Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

የአራዳ ልጅ ብሔር? –‎ሁኔ አቢሲኒያ‬

$
0
0

የአራዳ ልጅ ብሔር? ሲባል ምን እንደሚል ታውቃላችሁ? ”አልቦ ብሔር ” ነው። አልቦ ብሔር ማለት ብሔር የሌለኝ ግን ኢትዮዽያዊ ነኝ ሲላችሁ ነው። በ1960 ዎቹ መጨረሻ ላይ የተነሳው እና በ ¨ት ሃ ቶች¨ ታሽቶ በ 1987 ዓም ¨እስከ መገንጠል¨ የሚል ቃል አክሎ፤ በ ህገ መንግስቱ ላይ ጨምሮ ፤አስጨብጭቦ፣ ሰው በቋንቋ መከፋፈልን (¨ከ¨ ሲላላ) እና መከፋፈልን (¨ከ¨ ሲጠብቅ) በሃገሪቱ ላይ የነገሰው አስተሳሰብ በትክክል ግብአተ መሬቱ ሊከናወን ሰዓታትን መቁጠር ግድ ይለዋል። ይህ የሚሆነው በ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው።

የ ዘር ፖለቲካ ለ አለማችን አዲስ ክስተት አይደለም።የ አምባገነኖች መሸሸጊያ ጉረኖ ዘረኝነት እና የዘር መርዝ መንዛት ነው። ሂትለር የጦርነት ጥማቱን ለማርካት የ ጀርመንን ህዝብ የተለየ ህዝብ አድርጎ ማቅረብ ነበረበት። ¨እናንተ የ ጀርመን ህዝቦች የ ‘አርያን’ዘሮች ¨ እያለ ይሸነግል ነበር። መለስ ዜናዊም እንኳን ከእናንተ ተፈጠርኩኝ በማለት የትግራይ ህዝብ የተለየ ምርጥ ዘር ለማስመሰል ሲናገር ተደምጧል፡፡ ሰዎች በባህሪያችን ብልህ የመሆናችንን ያህል የመሆኑን ጅልነትም አያጣንም።ሰው እኮ በዛፍ የማመን፣ አምላክ ነው የማለት አስቂኝ ሞራል ያለው ፍጡር ነው።¨አንተ ዘርህ የ እገሌ ነው፤ታላቅ ነህ፤ ያንተ ዘር እገሌ ድሮ እንዲህ ያደረገ፤ እገሌ የተባለው መሪህ ካንተ መንደር የተወለድ¨ ሲባል ልቡ ደንገጥ የሚል ይጠፋል ብለን አናስብ።

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) “ሁሉም የሰው ልጆች ዝርያቸው አንድ ሲሆን ሁሉም ከአንድ የዘር ግንድ የመጡ ናቸው” ብሏል።—የዘርና የዘር ጥላቻ አዋጅ፣ 1978

ሼክስፒር የተባለው ደራሲ ደግሞ ምን አለ መሰላችሁ ” ትዕቢት ምቀኝነትና ዘረኝነት ከእውቀት ማነስ የሚመጡ መርዘኛ አመል ናቸው ።
እናም በመጨረሻ እኔ የአራዳ ልጅ ነኝ አልቦ ብሔር
‪#‎ሁኔ_አቢሲኒያ‬

Comment

The post የአራዳ ልጅ ብሔር? – ‎ሁኔ አቢሲኒያ‬ appeared first on Zehabesha Amharic.


የአንዳርጋቸውን የትግል መንገድ ሚሊዮኖች ይከተላሉ። –ሳሙኤል አሊ (ከኖርዌይ)

$
0
0

samuelወደ በረሃ ወርዶ የሰራውን ስራ በፎቶዎቹ  እያየው ነው እነዚህን ፎቶዎችን ሳይ አይኔ በእንባ ይሞላሉ ልቤ በእልህ ይቀጣጠላል የተዘበራረቀ ስሜት ወደ ውስጤ ሲገባ ይታወቀኛል የደስታ ስሜት፣ የእልህ ስሜት፣ የቆራጥነት ስሜት፣ የጽናት ስሜት፣ የእውነተኝነት ስሜት ብቻ ምን ልበላቹህ ተደበላልቀው ውስጤን ይወጥሩታል እናም ፎቶዎቹን ሳያቸው የሚያወሩኝ ያህል ደስታን ይሰጡኛል

አንድ ቀን ታድያ አንድ የጎረቤት አገር ሰው ሁል ጌዜ በተደጋጋሚ ጌዜ  የዚህን ሰውዬ ፎቶዎች  ተመስጠህ ታየዋለህ ለምንድነው አለኝ

የኔም መልስ አይ ደስ ስለሚለኝ ነው አልኩት። እርሱም መልሶ ጥያቄወችን ይጠይቀኝ ጀመር አባትህ ነው? ዘመድህ ነው? ገበሬ ነው? ወዛደር ነው? ወታደር ነው? ምንድ ነው? ንገረኝ ደጋግመህ  ስታየው አባትህ ከሆነ  ብዬ ነው አልያም ዘመድህ  ደግሞ ይሄኘው   ፎቶ ገበሬ ደግሜ  ያኛው  ወዛደር ይሄኛው ደግሞ ወታደር ይመስላል ማን ነው ንገረኝ አለኝ እኔም ስመልስለት ልክ ብለሃል  እንደአባቴ የማየው አባት ያውም የኔ ብቻ ሳይሆን ነጻነት ለተጠሙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አባት ነው።  ከገበሬም ገበሬ ነው ስለገበሬው ነጻነት የሚታገል የገበሬው ወዳጅ ነው። ከወዛደርም ወዛደር ነው ድንጋይ እየተሸከመ እንጨት እየፈለጠ ወዛደሩን ለማሳደግ የሚተጋ የፍቅር አባት ነው። ከወታደርም ወታደር ነው ወዳጅን ሳይሆን ጠላትን በህዝብ አናት ላይ ቁጭ ብሎ በብረት ረግጦ የነገሰና የሚገዛን አገር አፍራሽ ለመገርሰስ ወታደር ሆኖ ለአገሩ ነጻነት ዘብ የቆመ  ብርቅዬና ውድ የኢትዮጵያ ወታደር ነው  ብዬ ገለጽኩለት። ስሙም አንዳርጋቸው ጽጌ  ይባላል  ስምን መለአክ ያወጣዋል ይባላል እውነት ነው ስምና ተግባርን አዋህዶ  የያዘ  የዘመኑ የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጅ ነው።

አንድ አርጋቸው ማለት የተራራቀን ማቀራረብ፣ የተለያየን ማገናኘት፣ ያልጸናን ማጽናት፣ የሚለውን ትርጉም ሲሰጠን። ጽጌ ማለት ደግሞ አበባ ማለት ነው። ሲተረጉም  የአንድነት አበባ እንደውም  የትም የማይበቅለው ኢትዮ ጵያዊ አበባ የእግዛአብሔር ጸጋ የሚያበቅለው አደይ አበባችን ነው።

ታድያ ይህንን የኢትዮጵያ የሰላም ባንዲራ፣ የነጻነት መዝሙር፣ የፍቅር ቅኔ፣ የእውነት ታጋይ፣ የሆነውን ድንቅዬ መከታችንን  ከአመት በፊት የመኖች ሚልዮን ዶላሮችን ተቀብለው ለአገር አጥፊው እና ለአረመኔው ወያኔ አሳልፋ የሰጠችው አንዳርጋቸው ሰለ ኢትዮጵያ ነጻነት የታገለ  ታጋያችንን የመን አሳጣችን። በአሁኑ ሰዓት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያን የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ይገኛሉ። ወያኔ ግን ይሄን የወገን  ጥሪ የሚሰማበት ጆሮ አልፈጠረበትም። የዜጋቸው ደህንነት ያሳሰባቸውና ያስጨነቃቸው አገሮች ነገሩ ሳይብስ በጊዜው ዜጎቻቸውን አስወጥተዋል። ከ45 በላይ ኢትዮጵያን ግን የሚደርስላቸው አጥተው በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ አርበኛውን አንዳርጋቸው አፍኖ ለማምጣት የመን ድረስ አምርቶ  የነበረው ቦይንግ ዛሬ የጥይት ናዳ እየወረደባቸው ላለው ዜጎቻችን መድረስ አልቻለም።  አንዳርጋቸውን ለማሳፈኛ ለየመን ያወጡት በሚልዮን የሚቆጠር  ዶላር የዜጎቻችንን ነፍስ ለማዳን ሳይችሉ ቀርተዋል።  ይልቅ ለነሱ የወገን ድረሱልኝ ጥሪ ከወደ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በፌስ ቡክ መስኮት የተናገሩት ቢኖር ስልክ ቁጥር ነው። እንዴት አሳፋሪ ነገር እየሰሩ እናዳለ የሁል ግዜ ተግባራቸውን በድጋሚ አሳይተውናል።  እኔን ያሳዘነኝ ነገር የራሷን የቤት ስራ ሳትሰራ፣ የራሷን የውስጥ መረጋጋት ሳታመጣ፣ ሰለራሳ ሕዝብ ሳትጨነቅ፣ የኢትዮጵያን እውነተኛ ታጋይ አሳልፋ  መስጠትዋ <<የራስዋ አሮባት የሰው ታማስላለች>>  የሚለውን አባባል ያስታውሰኛል ቢሆንም ግን  የመን ለሰራችው ስራ ልትጠየቅ ይገባል።

አንዳርጋቸው በኢትዮጵያን ልቦና ውስጥ የፈጠረው የአንድነት መንፈስ ወያኔን የማስወገድ  ሃላፊነትን ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን መንገድ ያሳየ  በመሆኑ  እኛ ልጆችህ ያሰብከውን ዲሞክራስያዊት አገር የማየት ህልምህን እውን ለማድረግ በአንድ አንዳርጋቸው ምትክ ሚልዮኖች ተተክተው ወደትግሉ ጎራ ገብተናል። ገዳያችንን ልናጠፋ፣  አንባገነኖችን ልንገረስስ፣ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ  ቆርጠን ተነስተናል። እናም የተደወለው ደውል  የክተት ነውና  ሁሉም በያለበት  ወያኔ የተባለውን ሰው በላ አውሬ  ከኢትዮጵያ  ምድር እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ እና ጨርሶ እንዳያንሰራራ አድርጎ የማስወገድ ደውል ነውና  ሁላችንም ለዚህ ክተት ጥሪ ተሳታፊ ሆነን ትግሉን እንቀላቀል።  የነጻነት ታጋይ የአንዳርጋቸው ጽጌ ልጆች እንዳለን ዛሬ የምናሳይበት ጊዜ  ነውና ገዳያችንን ገለን፣ አሳዳጃችንን አሳደን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በስደት ከተበታተንበት ተሰባስበን በደስታና በሰላም የምንኖርባት  ዲሞክራሳዊት አገር እንዲኖረን ክተቱን ተቀብለን ነጻነታችንን እናመጣለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

08.04.2015

Samilost89@yahoo.com

The post የአንዳርጋቸውን የትግል መንገድ ሚሊዮኖች ይከተላሉ። – ሳሙኤል አሊ (ከኖርዌይ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ኣመልህን በጉያህ ስንቅህን በሲኖትራክ (በእውቀቱ ሥዩም)

$
0
0

Bewketu Seyoum – Very Funnyባንድ ወቅት የጨርቆሱ ጓደኛየ ኢልያስ ኣወቀ መኪናው ውስጥ ተቀምጦ ከዚያ በፊት ልብ ብሎት የማያውቀውን ኣንድ የቦብ ዘፈን ይሰማል፡፡ natural mysticከሚለው ዘፈኑ ነው፡፡

ቦብ ዘፍኖ ዘፍኖ የሆነ ቦታ ላይ ሲደርስ፤

Many more will have to suffer
Many more will have to die

ሲል ኢልያስ ገርሞት why? ኣለ፡፡

ቦብም Don’t ask me why ብሎ ቀጠለ፡፡

ዘፋኙና ኣድማጩ የዘመንን እና የቦታን ኣጥር ጥሰው ተገናኙና ተነጋገሩ፡፡ተዋሃዱ ማለት ይሻላል፡፡ ዮሃንስ ኣድማሱ ባንድ ግጥሙ “ዳንሱን ከዳንሰኛ መለየት ኣይቻልም” ያለው ይሄን ግጥም ኣይነቱን ኣጋጣሚ በደንብ ይገልጸዋል፡፡

ቦብ ፍልስፍናን መዝፈን እንደሚቻል ያሳየ ድምጻዊ ነው፡፡ እንደገባኝ የፍልስፍናው ዋና ጭብጥ“ ለውጥ በትግል ይመጣል” የሚል ነበር፡፡ ግን ታግሎ ታግሎ ወደ መጨረሻው የደከመው መሰለኝ፡፡ ከላይ የጠቀስኩት natural mystic የተባለ እንጉርግሮው ኣየሁት ታገልኩ ታገልኩ ተረታሁ የሚል ይመስላል፡፡ ። ግጥም ካንዱ ቋንቋ ወደ ኣንዱ መተርጎም ብዙ ኣያሰደስተኝም፡፡ከዚያ ይልቅ በወደድኩት ግጥም መንፈስ ያልወጣ የራሴን ሃሳብ መጫር እመርጣለሁ፡፡እና ቦብን በኣማርኛ ሳዳምጠው፤

“ኣይመረመሬው ከሃገረ ሰማይ
በፍጥረታቱ ላይ
መከራና ሞቱን እያፈራረቀ እንደሾላ ሲጥል
ኣሜን ብለህ ቀጥል”
የሚል ነው የሚመስለኝ፡፡
ዛሬ ትልልቅ ኣገሮች ለጥቅማቸው ሲሉ ትንንሾሽን ባንድ ሌሊት ኣፍርሰው በሚያድሩበት በዚህ ዘመን ፤ፈሪሃ እግዜር ኣለን የሚሉ ሰዎች ወንድሞቻቸውን በካሜራ ፊት ኣሰልፈው እንደ ፋሲካ በግ በሚያርዱበት በዚህ ዘመን፤ በርግጥ የሰው ልጅ ሊሸሻል የሚችል ፍጡር ነው? የሚለውን ጥያቄ ባዎንታ መመለስ ይከብዳል፡፡እና በዚህ ዘመን ማለዳ ላይ get up stand upየሚለውን ዘመን ኣዳምጣለሁ፤ ሲመሽ natural mysticየሚለውን ኣምናለሁ፡፡ከኔ የተሻለ ብሩህ ኣይን ያላቸው ወዳጆቼ ደግሞ በቦብ ዜማ ኣፍቅረዋል፡፡በቦብ ዜማ ደንሰዋል፡፡በቦብ ዜማ ኣስበዋል፡፡ በቦብ ዜማ ቀኖቻቸውን ኣስውበዋል፡፡

ቦብ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ኣምላክ ናቸው ይል ነበር ይባላል፡፡ልንታገሰው የሚገባ ጠቃሚ ተረት ነው፡፡የኣይሁድ የህንድ የፋርስ ነቢያት በመሲህነትና በኣምላክነት ደረጃ በሚመለኩበት ዓለም ውስጥ ኣንድ ኣፍሪካዊ ንጉስ እንዲህ ያለ ወግ ቢደርሰው ምን ችግር ኣለው?

ቦብ ማርሊ ቀንደኛ ኣጫሽ ስለሆነ መታሰቢያ ኣይገባውም እያሉ የሚከራከሩ ወዳጆች ገጥመውኛል ፡፡ ወይ የወንቃው ጊዮርጊስ! እንደዚህ ክርክር ከሆነ የቸርቺል ጎዳና መፍረሰ ኣለበት ማለት ነው፡፡ቸርቺል በዘመነ መንግስቱ ታታሪ ኣጫሽ ስለነበረ ዛሬ በስሙ ሲጃራ ተሰይሞለታል፡፡

ቦብ ከመወለዱ መቶ ኣመታት በፊት ጸጉርን መገማመድም ሆነ እጸ ፋርስ መጠቀም ለኢትዮጵያ እንግዳ ኣልነበረም፡፡ ኣለቃ ኣጽሜ የተባሉ የኣገራችን ታሪክ ጸሃፊ እጸ ፋርስ ማጨስ የተጀመረው በልብነድንግል ዘመን እንደሆነ ይገምታሉ፡፡ለኣእምሮ ብሩህነት ፍቱን ነው እየተባለ ብላቴናው ሁሉ በቂጣና በማር እየደባለቀ የሚበላው ኣብሾም የሃሽሽ ዝርያ ነው፡፡“ጠላ ያለ ጌሾ፤ ቅኔ ያለ ኣብሾ እየተባለ ኣዳሜ ያንን እየበላ ሲቀባዥር ኖሯል፡፡ ብዙ እጾች በስማቸው ሳይሆን በብእር ስማቸው ተሸፍነው ስለኖሩ የሌሉ ይመስላሉ፡፡እንኳን ተራው ሰው ኣንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች እንኳ ተጠቃሚ ነበሩ፡፡ቴዎድሮስን ያነገሱት የግብጹ ኣቡነ ሰላማ የኦፒየም ተጠቃሚ እንደነበሩ በመቅደላ ኣብሯቸው የተሳረው ሃኪም ሄነሪ ብላንክ ነግሮናል፡፡

ዛሬ ቦብ ማርሊ ሰው ይሁን ኣሞራ ለይተው የማያውቁ የጠረፍ ኣገር ባለኣገሮች ያለ ያእቆብ መሰላል ወደ ሰባተኛው ሰማይ ኣድርሶ የሚመልስ እጽ ያጨሳሉ፡፡ መቸስ ኣንዳንዱ ሰው በእንጀራ ብቻ ኣይኖርም፡፡ኣንዳንድ ነገሮችንም ይጨምራል፡፡

የላቀ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ከሌላው ልዩ ባደረጋቸው ችሎታ እንጂ ከሌላው ሰው ጋራ በሚጋሩት ድክመት መመዘን ኣሪፍ ኣደለም፡፡ ኣሁን ኣሁን በትልልቅ ሰዎች የግል ምርጫቸው ጥልቅ ብሎ መፈትፈትና ስማቸውን ማዋረድ የፊስቡክ ኣመል ሆኗል፡፡ ጥሩነሽ ውጭ ኣገር ወለደች ብሎ ርር ድብን የሚል ሰው በሃገር ፍቅር ስም ንፍገቱንና ድድብናውን እየገለጸ ነው፡፡ ኣስቡት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ኢትዮጵያን የመውደድና የመጥላት ምልክት እንዴት ሊሆን ይችላል? በክፉ ቀን የደረሱልን ኣለም ኣቀፍ ኣርቲስቶች የኢትዮጵያ ዜጋ ኣይደሉም፡ ፡በሌላ ገጽ፤ የምጽዋት እህል ሽጦ ታንክ የሚሸምት ኢትዮጵያዊ ባለበት ኣገር ውስጥ ዜግነትን እንደ ትልቅ የቅድስና መለኪያ ማድረግ ኣያሳምንም፡፡ የሰውን ኣገር ሰው በጭፍን መጥላትxenophobiaን ከሃገር ፍቅር ስሜት ጋር የሚያምታቱ በርክተዋል፡፡

ባገራችን ከስርኣት ኣልበኞች በላይ ግፍ ሲሠሩ የኖሩ ህዝብን ስርኣት እናስይዛለን የሚሉ ሰዎች ናቸው፡፡በኣጼ ዮሀንስ ኣራተኛ ዘመን ትምባሆ ሲያጨስ የተገኘ ሰው ኣፍንጫውንና ከንፈሩን ይፎነን (ይቆረጥ)ነበር፡፡ለዝርዝሩ Gerald h portal ፤ My mission to Abyssinia ገጽ 149፡፡
በሚያጨሰው እጽ ተገፋፍሮ ይህን መሰል ጭካኔ የሰራ ሰው መኖሩን ኣላውቅም፡፡

ወለላወቼ፤ ነገርን ነገር እየገፋ እዚህ ኣደረሰኝ እንጂ ስለ ማጨስን ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም ኣላማ የለኝም፡፡ ኣንድ የባነነ የጥንት ኣበሻ ተናገራት ኣባባል ኣለች፡፡“ኣመልህን በጉያህ ስንቅህን በኣህያህ ”ትላለች፡፡ኣንድ ግለሰብ የዜግነት ግዴታውን እስከተወጣ ድረስ፤ የግል ኣመሉ ሁላችንም የምንጋራውን ኣደባባይ የማይጋፋ እስከሆነ ድረስ፤ ስራው ያውጣው ብለን ልንተወው ይገባል ማለት ነው፡፡

The post ኣመልህን በጉያህ ስንቅህን በሲኖትራክ (በእውቀቱ ሥዩም) appeared first on Zehabesha Amharic.

ለነጻነት የሚደረግ እውነተኛ የትግል ጥሪ

$
0
0

ገዛኸኝ አበበበ

ወያኔ ኢህአዲግ የስልጣን ወንበሩን በሀይል ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ በስልጣን በቆየባቸው በሃያ ሶስት አመታቶች በየጊዜው በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና ጭቆና ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱ በአደባባይ የሚታይ እውነታ ሲሆን ከዚህም ጨቋኝና ገዳይ ስርዓት የተነሳ የሀገሪቷ ዚጓች በሀገራቸው ላይ በሰላም መኖርና የነጻነትን ሀየር መተንፈስ በማይችሉበት ክፉ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ::

በአሁኑ ጊዜ ከማንኛውም ጊዜ በተለየ መልኩ ገበሬው፣ ተማሪው፣ ፣ አስተማሪው ፣ ነጋዲው፣ ጋዜጠኛው ፣ ስፖርተኛው፣ ዘፋኙ፣ አርቲስቱ፣ ወዘተ……በማንኛውም እርከን ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገራቸው ላይ በነጻነት መኖርን ስላልቻሉ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሀገራቸውን ትተው እየወጡ በየጊዜው ለስደት ሲዳረጉ ይታያሉ:: ምክንያቱም ዜጓች በሀገራቸው በተረጋጋ ሁኔታ ለመኑር የሚያስፈልጋቸው ዋንኛውና ቁልፉ ነገር ሰላም እና ነጻነት ነውና::ማንኛውም ሰው በሚኖርበት ሀገር በሚኖርበት ሰፈር ወይም አካባቢ እና በሚኖርበት ቤት ውስጥ ሳይቀር በሰላምና በነጻነት መኖርን ይፈልጋል:: ነጻነት በምንም ዋጋ ሊተመን የማይችል ትልቅ ጸጋ ነውና:: ሰላም እና ነጻነት በሌለበት ሀገር የሚኖሩ ዜጓች፣ መብታቸው ይረገጣል ፣ ነጻነታቸው ይታፈናል ዜጓች ለእስር፣ ለሞት፣ እና ለስደት ይደጋሉ::በሀገራችን ኢትዮጵያ የምናየውም ይህንኑ ነው::

እንደ አለመታደል ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያም በአለም ላይ ካሉት ሀገራት በግንባር ቀደምነት የሰው ልጆች ነጻነታቸውን እና መብታቸውን ከሚገፈፉበት ሀገር ተርታ እንደምትገኝና የሀገሪቷ ዜጓች በጨቋኙ ገዥ ስርዓት ነጻነታቸውን ተገፈው ባሪያ ሆነው የሚኖሩበት ሀገር እንደሆነች በየጊዜው ከሚወጡ አለም አቀፍ ሪፖርቶች መረዳት ይቻላል::

ዜጓች በከፍተኛ ሁኔታ ለስደት እየተዳረጉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደረገው አፈና፣ እስራት እና ግድያው በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ የሚገኝ ሲሆን ይህም በገሃድ እየታየ ያለ እውነታ ነው :: በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች በፋሺስቱ የወያኔ ቡድን ነጻነቱ እየተገፈፈና መብቱ እየተረገጠ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከእንግዲህ ወዲህ ይሂን የወሮበሎች ቡድን እሽሩሩ እያሉ የመኖር አቅም ያለው አይመሰልም :.: በአሁኑ ጊዜ ከየአቅጣጫው ከሚሰሙ ነጻነት ናፋቂ የኢትዮጵያኖቸ ሕዝብ ጩኸት ድምጽ መረዳት እንደሚቻለው ሕዝባችን ለወያኔያዊ አንባገነን ስርዓት መገዛትን የጠላበትና ከመቺውም ጊዜ በተለየ መልኩ እምቢ አሻፈረኝ ብሎ ነጻነቱን ለማስመለስ በአንድነት ለመቋም የተነሳበት ዘመን ላይ የደረሰን በሚያስመስል መልኩ ከየቦታው የሚሰማው የነጻነትና የሰላም ናፋቂዎች የጀግንነት ድምጽ ምስክር ነው::
norway
በቅርቡ እንኳን እንደምናየው የቀድሞው የግንቦት የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄያአሁኑ አርበኞች ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሀፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከየመን ታግተው በወያኔ እስር ቤት ታስረው በግፍ እየተሰቃዩ እንዳለ ይታወቃል የነጻነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው በወያኔ ሴራ ከየመን ታግተው በወያኔ እጅ ላይ መውደቃቸው ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔን አውሬነት በይበልጥ በመረዳት ከዳር እስከ ዳር በአንድነት መቋሙን እያስመሰከረ ሲገኝ የፖለቲካ ግለቱም ጨምሮ የአረመኔው የወያኔን ቡድን በከፍተኛ ሁኔታ አርበድብዶት እንደሚገኝ ወያኔ ከሚሰራው ስራና ከሚያደርጋቸው ድርጊቷች ማወቅ ይቻላል::የአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ተከትሎ እየከረረ ያለውን የሕዝብን ቁጭትና ቁጣ ለማጥፋት በሚያስመስል መልኩ ይኼ አረመኔው መንግስት በአሁኑ ጊዜ በሀገር ቤት በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት በህጋዊ መንገድ እንኮን ሳይቀር እየታገሉ ያሉትን ሰዎች ከየመንገዱ እየለቀመ እስር ቤት አስገብቶ እያሰቃያቸው እንዳለ ይታወቃል ::ይህንንም ተከትሎ ሁላችንም እንደምናውቀው የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው ምክር ቤት አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና የሕዝብ ግንኙንት ኃላፊ አቶ አብረሃ ደስታና የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ የሸዋስ አሰፋን ጨምሮ ሌሎችም እጅግ ብዙ ለየጻነታቸው የሚታገሉ ኢትዮጵያን ወገኖቻችን የወያኔ መንግስት በግፍ አስሯቸው እያሰቃያቸው እንደሚገኝ ይታወቃል::

ይኼ መንግስት እሱን የሚቃወሙትን ሰዎችንና በድፍረት እየተጋፈጡት ያሉትን የፖለቲካ መሪዎች አአሸባሪ የሚል የታርጋ ስም እየለጠፈላቸው ወደ እስር ቤት መወርወር የተጠናወጠው ክፉ ባህሪው ሆኖል:: የፖለቲካ መሪዎችንና የፖለቲካ ሰዎችን ማፈንና እየያዙ ወደ እስር ቤት መወርወር ይበልጥኑ ትግሉን እያከረረውና የኢትዮጵያን ሕዝብ ይበልጥኑ ለነጻነቱ በመታገል ለድል እያነሳሳው ነው እንጂ ፈጽሞ ከትግል ወደ ኋላ እይመለሰው እንዳይደለ የወያኔ ባለስልጣኖች ጠንቅቀው ሊያውቁት የሚገባቸው ነገር ይመስለኛል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነትን ተጠምቷል ::Freedom is more than food በአሁኑ ሰአት በሀገር ቤትም ሆነው በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ይሁኑ ወይም በውጭ ሆነው በሁለገብ ትግል እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች አላማቸውም ሆነ ጥያቄያቸው አንድ ነው የስልጣን ወይም የገንዘብ ሳይሆን የነጻነት ጥያቄ ነው :: የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት ያስፈልገዋል ::እኛም ሰላምና ነጻነት የናፈቀን ህዝቦች መብታችንን ለማስከበር ለነጻነት ከሚታገሉ ድርጅቷች ጎን በመቆም ለነጻነታቸው ሲታገሉ በወያኔ አንባገነን ትህዛዝ ወደ እስር እየተወረወሩ እና በግፍ እየተሰቃዩ ላሉ ወገኖቻችን ከመንኛውም ጊዜ በተለየ መልኩ ሀገራዊ ስሜት ተሰሞቶን ልንጮህላቸውና የእነሱንም ፈለግ በመከተል ከሁለት አስርት አመታት በላይ የዜግነት መብታችንና እየረገጠና ነጻነታችንን እያፈነ ህዝባችንን ለስደት እያደረገ ያለውን ያለውን ይኼን ሰይጣናዊና አረመናዊውን ስርዓት በማንኛውም መንገድ በመታገል፣እውነተኛ ሰላምና ነጻነት በኢትዮጵያ ምድራችን እንዲመጣ ለማድረግ የወያኔን መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዳግም እንዳይነሳ አከርካሪውን ሰብሮ ለመጣል በእውነተኛ ኢትዮጵያዊ ስሜት መነሳት ይጠበቅብናል እላለው::

ለዚህ ወቅታዊ የነጻነት የትግል ጥሪ ምላሽ ለመስጠት የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አርበኞችን አስከትሎ መዋቀሩን በማሥፋት አርበኞ የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሚል አዲሥ ስያሜ ለቀረበው ሀገርን የማዳን የትብብር ጥሪ ምላሽ በዲሞክራሴዊ ለውጥ በኢትዮጵ ድጋፍ ድርጅት በኖረውይ አዘጋጅነት ለቀረበው የምክክርና የትብብር ጥሪ ነውሪነታቸው በኖሮዌይ የሆነ ኢትዮጵያዊያዊንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መልስ ለመስጠት ከምሥራቅ፣ ከምራብ፣ ከሰሜንና ደቡብ ኖርዌይ እንዲሁም ካአዋሳኝ የአውሮፓ ሀገሮች አፕሪል (April18,,2015) ወደ ኖርዌይ ኦስሎ ይተማሉ፥

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
09፣04፣2015
ሚያዚያ 1 2007 ዓ/ም

The post ለነጻነት የሚደረግ እውነተኛ የትግል ጥሪ appeared first on Zehabesha Amharic.

  ላመስግንህ –ተመስገን። –ከሥርጉተ –ሥላሴ

$
0
0

11.04.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

Temesgen Desalegn behindbar„ደጋግ ፡ ሰዎችስ፡ እግዚአብሄር፡ ከማይወደው፡ ሥራ፡ ሁሉ፡ ይርቃሉ። ይወዳቸዋል፡ ከመከራቸው፡ ሁሉ፡ እንደ፡ አደራ፡ ገንዘብ፡ ይጠብቃቸዋል። ሥርዓቱንና፡ ሕጉን፡ ዬሚወደውን፡ ሁሉ፡ ይጠብቃሉና፡ ኃጢያተኞች፡ ሰዎች፡ ግን፡ ሰይጣን፡ ይገዛቸዋል። (መጸሐፈ መቃብያን ካልዕ ምዕራፍ 9 ቁጥር 25 እስከ ፍፃሜው)“

በቅድሚያ ለክርስትና ዕምነት ወገኖቼ ለማህበረ – ምዕመናን እንኳን ለ2007 የጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ በዕለ – ትንሳኤ አደረሳችሁ – አደረሰን። እንዲሁም አርበኛና መምህር አቶ በቀለ ገርባን እንኳን ከጥብቆ ካቴና ወደ መጠነ ሰፊው ካቴናማ ህይወት አሸጋገረዎት። ቢያንስ ከቤተሰብ ጋር መከራውን በአንድ ጉልቻ መቀበልም አንድ ነገር ስለሆነ። ላደረጉልን መልካም ነገር ሁሉ ዝቅ ብዬ አመስግናለሁ – በአክብሮት። ውለታዎትንም ታሪክ ይክሰወታል ብዬም አስባለሁ። እግዚአብሄር ይስጥልን።

የዛሬው ባለጉዳዬ – አንድ ፍሬ ልጅ በተግባር የጎለመሰ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደፋር መሆኑ፤ መጪን ጊዜ ቀድሞ የማዬት አቅሙ እንደ ማግኔት ሳቢነቱ፤ የአቅጣጫን ትኩስነት የመለካት ብቃት ብቻ ሳይሆን፤ ስሜቱን ለታዳሚው በመላክ መንፈስን በቋሚነት በመዳፉ የመያዝ ስልቱ፤ ጭንቅ ጊዜን በጭብጥ ትንተና የማብቀል ልዩ ችሎታው፤ የአቀራረብ ይዘቱ ሁለመናነት ወጥ ሆኖ ነገር ግን ጥገኛ ሳይሆን በሃቅ ማሳ መልማቱ፤ ሚዛናዊነቱና – ማዕዘንነቱ፤ የሀቅ ትንፋሽን የማድመጥ ክህሎቱ፤ ለሙያው ያለው ተቆርቋሪነት አክሎ ብቃቱን በሁለገብ ሁኔታ ማዬት እንዲያስችል አበራክቶ የሰጠው ትንታግ የእውነት ዝማሬያችን ነው። ለእኛ የመንፈስ ሃብታችን ነው። ስለዚህም ይህችን ቋጠሮ ከምስጋና ጋር ልኮልምለት – ተሰናዳሁ። ኮቢዬንም ሳማክራት በሐሤት ፈነጠዘች። አዎን! የዛሬ እንግዳችን እሱ ነው እሱ ልጅ ተመሰገን ደሳለኝ …. የብርታት ሰዐቱ። የማግሥት ተስፋ ዋዜማ – የብሩኽ ራዕይ ዜማ።

ላመስግንህ – ተመስገን

      *******

አንተ ዬዕውነት – አርበኛ

የእኛ!

የሃቅ – ሁነኛ – ሥህነኛ

መዋኛ!

የፍቅር – ቤተኛ

ማተበኛ!

የሰው መሆን – ትርጉመኛ

የህሊና – ዳኛ!

የዘር – መገኛ

የዕንባ – ዘበኛ

ወደኛ

ውድዬኛ።

ሎሌነትን – የተጠዬፍክ

ጠፈፍ – ያልክ።

ለዕብለት – ያላደርክ …

ለሃሰት ጉዝጓዝ … ያለተነጠፍክ

ክርክም ያልክ

የልጅ አዋቂ – የአደራ መልክ።

ትግል – ጠርታኽ

አፍልቃኽ።

ነፃነት „ነፃ“ እንድታወጣት – አጭታኽ፤

አንተነትህን – ሰጠሃት

ሆንክላት።

ሰላም – ናፍቃኽ፤  ሽው ስትልህ፣

ከማያልቀው ፏፏቴዋ  – ከመዳህኒቷ ውስጥ ቀድታህ

ቀለጥክላት።

ራዕይ – አምናህ

ተሳካላት።

ላመስግንህ – ተመስገን፤ የማያልቅብህ – ብዕረኛ

ባለማተብ – ዕሴተኛ፣

ጮራ – የእኛ!

ባተሌ – ጋዜጠኛ

ባለቀለም – ዝናርኛ።

ግርማ – የእኛ

ሞገስ – ለእኛ

ማኛ!

ደፋር የኮቢ –  ወታደር

ለህግ ክብር ብር – አንባር።

ግብር የሆንክ ለዘረኛ

ውለኛ!

አንተ ——– የእኛ

የመሆን  —- ሁነኛ

የፋክት! – አርበኛ።

የእኛ እሸት – የእኛ ፍሬ፣

የእኛ ቀንበጥ፣ – የወንዜ ላሂ የሀገሬ

ዬብራና – ሳታና ገበሬ።

ዘንበል ብለህ፤ አዳመጥካት

የልዕልትህ – ድምጽህ ናት፤

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ – ደምህ

አንተን ለእኛ ሰጥታ

የታሪክ ምንጭ – ማሾ አብርታ

የሰጠችን የምልዕት ዕንባ – ጠብታ፤

የፍትህ ዕንብርት – የዕድምታ

የልዕልና አንኳር –  አግታ

ከእውነት ጋር ተጋብታ

ከዘመን ጋር ተጣብታ!

የሃቅ – ለጋ —- ለግላጋ፣

ምዕራፍ አንተን አወጋ፣

ሊያነጋ!

የሥርዓት — ቅጽ

የቅንነት —– አንቀጽ፤

ብላቴና፤

የውስጥነት – ገናና

የርትህ ፍቅር – ዝባድ ገና፤

ዬፎርቹን አራት ዓይናማ

ዛላማ!

የሴንቸሪ – ዘንጣፋ ዞማ።

ላመስግንህ – ወንድምዓለም ታንሽዬ ተመስገን

ደኑ የሆንክ፤ ለፈተና – ለመከራ

ልትደለድል የልዩነትን – ጋራ።

የቁም ነገር ዝና

ዋና!

ዬነፃነት – መምህሩ

ኪዳኑ ነው አዳሩ፤

የተስፋ ብርሃን ምግባሩ

ሰው መሆን ብቻ፣ ብቻ – ጠረኑ።

„እ — ፍ“ ብለው ያላጠፉህ

ቀጥተኛ – ደማምህ

ወጣትነትህን – ገበርክ፤

መንፈስህን – አምነህ ያከበርክ

ልክ!

መማገድህ በባዕትህ – ለባዕትህ

ጥልቀትህ!

የፈቀድከው – ሆነልህ

ከ-ሷው ጋራ ጨለማውን በካቴና፤ ————————-ህመምህ፤

በ-አብነትህ

ከ-ውስጥህ፣

እናት ሆዱ – ደግነትህ

ስስ – አንጀትህ

መሰከረ – ጣትህ

ትክክለኝነትን አበጀኸው – ሠራህ

ስለናትህ!

 

ሥጦታ፤ ዘመን ለሸለመን እጅግ ብርቱ ጋዜጠኛና ጣምራ ብቃት ለሰጠው ለወጣት ተመስገን ደሳለኝ ይሁንልኝ። ታናሼ ወንድምዬ ምህረቱንም አምላኬ ያምጣልህ አይዞህ ዬእኛ ብርቱ። /06.04.2015 ማርያሽታይን ገዳም – ባዝል/ ©ሥርጉተ – ሥላሴ።

 

በመጨረሻ የኔዎቹ ዛሬ ከልቤ ተደላድሎ በተቀመጠው በዚህ ብልህ – ብሂል ልሰናበት „አልቦ ብሄር“ የአንድ መጸሐፍ ያህል ቁምነገር ነው ያስተላለፉት ምርጥ ፍሬ – ውድድድድድ …. ዬእኔ – ጌጥ! http://www.zehabesha.com/amharic/archives/40350 መሸቢያ ሰንበት ማለፊያ ፆመ ሁዳዴ መፍቻ። ኑሩልኝ – የኔዎቹ።

 

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዜብሄር ይስጥልኝ።

The post   ላመስግንህ – ተመስገን። – ከሥርጉተ – ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

የማለዳ ወግ…በኳታር ታምና ያኮራችን እህት አንድነት * ”ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “

$
0
0

የማለዳ ወግ…በኳታር ታምና ያኮራችን እህት አንድነት
* ታማኟ ኢትዮጵያዊት አንድነት ዘለቀው በክብር ተሸለመች
* ” ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “
ታምና ያኮራችን እህት አንድነት ዘለቀው

ነቢዩ ሲራክ

አንድነት ዘለቀው ትባላለች ፣ አንድነት የ 32 ዓመት ዕድሜ ያላት ኢትዮጵያዊት ስትሆን በኳታር ዶሀ ውስጥ በሚገኘውና ኳታር ብሄራዊ ኮንቬንሽን ሴንተር Qatar National Convention Center (QNCC) ተብሎ በሚታወቀው አንድ ታዋቂ መስሪያ ቤት ውስጥ በጽዳት ሥራ ተቀጥራ መስራት የጀመረችው እጎአ ከ2011 ጀምሮ ነው ።
Quatar
ታማኟና ታታሪዋ ኢትዮጵያዊት አንድነት ዙሪያ ካሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በሰፊው እየተሰራጨ ያለው የሚያስደስት መረጃ ማረጋገጫ የተገኘው ግን ከትናንት በስቲያ ነበር ። አንድነት በመታጠቢያ ቤት የዘወትር የጽዳት ሥራዋን በመከወን ላይ ሳለች ሁለት በእንቁ ፈርጥ የተሸላለሙ የጋብቻ ቀለበቶች ታገኛለች ። የከበረ አልማዝ ያጌጡት ቀለበቶች ስለመሆናቸው ጠቋሚ ዋጋቸው የኳታር ገንዘብ QR470,000 US$129,000 ( አንድ መቶ ሀያ ዘጠኝ ሺ የአሜሪካ ዶላር) መሆኑ በቀለበቶቹ ላይ ተጽፏልና አውቃለች ። ታማኝ ናትና እንቁ አልማዙ አንድነትን አላጓጓትም ። እናም ሳታመነታ ወዲያውኑ ለምትሰራበት መስሪያ ቤት ኋላፊዎቿ ያገኘችውን የጣት ቀለበቶችን አስረከበች ። ስለ መልካም መግባሯና ታምኝነቷ የከብር ሽልማትን ተቀብላለች !

ሽልማቱን ያስረከቧት የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ሲናገሩ አንድነት የቀለበቶች ዋጋ ስላለባቸው ለሁለት ደቂቃ ያህል በእጆችዋ ለማቆየት አለመፈለጓን በእግራሞት የገለጹት ኃላፊው ኢትዮጵያዊቷ አንድነት ” ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “I believe in my life that honesty is the best policy.” ማለቷን ጠቅሰዋል !

ኳታር ብሄራዊ ኮንቬንሽን ሴንተር Qatar National Convention Center (QNCC) ተብሎ በሚታወቀው አንድ ታዋቂ መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና አስተዳደሩ የአንድነትን ታማኝ ሰራተኝነት በአደባባይ ከመመስከር አልፈው ጠቀም ያለ የገንዘብ ዳረንጎት እንዳደረጉላት ከኳታር ዶሃ የአንድነትን ታማኝነት የተሰጠውን ክብር አስመልክተው ባሰራጯቸው መረጃዎች አስታውቀዋል !

አንድነት ከዚህ ቀደምም ትሰራበት ከነበረው አል ሙክታር የጽዳት ኩባንያ Al Mukhtar Cleaning company በጽዳት ስራ ላይ እንዳለች ውድ እቃ አግኝታ ለአለቆቿ በማስረከብ ታማኝነትቷን ማረጋገጧ በመገናኛ ብዙሃኑ ተወስቷል … !
ደስ አይልም ? ኮራሁብሽ እቱ !
ከብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ!
ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 2 ቀን 2007 ዓም

The post የማለዳ ወግ…በኳታር ታምና ያኮራችን እህት አንድነት * ” ታማኝነት የህይወት መመሪያየ ነው! “ appeared first on Zehabesha Amharic.

በፋሲጋችን። –ዳዊት ዳባ

$
0
0

እንኳን በደህና ከዘመን ዘመን  አሸጋግሮ ለፈሲጋ በዓል  አደረሰን። በአሉን የፍቅር የሰላም ያድርግልን።

Anger at injustice as martin luter king wrote. Is the political expression of love?
የፋሲጋ ሳምንት (ህማማት)  ድንቅና አስገራሚም ነው። ፍቅር፤ መሰዋትነት፤ ክህደት፤ ታማኝነት፤ ፅናት፤ፍርደገምድልነት፤ምቀኝነት፤ ተንኮል፤ ደባ፤ አፍቅሮ ሰልጣን፤ አፍቅሮ ንዋይ፤ ሰም ማጥፋት፤ ይቅርታ፤ አብሮ መብላት፤ ጉቦ፤ ተስፋ፤ ሀዘን፤ ደስታ፤ ስቃይ፤ሞት፤ ይሰቀል{Mop Justice}፤  ብቻ ጠቅለል ባለ የዚህን አለም  ሂወታችንን በአንድ ሳምንት ውስጥ ሲከወን እናይበታለን።

ህማማቱ ከተፈፀመ ረጅም ጊዜ ሆነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አለም የሰው ልጅም በእጅጉ ተቀይሯል።  ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶ በዚህ ምድር ላይ የተመላለሰው በዚህ ዘመን ቢሆንስ ኖሮ ብለን ብንጠይቅ?። የሰው ልጆች ይህ ሁሉ ግፍ እንዲፈፀምበት፤ በመጨረሻም እንዲሞት አይፈቅዱም ማለት የሚቻልበት ደረጃ ድረስ ተለውጧል ማለት ይቻላል።  ሞቱም ሆነ ያን ሁሉ መከራን መቀበሉ ከንቱ አልቀረምና ስለተለገስነው ዘላለማዊ ሂወቱ ብቻ ሳይሆን ምድርን በዚህ ደረጃ ስለቀየረው  ደስ ያሰኛል። ይህ ግን ጠቅለል አድርገን በአለም ደረጃ ከወሰድነው ነው።  የዘመኑ ሀያል ህዝቦች በአደገ ስብእና ላይ እና ለሰው ልጅ ሂወት ክብር የሚሰጡ በመሆናቸው ነው ። ብቃት ደረጃ ደርሰዋል ባይባልም ፍትህ እንዳይጓደል አሰልሰው የሚጥሩና ለእውነት የሚቆሙ ስለሆነ ነው። አቅሙ ለሌላቸው ተቆርቋሪ መሆንን ስራቸው ያደረጉ ብዙዎች ያለቡት ማህበረሰብ ስለሆነም ነው። በዋናነት ክርስትናቸው ይህንኑ ታላቅ ቁም ነገር መሰረት ያደረገና  በሚታይ በሚጨበጥ  ስራ የታገዘ ስለሆነ ነው። ነጣጥለን በየሀጉሩና በየአገሩ  የሰው ልጅ ምን ደረጃ ላይ ነው ያለው? ብለን ካየነው ግን ግምታዊም ቢሆን የምንደርስበት ድምዳሜ በእጅጉ የተራራቀ በዙም በህማማቱ ዘመን ከነበሩ የሰው ልጆች ከነበራቸው  ስብእና ያልተለወጠ ሊሆን ይችላል።

አያድርገውና መመላለሱ በዚህ ዘመን ኢትዬጵያ ውስጥ ሆኖስ ቢሆን?። ጥያቄው ለበዛው አማኝ አናዳጅ የሚሆን አይመስለኝም። ሲጀመር ጥያቄውን ያስነሱት ሰባኪ ነን ያሉ ናቸው። ዝም ሲባል ይባስ ብለው ትንኮሳ ስለበዙ ነው። አሁንም ለምን ተነሳ ብለው  ይሰቀሉ የሚሉና አዋራ ሊያስነሱ ይችላሉ። መነሳት ግን የግድ አለበት። አዎ በዚህ በኛ ዘመን ህማማቱ  ኢትዬጵያ ውስጥ ቢሆንስ ኖሮ?።

ከሳሾች፤ አስገዳይና፤ ገዳዬች አሉን።  በእርግጥ በሰለጠነው ማህበረሰብ ውስጥ እነዚህን  በመንግስት ስልጣን ላይ አናገኛቸው ይሆናል። ቢኖሩም ስልጣናቸው የተገደበ ስለሆነ አይችሉም።  በየትኛው የአለም ክፍል ላይ ሊኖሩ ግን ይችላሉ። የውሸት ምስክሮችንም መግዛቱም ሆነ ፈራጆችን ማግኘቱ ቀላል እንደሆነ ከኑሯችን የምናያው ነው። ይህን አይነት እኩይ ወንጀል ቅቤ ቀብተው የሚያሰማምሩና ህዘብን የሚያደናግሩም የካድሬ መአት፤ ጋዜጠኛ ተብዬና አደርባይ ምሁራን ሞልተዋል። በዋናነት በየእምነቱ የቁጩ ሀዋርያቶችም እንዲሁ። ያም ሆኖ እነዚህ ሁሉ ተደምረው ከጠቅላለው ህዘብ ጥቂቶች ናቸውና እንደህዘብ ከሌሎች የሚያሳንሱን አይሆንም።

መክሰሻውም በገፍ ነው ያለን። ከአስተምሮቶቹ ውስጥ በቀላሉ በመምዘዝና ትርጉም በመስጠት።  በእምነቶች መሀል ግጭት በመፍጠር። በሽብርተኛነት፤ በአገር ክህደት፤ መንግስት ላይ በማሴር፤ የህዳሴ ጉዟችንን በማደናቀፍ  የሚለው ሁሉ በቀላሉ መክሰሻና ማሰቃያ ሲያልፍም መግደያ ሊሆን እንደሚችል ያለንበት ሁኔታ መስካሪ ነው። አይደለም አገርን አልፎም አለምን የሚያነቃንቅና የሚለውጥ መልካም ሀሳብ ይዞ የመጣው መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ትንሽ የሆነች አገራዊና ህዝባዊ  መልክም ሀሳብ ለዛውም ምድራዊ አላችሁ ተብለው ብዙ ንጹሀን ዜጎቻችን እየተገደሉ፤ ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው በየማጎርያ መኖራቸው የማንክደው ነው።  ያም ሆኖ ይህንኛውም በመንግስት ደረጃ የሚራመድ ስለሆነ እንደ ህዘብ  አያሳንሰንም ብለን እንውሰደው።

ዛሬም “ይሰቀል”፤ “ይሰቀል” ልንል የምንችል ምን ያህላችን ነን የሚለው ላይ ብዛታችን ነው  አስፈሪም አሳፋሪም ሊያደርገን የሚችለው ። ሲጀመር የመጠየቅ እድሉም ስለሌለን ይሰቀል ማለቱንም አንችልም። ወናው ጉዳይ  ይህ ሰው ንጹህ ነው፤  ሰቆቃ ሊፈጸምበት አይገባም  ብለን ልንመሰክር የምንችል ምን ያህላችን ነን?።  አጥብቀን የምንቃወም፤ ፍትህን የምንጠይቅና ድምጻችንም የምናሰማስ?። ወጋም የሚያስከፍል ቢሆን ለመክፈል የምንፈቅድስ?።  ንጽህናውን ልቦናችን እያወቀ  እሷስ ብትሆን በመጀመርያ “አጭር ቀሚስ ማን ልበሺ አላት” አይነት አመክነዬ መደርደሩም ሆነ የተካንበት ተጠቂው ላይ ጉድፍ መፈለጉ  ዘመንኛ መሆኑ ነው እንጂ ያው “ስቀለው” ውስጥ  የሚካተት ነው።

አምላክ በማቲዌስ ወንጌል 25፤31-46 ግልጽ አድርጎ ነግሮናል። አመክንዮ ለመደረድር  እንኳ እንዳያመቸን አድርጎ። ለተራቡት፤ ለተጠሙት፤ ለተጨቆኑት፤ ፍርድ ለተጓደለባቸው፤ ለሚሳደዱት፤ ባጠቃላይ ለሰው ልጆች አሁን በምድር ላይ የምናደርገውን ለሱ እንዳደረግነው አድርጎ እንደሚወስደው ነግሮናል። በዬሀንስ 4፤20 ደግሞ አጠገብህ ያሉ ወንድምና እህቶችህን ሳትወድ አምላክን እወዳለው ብትል እየቀጠፍክ ነው ብሎ መፈናፈኛ እንዳይኖር  ቁም ነገሩን አጠናክሮ ዘግቶታል። ቃሉን ላመሰጠርው ልሞክር። መንፈሳዊ ስራችን ሲገለፅ ስለውለታ፤ ስለጉልበተኛነት፤ ስለትውውቅ ሳይሆን  ስለሰባዊነት፤ ስለፍትህና ስላእውነት ለዛውም ከልባችን ደስ እያለን ብቻ የምናደርገው ይሁን ነው የሚለን።

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ከመጣ አይደል ‘ሀ’ ተብሎ ቀን መቆጠር የተጀመረው። አሁን 2007  ላይ ነን ።  በዚህ ረጅም ጊዜ ክርስትናው በአገራችን ብዙ ተከታዬች አፍርቷል። ብዙ አብያተ ቤተክርስትያናትና የአምልኮ ቦታዎች አሉን። ብዙ አስተማሪዎች ሰባኪዎች እንዲሁ። ጿሚው አገሬው ነው። ስሙን ከፍ ከፍ የሚያደርገውም እንዲሁ። በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ ሰላት የሚያደርሰውም ያገሬው ግማሽ ነው። ሁሉም አይነት እምነቶቹ ረጅም ዘመንን አገራችን ውስጥ አስቆጥረዋል። ታዲያ ለምን ነፃነት የበዛልን ዜጎች መሆን አልቻልንም?። ማን ሀላፊነቱን በአግባቡ ስላልተወጣ? ምንስ ስለጎደለ ነው?።

በዬሀንስ ወንጌል 2፤20 ላይ የአምላክ ቃል “ስራ የሌለው እምነት ሙት ነው ይላል።” በሌላ አገላላጽ ፍቅሩ አለ እንበልና እምነቱና ፍቅሩ መኖሩ የክርስትናው ግማሹ ነው። ሌላኛው ግማሽ ያን እምነትህና ፍቅርህን በስራ ላይ ማዋሉ ነው።  እምነታችን ስራ የሌለበት ቢሆን ነው እንጂ ይህ ሁሉ ችግረኛ፤ ይህን ያህል ጥላቻ፤ በዚህ ደረጃ የፍርድ መጓደል። ቆጥሮ መስፈርት የሌለው ተሰዳጅ፤ አድሎ፤ዘረኝነት…. ባጠቃላይ ስቃይና መከራ በአገራችን ባልነገሰ ነበር።

የዘመኑ ስልጣኔ እንደሁሉም ነገር የአምላክን ቃል ማግኘቱንና መረዳቱንም ቀላል አድርጎታል። ኮንቢዩተሬን ስለሌሎች መብት መከበርና ስለነፃነት ስለመቆም ቅዱስ መፀሀፍ ምን ይላል ብዬ ጠየኩት?። ከሰባ በላይ ጥቅሶች ሰጠኝ።  ለፍትህ ስለመቆምስ ምን ይላል ብዬ ጠየኩት። ከየትኛውም ቁምነገር በበዛ ወደ ሁለት መቶ ቦታዎች ላይ ስለፍትህ ግልፅ አድርጎ ይነግረናል። እንዲሁ  በራስ ስለመተማመንና አንገትን ቀና አድርጎ ስለመሄድስ ምን ይላል ብዬ ጠየኩት። ዘረገፈልኝ። እንዲህ እንዲህ እያልኩ ስጠይቅ አብዝቶ መልስ ሲሰጠኝ በመጨረሻ የደረሰኩበት ድምዳሜ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ አማኝና ፖለቲከኛ  ልዩነት የሌለው መሆኑን ነው።

ሲጀምር የበዛነው አይደለንም እያልን በግድ  ፖለቲከኛ መባላችን ይሰመርበት። ይህ እንግዲህ ለነጻነት፤ ለመብት፤ ስለፍትህና ስለእውነት የሚጮህው ሁሉም ባይሆን እንኳ የበዛው አማኝ መሆኑን ያውቃሉ። ከዘም በላይ አመነም አላመነም  ክርስትናው የሚያዘውን ነው የምናደርገው። እንደሚመስለኝ ፖለቲከኛና ፖለቲካ የሚለው ዘመቻ መልካም በሆነው ስራችን እያሳጣን ስለሆነ ያልተመቻቸው ክፍሎች አሸማቀው ዝም ሊያሰኙን ነው ፍላጎታቸው።   የሚገርመው ግን መሳጣቱ የተፈራው ለአምላክ  ወይስ ለምእመኑ?።

እወቁት መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር የተመላለሰው በዚህ ዘመን ኢትዬጵያ ውስጥ  ቢሆን ኖሮ። ይህው ፖለቲከኛ ተብሎ ልታሳንሱት የምታስቡት ወገናችሁ   በግፍ ለሚገደሉት፤ ፍትህ ለተነፈጉት፤ ከቄያቸው ለሚሳደዱት፤ አገር ለቀው ለተሰደዱት ወገኖቹ መቆምን ደስ እያለው የሚያደርገው፤ የሚታወቅበትና ለምድም ያደረገው ነው። በእርግጠኛነት ካሳዳጆቹ  ወገን አይቆምም ። ሌላው የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ጽዋው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለሁላችንም መዳረሱ አይቀርም። ነገ ለሁላችንም የሚጮህው ይህው ወገን ነው።  አለቀ።

 

Comment

 

The post በፋሲጋችን። – ዳዊት ዳባ appeared first on Zehabesha Amharic.

ስለቤተክርስቲያን ዝም አንልም!!! –ከምእመናን የተላለፈ የትንሳዔ መልእክት

$
0
0

08/01/2007 ዓ.ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን

” በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ” ሐዋ.20፡28
eotc-members
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለረጅም ዘመናት አንድነቷን ጠብቃ ኖራለች፤እስካሁንም ደርሳለች። አሁን ባለንበት ዘመን ግን በአባቶቻችን ጳጳሳት መካከል በተፈጠረው መለያየትና መወጋገዝ የተነሳ አንድነቷ እየታወከ ተከታዮቿም እርስ በርሳቸው እየተለያዩ ይስተዋላል። በተለይም በውጪው ዓለም የሚኖሩ የቤተክርስቲያኗ አማንያን በሚያሳዝን ሁኔታ እርስ በርሳቸው ሲጣሉና ሲከፋፈሉ ማየት፤ በ አህዛብ ፊት መሳለቂያ መሆናችን ልብ ያደማል አንገት ያስደፋል። በለንደን ቅድስት ማርያም፣ በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል፣ በሚኔሶታ መድኃኔዓለም፣ በላስቬጋስ ቅዱስ ሚካኤል፣በቴናሲ፣ በስዊድን፣በጀርምን ፣ ወዘተ የታዩት መለያየቶች እጅግ አሳዛኝ ከስተቶች ናቸው። ለዚህ ሁሉ አሳዛኝ ሁኔታ መከሰት ደገሞ በግንባር ቀደምትነት ተጠያቂዎቹ አባቶቻችን ጳጳሳት ናቸው።

በክርስቶስ ምሳሌ የተሾሙበትን የሰላምና የአንድነት ተምሳሌትነት ትተው የተሰጣቸውን ታላቅ አደራና ኃላፊነት ዘንግተው ረብ ለሌለው ሥልጣን ሲሉ እርስ በርሳቸው በመለያየታቸው ምእመናኑም የዚህኛው እና የዚያኛው ወገን ደጋፊ ሆነው ክርስቶስ የሞተለትን ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር ባደባባይ ሲያስነቅፉ ይስተዋላል።

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃሉ እነዳስተማረን እስከ መስቀል ሞት ያደረሰው የነገር ሁሉ ፍጻሜ ፣ የተግባራት ሁሉ ቁንጮና መጨረሻ የሆነው ፍቅር ነው። ፍቅር ኃያል ወልድን ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው እንዳለ ሊቁ።

እርሱ ራሱ አምላካችን ሕግጋትን ሁሉ በሁለት ከፍሎ አስቀምጧቸዋል። ፍቅረ እግዚአብሔር እና ፍቅረ ቢጽ/የባልንጀራ ፍቅር ብሎ ነው። የሚያስደንቀው ደግሞ የመጀመሪያው ሕግ ፍቅረ እግዚአብሔር የሚታወቀውና የሚገለጸው በፍቀረ ቢጽ ነው።

ፍቅረ ቢጽ ፍቅረ እግዚአብሔርንም ጨምሮ የያዘ ከሕገጋተ ሁሉ በላይ የሆነ ሕግ ነው። የሰው ልጅም በግርማ መለኮቱ ሲመጣ ፍጥረትም በፊቱ ለፍርድ ሲሰበሰብ የፍርድ ውሳኔ የሚተላለፈው በዚሁ በፍቅረ ቢጽ መመዘኛነት ነው። የተራበን ማብላት ፣የተጠማን ማጠጣት ፣ የታመመን መጠየቅ፣ የታሰረን መጎብኘት፣ ያዘነን ማጽናናት ፣የታረዘን ማልበስ፣ወዘተ እነኝሀን ነገሮች በማደረግና ባለማድረግ ነው ፍጥረት ሁሉ የሚጸድቀው ወይንም የሚኮነነው ።

” የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።
ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?ንጉሡም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።” ማቴ. ም.25 ቁ. 31-40

እንግዲህ ፍቅር በተለይ ለክረስቲያኖች ይህን ያህል የመጨረሻ እጣ ፋነታችን የሚወሰነበት ከሆነ ሰላምን አንድነትን እና ፍቅርን ምን ያህል ልንጠብቅ እንደሚገባን ዘወትር ልብ ልንልና ልናስተውል ያሰፈልጋል። በጠቢቡም አድሮ እግዚአብሔር ስድሰት ነገሮችን እንደሚጠላ ሰባተኛውንም ነፍሱ ፈጽማ የምትጸየፈው መሆኑን ይህም በወንድማማቾች መካከል ጸብ የሚዘራውን እንደሆነ አበከሮ ተናገሯል።
“እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤
ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፣ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።” ምሳሌ 6፡16-19።

በአንድ መቅደስ ውስጥ ሆነው ለብዙ አመታት በአነድነት እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ የነበሩ ሰዎችን አሁን ምን እና ማን ለያያቸው??? ይህን ያህልስ የኖሩበትን ቤተክርስቲያን ለማፍረስ ምን እዚህ አደረሳቸው? ክርስትና ያስነሱበትን ቤተክርስቲያን፣ያኢግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ታቦት የለም አይሰራም፣ የተቀበሉትን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ትክክል አይደለም ብለው እጅግ ከባድ የድፍረት ነገር እንዲፈጽሙ ያደረጋቸው ማነው? አላልንም አላደረግንም እንዳይሉ ፈጽሞ ከቤተክረስቲያን ሥርዓት በወጣ መልኩ በሥላሴ ላይ መድኃኔዓለምን ፣በሚካኤል ላይ ሚካኤልን ማድረጋቸው ሥራቸው ይመሰክርባቸዋል።

ሰዎች በጊዜ በተፈጠረ አንዳንድ ጊዚያዊ እና ጥቃቅን ነገሮች ላይ የሃሳብ መለያየት ቢኖራቸው ነገ ሁሉም ነገር የሚቀየር ነውና የዛሬውን የግድ ዛሬ እንደ እኛ ካላሰባችሁ ሊባሉ አይገባም። በተለይም በዚህ በአባቶች መለያየት ዙሪያ ባለው ሁኔታ ከዚህም ሆነ ከዚያ ወገን ያሉትን አባቶች እንደ አባትነታቸው ተቀብሎ ልዩነታቸውን እስኪያስወግዱና አንድ እስኪሆኑ ድረስ ዶግማና ቀኖና ያልሆነውን ኢምነት የስም መጥራት ነገር እንደ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ለምን ክርስቲያኖችን ይለያያሉ? ይህ አይነቱ የ አባቶች መጣላት በቀድሞ ጊዜም ይከሰት ነበር። በዚህም የተነሳ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እነዲህ ያለ ነገር በተከሰተ ጊዜ ሰዎችን ሳይሆን አነዱን ጌታ ብቻ እንድንመለከት እንዲህ ሲል ይመክረናል።

” ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ። ወንድሞቼ ሆይ፥ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተሰዎች አስታውቀውኛልና። ይህንም እላለሁ። እያንዳንዳችሁ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ። ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?” ስለዚህ ሁላችን የቤተክርስቲያን ልጆች በስም መጥራትና አለመጥራት መከፋፈል አይገባንም። ደስ ያለው ደስ ያለውን ይጥራ። አንድነት እስኪመጣ የሁለቱንም ወገን አንጠራም ያሉም መልካም እንደቃሉ ይኑሩ።

አባቶችም እባካችሁ ስለመረጣችሁ አምላክ ብላችሁ ይህን መለያየት አስወግዱ። አንድነትን እና ሰላምን አሳዩን፤ አስተምሩን። ልጆች አባቶቻቸውን ነውና የሚመስሉት።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፤አሜን።

The post ስለቤተክርስቲያን ዝም አንልም!!! – ከምእመናን የተላለፈ የትንሳዔ መልእክት appeared first on Zehabesha Amharic.


የአክራሪዎች፣ የተስፈንጣሪዎችና የአሸባሪዎች ዘመን –ይሄይስ አእምሮ

$
0
0

ወቅቱ ለክርስቲያኖች የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል ሰሞን እንደመሆኑ በዓሉ የሚመለከታቸውን አንባቢ ወገኖቼን “እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው [በሰላም] አደረሳችሁ” ማለትን እወዳለሁ፡፡ የደርግ ጊዜ አንድ ትዝታ አለኝ፡፡ በአብዛኛው በሀገር ወዳድ ደናቁርት የታጨቀው የደርግ መንግሥት ሠለጠንኩ ብሎ ሃይማኖተቢሱንና ሃይማኖተኝነትን ከልካዩን የሶሻሊዝም ሥርዓት ካወጀባት ጠማማ ዕለት ጀምሮ በዓል በመጣ ቁጥር በተለይም የአብዮቱ በዓል በሚከበርበት ወቅት “እንኳን ደረሳችሁ” ይል ነበር – ያ ለአገራችን ባዕድ የነበረ የአገዛዝ  ሥርዓት አንዲት ፊደል ላይ እንዲያ ይጨነቅ የነበረው፣ ሰው ለበዓሉ የደረሰው በራሱ እንጂ በፈጣሪ እንዳልሆነ ለማጠየቅ ነበር፤ የሥርዓቱ አቀንቃኞች በአብዛኛውና በግልጽ ይዞታቸው ሶሻሊስትና ኮሚኒስት እንጂ የሃይማኖት ሰዎች አልነበሩም – አንዳንዶች አምልኮታቸውን በኅቡዕ ያከናውኑ እንደነበርና ልጆቻቸውን ሣይቀር በድብቅ ክርስትና ያስነሱ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በመሠረቱ አንድ ሰው ምንም  ዓይነት እምነት ላይከተል ይችላል፡፡ መብቱም ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን ሃይማኖት አልባነትን በግድ መንግሥታዊ  ሥርዓት ውስጥ በማጫፈር በእምነትና በሃይማኖት ጸንቶ የኖረን ሕዝብ በአንዴ እግዜርን ወይም አላህን ወይም የምታመልከውን  ሌላ መንፈሣዊ አካልን  ክደህ ኮሚኒስት ሁን ማለት የደርግን ብልህነት ሣይሆን ጅልነት የሚያሣይ ነበር – ሠለጠነች ቢሏት ጊዜ የባሏን መጽሐፍ ያጠበችውን ሴት ዓይነት ጅልነት፡፡ መጨረሻው ባለማማሩ ይከተለው የነበረውንም የአካሄድ ሥርዓት አይረቤነት በእግረ መንገድ መረዳት አይከብድም፡፡ እንዲያው ትዝ ብሎኝ ነው፡፡

ርዕሴን በእንግሊዝኛ ብጽፈው ኖሮ “The Age of Terrorists, Extremists and Deviants” በሚል እንዲነበብ አደርገው ነበር፡፡ ያለንበትን ዘመን ከየአቅጣጫው ስንቃኘው ጥቂት የማይባሉ አክራሪዎች፣ ተስፈንጣሪዎችና አሸባሪዎች ዓለማችንን እያተረማመሱ እንደሚገኙ መገንዘብ አያስቸግርም፡፡ ሌላውን ዓለም ለአሁኑ እንተወውና ወዳገራችን ተስፈንጣሪዎችና ምናምንቴዎች እንመለስ፡፡ በነሱ ነውና መቅኖ አጥተን የቀረነው – “ትንቢትሰ ይቀድሞ ለነገር” የምትለዋን ሐረግ እንድታስታውሱልኝ ግን ልማጠን፡፡

ትናንት አንድ ወዳጄ ቤቴ መጥቶ በላፕቶፑ ከዩትዩብ ያወረዳቸውን አንዳንድ ድንቃድንቅ ቃለ መጠይቆችና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች አስኮመኮመኝ፡፡ ሁለቱን ተስፈንጣሪዎችና ጠብ ጫሪዎች የተመለከትኩት በዚያን ጊዜ ነው፡፡ አንደኛው ተስፈንጣሪ መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ ይባላል፡፡ እኔን የታሪክ ተመራማሪ ያድርገኝና የታሪክ ተመራማሪ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ አፄ ቴዎድሮስን እንዴት አድርጎ እንደሚስላቸው ብታዩ ትደመማላችሁ፡፡ አበሻቅጦ፣ አበሻቅጦ  ነው የለቀቃቸው፡፡ ሲናገር ደግሞ ታሪክን እንደሚተርክ ሣይሆን በስሜት እየተወራጨና ክፉኛ እየተቆጣ እዚያው እቦታው ላይ ያለ ያህል ሆኖ ነው፡፡ የታሪክ ተመራማሪና ተንታኝ – በኔ ጥራዝ ነጠቅ ግንዛቤ – ትንታኔውንና ሀተታውን ማቅረብ ያለበት በጥላቻና በበቀል ስሜት እየተንዘረዘረ ሣይሆን የሆነውን ነገር እንዳለ በተረጋጋና አድልዖ በሌለበት ሁኔታ ነው – ታሪክ ነዋ! የዛሬ ሣይሆን የዱሮ ዘመን ድርጊት ነው፡፡ ዛር ከፈረስ የመሆን ወገንተኝነት ለታሪክ ተመራማሪ የሚፈቀድ አይመስለኝም፡፡ ይህ የታሪክ ተመራማሪ ግን አንድ ቦታ ሲናገር እንደሰማሁት አንሻፍፌም ቢሆን እጠቅሳለሁ፤ “ሀፄ ዮሐንስ ምኒልክን ቢያስሩት ኖሮ ጥሩ ነበር፡፡ መታሰር ነበረበት፡፡ ሀገር ከሃዲና ሻጭ ስለነበረ የሀፄ ዮሐንስ መኳንንትና መሣፍንት ‹ይህን ሰው ነገር ሳያመጣ እንሰረው› ሲሉ ሀፄው በምሕረት ማለፋቸውና ‹መኳንንቴ ሊያስሩህ ይፈልጋሉና አምልጣቸው› ብለው የሸዋን ንጉሥ እንዲያመልጥ ማድረጋቸው ትክክል አልነበረም፡፡…”  እኔ የታሪክ ተማሪ አይደለሁም፡፡ ባልሆንም ግን እንዲህ ያለ ጭራሽ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ የታሪክ ትንተናና ቅጥ ያጣ ዘረኝነት ስመለከት የምናደድና ምሁር ተብዬውን የምቃወም መሆኔን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴን የተቸበትንም መንገድ ስመለከት አዝኛለሁ፡፡ ባህሩ ዘውዴ ኢትዮጵያ በአጸደ ሕይወት ካሏት ብርቅ የታሪክ ተመራማሪዎች አንዱ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ሁሉም ነገር ለከት ሊኖረው ይገባል፡፡ ዐፄ ምኒልክንና ዐፄ ቴዎድሮስን ለማቋሸሽና በሕዝብ እንዲጠሉ ለማድረግ ይህን ያህል ዘመቻ ማድረግ ትርፉ ለጊዜው ትዝብት ብቻ ቢሆንም እውነቱ ባለበት ይኖራልና የማስተባበሉን ዋና ኃላፊነት ለባለሙያዎቹ መተውን መርጫለሁ – አልተከታተልኩ ሆኖ እንጂ በጊዜው መልስ ተሰጥቶበትም ሊሆን ይችላል፡፡ ሰውዬው ግን በግብዝነቱ አሳዘነኝ፡፡ ደግሞም ሁለት ፀጉር ያበቀለ እንደኔው ትልቅ ሰው ይመስላል፡፡ ለምን ይህን ያህል ርቀት ተጉዞ ራሱን ትዝብት ውስጥ ማስገባት እንደፈለገ አልገባኝም –  የእውነት አንጻራዊነት ደግሞ አስደነቀኝ፤ እውነት ሺህ ጊዜ አንጻራዊ ትሁን እንጂ ደግሞ ይህ ሰው ይህን ያህል ማፈንገጡ በሰዎች ተፈጥሮ እንድገረም አስገድዶኛል፡፡ ነገሥታቱን በዘራቸው ምክንያትም ይሁን በሌላ አይጥላቸው ወይም በግድ ይውደዳቸው ማለቴ አይደለም፤ ነገሥታቱ ምንም ጥፋት የሌለባቸው ምሉዕ በኩልሄ ናቸው ማለቴም አይደለም – ሰዎች እንደመሆናቸው እንደማንኛችንም ተራ ዜጎች ያጠፋሉ፤ ያለማሉም፡፡(በነገራችን ላይ ስለትግራይ ነገሥታትም ሆነ መሣፍንት እንዲሁም ስለ ዳግማይ ወያኔ የአስተዳደር በደል አንድም ነገር ትንፍሽ አላለም፤ ይህ ደግሞ ፍጹማዊ አድልዖና ወገናዊነትን ያሳያል፤ ምራቅ ከዋጠና ፈሪሃ እግዚአብሔር ካለው ጨዋ የትግራይ ሕዝብ የተገኘ የታሪክ ተመራማሪ እንዲህ ያለ ጭፍን አስተያየት ይሰነዝራል ተብሎ በጭራሽ አይጠበቅም – በኔ ግምት ንግግሩ ደመ-ሞቃታዊ ግልብ አስተያየት እንጂ በምርምር የተደገፈ እውነተኛ ታሪክ ነው ማለትም ያስቸግራል)፡፡

እኔ እምለው ታዲያ ጥላቻችንንም ይሁን ውዴታችንን የምንገልጽበት መንገድ አግባብ ይኑረው ነው ፡፡ ስንወድ፣ ስንወድ ሰዎች ባልዋሉበት ጦር ሜዳ ሺዎችን እንደገደሉና እንደማረኩ እያስመሰልን የምንኳሽ ፣ ስንጠላ ስንጠላ ደግሞ ጥቁሩን ነጭ፣ ነጩን ጥቁር እያደረግን ጥላሸት የምንቀባ ከሆነ አመክንዮታዊ ተፈጥሯችንን ገደል ከተትነው ማለት ነው፤ እንዲህ ስናደርግ ታሪክ ሣይሆን ኩሸትና ምናባዊ ገድል እየጻፍን ነው – እንደዚህ ያለ ነገር መጻፍ ወይ መናገር ካማረን ደግሞ በታሪክ ትምህርት አሳብበን ሣይሆን በልቦለድ ውስጥ ስሜታችንን መግለጽ እንችላለንና ወደዚያ መግባት ነው – የሰውዬው አካሄድ አህያን ተገን አድርጎ ጅብን እንደመውጋት ነው – ትልቅ የስብዕና ኪሣራ፡፡ ሰው የተባለ ፍጡር ደግሞ እንዲህ እንዲሆን አይጠበቅበትም፡፡ እንስሳ ብንሆንም ማሰብና ማመዛዘን የምንችል የሌሎች እንስሳት አለቃዎች በመሆናችን የማስተዋል ጥበብን እስከዚህን ድረስ በወረደ ሁኔታ ልንነጠቅ አይገባም፡፡ የዘረኝነትን ጭምብል አውልቀን፣ የሆድ አምላኪነትን ምኩራብ አፍርሰን፣ የጥላቻን ግምብ ንደን በሃቅ መፍረድ ካልቻልን ሰው መሆናችን ይቀርና በአንዲት አጥንት ሣቢያ የሰገሌን ጦርነት እንደሚያስታውሱን ውሾች እንሆናለን፡፡ ይህ ደግሞ ከንቱነትና እንደነቢዩ ሰሎሞን አነጋገር ንፋስንም እንደመከተል ያለ ሞኝነት ነው፡፡ ለምኑ ብለን? ነገ ጧት ሁሉም እርግፍ ብሎ ለሚቀረው? አቅል ጀባ መምህር ገብረ ኪዳን! ከጥቂት ጊዜ በኋላ ትግሬና አማራ ይቅርና የሰው ዘር በአጠቃላይ የሚበጠርበትና የሚበራይበት ዘመን ይመጣል፡፡ ያኔ እውነት የምትነግሥበት፣ ሀሰት የምትዋረድበት አዲስ ዘመን ይብታል፡፡ ያኔ ላለማፈር አሁን ትንሽ ስንቅ መያዝ ይገባናል፡፡ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ መስበሩን ካላቆመ ድንጋዩም ቅል ለመሆን እንደሚመኝ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ከኅሊና መታወር አምላክ ይሠውረን!

ታሪክ ሲጻፍ በስማ በለው ሊሆን አይገባም፡፡ የስማ በለው ታሪክ አፈ-ታሪክ(ሌጄንድ) እንጂ እውናዊ ታሪክ ሊሆን አይችልም፡፡ ታሪኩን ወደድነውም ጠላነውም እኛ ግን እንዳለ ማስተላለፍ ይኖርብናል፡፡ አንድ ሃኪም ጠላቱ ታሞ ቢመጣ በመርፌ ወይ በከኒና ሊገድለው እንደማይገባ ሁሉ(በሙያዊ ሥነ ምግባር ኮዱ መሠረት አስቀድሞ መሃላም ገብቷልና) አንድ የታሪክ ቅንጫቢም እኛ ጋ ሲደርስ ስለማንፈልገው ብቻ አንሻፈን መናገሩ ወይም መጻፉ እኛን ለትዝብት ከሚዳርገን ውጪ ታሪኩን አንሰርዘውም፤ እውነት አትሰረዝምና፡፡ ስለሆነም ያ አፈንጋጭ የታሪክ ሰው ራሱን እንዲመረምር በዚህ አጋጣሚ ልጠቁመው እወዳለሁ፤ የጎመን ጥጋብ ያልፋል፤ የጉሽ ጠላ ስካርም ይበርዳል፡፡ ለነገሩ እንኳንስ ብዙም የሚያስደስት ነገር የሌለው የኢትዮጵያ ታሪክ ይቅርና ሰማይና ምድርም ያልፋሉ – ሊያውም ይህም ሊሆን የቀረው ጊዜ ከአንድና ሁለት ሐሙሶች የሚዘል አይመስለኝም፡፡ ጤናማ አተያይ ለሁላችን እንዲያድለን ፈጣሪን እለምናለሁ፡፡ ደግሞስ አንዳችን አንዳችንን አበሻቅጠን የት እንደርሳለን፡፡ የሁላችንም ታሪክ በየራሱ የቆመ ሣይን እርስ በርሱ የተጋመደ ነው፡፡ ትግሬ ውስጥ አማራ አለ፤ አማራ ውስጥ ትግሬና ኦሮሞ ሌላውም አለ፡፡ ተማርን የምንል ወገኖች ግን አይፈጥሩ ጠብና ቅራኔ እየፈጠርን ደጉን ባላገር ባናምሰው ይሻላል፡፡ ማወቃችንን በቅጡ እናድርገው፡፡ ልሂቅነት ለዕልቂት ከበሮ ጉሰማ ሣሆን ለዕርቅና ለዕድገት አቅጣጫ ትለማ እናውለው፡፡ ኃላችንን ወደ ማፈርስ ሣይሆን ወደመግናበት አናዙረው፡፡ ጥላቻን መዝራት ይብቃን፡፡ ወደፍቅርና መተሳሰብ አምባ እንውጣና ሌሎች ያበላሹትን እኛ እናቃና፡፡ በተበላሸና በተሰባበረ መንገድ እየተጓዝን ቁስላችን ይበልጥ እያመረቀዘ የሚሄድበትን ሥልት ከመንደፍ ይልቅ በምንፈወስበት ዘዴ ላይ ጊዜና መላ አቅማችንን እናፍስስ፡፡…

ሌላው አፈንጋጭ ወይም ተስፈንጣሪ  ደግሞ ያ የሰንበት ጽንስ ተስፋየ ገብረ“ባብ” የሚባለው ነው፡፡ ይህን ሰው አደብ የሚያስገዛ ጠፍቶ ይሄውና ሽብልቁን እየቀበቀበብን ከኛም አንዳንዶቻችን የሚቀበቀብብንን ሽብልቅ ባለማጤን እያጨበጨብንለት መቃቃርንና ግጭትን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ እየነዛ ይገኛል፡፡ ሼክስፒር እንደሚለው – እጠቅሳለሁ – “To do a great right do a little wrong” እንደሚለው ይህን የእባብ ልጅና አለምነው መኮንን የተባለውን የዲያብሎስ ውላጅ በአንዳች ጥበብ የሚያስወግድ ኃይል ቢኖር በኔ በኩል ድጋፌን እንደማልነፍግ እገልጻለሁ – የንስሃ ዕድሜ እንዳገኝ ከመጸለይ ጭምር፡፡ ሰይጣንን ማስወገድ ወይም ቢያንስ አደብ ማስገዛት ከኃጢኣት አይቆጠርም ባይ ነኝ፡፡ ጠላትን መውደድ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ስትወደው የሚጠላህን መሠሪ ጠላት ከይሁዳ እንጂ ከተራ ጠላት አትመድበውም፡፡ እነዚህን መሰል ፀረ-ሰውና ፀረ-እግዚአብሔር  ግለሰቦች ሰባት ጊዜ ሰባ ብቻም ሣይሆን ሰባ ጊዜ ሰባት መቶ ያህልም ይቅር ቢባሉ ተፈጥሯዊ የፀላኤ-ሠናያት ባሕርያቸውን ሊያቆሙ አይችሉም – ተፈጥሮን ደግሞ ተመክሮ አይመልሰውም፡፡ ይሁዳ ምሕረትን እንደማያገኝ ክርስቶስ በአንደበቱ ተናግሯል – “የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፎ የሚሰጥ የወፍጮ መጅ ባንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቁ ባህር ቢወረወር ይሻለዋል” በሚል ልዩ አንደበታዊ ማኅተም፡፡ ስለሆነም ተስፋዬ ገብረባብና ይሁዳ አንድ ናቸውና ሞት ቢያንሳቸው እንጂ አያንሳቸውም የሚል እምነት አለኝ፡፡ ጨካኝ ሆኜ ግን እንዳይመስላችሁ፡፡ በፍጹም፡፡ ያጨከነኝ ሥራቸው  ነው፡፡

ተስፋየን ይሁዳ ያልኩበት ምክንያት የበላበትን ወጪት በመስበሩና ያደገባቸውን ሁለት ማኅበረሰቦች ለማጋጨት ከራሱ ይሁን ከሌላ ተቀብሎ የተሸከመውን ታሪካዊ ኃላፊነት ሳይታክትና ሳይሰለች እየተወጣ የሚገኝ የእፉኝት ልጅ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ የእምዬ ኢትዮጵያን ጡቶች እየጠባ ቢያድግም አሁን እንደ ቀትር እባብ እየተቅነዘነዘ የሚያደርገውን ስንታዘብ ሰውዬው በማንነት ኪሣራ የተዘፈቀና ያን ለመርሳት በሚያደርገው ጥረትም የሚሠራውን እንደማያውቅ ሰው ትልቅ ጥፋት እያደረሰ መሆኑን ነው፡፡ በውነቱ ሰውዬው በራሱ አንደበት እንዳረጋገጠውና በድረገፆች በተጋለጠው መታወቂያውም  እንደተመለከትነው ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ ካልሆነ ታዲያ ስለኢትዮጵያ ይህን ያህል አብዝቶ መጨነቁ ለምን ይሆን ብሎ መጠየቅ አግባብ ነው፡፡ እኔ ለምሣሌ ስለ ኬንያና ታንዛንያ ከሀገሬ በላይ እንቅልፍ አጥቼ አልጨነቅም፡፡ “የራሷ አርሮባት የሰው ታማስል” እንዲሉ ካልሆነ በስተቀር ተስፋየ ሀገሬ ናት የሚላት የቀድሞዋ የኛም ሀገር ኤርትራ ብዙ የልማትና የብልጽግና ሥራ እንዲሠሩላት እጆቿን ዘርግታ ልጆቿን እየተማጸነች በምትገኝበት ወቅት ይህ ሰው ስለኢትዮጵያ እንዲህ መባዘኑ ይገርመኛል፡፡ ይህ ሁሉ መቸገሩ አለነገር እንዳልሆነ ደግሞ ለብዙዎቻችን የተሠወረ አይደለም፡፡ አንድ ሰው እንቅልፍ አጥቶ ማደር ያለበት ስለራሱ ጉዳይ መሆን አለበት፤ ከዚያ ውጪ ግን ያልበላውን እንደማከክ ነው፡፡ የሚያስደንቀው ደግሞ ህ ሰው እየባሰበት እንጂ እየቀነሰለት ሲሄድ አለመታየቱና ደህና የሚባሉ ኢትዮጵያውያን ሣይቀሩ የጥፋቱ ተባባሪዎች እየሆኑ መምጣታቸው ነው፡፡ “ዘይገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈኔ” ማለት ይሄኔ ነው፡፡ ዘመነ ግርምቢጥ!

በትናንትናው የጓደኛየ የቪዲዮ ግብዣ ኦ.ኤም.ኤን(ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ) የተባለ የሚዲያ አውታር ያሠራጨውን አንድ ዝግጅት ተመለከትኩ፡፡ የቀድሞ ወዳጄ በፈቃዱ ሞረዳ ጠያቂ ጋዜጠኛ፣ ተስፋየ ገብረባብ ተጠያቂ እንግዳ ሆነው ነበር “እንግዳ” በሚል ፕሮግራማቸው ይህን ጉደኛ ውሉደ ዲያብሎስ ያሳዩን፡፡ በፈቃዱን ሳውቀው ኢትዮጵያዊ ሆኖ ነው፡፡ አሁን ግን ያነሰብኝ መሰለኝ – ግምቴ ትክክል ከሆነ ደግሞ በጣም ነው የማዝነውና የምጨነቀው – በተጣባን ሾተላይ እተክዛለሁ፡፡ በቃለ ምልልሱ እንደተረዳሁት ተስፋየና በፈቃዱ ቀደም ሲል ዐይጥና ድመት ነበሩ – ያ ጥሩ አልነበረም፡፡ ያስታረቃቸው ነገር ሲታይ በፈቃዱ በተወሰኑ ሰዎች ግፊት ምክንያት ዘረኛ እንዲሆን መገደዱን “የሚያበሥር” ግጥም በኢትዮጵያ ዛሬ ድረገፅ ተስፋየ አንብቦ የምኞቱን ሥኬትና የዓላማ መመሳሰል ካስተዋለ በኋላ ሁሉንም ቂሙን/ቁርሾውን እርግፍ አድርጎ በመተው በፈቃዱን ሊወደው እንደቻለ ነው፡፡ ይህ ፍሩዳዊ የምላስ ወለምታ – ኧረ ግልጽ ነው  የምን ወለምታ – የሚያሳየን ተስፋየ የሚፈልገው ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ዜጋ እየተነሣ በየፈፋውና በየጢሻው በመውረድ ፍጹም ዘረኛና አንዱ ከአንዱ የማይስማማ ሌባና ፖሊስ እንዲሆን መሻቱን ለዚያ ዓላማ ሥኬትም የማይፈነቅለው ድንጋይ አለመኖሩን ነው፡፡ ይህ “የሰው ሀገር ሰው”  የራሱን የማንነት ኪሣራ ችግር ሳያስወግድ በበጎች መሀል እንደገባ ተኩላ ኢትዮጵያን ለመበታተን የሚጥሩ ታሪካዊ ጠላቶችን እያገለገለ የሚገኝ ሁለት አፍ እንዳለው ሠይፍና ጎራዴ ሊታይ የሚገባው መሠሪ ጠላት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ አደገኛ ሰው በእንጭጩ ካልተቀጨ – አሁንና ዛሬ ‹እንጭጭ› የሚልን ቃል መጠቀም ከቻልኩ – የዞረ ድምሩ ከባድና በቀላሉም የማይፈታ ነው፡፡

ስለተስፋየ አንዲት ነገር በምሳሌ ልናገር፡፡ እንደዛሬው ሣይሆን በዱሮው ዘመን ጦጣን የሰው ልጅ ይይዛታል፡፡ ከሰው ጋር የከረመችዋን ጦጣ ዘመዶቿ ጋር እንድትቀላቀል ወደ ጫካ ቢሰዷት እርሷ ዕውቀቷ አነስተኛና ጦጥኛ  በመሆኑ ልትቀላቀል ትሄዳለች፡፡ ነገር ግን በዚያን ደግ ዘመን ማኅበረጦጣ ያቺን ከሰው አምልጣ ወይም ነፃነቷን በሰዎች ይሁንታ አግኝታ የመጣች ጦጣ በቡጢና በክርን እየደለቀ ያባርራታል እንጂ አያስጠጋትም፡፡ ምክንያቱም ሰው ሰው ትሸታቸዋለችና የነሱ ቅርጽ ቢኖራትም በጠረኗ ምክንያት አያስጠጓትም፡፡ የሁለት አገር ሰው ፣ የሁለት አገር ፍጡር መሆን ዕዳ እንግዲህ እንደዚህ ነው – አጣምሞ እንዳይፈጥር ከመጸለይ ውጪ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ሁሉም በጥርጣሬ ዐይን ስለሚመለከተው የማንነት ቀውስ ውስጥ ይዘፈቅና ከሚደርስበት ሥነ ልቦናዊ ችግር  የተነሣ የወንጀለኝነትን ባሕርይ በቀላሉ ይላበሳል፡፡ ከዚያም የራሱ ጤናማ ኅሊናና ቀና አስተሳሰብ ስለማይኖረው እንደጠፍ አህያ ያገኘው ሁሉ የፈለገውን ይጭነዋል፤ ወደፈለገውም ይልከዋል፡፡ ሲላላክም መጠነኛ መቁሽሽ ስለሚሰጠው ስለሚያገኘው ድርጎ እንጂ ስለሚሠራው ዕኩይ ተግባር ቅንጣት አይጨነቅም – የሞራልና የሃይማኖት ዕሤቶችም ስለሌሉት ሕይወቱ በብዙ መልክ የተሰነካከለ ነው፤ በመጠጥ የሚናውዝ፣ በሴሰኝነት ካገኘው ጋር የሚከንፍ፣ በቃላባይነት ሁሉንም የሚያስቄም ከንቱ ዜጋ ሆኖ ይቀራል፡፡ ይህ ዓይነት ሰው እንደነዱሽ ነው – ልክ እንደሮቦት፡፡ ይህን መሰል ሰው ወደኅሊናው በቀላሉ አይመለስም፡፡ ቢመለስም ምናልባት እንደይሁዳ ራሱን ይገድል ይሆናል እንጂ በንስሃ ታጥቦና ተጸጽቶ ጥሩ ሰው የመሆን ዕድሉ በዜሮና በአንድ የመቶኛ ስሌት ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ከዚህ ይሠውር ውድ ወገኖቼ፡፡ በሀገራችን ስንትና ስንት እንደነዱሽ ቀፎ ራስ ሞልቷል መሰላችሁ! ሆዱ ከሞላ እናቱንም፣ሚስቱንም፣ ልጆቹንም ባወጡ የሚሸጥ ገነት ዘውዴንና አለምነው -ገዱ –  ልደቱ አያሌውን የመሰለ ብኩን ዜጋ ሞልቷል፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ እነዚህን “ሰዎች” ሳስብ ሰው ሆኜ መፈጠሬን እጸየፋለሁ፡፡ የጠራ ድህነት ወርቅ አይደለም እንዴ እባካችሁ!

ተስፋየ አቅሉን ስቶ የሚራወጠው ኢትዮጵያውያንን ለማደባደብ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ የነበፈቃዱ ዓላማ ግን ብዙም አልገባኝም፡፡ “ያልወለድኩት ልጅ ቢለኝ አባባ፣ አፌን አለው ዳባ ዳባ” ይባላል፡፡ ዛሬ ከመሬት ተነስቶ ተስፋየን “ኦሮሞ ነህ” ማለት መንስኤው ግልጽ ቢሆንም ውጤቱን ግን ማጤን ያስፈልግ ነበር፡፡ ተስፋዬ ለዓላማው ሥኬት ካዋጣው ልክ እንደወያኔ የማይሆነውና የማያደርገው ነገር የለም፡፡ የማርስና የቬኑስ ዜጋ ነህ ቢሉትም በደስታ ይቀበላል – እንዲህ ዓይነቱ ነገር በጣም ይስማማዋል(የቬኑስ ዜጋ እንኳን አሁንም ነው – ቬነስ ከወሲብ ጋር እንደምትገናኝ አስቡልኝ፤ ቬኔሪያል ዲዚዝ … ምናምን ከዚያ የመጣ ነው ይባላል፤ የሼክስፒርን ምናባዊ ፍጡር ሸፍጠኛውን ሻይሎክም (በቬኑሱ ነጋዴ ተውኔት) አስታውሱ)፡፡ ይህ ዓይነቱ “ማዕረግ” ለስንኩል ዓላማው ትልቅ እገዛ ያደርግለታል፡፡ ብዙም ባልተማረው ማኅበረሰባችን ውስጥ እንደዚህ ዓይነት የጭቡ ሥራ ምን ዓይነት ዳፋ ሊያስከትል እንደሚችል የቲያትሩ ደራሲያን ሊያስቡበት በተገባ ነበር፡፡ የሚያጣላ አላጣንም፡፡ የብሔር ማንነት ካባ ሳይደረብለት የሚያቆራቁሰን ሞልቶ ሳለ ይህን አሸባሪ ሰው – ይህን ተስፈንጣሪ ወጪት ሰባሪ – ይህን የአእምሮ በሽተኛ ሰው “ኦሮሞ ነህ” ማለት ትርጉምም ስሜትም የሚሰጥ አይደለም፡፡ ቀን ሲያልፍ የሚያስተዛዝብና እሳት የማያጫጭር፣ የማያቀባብርም አጉል ድርጊት መሥራት ሞኝነት ነው፡፡

በፈቃዱ ሞረዳም ትልቅ ሰው ነው፡፡  በጣም የማከብረውና በጦማር ጋዜጣው ስለእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ብዙ የደከመ ሰው ነው፡፡ ጉድና ጅራት እንዲሉ ሆኖ አሁን በማንኛውም ምክንያት ይሁን ወደታች ወርዶ ፈፋ ውስጥ ተወሽቆ ከሆነ ከምር አዝናለሁ፡፡ “የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ሉካንዳ ደጅ ታዬ” እንዲሉ ካልሆነ በስተቀር ወደላይ መሄድ ቢያቅት እንኳን ባሉበት መቆየትም ትልቅ ጠጋ ነው፡፡ ሰዎች ሰዎችን ለማሳሳት ሆን ብለውም ሆነ ሳያውቁ አንዳንድ ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ እነሱን በጭፍን ከተከተልን ገደል እንገባለን፡፡ እርጥቡን ከደረቅ እየለየን በአስተውሎት ከተራመድን ግን ጊዜ ይፍጅ እንጂ የተሳሳተን ለማረምና ወደ ፍጹም ሰውነት ለመቅረብ ይቻለናል – ፍጹም መሆን በሒሣባዊ ትወራ ይጠጌ አይነኬ ቢሆንም፡፡ ታጥቦ ጭቃ መሆን በታሪክም ይሁን በትውልድ ራስን ዝቅ ያደርጋል፡፡ የበላሁትን ቁርስ ያህል የማውቀው ፍቄ እንዲህ ሆኖ ከሆነ ለማመን ብቸገርም እንደሚመለስ ግን ተስፋ አለኝ፡፡ እርግጥ ነው – ተስፋ መቁረጥ ብዙ ዕዳ ውስጥ እንደሚከት አላጣውም – ቢሆንም ፍቄን በዚህ ጠርጥሬው አላውቅም፡፡ በሥነ ግጥሙ እንደተረዳሁት “በነሱ ግፊት እኔም ዘሬን አሽትቼ ወደዘሬ ተቀላቀልኩ” የሚለው አስተሳሰብ ደግሞ አይሠራም፡፡ እንደተስፋየ አጠራር ኢትዮ-አማሮች የሚባሉት “አክራሪዎች” የፍቄን ጽኑ አቋም አናግተውት ከሆነ ስህተቱ አሁንም ከፍቄ ራስ አይወርድም፤ እንዲያ ከሆነ ዱሮም ፍቄ ባላመነበት ኢትዮጵያዊነት ይዳክር ነበር ማለት ነውና፡፡ ለመሆኑ እነሱ እነማን ናቸው? ስንትስ ናቸው? እነሱ ዘረኛ ቢሆኑ እኛስ ስህተትን በስህተት ልናስተካክል ይገባናል ወይ? የምወደው ፍቄ ያስብበት፡፡ ይህን የምለው በተመለከትኩት ቃለ ምልልስ በግልጽ ሣይሆን በ“ሦስተኛው ዐይኔ” አማካይነት የተገነዘብኩት አንዳች ነገር ስላለኝ ነው፡፡ ግጥሚቱ ቀላል መልእክት አይደለም የታቀፈችው፡፡ “ዘረኛ ሆነው ዘረኛ አደረጉኝ” ትላለችና፡፡

የሁለቱ ሰዎች መታረቅ ደስ ይለኛል፡፡ የታረቁት በፀረ-ኢትዮጵያዊነት የዓላማ ቁርኝት ከሆነ ግን ዕርቃቸው አሳሳቢ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የሀገራችን ችግር የዘር አይደለም፡፡ ችግራችን የዴሞክራሲ ዕጦት ነው፤ የመልካም አስተዳደር ዕጦት ነው፤ የተማረና የተመራመረ ዜጋ ሥልጣኑን ያለመያዝና ሕዝባዊ ወደሆነ የዕድገትና ብልጽና አቅጣጫ ያለመግባት ችግር ነው ለዘመናት የተጠናወተን፤ የማይምነት መንሠራፋት ነው አበሳችን፤ የሆዳምነት መንገሥ ነው ችግራችን፤ የራስ ወዳድነት መንፈስ የሃይማኖት ያህል መስፋፋት ነው ራስ ምታታችን፤ በሙስናና በጉቦ መበስበስ ነው ናላ የሚያዞር ማኅበራዊ ነቀርሳችን፡፡ ዘረኝነቱ ጎልቶ የታየው ካለፉት 24 ዓመታት ወዲህ እንጂ ቀደም ሲል ይህን ያህል አሳሳቢ ችግር አልነበረም፡፡ ያገኛትን ትንሽ ቀዳዳ ተጠቅሞ ጎጃሜ ጎጃሜን ዌም ጎንደሬ ጎንደሬን   ቢቀጥር፣ ሐረርም ሐረሬን ወለጋም ጊምቢንና ነቀምቴን ይስብ ነበር፡፡ ሁሉም በየፊናው የፈለገውንና የመሰለውን ያደርግ ነበር እንጂ አንድ ዘውግ ተለይቶ የሚወቀስበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም፡፡ ይልቁንስ ፈታ እንድትሉ አንድ ቀልድ ቢጠየ ላስታውሳችሁ ከፈለጋችሁ፡- አንድ ኦሮምኛ ተናጋሪ ጄኔራል ወታደር ለመሆን ያመለከቱ ተመዝጋቢ ወጣቶችን በተርታ አሰልፈው የቅጥር ፎርም ለማስሞላት ወደግቢ ያስገባሉ አሉ፡፡ የሚያስገቡት ታዲያ ኦሮሞ ኦሮሞውን እየመረጡ ነው አሉ፡፡ ስማቸውን ሲጠይቁ ታዲያ ተሰላፊው ስሙን “ደቻሳ” ሲል ጄኔራሉ  “ግባ”፣ “ጉርሜሣ” ሲል “ግባ”፣ “ፈይሣ” ሲል “ግባ”፣ “መልካሣ” ሲል “ግባ”፣ “ድንቄሳ” ሲል “ግባ” … “ዓለማየሁ” ሲል “ውጣ”፣ “ስንሻው” ሲል “ውጣ”፣ “ደምመላሽ” ሲል “ውጣ” … እያሉ ሲያስገቡና ሲያስወጡ የታዘበ አንድ “ተንኮለኛ” አማራ እውነተኛ ስሙን ትቶ “እኔሳ” ሲል “ግባ” አሉት እየተባለ በጨዋታ መልክ ሲወራ ሰምቻለሁ፡፡ ነገሩ እንዳልኳችሁ ጨዋታ ነው፡፡ ግን እሳት በሌለበት ጪስ የለምና ይህ ዓይነቱ የዘርና የቋንቋ ልዩነት አልነበረም ብሎ መካድ ከእውነት መራቅ ነው፡፡ ይህን ነገር ታዲያ ሙሉ በሙሉ በአማራ ላይ ብቻ ማላከክ ትልቅ ነውረኝነት ነው፡፡ ሁሉም ያደርገው ነበር፡፡ ሁሉም ተሰዳድቧል፤ ሁሉም ተፈቃቅሯል፤ ሁሉም ተጎሻምጧል፤ ሁሉም በጋብቻ ተሳስሯል፤ ሁሉም አማራ ሆኗል፤ ሁሉም ትግሬ ሆኗል፤ ሁሉም ኦሮሞ ሆኗል፤ በጥቅሉ ሁሉም ሁሉንም ሆኗል፡፡ የትኛው ከየትኛው ይበልጥ ተሰድቧል ወይም ተበድሏል ብሎ ለመፍረድ ደግሞ መሥፈሪያ ቁና ወይም መለኪያ ሚዛን ያስፈልጋል፡፡ ያን ለማድረግ ደግሞ አስፈላጊነቱ አይታየኝም፡፡ ወደፊት መሄድ እየተቻለ ጉድጓድ መቆፈርና ስላለፈ ታሪክ መነታረክ ለምን አስፈለገ? “በቅሎ አባትሽ ማነው” ስትባል “እናቴ ፈረስ ነች” ያለችውን መለሳዊ ያልተገናኝቶ መልስ እናስታውስና ይልቁናስ የሚያዋጣን ነገር ወደኋላ መሮጥ ሣይሆን ወደፊት መገስገስ ነው፡፡ በዱሮ ታሪክ ማላዘን ሥራ-ፈትነት ይመስለናል፡፡ ሥንፍናና ድንቁርናም ነው፡፡ ከዘመን ጋር ለመራመድ ያለመቻል የአስተሳሰብና የአመለካከት ደካማነትም ነው፡፡

ተስፋየ እንደትልቅ ችግር ያነሳውና እርሱ መፍትሔ እንደሰጠው የጠቀሰው በእስካሁን የኢትዮጵያ ልቦለዶች ውስጥ አንድም የኦሮሞ ገጸ ባሕርይ አለመኖሩ ነው፡፡ እዚህ ላይ ከማስገረምም አልፎ አስቆኛል፡፡ በቡርቃ ዝምታና በሌሎች የዐዞ ዕንባ አጉራፊ ድርሰቶቹ የፈጠረውን ክፍተት ይበልጥ ያሰፋ መስሎት ይህን ቢልም ለዚህ ድምዳሜ ያበቃውን የጥናት ውጤት ግን አልገለጸም፡፡ በብዙ ሺዎች የሚገመቱትን የኢትዮጵያ ልቦለዶች ሁሉንም አንብቦ እንዲህ ሊል እንደማይችል መቼም ግልጽ ነው፡፡ ደግሞም ደራሲያን የኦሮሞ ስም እንዳይጠቀሙ የከለከለ አንድም የቀድሞ መንግሥት አላውቅም፡፡ ይህ ወዘና የሌለው ጠብ-ጫሪ ሃሳቡ ብቻ ይህን ተስፋየ የሚባልን ጋኔን ለማውገዝና አክ እንትፍ ብሎ ለመጣል በቂ ነው፡፡

በዱሮ ጊዜ እኔም ነበርኩ፡፡ ስምን በሚመለከት ከመንግሥት ጋር ምንም ትስስር በሌለው ሁኔታ ኅብረተሰቡ ራሱ በልማድ የሚተገብረው የስም አወጣጥ ሂደት ነበር፡፡ የኔ የአክስቴ ልጅ ለምሣሌ ከአማራው አካባቢ ስትመጣ የነበራት እገሊት የሚባል ስም አዲስ አበባ ላይ ስለሚያስቅባት ለውጣለች – ትሠራ የነበረችውም ቡና ቤት ነው ፤ የብዙዎች አማሮች ሴቶች የመጨረሻ መዳረሻ ሴተኛ አዳሪነት ነበርና፡፡ ያኔ አማራ መሆን የተለዬ ጥቅም አያስገኝም ነበር፤ እኔ ራሴ የአማራ ዝርያ እንዳለብኝ የተረዳሁት ብዙ ዘግይቼ በ83ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ቢሆንም የስም ለውጥን በተመለከተ እኔ ራሴ ከመጀመሪያ ስሜ አንዷን ሆሄ ከግዕዙ ወደ ራብዕ ፊደል በገዛ ሥልጣኔ ለውጫታለሁ – ዘመናዊ ለመባል፡፡ እነሸንተሞ፣ እነየዝና፣ እነጓንጉል፣ እነ አዝብጤ፣ እነአንጓች፣ እነጠጂቱ፣ እነወርቅያንጥፉ፣ እነግምብወግሽ፣ እነጉማታ፣ እነባንችይርጉ፣ እነታንጉት፣ እነጉዝጉዝ፣ እነጣፈጡ፣ እነማንጠግቦሽ … ስንቱን ጠቅሼው… እነዚህ አማሮች ሁሉ አዲስ አበባ ሲገቡ ስማቸውን ለመለወጥ ይገደዱ ነበር – “ዝናር ባንገቴ”ና “ዱቤ ክልክል ነው” የሚያስብልባቸውን የአንገትና የፊት ንቅሳታቸውን ለማጥፋት ስንቶች አማራ ሴቶች ገላቸውን በማስፈቅፈቅ መከራቸውን ያዩ ነበር፡፡ ስማቸውንና የፊት ገጽታቸውን እንደዘመኑ ማድረግ ካልቻሉ ደግሞ ከብት ባልዋለበት ኩበት ለመልቀም እየታከቱ የሚገኙት አዛኝ ቅቤ አንጓቾቹ እነተስፋየ እንደሚሉት መንግሥታዊ ተፅዕኖ ኖሮ  ሣይሆን ማኅበረሰቡ ራሱ ስለሚስቅባቸው ክፉኛ ይሳቀቁ ነበር፡፡ መንግሥትማ እንዴት ስምን ቀይሩ ሊል ይችላል? ኦሮሞና አማራው አጤ ምኒልክ፣ ጉራጌ፣ አማራ፣ የመኑና… ኦሮሞው አጤ ኃይለ ሥላሴ፣ አማራና ኦሮሞው መንግሥቱ ኃ/ማርያም፣ ተጋሩ አኅዋትና ፍስሐ ደስታና ጄኔራል አማን አንዶም፣ … በምን ድፍረታቸው ዜጎችን ከዚህ ወደዚያ ወይም ከዚያ ወደዚህ ስማችሁን ቀይሩ ሊሉ ይችላሉ? አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ ነው ነገሩ፡፡ ኤዲያ! ምን ዓይነት ጊዜ ላይ ደረስን ጎበዝ፡፡

ከዚህ መሠረታዊ ጭብጥ አንጻር የወለጋው ሰርቤሳ አዲስ አበባ ሲገባ ወይም የአርሲዋ ጫልቱ ናዝሬት ስትደርስ ኤርምያስና ሉሊት ብለው ስማቸውን ቢቀይሩ ተወቃሹ ማን ነው? ዕቁብ ያልበላን ሰው፣ ዕቁብ ስለመኖሩም የማያውቅን ሰው “የበላኸውን ዕቁብ ውለዳት!” ብለው በማይገባው ነገር ቢከሱትና ቢያደነቁሩት ምን ዋጋ አለው? ፍርድ ከራስ ነውና አማራ ያልሆናችሁ ሰዎች በተለይ ፍረዱኝ፡፡ የዚህን የተስፋየ ገብረባብ ሥውር ተልእኮ ደግሞ አስተውሉልኝ፡፡ ጊዜው የፈቀደው ፋሽን ሆኖ እንጂ ይህ የፈረደበት አማራ ያመጣው ፈሊጥ ሆኖ አልነበረም – አማራ እንደአማራ ሣይሆን በስሙ የነገዱና አሁንም ድረስ ሊነግዱበት የሚቋምጡ ጥቂት ቆሻሻ ዜጎች የሉም ለማለት እንዳልፈለግሁ ግን ተረዱልኝ፤ ክፋትና ደግነት በብሔረሰብና በብሔር የሚገደብ አይደለም፡፡  ደግነቱ “ሥራ ለሠሪው እሾ ላጣሪው” እንዲሉ ሁሉም ክፉዎች ዜጎች በጊዜያቸው የሥራቸውን ያገኛሉ – እንደመለስ ዜናዊና መሰል የከይሲው ልጆች፡፡ እነተስፋየ ተሟጋችና ተከላካይ የለውም ብለው በወደቀ ግንድ ላይ ምሣር ለመቀብቀብ ሌት ከቀን የሚተጉት ዘመናቸው የሰጣቸው ሰይጣናዊ ኃላፊነት በመሆኑ ሕዝብን  መከፋፈልና ማበጣበጥ ከዚያም የተላኩበትን መሠሪ ተልእኮ ሲፈጽሙ ከሀገራችን ግልጽና ድብቅ  ጠላቶች  የሚሠፈርላቸውን ድርጎ መቀበል ዓይነተኛ ሙያቸው ስለሆነ ነው፡፡ እነዚህ አፈንጋጮች ፀሐያቸው መጥለቋ አይቀርም – የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ደህና የነበርን ሰዎች ግን ከተስፋ መቁረጥ ተቆጥበን ታሪክ የሚያሳየንን ተዓምር በትግስት እንጠብቅ፡፡ ቀኑ ደርሷል፡፡ የነፃነትን መባቻ ቀን የሚያውቅ አንድዬ ብቻ ቢሆንም ቀኒቱ መቅረቧን የምንገነዘብባቸው ብዙ ምልክቶችን እያየን ነው፡፡

ሰማይ ክፉኛ ሲጠቋቁር፣ ደመናው ሲከብድ፣ ጭቆናውና እንግልቱ፣ ስደቱና ሰቆቃው ሲበረታ የቀኑን መቅረብ መገመት እንችላለን፡፡ የኢትዮጵያ ሰማይ ጭጋግ መልበስ ጀምሯል፡፡ ተራሮች ደም ቋጥረዋል፡፡ ሸለቆዎች አንዳች ነገር ሊያፈነዱ አቆብቁበዋል፡፡ ወንዞችና ሐይቆች አኩርፈዋል፡፡ … እንደቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ልበልና ልጨርስ – “የቆምን የሚመስለን ይበልጥ እንጠንቀቅ፤ የተቀመጠውን የሚያሳስበው መውደቅ የለምና፡፡” ለማንኛውም ልብ ይስጠን፡፡ እያለንም ሞተንም መኖር እንድንችል ለሚያደርገን አኩሪ ተግባር እንጂ እያለንም ሞተንም የሞት ሞት እንድንሞት ለሚያደርገን አስነዋሪ ድርጊት እንዳንጋለጥ ተግተን እንጸልይ፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

yiheyiseaemro@gmail.com

happy-easter

The post የአክራሪዎች፣ የተስፈንጣሪዎችና የአሸባሪዎች ዘመን – ይሄይስ አእምሮ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኹራፋተ አምሳሉ ፡- መረጃና ማስረጃ አልባው እንቶፈንቶİ –ዲ/ን ዶክተር መሐሪ ወሰን /ከጅማ/

$
0
0

ዶክተር ደረጄ ዓለማየሁ ይባላሉ፡፡መጋቢት 1992 ዓ.ም. ‹‹ በአጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ፡- መኢሶን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ውስጥ›› በሚል ርእስ በአቶ አንዳርጋቸው አሰግድ ተዘጋጅቶ በታተመው መጽሐፍ ውስጥ የጽሑፍ ድርሻ ነበራቸው፡፡ ይኸውም መቅድም መጻፍ ነበር፡፡ በጻፉት መቅድም ውስጥ በጥላቻ ቁመናው ከኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ጋራ ተመሳሳይ የሆነ ሰውን የጥላቻ ክርክር ጠቅሰዋል፡፡ እንዲህ ጽፈውታል፡፡

በደርግ ዘመን በየጊዜው ጤፍ ከአዲስ አበባ ይጠፋ እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡ በዚያው ዘመን ከአንድ የማውቀው (የተማረ) ሰው ጋር ጨዋታ ጀመርንና ጤፍ የጠፋው በአንቶኖቭ እየተጫነ ወደ ሶቭዬት ኅብረት ስለሚጓዝ ነው፤ አለኝ፡፡ ‹‹ራሽያኖች እንጀራ መብላት ጀመሩ እንዴ?›› ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ‹‹አይ ለቮድካ ሊጠቀሙበት ነው፤አለኝ›› መልሶ፡፡ ‹‹ኧረ ተው ኢትዮጵያ ውስጥ በዓመት የሚመረተው ጤፍ በሙሉ ወደ ሶቭዬት ኅብረት ቢጋዝ እዚያ በአንድ ቀን የሚወጣውን ቮድካ ለመጥመቅ አይበቃም፤›› አልኩት፡፡ ‹‹ አይ እንደ ቅመም ሊጠቀሙበት ነው አሉ፤›› አለኝ፡፡ ‹‹ተው እንጂ እንደ ቮድካ፣ እደ ውስኪ ያሉት ስመ ጥሩ መጠጦች ሲጠመቁ ዋናው ጥበብ እኮ ለዘመናት ተለምዶ የቆየ ጣዕማቸው እንዳይቀየር ማድረግ ነው፤ ስለዚህ ገና ያልተለመደ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኝ ቅመም ለመጨመር ምክንያት የሚኖራቸው አይመስለኝም፤ ብዬ ይህን የማይረባ ክርክር ዘጋሁ፡፡ (ደረጀ፤1992፣2)

በዚያን ወቅት ከዚህ ሰው ጋር ሶቭዬት ኅብረት በዓለም አቀፍ ደረጃና በተለይ በሀገራችን የምትከተለውን ፖለቲካ በሚመለከት ተቃሞውን (ኧረ እንደውም ጥላቻውን) ለመጋራት ችግር አልነበረብኝም፤ የሚሉት ዶክተር ደረጄ ዓለማየሁ፤‹‹ለእኔ ግን ይህን አቋም ለማጠናከር ሩሲያን በጤፍ ሌብነት መክሰስ አያስፈልገኝም ነበር፡፡ ይህ ወዳጄ ግን ለሩሲያ ተቃውሞውና ጥላቻው በምንም ላይ ያልተመሠረቱ ግምቶችን ጭምር መሰብሰብ ነበረበት፡፡ ከዚያም አልፎ ሩሲያ የተወሰነው የዓለም ክፍል ጨቋኝና በዝባዥ ነች፤ የጤፍ ሌባ ግን አይደለችም፤ ያለውን (ሁሉ) በሶቭዬት ኅብረት ደጋፊነት ከመክሰስ አይመለስም ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹መረጃ ላይ መመሥረት ያለበትን ታሪክ ነክ ወይም ፖለቲካ ነክ ክርክር ከእንደዚህ ዓይነት ሰው ጋር ማካኼድ አይቻልም›› ሲሉም አክለው ያስረዳሉ፡፡ (ደረጀ፤1992፣2)

ከዚህ አኳያ ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ከዶክተር ደረጄ ዓለማየሁ ወዳጅ የሚለየው፤ ከዐሥራ ሁለተኛ ክፍል የዘለቀ ትምህርት የሌለው የትምህርት ሽፍታ፣ በሠዓሊነቱም ስሙን እንደማዓረግ ይጠቀምበት ካልሆነ ከተግባሩ የሌለበት እና አማተር ፖለቲከኛ መሆኑ ብቻ እንጂ በጥላቻ ቁመናው በእጅጉ ይመሳሰላል፡፡

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የቱንም ያህል የሥርዓቱን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ጠላትነቱን የሚገልጹ ጽሑፎች ቢጽፍም፣ ቃለ መጠይቆችን ቢሰጥም፣ በኹራፊው አምሳሉ ደረጃ ወርዶ ወያኔን ‹‹የጤፍ ሌባ ነው›› ዓይነት ክስ እስካልከሰሰ ድረስ፤ ዳንኤልን በወያኔነት ከመክሰስ የማይመለስ ኹራፊ መሆኑን የሚያጋልጡ ሦስት ጽሑፎችን ከሰሞኑ አነበብኩ፡፡ የመጀመሪያው ‹‹ በአይሁዶች መርዘኛ ጥርስ የገባች ሀገር ኢትዮጵያ ! ››በተሰኘ ፀረ ሴማዊነት ርእስነት የለጠፈብንን ነው ፡፡ ሁለተኛ ‹‹የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጠላት ስውሩ ተኩላ ዳንኤል ክብረት›› በሚል ድልዝ ‹ርእስነት› የለጠፈውን የሐሳብ ውራጅ ሲሆን፤ ሢሰልስ ደግሞ ‹‹ዳንኤል ክብረትና ሌላው የወያኔያዊ ተግባሩ መግለጫ›› በሚል የተደባጨ ‹ርእስነት› የሰነቀረውን የአስተሳሰብ ስብራቱ ነው፡፡

በሐሳብ ውራጅ እና በአስተሳሰብ ስብራት ውስጥ የሚገኝ ኹራፊ ፍጥረት መሆኑን ያጋለጠበትን ቁርጥራጮች አንብቤ ስጨርስ ሦስት ዓይነት ስሜቶች ተሰምተውኛል፡፡ የመጀመሪያው የሐዘን ነው፡፡ የወያኔን የጥፋት ሥርዓት በተላላኪነትና በአስተኳሽነት እያገለገሉ የሚገኙት እንደ አምሳሉ ገብረ ኪዳን ዓይነት ኹራፊዎች ለቤተ ክርስቲያኒቱ ልዕልናና ክብር መመለስ አበክረው በሚታገሉት እንደ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያሉትን ቁርጥ የቤተ ክርስቲያንና የሃገር ልጆች በወያኔነት ሲፈርጆ ማየት እጅግ ያሳዝናል፡፡

ሁለተኛው የመደነቅ ነው፡፡ ትናንት ከአጉራ ዘለል ባሕታውያን ነን ከሚሉት ጋራ፣ ዛሬ ደግሞ አሸናፊ መኮንንን ከመሳሰሉት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንና ውጉዛን ጋራ በመወዳጀት የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረተ እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ትውፊትና ታሪክ በስውር እየቆነጻጸለ፣ እየቀሰጠ የሚገኘው ጎጠኛው አምሳሉ ገብረ ኪዳን፣ የዘመናችን ርቱዕ ሃይማኖትና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ጠበቃ የሆነውን ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን በሀገርና በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጠላነት ፈርጆ ሃይማኖቱን ሲጠራጠር ከመመልከት በላይ ምን ይደንቅ?

ሦስተኛው ደስታ ነው፡፡ ደስታው ደግሞ ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው ኹራፊው መምህራችንን ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን አጋጣለሁ ብሎ በጻፈው ቁርጥራጭ ራሱን ማጋለጡ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ራሱን በፀረ ወያኔነት ቆብ የገለጠው አምሳሉ ከማኅበረ ቅዱሳን አባላት እስከ ኤልያስ ገብሩ ያሉትን ወንድሞች እንዲሰልል የተሰጠውን ተልእኮ ሳይጨርስ፤ ከዚህ በኋላሰለአርሱ በተከታታይ እንድንጽፍ ምክንያት የሆነችውን አብሪ ጥይት ተኩሶ እኛን በመጋበዙ ነው፡፡ እነዚህ ሦስት በተጨባጭ እውነታ የተመሠረቱትን ስሜቶቼን ከግንዛቤ በማስገባት ለዛሬ በዋናነት ሦስቱን ቁርጥራጭ ‹‹ጽሑፎቹን›› ከእውነትነት፣ ከታሪካዊ ሁነት፣ ከቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ከፖለቲካዊ ቅሌት አንፃር ብቻ በመፈተሽ ተጋላጩ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ወይስ ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን የሚለው ወሳኝ ጥያቄ በመመለስ ጽሑፌን እደመድማለሁ፡፡

1 – በተቆርቋሪነት መለዮ የተሰነቀረ ኑፋቄ!

ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት አስመልክቶ በፌስ ቡክ ገጽ ላይ፤     ‹‹ … የመውለጃዋ ጊዜ በደረሰ ጊዜ ጌታዋ ፈጣሪዋ የኋላ ልጇ ለመለኮታዊ ክብሩ፣ ለልዑልነቱ፣ ለሁሉን ቻይነቱ፣ ለፈጣሪነቱ፣ ንጹሕ ነገር ፈላጊ፤ ለንጹሐ ባሕርይነቱ በምትስማማ መልኩ ምንም ምክንያት እንዳይገኝባት አድርጎ ንጹሕ ጽዱ ፍጹም ቅድስት አድርጎ ፈጥሮ አዘጋጃትና ሰዓቱ ሲደርስ ያንን ንጹሕ ፍጹም ጽዱ ሥጋዋን ወርሶ ተወለደባት ፤ በዚህ ሥጋውም ዓለሙን ሁሉ ተቤዠው፡፡›› የሚል ኑፋቄን ከእውነተኛው ትምህርት ጋራ የቀየጠ ጽሑፍ አስፍሮ ነበር፡፡

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ሦስት መሠረታዊ የኑፋቄ ትምህርቶች አሉበት፡፡ የመጀመሪያው ‹‹የኋላ ልጇ›› የሚለው ነው፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊት ሌላ ልጅ እንደአላት አድርጎ ጌታችንን ‹‹የኋላ ልጇ›› ሲል ኑፋቄውን ጽፏል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት እመቤታችን ድንግል ማርያም ምስጋና ይግባትና ተከታይም ሆነ ቀዳሚ ከሌለው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ሌላ የበኩር ልጅ የላትም፡፡ በዚህም ‹‹ በኩር›› የሚለው ቃል አንድ ወልድ በቀዳማዊ ልደቱም ሆነ በደኀራዊ ልደቱ ተቀዳሚ ተከታይ ተመሳሳይ እኩያ የሌለው መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡

ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን እንዲህ አድርጎ ያቀረበውን ኑፋቄያዊ አስተምህሮ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በቤተ ክርስቲያ አስተምህሮ መሠረትነት ‹‹ኦርቶዶክስ መልስ አላት›› በሚል ርእስ ከፕሮቴስታንቶች ለሚነሡ አንዳንድ ጥያቄዎች በሰጠው የመልስ መጽሐፍ ውስጥ እምነቱ የአደረገውን የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነት እደሚከተለው ገልጧል፡፡

‹‹ የበኩር ልጅ ማለት መጀመሪያ የተወለደ ማለት ነው፡፡ ወይም የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ማለት ነው፡፡ ‹ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳትም ማኅፀን የሚከፍት በኩር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ የእኔ ነው፤› ዘፀ. 13 ፥ 2፤ ይህ ትእዛዝ የሚፈጸመው ሌላ ልጅ እስኪወለድ ድረስ ተጠብቆ ሳይሆን ወዲያው ልጅ እንደተወለደ ነው፡፡ ምክንያቱም ያን ልጅ በኩር ለማሰኘት የግድ ሌላ ልጅ በቀጣይ መወለድ የለበትምና፡፡ አባ ሄሮኒመስ ይህንን የበለጠ ሲያብራራው፤‹ ለእናቱ አንድያ የሆነ ልጅ ሁሉ በኩር ነው፤ በኩር ሁሉ ግን አንድያ አይደለም፤›› (ዳንኤል፣2002፣89)

ከዚህም በተጨማሪ ዲያቆን ዳንኤል፤ እመቤታችን ጌታን ከመውለዷ በፊት ይቅርና በኋላም ልጅ እንዳልወለደች፤ የቤተ ክርስቲያችንን ትምህርት መሠረት በማረግ፤‹‹ እመቤታችን… ልጆች ቢኖሯት ኖሮ በአደራነት ለዮሐንስ ወንጌላዊዉ ባልተሰጠች ነበር፡፡ (ዮሐ. 19 ፥ 25) ጌታችን ዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሆኖ ከእመቤታችን እና ከዮሴፍ ጋር ወደ ቤተ መቅደስ በወጣ ጊዜ ዮሴፍ፣ እመቤታችን እና ጌታችን ብቻ ነበሩ፤ (ሉቃ. 2 ፥ 43)፡፡ በዐሥራ ሁለት ዓመታት ውስጥ ያልተወለዱ ልጆች ከየት ይመጣሉ?›› ሲል መልስ ሰጥቷል፡፡ (ዳንኤል፣2002፣96)

ሁለተኛው የኹራፊው አምሳሉ ኑፋቄ፤‹‹ ሥጋዋን ወርሶ ተወለደባት›› የሚለው ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን፤‹‹ሥጋዋን ነሥቶ ወይም ተዋሕዶ›› ይባላል እንጂ በፍጹም ‹‹ሥጋዋን ወርሶ›› አይባልም፡፡ ምስጢረ ተዋሕዶውም በእንዲህ ዓይነት ወሊጥ ቃል ተገልጾም አይታወቅም፡፡ ሲቀጥልም ‹‹ተወለደባት›› አይባልም፡፡ ‹‹ሥጋዋን ነሥቶ ወይም ተዋሕዶ ተወለደ፤›› እንላለን እንጂ ‹‹ሥጋዋን ወርሶ ተወለደባት›› አንልም፡፡ ‹‹ሥጋዋን ወርሶ ተወለደባት›› የምንል ከሆነ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤‹‹እንበለ ኅድረት – ያለ ኅድረት፤ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም በነሣው ወይም በተዋሐደው ሥጋ ተወለደ›› የሚለውን የቤተ ክርስቲያናችንን መሠረተ እምነት ያፋልሳል፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ ዓይነቱን ወሊጠ ቃል አትጠቀምም፡፡

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ግን ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን፤‹‹ ሥጋዋን ወርሶ ተወለደባት›› የሚለውን ኑፋቄያዊ ሕፀጽ፤ ‹‹ነገረ ድኅነት›› በሚል ርእስ በአዘጋጀው መጽሐፉ ላይ፤ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፤ እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን በነሣው ሥጋ‹‹አደረ›› ብላ አታምንም፤ አታስተምርምም፡፡ እንዲህ ብሎ ማስተማር ሥጋ ለቃል ማኅደሩ፣ ልብሱ ሆነ ብሎ ማስተማርም ማመንም ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ፤ ቃል እና ሥጋ እንደ ወዳጅ አብረው ይኖራሉ እንጂ ባሕርያዊና አካላዊ ተዋሕዶ የላቸውም፤ ብሎ እንደ መናፍቁ ንስጥሮስ ማመን ነው፡፡ በመሆኑም ሥጋ የቃል ማደሪያ፤ ቃልም በሥጋ ኀዳሪ አይደሉምና፡፡ በቃልና በሥጋ ተዋሕዶ ኅድረት የለባትም፡፡›› ሲል ያቀናዋል፡፡ (ነገረ ድኅነት፤ 1993፣19)

የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ትንተና የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ስለመሆኑ ሲረጋገጥ ቅዱስ ቄርሎስ በሃይማኖት አበው ያለውን እደሚከተለው መመልከት ጠቃሚ ነው፡፡

‹‹የባሕርይ አምላክ የሚሆን የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር እርሱ አንድ አካል፣ አንድ ባሕርይ ነው ብለን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፡፡ ከእግዚአብሔር አብ የተወለደ ቃል ከዘመናት አስቀድሞ ከእርሱ ጋር ነበር፡፡ በኋለኛው ዘመንም እርሱ ዳግመኛ ከድንግል ማርያም በሥጋ ተወለደ፤ የተዋሐደውን የተገዥ ባሕርይንም ራሱ ተዋሐደው እንጂ ሌላ ማኅደር አላደረገም፡፡›› (ሃይማኖተ አበው 77 ፣ 43)

የኹራፊው አማሳሉ ገብረ ኪዳን ሦስተኛው ኑፋቄያዊ ሕፀጽ፤‹‹… በዚህ ሥጋውም ዓለሙን ሁሉ ተቤዠው›› የሚለው ነው፡፡ ይህ ደግሞ በነገረ ድኅነት ትምህርታችን ትልቁ ኑፋቄ ነው፡፡ ይህም በሁለት መልኩ ይገለጻል፡፡ የመጀመሪያው፤ ‹‹ድኅነተ ዓለም የተፈጸመው በሥጋ ነው›› የሚል ኑፋቄን ሲያመጣ፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ፤‹‹ ሥጋ መለኮትን ውጦና አጥፍቶ በሩቅ ብእሲ ሥጋ ድኅነት ሆነ›› የሚለውን ኑፋቄ ያስከትላል፡፡ ይህ ደግሞ ቤዛ ዓለም አልተፈጸመም እንደማለት ነው፡፡

ቃል ከሥጋ ጋር በተዋሐደ ጊዜ ተዋሕዶው ፍልጠት የለበትም፡፡ ተዋሕዶው እንደ ነፍስና ሥጋ ነው፡፡ አንድ ሰው ሁለት ባሕርይ እንደማይባል ሁሉ መለኮትና ሥጋም ከተዋሕዶ በኋላ መንታነት፣ ሁለትነት የለም፡፡ ስለዚህ ሥጋው ብቻ ተነጥሎ ‹‹ዓለሙን ተቤዠው›› ማለት እጅግ ክህደት ነው፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ ከተዋሕዶ በኋላ ምንታዌ አለመኖሩን ሲገልጽ፤‹‹ከሥጋዌ በኋላ ይህ የቃል ነው፤ ያኛው የሥጋ ነው አይባልም፡፡… በክርስቶስ ሥጋዌ ምንታዌ የለምና፡፡›› ብሏል፡፡ (ጎርጎርዮስ፤1978፣136-138)

እንግዲህ አይደለም መለኮት በሥጋ ቢዋጥ ቢጠፋ ይቅርና፤ ሥጋ በመለኮት ቢዋጥ ቢጠፋ መለኮት ሊሞት አይችልምና ድኅነተ ዓለም ባልተገኘ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በተዋሕዶ ምንታዌ የለበትም፡፡ ከተዋሕዶ በኋላም ‹‹ሥጋ ተቤዠ፤ መለኮት ተቤዠ›› ተብሎ አይነገርም፡፡ ምክንያቱም ቡዐዴን ያስከትላልና፡፡

ታላቁ መምህራችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይህንን የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርት መሠረት በማድረግ የኹራፊውን የአምሳሉ ገብረ ኪዳንን ኑፋቄያዊ ሕፀጽ ‹‹ነገረ ድኅነት›› በተባለው መጽሐፉ፤‹‹ቡዐዴ መለየት መለያየት ማለት ነው፡፡ ሁለት ነገሮች አንድ ላይ ከሆኑ በኋላ መለየት መነጠል ሲቻል ቡዐዴ ይባላል፡፡… የክርስቶስ ሰው የመሆን ምስጢር ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ከተዋሕዶ በኋላ ሥጋና መለኮትን ለያይቶ ለየብቻ ይህ መለኮት ነው፡፡ ይህ ሥጋ ነው አይባልም፡፡ እንደ ብረትና እሳት ፍጹም ተዋሕዶ ስለሆነ መነጣጠል አይቻልም፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ሰው የሆነው እንበለ ቡዐዴን ነው፡፡›› በማለት ያብራራዋል፡፡ (ነገረ ድኅነት፤1993፣22)

ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የዲያቆን ዳንኤልን ትንታኔ ሊቃዊ ነፍስ ሲዘራበት፤ ‹‹ፍልብያኖስ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መለኮቱና ትስብእቱ የተለያዩ ሁለት አካላት ናቸው፤ ይላል፡፡ እኛ ግን ፈጣሪያችን መለኮትና ትስብእት ከተዋሐዱ በኋላ አንድ አካል አንድ ገጽ እላለን፡፡›› ብሏል፡፡ (መጽሐፈ ምስጢር፤2001፣3)

በአጭሩ የኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን፤‹፣ … የኋላ ልጇ … ሥጋዋን ወርሶ ተወለደባት ፤ በዚህ ሥጋውም ዓለሙን ተቤዠው፡፡›› የሚለው ፍጹም ኑፋቄያዊ ሕፀጽ፤ ‹‹ዓለምን የተቤዠው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንበለ ውላጤ፣ እንበለ ሚጠት፣ እንበለ ኅድረት፣ እንበለ ቡዐዴ፣ እንበለ ትድምርት፣ እንበለ ቱሳኤ በተዋሕዶ ነው፡፡›› ከሚለው ርቱዕ ትምህርት ጋር የሚጋጭ ክህደት ነው፡፡

ከዚህ አኳያ ከቤተ ክርስቲያናችን መሠረተ እምነት፣ ከሊቃውንቱ (ከቅዱስ ቄርሎስ እና ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ) ትንተና በተቃርኖና በፍንገጣ የቆመው ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ነው ወይስ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረተ እምነትን እምነቱ ያደረገውና በቅዱስ ቄርሎስ እና በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ትንተና የተመሠረተው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነው  በሃይማኖት መጠርጠር ያለበት? የቤተ ክርስቲያን ጠላትስ  ማነው? ለእኔ ጠላትም ሆነ ከሐዲው ኹራፊው አምሳሉ ገብ ኪዳን ነው፡፡

ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን መች ከዚህ ኑፋቄያዊ ሕፀጹ ብቻ ተገትቶ፡፡ ከተዘፈቁ አይቀር እንዲህ ነው፤ ‹‹በአይሁዶች መርዘኛ ጥርስ የገባች ሀገር ኢትዮጵያ!›› በሚል ርእስ ተሸካሚነት ፀረ ሴማዊነቱንና ለዚህ ፀራዊ ስሜቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት በማዛባት በገለጠበት በዚያ ማወየቢያ ጽሑፉ ውስጥ ሁለት ትምህርተ ሃይማኖታዊ ርእሰ ጉዳዮችን አዛብቶ አቅርቧል፡፡

የመጀመሪያው፤  ‹‹ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ‹ ለይሁዳ ወለዱ ወለ ዉሉደ ዉሉዱ ይደምሰስ › ትላለች፤›› ተብሎ፤ በማትለውና ግድፈት በተሞላበት ግእዝ የተገለጠው አሳበ ጥቅስ ነው፡፡ ተዛብቶ የቀረበውና ቤተ ክርስቲያን ብላው በማታውቀው (ግእዝ አይሉት አማርኛ) መንገድ የቀረበው አሳበ ጥቅስ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትለው ትክክለኛ ግእዝ ሲቀመጥ፤‹‹ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ››በሚል ነው፡፡ እንግዲህ ተመልከቱ በዕለተ ስቅለት ብቻ በቤተ ክርስቲያን የዋለ ሰው እንኳን የማይገድፈውን አሳበ ጥቅስ የገደፈው ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ነው፡፡ ይኸው ሰው ነው፤ የአባ ጊዮርጊስን ‹‹ውዳሴ መስቀል››፣ በ‹‹አራቱ ኃያላን›› መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱትን የአቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ የአቡነ ፊልጶስ፣ የአቡነ አኖሬዎስ እና የአቡነ አሮን ገድላትን ተርጉሞና ጥልቅ ጥናታዊ ማብራሪያ የሰጠውን ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን፤ ያለአንዳች ተጨባጭ ማስረጃ፤ በግእዝ ጨዋነት ለመጠርጠር የዳዳው፡፡

ኹራፊው አምሳሉ ይህ ግድፈቱ ሳያንሰው በዚሁ በገደፈው ግእዙ የራሱን ፀረ ሴማዊ ፍላጎት በመቀንበብ፤ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ››በሚል  የሚለውን አሳበ ጥቅስ በዕለተ ዓርብ የምትጠቀመው፤ ‹‹አይሁዶችን ለማውገዝ ነው›› ሲል የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በፀረ አይሁድነት ፈርጆ ሊያስፈርጃት ይጣጣራል፡፡

እውነታው ግን ወዲህ ነው፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ነበር፡፡ ነገር ግን የተመረጠበትን ሐዋርያዊ ተግባር ትቶ ከሰቃልያነ እግዚእ ጋር ተባብሮ ጌታውንና መምህሩን አሳልፎ በመስጠቱ፤ በኋላም በጥፋቱ ተፀፅቶ እንደ ጴጥሮስ ንስሐን ሳይሆን በብልጠት ምሕረትን ስለፈለገና ራሱን ስለገደለ የእርግማን እርግማን ተፈጽሞበታል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ለመዘከር፤ ልዩ ልዩ መዝሙራትን በማስተዛዘል በሚጸለይበት ጊዜ ‹‹ለይሁዳ ወልዱ ወዉሉዱ ይደምሰስ›› የሚል የመርገም ቃል አዝማች እንዲነገር ታደርጋለች፡፡ ይህንን ለማሳየት በትርዒት መልክ የሚፈጸም ሥርዓትም አላት፡፡ ይኸውም በመቋሚያ ጫፍ ላይ ጧፍ ተደርጎ (ታስሮ) አንደኛውን የዳዊት መዝሙር (መዝ. 1 ፥ 1 – 6) በማስተዛዘል ከተነበበ በኋላ፤ ‹‹ወፍኖቶሙሰ ለኃጥዕ ከመዝ ትጠፍዕ፤ የኃጥዓን መንገድ እንደዚህ ትጠፋለች›› ከሚለው ላይ ሲደረስ፤ ማኅበረ ካህናቱ በያዙት መቋሚያ በአንድ ላይ ውርጂብኝ በማውረድ በመቋሚያው ጫፍ ላይ የታሰረውን ጧፍ መብራት ያጠፉታል፡፡ ጧፍ ሰይጣን በልቡ የገባ የይሁዳ ምሳሌ ነው ፡፡ መቋሚያ የጌታ ምሳሌ ነው ፡፡ መቋሚያ ላይ መታሰሩ በክርስቶስ መሠረትነት ላይ ለሐዋርያነት ለዓለም ብርሃንነት መመረጡን ግን ይህን ክብሩን በማቃለሉ መውደቁን    ያመልክታል፡፡ ቀጥቅጠው ማጥፋታቸው ሰውን ያሳተው ዲያብሎስ በመስቀል ኃይል መመታቱን፣ ድል መነሳቱን ለማዘከር ነው፡፡

በመጨረሻም፤ ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ እንዘተሰብሐ፤ እግዚአብሔርን እናመስግነው የተመሰገነ ምስጉን›› በማለት የክርስቶስን ቤዛነቱን ያበሥራሉ፡፡ (ዐቢይ ጾምና ሰሙነ ሕማማት)፡፡ እናም ኩላዊት የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን፤ ‹‹ለይሁዳ ወልዱ ወዉሉዱ ይደምሰስ›› የሚለውን አሳበ ጥቅስ የምትጠቀመው ከላይ በገለጥነው አግባብ እንጂ ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን እንዳለው‹‹አይሁዶች ይወገዙበታል›› በሚለው አግባብ አይደለም፡፡

ከዚህ ፀራዊ አስተሳሰብ ብቻ እንኳን ተነሥተን እንፈርጅ (ፍረጃ ተገቢ ባይሆንም) ብንል፤ በፀረ ሴማዊነት እኩይ መንፈስ አብዶ ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት ለፀረ ሴማዊነት ወይም ለፀረ አይሁድነት ቅስቀሳ አዛብቶ በመጠቀም፤ ኩላዊት የሆነችውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በፀረ አይሁድነት ፈርጆ ሊያስፈርጅ እየዳከረ የሚገኘው ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ነው እንጂ፤ ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ፤ ‹‹አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፤ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፤ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና፡፡›› (ገላ. 3 ፥ 28) ያለውን የፀረ ዘረኛነት መልእክቱን መልእክቷ ያደረገችውን ቤተ ክርስቲያን፤ ከፀራውያን ጠብቆ፣ ፀራዊ አለመሆኗን ላለፉት ሃያ ዓመታት የሰበከው፣ የጻፈውና የተከራከረው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አይደለም ፡፡

በሁለተኛ ደረጃ፤ ‹‹በአይሁዶች መርዘኛ ጥርስ የገባች ሀገር ኢትዮጵያ!›› በሚል ጥላቻዊ ርእስነት በአተተው ጽሑፉ ውስጥ የዘራው ኑፋቄያዊ ሕፀጽ፤‹‹… በሥርዓቱ መሠረት አንድ ካህን በትዳር ሕይወት እያለ ባለቤቱ ወይም ሚስቱ ሰርቃ ከሌላ ወንድ ብትደርስና ከሌላ ወንድ መድረሷን አወቀም አላወቀ ከሌላ ከደረሰች በኋላ እሱ ቢደርስባት ሥልጣነ ክህነቱ ይፈርሳል፡፡ ከዚያ በኋላ በዚያ ሥልጣነ ክህነት መጠራትና ማገልገል አይችልም፤ መቅደስ ውስጥም መግባት ፈጽሞ አይችልም፡፡›› የሚለው ነው፡፡

በየትኛው ሥርዓት መሠረት እንደሆነና የሥርዓቱም ድንጋጌ በየትኛ አንቀጽና ቁጥር እንደሚገኝ ያልገለጸው ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን የራሱን ድንጋጌ ‹‹በሥርዓቱ መሠረት›› በሚል ሽፋን የዋሃንን ለማደናገር ቢሞክርም ለዛሬ አልተሳካለትም፡፡ በየትኛውም የሥርዓት መጽሐፋችን ውስጥ እንዲህ ዓይነት የቅጥፈት ድንጋጌ የለም፡፡

ዐይናማው ሊቅ (ነፍስ ኄር) ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ‹‹ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን›› በተባለው መጽሐፋቸው ውስጥ ሥልጣነ ክህነትን ከጋብቻ ጋራ ተያይዞ ስለሚፈርስበት ሁኔታ ፍትሕ መንፈሳዊን አንቀጽ ስድስትና ሰባትን መሠረት አድርገው ሲያብራሩ ቄስ ከሆነ፤ ‹‹ሁለት ጊዜ ያገባ፤ ሁለት ሚስት ያለው፤ ከሴሰኛ ሴት የደረሰ፤ በአገልግሎት ምክንያት ሚስቱን የተለየና የፈታ፤ እመነኩሳለሁ፣ ተባሕትዎ እይዛለሁ ብሎ ሚስቱን ያሰናበተ ካህን ከሹመቱ ይሻራል፡፡›› ብለዋል፡፡ ዲያቆን ከሆነ ደግሞ፤‹‹ሁለት ሴት ያገባ፣ ወይም በተሾመ ጊዜ ከሴት ርቄ ንጽሕና ጠብቄ እኖራለሁ ብሎ ተሥሎ ከተሾመ በኋላ ሥዕለቱን አፍርሶ ሚስት ያገባ ወይም ከዘማዊት ሴት የደረሰ፣ ተደብቆ ተክሊል ያደረሰ ወይም እመነኩሳለሁ ተባሕትዎ እይዛለሁ ብሎ ሚስቱን የፈታ ከዲቁናው ማዕረግ ይሻራል፡፡›› ሲሉ ያስረዳሉ፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፤ 1993፣ 120–123)

ይህን የሊቁን ትንታኔና የፍትሕ መንፈሳዊ ድንጋጌ ይዘን የኹራፊውን የአምሳሉ ገብረ ኪዳንን ግለ ድንጋጌ ስንፈትሽ፤ እውነት አልባ መሆኑን ከመረዳት ባሻገር፤ አንድ ካህን ያለ ራሱ በደል ክህነቱን የሚያጣበት ምንም ዓይነት ቀኖናዊ መሠረት የሌለ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ በሚስቱ ስርቆት ተፈጸመ ቢባልና ይህም በማስረጃ ተረጋገጠ ቢባል በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ሚስቱ በዝሙት ወድቃ ተገኝታለችና ጋብቻው ሊፈርስ ይችላል እንጂ ክህነቱ ሊፈርስ የሚችልበት ምንም ዓይነት ቀኖናዊ መሠረት የለውም፡፡

ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን እንዲህ አዛብቶና አጣሞ ያቀረበው የቤተ ክርስቲያን ጠላት ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ነው? ወይስ፤ ዕድሜ ዘመኑን ለቀኖና ቤተ ክርስቲያን ዋጋ የከፈለው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት?

ቤተ ክርስቲያን በሥርዓቷ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን ብላ የምትጠራቸው መሠረተ ዕምነቷን ያፋለሱትን፣ ሥርዓተ አምልኮዋን ያዛቡትንና ትምህርቷን የቀሰጡትን ጭምር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን በተጨባጭ እንደተመለከትነው፤ በነገረ ድኅነት ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያላትን መሠረተ እምነት አፋልሷል፡፡ የሥርዓተ አምልኮዋ ምሰሶ የሆነውን የሥርዓተ ክህነቷን ድንጋጌ አዛብቷል፡፡ የዕለተ ዓርብ ትምህርቷንና ተዕይንቷን በመቀሰጥ ለፀረ ሴማዊ ቅስቀሳው ተጠቅሞበታል፡፡ ይህ ድርጊቱ ደግሞ ከአፅራረ ቤተ ክርስቲያን እንደ አንዱ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡

 

2 – በታሪክ ‹ተፋለስ› ስም የተገለጠው መንደርተኝነት!

ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን አስቀድመን እንደገለጥነው ሃይማኖታዊ ድቀት ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ ድቀትም አግኝቶታል፡፡ አሰላለፉም ከወያኔያዊ ማንነቱ እንደሚመነጭ ያረጋገጠልንን ነጥቦችን እንመልከት፡፡

የመጀመሪያው፤ ‹‹ተኩላው፤ ‹‹ስማችሁ የለም›› በሚል ርእስ ባሳተመው መጽሐፍ ላይ እጅግ በጣም በሚገርም ድፍረት የወያኔነቱን ተልእኮ ከውኗል፡፡ በዚያ መጽሐፍ ውስጥ ‹‹የሌለውን ፍለጋ›› በሚል ርእስ በጻፈው ጽሑፍ ላይ… በክብረ ነገሥት ላይ ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶ የሚተረከውን በዓለማውያኑ የታሪክ ጸሐፍት ዘንድ ‹‹ሰሎሞናዊ›› በቤተ ክርስቲያን ደግሞ ‹‹የዳዊት መንግሥት›› እየተባለ የሚጠራውን ሥርዎ መንግሥት በሀገራችን አልነበረም በማለት ክብረ ነገሥትንና ይኼንን የክብረ ነገሥትን ታሪካዊ ትረካ የሚጠቅሱና የሚያረጋግጡ ከገድላት እስከ ድርሳናት፣ ከተአምራት እስከ ፍካሬያት፣ ከሊቃውንት እስከ ትርጓሜያት ያሉትን የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ሐሰተኞች አድርጓቸዋል፡፡›› በሚል ያልተባለውን እንደ ተባሉ አድርጎ ያቀረበው ነጥብ ነው፡፡

በአንደኛ ደረጃ በዚህ በኹራፊው ጽሑፍ ውስጥ የሐቅ (Fact) ችግር አለ፡፡ ይኸውም ዲያቆን ዳንኤል ክብረት‹‹የሌለውን ፍለጋ›› በሚል ርእስ፤ ኢትዮጵያዊ ዕሴቶችን በመናድ ለተጠመደው ተስፋዬ ገብረ አብ ምላሽ በሰጠበት ጽሑፍ ውስጥ፤ ‹‹… ‹ሰሎሞናዊ› የሚባል የተለየ መንግሥት አልነበረም፡፡ ነገሥታቶቻችን ሁሉ ራሳቸውን ከኢየሩሳሌም ጋር ያያይዙ ነበር፡፡ ዐፄ ካሌብም ከናግራን ዘመቻ መልስ ዘውዳቸውን ኢየሩሳሌም ነው የላኩት፡፡ የዐፄ ገብረ መስቀል ልጅ ሙሴም መጀመሪያ ወደ ኢየሩሳሌም በኋላም ወደ ሶርያ በመጓዝ በዚያ መንነው ገዳም መሥርተዋል፡፡ ገዳማቸውም ‹‹ሙሴ አል ሐበሽ ገዳም›› ይባላል፡፡ የዛግዌ ነገሥታትም ሰሎሞናውያን የማይሆኑበት ምክንያት የላቸውም፡፡ በገድሎቻቸው ላይ ኢየሩሳሌምን አብዝተው የሚያነሡ፣ ማኅተሞቻቸው ሁሉ የዳዊት ኮከብ የሆኑ፣ በውቅር ቤተ ክርስቲያኖቻቸው የዳዊትን ኮከብ የቀረፁ የዛጉዌ ነገሥታት እንዴት ሰሎሞናውያን አይሆኑም?›› አለ እንጂ ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን፤ ‹‹ሰሎሞናዊ ሥርዎ መንግሥት በሀገራችን አልነበረም›› ብሎ የገለጸው ዓይነት ዐረፍተ ነገር በዲያቆን ዳንኤል ጽሑፍ ውስጥ በጭራሽ የለም፡፡ (ስማችሁ የለም እና ሌሎች፤ 2006፣ 138)

ይህም ቢሆን ዛጉዌያውያንን አግልሎ በራሱ የቆመ ሥርዎ መንግሥት አለመኖሩን ለመግለጥ ነው እንጂ ኹራፊው እንደሚለው፤ ‹‹ገድላቱን የድርሳን መጻሕፍቱንና ትርጓሜያቱን ሐሰተኞች›› ለማስባል አይደለም፡፡ የእነርሱ እውነተኛነት በራሳቸው የሚለካ እንጂ በሌላው ትረካ የሚለካ አይደለም፡፡

በሁለተኛ ደረጃ፤ በዚህ በኹራፊው ጽሑፍ ውስጥ የእውቀት ችግር እናገኛለን፡፡ ይኸውም ‹‹በዓለማውያን የታሪክ ጸሐፍት ዘንድ ‹‹ሰሎሞናዊ›› በቤተ ክርስቲያን ደግሞ‹‹የዳዊት መንግሥት›› በማለት ሁለት የተለያዩ ፅንሰ ሐሳቦችን አንድ በማድረግ አቅርቧል፡፡ በመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያንም ‹‹ሰሎሞናዊ›› የሚለዉን ቃል እንደምትጠቀመው ሁሉ የታሪክ ጸሐፍቱም ‹‹የዳዊት መንግሥት›› የሚለውን ቃል ይጠቀማሉ፡፡ አንዱን ቃል ለአንዱ ብቻ መስጠት አይቻልም፡፡ ሲቀጥል ደግሞ የታሪክ ምሁራኑም ሆኑ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ‹‹የዳዊት መንግሥት›› የሚሉት ከዳዊት ዘር ሲወረስ ሲወራረስ የመጣውን ቅብዓ ንግሥና የፈጸምንና ስዩመ እግዚአብሔር ነን ብለው የዳዊትን ኮከብ የመንግሥታቸው መለያ ያደረጉ ነገሥታትን በሙሉ ሲሆን፤ ‹፣ሰሎሞናዊ›› የሚሉት ደግሞ በ1270 ዓ.ም. ተመለሰ የሚባለውን የይኩኖ አምላክን መንግሥት ነው፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ያሳያችሁ የእነዚህን ሁለተ ፅንሰ ሐሳቦች ልዩነት ሳያውቅ ነው የጨነገፈ ብዕሩን ለትችት ያነሣው፡፡

በሦስተኛ ደረጃ በዚህ በኹራፊው ጽሑፍ ውስጥ አምታችነት እናያለን፡፡ ይኸውም ‹‹ክብረ ነገሥትን እና ይኼንን የክብረ ነገሥትን ታሪካዊ ትረካ የሚጠቅሱና የሚያረጋግጡ ከገድላት እስከ ድርሳናት፣ ከተአምራት እስከ ፍካሬያት፣ ከሊቃውንት እስከ ትርጓሜያት ያሉትን መጻሕፍት ሐሰተኞች አድርጓቸዋል፡፡›› በሚል አምታቻዊነት ሰብዕና የቀረበው ሐሰት ነው፡፡ በመጀመሪያ ከገድላት እስከ ድርሳናት፣ ከተአምራት እስከ ፍካሬያት፣ ከሊቃውንት እስከ ትርጓሜያት ያሉት መጻሕፍት እውነተኛነትና ትክክለኛነት የሚረጋገጠው በራሳቸው በያዙት አሳበ ቁመና እንጂ በሌላው አሳበ ቁመና አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በይቀጥላል ደግሞ ክብረ ነገሥትን የሚጠቅሱም ሆኑ የሚያረጋግጡ አንተ የጠቀስካቸውን ዓይነት መጻሕፍት እስከ አሁን አልደረስኩባቸውምና የታተሙበትን ዓመተ ምሕረትና ገጻቸውን እየጠቀስክ ብትነግረኝ ጥሩ ነበር፡፡ እኔ ባለኝ መረጃ ግን ክብረ ነገሥትን የሚጠቅሱ ገድላትም ሆኑ የድርሳን መጻሕፍት፣ የተአምርም ሆኑ የትርጓሜ መጻሕፍት የሉም፡፡ እናም የሌለባቸውን አለባቸው በማለት መጻሕፍቱን ሐሰተኞች ያደረጋቸው ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን እንጂ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አይደለም፡፡

ሁለተኛው በታሪክ ‹‹ተፋለሰ›› ስም ጎጣዊ ደዌውን የገለጠበት፤

‹‹ከእነኝህ ክብረ ነገሥት ከሚተርከው የዳዊት (ሰሎሞናዊ) ሥርዎ መንግሥት ትረካ በተለያየ መንገድ ከሚያረጋግጡት ከሚተርኩት የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት አንዱ የሆነውን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል ይወስድና አቡነ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ የመንግሥት ሥልጣን በመሐል ከገቡት ከዛጉዌ ሥርዎ መንግሥት ተመልሶ ወደ ዳዊት ሥርዎ መንግሥት እንዲመለስ ስለማድረጋቸውና ከይኩኖ አምላክም ለቤተ ክርስቲያን ሲሦ ድርሻ ስለ መስጠታቸው የሚተርከውን የገድላቸውን ክፍል፤ እንዲህ የሚል ነገር በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል ላይ ፈጽሞ የለም ሲል ወያኔያዊ ክሕደቱን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ላይ ፈጽሟል፡፡… የደብረ ሊባኖስ ገዳም ያሳተመውን ‹ገድለ ተክለ ሃይማኖት› የሚለውን መጽሐፍ ገልጦ ምዕራፍ 26 ን እና 27 ን ቢያነብ ይኼ ተኩላ ያለአንዳች ፍርሐትና ሐፍረት በድንቁርና ድፍረት የለም ሲል የካደውን ታሪክ እንዳለ ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡ ተኩላው በጠቀሳቸውና ባልጠቀሳቸው ታላላቅ ገዳማት ያሉ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድላት ላይም ይኼ ታሪክ በሚገባ አለ፡፡ ተኩላው የለም የሚለው የሌለ መስሎት ወይም እንዳለ ሳያውቅ ቀርቶ እንዳይመስላችሁ በጎሳና በፀረ አማራ መርዘኛ መርፌ ተወግቶ ከተመረዘ በኋላ በወያኔነቱ መሥራት ካለበት ሥራችና ከተሰጠው ተልእኮ አንዱና ዋነኛው በመሆኑ እንጂ፤ … አገው ነኝ ባይ ሆኗል፡፡

ይህንን የክብረ ነገሥትንና የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ገድል ታሪክ ውሸት ነው፣ ተረት ነው፣ ፈጠራ ነው ሲል በሱ ቤት ዛጉዬዎች (አገዎች) ወገኖቹ ስለሆኑና የዳዊት (ሰሎሞናዊው) ደግሞ አማራ ስለሆነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካላቸው ቅድስና በአኀት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ካቸው ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት አንጻር በእሳቸው ገድል ላይ ይኼ ነገር ሰፍሮ መገኘቱ የታሪኩን እውነተኛነት ስለሚያረጋግጥ ለእሱና እሱን ለመሰሉት ደግሞ እንዲህ መሆኑ ስለማይመቻቸው ስለማይወዱት ስለማይፈልጉት ነው በገድላቸው የለም ሲል ዐይን ባወጣ የጅል ድፍረት ሸምጥጦ ሊክድ የቻለው፡፡›› የሚለው ማወረቅ ነው፡፡

በዚህ ንባቡ ውስጥ ዲያቆን ዳንኤል ‹‹የሌለውን ፍለጋ›› በሚለው ጽሑፉ በፍጹም ያላለውን ‹‹በገድለ ተክለ ሃይማኖት ውስጥ ስለ ሰሎሞናዊ ሥርዎ መንግሥትና ስለ ሲሦ ድርሻ የሚተርከውን ታሪክ የለም ብሎናል›› ሲል እንደ አለ አድርጎ አቅርቧል፡፡ ዳንኤል ግን፤ ‹‹ከላስታ ወደ ሸዋ የመንግሥት ዝውውር ሲደረግ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐይቅ እስጢፋኖስ በትምሕርት ላይ ነበሩ፤ (የሚጣቅ አማኑኤል ገድለ ተክለ ሃይማኖት እና ገድለ ኢየሱስ ሞአ በዝርዝር እንደሚተርከው) በዚህ የሥልጣን ዝውውር ላይ ይበልጥ ተሳታፊ የነበሩት አቡነ ኢየሱስ ሞአ ዘሐይቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ሐይቅ የዐቃቤ ሰዓትነት ሥልጣን ነበረው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሦ መንግሥት አግኝተዋል፤ የሚለው ትረካ፤ መንግሥት ወደ ጎንደር ከተቀየረ በኋላ (በ17ኛው መ. ክ. ዘ.) በተጻፈው በ‹ብዕለ ነገሥት› ላይ  የተገለጠ ነው፡፡ ብዕለ ነገሥት የነገሥታትን ሃብት ለማሳየት የተጻፈ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ነው፤ ከ ይኩኖ አምላክ ጋር ቃል ገብተዋል ተብሎ የተጻፈው፡፡›› አለ አንጂ ስለ ደብረ ሊባኖሱ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ያነሣው ነገር የለም፡፡ ቅጥፈት ይሉታል እንዲህ ነው፡፡

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን በገለጸው አግባብ ቢጽፍ እንኳን ስሕተቱ ምኑ ላይ ነው? የገድለ ተክለ ሃይማኖት ብዙ ቅጂዎች እዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ ቅጂዎች ውስጥ ደግሞ የመጀመሪያው ወይም ኦሪጂናል የሚባለው የገድለ ተክለ ሃይማኖት ቅጂ በአሥራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጻፈው በተለምዶ ‹የዋልድባው› የሚባለውና በፈረንሳይ ሙዚየም በ‹‹Bib. Nat 138›› መለያ ቁጥር ተመዝግቦ የሚገኘው እና የሐይቅ እስጢፋኖሱ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ነው፡፡ በእነዚህ ገድላት ውስጥ ‹‹ከዛግዌ ሥርወ መንግሥት ወደ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት የተደረገውን ሽግግር ያከናወኑ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ናቸው፡፡ ለዋሉት ውለታ ለቤተ ክርስቲያን ሲሦ መንግሥት ተሰጠ›› የሚል  የለም፡፡

ይህ ደግሞ በታሪክ ሊቃውንት ጭምር የተረጋገጠ ታሪካዊ እውነታ ነው፡፡ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት‹‹Church and State in Ethiopia››በተባለው ታዋቂ መጽሐፋቸው ይህንኑ ሲያረጋግጡ፤ አቶ አበባው አያሌው የተባሉ የታሪክ ምሁር ደግሞ በየካቲት 1998 ዓ.ም. ‹‹በታሪክ ጥናት ትልቁ ወንጀል›› በሚል ርእስ በ‹‹ሐመር›› መጽሔት ላይ በጻፉት መጣጥፍ፤ ‹‹… ዐፄ ይኩኖ አምላክ፤ ‹ ሲሦውን የግዛቴን ክፍል ለቤተ ክርስቲያን እሰጣለሁ፤› ለማለታቸው ምንም ዓይነት የታሪክ ምንጭና ማስረጃ የለም፡፡ ዘውድ ጭነው ንጉሠ ነገሥት ከሆኑ በኋላም እንደ ማንኛውም ንጉሠ ነገሥት ጉልት በመጎለት እና ሕንፃ በማሳነፅ ቤተ ክርስቲያንን ደገፉ እንጂ ከግዛታቸው ሲሦውን ለቤተ ክርስቲያን አልሰጡም፡፡ በእነዚህ በሁለቱ ተለምዶአዊ አነጋገሮችና አፈ ታሪኮች የተነሣ ለዘመናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአገሪቱ መሬት ሲሦ ባለቤት ተደርጋ ስትጠቀስ ኖራለች፡፡ ታሪካዊ እውነታው ግን ቤተ ክርስቲያኗ መሬት በጉልትነት ይዛ ኖራለች፤ ነገር ግን ይህ በጭራሽ የአገሪቱ ሲሦ መሬት አይደለም፡፡›› በማለት አጽንዖት ሰጥተው ነበር፡፡ /ሐመር፣1998 ፣ /

‹‹ሐመር›› መጽሔትም የገድላቱን ሐቀኛ ትረካ እና የምሁራኑን የታሪክ ትንተና በማስረገጥ (እንግዲህ ኹራፊው አምሳሉ እርምህን አውጣ)፤ ‹‹በአሥራ ሦስተኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ በዛግዌና ሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥቶች መካከል በነበረው የሥልጣን ሽኩቻ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሁለቱን ተቃራኒ ወገኖች በማስማማት፣ ዘውድ ከዛግዌ ሥርወ መንግሥት ወደ ሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት በሰላም እንዲተላለፍ አድርገዋል፡፡ አስቀድሞ ቃል በገባላቸው መሠረት ዐፄ ይኩኖ አምላክ ሲሦውን (1/3ኛውን) የግዛት ክፍል ለቤተ ክርስቲያን ሰጥቷቸዋል፤ የሚለው አፈ ታሪክ ነው፡፡›› ሲል ይደመድማል፡፡/ዝኒ ከማሁ፣ /

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይህን ገድላዊና ታሪካዊ ምንጭ ያለውን እውነታ በተጠየቃዊ መንገድ ‹‹የሌለውን ፍለጋ›› በተባለው ጽሑፉ፤ ‹‹ተስፋዬም ሆነ ሌሎች እንደሚሉት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከቅድስና ሥራ በቀር የገቡበት ፖለቲካ የለም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ደብረ አስቦ ሲገቡ ይኩኖ አምላክ በመንበሩ ላይ ነበር፡፡ ነገር ግን የጠበቃቸው ዘንዶ ይመለክበት የነበረ ዋሻ እንጂ ከሲሦ መንግሥት የተገኘ ግብር አልነበረም፡፡ … ሃያ ስምንት ዓመት በደብረ አስቦ ሲቀመጡም የጎበኛቸው ንጉሥ አልነበረም፡፡ ደቀ መዝሙሮቻቸው ከዝንጀሮ ጋር እየተሻሙ እህል ዘርተው ከማብቀል ውጪ የተለየ ርስት አልነበራቸውም፡፡››ሲል ምሁራዊ ምልከታውን አተመበት፡፡-(ስማችሁ የለም እና ሌሎች፤2006፣139)

3 – በጥላቻ የተለወሰው አማተር ፖለቲከኝነት!

እነዚህን በማስረጃ ላይ የተመሠረቱ ትንታኔዎች ለመገንዘብ የሚያስችለውን አእምሮ በጭፍን ጥላቻ ያጣው እና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹የሌለውን ፍለጋ›› በተባለው ጽሑፉ ያላለውን እንደ አለ አድርጎ በማቀረብ ስምዐ ሐሰት የሆነው ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን፤ በዚያ ዘባተሎ ‹‹ጽሑፉ›› ዲያቆን ዳንኤልን በፀረ አማራነት፣ በወያኔነት፣ በድንቁርና ከስሶታል፡፡ ለፀረ አማራነቱ ‹‹አገው›› መሆኑን ሲጠቅስ፤ ለወያኔነቱ ደግሞ የባለቤቱን ‹‹ትግሬነት››ና ‹‹ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥትና ሲሦ መንግሥት የለም›› ብሏል በማለት ጭራሽ በሐሰት በተሞላ የፈጠራ ክስ ነው፡፡

ሊቃውንቱ ‹‹ጨዋ ደፋር ነው›› እንደሚሉት ያለምንም ሐፍረት ያቀረሸውን የጎጠኛነትና የጥላቻ ፖለቲካዊ ቅርሻቱን እንመርምር፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እንደ ኹራፊው አምሳሉ አገላለጽ ከሆነ ‹‹አገው›› ማለት ፀረ አማራነት ነው፡፡ ኹራፊው አምሳሉ፤ አገዎች ‹‹ፀረ አማራዎች›› ስለሆኑና ዳንኤል ደግሞ አገው ስለሆነ ‹‹ፀረ አማራ›› ነው፤ አለን፡፡ ይህን ከራሱ ከአምሳሉ አመክንዮ አንጻር ስንገለብጠው አማራዎችም ፀረ አገው ናቸው ማለት ነው፡፡ ኹራፊው አምሳሉ ደግሞ ራሱን የአማራ ጠበቃ አድርጎ ስለአቀረበ ፀረ አገው ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በዲያቆን ዳንኤል ላይ በጥላቻ የተነሣው ከፀረ አገውነቱ እንጂ የተለየ በደል በ‹‹አገው›› ዳንኤል ላይ ስለአገኘበት አለመሆኑን አረጋገጠ፡፡ ይሁንና ከእውነታ አንፃር ግን ዲያቆን ዳንኤል የአገው ተወላጅ አይደለም፡፡ እኔ አገው ነኝ ብሎም አያውቅም፡፡ ሰለ አንድ ሕዝብ እውነትን ለመናገር ከዛ ሕዝብ መውለድ የግድ አያስፈልግም፡፡ ሰው መሆንና እውነተኛ መሆን ይበቃል፡፡ እነ ሲልቪያ ፓንክረስት ከኢትዮጵያ ምድር የተገኙ ኢትዮጵያውያን ሆነው አይደለም በዚያ በወረራ ዘመን ሰለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን አብዝተው የተናገሩት ፡፡ እንግዲህ እግዜር ያሳያችሁ ስለኢትዮጵያዊነት ለመቀባጠር የተነሣው እንዲህ ዓይነቱ ጎጠኛ ነው፡፡

ሲቀጥል ደግሞ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ወያኔ ነው ለማለት የጠቀሰው አንደኛ ማስረጃ የባለቤቱን ‹‹ትግሬነት›› ነው፡፡በዚህ ደግሞ የፖለቲካ አቋም ከጎጥ ማንነት እንደሚመነጭ አድርጎ ያቀርባል፡፡ ይህ ደግሞ ትግሬ የሆነ ሁሉ ወያኔ ነው ያስብላል፡፡ ይህ ደግሞ ትልቅ ስሕተት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የደመ ነፍስ ፍረጃ ደግሞ የኹራፊው አምሳሉ መገለጫ ነው፡፡ ከዚህ ማንነቱ በመነሣት ነው እንግዲህ ዳንኤል ባለቤቱ ትግሬ ስለሆነችና ትግሬ ደግሞ ወያኔ ስለሆነ በባለቤቱ በኩል ‹‹ወይኗል›› የሚል ድንቁርናን የሚሰብከን፡፡ እንግዲህ ትግሬነት ወያኔነት ከሆነና ወያኔነትም በጋብቻ የሚወረስ ከሆነ፤ አደንቃቸዋለሁ የሚላቸው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም የቀድሞ ሚስታቸው ትግሬ ናቸውና ፕሮፍ ወይነው ይሆን?

እንግዲህ በአምሳሉ ትንታኔ መሠረት ትግሬነት ወያኔነት ከሆነ ወያኔን በመቃወም ብቻ በወያኔ እስር ቤት መከራውን እያየ ያለው የነጻነት ታጋዩን አብርሃ ደስታን ወያኔ ልንለው ነው? በተቃውሞ ጎራ ተሰልፈው ለአለፉት ሃያ ዓመታት ወያኔን ሲታገሉ የነበሩት ዶክተር ኃይሉ አርአያ ትግሬ ናቸውና ወያኔ ይሆኑ?

ከእውነታ አንፃር ደግሞ እስቲ እንመልከት፤ የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ባለቤት ወ/ሮ ጽላት ጌታቸው ትባላለች፡፡ ምንም እንኳን ትግሬ መሆን ነውር ባይሆንምትግሬ አይደለችም፡፡ የአማራ ተወላጅ ከሆኑ ቤተሰቦች የተገኘች፣ አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች፣ ኢትዮጵያዊት ናት፡፡ ለማንኛውም ‹‹ጽላት›› በሚል የሚጠሩ ሁሉ ትግሬዎች ናቸው ከተባለ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ታቦታቱን ማደሪያ ያደረጉት ጽላቶች  ሁሉ ትግሬዎች ናቸው ማለት ነው? ይህ ደግሞ ‹‹ትግሬነት ወያኔነት ነው›› በሚለው የአምሳሉ ስሌት ከተኼደ ታቦታቱ ሁሉ ‹‹ወያኔዎች›› ናቸው ያስብላለል፡፡ ይህ ደግሞ ትልቅ ክሕደት ነው፡፡ ስለዚህ አምሳሉ ገብረ ኪዳን ከሐዲ ነው ያስብላል፡፡

ሌላው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹ወያኔ ነው›› ለማለት እንደ ማስረጃ የጠቀሰው ‹‹ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥትና ሲሦ መንግሥት የለም›› ብሏል፤ የሚለውን ነው፡፡ ይህን ከሦስት አቅጣጫ እንፈትሸው፡፡ የመጀመሪያው ከወያኔ የታሪክ ትንተና አቋም አንፃር ነው፡፡ ወያኔ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደሚለው፤ ‹‹ሰሎሞናዊ የሚባል የተለየ መንግሥት አልነበረንም፡፡ ሲሦ መንግሥት ለቤተ ክርስቲያን በአቡነ ተክለ ሃይማኖት በኩል አልተሰጠም፤›› አይልም፡፡ ወያኔ ‹‹አዲስ ራእይ›› በተባለው ንድፈ አሳባዊ መጽሔቱም ሆነ ለኢንዶክትሪኔሽን በአዘጋጀው መጻሕፍቱ፤ ‹‹በሰሎሞናዊው እና በዛግዌ ሥርወ መንግሥታት መካከል በነበረው ሽኩቻ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለይኩኖ አምላክ አድልተውና ይኩኖ አምላክም የሸዋ ሰው ስለሆነ ለዘራቸው አድልተው መንግሥትን ከዛዌ ሥርወ መንግሥት ወደ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት እንዲሸጋገር አድርገዋል፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በዋሉት ውለታ ለቤተ ክርስቲያን ሲሦ መንግሥት ተሰጠ፡፡›› ነው የሚለው፡፡ ይህ ደግሞ ተስፋዬ ገብረ አብ፤ ‹‹የስደተኛው ማስታወሻ›› በተሰኘ መጽሐፉ ውስጥ፤ ‹‹የፍስሐ ጽዮን ፖለቲካ›› በሚል ርእስ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጻፈውና የዚህ ጽሑፍ ቀጥታ ቅጂ ወይም ፎቶ ኮፒ ከሆነው ከኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን አቋም ጋር አንድ ነው፡፡

ስለዚህ በኹራፊው ስሌት መሠረት የአቋም ተጋሪነት የሚያወይን ከሆነ ከወያኔ አቋም በተቃራኒ፤ ‹‹ሰሎሞናዊ የሚባል የተለየ ሥርወ መንግሥት አልነበረንም፡፡ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት በኩል ሲሦ መንግሥት ለቤተ ክርስቲያን አልተሰጠም፡፡›› ያለው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሳይሆን፤ የወያኔን አቋም የራሳቸው አቋም አድረገው፤ ‹‹በዛግዌ እና ሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥታት መካከል በነበረው ሽኩቻ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለይኩኖ አምላክ አድልተውና ይኩኖ አምላክም የሸዋ ሰው ስለሆነ ለዘራቸው አድልተው መንግሥትን ከዛግዌ ሥርወ መንግሥት ወደ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት እንዲሸጋገር አድርገዋል፡፡ ለዚህም ውለታ ለቤተ ክርስቲያን ሲሦ መንግሥት ተሰጥቷቸዋል፡፡›› ያሉት ተስፋዬ ገብረ አብ እና ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ናቸው፤ የወየኑት ማለት ነው፡፡

ሁለተኛው ከታሪክ ምሁራኑ ትንታኔ አንፃር ነው፡፡ አስቀድመን በስም የጠቀስናቸው ፕሮፌሰር ታደሠ ታምራት፤ ‹‹Church and State in Ethiopia›› በሚል ርእስ ከዛሬ አርባ ሦስት ዓመታት በፊት በአሳተሙት መጽሐፋቸው፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር የሆኑት አቶ አበባው አያሌው ደግሞ፤ ‹‹በታሪክ ጥናት ትልቁ ወንጀል›› በተሰኘ ርእስ ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት በፊት በ‹‹ሐመር›› መጽሔት ላይ በጻፉት መጣጥፍ፤ ስለ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት እና ሲሦ መንግሥት፤ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከሚያራምዳቸው አቋሞች ጋር ተመሳሳይ አቋሞችን አራምደዋል፡፡ እንግዲህ በኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ስሌት መሠረት የዲያቆን ዳንኤልን ታሪካዊ ትንታኔ ምሁራዊ ምልከታን ያጎናጸፉትን እነዚህን የታሪክ ምሁራን ወይነዋል ልንል ነው?

ሦስተኛው ከ‹‹ሐመር›› መጽሔት ምልከታ አንፃር ነው፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ ‹‹ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለዘራቸው አድልተው መንግሥት ከዛግዌ ሥርወ መንግሥት ወደ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት እንዲሸጋገር አድርገዋል፡፡ በውለታም ለቤተ ክርስቲያን ሲሦ መሬት ተሰጥቷቸዋል፤›› የሚለውን ትረካ አጽንዖት ሰጥቶ ‹‹የለም›› ያለውን፤ ‹‹ሐመር›› መጽሔት ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ‹‹አፈ ታሪክ›› ብሎታል፡፡ ስለዚህ በኹራፊው በአምሳሉ ገብረ ኪዳን የፍረጃ ስሌት መሠረት ‹‹ሐመር›› መጽሔት እንዲህ በማለቷ ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት በፊት የወያኔ ልሳን   ነበረች ልንል ነው? የፖለቲካ ድንቁርና ይሉታል ይኼ ነው፡፡

ከላይ ከጠቀስናቸው የፍረጃ ነጥቦች ባሻገር ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን፤ ‹‹የወያኔ ተልእኮ አስፈጻሚ ነው›› ለሚለው አሉባልታው እንደ ማስረጃ የጠቀሰው፤ ‹‹የቅዱስ ሲኖዶስ መንበር አይሰደድም›› የሚለውን አቋም ነው፡፡ ይኼ አቋም ደግሞ የዲያቆን ዳንኤል አቋም ብቻ ሳይሆን የማኅበረ ቅዱሳንም የጸና አቋም ነው፡፡ የማኅበረ ቅዱሳንም ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንትና የእውነተኞቹ ኦርቶዶክሳውያን ምሁራን አቋምም ነው፡፡

ከዛሬ ሃያ ሦስት ዓመታት በፊት በዲያስጶራነት የሚገኙት አበው፤ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ስደተኛ ሲኖዶስ አቋቁመናል፤›› ብለው ሲያውጁ ማኅበረ ቅዱሳን፤ ‹‹ሐመረ ጽድቅ›› በተሰኘው ልዩ ዕትሙ ተቋቋመ ስለተባው ‹‹ስደተኛ ሲኖዶስ›› የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና ከመንበራቸው የተሰደዱ ቅዱሳን አባቶችን አብነት በመጥቀስ፤ ‹‹የቅዱስ ሲኖዶስ መንበር አይሰደድም›› የሚለውን አቋሙን ግልጽ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ማኅበረ ቅዱሳን በ1997 ዓ.ም ‹‹ሰው እንጂ መንበር አይሰደድም›› የሚለውን ሃይማኖታዊ አቋሙን ለመተንተንና ለኦርቶዶክሳውያን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ከአዘጋጀው ጽሑፍ ውስጥ፤ ምንም ዓይነት ምንጭ ሳይጠቅስ ራሱ እንዳዘጋጀው ጽሑፍ አድርጎ ያለ መልኩ ‹‹የስደት ሲኖዶስ›› መቋቋምን ትክክለኛነት ለማስረዳት ሲጠቀምበት አስተዋልኩ፡፡ በዚህም የዚህን ሰው ጤነኛነት በእጅጉ ተጠራጠርኩ፡፡ ያለ አንዳች ሐፍረት ደግሞ፤ ‹‹ለአራት ኪሎ አባቶች በመጽሔት ላይ መልስ ስሰጣቸው፤ እሽ የሳቸው (ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ) መሰደድ እንደ ጥፋት አይቆጠር ሲኖዶስ ግን አይሰደድም መንበረ ፓትርያርክም አይሰደድም ብለው እዚያ ማቋቋማቸው ትክክል አይደለም፤ ማለት አመጡ፡፡ እኔም አስከተልኩና… ›› እያለ ይቀጥልና፤ ‹‹ድርጊቱ ፀረ ክርስትና ነው›› በማለት ጎጣዊ ዝምድና የወለደውን ርካሽ ፖለቲካውን ይደሰኩራል፡፡ በመጀመሪያ በ‹‹አራት ኪሎ ያሉት አባቶች›› ያላቸው አባቶቻችን በየትኛውም ኦፊሴላዊ መግለጫዎቻቸው ሆነ በሌላ ‹‹የአቡነ መርቆርዮስ መሰደድ እንደ ጥፋት አይቆጠርም፤ ይቆጠራልምም፤›› ብለው አያውቁም፡፡ ሲቀጥል ደግሞ የኹራፊው የአምሳሉ ገብረ ኪዳን ጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምኑ ነውና ነው ‹‹የአቡነ መርቆርዮስ መሰደድ እንደ ጥፋት አይቆጠርም›› የሚል መግለጫ የሚሰጠው?  ማንስ አንብቦት ነው? ማንስ እሱነቱን አውቆ ነው? ይህ መቼም እጅግ ሲበዛ አቅምን እና ደረጃን አለማወቅ ድፍረት ነው፡፡

ወደ ጥንተ ነገራችን እንመለስና፤ ከማኅበረ ቅዱሳን ባሻገር ‹‹መንበር አይሰደድም›› የሚለውን የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ሃይማኖታዊ አቋም በመጋራት ‹‹መንበር ይሰደዳል›› የሚለውን ፖለቲካዊ አቋም በመንቀፍ ከጻፉት ምሁራን አንዱ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ናቸው፡፡ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከዛሬ ሰባት ዓመታት በፊት፤ ‹‹ በግሌ ሕይወቴ ከደረሰውና ካጋጠመኝ አንዳፍታ ላውጋችሁ›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለው ነበር ፡፡

‹‹ … መሠረታዊውና ዋናው ጥያቄ ግን ይህ ነው ፤ ሲኖዶስ እንደቤተ ክርስቲያን ፓርላማ ከታየ አሜሪካ ላይ የሚቋቋመው ሲኖዶስ የየትኛው ቤተ ክርስቲያን ፓርላማ ለመሆን ነው ?ለአንድ አገር ከአንድ የበለጠ ፓርላማ ሊኖረው እንደማይችል ሁሉ ለአንድ ቤተ ክርስሰቲያንም ከአንድ የበለጠ ሲኖዶስ ሊኖራት አይችልም ፡፡ ሲኖዶስ ፈጣሪዎቹ መፍትሔ አድርገው ያዩት ሌላ ቤተ ክርስቲያን ማቋቋም ነው ፡፡ እንግዲህ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግል መሆኑ ቀርቶ የነሱን ሲኖዶስ የምታገለግል ቤተ ክርስቲያን ሊፈጥሩ ነው ፡፡ … አሁን ደግሞ የስደተኞቹን ጳጳሳት ፍትወት ለማርካት ሌላ ግንጠላ ሊያመጡባት ተማምለው ተነሥተዋል ፡፡ …ጎጠኛ መሆን ቤተ ክርስቲያንን መክዳት መሆኑን ጎጠኞች ተከታዮቻቸው የተገነዘቡት አይመስለኝም ፡፡ ›› /ጌታቸው ኀይሌ፣2000 ፣251 /

ይኼንኑ አቋማቸውን በማጠናከር ደግሞ ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ‹‹እናት ቤተ ክርስቲያናችን አልተከፈለችም›› በሚል ርእስ በጻፉት መጣጥፍ ላይ እንደሚከተለው ብለው ነበር፡፡

‹‹ለአንድ ቤተ ክርስቲያን የሚኖራት አንድ ሲኖዶስ፣ አንድ አመራር ብቻ ነው፡፡  ይህንን ሕግ ሁለት ሲኖዶስ የፈጠሩት አዲስ አበባ ያሉትና ስደተኞቹ ካህናት ያውቁታል፡፡ ከኢትዮጵያ ውጪ ያለነው ሕዝበ ክርስቲያን፣ ካህናቱን ጨምሮ፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስደተኞች ነን፡፡ የምናደርገው ትግል ሀገራችን ነጻ ሆና እንድንኖርባት ነው እንጅ፤ ይህን ካላገኘን ብለን በተሰደድንበት ዓለም ኢትዮጵያዊ መንግሥትና ኢትዮጵያዊት ቤተ ክርስቲያን ልናቋቁም አይደለም፡፡ ስለዚህ የተሰደዱትን ካህናት የምጠይቃቸው፤‹‹የእኛን ሲኖዶስ ተከተሉ›› እያሉ ሕዝብ ማስጨነቃቸውንና የመከፋፈል ምክንያት መሆናቸውን ትተው፤ የድዮስጶራው ሕዝብ ወያኔን ሲቃወም ተጨማሪ ኃይል እንዲሆኑ ነው፡፡ ‹‹የእኛን ሲኖዶስ ተከተሉ›› ማለት የሃይማኖት ስደተኞች ሳንሆን፤ የሃይማኖት ስደተኞች ሁኑ፤ ከኢትዮጵያው ሕዝበ ክርስቲያን ተለዩ፤›› ማለት ነው፡፡ ብዙዎች የሚከተሏችሁ ወያኔ የተጠቃላቸው መስሏቸው ቢቸግራቸው ነው እንጂ፤ ኢትዮጵያ ካለው ሕዝበ ክርስቲያን መለየት ፈልጎ አይደለም፡፡ የአንድ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ማእከል ከሕዝቡ መካከል መሆን እንዳለበት መካድ አይቻልም፡፡ ስለዚህ በሕዝብ መሐል ያለውን የኢትዮጵያውን ጭቁን ሲኖዶስና ቤተ ክርስቲያንን አመራር ታግሎ፣ ከወያኔ እጅ ነጻ አውጥቶ ከመውሰድ ይልቅ፤ ከኢትዮጵያ ውጪ ሌላ ሲኖዶስ ማቋቋም ሕጋዊ አለመሆኑን ሲኖዶስ አቋቋሚዎቹ ያውቁታል፡፡ መፍትሔ አድርገው ያዩት የኢትዮጵያውን ሲኖዶስ፤ ‹ሕገ ወጥ› እነሱ ያቋቋሙትን፤ ‹ሕጋዊ› ማለት ነው፡፡ ግን ሁለቱም ሕገ ወጥ ናቸው፡፡ ልዩነቱ የኢትዮጵያው ሲኖዶስ ‹ሕገ ወጥ› የሆነው መንግሥት አስገድዶት ሲሆን፤ የውጪዎቹ ካህናት ሲኖዶስ ያቋቋሙት በስደተኛው ሕዝብ ብዛትና ብሶት በመጠቀም ነው፡፡ በወያኔ ጭቆና የተሰደደው ሕዝብ ብዙ ባይሆን፤ ስዱዳን ጳጳሳት ምንም ብዙ ቢሆኑ ብቻቸውን ሲኖዶስ አያቋቁሙም ነበር፡፡ በሲኖዶስ ስም የተደራጁት ለአገልግሎት እንዲመቻቸው ብቻ ከሆነ፤ ሕገ ወጥ ሲኖዶስ ሳያቋቁሙ የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠትና ሕዝበ ክርስቲያኑን አስተባብሮ የወያኔን ክንድ መመከት ይቻላል፡፡ ሕገ ወጥ ሲኖዶስ ማቋቋም ግን ሕዝብ ስለሚከፋፍል መንበሩን ከመልቀቅ የከፋ ጥፋት መጨመር ነው፡፡›› (ጌታቸው ኃይሌ፤2004፣4-5)

እንግዲህ ‹‹መንበር ይሰደዳል›› ብሎ ፖለቲካዊ አቋም ከያዘው ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ተለይቶ፤‹‹መንበር አይሰደድም›› ብሎ ሃይማኖታዊ አቋም የያዘውን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የወያኔ ተልእኮ አስፈጻሚ የሚያሰኘው ከሆነ፤ ኹራፊው ራሱ እንዳለው በየጊዜው የወያኔ ጅራፍ የሚያርፍበት ማኅበረ ቅዱሳን፤ ‹‹መንበር አይሰደድም›› የሚል ሃይማኖታዊ አቋም አለውና የወያኔ ተልእኮ አስፈጻሚ ነውን? ከተጠረጠሩ በአማራ ብሔርተኛነት እና በፀረ ወያኔነት ይጠረጠሩ ካልሆነ በስተቀር በወያኔ ተልእኮ አስፈጻሚነት በፍጹም የማይጠረጠሩት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፤‹‹መንበር አይሰደድም፤ ሕገ ወጥ ሲኖዶስ ማቋቋም ግን ሕዝብ ስለሚከፋፍል መንበሩን ከመልቀቅ የከፋ ሌላ ጥፋት መጨመር ነው፡፡›› የሚለውን ሃይማኖታዊ አቋም በፖለቲካ ተዋስዖ/Discourse / ተንትነው ያቀረቡት የወያኔ ተልእኮ አስፈጻሚ ስለሆኑ ይሆን? ከኹራፊዉ አምሳሉ ገብረ ኪዳን ውጪ ሌላ ሰው አዎን የሚል ያለ አይመስለኝም፡፡

4- አቅጣጫ የሳተና በተቃርኖ የተሞላ የሴራ ትንተና!

ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ኢስላማዊውን ነቢይ ‹‹መሐመድ ›› ብሎ ዘርጥጦ የጠራቸውን፤ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ኢስላማዊ ነቢይነታቸውን አክብሩ ‹‹ነቢዩ መሐመድ ›› ብሎ መጥራቱን እንደ ጥፋት በመቁጠር በ‹‹ደፋርነት›› ከስሱታል  ፡፡

በኢስላም አስተምህሮ አለማመን እና የእነርሱን ነቢያት አለመቀበል አንድ ነገር ሆኖ መሪያቸውን ክብረ ነክ በሆነ አጠራር መጥራትን ትክክል የሚያደርግ የክርስትና አስተምህሮ የለም ፡፡ሌላው ቢቀር ሰብአዊ ፍጡርነታቸው ያስከብራቸዋል ፡፡ ዲያቆን ዳንኤልም የፈጸመው ይህንኑ ነው ፡፡ ኹራፊው እንዳደረገው መሆን ግን ኢ ክርስትና ነው ፡፡

ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ምን ያህል ሚዛኑን የሳተ መሆኑን የሚያርጋግጥል በአንድ በኩል የሙስሊም ወንድሞቻችን ነቢይ የሆኑትን ነቢዩ መሐመድን በቃለ አክብሩ አትጥሯቸው ፤‹‹ መሐመድ በሉት›› እያለ በሌላ በኩል ደግሞ ከወያኔ ጋር የሚያደርጉትን ስላማዊ ትግል ለተንሻፈፈው ፖለቲካዊ ፍትወቱ ይጠቀምበታል ፡፡ መሪያቸውን እየዘረጠጡና ክብር እየነሱ በዲያቆን ዳንኤል የኦሪት ፍየልነት  የሰላማዊ ትግላቸው ተከባካቢና ጠባቂ ሆኖ መገለጥ አይቻልም ፡፡በተወሰኑ ሰዎች ዘንድ ተችሉም ከሆነ እጅግ ሲበዛ ሞራለቢስነት ነው ፡፡ወያኔስ የሚያደርገው ይህንኑ አይደለም ፡፡

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹አክራሪ እስልምና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስቸጋሪ ፈተና ›› በተሰኘው ጥልቅ ጥናታዊ ወረቀቱ  የክርስትናችን አስቸጋሪ ፈተና ‹‹ አክራሪ አስልምና ›› አለ እንጂ ኹራፊው አምሳሉ ‹‹የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጠላት ስውሩ ተኩላ ዳንኤል›› በተሰኘው ግልብ ጹሑፉ ላይ እንደተመለከተው የክርስትናችን አደጋ ‹‹ ከፊሉ እስላም ነው ›› አላለም ፡፡የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጥናት ለራሱ ለእስልምናውም ፈተና የሆኑትን አክራሪዎችን የክርስታናችን ፈተና አድርጉ ሲያቀርብ ፤የኹራፊው አምሳሉ ግልብ ጹሑፍ ግን ‹‹እስላም የሆነ ሁሉ አክራሪ ነው ›› በሚል ስሌት መሠረት ‹‹ ከፊሉ እስላም ››በሚል አገላጽ የክርስትናችን አደጋ ግማሹ ሙስሊም ሙሉ በሙሉ  እንደሆነ አድርጉ አቅርቧል፡፡ ሰለዚህ ኹራፊው አለ በሚለው ክርስቲያኑንና ሙሲሊሙን የማፋጠጥ የወያኔ ሴራ ሰተት ብሎ የገባው ኹራፊው እንጂ ዲያቆኑ አይደለም ማለት ነው ፡፡

ኹራፊው አቅጣጫ የሳተበትና በተቃርኖ የተሞላበት ሌላው ነጥብ ‹‹ ‹አራቱ ኀያላን › የሚለውን መጽሐፍ ያዘጋጀበት ምክንያት የአማራ ነገሥታትን ስምን ለማጥፋት በማሰብ ነው ፡፡ ›› የሚለው ነው ፡፡ይኸው ሰው ‹‹ አራቱ ኀያላን የሚለው መጽሐፍ የተጻፈው የአማራ ነገሥታትን ስም ለማጥፋት በማሰብ ነው ›› ብሎ ከደመደመ በኃላ ይህንኑ አገላለጹንእና ሰለዲያቆን ዳንኤል ያለውን የሐሰት ክስ በመቃርን ‹‹ዲ/ን ዳንኤል እየሠራ ያለው ሥራ በእውነት አጅግ የሚያስመሰግነው ነው ፡፡ … የዚህ መጽሐፍ (የአራቱ ኀያላን መጽሐፍ ማለቱ ነው) ዋነኛ ዓላማው የሚመስለኝ በዚህ ዘመን ያሉ አባቶች መንፈሳዊና ግብረ ገባዊ ብቃት ከቀድሞቹ አባቶቻችን ጋራ ሲነጻጻር ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለማሳየትና የቀደሙቱ አባቶቻችንን የዓላማ ጽናት በአርአያነት እንዲወስዱ ማድረግ የሚሞክር ወይም መሆን አለበት ፡፡ ›› በማለት ያፈርሰዋል ፡፡

ኹራፊው በመርሕ ላይ የተመሠረተ ተቃውሞም ሆነ ድጋፍ የማያደርግ መሆኑን ከዚህ መረዳት ይቻላል ፡፡ የትኛውንም አቋሙን በየትኛውም ጊዜ ለመተው በቂ ምክንያትና ማሰብ አያስፈልገውም ፡፡ ፕሮፌሰር መስፍንን ሲያወድስና ዲያቆን ዳንኤልን ሲያራክስ ምክንያት የለውም ፤ተስፋዩ ገብር አብን ደግፎ ፣ዲያቆን ዳንኤልን ሲቃወም ተጠየቅ የለውም ፤አቶ ኤርሚያስን ደግፎ፣ዲያቆን ዳንኤልን ሲቃወም አመክንዩ የለውም ፡፡በጭፍን ይደግፋል፤ በጭፍን ይቃወማል ፡፡ ለእርሱ መውደድና መጥላት በቂ ነው ፡፡ የዘመናችን ‹‹ድንግል በክልኤ›› እንግዲህ ይህ ነው ፡፡

ከዚሁ ጋራ በተጨባጭ የማውቀውን እንደሱሯጽ (as side issue)ልንገራችው ፡፡ኹራፊው አምሳሉ በተለይ ከአቶ ኤርሚያስም ለተስፋዬ የተሰጠው ምላሽ ያንገበገበው ስለ ሁለት ነገር ነው ፡፡አንደኛው በ1990ዎቹ ውስጥ የካድሬነት መልማይ የጡት አባት በመሆን ትንሽ የወያኔን ፍርፋሪ እንዲያገኘ ያደረገው ተስፋዬ ነበር ፡፡ሁለተኛው ሥራ በፈታባቸው ዓመታት ውስጥ እንጀራ የሆኑት የተስፋዬ የጥፋት መጻሕፍት ነበሩ ፤አሁን ደግሞ የአቶ ኤርሚያስ መጽሐፍ፡፡እኛም በመጽሐፍ ቅርጽ እያዘጋጀ የሚሸጣቸውን ፎቶ ኮፒ ‹መጽሐፍ› ገዝተን ያነበብ ነው እርሱ ከአሰማራቸው መጻሕፍት አዟሪዎች ነበር ፡፡ከእነዚህ በቀጥጣ ከማውቃቸው መረጃዎች ተነሰቼ ስደመደም ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አስቀድሞ ለተስፋዬ በኃላ ለአቶ ኤርሚያስ በሰጠው ጹሑፍ መደምደሚያ ላይ‹‹ ሌላውንም ነገር የሚነግሩን እንዲህ ሐሰት ይዘው ነው ማለት ነው›› ማለቱ አስቆጥቱታል ማለት ነው ፡፡ ዲያቆን ዳንኤል እንዲህ መደምደሙ መጻሕፍቱ በሰፊው ተሰራጭተው፣ ሰዉ አንብቧቸው ፣የሥርዐቱን ፀረ ዲሞክራሲያዊነት እንዳይረዱና የተአማኔነት ችግር እንዲገጥማቸው ሊያደርግ ይችላል ከሚል በጎ መንፈስ ሳይሆንመጻሕፍቱን መረጃ ተአማኔነት ዋጋ በማሳጣት ገዥ ሊያሳጣኝ ይችላል ከሚል ጥቅመኝነት የመነጨ ቁጣ ይመስለኛል ፡፡

ኹራፊው አምሰሉ ገብረ ኪዳን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹በአገሪቱ ስላለው ሰብአዊ መብት ገፈፋ፣ ስለሙስና መሰራፋት፣ ሰለኑሮ ውድነት፣ እምነትን በነጻነት የማራመድ መብት ማጣትን፣በዋልድባም ሆኑ በሌሎች ገዳማት ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች ላይ  አልጻፈም፤እንደጸሐፊ አይደለም እንደ ዜጋ እንኳን በእነዚህ ነገሮች ላይ አንድም ነገር ተናግሮ ተንፍሶ አያውቅም ፡፡ ››ሲልም በሐሰት ይከሰዋል ፡፡ክሱ ምን ያህል በሐሰት የተሞላ መሆኑን ለማረጋገጥ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ‹‹የሃይማኖት ፖሊሲ ፣ሕግና ተቋም የሌላት ሃይማኖተኛ ሀገር ፣‹‹ውልድብና ›› እና ኢውልድብና››፣ዝቋላ ሀገሩ የትነው? ፣100% ፣እኔ በሞትኩ በማግስቱ ፣ለምጣዱ ሲባል ፣‹‹ስኳሬ›› ‹‹ዘይቴ›› ፣ከ2000 ዓመት በኃላ እንደ አዲስ እንመዘገባለን ፣እንደ አዲስም እንታወቃለን ፣መጀመሪያ ሰው ነኝ ››በሚል ርእሶች ያዘጋጃቸውን እነዚህን ጹሑፎች ብቻ ማንበብ በቂ ነው ፡፡በርግጥ ጹሑፎቹ ወያኔን በሐሳብ ልዕልና ይሞግታሉ እንጂ እንደኹራፊው ‹‹ወያኔ የጤፍ ዱቄት ሌባ ነው›› ዐይነት ተራ አሉባልታዎች አይደሉም፡፡ የኹራፊው የ‹‹እንዲህ ››አላለም ‹ፖለቲካ› ጨዋታ የጨዋዎቹ በመሆኑ እዚህ ጋ አልሠራም ፡፡

ማጠቃለያ

ኹራፊው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ‹‹ዳንኤል ክብረትና ሌላው የወያኔያዊ ተግባሩ መገለጫ! ››በሚል ርእስ በለጠፈብን ማወረቅ ጹሑፉ ‹‹በሀገሬ ፣በቤተ ክርስቲያንና በዚህ ውድ ሕዝብ ሸፍጦች ሲፈጸሙ አልችልም ፡፡ … ዘለፋው ይገርማችሃል እንዴ ! እውነቴን ነው የምላቹህ ፈንጅ በእጄ ቢኖር አንድ ሰው የማስተርፍ አይምሰለኝም ፡፡›› ብሎንም ነበር ፡፡

የሆነው ግን ሌላ ነው፡፡ ነውረኛና በሐስት መርዝ የተለወሰውን ዘለፋውን በተግባር ያዋለው ለሀገሩ ፣ለቤተ ክርስቲያኑና ለውድ ሕዝቡ በሚደክመው በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ነው ፡፡ በሕሊናውም በፈንጅ ያጋየው ይኼንኑ የሀገር ፣የቤተ ክርስቲያንና የሕዝብ ባለውለታ የሆነውን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነው ፡፡ ነስፍ ገዳይነት የሚጀምረው በሕሊና ገዳይነት ነውና የዲያቆን ዳንኤል ክብረት አጥፊው ነፍስ በላው አምሳሉ ገብረ ኪዳን ነው ማለት ነው ፡፡ ይህ ደግሞ ከሞራል ተጠያቂነት ባሻገር የሕግ ተጠያቂነትን ያስከትላል ፡፡

ይሁንና ያልሆነው ግን ያለውን ነው ፡፡ ‹‹ በሀገሬ ፣በቤተ ክርስቲያንና በውድ ሕዝቧ ሸፍጥ ሲፈጸም አልችልም፤ በፈንጅ ነው የምፈጀው ›› እያለና እየቀባጠረ በፀረ ወያኔ ቆብ ከወያኔ ባልተናነሰ በወያኔያዊ መንገድ በሀራችን ሕዝብ አብሮነት ላይ ሸፍጥ እየፈጸመ የሚገኘው ተስፋዬ ገብረ አብን አይደለም በፈንጅ በብዕር ምንም አላለውም ፡፡ ተስፋዬ ‹‹ የቡርቃ ዝምታ ›› በተሰኘው መጽሐፉ ኦሮሞውንና ትግሬውን በአማራው ላይ ቀስቅሶበታል ፤ ‹‹በጋዜጠኛው ፣ በደራሲውና በስደተኛው ማስታወሻ ››በተሰኙ እኩይ መጻሕፍቱ አማራው ፣ ኦሮሞውና ሌላው ጎሳ በትግሬው ላይ እንዲነሳሳ ዘምቷል፤ ‹‹ የጀሚላ እናት ›› በተሰኘው ሰይጣናዊ መጽሐፉ ደግሞ ኦሮሞው በኢትዮጵያዊነት መቃብር ላይ ኦርቶዶክሳዊነትን እንዲቀብር አጥብቆ ሰብኳል ፡፡ዳሩ ግን የኹራፊው አምሳሉ ዶልዶም ብዕር የተሰበቀው ለእንዲህ ዐይነቱ ፀረ ኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክሳዊነት ሳይሆን በኢትዮጵያዊውና በኦርቶዶክሳዊው በዲያቆን ዳንኤል ነው ፤ኹራፊው በፀረ ወያኔያዊ ለምድ የተገለጠ የወያኔ ተኩላ የሚያሰኘውም አንዱ ይህ ነው ፡፡

በ‹‹ቤተ ክርስቲያኔ ሸፍጥ ሲፈጸም አልችልም፤በፈንጅነው የምፈጀው ›› ባዬ ኹራፊው አምሳሉ በፀረ ወያኔነት ካባ የታጀለውና የሻቢያ የጥፋት እጅ የሆነው ተስፋዬ ገብር አብ ‹‹የስደተኛው ማስታወሻ ››በተሰኘው የጥፋት መጽሐፉ የቤተ ክርስቲያናችን የመካከለኛው ዘመን የሐዋርያዊ አገልግሎት ማዕዘን በሆኑትን በጻዲቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ ‹‹የፍስሐ ጽዮን ፖለቲካ ››በሚል ርእስ በጻፈው ነውረኛ ጹሑፉ ሲሳለቅ  ምንም ሳይለው፣ በጸሎት ብዛት የተቆረጠውን እግራቸውን ‹‹ሰይጣን ፈንግሏቸው የተቆረጠ ነው››ብሎ ሲጽፍ ሳያንገበግበው ፣ዲያቆን ዳንኤል  ክብረት ‹‹የሌለውን ፍለጋ ›› በተሰኘው ጹሑፉ ‹‹ተስፋዬ‹የፍስሐ ጽዮን ፖለቲካ› በሚል ርእስ ሰለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የማያውቀውን ነገር ጽል፡፡ሰለማያውቀው ነገር የጻፈው ባለማወቁ ብቻ አይመስለኝም ፡፡አንድም ለማወቅ ባለመፈለጉ፣አሊያም ሆን ብሎ የማፍረስ ዓላማ ይዞ ይመስለኛል ፡፡›› ብሎ መልስ መስጠቱ አጥወለወለው፤ዳግም ለተስፋዬ ድፍረት ‹‹… ሰባት ዓመት ሙሉ ለጸሎት የቆሙበት እግራቸው በጸሎት ብዛት በመቆረጡ እንጂ ሰይጣን ‹‹ ፈንግሏቸው›› አለመሆኑን ኤርትራውያን እናቶች በሚገባ ያውቁታል፡፡..››ብሎ የሰጠው መልስም አንገበገበው፡፡እንግዲህ ይህ ሰው ነው ራሱን የኢትዩጵያዊነትና ኦርቶዶክሳዊነት ጠበቃ አድርጉ የሚቆጥረው ፡፡ እረ እፈር ሊባል የሚገባ ሰው ነው ፡፡

በመጨረሻ አንድ ነገር ብቻ ልበል ፡፡ ዶክተር ደረጄ በመቅድም ጹሑፋቸው እንደተመለከቱት የተቃውሞ ፖለቲካን ክርክርን በጤፍ ዱቄት ሌብነት ደረጃ አውርዶ ከሚያስበውና ይህንኑ የማያደርጉትን በወያኔነት ከሚፈርጀው ኹራፊ ጋር  ‹‹መረጃ ላይ መመሥረት ያለበትን ታሪክ ነክ ወይም ፖለቲካ ነክ ክርክር  ማካኼድ አይቻልም›› ፡፡ ይህም ጹሑፍ ሲዘጋጅ ይህን በመገንዘብና ኹራፊው ያዋረደውን አንባቢ በማክበር የተቃውሞ ፖለቲካን ክርክርን  ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ነው እንጂ ኹራፊውን በማሰብ አይደለም ፡፡ ሆኖም ግን የኹራፊው አምሳሉ ማወረቅ ጹሐፎች በርግጠኝነት አንድ ቁም ነገር ያስተምራሉ ፡፡ ይኸውም አንድ ጹሑፍ እንዴት እንደማይጻፍ!!

comment pic

The post ኹራፋተ አምሳሉ ፡- መረጃና ማስረጃ አልባው እንቶፈንቶİ – ዲ/ን ዶክተር መሐሪ ወሰን /ከጅማ/ appeared first on Zehabesha Amharic.

ይህቺ አገር ምስጢር ናት!!! –ከ-ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

Ketemaኢትዮጵያ የሚለው ስም የወጣላት ከ4000 አመት በፊት እንደሆነ  ይነገራል። የስም አወጣጡም ከኢትኤል እንደተሰየመ የታሪክ ተመራማሪው ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ ግለጽ በሆነ መልኩ አስቀምጠውታል። ከዛሬ ጀምሮ አንተ አብራም ሳይሆን አብርሃም ትባላለህ። አብርሃም ማለት፡- የብዙሃን አባት ማለት ነው ብሎ እግዚአብሔር ስሙን እንዳወጣለት ሁሉ… አንተ ከዛሬ ጀምሮ ከፋ ሳይሆን ጴጥሮስ ትባላለህ። ጴጥሮስ ማለት፡- አለት ማለት ነው። በአንተ አለትነት ቤተክርስቲያን እመሰርታለው ብሎ እግዚአብሔር ለጴትሮስ  ስምን  እንዳወጣለት ሁሉ… የኢትኤልን ከዛሬ ጀምሮ ኢትኤል ሳይሆን ኢትዮጵ ትባላለህ። ኢትዮጵ ማለት የቃሉ  ፊቺ  ኢቲ ማለት ቢጫ ወርቅ… ዮጲ ማለት ደሞ  ስጦታ ማለት ሲሆን …የኢትዮጵ ትርጉሙ ቢጫ የወርቅ ስጦታ ማለት ነው። ከኢትዮጵ ኢትዮጵያ የሚለው  ስያሜ  ተገኝቷል። ኢትዮጲ የመልከ ጸዲቅ ልጅ እንደሆነ እና ኢትዮጲያ የሚለውን ስም እግዚአብሔር እንዳወጣለት የታሪክ ሙሁሩ ዘርዝረው አስረድተውናል። የዚህን ዝርዝር ሁኔታ  በተብራራ መልኩ ለማወቅ የምትፈልጉ ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ  በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ገለጻ የሰጡበትን እና በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ የጻፉትን መጽሐፍ ብታነቡ ሰፋ ያለና የተብራራ ነገር እንደምታገኙ ለመጠቆም እወዳለው።

ኢትዮጵያ በመጻሀፍ ቅዱስ ላይ ከ 44 ግዜ በላይ የተጠቀሰች በእግዚአብሔር ስራ ውስጥ በተደጋጋሚ የምትገለጽ በህገ ልቦና ግዜ ህግ ለሙሴ  ሳይሰጠው በፊት እግዛአብሔር የምትመልክ አገር ነበረች። ህገ ኦሪት ለሙሴ ሲሰጠው ህገ ኦሪትን በመቀበል በህገ ኦሪት የኖረች አገር ነች። በህገ ወንጌል ግዜም ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህች ምድር መቶ የወንጌልን ህገ አዲስ ኪዳንን ሲሰጥ ኢትዮጵያን ከእስራኤል ቀጥላ ህገ ወንጌልን የተቀበለች ተቀበላም ጠብቃ ያቆየች አገር እንደሆነች ታሪክ ይነግረናል።

እስልምና ነብዩ መሐመድ በተነሳ ወቅት ከአገሩ ሰወች ከቆሬሾች ታላቅ ተቃውሞ በተነሳበት ግዜ  ሂዱ ወደ ኢትዮጰያ  ህዝብ የማይበድልባት መንግስት ያለባት አገር ነች ብሎ  የራሱ ዜጎች ሊገሏቸው እንደሚችል አውቆ ያቺ አገር ግን ሰው እንኳን አይበደልበትም ብሎ  የርሱ ወገኖች የሆኑትን ሰወች በመላክ እንዲጠለሉ አድርጓል።  ነብዩ መሐመድ ቆሬሽችን አሸንፎ ከመካ መዲና የእስልምናን እምነት በይፋ  ሲያውጅ  የመጀመርያን አዛን ያለው ቢላል የተባለው ኢትዮጵያዊ  መሆኑ በእስልምና  ታሪክ ተጽፎ እናገኘዋለን በዚህም ከሳውዲ አረቢያ ቀጥላ እስልምናን የተቀበለች አገር ኢትዮጵያ መሆና ታሪኮች ይነግሩናል።ሁለት ታላላቅ እምነቶችን ቀድማ  በመቀበል ከአለማችን ልዩ ያደርጋታል።

ቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ጾመዱጓ፣ ምዕራፍ፣ ዝማሬ፣ መዋለት፣ የተሰኙ  ድንቅና መለኮታዊ  ጥበብን  የተላበሱ መጽሐፍን በመጻፍ አለምን ያስደመመ ነው። እንደ ቅዱስ ያሬድ ታላቅ ሊቅና ጥበበኛን ያበቀለች አገር ናት። በዚህም የመላእክትን ዜማ የምታዜም የመላእክትን ሽብሻቦ የምታሸበሽብ ጥልቅ ምስጢር የሚነገርባት፣ የሚታይባት፣ እና ጥልቅ ምስጢር ያላት አገር ናት።

አክሱምን ያነጹ፣ ቤተ ጊዮርጊስን እና በዙርያው  ያሉትን ቤተ ክርስቲያንን ከወጥ ድንጋይ ፈልፍለው  ጥበብን የገለጹ፣ የሶፍ ዑመር ዋሻ ብዙ ምርምርን የሚጠይቅ ድንቅ ዋሻ የሚገኝባት፣ የሃረር ግንብ በጥንታዊ ጥበብ  የታነጸ፣ የጢያ ተክል ድንጋይ ተመራማሪወችን ብዙ ያስባለ፣ ድንቃ ድንቅ የፈጠራን ጥበቦች ለአለም ያበረከተች፣ አለም የተደመመባት፣ የቅርስ መሃደር፣ ከአስራ አራት በላይ በአለም ቅርስነት ያስመዘገበች የድንቅ ሚስጥር ባለቤት ይቺው አገር ናት።

ሉሲ (ድንቅነሽ) እና ሌሎችም የሰው ቅሪት አጽም  በተለያዩ አለማት ከተገኙ ቅሪቶች በብዙ ዘመን ቀዳሚነት ያለው የተገኙት ይህቺው ሚስጢራዊ አገር ውስጥ ነው። የአለም ሳይንትስቶች የሰው መገኛ ኢትዮጵያ እንደሆነችና  ከኢትዮጵያ ተነስተው ወደተለያየ የአለማችን ክፍል በመሄድ አሁን ላለው የሰው አሰፋፈር መሰረቷ ይችው አገራችን መሆናን አፋቸውን ሞልተው እየተናገሩ ነው።

በቅኝ ያልተገዝች፣ ለመላው አፍሪካ የነጻነት በር ከፋች የሆነች፣ ለጠላት አለሸነፍ ባይነትን፣ ለውጪ ወራሪ አልገዛ ባይነትን፣ ያሳየችው፣  የሰው ክብር የማትፈልገ የራሳንም ክብር አሳልፋ የማትሰጥ፣ ቅኝ ገዢወችን ለመጀመርያ ግዜ ያንበረከከች  ይችው ሚስጢራዊ አገር ነች።

የውጭ ጠላት የክፋት ድንጋይ ቢፈነቅሉ የማትሸነፍ፣ የጥፋት ቦንብ ቢያወርዱ የማትንበረከክ፣ አገር ስትሆን ሁል ጊዜም ከፈተኛ ጉዳት የሚደርስባት በአገር ጠላት ብቻ  ነው። እነዚህ አገር በቀል አንባ ገነኖች ሕዝባችንን ይበድላሉ፣ ያሰቃያሉ፣ የሚሰቃየውም ዜጋው የሚያሰቃየውም ዜጋው በመሆኑ ጉዳቱን አሳዛኝ ያደርገዋል። ለአገር አሳቢ በመምሰል  ስህተታቸውን እንደትክክለኝነት ይነግሩናል። ወንድሙን እየገደለ እንደ ጀግና ይፎክርብናል። ጥቂቶች ስልጣናቸውን ለማቆየት ባስታጠቋቸው ጢቂት ወታደሮች ሚሊዮኖችን እረግጠው ጀግና ነን እያሉ ሊኖሩ ይፈልጋሉ። እንግዲህ የገባው ይግባው ይህቺን አገር ሊያጠፋት የሚችል ማንም የለም። ትግሉ ከህዝቡ ጋር ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔርም ጋር ስለሆነ ሊታሰብበት ይገባል። ካለበለዛ ግን ከሰውነት ክፍል አንዷ በካንሰር ከተጎዳት ቆርቶ ማስወጣትና ከዛ በኋላ ጤነኛ ሆኖ መኖር ስለሚያስፈልግ ከላይ ተቀምጠው ህዝባችን ላይ ካንሰር የሆኑትን ቆርጠም ማስወገድ ግድ ይለናል።

የንጽሃኑን ሕዝብ መብት እረግጠው የማስተዳደር ፍላጎት ማሳየት እና ለርካሽ ፖለቲካ ጥቅማቸው ይችን ሚስጥራዊ የሆነች አገርን ለማፍረስ ህዝቦቻንም ለማጥፋት ይጥራሉ። ነገር ግን ሊያጠፋት የተመኙ ሁሉ ሲጠፉ እንጂ ስትጠፋ አላየንም። ሰፊውን ህዝባችንን ሲበድሉ እና  ሲያሰቃዩ የሚኖሩ ገዢዎች የዚች አገር ጠባቂ የእጃቸውን ቅጣት ሲስጣቸው እና ሲያጠፋቸው የምናይበትን እውነተኛ የሆኑትን ታሪኮችን እያየን ያለፍንበት ግዜ  ብዙ ናቸው። ዛሬም  የህዝብ ጠላት የሆነ  ስለርካሽ ፖለቲካቸው ብቻ በማሰብ ይችን  አገርን ሲበድሉ እና ሲጨቁኑ አመታቶችን አስቆጥረዋል።  ይህቺ አገር ለማጥፋት ማሰብ ለመጥፋት የቀረቡ የጥፋት ልጆች እንደሆኑ ለመናገር እወዳለው። ሚስጥርን የሚያውቅ እግዛአብሔር ብቻ ነው ሚስጢርን የሚፈታ እግዛአብሕር እና እርሱ የመረጣቸው ቅዱሳኑ እንደሆኑ እናውቃለን። ይቺን አገር ጠላቶች ማንበብ ወይም ማወቅ አይችሉም። ስትታይ አቅም የሌላት የምትመስል… ጠላት ሲመጣ እሳት ሆና የምትፋጅ ናት። ብዙ ተመራማሪወች አዳዲስ ግኝቶች እያገኙ አዲስ ነገር የሚናገሩላት  ድንቅ አገር በእግዚአብሔር የምትጠበቅ ይህቺ አገር ምስጢር ናት።

ይቆየን

ከ-ከተማ ዋቅጅራ

13.04.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

The post ይህቺ አገር ምስጢር ናት!!! – ከ-ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

(የሳዑዲ የመን ጉዳይ) –“የወሳኙ ማዕበል ”ዘመቻ የመሰንበቻው አበይት ክንውኖች!

$
0
0

የመረጃ ግብአት …
========================

የዘመቻው ቃል አቀባይ መግለጫ …
=======================

* የወሳኙ ማዕበል ሳውዲ መራሽ ዘመቻ በሁቲ አማጽያንን ላይ ከተጀመረ ወዲህ የአማጽያኑን የመከላከልና የማጥቃት አቅም ለማዳከም 1200 የአየር ጥቃቶች መደረጋቸውን የዘመቻው ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በሶስተኛ ሳምንት በደፈነው ዘመቻ ገለጻቸው አስታውቀዋል
saudi 1
* አማጽያኑ በተከፈተባቸው የህብረቱ አየር ድብደባ በከፍተኛ ሁኔታ የአየር ሀይልና የምድር ጦር መሽመድመ ዳቸውን ቃል አቀባዩ ሲያስታውቁ በየመን ግዛቶች በሸብዋን ፣ አብያን ፣ ላህጅና ያፍዕ በምድርም አማጽያኑን የሚቃወሙ ሀገር ወዳድ የጎሳ መሪ የመናውያን ጠመንጃ አንስተው እየተፋለሟቸው መሆኑን ጠቁመዋለል። የህብረቱ ቃል አቀባይ በማከልም በምድር የተጀመረውን የየመናውያን እንቅስቃሴ ህብረቱ ድጋፍ እንደሚሰጠውም ተናግረዋል
* የኢራንና የሂዝቦላህ ሁቲዎችን በመደገፍና በማሰልጠን በየመን ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸው አዲስ አለመሆኑን የጠቆሙት ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በመግለጫቸው ተያዙ ስለተባሉት ሁለት ኢራናውያን ተጠይቀው መያዛቸውን አረጋግጠዋል

* በየትኛውም የባህር ፣ የምድርም ሆነ በአየር መገናኛዎች የሁቲ አማጽያን ድጋፍ ሊያገኙ የሚችሉባቸው መንገዶች ሁሉ መዘጋጋታቸውም የሳውዲ መራሹ ዘመቻ ቃል አቀባይ ተጠቁሟል

* ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ 35 ሽህ ቶን ሰብአዊ እርዳታ የያዘች የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል አውሮፕላን ዘመቻው ለተጀመረ ለሁለተኛ ጊዜ የመን ሰንአ ገብታለች

* የፖኪስታን ፖርላማ የሀገሪቱ ጦር ለሳውዲ ህልውና ያለውን ጽኑ ድጋፍ ቢያረጋግጥም በሳውዲ የሚመራውን የአረብ ሀገራት በየመን ሁቲ ላይ የከፈቱትን የወሳኙ ማዕበል ዘመቻ ጦሩ እንደማይቀላቀል ውሳኔ ማሳለፉ የገልፍ ሀገራትን አላስደሰተም

* የኢራን ፕሬዚደንት ሀሰን ሮሄኒ የየመን ጦርነት በውይይት መፈታት አለበት ሲሉ የመንግስት የበላይ የሆኑት የሀይማኖት አባት አያቶላህ አሊ ሆሜኒ በበኩላቸው ሳውዲ አረቢያ በየመን የዘይዲ ጎሳ የሁቲ ተዋጊዎች ላይ የወሰደችውን የአየር ድብደባ ” የሰው ዘር ማጥፋት ነው !” ሲሉ ባሳለፍነው ሳምንት አጥብቀው ኮንነውታል

* በእስካሁኑ የየመን ግጭት 643 ነፍስ ሲቀጠፍ 2,200 ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የአለም አቀፍ ጥበቃ ድርጅት World Health Organisation መረጃ ጠቁሟል

የሳውዲ የመን ድንበር ውጥረት …
======================

* በነጅራንና በጀዛን በሚዋሰኑት የሳውዲ የመን የጠረፍ ከተሞች ከዚህ ቀደም ከሞቱት 3 የሳውዲ ድንበር ጠባቂ ወታደሮች በተጨማሪ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ 3 የሳውዲ ድንበር ወታደሮች በነጅራን ድንበር መሞታቸው ሲጠቆም 500 ያህል የሁቲ አማጽያን የወሳኙ ማዕበል ዘመቻ ከተጀመረ መገደላቸውን የህብረቱ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ አስታውቀዋል

* የሳውዲ የመን የጠረፍ የገጠር መንደሮች የሚገኙ ከ900 በላይ ሳውዲ አባዎራዎች ለደህንነታቸው ሲባል ከአካባቢው ተነስተው ወደ ውስጥ ከተማ እንዲሰፍሩ ተደርጓል

* ከየመን በጦርነቱ እየተፈናቀሉ እየሸሹ ወደ ሳውዲ የሚገቡት የመናውያን ቁጠር ከፍ እያለ መምጣቱ ተዘግቧል

* በሳውዲ የጠረፍ ከተሞች የሚገኙ ት ት/ቤቶች ለደህንነት ሲባል ተዘግተዋል

ኢትዮጵያውያን በየመን …
=================

* ዛሬም ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የየመን ከተሞች በጭንቅ ላይ ናቸው ፣ በሰንአ ጦርነቱን ተከትሎ ህገ ወጥነት ሲንሰራፋ ፣ ኑሮው ተወዶ እሳት ሆኗል ፣ ከተባበሩት መንግስታት መጠለያና ከመጠለያ ውጭ ያሉ ዜጎች በአደጋ በጦርነት መካከል የድረሱልን ዋይታቸውን እያሰሙ ነው

* በሰማይ የህብረቱ ጦር የአየር ድብደባ ፣ በምድር የሁቲና በተቃዋሚዎቻቸው ፍልሚያ ሰላሟን የነሳት ሁለተኛዋ የየመን ጥንታዊ የወደበረ ከተማ በኤደን ያሉ ኢትዮጵያውያን ከከባቸው አደጋ አንጻር የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዋል ፣ ደራሽ ባያገኙም “ድረሱልን!” እያሉ ነው!

* መሪ በሌላትና በጦርነት ሁከት እየፈራረሰች ባለችው ሀገረ የመን የተለያዩ ከተሞች ” በህገ ወጥ መንገድ ወደ የመን ገባችሁ! ” ተብለውና በሌላም ሌላ ጥቃቅን ጉዳዮች ለተለያዩ እስር የተዳረጉ ዜጎቻችን የረሃብ ጥማቱ ችጋር በርትቶባቸው በአደጋ ላይ መሆናቸውን እየሰማን ነው

* 700 ያህል ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት ሲያስረዳ ፣ ጠኔ ረሀቡ በርቶባቸው ከሰንአ አቅራቢያ ያለ አንድ እስር ቤትን ሰብረው ሊወጡ ሲሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን የመገደላቸውን ፣ 11 ያህል የመቁሰላቸውንና የተረፉት በጠባቂዎች ዱላ መነረታቸውን ከወደ ሰንአ ግሩም ተክለ ሀይማኖት የተገደሉት ኢትዮጵያን በፈሰሰበት መሬት ላይ ቆሞ እንደነበረ በገለጸልን ልብ ሰባሪ መረጃውን ጠቁሞናል

* ከአውሮፓ ሀገራት እስከ እስያና ሩቅ ምስራቅ ሀገራት በየመን ያሉ ዜጎቻቸውን ለማውጣት ተረባርበው ተሳክቶላቸዋል ።

* የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎችን ለማውጣት መዝገባ በጀመረ ማግስት 30 ዜጎቹ በኤደን በኩል በጅቡቲ አድርገው ወደ ሀገር ቤት መግታቸውን አስታውቋል ። ማን ረድቶ አሸጋገራቸው የሚለው አሁንም አወዛጋቢ ቢሆንም መግባታቸው ግን እውነት ነው

* መንግስት በቀጣይ ዜጎችን ከየመን ለመመለስ ” ጥረት እየተደረገ ነው !” ተብሎ እስካሁን 3000 ገደማ መታወቂያና ፖስፖርት ያላቸው ተመርጠው መመዝገባቸው ይጠቀሳል

* ከተመዘገቡት መካከል ወደ ሀገር ትመለሳላችሁ ተብለው ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ መሳፈሪያው ያመሩ ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል

* ምዝገባው መታወቂያና ፖስፖርት ያላቸውን ብቻ ስለሚያካትት በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መጠለያ የነበሩት ኢትዮጵያውያን እና በባህር የገቡ ፖስፖርትና መታወቂያ የሌላቸው ተንገዋለው መቅረታቸውን በምሬት እየተናገሩ ነው ። ያም ሁሉ ሆኖ መስፈርቱን አሟልተው እየተለዩ ከተመዘገቡት ውስጥ ወደ ሀገር የተመለሰ እስካሁን አልታየም ፣ አልተሰማም !

እስኪ ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 5 ቀን 2007 ዓም

The post (የሳዑዲ የመን ጉዳይ) – “የወሳኙ ማዕበል ” ዘመቻ የመሰንበቻው አበይት ክንውኖች! appeared first on Zehabesha Amharic.

የምሥራች! የአንድ ደሮ ዋጋ የዐርባ አምስት በሬ ዋጋ ሆነ!

$
0
0

ነፃነት ዘለቀ (አዲስ አበባ)

ክርስቲያን አንባቢዎቼ እንኳን ለ2007ዓ.ም የጌታችን የመድሓኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፡፡ ሙስሊሞችና ሌሎችም እንኳን ለኛ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ለእናንተም በዓል(ላት) በሰላም እንዲያደርሰን የጋራ የሆነውን ፈጣሪን በጋራ እንለምነው፡፡
ይቺ የዘንድሮ የትንሣኤ በዓል ከቀደሙት ትንሽ ለዬት ሳትል አትቀርም፡፡ ይሄ ግፋፎ ብር እዬለየለት መጥቷል፡፡ የሰሞኑ ገበያ በጣሙን ተበሻቅጧል፡፡ መንግሥቶቻችን ሲያቀብጣቸው ብሩ ላይ የወፍ ስዕል አኑረውበት ብሩ በዓለማችን የመጨረሻው ፈጣን ወፍ ሆነ፡፡ ሲበር ፍጥነቱ ልዩ ነው፤ በሣይንሳዊ መሣሪያ እገዛ ካልሆነ በዐይን ብቻ አይታይም፡፡ አቶ ብሩ ጉድ አፍልቷል፡፡ በአብዛኛው ከሆዱ ባለፈ የማይጨነቅ የልምድ ነጋዴ በሞላባት ሀገራችን ውስጥ በአቋራጭ ለመክበር የሚስገበገበው ሰው በዛና አቅልን የሳተ የገንዘብ ግንኙነት ነግሦ ሁላችንንም አቅል እያሳጣን ከሰውነት ተራ እያስወጣን ይገኛል፡፡ የዛሬው አዋዋሌ ራሱ ከወትሮው የተለዬ ሆኖብኝ በጣም ሲገርመኝ ውሎ አመሸ፡፡ ከማን ጋር እንደማወጋው ጨንቆኝ ሳለ እናንተ ትዝ አላችሁኝ፡፡ እስኪ ተንፈስ ልበል፡፡
chiken
ትዳር ያደረገ ልጄ(በትግርኛ አማርኛየ ቅር አትሰኙም መቼም) – ለአቅመ-በግ ያልደረሰ በቅርብ ትዳር ያደረገ ልጄ ደሮ አጋዛኝ ብሎ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ይደውልልኛል፡፡ ወዲያውኑ እንገናኝና የካ ሚካኤል አካባቢ ወዳለው ሾላ የደሮ ገበያ እንሄዳለን፡፡ ትርምሱ ሌላ ነው፡፡ ከቤት የቀረ ሰው ያለም አይመስልም፤ በዚያም ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እዳር ተመካክሮ ሰው ከማፍራት ውጪ ተኝቶ የሚያድር አይመስልም፤ የሰው ፋብሪካ በየቤታችን የተከልን እንመስላለን – ብዛታችን ሲታይ፡፡ ለማንኛውም ከልጄን ጋር የተለያዩ ሸቀጦችንና ዕቃዎችን ዋጋ በእግረ መንገድ እየጠያየቅን ወደደሮ ተራ አመራን፡፡ የሁሉም ነገር ዋጋ ሰማይ ነው፤ ከምናውቀው ሰማይ በላይ ሌላ ሰማይ ካለም ከዚያም በላይ፡፡ የሁሉም ሸቀጥና ዕቃ ዋጋ ያስደነግጣል፡፡ ሁሉም ነጋዴ ቁጥር የሚያውቅ አይመስልም፡፡ ቁጥሩ ቀላል የማይባለው ሸማችም እንዲሁ ቁጥር የሚያውቅ አይመስልም፡፡ ነጋዴው ስምንት መቶ የሚለውን የቻይና አቃጣይ ጫማ – ከሁለትና ሦስት ዓመታት በፊት ከሁለት መቶ በዘለለ የማይሸጠውን ጫማ ማለት ነው – ብዙም ሳይከራከር በሰባት መቶ ሃምሳ የሚሸምት ገዢ አለ፡፡ ተራዋ የላስቲክ ነጠላ ጫማ እንኳ ነፍስ አውቃ መቶና መቶ ሃምሳ ብር ስታወጣ ማየት ብርቅ ከመሆን አልፏል፡፡ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ደሞዝ ባለበት እየረገጠ የዕቃዎች ዋጋ በየሴከንዱ ሽቅብ እየተወነጨፈ እንዲህ ያለ ተናግዶት ማየት ገንዘቡ ከየት መጣ ያስብላል፤ አንዳንዱ ሰውማ ከቤቱ ውስጥ ገንዘብ ማተሚያ ማሽን ያለው ይመስላል፡፡

ኑሯችን ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ ተቆጣጣሪ ብሎ ነገር የለም፡፡ ያለውና የሌለው በምን ምክንያት እንዳለውና እንደሌለው ሊታወቅበት የሚያስችል አንድም ሕጋዊ መንገድ የለም፡፡ በሀገራችን መንግሥት አለ ማለት የሚያስችል ምንም ዓይነት ምልክት ደግሞ አይታይም፡፡ በኪነ ጥበቡ ውለን ከመግባታችን በስተቀር የመንግሥትን ቀርቶ የሕዝብን ኅልውና የሚያስረግጥ አንድም ነገር ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ዛሬ ሃያ ብር የሚሸጥ ነገር ነገ በትንሹ መቶ ብር ሲሸጥ ማየት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት የሚከብደው ሰው አይኖርም፡፡ የሀብት ክምችት እሽቅድምድሙ እንደመቶ ሜትር ሩጫ ፍጥነቱ ንፋሳዊና ብርሃናዊ ሆኗል፡፡ በዚህ ላይ ዳኛ የለ፤ ታዛቢ የለ፤ ሕግ የለ፤ አዳሜን እየረጋገጥህና እየረመረምክ ባዋጣህ መንገድ መሮጥና የምትፈልገው የሀብት ደረጃ ላይ ወጥተህ ፊጥ ማለት ነው፡፡ የመንግሥት አካላት ደግሞ አሯሯጮች ብቻ ሣይሆኑ ሯጮችም ናቸው፡፡ ስለዚህም በሩጫው ተረገጥኩ ብለህ የምታመለክትበት ቅሬታ ሰሚ ቢሮ የለም፡፡ ተጋግጠህ ከሩጫው ሜዳ ትወጣለህ ወይም እንደምንም ብለህ እዚያው ትንከላወሳለህ፡፡ እንዳሁኑ የጠበቀ ሕግ ሳይወጣለት በዱሮ ዘመን የእግር ኳስ ጨዋታም እንዲህ ነበር አሉ – ማንም ጉልበተኛ ኳሷን በጥበብ ሣይሆን በጉልበት ነጥቆ በመውሰድ እግብ የሚከትበት፡፡ በሀገራችን የአሁን ሁኔታ በገቢህ ላይ ምንም የተጨመረ ነገር ሳይኖር ዋጋዎች እንዲህ ሲንሩ ስታይ ሕይወትህ በነሲብ የሚነዳ እንጂ በህግና በሥርዓት የሚመራ አይመስልህም፡፡ ደናቁርት ደናቁርትን እየጎተቱ ወደ ገደል እየጨመሩ ናቸው፡፡

ዝኮነ ኮይኑ ልጄና እኔ ዶሮ ተራ ገባን፡፡ ከድስት የማይወጣ ጫጩት ዶሮ ዋጋው 250 ብር ይሉናል፡፡ እዚያም እዚህም ስንጠይቅ የተማከሩ ይመስል – ተማክረውም ሊሆን ይችላል – የሚጠሩትም ሆነ የሚሸጡበት ዋጋ አንድና አንድ ነው፡፡ እውነቴን ነው የምላችሁ – ብዙ ሰዎች ጫጩት ዶሮ በ200 ብርና ከዚያም በላይ በሆነ ዋጋ ሲገዙ አየን፡፡ አንዳንዱ ገዢማ ስለለመደው ይመስላል በዋጋው መናር ሲያቅማማ አይስተዋልም፡፡ እኛ ግን ደነገጥን፡፡ ሥጋ ቢኖረው ግዴለም፡፡ ግን ለወግና ባህል ሲባል ብቻ አንዲት ስትታረድ ከአየር ወርዶ መሬት የሚደርስ ደም እንኳን የሌላት ጫጩት ዶሮ በ200 ብር መግዛት ግፍ የሚሆንብን መሰለን፡፡ ልጄ ግን ሚስቱ አንደምትቆጣው አስረዳኝና እንደምንም ተከራክሮ በ190 ብር አንዱን ወንድ ጫጩት ገዝቶ በፌስታል ቋጠረው፡፡ ይህ እንግዲህ የድሆችን ዶሮዎች በሚመለከት የታዘብኩት ነው፡፡ የኮርማ ዶሮ ታሪክማ ሌላ ነው፡፡
ወደ ሀብታም ሰዎች የደሮ ግዢ ደግሞ ልውሰዳችሁ፡፡ አንዱ ሀብታም ሁለት ወፋፍራም ዶሮዎችን አነሳና ዋጋቸውን ጠየቀ፡፡ ለያንዳንዳቸው 375 ብር ተባለ፡፡ ብዙም አልተከራከረም፡፡ 700 ብር ውልቅ አድርጎ ከፈለና ሁለቱንም ገዝቶ እመኪናው ጀርባ ሸጉሮባቸው ሸመጠጠ፡፡ ያለው ማማሩ አልኩ – በልቤ፡፡ ወደሌላ የዶሮ መሸጫ ቦታ አመራሁ፡፡ የኔ ቤት ድስት የማይችለውን አንድ ዶሮ አንዷ ሴት ሀብታም ብድግ አደረገችና ዋጋውን ጠየቀች፡፡ አምስት መቶ ብር ተባለች፡፡ እንደነገሩ ተከራከረችና በአራት መቶ ሃምሳ ተስማምታ ይዛው እብስ አለች፡፡ አንድ ዶሮ አራት መቶ ሃምሳ ብር! ይህን ትክክለኛ መረጃ ከሌላ ቦታ የምታገኙት አይመስለኝም፡፡ አንድ ዶሮ አራት መቶ ሃምሳ የኢትዮጵያ ብር ሲሸጥ እቦታው ነበርኩ፡፡ ጉድ ነው፡፡ ዶሮው ግን እንዳልኳችሁ ፍሪዳን ያስነቃል፡፡ ቢሆንም ግን ዶሮ ነው፡፡ በሬ ወይም በግና ፍየል አይደለም፡፡ እናም ዶሮ 450 ብር ሲያወጣ አየሁ፡፡ በዱሮው ዘመን አሥር ብር ፍሪዳ ይገዛ ነበር፤ እናም ዘንድሮ አንድ ዶሮ የተገዛበት ብር በዱሮው ዘመን ዐርባ አምስት ፍሪዳ ይገዛበት ነበር ማለት ነው፡፡ የሒሣብ ዕውቀቴ ወንዝ ባያሻግርም ከዚች የዶሮ ግዢ ነጥብ አንጻር የገንዘባችን ግሽበት 4500% ይመስለኛል፡፡ ዱሮ በግራም ሁለትና ሦስት ብር ይሸጥ የነበረውን የ18 ካራት ወርቅ ከአሁኑ ሰባት መቶና ስምንት መቶ ብር ዋጋው ጋር ስታነጻጽሩትም ግሽበታዊ ሥሌቱ በድንጋጤ ደም ቀጥ ያደርጋል፡፡ በ“ሰው በላው ሥርዓት” በኪሎ አንድ ብር ይሸጥ የነበረው ቅቤ ዛሬ 210 ብር ሲሸጥ ዕድገታችንን ለመለካት ምን መሣሪያ መጠቀም እንዳለብን ለማወቅ ወያኔን መጠየቅ ነው፡፡ ዱሮ በ120 ብር የሚሸመተውና ማንም ተራ ዜጋ የሚለብሰው የእንግሊዝ እውነተኛ ከሱፍ የተሰፋ ሙሉ ልብስ ዛሬ ሌላ ነገር ተቀያይጦበት በአሥራዎቹና ሃያዎቹ ሺዎች ሲገዛና የደረጃ መለያ ሲሆን ዕድገታችን የደረሰበትን ጫፍ ማሰብ እንችላለን፡፡ በቅርብ በደርግ ዘመን እንኳን በሦስት ሺህ ይገዛ የነበረ ያማሃ ሞተር ሣይክል ዛሬ ከመቶ ሺ ብር በላይ ሲገዛ የገንዘባችንን “ጥንካሬ” ያሳያል – ሊያውም እኮ በወረፋ ለወራት ጠብቀህ፤ መኪናውም እንዲሁ ነው፡፡ አሁን ለጥገና ብቻ የምታወጣው ገንዘብ ዱሮ ብዙ መኪናዎችን ሊገዛልህ የሚችል ገንዘብ ነው፡፡ አሁን አንድ ቤት ለመሥራት አስበህ ለምስማር ብቻ የምታወጣውን ወደዱሮው ብትመነዝረው ያኔ አንድ ቪላ ቤት ሊሠራልህ ይችላል፡፡ ዱሮ አሥር ብር መንዝረህ ለመጨረስ “የጓደኛ ያለህ” እንዳላልክ ዛሬ አሥር ብር አንዲት ቡትሌ ቢራ እንኳን የማይገዛ ከንቱ ወረቀት መሆኑን ስትረዳ ሀገርህ ከየት ወዴት እያመራች እንደሆነ ቁልጭ ብሎ ይታይሃል፡፡ በሌላ አቅጣጫ ደግሞ ሚስቱ ልጅ ስለወለደችለት ፈረስ በሚያስጋልብ አዳራሽ ቅልጥ ያለ ድግስ ደግሶ ከአልማዝና ዕንቁ ውድ ስጦታዎች በተጨማሪ የ2.5 (ሁለት ነጥብ አምስት!) ሚሊዮን ብር መኪና ቁልፍ ለሚስቱ በስጦታ መልክ የሚያበረክት የትናንት ሙልጭ ድሃ የዛሬ ወፍዘራሽ ከበርቴ በቀየህ ትታዘብና የት እንዳለህ ታውቅ ዘንድ ዐይንህን ብታሽ ከድቅድቅ ጨለማ ውጭ የሚታይህ ሌላ ነገር የለም፡፡ ጥሬ እውነት ነው እየነገርኩህ ያለሁት – ለሥነ ጽሑፍ ውበት ብዬ ያጋነንኩ እንዳይመስልህ፡፡ …

በዕድሜየ ቆዳ መልስ ሁለትና ሦስት ብር በግና ፍየል ሲሸጥ አይቻለሁ፡፡ በዚያን ዘመን አንድ አነስተኛ ከብት(በሬ/መሲና) በግልም ሆነ በቡድን ለማረድ በትንሹ አሥር ብር ያስፈልግ እንደነበር ቀድሜ እንደጠቆምኩት እኔ ራሴ ኅያው ምሥክር ነኝ፡፡ ያኔ ከአሥር ብር እስከ ሃምሳ ብር ይሸጥ የነበረው በሬ ዛሬ እስከ ሃያ ሺህ ብርና ከዚያም ባለፈ እስከ ስልሣ ሺህ ብር ድረስ መቸብቸቡን፣ ያኔ ከ12 ዕንቁላሎች ጋር 10 ወይም 15 ሣንቲም ይሸጥ የነበረው ዶሮ ዛሬ ያለ አንዲትም ዕንቁላል 450 ብር መሸጡን ለታሪክ ፍጆታም ቢሆን መዝግቡልኝ፡፡ ዕንቁላልማ ቀድሞ በአንድ ብር መቶና ከዚያ በላይ የነበረው ዛሬ አንዲት ዕንቁላል ብቻ 3 ብር ከሃምሳ ገብታለች፡፡ ተረት ተረት የላም በረት! ኑሯችን ተረት ተረት ሆነ፡፡ የጥንቶቹ የኛን ኑሮ ኖሩና አለፉ፤ እኛ ደግሞ ዕዳ ከፋይ ብቻ ሆነን ቀረን፡፡ እናሳዝናለን – አዛኝ ቢኖር፡፡ መጨረሻችንን ማየት ጓጓሁ፡፡

የበጉንና የፍየሉን ገበያ ያየን እንደሆነም ያው ነው – የተለዬ ነገር የለውም፡፡ ጭቅላ በግና ፍየል ይዞ በሺዎች መጥራትና መሸጥ የተለመደ ነው፡፡ ሰውም ለምዶታል፡፡ ሀበሻ ደግሞ በዓመት ሦስቴና አራቴ ብቻ የሚኖር ይመስል በዓል በመጣ ቁጥር ቤቱን እያራቆተ ከሰው ላለማነስ በሚል ጅል ፈሊጥ በተጠየቀው ዋጋ ሁሉንም ነገር ይገዛል፡፡ አንዳንዱማ ሳይገዛ መተው ራሱ እንደምርጫ አይታየውም፡፡ ባይገዛ የሚሞት ይመስለዋል፡፡ ነገ ለማከክ የዛሬን በዓል በቅርጫም፣ በዶሮም፣ በበግ/በፍየልም ማሳለፍ ይወዳል፡፡ አብዛኛው ይህን የሚያደርገው ለባህሉና ለቤተሰብ ፍላጎት እንጂ አቅሙ ፈቅዶለት አይመስለኝም – ከእግር ጥፍሩ እስከራስ ፀጉሩ በዘመድ አዝማድ ብድርና በመሥሪያ ቤት ዕዳ የሚወጣጠረው ሰው ብዙ ነው – ይህ የከማን አንሼ ባህል ጠፍቶ የማይበት ዘመን ይናፍቀኛል፤ ብዙዎቻችንን ከሰው በታች እያደረገን ያለ ይሄው መጥፎ ልማድ ነው፡፡ በተረታችን “ሰው እንደቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ አይኖርም” የሚል ትክክለኛ ብሂል አለን – የሚተገብረው ግን ጥቂቱ ሰው ነው፡፡ የሠርግና የልደት ወይም የክርስትና ድግሶችን ብናይ ብዙ ያነጋግረናል፤ ምን አለፋችሁ የባህል አብዮት ማካሄድ ከምንም በላይ ያስፈልገናል፡፡ በዚህ ሰሞን በዓል ሲተረማመስ የሚታየው ሁሉ ወግና ልማድ ለማሟላት እንጂ ውስጡ አምኖበት እንዳልሆነ መገመት አይከብድም፡፡ አለባበሱ የተጎሳቆለ ሰው በሁለት መቶ ብር ዶሮና በሁለት መቶ አሥር ብር አንድ ኪሎ ቅቤ ገዝቶ ወደቤቱ ሊሄድ የታክሲ መሣፈሪያ እንኳን ቸግሮት በእግሩ ሲንጠራወዝ ስታዩት ምን ያህል የባህል እስረኛ እንደሆነ በማጤን ከልባችሁ ታዝኑለታላችሁ፡፡ መማር ዓይነቱና የጥራት ደረጃው ቢለያይም እንዳለመማር ያለ ክፉ ደዌ ግን ሊኖር አይችልም፡፡ የኛን ማኅበረሰብ ከልጅነት እስከዕውቀት ስታዘበው ብዙም የተለወጠ ነገር የለውም፡፡ ቀጣዩ መንግሥታችን ብዙ ሥራ ይጠብቀዋል፡፡ እግዜር ያጽናው፡፡ በሥርዓት ለመምራት ብቻ ሣይሆን በቅጡ ለመመራት የተዘጋጀ ዜጋ ማግኘትም ራሱ ከባድ መሆኑን ልናምን ይገባል፡፡ አስፈሪ ነው፤ እግዜር ይሁነን፡፡

ወደደሮኣችን እንመለስ፡፡ በበኩሌ ዋጋው ውድ ስለሆነብኝ ሳልገዛ ቤቴ ገባሁ፡፡ ማንጠግቦሽ አራስ ነብር ሆና ጠበቀችኝ፤ ክፉኛም ተቆጣችኝ፡፡ ራስሽ ሂጅና ግዢ ብዬ እኔም ተቆጣሁ – ለመቆጣት ማን ከማን ያንሳል፡፡ ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ከነበርኩበት ቦታ ተጣድፌ ስመጣ አጅሪት ምንም ሳትገዛ መጥታ “ነፁ፣ በጣም ይቅርታ አድርግልኝ፡፡ ጫጩት በሁለት መቶ ሃምሳ ብር ገዝቼ ከምመጣ ብዬ ተውኩት፡፡ ነገ ጧት ወደ … ትሄድና ሁለት ኪሎ ሥጋ ገዝተህ ጦማችንን እንገድፋለን፡፡…” አለችኝ፡፡ ያኔ በሃበሻዊ ያሸናፊነት ስሜት ኮራ አልኩና ተደሰትኩ፡፡ ሁሌ ተወቃሽ ነበርኩና ዛሬ ግን ከርሷው ከባለቤቴ በመምጣቱ በቤታችን ደም ያለመፍሰሱ እምብዝም እንግዳ ያልሆነ ክስተት የሁለታችንም ስምምነት በመሆኑ ከእስከዛሬው በበለጠ እኔን አስኮፈሰኝ፡፡ ሌላ ጊዜ “ገንዘብ እንዳታወጣ ብለህ እንጂ ደሮ መቼ ተወደደና…” እያለች ትነተርከኝ ነበርና፡፡

ቅቤ እንዳልኳችሁ 210 ብር አካባቢ ነው፡፡ ዱሮ በገረወይና 18 ብር የነበረ ቅቤ አሁን እንዲህ ሆነና ለመድሓኒትም ብርቅ ሆነ፡፡ ሊያውም ትክክለኛ ቅቤ፣ ትክክለኛ ዘይት፣ ትክክለኛ የበርበሬ ድልህ፣ ትክክለኛ ሥጋ፣ ትክክለኛ ቆጥረህ የማትዘልቀው ሸቀጥ ሁሉ በቀላሉ አይገኝም፤ ሀገር ምድሩን ያጥለቀለቀው የቀጣፊ “ፌክ”ና “ፎርጅድ” ምርት ነው፡፡ አስገራሚ ነገር ልንገርህ፡- አዲስ አበባ ውስጥ ጨለማን ተገን በማድረግ በየሠፈሩ የሚሠራ “ቅቤ” በአይሱዙ መኪና ይጫንና ወደሸኖ ይሄድልሃል፤ ከዚያ ከአይሱዙው ጋር ተጭነው የሄዱ ሰዎች – ሊፍት ተሰጥቷቸው ወይም ገንዘብ ከፍለው የተሣፈሩ ሰዎች – “የሸኖ ቅቤ ገዛን” እያሉ ተሣፍረው በሄዱበት መኪና ወደሸኖ የተጓዘውን “ንጹሕ ቅቤ” በውድ ዋጋ ገዝተው ይመለሳሉ፡፡ ሲያነጥሩት ግን ይምበከበክና ጥቂት ቅቤ ይወጣዋል አለዚያም የማይረባ ይሆንና ከናካቴው ይደፋል፡፡ በሌሎች ነገሮችም እንዲሁ ነው፡፡ አንድን ነገር በሊትርም ግዛ፣ በኪሎም ግዛ፣ በሜትርም ግዛ፣ በክንድ ልኬትም ግዛ በአብዛኛው ግን ትሸቀባለህ ወይም ውዳቂ ዕቃ ይዘህ ወደቤትህ ትሄዳለህ – ስንቱ ቀልጧል መሰለህ፡፡ በዚያ ላይ ዕድሜ ለቻይና እሷም ከስግብግብ ነጋዴ ጋር እየተሻረከች ከደረጃ በታች የሆነ ምርት ከከተማ እስከ ገጠር እያሰራጨች እስከመቅኒያችን ድረስ ገብታ እየመጠመጠችን ነው፤ አቤት የገባንበት ዕዳ! ከዚህ ሁሉ ሲዖላዊ ሕይወት የሚገላግለን አንድዬ እንጂ በሰው ትግል ብቻ የሚሆንልን አይመስለኝም፡፡
እኔ ወንደላጤ እያለሁ በኪሎ አንድ ብር የነበረ ምሥር ክክ አሁን 40 ብር አካባቢ ነው – አሁን እየጻፍኩ ሳለሁም ሊጨምር ይችላል፤ እኛ ሀገር ደግሞ መጨመር እንጂ መቀነስ ብሎ ነገር ሲያልፍ አይነካንም፡፡ የምግብ ዘይቱ፣ አተር ክኩ፣ አትክልቱ፣ ጤፉ፣ ሽምብራው፣ ከሰሉ፣ ላምባው፣ ስሚንቶው፣ አሸዋው፣ ጠጠሩ፣ ብረቱ፣ ኮረንቲው፣ ውኃው፣ ሥጋው፣ ወተቱ፣ ምኑም ምናምኑም የዘንድሮው ዋጋ ከዱሮው ጋር ሲነፃፀር በትንሹ 1000% አድጓል፡፡ ለምሣሌ እኔ ቤት ስሠራ 41 ብር የገዛሁት ባለ14 ቁጥር አንድ ቤርጋ የአርማታ ብረት አሁን ከአምስት መቶ ብር በላይ ነው፡፡ ይህን የዋጋ ንረት ያመጣው የኢኮኖሚ ዕድገት ነው ቢሉኝ ከመሣቅ ውጭ ሌላ አማራጭ የለኝም፡፡ እኔ ወጣት እያለሁ በብር ከስሙኒ እመገበው የነበረው ባለቅልጥም ቀይ ወጥ ዛሬ በአማካይ 60 ብር ገብቷል መባልን ስሰማ “ወይ ስምንተኛው ሺህ! እንዲህም አለ ለካ!” ከማለት ውጪ ምንም ማለት አልችልም – “የዕድገታችን ነፀብራቅ ነው” በሚል ልግጫ ግን ትዝብት ውስጥ ልገባ አልፈልግም፤ ዕድገት ጥቅሞችን የሚጨምር እንጂ የሚቀንስ ሊሆን አይገባውምና፡፡ ዱሮ ሰባት ብር የነበረው አንድ ኩንታል ስሚንቶ ዛሬ ሊያውም በጣም ረከሰ ተብሎ 320 ብር መሸጡን የሚያውቅ ሰው ሀገር መውደቋን ሣይሆን ማደጓን የሚያምን ከሆነ በኑሮና በቁጥር መካከል ያለውን ልዩነት መገንዘብ የማይችል ደደብ መሆን አለበት፡፡ ዱሮ በሃያ ሣንቲም የምንጠጣው አረንሻታ(ለስላሳ) ዛሬ በየሆቴል ቤቱ በአሥራዎቹና በሠላሣዎቹ ሲሸጥ እያዬ ሀገር አደገች የሚል ካለ ስለዕድገት ቅንጣት ግንዛቤ የሌለው የለዬለት ‹ጀዝባ› ነው፡፡ ዱሮ ዐርባ ሣንቲም ይሸጥ የነበረው እንደ እርጎ የሚገመጥ ቢራ ዛሬ ብሻን ጮረሬ ሆኖ በአሥራዎቹና በስልሳዎቹ ብር ሲቸበቸብ የሚያይ ሰው ሀገራችን አደገች ብሎ የሚፈነጥዝ ከሆነ ወያኔያዊ ወገናዊነቱ እንዳለ ሆኖ ወደሚቀርበው የዕብዶች ሆስፒታል መሄድ ይኖርበታል – የዕብድ ሆስፒታላችን ከአንድ ያነሰ ቢሆንም፡፡ ዱሮ ከአሥር ሣንቲም ባነሰ ዋጋ ይገመጥ የነበረው ጠረንገሎ ፓፓያ ዛሬ በኪሎ ከሃያ ብር በታች በቀላሉ እንደማይገኝ እየተረዳ “ኑሯችን ተሻሻለ” የሚል ገልቱ ዜጋ ካለ በርግጥም ገልቱነቱ የተመሠከረለት ነው፡፡ ዱሮ ሉካንዳ ቤት ተገብቶ በ”ከዚህ መልስ ቁረጥልኝ” ለኩሊዎች ሸክም የሚከብድ ሥጋ በአንድ ብርና በሁለት ብር ይገዛ እንዳልነበር ዛሬ በምሣሌ ሆቴልና በመሳሰሉት ሆቴሎች ተገብቶ ለኪሎ ቁርጥ/ጥብስ ከአምስት መቶ ብር በታች እንደማይከፈል የሚገነዘብ ሰው ይህን ዘመን የመቅሰፍት እንጂ የዕድገትና የበረከት እንደማይለው ጤናማ አእምሮ ያለው ሁሉ የሚፈርደው ነው፡፡ ዱሮ ውኃ ጠማኝ ለሚል መንገደኛ ከወተትና ከጠላ ውጪ መስጠት ያሣፍር ነበር፤ ቆየት ብሎ ሥልጣኔ ሲጀምር ደግሞ በቀን አንድ ሊትር ወተት እየተወሰደ በወር ሁለትና ሦስት ብር ይከፈል ነበር – በሊትር ከ10 ሣንቲም በታች መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ ግን አንዲት ሊትር ወተት ከ18 ብር በታች ማግኘት አይቻልም – ሻይ ባቅሟ በብዙ ተራ ቡና ቤቶች አምስት ብርን ካለፈች ቆየች፡፡ ይህ ጊዜ የዕድገት ነው ከተባለ ያኛውና በነሼኪ ሻይ ቤት በ35 ሣንቲም ፓስታ በዳቦ ምሣና ራት ግጥም አድርገን የምንበላበት ዘመን ምን ሊባል እንደሚችል አላውቅም፡፡ የሃያ ብር ኩንታል ጤፍ ሁለት ሺህ ብር ሲገባ የሀገር ዕድገት ከተባለ፣ የስሙኒ ስኳር ለወያኔው መንግሥት ምሥጋና ይድረሰውና ከፍተኛ ቁጥጥር ተደርጎበት ብር 16.50 ሲገባ ዕድገት ከተባለ፣ የ500 ብር 16ሜ.ኪ የግንባታ አሸዋ 11000 ብር ሲገባ ዕድገት ከተባለ፣ የሁለት ብር የቆርቆሮ ምሥማር ሃምሳ ብር ሲገባ ዕድገት ከተባለ፣ የ60 ሣንቲም ቤንዚን አሁን በዓለም ደረጃ ዋጋው በጣም ጥምቡን ጥሎ እንኳን 17ብር ከ43 ሣንቲም ሲገባ ዕድገት ከተባለ፣ ከሀገሬ ስመጣ 9 ብር ከአምስት ሳንቲም ያወጣሁበት መንገድ ዛሬ 150 ብር ግድም በመንግሥት አውቶቡስ ስጠየቅበት ዕድገት ከተባለ፣ አንዳች ነገር ቀምሶ ማደር የሚያቅተው የሕዝብ ቁጥር የትዬለሌ መሆኑ እየታወቀ በጥቂቶች መዘባነን ዕድገት የሚለካ ከሆነ፣ ከሁለትና ሦስት ሰዎች ስደት ተነስተን ብዙ ሚሊዮን ዜጎች አገዛዙን እየጠሉ ወደ ውጪ ሲጎርፉ አሁንም ዕድገት ከተባለ፣… “ዕድገት” የሚለው ቃል ከነባር ፍቺው ተዛንፏልና አዲስ ትርጓሜ ሊያገኝ ይገባዋል፡፡ ለማንኛውም በድጋሚ መልካም አዲስ ዘመን – ማነው – መልካም ትንሣኤ ይሁንልን፡፡
ለገምቢና አስተማሪ አስተያየት፡- nzeleke35@gmail.com

The post የምሥራች! የአንድ ደሮ ዋጋ የዐርባ አምስት በሬ ዋጋ ሆነ! appeared first on Zehabesha Amharic.

መማር እንችላለን ወይ? -አንዱዓለም ተፈራ

$
0
0

አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ

ረቡዕ፤ ሚያዝያ ፯ ቀን ፳፻፯ ዓመተ ምህረት ( 04/15/2015 )

eskemecheከ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረቱ የየካቲት ሕዝባዊ መነሳሳት ጀምሮ፤ ለመብት፣ ለነፃነትና በሰላም ሠርቶ ለመኖር ያለው ትግል፤ ሳያርፍ በተከታታይ አሁንም እየተካሄደ ነው። በነዚህ ባለፉት ፵ ዓመታት፤ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፤ በትግሉ ከሕዝብ ጎን ተሰልፈው ሕይወታቸውን ሠጥተዋል። ቆራጥ የሕዝብ ጠበቃዎች ወጥተዋል፤ ሕይወታቸውን ላመኑበት ዓላማ በቆራጥነት በመሥጠት በጀግንነት ተቆጥረዋል። ትውልድ አልፎ ትውልድ ተተክቷል። በግለሰብ ደረጃ፤ አጥንት የሚሰብሩ፣ ደም የሚነውጡ፣ ልብ የሚነኩ፣ አንጀት የሚያንሰፈስፉ፣ ጀግንነት የተሞላባቸው ተግባራት ተከናውነዋል። ድርጅቶች ተነስተዋል፣ ወድቀዋል። በድርጅቶች ደረጃ፤ ሕዝባዊ ጉዳዮችን መልክ ባለው መንገድ አመቻችተው ባደባባይ አውጥተዋቸዋል። አባሎቻቸው ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለውበታል። መሪዎቻቸው ከፍተኛ መሯሯጥን የኑሯቸው ማዕከል አድርገው መርተውበታል። በወቅቱ በተደረጉት ክንውኖች ላይ ጽሑፍት ጎርፈውባቸዋል። ግጥሞች ተደርሰውባቸዋል። መጽሐፍት ታትመውባቸዋል።

አሁንም እንድትናንቱ ትግሉ ቀጥሏል። አሁንም የነበሩት ጥያቄዎች ባሉበት ቆመዋል። አሁንም መብት፣ የሀገር ሰውነትና በሰላም ሠርቶ መኖር ማዕከላዊ ጥያቄዎች ናቸው። ለምን ወደፊት መሄድ አልተቻለም? ለምን ትግሉ ባህልና ቋሚ ሆኖ አብሮን ይኖራል? ለዚህ መልስ መሥጠት ቀላል አይደለም። በአንድነት፤ በሀገር ደረጃ፤ እስካሁ ካደረግነው ትግል ምን ትምህርት እናገኛለን? የሚለውን በመፈተሽ፤ የመጀመሪያውን ወደ ስኬት ለመሄድ የሚደረግ እርምጃ፤ መራመድ እንችላለን። ይህ የግድ መደረግ አለበት። ባንድ ጽሑፍ፣ ባንድ ውይይት፣ ባንድ ትዕይንተ ሕዝብ፣ ባንድ ምሽት፣ ባንድ ግጥም አይከናወንም። ካለፈው ካልተማርን፤ ያለፈውን ባለፈው መንገድ መድገማችን አያጠራጥርም። ለዚህም ይኼው ፵ ዓመት ባስቆጠረውና እየቀጠለ ባለው ትግላችን፤ እያስመሰከርነው ነው። የሚቀጥለው እንዲስተካከል፤ ያለፈው መመርመር፤ በጎና በጎ ያልሆኑ ጎኖቹ ተለይተው መውጣት፤ አለባቸው። እናም ለኛ ትምህርቱ ቢያንስ አሁን መጀመር አለበት። እስኪ እኔም፤ ለዚህ ከፍተኛ ትኩረት ተሠጥቶት፤ በብዙዎች ብዙ መጻፍ ባለበት ጉዳይ ላይ፤ በኔ አመለካከት ምን ነበርና ምን ትምህርት እንወስዳለን የሚለውን ልነካካ።

የ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረቱ የየካቲት ሕዝባዊ መነሳሳት የተከሰተው፤ የፖለቲካ ድርጅቶች በመድረክ ላይ በገሃድ ባልታዩበትና በአንድነት ተሰባስቦ የመታገል ልምዱ ባልዳበረበት ወቅት ነበር። በርግጥ የተማሪ ማኅበሩ፣ የአርሶ አደሮች በየቦታቸው በተደጋጋሚ ያደረጉት እንቅስቃሴ፣ አነስተኛ የነበረው የሠራተኛው ክፍል መነሳሳት፤ ለዚህ የ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረቱ የካቲት ሕዝባዊ መነሳሳት ያለጥርጥር መሠረቱ ነበር። ትልቁ ክፍተት የነበረው፤ ሀገራዊ ራዕይ ይዞ፣ ታዋቂነትን አንግቦ፣ መዋቅር ዘርጎቶ፣ ልምድና ዝግጅትን አከማችቶ፣ በሕዝቡ ዘንድ መርኀ-ግብሩን አሰምቶ፣ በቦታው የነበረውን ሕዝባዊ መነሳሳት መሪ የፖለቲካ ድርጅት አለመኖሩ ነው። እናም ትክክለኛ ሕዝባዊ ጥያቄዎች የትግሉን አየር ሞልተው በተመሙበት ወቅት፤ የሕዝቡን መነሳሳት ቀዳዳ ተጠቅመው፤ ሥልጣን ወዳድ ወጣት መኮንኖች፤ ሕዝቡን አግልለው፣ ትግሉን አኮላሽተው፣ ሀገር ወዳድ ተማሪውን ፈጅተው፣ ሀገራችንን ደም በደም ለቃልቀው፣ የደም ጥማታቸውን ካረኩ በኋላ፤ በወራዳውና ሰው በላ አረመኔ መሪያቸው፤ በመንግሥቱ ኃይለማርያም አማካኝነት፤ ለአሁኖቹ ተረኛ ተባዮች አስረከቡን። በዚህ ደርጋማ መንግሥት ዘመን ትግሉ ምን መልክ ያዘ? በዚህ ወቅት ሌሎች ምን ያደርጉ ነበር? ምን እንገነዘባለን ነው ከወቅቱ የምናገው ትምህርት።

በወቅቱ ዋነኛ ተጫዋቾች ከነበሩት የትግል ድርጅቶች መካከል፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢሕአፓ )፣ የመላ ኢትዮጵያዊያን ሶሺያሊስት ንቅናቄ ( መኢሶን )፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት ( ኢዲዩ )፣ ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ   ( ተሓኤ – ጀብሃ )፣ ሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ( ሕግሓኤ – ሸዓቢያ )፣ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ( ኦነግ )፣ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ( ትሕነግ – ህወሓት – ወያኔ )፣ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ትነግ – ጠርናፊት )፤ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ( ኦብነግ )፤ ነበሩበት። የኤርትራ ታጋይ ድርጅቶችን በነበሩበትና ባሉበት እተዋቸዋለሁ። ቀሪ ነፃ አውጪ ግንባሮችን ደግሞ፤ – ኦነግ፣ ትነግ፣ ኦብነግ – ነፃ ለመውጣት ያደረጉት ትግል ነበርና፤ እንደ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ልተቻቸውና ትግላቸውን ልመረምር መረጃውም ሆነ የሞራል ፍቃዱ የለኝም። በርግጥ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባርን ( ትሕነግ – ህወሓት – ወያኔ ) በሚመለከት፤ ብዙ የምለው አለኝ። ለምን? የሚለው ጥያቄ ከተነሳ፤ ከነፃ አውጪነቱ ወጥቶ ኢትዮጵያን በሙሉ ወሮ በአምባገነንነት እየገዛ ነውና!

በወቅቱ የነበሩት ድርጅቶች፤ ሲነሱ ሁሉም ዴሞክራሲ፣ ነፃነት፣ መብት፣ ሕዝባዊ ተሳትፎ፣ እኩልነት በማለት ነበር። የትግል ዓላማቸው፣ ግባቸውና ዘዴያቸው ምን ነበር? ለምን አልተሳካላቸውም? እኒህ ናቸው በአንድነት በሀገራዊ መልኩ መታየት ያለባቸው ጉዳዮች። ጎልቶ በትግል መድረኩ ላይ ከፍተኛ ሚና በተጫወተውና በመጠኑም ቢሆን አውቀዋለሁ በምለው በኢሕአፓ ልጀምር።

ኢሕአፓ፤ በተማሪው ትግል ዋናውን ሚና ይጫወቱ የነበሩ ወጣቶች፣ በተማሪ ትግሉ መሪና አስተባባሪ የነበሩ ወጣቶች፤ በተለይም በውጭ ሀገር የነበሩ ታጋይ ተማሪዎችና በሠራተኛው ክፍልም የሠራተኛውን እንቅስቃሴ ይመሩና ያቀናጁ የነበሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ያቋቋሙት ፓርቲ ነበር። በትምህርት ዓለም ውስጥ ያጠኑትን የዓለም የፖለቲካ ሂደትና የተገነዘቡትን የፖለቲካ አሰላለፍ በመመርመር፤ በወቅቱ በነበረው የሶስተኛው ዓለም የነፃነት ንቅናቄና በሶቪየት ኅብረት የቅኝ ግዛቶች ድጋፍ በመመሰጥ፤ የሶሺያሊዝም አቀንቃኝነቱን ወስደው፤ ኮሚኒዝም ከነበርንበት አዘቅት የሚያወጣ መፍትሔ ብለን በመውሰድ፤ ትግሉን የሶሺያሊስት ንቅናቄ አድርገን ተነሳን። በወቅቱ የተነሱት ጉዳዮች፤ ማለትም የዴሞክራሲ መብቶች አለመከበር፣ የደሃ ልጅ የትምህርት ገበታ ዕድሉ መነፈጉ፣ ሕክምና ወደ ገጠር አለመዛመቱ፣ የሴቶች በእኩልነት በኅብረተሰቡ አለመገኘት፣ መሬት በጥቂት የመሬት ባለቤቶች ተይዞ ጢሰኛው ባላባቱ በፈቀደለትና በፈቀደው መንገድ የሚነዳው እስረኛ መሆኑ፣ የመሬቱ ባላባት የሆነው የገዥው መደብ አባልና በመሬቱ የሚለፋው ጢሰኛ፤ የትውልድ ሀረጋቸው አንድ አለመሆኑና ቋንቋቸው የተለያየ መሆኑ በሀገሪቱ ያስከተለው የመበላለጥ ልዩነት፣ የሃይማኖቶች በእኩልነት አለመመዘን፣ የሠራተኛው ክፍል በሕግ የሚተዳደርበት ትክክለኛ አሠራር አለመኖሩ፣ የግብር አሰባሰቡ አርሶ አደሩን መበደሉ፤ እኒህ ሁሉ ትክክለኛ ጥያቄዎች ነበሩ። እኒህን በማንሳትና ኮምኒዝምን በማወጅ መካከል የነበሩትን ደረጃዎች በሽምጥጥ በማለፍ የተደረገው ጉዞ፤ ተሰናከለ።

በአንጻሩ ደግሞ፤ ይህ በፖለቲካ ትግል ሂደቱ የተፈጠረው የኢሕአፓ ፓርቲ፤ የሚመረኮዝበት ኢትዮጵያዊ ታሪኩም ሆነ ልምዱ ስላልነበረው፤ መነሻና መድረሻ አድርጎ የወሰደው የሌሎች ሀገር ተመክሮዎችን ነበር። እናም፤ በወቅቱ በሀገራችን የፖለቲካ ሀቅ ላይ የተመረኮዘ መፍትሔ ሳይሆን፤ ሌሎች ያራምዱት የነበረውን የሶሽያሊስት መርህ ተጠቅሞ፤ ከሀገራችን ጋር ባልተቀናጀ መንገድ ለመተግበር ተነሳ። የድርጅቱ ድክመት፤ ፍላጎቱና ጥረቱ ሳይሆን፤ የተጨባጭ ሁኔታውና ያደረገው ጥረት አለመጣጣም ነው። ፍጹም ኋላቀር በሆነች ሀገራችንና የላበደሩ ቁጥር ከዚህ ግባ በማይባልበት ደረጃ በነበረበት ወቅት፤ የሶሻሊዝምን ሥርዓት ለማንገሥ የተነሳው ኢሕአፓ፤ መሠረቱና ዕድገቱ በወጣት የከተማ ተማሪው ላይ ነበር። ይህ ክፍል በቆራጥነት ሕይወቱን ለትግሉ ሠጠ። ደርግ ደግሞ አረመኔነት በተሞላ አሰቃቂ መንገድ ይኼን ወጣት በላው። የዚህ ፓርቲያችን ተመክሮ ባጭሩ እንዲህ ነበር።

በወቅቱ በቦታው ሊያሳድገው የሚችለውን ኢትዮጵያዊ ሂደት ሳይከተል፤ በፍላጎቱ ላይ ብቻ ተመስርቶ ያደረገው ግስጋሴ፤ ውስን ሆኖ ቀረ። የድርጅት መሪዎች ዋና ተግባር፤ ወቅታዊ ለሆነው ጉዳይ ወቅታዊ የሆነ መልስ አዘጋጅተው፤ ተከታዮቻቸውን መምራት ነው። ለነበረው የፖለቲካ ጉዳይ፤ በኢሕአፓ አመራር የተሠጠው ትንታኔና መፍትሔ፤ ደረጃውን የጠበቀና ወቅታዊ አልነበረም። በርግጥ የደርግ በዚህ ድርጅት ላይ የተለየ ትኩረት ማድረጉና የህወሓት ሆን ብሎ ይኼን ድርጅት ለማጥፋት ያደረገው ጥረት ቀላል አልነበረም። ድርጅቱ፤ ዓላማው ላለመሳካቱ ምክንያት ፍለጋ ወደ ውጪ መመልከት የለበትም፤ ዋናው ምክንያት ከውስጥ ነበር። ወሳኝ የነበረው ውስጣዊ ማንነቱ ነበር። የመርኅ መሠረቱና የአመራሩ ችሎታ በቦታው አልተገኙም። እናም ድርጅቱ ሳይሳካለት ቀረ።

የመላ ኢትዮጵያዊያን ሶሺያሊስት ንቅናቄ ( መኢሶን ) እንደ ኢሕአፓ ከተማሪው እንቅስቃሴ የበቀለ ንቅናቄ ነበር። በዚያ ውስጥ ግን የሥልጣን ጥማቱ ያናወዛቸው ግለሰቦች ተሰግስገውበት ስለነበር፤ በአቋራጭ ሥልጣን ለማግኘት፤ ተሽቀዳድመው ቤተ መንግሥት በመግባት፤ የደርግ አገልጋይ ሆኑ። ደርግን ተጠቅመን እንነግሣለን ሲሉ፤ ደርግ እንሱን የኢሕአፓ መግደያ መሣሪያ አድርጎ፤ የተማሪውን መከፋፈያ አድርጎ፤ የደሙ መጥረጊያ ጨርቅ አድርጎ ቀደማቸውና፤ ሰለባቸው። ከመኢሶን ከዚህ የበለጠ የምንማረው ያለ አይመስለኝም።

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት ( ኢዴኅ – ኢዲዩ ) የፖለቲካ መርኀ ግብሩ ዴሞክራሲያዊ እያለ ቢያትትም፤ ከፖለቲካ መስመር ይልቅ፤ ፀረ-ወታደር በመሆን የድሮውን ለመመለስ በችኮላ የተቋቋመ ድርጅት ነበር። በርግጥ የድሮውን የወደዱና የወታደሩን ያለቦታው ዙፋኑ ላይ መቀመጥ ያልተቀበሉ፤ ጄኖራሎች፣ ሀገረ ገዥዎች፣ መሳፍንታትና አምባሳደሮች በችኮላ ተቀላቅለውታል። ከዚያ ያለፈ ግን መርኀ-ግብሩን ተረድተውና ለዓላማው በመቆም የተሰለፉ የነበሩ አይመስለኝም። ባጭር ጊዜ ለነበረው እድገታቸው ተመጣጣኝ አመራር ሠጪ አካልና ማዕከላዊ አሰራር ስላልነበራቸው፤ ከደርግም ሆነ ከሌሎች ታጋይ ድርጅቶች በገጠማቸው ተቃውሞ ተመናምነው ጠፉ። ከዚህ በላይ ስለ ኢዴኅ ማለት አልችልም።

የቀረው የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ( ትሕነግ – ህወሓት – ወያኔ ) ነው። ከአፄ ዮሐንስና ከትግራይ መሳፍንት ጋር የተያያዘው የትግራይ ወጣቶች የነፃነት ግንባር፤ ምንም እንኳ ከተማሪ ማኅበሩ የመጡ መሪዎችና ተከታዮች ቢኖሩበትም፤ ከጠባብ የትግራይ መሳፍንት ገዥነት ጋር የተያያዘ የነፃነት ትግል ነበር። ስለዚህ ይህን ግንባር ከተማሪ ትግሉ ጋር ማዛመድ ስህተት ነው። የዚህ ነፃ አውጪ ግንባር መሠረቱ የትግራይ ሪፑብሊክን መመሥረትና የአማራ ገዥነትን ማጣፋት ነው። በምንም መንገድ ከማርክሲዝምና ከላብ አደሩ አምባገነንነት ጋር ግንኙነት የለውም። ይህ ትግራይን ነፃ አድርጎ የራሷ ሀገር የመፍጠር ጉዳይ፤ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ፣ ከሀገር አቀፉ እንቅስቃሴ የተለየና በተቃዋሚነት የቆመ ነበር። ስለዚህም፤ ህወሓት በጠላትነት የፈረጃቸው፤ ደርግን ብቻ ሳይሆን፤ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ትነግ – ጠርናፊት )ን፣ ኢሕአፓን እና አማራን ነበር፤ አሁንም ነው። የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ትነግ – ጠርናፊት )ን ስላጠፋው ከቁጥር አስወጥቶታል። ኢሕአፓን በሚችለው መንገድ ወግቶታል። አማራውን አሁንም በማጥፋት ላይ ነው። የዚህ ድርጅት ተግባር ሕዝባዊም፤ ኢትዮጵያዊም አይደለም። ከዚህ የምንማረው ቢኖር፤ ይህ ድርጅት መጥፋት እንዳለበትና ይህም ባስቸኳይ መሆን እንዳለበት ነው።

ለመንደርደሪያ ያህል ይኼን ካስቀመጥኩ በኋላ፤ አጠቃላይ በሆነ መልኩ ወደፊት የሚመለከት መፍትሔ በመጠቆም፤ ጽሑፌን አስራለሁ። የ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ቱ ህዝባዊ እንቅስቃሴ መሠረታዊ ጥያቄዎች፤ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበሩ፣ መሬት ለአራሹ ይሁን፣ የሴቶች እኩልነት ይከበር፣ ሃይማኖት የግል ስለሆነ፤ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይግባ፣ ሁሉንም ሃይማኖቶች እኩል ይመልከት፣ ሕክምና በገጠር ይስፋፋ፣ የድሃ ልጅ ይማር፣ ለተራበው ወገናችን እርዳታ ይደረግለት፣ የገዥዎች ያላአግባብ በሀብት ማላገጥ ይቁም፣ የኑሮ ውድነት ይስተካከል፣ ለሠራተኛው ትክክለኛ ሕግ ወጥቶ በሕገ-ደንብ ይስተዳደርና የመሳሰሉት ነበሩ። እኒህ ሀገራዊ ጥያቄዎች ነበሩ። አሁንም አሉ። አሁንም ሀገራዊ ጥያቄዎች ናቸው። በአንድነት ተነስተን በአንድነት ለማስከበር የምንቆምላቸው ነበሩ። ያኔ አልተደረገም። አሁንም እየተደረገ አይደለም።

የያዝነው ትግል ውጤቱ እንዲቃና፤ እስካሁን ከተደረገው ትግል ተምረን፤ ትግሉን በተስተካከለ መንገድ ማካሄድ አለብን። ጥያቄዎቹ ቀለም ይቀቡና ሌላ መልክ ይያዙ እንጂ እኒሁ ናቸው። ተጎጅው ደግሞ ያው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ትግሉ የሕዝቡ ነውና የሕዝቡን ባለቤትነትና የበላይነት መቀበል ዋነኛ መሠረታዊ ግዴታ ነው። ቀጥሎ ደግሞ፤ ያለውን የሀገራችንን የፖለቲካ እውነታ በትክክል ተንትኖ፤ ለዚህ ወቅታዊ የፖለቲካ ሀቅ ትክክለኛ መፍትሔ ማቅረቡ ነው። በኔ እምነት፤ በኢትዮጵያ ያለው ወራሪ መንግሥት ነው። ይኼን ወራሪ መንግሥት መታገል ያለብን፤ ጥቂት መሠረታዊ የሆኑ ሀገራዊ የትግል ዕሴቶችን በማውጣት፤ አንድ የኢትዮጵያዊያን ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ መሥርተን በመነሳት ነው። መታገያ ዕሴቶቻችን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት መከበሩ፣ የኢትዮጵያ ሀገራችን ዳር ደንበር መጠበቁ ለሙ መሬቷ ለኢትዮጵያዊያን መዋሉ፣ የያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ መብት መከበሩ፣ እና የሕግ የበላይነት መረጋገጡ ናቸው። በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያለነው በአንድነት በነዚህ ሀገራዊ አንገብጋቢ ዕሴቶቻችን ዙርያ በመሰባሰብ መነሳት አለብን።

ከነዚህ አንገብጋቢ ዕሴቶቻችን ውጪ ያለው ጉዳይ፤ በመሠረቱ የሕዝቡን የትግሉ ባለቤትነትና የበላይነት እስከተቀበልን ድረስ፤ በሂደት ሕዝቡ በትግሉ ስለሚያነሳቸውና መፍትሔ ስለሚሠጣቸው፤ ላሁኑ በቆይታ ይታያሉ። እናም በነዚህ ዙርያ ተጠማጥመን እንቅስቃሴውን በአንድነት በአንድ ድርጅት ከውጪ ያለነው እናካሂደው። ካለፈው እንማርና፤ ለዚሁ አንድ ጉዳይ፤ ባንድ ተሰልፈን፤ ቆመን እንቆጠር። መማር ማለት፤ ከትናንት ተሽሎ መገኘት ማለት ነው። መማር ማለት ባሉበት መርገጥ ማለት አይደለም። መማር ማለት ማደግ ማለት ነው።

The post መማር እንችላለን ወይ? -አንዱዓለም ተፈራ appeared first on Zehabesha Amharic.

(የቡና ቁርስ) በዚህ ሳምንት የተማርናቸው ሦስት ነገሮች * ኬንያም ኢትዮጵያም ሽብርተኝነት ላይ ሚዛን ስተዋል * ዶናልድ ሌቪን የኔታ ናቸው * ድምጻችን ይሰማ ብርቱ ነው

$
0
0

1ኛ) ኬንያም ኢትዮጵያም ሽብርተኝነት ላይ ሚዛን ስተዋል 

ከሁለት ዓመት በፊት ዘ-ኢኮኖሚስት መጽሔት ጎረቤታሞቹ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሚከተሏቸው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አስተዳደር ሞዴሎች መካከል ያለውን ልዩነት የሚገልጽ ጽሑፍ አስነብቦን ነበር። ጽሑፉ የሚጀምረው ሁለት የድንበር ከተሞችን በማነጻጸር ነበር፤ መተማን እና የኬንያ ሞያሌን። በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ጥብቅ በኾነ የፍተሻ ሂደት ውስጥ ማለፍ ግድ ይላል። ድንበር ጠባቂዎቹ የተጓዦች ፓስፖርቶችን በእጅ ጽሑፍ ከተጻፈ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ የተከለከሉ ሰዎችን ስም ዝርዝር ከያዘ ዶክመንት ጋራ ያመሳክራሉ። ፓስፖርቶቹ የሐሰት እንዳልኾኑ በጥንቃቄ ይመረምራሉ፤ ግልምጥምጥ እያደረጉ እና ኮስተርተር እያሉ ጥያቄ ይጠይቃሉ። በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ለመግባት ግን ይህ ሁሉ ጣጣ የለም። የደንህንነት መኮንኖቹ ፓስፖርት ሲመለከቱ ፈታ፣ ዘና ብለው ነው። ጥበቃው ልል ከመኾኑ የተነሳ “የድንበር ፍተሻ ሳይኾን የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ይመስላል” ይላል ዘ-ኢኮኖሚስት። የኢትዮጵያ የአስተዳደር ሞዴል መተማን ይመስላል፤ መንግሥት ሁሉ አወቅ የኾነበት እና ከዳር እስከ ዳር ሥልጣኑንና ቁጥጥሩን ያረጋገጠበት። የኬንያ መንግሥት በተቃራኒው የቁጥጥር ድክመት ያለበት እና ክፍትነት የሚታይበት ነው።

BEN CURTIS, FILE — AP Photo Read more here: http://www.adn.com/2013/10/10/3119796/africa-vs-icc-quotes-on-court.html#storylink=cpy

BEN CURTIS, FILE — AP Photo
Read more here: http://www.adn.com/2013/10/10/3119796/africa-vs-icc-quotes-on-court.html#storylink=cpy

ባለፈው ሳምንት በጋሪሳ 147 ሰዎች ያለቁበትን የሽብር ጥቃት ተከትሎ በእነዚህ ሁለት ተቃራኒ ሞዴሎች ጉዳይ ክርክር ተጀምሯል። በኬንያ እንዲህ ዐይነት የሽብር ጥቃት ሲፈጸም የመጀመርያው አይደለም። በተቃራኒው በኢትዮጵያ ከ1999 ዓ.ም በኋላ መጠነ ሰፊ የሽብር ጥቃት አልተፈጸመም። አልሸባብ ሁለቱንም አገሮች (በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያን) እንደ ከባድ ጠላት ይመለከታል። ነገር ግን የኬንያ ስኬቱን በኢትዮጵያ ሊደግመው አልቻለም። ይህን ያስተዋሉ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን የአስተዳደር ሞዴል አንቆለጳጵሰውታል። እንዲህ ያሉ ክስተቶችን ተገን አድርገው ቋጥኝ የሚያካክሉ መደምደሚያዎች ላይ የሚደርሱ ሙግቶችን እና ትንተናዎች (ad hoc reasoning) ፋይዳ አነስተኛ ነው። ሲስተሞችን እና ሞዴሎችን በርትዕ እንዳንማር ያደርጉናል። ትልቁን ሥዕል እንዳንመለከት ዐይኖቻችንን ይጋርዷቸዋል። ይልቁንስ የሞዴሎችን ብቃት ለማወቅ መለኪያዎችን አውጥቶ መገምገም የተሻለ መንገድ ነው።

የፖለቲካ ፈላስፋዋ ሴይላ ቤን ሃቢብ ውስብስብ የፖለቲካ ማኅበረሰቦች አራት እሴቶች እንዳሏቸው ያስቀምጣሉ፤ ሌጂትሜሲ፣ የኢኮኖሚ ዋስትና፣ ደኅንነት እና አመክኗዊ የጋራ ማንነት። እነዚህ ግቦች በብዙኀኑ የፖለቲካ ማኅበረሰቦች አባላት የሚደገፉ ናቸው፤ በትርጉማቸው እና በይዘታቸው ላይ በየማኅበረሰቡ ጠንካራ ሙግቶች እና ያለ መስማማቶች ቢኖሩም። እነዚህ ግቦች እርስ በእርሳቸው የተወሳሰበ መስተጋብር አላቸው። አንዱን በተትረፈረፈ ኹኔታ ማግኘት ሌላውን ሊያሳጣ ይችላል። ለምሳሌ፦ ሌጂትሜሲን ለማምጣት እጅግ ክፍትና ነጻ የኾነ ሥርዐት ፈጥረን ደህንነትን አደጋ ላይ ልንጥል እንችላለን። የኢኮኖሚ ዋስትናን ለመጨመር ደግሞ የሰዎች ነጻነት ላይ ከመጠን ያለፈ ገደብ እናስቀምጥ ይኾናል። የጋራ ማንነታችንን ለማጠናከር ውህዳንን (minorities) እንጨቁናለን። የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሞዴሎች ብስለት እና ብቃት የሚለካው እነዚህን አራት እሴቶች አመዛዝኖ በማቅረብ ችሎታቸው ነው። በእነዚህ መለኪያዎች እንደ ኢትዮጵያ ያለ እጅግ ጣልቃ ገብና ሁሉን ዐወቅ መንግሥት በሳል ነው ለማለት ያስቸግረናል። ሕዝቡን መንግሥታዊ ካልኾነ ሽብር ለመጠበቅ ቢችልም፤ ይህን የሚያደርገው ሌጂትሜሲን እና የጋራ ማንነትን አደጋ ላይ በመጣል ነው። ለምሳሌ በ1999 ዓ.ም በኦጋዴን የተፈጠረውን ክስተት እናንሳ። የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ታጋዮች በቻይና የነዳጅ ኩባንያ ላይ ጥቃት ፈጽመው 74 ሠራተኞችን ገደሉ፤ ብዙ ንብረት አወደሙ። የኢትዮጵያ መንግሥት በአጸፋው ለሦስት ዓመታት ሳያሰልስ የቀጠለ መሬት አንዳጅ፤ ጅምላ ጨራሽ ወታደራዊ እርምጃ ወሰደ። በርካታ የኦጋዴን ነዋሪዎች ተገደሉ፤ ተገረፉ፣ ተሰቃዩ፣ ቀያቸውን ለቀው ተሰደዱ። ይህ ጥቃት ኦብነግን ቢያሽመደምደውም የኦጋዴን ነዋሪዎችን መብቶች ክፉኛ የጣሰ እና ኢትዮጵያዊ ማንነታቸውን የበለጠ እንዲጠይቁ ያደረገ ነበር። አራቱን እሴቶች የሚያመዛዝን ሳይኾን ወደ አንዱ እሴት በእጅጉ ያዘነበለ ጥቃት ነበር። የተከፈለው ዋጋ የፖለቲካ ማኅበረሰባችንን አናግቷል። ኬንያ ከኢትዮጵያ በተቃራኒ ጫፍ ላይ ያለ የራሷ የኾነ አመዛዝኖ የማቅረብ ችግር አለባት። ለብሔራዊ ደህንነት የምትሰጠው ዋጋና ክብር አነስተኛ ነው። በኬንያ ላይ ጣታቸውን የቀሰሩ ኢትዮጵያውያን ይህን በሚገባ አብራርተውታል። ችግሩ ሦስቱ ጣቶቻቸው ወደራሳቸው እንደሚጠቁሙ መዘንጋታቸው ነው።

2ኛ) ዶናልድ ሌቪን የኔታ ናቸው

ታላቁ አሜሪካዊ የፖለቲካ ፈላስፋ ጆን ሮውልስ ከወጥ ሥራዎቹ በተጨማሪ በአንድ ነገር ይታወቃል፤ በየኔታነት (mentorship)። ለተማሪዎቹ የቅርብ ጓደኛ ኾኖ ሥራቸውን መከታተል እና ማበረታታት እንደ ምሁራዊ ግዴታው ይመለከት ነበር። ይህ ጠባዩ በርካታ ድንቅ ፈላስፎችን እንዲፈጥር ከማስቻሉም በተጨማሪ ተክለ ሰብእናውን እና ምሁራዊ ብቃቱን የሚያበስሩ ደቀ መዛሙርት እንዲያፈራ አድርጎታል። የምሁራን ስኬት በሥራቸው ብቃት ብቻ ሳይኾን በሌሎች ምሁራን ዘንድ ባላቸው ማኅበራዊ ካፒታል (social capital) ይወሰናል። ባለፈው ሳምንት በሞት የተለዩን የኢትዮጵያ ጥናቶች ታላቅ ሊቅ አሜሪካዊው ሶሲዮሎጂስት ዶናልድ ሌቪን ይህን እውነታ በሚገባ የተረዱ ነበሩ።

Oromo Narrative: Professor Donald Levineፕሮፌሰር ሌቪን በኢትዮጵያ ላይ የጻፏቸው ሁለት ታላላቅ መጻሕፍት ከታተሙ ቢያንስ አርባ ዓመታት አስቆጥረዋል። ከዚያ በኋላ የእርሳቸውን ሥራዎች የሚያፈርሱ እና በጥብቅ የሚሄይሱ ጥናቶች ታትመዋል። የተሻሉ ቲዮሪዎች እና ኢምፔሪካል ግኝቶች ተከትለዋል፤ የኢትዮጵያ ጥናቶች አድገዋል፤ ተመንድገዋል። መጻሕፎቻቸው በብዙ ወጣት ምሁራን ሥራዎች ውስጥ ቢጠቀሱም ሌቪኒዝምን አልፈጠሩም። በተጨማሪም ፕሮፌሰር ሌቪን ከምሁራዊ ሥራቸው አልፈው በኢትዮጵያ ፖለቲካ መጀመርያ ንጉሡን የሚቃወሙ ኀይሎችን በመርዳት በኋላም የቅንጅት ታሳሪዎች እና ኢሕአዴግን ለማደራደር በሽማግሌነት ያደረጓቸው ጥረቶች ያልተሳኩ ነበሩ። በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ላይ የጻፏቸው መጣጥፎች ብዙም ተቀባይነት አላገኙም፤ እንዲያውም ከአንዳንዶች ጠንካራ ትችት ተሰንዝሮባቸዋል። ይኹንና በዶናልድ ሌቪን ሞት ተቺዎቻቸውን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ከልብ የመነጨ ሐዘናቸውን ሲገልጹ ሰንብተዋል። እነዚህ ምሁራን የሦስት ትውልድ አባላት ናቸው። አብዛኞቹ በሐዘን መግለጫቸው ከሌቪን አካዳሚያዊ ሥራዎች በተጨማሪ ከፕሮፌሰሩ ጋራ የነበራቸውን የጓደኝነት እና የተማሪ -መምህር ግንኙነት አንስተዋል። ሌቪን ከወጣት እስከ አዛውንት ከምሁራን ጋራ በመቀራረብ፣ ሳይታክቱ የደብዳቤ እና የኢ-ሜይል ልውውጦችን በማድረግ የድጋፍ ደብዳቤዎችን በመጻፍ፣ በአካዳሚያዊ ኮንፈረንሶች እና ሌሎች የትምህርት አውድማዎች በመገኘት ተፈንክቶና ተዘርዝሮ የማያልቅ ማኅበራዊ ካፒታል አዳብረዋል። ይህ ካፒታል የፖለቲካ ስህተት ሲሠሩ ሳይቀር ስማቸውን ከሚያበሻቅጥ ጥቃት እና ዝቅ አድርጎ ከሚያይ አስተያየት ጠብቋቸዋል። የኔታ ሊበን አፈር ይቅላለቸው።

3ኛ) ድምጻችን ይሰማ ብርቱ ነው

በአምባገነን ሥርዐቶች መንግሥታት ላይ ግፊት የሚያደርጉ ማኅበራዊ ንቅናቄዎች ዕድሜ እጅግ አጭር ነው። ከምሥረታቸው አንስቶ የማኅበራዊ ድርጊት ችግሮች (collective action problems) ይገጥሟቸዋል። መንግሥት ሰርጎ ገቦችን ያዘልቅባቸዋል፤ መሪዎቻቸው እና አባሎቻቸው ይታሠራሉ፤ ተለጣፊ ቡድኖች ይፈጠሩባቸዋል። በአጠቃላይ በእነዚህ ንቅናቄዎች ውስጥ የመሳተፍ ዋጋ (cost of participation) ይሰቀላል። ብዙዎች ተስፋ ቆርጠው ንቅናቄውን እንዲተዉ ያደርጋል፤ ዋጋ ሳይከፍሉ ስኬት መካፈል የሚፈልጉ ሰዎችን (free riders) ያበራክታል። ማኅበራዊ ንቅናቄዎች ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በበለጠ ለእንደዚህ ዐይነቶቹ የአምባገነን መንግሥት ጥቃቶች የሚጋለጡባቸው የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። ማኅበራዊ ንቅናቄዎች የአይዲዮሎጂ ጥራት እና ጥልቀት ይጎድላቸዋል፤ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የበለጠ ሰፊ እና ልል ናቸው፤ አባላቶቻቸውን የሚያጣሩበት ወንፊት ዘርዘር ያለ ነው። ይኼን ሁሉ ግምት ውስጥ ስናስገባ ከአራት ዓመታት በላይ የቆየው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ድማጻችን ይሰማ ንቅናቄ ቀጣይነት ያስገርማል።

yisemaድምጻችን ይሰማ እንደ ብዙ ማኅበራዊ ንቅናቄዎች ሁሉ ልል ነው። በአባላቱ መካከል የስትራቴጂ፣ የታክቲክ እና አንዳንዴም የአይዲዮሎጂ ልዩነት ይታያል። ለምሳሌ፦ አንዳንዶቹ ሌማት ጠያቂዎች (maximalist) ሲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ኩርማን ጠያቂዎች (minimalist) ናቸው። በርካታ አባላት ጥያቄው ከሕገ መንግሥት እና ከአጠቃላይ የሰብአዊ መብት ጽንሰ ሐሳብ ጋር ብቻ የተገናኘ ዓለማዊ (secular) እንዲኾን ይፈልጋሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ንቅናቄው ሃይማኖታዊነቱን እንዲያስረግጥ ይሻሉ። ጥቂት የማይባሉ አባላት ደግሞ መንግሥት በሃይማኖት ላይ ያለውን ጣልቃ ገብነት ካቆመ አጨብጭበው ወደ ቤታቸው መመለስ ይፈልጋሉ፤ ከእነርሱ በተቃራኒ አንድ ጥያቄ ሲመለስ ሌላ እየጨመሩ ማኅበራዊ ንቅናቄው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በቀጣይነት መሳተፍ እንዳለበት የሚያምኑ አሉ። ከሌሎች የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ንቅናቄዎች ጋር መሥራት በሚፈልጉና በማይፈልጉ መካከል ልዩነት አለ። እንደዚህ ዐይነት የውስጥ ሙግቶች እንደ ድክመት ሳይኾን የማኅበራዊ ንቅናቄ ባሕርያት (features) መታየት አለባቸው። መንግሥት ልዩነቶቹን በመጠቀም ንቅናቄውን ለመከፋፈል ሞክሯል። በዚያ ስላልተሳካለት ቀጥተኛ የጭፍለቃ ርምጃዎችን ወስዷል። ይኹንና በዚህ ሳምንት በአውሮፓ እና በአሜሪካ ያንሰራራው እንቅስቃሴ እንደሚያሳየው ንቅናቄው ቢዳከምም አልከሰመም። ከ1966ቱ አብዮት በኋላ ተፈጥረው ለረጅም ጊዜ የቆዩ ማኅበራዊ ንቅናቄዎችን ታሪክ ስናጠና እጅግ በርካቶቹ በነጻ አውጪ ግንባሮች ጥላ ሥር የተሰበሰቡ ኾነው እናገኛቸዋለን። ድምጻችን ይሰማ ከእነዚህ የተለየ ነው። ድምጻችን ይሰማ ያለ ነጻ አውጪ ግንባሮች እና ፖለቲካ ፓርቲዎች ሞግዚትነት በአንጻራዊ ብቻውን ቆሞ ለረዥም ጊዜ መቆየቱ ልዩ ያደርገዋል።

• Source: ሰባት ኪሎ

The post (የቡና ቁርስ) በዚህ ሳምንት የተማርናቸው ሦስት ነገሮች * ኬንያም ኢትዮጵያም ሽብርተኝነት ላይ ሚዛን ስተዋል * ዶናልድ ሌቪን የኔታ ናቸው * ድምጻችን ይሰማ ብርቱ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


የወያኔ  ዜማ በደቡብ አፍሪካ ተሰማ –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

Ketemaበደል በደልን ይወልዳል እንጂ አያጠፋውም። ችግር ችግርን ይፈጥረዋል እንጂ አያስወግደውም። በደል ፈጣሪ ከላይ ከተቀመጠ… መከራን አምጪ ስልጣን ላይ ካለ… የምንሰማው እና የምናየው ሁሉ ሰቆቃና ዋይታ ነው። ሰቆቃ እና ዋይታ ግዜውን እየጠበቀ የሚፈነዳ የህዝባችን ፍዳ ከሆነ ሰነባብቷል። ሰቆቃ  ፈጻሚዎች እና ናፋቂዎች አናት ላይ ከተቀመጡ ሰቆቃችን ማብቂያ  የለውም። ለኛ የሃዘን እንባችን ለወያኔ ደግሞ  የመዝናኛው ዜማው የሆነ አሳዛኝ ድርጊት ከወደ ደቡብ አፍሪካ እየተሰማ ነው።

የኢትዮጵያ መከራዋ  በይፋ  ከተበሰረበት ግዜ አንስቶ  ከእለት ወደ  እለት ህዝባችን ከሚወዳት አገሩ ሳይወድ በግዱ ተሰዳጅ እየሆነ  ነው። እግዚአብሔር የተፈጥሮ  ጸጋውን አልብሶን እንኳን ለራሳችን ለአለም የሚተርፍ ሃብት በጉያችን ይዘን እንደ  ርሃብተኛ እንሰደዳለን። በልጆቿ የዳበረ እውቀት በልጆቿ የፈረጠመ  ጉልበት በተፈጥሮዎአ ላይ የሚዘምቱ ኃያል ልጆች ኖሮን ሰርተንና በልጽገን አለምን የሚያስደምም እውቀትና ተፈጥሮ ኖሮን ሳለ ገዳይ ነግሶብን አንባ ገነን ተሾሞብን በየአለማቱ ተበተንን። የወገኖቻችንን  ሰቆቃ  በተቃጠለ  ስሜት የደም እንባ እናነባለን። ከአጋም ጋር የተጠጋ  ቁልቋል ሲያለቅስ ይኖራል እንደሚባለው ወያኔ ለሆዱ፣ ለስልጣኑ፣ ብሎ ህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግፍና  በደል ህዝባችንን ተሰዳጅ አደረገው። ዛሬ በስደት ላይ ያሉ ወገኖቻችን ለሚደርስባቸው ዘግናኝ ድርጊት ተጠያቂው ወያኔ  ነው።

ከጥቂት ግዜ በፊት የኢትዮጵያ መንግስት ከሳውዲ መንግስ ጋር ከአርባ አምስት ሺህ በላይ የሰራተኛ ግብይት ተፈራርሞ ነበረ። ፊርማው ሳይደርቅ የሳውዲ መንግስ በዜጎቻችን ላይ የሰራውን አሳፋሪ እና  ዘግናኝ በደል እርጉዝ ሴት እህቶቻችን ለብዙ በመድፈር ለሞት ሲዳርጉ በአደባባይ በስለት ሲታረዱ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደው እርምጃ አለመኖሩ ስናይ በደላችን የተዳፈነ  ፍም ሆኖ በውስጣችን ተቀምጧል። ሌላው ቀርቶ በሳውዲ አረብያ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል ለመቃወም በአዲስ አበባ ሳውዲ ኤምባሲ ሰልፍ በመውጣት ብሶቱን ለማሰማት የወጣውን ህዝብ የወያኔ ቅልብ ፌደራል በድፍን አምሮው በያዘው በድፍን ዱላ ህዘባችን እየቀጠቀጠ ሳውዲ የወሰደችው እርምጃ  ትክክል ነው ብሎ ነግረውናል።

በመቀጠል በየመን ከ200 ሺህ ሕዝብ በላይ ኢትዮጵያን ይኖራሉ በየመን በተነሳው ግጭት ሳብያ ኢትዮጵያኑ እንደቅጠል እየረገፉ ነው በዚህ መሃል ቀልደኛው መንግስታችን በዚህ ስልክ ቁጥር ደውሉ አልነሳ ካላቹህ መልሳቹህ መልሳቹህ ሞክሩት አልያም መልክት አስቀምጡ የሚል በፌስ ቡክ መስኮት ብቅ ብሎ ነግሮናል። ለየመን ባላሀብት ሲጋራ ሞኖፖልን ከምትሸጡ ይልቅ ለሳዊዲ ባለሃብት፣ ለህንድ እንዲሁም ለገብረመድህን፣ ለኪሮስ፣ ለግደይ፣ ለአላሙዲ፣ የአገሪቱን ለም መሬት ከምትቸበችቡ በችግር ላይ ላለው ዜጋ ለሆኑ አገራቸውን እያለሙ እራሳቸውን እንዲችሉ የአገር ለውጥ በአገር ልጅ የሚለውን   መርሆ  ብትከተሉ  ምን  አለበት? ለነገሩ የሰይጣን መልእክተኛ  አልያም በውስጡ ሰይጣናዊ ሃሳብ ያለበት ይሄን ማድረግ አይቻለውም።

ችግር ፈጣሪው እስካለ  ችግሩ አይቀሬ ነው ።  እናም በሱዳን በኬንያ በዛንብያ በግብጽ ችግሮች እንዳሉ ቢታወቅም እንደ  እሳተ ጎመራ የፈነዳው አዲስ ክስተት በደቡብ አፍሪካ ተከሰተ፡ ትናንት በችግራቸው ጊዜ  ችግራቸውን የሸፈንላቸው ሁሉ ዛሬ እነሱ በኛ ላይ ተነሱ። ሳውዲን ብንወስድ ቆሬሾች ሊገሏቸው ሲያሷድዷቸው የነብዪ መሀመድ ወገኖችን  በጉያዋ ያስቀመጠች  በኔ የተከለሉትን በራሳቸው ፍቃድ ካልሆነ ለማንም  አንባገነን አሳልፌ  አልሰጥም ብላ ህይወታቸውን የታደገች አገር….  ለደቡብ አፍሪካም  የነጻነት መሪ የተባለውን ማንዴላን ተቀብላ አሰልጥና የኢትዮጵያን ፓስፖርት ሰጥታ በክብር የሸኝች አገር ዛሬ ያሁሉ ተረሳና የስቃይ ጅራፍ ውለታ ለዋለችላቸው አገር ሲያደርጉ ያሳዝናል። ታሪክ ይውቀሳቸው እውነት ይፋረዳቸው።

ደቡብ አፍሪካዎች ምን ነካቸው? የማንዴላ ህዝቦች ምን አጋጥሟቸው ነው? እንደዚ ወደ አውሬነት የተለወጡት። እግዚአብሔር ብድራትን ይመልስላቸው በሰይፍ ያጠፋ በሰይፍ ይጠፋል ይላል። ፍርዱን ለፈጣሪ በመተው ከኛ የሚጠበቅብንን ማድረግ ግድ ይለናል።

ነገሮች ሲወጣጠሩ ማስተንፈሻ በመፈለግ ወደ ሰባራ ተግባር የሚሄደው የወያኔ መንግስት ሁሉም ህብረተሰቡ ትኩረት አድርገው ስለ አገራቸው በሚያስቡበት እና በሚሰሩበት ግዜ  በደቡብ አፍሪካ  እንደዚህ አይነቱ ክስተት መከሰቱ ለወያኔ ዜማው ነው። የወያኔ መንግስት ሃሳባቸው ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ስለስልጣናቸው ብቻ የሚያስቡ በመሆኑ የህዝብ በደል ወይም እልቂት ያስደስታቸዋል ምክንያቱም የፖለቲካ አቅጣጫውን ስለሚጠመዝዝላቸው። ለደቡብ አፍሪካ ጭፍጨፋ የአፍሪካ መሪዎች በዜጎቻቸው እየደረሰ ያለውን  ግፍ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ..በጦርነት እየታመሰች ያለችው ሱማሊያ ስለዜጎቿ ስትቆም… ወያኔዎች ግን ምንም ያሉት የለም። በርግጥ ከወያኔ ምንም አንጠብቅም። ምክንያቱም አይተናቸዋልም አውቀናቸዋልም። የሚጠበቀው ከኛው ነው።  እኛው ለኛው።

የህዝባችን እሮሮ ማስቆም የሚቻለው በመጀመሪያ  እሮሮ አምጪውን አናታች ላይ የተቀመጠውን ጨቋኝ አገዛዝ  አውርደን መጣል ስንችል ከዛ በኋላ ዜጋዬ ተበደለ ብለን ስለህዝባችን ፈጥነን መድነስ የምንችለው። ወያኔ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ በህዝባችን ላይ መከራ ቢደርስበት ግድ የለውም። ካሁን በኋላ ወያኔ ህዝባችንን እንዲታደግልን አንጠይቀውም። ለህዝባችን የቆመ መንግስት ነው ብሎም መቀበል አይቻልም። ነገር ግን በህዝባችን ስም በመነገድ ስልጣኑን የሚያራዝመውን ተግባር በማክሸፍ ህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ እናስቁም። ለዚህም ግዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም። በሳውዲ በደረሰው የህዝባችን ሰቆቃ  ምንም ያልፈየደው ወያኔ ሙሉውን ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት ተሸፍኖ ከሳውዲ እንዲመጡ አድርገናል። ከሳውዲ ለመጡት መቋቋሚያ የሚሆናቸውን ገንዘብ እንረዳለን ብለው በአደባባይ የዋሸን መንግስት….. በየመን በደረሰው የወገናችን መከራ የሁሉም አገር መንግስት አውሮፕላን፣ መርከብ በመላክ ህዝባቸውን ሲታደጉ የኛው መንግስት ተብዬው ግን የስልክ ቁጥር ፌስብክ ላይ በመለጠፍ ህዝባችን ላይ የሚያሾፍ መንግስት ተብዬ…. ዛሬ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ በህዝባችን ላይ በሚደርሰው ግፍ ሊነግሩን የሚፈልጉት ፌዝ እንዳለ  እናውቃለን። የኛ ውሳኔ ግን ፌዘኛን መስማት ሳይሆን ፌዜኞችን በማስወገድ ለህዝብ የቆመ መንግስት እንዲኖረን ማድረግ ተገቢ ነው።

ከተማ ዋቅጅራ

16.04.2015

Emeil- waqjirak@yahoo.com

The post የወያኔ  ዜማ በደቡብ አፍሪካ ተሰማ – ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

የደቡብ አፍሪካው የስደተኛ ጠልነት መነሻው ምንድነው? (የሰባት ኪሎ ወቅታዊ አጭር ትንተና)

$
0
0

ethiopia south africa
ደቡብ አፍሪካን በቅርቡ የማይከታተሉ ሰዎችን በእጅጉ ያስደነገጠ ቢኾንም በአገሪቱ ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ ኹከት ሲካሄድ የአሁኑ የመጀመርያው አይደለም። እ.ኤ.አ በግንቦት ወር 2008 አሌክሳንደር በተባለ የጆሃንስበርግ ታውንሺፕ የተነሳ ኹከት ወደ ደርባን እና ሌሎች ከተሞች ተዛምቶ ቢያንስ ለዐርባ ስደተኞች መሞት ምክንያት ኾኗል። በኹከቱ ብዙ ንብረት ወድሟል። ከዚያ በፊት እና በኋላም ቢኾን ሌሎች በርካታ አነስተኛ ጥፋቶች ተፈጽመዋል። ይህ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነው “በጉርብትና የሚኖሩ ሰላማዊ ስደተኞችን በእንደዚህ ዐይነት ጭካኔ ማቃጠል፣ መግደል እና መደብደብ ለምን?” የሚለው ጥያቄ ተደጋግሞ ይነሳል። በደቡብ አፍሪካ እንዲህ ዐይነት ከፍተኛ የኾነ ስደተኛ ጠልነት ለምን ተስፋፋ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ምናልባትም ወደ አገሪቱ የመጀመርያዎቹ የዴሞክራሲ ዓመታት መለስ ብሎ መመልከት አስፈላጊ ነው።
gejera south africa

ከኻያ ዓመታት በፊት አፓርታይድ ተገርስሶ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ሲጀመር በደቡብ አፍሪካ ሁለት ነገሮች ተፈጠሩ። በመጀመርያ ብዙኃኑ ጥቁሮች ከጥቂት ነጮች ጭቆና ተላቀው እነርሱ በመረጡት መንግሥት አስተዳደር አማካኝነት ከነበሩበት የኢኮኖሚ ችግር እንደሚወጡ ተስፋ ሰነቁ። በጊዜው የወጡ የሕዝብ አስተያየት ጥናቶች እንደሚያሳዩት በርካቶች ከነጭ ሀብታሞች ተቀንሶ ለድኾች የሚሠጥበት የኢኮኖሚ መልሶ ማከፋፈል (economic redistribution) ይኖራል የሚል ተስፋ ነበራቸው። ከፍ ያለ የትምህርት ዕድል፣ ቀስ በቀስ የሚያድግ ገቢ፣ የተሻለ የመኖርያ ቤት የማግኘት ፍላጎት ጨመረ። በሌላ በኩል በተለይ በምዕራብ አገሮች መንግሥታት እና ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ዘንድ አዲሱ ዴሞክራሲ የንብረት መብትን ይሸረሽራል፣ የኤኤንሲ መንግሥት ከመራጮች በሚመጣ ጫናም ይኹን በውስጥ ፖለቲካው ምክንያት መልሶ ለማከፋፈል ሲል ንብረት ይወርሳል፣ ከባድ ግብር ይጥላል ወዘተ . . . የሚል ስጋት ነበር።

ይኹንና የድኻ ጥቁሮች ተስፋም ይኹን የሌሎቹ ስጋት እውን አልኾነም። ማርቲን ፕላውት እና ፖል ሆልደን “Who rules South Africa?” በሚል መጽሐፋቸው እንደሚያትቱት ኤኤንሲ ሥልጣን ላይ እንደወጣ ከወሰዳቸው የመጀመርያ ‘ርምጃዎች መካከል አንዱ እ.ኤ.አ በ1955 የነጻነት ቻርተር ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ይዞት የቆየውን ሶሻሊስታዊ ኢኮኖሚ አስተሳሰብ ትቶ በቅይጥ ኢኮኖሚ መተካቱ ነበር። የቅይጥ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎቹም ቢኾኑ ብዙም ተግባራዊ ሳይደረጉ ተራግፈዋል። ግራ ዘመም የሚባለው እና በኔልሰን ማንዴላ ይደገፍ የነበረው መልሶ የመገንባት እና የልማት ፕሮግራም (Reconstruction and Development Programme) ለሁለት ዓመታት እንኳን በቅጡ ተግባራዊ ሳይኾን በጊዜው ምክትል ፕሬዝዳንት በነበሩት እና አሁን በተለያዩ የአፍሪካ አገራት እየተዘዋወሩ ‘ኒዮ-ሊበራሊዝምን እቃወማለሁ’ እያሉ በሚናገሩት ታቦ ምቤኪ ውትወታ ወደ ቀኝ ባዘመመው የዕድገት፣ የሥራ እና የመልሶ ማከፋፈል ስትራቴጂ (Growth, Employment and Redistribution Strategy) ተተካ። በመጀመርያው ፕሮግራም ተጀምረው የነበሩ የመኖርያ ቤት አቅርቦት ፕሮጀክቶች፣ ለድኾች የሚሰጡ የተለያዩ ድጎማዎች፣ የመጠጥ ውሃ፣ ንጹሕ የመጻዳጃ ቤቶች እና መብራት ማስፋፋት በሁለተኛው ፕሮግራም እየተዳከሙ መጡ። እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ ለድኻ ደጋፊ ፖሊሲዎች ብዙ ቁብ ያልነበረው የዓለም ባንክ ሳይቀር ይህ የፖሊሲ ለውጥ አስጨንቆት የደቡብ አፍሪካ መንግሥት መጠነኛ ማሻሻያ እንዲያደርግ ምክር ለግሶ ነበር። ኤኤንሲ ሥልጣን ላይ ከወጣ ከዐሥር ዓመታት በኋላ በአገሪቱ የተመዘገበው ኢ-እኩልነት እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ እና በ1980ዎቹ በአፓርታይድ ሥርዐት ወቅት ከነበረው ጋር ተስተካከለ። ከዚያም በኋላ ብልጫ አሳየ። የሚገርመው ኢ-እኩልነቱ በፍጥነት የጨመረው የደቡብ አፍሪካ አማካይ ዕድገት አመርቂ ነው በሚባልበት ወቅት ነበር። ድህነት ቀነሰ ቢባልም ፍጥነቱ እጅግ ዝግ ያለ ነበር። በርግጥ ጥቂት ጥቁር ልሂቃን እና ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸው ነጋዴዎች በተለይ የጥቁሮችን የኢኮኖሚ ኃይል ለማሳደግ በወጣው Black Economic Empowerment ፖሊሲ ተጠቅመው የበለጸጉ ቢኾንም ለብዙኃኑ ደቡብ አፍሪካውያን አዲሱ የዴሞክራሲ ሥርዐት ያመጣው የኢኮኖሚ ጥቅም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በዚህም ምክንያት የብዙዎች ተስፋ ተቀጨ። ቁጣ እና ንዴት ጨመረ፤ ድህነት፣ ሥራ አጥነት እና የአገልግሎት አቅርቦት ችግር ተስፋፋ፣ በየታውንሺፑ በየጊዜው የሚደረጉ ከአገልግሎት አቅርቦት ችግር ጋራ የተገናኙ ዐመጾች ተበራከቱ። ለዚህ እና ለሌሎች ኢኮኖሚ ነክ ዐመጾች መንግሥት የሚሰጠው ምላሽ አንዳንዴ እንዳልተፈጠሩ እና እንዳልነበሩ አድርጎ መርሳት፣ አንዳንዴ ኃይል የተቀላቀለበት ጨካኝ ርምጃ መውሰድ፣ ምርጫ ሲደርስ ደግሞ ሥንዝር ጉቦ እየሰጡ ለማማለል መሞከር ነው። ለምሳሌ፦ እ.ኤ.አ ነሐሴ 2012 የደሞዝ ጭማሪ የጠየቁ በማሪካና አካባቢ በማዕድን ቁፋሮ ላይ የተሰማሩ ጥቁር ሠራተኞች ላይ መንግሥት ተኩስ ከፍቶ 34 አድመኞችን ሲገድል 78 አቁስሏል።
Gejera south africa

ደቡብ አፍሪካ ዴሞክራሲ ስትጀምር ሌላው የተፈጠረ ነገር ወደ አገሪቱ የሚመጡ ስደተኞች ቁጥር (በተለይ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት) በፍጥነት መጨመር ነበር። የኤኤንሲ መሪዎች ቀስተ ደመናዋ አገር (the rainbow nation) የሚል አገሪቱ ብዙ ዘሮች፣ ብሔረሰቦች እና ጎሳዎች በሰላም፣ በፍትህ እና በፖለቲካ እኩልነት የሚኖሩባት መኾኗን የሚያበስር አካታች (inclusive) መመርያ ይዘው ሥልጣን ላይ ወጡ። በርግጥ ይህ አካታች እሴት የሚመለከተው ደቡብ አፍሪካውያንን ብቻ ይኹን ወይም የውጪ ዜጎችን ይጨምር ግልጽ አልነበረም። በደንብ አልተተነተነም፤ ክርክር አልተደረገበትም። ነገር ግን በተለይ በዴሞክራሲው የመጀመርያ ዓመታት የኮንግረሱ አመራሮች በተግባር ሐሳቡ የውጪ ዜጎችንም እንዲጨምር አድርገውት ነበር። በእነዚሁ ዓመታት ለበርካታ ስደተኞች የመኖርያ ፈቃድ ተሰጥቷል። ደቡብ አፍሪካ ነጻነቷን ስትቀዳጅ በብዙ የአፍሪካ አገራት የፖለቲካ ግጭት እሳቶች ይነዱ ነበር። ከእነዚህ ግጭቶች የሚያመልጡ በርካታ ስደተኞች አገሪቱን መጠለያ አደረጉ። በተጨማሪም ደቡብ አፍሪካ ከብዙ የአፍሪካ አገሮች የተሻለ የኢኮኖሚ የዕድገት ደረጃ ላይ ያለች እና የገቢ መሻሻል ዕድል የምትሰጥ በመኾኗ የኢኮኖሚ ስደተኞች ማግኔት ኾነች። ከሞዛምቢክ፣ ከዚምባቡዌ፣ እና ከኮንጎ በነፍስ ወከፍ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ አገሪቱ ገቡ። ከምዕራብ እና ምሥራቅ አፍሪካም ቢኾን ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሰዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ አቀኑ። ከእነዚህ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ቀያቸው ያደረጓቸው ጥቁር ድኻ ደቡብ አፍሪካውያን የሚኖሩባቸውን ታውንሺፖች ነው። የስደተኞቹ የኢኮኖሚ ኹኔታዎች ከፍ እና ዝቅ ያለ ቢኾንም ጥናቶች እንደሚያሳዩት እነዚህ ስደተኞች በታውንሺፖች ያሉትን የኢኮኖሚ ችግሮች እና ኹከቶች ለመቋቋም ጠንካራ የዋስትና ማኅበራዊ መረቦችን ዘርግተዋል፤ በጥቃቅን ንግዶች እና በጥቁር ኢኮኖሚ በብዛት ይሳተፋሉ፣ እጅግ በዝባዥ በኾነ ዋጋ ተቀጥረው ሥራ ለመሥራትም አያቅማሙም።

በብዙ አገራት እንደምንመለከተው እነዚህ ሁለት ነገሮች- በመንግሥት የፖሊሲ ክሽፈት የተባባሰ ድህነት፣ ተስፋ መቁረጥ እና መጠነ ሰፊ ስደት- ሲገናኙ ማኅበራዊ ፈንጂ የመፈጠር ዕድሉ ከፍ ይላል። ፖለቲከኞች (ከፍተኛም ይኹን ዝቅተኛ እርከን ሥልጣን) በራሳቸው ድክመት የመጣ ችግርን ለመሸፈን ጣታቸውን ስደተኞች ላይ መጠቆማቸው ያልተለመደ ድርጊት አይደለም። በግጭት የሚጠቀሙ ነጋዴዎች (conflict entrepreneurs) ይህን አጋጣሚ አያልፉትም። ለምሳሌ፦ በ2008ቱ ኹከት ላይ የተሠሩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከኤኤንሲ ቀበሌ አደራጆች እስከ የታውንሺፕ ፖለቲካ እና ማኅበራዊ መዋቅር አንቀሳቃሾች በኹከት ቅስቀሳ ላይ ተሰማርተው ነበር። እነዚሁ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የደቡብ አፍሪካውያን የአገልግሎት አቅርቦት ጥያቄዎች ሲጨምሩ- የመዋቅሩ መሪዎች ድጋፍ እና ተደማጭነት እያሽቆለቆለ ሲመጣ – ስደተኞች ላይ የሚያደርጉት ቅስቀሳ ያይላል። የቅስቀሳዎቹ ዋነኛ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦ የደቡብ አፍሪካ ድኾች ከችግራቸው ሊወጡ ያልቻሉት ሥራቸውን በስደተኞች ስለሚነጠቁ ነው፤ ገቢያቸው ከስደተኞች በሚመጣ ፉክክር ይቀንሳል፤ በስደተኞች መብዛት ምክንያት በመኖርያ ቤቶች አቅርቦት ላይ የሚደርሰው ጫና ከፍተኛ ነው። እነዚህ በሙሉ የአስተዳደርን ክሽፈት የሚደብቁ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ የቀስተ ደመናዋ አገር የሚለው ሐሳብ ለደቡብ አፍሪካውያን እንጂ ለውጪ አገር ዜጎች አይሠራም የሚለው አጠቃላይ አመለካከት አግላይ ብሔረተኝነት (exclusive nationalism) በመፍጠር ልዩነቱን አባብሶታል። ከዴሞክራሲ የመጀመርያዎቹ ዓመታት ውጭ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት መሪዎች በንግግራቸው፣ በተግባራቸው እና በፖሊሲያቸው የቀስተ ደመናን ሐሳብ የውጪ ዜጎችን በሚያካትት ኹኔታ ለማስፋት ፍላጎት እንደሌላቸው አሳይተዋል።

የጥላቻ ቅስቀሳ፣ አሉታዊ እና አግላይ ብሔረተኝነት የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ካለው ደኅንነትን የመጠበቅ ድክመት ጋር ተያይዞ በየጊዜው ስደተኛ ጠል ጥቃቶች እንዲጀመሩ እና በቀላሉ እንዲባባሱ ምክንያት ኾኗል። ለምሳሌ፦ የ2008ቱ ኹከት ሲቀጣጠል እና ሲስፋፋ የምቤኪ መንግሥት ለቀናት ከሩቅ ተመልካችነት ያለፈ ሚና አልነበረውም። በመጨረሻ ከብዙ ማመንታት በኋላ ኹከት ወዳለባቸው ሥፍራዎች ወታደሮችን በመላክ ጥቃቱን አስቁሞታል። የዙማ መንግሥትስ ይኼን ለማድረግ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅበት ይኾን?

Source: ሰባት ኪሎ

The post የደቡብ አፍሪካው የስደተኛ ጠልነት መነሻው ምንድነው? (የሰባት ኪሎ ወቅታዊ አጭር ትንተና) appeared first on Zehabesha Amharic.

!ይቅናህ! –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

18.04.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

„ምንም፡ እንኳን፡ በለስም፡ ባታፈራ፣ በወይን፡ ሐረግ፡ ፍሬ፡ ባይገኝ፣ የወይራ፡ ሥራ፡ ቢጓደል፣ እርሾችም፡ መብልን፡ ባይሰጡ፣ በጎች፡ ከበረቱ፡ ቢጠፉ፣ ላሞችም፡ በጋጡ፡ ውስጥ፡ ባይገኙ፣ እኔ፡ ግን፡ በእግዚአብሔር፡ ደስ፡ ይለኛል፣ በመዳህኒቴ፡ አምላክ፡ ሐሤት፡ አደርጋለሁ። ጌታ፡ እግዚአብሄር፡ ሃይሌ ነው፤“

/ትንቢተ – ዕንምባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17-19/

እንዴት ሰነበታችሁልኝ የኔዎቹ – ደህና ናችሁን? ትናንት ሲፈናቀል እጅግ ይከፋኛል። ትናንትን የገነባው፤ ዛሬን ያስገኘው የነገም አስኳል ሊሆን የሚችል ዕውነት ጥግ ሲያጣ ወይንም አትኩሮት ሲነፈገው ወይንም በቅጡ ማስተዳደር ሲሳነን – ያርመጠምጠኛል። ስንት ጊዜ ይማጥ ይሆን?

በፈተና ውስጥ አብዝተው ዋጋ የሚከፍሉ የምናፍቃቸውና የምሳሳላቸው ወገኖቼ ከእነሱ በከፋ ሁኔታ ያሉም እንደሉ ልብ ሊሉት ይገባል ባይ ነኝ፤ እኔው ሥርጉተ ሥላሴ። ከሁሉም እጅግ የከፋው ጎምዛዛ ገጠመኝ በሰው እጅ ቁጥጥር ሥር መሆን ነው። በሰው ቁጥጥር ሥርነት ክስ ደግሞ በስውርም በግልጽም ሊሆን ይችላል። በስለላ ወይንም በካቴና። „ለወንጀለኝነቱም“ ሎቶ ስብኃት ስለ ቃሉ፤ ሳቢያ ይፈለግለታል። በዘመነ ናዚ፤ የናዚን ፓሊሲ የተቃወሙ፤ የስድስት ሚሊዎንን አይሁዳዊ ህይወት ቀድመው ለመታደግ፤ ሀገራዊ ታሪካቻውንም ለማዳን ይተጉ የነበሩ „አሸባሪ“ ይባሉ ነበር። ለአዶልፍ ሂትለር እነኛ የሰብዕዊነት ደቀመዝሙሮች በአደባባይ „አሸባሪ“ ተብለው ተወገዘዋል፣ ፍዳ መከራቸውን አይተዋል፤ ደማቸውንም አፍሰዋል። በዘመነ አፓርታይድም የሰላም አባት የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላም „አሸባሪ“ ይባሉ ነበር። በእኛም የሄሮድስ ራዕይ የፈበረከው ዘር የማክሰል ዘመቻዊ አፓርታይዳዊውን፤ ዘመነ ሱባኤ የተቃወሙ፣ የተሟገቱ „አሸባሪ ወንጀለኛ ናቸው“ ምንም እንኳን ለታደሉት ቀና ብሎ ለመናገር እውነት መድፈር የትውልድ ክብርና ጌጥ፤ ልዩ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ አስገኝ ኃይል፤ ልዩ አዲስ ቀለም ቢሆንም፤ ለእኛ ግን እነሱ የተከደኑ ሲሳዮቻችን፣ ታሪኮቻችን፣ ጀግኖቻችን ናቸው። የመንፈስ ሃብታት፤ ሽልማትም!

አብሶ ፋሽስት በነገሠበት ወቅት የነፃነት ቀማኛው አፈጻጸሙ ሴራማ፤ ሥሩም ትብትብ ነው። ስለዚህም በአንድም በሌላም መንገድ በፈተና አጥር ያሉ ወገኖች ከእነሱ እጅግ በባሰ ጥምዝዝ ገጠመኝ ላሉት፣ በፍም ድቅድቅ ውስጥ ለተማገዱት ደሞቻቸው ማሰብ ይገባቸዋል። ልሳናቸውን ወደ ህዝብ ሲልኩ ጥበብ ያስፈልጋቸዋል – ይመስለኛል። ለደራጎን ማመሳከሪያ – መረጋገጫ ገበር ከመሆን በእጅጉ መቆጠብ አለባቸው። እንዲሁም ቀጣይ አቅም ተስፋ አጥ እንዳይሆንም ከልባቸው ሆነው ሊመትሩት ይገባል። ተስፋ – ያውላል – ያሳድራል – ያኖራልና። ተስፋ የማይለቅበት የሩኽ ስንቅ ነው።

በሌላ በኩል ለአማንያን የመንገድ ምርጫ ጌታ መዳህኒት ፈጣሪ አምላክ ስለመሆኑም  „አለሙን፡ ሁሉን፡ ከፈጠረ፡ ከእግዚአብሄር፡ ከህጉ፡ ከሥርዓቱ፡ የወጣ፡ የለም፡ በሰማይ፡ የሚበር፡ ያሞራ፡ ፍለጋ፡ ቢሆን፡ ወደ፡ ወደደበት፡ መሄጃውን፡ እሱ፡ ያዛል።“ / መጽሐፈ መቃብያን ሣልሳ ምዕራፍ 9 ቁጥር 2/። „ … ያሞራ ፍለጋ ቢሆን ወደ ወደደበት መሄጃውን እሱ ያዛል“ ይላል አካል የሌለው የእግዚአብሄር ትጉኽ አገልጋይ ወንጌል፤ እንኳንስ የሰው ልጅ። የነፃነት ቀማኛው ቀንዶና ቁጭሎቹ እጅግ በበረከቱበት፤ ገደብ አልፎ የነፃነት ጥሰቱ አና ባለበት በዛሬው ጊዜ፤ እዳሪ ላይ በግፍ የወደቀ ነፍስ እልፍ በሆነበት ህማማተ – ዘመን፤ ባለቤት ያጣ ህዝብና አፈር – ለባዕቱ በባዕድነት የተገፋ ህሊና የሚችለውን ሁሉ፤ በቻለው መንገድ እንደምርጫው እንዲከውን የፈቀደለት አምላኩ ብቻ ነው። ስለሆነም ግፊያ አያስፈልግም።

ከእንሰሳ በታች ክብሩ ተገፎ በዬሄደበት እዬታደነ የሚቃጠለው ሥጋና ደም ጪስ እረፍት የነሳው ወገን በአሻው መንገድ የድርሻውን ሊወጣ መሰናዳቱ ሆነ፤ ውጤቱን በአግባቡ ቢተረጎም መልካም ነው። „ነፍሴን ለሀገሬና ለህዝቤ ክብር ብሎ ለመማገድ መቁረጥ“ በራሱ የድል ዋዜማ ነው። ለአንድ ነፃነትን ፈላጊ ድርጅት ወይንም ግለሰብ ወይንም ማህበር ሊሆን ይችላል፤ የነፃነት ፍቅረኛነቱን ከእሱ ለዬት ያለ የነፃነትን መገኛ አማራጭ መንፈስን ቢያንስ በህሊናው ጥበቃ የማደረግ አቅሙ ባለቤቱን ይለካዋል። ስለምንስ ምስጋናው ቀርቶበት፤ ሞትን ቆርጦ ለተሸከመ ሰላሙ ይተዋካል? ነፃነቱን ይቃማል? አይገባኝም። እንዲገባኝም – አልፈልግም።

ጤፍ እንጀራ በእርጎ እኔ መች ጠልቼ፤ ? ? ?

ሲበሉ ለማዬት – ፈቃድ ተነስቼ፤ ? ? ?

ጉሮሮ ለማርጠብ እንዲህም  – ተሟሙቼ፤ ? ? ?

በእቃ ተገምቼ – እንደ ዕቃም ታይቼ

ቢቸግረኝ እንጂ፤ —- መች ክብር ጠልቼ!

ቢከፋኝ ነው እንጂ፣ – ዱሩን ተመኝቼ

መጠለያ ከፈን አፈሩን በልቼ

ቅንቅን በቋጠሮ – ዕንባነን አውግቼ።

የነፃነት ፍለጋ መንገድ ሎተሪ አይደለም። ደግሞም ቀኑ ቢረዝምም ሀሰትን ተስፋ ያለደረገ መንፈስ መጨረሻው አሸናፊ ነው። ውዶቼ – የኔዎቹ – ይህን ግጥም ስጸፈው መንፈሴን እያመመኝ መሆኑን ጨምሬ እገልጻለሁ። ህመሙ ሥም የለሽ ነው። ምክንያቱም፤ እንዴት ያደርግሻል? ብባል መግለጽ እችል ዘንድ አልተሰናዳሁምና። ብልህነት ብልጫ ነው። ብልጫው ደግሞ ብርቅነትን – ያሰነብታል። ብርቅነትን ለማዝለቅ ለብዙኃኑ መንፈስ ፅኑ ጠባቂና ጠንቃቃ መሆንን ይጠይቃል። የመንፈስ ሃብት ዕትብታዊ ትቅቅፉ ረቂቅ ነው። አንዱን ሲነኩት ሌላው ይነቃነቃል ወይንም ይናጋል። መስተጋብራዊ ውህደቱ ሰውኛ አይደለም እና። እንደ ተለመደው ቃናው ሆነ ምቱ ሁልጊዜ በአንድ ማስኬድ አይቻልም። ድምጽ ላይ ሲወጣና በልክ ሲጓዝ ወይንም ጥልቀትን ሲመርጥ የሙዚቃ ባህሬ ብቻ ሳይሆን ዓይነቱም ሆነ መደቡ ይለወጣል። ባለሮኩ እንደ ባለሀገረሰቡ፤ ባለሀገረሰቡ እንደ ፖፑ፤ ባለፖፑም እንደ ቴክኖ ወዘተ … አያስኬዱትም። ፍቅር አብሶ የህዝብ ፍቅር ጥሩ አስተዳዳሪነትን ይሻል። በስተቀር – ይፈሳል። ለማንኛውም በዓይኔ ዞር የምትሉት እትብቶቼ ውስጤ ይሄውላችሁ –

!ይቅናህ!“

*

ከሆንልህ – እልል ልበልልህ።

ከታሳካልህ – ሆ! ብዬ ማጫ ልሁንልህ።

ግን ለባለዛገ ጆሮ አታውስኝ

አትንቀሰኝ – አትውቀሰኝ

የወጨፎ ማዕትህ እኮ – በላኝ

ተለተለኝ፤

እንደ ተመቸህ – እባክህን አትሰልቀኝ?

ይበቃኛል! የባለጊዜ፤ – የጎጠኛ አባዜ

የዘመንተኛ ጃርተ – ሟርት፤  የለዛዜ።

አንተም ባሻህ፤ እኔም ባሻኝ

የአቅሜን መሻቴን እባክህን? – አክብርልኝ።

አይዋ! የኔው በሻ – አታድርገኝ ሆደባሻ

እንደ ልቤ ሸኜኝ፤ እንደ ልብህ ልሸኝህ።

ግን! አዎን! ግን – አትውቃኝ

አትሰቅዘኝ፤

ዬአፓርታይዱ ላይበቃኝ! አንተ ተደምረህ – አታጣውረኝ፣

አታ—-ሳ—-ጣኝ። አታ —- ሥ —- ጣኝ።

አ-ት-ቀ-ረ-ጣ-ጥ-ፈ-ኝ

በመስቃ  አ-ት-ሰ-ነ-ጣ-ጥ-ቀ-ኝ

አትሰልቀኝ፣

አታዋክበኝ ——አትበጣጥሰኝ።

ህም! —- የደም አንባር አይደለሁ፤

መውጫ ባጣ አማራጩን ለተስፋችን ተመኜሁ …..

ዱር ገደሉን ለወላችን – ሞረሽ አልሁ፤

እንጅ፤ እኔማ! ቢያቀማጥሉኝ መቼ ጠላሁ?!

እኮ አንተስ!!? አንተስ፤ ብትሆን ሰኞኛ

ሰውኛ ሁነህ ብትቦጭቀኝ – አይቀርብኝ – ድርሻዬ ይቀልልኝ

ኃጢያቴ – ይሠርይልኝ፤

ብቻ አዎን ብቻ፤ ታናሼዋ – ዳኛው ህዝብ ነው ይፋረደኝ።

እኔ ከሆንኩኝ ጥፋተኛ … ?

…. የማገዶ – አስቀማኛ?

የትውልድ – ቀበኛ …..?

—- የቀንበጥ – እግረኛ?

የደም ጥማተኛ ….?

…. የበቀል – ጉሮሮኛ?

ሀገራዊ – በደለኛ …..?

~~~~~~አድሎኛ~~~~~~~?

እ! ተጠያቂ ለዛውም – ዕንቡጤን አሳልፌ አሰጪ ለዱለኛ —-?

? ? ? ? —-

ለዘር – ብለኛ?

እም! –

የራስ – ህመም -

እማዳግም?

ይሁንልህ ብቻ – አዎን! ብቻ ይፋረደኝ – ዘመን

ይዘምዝመኝ – ይፍተለኝ

እንዳሻው – ያፍተልትለኝ።

ምነው እግረ ተከሉ ታናሼ? ክንድዬ – ታሪክንም ቢሆን አሳርፈው -

አትወርፈው!

ምን ባጣፋ እንዲህ ታቁስለው?

ቁም – ተቀመጥ፤ አትበለው?

አታሳቅለው -

ይበቃዋል – የእነሱ

የነማተበቢሱ።

ለቀን ያደረሰን እሱው ነው ———–በቅኔ ቤት ለካው፤

ባለ አፈር፤ ባለ ቋንቋ፤ ባለማተብ፤ ባለመቀነት – ጥቁር ንጡር አልማዝ እሱውልህ

አስላው – በሚያበለው – ፤

ውልህ።

የአፍሪካ ሰንደቅ፣ የጥቁር ዓርማ። ባርነትን ሰንጥቅ፣ – ድንቅ – እፁብ ፍልቅ፤

እንደ እንሰሳ መሬት ላይ ያላስጎተተኝ/ተህ/

ቀና አድርጎ ያናገረኝ/ህ/ — የትናንቱ የ3000 ከዚህም በላይ ውለኛ። የእናት ያባትህ – ርስትህ – ዋጋ አስራትህ፤

የራስህ ——

ትርሲትህ፤

ቅርስህ።

አያ አንቫዬ! ይልቅ ሥራህን – ሥራ ———

ሥራህ በርቶ ዴሞክራሲን – እስኪያበራ፤ – እስኪናገር – እስኪያወራ ከታሪክ ጋራ

ድምፅ መራሽ ሸንጎ እስክታለማ ——

እስክትሁን – ጉልት ማማ።

ትእግስት ሸምት ከእዮብ ጎራ፤

ከአባ መሆን ጎመራ

ከቅድስና አውራ።

ተወኝ! አልኩኝ – ይበቃኛል የእነሱ

እባክህን! አትነስተኝ ቀልቤ ሆኗል ስሱ፤

የእናት ሀገር ፍቅር ትዝታ – ስስቱ

የአደራ ጥሪት ትሩፋቱ

ሳልመልሰው ገድላዊ ታምራቱ

አቫዝቶኛል ቀን መግፋቱ።

እኮ!

እኮ! ከእኔ ምን አለህ?! – የእናቴ ልጅ በፈቀድከው ባሰኘህ መጪ በል …..

ከሳቱ ላይ እያለህ – አንተም ተረመጥኽ

እያንገበገቡህ – እዬወቁኽ

ከ—–ዘመንተኛ ልቀህ አትዘልዝለኝ – አትዘቅዝቀኝ፤

አትጎልጉለኝ – አትፈርፍረኝ።

ቁጥሩስ ቢሆን ጋሻዬ፤  እኩል – ለእኩል

እኔም አንተም ዬባለ24 ክናድ ባለኩል

የዕንባ – ኩልል።

ልንተያዬ ቀናት ሲያፈጥ——–

ምነው እንዲህ ቸኮልክ – ለማፋጠጥ!?

ይዘኸዋል – ታዬዋለህ

ብቻ ከእኔ ወረድ በል።

አሪወሱ – ባለ ጎራዴ

ተስፋ በቀረመት ጎራርዴ

አለልህ ቋሰኛው – ሸለሸሉ ጉርዴ።

እኔን ለቀቀ! እሱን ጠበቅ!

ጉባኤውን በድል ጥልቅ!

ዳኝነቱን ለህሊና አጥልቅ።

ወልደህ እዬው እንዳልልህ …

አንተም ህዋሴ ሆንክና፤ ምርቃቴን ላኩልህ።

እኔ እንዳተ አይደለሁም። ክብሬ – መንፈሴ – ጥንዴ – አልኩህ

የእኔ ጌጤ ብዬ፤ ውስጤን መርቄ ሸለምኩህ።

ሥጦታነትህን – በውስጥነት አወጅኩልህ

መንገድህን ይቅናህ! ይቅናልኝ፤ ድል ያቅናልኝም – አልኩህ!

እደግልን – ዘለግ ይበል ድልህ

አሁንም እልሃለሁ – በአጭሩ ከደመደመክ – ይሳካልህ~!

አርጎትነው አዶናይ! … እሰይ … እሰይ … ይሁንልን – ይሁንልህ፣

የእመቤቴም ጥበቃዋ አይለይህ፤

መቋጫውን ሐሤትማ – አማንዬ ያድርግልህ

አንደ ልብህ – አንድያዋ – ያሳማማልህ።

ሥጦታ – ለቁስለኛ – ከቁስለኛ።

© Seregute Selassie ሥርጉተ ሥላሴ –  08.04.2015 ሲዊዘርላንድ – ቪንተርቱር።

የኔዎቹ መሸቢያ ሰንበት ተመኝቼ የቤት ሥራ እንሆ – ብትህትና፤ ይህቺን ድግም – ድግምግም አድርጋችሁ ብታነቧት  ትፈወሳላችሁ። „ይህቺ ሐገር ሚስጢር ናት“ ከጸሐፊ ከተማ ዋቅጅራ – እግዚአብሄር ይስጥልኝ። በህሊናችን ሰሌዳ ዓምድ የሆነ ወርቅ አገላለጽ ከጭብጥ ተነስቶ በዕውነት አምክንዮ – የሰከነ። እጅ ይባርክ! http://www.zehabesha.com/amharic/ ውድ ዘሃበሻ – ውድድድ – ኑሩልኝ!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

ኢትዮጵያ አላዛር ናት!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

The post !ይቅናህ! – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሳይንቲስቱ ልጅ ጥያቄ –ከዳንኤል ክብረት (ዲ/ን)

$
0
0

ባለፈው እሑድ፣ የትንሣኤ ዕለትማልዳ ነው ከዕንቅልፏ የተነሣቺው፡፡ እናቷ ቤተ ክርስቲያን አድራ፣ አባቷ ደግሞ ሌሊት ከውጭ ሀገር ገብቶ ደክሟቸው እንደተኙ አልተነሡም፡፡እርሷም በጠዋት የተነሣቺው ጓደኛዋ አደራ ስላለቻት ነው፡፡ ‹‹የቴሌቭዥን የትንሣኤ ፕሮግራም የተቀረጸው እኛ ቤት ነው›› ብላ አጓጉታታለቺ፡፡የተነሣቺው ጓደኛዋን በቴሌቭዥን ለማየት ስትል ነው፡፡ ደግሞ ‹ዘፈን ምናምን አቅርቤያለሁ› ብላታለቺ፡፡ የጓደኛዋ አባት ‹ፍቅርእዚህም እዚያም›፣ ‹ትሄጅብኛለሽ› እና ‹ፍቅር በኪችን ውስጥ› የተሰኙ ሦስት አስቂኝ የፍቅር ፊልሞች ላይ የሠራ ‹ታዋቂ አርቲስት›ነው፡፡ ጓደኛዋ እንደነገረቻት ከሆነ የበዓሉ ፕሮግራም እነርሱ ቤት ሲቀረጽ የቀረ አርቲስት የለም፡፡ በዓሉ ራሱ ሕዝቡን ሊያዝናናስለማይችል ‹ዘና እንዲያደርጉት› ተብሎ ቀልደኞቹ ሁሉ እነርሱ ቤት መጥተው ነበር፡፡
daniel
ከቀረፃው ማግሥት ጓደኛዋ ትምህርትቤት ስትመጣ የታዋቂ አርቲስቶችን ፊርማ በየደብተሯ ሰብስባ መጥታ ጓደኞቿን ሁሉ ስታስቀናቸው ነበር፡፡ በርግጥ ክፍል ውስጥ እርሷናጓደኞቿ ትምህርታቸውን ረስተው የአርቲስቶችን ፊርማ ሲያደንቁ ያዩዋቸው መምህራቸው እንደ መገሰጽ ቢያደርጉም፣ እንደመስማት ያላቸውተማሪ ግን አልነበረም፡፡ ምክንያቱም እርሳቸው ታዋቂ አይደሉማ፡፡ ደግሞ መምህር ከመቼ ወዲህ ነው ታዋቂ የሚሆነው፡፡ ይኼው ስንቱአርብቶ አደርና አርሶ አደር ሲሸለም መምህር መቼ ተሸልሞ ያውቃል፡፡ በተለይ ደግሞ ብዙዎችን ተማሪዎች ያናደዳቸው ‹‹የዘፈነም፣የተወነም፣ ፊልም የሠራም፣ ማስታወቂያ የሠራም አርቲስት አይባልም›› ያሉት ነገር ነው፡፡ ‹‹አርቲስት የሚለው ስም ለሰዓሊዎች የሚሰጥስም ነው፡፡ ያውም ስካልፕቸርና ፔይንቲንግ ለሚሠሩት ብቻ፡፡ እርሱምቢሆን እንደ ደጃዝማችና ግራ አዝማች ማዕረግ ሳይሆን የሞያ መጠሪያ ነው፡፡ እስኪ አሁን አርቲስት ማይክል ጃክሰን፣ አርቲስት ቢዮንሴሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ሰው ማዕረግ የሚያበዛው ስሙ ብቻውን ለመቆም ዐቅም ስለሚያጣ ነው፡፡ እስኪ ተመልከቱ፡፡ ዳቪንቼ፣ ሼክስፒር፣ሞዛርት፣ ፒካሶ የሚለው ስምኮ ብቻውን የሚቆም ነው፡፡ ዕዝል ቅጽል አያስፈልገውም፡፡›› ያሉትን ነገር ተማሪዎቻቸው ‹‹እርሳቸውከቴሌቭዥን ሊበልጡ ነው እንዴ›› ብለው ሙድ ያዙባቸው፡፡

ለነገሩ እርሳቸውም አብዝተውታል፡፡‹አርሶ አደርና አርብቶ አደር፣ ሠልጣኝና የትራፊክ ፖሊስ፣ ታራሚና ፍርደኛ፣ ጋዜጠኛና ጎዳና ተዳዳሪ ማዕረግ ሆነው ከስም በፊትበሚቀጸሉባት ሀገር ‹አርቲስት› ማዕረግ አይደለም ብለው ተማሪን ማሸበር በአሸባሪነት የሚያስከስስ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ እንዲያውምኢቲቪ ቢሰማቸው ‹በአሸባሪነት ሊያስከስስ ይገባል ሲሉ አንዳንድ የሕግ ምሁራን አስገነዘቡ› ብሎ ለዜና ጥብስ ያውላቸው ነበር፡፡
እርሷ ሶፋ ወንበር ላይ ተቀምጣይኼንን ሁሉ ስታስብ ጓደኛዋ በቴሌ ቭዥን ዘገየች፡፡ እስኪጀመር ድረስ ያቺ የ12 ዓመት የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ማሰቧን ቀጠለች፡፡‹‹ቆይ ግን አባዬ ምንድን ነው? አንድም ቀንኮ በቴሌቭዥን ታይቶ አያውቅም፡፡ ይኼው ኤልዳና እንኳን ስንት ጊዜ በቲቪ ልትታዪ ነው፡፡አባዬ ግን ዶክተር ምናምን ከሚሆን አርቲስት ቢሆን ነበር ጥሩ፡፡ እርሱ ዶክተር ሆኖ ምንም አልጠቀመንም፡፡ አንዴ አሜሪካ አንዴጃፓን፣ አንዴ ጀርመን ለወርክ ሾፕ መሮጥ ብቻ ነው፡፡ በርግጥ የኤልዳናም አባት ውጭ ይኼዳል፡፡ ግን እርሱ ሲሄድም ሲመጣም በሚዲያይነገርለታል፡፡ ሊሄድ ነው፣ እየሄደ ነው፣ ሊደርስ ነው፣ ደረሰ ይባልለታል፡፡ የኔን አባት መሄድና መምጣት ግን እኛና የኢትዮጵያአየር መንገድ ብቻ ነን የምናውቀው፡፡

ደግሞ የኤልዳና አባት ውጭ ሲሄድሰው ይከበዋል፣ ጉርድ ቀሚስ ያደረጉ ሴቶች፣ ቁጥርጥር የተሠሩ ወንዶች፣ አጅበውት ፎቶ ይነሣሉ፡፡ የኔ አባት ግን ፎቶዎቹን ሁሉሳይ ወይ ከራሰ በራ ሰው ጋር ወይ ድክምክም ካሉ ሴቶች ጋር ነው የሚነሣው፡፡ ደግሞኮ የኤልዳና አባት ሁልጊዜ የአበባ ጉንጉን ሲቀበልነው የሚታየው፡፡ የኔ አባት ግን ሯጭ ይመስል ሜዳልያ ሲቀበል ነው የምናየው፡፡ ኤልዳና ቪዲዮውን በስልኳ ስታሳየን ሰው ሁሉ ኡኡእያለ አዳራሽ ውስጥ ለአባቷ ይጨፍርለታል፡፡ የኔ አባት ግን አንድ ጠረጴዛ ነገር አጠገብ ይቆማል፤ የሆነ ነገር በፓወር ፖይንትያሳያል፤ አንድ ጊዜ ይጨበጨብለታል፡፡ በቃ፡፡ አንድም የሚጨፍር ሰው አይታይም፡፡ አባዬ ግን ምንድን ነው?

ቆይ ግን እኛ ቤት ኢቲቪዎች የማይመጡትለምንድን ነው? አባቴ አርቲስት ስላልሆነ ነው አይደል፡፡ የኔ አባትኮ እንኳን ለፋሲካ ለአርሂቡ ቀርቦ አያውቅም፡፡ እውነታቸው ነው፡፡በአርሂቡኮ አርቲስቶች ሲቀርቡ ‹እንትናዬ አድናቂህ ነኝ፣ እወድሃለሁ፤ ቀጣዩ አልበምህ መቼ ነው የሚወጣው? ምን ፊልም ልትሠራልንነው?›› የሚል ሰው ይደውልላቸዋል፡፡ አሁን አባዬ አርሂቡ ላይ ቢቀርብ ምን ሊባል ነው? ምን ተብሎ ሊጠየቅ ነው? ደግሞ ማንምአድናቂ አያገኝም፡፡ አልበም የለው፤ ፊልም የለው፣ ሰዎች በምን ያውቁታል፡፡

አባዬ ግን አርቲስት መሆን ነበረበት፡፡ዶክተርነት ምን ያደርግለታል፡፡ አርቲስት ቢሆን ኖሮ በኋላ ሲያረጅ ‹የክብር ዶክትሬት› ተብሎ ይሰጠው ነበር፡፡ ‹የክብር አርቲስት›ብሎ ግን ማንም አሁን አይሰጠውም፡፡ ዶክተርነት ይደረስበታል፡፡ አርቲስትነት ግን አይደረስበትም፡፡ እንዲያውም እነርሱ ሲጠሩ ‹ክቡርዶክተር› ነው የሚባሉት የኔ አባት ግን ‹ዶክተር› ብቻ ነው፡፡

እርሷ ይህንን ስታወጣና ስታወርድየቴሌቭዥኑ ፕሮግራም ጀመረ፡፡ ጋዜጠኛውም ‹እያዝናናን እናስተምራለን› ብሎ የጓደኛዋን ቤት አሳየ፡፡ ምንም እንኳን የተቀረጸው በጾምጊዜ ቢሆን ዶሮው፣ በጉ፣ ክትፎው፣ ቅቤው፣ ዕንቁላሉ ይታያል፡፡ ለነገሩ እንደ ኢቲቪ አቆጣጠር ጾሙ አንድ ሳምንት ሲቀረው ያልቃል፡፡ከዚያ በኋላ ቀረጻ ይቻላል፡፡ ጓደኛዋን አየቻት፡፡ ቤታቸው እየታየ ነው፡፡
እየሮጠች አባቷን ቀሰቀሰቺው፡፡
‹‹ጓደኛዬ በቴሌቭዥን እየታየችነው›› ስትለው ድካሙ ባይለቀውም እርሷን ለማስደሰት ተነሥቶ ዓይኑን እያሸ ወደ ሳሎን መጣ፡፡ ‹እያት ኤልዳናን› አለቺው፡፡ ኤልዳናእየተጠየቀቺ ነው፡፡ ቃለ መጠይቁ ሲያልቅ ‹አባዬ አንተ መቼ ነው በቲቪ የምትቀርበው› አለቺው ልጁ፡፡

‹‹ሚዲያችን ከታዋቂ ይልቅ ለዐዋቂቦታ ሲኖረው›› አላት አባቷ፡፡
‹‹አንተ ግን ለምን ታዋቂ አልሆንክም››

‹‹ልጄ እኔኮ ታዋቂ ነኝ፡፡ የኢቲቪጋዜጠኞች ግን አያውቁኝም፡፡ የቢቢሲ፣ የሲኤንኤን፣ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ያውቁኛል፡፡ እኔ አንድ ነገር ስለ ግብርና ከተናገርኩ ወይምከጻፍኩ ያ ዜና ይሆናል፡፡ እዚህ አገር ግን ዕውቀት ዜና አይሆንም ልጄ፡፡ እዚህ ሀገር ዜና የሚሆነው ፖለቲካና ቀልድ ነው፡፡››
‹‹እሺ ለምን አርሂቡ ላይ አትቀርብም››
‹‹ያማ ጋዜጠኛውን ማሰቃየት ነውልጄ››
‹‹ለምን ይሰቃያል?››

‹‹ምን ይጠይቀኛል? ጥናታዊ ጽሑፎቼንማንበብ ሊኖርበት ነው፡፡ ምርምሮቼን መቃኘት ሊኖርበት ነው፡፡ ስለ እኔ የተሰጡ የሌሎች ሳይንቲስቶችን ምስክርነት ማገላበጥ ሊኖርበትነው፡፡ ይሰቃያል ልጄ፡፡ ቀልድ የለመደን ሰው ዕውቀት ያሰቃየዋል፡፡በቀለላሉ የመጀመሪያ አልበምህ መቼ አወጣኸው? የመጀመሪያው ፊልምህምን ነበር? ገጠመኝህ ምንድን ነው? እያለ ሰዓቱን መሙላት ሲችል ምን በወጣው ሳይንቲስ አቅርቦ ይሰቃያል፡፡ ጋዜጠኞቹ መዘጋጀትስለማይችሉም ስለማይፈልጉም አይደል እንዴ ‹እስኪ ራስሽን ለአድማጮች አስተዋውቂ› የሚሉሽ፡፡ ይኼኮ የጋዜጠኛው ሥራ ነበር፡፡ አንብቦ፣ ፕሮፋይል ሠርቶ ቢመጣ ኖሮእንዲህ አይልም፡፡ ደግሞም አለቆቹም ላይወዱለት ይችላሉ፡፡ ዕውቀት የመለወጥ ኃይል አለው፡፡ ሕዝቡ ደግሞ እንዲዝናና እንጂ እንዲለወጥ አይፈለግም፡፡››
‹‹ተዪው እኔን፡፡ አንድ ገበሬበዓል እንዴት ነው የሚያከብረው? ድንበር ላይ ባሉ ወታደሮች ዘንድ እንዴት ይከበራል? ተረኛ ሆነው ሆስፒታል ወይም እሳት አደጋመከላከያ ውስጥ ባሉ ባለሞያዎች ዘንድ ፋሲካ ምን ዓይነት በዓል ነው? በዕለቱ አየር ላይ በሚሆኑ የአውሮፕላን አብራሪዎችና አስተናጋጆች፣መርከብ ላይ በሚሠሩ ኢትዮጵያውያን፣ ሆስፒታል በተኙ ሕሙማን፣ በዓል እንዴት ይከበራል? የሚለውን እንኳን መች ያሳዩናል፡፡ ለምንይመስልሻል?

‹‹እነርሱ ታድያ አርቲስት ናቸውእንዴ?››

ልጄ የኑሮ አርቱማ ያለው እዚያውስጥ ነበር፡፡ የኛነታችንን ሌላ ገጽታ የምናየውማ እዚያ ውስጥ ነበር፡፡ ግን ይኼ ማሰብ ይጠይቃል፤ መመራመርን፣ ማንበብን፣ መዘጋጀትንይጠይቃል፡፡ ማሰብ፣ ማንበብና መዘጋጀት ደግሞ እዚያ ቤት የሚወደዱ አይመስሉኝም››
‹‹እሺ ታድያ መቼ ነው የኛ ቤትበቴሌቭዥን የሚቀርበው?››
‹‹ወይ እኔ መቀለድ፣ ወይ እነርሱማወቅ ሲጀምሩ››

The post የሳይንቲስቱ ልጅ ጥያቄ – ከዳንኤል ክብረት (ዲ/ን) appeared first on Zehabesha Amharic.

እንኳን ደቡብ አፍሪካ አልሆንሽ ! [ካልሆነሽ] – (ቴዲ ድንቅ) –አትላንታ

$
0
0

ከጥቂት ወራት በፊት አንዲት እህታችን “መጀመሪያ እንትን ነኝ” እንጂ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ስትል ባንዲራ ስታቃጥል፣ ተንቀሳቃሽ ምስሏን ፌስ ቡክ ላይ መለጠፏ ይታወሳል። ይህች እህታችን እንኳን በዚህ ሰአት ደቡብ አፍሪካ አልሆነች። [ካልሆነች]
south africa

south africa news

South Africa Immigrants Attacks
ደቡብ አፍሪካውያን ካገራችን ውጡ እያሉ በጎራዴና በገጀራ ሲቆራርጡና ፣ በ እሳት ሲያጋዩ የታዩት ፣ ኢትዮጵያዊ የሆነውን ሁሉ ነው። “መጀመሪያ እንትን ነኝ” ብሎ የጎሳ ስም ጠርቶ ያመለጠ ሰው የለም። እነሱም የሚያውቁን (ደግሞም የሆነነውን) ኢትዮጵያዊነታችንን እንጂ ጎሳችንን አይደለም። ያቺ ባንዲራ ያቃጠለች ውብ ኢትዮጵያዊት፣ የጎሳዋን ስም ጠርታ ልታመልጥ አትችልም፣ ደቡብ አፍሪካውያንም ሆነ ሌላው ዓለም የሚያውቃት፣ እሷ ብትክደውም፣ በኢትዮጵያዊነቷ ነው።

በጎሳው ምክንያት ከደቡብ አፍሪካው እልቂት የተረፈ የለም። “መጀመሪያ አማራ ነኝ፣ መጀመሪያ ጉራጌ ነኝ፣ መጀመሪያ ትግሬ ነኝ፣ መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ .. ወላይታ ነኝ .. ሃረሪ ነኝ ..” በፈተና ሰአት አያድንም። ዓለም የሚያውቀን፣ ደቡብ አፍሪካዎቹም ውጡልን ብለው ያረዱን በኢትዮጵያዊነታችን ነው።

ያቺም እህታችን በዚህ ክፉ ሰአት ደቡብ አፍሪካ ብትሆን ኖሮ የአንዱ ገጀራ ሰለባ ልትሆን ትችል ነበር። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊት ነቻ! ከሳውዲም በጅምላ እየተገረፍን ስንባረር “ኢትዮጵያዊ አይደለሁም፣ ከዚህ ጎሳ ነኝ” ብሎ የተረፈ ሰው አልነበረም። እናም እህቴ በዚህ ወቅት ደቡብ አፍሪካ ካልሆንሽ – በኢትዮጵያዊነትሽ መጤ ተብለሽ ይህን ሰአት የችግሩ ሰለባ ትሆኚ ነበረና በመትረፍሽ ደስ ብሎኛል – ያገሬ ልጅ ነሻ!

ግን ምናልባት … ምናልባት .. ድንገት ደቡብ አፍሪካ ያለሽ ከሆነና ንብረትሽ ተዘርፎ አንቺም ውጪ ተብለሽ ችግር ውስጥ ከሆነ ያለሽው .. እየጮህን ያለነው፣ ሰልፍ የምንወጣው፣ አይዟችሁ እያለን የምንጸልየው፣ የምናለቅሰውና ይህ ሁሉ ወገንሽ እያዘነ ያለው ፣ ላንቺም ጭምር መሆኑን ተረጂልን።

The post እንኳን ደቡብ አፍሪካ አልሆንሽ ! [ካልሆነሽ] – (ቴዲ ድንቅ) – አትላንታ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>