ከሥርጉተ ሥላሴ 04.08.2015 /ሲዊዘርላንድ ዙሪክ/
እኔ ሥርጉተ ሥላሴ የድምጻችን ይሰማ አባል ነኝ። „ድማፃችን ይሰማ!“
ጥያቄዎች ፍጹም ዬሰላማዊ መብት ጥያቄዎች ነበሩ። በምድር ሆኖ የማያውቅ የሰላማዊ ተጋድሎ ታሪክ ያሳዬው ብልሁና ሥልጡኑ „የድምጻችን ይሰማ“ የትግል ሂደት አብነት ነው።„መሪዎቻችን እኛ እንመርጥ መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ አይገባም።“ ነበረ። በዚህ አያያዝ ይህ ጥያቄ መቼውንም – አይፈታም። በዘመነ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ – ታሥሯል። ጀግኖቻችን ከ7 ዓመት እስከ 22 ዓመት ታሥረው እንኳን ቢፈቱ የከፈሉት መስዋዕትንት፤ የሞቱት፤ የተሰደዱት፤ የተደበደቡት ሁሉ ጥያቄያቸው ምላሽ የለውም። ይህ ነው እንግዲህ ፍርደ ገምድልነቱ – በዘረኝነት።
ሌላው ትልቁ ስላቅ ደግሞ እነሱን ተከትሎ ይህን ጥያቄ ዬሚያነሳ የሚጠብቅህ ይህ ነው በማለት ለመቀጣጫ የተወሰደ እርምጃ ነው።
ስለዚህ እጅናህ እግርህን አጣማረህ ዕምነትህን ሳይቀር ቀምቼህ ተንበርክከህ ተገዛ ነው። እዬዳህ ኑር። መሠረታዊው ጥያቄ እስከ 22 ዓመት ተፈርዶበታል፤ ከፍርዱ ከውሳኔው ተፈጻሚነት በኋላም ቢሆን ተቀብለህ ጸጥ እረጭ ብለህ መቀመጥ ነው ዕጣ ፈንታህ! ሌሎችም ጠብቁ ተራችሁን ነው። ትዕቢትም ነው።
ፍርዱ ለእስልማና ህገ – ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በአብሮነቱ ተምሳሌት የሆነው የ90 ሚሊዮንም የኢትዮጵያዊ ህዝብ ላይ የተፈረደ ነው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ዕድሜ መራዘም መሠረታዊ የቀጣይነት ባህሬ ከእኔ እስኪ ደርስ ድረስ ተመቻችቼ መጠበቄ ብቻ ነው። ዬወያኔ ሃርነት ትግሬ ማንፌስቶ ለማንም ለምንም የማይሆን ጠፍ ስለሆነ፤ ከሥሩ ለመንቀል መታገል ነው – አማራጩ። መስመሩ አንድ ብቻ ነው። ስለዚህ የትግሉ ስልት ወደ ዘላቂ እኩልነት ሊያመራ ወደሚችል የነፃነት መንፈስ ዝውውር ወይንም ሽግግር ማድረግ አለበት። ይህን መርኃችን እስካላደረግን ድረስ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በራሱ የትግሉን ሂደት ጠንከር ብሎ እንዲሄድ ጉልበት እዬሰጠው ነው። ሞት ሁልጊዜ አዲስ ነው ይባላል። ይህ መሰል ፍርደ ገምደልነት ሌሎች አርበኞቻችን – ያለፉበት ታሪክ ነው። እኛ ሁልጊዜ አዲስ እንሆናለን እንጂ ከመለሲዝም ፋሺዘም ብጣቂ በጎ ነገር መጠበቅ እራስን መርሳት ወይንም እንደ ሰው መፈጠርን መሸሸት ነው።
አቅልሙት በቃኝን – ይሁን መሻገሪያ።
የፍጥረት መገኛ – አንቺ የጥቁር መሬት፤ አፈርሽን ወድጂ፤ ወትትሽን ጠጥቼ – ጡትሽን ጠብቼ
አንዲህ ተገፍቼ እንዲህ ተገፍትሬ —————–ሰብዕና አጥቼ
እትብቴ መንደሬ አንች ነሽ – ባዕቴ
መራር ሆነብኝ ———————– ባይታዋርነቴ።
ገለማኝ – ገለማኝ – ሠራኝ እንደ ገና
ዜጋዋ መሆኔ እንዲህ – ተዘነጋ።
መከራዬ መራኝ —– ገነነ – ፍዳዬ
ተግባርን አዝርቼ ሰብሌንም – አምርቼ
ዕምነቴን ተቀማሁ ሰማሁኝ – ሰንብቼ።
የቋሳ ማምረቻ ጉትቻ ————- መሆኔ
ሱባኤ ላይ አለሁ ከሁሉ ————–መንኜ።
አለቀዘቀዘኝም ደልቶኛል – ኑሬዬ
ትውልድ ይዳኘው ዘንድ ይሄው ነው —–ፍሬዬ።
ወርቅነው ፍዳዬ ያባራል————–ዓርማዬ!
እኔን–ስ ፈርቶኛል – አንተ ምን ትላለህ?!
እኔነ —ስ ፈርቶኛል – አንችስ ምን ትያለሽ?!
መናቅ ኮሶ ሆኖሏ ሥሩለት —- መሻሪያ
አቅልሙት በቃኝን ይሁን ———-መሻገሪያ!
ሥጦታ – ለድምጻችን ይሰማ ጀግኖች። 04.08.2015 ሲዊዘርላንድ
አባቱ የእኔ ጀግና ናትናኤልሻ እሺ – እኔ ታዘዛዥህ ነኝ። በጹሑፎቼ ሁሉ መልእክትህን እለጥፋለሁ። በራዲዮ ፕሮግራሜም በድምጽ መልእክትህን ሙሉውን – አስተላልፋለሁ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45527
ቀደም ሲል በሠራሁት አጭር ፊልም አንተም ሆንክ አርበኞቻችን – አሉበት። እጅግ ቁልፍ ለሆኑ የሀገር መሪዎች ዓለምአቀፍ ዬሰብዕዊ መብት አስጠባቂ ድርጅቶች ከታህሳስ 10 2014 እስከ 2015 የካቲት 8 ድረስ ድረስ በተለያዬ ሁኔታዎች – ተልዕኳል። አይዛችሁ የእኛ አንበሶች። https://www.youtube.com/watch?v=FmeGfeOaM_I&list=PLBwFEncxyNfuRqJSALv9zTCXJTUf0nOHd
ድማጻችን ይሰማ!
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።