ሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገፆች እዬተናፈሰ ያለውን ወሬ ለጎልጉል እንዲሁም ለዘ ሃበሻ ኔት የተሳሳተ መረጃ ያቀበሉት ኢንጅነሩ ቢሆኑም እንደ ሚዲያ መጀመሪያ ፅሁፉን ከመለጠፍ በፊት ይመለከተዋል የተባለውን አካል አነጋግሮ እውነታውን ማጣራት ተገቢ ነበር:: ሆኖም ያሳሆን በችኮላም ይሁን በግድዬለሽነት ፅሁፉ ተለጥፎ በአንዳንድ ሙስሊም ወገኖች ዘንድ ብዥታን የፈጠረ ሲሆን እውነታው ግን ከዚህ በፍፁም የተለዬ መሆኑ ለኢንጅነሩ ምናልባት ያልተረዱት እውነታ ወይም ግላዊ ጥላቻ ካላቸው ስለ «ፅናት» የማውቀውን እውነታ ለማቅረብ እሞክራለሁ።
ፅናት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማህበር በሂጅራ አቆጣጠር 16/3/1435 የዛሬ አመት ከመንፈቅ አካባቢ የተመሰረተ ሲሆን
መስራቾቹም በሃገራችን ሙስሊሞችላይ መንግስት እዬወሰደ ካለው መራር ግፍና መከራ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የሆኑ በሃገራቸው በተለያዩ የዲን ዘርፍ አንቱታን ያተረፉ የብዙሃን ሂወቶችን ወደቀጥተኛው ጎዳና ወደ ኢስላም በአላህ ፈቃድ የለወጡ ታላላቅ ኡለማዎች ናቸው እንግዲህ እንደ ኢንጅነሩ ሃሳብ እነዚህ በችግሩ ምክንያት በሃገራቸው መብታቸው ተነፍጎ መኖር ስላልቻሉ ከሚወዱት ህዝብና ቤተሰቦቻቸው ተለይተው በተለያዩ ሃገራቶች በስደት የሚኖሩ ኡለማዎችን ከበሬ ወለደ ግላዊ ጥላቻቸው በመነሳት ቀጥታ ከህዋሃት ስውር ሴራ ጋር እነሱን ማያያዛቸውና መፈረጃቸው ምናልባት እንደሙስሊምነታችን እንድ ነገር ወደኛ በመጣ ጊዜ የነገሩን እውነታ ሳናጣራ በስሜት ተነሳስቶ መፈረጁ የታላቁን ቁርአን ህግ በመጣስ በሰዎቹ ላይ የውሸት ውንጀላ ማቅረቡ ከባድ ስህተት መሆኑን ቢረዱት መልካም ነው ።
እንግዲህ እነዚህ ብርቅዬ ኡለማዎቻችን ከሃገር ተሰደውም ቢሆን በሃገራቸው ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ ስለሚያሳስባቸውና ስለሚያስጨንቃቸው «ፅናትን»ለመመስረት በቁ አላማቸውም እንደ ማለዳ ጮራ ፍንትው ያለ ምንም ብዥታ የሌለበት ነው ይኼውም በኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል በሁለንተናዊ መልኩ ችግሩን መካፈል ማለትም በዚህ ችግር ሳቢያ የተዘጉ መድረሳዎችን አገልግሎት እንዲሰጡ የተለያዩ ኡለማዎችን የወር ደመዛቸውን በመክፈል በተለይም ታዳጊ ህፃናት የቁርአንን ብርሃን አግኝተው እነሱም ያንፀባርቁ ዘንድ እስካሁን ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች ይህ ነው የማይባል ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ
በተጨማሪም በትግሉ ምክንያት በተለያዬ ምክንያተ ችግር ላይ የወደቁ ወንድሞችን እና እህቶችን በተለይም የጠበቃ መክፈል ሳይችሉ ቀርተው በሃገራችን የነገሰው የፍርድ ድርቅ ምንም እንኳን ተስፋ አስቆራጭና «ከዝንብ ማር» የማይጠበቅ ቢሆንም ለነዚህ በተለያዩ ሃገራት እስርቤት ለሚሰቃዩ ታጋዮች የጠበቃ እና የቤተሰቦቻቸውን በመሸፈን የተለያዩ እገዛዎችን እያደረጉ ይገኛሉ ።
ሌላው ኢንጅነሩ የተሳሳቱት መረጃ ቢኖር እንዳሳቸው አባባል «በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ሴት እህቶቻችንን በማሳሳት ገቢያቸውን ያደልባሉ» ኢንጅነር ሆይ እንደርሰዎ ጭፍን ጥላቻ ሳይሆን የፅናት የገቢ ምንጭ ከመላው አለም የሚገኙትን ከማህበሩ አባላት ከወንዱም ከሴቶች እህቶቻችንንም በየወሩ ከሚሰበሰብ አነስተኛ የአባላት መዋጮና እንደዬ አባሉ በጎ ፍቃድ በሚነዬቱ (በሚለገሱ) ገቢዎች ከላይ የጠቀስኳቸወወን እና ሌሎች መሰል በጎ ተግባራቶችን በመስራት ትግሉን በሚችሉት መልኩ እዬደገፉ ይገኛሉ ።
ኢንጅነሩ ከመረጃ የራቁና ስለፅናት ያላቸውን ጥላቻ ያሳዩበት ሌላው ስህተት ደግሞ በውድና ጀግና ኮሚቴዎቻችን የተፃፉ መፅሃፎችን ማለትም የኡስታዝ ያሲን ኑሩን «ግብህን ቅረፅ »እና የታሪክ ሙሁሩን አህመዲን ጀበል«ፈርኦን የአምባገነኖች ተምሳሌት» የተሰኙትን መፅሃፍ በማሳተም ገቢውን ወደኪሳቸው አስገብተዋል ሲሉ ምንም መሰረት የሌለው ካባድ ስህተት ተስተው አሳስተዋል እውነታው ግን «ፅናት የሙስሊሞች ማህበር» ከ«ድምፃችን ይሰማ» ጋር በመተባበር «ድምፃችን ይሰማ በሳውዲ አረቢያ» ያሳተማቸውን መፅሃፎች የታሪክ ሙሁሩ አህመዲን ጀበል «ኒፋቅና የሙናፊቆች ማንነት ሲጋለጥ» እንዲሁም «በድምፃችን ይሰማ»የተዘጋጀውን «የተዘነበለ ፍትህ» የተሰኙትን መፅሃፍት ከምርቃቱ ጀምሮ መፅሃፍቶቹን ለአባላቱ በማስተዋወቅ እና በማሻሻጥ እንዲሁም «ድምፃችን ይሰማ በሳውዲ አረቢያ»በሚያወጣቸው የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ በመገኘት አጋርነቱን በተግባር ቢያረጋግጥም ኢንጅነሩ ግን መሰረት የሌለው የሐሰት ውንጀላቸውን ጭራሽ ይባስ ብለው «ድምፃችን ይሰማ በሳውዲ አረቢያን» ለመንግስት ለማጋለጥ ሲሰሩ ነበር ሲሉ ኮንነዋል። «ፅናት»በመነጋገር በመወያዬት ክፍተት ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮችን በመተው በአንድነትና በወንድማማችነት በጋራ ወደምንጓጓለት የድል ምእራፍ ተሸጋግሮ ህዝበ ሙስሊሙ በሰላም በገዛ ሃገሩ በነፃነት እምነቱን ይተገብር ዘንድ ለሚተላለፉት የሰላማዊ ትግል ስልቶች ግንባ ቀደም ተሰላፊ በመሆን
«ከድምፃችን ይሰማ በሳውዲ አረቢያ»ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከሩን ያሳያል።
እንግዲህ ኢንጅነሩ ከላይ የጠቀሱዋቸውን መፅሃፍት በፅናት ታትመል ሲሉ ነጭ ውሸትን ዋሽተዋል
ሌላውና ትልቁ ጉዳይ« ፅናት» «በድምፃችን ይሰማ » አመራር ላይ እንቅፋት ፈጥረዋል ብለው የወነጀሉት ሲሆን« ፅናት የሙስሊሞች ማህበር»እንደ ዋና ተግባር ከያዛቸው ስራዎቹ አንዱ ለድምፃችን ይሰማ ታዛዥ መሆኑን እና በሚወጡ የትግል መርሃዊ ግብሮችላይ በንቃት በመሳተፍ መተግበር መሆኑ እስካሁን ድረስ እያረጋገጠው ያለ እውነታ ነው ።
በመጨረሻም በተደጋጋሚ ብዙ የዋትሳፕ ግሩፖችን ከፍተው ሙስሊሙን ይበዘብዛሉ እያሉ ኢንጅነሩ ሲወቅሱ ነበር እውነታውግን በተለያዩ የዋትሳፕ ግሩፖች የተሰባሰቡ አባላቶችን በተለያዩ የማህበሩ መስራች ኡለማዎች አማካኝነት የአባላትን እውቀት ከፍ ሊያደርግ የሚችሉ የዲን ትምህርቶችን ማለትም
ተውሂድ
ፊቂህ
ተፍሲር
ሲራ
ብሉግ እና ሌሎችም መሰል የዲን ትምህርቶቹን በቀላሉ ለሙስሊሙ ኡማና ለአባላቶቹ በዋትስአፕ በማዳረስ ከማያልቀው የእውቀት ማእድ በማቋደስ ትውልድን በመነፅ ላይ ይገኛል ።
እንግዲህ ውድ አንባቢያን ስለፅናት የማውቀው ትክክለኛ እውነታ ይሄ ነው ምናልባት ኢንጅነሩ ደርሷቸው እውነታውን ሲረዱ የማስተካከያ ፅሁፍ እንደሚሰጡን ተስፋ አደርጋለሁ
ድል ፍትህ ለተጠማው ኡማ !!!