መግቢያ፦ ልማድ ሆኖብን እኛ ኢትዮጵያውያን በደም በተቦካ አጥንት ተከብሮና ታፍሮ የኖረውን ዳር-ድንበራችን አስደፍረን አገራችን ለወራሪ አጋልጠን ሰጥተን በአውሮፓ ኮሎኒያሊስቶች ያልተደፈረች አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት እያልን ወደ ኋላ ሄደን የጀግኖችን ታሪክ እያወራን አሁን መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ዘለነው እንሄዳለን ረጋ ብሎ ማሰብም ተስኖናል።በርግጥ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የነፃነት ታሪክ አላት፤ለውጭ ወራሪም የተመቸ ሕዝብና ምድር አይደለችም ያ !! ግን አሁን አይደለም ከእምየ ምኒልክ የአድዋ ጦርነትና የጣሊያን ድል መሆን በኋላ ኮሎኒያሊስቶች ያልተኙ መሆናቸውን አሳይተውናል የ1928 ሁለተኛ የጣሊያን ወረራ አንዱ መገለጫ ነበር።በዚህ ያልባነነው ኢትዮጵያዊ ምሁርና ፖለቲከኛ ዝና ለማትረፍ ራሱን ወደ ሥልጣን ለማውጣት ከመባከን አልፎ የውጭም ሆነ የውስጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች በፖለቲካ፤ኢኮኖሚውና ማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ እንዴት እየሰረሰሩ ገብተው መዋቅራቸውን እንደዘረጉና ዛሬ እዚህ ላይ እንደደረሱ ያለመ ወይም ያሰበበት አልነበረም።
ማሳያዎቼ ባጭሩ
ምዕራባውያን ወራሪዎች መላው አፍሪካን እጃቸው ሥር ለማስገባት መጀመሪያ ኢትዮጵያን ማጥፋት ወይም መዳፋቸው ሥር ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ ያደረጉትም ይኸውኑ ነው።ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የአገር ውስጥ ቅጥረኞችን እንደ ዋና መሣርያ ተጠቅመው ያለምንም ኪሣራና መስእዋትነት ኢትዮጵያ አገራችን እየበዘበዙ ይገኛሉ።ዛሬ ታሪካዊ ቅርሶቻችን እየፈረሱ፤ባሕላችን፤ወግ ልማዳችን እየተደፈረና ባእዳዊ ባሕል ወግና ልምድን እንድንቀበል እየተገደድን ያለንበት ወቅት ሲሆን ኢትዮጵያዊ ባለሀብቶች ገለል በሉ ተብለው የንግዱና የእርሻው ዘርፍ ከውጭ በገቡ ባለሀብቶች እጅ ውስጥ ገብቷል።ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ሀገር እስረኛ፤ስደተኛና ዜግነታቸውን ተነፍገው በመንገለታት ላይ ይገኛሉ።አብዛኛው በተለይም ወጣቱ ትውልድ ስደትን እንደመፍትሔ በማየት በውቅያኖስ ሲጓዝ በከፋ አደጋ እያለቀ እየተመለክትን ነው፤በበርሃ የሠሃራን በርሃ ሲያቌርጥ በውሃ ጥማት፤በርሃብና በአውሬ እየተበላ እያለቀ ነው።በለስ ቀንቷቸው ዐረብ አገር የደረሱትም በዘመናዊ ባርነት እየተሰቃዩ ሲሆን በዐረብ ቱጃሮች እንደ ዕቃ ከፎቅ ላይ ሲወረወሩ፤በፈላ ዘይትና ውሃ ሲቀቀሉ እየሰማን እየተመለከትን ነው።ሴት እህቶቻችን በዐረብ ጎረምሣ እየተደፈሩ ወጣት ወንዶች በገጀራ በቀን አደባባይ ላይ ሲታረዱ እያየን እየሰማን ነው።
ዴሞክራሲ የሚባልና የመልካም አስተዳደር ሥነ-ምግባሮች፤ፍትሕ ተቀብረው አገር መራሹ ጎጠኛውና ዘረኛው የህወሃት አገዛዝ የአገሪቱን ሕዝብ እንደ እርጉዝ አስጨንቆ እንደ ሞፈር አርቆ መተንፈሻ በማሳጣት ቀጥቅጦ እየገዛ ይገኛል።መሠረታዊ የሆኑት የሕዝብ ነፃነቶች ታፍነው ሕዝብ የመደራጀት፤የመሰብሰብ፤ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ፤የትቃውሞ ትእይንተ ህዝብ ማድረግ የሚያሳስሩ የሚያስገድሉ፤የሚያሰድዱ ሆነዋል።የገዥው ፓርቲ ደጋፊና አባል ያልሆነ የቤት፤የንብረት ባለቤት መሆን ቀርቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ተዘዋውሮ በፈለጉት ሠርቶ መብላትና መኖር የማይቻልበት ወቅት ላይ እንገኛለን።በተለይም ነገ የኢትዮጵያ ተረካቢ የምንላቸውን ወጣቶችንና አማራውን ኢላማ ያደረገ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በስፋት እየተካሄደ ነው።
«የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል»እንዲሉ ህወሃትን በሰላማዊ መንገድ ታግለን በምርጫ እናቸንፋለን ያሉት የተቃዋሚ ድርጅቶች(ኃይሎች) በሚያደርጉት ጥረት እያደነቅሁ ነገር ግን መጀመርያ የጋራ ግንባር ፈጥሮ አለመታገል አንዱ ችግር ነው ብየ አምናለሁ በሁለተኛ ደረጃ የገዥውን ቡድን አረመኔነት በግልጽ እያወቁ ሁሌ አንድ አይነት ጉዞ መጓዝ ስልቶችን እየቀያየሩ አገዛዙን በመነወጥ ላይ እንዲሁም ወደታች ወርዶ ህዝቡን ለማደራጀት የሚደረገው ሂደት በአገዛዙ ካድሬ የሚወርድባቸውን አበሳ ቢገባኝም በሕቡእ አለመደራጀት ስንቶችን እንዳስበላና ወደፊትም ሊያስበላ እንደሚችል ለዚህም የመከላከል አቅማቸው ደካማ በመሆኑ በየሰላማዊ ሰልፉ አደጋ የደረሰባቸው፤የተደበደቡ፤የታሰሩትን ስንመለከት ድርጅቶች በዚህ ከቀጠሉ የሚተርፍ ህዝብ እንደማይኖር ያመለክታል።
ዮዲት ጉዲት ፤ ግራኝ መሀመድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ናቸው ነገር ግን የፈጁት የራሳቸውን ህዝብ ነበር።ህወሃትም በትውልድ ደረጃ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ቢሆንም በተግባር ግን ከደርግ የከፋ፤ከድርቡሽና ጣሊያን የማይተናነስ የዮዲትንና የግራኝ መሀመድን ጭካኔ የትሞላበት ድርጊት ፈጽሟል አሁንም ይህን አውሬያዊ ባህርዩን አሻሽሎ ቀጥሎበታል።ከተለያዩ ድሕረ-ገጾች የሚወጡ ጹሑፎችንና ከአንዳንድ መጽሐፍት አንብቤ እንደተረዳሁት ከውጭ የመጡ ወራሪዎችና የአገር በቀል ወራሪዎች እንደ ህወሃት ረጅም ጊዜ ባይኖራቸውም ጊዜ ቢያገኙም እንደ ህወሃት በረቀቀና ስውር በሆነ መንገድ ህወሃት የፈጀውን ሕዝብ ያህል ይጨርሱ ነበር ብየ ለማመን ይቸግረኛል።ህወሃት በጫካ በነበረበት ወቅት በየመንደሩ ገበያውና ቤተክርስትያኑ፤እንዲሁም የተራበውን ሕዝብ እንዲሰደድና የእርዳታ መለመኛ በማድረግ በሕዝብ ስም የተገኘውን እርዳታ የድርጅት ማጠንከርያ በማድረግ ህዝብ በርሃብ እንዲያልቅ ያደረገ አረመኔ ድርጅት ነው።ህወሃት በ1983 ወደ ሥልጣን ከወጣ በኋላም የየቀኑ ዜናዎች ህወሃት ያሰረው፤የገደለውና ያስገደለው፤ሰውሮ ደብዛውን ያጠፋው ህዝብ ብዛት ቤት ይቁጠረው ተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን በውል መታወቅ ያለበትና ህወሃት ተገቢውን ዋጋ እንዲከፈለው ማድረግ ተገቢ ነው።
የህወሃትን የጫካ ጭፍጨፋ ሳንነካ ሥልጣንን መከታ በማድረግ በመላ ሀገሪቱ ቅልብ ደህንነት፤የፌደራል ፖሊስ፤ፖሊስ፤የክልል ፈጥኖ ደራሽ፤በመከላከያ ሠራዊቱና በካድሬው ያስፈጀውን ህዝብ ብንወስድ ከአንድ ነገድ ሕዝብ ከአማራው ብቻ አምስት(5)ሚሊዮን የአማራ ሕዝብ ፈጅቷል።በርግጥ አማራው ምን ጊዜም ቢሆን የህወሃት ኢላማ መሆኑ ቢታወቅም ህወሃት አምስት ሚሊዮን የአማራ ነገድ ሕዝብ ጨፈጨፈ ተብሎ ሲቀርብ ሊሆን አይችልም ብሎ ሊሞግት የሚነሳ ሊኖር እንደሚችል ግምት ውስጥ በማስገባት ከሁለት ወረዳዎች ብቻ ቃብቲያና አዲረመጥ 6ሽህ የማያንሱ ንጹሃን ዜጎችን በከንቱ ደማቸው እንዲፈስ ያደረገ ድርጅት ነው።ወተር፤በድኖ፤አርባጉጉ፤ጉራፈርዳ፤ቤንሻንጉል ያለቁት አማራዎች ናቸው።አሁንም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ህገ-መንግሥቱን ሊንዱ፤ሽበራ ለመፍጠር ወዘተ… በማለት ሰላማዊ ትግልና ሰላማዊ ሰልፍ በሚደረግበት ቦታ ሁሉ ኢላማ እንዲሆን የሚደረገው አማራው ነው።የአማራው ጠላት የህወሃት ሥርአት ብቻ ሳይሆን አማራውም የአማራ ጠላት በመሆን በአማራ ነገድ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋትና እልቂት ዘመቻ ላይ ከፍተኛ ርብርብ አድርጓል። በዚህ ጉዳይ በዋናነት ሊጠቀስ የሚችለው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) ሲሆን በግለሰብ ደረጃም በቁጥር በርከት ያሉ ሆዳም አማራዎች በእልቂቱና ደም በማፋሰስ የማይናቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።ይህን ሀቅ የብአዴን ካድሬና ነባሩ የኢህዴን አባል አይክደውም እነ ታደሰ ካሣ፤ህላዊና አዲሱም ዛሬ ሊመሰክሩ ባይችሉም አማራው ላይ የተፈጸመውን ግፍ ያውቃሉ።ምክንያቱም ጠቋሚዎችና መንገድ መሪዎች እነሱ ናቸውና።
የጹሑፌን ርእስ 5ሚሊዮን የአማራ ነገድ ሕዝብ የት ደረሰ? ያልኩበት ምክንያትም ከዚህ በላይ ለዘረዘርኳቸው ማሳያና ወደፊትስ እንዲሁ የአማራው ነገድ ሕዝብ እንደ አውደ አመት በግና ዶሮ ተራ በተራ እየታነቀ ማለቅ ወንስ ራሱን አደርጅቶ ራሱን መከላከል?በዚህ ዙርያ ብዙ ሞጋች ነገሮች ገጥመውኛል እንዴት አማራው ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ደሙን አፍስሦ፤አጥንቱን ከስክሶ ባቆያት አገር እንደ ህወሃት በጠበበ መንገድ ይሄዳል የሚሉ በብዛት ይገኛሉ። የሌላው ነገድ ህዝቦችም ይህንኑ ይደግሙታል ይህ ማለት በገደምዳሜው ህወሃት በጀመረው መንገድ አማራውን ይፍጀው አማራውም እጁን አጣጥፎ ሞቱን በተራ ይጠብቅ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
የአማራ ነገድ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምንና የሚኮራ፤ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ ተከብሮና ታፍሮ ተጠብቆ እንዲኖር የሚፈልግ፤በኢትዮጵያ ጉዳይ ማናቸውንም መስእዋትነት የከፈለ የሚከፍልና ዝግጁ የሆነ፤ከሌሎች አጋር ነገዶች ጋር በአንድነት በሰላምና በእኩልነት፤በፍቅርና በመተሳሰብ አብሮ የኖረና የሚኖር፤አርቆ አሳቢና አስተዋይ፤ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበት፤አትንኩኝ ባይ ማንንም የማይነካ ኩሩ ህዝብ መሆኑን ያስመሰከረ ስለሆነ ጠባቦችና ጎጠኞች በነጎዱበት የሚነጉድ አለመሆኑን ልናምን ይገባናል።በሀገር ልማትና እድገት ስም በየዐረብ አገሩና በምእራባውያን አገራት እርዳታና ብድር እየቀላወጡ በሚገኘው ልገሳ አዲስ አገር ለመገንባት መሽቆጥቆጥና የሀገርን ሀብት አሟጥጦ መዝረፍ፤የመሬት ማስፋፋት ፍላጎት አባዜን ለማርካት ሕዝብን ከቀየው ማፈናቀልና በጅምላ ዘርን ማጥፋት የህወሃት ተግባር እንጅ የአማራው ነገድ ሕዝብ ተግባር እንደማይሆን በርግጠኛነት መናገር ይቻላል።
ህወሃትን ማን እንዳሳደገውና አሁንም ከኋላ በመሆን አይዞህ የሚሉት ምእራባውያን፤ያለ ምንም ጦርነት ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ያስገቡት ቻይናውያንና ህንዳውያን ድጋፍ የዐረብ የነዳጅ ዘይት ገንዘብ ድጎማ ነገ የህወሃት የኃይል ሚዛን ሲያጋድል ፊታቸውን ወደ የት እንደሚያዞሩ ለመናገር ነብይነትን አይጠይቅም።ህወሃትን ሊያድነው የሚችለው መንገድ ሚዛናዊ የሆነ ፍትሕ፤መልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ነፃነትን በማስፈን እንጅ በተዘረፈና በብድር በተገኘ ገንዘብ፤በዘመናዊ መሣርያና በመጠነ ብዙ ግዙፍ ሠራዊት ግንባታና ትጥቅ አይደለም።አባቶቻችን የውጭ ወራሪዎችን ሲገጥሙና አሳፍረው ሲመልሱ ይህ የዛሬው አይነት በሳይንስና ቴክኖሎጅ ያደገ ትጥቅ ይዘው አልነበረም።ይልቁንስ ህወሃት የተጨማለቀብን እኛን መስሎ የእኛን ቋንቋ እየተናገረ፤ከእኛ ጋር እየዋለና እያደረ፤ከእኛ ጋር እየተሰደደ በመሃላችን እየገባ በዘር፤በሃይማኖት እንድንጋጭና በጥርጣሬ አይን እንድንተያይ፤በአንድነት እንዳንቆም እንድንከፋፈል በማድረጉና እኛም በሩን ከፍተን በመስጠታችን እንጅ የህወሃት ድርጊት የጣሊያኑ ሞሶሎኒና የጀርመኑ ሂትለር ከፈጸሙት የከፋ እንጅ ከዚያ ያነሰ አይደለም።ስለዚህ ህወሃት መወገድ አለበት ስንል እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ወስደን ሳይሆን እንደ መሐዲስ ወይም እንደ ጣሊያንና እንግሊዝ ወራሪ ኃይሎች ተመልክተን መሆን አለበት።
አማራ ራስህን ለመታደግ ራስህ መነሳት አለብህ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
ነብሮ ነኝ።
The post አምስት(5) ሚሊዮን የአማራ ነገድ ሕዝብ የት ደረሰ? appeared first on Zehabesha Amharic.