Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » Opinion & Analysis
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

የተቃጠለ ካርቦን ነው ዬጥገና (Reform) ህልመኛነት መንፈስ (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 24.082015 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ጤና ይስጥልኝ እንዴትናችሁ ወገኖቼ። ከተለመደው ጊዜዬ ቀድሜ መምጣት ግድ አለኝ። ይህ የጥገና ወይንም የማሻሻያ Reform ለውጥ ህለመኝነት ከዚሕው ከቤቴ ከዘሃበሻ ተለጥፎ ማዬቴ ስላልተመቸኝ ነው ባልተራራቀ ቀን ብቅ ያልኩት።

reformዬወያኔ ሃርነት ትግራይ የታዛ ዕድሜ ለማኞች አዲስ ውሃ ያልነካው ወጀብ Reform ጥገናዊ ለውጥ አምላኪነትን ይዘው ከች ብለዋል። ትችቱም ከአንጀት ጠብ አይልም።ይህ ቅብ ወቀሳ የተለመደ ነው። እንዲህ መሰል የደካማቸው መንፈሶች እሳት መጫሪያ አጀንዳ አዘጋጅተው በዬጊዜው ነውጥ ፈጥረው የብሄራዊ ነፃነት ትግሉን አቅም ሲበሉ – ኖረዋል። አሁን ብሄራዊ ዬነፃነት ትግላችን በቆራጥ አርበኞቻችን ዱር ቤቴነት አብነት የመሠረቱ ፍላጎት መደላደል፤ ፍጹም ከማይችሉት ደረጃ ሲደርስ ደግሞ አዲስ ቅጥል ተስፈኝነት እያቆለማጡ ይገኛሉ – ይሄኛው እንዲህ እንዲያ ቢሆን ይሉናል። ይህን መሰሉን ዝል መንፈስ ተመገብው ደግሞ ያው የምናውቃቸው መደበኛ ሱቅ በደረቴያቸውን ከፍተው የሃሳብ ችርቻሮ – ይጀመራሉ። ቢገለባበጡም እነሱው ናቸው።

የአሜሪካው ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም በአዳዲስ አጀንዳዎች ዙሪያ በማር የተለወሱ መርዞችን ሰፋፊ ጊዜ እዬሰጠ አና ብሎ ተያይዞታል። ሰሞኑን ደግሞ የጠቅላይ ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንቆቅልሽ – ምን አውቅልሽ ገባጣም አስደመጠን፤ ያው በአንድ ምዕራፍ ከፌስቡክ ደንበኛው ከዶር. ቴወድርስ አድሃኖም አንካሳ መንፈስ ጋር በአንድ ካሊም የሚጠቃለል ነው። መቼም ጠ/ሚሩ መደባቸው የትኛውን ህበረተስብ እንደሚውክሉ ግራ ነው። ስለ አብሮነት ስለ ዘውገ ተከል አስተዳደር ጠንቅነት እዬሰበኩን ነው። የዞረባቸው። ሥልጣኑን የሰጣቸው እኮ ይሄው ዘውገ መራሽ ማንፌስቶ መሆኑን ሙልጭ አድርገው – እረስተውታል። ይህን እንዲያስፈጽሙ እኮ ነው የተሾሙት። …. „ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮኃል።“ ለነገሩ ከጤናቸው ጋር ስለመሆናቸው እጅግ – እጠራጠራለሁ። ነጋ መሼ ዝብርቅርቅ ባለ ግፋፎ – የጉሸ መንፈስ ላይና ታች ሲባዝኑ፤ በግድፈት ተንጠው ሲነዝሩ – ሲወድቁ፤ እላፊም ሲሄዱ ነው የሚታዩት …. ቢያንስ መካሪ የትዳር አጋርም የላቸውም እስኪያሰኝ ድረስ። እንጃ የሚያነቡትን ነገር ጋርም የሚተዋወቁ – አይመስለኝም። እውር ድንብሱን እኮ ነው የሚራመዱት። ቅጥ – አንብሩ ጠፍቶባቸዋል። ወረቀቱም ፈርዶበት በውልቅልቅ ፍላጎቶች ታጭቆ ተነበብ – ይባላል።

በሌላ በኩል የህግ ከፍተኛ ባለሙያው ከሆኑት ከተከበሩ ዶር. አበራ ደገፉም ስለ ህግ አፈጻጻም፤ ሥርዕተ ህገ መንግሥቱ ሞቶ ከተቀበረ ከስንት ዓመት በኋላ ሙያዊ የበቃ ትንተና ሲሰጡ እያዳምጥን ነው።  እኔ እንዲያውም ካነሱት ላይቀር በአዲስ አበባ ዩንቨርሰቲ የህግ ፋክሊቲ ስለሚባለው ለምን አይዘጉትም ስል ነበር – በግሌ። ፍትህ ለመቅበር ወጣቶችን ማስልጠን፣ መዋለ ንዋይ ማፈሰስ የሚያስፈልግ ስለማይመስለኝ። ጥቁሩን የክብር ልብስ ለመልበስ ከሆነ ምኞተኛው በግሉ አሰፍቶ መልበስ ይችላል። ሙያው ከተፈጥሮው ወጥቶ በዝርዝር የአፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ያተኮረ፤ ባለቤት የሌላው፣ ጎዳና አደር ከሆነ እኮ ዓመታት ተቆጠሩ። ለመሆኑ አሁን ነው የሚታያቸው የህግ ሥርዓት በኢትዮጵያ ከአፈር በታች መሆኑ ወይንስ አልኩ ለማለት ነው?! መጀመሪያ ከዛው ከዩንቨርስቲው ካለአግባብ የሚፈጸሙ ህገ ወጥ የመምህራንና የተማሪዎችን የመብት ጥሰትን የመከላከል፣ የማስቆም አቅም ይኑረው የህግ ፋክልቲ – ተብዬው። በዩነቨርስቲው ቅጽር ግቢ በአስተዳደሩ ከህግ በላይ ያሉትን የህወሓት ካድሬዎችን መልክ ለማስያዝ ኩስሙን አቅሙን ያነጋግር፤ ይህቺን ለማድረግ ያልቻለ የህግ ሙያተኛ ለእኔ የሚፈጥራቸው አዲስ የህግ ሰልጣኞች ለገቢ ማስገኛ ስምሪት በጥቃቅን ሸቀጦች ተደራጅተው ለጉሮሯቸው ከማደር በስተቀር ከሙያው ሥነ – ምግባር ጋር ፍቺ ከተፈጸመ እኮ ከ20ዎቹ ዓመታት በላይ ተቆጠረ። የተኛ ነገር ነው በሁሉም ዘርፍ የሚታዬው፤ በቅድሚያ እስኪ ከራሱ ይነሳ ….. እራሱን በግልጽ ወቅሶና ገምግሞ አለሠራኝም ካለው የሙያ አካዳሚያዊ ነፃነት አፈና ጋር ፊት ለፊት ተሟግቶ „በቃኝን“ በተግባር ያስጊጥ። ይህ ነበር ግንባር ቀደም ተልዕኮው …። እራሱን ማሰከበር ይቀደም። ለማንኛውም መልካም ምኞት ከሆነም ሁሉን በእኩልነት አሳታፊ ሥራአት ሲደራጅ በራሱ ጊዜ ይህ መረን የለቀቀ ጋጠ ወጥ መስመር መልክ ይይዛል። በጥገናዊ ለውጥ – አይተሰብም፤ በሥር ነቀል ለውጥ እንጂ። እራሳችንም በአብዮታዊ መንፈስ ውስጥ አስገብተን እንሞራርደው።

እንዲሁም ስለነፃነት ተማጋችነቴ ማን ከእኔ በላይ የሚለን ለበጠኛው ባለድርጎ ተሰፋሪ ሪፖርትር ጋዜጣም ቢሆን የት ነበረ እስከ ዛሬ ድረስ?! ለአፓርታይድ ፋሽስታዊ ሥርዓት ድርና ማግ በመሆን በቃል አቀባይነት፣ በአቀንቃኝነት፣ በአፍቅሮተ ዘውገኝነት፤ በሙሉ ድጋፍ ሰጪነት፤ በሽፋን ጠገብ የህወሓት ሞሾሪነት በቆዬበት ግድፈት ዘለቅ ዘመን ለመሆኑ ምን ያህል ዓመት በህዝብ ሰቆቃ እንደ ተኛ ያውቀዋልን? ምን ያህል ሰዓትስ በግፍ የደም ፍስት ፍራሽ እንቅልፍ ላይ እንደ ነበርስ? አንዱ ቀን 24 ሰዓት አለው፤ በዐመታት ሲሰላ ደግሞ የት እዬለሌ ነው። ለመሆኑ አሁን ደግሞ አይዋ ሪፖርተር የሚተጋው ምን ፈልጎ ነው? ምን አምጣ ነው የሚለው የ90 ሚሊዮን የህዝብ ዕንባን? አለዬነም እሱ ብሎ መካሪ – ዘካሪ። ይልቅ በህዝብ ደምና ዕንባ ሲነግድና ሲያስነግድ የኖረበትን ዘመን አንድ … ሁለት እያለ ስሌቱን ቢያስኬደው ምን ያህል ከሰመጠ ጉድጓድ ውስጥ እራሱ እንደ በቀለ መስታውት ገዝቶ ቢያዬው መልካም ነው። ባንዳነት አድሮ የማይገኝ አሳፋሪ፤ ተላምጦ የተጣለ አገዳ ወይንም ውሃ ሲሄደበት የከረመ አለትነት ነው።

አዎን የዘር አጀንዳ፤ የታሪክ አጀንዳ፤ የሰፈር አጀንዳ፤ የሃይማኖት አጀንዳ፤ የከተማና የገጠር አጀንዳ ክርችም ሲል ሌላ ጊዜ መግዣ የጥገና ለውጥ Reform አጀንዳ ደግሞ አሁን ጅራቱን እዬቆላ ይገኛል በህወሓት አጋፋሪ በአይዋ ሪፖርተር። ቀጣዩ ደግሞ „ይኸው ይህን ህወሓት አሻሻለ፤ ይኸው ይሄኛውን ህወሓት ማሻሻያ ደገመ። ይኸው – ይኽኛው ተሰለሰ፤ ይኽው ይህን ያህል እስረኛ – ተለቀቀ፣ ህወሓት መማር ማስተካከል ጀመረ፤  በማለት አዘናግቶ ሌላ የራህብ፤ የሰቆቃ፤ የፍዳ፤ የዕንባ፤ የብሄራዊ ውርደት ዘመን አንድ ሁለት ሦስት አራት እያልን ወደ አይቀሬው ዬምርጫ ዙር ተብዬ ሽግግር – ይደረጋል። ከዛም 96 ፕርሰንት አሸነፈ ህወሓት ተቃዋሚውም ደግሞ 4 ፐርሰንት አግኝቷል በዚህች እንተክዝ …. በሚቀጥለው … በሚቀጥለው ደግሞ የአንድ ፐርሰንት ምራቂ ትኖረናለች“  ወዘተ ወዘተ ተረት – ተረት፤ ለዚህም ነው የአሁኑ ዓይን ያወጣ አዲስ ትጥቅ አስፈቺና አዘናጊ የጥገና Reform አጀንዳ … አና ብሎ ዕወጃ በዬአቅጣጫው ነጋሪቱን እዬጎሰመ ያለው። ቀልዱ ይቁም! ተረቡ ጠርዝ ይኑረው! በዕንባ ዘመናይነቱ ገደብ ይኑረው! ሪፎርምር ሪፖርተር ጋዜጣም ለከት ይኑርህ!

…. ያው የሳይበር አማሾች ደግሞ  እንደ ተለመደው አጀንዳቸው ሁሉ አይሆኑ ሆኖ አፈር ቅሞ ማርቶ አፈር ስለገባ። በለመደባቸውና በሰለጠኑበት የዕድሜ ለማኝነት አዲስ ነጠላ ዜማዋን ትናንሽ ኮርስ ይወስዱና ሰብሰብ ብለው „አይተን የመጣነው፤ ግን ሊስተካካል ይቻላል ተብሎ ቃል የተገባልን እዬሆነ ነው፤ ህወሓት ተሻሻለ¡ አሻሻለ አስተካከለ¡“ በማለት ይቀጥላሉ። ድሪቶ – በድሪቶ። አጃቢዎቻቸውም የእንኳን ደህና መጣችሁልን አቀባበላቸውን የሚገልጡበት መድርክ ይባልና በደማም ቃላት፣ በቀለም የተለቀለቁ ልስን አዳዲስ ብሎጎች፣ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት የተንቆጠቆጡ ድህረ ገፆች – በአዲስ፤ ጥገናዊ Reform የሚከበክብ የሚከብ፤ የሚያነጥፍ የሚጎዘጉዝ የመወያያ መድረክ – አዲስ ፓልቶክ፤ የተዘጉትም የውይይት መድረኮች በተሃድሶ መንፈስ – ይከፈታሉ። ራዲዮም አዲስ ይጀማመራል —- በዛው ልክ ፌስቡኩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች በስፋት ይዘረጋሉ። የተቃጠሉ ካርቦኖች። ጭስ!

አጅሬው – ህወሓት ደግሞ ዶላሩን በአፍ አፋቸው ያጎራርሳና አታሞውን ተመልካች – ይሆናል። በገፍ ያሰማራቸው ሰላዮችም በአዲስ የባንዳነት ቃና ጠብ እርግፍ – ይላሉ። ነገር ግን ሁሎቹም በረገበ አልጋ፤ በሰመጠ መርከብ ላይ መሆናቸው አይታያቸውም። እንዲያውም „አዲስ የኃይል አሰላለፍ ተፈጠረ በማለት ለዚህ ነበር የደከምነው – የታገልነው“ ይባልልናል። ልክ ለውሻ እንደሚጣለው ቅንጥብጣቢ ሥጋ ያን ከገዢያቸው ከትግራይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ የሚወረውረውን ቅንጥብጣቢ ዬሥጋ ቁራጭ ለመንፈሳቸው አቀብለው ብሄራዊ ዘላቂ ዬነፃነት ፍላጎታችን ለመቦርቦር ዬዳንሱ አርንቋ ትዕይንት – ይያያዙታል።

የፖለቲካ ተንተኞቻቸውም „አደብ ገዝተን ማደመጥ ይገባል¡ ያጸደቁትን ህገ መንግሥታቸውን በራሳቸው ጊዜ እዬሸራረፉት ነው¡“ በማለት በብዕራቸው፤ በማይካቸው ተግተው ስብከታቸውን „ቀስ እዬተባለ¡ እዬተስተዋለ¡“ እያሉ የፕሮፓጋንዳ ጥፈት – ይለጣጥፋሉ። ይህ ለእኔ እርባናው ያለቀ የተቃጠለ ካርቦን አዲስ የምኞት መቃብር ድራማ ነው። የሚያሳዝኑኝ ግን ቅኖች ህሊናቸው ከዕለት ዕለት ታቱ ዥግራ ማለቱ ነው።

የሰው ልጅ እራሱን መተርጎም የሚችለው መቆም ቀጥ ብሎ ሲችል ብቻ ነው። መቆሙንም ማረጋገጥ ይኖርበታል። በዚህ ወጣ ገብ በሆነ ወጀብ መናጥ፤ መቆም አለመቻል የተፈጥሮ ሽሽት ወይንም የራስነት ውስት ብቻ ሳይሆን ከበታችነት የመነጨ ፍርሃትም ነው። በተለያዩ ክሮች ትስስር ከፋሽስቱ ወያኔ ጋር ጋብቻው አለ። እዬታዬ ያለው ያን ክር መበጠስ ድፍረቱን የሚቀማ የጥቅማጥቅም ድልድይ ወይንም የተስፈኝነት ሙት መንፈስ መንገታተገት ነው፤ የበሰበሰ ነገር መወገድ እንጂ ጥገናዊ ለውጥ በፍጹም ሁኔታ አያስፈልገውም። ጊዜው ያለፈበት ምግብ በሽታ ስለሆነ ዕጣ ፈንታው መደፋት ብቻ ወይንም ቆሻሻ ኮንቴይነር ውስጥ መጨመር ነው። ዬህወሓት መንፈስ ማርጀት አይደለም፤ ሞቷል። ደግሞ መነሳት ቀርቶ ዳግም ለመነሳት ማሰብም አይችልም። በቅቶታትል። ታሪክ – ተፍቶታል። ከውርርስ ቅርስነትም ውጪ ነው። ህወሓት ዕድሉን ያባከነው ዛሬ ሳይሆን ከ10 ዓመት በፊት በዘመነ ቅንጅት ወይንም ከዛ በፊት በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ዘመን ነበር። ያን ጊዜ ታሪክ እራሱን አይቶ ከገደል ጫፍ የሚድነበትን ሁለት ትላልቅ መስተዋቶች ገዝቶለት ነበር። አሱ ግን ከመስታውቱ ላይ በመቆም ዕድሉን በመታበይ – ሰባብሮታል። የተቃጠለ ካርቦን።

የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ ሐገራችን ዘመነ መሳፍንትን፤ ዬዓፄ ሥርዓትን፤ የወታደራዊ ሥርዓት በሶሻሊስት – ርዕዮትዓለምን። እንደዬዘመኑ በተለያዩ ፈተናዎች ተወጥራ አስተናግዳለች። ከዘመን ባፈነገጠው በቬርሙዳ ትርያንግሉ ጠፍ አስተዳደር በህወሓት ደግሞ በዓለም የሌላ፣ ዘመንም የተፋው፣ ታሪክም የሚጸዬፈው፣ አደራም ያቃረው፤ ባህልም የፋቀው የዘውገ ሥርዓትን በአልባንያ አብዬት ጥንዝል ተመክሮ በፍዳ፣ በመከራ፣ በስቃይ ተቃጥላ፣ ተንገብግባ፣ ተርመጥምጣ አሳልፋለች። ሁሉንም – አይታለች። ለሁሉም መከራዊ ዘመን መፈተኛ ሆናለች።

አሁን ግን ዘመኑ የፈቀደላት ሌላ የፍትህ አዲስ የዲሞክራሲ የሽግግር ሥርዓት ያስፈልጋታል። በቅድሚያ እንዲያውም ብሄራዊ ነፃነት። ኢትዮጵያ ከጠላቷ ከህወሓት እስር ቤት መውጣት አለባት። ከዚያ በኋላ ሂደቱ ሁሉን ዜጎቿን በ እኩልነት ያሳተፈ አዲስ ሥርዓት አቅምና ህግ በድምጽ ብልጫ ሊመራት የሚችል ሀገር መሆን። ሰው የሚለውን ማዕከላዊ የተፈጥሮ አጀንዳ ተርጉሞ፤ በፈጣሪ አምላካችን የተሰጠው ዬሰው ልጅ ክብር ሙሉ መብት ሳይገፈፍና ሰይገሰሰ በዜግነት እኩልነት ላይ የተመሰረተ የተስፋ ሥርዓት መዝርጋትን ነው – የፍላጎቷ ህልመ – አስኳል። ለዚህ ደግሞ ዛሬ – የሞቀ የደመቀ ዬአብዛኛውን መንፈስ የገዛ አዲስ ብረሁኽ የለወጥ መንፈስ ላይ እንገኛለን። አቅማችን፣ ኃይላችን፣ አቅላችን፣ ህልማችን፣ ናፍቆታችን፣ ጸሎታችን እንደ ዕምነታችን ተማክሎ ከዛ ላይ በአርበኞቻችን ባረፈበት በአሁኑ ጊዜ የሪፖርትርን Reform የዕድሜ ልምና፣ የሱባኤ ነጋሪት ማስታመም፣ ማቆላመጥ ሆነ ማንቆላበስ ወይንም ማሽሞንሞን የተገባ አይመስለኝም። በምልአት ደምና ሰቆቃ መነገድ ነውም። የደም ንግድ ይቁም!

ሁሉመናን ለወሰደ – ቀማኛ ሽፍታ፤ ውሸታም፤ ዘራፊ፤ ይሉንታ ቢስ፤ ለበቀል ዞጋዊ ፖሊሲ አራማጅ አረመኔያዊ የህወሓት ሥርዓት ብጣቂ ጊዜ ልናውሰው ፈጽሞ – አይገባም። ይህ ያሰኘናል የሚሉ ሸጎሬዎች አብረው ድንኳን ጥለው ያስተዛዝኑ …. ሳልስቱንም፣ ሰባቱንም አርባውንም – ያውጡ። ይህ የእኛ መደባችን አይደለም። እኛን እኛን የማይሸት፣ ሰውኛ ያልሆነ የሳጥናኤልን ቀጠናን ቅብጥና ቅልጥ የሚያድርግ የራዕያችን ትንፋሽ ቅበረት ዘመቻ ስለሆነ „በቃን“ ልንለው ይገባል።

በቃን“ ማለት እኮ እንዲህ አይነት የሚያላዝኑ ዝልብ – ስንጥቅ – ትርትር – ቀዳዳ ፍላጎቶቹን ማስፈንጠር ነው። ዬአሞሌ ጨው መላሾነት ለከብት እንጂ ለሰው ልጅ ክብር – አይመጥነውም። ለነገሩ ይህ „በቃን“ የሚለው ቃል ትርጉሙም የገባን አይመስለኝም። „በቃን“ ሲባል እኮ ማናቸውም ወያኔ ነክ መንፈሶችን ሁሉ መጸዬፍ፣ መገፍተር ማለት እንጂ እንደ ገደል ማሚቶ ደግሞ ማስተገባት አይደለም። ይህ በዕውነቱ 25 ዓመት የፈሰሰውን የወገኖቻችን ደም መርገጥ ነው። የእናት ኢትዮጵያን ዬኤሉሄዋ የምጥ ድምጽም እንደ መጠቅጠቅ ነው።

ለመሆኑ ስንት ጊዜ ነው ዕድላችን ለጆፌ አሞራ የምንቀልበው!? አይበቃም?!  በደል አይረሰም – ያገረሻል እንጂ። …. ይህ የፋታ ፖሊሲ ቃር ነው። ስለሆነም አንቅረን ልንተፋው – ይገባል። ንቀን ስንተዎው ወደ ገደሉ ተመልሶ – ይቀበራል። አፈሩን ተከናንቦም ለሽ ይላል። እኛን በእኛነት ሊያከብር ለተነሳው የአርበኝነትን መንፈስ ውስጣችን ገልጠን ለእሱ – እናስረክብ። ለመሆኑ እነዛ እስር ቤት ውስጥ ሆነው „እኔ ዬአርበኞች ግንቦት 7 ነኝ!“ ያሉን ቀንበጦች መልዕክት ከሰው አንደበት የወጣ ይመስላችኋልን?! የጀግና ጋዜጠኛ አበበ ገላው በሬግን ህንፃ በሀገረ አሜሪካ በፈጣሪ አምላኩ የተመረጠለት መክሊት ድምጽ አኮ ነው፤ ዛሬም በኢትዮጵያ ምድር በድፍረት በአራዊቶች ካቴና ላይ ሆኖ ድምጹን ለብላቴናዎቹ አምላካችን መዳህኒተዓለም አቀብሎ ያውም በህብረት አንደ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ብሄራዊ ጥሪ የላከልን። ጥሪው እኮ ዬፈጣሪ አምላካችን ዬአማኑኤል ነው። ፈጣሪያችን እራሱ በሳጥናኤላዊ ህወሓት አመራሩ ከምር – አዝኗል። ታምራትን የእኛ እንበለቸው።

ወገኖቼ ጊዜው ደርሷል። ማቄን ጨርቄን – አንበል። ቢያንስ የፈጣሪን ድምጽ ለማድመጥ – እንፍቀድ። –  ጥሪውንም እንቀበል! ታጥቦ ጭቃም አንሁን ልክ እንደ ሦስት ዓመት – ህፃን። ቢያንስ መንፈሳችን እንደ ዕድሚያችን የማሰብ አቅሙን – እናሳድገው። መዳህ መዳህ —- መሬት ላይ ለመቅረት መሆን አይገባውም። ዘመንም ጊዜም ማድመጥ መተርጎም አብሮ ለመሆን መፍቀድ – ያስፈልጋል። በስተቀር ድንጋይ ነው ተብሎ መወርወርም አለ ….. ይበቃል ግልምቷል ግምቷል ህወሓትና ፖሊሲው። መልካም ሰሞናት።

ምንጭ  –

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት ቦታ የለውም›› ዶ/ር አበራ ደገፋ፣ የሕገ መንግሥት ኤክስፐርት http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46121#sthash.S8L3yZti.dpuf

ኢሕአዴግ ራሱን ይመልከት! ጋዜጣው ሪፖርተር ርዕሰ አንቀጽበጋዜጣው ሪፖርተር

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46125

 

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1664

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>