የጎንደር ህብረት ዛሬ ይህንን መግለጫ ለማዉጣት የተገደደዉ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ወደ ነባር የእናት ጎንደር አስተዳደር ለመመለሥ መብቱን ለማስከበር የጠየቀዉን ጥያቄ የወያኔ መንግስት ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎ እስከ አሁን ምላሽ ሳይሰጥ እሥራትና ግድያዉ እየባሰ መምጣቱ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ለዓለም ህዝብ ለማሳወቅ ሲሆን፤ እንዲሁም በሱዳን በኩል መሬት አሳልፎ የመስጠቱ ድብቅ ሤራ እስከ አሁኑ ሰዓት ቀጥሎ የትግራይ ታጣቂ ሚሊሻና የሱዳን ወታደሮችን ተመሳሳይ መለዮ ለብሰዉ በመተባበር በጎንደር ህዝብ ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ለመላዉ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስገንዘብ ነዉ።
የሁመራ፤ ወልቃይት ጠገዴ እና የጠለምት ህዝብ ሥብዕናዉን ተገፎ፤ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበት፤ የሞተዉ ሙቶ የተረፈዉ ለስደት ተዳርጎ በባዕድ አገር እየታረደ፤ ሃገራዊ ዉርደት ደርሶብን በቁጭት ሃዘን ላይ አለን። አሁንም በአርማጭሆ፤ በመተማና በቋራ በኩል ከዉጭ ኃይል ጋር ተመሳጥሮ ቀስ በቀስ አራሽ ጎንደሬዉን ማፈናቀሉን አላቆመም። የወገኖቻችን ህይዎት በየቀኑ እየተቀጠፈ፤ ቤት ንብረታቸዉ እየወደመ ነዉ። ከዚህ ሁሉ ግፍ እና በደል የተረፉትን ወንድምና እህቶቻችን ወደባእድ አገር እንዲሄዱ የእርጎ ባህር በማሳዬት፤ በራሱ የደህንነት መስመር የኮንትሮባንድ ንግድ ከፍቶ እያጓጓዘ ገንዘብ የሚቸበችበዉ፤ የሚያሳርደዉ፤ ውቅያኖስ እና በረሃ እንዲበላቸው፤ በሳት እንዲቃጠሉ ምክንያት የሆነው እራሱ አሸባሪዉ ወያኔ ነዉ። — [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—- —
The post ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ ቁጥር #6 “ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” appeared first on Zehabesha Amharic.