አርባ ዓመት ሸፍቶ የወረረን ጥልመት፤
ጋዜጠኛ ስለሺ የተደበደበው ሰውነቱ በፋሻ ተጠቅልሎ ይታያል
አሳር አቆራኝቶ የሚወጋን ባጥንት፤
ከሰይፍ የከፋ ‘በሙት ዓጽም’ ጉልጥምት፤
ሽል እየከፈለ እያብጠለጠለ እየቆረጠ እትብት፤
ይህ የምታዩት የስለሺ ሐጎስ የተሰበረ አጥንት ነው። እንግዲህ ይሄ እስኪሆን ድረስ ነው ይህን ሰላማዊ ወጣት የደበደቡት !!!! በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ተመልከቱ። እነዚህ አጥንቶች የተሰባበሩት ለከንቱ ነገር አይደለም። ለነጻነት ነው። ለኢትዮጵያ አንድነት ነው። ለፍትህ ነው። ለእኩልነት ነው። ሕወሃት ስጋችንን ሊበላ ፣ አጥንቶቻችን ሊሰብር ይችላል። ሆኖም መንፈሳችንን፣ ወኔያችንን፣ አንድነታችንን ሊሰብር አይችልም። አንፈራም። አናቀረቅረም። አንገታችንን አንደፋም። አናፈገፍግም። ዝም አልንም። ድምጻችንን እናሰማለን ! ከያለንበት፣ በዘር፣ በቋንቋ ም በድርጅት ሳንከፋፈል እንነሳለን። ይህ አይነት፣ ጨካኝ ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲወገድ እንሰራለን ! አራት ኪሎንን እና የሕወሃት ጽ/ቤትን የተቆጣጠረው፣ በሕዝባችንን ደም እየጠጣ የሚረካው አጋንንት ከአገራችን እናባረራለን። የፊታችን እሁድ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች አሉ። ለሰለፎቹ እንዘጋጅ!!!!! ዱላና ማስፈራሪያ እንደማይበግረን እናሳያቸዋለን !!!
The post “ወያኔያዊ አይሲስ” – የጐንቻው! appeared first on Zehabesha Amharic.