07.08.2015 /ሲወዘርላንድ – ዙሪክ/
ከዚህ በኋላ ሌላ የነፃነት መንፈስ እረኛ እኔ አልጠብቅም። የኢትዮጵያዊነትን መዳኛ ዘመንና አምላኬ ሰጥተውኛል እና። ልዕልት ሐገሬ ሰው አላት! ሐገሬ ንግሥት ኢትዮጵያ ሁነኛ አላት! አዎን! እንደ ሰማነው እነሆ አዬነ – ኢትዮጵያችን ጀግና አላት!
ምዕርፍ አንድ ….
እንዴት አላችሁልኝ – የሐገሬ ልጆች?! የጦፈ የሳይበር ጦርነት – ያስነሳል። እፈቅደዋለሁ። ቀልድ ዳር ደንበር ሊኖረው – ይገባል። እኔ ሥርጉተ እንደ አንድ ዜጋ ትርምስና ቧልት አሽኮኮ ተደርጎ ብሄራዊ ዬነፃነት ምኞቴ ዬሙት መሬት ብትን አፈር ለማኝ እንዲሆን – አልሻም። እሱንማ 24 ዓመት ተኖረበት ለ547 መቀመጫ በዬ 5 ዓመቱ ወንበር አምስት ተመራጮቻች ቢይዙት በስንተኛው ዙር ምርጫ ነው 547 ሙሉውን ወንበር ዬሚይዘው? ስንት የዙር ምርጫ – ያስፈልገናል? የፋሽስቱን ማንፌስቶ ለመርታት። ዬቅልሞሽ ጨዋታ ነው። አስቡ ወገኖቼ የወያኔ ሃርነት የምርጫ ዙር እስካሁን 5 ዙር ተጉዟል። የፋዳሰው ቅል ዕሳቤ ደግሞ በዜሮ ተበዛቶና ተካፍሎ ዜሮ ሁኖ ሲንከባለል በትዕቢተኛው ወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ – አይተናል። የዚህ ሃሳብ ተሸካሚ አደንዛዢ ዕጽ እንኳንስ እግረ ተከል ሊሆን ሲድህ እንኳን – አላዬነም። ስለዚህ እንዲህ ያሉ የተጋጋጡ አድራሻ ቢስ መሃን ዕይታዎች መልክ መያዝ አለባቸው። ህሊናን – በተከታታይነት እናደራጅ፤ የምናደራጀውን ሥነ ልቦና ህሊና በሠራነው መጠን ልክ በእጃችን – እናስገባ። በዬአምስት ዓመቱ ና ውረድ – ተሰቀል እያልን ከምናጣውር ……
የሆነ ሆኖ ሐገራችን ኢትዮጵያ አቅም ሊመራት በሚችል መልኩ አዲስ ሥርዓት አንዲኖራት መስምሩ ጉልበቱ ሊደፈርና ሊገሰስ የማይችል መንፈስና ክህሎትን – ይጠይቃል። ከእንግዲህ አሳምነኝ ወይንም ተከራከረኝ በማለት /debate or dialogue-/ የምናሽሞነምንበት ምንም ስውር ሽጉጥ አጀንዳ ሊኖር – አይገባም። በግራ ቀኙን አንደምታዘበው ፍሬ ነገሩ የሃሳብ ልዩነት – ሆኖ አላገኘሁትም። በፍጹም። ቁልጭ ብሎ – ወጥቷል። „አናሳው ብሄረሰብ ጉራጌ አይመራንም ነው“ አቅም ከኖራችሁ ማን ከለከላችሁ? የኢህአፓ ቁልፍ መሬዎችስ የላይኛው ዬመዋቅሩ ዘዋሪዎች ለመሆኑ ዬዬትኛው ብሄረሰብ ቤተኛ ናቸው? አንብቡ። አሁን ታዲያ ለምን ጭንቅ ዋጣችሁ?! ያነሰ አቅም ሲወጣ ጭጭ – ረጭ – ብላችሁ አደብ ትገዛላችሁ። ምክንያቱም ከታቻችን ነው የትም አይሄድም – ስለምትሉ። እንዲህ ማማ ላይ ያለ የማትደርሱበት ክህሎት ሲሆን ደግሞ እንደ ጦር ስለምትፈሩት – ዳንኪራ! የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጀግና አርበኛ አንዳርጋቸው አግዶ ከእጁ ለማስገባት ያወጣው መዋለ ንዋይ ስንት ሀገር ጠቀም ነገር በገነባ? ህግም – አውጥቷል? በሽብርተኛም – ፈርጇል። ያውቃላ … ሊፈነግለው የሚችለው ከእሱ የባህር ወለል በላይ የሆነውን ብቃት – መሆኑን። ስለሆነም ከወያኔ ሃርነት ትግራይ የጫካ ሥነ ልቦናዊ ተመክሮ እንኳን መድረስ አልቻላችሁም – እናንተው። ከእንግዲህ የቁርሾ ድሪቶ ሳይሆን የሥርዬት መሳላልና አቅም ነው ሀገረ ኢትዮጵያን እንዲመራት – የምንፈልገው። በቃን! ህወሓትን ብቻ ሳይሆን እናንተንም መጎብኘት አለበት። ከተንጠላጠላችሁበት የምናዕብ ዓለምም ሊያወርዳችሁ – ይገባል።
የሆነ ሆኖ ተሰቅዞ ያለው ህውከታዊ መንፈስ ዬኢትዮጵያዊነታችን የማንነታችን ቀለማም ገጸ ባህሪ ንጥረ – ክህሎትን አብዝቶ የሚፈታተን ዬጫጫታ አጀንዳን በመሆኑ፤ እኛው የብሄራዊ ነፃነት ራህብተኞች መቀማት አለብን /በተለይም ወጣቶች ለዚህ እባካችሁ ትጉ/ ይህ የሚሆነው ደግሞ ዬተጠቀለለበትን ሽፋን ዕንብርት ተጭነን ስናስተነፍሰው ብቻ ይሆናል።
ሌላው በጉሻማ ቀውላላ መንፈሶች፤ ብቅ ጥልቅ እያሉ ሲያውኩ የኖሩት ዕሳቤዎች፤ ወይንም ሃሳቦች – ጠቅለል ብለው – ለይቶላቸዋል። የሳጅን አይጋ ፎረም ቤተኛ ብቻም ሳይሆኑ ባለ አልጋም – ሆነዋል። ግን አልጋው የረገበ በመሆኑ አከርካሪን – ያነኩታል። እሱ በኪነ – ጥበቡ መንገዱ ስላጸዳልን አምላካችን – እናመሰግናለን። ስለለዚህም የተለመደው የተለጠፈ የማስታዋቂያ /poster/ ዬትግል አቅጣጫው ሆነ፤ የቅራኔውን መሥመር ሁለት ብቻ – እንዲሆን አድርጎልናል። ተመስገን! ሾላኪው ይንጠባጠባል ብሩኹ ሞገዱ ደግሞ በሙሉ ብቃት – ይራመዳል። ሃሳብን – መንፈስን – ፍላጎትን – ራዕይን ሰብሳቢ ባለቤት አግኝቷል፤ መሪ አለው።
አሁን ያሉት ሁለት ብቻ ናቸው። አንዱ መስምር ጉልበታሙን ወያኔ ሃርነት ትግራይን በሁሉም መስክ ፊት ለፈትም አስጨንቆ እንዲሁም ክብሩንም ነቅሎ ማስወገድ ሲሆን፤ ሌላው ሞለጭላጫ ላንቁሶ ሃሳብ ደግሞ የጉቶው ዬወያኔ ሃርነት ዕድሜ ለማኝ ቀጠና እድፍ ጥራዝ – ነው። ሃቁ ይህ ነው – እንድፈረው። ሐረጉም መስምሩም ግልጽ ነው። ታምቆ በቁስል የተከዘነው ሃሳብ ከሽፋኑ ወጥቶ ቁልጭ ብሎ ሽሉ የአደባባይ ሲሳይ – ሆኗል።
በሌላ በኩልም ቀደም ሲል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በትናንሽ ጎጆዎች ሥም፤ በሲቢክስ ድርጅቶች ሥም ተጥልለው የነበሩት የአንባጓሮ ሃሳቦች ሲፈተሹ፤ የተከበሩ ዬኢንጂኔር ኃይሉ ሻውል ቅይጥ ዕምቅ ፍላጎትን ያዘሉ የትርምስ ግንባሮች ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። ከአምስት ወይንም ከስድስት ዓመት በፊት በተለያዬ ሁኔታ የተሰጡ ቃለ-ምልልሶችን በምልሰት ቃኘት – አድርጓቸው። እያዬን ያለነው የሃቁ ኣናት ዘሩ ሆነ ፍሬ ነገሩ ይኽው ብቻ ነው። ድሮም የቅንጅት ራዕይ ለዛ መራራ ስንበት የተዳረገው ዛሬ ላይ ሆኖ በፖለቲካ ትንታና ስንመነዝረው አማሽ ቅርንጫፎችን ሆኑ ጅረቶቹ ሁሉ ምልከታቸው ይሄው መሆኑን ነው የሴራቸው መልእክቶች – የሚያውጁት። የትግላችን ማጥና ድጥ መሠረቱ ይሄው ብቻ ነው። ወዲህና ወዲያ ቢቅዘመዘም መሥፈሪያው ሆነ ማዕከላዊ አጀንዳው ያ ገናና የሁሉም የሆነው ተፈሪው ኢትዮጵያዊነት – አይደለም። የብሄራዊ ዬነፃነት ራህብም አይደለም። እናት ሐገራችን ኢትዮጵያን ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ወራሪ ማዳንም አይደለም። የነበረው የምኞት መቃብር ብቻ ነው። አ – ን – ሸ – ን – ግ – ለ- ው። ይህ የስለላ መረብ ዬዜጎችን ሰብዕዊ መብት ካለርህራሄ የሚቆርጥ – ማጭድ ነው። በዛች ምድር አንዱ ጭንቅላት ሌላው እግር ሊሆን – አይገባም። አንዱ እጬጌ ሌላው ሎሌ – ሊሆን አይገባም። አንዱ ባለቤት ሌላው ባይታዋር መሆንም – የለበትም። የልዕልት ኢትዮጵያ ልጆች ሁሎችም ለባዕታቸው እጬጌዎቿና ጀግኖቿ የማህጸኗ ዓውድ ፍሬ ዘሮች ናቸው። እኩል! በተለዬ ቤት የተለዬ ልጅነት የለም። ቤቷን ያነጹት ሁሉችም ናቸው። የታሪክ ልጅና እንጀራ ልጅም የለም። ቅልቅል ሳንሆን ውህድ ነን። ውበት የሚባለው ለላንቲካ መሆን – አይገባውም። ተግባር ላይ ወገቤን – አትበሉ።
እርግጥ ቀደም ባለው ጊዜ ቅኖች በዛ ወጀባዊ ቅንቅን በላሽ መሥመር በወቅቱ አልነበሩም ማለት – አይቻልም – ዛሬም። ወገኖቻችን ያን ጊዜም የቅንጅት ዓላማን ነበር የተጠጉት፤ ዛሬም ከእውነት ጋር ይሆናሉ ብዬ – አስባለሁ። ቅኖችን የሚመራቸው ነገድ ሳይሆን የሃቅ አውደ ምህረት ብቻ ነውና። ስለዚህም ሊመሰገኑ ይገባል እንጂ ያን ጊዜ እንዲህ፤ ዛሬ እንዲህ ተብለው ሊወቀሱ ከቶውንም – አይገባም። አስቀድመው ዬአቅጣጫውን ሰባራነት ያዩትም ቢሆኑ ስለምን እንደ እኔ አላያችሁም ብለው ሊወቅሷቸው – አይገባም። የአቅማችን መቅኖ የሁሉንም ድርሻ እንደ ችሎታው – ይሻል። በነፃነት መንፈስ ሥር የነበሩትን ሁሉ መፈተሽና ማዬት መብትም – ነበር። ቅብ የነበሩ መሆናቸውን ያጋለጠው ዘመንና – ተግባር ነው። አካሄድን ከሥሩ ነው መፈተሽ የሚገባው። ከመሠረቱ የተነቀለ ጥውልግ ነበር። ጥንዝል – አያቆጠቁጥም። አይለመልም – አያድግም — ድንክ አንደሆነ ተፈጥሮው ግብዕተ መሬት።
ከዚህ ጋር አብክሬ ዬማስገነዝበው ቁም ነገር ግን የተጓዝንበት ተመክሮ እንክርዳድና ስንዴን የመለዬት አቅሙ ብቁ እንዲሆን ከማድረጉ ላይ መበርታት – ይኖርብናል። የተምክሮውን ዕድሜ ጠገብ ሂደት መምህር ምርት በመሆኑ ፍስ፣ ልዝ፣ ፍዝና ቦዝ አናድርግው። የህሊናችን የነቃው ክፍል አልሚ ምግብ አንዲሆን – እንፍቅደለት። ይህን ስናደርግ የፈለገው ዓይነት ወጀብ ዝር አይልም። ስለሆነም ለጅባማ ገዳዳ ስሜት ተጨማሪ ጊዜ ከእንግዲህ ማቃጠል – አያስፈልግም። ተጨማሪ አቅም በፍጹም ሁኔታ ማባከን አይገባም። ጊዜና ብልህ ተመክሮ ሰባኪያችን፤ ሐዋርያችን እንዲሆን ልንፈቅድለት – ይገባል።
አሁንም በወጀቡ ሊጠፉ የተቃርቡ ቅን ወገኖች አሉና በፍቅርና በትህትና አያያዝ ወደ እኛ እንዲመጡ ጥረቱን በባለቤትነት መውስድ – ይገባል። ትውልዳዊ ድርሻችን ለመወጣት – እንወስን። መወሰንና መቁረጥ ነው ለቀጣይ እርምጃ – የሚያዘጋጀው፤ ዜግነት መሥፈሪያው ዜግነት ብቻ ነው እንጂ ቤተ – ነገዱ አይደለም። የቤተ – ነገዱ ማንነት መነሻውም መድረሻውም የእሱን ወርቅ ዘለቅ ሥነ – ተፈጥሮውን የሚገልጸው የዜግነቱ ቅንብረ ጭማቂ በረከት ብቻ ነው። ሃይማኖትህን፤ ሙያህን፤ መክሊትህን፤ ፍላጎትህን፤ ፈጠራህን፤ ህልምህን ማሳካት የምትችልበት ማህጸኑ በዜግነት የእኩልነት ምኽዋር ብቻ ነው። ህዋስ ነው ዜግነት ለደማሙ ማንነት። የዜግነት መግለጫዎች የዳር – የጫፍ ወይንም ጠርዝ ወይንም ወገብ አይደለም። ድንበር አልባ ወሰን የለሽ በውስጥነት የሚስጢር ቅኔ የሚቀዳበት ነው። ሙሉ ሰብዕናን ለመውለድ ከመንፈሳችን ጋር እንታረቅ።
አሁን እያዬኋቸው ያሉት መቧደን ኋላቀርነት ብቻም ሳይሆን የአስተሳሰብ ድህነት ነው። ለነገሩ ገና ናቸው። ከአንዲት ነቁጣዊ ደብር ከደንበጫ ወይንም ከ20 ጋሻ ክልል ተነስተው ግሎባል ጭብጦችን ወደ እራሳቸው በማስጠጋት እራስን ማስማማት ወይንም ማንነትን መተርጎም የሚያስችል የሚመጥን አቅም ለመገንባት – አይችሉም። ከዬት መጥቶ? ችግሩ ይህ ነው። እሰቡት ከዛች የገጠር ትንሽዬ ቁጥቋጦ መንደር – አሜሪካ ወይንም አውሮፓ። ኢትዮጵያን ቀርቶ ዬጎንደር ከተማን ክ/ሐገሯን – በቅጡ ውስጧን ጸጋዋን ክብረቷን – አያውቋትም። ለዚህም ነው ሁልጊዜ ተሸከሙን በማለት ጫን ጫን እዬተነፈሱ ዬዝክንትል ጭነቶች የሚሆኑት። ዛሬ ዓለም ለሰው ልጆች ሁልአቀፍ መብት globalisation ላይ ነው ያለው። አነሱ ጥብቆ ውስጥ ሆነው ብሄራዊ የነፃነት ትግሉ በጭቃ ሹም ይመራ – ይሉናል። አፍሪካዊነትማ pan africanism – ትንፋሹ እንኳን አያወቃቸውም – እንኳንስ ቅርሱ።
የጃርት ጉባኤ ርደት።
ባድማ በጃራት ተሰቅዛ …
በአረማሞ አራሙቻ ናውዛ።
እህህን ሰንቃ ደንዝዛ …
ሰቀቀን ታጥቃ አርግዛ።
በ‘ሬት ጨጎጎት ተደልዛ …
ቁም ስቅሏን አዬች
ይሄው በልዛ።
ይህ ሥነ ግጥም ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ማኒፌስቶ ላደረሰው ብሄራዊ ድቀት – በደል – መታበይ ብቻ አለነበረም – የጻፍኩት። ለዛሬም ሆነ ለወደፊት አካለ ጎደሎና ጠናና ለሆኑ፤ ለሚሆኑ አስተሳቦችም ጭምር ነበር። የኔዎቹ – እርአሱን ለጉጉል አጉርሱትና ሙሉውን – ይሰጣችኋል።
የሆነ ሆኖ ቤዛ በወጣትነቱ ያደገበት ቀዬ ዬበሞቴ አፈር ስሆን ልባዊ ናሙና የሆነው ጎንደር አሁንም እልል ብሎ – ይቀበለዋል። በጣም በእርግጠኝነት። ራስን መስጠት የፍቅሮች ሁሉ ጉልላት – ጉልትም መሆኑን ብልሁ ሕዝብ አሳምሮ – ይረዳል። „እኔ ለመሰዋት ልቅደምላችሁ፤ እኔ ልሙትላችሁ፤ ብቻችሁን አይደላችሁም፤ እኔ አልሁላችሁ“ ብሎ ነው የአፍላ የልጅነት ጊዜውን ባሳለፈበትና ባደገበት በዛ የህይወት ፈታናዎች ሁሉ በከተሙበት ቦታ የአርማጭሆ በርሃ እንደገና ተመልሶ ዱር ገደል ለዛውም በዚህ በማረፊያ ዕድሜው ክልትምትም ሊል የቆረጠው፤ ይህ የኢትዮጵያ ሳህሊ የቁርጥ ቀን ልጅ፤ ዳግሚያ ቴወድሮስ ነው ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ። የጥቃት ማርከሻ! ዬውሳኔወቹ መጻዒ ዕድል የተወሳሰቡ ክስተቶች ሁሉ እሱን እራሱን ሊያሳጣ የሚያስችል የገጠመኝ አጋጣሚዎችን፤ የመስዋዕትነት ረቂቅ ህዋስ አደገኝነት ያላቸው ቢሆኑም፤ ሥህነ – ቤዛ ግን ሁለቀፍ ስጋትን ድል ነስቶ ከወገኖቹ ጋር ለመከራ ሲል በግንባር – በልጦ ተገኘ። ለሞት ፊት ላይ ተገኘ፤ የግንባር ሥጋነት የሐቅ አርበኝነት ነው። „እኔ ልሙትላችሁ፤ እኔ ልቅለጥላችሁ“ ማለት ከዚህ በላይ ውሳኔ፤ ከዚህስ በላይስ የመሆን ገናና ልዕልና – ቀንዲልነት ምን ያስፈልግ ይሆን? ይህ ሥህነ – ቤዛን ሊያስከብረው ይገባል እንጂ ከቶውንም ሊያስወቅሰው – አይገባም። እውነት ለመናገር አ -ት – መ – ጥ – ኑ -ት – ም። ከእሱ ለመድረስ አንደ እሱ መሆንን – ይጠይቃል። መሬት ላይ በፈለጋችሁት አኳኋን ተገኙና – እንያችሁ። ህዝብን አሰባስቦ ለግዳጅ ለማሰማራት mobilize ለማድረግ ያችን ምድር ደፍሮ – መርገጥን ይጠይቃል። በአንቀልባ – አይሆንም። የሰው ልጅ ለሚያው ዕውነት ታማኝ መሆን አለበት። የተመለከትነውን መመስከር አለብን። በስተቀር በቁማችን የጉም ሽንት ሆነናል።
ሳይማገዱ ቁብ የለም – ከእንግዲህ። እኩልነት የቃላት ድርድር ካብም አይደለም። የድርጊት እጬጌነት እንጂ። መብለጥ በመፈክር አይደለም በተግባር ጌትነት ጌጥነት እንጂ። መቼ ነው አናንተ ከሶፋችሁ ብድግ ብላችሁ አለንላችሁ ብላችሁ በተግባር የደረሳችሁለት – እንደዛ በሱዳን ጦርና በወያኔ ጦር ተሰቅዞ ሲያልቅ የጎንደር ህዝብ ዬሄዳችሁለት? እናንተም ተራ ይድረሳችሁ ተጠዬቁ? መቼ ነው ለፍላጎት ከራቀው መስመራችሁ remote control ጋር የምትፋቱት? መቼ ነው ጉልቻውን አፍራርሳችሁ መሬት ላይ የምትገኙት?!
ሥህነ – ቤዛችን – ለእኛ ዬቅኔ መጸሐፋችን – ነው። ቅኔ ወደሚቀዳበት ወደ አሳደገው የተጋድሎ ዬትግል ሜዳ ነው ዬሄደው። ሚስጢር ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ። ዬሁሉንም ልብ በድርጊቱ – አሸንፏል። ተቀድማችኋል። ዛሬ ጀግና አንዳርጋቸው ታሰረ አይልም – ያ ድርጁ መንፈሱ። መምህር በመሆኑ፣ መምህርነት ደግሞ የትውልድ አባትነት ስለሆነ ነው ዛሬ ካለወትሮዬ በቅርበት „አንተ“ ማለትን የመረጥኩት። ይቅርታ መጠዬቅ ካለብኝ ይቅርታ – እጠይቃለሁ – እኔ የአብነት ተማሪው። አንጀቴ ነው የተንሰፈሰፈው እነዛን አርበኞች እቅፍ አድርጎ ሞታቸውን ለመጋራት እንደዛ የጎለጎታን ቃል ኪዳን የፍቅር ቀለበት ሲያስርላቸው በዕውን ስመለከት። ዬእውነተኛ ታሪክ ዘሩ – ግንዱ – ቅርንጫፉ – ፍሬው – ሰብሎ አዬነው – አስተዋልነው – ከልብ ሆነንም – አዳመጥነው። ይህ ልብ ወለድ ወይንም በምናዕብ ላይ ብቻ የተኮፈሰ ተረተረት fiction or fantasy። አይደለም። ተግባር የደፈረው የነጠረ የዕንቁ ጭማቂ – የመሆን መቻል ልቅና ድህነት እንጂ።
እነሆ ዛሬ – ከበለጸገ በተግባር ከዳጎሰ የታሪክ ምዕራፍ ላይ – እንገኛለን። ሁኔታውን ሁሉ ሳስበው ከዕምሮዬ ውስጥ ሊወጣ አልቻለም። ተደላድሎ – ተቀመጠ። ይህን የዕውነት ማህለቅ ማንም እና ምንም ሊዘርፈው ከቶ – አይችልም። ታ – ት – ሟ – ል! እንዲህ በቀላል ግጥምጥሞሽ ሆነ ገጭ ገው የነጋውን ብርሃን ቅዱስ መንፈስ ከውስጥ ማውጣት – አይቻልም። በሚታይ በሚጨበጥ ማገዶነት ብቻ ከሥህነ – ቤዛ ጋር እኩል መሆን ይቻላል። ሥህነ – ቤዛ የሰጠን የነጠረ ቅዱሱን ፍቅርን ነው፤ — ሳይሳሳ በልግሥና ፍቅርን አስጊጦ – ሸለመን! ተስፋን – አጣፍጦ አጎረሰን። ከራዕያችን ጋር እንሆን ዘንድም – በመስተፋቅር – አዋደደን።
እኛስ እኮ! እኛስ – አቅም አለን?! እሱ ከሰጠን አቻ ቀርቶ ብጣቂ ብናኝ ነገር ቀረብ የሚል ፍቅርን ለመስጠት? እሱ ከሰጠን የማይጠገብ ቅዱስ ፍቅር ጎን መቀመጥ የሚችል በውስጣችን ብናኝ ፍቅር አለን? በአጠገቡ ለመቀመጥ አቅም ያለው ብጣቂ የፍቅር ሥነ – ምግባር አለን?! ሌላው ይቅር ፍቅራዊ ድርሻን ለማበርከት ሙሉ አቅም – አለን?! እ -ና – መ – ስ – ግ -ን – ሃ – አ – ለ -ን ለማለት፤ እግዚአብሄር ይስጥልን ለማለት፤ ኑርልን ለማለት፤ ሁል ጊዜ አቅምን ሸሽተን አቅምን ፈርተን ጎብጦ መኖር። „ፈራን ፍቅር ፈራን፤ ልጅነት የለገሰንን የፍቅር አምላክ የሰጠን፤ ፈራን ፍቅር ፈራን“ ይህ የቅኔው ልዑል የብላቴ ጌታ ሎርዬት ጸጋዬ ገ/መድህን ትንቢት በእናንተ ላይ ይፈጸም ዘንድ ነው – ቅኝቱ።
ከሰውነት ደራጃ ሳንወርድ እኔ – አንተ – አንቺ – እርስዎ – እኛ ያለደረግነውን ለሚያደርግ፤ ለቃሉ ለሚገኝ፤ ስለቃሉ ለሆነ ቢያንስ ክብር ሊኖረን ይገባል። እኔም እኮ ሞቼ – ደምቼ – ቆስዬ – ነው ነፃነቴን ማግኘት ያለብኝ። መቆስቆሻ – ሳልፈልግ ወይንም ማገዶ ሳልመኝ። ታዲያ እኔ ተቀምጬ አሥራትና በኲራት ልሁንልሽ ሲለኝ አንዴትስ ልዩዬ እንዴትስ የእኔ እንዴትስ ግርማዬ እንዴትስ ሞገሴ እንዴትስ ክብሬ ማለት ይሳነኛል? እኮ እንዴት? የነቀዞች – ዝንጠላው በዛ – ገለማም። በእግዚአብሄር ፊትም ያስጠይቃል? ወመኔ ጠላት አለን አቅም ካላችሁ መሬት ላይ ወርዳችሁ ለነፃነት ትግሉ ድርና ማግ ሁኑ። በስተቀር የተግባርን ዓይን ለማጥፋት የምትሰነዝሩትን ጦር ወደ አፎቱ መልሱት። የነፈሰበት ነውና። ህሊናችሁን ለባንዳነት – አትሽጡት። በተመሳሳይ መለከት አታናፉ።በጥልቀትና በጥናት የበሰለው የነፃነት ትግሉ አርበኛ መንፈስን – አትወኩ። ሥህነ – ቤዛ ለሽርሽር – ለጉብኝት – ለጫጉላ ጊዜ ማሳለፊያ – አይደለም በርሃ – የገባው። ስለ እኛ ብሎ ነው። እሱማ ምን አጥቶ? ምን ጎድሎበት? ነፍሱንም ሥጋውንም የሰጠው ለታሪካዊት ኢትዮጵያና ለጉስቁሉ ህዝቧ ነው። የዕንባ ባለደራ ነው – የተመረጠ። ያባከነው ጊዜ በሕይወቱም – የለም።
ይህም መወቀሻ ሆነ። አዬ! አለመታደል። አዝናለሁ የዚህ ውለታ ቢስ ዘመን ታዳሚ – በመሆኔ። ደግሞስ ከዚህ በላይ ባለውለታነት ምን አለና?! የቀደምቶቹ ገድላማ ታሪካችን መኩሪያችን ብለን የምንኮፈስበት ፍታውራሪ ከትናንት ወዲያ እኮ ያለፈው እንዲህ በተግባር ሃዲድ ነበር። በአመራር እጦት ሲጠቃ መስዋዕትነቱ ዕሴት አልቦሽ ሆኖ ለኖረውን ለዛ ደሃ – ትክሻ – ጋሻ – መከታ፤ ጃኖ መሆን በፈጣሪ ዘንድም ጽዱቅ መርኽ ነው። ጉዞው የዶግማ ያህል ዕብለት ሆነ ማባጨል የማይደፍረው ገናና ነው። ከተግባር ድምጽ በላይ በምድር ምንም የጎላ – ምንስ የጎመራ ሞገዳዊ ነጉድጓዳዊ ድምጽ – አለና። እኔስ እላለሁ – ! እኔስ እላለሁ ዋቢ ጠበቃዬ። ማን እንደ አንተ – የእኛ ዋሲሁን! ተስፋሁን! እግዚአብሄር ይስጥልን። ኑርልን። አንተ የተፈጠርክባት ዕለት ምንኛ የእኛ ለእኛ ስለ እኛ የቃል ኪዳን ሚስጢር – ነበረች። ስንት ጊዜ ይሆን እልል የተባለልህ ይህችን መሬት የረገጥካት ቀን – ዕልልታው ድርብ መሆን ነበረበት። የጥቃታችን – ሁነኛ አንተ የታሪክ ዓምደኛ!
አዎን! የምስክሩ መጸሐፍ ማደሪያው አስራትነት – በኰራትነት ነው። መታመንን ተግባር – ይወልደዋል። መወደድን ድርጊት -ሰጥቶናል። መናፈቀን መሆን – ሸልሞናል። ለድርጊት ፕሮፓጋንዲስት – ወይንም የተለጠፈ ማስታዋቂያ /poster/ አያስፈልገውም። የፖለቲካ ተግባር ቆም ብሎ ማስተዋልን እንጂ የአድርሽኝ ጸበለ ፃዲቅ – አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት መለኪያው ይሄው ብቻ ነው። የቆሰለውን የኢትዮጵያዊነት በደል መሻር፤ ጉዳቱን መካስ፤ ዋጋ እንዲኖረው የሚያደርገውም ይሄው የተግባር አዝመራ ብቻ ነው። ቀንን – ማድመጥ፤ ከወንጌል ቃል ጋር ስምምነት – መፍጠር። ለዘመን ሥጦታዎች ክብር መስጠት። እጣታችን ይበላለጣል አይደል – የኔዎቹ? መክሊታችንም – እንዲሁ።
ፕሮፌስር ብራሃኑ ነጋ ሥሙም ተግባር ነው። ለጎንደር ሰው የታማኝነት መነሻው እራሱ ሥሙን በቅኔ ዘጉባኤ – በቅኔ ይዘርፋውል። ጎጃምም …. እንዲሁ። ሥም ነብይ ነው። ይናገራል – ያናገርል ሥሙ ሳይቀር። ሥም ዬተስፋ – ወጋገን ነው። ሥም የመላዕክታን ቅዱስ መንፈስ ማረፊያ ጽዑመ – ዜማ ነው። ሥም የዝማሬ መግቢያ መዳረሻም ነው። ብርሃኑ ነጋ! ለዚህም ነው „ሥምን መላዕክ ያወጣዋል“ የሚባለው። ከእሱ በፊት ሥሙ ራሱ „እንኳን ደህና መጣህልን“ ብሎ በጉጉት እንደጠበቅ ያደርገዋል። እንዲህ ሥነ – ግጥም የሆነ ሥህነ ቤዛ ራዕይ …. ሊያባራ – ሊያነጋ።
… እንደ ጨለመ አይቀርም ይነጋል – በያነጋል። ግን መንፈሳችን ለሥነ ጥበባዊ አድምታ ስናስገዛ …. እኛም ለሥነ ልቦናው ጥበቃና ጥንቃቄ – ስናደርግለት። ለትጋቱ ዕውቅና ስንሰጠው። አንድ ሃቅ አለ። ምድር እንዲህ ቀውጢ መሆኗ ዛሬ ብቁ አቅም ላይ በመሆናችን ነው። ይህን እንዳትረሱት። ክታባችሁ ይሁን – የምናፍቃችሁ ወገኖቼ። ፍልሰቲት ገባች እኛም እንጠይቃት …. እንደምንጠይቃት የናፍቆታችን ልኬታ ትሆናለችና ንግሥት ድንግል – እናታች። አርበኞቻችን ትጎብኝልን። ድስስ ታድርግልን — የጎደለውንም በታምር ይሞላ ዘንድ የወይኖችን ጋኖችም ጎብኘት – ታድርግልን። እናተዊነቷ ያደርገዋል።
የንጋት – ንጋቱ
የቅኔ – ወተቱ
የተስፋ —————————————————————————————————-ግብዕቱ፤
ተግባር ነው ————————————————————————————————— ሥበቱ፤
መሆን ነው—————————————————————————————————–ውበቱ፤
ብርሃን – ሕይወቱ!
ለሥህነ – ቤዛ ይሁንልኝ። 04.08.2015
በማህሌት ደጋፊነት በትጋት ማዕለተ – ተሌሊት ሰዓታት የቆሙት የ24 ዓመታት ቅዱሳን የዕንባ ሱባኤ፣ ጻድቅ የዕንባ – ዘጉባኤ፤ …. መልክ ያዘ። ዘመነ – ሱባኤው በድል – ይሰክናል። ተግባርን የሚረታው በእኩል የተግባር ወቄት ብቻ ነው።
ክወና — የኔዎቹ የምወዳችሁና የማከብራችሁ ክብረቶቼ – መሸቢያ ሰንበት። ምልካም የሱባኤ መያዣ፤ ከፆም መያዣው በኋላም ተከታዩ ምዕራፍ ሁለት ይቀጥላል ….. ቀጠሮ ለዛሬ ሳምንት …..
ማሳሰቢያ – አባቱ የእኔ ጀግና ናትናኤልሻ እሺ – እኔ ሎሌህ ነኝ። በጹሑፎቼ ሁሉ መልእክትህን እለጥፋለሁ። በራዲዮ ፕሮግራሜም የበጋው እረፍት ሲያልቅ በድምጽ መልእክትህን ሙሉውን – አስተላልፋለሁ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45527
ቀደም ሲል በሠራሁት አጭር ፊልም https://www.youtube.com/watch?v=FmeGfeOaM_I&list=PLBwFEncxyNfuRqJSALv9zTCXJTUf0nOHd
ወሳኝ ለሆኑ የሐገር መሪዎችና ሰብዕዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች ከታህሳ 10 ቀን 2014 ጀምሮ እስከ የካቲት 8 ቀን 2015 ድረስ ልኬዋያለሁ። በፊልሙ ውስጥ አንተም አለህ። የመከራው ዘመን የፊት ታዳሚ ነህና – ማገዶ። አይዛችሁ። ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ያልፋል። ይነጋል – በያነጋል።
በእግዚብሄር ሥራ አትቅኑ!
የሥልጣን ጉምጅት ሱስ በፈጣሪ ሥነ ጥበብ ርትህ – ያገኛል!
አርበኞቻችን መርሆቻችን – መንገዶቻችን ናቸው!
ኢተዮጵያዊነት ያሸንፋል!
እግዚአብሄር ይሰጥልኝ።