Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ዲሞክራሲአዊቷ አገር ጥምር ሪከርድ ሰበረች። -ከ-ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0
Ketema

ከተማ ዋቅጅራ

መቼስ ሪከርድ ተሰበረ ስል ቀነኒሳ በቀለ ወይም መሰረት ደፋር ወይም ጥሩነሽ ዲባባ አልያም ገንዘቤ ዲባባ ሌላም ሌላም ብላችሁ ግምታችሁን ለአትሌቶቻችን እንደምትሰጡ ተስፋ አደርጋለው። የምነግራችሁ ግን በአትሌቶቻችን የተሰበረ ሪከርድ አይደለም። ዲሞክራት ከሆኑ አገሮች መኃል በዲሞክራቷ የተሰበረ ሪከርድ ነው። ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ነገሰባት እየተባለች የሚነገርባት ለዚች አገር ዲሞክራሲ አመጣን የሚሉትም የሚዘፍኑላት ከበሮ  ድድም ድድም ደርብ ደርብ ተብሎ የሚጨፈርላት አገር.. የዲሞክራሲ ውጤቶችን በከፊል እንይ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ንቀትና ጥላቻው እስከ አፍንጫው የደረሰው የደደቢቱ ዲሞክራሲ አምጪ በሰላሌ ከተማ ላይ የኦሮሞ ገበሬ አርሶ አብቅሎ ህዝብን የሚመግበውን ገበሬ ንጽሃኑን እና ለአገሩ ለፍቶ የሚያድረውን ገበሬ በነዋሪው ፊት አስክሬናቸውን መሬት ለመሬት ከጎተተ በኋላ አስክሬናቸውን በአደባባይ በመስቀል ዲሞክራሲ አራማጅ ከሆኑት አገሮች ሁሉ እንዲሁም ዲሞክራሲ አምጪው ካረቀቀው ህግ ውጪ ለተመልካች በሚዘገንን ሁሌታ ለሰሚም በሚከብድ ሁኔታ በዚህ ዘመን ሊፈጸም ቀርቶ ሊታሰብ የሚከብድ ዘግናኝ እና ሰው ሆኖ እንደ ሰው ከሚያስብ የማይጠበቅ ተግባር በመፈጸም ንጹሃንን ዜጋ ገድለው በአደባባይ አስክሬንን በመስቀል ዲሞክራሲ ከሆኑ አገሮች አንደኛ በመውጣት የአለማችን ግፈኛውና አረመኔው ዲሞክራሲ አራማጇ አገር በሚል ከዲሞክራሲ አገሮች  አንደኛ በመውጣት ሌሎች በማይደርሱበት አኳኃን አርቆ በመስበር ኢትዮጵያ  አንደኛ ሆናለች።

የደደቢቱ ጥምር ሪከርድ ሰባሪ ኢትዮጵያ በየአመቱ በዚህ ፐርሰንት እድገት በማምጣት እድገት አሳይታለች ከመሃከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ተሰልፋለች የሚለን ህዝቡ የኑሮ ውድነት የፖለቲካ ጫና የሰላም እጦት ከአቅሙ በላይ ሆኖ ሰላምን ፍለጋ ከአገር ቤት የሚሰደደው ህዝብ ቁጥር ከእለት ወደ እለት በሚያስደነግጥ መልኩ  እየጨመረ  መጥቷል። ከዲሞክራት አገር እና እድገት ከሚያመጡ አገራት መሃል በአመት ከ 100,000(መቶ ሺ) በላይ የሚሰደዱባት አገር ሆና ባስመዘገበችው ውጤት ከአለም ዲሪሞክራት አገራት መሃል በተደረገው ጥናት ኢትዮጵያ አንደኛ በመውጣት ሪከድር ሰብራለች።

የTPLF ዲሞክራሲ እና እድገት   አምጪዎች በየአመቱ የተማረ ሃይልን በማፍራት በተማረ ሃይል ዲሞክራሲ ከሚከተሉት አገራት ከፍተኛ ቁጥር በማስመዝገብ የተማረ ኃይል እና የሰራ እድል ፈጥረናል ..የሚለው መሬት ላይ ያለው እውነት ግን ወጣቱ ተምሮ እና ተመርቆ ስራ በማጣቱ ተስፋ ቆርጦ ወደተለያየ ሱስ በመግባት ላይ ነው። ከዲሞክራት ገራት ወጣቱን ተስፋ እንዲቆርጥ በማድረግ እና  ወደተለያየ  ሱስ እንዲገቡ ያደረገ መንግስት የTPLF መንግስት በመሆን ከአለማችን ዲሞክራት አገሮች መሃከል አንደኛ በመውጣት ሪከርድን አስመዝግቧል።

የፖለቲካ አመለካከት የተለየ ከሆነና ወያኔን የምትቃወም ከሆነ እንዲሁም ብዕር የያዙትን ጋዜጠኞችን አልያም ጸሐፊዎችን ፖለቲከኛው በፖለቲካ አመለካከቱ፣ ጋዘጠኛው በሚዘግበው ዘገባ፣ ጸሐፊው በሚጽፈው ጽሁፍ ከወያኔ ሃሳብ የተለየ ከሆነ እንደነዚ ያሉት በሙሉ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ከሚከተሉ አገራት ለየት ባለ  መልኩ የተለየ የፖለቲካ አመለከካከት በመያዛቸው ብቻ  እንዲሁም ጋዜጠኛው ለየት ያለ ዘገባ በመዘገቡ ወይማ  ጸሃፊዎችም ከምንግስት ኃሳብ የተለየ በመጻፋቸው አሸባሪዎች ናቸው ብላ እስከ ሞት ቅጣት የምትቀጣ ከዲሞክራሲ ተከታይ አገሮች ብቸኛዋ አገር በመሆኗ ጥምር ሪከርዶችን አስመዝግባለች።

ከላይ እንደመነሻነት የጠቀስኳቸው ነገሮች እውነት የማይመስሉ ነገር ግን እውነት የሆኑ እና በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸሙ እና እየተፈጸሙ ያሉ ዘግናኝ እና አሳፋሪ ድርጊቶች እየተሰራባት ያለች አገር መሆኗ ነው። እንደ መንደርደሪያ ኃሳብ ይህንን አልኩኝ እንጂ እጅግ በጣም ብዙ ኢሰብአዊ ድርጊት እንደሚፈጸም እሙን ነው። በኢትዮጵያ ከእለት ወደ እለት እየመጣ ያለው ቅጥ ያጣ ግፍ በአደባባይ በመቃወም እና በመግለጽ በህዝባችን ላይ የሚፈጸመውን በደል ለማስቆም ቆራጥ እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ማወቅ ያለንበት ግዜ ላይ ደርሰናል።

እስቲ እንወያይበት በሁሉም አቅጣጫ ያለውን እንቅስቃሴ እንቃኘው። ነገር ግን ፍርሃትን ከልቦናችን እናስወጣ ቆራጥነት እና እውነተኝነት ይዘን እንቀሳቀስ። ለመወያያ ሃሳብ እና ሁሉም የሚያውቀውን ነገር እንዲያካፍለን ዲሞክራሲ እንከተላለን ከሚሉ አገራት ውስጥ ያልተከሰቱ ክስተቶችን በአገራችን ግን ከግፍ በላይ ግፍ የሚሰራባት አገር እንደሆነች ትንሽ ብያለው። አንባቢው ደግሞ  ያየውንና የተሰማውን ማስነበብ ይችላል። ያወቅነውን ስንናገር ያሰብነውን ስናካፍል ያኔ ለህዝቡ ጥሩ ግንዛቤ በመስጠት ጥሩ ነገር ላይ እንደርሳለን። ብረት ወይም አፈሙዝ ሰውን በግድ ለጊዜው ያሳመነ ይመስለን ይሆናል። ብዕር ግን ሰውን አሳውቆ እና አስተምሮ ያሳምናል። ስለዚህ ሃሳባችሁን አካፍሉ የምታውቁትንም ጻፉ ብዙሃኑ ይማርበታልና። ህዝብን  በአፋኞች ኃሳብ ተመርቶ ወደ አንድ አቅጣጫ በመሄድ ስህተት እንዳይሰራ ያደርጋልና። መንግስት ህዝብን ለማፈን የሚጠቀምበትን ነገር ግፈኞች ህዝባችን ላይ የሚያደርሱትን በደል ከዛም አልፎ አገር ላይ የሚመጣውን ጥፋት ቀድሞ በማወቅ እና በማሳወቅ አገርን ከበደል እና ከጥፋት መታደግ እንችላለንና። የምታውቁትን ነገሮ መረጃዎች በቪዲዮ ይሁን በጽሁፍ ለሚዲያ በመላክ ህዝብ እንዲያውቀው በማድረግ የበኩላችንን እንወጣ በማለት መልዕክቴን አስተላልፋለው።

ከ-ከተማ ዋቅጅራ

14.02.2015

Email-waqjirak@yahoo.com

The post ዲሞክራሲአዊቷ አገር ጥምር ሪከርድ ሰበረች። -ከ-ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>