ዘ-ሐበሻ ተከታታይ ቭዲዮዎችን እስከምትለቅ ድረስ ይህን ዘገባ ያንብቡ
ዘንድሮ ለ32ኛ ጊዜ በሰሜን አሜሪካ የስፓርት ፈዴሪሽን የተዘጋጀው የእግር ኮስ ጨዋታ በሜሪላንድ ግዛት ዋሽግተን ነበር ሜሪላንድ በውብ ኢትዪጵያውያን አምራና ተውባ ነበር የከረመች።
የዘንድሮ እግር ኮስ ዝግጅት እንደወትሮው ነገር ግን በጣም ባማረና በደመቀ ሁኔታ የእግር ኳስ ጨዋታው ፣ የንግድ ልውውጡ፣ባህላዊናዘመናዊ የሙዚቃ ፊስቲቫሉ ፣ኢትዪጵያን መሰረት ያደረገ ፓለቲካ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች ወዘተ የተከናወነበት ነው።
በሁሉም ክንውኖች አቅም እንደፈቀደ ተሳታፊና ታዳሚ ሁኛለሁ ከሁሉ በላይ አቅሌን የሳበኝና የማረከኝ በአዲስ ድምፅ ራዲዪ በአበበ በለው አዘጋጅነት የነበረው የጋዜጠኞችና የሜዴያ አዘጆች ሚና በኢትዪጵያ የዲሞክራሲና የነፃነት ትግል ምን መሆን አለበት? በሚል የመወያያ ርእስ የቀረበው ውይይት እጅግ አስተማሪና ሚዲያዎች ያለባቸውን ችግር በግልፅ የተነጋገሩበት በመሆኑ በአይነቱ የተለየ ነበር።
በዚህ ስብሰባ በፓናል የውይይት አቅራቢ የነበሩት ታዋቂው፣ አንጋፋው ኢኮኖሚስትና አክትቢስት ዶ/ር አክሎክ ቢራራ ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ሶሊያና ሽመልስ፣የኢትዩጵያ ሪቭው አዘጋጅ ኢልያስ ክፍሌ፣የኢትዪጵያ ሜዲያ ፎረም (EMF) አዘጋጅ ክንፉ አሰፋ፣ ታዋቂው አክቲቭስት አበበ ገላውና የአዲስ ድምፅ አዘጋጅ አበበ በለው በየተራ ርእሱን መሰረት በማድረግ በሳልና ጠቃሚ ንግግር አድርገዋል።
የስብሰባው መሪ አቶ ዳዊት ተገኘ በመጀመሪያ ንግግራቸው ባለፈው ሀያ አራት ዓመት አምባገነኑን የወያኔን ኢህአደግ አስተዳደር በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ኢስብአዊ የሆነ ጭፍጨፋና ግድያ፣ ህዝባችንን በዘርና በኃይማኖት በመከፋፈል ማቆሚያ የሌለው እልቂትና ፍጅት በመፍጠር የሚሰራቸውን ሴራና ደባዎችን በማጋለጥና መረጃ በመስጠት፤ በተለይ በምርጫ 97 ኢትዪጵውያን ጋዜጠኞች የሰሩት ስራናያደረጉት አስተዋፅኦ በታሪክ የሚረሳ አይደለም።
እንደ እውነቱ ከሆነ ይህን ሥርአት ፊት ለፊት የታገሉትና እርቃነን ሥጋውን በማጋለጥ ለኢትዪጵያ ህዝብና ለዓለም ህብረሰብ ያሳወቁት ኢትዪጵያውያን ጋዜጠኞችና የሜዴያ ሰዎች ናቸው። በውጭም ማለት በዲያስፓራው ህዝቡን በማነቃነቅና በማደራጀት መረጃ በመስጠት፣ ትግሉና ምርጫ ለውጤት እንዲደርስ ከማንም በላይ ከፊት ሁነው የሰሩት በውጭ አገር ያሉ ጋዜጠኞች ና የሚድያ ሰዎች ናቸው። ለአብነት ያህል ከመሀላችን ካሉት የኢትዪጵያ ሪቭው አዘጋጅ ኢልያስ ክፍሌ፣ የኢኤምኤፍ (EMF) አዘጋጅ ክንፈ አሰፋ፣ የአዲስ ድምፅ አዘጋጅ አበበ በለው እነዚህ ወንድሞች በምርጫ 97 በተደረገው ትግልና ለቀጣዩ የዲሞክራሲ ና የነፃነት ትግል መሪ ተዋናይና ግንባር ቀደም አንቂና አስተባባሪዎች ናቸው ለእዚህ ነው አምባገነኑ የወያኔ ሥርዐት በለሉበት የረጅም አመት እድሜ የፈረደባቸው ዘረኛውን የወያኔ ከፋፋይና ፀረ ዲሞክራሲና አፋኝ ሥርዐት በሰላ ብእራቸው በማጋለጣቸውና በመታገላቸው በአምባገነኑ ሥርአት ሰለባ ሁነው በመከራ ቤት በእስር የሚገኙትን እነ እስክድር ነጋን፣ርእዪት አለሙ፣እነ ተመስገንን፣እነ ውብሸትን ወዘተ ስናስታውስ እና ለዲሞክራሲና ለነፃነት በመናገራቸው ና በመፃፋቸው ከግፈኛው ስርአት ደህንነቶች አምልጠው የሚወዶቸውን ልጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ተለይተው ሳድይወድ በግድ ተሰደው በባእድ ሀገር በአፍሪካና በመካከለኛ አረብ በስደትና በመከራ ያሉት ስናስውስ የኢትዩጵያ ጋዜጠኞችና የሚድያ ሰዎች ይህን ሥርአት ምን ያህል እንደታገሉትና ዋጋ እንደከፈሉበት የሚሳይ ነው።
አቶ ዳዊት ንግግሩን በመቀጠልበእስር፣ በግዞትና በስደት የሚገኙ ጋዜጠኞች መስዋአትነት የሚስተምረን ሁለት አደራ አለ። አንደኛው ለማይቀረው የነፃነት ትግል በርትተንናተጠናክረን እንድንታገል። ሁለተኛው ኢትዪጵውያን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊኖራቸው ስለሚገባ የዲሞክራሲ መብት ማለት የመናገር፣የመፃፍ፣የመደገፍ፣ የመቃወምና የመተቸት ወዘተ.. እንደ ሰው ልጅ ማግኘት ማስከበርና ለዚህ የዲሞክራሲ መብትና ነፃነት በየትኛው ደረጃና በየትኛውም ቦታ መታገል እንዳለብን; በእነርሱ መስዋእትነት አስተምረውናል:: አደራ ብለውናል:: ከዚህ አንፃር እናንተ በውጭ ማለት በዲያስፖራ የምትገኙ ጋዜጠኞች ና የሜዴያ ሰዎች ምን ያህል ነፃ ናችሁ? ለህዝብ የምታቀርቡት ዘገባና ዜና ምን ያህል ከቀረቤታና ከፓለቲካ ድርጅት አፍቃሪነት ገለልተኛ ነው? የፓለቲካ ድርጅቶች ገለልተኛና ነፃ ሜዲያ መሆናችሁን አምነው ምን ያህል መብቶቻችሁን ያከብራሉ? የመሳሰሉት ጥያቄዎች በማቅረብ ለስብሰባው ታዳሚ ውይይቱን ክፍት አድርገውታል።
በቤቱ ተመሳሳይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል:: አብዛኛውን ከቀረቡት አስተያያቶች በአብዛኛው ያነጣጠረው የግለሰቦችን የመናገርናየመተቸት መብት እየተጋፋ ያለው ግንቦት ሰባት በሀገራችን ጉዳይ በተለይ ኤርትራና ሻዕቢያ በተመለከተ የሚደረጉትን ውይይቶች ህዝብ እንዳይወያይበትና አስተያየት እንዳይሰጥበት የሚደርገው የጉልቤና የአፈና አካሄድ መቆም አለበት በሀያ አራት አመት ትግል ፀንተው በፀረ ወያኔና ሻቢያ አቆም ታግለው ያታገሉ ወንድሞችን ስለ ሻቢያና ኢሳያስ አፈወርቂ አነሳችሁ በሚል እናንት የወያኔ ተላላኪዎች ተብለው እየተሰደቡ ነው።ይህን አካሄድም ትክክል አለመሆኑና ለማስቆም የድርጅቱ መሪዎች ያደረጉት ጥረት የለም ይልቁንም የድርጅቱ መሰረታዊ ፍልስፍ ናስድብ፣ ጩሆትና አድማ እስኪመስል ድረስ ቀጥለውበታል::
ታዳሜው ይህን አካሄድ ከምንትልገለው የወያኔ ሥርአት ተለይቶ ስለማይታይ አካሄድን እንታገለዋለን:: በተረፈ ትናንት በኢትዪጵያ ሪቭው አዘጋጅ በኢልያስ ክፍሌ ዛሬ በአዲስ ድምፅ አዘጋጅ በአበበ በለው እየተደረገና በመደረግ ላይ ያለው ጋጠ ወጥ ዘመቻ የተሰለፍበትን ድርጅት ሰብእና የሚሳይ ስለሆነ ሊታረም ይገባል። ኢልያስ ክፍሌ ሆነ አበበ በለውን ወያኔ ለማለት ቀርቶ ደጋፊዎች ሌላውም የሞራል ብቃት የላቸውም። በዚህ ጉዳይ በአጽኖኦት የተገለጠው ለግንቦት ሰባት ድርጅትና ለለውጥ ፈላጊው አባላት ከፍተኛ አክብሮት እንዳለው አስምሮበታል::
ድርጅቶችን አንተች የሚለው አባባል ስህተትና ወቅታዊ አለመሆኑ ተተችቶበታል:: ወያኔ ሀያ አራት አመት በግፍና በበደል ህዝባችንን እየከፋፈለና እያሰቃየ በአምባገነንነት መግዛቱን እኛም ያለመስልቸት በፅናት ሀያ አራት ዓመት አጋልጠነዋል:: ነገር ግን ህዝቡን መርተውና አደራጅተው ለድል ያበቁታል ያልናቸው የፓለቲካ ድርጅቶች ህዝቡን ለድልና ለነፃነት አለማብቃት ብቻ ሳይሆን ራሳቸው ወደህብረትና አንድነት ባለመምጣት የትግሉና የፖለቲካው አቅጣጫ ያጡ ይመስላሉ ስለዚህ ድርጅቶችን ራሳቸውን ሊያዩና እንዲፈትሹ ጥሪ ማድረግ እኛም ሆነ ህዝቡ ልንተቻቸውና ልንገመግማቸው ይገባል ይህ አካሄድ ለድርጅቶች ና ለትግሉ ብርታትና ጥንካሪ ይሰጣቸዋል:: የህዝብ ትችት የሚፈራ አምባገነን መንግስትና ራሱን በትእቢት ያሳበጠ ውስጡ በባዶ ጩኸት የሞላ ኃይል ብቻ ነው።
በመጨረሻ በፓናልአቅራቢዎችና በታዳሚው የተደረስበት መንፈስ
1ኛ/ የፓለቲካድርጅቶች፣አባሎቻቸ ውና ሊላው ማህብረተስብ የነፃ ሚድያን ሚና እንዲረድልን ጥረ ማድረግ፣ በሚድያ አቀራረብ በፅሁፍ ዘገባ፣ በዜና ሆነ በቃለ መጠይቅ የሚስራው ጥንቅር አቅራቢው ጋዜጠኛ ህዝብ ሊያውቀው ይገባል ብሎ ያመነበትን የማቅረብ ሙሉ መብት እንዳለው። አዘጋጅው ይህን ማቅረብ የእገሊን ድርጅት ያስከፋብኛል በሚል ስነ ልቦናዊ ሰቀቀን እንዲፈጠር የሚደረገው ዘመቻ መቆም አለበት ድርጅቶች ነፃ ሚዲያዎችን የእነርሱ ልሳን እንዲሆኑ በቀጥታ ሆነ በተዘዋሪ መሞከር ወንጀል ነው።ድርጅቶች የነፃ ሚድያዎችን ሽፋን ማግኘት የሚችሉት በሚሰሩት ሥራና መሪት ላይ በተግባር በሚደርጉት አስተዋፅኦ እንጅ ሚዲያዎችንና አዘጋጆችን በማንቆሸሽ ና በማሸበር አይደለም።
2/ኛ የሜዲያ አዘጋጆች የተመክሮ ልውውጥ ማድረግ አለብን በሚል የህሊና ራዲዮ አዘጋጅ ሳምሶም ውብሽት የሙያ ትንተና ትምህርት ሰጭ በመሆኑና በትክክል ከነፃ ሚድያነት አንፃር እየሰራን ስለመሆኑ ትምህርታዊ ግምገማ ለማድረግ አንድ ፎረም ማቋቋም ጠቃሚ በመሆኑ የአዲስ ድምፅ አዘጋጅ አበበ በለው በአስተባባሪነት ተመርጦ ሌሎች የሚዴያ ባለ ቤቶችን ጨምሮ አንድ ፎረም እንዲቆቆም ተወስኖአል።
3/ኛ በተለይ ዘ ሀበሻ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሄኖክ በሰጠው ማሳሰቢያ መሰረት ለሀገራቸው፣ ለህዝባቸው ነፃነት ሲሉ ሥርአቱን ተችታችኋል; ህዝብን አነሳስታችሆል በሚል በእስር ና በስደት የሚገኙ የጋዜጠኛ ቤተሰቦች ልንረዳቸውና ልናበረታታቸው ይገባል።ሄኖክ በመቀጠል በትናንት ቀን እኔና እዚህ ቤት ያለን የሚድያ ሰዎች የጀግናው ጋዜጠኛ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለምና ልጇን በማየታቸውና በመጎብኘታቸው ከፍተኛ የህሊና ደስታ እንደተሰማው ገልፆ እኛ በውጭ የምንገኝ ጋዜጠኞች፣ የፓለቲካ ድርጅቶችሆነ ዲያስፖራው እነዚህን ለህዝብ ልሳን በመሆን በወይኔ እስር ቤት ያሉ ፋኖ ቀዳጅ የሆኑ ትንና በስደት የሚገኙትን ልንረሳቸው አይገባም:: ስለዚህ የምንመሰርተው ፎረም በአገዛዙ እጅ የወደቁትንና ቧእድ ሀገር የተሰደድትን ጋዜጠኞችንና ቤተሰባቸውን የምረዳበት የምንደግፍበትና የምንዘክርበት መሆን አለበት ብሎል።
በአጠቃላይ ስብሰባው በጥሩ መንፈስና በበሳል አካሄድ የተካሄደ ነበር። ታዳሚው የሁሉንም ማህረሰብ አባላት ያካልተተ ሲሆን የቆየ የፓለቲካ ተመክሮ ያላቸው ፣ የፓለቲካ ንድፍ ፀሀፊዎች፣ ጦማርያንና የፓልቶክ ባለቤቶችን ያከተተ ነበር። በታዳሚነት ካየሆቸው መሀል ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተማጎች ኦባንግ ሜቶና ታምረኛው ብእረኛ ተክሌ አበበ ነበሩ።
The post ትምህርት ሰጭ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ * – ከእሸቴ ውለታው appeared first on Zehabesha Amharic.