ስለ ሞረሽ ከመናገራችን በፊት የሞረሽን ምንነት መገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነገሮችን በቅጡ ከተረዱ ለማማትም መረጃን መሰረት ማድረጉ የተሻለ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፤
ሞረሽ የሚለውን ቃል ከደስታ ተክለወልድ መዝገበ ቃላት ስንፈልገው ከዚህ በታች ያለውን ትርጉም ይሰጣል፤
ሞረሽ (የሌሊት ጥሪ፥ እከሌ ሞተ፦አለፈ ተጎዳ ወዘt) ብሎ ይፈታዋል።
ልክ ስሙም እንደሚያመለክተው ሞረሽ ያለ ረዳት ከኖሩበት፦ እትብታቸውን ከቀበሩበት፦ ከከበሩበት በመንግስት አስተባባሪነት ለሚፈናቀሉት፦ ለሚገደሉት፦ አማሮች ጩኸታቸውን ለማሰማት የተመሰረተ ማሕበራዊ (civic) ድርጅት እንጂ አልፎ አልፎ በአንዳንድ ዜና ማሰራጫዎች እንደሚወራው የአማራ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም አላማውም አማራውን ስልጣን ለማቆናጠጥ የሚታገልም አይዶለም።
ከዚህ ቀደም መአህድ የሚባል ነፍሳቸውን ይማርና ሕክምና በወያኔ እስር ቤት ተነፍገው በሞቱት በፕሮፌሰር አስራት የሚመራ ድርጅት ነበር፤ ይህ ድርጅት አመሰራረቱ አማራው ከሚደርስበትና እየደረሰበት ከነበረው ጥቃት ለመከላከል እንጂ የአማራን የበላይነት ለማንጸባረቅ አልነበረም፤ ከፕሮፌሰሩ ሕይወተ ህልፈት ማግስት ግን ውስጣቸው በነበረ ሽኩቻ ድርጅቱ ፈርሶ በመትኩ መኢአድ ተቋቁሟል።
ሞረሽን ከመአህድ የሚለየው ታዲያ ምንድን ነው? ለሚለው መልሱ አጭር ነው ይኸውም የፖለቲካ ድርጅት አለመሆኑ ነው፦ ስልጣን ላይ ለመውጣት የሚታገል ቡድን አለመሆኑ ነው፤
በኔ እምነት አማራ የሚባለው ማነው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ እንደመላሾቹ ማንነት የተለያየ ትርጉም አግኝቷል፤ እኔ እንደምረዳው አፉን በአማርኛ የፈታ ሁሉ አማራ ነው፤ ሁላችንም እንደምናውቀው ጎዣም፦ ጎንደር፦ ሰሜን ሸዋ፦ ከፊል ወሎ (ጥንት ስሙ ድፍን ወሎ ቤተ አምሐራ) በአማራነት ይታወቃሉ ስማቸው ግን አማሮች ሳይሆን ጎዣሜ፦ጎንደሬ፦ ወሎዬ፦ መንዜ ወዘተ በመባል ነው።
“እንደ ወያኔና መሰሎቹ ቲኦሪ ግን “አማራ ” የሚለው ቃል፦ አማርኛ ቋንቋ በሚነገርባቸው አካባቢዎች ውስጥ የሚኖረው አማርኛ ተናጋሪ ሕዝብ በሙሉ በአንድ ላይ ሁኖ የሚታወቅበት መለያ ነው፤ ወያኔና መሰሎቹ……የሚሰጉትን ሕዝብ በመነጠል ለማጥቃት የሚያስቸልን ስልት ለመንደፍ ከማሰብ የተከተለ ትርጉም ነው። እንዲህ አይነቱ አካሄድ ደግሞ በወያኔና በኦነግ ዛሬ የተጀመረ አይደለም። በተለያዩ ግዜያት ኢትዮጵያን ለማጥቃት የመጡ የውጭ ሃይሎች በሙሉ ሀገሪቱን ለማዳከምና ለመከፋፈል ሲሉ በነደፏቸው ስልቶች ውስጥ ማእከላዊ ስፍራን ይዞ ይገኝ የነበረ ነው። የኢትዮጵያዊነት እና የአማራነት መለያዎች ህብር ከዘላለም ቁምላቸው gve 54″
ህዋሃት እንደ ትልቅ ጠላት የሚያያቸው ታላቁ አጼ ምኒሊክ የጦር መሪዎቻቸውን ስናይ (ደጃዝማች መሸሻን፦ ደጃዛማቸ ባልቻን፦ ራስ ጎበናን፦ ራስ አሉላን፦ ፊታውራሪ ሀብተግዮርጊስን ወዘተ) አንድ ያደረጋቸውና በሹመት ያሳደጋቸው ኢትዮጵያዊነት እንጂ ጎሳቸው አልነበረም። ዛሬ በወያኔ ዘመን ከዋኖቹ 25 ታላላቅ ጀኔራሎች 20 ትግሬዎች ናቸው፤ የየከፍለ ጦሩ ዋና አዛዦች በሙሉ ትግሬዎች ናቸው።
ሲገዛ የኖረው ጨቋኝ አማራ እየተባለ በወያኔና በመሰሎቹ የሚወራው ፤ ለምሳሌ የመጨረሻውን የኢትዮጵያ ንጉስ ተፈሪ መኮንንን ስንመለከት በእናታቸው አባት ኦሮሞ ሲሆኑ በእናታቸው እናት ደግሞ ጉራጌ ናቸው፤ አባታቸውን ስንመለከት ራስ መኮንን አባታቸው ኦሮሞ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ አማራ ናቸው፤ ስለዚህ ከራስ ተፈሪ አማራነት ኦሮሞነታቸው ያመዝናል፤ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማሮች አማርነታቸው አፋቸውን በአማርኛ በመፍታታቸው እራሳቸውን ከአማራ መመደባቸው ነው፤ ይህ ደግሞ ምንም እንኳን በጎሳ እራሳቸውን ላደራጁ ባይመቸም የግለሰቦች መብት ነው፤ የኔም አማራነት ከንደዚህ አይነቱ የተለየ አይዶለም።
በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ የተቀረው ከዛ የሚከተል ነው፤ እንደ ሰው እንደ ሰብአዊ ፍጡር የህዋሃት መንግስት ትግል ከጀመረበት ግዜ አንስቶ እስከዛሬ በተለይ በአማራው ላይ የሚያካሄደው የጠላትነት ዘመቻ ይህንን አዲሱን አመለካከቴን እንድይዝ አስገድዶኛል።
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስለ ኢትዮጵያዊነት ይህንን ይላሉ “ኢትዮጵያዊነት ብዙ የተለያዩ ህብረተሰቦች የተዋሃዱበት አካል መሆን ነው፤ ኢትዮጵያዊነት ከጎሰኝነት በላይና ውጭ የሆነ አጠቃላይ ማንነት ነው፤ ገጽ 31 ኢትዮጵያ ከየት ወዴት”
ስልጣን ላይ የወጣው መንግስት ስለ አማሮች እንዲህ ያስባል “የአማራ ገዢ መደቦች የትግራይ ሕዝብ ጠላቶች ናቸው፤ ታሪካችንና ቅርሶቻችንን ያጠፉት አማራዎች ናቸው፤ ለድህነትና ለስደት የዳረጉን አማራዎች ናቸው፤ በአማራ የተወሰዱት እንደ ወልቃይት ጸገዴ፦ሑመራ አሉ ውሃና ሌሎች የትግራይ መሬቶች እናስመልሳለን ታሪክ አጉዳፊው ገጽ 71 ከገሰሰው እንግዳ” ታጋይ ገሰሰ ውስጥ አዋቂና የወያኔ የትግል አጋር የነበሩ በመሆናቸው ወያኔን ጠንቅቀው ያውቃሉ፤
በተባለውም መሰረት ከአማራው ላይ የተጠቀሱት ቦታዎች ተወስደው ወደ ትግራይ ተደምረዋል፤ አማራውንም ጨቋኝ ብሎ በመሰየም በሌሎች ጎሳዎች ያለ ተከላካይ እንዲመታ አድርገዋል፤ ዛሬ በአሜሪካ ከሕዝብ በዘረፉት ብር ነዳጅ ጣቢያ ከፍተው የተንደላቀቀ ኑሮአቸውን የሚመሩት ታምራት ላይኔ ህዋሃትን ወክለው በምስራቅ ኢትዮጵያ አማራውን ካስጨፈጨፉት አንዱና ዋንኛው ናቸው።
አማርኛ ተናጋሪውን ወገን በጠላትነት መድበው ጨቋኝ ብሔር ይሉታል፤ ሌሎቹ ሁሉም በጀምላ ተጨቋኝ ብሔሮች ሆነዋል።
የአማራውን ቁጥር ለመቀነስ በሚደረገው ትግል ለሌላ በሽታ መከላከያ ነው እየተባለ ሴቶቸን በአማራው ክልል ብቻ በግዳጅ የእርግዝና መከላከያ መርፌ እንዲወጉ ይደረጋል፤ አሉባልታ ሳይሆን በተጨባጭ መረጃዎች ተገኝተዋል የዋሆቹ ሴቶች ለምን መውለድ እንዳቃታቸው ስለማያውቁ በየአድባራቱ ስለት ይሳላሉ፤ ይህ አንድን ዘር ለማጥፋት የሚደረግ በመንግስት የተቀነባበረ ስራ ከዘር ማጥፋት ወንጀል የሚለይ አይደለም፤
እነ መለስ ይላሉ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ” አማርኛ ተናጋሪውንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዩን የሚመነጥሩት ኢትዮጵያን ለማጥፋት በሚሞክሩበት ግዜ አላስኬድ ስላላቸው ነው” በቅርቡ የወያኔ ቁንጮ የሆኑት ስብሃት ነጋ በመኩራራት አማራውንና ኦርቶዶክሱን እንዳያሰራራ አርገን መተነዋል ብለዋል።
ለመንግስትም ያመጣለት ውጤት የአማራው ሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል ነው በሀዋሃት መረጃ መሰረት የአማራው ሕዝብ ቁጥር በሁለት,ት ሚሊዮን ወርዷል።
ወያኔ ባስተባበረው ጦርነት ሀረርጌ አርባ ጉጉ አማሮች ከነሕይወታቸው ገደል ተከተዋል፦ ቤታቸው ውስጥ ሰዎች እያሉ ተቃጥሏል፦ቆዳቸው እንደእንስሳ ተገፏል፦ ይህ ሁሉ በፊልም የተደገፈ መረጃ አለው፤ በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የተፈረመበት ማዘዣ በቅርቡ ከቤንቺ ማጂ ዞን ጉራ ፋርዳ ህገ ወጥ ተብለው አማሮች መፈናቀላቸው በምትካቸው ደግሞ ቻይኖች፦ ቱርኮች፦ አረቦች እየተጠሩ መሬት ይታደላሉ; ይህ መፈናቀል በዚህ አላበቃም ወደሌሎች ቦታዎችም ተዛምቷል። ቤንሻንጉል ጉምዝ ተመሳሳይ ግፍ ተፈጽሟል።
ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ወይም በህጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ዉስጥ የሚገኝ የዉጭ ዜጋ በመረጠዉ የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖርያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለገዉ ጊዜ ከሀገር የመዉጣት ነፃነት አለዉ ይላል የሀገሪቱ ሕገመነግስት ነገር ግን ይህ መብት አማራን አይመለከትም የሚል ስንኝ ባይሰፍርበትም በመካሄድ ላይ ያለው ግን የአማራውን ቦታ ከሕግ ውጪ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚኖሩ የውጭ ዜጎች ነው።
እንግዴህ ይህን ሁሉ ከላይ ያሰፈርኩትንና ሌሎች ያላሰፈርኳቸውን በአማራው ላይ የሚደረገውን ግፍ በራሴ ላይ ካልመጣ አያገባኝም ማለት ስለአላስቻለኝ ሞረሽን ለመተባበር ተነስቻለሁ፤ አማራ ባትሆኑም እንደሰብአዊ ፍጡር አንድ ሰው አማራ ስለሆነ ብቻ ይሄ ሁሉ ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፍ ሊፈጸምበት አይገባም ብለን ኢትዮጵያውያን በሙሉ በህብረት ልንነሳ ይገባል፤ ወያኔ አማራን የጠላው በኢትዮጵያዊነት አቋሙ እንጂ በሌላ አይደለም፤ ይህ አቋም ደግሞ መቼም ፍንክች አይልም።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ታዛቢው
↧
የሞረሽ አባል ነኝ- ለምን ሞረሽ?
↧