድጭርስ ብትፈቅድልኝ፡-<br />
የኔ ልጅ፣<br />
እውነት ጽድቅ እንዳይመስልሽ፣ ኲነኔ ነው እውነት ያማል፤<br />
አይታከሙት ደዌ፣ ያከሳል ያጎሳቁላል<br />
ኹሌ አያስከብርሽም፣ አንዳንዴ ሕይወት ያስከፍላል፡፡<br />
እውነቱ ነው ጀግንነቱ፣ ቴዎድሮስ ራሱን ቢያጠፋ፤<br />
ከዙሪያ ገባው እውነት፣ የራሱ ሐቅ ቢገዝፍ፣ የራስ እምነቱ ቢሰፋ፤<br />
ቊርባኑን አላፈርስ ብሎ፣ ከእውነቱ አልተጣላ፤<br />
ማተቡን አልበጥስ ብሎ ነው፣ የወደቀው ከመቅደላ፡፡ …<br />
አቡነ ጴጥሮስ በዐደባበይ፣ በጥይት የተደበደበ፣<br />
                     ደብር እንደፈታ ሽፍታ<br />
እውነቱና ሕይወቱ፣ ሕይወቱና እምነቱ፣ ብሎት ነው አልፋታ፡፡ ...<br />
አጥተውት መሰለሽ ልጄ፣<br />
በላይ ዘለቀ አድር ቢል፣ እጅ ቢነሣ አስመስሎ፣<br />
ጴጥሮስ ለፋሽስት ቢሰብክ፣ የአገር ወገን እውነቱን፤<br />
የአካል የመንፈስ፣ እምነቱን ጥሎ፤<br />
ጊዜ አጨብጭቦ፣ ወርቅ ተሸልመው፤<br />
እንበለ ኃጢአት፣ ቅዱሳን ተብለው፤<br />
በሕይወት እንደሚኖሩ፤<br />
እውነትን ሽረው እንደሚከብሩ፤…<br />
ልጄ፣ እውነት ከሕይወት ይከብዳል፤<br />
በመኖር ከሕይወት ተገኝቶ መልሶ ሕይወትን ይበላል፡፡<br />
(ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ ቅጽ 03፣ ቁጥር 101፣ ረቡዕ መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም)'

The post ‹‹አስተማሪነት የተከበረ ሞያ በመኾኑ፣ በልመና እና በፍርድ ቤት ውሳኔ መምህር ለመኾን መሞከሩ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም፡፡›› ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዘንባባው እሑድ –የሆሳዕና በዓል

$
0
0

ሔኖክ ያሬድ

የዘንድሮው ትንሣኤ በዓል ሊከበር አንድ ሳምንት ቀርቶታል፡፡ የሚያዝያን አራተኛ ቀንን ይጠብቃል፡፡ ዛሬ መጋቢት 27 ቀን ሆሳዕና ከእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና ዋና በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡

ክርስቶስ ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ይታሰብበታል፡፡ በወቅቱ ተሰባስበው የነበሩት የዘንባባና የወይራ ዝንጣፊ ይዘው በደስታ በዝማሬ ‹‹ሆሳዕና የዳዊት ልጅ›› እያሉ በምስጋና ተቀብለውታል፡፡
hosaena
‹‹ሆሳዕና›› የአራማይስጥ (አራማይክ) ቃል ሲሆን ፍችውም ‹‹አድነን›› ማለት ነው፡፡ በዕብራይስጥም በግእዝም ተመሳሳይ ፍች አለው፡፡ በዚያ ዘመን አይሁዶች በሮማውያን ቀንበር ውስጥ ወድቀው ነበርና ምድራዊ ንጉሥ መጥቶ ነፃ እንደሚያወጣቸውና እንደሚያድናቸው ይጠብቁ ነበር፡፡ በመጻሕፍት እንደተጻፈው፣ በዚሁ ቀን እንዲሁ እግዚእ ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብቶ ሃይማኖት የንግድ ቦታ አይደለም በማለት ቁጣውን ያሳየበትና ነጋዴዎችንና ቀራጮችንም ያባረረበት ነበር፡፡

ቤተመቅደሱ የጸሎት ቤት መሆኑን ያወጀበትና ክብሩንም የገለጸበት ነው፡፡ የሆሳዕና ሥርዓት ዐቢይ ጾም በተጀመረ በስምንተኛው ሳምንት፣ ከትንሣኤ (ፋሲካ) አንድ ሳምንት በፊት የሚከበረው ሆሳዕና ከጌታ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሆሳዕና እሑድ በሁለት ነገሮች ይዘከራል፡፡ አንደኛው በቅዳሴ ጊዜ ‹‹ያለ ሕማምና ያለ ደዌ፣ ያለ ድካምም ለከርሞም ያድርሰን ያድርሳችሁ›› እያሉ ካህናቱ ዘንባባ የሚያድሉበት ሲሆን፣ ሁለተኛው ካህናቱና ምዕመናኑ በቤተ ክርስቲያኑ ዙርያ የሚያደርጉት ዑደት ነው፡፡ ‹‹በታወቀችው በዓላችን መለከቱን ንፉ›› እያሉ የቅዱስ ያሬድ መዝሙር እየተዘመረ በዐራቱም ማዕዘናት ዕለቱን በተመለከተ ዐራቱ ወንጌላት እየተነበቡ ይከበራል፡፡

ዕለቱ የሰሙነ ሕማማት ዋዜማ ስለሆነና ሰሙነ ሕማማት ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረው ‹‹የዓመተ ፍዳ የዓመተ ኩነኔ›› መታሰቢያ ሳምንት በመሆኑ ጸሎተ ቡራኬ ለሙታን የፍትሐት ጸሎት ስለማይፈጸምበት በሆሳዕና እሑድ በሳምንቱ ውስጥ ለሚያርፉት የሚገባው ሁሉ አስቀድሞ ይፈጸማል፡፡

ከሆሳዕና በኋላ ከትንሣኤ በፊት ያሉት ሰሙነ ሕማማትና ዓርብ ስቅለት በተለይ በጾምና በስግደት የሚከበሩ ናቸው፡፡ በወይራ ቅጠል ጥብጠባ በማሳረጊያው ይደረጋል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ሥርዓት መሠረት ከሆሳዕና ሰኞ እስከ ጸሎተ ኀሙስ ያሉት ቀናት ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበሩትን 5500 ዓመታት (አምስት ተኩል ቀናት) “የዓመተ ፍዳ” መታሰቢያ ሆነው ተሠርተዋል፡፡ ሆሳዕና ባህላዊ ገጽታዎች የሚታዩበት ነው፡፡ በሁሉም የአገሪቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ዐውደ ምሕረት ምእመናኑ እየተገኙ የዘንባባ ዝንጣፊ ከመያዝ ባሻገር፣ ከአዋቂ እስከ ሕፃን በዘንባባው ቅጠል ለጣታቸው ቀለበት፣ ለእጃቸው እንደ አልቦ፣ ለራሳቸው እንደ አክሊል የሚጠለቅ አድርገው ያዘጋጃሉ፡፡ ምዕመናኑም የመስቀል ምልክት በመሥራት በቤታቸው ይሰቅሉታል፡፡

በሆሳዕና እሑድ ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁነት በማስታወስ በአንዳንድ አድባራት ተመሳሳይ ሥርዓት ይከናወናል፡፡ በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ትርዒቱ የተካሄደው ከ109 ዓመት በፊት ነበር፡፡ ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ “የዘመን ታሪክ ትዝታዬ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት” በሚለው የትዝታ ድርሳናቸው እንደጻፉት፣ የሆሳዕና በዓል በአክሱም ሥርዓት ዓይነት ሆኖ እንጦጦ ላይ መከበር የተጀመረው በ1898 ዓ.ም መጋቢት 30 በሆሳዕና ዕለት ነው፡፡ ከአክሱም የመጡ አንድ መምህር ከበዓሉ ቀን ቀደም ብለው ጀምረው የሥነ ሥርዓቱን አፈጻጸም ለደብሩ ካህናትና ለሕፃናት መዝሙር አስጠንተዋል፡፡

በበዓሉ ዕለት አንዲቱን የበቅሎ ግልገል በወርቅ ጥልፍ የተለጠፈ ባለመረሻት (የበቅሎ የማዕርግ ልብስ፣ በልዩ ልዩ ሐሮች ተጠልፎ የተዘጋጀ ወርቀ ዘቦ) ኮርቻ ተጭኖባት ድባብ ደብበውላትና አጅበዋት ወደ ቤተ ክርስቲያን አመጡዋት፡፡ ዑደት ተደረገ፡፡ ከአክሱም የመጣው ያ የሆሳዕና በዓል ሥነ ሥርዓት ጃንሆይ ዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ መኳንንትም ሁሉ ባሉበት መከበሩ ተመዝግቧል፡፡

The post የዘንባባው እሑድ – የሆሳዕና በዓል appeared first on Zehabesha Amharic.

ታሪክ ይፋረደናል!

$
0
0

አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ
ቅዳሜ፤ መጋቢት ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓመተ ምህረት – 04/04/2015

እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ገዥ ቡድን በእብሪት ተወጥሮ ሀገራችንን ሲጫወትባት፤ “እኛ የኔ ድርጅት! የለም የኔ ድርጅት!” “እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ! የለም እኔ ልምራ እናንተ ተከተሉኝ!” “እኔ እበልጣለሁ! የለም እኔ እበልጣለሁ!” እየተባባልን፤ በሌለ ሥልጣን ሽሚያ ልባችን ተወጥሮ፤ ዛሬ ትናንት፤ ነገ ደግሞ ዛሬ እየሆነ ዓመታትን አስቆጠርን። ለምን? የሀገር ጉዳይ እያንዳንዳችንን የሀገሯ ተወላጆች እኩል አይሸነቅጠንም? ምን እንስኪሆን ድረስ ነው የምንጠብቀው? በየድረገጹ የማነበው፣ በየፓልቶኩ ክፍል የማዳምጠው፣ በየሬዲዮኖች የሚተላለፈው፤ በአንድነት እስካልተነሳን ድረስ፤ ትግሉ አይሳካም! የነገውም ሂደት አያስተማምንም! ነው። ለምን በዚህ አውቶቡስ ሁላችን አንሳፈርም? ኧረ ተው! ታሪክ ይፋረደናል!
Tensaye
አሜሪካ ፈልጌውና ጓጉቼለት የመጣሁበት ሀገር አይደለም። የዴሞክራሲ ሥርዓቱ ናፍቆኝም አይደለም የመጣሁት። የተሰማራሁበት ትግል ሂደት ተሰናክሎ፣ ቀኑ ጨልሞብኝ፣ በሰደት ከነበርኩበት የኑሮ ዝግመት ማምለጫ ስለሆነልኝ ነበር። መጥቼ ደግሞ በአድናቆት ተውጬ ማንነቴን ረስቼ አልቧረቅሁበትም። በርግጥ ያገኘሁትን ዕድል በመጠቀም ኑሮዬን ገፍቻለሁ። ይኼው ከመጣሁ ሰላሳ ዓመታት አልፈዉኛል። የአሜሪካን የዴሞክራሲ ሥርዓት አካሄድ ስገነዘብ፤ ያላቸውን ድክመት ደግሞ በዚያው ጎን ለጎን አጢኛለሁ። ለሀገሬ ከማደርገው መሯሯጥ ጋር፤ በአሜሪካ ሀገር ያለሁበትን ሀገር የፖለቲካ ሀቅ ለማስተካከል፤ እንዲህ መሆን ሲገባው ለምን አልሆነም? እያልኩ ከማማረር አልቦዘንኩም። አሜሪካኖች የራሳቸውን የዴሞክራሲ አካሄድ “ፍጹም ወደ መሆን እያዘገምን ነው።” ብለው ነው የሚያምኑት። “ፍጹም ነው!” አይሉም። በምችለውና ባጋጠመኝ መንገድ ሁሉ፤ ይኼን ፍጹም ወደመሆን የሚጓዘውን ሂደታቸውን፤ በንቃት በመሳተፍ እየረዳሁ ነው።

አሁን በሀገራችን የኑሮ ሀቅ፤ የወሃ ጥማት፣ የምግብ ማጣት፣ በሰላም የገበያ አገልግሎት፣ የመንገድ አለመሠራት፣ የትምህርትና ሕክምና አለመስፋፋት፣ የመናገርና የመጻፍ፣ የመሰባሰብና ተቃውሞን የመግለጽ፣ የአድልዕና ሙስና መንገሥ፤ መሠረታዊ የኅብረተሰቡ ጥያቄዎች፤ የፖለቲካውን መድረክ ማዕከላዊ ቦታ አልያዙም። ለዚህ ተጠያቂ የሆነውን መንግሥት በመወንጀል ባንድነት የመነሳት ግዴታችንን በውል አልጨበጥነውም። በርግጥ ከአሜሪካ ጋር የኛን ሀገርና የኛን ሁኔታ እያወዳደርኩ አይደለም። አዎ እንደነሱ በሀብት የበለጸግን አይደለንም። ግን ይኼ ላለንበት ሁኔታ ወሳኝነት የለውም።

የሀብት ጉዳይ ከተነሳ፤ በሀብት ያልበለጸግን መሆናችን አዲስ አይደለም። ከሕዝቡ ጥቅምና ከሀገሪቱ ዕድገት ይልቅ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ቅድሚያ የሠጡ ገዥዎች በነበሩበት ዘመን፤ አጠቃላይ የሀገሪቱን እውነታ ፈትሸው፤ ለረጅሙ የወደፊት ብልጽግና በማቀድ እርምጃ ስላልወሰዱ፤ ድኅነቱ አብሮን ኖሯል። እዚህ ላይ አንዳንዶቹ ያደረጉትን የልብ አስተዋፅዖ በምንም መንገድ ልስት አልችልም። ከነዚህ መካከል ባገኘሁት ዕድል ሁሉ፤ መጽሐፍትን በማገላበጥ ለማወቅ ጥረት ከማደርጋቸው መሪዎች መካከል፤ አፄ ዘርዓ ያዕቆብንና አፄ ቴዎድሮስን እጠቅሳለሁ። በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ምን ነበር? ያሁኑስ ዘመን ከዚያ ዘመን በምን ይለያል?

ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመን የአሁኑ ዘመን የሚለየው፤ ያኔ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ትልቅ ክብር የነበራቸው ሲሆን፤ አፈሩ እንኳ ሳይቀር የተከበረበት ዘመን ነበር። አፄ ቴዎድሮስ፤ ከሕዝቡ በመጠቀ ደረጃ፤ ከራሳቸው የወቅቱ ክብር ይልቅ፤ የሀገራቸው እድገትና በአካባቢያቸው የተኮለኮሉት የውጭ ጠላቶች እንቅስቃሴ፤ የዕለት ተዕለት ጭንቀታቸው ነበር። የተበታተነች ኢትዮጵያን ለመመለስና የቀድሞ ቦታዋን ለማስያዝ የሕይወታቸው ዋና ማዕከላዊ ትርጉም አድርገው ጣሩ። ለራሳቸው የስም ማስጠሪያ ግንብ ወይንም ቤተክርስትያን ከማሠራት ይልቅ፤ ለሀገራቸው መጠበቂያ የጦር መሣሪያ እንዲያበጁላቸው ነበር የውጭ ሀገር ሰዎችን የጠየቋቸው። ምንም እንኳ አሁን ምሁር ነን ባዮች፤ የአፄ ቴዎድሮስ ጠላቶች በውጭም ሆነ በውስጥ የነበሩት የጻፉትንና ያሉትን ተሸክመው ቢይጥላሏቸውም፤ እኒህ መሪ በተወለዱበት ዘመንና በቦታው የነበራቸውን የፖለቲካ ድርሻ አጢነው ቢመረምሩ፤ ከማንም መሪ የበለጠ ሊያደንቋቸው በተገባ ነበር።

የበዕደ ማርያም መምህሬ ዶክተር ገብሩ አስራት ለቀረበላቸው ጥያቄ የሠጡት መልስ እጅግ በጣም አርክቶኛል። ከነበሩት መሪዎች ሁሉ አንደኛ አድርገው የሚያደንቁትን ቃለ መጠይቅ አቅራቢዋ እንድትነግራቸው ስትጠይቃቸው፤ ያለምንም ማመናታት “ፄ ቴዎድሮስ ናቸው!” በማለት በኩራት አስቀምጠውላታል። ልክ ድሮ ሲያስተምሩኝ እንዳደነቅኋቸው ሁሉ፤ አሁንም መምሬ ሆነው አገኘኋቸው። ከመሬት ተነስተው፤ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ሀገራዊ ሕልውና፤ የመሠረቱን ደንጋይ ያስቀመጡ አፄ ቴዎድሮስ ናቸው። ከግለሰብ ማንነታቸው ይልቅ፤ የሀገራቸው መሪነታቸው ነበር ልባቸውን የሞላው። ያኔ በሕዝቡም መካከል፤ ከግለሰብ ምንነታችን ይልቅ የስብስብ ማንነታችን ማዕከላዊ ቦታውን የያዘ ነበር። ዛሬ በኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያዊነት አፈር የተንከባለለበት፤ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ኢትዮጵያዊ አለመሆን የተወደደበት፣ ከኢትዮጵያዊያን ስም ይልቅ የውጪ ሀገር ስሞች የተመረጡበት፣ ከራሳችን ቋንቋ ይልቅ የውጪ ቋንቋ፣ ከራሳችን እምነት ይልቅ የውጪ እምነት፣ ከራሳችን ምግብ ይልቅ የውጪ፤ ባጠቃላይም ከራሳችን ማንነት ይልቅ የውጪውን መቅዳትና መስሎ መገኘት የጎላበት ክስተት፤ ሀቅ ሆኖ ይታያል። ለምን? ዋናውን ማዕከላዊ ቦታ ይዞ በተጠያቂነት የቆመው ያለው ገዥ ቡድን ነው። ዋና ሥራዬ ብሎ የያዘው፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው። ይኼንንም በትውልድ ማንነት ተክቶታል። እናም ከራሱ የገማን አሣ . . . እንደሚባለው ቆርጦ መጣል ያለበት ገዥው ክፍል ነው።

አሁንም ያኔም ኢትዮጵያዊነት፤ ኢትዮጵያዊነት ነው። አሁን ግንዛቤያችን ፈሩን ለቋል። የብሔር ብሔረሰብ ጥያቄ የፖለቲካውን ማኅደር አጥለቅልቆታል። ምኑም ሆነ ምኑ የሀገራችን ሀቅ፤ ከዚህና ከዚህ ብቻ እንዲታይ ተደርጓል። ይህ ደግሞ በገዥው ክፍል ብቻ ሳይሆን በታጋዩም ወገን ያለ እውነታ ነው። በዚህ ተለጉመን፤ መሠረታዊ የመኖርና ያለመኖር የሕልውና አምዶች፤ ቦታ ተነፍገዋል። የፍትኅ መጓደል፣ የትምህርት ጥራትና ዕድገት ወደ ታች ማሽቆልቆል፣ የሕክምና አለመሟላት፣ የምግብ እጥረትና ረሃብን የመቋቋም ዕቅዶች አለመኖር፣ የሴቶችን እኩልነት አለመቀበልና ተሳትፏቸውን አለማሳደግ፣ አድልዕና ሙስና፤ እነዚህ መሠረታዊ የሕልውና ጥያቄ ናቸው። መስመሩ የተዘጋበት የውሃ ፈሰስ፤ ዙሪያውን ይዳስሳል። የተገደበበትን መዝጊያ መጋፋቱን፤ በጎን መፋሰሻ ከመፈለግ ጋር በእኩል ይዳስሳል። ተገድቤያለሁ ብሎ ተስፋ በመቁረጥ አይረጋም። ከግድቡ ጋር ብቻም አይታገልም። ዙሪያውን በሙሉ ነው ጥረት የሚያደርገው። በግድቡ አናት፣ በግድቡ ሥር፣ ከታቆረበት ዙሪያ ይውዘገዘጋል። የታፈነ በመሆኑ ቦርቅቆ ለመውጣት ይፍጨረጨራል።

ወገኖቻችን በየበረሃው መንገላታታቸው፣ እህቶቻችን በአረብ ሀገሮች መጎሳቆላቸው፣ በገዛ ሀገራቸው ወገኖቻችን መፈናቀላቸው፣ በገዛ ሀገራቸው ወንድምና እህቶቻችን በረሃብ ተጠምደው ለማኝና ሀገሪቱ በሞላ የውጭ ሀገር ምጽዋተኛ መሆናቸው፤ አእምሯችንን በማስጨነቅ የፖለቲካ ምኅዳሩን ሊያናጉት ይገባል። በርግጥ በአሁኑ ሰዓት የፖለቲካ ውይይቱ ተጧጡፏል። ይህ በምን ዓይነት ውጥረት ላይ መሆናችንን አመልካች ነው። ነገር ግን መፍትሔ አፈላለጉ ላይ ለየብቻ እየሮጥን ነው። ለየብቻ ሮጦ የግብ መሰመሩ ላይ ለየብቻ ነው የሚደረሰው። ታዲያ ምን ዋጋ አለው? ግቡ የማንም ግለሰብ ወይንም ቡድን የግል መኖሪያ አይደለም። የሁላችንም ነው። ባንድ ላይ መሯሯጥ አለብን። የተጎተቱ ካሉ፤ አብረን መሳብና መሳሳብ እንጂ፤ እኔ ቀድሜ ሄጄ እሸለማለሁ ወይንም ሌሎችን እጎትታለሁ የሚባልበት አይደለም። አብረን ስንነሳ፤ ቀዳሚ ሆነው የቆሙት ሲመሩ፤ የተጎተቱት ደግሞ ሲከተሉ፤ ባንድነት ከግባችን እንደርሳለን። ታሪክ ደግሞ ከኛ ጋር አብሮ ይኖራል። ተወቃሽ አያደርገንም። ከታሪክ ተወቃሽነት መዳን አለብን። በሕይወት እስካለን ድረስ፤ ሆዳችን መሙላቱን ሳይሆን፤ በሕይወት የኖርንበትን ወቅት ትርጉም መሥጠቱ ላይ ማተኮር አለብን። ቆመን እንቆጠር። አብረን እንሰለፍ። eske.meche@yahoo.com

The post ታሪክ ይፋረደናል! appeared first on Zehabesha Amharic.

“ያሳደግኹት ውሻ አሳጣኝ መድረሻ” ፥ የአቶ ገብሩ ዐሥራት እና ሊነበብ የሚገባው አነጋጋሪ መጽሐፋቸው

$
0
0

(ኄኖክ የማነ)
ከአቶ ገብሩ ሕይወት ጋራ የሚመሳሰሉ ታሪኮችን ከገሃዱ ዓለም ይልቅ በልብ ወለዶች ወይም በሕይወት ትርጉም ላይ በሚያተኩሩ የፍልስፍና መጽሐፍት ውስጥ በቀላሉ ማግኘት ሳይቀል አይቀርም። የሕይወትን ትርጉም የተለያዩ ጸሐፍት አያሌ መመዘኛዎችን በመጠቀም ለማብራራት ይሞክራሉ። ከነዚህ አከራካሪ መመዘኛዎች አንዱ ሰዎች በኋለኛው የዕድሜ ዘመናቸው ላይ ኾነው ያሳለፉትን የሕይወት ዘመን የኋልዮሽ በመመልከት “ሕይወቴ የተሳካ ነበረ?” ለሚለው ጥያቄ በሚሰጡት መልስ ላይ ይመሠረታል። በዚህ ውጤት አግናኝ መመዘኛ ከተለካ የአቶ ገብሩ ሕይወት “እዚህ ግባ” የሚባል ትርጉም አልነበረውም ብሎ መከራከር ይቻላል። ለዚህ አስተያየት እንደ ምክንያት ሊቀርብ የሚችለው ነገር ደግሞ የቀድሞው የሕወሓት ባለሥልጣን ከዐሥራዎቹ ዕድሜያቸው ጀምሮ መላ ሕይወታቸውን የገበሩለት የትጥቅ ትግልም ኾነ የፖለቲካ ዓላማ በ64 ዓመታቸው በተሻለ ብስለት እና ስክነት ሲገመግሙት “ኢትዮጵያ በፍጥነት ሊቀየር የሚገባው አሳሳቢ ኹኔታ ላይ ትገኛለች።” የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው ነው።
gebru-book
አቶ ገብሩ በቅርቡ “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፋቸው መግቢያ ላይ የትግልና የፖለቲካ ሕይወታቸውን ትርጉም የሚመለከቱ ከባድ ጥያቄዎች ያነሳሉ፤ “ያለፈውን ጊዜህን ይኼን ያህል ከተቸህ ጉዞህ ኹሉ ከንቱ ነበረ ወይ?፥ ባደረግኸውስ ትጸጸታለህ ወይ?” ፥ እና “ለመብትና ለነጻነት ሲሉ በሕወሓት/ኢሕአዴግ ተደራጅተው የተፋለሙትን፥ አካላቸውን እና ሕይወታቸውን ያጡትን ወገኖች አስተዋጽዖ መና አስቀረኸው ወይ?” ሊባሉ እንደሚችሉ ይጠቅሳሉ። ጸሐፊው ለነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡት መልስ ለሦስት ዐሠርት ዓመታት ከልቡ አምኖበት ብዙ መስዋዕትነት የከፈለለት ዓላማ ያመጣውን ውጤት አጥብቆ የሚቃወም ሰው ሊፈጠርበት የሚችለውን አስጨናቂ የተቃርኖ ስሜት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። ይኼም ብቻ አይደለም፤ መልሱ በመጽሐፉ ውስጥ የሚስተዋለውን የአቶ ገብሩን በፖለቲካው ዓለም ብርቅ የኾነውን ቀጥተኝነትም ያንጸባርቃል። “በኔ ዕምነት በሕወሓት/ኢሕአዴግ የተሰለፍነውም ኾነ በሌሎች ድርጅቶች ተሰልፈው ደርግን የተፋለሙት ታጋዮች ኹሉ ታሪክ በአዎንታ መዝግቧቸዋል። እዚህ ላይ መታየት ያለበት እነዚህ ታጋዮች ያስገኙት ውጤት ሳይኾን ያነገቡት አምባገነንነትን ገርስሶ ፍትሐዊ ሥርዐትን የማስፈን ዓላማቸው ነው። ለዚህ ክቡር ዓላማ ማንኛውንም መስዋዕትነት የከፈለ ዜጋ ክቡር በመኾኑም በአገራችን ታሪክ ሊዘከር ይገባዋል።” ይላሉ አቶ ገብሩ ምላሻቸውን ሲሰጡ። በማስከተልም “ ይኽ ማለት ግን በዚህ የትግል ጉዞ የነበረው የፖለቲካ አካሄድ ቢያንስ ከዴሞክራሲ እና ከአገር ጥቅም አንጻር የነበረበትን መሠረታዊ ጉድለት መመርመር የለበትም ማለት ኣይደለም። የዕውነተኛ የፖለቲካ መጽሐፍ ፋይዳም ያሁኑንም ይኹን ያለፈውን ታሪክ ያለምንም ፍርሐት እና ወገናዊነት በነጻነት እንዲታወቅ ማድረግ ነው። ስለኾነም በዚህ መጽሐፍ ለኅሊናዬ ትክክል የመሰለኝን ኹሉ ለማስፈር በመሞከሬም ሰማዕታቱ የተሰዉለትን ዓላማ ለማክበር ሞክሬአለሁ” በማለት አቋማቸውን ይገልጻሉ።
ይህ የአቶ ገብሩ አመለካከት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ካሉ የተለያዮ አቋሞች አንጻር ሲታይ አወዛጋቢ ሊኾን ቢችልም፤ የታገሉለት ዓላማ አቅጣጫውን ስቶ አገሪቷን ከባድ ችግር ውስጥ እንደከተታት ቢያምኑም ቢያንስ በአንድ መመዘኛ ሕይወታቸው ጉልህ ትርጉም እንዳለው መከራከር ይቻላል። የቀድሞው ታጋይ እና ባለሥልጣን ዘግይተውም ቢኾን (በተወሰነ መልኩ ሳይፈልጉም ቢኾን) ራሳቸውን በጥልቀት መርምረው፥ ስህተት ነው የሚሉትን ተቀብለው፥ እንደ ጣዖት ይመለክ የነበረውን የቀድሞ ድርጅታቸውን በአደባባይ ለመተቸት እና ንስሐ ለመግባት፤ እንዲሁም ለሌላ ለውጥ ለመታገል እና ስህተታቸውን ለማረም ዕድል አግኝተዋል። ብዙ ነገር ቢያጡም ትልቅ ዋጋ ያለው አንድ ነገር አግኝተዋል ማለት ይቻላል።
Gebru Asrat
በዚህ ኹሉ መካከል ግን አንድ በማሻማ ኹኔታ ግልጽ የኾነ ነገር አለ፤ በአቶ ገብሩ ሕይወት ውስጥ የሚስተዋለው መራር የፖለቲካ እና የታሪክ ምጸት። እርሳቸው እንደሚያምኑት አምባገነናዊ ሥርዐትን እና ኢፍትሐዊነት ለማስወገድ የተደረገው መራር ትግል ያስከተለው ነገር ቢኖር- በደምሳሳው ሲታይ- በቅርጽ የተለየ በይዘቱ ግን አምባገነናዊ እና ኢፍትሐዊ የኾነ ሥርዐት “ማንገስ” ነው። ይኽ እጅግ መራር ምጸት ነው።
በመጽሐፋቸው ምረቃ ላይ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ አንድ አዳራሽ ውስጥ ከመገናኘታችን በፊት አቶ ገብሩን የማውቃቸው እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በመገናኛ ብዙኃን ነበር። ስለ እርሳቸው የነበረኝ አመለካከት ደግሞ ከሕወሓት ክፍፍል በኋላ አሸናፊው ወገን ስለ “አንጃው” መሪዎች በሚያሰራጫቸው መረጃዎች ተጽዕኖ ሥር የወደቀ ነበር። “ በድሮ በሬ ለማረስ የሚሞክሩ ተቸካይ ማርክሲስት ሌኒኒስት”፥ እንዲሁም ጽንፈኛ የትግራይ ብሔረተኛ እንደኾኑ አምን ነበር። ወደ ምረቃ አዳራሹ የሄድኹት በበርካታ ንዑስ ርዕሶች ከተከፋፈለው የመጽሐፉ ማውጫ ወደ ዐራት የሚጠጉ ትኩረቴን የሳቡ ጉዳዮችን ብቻ በዋዜማው አንብቤ ነበር። ዐራቱ ጉዳዮች የተደበላለቀ ስሜት የፈጠሩብኝ ቢኾንም፥ የመጽሐፉ ድርጁ ይዘት መጽሐፉን ሙሉ በሙሉ ለማንበብ ከፍተኛ ፍላጎት ፈጥሮብኝ ነበር። በምረቃው ላይ ለተነሱት ጥያቄዎች ደራሲው መልስ የሰጡበት መንገድ ደግሞ የማንበብ ፍላጎቴን ብቻ ሳይኾን ጸሐፊውን የማግኘት ፍላጎቴን አነሳሳው። በቀድሞው የ”ኢትኦጵ” ጋዜጠኛ አርዐያ ተስፋማርያም በኩል አንድ ቅዳሜ ተገናኝተን ለዐራት ሰዓታት ያህል ጥያቄዎቼን ሳዥጎደጉድባቸው ቆየኹ። ጥያቄዎቼን በተለመደው ‘ርጋታቸው በተቻላቸው ኹሉ ቀጥተኛ እና ግልጽ በኾነ መንገድ በትዕግስት መለሱልኝ። ይከተሉት የነበረው ርዕዮተ ዓለም ስህተት መኾኑን ለመረዳት ለምን የሕወሓት መከፋፈል አስፈላጊ እንደ ነበር፥ የአቶ መለስ አንዳንድ አስገራሚ ግለሰባዊ ባህርያት፥ ከሕወሓት ከተሰናበቱ በኋላ ስለደረሰባቸው ችግር እና ስለ ሌሎችም መጽሐፋቸው ውስጥ ያልተካተቱ ብዙ አስገራሚ ነገሮች አጫውተውኛል። አቶ ገብሩ እጅግ ትሑትም ናቸው። ተቋማዊ፥ ቤተሰባዊ፥ እና ግለሰባዊ ንቅዘት በተንሰራፋበት አገዛዝ ውስጥ በከፍተኛ ባለሥልጣንነት ቆይተው በሙስና ጨርሶ አለመታማታቸውን ሳስብ ደግሞ መጽሐፋቸውን የመገምገም ሥራዬን ወገናዊነት እንዳይጫነው መስጋቴ አልቀረም።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ በቀድሞ ባለሥልጣናት ከተጻፉ የፖለቲካ ግለታሪክ እና የትውስታ መጻሕፍት “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” ከአገራዊ ፋይዳ፥ ከግልጽነት እና ከተጠያቂነት፥ ከስፋት እና ከጥልቀት አንጻር ሲታይ ከሁሉም ከፍ ብሎ በሚገኝ ማማ ላይ ለብቻው ተቀምጧል ቢባል ማጋነን አይመስለኝም።በነዚህ መስፈርት በማያጠራጥር ኹኔታ ከወለል በታች የሚገኘው (አሁንም ሥልጣን ላይ እንዳሉ የሚያስቡ በሚመስሉት) በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የተደረሰው “ትግላችን” የተባለው መጽሐፍ ነው። በግል፥ በውስን፥ እና በጠባብ አጀንዳዎች ላይ የሚሽከረከረው የአቶ ስየ አብርሃ “ነጻነት እና ዳኝነት በኢትዮጵያ” ፥ የግብር ይውጣ በሚመስል ኹኔታ ይቅርታ ለመጠየቅ የሚዳዳው እና የደርግን ሥርዐት ወደ መከላከል የሚያዘነብል የሚመስለው የሻምበል ፍቅረሥላሴ “እኛና አብዮቱ” ከፍተኛ ትኩረት እና ተቀባይነት ያገኘው ነገር ግን “ይቅርታ” የሚባል ቃል የማይወጣው የአቶ ኤርምያስ ለገሠ “የመለስ ትሩፋቶች” ፥ ጠንከር ያለ የትንተና ችግር የሚታይበት እና የሕወሓትን የሽምቅ ውጊያ ታሪክ በማንቆለጳጰስ የተጠመደው የአቶ አስገደ ገብረሥላሴ “ጋሕዲ” እና የመሳሰሉት የየራሳቸው ሊጠቀሱላቸው የሚችሉ ጠንካራ ጎኖች እንዳሏቸው ባይካድም (ይኽ ምልከታ“ትግላችን” የሚመለከት አይመስለኝም) አቶ ገብሩ በመጽሐፋቸው በተደጋጋሚ እና በየአጋጣሚው አቋማቸውን እየፈተሹ ስህተት ኾኖ ያገኙትን “ ስህተት ነው” ማለታቸው፥ አስፈላጊ ሲኾንም ኃላፊነት መውሰዳቸው፤ በተጨማሪም ትልቁን አገራዊ ሥዕል በመመልከት ይበጃል የሚሉትን አቅጣጫ በጥናት ላይ ተመሥርተው ለማቅረብ መሞከራቸው መጽሐፋቸውን ልዩ ያደርገዋል።
“ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ”ም ቢኾን ግን እንከን አልባ አይደለም፤ በጭራሽ። እንደውም ያደነቅኹትን ግልጽነታቸውን እና ሃቀኝነታቸውን እስከ መጠራጠር ያደረሱኝ በመጽሐፉ ውስጥ ኾን ተብለው የተድበሰበሱ የሚመስሉ ፥ ፈጽሞ ያልተስተዋሉ እና ያልተወሱ አንገብጋቢ ጉዳዮችን ታዝቤአለሁ። ታዲያ አቶ ገብሩ ዐሥራትን ተጣድፌ አወድሻቸው ይኾን?

አቶ ገብሩ የድርሰታቸውን ጽሕፈተ-ምክንያት በሁለት ዐበይት ዓላማዎች ዙሪያ እንደሚያጠነጥን ያወሳሉ። አንደኛው “በሕይወት እያለን የምናውቀውን ታሪክ የሕወሓት/ኢሕአዴግ አመራር እያዛባው እና እየከለሰው ለአገዛዙ እንደሚመች የሚያቀርበውን ታሪክ በማስተካከል ረገድ የበኩሌን አስተዋጽዖ ለማድረግ” ሲኾን ኹለተኛው ደግሞ “ዕውነትን ፍለጋ ለሚሯሯጡት ይኼን ዐይነት መጽሐፍ ማዘጋጀቱ እንደ መነሻ እና እንደ አማራጭ ሊጠቅማቸው ይችላል” በሚል ዕምነት ነው። የመጽሐፉ ስኬት ከነዚህ ዓላማዎች አንጻር ከተለካ አቶ ገብሩ እጅግ ስኬታማ ኾነዋል ማለት ይቻላል። በዚህ ዳሰሳ “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ”ን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጭብጦች አንጻር ለመቃኘት እሞክራለሁ።

1. ቅርጽ፥ አቀራረብ፥ መጠነ-ቅኝት (Scope)፥ እና ጥልቀት

እነዚህ ነጥቦች ከመጽሐፉ ይዘት ጋራ ቀጥተኛ ግንኙነት ባይኖራቸውም፤ ይዘቱ ሊፈጥረው በሚችለው ተጽዕኖ ላይ የማይናቅ ሚና ሊኖራቸው ይችላል። ከዚህ አንጻር ሲታይ መጽሐፉ የተለያዩ የአጻጻፍ ዘርፎች (Genres) ባህርያትን ቀላቅሎ የያዘ መኾኑ ደራሲው የሚፈልጉትን መልዕክት በጥሩ ኹኔታ ለማስተላለፍ ‘ረድቷቸዋል፤ ኾኖም አንዳንድ እንከኖችም ይታዩበታል።

2. ማርክሲዝም- ሌኒኒዝም እና ሕወሓት

አቶ ገብሩ በዝርዝር እና በተደጋጋሚ ከሚያነሷቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ የማሌ ንድፈ-ኃሳብ እና በሕወሓት፥ አልፎም በኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ የተጫወተው ወሳኝ ሚና ነው። በመጽሐፉ ውስጥ ከሠፈሩት ነገሮች ሰቅዘው ከያዙኝ (ካሳዘኑኝ እና ካሳቁኝ) መካከል ይገኙበታል።

3. አቶ መለስ ዜናዊ
“ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” ውስጥ የሚገኙት አቶ መለስ ዜናዊ ፍጹም አስደናቂ ከመኾናቸው የተነሳ መጽሐፉን ለመክደን አዳጋች ያደርጉታል። አቶ መለስ ኒኮሎ ማኪያቬሊን ራሱን በመቃብሩ ውስጥ በኩራት ደረት ሊያስነፉ የሚችሉ፥ ከማኪያቬሊም በላይ ማኪያቬላዊ ናቸው። አቶ ገብሩም አንድ ቦታ ላይ አቶ መለስን በቀጥታ ሳይኾን ተግባራቸውን “ማኪያቬላዊ” በማለት ይገልጹታል። ከአቶ ገብሩ መጽሐፍ ለመረዳት እንደሚቻለው ሟች የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ ወጥ አቋም ያሳያሉ፤ ለሥልጣናቸው አደጋ ሊፈጥር እንደሚችል እያወቁም ጭምር። በአዕምሮ ብቃታቸው እና በንድፈ ኃሳብ ትንተና ችሎታቸው ደግሞ በሕወሓት ውስጥ እምብዛም የሚገዳደር ተፎካካሪ የነበራቸው አይመስሉም።

4. ሉዓላዊነት እና ማኅበረ – ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ

የ“ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” አንኳር ድክመቶች በአብዛኛው ሉዓላዊነት እና ማኅበረ – ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ ላይ ያጠነጥናሉ። ለአቶ ገብሩ “ሉዓላዊነት ማለት በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል በቻ ያለ የድንበር ጥያቄ ነው እንዴ?” የሚል መጠይቅ የሚያጭሩ ከመጽሐፉ ሽፋን ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች ማንሳት ይቻላል። ውስጣዊ ሉዓላዊነት እና በሌሎች የኢትዮጵያ ጠረፎች ያሉ የድንበር ውዝግቦች የአቶ ገብሩን ትኩረት ብዙም የሳቡ አይመስሉም። ስለ ኢትዮጵያ የወደፊት አቅጣጫ በሚናገሩበት የመጽሐፉ የመጨረሻ ክፍል ደግሞ የማኅበረ – ኢኮኖሚያዊ ፍትሕን ወሳኝነት አስረግጠው ቢያብራሩም ከጉዳዩ ጋራ የተቆላለፈ እና ለማኅበረ – ኢኮኖሚያዊ ፍትሕ ግዙፍ እንቅፋት የኾነን ዐብይ ጉዳይ ቀደም ባሉት የመጽሐፉ ገጾች እንደነገሩ አከክ-አከክ አድርገው ያልፉታል።

Source: 7killo Magazine

The post “ያሳደግኹት ውሻ አሳጣኝ መድረሻ” ፥ የአቶ ገብሩ ዐሥራት እና ሊነበብ የሚገባው አነጋጋሪ መጽሐፋቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>