„አለባብሰው ቢያርሱት በአረም ይመለሱ“ – ሙግት።
ከሥርጉተ ሥላሴ 11.07.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/
ወደ እርሱ ከመግባቴ በፊት በዝና ዬማውቀውና የማከብረው ወንድሜ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ „ለውስጤ“ መልስ ሰጥቶበታል። የመልስ መልስ – እራሱን አስችዬ አላስፈለገኝም። ጹሑፉ ቅን ስለሆነ። ፍርድና ዳኝነቱን ደግሞ የጋራ ታዳሚዎቻችንም – አሉ። መማር ያለብኝን ግን ከልምድ ዘለቅ ወንድሜ – የምማርባቸውን ዘርፎች – እፈቅዳለሁ። የአንተን እኔ ወስጄ አንተ የእኔን ሙሉውን ውድቅ ብታደርገውም እንኳን ግድ አይሰጠኝም። ማንበብህ ብቻ – ይበቃኛል። መደማመጡ ነው – ነገን የሚያድነው። ጥቂት ነገሮች ተንጠልጥለው እንዳይቀሩ ትንሽ ልበል፤ ከዕለቱ እርእሴ ጋርም ተቀራራቢ ነው። አቶ ሄኖክ ሰማእግዚር ዴሞክራሲን በቲወሪ ሳይሆን እዬኖረበት እያለ በነፃነት ላይ ሆኖ፤ መሃያውን ከሌላ አካል እያገኘ ነው ዬጎጥ ፖለቲካ ፍለጋ – የሚማስነው። ለዛውም ሊተረጎም የማይችል ረቂቅ መክሊት ካላቸው የሙያው አዛውንታት ጋር እዬሠራ – እያዬ፤ ሀገራዊ መከራውን እዬሰማ – እያለ፤ ጭራሽ በሰለጠነው ሙያ በጋዜጠኝነት ሥም ሲሆን ደግሞ – ያማል፤ እያወቀ ነው የሚያደርገው። እኔ ወጣት ከነበርኩበት ጋር ለማነፃጸር ግን ዘመኑም ሆነ የኃላፊነት ደረጃው፤ እንዲሁም የሙያው ዓይነቱም በፍጹም ሁኔታ – አይገናኝም። የሆነ ሆኖ የእኔ አባት „ለሰው ልጅ“ ጥብቅና መቆምህን እጅግ አደንቃለሁ – አከብርማለሁ። እንዲያውም አዲስ ፕሮጀክት ጅምር ላይ ነው። አዲሷ እንቡጢጣ ብሎጌ „ነገና የተፈጥሮ ሥጦታ እንዴት ይታረቁ“ የሚል አምክንዮ – አለው። በርከት ያሉ ተያያዥ ንድፎቼንም ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ – ልኬያለሁ። የፖሊሲና የበጀት ጥያቄ ስለመሆኑም መልስ – ሰጥተውኛል። ነገር ግን ባጀትም ፖሊሲም ሳይስፈለግ አዬር ላይ ክርክሩን በትንሹ መጀመር – ይቻላል። እርግጥ የቀረኝ የቪዲዮ ተግባር – አለብኝ፤
ሌላው — የአንተ ሃሳብን የደገፈ ወይንም ጎሽ ያለ ሌላ ጹሑፍም – አይቻለሁ። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ለፋሺዝም ቃል አቀባይ ጥብቅና – አልቆምም። ዬአሜሪካ ድምጽ ዬአማርኛው ክፍል ቢሆን እንደ ታላቅነቱ – አንጋፋነቱ፣ ተከባሪነቱና ተደማጭነቱም እንዲሁም ተወዳጅነቱ እንዲቀጥል ከተፈለገ፤ ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ፖለቲካዊ አጀንዳ ፍላጎት አስፈፃሚዎችን፤ ዓለምአቀፍ የነፃ ሚዲያ ሥነ ምግብር የማይከተሉ ከሆነ እርምጃ መውስድ – ይኖርበታል። ደረጃውን የጠበቀ አመራር ሊኖረው – ይገባል። ሃግ በዛም ገለማም ሊሉትም – ይገባል። ለራዲዮ ፋና ቅርንጫፍ ማህያ እዬከፈለ ሊያቆስለን – አይገባም። ከዚህ ላይ አንድ ብጣቂ ማጣቀሻ ላስታውስህ እሻለሁ የሥነ ጥበብ ኮርስ እወስድ በነበረበት ጊዜ በሸበጥ ጫማ ምንም የመማሪያ ቁሶችን ሳይዝ ተከርችሞ ገብቶ ተከርችሞ የሚወጣ አንድ ወጣት ነበር። ሌላ ጊዜ ፋቲኩን ለብሶ – አገኘሁት። ስለሰው መጠዬቅ የእኔ ዓለም ስላልሆነ ሰላምታ ተለዋውጠን የነገረኝን አድምጬ – ተለያዬን። እነሱ ለዘራዊ ድርጅታቸው ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራ ሥነ ምግብር – አላቸው። ስለዚህ ለፋሽስት ፋቲክ ዋቢነት – አይመችኝም። „አመጽ“ የሚለውን በሚመለከት – ውሳኔን – ሃሳብን አልቀበለም ማለት እንቢኝ ብሎ ወይንም አሻምን ተቀብሎ ቤት መቀመጥ አመጽ – አይደለም። ሃሳቡን ዓላማውን ውሳኔውን አልተመቸኝም፤ አልተቀበልኩትም ብሎ ያልመቸውን ሃሳብ፣ ዓላማ፣ ውሳኔ ለመታገል መንፈሱን አሸፍቶ አደባባይ ፊት ለፊት መውጣት ደግሞ በሃሳቡ በዓላማው በውሳኔው ላይ „ማመጽ“ ነው። የግድ የብርት ኳኳቴ – አያስፈልገውም። ሃሳብና ሃሳብ ነው የሚፋጩት – የሚቧከሱት። ይኸው እኔና አንተ በብዕር እንፋለም የለም? እንደዛ …..
እናትዬ – የአቤን ተዎው …. አላወቀበትም። አጠረ! ያልገባህ ነገርም እንዳለ ገልጸኽልኛል። አቤን ከውስጥ አድርገህ – ሊታይህ አይችልም። የሀገራችን የፖለቲካ ጉዳይም ይኸው ነው። በውስጥ ያለውን ጽንስ ውጪ አድርጎ የመተንተን አቅም – ማነስ። ሰፍ የምትልለትን አምክንዮ ሆነ የምትጠላውንም ቢሆን ሞጥጠኽ ከውስጥህ ወጣ አድርገህ – ለዓፄ ዕንባ ዳኝነቱን ብትፈቅድ ከወቅት፣ ከውጪያዊና ውስጣዊ፤ ከብሄራዊና ዓለምአቀፋዊ ተጫባጭ ሁኔታ ጋር ያለውን ተዛምዶና ተቃርኖ ሚዛን ላይ – ማስቀመጥ ያስችላል። ለማንኛውም አቤዋን በሚመለከት በቅንጅት ጊዜ አይበት የነበረው የበዛ ቅንነት ዛሬ ማዬት – አልቻልኩም። እልህና ውድድር ግን እያዬሁበት ነው። አንድ አቅጣጫ ብቻ እእ፤ ተቆርቋሪነትን – ለማስደሰት ሆነ ከተፈለገ ለናሙና ዘሃበሻን ማዬት – ይቻላል። የተቋረጥነውን ሁሉ ነው እቅፍ ድግፍ አድርጎ በአክብሮት – የያዘን፤ ለዛውም ማንና ምን እንደሆን ሳያውቀን – አብሶ እኔን በሚመለከት በጎንዬሽ ያለበትን ጫና ሁሉ ጥሶ መለኪያውን ኢትዮጵዊነትን ብቻ መሆኑን አሰተማረበት። የጎደለውን እያዩ – መደጋገፍ፤ ቀዳዳን – መድፈን፤ ስሱን – ቦታ ፈልጎ መጠገን። ዕንባን አይዞኽ – ይላል። ሁሉ ሰው አንድ ቦታ ላይ መታጨቅ – የለበትም። ብዙ ሰው ያልደረሰባቸው ክፍት የሥራና የኃላፊነት ቦታዎች አሉ። በተረፈ እናትዬ እግዚአብሄር ይስጥልኝ – ያክብርልኝም። ለዚህ ያበቃን ዘሃበሻ ድህረ ገጽንም – አመሰግናለሁ። እንዲህ ዓይነት ክርክሮችና ሙግቶችን መፍቀዱ ህይወት ነውና። ለነገም – ተቋምነት። አቶ ሄኖክ ሰማእግዚር ከተማረበት በፍቅር እብድ የሚልለት ማንፌስቶ የሚያደርገውን መራር ሃዘን የእህቱን፤ የነገን ጽንስ የጮርቃውንም ፍርጃ ፍዳና ስቃይ በዚህ ሊንክ ቢያደምጠው ደስ – ይለኛል። ሌላም አያስፈልገወም ወደ ብሄራዊነት – ለመምጣት። “Esat Menalesh Meti – Ethiopian Women and the struggle for freedom …”
http://ethsat.com/video/2015/05/18/esat-menalesh-meti-ethiopian-women-and-the-struggle-for-freedom/
ባዘገዬውም ሰላምታውን – እንዴት ናችሁ – ቤቶች! ሰሞኑን በጠ/ሚር ሃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ላይ ወክ እንዲህ ልል አሰኝቶኝ ሳለ፤ የተከበሩ ጸሐፊ አቶ ይገርም ዓለሙ ጹሑፍ ገጠመኝና ኃይለ – ቃሏን ብቻ ነጠል አድርጊ አውጥቼ ጠረጴዛዬ ወለል ላይ አስቀምጬ – እንድንፈታተሽ – ፈቀድኩኝ።
መግቢያ በር
እልፍኝ ዬሙግት – ዝመት ላሰኘው ሃሳብ፤
„ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት – ይገረም አለሙ” ዋው¡
“ወያኔዎች ትናንትም ሆነ ዛሬ አላማ ፍላጎታቸው ስልጣን ነው ከራስ ጥቅም ያለፈ አላማም አጀንዳም ያላቸው አይደሉም” ምን? በህግ አምላክ!
“እኛ መጠራት ያለብን እሱ ነኝ በሚለው ማንነቱን በማይገልጸው ሳይሆን ለማንነቱ በሚመጥነው ለግብሩ መገለጫ በሚሆን መጠሪያ መሆን አለበት፡፡ አሁን ልማታዊ መንግሥት እያለ ራሱን እየጠራ ነው ታዲያ እኛ በዚህ እንጠራዋለን?“ ዖዬ!
“ሁለተኛው ግንባር የሚለው ነው፡ከመጠሪያው ጋር ሊቀራረብ የሚችለው ህወኽት ነው እሱ ደግሞ ግንባር አይደለም፤ ግንባሩ ኢህአዴግ ነው፡፡ እሱን በጥቅሉ የትግሬ ነጻ አውጪ ለማለት ተፈልጎ ከሆነ ደግሞ ወያኔ ሀገራዊውን የፖለቲካ ትግል የጎሳ ትግል ለማድረግ ሌት ከቀን የሚማስንበትን ስራ እያሳካንለት ነው ማለት ነውና አደጋ አለው፡፡” ህም!
“የወያኔ ስብከትና ማስፈራራያ ያልበገራቸው በርካታ ትግረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በተቃውሞው ጎራ ጥንቃቄ የጎደለው ተግባር ያለፍላጎታቸው ወያኔን ለመደገፍ መገደዳቸው የአደባባይ ምስጢር ይመስለኛል፡፡ የሚወዱትን ሲያጡ እንደሚባለው ሆኖባቸው፡፡” ኦኦ!
ምንጭ —- http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44875
እንዴት አሉልኝ የተከበሩ ጸሐፊ አቶ ይገርም ዓለሙ። እኔ ኦድዮን ወይንም ራዲዮን ከማድመጥ ፍቀረኛነቴ እነዛን ማራኪ፣ ታይተው የማይጠገቡ ፍልቅ የብቻችን ጠረናችን የሆኑትን – ፀሐያዊ ፊደሎችን እያዬሁ ማንበብ ነው የሐሤቴ ቅምረቱ፤
የ40 ዓመቱን ሥያሜ በተለጣፊ ሥያሜ ይቀዬር ነው የጹሑፎዎት – እድምታው። ይህ በቀጥታ የሚወስደን ወደ አቶ ገብሩ አስራት ቲወሪ ነው። እኔ ደግሞ የአቶ ገብሩ አስራት ቲዎሪ ከማይመቻቸው ሰዎች አንዷ – ነኝ። የደም ሥርን በጥሶ „ገድሎ እግዚአብሄር ይማርህ“ ዓይነት ስለሚሆን በትግራይ መሳፍንት የመሬት ወራራ እንኳን ትንትና ለመስጠት ድፍረት – ስለሚያንሳቸው – ግጥሜ አይደሉም፤ ይበሉ ወገኔ ላነሱት ነጥብ እንዲህ ልሞግትዎት ….. ስለ መለሲዝም ፋሺዝም ጎጣዊ ዶክተሪን ትርፋ ትርፎች፤ እርግጥ ተዘርዝሮ ስለማያልቅ በጥቂት ጭብጦች ዙሪያ ብቻ —
„የልማታዊ መንግሥት“ በለው! ይህም በራሱ አቅሙ – አይደለም። ያለማው አካባቢ ካለ ጥብቅና – ይቆምለት። ምን አልባት በልጥፍነት ወይንም እንደ ፍሉ ማርኬት ይጠቅማል ካሉ የተከበሩት ጸሐፊ አቶ ይገርም አለሙ ምርጫው – የእርስዎ ይሆናል።
የወያኔ ሃርነት ትግራይ፤ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር / The Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF) (Ge’ez: ህወሓት), https://en.wikipedia.org/wiki/Tigrayan_People’s_Liberation_Front ይህ የወያኔ ሃርነት ግንባር ትክክለኛ መጠሪያ መለያ ሥሙ ነው። ዓለም የሚያውቀው። ለምን እንደሚቆላመጥ፤ ደፍሮ ለመጥራት ጭንቅ የሚሆንበት አምክንዮ አብርን ስለኖርን በሚገባ አሳምሬ – አውቀዋለሁ። ለሥሙም ጥገና መጠለያ – ይፈለግለታል፤ ለበደሉ ደግሞ መሸሸጊያ – ግርዶሽ ነገር – ጉድብ። በዚህ ማንፌስቶ በነቂስ ከማህል እስከ ደንበር አንገቱ ቀና ብሎ የሚሄደው ጥቂቱ አንገቱ ተስብሮ ጎብጦ ለመሄድ ያልተፈቀደለት ደግሞ – ዕልፉ ነው። ለዚህም ነው ይህ ዬቅብረት ማንፌስቶ በጥገና ሳይሆን ከሥሩ መነቀል እንደለበት በፅናት እማምነውም።
ክቡርነተዎት – እንደሚሉት ድርጅቱ በሥም ብቻ የቀረም አይደለም። ለሥልጣን ብቻም አይደለም። ተልዕኮና ግብ ነበረው አለውም። የእርስዎ ትንተና ደግሞ ተልዕኮው ምንም አላሰም አልቀመሰም ነው የጸሑፎዎት ነገርዬው፤ እንኳንስ እኛ ያልተወለዱን – ያውቁታል። በሌላ በኩል ተበድላችሁም – ተቀጥቅጣችሁም – ተገፍታችሁም – የገፋችሁን የቀጠቀጣችሁን ዋጥ አድርጋችሁ የተገላቢጦሽ ይቅርታ መጠዬቅ አለባችሁም – ወይንም አትነካኩት – ይመስላል። እኛ የዚህ አጥፊ ሥም አፍቅሮት የለንም፤ ድርጊቱ ግን ከተነሳለት ዓላማ ፈቅ ሳይል በቁርሾ ኢትዮጵያን ሲያነዳት ነው – ያዬነው። ሥሙን ቢቀይር እንኳን የለበጣ ነው የሚሆነው – ማባጨል።
የወያኔ ሃርነት ትግራይ ለታላቋ ትግራይ ህልሙ“ ለ24 ዓመት ዬበታችነት ስሜታዊ ህመሙን ለማስታገስ ቀጥቅጦ፣ ጨቅኖ በበቀል የገዛበት ብሄራዊ ማንነትን – የገነዘበት፤ ታሪክን – የገዘገዘበት፤ ትውፊትን – ያረደበት፤ ሰንድቅዓላማን እግር ከወርች ያሰረበትን ሂደት በስማ በለው ሳይሆን በዕድሜያችን ያዬነው በደም የጨቀዬ ሃቅ ነው። የተመሰረተበት የተደራጀበት ዓላማውና ተግባሩ ለአንድ አካባቢያዊ ስሜት ልዕልና ልቅና አለቅነት ወይንም ንጉሣዊ መሳፍንታዊ ሥርዓት ነው። ከዘርም – ዘር፤ ከመሬትም – መሬት በላይ በማደረግ እጅግ በተንጠራራ በተወጠረ ትዕቢታዊ – ትምክህት በዘረኝነት ስሜት። ጀርሞኖች ናዚዝም አካላቸው እንደ ነበረ – ያምናሉ። ግን በመጸዬፍ ነው። የኛዎቹ ደግሞ የተገለበጠ ነው። አብዛኞቹ ሲከበክቡት ነው – የሚታዩት። በለስ የቀናው የመንደር ድርጅት ያስገኘው ብጣቂ ብናኝ ነገር ለትግራይ ህዝብ ምንም የለም የምትሉት ነገር ካለ፤ አንድ ሁለት ተብሎ ይቅረብና በዛም ነጥብ ዙሪያ መከራከር ዲቤት ማደረግ – ይቻላል። ምላሱን የተጠቆረ የለም። አቅም አለን!
ወያኔ „ሀ“ ብሎ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት ዕለት ጀምሮ የውጭ ሀገር ጸሐፊዎች በሚጽፏቸው ታሪክ ቀመስ መጸሐፍት ሁሉም ባህሉ የትግራይ ነው። ዕምነቱም – የትግራይ ነው። ትውፊቱም – የትግራይ ነው። ድንቅነቱም – የትግራይ ነው። ከመገልገያ አቅም እንኳን። ይህን በቅርበት ካሉ የውጭ ሀገር ቤተመጸሐፍ ጎራ ይበሉና – ይቃኙት። የአራስነት ቆይታ – የትግራይ፤ ክርስትና – ትግራይ፤ ሠርግ – የትግራይ፤ እንጀራ – ትግራይ፤ ቡና – ትግራይ፤ ድልህ – ትግራይ መሪ ትግራይ ጳጳስ ትግራይ …. ምን ያልተወረረ ነገር አለና። ኢትዮጵያ በመንፈስ – ተደምስሳለች። በተክለ ሰውነት በመዳፋችን ውስጥም – አይደለችም። ዕሴት አልባነቷ በረቂቅ ዕውቅና እያገኘ ነው። ትግራይ አካላችን ነው በራሱ የነበረው እራሱ ይበቃውም ነበር። የብሄራዊነት ሃብታት ትሩፋትን እንዲህ በጠራራ ፀሐይ ተዘርፎ – ሳይሸለም። ባለፈው ወር CNN ሰፊ ሽፋን የሰጠው ዝግጅት – ነበረው። ትግራይ ላይ ነው የተጀመረው ደቡብ ደርሶ ማህል ሀገር ተንሸራሽሮ ትግራይ ላይ – ሰከነ። ማህል ሀገር ሳይቀር ተጠያቂዎች በሙሉ …. እሱ – በእሱ። ውዶቼ ዝም ብላችሁ ነው አምታዩት — ወይንም ልብ ሰጥታችሁ ትመለከቱታላችሁ ….? ጥቋቁር ነገሮች እኮ – ናቸው። በደሉም የሚገባን ከውስጥ ሆነን ማዳመጥ ስንችል ብቻ ነው። ወጣ ገብ አቋምም የማይኖረን ተጨባጭ መረጃዎችን ቀረብ አድርገን ጠረናቸውን ዬእኛ ብለን ማሽተት ስንችል ብቻ ነው። በስተቀር የተቆራረጠ ፍላጎት ነው የሚኖረን —- ይህም ብቻ አይደለም። ነገም መፍትሄ አመንጭነቱ ኮሳሳና የተደበቀ ነው – የሚሆነው። የተበደለ መካስ – አለበት። ቢያንስ ይቅርታ ሊጠዬቅ – ይገባዋል። በጀምላ ንግድ ከሆነ ግን ተመልሶ – እንቦጭ ነው።
የሥልጣን ክፍፍሉ፣ የልማት ሥርጭቱ ሚዛናዊነት ቀርቶ በነቂስ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ያልታዩ ያልተወለዱ ጽንሶች ሳይቀሩ በቁርሾ በቂምና በበቀል ያልተቀጠቀጠ አካባቢ ዞን ክፍል ተቋም አለ ብሎ ለመናገር ከሃቅ ጋር ዬመፋለም ያህል – ይሆናል። የትግራይ ወያኔ ሃርነት አባልነት ትግሬነት ብቻ ነው። ይህም ብቻ አይደለም በሌለች ድርጅቶችም በድርብ አባልነትና አካልነት የተፈቀደ ነው። ይህ ደግሞ የትም አካባቢ ለሚኖር ሁሉ ልዩ መለያ፤ የተዋረድ ሥልጣን መከትከቻው ነው። አሁን በምርጫው ከአረና በሰማዕት ታንቆ ያለፈው ሲቲት ሁመራ ላይ ነው። በዚህ አካባቢ የሚወለዱ ልጆች ሥም የምናውቀው የጎንደር ከወልቃይት ከጠገዴ ከቃብቲያ ከአዲረመጽ ሥሞች – ጋር ተመሳሳይ ነው። ለማንኛውም ኢትዮጵያን ሌላ የውጭ ሀገር ቅኝ ገዢ ገዝቷት ቢሆን እንኳን ሊታይ የማይችል የአድሎዊነት ዬመገለል ሰቆቃ ዘመን ነው። ልዕልት ኢትዮጵያን የውጭ ሃይሎች ቢይዟት እንኳን ሊደርስ የማይችል መከራና ፍዳ ያስተናገደችበት ግፋዊ የጠቀራ ዘመነ፤ ህማማታዊ የፍዳ ዘመኗ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለእኛ ምናችንም አይደለም – መጠለያ ጥግ ለሆናቸው ደግሞ – ትንፋሻቸው። ዲታዎችም ናቸው፤ ማንስ ነክቷቸው? እነሱ እራሳቸው ለተገፋው ዜጋ ይለፎች ወይንም ልዩ ቪዛዎች ናቸው – ለማኖር። …. እባካዎትን የማከብረዎት በቅርፊቱ ሳይሆን ውስጡ ለውስጥ መንገዱንም ይድፈሩትና – ይሂዱበት።
„መንግሥት“ የሚለው እራሱ ለእኔ – አይመቸኝም። ኢትዮጵያ መንግሥት የላትም። ብዬም ጽፌ አላውቅም። ስለምን? ብሄራዊ ኃላፊነት ከመወጣት አንፃር አቅሙ ስላልሆነ። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ከሌሎች ሀገሮች ገልብጦ ላወጣው ህግ እንኳን ተገዝቶ – ስለማያውቅ። ሥርዓቱም ሆነ አስተዳደሩ ለናሙና የሚመስለው አንዳችም ሀገር – ስሌለ። አንድ መንግሥት የኃላፊነትና ዬተጠያቂነቱ ህግ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅሙ ከራሱ መጀመር መቻል አለበት። ቃሉን በሚመለከት በአለም ሸበላ ቃሎች ሁሉ በገፍ ወደ ኢትዮጵያ በስደት – ገብተዋል፤ በአንቀፃትም ቅኝ – ተገዢነት። ቀሰማው ግን በማንነቱ ውስጥ ተቀብሮ – ቀርቷል። ያ ማንነቱ የቆመለት „ዬታላቁ ትግራይ ራዕይ ነው።“ ሌላውን ግን እንደ አደስ በመደቆስና – በመፍጨት። ስለዚህ እኔ ባይገርመወት የጎጥ አስተዳደር ወይንም ሥርዓት እያልኩ ነው እምጠራው ….. „አስተዳደርም“ መጥኖት አይደለም፤ ትንሽ ቢቀርብ ብዬ በማጠጋጋት ወይንም በማሸጋሸግ – እንጂ፤
እንደሚያውቁት ሦስቱ የመንግሥት አደረጃጀቶች አሉ። ፌድራሊዝም፣ ወጥ ወይንም ኮንፈዴሬሽን። ከነዚህ ውስጥ ሥሙን መያዝ አይደለም ቁም ነገሩ። ቁምነገሩ የሥልጣኑ ምንጭ የህዝብ ፈቃድና የህዝብ ባለመብትነት ከህይወቱ ከውስጡ በመሆን በድርጊት ሲቀልም ብቻ ነው። ኢትዮጵያ የምትማራው በመለሲዝም – ሄሮዲዝም ፋሺዝም – ዶክተሪን ነው።
„ግንባር“ ተለጣፊ ናቸው። ውህደት – የላቸውም። በውህደት የተቀረጸ ደንብና ፕሮግራም – የላቸውም። ሥልጣኑንም፤ መንፈሳዊ ሃብቱም፤ ቁሳዊ ምንጩም ወደ አንድ የተማከለበት ሆኖ ነው – የሚገኘው። የአፈሯ ቡቃዬ ነኝ የሚል ማንኛውም ዜጋ ድራሹ እስኪጠፋ ድረስ በተገኘው የሚወቃበት – ባለ ሎቲዎች ግን አብዛኞቹ ተለይተው እጬጌ የሆኑበት … የክትና የዘወትር፤ ወርቅና ነሃስ በጎጥ ግንብ የተለዬበት። ቢመርም የ24 ዓመት የጨለማ ዘመን ሸክም ነውና መዋጥ ግድ – ይላል። ተጠያቂው ደግሞ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንጂ ሌላ ከቶ ሊሆን አይችልም። ደጋፊውም ቢሆን ትራሱ እሱ – በእሱ ነው። አንዲት ኢትዮጵያዊ ሴት ከትግራዊቷ ሴት ጋር እኩል ተቀባይነት – የላትም። ብቃት አይደለም መለኬያው፤ ዜግነትም አይደለም፤ መንደር – እንጂ —-
በዘመነ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነፃ ውጪ አስተዳደር እያንዳንዱ የእንቅስቃሴ ነጥብ በመርዝ የተበከለ ስለሆነ ሌላ የሰከነ የመንፈስ አብዮት የሚጠይቅ ተግባር ከፊት ለፊት ብሄራዊ ነፃነት ፈላጊውን ህዝብ – ይጠብቀዋል። ወንድሜ ሆይ! ይህ የሚጎረብጠዎት ከሆነ ይህን ይስሙት ሳይሆን – ያዳምጡት።
http://ecadforum.com/ethiopianvideo/2015/02/03/u-s-policy-ethiopia-a-failed-state-documentary
በማድመጥና በመስማት፤ በማዬትና በመመልከት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። ማዬት ዓይን ያለው ሁሉ – ያያል፤ መመልከት ግን ህሊና ያለው ብቻ ነው የሚያስተውለው። ማድመጥም ጆሮ ያለው ሁሉ ይሰማል፤ ማድመጥ ግን ልብ ያለው ብቻ፤ 24 ዓመት ሁሉን በተደሞ የመረመሩት ሥልጡኑ የአውሮፓ ማህበረሰብ „የትግሬ መንግሥት“ ብለዎታል አቅም ካለዎት እሱን – ይሞገቱት። እኔም ለዬትኛውም ድርጅት ስጽፍ የአንድ መንደር ድርጀት አይልኩ ነው – „ቁርጥ ያጠግባል“ ይላል ጎንደሬ።
የአንድ ሀገር ህዝብ መለያው ዓለምዓቀፍ ዕውቅና ያለው መልክዕምድራዊ አቀማመጡ ነው። በሥሩ ያሉ ለአስተዳደር እንዲያመች ተብለው የሚደራጁት አካባቢያዊ ቤተ – አካሎችም በዚህው ተፈጥሯዊ ሥር ነው የሚታደሙት። ዛሬ ያነ አለ ወይ ሲባል – ፈልሷል። „ለታላቋ ትግራይ ህልምና ራዕይ“ ሲባል …. ተፈጥሯዊ ደንበሮች ተጥሰው ታላቅ የቅረስ ዘረፋና የታሪክ ቅጥፈት – ተከውኖበታል። ለምን? ይህ የሆነበት ምክንያት በፌድራሊዝም አደረጃጀት አንድ አካባቢ በአቅሙ ልክ ነው የአስተዳደር ውክልና ማግኘት – የሚችለው። የሥልጣን ደረጃውም – የሚዋቀረው። ስለዚህ ቀደም ባለው የትግራይ ክ/ሃገር ትግራይን በራሷ የኢኮኖሚ አቅምና ጥሪት አውጥቶ እራሷን ችላ እንድትቆም የፌድራሊዝም ተጠሪ ሊያደርጋት – አይችልም። የኢኮኖሚ አቅም ምንጭ ደረጃው ዝቅተኛ ስለሆነ፤ ስለዚህ አባል ሳትሆን ግን ተሳታፊ ብቻ እንድትሆን ሊያደርግ የሚችል የውክልና ሁኔታ መምጣቱን የሚውቁት ሄሮድስ መለስ ዜናው ቋንቋን መከለያ አደረጉት። …. ይህም የሚሠራ አይደለም። ለምሳሌ ጎጃም ቤተ – አገው አለ፤ ወሎም – እንዲሁ። ቋንቋ ይሁን ሲባል እነዚህን እንዴት አንድ ላይ ማደረግ ይቻላል? ተፈጥሯዊ መነሻ መሬታቸው በጣም – የተራራቀ ነው። ይህ በቤተ አገው ላይ አልሰራም። በትግራይ የመስፋፋት የወረራ ህልም ላይ ግን – ሠርቷል። ሌላም ምሳሌ ቤተ – ቅማንት ጭልጋ አውራጃና ጎንደር አውራጃ አለ። አሰፋፈራቸው ግን አንድ ላይ ለማድረግ – አይመችም፤ በሌላ በኩልም ጎንደር ከዕርዕሰ ከተማው ዙሪያ ያሉትና የጭልጋዎች ሥነ ልቦናዊ ሁኔታም ያደጉበትን አካባቢያዊ ሁኔታን የተቀበለና የለመደ ሆኖ – እናገኘዋለን። እኔ ሁለቱንም ቦታዎች አሳምሬ ማውቅ ብቻ ሳይሆን ኑሬ ሠርባቸዋለሁ – ለዛውም እያንዳንዱን የገጠር ጣቢያ። በብሄረሰብነት ለማጠቃለል የወሰን የደንበር ቅርበት ፈጽሞ – የላቸውም። አንዱ መተማ በር ሌላው ወገራ በር ነው። ሥነ ልቦናቸውም – እንዲሁ። ስለዚህ በዚህም አያስኬድም፤ አሜሪካ ከ100 አመት ላለነሰ በእንግሊዝ ቅኝ ነበረች። ፌድራሊዝምን ስትገነባ ከዚህ ሀገር ከዚህ ዘር አልተባለም፤ ህዝቡ በለመደውና ተሳስሮ በቆዬው ትውፊታዊ ዕሴቱ ላይ ነበር የቀጠለው፤ ይህም በመሆኑ ዛሬ ከሀገሯ አልፋ አሜሪካ የዕልፎች መጠጊያ ባለጸጋ ሀገር ሆነች። የህዝብን ስሜት የዋጠ እርምጃ ትውልድን ከፍርሰት – ያድናል።
ዬፌድራሊዝም አደረጃጀት ከሌሎች ሀገሮች – የተቀሰመ ሲሆን፤ ሲቀሰም ግን ለራስ እንዲያመች ሆኖ – ተቀልብሷል። ጀርመኖችም ፌድራሊዝምን ሲያደራጁ የነበረው አካባቢያዊ ስሜትና ቅርስ፤ ትውልዳዊ ትስስር፤ ተፈጥሯዊ ደንበሮች ንክት ሳይሉ ነበር የከወኑት። ቋንቋቸው አንድ ቢሆንም ዘይቤው የተለያዬ ነው። በባህላዊ አለባበሳቸውም የተለዩ አሉ። ግን ሁሉንም ሳይናድ ነበር የተከወነው። ዛሬ ያን የጨለማ ዘመን አልፈው የአውሮፓ ጭንቅላት መሆን የቻሉትም በዚህ አመክንዮ ውስጥ ብልህ የሆነ ሥልጡን ተግባር በመከወናቸው ነው። ህዝቦች ቀድመው በኖሩበት፣ በተዋህዳቸው በሚያውቁት አካባቢ ሥነ ልቦናቸው ጫና ሳይኖርበት፤ ሳይከፋቸው እንዲኖሩ በቅናዊ አስተዳደር ነው በሌሎች ሀገሮች – የተደራጁት። ይህን ቁልጭ ባለ መልኩ ከጀርመን ሆነ ከአሜሪካ የፌድራሊዘም የአደረጃጃት ታሪኮች ማዬት ይቻላል።
ሰሞኑን ጠቅላይ ሚር/ ሃይለማርያም ደሳለኝ ያጎረሷቸውን ሲነግሩን ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵውያን ላይ ያለውን የመብት መደፍጠጥ ሲያቀርቡ ሃስት በማለት ሲያቅራቸው፣ ሲያጣጥሉ ባዳመጥንበት ጆሮ ዛሬ ደግሞ ከ100000 ላለኑሱ የኤርትራ ወጣት ስደተኞች በተቆርቋሪነት የዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ያቀረበው ሪፖርት እውቅና ሲሰጡ በተመሳሳይ ምላስ – አዳምጠናል። ኢትዮጵያ ላይ ሲሆን – አይሰራም። የፌድራሊዝም አከላልም – እንዲሁ ነው። ሙልጭ ያለ ቅጠፈቱ በእያንዳንዱ አመክንዮዊ ጉዳይም ትግራይን በማላቅ በማስመቸት ነው። ስለዚህ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ለትግራይ ምንም አላደረገም – የሚለው መከራከሪያው ደመ ነፍስ ነው። ግጥም አድርጎ የፈለገውን ከውኗል። መንፈሳዊና ሥነ ልቦናዊ ጥበቃ በተለዬ ሁኔታ – ተከናውኖበታል። ይህ በቀላሉ ሊታይ የሚችል አይደለም እጅግ – ረቂቅ ነው። ከጠባብ ቤት ሰፊ ቤት የበለጠ – ይደላል፤ ከኢትዮጵያዊ ዜግነት ይልቅ ዛሬ ትግሬነት አልጋ ባልጋ ነው። ሌላው ቀርቶ ቋንቋውን መናገር ልዩ ሽልማት – ያሰጣል። ከአዲስ አባባ ወይንም ከጎንደር ተነስተው ለክርስትና ትግራይ ድረስ መሄድ የተለመደ – ሆኗል። ካለው ተጠጋ … እንዲሉ ሆኖ እዬታዬ ነው። ለደጅ ጥናት። እኔ ይሄንን ዘመነ የትግራይ መሳፍንት እለዋለሁ። እኔ በጣም እማወቀው ዲታ ሰው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስልጣን እንደያዘ አክሱም ጽዮን – ሄዷል፤ ደጅ ጥናቱ ለማይገሰሰው የመዳህኒዓለም ቤት – አይደለም።
… እእ ደጅ ጥናቱ ለትግራይ ነፃ አውጪ አስተዳደር ግብር ለማስገባት ነበር፤ ምክንያቱም ከዛ በፊት መሄድ ይቻል ነበር። እንደ ቁልቢው ጉዞ …. ሰው እሱነቱን እያወጣ እዬጣለ በራሱ ላይ የሥነ ልቦና ጥቃት ሁሉ ፈቅዶ ፈጽሟል – የብሄራዊነት – ንደት፤ ይህም ብቻ አይደለም ዕድምታው ማንነትን በፈቃዱ – ይሸረሽራል። እራሱን – ይሸጣል – ይለውጣል። የመንፈስ ወራራ፤ የታሪክ ወራራ፤ የመሬት ወራራ፤ የትውፊት ወረራ – የሃብት ወረራ – ገኗል፤ በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ዘር ቆጥሮ መጠጋት የመኖር ህልውና ጉዳይ ሆኗል። „ከትግራዊነት ጋር ተጋብቶም ተዋልዶም ክርስትናም ተናስቶም ብቻ በሆነ ክር ከዘመንተኛው ጋር ተዛምዶ መኖር ነው መስፈሪያው – ልኩ፤ ቀና ብሎ እንዲሄድ የሚያደርግ ልዩ ጆከር“ ይህን እውነት ዳጡት ነው የእርስዎ አምክንዮ …. እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ደግሞ – አስፈንጥረዋለሁ። አላስጠጋውም! አንድ ቀን ብርሃን የወጣ ዕለት ድህነት – ምህረት – ይቅርታ ማውረድ የሚቻለውም ዕውነቱን ስንደፍር ብቻ ነው። እንደጎበጥክ የአንጀትህ ሴል እንደረገፈ ተሸከም ግን ሌላ የጭንቅ ዘመንን – ይተካል። ቢያንስ የመንፈስ – ካሳ፤ የተቀጠቀጠው መንፈስ እንዲያገግም ጥንቃቄነት ያልተለዬው የአያያዝ ልዩ ጥበብና እንክብካቤ – ብልህነትም ያስፈልገዋል። ድርድር ሊደርግባቸው በማይገቡ የመሬት ጉዳዮች ላይ ቁልጭ ያለ ግልጽነት ያለው በህግ የተደነገገ ደንበር መሥራት ግድ – ይላል። በስተቀር አይቀሬው – አይቀሬ ይሆናል።
ለነገሩ ተዘርዝሮም አያልቅም ጥቂቶችን ግን እንሆ ====
- ዛሬ ከጣና ለተሳበው የኤሌትሪክ አገልግሎት መብራቱ ለትግራይ ነው። ዘበኛው በተራ ሌትና ቀን የሚጠብቀው ግን በመስመሩ የሚልፍባቸው ደሃ ጨርቅ ለባሾች ገበሬዎች – ናቸው – እነ መከረኛ። ጨለማ ውስጥ በእንጨት ጭስ ብልጫታ እንደ ዛሬ ሺህ ዓመታት ይኖራል – የሁሉም ነገር መፈተኛው፤ ቢያንስ መብራት ይዞ ማብላቱን እርሰዎ እንደ ሰው ምን ይሉታል? !!!!! ?
- የአባይ አጀንዳ አበቃለት መሰል፤ ጭጭ ሆኗል፤ እሱም ቢሆን የራሱ ትዕይንት ተቀመሮለት የተከወነ ነው። አባይን እስከ ምንጩ ለመቆጣጠር —-
- ማትሪክን አልፎ ለመግባት „ትግረኛ ቋንቋ“ አብይ መሥፈርት ነው። + ሆነለት ማለት ነው።
- ዬመተማ ወደብነት ለሱዳን ግንኙነት – ይህም የእግር እሳት – ስለሆነ፤ ቀጥታ ወደ ትግራይ የሚገባ መስመር ከመንፈስ አልፎ መሬት ላይም የወረደ ተግባር እዬሆነ ነው ….
- የኢፍርት ህዝባዊ ሃብትነት ብሄራዊ ሲሆን ጥሪቱ ተሟጦ ዬት ላይ እንደ ሆነ ልበዎት – ያውቀዋል። ቀድሞ ነገር አንድ ሀገርን የሚመራ ድርጀት ከብሄራዊ ሃብት ማፊሪያ ውጪ ይፋ የሆነ ግንጥል የኤኮኖሚ ተቋም ሲኖር የወያኔ ሃርነት ትግራይ በዓለም የመጀመሪያው ነው።
- ሰሞኑን ትንሽ ገጭ ገው ቢኖርበትም፤ ከጁቡቲ ትግራይ አሰብን አቋርጦም ከአዲስ አበባ ጁቡቲ የነበረወን የንጉሦች ንጉሥ የዓጤ ሚኒሊክን ጥሪት ለመፋቅ የታሰበ ሌላው ጉዳይ ነው፤
- በትምህርት ዘርፍ ዛሬ ማዬት አይቻልም ትምህርት የረጅም ጊዜ ሂደት ውጤት በመሆኑ (education) ፤ በዚህም ዘርፍ ኮንፒተራይዝድ የማደረጉ ተግባር መሬት ላይ እዬወረደ ነው ….
- ለማናቸውም ናሙናዊ እድገት ዬልምድ ልውውጥ ትግራይ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል …. ሌሎች ለምስልና ለሽፋን ነው፤
- ለተቋማት ምስረታም ሩጫ ማራቶን ሽልማቱ ያው ለትግራይ ነው ….. የአሸናፊዎች አሸናፊ ተወዳዳሪ አልቦሽ።
- ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አቅጣጫቸው ወደ ትግራይ ነው …..
- በስፖርት፤ በባህል፤ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፤ በከፍተኛ የትምህርት የውጪ ሥልጠና፤ ቅድሚያ ኢትዮጵያዊ ዜግነት አይደለም። ትግራዊነት ነው፤ ዛሬ ሯጭ ከደቡብ ብቻ አይደለም – ትልቁ የሥልጠና ማዕከል ትግራይ ላይ ነው።
- ቶሎ ጉዳይን በማስፈጸም፤ ቶሎ መረጃ በማግኘት፤ ተሎ ተደማጭ በመሆንም፤ ቶሎ እውቅና በማግኘት የተሻለ አክሰስ ያለው የትግራይ ተወላጅነት ነው።
- ታሪክ ባህል ጉብኝት ሁሉም ማዕከሉ – የትግራይ ነው። ….
- አቤት! ስንት የቲያትር የፊልም ተዋናዮች ፈሩ …. „ቅመሞች“ ካለነሱ ቅስቅስ የሚል አንድም ፕሮጀክት – የለም። አላበደም አንድ የፕሮጀክት ማናጀር ከእነሱ ውጪ ….
- ከስሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምእራብ ከላይኛው ማዕከለዊ መዋቅር እስከ ገጠር የከተማ ሱቆች ድረስ ሁሉም የሃብት ቁጥጥር በአንድ ጎሳ ሥር የተጠቃለለ ነው። የእኛም ስጋት ይሄው ነው። እንደ ሰው ለምናስበው፤ አንድ ነገር ቢፈጠር በአግባቡ ማስተዳደር ካልተቻል ቅድመ ሁኔታውን በላቀ ሥልጡን አማራር ማስተዳደር ካልተቻለ መከራው እጅግ አሰቃቂ እንደሚሆን – ስጋቱ እንቅልፍ አልባ – ያደርጋል። የቂም ውርርስን ሰብዕናችን – ስለሚጸዬፈው። የነገ ኢትዮጵያ መከራው በቁርሾ እንዳይወራረድ በመቻቻል እንዲሰክን – እንሻለን። ግን ዛሬ ያለውን ሃቅና በደል በመረገጥ – አይደለም። ለበደሉ መታመንን አብዝቶ ይጠይቃል ዘመኑ – መከራን ለተቀበለ መንፈስ ታማኝነት ይጠይቃል – በአንክሮ።
- ብዙም እሩቅ አይደለም በቅርቡ አዬር መንገድ ካሰለጠናቸው 50 ቴክኒሻኖች 48ቱ የትግራይ ልጆች ነበሩ። ይህ ለናሙናነት እንጂ የትግራይ ወያኔ ሃርነት አባላት የዬትኛውም ቦታ አዛዥ ናዛዥ እንሱ ናቸው። ለድርጀቱ አባልነት ፈቃድ የሚሰጠው ደግሞ መስፈርቱ „ትግሬነት“ ነው። ከቶ ይህ ከስታስቲክ ውጪ ሆኖ ይሆን – ለርስዎ?
- የደረጃ እድገት፤ ለሁለተኛ ለሦስተኛ ቀጣይ የትህርት ዕድል፤ የአክስዮን ድርሻ ስንቱ ይዘረዘራል …. ነጭ ለባሾች እነሱ ናቸው።
- በተገኙባቸው ድርጅቶች መዋቅሮች ፈቃድ መዋቅራዊ መንግስታዊ አይደለም የትግራይ ወያኔ ሃርነት አባልነት ብቻ ነው። ማናጀሩ የሌላ አካባቢ ሰው ከሆነ „ፎቶ“ ብቻ ነው የሚሆነው። አንዱ ብቻ ብዙ የተከማቸ ሥልጣን አለው – ተራው ካድሬ ማለት ነው። ካድሬ ባይሆንም። ….. ሌላው ደግሞ የበይ ተመልካች እንዲሆን እንኳን አልፈቀድለት ብሎ – በሳንጃ፤ ጎራዴውም አልበቃ ብሎ – በማደንዘዣ ….
- የኢትዮጵያን የአፍሪካ ቀንድነት ወሳኝ ጂኦ ፓለቲካል መልካምድራዊ አቀማመጧን እንዲለወጥ በማድረግ ክብሯን ሲቀንሱ ኤትርትራ የምትባል ሀገር ፈጥረው ነው። ጸሑፎዎት ይህን መሰረታዊ ጉዳይ በአግድሞሽም ይሁን በሰቃዊነት ዘሎት አልፏል፤ ዛሬ ደግሞ እነሱዎ ለሠሩት ኡኡ ሲሉ ይደመጣሉ፤ ኢትዮጵያ ግን አምላክ አላት ሰው ሠራሽ ሴራን የጨው ውሃ የሚያደርግ። አናቆራቸው።
ለኢትዮጵያ ህዝብ ለገጠሩም ለከተማውም መሬት የደም – ቧንቧው ነው። በዚህ ዘርፍም ተመሳሳይ የተዛባ ስርጭት ነው የሚታዬው፤ ከዚህም አልፎ ሰፊ መሬት ተቆርሶ ከወሎና ከጎንደር ወደ ትግራይ ተክልሏ። ትናንት አባቶቻችን ሲነገሩን እስከ ሃይቅ እስከ ባህርዳር የጎንደር ነበር ይባል ነበር። ጋብቻውም እንዲሁ። ዛሬ ያ ተርስቷል። አሁንም ከሁለቱ ክ/ሀገሮች የተዘረፉ መሬቶች ተረተረት እንዲሆኑ እዬተፈለገ ነው። ልምምድ – እዬተደረገባቸው ነው። የአነ አቶ ገብሩ አሥራት ቲወሪም ይሄው ነው „ህዝብን እዩ“ ይሉናል ማላገጥ።:፡ አሁን ጎንደር የፌድራሊዝም ደረጃ ይሰጠኝ ብትል – አትችልም። ለምን የኢኮኖሚ አቅሟ – አይፈቅድም፤ ጎንደር ስሜኑ አራት አውራጃዎች ነበሩት ጭልጋ – ወገራ – ጎንደር – ስሜን አራቱም አውራጃዎች ተቀራምተዋል፤ በጭልጋ አውራጃ በኩል መተማ ለጉምዝና – ለሱዳን፤ ወገራ – ስሜን – አውራጃና ከጎንደር አውራጃም ዬአርማጭሆ አካባቢ ለትግራይ – ተስጥቷል፤ ዩኒስኮ በቅርስነት የመዘገበው ፋሲል ግንብ ብቻውን ኤሉሄ እያለ ነው። በተከበሩ ጓድ ገዛህኝ ወርቄ ስልታዊ የማፈግፈግ ሂደት የዳነው ፋሲል ግንብ ዛሬም የስጋት ምንጭ ነው – ለሥርጉተ። ፈንጅ ይቀበርበት ይሆን ወይንስ ያ የቅርስ የታሪክ ጌታ ዘመኑ በምን ይጠቃለል ይሆን? ዕንቅልፍ የሚነሳኝ ጉዳይ ነው። ማፍለስ ነውና የወያኔ ሃርነት ትግራይ – ተልዕኮ፤ ተዘርዝረው የማያልቁ ተጽፈው ያማይዘለቁ የተዛነፉ ግፎች – ተፈጽመዋል። አልተጠቀመም የትግራይ ህዝብ ለማለት በፍጹም – አይቻልም። የጥንታዊ ቤተ ክርስትያን ቅርሰ ቅርስማ ስንቱ … አጋፏል – እስኪበቃው። አንዲት ነገር ግን ከትግራይ ንክች – አላለችም። ከቅርሰም ከትውፊትም።ማን ደፍሮ! አፋርም – ያሰጋዋል – ካልበረታ። የሰው ዘር ምንጭነቱ የበታችነት ስሜት ለሚያናውዘው የጎጥ ድርጅት የእግር እሳት ነውና። እነዛ በዬቦታው አሉ የሚባሉት ዲታዎች እኮ ዘረ መነሻቸው – ትግራይ ነው። አንዱ ሲዳላው ሲመቻው ቤተሰቡም ቀና ይላል። በአማካኝ አምስት ሰው ይዞ – ይበላል። ለነገሩ እነሱም – አይሉም፤ ምን አልባት ቁስለኛ ላልሆነ ሰው ባዕዱ ሊሆን – ይችላል። ቀን አይቶ የማይከዳው ንጉሥ ዕውነት ግን ይሟገታል – ታሪክም ጥብቅና ይቆማል። ወገኖቼ ሁመራና መተማ ማለት እኮ ካሽ ክሮፕ እኮ cash crops ነው። ዶላር እኮ ነው የሚታፈሰው። ተዝቆ የማያልቅ የሃብት ክምችት ነው ያለው ከዛ። ግን በዕብሪት ተዘረፈ። ሥነ – ልቦናውም በጩቤ ተዘለዘለ።
ለዚህም ነው ከዚህ አቋም ለዬት ብለው የሚወጡትን እጅግ ጥቂት የትግራይ ልጆችን እንደ ብርቅና እንደ ድንቅ የሚታዩት። ወደ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲም ሲቀላቀሉ እንደ ሌላው አይደለም። ተነጥፎ ተጎዝጉዞ በተለዬ ሥርዓትና ወግ ነው። ለምን? ከህሊናዎት ጋር ቁጭ ብለው ይፋረዱ ….. የነገይቱ ኢትዮጵያ ይህን የተዛበ ሥርጭት፤ አካለ ጎደሎ የሆነ ዬአያያዝ ክርጭጭት ማስወገድ- ይኖርባታል። አንድ ዜጋ በሀገሩ እኩል ነው። አንድ ዜጋ በሀገሩ እኩል መብትና ግዴታ አለበት። ለዜግነት የክትና የዘወትር የለም። ይህ በተራ ቀላጤ ሳይሆን በህግ ሽፋንነት ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ የሰብዕ መብት ነው። በመዋቅር አስፈጻሚነት እዬተከወነ ያለው አድሎዊና አግላዊ ሥርዓት መልክ ሊያስይዝ የሚችል፤ በዚህ የዘበጡ ጉዳዩች ላይ ደፍሮ እርምጃ መውሰድ የሚችል ሥርዓት ነው እኔን የሚናፍቀኝ ….. ህግ የሚዳኘው። እራሱም በህግ የሚተዳደር ግልጽነት ተክለ – ቁመናው የሆነ በስተቀር „አለባብሰው ቢያርሱት በአረም ይመለሱ“ ነው የሚሆነው …
አዎን ገዢያችን የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ወይንም ግንባር ህወሃት ነው። እኛ ኢትዮጵውያን ባሪያዎች እነሱ ደግሞ ዘመን ላይ ያንጠለጠላቸው – ጌቶቻችን ናቸው። ዛሬ የባሬያና የጌታ፤ የጌታና የሎሌ ሥርዓት ነው ያለው …. ከባርነት ነፃ ለመውጣት መጀመሪያ በችግሩ ላይ ግልጽነት ያለው ያልተደበሰበ አጋሰስ ያልሆነ አቋም ሊኖርን – ይገባል። ድፍርስ በሽታ ነው። የተበደለውን ህዝባችንም ባናስከፋው ጥሩ ነው። ቢያንስ ለተቀጠቀጠው መንፈሱ ጥብቅና መቆም – የአባት።
አዎን እርግጥ ነው። ዘመናዮች በሚታይ ነገር ማለቴ ነው ጥቂት የትግራይ ልጆች ሊሆኑ ይችላሉ፤ በማይታይና በረጅም የማደራጀት መልሶ – ዬማቋቋም፤ በተረጋጋ የማስልጠን ተግባር ሲታይ ደግሞ እስከ ልጅ- ልጅ ሊዘልቅ የሚችል የትግራይን ህዝብ በተጠቃሚነት ሊስቀጥል የሚችል ዘርፈ ብዙ አልሚ ፕሮጀክቶች ሌትና ቀን እዬባተሉበት ነው – በኢትዮጵውያን ሃብት። እርግጥ ዛሬም ትግራይ ላይ በባዶ በእግራቸው የሚሄዱ ገበሬዎች ሊኖሩ – ይቻላሉ፤ በመሸታ ሊተዳደሩ የሚችሉ ሴት እህቶቻችን ሊኖሩ ይችላሉ። ዘለግ ብለው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን፤ የተጣሉ መሰረቶችን ስናይ ግን ከደቡብ አፍሪካ የተመክሮ ማሳ መማር ያለብን – ይመስለኛል። ዛሬ ዬምናዬው የሃቅ ወርቅ አለ። እንደገናም ዛሬ የማናዬው ከ20፣30 ዓመት በኋላም የሚታዮ ምጥቀቶች አሉ። ለማናቸው ነገር ለመንፈስ – ለሥነ ልቦና በዬነጥብ ጣቢያው ይህንን ተልዕኮ ጥበቃ የሚያደርግ ጥግ ይዘው የተቀመጡ ግን በአግባቡና በውል የተደራጁ የቀደሙ ደጀኖችም – አሏቸው። በተቃዋሚነት – ሥምም። የኛው የተቀጠቀጠው መንፈስ ደግሞ አውላላ ሜዳ ላይ ነው ያለው። ሳሩን እንጂ ገደሉን – አላዬም። መሰናዶውም – እንብዛም ነው። ባሊህ ባዩም – እስተዚህም ነው። አንደኛው እንዲህ አይነት መንፈስን የሚያዝሉ ጹሑፎች እና በማር የተለወሱ መርዝ የሚተፉ መጸሐፍቶች ናቸው። እኔ የልጆችን መጸሐፍት ስጽፍ እንዴት ተጨንቄ እንደፃፍኩት፤ ምን ያህል ጊዜም እንደበላብኝም – አውቃለሁ። እኛ ባለፍነበት ንትርክ እነሱ ማለፍ ስለለባቸው ነበር ያን ያህል በጥበብ ድክም ብዬ – የሠራሁት። የልጆች ራዲዮ ዝግጅቴም እንዲሁ ፍቅርን – ለማውረስ ይተጋል። ለማንኛውም አስከ ዛሬ ከአጠገባቸው ድርሽ ያላልንባቸው ያላዬናቸውም የተኛንባቸው ሃቆችን ቢያንስ ዛሬ ዓይናችነን ከፍተን ማዬት – ይኖርብናል። የተበደልን – ወገኖች። ለዚህም ነው እኔ የጥገናዊ ለውጥ ግጥሜ – የማይሆነው። ጎጠኝነት ከሥሩ በህግ መነቀል – መታገድም አለበት ባይ ነኝ። ሀገረ አሜሪካን ያዳነውም ይሄው ነው። ጀርመን ውስጥም፤ አፈንግጠው ሊወጡ የሚችሉ ረባሽ መንፈሶች በህግ ቀደመው – ስለታሠሩ። እርግጥ መታሠራቸው ብቻ በቂም አይደለም፤ ጥበቃ የሚያደርግ የህግ አስፈጻሚ፣ የቁጥጥር አካሉ የመሰረቱ አስኳል ህዝባዊ መሆን – ይኖርበታል። የቃላት ድርድር ሳይሆን ከእብለት ጋር የማያድም ወይንም የማይደራደር – ልቅና። ፖለቲካና የሰው ልጅ መብት መከበር ለአንድነታቸውም ለልዩነታቸውም ዘርፍ አለው። ብልሆች ብቻ ያውቁታል። የፖለቲካ ትርፍ የሰብ ውስጥን ማፍካት ካልቻለ ንቃቃት – ያስከትላል።
የነፃነት ትግሉ በሥነ ልቦናዊ ዘርፍም ጥበቃ ማድረግ – ያስፈልገዋል። እኔ እርስዎ የጻፉት ጹሑፍ የፈንጅ ያህል ነው – ያቆሰለኝ። አይደለም – ሌላውን። እያቅለሸለሸኝ ነው – ያነበብኩት፤ ስለምን? በአጋጣሚዎች ምክንያት ብዙ ነገሮችን በጥልቀት ስለማዳምጣቸው። እርግጥ ነው እማደንቀው አቋም አለዎት – በቀደምቶቹ ጹሑፎዎት፤ በዚህ ፁሑፍ ግን መገናኘት አይደለም መቀራረብ የሚያስችል አቋም የለኝም። እና ደግሞ ተግቼ – እታገለዋለሁ። ሚዘኑን የሳተ ትንተና ነውና። ውሎው ጦር ሜዳ ነበር – የብዕሩ ማለቴ ነው። የሆነ ሆኖ በዚህ ሥርዓት ተጠቃሚ የሆነውም ቢሆን የሚበልጥበትን መምረጥ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን – ያደርገዋል። በዚህ የመከራ ዘመን መከራን የመረጡ፣ እስራትና እንግልትን የመረጡ እጅግ ጥቂት – ደሞቻችን አሉ። እንደነሱ መሆን መቻልን አብዝቶ ዘመኑ – ይጠይቃል። አንስቼ የማልጠገበው ዬውዴን ዬአብርሽን አርያነት መከተሉ መንገዱ ይህ ብቻ ይመስለኛል – መፍትሄውም። ጎጠኝነትህ ከረፋን – ኢትዮጵዊነታችን ይበልጥብናል፤ ከብዙሃን መከራ ጋር መኖር ይሻለናል ማለት – አለባቸው። ድሎት ያገኙባቸው አመክንዮችንም ቢሆን የእኛ አይደሉም የዘረፋ ነው፤ ለሥጋም ለነፍስም የማይሆን በማለት …. መሞገት ይኖርባቸዋል – የአካባቢው ተወላጆች፤ … በተዘረፈ ሃብትና ንብረት ዬወርቅና የጨርቅ መተያያ ቅብጥና ቅልጥ ዘመኑን ከሚያደርጉት፤ በዬሾጎሬው በወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽሙትንም በደልንም – ቢያስታግስት። ጭንቅላት መፈጥፈጥ ልጅ -አያወጣም። የሁሉም ዳኛ ደግሞ አለ ከላይ። ወደ ላይ የሚረጭ ዕንባ፤ ቀን እንደ ጠቆረ አይቀርም – ያልፋል። ይህም ያልፋል፤ ያ እንዳለፈው ሁሉ፤ ለማንኛውም ….. ተለይተው ገፍትረው መውጣት – ይኖርባቸዋል። ተለይቶ ሲወጣ ግን በተጋደመ ወይንም በተጣነነ ወይንም በተንጠባጠበ ዕሳቤ ሳይሆን ቁልጭ ካለው ሃቅ ጋር ፊት ለፊት መተያያት በመቻል – ድፍረት።
መውጫ በር …
በጣም ክብካብ የሚደረግላት እንደትነካ የምትሻ ጉዳይን ወኔን – ትሻለች። ስንደፍራት መዳህኒትና ፈውስ ናት። በስተቀር ነቀርሳ ትሆናለች። ዬነቀርሳነቷ ዘመን ተሻጋሪነቱ አይቀሬ ነው። …. ቀደም ብዬም ለሌላ ጉዳይ ለንጽጽር ያቀረብኩት የአንድነቱ ልዑል የአባ አሉላ ነጋ ልጆች ዬህብረ ብሄር ፓርቲን ሊቀላቀሉ ሲመጡ ብርቅ – ሲሆኑ በተደጋጋሚ – አይቻለሁ። ይነጠፋል – ይጎዘጎዘል። ሚዲያው ሁሉ ውደሳውን ተቀብሎ – ያስተጋባል። ሥርጉተ ደግሞ – ትስቃለች። ስለምን? ይህ እኔ ለአንድነቱ ልዑል ለአሉላ አባ ነጋ ልጆች ክብር – ስለማይመስለኝ። ኢትዮጵያዊነትን ‚ሀ‘ ብሎ መጀመር ዓይነት ስለሚሆን ፊኖሚናላዊ አምክንዮው ድንብስ – ይሆንብኛል። እንደገናም ዬግንዛቤ ደረጃውም ቢሆን ልል ሰብዕናን – ይጋብዛል፤ ስለዚህ ሊቀበሉትም ሆነ ሊደሰቱበትም አይገባም – ባይ ነኝ። ስለዚህም አንቴናቸውን ወደ ቀደምቱ ቢያደርጉ ብዙ ነገር ያተርፋሉ – እላለሁ። ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነውና። ጣዕሙም – ለዛውም – ውበቱም – ልቅናውም ፍጹም ነው ኢትዮጵያዊነት! ኢትዮጵያ ሁሉንም ናት! ዛሬ ከእጃችን ወጥታለች …. ሁነን እንሁንላት!- ትግሉ ለዚህ መሆን አለበት። ከውስጣችን ይክፋን – ስለእሷ!
ስማንም አይነም ዕውነት አርበኞች አሏት፤ እውነት ገበሬዎች አሏት፤ እውነት ደጀን ናትና በእሷ መሪነት ፍልሚያው ይቀጥላል። ኑ እስኪለን ድረስ ለታሪክና ለትውልድ በሚበጅ መልኩ ታሪካችን አደራጅተን ማለፍ ግድ -ይላል። ኑ ወደ እውነት፤ በመጨረሻ – ዘመናይነቱ ሆነ መረማማጃው በቁስል ላይ ባይሆን መልካም ነው።
የኔዎቹ ለነበረን ሸበላ የመደማማጥ ጊዜ አከበርኳችሁ። መልካም ሰንበት! ቸር – ያሰማን።
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
ኑ ወደ እውነት!
የትግራይ ፋሽዝም ገለማኝ!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።