Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

እናንተ ለአገልግሎት ነበር። እነሱ ዘበኛ ነው የሚፈልጉት። –ዳዊት ዳባ

$
0
0

እርጉዝ ነኝ እያለችህ ሴትን ልጅ ሆዷን ረግጠህ ፅንስ አስወረድክ። አሮጊትና ሽማግሌ በጫማ ጥፊ ሳይቀር የሚደበድቡ  አሉ።  አንድን ሚስኪን ወገን አስርና አስራ አምስት ሆነው ለጉድ ሲቀጠቅጡም በተደጋጋሚ አየን። መፍክር ብቻ በጁ ይዞ የጋራ ለሆነ መብትና በደል  ሊያሰማ አደባባይ የወጣ ዜጋ  አቅማቸውን ለማሳየት በብዙ ቁጥር ደግሞ ስልጠናችውን የጠቀማሉ። የማጥቂያ እቅድ ይሰጣቸዋል። ቆረጣው፤ ከብባአድርገው፤ አደፍጠው ብቻ ያለ ወታደራዊ እውቀት ሁሉ ተፈፃሚ ማድረጉ እንዳቅሚቲ  አይቀራቸውም ። ይህ ሁሉ መሀል ከተማ  አዲስ አበባ ውስጥም ነው እየተፈፀመ ያለው። በዚህ ሰሞን እንደገና አገረሸ እንጂ ይህን አይነቱ ታሪክ ሀያ አራት አመት አለው። ብዙ ንፅሁን ዜጎች መገደላቸውን፤ አካለ ጎዶሎ መሆናቸውንና ስብእናቸው መደፈሩ ተመዝግቧል። ሁላችንም ሳንሰማው ያልቀረነው። በአገር አይቻል ሆኖ ለሰው ልጅ ሂወት ክብር በሚሰጡ በሌሎች አገሮች ፍርድ ቤት እየታየ ያለውና  በአለማቀፍ ፍርድ ቤት  ተራ እየጠበቁ ያሉ ዘር ማጥፋት፤ ዘር ማፅዳት፤ በንፅሀን ላይ የተፈፀመ ፍጅት የመሳሰሉ ከባባድ ኢትዬጵያዊ ክሶች ገዥዎቻችን  ስማቸው ተጠርቶ ቢከሰሱበትም  እነሱ ወርደው ተኩሰው ስለገደሉ እንዳልሆነ  ግልፅ ነው።

ለተቀደሰ አገራዊ  ተግባር፤ የሂወት መሰዋትነት ድረስ የሚሻ ግልጋሎት ለመስጠት የፈቀዳችሁ ብዙ መቶ ሺዎች ናችሁ። በቀጥታ የዚህ አይነት ወንጀሎች ላይ ድርሻ ያላቸውን ከውስጣችሁ ማጥራትና ማወቅ ቢቻል ቁጥራቸው እጅግ ጥቂት ሊሆኑ ይችላል ይባል። ከዚህም አልፎ ከውስጣችሁ በዘር ወይ በፖለቲካ አመለካከት ተመርጦ ተመሳሳይ ለሆኑ የሰራዊቱ አባላት ግድጅ የሚሰጥበትና ወንጀሉ የሚፈፀምበት ሁኔታም መኖሩ አይቀርም። እውነታው ይህ  ቢሆን እንኳ ለጥቃቱ ሰላበዎች ሆነ ለጠቅላላው ዜጋ በዚህ ደረጃ አስፍቶና በትኖ የማየት ግዴታ ግን  የለበትም። እውነት ለመናገርም መረጃውም የለውም።  የሚያውቀው ከወንጀሉ ስፋት፤ ለረጅም ጊዜ የቀጠለ መሆኑንና ከተጎጂዎች ብዛት አኳያ  ቀላል የማይባል ቁጥር የላቸው ጓዶቻችሁ ድርሻ እያደረጉበት እንዳለ ነው። በዚህ እናንተም ብትሆኑ የምትስማሙበት ነው።

አዎ ዜጋው የሚረዳውም ሆነ የሚያውቀው  ሰራዊትነቱን፤ ፖሊስነቱን  ዩኒፎርሙን በአጠቃላይ ሞያው   የጋራ መለያችሁ መሆኑን  ነው።  ግን ለምን? ለሚለው ጥያቆም ሆነ ወንጀለኞቹ ጣሰው ይሁን መገርሳ ወይ ገብሬ የሚያውቀው ነገር የለም።  እናንተ ግን ታውቋችዋላችሁ። ስለዚህም በስልጠና በማደንዘዝም ይሁን በማስፈራራት ወገናዊነቱን ጨርሰው ክውስጣችሁ ካልሟጠጡት አንድ ነገር ማድርግያው ጊዜው አሁን ነው። ለወገን ፤ ለእውነት፤ አቅም ለሌው የመቆሙ ስብእና ከሌለ እንኳ ቅንጣት ታክል ለራሳችሁ የምትሰጡት ክብር ካል እባካችሁ ይህ  ፍፁም ሰላማዊና ንፁሀን የሆኑ ወገናችሁን፤  ህፃን፤ ሴት፤ አሮጊት  ሳይለይ  የተያያዙት ፍጅት ይብቃ ይባል። ዋጋም ቢያስከፍልም  በኛ ስም አይደረግ ወይ አናደርግም  ማለት የግድም የቶሎም ሆኗል።  አሳሳቢ ያደረገው ይህ ፍጅት በመላ አገሪቱ ለሀያ ሶስት አመት የቀጠለ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከጊዜ ግዜ እየጨመረና ዘግናኝ እየሆነ መሄዱም ነው።

ለመሆኑ ማን ነህ አንተ?። ማን ናችሁ?።  ይህን ደጋግሞ መጠየቅና ማስታወስ የግዜው አንገብጋቢ ቁምነገር ሆኗል። ብዙ ብዥታ ውስጥ ያሉ አሉና። ሁላችሁም ሊሰኝ በሚችል ዝቅተኛ ኑሮ ካለው ቤተሰብ እንደውም እንደኔ ከደሀ ቤተሰብ የመጣችሁ ናችሁ። አብዛኛዎቻችሁ ፍዳ እያየ ያለው የገበሬ ልጆች ናችሁ። ገዳዬቹም ቢሆኑ ይህ ውሸት ነው መቼም አይሉም። ካሉ ግን ከትላልቆቹ ባለስልጣናት ግዴለም ይቅር። ከሚታወቁ ከመለስተኛ ባለስልጣናትና ከባለ ጊዜዎች አብረዋችሁ የሚያገለግሉ አስር የሰራዊት አባላትን  ቁጠሩ እስቲ?። እሺ አምስት።  ከሶስት መቶ ሺ ከሚጠጋ ብዛት  በእርግጠኛነት ለስም አንድ እንኳ እንትና ማለት አይቻልም። የለማ። መራርም ቢሆን እውነታው ሁላችሁም ከሚገደለው፤ ከሚደበደበው፤ ከሚዋረደውና ነፃነቱን ከተቀማው ወገን ናችሁ። ቪላ ውስጥ አትኖሩም። በመኪና ሽር ነው እንዴ የምትሉት። የሚከራይ ሀንፃ ባለቤት ናችሁ። የፋብሪካስ ወይ የባንክ ሼር ሆልደርስ። ነው ያስመጪና ላኪ ንግድ እያጧጧፋችሁ ነው። መልሱዋ።

በግልፅ መቀመጥም ያለበት  ሁሌም ወታደራዊ ስልጠና ስትወሰዱ በተወሰነ ደረጃ ለትልቅ አገራዊ ፋይዳ ሲባል ማንነታችሁን እንደ አዲስ ለመፍጠር ነው። ወይ እንደሚፈለገው ለመሞረድ፤ ለማስተካከል፤ ታዛዥና ጨከን ያላችሁ እንድትሆኑ ላመድረግ ነው። ይህ አዲስም አይደለም። የትም የሚሰራባት ነው። ለሁሌው በዋናነት  አላማው አገራችሁንና ወገናችሁን ከጥቃት በመከላከል ግልጋሎታችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ ሰለሚጠቅም ታስቦበትና ታውቆ የሚደረግ ነው። የመከላከያ ሰራዊት፤ የፖሊስ ሰራዊት የተቀደሰና ክብር ያለው በምንም አይነት ወጋ ሊተመን የማይችል ከባድ የሆነ “ግልጋሎት” ያደረገውም ይህ ለሌሎች ሲባል  እራስን እንዳዲስ ለመቀረፅ ፍቃደኛ መሆንና የሂወት መሰዋትነት መክፈል ድረስ የሚሄድ አገልግሎት ያለበት መሆኑ ነው።

መጥፎነቱ  የአገር ሉአላዊነት ማስጠበቅና ወገንታዊነት ከውስጡ ሲወጣ  ዘበኝነት ሆኖ ቁጭ ይላል። አሁን  በአገራችን እንዳለው ማለት ነው። አላማው አንድና አንድ  ስልጣንና ባለስልጣን መጠበቅ ሲሆን። ባልስልጣናቱ እንደሁላችንም እንደናንተም ጭምር ሰውም  ዜጋም ናቸው አለቀ። የምትጠብቁት ለአገር አለን የሚሉትን  እርአይ፤ ሀሳብና አላማም ቢሆን እንኳ ያው ዘበኝነት ነው የሚሆነው። ለምን ለምትሉ ? መልካም የሆነ ሀሳብና እርአይ ኖሯቸው ሆኖ ቢሆን እንኳ እርአያቸው እናንተም ሌሎቻችንም ለአገራችንና ለህዘባችን ከለን እርአይና ሀሳብ ጋር ተወዳድሮ ማሸነፍ እንጂ መጠበቅም ዘበኛ ሊቆምለትም በጭራሽ አይገባም ነበር። ለነገሩ ነው እንጂ ካልተካካድን በሁኗ ኢትዬጵያችን እየተጠበቀ ያለው ከዚህም እጅጉኑ በጣም በጣም ይወርዳል። የገዢዎች  ምቾት፤ ጥቅም፤   ወንጀል፤ብልግና፤ጥጋብ የቀረውን  ጨምሩበት። ታዲያ  ይህ ዘበኝነት አይደለም የሚል ካለ ምን ሊባል ነው።  ዘበኝነት በሚያደርጉት በእነዚህ ምክንያቶች ላይ በያንዳንዳቸው ላይ ብዙ ማስረጃዎችን መደርደር ይቻላል። ላለማብዛት ሁላችንም የምናውቀውን አንድ እውነት ብቻ በበቂ ገላጭ ነው። ሁሉም ትናንት በነጠላ ጫማ መጥተው ዛሬ ምሳ አዲስ አበባ እራት ዱባይ የሚበሉ ሚሊዬነሮች ናቸው። የሆኑት ደግሞ ሰርቀው ነው።እንዳይጠየቁ ግርጋድ ሆናችሁ በየት በኩል።

ሌላው በግልፅ መታወቅ ያለበት ቅዱስ የሆነውን አገራዊ አገልግሎት ወደዘበኝነት የመቀየሩ ጥረትና ጉጉት የየትኛዎቹም አንባገነንች ሁሉ ወና ስራም የሁሌም ያላሰለሰ ጥረት መሆኑን ነው። ይህም እንግዳም አዲስም አይደለም። አንባገነኖች በነበሩበት ግዜ ሁሉ የተፈፀመና ታሪክ ጥርት አድርጎ በተደጋግሞ የመዘገበው እውነት ነው። ከአንባገነኖች በኩል ሆኖ “ግን ለምን?” ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠቱም እጅግ ቀላል ነው። ስልጣን ላይ የመዘባነኛው ጉልበት በነሱ እጅ እንዳልሆነ ስለሚያውቁ ነው። ባጭሩ ጉልበቱ በጁ የሆነው (ሰራዊቱ)  ሊጠብቃቸው ፍቃደኛ እስከሆነ ጊዜ ብቻ የስልጣን እድሜያቸው ቀጠይ መሆኑን አሳምረው ስለሚያውቁ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት የአደረጉ ሁሉ የሚስማሙበትና አጥጋቢ መልስ ሊያገኙለት ስላልቻሉ  “ታልቅ  የሆነ እንቆቅልሽ” ብለው የሚደመድሙት መሳርያ በጁ ካለውና ጉልባትም ከሆነው ወገን ሆነው “ግን ለምን?” ለሚለው ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት ሲሞከሩ ነው።

ቀጣይ ባይሆንም ያሁኖቹ የኛ አንባገነኖች ጥሩ ዘበኛ መፍጠሩ ላይ አብዝቶ ተሳክቶላቸውል።ተሳክቶላቸዋል የሚያሰኘው በመጀመርያ ሀያ አራት አመት ረጅም ጊዜ ነው።  በዛ ላይ በዚህ ረጅም ጊዜ ይህ ነው የሚባል እንቢተኛነትና ማንገራገር ሳይገጥማቸውና ሳይፈሩ መጠበቅ ስለቻሉም ነው። የአሁኑን የኛን በጣም አስገራሚና የበለጠ እንቆቅል የሚያደርገውም ጉዳይ ደግሞ አለ። ከመነሻው በአገር ፍቅርና በወገንታዊነት አልታሰራችሁም። ስለመብት፤ ስለአድሎ፤ ስለክብርና ስለምቾት ስለመሳሰሉት ተደርጎ እንዳይወሰድ በነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ትግሉ ላይ ከመጀመርያው ረድፍ ላይ መቆም ይገባችሁ የነበራችሁ ናችሁ መሳርያ ይዛችሁ ሰጥ ለጥ ባለ ሁኔታ ዘበኝነትን ምርጫ ያደረጋችሁት።  እየሰነዘርኩ ያለሁት ወቀሳ ከባድም  በጅምላም ነው።ወግዱ ብለው የተገደሉና ዛሬም ድረስ ታስረው ፍዳ እያዩ ያሉ እንዳሉ ይታወቃል። ጥለው የወጡም ብዙ ናቸው። ይህ እየጣሉ መውጣቱ እራሱ እየበዛ መሄዱ ብቻ ሳይሆን  ዞሮ መውጋት ድረስ ሁሉ ሄዷል። ያም ሆኖ ወቀሳዬ አግባብ ያለውና ግልፅ ብሎ የሚታይ ጥቁር እውነታ ያለው ነዋ። ከውስጣችሁ ጥቂቶች ለነፃነት ሲሉ የወሰዷቸው እነዚህ እርምጃዎች የቀራችሁትን የሚያስከብርና የሚያስፈራ ገና በድንብ አልሆነም። ለዚህ ዛሬም ድረስ ተቀያይረው ይሆናል እንጂ ለሀያ አራት አመት  የሚያዟችሁ ተጋዳላይ የነበሩ ትግሬዎች መሆናቸውን  ማስታወሱ በቂ ነው።

ከላይ እነሱ የተንደላቀቁ ገዢዎች እናንተ በዘበኝነት ይህን አይነቱ ግንኙነት የግዜ ጉዳይ ነው አይቀጥልም ብያለው።  ለማቀሳሰር ግን በጭራሽ አይደለም። እንደእስከአሁኑ ግንኙነታችሁን በያዙበት መንገድ ለዛውም “አድሎ” ኖሮበት አይደለም መሳርያ በጁ ያለውን በማክበር፤ በጥቅማ ጥቅም በመደለልና  ሙጫ በመሆን  ተሞክሮም የተፋረሰ፤ የማይፀና የማያዛልቅ ግንኙነት እንደሆነ ተደጋግሞ የታየ ስለሆነና አሳምሬ ስለማውቅ ነው።   አስተውላችሁ ከሆነ ደግሞ ገዢዎቻችን በዚህ መንገድ መቀጠሉ አመፀኛውን እያሳደገ መሄዱ  ያሳስባቸው ስለጀመረ   የስትራተጂ ለውጥ አድርገዋል።  ይሄ አሁን የምታዩት የሰራዊት ቀን፤ ደርሶ አክባሪና ተቆርቋሪ ሆኖ መታየቱና የሞራል ግንባታው ሁሉ አላማው አንድና አንድ እራስችሁን ቻሉ እንዳይመጣ ነው። ይህን አይነቱ ነገር ገና እየጨመረ የሚሄድ ሆያ ሆዬ ነው። እመኑኝ ወደፊትም የማይፈጥሩት  የማይሞክሩት ነገር አይኖርም። እሹሩሩው ገና ላዛ ያጣል። ሰሞኑን በቴሌቪዥን አያየሁ ነው። ፈዳላ የኪነት ሰዎችና ተሰሚነት ያላቸው ዜጎች አፍ መጠቀም ሁሉ  ግድ ብሏል። እስከቦርጫቸው ቡሽ-አብ  ከናንተ ጋር እያስመቷቸው ነው አይደል?።

ለማንኛውም ያለመዋትነት የሚመጣ ነፃነት የለም የሚለው አባባል እውነት ነው። እኛ ግን መሰዋትነት እስከተከፈለ ድል የግድ ብለን እንነሳ።  ይህም ብቻ አይደለም መሰዋትነቱ እጅግ እጅግ በቀነሰ የሚለውም  መመርያችን መሆን አለበት። ከተናበብንና ከቀናጀነው ያለ መሰዋትነትም ነፃነታችንን ልናገኝ የምንችልበት ክፍተት አይታያችሁም።  ለኔ ይታየኛል። ድግሞም አለ።

ናፃ አውጪ ሆናችሁ ከዱር ላልመጣችሁ የሰራዊቱ አባላት በሙሉ።እንኳን ለአራተኛ አመት የሰራዊቱ ቀን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ። አገልግሎቱ የተቀደሰ ነው። በመጀመርያ ሰራዊቱን ለተቀላቀላችሁበት አላማ ዜጎች ሁሉ ክብሩ አለን። የኛንና የናንተን ጉዳይ በዚህ ልዝጋው።

ስነሳ ለመፃፍ ያሰብኩት በቅርቡ  “እና አሁን ምንድን ነው መደረግ ያለበት” በሚል የፃፍኩት ፅሁፍ ላይ ቆያይቶ የታሰሰበኝን ይጠቅማል ወቅታዊም ነው ብዬ ስለሳበኩ እላዩ ላይ ለመጨመር ነበር። የእህታችን መደብደብና ልጇን ብግፍ ማጣቷን መስማቴ አስመመኝ እና ሳልወድ ሀሳቤ ከጥቃቱ ላይ መውረድ አልቻለም መሰለኝ ወደሰራዊቱ መንፈሴ ተሳበ። በተደጋጋሚ አርእስት መቀየር ነበረብኝ። ስብሰለሰልበት የነበረ ስለሆነ ግን ትንሽ የተነሳሁበት ላይ እላለው።

ተስማማን አልተሰማማን የዚህ ምርጫ ጠቅላላ ሂደቱ  ተቃውሞ፤ እንቢታ፤ ወግዱልንም ነው። ጥያቄው ሂደቱን ጉልበታም በሆነ በዚህኛው መንገድ በሚታይ መንገድ ልንጠቀመብት እንችላለን አንችልም? የሚለው ነው። ለማስኬድ የሚያስችለንን ዝግጅት ሰርተናል ወይ? አለን ወይ? የሚለው ነው።  ከምልከታም አኳያ ብንወስደው የዚህ ምርጫ ትግሉ ላይ ሊኖረው ሚችል ጠቀሜታ የምርጫ ካርድ መውሰድ። ከዛም ከመምረጥ። ድምፁ በአግባቡ ከመቆጠር፤ ከዛም የሸነፈ ስልጣን ይወስዳል ከሚለው አንድ አቅጣጫ ከሆነ ምልከታ ወጥተን ካየነው ብቻ ነው  ሊታየን የሚችለው። ይህም ሆኖ  የመጨረሻውን ውሳኔ አገር ውስጥ ላሉት ድርጅቶች መተው የብልህም አስተውሎትም ያለው ያደርገው ነበር። ሊተውላቸውም ይገባቸውም ነበር። እነሱ መታገሉ በቃን ይህ መንገድ አያዋጣም ሳይሉ የሌሎቻችን አቋም ሆነ ውሳኔ የሚጎዳው ወያኔን ሳይሆን በከፋ ሁኔታ ውስጥ እየጣሩ ያሉትን ነው። በእጅጉ ጥረታቸው ላይ ተእፅኖ አሳዳሪ ነው። ይህ ደግሞ የትኛውንም አይነት ትግል ቅንጣት ታክል አይበረታውም። ጉዳት እንጂ ግዚያዊም እንኳ ፖለቲካል ትርፍም የለውም።  መታወቅ ያለበት ህዝባዊ አንቢታ ዝም ብሎ አይወለድም። በዋናነት ማጫርያ፤ የብዙዎች ትኩረትና ከፍተኛ ደረጃ የሚገኝ ፖለቲካዊ የህዝብ ተሳትፎና ንቃት እንዲሁም በሀሳቡ ያበረና የተሳሰረ ህዝብ ይፈልጋል።

ምርጫ አለ ብሏል ከፈለገ  ሀሳባችንን ቀይረናል የለም ይበሉ። ወይ ሰማያዊ ፓርቲን ያግድ። በኛ በኩል እነሱ ከሚፈልጉትና ሊጫወቱት ከሚፈልጉት  ምርጫ ካርድ ከመያዝና ከዛም መርጦ አርፎ ከመቀመጥ የፈዛዛ ነገር ሂደቱን ልናተለቅው ግን ይገባል። አንድነቶች ሰማያዊ ፓርቲን እየተቀላቀሉ ነው።  ይህንን ሌሎቻችንም በገፍ ድርሻ አድርገንበትና  እናስፈው። እየተሰባሰብን ቀነ ቀጠሮ እያስያዝን ሰማያዊ ቢሮ በመሄድ ምን እናግዝ ማለቱ አንዱ መንገድ ነው። የከፍተኛ ደረጃ ተማሪዎች፤ ቤተሰቦቻቸው በወያኔ የተገደሉባቻውና የታሰሩባቸው ቤተሰቦች፤ ያለአግባብ ከስራ የተባረራችሁ ዜጎች፤ ቤታቸሁ የፈረሰና የተፈናቀላችሁ ዜጎች፤ ስራ አጦች፤የአገዛዙ በሀይማኖታቸረሁ ጣልቃ መግባቱ የስመረራችሁ ዜጎች፤ ሞያችሁን በነፃነት መተግበር የተቸገራችሁ ዜጎች። የህግ ሰዎች፤ መምህራን፤ ዶክተሮች። ለተለየ መብት ተቆርቋሪ ዜጎች። ሴቶች፤ ያካል ጉዳተኞች፤ በረንዳ ተዳዳሪዎች፤ ነዲያን። የመኖርያ ቤት ችግርተኞች። ውሀ እየጠፋ የምትቸገሩና መግዘት የመረራችሁ ዜጎች። ካስፈለገ ጄሪካል ይዛችሁ። በመብራት መጥፋት የተማረረችሁ ዜጎች።  በአጠቃላይ በዚህ ስርአት እየተጎዳ ያለው እንደው አገሬው ነው። በየምድብህ ተራ እየገባህ እየተሰባሰብክ ወደሰማያዊ ትመም። ሳትጠራ ላግዝ ብለህ። ቅስቀሳ ላይ ስብሰባ ላይ በሚሊዬኖች ተገኝ። ፖለቲካዊ አየሩን በመላ አገሪቱ በለውጥ ፈላጊው  ምኞትና ፍላጎት ሙላው። ሀሳባቸውን ከበህና አይለህበት መተንፈሻ አየር አሳጣው። እንደማንፈልጋቸው፤ እንዳልተመቹን ዛሬውኑ ግልፅ ይሁንላቸው።  ይህ አይነቱ ትግል ሰዎቻችንን ስለሚታወቁ ነው እንጂ ከደህንነት አኳአ እንከን የማይወጣለት ነው። ያም ሆኖ ያነሰ መሰዋትነት ያለው። ለጥቃት ይህን ያህል የማያጋልጥ። ቀላል፤ ሰላማዊ ከዛም በላይ ህጋዊም ለጊዜው የተፈቀደ ነው። ከተንጓተትን አናሳካውም መፍጠንና መረባረብን ይፈልጋል። አስጀማሪ ጀግኖችንም ይፈልጋል።

በውጪ ገና የትግል አይነት አፎካክረንና ትንታኔ ሰጥተን አልጨረስንም። እገዛችን ቢኖርም እንደተለመደው ዘግይቶ ምን አልባትም መታሰር ስትጀምሩ ወይ ሰረቁ ስንል ነው የሚደርሰው። ከአስር አመት በሗላም ይህው ለምን አልባቱ ትግሉን የሚያስቀጥል ያበረና ደርሶ ደግሞ የማይጨቃጨቅ አካል ማቆም አልሆነላቸውም። ቢያውቁበት ድሮ ዝግጅቱ አልቆ ሊኖር የሚችልን የገንዘብ ችግር ቀርፈው ነበር። ተሰሚነታቸው ጎልብቶ ተነስ፤ ትመም ተረባረብ ነበር መሆን ያለበት። ለማንኛውም ለሁላችንም በብዙ ቁጥር ትግሉ ላይ ፍቱን ነው። ከተቻለ በደሌ ቢራ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ ሆይ ጊዜው አሁን ነበር።

 

2007 election

The post እናንተ ለአገልግሎት ነበር። እነሱ ዘበኛ ነው የሚፈልጉት። – ዳዊት ዳባ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>