Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all 1664 articles
Browse latest View live

ሥህነ –ቤዛ! ቅኝተ –ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ! (ሥርጉተ ሥላሴ )

$
0
0

15.08.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

ምዕርፍ ሁለት ….

Birhanuእንደ መግቢያ በር – እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? የአንድ ሃሳብ ዕድሜ ዘላቂነት ሆነ ታላቅነት መለኪያው ዬተግባሩ ሥነ -ምግባሩ ብቻ ነው። አቅጣጫ ቢሱን፤ መደምደሚያ ቢሱን፤ ማለቂያ – አልቦውን እስከ ትብትባዊ ዝክትንትሉ፤ እንዲሁም በብዙ ቋሳ የዘለበውን ችግር –  እስከ ጉስቁሉ ጥንዙል ተስፋችን፣ እንደአለ በሙሉ ፈቃደኝነት፤ ለዛውም ከነገመናው ለመሸከም መፍቀድ ብቻ ሳይሆን፤ መፍትሄ አመንጭነቱንም መሬት ያሳያዝ፤ በተጨማሪም ኃላፊነት የሚሰማውን ጥንቁቅ ብልሃትን የሰጠን፤  አቤቱታችነን በተጠያቂነት – ያዳመጠ፤ በነጠፈ ሌማት የራህብ መና ላዘጋጀልን፤ በምድረበዳ የጥማት ማርኪያ የምንጭ ውሃ ያፈለቅልን ፈጣሪ አምላካችን ልዑል እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን – አሜን!

እንዲህ ሆኖ ነበር። ያን ክፉ ዘመን ይቋቋሙ ዘንድ ቤተ – እስራኤላውያን አምላካችን ያዘጋጀላቸው የሚገዛ አለቃ አልነበረም የነብያትን መሪነት ነበር መርቆ የሰጣቸው። እኛስ በእግዚአብሄር መንበር ፊት እንደ እስራላውያን አምሳል አይደለንም? ፈጣሪ አምላክ – አያዳላም። በፈጣሪያችን ዘንድ ዕንባችን እኩልነት አለው። ከሰማዩ ችሎቱ ፊት – ለፊት ለመቆም ሙሉ ዕውቅና – አለው። በዛ የሱራፌል ዙፋን አቤቱታው ለመደመጥ ሙሉ አቅም አለው።

ያለንበትን የረረበት ዘመን ፈጣሪያችን  – ያውቃል። ጽናታችን ሊፈትን ነው። ከመከራው በስተጀርባ ትልቅ ክብር አለና። ይህ ዘመን ……  ሽምግልና የታሰረበት – ዘመን! መፍትሄ የተገነዘበት – ዘመን። ዬእርቅ ጥያቄ የተወገረበትና  የተቀጠቀጠበት ጠቀራማ ዘመን ነው። የሃይማኖት አቨው እንደ አልባሌ እቃ የተወረወሩበት – የተንዘገዘጉበት – ከትቢያ በታች የታዩበት ዘመነ፤ ዘመነ – ጉግ ማንጉግ … ዘመነ – ሲዖል፤ ዘመነ – ረመጥ —-

የኔዎቹ – ወገኖቼ። ምዕራፍ አንድ የምዕራፍ ሁለት ዋዜማ ነውና …. ማወራረስ እንዲቻል ምዕረፍ አንድን የከወንቡበት ፍሬ ነገር እንዲህ ይል ነበር።

„በማህሌት ደጋፊነት በትጋት ማዕለተ – ተሌሊት ሰዓታት የቆሙት የ24 ዓመታት ዬቅዱሳን የዕንባ ሱባኤ፣ ጻድቅ የዕንባ ዘጉባኤ፤  …. መልክ ያዘ። ዘመነ  – ሱባኤው በድል – ይሰክናል። ተግባርን የሚረታው በእኩል የተግባር ወቄት ቢሆንም ፈቃዱም ታትሞበታል።የኔዎቹ – የማከብራችሁ ዛሬም ውስጤ የሚሰማውን ላጋራችሁ ነውና፤ በተመቻችሁ ሁኔታ ትምረምሩት ዘንድ በትህታና ገልጬ …. መብቱም ፈቃዱም የውዶቼ ነውና የቤት ሥራውን ለእናንተው ለውዶቼ  – ልተዎው።

እርግጥ ነው  ቅዱሳን አባቶቼ የሐገሬ ዬአንድምታ ሊቀ ሊቃውንታት ትርጓሜውን ሆነ ሚስጢሩን መፍታት ሰማያዊ ጸጋ ባለቤቶች ናቸውና ይህን ለደጋግ አቨው ለአባቶቼ  ትቼ ፤ እኔ ሳይገባኝና ሳልመቸው ግን ውስጤ አስጨንቆ ያስገደደኝን እገልጸው ዘንድ የፈቀደልኝ ጌታ አምላኬን – አመሰግነዋለሁ፤ እኔ ትቢያዋና ደካማዋ የሥላሴ ባርያ ንባቡን ብቻ አንዲህ ልሂድበት። ሸበላ የመደማመጥ ጊዜ ተመኘሁ – ለክብሮቼ – ለጹሑፌ ታዳሚዎች።

በቃሉ።

„እግዚአብሄርም፣ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣ – ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፣ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከዬአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር ከአለቆቻቸው ከዬአባቶቻቸው ቤት „አሥራ ሁለት በትሮች“ ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ሥም በዬበትሩ ላይ ፃፍ፤ „አንድ በትርም ለአባቶቻቸው ቤት አለቃ ይሆናልና፤“ „በሌዌ በትር“ ላይ ያሮንን ስም ፃፈ። እኔ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት „በመገናኛ ድንኳን“ ውስጥ „በምስክሩ ፊት አኑራቸው።“ እንዲህም ይሆናል። „የመረጥኩት ሰው በትር ታቈጥቈጣለች።“ በእናንተም ላይ „የሚያጕረመርምባችሁን“ የእስራልን ልጆች „ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።“ ሙሴም ለእስራል ልጆች ተናገራቸው፤ አለቆቻቸው ሁሉ አሥራ ሁለት በትሮች እያንዳንዱም አለቃ በዬአባቱ ቤት አንድ አንድ በትር ሰጡት፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች። ሙሴም በትሮቹን በእግዚአብሄር ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው። እንዲህም ሆነ „በነጋው“ ሙሴም ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ። እነሆም „ለሌዊ ቤት“ የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፤ ለመለመችም፤ አበባም አወጣች፣ የበሰለ ለወዝም አፈራች። ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከእግዚአብሄር ፊት ወደ እስራል ልጆች አወጣቸው፤ „እነርሱም አዩ፤“ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ“ ኦሪት ዘኊልቍ ምዕራፍ 17 ቁጥር 1 እስከ 9

 

እንደ – ቃሉ!  

  • በመገናኛ ድንኳን“ ሥህነ – ቤዛ በባዕቱ ሆኖ የነፃነት ፍላጎቱ ስኬታማ – አልሆነም። ፈቃዱ አልነበረምና። ምልክት ግን ታይቷል፤ ምልክት ነውና። ተሰዶም በተሟላ ኑሮ መንፈሱ መጠለያ – አላገኘም። ከእሱ የቀደሙም ወገኖቹ በቦታው – ተገኝተውበታል። /ሳይንቲስቱም ሆነ ፕሮፌሰሩም/ ሳይቀሩ ግን ያ መንፈስ ባልተሰበ ሁኔታ መቋረጥ – ገጥሞታል። ፈጣሪ አምላካችን የሚጠብቀው ልዩ ማዕዶት ነበረው። የተመረጠ ዬቀን አገልግል ነበር። እንሆ ሌላ ሚስጢር እግዚአብሄር – ገለጠ። እግዚአብሄር የፈቀደለትና የመረቀለት „በድንኳኑ ቤት“ ብቻ ሆኖ ራዕዩን ማነጋገር እንዲችል – ነበር። ለዚህም እንዲህም ሆነ — ድንኳኑን እንደ አምላኩ ፈቃዱ መረጠ – ድንኳኗ ስንት ሰማያዊ ገድል የተቀዳበት የቀዩ ባህር ክፍለ አካል ጋር በተአምር – ተወዳጀ። በድንኳኑ ትንቢት – ተተከለ፤ ሊጸድቅ።  ….  የተለያዩ እትብታዊ ልጆቹ መገናኛ! ነገም ብሩኽ ነው። በቃሉ ስለቃሉ ለቃሉ – አትጠራጠሩ! መገናኛ ዘመን – መጣ። ዬስጋትን አንጥሽት ውሃውን የሚያፈሰው መዳህኒዓለም ነውና።
  • „በምስክሩ ፊት አኑራቸው።“ የኢትዮጵያ ህዝብና የኤርትራም ህዝብ ለዳኝነት የተሰጠው ክህሎት ብቃቱን – ይገልጣል፤ እነሆ ብዙዎቹ ቃሉን – ፈቀዱት ጥጋቸው አደረጉት። ወደዱት፤ አከበሩት። ከበከቡት፤ተከተሉት = በፍቅር ሞሸሩትም።
  • „የመረጥኩት ሰው በትር ታቈጥቈጣለች።“ ይሄው በዬደቂቃው የመንፈስ ለውጥ አብዬት ላይ – እንገኛለን። የብዙዎች ውስጥ ታጠበ – ንጹህ ህሊናን አበራከተ። የተመረጠችው ቅድሰት በትረ በሁሉም መስክ በዬደቂቃው ማቆጥቆጥ ጀመራለች እና … ከእኛ ይልቅ ብላቴናዎቹ ቀድመውን አዳመጡ – ከልብ ሆነው። ታቦሩ ላይ ሊያበራ! ዓለምም አዳመጠ – በማስተዋል ሆኖ፤ አደብ ግዙ! ፍለጋው የነፃነት ነው በማለት በዓለሙ መሪ አንደበት ተከፍቶ ማህተም – ታታመ። መንገዱ ዬነፃነት ቅኔ ነው ተብሎ ዕውቅና አገኘ። እግዚአብሄር ሲመርጥ መግቢያውንም መውጫውንም በር በቅድስና ከፍቶ ነውና።- … መንገዱ ዬቀና ነው ….. ተስፋ በዜማ ይዘምር … ራዕይ ማህሌት ይቁም፤ ናፍቆትም በሰዓታት ፈጣሪውን ያመስግን፤ ፍቅርም ድዋ ይያዝ …. የኔዎቹ – አትጣራጠሩ ስለክብሩ መገለጥ አመስግኑ እንጂ …
  • „አሥራ ሁለት በትሮች“ ከ80 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ቤተ ነገዶችን ያመልክታል …. ሁሉንም በእኩልነት መርምሯል አምላካችን። የመረጠውን ሥጦታ በመረጠበት አምላካዊ ሚዛኑ እንሆ – ቀብቶታል። ፈጣሪያችን ከሁሉ በላይ ንጡህ ልቦናን፤ መንፈሱ ቤተመቅደሱ ሊሆን የሚችለውን እንደ ትእዛዙ የፈቀደውን ቅን አልቆ በሰማያዊ ሥነ ጥበቡ ይመርጣልና ….. እንሆ በፈጣሪ ቃል በፈተና የነጠረው ወርቅ ያበራል – ያነጋል …. መርሁ እግዚአብሄርም ለእኔ ተውሉኝ ብሎታል። የኔ ነው ብሎታል፤ ከዬነገዶቹ አልተቆጠረም ለማዕከላዊ እርስተ መንፈሱ ብቻ የታጨ ስለሆነ። ለታላቅ ተልዕኮ – ለኢትዮጵያዊነት!
  • „የሚያጕረመርምባችሁን“ ከቃልህ በመራቃችን ብቻ ማስተዋሉን አዘገዬነው እንጂ አዎን! ነጠል ብለው ተለይተው ወጠተው ወገኖቻችን ሲያጉረመርሙ – አይተናል። እነሱም የእኛ ናቸውና ምህረትህ ጎብኝቷቸው የቃልህን ድምጽ ያደምጡ ዘንድ አንተ – ፍቀድላቸው። ለንሥኃም አብቃቸው። ዕዝነ ልቦናቸውን በምርቃት – ክፈትላቸው። እኛም የቂም በቀል ደጀን አንዳንሆን ልቦናችን አቤቱ! – ጥረግልን። የጨለመውን ሥነ -ልቦናችን አንጋልን። አቤቱ! በቃችሁም በለን።
  • „ለሌዊ ቤት“ ከቤተ ነገዶች ለእረኝነት የተመረጠው አንዱ ቤተ – መዳፍ ብቻ መሆኑን – ይሄው አዬን፤ በድረጊት ሲከበር ተመለከትን፤ ፈቃደ እግዚአብሄር ነውና አብሮነት በአኃቲነት ዕርገት አደረገ። በዚህ መሥመርም የቆሸሸ ስብዕና ያልታዬበትን ንጡህ መንፈስ ቤቱ አደረገ – ፈጣሪው ….. መረቆታልና እረኛውን፤ ስኬት መንገዱ ይሆናል፤ ለእኛ ብቻ አይደልም እንሆ አፍሪካም …. ምስብክህ …. አፍሪካኒዝምን – ያልቃል። የቆዬ ሰው ይይው። እንደተመኘነው – ይሆናል። ጧፉ ይበራል በእማዋይሽ – አፍሪካ። – ያበራል – ይመራል – ተስፋችን – ይሠራል።
  • „ ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።“ ጕርምርታው ጽንስ ጎልቶ የወጣው፤- – የተነሳው በአዋጅ ተናጋሪዎች በመለከት ቤተሰቦች ላይ – ነበር። ሳሎኑም መኝታ ቤቱም ኮሪደሩም ከማህል አስከ ጠርዙ እነዛው አውታራዊ ዘርፎች ነበሩ። በአንድም በሌላም መንገድ። ህውክቱ ሰላምን ጠጥቶ ችግሩ ፍቺ አግኝቶ ካለ ይግባኝ በአሸናፊነት የሰከነውም በዕወጃው ቤተ መንበር ላይ – ነበር። ጉርምርምታውን በግነት በለው እያለ – „አዲስ ድምጽ“ ጀመረው፤ ከዛው ላይም ምህረት ወርዶ እንደ ንሥኃ አበበ እያለ ደግሞ እንሆ – አዳመጥን። ተመስገን አንተ የሰማይና የምድር ንጉሥ አልን። የጉዞውን መልካም ምኞትም ተከታዩ ቀላጤ – ብራና ላይ ተነበበ፤ አሁንም የሁሉን ጌታ አንተን – አመሰገን። ሁሉንም የምሥራች አዳመጥን – ሐሴትም አደረግን።

እንዲሁም በልዕልት ሀገራችን በኢትዮጵያ ፈቃደ እግዚአብሄር ታምሩን ይገልጥ ዘንድ ከሹክሽክታ ወጥቶ የተመረጠችው በትር ታቆጠቆጥ – ታንቆጠቁጥም ዘንድ የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ዬተከበሩ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን አነሳስቶ ለምክንያት በምድሯ ወስዶ በምድሯ ጥልቅ ታምሩን – ገለጠ። እኛ ግን ከፈጣሪ ገድለ ረቂቅ ምርቃት ውጪ ነበርን።  በዕወጃ  ጉባኤ በኢትዮጵያ መሬት ከሁሉ የቀደመው ጥያቄ የታወከው ጀውጃዋ መንፈስን አዝሎ ሊያዝል ፀላዬ ሰናይ ሲነሳ ከዛው ላይ በሽንፈት – ከነሸንኮፉ በዓለም አዳባይ – ከሰመ – ምኞት መቃበር ሲሰምጥ – አስተዋልንበት።

የፈጣሪ ጥበብ እንዲህ ነው። ከተወረወረ ቀስት እንድን ዘንድ ቃሉ አናገረ …. ቃሉ አሸናፊ ሆነ። ቃሉ ገዢ መሬቱን ተቆጣጠረ …. ቃሉ ነገን አናገረ …. ተመስገን!

ታመርህ ምንኛ ድንቅ ነው። እረኛው አምላክ ወደ ጠራው የሱባኤ ድንኳን የተጓዘው ሰሞናቱም ይሄው የታምራትህ መገለጫ ወቅታት ነበሩ፤ የዓለሙ መሪም እረኛው ደልቶት ከሚኖርበት ቦታ ተነስተው እረኛው ባዕቱን በግፍ ወደ ተቀማበት እትብቱ ከተቀበረበት ቦታ – ተገኙ። ረቂቅ ታምሩ እንዲህ ነው። የታላቋ ሐገር የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዬኢትዮጵያዊነት ቤተሰብነታቸውን በልበ ሙሉነት – አረጋገጡ። በእምቤት ኢትዮጵያ … ትንግርት ተመሳጠረ፤ ገድል በቅኔ – ተቀዳ። …. እያንዳንዷ ቀንና ጉዞ በሚስጢር የተቃኘች የቅኔ ቤተኛ ሆነች። የሆነው ሁሉ ለምክንያት ነበር። ስለ ተከደነውን ሲሳይ ስለ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ዘለግ ብለን በአርምሞና በተደሞ እንድናስተውል – ሆነልን። ስለሆነም ጥበቃው የላይኛው ነውና በቅቶ ግን ተከድኖ የኖረው ቀለም የሥርዬት መንገድ እንሆ። ይቻላል በሚያስችለው አምላክ። የድህነት ትልም ነው። የፍውሰት መርኽ ነው። መርኹ ደማችን እንሆ – ሆነ።

አሁንም ሰላምንና ፍቅርን – ይሰብካል። „ግራ ቀኙ የኔ ናቸው አለ“ ለዚህ ያበቃን አምላክ ክብር ምስጋና ለእሱ ይሁን። ስጋት ያለባችሁ ወገኖቼ አቶ እገሌ፤ ጄኒራል እግሌ፤ የውቅያኖስ ያህል ብራናው በቀለም ቢለቀለቅ ከዚህ ከጸደቀው ታዕምር ጋር መቀባትን የማጉበጥ አቅም – የለውም።  ህውከት ፈጣሪ ወጀቦች ማረፊያ ብትን አፈር – የላቸውም። ይባናሉ። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያዊነት በደጅ ጥናት ነው የሚገኘው። የሸፈተው ልብ ሁሉ የሚመለሰብት ጊዜ ነው ወደ ውበቱ። ኑ እዩ ኢትዮጵያዊነት ሲያበራ! በብርሃኑ መንገድ ሁኑበት። በውስጣችሁ በክብር ኑሩበት! አንድዬን – እመኑ! ድሉ ለተመረጠው እረኛ እሱ አዶናይ – ሰጥቶታል። ይህን ትብትብ እጅግም ውስብስብ ፈተናዎችን ለመሸከም የመከራ ዘመን ለመታደግ፤ ይህን የውርዴት ዘመን ይፍታህ ለማለት መመረጥም – ነብይነት ነው። ሐዋርያነት ነው። ሰማዕትነት ነው። ሃገሬ መከራዋ ብዙ ነው፤ ግን ቁልፍ አለኝ ብሏል – አማኑኤል። የተመረጠው ቀኑን ቀን ማድረግ የሚችለው በተሰጠው የፈጣሪ ምርቃት ብቻ ነው። አቅሙ ከሰማዬ ሰማይት ነው የሚቀዳው። ከገሃዱ ዓለም ሳይሆን ከመንፈሳዊው ቅዱስ አለም። እሱም እራሱ ሱባኤ ይያዝ – ሥጦታውን ያክብር። ፈጣሪውን ተንበርክኮ ያመስግን። መጠነ ሰፊውን ፍቅር ይሰነብትለት ዘንድ – አምላኩን – ይማጠን። ፈጣሪው መንገዱን ጠርጎለታልና …. የተሰጠውን በረከቱን አብዝቶ ይጠንቀቅለት። ከምድር ሃብታት ሁሉ እጅግ የላቀ ነውና የዕንባ መዳህኒትነት – በፍቅራዊነት (Loveism) ሲሞሸር።

  • „ለሌዊ ቤት“ ቤተ መዳፍ ተመረጠ። ይህ ቃለ ምህዳን የሆነው የቤተ – መዳፍ በትር አቈጠቈጠች፤ ለመለመችም፤ አበባም አወጣች፣ የበሰለ ለወዝም አፈራች ይላል ቃሉ።። ጥርጣሬን የሚፈውሰው የመዳህኒት ቃል ነው። ሥጋትን የሚበትነውም እሱ ቃሉ ነው። መሻሪያው ቃሉ ነው። ልሳናችን ሳይሆን ልባችን ለፈጠረው ፈጣሪ – ከሰጠነው። ቢያንስ ለመዳህኒተ – ዓለም ቃለ ወንጌል መንፈሳችን ካላሸፈትናው። እባካችሁን! በፈጣሪ ሥጦታ አትቅኑ! የድርሻችሁን የተገባችሁን በልካችሁ ሰጥቷችኋል ፈጣሪያችን። – ፈቃዱን አትተላለፉ ….. የኔዎቹ ውዶቼ።
  • „በነጋው“ ወገኖቼ አስተውለን እንዬው ይህን ቃል። በቃሉ መሃከል ጠባቂ ዘቦች አሉ። ጠበቂ ዘቦች ‚በ‘ እና ው‘ ናቸው። በመሃላቸው ያለው ኃይለ በትረ ሥም „ነጋ“ ነው። ተልዕኮውም ጉምን ገፎ – ምህረትን፣ ልዩነትን እረትቶ እርቅን፤ ጥላቻን ንዶ – ስምምነትን፤ ቂምን ሸኝቶ – ሥርዬትን፤ ጨላማን ገፎ የትውልድን ተስፋ ማብራት አዎን ሊያነጋ ….. ነው፤ ፍቅርን አውጆ ተስፋን – ሊያሰብል። በዚያ ወቅት አሸናፊው ቃሉ ብቻ ነው። ድሉ የባለቃሉ የህዝብ ልጅ ነው። „በ ሆነ ው“ አብረውት የተጓዙት ምርጦቹ ናቸው። እነሱም የተመረጡ ዮሴፎች – ናቸው። ጠባቂዎቹን ሳይቀር መርጦለታል። ሥህን – ቤዛን የእኔ ነው ብሎታልና ለአደራ ይበቁ ዘንድ በፀሎት – ይትጉ። የረገጣት መሬት ሁሉ ብሩክ ናት። የተጠጋት ትልም ለምለም ናት። የጀመራት ተከታይ ፍጻሜም አላት።
  • „ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከእግዚአብሄር ፊት ወደ እስራል ልጆች አወጣቸው፤“ ሁሉም የተሰጠውን የተፈቀደለትን ብቻ ይከውን ነው ቃሉ የሚለው። ድርሻ አለን ሁላችንም። የድርሻችን ደንበሩን የወሰነው የሰማዩ ዳኛ አምላከችን ብቻ ነውይህ ሰው ሰራሽ – አይደለም። ምድባችን ሰማያዊ ነውና። በዬተመደብንበት አቅማችን ለጥሪያችን – እናውል።
  • „እነርሱም አዩ፤“ አዎን! አቤቱ አምላኬ ሆይ! እኔም ባሪያህ እነሆ በአንተ ፈቃድ ዓይኖቼ ከበፊቱ በበለጠ ጉልላታማና ብቁ አድማጭ ሆነው ቦግ ብለው – ተገለጡ፤ ለዐይኔ ውሃዎች ለጠረናቸው ሆነ ለጥራታቸው በድርጊት የተባን ተስፋን – ሸልምካቸው። አቤቱ ጌታዬ ሆይ! – አመስግንሃለሁ። አባ ቅንዬንም ይምራሽ ብለህ ከነ መክሊቱ ስልፈቀድክልኝ አቤቱ – ሰገድኩልህ። የኢትዮጵያዊነትን መዳኛ እግዚአብሄር ሰጥቶኛል። አምላኬንም ክብሬን ስለሰጠኝ ደግሜ – እንሆ አመስግናለሁ። ፍለሰቲትን ሆነ ተከታትዬም ፆመ ጽጌንም ሥጦታውን – አክበርበታለሁ። ለዛሬም ብቻ ሳይሆን ለወደፊትም የተመረጠው „ባለ ቅብዕ በትር“ ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ ሌላ መዳህኒት እኔ አልጠብቅም። ሥህነ ቤዛን ዘመንና አምላኬ ሰጥተውኛል እና። ተስፋዬን ከ24 የህልም ጉዞ  በኋላ – በዕውን አግኝቻለሁ። „ጊዜ ገቢረ ለእግዚአበሄር“ እንሆ አሁን ሆነ። አዎን ሆነ። ይቻላል ሆነ። ማድረግን ሆነ። ነፃነት የራባቸው አንስት እህቶቼም በተሰጣቸው ድርሻ ብቻ – ይትጉ! ተግተውም ጥላ ከለላ ሆነው – ይርዱት! ወንድማቸውን –  ይገዙትም። አባታቸውን አለንልህ ይበሉት። አማንያን ተግተው በፀሎት አጥር ይጠብቁት ዘንድ በትህትና እኔ ሎሌያቸው ዝቅ ብዬ አሳስባለሁ። እግዚአብሄር ይመስገን። አቤቱ መዳህኒታችን የተሰደዱ መንፈሶችን ሁሉ ዬቃልህ ሚስጢር፤ የፈቃድህ ትንግረት ጉልበት አለውና – ይሰብሰብልን። አሜን!
  • „አንድ በትርም ለአባቶቻቸው ቤት አለቃ ይሆናልና፤“ ሥህነ – ቤዛ የቃለ እግዚአብሄር ሥጦታ ነው። ሁሉም ነገር እስከ ዛሬ የሆነው ለምክንያት ነበር። „ስለምን ቅንጅት ተመረጠው ህዝቡን መልሰው እንግባ አንግባ ብለው ጠዬቁ ወዘተ… ፤“ እንደ ትልቅ ወንጀል ዛሬ ድረስ እንደ አዲስ የሚነሳሱ ነገሮ አሉ ነው። የመርኽ ጉዳዮች ነበሩ። በጠጨማሪም ያ ፈቃደ እግዚብሔር ምልክቱን ለማሳየት ብቻ ያመሳጠረበት ሂደት ነበር። የቀደመውን የመንገድ ጠራጊውንም የፍላጎት እትብትንም በማስተዋል እዩት። የፍቅር ሚዛኑ – የተቀባይነት ልኩ – የፈተና ተቀባይነት አቅሙን –  በዬትኛው በትር ላይ እንደሆነ ሚስጢሩን ይገልጥበት ዘንድ የሆነ ነው። እርግጥ አይደለም ያን ጊዜ አሁንም ጥቂቶችች ሊያሰተውሉት – አልፈቀዱም። ልባቸውን – ስለቆለፉት። ክብር „ከእኔ“ ይጀምር፤ ተቀባይነትም በእኔ ይጽደቅ የሚለውን መታበይ ተሸናፊ ማድረግ – ስላልቻሉ። እሩቅ ከማሰብ፤ የማይቻልን ከመተለም በፊት ከግንባር ካለው መጀመር ብልህነት ነው። እሱም ራስን ማሸነፍ። ሁሉም ለምክንያት ነበር፤ አፍላነቱን በምልሰት ጉልምስናውን በተደሞ ሁሉ ለመልካም ነበር።
  • ሌላም ሚስጥር ተቀና። የዓለሙ መሪ በቅኔ ዘጉባኤ ቅኔውን ዘረፉልን የተከበሩ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የዚያን የቅኔው ንጉሥ የብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ትንቢት ተቃኙት፤ ጋሼ ጸጋዬ እኮ ነብይ ነበር። ለዚህም ነው ለእኔ ህይወት አባቴ እጬጌዬ – የሆነው። የቅዱሱና የሰማዕቱ አባት የአቡነ ጴጥሮስ „ምድሪቱ ለፋሽስት አንዳትገዛ ግዝት“ ሰማዕትነት ጉባኤም በሰሞናቱ ነበር በሃምሌ 22 ቀን ነበር። አሁንም ድህነትን መሬታችን ጠይቃለች! የጸሐፊ ምስብዕከ ወርቁ „ዴርቶ ጋዳ” ራዕያዊ ጥበብ፤ የቅኔው ዕንቡጥ ዬቴዲ አፍሮ „ፍቅር ያሸንፋል” አንዲህ ቀስተ ዳመና ላይ በክብር – ሰከነ። ተባረከልን። የቀስተዳመና ፓርቲ መሥራች  መርኹ ትንቢቱን እንዲህ – አገናኛው። የመክሊት መገናኛ። የቅኔ ትንቢት መዳረሻ። “Here is the land where the first harmony in the rainbow was born. We walk on the bed rock of our planet’s first continent. Here is the root of the Genesis of Life; the human family was first planted here by the evolutionary hand of Time….We walk on the footprints of the evolutionary ancestors of Man.”

ይሄ ነው ቃሉ። በቀስተዳመናችን ሥር የፈጣሪያችን ፍላጎት ስለመሆኑ  – እናዳምጥ። አቅማችን – ፍላጎታችን – ሰብስበን ለብሄራዊ ነፃነታችን – እናውል። የሐገሬ ልጆች ስጋትን – ወርውሩት። የፈጣሪ ቃል ሁሉንም የማሸነፍ አቅም – አለው። የአምላካችን ምርቃት ሁሉንም መርታት – ይችላል። የፈርዖን ልብ በፈጣሪ ቃል አልተገራንም? ኢትዮጵያ ሁልጊዜም መንበር ናት – የዕምነት ንጥህና – ቅድስና ሀገር! ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተመረጠ ነው። ኢትዮጵያ ትልቅ ሐገር ናት። ለሁላችሁም አቅም ላላችሁ ሙሁር ሊቅ ልጆቿ – ትበቃለች። ብዙ ብዙ መጠነ ሰፊ አቅምን የሚጠይቁ ክፍት ቦታዎች አሉ። ቅንነትን እንዳ እዬብ ከታጠቃችሁ – የብሩኽ ዕውቀት ባለድርሻ ወገኖቼ።

ስንት ነገር አዬን – ሙሉ ተስፋ ሰንቀን ኢዲህቅን – አማራጩንም – ህበረቱንም – ቅንጅቱንም – አንድነቱንም – መድረኩንም – በዬቤት ቤታቸው የተደራጁትንም – /ሰማያዊውንም ገና ለጋ ወጣት ነው/ አዬን፤ አዎን! ተመለከትን። አዳመጥን። ተሳተፍን። ግን ተከፍተን – ኖርን። ግን በሃዘን ተቆራምድን ኖርን። አሁን ግን ለቀኑ ቀኑ ተክሊል – ደፋለት። ቤተ መዳፍ በክፉ ቀን ቀልጦ እንዲያበራተፈቀደ። ለሠርግ እኮ አልሄደም። ለሽርሽርም አይደለም። ለጉብኝትም አይደለም። እናስተውል ከልብ ሆነን ሞትን ወዶ ፈቅዶ እጅግ አጣብቂኝና አስጊ እርምጃን ነው የወሰደው። አዎን በሰከነ ብልህ እርምጃው አውሎ እረፍት አደረገ – በረዶውም ተግ አለ። ወጮፈውም ቢሆን በመጣበት – ተመለሰ። ነጕድጓዱም እግሬን አውጪኝ አለ። ነፋሻማና ሳቂተኛ፤ ባለ ሙሉ ልብ በቃሉ ውሎ ውሉን አዬን። ኪዳኑን በተግባር ቀለበት – አሰረ፤ ስለቃሉ ሙሉ ቃል ሆነ። እኛም – ተመስገን አለን።

ተስፋዬን ቀለብኩት

ይሁንልኝ ብዬ አምላኬን —- ለመንኩት፤

የልቤ እንዲሆን እንዲህ —  ተማጸንኩት፤

ተስፋዬ ነውና – ተስፋዬን  — ቀለብኩት

የመሆን ነውና – በውስጤ አኖርኩት

ቤዛዬ ነውና መንፈሴን – ሸለምኩት!

እርገት ይሁን አይደል – የኔዎቹ?! ለእኛ ቁርባናችን – ታቦታችን – ጸሎታችን – ስግደታችን – ሳላዳችን – የወልዮሽ የባህል ዝክረ ነገራችን – የሃይማኖት ማዕዳችን – ቤተ አምልኳችን ንግሥት ኢትዮጵያ ናት። ለነፃነት ፍላጎታችን ማደሪያ የተመረጠው ደግሞ ሥህነቤዛ ነው። እሱ የአርቅ ጉባኤን ከአድማስ ወዲህና ባሻገር መሳላል – የሥርዬት መክሊት መገናኛ መርከባችን አንባችን – ነው።

በተረፈ – በአጋጣሚው ትንሽ ነገር ልከል፤ ከመሆን በላይ ሌላ የመሆን ፍሬ ነገር መጠበቅ እራስን ማተለል መሆኑን አብክሬ መግለጽ እሻለሁ። እራሱን የሸነገለ ህውከት፤ ጦሮ ንፋስን ፈቅዶ አምላካችን ያስከፋ፤ የውስጥ ሰላምን መንጠቅም እንዳለ ይገንዘብ። ለተግባር ገበሬ፤ – እራሱን ችሎ ለግለግ ብሎ ለወጣ ዬዕውነት የቀስተዳመና ዓላማ፤ ምስክርነት – ያስፈልገዋል። አለንልህ ልጆችህ፤ አለንልህ የአብነት ተማሪዎችህ፤ አይዞኽ ማለትም በልበሙሉነት – ይገባል። እግዚአብሄር ይስጥልኝም ማለት – የተገባ ነው። ልዑል እግዚአብሄር ሚስጢሩን ገልጦ ይህን ለመሰለ ለተምሳሌነት ያበቃ አምላክ ጥንካሬውን ብርታቱን፤ ጥበቃውን ይስጥልኝ – ለአርበኞቼ! ድንግልዬ ድስስ ታድርግ፤ የጎደለውንም ትሙላ – እናት!

መሸቢያ ሰንበት – ለእኔዎቹ። ውድ ዘሃበሻ ኑሩልኝ – የመንፈስ ጥሪቶቼ። ምዕራፍ ሦስት ይቀጥላል።

ማሳሰቢያ – አባቱ የእኔ ጀግና ናትናኤልሻ እሺ –  እኔ ሎሌህ ነኝ። በጹሑፎቼ ሁሉ መልእክትህን እለጥፋለሁ። በራዲዮ ፕሮግራሜም በድምጽ መልእክትህን ሙሉውን – አስተላልፋለሁ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45527

ፈጣሪ አምላክ እኛን ስለሰጠን እናመስግን!

ወስብሃት ለእግዚአብሄር።

 


የኔ አባት ገበሬው (ሄኖክ የሺጥላ)

$
0
0

Henok

የኔ አባት ገበሬው ( ሄኖክ የሺጥላ )
የኔ አባት እሱ ነው
አባይ ስር የነቃ
ሃገሩን ያነቃ
አንቅቶ ያለፈ
አልፎ የገዘፈ ።

የኔ አባት ገበሬው
ቃላት እና ዘየው
ዘየና ዝማሬው
ዝማሬና ስራው
የሲና ላይ በትር
ጦሩን ሲነቀንቅ
ቀስቱን ሲያነጣጥር
አነጣጥሮ ሲጥል
የጣለው ሲያጣጥር
እዩት ሲንጎማለል
ዝናር በወገቡ
ጋሻና ጥሩሩ
ኢትዮጵያ ናት ክብሩ !

የኔ አባት ገበሬው
አፈሩን ሲገፋ
ሲገፋ ሲለፋ
ዋሽንቱን ሲነፋ
ነዶውን ሲቀምር
በሮቹን ሲጠምር
ሲወቃ ሲያ-በራይ
አገዳን ከግቻ
ሲነጥል ሲለያይ ።

የኔ አባት ገበሬው
አልቤኑ ነው አልቦው
ሰኔ-ጎሎጎታው ፣ ማረሻና ወገሉ
ግማሽ ጎን አካሉ
ፍቅር ነው እምነቱ
እምነቱ ነው-ቃሉ !

የኔ አባት ገበሬው
አሂዶ ያስሄደ
ጤፍን ያስዘመመ
አደይ ያነጠፈ
ለሀገር እዮሃ ዘርዶ የዘነጠፈ
ግልገል እና ደቦል አጣምሮ ያቀፈ ።

የኔ አባት ገበሬው
እምነቱ ነው ሃብቱ
ፍቅሩ ነው ንብረቱ
ተዋዶ መኖሩ
ተካፍሎ መብላቱ !
የኔ አባት ገበሬው
የኦፊር ስጦታ
የራማ ነጭ እጣን
ሚኒሊክ ሚኒሊክ ፣ የሶሎሞን እጣን
የሰብ’አ ጥር
ውልደትን አብሳሪ
ተጏዥ በጨረቃ
በኮከብ ምልክት ፣ በአምላክ ፍቅር ሲቃ
የኩሽ ምድር ንጉስ የግብጦች አለቃ !

የኔ አባት ገበሬው ነጻነት አይነቱ
የደሙ ቀለም ነው እምቢ ወንድነቱ !

ሞትን የደፈረ
በመድፈር የኖረ
በሕይወት ምልአት
በዜማ ቅኔ ቤት
የተገመደ እውነት ።

ላገሩ ነጻነት
ጥይት ለነብሱ ሕይወት
አ! ብሎ የጠጣ
ጠጥቶ ያለፈ
አልፎ የገዘፈ !

እምቢ ዝባዝንኬ
ዝባዝንኬ ዘኬ
ላገሬ ነጻነት
አባቴ ነው ልኬ
አባቴ ነው መልኬ
እንቢ ! እንቢ ! እንቢ ! እንቢ ! እንቢ !

Henoke Yeshetlla's photo.

Henoke Yeshetlla's photo.

በሐብታሟ ምድር …የርሃብ ችግር (ከተማ ዋቅጅራ)

$
0
0

b3ce60ceየአለማችን ጠበብቶች የሰው መገኛ ኢትዮጵያ እንደሆነች ብዙ ብዙ ብለዋል። እየሄድኩበት ያለሁት እንደ ሳይንስ ገለጻ እንጂ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳልሆነ ይረዱልኝ ። ሳይንስ የምድርን እድሜ በሚሊዮን ሲቆጥር መጽሐፍ ቅድስ ደግሞ  መሺዎች ይቆጥራል። እናም ስለ ድንቅነሽ (ሉሲ)ሳይንሱን ተከትዬ መግለጼን ልብ ይበሉልኝ።

ድንቅነሽ (ሉሲ) በኢትዮጵያ መኖር ከጀመረች ከሶስት ሚሊዮን አመት በፊት እድሜ እንዳላት ተመራማሪዎች ነግረውናል። በዚህም የተነሳ  ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ አገር እንደሆነች እና የሰው ዘር ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ ተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በመሄድ አሁን ያለውን የሰው ዘር ስብጥር እንደተፈጠረ  ተመራማሪዎቹ ማስነበብ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ድንቅነሽ (ሉሲ) ከአዲስ አበባ ሙዚዬም ተነስታ ወደ አሜሪካ በመውሰድ ትላልቅ የአለማችን ሰዎች እንዳዩአት እና ሳይንስቶችም ከፍተኛ ጥናት እንዳደረጉበት ይታወቃል። ድንቅነሽ (ሉሲ) ለምን መሄድ አስፈለጋት? ያስገኘችውስ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳስ ምንድን  ነው? ለሚለው ጥያቄ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲገለጽልን ሰምተን አናውቅም። የሆነው ሆኖ በጉብኝቷ ወቅት ያስገኘችው ገቢ ቀላል የሚባል እንዳይደለ ይታወቃል። በትንሹ ለክልሉ ተወላጆች ሃምሳ የውሃ ጉድጓድ በስሟ አስቆፈረው ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ቢደረግ በተወሰነ መልኩ የሚታየውን የውሃ እጥረት መቅረፍ በቻለ ነበረ።

ኖርዌይ ያራ የሚባለው ካንፓኒ ከአፋር ምድር ፖታሽ (potash) ለማውጣት ከገዚው ፓርቲ ተፈራርመዋል። የማጓጓዛዋ አገር በጅቡቲ ወደብ እንደሆነ ታውቋል። ከፖታሹ ብዛት የተነሳ የኖርዌይ የማዕድን አውጪ ካንፓኒ አጋር አገር እያፈላለገ እንደሆነ ተዘግቧል። ስራውን ሲጀምር በየአመቱ ከፍተኛ ፖታሽ (potash) እንደሚያወጣ አሳውቆናል። ለአገር ገቢ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረገች አፋር ከሚገኘው ገቢ መትንሹ መቶ የውሃ ጉድጓድ ተቆፍሮ ለህብረተሰቡ ቢሰጣቸው ኖሮ እንስሳታቸውም አይሞቱም አገሪቷም በድርቅ ምክንያት ከሚመጣው ችግር ባልተጋለጠች ነበረ። በሚገኘው ገቢ የግለሰብ ኪስ ሲሞላ እንጂ የህብረተሰቡ ኑሮ ሲሞላ አላየንም። የግለሰቦች ሃብት ሲጨምር እንጂ የአገር ሃብት ሲጨምር አላየንም። አፋር ላይ ያየነውም የዚህ ነጸብራቅ ነው።

በድስ ውስት ሆና እንደምትተንተከተክ ሽሮ በኤርታሌ የሚታየው የሳተ ጎሞራ ሁኔታ የሚያሳየን ይሄንኑ ነው። ተመራማሪዎችን ትኩረት የሳበ ስለ እሳተ ጎሞራ ባህሪ ለማጥና ከአለማት የሚመጡባት አገር ናት። ቱሪዝምን በመሳብ በድንቅ ተፈጥሮዋ በብዙ ጎብኚዎች የምትጎበኘው ምድር ከቱሪዝም ከሚገኘው ፍሰት ለአካባቢው ነዋሪዎች የሚያስፈልጋቸው ቀዳሚ ነገር የውሃ ፍላጎታቸው ተሟልቶ ቢሆን ኖሮ ዛሬ የተከሰተው ድርቅን ባላየን ነበረ።

የአሞሌ ጨው ክምር ሜሬት ላይ ተነጥፎ በቀላሉ ተቆፍሮ የሚወጣባት አገር ሁሉ ነገር ኖሯት ሃብታም ሆና ሳለ ምንም እንደሌላት በውሃ እጦት እንሰሳዎቿ በውሃ እጦት ሲረግፉባት ማየት ለኢትዮጵያን ሞት ነው።

ጅቡቲን ውሃ ለማጠጣት የውሃ ጉድጓድ በመቆፈር ያውም በነጻ ሲለግስ የሱማሌ ክልል ምድሪቷ ሃብት ኖሯት ውሃ ተጠማን እያሉ መስማት ለኢትዮጵያን የሚያም ጉዳይ ነው። የአልሙኒዬም መአድን እንዲሁም የጋዝ ክምችት ያላት አገር ለወገን አሳቢ መንግስት ስሌለ ብቻ የኢትዮጵያ ልጆች ማደግ ስንችል መበልጸግ ሲኖርብን ከራሳችን አልፈን ሌሌላው የሚተርፍ ስራ መስራት እየቻልን የአገሩን ዜጋ ሳያጠጣ ለጎረቤት አገር በነጻ የሚሰጥ መንግስት በመኖሩ …በውሃ እጦት እንስሳታቸው እየሞቱባቸው ነው? ዜጎች ከፍተኛ አደጋ ላይ ናቸው? የሚለው ጥያቄ ህዝብን እንጂ መንግስትን የሚያሳስበው ጉዳይ እንዳልሆነ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው።

የወያኔ መንግስት ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ህይወት የሚጨነቅ ወይም የሚያስብ ሳይሆን ከውጪ መንግስታት ስለሚያገኘው ጥቅማ ጥቅም ወደ ግል ካዝናቸው የሚገባበትን ጉዳይ አብዝተው የሚጨነቅ ስለሆኑ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ምንም ሃላፊነት የሚሰማው ስላልሆኑ ህዝባችን በተለያየ አካባቢ ከፍተኛ ችግር እየተጋለጠ ይገኛል። አንድ ቢሊዮን ዶላር በማውጣት የነጻ ሚድያዎችን እና ዌብ ሳይቶችን ለማፈን ወጪ ከምታደርጉ ይልቅ በዚህ ብር የዝናብ እጥረት የሚታዩበትን የኢትዮጵያ አካባቢዎች የውሃ ጉድጓድ ለህዝቡ ቢዳረስ ኖሮ ከእንደዚህ አስከፊ የድርቅ ችግር ሆነ የእንስሳት እልቂት ባልተከሰተ ቀድሞ መቆጣጠር በተቻለም ነበረ። ከሁሉ በፊት ስለ ህዝብ አስቡ! ከሁሉ በፊት ስለ ሰው ክብር እወቁ! ከሁሉ በፊት ስለ ግለሰብ መብት እንዲከበር ስሩ! ከሁሉ በፊት ስለ አገር ክብር ስለ ህዝብ ችግር ቀደሞ ለመገኘት ጣሩ እላለው። ለነገሩ ህዝብና መንግስት በሃሳብም ሆነ በማንኛውም ነገር አልተገናኝቶም።

ከተማ ዋቅጅራ

16.08.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

አቶ መለስ ምን አዲስ ነገር አበረከቱ? –ጌታቸው ሺፈራው

$
0
0

(የግል አስተያየት)

አቶ መለስ እንደ አንድ ‹‹ኢትዮጵያዊ መሪ›› የሚገባቸው ክብር ካለ ቢሰጣቸው ክፋት አልነበረውም፡፡ ሆኖም እየተደረገ የሚገኘው ከሚገባቸው በላይ ማግነን ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ አቶ መለስ የሞቱበትን ጊዜ ያመነበትን ሶስተኛ አመትን አስመክክቶም ይህ ለአቶ መለስ የማይገባ ክብር ገዥው ፓርቲ በያዛቸው ሚዲያዎች በኩል ቀጥሏል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ አቶ መለስን ለህዝብ ‹‹የተፈጠሩ፣ ለህዝብ የኖሩና ለህዝብ የተሰዉ›› ሲል ከአምላክ የተላኩ ያህል እያስመሰላቸው ነው፡፡ ከዚህ አለፍ ሲል ደግሞ ‹‹የተላኩ›› ከማስመሰል አልፈው የፈጣሪነት ሚና ሰጥተዋቸዋል፡፡ አቶ መለስ ለሁሉም እቅዶች፣ ፖሊሲዎች፣ መፍትሄዎች አመንጭ፣ የሁሉም መጽሐፍት ጸሃፊና ሁሉንም ተቋማት የመሩ ተደርገው እየተወራላቸው ነው፡፡ አቶ መለስ ምን ያህል ጊዜ ቢኖራቸው ነው ይህን ሁሉ መጽሐፍ የጻፉት? ተቋማት፣ ባለሙያዎች፣ አማካሪዎቻቸውና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ምን እየሰሩ ነበር? ይህን ያህል ተዓምር ሰሩ በሚል ሳይሆን ታማኞቻቸውን በመጠቀም ተቋማትንና አጠቃላይ አገሪቱን በራሳቸው አስተሳሰብ እንደሚያጠምቁ በመግለጽ ተቃዋሚዎች መለስ አገሪቱን በብቸኝነት እያስተዳደሩ መሆናቸውን ሲወተውቱ በተቃራኒው ኢህአዴግ ‹‹ፓርቲው የሚከተለው የጋርዮሽ አመራር ነው!›› ሲል የነበረውን ከመቼው ረስቶት ይሆን? ነው ይህ ኢህአዴግ የፈጣሪነት ሚና የሰጣቸው አቶ መለስ እነዚህ ተግባራት በመለኮታዊ ኃይል አከናውነዋቸው ይሆን?
meles zenawi
በ1993 ዓ/ም ህወሓት ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ አቶ መለስ በበላይነት የመሯቸው የተለያዩ ስብሰባዎች ተካሂደዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል አንዱ ስለ ቦናፓርቲዝም መበስበስ የተወራበት ስብሰባ ነው፡፡ በዚህ ስብሰባ አቶ መለስ ስለጉዳዩ የሚያትት አንድ መጽሐፍን በማንበብ ለውይይት ሶስት ጽሁፎችን አቅርበዋል፡፡ በተለይ ሁለቱ የመጀመሪያ ጽሁፎች ከተሰብሳቢዎች በርካታ ጥያቄዎች ተነስቶባቸዋል፡፡ አድበስብሰው ሊያልፉ ቢሞክሩም ታጋይነታቸውን እንደዛሬው ጣል እርግፍ አድርገው በፍጹም ታማኝነት ያልቀየሩት የያኔዎቹ ፖለቲከኞች የዋዛ አልነበሩምና መለስን እስከመጨረሻው ሞግተዋቸዋል፡፡ በመሆኑም ሶስተኛና ማጠቃለያ ጽሁፋቸውን ሲያቀርቡ ስህተታቻቸውን ለአፋጠጧቸው ታጋዮች በግልጽ ከመናገር ውጭ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡

‹‹ባለፉት ሁለት ጥናቶች EIGHTEENTH BRUMAIRE የሚባለውን መጽሐፍ ገረፍ ገረፍ አድርጌው የነበረ ቢሆንም ባመዛኙ ቀደም ሲል ካነበብኳቸው ተነስቼ ነበር የጻፍኩት፡፡ ….ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን ጽሁፍ እንደማንኛውም ሰው በተደጋጋሚ ያነበብኩት ቢሆንም በትክክል አልተረዳሁትም ነበር፡፡ ቦናፓርቲዝምን፣ ቢዝማርኪዝምንና አብሶሊውቲዝም (ፍጹም ዘውዳዊ አገዛዝን) አንጻራዊ ነጻነት እንዳላቸው ሶስት የተለያዩ አይነት መንግስታት ነበር የወሰድኳቸው፡፡ አሁን ግን እንዳልሆኑ ተረድቻለሁ፡፡›› ብለው ሂሳቸውን ውጠዋል አቶ መለስ፡፡

እንግዲህ አቶ መለስ ፓርቲው አደጋ በተደቀነበት ወቅትና ከፖለቲከኞች ከባድ ፈተና ሲገጥማቸው በነበረው ጊዜ በአንድ ወቅት ገረፍ ገረፍ አድርገው ያነበቡትን አንድ መጽሐፍ ወደ ኢትዮጵያ በመገልበጥ ለማሳመን መሞከራቸውን ራሳቸው በአንደበታቸው ገልጸውታል፡፡ ይህ ከምንም በላይ ትኩረት እንደሚሰጡት የሚታወቀው የራሳቸው ስልጣን ጉዳይ እንጂ የፓርቲ ስልጣን አሊያም በተደጋጋሚ ቸልተኝነታቸውን ያስመሰከሩበት አገራዊ ጉዳይ አልነበረም፡፡ ከምንም በላይ ስልጣናቸውን ለሚወዱት አቶ መለስ ተቀናቃኞቻቸውን ለመርታት በጊዜው ሞጋች ታጋዮች ፊት ሊያቀርቡት ይችል የነበረው ጽሁፍ ከዚህ የተሻለ መሆን ነበረበት፡፡ በእርግጥ አቶ መለስ ያቅርቡት እንጂ ለጸሁፉ በቅርበት ይገኙ የነበሩ ጓዶቻቸውና አማካሪዎቻቸውም ሚና ሊኖር እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡ ያም ሆኖ አቶ መለስ ኢትዮጵያንም ሆነ ፓርቲያቸውን ይመሩ የነበሩት ገረፍ ገረፍ አድርገው ያነበቡትን መጽሃፍት በመገልበጥ መሆኑን ከራሳቸው አንደበት መረዳት ይቻላል፡፡ ተቃውሞ ሲገጥማቸው ደግሞ ይኸውን መጽሐፍ እንደገና አንብበውም ሆነ አስነብበው ከማቅረብ ውጭ የራሳቸው የሚባል አዲስ አመለካከትም ያበረከቱበት ጊዜ አልነበረም፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ የኖሩት ገረፍ ገረፍ በተደረጉ ጥናቶች ተደጋጋሚ ሙከራ (trial and error) ስልት ነበር ማለት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ከማርክሲዝም፣ ሌኒኒዝም፣ ስታሊኒዝም፣ ማኦይዝም፣ ኒዮሊብራሊዘም፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ…..የመሳሰሉት አስተሳሰቦች እንደወረዱም ሆነ ተዳቅለው የተወሰዱ ፖሊሲዎች ኢትዮጵያን ቤተ ሙከራ አድርገዋታል፡፡

ከ1993 በፊት በህወሓት ውስጥ ችግር ሳይከሰት በተለይም በትግል ስልቱ ወቅትም መለስ፣ ህወሓትና ኢህአዴግ ይጠቀሙት የነበረው ተመሳሳይ ስልትን ነው፡፡ የሌኒን የፖለቲካ ስልቶችን በመገልበጥ ‹‹የትግራይ ማርክሲስት ሊኒኒስት ሊግ›› የመሳሰሉትን ጨምሮ ስሞች፣ይወጡ የነበሩ ፖሊሲዎችና ስልቶች በሩሲያና በኢትዮጵያ ምንም ልዩነት ሳይደረግባቸው በቀጥታ የሚተገበሩ ነበሩ፡፡ ምንም እንኳ አቶ መለስን እንደ ወታደራዊ መሃንዲስ ተደርገው የሚቀርቡበት ሁኔታ ከሚገባው በላይ የተጋነነ ቢሆንም አቶ መለስም ሆነ ህወሓት አዲስ ሳይሆን የማኦንን ወታደራዊ ስልት ገልብጠው እንደተጠቀሙበት ይታወቃል፡፡ ሞስኮ፣ ቤጂንግ ወይንም ምስራቅ ጀርመን የታተመ አንድ ግራዘመም መጽሄት ውስጥ የተቀመጠን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስልት ሳይቀር ህወሓት/ኢህአዴግ እየገለበጠ ኢትዮጵያ ላይ ሲተገብር እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

ከ1993 በኋላ ያለው ደግሞ ከዚህም የባሰ ሆነ፡፡ አቶ መለስ ገረፍ ገረፍ አድርገው ጽሁፍ ሲያቀርቡባቸው በነበሩት ስብሰባዎች ተቀናቃኞቻቸውን አሸንፈው ብቸኛው የስልጣን ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ታጋዮች አቶ መለስን በጥያቄ ሲያጣድፉት የነበሩትና ‹‹የተራገፉት›› ጓዶቻቸው እጣ ፈንታ እንዳይገጥማቸው አቶ መለስ መጽሐፍ ጠቀሱ አልጠቀሱ ያሉትን በሙሉ ተቀብለው የሚያስተገብሩ ታማኞች ለመሆን ተገደዋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ አቶ መለስ ገረፍ ገረፍ አድርገውም ሆነ ‹‹አስታውሸዋለሁ!›› ብለው ያቀረቡት ጽሁፍ ሁሉ በጥልቅ ምርምራዊ ጥናትነት መቅረብ የጀመረበት ወቅት ነው፡፡
MelesCisor3
በእርግጥ ኢህአዴግ አሁን እያለ ከሚገኘው በተቃራኒ አቶ መለስ ስብሰባ ላይ የሚያቀርቡት ‹‹ጥናታዊ ጽሁፍ›› ሁሉ የእርሳቸው ስራ አልነበረም፡፡ በተለይ ከ1993 በኋላ ለፓርቲውም ሆነ ለአገሪቱ የቀረቡት ስልትና ስትራቴጅዎች እንዲሁም ፖሊሲዎች በተቋማት የተሰሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ጥናቶች የፓርቲና አገራዊ ጉዳዮች ስም እንጂ በክፍፍሉ ወቅት ስልጣንን ለማዳን እንደተደረገው በሚስጥራዊነት ሳይሆን ተቋማት፣ አማካሪዎችና ሌሎችም ግለሰቦች ሊሰሯቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህል ከ1993 ዓ.ም ክፍፍል አንድ አመት በኋላ የወጡት የውጭ ጉዳይ፣ የአቅም ግንባታ፣ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ፖሊሲና ስትራቴጂ የሚያብራሩትን ጥራዞች በማስታወቂያ ሚኒስተር የፕሬስና ኦዶቪዥዋል መምሪያ የተዘጋጁ መሆናቸውን በመጽሐፍቱ መግቢያ ላይ ተቀምጧል፡፡ አቶ መለስ በወቅቱ በማስታወቂያ ሚኒስተር የፕሬስና ኦዶቪዥዋል መምሪያ ውስጥ ተመራማሪ ሆነው ሰርተውም ይሁን የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን ጉዳዮች አያነባቸውም ተብሎ እነዚህ መጽሐፍቶች ለአቶ መለስ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡

አንድ የግብርና ፖሊሲና ስትራቴጅን የሚተነትን ጥራዝ ለማዘጋጀት ከአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ጋር የሚውሉት የግብርና ሰራተኞች የሚሰበስቡት መረጃ በየአካባቢው በሚገኘው መስሪያ ቤታቸው ጥናት ይደረግበታል፡፡ በመሆኑም በወረዳ፣ ዞንና ክልል ባሉት ተቋማት በየደረጃው ጥናቱ ተሰርቶና ውይይት ተደርጎበት ለግብርና ሚኒስቴር እና ሌሎች አጋር አካላት ጨምሮ መሪው ቢሮ (ጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ) ድረስ ያሉ አካላት ለፖሊሲው ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ ለመሆኑ አቶ መለስ የግብርና ፖሊሲን የሚጽፉት የግብርና ሚኒስትር ሰራተኞች፣ አመራሮቻቸው፣ አማካሪዎቻቸው፣ የአቶ መለስ የግብርና አማካሪና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የት ሄደው ነው?

በውጭ ጉዳይ ላይም ያለው እውነት ተመሳሳይ ነው፡፡ በአንድ አገር ኤምባሲ የሚላኩ የየመስኩ አታሼዎች የራሳቸውን ጥናት ሰርተው ኤምባሲው በየወቅቱ ጥናት ይሰራል፡፡ በየአገራቱ የሚገኙ ኤምባሲዎች፣ ስለአገራቱ እውቀት ያላቸው ምሁራን፣ ተቋማት ያደረጉት ጥልቅና ዝርዝር ጥናት አጠር ባለ መልኩ አንዲት አገር አጠቃላይ የውጭ ፖሊሲ እስትራቴጅን የሚመራበት ጭምቅ ፖሊሲ ይወጣዋል፡፡ አቶ መለስ የዓለምን አገራት ተጽዕኖ፣ መልካም ተሞክሮ፣ ለኢትዮጵያ የሚኖራቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና የደህንነት ጥቅምና ጉዳት በዝርዝር ተረድተው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን የመጻፍ ጊዜውም ሙያዊ ብቃቱም አልነበራቸውም፡፡ በአንጻሩ ከ50 በላይ በውጭ አገር የሚገኙ ኤምባሲዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት፣ የጠቅላይ ሚኒስተሩ አማካሪዎችና ቢሮ ከአቶ መለስ በተሻለ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጥራዙ ላይ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል፡፡

ከዚህም አለፍ ሲል ኢህአዴግ በተለያዩ መስኮች እውቀት አላቸው ብሎ ያመነባቸውን የውጭ አማካሪዎች ሁሉ በከፍተኛ ደሞዝ ምኒልክ ቤተ-መንግስት ድረስ አስመጥቶ ሀሳብ እንዲያካፍሉት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም አቶ መለስ በበላይነት የመምራት እንጂ በየመስኩ ጥናት ለማድረግም ጊዜም ሆነ እውቀት አልነበራቸውም፡፡ እንደ እነ ሌኒን ያሉት መሪዎች አዲስ ሀሳብ ያመነጩ (ቢያንስ ማርክሲዝምን አሻሽሎታልና) የአገሪቱ ፖሊሲዎች በራሳቸው ርዕዮት መነጸር እንዲዘጋጁ ከማድረግና ከመቆጣጠር ውጭ ዝርዝር ፖሊሲዎችን የሚሰሩ አልነበሩም፡፡ ሌኒን ስለ ኢትዮጵያና ሶቬት ህብረት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊና ማህበራዊ ግንኙነት የሚሰራበት ጊዜም ዝርዝር እውቀት (መረጃ) አልነበረውም፡፡ አቶ መለስን በመለኮታዊ መነጸር ለማሳየት የፈለገው ህወሓት/ኢህአዴግ ግን የኢትዮጵያ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችን፣ አማካሪዎች፣ የጠቅላይ ሚኒስተሩ ቢሮ፣ ሌሎች የኢህአዴግ ፖለቲከኞች፣ የአገር ውስጥና የውጭ ምሁራን የነበራቸውን ሚና ያለ ሀፍረት ለአቶ መለስ ብቻ አስረክቧል፡፡

ሌላው ይቅርና አቶ መለስ ለመመረቂያ ጻፉት የሚባለውን ጽሁፍ ጭምርም የአማካሪዎቻቸውና የሌሎች ተሳትፎ እንደሚኖርበት አያጠራጥርም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚቀርብን ጽሁፍ አቶ መለስ ገረፍ ገረፍ አድርገው አንብበው ከማቅረብ ይልቅ አማካሪዎቻቸውንም ተጠቅመው ጥልቅ ጽሁፍ ለማድረግ ስለሚጥሩ ነው፡፡ ይህ ጽሁፍ የራሳቸው ነው ቢባል እንኳ አቶ መለስን ልዩ አያደርጋቸውም፡፡ ከአቶ መለስ በተጨማሪ በርካታ አምባገነኖች መጽሐፎችን ‹‹ጽፈዋል››፡፡ ለምሳሌ ያህል ሞሶቬኒ እና ጋዳፌ መጽሐፍ ከጻፉት የአፍሪካ አምባገነኖች መካከል በቀዳሚነት የሚወሱት ናቸው፡፡ የሞሶቬኒ መጽሃፍ ከአቶ መለስ በርዕዮት፣ ፓርቲውን በማጋነንና በመሳሰሉት የሚመሳሰል ነው፡፡ የሞሶቬኒ መጽሐፍትና የአቶ መለስ መመረቂያ የሌሎች ጽሃፍትን ሀሳብ በማጣቀሻነት በመውሰድ የተሰሩ እንጂ አዲስ የፍልስፍና ውጤቶች አይደሉም፡፡

በተቃራኒው ‹‹አረንጓዴው መጽሐፍ›› የሚባለው እና ሶስት ጥራዝ ያሉትን መጽሃፍ የጻፈው ጋዳፌ ሀሳብ አዲስ ፍልስፍናዎች ያካተተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የአቶ መለስና ሞሴቬኒ ‹‹የምስራቁን ዓለም›› ተሞክሮ በማድነቅና የምዕራባዊያን ስርዓት በመውቀስ ላይ የሚያተኩሩ ሲሆን መንግስት ከፓርላሜንታዊ ዴሞክራሲ የተለየ በአገር ሽማግሌዎችና በሌሎች በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ባላቸው አካላት ሊመሰረት ይገባዋል ያለውን ባህላዊ ስርዓት የሚያስቀምጠው የጋዳፌ መጽሃፍ በአንጻራዊነት አዲስ ሀሳብን የያዘ ነው፡፡ የአቶ መለስ አስተሳሰብና ጻፉት የሚባለው የጋዳፌን ያህል አዲስ ሀሳብ ሳያነሳ ከእነ ሌኒን፣ ማርክስና ሌሎች የራሳቸውን ርዕዮት ያፈለቁ ሰዎች በላይ እየጋነነ ይገኛል፡፡
MDG : Ethiopia : Meles Zenawi
የፖሊሲ ጥራዞችና መጽሐፍት ይቅርና የአቶ መለስ ንግግሮች ላይ የሌሎች አካላት ሚና ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በዓለም ደረጃ የመሪዎችን ንግግር የሚጽፉ ሰዎች (speech writers) ለአብዛኛው የአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እውቀት ያካበቱ ናቸው፡፡ የመሪዎቹን ቃላት የሚፈጥሩ፣ የሚገሩ፣ የሚያሳምሩ ወይንም የሚያስተካክሉ በመሆናቸውም ‹‹word smiths›› ይሏቸዋል፡፡ ባራክ ኦባማ ከምርጫ ዘመቻው ጀምሮ አብዛኛዎቹን ጥቁሮች ያስለቀሰበት፣ ሌሎችን የአሜሪካና የዓለም ህዝቦች አፍ ያስከፈተበት ንግግር ጆን ፋቭሬአው የተባለ ወጣት የንግግር ጸሃፊ ድርሰቶች ናቸው፡፡ ጸሃፊዎች አንድ መሪ ፖሊሲውን፣ አቋሙን ለህዝብ በሚገባ መልኩ፣ ድምጸት፣ ምክንያትና ቋንቋ እንዲገልጽ ያድርጉታል፡፡ በአጭሩ እነዚህ ጸሃፊዎች የአዕምሮ ንብረት የሌላቸው ደራሲዎች ናቸው፡፡ የመሪዎች ወርቃማ አባባሎች እየተባሉ የሚነገሩት ሁሉም የንግግር ጸሃፊዎች አባባሎች ናቸው፡፡ የአንዲት አገር መሪ ብቻ ሳይሆን በየደረጃው የሚገኙ የተቋማት መሪዎችም የንግግር ጸሃፊዎች (speech writers) አላቸው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥም የሚደረገው ተመሳሳይ ነውና ለአቶ መለስ ንግግሮች ስሙ ያልተጠቀሰልን ደራሲ መኖሩ የግድ ነው፡፡ አቶ መለስ አገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያደርጉት እያንዳንዱ ንግግር በስተጀርባ የንግግር ጸሃፊዎች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ አቶ መለስ የሚነቀፉባቸውን ለጊዜው ትተን ኢህአዴግ አሁን እንዲወደሱ የሚጥርባቸው የአፍሪካ ህብረት ላይ ያደረጉት ቀስቃሽ ንግግር እና ሌሎችም ንግግሮች የራሳቸው አይደሉም፡፡ የንግግር ጸሃፊዎች የአእምሮ ንብረት ባለቤትነት የላቸውምና የአቶ መለስ ወርቃማ ንግግሮች ተብለው በኢቲቪና ኢህአዴግ የሚቀርቡትን የእነዚህ ሰዎች ድርሰቶች መሆናቸው ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ሆኖም አቶ መለስ እነዚህን ድርሰቶች በመተወን የተዋጣላቸው መሆናቸው የማይካድ ነው፡፡

ኢህአዴግ እንደሚያጋንነው ግን አቶ መለስ አዲስ የሌኒን፣ ስታሊንን፣ ማኦን፣ ማርክስንና ሌሎችን አስተሳሰቦች በተቋማት፣ ታማኞቻቸው፣ አማካሪዎችና ሌሎችንም ተጠቅመው ለስልጣን በሚጠቅማቸው መልኩ ከማዳቀልና ከማስመሰል ውጭ አዲስ አስተሳሰብ አላሳዩንም፡፡ ልማታዊ መንግስትን በስም ደረጃ ከምስራቅ ኤሲያ፣ የመገንጠል መብትን ከስታሊኗ ሶቬት፣ የሲቪክ ማህበረሰቦች አዋጅን ከሩሲያ፣ ግብጽና ዚምባብዌ፤ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ከአልባኒያና ቻይና፣ ጠባብ ብሄርተኝነትን ከሶማሊያና ይጎዝላቪያ ‹‹በመልካም ተሞክሮነት›› ከመገልበጥ ውጭ የማሻሻልም ሆነ አዲስ ነገር ሲፈጠር አላየንም፡፡ ይባስ ብሎም ሌኒኒዝም፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ ልማታዊ መንግስትና የመሳሰሉት በስም ደረጃ አሊያም አሉታዊ ጎናቸው እንጂ አወንታዊ ጎናቸው ሲተገበሩ የማይታዩ ገረፍ ገረፍ ተደርገው ለአቶ መለስና ለህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ብቻ በሚጠቅም መልኩ የተቃኙ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ ስለ ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ ታሪካዊ ግንኙነቶች ይናገራሉ

$
0
0

ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ፤ የ “Ethiopia and the United States: History, Diplomacy, and Analysis” መጽሐፍ ደራሲ ስለ ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ ታሪካዊ ግንኙነቶችና የፕሬዚደንት ባራክ ኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክተው ይናገራሉ።

ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ ስለ ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ ታሪካዊ ግንኙነቶች ይናገራሉ

ስለ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቅዐገኘሁ…

$
0
0

በተድላ ደ. ተክሌ
ነሃሴ 12, 2007

ከስራና ትምህርት መስተጋጎል፣ ቤተሰብን እና አዛወንት ወላጆችን ከእስር ቤት ፍርድ ቤት ማንገላታት፣ ያለተጠበቁ የገንዘብ ወጪዎችን ማውጣት፥ ለጠበቃ፣ ለትራንስፖርት፣ ለምግብ፣ ቤተሰብ: ያለጧሪ ወይም ረዳት መቅረት፣ በተለይ ደሞ በአሸባሪነት መከሰስ፣ ከዛም መታሰር ፣ታስሮም በሰቆቃዎች መቀጣት፣ በእስር ወቅትም በሽታን መሸመት እነዚህ ሁሉ ማናችንም ላይ እንዲከሰቱ የማንፈልጋቸው ግን የተከሰቱ ናቸው።

Drawing of  De Birhan’s co-blogger Zelalem Workagegnehu by Melody Sundberg

Drawing of De Birhan’s co-blogger Zelalem Workagegnehu by Melody Sundberg

ዘላለም ወርቃገኘሁ ጋሻው የረጅም ግዜ ጒደኛዬና ደ ብርሃን ብሎግ ላይ ሲጦምር የቆየ ፅኑ ሰው ነው። በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ ሲባል መቼም ሰምታችዃል። ዘላለም ከታሰረና ከላይ የገለፅኳቸውን መከራዎች መቀበል ከጀመረ ኣሁን አንድ አመት ከአንድ ወር ሆነው። ህዳር ፪፻፯ አገር ቤት በሚታተም ጋዜጣ ታትሞ የወጣው ክስ እንዲህ ይላል “የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ሕግና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር ፮፭፪፨፪፻፩ን በመጥቀስ፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፩፱ኛ ወንጀል ችሎት፣ ጥቅምት ፪፩ ቀን ፪፻፯ ዓ።ም። ከቀኑ ፲፡፴ ሰዓት በኋላ ክስ የመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች፣ ዘላለም ወርቅነህ (የታይፕ ስሕተት ነው ወርቅዐገኘሁ ለማለት ነው )፣ ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰለሞን፣ ሰለሞን ግርማ፣ ባህሩ ደጉ፣ ተስፋዬ ተፈራ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሽና የሸዋስ አሰፋ ናቸው፡፡”

የተጠርጣሪዎቹ የክስ መዝገብ መጠሪያና አንደኛ ተከሳሽ የሆነው ዘላለም (ወርቅዐገኘሁ) የተባለው ተጠርጣሪ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪና የግል ሠራተኛ መሆኑ በክሱ ተጠቅሷል፡፡ ተጠርጣሪው የግንቦት ፯ አመራር ነው ከተባለው ተድላ ደስታ (እኔን ነው) ከሚባለው ግለሰብ ጋር ከ፪፲፻ ዓ።ም። ጀምሮ በስልክና በፌስቡክ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዴት እንደሚመጣ ሲመካከሩ ከርመው፣ በ፪፻፫ ዓ።ም። ግንቦት ወር ላይ የግንቦት ፯ አባል መሆኑንም ተጠቁሟል፡፡ የሁለቱ ግንኙነት እንዳይታወቅ deresetariku@gmail.com የሚል አድራሻ በመክፈት፣ ግንኙነታቸውን ማጠናከራቸውን የሚገልጸው የዓቃቤ ሕግ ክስ፣ በ፪፻፬ ዓ።ም። ደግሞ ለግንቦት ፯ አባል የሚሆኑ እየመለመለ እንዲልክና በዓረቡ አገር የተከሰተው ሽብር በኢትዮጵያም ተከስቶ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመጣል በሴል እንዲያደራጅ፣ ከተድላ ደስታ ጋር መወያየታቸውን ክሱ ያብራራል፤ ዘላለም ወርቅነህ (ወርቅዐገኘሁ) የሚጠቀምበት አሥር ሺሕ ብር ከግንቦት ፯ አመራረ ተልኮለት መቀበሉንም ክሱ ይጠቁማል፡፡ ዘላለም ወርቅነህ deresetariku@gmail.com የሚለው አድራሻና የፌስቡክ አድራሻቸው እንዳይታወቅ Debirhanblogandargachewtsige@facebook.com የሚል ሌላ ማኅበራዊ ድረ ገጽ በመክፈት፣ በአንድ አገር በአመጽና በግጭት ማኅበራዊ ለውጥ የሚመጣበትን ማብራሪያ የሚጠይቅ መልዕክት መላላካቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያን በአመጽ እንዲዘጋ ቢደረግ ውጤት ሊመጣ እንደሚችልም መምከሩን ክሱ ያመለክታል፡፡” ይሄ ብቻ አደለም። የዘላለም ክሶች ሌሎችም ናቸው። ስለጎንደር ዩንቨርሲቲ ረብሻ በፈረንጆች አቆጣጠር ፳፩፩ መፃፉና ይህም በውጭ አገር ባሉ ድህረ ገፆች ላይ መውጣቱ፣ ሃገር ቤት ውስጥ ካሉ ጓደኞቹ ጋራ ስለፖለቲካ መወያየቱ መምከሩ ሁሉ በክሱ ወስጥ ተጠቅሰዋል።

የተከበሩ ከሳሾች ከፍተኛ የሆነ ስልጣን ለኔም ለዘላለም ወርቃገኘሁም አሽረውናል። ለዛውም አመራር!

ከዘላለም ጋራ ሌሎች ሶስት ጓደኞቹ ታስረዋል: ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰለሞንና ባህሩ ደጉ፣ ጥፋታቸው ደሞ አንድ አሜሪካን አገር ያለ ኢትዮጲያውዊ ጋዜጠኛ አለ ባለው የኢንተርኔት ስልጠና ላይ ለመካፈል በማመልከታቸው። ክሱ ግን የሽብር ስልጠና ነው ይለዋል። ስለዚህ ጉዳይ ወደፊት በሰፊው እናገራለው። ለዐሁኑ ግን ዘላለም ላይ ላተኩር።
የክሱን ትንተና ለናንተ ልተወው ነገር ግን እኔም እሱም የማንኛውም የፖላቲካ ፓርቲ አባል አደለንም። ነገር ግን ለተጎዱ አዝነናል። ላዘኑና ለተከዙ፤ ለተበደሉ ሁሉ ከከንፈር መምጠጥ በላይ እንጥራለን። ስለገዢዎች ሳይሆን ስለተጠቂዎች ብለን ፅፈናል የቻልነውንም ሞክረናል። ይሄ እንግዲህ በዘመነ ሽብር ሐጢያት ነው። በነገራችን ላይ ገዢና ተጠቂ እንደተመልካቹ ነው። እኛ ራሳችንን እንደተበዳዮች ስናይ አሳሪዎቻችን ደግሞ ራሳቸውን እንደ ተባዳይ ያዩ ይሆናል።

አንድ እማልክደው አቋም ግን ኢትዮጲያ ውስጥ መልካም አስተዳደር መስፈን እንዳለበት በተለይ ደሞ የብሄሮች የበታችነትና የበላይነት (ethnic hegemony) አብቅቶ የብሄር እኩልነት (ethnic equality) መስፈን ለዐሁኗ ኢትዮጲያ ችግሮች መፍትሄ ነው ብዬ አምናለሁ ለዚህም እስከመጨረሻው የምችለውን ሁሉ አደርጋለው። ይሄም ሽብር ይሆን?

ዘላለም በሰላሳዎቹ የመጀመሪያ እድሜ ክልል የሚገኘ ወጣት ነው። በትምህርቱ በጣም ጎበዝ ከሚባሉት ወስጥ ሊምደብ ይችላል። የመጀመሪያ ዲግሪውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ጨርሶ ወደ ቤተሰቦቹ ቤት አዲስ አበባ ከተመለሰ በሁዋላ የተላያዩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የግሉን ንግድ ሲሰራ ነበር። ለምሳሌ መቂ አካባቢ እርሻ ጀምሮ ነበር። የተወሰኑት ቢዝነሶቹ ሲቀጥሉ ሌሎቹ ደግሞ ቆመዋል። ከብዙ አመታት እረፍት በሁዋላ ደግሞ ወደ ትምህርት በመመለስ የማስትርስ ዲግሪ ትምህርቱን በ፪፻፮ አም ጀምሮ ነበር። በታሰረበትም ወቅት የመመረቂያ ርእሱን መርጦ ጨርሶ መፃፍ ብቻ ነበር የቀረው። አሁን ቂሊንጦ ወስጥ ምርጥ የመመረቂያ ፅሁፍ ርእሶች እንዳገኘ አምናለሁ። ትምህርቱን ሲጀምር ብዙ ግዜውን ከፌስቡክ ርቆ ላይብረሪ ያሳልፍ ስለነበር እኔም በግል ህይወቴ በተፈጠሩ ለውጦች ምክንያት ግንኙነታችን ቀንሶ ነበር። አልፎ አልፎ ግን እንነጋገር ነበር።

ስለዘላለም በሃሪ አብረውት ታስረው በቅርብ የተፈቱ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች እንዲሁም እስርቤት ለጉብኝት ሲሄዱ የተዋወቁት ሰዎች ሁሉም “በጣም ትሁትና ጨዋ” ብለው ይገልፁታል። ዘላለም በጣም ጥሩ በሆነ ቤተሰብና ሰፈር ውስጥ ታንፆ ያደገ ልጅ ነው። ሀገሩን የሚወድ ፤ በተለያዩ የምእራብ ሃገሮች ወንድምና እህቶች ቢኖሩትም ፈረንጅ ሃገር ሄዶ ለመኖር የማይጓጓ፤ በሃገሩ ሰርቶ መለወጥን የሚሻ; ብልጭልጭ የማይደንቀው ሰው ነው።

እንደ ዘላላም ያሉ ምሁሮች የትኛውም መንግስት ቢሆን ለሃገሪቱ እድገት ሲል እስር ቤት ውስጥ ሳይሆን የሃሳብ ማፍለቂያና ማንሸራሸሪያ መዐከል ከፍቶ ሊጠቀምባቸው የሚጋባ ዜጎች ናቸው። ይህን የምለው ዘላለምን እንደግላሰብና እንደ አንድ ብዙ ግዜ አብሮት እንደተወያየ ሰው ሆኜ ነው። በደ ብርሃን ብሎግ ላይ እምፅፋቸው ትንታኔዎች ብዙዎቹ ከዘላላም የፈለቁ የሃሳብ ውልዶች ናቸው። ከግጭት አፈታት ዘዴዎች መሃል አንዱ አንዱን የሚረታበት ዊንሉዝ (win-lose) ሲስተም ሲባል ሁለቱም ወገኖች የሚያሸንፉበት ዊንዊን(win-win) ይባለል ሶስትተኛው ደሞ ክሪኤቲቪቲ (creativity) ወይም ደሞ አዲስ ያልታሰበ አማራጭ ማመንጨት ነው። ይሄ ቀላል አደለም። የዘላለምን የክሪኤቲቪቲ ችሎታ ለማሳየት የሚከተለውን ምሳሌ ልጥቀስ። ከጥቂት አመታት በፊት የአባይ ግድብ ጉዳይ በግብፅና በኢትዮጲያ የከረረ አለመግባባት በፈጠረበት ወቅት ፤ እኛም ስለዚህ ጉዳይ ለምን አንፅፍም ብለን ሃሳብ በፌስቡክ መላዋወጥ ጀመርን። ዘላለም እንዲህ አለኝ። ግብፅ ዛፍ መትከል አለባት። ለዛፍ ተከላውም ማገዝ አለብን። ሃሳቡ እንዲህ ነው ኢትዮጲያ በዐባይ የመጠቀም ሙሉ መብት አላት፤ ግብፃውያንም በውሃ ጥም እንዳያልቁ የሰብዐዊ ግዴታ አለብን ስለዚህ ሁሉንም የማይጎዳ መፍትሄ ያስፈልጋል። ግብፅ አብዝታ ዛፍ ብትተክል ለዚህም ብትረዳ በቂ ዝናብና ውሃ ይኖራታል። ይሄ ታድያ ሰፋ ብሎ ቢጠና ምርጥ የፖሊሲ አማራጭ አደለም? እንዲህ አይነት ኢትዮጲያውያንን መንከባከብ አይስፈልግም?

ዘላለምን ለማስፈታት
ዘላለምን ለማስፈታት አንድ አመት ሙሉ ዲፕሎማቶች፤ ሸምጋዮችንና እነሱን ሊቀርቡ ይችላሉ የተባሉ አካላትን ሁሉ ተማፀንን: ጠየቅን። የሁሉንም ወገኖች ሃሳቦች የምናስተናግድ መሆናችንን ለማሳየት ሞከርን። ይሄን ሁሉ የዝምታ ዲፕሎማሲ (quiet diplomacy) ስናካሂድ ልንከላከለው የሞከርነው ነገር ሁሉ ለካ ተከስቷል (the damage was done) መከሰትም ብቻ አደለም ኖረነዋል። ሊያደርሱብን የሚችሉትን ሁሉ አድርሰዋል: የክሶችም ክስ የሆነው የሽብርተኘነት ክሱም (slander) ቀጥሏል ።
የሽብርተኘነት ክስ ሲነሳ ሁልጊዜ የሚገርመኘ ነገር አለ። ክፉው የደርግ ስርዐት ፖለቲካንና ጋዜጠኘነትን ሞት የሚል ትርጉም እንዲኖራቸው: አይነኬ አይጠጌ አድርጎ አልፏል። አሁን ደሞ ፖለቲካና ጋዜጠኘነት ሽብር ማለት ሆነዋል። የኢትዮጲያ ጸረ ሽብር ህግ ከአሜሪካንና ከእንግሊዝ የጸረ ሽብር ህጎች ሙሉ በሙሉ የተወሰደ ነው ብለው የዐገሪቱ መሪዎች በብዛት ይከራከራሉ። መቶ ፐርሰንት ኩረጃ! ምንም እንኳን አሽባሪነት በግልፅ የሚያሰጋን ችግርና ሕግም አሥፈላጊ ቢሆንም አሁን ባለው መልኩ ግን መሆን የለበትም እላለሁ። በመጀመሪያ ችግሩ የሚመነጨው በቀልን ያማከለ ህግ አወጣጥ መኖሩ ነው። እሱ ብቻ አደለም አይምሮውን ተጠቅሞ ነባራዊ ሁኔታዎችንና ችግሮቹን አጥንቶ ተገቢ የሆነ ህግ እሚያወጣ ታላቅ መሪ እና ሲስተም አለመኖሩ ነው። ታላቅ መሪ የራሱን ወገን በፖለቲካዊ ልዩነቶች ብቻ አሽባሪ ብሎ አይፈርጅም፣ አይከስም። ታላቅ መሪ በጥናት እና ምርምር ላይ የተመሰረተ ሽብርን የሚከላከል (ግዴታ ጸረ ሽብር ህግ መባል የለበትም) ህግ ይቀርፃል። ይኸው በዚህ መቶ ፐርሰንት ኩረጃ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ታስረዋል ቀሪው ህዝብ ደሞ ፈርቷል።

ከዐመት በፊት ዘላለም ሲታሰር ሊያስሩት የመጡት ፖሊሶች በጥቆማ ነው የመጣነው ማለታቸውን ሰምቻለው። ከዐንድ አመት በላይም በጠቋሚዎቹ መረጃ መሰረት ዘላለምና ጓደኞቹ ታስረው አካላዊና አእሮአዊ ጥቃቶችን አስተናግደው ተከሰው ፍርድ እየተጠባበቁ ነው። እዚህጋ ነው እንግዲህ የዐሳሪዎቹም የከሳሾቹም የስሌት ስሕተት እሚታየው። አጥፍተውም ቢሆን እንኳን በምክርና ማስጠንቂያ ሊታለፉ የሚችሉ ልጆችን ወደ ቂሊንጦ ሲልኩ የጠቆሙትን ደሞ ወደ ቪላ ቤት ልከዋል። ህሊናው የታሰረው ግን የቱ ነው? የቪላው ወይስ የቂሊንጦው? እነዚህን ልጆች ቂሊንጦ በመላክና እዛው በማክረም ህጋዊም ፖለቲካዊም ትርፍ ይገኛልን? ይህን እንግዲህ በጊዜ እናየዋለን። ለኔ ግን የተሳሳተ ስሌት ነው።

የነዚህ ግለሰቦች ብዙ መከራከሪያዎቻቸው በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርገው፤ ከአንድ አመት በላይ ከሆነ እስር በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በነፃ ይሰናበቱ ወይንም ይከራከሩ የሚለውን ለመወሰን ለብይን ለሃሙስ ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ማን እንደሆነ ባላስታውስም ይህን የዐንድ አውሮፓዊ አባባልን ልጥቀስ “ክፋትን፤ ውሽትን፤ ጭቆናን ከመጥላትና እነሱንም ለመቀየር የቆሙ ጣእማቸው፤ ኩራታቸውና ጥንካሬያቸው በመከራ ውስጥም አይክዳቸውም፤ አካላቸው ቢሞት እንኳን ይኖራል። ህይወት ከሞት ወስጥ ይመነጫል። ከመስዋእትነት። ከጀግኖች መቃብር ደግሞ ነፍስ ያላቸው ሃገራት ይወለዳሉ::” የኢትዮጲያና የኢትዮጲያውያን ችግር እንዲህ ተቆጥሮ እሚያልቅ አደላም፤ ከሃገር ቤት እስከውጭ አገሮች። ብዙዎቹ ችግሮች ሃገሪቱን በእርቅና በፍቅር ዳግም በማዋለድ ሊፈቱ ይችላሉ፤ ሌሎቹ ደሞ በሌሎች መንገዶች።

እነዘላለም ከዐመት በላይ ያለፍርድ እስር ቤት ናቸው። በፍርሃትም በግል ህይወት ምክንያት የሚጠይቋቸውም አብረዋቸው የሚቆሙት ሰዎች ቁጥር ሊቀንስ ይችላል። እኔ ግን ዛሬም እንደ ትላንቱ እስከመጨረሻው ከዘላለም ጎን እቆማለሁ!

 

በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በሚኖሩ ዐማሮች ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል

$
0
0

በዐማሮች ላይ የተፈፀመ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ልዩ ዘገባ
ቅፅ ፫፣ ቁጥር ፩

ማክሰኞ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም.
ለመስማትም ሆነ ለማውራት ይዘገንናል!!
በምን ቋንቋ እንግለጸው! ሰውን ሰው በላው!
ጉምዞች ዐማሮችን አርደው በሏቸው!

ሀ) መግቢያ
ሞረሽ-ወገኔ ይህ አስደንጋጭ ዜና እንደደረሰው የድርጊቱን ዘግናኝነት እና ፍፁም ኢሰብዓዊነት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ ከዚያም አልፎ ያለአግባብ ግለሰቦችንም ሆነ ድርጅቶችን ላለመወንጀል፣ ስለሁኔታው ከሥር መሠረቱ መረጃዎችን ለማጣራት ሙከራ አድርጓል። ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እና ሰብዓዊነት የሚሰማችሁ ግለሰቦች ሁሉ እንድትገነዘቡልን የምንፈልገው፣ በእንዲህ ዓይነት እጅግ የሚሠቀጥጥ ድርጊት ላይ ዘገባ ለማዘጋጀት ምን ያህል ከባድ የኅሊና ፈተና እንደሚደቅን ንፁሕ ኅሊና እና አስተዋይ አዕምሮ ያለው ሰው ይስተዋል አልባልም።
Benishangul

አንዳንድ ጊዜ «ቋንቋ ኃሣብን በትክክል ለመግለጽ ያስቸግራል» ይባላል። ዕውነት ነው፣ እንደዚህ ያለ ለመስማትም ሆነ ለመናገርም የሚቀፍ እና የሚከብድን ድርጊት፣ ድርጊቱን ባየው ሰው፣ በተረዳው እና በገባው መልክ ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ወገን ለመግለጽ ይቸገራል። የቋንቋ ሊቃውንቱም «ቋንቋ አንዳንድ ጊዜ ኃሣብን በትክክል አይገልጽም» የሚሉት እንደዚህ ያሉ ድርጊቶችን በአዕምሯቸው በተቀረጸው መንገድ በቃላት አሳክቶ ለመግለጽ ሲፈልጉ ተስማሚ ቃል ስለሚያጡ ነው። በዚህ በምንኖርበት በ፳፩ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ ያውም የክርስትና ኃይማኖትን ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ተቀብሎ በኖረ እንደ ኢትዮጵያ ባለ የረጅም ዘመን ታሪክ ባለቤት በሆነ ሕዝብ መሃል፣ «ሰውን ሰው በላው፣» «ጉምዝ የተባለው ጎሣ አባሎች የዐማራውን ነገድ አባሎች በጠላትነት ስሜት ተነሳስተው ከወያኔ በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት አርደው በሏቸው» የሚለውን ክፉ ዜና ላልሰሙና ላላወቁ ሰዎች ማስረዳት እጅግ ይከብዳል፣ ይቀፋል፣ በምን ቃላትም ለመግለጽ እንደሚቻል ያስቸግራል። ድርጊቱ ግን በአሳዛኝ መልኩ ተፈጽሟል። በዕውነትም አንበሣ፣ ጅብ ወይም ሌሎች ሥጋ-በል አራዊት በመሰሎቻቸው ላይ የማይፈጽሙትን ድርጊት፣ ሰው ፣ሰውን አርዶ በሚጥሚጣ አጣጥሞ ሲበላው ላየ ሰው፣ ለሌላ ወገኑ ለመግለጽ ቃላት ያጥረዋል። የአገላለጽ መንገዱም ይጠፋዋል፤ ይከብደዋል። «ሰው ሰውን በላው» ማለት ተራ አባባል ይሆናል፤ የተለመደ ተራ አጠቃቀም ይሆናል። በምን ቃል ቢገለጽ ነው ድርጊቱ «ትንግርት፣ ጉድ፣ እግዚኦ የፈጣሪ ያለህ» የሚያሰኘው! ይህ ነው እንግዲህ «አንዳንድ ጊዜ ቋንቋ ኃሣብን በትክክል ለመግለጽ አያስችልም» የሚባለው። የሰው ልጅ ከጅብ እና ከአንበሣ፤ በአጠቃላይ ሥጋ- በል ከሆኑ እንስሶች የከፋ አውሬ መሆኑ እንዴት ይገለጻል?

Read Full Story in PDF/ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የፕሬዝደንት ኦባማ “ታሪካዊ ጉብኝት” አምባገነን አወዳሽ ወይንስ ዲሞክራሲ አጎልማሽ? –አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

$
0
0
ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

የዚህ ሃተታ ዓላማ የፕሬዝደንት ኦባማን ጉብኝት አግባብና ሚዛናዊ ባለው መንገድ ተንትኖ አሉታዊና አወንታዊ ገጽታወቹን ለአማርኛ ተናጋሪዎች ለማቅረብ፤ የወደፊቱ የኢትዮጱያ ህልውና አስተማማኝ ሆኖ፤ የሰብአዊ መብቶችና የሕግ የበላይነት መከበር አለባቸውና የዲሞክራሳዊ አገዛዝ ምስረታ ሂደቶች ሕዝብን ማእከል ማድረግ አለባቸው የሚለው ብሂል ያገባናል የሚሉ ክፍሎች፤ ፈቃደኛነት ካላቸው፤ በጋራና በተናጠል ሊሰሯቸው የሚችሉትን የተወሰኑ መንደርደሪያ ሃሳቦች ለማቅረብ ነው። ባለፈው ሳምንት በድህረ ገጾች ላይ የተሰራጨው ተመሳሳይ ትችት ሆነ ተብሎ ለእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች፤ በተለይ ለአሜሪካ ሕዝብ ቀርቧል፤ ብዙ ጠቃሚና የተለመደው “ለምን ይኼ ተባለ፤ ለምን ይኼ አልተባለም” የሚሉ ትችቶች ተሰራጭተዋል። ሁለቱንም አስተናግዳለሁ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 


በፍትህ እንዲህ የተቀለደበት ዘመን ይኖር ይሆን?

$
0
0

ከፋሲል የኔዓለም
(የኢሳት ጋዜጠኛ)

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ወንድሞቼ ዳንኤል፣ አብርሃም፣ የሽዋስና ሃብታሙ ይፈታሉ በመባሉ በጣም ደስ ብሎኛል። በመፈታታቸው ደስ እየተሰኝን የአገዛዙን ፖለቲካዊ ጨዋታ ማየቱም አይከፋም። ከዚህ ቀድም እንዳልኩት ነው፤ አገዛዙ እድሜውን የሚያራዝመው በሰላማዊ ትግል እና በትጥቅ ትግል መካከል ያለውን የሃሳብ ልዩነት በማራገብ ነው። ሰላማዊ ትግልን የሚያቀነቅኑ ሃይሎች እየጠነከሩ ሲመጡ፣ የትግሉን መሪዎች ያስርና ህዝቡ “ሰላማዊ ትግል አያዋጣንም” ብሎ ወደ ትጥቅ ትግል ፊቱን እንዲያዞር አድርጎ አደጋውን ይቀንሰዋል። የህዝቡ ትኩረት ወደ ትጥቅ ትግል ሲዞር ደግሞ፣ የታሰሩ ሰላማዊ ታጋዮችን ይፈታና የፖለቲካ ምህዳሩንም ትንሽ ከፈት አድርጎ ” አዲስ የተስፋ ዳቦ” ይሰቅላል ። ህዝቡም እንደገና በሰላማዊ ትግል ተስፋ ያደርግና ትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ልቡ ያመነታል- የታጋዩን ልብ እየከፋፈሉ የመግዛት ፖለቲካ ። የእነ አብርሃን መፈታት “ሃሳብን ከፋፍሎ በመግዛት የፖለቲካ ስልት ” ካየነው ስሜት ይሰጣል።

የተፈቱትም ሆነ ለወደፊቱ የሚፈቱት ታጋዮች ቆራጥ የሰላማዊ ትግል አቀንቃኞች ናቸው፤ ከመጀመሪያውም የታሰሩት ሰላማዊ ትግሉ በምርጫው ላይ ተጽኖ እንደሚፈጥር ስለታወቀ ነው። ከምርጫው በሁዋላ፣ በተለይም ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጓዙን ጠቅልሎ የትጥቅ ትግል ወደሚደረግበት በረሃ ሲወርድ፣ ህዝባዊ ንቅናቄው በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። ይህን ህዝባዊ ንቅናቄ ለመቀልበስ አገዛዙ ፣ ሰላማዊ ታጋዮችን በመፍታትና የፖለቲካ ምህዳሩን ትንሽ ገርበብ በማድረግ የህዝቡን ልብ ለመከፋፈል የተለመደ ስልቱን ተግባራዊ ለማድረግ አቅዷል። ይህ ስትራቴጂ የተበላ እቁብ በመሆኑ ከእንግዲህ ውጤት ያመጣል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው። አንደኛው የትግል አማራጭ ( የትጥቅ ትግሉ) ጉልምስና እድሜ ላይ ደርሷል፤ አገራችን በውጭ ስትወረር ካልሆነ በስተቀር ህዝቡ በዚህ ደረጃ ተነቃንቆ ትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ፍላጎት ሲያሳይ ስመለከት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ” ትግሉን መቀላቀል እንፈልጋለን” እየተባለ ከአገር ቤት በየቀኑ የሚደወለው ስልክ አስገራሚ ነው፤ እንዲያውም ስልክ የምታነሳው ባልደረባዬ ” የኢትዮጵያ ህዝብ በመሉ ጫካ ከገባ ነጻ አውጪዎች ነጻ የሚያወጡት ማንን ነው? በማለት በጣም ተገርማ ጠይቃኛለች ። ከአገር ቤት ስለሚደወሉ ስልኮች ደግሞ አገዛዙ በቂ መረጃ አለው፤ የህዝቡንም ስሜት ያውቀዋል። ይህን የተባለበትን ቁማር እንደገና ለመቆመር የተነሳውም ለዚህ ነው። እኔ ሁለቱም የትግል ስልቶች በስልት ከተካሄዱ ተደጋጋፊ ናቸው ብዬ አምናለሁ። ስርዓቱን በውስጥም በውጭም በመወጠር፣ ልክ እሱ የታጋዮችን የትኩረት አቅጣጫ በመከፋፈል የነጻነት ትግሉን ለማዳከም እንደሚሞክረው ሁሉ፣ ታጋዮችም በተመሳሳይ ስልት የእሱን የትኩረት አቅጠጫ በማሳት ሊያዳክሙት ይችላሉ። የእነ ዳንኤል መፈታት ትግሉን ወደፊት ይገፋዋል እንጅ አያዳክመውም።
habitamu
እግረ-መንገዴን ስለሚያብከነክነኝ አንድ ነገር ትንሽ ልበል። ሃሳቡን ዮና ብር የተባለ ጎበዝ ጸሃፊ አንስቶት አይቻለሁ ። እንደሚታወቀው በዘፈቀደ እየታፈሱ የሚታሰሩና የሚፈቱ የአገሬ ብርቅዬ ልጆች ይቅርታም ካሳም ተከፍሏቸው አያውቅም። ዘመዶቻቸው እነሱን ለመጠየቅ ሲመላለሱ የገንዘብ ፣ የጊዜና የጉልበት ኪሳራ አጋጥሟቸዋል። ልጆቻቸው የወላጆቻቸውን ፍቅር እንዳያገኙ በመከልከላቸው በአእምሮ እድገታቸው እና በወደፊቱ ህይወታቸውም ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽኖ ይፈጠርባቸዋል። ስራ መስራት ባለመቻላቸው የኑሮ ቀውስ ያጋጥማቸዋል። ሽብርተኛ በመባላቸውም የሞራል ኪሳራ ይደርስባቸዋል። የግል ህይወቴን የተመለከቱ ጉዳዮችን ማንሳት ባልፈልግም፣ ለዚህ ውይይት ስለሚጠቅም ለዛሬ አንድ ነገር አነሳለሁ። ከ5 ዓመታት በፊት፣ ወደ ሆላንድ ከመጣሁ በሁለተኛው አመት፣ የገጠመኝ አንድ ትልቅ ችግር ነበር። ኢሳት እንደተቋቋመ፣ እንደዛሬው በቂ የሰው ሃይል ሳይኖርና በየአገሩ ስቱዲዮዎች ሳይመሰረቱ፣ የሆኑ ሃይሎች “ኢሳትን ማስቆም አለብን” ብለው ተነሱና በእኔ ላይ ክስ መሰረቱ። እነዚህ እኩይ ሰዎች፣ ” ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ይሰራል፤ ህገወጥ ገንዘብ ያገኛል፣ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ያስገባል ወዘተ” የሚል ደብዳቤ ጽፈው ለፖሊስ አስገቡ። የተጠቀሱት ወንጀሎች በጣም አደገኛና ከአገር የሚያስባርሩ ወይም የሚያሳስሩ ናቸው። ያው ጥቆማ ቀርቧልና ፖሊስም ምርመራ ጀመረ። ሁለት ጊዜ ተጠርቼ ተጠየኩ፤ መርማሪዎች ቤታችን ድረስ መጥተው አኗኗራችንን አዩት። የባንክ አካውንቴ ተመረመረ፣ ስለኢሳት አጀማመርና የገንዘብ ምንጭ ሳይቀር ተጠየቀኩ፣ የሁዋላ ታሪኬ ሁሉ ተመረመረ። የመንግስት ክፍያም ለሁለት ወራት በግማሽ ቀነሰ። ሰዎች መከሩኝና በነጻ ጠበቃ ወደሚያቆም ድርጅት ሄድኩ። በሳምንቱ፣ ከጠበቃዬ ጋር ፍርድ ቤት ቀረብኩ። ፍርድ ቤቱ ፋይሉን አገላብጦ እንደቆምኩ ውሳኔ ሰጠ። “በአጉል ጥርጣሬ ለተደረገው ምርምራ የይቅርታ ደብዳቤ ይጻፍ፣ ለቃለምልልስ በሚል ሁለት ቀናት ስራ በመፍታቴ ክፍያ ይከፈለው፣ የታገደው የሁለት ወር ክፍያ ይለቀቅለት እንዲሁም በእሱና በቤተሰቡ ላይ ለደረሰው የሞራል ካሳ መዘጋጃው በመስፈርቱ መሰረት ይክፈለው” አለ። አጠቃላይ የገንዘብ መጠኑ ተስልቶ እንደሚነገረኝ፤ በክፍያው ላይ ቅሬታ ካለኝመ ይግባኝ እንድል፣ ስራዬን እንደሚያደንቁ አበረታተው አሰናበቱኝ። በፍጹም ማመን አልቻልኩም። ከቀናት በሁዋላ የይቅርታ እና የገንዘብ ዝርዝር የያዘ ወፍራም ደብዳቤ ደረሰኝ። ጠበቃው ” ገንዘብ አንሶኛል የምትል ከሆነ ይግባኝ እጠይቃለሁ” አለኝ። (እሱም ራሱ ለአንድ ቀን ፍርድ ቤት ስለቀረበ ብቻ ጠቀም ያለ ክፍያ አግኝቷል። ) አይሆንም አልኩት።

የ97ቱን ምርጫ ተከትሎ ከሌሎች ጋደኞቼ ጋር ለአንድ አመት ከ ስምንት ወር ያክል ጊዜ ታስሬ በነጻ ተለቅቄያለሁ። በታሰርኩባቸው ወራት ስራ ብሰራ ኖሮ ላገኝ የምችለውን ገንዘብ እንርሳውና በተለያዩ ምክንያቶች ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ኪሳራ ደርሶብኛል። ባለንብረት የነበርኩ ሰው ንብረት አልባ ሆኜ ተፈትቻለሁ፤ ለዚህ ሁሉ ግን ካሳ ሊከፈለኝ ቀርቶ የተወሰደብኝ ኮምፒዩተር እንኳ አልተመለሰልኝም፤ ስጠይቃቸው ” ገና መቼ ተነካህና ነው” ብለው አሰናብተውኛል። በሰው አገር ለሁለት ቀናት ተጠርቼ በመጠየቄ ብቻ ጠቀም ያለ የሞራል ካሳ ክፍያ ሲከፈለኝ፣ በአገሬ ለረጅም ጊዜ ታስሬ ስፈታ፣ የሞራል ካሳ ሊከፈለኝ ቀርቶ የተወሰደብኝ ንብረት እንኳ በወጉ አልተመለሰልኝም። ልብ በሉ! ለአንድ ቀን ታስሬ ብፈታ ኖሮ የሚሰጠኝ የሞራል ካሳ በዚያው ልክ ይጨምር ነበር። እነርዕዮት፣ የሽዋስ፣ ሃብታሙና ሌሎችም በግፍ የታሰሩት ወገኖቻችን ሁሉ ፍትህ የሚያገኙበት ቀን እሩቅ ባለመሆኑ እንጽናናለን እንጅ፣ የደረሰው ጉዳትስ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም።

ወያኔ ያሰረው ህግን ነው! –ሳሙኤል አሊ

$
0
0

ሳሙኤል አሊ ከ- ኖርዌይ

habitamuህግ በታሰረበት አገር ሰለ ህግ ማውራት ቀልድ ሊሆን ይችላ ይሆናል። ነገር ግን  ትግልን የሚወልደው ወይም ታጋይን የሚያበዛው የህግ የበላይነት ሲጠፋ ነው። ህግ ባልተከበረባት አገር ዜጎች ሁል ግዜም ሰቆቃ ውስጥ እንደሆኑ ማሰብ አለብን። ህግ እራሱ ሰለታሰረ ፍርድ ቤቶች የቧልት ቤት ሆነዋል።

የፖለቲካ እስረኞች ጋዜጠኞች ጦማሪያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አሸባሪ በሚል ታርጋ ወደ እስር ቤት ተወርውረው የመከራና የሰቆቃ ግዜአቶችን ሲያሳልፉ ምን ባደረጉት ወንጀል ነው የሚል  በሁሉም ልብ ውስጥ ጥያቄ መጫሩ አይቀሬ ነው። ታዲያ የሚፈለገው እኮ እርሱ ነው  እነዚህ ሰወች እኮ  ለኛ ትልቅ የትምህርት ተቋም  መምህሮቻችን ናቸው። የወያኔን ስርአት ቁልጭ አድርገው ያሳዩን በነዚህ በእውነተኛ ብዕረኞችና ፖለቲከኞች ነውና ። ኢትዮጵያዊው ሁሉ ጎበዝ ተማሪ ሆኖ የታሰረውን ህግ ማስፈታት የሚችል እንደ መምህሮቻችን ቆራጥና  ጀግና  የሚሆን ትውልድ  እነደ ሰደድ እሳት ውስጥ ውስጡን ሊቀጣጠል ይገባል። ጊዜው በኢትዮጵያ የታሰረውን ህግ በማስፈታት ነጻና እውነተኛ ፍታዊ ስረአትን መዘርጋት  እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል እንጂ፡ ህግ አሳሪን አስወግደን በምትኩ ሌላ ህግ ጨፍላቂ ለመተካት አለመሆኑ ይታወቅ።

ምርጫ በቀረበ ቁጥር ጭንቅ ጥብብ የሚለው ወያኔ አሉ አሉ የተባሉትን ፖለቲከኞች እና ፀሐፍትን፤ ጋዜጠኞችን፤ ለቅሞ ማሰር የተለመደ ተግባሩ ነው። ምክንያቱም በክፍተኛ ሁኔታ ሕዝቡን ሊያነሳሱት ይችላሉ በማለት እና ሕዝቡንም መሪወቻቹህ እና ጋዜጠኞቻቹህ ታስረዋል እናተም አንዳች ነገር አደርጋለው ካልቹህ ካለችሁበት ተለቃቅማቹህ  እነሱ የገቡበት ትገባላቹህ የሚል መልእክት ማስተላለፊያ መንገድ ነው።  ሰለዚህ የኢትዮጵያ ህግ ቀድሞ ስለታሰረ የህግ ከለላ ማግኘት አይችሉም።

ታዲያ እኛ እንሱ ሲታሰሩ እሪ ብሎ ማልቀስና መጮህ ሲፈቱ ደግሞ እልል ብሎ መዘመር ነው እኔዴ ስራችን? ይሄ አይደለም የኛ ኢትዮጵያን ስራ ሊሆን የሚገባው ስታስሩ ለምን? ሲፈቱስ በምን የህግ አግባብ ተፈቱ? ብሎ የመጠየቅ ሃላፊነት አለብን። እዚህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባው አሳሪውም ማን ነው? ፈቺውስ ማን ነው? አሳሪውም ፈቺውም በህግ ሊጠየቁ ይገባል ለምንስ አሰርካቸው ለምንስ ፈታሃቸው?

ዛሬ የፈታቸውን ነገ አለማሰሩ ምን ዋስትና አለ? ዛሬ ነጻ ናቸው የተባሉት ነገ ወንጀለኛ ናቹሁ ተብለው አለመያዛቸው ምንስ ማረጋገጫ አለ? ወያኔ ሲጨንቀው ማሰር ሲጠበው ሊፈታ የሚችልበትን ህግ ማን ሰጠው ይህ ሁሉ ዘግናኝ ስህተቶች እየተፈጸሙ ያሉት እራሱ ህግ እሰር ላይ ስለሆነ ነው።

እንጠይቃለን፦

1 ህግ (ፍርድ ቤቱ) ይፈታልን ነጻ ይሁንልን።

2 ያለወንጀላቸው አሸባሪ ተብለው ንጹሃን የኢትዮጵያ ልጆች በእስር መማቀቃቸው ይታወቃል ስለዚህ እነዚህ ንጹሐን ወደ እስር ያስገባቸው አካል በአስቸካይ ለፍርድ ይቅረብልን።

3 ያለ በቂ ማስረጃ ታስረው ቆይተው አሁን ላይ ነጻ ናቹህ ብሎ የለቀቃቸው አካል የደረሰባቸውን የሞራል፤ የጊዜ ፤ የስነ ልቦና ጉዳት፤ ሳይመለከት ነጻ ናቹህ ብሎ አሳሪወችን  ለፍርድ ሳያቀርብ የፈታው አካል  ለፍርድ ይቅረብልን።

4 በነዚህ ንጹሃን ኢትዮጵያን ላይ የተሰራው ግፍ በነሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ እየተፈጸመ ያለ ጉዳይ ስለሆነ  ያለምክንያት ከተያዙበት ጊዜና ሰዓት ጀምሮ  ሰለደረሰባቸው የሞራልና እና እንዲሁም ያለአግባብ በእስር ስላባከኑት ጊዜ ተገቢውን ካሳ እንዲከፈላቸው እንጠይቃለን።

5 ሌሎች ንጹሃን ኢትዮጵያን በወያኔ ጉጅሌ  የፈጠራ አኬል ዳማ ድርሰት የታሰሩት በአፋጣኝ ተፈተው ተገቢውን ካሳ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን።

ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው። ወያኔ ከአሁን በሃላ በአንተ ስራ ማንም አይታለልም የካንጋሮ ፍርድ ቤትህንም ማንም ኢትዮጵያዊ አያምነውም የምንታገለው የታሰረው ህግ እስከሚፈታ ድረስ ነው እንጂ በፈጠራ ድርሰት ያሰርካቸው ብቻ  እስኪፈቱ አይደለም። የምንታገለው ህግን ያሰሩትን እና  ሕዝብን የሚያሰቃዩበትን ህግን አስፈትተን ህዝባችን ነጻ አደርገን ህግ አሳሪ እና ሕዝብ ጨቋኝ የነበሩትን ለፍርድ ለማቅረብ ነው። አገራችን ነጻ እስከምትሆን ድረስ ነጻ የሆነውን ህዝባችንን ልታሰቃዩ  ትችሉ ይሆናል፡ አሳሪ እና ገዳይ እንዲሁም አረመኔ የሆነው ወያኔን አስወግደን የሁላችን አገር እስከምናደርጋት ድረስ ልታስሩን ልትገድሉን ትችሉ ይሆናል፡ በደል ጭቆና እስራት እንግልት ግድያ የመብት ጥሰት  ሲበዛ  ሰው ፈሪ ይሆናል ብላቹሁ አስባቹ ከሆነ በወያኔ  አእምሮአችሁ ማለትም በጠባብ እና እውቀት በሌለው ማሰቢያቹህ የተጨቆነ ሕዝብ የሚባላ አብዮት እንደሆነ የምታዩበት ጊዜ  ቅርብ ነው። ህዝብ አብዮት ነው አብዮት የሚመጣው የተጨቆኑ ህብረተሰብ ለለውጥ የሚነሳበት አንባገነኖች የሚያለቅሱበት  የማይጠፋ እሳተ ገሞራ ነው ይሄም ሕዝባዊ አብዮት አንባገነኖችን የሚያጠፋ እሳት ነው።

ጋዜጠኞች እንዲሁም ፖለቲከኞች እንዲሁም ፀሃፊያኖች በመፈታታችሁ ደስተኛ ነኝ።  አሁን  ግን ትግሉ ኢትዮጵያን ለማስፈታት ነውና ትግሉን ሁሉም በአንድነት ተቀላቀሉ  ኢትዮጵያዊ ሁል ጊዜ አሸናፊ ነው።

 

ድል ለሰፊውየኢትዮጵያ ሕዝብ

ሞት ለዘረኛው ወያኔ ይሁን

 

ሳሙኤል አሊ ከ-ኖርዌይ

Email samilost89@yahoo.com

የአዲሱ ህውሀት መንግስት መጥፎ አጋጣሚ!! –ከኤርሚያስ ለገሠ

$
0
0

ከኤርሚያስ ለገሠ

1• ደስታ እና ሀዘን

ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ ሊያነሳት በመቻሉ ደስ ይለኛል። እንኳን ለዚህ አበቃህም ማለት እፈልጋለሁ።
ermias copy
በሌላ በኩል ገዥው ቡድን በምክንያት እያሰረ በምክንያት የሚፈታበት ሁኔታ ለራሱ ስልጣን መቆያ ትክክል ቢሆንም ለኢትዬጲያ የፍትህ ስርአት ምን ያህል ንቀት እንዳለው የሚያሳይ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው። ሰዎች በህውሀት ላይ አደጋ ሲጋርጡ በፓለቲካ ውሳኔ ይታሰራሉ…ህውሀታዊ ምክንያት !። ገዥው ቡድን ላይ የተጋረጠው አደጋ በሌላ ጐን ሲያጋድል ደግሞ በእጁ ይዞ የሚያሰቃያቸውን ይፈታል…ህውሀታዊ የመፍታት ምክንያት!!

ሀብታሙ አያሌውና ድርጅቱ ” አንድነት” ህውሀትን በሰላማዊ ትግል ፈተና ውስጥ ለመክተት ስትራቴጂ ነድፈው ሰፊ እንቅስቃሴ ጀመሩ። የለውጥ ንፋስም በስሱ መንፈስ ጀመረ። እነ ሀብታሙ በአደባባይ ” እመኑኝ ኢህአዴግም ይወድቃል! ኢትዬጲያም ነጳ ትወጣለች!” በሚል መሪ መፈክር ገዥዎችን አስጨነቁ። የስርአቱን ባህሪያት በቅርብ የምናውቅ ሰዎች የእነ ሀብታሙ እድሜ አጭር እንደሚሆን አሳወቅን። ርግጥም ” ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም!” በሚል መርህ የሚመራው ገዥ ቡድን እነ ሀብታሙን የውሸት ክስ በማዘጋጀት ወደ ማእከላዊ ወረወረ። ” አንድነት” ፓርቲንም አፈረሰ። ኩሸቱን በመደጋገም የራሱን እውነት ፈጠረ። እነ ሱዛን ራይዝን “በ100%” ጦሽ ብለው እንዲስቁ አደረገ።

በሌላ በኩል ለውጥ በሁሉን አቀፍ ትግል ብቻ መምጣት እንዳለበት የሚያምኑ ኢትዬጲያውያን የለውጥ እንቅስቃሴውን በግላጭ ማቀጣጠል ጀመሩ። ምሁራን ዱር ቤቴ በማለት ወደ በረሀ ተመሙ። አዲስ ህልምና አዲስ አቅጣጫ ይዘው የነጳነት ትግሉን ዙር አከረሩት። እናቶች ከጣታቸው ቀለበት፣ ከአንገታቸው ሀብላቸውን እያወለቁ ትግሉን ወደማገዝ ተሸጋገሩ። የመኪናቸውን ቁልፍ ለአርበኞች አስረከቡ። በየቦታው አዳራሽ ሞልቶ እስኪፈስ ድረስ ” እኔ አርበኞች ግንቦት ሰባት ነኝ!”፣… ” እኔ አንዳርጋቸው፣ ብርሀኑ፣ ኤፍሬም፣ ንአምን… ነኝ!” የሚል ቃልኪዳን ከመግባት ባሻገር እስከ መቶ ሺህ ዶላር መዋጣት ተጀመረ። ይህን የለውጥ ስሜት በስማ ስማ ሳይሆን በአይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ። ቆም ብዬም ለማሰላሰል ሞክሬያለሁ።

እንደ እውነቱ ከሆነ ህውሀት ቆም ብሎ ለትክክለኛው መፍትሔ የማሰቢያው ግዜ ነበር። ይሁን እንጂ አፈጣጠሩ፣ ባህሪውና የበታችነት ስሜቱ ይህን ስለማይፈቅድለት ሌላ መፍትሔ ማሰብ ነበረበት። ከእነዚህም ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባሉት አንዳርጋቸው ጵጌ ስም መጵሀፍ መጳፍና እንደ ሀብታሙ አያሌው ያሉትን የፓለቲካ እስረኞች መፍታት የሚጠቀሱ ናቸው። በበረከት ፀሀፊነት በአንዳርጋቸው ስም የሚወጣው መጵሀፍ ” የሶስት ምርጫዎች ወግ!” ( ስያሜው የእኔ ነው) ገና ባይወጣም በቅርብ ቀን እንደሚወጣ ይጠበቃል። ምርቃቱም ሸራተን አዲስ አንዳርጋቸው በሌለበት ይሆናል። …እነ ሀብታሙ አያሌውም ተፈተዋል።

( ” የሶስት ምርጫዎች ወግ” በተመለከተ ” የነጳነት ትግሉና ስድስት የህውሀት ማደናገሪያ ነጥቦች” በሚለው ሀሳብ ውስጥ አካትቼ በዳላስ ቴክሳስ በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ አቅርቤ ነበር። ብዙዎች እንዲለጠፍ ስለጠየቁኝ በሌላ ክፍል እንደምመለስበት ተስፋ አደርጋለሁ።)

2• ” መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል”

አዲሱ የህውሀት መንግስት ሁለተኛው መጥፎ አጋጣሚ በኢትዬጲያ ሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ነው። እነዚህ ለሀይማኖታቸው ነጳነት የሚታገሉ ታጋዬች የያዙት አቋም ገዥው ቡድንን ወደ ከፍተኛ ፈተና ጐትቶ ወስዶታል። ይህን ለማለት ያስደፈረኝ ያለምክንያት አይደለም። ከልምድ በመነሳት እንጂ!

የዛሬ ሰባት አመት በዚህ አካባቢ የአዲስ አመት መምጫ በድርቡም የኢትዬጲያ ሚሊኒየም መግቢያ ነበር። በመላው ኢትዬጲያ በተለይም በከተሞች የቅንጅት መሪዎች ካልተፈቱ ” በሚሊኒየም ምንም የለም!” የሚሉ መፈክሮች ተስተጋቡ። ሁኔታዎች አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር (” ታላቁ መሪ” ባለማለቴ እቴጌን ከወዲሁ ይቅርታ እየጠየኩ) መውጫ መንገድ ፈለገ። “የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መጠቀም” የሚል የውስጠ ድርጅት ሰነድ እንዲዘጋጅ አደረገ። ይህ ሰነድ የታሰሩ ተቃዋሚዎችን በይቅርታ የመፍታት ፋይዳውን የሚተነትን ነበር። በዚህ ጵሁፍ ህዝቡ የይቱልን ጥያቄ ያለማቋረጥ እያነሳ ያለው ከአርቆ አስተዋይነት የመነጨ እንደሆነ ዘረዘረ። ህዝቡ ይፈቱልን የሚል ጥያቄ እያነሳ ያለው ” እኔው መርጬ ለዚህ አደረስኳቸው” ከሚል የህሊና ፀፀት እንደሆነ ተገለፀ። በመሆኑም ታሳሪዎችን በይቅርታ መፍታት ህዝቡን ከፀፀት የማውጣት ሁኔታ ስለሚፈጥር መንግስት የሚፈታበት ሁኔታ ማማተር እንዳለበት በሰፊው ተነገረ።

ታሳሪዎች የይቅርታ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የፍርዱ ሂደት እንዲፋጠን ተደረገ። በአስቂኝና ባዶ ማስረጃ ታሳሪዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲወሰን አደረገ። ( በነገራችን ላይ በመስካሪነት የቀረቡት የቀበሌ ካድሬዎች የነበሩት እነ አበባ ሽመልስ ከማል ልምምድ የሚያደርግላቸው በኢህአዴግ ቢሮ ነበር) ። የፍርድ ውሳኔውን አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እስከ እድሜ ይፍታህ አምዘገዘገው። ይህ ውሳኔ ታሳሪዎችና ቤተሰባቸው ተደናግጠው ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት ይገባሉ የሚል ታሳቢን የወሰደ ነበር። በወቅቱ በታሳሪዎች መስመር ያለውን ተጵእኖ በቀጥታ ከራሳቸው መስማት የምችልበት እድል ባይኖርም በአንዳንድ የቅንጅት አመራሮች እና ቤተሰባቸው ዘንድ ተጵእኖ እንዳሳደረ ሰምቻለሁ። በሌላም በኩል እንደ አንዱአለም አራጌ ያሉ አመራሮች ውሳኔውን ከመቄብ ባለመቁጠር ይቅርታ ለመጠየቅ እንዳስቸገሩ በተባራሪ ሰምተናል።

ዞሮ ዞሮ ህውሀት የገባበት አጣብቂኝ የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መፍትሔ ሊያገኝ ቻለ። ይህን አስመልክቶ አቶ በረከት በጳፈውና የህውሀትን ገድል በሚያሳየው መጵሀፋ ገጵ 233 ላይ እንደሚከተለው አስፍሮ እንመለከታለን፣

” …የፍርድ ሂደቱ ነጳ መሆን በግልፅ መታየቱና መንግስት የቅንጅት መሪዎች የተከሰሱባቸውን ወንጀሎች ከበቂ በላይ በማስረጃ አቅርቦ በማረጋገጡ ህብረተሰቡ የሰዎቹን ጥፋተኝነት በጥያቄ ውስጥ የሚጥልበት አልነበረም። በመሆኑም መንግስት በህዝቡ የቀረበው የይፈቱ ጥያቄ ፣ ማንኛውም ህዝብ በአርቆ አስተዋይነቱ የሚያደርገው… እኔ መርጬ ለእስር አበቃኃቸው ከሚል የህሊና ፀፀት ነጳ ለመውጣት በመፈለግ ያቀረበው ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝቧል። ለዚህ አይነቱ የህዝብ ጥያቄ በጐ ምላሽ መስጠት ምንግዜም ቢሆን ግዴታው እንደሆነ የሚገነዘበው መንግስት፣ ጥያቄው የህግ የበላይነት ለድርድር ሳያቀርብ ሊመለስ እንደሚችል አምኗል። እናም በአንድ በኩል የህግ የበላይነትን እያስከበረ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝብን የይፈቱ ጥያቄ ለማስተናገድ የሚችልበትን ሁኔታ ማማተር ነበረበት። በዚህ አኳኃን ነው የኢትዬጲያ ሚሌኒየም ራሱን እንደ መልካም አጋጣሚ የከሰተው” ይለናል።

እንግዲህ ከዚህ ልምድ በመነሳት የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጣቸው። ውሳኔውን መሰረት በማድረግ እስከ ሀያ አመት የሚደርስ እስራት ተፈረደባቸው። ይህ ለመጥራት የሚዘገንን ቁጥር የተበየነበት ምክንያት ታሳሪዎችን ለማስደንገጥ እና ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት እንዲገቡ ታስቦ እንደሆነ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። አንድ ግጥም አቅርበሀል የተባለ ወጣት የተፈረደበትን አመት ለተመለከተ ደግሞ በህውሀት የተጠነሰሰውን ሴራ ለመገንዘብ የእነሱን ያክል ማሰብ ከቻለ በቂው ይሆናል።

ይሁን እንጂ ይህ “የይቅርታ ይደረግልን” ሴራ ቅንጅት ላይ እንደሰራው በሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎቹ ላይ የሚሰራ አይደለም። ሲጀመር የመጀመሪያዉ ፓለቲካዊ፣ የአሁኑ ደግሞ ሀይማኖታዊ ነጳነትን በግንባር ቀደምትነት ያስቀመጠ በመሆኑ በባህሪ የተለያዩ ናቸው። ርግጥ ፓለቲካዊ መብቶች ባልተከበረበት ሀይማኖታዊ መብቶች ይከበራሉ ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ቢሆንም። ከዚህም በተጨማሪ የሀይማኖታዊ ነጳነታዊ ጥያቄዎች ለድርድር የመቅረብ እድላቸው እጅግ ጠባብ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው።

ከላይ የተቀመጠውን ከግምት በመውሰድ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴው አባላት አጥፍተናል እና ይቅርታ ይደረግልን የሚሉ ከሆነ እስከዛሬ ያነሷቸው ሶስት ጥያቄዎች ( ለጊዜው የማውቃቸው) ትክክል አልነበሩም፣ አሊያም ምላሽ አግኝተዋል የሚል እንድምታ ይኖረዋል። ይህም የህውሀትን ድል አድራጊነት ከማረጋገጥ ባሻገር የኢትዬጲያ ሙስሊሞችን የሶስት አመት ትግል ውሀ ይቸልስበታል። ወደ ኃላ የመመለስና በቀላሉ የመክሰም እድል ያጋጥመዋል። የኮሚቴዎቹ አባላት ይህን በመገንዘብ ይመስላል አስደንጋጩ ብይን ሲሠጣቸው ያለምንም መደናገጥ የትግል ጵናታቸውን ለማሳየት የቻሉት። ቤተሰቦቻቸውም ቢሆን የኮሚቴው አባላት እየከፈሉ ያሉት መስዋእትነት ለሀይማኖታቸው ነጳነት መሆኑን በመገንዘብ ከጐናቸው የቆሙት።

ስለዚህ እነዚህ የኮሚቴ አባላት እንደ ቡድን የይቅርታ ጥያቄ ያቀርባሉ ብሎ ማሰብ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደመውጣት ይሆናል። በግለሰብ ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች የይቅርታ ሂደት ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም። ይህ አማራጭ ዝግ ሆነ ማለት ህውሀት መራሹ አዲሱ መንግስት ዝም ብሎ ይቀመጣል ማለት አይደለም። በሁኔታዎች አስገዳጅነት ያለ ይቅርታ ጥያቄ ምህረት የማድረግ ግን ደግሞ በፍርድ ቤት እንዲወሰን ያደረገውን የህዝብ እንቅስቃሴ ገደብ ያለማንሳት ሊኖር ይችላል። ይህም ኮሚቴዎቹን በአይነ ቁራኛ በመከታተል የቁም እስረኛ ወደ ማድረግ መሸጋገር ይሆናል። ይህም ቢሆን ለገዥው ቡድን የሚያመጣለት አንዳችም ፓለቲካዊ ትርፍ አይኖረውም።

ግራም ነፈሰ ቀኝ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የአላማ ጵናት ለአዲሱ የህውሀት መራሹ መንግስት የእግር እሳት እንደሆነ ይቀጥላል። የኢትዬጲያ ሙስሊሞች የነጳነት ትግልም በኢትዬጲያ ታሪክ ውስጥ የሚኖረውን የላቀ ደረጃ እንደጠበቀ ይኖራል!…”መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል” ይሉሀል ይህ ነው!!

የሰላም ትግሉ በኢትዮጵያ (መዝጊያ) –አንዱዓለም ተፈራ –የእስከመቼ አዘጋጅ

$
0
0

ረቡዕ፤ ሰኔ ፲ ቀን፤ ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህቱረት ( 6/17/2015 )

እንዴት ትግሉን በትክክል ወደ ፊት ማስኬድ ይቻላል?
eskemecheበመጀመሪያ ደረጃ ሁላችን መረዳት ያለብን፤ ይህ ትግል በአምባገነኑ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ብቻ ነው። ይህ መነሻና መድረሻ ተደርጎ መወሰድ አለበት። አሁን ሁላችንንም ወጥሮ የያዘን፤ ትግሉን ለምን በአንድነት፤ የሀገራችን የነፃነት ትግል አናደርገውም? የሚለው ጥያቄ ነው። አንዳችን ከሌላችን የተለየ አመለካከት ስለያዝን ብቻ፤ በመካከላችን ጠላትነት ነግሦ፤ “አንተ ወያኔ ነህ!” የሚል ወፍ ዘራሽ ውንጀላ አስቀድሞ መወርወር ትክክል አይደለም። በመደማመጥ በውይይት ሊፈታ የሚችለውን የሃሳብ ልዩነት፤ እንደ የፖለቲካ ውጊያ አድርጎ መበጣጠሱ ጎድቶናል። የተለያየ ሃሳብ ይዞ፤ በሚስማሙበት አብሮ መስራት ይቻላል። የግድ በሁሉም ነገር ሁላችን መስማማት የለብንም። ይህ መሠረታዊ የዴሞክራሲን ሀ ሁ የተቀበሉ ሁሉ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ታዲያ ለምንድን ነው በመካከላችን መግባባት ያልቻልነው? የዛሬው የማጠቃለያ ጽሑፍ የሚያተኩረው፤ በመካከላችን መግባባትን እንዴት መፍጠር እንችላለን? ምንስ ብናደርግ ትግሉን ወደፊት ማስኬድ እንችላለን? ካለንበት የምስቅልቅል ሀቅ ወጥተን ወደፊት ለመሄድ ከየት እንጀምር? ለሚሉት መልስ በመሥጠት፤ ትክክለኛ አስተባባሪና አስተማማኝ መፍትሔ አቅርቦ፤ ትግሉ በትክክል እንዲመራና ወደ ሕዝባዊ ድሉ ጉዟችን እንዲያቀና መጋበዝ ላይ ነው።

ትግል ወደው የሚገቡበት ክስተት አይደለም። ትግል የሙያ መስክ አይደለም። ትግል ግድ ብሎ የሚመጣ የኅብረተሰብ ክንውን ነው። የአንድ ሀገር ነዋሪዎች፤ በሀገራቸው ያለው ሥርዓት “ትክክለኛ አይደለም!” “ከመስመር ወጥቷል!” ብለው ሲነሱና የሥርዓቱ አራማጅ እንጃላችሁ ሲል፤ ሕዝቡ በእምቢታ ሲነሳ፤ ሕዝባዊ ትግል ነው። ይህ ደግሞ ሁሌ የሚደረግና ለአንዳንዶቹ የሙያ ዘርፍ ሆኖላቸው የሚከርሙበት መኖሪያ አይደለም። በአንድ የታሪክ አጋጣሚ የሚከሰት ነው። አሁን ሀገራችን ላለችበት ሁኔታና ታጋዮች ላለንበት ሀቅ፤ በቂ ምክንያት አለ። ምክንያቱን መርምረን ማግኘት አለብን። ሌሎችን ለዚህ ምክንያት ተጠያቂ ማድረጉ አግባብነት የለውም። ያንን ምክንያት የፈጠርነውና አስተካክለንም ወደፊት መሄድ የምንችለው፤ እኛው ነን። ለየብቻችን መፍትሔ ፈላጊዎች ብቻ ሳንሆን፤ ለየብቻችን ተግባሪዎቹም በመሆን በየበኩላችን ሩጫ ይዘናል። ለምን? ይህ የሀገራችን የሁላችን ጉዳይ አይደለም! ታዲያ ለምን በአንድነት የምንዘምትበትን መንገድ አንፈልግም። በመካከላችን ያለው፤ የትግሉን መንገድ በሚመለከት ያለ ልዩነት አይደለም። በኔ አመለካከት፤ ያሉትን ልዩነቶች በሶስት ከፍዬ አስቀምጭቸዋለሁ።

የመጀመሪያውና ዋናው ማጠንጠኛ፤ የትግሉን መሠረታዊ ምንነት በሚመለከት ያለው ልዩነት ነው። ይህ የትግሉን ሂደት ቅደም ተከተል በሚመለከት የተወሰነ አይደለም። ይህ መሠረታዊ የሆነውን ለምን እንደምንታገል የሚደነግገውን ጉዳይ የሚመለከት ነው። “በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሀቅ ምንድን ነው?” የሚለውን መመለሱ ላይ ነው። ለዚህ የሚሠጠው መልስ ወሳኝ ነው። ከዚህ ተነስቶ ነው የትግሉ እጅና እግር የሚታወቀው። በሀገራችን ምን ዓይነት ሥርዓት አለ? ምን ዓይነት የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ ያቀነቅናል። የዚህ ሥርዓት ጉዳቱ ምንድን ነው? የሥርዓቱስ ባለቤት ማነው? በዚህ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ይላል? የት ነው የምንቆመው? ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ወይንስ ከአምባገነኑ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ጋር? እዚህ ላይ፤ ትግሉ የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚደረግ ሩጫ አይደለም። ትግሉ የነፃነት ጥያቄ ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎችን ምርጫ አይደለም የያዝነው። ሁለት ሰፈሮች ብቻ ነው ያሉት። አንደኛው የአምባገነኑ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሲሆን ሌላው የሕዝቡ ሰፈር ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ሆኖ ነው፤ አምባገነኑን ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር እምቢ ያለው። ስለዚህ አንድ ኢትዮጵያዊነት ብለን፣ አንድ ወገናችን ብለን፣ አንድ ሀገራችን ብለን፣ አንድ ትግል ብለን መነሳት አለብን።

ሁለተኛው ደግሞ፤ የሀገርን ጉዳይ ለድርጅቶች ኃላፊነቱን መሥጠቱ ላይ ነው። ትግሉን አሽከርካሪዎች ድርጅቶች ናቸው ብለን፤ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ኃላፊነቱን በነሱ ላይ ጥለናል። ሀገሪቱ እኮ ለተደራጁት ብቻ አይደለችም። ለሁላችንም እኩል ነች። ታዲያ ኃላፊነቱን ሁላችን እኩል መካፈል የለብንም? በርግጥ በድርጅት የተሰባሰቡ ሰዎች ጠርቀም ያለ ጉልበት አላቸው። እናም ቅድሚያ ይሰለፋሉ። ይህ ማለት ግን፤ ኃላፊነቱ የነሱና የነሱ ብቻ ነው ማለት አይደለም። ይልቁንም በሀገራችን ላይ ባለው ሀቅ፤ ቅድሚያ መስለፉን ዘንግተውታል። እናም በየድርጅቶቻቸው መርኀ-ግብር ተቆልፈው፤ ከመጠጋጋት ይልቅ መራራቁን መርጠው፤ ከመፍትሔ ይልቅ የችግሩ አካል ሆነዋል። ስለዚህ፤ ኃላፊነቱ በሌሎች፤ ማለትም በግለሰብ ባለነው ሀገር ወዳዶች ላይ ተጥሏል። ለሀገር መታገልና ለድርጅት መታገል አንድ አይደለም። በርግጥ ትግል ሳይደራጁ አይካሄድም። ያ ድርጅት ደግሞ ትግሉ ምን ዓይነት መስመር እየተከተልን መሆናችንን ይናገራል። ለድርጅት መታገል ማለት፤ ድርጅትን መነሻና መድረሻ አድርጎ፣ የኔ ድርጅት ትክክለኛ ስለሆነ፤ በኔ ድርጅት ብቻ ተመርታችሁ ትግሉን ቀጥሉ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ማስተላለፍ ነው። በርግጥ ይሄ በብዙ የተለያየ የሚመስል ነገር፤ ነገር ግን መሠረቱ አንድ በሆነ መልክ ይከሰታል። መሠረቱ ደግሞ፤ ለግል ማስብና ለሀገር ማሰብ በሚለው መካከል ያለው ልዩነት ነው። የያዝነው ትግል የግል ትግል አይደለም። የሀገር፣ የነፃነት ትግል ነው።

ሶስተኛውና ማጠቃለያው፤ መፍትሔውን በሚመለከት ያለው ልዩነት ነው። አንድ ሀገር፣ አንድ ኢትዮጵያዊነት፣ አንድ ትግል ብለን ከተነሳን፤ የአንድነቱ ትግል ዋናና አማራጭ የሌለው ነው። አንድነትን ከግል የተግባር እርምጃ ማስቀደም አለብን። አዎ! ትግሉ ተጀምሯል። ሰዎች በተለያየ የትግል መስክና ሁኔታ ከገዥው ቡድን ጋር እየተፋለሙ ናቸው። ነገር ግን ትግሉ ትክክለኛ ስኬት እንዲኖረው መቀጠል ያለበት፤ ከዓላማ ጋር ተቆራኝቶ እንዲቀርብ ሲደረግ ነው። ግቡ አንድነትን የሚመሠርት፣ አስተማማኝ የሆነና፤ ሁሉን ለአንድ ዓላማ አሰባስቦ የሚያታግል እንዲሆን፤ አንድነቱ አሁኑኑ፤ ባለንበት ደረጃ ቅድሚያ ሊሠጠው ይገባል። ይህ ማለት፤ አንድ ሳንሆን የተያዘው ትግል አደጋው ከፍተኛ ስለሆነ፤ ታጋዮች በየደረሱበት የትግላቸው ሂደት፤ ከሌሎች ጋር እንዲሆን ማድረግ ነው። ይህ ግድ የሚለው፤ የሚከተለውን አደጋ ተረድተው፤ የያዙትን ትግል ለአንድነቱ እንዲገዛ አድርው፤ ድሉንም ሆነ ጉዳቱን ለአንድነቱ እንዲያስረክቡ ነው። ይህ ማለት፤ በመሰባሰብ ለሚመሠረተው የአንድነት ድርጅት፤ ሙሉ ተገዥ ሆኖ፤ በሙሉ ልብ በኢትዮጵያዊነት መምጣት ነው። በተደጋጋሚ የተገለጹትን የትግሉ ራዕይና መታገያ ዕሴቶች በመቀበል ወይንም አስፈላጊ የሆኑ ማሻሻያዎችን በማድረግ፤ አንድ ድርጅት፣ አንድ ትግል፣ አንዲት ኢትዮጵያ፣ አንድ ኢትዮጵያዊነት ብሎ መነሳት ነው። መታገያ ዕሴቶቻችን የሚከተሉት ናቸው፤

፩ኛ.   በኢትዮጵያዊነታችን አንድ ነን። በሀገራችን፤ በኢትዮጵያዊነታችን  የፖለቲካ ተሳትፏችን እናደርጋለን።

፪ኛ.   ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ ዳር ድንበሯን አስጠብቀን ለኛው ለኢትዮጵያዊያን እናደርጋታለን።

፫ኛ.   በሀገራችን በኢትዮጵያ፤ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን እናደርጋለን።

፬ኛ.   በኢትዮጵያዊነታችን የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችንን እናስከብራለን።

እንግዲህ ከላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ትኩረት ሠጥተናቸው፤ በቁጥር ፩, ፪, ፫ ትና ፬ የሰፈሩትን መታገያ ዕሴቶች አንግበን፤እና አሁን ያለንበትን የያንዳንዳችንን ሁኔታ ራሳችን መርምረን፤ በግለ ሰብ ደረጃ፤ እኔ በኢትዮጵያዊነቴ ምን ማድረግ እችላለሁ? የሚለውን እኔ በኢትዮጵያዊነቴ ምን ማድረግ አለብኝ? ከሚለው ጋር አቆራኝተን፤ መሰባሰብ አለብን። በድጋሜ፤ እያንዳንዱ ድርጅት የያዘው የራሱን ድርጅት ትግል አንጂ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግል አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነት ትግል የሚካሄደው በኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ነው። እናም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነት የነፃነት ትግል ጥረት እናድርግ። የዚያ አካል እንሁን። ይሄን በሚመለከት ለመተባበር ዝግጁ የሆናችሁ ጥሩኝ፤ ወይንም ወደኔ መልዕከት በመላክ ቅረቡ። የዚህ ትግል ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ፤ አንድ ግለሰብ ወይንም አንድ ድርጅት አይደለም።

eske.meche@yahoo.com   http://nigatu.wordpress.com

ነጻነታችን በእጃችን፣ ህወሃትን ካልተገረሰሰ እስሩም ግድያውም ይቀጥላል!

$
0
0

ተስፋዬ ነጋ (ዋሽንግተን፣ ዲሲ)

habitamuዛሬ እነሆ እነ ሀምታሙ አያሌው፣ ዳኤል ሽበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና፣ አብርሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ የወያኔ ፍርድ ቤት ወስኗል የሚል ዜና ሰማሁ። እንኳንም በውሸት ክስ የታሰሩት ወደየቤተሰቦቻቸው በሰላም ተቀላቀሉ። ከሚወዱት ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ እጅግ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥራል። የቤተሰቦቻቸውን ናፍቆታቸውን በአግባቡ እንዲያጣጥሙ ምኞቴ ነው። እውነት መጨረሻ ላይ እውነት ሆና መውጣቷ አይቀርም፣ ይኸው እውነት ነጻ አወጣቻቸው።

የሆኖው ሆኖ እነዚህ ወጣቶች ከመጀመሪያውም መታሰር አልነበረባቸውም። በወንጀል ደም ተጨማልቀው የሚዋዥቁ አረመኔዎች አልነበሩም። ለአገራቸውና ለህዝባቸው ከፍተኛ ራዕይ የሰነቁ ንጹህ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፣ አሁንም ንጹሃን ናቸው። ወያኔዎች ሰላማዊ ዜጎችን በማሰር የፖለቲካ ትርፍ እናገኛለን ብለው ቢያስቡም፣ የእነአብርሃ ደስታ መታሰር የህወሃትን ድንቁርና ከማጋለጥ ውጭ በተቃዋሚው ወገን ላይ ያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ የለም። እንዲያውም ተቃዋሚዎች የትግሉን ዳራ በጥልቅ እንዲመረምሩና የወደፊቱን የትግል አቅጣጫ በጥንቃቄ እንዲቀይሱ አደረጋቸው እንጂ! የታሳሪዎችን ንጹህነት ደግሞ ህወሃቶችም (እዉነትና ውሸት የማያገናዝቡ ሆዳም ካድሬዎችም ጭምር) በሚገባ የሚመሰክሩ ይመስለኛል፣ ያው የሞት ሽረት ነገር ሆኖባቸው  ቢያስሯቸውም! የህወሃት ሰዎች ለስልጣናቸው የሚያሰጋቸውን ሁሉ በሃሰት ክስ ከመወንጀል ተቆጥበው አያውቁም፣ እነዚሁ ፖለቲከኛ ወጣቶች በምሳሌነት ሊቀርቡ ይችላሉ፣ የእስሩ ገፈት ቀማሾች ዞን 9ኞችም ሌሎች ሰለባዎች ናቸው። ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙ፣ ውብሸት ታዬ የፈሪው ህወሃት የሃሰት ፍርድ በትር ተጎጂዎች ናቸው። የህወሃት መንግስት በውሸት የተካነ፣ የፈጠራ ክስ ጸሃፈ-ተውኔት እንደሆነ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ህወሃቶች ተቃዋሚ የመሰላቸውን ሁሉ በፈለጉ ጊዜ ሲያስሩ፣ በፈለጉ ጊዜ ሲፈቱ ኖረዋል፣ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ሲመጣ ከመግደል ወደኋላ አይመለሱም። ህወሃት በ1996 ዓም ሰላማዊ ሰልፈኞችንና ህጻናትን ሳይቀር በጠራራ ጸሃይ በካሊበር ጥይት በሳስቶ ገሏቸዋል። ወደፊትም የፈጠራ ክስ ማቀናበር፣ ማሰር፣ መፍታት፣ መግደል፣ ስራቸው ሆኖ ይቀጥላል።

ሕወሃት ሁለት መገለጫዎች አሉት። የመጀመሪያው የጦር ሃይሉን በመተማመን፣ በጉልበት ስልጣን ላይ እንደተቆናጠጠ ዘላለም እገዛለሁ ብሎ ማሰቡ ነው። የመሳሪያ ባለቤት በመሆኑ፣ የተቃወመኝን እያሰርኩ፣ ጠላቴን እየገደልኩ፣ እንዲሁም ከተቃውሞ የማይታቀበውን እያስፈራራሁ ለረጅም ጊዜ እኖራለሁ ብሎ ያምናል። እዉነትም ህወሃት በከፊል ትክክል ነበር፣ በጉልበት እያስፈራራ፣ እያሰረ፣ እየገደለ ለ25 አመታት ያለምንም ችግር ዘልቋል። ከራሱ ከህወሃት የተፈጠሩ የጦር መኮንኖችን ብቻ ስልጣን ላይ አስቀምጦ፣ በሙስና እንዲዘፈቁ በማበረታታትና፣ የሚያማልል ስጦታ በመስጠት፣ እንዲሁም እነዚሁን የጦር መኮንኖች የወንጀል ተባባሪና መሪ በማድረግ የ”አብረን እንዝለቅ” ጨዋታ ተክኖበታል። ሁሉንም የጦር መኮንኖች ከአንድ ብሄር ብቻ በመሾም፣ ለተቃዋሚ እንዳያደሉ “ከካዳችሁን በጦር ወንጀለኝነት ትፈለጋላችሁ፣ የትግራይን ህዝብ ታስጨርሳላችሁ” በሚል ሰንካላ ማስፈራሪያ ከሌላው የኢትዮጵያዊ ጋር እንዳይነናኙና እንዳይተባበሩ አድርገዋቸዋል።

ሁለተኛው የህወሃት መገለጫ ደግሞ ከመንግስት ባለስልጣናት ያውም ከሚኒስትሮች የማይጠበቁ ዘረኝነት፣ ስግብግብነት፣ ውሸትና፣ የሞራል ዝቅጠት ነው። አብዛኞቹ ባለስልጣናት በዘረኝነት ዛር የሰከሩ ወፈፌዎች ናቸው። የራሳቸውን ብሄር “ወርቅ” በማለት የሚያሞካሹ፣ ሌላውን ብሄረሰብ ግን “ትምክህተኛ፣ አክራሪ፣ ብሄርተኛ” የሚል ታፔላ በመለጠፍ በጅምላ የሚሳደቡ [የራሳቸውን ቃል ልጠቀምና] “ወራዳ” ናቸው። በተለይም ለአማራና ለኦሮሞ ብሄረሰቦች ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸውና በካድሬዎቻቸው አማካኝነት እስከዛሬ ድረስ አርሶ አደር ገበሬዎችን በማፈናቀል የተካኑ በክፋት ሃሴት የሚዝናኑ ናቸው።።

አቶ መለስና የህወሃት ባለስልጣናት ዋና ዋና መስሪያ ቤቶችን፣ ወታደራዊ ተቋማትን፣ የገንዘብ ተቋማትን፣ የፖለቲካ ተቋማትን፣ የማህበራዊ አገልግሎት ድርጅቶችን በብቸኝነት በመቆጣጠር ለግላቸው ስልጣን ማስረዘሚያና ኪስ ማድለቢያ ማድረጋቸው አሌ የማይባል ሃቅ ነው። ዛሬም የአየር መንገድን፣ የኮንስትራክሽንና የንግድ ድርጅቶችን፣ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን፣ የውጭ ንግድንና የአገር ውስጥ ገቢን፣ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን፣ ብሄራዊ ባንክን መብራት ሃይልንና ቴሌኮም የመሳሰሉትን ዋና ዋና ተቋማትን ምንም ሃፍረት ሳይሰማቸው ከአንድ ብሄር በተውጣጡ ቡድኖች ቁጥጥር ስር በማድረግ፣ ወይም ደግሞ “ታኮ” ከመጋረጃ ጀርባ በማስቀመጥ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል። ከላይ እንደተገለጸው የትግራይ ተወላጅ ሃላፊዎችን በሙስና እንዲዘፈቁ በማድረግ፣ ወይም ሙስና ውስጥ ሲዘፈቁ አይቶ እንዳላዩ ሆኖ በማለፍ፣ በመፍቀድና፣  በማበረታታት የመንግስት ለውጥ ቢታሰብ እንኳን ከተቃዋሚው ጋር ተባባሪ እንዳይሆኑ የማስፈራሪያ ሪሞት ኮንትሮል ገጥመውላቸዋል።  ይህ ስግብግብ ባህርያቸው እንቆረቆርለታለን ለሚሉት ለትግራይ ህዝብም እንቆቅልሽ እንደሆነ ነው የሚሰማው። በጦርነቱ ወቅት የትግራይ ህዝብ እነዚህን ግፈኞችን የደገፋቸው ታጋዮቹ እንዲህ አይነት የግለኝነት እና የአምባገነንነት ባህርይ ይኖራቸዋል ብሎ ሳይገነዘብ ነበር። የትግራይ ህዝብ የህወሃት ባለስልጣናት በጊዜው የደገፋቸው ዛሬ ለራሳቸው እልል ያለ ቪላ ቤት እንዲሰሩ፣ ለራሳቸው እጅግ ውብና ውድ መኪና እንዲገዙ፣ ከድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ በመንጠቅና በውጭ አገር በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለግላቸው እንዲያስቀምጡ አልነበረም። ለስልጣናቸው ሲሉ የሃውዜንን ምስኪን ህዝብ በአውሮፕላን ያስጨፈጨፉ እጅግ እኩይ ሰዎች ናቸው። አቶ መለስ ሞት ባይገላግላቸው ኖሮ ከ22 አመት በኋላም ቢሆን ስልጣናቸውን ለመልቀቅ፣ ተተኪም ለማዘጋጀት ፈቃደኛ አልነበሩም።

የህወሃት ባለስልጣናት የራሳቸው ኪስ ስለደለበ ብቻ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የደላው ስለሚመስላቸው የውሸት የእድገት ቁጥር ጨዋታ ያቀርባሉ። እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ከ22 አመታት በኋላም ቢሆን ከችግር፣ ረሃብና፣ እርዛት ኣልተላቀቀም። የህወሃት ባለስልጣናት ግን ገንዘብ ተርፏቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወደ ውጭ አገር እያሸሹ እንደሆነ አለም የሚያውቀው ሃቅ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይኸው ከ 24 አመት የስልጣን ጊዜ በኋላም ከ24 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን እርዳታ ይፈልጋሉ። የህወሃት ሰዎች ግን ሌላ መልስ አላቸው። ኢትዮጵያ፣ ከካሊፎርኒያ፣ ወይም ከአውስትራሊያ በተለየ መልኩ ድርቅ አልጎዳትም። እኔ ግን ለእነዚህ ሰዎች ጥያቄ አለኝ። በየትኛው ስሌት ነው የካሊፎርኒያና የአውስትራልያ ድርቅ ከኢትዮጵያ ድርቅ ጋር የሚወዳደረው? በካሊፎርኒያ በድርቅ ሳቢያ የተራበ ሰው የለም። አውስትራሊያም ቢሆን በድርቅ የተነሳ እርዳታ የሚቀበል ሰው የለም። እኛም ጋ በድርቅ ሳቢያ የተራበ ሰው የለም ሊሉን ይሆን? ካሊፎርኒያም ይሁን አውስትራሊያ በድርቅ ምክንያት የቤት እንስሳት አልሞቱም፥ አዝርዕት አልተበላሸም። ቢሆንም በቂ ክምችት አላቸው። የእኛስ?  በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ አርብቶ አደር ወይም ገበሬ ነው፥ ያውም ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ምርት የሚያመርት ወይም ከእንስሳት ተዋጽኦ ተጠቃሚ። አዝርዕቱ ከደረቀ፣ ከብቶቹ ከሞቱበት ምን ይሆናል? አቶ ሃይለማሪያም የህወሃት የትሮይ ፈረስ ሆነው እንጂ ይህንን ከመናገራቸው በፊት ሊያስቡበት ይገባ ነበር። ውድድሩን ከማድረጋቸው በፊት የካሊፎርኒያስ ድርቅ ምን ይመስላል? የአውስትራሊያስ? የውሃ አጠቃቀማችንስ እንዴት ነው? የቁም እንስሳት አያያዛችንስ ምን ይመስላል? የሚለውን ሃሳብ እንኳን የማያገናዝቡ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በጭብጨባ በታጀበ መግለጫ አፋቸውን ሞልተው ሶስቱን አገሮች (?) በአንድ ሚዛን ሲለኩ ሰማሁ።  የህወሃት የትሮይ ፈረስ ማለት እኚህ ናቸው። ህወሃቶች የሚፈልጉትን ሁሉ በእሳቸው ተመስለው የሚፈልጉትን መልዕክት ያስተላልፋሉ፣ እውነታው ግን ሌላ ነው። አቶ ሬድዋንም ቢሆኑ ያው “አርብቶአደሮቹ በጊዜው ውሃ ስላላጠጧቸው ነው ከብቶቹ ያለቁት” አሉ። አጃኢብ ነው! ከባለቤቱ በላይ ያወቀ ቡዳ ነው ይባል የለ! ጋዜጣዊ መግለጫውን የባዮሎጂ ክፍለጊዜ አስመሰሉት እኮ!

የህወሃት አሽከሮችና ጭፍሮቻቸው በምግብ ራሳችንን ችለናል የሚል ልፈፋ ሲያሰሙ ከርመው ነበር። የታል ታዲያ? እርግጥ ነው የህወሃት ባለስልጣናት ኪስ በ11 ሚሊዮን % አድጓል። የህዝቡ ኑሮ ግን 1% እንኳን ከፍ አላላም። እርግጥ ነው በህወሃት መንደር እና ሎሌዎቻቸው ቤት ምግብ ተትረፍርፏል፣ በሱማሌ፣ በአፋርና፣ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች፣ የገበሬዎች የቤት እንስሳትና የቀንድ ከብቶች ተረፍርፈዋል።

በጣም የሚገርመው የህወሃት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አይነት የፖለቲካ ግንዛቤ የለውም ብለው ማሰባቸው ነው። ያኔ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኋላ አቶ ስዩም መስፍን ባድመ ለኢትዮጵያ ተሰጠች ብለው አስጨፈሩን፣ በኋላ ስንሰማ ግን የጨፈርነው በሞት ለገበርናቸው ወንድሞቻችን ደም ላይ ነበር!

ሌላው ህወሃት ኢትዮጵያ ውስጥ በማህበረሰባችን በነውርነት የሚታወቀው የውሸት ልማድ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው። ትውልድ ከእነዚህ መሃይማን ምን ይማራል? የህወሃት ቁልፍ የበላይ ሃላፊዎች ድርጀቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀመሮ በሸፍጥ፣ በመግደል፣ በማሳደድ፣ በማሰር፣ በማሸማቀቅ እዚህ ለመድረስ በቅተዋል። በህልማቸው እንኳን አስበውት የማያውቁትን ሃብት አካብተዋል፣ አቅማቸው የማይፈቅድላቸውን ስራ ሰርተዋል፣ በማይመጥናቸው ወንበር ተቀምጠዋል፣ ታዛዥ መሆን ሲኖርባቸው በተገላቢጦሽ አዛዥ ሆነዋል። ከሁሉም በላይ ይቅርታ የማያስደርግ ወንጀል ውስጥ ተዘፍቀዋል። 100% የፓርላማና የአካባቢ ምርጫ አሸነፍን ብለዋል። ከህወሃት በላይ ጀግና የለም፣ አገሪቷን ከፈለግን እንደዶሮ ብልት ገነጣጥለን እንሄዳለን ብለዋል፥ አፍርሰን እንሰራለንም ብለዋል… ሌላም ሌላም።

የህወሃት ሰዎች የተከበሩ ተቋማትን አዋርደዋል። በአገራችን ውስጥ ለረጅም ጊዜ የተከበረው ሽምግልና በነፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ አማካኝነት   ፈሩን ስቶ ገደል ገብቷል። ፍርድ ቤቶች የህወሃት የፖለቲካ መሳሪያ በመሆን በንጽሃን ላይ የውሸት ክስ በመመስረት ታሪክ ይቅር የማይለውን ፍርድ አስተላልፈዋል። በተለይም ወጣቶቹ የሚሰሩበትን የወጣትነት ጊዜያቸውን በግፍ በወህኒ ቤትና እንዲያሳልፉ በውሸት ክስ ከአሸባሪዎች ጋር በማያያዝ አስረዋቸው፣ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፈተዋቸዋል። ለምሳሌ የዞን 9 ጦማሪያን በአሸባሪነት ክስ ተከሰው በወህኒ ቤት ከአንድ አመት በላይ ሲማቅቁ ቆይተው ፕሬዚደንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ያለምንም የፍርድ ቤት ሂደት ፈተዋቸዋል። እንግዲህ ህወሃቶች ለስልጣናቸው ሊያሰጋቸው የሚችል ሰው ባይሆንም እንኳን ለሆድ የማይደለል ተቃዋሚ ወይም ጋዜጠኛ ባጋጠማቸው ቁጥር በመጀመሪያ ማስፈራራትና ማሰር፣ ካልሆነም መግደል ለአስርተ-አመታት የተካኑበት አሳዛኝ ድራማ ነው። እናም በኢትዮጵያ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በውሸት ፖለቲካዊ ክስ ተፈርዶባቸው የሚማቅቁ ኢትዮጵያውያንን ማዕካላዊ፣ ቂሊንጦ፣ ዝዋይ፣ ሸዋሮቢት፣ እና ስማቸው የማይታወቁት የጨለማ እስርቤቶች ይቁጠሯቸው!

እንግዲህ ምርጫ በመጣ ቁጥር ተቃዋሚዎችን እያደኑ ማሰር ምርጫው ካለፈ በኋላ እንደገና መልሶ መፍታት የተነቃበት የህወሃት ታክቲክ ከሆነ ሰነባብቷል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ጋዜጠኞችን ሰሞኑን የተፈቱበት ሁኔታም ይኸው ነው። ወቅቱ ስለተቀየረ፣ ተፈተዋል። በሌላ ወቅት ደግሞ እነሱን ብቻም ሳይሆኑ ሌሎች ወጣቶች እንዲሁ ዘብጥያ መውረዳቸው አይቀርም። ሀብታሙ አያሌው፣ ዳኤል ሽበሽ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሸዋስ አሰፋ፣ አብሃም ሰለሞን ሲፈቱ ሌሎች ባለሳምንት ደግሞ በቅርቡ ይገባሉ። እነዚህ ፖለቲከኞች አሁን የተፈቱበት ምክንያት የጦዘውን ፖለቲካዊ ተቃውሞ ለማቀዝቀዝ ይሆናል። ሰሞኑን ህወሃት ከባድ ፈተና ገጥሞታል። በአንድ በኩል ከልዕለ-ሃያላን ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶታል። በሌላ መልኩ ደግሞ ህወሃት ለማድረግ የፈለገው አንድ ነገር ይኖራል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድል ገንኖ መውጣት የመጀመሪያው ሲሆን፣ በኤርትራ በኩል የሚመጣውን ማንኛውንም ሃይል ለመምታት ያኮረፈውን የኢትዮጵያ ህዝብ “5 የፖለቲካ እስረኞችን” በመፍታት መካስ ይፈልጋል። በመሆኑም እነዚህን የተፈቱት የፖለቲካ እስረኞች ለኢትዮጵያ ህዝብ የቀረቡ የእርቅ ገጸበረከቶች መሆናቸው ነው።

በአሁኑ ሰአት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይህ የህወሃት መንግስት በሰላማዊ መንገድ ስልጣን እንደማይለቅ በጥብቅ ያምናል። በሌላ በኩል በጉልበት ስልጣን ላይ የወጣ እና በሙስና በአንድ ዘር የበላይነት የነገሰ “መንግስት” በምንም መልኩ አሁን ያለውን ጥቅሙንና ክብሩን ለመልቀቅ አይፈልግም። የራሱን ህልውና ሊያጠፋ የሚችል ነገር  በምንም መልክ ይሆን ማዳፈን የመጀመሪያ ስራው ነው። በመሆኑም ትናንሽ መደለያዎችን በማቅረብ ህዝቡን ለማታለል መሞከር ከፍተኛ ጅልነት ነው።  አቶ ሃይለማሪያም እንዳሉት፣ “የኢትዮጵያ ህዝብን ፈቃድ ጠይቀን ከኤርትራ ጋር ጦርነት እንገጥማለን” የሚል ጨዋታ ከዚህ በኋላ ሰሚ ጆሮ የለውም። ኣንደከዚህ በፊቱ ህዝቡ ሆ ብሎ ሻዕቢያን (አሁን ደግሞ  አርበኞች ግንቦት ሰባትን) ለመደምሰስ በነቂስ ይወጣል ብለው ማሰባቸው ምን ያክል ህዝቡን እንደናቁት ያሳያል።

አሁን የጨዋታው ህግ ተቀይሯል። እንደከዚህ በፊቱ ሆ የሚወጣላቸው ተቃዋሚ ወይም ህዝብ አይኖርም። ህወሃሃት የራሷን አባላት ይዛ መዝመት ተችላለች። የአባላቱ ቁጥር ስንት ነበር? 7 ሚሊዮን? አዎ ሰባት ሚሊዮን አባል ለዘመቻ ብቻ ሳይሆን አገር ለመመስረትም በቂ ነው። 85 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብን ግን ይተውት! አይሆንም! ህዝቡ ጠላቶቹና አሸባሪዎቹ እነማን እንደሆኑ አብጠርጥሮ ስለሚያውቅ ከሁለት አስርተ አመታት በላይ ሲያሸብሩ የኖሩ ወያኔዎች ላይ አፈሙዙን ማዞሩ አይቀርም። አዎ! ህወሃት የአየር ሰአቷን አሟጥጣ ጨርሳለች። የተወሰኑ ሰዎችን በመፍታት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘትና ስልጣናቸውን በጦርነት ለማስረዘም መሞከር በፊት አዋጥቷቸው ይሆናል፣ ለሁለተኛ ጊዜ ግን አያዋጣም። ህዝቡ ነቄ ብሏል፥ ህወሃት እስረኞችን ስለፈታች ተለውጣለች ማለት እንዳይደለ በደንብ ተገንዝቧል። ነገ ደግሞ ሌሎችን ማሰሯ እንደማይቀር ከልምድ የተማረው ህዝብ የህወሃትን ልብና ኩላሊት በደንብ መርምሯል።

ስለዚህ መቀየር ያለበት የህወሃት ሶፍትዌር ነው። አርጅቷል። በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት የዘረኝነት፣ የአምባገነንነት፣ የማን አለብኝ ባይነት፣ አድሏዊና የቂመኝነት አስተሳሰብ ይዞ አገርን የሚያክል ግዙፍ ነገር መምራት አይቻልም። ስለሆነም በአዲስ አሰተሳሰብ መቀየር አለበት። ከአርባ አመት ከፊት በነበረ ሶፍትዌር አሁንም አገር እየመሩ ያሉ ቡድኖች መፍረስ አለባቸው። ያ የሚሆነ ደግሞ የህወሃት ዘረኞችን ከስልጣን በማባረር ነው። ትግል መደረግ ያለበት ከሻቢያ ወይም ከግንቦት ሰባት ጋር አይደለም ፣ ከወያኔ ጋር ነው። ወያኔ ከተለወጠ ዘላቂ ሰላም ያመጣል፣ የሚገደል፣ በውሸት ክስ የሚታሰር አይኖርም። ከሁሉም በላይ ውሸት የሚፈበርክ ተቋም አይኖርም!

 

ሥህነ-ቤዛ! ቅኝተ-ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 21.08.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

„ … በሀገሬ ውስጥ በነፃነት መኖር የሰው ልጅነቴ መለኪያ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህን የሚከለክለኝን ማንኛውም ኃይል ከመቃወምና የምችለውን ከማድረግ ወደኋላ አልልም። ይህን ሳደርግ የሚመጣውን ዕዳ ተቀብዬ ነው።“ የሞት ፍርድ በወያኔ  ሃርነት ትግራይ ዘራዊ አስተዳደር የተፈረደበት ዬአርበኛ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ – ቃል።

ምዕራፍ – ሦስት፤

Birhanu nega asmera erእንዴት ናችሁ የሐገሬ ልጆች?! ደህና ናችሁ ወይ? በጨለመ የጥላቻ ዋሻ ውስጥ ተሁኖ ተጫባጭ እውነትን ማዬት አይቻልም። ባለገርዶሹን የጥላቻ ጥቁር ዋሻ በመደርመስ ብቻ ፀሐይ ትወጣለች። ጸሐይዋ ስትወጣ ይነጋል – የጥነት ሆነ የቅናት ቅጥም – ይራገፋል።

የማከብራችሁ – ባለፈው ጊዜ ክፍል ሁለትን በዚህ ነበር የቋጨሁት፤

„ለእኛ ቁርባናችን – ታቦታችን – ጸሎታችንስግደታችንሳላታችንየወልዮሽ የባህል ዝክረ ነገራችንየሃይማኖት ማዕዳችን – ቤተ አምልኳችን ንግሥት ኢትዮጵያ ናት። ለነፃነት ፍላጎታችን ማደሪያ የተመረጠው ደግሞ ሥህነ – ቤዛ ነው። እሱ የእርቅ ጉባኤን ከአድማስ ወዲህና ባሻገር መሳላል – የሥርዬት መክሊት መገናኛ መርከባችን አንባችን – ነው።“

ከብሄራዊ ፍላጎት ጋር መፈጠር – አነባቢ (Vowel።)

ኢትዮጵያዊነትን አሳምሮ ይተርጉመዋል – አናባቢ (Vowel) ስለሆነ፤ ሥህነ – ቤዛ ኢትዮጵያዊነትን አደላድሎ – የማመሳጠር አቅሙ በውስጥነት ውስጡ አድርጎ ነው።

አናባቢ ከሌላ ተነባቢ ቃል አይኖርም። (BCDFGHJK) (ሀለመሰሸቀበተ) አናባቢ ባይኖር ዬዓለም የማድመጫ ዓይኖች እውር በሆኑ ነበር። የኑሮም የማሰቢያ ጭንቅላቱ ትንፋሽ አልቦሽ ግዑዝ በሆነ ነበር። ወንጌላዊው ዮኋንስ „በመጀመሪያ ቃል ነበረ። ቃልም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ፣ ቃልም እግዚአብሄር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፣ ከሆነውም አንዳችስ ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በእርሱ ሕይወት ነበረች፣ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ይበራል፣ ጨላማም አላሸነፈውም። ዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 1 ከቁጥር 1 እስከ 5“ ሲል ያስተማረው የቃልን ህይወት የመፈጠር ሆነ የመነበብን ሚስጢር በመኖር ሲያመሳጥልርን ነው። ያ ቃል ነው ዓለምን፣ ሰማይና ምድርን፣ ህይወት ያላቸውንና የሌላቸውን የፈጠረ። ስለዚህ ለእኔ የኢትዮጵያዊነት ዜግነትን ታማኝ ህዋስ ጥልቅ ሚስጢሩን ተነባቢም – አናባቢም ሆኖ በመገኘት እረገድ ሥህነ – ቤዛ ቤተኛነቱ በመሆን ያከበረ ህብራዊ ቃል – ኢትዮጵያዊ ቋንቋ መሆኑን በጥልቀት – አስተውዬበታለሁ። እንዲህ በተዋርድንበትና በተናቅንበት ዘመን በ እውቀት ላይ የተመሠረተ ንጥር ሁለገብ ብቃቱ – መካሻ! ይህም ብቻ ሳይሆን የሀገሩ የኢትዮጵያ ሁለመና ባለትርጉም መምህር መሆኑንም በሚገባ በጥልቀት – ተርድቻለሁ። መነሻው ኢትዮጵያ መድረሻው ኢትዮጵያ፤ እንዲያውም አለፍ ብሎ አፍሪካንም! ኢትዮጵያ ተኮር ዝንባሌውን እና የአፍሪካዊ ፓለቲካዊ ችግሮች በሚመለከት „ዬአፍሪካ ቀንድ የውይይት ፕሮግራምን“ በአሜሪካን ሀገር በኒዎርክ ከተማ በመስራችነትና በንቁ ተሳትፎ ለአምስት ተካተታይ ዓመት ያደረጋቸው፤ የአዲስ ዓለም ራዕይ የቀደምቶች መንገድ የተከተለ፣ የፓን አፍሪካንዚም ንድፍ ተግባራዊነት – የተመነ መሆኑን ያመሳክራል። በአሜሪካን ሀገር ፊላደልፊያ ላይም „ኢንቢልታ“ መጽሄት  የእናቱን ሐገሩን ሁለንትና ችግር ለመጋራት ውስጥነቱን ያሳዬበት መድረክ ነበር። ስለዚህም ጎጥ ላይ ያልተቀረቀረው ውድ ሰብዕናው ፈተናውን በአጥጋቢ ውጤት አልፏል!

በፅሞና በቂ ጊዜ ወስጄ ያለፈባቸውን ሂደቶች፣ ውስጡን የገለጸበት መንገዶችን – በተደሞ፣ ከመሬት ሰቅ ላይ በትክክሉ ሆኜ በአራቱም ማዕዘን በአንክሮ ሁሉን ተመክሮዎቹን  – መረመርኳቸው፤ ከኢትዮጵያ ህዝብ ወላዊ ብሄራዊ ጸጋ ሆነ ማዕከላዊ አጀንዳ ማዕቀፍ የወጣበት አንዲት ዬነቁጥ ግድፈት – አላገኘሁበትም። ስለዚህም በተለይ ዬአዲስ አዕምሮ ብቁ ሰለዴ ባለቤቶች የሆናችሁ የእኔ ወጣቶቼ /ጌቶቼና ልዕልቶቼ/ መምህራቸውን ይከተሉ ዘንድ ተግቼ በዚህ ዙሪያ መሥራት እንዳለብኝ – ወስኛለሁ። ግዴታዬም ነው። ለእኔ ነገ ነግቶ – ታይቶኛልና። በአርበኝነት ግንባር ላይ ሆነ በማናቸውም ሁኔታ ያሉት ወገኖቼ ቢሆኑ ሥጦታቸውን ያከብሩት ዘንድ አብክሬ በአፅህኖት ላስገነዝባቸው – እወዳለሁ። ሥህነ – ቤዛ ወላፈኑ በግራ በቀኝ  የበዛበት ምክንያቱን እኔ ሳዳምጠው የመዳኛችን ፈውስ መንገድን በመምረጡ ነው። በመልካም ነገሮች ዙሪያ ፈተናው – መጠራቅቁ ያዬለ፣ መንገዱም እጅግ ጠባብ ነው፤ ሲያልፉት ግን ገነት! ሁልጊዜም በግል ህይወት ሆነ በማህበራዊ ህይወት፤ እንዲሁም በፖለቲካ ይሆን በሃይማኖታዊ አቋም፤ በተጨማሪም በሙያዊ መብትና ግዴታም ዙሪያ ቢሆን በተዕቅቦ የሰከኑ ሥነ – ምግባሮች ተፈታታኝ ወይንም ተቀናቃኝ መንፈሶች አዘውትረው ወጆቦችን – ያበራክቱባቸዋል። ስለምን? እራሳቸውን መሆን ዬቻሉ ብስል ወገኖች ያልተገቡትን ሥነ -ምግባሮች – ስለማያስጠጉ፣ ፊትም ስለማይሰጡ። ጥንቃቄያቸው ብልሃት – ዘለቅ፣ ዓላማቸው ስልት – ቀደም፤ ሥልጣኔያቸው መርህ – ገብ ስለሚሆን አውሎው ያዬለ ነው። ቀናዎች ወይንም የአዎንታ አርበኛ መንፈሶች ሥነ – ድንግልና በመንደርተኝነት ዕሳቤ ወይንም በአስተሳሰብ ድህነት ለማስገሰስ ስለማይፈቅዱ። የሰብዕናቸው ሁለንትናው ፀ ———-አዳ፤

ዬመንትዮሹ መስተጋብራዊ ውህድ መንፈስ ከእኛ የሚጠብቀው ብሄራዊ ግዴታ።

የአናባቢነት ውህድ መንፈስ የመንገድ ጠራጊው ዬድርጁው የጀግና አንዳርጋቸው ጽጌ መንፈስ የማያንቃላፋ የማይሞት ስለመሆኑ በፍቅር በመስተጋብር ያዋድዱት ዘንድም በትህትና  – ለቅኖቹ ዝቅ ብዬ አሳስባለሁ። ወጣቶችና ቅንነት ያልነጠፈባቸው ወገኖቼ በራሱ የተማመነ ማስተዋልን እንዲፈቅዱለት – አሳስባቸዋለሁ። ከዚህ ላይ ብልህነትን የሚጠይቅ ብሄራዊና ወቅታዊ ግዴታ አለብን። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዬጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌ የህዝብ ፍቅር መንፈስ ገናናነት „እራቁት¡“ ለማድረግ በቅናት ድብን ብሎ ስለ አበደ፤ የለመደበትን ዬስውር ደባ ሥራ ማስኬጃ የሆነውን የአቶ መብራቱ ገ/ህይወት ወይንም በበርሃ ሥማቸው የአቶ በረከት ስዕሞንን እውር ራዕይ፤ ቹቻን ተንትርሶ የተዘጋጀውን የኑዛዜ በድን ድምጽ አመድ ማድረግ የቅድሚያ ተግባራችን ሊሆን ይገባል። ይህም ማለት በፈላስማው አንዳርጋቸው ፅጌ ሥም ይወጣል የተባለውን መጸሐፍ ዬኢትዮጵውያንን ክብራችን ገፎ ለውርዴት የዳረገን፤ በእስር ቤት እንኳን ብትን አፈር የነፈገን ሥርዓትን „በቃኝ“ ከምንልባቸው ጉልበታም እርምጃዎች ቀዳሚው በመሆኑ፤ ይህ ደባ የታሪካችን ውርዴም ስለሆነ – አዲሱን የለበጣ ሴራ የበቀል ማዋራረጃ መጸሐፉ ነውና፤ ከገብያ ውጪ በማድረግ የመጋዝን እራት እንዲሆን ቁጣችን – ፀፀታችን – እልሃችን – ቁጭታችን አቅማችነን በማጥገብ „አንገዛውም“ በማለት ተግባር ላይ እንገኝ ዘንድ እንደ አንድ ኢትዮጵያው ዜጋ ጥሪዬን – በአክብሮት አቀርባለሁ። እስኪ ልዬው፣ እስኪ ልፈትሸው ብለን ውርዴታችን በገንዘብ በመሸመት የንጹህ መንፈሳችን ቤተኛ እንዳናድርገው! በነፃ ህወሓት ቢያድለው እንኳን – እንዳናስጠጋው። ያን የጀግና መንፈስ ስቃይ እንዴትስ – አንገዛዋለን? ያ የድብደባ የወገኞቻችን የስቃይ ዬጩኽት መንፈስን በራችን ከፍተን ቤት ለእንግዳ እንዴትስ እንለዋለን?፤! የዛ ዬኢትዮጵያዊነት የማንነታችን ሰቆቃ ረስተን መጸሐፉን ብንገዛው ለብሄራዊ ዕንባችን ድፍረትም ንቀትም ነው። ቢያንስ በገንዘባችን ሀገራዊ ወኔን ሁነኛችን እናድርገው! ይህ ለይደር የሚቀጠር አይደለም። „ቁርጥ ያጠግባል“ ቁርጣቸውን ማሳወቅ – በተባ እርምጃ። ከእነሱ ጋር ሆነ ከጄሌዎቻችው ጋር እራሱን ላልቻለ ጥገኛ መንፈስ ህብረትም ትብብርም ሊኖረን አይገባም። እራሱን ችሎ የቆመ ብቁ ርቁቅ ሥልጡን – ቅዱስ – መሪ መንፈስ አለን- እኛ! የምን ብድር የምን ውሰት – ለባንዳነት ————-?~!

ክብረቶቼ – ኢትዮጵያዊነታችን እምናበለጽገው ቢያንስ በእጃችን በሚገኘው ሙሉ አቅም፣ በተጻራሪ የቆመውን መንፈስ ቅስሙን ለመስበር አሁኑን ተግባርን ስንውጥ ብቻ ይሆናል። „በቃን!“ ቃሉ እራሱ ሁለገብ ነው። የህወሓት ጠረን ሁሉ ድብዛውን ለማጥፋት መዶሻችን ነው „በቃን!“ እርግጥ ነው አካ – ደጅጠኝ – ፍርፋሪ ለቃሚ – እፎዎ መንፈሶች ዝቅ ብለው ለአራጃቸው – ያረግሩ ዝል መንፈሳቸውን – ይገበሩ፣ ድብድባ የወጣውን የበታችነታቸውንም –  ያቆላምጡ። እኛ ግን ደማችን ውርደትን – ባርነትን – የበታችነትን፤ ሥነ – ልቦናዊ ቅኝ ተገዢነትን ይጸዬፈዋልና ልዩ ቃናችን ኢትዮጵዊነታችነን ድርጊት እናስታጥቀው። ዛሬ እስር ቤት ውስጥ የዱካ ማስቀመጫ ብትን አፈር ቦታ ተነፍጎል፤ አንድ ጆሮውም አይሰማም የጀግናችን ዬጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ አካል የሌለው አገልጋይ ቃለ ወንጌል ሳይቀር ፈቃድ ተነስቶ አባ ትርጉም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መንፈሱን ጉስቁል ለማድረግ፤ በሥነ ልቦናው እዬትዘናኑ እዬተሳለቁ ይገኛሉ – አራዊቶች፤ ዛሬ የአርበኛ አበበ ካሴ ጥፍር በግፍ ተነቅሎ የመክራ ዝክረ ሙዚዬም እየሆነ ነው፤ የእመቤቴ የጀግኒት ዬወይንዬ ሞላ ማህጸንስ ነገ ፍሬ ያበቅል ይሆን? በካቴና ቃለ ምልስስ ላይ ያዬነው የአርበኛ አቡበክርስ – ዛሬ የወንጀል ቅጥረኞችን በእስር ቤት በማሰማራት ማገዶውን አንዱአለም አራጌን ያስደበድባሉ – ለነፃነት የቁም ሰማዕትነት። ሌሎችንም፤  ምን ዬማያደርጉት አለና …. ምን የማይሰማ መራራ ዜና አለና፤  ይህን መጸሐፍ ከገዛን እኛ ስቃዩን እንደ ፈጸምን አንደ ፋሽስንትም እንደ ተባበርን ያስቆጥራል።

ስለ እስር ቤት ካነሳሁ ትንሽ ምራቂ ነገር ልበል። ወላጅ እናቴ ምህርት ጠይቃ በተሰጠኝ ምህረት የጫካ ኑሮዬን ትቼ አንድገባ አደረገችኝ። እውነት ለመናገርም የግንኙነቴ መስመሩ ስለተቋረጥ ሎጅስቲኩ ሆነ ሁሉ ነገር ከባድ ስለሆነ ግድም ነበር። በምህረት ከገባሁ በኋላ ግን ጎንደር ባታ እስር ቤት ታሰርኩኝ። ሰው በምህረት ገብቶ እንዴት ይታሠራል?! በቬርሙዳ ትርያንግል ሥርአት እኮ ነው ህወሓት የሚመራው። ስፈታ ደግሞ ያን ጊዜ ብዙ ነው በ50000 የኢትዮጵያ ብር ዋስ በቁም እስር ነበር። መንፈሴም አካሌም ሥነ – ልቦናዬም ታስሮ። ዋሴንም የተከበሩ ሸሕ ሲራጅን ሊያስቀምጧቸው ስላልቻሉ ሀገራቸውን – ለቀቁላቸው። ቅብም ቢሆን ፍርድ ቤት፣ ክስ፣ ምስክር የሚበላው በመዲናችን አዲስ አባባ ላይ ብቻ ነው የሚሠራው። የዛሬን ባላውቅም ያን ጊዜ ከክ/ ሀገር ጀምሮ እስከ ነጥብ ጣቢያ አንድ የህወሓት ባለዘር ሜዳሊያ ባለጊዜ ካድሬ ያሰረውን፤ አስተውሉ ወገኖቼ አሳሪው ሀገር ቢለቅ ወይንም ቢሞት ወይንም ከድርጅቱ ቢባረር ሌላው – አይፈታውም። እዛው ተረጅቶ ሞት ብቻ ይጠብቀዋል – ወገናችን። ሌላው ማጣሪያ የሚባለው ነገር ደግሞ የላሜ ወለደች ዓይነት ነው። የእስረኞች ሥም ዝርዝር በከተማ የህዝብ አደባባዮች – ይለጠፋል። በፈለገው ዓይነት በቂም፤ በቅናት፤ በክፋት አንድ ሰው ከጠቆመ ያ እስረኛ መፈቻ የለውም። ምርመራው ደግሞ ታሥራችሁ ልማዳችሁን አንድታቀኑ መገደድ ነው። ግራ እኮ ናቸው። የቬርሙዳ ትርያንግሉ ሥርዓተ አራዊት እንዲህ ነው። በፍጹም ሁኔታ በክ/ሀገርና ከዛ በታች ያሉ የእስረኛ አያያዝ ሁኔታ ከአዲስ አባባ ጋር መወዳደር ቀርቶ – አይቀራረብም። ዓይነቱም ይዘቱም የተለዬ ጭፍን ሸጎሬ ነው። ድፍን ታውቃላችሁን?!

ሚስጢር ዘለቁ – ነገረ ኢትዮጵያዊነት፤

ያደለው ከሚስጢሩ ጋር መፈጠሩ ብቻ ሳይሆን በቁምነገር አብሮ ይኖራል። ነገረ ኢትዮጵያ የሚስጢራት ሁሉ የሥነ – ፍጥረት ሁሉ ነፍስ ነው። ኢትዮጵያዊነት የገድላት – ሩኽ ነው። ኢትዮጵያዊነት የፍጥረት – ህሊና ሥነ – ምግባር ነው። ኢትዮጵያዊነት የጸሎት መንፈስ ነው። ይመራል – ያስተዳድራል፤ ስናጠፋ – ይመክራል ብቁ መካር ነውና። ስናኮርፈው ያቆላምጣል – ሩህሩህ ነው፤ ህጉን አብዝተን ስንተላለፍ ደግሞ ቆንጠጥ አድርጎ – ይገስጻል፤ ስንዳፈረውም ይፈራዳል – ይቀጣል። ዳኝነቱ ሚዛናዊ ከመሆኑ በላይ ራሱን የቻለ ተቋም ነው – ህሊና ላለው፤ ዜግነቱ ውስጡ ለሆነ ሁሉ መዕዋለ ህይወቱ ት/ቤት ነውና – ያስተምራል።

የአትዮጵያዊነት ሥነ – ህግጋቱ የመሆን መቻል ሰማይና ምድር ናቸው። ገሃዱ ዓለም እና መንፈሳዊውን ዓለም ያስማማ በትረ – ዓምድ፤ በፍቅር እያዋዛ ያዋደደ የዘመናት የተደሞ አናት ነው – ኢትዮጵያዊነት። ኢትዮጵያዊነት የቀለሞች ሁሉ አዲስ ቀለም ነው። ኢትዮጵያዊነት የነገዎች ሁሉ አዲስ ቀን ነው። ኢትዮጵያዊነት ሲፈጠር ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ የሚስጢር ሊቀ – ሊቃውንት ነው። ኢትዮጵያዊነት እንደ ወንዝ ዳር ዕጽዋት በጋ ከክረምት፤ መኸር ከጸደይ እዬለመለመ እያሸተ የሚሄድ፤ እርጅና ከቶውንም ዝር የማይልበት ሁልጊዜ ለሁለመና በነፋሻማ ጤናማ አዬር የሚጎበኝ የጤና ፍውሰት ነው። ሙቅ የሆነው ወጣት ፍቅሩ ከቶም አይጠገብም። ቋሚ መንፈሱ ትጉኽ ገበሬ ነው፤ ማራኪ አቀራረቡ በቁሙ የጸደቀ የሁሉዬ በመሆን እኩላዊ፣ ራስነትን የፈቀደ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ከኩራት በላይ መኩሪያ፤ ከጋሻ በላይ መከታ፤ ከጥላ በላይ መጠለያ፤ ከመቻል በላይ መቻቻል፤ ከማክበር በላይ መክበር፤ ከማድመጥ በላይ መደመጥ፤ ከሚስጢር በላይ መመሳጠር፤ ከታማኝነት በላይ ታማኝ፤ ከትህትና በላይ ትሁት፤ ከፍቅር በላይ ፍቅራዊነት (Loveism)፤ ከትእግስት በላይ ታጋሽነት፤ ከአብሮነት በላይ ዬአብሮዊነት ልዕልና ነው። ኢትዮጵያዊነት በራስ የመተማመን የደም ማህተም ነው። የነጠረው መንፈሱ ቅኝ ተገዝቶ በፍጹም – አያውቅምና። እራሱን ሆኖ የኖረ ብቻም ሳይሆን ሌላውንም በውስጡ ያኖረ የአደራ ትውፊት ነው። የእኔ የሚለው – ሁሉ ያለው፤ ሁሉንም – የሆነ፤ ለሁሉም ለመሆን የሚችል – ኩን የመኖር ሥነ – ደንብ ነው – ኢትዮጵያዊነት። ተዝቆ የማያልቀው መክሊቱ የፈለቀው ከእውነት ማህደር ብቻ ነውና። ተመርቆ የተፈጠረ በመሆኑ አስተዳደራዊ ሆነ ጣልቃ ገቢያዊ ፈተና አያጣውም፤ ግን ተቀናቃኙን ድል የመንሳት ተስጥዖው ደግሞ ገድላማ ነው። ዬኢትዮጵያዊነት ድፍረቱ የሚቀደው ከምንጩ ከአለው ረቂቅ ጸጋው – ከራሱ ነው። አለው! ትውስት ክፍሉ አይደለም፤

በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊነት ለመንፈስ የርትህ ብሩኽ የችሎት አደባባይ ነው። ኢትዮጵያዊነት በተፈጥሮው የዳኝነት ውሎ ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን ህግ ናት። የተፃፈውም ሆነ ያልተጻፈው ህጓ እሷን ለዬት ብላ፤ እኛ ልጆቿም ኢትዮጵያውያንን ለዬት ብለን ኑሯችን እንድናስተዳድር ይመራል። በኢትዮጵያ ማህጸን ውስጥ የተፈጠረው ኢትዮጵያዊነት አማናዊው ሲሆን በክርስትና እምነት ከዘመነ ብሉያት በፊት በህገ ልቦና አምላኩን የተቀበለ፤ ሃዲስ ኪዳንንም የወደደ ዬፈርኃ እግዚአብሄር ማማ ሲሆን፤ ዬእስልምናም ሃይማኖትን በሚመለከትም፣ ታሪክን የቀደመ፣ የሐዋርያነት ተግባር የፈጸመ የተግባር አንቱ ጉልላት ነው። ለኢትዮጵያዊነት ሃይማኖት አለኝ፤ እማመልከው አምላክ አለኝ ብሎ ማመን ርስተ – ጉልቱ ነው። ተፈጥሮው ነው ማለት ይቻላል። እርግጥ ነው በተፈጥሮ የሚያምኑትንም የራሱን አካላትንም – አይጋፋም። ሳሃ የሌለበት ሥልጡኑ ማንነት – ኢትዮጵያዊነት!

ኢትዮጵያዊነት በግጭቶች ማህል እንኳን ዬስምምነትን ስበት የመወለድ አቅሙ ከጸሐይ ጉልበት በላይ ነው። ኢትዮጵያዊነት ሥርዬት ፈላጊነቱ  የመልካም ነገሮች ዓውደ ምህረት እንዲሆን – አድርጎታል። ኢትዮጵያዊነት ነብያትን ቀድሞ ያናገረ፤ ሳይንቲስትን የመራ፤ ቅዱሳንና የፈጠረና ከተለያዩ የዓለም ክፍላት ሰማዕታትን ደናግላንን ሐዋርያትን ሳይቀር በብቃቱ ዬጠራ፤ በብልህነት ያስተናገደ – የገሃዱ ዓለምና የመንፈሳውው ዓለም  ፍጹማዊ ዬመርኽ  የአብርኃሙ ማዕዶት ነው።

ኢትዮጵያዊነት ጠላቱን የሚያስተምረው ምክንያት ፈልጎ ነው። በዬአጋጣሚዎች እሱን ለማጥቃት የሚነሱትን የዶግ አመድ የሚያደርግበት አቅሙ የሚቀዳው ከሰማዩ ዳኛ ነው። እንሆ የወያኔ ሃርነት ትግራይን በ40 ዓመት ህይወቱ ሉሲ ድንቅነሽን አስቀድሞ  ዕውቅና አሰጥቶ፤ ህወሓት በተኛ በ40 ዓመቱ ከእንቅልፉ የቀሰቀሰ፤ የማያልቅ ወይንም የማይቋረጥ ትኩስ ዬአቮል ቡና ፏፏቴ ነው። የማንቃት መዳህኒት በመዳፉ ያለው፤ ቅንኛ – ቀና – ቅኔኛም። ወንዳታ! ዛሬ በጠላቱ በህወሓት መንፈስ አስለፍልፍን አስርፆ ነጋ ጠባ „ኢትዮጵያዊነት፤ ሐገራችን፤ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን“ እያሰኜ ጠላቶቹ በፖሊሲ ያሰሩትን፤ ገድለን ቀብረነዋል ያሉትን ቅዱስ መንፈስ በልሳናቸው ሲቃጁ ውለው እንዲያድሩ ያደረገ የጀግኖች ቁንጮ፤ አንበሳ ነው ኢትዮጵያዊነት!  የመሆን የትጋት – የንጋት ገበሬ!

አዬ! ዓፄ  ዘመን እንዴትና እንዴት አድርገህ ነው ኢትዮጵያዊነት – የምትከሰው! ብርሃኑ ሲነጋ  በሃቅ – ታታመ። በእንቁላል ውሃ ተገናባ። ዬማግስትነት ክብሩ – ታወጀ። ዘመን ተናገረ – ያደመጠውን በሐዋርያነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ልቅና ዓለም መሰከረ ….. ሲፈጠር ከብሄራዊ ፍላጎት ጋር የሆነው ሥህነ – ቤዛችንም እንኳን ደስ አለህ። ትጋትህ ከጥዋቱ ለዚህ ልቅና ነበር፤ … ለጋ ዕድሜህን ለበርሃ የሸለምከው። ዝንፍ ሳትልም በዞግ ንክኪ ከቶውንም ሳትጠመድ በማተብህ የጸናኽው፤ በተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ ብሄራዊ ፍላጎትን ዕውን ለማድረግ አፍላነትህን – የሰጠኽው። ጉልምስናህንም ለሀገርህ ለኢትዮጵያ እንደ ዘመኑ እድገትና ብልጽግና በነፃነትና በዴሞክራሲ አሰራር ያለህን እምነት ውስጥህ በማድረግ፤ የናፈቀህን ዴሞክራሲ ርትህ ዕውን አንዲሆን፤ የምትፈልገውን የእኩልነት ምድር እናትህን ለማድረግ ወደ ኋላ የማትል የኢትዮጵያ ዘላቂ ልጅ። ለአንዲት ሰከንድ በእምስ ዬመንደርተኛነት አጀንዳ ጊዜህን ያለባከንክ የልዕልት ኢትዮጵያ የተቋማት – ምርጥ ተስፋ። …. ኢትዮጵያዊነት ህግህ ያደረክ፤ ለኢትዮጵያዊነት ፍጹም ታማኝ የሆንክ የአዮ ትሩፋት …

ውድ ታዳሚዎቼ – በምዕራፍ ሁለት ጹሑፌ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ሚስጢር ነው ብያለሁ። ስለምን?  ሚስጢር መሆኑ ስለተገለጠለት። ስደት ሽርሽርሽር አይደለም፤ ፈተናው ያላችሁበት ነውና – ታውቁታላችሁ። ሁለተኛ ዜግነት መውሰድ – የስደቱን ውሃ ያዘለ ተራራ ለመሸከም፤ ጊዜያዊ ሆነ ዘላቂ ችግር መፍቻ የሚሆኑ ቁልፎችን ለማግኘት፤ ወይንም ቤተሰብ ከተመሰረተ በኋላ በስደቱ መንደር ዬልጆችን የተስፋ ትልም ለማሳካት፤ ቤተሰባዊ ኑሮን በአንድ ለማድረግ፤ ረቂቅና ወስብስብ ፈተናን ለማሸነፍ፤ ባይታዋርነትን ከግንባር ገፋ ለማድረግ ግድ የሚሉ ነገሮች – ይገጥማሉ። ባትወዱትም – ባትፈልጉትም። በማናቸውም ሁኔታ ይህን እርምጃ መወስድን አስፈላጊ የሚያደርጉ የተጽዕኖ ምሽጎች በዬአቅጣጫው ጦርነት – ይከፍታሉ። ታዲያ ትውልደ ኢትዮጵያዊነትን እንደያዙ በተደራቢነት ችግርን ለማስተጋስ ወይንም ለማሸነፍ ወይንም መንፈስን ለመረጋጋት እርምጃው ይወሰዳል – ዬተጨማሪ ዜግነት። ይህ ወንጀል አይደለም። የታህሳስ 10. 1948 ዓለምአቀፍ የሰብዕዊ መብት አስከባሪ ህግ „አንቀጽ 15 እንዲህ ሲል መብት ስለመሆኑ በአጽህኖት – ደንግጎታል።

  1. እያንዳንዱ ሰው የዜግነት መብት አለው።
  2. ማንም ሰው ያለፍርድ ዜግነቱ አይወሰድበትም፤ ወይንም ዜግነቱን የመለወጥ መብት አይነፈገውም“። ስደትና መከራውን – በስደት ያለፈ ሁሉ ስለምን ሁለተኛ ዜግነት መውሰድ እንዳለበት፤ ወሳኝና አስፈላጊ እንደሆነ – ይገነዘበዋል።

ወገኖቼ – ይህን ነጥብ ነጥዬ ማንሳት የፈለግኩት መሰረታዊ ምክንያት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን  „ኢትዮጵያዊነትን አግላይ“ የሚል ተቀናቃኝ ተቀጥላ ሃሳብ ጎልቶ ስለወጣ ነው፤ ያን ከሥሩ የፈለሰ ሃሳብን በተጨበጠ ዕውነትን fact አቅርቤ እርባና ቢሱን፣ የፋደሰ ከንቱ የላመ አጀንዳ መቅበርም – ስላልብኝ ነው። በሌላ በኩልም ሚስጢር ከሚስጢሩ ጋር ስለመኖሩ የጭብጥ አቅም ያነሳቸው ትችቶች በተያያዥነት ስለ ነበሩ ብኩን ስለመሆናቸውም አስረግጬ ለመግለጽ ነው። እገረ መንገዴን ጠረግ ለማድረግም ጭምር ነው። አንቱው አመክንዮ „ታላቋን አሜሪካን የፈጠረ የኔ ማንነት ነውና እኔ ያለኝ ነገር ሌላው የሌላው ብቻም ሳይሆን፤ ዓለምን ፈጣሪ ስለሆነ ስለምን ብድር እሄዳለሁ? ማንነቴ ኢትዮጵያዊነቴ ይበቃኛል – መቅድም ነውና“ ማለት፤ ለዛውም ሁሉ ነገር እያለው፤ እዬቻለ፤ እራሴን ሆኜ መኖሬ የክብር ክብር፤ የግርማ ግርማ፤ የሐሤት ሐሤት፤ መርሄ  ነው ብሎ ኢትዮጵያዊነቱን የፈቀደ፤ ኢትዮጵያዊነቱን የመረጠ፤ ኢትዮጵያዊነቱን የወደደ ከዚህ ጋር የተያያዙ ማናቸውም የስደት ውጣ ውረዶች ለዛውም በወጣትነት ዘመን ብዙ ወጣ ገብ ችግሮች ሳይበግሩት – መልካም ዕድሎችም ሳያታልሉት፤ እንዲህ በውሳኔው መዝለቅ የቀደመ – ሐዋርያነት ነው ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ። ሥህነ – ቤዛ የትኛውም የስደት ፈተና አላሸነፈውም። ችግሮችን ተጋፈጦ ገዢ መሬቱን – ተቆጣጥሯል።

በዚህ ውስጥ ድፍረቱን፣ ቁርጠኝነቱን፣ ውሳኔ የመስጠት ጉልበታም አቅሙን፤ እራሱን ለመምራት ያለውን አቅም ወቄትም ማዬት ይቻላል። እራስን ማሸነፍ የወርቅ አንክብል ነው። እንዲህ ያለውን በውስጡ ለውስጥነት መርኽ የተገዛ መንፈስ ለሁላችንንም ዬአብነቱ ተመስጦ – ትውፊትን ቀልቦናል። ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ውህደትም በአካል ሥህነ ቤዛ ያልተገኘበት መሠረታዊ ምክንያት የመጓጓዣ ሰነዱ ጊዜ ያስፈልገው እንደ ነበር – ከኢሳት አምስተርዳም – አዳምጠናል። ሳያበራ ብዕር የጨበጠ፣ ዬማይክ ራህብተኛ፤ የአትራኖስ ጉጉተኛ መንፈስ ሁሉ ዱላ /ቆመጥ/ ባለማቋረጥ ይቆረጣል፤ ዱላው ወይንም ቆመጡን አስተካክሎ ዓይንህ ጥርስህ ብሎ ከርክሞ ይዘጋጃል፤ ያው መሰናዶው ተዘውትሮ ለፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋና ለመንትያው ይሆናል። አቤት! – ትእግስቱ! እንዲህ ዓይነት ሆደ ሰፊነት ብቻ ነው ኢትዮጵያን ከእነህልቆ መከራዋና ችግሮቿ መሸከም – የሚችለው። ሰለጠነበት – በመከራው። ኖረበትም። ፍጹም ያልተገባ፤ ከፖለቲካዊ መንገዶች የወጡ ከኢትዮጵያዊነት ሥነ ተፈጥሮም ያፈነገጡ ዬተቸዎችን – ከሰብዕ ዝቅ የሚያደርግ ዘለፋ ሁሉንም አስመችቶ – ቻለ። ይህ ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራው ጥንካሬውና ብርታቱ ደግሞ እልፎች አጥር ቅጥር እንዲሆኑለት ግድ አላቸው። የመንደር ሆነ የጎጥ ሪጋ ቤት ባልደረባ ያልሆነው – ጥልቅነቱን ለማዳመጥ እንፈቅዳለን! ተግባሩ ብቻ ነው የስምሪታችን መሃንዲስ! ሩቅ አሳቢነቱ ቅዱስ መንፈሳችን ነው! …. የመሪነት ጥራቱ ርትህ ሰጪ ትርጉማችን ነው! ዓይናችን የህሊናችን ሚዛን ነው! እሱ ራሱ ነፃነት ነው።

ጽናትን ለዋጠ ኢትዮጵያዊነት – እኔ ምን እላላሁ? ምንስ አቅም አለኝ? እግዚአብሄር ይስጥልን ከማለት በስተቀር። ይህ ሰው በጣም እጅግ ሩቅ ነው። ይህን በእውነቱ በመከራ ብዛት ከሃገሩ ለሚፈልሰው ወጣት የዜግነት ብቃት ት/ቤት ተቋም ነው። በህልሜም በውኔም የሚነስተኝ በሀገሬ በኢትዮጵያ ብሄራዊነትን አጀንዳው ያደረገ ትምህርተ – ዜግነት፤ ፍትህን ማዕከሉ የሆነ ትምህርተ ሥነ – እኩልነት፤ ሰማያዊ የተፈጥሮ ሥጦታዎችን በአስኳልነት የተንተራሰ ትምህርተ ሥነ – ፍቅራዊነት በመደበኛ ትምህርትነት ሥርዓት ተቀርፆላቸው በመደበኛ ት/ቤት የሚሰጥበት፤ ሙያም ሆነ ዬሥራ መስክም አንዲሆኑ ምንአልባትም ወደ ኮሌጆች ወይንም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያም መስፈርት እንዲሆኑ መስከረምን እጠብቅ ነበር። እንሆ የአሁኑ መንገዱ ድባባዊ ውበት አለው። ዬዋዜማው ጣፋጭ ጠረን እያወደን ነው። እኔስ እላለሁ እንዲህ ዓይነት ስንዱነት፤ ቀዳዳውን ሁሉ ቀድሞ የደፈነ አንበሳነት፤ ልዑቅ ብልህነት ለወለደችህ እናትህ፤ ለምትማራቸው የፖለቲካ ድርጅት አካላትና አባላት ብቻም ሳይሆን እርምጃህ – ውሳኔህ – በፈተና የመጽናት በርነትህ የትውልድ አዲስ የሰንደቅዓላማ ትምህርት ቤት ስለሆነ – ታኮራለህ!  እኛ የስደቱን መከራ መቋቋም ተስኖን የሌላ ሀገር ዜግነት ለማግኘት እንጠቁራለን – እንከስላለን፤ አንተ ግን የአብነቶች ቀንዲል ብርኃነ – ሞገስ ሆንክለት – ለኢትዮጵያዊ ዜግነትህ። ….. እንዲህ ነው ተምሳሌነት፤ እንዲህ ነው የመሆን መቻል አርበኝነት። እኔስ ኮራሁብህ። እኔስ አምነቴን ጣልኩብህ። እልፎችም ይህን መሠረታዊ በኽረ ጉዳይ ልብ ይሉት ዘንድም በትህትና – አመለክታለሁ፤ አብሶ ለነገ ዕንቡጥ ወጣቶቻችን። ነገ ማደሪያው በውል – የመንፈስ ማረፊያ አግኝቷል። ልጆች ከሚስሙት ነገር ይልቅ ከሚያዩት ነገር ብዙ ይማራሉ። ከሚጨበጥ ሃቅ ዕውቀትን – ይገበያሉ። „ልብ ያለው ሸብ“ ይላል ጎንደሬ ሲተርት ….

ሰሞኑን ኢትዮ ሚዲያ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7 ለፍትህ ለነፃነትና ለዴሞክራሲ ሲዋህዱ „ዬኢትዮጵያ ህዝብ“ የቀረበትን ተያያዥ ጉዳዮችን ያብራራ – ክፍል ሦስት ከክፍል ሁለት ቀድሞ ከወንድሜ ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ አንድ ጹሑፍ አንብቤያለሁ። በጹሑፉ ጭብጥ ዙሪያ እምለው – አይኖረኝም። ቀደም ባሉት ጹሑፎቼ በአግባቡ ከውኘዋለሁና። ለአለቀበት ለተሸናፊ አጀንዳም ጊዜ ማዋስም አስፈላጊ – አይደለም። ነገር ግን የህሊና ዓይን የሚሆን ቁምነገር ባለው ዕውነት ላይ የተቃጣውን ዘላላ ስንኝ ከእርእሴ ጋር የሚሄደውን ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት እሱን ልሂድበት ወደድኩኝ። ወሳኝ ጉዳይ ነውና። ማስተዋልን –  „ታላቋ አሜሪካን ሆነ ዓለምን የፈጠረው ማንነቴ ኢትዮጵያዊነት ዜግነቴን ለሚዛን ሊያቀርብ አይችልም፤ ምርጫዬም ህይወቴም“ ያለው አንበሳ እኮ ነው የግንቦት 7 ሊቀመንበር በቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ ሃሳቡን አፍላቂ፤ በኋላም መሥራችነቱ ደግሞ ከመንፈስ መንትያ ወንድሙ ጋር በሀገረ – አሜሪካ። ይህ ድንግልናው ያልተገሰሰ መንፈስ ነው ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር መንፈስ ጋር የተዋህደው። የሥህነ – ቤዛን ተቀናቃኞቹን መፈናፈኛ የሚያሳጣ አሸናፊው የቀደመ ዝግጁነት፤ ተመስጥሮ የከተመበት ረቂቅ እጅግ ጥልቅ መንፈስን አለማወቁ ነበር ፆምን – ያስገደፈው።

„አያውቁንም እኛን አያውቁንም“ ይላሉ በህብረ ዜማ – ሁለመናው። በምንም ብሄራዊ አምክንዮ ግድፈት የሚታማባት ነገር የለም። ስንዱ ነው። …. እርግጥ ነው ያላወቅነው፣ ውስጡን ዘልቀን ለመመርምር ያልፈቀድን ወይንም የተሰወረብን ግን ተከድኖ የኖረ የራሳችን የእኛ ሲሳያችነን  ዕውቅና ለመስጠት ድፍረት ስለሚያንሰን ብቻ ነው። ስለምን? ኢጎና የበታችነት ስሜት ቤተ ዘመዶቻችን –  ስላደረግናቸው። እኔ እንደማዬው ፓለቲካ ሳይንስ መሆኑ ቀርቶ ግላዊ ጥላችን ጥግ ነው ብለን ስለምናምን። ፓለቲካ በተጨባጭ እውነት ላይ ስምምነት፤ ትብብር፤ መወያዬት፤ መግባባት፤ ለብዙሃኑ ፍላጎት ራስን ለማስገዛት መፍቀድ፤ ሰጥቶ መቀበል ወዘተ … መሆንም ረሳነው። በእውነቱ በብሄራዊ ሐገራዊ ጉዳይ ሙሉ ተሳታፊ ለመሆን እኔን ጨምሮ የውስጥ ለውጥ – ያስፈልገናል። ቀናዎች አይደለንም። ኃይል ፈጣሪነታችን ለአሉታዊ ነገሮች ብቻ ነው። ህወሓትማ – ተራሳ። በጎዊ ለሆኑ ለውጦች ጥቂቶች አልተዘጋጀነም – አንፈቅድም። ጎጥን መሻገር ነው የሰውነት መለኪያው። ኢጎን መደርመስ ነው ጀግንነት፤ መንደርተኝነትን ማሸነፍ ነው ለቀጣዩ ብሄራዊ ቀልም – ስምረት። አቅምን መለካት ነው ሥልጡንነት። በ እጅ በአለ ሃብት ብቻ መተንበይ ነው ብልህነት።

ወገኖቼ ኢትዮጵያዊነት የሚንጠለጠል፤ የሚለጠፍ፤ በጎን የሚታደርበት፤ ወይንም የሚለበጥ አይደለም፤ በውስጡ የሚኖርበት ሚስጢር እንጂ። አፈፃጸሙ፤ አተረጓጎሙ፤ አካሄዱ እንደ ተፈጠረበት መክሊት ይሆናል። ውድ የሐገሬ ልጆች ሥህነ – ቤዛ  ዬአሜሪካ ዜግነት ባለመውሰዱ ወይንም አሜሪካዊ ባለመሆኑ እንደ አሻው መንቀሳቀስ – አይችልም። ሌላም በፖለቲካ አቋሙ የሚደርስበትን ማናቸውም ቅጣቱን መቋቋም የሚችልበት መጠለያ ተደራቢ ዜግነት – የለውም። ከኢትዮጵያዊነቱ ውጩ ጥበቃ የሚያደርግለት ምንም ምድራዊ ነገር የለም። በጣም የሚገርም የራስ መተማመን ጣዝማ ባለሃብት ነው። ብልህ ሆናችሁ ውስጡን አዳምጡት – በትህትና። ለዛውም እንዲህ  በዬአቅጣጫው ጦር በተመዘዘበት ሁኔታ። … ህሊና የሚባለው ነገር እኮ ሚዛን ሊኖረው ይገባል። ለትችቱም – ለወቀሳውም። አሁን አሁን ሳስበው የበታችንት ስሜት አብዝቶ የሚንጣቸው የራሳችን ናቸው የሚባሉት ሳይቀሩ ፊት ለፊት ቢያገኙት ምን ያደርጉት ይሆን እንዲህ በደም ፍላት ሲወራጩ – እላለሁ። አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲታሠር ድምጽ ያላሰሙትም ዛሬ በተቆርቋሪነት ስለ አስተሳሰሩ ሂደት በፖለቲካ ተንታኝነት ይሁን በልብ ወለድ ጸሐፊነት ተስልፈው እያዬሁ ነው። ይህ ለእኔ ቆዳ መልስ ንሰኃ እንደ መግባት ነው። ያን ሰቅጣጭ ጥቃት – ጥቃቴ ነው ብሎ ለመቀበል ጊዜ ሊቀለበው ባልተጋባ ነበር። እስኪ ልሰብበት የሚያሰኝ አልነበረም። ዬብሄራዊ ውርዴት ብስጩነት አደብ ወይንም ታዛቢነት ሊሸለመው ባልተጋበ ነበር። የጥቃት ትኩስ እሬሳን አስቀምጦ ሠርግና መልስን – አዳምጠናል – ዛሬም እንዲሁ ተዛነፍ ነገር እናዳምጣለን ዘመኑን የምንታዘብ ሰዎች። ቢያንስ ፈጣሪ አምላክ „ሰው“ ብሎ ሲፈጥር የሠራለትን ሰማያዊ ህግ የእኛ – እንበለው።

መከራን መጋራት ኢትዮጵያዊ መለያችን ነበር። ችግርን መካፈል ፍጹማዊ ዓርማችን ነበር። ጥቃትን አለማስመችት የአደራ ሥጦታችን ነበር። እራቅነው ልበል ወይንስ አራቆትነው?! የሆነ ሆኖ የኔዎቹ – የኢትዮጵያዊነት ንባቡን ትርጓሜውና ሚስጥሩን እናመሳጥር፤ በተደሞና በአርምሞ ቢባል „ከአሜሪካው ዜግነት ኢትዮጵያዊነት ይበልጥብኛል። እንዲያውም አይመጣጠኑም“ ላለ የቀደመ መንፈስ ከዚህ በላይ ስለ ኢትዮጵያዊነቱ ከቶ ምን ሊገልጸው ይችላል? ምን አምክንዮ አለ ይህን ዕውንት (fact) ታግሎ ሞግቶ የሚረታ? የአውነት ጭብጥ ብቻ ነው የሰውን ልብ ቀልብ – የሚገዛው እንጂ የተገለበ ስሜት አይደለም። በስሜት ፌስታ አንጂ ውስጥን ማንበብ ሆነ መተርጎም  – አይቻልም። በጥላቻም አምላክን ማስከፋት፤ የሆኖ ሆኖ ከተወረወረ ቀስት የሚጠብቀው አምላክ ጠበቀው እንጂ …. እንደሚቃጣው ጦርማ ….

የብልጹጉ ቅብዕ በብሄራዊ ፍቅር  – ህትምተ።

አውነት ለመናገር እንዛ ቀኑን በሐሩር ጨለማውን ደግሞ በግርማ ሌሊት የሚተጉት ቅዱሳን ደናግል ዬአቨው እና ዬእናቶቻችን ጸሎት የሰጠን ሙሴ ነው ፕሮፌስር ዶር. ብርሃኑ ነጋ። ባለቤት ያልነበረው ዬብሄራዊ አመክንዮ መንፈሱ ጥግ አገኘ። ስለዚህም ሥጦታውን አናቅለው! ይህን የእውነት ውቅያኖስ እንቀበለው ዘንድም አቅም እንዲኖረን ፈጣሪያችን በፀሎት – እንጠይቅ። በፍቅር አሸናፊነቱ በእሱ ክህሎት ብቻ የተከወነ – አይደለም። የቀደመ ቅብዕ“ አለበት። እደግመዋለሁ ይህን ቃል ህቅ የሚላቸው ደሞቼ ስላላችሁ የቀደመ „ቅብዕ“ አለበት። „ቅብዕው“ የጸሎት አጥር ከምንም ነገር በላይ ያስፈልገዋልና ሱባኤ በግል አቅም ያላችሁ፤ ህይወቱ ያላችሁ ትተጉበት ዘንድ እኔ ሎሌያችሁ ሥርጉተ ሥላሴ በአጋጣሚው በትህትና አሳስባለሁ። ትውልዱ ትውልድ እንዲሆን የምትሹ ቅን ወገኖቼ – መሆን ብቻ አንዲመራችሁ እባካችሁን – ፍቀዱ። የህልም ስኬት የሚገኘው በመሆን አውራ መንገድ ብቻ ነው እንጂ ገብያው በተፈታ በትነት ንድፈ ሃሳብ አይደለም።

ይህ ፎቶው ላይ ያለው  ዬሥህነ – ቤዛ ህይወቱን ለመስጠት ቃል ያሰረባት የተግባሩ ቀለበት ነው፤ ለእርቃንነት አባት ለነበሩት ለሟቹ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ የህቅታ ቋት፤ የኮሶ ተክል – ነበር። ሲዮት ያንገፈግፋቸው ነበር። በሽታቸውም ይነሳ ነበር።  ሰንደቅአላማችን አይደለም በእጃቸው ለአንድም ደቂቃ በጎናቸው ተቀምጦ – አያውቅም። በመጤ እንደራሴ የተናጡ ስለነበሩ። „ሐገሬ“ ማለት „ኢትዮጵያ“ „ሰንደቅአለማዬ“ ማለት ዛራቸውን ያስነሳ ነበር። የሌለህን ነገር ከአንተ ሥር ያሉ ወይንም በቅርብህ የሚገኙ ሰዎች ሲያደርጉት ወይንም ሲኖራቸው የህሊና ስውር ቅጣቱ ስለሚነስትህ ያን የማዬት አቅም ምሶ መቅበር ቀዳሚ ተግባርህ ይሆናል። ለዚህም ነበር ለሰንደቅዓላማችን የማሰሪያ ህግ ተረቆ – የጸደቀበት። አርበኛ ያልሆነ የሐገር መሪ ባንዳን ይሾማል – ይሸልማል። ስለምን? አርበኛው ደረቱን ነፍቶ ቀና ብሎ የመሄድ አቅም ስለሚኖረው አርበኝነት አልቦሹ መሪ መንፈሱ እያዬ እንዳይቀጣ መሰሎቹን – ይመርጣል። ጀግኖችንና አቅም ያላቸውን ያባራቸዋል ወይንም ያገላቸዋል። ጎባጣው የሚፈልገው እንደ እሱ የጎበጠውን ወይንም ተጎንብሶ የሚሄደውን ነው። ቀና ብሎ የሚሄደውን የመቋቋም አቅሙ ሙት መሬትን የሙጥኝ ስለሚል። በነፃነት ትግሉም በዬነጥብ ጣቢያው አቅምን የሚበላው የዚህ በሽታ ውርስነት ነው። በአጋጣሚው አቅም ያላችሁም – አንድ በሉት። ለነገም ነቀርሳ ስለሆነ። የነፃነት ትግሉ ሰብል ትርጉሙ ከትንሹ ዛሬ መጀመርም አለበት።

ለዚህም ነበር ሄሮድስ መለስ ዜናው ከአርበኝነት ጋር የነበሩ የቦታ ሥሞች ሳይቀር እያደኑ፤ ኢትዮጵዊ ተቋሞቿን – እያሳደዱ፤  ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ክብር እዬረገጡና እዬገፈፉም፤  ማናቸውንም የክብር መግለጫዎቻችን በሙሉ በጥርሳቸው እንዳያዟቸው ማለፍ አይቀርምና – ያለፉት፤ ለእርሳቸው ባንዳዊ መንፈስ ፍሰኃ ሲሉ፤ ያ የክብር – የሞገስ ተክሊል ባላውለታችን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅዓላማችን በሽታቸው ነበር። ለነገሩ – አይመጣጠኑም፤ ከወላጃቸው የወረሱት ባንዳነትን ነበርና። ለመሰሎቻቸውም ቢሆን ዛሬም – ይበጠብጣቸዋል። እንደ ጎደለ እንስራ ውሃ – ያንቦጫቡጫቸዋል። ለአርበኛው ደም ግን ዘውዱ ነው! ነገም ከኢትዮጵያ ህዝብና ከመሬቷ ከደረሰው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማኒፌስቶ በደል ባላነሰ ብሄራዊ ቋሚ ሰንድቅዓላማችን ያሳለፈውን የ24 ዓመት የአፓርታይድ ዬተገላይነት ዘመን አሳር ሊክስለት የሚችለው ፍሬ ነገር ዬአንድ ዬአምክንዮ ዕሴት ብቻ ነው። ይህ ትውልድ ያሸነፈ ፓርቲ ቢያሸንፍ፤ ከንጹህ ተፈጥሮ ላይ ምንም ዓይነት የፍላጎት ነቁጥ እንዲኖርበት መፍቀድ – የለበትም። ከነተፈጥሮው እንዲዘልቅ እሱን ማስቀደም የመንፈሳችን ዓይን ሊሆን ይገባል። ይህ እንደ አንድ ተራ ዜጋ የአደራ ቃሌ ነው። ሰንደቅዓላማችን ይበቃዋል – ተቃጥሏል – ተቃሏል – ታስሯል – ተቀዷል፤ ከረጢት ሆኗል፤ በፍዳ ተቀቅሏል፤  „ቀብረነዋልም“ ብለውናል። የቻሉትን ያህል የቂምና የቋሳ መገበሪያ – አድርገውታል። „በቃን!“ የሰንደቅአላማችን መከራ የነፃነት ትግላችን መሪ መርህም ሊሆን ይገባል። የብሄራዊ ዜግነታችን መለያ የጋራ ጋሻ አሻራ ዓርማችን፤ የሁለንትናችን ቀላማም ውበት – ማራኪነት – ተወዳጅነት – አድማቂነት፤ ሳቢነት፤ ተፈቃሪነት ብቁ ገላጫችን ነውና። ሰንደቅዓላማችን ምራቁን የዋጣ የተረጋጋ ምሩቅ የድል ዋዜማችን – ዝልቅ ቅርሳችን ነው።

እርግጥ ነው። ሥህነ – ቤዛ ከድንኳኑ ሲደርስ ዓርማውን  ፎቶው ላይ እንደምታዩት በእጁ ይዞ ትልሙንም አደራ ሰጥቶ ነው። አሁን ተመስገን ነው። ጊዜና ዘመን የማይሽረው ሰንደቅዓላማችን በእጁ ብቻ ሳይሆን በመንፈሱ የታታመ ሥህነ – ሙሴ ፈጣሪ በሥነ ጥበቡ – ፈጠረ። በቅጡ 17 ዓመት ሳይሞላው ነበር ገና በታዳጊ ወጣትነቱ ሐገሬ ውስጤ፤ ፍላጎትሽ – ፍላጎቴ፤ መንፈስሽ – መንፈሴ፤ ራዕይሽ – ራዕዬ፤ ችግርሽ – ችግሬ በማለት ልዕልቱን በልቡ አስቀምጦ አጋጣሚዎችን ሳያሾልክ ወይንም በአጋጣሚዎች ሳይሾልክ፤ ሁሉንም እንደፈቀደለት በተድሞና በበዛ ታጋሽነት – የታደመበት። መቻልን – በመቻቻል አስጊጦ ኖረበት። በርሃም ቤቱ ነበር። ዱር ገደሉም በአርበኝነት ቤቱ ነበር። ስደትም ጊዜያዊ መጠለያው ነበር። ወደ ሀገሩ ተመልሶ በስብዕዊነት ዙሪያ፤ በነፃነት አኩልነት የዲሞክራሲያዊ ፈለግ ዙሪያ የበኩልን ሙሉ ድርሻ በቅንነት አበርክቷል፤ ችግርን በዬአይነቱ አስተናግዷል። እግር ብረቱንም ቢሆን በስደት በኢህአፓ ሱዳን መሬት ላይ፤ በሀገሩም በህወሓት በማዕከላዊና በቃሊቲ አዲስ አባባ ሁለም እንዳይቀርበት አይቶታል። አብሶ እስር ቤት ሌላ የህይወት ምዕራፍ ነው። ጣፍጭነቱ የህዝብን ፍላጎት ፈቅደህ ለመስዋዕትነት ቤተኝነት ስለሆነ በቁም የመጽደቅ ያህል ነው – ለእኔ።  ሥህነ ቤዛ ሁሉንም የመኖር ዓይነቶች ረሃብን ሳይቀር ኑሮ እንሆ የፋፋ ተግባር አኖረ። ዛሬም ቀን በጠፋን፣  ኢትዮጵያዊው ቀን በዘረኝነትና በጭቆና በተጠፈረበት ጭንቅ ወቅት፣ ለእስርኛው ኢትዮጵያዊነት ለአዲስ ቀን ተስፋ ጥብቅና ቆሞ ዱር ቤቴ አለ። ዋቢ!

የናፍቆት እፍታ።

ሥህነ – ቤዛ እናት ሐገሩን ከምንምና ከማንም በላይ – ይወዳል። ጠረኗ አዘውትሮ – ይናፍቀዋል። ገፆዋ በፍቅር – ይጠራዋል። ውስጧ አሳምሮ – ይመራዋል። መንፈሷ በትህትና  – ይገዛዋል። ወዟ – ይስበዋል። እናቱን — ይናፍቃታል ሽው — ትዝ  ትለዋለች። አልሆንለት ብሎ እንጂ ከእሷ ተለይቶ መኖሩ ባዕዱ ነው። ለዚህም ነው በነበረው ቀዳዳ ወደ እናት ሀገሩ ሁለመናውን ይዞ በቅንነት ለማገልገል – የተመለሰው። ከፍቅሩ ጥልቅነት የተነሳ የተወሰደ፤ ከናፍቆቱ ርህርና የተቀዳ ውሳኔ ነበር። በሙያው ሀገሩን ለመጥቀም አስልቶ ነበር። በዛን ጊዜም  ዬእናቱን ውለታ ለመወጣት ናፍቆቱን ያወራረደው በመሃያ አልነበረም። ፍቅሩን የገለጠበት መንገዱ ከማንኛችም እጅግ በረቀቀ መልኩ በነፃ እልፍኝ ነበር። በሂሳባዊ ስሌት ከእናቴ ጋር እንዴት ተብሎ ብሎ ነበር ትጋቱን – ያስመሰከረው። ይህም ሌላ ወግ ያለው ዘለግ አድርገን ለማዬት ያልፈቀድንለት ንጡር አንጡራ ሚስጢር ነው፤ ለነገ መገኘት፤ ለነገ መዋል፤ ለነገ – ማደር ብቻ ሳይሆን – ለነገ መሰንበት፤ አልፎ ተርፎ ለነገ – ተወዲያም ደልደል ያለ ድልድል ለመሆን – በመፍቀድ፤ የሚገርመው እስከ ዛሬ በአበረከተው መልካም ነገር ሳይዝናና፤ ሳይኩራራ፤ ሳይዝልም አለ እንደአለ። አንዲት ብጣቂ ሽልማት ሳናዘጋጅለት፤ የምስጋና ቀን ሳናዘጋጅለት። እናት ሐገሩን ኢትዮጵያን ጽላቱ እንደ አደረገ – ኖረበት። መታደል ነው። ዘመን የማይሽረው፤ ድንበር ያለወሰነው የእናትና የልጅ ንጡሕ ጡታዊ ሃዲድ፤ እትብታዊ ትስስር በፍቅራዊነት ክህሎት ሲመነዘር እናት ሆዱ ያሰኘዋል። የእትብት ጥሪኝ አንዲህ ረቂቅ ግን ብቁና ብልህ አስተዳዳሪነት ነው። እራሱን በዜግነት ፕሮግራም ወይንም ማኒፌስቶ ለመምራት የቻለ ዘላቂ ተስፋችን መምራት ስለመቻሉ ምስክሩ ተግባሩ ብቻ ነው። ያዬነው ከመሆን ተነስቶ ነው ወደ መሆን ሲሄድ ነው።

ክወና።

አዎን! ሥህነ ቤዛ ከግብዝነት ጋርም የተፋታ ነው፤ በተለያዬ ጊዜ ከሰጣቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች፤ ቃለ ምልልሶች እንዲሁም የስብሰባ ሂደቶች፣ የተረዳሁት ቁም ነገር …  እጅግም አሳንሶ የነፃነት ጎህ ሲቀድ መጸሐፉን “ ይህቺው የኔው ጹሑፍ መውጣቷ … ልክ እንደ ተራ መጣጥፍ ፤ ክቡር አትበሉኝ – በቁጣ፤ ዶር. የሚለው ይበቃኛል – በትህትና ፤ የተለዬ ጸጋ እኔ የለኝም – ዝቅ ባለ ሙሁራዊ ሥነ ምግባር። እኔ በግሌ ይህን አደርኩት የምለው የለም – ከግል ኢጎ ጋር ፍቺ በመፈጸም፤ ከእኔም የተሻሉ ወገኖቼ አሉ – በልዩ ውስጣዊ አክብሮት“  ይለናል። ስለሆነም እንደ ዘመኑ ታዳሚነታችን ያዬነው ወይንም የሰማነውን ወይንም ካነበብነው ያገናዘብነው፤ እሱን የተረጎምንበትን ሆነ ወደ ውስጡ ዘልቀን መክሊቱን ያደመጥነው ነገር ምን ሌላስ ይኖረው ይሆን? ወጣቱ መማር ያለበትን፤ መከተል ያለበትን ትክክለኛ መንገድ ማሳያት ድርሻዬ ነውና በምዕራፍ አራት እንገናኝ ዘንድ – በቀጠሮ። ከስንብት በፊት ግን ትንሽ ቋጠሮ …

በቃኝ! ቤቱን ሠርቶ፤ ጉልቻ – ጎልቶ

ኪዳን – አሰማርቶ፤ መሆንን – አስልቶ፤

ከሥሩ – ተብራርቶ፤ ይሁን – አጎልብቶ

እሺታን – ጠጥቶ፤ አለልኝ – መጥቶ

ድምጽ ለቃል ሰጥቶ፤ መቻልን ገንብቶ

ሰንደቁን አስልቶ፤ ኢትዮጵያዊነትን ከሁሉ – አጉልቶ

ጀግና መንገድ ያዘ አደራን አንግቶ!

ሥጦታ – ለአርበኞቼ። እርእሱ በጉልህ የተጻፈው መጨረሻ ላይ ያለው ነው። ይህ የእኔ መንገድ ነው። 18.08.2015

ዛሬን ባርኮ እንዲህ በማዕዳችን በሃበሻ ቤት ያገናኘን አምላክ ልዑል እግዚአብሄርን አመስግኜ ልሰናበት – ወደድኩኝ። መሸቢያ ሰንበት – የኔዎቹ። ጌጤን ዘሃበሻን – ከውስጤ አመሰገንኩኝ – ኑሩልኝ።

ማሳሰቢያ – አባቱ የእኔ ጀግና ናትናኤልሻ እሺ –  እኔ ሎሌህ ነኝ። በጹሑፎቼ መልእክትህን – እለጥፋለሁ። በራዲዮ ፕሮግራሜም ከበጋ እረፍት በኋላ በድምጽ መልእክትህን ሙሉውን – አስተላልፋለሁ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45527

የብሄራዊ ነፃነት ትግላችን ለህወሓት ብጣቄ መላሾ አያጎበድድም!

ዬነፃነት ትግላችን የብሄራዊ ማንታችን ክብር ጉልህ መግለጫ ቁልፋችን ነው!

የነፃነት ትግሉ መሠረታዊ ዓላማ 90 ሚሊዮን ህዝብ ከህወሓት የባርነት እስር ቤት ማስለቀቅ ነው!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

በአዲስ ዓመት ፍቅር ብንመሰርት –ይገረም አለሙ

$
0
0

ፍቅር ያስታግሳል፣ፍቅር ያስተዛዝናል ፣ፍቅር አያቀናናም፣ፍቅር አያስመካም፣ፍቅር አያስታብይም፤ብቻየን ይድላኝ አየሰኝም፤አያበሳጭም፤ክፉ ነገርን አያሳስብም፤ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል አንጂ ስለ አመጻ ደስ አይለውም ሁሉን ይታገሳል፣ሁሉን ያምናል፣ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣በሁሉ ይጸናል፡፡
( ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 ም13 ቁ.1-7)

ethiopian newyear 2008
ከቁጥር መለወጥ ውጪ አዲስ ዓመት የመባሉ አዲስነት ምንነት የማይታወቅበት የአዲስ አመት መባቻ ላይ አንገኛለን፡፡ በሀገራችን የተለመደ በሆነው ይህን…ልዩ የሚያደርገው በሚለው አነጋገር ካየነው ይህን የአዲስ አመት ጅማሮ ልዩ የሚያደርጉ ሁለት ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው ሀያ አራት አመታት ኢትዮጵያን የገዛው ወያኔ በመቶ ከመቶ አሸናፊነት ለቀጣይ አምስት አመታት አገዛዝ መንግስት የሚመስርትበት ዋዜማ መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው የነጻነት ታጋዮች ወደ ተግባር የተሸጋገሩበት ማግስት መሆኑ ነው፡፡
እንዳንችል የሚያደርጉ ግለሰባዊ ባህሪያቶቻችን አላስችል እያሉን እንጂ ይህን አዲስ ዐመት ልዩ የሚያደርገው የሚያስብል ከላይ ከተጠቀሱት ከሁለቱም የሚልቅና የሚበጅ ነገር ማከናወን እንችል ነበር፡አለመታደላች ይሆን ወይንም እንደሚባለው ርግማ ኖሮብን ማድረግ እየቻልን ባለመቻላችን ብዙዎች በጥቂቶች ለመገዛታችን እኛው ምክንያት ሆነን እንገኛለን፡፡

አነርሱ የአገዛዝ ዘመናቸውን በመቶ ከመቶ ውጤት አድርሰው ለአምስት አመታት እየተዘጋጁ ለሀያና ሰላሳ አመትም ሊገዙን እያሰቡ ናቸው፡፡ እኛ ደግሞ አገዛዙን ለማውገዝ ለመርገም አንድ ሆነን ከምናወግዘው አገዛዝ ለመላቀቅ ለሚያስችለው ትግል ግን አንድ ሆነን መቆም ተስኖናል፡፡ ይህ ደግሞ ዛሬ የጀመረ ሳይሆን በየዘመናቱ የነበረ የማያረጅ የማይለወጥ የራሳችን ጠላት ራሳችን እንድንሆን ያደረገን መጥፎ በሽታ ነው፡፡
ታዲያ ከዚህ በሽታ የመዳኛችንን መድሀኒት ብናገኘው ይህን የአዲስ አመት መባቻ ከልዩም ልዩ አያደርገውም ነበር ትላላችሁ! ከራስ በላይ ለሀገር ማሰብ በመጥፋቱ፣ በቃል የሚናሩትን በተግባር ሆኖ መገኘት አለመቻሉ፣ ከህዝብ ነጻነት ይልቅ የራስን ጥቅም ማስቀደሙ ወዘተ ግድግዳ ሆኖ አላገናኝ ማለቱ እንጂ ጉዳዩ የማይቻል ከባድ ነገር ሆኖ አይደለም፡፡ የበርሊንም ግንብ ፈርሷል፡፡

እስቲ ይታያችሁ፣ደግሞም ይቆጭ ያንገብግባችሁ፣በኢትጵያዊነታችን አንድ ነን፣ ወያኔ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ መወገድ ያለበት ዘረኛና አንባገነን አገዛዝ በመሆኑ ላይ ልዩነት የለንም፡፡ ኢትዮጵያ የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤት ነገር ግን የዴሞክራሲ ባይተዋር መሆኗ አብቅቶ የህግ ልዕልና የተረጋገጠባት፣ ሰብአዊ መብት የተከበረባት ልጆቿ በሰላም፣ በፍቅር፣ በእኩልነትና በነጻነት የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር እንድትሆን በመመኘትም ልዩነት ያለን አይመስለኝም፡፡ታዲያ እነርሱ ጥቂቶቹ ህውሀቶች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ የአገዛዝ ዘመናቸውን ለማራዘም አንድ ሆነው በአንድ ተሰልፈው የበደል ናዳ ሲያወርዱብን እኛ ኢትዮጵያውያን ናዳውን ለመመከትና የአገዛዝ ዘመናችንን ለማሳጠር አንድ ሆነን የማንቆምበት፣ በአንድ ተሰልፈን የማንታገልበት ምክንያት ምን ይሆን፡፡ እንዳይቻል ያደረግነው እኛው ራሳችን ነን እንጂ ይቻላል፡፡ጥቂቶች በአንድነትና በጽናት ቆመው ሲገዙን እኛ ብዙ ሆነን በጽናት ጉድለትና አንድነት በማጣት ሀያ አራት አመታት መገዛታችን አያስቆጭም፡ውጤት አልባ የእድሜ ልክ ተቀዋሚነትስ አያሳፍርም፣አረ በቃ እንበል፡፡ ካልን ደግሞ ወንድም እህቶቻችን እየከፈሉት ካለው መስዋዕትነት አንጻር ይህ ብዙም የሚባል አይሆንምና አሁኑኑ በአዲስ አመት ዋዜማ ተግባራዊ እናድርገው፡፡

በሀገራችን ባህል/ልማድ በተለይ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በከተማም ከጥንቱ ባህል ጨርሶ ባልተለያዩት ዘንድ በአዲስ አመት መግቢያ የቅዱስ ዮሐንስ እለት ችቦ ተለኩሶ ከቤት ሲወጣ ከቤቱ በር ግራና ቀኝ እየተተረኮሰ የጎመን ምንቸት ውጣ የገንፎ ምንቸት ግባ ይባላል፡፡ ይህ መልእክቱ ግልጽ ነውና ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡

እኛስ አገዛዝ በቃ የምንል ኢትዮጵያውያን በያለንበት ችቦ ለኩሰን አንደ ባህል ወጉ እየተረኮስን ባይሆንም በዚህ የዘመን መለወጫ እለት የድምጻዊት አስቴር አወቀን አንድ አድርገን ጌታ የሚለውን ዘፈን እያንጎራጎርን የጥል ምንቸት ውጣ የፍቅር ምንቸት ግባ፣ የበቀል ምንቸት ውጣ የይቅርታ ምንቸት ግባ፣ የጥርጣሬ የሸፍጥና የሴራ ምንቸት ውጣ፣ የመተማመን የቀናነትና የግልጽነት ምንቸት ግባ የማቃር ምንቸት ውጣ የመግባባት ምንቸት ግባ ወዘተ ማለት ብንችል ምንኛ መታደል ነበር፡፡

ለሀገር ይበጃሉ የተባሉ ያልተነገሩ ያልተጻፉ ነሮች የሉም ተግባራዊነት የለም እንጂ፡፡ ሌላው ቀርቶ በተቃውሞው ጎራ የነበሩና ያሉ ከተናገሩትና ከጻፉት ከፊሉን እንኳን ተግባራዊ ማድረግ ችለው ቢሆን ሀገራችን ዛሬ ካለችበት በብዙ መልኩ የተለወጠች ለመሆን በቻለች ነበር፡፡ እናም ከላይ የገለጽኩትን ለማለት መድፈሩ የመጀመሪያ ርምጃ ሆኖ ያሉትን ለመፈጸም መቻል ደግሞ ዋናውና ወሳኙ ጉዳይ ይሆናል፡፡ የምንለውን ተፈጻሚ ለማድረግ ለቃል የመታምን፣ ለህሊና የመገዛትና ከራስ በላይ የማሰብ ቁርጠኝነቱ ካለ 2008ን ለአስተማማኝ ለውጥ የሚያበቃንን ጠንካራ መሰረት የምንጥልበት አመት ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህን ማድረግ ቻልን ማለት ደግሞ ለለውጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ትውልድ ተሻጋሪ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት የሚያበቃንን ጥርጊያ ጎዳና ተያያዝነው ማለት ነበር፡፡ ለሀገርና ለትውልድ ማሰብ ካለ ይህ የማይቻልም የሚገድም አይደለም፡፡ ይቻላል!
ዛሬም እንደ ትናንቱ ወያኔን በማውገዝ አንድ ሆነን ከወያኔ አገዛዝ ለመላቀቅ ግን በየሰበብ ምክንያቱ አንድ ሆነን መቆም ካልቻልን የነጻነቱን ቀን እናራዝመዋልን፡፡ ነገር ግን ዘላለማዊ ምድራዊ ሥልጣን የለምና አንድ ቀን ወያኔና የምንይልክ ቤተ መንግሥት መለያየታቸው አይቀርም፡፡ የሚቻለው እንዳይቻል እንቅፋት ሆነን መስዋእትነቱ እንዲከብድና የወያኔ አገዛዝ ዘመን እንዲራዘም ያደረግን ወገኖች ያኔ ታሪክ ይመሰክርብናል ትውልድም ይፈርድብናል፡፡

በአንድ ሀገር ልጅነት መንፈስ ለጋራ ሀገራችን እንዳንቆም የሚያደርጉንን ሳንካዎች ከውስጣችን አስወጥተን የሀሳብ ልዩነት ያለ፣የሚኖር፣ሊጠፋም የማይችል መሆኑን ተገንዝበን አንድነታችንን አጠንክረን በልዩነቶቻችን ተከባብረን መተማመን፣ ፍቅርና አንድነት በመፍጠር ከወያኔ አገዛዝ ለመላቀቅ የሚያስችለንን መንገድ ለመያዝ ዋናው ቁልፍ መነጋገር መቻል ነው፡፡መቀራረብ መደማመጥ፤

የቱንም ያህል ስንቆፍር ውለን ስንቆፍር ብናድር የሚያለያዩን ጉዳዮች አንድ ከሚያደርጉን በዝተውም ልቀውም ሊገኙ አይችሉም፡፡ እንደውም በሀቅና በንጹህ ህሊና በንጽጽር ከተፈተሸ የሚያለያዩን ሚዛን የማይደፉ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ገነውና ጎልተው ማዶና ማዶ እንድንቆም ለማድረግ የሚያስችል አቅም ያገኙት ከእኔ በላይ የሚል አጋንንት ሰፍሮብን የመነጋገር ፈቃደኝነት፣ የመወያየት ባህል፤ የመደማመጥ ትእግሰት ያሳጣን በመሆናችን ነው፡፡ እናም በዚህ አዲስ አመት ዋዜማ ይህን አጋንንት እናስወጣና የፍቅርን አምላክ ወደ ውስጣችን እናስገባ፡፡


ከመድፍ ድምጽ አይሎ የተሰማ የጽናት ቃል (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

$
0
0

birhanu tekleከመድፍ ድምጽ ያየለ፣ ጽናትን፣ እምነትንና ጥንካሬን የሚያሳይ ታላቅ ድምጽ በመዲናችን ተሰማ። ማንም ቀስቃሽ ከሚያደርገው ጥሪ በላይ የክተት አዋጅ የመሰለ የእምነት ቃል ፈጽሞ ሊሆን ይችላል ተብሎ ከማይጠበቅበት አቅጣጫ ተሰማ! አዎ ለፍልሚያው ቆርጫለሁ እናንተን ከመንበረ ሥልጣኑ ለማንሳት በኔ አቅም ያለውን ሁሉ ለማድረግ ጉዞ ጀምሬአለሁ። በአካል ከስፍራው አልደረስኩም እንጂ በመንፈስ ሸፍቻለሁ ይህንን አምናለሁ ግን ግን ፈጽሞ ጥፋተኛ አይደለሁም! አሁንም ባለሁበት ሁኔታና ካለሁበት ለመታገል ከቶውንም ወደሗላ አልልም!

በእርግጥም ከነጎድጓድ ያየለ ከመድፍ ድምጽ አስርሺህ ጊዜ የበለጠ ሃያል ድምጽ በ‘አንበርካኪዎቹ’ ማማ ላይ በ‘አስጎንባሾቹ’ መድረክ ላይ ተሰማ። ኢትዮጵያ ያልታደለ ሕዝብ የሚኖርባት ግን የታደለች ሀገር ናት። አፈርና ውሀዋ የሰራው ዜጋዋ ከአየሩ ጋር አብሮ ከሚተነፍሰው የነፃነት መንፈስ ጋር ተዳምሮ ከዘመን ዘመን በኩራት እንዲረማመድ ሆኖ የተሰራ ነው። ለዚህም ነበር የጥቁር አፍሪካ ፈርጥ ለነፃነት ፈላጊዎች የመንፈስ ምርኩዝ ተብሎ የሚጠራው። ግና የእናት ሆድ ዥጉርጉር እንዲሉ ባርነትን የተከተቡ፣ ጥላቻ የተጠናወታቸው በአእምሮ ድህነት የሚሰቃዩ ከዚችው ኢትዮጵያ የተፈጠሩ የሰው አረሞች ቁልቁል ደፍቀው እምነትና ነፃነቱን ክፉኛ ፈትነውታል። አወቅን ባይ የትምክህት ባሮች እንቅፋት እየሆኑት በጠላት ወጥመድ ውስጥም እየጣሉት ከችግር ወደመከራ ከበረዶ ወደ እሳት የሚገላበጥበትን ገሃነማዊ ህይወት እንዲመራ አድርገውታል። የትግራይ ጎጠኞች ተስፋውን ያሟጠጠ እንዳሻን የምናደርገው ፈሪ ሕዝብ ፈጥረናል በሚሉበት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ አለንልሽ የሚሏት ለክብሯ ለነፃነቷ ሊሞቱላት የቆርጡ ጀግኖች ወደ ትግል ሜዳ ሲተሙ፣ በያሉበት ስንደቅዓላማዋን ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ ለተመለከተ ግን እውነትም የታደለች አገር! እንዲል ያስገድደዋል።

ይህ ያበቃለት የመሰለው የራሱ ወገኖች ደካማና ፈሪ አድርገው የሚስሉት ሕዝብ ጀግንነትና ቆራጥነት በደሙ ውስጥ መመላለሱን የሚያረጋግጥና ያለነፃነት ከመኖር ማናቸውንም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ግን ዕለት በዕለት እያስመሰከረ ነው። በየአደባባዩ፣ በየጉድባውና ሰርጣ ሰርጡ ጣዕረሞት ከመሰሉት የሀገርና የሕዝብ ጠላቶች ጋር ለመፋለም መቁረጣቸውን የሰማ ሁሉ ተስፋ በውስጡ እያበበች ነው። በርገር በሊታዎቹ ቂጣ ለመብላት የተዘጋጀ ስነልቦና እንዳላቸው አስመስክረዋል። ስሜታቸው ብቻ ሳይሆን አጥንታቸው የሟሟ የሚመስል በወያኔ እስር ውስጥ ተጠፍረው ያሉ ከአሳሪዎቻቸው ገዝፈውና ታላቅ ሆነው ደካሞቹን ቁልቁል ሲመለከቱ ማየትም ያለውን እምቅ ሃይል አመላካች ነው። የርዕዮት ብዕር ወረቀት ማድማቱን ማየት ስሜት የሚያሞቅ ነው። እነ አብርሃ ደስታ ቁም ነገር ሊከትቡ ወደ ትልቁ እስር ቤት መመለሳቸው እነ ሃብታሙ ‘እመነኝ!’ ሲሉ እንደገና ልንሰማ መሆኑን ማሰብ ደስ ያሰኛል።

በሌላ ወገን ወያኔ የተማመነበት ሰራዊት ኢትዮጵያዊነቱ በልጦበት እየከዳ ነው። መሳርያውንም ወደ አገር አፍራሽ ጎጠኞች እንደሚያዞር ምልክቶቹ ሁሉ እየታዩ ነው። ስማቸውን ያልሰማን ማንነታቸውን ያላወቅን ለጊዜው ማወቅም የማይገባን በርካታ ጀግኖች በዚህ የትግል መስመር ገብተው ለፍልሚያ ስለመዘጋጀታቸው ከቶወንም ጥርጣሬ የለንም። የሰላም በር ሲዘጋ የፍልሚያ መስኮቶች ይበረገዳሉና በየአቅጣጫው መነሳሳትን ማየታችንም ለዚሁ ነው። ከተሞች ሁሉ የትግል አምባ ወደመሆንና ጎጠኞችንና የሀገር ጠላቶችን በህግም በትጥቅም ቢሆን ለመፋለም ዝግጁነታቸውን እያረጋገጡ ነው። ፍርሃት ያራዳቸው የወያኔ ጉልተኞች ብር በሻንጣ ይዞ መሮጥ መጀመራቸውም የዚሁ አይነተኛ የውድቀት ምልክት ነው።

ወደ ጀመርኩት ርዕስ ልመለስና የነብርሃኑ ተክለያሬድን ዜና እንደሰማሁ ኢካድፍ የለጠፈውን ምስል ተመለከትኩ ሰውነት የሚወር ስሜት ተሰማኝ በወጣቶች ያለኝ ጽኑ እምነት ታደሰ። ኢየሩሳሌምን በስስት ዐይን ተመለከትኩ፣ የጀግና ክብር የሚገባት የጣይቱ ልጅ በሰላሙም ጎዳና ሁሉን ችላ በፅናት የሄደችበት ጀግናዬ ናት። ሽንታም እያሉ ለሚሳደቡት እንደኛ ለመሆን የጫካውን መንገድ ሞክሩ ለሚሉና ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሆነው ኢትዮጵያን ወግተው በፈረንጅና በተጃጃሉ ኢትዮጵያውያን ትከሻ ስልጣን ላይ የወጡትን እብሪተኞች ለመፋለም ጉዞውን የጀመሩትን ጀግኖች አንኳን እኔ ጠላትም እንዲያደንቃቸውና እንዲያከብራቸው ግድ ይለዋል። መድረኩን አገኙ ቃላቸውን ሰጡ። ቃላቸው ግን ድፍን የኢትዮጵያ ወጣቶችን የሚያስሸፍት እንዲሆን ቅንጣት ታክል አልጠራጠርም።

ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ኢየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ ዳሴ ካሳሁን ክብር ለናንተ ይሁን። ካሰባችሁበት ያልደረሳችሁ መስሏችህ ከሆነ አትሳሳቱ ማናችንም ከምናሰበው በላይ ግዳጃችሁን ተወጥታችሗል። መድረስ ብቻ አይደለም አልፋችሁ ሄዳችሗል። ከጠላት ምሽግ ገብቶ የጨበጣ ውጊያ ከመግጠም በላይ የእምነት ቃላችሁ ስራውን ሰርቷል። በዚህ በርካቶች አንገት በደፉበት ሰዐት፣ በርካቶች በሌሎች ትከሻ መሸጋገርን በሚሹበት ጊዜ እናንተ ድልድይም መስዋዕትም ሆናችሁ ለታሪክ የሚተርፍ ገድል ፈጽማችሗል። አዎ ጥፋተኛ ሳትሆኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግኖቹ ናችሁና ደስ ይበላችሁ። ፈለጋችሁን የሚከተሉ በረሃ የሚዘልቁም ሆነ ባሉበት ሆነው በተጠንቀቅ የሚጠብቁ በርካቶችን በማነሳሳታችሁ ክብር ለእናንተ ይሁን።

ኢትዮጵያ በነፃነትና በክብር ለዘለዐለም ትኑር!

ኢሕአዴግ ራሱን ይመልከት! ጋዜጣው ሪፖርተር ርዕሰ አንቀጽ

$
0
0

በጋዜጣው ሪፖርተር

85e2b2dbb35ca49ffb94675c848f9135_Lኢሕአዴግ አሥረኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ በመጪው መስከረም ወር አራተኛ ሳምንት ላይ ደግሞ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አገሪቱን ለመምራት የሚያስችለውን ፓርላማ ሥራ ያስጀምራል፡፡

ላለፉት 24 ዓመታት አገሪቱን በማስተዳደር ላይ ያለው ኢሕአዴግ አሁን ቆም ብሎ በአንክሮ ራሱን መገምገም አለበት፡፡ ውስጡን አብጠርጥሮ መፈተሽ አለበት፡፡ የተሸከማቸውን ጉድፎች አራግፎ በሥርዓት አገር ማስተዳደር አለበት፡፡ በስኬቶቹ የሚመፃደቀው ኢሕአዴግ በጣም በርካታ ጉድለቶች ስላሉት መፍትሔ ያስፈልገዋል፡፡ ኢሕአዴግ ራሱን ያጥራ! ራሱን ይመልከት!

ኢሕአዴግ በአሥረኛው ድርጅታዊ ጉባዔው የመጀመሪያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም፣ ሁለተኛውን ዕቅድ አጠናክሮ ለመቀጠል ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባለፉት 12 ዓመታት በኢሕአዴግ አመራር የተመዘገበውን ዕድገት ለማስቀጠል፣ ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ለውጥና ትራንስፎርሜሽን ቀጣዩ ትኩረት እንደሚሆንም እንዲሁ ትልቅ ግምት የተሰጠው አጀንዳ ነው፡፡ ይህ ለአገር ጠቃሚ በመሆኑ ድጋፍ ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን ዕድገቱም ሆነ ትራንስፎርሜሽኑ ሰው ሰው ካልሸተተ፣ የዜጎችን መሠረታዊ መብቶች ካላከተተ፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ካልተመቸ፣ የሕዝቡን የነቃና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ተሳትፎ ካላረጋገጠ፣ ሙስናን ከሥሩ መንግሎ ካልጣለ፣ ፀረ ዴሞክራሲ ተግባራትን ካላስወገደ፣ ሕገወጥ ተግባራትን ካላጠፋ፣ ወዘተ ልፋቱ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡

አንድ አገር ሰላሟና ብልፅግናዋ ዘላቂና አስተማማኝ የሚሆነው የሕግ የበላይነት በተግባር ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ዜጎች በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውን ሲያምኑ፣ ሕግም ለሁሉም ዜጎች እኩል ጥበቃ ሲያደርግ፣ ፍትሕ ለሁሉም ተደራሽ ሲሆንና የፍትሕ ሥርዓቱ በነፃነት ሲንቀሳቀስ የሕግ የበላይነት መኖሩ ይረጋገጣል፡፡ ‹‹አንድን ንፁኅ ዜጋ ከማሰር ይልቅ አንድ ሺሕ ዜጎችን መፍታት የተሻለ ነው›› የማለው የሕግ ጽንሰ ሐሳብ በአንድ አገር ውስጥ ተግባራዊ ሲደረግ፣ ዜጎች በነፃነት በአገራቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ውስጥ በንቃት ይሳተፋሉ፡፡ ነገር ግን በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ሰበብ እየተፈለገላቸው በሚከሰሱና በሚታሰሩ ዜጎች ምክንያት አገራችን ውስጥ በፍትሕ ላይ መተማመን ጠፍቷል፡፡ ኢሕአዴግ ይኼ ካላሳሰበው ሌላ ምን ያሳስበዋል? ሰዎች ያለጥፋታቸው ታስረው የቀረበባቸው ክስ የማያወላዳ በመሆኑ በነፃ ሲሰናበቱ አሁን መታየት ጀምሯል፡፡ የአንዳንዶችም ክስ ሲቋረጥም ተስተውሏል፡፡ ከመነሻው እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ተግባር ለምን ይፈጠራል? የፍትሕ ሥርዓቱስ ለምን ይሳጣል? ለሕግ የበላይነት ለምን ቅድሚያ አይሰጥም? ብዙ ማለት ይቻላል፡፡

ዜጎች በገዛ አገራቸው ሰብዓዊ መብታቸው ሲጣስ ዝም ይባላል፡፡ በአመለካከታቸው ምክንያት መደብደብ፣ መታሰር፣ መንገላታት፣ ከሥራ መባረር፣ የቤተሰብ መበተን፣ ወዘተ ሲደርስባቸውና ጩኸቱ ሲበረክት በተደጋጋሚ ተሰምቷል፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላቶቻቸው እንደተገደሉባቸው በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡ በታዳጊ ዴሞክራሲ ውስጥ የሚያጋጥም ነው እየተባለ ዜጎች በገዛ አገራቸው ሲሰቃዩ እስከ መቼ ይቀጥላል? የመልካም አስተዳደር እጦት ምሬት ከዳር እስከ ዳር ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ሥራ መሥራት ያቃታቸው ሹማምንት የተመደቡበት ኃላፊነታቸውን መወጣት ሳይችሉ በመቅረታቸውና ለአገር ደንታ የሌላቸው ሹማምንት የግል ጥቅማቸውን እያሳደዱ ሕዝብ ሲያስለቅሱ ዝምታው ምንድነው? ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ እነዚህን ችግሮች መፍታት ያቃተው ለምንድነው? ችግሮቹስ ለምን ይድበሰበሳሉ? በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡

የዴሞክራቲክ ተቋማት አለመጠናከርና በፍርኃት ቆፈን መያዝ፣ የሲቪል ማኅበረሰቡ ደብዛው መጥፋት፣ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱ ደብዝዞ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት መንገሥ፣ የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ሕግ የማውጣትና አስፈጻሚውን የመቆጣጠር አቅም አለመጠንከር፣ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያሉ መገናኛ ብዙኃን የገዥው ፓርቲ ብቻ አገልጋዮች መሆን፣ የግሉ ሚዲያ መፍረክረክ፣ ወዘተ ግልጽነትና ተጠያቂነትን እያጠፋ ነው፡፡ በየቦታው ትንንሽ አምባገነኖች እየተፈለፈሉ ነው፡፡ ለአገር አደጋ ነው፡፡

ሙሰኞች የአገር ሀብት እየዘረፉ ሲከብሩ ዞር ብሎ የሚያያቸው የለም፡፡ ጭራሽ በድርጅት አባልነት ከለላ፣ በሹማምንት ትውውቅና ኔትወርክ ዕውቅና የተሰጠው ሙስና ግለሰቦችን በቀናት ውስጥ ሚሊየነር ሲያደርግ ዝም ይባላል፡፡ የፀረ ሙስና ትግሉ የለም እንዳይባል ያህል እዚህም እዚያም በአለፍ ገደም አንዳንድ የሚጠየቁ ግለሰቦች ቢኖሩም፣ ሙስና የሥርዓቱ መግለጫ እስኪመስል ከተራ ዜጋ እስከ ውጭ ኢንቨስተር ድረስ የምሬት ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ በሕገወጥ የመሬት ወረራ፣ በሕንፃ ግንባታና ዕድሳት ፈቃድ፣ በወጪና ገቢ ንግድ የጉምሩክ ኬላዎች፣ በአገር ውስጥ ገቢ፣ በአነስተኛና በትልልቅ ግዢዎችና ጨረታ፣ በንግድ ፈቃድ ምዝገባና በብቃት ማረጋገጫ፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጀት ምዝበራ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርፊያ፣ በኤሌክትሪክ፣ በውኃና በስልክ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎች፣ በመንገድ ግንባታዎችና በመሳሰሉት አገሪቱንም ሕዝቡንም ራቁታቸውን የሚያስቀሩ የሙስና ተግባራት እየተፈጸሙ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ሆይ የት ይሆን ያለኸው? አባላትህና ደጋፊዎችህ ምን እያደረጉ ነው? የምዝበራው ተሳታፊ ወይስ የዳር ተመልካች? ይኼም በደንብ ይፈተሽ፡፡ ራስህን ተመልከት፡

አገሪቱ ከነበረችበት የድህነት አረንቋ ውስጥ ለማውጣት የሚደረገውን ጥረት ሕዝቡ መስዋዕትነት እየከፈለበት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሕዝብ አሁንም በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተመታ ነው፡፡ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች በየቀኑ ዋጋቸው እየጨመረ ኑሮን መቋቋም ተስኖታል፡፡ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ ከአቅም በላይ እየሆነበት ነው፡፡ የቤት ኪራይ ክፍያ ከሚቋቋመው በላይ ነው፡፡ በትራንስፖርት እጦት በፀሐይና በዝናብ ይንገላታል፡፡ ፈረቃ በይፋ ያልታወጀላቸው ኤሌክትሪክና ውኃ ለቀናት እየጠፉበት ይሰቃያል፡፡ ይህንን ሁሉ ጫና ተቋቁሞ አገሩን የሚገነባ ሕዝብ እንዴት ነው ድጋፍ ማግኘት ያለበት? በስሙ በድጎማ የሚመጡትን ዘይትና ስንዴ በጥቅም የተሳሰሩ ሌቦችና ደላሎች አየር በአየር ይሸጡበታል፡፡ የግብይት ሥርዓቱ እጅግ በጣም ኋላቀርና ተቆጣጣሪ የሌለው ከመሆኑ የተነሳ ሕዝቡን በቁሙ እየገደለው ነው፡፡ ኢሕአዴግ እስከ መቼ ጆሮ ዳባ ልበስ ይላል? አስቸኳይ መፍትሔ ያስፈልጋል፡፡ ኢሕአዴግ ራሱን ይመልከት፡፡

ዜጎች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችም ሆነ በተለያዩ መንገዶች የሚያቀርቡዋቸው አቤቱታዎችና ብሶቶች አይደመጡም፡፡ ቅሬታዎች በአግባቡ አይስተናገዱም፡፡ ችግሮች ሲፈጠሩ ጥድፊያው ለማድበስበስ እንጂ መፍትሔ ለመፈለግ አይደለም፡፡ ኢሕአዴግ ስኬቱን እያወደሱ የሚያሞካሹትን ጆሮውን ሰጥቶ የሚያዳምጠውን ያህል ለምን ተቃውሞዎችን፣ ምክሮችንና ቅሬታዎችን ለማዳመጥ አይተጋም? በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ከነአጋሮቹ ያገኘው መቶ በመቶ የፓርላማ መቀመጫዎችን እንጂ፣ መቶ በመቶ የሕዝቡን ይሁንታ አይደለም፡፡ ካገኘው የሕዝብ ድጋፍ ጋር ባይወዳደርም የማይናቅ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ይቃወሙታል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ኢሕአዴግ በውስጡ ከሕግ በላይ የሆኑ ግለሰቦችን በመያዙ፣ አድርባዮችና ሌቦችን በማቀፉ፣ ፀረ ዴሞክራሲና አምባገነን በህሪያት ይንፀባረቁበታል በሚል ነው፡፡ ይኼም በተደጋጋሚ ተተችቶበታል፡፡ አገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት የሚያገለግሉ እየተገፉና ዕድገት እየተከለከሉ ወረበሎች አገር እየበደሉ ነው፡፡ ኢሕአዴግንም እያስተቹት ነው፡፡ ይኼም መፍትሔ ይፈልጋል፡፡

ኢሕአዴግ አሥረኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ ሲያካሂድ ወሳኝ የሆነ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጨክኖ መወሰን አለበት፡፡ ፀረ ዴሞክራቲክ ተግባራት ይወገዱ፡፡ የተዘጋጋው የፖለቲካ ምኅዳር ይከፈት፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት ይንቀሳቀሱ፡፡ ጦር አንስተው የሚፎክሩ ኃይሎች ሳይቀሩ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግሉ እንዲመለሱ ሁኔታዎች ይመቻቹ፡፡ ሰብዓዊ መብቶች ይከበሩ፡፡ ኢትዮጵያ ማንም እየተነሳ የሚፈነጭባት አገር እንዳትሆን የሕግ የበላይነት በተግባር ይረጋገጥ፡፡ ሙሰኞችና ሌቦች ለሕግ ይቅረቡ፡፡ ብቃት የሌላቸው ይሰናበቱ፡፡ አቅም ያላቸው ለሹመት ይታጩ፡፡ ሕዝቡን ደስ የሚያሰኙ ተግባራት ይከናወኑ፡፡ አስመሳዮችና አድርባዮች ይወገዱ፡፡ ኢትዮጵያ የሰላም፣ የነፃነትና የብልፅግና አገር ትሁን፡፡ ኢሕአዴግም ራሱን ይመልከት!

Source:: Ethiopian Reporter

 

የተቃጠለ ካርቦን ነው ዬጥገና (Reform) ህልመኛነት መንፈስ (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 24.082015 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ጤና ይስጥልኝ እንዴትናችሁ ወገኖቼ። ከተለመደው ጊዜዬ ቀድሜ መምጣት ግድ አለኝ። ይህ የጥገና ወይንም የማሻሻያ Reform ለውጥ ህለመኝነት ከዚሕው ከቤቴ ከዘሃበሻ ተለጥፎ ማዬቴ ስላልተመቸኝ ነው ባልተራራቀ ቀን ብቅ ያልኩት።

reformዬወያኔ ሃርነት ትግራይ የታዛ ዕድሜ ለማኞች አዲስ ውሃ ያልነካው ወጀብ Reform ጥገናዊ ለውጥ አምላኪነትን ይዘው ከች ብለዋል። ትችቱም ከአንጀት ጠብ አይልም።ይህ ቅብ ወቀሳ የተለመደ ነው። እንዲህ መሰል የደካማቸው መንፈሶች እሳት መጫሪያ አጀንዳ አዘጋጅተው በዬጊዜው ነውጥ ፈጥረው የብሄራዊ ነፃነት ትግሉን አቅም ሲበሉ – ኖረዋል። አሁን ብሄራዊ ዬነፃነት ትግላችን በቆራጥ አርበኞቻችን ዱር ቤቴነት አብነት የመሠረቱ ፍላጎት መደላደል፤ ፍጹም ከማይችሉት ደረጃ ሲደርስ ደግሞ አዲስ ቅጥል ተስፈኝነት እያቆለማጡ ይገኛሉ – ይሄኛው እንዲህ እንዲያ ቢሆን ይሉናል። ይህን መሰሉን ዝል መንፈስ ተመገብው ደግሞ ያው የምናውቃቸው መደበኛ ሱቅ በደረቴያቸውን ከፍተው የሃሳብ ችርቻሮ – ይጀመራሉ። ቢገለባበጡም እነሱው ናቸው።

የአሜሪካው ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም በአዳዲስ አጀንዳዎች ዙሪያ በማር የተለወሱ መርዞችን ሰፋፊ ጊዜ እዬሰጠ አና ብሎ ተያይዞታል። ሰሞኑን ደግሞ የጠቅላይ ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንቆቅልሽ – ምን አውቅልሽ ገባጣም አስደመጠን፤ ያው በአንድ ምዕራፍ ከፌስቡክ ደንበኛው ከዶር. ቴወድርስ አድሃኖም አንካሳ መንፈስ ጋር በአንድ ካሊም የሚጠቃለል ነው። መቼም ጠ/ሚሩ መደባቸው የትኛውን ህበረተስብ እንደሚውክሉ ግራ ነው። ስለ አብሮነት ስለ ዘውገ ተከል አስተዳደር ጠንቅነት እዬሰበኩን ነው። የዞረባቸው። ሥልጣኑን የሰጣቸው እኮ ይሄው ዘውገ መራሽ ማንፌስቶ መሆኑን ሙልጭ አድርገው – እረስተውታል። ይህን እንዲያስፈጽሙ እኮ ነው የተሾሙት። …. „ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮኃል።“ ለነገሩ ከጤናቸው ጋር ስለመሆናቸው እጅግ – እጠራጠራለሁ። ነጋ መሼ ዝብርቅርቅ ባለ ግፋፎ – የጉሸ መንፈስ ላይና ታች ሲባዝኑ፤ በግድፈት ተንጠው ሲነዝሩ – ሲወድቁ፤ እላፊም ሲሄዱ ነው የሚታዩት …. ቢያንስ መካሪ የትዳር አጋርም የላቸውም እስኪያሰኝ ድረስ። እንጃ የሚያነቡትን ነገር ጋርም የሚተዋወቁ – አይመስለኝም። እውር ድንብሱን እኮ ነው የሚራመዱት። ቅጥ – አንብሩ ጠፍቶባቸዋል። ወረቀቱም ፈርዶበት በውልቅልቅ ፍላጎቶች ታጭቆ ተነበብ – ይባላል።

በሌላ በኩል የህግ ከፍተኛ ባለሙያው ከሆኑት ከተከበሩ ዶር. አበራ ደገፉም ስለ ህግ አፈጻጻም፤ ሥርዕተ ህገ መንግሥቱ ሞቶ ከተቀበረ ከስንት ዓመት በኋላ ሙያዊ የበቃ ትንተና ሲሰጡ እያዳምጥን ነው።  እኔ እንዲያውም ካነሱት ላይቀር በአዲስ አበባ ዩንቨርሰቲ የህግ ፋክሊቲ ስለሚባለው ለምን አይዘጉትም ስል ነበር – በግሌ። ፍትህ ለመቅበር ወጣቶችን ማስልጠን፣ መዋለ ንዋይ ማፈሰስ የሚያስፈልግ ስለማይመስለኝ። ጥቁሩን የክብር ልብስ ለመልበስ ከሆነ ምኞተኛው በግሉ አሰፍቶ መልበስ ይችላል። ሙያው ከተፈጥሮው ወጥቶ በዝርዝር የአፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ያተኮረ፤ ባለቤት የሌላው፣ ጎዳና አደር ከሆነ እኮ ዓመታት ተቆጠሩ። ለመሆኑ አሁን ነው የሚታያቸው የህግ ሥርዓት በኢትዮጵያ ከአፈር በታች መሆኑ ወይንስ አልኩ ለማለት ነው?! መጀመሪያ ከዛው ከዩንቨርስቲው ካለአግባብ የሚፈጸሙ ህገ ወጥ የመምህራንና የተማሪዎችን የመብት ጥሰትን የመከላከል፣ የማስቆም አቅም ይኑረው የህግ ፋክልቲ – ተብዬው። በዩነቨርስቲው ቅጽር ግቢ በአስተዳደሩ ከህግ በላይ ያሉትን የህወሓት ካድሬዎችን መልክ ለማስያዝ ኩስሙን አቅሙን ያነጋግር፤ ይህቺን ለማድረግ ያልቻለ የህግ ሙያተኛ ለእኔ የሚፈጥራቸው አዲስ የህግ ሰልጣኞች ለገቢ ማስገኛ ስምሪት በጥቃቅን ሸቀጦች ተደራጅተው ለጉሮሯቸው ከማደር በስተቀር ከሙያው ሥነ – ምግባር ጋር ፍቺ ከተፈጸመ እኮ ከ20ዎቹ ዓመታት በላይ ተቆጠረ። የተኛ ነገር ነው በሁሉም ዘርፍ የሚታዬው፤ በቅድሚያ እስኪ ከራሱ ይነሳ ….. እራሱን በግልጽ ወቅሶና ገምግሞ አለሠራኝም ካለው የሙያ አካዳሚያዊ ነፃነት አፈና ጋር ፊት ለፊት ተሟግቶ „በቃኝን“ በተግባር ያስጊጥ። ይህ ነበር ግንባር ቀደም ተልዕኮው …። እራሱን ማሰከበር ይቀደም። ለማንኛውም መልካም ምኞት ከሆነም ሁሉን በእኩልነት አሳታፊ ሥራአት ሲደራጅ በራሱ ጊዜ ይህ መረን የለቀቀ ጋጠ ወጥ መስመር መልክ ይይዛል። በጥገናዊ ለውጥ – አይተሰብም፤ በሥር ነቀል ለውጥ እንጂ። እራሳችንም በአብዮታዊ መንፈስ ውስጥ አስገብተን እንሞራርደው።

እንዲሁም ስለነፃነት ተማጋችነቴ ማን ከእኔ በላይ የሚለን ለበጠኛው ባለድርጎ ተሰፋሪ ሪፖርትር ጋዜጣም ቢሆን የት ነበረ እስከ ዛሬ ድረስ?! ለአፓርታይድ ፋሽስታዊ ሥርዓት ድርና ማግ በመሆን በቃል አቀባይነት፣ በአቀንቃኝነት፣ በአፍቅሮተ ዘውገኝነት፤ በሙሉ ድጋፍ ሰጪነት፤ በሽፋን ጠገብ የህወሓት ሞሾሪነት በቆዬበት ግድፈት ዘለቅ ዘመን ለመሆኑ ምን ያህል ዓመት በህዝብ ሰቆቃ እንደ ተኛ ያውቀዋልን? ምን ያህል ሰዓትስ በግፍ የደም ፍስት ፍራሽ እንቅልፍ ላይ እንደ ነበርስ? አንዱ ቀን 24 ሰዓት አለው፤ በዐመታት ሲሰላ ደግሞ የት እዬለሌ ነው። ለመሆኑ አሁን ደግሞ አይዋ ሪፖርተር የሚተጋው ምን ፈልጎ ነው? ምን አምጣ ነው የሚለው የ90 ሚሊዮን የህዝብ ዕንባን? አለዬነም እሱ ብሎ መካሪ – ዘካሪ። ይልቅ በህዝብ ደምና ዕንባ ሲነግድና ሲያስነግድ የኖረበትን ዘመን አንድ … ሁለት እያለ ስሌቱን ቢያስኬደው ምን ያህል ከሰመጠ ጉድጓድ ውስጥ እራሱ እንደ በቀለ መስታውት ገዝቶ ቢያዬው መልካም ነው። ባንዳነት አድሮ የማይገኝ አሳፋሪ፤ ተላምጦ የተጣለ አገዳ ወይንም ውሃ ሲሄደበት የከረመ አለትነት ነው።

አዎን የዘር አጀንዳ፤ የታሪክ አጀንዳ፤ የሰፈር አጀንዳ፤ የሃይማኖት አጀንዳ፤ የከተማና የገጠር አጀንዳ ክርችም ሲል ሌላ ጊዜ መግዣ የጥገና ለውጥ Reform አጀንዳ ደግሞ አሁን ጅራቱን እዬቆላ ይገኛል በህወሓት አጋፋሪ በአይዋ ሪፖርተር። ቀጣዩ ደግሞ „ይኸው ይህን ህወሓት አሻሻለ፤ ይኸው ይሄኛውን ህወሓት ማሻሻያ ደገመ። ይኸው – ይኽኛው ተሰለሰ፤ ይኽው ይህን ያህል እስረኛ – ተለቀቀ፣ ህወሓት መማር ማስተካከል ጀመረ፤  በማለት አዘናግቶ ሌላ የራህብ፤ የሰቆቃ፤ የፍዳ፤ የዕንባ፤ የብሄራዊ ውርደት ዘመን አንድ ሁለት ሦስት አራት እያልን ወደ አይቀሬው ዬምርጫ ዙር ተብዬ ሽግግር – ይደረጋል። ከዛም 96 ፕርሰንት አሸነፈ ህወሓት ተቃዋሚውም ደግሞ 4 ፐርሰንት አግኝቷል በዚህች እንተክዝ …. በሚቀጥለው … በሚቀጥለው ደግሞ የአንድ ፐርሰንት ምራቂ ትኖረናለች“  ወዘተ ወዘተ ተረት – ተረት፤ ለዚህም ነው የአሁኑ ዓይን ያወጣ አዲስ ትጥቅ አስፈቺና አዘናጊ የጥገና Reform አጀንዳ … አና ብሎ ዕወጃ በዬአቅጣጫው ነጋሪቱን እዬጎሰመ ያለው። ቀልዱ ይቁም! ተረቡ ጠርዝ ይኑረው! በዕንባ ዘመናይነቱ ገደብ ይኑረው! ሪፎርምር ሪፖርተር ጋዜጣም ለከት ይኑርህ!

…. ያው የሳይበር አማሾች ደግሞ  እንደ ተለመደው አጀንዳቸው ሁሉ አይሆኑ ሆኖ አፈር ቅሞ ማርቶ አፈር ስለገባ። በለመደባቸውና በሰለጠኑበት የዕድሜ ለማኝነት አዲስ ነጠላ ዜማዋን ትናንሽ ኮርስ ይወስዱና ሰብሰብ ብለው „አይተን የመጣነው፤ ግን ሊስተካካል ይቻላል ተብሎ ቃል የተገባልን እዬሆነ ነው፤ ህወሓት ተሻሻለ¡ አሻሻለ አስተካከለ¡“ በማለት ይቀጥላሉ። ድሪቶ – በድሪቶ። አጃቢዎቻቸውም የእንኳን ደህና መጣችሁልን አቀባበላቸውን የሚገልጡበት መድርክ ይባልና በደማም ቃላት፣ በቀለም የተለቀለቁ ልስን አዳዲስ ብሎጎች፣ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት የተንቆጠቆጡ ድህረ ገፆች – በአዲስ፤ ጥገናዊ Reform የሚከበክብ የሚከብ፤ የሚያነጥፍ የሚጎዘጉዝ የመወያያ መድረክ – አዲስ ፓልቶክ፤ የተዘጉትም የውይይት መድረኮች በተሃድሶ መንፈስ – ይከፈታሉ። ራዲዮም አዲስ ይጀማመራል —- በዛው ልክ ፌስቡኩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች በስፋት ይዘረጋሉ። የተቃጠሉ ካርቦኖች። ጭስ!

አጅሬው – ህወሓት ደግሞ ዶላሩን በአፍ አፋቸው ያጎራርሳና አታሞውን ተመልካች – ይሆናል። በገፍ ያሰማራቸው ሰላዮችም በአዲስ የባንዳነት ቃና ጠብ እርግፍ – ይላሉ። ነገር ግን ሁሎቹም በረገበ አልጋ፤ በሰመጠ መርከብ ላይ መሆናቸው አይታያቸውም። እንዲያውም „አዲስ የኃይል አሰላለፍ ተፈጠረ በማለት ለዚህ ነበር የደከምነው – የታገልነው“ ይባልልናል። ልክ ለውሻ እንደሚጣለው ቅንጥብጣቢ ሥጋ ያን ከገዢያቸው ከትግራይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ የሚወረውረውን ቅንጥብጣቢ ዬሥጋ ቁራጭ ለመንፈሳቸው አቀብለው ብሄራዊ ዘላቂ ዬነፃነት ፍላጎታችን ለመቦርቦር ዬዳንሱ አርንቋ ትዕይንት – ይያያዙታል።

የፖለቲካ ተንተኞቻቸውም „አደብ ገዝተን ማደመጥ ይገባል¡ ያጸደቁትን ህገ መንግሥታቸውን በራሳቸው ጊዜ እዬሸራረፉት ነው¡“ በማለት በብዕራቸው፤ በማይካቸው ተግተው ስብከታቸውን „ቀስ እዬተባለ¡ እዬተስተዋለ¡“ እያሉ የፕሮፓጋንዳ ጥፈት – ይለጣጥፋሉ። ይህ ለእኔ እርባናው ያለቀ የተቃጠለ ካርቦን አዲስ የምኞት መቃብር ድራማ ነው። የሚያሳዝኑኝ ግን ቅኖች ህሊናቸው ከዕለት ዕለት ታቱ ዥግራ ማለቱ ነው።

የሰው ልጅ እራሱን መተርጎም የሚችለው መቆም ቀጥ ብሎ ሲችል ብቻ ነው። መቆሙንም ማረጋገጥ ይኖርበታል። በዚህ ወጣ ገብ በሆነ ወጀብ መናጥ፤ መቆም አለመቻል የተፈጥሮ ሽሽት ወይንም የራስነት ውስት ብቻ ሳይሆን ከበታችነት የመነጨ ፍርሃትም ነው። በተለያዩ ክሮች ትስስር ከፋሽስቱ ወያኔ ጋር ጋብቻው አለ። እዬታዬ ያለው ያን ክር መበጠስ ድፍረቱን የሚቀማ የጥቅማጥቅም ድልድይ ወይንም የተስፈኝነት ሙት መንፈስ መንገታተገት ነው፤ የበሰበሰ ነገር መወገድ እንጂ ጥገናዊ ለውጥ በፍጹም ሁኔታ አያስፈልገውም። ጊዜው ያለፈበት ምግብ በሽታ ስለሆነ ዕጣ ፈንታው መደፋት ብቻ ወይንም ቆሻሻ ኮንቴይነር ውስጥ መጨመር ነው። ዬህወሓት መንፈስ ማርጀት አይደለም፤ ሞቷል። ደግሞ መነሳት ቀርቶ ዳግም ለመነሳት ማሰብም አይችልም። በቅቶታትል። ታሪክ – ተፍቶታል። ከውርርስ ቅርስነትም ውጪ ነው። ህወሓት ዕድሉን ያባከነው ዛሬ ሳይሆን ከ10 ዓመት በፊት በዘመነ ቅንጅት ወይንም ከዛ በፊት በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ዘመን ነበር። ያን ጊዜ ታሪክ እራሱን አይቶ ከገደል ጫፍ የሚድነበትን ሁለት ትላልቅ መስተዋቶች ገዝቶለት ነበር። አሱ ግን ከመስታውቱ ላይ በመቆም ዕድሉን በመታበይ – ሰባብሮታል። የተቃጠለ ካርቦን።

የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ ሐገራችን ዘመነ መሳፍንትን፤ ዬዓፄ ሥርዓትን፤ የወታደራዊ ሥርዓት በሶሻሊስት – ርዕዮትዓለምን። እንደዬዘመኑ በተለያዩ ፈተናዎች ተወጥራ አስተናግዳለች። ከዘመን ባፈነገጠው በቬርሙዳ ትርያንግሉ ጠፍ አስተዳደር በህወሓት ደግሞ በዓለም የሌላ፣ ዘመንም የተፋው፣ ታሪክም የሚጸዬፈው፣ አደራም ያቃረው፤ ባህልም የፋቀው የዘውገ ሥርዓትን በአልባንያ አብዬት ጥንዝል ተመክሮ በፍዳ፣ በመከራ፣ በስቃይ ተቃጥላ፣ ተንገብግባ፣ ተርመጥምጣ አሳልፋለች። ሁሉንም – አይታለች። ለሁሉም መከራዊ ዘመን መፈተኛ ሆናለች።

አሁን ግን ዘመኑ የፈቀደላት ሌላ የፍትህ አዲስ የዲሞክራሲ የሽግግር ሥርዓት ያስፈልጋታል። በቅድሚያ እንዲያውም ብሄራዊ ነፃነት። ኢትዮጵያ ከጠላቷ ከህወሓት እስር ቤት መውጣት አለባት። ከዚያ በኋላ ሂደቱ ሁሉን ዜጎቿን በ እኩልነት ያሳተፈ አዲስ ሥርዓት አቅምና ህግ በድምጽ ብልጫ ሊመራት የሚችል ሀገር መሆን። ሰው የሚለውን ማዕከላዊ የተፈጥሮ አጀንዳ ተርጉሞ፤ በፈጣሪ አምላካችን የተሰጠው ዬሰው ልጅ ክብር ሙሉ መብት ሳይገፈፍና ሰይገሰሰ በዜግነት እኩልነት ላይ የተመሰረተ የተስፋ ሥርዓት መዝርጋትን ነው – የፍላጎቷ ህልመ – አስኳል። ለዚህ ደግሞ ዛሬ – የሞቀ የደመቀ ዬአብዛኛውን መንፈስ የገዛ አዲስ ብረሁኽ የለወጥ መንፈስ ላይ እንገኛለን። አቅማችን፣ ኃይላችን፣ አቅላችን፣ ህልማችን፣ ናፍቆታችን፣ ጸሎታችን እንደ ዕምነታችን ተማክሎ ከዛ ላይ በአርበኞቻችን ባረፈበት በአሁኑ ጊዜ የሪፖርትርን Reform የዕድሜ ልምና፣ የሱባኤ ነጋሪት ማስታመም፣ ማቆላመጥ ሆነ ማንቆላበስ ወይንም ማሽሞንሞን የተገባ አይመስለኝም። በምልአት ደምና ሰቆቃ መነገድ ነውም። የደም ንግድ ይቁም!

ሁሉመናን ለወሰደ – ቀማኛ ሽፍታ፤ ውሸታም፤ ዘራፊ፤ ይሉንታ ቢስ፤ ለበቀል ዞጋዊ ፖሊሲ አራማጅ አረመኔያዊ የህወሓት ሥርዓት ብጣቂ ጊዜ ልናውሰው ፈጽሞ – አይገባም። ይህ ያሰኘናል የሚሉ ሸጎሬዎች አብረው ድንኳን ጥለው ያስተዛዝኑ …. ሳልስቱንም፣ ሰባቱንም አርባውንም – ያውጡ። ይህ የእኛ መደባችን አይደለም። እኛን እኛን የማይሸት፣ ሰውኛ ያልሆነ የሳጥናኤልን ቀጠናን ቅብጥና ቅልጥ የሚያድርግ የራዕያችን ትንፋሽ ቅበረት ዘመቻ ስለሆነ „በቃን“ ልንለው ይገባል።

በቃን“ ማለት እኮ እንዲህ አይነት የሚያላዝኑ ዝልብ – ስንጥቅ – ትርትር – ቀዳዳ ፍላጎቶቹን ማስፈንጠር ነው። ዬአሞሌ ጨው መላሾነት ለከብት እንጂ ለሰው ልጅ ክብር – አይመጥነውም። ለነገሩ ይህ „በቃን“ የሚለው ቃል ትርጉሙም የገባን አይመስለኝም። „በቃን“ ሲባል እኮ ማናቸውም ወያኔ ነክ መንፈሶችን ሁሉ መጸዬፍ፣ መገፍተር ማለት እንጂ እንደ ገደል ማሚቶ ደግሞ ማስተገባት አይደለም። ይህ በዕውነቱ 25 ዓመት የፈሰሰውን የወገኖቻችን ደም መርገጥ ነው። የእናት ኢትዮጵያን ዬኤሉሄዋ የምጥ ድምጽም እንደ መጠቅጠቅ ነው።

ለመሆኑ ስንት ጊዜ ነው ዕድላችን ለጆፌ አሞራ የምንቀልበው!? አይበቃም?!  በደል አይረሰም – ያገረሻል እንጂ። …. ይህ የፋታ ፖሊሲ ቃር ነው። ስለሆነም አንቅረን ልንተፋው – ይገባል። ንቀን ስንተዎው ወደ ገደሉ ተመልሶ – ይቀበራል። አፈሩን ተከናንቦም ለሽ ይላል። እኛን በእኛነት ሊያከብር ለተነሳው የአርበኝነትን መንፈስ ውስጣችን ገልጠን ለእሱ – እናስረክብ። ለመሆኑ እነዛ እስር ቤት ውስጥ ሆነው „እኔ ዬአርበኞች ግንቦት 7 ነኝ!“ ያሉን ቀንበጦች መልዕክት ከሰው አንደበት የወጣ ይመስላችኋልን?! የጀግና ጋዜጠኛ አበበ ገላው በሬግን ህንፃ በሀገረ አሜሪካ በፈጣሪ አምላኩ የተመረጠለት መክሊት ድምጽ አኮ ነው፤ ዛሬም በኢትዮጵያ ምድር በድፍረት በአራዊቶች ካቴና ላይ ሆኖ ድምጹን ለብላቴናዎቹ አምላካችን መዳህኒተዓለም አቀብሎ ያውም በህብረት አንደ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ብሄራዊ ጥሪ የላከልን። ጥሪው እኮ ዬፈጣሪ አምላካችን ዬአማኑኤል ነው። ፈጣሪያችን እራሱ በሳጥናኤላዊ ህወሓት አመራሩ ከምር – አዝኗል። ታምራትን የእኛ እንበለቸው።

ወገኖቼ ጊዜው ደርሷል። ማቄን ጨርቄን – አንበል። ቢያንስ የፈጣሪን ድምጽ ለማድመጥ – እንፍቀድ። –  ጥሪውንም እንቀበል! ታጥቦ ጭቃም አንሁን ልክ እንደ ሦስት ዓመት – ህፃን። ቢያንስ መንፈሳችን እንደ ዕድሚያችን የማሰብ አቅሙን – እናሳድገው። መዳህ መዳህ —- መሬት ላይ ለመቅረት መሆን አይገባውም። ዘመንም ጊዜም ማድመጥ መተርጎም አብሮ ለመሆን መፍቀድ – ያስፈልጋል። በስተቀር ድንጋይ ነው ተብሎ መወርወርም አለ ….. ይበቃል ግልምቷል ግምቷል ህወሓትና ፖሊሲው። መልካም ሰሞናት።

ምንጭ  –

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት ቦታ የለውም›› ዶ/ር አበራ ደገፋ፣ የሕገ መንግሥት ኤክስፐርት http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46121#sthash.S8L3yZti.dpuf

ኢሕአዴግ ራሱን ይመልከት! ጋዜጣው ሪፖርተር ርዕሰ አንቀጽበጋዜጣው ሪፖርተር

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46125

 

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ርዕዮት አለሙ አራዳ ነች (ከተማ ዋቅጅራ)

$
0
0
(ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ)

(ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ)

አባቴ ሁሌ የሚነግረኝ ነገር ነበር አራዳ ማለት ይለኛል  አራዳ ማለት፡-  ለነብሱ ያደረ፣ እውነተኛ፣ ፈሪ ያልሆነ፣  አላማውን በእውነት የሚገልጽ፣ ታዛዥ፣ ህብረተሰቡን በቅን የሚያገለግል፣ የሚያውቀውን በቅንነት የሚያሳውቅ፣ የፍቅር ሰባኪ፣ የሰላም መዝሙረኛ፣ የጥበብ ቅኝት ተቀኚ፣ የፍልስፍና አባት፣ የተበላሹ መንገዶችን ጠራጊ፣ ማስተዋልና ጥበብን በልቡ አስቀማጭ፣ በእውነት የዘነጠ፣  ለውሸት ቦታ የሌለው፣ ስጋን አደላዳይ፣ ነፍሱን አዳኝ፣ ከፍ ባለ ማማ ተቀምጦ ከአትሮኑሱ ስር የሚገኝ፣ የእውቀት ጫፍ ላይ ደረሶ ከፊደል ቆጣሪወች ጋር ፊደል የሚቆጥር፣ ከራሱ ከፍታ የህዝቡ ከፍታን የሚወድ፣ ከራሱ ድምቀት የአገርን መድመቅን የሚናፍቅ፣ ለታናሹ ታዛዥ፣ ለታላቁ አገልጋይ፣ አባቶቹን አክባሪ፣ እናቶቹን አፍቃሪ፣ ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል፣ ቢዘምር ላገሩ፣ ቅኔ ቢቀኝ ለህዝቡ፣ ለነብሱም ለስጋውም ያደረ ማለት ነው። ይለኝ ነበር

ሁሉም ሰው እኩል ተሰጥኦ አይሰጠውም ለአንዱ ድምጽ፣ ለሌላው ደራሲነት፣ ለአንዱ መካሪ፣ ለሌላው አስተማሪ፣ ለአንዱ ቀዳሽ፣ ሌሌላው አራሽ፣ ብቻ ሁሉም የራሱ ተሰጥኦ አለው ዋናው ነገር ተሰጥኦህን በአግባቡ እና በእውነተኛ መንገድ መጠቀሙ ነው። እናም ርዕዮት ንጽ አእምሮ፣ ቆራጥ ልቦና፣ እውነት የሚናገር ብዕር፣ ተሰጥቷታል። ለዚህም ምስክር የምትጽፋቸው ጽሁፍ ይናገራል። እስር ሳይበግራት ጥንካሬዋን ያሳየች ከስር ከወጣችም በኃላ የብዕሯ ቀለም ሳይነጥብባት ስራዋን የቀጠለች ንጹህ  ህሊና ያላት ያወቀችውን የምታሳውቅ የአገር አለኝታ የህዝብ መከታ የሆነች በኢትዮጵያዊያኑ ልቦና  ውስጥ የሴት ጀግና ሆና የተቀመጠች አራዳ ነች።

እንዲህም ሆኗል ሁለት ጓደኛሞች ቡና እና ጊዮርጊስ ሲጫወቱ አንድ የጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊ ሌላኛው  ደግሞ የቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊ ናቸው። ዘንድሮማ የደጋፊ ነገር ችግር የለብንም ንብ ደግፉ፣ ቢራቢሮን ደግፉ፣ ዝንብን ደግፉ፣ ጢንዝዛን ደግፉ፣ በግድም በእጅም ግንቦት20 ደግፉ፣ የሚባልበት ጊዜ ላይ ስለደረስን ድጋፌን በደንብ ትረዱታላቹሁ ብዬ እገምታለው። እናም የቡናው ደጋፊ ቡና ያሸንፋል  የጊዮርጊስ ደጋፊ ጊዮርጊስ ያሸንፋል በማለት በ 1000 ብር ያሲዛሉ።  ለማንኛው እንድንተማመን  ውል ተጻጽፈን እንፈራረም ይላሉ። በውሉ መሰረት እንደሚተገበር ይስማማሉ። እንዲህ ይል ነበር ውሉ፡-

እከሌ የተባለው እና እከሌ  የተባለው ዛሬ በዚህ ቀን ቡና እና ጊዮርጊስ በሚያደርጉት የእግር ኳስ ጨዋታ ቡና ካሸነፈም፣ ቡና ከተሸነፈ፣  እንዲሁም አቻ ከወጣ የቡና ደጋፊ የሆነው  2000 ብር የእከሌ መሆኑን በፊርማችን  እናረጋግጣለን ብሎው ተፈራርመው ወደ እስታዲዮሙ ይገባሉ። በጨዋታውም ጊዮርጊስ ያሸንፍና በል ብሬን ብሬን እኛ እንደዚህ ነን ይለዋል የጊዮርጊስ ደጋፊ። የጎርጊሱ ደጋፊ መጻፍና ማንበብ አይችልም ነበር።   ውሉን ምን እንደሚል ስላልተረዳው  ክርክር ተጀመረ። በኋላ ላይ ክርክሩ ሲያይል ወደ ጋደኞቻቸው ወሰዱት ዳኝነትን ጠየቁ ጋደኞቻቸው ውሉን ሲያዩት በጣም ሳቁ። ቡና ቢያሸንፍም ቢሸነፍም አቻ ቢወጣም እሱ ይውሰደው ብለህ ነው እኮ ነው የፈረምከው አሉት። የዚህን ጊዜ በጣም ተናደደ። ብር ከመቁጠርህ በፊት ፊደል ቁጠር አሉት። እስከአሁንም እንዲህ እየተባለ ይቀለድበታል።

የብዕር አርበኛዋ ርዕዮት አለሙ በአንድ ብእር 17 አመት ጫካ ነበርን፣ ጀግና ነበርን፣ የሚሉትን ያርበደበደ ታንክ አለን፣ አዳፍኔ አለን፣ የሚሉትን ያዳፈነች። እውነት በመጻፏ ሽብር የመሰላቸው፣ ብዕሯን ከወረቀትጋር በማዋሃዷ ጀግና ነን ብለው የተኮፈሱትን ያራደች፣ የድንጋይ መሰረት ሳይሆኑ የእንቧይ ካብ መሆናቸውን ያሳየች፣ ብዕርተኛ ነች። የእርዮት ብእር ሰለ ሕዝብ ነጻነት የሚናገር፣ ሰለ አገሯ ክብር ቀለምን የሚተፋ፣ አስተማሪ ብእር ነው።  መለስ ዜናዊ |<<ከሺ ጦር ባተሌ አንድ ብዕር የያዘ ሰው ለኛ ከባድ ነው>> ብለው እንደተናገሩት በአንዲት ብዕር ማንም አይደፈረንም ብለው  የውሸት ፕሮፖጋንዳ ሲናገር የነበረውን የወያኔን ምሽግ ሚግ አብራሪ  ወይም ታንከኛ ሆና ሳይሆን ያራደችው፣ ብዕሯ አሁን ስልጣን ላይ ያለውን ገዥ ፓርቲ ምን እንደሚል ያልገባቸው አልያም እውነት ውስጣቸው ስለሌ  በብዕሯ ቀለም የተሸበሩት። እርሷ ግን  እውነትን በመግለጽ፣ አገርን በመውደድ፣ ህዝብን በማክበር ብዕራን ያነሳች አራዳ ነች። እናም ብር ከመቁጠር  ፊደል መቁጠር ይሻላል የሚለውን አባባል ጋብዥያቸዋለው። በእውቀት የበለጸገ እና በእውነተኛ መንገድ ላይ የቆመ  ብዕር ያስተምረዋል እንጂ አያስፈራውምና ነው በብዕር የሚሸበር ያልተማረ ወይም  በእውነተኛ መንገድ ያልቆመ ብቻ ነው።

እርዮት ስጋዋ የታሰረ ህሊናዋ ያልታሰረ ብዕርተና ነች። ገራፊን ገርፈሃል፣ አሳሪን አስረሃል፣ ገዳይን ገድለሃል፣ የምትል የእውነት ብዕር ያነሳች  በዕረኛ ነች። ስጋችን ሲያገኝ የሚወፍር፣ ሲያጣ ደግሞ የሚከሳ ነው። አእምሮአችን ግን እውነትን ስንሰጠው ብቻ ነጻ አድርጎ የሚያኖረን የራሳችን ፍርድ ቤት ነው። ለአእምሮዋ እውነትን ያስገባች፣ እውነትንም ያወጣች፣ ከዘላለም ጸጸት የጸዳች፣ ከራሳ ጋር የተስማማች ብዕርተኛ ነች። ሕዝብ ማለት እሷ፣  እሷ ማለት ሕዝብ፣ መሆኑን ያስመሰከረች የዘመኑ የሴት ተምሳሌት የሆነች አራዳ ነች።

እንጂ  አራዳ የሚለው ትርጉም እንደኛ ዘመን ትርጉም እንደተሰጠው  የቃመና ያስቃመ፣ ያጨሰና ያስጨሰ፣  የጠጣና ያስጠጣ፣ ከፍ ብሎ የዘለለ እና የወደቀ፣  የሰረቀና ያሰረቀ፣ ያመሸና ያስመሸ፣ የጨፈረ እና ያስጨፈረ፣ እስታ በል፣ ላሽ በል፣ ተቄ በል፣ ጩባ፣ ፍሉስ፣ ሼባው፣ ጌጃው፣ ማኛው ,… የሚለው የሚጠቀም እና የሚያደርግ አራዳ አይደለም። እንደዚ አይነቱ ከራስ መጣላት፣ ከቤተሰብ መጣላት፣ ከጎረቤት መጣላት፣ ከህብረተሰብ መጣላት፣ ከአገር መጣላት፣ ብሎም ከእግዛቤሔር ጋርም መጣላት ነው። ስጋውንም ነብሱንም የሚጎዳ አራዳ የሚለው ትርጉምን አይስማማውም።

ሁላችንም አራዳ ለመሆን የአባቶቻችንን ምክር እንስማ እላለው። አራዳ በኢትዮጵያ ምድር በዝቶ ይብቀልባት፣ ይውጣባት፣ ይታይባት፣ ያብብባት።  አራዳ ዶክተር ወላ እንጅነር፣ አራዳ ወታደር ወላ መምህር፣ አራዳ አርሶ አደር ወላ ኢንቨስተር፣ አራዳ ደራሲ ወላ ሃያሲ፣, አራዳ ሳይንቲስት ወላ ጂኦሎጂስት፣ አራዳ ፖለቲከኛ ወላ ዳኛ፣ አራዳ መሪ ..ሆኖ ታታሪ.. በህግ አዳሪ.. ህዝቡን አስከባሪ.. ያብዛልን ፈጣሪ።

 

ከተማ ዋቅጅራ

21.08.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

Je Suis ኢትዮጵያዊ!

$
0
0

hailemariam

ገለታው ዘለቀ

ከብሄር ፖለቲካ እንውጣ!
የተባበረችውን ኢትዮጵያን እንገንባ!

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሲናገሩ ኣገራችንን የሚበትኑ ኣጥፊ ዘሮች ያሏቸውን ሶስት ጉዳዮች ኣነሱ። ኣንደኛው ጠባብነት፣ ሁለተኛው ትምክህተኛነት፣ ሶስተኛው በሃይማኖት ሽፋን የሚራመድ ኣክራሪነት ናቸው ኣሉ። በመሰረቱ እነዚህን ጉዳዮች ኣቶ ሃይለማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሷቸው ጉዳዮች ኣይደሉም። በ”ኢህዓዴግ” ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚነሱ ሁሌም ሲባሉ የነበሩ ናቸው። ኣቶ ሃይለማርያም ኣዲስ ነገር ኣልተናገሩም ።
ለማናቸውም ግን እነዚህ ኣደገኛ ዘሮች ከየት መጡ? ኣገሪቱንስ ወዴት እየወሰዱ ነው? በርግጥ ከብሄር ፖለቲካው ኣዝማሪዎች ኣልፎ ወደ ታች ወርዶ የኔብጤው ተራው ህዝብ ኣካባቢ እነዚህ ዘሮች ጎልተው እየታዩ ነው ወይ? የሚለው ጉዳይና ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ያለመቻሏ ጉዳይ፣ የሰብዓዊ መብት ኣያያዝ ጉዳይ ሃላፊነት ለሚሰማው ኢትዮጵያዊ፣ ለዓለማቀፍ ተቋማትና ለኢትዮጵያ ወዳጅ ሃገራት ዲፕሎማቶች በጣም ኣሳሳቢ ጉዳይ ሆኖባቸው ኣያለሁ።
ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግሩ እንመለስና በመጀመሪያ እሳቸው ራሳቸው ያመኗቸው እነዚህ ሶስት ጉዳዮች በሰፊው የሚታዮት በኣንድ ሃገር ውስጥ ፖለቲካው በጠባቡ ሲቀረጽ፣ ወይም በየቤትህ እደር ኣይነት የፖለቲካ ጨዋታ ሲጀመር ወይም የፖለቲካው ጥብቆ ሲጠብ ነው። ሳይንሳዊ በሆነ ኣገላለጽ የማንነት ፖለቲካ (Identity Politics) የሚባለው ሲሆን በተለይ ብዙህ በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ይህ የፖለቲካ ስርዓት ሲዘረጋ የሚያመጣቸው ወይም ከዚያ የሚፈለፈሉ ችግሮች ብዙ ናቸው። የብሄር ፖለቲካ የማህበራዊ ካፒታል ምስጥ ነው። ለዚህም ነው ምሁሩ፣ ተማሪው፣ የተማረው፣ ያልተማረው ሁሉ ላለፉት ሃያ ዓመታት በላይ የብሄር ፖለቲካን ሲነቅፍ የነበረው:: የማንነት ፖለቲካ እነዚህን ኣደገኛ ነገሮች እንደሚያመጣ ብዙ ሳይንሳዊ ምርምር የሚጠይቅም ኣልነበረም። የብሄር ፖለቲካ ስነ- ልቦናው ራሱ ጠባብነት ነው። ከጎሳው ያላለፈ የፖለቲካ ስብእና ይዞ እንዲያድግ የሚያደርግ የፖለቲካ ኣስተሳሰብ የተጫነው በመሆኑ የጠባብነት መነሻው ይሄው የብሄር ፖለቲካ ነው።

ትምክህተኝነት የሚባለውም ከዚሁ ከጠባብ ኣስተሳሰብ የሚመነጭ የኣንድ ዛፍ ቅርንጫፍ ነው። ሰው ጠባብ ሲሆን ነው የሚመካው። በወንዙ በጎሳው ሲመካ ጠባብ ሆኖ ነውና። ጠባቦች ሁል ጊዜም ትምክህተኝነት ኣያጣቸውም። ሁለቱም ባህርያት የተያያዙ ከኣንድ መራራ የብሄር ፖለቲካ ምንጭ የሚቀዱ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲናገሩ ተማሪው ላይ ተጽእኖው ይታያል እንጂ እነዚህን ዘሮች የሚዘራው ኣስተማሪው ነው ኣሉ። ማን ነው የጠባብነትን ፖለቲካ የሚያስተምረው? ህወሃት “ኢህኣዴግ” ኣይደለምን? ህወሃት “ኢህዓዴግ” ከመምጣቱ በፊት ትግሬው፣ዓማራው፣ኦሮሞው ወዘተ. ኣብሮ ቁጭ ብሎ ሲጫወት መች የብሄር ነገር ትዝ ብሎት ያውቅ ነበር? ቢታወሰውም እየተቀላለደ ከመኖር ውጭ መራራ ስር ኣልነበረውም። ለእነዚህ ኣደገኛ ዘሮች መፈጠርና ማደግ ጥሩ መፈልፈያ የሆነው ራሱ የፖለቲካው ቤት መሆኑን መረዳት ብዙ ምርምር ኣልጠየቀም።

ቡድኖች ለምንድነው የብሄር ወይም የሃይማኖት ማንነታቸውን ይዘው ወደ ፖለቲካ የሚሳቡት? ካልን የፖለቲካን ሃይል መሳሪያ በማድረግ የቡድንን የወል ጥቅምና የበላይነት ለማረጋገጥ ነው። የፖለቲካው ስልጣን የመሳሪያ ሃይል ያለውንና የኢኮኖሚውን ክፍል ስለሚያዝ ያንን ቡድኖች መቆጣጠር ከቻሉ ለቡድናቸው ኣቋራጭ እድገት ዓይነተኛ መሳሪያ ሆኖ ስለሚያዩት ነው። በዚህ የፖለቲካ ድባብ ውስጥ ኣክራሪነት፣ ልዮነትን ማድመቅ የመከሰታቸው እውነት ለምን ጥያቄ ውስጥ ይከተናል? ሃይማኖታዊ ኣክራሪነትም የሚከሰተው ኣጠቃላይ የፖለቲካው ቅርጽ በማንነት ላይ ሲረብብ ሃይማኖታዊ ማንነታቸውን ይዘው ወደ ስልጣን እንዲሳቡ የሚያደርግ ስነ ልቡናዊ ድባብ ሲፈጠር ነው። በመሰረቱ ሃይማኖትን ማጥበቅ ማለት ኣይደለም ኣክራሪነት ማለት። ሃይማኖታዊ ኣክራሪነት የሚፈጠረው በሃይማኖቱ መሰረት ላይ የቆመ ፖለቲካ ለመመስረት መጣርና በጋራ ህልውና (coexistence) ኣለማመን ነው። በግለሰብ ደረጃም ሆነ በቡድን እንዲህ ዓይነት ባህርያት ሲገለጹ ኣክራሪነት መጣ እንላለን። ይህ ኣክራሪነት በኢትዮጵያ ከታየ ኣካባቢያዊ ኣስተዋጾዎች እንዳሉ ሆነው ራሱ የፖለቲካው ተፈጥሮና የመንግስት ኣያያዝ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ማድረጋቸው ኣይካድም። በኣጠቃላይ ምንጩ የማንነት ፖለቲካ ሆኖ ሳለ ለምን የመንግስት ሰዎች እነዚህን ችግሮች እየጠቀሱ ኣጥፊዎች ናቸው እንደሚሉ ዶክተር ዳኛቸው በቅርቡ በ VOA እንዳስረዱት ለማንም ኣይገባም። “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል” ነው ያሉት?

ጠቅላይ ሚንስትሩ ራሳቸው እኮ ቢያንስ እንደ ብሄር ራሳቸውን የሚገልጹበት ታእታይ የፖለቲካ ስብእና ባይኖራቸውም በመልክዓምድር በተወሰነ የፖለቲካ ታእታይ ስብእና የታጠሩና ለፈጠራቸው ህወሃት ኣድርባይ ናቸው። የህወሃት ኣባላትም እንዲሁ የፖለቲካ ውስጣዊ ወይም ታእታይ ሰውነታቸው በብሄር ላይ የቆመ ጠባብ ነው። በርግጥ “ኢህዓዴግ” የሚባለውን ለብሰናል ለማለት ከሆነ ህዝቡ ኣይዋጥለትም። ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት “ኢህዓዴግ” የሚባል ድርጅትም በዓለም ላይ የለም። ለምን የለም? ከተባለ ከማንነት ፖለቲካ ተፈጥሮ ጋር ያለውን ፍልስፍናዊውን ጉዳይ ልተወውና ኣንድ ጥቂት ተግባራዊ ነገር በማንሳት ላሳይ።

የዛሬ 40 ኣመት ገደማ ሁሉም እንደሚያውቀው ህወሃት ይቋቋማል።በዚህ ወቅት ህወሃት ሲፈጠር የነበረውን ህልም ተግባራዊ ለማድረግ ውሎ ኣድሮ ያስባል። ወደዚያ የሚያደርሰው ኣድራሽ፣ ኣድራሽ ብቻ ሳይሆን እስከ ፈለገው ጊዜ እንዲቆይ፣ ጊዜ እንዲያገኝ የሚያደርገው፣ የሚያግዘው የፕሮጀክት ግብዓት ፈለገ። ጥሩ ኣድራሽና ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚሆነው የተለያዩ ብሄሮችን ስም የያዙ የፖለቲካ ድርጅቶችን መፈልፈል ሆኖ ኣገኘው:: በመሆኑም እንደ ኦህዴድ፣ ብዓዴን የመሳሰሉትን ሁሉ ፈለፈለ። እነዚህ ድርጅቶች የህዝብ ብሶት የወለዳቸው፣ ህዝብ የጠየቃቸው ኣይደሉም። ህወሃት ራሱ ለፕሮጀክቱ ግብዓት ይሆኑለት ዘንድ በኣምሳሉ የቀረጻቸው ናቸው። በሌላ ኣገላለጽ እነዚህ ድርጅቶች ራሳቸው ህወሃት ናቸው። ምንምን እንኳን የተለያየ ብሄር ኣባላትን ይዘው ቢመሰረቱም ተገትረው ብናይም በህወሃት ብሶት፣ በህወሃት ራእይ፣ በህወሃት እጅ የተፈጠሩ በህወሃት የህወሃት ናቸው። ኣንዳንዶቹ ድርጅቶች በተለይም ኦህዴድ እንደሚወራው ኣንዳንድ መሪዎቹ የህወሃት ኣባላት ስማቸውን እየቀየሩ ኣመራር ላይ የነበሩበት ሁኔታም ነበር።

ኣቶ በረከት ስምዖን በህወሃት 40ኛ ዓመት ላይ ንግግር ሲያደርጉ እንዲህ ኣሉ
“እኛ ብአዴኖችም ሁሌም ቢሆን ራሳችንን ከህወሓት ነጥለን ያየንበት ጊዜ የለም። ሁላችንም “ወየንቲ ኢና” (ወያኔዎች ነን) ነው የምንለው።”

(በረከት ስምዖን)

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም ደግሞ ይህንን ያስረግጡልናል።
“አንዳንድ ወገኖች …. ስድብ መስሏቸው “ወያኔ” አሉኝ ከጥቂት አመታት በፊት ለተመሳሳይ ጉዳይ በረከት ስምዖን ያለውን አስታወሱኝ “ሁላችንም ወያኔ ነን” አዎ አሁንም ሁላችንም ወያኔን ነን…..እኔ ወያኔ ኢህአዴግ ነኝ! Je Suis Woyane! …. በዚህም ኩራት ይሰማኛል፡፡ እኔ ወያኔ ነኝ! ሁላችንም ወያኔ ነን! ይህን ችግር የሚፈታውም በወያኔነት ነው! …እንበርታ፡፡”
(ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም)

በኣንጻሩ ከህወሃት ኣባላት መንደር ሁላችንም ኦህዴድ ነን ወይም ደህዴግ ወይም ብዓዴን ለማለት ጨርሶ ታስቦ የማያውቅ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ድርጅቶች እንደ ፖለቲካ ድርጅት በህወሃት ህሊና የሉምና። እንዴውም ኣቶ መለስ እንኳን ከዚህ ቡድን ተወለድኩ ብለው ጠባብና ትምክህተኛነታቸውን በኣደባባይ ሲናገሩ ተደምጠው ነበር። ይሄ ነው ጠባብነት፣ ትምክህትና ኣክራሪነት የሚባለው።
በኣጠቃላይ የሆነ ኣጀንዳ ይዞ የተነሳው ህወሃት ሲሆን በየመንገዱ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚሆኑትን የፖለቲካ ድርጅቶችን የፈለፈለ ሲሆን እነዚህን ግብዓቶች ይዞ ሁዋላ ላይ “ኢህዓዴግ” የሚል ስያሜ ይዞ ብቅ ይላል። “ኢህዓዴግ” የራሱ የህወሃት ፕሮጀክት ማስፈጽሚያ ሲሆን እንደ ፖለቲካ ድርጅት ግን ኣለ ማለት ኣይቻልም። ለዚህም ነው ራሱ በኣድራሽነት የተሰራውና የሚኖረውም። ግንባር በተፈጥሮው ኣድራሽ ሲሆን ይህ በግንባርነት የተዋቀረ ቤት የዚሁ የህወሃት ሌላው የኣዲስ ኣበባ ቤት ነው። በርግጥ ወደ ተራው ኣባል ኣካባቢ ስናይ የዋህነት ሊኖር ይችላል። ተሰብስበው ግምገማ ሲባል፣ እቅድ ኣውጡ ኣውርዱ ሲባል “ኢህዓዴግ” በህይወት ያለ ይመስላቸው ይሆናል። የለም። ተላላ መሆን ኣያስፈልግም። ህወሃት እነዚህን ድርጅቶች ሲያቆም ኣዲስ ኣበባን ለመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን ከዚያ በሁዋላ ደህንነቱንና ወታደሩን እንዲሁም ኢኮኖሚውን እስኪቆጣጠር ግብዓት ስለሚሆኑት ነው። በርግጥም በኣሁኑ ሰዓት በነዚህ ድርጅቶች እገዛ ህወሃት እነዚህን ህልሞቹን ኣሳክቷል። ኣቅጣጫ ነው ያጣው። በመሆኑም የነዚህ ድርጅቶች ኣባላት መታለሉን ማቆም ኣለባቸው። መንቃትና ለለውጥ መነሳት ያስፈልጋል። በቂምና በበቀል ላይ ሳይሆን ሁሉን ነጻ የሚያወጣ የወደፊቱን በማሰብ ላይ የተመሰረተ ቢሆን ነው የሚሻለው።
በኣጠቃላይ የሚንስትሮቻችን የመሪዎቻችን ታእታይ የፖለቲካ መሰረት የወንዝ ፖለቲካ በመሆኑ ከዚህ የብሄር ፖለቲካ ዘር የሚወለደው ያው ጠባብነትና ኣክራሪነት ከመሆን ኣያልፍም።ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም ከፍ ሲል እንዳየነው እኔ “Je Suis ወያኔ ነኝ” ብለዋል። ይሄ እውነተኛ የፖለቲካ መሰረታቸው ሊሆን ይችላል። የሚገርመው ግን እኚህ ሰው ኣንድ ጊዜ ኒዮርክ በተደረገ ስብሰባ ላይ “ ኒውዮርክ ሜልቲንግ ፖት ናት” ብለው በስሜት ተናገሩ። መልቲንግ ፖት የህወሃት ኣስተሳሰብ ጸር ነው። ባህላዊ ውህደት ማለት ነው ሜልቲንግ ፓት ማለት። እኚህ ሰው ምን ኣልባት ተለውጠው ከሆነ ይህን ያሉት እንዳንል የኒውዮርኩን ንግግር ካደረጉ በሁዋላ ነው እኔ “ Je Suis ወያኔ ነኝ” የሚሉን። እሳቸው ይህን ይበሉ ፣ እኔ ደግሞ Je Suis ኢትዮጵያዊ! እናንተስ?

እንግዲህ ጠቅላይ ሚንስትር ኣቶ ሃይለማርያም ይህን ዘር ኣጥፊ ነው ብለው ካመኑ በዚህ የወንዜ ፖለቲካ ቤት ውስጥ መዋል ማደር የለባቸውም። ሌሎች ምስጢሩ ያልገባቸው የዋህ የህወሃት፣ የብኣዴን፣የደህዴግ ወዘተ ኣባላት ከዚህ የፖለቲካ ኣስተሳሰብ ወጥተው ጠባብነትን የህወሃትን የበላይነት መዋጋት ኣለባቸው። የጠባብነትና የትምክህት ዋና የሆነውን የብሄር ፓለቲካ ቤት ግድግዳውንና ጣራውን ለመንደል የውስጥ ኣርበኞች መሆን ኣለባቸው። ለለውጥ መነሳት ኣለባቸው።የተባበረችውን ኢትዮጵያን ለመገንባት ትውልዱ ሁሉ ኣምርሮ መነሳት ኣለበት።የተባበረችውን ኢትዮጵያን የምንገነባው ደግሞ ከብሄር ፖለቲካ ስንወጣ፣ ስምምነት ውስጥ ስንገባ ነው። ይህ ስምምነት የህዝብ ውክልና በሌላቸው በዚህ ኣርባ ኣመት ባፈራናቸው እዚህም እዚያም በተኮለኮሉ ፓርቲዎች መካከል ኣይደለም። ወደ ባህላዊ ቡድኖች ታች ድረስ ወርዶ ህዝቡ ተወያይቶ ቁሳዊና መንፈሳዊ ባህሉን ኣዋጥቶ ኣገሩን እንዲገነባ የሚያደረግ ሰፊ ስምምነት ነው።ለዚህ ደግሞ ኣገሪቱ የሆነ የጽሞናና የሽግግር ጊዜ የሚያስፈልጋት ሲሆን በዚህ ከፍተኛ ኣሳብ ላይ ሁሉም መጠቅለል ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ህወሃት የዘራው ዘር ከፍተኛ ኣደጋ ውስጥ ሊጥለን ይችላል።

ኣዲሲቱ የተባበረችው ኢትዮጵያ ከብሄር ፖለቲካ ወጥታ በተሻለ ውቅር ልትሰራ ይገባል። የማንነት ኪሳራ እንዳይመጣብን በኣንድ በኩል የተደራጀ የባህል መንግስት መስርተን ባህላችንን እየተንከባከብንና እየተደሰትን በሌላ በኩል ፖለቲካዊ ቤት መስራት እንችላለን። እንደ ኢትዮጵያ ብዙ መልካም ታሪክና ባህላዊ እሴቶች ያሉዋትን ኣገር ለማስተዳደር የዚህ ዓይነት ሲስተም መዘርጋቱ ሰላምን፣ ልማትና ዴሞክራሲን ያፋጥንልናል። ከዚህም በላይ ለዜጎች ርካታን ይሰጣል።
ከልጅነት ጊዜየ ጀምሮ በእድሜ የበሰሉ ሰዎች የሚሰጡት ትምህርት ይማርከኝ ነበር። ኣረጋውያን ሲያወሩ ጠጋ ብሎ ማዳመጥ ርካታን ይሰጠኛል ። ከእለታት ኣንድ ቀን እንዲሁ ኣንድ የእድሜ ባለጸጋ ኣገኘሁና በተፈታ ስሜት ወግ ጀመርን:: እኚህ ሰው ከሚናገሩት የሚበዛው ያለፈው ዘመን ምን ያህል የተሻለ እንደነበር ነው። ምን ኣልባት በኢኮኖሚ ጥንት የተሻሉ ነበሩ ማለት ነው፣ ኣሁን ኑሯቸው ኣሽቆልቁሏል ማለት ነው፣ ብየ እንዳላስብ ኣይደለም። ልጆቻቸው የተሻለ ገቢ ኣላቸው። እሳቸውም ድሃ የሚባሉ እንዳይደሉ ኣውቃለሁ። ምንድነው ወደ ኋላ የሚጎትታቸው? ምን ኣጥተው ነው? የሚል ጥያቄ ይዞኝ ነበር። በሳቸው የልጅነት ጊዜ በእግር ነበር ይጓዙ የነበሩት፣ ኣሁን በመኪና ይሄዳሉ፣ የተሻለ ልብስ ፣ የተሻለ ጫማ፣ የተሻለ ምግብ፣ የተሻለ ነገር…. እንዳላቸው መረዳት ችያለሁ። እኚህ ሰውም ይህንን ሁሉ ይደሰቱበታል። ይሁን እንጂ ያጡት ነገር ደግሞ ወደ ሁዋላ ሲጎትታቸው ኣየሁና ሁዋላ ላይ ለራሴ የተረዳሁት ነገር እኚህ ሰው ያጡት ባህል ነው ማለት ነው ብየ ደመደምኩ። በለውጥ ስም የሚወዱዋቸውን ባህሎቻቸውን ኣጥተዋል። ኣንቱ የተባሉ ሽማግሌዎችን ከሰፈራቸው ኣያዩም፣ ክብረ በዓላትን ሲያዩ ይገረማሉ፣ የጠፉ ባህላዊ ተቋማት ይናፍቋቸዋል፣ ወዘተ.

እኚህ ሰው ዘመናዊውን ዴሞክራቲክ የሆነ መንግስት ማየት ይፈልጋሉ። በርግጥ ደግሞ ባህላዊ ተቋሞቻቸው ቢያንስ ከነ ሙሉ ሃይላቸውም ባይሆን በቅርስነት በህይወት ማየት እንደሚፈልጉ ተማርኩ። እኚህ ሰው ኢትዮጵያን ቢወዱም ኣገራቸው የድሮ ሞገሷን የተገፈፈች ኣድርገው እንደሚያስቡ ገመትኩ። ርግጥ ነው ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ባህልን ማጣት እንደ ሃገርም እንደ ዜጋም ይከነክናል ይጎዳልም።ሌሎች የኢኮኖሚ ህይወታቸው እያደር እየደቀቀ የመጣ ሰዎችም እንዲሁ የድሮውን ጊዜ ሲናፍቁ ብዙ ጊዜ እሰማለሁ። ጥያቄያቸው ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ባህላቸውንም እንደናፈቁ መረዳት ይቻላል። ለዚህ ነው ኣዲሲቱ ኢትዮጵያ የተደባለቀውን ፖለቲካዊ ማንነትና ባህላዊ ማንነት በመለየትና በተለያየ ቤት እንዲያድሩ በማድረግ የተሻለ ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋታል የሚያስብለን ። የተባበረችውን ኢትዮጵያን የምንመሰርተውም እንዲህ በጠነከረ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መሰረት ላይ መሆን ኣለበት። ለዴሞክራሲ፣ ለለውጥ የምናደርገው ትግል ሁሉ Je Suis ኢትዮጵያ መርሃችን ኣድርገን የተባበረችውን ኢትዮጵያን እንገንባ። ኢትዮጵያውያን የተባበረችውን ኢትዮጵያን ገንብተን ትኩረታችንን ሁሉ በምግብ ዋስትና ላይ ልናደርግ ይገባናል። ተመልከቱ እስቲ። ኢትዮጵያ ባለፉት ኣስር ኣመታት ያለማቋረጥ በጥንድ ቁጥር እያደገች ነው ተባለ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በቅርብ ጊዜ ኢትዮጵያ በምግብ በብሄራዊ ደረጃ ራሷን ቻለች ኣሉ። እነሆ በማግስቱ ዛሬ በጥቂት ወራት ውስጥ ለ4.5 ሚሊዮን ህዝብ ኣስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል ተባለ። የተባበሩት ህዝቦች ድርጅት የሰባዊ መብት ኣጋር ድርጅትና መንግስት ይህን ገልጸዋል። በእኔ እምነት ይህም ይፋ የሆነው በተባበሩት ህዝቦች ድርጅት ቅስቀሳ እንጂ መንግስት ይህ ነገር ወደ ኣደባባይ ሳይወጣ የሆነው ቢሆን የሚመርጥ ነው የሚመስለኝ። የሚገርመው ዛሬ በብሄራዊ ደረጃ ራሳችንን በምግብ ቻልን ያሉን ጠቅላይ ሚንስትር ለተራቡ ሰዎች ቀለብ ለመግዛት ከሚያስፈልገው ተጨማሪ $ 230 ሚሊዮን ውስጥ $33 ሚሊዮን የሚሆነውን ብቻ ነው መንግስት መሸፈን የሚችለው። ቀሪውን 200 ሚሊዮን ገደማ ዶላር ባስቸኳይ የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ርዳታ እንዲያደርግ ልመና ጀምረናል። ይህ ማለት ደግሞ በምግብ በብሄራዊ ደረጃ ራሳችንን ኣልቻልንም ነበር ማለት ነው። ለብዙ ዓመታት በጥንድ ቁጥር ኣድጊያለሁ ዓለም ያጨብጭብልኝ ስትል የነበረች ኣገር ዛሬ ለጥቂት ወራት እንኳን ዜጎቿን መታደግ ኣልቻለችም። ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብስ ምነው ዛሬ ጠዋት በምግብ ራሳችንን ቻልን ብልችሁ የለም እንዴ? ቢለን ……ያሳፍራል። ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች በውነት ኣጃንዳቸው ሁሉ ይህ ነው ሊሆን የሚገባው። ይህቺን ኣገር በምግብ ራስዋን የማስቻል ስራ ነው መቅደም ያለበት። ሰው በሚራብበት ኣገር የብሄር ፖለቲካ ቅብጥርሴ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው። ለውጥና ሪፎርሜሽን ይመግበናል፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻችንን ይፈታልና ለለውጥ ታጥቀን እንነሳ።

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

geletawzeleke@gmail.com

Viewing all 1664 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>