Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የዛሬ የኢሳትን የመጀመሪያ ዜና ሳይ በትዝታ ወደ ኋላ ነጐድኩ፣ ( ቪሽየስ ሰርክል) –ከኤርሚያስ ለገሰ

$
0
0

ermias copy
” ሀሎ አቶ ሽመልስ ከማል?”
” አዎ! ማን ልበል?”
” ጤና ይስጥልኝ ፣ የብሉንበርግ ጋዜጠኛ ሚስተር እከሌ ነኝ።”
” እሺ ሚስተር እከሌ! ምን ልርዳህ?”
” የእንግሊዝ መንግሥት በጋዜጠኞችና ተቃዋሚዎች ላይ መንግሥትዎ ጫና ያደርሳል በማለት ልትሰጥ የነበረውን ወደ አንድ ቢሊዬን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ አግዳለች የሚል ዜና ደርሶን ነው። በዚህ ላይ የመንግስትዎ ምላሽ ምንድነው?”
ሽመልስ ፣ ” ስብሰባ ላይ ነኝ። ትንሽ ቆይቼ እደውልልሀለው።”
” እሺ ጌታዬ! ምላሾትን እጠብቃለሁ።”
ስልኩ ተዘጋ።
ሽሜ እየሮጠ ወደ ሁለተኛ ፎቅ ሬድዋን ሁሴን ጋር ሄደ። የብሉንበርግ ጋዜጠኛው የጠየቀውን ነገረው። ሁለቱም ለትንሽ ሰአት በአርምሞና ጥልቅ ትካዜ አሳለፋ። ከደቂቃዊች በኃላ ሬድዋን እንደ ሐሳብ አፍላቂ ሆኖ፣
” ሽሜ ለምን ለድርጅቱ አንደውልለትም?” በማለት ጠየቀው።
ሽሜ አንገቱን ከላይ ወደ ታች በመነቅነቅ ተስማማ። ሬድዋን ኢንተርኮሙን በጣቶቹ አንቀጫቀጨ።
” ሀሎ ”
” ሀይ በረከት እንዴት ነህ? ሬድዋን ነኝ። ሽሜም አጠገቤ አለ እየሰማህ ነው።”
” እሺ! እናንተ ሞገደኞች። ምን አዲስ ነገር አለ። ምን ልታዘዝ?” እየሳቀ በታዛዥነት ውስጥ ሆኖ ጠየቃቸው።
ሬድዋን ሽሜ የነገረውን ቃል በቃል ነገረው። አስከትሎም፣
” ጋዜጠኛው እየጠበቀ ስለሆነ ምን ምላሽ እንስጠው? ”
በረከት በቁጣ ውስጥ ሆኖ፣
” አይደለም እርዳታ ኤምባሲያችሁንም ዘግተው ጥርግ ማለት ይችላሉ ብላችሁ ንገሩት።”
ሬድዋን የድል አድራጊነት መንፈስ ተላብሶ፣
” እውነትህን ነው። ለእነሱ እርዳታ ብለን በዴሞክራሲ ጉዟችን ላይ አንደራደርም ። ጥርግ ማለት ይችላሉ።” በማለት በኩራት መለሰለት።
በመሀል ሽሜ ጣልቃ ገብቶና ድምፁን ከፍ አድርጐ ፣
” እነዚህ ኒዬ ሊብራሎች ከሃገራችን ኪራይ ሰብሳቢዎች ጋር በመቀናጀት እንከን የለሹን የምርጫ ሂደት ጭላሸት ለመቀባት እየተሯሯጡ ስለሆነ ልክ ልኩን እነግራቸዋለን። ” በማለት እየተናገረ ሳለ በረከት አቋርጦት ፣
” ሬድዋን ! ሽሜ አንድ ጊዜ አስቸካይ ስልክ መጣብኝ ። ከአስር ደቂቃ በኃላ መልሼ እደውልና እንቋጨዋለን። እዛው ጠብቁኝ።” በማለት ስልኩን ዘጋው ።
ሬድዋን እና ሽሜ ሲጋራቸውን ለኩሰው ቦምብ የሆነ ምላሽ እንዴት እንደሚሰጡ መነጋገር ጀመሩ። ውሻ ከዳገት የማይጐትታቸው የእንግሊዘኛ ቃላት መፈለግ ጀመሩ። አስሯ ደቂቃ ደረሰችና የበረከት ስልክ ተንጫረረች።
” ሀሎ ሬድዋን! ሽሜ! አላችሁ?”
” አለን፣ እየጠበቅንህ ነው” ሬድዋን ፊቱን ወደ ኢንተርኮሙ አዙሮ ምላሽ ሰጠ።
” ጥሩ! አሁን ከጓዶች ጋር አውርተን ነበር። ለእነዚህ ደደቦች ምንም አይነት ምላሽ መስጠት እንደማያስፈልግ ተግባብተናል። ምላሽ ስንነፍጋቸው እንደ ተናቁ ስለሚቆጥሩ ይበልጥ ይንጨረጨራሉ። ስለዚህ ለጋዜጠኛው ምላሽ አትስጡ። ስልኩንም አትመልሱ። ከዛ ይልቅ ” የልማታዊ ዴሞክራሲ ጉዞአችን በጣልቃ ገቦች አይደናቀፍም” የሚሉ የተለያዩ ጱሁፎች አዘጋጁና ለአዲስ ዘመን፣ ለሪፓርተር ፣ ለሰንደቅ፣ ኢትዬ ቻናልና ለሚሚ ስብሀቱ ላኩላቸው። ለአይጋ ፎረም እኔ አዘጋጅቼ ነገ እልክላቸዋለው። በተረፈ ለሁሉም ተቋማት ህዝብ ግንኙነቶች ኦረንቴሽን ስጧቸው።በአስቸኳይ ለዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም ደውሉና የትኛውም ኤምባሲ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዳይሰጥ በጥብቅ ይንገራቸው። ይቅርታ ሌላ አስቸኳይ ስልክ መጣብኝ ነገ እደውላለሁ። እንዳልኳችሁ አድርጉ ። ቻው! ቻው!።”
ስልኩ ተዘጋ። ነገም ኡደታዊ እንቅስቃሴው በዚህ መልኩ ይቀጥላል። ስንት አመት እንኖር ይሆን??

The post የዛሬ የኢሳትን የመጀመሪያ ዜና ሳይ በትዝታ ወደ ኋላ ነጐድኩ፣ ( ቪሽየስ ሰርክል) – ከኤርሚያስ ለገሰ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>