Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ህወሃት/ብአዴን በጨለማ ጐንደርን በታንክ ምን ለማድረግ !!?

$
0
0

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)


ነብሮ ከሰ/አሜሪካ

ኢዲዩ በወገራ፤ጎንደርና ጭልጋ አውራጃዎች ኃይሉን አጠናክሮ ወደ ጎንደር ከተማ እየገሰገሰ ይሄድ በነበረበት ወቅት በጎንደር ክፍለ ሀገር የነበረው የደርግ ወታደራዊ አቅም ደካማ ነበር።በኋላ ግን ከየክፍለ ጦሩ በመሳብ ገስጥ በሚባለው ክፍለ ጦር የተካተተ ከፍተኛ የጦር ክምችት ወደ ጐንደር ዘመተ። ከአዘዞ እስከ ብልኮ ጎንደር በደርግ ብረት ለበስና መድፍ በጫኑ የጦር ኃይል ካሚዮኖች ተጨናነቀች።በዚያች ቀንና ሰአት በሕዝቡ ዘንድ የተለያዩ አመለካከቶች ይንፀባረቁ ነበር። ተማሪው አስተማሪው፤ የከተማ ነዋሪውና የመንግሥት ሠራተኛው፤ነጋዴው በኢዲዩ፤በደርግና ኢህአፓ አመለካከት ውስጥ ተከፋፍሎ ሲመሽግ እንደነበር የአይን እማኝ ሆኜ መናገር እችላለሁ።በወገራና ጭልጋ ያመራውን የደርግ ጦር እንቅስቃሴ ለመከታተል አቅሙና ጊዜው ስለአልነበረኝ ከጐንደር ወደ ሁመራ ያቀናውን እንቅስቃሴ ለመከታተል ሁኔታዎች ረድተውኝ ነበርና የሚከተለው ነበር።

ጦርነቱ ከጐንደር ከተማ ወጣ ብሎ የተጀመረ ሲሆን የደርግ ኃይል ከፍተኛ የጦርነት ልምድ ያለው በትጥቅና ወታደራዊ ሎጅስቲክ የተደራጀ ስለነበር በኢዲዩ በኩል የነበረው ሠራዊቱ የጥቂት ጊዜ የጦርነት ልምድና አብዛኛው ሕዝባዊ ሠራዊት በመሆኑ ደርግ አቅም አግኝቶ የላይ አርማጭሆ ወረዳ ዋና ከተማ ትክል ድንጋይን አልፎ መሄድ ጀመረ።ከዚያ በኋላ ግን ደርግ ያላሰበው ሁኔታ ገጠመው። ገና ቆልማሜ ላይ እንደደረሰ የአርማጭሆ የመሬት ቀማመጥ ራሱ ሌላ ጦር በመሆን ደርግን ይፈታተነው ጀመር። ከቆልማሜ እስከ ሙሴ ባምብ የነበረው የደርግ ጉዞ ደርግን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍለው ሳይወድ በግድ እንዲገነዘብ አደረገው።ደርግ ወደ ሥልጣን ከወጣ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የዚያ አይነት ፈተና ሲገጥመው ቆም ብሎ ማስብና የችግሩን መፍትሄ ማፈላለግ ሲገባው ግፋ በለው በማለት ቀጠለ።

ከትክል ድንጋይ እስከ አሸሬ በቀኝና በግራ በኩል ነዋሪ የሆነው የአርማጭሆ ሕዝብ አካባቢያውን በመልቀቅ ቤተሰቡን ከደርግ ጦርና ተወንጫፊ መድፎች በማራቅ የኢዲዩን ጦር በማናቸውም አይነት መተባበርና ማገዙን ቀጠለ። አንድ የገስጥ ክፍለ ጦር አባል የነበረ ሙሴ ባንምብ በጥይት ተመትቶ የነበረ እኔም ኢህአፓ አባላቱን ሲያሰናብት አንዱ ተሰናባች ስለነበርኩ ሁለታችንም በአንድ ክላስ(ክፍል) አብረን መማር ስንጀምር ከቀናት አንድ ቀን ትንሽ ጥያቄዎች አቀረብኩለትና ብዙ ገጠመኞችን አጫወተኝ። ይኸውም የገስጥ ጦር ያከተመለት ሙሴ ባንምብ ነበር።

ነገር ግን በኢዲዩ በኩል አንድ ወጥ አመራር ስለአልነበረ የገስጥ ጦር ባለበት ሆኖ አቅሙን አጠናክሮ የመከላከል ወይም ወደ ኋላ ማፈግፈግ ከሚል ነጥብ ደረጃ ደርሶ እያለ አንድ የገስጥ ጦር ሻምበል ምልክት አሳየ (ባውዛ )አበራ ያ ማለት ወደፊት ግፋ በለው የሚል መልዕክት ነበረ:- ይሁን እንጅ ከአንገረብ ማዶ ጠገዴ ወልቃይትና ጠለምት በቀኝ አርማጭሆ በግራ የገስጥን ጦር እርሳስ እየቀለቡ በመጓዝ ላይ እንዳለ እኔ ኩፉኛ ቆስየ ስልነበር ወደ ክምና ሄድኩ የገስጥ ጦር ግን የሚከፍለውን መስዋዕትነት እየከፈለ ሁመራ ደረሰ ያ ጊዜ በደርግ ታሪክ መጥፎ ገጠመኝ ነበር ብሎ ነበር በአጭሩ የተረከልኝ።

አንድ በውል ያልተመለከትነውና የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ግራኝ መሀመድ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ኢትዮጵያን ሲወር የገሰገሰው ወደ ጐንደር ነበር፤ድርቡሽ(መሐዲስት) ከሱዳን ተነስቶ ኢትዮጵያን ሊወር ሲመጣ መጀመርያ ያቀናው ወደ ጎንደር ነበር፤የፋሽስት ጣሊያን ወራሪ ጦር ከኤርትራ በመነሳት በሁመራ አድርጎ የገሰገሰውም ወደ ጐንደር ነበር፤ ዘረኛውና ቅጥረኛው ህወሃትም ብረት ለበስ ታንኮቹን አሰልፎ ከመቀሌ የገሰገሰው ወደ ጐንደር ነው።

በሥነ-ምግባር ብልሹ የሆኑ አስተዳዳሪዎች የሚሾሙት ጐንደር ነው። በሀገር ደረጃ አንዳንድ ፖለቲካዊ ውጥረቶች ሲከሰቱ የሚጠረጠረውና ጣት የሚቀሰርበትም ጐንደሬው ነው።የትምህርት እድልና የደረጃ እድገት እንዳያገኝ የሚደረገው ጐንደሬው ነው።በመጥፎ አርአያነት ቆርጦ ቀጥል ስም የሚለጠፈውም ለጐንደሬው ነው።የህወሃት የመሬት ቅርምት ትኩረትም በጐንደር ነው።በደርግ ጨፍጫፊ ሥርዓት የጥይት ሰለባ የሆነው ጐንደሬው ነው።መንግሥት እገለብጣለሁ ያለው ሁሉ የሚመሽገውና አካባቢውን የጦርነት ቀጠና የሚያደርገው በጐንደር አካባቢ ነው።ይህ ሁሉ ደባ ሲፈፀም የጐንደርን ሕዝብ ድምጽ የሚሰማና ቀና ብሎ የተመለከተው የለም።

እኔ እስከማውቀው ድረስ የጐንደር ክፍለ ሐገር ሕዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ቀዳሚውን ቦታ ሊይዝ እንደሚገባውና ዳር ድንበሩን ያለመንግሥት ኃይል በራሱ አስከብሮ የኖረ ሀገር ወዳድና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ሕዝብ ነው።ይህን ስል አእምሯቸው ነገር እንደ ግራምጣ ለመሰንጠቅ የተፈጠሩ አዋቂ ነን የሚሉ ከጠባብነት ጋር ሊያላትሙት እንደሚከጅላቸው ይገባኛል። የኔ መነሻ ግን እሱ አይደለም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይህ የዘረኝነት ወረርሽኝ (ቫይረስ)ከመምጣቱ በፊት ክርስቲያን እስላም፤ ትግሬ ኦሮሞ፤አማራ አፋር፤ሀድያ ጉራጌ….ወዘተ ሳይባባል በጀግንነት፤በጋራና በአንድነት የሀገሩን ዳር ድንበር ሳያስደፍር ሉዓላዊነቷን ጠብቆ ያቆየ ሕዝብ መሆኑን ዘንግቼ አይደለም።የጹሑፌ መነሻ ሰሞኑን ህወሃት የትግራይ ሚሊሻዎችን በማስታጠቅ በአማራ ክልል ከሚኖረው የጎንደር ሕዝብ ጋር ለማጋጨት የሰነዘረውን ጦርነት መሠረት በማድረግ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለአካባቢው ሕዝብ ድምጽ መሆንና ነገሩን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የሁለቱ ክልሎች ሕዝብ አጽዕኖት በመስጠት በተለመደው ባህላዊ የችግር አፈታት ጥበብ የተከሰተውን ችግር እንዲያስወግዱትና ወደ ድሮው አንድነታቸው፤አጋርነታቸው እንዲመለሱና ችግሩን እየገፋ ያመጣውና ጠንሳሹም ህወሃት እንደሆነ እንዲገነዘቡ ለማድረግ ነው።

የድሮዎቹ ደጋግ ወላጆቻችን እንዲህ አይነቱን ጠብ አጫሪነት ሲመለከቱ አትስሙት ** ውሃው ሂያጅ ድንጋዩ ቀሪ ነው ** ይሉት ነበር ሰው(ሕዝብ) ድንጋይ ነው ማለታቸው ሳይሆን በምሳሌያዊ አነጋገር መንግሥት ይሄዳል ሌላ መንግሥት ይመጣል ሕዝብ ግን አይቀያየርም ለማለት ነው። ስለዚህ መንግሥትን ወይንም ማንኛውንም እንደ ህወሃት ያለ ወራሪ እንደ ውሃ ሕዝብን ደግሞ ቀየውን እንደማይለቅ ድንጋይ አስመስለው ይናገሩት ነበር። የአሁኑ ትውልድ በዚያ ምሳሌያዊ ዘዴ የተሞላበት አነጋገር ያምናል አያምንም ብሎ ለመናገር በጣም ይከብዳል።ሆዳምነት ፤አድር ባይነት፤ስግብግብነት የተጠናወተን ዞሮ ማየት የተሳነን የሰውን ሰብአዊነት እንደጨርቅ የምንቦጭቅ፤ተራ በተራ ለግዳይ የምንቀርብ፤ለመተማመን የተቸገርን ትውልዶች ነው በአሁኑ ሰአት ያለነው።

የሠሐራን በርሃ አቋርጦ ወደ ዐረብ አገር በእግር መጓዝ ፤አይከፍሉ ከፍሎ በመርከብ ወደ ዐረብ አገር መንጎድ ሞትን በመፍራት ነው ወይም የኢኮኖሚ ችግርን ለመፍታት ነው። ዳሩ ግን ችግሩን መፍታትም ሆነ ከሞት ማምለጥ እንዳልቻሉ አይተናል። ይህን ጦስ ያስከተለው አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የህወሃት ቅጥረኛ ኃይል ነው።ይባስ ብሎም በነዚህ የኢትዮጵያዊነት ዜግነት ባላቸው አብዛኛዎቹ ገና ሕፃናት ወጣቶች ላይ የደረሰውን አስደንጋጭ የሞት አደጋና ሌላ ለመግለጽ እጅግ የሚዘገንኑ ሁኔታዎች ሲፈጸሙ የዓለም ሕዝብ ሳይቀር ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ሀዘኑን ሲካፈለን የህወሃት/ኢሃዲግ መሪዎችና አባላት አንድም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም በማለት በአራት ነጥብ ደመደሙ።

ወደዚህ ነጥብ እንድገባ የገፋፋኝ ሞት ካልቀረ ለምን የሚገድለንን እየገድለን አንሞትም?ምናልባት እንዴት እንጀምረው የሚለው ሊያስቸግር ይችል ይሆናል ልቡ ለቆረጠና ለወሰነ ግን ቀላል ነው። መድረሻቸው ይህ ነው ለማለት ባልችልም የከፋው ፤ግፍና በደል የተፈፀመበት፤የዜግነት መብቱ የተገፈፈበት፤ፍትህ ያጣ ኢትዮጵያዊ የህወሃትን ሥርዓት ማስወገድ አለብኝ ብሎ ማመን አለበት። በዚህ ከተማመን ዛሬ ነፍጥ አንስተው እየተፋለሙ ያሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ቁጥር የሚናቅ አይደለም ከሚመስለው ጋር ተሰልፎ የጋራ ጠላትን ታግሎ መጣል ይቻላል።

ህወሃቶችና አጋፋሪዎች፦እንድታውቁት የሚያስፈልግ ነገር ቢኖር የአክሱምን ሥርዎ መንግሥት የደመሰሰችው ዩዲት ጉዲት እንጅ የጎንደር ሕዝብ አይደለም። የጎንደር ሕዝብ እንደ ግራኝ መሐመድ፤ጣሊያን፤ድርቡሽና ህወሃት ግፍ አልፈፀመም። የሌላውን አገር ወይም አካባቢ ሊወር አልተነሳም ይልቁንስ በደም በተቦካ አጥንቱ ድንበሩን ጠብቆና አስከብሮ የመንግሥት ግብር ገብሮ የኖረ ጎንደሬ ሆኖ በኢትዮጵያዊነቱ እጅግ የሚኮራ ሕዝብ ነው የጎንደር ሕዝብ ።

አይን ያማረውን ሁሉ የራስ ለማድረግ በሚቋምጥ ስግብግብ አስተሳሰብና ቀሽም ብልጣ-ብልጥነት ጥቂቶች ብዙዎቹን አጭበርብረው ሊሳካላቸው የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።ከዚያ በኋላ ያለው ባለቤቱ እንጉልቻም ካልሆነ ፈላጊው ቢሞክርም በል ተመለስ ድንበሩ እሱ ነው ብሎ ባፍ ጢሙ እንዲደፋ ማድረግ ይቻላል።የወልቃይት ጥገዴ የአርማጭሆ፤የጠለምት ፤ አዳኝ አገር ጫቆ እና የጎንደር ሕዝብ በቅርቡ ያደረገው ይህንኑ ነው። ይህም ተጀመረ እንጅ የመጨረሻው አይደለም። እንዲያ ነው የአገሬ ሕዝብ!! ሽንፋ ፤ቋራ መተማ፤ጭልጋ፤አለፋ ጣቁሳ፤ደምብያ፤ጠዳ፤በለሳ፤ሰሜን፤አምባጊዮርጊስና ዳባት፤አዳርቃይ፤አዲሰላም፤በየዳ ጃናሞራና በለሳ ይዞህ ብቻህን አይደለህም በርታ።ከጎንህ የምንሰለፍበት ቀን ሩቅ አይደለም።

በመጨረሻም ለህወሃት የመከላከያ ሠራዊት ጥብቅ ማሳሰቢያየ ይድረስ፦አሁን እየገደልከው ካለው ሕዝብ አብራክ መፈጠርህን የምትክድ አይመስለኝም። በተግባርህና በአስተሳሰብህ ግን ክህደትህን አጉልቶ የሚያሳይ በርከት ያሉ ማስረጃዎችን ከአራቱም ማዕከል እየመዘዙ ማቅረብ ይቻላል።አለቆችህ ዛሬ ባለፎቅ፤ባለ ዶላርና የተንደላቀቀ ኑሮ እየኖሩ እንዳሉ ታውቃለህ።ይህን አይነት የደላ ኑሮ ለመኖር አንተ ህዝብን በጅምላ መፍጀት ይገባሃል ወይ?የዛሬዎቹ ጌቶችህ ይህ አሁን የመሣሪያህን አፈሙዝ አዙረህ በምትገድለው ህዝብ ከዚህ እንደ ደረሱ በግልጽ ልነግርህ እወዳለሁ።ሰፊ ዘገባ ይዥ እስከምቀርብ ለዛሬ ያለኝ መልእክት ህወሃት ከፊትህ ለህዝብ ነፃነት ከሚፋለሙ ጀግኖች መሣሪያ የሚተፋው እርሳስ ከኋላህ ህወሃት ያሰማራው ገዳይ ኃይል በሚተኩሰው ጥይት ጀርባህንና ግንባርህን እየተመታህ የአሞራ ቀለብ ከመሆን ራስህን በራስህ ልትታደገው ይገባል።እንደ ድሮው ቤት ያፈራውን አካፍሎ የታመመ አስታሞ የቆሰለን እስኪያገግም ሸሽጎና የሞተን እየቀበረ መውጫ መግቢያውን እየመራህ የሚሄድ ሕዝብ የለም።ያለህ አማራጭ የህዝቡን ትግል መቀላቀል ወይም የሰው በላው ሥርዓት ማገዶ በመሆን ማለቅ ብቻ ነው። የአገር መከላከያ ሠራዊት ሳይሆን የህወሃት የእድሜ ዘመን እንዲረዝም የሕዝብን መብት በማፈን ተግባርህ መቀጠል አይገባህም።ዛሬ ብዙ አማራጮች አሉህ።እነዚህ አማራጮች ሳይጠቡ ተጠቀምባቸው ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ከሚዋደቁት ጎን ተሰለፍ፤የሕዝብ ልጅ በመሆን ታሪክ ሥራ ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>