Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

ስለቀጣዩ ትግል ሳስብ ! –ከይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ አመራር)

$
0
0

holeta
ዲሞክራሳዊ ምርጫ ሰላማዊ ወይም ጠበንጃ አልባ የትግል ስልት ከሆኑት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ሆኖም ግን በአገራችን ለሃያ አንድ አመት ወይም ለ5 ዙር ምርጫ የተካሄደ ቢሆንም ህውሓት/ኢህአዴግ የግንቦት ሃያ 24ኛ አመት በሚያከብሩበት ማግስት 100 % በምርጫ ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኛለው ማላት፣ ህውሓት/ኢህአዴግ ለዲሞክራሳዊ ምርጫ የተዘጋጀ አለመሆኑ በሚገባ ያረጋገጠ አጋጣሚ ነው ፡፡የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር እና አባላት የህውሓት/ኢህአዴግ አምባገነናዊ የምርጫ ሥርዓት እግር-በእግር በመከተል ለማጋለጥ ችለዋል ! ለዚህም አኩራ ተግባራቸው አድናቆት እና ምስጋና መስጠት ተገቢና አስፈላጊ ነው፡፡

ሆኖም ግን ከዚህ በኋላ ሌሎች ጠበንጃ አልባ ወይም ሰላማዊ የሆነ ትግል ስልቶችን በመተግበር ሕዝባዊ መንግስት አስኪቋቋም “በአገር ውስጥ” የሚንቀሳቀሱ የዲሞክራሲ ሃይሎች አማራጭ የሰላማዊ ትግል ስልት በመከተል፣ ከሌላው ጊዜ በተሻለ እና በተቀናጀ መልኩ የተጀመረው ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል መምራት እንደሚያስፈልግ ከምንፈልገው ለውጥ አንፃር ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም፡፡ይህን ሃቅ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር እና አባላት አጥብቀው የሚረዱት እውነት እንደሆነ እምነቴና ተስፋዬ የበዛ ነው፡፡

ለውጥ ፈላጊው የሆነው ጭቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሣይሰለች የለውጡ ሂደት እንዲፋጠን ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጎን በመቆም ያሣየው ጥረት እና ፍላጎት እንዲሁም ድጋፍ ለዲሞክራሲ ሃይሎች የሁል-ጊዜ ብርታትን የሚሰጥ ነው !ለዚህም የላቀ ተግባር ከበሬታ መስጠት ድጋፍ ለተቸራቸው የተቃወሚ ሃይሎች በፖለቲካ ሥራችን በግብረ-መልስ የሚሰጡት በጎ ምላሽ መሆን እንዳለበት ማረጋገጥ አለብን ፡፡ ይህም በመሆኑ የህብረተሰቡ የለውጥ ፍላጎት ለዲሞክራሲ ሃይሎች ከምንም በላይ ዋንኛ ግባት ነው፡፡
በውጪ ሀገር የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በገንዘብ እና በሃሳብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በአገራችን በሰላማዊ መንገድ የመንግሰት አስተዳዳር ለውጥ እንዲመጣ የከፈሉት መሰዋትነት ቀላል የሚባል አይደለም ! ይህ-ቀረ የማይባልበት የሁል ጊዜ ድጋፋቸውም በቀጣይም ከሰላማዊ ትግል ጎን የማይለይ መሆኑ እርግጥ ነው፡፡

ማስታወሻ ፡- ይህ ፁሑፍ የእኔን አስተሳሰብ እንጂ የፓርቲዬን አቋም የሚመለከት አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

The post ስለቀጣዩ ትግል ሳስብ ! – ከይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ አመራር) appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>